id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
52433117
https://www.bbc.com/amharic/52433117
በሊባኖስ ለሽያጭ የቀረበችው ናይጄሪያዊት ተረፈች
በሊባኖስ ለሽያጭ ቀርባ የነበረችው ናይጄሪያዊት ከመሸጥና ከመለወጥ ተርፋለች።
የሽያጯ ማስታወቂያ በፌስቡክ ላይ ወጥቶ የነበረ ሲሆን፣ ከቀናት በኋላም ማስታወቂያውን በመለጠፍ ተሳትፏል የተባለ ግለሰብም በቁጥጥር ስር ውሏል። የግለሰቧ የሽያጭ ማስታወቂያ በናይጄሪያውያን ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል። •ስለቫይረሱ ከሚናፈሱት በጥቂቱ፡ የአሪቲ መድኃኒትነት፣ የአለምን ህዝብ መቆጣጠሪያ መንገድ •ሞተዋል የተባሉት ሴት "አልሞትኩም እህቴ ጋር ደውሉልኝ" አሉ የዲያስፖራ ናይጄሪያውያን ኮሚሽን ሊቀ መንበር አቢኬ ዳቢሪ ኤሬዋ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ለሽያጭ ቀርባ የነበረችው የ30 አመቷ ናይጄሪያዊት አሁን በደህና ሁኔታ ላይ እንዳለችና ቤይሩት ውስጥ በሚገኘው የናይጄሪያ ኤምባሲም እንደምትገኝ አረጋግጠዋል። ሊቀመንበሩ አክለውም የሊባኖስ ባለስልጣናት እንዳዳኗት ገልፀው ነገር ግን በምን መንገድ እንደሆነ ዝርዝር ከመስጠት ተቆጥበዋል። ሆኖም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መዛመትን ለመቆጣጠር የተላለፈው የቤት መቀመጥ ውሳኔ ሴትዮዋን ፈልጎ ለማግኘት እንደረዳ ገልፀዋል። በቤት ሰራኝነት የምትተዳደረውን ይህችን ግለሰብ በአንድ ሺ ዶላር ለመሸጥም ፌስቡክ ላይ ማስታወቂያ ወጥቶ ነበር። በማስታወቂያው ላይም የግለሰቧ የፓስፖርት ፎቶ በግልፅ የሚታይ ሲሆን በርካታ ሰዎች መጋራታቸውን ተከትሎም፤ ቁጣና ውግዘትም እየተስተናገደ ነው። •በአትላንታ የኮቪድ-19 በነፃ የሚመረምር ክሊኒክ ያቋቋሙት ኢትዮጵያዊ የተባበሩት መንግሥታት መረጃ እንደሚያሳየው ከናይጄሪያ እንዲሁም ከሌሎች አፍሪካ አገራት ታዳጊ በተለያየ የእድሜ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሴቶች በአዘዋዋሪዎች እንደሚሸጡ ነው። ብዙዎችም በአውሮፓና በእስያ የተሻለ ስራ ታገኛላችሁ በሚል ከቤታቸው ተታለው ወጥተው በቤት ሰራተኝነት እንዲሁም በወሲብ ንግድ እንደሚሰማሩና ብዙዎችም ለብዝበዛ እንደሚዳረጉ የተገኘው መረጃ ያሳያል።
news-44707683
https://www.bbc.com/amharic/news-44707683
ኬንያዊው በኮንዶም ምክንያት መንግሥትን ከሰሰ
አንድ ኬንያዊ ግለሰብ "ኮንዶም ተጥቅሜ ግብረ-ስጋ ብፈፅምም ለአባላዘር በሽታ ተጋልጫለሁ" በማለት መንግሥትን ከሷል።
ግለሰቡ የከሰሰው የመንግሥት ጥራት ተቆጣጣሪ፣ የገቢዎች መሥሪያ ቤትንና ቤታ የተሰኘ መድሃኒት አስመጪ ድርጅትን ነው። ስሙ እንዲጠቀስ ያልተፈለገው ይህ ግለሰብ "ሶስቱ መሥሪያ ቤቶች ተጠቃሚዎችን ከመሰል ክስተቶች መጠበቅ አልቻሉም" ሲል ወንጅሏል። መሥሪያ ቤቶቹ ስለክሱ ያሉት ነገር እስካሁን መገናኛ ብዙሃን ጆሮ አልደረሰም። ግለሰቡ በሽታው ወደባለቤቱ መተላለፉን በመግለፅ ሁኔታው 'ከባድ' መሆኑን አፅንኦት ሰጥቶ ተናግሯል። "ኮንዶሞቹን የገዛሁት የዛሬ አራት ዓመት ገደማ ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ነው" ያለው ከሳሽ ትንሽ ቆይቶ ህመም ይሰማው እንደጀመር አሳውቋል። "ሁኔታው እጅግ ቢጨንቀኝ ጊዜ ነው ወደ ባህል ሃኪም የሄድኩት" ያለው ከሳሽ ኮንዶሙ ለህመሙ ምክንያት መሆኑን ለመረዳት ብዙ እንዳልፈጀበት አሳውቋል። "ክስተቱ ጎድቶኛል፤ ተቃውሻለሁ፤ መጠጥ ማዘውተርም የጀመርኩት ከዚያ በኋላ ነው" ሲል ከሳሽ ክሱን አሰምቷል። በዚህ ምክንያት ሥራውንና ቤተሰቡን እንዳጣ የተናገረው ግለሰብ የፍርድ ያለህ እያለ ይገኛል።
news-54389480
https://www.bbc.com/amharic/news-54389480
አትሌቲክስ፡ ቀነኒሳ በቀለ በጉዳት ምክንያት ከለንደን ማራቶን ራሱን አገለለ
በረዥም ርቀት ሩጫ ከፍተኛ ዝናን የተጎናፀፈው ቀነኒሳ በቀለ ባቱ ላይ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ከለንደን ማራቶን ራሱን አግልሏል።
በመጪው እሁድ በሚካሄደው የለንደን ማራቶን ውድድርም እንደማይሳተፍ አዘጋጁ፣ ቨርጂን መኒ ለንደን ማራቶን በድረገፁ አስታውቋል። በባለፈው አመት መስከረም ላይ በርሊን በተካሄደው ማራቶን በ2፡01፡41 ሰዓት ውድድሩን አሸንፎ የነበረው ቀነኒሳ የለንደኑ ከዚያ በኋላ ሁለተኛ ውድድሩ ቢሆንም በዚህ ውድድር ላይ አለመሳተፉ እንዳሳዘነው ገልጿል። "በእሁዱ ውድድር ላይ ባለመሳተፌ በጣም አዝኛለሁ" በማለት የገለፀው አትሌቱ "በወረርሽኙ ምክንያት የቡድኑን አባላት ሳላገኝ መዘጋጀቱ ፈታኝ ነበር። ሆኖም በጣም በጥሩ ሁኔታ ላይ የነበርኩ ቢሆንም በግራ ባቴ በኩል የሚነዘንዝ ህመም በባለፉት ሳምንታት እየተሰማኝ ነው። ሁለት ፈጣን ስልጠናዎች ካደረግኩ በኋላም ነው የህመሙ ስሜት እየተሰማኝ ያለው" ብሏል። አክሎም "ህመሙ ከተሰማኝ ጀምሮም ህክምና እያደረግኩ የነበረና ለውድድሩም ዝግጁ እሆናለሁ ብዬ በሙሉ ልቤም አስቤ የነበረ ቢሆንም ዛሬ ግን በጣም ከፍቶ በዚህ ሁኔታ መወዳደር እንደማልችል አወቅኩ" በማለት አስታውቋል። "የለንደኑ ማራቶን ለኔ በጣም ጠቃሚ ነበር። ባለፈው አመት በበርሊን ያደረግኩት ውድድር ከፍተኛ በራሰ መተማመኔን ጨምሮልኛል፤ መነቃቃትም ፈጥሮልኛል። እናም ያንን ለማሳየት በከፍተኛ ሁኔታ ጠንክሬ ዝግቴን እያደረግኩ ነበር። በአለማችን ያሉ በርካታ ሰዎች ይህንን ውድድር በጉጉት እየጠበቁት እንደነበር አውቃለሁ። አድናቂዎቼን፣ አዘጋጆቹንና ተወዳዳሪዎቹን ቅር በማሰኘቴ አዝናለሁ። ለማገገምና እንደገና ዝግጁ ለመሆን ጊዜዬንም እወስዳለሁ። በሚቀጥለው አመትም ለንደን እንደምመለስ ተስፋ አደርጋለሁ" ብሏል። የቨርጂን መኒ ለንደን ማራቶን የዝግጅት ዳይሬክተር በበኩላቸው "አለም የቀነኒሳ በቀለንና የኢሉይድ ኪፕቾጌን ውድድር በጉጉት እየተጠበቀ ነበር። ቀነኒሳ ምን ያህል ቅር እንደተሰኘና እንዳዘነ እናውቃለን። በፍጥነትም እንዲያገግም እንመኝለታለን"ብለዋል። ሆኖም ይሄ ውድድር የሁለት ሰዎች ብቻ ሳይሆን በማራቶን ውድድር አስሩ ፈጣን ከሚባሉት አራቱ የሚሳተፉበትና ስድስቱ ደግሞ የ2፡05 ሬኮርድን የሰበሩ መሆናቸውንም አስታውቀዋል። ከነዚህም መካከል በባለፈው አመት ሁለተኛና ሶስተኛ የወጡት ሞስነት ገረመውና ሙሌ ዋሲሁን ይሳተፋሉ ማለታቸውንም በድረገፁ ላይ ሰፍሯል። በመጪው እሁድ በበይነ መረብ በሚካሄደው የለንደን ማራቶንም ከ109 አገራት የተውጣጡ 45 ሺህ ያህል ሰዎች በውድድሩ ለመሳተፍ ተመዝግበዋል። ይህ አርባኛው ውድድርም ከቤታቸው ወይም ካሉበት ሆነው በኢንተርኔት አማካኝነት ተሳታፊ ይሆናሉ።
news-47092451
https://www.bbc.com/amharic/news-47092451
በቴፒ ለተፈጠረው ግጭት ምክንያቱ ምንድን ነው?
በቴፒ ከተማ ከትናንት በስቲያ ጥር 22/2011 ዓ.ም በተነሳ ግጭት ሰባት ሰዎች መሞታቸውን የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ የሽዋስ አለሙ ለቢቢሲ ገለፁ።
ግጭቱን ተከትሎም ጥር 5/2011 ዓ. ም የዓመቱን ትምህርት መስጠት የጀመረው የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቴፒ ግቢ ትምህርት መቋረጡን ሰምተናል። • የብሔር ግጭት የሚንጣት ሀገር ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገው በዩኒቨርሲቲው ቴፒ ግቢ ተማሪ እንዳለው ከትናንት በስቲያ ግጭቱ ሲፈጠር መስጊድ ሰፈር (ባጃጅ ሰፍር) አካባቢ ከጓደኞቹ ጋር ወጣ ብሎ ነበር። "በድንገት አካባቢው በግርግር ተናወጠ፤ በተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ ይሰማ ነበር፤ ማን ለማን እንደሚተኩስ አይታወቅም፤ ቀውጢ ተፈጠረ" ይላል። በወቅቱም እነርሱም ራሳቸውን ለማዳን መንደር ለመንደር እየተሹለከለኩ ወደ ግቢያቸው እንዳመሩ ይናገራል። በጊዜው በቴፒ ካምፓስ የተማሪዎች የምግብ አቅርቦት ችግር አጋጥሞ ስለነበር በግቢው ውስጥም ውጥረት ነግሶ ነበር ይላል። ምክንያቱ ምን እንደነበር እርግጠኛ ባይሆንም በከተማው ውስጥ ባለው አለመረጋጋት ሳቢያ ምግብ አብሳዮቹ በሥራ ገበታቸው ላይ ባለመገኘታቸው መሆኑን ለቢቢሲ ገልጿል። አካባቢው ከተረጋጋም በኋላ በርካታ ቤቶች ወደተቃጠሉበት ስፍራ እንደሄዱና 'ጀምበሬ' እየተባለ የሚጠራው ሰፈር ሙሉ በሙሉ መውደሙን እንደተመለከተ ተናግሯል። በዩኒቨርሲቲው የ3ኛ ዓመት ተማሪ የሆነው ይህ የዓይን እማኝ እንደሚለው በአካባቢው በየዓመቱ ችግር እንደሚነሳ በማስታወስ አሁንም በግጭቱ ምክንያት ትምህርት ተቋርጧል። በሚዛን ቴፒ አካባቢ የቆየ የመዋቅር ጥያቄ ነበር የሚሉት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የቴፒ ከተማ ነዋሪ እንደገለፁት በተፈጠረው ግጭት ምክንያት በግምት የአንድ ትልቅ ቀበሌ 1/3ኛ የሚሆን ሰፈር ሙሉ በሙሉ ወድሟል። • በጂግጂጋ በተከሰተ ግጭት ሁለት ሰዎች ተገደሉ "ከዚህ በፊት ቴፒ በሸካ ዞን ሲተዳደር ቆይቷል፤ ሕዝቡ ያንን በመቃወም በዞኑ መተዳደር አንፈልግም የሚል ጥያቄ በማቅረቡ እርሱን ሰበብ ተደርጎ ጉዳዩ ወደ ብሔር ግጭት አመራ" ይላሉ። ህዝቡ የተለያየ ኮሚቴ አዋቅሮ ለጥያቄው መልስ ለማግኘት እየተጠባበቀ ባለበት በአሁኑ ሰዓት ባልታሰበ ሁኔታ ሌሊት ላይ ጥቃት መፈፀሙን ይናገራሉ። እርሳቸው እንደሚሉት ጥቃቱ ከትናንት በስቲያ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድንጋይ በመወራወር ተጀምሮ በመንገድ ዳር ያሉ የሚከራዩ ቤቶችን በማቃጠል ነው የተጀመረው። ጥቃቱ ቀን ጋብ ብሎ ከቆየ በኋላ ሌሊት ከ9፡00 ሰዓት በኋላ በርካታ ቤቶች እንደተቃጠሉና ንጋት ላይ ወደ ጫካ ሸሽተው የነበሩት የሰፈሩ ነዋሪዎች ደርሰው ለማጥፋት ሲሞክሩ እንደነበር ይናገራሉ። ሰዎች በተኙበት ቤቶችና መጋዘኖች ተቃጥለዋል፤ አሰቃቂ ግድያ ተፈፅሟል የሚሉት መምህሩ፤ "በወቅቱ ሰዎች ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ እርስ በርስ እየተጠራሩ ወደ ጫካ ሸሹ፤ ይሁን እንጂ አዛውንቱ የጓደኛዬ አባት አገር ሰላም ብለው በተኙበት በስለት ተገድለዋል" ይላሉ። "የእኔ ቤተሰቦች ንብረታቸው ተዘርፏል፤ ቤታቸው ወድሟል" ሲሉ በሃዘን ይገልፃሉ። • የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ስጋት ነግሶበታል ትናንት በቴፒ ከተማ በየመንገዱ ላይ የሚቃጠሉ የመኪና ጎማዎች፤ በቁጣ የተነሱ ወጣቶችና ነበር የሚታየው፤ የተኩስ ድምፅም ይሰማ ነበር። በአንፃሩ ዛሬ የከተማው ነዋሪዎች በግጭቱ የሞቱትን ሰዎች ለመቅበር በተለያየ ቦታ ተበታትነው ስለሚገኙ በአንፃሩ መረጋጋት ይታይበታል ብለዋል። በወቅቱ ሕዝቡ የፀጥታ ኃይሎች ጣልቃ ይገባሉ ብሎ ቢጠባበቅም ግጭቱን ለማስቆም ምንም እርምጃ ባለመወሰዱ ጉዳት መድረሱንና ችግሩ ከተከሰተ በኋላ ከስፍራው መድረሳቸውን ተናግረዋል። መምህሩ አክለውም ዩኒቨርሲቲው ትምህርት የጀመረው ዘግይቶ ቢሆንም አሁንም በዚሁ ግጭት ምክንያት በቴፒ ካምፓስ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ትምህርት መቋረጡን ይገልፃሉ። እርሳቸው እንደሚሉት ለተማሪዎቹ ደህንነት ሲባል ተማሪዎች በግቢው ውስጥ እንዲቆዩ የተደረገ ሲሆን በዩኒቨርስቲው ሁለት ግቢዎች ውጥረትና ስጋት ይታያል። የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳረ አቶ የሽዋስ አለሙ በበኩላቸው ራስን በራስ የማስተዳደር የቆየ ጥያቄ ቢኖርም የአሁኑ ግጭት መነሻ ግን ተቋርጦ የነበረ የትራንስፖርት አገልግሎት መጀመር ነው ይላሉ። አስተዳዳሪው እንዳሉት በግጭቱ 7 ሰዎች ሲሞቱ 100 የሚጠጉ ቤቶች ተቃጥለዋል፤ 1500 ሰዎችም ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። የፌደራል፣ የክልልና የመከላከያ የፀጥታ ኃይሎች በአካባቢው ፀጥታ ለማስፈን እየሰሩ መሆናቸውን አስተዳዳሪው ለቢቢሲ ገልፀዋል።
50969761
https://www.bbc.com/amharic/50969761
ሲጃራ የሚያጤሱም ሆኑ ያቋረጡ 'የሚኖሩት በከፍተኛ በስቃይ ነው'
ሲጃራ የሚያጤሱም ሆነ ማጤስ ያቆሙ የሲጃራ ሱስ ከሌለባቸው ሰዎች አንጻር ሲታዩ የሚኖሩት በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ መሆኑን አንድ ጥናት ይፋ አደረገ።
ጥናቱ የተደረገው 220 ሺህ ሰዎች ላይ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ተመራማሪዎቹ እንዳሉት ለስቃዩ ምክንያት የሆነው ጉዳይ ምን እነደሆነ አላወቅንም በማለት ነገር ግን ሲጋራ ማጨስ ሰውነታችን ላይ ቋሚ ለውጥ ያስከትላል ሲሉ ተናግረዋል። • በሙስሊሞች የሚጠበቀው የአይሁዶች ቤተ መቅደስ • 2019 የአውሮፕላን አደጋ ተጎጂዎች ቁጥር የቀነሰበት ነው ተባለ • የቀድሞ የጊኒ ቢሳው ጠቅላይ ሚኒስትር ፕሬዚደንት ሆነው ተመረጡ የፀረ ሲጃራ ቡድኖች ደግሞ ይህ ምኑ ይደንቃል ሲሉ ግኝቱ እንደ ትልቅ ነገር መታየት እንደሌለበት ተናግረዋል። ተመራማሪዎች ከ2009 እስከ 2013 ድረስ የተሰበሰበ መረጃን መሰረት አድርገው ጥናታቸውን አከናውነዋል። አጢሰው የማያውቁ፣ በቀን አንዴ ያጤሱ ከነበሩ ወይንም ደግሞ አሁን እያጤሱ ያሉ በሚል ከፍለው ማጥናታቸውን ያስረዳሉ። ጥናቱ የተደረገባቸው ግለሰቦች ምን ያህል ሕመምና ስቃይ እንደሚሰማቸው የተጠየቁ ሲሆን፣ የሚሰማቸው ሕመምንም ከ 0 እስከ 100 ድረስ ደረጃ ሰጥተውታል። የሚሰጡት ቁጥር ከፍ ባለ ቁጥር ስቃዩም ከፍ ያለ ይሆናል ማለት ነው። አሁን የሚያጤሱ አልያም ያጤሱ የነበሩ ግለሰቦች አጢሰው ከማያውቁ ሰዎች አንጻር ሲታዩ፣ የሰጡት ነጥብ በአንድ ወይንም በሁለት ነጥብ ከፍ ያለ መሆኑን የጥናት ቡድኑ ይፋ አድርጓል። "የግኝታችን ዋና ፍሬ ነገር ማጤስ ያቆሙ ሰዎች አሁንም ድረስ ህመሙ እንደሚሰማቸው ማወቃችን ነው" ብላለች ዶ/ር ኦልጋ ፐርስኪ ለቢቢሲ። ዶ/ር ፐርስኪ አክላም ከግኝታቸው ሁሉ ይበልጥ ያስደነቃት ከፍተኛ ሕመም የሚሰማቸው ሆነው የተገኙት እድሜያቸው ከ16-34 ድረስ ያሉ ወጣት አጢያሾች መሆናቸው ነው። ማጤስ ባቆሙ ሰዎች ላይ እስካሁን ድረስ ህምመ ሊሰማቸው የቻለበትን ምክንያት ፍርጥርጥ አድርጎ ማብራራት የተሳነው ይህ ጥናት መላምት ነው ያለውን ግን አስቀምጧል። አንደኛው መላምት በትምባሆ ውስጥ ያለው ኬሚካል በቋሚነት የቲሹ ጉዳት ስለሚያስከትል ሊሆን ይችላል የተባለ ሲሆን፣ ሌላው ደግሞ ሲጋራ ማጤስ በሰውነታችን የሆርሞን ስርዓት ላይ ቋሚ ጉዳት ሊያስከትል መቻሉ ነው። ሲጃራ ማጤስ የሳንባ ካንሰርን እንደሚያመጣ የተረጋገጠው እኤአ በ1950ዎቹ ሲሆን ከዚያ በኋላ በተደረጉ ምርምሮች አጢያሾች የሚደረግላቸው ሕክምና ውጤታማ እንዳይሆን እንደሚያደርግም ተረጋግጧል። አጢያሾች በካንሰር፣ በልብ፣ በመተንፈሻ አካል፣ የመስማትም ሆነ የስኳር ሕምም ቢገጥማቸው ታክመው ለመዳን ከፍተኛ ችግር ይገጥማቸዋል። አጫሾች የቀዶ ጥገና ህክምና ከተደረገላቸውም በኋላ ለማገገም ከፍተኛ ጊዜ ይፈጅባቸዋል።
news-50149459
https://www.bbc.com/amharic/news-50149459
ፌስቡክ ሐሰተኛ ዜናዎችን መለየት ሊጀምር ነው
ፌስቡክ የሚሠራጩ ሐሰተኛ መረጃዎችን ለመከላከል ያለመ አዲስ ስልት ሊተገብር መሆኑን አስታወቀ።
አንጋፋው የማህበራዊ ሚዲያ መድረክ የሆነው ፌስቡክ፤ በመግለጫው ላይ እንዳለው በፌስቡክና በኢንስታግራም ላይ የሚሠራጩ ሐሰተኛ ዜናዎችን ሦስተኛ ወገንን በመጠቀም ጥሬ ሐቁን ሊያጠራ እንደሆነ ገልጿል። ፌስቡክ በቅርቡ ጥሬ ሐቅ አረጋጋጭ ፕሮግራሙን ከሰሃራ በታች ባሉ 10 አገራት ያስፋፋ ሲሆን እነዚህም ኢትዮጵያ፣ ዛምቢያ፣ ሶማሊያ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ አይቮሪ ኮስት፣ ጊኒ እና ጋና ናቸው። • ጠብ አጫሪና ጥቃት አድራሽ የፌስቡክ ፖስቶችን እንዴት ሪፖርት ማድረግ ይቻላል? • የዋትስአፕ መልዕክትዎን የሚያጣምመው መተግበሪያ የአፍሪካ ፖሊሲ ዋና ኃላፊ ኮጆ ቦክይ እንዳሉት ፕሮግራሙ እንደ አፍሪካ ቼክ፣ ፔሳ ቼክ፣ ዱባዋ፣ ፍራንስ 24 እና ኤ ኤፍ ፒ ፋክት ቼክ ካሉ አጋር ድርጅቶቻቸው ጋር በጋራ በመሆን ይተገበራል። እነዚህ ድርጅቶች በፌስቡክ ላይ የሚሠራጩ ሐሰተኛ መረጃዎችን ለመቆጣጠር በጨረታው ተሳትፈዋል። "በፌስቡክ ላይ የሚሠራጩ ሐሰተኛ መረጃዎችን መዋጋት ትኩረት የምንሰጠው ጉዳይ ነው። ሐሰተኛ ዜና ምን ያህል ችግር እንደሆነ እናውቃለን፤ በመሆኑም ችግሩን ለመፍታት እነዚህ እርምጃዎች ወሳኝ ናቸው" ብለዋል ኃላፊው። ኮጆ ቦክይ አክለውም ሦስተኛ ወገን ጥሬ ሐቅ አረጋጋጭ ብቻውን ለችግሩ መፍትሔ ባይሆንም፤ ሰዎች ፌስቡክ ላይ የሚያዩዋቸውን መረጃዎች ጥራት ለማሻሻል ከሚያከናውኗቸው በርካታ ተግባራት መካከል ይህ አንዱ ነው። "በርካታ ሥራዎችን አከናውነናል፤ አሁንም ፌስቡክ የበርካታ ሃሳቦች መንሸራሸሪያ እንዲሆን ለማረጋጋጥ እንጂ የሀሰተኛ መረጃዎች መናሃሪያ እንዲሆን አንፈልግም" ብለዋል።።
news-49329882
https://www.bbc.com/amharic/news-49329882
ቫኑዋቱ፡ አንድም ሴት የፓርላማ አባል የሌላት ሃገር
ቫኑዋቱ ስለምትባል ሃገር ሰምተው ያውቃሉ? ቫኑዋቱ በዜናዎች ላይ ብዙም ባትነሳም አሁን ግን አንዲትም ሴት አባል በፓርላማዋ ውስጥ ባለመኖሯ መነጋገሪያ ሆናለች።
ያስሚን ቫኑዋቱ በደቡባዊ ፓሲፊክ ውቅያኖስ 1300 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ያሉ 80 ደሴቶችን የያዘች ሃገር ስትሆን ፓርላማዋም 52 አባላት ያሉት ሲሆን ሁሉም እንደራሴዎች ግን ወንዶች ናቸው። • ለሴቶች የተከለከለ ተራራን የወጣችው የመጀመሪያ ሴት • የፓርላማ አባሉ ሴት ባልደረባቸውን በመምታታቸው ተያዙ በዚህም ሳቢያ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ከፍተኛ እንደሆነ በመጥቀስ በሕግ አውጪው ምክር ቤት ሴቶች እንዲወከሉና የሴቶች እኩልነት ጉዳይ ትኩረት እንዲያገኝ ጥረት የምታደርገው ያስሚን ትናገራለች። ለነገሩ ወንዶች ብቻ የሚሳተፉበት ፓርላማ ያላት ቫኑዋቱ ብቻ ሳትሆን በዓለማችን ሌሎች ሁለት ሃገራትም በምክር ቤታቸው ውስጥ አንዲትም ሴት በአባልነት አትገኝም። በአጋጣሚ በፓርላማቸው ውስጥ ሴት የምክር ቤት አባላት የሌላቸው ሃገራት ቫኑዋቱን ጨምሮ ሦስቱም በፓሲፊክ ውቅያኖስ ላይ ያሉ ደሴቶች ናቸው። ሁለቱ ሃገራትም ማክሮኔዢያና ፓፑዋ ኒው ጊኒ ናቸው። "ለሴቶች ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮችና ጉዳዮች በሃገሪቱ ከፍተኛ የሕግ አውጪ አካል ውስጥ ውክልና የላቸውም" ስትል ያስሚን ትናገራለች። የቀድሞዋ ፓርላማ አባል ሄልዳ ሊኒ በሃገሪቱ ያሉ ምክር ቤቶች ሁሉም ወንዶች በሆኑ የአካባቢ አለቆች የሚመራ ሲሆን ለፓርላማ አባልነት በእጩነት የሚቀርቡትን የሚጠቁሙትም እነሱው ናቸው። "በሃገሪቱ ውስጥ ያሉት ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚመሩት በወንዶች ነው። እጩዎችን እራሳቸው ይጠቁማሉ፤ የሚወዳደሩት እነሱው ስለሆኑ እነሱው ይመረጣሉ። በዚህም ፓርላማው ሙሉ ለሙሉ በወንዶች ይያዛል" ሲሉ የመጀመሪያዋ የቫኑዋቱ ሴት የቀድሞ የፓርላማ ሊኒ አባል ይናገራሉ። የቀድሞዋ የፓርላማ አባል አክለውም በሕግ አውጪው ምክር ቤት ውስጥ የሴቶች አለመኖር በሃገሪቱ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖን እያስከተለ መሆኑን ይናገራሉ። ለዚህም በቤት ውስጥ በሴቶች ላይ የሚፈጸምን ጥቃት የሚመለከተውና እስካሁንም በአግባቡ ተግባር ላይ አልዋለም የሚሉትን የቤተሰብ ጥበቃ ሕግ ለማውጣት ዘጠኝ ዓመታትን እንደፈጀ በምሳሌነት ያነሳሉ። በአሁኑ ጊዜ በቫኑዋቱ የሚገኙ ሴቶች በፆታዎች መካከል ያለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አለመመጣጠን እንዲያበቃ ለማድረግ ጥረት እያደረጉ ነው። ከሐይማኖታዊ አስተምህሮ አንጻር የወንዶች የበላይነት በስፋት በሚታይባት ቫኑዋቱ፤ ወንዶች ሴቶች ለፍተው ያገኙትን ገንዘብ የመውሰድና የማስተዳደር ሁኔታ የተለመደና በስፋት የሚታይ ነገር መሆኑን የቢቢሲ ዘጋቢ ተመልክቷል። • ልጃቸውን ወደ ፓርላማ ይዘው የመጡት አባል ከምክር ቤቱ ተባረሩ አብዛኛው ሕዝቧ በድህነት ውስጥ የሚኖርባት ይህች ሃገር ዕድገትን ለማምጣት የምትፈልግ ከሆነ በፆታዎች መካከል ያለውን የሰፋ ልዩነት መፍትሄ ልታበጅለት እንደሚገባ የዓለም ባንክ መክረዋል። 275 ሺህ ያህል ብቻ ሕዝብ ባላት ቫኑዋቱ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችና ወንጀሎች ከፍተኛ እንደሆነ ይነገራል። "ከሦስት ሴቶች አንዷ አስራ አምስት ዓመት ከመድረሷ በፊት አንድ አይነት ወሲባዊ ጥቃት ይፈጸምባታል" ትላለች ያስሚን። ያስሚን አክላም በእስር ላይ ከሚገኙ ታራሚዎች 60 በመቶ የሚደርሱት ወሲባዊ ወንጀል የፈጸሙ ሲሆኑ፤ 90 በመቶው በሴቶች ላይ የሚያጋጥሙ ጥቃቶች በሚያውቋቸው ሰዎች አማካይነት እንደሚፈፀሙ ትናገራለች። የሴቶች ብቻ ፓርቲ የመሰረቱት ሴት ፖለቲከኞች በቫኑዋቱ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ተጽዕኖዎችን ለማስቀረት የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ነው። በፖለቲካው መስክ ያለውን የወንዶች የበላይነት ለመለወጥ በእድሜ ጠና ያሉ ሴቶች ተሰባስበው ሴቶች ብቻ አባል የሆኑበት ፓርቲ መስርተዋል። በቀድሞዋ የፓርላማ አባል ሄልዳ ሊኒ የሚመራው ይህ ፓርቲ በቀጣዩ ዓመት በሚካሄደው ብሔራዊ ምርጫ ላይ ሴቶች እንደሚሳተፉ ያሳወቁ ሲሆን ከሃገሪቱ ፓርላማ መቀመጫዎች ግማሹ ለሴቶች ብቻ እንዲደረግ ቅስቀሳ እያደረጉ ናቸው። በዓለም ላይ በፓርላማቸው ውስጥ ከግማሽ በላይ ሴት እንደራሴዎች ያሏቸው ሃገራት ሦስት ብቻ ናቸው። እነሱም አፍሪካዊቷ ሩዋንዳ 61 በመቶ ሴት የፓርላማ አባላትን በመያዝ ከዓለም ቀዳሚ ስትሆን፤ ኩባ በ53.2 በመቶ ሁለተኛ ቦሊቪያ በ53.1 በመቶ ሦስተኛ ናቸው።
news-54175925
https://www.bbc.com/amharic/news-54175925
የመቀለ ዩኒቨርስቲ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት ፕሮፌሰር ፈቴን ማን ናቸው?
በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ፕሮፌሰር ፈቴን አባይ የመቀለ ዩኒቨርስቲ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ሆነው መሾማቸው ተሰምቷል።
ፕሮፌሰሯ ይህንን ኃላፊነት የተቀበሉት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሕይወት የኃላፊነት ጊዜያቸው አብቅቶ መነሳታቸውን ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል። ፕሮፌሰር ፈቲን በዚህ ዩኒቨርስቲ ይህንን ኃላፊነት ሲያገኙ የመጀመሪያዋ ሴት ናቸው። ፕሮፌሰሯ አብረዋቸው በሚሰሩ እና በሚያውቋቸው ዘንድ በርካታ ምርምሮችን በመስራት በስፋት የሚታወቁ ምሁር መሆናቸው ይገለፃል። ለመሆኑ ፕሮፌሰሯ ማን ናቸው? ፕሮፌሰር ፈቴን የተወለዱት ከመቀለ 45 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ውቅሮ ከተማ ነው። የፕሮፌሰሯ ቤተሰቦች 12 ልጆች ያፈሩ ሲሆን እርሳቸውም ለቤተሰቡ የመጨረሻ ልጅ ናቸው። ፕሬፌሰር ፈቴን ገና የ12 ዓመት ልጅ ሳሉ ሦስት ጉልቻ እንዲመሰርቱ ታስቦ እንደነበር የሚያስታውሱት ፈቴን፤ ለትዳር የታጨላቸው ግለሰብ ደግሞ በእድሜ በሦስት እጥፍ የሚበልጣቸው እንደነበረ ይናገራሉ። ፕሮፌሰር ፈቴንን ከእዚህ በርካታ ኢትዮጵያውያን ታዳጊ ሴቶች ከሚገጥማቸው ካለ እድሜ የመዳር አጋጣሚ ያዳኗቸው እናታቸው መሆናቸውን ይናገራሉ። ከዚህ በኋላ ነበር ነበር ወደ ትምህርት ቤት ገብተው የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአጥጋቢ ሁኔታ ተከታተሉ። ከዚያም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ወስደው ለኮሌጅ መግቢያ የሚያበቃ ውጤት በማግኘታቸው በሐዋሳ የግብርና ኮሌጅ የእጽዋት ሳይንስ አጥንተው በዲፕሎማ ተመርቀዋል። ትምህርታቸውን ካተናቀቁ በኋላም ከአስር ዓመታት በላይ በገጠራማ የኦሮሚያ እና የአማራ ክልል አካባቢዎች በመሰመራት በሙያቸው ተሰርተው አገልግለዋል። ፕሮፌሰር ፈቴን ተመርቀው ወደ ሥራ ከገቡበት ጊዜ አንስቶ ከአርሶ አደሮች ጋር ውጤታማ የሆኑ ሥራዎች በመስራት የሚታወቁ ሲሆን፤ ለዚህም ሥራቸው ከማኅበረሰቡም ሆነ ከተለያዩ የመንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ አካላት እውቅናን አግኝተዋል። በተለይ የምዕራብ ሐረርጌ አርሶ አደሮች ፕሮፌሰሯ በአካባቢው በሚሰሩበት ወቅት በጥረታቸው የውሃ ምንጭ እንዲያገኙ በማድረጋቸው ለክብራቸው ሲሉ በስማቸው እንደሰየሙት ይጠቀሳል። ከዚህ ጎን ለጎን በሐረማያ ዩኒቨርስቲ የዲግሪ ፕሮግራም የመማር እድል አግኝተው ትምህርታቸውን በመቀጠል በ1991 ተመርቀዋል። የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ካገኙ በኋላም በእርሻ ምርምር ኢንስቲትዩት ተመራማሪ በመሆን ሰርተዋል። ከሁለት ዓመት በኋላ በ1993 ዓ.ም በመቀለ ዩኒቨርስቲ የምርምር እና የማስተማር ሥራቸውን ቀጠሉ። ፕሮፌሰር ፈቴን በመቀጠልም ወደ እንግሊዝ በመጓዝ ትምህርታቸውን የቀጠሉ ሲሆን፤ እዚያም በገጠር የተፈጥሮ ሀብት አስተዳደር ሁለተኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል። ረዘም ላለ ጊዜ በመቀለ ዩኒቨርስቲ በመማርና ማስተማር እንዲሁም ጥናት በመስራት ቆይተው በ2007 የዶክትሬት ዲግሪ ለማግኘት የሚያስችላቸውን ትምህርት ለመከታተል ወደ ኖርዌይ አቅንተው በዘርና እጽዋት ሳይንስ ሦስተኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል። ፕሮፌሰሯ በትግራይ ከተለያዩ አርሶ አደሮች ጋር በጋራ በመስራት የተለያዩ ሰብሎችን ዘር የማሻሻል ሥራዎችን አከናውነዋል። በተጨማሪም የእርሻ ልማትን በማሳደግ ላይ ያተኮሩ ከ45 በላይ የምርምር ጽሁፎች በማዘጋጀት በዓለም አቀፍ ጆርናሎች ላይ አሳትመዋል። በ2015 ደግሞ በኢትዮጵያ በዘር ማዳቀል ምርምር ላይ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሮፌሰር ለመሆን ችለዋል። እንዲሁም በአትክልትና እጽዋት ላይ ለሚደረጉ ምርምሮች በአገር አፍ ደረጃ ሦስተኛዋ ፕሮፌሰር ናቸው። ፕሮፌሰር ፈቴን በኢትዮጵያ ውሃና የአፈር ጥበቃ እንዲሁም የዘር አያያዝን በሚመለከት ከአርሶ አደሮች ጋር አብሮ ሲሰሩ የአርሶ አደሮቹን ነባር እውቀት በመጠቀም ከሳይንስ ጋር በማስተሳሰር ሲሰሩ እንደቆዩ ይናገራሉ። በዚህም መስክ ለአምስት ዓመታት ያህል ሲሰሩ እና ግንዛቤ የማስጨበት ሥራ ሲያከናውኑ ቆይተው ወደ ዘር ማዳቀል ምርምር ተሸጋግረዋል። እንደ ፕሮፌሰር ፈቴን ከሆነ ይህንን የምርምር ሥራ የሚሰሩት በአርሶ አደሮች በራሳቸው ምርጫና ውሳኔ መሰረት ነው። ከዚህ በመነሳት ከ19997 እስከ 2001 በኔዘርላንድ መንግሥት ድጋፍ የተደረገለትን የውሃና የአፈር ጥበቃ ጥናት ፕሮጀክትን አስተባብረዋል። ይህ የዓለም አቀፍ ፕሮግራም በሰባት የአፍሪካ አገሮች የሚሰራ ሲሆን ፕሮፌሰሯ የዚህን ፕሮጀክት በትግራይ ሲያስተባብሩ ቆይተዋል። ፕሮፌሰሯ በዚህ ፕሮጀክት ሴቶች በእርሻና በተፈጥሮ ሀብት አስተዳደር ያላቸው ሚና እንዲጎላ ማድረጋቸውን ይናገራሉ። ይህ ፕሮጀክት በአሁኑ ጊዜ በአገር አቀፍ ደረጃ አድጎ እየተሰራበት ሲሆን፤ በ18 የአፍሪካ አገሮች፣ በእስያና በላቲን አሜሪካ አገራት የሚገኙ መንግሥታዊ ከሆኑና ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባበር እየተሰራ ነው። ፕሮፌሰር ፈቴን ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ ደግሞ የሥነ ምህዳር ሥርዓተ ጾታ ልማት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ሆነው የ'ድራይ ላንድ አግሪካልቸር' መጽሔትም ተባባሪ ኤዲተር ነች። ፈጠራና ሽልማት ፕሮፌሰር ፈቴን የገብስ ዝርያ በማዳቀል በሰሯቸው ምርምሮች ሽልማት አግኝተዋል። የአየር ለውጥ እና ድርቅን የሚቋቋም፣ ከፍተኛ ጣዕም ያለው ሦስት አይነት የገብስ ዝርያ ማዳቀላቸውን ይታወቃል። እነዚህ የገብስ ዝርያዎች በአንድ ሄክታር ከ4.5 እስከ 5.2 ቶን ምርት ሊሰጡ የሚችሉ ሆነው፣ ከሌሎች ዝርያዎች በበለጠ ከስልሳ በመቶ በላይ የምርታማነት ጭማሬ አላቸው ተብሏል። በዚህ የምርምር ሥራም ከ30 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሲደረግ፣ ከ500 ሄክታር በላይ የሸፈነ ዝርያ ነበር። እነዚህ የገብስ ዝርያዎች ፈላሚት፣ ህሪት፣ ፈቴን የሚል ስያሜ በዩኒቨርስቲው ተሰይሞላቸዋል፟። ፕሮፌሰር ፈቴን በ2009 የሴት ባለሙያ ከአምስት የአፍሪካ ተመራማሪ ሴቶች አንዷ ሆነው በአዝርዕት ምርምር ተሸልመዋል። የኢትዮጵያ መንግሥትም በ2010 ሳይንስን ከአርሶ አደሮች ጋር ለማስተሳሰር ባደረጉት ጥረት ሸልሟቸዋል። በተጨማሪ የአፍሪካ ሕብረት በሳይንስ ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋፍኦ የኩዋሜ ንክሩማህ ሽልማት የምሥራቅ አፍሪካ ሎሬት በመባል አሸናፊ ሆነዋል።
news-55174932
https://www.bbc.com/amharic/news-55174932
"ጦርነት የለም፤ ህወሓት ጦርነት ለማድረግ የሚያስችል ወታደራዊ ቁመና የለውም" አቶ ዛዲግ አብርሃ
በአሁኑ ጊዜ ትግራይ ውስጥ የሚካሄድ ጦርነት እንደሌለና እየተደረገ ያለው የህወሓት አመራሮችን በማደን በቁጥጥር ስር የማዋል እርምጃ እንደሆነ አቶ ዛዲግ አብረሃ ገለጹ።
የዲሞክራሲ ግንባታ ሚንስትሩ አቶ ዛዲግ አብርሃ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በክልሉ የተካሄደው ጦርነት ማብቃቱን ጠቁመው በዚህ ወቅት "ጦርነት የሚባል ነገር የለም። አሁን ጥቂት የሚባሉ የአሸባሪ ቡድን አባላትን እየተከታተሉ መያዝ ነው የቀረው" ሲሉ ገልጸዋል። መንግሥት ሕግ የማስከበር ያለው ዘመቻ የፌደራል መከላከያ ሠራዊት የክልሉን ዋና ከተማ መቀለን መቆጣጠሩን ተከትሎ ማብቃቱን ነገ ቅዳሜ አንድ ሳምንት የሚሞላው ሲሆን በመንግሥት ኃይሎች እየተፈለጉ ያሉት የህወሓት አመራሮች ግን ፍልሚያ ላይ እንደሆኑ እየተናገሩ ነው። ቀደም ሲል የህወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል እንደሁም የቡድኑ ከፍተኛ አመራር አባል አቶ ጌታቸው ረዳ ደግሞ ትናንት ለትግራይ ቴሌቭዥን እንደገለጹት "ጦርነቱ አልተገባደደም። አይገባደድምም" ብለዋል። ነገር ግን ሚኒስትሩ አቶ ዛዲግ አብረሃ እየተካሄደ ያለው ተፈላጊዎችን የመያዝ ተግባር መሆኑን አመልክተው፤ በአሁኑ ወቅት "ህወሓት ጦርነት ማድረግ የሚያስችል ወታደራዊ ቁመና የለውም። ወታደር የለውም። ትልልቅ መሣሪያዎች የሉትም። የሕዝብ ድጋፍም የለውም" ብለዋል። ከሳምንት በፊት በተደረጉ ውጊያዎች ዋና ዋና የትግራይ ከተሞች በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት እጅ ውስጥ ከገቡ በኋላ የህወሓት አመራር መቀለን ጥሎ ቢወጣም ጦርነቱን እንደሚገፋበት ማስታወቁ ይታወሳል። አቶ ጌታቸው ረዳም ሠራዊቱ መቀለን መቆጣጠሩን አረጋግጠው የሚቀር ነገር እንዳለ "መቀለ ገብተዋል። መቀለን ተቆጣጠሩ ማለት ግን አይደለም። መቀለን መቆጣጠር የሕዝብን መንፈስና ልቦና መግዛት ይጠይቃል" ሲሉም ተደምጠዋል። የመቀለ ከተማን ለመያዝ በተካሄደ ዘመቻ ወቅት ከተዋጊዎች ውጪ ባሉ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የሚያመለክቱ መረጃዎች እየወጡ መሆናቸውን በመጥቀስ፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት "አንድም ሰላማዊ ሰው አልተጎዳም" ማለታቸውን በተመለከተ ቢቢሲ አቶ ዛዲግ አብረሃን ጠይቆ ነበር። በሰጡትም ምላሽ ጠቅላይ ሚንስትሩ እተካሄደ ስለነበረው ዘመቻ ትክክለኛ መረጃ እንዳላቸውና የአገሪቱ ሠራዊትና የጸጥታ አካላት በክልሉ ውስጥ በቅንጅት እንደሚሰሩ ጠቁመው "የሕግ ማስከበር ዘመቻው ስትራቴጂ ሲወጣ አንድም ስህተት ላለመሥራት ለይቶ በማትቃት [በሰርጂካል ኦፕሬሽን] ላይ የተመሠረተ ነው። ስለዚህ በእኛ በኩል የሲቪል ጉዳትን ሙሉ በሙሉ አስወግደናል" ብለዋል። በመንግሥት በኩል በዚህ ዘመቻ ትግራይ ውስጥ ያለው ሕዝብ እንዲጎዳ እንዳልተፈለገ ጠቅሰው ለዚህም አስፈላጊው ጥንቃቄ እንደተደረገ ተናግረዋል። "ጸቡም የሕግ ማስከበር ዘመቻውም በህወሓት ላይ እንጂ በሕዝብ ላይ የሚካሄድ አይደለም" ሲሉም አክለዋል። አቶ ዛዲግ በተጨማሪም፤ "በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት አልደረሰም ስንል በእኛ በኩል እንጂ በእነሱ [በህወሓት] በኩል ማለታችን አይደለም። ሰላማዊ ሰዎችን እንደ ከለላ [ጋሻ] በመጠቀም ሕይወታቸውን ለማቆየት ሞክረዋል። በዚያ ምክንያት የመጣ ጉዳት ሊሆን ይችላል" ሲሉም ተናግረዋል። ከዚህ አንጻር በሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሰ ጉዳትን በተመለከተ መረጃ እንደሌላቸው የተናገሩት ሚኒስትሩ፤ ዋና ከተማዋ መቀለ በአሁኑ ጊዜ እየተረጋጋች በመምጣቷ በቀጣይ መረጃ ሊያገኙ እንደሚችሉም ጠቁመዋል። የህወሓት አመራሮች ግን በዘመቻው ሂደት ከተዋጊዎች ውጪ ባሉ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን በመግለጽ በተደጋጋሚ መንግሥትን ሲከሱ ቆይተዋል። በትግራይ ክልል ግጭቱ ከተቀሰቀሰበት ዕለት አንስቶ የስልክ እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ በመቆየቱ በክልሉ ውስጥ ስላለው ሁኔታ ከገለልተኛ ወገን ለማረጋገጥ አልተቻለም። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ትግራይ ውስጥ ይሠሩ የነበሩ አራት የበጎ አድራጎት ሠራተኞች በግጭቱ ወቅት መገደላቸው ተዘግቧል። ሮይተርስ የዜና ወኪል የዲፕሎማቲክና የሰብአዊ እርዳታ ድርጅት ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ በሁለት የተለያዩ የውጪ የተራድኦ ድርጅቶች ተቀጥረው ይሠሩ የነበሩ አራት ኢትዮጵያውያን የሰብአዊ እርዳታ ሠራተኞች በኢትዮጵያና በኤርትራ ድንበር አቅራቢያ ተገድለዋል። ስለዚህ ጉዳዩ የሚያውቁት ነገር እንዳለ በቢቢሲ የተጠየቁት አቶ ዛዲግ አብረሃ ፤ "አሁን ስለዚህ ጉዳይ የማውቀው ነገር የለም። ገና መረጃው እየተጠራ ነው ያለው። የስልክ አገልግሎትን እየመለስን፣ መንገዶችን እያስተካከልን ነው ያለነው" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። በትግራይ ክልል ውስጥ የተካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ መጠናቀቁ ከተገለጸ በኋላ መንግሥት መረጋጋት ማስፈን፣ የተጎዱ መሰረተ ልማቶችን መልሶ መገንባትና የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው በመመለስ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ እንዲቋቋሙ ማድረግ ዋነኛ ትኩረቱ ማድረጉን ገልጿል። በፌደራል መንግሥቱና የትግራይ ክልልን ሲያስተዳድር በነበረው ህወሓት መካከል ለወራት የቆየው ውዝግብ ባለፈው ዓመት ሊካሄድ የነበረው አገራዊ ምርጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽን ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ መሸጋገሩን ተከትሎ በከፍተኛ ሁኔታ መካረሩ ይታወሳል። ይህንን የፌደራል መንግሥቱን ውሳኔ ባለመቀበል በትግራይ ክልል የተካሄደው የተናጠል ምርጫ የፌደራል መንግሥቱን ተቀባይነት ካለማግኘቱ በተጨማሪ በአገሪቱ ምክር ቤቶች ሕገ ወጥ ተብሎ ውድቅ ተደርጓል። የክልሉ ባለስልጣናትም በበኩላቸው ፌደራል መንግሥቱ በኮቪድ ሰበብ ምርጫን ማራዘሙ "ሕገመንግስቱ ከሚፈቅደው ውጭ ነው ስልጣኑን አራዝሟል" በማለት የፌደራሉን መንግሥት "ሕገወጥ" ብለው እውቅና መንፈጋቸው አይዘነጋም። የፌዴሬሽን ምክር ቤትም የክልሉን አስተዳዳሪዎች ሕገ መንግሥቱን በመጣስና ከሕግ ውጪ ተንቀሳቅሰዋል በማለት የፌደራል መንግሥቱ ከትግራይ ክልል ክልል አስተዳደር ጋር የነበረውን የቀጥታ ግንኙነት አቋርጦ የበጀት ዕቀባ ጥሎ ነበር። አለመግባባቱና መካሰሱ ያለማቋረጥ በቀጠለበት ሁኔታ ጥቅም 24/2013 ዓ.ም ምሽት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በትግራይ ክልል በነበሩት የሠሜን ዕዝ አባላት ላይ በህወሓት ኃይሎች ጥቃት መፈጸሙን ይፋ ካደረጉ በኋላ የፌደራሉ ሠራዊት በህወሓት ኃይሎች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩ ይታወሳል። ባለፈው ቅዳሜ የክልሉ ዋና ከተማ መቀለ በፌደራል መንግሥት ሠራዊት ቁጥጥር ሰር ከዋለች በኋላ ወታደራዊ ዘመቻው መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አሳውቀዋል።
news-56855691
https://www.bbc.com/amharic/news-56855691
የአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሥልጣናቸውን ማራዘማቸውን ተቃወመ
የአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፎርማጆ የሥልጣን ዘመናቸውን ማራዘማቸውን ተቃወመ።
ሕብረቱ ልዩ መልዕክተኛ ወደ ሞጋዲሾ በመላክ የፖለቲካ ውጥንቅጡን ለመፍትታ እንደሚሞክርም አስታውቋል። የአፍሪካ ሕብረት ሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት ለሰዓታት ዝግ ስብሰባ ካካሄደ በኋላ ነው የሶማሊያን ፖለቲካዊ ችግር እፈታለሁ ያለው። ሐሙስ ዕለት ከተካሄደው ስብሰባ በኋላ የተለቀቀው መግለጫ ሁሉም በአገሪቱ ውስጥ ያሉ ፓርቲዎች በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲመክሩ አሳስቧል። ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት መስከረም የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥትና ክልላዊ አስተዳደሮች እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች መክረው ነበር። በዚህ ውይይት ወቅት በሶማሊያ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ እንዲደረግ ተስሰማምተው ነበር። ነገር ግን ባለፈው ሳምንት ፕሬዝደንት ፎርማጆ የሥልጣን ዘመናቸውን እንዲራዘም የሚያትት ረቂቅ አፅድቀዋል። የፕሬዝደንቱ አወዛጋቢ ውሳኔ ከብዙዎች ዘንድ ተቃውሞ እንዲገጥማቸው አድርጓል። ዩናይትድ ስቴትስ፣ ብሪታኒያ፣ የተባበሩት መንግሥታትና የአውሮፓ ሕብረት የፕሬዝደንቱን እርምጃ ከተቃወሙ መካከል ናቸው። "የመስከረም 2020 ስምምነት ለወደፊቱ ሶማሊያ አዋጭ የሆነ ዕቅድ ይዟል። ይህም ተዓማናኒ ነፃ ምርጫ ማድረግ ነው" ይላል ሕብረቱ የለቀቀው መግለጫ። የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት የሶማሊያ ፖለቲካዊ አመራሮች ነገሮች የበለጠ የሚያከሩ ድርጊቶች ከመፈፀም እንዲቆጠቡም አሳስቧል። ምክር ቤቱ ይህ ሆነ ማለት የሶማሊያ፣ የአፍሪካ ቀንድና የመላው አፍሪካ ሰላም ደፈረሰ ማለት ነው ሲል በመግለጫ አትቷል። የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት በዝግ ባካሄደው ስብሰባ በቻድ ስላለው ሁኔታም ቢመክርም ለጊዜው ምንም ዓይነት ውሳኔ ላይ አልደረሰም። የቻዱ ፕሬዝደንት ኢድሪስ ዴቢ ከታጣቂዎች ጋር በተደረገ ውጊያ ሕይወታቸው ማለፉን ይታወሳል። የአፍሪካ ሃገራት መሪዎች በዴቢ ቀብር ላይ ለመገኘት ወደ ቻድ እያመሩ ይገኛሉ።
news-50080906
https://www.bbc.com/amharic/news-50080906
ታንዛኒያ ያጋጠማትን የኮንዶም እጥረት ለመቅረፍ 30 ሚሊዮን ኮንዶሞች ከውጭ አስገባች
በታንዛኒያ ከወራት በፊት የኮንዶም እጥረት እንዳጋጠመ ከተነገረ በኋላ የጤና ጥበቃ ባለስልጣናት እጥረቱን ለማቃለል 30 ሚሊዮን ኮንዶሞችን ወደ አገሪቱ አስገቡ።
የቢቢሲ ዘጋቢ እንዳለው በርካታ ታንዛኒያዊያን በመንግሥት የሚሰራጨው የኮንዶም አቅርቦት እየቀነሰ በመምጣቱ የኮንዶም መግዣ ዋጋ ላይ እየታየ ያለው ጭማሪ አሳስቧቸዋል። ዋና ከተማና የቱሪስቶች መናኸሪያ በሆነችው ዳሬሰላም ውሰጥ ሚገኙ አንዳንድ የእንግዳ ማረፊያዎች እርግዝናንና በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመከላከል የሚያገለግለውን ኮንዶም ለደንበኞቻቸው ማቅረብ አቁመዋል። • ለአንዲት ታካሚ ብቻ የተሠራው መድሃኒት • እውን ድህነትን እየቀነስን ነው? • የመደፈሬን ታሪክ ከስልሳ ሰባት ዓመታት በኋላ የተናገርኩበት ምክንያት "አንዳንድ መደብሮች እንደ የኮንዶሞቹ አይነት ከአንድ እስከ ሦስት ዶላር በላይ ወጪን ስለሚጠይቁ፤ ይህን ያህል ወጪ አውጥተን ኮንዶም ማቅረብ ስለማንችል አሁን ደንበኞች ራሳቸው ይዘው መምጣት አለባቸው" ሲል አንድ የሆቴል ሰራተኛ ለቢቢሲ ተናግሯል። የታንዛኒያ ረዳት የጤና ሚኒስትር የሆኑት ዶክተር ፋውስቲን ንዱጉሊል እንደተናገሩት አሁን የሚፈለገው የኮንዶም መጠን ቀርቧል። "ከ30 ሚሊዮን በላይ ኮንዶሞች አዝዘናል። አሁን የተቀየረው ኮንዶሞቹ የሚሰራጩበት መንገድ ነው፤ ቀደም ባለው ጊዜ ኮንዶሞችን የሚያሰራጩ ተቋማት ነበሩ። አሁን ግን የማሰራጨቱን ኃላፊነት የተሰጣቸው አዳዲስ ተቋማት አሉን።" ያሉት ረዳት ሚኒስትሩ አክለውም "እኛ ማድረግ የፈለግነው አዲሱ አሰራራችን በተገቢው ሁኔታ መስራቱን ማረጋገጥ ነው። በተጨማሪም ግንዛቤ ለመፍጠር እያደረግነው ያለው ዘመቻ ትኩረት ወደ አደረግንባቸው ሰዎች ሲደርስ ኮንዶም እንደተፈለገው ማግኘት ይቻላል" ብለዋል።
news-50232431
https://www.bbc.com/amharic/news-50232431
የአል ሻባብ ታጣቂዎች በኬንያ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት ፈጸሙ
የሶማሊያው እስላማዊ ቡድን አል ሻባብ በሰሜን ምሥራቅ ኬንያ ውስጥ ዋጂር በተባለ አካባቢ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት መፈጸሙ ተዘገበ።
የእስላማዊው ቡድን ታጣቂዎች ዋጂር በሚባለው አካባቢ ደቡባዊ ክፍል በሚገኘው ዳዳጃቡላ ተብሎ በሚጠራው ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃቱን የፈጸሙት ዛሬ ረቡዕ ጠዋት ነው። ታጣቂዎቹ በፖሊስ ጣቢያው ላይ ጥቃቱን የፈጸሙት ከባድ መድፍና ላውቸር ጭምር ተጠቅመው እንደሆነ ተዘግቧል። • ሞቷል ተብሎ የነበረው የአል ሸባብ መሪ በህይወት እንዳለ ተነገረ • ወደ አዲስ አበባ ሊጓዝ የነበረው እስረኛ ጥቃት ደረሰበት አንድ የአካባቢው ባለስልጣን ስለጥቃቱ እንደተናገሩት እስላመዊ ቡድኑ ፖሊስ ጣቢያውን ኢላማ ያደረገው ሁለት አባላቱ በቁጥጥር ስር ሆነው ፖሊስ ጣቢያው ውስጥ በመገኘታቸው ነው። ጥቃቱን ተከትሎ በተካሄደው የተኩስ ልውውጥ ውስጥ በፖሊስ ጣቢያው ታስረው የነበሩት ሁለቱ የአል ሻባብ አባላት የተገደሉ ሲሆን ሁለት የፖሊስ አባላትና አንድ የአካባቢው ታጣቂ ላይ የመቁሰል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል።
48062521
https://www.bbc.com/amharic/48062521
በስሪ ላንካ በደረሰው ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር በ100 ቀነሰ
የስሪ ላንካ ጤና ጥበቃ መሥሪያ ቤት ኃላፊ ባለፈው እሁድ በደረሰው ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር በ100 የተጋነነ ነው ብለዋል።
ባለፈው እሁድ ነበር ስሪ ላንካውያን ሃገር ሰላም ብለው የፋሲካ በዓልን ሲያከብሩ የነበሩት። ነገር ግን በቀኝ አውለኝ ብለው የጀመሩት ቀን ጥቁር ለበሰ። በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች በደረሱ ጥቃቶች ምክንያት። በወቅቱ የሟቾች ቁጥር 290 ገደማ እንደደረሰ ተዘግቦ ነበር። ትንሽ ቆየት ብሎም ቁጥሩ ወደ 353 እንዳሻቀበ ተነገረ። አሁን ግን የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ በተፈጠረው ግርግር ምክንያት የሟቾችን ቁጥር በትክክል ማስላት ባለመቻሉ ነው ቁጥሩ የተጋነነው ሲሉ ተደምጠዋል። • የስሪላንካ ጥቃት፡ የሟቾች ቁጥር 290 ደርሷል አሉ በተባሉ ቅንጡ ሆቴሎችና በክርስትና ቤተ-እምነቶች ላይ በተፈፀመው ጥቃት በርካታ የሃገሪቱ ሰዎች እና የውጭ ሃገር ዜጎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ፖሊስ ጥቃቱን አድርሰዋል ያላቸውን ዘጠኝ ሰዎች አድኖ ለመያዝ ወዲያ ወዲህ እያለ እንደሆነ አስታውቋል። ባለሥልጣናት ጥቃቱን የሰነዘረው 'ናሽናል ቶውሂድ ጃማት' የተሰኘውን አክራሪ እስላማዊ ቡድን በሚል እየኮነኑት ይገኛሉ። አይኤስ የተሰኘው ቡድን በበኩሉ ከጥቃቱ ጀርባ ያለሁት እኔ ነኝ የሚል ተንቀሳቃሽ ምስል ቢለቅም ማስረጃ ግን ሊገኝ አልቻለም። የስሪ ላንካ መከላከያ ሚኒስትር ሐሙስ ዕለት በገዛ ፍቃዳቸው ራሳቸውን ከሥልጣን ማግለላቸው ሌላ ትልቅ ዜና ነበር። ምክንያታቸው ደግሞ የደህንነቱ ኃይሉ ጥቃቱን ማስቆም አለመቻሉ ነው። • ሴቶች ስለምን የአሸባሪ ቡድኖች አባል ይሆናሉ?
news-53025567
https://www.bbc.com/amharic/news-53025567
በሊባኖስ የኢኮኖሚ ቀውሱን ተከትሎ ተቃውሞዎች እየተባባሱ ነው
ሊባኖስ ያጋጠማትን የመገበያያ ገንዘቧ መድከምን ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተዋል፡፡
የሊባኖስ መገበያያ ገንዘብ ዋጋ በታሪኳ ዝቅተኛ ወደሚባል ደረጃ በመውረዱና 70 በመቶ የሚሆነውን አቅሙን በማጣቱ ከጥቅምት ወር ጀምሮ አገሪቷ ተቃውሞዎችን እያስተናገደች ነው፡፡ ቁጣዎችም ተባብሰዋል፡፡ የአገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስተርም የኢኮኖሚ ቀውስ ላይ ውይይት ለማድረግ አስቸኳይ የካቢኔ ስብሰባ ጠርተዋል፡፡ ተቃውሞዎቹ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ በተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ ሳቢያ ጋብ ብሎ የነበረ ቢሆንም በቅርቡ እንደገና ተጀምሯል፡፡ የሊባኖስ ፓውንድ ዋጋ መውደቅ አገሪቷን በአስርት ዓመታት ውስጥ አስከፊ ወደ ሆነ የኢኮኖሚ ቀውስ ከቷታል፡፡ በጥሬ ገንዘብ ምንዛሬ ላይ የተሰማሩ አብዛኞቹ ሊባኖሳዊያንም ለድህነት ተዳርገዋል፡፡ በወረርሽኙ ወቅትም ችግራቸው ተባብሷል፡፡ በሊባኖሷ ከተማ ቤሩት የቢቢሲ ዘጋቢ ሊና ሲንጃብ እንደገለጸችው፤ ሐሙስ ዕለት ምሽት በከተማዋ እንብርት ላይ ተሰባስበው የነበሩ ተቃዋሚዎች እሳት በማቀጣጠል እና መንገዶችን በመዝጋት ቁጣቸውን ገልጸዋል፡፡ ምንም እንኳን የአኮኖሚ ቀውሱን ተከትሎ በመጀመሪያዎቹ ወራት በነበሩት ተቃውሞዎች ፖለቲካዊ ለውጥ ለመጠየቅ የተደረጉ ቢሆንም የአሁኑ ግን መነሻው ርሃብ ነው፡፡ በአገሪቷ የሥራ አጦች ቁጥር ከፍተኛ ሆኗል፡፡ አብዛኞቹ ሊባኖሳዊያንም ለሰሩበት የሚከፈላቸው ዋጋው በወደቀው የአገሪቷ ገንዘብ ነው፡፡ በመሆኑም ለአብዛኞቹ ቤተሰቦች ምግብና መሰረታዊ ፍላጎትን ማሟላት ፈታኝ ሆኗል፡፡ ከተቃዋሚዎቹ መካከል አንዷ "ሊባኖስ ሁል ጊዜ በተቃውሞ ውስጥ ነው ያለችው ፤ ይህ ማለት ጥረታችን እና ጩኸታችን ለውጥ ማምጣት አልቻለም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ በበለጠ ተቃውሞ ማሰማት አለብን" ብለዋል፡፡ ይሁን እንጅ አብዛኞቹ አሁን እየታየ ያለው ችግር እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ 1975 ሊባኖስ ወደ እርስ በርስ ጦርነት ቀድሞ የነበረውን ጊዜ እንደሚያስታውሳቸው እና ተቃውሞው በዚህ ሁኔታ እየቀጠለ ከሄደ ወዴት ሊያመራ እንደሚችል አሳስቧቸዋል፡፡ ሌላኛው ተቃዋሚም "ዛሬ የአንድ ዶላር ምንዛሬ 7ሺህ የሊባኖስ ፓውንድ ደርሷል፡፡ የቤት ኪራይ ለመክፈልም ሆነ ምግብ ለመመገብ አልቻልንም ፤ በመሆኑም የዶላር ምንዛሬው ዝቅ ካላላ በስተቀር እና ጥያቄዎቻችን ካልተመለሱ እዚሁ እንቆያለን ፤ ያገኘነው ጠቅላይ ሚኒስተርም ከዚህ ቀደም ከነበረው የባሰ ነው" ብለዋል፡፡ ከቤሩት ውጭ ያሉ በርካታ መንገዶች አሁንም እንደተዘጉ ናቸው፡፡ ከኮሮናቫይረስ ወረርሽን ቀድሞም ሌባኖስ በታሪኳ አጋጥሟት የማያውቅ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ገብታለች፡፡ ይህም ባለፈው ዓመት ጸረ መንግሥት ተቃውሞዎችን አስነስቷል፡፡ ምንም እንኳን የአገሪቷ መንግሥት የኮሮናቫይረስን ለመከላከል በሰጠው ምላሽ ቢመሰገንም ግማሽ የሚሆነው ሕዝብ የሚኖረው ከድህነት ወለል በታች ነው፡፡ የመገበያያ ገንዘብ ዋጋው መውደቅም የዋጋ ግሽበት በማስከተሉ የገቢ ንግድ ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል፡፡ በሺህዎች የሚቆጠሩ የንግድ ተቋማት ኪሳራ አጋጥሟቸዋል፡፡ አንድ ሦስተኛ የሚሆነው ህዝቧም ሥራ አጥ ሆኗል፡፡
51131137
https://www.bbc.com/amharic/51131137
የሩስያ መንግሥት ስራ ለቅቂያለሁ ብሏል። ምን ማለት ይሆን?
የሩስያ መንግሥት ሥራ ለቅቋል። ይህ የሆነው ደግሞ ፕሬዝደንት ፑቲን ሕገ-መንግሥታዊ ለውጥ ያሻል የሚል ሃሳብ ካቀረቡ በኋላ ነው። ለመሆኑ የዚህ ትርጉሙ ምንድነው?
ሕገ-መንግሥታዊ ለውጡ በሕዝበ-ውሳኔ አብላጫ ድምፅ ካገኘ ሩስያ ከፕሬዝደንታዊ የመንግሥት አስተዳደር ወደ ፓርላሜታሪያዊ ትቀየራለች ማለት ነው። ፕሬዝደንት ፑቲን በግሪጎሪያን አቆጣጠር 2024 ላይ ሥልጣን በቃኝ እንዲሉ ሕገ-መንግሥቱ ያዝዛል። ነገር ግን ለአራት የስልጣን ዘመናት ሩሲያን ያስተዳደሩት ፑቲን አዲስ መላ ይፈልጋሉ እንጂ ሥልጣን በቃኝ ይላሉ ተብሎ አይታሰብም ይላሉ ተንታኞች። ፑቲን በዓመታዊው ሃተታቸው ላይ ነው አዲሱን ዕቅዳቸውን ይፋ ያደረጉት። ከንግግራቸው በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ ፑቲን ያቀረቡት ሃሳብ እንዲፀድቅ በማሰብ የሩስያ መንግሥት ሥልጣን ለቅቋል ሲሉ ተደመጡ። «በጣም ያልጠበቅነው ነገር ነው የሆነው» ሲሉ አንድ ምንጭ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የፑቲን ሃሳብ ምንድነው? በዓመታዊው የላዕላይና ታህታይ ሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት መክፈቻ ላይ ንግግር ያሰሙት ፕሬዝዳንት ፑቲን፤ ከፕሬዝደንታዊ ወደ ፓርላሜንታዊ ስርዓት በሚደረግበት ሽግግር ላይ ሕዝበ-ውሳኔ እንደሚደረግ አሳውቀዋል። ይህ ማለት ፑቲን፤ ሩስያ ከፕሬዝደንታዊ አስተዳደር ልክ እንደ ኢትዮጵያ በፓርቲ ወደ ሚመረጥ ጠቅላይ ሚኒስቴርነት አስተዳደር እንደትሸጋገር ይሻሉ ማለት ነው። አሁን ባለው የአስተዳደር ሥርዓት በፕሬዝደንቱ የሚመረጡት ጠቅላይ ሚኒስትር የረባ ሥልጣን የላቸውም። ሌላኛው የፑቲን ሃሳብ 'ስቴት ካውንስል' የተሰኘው ምክር ቤት አቅም እንዲጎለብት ነው። ፑቲን የሚመሩት ይህ ምክር ቤት በክልል ኃላፊዎችን ያዋቀረ ነው። ፑቲን ካነሷቸው ሌሎች ሃሳቦች መካከል የዓለም አቀፍ ሕጎችን ጫና መቀነስ፣ የፕሬዝደንት ሥልጣን ላይ መቆያ ጊዜ እንዲራዘም ማድረግ፣ የሌላ ሃገር ዜግነት ወይም የሥራ ፈቃድ ያላቸው ፖለቲከኞች ጉዳይ ይገኙበታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሜድቬዴቭ የሩስያ መንግሥት ሥልጣን ለቅቋል ብለው ሲያውጁ ከአጠገባቸው ፕሬዝደንት ፑቲን ነበሩ። ማሻሻያው ያስፈለገው የሕግ አውጭውን፣ ተርጓሚውንና አስፈፃሚውን አሠራር ለመናጥ ነው ሲሉም ተደምጠዋል። ጠቅላይ ሚኒስትራቸውን ያመሰገኑት ፑቲን እሳቸው በሚመሩት የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት በምክትልነት እንዲያገለግሏቸው ጠይቀዋል። አክለውም የሩስያ ቀረጥ አግልግሎት መሥሪያ ቤት ኃላፊ ሚካይል ሚሹስቲን የሜድቬዴቭን ቦታ ተክተው እንዲሰሩ ሾመዋል። የሩስያ ሕገ-መንግሥት አንድ ፕሬዝድንት በተከታታይ ከሁለት ጊዜ በላይ እንዲያገለግል አይፈቅድም። ፑቲን ሁለት ጊዜ ካገለገሉ በኋላ ታማኝ አገልጋያቸው እንደሆኑ የሚነገርላቸው ሜድቬዴቭ ለአራት ዓመታት ፕሬዝደንት ሆነው አገልግለዋል። በወቅቱ ፑቲን ጠቅላይ ሚኒስትር ነበሩ፤ ሥልጣኑ የነበረው በእሳቸው እጅ ነው የሚሉ በርካቶች ቢሆኑም። ተቃዋሚዎች ፑቲን ያሰቡት ሕገ-መንግሥታዊ ማሻሻያ የሥልጣን ጊዜያቸው እያበቃ ስለሆነ ያዘጋጁት ድራማ እንጂ ለውጥ ታስቦ አይደለም ይላሉ። በፈረንጆቹ 1999 ላይ ፕሬዝደንት ቦሪስ የልቲስንን ተክተው ሥልጣን የያዙት ፑቲን በፕሬዝደንትነትና በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሃገራቸው ለ20 ዓመታት አገልግለዋል። መንበራቸውን እንዲሁ በቀላሉ ይለቃሉ ብሎ ማሰብ ዘበት ነው የሚሉ በርካቶች ናቸው።
55752214
https://www.bbc.com/amharic/55752214
ደቡብ አፍሪካና የዘር መድልዎ
እአአ በ2017 ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የተከሰተ ነው። ግለን ሲንማን የተባለ መምህር ሥራ ሲያመለክት የቀረበለት ሰነድ ላይ "አፍሪካዊ" የሚለው ሰንጠረዥ ውስጥ ራሱን አስቀመጠ።
መምህሩ ከሦስት ወራት በፊት በማጭበርበር ተከሷል። ግለን የተወለደው ከጥቁርና ነጭ ቤተሰብ ነው። የተመሠረተበት ክስ ቢነሳለትም፤ በአገሪቱ ያለው የዘር ክፍፍል ላይ ጥያቄ ያጫረ ክስተት ነው። አፓርታይድ የዘር ልዩነትን መሠረት ያደረገ መድልዎን አስፋፍቷል። በ1950ዎቹ የወጣ ፖሊሲ ነጭ፣ አፍሪካዊ፣ ክልስ እና ሕንዳዊ በሚል አገሪቱን ለአራት ከፍሏል። በ1991 ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ሲመረጥ ይህ ፖሊሲ ቢሻርም ዘርን መሠረት ያደረገ ክፍፍል አሁንም ተወግዷል ማለት አይቻልም። መንግሥት የምጣኔ ሀብት ልዩነትን ሲቃኝ ይህንን ክፍፍል ተመርኩዞ ነው። ግለን 2010 ላይ ዘርን መሠረት ያደረገ ክፍፍል መኖር የለበትም ብለው ማኅበር ካቋቋሙ አንዱ ነው። "በዘር ሰዎችን የሚከፋፍለው ፓሊሲ ተሰርዟል። በመንግሥት ወይም በግል የሥራ ቅጥር ላይ ሰፊ እድልም ይሰጣል" ሲል ለአገሪቱ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ደብዳቤ ጽፏል። "መደብ ላይ እናተኩር" መምህሩ እንደሚለው መንግሥት ለመደብ ልዩነት ትኩረት መስጠት አለበት። "መንግሥት የዘር ሀረጋችን ላይ ሳይሆን ምን አይነት ሥራና አገልግሎት እንደምንፈልግ ለማወቅ መሞከር አለበት" ይላል። ማንነትን መሠረት ያደረገ መድልዎ ተወግዶ እኩል እድል እንዲፈጠር ይሻል። የቀድሞ የጋዜጣ አርታኢ ራይልድ ፊሸር "ለመደብ ቅድሚያ ከሰጠን የበርካታ ጥቁሮችን ሕይወት መለወጥ እንችላለን" ይላል። ደቡብ አፍሪካ ውስጥ አብላጫውን ቁጥር የያዙት ጥቁሮች ቢሆኑም በድህነት የሚኖሩትም ጥቁሮች እንደሆኑ ያጣቅሳል። በ1970ዎቹ የጸረ አፓርታይድ ትግል ሲፋፋም ከመብት ተሟጋቹ ስቲቭ ቢኮና የተማሪዎች ሕብረት ጋር አብሮነታቸውን ያሳዩት አፍሪካዊ፣ ሕንዳዊና ክልስ በሚል ተከፋፍለው የነበሩት ባጠቃላይ ነበሩ። "ጥቁር ነን" መምህሩ ክስ ሲመሰረትበት የደቡብ አፍሪካ አስተማሪዎች ማኅበር ደግፎታል። የማኅበሩ ቃል አቀባይ ጆናቮን ረስቲን "አብዛኞቻችን በአፓርታይድ ዘመን የነበረውን የዘር ክፍፍል ላለመቀበል መርጠናል። ራሳችንን የምናየው እንደ ጥቁር፣ አፍሪካዊ፣ ደቡብ አፍሪካዊ ነው " ይላሉ። አንዳንዶች የዙሉ፣ የኮሳ፣ የአፍሪካን እና ሌሎችም ጎሳዎች አባልነታቸውን በማንነታቸው ውስጥ አጉልተው እንደሚያዩም አያይዘው ያስረዳሉ። የደቡብ አፍሪካውያን የምጣኔ ሀብት ትስስር ኮሚሽነር ዞእዋ ንቴሊ፤ መንግሥት በቀደመው ሥርዓት ከነበረው የዘር ክፍፍል መላቀቅ አለበት ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። በዘመነ አፓርታይድ አፍሪካውያን፣ ሕንዳውያን እንዲሁም ክልስ ሰዎች ይደርስባቸው የነበረው መድልዎና ጫና ዛሬም ድረስ ነጮች የምጣኔ ሀብት የበላይነቱን እንዲይዙ ምክንያት መሆኑን ይናገራሉ። "ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ማንም በዘርና በፆታ ምክንያት ማዳላት አይችልም። መብትን መንፈግና መጨቆን ሕገ ወጥ ነው" ይላሉ። የጥቁሮች የቢዝነስ ካውንስል ኃላፊ ኪጋንኪ ማራቤኒ፤ ደቡብ አፍሪካ በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መተዳደር ከጀመረች 27 ዓመታት ቢቆጠሩም፤ አሁንም ያለፈው ዘመን ጫና ሙሉ በሙሉ እንዳልተወገደ ይናገራል። "የተፈጠረውን ክፍተት ማጥበብ ችለናል? ብለን ራሳችንን መጠየቅ አለብን። በጆሀንስበርግ የአክስዮን ገበያ የመጀመሪያውን 100 ደረጃ ከያዙት 75 በመቶ የሚሆኑት ነጭ ወንዶች ናቸው" ይላል። እንደ መፍትሔ የሚያስቀምጠው፤ ከመደብ ይልቅ ለቆዳ ቀለም ትኩረት መስጠትን ነው። አፓርታይድ ያደረሰው የዘር መድልዎ ሊሸረሸር የሚችለው ዘርን መሠረት ባደረገ የእኩልነት እርምጃ እንደሆነም ያምናል። ኬፕ ታውን ውስጥ የሚኖሩና ክልስ የሆኑ ሰዎች 2018 ላይ በፌስቡክ ንቅናቄ ጀምረው ነበር። መሪው ፋዲል አዳምስ እንዳለው፤ በማንነታቸው የተነሳ የምጣኔ ሀብት ተጠቃሚነታቸው ጥያቄ ውስጥ ገብቷል። በአካባቢው ቁጥራቸው ብዙ ቢሆንም ሥራ ሲቀጠሩ አይስተዋልም። የአገሪቱ ገዢ ፓርቲ ኤኤንሲ የዘር ልዩነትን እንዳሰፋ የሚተቹ አሉ። "ኤኤንሲ ክልስ ነን የሚሉ ሰዎችን ያካተተ አካሄድ አልተከተለም " ሲል ይተቻል። የሥነ ልቦና ምሁር ዶ/ር ሳት ኩፐር፤ ለዘር ልዩነት የተሰጠው ቦታ የሰው ልጅ በሰውነቱ ቅድሚያ እንዳያገኝ መሰናክል እንደሆነ ያምናሉ። "ከምንም ነገር በፊት ሰው መሆናችንን ዘንግተናል። ለቆዳ ቀለምና ሌሎች መገለጫዎች ነው ቅድሚያ የምንሰጠው። በቋንቋ፣ በሃይማኖትና በሌላም መስፈርት ልዩነታችንን እናሰፋለን" ሲሉ ያስረዳሉ። ደቡብ አፍሪካዊ ማንነት ለሚለው ዋጋ መሰጠት እንዳለበትና ልዩነትን የሚያሰፉ ክፍፍሎችን መንግሥት ማስወገድ እንደሚገባው ያሳስባሉ።
news-53879103
https://www.bbc.com/amharic/news-53879103
ቴክኖሎጂ፡ ቻይና ሰራሹ ቲክቶክ የትራምፕ እግድ ላይ ህጋዊ እርምጃን እንደሚወስድ አስታወቀ
ቻይና ሰራሹ የተንቀሳቃሽ ምሥል መጋሪያ ቲክቶክ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ እንዳይሰራ የጣሉትን እግድ እንደማይቀበለውና ህጋዊ እርምጃንም እወስዳለሁ ብሏል።
ዶናልድ ትራምፕ ከቲክቶክ ባለቤት ባይት ዳንስ ጋር የሚደረግ ማንኛውንም የንግድ ግብይትም ሆነ ስምምነት ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ተቀባይነት እንደሌለው ፍፁማዊ ፕሬዚዳንታዊ ስልጣናቸውን በመጠቀም ትእዛዝ አስተላልፈዋል። ቲክቶክም አሜሪካ ምድር ላይ እንዳይሰራ ውሳኔያቸውን አስተላልፈዋል። የዋሽንግተን ባለስልጣናት ቲክቶክ የአሜሪካውያንን መረጃ ለቻይና መንግሥት አሳልፎ ይሰጣል የሚል ስጋታቸውን ያሰማሉ። ቲክቶክ በበኩሉ ለቻይና መንግሥት ምንም አይት መረጃ እንደማያቀብል እንዲሁም ቁጥጥር እንደማይደረግበት በተደጋጋሚ ሲያስተባብል ቆይቷል። ቲክቶክ በአሜሪካ ብቻ 80 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች አሉት። ለአመት ያህልም ከትራምፕ አስተዳደር ጋር ልዩነቶችን ለመፍታት ቢሞክርም አስተዳደሩ "እውነታንና ተጨባጭ መረጃዎችን" መሰረት ያላደረገ በመሆኑ ችግር ገጥሞኛል በማለት ኩባንያው ከሰሞኑ ገልጿል። "የህግ የበላይነት ወደ ጎን እንዳይባልና፣ ኩባንያችንም ሆነ የደንበኞቻችን ተጠቃሚነት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ እንዲታይ የፕሬዚዳንቱን ትዕዛዝ ለመቃወም ወደ ፍርድ ቤት እናመራለን" በማለት የኩባንያው ቃለ አቀባይ ተናግረዋል። ህጋዊ ሂደቱን በዚህ ሳምንት እንደሚጀምር ቲክቶክ ለቢቢሲ ቢዝነስ ሪፖርተን ቪቪየን ኑኒስ አሳውቋል። በዚህ ሳምንት አርብ እንዲሁ ቻይናዊ አሜሪካውያን የሆኑ ግለሰቦች ትራምፕ ዊ ቻት የተባለው የማህበራዊ ሚዲያ ላይ የጣሉትን እግድ ለመቃወም ሌላ ክስ ጀምረዋል። ዊ ቻት የቻይናው ኩባንያ ቴንስንት ንብረት ነው። በወጣቶች በተለይም ከሃያ አመት በታች ባሉት ከፍተኛ ተቀባይነት ያለው ቲክቶክ ዳንስ፣ አለም አቀፍ ፖለቲካ ሌሎችንም ጉዳዮችን በተመለከተ አጠር ያለ ቪዲዮ የሚጋራበት መተግበሪያ ነው። በተለይም በቅርብ ወራት ከፍተኛ የሆነ የዝና ጣራ ላይ የወጣ ሲሆን የመተግበሪያው ቪዲዮዎች በቢሊዮን በሚቆጠር ጊዜ ዳውንሎድ ተደርገዋል። ትራምፕ በበኩላቸው ቻይና የፌደራል መንግሥት ሰራተኞችን መዋያ ቦታ ለማወቅ፣ መረጃዎችን በመሰብሰብ ለማስፈራራትና በኩባንያዎችም ላይ ለመሰለል ቲክቶክን ትጠቀምበታለች በማለት ይወነጅላሉ። በቻይና ኩባንያዎች የሚመረቱ የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያዎች መጨመርም "ለብሄራዊ ደህንነት ስጋት እንዲሁም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ፣ ምጣኔ ኃብትን ላይ ጫና የሚያሳድር ነው "ብለዋል ትራምፕ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ስልጣን ከያዙ ጀምሮ በቻይና ላይ የንግድ ጦርነት ሲያውጁ ስለነበር በቲክቶክና በዊቻት ላይ የጣሉት እገዳ ብዙ የሚያስገርም አልሆነም። ቲክቶክን ያገደችው አሜሪካ ብቻ ሳትሆን ህንድም አግዳለች፣ አውስትራሊያም ተመሳሳይ እርምጃ ለመውሰድ ከጫፍ ላይ ናት።
news-54245654
https://www.bbc.com/amharic/news-54245654
አሜሪካ የኮሎምቢያው ነፃ አውጭ ጦር መሪን ላስያዘ 5 ሚሊዮን ዶላር እሸልማለሁ አለች
አሜሪካ የኮሎምቢያ ብሔራዊ ነፃ አውጭ ጦር (ናሽናል ሊበሬሽን አርሚ) መሪን ያለበትን ለጠቆመና ላስያዘ አምስት ሚሊዮን ዶላር ሽልማት አዘጋጅቻለሁ አለች።
የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ኃላፊ ማይክ ፖምፔዮ የነፃ አውጭ ጦሩ በምህፃረ ቃል ኢኤልኤን መሪ ዊልቨር ቪሌጋስን "በዕፅ የተወነጀለ አሸባሪ" በማለት በትዊተር ገፃቸው ወርፈውታል። ማይክ ፖምፔዮ ኮሎምቢያን ከጎበኙ ከሁለት ቀናት በኋላ ነው ይህንን ያሉት። ምንም እንኳን ማይክ ፖምፔዮ ይህንን ይበሉ እንጂ ኢኤልኤ ከአምሳ አመት በፊት ኢፍትሃዊነትን ለመታገል የተመሰረተ የማርክሲስት ርዕዮተ አለምን የሚከተል ነፃ አውጭ ድርጅት ነኝ ይላል። የነፃ አውጭው ጦር የአሁኑ መሪ የ38 አመቱ ዊልቨር ቪሌጋስ ፓላሚኖን ለባለፉት 20 አመታት ኮኬይን ከኮሎምቢያ ወደ አሜሪካ በማዘዋወር ኢኤልኤን ይደጉማል በማለት ወንጅለውታል። ማይክ ፖምፔዮ በተጨማሪም የኮሎምቢያ መንግሥት "እነዚህን ወንጀለኛ ድርጅቶች ለመገርስስ በሚያደርገው ትግልም አሜሪካ ቀኝ እጅ ትሆናለች" ብለዋል። ስለ ኢኤልኤን በጥቂቱ የኮሎምቢያ መንግሥት ድርጅቱን በአሸባሪነት የሚወነጅለው ሲሆን በ2016ም ጁዋን ማኑኤል ሳንቶስ ፕሬዚዳንት በነበሩበት ወቅት ከሌላኛው የግራ ክንፍ ታጣቂ ፋርክ ጋር ስምምነት ቢፈጥሩም ከኢኤል ኤን ጋር ግን በጊዜ ይደር ትተውት ነበር። በተለይም አዲሱ ፕሬዚዳንት ዱኬስ ከመጡ በኋላም ቡድኑ በዋና መዲናዋ ቦጎታ የሚገኝ የፖሊስ ማሰልጠኛ አካዳሚን በቦምብ በማፈንዳት፤ ለ21 ሰዎች ህልፈት ተጠያቂ አድርገውታል። ከዚህም በተጨማሪ በደቡብ ናሪኖ ግዛት ለደረሱ ግድያዎችም ተጠያቂ መንግሥት ቢያደርገውም ኢኤልኤን ፍፁም ውንጀላ ነው በማለት ክዶታል።
48538338
https://www.bbc.com/amharic/48538338
ስለ ግንቦት 27፤ 1983 የጎተራው ግምጃ ቤት ፍንዳታ ምን ያስታውሳሉ?
ግንቦት 27፤ 1983 ዓ.ም.፤ ደርግ ወድቆ ጊዜያዊ አስተዳደር ሥልጣን ከያዘ አንድ ሳምንት ሞልቶታል። አዲስ አበባ ከጥይት እና መሰል ድምፆች ጋብ ብላ በእርጋት ማሰብ የጀመረችበት ወቅት ነበር።
ነገር ግን ሌሊት 10 ገደማ የሆነውን ማንም አልጠበቀውም። ሃገር ሰላም ብለው እንቅልፍ ላይ ያሉ አዲስ አበባውያንን ቀልብ የገፈፈ ክስተት። ከ100 በላይ ሰዎችን የቀጠፈ ጉድ። ኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ በዕለቱ ያወጣው ዕትም ላይ የአዲስ አበባ ሕዝብ ቁጥር በግምት 3 ሚሊዮን ይሆናል ይላል። ታድያ ይህን ሁሉ ሰው በአንዴ 'ክው' የሚያደርግ ምን ሊሆን ይችላል? የተሰማው ፍንዳታ ነበር። ከበ...ድ ያለ ፍንዳታ። ከጎተራ እስከ ሰሜን ሆቴል የተሰማ። ከአቃቂ እስከ ኮተቤ ቀልብን የገፈፈ። መታሰቢያ ሸዋዬ ይልማ የዛኔ የ12 ዓመት ታዳጊ ነበርኩ ትላለች፤ የ7ኛ ክፍል ተማሪ። ቢሆንም ክስተቱን መቼም አትረሣውም። «የዛን ሰሞን ከሁለት ሳምንት ጀምሮ ትምህርት ተዘግቶ ነበር። ልክ ጓድ መንግሥቱ ኃይላማርያም ከሃገር ኮበለሉ ተብሎ የተነገረ 'ለት [ግንቦት 13] ቤተሰቦቻችን ለቅመውን ወደ ቤት ገባን። ከዚያ በኋላ ትምህርት አልነበረም። አስጨናቂ ሳምንት ነበር። ልክ በሳምንቱ [ግንቦት 20] የኢህአዴግ ሠራዊት አዲስ አበባ ገባ። ከዚያ በኋላ የጥይት ድምፅ አልነበረም፤ ትንሽ ጋብ ብሎ ነበር።» • የዛሬ 30 ዓመት... የኮ/ል መንግሥቱ አውሮፕላን ለምን አልጋየም? አዲስ አበባ ከዚያ በፊት በነበሩት ሳምንታት የጥይት ይሁን መሰል ፍንዳታዎች ድምፅ ይህን ያህል ብርቋ አልነበረም። መታሰቢያ ትቀጥላለች. . . «ከእንቅልፋችን የቀሰቀሰን ፍንዳታው ነበር። መሬት 'ሚያንቀጠቅጥ ዓይነት ፍንዳታ ነበር። በዚያ ላይ ጨለማ ነው። ምን እንደሆነ አላወቅንም፤ እስከዛን 'ለት ከሰማናቸው ፍንዳታዎችም በጣም የተለየ ነበር። ሁሉም ሰው ተነሳ፤ ነገር ግን ግራ በገባው ስሜት ውስጥ ነበር። ጦርነት ነው እንዳንል ጦርነቱ አልቋል. . .ምን እንበለው? አየቆየ ሲመጣ የጥይት የሚመስሉ ትንንሽ ፍንዳታዎች መስማት ጀመርን።» ፍንዳታውን የሸሹ ሰዎች እግራቸው ወደመራቸው መትመም ያዙ። ወደ እነመታሰቢያ ሠፈርም የመጡ አልጠፉም። «እንግዲህ አስበው ሠፈራችን ሰሜና ማዘጋጃ ነው። ግን ፍንዳታውን የሸሹ ሰዎች በግምት ከፍንዳታው አንድ ሁለት ሰዓት በኋላ እኛ ሠፈር ደርሰዋል። ወላጆቼ ወጥተው ሲጠይቁ ፍንዳታ እንደሆነ ተረዱ። የሚቀጣጠል ነገር እንዳለም ከሰዎቹ ሰሙ። ወላጆቼም ግራ ገብቷቸው ነበር። እኛም እንውጣ ወይስ ትንሽ እንጠብቅ ዓይነት ነገር ነበር የነበረው። መጨረሻ ላይ አንድ ድብል...ቅ ያለ ፍንዳታ ተሰማ። በጣም ከባድ ከመሆኑ የተነሳ መስኮታችን ሁላ የሚረግፍ ነበር የመሰለው። ከዚያ በኋላ ነው ፍንዳታውም የተረጋጋው፤ ቀኑም እየነጋ መጣ።» የጦር መሣሪያ ማከማቻ ይድነቅ አብርሃ ክስተቱን ለመዘገብ ካሜራቸውን አንግበው ወደሥፍራው ካመሩ ሰዎች መካከል ነበር። ይድነቅ በወቅቱ የሚያነሳቸውን ፎቶዎችን እና ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለሕወሓት ማሕደር ክፍል ያስረክባል። ቢሯቸው የነበረው ደግሞ አቡነ ጴጥሮስ አካባቢ የነበረው የኢትዮጵያ ራድዮ ዋና መሥሪያ ቤት። «ፍንዳታውን ስንሰማ የኛ 'ክሩ' ቪዲዮ እና ፎቶግራፍ ለማንሳት ወደዚያ ሄደ። የፈነዳው የጦር መሣሪያ ማከማቻ የነበረ ሥፍራ ነበር፤ በርካታ ብረታብረቶችም ነበሩ ሥፍራው ላይ። ፍንዳታው አካባቢው በጭስ እንዲዋጥ አድርጎ ነበር። ብዙ ተጎጅዎችም ነበሩ። በርካቶች ሞተዋል፤ የቆሰሉም የትየለሌ ነበሩ። እኛ ፎቶ እና ቪደዮ ስናነሳ የነበረው እዚያ የነበረውን ሁኔታ ነበር።» ያኔ ጎተራ፤ እንደዛሬ በማሳለጫ ሳትከበብ ግዙፍ የነዳጅ ማከማቻ እና የለስላሳ ፋብሪካ አልተለይዋትም ነበር። የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት መናኸሪያም ነበረች ጎተራ። «በጣም አስገራሚው ነገር እንዲያውም ነዳጅ ማደያው አለመፈንዳቱ ነው» ትላለች መታሰቢያ። «ጎተራ፤ አሁን ያለውን ቅርፅ ሳይዝ በፊት 'ኮንፊውዥን ስኩዌር' ነበር የምንለው። መዓት አስፋልቶች የሚገናኙበት ነበር፤ ባቡሩም ያልፍ ነበር በዚያ በኩል። በሁለቱም አቅጣጫ ነዳጅ ማከማቻዎች ነበሩ፤ የእህል ጎተራው አለ፤ ለስላሳ ፍብሪካው አለ። ሰዉ በኋላ ላይ እንደ ተዓምር ያወራው 'ነዳጅ ማደያዎቹ አለመፈንዳታቸው' እያለ ነበር። ምክንያቱም አደጋ የበለጠ የከፋ ይሆን ነበር። በወቅቱ በፍንዳታው ምክንያት ከ100 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተነገረ። የቆሰሉም በርካታ ነበሩ። ያኔ የነበረው ጊዜያዊ አስተዳደር ጣቱን በደርግ ሰዎች ላይ ቀሰረ። ማካማቸውን ሆን ብለው ያፈነዱት የደርግ 'ርዝራሾች' ናቸው አለ። ምሽት ላይ ዜና ሲነበብ ከአደጋው ሌላ አስደንጋጭ ዜና ተሰማ፤ ታዋቂው ጋዜጠኛ ሞሐመድ አሚን በፍንዳታው ምክንያት አንድ እጁን ማጣቱ። • ኮሎኔል መንግሥቱ ለህፃናት አምባ ልጆች ደብዳቤ ላኩ ሞሃመድ አሚን ይድነቅ ስለ ሞሐመድ የሚያስታውሰውን ሲወጋ «እኛ በሥፍራው ስንደርስ ሞሐመድ እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች ፎቶ እያነሱ ነበር» ይላል። ሞሐመድ አሚን እጁ ላይ ጉዳት የደረሰበት በሁለተኛው ፍንዳታ ነው። ከዚያ በፊት ግን ፍንዳታውን እና አካባቢውን እየዞረ ሲቃኝ፤ ምስልም ሲወስድ ነበር። ነገር ግን ሁለተኛው ፍንዳታ የእርሱን ግራ እጅ የባልደረባው ጆን ማታይን ነብስ ሊወስድ ግድ ሆነ። «እነዚህማ ለገንዘብ ብለው ነው እንጂ እንዴት እንዲህ ዓይነት ሥፍራ እየገቡ ፎቶ ያነሳሉ በማለት ራቅ ብለን የቆምነው እኔና የኛ ካሜራ ክሩ ስናወጋ ነበር» ይላል ይድነቅ የሞን ጀግንነት ሲያስታውስ። «አደጋው ሲደርስ በሥፈራው የነበረው አምቡላንስ ወደ ሆስፒታል ወሰዳቸው። ሥራው ግርግር ነበረው። ካሜራቸውን ጥለው ነበር የሄዱት። እኛ ነን ካሜራቸውን ሰብስበን ያስቀመጥንላቸው።» እርግጥ የዛኔ ታዳጊ ነበርሽ። ቢሆንም የአደጋው ምክንያት ምን እንደነበር ታስታውሻለች? ለመታሰቢያ ያቀረብንላት ጥያቄ. . . «እኔ እሱ ነገር ምንም ትዝ አይለኝም። ቀልቤን ስቦት የነበረው ምሽት ላይ የተነገረው ዜና ነው። ሞሐማድ አሚን በፍንዳታው ምክንያት ጉዳት ደረሰበት ተብሎ ሲነገር። ሞሐመድ አሚን ለእኔ በጣም ትልቅ 'አይዶል' ብዬ የምለው ጋዜጠኛ፤ ከኢትዯጵያ ጋር ልዩ ቁርኝት ያለው ሰው ነው።» ሞሐመድ አሚን አንድ እጁ ጉዳት ደርሶበት እንኳ በአንዱ እጁ ይቀርፅ ነበር አሉ። እውነት ይሆን? ማን ያውጋ የነበረ. . .እንዲሉ ይህን ጥያቄ ለይድነቅ ሰነዘርንለት። «አይይይይይ. . .እውነት አይደለም። ብዙ ደም እየፈሰሰው ነበር እኮ። ኋላ ላይ በሕክምና ተቆረጠ አንጅ፤ አንድ እጁ ተንጠልጥሎ ነበር። 'ሬዚዝታንስም' አልነበረውም፤ ያ ሁሉ ደም እየፈሰሰ እንዴት ብሎ? ካሜራው እኮ ወድቋል። አምቡላንስ ለሕክምና ወሰደው፤ ንብረቱን ደግሞ እኛ ይዘንለት ሄድን። በኋላ ነው መጥቶ የተረከበው።» ድኀረ-ኢሕአዴግ ትውልድ ስለ ጎተራው ፍንዳታ እምብዛም ትዝታ ላይኖረው ይችል ይሆናል። በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቅ ሥፍራ ካለው ወርሃ ግንቦት ክስተቶች አንዱ መሆኑ ግን አልቀረም። እኛም ለማጣቀሻ ይሆን ዘንድ ይህችን ከተብናት። • በመፈንቅለ መንግሥቱ ዙሪያ ያልተመለሱት አምስቱ ጥያቄዎች
news-47823796
https://www.bbc.com/amharic/news-47823796
የአማዞን ባለቤት፤ ጄፍ ቤዞስ ቢሊየኖች ከፍሎ ትዳሩን ለማፍረስ ተስማማ
የአለማችን ቀንደኛ ሃብታም ጄፍ ቤዞስ እና ባለቤቱ ማክኬንዚ ትዳራቸውን ለማፍረስ ተስማሙ። ፍቺው ግን እንዲሁ በባዶ እጅ አጨብጭበው የሚወጡበት አልሆነም። ባለቤቱ የድርሻዋ ነው የተባለውን 35 ቢሊየን ዶላር ታገኛለች።
35 ቢሊዮን ዶላር ድርሻዋን የምትቀበለው ማክኬንዚን ከዓለማችን ሃብታም ሴቶች ዝርዝር ውስጥ ያካትታታል። ይህ ብቻ ሳይሆን ባለቤቷ ከዛሬ 25 አመት በፊት ከመሰረትውና በአለማችን ቁጥር አንድ ከሆነው የኢንተርኔት የችርቻሮ ግብይት ድርጅት አማዞን የአራት በመቶ ድርሻ ይኖራታል። በምትኩ ዋሽንግተን ፖስት ላይ ያላትን እና የሕዋ ላይ ጎዞ ከሚያደርገው ኩባንያው ላይ ያላትን ድርሻ ትተዋለች። ከዚህ ቀደም ትዳሩን ለማፍረስ ለአጋሩ ውድ ክፍያ የፈፀመው የኪነጥበብ ስራዎችን በማሻሻጥ የሚታወቀው አሌክ ዋይልደንአንስታይን የነበረ ሲሆን እርሱም የ 3 ቢሊየን ዶላር ክፍያ ፈፅሟል። ጄፍ ቤዞስ ፍቺውን ለህዝብ ይፋ ያደረገው በቲውተር ገፁ ላይ ሲሆን ጉዳዩም በመስማማት መከናወኑን ጠቅሷል። • ''አብራሪዎቹ ትክክለኛው መመሪያ ተከትለዋል'' • የበረራ አስተናጋጆች ከአደጋው በኋላ በነበራቸው በረራ ምን ተሰማቸው? • የልጇን ልጅ የወለደችው አያት ከፍቺው በፊት እርሷ በአማዞን ውስጥ የ16.3% ድርሻ የነበራት ሲሆን ጄፍ አሁንም 75 በመቶ ድርሻውን እንደያዘ ነው፤ የቀድሞ ባለቤቱ ድምፅ የመስጠት መብቷንም ጨምራ ሰጥታዋለች። ጥንዶቹ ትዳራቸውን የመሰረቱት ጄፍ ቤዞስ አማዞንን ከማቋቋሙ በፊት በአንድ ድርጅት ተቀጣሪ ሆኖ እየሰራ ሳለ ሲሆን አራት ልጆችንም አፍርተዋል። አማዞን በአሁን ሰአት በኢንተርኔት ግብይት ቀዳሚው ሲሆን ባለፈው አመት ብቻ 232.8 ቢሊየን ዶላር ገቢ አስገኝቷል። ይህም እንደ ፎርብስ ዘገባ ከሆነ የትዳር አጋሮቹን 131 ቢሊየን ዶላር ትርፍ እንዲሰበስቡ አድርጓቸው ነበር። ባለቤቱ ማክኬንዚም ብትሆን ስሟ የሚጠቀስ ደራሲ ናት። ሁለት ልብወለዶችን ለገበያ በማብቃት የተሳካ ሽያጭ አከናውናለች። • የዓለማችን ቱጃር 2 ቢሊየን ዶላር ለድሆች ሊለግሱ ነው • ወንዶች ከሴቶች በበለጠ ለምን እራሳቸውን ያጠፋሉ? ለትዳራቸው መፍረስ እንደምክንያት የተቀመጠው ጄፍ ከትዳር ውጪ ግንኙነት መስርቷል ተብሎ የተወራው እንደሆነ የወጡ ዘገባዎች ያሳያሉ።
news-46423355
https://www.bbc.com/amharic/news-46423355
ግብፃዊቷ ተዋናይት ራኒያ ዮሱፍ በአለባበሷ ምክንያት ክስ ቀረበባት
ግብፃዊቷ ተዋናይት በካይሮ በተካሄደው የፊልም ፌስቲቫል ላይ ሰውነቷን የሚያጋልጥ ልብስ በመልበሷ ክስ ቀረበባት።
ራኒያ ዮሱፍ ካይሮ በተካሄደው የፊልም ፌስቲቫል ላይ ተዋናይቷ ጥቁር፣ እግሮቿን የሚያጋልጥ ቀሚስ በመልበሷ ግብፃውያንን አስቆጥቷል። በድርጊቷ ጥፋተኛ ሆና ከተገኘችም 5 ዓመት የሚደርስ እስር ሊጠብቃት እንደሚችል ተነግሯል። እርሷ ግን "አስቤበት አይደለም የለበስኩት" ስትል ይቀርታ ጠይቃለች። • ሳዑዲ ሴቶች ወደ ስታዲየም እንዲገቡ ልትፈቅድ ነው • በአዲስ አበባ አፍላ ወጣቶች በከፍተኛ መጠን በኤች አይቪ እየተያዙ ነው • የሰከረው ጃፓናዊ አብራሪ የ10 ወራት እስር ተበየነበት የ44 ዓመቷ ተዋናይት አለባበሷ እንደዚህ መነጋገሪያ እንደሚሆን ብታውቅ ኖሮ ልብሱን እንደማትለብስ ተናግራለች። የእርሷን ጉዳይ ወደ ፍርድ ቤት የወሰዱት የህግ ባለሙያዎቹ አምሮ አብደል ሳላም እና ሳሚር ሳብሪ በተመሳሳይ ድርጊት ዝነኞችን ፍርድ ቤት በማቆም ይታወቃሉ። የተዋናይቷ አለባበስ "የማህበረሰቡን እሴት፣ ባህልና ሞራል ያላገናዘበ አንዲሁም የፌስቲቫሉን ገፅታ ያበላሸና የግብፅ ሴቶችን ያሰደበ" በማለት የህግ ባለሙያው አምሮ አብደል ተናግረዋል። ተዋናይቷ በበኩሏ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ባስተላለፈችው መልዕክት "እንደዚህ ዓይነት ልብስ ስለብስ ይህ የመጀመሪያ ጊዜዬ ነው፤ እንዲህ ዓይነት ቁጣን ይቀሰቅሳል ብዬም አልገመትኩም" በማለት አስባበት እንዳለበሰች አስታውቃለች። እንዲህ ማለቷ ከመጠየቅ ባያስጥላትም በድርጊቷ በመፀፀት ያደገችበትን የግብፃውያን ባህልና እሴት ለመጠበቅም ቃል ገብታለች። ሌላኛዋ የግብፅ ተዋናይ በበኩሏ እርሷ ብቻ ሳትሆን ተጋባዥ እንግዶች መድረኩን ያላገናዘበ አለባበስ ለብሰው እንደነበር ተችታለች። ባለፈው ዓመት የግብፁ ፍርድ ቤት ድምፃዊት ሻማ አህመድ በውስጥ ሱሪ ብቻ ሆና በሙዚቃ ቪዲዮ ላይ በመታየቷና በወቅቱም ወሲብ ቀስቃሽ ሙዚቃ ባቀነቀነችበት ቪዲዮ የ2 ዓመት እስር ተፈርዶባታል፤ ምንም እንኳን በኋላ ላይ ወደ አንድ ዓመት ዝቅ ቢደረግላትም። በተመሳሳይ መልኩ ባሳለፍነው የአውሮፓውያኖቹ ጥር ወር ላይ አምር የተባለች ድምፃዊት ያልተገባ ዳንስ በማሳየቷ በቁጥጥር ስር መዋሏ መነጋገሪያ መሆኑ የሚታወስ ነው።
news-53583162
https://www.bbc.com/amharic/news-53583162
በዚምባብዌ ሆስፒታል በአንድ ምሽት ሰባት አራስ ሕፃናት መሞታቸው ተነገረ
በዚምባብዌ ዋና መዲና ሃራሬ በሚገኝ የእናቶችና ሕፃናት ሆስፒታል በአንድ ምሽት ሰባት አራስ ሕፃናት መሞታቸው ተገለፀ።
ሕፃናቱ ለህልፈት የተዳረጉት የሆስፒታሉ ነርሶች ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ አድማ ላይ ስለነበሩና በሆስፒታሉ በተፈጠረ መጨናነቅ እንደሆነ ተነግሯል። ለማዋለጃ ክፍሉ ቅርበት ያላቸውና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ሁለት ዶክተሮች የህፃናቱን መሞት ለቢቢሲ አረጋግጠው ሕፃናቱ የተወለዱት ሰኞ ዕለት በቀዶ ሕክምና እንደነበር ተናግረዋል። በዚያን ምሽት ስምንት ሕፃናት መወለዳቸውን ጠቅሰው ከስምንቱ ሰባቱ ሞተው እንደተወለዱ አክለዋል። የማዋለጃ ክፍሉ በጣም የተጨናነቀ በመሆኑ ሕይወታቸው ሊያልፍ ችሏል ያሉት ዶክተሮቹ፤ ይህ ያለውን ከፍተኛ ችግር የሚያሳይ ክስተት ነው ብለዋል። የአራስ ሕፃናቱን የሞት ዜና በመጀመሪያ ያወጡት ዶ/ር ፒተር ማጎምቤይ ሲሆኑ "ያልተወለዱ ሕፃናትን ጨምሮ ወደ ፊታችንን እየተነጠቅን ነው፤ እባካችሁ ዘረፋውን አቁሙ" ሲሉ ነበር ዶ/ሩ በትዊተር ገፃቸው አሳዛኙን ዜና ያሰፈሩት። ሁለቱ ነፍሰ ጡር እናቶች በእርግዝና በሚፈጠር ውስብስብ የጤና ችግር ያለክትትል ለቀናት በሆስፒታሉ እንዲቆዩ የተተው ሲሆን፤ የተደረገላቸው ሕክምናም በጣም የዘገየ እንደነበር ከዶክተሮቹ አንዱ ተናግሯል። " ሁለቱ እናቶች ባጋጠማቸው ውስብስብ የወሊድ ችግር ሳቢያ ቀዶ ሕክምና ሊሰራላቸው የሚገባው ቀድሞ ነበር፤ ቀዶ ሕክምናው ያስፈለጋቸው በምጥ መውለድ ባለመቻላቸው ነበር፤ ነገር ግን በጊዜ አልተሰራላቸውም፤ ረፍዷል " ብሏል። ሌላኛው ዶክተር በበኩሉ "ይህ የተለየ ክስተት አይደለም። በየቀኑ የሚያጋጥም ነው፤ ማድረግ የምንችለው ሲሞቱ ማየት ብቻ ነው ፤ ይህ ለቤተሰብና ለጀማሪ ዶክተሮች ስቃይ ነው" ብሏል። ዶክተሮቹ በሆስፒታሉ ውስጥ የመድሃኒት ፣ የደም አቅርቦት እንዲሁም የበሽታ መከላከያ የሕክምና ግብዓት አለመኖሩን ተናግረዋል። በወቅቱ ነርሶች የኮሮናቫይረስ መከላከያ የሕክምና ግብዓት እጥረቶች መኖራቸውን ተከትሎ አድማ ላይ እንደነበሩ የገለፁት ዶክተሮቹ፤ በወቅቱ ያሉት ዶክተሮችም በሥራ ተጨናንቀው ነበር ብለዋል። " ጥቂት ዶክተሮችና ነርሶች ነበሩ፤ ዶክተሮቹ የሚችሉትን አደረጉ ግን ተዳክመው ነበር፤ ጀማሪ ዶክተሮች ደግሞ በእርግዝና ወቅት የሚያጋጥሙ ውስብስብ የጤና ችግሮችን በቀላሉ ማወቅ አይችሉም" ይላሉ እኝህ ቢቢሲ ያነጋገራቸው ዶክተሮች። ከኮቪድ -19፣ ከበሽታ መከላከያ የሕክምና ግብዓቶች እጥረት፣ ከዋጋ ግሽበትና ከኢኮኖሚ ቀውስ ጋር በተያያዘ በሃራሬ የሚገኙ በርካታ ክሊኒኮችም ተዘግተዋል። ይህም ነፍሰጡር ሴቶች በከተማው ወደሚገኘው ትልቅ የመንግሥት ሆስፒታል ብቻ እንዲሄዱ አስገድዷቸዋል። ሆስፒታሎቹም ይህንን ለማስተናገድ ከአቅማቸው በላይ ሆኖባቸዋል። "ያለው ሁኔታው በጣም አስከፊ ነው" ሲል አንዱ ዶክተር ያለውን ሁኔታ አስረድቷል። የዚምባብዌ የማህፀንና ፅንስ ሐኪሞች ማህበር ባወጣው መግለጫ ሁኔታውን አሳዛኝ እና ከአስከፊነት በላይ ነው ሲሉ ገልፀውታል። " ሴቶች እየተሰቃዩ ነው። ባለድርሻ አካላት ፣ መንግሥት ፣ የህክምና ባለሙያዎች፣ ሲቪል ሶሳይቲ እና ግለሰቦች ድምፅ የሌላቸውን እናቶችና ሕፃናት ለማዳን የበኩላቸውን እንደሚያደርጉ እናምናለን" ብለዋል በመግለጫቸው። እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ መረጃ ከሆነ በዚምባብዌ እስካሁን ወደ 2 ሺህ 800 የሚጠጉ ሰዎች በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሲሆን 40 ሰዎች ደግሞ በበሽታው ሳቢያ ሕይወታቸው አልፏል። በአገሪቷ የተከሰተውን የዋጋ ግሽበት ዚምባብዌ ከቅኝ ግዛት ከተላቀቀች ጀምሮ አገሪቷን እየመራ ያለውን ዛኑ ፒ ኤፍ ፓርቲን የሚቃወም ሰልፍ አርብ ይኖራል በሚል ውጥረት ነግሷል።
48960445
https://www.bbc.com/amharic/48960445
ኢንዶኔዥያ፡ የሟቾች ቤተሰቦች በቦይንግ ካሳ ተጭበርብረናል አሉ
ባለፈው ዓመት ኢንዶኔዥያ ውስጥ በተከሰከሰው ቦይንግ ማክስ 737 ቤተሰቦቻቸውን ያጡ ሰዎች፤ በቦይንግ የካሳ ክፍያ መጭበርበራቸውን ጠበቃቸው ተናገሩ።
ጠበቃው ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ቤተሰቦቹ ቦይንግን እንዲሁም ላየን ኤርን እንዳይከሱ የሚከለክል ሰነድ እንዲፈርሙ ተደርገዋል። ሁለት አውሮፕላኖች ከተከሰሱ በኋላ፤ ቤተሰቦች ቦይንግን መክሰስ እንዳይቻሉ የሚያደርጉ ስምምነቶች እንደፈረሙ ቢቢሲ ደርሶበታል። ስምምነቶቹ በአደጋው የሞቱ ሰዎች ቤተሰቦች፤ ቦይንግን አሜሪካ ውስጥ እንዳይከሱ ያግዳሉ። ቦይንግ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠት ፍቃደኛ አይደለም። • ቦይንግ ለተጎጂ ቤተሰቦች 100ሚ. ዶላር ሊሰጥ ነው ባለፈው ዓመት ከኢንዶኔዥያ መዲና ጃካርታ የተነሳው ቦይንግ 737 ማክስ በረራ ከጀመረ ከ13 ደቂቃ በኋላ ተከስክሶ፤ 189 ተሳፋሪዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። የሟቾች ቤተሰቦች በኢንሹራንስ አማካይነት ካሳ የቀረበላቸው አደጋው ከተከሰተ ከሳምንታት በኋላ ነበር። የካሳ ገንዘቡን ለማግኘትም ቤተሰቦቹ ስምምነት መፈረም ነበረባቸው። ስምምነቱ ቦይንግን ወይም ላየን ኤርን ከመክሰስ የሚያግዳቸው ነበር። በአደጋው ባለቤቷን ያጣችው ሜርዲያን ኦገስቲን እንደምትለው፤ የኢንሹራንሱ ጠበቆች የመክሰስ መብቷን እንድታነሳ የሚያደርግ ሰነድ እንድትፈርም ገፋፍተዋታል። "ሰነዶች እንድፈርም ሰጡኝ፤ ሰነዶቹ ካሳ መውሰድ ብችልም ላየን ኤርንና ቦይንግን መክሰስ እንደማልችል ይገልጻሉ።" • የቱሉ ፈራ ደጋግ ኢትዮጵያዊ ልቦች ሰነዱን ከፈረመች ከአንድ ወይም ከሁለት ሰዓት በኋላ ገንዘቡን እንደምታገኝ ገልጸውላት ነበር። "ገንዘቡን ወስደሽ ሕይወትሽን ቀጥይ አሉኝ፤ እኔ ግን አልፈልገውም ነበር። ለእኔ ሚዛን የሚደፋው ገንዘቡ ሳይሆን የባለቤቴ ሕይወት ነው።" ሜርድያን ሰነዱን ባትፈርምም ወደ 50 ቤተሰቦች እንደፈረሙ ይታመናል። እያንዳዳቸው የሚያገኙት ከ74 ሺህ ዩሮ በታች ካሳ ነው። በኢንዶኔዥያ ሕግ ቤተሰቦች 71 ሺህ ዩሮ ካሳ የማግኘት መብት ስላላቸው ካሳው አከራካሪ ሆኗል። ከሟቾች ቤተሰቦች የጥቂቱ ጠበቃ ሳንጂቭ ሳይኝ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ቤተሰቦች መብታቸውን አሳልፈው እንዲሰጡ ግፊት ተደርጎባቸዋል። "የፈረሙት ቤተሰቦች ክፍያው አልተሰጣቸውም። የኢንሹራንሱና የኢንሹራንሱ አማካሪዎች አጭበርብረዋቸዋል። በዚህም የተጠቀመው ቦይንግን ነው" ብለዋል። • ቦይንግ ለተጎጂ ቤተሰቦች ያቀረበው ካሳ ተቃውሞን ቀሰቀሰ ቤተሰቦቹ በሚሊየን ዶላር የሚቆጠር ካሳ የማግኘት መብት ነበራቸው። ቦይንግ መሰል አይነት ሰነዶች በማስፈረም ተጠቃሚ ሲሆን የመጀመሪያው እንዳልሆነም ተናግረዋል። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ2005፤ የቦይንግ ማክስ 737 ኢንዶኔዥያ ውስጥ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ተከስክሰሶ 149 ሰዎች ሞተዋል። የሟቾች ቤተሰቦች ቦይንግን አሜሪካ ውስጥ ላለመክሰስ ስምምነት ተፈራረመው ነበር። ቦይንግ ማክስ 737፤ 2007 ላይ ተከስክሶ 102 ሰዎች ሲሞቱም ተመሳሳይ ስምምነት ተፈርሞ ነበር። አንድ ስሙ ያልተጠቀሰ የኢንሹራንስ ጠበቃ በሦስቱም ስምምነቶች እጁ እንዳለበት ተገልጿል። ሳንጂቭ ሳይኝ እንደሚሉት፤ የቦይንግን የቀደሙ ሰምምነቶች ከግምት በማስገባት፤ ቦይንግ ከላየን ኤር አደጋ በኋላ የሟቾችን ቤተሰቦችም አስፈርሟል ተብሎ ይታመናል። "ቦይንግ ሰነዶቹ ስለመፈረማቸው መረጃው የለውም ለማለት ይከብዳል። ለስምምነቱ ተባብረው ይሆናል የሚል ጥያቄም ያስነሳል" ቦይንግ ስለነዚህ ስምምነቶችና ስምምነቶቹን ስላቀነባበረው ኢንሹራንስ ጠበቃ መረጃ እንዳለው ተጠይቆ ምላሽ አልሰጠም። ሆኖም፤ "ቦይንግ የሰዎች ሕይወት በመጥፋቱ ጥልቅ ሀዘን ይሰማዋል። ከደንበኞቹና ከበበራው ዘርፍ ጋር በመሆን ተጎጂዎች እንዲያገግሙ ይጥራል። በእንደዚህ አይነት አጋጣሚዎች እንደሚደረገው፤ የቦይንግ ኢንሹራንስ ከሌሎች ኢንሹራንሶች ጋር እየተመካከረ ነው" ብሏል። የላየን ኤርና የቦይንግ ኢንሹራንስ የእንግሊዙ 'ግሎባል ኤሮስፔስ' ነው። 'ግሎባል ኤሮስፔስ' የቀረበበትን ክስ ባይቀበልም፤ የደንበኞችን ሚስጥር ማውጣት አይቻልም በሚል በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠጥ ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። "የበረራ ኢንሹራንስ በአንድ አደጋ ውስጥ የተሳተፉ ከአንድ በላይ አካላት መወከል ይችላል። የተለያዩ ደንበኞችን ጉዳይ በተናጠል እያየን፤ ተገቢ ባልሆነ መንገድ መረጃ እንዳይሰራጭም እያደረግን ነው" ብሏል። እንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ አየር መንገድንና የአውሮፕላን አምራችን ለወደፊት ከመከሰስ መከላከል የተለመደ ነውም ብሏል። • የ737-8 ማክስ መከስከስ ለቦይንግ ምን ማለት ነው? ቦይንግ፤ ማክስ 737 አውሮፕላን ተከስክሶ (የኢትዮጵያ አየር መንገድና ላየን ኤር) ሕይወታቸውን ላጡ ሰዎች ቤተሰቦች የ100 ሚሊየን ዶላር ካሳ እንደሚሰጥ ባለፈው ሳምንት መግለጹ ይታወሳል። የቤተሰቦቹ ጠበቆች ስለ ገንዘቡ ዝርዝር መረጃ እንዳልደረሳቸው ገልጸዋል።
48277731
https://www.bbc.com/amharic/48277731
"አብጃታን ሀይቅ ለማለት ይከብዳል" የአብጃታ ሻላ ሀይቅ ብሔራዊ ፓርክ ኃላፊ
አብጃታ ሀይቅ በቀጣይ አምስት ዓመታት ውስጥ ሊጠፋ እንደሚችል ይፋ የተደረገው በቅርቡ ነበር። ቀድሞ ስፋቱ 194 ኪሎ ሜትር የነበረው ሀይቅ ዛሬ 73 ኪሎ ሜትር ሆኗል። ጥልቀቱ ደግሞ ከ14 ሜትር ወደ 2.5 ሜትር ማሽቆልቆሉ ተገልጿል።
የአብጃታ ሻላ ሀይቅ ብሔራዊ ፓርክ ኃላፊ አቶ ባንኪ ሙደሞ እንደሚሉት፤ ሀይቁ ለመጥፋት የተቃረበው የተለያዩ ሰው ሰራሽ ተጽዕኖዎች ስር ስለወደቀ ነው። ሀይቁን ከሚቀላቀሉ ገባር ወንዞች አንዱ ከዝዋይ ሀይቅ የሚሄደው ቡልቡላ ወንዝ ነው። ይህም ወንዝ ሰው ሰራሽ ጫና ውስጥ መውደቁ ወንዙን ሙሉ በሙሉ አድርቆታል። • የጣና ሐይቅን ሌሎችም አረሞች ያሰጉታል "በዝዋይ አካባቢ የሚገኙ አንዳንድ ድርጅቶች የሚጠቀሙት የወንዙን ውሀ ነው። የሶዳ አሽ ድርጅት ከአቢጃታ ሀይቅ ውሀ በቱቦ እየሳበ ለፋብሪካው ሥራ ያውላል። ወደ 30 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ በዓመት ይጠቀማሉ" ይላሉ አቶ ባንኪ። ከዚህ በተጨማሪ በሀይቁ ዙሪያ የሚገኘው ደን ተመናምኗል። የአፈር መሸርሸር ሀይቁ በደለል እንዲሞላ አድርጓል። በደለሉ ምክንያት ሰዎችና የዱር እንስሳትም መንቀሳቀስ አልቻሉም። ፓርኩ ውስጥ ወደ 60 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች የሚኖሩ ሲሆን፤ የነዋሪዎቹ እንቅስቃሴ ለሀይቁ መድረቅ ምክንያት መሆኑን ኃላፊው ያስረዳሉ። የቀንድ ከብቶች መሰማራት ያስከተለው ገደብ የለሽ ግጦሽ እንዲሁም የደን ጭፍጨፋ የፓርኩንና የሀይቁንም ደህንነት አደጋ ውስጥ ጥለውታል። አቶ ባንኪ "ሀይቁን ሀይቅ ለማለት ይከብዳል" ሲሉ አቢጃታ የሚገኝበትን አሳሳቢ ሁኔታ ይናገራሉ። • የ21ኛው ክፍለ ዘመን ነዳጅ. . . ውሃ! የሀይቁ መጠን ስለቀነሰ ሀይቁ ላይ የሚኖሩ አእዋፋት ቁጥር ተመናምኗል። ቡልቡላ ወንዝን የሚጠቀመው አካል ከድርጊቱ ተቆጥቦ ወንዙ በቀጥታ ወደ ሀይቁ መፍሰስ ካልጀመረ አብጃታ ተስፋ አለው ለማለት ይቸገራሉ። አብጃታ እንደማሳያ ተጠቀሰ እንጂ አብኞቹ የኢትዮጵያ ሀይቆች የመጥፋት አደጋ ተጋርጦባቸዋል። እንደ ሀሮማያ ሀይቅ የጠፉ የውሀ ሀብቶችም አሉ። "የአፍሪካ የውሀ ሀብት ማማ" እየተባለች የምትሞካሸው ኢትዮጵያ ሀይቆቿን መጠበቅ እንደተሳናት የዘርፉ ባለሙያዎች በተደጋጋሚ ይናገራሉ። ይህ ሀይቅ ሊጠፋ ነው፤ ያ ሀይቅ ሊከስም ይህን ያህል ዓመት ቀርቶታል የሚሉ ዜናዎች መስማትም እየተለመደ መጥቷል። ሀይቅ ለማለት የማያስደፍሩ "ሀይቆች" አብጃታ ሻላ ሀይቅ ብሔራዊ ፓርክ ከተለያዩ አህጉሮች ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ስደተኛ አእዋፋት መገኛ ነበር። ቱሪስቶች ከሚያዘወትሯቸው ፓርኮች አንዱ ሲሆን፤ እንደ ፍላሚንጎ ያለ ወፍን ጨምሮ የተለያዩ እንስሳት መኖሪያ ነው። የአቢጃታ መጥፋት ብዝሀ ሕይወት ላይ ከሚያሳድረው ተጽእኖ ባሻገር የቱሪስት ፍሰት ሲቀንስ ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖም ይኖረዋል። የተለያዩ የኢትዮጵያ ሀይቆች ህልውና ለምን አስጊ ሆነ? ስንል የብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የደንና ግጦሽ መሬት፤ እጽዋት ብዝሀ ህይወት ዳይሬክተር ዶ/ር ዴቢሳ ለሜሳን ጠይቀን ነበር። • ክፍል 1 ፡በፅኑ የታመመው የዓባይ ወንዝ እሳቸው እንደሚሉት፤ እንደ አቢጃታ፣ ጨለለቃ፣ ዝዋይ ያሉ ሀይቆች አሳሳቢ ደረጃ ላይ ከደረሱባቸው ምክንያቶች አንዱ በሀይቆቹ ዙርያ ግብርና መካሄዱ ነው። የእርሻ ሥራ እንደናይትሮጂን፣ ፎስፈረስ ያሉ ንጥረ ነገሮችን ከመውሰዱ በመጨማሪ ደለልም ይፈጥራል። ሀይቅን ጨምሮ ሌሎችም የውሀ አካላት ሲጠፉ አሳ፣ የተለያዩ እጽዋትና አዕዋፍትም ይመናመናሉ። "ውሀማ አካላትን ከግምት ያላስገቡ ኢንቨስትመንቶች አንድ የችግሩ መንስኤ ናቸው። ስምጥ ሸለቆ ውስጥ ያሉትን እንደ አቢጃታ ያሉት ሀይቆች በዚህ ተጎጂ ናቸው። አቢጃታ ሻላ አካባቢ የሶዳ አሽና የአበባ ፋብሪካዎች አሉ" ይላሉ። የፋብሪካዎች ተረፈ ምርት በአግባቡ አለመወገዱ ወደ ውሀ አካል ከሚለቀቀው ኬሚካል ጋር ተደማምሮ የውሀ አካላት ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል። ዶ/ር ዴቢሳ እንደ ማሳያ በሚጠቅሱት ጨለለቃ ሀይቅ አካባቢ የጀልባ መዝናኛ ነበር። አሁን ግን ግብርና በመስፋፋቱ የውሀ ሀብቱ እየጠፋ ሰለሆነ ወደ አካባቢው ለመዝናናት መሄድ አይታሰብም። "ተፈጥሮ ላይ ሊደርስ ስለሚችለው ተጽዕኖ ተገቢው ጥናት ሳይደረግ የሚሠሩ መንገዶችና ድልድዮች እንስሳትና እጽዋት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራሉ" ይላሉ ዳይሬክተሩ። ምን ተጽዕኖ አሳደረ? የውሀ አካላት መጥፋት ተፈጥሯዊ፣ ማኅበራዊ፣ ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ ያሳድራል። ሀይቅና ሌሎችም የውሀ አካላት መጥፋታቸው ለአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ከሆኑት መካከል አንዱ ነው። አብዛኛው የመሬት ክፍል ውሀ እንደመሆኑ፤ የውሀ አካል ሲጠፋ ለእንስሳትና እጽዋት ብቻ ሳይሆን ለሰው ልጆች ህልውናም ስጋት ይሆናል። አሁን እያገገመ እንደሆነ የሚነገርለት ሀሮማያ በጠፋበት ወቅት ያነጋገርናቸው የሀሮማያ አካባቢ ነዋሪዎች የሀይቁ መጥፋት በእለት ከእለት ህይወታቸው ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ ገልጸውልን ነበር። • ወንዶች የማያወሯቸው አምስት አሳሳቢ ነገሮች በድሪ የሱፍ የተባሉ የአካባቢው ነዋሪ አሳ ማስገር እንዲሁም አትክልትና ፍራፍሬ ማምረት መቸገራቸውን ነግረውን ነበር። በውሀ እጥረት ምክንያት የቀንድ ከብቶቻቸውን እንዳጡ፤ አካባቢውን ለመጎብኘት ከጅቡቲ እና ሌሎችም አካባቢዎች ይሄዱ የነበሩ ቱሪስቶች ፍሰት መቋረጡንም ተናግረዋል። በአካባቢው የሚመረተው ሀረር ቢራና የሀሮማያ ዩኒቨርስቲ ሀሮማያ ሀይቅን መጠቀማቸው ሀይቁ ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገረውም ነበር። እንክብካቤና ጥበቃ ካልተደረገለት ሊጠፋ ተቃርቧል የተባለው አቢጃታ ሀይቅም ተመሳሳይ ስጋት አለበት። ይህም ተፈጥሮውን ተከትⶀ የሚመጣውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ማጣት ነው። ዶ/ር ዴቢሳ የውሀ አካላት የማኅበረሰቡ ባህላዊ ሥነ ሥርዓቶች የሚከናወናወኑባቸው መሆናቸውን የሚናገሩት እንደ እሬቻና ጨንበላላ ያሉ ሥርዓቶችን በማጣቀስ ነው። የሀይቆች ጉዳይ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች መነጋገሪያም ነው። ምን መደረግ አለበት? ዶ/ር ዴቢሳ እንደሚሉት፤ ሀይቆችን ጨምሮ የውሀ ሀብቶች የሚጠበቁበት ግልጽ መርህ ያስፈልጋል። "አሁን እንደ ፖሊሲ ያለው እንደመስኖና ኢነርጂ፣ ግብርና፣ ደን ልማት ባሉ ዘርፎች ነው። ራሱን የቻለ የውሀ ክፍልን የሚያስጠቅ ሕግ ያስፈልጋል" ይላሉ። የውሀ ሀብት ጥበቃ በተለያዩ ዘርፎች ተበታትኖ የሚሠራ ሳይሆን በአንድ ተቋምና በወጥ መርህ የሚመራ መሆን እንዳለበት ያስረጋጣሉ። አሁን ላይ የውሀ ሀብት ላይ ያተኮረ ፖሊሲ ተረቆ እስከሚጸድቅ እየተጠበቀ ይገኛል። በአንድ አካባቢ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ሲካሄድ ከጀርባው ባሉ ተቋማት መካካል መናበብ ሊኖር እንደሚገባ ይናገራሉ። ኃይል ሲመነጭ ውሀ የሚጠፋ ከሆነ፤ መንገድ ሲሠራ ዛፍ የሚቆረጥ ከሆነ ከጥቅሙ ጉዳቱ እያመዘነ ይሄዳልና። • እናት አልባዎቹ መንደሮች ዶ/ር ዴቤሳ ሀይቆች ከተጋረጠባቸው አደጋ መውጣት የሚችሉት ሀገር አቀፍ ፖሊሲ ሲጸድቅና ተቋሞች ሲናበቡ ነው ሲሉ፤ አቶ ባንኪ በበኩላቸው ማኅበረሰቡ የተፈጥሮ ሀብቱን መንከባከብ እንዳለበት ይናገራሉ። እሳቸው የሚያስተዳድሩት የአቢጃታ ሻላ ፓርክ አቅራቢያ ያለው ማኅበረሰብ ደን እንዳይጨፈጭፍና ከብቶች እንዳያሰማራ እንዲሁም ወጣቶች አካባቢውን እንዲያለሙ የጀመሯቸው እንቅስቃሴዎች ፍሬያማ ካልሆኑም አቢጃታን ዳግም አናየው ይሆናል።
news-48174989
https://www.bbc.com/amharic/news-48174989
ቦይንግ አደጋው ከመድረሱ ከዓመት በፊት ችግሩን አውቅ ነበር አለ
አውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ሁለቱም 737 ማክስ አውሮፕላኖች ላይ አደጋ ከማጋጠሙ አንድ ዓመት በፊት ችግር እንደነበረባቸው ያውቅ እንደነበርና ምንም እርምጃ አለመውሰዱን አመነ።
ድርጅቱ እንዳስታወቀው አውሮፕላኖቹ ችግር እንዳለባቸው ባወቀ ጊዜ የጥንቃቄ ስርዓቶችን ከመዘርጋት ይልቅ የአደጋ ጊዜ መጠቆሚያ መተግበሪያዎችን ብቻ ነበር ያዘጋጀው። ይህ እርምጃም አውሮፕላኖቹ ላይ ምንም ችግር አልፈጠረም ብሏል። 149 መንገደኞችንና 8 የበረራ ሰራተኞችን አሳፍሮ ወደ ናይሮቢ ይጓዝ የነበረው ET 302 ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ከቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ከተነሳ ከ6 ደቂቃዎች በኋላ ከአብራሪዎቹ ጋር ይደረግ የነበረው ግንኙነት ተቋርጦ ቢሾፍቱ አካባቢ አውሮፕላኑ የመከስከስ አደጋ ማጋጠሙ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። ይህንን ተከትሎም 387 የሚሆኑ ቦይንግ ማክስ 737 አውሮፕላኖች በመላው ዓለም ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ታግደዋል። ባለፈው ጥቅምት ወርም የኢንዶኔዢያ ላየን አየር መንገድ ንብረት የሆነ ተመሳሳይ አውሮፕላን ለበረራ ከተነሳ ከደቂቃዎች በኋላ በከፍተኛ ፍጥነት ቁልቁል ወደ ባህር በመከስከሱ የ189 ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል። • ''አብራሪዎቹ ትክክለኛው መመሪያ ተከትለዋል'' • አደጋው የደረሰበት ቦይንግ 737 የገጠመው ምን ነበር ? ቦይንግ ለችግሩ መፍትሄ የሚሆነውን አሰራር በመላው ዓለም ተግባራዊ ለማድረግ አስቦ የነበረ ቢሆንም አውሮፕላኖቹን ለአየር መንገዶች ማስረከብ እስከሚጀመርበት ሰዓት ድረስ አለማጠናቀቁን አምኗል። አየር መንገዶችም አውሮፕላኖቹን ከገዙ በኋላ እንደገና አዲሱን የመተግበሪያ ስርዓት እንዲገዙ ሆኗል። ችግሩንም በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመፍታት የማሻሻያ ሥራ እየሰራሁ ነበር ብሏል ቦይንግ። ሁለቱም 737 አውሮፕላኖች ላይ አደጋ ከማጋጠሙ ከወራት በፊት ችግር እንዳለባቸው ባውቅም፤ አደጋው ያጋጠማቸው በዚሁ ችግር ምክንያት ነው የሚለው ግን ገና በምርመራ የሚታወቅ ነው ብሏል። የበረራ መረጃ መቅጃው የያዘው መረጃ እንዳሳየው አውሮፕላኑ የተሳሳተ ማዕዘን ጠቋሚ (አንግል ኦፍ አታክ ሴንሰር) ግብዓት ስለነበረው የደህንነት መቆጣጠሪያ ሥርዓቱ (ኤምካስ) ሥራውን እንዲያከናውን ማድረጉ የፓይለቶቹ ጥፋት አይደለም፤ ይህ ደግሞ የሆነው ፓይለቶቹ ሊያጋጥም ስለሚችለው አደጋ ከቦይንግ ሊሰጣቸው የሚገባውን የማሻሻያ ስርዓት አለማግኘታቸውን ያመላክታል። • አደጋው ስፍራ በየቀኑ እየሄዱ የሚያለቅሱት እናት ማን ናቸው? • "የሞተው የኔ ያሬድ ነው ብዬ አላሰብኩም" የካፕቴን ያሬድ የ11 አመት ጓደኛ በተሳሳተ መረጃ ኤምካስ (ማኑቬሪንግ ካራክተሪስቲክስ ኦጉመንቴሽን ሲስተም) አክቲቬት እንዳይሆን የተሻሻለ ሶፍትዌር እያዘጋጀ እንደነበረና፣ ለአብራሪዎች ስልጠና እና 737 ማክስን በተመለከተ የሥልጠና ፕሮግራሞችን እንዳረቀቀ ገልጿል። አደጋዎቹም ይህንን ከማድረጉ በፊት መከሰታቸው አሳዛኝ አጋጣሚ ቢሆንም አሁንም ቢሆን አደጋው ከዚህ ጋር ይያያዝ አይያያዝ የታወቀ ነገር የለም ብሏል በመግለጫው። የአሜሪካው የፌደራል አቪዬሽን ቁጥጥር ባለስልጣን በበኩሉ ቦይንግ ስለችግሩ የኢንዶኔዢያው አየር መንገድ አውሮፕላን ከተከሰከሰ አንደ ወር በኋላ ነው ያሳወቀኝ ብሏል። ባለስልጣኑ ችግሩን እንደ አነስተኛ ችግር ቢመድበውም ቦይንግ ቀደም ብሎ ማሳወቁ ግን አደጋዎችን ለመከላከል ይጠቅሙ ነበር ብሏል።
news-54730313
https://www.bbc.com/amharic/news-54730313
በሶማሊያ ፀረ-ፈረንሳይ ሰልፍ ተካሄደ
በሶማሊያ በርካታ ከተሞች ፈረንሳይንና ፕሬዚዳንት ማክሮንን የሚያወግዙ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሄዱ።
ሰልፉ ፈረንሳይ የነብዩ መሃመድ የካርቱን ምስል በማተሟ እንዲሁም ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ይህንኑ ደግፈው የሰጡትን አስተያየትም በተመለከተ የተደረገ የተቃውሞ ምላሽ ነው። በመዲናዋ ሞቃዲሾ የተቃውሞ ሰልፈኞቹ ዋና አውራ ጎዳናዎችን ከመዝጋት በተጨማሪ መፈክሮችን እያሰሙ እንዲሁም የፈረንሳይን ሰንደቅ አላማን በመርገጥና በመቃጠል ተቃውሟቸውን ገልፀዋል። አንደኛው ተቃዋሚ ሂላል አብዱራህማን ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደተናገረው በእንደዚህ አይነት የተቃውሞ ሰልፍ ሲሳተፍ የመጀመሪያው መሆኑን ነው። አክሎም በዚህ የተቃውሞ ሰልፍ ባይሳተፍ "በራሱ ያፍር" እንደነበር ገልፆ ማክሮን ላይ የተሰማውን ንዴትም መግለፅ እንደነበረበት አበክሮ ተናግሯል። "ማክሮን ነብያችን መሃመድ እንዲሰደቡ ድጋፍ አድርገዋል። ነብያችን ከፍ ያድርጋቸውና" ብሏል። ሌላኛው ተቃዋሚ አህመድ ሼክ ሚሬም በበኩሉ "ማክሮን በርካታ የእስልምና እምነት ተከታዮችን ቆስቁሰዋል፤ በአሁኑ ወቅት አማኙም በፈረንሳይ ላይ ያለውን ቁጣ በመግለፅ ላይ ነው። ይሄ ሁሉ የማክሮን ስራ ነው" ብሏል። በሶማሊያ ብቻ ሳይሆን በርካታ የእስልምና እምነት ተከታዮች ባሏቸው አገራትም ፕሬዚዳንት ማክሮን በሰጡት አስተያየት ቁጣቸውን እየገለፁ ይገኛሉ። በርካታ የእስልምና እምነት ተከታዮች ባሉዋቸው ባንግላዴሽ፣ ኩዌት፣ ዮርዳኖስና ሊቢያ በመሳሰሉት አገራትም የፈረንሳይ ምርቶችን አንገዛም በሚል የማእቀብ ጥሪ ተደርጓል። ውዝግቡ በተለይ የተጧጧፈው የነብዩ መሃመድን ካርቱን በክፍል ውስጥ በማሳየቱ በአሰቃቂ ሁኔታ ተቀልቶ የተገደለው ፈረንሳያዊው መምህርን ተከትሎ ፕሬዚዳንቱ ባደረጓቸው ንግግር ነው። ፕሬዚዳንት ማክሮን መምህር ሳሙኤል ፓቲ "የተገደለበት ምክንያት የእስልምና እምነት ተከታዮች የወደፊቱ እጣ ፈንታችንን መቆጣጠር ስለሚፈልጉ ነው። ፈረንሳይ ካርቱኗንም ቢሆን አሳልፋ አትሰጥም" ብለዋል። የነብዩ መሃመድን ምስል በየትኛውም ሁኔታ ማሳየት በእስልምና እምነት ነውርና አፀያፊ ተደርጎም ይቆጠራል። ሆኖም ፈረንሳይ ከእምነት ውጭ ያለ አገዛዝን እንደመከተሏ መጠን የመናገር ነፃነትን የሚቀለብስ ነው ነው በማለትም ትከራከራለች።
news-53813969
https://www.bbc.com/amharic/news-53813969
ማሊ፡ በማሊ መፈንቅለ መንግሥት ተደረገ
የማሊ ፕሬዝዳንት ኢብራሒም ባውባካር ኬታ ‹‹ሥልጣን ለቅቂያለሁ፣ ፓርላማውንም በትኛለሁ፤ ይህን የማደርገው ደም አይፍሰስ ብዬ ነው›› ብለዋል በብሔራዊ ቴሌቪዥን ቀርበው፡፡
ፕሬዝዳንት ኬታ ለ2ኛ ጊዜ ምርጫ አሸነፍኩ ያሉት በ2018 ዓ.ም ነበር ፕሬዝዳንቱ ይህን የተናገሩት ባመጹ በገዛ ወታደሮቻቸው ከታገቱ በኋላ ነው፡፡ ‹‹እኔ ሥልጣን ላይ ለማቆየት ተብሎ ለምን ደም ይፈሳል?›› ፕሬዝዳንቱ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ባቦ በወታደሮች ታግተው ዋና ከተማዋ ባማኮ አቅራቢያ ወደሚገኝ የወታደር ካምፕ ውስጥ ተወስደዋል የሚሉ መረጃዎች ሲወጡ ነበር፡፡ አገሪቱ ላይ ትልቅ ተጽእኖ ያላት ፈረንሳይና የአካባቢው አገራት መፈንቅለ መንግሥቱን አውግዘዋል፡፡ ‹‹ዛሬ የተወሰኑ ታጣቂ ወታደሮች ሁኔታዎች እንዲለወጡ ጣልቃ ገብተው ካገቱኝ፣ የቀረኝ አማራጭ አለ ወይ?›› ብለዋል ፕሬዝዳንቱ ከታገቱበት ሆነው፡፡ በአገሪቱ ወታደሮች ዘንድ ከከፍያ መዘግየት ጋር በተያያዘ እንዲሁም ከጂሀዲስቶች ጋር በሚደረግ የተራዘመ ጦርነት ምክንያት መሰላቸትና ቁጣ እንደነበር ይነገራል፡፡ ማሊ ከፍተኛ የድህነት አዘቅት ውስጥ ከሚገኙ የአፍሪካ አገራት ተርታ ትመደባለች፡፡ ፕሬዝዳንት ኬታ ለ2ኛ ጊዜ ምርጫ አሸነፍኩ ያሉት በ2018 ዓ.ም ነበር፡፡ ሆኖም በጥቅሉ በተፍረከረከው መንግሥታዊ አስተዳደራቸው ላይ እንዲሁም በዛች አገር በተንሰራፋ ንቅዘት እና የኢኮኖሚ ድቀት ምክንያት በማሊ ሕዝብ ዘንድ ቅሬታ አድሮ ቆይቷል፡፡ ለዚያም ነው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተከታታይ ተቃውሞዎች ይደረጉ የነበረው፡፡ በኢማም መሐመድ ዲኮ የሚመራው አዲሱ የተቃዋሚዎች ጥምረት ሁኔታዎች እንዲሻሻሉ ሲጠይቅ ቆይቷል፡፡ መፈንቅለ መንግሥቱን ማን መራው? የካቲ ወታደራዊ ካምፕ ምክትል ኃላፊ ኮሌኔል ማሊክ ዳያው ከጥቂት ኮማንደሮች እና ከጄኔራል ሳዲዮ ካማራ ጋር በመሆን ነው ይህንን ስዒረ መንግሥት ያሳኩት ይላል የቢቢሲ አፍሪቅ ዘጋቢ አብዱል ባ ከባማኮ ባስተላለፈው ዘገባ፡፡ ካቲ ወታደራዊ ካምፕ የሚገኘው ከባማኮ 15 ኪሎ ሜትር ርቆ ነው፡፡ መጀመርያ ይህንን ካምፕ ከተቆጣጠሩ በኋላ ነበር ወታደሮቹ ወደ ዋና ከተማዋ ዘልቀው ፕሬዝዳንቱን ማገት የቻሉት፡፡ ወታደሮቹ ወደ ከተማው ሲጓዙ ሕዝብ አደባባይ ወጥቶ ድጋፉን ሲሰጣቸው ታይቷል፡፡ ማክሰኞ ከሰዓቱን የፕሬዝዳንቱን ቤት ሰብረው በመግባት ፕሬዝዳንቱንም ጠቅላይ ሚኒስትሩንም በቁጥጥር ሥር አድርገዋል፡፡ በአጋጣሚ ጠቅላይ ሚኒስትሩም በፕሬዝዳንቱ መኖርያ ቤት ነበሩ፡፡ የብሔራዊ ምክር ቤቱ አፈጉባኤ የሆኑት የፕሬዝዳንቱ ልጅ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩና የፋይናንስ ሚኒስትሩም በወታደሮቹ ታግተዋል፡፡ በዚህ የወታደሮች አመጽ ውስጥ ምን ያህል ወታደሮች ናቸው የተሳተፉት የሚለው ገና ምላሽ አላገኘም፡፡ የአፍሪካ ኅብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የወታደሮቹን ድርጊት አውግዘው የታገቱት ባለሥልጣናት በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጠይቀዋል፡፡ የምዕራብ አፍሪካ ኮሚኒቲ የትብብር መድረክ (ኢኮዋስ) በበኩሉ ሁሉም አባል አገራት ከማሊ ጋር ያላቸውን ድንበር እንዲዘጉ ወስኗል፡፡ ማንኛውም ገንዘብና የንግድ ትስስር ለጊዜው እንዲቆምም አዟል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ለዛሬ ጠርቷል፡፡ ማሊን በቅኝ የገዛቻት ፈረንሳይ መፈንቅለ መንግሥቱን ለማውገዝ የቀደማት የለም፡፡ የፈረንሳይ የመከላከያ ሚኒስትር የማሊ አማጺ ወታደሮች ወደ ካምፓቸው እንዲመለሱ ጠይቀዋል፡፡ ፈረንሳይ በሳሀል ክልል ጽንፈኛ ኢስላማዊ ሰርጎ ገቦችን ለማጥፋት በሚል በማሊ ወታደሮቿን አስፍራለች፡፡
news-53798540
https://www.bbc.com/amharic/news-53798540
ስፖርት፡ የታዋቂው ቅርጫት ኳስ ተጫዋች ማይክል ጆርዳን ጫማ በ23 ሚሊዮን ብር በጨረታ ተሸጠ
ታዋቂው የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ማይክል ጆርዳን የተጫማው ጫማ 615 ሺህ ዶላር (23 ሚሊዮን ብር በሚገመት) በጨረታ ተሸጧል።
በ23 ሚሊዮን ብር በጨረታ የተሸጠው የማይክል ጆርዳን ናይክ ኤይር ጆርዳን ስኒከር በዚህ ሳምንት በበይነ መረብ በነበረው ጨረታ ላይ ናይክ ኤይር ጆርዳን 1 የተባለው የስፖርተኛው ጫማ መሸጡም ተገልጿል። ጫማውም በቺካጎ ቡልስ ቡድን ይጫወት በነበረበት ወቅት በጎርጎሳውያኑ 1985 ያጠለቀው ነው ተብሏል። በዚህ ጫማም ወደላይ በመዝለል በርካታ ኳሶችን በመረቡ በማስቆጠርም በታሪካዊነቱ የተመዘገበ ነው። በርካታ ስፖርታዊና የስነ ጥበብ ጨረታዎችን በማካሄድ የሚታወቀው ክርስቲስ የተባለው ኩባንያ እስካሁን ድረስ ዘጠኝ የማይክል ጆርዳን ጫማዎችን ሸጧል። እነዚህ ጫማዎችም ማይክል ጆርዳን ለአስራ አራት አመታት የነገሰበትን የቺካጎ ቡልስ ቡድን ቆይታውን ለመዘከርም ነው። ጫማው ስታዲየም ጉድስ የተባለ የአሜሪካ ኩባንያ ንብረት ሲሆን፤ ከማይክል ጆርዳን ታሪካዊ ጫማዎች ውስጥ ምርጡም ነው ተብሏል። ሁሉም ጫማዎች ማይክልን ስፖንሰር ያደርገው በነበረው ናይኪ የአልባሳትና ጫማ አምራች ኩባንያ የተመረቱ ናቸው። ብርቅና ድንቅ የተባለውን ይህንን ጫማ ጨምሮ ሌሎች ጫማዎችን መሰብሰብ የሚፈልጉ ስላሉ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስም እየሸመቱ መሆናቸውንም ኩባንያው አስታውቋል። ከዚህ ጫማም በተጨማሪ በጎርጎሳውያኑ 1992 ኦሎምፒክስ ላይ አሜሪካን ለድል ያበቃትን ጨዋታ የተጫወተብትን ኤይር ጆርዳን 7 በ11 ሺህ 500 ዶላር (413 ሺህ ብር) ተሸጧል። ሌሎች ስብስቦችም እንዲሁ በ21 ሺህ 500 ዶላርና (772 ሺህ ብር)፣ 8 ሺህ 750 ዶላር (314 ሺህ) ለሽያጭ ቀርበዋል። በገበያው ላይ ያለው ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜም እየጨመረ መሆኑንም ኩባንያው አመላክቷል። በቅርጫት ኳስ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠው ማይክል ጆርዳን የቅርጫት ንጉስና ድንቅ ተጫዋችም ተብሎ ይሞካሸል። በአለም ስፓርትም ዘንድ ከፍተኛ ዝናን የተጎናፀፈው ማይክል በተለይም በጎርጎሳውያኑ 1980ዎቹና 90ዎቹ የቅርጫት ኳስ ስፖርትን በአለም አቀፉ መድረክ በማስተዋወቅ ረገድም ሚናን በመጫወቱም ስሙ ይወሳል። በቅርቡ በስፖርተኛው ህይወት ዙሪያ የሚያጠነጠነው 'ዘ ላስት ዳንስ' የሚል ርዕስ የተሰጠውም ተከታታይ ፊልም በኔትፍሊክስ መውጣቱን ተከትሎ የማይክል ጆርዳን ዝናም እንደገና እየተነሳ ይመስላል።
news-53148773
https://www.bbc.com/amharic/news-53148773
ታንዛኒያዊው ባሕላዊ ማዕድን አውጪ በአንድ ቀን ሚሊየነር ያደረገውን ማዕድን አገኘ።
ታንዛኒያዊው ባሕላዊ ማዕድን ቆፋሪ አንድ ላይ 15 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ ሁለት ግዙፍ ውድ የሆነውን ታንዛናይት ማዕድን በማግኘቱ በአንድ ቀን ሚሊየነር ሆነ።
ባሕላዊ ማዕድን ቆፋሪው ሳኒኑ ላይዘር ያገኘውን የከበረ ድንጋይ ይዞ ሁለቱ የከበሩ የማዕድን ድንጋዮች እስካሁን በቁፋሮ ከተገኙ መካከል ግዙፎቹ ሳይሆኑ እንደማይቀሩ ተገምቷል። አንዳንድ ምንጮች እንዳሉት እስካሁን የተገኘ ግዙፉ የታንዛናይት ማዕድን የሚመዝነው አራት ኪሎ ግራም የማይሞላ ሲሆን የተገኘውም ከ15 ዓመት በፊት እዚያው ታንዛንያ ውስጥ ነበረ። በሰሜናዊ ታንዛኒያ ነዋሪ የሆነው ባሕላዊ ማዕድን ቆፋሪ ሳኒኑ ላይዘር በቁፋሮ ያገኛቸው ሁለቱ የከበሩ ድንጋዮች 9.2 እና 5.8 ኪሎ ግራም በመመዘን ነው ክብረወሰኑን በመያዝ ግለሰቡንም ለሚሊየነርነት ያበቁት ተብሏል። ሳኒኑ እነዚህን የማዕድናት መቼ እንዳገኛቸው የታወቀ ነገር ባይኖርም ነገር ግን ዛሬ ለአገሪቱ መንግሥት የማዕድን ሚኒስቴር በአጠቃላይ በ7.8 ቢሊየን የታንዛንያ ሽልንግ ወይም በ3.43 ሚሊየን ዶላር ሸጧቸዋል። በሽያጩ ወቅት የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ ስልክ ደውለው ሳኒኑ ላይዘርን እንኳን ደስ ያለህ ብለውታል። ፕሬዝዳንቱ ጨምረውም "ይህ የባሕላዊ ማዕድን አውጪዎች ጥቅም ሲሆን ታንዛኒያም ምንያህል ባለጸጋ መሆኗን የሚያሳይ ነው" ብለዋል። ማጉፉሊ ወደ ስልጣን በመጡበት ጊዜ አገሪቱ ካላት የማዕድን ሃብት ተጠቃሚ እንደሚያደርጉና ከዘርፉ መንግሥት የሚያገኘው ገቢ ከፍ እንዲል እንደሚጥሩ ቃል ገብተው ነበር። ከሦስት ዓመት በፊት በዓለም ብቸኛው የታንዛናይት ማዕድን ማውጫ ነው የሚባለውን በሰሜናው የአገሪቱ ክፍል ከኪሊማንጃሮ ተራራ ግርጌ የሚገኘውን አካባቢ በጦር ሠራዊታቸው እንዲጠበቅ አድርገዋል። ታንዛናይት በምድር ላይ በብዛት ከማይገኙ ውድ ማዕድናት መካከል ሲሆን የፔኒሲልቫንያ ዩኒቨርስቲ በአካባቢው የሚገኝ የማዕድን ጥናት ባለሙያን ጠቅሶ እንዳለው ማዕድኑ በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ውስጥ ሊመናመንና ሊያልቅ ይችላል።
news-53740809
https://www.bbc.com/amharic/news-53740809
በአንድ ቀን የተወለዱ ልጆች በስሟ እንዲጠሩ ስለተደረገላት አትሌት ያውቃሉ?
ናዋል ኤል ሞውታዋኬል ሞሮኳዊት አትሌት ናት። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ነሐሴ 8፣ 1984 በሎስ አንጀለስ ኦሎምፒክ ድል ተቀዳጅታለች።
ማሸነፏ እጅግ ያስደሰታቸው ሞሮኳዊው ንጉሥ ሐሰን በእለቱ የተወለዱ ሴቶች ባጠቃላይ ናዋል ተብለው እንዲጠሩ ውሳኔ አስተላልፈዋል። ሰሞኑን 36ኛ ዓመት ልደታቸውን የሚያከብሩ የሞሮኮ ሴቶች ስማቸው ናዋል የመሆን እድሉ ሰፊ ነው። ናዋል በኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳልያ ያገኘች የመጀመሪያዋ ሞሮኳዊት ናት። በ400 ሜትር የመሰናክል ዝላይ ያሸነፈች የመጀመሪያዋ ሴትም ናት። በሎስ አንጀለሱ ኦሎምፒክ ላይ የተገኘች ብቸኛዋ ሞሮኳዊት ሴት ናዋል ነበረች። በኦሎምፒክ ታሪክ ድል የተቀዳጀች የመጀመሪያዋ ሴት አረብ አፍሪካዊትም ናት። የውድድሩ ተካፋይ የነበረው ሰዒድ አዊታ በ500 ሜትር ሩጫ ያሸነፈው ምናልባትም በናዋል ድል ተነሳስቶ ይሆናል። “ስለውድድሩ ሳስብ ሌሊቱን በሙሉ እንቅልፍ አልወሰደኝም” ናዋል ከውድድሩ አንድ ቀን በፊት ሲያቃዣት ነበር። መሰናክል ዘላ አንዳች ጉድጓድ ውስጥ እንደምትገባ ይሰማት እንደነበር ታስታውሳለች። “በጣም ፈርቼ ነበር። ብቸኛዋ ሞሮኳዊት ሴት ስለነበርኩ ሁሉም የቡድኑ አባላት ተስፋ ጥለውብኝ ነበር።” ውድድሩን ከማሸነፏ በፊት የነበረውን ምሽት እንዲህ ታስታውሰዋለች። “ስለ ውድድሩ ሳስብ ሌሊቱን በሙሉ እንቅልፍ አልወሰደኝም ነበር። ሲያቃዠኝ፣ ሲያልበኝ ስለነበር መተኛት አልቻልኩም። ዝግ ብዬ ስሮጥ ይታየኝ ነበር።” በችሎታዋ አምና በውድድሩ ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ ትፈልግ ነበር። “ያሰብኩት ከመጨረሻዎቹ ስምንት ተወዳዳሪዎች አንዷ እንደምሆን ነበር። አሰልጣኞቼ እንደማሸንፍ ስላሰቡ በራሴ እንድተማመን ደጋግመው ይነግሩኝ ነበር።” ናዋል እና አሰልጣኞቿ ከመጨረሻው ውድድር በፊት የሷና የተፎካካሪዎቿን ያለፉ ውድድሮች ቪድዮ ይመለከቱ እንደነበር ታስታውሳለች። የሷን ደካማና ጠንካራ ጎኖች ከተፎካካሪዎቿ ጋር ያነጻጽሩም ነበር። “ላሸንፍ ስለምችል ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ጠንካራ መሆን እንዳለብኝ ይነግሩኝ ነበር” ትላለች። ናዋል እንደምታሸንፍ ማመኗ የስኬቷ ሚስጥር ነበር። እራሷን “ያንቺ ጊዜ ነው። ድል ሊያመልጥሽ አይገባም” እያለችም ነበር። የናዋል አሜሪካዊት ጓደና ጁዲ ብራውንም የውድድሩ ተሳታፊ ነበረች። በእርግጥ የውድድሩ ተመልካቾች የ22 ዓመቷ ናዋል ደጋፊ አልነበሩም። ጋዜጠኞች ውድድሩን በአንክሮ ይከታተላሉ ነበር። ውድድሩ በይፋ ከመከፈቱ በፊት ናዋል በስህተት የጀመረች መስሏት ተደናግጣ ነበር። ኋላ ላይ ግን ተረጋጋች። “የመጀሪያውን፣ ሁለተኛውንና ሦስተኛውን መሰናክል በግራ እግሬ ዘለልኩ። ከዛ እስከ መጨረሻው ድረስ ቀኝና ግራ እግሬን መለዋወጥ ጀመርኩ።” ተፎካካሪዎቿን በቅርብ ርቀት ማየት ስላልቻለች ግራ ተጋብታ እንደነበር ታስታውሳለች። “ሌሎቹ ሯጮች የት ገቡ? ብዬ አሰብኩ። ለካ በጣም ቀድሜያቸዋለሁ። የመጨረሻውን ነጥብ ከማለፌ በፊት እኔ ብቻ እያለፍኩ መሆኑን ለማረጋገጥ ወደ ግራና ቀኝ ተመለከትኩ።” “አባቴ በቦታው ባለመኖሩ ከፍቶኝ ነበር” ናዋል ወርቅ ስታገኝ ጓደኛዋ ጁዲ ብራውን ብር አግኝታለች። “ሳሸንፍ በጣም ነው ደስ ያለኝ። ግን አባቴ በቦታው ባለመኖሩ ከፍቶኝ ነበር። ሁሌም ይደግፈኝ የነበረው አባቴ ከውድድሩ ከወራት በፊት ሕይወቱ አልፏል።” የናዋል ቤተሰቦች ስፖርት ወዳጅ ናቸው። አባቷ የጁዶካ ተጫዋች (እንደ ማርሻል አርት አይነት ውድድር) እናቷ ደግሞ መረብ ኳስ ተጫዋች ነበሩ። ናዋል ህልሟን እንድታሳካ ቤተሰቦቿ ይደግፏት ነበር። “ማሸነፌ ለአገሬ ትልቅ ዜና ነበር። ማንም ያልጠበቀው ድል ነው። አንዲት ታዳጊ ሞሮኳዊት ከምርጥ አትሌቶች ጋር ተፎካክራ አሸንፋ ወርቅ ታገኛለች ብሎ ማንም አላሰበም። በልቤና በአዕምሮዬ እስከወዲያኛው የሚኖር ታሪካዊ ቅጽበት ነው።” የናዋል ድል በወግ አጥባቂ አረብና ሙስሊም አገሮች ለሚኖሩ ብዙ ሴቶች በር ከፍቷል። “ከዛ በኋላ ብዙ ሞሮኳዊ ሴቶች አሸንፈዋል። በአልጄሪያ፣ ቱኒዚያ፣ ግብፅ እና ባህሬን የሚኖሩ ሴቶችም እንዲሁ። በኦሎምፒክስ ላይ ሴቶች አሳትፈው የማያውቁ አገሮች፤ ሴቶችን ለተሳትፎ ብቻ በቡድናቸው ከማካተት አልፈዋል። ሴቶች የሚካተቱት ለተሳትፎ ሳይሆን ለማሸነፍ ሆኗል” ትላለች አትሌቷ።
news-54137673
https://www.bbc.com/amharic/news-54137673
አውስትራሊያ፡ የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪው ከፖሊስ መኪና ጋር በመጋጨቱ በቁጥጥር ስር ዋለ
በአውስትራሊያ የአደንዛዥ ዕፅ አፀዋዋሪ ግለሰብ ከቆሙ የሁለት ፖሊሶች ጋር መጋጨቱን ተከትሎ በቁጥጥር ስር ዋለ።
ግለሰቡ ሜታምፌታሚንስ ወይም አይስ ተብሎ የሚታወቀውን አደንዛዥ እፅ በመኪናው ውስጥ ጭኖ ነበር። ሲሞን ቱ የተባለው ይህ ግለሰብ 260 ኪሎግራም ሜታምፌታሚንስ በመኪናው ውስጥ ይዞ የነበረ ሲሆን ድንገት መኪናውን ሲያዞርም ከፖሊስ መኪኖች ጋር ከአመት በፊት ተጋጭቷል። ግለሰቡ መኪኖቹን ገጭቶ እየተጣደፈ ለማምለጥ ቢሞክርም ፖሊሶች ተከታትለው በቁጥጥር ስር ያዋሉት ሲሆን መኪናው ውስጥም 95 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት እፅም አግኝተዋል። ስድስት አመት ተኩልም እስር ተፈርዶበታል። በቁጥጥር ስር በዋለበት ወቅትም መርማሪው ኢንስፔክተር ግሌን ቤከር ለሪፖርተሮች እንደተናገሩት "ፖሊስ በቀላሉ በአጋጣሚ በቀላሉ እጅ ከፍንጅ የያዘው አደንዛዥ እፅ አዘዋዋሪ" ብለውታል ሲሞን ቱ መኪኖቹን በቆሙበት በገጨበት ወቅት በአንደኛው ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሶበት ነበር። ከገጨ በኋላ ሳያቆም ዝም ብሎ ቢነዳም ሁኔታው በሲሲቲቪ ካሜራ በመቀረፁ እንዲሁም ምስክሮች ስለ መኪናው ዝርዝር መረጃ በመስጠታቸው ፖሊስ በቀላሉ በቁጥጥር ስር ሊያውለው ችሏል። ከአንድ ሰዓት በኋለም ሲሞን ቱን አግኝተውታል። ሲሞንም ምግብ እያደረሰ እንደሆነና መኪናውንም አላስፈትሽም በማለት ፀንቶ ነበር። መኪናው ውስጥ 13 ሳጥን ወይም 260 ኪሎ ግራም ሜታምፌታሚንስ ወይም አይስ ተብሎ የሚጠራውን አደንዛዥ እፅ ይዞ ነበር። ግለሰቡ ከፍተኛ ዕዳ እንደነበረበትና በየቀኑም የአልኮል መጠጥና ኮኬይንም ይወስድ እንደነበር ተገልጿል። ዳኛ ፔኑ ሃንኮክ አርብ እለት የእስሩን ብይን አሳልፈዋል። ዳኛው ውሳኔውን ባስተላለፉበትም ወቅት ምንም እንኳን ለጥፋተኛው ግለሰብ መጥፎ አጋጣሚ ቢሆንም ለህዝቡ ግን ጠቃሚ ነው ብለዋል። ሜታምፌታሚንስ በቅርብ አመታት በአውስትራሊያ ቢቀንስም መንግሥት ግን አደንዛዥ እፁ የሚያደርሰው ጉዳት ከአመት አመት እየጨመረ ነው ብሏል።
news-49102031
https://www.bbc.com/amharic/news-49102031
ስለ አቶ ዱቤ ጅሎ ሽልማት ምን እናውቃለን?
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ቴክኒካል ዳይሬክተርነት እያገለገሉ የሚገኙት አቶ ዱቤ ጅሎ ለኢትዮጵያዊ የመጀመሪያ ነው የተባለውን ሽልማት ሊያገኙ ነው።
የአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን (አይኤኤፍ) 'ቬተራን ፒን' የሚል ስያሜ ያለው ይህ ሽልማት ዜና ከአይኤኤፍ ፕሬዝዳንት ከጥቂት ቀናት በፊት እንደደረሳቸው አቶ ዱቤ ለቢቢሲ ገልፀዋል። •"ሥልጣን ለደም ግፊት አጋልጦኛል" ኃይሌ ገብረሥላሴ •በታላቁ ሩጫ ላይ የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች ላይ የአበረታች መድኃኒት ምርመራ ሊካሄድ ነው ይህንን ሽልማት ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያዊ አግኝቶት እንደማያውቅም አቶ ዱቤና ሌላ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተጠባባቂ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ብስራት ገልፀዋል። ሽልማቱ ከዚህ ቀደም አትሌት የነበሩና ለስፖርቱ ዕድገትና ልማት አስተዋፅኦ ላበረከቱ የሚሰጥ ሲሆን ከዚህም በፊት ኬንያዊው አትሌት ፖል ቴርጋት ተሸልሟል። የአፍሪካው አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን መርጦ ወደ ዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በመላክ የሽልማቱ ሂደት ይከናወናል። ሽልማቱ መስከረም ወር ላይ ዶሃ በሚዘጋጀው የአለም አቀፍ አትሌቲክስ ሻምፒዮን በመስከረም ወር የሚሰጥ ይሆናል። •ታይላንዳዊው ቦክሰኛ በውድድር ሳቢያ ሕይወቱ አለፈ ሽልማቱን ያገኙበት ምክንያት ሽልማቱ ዕውቅና መስጠት ነው የሚሉት አቶ ዱቤ "ከአስር አመታት በላይ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ እድገት አስተዋፅኦ ላደረግኩት የሚበረከት ነው። "በወቅቱም ውጤታማ አፈፃፀሞች ላሳየሁባቸው እውቅና መስጠት ነው" ብለዋል። በሽልማቱ መደሰታቸውን ገልፀው የበለጠ ለስራ እንደሚያነሳሳቸው ይናገራሉ። "ከዚህም ቀደም ቬተራን (የአንጋፋነት) ፒን የሚባል ሽልማት የተሸለመ ኢትዮጵያዊ እንደሌለ" የሚናገሩት አቶ ዱቤ ለአመታት የአትሌቶች ተወካይና ቴክኒካል ዳይሬክተር ሆነው ማገልገላቸው ለዚህ እንዳበቃቸው ገልፀዋል። ከአይኤኤፍ ፕሬዝዳንት ጆን ሪድጌዎን የተላከላቸው ደብዳቤም 'ለረዥም ጊዜ ለሽልማት የሚገባ ስራ በአትሌቲክሱ ስለሰሩ ሽልማቱ ተበርክቶላቸዋል' የሚል ነው። አቶ ስለሺ ብስራት በበኩላቸው "የተሸለሙት ፈጣን የሆነ ኮሚዩኒኬሽን ስላላቸው ነው" ብለዋል። "በጥሩ ዲፕሎማሲ ኢትዮጵያ የተመረጠች ሲሆን" ይህንን ደግሞ የሚመሩት አቶ ዱቤ ጅሎ መሆናቸውን አቶ ስለሺ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሁለቱም ኃላፊዎች ሽልማቱ ትልቅ እንደሆነ ይናገራሉ። አቶ ዱቤ በአሁኑ ወቅት በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ውስጥ የአትሌቲክስ ጥናት ውድድርና የአትሌቲክስ ልማት ይመራሉ። አቶ ዱቤ ጅሎ ማናቸው?
news-42771008
https://www.bbc.com/amharic/news-42771008
የአሜሪካ ምክር ቤት አባላት በበጀት ጉዳይ አልተስማሙም
እንደ አውሮፓውያኑ የ2018 የአገሪቱን በጀት በሚመለከት የአሜሪካ ሴኔት አባላት ስምምነት ላይ መድረስ ተስኗቸዋል። በአገሪቱ ሁሌም የበጀት ዓመት የሚጀምረው ጥቅምት አንድ ላይ ቢሆንም ሴኔቱ ስምምነት ላይ መድረስ ባለመቻሉ ይህ ቀነ ገደብ ተጥሷል።
የመንግሥት ተቋማትም በጊዜያዊነት ካለፈው ዓመት በተራዘመ በጀት ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል። አሁን ግን ቀነ ገደቡን መጠበቅ ባለመቻሉ የመንግሥት ተቋማት ከተዘጉ ሁለት ቀናት ተቆጥረዋል። ለዚህ ደግሞ ሪፐብሊካንና ዲሞክራቶች እርስ በርስ እየተወነጃጀሉ ነው። ትናንት በተደረገው የሴኔቱ ስብሰባ ስምምነት ላይ መድረስ ባለመቻሉ ንግግሩ እንደገና ወደ ሰኞ እኩለ ቀን ተላልፏል። ዲሞክራቶች ስምምነት ላይ መደረስ ካለበት ትራምፕ የስደት ጉዳይን በበጀቱ ውስጥ ታሳቢ ሊያደርጉ ይገባል ሲሉ፤ ሪፐብሊካን ደግሞ የመንግሥት ተቋማት ዝግ ሆነው እያለ ምንም አይነት ስምምነት ማድረግ አይቻልም ብለዋል። ትራምፕ የሴኔቱ አለመግባባት በአብላጫ ድምፅ እንዲፈታ ጥሪ አስተላልፈዋል። በሴኔቱ ደንብ በጀቱን የሚመለከተው አዋጅ ለመፅደቅ 60 ድምፅ ሊያገኝ ይገባል። ይህ ማለት ደግሞ ከሴኔቱ መቶ መቀመጫ 51ዱን የያዙት ሪፐብሊካን ይህ አዋጅ እንዲፀድቅ የተወሰኑ ዲሞክራቶች ድምፅ ያስፈልጋቸዋል። ትራምፕ ግን አብላጫ ድምፅ አለመግባባቱን ይቋጨዋል እያሉ ነው። እሳቸው የሰነዘሩት ይህ መፍትሄ ግን ብዙም ግልፅ አይደለም ተብሏል። አንድ ፓርቲ ማለትም ሪፐብሊካኖች ኮንግረሱንም ዋይት ሃውስንም ተቆጣጥረው እያለ የመንግሥት ተቋማት በበጀት አለመፅደቅ ሲዘጉ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። አርብ እለት የተካሄደው ድምፅ አሰጣጥ 50 ለ49 ነበር። ዲሞክራቶች በልጅነታቸው ወደ አሜሪካ የገቡ 700 ሺህ ስደተኞች ከአሜሪካ እንዳይባረሩ ከለላ እንዲሰጣቸው፤ ለዚህም በጀት እንዲመደብ ይፈልጋሉ። በበጀት ስምምነት ላይ የሚያስቀምጡት ዋና ቅድመ ሁኔታም ይህው ነው። በተቃራኒው ሪፐብሊካኖች ደግሞ ድንበርን በግምብ ማጠርን ጨምሮ ለድንበር ደህንነት በጀት እንዲመደብ፣ የአገሪቱ የስደተኞች ፖሊሲ ላይም ማሻሻያ እንዲደረግ ይፈልጋሉ። ለጦር ኃይልም የሚበጀተውም እንዲጨምር ይሻሉ።
news-50157403
https://www.bbc.com/amharic/news-50157403
ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን በቅርቡ በረራ ሊጀምር ነው
ቦይንግ የተሰኘው አውሮፕላን አምራች ኩባንያ 737 ማክስ በጎርጎሮሳውያኑ አዲስ ዓመት ወደ በረራ እንደሚመለስ አሳውቋል።
737 ማክስ በአንድ ዓመት ውስጥ ከተሰከቱ ሁለት አደጋዎች በኋላ ሰማይ ላይ እንዳይታይ እግድ ተጥሎበት ይገኛል። የአንዶኔዥያው ላየን ኤይር ንብረት የሆነው ማክስ 737 ተከስክሶ አሳፍሯቸው የነበራቸው 189 ሰዎች ማለቃቸው ይታወሳል። አደጋው በተከሰተበት ወቅት የኢንዶኔዥያ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች አደጋው አውሮፕላኑ ላይ በነበረ እክል ምክንያት ነው የተከሰተው ቢሉም ድርጅቱ እጄ የለበትም ማለቱ ይታወሳል። ድርጅቱ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ወደ ሰማይ እንዲመለስ ከፈቃድ ሰጭ አካላት ጋር በቅርብ እየሠራሁ ነው ብሏል። አስፈላጊውን ሥልጠና አዘጋጅቻለሁ የሚለው ቦይንግ ቀጣይ የጎርጎርያውን አዲስ ዓመት [2020] ከመግባቱ በፊት 737 ማክስ በረራ ሊጀምር እንደሚችል እምነት አለኝ ይላል። ባፈለው ዓመት ጥቅምት ነበር የላየን ኤይር ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን የተከሰከሰው። የአደጋውን ምክንያት ሲመረምሩ የነበሩ ግሰለቦች መካኒካዊ እና የዲዛይን ችግሮች ከበረራ መቆጣጠሪያው ጋር ተደባልቀው ነው አደጋው የተከሰተው ሲሉ መግለጫ አውጥተዋል። አደጋ መርማሪዎቹ አውሮፕላኑ ወደ ላይ ቀና እንዲል ወይም አፍንጫውን እንዲደፋ የሚያደርገውን ክስተት ለማስተካከል ተብሎ ቦይንግ የገጠመው ሥርዓት ነው ለአደጋው ምክንያት የሆነው ይላሉ። የላየን ኤይር አደጋ ሙሉ ዘገባ አርብ ዕለት ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል። ነገር ግን የአደጋው ተጠቂ ቤተሰቦች ስለ አደጋው ዝርዝር መረጃ ተሰጥቷቸዋል ተብሏል። ቦይንግ 737 ማክስ ከኢንዶኔዥያው አደጋ በኋላም ጥቅም ላይ እየዋለ ነበር። ነገር ግን ከጥቂት ወራት በኋላ ተመሳሳይ ባሕርይ ያለው አደጋ የኢትዮጵያ ንብረት በሆነ አውሮፕላን ላይ ደረሰ። ከዚህ አደጋ በኋላ ነው አውሮፕላኑ አገልግሎት እንዳይሰጥ የታገደው። የቦይንግ ነገር ገና ሳይበርድ ነው ታድያ የድርጅቱ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሆኑት ኬቪን ማክአሊስተር ከመንበራቸው የተነሱት። ማክአሊስተር የቦይንግ የንግድ አውሮፕላኖች ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል። • ቦይንግ 737 ወንዝ ውስጥ ገባ ቦይንግ በ737 ማክስ አውሮፕላን ሳቢያ ትርፌ በግማሽ ቀንሷል ሲል ተደምጧል። አልፎም የ787 ድሪምላይነር አውሮፕላን ምርቱን በግማሽ ለመቀነስ ወስኗል። የቢቢሲው ተንታኝ ቶም ባሪጅ ቦይንግ 737 ማክስ በቅርቡ በአሜሪካ ሰማይ ላይ ይታያል ብሎ መገመት ከባድ ነው ይላል። አሜሪካውያን ፈቃድ ሰጭዎች ይሁን ቢሉ እንኳ የአውሮጳ ተቆጣጣሪዎች በቀላሉ ፈቃድ ይሰጣሉ ማለት ዘበት ነው ሲል ይተነትናል።
news-55745102
https://www.bbc.com/amharic/news-55745102
ትግራይ፡ የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደና ጓደኛው በመቀለ ከተማ ተገደሉ
የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ የነበረው ዳዊት ከበደ አርአያ ወደ ሥራው ከተመለሰ ከቀናት በኋላ በመቀለ ከተማ ውስጥ ተገድሎ መገኘቱ ተዘገበ ።
ዳዊት ከበደ አርአያ የሥራ ባልደረቦቹ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የትግራይ ክልላዊ መንግሥት በሚያስተዳድረው ቴሌቪዥን ጣቢያ በጋዜጠኝነት ይሰራ የነበረው ዳዊት ተገድሎ የተገኘው ረቡዕ ዕለት ጥር 12/ 2013 ዓ.ም በመኪና ውስጥ ነው። ከዳዊት ከበደም አርአያ በተጨማሪ አንድ ሌላ ጓደኛውም መቀሌ ውስጥ በምትገኝ አዲ ሃውሲ በምትባል ሰፈር መገደላቸውን ባልደረቦቹ ተናግረዋል። የቀይ መስቀል ሠራተኞች የዳዊትንና አብሮት የነበረውን ግለሰብ አስከሬን ካነሱ በኋላ በትግራይ ቴሌቪዥን ለሚሰሩ የሥረራ ባልደረቦቹ ማሳወቃቸውም ተጠቅሷል። ስለ ግድያው እስካሁን ድረስ ክልሉን ከሚያስተዳድሩት ባለስልጣናት የተሰጠ መረጃ የለም። አዲስ በተቋቋመው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የደኅንነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ዋልታ ሐረጎትን ስለ ጋዜጠኛው አሟሟት ቢቢሲ በጠየቃቸው ወቅት ምንም መረጃ እንደሌላቸውና፤ መረጃዎችን ሰብስበውና አጠናቅረው ይፋ እንደሚያደርጉም ቃል ገብተዋል። ስሜ አይጠቀስ ያለ አንድ የዳዊት የሥራ ባልደረባ ለቢቢሲ ትግርኛ እንደተናገረው ሁለቱ ግለሰቦች የተገደሉት በተተኮሰባቸው ጥይት ነው። ይህንን መረጃ ከአካባቢው የፀጥታና ደኅንነት ኃላፊዎች ማረጋገጥ አልተቻለም። ሁለተኛው የተገደለው ግለሰብ ማንነትንም በተመለከተ ቢቢሲ ባደረገው ማጣራት በትግራይ ቴሌቪዥን የሚሰራ ሌላ ጋዜጠኛ ወንድም መሆኑን መረዳት ችሏል። ወደ ሥራ መመለስ በትግራይ ክልል ወታደራዊ ግጭት በተፋፋመበት በኅዳር ወር ሥራ አቋርጦ እንደነበር የተነገረው ዳዊት ከበደ አርአያ በቅርቡ ወደ ሥራው ተመልሶ ነበር ተብሏል። የመከላከያ ሠራዊት መቀለን መቆጣጠሩን ተከትሎ ተቋርጦ የነበረውም የክልሉ ቴሌቪዥን ፕሮግራም ስርጭት መተላለፍ የጀመረ ሲሆን ሠራተኞቹም ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ ጥሪ አድርጓል። ዳዊት ወደ ሥራ ተመልሶ ቢሮ በገባበት ወቅት ተይዞ ለቀናትም ያህል በቁጥጥር ስር የነበረ መሆኑን አንድ በቴሌቪዥን ጣቢያ የሥራ ባልደረባው አሳውቀዋል። እስሩን በተመለከተ የአካባቢው ባለስልጣናት ያሉት ነገር ባይኖርም የሥራ ባልደረባው ግን ከመገደሉ በፊት ለሦስት ቀናት በእስር ላይ እንደነበረ ተናግረዋል። "የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳዳሪዎች የቀድሞ ጋዜጠኞችንና የካሜራ ባለሙያዎችን እያናገሩ ነበር። ካናገሩዋቸው ጋዜጠኞች መካከል አንዱ ዳዊት ነው" በማለትም ባልደረባው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከህዳር 19/2013 ዓ.ም ጀምሮ በመከላከያ ቁጥጥር ስር ባለችው መቀለ የምሽት ሰዓት እላፊ የተጣለ ሲሆን በዚያ ሰዓትም በከተማው ማንኛውም እንቅስቃሴ የተከለከለ ነው። ዳዊት ከበደ አርአያ ማን ነው? ዳዊት በትግራይ ቴሌቪዥን ተቀጥሮ ከመስራቱ በፊት ለበርካታ ዓመታት በብሔራዊው የቴሌቪዥን ጣቢያ ኢቲቪ ሰርቷል። ኢቲቪን ከለቀቀ በኋላ የራሱን የትግርኛ መፅሔት በማቋቋም ለበርካታ ዓመታት ፅሁፍ ሲያበረክት ነበር። በኋላም ባለፈው ዓመት እስከ ተዘጋበት ድረስ አዲስ አበባ በሚገኘው የትግራይ ቴሌቪዥን ቅርንጫፍ ውስጥ እያገለገለ ነበር። የአዲስ አበባ ቅርንጫፉን መዘጋት ተከትሎ መቀለ ወደሚገኘውም ዋና ጣቢያ በመመለስ በቴሌቪዥን ጣቢያው ሲሰራ ነበር። የሁለቱ፣ የዳዊትና አብሮት የነበረው ግለሰብ የሥርዓተ ቀብር በትናንትናው ዕለት ጥር 12/ 2013 ዓ.ም አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን ተፈፅሟል።
news-48724172
https://www.bbc.com/amharic/news-48724172
ኢትዮጵያ፡ በጂንስ የተሞሸሩት ጥንዶች
ኦልያድ ኤልያስ እና ቢፍቱ ኦላና ባሳለፍነው እሁድ ነበር የሠርግ ስነ ስርአታቸውን የፈጸሙት። ታዲያ በሰርጋቸው ዕለት ሙሽራዋ በቬሎ ቀሚስ አጊጣ ሙሽራውም ሙሉ ልብሱን ሽክ ብሎ አልነበረም የተሞሸሩት።
ኦልያድ እና ቢፍቱ ቃለ መሃላ ሲፈጽሙ ጥቅስ የተጻፈበት ተመሳሳይ ቲሸርትና የየራሳቸውን ጅንስ ሱሪ ነበር ሁለቱም ሙሽሮች የለበሱት። የተጠራ ዘመድ አዝማድም የለም፤ ጥቂት ጓደኞች ብቻ አጀብ አድርገዋቸዋል። • ቻይና ቅጥ ያጡ ሰርጎችን ልትቆጣጠር ነው • ቤተሰብና ጓደኛ የሚያከራየው ድርጅትበኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተሞሸሩት ጥንዶች ኦልያድና ቢፍቱ ምን አነሳስቷቸው ይሆን ? ኦልያድ እንደሚለው ከባለቤቱ ቢፍቱ ጋር ከድሮም ጀምሮ በዚሁ ጉዳይ ላይ ሲወያዩ ከባድ የሰርግ ድግስ አስፈላጊ አለመሆኑን ተስማምተዋል። ዋናው ምክንያታቸው ደግሞ ድል ያለ ሰርግ ለመደገስ ሲባል የሚወጣው ወጪ ለማስቀረትና ቤተሰብና ዘመድ አዝማድን ከድካም ለማዳን እንደሆነ ይናገራል። አክሎም ''ምንም እንኳን ዋና ሚዜ ሆኜ ባላውቅም አንድ ሁለቴ ሰርግ ሄጄ አውቃለሁ። ሰርጎች ላይ በማየው ነገርም ብዙም ደስተኛ አልነበርኩም። ሰዎች ተቸግረው ሲደግሱ ሳይ ለምን ይህን ያክል እላለሁ'' ይላል። የኦሊያድ እናት የሆኑት ወ/ሮ ዝናዬ ወዳጆ ደግሞ ልጃቸው ላገባ ነው ማለቱ ሳይሆን ያሳሰባቸው በዚህ ዓመት ትምህርት መጨረሱ ነው። እንደ እናት ጥቂት ጊዜ አረፍ ቢል ሳይሉ አልቀረም። ልጃቸው ግን ሊያገባ ወሰነ፤ ሰኔ ዘጠኝ 2011ዓ.ም ደግሞ ጋብቻው የሚፈፀምበት ቀን ሆኖ ተቆርጧል። ኦልያድ ሰኔ ዘጠኝ ማለዳ ከቤቱ ሲወጣ የሰርጉ ዕለት እንደሆነ ቢያውቅም ምንም የተለየ ነገር አላደረገም። ልክ እንደ ሌላ ጊዜው ወደ ቤተክርስቲያን በመሄድ የዕለቱን ትምህርት ተከታትሏል። ፕሮግራሙ ሲያልቅም ለምሳ ከወጣ በኋላ በቤተክርስቲያኒቱ የሚደረገውና ከ8 ሰአት ጀምሮ 10 ሰዓት የሚያልቀውን የወጣቶች ዝግጅት ለመከታተል ተመልሶ ሄደ። የወጣቶች ትምህርት እየተከታተለ ሳለም እጮኛው ቢፍቱ በቤተክርስቲያኑ ደረሰች። የቤተክርስቲያኑ አባቶችም ስለጉዳዩ ቀድመው ያውቁ ስለነበር በፕሮግራሙ መሃል አንደኛው የሃይማኖት አባት ጥንዶቹ ቃል ኪዳን እንዲፈጽሙ ካደረጉ በኋላ ወደ ዕለቱ ትምህርት ተመለሱ። ''በወቅቱ እኔ እና ባለቤቴ የለበስነው ቲሸርት ተመሳሳይ ነበር። ቲሸርቱ ጥቅስ የተጻፈበት ሲሆን ሌላ ለየት ያለ ምንም አይነት አለባበስ አልነበረም። እኔም ጂንስ ሱሪ ነበር ያደረግኩት።'' ''እኔና ባለቤቴ ስለሰርጉ ስነስርአት ቀድመን ስለተስማማን ምንም አለመግባባት አልተፈጠረም። እንደውም ከቤተሰብና ጓደኞች ትንሽ ጫና ነበር። ሁሉም ሰው በቀላሉ ሊቀበለን ፈቃደኛ አልነበረም'' በማለት ኦልያድ ስለሁኔታው ያስረዳል። • በሠርግ ዕለት ማታ በጉጉት የሚጠበቀው 'የደም ሸማ' • ሁለት እምነቶችን በአንድ ጣራ ለአስርታት ያሳደሩ ጥንዶች ወ/ሮ ዝናዬም የሀገርን ወግና ባህል በማሰብ የልጃቸው ሰርግ እንዲህ በጅንስ ብቻ መሆኑ፣ ወገን እንደሌለው በሰው አለመከበባቸውን መቀበል እንደከበዳቸው አልሸሸጉም። በኋላ ግን የልጆቹን ፍቅር በማየት ይሁንታቸውን ሰጡ። "ሠርጉ በእንዲህ አይነት ሁኔታ መከናወኑ፣ ዘመድ አዝማድ ባለመጠራቱ የተሰማኝ ቅሬታ የለም" ይላሉ። ሙሽሪት ቢፍቱ ኦላና በበኩሏ የእኛን ሰርግ ከተመለከቱ በኋላ እንደ ትምህርት ሊወስዱት የሚችሉ ይመስለኛል፤ እንደውም ድል ያሉ የሰርግ ድግሶች እየቀሩ የሚሄዱ ይመስለኛል ትላለች። ''ልክ ሰርግ ሲባል ወደ ጭንቅላታችን የሚመጣው ቬሎ ቀሚስና የወንዶቹ ሙሉ ልብስ መቅረት አለበት ብዬ አስባለሁ። የጋብቻው ዋና አካል ተደርጎ ባይታሰብ ጥሩ ነው። ለትዳር ምንም የሚጨምረው ነገር የለም።'' ስትል ለምን በሰርጋቸው ዕለት ቲሸርትና ሱሪ እንደለበሱ ታስረዳለች። ጓደኞችሽ ምን አሉሽ በሚል ለቀረበላት ጥያቄ ቢፍቱ ስትመልስ '' ከበፊትም ጀምሮ እነግራቸው ስለነበር አልተገረሙም። ግርግር የበዛበት ነገር እንደማልወድ ያውቁ ነበር።'' ብላለች። ኦልያድ እና ቢፍቱ በሰርጋቸው ዕለት ወዳጆቿ በሱሪና ቲሸርት የቨርግን እለት ማሳለፍ የሚለውን ሃሳብ ሲሰሙ አብዛኛዎቹ ደስተኛ እንዳልነበሩና ትንሽ እንደከበዳቸው አልሸሸገችም። ጓደኞቿ የባህል ልብስ ወይም ሌላ ለየት ያለ ነገር ጠብቀው እንደነበረም ታስታውሳለች። '' በቬሎ ደምቆ ከመሞሸሩ ይልቅ ከቤተክርስቲያን አባቶች ምርቃት አግኝቶ ሰርጌን ማሳለፍ ለእኔ ትልቅ ቦታ አለው። ጓደኞቼም ሰርጌን ከተመለከቱ በኋላ በጣም ደስ እንዳላቸውና ብዙ ትምህርት እንደወሰዱበት ነግረውኛል'' ብላለች። የሰርጋቸው ለየት የማለት ጉዳይ እንደዚህ የብዙ ሰዎችን ቀልብ ሊስብ እንደሚችል አለመገመታቸውን የምትናገረው ቢፍቱ ለየት ብሎ ለመታየት ብለው ያደረጉት ነገር አንዳልሆነ ገልጻለች። ከቤተሰብ ስለነበረባቸው ጫና ስታስረዳም '' በልጅነት አእምሮ አስባችሁት ነው፤ በኋላ ይቆጫችኋል'' ተብለው እንደነበር ትናገራለች። ብዙ የቤተሰብ አባላትና ዘመድ አዝማዶችም እኛ እንረዳችኋለን፤ ወጪውን በእኛ ጣሉት የሚል ሃሳብ ቢያቀርቡም ኦልያድ እና ቢፍቱ ግን አሻፈረኝ በማለት የሚያስቡትን አይነት ሰርግ ማከናወን ችለዋል።
news-57333179
https://www.bbc.com/amharic/news-57333179
ምርጫ 2013፡ ቦርዱ በተለያዩ ክልሎች መጪው ምርጫ የማይካሄድባቸውን ስፍራዎች አስታወቀ
ኢትዮጵያ ሰኔ 14/2013 ዓ.ም በምታደርገው አገር አቀፍ ምርጫ በተለያዩ ክልሎች ውስጥ ምርጫ የማይካሄድባቸውን ቦታዎች ዝርዝር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
ምርጫ ቦርድ ማክሰኞ ዕለት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በሶማሌና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ውስጥ ምርጫ የማይካሄድባቸው ቦታዎችን ዝርዝር ይፋ አድርጓል። በእነዚህ ስፍራዎች ምርጫ የማይካሄደው በጸጥታ ችግር ምክንያት የመራጮች ምዝገባ ባለመጀመሩ፣ የመራጮች ምዝገባ ተጀምሮ በመቋረጡና የመራጮች ምዝገባ ሂደት ላይ አቤቱታ የቀረበ መሆኑን ቦርዱ ከዚህ ቀደም ባወጣው መግለጫ አስታውቆ ነበር። ከዚህ በተጨማሪ ቦርዱ የመራጮች ምዝገባ ሂደቱ ላይ ጉልህ የአሰራር ችግር በማየቱ ማጣራት እንዲካሄድ የወሰነባቸው ቦታዎችም እንዲሁ ምርጫው እንደማይከናወን አስታውቋል። ከእነዚህም ውስጥ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቦርዱ ምርጫ አይካሄድባቸውም ያላቸው የምርጫ ክልሎች መተከል፣ ሺናሻ ልዩ፣ ካማሺ እና ዳለቲ ናቸው። በኦሮሚያ ክልል በሰባት ምርጫ ክልሎች ማለትም በቤጊ፣ በሰኞ ገበያ፣ አያና፣ ገሊላ፣ አሊቦ፣ ጊዳሚና ኮምቦልቻ ምርጫ የማይከናወንባቸው ሲሆን ፤ እነዚህ አካባቢዎች በፀጥታ ችግር የመራጮች ምዝገባ ያልተጀመረባቸው ናቸው። በአማራ ክልል ከዚህ ቀደም በፀጥታ ችግር ምክንያት የመራጮች ምዝገባ ያልተጀመረባቸው ስምንት የምርጫ ክልሎች ድምፅ መስጠት እንደማይከናወን ቢያሳውቅም በትናንትናው መግለጫ ምርጫ እንደማይካሄድ ተገልፃ የነበረችው ድልይብዛ ምርጫ ክልል ሰኔ 14 ምርጫ እንዲካሄድ መወሰኑን አስታውቋል። በክልሉ በማጀቴ፣ በአርጎባ፣ በሸዋሮቢት፣ በኤፌሶን፣ በጭልጋ አንድና በጭልጋ ሁለት፣ በላይ አርማጭሆ እንዲሁም በአንኮበር የምርጫ ክልሎች ድምፅ እንደማይሰጥ ገልጿል። ለዚህም ቦርዱ እንደ ምክንያትነት የጠቀሰው የአርጎባ ልዩ ምርጫ ክልል ላይ የሚመርጡ ዜጎች ለክልል ምክር ቤት በዚህ ምርጫ ክልል ድምፅ የሚሰጡ በመሆኑ እና በአካባቢው ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት ባለመመዝገባቸው ነው ብሏል። ቦርዱ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል በሰባት ምርጫ ክልሎች ምርጫ አይካሄድም ብሏል። በነዚህ ስፍራዎች ከፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ የመራጮች ምዝገባ እንዳልተጀመረም አስታውቋል። ከዚህ ቀደም ቦርዱ ባወጣው መግለጫ ቀይ አፈር መደበኛ፣ ሱርማ ልዩ፣ ዲዚ ልዩ፣ የምርጫ ክልሎች ድምፅ እንደማይሰጥ ያሳወቀ ሲሆን፤ በተጨማሪም ማጀት መደበኛ፣ ጉራፈርዳ፣ ሽኮ፣ና ቴፒ የምርጫ ክልሎችም በእለቱ ድምፅ ይሰጥም ብሏል። በሶማሌ ክልል በአሁኑ ወቅት 14 የምርጫ ክልሎች ላይ ድምፅ የመስጠት ሂደት ላይ ችግር አለ የሚል ሪፖርት ደርሶት በዚህም መሰረት ምርመራ እያደረገ መሆኑንም ቦርዱ አስታውቋል። አስራ አንዱ የምርጫ ክልሎች ምርመራ ላይ ያሉ መሆኑን ምርጫ ቦርዱ ገልፆ የመራጮች ምዝገባ ላይ መጠነ ሰፊ የአሰራር ችግር አለ በሚል የቀረበለትን ሪፖርት ለመገምገም አጣሪ ቡድን አሰማርቶ የማጣራት ተግባሩን ማከናወኑን በመግለጫው ላይ አስፍሯል። የአጣሪውን ቡድን ሪፖርት መሰረት በማድረግ ምርጫ የሚካሄድባቸውን የምርጫ ክልሎች እንደሚያሳውቅም ገልጿል። በመራጮች ምዝገባ ሂደት ላይ አቤቱታ የቀረበባቸው እና የማጣራት ሂደቱ ላይ የሚወሰኑ ተብለው በምርጫ ቦርዱ የተጠቀሱት አራቢ፣ ደግሃመዶ፣ ጎዴ፣ ጂግጂጋ 1፣ ጂግጂጋ 2፣ ቀብሪደሃር፣ ቀላፎ፣ ዋርዴር፣ ፊቅ፣ ገላዲንና ደገሃቡር ናቸው። የመራጮች ምዝገባ ሂደት በክልሉ የተቋረጠባቸው ደግሞ አይሻ፣ ኤረርና ሽን የምርጫ ክልሎች ናቸው። ግንቦት 28/2013 ዓ.ም ሊካሄድ ቀን ተቆርጦለት የነበረው ብሔራዊ ምርጫ፣ የመራጮች ምዝገባ እና ሌሎች ሥራዎች በተያዘላቸው ጊዜ ባለመጠነቃቀቸው የተነሳ ምርጫው ለሁለት ሳምንታት እንዲገፋ ሆኖ ሰኔ 14 እንዲካሄድ ተወስኗል። ኢትዮጵያ በየአምስት ዓመቱ የምታካሂደው ምርጫ መካሄድ የነበረበት ባለፈው ዓመት ቢሆንም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ምርጫው እንዲራዘም መደረጉ የሚታወስ ነው።
51009970
https://www.bbc.com/amharic/51009970
በስህተት የገባላቸውን አንድ ሚሊየን የመለሱት የመቀለ ነዋሪ
ከሰሞኑ በስህተት የተላከላቸው 1 ሚልዯን ብር ለባንኩ ወስደው ያስረከቡት የመቀለ ከተማ ነዋሪው ድርጊት ብዙዎችን አጀብ አሰኝቷል። የገንዘቡ ባለቤትም ገንዘቡን ተቀብሏል።
ነገሩ ወዲህ ነው። ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩት አቶ ደሳለኝ ብስራት ዕለተ ቅዳሜ ታኃሣሥ 18 አመሻሽ ላይ ቁጭ ባሉበት በተንቀሳቃሽ ስልካቸው አንድ መልዕክት ይደርሳቸዋል። ይህም 'አንበሳ ኢንተርናሸናል' ከተባለ የተላከ መልዕክት '1 ሚልዮን ብር ገብቶልሃል' ሲል ይነበባል። «ስህተት መሆኑ ገባኝ የአንበሳ ባንክ አካውንቴ አዲስ መሆኑን ሳስብ ነው። ሌላ አካውንት ቢሆን ሰው አድርጎልኛል ብዬ አስብ ነበር። አካውንቱ አዲስ ስለሆነ ግን ብዙ ሰው አያቀውም ተሳስተው ነው ብዬ ሰኞ ጥዋት ወደ ባንክ ቤት ሄድኩኝ።» ስህተቱ እንዴት ሊፈጠር ቻለ? ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የመርካቶ ነጋዴ ከአንድ ሌላ ቻይናዊ ጋር ባላቸው ውል መሠረት 1 ሚሊዮን ብር ለሌላ ግለሰብ መላክ ነበረባቸው። ቻይናዊው ብር የሚላክለትን ግለሰብ የሂሳብ ደብተር ቁጥርም ይሰጣቸዋል፤ እኝህ ግለሰብም እነደተባሉት ገንዘቡን ለመላክ ወደ አንበሳ ባንክ ያመራሉ። ባንክ ሲደርሱ ግን የተሰጣቸው የሂሳብ ደብተር ቁጥር እና የባለቤቱ ስም እሚመሳሰል አልነበረም። በግዜውም ጉዳዩን ለማጣራት የሞከሩት የገንዘቡ ላኪ ወደ ቻይናዊው አጋራቸው ደውለው ሁኔታውን ያስረዱታል። ነገር ግን ወከባ ውስጥ የነበረው ቻይናዊ አጋራቸው «እንግዲህ እኔ ስም ተሳስቼ ይሆናል እንጂ ቁጥሩስ ትክልል ነው ግድየለህም አስገባው» ይላቸዋል። አንድ ሚሊዮን ብሩም ዘሎ የአቶ ደሣለኝ አካውንት ወስጥ ዘው ማለት። የአንበሳ ባንክ የራጉኤል ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ መድሃንዬ ኪዳነ ከመቐለ ወደ ቅርንጫፋቸው ሲደወል «በወቅቱ እኛ የተሳሳትን መስሎን ነበር» ይላሉ። ሆኖም ብሩ የተላከበት ማስረጃ ሲታይ ምንም ስህተት የለም። ይሄኔ ለገንዘቡ ላኪ ደውለው ሁኔታውን እነደነገሯቸው ያስረዳሉ። ላኪው የመርካቶ ነጋዴ ሁኔታውን ሲሰሙ እግጅ እንደተደናገጡ ያወሳሉ። «ተጠቀምበትና ጠያቂ ከመጣ በኋላ ትመልሰዋለህ» ክስተቱን የሰሙ የአቶ ደሣለኝ ወዳጆች በሁኔታው አፋቸውን ሸፍነው ተገረሙ። ግማሹ መልካም ነገር ነው ያደረግከው ይለኛል፤ ግማሹ ደግሞ ምነው ደሣለኝ? የሚል አስተያየት ይሰጣቸዋል። «አውጥተህ አሰቀምጠው»፤ «ዝም ብለህ ተጠቀምበትና ጠያቂ ከመጣ በኋላ ትመልሰዋለህ» ያሏቸውም እነደነበሩ አልደበቁም። እሳቸው ግን «መመለስ ካለብኝ በጊዜ ነው መመለስ ያለብኝ ብዬ መልሽላሁ» ይላሉ። አቶ ደሳለኝ በምላሹ ምን አገኙ? አንበሳ ባንክ ለአቶ ደሣለኝ የምስጋና ደብዳቤ በመስጠት ለቅን ተግባራቸው እውቅና እንደሰጣቸው አቶ መድሃዬ ይናገራሉ። «የአቶ ደሳለኝ ተግባር ከአእምሮ በላይ ነው ብዙ ነገር በሚበላሽበት ዘበን» ሲሉ ክስተቱን ይገልፁታል። ተገልጋዮችም የሚልኩበትን የሂሳብ ደብተር ቁጥር በትክክል ከቻሉም የሂሳብ ደብተሩ ባለቤት ስም ከአባት እና አያት ጭምር ቢያውቁ መልካም ነው ሲል ምክር የጣል ያደርጋሉ።
news-56599701
https://www.bbc.com/amharic/news-56599701
ህዳሴ ግድብ፡ በኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ መካከል የሚደረገው ውይይት ሊጀመር ነው
በታላቁ የህዳሴ ግድም ዙሪያ በኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ መካከል የሚካሄደው ውይይት በመጪው ቅዳሜና እሁድ እንደሚጀመር ኢትዮጵያ አስታወቀች።
ኢትዮጵያ እየነባችው ባለው ግዙፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ የውሃ አሞላልና ቀጣይ ሂደት ላይ እየተጀመረ ሲቋረጥ የቆየው የሦስትዮሽ ድርድር ለረጅም ጊዜ ከተስተጓጎለ በኋላ ነው አሁን እንደሚቀጥል የተነገረው። የኢትዮጵያ ውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር የሆኑት ስለሺ በቀለ (ዶ/ር፣ ኢንጂ) በትዊተር ሰሌዳቸው ላይ እንዳሰፈሩት በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ የሚደረገው ውይይት በቅርቡ የአፍሪካ ሕብረትን የሊቀመንበርነት ቦታን ከደቡብ አፍሪካ የተረከበችው ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ትመራዋለች። ከሊቀመንበሩ ለሦስቱ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እንዲሁም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስተሮች በቀረበ ግብዣ መሰረት ውይይቱ እንደሚጀመር ሚኒስትር ስለሺ ገልጸዋል። በውይይቱ ላይ ከሦስቱ አገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት በተጨማሪ የአፍሪካ ሕብረት ባለሙያዎች፣ ታዛቢዎችና ሌሎች ባለሙያዎች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ይጠበቃል። ሚኒስትሩ በትዊተር መልዕክታቸው ላይ ኢትዮጵያ በተፋሰሱ አገራት ላይ የጎላ ጉዳትን በማያስከትል ሁኔታ በመርህ ላይ የተመሰረተ፣ ፍትሃዊና ምክንያታዊ የሆነ የውሃ አጠቃቀም እንዲኖር ቁርጠኛ ናት ብለዋል። አባይ ድንበር ተሻጋሪ ውሃ ነው፤ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ደግሞ ለኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት በጣም አስፈላጊ መሰረት ልማት ሲሆን ለተፋሰሱ የታችኛው አገራት ደግሞ ይህንን ውድ የተፈጥሮ ሃብት ለማልማትና በተሻለ ሁኔታ ለመጠቀም ያስችላቸዋል ብለዋል። ድርድሩ ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ ተቋርጦ የቆየ ሲሆን ምንም እንኳን ተቀባይነት ባያገኝም ሱዳንና ግብጽ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ዙር የግድቡን የውሃ ሙሌት ከመጀመሯ በፊት አሳሪና ሕጋዊ ስምምነት እንድትፈርም በተደጋጋሚ ሲጠይቁ ቆይተዋል። ጨምረውም ውይይቱን አሁን እየመራው ካለው የአፍሪካ ሕብረት በተጨማሪ ሌሎች ዓለም አቀፍ አደራዳሪዎች እንዲሳተፉበት ሲወተውቱ ቢቆይም፤ ከኢትዮጵያ በኩል ተቀባይነት ሊያገኝ አልቻለም። ግንባታው ከተጀመረ አስር ዓመታትን ያስቆጠረው ታላቁ የህዳሴ ግድም ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የተደረገበት ሲሆን ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ ለአገሪቱና ለአካባቢው አገራት ዋነኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ምንጭ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። የግብጽ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አልሲሲ ባለፈው ማክሰኞ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ እየገነባችው ባለው ግድብ ሳቢያ አገራቸው በምታገኘው የውሃ መጠን ላይ ተጽእኖ የሚፈጠር ከሆነ 'የከፋ አካባቢያዊ ችግር' ይፈጠራል ሲሉ አስጠነቅቀው ነበር። ፕሬዝዳንቱ "ማንም ከግብጽ ውሃ ላይ አንዲት ጠብታ መውሰድ አይችልም፤ ይህ ከሆነ ደግሞ ከሚታሰበው በላይ አደገኛ አለመረጋጋት በአካባቢው ይፈጠራል" ብለዋል። ኢትዮጵያ ግድቡን የምትጠቀመው ውሃውን በግዛቷ ውስጥ ለሚያስቀሩ ፕሮጀክቶች እንዳልሆነ በተደጋጋሚ ብታስረዳም ሱዳን በተለይም ግብጽ የትኛውም አይነት በውሃው ላይ የሚከናወን ሥራ የእነሱን ይሁንታ ሳያገኝ መካሄድ እንደሌለበት ሲገልጹ ቆይተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ በአገሪቱ ምክር ቤት ላይ ባደረጉት ንግግር "ውሃ አሞላሉን በተመለከተ ተደራድረን ስናበቃ እንሙላ ካልን ክረምቱ ያልፍና በዓመት 1 ቢሊየን ዶላር እናጣለን" ሲሉ የውሃ ሙሌቱን ማዘግየት እንደማይቻል አመልክተዋል። የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር የሆኑት ስለሺ በቀለም (ዶ/ር፣ ኢንጂ.) ኢትዮጵያ ወደ መጠናቀቁ የተቃረበውን የህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በምንም ዓይነት መልኩ እንደማታራዝመውና ለዚህም የሚያበቃ አሰራርና ምክንያትም እንደሌለ ተናግረዋል። ይህ በአፍሪካ ትልቁ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ይሆናል የተባለው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣ በአሁኑ ጊዜ 80 በመቶ ያህሉ ግንባታው የተጠናቀቀ ሲሆን በሚቀጥለው ዓመት በተወሰነ ደረጃ ኤሌክትሪክ ማመንጨት እንደሚጀመር ይጠበቃል። የአባይ ወንዝን 85 በመቶ ያህሉን ውሃ የምታመነጨው ኢትዮጵያ አስካሁን ድረስ የረባ ጥቅም ሳታገኝ የቆየች ሲሆን ግብጽና ሱዳን ግን ሙሉ ለሙሉ በሚባል ሁኔታ የአባይ ወንዝን ለተለያዩ ግልጋሎቶች እያዋሉት ይገኛሉ። በዚህም ሳቢያ በአባይ ወንዝ ውሃ ላይ ጥገኛ የሆነችው ግብጽ፣ ግድቡ በሚደርሳት የውሃ መጠን ላይ ከፍተኛ መቀነስን ያስከትላል በማለት ስጋቷን በይፋ ስትገልጽ ቆይታለች።
47439065
https://www.bbc.com/amharic/47439065
"ሲጀመርም መጠለያው መንግሥትና ህዝብ ሳይግባቡ የተሰራ ነው" የላሊበላ ከተማ ከንቲባ
ለላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት የተሰራው የአደጋ መከላከያ መጠለያ ራሱ ለቅርሱ አደጋ ሆኗል በማለት የከተማዋ ነዋሪዎች በተለያየ ጊዜ ቅሬታቸውን ለመንግሥት አቅርበዋል። በጥቅምት ወር 2011 ዓ.ምም ከከተማዋ የተወጣጣ ኮሚቴ ም/ጠ/ሚ/ር ደመቀ መኮንን ድረስ በመሄድ ይህንኑ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
በወቅቱ ም/ጠቅላይ ሚንስትሩ ጥቅምት ወር ሳያልቅ የገቢ ማሰባሰቢያ መድረክ ተዘጋጅቶ መጠለያውን ለማንሳትና ጥገናውን ለማከናወን የሚጠበቀውን 300 ሚሊዮን ብር እንደሚሰበሰብ ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል። •ያልታበሰው የላሊበላ እንባ •ኢትዮጵያ ሳተላይት ማምጠቅ ለምን አስፈለጋት? በሳምንታት ልዩነት ደግሞ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ በስፍራው በመገኘት መንግሥት ቅርሱን እንደሚጠግን ለነዋሪዎቹ ቃል ገብተው ነበር። ይህን ተከትሎ ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ አወሮፓ ባመሩበት ወቅት ቅርሱ የሚጠገንበትን ድጋፍ ጠይቀው ከፈረንሳይ መንግሥት አዎንታዊ ምላሽ አግኝተዋል። ይሁንና የተሰራው ጊዜያዊ መጠለያ አንደኛ ምሰሶው የተተከለው የቅርሱ አለት ላይ በመሆኑ በነፋስ ሃይል በሚወዛወዝበት ጊዜ ቅርሱ እንዲሰነጠቅ እያደረገው ነው፣ ሁለተኛ መጠለያው ለአመታት የቆየ በመሆኑ ቅርሱ ዝናብና ጸሐይ ስለማያገኝ የቅርሱ ጣሪያ ወደ አፈርነት እየተቀየረ ነው፤ በአጠቃላይ ደግሞ የመጠለያው የአገልግሎት ዘመን ስላለቀ በቅርሱ ላይ ወድቆ አብያተ ክርስቲያናቱን ያወድማል የሚል ስጋት እንዳላቸው ነዋሪዎቹ በተደጋጋሚ ያነሳሉ። የላሊበላ ከተማ ከንቲባ ሙሉጌታ ወልደሚካኤል እንደሚሉት ደግሞ "መጠለያው ሲደረግ በሃላፊነት ስሜት ፣ በግልጸኝነት እና ህዝቡን ባሳተፈ መልኩ የተሰራ ባለመሆኑ በዘላቂነት ቅርሶቹን መታደግ አልተቻለም"። •ኢኮኖሚያዊ ተቃውሞና ያስከተለው ውጤት የባህልና ቱሪዝም ሚንስትሯ ዶር ሂሩት ካሳው ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ "የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት መንግሥት አስፈላጊውን ጥገና ለማድረግ እየሰራ ነው" ብለዋል። ላሊበላ ከ900 አመት በፊት በኢትዮጵያውያን ተሰርቶ አሁን ግን የአውሮፓውያንን እርዳታ እየሻተ ነው። ከ10 አመት በፊት አሁን ያሉት መጠለያዎች በጣሊያን ኩባንያ የተሰሩ ናቸው። እነዚህ መጠለያዎች የአገልግሎት ዘመናቸው ስላለፈ መነሳት የነበረባቸው ከአመታት በፊት ነው። መጠለያውን ለማንሳትና ጥገናውን ለማከናወን 300 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ የሃገር ውስጥ ባለሙያዎች አረጋግጠዋል። 'ኢትዮጵያ ግን ለላሊበላ የሚሆን 300 ሚሊዮን ብር የለኝም አለች'። እናም አሁንም የተማጽኖ እጆቿን ወደ አውሮፓ ዘርግታለች። ፈረንሳዮቹ ቃል ከገቡበት ጊዜ ጀምረው በትኩረት እየሰሩ ነው ያሉት ዶ/ር ሂሩት "ፈረንሳዮቹ በግላቸው የ10 አመት ጥናት ስለነበራቸው ለኛ አቅርበውልን ከሃገር ውስጥ ሙያተኞች ጥናት ጋር ተመሳሳይ በመሆኑ ቀጣይ ስራዎችን እየሰራን ነው" ብለዋል። •የማንነት ጥያቄዎች የጎሉበት የአማራ ክልል ከተሞች ሰልፍ ሁሉንም ስራ ባስቀመጡት እቅድ መሰረት እየሰሩ አንደሆነ የገለጹት ሚንስትሯ "የሚሰራው ስራ ቅርሱን መጠገንና መጠለያውን ማንሳት ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ መልክዓ ምድራዊ (landscape) ስራ ይሰራል" ብለዋል። ቅርሱ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ተፈሰሶችን መሰራት እና የአረንጓዴ አካባቢዎችን ከማልማት ባሻገር አጠቃላይ የቅርሱን ታሪክ የሚያትቱ መጽሃፋት የሚቀመጡበት ቤተ መጽሐፍ ግንባታን ያካተተ ስራ ይሰራል ነው ያሉት። የከተማዋ ነዋሪ አቶ ሃይለማርያም ታደሰ በስራው ደስተኛ መሆናቸውንና ከፈረንሳዮቹ ጋርም ውይይት አድርገው መስማማታቸውን ገልፀዋል። ነገር ግን የእሳቸውም የሌላውም ነዋሪ ፍላጎት መጠለያው ተነስቶ ማየት ነው። •ኢትዮጵያውያን ዛሬም ከአለት አብያተ-ክርስትያናትን ያንፃሉ ዶር ሂሩት እንደሚሉት ደግሞ "መጠለያው በመኖሩ ቅርሱ ለብዙ ጊዜ ዝናብና ጸሃይ ስላላየ መጠለያው ቶሎ ቢነሳ ጉዳት ሊኖር ስለሚችል ጥገናው እየተካሄደ ነው መጠለያው የሚነሳው" ብለዋል። ከንቲባው ሙሉጌታ በአሁኑ ወቅት ለቅርሱ የተሰጠው ትኩረት የሚያስደስት መሆኑን ተነግረዋል። ነገር ግን "በባለሞያዎች የተሰጠው መጠለያውን የማንሳት ጊዜ መራዘምና ህዝቡ ደግሞ አሁኑኑ እንዲነሳ ያለውን ፍላጎት ማጣጣም አለመቻሉ ግን ችግር ሆኖብናል" ብለዋል። መጠለያውን ማንሳት ብቻ በቂ መፍትሄ አይደለም የሚሉት ሚኒስትሯ ቅርሱ በዘላቂነት የሚጠገንበትን መንገድ እየተፈለገ እንደሆነና በተደጋጋሚ በሚነካካበት ወቅት ችግሩ እየተባባሰ በመሄዱ የሁለቱ ሃገራት ሞያተኞች በጥምረት ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ ነው። መጠለያውን የፈረንጆቹ 2019 ከማለቁ በፊት ለማንሳት እቅድ መያዙን የገለጹት ሚንስትሯ በቀጣዮቹ ሳምንታትም የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ስራውን በይፋ የሚያስጀምሩ መሆኑንም ተናግረዋል።
news-51059823
https://www.bbc.com/amharic/news-51059823
በቻይና የተከሰተው አዲስ ቫይረስ ምን ያህል አስጊ ነው?
ቀደም ሲል በሳይንስ የማይታወቅ እና የሳንባ በሽታን የሚያስከትል ግራ የሚያጋባ ቫይረስ በቻይናዋ ከተማ ውሀን መከሰቱ ተሰምቷል።
ቫይረሱ የተከሰተው በደቡብ ቤጅንግ ውሀን ከተማ ነው። ከ50 የሚበልጡ ሰዎችም በቫይረሱ ተይዘዋል። ከእነዚህ መካከል ሰባቱ በአስጊ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ። ይሄው አዲሱ ቫይረስ ታማሚዎችን ለሳንባ ምች የሚያጋልጥ ሲሆን፤ በዓለም የሚገኙ የጤና ባለሥልጣናትን ስጋት ውስጥ ከትቷል። ይሁን እንጅ ዛሬ ተከስቶ ነገ የሚጠፋ ቫይረስ ይሁን፤ አሊያም በጣም አደገኛ የሆነ ቫይረስ ምልክት ይሆን? የሚለው እያወዛገበ ነው። በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ናሙና ተወስዶ በቤተ ሙከራ ምርመራ እየተደረገበት ነው። በቻይና የሚገኙ ባለሥልጣናት እና የዓለም ጤና ድርጅት የተከሰተው ቫይረስ 'ኮሮናቫይረስ' የተባለና በአፍንጫ እና በላይኛው ጉሮሮ ክፍል የሚከሰት የተለመደ ኢንፌክሽን እንደሆነ ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል። • መጻሕፍትን ማንበብና መጻፍ ለአዕምሮ ጤና • ዛፎችና የአእምሮ ጤና ምን ያገናኛቸዋል? የዚህ ቫይረስ ዓይነቶች አንዳንዶቹ በጣም አስጊዎች ሲሆኑ ሌሎቹ የተለመዱና በቀላሉ የሚድኑ ናቸው። ኮሮናቫይረስ በርካታ ዓይነቶች ያሉት ሲሆን ስድስቱ ብቻ በሰው ላይ በሚያስከትሉት ጉዳት ይታወቃሉ። በእርግጥ አዲስ የተከሰተው ቫይረስ ቁጥሩን ሰባት አድርሶታል። በኮሮናቫይረስ የሚመጣውና 'ሪስፓራቶሪ ሲንድረም' (የመተንፈሻ አካላትን የሚጎዳው ቫይረስ) በቻይና መከሰት ከጀመረበት የአውሮፓዊያኑ 2002 ጀምሮ 774 ሰዎችን ሲገድል 8,098 ሰዎች ተይዘዋል። "ከዚህ በፊት የተከሰተው ቫይረስ ያስከተለው የሚዘነጋ አይደለም፤ ለዚያ ነው አሁን በርካታ ስጋቶች እየተፈጠሩ ያሉት፤ ነገርግን እንዲህ ዓይነት በሽታዎችን ለመከላከል ተዘጋጅተናል" ሲሉ ዌልካም ትረስት ከተሰኘ የምርምር ተቋም ዶክተር ጆሴ ጎልዲንግ ተናግረዋል። ቫይረሱ ምን ያህል አስጊ ነው? ኮሮናቫይረስ የጉንፋን ዓይነት ምልክቶች ያሉት ሲሆን እስከ ሞት ሊያደርስ ይችላል። ይህም አዲስ ቫይረስ በእነዚህ መካከል ላለ የጤና ችግር ሊዳርግ ይችላል ተብሏል። ቀላልም ያልሆነ ለሞትም የማይዳርግ። "አዲሱን ኮሮናቫይረስ ምልክቶቹ ምን ያህል አስጊ እንደሆኑ ማወቅ እንፈልጋለን። ምልክቶቹ ከጉንፋን የበረቱ ናቸው፤ ስለዚህ ያ ነው ትኩረት የሚስበው፤ ይሁን እንጅ እንደ መተንፈሻ አካል ችግር ከባድ ላይሆን ይችላል" ሲሉ በኢድንበርግ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ማርክ ውል ሃውስ ተናግረዋል። በሰዎች ላይ የጤና እክል የሚፈጥሩ ስድስት ዓይነት ኮሮናቫይረስ ነበሩ ቫይረሱ ከየት መጣ? በየጊዜው አዳዲስ ቫይረሶች ይከሰታሉ። ከአንደኛው ዝርያ ወደ ሌላ ዝርያ ይለወጣሉ፤ ነገር ግን በሰዎች ላይ ሲከሰቱ ልብ ተብለው አያውቁም። "ከዚህ በፊት የተከሰተውን ካሰብን እና የተከሰተው አዲስ ኮሮናቫይረስ የመጣው ከእንስሳት ውሃ መጠጫ ነው" ሲሉ በኖቲንግሃም ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ጆናታን ቦል አስረድተዋል። የመተንፈሻ አካል ላይ የሚከሰተው የጤና እክል በአብዛኛው በኤዥያ ከሚገኙ ትንንሽ ድመቶች ወደ ሰዎች ይተላለፋል። የግመል ጉንፋን በመባል የሚታወቀው የመካከለኛው ምስራቅ በሽታ ከተቀሰቀሰበት የአውሮፓዊያኑ 2012 ጀምሮ ከተመዘገቡ 2 ሺህ 494 ምልክቱ ከታየባቸው ታማሚዎች 858ቱ ሞተዋል። የትኞቹ እንስሳት ያስተላልፋሉ? በውሃ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ እንደ አሳ ነባሪ ያሉ አጥቢ እንስሳት ኮሮናቫይረስ ሊሸከሙ ይችላሉ። ሌሎች እንደ ዶሮ፣ ጥንቸል ፣ እባብ፣ የሌሊት ወፍ የቫይረሱ ምንጭ ሊሆኑ ይችላሉ። በዚህም ምክንያት ቫይረሱ በደቡባዊ ቻይና ውሀ፤ የባህር ምግቦች መሸጫ ገበያዎች ጋርም ተያይዟል፤ ነገር ግን ቫይረሱ የሚገኝበት ምንጭ ከተለየ በቀላሉ መከላከል ይቻላል ተብሏል። • ለወሲብ ባርነት ወደ ቻይና የሚወሰዱት ሴቶች ምንም እንኳን ከመተንፈሻ አካላት ጋር የተገናኙ ህመሞች ከሰው ወደ ሰው ቢተላለፉም አሁን ላይ ያለው መረጃ እንደሚያመለክተው ቫይረሱ ከሰው ወደ ሰው አይተላለፍም። የሥርጭት መጠኑም ያን ያህል የተፋጠነ አይደለም። ምልክቱ የታየባቸው 59 ሰዎች ሃያ ቀናት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ምልክቱ የታየባቸው ሲሆን፤ ከዚያ በኋላ የተመዘገበ ታማሚ አለመኖሩም ለዚህ ማሳያ ነው። በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ተለይቶ በተዘጋጀ ቦታ ህክምና እየወሰዱ ሲሆን፤ ከተያዙ ሰዎች ጋር ግንኙነት የነበራቸው 150 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ክትትል እየተደረገላቸው ነው። ተጓዦችን የሚመረምር የሙቀት መለኪያም ተዘጋጅቷል። የባህር ምግቦች ገበያዎች ለፅዳት ሲባል ተዘግተዋል። ዶክተር ጎልዲንግ "በአሁኑ ሰዓት ተጨማሪ መረጃ እስከምናገኝ ድረስ ምን ያህል መጨነቅ እንዳለብን ማወቅ አስቸጋሪ ነው" ብለዋል። "የቫይረሱ ምንጭ ማረጋጋጫ እስክናገኝ ድረስ ግን ጉዳዩን ቀላል ነው ማለት አይቻልም" ሲሉም አክለዋል።
50612202
https://www.bbc.com/amharic/50612202
ብሩንዲ መጠጥ ቤቶች በጊዜ እንዲዘጉ አዘዘች
ብሩንዲ በተወሰኑ ከተሞች የሚገኙ መጠጥ ቤቶች በጊዜ አንዲዘጉ ውሳኔ አስተላለፈች። መጠጥ ቤቶቹ በአገሬው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ ሶስት ሰዓት በኋላ እንዲዘጉ መወሰኑ ተሰምቷል።
ይህ ትዕዛዝ ተፈጻሚ የሚሆንባቸው ከተሞች በዋና ከተማዋ ቡጁንቡራ፣ ጊቲጋና በሰሜናዊ ሙያንጋ አውራጃ መሆኑ ታውቋል። እስካሁን ድረስ ስለ መዝጊያ ሰዓቱ እንጂ ከስንት ሰዓት ጀምረው መጠጥ መሸጥ እንዳለባቸው የተደነገገ ነገር የለም። • በምዕራብ ኦሮሚያ በ12 ወራት ቢያንስ 8 የአካባቢው ባለስልጣናት ተገድለዋል • መጠጥና ሩሲያውያን ሆድና ጀርባ እየሆኑ ነው • ለአንድ ወር ከአልኮል መታቀብ የሚኖረው አስደናቂ ውጤት የቡጁንቡራ ከተማ ከንቲባ ውሳኔው ሰዎች በልክ አንዲጠጡ ያለመ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ብሩንዲያውያን ጠጪዎች ግን ይህ የመንግሥት ውሳኔ አስቆጥቷቸዋል። ይህ እርምጃ ከጸጥታና ደህንነት ጋር የተያያዘ እንጂ የምንጠጣውን ልክ ከመሥፈር ጋር አይያያዝም ሲሉም ተሰምቷል። ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በቡጁንቡራ በሚገኝ መጠጥ ቤት ውስጥ በተተኮሰ ጥይት የሰው ሕይወት አልፏል። በስራ ቀናት መጠጥ ቤቶች ከ11 ሰዓት እስከ 3 ሰዓት ድረስ እንዲሰሩ የተፈቀደ ሲሆን፤ ቅዳሜና እሁድ ግን ከ7 ሰዓት እስከ 3 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሰራሉ ተብሏል። "መጠጥ ቤቶች በጊዜ በራቸውን እንደሚዘጉ መስማት በጣም ያሳዝናል" ሲል ተናግሯል አንድ የጊቴጋ ነዋሪ ለቢቢሲ። አንዲት የ28 ዓመት ወጣት በበኩሏ "በርካታ ወጣቶች ይህንን ትዕዛዝ በመተላለፋቸው ብቻ ወደ ዘብጥያ ይወርዳሉ ማለት ነው" ስትል ስጋቷን ተናግራለች። ቡጁምቡራ የሚኖር አንድ ግለሰብ በበኩሉ የቡና ቤት ባለቤቶችና ሰራተኞች መጠጥ ቤቶች እንዲዘጉ የተወሰነበት ሰዓት ጠጪዎች ወደ መጠጥ ቤት የሚመጡበት በመሆኑ ማዘናቸውን ይናገራል። "በርካታ ሰዎች ቀኑን ሙሉ በስራ የዛለ አእምሯቸውን የሚያፍታቱበት በዚያ ሰዓት ወደ መጠጥ ቤት ጎራ በማለት ነው" በማለትም "በርካታ ሰዎች ወደ መጠጥ ቤት የሚመጡት ለተለያየ ምክንያት ነው፤ ብዙ ጊዜ በሸጋ የግል ምክንያት። በመሪዎቻችን ትዕዛዝ እናምናለን፤ ነገር ግን ይህ ውሳኔ አያስደስተንም፤ የምንፈልገውን በምንፈልገው ሰዓት ለመውሰድ መከልከል አያስደስትም" ብሏል። አንድ እድሜው በ30ዎቹ የሚገኝ ግለሰብ በበኩሉ ለቢቢሲ እንደሰጠው ቃል፤ የመንግሥት ውሳኔ በዋና ከተማዋ ያለውን የደህንነት ስጋት ያሻሽለዋል ብሎ ስለሚያመንን አንደሚደግፈው ተናግሯል።
news-53359536
https://www.bbc.com/amharic/news-53359536
በሶሪያ በሚገኙ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ይጨምራል የሚል ስጋት ተፈጥሯል
በሶሪያ ሰሜን ምዕራብ ግዛት፣ አብዛኛው አካባቢ በአማፂያን ቁጥጥር ስር ያለ ሲሆን የመጀመሪያው በኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው መገኘት በተጨናነቀው የስደተኞች መጠለያ ቫይረሱ በፍጥነት ሊዛመት ይችላል የሚል ስጋት አጭሯል።
የእርዳታ ድርጅቶች ቡድን እንዳለው በቫይረሱ የተያዘው ዶክተር ሲሆን፣ ይሰራ የነበረውም በቱርክ ድንበር አቅራብያ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ ነው ተብሏል። ዶክተሩ በአሁኑ ሰዓት ራሱን ለይቶ ያለ ሲሆን ከእርሱ ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የመለየት ስራ እየተሰራ ነው። ዶክተሩ ይሰራበት የነበረው ሆስፒታል መዘጋቱን በቱርክ የሚገኘው የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። ለወራት የእርዳታ ድርጅቶች ቡድን በሰሜን ምዕራብ የስደተኞች መጠለያ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሊከሰት ይችላል እያሉ ሲያስጠነቅቁ ነበር። ባለፈው ዓመት፣ የሶሪያ መንግሥት ኢድሊብን ለመቆጣጣር ሰፊ ጥቃት ከፍቶ ነበር። ከባለፈው ሕዳር ር ጀምሮ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው ወደ መጠለያ ካምፑ የመጡ ሲሆን በስፍራው ተጨናንቀው ለሚኖሩት ሶሪያውያን ስደተኞች በቂ የሆነ የጤና ማዕከል፣ ንፁህ ውሃ እንዲሁም ባለሙያ አለመኖሩ ተገልጿል። በመጠለያ ጣብያው ተጋላጭ የሆኑ ህብረተሰቦች መካከል ደካማ የጤና ስርዓት ባለበት ሁናቴ ቫይረሱ በፍጥነት ሊስፋፋ እንደሚችል ፍርሃት አለ። ሶሪያ ውስጥ ከጎርጎሳውያኑ 2011 ጀምሮ በተቀሰቀሰ የእርስ በእርስ ግጭት ወደ ስድስት ሚሊዮን ሰዎች መፈናቀላቸው ይገለፃል። ሶሪያ እስካሁን ድረስ 372 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን በምርመራ ስታረጋግጥ ከእነዚህም መካከል 14 ሰዎች ሞተዋል። በሶሪያ የኮቪድ-19 ምርመራ የማድረግ አቅም ደካማ መሆን፣ በቫይረሱ የሚያዙና የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።
news-54781123
https://www.bbc.com/amharic/news-54781123
የግማሽ ሚሊዮን ብር ሰዓት ለሠራተኞቻቸው የሸለሙት አለቃ ሥራ ለቀቁ
የአውስትራሊያ ፓስታ ቤት ኃላፊ ለአራት ሠራተኞቻቸው ዋጋው የከበደ ሰዓት በመሸለማቸው ምክንያት ሥራ ለቀዋል።
የብሔራዊ ፓስታ አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ክሪስቲን ሆልጌት ከአውሮፓውያኑ 2017 ጀምሮ ድርጅቱን ሲያገለግሉ ነበር። ነገር ግን ለአራት ሠራተኞቻቸው 20 ሺህ የአውስትራሊያ ዶላር [ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ] የሚያወጡ ሰዓቶች ለአራት ሠራተኞቻቸው በመሸለማቸው ምክንያት ነው ራሳቸውን ከሥልጣን ያገለሉት። የሴትዬዋ ድርጊት የሕዝብን ንብረት ያለአግባብ ማባከን ነው ተብሏል። ካርቲዬል የተሰኘውን ሰዓት በ2018 [በአውሮፓውያኑ] ነበር 'ጠንካራ ሠራተኞቼ ናቸው' ላሏቸው ባልደረቦች የሸለሙት። የሃገሪቱ ፓርላማ ከሰሞኑ ይህን ጉዳይ መዞ ምርመራ እንዲደረግባቸው ወስኗል። ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን በወጪው 'እጅግ እንደተገረሙ' ተናግረዋል። አልፎም እንግሊዛዊቷ ሥራ አስኪያጅ ከኃላፊነቱ እንድትነሳ አዘዋል። "በአውስትራሊያ ፓስት አግልግሎት ውስጥ ያለች እያንዳንዷ ዶላር የግብር ከፋዩ ናት። ወጪም ቢሆን ሕዝብን ያከበረ መሆን አለበት" ሲሉ ተደምጠዋል። የአውስትራሊያ ፖስታ አግልግሎት ባለቤትነቱ የመንግሥቱ ይሁን እንጂ የሚተዳደረው በግል ነው። ኃላፊዋ ሰኞ ዕለት ሥልጣናቸውን እንደለቀቁ አሳውቀዋል። ሥራ አስኪያጇ 'ሠራተኞች ለጠንካራ ሥራቸው ሊመሰገኑ ይገባል' ሲሉ ድርጊታቸውን በተደጋጋሚ ተከላክለዋል። ሽልማቱ የተሰጣቸው ሠራተኞች ለአውስትራሊያ ፖስታ አግልግሎት 220 ሚሊዪን የአውስትራሊያ ዶላር አምጥተዋል፤ ይህ ደግሞ የፋይናንስ አቅማችንን አጠናክሯል ብለዋል። 'ነገር ግን በ2018 የወሰንነው ውሳኔ እንዲህ ዓይነት ነገር መፍጠሩ ይፀፅተኛል' ሲሉ በመግለጫቸው አትተተዋል። የአውስትራሊያ ፖስታ አገልግሎት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት ምርትና አገልግሎት በማጓጓዝ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። ኃላፊዋ፤ ወረርሽኙ ከተጀመረ ወዲህ 300 ሚሊዮን ገደማ ዓይነቶችን እንዳጓጓዙና 80 በመቶ የበይነ መረብ ግብይትን እንደተወጡ አሳውቀዋል። የአውስትራሊያ ፖስታ አገልግሎት ኃላፊ ሆነው ከመሾማቸው በፊት የአውስትራሊያ ቫይታሚን ኩባንያ የሆነው ብላክሞርስ ኃላፊ ሆነው ሠርተዋል። እሳቸውን ተክቶ የፓስታ ቤት ኃላፊ የሚሆነው ግለሰብ በቅርቡ ይፋ ይሆናል።
news-54963944
https://www.bbc.com/amharic/news-54963944
ትግራይ ፡ የኡጋንዳው ፕሬዝደንት ስለኢትዮጵያ 'ውይይት' የፃፉትን መልዕክት አነሱ
የኡጋንዳው ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ኢትዮጵያ ውስጥ የተቀሰቀሰውን ግጭት ለማርገብ ሁለቱንም አካላት የሚያወይይ መኖር አለበት ብለው የፃፉትን አነሱ።
ሙሴቬኒ በትዊተር ሰሌዳቸው ላይ እንዳሰፈሩት ይህ የማይሆን ከሆነ "አላስፈላጊ የነብስ ጥፋት ያስከትላል፤ የአገሪቱንም ምጣኔ ሃብት ይጎዳል" ብለው ነበር። ሙሴቬኒ ይህንን መልዕክት በትዊተር ገፃቸው ያሰፈሩት ከኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ኡጋንዳ ውስጥ ከተገናኙ በኋላ ነው። ነገር ግን ትዊተር ገፃቸው ላይ ካሰፈሩት ተከታታይ መልዕክት [ትሬድ] መካከል ስለ ውይይት የፃፉትን ቆየት ብለው አጥፍተውታል። ሙሴቬኒ ይህንን ሃሳብ ለምን እንዳጠፉት ይፋ ባይሆንም የኢትዮጵያ መንግሥት ከህወሓት ጋር የሚደረግ ማንኛውም ዓይነት ውይይት እንደማይቀበል በተደጋጋሚ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። የኢትዮጵያ መንግሥት ትግራይ ክልል ውስጥ "ሕግ የማስከበር ዘመቻ ላይ ነኝ" ማለቱ አይዘነጋም። በጦርነቱ ሳቢያ በሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሱዳን እየተሰደዱ ሲሆን በመቶዎች የሚቆጠሩ እንደሞቱ ተነግሯል። ትግራይ ክልል ውስጥ የበይነ መረብና የስልክ አገልግሎት በመቋረጡ ምክንያት ትክክለኛ መረጃ ማግኘት ከባድ ሆኗል። ፕሬዝደንት ሙሴቬኒ በሁለቱ ኃይሎች መካከል ድርድር ለማድረግ እየሞከሩ ነው የሚሉ ዜናዎች መውጣታቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት ይህ ዘገባ ሐሰት ነው ሲል አስተባብሏል። ሙሴቬኒ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ ጋር ያደረጉት ውይይት "ኢትዮጵያ ውስጥ እየተስተዋለ ካለው የሰላምና የፀጥታ ጉዳይ" ጋር የተገናኘ እንደሆነ ጽፈዋል። ሙሴቬኒ አክለውም "እኔ ብሔር ላይ የተመሠረተ ፌዴራሊዝምን አልደግፍም። ትኩረት መስጠት ያለብን ለአንድነትና ለተመሳሳይ ፍላጎት ነው። ይህ ብቸኛው የምንበለጽግበት መንገድ ነው" ብለዋል። በሌላ በኩል የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝደንት ኦሌሴጉን ኦባሳንጆ በኢትዮጵያ መንግሥትና በህወሓት መካከል ድርድር ለማስጀመር ወደ ኢትዮጵያ ሄደዋል ሲል ኤኤፍፒ የተሰኘው የዜና ወኪል ዘግቧል። ድርድርን በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግሥት አቋም አሁንም ባይቀየርም ኦባሳንጆ አዲስ አበባ ገብተዋል ይላል ኤኤፍፒ። "ድርድር ለማድረግ መሞከር ተጠያቂ ያለመሆንና ሕገ ወጥነትን የሚያበረታታ ነው" ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታና የአስቸኳይ ጊዜ ቃል አቀባይ ሬድዋን ሁሴን ተናግረዋል። "የትኛውም አገር ሮኬትና ሚሳዔል አለኝ ከሚልና ጥቃት ለመሰንዘር ከሚዝት ኃይል ጋር ቁጭ ብሎ አይወያይም" ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታው። ኦባሳንጆ ወደ አዲስ አበባ እያቀኑ መሆኑን ለፈረንሳዩ ዜና ወኪል ኤኤፍፒ ያሳወቁት ቃል አቀባያቸው ኬሂንዴ አኪንዬሚ ናቸው። "ወደዚያ ያቀኑት ለድርድር ነው" ከማለት ውጪ ዝርዝር መረጃ አልሰጡም። የኢትዮጵያ መንግሥት ሠሜናዊውን የአገሪቱን ክልል የሚመራው ህወሓት ጋር ከውዝግብ አልፎ ወደ ጦርነት ከገባ ሁለት ሳምንታት ሊሆነው የተቃረበ ሲሆን፤ ከተለያዩ ወገኖች የድርድር ሐሳብ ቢቀርብም መንግሥት የሚወሰደው ወታደራዊ እርምጃ ሕግ የማስከበር ሂደት ስለሆነ ከቡድኑ ጋር ውይይት እንደማይኖር በተደጋጋሚ ማሳወቁ ይታወቃል።
news-56087610
https://www.bbc.com/amharic/news-56087610
የዱባዩ መሪ ልጅ "በአባቴ ታግቻለሁ" አለች
የዱባዩ መሪ ልጅ አባቷ እንዳገቷትና ለህይወቷ በከፍተኛ ሁኔታም እንደምትሰጋ በቅርቡ በወጣ ሚስጥራዊ ቪዲዮ ላይ ገልፃለች።
በአሁኑ ወቅት በአንድ ቪላ ውስጥ ተዘግቶባት እንምትገኝና ነፃ አውጡኝ ስትል ተማፅናለች። ልዕልት ላቲፋ አል ማክቱም ከሶስት አመታት በፊት ከአገር ሸሽታ ልትወጣ ሞክራም ነበር። በውቅቱም በጀልባ ተሳፍራ ልታመልጥ የነበረ ሲሆን የጦር ኮማንዶዎች አፍነው እንደወሰዷትና በእስር ላይ እንደምትገኝ ልዕልት ላቲፋ አል ማክቱም ተናግራለች። አጠር ያለ ሚስጥራዊ የቪዲዮ መልዕክቷን ተከትሎ ጓደኞቿ የተባበሩት መንግሥታት ጣልቃ እንዲገባ እየጠየቁ ነው። የዱባይም ሆነ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ባለስልጣናት ከዚህ ቀደም በቤተሰቦቿ እንክብካቤ ውስጥ እንደሆነችና ደህንነቷም የተጠበቀ ነው የሚል መግለጫ ሰጥተው ነበር። የቀድሞ የተባባሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ልዩ መልዕክተኛ ሜሪ ሮቢንሰን ከሶስት አመት በፊት ልዕልቲቷን ባገኟት ወቅት "የተረበሸች ወጣት" በሚል የገለጿት ሲሆን በአሁኑ ወቅት ግን በልዕልቲቱ ቤተሰብ በአሳዛኝ ሁኔታ እንደተሸወዱ ተናግረዋል። የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነርና የአየርላንድ ፕሬዚዳንት ልዕልት ላቲፋ ያለችበት ሁኔታና ቦታ እንዲገለፅ አለማቀፋዊ ጫና እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል። "የላቲፋህ ሁኔታ በጣም አስጨናቂ ነው። ሁሉ ነገር ተዳፍኖ ነው ያለው። ምርመራ ሊከፈት ይገባል" ብለዋል። የላቲፋህ አባት ሼክ መሃመድ ቢን ራሺል አል ማክቱም በአለማችን ካሉ መሪዎች አንደኛ ሃብታም ሲሆኑ ፤ የዱባይ መሪ እንዲሁም የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ናቸው። በቅርቡ የወጣው ቪዲዮ የተቀረፀው ተይዛ ወደ ዱባይ እንድትመለስ ከተደረገች ከአመት በኋላ በነበሩት ወራት ውስጥ ነው። ቪዲዮውንም በመታጠቢያ ቤት ሲሆን የቀረፀችው ይህም ከውስጥ መቆለፍ የምትችለው ክፍል እሱ ብቻ ስለሆነ ነው ተብሏል። ታግታና በእስር ላይ እንዳለች በገለፀችበት ቪዲዮ የዘረዘረቻቸው ጉዳዮች፦ የላቲፋን መያዝና እስር አስመልክቶ ያጋለጡት ቅርብ ጓደኛዋ ቲና ጁሃይነን፣ የአጎቷ ልጅ ማርከስ ኢሳብሪና ተሟጋቹ ዴቪድ ሃይ ሲሆኑ ሁሉም ላቲፋ ነፃ እንድትወጣ ዘመቻን እያካሄዱ ይገኛሉ። የላቲፋ ደህንነት በከፍተኛ ሁኔታ ስላሰጋቸው ቪዲዮውን አሁን ለመልቀቅ ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን ተናግረዋል። ላቲፋ በዱባይ መስኮትና በሩ በተዘጋበት ቤት እንዲሁም ፖሊሶች በሚጠብቁት ቪላ ውስጥ እያለች ማግኘት ችለው እንደነበር ተገልጿል። ቢቢሲም ቢሆን ልዕልቲቷ የታገተችበትን ቦታ በገለልተኛ አካል ማጣራት ችሏል። ሼክ መሃመድ ዱባይን እንድትበለፅግ ማድረጋቸው ቢያስወድሳቸውም አስተዳደራቸው ተቃዋሚዎችን ዝም በማሰኘት እንዲሁም የፍትህ ስርአቱ ሴቶችን በማግለል ይተቻሉ። ከዚህም በተጨማሪ በልጃቸው ልዕልት ላቲፋና በባለቤታቸው ፕሪንሰስ ሃያ ቢንት አሊ ሁሴን አያያዝ ከፍተኛ ትችት ይቀርብባቸዋል። ባለቤታቸው ከሁለት ልጆቻቸው ጋር ከሁለት አመት በፊት ወደ ለንደን አቅንተዋል። የ35 አመቷ ልዕልት ላቲፋ መጀመሪያ ልታመልጥ የሞከረችው በ16 አመቷ ሲሆን በወቅቱም ሄርቬ ጃውበርት ከተባለ ፈረንሳያዊ ነጋዴ ጋር እቅድም ታቅዶ ነበር። በወቅቱም ስፖርት ታሰለጥናት የነበረችው አስተማሪም አማካኝነት ነበር የማምለጥ እቅዱ የተወጠነው። ከሰባት አመታት በኋላ፣ በአውሮፓውያኑ 2018 ልዕልት ላቲፋና አስተማሪዋ በጀልባ አለም አቀፍ ውሃዎች የደረሱ ሲሆን፤ የአሜሪካ ሰንደቅ አላማ ያለበት መርከብም እየጠበቁ ነበር። ከስምንት ቀናት በኋላ ወደ ህንድ አካባቢ ሲደርሱ የጦር ኮማንዶዎች ጀልባዋን በቁጥጥር ስር አውለዋታል። የስፖርት መምህሯ እንደምትለው አስለቃሽ ጋዝ በማፈንዳት ላቲፋ ከተደበቀችበት መታጠቢያ ቤት እንድትወጣ ያደረጓት ሲሆን ሽጉጥም ደግነውበታል ነበር ተብሏል። ላቲፋ ዱባይ ከተመለሰች በኋላ ተሰውራለች። የስፖርት መምህሯ እንዲሁም ሌሎች የመርከቡ ሰራተኞች በዱባይ በቁጥጥር ስር ለሁለት ሳምንታት ከቆዩ በኋላ ነፃ ወጥተዋል። የህንድ መንግሥት በልዕልቷ ቁጥጥር ስር መዋል የነበረው ሚናን በተመለከተ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል። ከሶስት አመታት በፊት ለማምለጥ ከመሞከሯ በፊት ልዕልት ላቲፋ ዩቲዪብ ላይ የተለቀቀ አንድ ቪዲዮ ላይም "ይሄንን ቪዲዮ የምትመለከቱ ከሆነ ጥሩ ሁኔታ ላይ አይደለሁም ማለት ነው። ሞቼያለሁ ወይም ክፉኛ በሆነ መጥፎ ሁኔታ ላይ ነው ያለሁት" የሚል ነበር። ቪዲዮው የወጣው ከታገተችና ከታሰረች በኋላ ነበር። ይህም ቪዲዮ ነው ልዕልቷ እንድትፈታ አለም አቀፍ ግፊቶችንና ጫናዎችን ያመጣው።
news-50953901
https://www.bbc.com/amharic/news-50953901
"ምርጫ ቦርድ ከጨዋታ ውጭ ሊያደርገን ይፈልጋል" መረራ ጉዲና (ፕ/ር)
ከጥቂት ወራት በፊት በፓርላማ የፀደው የምርጫ አዋጅ በተቃዋሚ ፖለቲከኞች ብዙ ተቃውሞዎች ቀርበውበታል። በተለይም እንደ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስና ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ያሉ አንጋፋ ፖለቲከኞች የተወሰኑት የአዋጁ አንቀፆች ላይ ብርቱ ትችት ሲሰነዝሩ ቆይተዋል።
"ኋላ ቀር በሆነ አገር ከመንግሥት ጋር መካሰስ የትም የሚያደርስ አይደለም። ቂም ይያዝብናል ለቀጣዩ እንቅስቃሴያችን ሁሉ ችግር ይፈጥርብናል" አዋጁ ፓርቲዎች ለመመዝገብ የአስር ሺህ መስራች አባላት ፊርማ ማሰባሰብ አለባቸው ማለቱ በተለይም እንደ እነሱ ላሉ ነባርና ከዚህ ቀደምም በተደጋጋሚ በምርጫ የተሳተፉ ፓርቲዎች ፍትሃዊ አይደለም በማለት ሲተቹና ሲከራከሩ ቆይተዋል። ፕ/ር መረራና ፕ/ር በየነ ቀደም ባሉት ዓመታት እንደ አቶ መለስ ዜናዊና አቶ በረከት ስምኦን ካሉ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ጋር ተከራክረው ያስቀሯቸው ተገቢ ያልሆኑ አንቀፆች በዚህ አዲስ አዋጅ ተካትተው እንዲፀድቁ መደረጉን ይኮንናሉ። • "ምን ተይዞ ምርጫ?" እና "ምንም ይሁን ምን ምርጫው ይካሄድ" ተቃዋሚዎች • ጃዋር ኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስን መቀላቀሉ ተረጋገጠ • በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንቅስቃሴ ላይ ጊዜያዊ ገደብ ተጣለ ቀደም ሲል ፕ/ር መረራ አስር ሺህ የመስራች አባላት ፊርማ ማሰባሰብ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚጠይቃቸው ሲገልፁ፤ ፕ/ር በየነ ደግሞ ነባር ፓርቲ ሆነው ሳሉ እንደ አዲስ ተመዝገቡ መባላቸው ፍትሃዊ ስላልሆነ ጉዳዩን ወደ ህግ ለመውሰድም እያሰቡ እንደሆነ ገልፀውልን ነበር። እስካሁን እየተባለ ባለው ምርጫው ሊካሄድ አራት ወራት ገደማ ቀርተውታል። በእነዚህ አንጋፋ ፖለቲከኞች የሚመሩት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ( ኦፌኮ) እና የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራት ፓርቲ የምዝገባቸውን ጉዳይ ከምን አደረሱት? ምንም እንኳ 70 የሚሆኑ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጁ ላይ ተቃውሟቸውን እያሰሙ ቢሆንም ምርጫ ቦርድ ነገሮችን በጀመረው መንገድ ማስኬድ ቀጥሏል የሚሉት ፕ/ር በየነ ባለፈው ሳምንት ቦርዱ ቀነ ገደብ ሊያስቀምጥ በመሆኑ ቅድመ ሁኔታዎችን አጠናቅቀው እንዲቀርቡ እንዳስታወቃቸው ይገልፃሉ። ቀደም ሲል እንዳሉት ነባር ፓርቲዎች ፊርማ ሰብስበው እንደ አዲስ ይመዝገቡ የመባሉን ጉዳይ ወደ ህግ እንወስዳለን ቢሉም እርምጃው ምን ያህል ያዋጣል? በሚል ግምገማና በሰዎችም ምክር ሃሳባቸውን መቀየራቸውን ይናገራሉ። "ኋላ ቀር በሆነ አገር ከመንግሥት ጋር መካሰስ የትም የሚያደርስ አይደለም። ቂም ይያዝብናል ለቀጣዩ እንቅስቃሴያችን ሁሉ ችግር ይፈጥርብናል" በማለት ውሳኔያቸውን ያብራራሉ። በተግባር እያደረገ ካለው ነገር በመነሳት ምርጫ ቦርድ ነባር ፓርቲዎችን ከጨዋታ ውጭ የማድረግ ፍላጎት አለው ብለውም ያምናሉ። አዋጁን አጥብቀው ቢቃወሙም መመዝገባቸው ግድ ስለሆነ በየቅርንጫፎቻቸው የአባሎቻቸውን ፊርማ ለማሰባሰብ መመሪያ ሰጥተው እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ፕ/ር በየነ ጠቁመዋል። "በህግ አምላክ ብንልም የሚሰማን አጥተናል" የሚሉት ፕ/ር በየነ ምናልባትም እንደሚፈለገው 'አቅም አጥተው ሲያቅታቸው ቤታቸው ገቡ' እንዳይባል የሚችሉትን ሁሉ እንደሚያደርጉ ይናገራሉ። ምን ያህል ይሳካላቸዋል የሚለው ወደ ፊት የሚታይ ነው። • ምርጫ ፡ የተቃዋሚዎችና የመንግሥት ወግ? "እንደ ምገምተው በሁለት ወር ውስጥ ጨርሱ የሚል ቀነ ገደብ ይመጣል። ምርጫ ቦርድ አሁን እያሳየ ካለው የማይገመት ባህሪ አንፃር በ15 ቀን ውስጥ ጨርሱ ሊልም ይችላል" ሲሉ ግምታቸውን ያስቀምጣሉ። በሌላ በኩል ፕ/ር መረራም ተገድደው አዲሱ የምርጫ አዋጅ በሚለው መንገድ ለመመዝገብ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ይናገራሉ። "በውዴታ ሳይሆን በግዴታ ወደዚህ ነገር ውስጥ ገብተናል። ግን ተቃውሟችንን እንቀጥላለን" የሚሉት ፕ/ር መረራ በፀደቀ አዋጅ እንዲሁም ምርጫ ሊካሄድ ከአራት ወር ብዙም የማይበልጥ ጊዜ ተቃውሞ ውጤት ያመጣል ወይ? የሚል ጥያቄ አንስተን ነበር። "ምናልባትም የታሰበው እኛን ከጨዋታ ውጭ ለማድረግ ስለሆነ ከምርጫ ውጭ እንዳንሆን ነገሮቻችንን መስራት እንጀምራለን ማለት ነው" የሚል ምላሽ ነበር የሰጡት። ሁለቱም የፓርቲ መሪዎች ምዝገባን ከሚመለከተው አንቀፅ ባሻገር በምርጫ የሚሳተፉ የመንግሥት ሰራተኞችን የሚመለከተውን አንቀፅም ይኮንናሉ። ቀደም ሲል ባነጋገርናቸው ወቅት ፕ/ር መረራ "የመንግሥት ሰራተኞች በምርጫ የሚወዳደሩ ከሆነ ስራ ይለቃሉ የሚለው አዋጁ እጅግ ነውር ነው" ብለው ነበር።
news-49303602
https://www.bbc.com/amharic/news-49303602
ብልትን መታጠን ጉዳት እንዳለው ባለሙያዎች አስጠነቀቁ
አንዲት ካናዳዊት ሴት ብልቷን ለመታጠን ባደረገችው ሙከራ ራሷን ካቃጠለች በኋላ የማህፀን ሀኪሞች ብልትን መታጠን ሊያስከትሉ ስለሚችሉ አደጋዎች እያስጠነቀቁ ይገኛሉ።
የ62 ዓመቷን ካናዳዊትን ተሞክሮ ያካተተው ይህ ጥናት ታትሞ የወጣው በካናዳ በሆድና የማሕፀን ጤና ላይ በሚያተኩር ጆርናል ላይ ነበር። ይህች በጥናቱ ላይ የተሳተፈችው ሴት የብልት መገልበጥ ሕመም ስትሰቃይ የነበረ ሲሆን ቀዶ ሕክምና ሳታደርግ በሌሎች የሕክምና ዘዴዎች ፈውስ ማግኘት እንደምትችል እምነት ነበራት። • መቀመጫቸውን ለማስተለቅ የሚታትሩ ሴቶች እየሞቱ ነው • ከማህጸን ስለሚወጣ ፈሳሽ ምን ያህል ያውቃሉ? ብልትን መታጠን፣ በሞቀ ውሃ ላይ መቀመጥ፣ በውሃው ላይ ባህላዊ መድሃኒቶችን መጠቀም እየተለመደ የመጣ ተግባር ነው። በውጫዊ የብልት አካባቢ ያሉ አካላትን ለመንከባከብ በሚል ዘመናዊ በሆኑ የውበት መጠበቂያ ቤቶችና ስፓዎች ሳይቀር ለሚፈልጉ ደንበኞች አገልግሎቱን ይሰጣል። ይህንን ብልትን የመታጠን ልማድ በሚመለከት ኤል ኤ ታይምስ በአውሮፓዊያኑ 2010 ለመጀመሪያ ጊዜ ሪፖርት ያደረገ ሲሆን ከዚያ በኋላ ግውይኔት ፓልትሮው ጉፕ ብራንድ እንዲጠቀሙት ከመከረ በኋላ ግን የበርካቶችን ትኩረት ስቧል። ባለፈው ዓመት አሜሪካዊቷ ሞዴል ክሪሲይ ቴገን ብልቷን ስትታጠን የሚያሳይ ፎቶግራፏን አጋርታለች። የውበት መጠበቂያ ቤቶችና ስፓ ማስታወቂያዎችም ብልትን መታጠን እስያና አፍሪካ በዘመናቸው ሁሉ ሲጠቀሙበት የኖሩት መድሃኒት እያሉ ያስተዋውቃሉ፤ እንዲያውም ይህንን ልማድ አንዳንጊዜ 'ዮኒ ስቲሚንግ ' እያሉ ይጠሩታል። ድርጊቱም ብልትን የሚመርዝ ነገርን የማስወገድ ተግባር እንደሆነ ይነገራል። ባለሙያዎች ግን እነዚህ ድርጊቶች አደገኛ ሊሆኑ ይችላሉ ሲሉ ይመክራሉ- በወር አበባ ወቅት የሚከሰትን ህመም ያስታግሳል፣ መካንነትን ይከላከላል የሚሉትን ጨምሮ ስለሌሎች ጠቀሜታውና ፋይዳው እስካሁን የወጡ ማረጋገጫዎች አለመኖራቸውን በመጥቀስ። በሮያል ኮሌጅ የሆድ አካልና ማሕፀን ሕክምና ክፍል አማካሪና ቃል አቀባይ የሆኑት ዶ/ር ቫንሳ ማኬይ የሴቶች ብልት የተለየ እንክብካቤና ከመጠን ያለፈ ፅዳት ያስፈለግዋል መባሉን ' አፈ ታሪክ' ነው ይሉታል። ይሁን እንጂ ሽታ በሌላቸው ሳሙናዎች ውጫዊ የሆነውን የብልት ክፍል ማፅዳት እንደሚያስፈልግ ይመክራሉ። "የሴቶች ብልት ጠቃሚ የሆኑ ባክቴሪያዎችን ይዟል፤ ባክቴሪያዎቹ እርሱን ለመጠበቅ የተቀመጡ ናቸው " ሲሉ በመግለጫቸው አክለዋል። በመሆኑም ብልትን መታጠን በውስጡ ያሉ ባክቴሪያዎች ላይ የጤና መናጋት ያስከትላል፤ የ'ፒ ኤች' መጠንንም ሊቀንስ ይችላል፤ ከዚህም ባሻገር ማሳከክ፣ መቆጣት፣ ማቃጠል እና ኢንፌክሽን ሊያስከትል ይችላል ብለዋል። ይህም ብቻ ሳይሆን በብልት አካባቢ ያለ ለስላሳ ቆዳ [vulva] ላይ ቃጠሎም ሊያስከትል ይችላል ሲሉ ያስጠነቅቃሉ። • የወንድ የእርግዝና መከላከያ፤ ለምን እስካሁን ዘገየ? በርካታ ሐኪሞችም ብልትን መታጠን የሚያስከትለውን ጉዳት ለማሳየት በካናዳዊቷ ሴት ላይ የሆነውን ሁሉ በተለያየ መልኩ እያጋሩት ይገኛሉ። የእርሷን አጋጣሚ የጻፉት ዶ/ር ማጋሊ ሮበርት በበኩላቸው ሴትዮዋ በአንድ ቻይናዊ ዶክተር ምክር ብልቷን ለመታጠን ስትሞክር ጉዳቱ እንዳጋጠማት አስረድተዋል። ይህች ታሪኳ ለሌሎች ትምህርት እንዲሆን ለማጋራት ፈቃደኛ የሆነችው ሴት፤ ብልቷን ለመታጠን ለሁለት ተከታታይ ቀናት ለ20 ደቂቃዎች ያህል የሞቀ ውሃ ላይ ተቀምጣ ነበር ። ያጋጠማት ጉዳትም ሁለተኛ ደረጃ ቃጠሎ ሲሆን ከጉዳቷ ስታገግም ቀዶ ሕክምና እንደሚደረግላት ተገልጿል። በካልጋሪ ከእንብርት በታች ያሉ ክፍሎች ሕክምና የሚያደርጉትና የቀዶ ሕክምና ባለሙያው ዶ/ር ሮበርት እንዳሉት እንደ መታጠን ያሉ ልማዳዊ ህክምናዎች በኢንተርኔትና በወሬ የሚዛመቱ ናቸው ብለዋል። " የጤና ባለሙያዎች ለሴቶች አማራጭ ሕክምናዎችን እንዳሉ ማስገንዘብ አለባቸው፤ ይህም ጠቃሚ የህክምና ዘዴዎችን እንዲመርጡ ያስችላቸዋል፤ ሊያጋጥማቸው ከሚችል ጉዳትም ይጠበቃሉ" ሲሉ በፅሁፋቸው ላይ አስያየታቸውን ሰጥተዋል።
news-52730295
https://www.bbc.com/amharic/news-52730295
ሱዳን በምስራቅ አፍሪካ የአሜሪካ ኤምባሲዎች ጥቃት ለተጎዱ ካሳ መክፈል አለባት ተባለ
ሱዳን በጎርጎሮሳዊያኑ 1998 ኬንያና ታንዛኒያ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ አልቃይዳ በፈጸመው የቦምብ ጥቃት ለተጎዱ ካሳ እንዲትከፍል የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ አሳለፈ።
በጥቃቱ ከ200 በላይ ሰዎች የሞቱ ሲሆን በሺህዎች የሚቆጠሩ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ሱዳን ለአልቃይዳ እና ለቡድኑ መሪ ኦሳማ ቢንላደን ቴክኒካዊ እንዲሁም የገንዘብ ድጋፍ አድርጋለች በሚል ነበር የተከሰሰችው። ውሳኔው የተላለፈውም አዲሱ የሱዳን መንግሥት አሜሪካ ሽብርተኛን ይደግፋሉ ካለቻቸው አገራት ዝርዝር ውስጥ አገራቸው እንድትሰረዝ ግፊት ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው። ሱዳንን የወከሉት ክርስቶፈር ኩራን፤ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የተላለፈው ውሳኔ በጎርጎሮሳዊያኑ 2011 የተላለፈውንና ከ4 ቢሊየን ዶላር በላይ ቅጣት ውስጥ 800 ሚሊየን ዶላር ለጉዳት ካሳ ያቀረበችው ገንዘብ እንደገና ተነስቷል ማለታቸውን ጠቅሶ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። ከ9 ዓመታትም በፊት በዋሽንግተን የፌደራል ፍርድ ቤት ሱዳን 6 ቢሊየን ዶላር ካሳ እንዲሁም 4 ቢሊየን ዶላር የጉዳት ቅጣት እንድትከፍል ማዘዙን ኒው ዮርክ ታይምስ ዘግቧል። በጎርጎሮሳዊያኑ 2017 ደግሞ ሱዳን የቅጣት ውሳኔውን ተከትሎ ክሱ የተመሰረተው በ2008 በተሻሻለው ሕግ ሲሆን ይህም ከ20 ዓመታት በፊት ለሆነ ነገር አይሰራም ስትል ስትከራከር ቆይታለች። ይሁን እንጂ ጠቅላይ ፍድ ቤቱ ኮንግረንሱ ሕጉን ወደኋላ ተመልሶ መጠቀም ይችላል በማለቱ ሰኞ ዕለት ውሳኔውን አስተላልፏል። እንደ ሁልጊዜው ሁሉ ሱዳን በሽብር ጥቃቱ ለተጎዱት የተሰማትን ሃዘን ትገልጻለች፤ ነገር ግን በእንደዚህ ዓይነት የተሳሳተ ተግባር ላይ ተሳታፊ እንዳልነበረችና ምንም ግንኙነት እንደሌላት ኩራን ተናግረዋል። አዲሱ የሱዳን መንግሥት ባለፈው ዓመት ለረዥም ዓመታት ሱዳንን ያስተዳደሩት ኦማር አል በሽር ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ አገሪቷ ከኢኮኖሚ መገለሉን ለማቆም የሚረዳትንና ከአሜሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማደስ እየሞከረች ነው። ኦማር አል በሽር በሙስና ወንጀል ክስ ከተመሰረተባቸው በኋላ እስር ቤት የሚገኙ ሲሆን በአሜሪካ መርከብና እና ኤምባሲዎች ላይ ጥቃት ሲፈጸም በሥልጣን ላይ ነበሩ።
43972610
https://www.bbc.com/amharic/43972610
ስዕልን በኮምፒውተር
ወይንሸት ጎሹ የአራተኛ ዓመት የኪነ-ህንፃ ተማሪ ናት። "ኦርዲነሪ ቢውቲ" የተሰኘው የዲጂታል ሥነ-ጥበብ ሥራዋ በየዕለቱ የሚታዩ ነገር ግን ብዙም ትኩረት ያልተሰጣቸው መስተጋብሮችን እንደሚያንፀባርቅ ትናገራለች።
ወይንሸት ሥራዎቿን ፌስቡክና ቴሌግራምን በመሰሉ ማህበራዊ ድረ-ገፆች ትለጠፋለች። እንደሷው የዲጂታል ሥነ-ጥበብ ሙያተኞችና ጓደኞቿ የሥራዎቿ ተመልካቾች ናቸው። በኮምፒውተር ሶፍትዌሮች በመታገዘ የሥነ-ጥበብ ሥራዎችን መፍጠር (ዲጂታል አርት)፣ በተቀረው ዓለም ታዋቂ ቢሆንም እንደ ወይንሸት ያሉ ኢትዮጵያዊያን አርቲስቶች ገና እውቅና አላገኙም። ወይንሸት፤ "ኦርዲነሪ ቢውቲ" የተሰኘውን ሥራዋን ከማህበራዊ ድረ-ገፅ ባሻገር በሥነ-ጥበብ ዐውደ ርዕይ ለመጀመርያ ግዜ የማሳየት እድል ያገኘችው ባለፈው ሳምንት ነበር። ዲጂታል ሥነ-ጥበብ ብዙም አለመታወቁና እንደ ሥነ-ጥበብ ዘርፍ አለመወሰዱ፤ የዲጂታል ሥነ-ጥበብ ዐውደ ርዕይ እንዳይዘጋጅ ምክንያት ነበር። ይህንን እውነታ ለመቀየር ዳግም ወርቁ፣ ነስረዲን መሀመድና ወንዱ ጉዲሳ "የሃ" የተሰኘ የዲጂታል ሥነ-ጥበብ ዐውደ ርዕይ ማሰናዳተቸውን ይናገራሉ። በአውደ ርዕዩ ሥራቸውን የሚያሳዩ ወጣቶች ለማግኘትም ማህበራዊ ድረ-ገፆችን ማሰስ ነበረባቸው። በኢንስታግራም ወይም በፌስቡክ ሥራዎቻቸውን ለተመልካች ከሚያደርሱ ወጣቶች መካከል ስድስቱን መረጡ። ወይንሸት ከአርቲስቶቹ አንዷ ስትሆን፣ ቤተልሔም ሞላ፣ ኤርምያስ አሰፋ፣ ፋኑኤል ልዑል፣ ኦማር ያሲን፣ ተካ ሀይሌና ዮሐንስ ባልቻም ተካተዋል። በቦስተን ደይ ስፓ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ፤ ዲጂታል ሥነ-ጥበበኞችና ማህበረሰቡን ለማቀራረብ ታስቦ መዘጋጀቱን የሲቪል ኢንጅነሪንግ ምሩቁ ዳግም ይናገራል። "በኮምፒውተር በመታገዝ የሚሰራው ዲጂታል ሥነ-ጥበብ ለኢትዮጵያ አዲስ ነው። ወጣቶች በየቤታቸው ሰርተው በማህበራዊ ድረ-ገፅ ላይ ያቀርባሉ" ይላል። ወጣቶቹ አዶቤ ፎቶሾፕና ኢሉስትሬተር የተሰኙ መተግበሪያዎችን ተጠቅመው ስዕሎች ይሰራሉ። ሆኖም ከማህበራዊ ድረ-ገፅ የዘለለ መድረክ እንደሌላቸው ነስረዲን ያስረዳል። ዲጂታል ሥነ-ጥበበኛው ነስረዲን "በፌስቡክ ጠንካራ የዲጂታል ሥነ-ጥበብ ባህል ቢኖርም፣ አደባባይ አልወጣምና ዐውደ ርዕዩን በየጊዜው ደጋግሞ ማዘጋጀት ያስፈልጋል" ይላል። ያሰባሰቧቸው አርቲስቶች የኪነ-ህንፃ፣ የኢንዱስትሪያል ዲዛይንና ሥነ-ጥበብ መነሻ ያላቸው ናቸው። "በብዙሀኑ ዘንድ እንደ ሥነ-ጥበብ ተቀባይነት ያለው በእርሳስና ወረቀት ወይም በብሩሽና ሸራ የተሰራ ስዕል ነወ። ይህን የማህበረሰቡን ምልከታ መለወጥ እንፈልጋለን" ሲል ነስረዲን ይናገራል። በአውደ ርዕዩ ከቀረቡ ሥራዎቹ መሀከል በቀለም ማከል (ከለራይዚንግ) የተዘጋጁት ይጠቀሳሉ። በንጉሡ ዘመን የተነሱ ጥቁርና ነጭ ፎቶዎችን በኮምፒውተር ቀለም ጨምሮ የማቅረብ ጥበብ ነው። የሦስት አውታር (ስሪዲ) ሥራዎችም ተካተዋል። "ዲጂታል ሥነ-ጥበብ ቦታ እንዲሰጠውና እንደ ጥበብ እንዲቆጠር እንፈልጋለን" በማለት ነስረዲን ይጠይቃል። ወይንሸት እንደምትለው ጥበብ በኮምፒውተር ሲታገዘ የፈጠራና ጥበባዊ ዋጋው የሚወርድ የሚመስላቸው አሉ። "አብዛኛው ሰው ሥራውን ኮምፒውተር የሚሰራው ይመስለዋል። ሀሳቡን ከማመንጨት ጀምሮ ሙሉ ሥራው የአርቲስቱ ድርሻ ስለሆነ እንደሌላው ጥበብ ነው" ትላለች። ዐውደ ርዕዩ ግንዛቤ ፈጥሮ የጥበቡን ተዳራሽነት እንደሚያሰፋውም ተስፋ ታደርጋለች።
news-49740045
https://www.bbc.com/amharic/news-49740045
እስር ላይ የሚገኙት የ'ቡድን 15' የቀድሞ የኤርትራ ባለስልጣናት እነማን ናቸው?
ኤርትራ እንደ ነጻ አገር ከተመሰረተች በኋላ አገሪቱን በፕሬዝዳንትነት እየመሩ ያሉት ኢሳያስ አፈወርቂ፤ ፖለቲካዊ ለውጦችን እንዲያካሂዱ በይፋ ጥያቄ ያቀረቡት ከፍተኛ ባለስልጣናት 15 ነበሩ።
በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ ባልና ሚስት ማህመድ አህመድ ሸሪፎና አስቴር ፍስሐጽዮን በነጻነት ትግሉ ውስጥና በኋላም በነበሩት ዓመታት በከፍተኛ ሥልጣን ላይ ከነበሩት አመራሮች መካከል የሆኑት እነዚህ 15 ባለስልጣናት፤ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ምርጫ እንዲካሄዱ፣ አገሪቱም በሕገ መንግሥት እንድትተዳደር የሚጠይቅ ግልጽ ደብዳቤ 1994 ዓ. ም. ጽፈው አሰራጭተው ነበር። • ኤርትራ ፖለቲከኞችን እና ጋዜጠኞችን እንድትለቅ ተጠየቀ ፕሬዝዳንቱ ለውጥ እንዲያደርጉ በደብዳቤ ጥያቄ ካቀረቡት መካከል 11ዱ በኤርትራ የጸጥታ ኃይሎች ወዲያዉኑ ሲያዙ፤ አራቱ ግን ሳይያዙ ቀርተዋል። በግልጽ ደብዳቤው ላይ የፖለቲካና የአስተዳደር መሻሻል እንዲደረግ ጥያቄ በማቅረባቸው ለእስር የተዳረጉት ባለስልጣናት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ፣ የት እንዳሉ በይፋ ሳይገለጽ እነሆ 18 ዓመት ሆናቸው። አራቱ እስር ሸሽተው እስካሁን ድረስ በስደት ላይ ይገኛሉ። በእስር ላይ የሚገኙት ባለስልጣናት ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተ በተለያዩ ጊዜያት ከተለያዩ ምንጮች ከሚወጡ መረጃዎች በስተቀር ምንም አይነት አስተማማኝ ነገር የለም። • ጄነራል ስብሐት ኤፍሬም ወደ ኤርትራ ተመለሱ ታሳሪዎቹ ባለፉት 18 የእስር ዓመታት ውስጥ ስላሉበት ሁኔታ የቤተሰብ አባሎቻቸውም ይሁኑ ሌሎች ወገኖች የሚያውቁት ነገር ስለሌለ የደህንነታቸው ሁኔታ አሳሳቢ እንደሆነ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ይናገራሉ። እነዚህ 'ቡድን 15' ተብለው የሚታወቁት ግለሰቦች እነማን ናቸው? ኡቁባይ አብረሐ፡ የጦር ሠራዊት ጀነራል የነበሩ ሲሆን፤ ቀደም ሲል የኤርትራ መከላከያ ሠራዊት ኤታማዦር ሹም፣ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር እንዲሁም የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ሠርተዋል። ግለሰቡ እጅግ የከፋ የአስም ህመም እንዳለባቸው ይነገራል። ኡቁባይ አብረሐ አስቴር ፍስሐጽዮን፡ በሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ ዳይሬክተር፣ የኤርትራ ብሔራዊ የሴቶች ማህበር ሥራ አስፈጻሚ አባል፣ ከ1977 (እአአ) ጀምሮ የኤርትራ ሕዝብ ነጸነት ግንባር ባለስልጣን፣ ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩትና አሁን በእስር ላይ የሚገኙት ማህመድ አህመድ ሸሪፎ የቀድሞ ባለቤት ሲሆኑ፤ የሆድ እቃ አልሰር እንዳለባቸው ይነገራል። አስቴር ፍስሐጽዮን ብርሐነ ገብረእግዚአብሔር፡ በጦር ሠራዊቱ ውስጥ የሜጀር ጄነራልነት ማዕረግ የነበራቸው ሲሆን፤ የአገሪቱ ተጠባባቂ ሠራዊት ዋና ኃላፊና ከ1977 (እአአ) ጀምሮ የኤርትራ ሕዝብ ነጻነት ግንባር የፖለቲካ ቢሮ አባል ነበሩ። • ኤርትራ፡"እያስተማሩን ሳይሆን ባሪያ እያደረጉን ነው" ባራኺ ገብረሥላሤ፡ እስከ ግንቦት 2001 (እአአ) ድረስ በጀርመን የኤርትራ አምባሳደር የነበሩ ሲሆን፤ ቀደም ሲል ደግሞ የትምህርት እንዲሁም የማስታወቂያና ባህል ሚኒስትር ሆነው ሠርተዋል። ባራኺ ገብረሥላሤ፡ ሐማድ ሐሚድ ሐማድ፡ በኤርትራ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ የመካከለኛው ምሥራቅ ክፍል ኃላፊ እንዲሆም በሱዳን የኤርትራ አምባሳደር በመሆን አገልግለዋል። ማህመድ አህመድ ሸሪፎ፡ ምክትል ፕሬዝዳንት፣ የአገር ውስጥ አስተዳደር ሚኒስትር፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ከመሆናቸው በተጨማሪ የኤርትራ ሕዝብ ነጸነት ግንባርን ከመሰረቱት አንዱ ናቸው። ማህመድ አህመድ ሸሪፎ ሳሌህ ኬኪያ፡ የትራንስፖርትና ኮሚዩኒኬሽን ሚኒስትር፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር እንዲሁም የፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት ኃላፊ በመሆን ሠርተዋል። ጴጥሮስ ሰለሞን፡ የባሕር ኃብት ሚኒስትር፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የኤርትራ ሕዝብ ነጸነት ግንባር ሠራዊት አዛዥና የደህንነት ኃላፊ የነበሩ ሲሆን፤ ከ1977 (እአአ) ጀምሮም የግንባሩ ፖለቲካ ቢሮ አባል ነበሩ። ጴጥሮስ ሰለሞን እስጢፋኖስ ስዩም፡ በሠራዊቱ ውስጥ እያሉ የብርጋዲዬር ጀነራልነት ማዕረግ የነበራቸው ሲሆን፤ እስከታሰሩበት ጊዜ ድረስ ደግሞ የአገር ውስጥ ገቢ አገልግሎት ኃላፊ በመሆን ሠርተዋል። ኃይሌ ወልደተንሳይ፡ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር፣ በድንበር ጦርነቱ ወቅት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የገንዘብ ሚኒስትር እንዲሁም የኤርትራ ሕዝብ ነጸነት ግንባር የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊና ከ1977 (እአአ) ጀምሮም የግንባሩ ፖለቲካ ቢሮ አባል ነበሩ። የስኳር ህምም እንዳለባቸው ይነገራል። ኃይሌ ወልደተንሳይ፡ ጀርማኖ ናቲ፡ የክልል አስተዳዳሪ። እነዚህ ሁለት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ ያሉበት ሁኔታ ሳይገለጽ ኤርትራ ውስጥ በእስር ላይ የሚገኙ የቀድሞ የኤርትራ ሕዝብ ነጸነት ግንባርና የኤርትራ መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናት ናቸው። በተለያዩ አገራት በስደት ላይ የሚገኙት የ'ቡድን 15' አባላት ደግሞ መስፍን ሐጎስ፣ አድሐኖም ገብረማሪያም፣ መሐመድ ብርሐን እና ኃይለ መንቆሪዮስ ናቸው። የኤርትራ መንግሥት ምን ይላል? በጥር 1995 ዓ. ም. የአገሪቱ ምክር ቤት ባደረገው ስብሰባ እነዚህ 'ቡድን 15' ተብለው የሚታወቁትን ፖለቲከኞች "ከዳተኞች እና ከፋፋዮች" ሲል ገልጿቸው ነበር። "ፕረዝዳንቱን በኃይል ከስልጣን ለማስወገድ ሞክረዋል" ሲልም ከሷቸዋል። • "አሁን ያገኘነው ሰላም ከሰው ሳይሆን ከአምላክ ነው"- ዘማሪ ሳሙኤል ተስፋሚካኤል ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ግን ስለ 'ቡድን 15'ም ሆነ በእስር ላይ ስለሚገኙት የቡድኑ አባላት በየትኛው አጋጣሚ ከመናገር ይቆጠባሉ። ከዘጠኝ ዓመት በፊት በአንድ የኳታር ጋዜጠኛ ሰለእነዚህ እስረኞች የተጠየቁት ፕሬዝዳንቱ፤ "ስለጉዳዩ የማውቀው ነገር የለም፤ ይህ ጉዳይ ቢረሳ ይበጃል" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። በተመሳሳይም ይኸው ጥያቄ ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ፤ በአልጀዚራ ጋዜጠኛ ቀርቦላቸው፤ "የታሰሩ አልነበሩም፣ የታሰሩ የሉም፤ የተሳሳተ መረጃ ነው ያለህ" ብለው ፈርጠም ያለ ምላሽ ሰጥተው ነበር።
43958908
https://www.bbc.com/amharic/43958908
ጅቡቲ በኢትዮጵያ ቴሌኮም ዘርፍ
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከሀገር ውስጥ ጉብኝታቸው በተጨማሪ ወደ ጂቡቲ አምርተው ኢትዮጵያ በወደቡ ላይ የባለቤትነት ድርሻ እንዲኖራት ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጅቡቲ ፓርላማ ፊት ቀርበውም ንግግር አድርገዋል፤ አልፎም በሁለት ቀናት ጉብኝታቸው ወቅት የሁለቱ ሀገራት የኢኮኖሚ ውህደትን እውን ለማድረግ ተስማምተዋል፡፡ ኢትዯጵያ ለአስርታት በተጠቀመበች የጂቡቲ ወደብ በየዓመቱ 1.5 እስከ 2 ቢሊዮን ዶላር መዋዕለ-ንዋይ እንደምታፈስ በጂቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ሻምቦ ፊታሞ ይናገራሉ። ይህም 70 በመቶ የጂቡቲ በጀት ያክል እንደሆነ ነው ጨምረው የሚያስረዱት። ኢትዮጵያስ ለወደብ ስምምነቱ በምላሹ ምን ይዛ ትቀርባለች? እንዲሁም የስምምነቱ ዝርዝር ምን ይሆን የሚሉት በበርካቶች ዘንድ የሚመላለሱ ጥያቄዎች ናቸው። ሀገራቱ በጋራ የሚያስተዳድሩት ወደብ ለማልማት በሐሳብ ደረጃ መስማማታቸው መነገሩ ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጉብኝት አስፈላጊነት ከፍ እንደሚያደርገው እየተነገረ ይገኛል። "የሁለቱ ሀገራት ስምምነትን ዝርዝር አፈፃፀም ለማየት በሁለቱ ሀገራት ሚኒስትሮች የሚመራ ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን የወደቡ ድርሻ ምን ያህል ይሆናል የሚለውን በቀጣይ የሚሰራ ነው" ይላሉ በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሻሜቦ ፊታሞ። ኢትዮጵያ ለበርካታ አመታት እየተጠቀመችበት ላለው የጂቡቲ ወደብ በየዓመቱ ከ1.5 እስከ 2 ቢሊዮን ዶላር መዋዕለ-ንዋይ እንደምታፈስ አምባሳደሩ ይናገራሉ። እንደ አምባሳደሩ አገላለፅ ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ በነባር ወደቦችም ይሁን ወደፊት በሚሰሩ ወደቦች ድርሻ እንዲኖራት የሚያደርግ ነው። ይህም ማለት ወደቦቹን በጋራ የማልማት ዕድል ኢትዮጵያ ታገኛለች። አምባሳደሩ "ኢትዮጵያ ወደቦቹን በጋራ የማልማት እድል ስታገኝ የወደቡን አገልግሎት አሰጣጥ እና ለምጣኔ ሃብት እመርታ ቅልጥፍና ሊሰጥ የሚችል የወደብ አገልግሎት እንዲኖር አብራ የማስተካከል፤ ችግሮች ካሉም አብሮ የማረም ስራ መስራት ያስችላታል" ባይ ናቸው። "ይህ የወደብ ስምምነት በሁለቱ ሀገራት መካከል የሚኖረውን የኢኮኖሚ ውህደትን የሚያሳይ እና በቀጣይም የሁለቱን ሀገራት የፖሊሲዎች የማጣጣም ስራም ይሰራል" ሲሉ ይገልፃሉ አምባሳደሩ። ይህ የወደብ ስምምነት ለሁለቱ ሀገራት የኢኮኖሚ ውህደቱ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ሲሉም ሃሳባቸውን ያስረግጣሉ። "ጅቡቲም ሆነ ኢትዮጵያ የጋራ ኢኮኖሚ ውህደት ቀይሰው ብዙ ፕሮጀክቶችን ያካሄዱ ሃገራት ናቸው ኢትዮጵያ በኢትዮ ጅቡቲ ኮሪደር ላይ የ12 ቢሊየን ዶላር ወጪ በማውጣት ባቡርን ጨምሮ የተለያዩ የማስፋፊያ ግንባታዎች እና አዳዲስ መሰረተ ልማት ግንባታዎችን አካሂዳለች።" አሁንም ጅቡቲ በኢትዮጵያ እንደ ቴሌኮም ዘርፍ ያሉ የአገልግሎት ሰጭ ተቋማት እና የምግብ ዋስትናቸውን እንዲያረጋግጡ የሚያስችላቸው የግብርና ዘርፍ ላይ እንዲሰማሩ ስምምነት ላይ መደረሱን አምባሳደሩ ጠቅሰዋል። ይህም የሆነው ኢትዮጵያ የፖሊሲ ለውጥ አድርጋ ለውጭ ባለሃብቶች የቴሌ ኮም ዘርፉን ከፍታ ሳይሆን አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመፍጠር እና ትስስሩን ለመፍጠር ታልሞ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ለጅቡቲ መንግሥት የኤሌክትሪክ ሐይል፣ ለእርሻ የሚሆን ሰፊ ሄክታር መሬት፣ ለመጠጥ ውሃ የሚሆን የከርሰምድር ውሃ ያለበት ቦታ መስጠቷ ይታወሳል።
50792399
https://www.bbc.com/amharic/50792399
የተባበሩት መንግሥታት የቺሊ ፖሊሶች ሰብዓዊ መብት ጥሰዋል አለ
በቅርቡ ከተቀሰቀሰው የቺሊ ሕዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ፤ የተባበሩት መንግሥታት የአገሪቱ ፖሊሶችና ወታደሮች ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል አለ።
ድርጅቱ፤ በአራት ግለሰቦች ግድያ የጸጥታ ኃይሎች እጅ እንዳለበት በምርመራ ደርሼበታለሁ ብሏል። 345 ሰዎች ከተረፈ ምርት የተሠራ ፕላስቲክ ተወርውሮባቸው አይናቸው መጎዳቱን፤ ሌሎች ደግሞ ወሲባዊ ጥቃት እንደደረሰባቸውም ድርጅቱ አመልክቷል። ባለፈው ኅዳር አጋማሽ ከታገቱት 28,000 ሰዎች መካከል 1,600 ያህሉ ለቅድመ ምርመራ እንደተያዙ ናቸው። የቺሊ ተቃዋሚዎች ማኅበራዊ ለውጥ እንዲመጣ እንዲሁም የአገሪቱ ሕገ መንግሥት ማሻሻያ እንዲደረግበት ጠይቀዋል። • በዓለማችን የተበራከቱት የተቃውሞ ሰልፎች የሚያመሳስላቸው ነገር ይኖር ይሆን? • ሰዎች 'የተቆጡ ሕጻናትን' ዝቅ አድርገው ይመለከታሉ • ከመጀመሪያው 'የብላክ ሆል' ምስል ጀርባ ያለችው ሴት ተቃውሞ ከተነሳበት ጊዜ አንስቶ ቢያንስ 26 ሰዎች ተገድለዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም ጉዳት ደርሶባቸዋል። የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ክፍል እንዳሳወቀው፤ የቺሊ መንግሥት ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ከ4,900 በላይ ናቸው ቢልም፤ ቁጥሩ ከዛም ሊጨምር እንደሚችል የገለጹ አካላት አሉ። የተባበሩት መንግሥታት፤ 113 አካላዊ እንግልት የደረሰባቸው ሰዎችን ጉዳይ መዝግቧል። ፖሊሶች፤ 24 ሴቶችና ወንዶች ላይ ወሲባዊ ጥቃት ማድረሳቸውን አሳውቋል። በተጨማሪም መሣሪያና አስለቃሽ ጭስ ያላግባብ ጥቅም ላይ እንደዋሉም ተመልክቷል። የድርጅቱ የቡድን መሪ፤ ኢማ ጉሬስ ዴላጋዶ እንደተናገሩት፤ ፖሊሶች ከፍተኛ ጭቆና ማሳደራቸውን ደርሰውበታል። በቺሊ መዲና ሳንድያጎ የሕዝብ መጓጓዣ ዋጋ ይጨምራል መባሉን ተከትሎ የተነሳው ተቃውሞ በመላው አገሪቱ ተሰራጭቷል። ኢ-ፍትሐዊነትን፣ የህክምና እና የትምህርት ዋጋ መናርን በመቃወምም ሕዝባዊ ሰልፉ ቀጥሏል። የፖሊሶች ጭካኔ የተሞላ እርምጃ የሕዝቡን ቁጣ ያጋጋለው ሲሆን፤ ፕሬዘዳንት ሰባስሽን ፒኔራ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል።
news-57167688
https://www.bbc.com/amharic/news-57167688
የሕዳሴው ግድብ፡ ኢትዮጵያ ከሕዳሴው ግድብ ሙሌት የሚያደናቅፋት ኃይል እንደሌለ ገለጸች
ኢትዮጵያ በመጭው የክረምት ወራት በታላቁ ሕዳሴ ግድብ የሙከራ ኃይል ማመንጨት እንደምትጀምር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ኢትዮጵያ ይህን ያለችው በመጭው ክረምት ለሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት እየተዘጋጀች ባለችበት ወቅት ነው። ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ከግድቡ ሙሌት እና ግንባታ ጋር ተያይዞ የአሠራር ሂደቱን "ምንም ዓይነት ኃይል እንደማያደናቅፈው" ገልጿል። ኢትዮጵያ ትናንት ረቡዕ የግድቡ ግንባታ 80 በመቶ መድረሱን አስታውቃለች። የግድቡ ተደራዳሪዎች ቴክኒክ ቡድን አባል በለጠ ብርሃኑ (ዶ/ር) ለብሔራዊ ጣቢያው በሰጡት አስተያየት የግድቡ አጠቃላይ ግንባታ 80 በመቶ መድረሱን ገልጸዋል። የግድቡ የሲቪል ግንባታ 91.8፣ የኤሌክትሮ መካኒካል ግንባታው 54.5 በመቶ እንዲሁም የኃይድሮሊክ ስትራክቸር ሥራው ደግሞ 55.2 በመቶ መድረሱንም አስረድተዋል። በመሆኑም ግድቡን ለማጠናቀቅ የሚቀረው 20 በመቶ ግንባታ እንደሆነ ተናግረዋል። በሌላ በኩል የግብጽ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሽኩሪ በቀጣዩ ክረምት ኢትዮጵያ የምታከናውነው የውሃ ሙሌት አገራቸው ላይ የጎላ ተጽዕኖ እንደማይኖረው መናገራቸው የግብጽ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ታላቁ የአስዋን ግድብ በቂ ውሃ በመያዙ የሕዳሴ ግድቡ በመጪው ክረምት ውሃ መያዙ ግብጽን አይጎዳም ሲሉ ነው ሳሚ ሽኩሪ የተናግሩት። የሕዳሴ ግድቡ በመጪው ክረምት ውሃ ከመያዝ በተጨማሪ በተያዘው ዓመት መገባደጃ ላይ ቅድመ ኃይል እንደሚያመነጭም በለጠ (ዶ/ር) ገልጸዋል። በተያዘው ዓመት የሕዳሴው ግድብ 13 ነጥብ 5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ እንደሚይዘ መንግሥት የገለጸ ሲሆን ይህም ባለፈው ዓመት ካቆረው 4 ነጥብ 9 ቢሊዮን ኪዮቢክ ሜትር ውሃ ጋር በዓመቱ መጨረሻ የውሃውን መጠን ወደ 18 ቢሊዮን ከፍ ያደርገዋል። የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበርና የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት ፊሊክስ ሴሸዴኪ በሕዳሴ ግድቡ ዙሪያ ሦስቱን አገራት ሊያግባባ የሚችል አዲስ ሃሳብ ማቅረባቸው ተስምቷል። የሦስቱን አገራት መሪዎች ተዘዋውረው ያነጋገሩት ፕሬዝዳንቱ ላመነጩት ሀሳብ ውጤታማነት የተባበሩት መንግሥታትና የአውሮፓ ሕብረት ድጋፋ እንደሚያደርጉ አል ሞኒተር የተባለ የዜና ተቋም ዘግቧል። ሀሳቡ በግድቡ ሙሊት ዙሪያ ኢትዮጵያ የጊዜ ሰሌዳዋንና የውሃውን መጠን መረጃ የምትሰጥበት ሆኖ አገራቱ ከሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት ላይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ያስችላል ነው የተባለው። በአባይ ወንዝ ላይ የተመሠረቱት ግብጽ እና ሱዳን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ውሃ ሙሌትና ግንባታ በፊት በቅድሚያ ከስምምነት ላይ መደረስ እንደሚገባ በተደጋጋሚ አቋማቸውን ገልጸዋል። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከ10 ዓመታት በፊት ሲጀመር የጀመረው ይኸው የሕዳሴው ግድብ ድርድር ለበካታ ጊዜያት ያለስምምነት መቋረጡ በቀጠናው ስጋት ፈጥሯል።
44964861
https://www.bbc.com/amharic/44964861
በወልዲያ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ ሁለት ሰዎች ሞቱ
በወልዲያ ማረሚያ ቤት ትናንት በተነሳ የእሳት ቃጠሎ ሁለት ታራሚዎች ሲሞቱ ሦስቱ ላይ ደግሞ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደረሰ።
ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል አንድ ታራሚ በወልዲያ ሆስፒታል ህክምና አግኝቶ ማታውኑ ሲመለስ አንዱ በሆስፒታል ተኝቶ እየታከመ ይገኛል። ሌላኛው ታራሚ ግን ጉዳቱ ከፍ ያለ በመሆኑ ወደ ደሴ ሆስፒታል ለተሻለ ህክምና ተልኳል በማለት የወልዲያ ማረሚያ ቤት አዛዥ ኮማንደር ፈንታው ደሳለኝ ለቢቢሲ ገልፀዋል። • በወልዲያ እና ፍኖተ-ሰላም ማረሚያ ቤቶች የእሳት አደጋ ደረሰ • የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ መኪናቸው ውስጥ ሞተው ተገኙ ዛሬ ማለዳ በድጋሚ ታራሚዎች የምህረት አዋጁ እኛን ለምን አላካተተንም በሚል ግርግር ለማንሳት የሞከሩ መሆናቸውን አንስተው፤ ነገር ግን ገብተው እንዳነጋገሯቸውና አሁን በማረሚያ ቤቶቹ መረጋጋት መታየቱን ለቢቢሲ ተናግረዋል። በአሁኑ ሰዓት በቃጠሎው ጉዳት የደረሰባቸውን ቤቶች ጥገና በማድረግ ላይ እንደሆኑም ማወቅ ችለናል። በተመሳሳይ ትናንት ሐምሌ 18 ቀን 2010 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በመቀሌ ማረሚያ ቤት በደረሰ የእሳት ቃጠሎ ሁለት እስረኞች መሞታቸውንና ሌሎች መጎዳታቸውን የማረሚያ ቤቱ ኃላፊ ኮማንደር ይትባረክ አለነ ለቢቢሲ እንደገለፁ መዘገባችን ይታወሳል። • በደብረ ማርቆስ ማረሚያ ቤት እሳት ተነሳ • በደሴ ከተማ የሸዋበር መስጂድ ላይ በደረሰ ጥቃት ሰዎች ተጎዱ ማክሰኞ ዕለት ግርግርና ቃጠሎ አጋጥሞት የነበረው የደብረ ማርቆስ ማረሚያ ቤትም በዛሬ ጠዋት የተቃውሞና ግርግር አዝማሚያዎች እንደነበሩና የአካባቢው ሽማግሌዎች ወደ ማረሚያ ቤቱ በመግባት ታራሚዎቹን በማነጋገር ለማረጋጋት ጥረት እንዳደሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
news-49288810
https://www.bbc.com/amharic/news-49288810
የጅግጅጋ የአንድ ዓመት ክራሞት ምን ይመስላል?
ቅዳሜ ሐምሌ 28 ቀን 2010 ዓ.ም.፤ በጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች ዘንድ ጠባሳን ጥሎ ያለፈ ቀን ነበር። ማንነትንና ኃይማኖትን መሠረት ያደረገው ጥቃት የበርካታ ሰዎች ሕይወትን ቀጥፏል፣ በርካቶችን አፈናቅሏል፣ ንብረትም አውድሟል።
ከአንድ ዓመት በኋላ ሐምሌ 28 ቀን 2011 ዓ.ም. ላይ፤ ጥቃቱን በመሸሽ ከጅግጅጋ ወጥተው የነበሩ በርካታ ነዋሪዎች ወደ ቀያቸው ተመልሰዋል። የከተማዋ ነዋሪዎች ወደቀደመ የተረጋጋ ሕይወታቸው ተመልሰዋል። ተቃጥለው ከነበሩት አብያት ቤተ-ክርስቲያናት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ተመልሰው ተገንብተዋል። • በምዕራብ ሀረርጌ ዞን በተሰነዘረ ጥቃት ሰባት ሰዎች መሞታቸው ተገለፀ ከእነዚህ መካከል ደግሞ አንዷ የሆነችውና በጅግጅጋ ከተማ የምትገኘው ኪዳነ-ምህረት ቤተክርስቲያን በዓመቱ ዳግም ተገንብታ ለምረቃ በቅታለች። "ጅግጅጋ ሃገሬ!" ብርቱኳን ለገሰ ምንም እንኳ ጅግጅጋን ተወልዳ ባታድግባትም፤ 20 ዓመት ያህል ኖራባታለች። ሁለት ልጆቿን ወልዳ ለመሳም የበቃችው እዚሁ ጅግጅጋ ውስጥ ነው። ብርቱኳንን ኪዳነ ምህረት ቤተ-ክርስቲያን ግቢ ውስጥ ስናገኛት ወሬ የጀመረችው የባለፈውን ዓመት በማስታወስ ነው። "ከአንድ ዓመት በፊት የተፈጸመብን የፖለቲካ ሴራ እንጂ የሶማሌ ሕዝብ እንዲህ አያደርግም። ከ20 ዓመታት በላይ በዚህ ከተማ ስኖር ሕዝቡን አውቀዋለሁ። እነዛ ወጣቶች በገንዘብ ተገዝተው ነበር" ትላለች። • "የወ/ሮ መዓዛ ንግግር ሌሎችንም [ክልሎች] የተመለከተ ነበር" የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ላይ የ3 ልጆች እናት የሆነችው ብርቱኳን፤ ሐምሌ 28 የሶማሌ ክልል ተወላጅ ባልሆኑ ዜጎች ላይ ጥቃቱ ሲፈጸም፤ የ7 ወር ነብሰ ጡር ነበረች። "በዕለቱ የማደርገው ጠፍቶኝ ነፍሴ ተጨንቃ ልጆቼን የምደብቅበት አጥቼ በጨርቅ ሸፍኜያቸው ነበር" በማለት ትናገራለች። "የ7 ወር ነፍሰጡር ስለነበርኩ ቤተሰቦቼ ጋር ሄጄ ወለድኩኝ። ከዛ ልጄ የሁለት ወር ጨቅላ እያለ የጥምቀት በዓልን የማከብረው ሃገሬ ጅግጅጋ ላይ ነው ብዬ ተመለስኩ" ትላለች። መልዓከ ሙሄ አባ ጽጌ ደስታ የጅግጅጋ ቅዱስ ሚካዔል ደብር አስተዳዳሪ ናቸው። ከአንድ ዓመት በፊት በተቃጣው ጥቃት በቅድሚያ ዒላማ ተደርጋ የነበረችው ቤተ-ክርስቲያን መሆኗን እና ከተቃጠሉት አስሩ አብያተ-ቤተክርስቲያነት ሰባቱ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ወድመው እንደነበረ ያስታውሳሉ። እንደ ብርቱኳን ሁሉ አባ ጽጌም በቤተ-ክርስቲያን እና በሌሎች ላይ የተቃጣው ጥቃት እንዲፈጸም የተደረገው በተቀነባበረ የፖለቲካ ሴራ መሆኑን ያምናሉ። "ችግሩ ከተከሰተ በኋላ በቤተ-ክርስቲያን ጉዳዮች ተይዤ በ13ኛው ቀን ነበር ወደ ቤቴ የተመለስኩት። እስከዚያው ድረስ ልጆቼን ጠብቆ ያቆየልኝ ሶማሌ ነው።" ይላሉ። የ30 ዓመቱ ወጣት ይድነቃቸው ታደለ፤ ትውልድ እና እድገቱ ጅግጅጋ ነው። የተቃጠሉ አብያተ-ክርስቲያናት አሰሪ እና አስመራቂ ኮሚቴ አባል ነው። "የማይቻለውን ችለን አልፈናል። ያን ወቅት እናልፈዋለን ብለን አላሰብንም ነበር። ፈጣሪ የሚሳነው የለም" የሚለው ይድነቃቸው፤ "ያን ሁሉ መዓት ባሳለፍንበት ዕለት የሞት አዋጁ ተሽሮ ይህን የመሰለ ቤተ-ክርስቲያን አስገንብተን ለማስመረቅ በመብቃታችን ደስታችን እጥፍ ድርብ ነው" በማለት ስሜቱን ይገልጻል። ሙሰጠፋ ሙሐመድ ኢጋል ደግሞ የሃገር ሽማግሌና ኡለማ ናቸው። • "የክልሎች ልዩ ኃይልን በተመለከተ ውይይት ያስፈልጋል" የሶማሌ ክልል ም/ፕሬዝደንት "አንድ መደብር ከመሸ ክፍት አይሆንም ነበር። ከምሽቱ አንድ ሰዓት ሲሆን ሁሉም እያስቆመህ መታወቂያ ይጠይቅህ ነበር። አሁን ግን እንደፈለግህ ትንቀሳቀሳለህ። እስከ አምስት ሰዓት ድረስ ሱቅ ክፍት ነው።" በማለት ከአንድ ዓመት በፊት የነበረውን የጅግጅጋ ሁኔታ ከዛሬው ጋር ያነጻጽራሉ። "በጅግጅጋ ያሉ ብሄሮች አብረው ይነግዳሉ፣ አብረው ይጫወታሉ፣ አብረው ጫት ይቅማሉ። አሁን ሁሉም ሰላም ነው።" ይላሉ አቶ ሙሰጠፋ። በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረጉት የሶማሌ ክልል ፕሬዝደንት ሙሰጠፌ ሙሐመድ፤ "ዋናው ትኩረታችን መሰል ጥቃቶች በክልላችን ዳግም እንዳይከሰቱ ማድረግ ነው። ባለፈው አንድ ዓመት ምንም ዓይነት ችግር አልተከሰተም። ማንም ሰው የየትኛውም ሃይማኖት ተከታይ ሆኖ መኖር ይችላል። ለዚህም የክልሉ መንግሥት ኃላፊነቱን ይወስዳል" ሲሉ በክልሉ የሚኖሩ የሌላ አካባቢ ተወላጆችና የተለያዩ ኃይማኖት ተከታዮች ስጋት እንዳይገባቸው ማረጋገጫ ሰጥተዋል። ነዋሪውስ ምን ይላል? "ከዚህ በፊት እንዲህ ያለ ነገር ገጥሞን አያውቅም። ወደፊትም ቢሆን ከዛ የከፋ ነገር ይከሰታል ብዬ አልጠብቅም። . . . በጭራሽ ይሄ ዳግም ይመጣል ብዬ አላስብም። ድሮስ ቢሆን ይሄ ይመጣል ብለን ጠብቀናል?" ያለችው ብርቱኳን ለገሰ ነች። ብርቱኳን በልበ ሙሉነት ይህን መሰል ጥቃት ወደፊት አይከሰትም እንድትል ካስቻሏት ምክንያቶች አንዱ፤ በክልሉ አስተዳደር ላይ ያላት እምነት ነው። "ያን ችግር ያመጣብን ፕሬዝደንት ሄዷል። አዲሱ ፕሬዝደንታችን ሙሰጠፌ ጥሩ አካሄድ ላይ ነው ያለው።" ትላለች። • መንግሥት በምን የሕግ አግባብ ኢንተርኔት ይዘጋል? • "ኦሮሞ እና ማዳጋስካርን የሚያገናኝ ፖለቲካ እንዳለ አላውቅም" የትነበርሽ ንጉሤ "ሁልጊዜም ቤተ-ክርስቲያን በፈተና መካከል ነው የምትኖረው። ፈተና ግን አያሸንፋትም" የሚሉት አባ ጽጌ "በአሁኑ ሰዓት ግን ለፈተና የሚያጋልጡ ትንኮሳዎች የሉብንም። ከክልሉ መንግሥት ጋር ጠንካራ ግንኙነት አለን" ይላሉ። "ፕሬዝዳንቱ መንበረ ሥልጣናቸውን እንደተረከቡ ቀድመው የመጡት ወደ እኛ ነው። ጎብኝተውን አጽናንተውናል።" ሲሉ መልካም አስተዳደር ስለዘረጉም ከቤተ-ክርስቲያኗ ሽልማት እንደተበረከተላቸው ይናገራሉ። ይድነቃቸው በበኩሉ፤ "ይከሰታል የሚል እምነት የለኝም፤ ግን እርግጠኛ መሆን አይቻልም። ምክንያቱም ተወልጄ ያደኩት እዚሁ ነው። እድሜዬ 30 ነው። በዚህ ሁሉ እድሜዬ ውስጥ እንዲ ያለ ነገር ይከሰታል ብዬ አልጠበቅም ነበር። ግን ተከሰተ። በሌላ በኩል ደግሞ የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ሙሰጠፌ ይህን ነገር እንደሚከላከሉ እምነት አለኝ" በማለት መጪውን መገመት አዳጋች እንደሚሆንበት ያስረዳል። አቶ ሙስጠፌ ደግሞ "ሐምሌ 28 በጣም ችግር ፈጥሮ ነበር። ይህን የፈጠረው ግን ሕዝብ ሳይሆን የፖለቲካ ደላላዎች ናቸው።" ይላሉ። "የፖለቲካ ደላላዎች ናቸው ሰው የሚያጋጩት። እዚያ እየሄዱ ኦሮሞ ሶማሌን ገደለ ይላሉ። እዚህ ደግሞ ራሳቸው ገድለው ሶማሌ ኦሮሞን ገደለ ይላሉ። እኛ እኮ እውነቱን እናውቃለን" ብለዋል። አቶ ሙሰጠፌ የሃገር ሽማግሌ እና የኃይማኖት መሪ እንደመሆናቸው ቀድሞውኑ ግጭቶች እንዳይከሰቱ የበኩላቸውን ለምን እንዳልተወጡ ሲያስረዱ "ሁሉ ሰው ጄል ኦጋዴንን ይፈራል። ትንሽ ከተናገርክ ጄል ኦጋዴን ትገባለህ። ከዛ 30 ዓመት 40 ዓመት ትቀመጣለህ። አሁን ግን አዲስ ነገር መጣ። ጄል ኦጋዴን ተዘጋ። መናገር ይቻላል። ከአሁን በኋላ ማንም አያጣላንም።" ሲሉ ተስፋቸውን ያገልፃሉ።
news-46286704
https://www.bbc.com/amharic/news-46286704
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አመፅን በፎቶ
የሮ አዱኛ ፎቶ አንሺ ነው። ባለፉት ሁለትና ሦስት ዓመታት የነበረውን ሀገር አቀፍ ተቃውሞ የሚያሳይ የፎቶግራፍና የቪድዮ ዐውደ ርዕይ በጉራምዓይኔ የሥነ ጥበብ ማዕከልና በጀርመን ባህል ማዕከል (ጎተ ኢንስቲትዮት) አሳይቷል።
በዐውደ ርዕዩ ከተካተቱ ፎቶዎች አንዱ ዐውደ ርዕዩ ከሀገራዊው አመፅ ባሻገር ባለፉት ጥቂት ወራት የተስተዋለውን አንጻራዊ ለውጥም ያንጸባርቃል። ፎቶ አንሺው ለውጡን ያሳይልኛል ብሎ ያመነው፤ ተፎካካሪ ፖለቲከኞችና የኪነ ጥበብ ሰዎች ወደ ሀገር ቤት ሲመለሱ የተደረገላቸውን አቀባበል ነው። • ስለኢትዮጵያ የቤተ ክርስቲያን ስዕሎች ምን ያህል ያውቃሉ? • የኢትዮጵያ ተረት ገፀ-ባህሪን በአኒሜሽን የፎቶግራፍና ቪድዮ ስብስቡ "የሮ ኬኛ" የሚል መጠሪያ ተሰጥቶታል። ከአፋን ኦሮሞ ወደ አማርኛ ሲመለሰስ "የኛ ጊዜ" ማለት ነው። የሮ "የኔ ጊዜ" የሚለውን ያለንበትን ዘመን በካሜራው መዝግቦ ለታሪክ ማስቀመጥ ግዴታው እንደሆነ ይናገራል። የተሰባበሩ የሰላም አውቶብሶችም በዐውደ ርዕዩ ይገኙበታል ሀገራዊው አመፅ የደረሰበትን ጥግ ማሳያ እንዲሆን የመረጠው ሰላም አውቶብሶች በድንጋይ ተሰባብረው፤ በእሳት ጋይተው የሚያሳዩ ፎቶግራፎችን ነው። ፎቶዎቹ በተለያዩ አካባቢዎች ተዘዋውሮ ያነሳቸው ናቸው። "ያኔ ሰላም አውቶብስን መሄጃ አሳጥተውት ነበር። ፎቶዎቹ ቄሮ፣ ዘርማና ሌሎቹም የወጣቶች ቡድኖች ተቃውሟቸውን ያሰሙበት መንገድ ትውስታ ናቸው።" • ወሎ በነዳጅ 'ልትባረክ' ይሆን? • ትራምፕ ውግዘት ከደረሰባት ሳዑዲ ጎን ቆመዋል ከቀረጻቸው ቪድዮዎች መካከል ማኅበረሰቡ ተቃውሞውን በጋራ ሲገልጽ፤ በደቦ አንድ ግለሰብ ላይ ወይም ንብረት ላይ እርምጃ ሲወሰድ የሚያሳዩም ይገኙበታል። "አንድ ሰው 'ቦንብ ይዟል' ቢባል እውነት መሆኑ ሳይጣራ መኪናው ይቃጠላል፤ 'ወያኔ ዝም፤ ወያኔ ዝም' እያሉ ነበር" የሚለው የሮ፤ የቡድን ስሜቱ ከአንድ ሰው ወደሌላው ሲጋባ የሚፈጠረውን ድባብ ቦታው ላይ ተገኝቶ ማስተዋሉን ያስረዳል። ነገሮች ተለውጠው ለዓመታት የሀገራቸውን መሬት መርገጥ ያልቻሉ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞችና ኪነ ጥበበኞች ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸው ሌላው የዐውደ ርዕዩ ትኩረት ነው። ለዓለምፀሐይ ወዳጆ፣ ለጀዋር መሐመድ እና ዳውድ ኢብሳ የተደረገውን አቀባበል አካቷል። "የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ሲደረግ፤ እኔም በፎቶና በቪድዮ ተቀበልኳቸው። እነሱን ፎቶ ማንሳት መቻል በራሱ ለውጡን አሳይቶኛል።" ለጀዋር የተደረገለት አቀባበል ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አህመድ ለተፎካካሪ ፖለቲከኞች 'ወደ ሀገራችሁ ግቡ' የሚል ጥሪ ካቀረቡ በኋላ፤ ጥሪው እውን መሆኑን ያረጋገጠው ለፖለቲከኞቹ ደማቅ አቀባበል ሲደረግላቸው መሆኑን ይናገራል። "ሰውን ምን ያህል ብትወጂው ነው ከነቀምት፣ ከአርሲ. . . በእግር አዲስ አበባ ድረስ መጥተሽ የምትቀበይው?" ሲል ይጠይቃል። አቀባበል በተደረገ ቁጥር ወደ አውሮፕላን ማረፊያ ያቀናውም በሁኔታው ስለተገረመ ነው። "የደስታ ስሜቱን ማየት ለኔ ትልቅ ታሪክ ነው፤ ፎቶዎቹና ቪድዮዎቹም የተከተሰውን ግዙፍ ነገር ያሳያሉ፤ ይህንን ለሰው ማካፈል ግዴታዬ ነው፤ በሥራዎቼ አንዱን የኢትዮጵያ ታሪክ ክፍል አሳያለሁ።" ዓለምፀሐይ ወዳጆ ታሰለጥናቸው የነበሩ የቀድሞው የህጻናት አምባ ልጆች፤ ዛሬ ነፍስ አውቀው መዝሙር ሲዘምሩላት ማየት፤ ሕዝብ ጀዋርን በአምቦ፣ በጊንጪ፣ በሀዋሳ፣ በሻሸመኔ ሲቀበለው ማየት የማይዘነጋው ታሪክ ነው። እንደ ፎቶ አንሺነቱ ታሪክን ይሰንዳል። የየእለቱ ክስተት የቀደመውን ቀን ታሪክ እየሸፈነ ስለሚሄድም፤ 'ትላንት ይህንን ይመስል ነበር' ለማለት ካሜራውን ይጠቀምበታል። ሥራዎቹን አሰባስቦ መጽሐፍ ማሳተም ያቀደውም ለዚሁ ነው። "ተወልጄ እስክሞት ያለው የኔ ጊዜ ነው። የአሁኑ ዘመን የኛም ጊዜ ነው። ስሜም የሮ [ጊዜ ማለት] ነው። ስለዚህ ጊዜን [የጊዜ ሀሳብን] ጠቅልዬ ዐውደ ርዕዩን "የኛ ጊዜ" ብዬዋለሁ።"
news-52437692
https://www.bbc.com/amharic/news-52437692
ኮሮናቫይረስ፡ ዓለም የኮሮናቫይረስ ክትባትን ለማግኘት ፊቱን ወደ ህንድ ያዞራል
የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፔዮ አገራቸው ዩናይትድ ስቴትስ ከህንድ ጋር በመሆን ለኮሮናቫይረስ የሚሆን ክትባት በማዘጋጀት ላይ መሆኗን አሳውቀዋል።
የሰውየው ንግግር ብዙም ያልተጠበቀ አልነበረም። ህንድና አሜሪካ ለ30 ዓመታት ያክል መድኃኒትና ክትባት በጋራ ሲያመርቱ ከርመዋል። የወባ መድኃኒት፣ ታይፎይድ ክኒን፣ ኢንፍኡዌንዛና የቲቢ በሽታን የሚያክሙ መድኃኒቶችን በጋር አምርተዋል። የወባ ክትባት ለማዘጋጀትም በጋራ እየሠሩ ነው። ህንድ መድኃኒትና ክትባት በማምረት በዓለማችን ቁንጮ ከሚባሉ አገራት መካከል ናት። የፖሊዮ፣ የማጅራት ገትር፣ የሳንባ ምች፣ የኩፍኝን ጨምሮ የሌሎችም በሽታዎች ክትባቶችን የሚያመርቱ ድርጅቶችም አሏት። የኮሮናቫይረስ ክትባትን ለማግኘት ደፋ ቀና ከሚሉ ድርጅቶች መካከል ስድስቱ ህንድ ነው የሚገኙት። ከእነዚህም አንዱ ሴረም የተባለው ድርጅት ነው። ይህ ድርጅት ክትባት አምርቶ በመሸጥ በዓለም የሚስተካከለው የለም። ይህ በሥራው ላእ ከ50 ዓመት በላይ የቆየ ድርጅት በዓመት 1.5 ቢሊዮን መድኃኒቶችና ክትባቶች ያመርታል። ፋብሪካው ህንድ ውስጥ ሁለት ትላልቅ ፋብሪካዎች አሉት። ኔዘርላንድስና ቼክ ሪፐብሊክም ውስጥ ማምረቻዎች ገንብቷል። ድርጅቱ 7 ሺህ ያህል ሠራተኞች እንዳሉት ይነገራል። ኩባንያው 20 የክትባት ዓይነቶችን ለ165 አገራት ያቀርባል። 80 በመቶ ምርቶቹ በጣም ተመጣጣኝ በሚባል ዋጋ የሚቀርቡ ናቸው። ድርጅቱ አሁን ኮዳጄኒክስ ከሚባል የአሜሪካ ባዮቴክ ኩባንያ ጋር 'ላይቭ አቴንዌትድ' የተሰኘ ክትባት ለማምረት እየጣረ ይገኛል። ክትባቱ የቫይረሱን ጎጂ ባሕሪ መቀነስ ወይም ማስወገድ ነው ሥራው። ''በወርሃ ሚያዚያ መጨረሻ ክትባቱን እንስሳት ላይ ለመሞከር ነው ዕቅዳችን'' ይላሉ የሴረም የህንድ ኃላፊ አዳር ፑናዋላ። ድርጅቱ ከዚህም አልፎ የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እየሠራው ያለውን ክትባት በገፍ ለማምረት እየተዘጋጀ ነው። ባለፈው ሐሙስ የኦክስፎርድ ተመራማሪዎች ክትባቱን ሰው ላይ መሞከር ጀምረዋል። ሁሉም ነገር እንደውጥናቸው ከሄድ የሳይንቲስቶቹ ዕቅድ መስከረም ላይ አንድ ሚሊዮን ክትባቶች ማምረት ነው። የኦክስፎርድ ዩኒቨርሰቲው ፕሮፌሰር አድሪያን ሂል ''በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ክትባቶች እንደሚያስፈልጉን እርግጥ ነው። በያዝነው ዓመት መጨረሻ [2020] ይህንን ወረርሽኝ ማስወገድ ነው ዋናው ዓላማው፤ ከዚያም በነፃነት መንቀሳቀስ ነው'' ይላሉ። የሕንዱ ኩባንያው ሴረም እስከ 500 ሚሊዮን ክትባቶች የማምረት አቅም አለው። ሌላኛው የህንድ ኩባንያ ባሃራት ባዮቴክ የአሜሪካው ዊስኮንሲን ዪነቨርሲቲ የሚሠራውን ክትባት 300 ሚሊዮን አምርቶ ለመላው ዓለም ለማከፋፈል ተዋውሏል። የዓለም ጤና ድርጅት ለህንድ መድኃኒት ተቋማት ያለውን አድናቆት ለመግለፅ ቃላት የሚያጥረው ይመስላል። መድኃኒት በጥራትና በብዛት ማምረት ከመቻላቸው በላይ ይህንን ወረርሽኝ በማጥፋት ለዓለም በጎ መዋል ይፈልጋሉ ሲል ይገልፃቸዋል። የጤና ባለሙያዎች ግን እንዲህ ይላሉ - ክትባት እንዲሁ በቀላሉ አይሠራምና በሁለት በሦስት ወራት ገበያ ላይ ይገኛል ብላችሁ እንዳትጠብቁ። በዓለም በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 3 ሚሊዮን እየተጠጋ ነው። የሟቾች ቁጥር ደግሞ ከ200 ሺህ በላይ ሆኗል። አስተማማኝነቱ የተረጋገጠ ክትባት አግኝቶ በብዛት ማምረትና ማከፋፈል ቢያንስ አንድ ዓመት ሊወስድ ይችላል። ቢሆንም ክትባት ማግኘታችን አይቀሬ ይመስላል።
news-49044912
https://www.bbc.com/amharic/news-49044912
አማራ ክልል፡ በእስር ላይ የርሃብ አድማ የመቱት የጸጥታ ኃላፊዎች
ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በአማራ ክልል ተሞከረ ከተባለው 'መፈንቅለ መንግሥት' ጋር በተያያዘ የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊዎችን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተካሄደ እንደሆነ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አስታወቁ።
ብ/ጄ ተፈራ ማሞና ኮሎ. አለበል አማረ • የብ/ጄነራል አሳምነው ፅጌ ሚስት መታሰራቸውን ልጃቸው ገለጸች • “የኢህአፓና መኢሶን ነገር አማራ ክልል ላይ ሊከሰት ይችላል ብዬ ነበር” ከእነዚህ ተጠርጣሪዎች መካከል የክልሉ የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊዎች የነበሩትን ብርጋዲየር ጀኔራል ተፈራ ማሞ፣ ኮሎኔል አለበል አማረ፣ ኮሎኔል ባምላኩ፣ ኮሎኔል አለባቸውና እና ሻለቃ እሸቱ ይገኙበታል። ሰኔ 16 ቀን 2011 ዓ.ም አንስቶ በእስር ላይ የሚገኙት ተጠርጣሪዎቹ ከሦስት ቀናት ፊት ጀምሮ 'ፍትህ እንሻለን' በማለት የርሃብ አድማ ላይ መቆታቸውን ቤተሰቦቻቸው ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በእስር ላይ ከዋሉ ጀምሮ በየቀኑ የምትጠይቃቸውና ጉዳያቸውን በቅርበት የምትከታተለው የብርጋዲየር ጀኔራል ተፈራ ማሞ ቤተሰብ መነን ኃይለ ማሪያም 'ፍትህ የለም፤ ምንም ባላደረግነው ነገር ነው የታሰርነው፤ እኛም ታግተን እንደነበር እየታወቀ ያለምንም ምክንያት እንንገላታለን' በሚል የርሃብ አድማውን እንዳደረጉ ትናገራለች። ለሦስት ቀናት የርሃብ አድማ ላይ የነበሩት ተጠርጣሪዎቹ በትናንትናው እለት የኃይማኖት አባቶች ሄደው ስለገዘቷቸው ትናንት ከቀኑ ስድስት ሰዓት ጀምሮ ምግብ መቅመስ መጀመራቸውን መነን ገልጻለች። ከዚህ ቀደም ተቀራርቦ መነጋገር እንደማይቻል የምታስታውሰው መነን የምንግባባው በርቀት በእጅ ምልክት ብቻ ስለነበር ፍላጎታቸውን ቀርበው ለመረዳት አለመቻላቸውን ታስረዳለች። • አብን ከ100 በላይ አባላቶቼ ታስረዋል አለ ክስተቱ ከተፈጠረ በኋላ ተጠርጣሪ ግለሰቦቹ ወደ ፌደራል ሊወሰዱ የነበረ ሲሆን ክልሉ እንዳስቀራቸውና ጉዳዩ በክልሉ እንዲታይ ማድረጉን እንደምታውቅም አክላለች። በተጨማሪም "ከዚህ በፊት በነበረው የፍርድ ቤት ቀጠሮ ክሳቸው ምን እንደሆነ አይነገራቸውም፤ ዝም ብለን ገብተን ነበር የምንወጣው፤ ገና ትናንት ነው ጠበቃ ማናገር ትችላላችሁ ተብለው ጠበቃ ወስደን ያነጋገርናቸው" ትላለች። እርሷ እንደምትለው ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ በኢትዮ - ኤርትራ ጦርነት ወቅት በጥይት ተመትተው እግራቸው ላይ ያልወጣ ስምንት ጥይት በመኖሩ አሁን ያሉበት ሁኔታ ሕመማቸውን አባብሶታል። "ከዚህ ቀደምም ጥይቶቹን አስወጣለሁ እያለ ባለበት ሰዓት ነበር ዘጠኝ ዓመታት የታሰረው፤ አሁንም ይሄው በዚህ ሁኔታ ነው የሚገኘው" በማለት ሌሎቹም እንዲሁ የተለያየ የጤና እክል እንዳጋጠማቸው ተናግራለች። ለሕይወታቸው ዋስትና ወስዶ የሚያክማቸው አካል ማነው? የሚለውም ስጋት እንደሆነባቸው አልደበቀችም። መነን አክላም በማህበራዊ ሚዲያ ከነ ጀኔራል ተፈራ ማሞ የተላለፈ መልዕክት ተብሎ የሚሰራጨው ሀሰት መሆኑንና ይህን መልዕክት ለመለዋወጥ ምንም ዓይነት እድል እንዳልነበር ገልጻለች። የኮሎኔል አለበል ልጅ ናትናኤል በበኩሉ እስከዛሬ ድረስ ቀርቦ መነጋገር ባይቻልም ከትናንት ጀምሮ ከቤተሰብም ሆነ ከሕግ ባለሙያዎች ጋር ተቀራርበው መነጋገር እንደቻሉ ገልፆልናል። "ላለፉት ሦስት ቀናት ምግብም ስናቀርብላቸው አይቀበሉንም ነበር" የሚለው ናትናኤል ከሰኔ 15ቱ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የክልሉን ሰላም ለመጠበቅ በሚጣደፉበት ጊዜ በወንድሞቻቸው ተጠርጥረው ለእስር መዳረጋችው ሕሊናቸውን ሳይፈታተነው እንዳልቀረ ተናግሯል። "በቁጥጥር ሥር ሲውሉ ወደ ፌደራል ሊወሰዱ እንደነበርና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፤ ጉዳዩን እዚህ ማየት ይችላል በሚል ታግለው እንዳስቀሯቸው አባቴ አጫውቶኛል" ብሏል። በርሃብ አድማው ላይ የተወሰነ የጤና እክል እንዳጋጠማቸው የሚናገረው ናትናኤል የታሰሩት እነርሱ ብቻ ሳይሆኑ የውትድርና እውቀት ያላቸው ጠንካራ ግለሰቦችም እንደሚገኙ አክሏል። "ክስ አልተመሰረተባቸውም፤ ማን እንደከሰሳቸው የተገለፀ ነገር የለም፤ በምን እንደተጠረጠሩም በግልፅ የሚያውቁት ነገር የለም" የሚለው ናትናኤል ከትናንት ጀምሮ ከጠበቆች ጋር እንዲገናኙና እንዲጠየቁ ሁኔታዎች መመቻቸታቸውን ነግሮናል። ቀጣይ ቀጠሯቸውም ሐምሌ 19 ቀን 2011 ዓ.ም እንደሆነም ታውቋል። • "በዚህ መንገድ መገደላቸው ከፍተኛ የፀጥታ ችግር መኖሩን ያሳያል" ጄነራል ፃድቃን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ በክልሉ አመራሮች ላይ ከተፈፀመ ግድያ ጋር ተያይዞ ከጉዳዩ ጋር ቅርበት አላቸው የሚባሉ የጸጥታ አካላትና ሌሎችም ተጠርጣሪዎች መኖራቸውን ይጠቅሳሉ። በመሆኑም እነዚህ ግለሰቦች በተጠረጠሩበት ጉዳይ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንና ምርመራ እየተካሄደ እንደሆነ ኮሚሽነሩ አስረድተዋል። "የማጣራቱ ሥራ ጊዜ ይፈልጋል" የሚሉት ኮሚሽነሩ ሥራው ሲጠናቀቅ ፖሊስ ጉዳዩን ለአቃቤ ሕግ እንደሚመራ ይናገራሉ። ፖሊስ ግለሰቦቹን ጠርጥሮ የያዛቸው በምን ምክንያት ነው ስንል የጠየቅናቸው ኮሚሽነር አበረ "እሱ ምርመራ ላይ ያለ ጉዳይ ስለሆነ ለሚዲያ ማብቃት ለእነርሱም ለአድማጭም አይጠቅምም" ሲሉ በአጭሩ መልሰዋል። ሰኔ 15 በተፈፀመው ጉዳይ ነው የተጠረጠሩት ከሚል መልስ በስተቀር ዝርዝር ሃሳብ ከመስጠትም ተቆጥበዋል። ምርመራውን በዋናነት የሚመራው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መሆኑን የገለፁት ኮሚሽነሩ "የፌደራል መንግሥት አስተዋፅኦ ምንም ነው ማለት ግን ስህተት ነው" ብለዋል- በትብብር እየሰሩ እንዳሉ በመግለፅ። 'የአደራ እስረኞች' ናቸው የተባለው የአገላለፅ ችግር መሆኑን በመጥቀስ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የራሱ ማቆያ ጣቢያ ስለሌለው በ6ኛ ፖሊስ ጣቢያ የሚገኙት ተጠርጣሪዎቹ የጣቢያው እስረኞች አይደሉም ለማለት እንደሆነ ኮሚሽነሩ አብራርተዋል። "አደራ ለዕቃ ነው፤ ለሰው አይደለም፤ የአደራ እስረኛ የሚባል የለም፤ ምርመራውን የሚያጣራው ጣቢያው አለመሆኑን ለመግለፅ ነው" ብለዋል። "እነዚህ ሰዎች ከማንም በላይ ጓደኞቼ ነበሩ ፤ አሁንም ጓደኞቼ ናቸው። ነገርግን ተጠርጥረው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው" የሚሉት ኮሚሽነሩ በቅርበት ሄደው እንዳነጋገሯቸው ገልፀዋል። ኮሚሽነሩ አክለውም "በእነሱ ስም ሌላ ኃይል የማይሆን ነገር እያለ ህዝቡን እንዳይረብሽ፤ እነርሱም ኃላፊነት እንዳለባቸው ተነጋግረናል። ጠበቃ እንዲቆምላቸው፣ ቤተሰብ እንዲጠይቃቸው፣ ምግብ እንዲመገቡ ተነጋግረን ተስማምተን ነው የተለያየነው" ብለዋል። ከሰኔ 15ቱ ግድያ ጋር በተያያዘ የተጠርጣሪዎች ቁጥር በየጊዜው የሚለዋወጥ ቢሆንም በሁለት መቶዎች የሚቆጠሩ ተይዘው ከመቶ በላይ የሚሆኑት ተፈተዋል ብለዋል- ኮሚሽነሩ። "አሁንም እያጣራን ማሰሩም፤ መፍታቱም ይቀጥላል" ሲሉ ተናግረዋል። በመጨረሻም በአሁኑ ሰዓት ክልሉ መረጋጋቱን ኮሚሽነር አበረ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
news-50709712
https://www.bbc.com/amharic/news-50709712
ለስድስት ሰአታት ልቧ መምታት ያቆመው ሴት በህይወት ተረፈች
አንዲት እንግሊዛዊት ልቧ ለስድስት ሰአታት መምታት ካቆመ በኋላ እንደገና መተንፈስ መጀመሯ የህክምና ባለሙያዎችን ግራ አጋብቷል።
የህክምና ባለሙያዎችም አጋጣሚውን እጅግ የተለየና ከስንት ጊዜ አንዴ ሊከሰት የሚችል ነው ብለውታል። ኦድሪ ሹማን ባለፈው ወር ነበር ስፔን ውስጥ ተራራ በመውጣት ላይ ሳለች ከበረዶ ጋር የተቀላቀለ ንፋስ የመታት። ከአደጋው በኋላ ሰውነቷ መቋቋም ከሚችለው በላይ ቅዝቃዜ ስላጋጠመው ልቧ መምታቱን አቁሟል። • በኡጋንዳ 16 ሰዎች በጎርፍ ተወስደው ሞቱ • ሳዑዲ ምግብ ቤቶች በጾታ የተለየ መግቢያ በሮችን መጠቀም የለባቸውም አለች የ 34 ዓመቷ ኦድሪ ስፔን ባርሴሎና ውስጥ የምትኖር ሲሆን አደጋው ካጋጠማት በኋላ መተንፈስ አቅቷት ነበር። በወቅቱ አብሯት የነበረው ባለቤቷ ሁኔታዋ አሳሳቢ ስለነበር ወዲያው የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችን እንደጠራ ገልጿል። '' የልብ ምቷን ለማዳመጥ ስሞክር ምንም ነገር የለም። ምንም አይነት ትንፋሽም አልነበራትም። በወቅቱ እንደሞተች እርግጠኛ ነበርኩ'' ብሏል። ከስድስት ሰአታት ለሞት የቀረበ ቆይታ በኋላ ኦድሪ አገግማ ወደ ሙሉ ጤንነቷ ስትመለስ በድጋሚ ተራራ መውጣት መጀመር እንደምትፈልግ አስታውቃለች። የባለቤቷን የድረሱልን ጥሪ ተከትሎ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ከሁለት ሰአት በኋላ በቦታው ሲደርሱ የኦድሪ ሰውነት የሙቀት መጠን 18 ዲግሪ ሴልሺየስ ደርሶ ነበር። ባርሴሎና የሚገኘው ቫል ዴብሮን ሆስፒታል ስትደርስም ምንም አይነት ትንፋሽም ሆነ የልብ ምት አልነበራትም። ነገር ግን በሞት አፋፍ ላይ አድርሷት የነበረው ከባድ ቅዝቃዜ ሕይወቷን ለማትረፍ ከፍተኛ ሚና እንደተጫወተ ሲከታተሏት የነበሩት ዶክተር ኤድዋርድ አርጉዶ ለጋዜጠኞች ገልጸዋል። '' ምንም እንኳን ሁኔታዋ ሙሉ በሙሉ እንደሞተ ሰው ቢሆንም ከባድ ቅዝቃዜ ከሞት የመከላከልም አቅም እንዳለው እናውቃለን።'' ''ምንም እንኳን ኦድሪ በበረዶው ምክንያት ሞት አፋፍ ላይ ብትደርስም እራሷን ስታ በነበረበት ወቅት ከባዱ ቅዝቃዜ ሰውነቷ እና አንጎሏ ከጥቅም ውጪ እንዳይሆኑ አቀዝቅዞ አቆይቷቸዋል'' ብለዋል ዶክተር ኤድዋርድ። ''ሰውነቷ የተለመደውና ጤናማ ሰው ያለው ሙቀት ኖሮት ልቧ መምታቱን ቢያቆም ኖሮ ያለምንም ጥርጥር ትሞት ነበር'' ሲሉ አክለዋል። ኦድሪና ሕይወቷን ያተረፉት ባለሙያዎች ኦድሪ ከ 12 ቀናት የሆስፒታል ቆይታ በኋላ ወደ ቤቷ የተመለሰች ሲሆን እጇ ላይ ካጋጠማት መለስተኛ ጉዳትና የመንቀሳቀስ ችግር ውጪ ጤናማ ሆናለች። • የቀድሞ የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ልጅ መደፈሯን እንዳትናገር አባቷ እንደተጫኗት አሳወቀች ከሆስፒታል ስትወጣም ከአደጋው በኋላ ስለነበሩት ስድስት ሰአታትም ሆነ ቀጣይ ቀናት ምንም የምታስታውሰው ነገር እንደሌለ ገልጻለች። '' ለሁለት ቀናት ያክል ምን እንደተፈጠረ የማውቀው ነገር አልነበረም። ስነቃ ሆስፒታል ውስጥ ነኝ። አሁን አንዳንድ መጽፍት ማንበብ ጀምሬያለሁ፤ በተለይ ደግሞ ስለ ቅዝቃዜና ስላሉት ጥቅምና ጉዳቶች'' ብላለች። በቅርቡም ወደ ተራራ መውጣት መመለስ እንደምትፈልግ ገልጻለች።
news-46652802
https://www.bbc.com/amharic/news-46652802
ኦነግ ከመንግሥት ጋር ያደረኩት ስምምነት አልተከበረም አለ
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ድርጅታቸው ከመንግሥት ጋር ከስምምነት ላይ የደረሰባቸው ጉዳዮች ተግባራዊ እንዳልተደረጉ ተናገሩ።
አቶ ዳውድ ጉለሌ በሚገኘው የኦነግ ጽህፈት ቤት ውስጥ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ''እየተጣሰ ነው'' ያሉት ከመንግሥት ጋር የደረሱት ስምምነት ምን እንደነበረ ዘርዝረዋል። በዚህ መሰረትም የተኩስ አቁም ስምምነቱ መከበር ፣ የመንግሥት የጸጥታ ኃይል አስከባሪ እና ደህንነት አካል ገለልተኛ እንዲሆን ማድረግ፣ የኦነግ ሠራዊት ወደ መንግሥት ኃይል እንዲካተት ማድረግ ከኦነግ ሠራዊት አንፃር ከመንግሥት ጋር የተስማሙባቸው እንደሆኑ አመልክተዋል። በተጨማሪም ባለፉት 27 ዓመታት የገቡበት ያልታወቁ የኦሮሞ ልጆች መጨረሻቸው ምን እንደሆነ መንግሥት ለህዝቡ እንዲያሳውቅ፣ ባለፉት 27 ዓመታት ወንጀል የፈጸሙ ግለሰቦች ለሕግ እንዲቀርቡ ማድረግና ለውጡ ሁሉን አቀፍ እንዲሆን በሚሉ ነጥቦች ላይ ከስምምነት ላይ ደርሰው እንደነበር ተናግረዋል። • "በኢትዮጵያ ፖለቲካ የኦነግ ስም ቅመም ነው" የኦነግ የፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ • «ኦነግ ሀገር ለመገንጠል ነው የምሠራው ብሎ አያውቅም» ሽጉጥ ገለታ (ዶ/ር) • “ትጥቅ መፍታት ለድርድር አይቀርብም”፡ መንግሥት ነገር ግን የተጠቀሱት የስምምነት ነጥቦች ተግባራዊ እንዳልሆኑና እየተጣሱ መሆናቸውን ገልጸው፤ በምሳሌነትም ለተሃድሶ ስልጠና አርዳይታ ገብተው የቆዩ የድርጅቱ ወታደሮች አያያዝን አንስተዋል። በስምምነቱ መሰረት 1300 የሚሆኑ የኦነግ ወታደሮች ስልጠና ወስደው የመንግሥት የጸጥታ አስከባሪ አካልን እንዲቀላሉ ወደ ማስልጠኛ እንዲገቡ መደረጋቸውን ተናግረዋል። "ይሁን እንጂ የኦነግ አመራሮች የሠራዊት አባላቱን እንዳይጎበኙ ተከልክለዋል፣ አንድ ፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም እንዲሰለጥኑ ይደረጋሉ፣ በካምፑ ውስጥ የጦሩ አያያዝ እንደ እስረኛ እንጂ ሰልጣኝ አይደለም" በማለት ከስምምነት ያፈነገጡ ተግባራት እየተፈጸሙ እንደሆነ ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪ አቶ ዳውድ የኦነግ አባላት በአዲስ አበባ ከተማ በደህንነቶች እየታፈኑ እየተወሰዱ ነው ብለዋል። ከዚህ ቀደምም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ አመራሮችን በመግደል ለግጭት መንስዔ የሆነው ኦነግ ነው ተብሎ የስም ማጥፋት እንደተፈፀመበት አመልክተው ክሱ ከእውነት የራቀ ነው ብለዋል። • "ገዳ የወደፊቱ የፖለቲካ ስርዓት መሆን ይችላል" ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ
news-43222465
https://www.bbc.com/amharic/news-43222465
ግብጻዊቷ ዘፋኝ አባይ ላይ ቀልደሻል ተብላ እስር ተፈረደባት
ግብጻዊቷ ዘፋኝ ሼሪን አብድል ዋህብ በአባይ ወንዝ ንጽህና ላይ በመቀለዷ ለስድስት ወራት በእስር እንድትቆይ ተፈረደባት።
ሼሪን በጣም ታዋቂ ግብጻዊት ዘፋኝ ናት በግብጽ ታዋቂ ከሆኑ ዘፋኞች አንዷ የሆነችው ሼሪን ለአድናቂዎቿ ከወንዙ ውሃ መጠጣት በፓራሳይት እንዲጠቁ ሊያደርጋቸው እንደሚቸል ገልጻላቸዋለች። "ይልቅ ኤቪያን የተባለውን የታሸገ ውሃ ጠጡ" ብላ ቀልዳለች። ላይላ አሜር የተባለች ሌላ ዘፋኝም በአንድ የሙዚቃ ቪዲዮዋ ምክንያት ባለፈው ማክሰኞ የሁለት ዓመት እስር ተፈርዶባታል። የሼሪንን ያህል ታዋቂነት የሌላት አሜር "መጥፎ ተግባር እና ለሥነ-ምግባር ተቃራኒ የሆነ መልዕክት አስተላልፋለች" በሚል ነው ጥፋተኛ የተባለችው። የሙዚቃ ቪዲዮው ዳይሬክተር እና ሌላ ተዋናይም እስር ተፈርዶባቸዋል። ካይሮ የሚገኝ ፍርድ ቤት ነው ሼሪንን ሃሰተኛ ዜና በማሰራጨት የፈረደባት። ጉዳዩ ሙሉ ለሙሉ እስኪጠናቀቅም የዋስትና ገንዘብ አስይዛ ነጻ መሆን እንደምትችል አህራም የተባለው ሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። ሼሪን 'ማሽረብቴሽ ሜን ኒልሃ' (ከአባይ ወንዝ ጠጥተዋል?) የሚለውን ዘፈን እንድትዘፍን ስትጠየቅ የሚያሳይ ቪዲዮ ከተለቀቀ በኋላ ነበር ባለፈው ህዳር ክስ የተመሰረተባት። "ከአባይ ውሃ መጠጣት በቢልሃርዚያ በሽታ እንድጠቃ ያደርገኛል" ብላ መልሳለች። ከተመሰረተባት ክስ በተጨማሪ የግብጽ ሙዚቀኞች ማህበር "በግብጽ ላይ በመቀለዷ ምክንያት" ሥራዎቿን እንዳታቀርብ ማገዱን አስታውቋል። ሼሪን በኮንሰርቱ ላይ "ለማይገባው ቀልዷ" ይቅርታ የጠየቀች ሲሆን፤ ስለጉዳዩ የተናገረችው ከአንድ ዓመት በፊት የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ውስጥ መሆኑን ጠቁማለች። "ውዷ ሃገሬ ግብጽ እና የግብጽ ልጆች ላይ ለፈጠርኩባችሁ ቁስል በሙሉ ልቤ ይቅርታ እጠይቃለሁ" ብላለች። የቢልሃርዚያ በሽታ በግብጽ ታሪክ ውስጥ ረዥም ጊዜ ያስቆጠረ ሲሆን በሽታው ለብዙ ሺህ ዓመታት እንዳይበላሹ ተደርገው በተቀመጡ አስከሬኖች ውስጥም ተገኝቷል። ሆኖም ግን ባለፉት አስር ዓመታት በተደረገ የጤና ፕሮግራም ችግሩን በከፍተኛ ደረጃ ለመቀነስ ተችሏል።
news-43845369
https://www.bbc.com/amharic/news-43845369
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የወልቃይት ንግግራቸውን አስመልክቶ ምላሽ ሰጡ
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ረፋድ ላይ በፋሲለደስ ስታዲየም ባሰሙት ንግግር ጎንደር በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ያላትን ቦታና እና የስኬት እና የጀግንነት ታሪኮች ካነሳሱ በኃላ አሁንም ህዝቡ "በትዕግስትና በአርቆ አሳቢነት'' ከጎናቸው እንዲቆም ጠይቀዋል።
"የስልጣኔ መሰረት፣ የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ጌጥና የኩሩ ህዝብ ምድር'' የሚሉ ሙገሳዎችን ያሰሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የነዋሪዎችን ፍላጎት ለማሳካት የክልሉና የፌደራል መንግስት እንደሚተጉ ቃል ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብይ ከሰዓት በኋላ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከተውጣጡ የከተማዋ ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል። በጎሃ ሆቴል በተካሄደው በዚህ ውይይት ላይ የወልቃይት ማንነት ጉዳይ እና ''መሬት ለሱዳን ያለ አግባብ ተሰጥቷል'' በሚል ቅሬታ ሲቀርብበት ስለነበረው ጉዳይ እንዲሁም ሌሎች በህዝቡ ዘንድ ቅሬታን የፈጠሩ ጉዳዮች እንደተጠየቁ በውይይቱ የተሳተፉ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወልቃይትን አስመልክቶ ምላሽ ሰጡ በተለይ የወልቃይት ጉዳይ በተመለከተ በመቀሌ ጉብኝታቸው ላይ ለቀረበ ጥያቄ በሰጡት መልስ 'የወልቃይትን ጉዳይ ከማንነት ጋር ሳይሆን ከመሰረተ ልማት ጥያቄ ጋር አዳብለውታል፤" ጥያቄውን አቅልለዋል በሚል ከሰሞኑ ቅሬታ ሲሰማ እንደነበረ ይታወሳል። ይሄንን በመለከተ ከወልቃይት ማንነት መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ስራ አስፈጻሚዎች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ አታላይ ዛፌን ጨምሮ ከሌሎችም ጥያቄ የቀረበላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመቀሌው ቆይታቸው የሰጡት መልስ ወልቃይትን በሚመለከት ለቀረበ ጥያቄ የተሰጠ መልስ ሳይሆን መሰረተ ልማትን በተመለከተ ለተጠየቀ ሌላ ጥያቄ የተሰጠ መልስ መሆኑን ለማብራራት እንደሞከሩ በስብሰባው ላይ የተገኙ ነዋሪዎች በተጨማሪ ለቢቢሲ ገልፀዋል። ከሁለት ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ ተንሰራፍቶ በነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ የጎንደር በከፍተኛነቱ ይታወሳል።
news-43946080
https://www.bbc.com/amharic/news-43946080
ማክሮንና ሩሃኒ በቀጭኑ ሽቦ
የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑዔል ማክሮን ከኢራን አቻቸው ሃሳን ሩሃኒ ጋር በኒውክሊዬር ጉዳይ ላይ በስልክ እንደተወያዩና ኢራን ወደ ድርድሩ እንትገባ እንዳሳሰቧቸው እየተነገረ ነው።
በስልኩ ውይይት እያካሄዱ ሳለ የኢራኑ ፕሬዚደንት ሩሃኒ ሰባት ሃገራት ተሳታፊ እየሆኑበት ያለው ውይይት ለድርድር የማይቅርብ እንደሆነ ለማክሮን ነገረዋቸዋል። ቀደም ብሎ ፈረንሳይ፣ እንግሊዝ እና ጀርመን ኢራን የኒውክሊዬር መሠሪያ ማብላላቷን እንድታቆም ዋነኛው መፍትሄ ውይይት ነው ብለው አቋም መያዛቸው ተዘግቦ ነበር። ቢሆንም የአሜሪካው ፕሬዝደንት ትራምፕ ያነሷቸው ጉዳዮችም ከግምት ውስጥ መግባት እንዳለባቸው ሃገራቱ አልሸሸጉም። ትራምፕ "የማይረባ" እያሉ የሚጠሩትን በአውሮፓውያኑ 2015 የተደረሰው ስምምነት በሚቀጥሉት ሳምንታት ሊያፈርሱት እንደሚችሉም ስጋት አለ። ለአንድ ሰዓት ያህል ዘለቀ በተባለው ውይይት ማክሮን በኒውክሊዬር ጉዳይ መወያየትን የመሰለ ነገር እንደሌ አፅንኦት ሰጥተው እንደበርና ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ያላትን ጣልቃ ገብነት ልብ እንድትል ለሩሃኒ እንደነገሯቸው ታውቋል። ሩሃኒ በበኩላቸው "ኢራን ቃል ከገባችው ውጭ የሆነ ነገር ላትቀበል ዝግጁ መሆኗን" ለማክሮን በግልፅ ነግረዋቸዋል። አሜሪካ ስምምነቱን አፈረሰቸው አላፈረሰቸው ኢራን እንደማያስጨንቃት፤ ይልቁንም የትራም የቅርብ ጊዜ ድርጊት እንዳሳቆጣቸው ነው ሩሃኒ የተናገሩት። ቢሆንም ኢራን ከፈረንሳይ ጋር ያላትን በጎ ግንኙነት ለማጠንከር ይበልጥ እንደሚተጉ አሳውቀዋል።
54347644
https://www.bbc.com/amharic/54347644
ቱርክ አውሮፕላኔን ተኩሳ ጣለችብኝ ስትል አርሜኒያ ከሰሰች
አርሜኒያና አዘርባጃን ወደለየለት ጦርነት እየገቡ ይመስላሉ። ወደ ግጭት ከገቡ ዛሬ አራተኛ ቀናቸውን ይዘዋል።
አርሜኒያ ከሰዓታት በፊት በሰጠችው መግለጫ ተዋጊ አውሮፕላኔን ቱርክ ተኩሳ ጥላብኛለች ብላለች። ቱርክ በዚህ ጦርነት ውስጥ ያለማወላወል ለአዘርባጃን ድጋፍ እየሰጠች ይገኛል። አርሜኒያና አዘርባጃን ወደ ግጭት የገቡት ናጎርኖ-ካራባ በተባለ ክልል የይገባኛል ጥያቄ ምክንያት ነው። አርሜኒያ ሶቪየት ሰራሹ SU-25 ተዋጊ አውሮፕላኗ ውስጥ የነበረው አብራሪ በዚህ ጥቃት እንደተገደለባት አምናለች። ቱርክ በበኩሏ ይህ ሐሰት ነው ብላለች። ግጭቱ እንደ አዲስ ከተቀሰቀሰ ጀምሮ ባለፉት ሦስት ቀናት ብቻ ከመቶ ሰዎች በላይ ተገድለዋል። ይህ ናጎርኖ-ካራባ የተሰኘው ክልል የአዘርባጃን እንደሆነ ነው የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሚያውቀው። የተባበሩት መንግሥታትም ይህንኑ ያረጋግጣል። ሆኖም አካባቢውን የሚገዙት በብሔር አርሜኒያዊያን የሆኑት ናቸው። ሁለቱ የቀድሞ ሶቭየት ኅብረት አገራት እንደ አውሮጳዊያኑ ከ1988 ጀምሮ ለ6 ዓመታት ጦርነት አድርገዋል። በዚህ ጦርነት 30ሺ ሰዎች ተገድለዋል። አንድ ሚሊዮን ሰዎች ተፈናቅለዋል። አሁን ጦርነቱ ከሁለቱ አገራት ባሻገር እንዳይሄድ ስጋት አለ። ቱርክ አዘርባጃንን በግልጽ እየደገፈች ሲሆን ሩሲያ በአርሜኒያ የጦር ሰፈር አላት። ሆኖም ግን ከአዘርባጃን ጋር ወዳጅ አገር ናት። ለዚህም ይሆናል በጦርነቱ በቀጥታ ከመሳተፍ ይልቅ ሩሲያ አገራቱ የጦር አቁም ስምምነት እንዲያደርጉ እየሞከረች ያለችው። ናጎርኖ ካራባህ ምንድነው? ይህ ስፍራ ተራራማ ክልል ነው። ስፋቱ 4ሺህ 400 ስኳየር ኪሎ ሜትር ነው። በአመዛኙ ክርስቲያን አርመኖችና ሙስሊም የቱርክ ዘርያ ያላቸው ሰዎች ይኖሩበታል። በሶቭየት ኅብረት ጊዜ የአዘርባጃን ግዛት ሆኖ ነገር ግን ራስ ገዝ አስተዳደር ነበር። በዓለም ማኅበረሰብ ዘንድ የአዘርባጃን ግዛት እንደሆነ ቢታወቅም ነዋሪዎቹ ግን የአርመን ዝርያ ያላቸው ዜጎች ናቸው። የራስ ገዝ አስተዳደሩ በተባበሩት መንግሥታት ብቻም ሳይሆን በአርሜኒያም እውቅና የተሰጠው አይደለም። አሁን ፈረንሳይ፣ አሜሪካና ሩሲያ የተኩስ አቁም እንዲካሄድ እየወተወቱ ይገኛሉ።
news-49984209
https://www.bbc.com/amharic/news-49984209
ሜክሲኮ ውስጥ አንድ ከንቲባ በመራጮቻቸው መኪና ላይ ታስረው ተጎተቱ
በደቡባዊ ሜክሲኮ የአንድ አካባቢን ከንቲባ ከጽህፈት ቤቱ አስወጥተው የጭነት መኪና ኋላ አስረው ጎዳናዎች ላይ ጎትተዋል ተብለው የተጠረጠሩ አስራ አንድ ሰዎች ተያዙ።
ከንቲባው ከመኪና ጋር ታስረው ሲጎተቱ ከሚያሳየው ቪዲዮ ላይ የተገኘ ምስል በከንቲባው ልዊስ ኤስካንደን ላይ ድርጊቱ ሲፈጸም ፖሊስ ጣልቃ ገብቶ ያስቆመ ሲሆን ከንቲባውም ከባድ ጉዳት ሳይደርስባቸው መትረፋቸውም ተነግሯል። ከንቲባው የምርጫ ቅስቀሳ በሚያደርጉበት ጊዜ የአካባቢውን መንገድ እጠግናለሁ ብለው የገቡትን ቃል አልፈጸሙም በሚል ነው ይህ ጥቃት የተሰነዘረባቸው። የአካባቢው አርሶ አደሮች በከንቲባው ላይ ጥቃት ሲፈጸሙ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የኖቤል የሰላም ሽልማትን ሊያሸንፉ እንደሚችሉ ግምቶች አሉ ከጥቃቱ በኋላ ጸጥታ ለማስከበር ተጨማሪ የፖሊስ መኮንኖች ወደ ቺያፓስ ግዛት መሰማራታቸው ተነግሯል። ሜክሲኮ ውስጥ ከንቲባዎችና ፖለቲከኞች ዕፅ አዘዋዋሪዎች የሚጠይቋቸውን ነገር አላሟላም ወይም አልተባበርም በሚሉ ጊዜ ለጥቃት መጋለጣቸው የተለመደ ነገር ሲሆን፤ ፖለቲከኞች በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የገቡትን ቃል መፈጸም ሲሳናቸው እንዲህ አይነት ጥቃት መሰንዘር የተለመደ አይደለም። ጥቃቱ የተፈጸመባቸው ከንቲባም በድርጊቱ ፈጻሚዎች ላይ የአፈናና የግድያ ሙከራ ወንጀል ክስ እመሰርታለሁ ብለዋል። በአካባቢው የነበሩ ሰዎች የቀረጹት ነው በተባለ ቪዲዮ ላይ ጥቃት ፈጻሚዎቹ ከንቲባውን ከጽህፈት ቤታቸው ጎትተው በማስወጣት ከመኪናው ኋላ በጉልበት ሲጭኗቸው ይታያል። መንገድ ላይ ከተተከሉ የደህንነት ካሜራዎች የተገኘው ምስል ደግሞ የከንቲባው አንገት ላይ ገመድ ታስሮ ሳንታ ሪታ በተባለው ጎዳና ላይ በመኪናው ሲጎተቱ ያሳያል። • አሥመራን አየናት፡ እንደነበረች ያለችው አሥመራ መኪናውን በማስቆም ከንቲባውን ከዚህ ጥቃት ለማስጣል በርካታ ፖሊሶች ጥረት ያደረጉ ሲሆን፤ በጥቃት አድራሾቹን በፖሊሶች መካከል በተፈጠረው ግብግብ ብዙ ሰዎች የመቁሰል ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከአራት ወራት በፊት ደግሞ ከንቲባው ላይ ጥቃት ለማድረስ ወደ ጽህፈት ቤታቸው የሄዱ ሰዎች ቢሯቸው ውስጥ ስላላገኟቸው ንብረት አውድመው መሄዳቸው ተነግሯል። ለከንቲባነት ከተደረገው ውድድር ቀደም ብሎ አሁን ጥቃት የተፈጸመባቸው ከንቲባ ከእጩ ተፎካካሪያቸው ደጋፊዎች ጋር አምባጓሮ ውስጥ ገብተው ነበር ተብለው ተጠርጥረው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ነበር። በኋላ ግን ማስረጃ ስላልተገኘ ተለቀዋል።
news-41471131
https://www.bbc.com/amharic/news-41471131
በአንድ ቦታ የተሰበሰቡ ሰዎችን ቁጥር እንዴት ማወቅ ይቻላል?
በተለያየ ምክንያት በአንድ ቦታ የተሰባሰቡ ሰዎችን ቁጥር መገመት ብዙ ጊዜ አከራካሪ ርዕስ ይሆናል።
በኢትዮጵያም በበዓላት፣ በፖለቲካ ስብሰባዎችና ሠልፎች እንዲሁም በሌሎችም ጉዳዮች በአንድ ቦታ የተሰባሰቡ ሰዎች ቁጥር በተደጋጋሚ ውዝግብ ሲፈጥር ይስተዋላል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበዓለ ሲመታቸው ላይ ከተገኘው የህዝብ ቁጥጥር ጋር በተያያዘ የመገናኛ ብዙሃንን ሲተቹ ቆይተዋል። ትራምፕ ወቀሳውን ያቀረቡት በቀድሞው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በዓለ ሲመት ላይ የተገኙ ሰዎች በቁጥር ይበልጣሉ በሚል መገናኛ ብዙሃን መዘገባቸውን ተከትሎ ነው። ትራምፕ በዓለ ሲመታቸው ላይ የተገኘው የህዝብ ብዛት 1.5 ሚሊዮን ነው ቢሉም መገናኛ ብዘሃን ግን ቁጥሩን ከ500 ሺህ ብዙም ያልዘለለ ነው ይላሉ። ስለዚህ በአንድ ቦታ የተሰበሰቡ ሰዎችን ቁጥር ለማወቅ እንዴት ማስላት እንችላለን? ባለሙያዎች እንደሚሉት በአንድ ቦታ የተሰባሰቡ ሰዎችን ቁጥር በትክክል ማወቅ ይከብዳል። በተለይ ደግሞ ሰዎች በሚንቀሳቀሱበት እና በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ሲሰባሰቡ ቁጥሩ ለፕሮፖጋንዳ ተግባር ስለሚውል በተቃራኒ ቡድኖች መካከል የውዝግብ ምንጭ ይሆናል። ባለሙያዎች ይህንን ለማስታረቅ የሚረዱ የተለያዩ ዘዴዎች እንዳሉ ይጠቁማሉ፡ 1. መሠረታዊ ጥያቄዎችን ይጠይቁ ስፖርታዊ ውድድሮችን ወይም የሙዚቃ ኮንሰርቶችን የሚታደሙ ሰዎች ብዛት በቀላሉ የሚታወቅ ነው። የተዘጋጁ ቲኬቶች ብዛት ከመታወቁም በላይ ሰዎች ወደ ቦታው ሲሄዱ ተቆጥረው መግባት ይችላሉ። ወደ ቦታው ሰዎችን ያጓጓዙ ባቡሮች እና መኪናዎች ትኬቶች ቁጥርም ሌላው መለኪያ ሊሆን ይችላል። 2. የቦታውን ስፋትና መያዝ የሚችለውን ቁጥር ማስላት የሚሰበሰቡት ሰዎች የሚይዙትን ቦታ መጠን ማወቅ አስፈላጊ ነው። ይህን ለማወቅ ካርታ መጠቀም ወይም ሰዎቹ የተሰባሰቡበትን ቦታ ከመሰባሰባቸው በፊት ወይንም በኋላ በመለካት ማወቅ ይቻላል። ሰዎቹ በሚሰባሰቡበት ወቅት የያዙትን ቦታ በትክክል ማወቅ ከፍተኛ እገዛ አለው። እዚህ ፎቶ ላይ ምን ያህል ስዎች ይታያሉ? 3. የጃኮብስ ክራውድ ቀመርን መተግብር ይህ ቀመር ሰዎች የተሰባሰቡበትን ቦታ በአራት ማዕዘኖች በመከፋፈል እያንዳንዱ አራት ማዕዘን ምን ያህል ሰው እንደሚይዝ ማስላት ነው። ቀመሩ ጋዜጠኛ በሆነው ፕሮፌሰር ሄርበርት ጃኮብስ የተሰራ ሲሆን በዚሁ መሠረትም አነስተኛ ሰው በተሰበሰበበት ቦታ፤ አንድ ካሬ ሜትር አንድ ሰው ይይዛል። በሌላ በኩል ብዙ ሰው በተሰበሰበበት አንድ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ 2.5 ሰዎች ሲኖሩ እጅግ የበዛ ሰው በተሰበሰበበት ቦታ ላይ ደግሞ በአንድ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ አራት ሰዎች ተጨናንቀው ሊኖሩ ይችላሉ። 4. ፎቶ መጠቀም ክፍተኛ ጥራት ያለውና ከሰማይ ላይ ወይንም ከሳተላይት የተነሳ ፎቶ በቀላሉ በርከት ብለው የተሰበሰቡ ሰዎችን ለመቁጠር ያስችላል። ሰዎችን በራሱ ቆጥሮ ውጤቱን ይፋ ለማድረግ የሚያስችል ሶፍት ዌርም ተግባራዊ ተደርጓል። ካልሆነም አሁንም የጃኮብስን ቀመር ተግባራዊ ይደረጋል። ፎቶን መጠቀም አስቸጋሪ የሚያደርገው ነገር ቢኖር የሰዎች ቁጥር በየጊዜው ተለዋዋጭ ከሆነ ነው። ይህ ከሆነ ደግሞ ሰዎች በተነሳው ፎቶ ላይ በዝተው ወይንም አንሰው ሊታዩ ይችላሉ። በተጨማሪም ሰዎች በጨለማ፣ በህንጻዎች፣ በዛፎች እና በሌሎች ምክንያቶች ካሜራ ውስጥ ላይገቡ ይችላሉ። 5. የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን ለመቁጠር አንድ ቦታ ላይ በመሆን የመቁጠር ዘዴን ይጠቀሙ ሰዎች ተሰብስበው የሚያልፉበት አማካይ ቦታ ላይ በተወሰነ ሰዓት የሚያልፉ ሰዎችን መቁጠር። በዚህ መሠረት ሁሉም ሰው የሚያልፍበትን የጊዜ መጠን በመለየት ምን ያህል ሰዎች እንደተሳተፉ ማወቅ ይቻላል። እነዚህ ሁሉ ዘዴዎች ትክክለኛ ቁጥር ባይሰጡም ለመገመት ግን ከፍተኛ እገዛ ያደርጋሉ።
news-52450156
https://www.bbc.com/amharic/news-52450156
እውን የትግራይ ክልል የራሱን ምርጫ ማካሄድ ይችላል?
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ በነሐሴ ወር ሊካሄድ ታስቦ የነበረው አገር አቀፍ ምርጫ እንዲራዘም መደረጉ ይታወሳል።
ከአምስት ዓመት በፊት በተካሄደው ምርጫ ድምጽ የሰጡ ሴት ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ አገራዊው ምርጫ በጊዜው እንዲካሄድ ሲጠይቅ የነበረው ህወሓት፤ የ2012 አገራዊ ምርጫ በማንኛውም ሁኔታ መካሄድ አለበት፤ ምርጫ የማይካሄድ ከሆነ በክልል ደረጃ ምርጫ እናካሂዳለን የሚል ይዘት ያለው የአቋም መግለጫ ከአምስት ወር በፊት አስነብቦ ነበር። ይህንኑ አቋሙን ሰሞኑን በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ላይ በድጋሚ አስነብቧል። በዚህም የተነሳ በእርግጥ የትግራይ ክልል የራሱን ምርጫ ማካሄድ ይችላል? የሚለው የበርካቶች ጥያቄ ሆኗል። የህወሓት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ነጋ ተገኝ፤ ይህ ቀደም ብሎ የነበረ አቋም መሆኑን በመግለጽ አዲስ የተወሰነ ውሳኔ መኖሩን እንደማያውቁ ይናገራሉ። "በቅርቡ በዚህ ጉዳይ ላይ አልተነጋገርንም፤ ቀደም ብሎ የወሰድነው አቋም ነው" ያሉት አቶ ነጋ ምናልባት የሥራ አስፈፃሚው አባላት ተነጋግረው ጽሑፉ በፌስ ቡክ ላይ እንዲወጣ አድርገው እንደሆነ መረጃው እንደሌላቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከዚህ በፊት ግን አገሪቷ ላይ ምርጫ የማይደረግ ከሆነ እኛ እናካሂዳለን የሚል አቋም በመያዝ ምርጫውን እንዴት ማስፈፀም ይቻላል በሚለው ላይ በደንብ መወያየት እንዳለባቸው መነጋገራቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። "በዚህ ወቅት ግን በማዕከላዊ ኮሚቴ ደረጃ በዚህ ጉዳይ አልተነጋገርንም" ያሉት አቶ ነጋ ህወሓት ምርጫው መካሄድ እንዳለበት የያዘው አቋም ከስምንት ወራት በፊት የነበረ መሆኑን ያስታውሳሉ። በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት የፓርቲው ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ተጠሪ ጋር ብንደውልም ኃላፊውን ማግኘት ሳንችል ቀርተናል። በርግጥ የህወሓት የምርጫ አካሄዳለሁ አቋም ሕጋዊ መሰረት አለው? ዶ/ር አደም ካሴ በኔዘርላንድስ የአስተዳደር እና ዲሞክራሲ አማካሪ ናቸው። ምርጫን የማካሄድ፣ የምርጫ ሕግን የማውጣት፣ የወጣውን ደግሞ ማስተዳደር ሥልጣን ያለው የፌደራሉ መንግሥቱና ምርጫ ቦርድ ነው ሲሉ ይናገራሉ። ከዚያ ውጪ የህወሓት አመራሮች ሕጉን ተከትለው ካልተቃወሙ በስተቀር በራሳቸው ዝም ብሎ መሄድ ስልጣኑም የላቸውም ይላሉ። በዚህ ሃሳብ የሚስማሙት ደግሞ የሕግ አማካሪው አቶ ኤፍሬም ታምራት ናቸው። አቶ ኤፍሬም "ምርጫን በሚመለከት ሊጠሩ የሚገቡ ነጥቦች አሉ ብዬ አስባለሁ" ካሉ በኋላ ምርጫ በዋናነት አላማው ዜጎች በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ራሳቸው በቀጥታ ወይንም በተወካዮቻቸው አማካኝነት የመሳተፍ መብት ከሚለው እሳቤ መመንጨቱን ያስረዳሉ። በዚህም የተነሳ የምርጫ ሥርዓት መዘርጋቱን፣ ዜጎችም መምረጥና የመመረጥ መብት እንደሚኖራቸው ይገልፃሉ። "መንግሥት የሕዝቦች ፈቃድ ነው ስለሚባል ዜጎችን በመምረጥና በመመረጥ ማሳተፍ ብቻ ሳይሆን ምርጫው ነፃና ገለልተኛ መሆን አለበት" የሚሉት አቶ ኤፍሬም፤ በዚህም የተነሳ በሕገ መንግሥቱ ምርጫ ቦርድ ነጻና ገለልተኛ ሆኖ መቋቋሙን ይናገራሉ። "ይህ ምርጫ ቦርድ የፌደራል የዲሞክራሲያዊ ተቋም ነው። በክልል ጽህፈት ቤቶች አሉት። አገር አቀፍ ምርጫ ባልተደረገበት በክልል ምርጫ እንደርጋለን ማለት፣ የፌደራል ዲሞክራሲያዊ ተቋም ባልተሳተፈበት፣ ባልታዘበበት ምርጫ ማድረግ የምርጫውን ሕጋዊነት፣ ነፃና ገለልተኝነት ጥያቄ ውስጥ ይጥለዋል" በማለትም ክልሉን የሚያስተዳድረው ፓርቲ ህወሓት፤ ምርጫ ማካሄድ እንደማይችል ያብራራሉ። "ምርጫ ሲባል ዝም ብሎ አንድ ቀን ሄዶ መምረጥ አይደለም" የሚሉት ዶ/ር አደም በበኩላቸው "በቅድሚያ የምርጫ ወረዳዎች መወሰን አለባቸው። ያለውን እንኳ ይጠቀማሉ ቢባል ያም እንደገና መወሰን አለበት። ከዚያም ሲያልፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች መመዝገብ ያስፈልጋቸዋል" በማለት ሂደቱን ያብራራሉ። የፖለቲካ ፓርቲዎች ከተመዘገቡ በኋላ ምልክታቸውን ማሳወቅ፣ መራጮች መመዝገብ፣ ቅስቀሳ ማካሄድ እንደሚያስፈልግ በማስታወስ ህወሓት "ሁሉን ነገር የማድረግ የሕግ ሥልጣን ብቻ ሳይሆን በተግባር አቅምም፤ ተቋማዊ ዝግጅትም አለው ብዬ አላስብም" ይላሉ። የሕግ ባለሙያው አቶ ኤፍሬም በበኩላቸው ምርጫ ቦርድ አገራዊ ምርጫውን ሲያራዝም አገሪቱ በኮሮናቫይረስ ውስጥ ስላለች ነው በማለት "አሁን ባለንበት ሁኔታ የተለያዩ የሲቪልና ፖለቲካዊ መብቶች ይገደባሉ" ይላሉ። እነዚህ መብቶች መካከል ደግሞ የመመረጥና የመምረጥ መብት እንደሚገኝበት በመግለጽ ይህ ጉዳይ ሕገ መንግሥቱ ላይ የሰፈረ፣ ምርጫ ቦርድም በሕገ መንግሥቱ መነሻነት ያንን ውሳኔ ማሳለፉን ይገልፃሉ። "ስለዚህ ሁኔታዎች ተሻሽለው ወደ መደበኛው ሕይወት እስክንመለስ ድረስ ስለምርጫ የምናወራበት ሕገ መንግሥታዊ መሰረት ያለን አይመስለኝም" ይላሉ። ዶ/ር አደም በበኩላቸው የክልሉ መንግሥት ወይንም ህወሓት ምርጫውን አደርጋለሁ ብሎ እርምጃ ቢጀምር ያ ተቋም ነፃነት አለው ወይ? በሌሎቹ ይታመናል ወይ? እንደምርጫ ቦርድ ሆኖ የሚያገለግል ተቋማዊ መዋቅር ይኖረዋል? የሚሉ ጥያቄዎችን በማንሳት "እኔ ግን አለው ብዬ አላምንም" ይላሉ። መፍትሔው ታዲያ ምንድን ነው? የሕግ ባለሙያው አቶ ኤፍሬምም ሆኑ የአስተዳደርና ዲሞክራሲ አማካሪው ዶ/ር አደም ለተፈጠረው ፖለቲካዊ አለመግባባት ከመነጋገር የተሻለ ሌላ አማራጭ አይታያቸውም። "የዚህ ችግር ምንጩ በአዲሱ የብልጽግና ፓርቲና በህወሓት ወይንም በነባሩ ኢህአዴግ መካከል ያለ የፖለቲካ ግጭት ነው" የሚሉት ዶ/ር አደም "የተወሰዱ እርምጃዎችና ውሳኔዎች ሕጉን ይጥሳሉ ወይም ይቃረናሉ የሚሉ ከሆነ፤ አይ እኔ ምርጫ አካሄዳለሁ ማለት ሳይሆን . . . ወደ ሕገ መንግሥት አጣሪ ኮሚቴ፣ ከዚያም አልፎ ወደ ፌደሬሽን ምክር ቤት ሄዶ ለመፍታት መሞከር ይሻላል" በማለት ይመክራሉ። "ምናልባት እነርሱ ሕጉን ጥሰዋል እኛም ሕጉን እንጥሳለን ከሆነ፤ የአንድ ጥሰት ሌላኛውን ጥሰት ትክክል አያደርገውም" በማለትም እንዲህ አይነት ቅራኔ ምንጩ ፖለቲካዊ ግጭት በመሆኑ ከሕግ ይልቅ ፖለቲካዊ ውሳኔ መፍትሄ ሊያመጣ እንደሚችል ይጠቁማሉ። ጉዳዩ ላይ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አቋም ምን እንደሆነ ለማወቅ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ እና የቦርዱ ቃል አቀባይ የእጅ ስልክ ላይ ብንደውልም ልናገኛቸው አልቻልንም።
news-52932156
https://www.bbc.com/amharic/news-52932156
በአሜሪካ በርካታ የፖሊስ አባላት ሥራቸውን ለቀቁ
የጭካኔ ተግባር ፈጽመዋል የተባሉ ሁለት ባልደረቦቻቸው ያለደሞዝ እረፍት እንዲወጡ መደረጋቸውን በመቃወም መኮንኖቹ የነበሩበት የነበሩበት ቡድን አጠቃላይ ሥራ አቁሙ።
The man approached police in Buffalo before being pushed backwards ሐመስ ዕለት በስፋት በተሰራጨው ቪዲዮ ላይ በኒውዮርክ ግዛት ቡፋሎ በተባለ ከተማ ውስጥ የፖሊስ መኮንኖቹ አንድ አዛውንትን ገፍትረው ወደ መሬት ሲጥሏቸው ታይቷል። የፖሊስ መኮንኖቹ አፍሪካ አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ በአንድ ፖሊስ መተንፈስ እስኪያቅተው ድረስ አንገቱ ላይ በጉልበቱ ቆሞ ከተገደለ በኋላ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ለማርገብ የተጣለውን ሰዓት እላፊ ለማስከበር በአካባቢው በተሰማሩበት ወቅት ነበር ጉዳቱ ያጋጠመው። በዚህም ሳቢያ የ75 ዓመቱ አዛውንት ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። ድርጊቱን ተከትሎም ሁለት ፖሊሶች ከሥራ የታገዱ ሲሆን እርምጃውን በመቃወም በአድማ በታኝ ቡድኑ ውስጥ ያሉ ሁሉም 57 አባላት ሥራቸውን ለቀዋል። ቡፋሎ ኒውስ እንደዘገበው ሁለቱ የፖሊስ አባላት ላይ የተወሰደው እርምጃ ድንገተኛ ምላሽ ከሚሰጠው ቡድን እንጂ በአጠቃላይ ከፖሊስ ኃይሉ እንዳልታገዱ አመልክቷል። የአካባቢው ፖሊሶች ማህበር ፕሬዝዳንት የሆኑት ጆን ኢቫንስ ለጋዜጠኞች እንዳሉት ሁለቱ ፖሊሶች በምክትል ፖሊስ ኮሚሽነሩ የተሰጣቸውን አደባባዩን ከሰዎች እንቅስቃሴ ነጻ የማድረግ ትዕዛዝ ተግባራዊ እያደረጉ ባሉበት ጊዜ ነው ከሰውዬው ጋር ተገናኝተው አደጋው የተፈጠው ብለዋል። የኒው ዮርክ ገዢ አንድሩ ኩሞ ክስተቱን ተከትሎ ሁለቱ ፖሊሶች ከሥራቸው መባረር እንዳለባቸውና "የወንጀል ክስ ለመመስረት የሚያስችል" ምርመራ እንዲደረግ ጠይቀዋል። ጉዳቱ የደረሰባቸው አዛውንት በጎና ላይ በቡድን ሆነው ወደሚጓዙ የፖሊስ አባላት ሲጠጉ ተንቀሳቃሽ ምስሉ የሚያሳይ ሲሆን ፖሊሶቹም መንገድ ለማስለቀቅ እንደገፈተሯቸው ይታያል። ወድቀው ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰብ ማርቲን ጉጊኖ እንደሚባሉና አሁን ሆስፒታል ውስጥ ሁኔታቸው ከባድ ቢሆንም በተረጋጋ ሁኔታ ላይ እንሚገኙ ባለስልጣናት ገልጸዋል። አዛውንቱ ለረጅም ዘመናት የማኅበራዊ ፍትሕ ተከራካሪ ሆነው የተለያዩ ኢ-ፍትሃዊ ድርጊቶችን ሲቃወሙ የነበሩ እንደሆኑ አንድ የመብት ተከራካሪ ቡድን ከክስተቱ በኋላ ባወጣው መግለጫ ላይ አመልክቷል።
news-46381918
https://www.bbc.com/amharic/news-46381918
ቻይናዊው ሳይንቲስት መንትዮች ኤች አይ ቪ እንዳይዛቸው ዘረ መላቸውን ማስተካከሉ ወቀሳ አስነሳ
ቻይናዊው ሳይንቲስት የመንታዎቹ "ዘረ መል" ማስተካከል ትክክል ነው ሲል ተከራከረ።
ሳይንቲስቱ ሆንግ ኮንግ በተካሄደ የዘረ መል (ስነ ባህርይ) ስብሰባ ላይ ባደረገው ንግግር የመንታዎቹን ፅንስ ኤች አይ ቪ ኤድስ እንዳይዛቸው አድርጎ ውስጣዊ አወቃቀራቸውን ማስተካከሉ የሚኮራበት እንደሆነ ተናግሯል። በዚህ ሳምንት ይፋ ያደረገው ስራው ገና አልተረጋገጠም። •"ፓስፖርት መስጠት አልተከለከለም" የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች ተቋም •ታሪክ እየቀየሩ ያሉት ሴቶች •በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ወደ ፅዮን ውሰዱን ተማፅኖ የተለያዩ ሳይንቲስቶች የሳይንቲስቱን ስራ ያወገዙ ሲሆን፤ ቻይናን ጨምሮ በተለያዩ ሃገራት ዘረ መልን መቀየር የተከለከለ ነው። ሳይንቲስቱ የሚሰራበት ሸንዘን የሚገኘው ሳውዘርን ዩኒቨርስቲ ኦፍ ሳይንስ ኤንድ ቴክኖሎጂ ስለ ምርምሩ ምንም እንደማያውቅ ጠቅሶ በአስቸኳይ ምርመራ እንደሚጀምርም አሳውቋል። ሳይንቲስቱ ከየካቲት ወር ጀምሮም ሳይከፈለው እረፍት እንደወጣም ዩኒቨርስቲው ጨምሮ አስታውቋል። ሳይንቲስቱም የምርምር ስራውን በተመለከተ ዩኒቨርስቲው ምንም እንደማያውቅና የሙከራ ስራውንም በራሱ ገንዘብ እንደሸፈነ ገልጿል። ሉሉና ናና የሚባሉት መንትዮች በጤናማ ሁኔታ እንደተወለዱና ለቀጣዩ 18 ዓመታትም ክትትል እንደሚያደርግላቸው ገልጿል። ለዚህ የሙከራ ስራ ስምንት ኤችአይቪ ቫይረስ ያለባቸው አባቶችና ኤች አይቪ ቫይረስ ነፃ የሆኑ እናቶች ባለትዳሮች በፈቃደኝነት የተሳተፉ ሲሆን ሁለት ባለትዳሮች ሙከራውን አቋርጠው ጥለው እንደወጡም ገልጿል። ሳይንቲስቱ የምርምር ስራውን ለግምገማ ወደ አንድ ሳይንሳዊ የምርምር ስራዎች የሚወጡበት ቦታ ልኬዋለሁ ቢልም ስሙን ከመጥቀስ ተቆጥቧል። በአሁኑ ወቅትም እንዲሁ ሌላ ፅንስ ላይ ሙከራ እያደረገ መሆኑን ጠቅሶ "ምርምሩ ሳይጠበቅ ይፋ በመውጣቱ ይቅርታ ጠይቋል" ሳይንቲስቶች ግን ፅንሱ ላይ የተቀየረው የዘረ መል ባህርይ ወደፊት ለሚቀጥለው ትውልድ የሚተላለፍ መሆኑን በመስጋት በተፈጥሮ ጣልቃ መግባት መሆኑን አስምረውበታል።
news-44843963
https://www.bbc.com/amharic/news-44843963
የኤርትራና የኢትዮጵያ መሪዎች ተገናኝተው ተወያይተዋል፤ ቀጣዩስ ?
ከጥቂት ወራት በፊት በሁለቱ ሃገራት መካከል በጥቂት ጊዜ ውስጥ ሰላም ይፈጠራል እንዲሁም መሪዎቹም ተገናኝተው ፊት ለፊት ይነጋገራሉ ብሎ ያሰበ አልነበረም።
መሪዎቹ መገናኝት ዕውን ሆኖ፤ የሁለቱ ሃገራት ህዝቦችም ዜናውን በደስታ ነው የተቀበሉት፣ ዘፈኑም፣ ጭፈራውም በደስታ ያነቡም አልታጡም። ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂም ሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በተደጋጋሚ ዕለቱ ታሪካዊ እንደሆነና እነዚህ ተቃቅረው የነበሩ ህዘቦችን አንድ ላይ እንዴት ማምጣት እንደሚገባ ተናግረዋል። • የኢትዮጵያና ኤርትራን የአብሮነት እርምጃ ምን ይፈትነዋል? • የፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀባበል በፎቶ ይህ ግን የታሪክ ጅማሮ ነው፤ በተለይም ሀገራቱ በጦርነት ከመቋሰላቸው አንፃርና ያልተፈቱ ጉዳዮች በመኖራቸው መጪውን ጊዜ ፈታኝና አስቸጋሪ ያደርገዋል። ከመቶ ሺህዎችን በላይ በቀጠፈው፣ የኢኮኖሚ ኪሳራ ባደረሰው የዚህ ጦርነት ጦስ በቀላሉ በሁለቱ መሪዎች ስብሰባ የሚፈታ አይደለም፤ ከዚህም በላይ ስር ነቀል የሆነና ጥልቀት ያለው መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል። የድንበር አተገባበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደስልጣን ከመጡ በኋላ ለኤርትራ መንግሥት የሰላም ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፤ ሰላምና ጦርነት በሌለበት ሁኔታ የሁለቱ ሃገራት ፍጥጫም ሊያበቃ እንደሚበቃ ተናግረው ነበር። በምላሹም የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል"የኢትዮጵያ መንግሥት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የድንበር ውሳኔውን ሲያከብር ነው፤ ይህ እውን የሚሆነው"በማለት በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል። የተባበሩት መንግሥታት የድንበር ኮሚሽን ከጦርነቱ በኋላ የባድመ ግዛትን ለኤርትራ መስጠቱ የሚታወስ ነው። የጦርነቱ መቋጫ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት የድንበር ኮሚሽኑን ማንኛውንም ውሳኔውን እቀበላለሁ ቢልም ከሁለት ዓመታት በኋላ ባድመ ለኤርትራ መወሰኗን ተከትሎ ተግባራዊ ሳያደርገው ቆይቷል። • ወደ አሥመራ ለመጓዝ ማወቅ የሚገባዎ 6 ነጥቦች የኢትዮጵያ መንግሥት ጦር ሰራዊት በባድመ ሰፍሮ ቆይቷል። በቅርቡም ኢህአዴግ የአልጀርስን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ አደርጋለሁ ማለቱ በሁለቱ ኃገራት የነበረውን ሁኔታ ሙሉ በሙሉ የቀየረ ነበር። አሁንም አፈፃፀሙ ላይ የሚነሱ ብዙ ጥያቄዎች ያሉ ሲሆን ሁለቱም ሀገራት ጦራቸውን በተጠንቀቅ ለረዥም ጊዜ አቁመዋል። እነዚህ ወታደሮች የሚነሱበት ወቅት፤ከበላይ ሆኖ የሚቆጣጠረው አካልና ሂደቱስ ምነ ይመስላል የሚለው ጥያቄ ምላሽ ያላገኘ ሲሆን ዘላቂ ሰላም እንዲመጣም ሁለቱ ሃገራት ሊያዩዋቸው የሚገቡ ጉዳዮች ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ በድንበር አካባቢ የሚኖሩትን ማህበረሰብ ዕጣፈንታም አልተመለሰም። ኢትዮጵያ የአልጀርስን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ አደርጋለሁ ማለቷን ተከትሎ የባድመና የኢሮብ ህዝቦች ተቃውሞች አንስተው ነበር፤ ይህም ሁኔታው በቀላሉ ሊፈታ እንደማይችል ጠቋሚ ነው። ካሳ የሁለቱ ሃገራት ጦርነት ከመቶ ሺህዎች በላይ ህይወት ቀጥፏል፣ የኢኮኖሚ ውድመትን አስከትሏል። ከጦርነቱ ማብቂያ በኋላም የሰላም ሂደቱን ለማፋጠንና የተጎዱትን ለመካስ የካሳ ኮሚሽን በአውሮፓውያኑ 2009 ተቋቁሞ ነበር። ሃገራቱ የጦርነት ህጎችን ሳያከብሩ፤ የጦር ምርኮኞችንና የሰዎችን መብት በመጣስና ነዋሪዎችን ለአደጋ በማጋለጥ ጥፋተኛ ሆነውም ስለተገኙ ኮሚሽኑ ካሳ እንዲከፍሉ አዟቸዋል። በውሳኔውም መሰረት የኤርትራ መንግሥት 175 ሚሊዮን ዶላር፣ ኢትዮጵያ ደግሞ 161 ሚሊዮን ዶላር ለኤርትራ መንግሥት፣ በተጨማሪ 2 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ይገባናል ብለው ለጠየቁ ኤርትራውያን ሊሰጥ እንደሚገባ ወስኗል። ውሳኔው ዓመታትን ቢያስቆጥርም ሁለቱም ሃገራት እስካሁን ካሳውን አልከፈሉም። በመሪዎቹም ዘንድ ካሳውን በተመለከተ ውይይት አድርገው ከሆነም የታወቀ ነገር የለም። ካሳውን በተመለከተም ምንም ዓይነት ይፋዊ መረጃዎች ግልፅ አልሆኑም።
news-41925357
https://www.bbc.com/amharic/news-41925357
ቻይና የገቡት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ትራምፕ ጂንፒንግን አድንቀዋል
በእስያ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ትራምፕ ቻይና ሲገቡ ሞቅ ያለ አቀባበል በቤጂንግ የተደረገላቸው ሲሆን ጂንፒንግ ሰሜን ኮሪያን እየያዘ ያለበት መንገድ የሚደነቅ ነው ብለዋል።
ሆኖም ፕሬዝደንት "ዢ ሰሜን ኮሪያ የኒውክሊዬር መሣሪያዋን ከጥቅም ውጭ እንድታደርግ የበለጠ ጠንክሮ ሊሠራ ይገባል" ሲሉም አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። "ቤጂንግ በንግድ ጉዳይ ከአሜሪካ የተሻለች ሆና መገኘቷ ቻይና ተጠያቂ አያደርግም" ሲሉ መናገረቸው ግን ብዙዎችን ያስደነገጠ ነበር። የሰሜን ኮሪያ ዋነኛ የምጣኔ ሃብት አጋር እንደሆነች በሚነገርላት ቻይና የሚገኙት ትራምፕ ዋነኛ ትኩረታቸውን የኪም ጁንግ ኡን ኒውክሊዬር መሣሪያ ማምከን ላይ አድረገዋል። ትራምፕና ዢ የ250 ቢሊዮን ዶላር የንግድ ስምምነት የተፈራረሙ እንደሆነም አሳውቀዋል፤ ነገር ግን ምን ያህሉ አዲስ ምን ያህሉ ደግሞ የቆየ ስምምነት እንደሆነ የታወቀ ነገር የለም። ከቻይና በፊት በደቡብ ኮሪያ ጉብኝት ያደረጉት ትራምፕ ሰሜን ኮሪያ ወደ ስምምነት እንድትመጣ ጠይቀው ፒዮንግያንግ አሜሪካንና ሌላውን ዓለም ልትነካ ባትሞክር እንደሚሻላት አስጠንቅቀዋል። • ዶናልድ ትራምፕ ለሰሜን ኮሪያ፡ "እንዳትሞክሩን" አልፎም ቻይና ከሰሜን ኮሪያ ጋር ያላትን ግንኙነት እንድታቋርጥና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰሜን ኮሪያ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ ተግባራዊ እንድታደርግም ጠይቀዋል። ትዊተር የተሰኘው ማሕበራዊ ድር-ገጽ በተከለከለባት ሃገረ ቻይና ከደረሱ በኋላ ትራምፕ ቢያንስ አራት ጊዜ በትዊተር ገፃቸው ላይ ሃሳባቸውን ያሰፈሩ ሲሆን ስለጉዳዩ የተጠየቁት የዋይት ሃውስ ባለሥልጣን "የፈለጉትን ነገር መፃፍ ይችላሉ" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ትራምፕ ዕለተ ሐሙስ በቻይና ቤተ-መንግሥት የእራት ግብዣ ካደረጉ በኋላ ወደ ቪየትናም እንደሚሄዱም ይጠበቃል።
news-51500324
https://www.bbc.com/amharic/news-51500324
ምርጫው ይደረጋል የተባለበት ቀን ወደፊት ተገፋ
ነሐሴ 10 የድምጽ መስጫ ቀን ይሆናል ተብሎ ሃሳብ ቀርቦ የነበረው ቢሆንም፤ የድምጽ መስጫ ቀኑ በአስራ ሦስት ቀናት ተገፍቶ በነሐሴ ወር መጨረሻ እንደሚካሄድ ተገለጸ።
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንዳስታወቀው የ2012 አጠቃላይ አገራዊ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ነሐሴ 23/2012 ዓ.ም ድምጽ መስጫ ቀን ይሆናል። ቀደም ሲል ለውይይት በቀረበው የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ላይ የተለያዩ ወገኖች ወቅቱ ክረምት በመሆኑ ለመራጩ አስቸጋሪ ይሆናል በሚል ቅሬታ የቀረበ ሲሆን አሁን በወጣው መረሃ ግብር ምርጫው የሚካሄድበት ቀን በ13 ቀናት ወደፊት ተገፍቷል። የምረጫው ዕለት ወደ ፊት ለመገፋቱ እንደምክንያት የቀረበው በነሐሴ አጋማሽ ላይ ከሚኖረው ዝናብ ይልቅ በወሩ መጨረሻ ላይ የዝናቡ ሁኔታ ይቀንሳል የሚል እንደሆነ ተነግሯል። በመረሃ ግብሩ መሰረት መጋቢት 01 የምርጫ ክልል ካርታ ይፋ የሚደረግ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ የምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር መጋቢት 28 ቀን ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል። በምርጫው ድምጽ የሚሰጡ መራጮች ምዝገባ ከሚያዝያ 14 እስከ ግንቦት 23 ድረስ የሚካሄድ ሲሆን በምርጫው የሚወዳደሩ እጩዎች ምዝገባ ደግሞ ከግንቦት 05 እስከ 19 እንደሚሆን ተጠቅሷል። በተጨማሪም የምርጫ ቅስቀሳ የሚካሄደው ከግንቦት 21 እስከ ነሐሴ 18/2012 ድረስ ባለው ለሦስት ወራት ለሚጠጋ ጊዜ እንደሚሆን ይፋ የተደረገው የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ አመልክቷል። ይህንንም ተከትሎ ከነሐሴ 19 እስከ የድምጽ መስጫው ቀን ዋዜማ ድረስ የምርጫ ቅስቀሳ የማይደረግባቸው ቀናት ሲሆኑ ነሐሴ 23 ቀን መራጮች ድምጻቸውን የሚሰጡበት የምርጫ ቀን ይሆናል። ከነሐሴ 24 እስከ ጳጉሜ 03/2012 ዓ.ም ድረስ ባሉት አስር ቀናት ውስጥ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተረጋገጡ የምርጫ ውጤቶች ይፋ የሚደረግባቸው ቀናት እንደሚሆኑ ተገልጿል። ይህ ይፋ የሆነው የ2012 የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ የመጨረሻው ይሁን ወይም ከፓርቲዎች ጋር በሚደረግ ውይይት ማስተካከያ ማድረግ የሚቻልበት አይሁን የተገለጸ ነገር የለም።
55012490
https://www.bbc.com/amharic/55012490
የፖፕ ፍራንሲስ ኢንስታግራም ገጽ ሞዴሏን 'ላይክ' ካደረገ በኋላ ምርመራ ተከፈተ
የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ይፋዊ የኢኒስታግራም ገጽ አንድ ያልተጠበቀ ምሥልን "ላይክ" አድርጓል በሚል አዲስ ምርመራ እየተደረገበት ነው።
የሳቸው ገጽ "ላይክ" ያደረገው ምሥል ገላጣ ልብስ የለበሰች የብራዚል ሞዴል ፎቶ መሆኑ ነው ነገሩን አነጋጋሪ ያደረገው። በፎቶው ላይ ብራዚላዊቷ ናታሊያ ጋሪቦቶ በትምህርት ቤት የደንብ ልብስ ትታያለች። የዜና አገልግሎቶች በጉዳዩ ላይ ተከታታይ ዘገባ ማቅረብ የጀመሩት ከባለፈው አርብ ጀምሮ ነው። የሊቀ ጳጳሱ የኢኒስታግራም ገጽ ከዚህ ዘገባ መውጣት በኋላ የሞዴሏን ፎቶ "አንላይክ" አድርጎታል። ሆኖም ይህ ሁኔታ እንዴት ሊፈጠር ቻለ በሚለው ላይ ምርመራ ተጀምሯል። የቫቲካን ቃል አቀባይ ለጋርዲያን ጋዜጣ በሰጡት ቃል "ያው ላይክ መደረጉ ከሊቀ ጳጳሳችን ባለመሆኑ ኢኒስታግራም ነገሩን እንዲመረምር ጥያቄ አቅርበናል" ብለዋል። የሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ ኢኒስታግራም ገጽ "ፍራንሲስከስ" የሚል ስም ያለው ሲሆን ከ7 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች አሉት። የቫቲካን ከፍተኛ ኃላፊዎች ለካቶሊክ ዜና አገልግሎት ማክሰኞ ዕለት እንደተናገሩት የሊቀጳጳሱ ኢኒስታግራም አካውንት የሚንቀሳቀሰው ይህንኑ እንዲያደርጉ በተቀጠሩ ሰራተኞች ነው። ስለዚህም ነው የውስጥ ምርመራ በመደረግ ላይ ያለው። ብራዚላዊቷ ሞዴል በሊቀ ጳጳሱ ስም በተከፈተው ገጽ መወደዷን ተከትሎ ዝናዋ የጨመረ ሲሆን እሷም ክስተቱን ተንተርሳ ሳቅ ለመፍጠር ሞክራለች። "በሳቸው መወደዴ ቢያንስ መንግሥተ ሰማያትን እንደምወርስ ጠቋሚ ነው" ስትልም በትዊተር ሰሌዳዋ ጽፋለች።
43300023
https://www.bbc.com/amharic/43300023
የሕፃናት ጋብቻ ቀንሷል- ዩኒሴፍ
በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕፃናት ወደ ትዳር የመግባታቸው አሃዝ በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱን የተባበሩት መንግሥታት ሕፃናት ድርጅት አስታወቀ።
የሴቶች ትምህርት የህጻናት ጋብቻን ለመቀነስ ረድቷል እንደዩኒሴፍ ከሆነ ባለፉት አስር ዓመታት 25 ሚሊዮን የሕፃናት ጋብቻን መከላከል ተችሏል። በአሁኑ ወቅት ከ18 ዓመት በታች ከሆናቸው አምስት ልጆች አንዳቸው የሚዳሩ ሲሆን ይህ ቁጥር ከአስር ዓመት በፊት ከአራት ልጆችን አንድ ነበር። እንደ አለም አቀፉ የሕፃናት ድርጅት ከሆነ የደቡብ ኤስያ ሀገራት የሕፃናት ጋብቻ ቁጥርን በከፍተኛ ደረጃ በመቀነስ ተጠቃሽ ሆነዋል። በህንድ ይህ ሊሳካ የቻለው የተሻለ ትምህርት በመስጠት እና የሕፃናት ጋብቻ ያለውን ጉዳት በማሳወቅ በተሰራው ሥራ ነው። ኢትዮጵያ የሕፃናት ጋብቻን በአንድ ሶስተኛ መቀነስ ብትችልም ችግሩ በአፍሪካ ሃገራት አሁንም ከፍተኛ ነው። ዩኒሴፍ የጾታ ጉዳይ አማካሪ የሆኑት አንጁ ማልሆርታ እንደሚሉት የሕፃናት ጋብቻ በተለይ ሴቶች ህይወት ላይ ከሚያደርሰው ተጽእኖ አንጻር "የትኛውም መቀነስ የሚያስደስት ዜና ቢሆን ገና ብዙ ርቀት መጓዝ ይጠበቅብናል።" "ሴቶች በልጅነታቸው እንዲያገቡ ሲገደዱ ወዲያውም ሆነ በቀሪው ህይወታቸው ላይ ችግሮች ይከሰታሉ" ብለዋል። "ትምህርት የመጨረስ ዕድሏ ሲቀንስ፤ በባሏ ጥቃት የማስተናገድ እና በወሊድ ጊዜ ለሚደርሱ ችግሮች የመጋለጥ ዕድሏ ከፍተኛ ይሆናል። ትልቅ ማህበረሰባዊ ችግሮች እና ከትውልድ ወደ ትውልድ ለሚዘልቅ ድህነት የመጋለጥ ዕድሏም ከፍተኛ ነው።" እንደሪፖርቱ ከሆነ የሕፃናት ጋብቻ ችግር ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት አካባቢ እየሆነ መጥቷል። ከአስር ዓመታት በፊት ከአምስት የሕፃናት ጋብቻ አንዱ ብቻ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሃገራት የሚመዘገብ ሲሆን ይህ ቁጥር ወደ አንድ ሶስተኛ ከፍ ማለቱን ዩኒሴፍ አስታውቋል። የዓለም ሃገራት መሪዎች በተባበሩት መንግስታት ዘላቂ የልማት ጎሎች መሠረት የሕፃናት ጋብቻን በአውሮፓዊያኑ 2030 ለማስቀረት ቃል ገብተዋል። ይህን ግብ ለማሳካት ጥረቱን በማጠናከር "በዚህ መጥፎ ተግባር ምክንያት የልጅነት ጊዜያቸው የሚነጠቅባቸው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህጻናትን መታደግ ይገባናል" ሲሉ ማልሆትራ አስታውቀዋል።
54437958
https://www.bbc.com/amharic/54437958
አንበጣ መንጋ፡ በምሥራቅ ሐረርጌ ጸረ አንበጣ ኬሚካል በመርጨት ላይ የነበረ አውሮፕላን ወደቀ
በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ጃርሶ ወረዳ የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል ኬሚካል በመርጨት ላይ የነበረ አነስተኛ አውሮፕላን ዛሬ ሐሙስ መውደቁ ተገለጸ።
የጃርሶ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አብዱል ቃድር ደዚ ለቢቢሲ፣ አውሮፕላኗ ዛሬ ሐሙስ፣ ከቀኑ ስድስት ሰዓት አካባቢ ጊደያ በሃ በምትበል ቀበሌ ውስጥ የአንበጣ መንጋ ለመከላከል ኬሚካል ለመርጨት በቅኝት ላይ የነበረ አነስተኛ አውሮፕላን መውደቁን ለቢበሲ ተናግረዋል። "የአንበጣ ወረርሽኝ በቀበሌዋ ከተከሰተ አራተኛ ቀኑን ይዟል። አንበጣው በጣም ከመብዛቱ የተነሳ በአራት ቀበሌዎች በሚገኝ ሰብል ላይ ጉዳት እያደረሰ ነበር። ለዚህም አውሮፕላኑ በመምጣት እየዞረ እያለ ድንገተኛ አደጋ ገጥሟታል" ብለዋል። ዛሬ በምሥራቅ ሐረርጌ ጃርሶ ወረዳ ጊደያ በሃ ቀበሌ በደረሰው አደጋ በአውሮፕላኑ ውስጥ አብራሪው ብቻ የነበረ መሆኑን አስተዳዳሪው ገልፀው፣ ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰበት ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። "ወዲያውኑ እኛ ከወረዳው አምቡላንስ አስመጥተን የነበረ ቢሆንም ሌላ አውሮፕላን መጥቶ ይዞት ሄዷል" ሲሉም አክለዋል። "አብራሪው አልተጎዳም፤ በጥሩ ሁኔታ ላይ ነው ወደ ድሬዳዋ የተወሰደው፤ አውሮፕላኑ ጎማው ላይ ብቻ ጉዳት የደረሰበት ሲሆን ቀሪው የአካል ክፍሉ ላይ ምንም ጉዳት አልደረሰም" ሲሉ ተናግረዋል። በጃርሶ ወረዳ በሚገኙ አራት ቀበሌዎች ውስጥ የአምበጣ መንጋ በማሽላ እና በቆሎ የመሳሰሉ የሰብል አይነቶች ላይ ጉዳት ማድረሱንም አቶ አብዱል ቃድር ለበቢሲ ጨምረው አስረድተዋል። ባለፈው ሳምንት፣ መስከረም 22/2013 ዓ.ም በአማራ ክልል ወረባቦ ወረዳ የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል ኬሚካል በመርጨት ላይ የነበረ አውሮፕላን ፍራንጉል በሚባል ቦታ ወድቆ መከስከሱ ይታወሳል። በወቅቱ የወረዳው የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሳዳም ሽመልስ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በአደጋው በሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን ገልፀው፣ የሄሊኮፕተሩ አብራሪ መጠነኛ ጉዳት አጋጥሞት በሰመራ ሆስፒታል የሕክምና ክትትል እየተደረገለት እንደነበር አመልክተዋል። በምሥራቅ አማራ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች የተከሰተው የአንበጣ መንጋ እንዲሁ በሰብል ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው። በደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳ የተከሰተው መንጋ የጉዳት መጠኑ ከፍተኛ መሆኑን የወረዳው ኃላፊዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በወረዳው የተከሰተው የበረሃ አንበጣ መንጋ 24 ሺህ ሄክታር የሚሆን መሬት የወረረ ሲሆን በወረዳው በ11 ቀበሌዎች ይገኝ የነበረ ሰብል ላይ ከ10 እስከ 100 በመቶ ጉዳት አድርሷል። በተመሳሳይ የአንበጣ መንጋው በትግራይ ክልል ደቡባዊ ትግራይ ዞን ሦስት ወረዳዎች ማለትም ራያ አዘቦ፣ ራያ አላማጣ ፣ ራያ ጨርጨር ተከስቷል። በዞኑ የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ በባህላዊ መንገድ ለመከላከል ኅብረተሰቡ ጥረት እያደረገ ይገኛል።
49080507
https://www.bbc.com/amharic/49080507
ኢራን የ 'ሲአይኤ ሰላይ' ያለቻቸውን በሞት እቀጣለሁ አለች
ኢራን ለሲአይኤ እየሠሩ ነበር ያለቻቸውን 17 ሰላዮች በቁጥጥር ሥር ማዋሏን ይፋ አደረገች። ከነዚህ ገሚሱ ሞት ተፈርዶባቸዋል ተብሏል።
የኢራን የደህንነት ሚንስትር እንዳለው፤ ተጠርጣሪዎቹ ስለ ኒውክሌር፣ መከላከያ እና ሌሎችም ዘርፎች መረጃ እየሰበሰቡ ነበር። የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራንን ክስ "ሀሰት ነው" ሲሉ አጣጥለዋል። በኢራን የኒውክሌር ፕሮግራም ሳቢያ ሁለቱ አገራት እንደተፋጠጡ ነው። ትራምፕ ከዓለም አቀፉ የኒውክሌር ስምምነት ባለፈው ዓመት ወጥተው ኢራን ላይ የንግድ ማእቀብ መጣላቸው ይታወሳል። • ኢራን የአሜሪካ የቅኝት ድሮንን መትታ ጣለች • እንግሊዝ፦ 'ከኢራን ጎን ነኝ' ኢራን እስሩን እንዳሳወቀች "ከኢራን ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ እየተቸገርኩ ነው" ሲሉ ትራምፕ ተናግረዋል። ስለ 'ሰላዮቹ' እስካሁን የምናውቀው ኢራን ለአሜሪካው የስለላ ድርጅት ሲአይኤ ይሰራሉ ያለቻቸውን ግለሰቦች ያሠረችው ባለፉት 12 ወራት እንደሆነ ተናግራለች። 17ቱም ኢራናዊ ሲሆኑ፤ በመከላከያና ኒውክሌር ማዕከሎች አካባቢ ሲንቀሳቀሱ እንደነበር አንድ የኢራን ከፍተኛ የደህንነት ኃላፊ ገልጸዋል። ከታሠሩት መካከል ምን ያህሉ ሞት እንደተፈረደባቸው ያሉት ነገር የለም። የኢራን የደህንነት ሚንስትር መሀሙድ አልቪ "ከአሜሪካ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰላዮችን እሥር የተመለከተ ዘጋቢ ፊልም በኢራን ቴሌቭዥን ይታያል" ብለዋል። የደህንነት ተቋሙ የዘጋቢ ፊልሙን ቅንጫቢ የያዘ ሲዲ ለቋል። በሲዲው የሰላዮች ስብሰባና ቃለ ምልልስን በማስመሰል የተሠራ ትዕይንትም ይታያል። ሚንስትሩ እንዳሉት በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ግለሰቦች መካከል የአሜሪካ ቪዛ ለማግኘት ጥረት እያደረጉ ሳለ በሲአይኤ የተመለመሉ ይገኙበታል። አንዳንዶቹ ደግሞ የአሜሪካ ቪዛቸውን ለማሳደስ ሲሞክሩ ሲአይኤ ተጽዕኖ አድርጎ የመለመላቸው ናቸው ብለዋል። የተቀሩት በገንዘብ፣ በህክምና አገልግሎትና ሌሎችም ጥቅማ ጥቅሞች ተደልለዋል ሲሉም አክለዋል። • ኢራን አሜሪካ ዳግም የጣለችውን ማዕቀብ አወገዘች • ትራምፕ ጦርነት ከተጀመረ ኢራን ከምድረ ገጽ ትጠፋለች ሲሉ አስጠነቀቁ ባለፈው ወር ኢራን ከ "ሲአይኤ የስለላ ሰንሰለት ጋር የተገናኘ" ነው ያለችውን መስመር መበጣጠሷን አሳውቃ ነበር። የአሁኑ ከዚህ ሰንሰለት ጋር የተገናኘ ስለመሆኑ የተባለ ነገር የለም። ተንታኞች ምን ይላሉ? የአካባቢውን ፖለቲካ በቅርበት የሚከታተሉ ተንታኞች የኢራን መግለጫን በጥርጣሬ ያዩታል። የኢራን ደህንነት ሚንስትር ባለፈው ወር የሲአይኤን የስለላ ሰንሰለት በጣጥሻለሁ ብትልም፤ አሁን ደግሞ 17 ተጠርጣሪዎችን አሥሬያለሁ ብላለች። አንዳንዶች እንደሚሉት 17ቱ ግለሰቦች ለበርካታ ዓመታት በስለላ የተጠረሩ ሊሆኑ ይችላሉ። ኢራን ውስጥ ለተለያዩ አገራት ሲሰልሉ ነበር በሚል የተጠረጠሩ ብዙ እስረኞች አሉ። የኢራን የደህንነት ሚንስትር መግለጫ ያወጣው አዳዲስ ተጠርጣሪዎች አሥሮ ሳይሆን፤ ከሪቮሉሽነሪ ጋርዶች ጋር እየተደረገ ያለውን ፉክክር አስታክኮ ነው የሚሉም አሉ። • ኢራንና እንግሊዝ ተፋጠዋል ከሁለት ሳምንት በፊት የኢራን ቴሌቭዥን የኢራንን የደህንነት ተቋም የሚያሞግስ ዘጋቢ ፊልም አቅርቦ ነበር። አሁን ደግሞ የደህንነት ሚንስትሩ ስኬቱን የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም ሊያቀርብ ነው። በኢራን ውስጥ ያሉት ተፎካካሪ ተቋሞች አንዳቸው ከሌላቸው የተሻሉ መሆናቸውን ለማሳየት የሚያደርጉት ጥረትም ይመስላል። የፍጥጫው መንስኤ ምንድን ነው? ተከታዮቹ ክስተቶች በኢራን፣ አሜሪካና እንግሊዝ መካከል ያለውን ፍጥጫ ለመረዳት ያግዛሉ።
56534020
https://www.bbc.com/amharic/56534020
ሱዊዝ ቦይ በመዘጋቱ በየቀኑ የ9.6 ቢሊዮን ዶላር ምርት መተላለፍ አልቻለም
የግብጹ ሱዊዝ የባሕር ላይ ማቋረጫ ቦይ በመዘጋቱ በየቀኑ 9.6 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶች መተላለፍ እንዳልቻሉ ተገለጸ።
ግዙፏ መርከብ መተላለፊያውን ዘግታ በሱዊዝ መተላለፊያ ላይ አንድ ግዙፍ የጭነት መርከብ ባሕሩን ዘግቶ ከማክሰኞ ዕለት ጀምሮ በመቆሙ ምክንያት እንቅስቃሴ መገታቱ ይታወሳል። ሎይድስ ሊስት የተባለው የመርከብ ጉዞ ድርጅት እንደሚለው፤ በቀን ውስጥ ከምዕራብ አቅጣጫ ይመጡ የነበሩ 5.1 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶች መጓጓዝ አልቻሉም። ከምሥራቅ አቅጣጫ ይመጡ የነበሩና የተስተጓጎሉ ምርቶች ደግሞ 4.5 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ናቸው። የባሕሩን መተላለፊያ የዘጋው መርከብ እንቅስቃሴ እንዲጀምር ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ሳምንታት ሊወስድ እንደሚችል ባለሙያዎች ተናግረዋል። በታይዋኑ ኤቨርግሪን ማሪን ሥር ያለው ኤቨር ጊቭን መርከብ በዓለም ትልቁ ኮንቴነር ጫኝ ሲሆን፤ 200,000 ቶን የሚመዝን እንዲሁም 20,000 ኮንቴነር ማጓጓዝ የሚችል ነው። መርከቡ በመቆሙ ሳቢያ ሌሎች መርከቦች ለቀናት መተላለፍ አልቻሉም። የባሕር ላይ ጉዞ አማካሪ ድርጅት ባለቤት ጆን ሞንሮይ ብዙ ወደቦች ላይ የሚገኙና መጓጓዝ ያልቻሉ ኮንቴነሮች እንዳሉ ይናገራል። መተላለፊያው በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምሥራቅ መካከል ምርቶች የሚተላለፉበት ሲሆን፤ የጦፈ ንግድ የሚካሄድበት መስመር ነው። መተላለፊያውን የዘጋችውን መርከብ ለማንቀሳቀስ ጥረት እየተደረገ ከመላው ዓለም የባሕር ንግድም 12 በመቶው የሚያልፈውም በዚሁ የግብጽ የባሕር ላይ ማቋረጫ መስመር በኩል ነው። ሎይድስ ሊስት ባወጣው አሃዝ መሠረት፤ በአሁኑ ጊዜ 160 መርከቦች በሱዊዝ ቦይ በኩል ለማለፍ እየጠበቁ ነው። ከእነዚህ መካከል 41 የሚሆኑት የተለያዩ ምርቶች ሲይዙ 24 ደግሞ ነዳጅ ጫኝ ናቸው። ቢአይኤምሲኦ የተባለው ዓለም አቀፍ የመርከበኞች ማኅበር እንደሚለው መተላለፊያው ተዘግቶ ከቆየ የምርት አቅርቦት ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ አይቀርም። የሎጂስቲክስ ተቋሙ ኦኤል ዩኤስኤ ፕሬዘዳንት አለን ባይር "በእያንዳንዱ ቀን ያልተጓጓዙ ምርቶችን ለማሳለፍ ተጨማሪ ሁለት ቀናት ይጠይቃል" ብለዋል። እስካሁን ለሦስት ቀናት መተላለፍ ያልቻሉትን ምርቶች ለማጓጓዝ ስድስት ቀናት ገደማ ሊያስፈልግ እንደሚችልም ግምታቸውን አስቀምጠዋል። መተላለፊያው እስኪከፈት ድረስ ቀናት ወይም ሳምንታት ሊወስድ እንደሚችል የተጠቆመ ሲሆን፤ ይህ ደግሞ በመላው ዓለም የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ጫና ያሳድራል። የዓለም የንግድ እንቅስቃሴ ይህ የግብጽ የባሕር ላይ መተላለፊያ ከመዘጋቱ በፊት በኮቪድ-19 ምክንያት መቀዛቀዝ አጋትሞት ነበር። አለን እንደሚሉት፤ መርከቦች ሌላ አማራጭ የጉዞ መስምር ከፈለጉ በምዕራብ አፍሪካ በኩል በመዞር ጉዟቸውን ሊቀጥሉ ብችሉም ይህ ጉዞ ግን ከሰባት እስከ ዘጠኝ ቀናት ሊፈጅ ይችላል። አንዳንድ ተቋሞች መተላለፍ ባልቻሉ ምርቶቻቸው ምትክ ሌሎች ምርቶችን በአውሮፕላን ወይም በባቡር መላክን እንደ አማራጭ ሊወስዱ ይችላሉ። እስካሁን ድረስ ሜርስክ እና ሀፓግ ሎይድ የተባሉ ተቋሞች ከሱዩዝ መተላለፊያ መስመር ውጪ ያሉ አማራጮችን እንደሚጠቀሙ አስታውቀዋል። የግብጹ የሱዊዝ መተላለፊያ ባለሥልጣን ባሕሩን የዘጋውን መርከብ ለማስነሳት የቻለውን ሁሉ እየሞከረ እንደሆነ አስታውቋል።
news-54950899
https://www.bbc.com/amharic/news-54950899
ትራምፕ ወታደሮቻቸውን ከአፍጋኒስታንና ከኢራቅ ሊያስወጡ ነው
ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ወታደሮችን ከኢራቅና ከአፍጋኒስታን ያስወጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የአሜሪካ ሚዲያዎች እየዘገቡ ነው።
በአፍጋኒስታን ከሚገኙት 5ሺህ ወታደሮች ቢያንስ ግማሹ ተመላሽ እንደሚደረጉ ባለሥልጣናት ጠቁመዋል። በኢራቅ ደግሞ ከ3ሺህ ወታደሮች ውስጥ ቢያንስ 500 ያህሉ ተቀናሽ ተደርገው ይመለሳሉ። 2ሺ 500ዎቹ እዚያው ይቆያሉ። ትራምፕ በተደጋጋሚ ሁሉም ወታደሮች ከገና በፊት ለአገራቸው ይበቃሉ ሲሉ ተደምጠዋል። ሆኖም ተግባራዊ ሆኖ አያውቅም። ከአራት ዓመታት በፊት በምርጫ ቅስቀሳ ወቅትም ውጭ አገር የሚገኙ የአሜሪካ ወታደሮችን 'ለእናት አገራቸው አበቃቸዋለሁ' ሲሉ ቃል ገብተው ነበር። ዶናልድ ትራምፕ አሁን በጆ ባይደን በማያሻማ ሁኔታ ቢሸነፉም ሽንፈታቸውን ተቀብለው ለአሸናፊው ፕሬዝዳንት እጩ እንኳን ደስ ያለህ ለማለት በተቸገሩበት ወቅት ነው ወታደሮችን እንደሚያስወጡ የገለጹት። አሁን ከኢራቅና አፍጋኒስታን ይለቃሉ የተባሉት አሜሪካዊ ወታደሮች በ'ጃንዋሪ' 15 ተጠቃለው አገራቸው ይገባሉ ተብሏል። ይህም ማለት ወታደሮቹ የሚመለሱት ከጆ ባይደን ወደ ዋይት ሐውስ መግቢያ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ነው። ይህ የትራምፕ እርምጃ ባልተለመደ መልኩ ከሪፐብሊካን ሴናተር ሚች መከኔል ተቃውሞ ገጥሞታል። ምክንያቱ ደግሞ እርምጃው በአፍጋኒስታንና በኢራቅ የሚገኙ አማጺዎችንና አክራሪ ኃይሎችን የሚያበረታታ ነው በሚል ነው። ትራምፕ በበኩላቸው የአሜሪካዊያን ወታደሮች በውጭ አገር መቀመጥ አገራቸውን ለከፍተኛ ወጪ የሚዳርግ ነው ይላሉ። ባለፈው መስከረም ፔንታገን በኢራቅ ከሚገኙ ወታደሮቹ አንድ ሦስተኛውን እንደሚያስወጣ ይፋ አድርጎ ነበር። ይህም በሳምንታት ውስጥ እንደሚፈጸም ተናግሮ እንደነበር ይታወሳል። እዚያ የሚገኙት የተወሰኑ መታደሮች የኢራቅን መከላከያ በማሰልጠን ደረጃ እንደሚወሰኑም ተገልጾ ነበር። የአሜሪካ ወታደሮች ኢራቅ ከተወረረችበት ከ2003 ጀምሮ በኢራቅ ይገኛሉ። ከ2001 ጀምሮ ደግሞ በአፍጋኒስታን ቆይተዋል።
43876269
https://www.bbc.com/amharic/43876269
የቀይ ባሕር ሰላዮች፡ ሞሳድ ቤተ-እስራኤላዊያንን ለመታደግ የፈጠረው ሐሳዊ ሪዞርት
ከአርባ ዓመታት በፊት በወቅቱ የእራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ለሞሳድ በሰጡት ቀጥተኛ ትዕዛዝ ቤተ እስራኤላዊያንን በድብቅ በሱዳን በኩል ወደ እስራኤል ተወስደዋል።
ለዚህም የእስራኤል የስለላ ተቋም አባላት እንደ ሽፋን አሮስ በምትባለው የሱዳኗ የባሕር ዳርቻ ሐሰተኛ ቅንጡ መዝናኛ ሆቴልን ለዚህ ተልዕኮ ተጠቅመው ነበር። የቢቢሲው ጋዜጠኛ ራፊ በርግም ይህንን አስደናቂ የስለላ ተልዕኮን ታሪክ የሚያወሳ "ሬድ ሲ ስፓይስ" የተባለ መጽሐፍ ጽፏል። ይህንን ተልዕኮ በተወሰነ ደረጃ የሚያሳይ ታሪክ ከዚህ ቀደም ቢቢሲ አቅርቦ ነበር፤ እነሆ . . . በደርግ መውደቂያ ዋዜማ እስራኤል ስላካሄደችው «ዘመቻ ሰለሞን» ብዙ ሰው ያወጋል። 14 ሺህ ቤተ-እስራኤላዊያንን ከታደገው ከዚህ ምስጢራዊ ዘመቻ አስር ዓመት በፊት በሱዳን ስለሆነው ነገር የሚያውቅ ግን እምብዛም ነው። አሮስ ይባላል። ሱዳን በረሀ ላይ በቀይ ባህር ዳርቻ ተንጣሎ የሚገኝ መንሸራሸሪያ፤ ቅምጥል ሪዞርት፤ የማይጠገብ። ይህ ሥፍራ እስራኤል ሠራሽ ሐሳዊ መንሸራሸሪያ ነበር ቢባል ብዙ ሰው ለማመን የሚቸገረውም ለዚሁ ነው። ስለዚህ ሪዞርት መልካምነት የሚያትቱ ሺህ በራሪ ወረቀቶች በጉዞ ወኪሎች በኩል ተበትነዋል። መዝናኛው በጄኔቫ በከፈተው ወኪል ቢሮው በኩል ለበርካታ «ቱሪስቶች» ትኬት ሽጧል። በመሆኑም አሮስን ማንም የሰላዮች ቤት አድርጎ ሊገምተው አይቻለውም ነበር። "ሱዳን ውስጥ በጊዜው ከነበሩት መዝናኛዎች ጋር ሳወዳድረው፣ እኛ እንሰጥ የነበረው አገልግሎት ከሂልተን ሆቴል ቢበልጥ እንጂ አያንስም፤ እጅግ የሚያምር ቦታ ነበር፤ የሆነ «ከአረቢያን ናይትስ» ተረቶች ውስጥ አንዱን ነበር የሚመስለው። በውበቱ አፈዝ አደንግዝ ነገር ነበር» ይላል እስራኤላዊው የሞሳድ ባልደረባ ጋድ ሺምሮን ስለ አሮስ ሪዞርት ትዝታውን ሲያወጋ። የሱዳን ቱሪስት ኮርፖሬሽን ራሱ የሚኩራሩበት ቦታ ነበር። ሥፍራውን እያከራየ ረብጣ ሪያል ሲያፍስ ነበር። ራሳቸውን አውሮፓዊ ባለሐብቶች ብለው ላስመዘገቡ የጎብኚ ቡድን አባላት ቦታውን እያከራየ፣ እያስጎበኘ ኖሯል። ስለነገሩ አንደም ሳያውቅ። ጨረቃና ከዋክብት ወከክ ብለው የሚታዩበት፣ ሕልም እንጂ እውን የማይመስል የነበረው ይህ ሪዞርት፤ ጎብኚዎች ከዓመት በፊት ትኬት ቆርጠው ለጉዞ ተንሰፍስፈው የሚጠብቁት ነበር። ይህ ብዙ የተባለለት የበረሀ ገነት ለካንስ ሞሳድ የፈጠረው ሐሳዊ መዝናኛ እንጂ ሌላ አልነበረም። ለምን ዓላማ ማለት ተገቢ ጥያቄ ይመስላል። መልሱ "ኢትዮጵያዊ ቤተ-እስራኤላዊያንን ለመታደግ" የሚል ነው። ከ1980ዎቹ አንስቶ ለአራት ዓመታት የሥራ ላይ የነበረው ይህ ሪዞርት ሞሳድ አምጦ የወለደው ኅቡዕ የሰላዮች መናኸሪያ እንደነበር የታወቀው እጅግ ዘግይቶ ነው። በሺ የሚቆጠሩ ከኢትዯጵያ የሾለኩ ቤተ እስራኤላዊያንን በጥንቃቄ ወደ እስራኤል ምድር ለመጓጓዝ ነበር ይህ ሁሉ የሆነው። ምክንያቱም ሱዳን በዚያን ወቅት ለእስራኤል በጄ የምትል አገር አልነበረችም፤ እንዲያውም ከአረብ ጠላቶቿ አንዷ ነበረች። ይህ ኀቡእ ዘመቻ ታውቆ ቢሆን የብዙ ሺህ ቤተ-እስራኤላዊያን ሕይወት አደጋ ላይ ሊወድቅ ይችል ነበር። «ጥብቅ የአገር ምስጢር ነበር። ቤተሰቦቼ እንኳ ስለነገሩ የሚያውቁት ነገር አልነበረም» ይላል ጋድ ሺምሮን፣ የቀድሞ የሞሳድ ባልደረባ። ኦሪትን የሚከተሉትን ቤተ-እስረኤላዊያን ሃይማኖታቸውንም ሆነ ማንነታቸውን ለማንም እንዳይገልጡ፣ ማንነታቸው ከታወቀ ግን በሱዳን የጸጥታ ኃይሎች አደጋ እንደሚጋረጥባቸው ይነገራቸው የነበረው መቀመጫውን በአሮስ መዝናኛ ባደረገው በዚህ ኅቡዕ የሞሳድ ቡድን በኩል ነበር። ቤተ-እስራኤላዊያን በተመለከተ መላ ምቱ ብዙ ነው። ከአስሩ የጠፉ የእስራኤል ነገዶች ዝርያቸው የሚመዘዝ እንደሆነ ይነገራል። ሌሎች ሰነዶች ደግሞ ከክርስቶስ ልደት በፊት 950 ዓመተ ዓለም አካባቢ የንግሥት ሳባና የንጉሥ ሰለሞንን ልጅ አጅበው ወደ ኢትዮጵያ ምድር የመጡ እስራኤሎች የልጅ ልጅ ልጆች እንደሆኑ ይገምታሉ። ሌሎች ደግሞ ትልቁ የአይሁድ ቤተ አምልኮ በ586 ዓመተ-ዓለም ሲፈርስ ወደ ሐበሻ ምድር የተሰደዱ እንደሆኑ ይገምታሉ። ሞሳዶች አሮስ መዝናኛን ገንብቶ ለመክፈት 12 ወራትን ወስዶባቸዋል። ከአገሬው 15 የሚሆኑ የቤት ሠራተኞችን፣ ሾፌሮችን፣ የወጥ ቤት ሠራተኞችን ቀጥረዋል። አንዳቸውም ግን የሆቴሉን ኅቡዕ ተግባር አያውቁም ነበር። አለቆቻቸው የሞሳድ ሰዎች እንጂ የወጥ ቤት ሰዎች እንዳልሆኑ ያወቁት ከብዙ ዘመን በኋላ ነበር። ምድር ቤት የሚገኘው እቃ ቤት ግን ማንም ዘው ብሎ ገብቶ አያውቅም፣ እዚያ ከድስቶች ጋር የርቀት መነጋገሪያ ስልኮች ነበሩ። ከቴላቪቭ የሚያገናኙ።
news-52059442
https://www.bbc.com/amharic/news-52059442
ኮሮናቫይረስ፡ የፋይናንስ ዘርፉን ለመደገፍ ብሔራዊ ባንክ ተጨማሪ 15 ቢሊየን ብር ለግል ባንኮች እንዲሰጥ ተወሰነ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 16 በመድረሱ እና ቫይረሱ የበለጠ እንዳይዛመት ለመግታት ተጨማሪ መመሪያዎችን ይፋ አደረጉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እነዚህን ውሳኔዎች ያሳለፉት ኮቪድ-19ን ለመከላከል ከተቋቋመው ኮሚቴ ጋር ከተወያዩ በኋላ መሆኑ ተገልጿል። በዚህም መሰረት ከዛሬ ከሰዓት ጀምሮ ከባህር ማዶ መጥተው በተዘጋጁት ሆቴሎች ለመቆየት አቅም የሌላቸው ግለሰቦች ወደ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ እንዲዛወሩ መወሰኑ ተገልጿል። • ሴንጋፖር አካላዊ እርቀትን የማይጠብቁ ሰዎችን በገንዘብና በእስር ልትቀጣ ነው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ጨምሮ፣ ትምህርት ቤቶች ለተጨማሪ ሁለት ሳምንታት ተዘግተው እንዲቆዩ መወሰኑም ተገልጿል። ዜጎች በየትኛውም ስፍራ የማኅበራዊ ርቀት የመጠበቅን መመሪያን ተግባራዊ እንዲያደርጉ በድጋሚ ጥሪ የቀረበ ሲሆን ሁኔታው ተጨማሪ ድጋፍን የሚጠይቅ ከሆነ በሚል ሁሉም ጡረታ የወጡ እንዲሁም በትምህርት ላይ ያሉ የሕክምና ባለሙያዎች ለብሔራዊ ግዳጅ እንዲዘጋጁ ጥሪ ቀርቦላቸዋል። የተለያየ መጠን እና ዓይነት ያላቸው መገልገያዎችን የያዙ ከ134 በላይ ተቋማት ለለይቶ መከታተያ፣ ለይቶ ማቆያ እና ሕክምና እንዲሆኑ ተለይተዋል ያለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ፤ የብሔራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ የተለያዩ አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል። የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያስፈልጉ የገቢ ዕቃዎች እና ግብአቶች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ የመወሰኑን የገለፀው ይህ መግለጫ ባንኮች በኮቪድ-19 ቫይረስ ለተጎዱ ደንበኞቻቸው ጊዜያዊ የብድር እፎይታ እና ተጨማሪ ብድር ለመስጠት እንዲያስችላቸው፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተጨማሪ 15 ቢሊየን ብር ለግል ባንኮች እንዲሰጥ መወሰኑ ተገልጿል። የውጪ ምንዛሬ የሚያስፈልጋቸው እና የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያስችሉ ዕቃዎችን እና ግብአቶችን ወደ ሀገር ውስጥ ለሚያስገቡ አስመጪዎች ባንኮች ቅድሚያ በመስጠት እንዲያስተናግዱ ይደረጋል በማለትም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለውጭ ገበያ በሚቀርብ አበባ ላይ የጣለው ዝቅተኛ የመሸጫ ዋጋ ገደብ በጊዜያዊነት እንዲነሳ መደረጉ ተነግሯል።
news-56127788
https://www.bbc.com/amharic/news-56127788
ሕንድና ፓኪስታንን ያቀራረበው የአምስት ሰከንድ ቪዲዮ
ለአምስት ሰከንዶች የሚቆይ ተንቀሳቃሽ ምስል የማይታሰበውን ነገር ማድረግ ችሏል። ተንቀሳቃሽ ምስሉ የሕንድና ፓኪስታን ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን አንድ ላይ እንዳመጣ ተገልጿል።
ዳናኒር ሞቢን የተባለችው ፓኪስታናዊት የተንቀሳቃሽ ምስል ባለሙያ ኢንስታግራም ላይ የራሷን ቪዲዮ የለቀቀችው ከሁለት ሳምንታት በፊት ነበር። ነገር ግን በአንድ ምሽት ለማለት በሚያስደፍር መልኩ በሁለቱም አገራት ታዋቂና ተወዳጅ ሰው እሆናለሁ ብላ አላሰበችም ነበር። ይህች ግለሰብ የለቀቀችው ምን አይነት ቪዲዮ ቢሆን ነው? ብላችሁ ልትጠይቁ ትችላላችሁ። ቪዲዮው ምንም የተለየ ነገር የለውም ትላለች ሞቢን። ''ይህ የእኛ መኪና ነው፤ እኛም እዚሁ ነን፤ ይሄ ደግሞ የጭፈራ ዝጅግታችን ነው'' ብቻ ነው ያልኩት ትላለች። በቪዲዮው ላይ ጥቂት ወጣቶች ተሰብስበው ሲዝናኑም ይታያል። ዋናው ነገር ያለው እዛ ጋር ነው። በቅርብ ሳምንታት ሞትና ሀዘን ብቻ ለሚሰማባቸው ሁለቱ አገራት ሰዎች ደስ ብሏለቸው ሲዝናኑና ጥሩ ጊዜ ሲያሳልፉ ማየት በርካቶችን አስደስቷል። በተለይ ደግሞ ለበርካታ አስርት ዓመታት የቆየው የሁለቱ አገራት ደም አፋሳሽ ግጭትን ተከትሎ ዜጎች እንዲህ ባለ ሁኔታ በአንድ ጉዳይ ላይ ሲስማሙ አይታይም። ''በድንበሩ አካባቢ ደስታና ጥሩ ጊዜ ከሰዎች ጋር እንደማሳለፍ የመሰለ ምን ነገር አለ። ዓለም በክፍፍልና በችግር በተሞላችበት ወቅት ደስታን መካፈልን የመሰለ ነገር የለም'' ስትል ለቢቢሲ ገልጻለች። ''በለቀቅኩት ቪዲዮ ምክንያት ጎረቤቶቼ (ሕንዳውያን) እና እኔ በአንድ ላይ በመደሰታችን ተገርሜያለው'' ብላለች። ዳናኒር ሞቢን የ19 ዓመት ወጣት ስትሆን በኢንስታግራም ላይ ታዋቂ ነች። ከፓኪስታኗ ሰሜናዊ ከተማ ፔሽዋር ነው የመጣችው። የምትለቃቸው ቪዲዮዎች አብዛኛውን ጊዜ ፋሽን እና ሜካፕ ላይ ያተኮሩ ናቸው። ከቪዲዮው በታች ባስቀመጠቸው ጽሁፍ ላይ 'በተራሮች ወደተከበበችው ሰሜናዊት ፓኪስታን መጥታችሁ የእረፍት ጊዜያችሁን አሳልፉ' የሚል መልዕክትም አስተላልፋለች። ይህን ተንቀሳቃሽ ምስል የተመለከቱ ሌሎች ታዋቂ ፓኪስታናውያንም ቪዲዮውን በድጋሚ በመስራትና አስቂኝ ነገሮችን በመጨመር እንዲሁም ወደ ሌላኛው ማህበራዊ ሚዲያ ትዊተር በመውሰድ ይበልጥ ታዋቂ አደረጓት። ወዲያውም በርካታ ታዋቂ ፊልም ሰሪዎችና ክሪኬት ተጫዋቾች ይቀባበሉት ጀመር። የፓኪስታን ክሪኬት ቦርድም ቢሆን የአገሪቱ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች ቪዲዮውን በድጋሚ ሰርተው የሚታዩበትን ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አጋርቷል። በመቀጠል ደግሞ አንድ ታዋቂ የሕንድ ዲጄ ቪዲዮውን በመጠቀም የሰራው ሙዚቃ የ19 ዓመቷ ዳናኒር ሞቢን ከፓኪስታን አልፋ በሕንድም ታዋቂ እንድትሆን አድርጓታል።
news-52147218
https://www.bbc.com/amharic/news-52147218
የኮሮናቫይረስ ወርረሽኝ የሴቶችን ሰቆቃ እያባባሰ ይሆን ?
ብዙ አገራት በራቸውን ቆልፈዋል፤ መሪዎች ዜጎቻቸው ላይ በር ከርችመዋል። እንደ ፊሊፒንሱ መሪ ያሉት ደግሞ ደጅ የወጡ ዜጎችን ተኩሱባቸው እስከ ማለት ደፍረዋል።
እያንዳንዱ ቤት የያዘው አመል ብዙ ነው። አንዳንድ ሰዎች ቤት ሲውሉ የሚያሳዩት ባህሪ ግራ ነው። በተለይም በትዳር ውስጥ በሴቶች ላይ ጥቃት የማድረስ አመል የጸናባቸው ወንዶች ቤት ሲውሉ ለሴቶች ሰቀቀን ይሆናሉ። ቢቢሲ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ከባሎቻቸው ጋር ቤት እንዲውሉ በመገደዳቸው መከራቸውን እየበሉ ያሉ ሁለት ሴቶችን አነጋግሯል። ለደኅንነታቸው ሲል ስማቸውን ተቀይሯል። 1. ጊታ፤ ሕንድ ባሌ ፀጉሬን ይዞ ከግድግዳ ጋር ያጋጨኛል… ጠዋት 11፡00 ሰዓት እነሳለሁ። ባሌ ከጎኔ ቁጭ ብሎ ያንቋርራል። ሲያንኮራፋ ጎረቤት ይቀሰቅሳል። ትናንትና ማታ ሰክሮ ነው የገባው። ባጃጅ ነው የሚነዳው። በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሰው ውጭ ስለማይኖር ገቢያችን ቀንሷል። 1500 ሩፒ [የህንድ ገንዘብ] ያገኝ ነበር። አሁን ያ የለም። ስለዚህ ይበሳጫል። "እስከመቼ ነው እንዲህ ቤት ቆልፈው የሚቀልዱብን" እያለ ግድግዳውን በቡጢ ይነርተዋል። አጠገቡ ያለ ብርጭቆ ይሰብራል። እሱ ይህን ባደረገ ቁጥር ልጆቼ ይበረግጋሉ፤ ጉያዬ ውስጥ ይደበቃሉ። ቁጣው ሲበርድለት ሁላችንም ወደምንተኛባት ፍራሽ ሄዶ ይጋደማል። በድጋሚ እንቅልፍ ይጥለዋል። ለጊዜውም ቢሆን እፎይ እንላለን። እሱ ቦግ ባለ ቁጥር ልጆቼን ማረጋጋት ለእኔ ፈተና ነው። በእርግጥ እንዲህ ሲቆጣና ቤቱን በአንድ እግሩ ሲያቆመው ሁልጊዜም ያዩታል። ነገር ግን ቀኑን ሙሉ ቤት ስለማይውል የእፎይታ አፍታ ነበራቸው። አሁን ኮሮናቫይረስ ከመጣ በኋላ እያንዳንዱ ቀን ጭንቅ ሆኗል። አንዳንድ ጊዜ ወደ ግድግዳው እያላጋ የሚሰብረው ነገር ሲያጣ የእኔን ጸጉር እየጎተተ ከግድግዳው ጋር ያላትመኛል። ልጆቼ ፊት ነው ታዲያ ይሄ ሁሉ የሚሆነው። ባሌ ለመጀመርያ ጊዜ የደበደበኝ የሠርጋችን ዕለት ነበር። ነገሮች ይሻሻላሉ ስል ቆየሁ። በኋላ አምርሬ ጥዬው ልጠፋ ስል ልጆቼን አልሰጥም አለኝ። ልጆቼን ለእሱ ጥዬ ወዴት እሄዳለሁ? አርፌ ተቀመጥኩ። የምንኖረው ሞሃላ በሚባል የድሆች ሰፈር ነው። ውሃ ለማምጣት በየቀኑ ሩቅ ኪሎ ሜትር እጓዛለሁ። ከዚያ ትንሽ ከጎረቤቶቼ ጋር አወራና አትክልት ቸርቻሪዎች ሲመጡ ከእነሱ አስቤዛ እገዛለሁ። ለዚያች ቀን ብቻ የሚሆን አስቤዛ ከገዛሁ በኋላ ምግብ አበስላለሁ። ባሌን ቁርስ አብልቼው ወደ 1 ሰዓት ገደማ ወደ ሥራ ይሄዳል። ከዚያ ለምሳ ይመለሳል። በልቶ ትንሽ ከተኛ በኋላ ወደ ሥራ ይወጣል። ነገሮች መለወጥ የጀመሩት ከኮሮናቫይረስ በኋላ ነው። ልጆቼ ቤት መዋል ሲጀምሩ እሱም ነውጠኛ ሆነ። ልጆቹ ሲጫወቱ ይበሳጫል። ብስጭቱን የሚወጣው ግን በእኔ ላይ ነው፡፡ መጀመርያ እነሱ ላይ ይጮኻል። ፈርተውት ጸጥ ይሉና እንደገና ጨዋታቸውን ይቀጥላሉ። የልጅ ነገር! ከዚያ ብስጭቱን አጠረቃቅሞ እኔ ላይ ይወጣዋል። በትንሽ ነገር ነው የሚናደደው። ለምሳሌ የሻይ ኩባያው ለምን ከጠረጴዛው አልተነሳም ብሎ አገር ይያዝልኝ ሊል ይችላል። ልጆቹ ላይ ሲጮኽ ትኩረቱን ለማስቀየር አውቄ የባጥ የቆጡን አወራለሁ። ልጆቼ እንዳይደነግጡብኝኮ ነው. . . . እንደዛሬው በኮሮናቫይረስ ምክንያት አብረን መዋል ከመጀመራቸው በፊት ልክ እግሩ እንደወጣ ወደ ትምህርት ቤት እሄዳለሁ። የምማረው ልብስ ስፌት ነው። በተጨማሪም ማንበብና መጻፍ ያስተምረኛል ሰፈሬ ውስጥ ያለ አንድ ማኅበር፡፡ እኔ እየተማርኩ እንደሆነ ባሌ ቢያውቅ ይገድለኛል። አሁን ምኞቴ የራሴ ገቢ ኖሮኝ ልጆቼን ይዤ ከእርሱ መለየት ብቻ ነው። ኮሮናቫይረስ እንዲጠፋ የምመኘውም ባሌ ቀን ቀን ወደ ሥራ እንዲሄድ ከመሻት ነው፡፡ 2. ካይ፤ ኒው ዮርክ አባቴ ማታ ማታ የወሲብ ፊልም ያያል. . . ካይ ወጣት ሴት ናት። ጥቃት የሚያደርስባት ደግሞ አባቷ ነው። ስልኳን መዥረጥ አድርጋ አወጣችና "ማሚ ካንተ ጋር እንድቆይ ብላኛለች" የሚል ጽሑፍ ላከች። ከአባቷ ፈጣን ምላሽ አገኘች። "ምንም ቸግር የለም፤ ነይ" የሚል። ካይ ታሪኳን እንዲህ ትቀጥላለች። ባለፈው ሳምንት መቼም አልመለስበትም ወዳልኩበት የአባቴ ቤት ተመለስኩ። ልክ እንደገባሁ መላ ሰውነቴ እንደ ሬሳ ቀዘቀዘ። ስሜት አልባ ሆንኩ። አልናገር አልጋገር። አባቴ ለዓመታት በስሜትም በአካላዊ ጥቃትም ሲጎዳኝ ነው የኖረው። መጀመርያ ኮሮናቫይረስ መጣ ሲባል ተራ ጉዳይ ነበር የመሰለኝ። ቫይረሱ ኒው ዮርክ መድረሱ ሲዘገብ ግን ነገሮች መልካቸውን ቀየሩ። እናቴ አንድ መደብር ውስጥ ነበር የምትሰራው። ከብዙ ደንበኞች ጋር መገናኘት ትገደዳለች። ወዲያውኑ ግን የምትሰራበት መስሪያ ቤት በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሥራ መዝጋቱን አስታወቀ። ድርጅቱ ሲዘጋ እናቴ በሰዓት 15 ዶላር ገቢዋን አጣች። የጤና መድኅኗ ሊቃጠል አምስት ቀናት ብቻ ነበር የቀሩት። ምን ተሻለ? በጭንቀት የአእምሮ ታማሚ ሆነች። ድሮም አለፍ አለፍ እያለ ይነሳባት ነበር። ከኮሮናቫይረስ በኋላ ግን እየባሰባት መጣ። ድንገት ትጮኻለች። "ውጪልኝ፤ አባትሽ ጋ ሂጂ፤ ውጪ!" እያለች። ወደ አባቴ በፍጹም መሄድ አልፈለኩም። አንድ ክፍል ቆልፌ ተቀመጥኩ። ሆኖም ልታስቀምጠኝ አልቻለችም። በሩን እየደበደበች "አሁንም እዚህ ነው ያለሽው? ውጪልኝ አላልኩም! አይንሽን እንዳላየው" ትለኛለች። እናቴ አእምሮዋን ስለሚያማት ነው እንጂ አባቴ የሚያደርስብኝ ጥቃት ጠፍቷት አይደለም። አባቴ ገና ድክ ድክ ማለት ሳልጀምር ነበር ሁሉን አይነት ጥቃት ይፈጽምብኝ የነበረው። ጠባሳው አሁንም አለ። ሆኖም ያደረሰብኝን ሁሉ ለእናቴ ነግሪያታለሁ ማለት አልችልም። ኮሮናቫይረስ ከመምጣቱ ቀደም ብሎ በልጅነቴ አባቴ ያደረሰብኝን ሥነ ልቡናዊ ጥቃት ለማከም ቴራፒስት ሐኪም ጋር እመላለስ ነበር። ጥሩ መሻሻል እያሳየሁ ሳለ ነው ይህ ወረርሽኝ የመጣው። ሐኪም ቤቱም ተዘጋ። ምንም አማራጭ የለም፤ መውደቂያ ስላጣሁ ወደ አባቴ ሄድኩ። እዚህ አባቴ ጋ ከመጣሁ ጀምሮ አውርተን አናውቅም። ቀን ላይ በኮምፒውተሩ ዜና ሲያይ ይውላል። ማታ ማታ ደግሞ የወሲብ ፊልሞችን ሲያይ እመለከተዋለሁ። ጠዋት መነሳቱን የማውቀው የፍራፍሬ ጭማቂ ማሽኑ ሲጮኸ ነው። ይህ የማሽን ድምጽ ለእኔ በጣም አስቀያሚ ደውል ነው። ምክንያቱም የአስጨናቂው ቀን መጀመርን ስለሚያረዳኝ። ቀኑ ብቻ ሳይሆን ማታም ጭንቅ ነው። የክፍሌ በር አይዘጋም። ስለዚህ እንቅልፍ አልባ ሌሊት ነው የማሳልፈው። አባቴ በማንኛውም ሰዓት ገብቶ ጥቃት ሊፈጽምብኝ እንደሚችል አውቃለሁ። ከክፍሌ የምወጣው ወይ ለሽንት ነው ወይም ደግሞ ሲርበኝ ማዕድ ቤት ምግብ ለማብሰል ነው። ከአባቴ ጋር በፍጹም ላለመነጋገር እሞክራለሁ፡፡ ምክንያቱም ጥቃት የሚሰነዝርብኝ ብዙውን ጊዜ ተነጋግረን ሳንግባባ ስንቀርና ሲናደድብኝ ነው። የኮሮና ወረርሽኝ ቶሎ እንዲቆም እሻለሁ። ለሌላ አይደለም። ቶሎ ወደ እናቴ ለመመለስ። አባቴን ማየት አልፈልግም! ሕመም ነው!
55962693
https://www.bbc.com/amharic/55962693
የዓለም ንግድ ድርጅት ቀጣይ መሪ ይሆናሉ ተብለው የሚጠበቁት ናይጄሪያዊት
የጆ ባይደን አስተዳደር ቀጣዩ የዓለም ንግድ ድርጅት መሪ ማን ይሁን ለሚለው አጣብቂኝ ምላሽ መስጠቱ ተሰምቷል።
የ66 ዓመቷ የናይጄሪያ የቀድሞ ፋይናንስ ሚኒስትር እና ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ኦኮንጆ ኢዌላ የጆ ባይደን አስተዳደር ለቀድሞዋ የናይጄሪያ ፋይናንስ ሚኒስትር ድጋፉን በመግለጽ ለረዥም ወራት ምላሽ ያላገኘውን ፉክክር መቋጫ አበጅቶለታል። ንጎዚ ኦኮንጆ ኢዌላ ፕሬዝዳነት ትራምፕ ስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት የዓለም ንግድ ድርጅትን ለመምራት በሚደረገው ፉክክር ወቅት ከደቡብ ኮሪያዋ፣ ዩ ሚዩንግ ሂ ጋር ብርቱ ተፎካካሪ ነበሩ። ወይዘሪት ዮ ከተፎካካሪነታቸው ራሳቸውን አግልለዋል። የናይጄሪያ የቀድሞ ፋይናንስ ሚኒስትር የነበሩት ሴት የዓለም ንግድ ድርጅትን እንዲመሩ መመረጣቸው ይፋ ከሆነ ዶ/ር ኦኮንጆ ኢዌላ የዓለም ንግድ ድርጅት መሪ በመሆን የመጀመሪያዋ ሴት እና አፍሪካዊት ይሆናሉ ማለት ነው። ዶ/ር ኦኮንጆ ኢዌላ አርብ ዕለት ተፎካካሪያቸው የነበሩትን ደቡብ ኮሪያዊት አንቆለጳጵሰው "አብረን የምንሠራቸው ቁልፍ ሥራዎች ከፊታችን ይጠብቁናል" ሲሉ በማህበራዊ ሚዲያቸው ላይ አስፍረዋል። የዓለም ንግድ ድርጅት አስመራጭ ኮሚቴ በጥቅምት ወር ለ164 አባላቱ ዶ/ር ኦኮንጆ ኢዌላን በተሰናባቹ ሮቤርቶ አዝቬዶ ምትክ እንዲሾም ጠይቀው ነበር። በወቅቱ ቃል አቀባይ የነበሩት ግለሰብ "ከአንዱ በስተቀር ሁሉም ሹመቱን አጽድቀውታል" ብለው ነበር። ዓለም ንግድ ድርጅትን " አሳፈሪ" እና ለቻይና ያደላል ሲሉ የገለፁት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ የደቡብ ኮርያ ንግድ ሚኒስትር የሆኑት ወይዘሪት ዮ ቦታውን እንዲያገኙ ፈልገው ነበር። ወይዘሪት ዮ አርብ ዕለት ከተፎካካሪነት ራሳቸውን ሲያገሉ እንደተናገሩት እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት ከአሜሪካ ጋር "በቅርበት በመመካከር" መሆኑን ገልፀዋል። ዋይት ሐውስም ወይዘሪት ዮን ላደረጉት ጠንካራ የምረጡኝ ዘመቻ አመስግኗል። አሜሪካም ሆኑ ደቡብ ኮሪያ ቀጣዩ የዓለም ንግድ ድርጅት ኃላፊ ማን መሆን እንዳለበት በሚወሰነው ውሳኔ ላይ የነቃ ተሳትፎ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።
news-46111426
https://www.bbc.com/amharic/news-46111426
የቤት ውስጥ አየር መበከል ለጤናችን ጠንቅ እንደሚሆን? አምስት የመፍትሄ ሃሳቦችን እነሆ
የአየር ብክለት ለብዙ ሃገራት ፈተና እየሆነ የመጣ ጉዳይ ሲሆን፤ በየዓመቱ እስከ ሰባት ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች ከዚህ ጋር በተያያዘ ህይወታቸው ያልፋል።
ቤት ውስጥ ሲጋራ ማጨስ የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ ነው አሁን እየኖርንበት ባለው ዓለም ከአስር ሰዎች ዘጠኙ ሲተነፍሱ የሳንባ ካንሰርን ለመሳሰሉ በሽታዎች ይጋለጣሉ። እነዚህ በአይን የማይታዩ በካይ ንጥረ-ነገሮች በቤት ውስጥ ስንሆን ደግሞ ጉዳታቸው ከፍተኛ ነው። አዲስ በተሰራ አንድ ጥናት መሰረትም በቤት ውስጥ የሚከሰት ብክለት የሚያደርሰው ጉዳት ከውጪው ጋር ሲነጻጸር ከሁለት እስከ አምስት እጥፍ ይበልጣል። • አትክልት ብቻ ስለሚመገቡ ሰዎች ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮች ነገር ግን ይህንን ጉዳት ለመቀነስ የተለያዩ መንገዶችን መጠቀም አሉ። እንዚህ አምስት የመፍትሄ እርምጃዎች በቤት ውስጥ ሊያጋጥመን የሚችልን ብክለት ለመከላከል ጠቃሚ ምክሮኦች ናቸው። 1. አየር እንደልብ እንዲዘዋወር ያድርጉ አየር በቤት ውስጥ በደንብ የማይንሸራሸር ከሆነ፤ በካይ ንጥረ-ነገሮች በቤት ውስጥ ይቀራሉ። • ትላልቅ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድቦች "አዋጭ አይደሉም" የቤት ውስጥ በሮችና መስኮቶች ቢያንስ በቀን ከሁለት እስከ ሦስት ጊዜ ቢከፈቱና ለሃያ ደቂቃዎች ቤቱ ቢናፈስ፤ በካይ የሆኑት ንጥረ-ነገሮች ከአዲሱ አየር ጋር ተቀላቅለው የመውጣት እድላቸው ሰፊ ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪም ምግብ ካበሰሉ በኋላና ገላዎትን ከታጠቡ በኋላም ቤትዎን ማናፈስ ተገቢ ነው። የቤትን በርና መስኮት በመክፈት አየር እንዲዘዋወር ማድረግ 2. በቤት ውስጥ ተክሎች እንዲኖሮ ያድርጉ ቤትን በአትክልት መሙላት ከሚኖረው ጥቅም በተጨማሪ ለመመልከትም ማራኪ ነው። አንዳንድ ተክሎች በአየር ውስጥ የሚገኙ ጎጂ ንጥረ-ነገሮችን የማስወገድ አቅም ያላቸው ሲሆን፤ ካርቦንዳይ ኦክሳይድን አፍኖ በመያዝ ለአካባቢያችንም ከፍተኛ ጠቀሜታን ያበረከታሉ። • በኢትዮጵያ የቢጫ ወባ ወረርሽኝ 10 ሰዎችን ገደለ ነገር ግን በቤታችን ውስጥ የምናስቀምጣቸው ተክሎች እንክብካቤ የማናደርግላቸው ከሆነ፤ እንደውም ጎጂ የሆኑ ንጥረ-ነገሮችን ወደ አየር ሊለቁ ይችላሉ። ስለዚህ ሁሌም ቢሆን ሌላው ቢቀር ውሃና ጥሩ አየር እንዲያገኙ ማድረግ ያስፈልጋል። 3. ሽታ ያላቸው ፈሳሾችን ያስወግዱ በማንኛውም ጊዜ በቤት ውስጥ የሚጠቀሟቸው ሽቶዎች፣ ዲኦድራንቶችና የአየር ጠረን መቀየሪያ ምርቶች ትተውት የሚሄዱት ጎጂ ንጥረ-ነገር አለ። ይህ ደግሞ ሰውነታችን ላይ በተለይ ደግሞ ሳንባችን ላይ ያለው አሉታዊ ተጽዕኖው ከፍተኛ ነው። የተለያዩ አይነት የቤት ውስጥ ተክሎች መትከል 4. በቤት ውስጥ ሲጋራ አያጭሱ ማጨስ በራሱ ከፍተኛ ጉዳት ያለው ሲሆን፤ ቤት ውስጥ ማጨስ ደግሞ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደማለት ነው። የሲጋራ ጭስ በቤት ውስጥ ሲጠራቀም በተለይ ደግሞ በሮች ተዘግተው ከሆነ የሚኖረው ጉዳት እንኳን ለማያጨስ ሰው፤ ለሚያጨሰው ሰው በራሱ ከፍተኛ ጉዳት አለው። በቤት ውስጥ ሲጋራ ከሚያጨሱ ቤተሰቦች የሚወለዱ ህጻናት ደግሞ ለድንገተኛ ሞት የተጋለጡ ናቸው። • አደገኛ የተባለ የወባ በሽታ በበርካታ ሀገራት ስጋት ፈጥሯል። በኢትዮጵያስ? 5. የቤትዎን ንጽህና ይጠብቁ
50997426
https://www.bbc.com/amharic/50997426
ለማርስ የተጻፈው ብሔራዊ መዝሙር
ሕንዳዊው የቀድሞ የሶፍትዌር ባለሙያ አሁን ኦፔራ ሙዚቃ ዘንድ ስሙን የተከለ ባለሙያ ነው። ይህ ደግሞ ለማርስ ብሔራዊ መዝሙር እንዲጽፍና እንዲያቀናብር አሳጭቶታል።
ማን የብሔራዊ መዝሙር የሌለው አለ? ሀገራት? የእግር ኳስ ቡድኖች? የፖለቲካ ፓርቲዎች? የነጻነት ታጋዮች? ሁሉም ሕልማቸውን ያዘለ፣ ትግላቸውን የሳለ ብሔራዊ መዝሙር ያዘጋጃሉ። ኦስካር ካስቴሊኖም በዩኬ ማርስ ሶሳይቲ ለቀይዋ ፕላኔት ብሔራዊ መዝሙር እንዲያዘጋጅ የቤት ስራ የተሰጠው ይህ ሁሉ ከግምት ገብቶ ነው። • ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ74 የዩኒቨርሲቲው ማሕበረሰብ ላይ እርምጃ ወሰደ • "'እኛ ድሆች ነን፤ ገንዘብ ከየት እናመጣለን' እያልን ስንደራደር ነበር" በጠገዴ ታግቶ የተገደለው ታዳጊ አባት ዓላማው የሰው ልጅ አንድ ቀን በፕላኔቷ ላይ መኖር ቢጀመር የራሱ የሆነ ብሔራዊ መዝሙር ያስፈልገዋል የሚል ነው። ሰዎች ሲሰሙትም ሆነ ሲዘምሩት ይላል ኦስካር ካስቴሊኖ "ልጆቻችን፣ ልጆቻቸው ያለንን መጻኢ እድል እንዲያስቡ፣ እንዲያልሙ እፈልጋለሁ።" ይህንን እንዲያስቡ የሚፈለገው ግን ምድርን ለቅቆ በማርስ ስለመኖር፣ ማርስን መርገጥና ማርስ ላይ መኖርን መልመድ ያለውን ውስጣዊ ትፍስህት ብቻ ሳይሆን፣ አብረው ህልምን የማሳካት ብርቱ ጥረትን እንዲያስቡም እንደሚፈለግ ይናገራል። የብሔራዊ መዝሙሩ ግጥም እንዲህ የሚሉ ስንኞች አሉበት። 'Rise to mars men and women' 'Dare to dream Dare to strive!' 'Bulid a home for our children' 'Make this desert come alive' ኦስካር ካስቴሊኖ ያደገው በሕንድ የሒማሊያ ተራራማ ግርጌዎች አካባቢ ነው። ባደገበት አካባቢ ከዋክብት ፍንትው ብለው ይታዩ ነበር ሲል የልጅነት ትውስታውን ለቢቢሲ አጋርቷል። • የኃይማኖት መፃዒ ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል? ግጥሞቹን ለመጻፍ ይህ የልጅነት ትውስታው እንደረዳው በመግለጽ ሁሌም ከከዋክብቱ ባሻገር ስልጣኔ የሚሉት ነገር ይኖር ይሆን? እንደው ሰውስ ይኖር ይሆን? ሌላ ንፍቀ ዓለምስ አለ? የሚሉ የልጅነት ጥያቄዎቹን ያስታውሳል። ዩኬ ማርስ ሶሳይቲ፣ ማርስ በሚገባ እንድትጠናና እዚያ ሰው ልጅ ቤቱን ሰርቶ እንዲከትም የሚሰሩ ሰዎች የተሰባሰቡበት ድርጅት ነው። ኦስካር ለማርስ ብሔራዊ መዝሙር እንዲጽፍ የተነገረውም በተቋሙ መሆኑን የድርጅቱ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሮበርት ዙብሪን ይናገራሉ። የተሳካ እንቅስቃሴ ሆኖ ብሄራዊ መዝሙር ሳይኖረው የቀረ ማን ነው? ብለው የሚጠይቁት ፕሬዝዳንቱ ሙዚቃ ነፍስን እንደሚወዘውዝ በማስታወስ መዝሙሩን ለማዘጋጀት መወሰናቸውን ይናገራሉ። "ማርስ ላይ ደሳሳ ጎጆ ቀልሰን፣ ወልደን ከብደን መኖር ስንጀምር ትልቅ ስኬት ነው" የሚለው ኦስካር፣ በፕላኔቶች መካከል እየተመላለሱ የሚያቀርቡት ዓይነት ትርዒት ነው በማለት ስሜቱን ይገልፃል። በምድር ያሉ በማርስ ከሚኖሩ ጋር በአንድነት የሚዘምሩት ብሔራዊ መዝሙር። ይህ ብሔራዊ መዝሙር ስለማርስ ብቻ አይደለም። የሰው ልጅ ትልቅ እመርታን ማሳየቱን የሚያወድስ ጭምር ነው። ይህ ብሔራዊ መዝሙር ሰዎች እንዲያልሙ፣ ትልቅ እንዲያስቡና ማርስንና ከማርስ ባሻገር አሻግረው እንዲመለከቱ እንደሚያነሳሳቸው እምነት አለን ሲልም ሃሳቡን ያጠቃልላል።
41563920
https://www.bbc.com/amharic/41563920
በካሊፎርኒያ ግዛት የተነሳው ሰደድ እሣት ሕይወት እና ንብረት እያጠፋ ነው
ቢያንስ 1500 ቤቶች ወድመዋል። በካሊፎርኒያዋ ሶኖማ በተባለ አካባቢ ደግሞ ሰባት ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን የግዛቲቱ ባለስልጣናት አሳውቀዋል።
በካሊፎርኒያ ታሪክ እጅግ አስከፊው በተባለለት የሰደድ እሣት ምክንያት 20ሺህ ሰዎች ከናፓ፣ ሶኖማ እንዲሁም ዩባ አካባቢዎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው ሸሽተዋል። የካሊፎርንያ አስተዳዳሪም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል። "እሣቱ ቤት ንብረት ላይ እያደረሰ ያለው አደጋ እጅግ ከፍተኛ ስለሆነ ሰዎችን ወደሌላ ቦታ ማሸሽ ግድ ይላል" ሲል አዋጁ ያትታል። በሰደድ እሳቱ ምክንያት ብዙ አደጋዎች እንደተመዘገቡና የተወሰኑ ሰዎች አሁንም ያሉበት እንደማይታወቅ ተዘግቧል። የካሊፎርኒያ እሣት አደጋ መከላከል ክፍል ኀላፊ እንደተናገሩት ወደ 1500 ቤቶች በሰደዱ ምክንያት ወድመዋል። እሣቱ ዕለተ-እሁድ ማታ በምን ምክንያት ሊነሳ እንደቻለ አሁንም ማወቅ አልተቻለም። ናፓ በተሰኘችው አካባቢ የእሣት አደጋ ሰራተኞች ሥራቸውን መከወን ባለመቻላቸው ከፌደራል መንግሥት እርዳታ እንሚያሻቸው የአካባቢዋ አስተዳዳሪ አስታውቀዋል። በወይን ፋብሪካ ይሰሩ የነበሩ በአስራዎቹ የሚቆጠሩ ሰዎች በተደረገ ርብርብ ከአደጋው መትረፍ መቻላቸውም ተዘግቧል። የአየር ሁኔታው እና በከፍተኛ ሁኔታ የሚነፍሰው ንፋስ ለሰደዱ መስፋፋት ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ እንዳለም ማወቅ ተችሏል። የአሜሪካ አየር ሁኔታ መሥሪያ ቤት ሰደድ እሣቱ ወደ ሳን ፍራንሲስኮ ግዛትም ሊዛመት እንደሚችል ፍንጭ ስላለ ሰዎች ጥንቃቄ እንዳይለያቸው አሳስቧል። አንድ የወይን ፋብሪካ ባለቤት ለኤል.ኤ ታይምስ ጋዜጣ ሲናገር "ምንም እንኳ ንብረቴ ቢወድም ቤተሰቦቼን ይዤ ዕሁድ ማታ ማምለጥ ችያለሁ" ብሏል። የካሊፎርኒያ እሣት አደጋ መስሪያ ቤት እንደሚገምተው ሰደዱ ከ26 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት እንዳዳረሰ እና በካሊፎርንያ ታሪክ እጅግ አጥፊው እንደሆነ ነው። ባለፈው ወር የካሊፎርንያዋ ሎስ አንጀለስ በታሪኳ ከፍተኛ የተባለ እሣት አስተናግዳ እንደነበረ የሚታወስ ነው።
56993238
https://www.bbc.com/amharic/56993238
አሜሪካ በኮቪድ ክትባቶች ላይ የአእምሯዊ መብት ጥበቃ እንዲነሳ ድጋፍ ሰጠች
አሜሪካ በዓለም ንግድ ድርጅት መድረክ ላይ በኮቪድ-19 ክትባቶች ላይ የአእምሯዊ መብት ጥበቃ እንዲነሳ ድጋፍ ሰጠች።
የዓለም ንግድ ድርጅት አባል አገራት ለኮቪድ-19 ክትባቶች የባለቤትነት ጥበቃ እንዳይደረግ ቢስማሙ፤ ደሃ አገራትን ጨምሮ በርካቶች ክትባቶቹን ማምረት እና በዝቅተኛ ዋጋ ለተጠቃሚ ማድረስ ይችላሉ ተብሏል። ከዚህ ቀደም ሕንድ እና ደቡብ አፍሪካ የክትባት አበልጻጊዎቹ የያዙት የአእምሯዊ መብት ጥበቃ እንዲነሳ አጥብቀው ሲወተውቱ ቆይተዋል። ይሁን የእንጂ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝደንት አስተዳደር፣ የአውሮፓ ሕብረት እና ዩናይትድ ኪንግደም የክትባቶቹ የአእምሯዊ መብት መጠበቅ አለበት ሲሉ ቆይተዋል። መድሃኒት አምራች ኩባንያዎችም የአእምሯዊ መብት እንዲነሳ መደረጉ የተፈለገውን ውጤት ሊያመጣ አይችልም በሚል የጆ ባይደንን አስተዳደር ትችተዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የፕሬዝደንት ጆ ባይደንን ውሳኔ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመዋጋት ቁልፍ እርምጃ ነው ብለዋል። የዚህ ሃሳብ ደጋፊዎች እንደሚሉት፤ በክትባቱ ዙሪያ ያሉ የአእምሯዊ መብት ጥበቃዎች እንዲነሱ ቢደረግ ክትባቱን በበርካታ ቦታዎች በብዛት ማምረት እና ሚሊዮኖችን ተጠቃሚ ማድረግ ይቻላል። አገራት ክትባቱን በአገራቸው እንዳያመርቱ ከመብት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች እንቅፋት እንደሆኑባቸው ሲገልጹ ነበር። የአሜሪካ የንግድ ተወካይ በዓለም አቀፍ የንግድ ድርጅት መድረክ ላይ አገራቸው በክትባቶቹ ዙሪያ ያለውን የመብት ጥበቃዎች እንዲነሱ ተወተውታለች ብለዋል። በክትባቶቹ ዙሪያ ያሉት የመብት ጥበቃዎች የሚነሱት 164 የድርጅቱ አባል አገራት በሙሉ ሲስማሙ ነው ተብሏል። የክትባት ባለቤት የሆኑ ድርጅቶችን የአእምሯዊ መብት ለማንሳት ረጅም ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል ተገልጿል። የፕሬዝደንት ጆ ባይደን ውሳኔን "አሳዛኝ" ያለው ሲል የዓለም የመድሃኒት አምራች ኩባንያዎች ማህበር ገልጾታል። ማህበሩ "የአምራቾችን መብት ማንሳት ውስብስብ ለሆነ ችግር ትክክል ያልሆነ መልስ መስጠት ነው" ብሏል።
news-53605349
https://www.bbc.com/amharic/news-53605349
ከኮሮናቫይረስ በእጅጉ እያተረፉ ያሉት ትልልቅ ድርጅቶች
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የበርካታ አገራት ኢኮኖሚ ላይ ከባድ ጫና እያደረሰ ቢሆንም ትልልቅ የሚባሉት የዓለማችን የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ግን ጥሩ የሚባል ትርፍ እየሰበሰቡ ነው።
ኩባንያ በበይነ መረብ አማካይነት የተለያዩ አይት መገልገያዎችን የሚሸጠው አማዞን ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ማግስት ባሉት ሶስት ወራት ብቻ ሽያጩ 40 በመቶ ከፍ እንዳለለት ያስታወቀ ሲሆን ታዋቂው የስልክና የላፕቶፕ አምራች አፕል ደግሞ የአይፎንና ሌሎች መቀየሪያ መሳሪያዎች በደንብ እንደተቸበቸቡለት ገልጿል። ፌስቡክ ደግሞ በስሬ በማስተዳድራቸው እንደ ዋትስአፕና ኢንስታግራም ባሉ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተጠቃሚዎች ቁጥር 15 በመቶ ከፍ ብሎልኛል ብሏል። • በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ትርፉ መጨመሩን ሳምሰንግ አስታወቀ • ኮሮናቫይረስ የቀሰቀሳቸው የአና የሚበሉ ሥዕሎች • ከኮሮናቫይረስ የትኞቹ ድርጅቶች አተረፉ? እነማንስ ከሰሩ? የአማዞን የሩብ ዓመት ትርፍ 5.2 ቢሊየን ዶላር ሲሆን ድርጅቱ ከተቋቋመበት ከአውሮፓውያኑ 1994 ጀምሮ ይህ ከፍተኛው ነው ተብሏል። ድርጅቱ እንደውም ከኮሮናቫይረስ መከሰት በኋላ ለሰራተⶉቹ መከላከያ መሳሪያዎችን ለመግዛትና የመከላከያ ጥንቃቄዎችን ለማድረግ ከፍተኛ ወጪ ማውጣቱ ትርፉን ዝቅ ያደርገዋል ተብሎ ተፈርቶ ነበር። በአጠቃላይ በበይነ መረብ የሚካሄዱ ንግዶች የሽያጭ መጠኑ 40 በመቶ ከፍ ብሏል። እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ባሉት ሶስት ወራት ደግሞ በአጠቃላይ 88.9 ቢሊየን ዶላር አንቀሳቅሷል። ትርፍም ቢሆን በአስገራሚ ሁኔታ ባለፈው ዓመት ከነበረበት 2.6 ቢሊየን ዶላር ወደ 5.2 ቢሊየን ዶላር ከፍ ብሏል። በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በወረርሽኙ ምክንያት ቤት ውስጥ ብዙ ጊዜያቸውን ማሳለፋቸውን ተከትሎ የበይነ መረብ ሽያጭ በእጅጉ ተጧጡፏል። አማዞንም ቢሆን የደንበኞቹን ፍላጎት ለማሟላት በሩብ ዓመቱ ብቻ ተጨማሪ 175 ሺ ሰራተኞችን ቀጥሯል። ፍላጎቱ በዚሁ መቀጠሉ ስለማይቀር በርካታ መጋዘኖችንና ሰራተኞችን ለመጨመርም እያሰበ ነው። የአፕል የሩብ ዓመት ትርፍ ደግሞ ባለፈው ዓመት ከነበረበት 11 በመቶ በመጨመር 59.7 ቢሊየን ደርሷል። ሰዎች ስራቸውን ከቤታቸው ሆነው መስራታቸው የተለያዩ መገልገያዎችን እንዲጠቀሙ አድርጓቸዋል። በዚህም ምክንያት የማክ ላፕቶፖችና አይፓዶች በእጅጉ ተፈላጊ ነበሩ። ሁለቱም የአፕል ምርቶች ከወረርሽኙ መከሰት በኋላ ገበያቸው እንደደራ ድርጅቱ አስታውቋል። በዚህም ምክንያት ባለፈው ከነበረው 10 ቢሊየን ዶላር ትርፍ ወደ 11.25 ቢሊየን ዶላር ከፍ ብሏል። ፌስቡክ ደግሞ ከኮሮናቫይረስ በኋላ ትርፉ በእጅጉ እንደሚቀንስ ቢጠበቅም እንደውም የ 11 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። አነስተኛ ድርጅቶች ያሏቸው ሰዎች ለማስታወቂያ ወደ ፌስቡክ ላይሄዱ እንደሚችሉ ባለሙያዎች ተንብየው ነበር። ነገር ግን ወረርሽኙን ተከትሎ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ቁጥር በእጅጉ በመጨመሩ ምክንያት ለማስታወቂያ የሚመጡ ድርጅቶችም ቁጥር አብሮ ከፍ ብሏል። በዚህም ምክንያት የድርጅቱ የሩብ ዓመት ትርፍ 5.2 ቢሊየን ዶላር እንዲደርስ ሆኗል። ፌስቡክ እንደሚለው ባለፈው ሰኔ ወር ብቻ በሁሉም የማህበራዊ ሚዲያዎቸ ላይ 2.4 ቢሊየን ተጠቃሚዎች የነበሩ ሲሆን ይህም የ15 በመቶ ጭማሪ አለው። ከአራቱ ትልልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች አንዱ የሆነው አልፋቤትም ቢሆን እንደ ሌሎቹ ባይሆንም ትርፋማ ሆኗል። ድርጅቱ በስሩ ጉግልና ዩቲዩብን የያዘ ሲሆን እስካሁን ያገኘሁት ትርፍ 38.3 ቢሊየን ዶላር ነው ብሏል። ይህ ደግሞ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የሁለት በመቶ ቅናሽ ያሳያል።
50218917
https://www.bbc.com/amharic/50218917
የባልደራስ፣ የአብን አባላትና የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ ባለቤት ተፈቱ
የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት፣ የአብን ፓርቲ አባላት እንዲሁም የብርጋዴል ጄነራል አሳምነው ጽጌ ባለቤት በዛሬው ዕለት ተፈተዋል
ግለሰቦቹ የተታሰሩት ከሰኔ 15 ግድያ ጋር በተያየያዘ በሽብር ተጠርጥረው ሲሆን አቃቤ ሕግ ክስ የመመስረቻ ጊዜ ቢሰጠውም ክስ ሳይመሰርት መለቀቃቸውን በዛሬው ዕለት ከእስር የተፈቱት አቶ ስንታየሁ ቸኮል ለቢቢሲ በስልክ ገልፀዋል። የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት (ባልደራስ) አባላት ጠበቃ የሆኑት አቶ ሔኖክ አክሊሉ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ላለፉት አራት ወራት በእስር ላይ ያሳለፉት ደንበኞቻቸው የተለቀቁት በመታወቂያ ዋስ መሆኑን ተናግረው ምንም ዓይነት ክስ ሳይመሰረት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፈታታቸውን ገልፀዋል። •"ከጄ/ል አሳምነው ጋ በምንም ጉዳይ ያወራሁበት አጋጣሚ የለም" እስክንድር ነጋ •በአዲስ አበባ ህዝባዊ ውይይት የታሰሩ ተለቀቁ የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት ህዝብ ግንኙነት ከሆኑት አቶ ስንታየሁ ቸኮል በተጨማሪ የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት አባላት የሆኑት አቶ መርከቡ ኃይሌ፣ ኤሊያስ ገብሩ እንዲሁም አዳም ጂራ መፈታታቸውን አቶ ሔኖክ ገልጸዋል። በተለምዶ ሶስተኛ የሚባለው አዲስ አበባ ፓሊስ ጣቢያ ለወራት ታስረው የነበሩት አቶ ስንታየሁ እንደሚፈቱ የሰሙት ዛሬ ከሰዓት እንደነበር ተናግረዋል። "ፖሊስ የምርመራ ጊዜ ወስዶ ቢመረመርም ያገኘብን መረጃ ስለሌለ በነጻ ተለቀናል" ያሉት አቶ ስንታየሁ " እኛ ሳንሆን እውነት ነው ያሸነፈው" ብለዋል። አቶ ስንታየሁ አክለውም መጀመሪያም "የህሊና እስረኞች ነበርን በነጻ ተለቅቀናል፤ ዛሬ ተፈታን ብለን ነገ ከትግል የምንሸሽበት መንገድ የለም አሸናፊ ሆነን ነው የወጣነው" ብለዋል። የእስር ቆይታቸው ፈታኝ እንደነበር የሚናገሩት አቶ ስንታየሁ በጨለማ ቤት ውስጥ ከሁለት ወር በላይ ማሳለፋቸውን ለቢቢሲ አስረድታዋል። •"ሰልፍ የዜጎች መሰረታዊ መብት ነው" መስፍን ነጋሽ "መንፈሳችንን ለመስበር ቢሞክሩም አልተሳካላቸውም፤ የሕዝብ ጥያቄ በመያዛችን ከትግል የምናቆምበት ነገር የለም" ሲሉ ከተፈቱ በኋላ ተናግረዋል። አክለውም "እስር ቤት ውስጥ ሆነን አልተጎዳንም ፤ሕዝቡ እየመጣ እያጽናን ነው የነበረው። በመታሰር ውስጥም አሸንፈናል" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ቀጣይ ብዙ ትግል አለ የሚሉት አቶ ስንታየሁ "እኔ ብፈታም ጥያቄያችን አልተፈታም" በማለት የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት የያዘው ጥያቄ መፈታት እንዳለበትም አስረድተዋል። በሌላ በኩል አስራ አራት የአብን አመራሮችና ደጋፊዎች በዛሬው እለት መፈታታቸውን ጠበቃቸው አቶ አበረ መንግሥቴ ለቢቢሲ ገልፀዋል። ከዚህም በተጨማሪ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትና ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ክስ ካልቀረበ ይፈቱ በሚል ውሳኔ ካገኙት ውስጥ አምስት ሰዎች ለጊዜው እንዳልተፈረመላቸው ጠቅሰው ክስ ይመስረት አይመስረት የሚለው ጉዳይም ግልፅ አይደለም ብለዋል። የፓርቲው አባላት ከመታወቂያ ጀምሮ፣ አምስት ሺ፣ ሰባት ሺና አስር ሺ ብር ዋስ መፈታታቸውን ጠበቃቸው ጨምረው አስረድተዋል። የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ ፍርድ ቤት ከዚህ ቀደም ቀርበው የአስራ አምስት ቀን የክስ መመስረቻ የተጠየቀባቸው ሲሆን በመጪው አርብም ይጠናቀቃል። እስከ አርብ ባለው ጊዜም ውስጥ ክስ ካልተመሰረተ የዋስትና መብታቸውንም ማቅረብ እንደሚችሉ ተነግሯቸዋል። የዋስ መብታቸው ተጠብቆ በዛ አግባብ ነው የተፈቱት ስለ አፈታታቸው ሁኔታም እስካሁን ባለው እንደማይታወቅና ክስ የሚያስመሰርት ሁኔታ ይኑር አይኑር እንዲሁም ሌሎች ዝርዝር ሁኔታዎች በመጪው ቀናት እንደሚታወቁም ተናግረዋል። አቶ ክርስቲያንን ጨምሮ ዘጠኝ አባላት እንዳልተፈቱም አቶ አበረ አስረድተዋል። የብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ጽጌ ባለቤት ወ/ሮ ደስታ አሰፋ በዛሬው ዕለት መፈታታቸውንም ጠበቃቸው ነግረውናል።
news-43252765
https://www.bbc.com/amharic/news-43252765
በሶሪያ ግጭት የቱርክ ኃይሎች ላይ ከባድ ጥቃት ተሰነዘረ
በሰሜናዊ ሶሪያ አፍሪን ስምንት የቱርክ ወታደሮች ሲገደሉ 13 ደግሞ ቆስለዋል።
የቱርክ ሰራዊት የኩርድ ተዋጊዎችን መፋለም ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ እንዲህ ያለ ከባድ ጥቃት ደርሶበት አያውቅም። የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ካውንስል ደግሞ በምሥራቃዊው የሃገሪቱ ክፍል ጎታ እየደረሰ ያለው ሰብአዊ ቀውስ ላይ ዛሬ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ ውይይት እንዲካሄድ ጥሪ ያቀረበችው እንግሊዝ ስትሆን በጎታ እየደረሰ ያለው የሰብአዊ ቀውስ ችላ መባሉንና በተደጋጋሚ የህክምና ተቋማት ላይ ጥቃት መሰንዘሩን አውግዛለች። በአማፅያን ቁጥጥር ስር በሆነችውና ከደማስቆ ቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ጎታ ላይ በሶሪያ መንግሥትና በአጋሮቹ የቦምብ ድብደባ ከ580 ሰዎች በላይ ተገድለዋል። 393 ሺህ ንፁሃን ዜጎች ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ሲወድቁ ብዙዎችም ለምግብና ለመድሃኒት እጥረት ተጋልጠዋል። የቆሰሉ ወታደሮችን ለመርዳት ቱርክ ሄሊኮፕተሮችን የላከች ሲሆን የጦር ኃይሉ ስለጥቃቱ የገለፀው ትናትና ነበር።
news-57333188
https://www.bbc.com/amharic/news-57333188
የእስራኤል ተቃዋሚዎች አዲስ የአንድነት መንግሥት ለማቋቋም ተስማሙ
የእስራኤል ተቃዋሚ ፓርቲዎች የቤንጃሚን ኔታንያሁን የ 12 ዓመታት ጠቅላይ ሚኒስትርነት የሚያከትም አዲስ መንግሥት ለማቋቋም ከስምምነት ደረሱ፡፡
የየሽ አቲድ ፓርቲ መሪው ያይር ላፒድ በስምንት ቡድኖች የተቋቋመ ጥምረት መመስረቱን አስታውቀዋል፡፡ ሥልጣን በዙር በሚከፋልበት በዚሁ ስምምነት መሠረት የያሚና ፓርቲው አለቃ ናፍታሊ ቤኔት በቀዳሚነት ጠቅላይ ሚንስትር ይሆናሉ። በቀጣይ ላፒድ ሥልጣኑን ይረከቧቸዋል። መንግሥት ለመመስረት ቃለ መሐላ ከመፈጸሙ በፊት የፓርላማዉ ይሁንታ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል፡፡ ላፒድ በሰጡት መግለጫ ስለስምምነቱ ለፕሬዚዳንት ሬውቨን ሪቭሊን ማሳወቃቸውን ገልጸዋል። "ይህ መንግስት ሁሉንም የእስራኤል ዜጎች፣ የመረጡትንም ሆነ ያልመረጡትን ለማገልገል እንደሚሠራ ቃል እገባለሁ" ብለዋል፡፡ "ተቃዋሚዎቻቸውን የሚያከብር ሲሆን ሁሉንም የእስራኤልን የህብረተሰብ ክፍሎች አንድ ለማድረግ እና ለማገናኘት የቻለውን ሁሉ ያደርጋል" ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በእስራኤል የመገናኛ ብዙሃን በተሰራጨ ምስል ላፒድ፣ ቤኔት እና የአረብ ኢስላሚስት ራም ፓርቲ ሊቀመንበር ማንሱር አባስ ስምምነቱን ሲፈርሙ ቢታዩም ብዙዎች የማይቻል መስሏቸው ነበር፡፡ አባስ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት "ውሳኔው ከባድ እና በርካታ ክርክሮች ነበሩት። ስምምነቶቹ ላይ መድረስ ግን አስፈላጊ ነበር፡፡ በዚህ ስምምነት ለአረብ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚጠቅም ብዙ ነገሮች አሉት" ብለዋል ፡፡ ላፒድ ለፕሬዚዳንቱ በላኩት ማስታወሻ እአአ ነሐሴ 27/2023 ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው እስከሚሾሙ ድረስ ከቤኔት ጋር በመሆን መንግስትን እመራለሁ ብለዋል፡፡ ሪቭሊን በጉዳዩ ላይ የመተማመኛ ድምጽን በተመለከተ ውሳኔ እንዲያስተላልፍ ፓርላማው በተቻለ ፍጥነት እንዲሰበሰብ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ህብረቱ በ 120 መቀመጫዎች ባሉት ክኔሴት (የእስራኤል ፓርላማ) የአብላጫውን ድጋፍ ማግኘት ካልቻለ ሃገሪቱ በሁለት ዓመታት ውስጥ ለአምስተኛ ጊዜ ምርጫ ለማካሄድ ትገደዳለች፡፡ ጥምረት የፈጠሩት ፓርቲዎች የእስራኤልን ፖለቲካ ሙሉ ገጽታ ያሳያሉ ተብሏል፡፡ ፓርቲዎቹ ኔታንያሁን ለመተካት ከማቀድ ውጭ በፖለቲካዊ ጉዳዮች ብዙም የሚያመሳስላቸው ነገር የለም፡፡ ረቡዕ ዕለት ረዥም ሰዓታትን የወሰደው ውይይት በቴሌ አቪቭ አቅራቢያ በሚገኝ አንድ ሆቴል የተካሄደ ሲሆን ዕፀ ፋርስን ህጋዊ ከማድረግ ጀምሮ በርካታ ጉዳዮች አጀንዳ ሆነው ተነስተዋል። የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን ሁሉም ሃሳቦች ተነስተው ከስምምነት አልተደረሰም ያሉ ሲሆን ይህም ጥምረቱ የመተማመኛ ድምጹን ያሸንፋል በሚለው ላይ ጥርጣሬ ጭሯል፡፡ የኔታንያሁ ሊኩድ ፓርቲ ከወራት በፊት በተደረገው ምርጫ ብዙ ወንበር ቢያገኝም ስልጣን የሚያስገኝለትን ጥምረት መመስረት አልቻለም። ኔታንያሁ የታቀደው አዲስ መንግስት "የክፍለ ዘመኑ ማጭበርበር" ሲሉ ገልጸው የእስራኤልን መንግሥት እና ህዝቡን አደጋ ላይ የሚጥል ብለውታል፡፡
news-48197545
https://www.bbc.com/amharic/news-48197545
በአማዞን ሥራ ቀጣሪና አባራሪ እየሆነ የመጣው ሮቦት
ሮቦቶች የሰዎችን ሥራ ይነጥቃሉ ተብሎ መወራት ከጀመረ ከራረመ። አሁን ተራ ወዛደር ብቻ ሳእሆን የሰው ኃእል አስተዳደር ሆኖም መግቢኣ መውጫ ሰዓትን ይቆጣጠራል፤ በሥራ ላይ ያለዎትን አፈፃፀም ይከታተላል። ይሾማል ይሸልማል፤ ካልሆነ ያባርራል።
ኮምፒውተር የቀን በቀን ሥራዎትን ሲከታተል ምን ይሰማዎታል? ይህ ጉዳይ ተግባራዊ ጉዳዩ መገናኛ ብዙኃን ጆሮ የደረሰው ደግሞ አማዞን ውስጥ ነው። ግዙፉ የአማዞን ድርጅት ውስጥ ካሰቡት በተለየ ሁኔታ ሠራተኞችን በማባረር የሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ ስራ ላይ ውሏል ይላል ዘገባው። ዘ ቨርጅ የተሰኘው የቴክኖሎጂ ዘጋቢ እንዳስነበበው አማዞን ውስጥ ኮምፒውተሮች የሰራተኞችን ውጤታማነት እየመዘኑ እስከማባረር ደርሰዋል። • ማይክሮሶፍት ጽሁፍን የሚያቀል አሰራር ፈጠረ አማዞን በዝቅተኛ ክፍያና ከባድ የስራ ጫና ምክንያት በተደጋጋሚ ከሠራተኞች ቅሬታ የቀረበበት ሲሆን አንድ ሠራተኛ ድርጅቱ የሚመለከተን እንደ "ሮቦት" ነው ሲል ምሬቱን ገልጿል። ዘ ቨርጅ እንደዘገበው ብዙ ሠራተኞች በየዓመቱ እቃዎችን በፍጥነት ማንቀሳቀስ ባለመቻላቸው ከሥራቸው ይባረራሉ። ይህ ሁኔታ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሰዎች አለቃ እየሆነ እንደመጣ ያሳያል የሚሉ የዘርፉ ባለሙያዎች አሉ። ቴክኖሎጂው የሰዎችን ውጤታማነት ተከታትሎና መዝኖ ማስጠንቀቂያ መስጠት እስከመቻል ደርሷል። በሂደቱም ሁለተኛ እድል መጠየቅ እንደሚቻል ዘ ቨርጅ በዘገባው ላይ አመልክቷል። ወደፊት ሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ ሠራተኞችን ያባርር ይሆን? በሮቦቶች እንደ ሮቦት መታየት በንግድ ሥራዎች ላይ የህግ ባለሙያ የሆኑት ስታንሲ ሚቼል "አማዞን ውስጥ የሚሠሩ ሰዎች በሮቦቶች እንደ ሮቦት ነው የሚታዩት" ይላሉ። ሠራተኞቹ እንዲያሳኩ የሚጠበቅባቸው የሥራ መጠንም ሆነ የውጤታማነት መለኪያዎቹ በውል አይታወቅም ሲሉም ያክላሉ። አማዞን ለቢቢሲ በሰጠው መግለጫ "ሠራተኞች በኮምፒውር ውሳኔ ይባረራሉ የሚባለው ወሬ ፍፁም ውሸት ነው። እንደማንኛውም ድርጅት ለሠራተኞቻችን የሥራ ውጤታማነት መመዘኛ መንገድ ያለን ሲሆን ማንንም ግን ራሳቸውን እንዲያሻሽሉ እገዛ ሳናደርግ አናባርርም። በፍጥነት የሚያድግ ድርጅት ስላለን በዘላቂ የሙያ ድጋፍ የሠራተኞቻችንን ብቃት ለማሻሻል እንተጋለን" ብሏል። ድርጅቱ ምን ያህል በኮምፒውተር ቴክኖሎጂ እንደተደገፈና ሠራተኞችን ለማባረር እየተጠቀመ እንደሆነ በግልፅ አልገለፀም። • ጄፍ ቤዞስ በ35 ቢሊዮን ዶላር ክፍያ ትዳሩን ለማፍረስ ተስማማ • አፕል ቲቪ ጀመረ አማዞን ከአንድ ሳምንት በፊት ለደንበኞቹ ዕቃዎችን ያሉበት ድረስ ለማድረስ የሚወስድበትን ጊዜ ለመቀነስ ቃል የገባ ሲሆን ለዚህ መስዋትነት የሚከፍሉት ሠራተኞቹ ይሆኑ ሮቦቶች ግልፅ ያለ ነገር የለም። በሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ መከታተልና ማባረር ሠራተኞች ላይ ጫና ይሆረው ይሆን? የወደፊቱ የሥራ ሁኔታ አማዞን ሠራተኞችን በሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ ውሳኔ ለማባረር የመጀመሪያው አይደለም፤ የመጨረሻውም አይሆንም። ታዲያ ይህ ለወደፊቱ የሥራ ሂደት ምን ያስከትላል? ድርጅቶች ሠራተኞቻቸውን ለመቆጣጠርና ውጤታማነታቸውን ለመመዘን የሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ ለዓመታት ሲጠቀሙ ቆይተዋል። ይህንም ተከትሎ ብዙ ጥያቄዎች ይነሳሉ። ሠራተኞችን በመመዘን ምን ያህል ውጤታማ ነው? ሠራተኞች ለሚሰሩበት ድርጅት ያላቸውን አስተያየት እንዴት ይቀይራል? ቴክኖሎጂው በውሳኔው የሰው ድጋፍ ያስፈልገው ይሆን? • የዓለማችን ቱጃር 2 ቢሊየን ዶላር ለድሆች ሊለግሱ ነው ዘ ቨርጅ ባወጣው ዘገባ "በአማዞን ሠራተኞች በየጊዜው በሚሻሻሉ የሥራ መስፈርት መለኪያዎች ይመዘናሉ። አንድ የውጤታማነት መመዘኛ ወጥቶ 75 በመቶ የሚሆኑት ሠራተኞች ግቡን ከመቱ በኋላ መመዘኛው ይሻሻላል" ይላል። ይህንም ተከትሎ የተሻሻለውን የሥራ መመዘኛ ማሟላት ያልቻሉ ሠራተኞች ሊባረሩ ይችላሉ። ስታንሲ "ሥራህን ለማትረፍ ሁሌም ሩጫ ነው። አንዴ በጣም ውጤታማው ሠራተኛ ልትሆን ትችላለህ ግን እሱ ምንም ፋእዳ የለውም" ይላል። የሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ ሰራተኖች ላይና ድርጅቶች ላይ ከፍተኛ ጥያቄ እያስነሳ ነው ሠራተኞች ላይ ምን ጫና ሊኖረው ይችላል? ዴቪድ ዲቪዛ ድርጅቶች ሠራተኞችን እንደ መቅጠርና ማባረር የመሳሰሉ መሠረታዊ የሃላፊነት ቦታዎችን በሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂዎች ከመተካታቸው በፊት በደንብ ጥናት እንዲያደርጉ ያሳስባል። "አንዳንድ ሥራዎች በቴክኖሎጂ መሠራት መቻላቸው ብቻ እንዲቀየሩ አያደርጋቸውም። በቴክኖሎጂ ስለተሰሩም የተሻለ ውጤታማ ናቸው ለማለት ያስቸግራል። ሠራተኞች ሊከበሩ ይገባል፤ የሚገባቸውንም ክብር በኮድ በተደገፈ ቴክኖሎጂ ለመስጠት ያስቸግራል" ይላል። እ.ኤ.አ 2018 ዲአሎ ከስራው በሃላፊው ሳይሆን በኮምፒውተር ትዕዛዝ ነበር የተባረረው። ለቢቢሲ እንደተናገረው ሃላፊው ስለመባረሩ ምንም ማድረግ አልቻለም ነበር። ዲአሎ የእርሱ አጋጣሚ ለሌሎች ተቋማት ምሳሌ እንዲሆን ተስፋ ያደርጋል አለበለዚያ ግን ሠራተኞች ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራል ይላል።
44435409
https://www.bbc.com/amharic/44435409
ለፌስቡክ ሱሰኞች የተገነባው አስፋልት ተመረቀ
ለዐይነ ሥውራን ምቹ አስፋልት ተሠርቶ ያውቃል። ለብስክሌት ጋላቢዎችም ጎዳና ተዘርግቶ ያውቃል። በስልክ ሱስ ለናወዙ ተብሎ ግን አስፋልት ሲሠራ ይህ የመጀመርያው ነው ተብሏል።
የብስክሌት ጋላቢዎችና የእግረኞች መንገድ ብቻ በቂ አይደለም፤ ለፌስ ቡክ ሱሰኞችም መንገድ ተገንብቷል በብዙ ዘመነኛ ከተሞች ወጣቶች ሞባይሎቻቸው ላይ አቀርቅረው ስለሚራመዱ ከስልክ እንጨት ጋር ይላተማሉ። ለመኪና አደጋም የተጋለጡ አሉ። ሰሜን ቻይና የምትገኝ አንዲት ከተማ ለእነዚህ ሱሰኞቿ መላ ዘይዳለች። ለእነርሱ ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ ጎዳናን አስመረቅላች። ያንታ ጎዳና የሚባለውና ዢያን በምትባለው በዚች ትንሽ ከተማ የሚገኘው ይህ ጥርጊያ ዓለምን ለረሱና በሞባይል ሱስ ለናወዙ ብቻ የሚሆን ነው ተብሏል። አስፋልቱ ቀይ፣ አረንጓዴና ሰማያዊ ቀለም ተቀብቷል። ወርዱ 80 ሴንቲ ሜትር ቁመቱ ደግሞ 100 ሜትር እንደሚሰፋም ተመልክቷል። ከተራ የእግረኛ መንገድ የሚለየው የተንቀሳቃሽ ስልክ ምልክትም በአስፋልቱ ላይ ታትሞበታል። የአካባቢው ተወላጆች በዚህ ጎዳና መሠራት እጅግ ተደስተዋል ተብሏል። በታዋቂው የቻይና ወይቦ ብሎግ ላይ አስተያየታቸውን ከሰጡ ዜጎች መሐል የአዲሱ ትውልድ ከስልክ ጋር ያለው ቁርኝት በድሮ የቻይና ዳይናስቲ ለኦፒየም ከነበረው ሱስ ጋር የሚመሳሰል ነው ይላል። ሌላ አስተየየት ሰጪ በበኩሉ እነዚህ ሱሰኞች አሁንም ቢሆን እርስበርስ መላተማቸው አይቀርም ሲል የአዲሱ አስፋልት መገንባት ከመላተም እንደማያድናቸው ጠቁሟል።
news-57056787
https://www.bbc.com/amharic/news-57056787
በልደት ዝግጅት ላይ አልተጠራሁም ያለው ፍቅረኛውን ጨምሮ 6 ሰዎችን ገደለ
በአሜሪካዋ ኮሎራዶ ግዛት ፍቅረኛውን ጨምሮ ስድስት ሰዎችን የገደለው ግለሰብ ድርጊቱን የፈጸመው በልደት ዝግጅቱ ላይ አልተጠራሁም በሚል ምክንያት መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ።
በጥቃቱ ዘመዶቻቸውን ያጡ የቤተሰብ አባላት ባሳለፍነው እሁድ የ28 ዓመት ወጣቱ ቲዎዶር ማኪአስ በልደት ዝግጅቱ ላይ ሲታደሙ የነበሩ ስድስት ሰዎችን ተኩሶ ከገደለ በኋላ እራሱን አጥፍቷል። ሟቾቹ የ28 ዓመት ፍቅረኛው ሳንድራ ኢብራ-ፔሬዝ እና ዘመዶቿ ናቸው ብሏል ፖሊስ። ሰኞ ዕለት የኮሮሎራዶ ስፕሪንግ ፖሊስ "ግለሰቡ መጀመሪያ እያሽከረከረ ወደ ቦታው መጣ። ራሱን ከማጥፋቱ በፊት በልደት ዝግጅቱ ላይ እየታደሙ የነበሩ ሰዎች ላይ በዘፈቀደ ተኩስ ከፈተ" ሲል ገልጾ ነበር። ፖሊስ እንደሚለው ጥቃቱን ያደረሰው ወጣት ከአንድ ሳምንት በፊት ከፍቅረኛው ቤተሰብ አባላት ጋር አለመግባባት ተፈጥሮ ነበር። "ቅናተኛ ፍቅረኛ ነበር" የተባለው ወጣት፤ በልደት ዝግጅቱ ላይ ባለመጋበዙ ተኩስ በመክፈት ምላሽ ሰጥቷል ሲሉ የአከባቢው የፖሊስ አዛዥ ቪንስ ኒስኪ ተናግረዋል። ወጣቱ ተኩሶ ከገደላት ፍቅረኛው ጋር ለአንድ ዓመት ያክል በፍቅር መቆየታቸውን እና ከዚህ ቀደም የወንጀል ሪኮርድ እንደሌለበት ፖሊስ ጨምሮ አስታውቋል። የጥቃቱ ሰለባዎች በሙሉ አዋቂዎች ቢሆኑም በድግሱ ላይ ግን ህፃናትም ታድመው ነበር። "በድግሱ ላይ ህጻናት ታድመው የነበረ ቢሆንም ከመሃላቸው ማንም አልተጎዳም" ብሏል ፖሊስ። ጥቃቱ ሲደርስ በስፍራው የነበሩ የ2፣ 5 እና የ11 ዓመት እድሜ ያላቸው ልጆች ምንም አይነት አካላዊ ጉዳት አልደረሰባቸውም። የሟቾች ቤተሰብ የሆነችው ኑቢያ ማርኬዝ ለኮሎራዲ ስፕሪንግስ ጋዜጣ ስትናገር ከሟቾቹ መካከል ሶስቱ በተመሳሳይ ሳምንት ልደታቸውን እንደሆነና ሁሌም አብረው እንደሚያከብሩ ገልጻለች። ፖሊስ እንደሚለው ጥቃት አድራሹ የተጠቀመው ሽጉጥ በሕጋዊ መንገድ የተመዘገበ አይደለም። የኮሎራዶ አስተዳዳሪ ዕሁድ ዕለት ባወጡት መግለጫ ላይ ''በጣም የሚያሳዝን ጥቃት ነው። ሁላችንም የእናቶችን ቀን ለማክበር ደፋ ቀና በምንልበት ወቅት ጥቃቱ መፈጸሙ አሳዝኖኛል'' ብለዋል።
news-47702925
https://www.bbc.com/amharic/news-47702925
የአማራ ክልል ተፈናቃዮች ስለ ንግድ ባንክ እርዳታ ምን ይላሉ?
በአማራ ክልል የሚገኙ ከ90 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ነው።
በዚሁ መሰረት ተቋማትና ግለሰቦች እጃቸውን እየዘረጉ ነው። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም በአገሪቱ የተለያዩ ክልሎች በተለያየ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ ይሆን ዘንድ ገንዘብ ለግሷል። ንግድ ባንክ ተፈናቃዮችን ለመደገፍ የመደበው መቶ ሚሊዮን ብር ሲሆን ከዚህ ውስጥ ለአማራ ክልል ተፈናቃዮች የመደበው 4.789 ሚሊዮን ብር ሲሆን የክልሉ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ይህን እርዳታ አልቀበልም ማለቱ ብዙ አስብሏል፤ ብዙዎችንም አነጋግሯል። • የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ተፈናቃዮች ለችግር ተዳረግን አሉ ለተፈናቃዮች የሚውል የእርዳታና የድጋፍ ያለህ እየተባለ ባለበት በዚህ ወቅት እንዴት እርዳታ አያስፈልገኝም ይባላል? ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው እርዳታውን እንደማይቀበል ማሳወቁን ተከትሎ ብዙዎች ያነሱት ጥያቄ ነው። የክልሉ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አገኘሁ ተሻገር "ምክንያታችን ለንግድ ባንክ ካለን ክብር የመነጨ ምላሽ ነው የሰጠነው" ይላሉ። ተፈናቃዮችን ለማቋቋም ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የድጋፍ ጥያቄ አቅርበን ነበር የሚሉት ሰብሳቢው ንግድ ባንክ በመላ አገሪቱ ያሉ ተፈናቃዮችን ለመደገፍ እንደሚፈልግ እንደገለፀላቸው ያነሳሉ። እርሳቸው እንደሚሉት ከተለያዩ ባንኮች ከ5 ሚሊዮን ብር ጀምሮ የተለያዩ ድጋፎችን ተቀብለዋል። ይሁን እንጂ ከንግድ ባንክ ያገኙት የድጋፍ ክፍፍል የችግር መጠን ያላገናዘበና ከሚፈለገው በታች ሆኖ ስላገኙት ድጋፉን ላለመቀበል መወሰናቸውን ይናገራሉ። "የድጋፍ አሰጣጡ ቀመር ስላልገባን ይህንን ድጋፍ ተቀብለን የንግድ ባንክን ክብር ከምንነካ፣ ይህ ዝቅተኛ ድጋፍ ለአማራ ህዝብ የሚመጥን ባለመሆኑ አለመቀበል ይሻላል" በሚል ከውሳኔው ላይ እንደደረሱ ለቢቢሲ ገልፀዋል። • ጌዲዮ በዐቢይ ጉብኝት ማግስት ንግድ ባንክ እርዳታውን የበጀተበትን ቀመር አለማወቅ ብቻም ሳይሆን ቀመር መስራትም አያስፈልገው ነበር ሲሉ ይከራከራሉ አቶ አገኘሁ። እሳቸው እንደሚሉት ንግድ ባንክ ማድረግ የነበረበት የመደበውን የእርዳታ ገንዘብ ለዚሁ ዓላማ በመንግሥት ለተቋቋመው ለአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን በመስጠት ኮሚሽኑ በተፈናቃይ ልክና በጉዳት መጠን ለክልሎች እንዲያከፋፍል መተው ነበር። ያነጋገርናቸው በአማራ ክልል ጊዜያዊ መጠለያ የሚገኙ አንዳንድ ተፈናቃዮች በበኩላቸው ያገኙትን ድጋፍ ይዘው ወደ ቀያቸው የመመለስ ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው ከመሆኑ አንፃር ይህን የንግድ ባንክ ድጋፍ አልቀበልም ማለት ትክክል እንዳልሆነ ገልፀውልናል። "ይህ ነገር ስህተት ነው፤ ምክንያቱም ብዙ ሰዎች አደጋ ላይ ነው ያሉት። ለምሳሌ እንደ ግራር አውራጃ ብዙ ሰዎች ቤታቸው ተቃጥሏል፣ ንብረታቸው ወድሟል፣ አምስትም አስር ብርም ቢደርሳቸው ለእነሱ ጥቅም ነው ብዬ ነው የማስበው" ስትል ሳሮን ባይሳ የተባለች ተፈናቃይ ለቢቢሲ ተናግራለች። • ቻይና 300 የኤርባስ አውሮፕላኖችን ልትገዛ ነው ይህ ውሳኔ ያለምክንያት እንዳልሆነ የሚገምቱ ተፈናቃዮችም ያሉ ሲሆን የዚህ አይነት ስሜት ካላቸው ሌላኛው ተፈናቃይ አንዱዓለም ነበይ "መቼም ከውስጡ የሆነ ነገር ይኖረዋል እንጂ ህብረተሰቡ በችግር ላይ ነው ያለው፤ እርዳታው ተፈላጊ ነው" ብለውናል። በክልሉ ነፍሰጡር እናቶች፣ ህፃናትና አዛውንት ተፈናቃዮች ከባድ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ ቢቢሲ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በርካታ ተፈናቃዮች በሚገኙበት በአይምባ መጠለያ ተገኝቶ ዘገባ ሰርቶ ነበር። • የአሜሪካው ኩባንያ በኬንያ ካናቢስ ለማብቀል ፍቃድ አገኘ ተባለ በክልሉ ተፈናቃዮች ያሉበትን ፈታኝ ሁኔታ በመገንዘብ እርዳታውን አልቀበልም ያለው የድጋፍ አሰባሳቢው ኮሚቴ ላይ 'ኩራት ወይስ ዳቦ ?' የሚል ጠንካራ ትችት የሰነዘሩም እንዳሉ ያነሳንላቸው የኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ አገኘሁም የዚህ አይነቱ ሃሳብ "የፅንፈኞችና ለአማራ ክልል ህዝብ ንቀት ያላቸው ሰዎች ሃሳብ ነው" በማለት ጠንከር ያለ ምላሽ ይሰጣሉ። "የአማራ ህዝብ አይኮራም፤ ኮርቶም አያውቅም። ከኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋር በእኩልነት የሚያምን ህዝብ ነው" ይላሉ። የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴውን መግለጫ ተከትሎ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሰጠው ምላሽ እንደሌለ አቶ አገኘሁ ጨምረው ተናግረዋል።
news-49786524
https://www.bbc.com/amharic/news-49786524
ከ34 ዓመት በፊት በአውሮፕላን ጠለፋ የተጠረጠረው በቁጥጥር ስር ዋለ
እ.አ.አ. 1985 በአሜሪካ አየር መንገድ ንብረት በሆነ አውሮፕላን ላይ በተፈጸመው ጠለፋ እጁ አለበት የተባለው የ65 ዓመት ሊባኖሳዊ ግሪክ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።
ስሙ ያልተጠቀሰው ተጠርጣሪ ባሳለፍነው ሐሙስ ነበር ሚይኮኖስ በተባለ ደሴት በቁጥጥር ሥር የዋለው። ተጠርጣሪው በጉዞ ላይ በነበረበት ወቅት ፓስፖርቱ ሲታይ ጀርመን ውስጥ ተፈላጊ እንደሆነ ተደርሶበታል። • ሌሎችን ለመርዳት የሚተጉት የሁለቱ ሴት ኢትዮጵያዊያን ልምድ • ኢትዮጵያ ውስጥ የተያዙት የአል ሸባብና የአይ ኤስ አባላት ማንነት ይፋ ሆነ 'ቲደብልዩኤ' የበረራ ቁጥር 487 የነበረው አውሮፕላን መሳሪያ ታጥቀው በነበሩ ሂዝቦላህ የተባለው ኢስላማዊ ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር ሆኖ ነበር። ምንም እንኳን ሂዝቦላህ ድርጊቱን አለመፈጸሙን ቢክድም። ተጠርጣሪው እ.አ.አ. በ1987 ፈጽሞታል በተባለው የጠለፋና ሰዎችን በማገት ወንጀል ነበር በጀርመን ባለስልጣናት ይፈለግ የነበረው። በአሁኑ ሰዓት ተጠርጣሪው ከፍተኛ ጥበቃ በሚደረግለት የግሪክ ማረሚያ ቤት ውስጥ ይገኛል። ወንጀሉን ፈጽሟል ከተባለ ከሁለት ዓመታት በኋላ ጀርምን ውስጥ በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረ ሲሆን ቤሩት ውስጥ ታግተው የነበሩ ሁለት ጀርመናውያንን ለማስቀቅ ወደ ሊባኖስ በነጻ ተለቆ ነበር። እ.አ.አ. በ1985 የትራንስ ወርልድ አየር መንገድ ንብረት የሆነው አውሮፕላን ከካይሮ ተነስቶ በአቴንስ፣ ሮም፣ ቦስተን እና ሎስ አንጀለስ አድርጎ ወደ ሳንዲዬጎ በመብረር ላይ ሳለ ነበር ከአቴንስ ሲነሳ ጠላፊዎቹ አስገድደው ቤሩት እንዲያርፍ ያደረጉት። • ግብፃውያን ፕሬዝዳንት አል-ሲሲን በመቃወም ሰልፍ ወጡ • ላሊበላ፡ የመፍትሔ ያለህ የሚለው ብሔራዊ ቅርስ 153 የአውሮፕላኑ ተሳፋሪዎችና ሰራተኞች ለ17 ቀናት በቆየው አጋች ታጋች ድራማ በአውሮፕላኑ ውስጥ ቆይተዋል። ጠላፊዎቹም በእስራኤል ተይዘው የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ የሊባኖች ዜጎች ይፈቱልን በማለት ታጋቾቹን በማሰርና በመደብደብ በኋላ እንደሚገድሏቸው ሲያስፈራሩ ነበር። በእስራኤል የሚገኙት ታሳሪዎች ሳይለቀቁ ሲቀር በአውሮፕላኑ ውስጥ ተሳፋሪ የነበረ አንድ የ23 ዓመት አሜሪካዊ የውሃ ጠላቂ ወታደር ተተኩሶበት የተገደለ ሲሆን ሬሳውም ወደ ውጪ ተወርውሮ ነበር። በመጨረሻ ግን ጠላፊዎቹ ታጋቾቹን ለቀዋል። እንደ ኤፍቢአይ ከሆነ አውሮፕላኑን በመጥለፍ ወንጀል ውስጥ ቢያንስ አራት ሰዎች ቀጥተኛ ተሳትፎ ነበራቸው። እአአ 1986 ላይ የተለቀቀው እና 'ዘ ዴልታ ፎርስ' (The Delta Force) የሚል ስያሜ የተሰጠው ፊልም ይህን የአውሮፕላን ጠለፋ ላይ መሰረት ተድርጎ የተሰራ ነው።
news-42114523
https://www.bbc.com/amharic/news-42114523
ካለሁበት 11፡ እንግሊዝ ሃገር ብቸኝነት ብዙ ሰዎችን ለአእምሮ ሕመም ያጋልጣል
አብዲ ቦሩ እባላለሁ። የሁለት ወንድ ልጆችና የአንድ ሴት ልጅ አባት ነኝ። አሁን ስልጣን ላይ ባለው መንግሥት በደረሰብኝ በደልና ተደጋጋሚ ውንጀላ ከሃገሬ ወጣሁ።
ሲደርስብኝ የነበረው በደል በሃገሬ ላይ በሠላም ሰርቶ የመኖር መብቴን ስለነፈገኝና እየባሰም በመምጣቱ መጨረሻ ላይ ሁሉን ትቼ የስደት ኑሮ እንድመርጥ አደረገኝ። ስለዚህ እ.አ.አ በ2006 መጀመሪያ ላይ ሞያሌ ድንበር በማቋረጥ ወደ ኬንያ በስደት ገባሁ። ለ10 ዓመት ያህል በካኩማ የስደተኞች ካምፕ ስኖር ከቆየሁ በኋላ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽን እና በእንግሊዝ መንግስት በኩል እድል አግኝቼ በ2015 ነሐሴ ደቡባዊ ዮርክሻየር በምትገኘዋ በሼፊልድ ከተማ ባለ ሙሉ መብት ነዋሪ ሆንኩ። እንግሊዝ ከሃገራችን የሚለያት ትልቁ ነገር ቢኖር የሚታየው እድገት፣ ብልፅግና እና ስልጣኔ ሳይሆን ለሰው ልጅ መብት ያላቸው የላቀ አክብሮት ነው። ሁሉም ሰው ሃሳቡን በነፃነት የመግለፅ መብቱ የተጠበቀ መሆኑና በማንኛውም ጉዳይ ዙሪያ ያለአድልኦ እኩል መብት መኖሩ ከሃገራችን በትልቁ እንድትለይ ያደርጋታል። ሁልጊዜ ሀገሬን እንድናፍቅ ከሚያደርጉኝ ነገሮች አንዱና ዋነኛው የለመድነው ማህበራዊ ኑሮ ነው። እዚህ አገር ማህበራዊ ኑሮ የሚባል ነገር የለም፡። ከቤተሰብ፣ ከዘመድ እንዲሁም ከጎረቤት ጋር መኖር ወይንም ኑሮን መጋራት የለም። የምኖረው አፓርታማ ላይ ነው። ፎቅ ላይ ከቤታችን በላይ፣ በታች እና በጎን ሰዎች ይኖራሉ። ሆኖም ግን ከቤታችን ቀጥሎ ያሉትን እንኳ ማን እንደሆኑ አናውቅም፤ እነሱም እንደዚሁ። በችግር ጊዜም ሆነ በደስታ መጠያየቅ የለም። ሁሉም የየራሱን ኑሮ ይኖራል። ይህንን ማህበራዊ ኑሮ ማጣት ነው እንግዲህ ሃገሬን እንድናፍቅ የሚያደርገኝ። ከሼፊልድ ከተማ ዊንተር ጋርደን የሚባለውን ስፍራ እወደዋለሁ። ይህ የመዝናኛ ቦታ ሁሉን ነገር ያሟላ ነው። በክረምት ወቅት አየሩ በጣም ቀዝቀቃዛ ቢሆንም እዚያ ውስጥ ግን እንዳይቀዘቅዝ ሆኖ የተሰራ ነው። በጣም በሚሞቅበት የበጋ ወቅትም አየሩ ለሰዎች ተስማሚ በሚሆን መልኩ የተዘጋጀ ስፍራ ነው። ይህ ብቻ አይደለም የተለያዩ ምስሎችም ይገኙበታል። ከቤተሰብ ጋር በመሆን የሚዝናኑበትና ምግብ የሚበሉበት ስፍራ አለው። ወደላይ የሚወረወር የውሃ ፏፏቴዎችም አሉት። በተለይ ልጆች የሚሽከረከሩበት የውሃ መዝናኛዎችም አሉት። እነኝህና ሌሎችም ብዙ የመጫወቻና መዝናኛዎች ስላሉት ልጆቼ ይህንን ስፍራ በጣም ይወዱታል። ትምህርት ቤት ሲዘጋና በእረፍት ጊዜያቸው ልጆቻችንን እዚህ እያመጣን እነሱንም ራሳችንንም እናዝናናለን። ሰብዓዊ መብቱ ተነፍጎ ከሃገሩ በስደት እንደወጣ ሰው ሁሉ እኔም እዚህ አገር በመድረሴ በጣም የሚያስደስተኝ ነገር ቢኖር ለደህንነቴ አለመስጋቴ ነው። በተጨማሪም ልጆቼ ጥራቱን የጠበቀ ከእድሜያቸውና ከችሎታቸው ጋር የሚመጠጥን ትምህርት ማግኘት መቻላቸው በጣም ያስደስተኛል። ወደዚህ ሃገር ከመምጣቴ በፊት ለደህንነቴ በጣም እሰጋ ነበር። ምን ይደርስብኝ ይሆን እያልኩም አስብና እጨነቅ ነበር። በወቅቱ በህይወት ኖሬ ቤተሰቦቼን ተመልሼ አይ ይሆን የሚለው ትልቁ ጭንቀቴ ነበር። ስለዚህ ከዚህ ሃገር ተጠቀምኩ የምለው ደህንነቴ ተረጋግጦ የአእምሮ እረፍት የማግኘቴ ጉዳይ ነው። አንዳንዴ ከከተማ ውጭ ገጠሩን አቋርጬ ወደ ሌላ ቦታ ስሄድ የማየው ማሳ፣ ስንዴው፣ ገብሱ፣ ከብቶቹ፣ በጎቹ፣ ፈረሶቹ፣ ወንዙ የአባቴ ማሳ፣ ከብቶቹን፣ እንዲሁም የሃገሬን መልከአምድርን እያስታወሰኝ ናፍቆት ይቀሰቅቀስብኛል። አንድ የተለየ ሃይል ወይም ስልጣን ቢኖረኝ በዚች የምኖርባት ከተማም ሆነ በሌሎች የእንግሊዝ ከተሞች ውስጥ መለወጥ የምፈልገው ነገር መንገዱን ነው። የዚህ ሃገር መንገድ ጥበት በጣም አሳሳቢ ነው። እዚህ ትንሹም ሆነ ትልቁ በመኪና ነው የሚንቀሳቀሰው። እግረኛ የሚባል ነገር የለም ማለት ይቻላል። በዚህ የተነሳም ወደስራ ለመሄድም ሆነ ከስራ ለመመለስ ረዥም ሰአት ይወስዳል። ስለዚህ የመንገድ ጥበት መለወጥ ብችል ደስ ይለኛል። በዚህ ሃገር አስቸጋሪ ነገር ገጥሞኛል የምለው ብቸኝነት ነው። እንደሃገራችን አብሮ መጫወት፣ መነጋገር ፣አብሮ ማሳለፍ በአጠቃላይ ማህበራዊ ኑሮ የለም። ብቻ መብላት፣ ብቻ መኖር፣ በሃዘንም ሆነ በደስታ ጊዜ ተገናኝቶ አለመነጋገር፣ በተለይም እንደኛ ከሌሎች ሃገሮች ለሚመጡና ማህበራዊ ኑሮን ለለመዱ ከባድ ነው፤ ብቻቸውን ለመጡ ሰዎች ደግሞ ሁኔታው ይብሳል። ብዙዎች ለአእምሮ በሽታ ተዳርገው ጎዳና ላይ ወዲህና ወዲያ ሲሉ ይታያሉ። ልጆችም በሱስ ተጠምደው ይበላሻሉ፤ አልባሌ ቦታም ይውላሉ። እኔ እንኳ ፈጣሪ ይመስገን ከቤተሰቦቼ ጋር ስለመጣሁ ለዚህ አይነት ችግር አልተዳረኩም። ሆኖም ግን ማህበራዊ ኑሮ አሁንም ይናፍቀኛል። የዚህ ሃገር ምግብ አያስደስተኝም። ሁሉ ነገር ቢኖራቸውም ምንም የሚጥመኝ ነገር የለም። የምግብ አዘገጃጀትና አቀራረቡ አይጥመኝም። ብዙ ጊዜ የነሱ ምግብ ፋስት ፉድ ነው፤ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንኳ የሚመገቡበት ጊዜ የላቸውም። ወደ ስራ ቦታ፤ ወደ ቤት ሲሄዱ ወይም መኪናቸው ውስጥ ገዝተው ይመገባሉ። ልጆቼ ግን ፒዛ፣ ዶሮና ድንች ጥብስ መብላት ይወዳሉ። እኔና ባለቤቴ ደግሞ ከሌሎች የአፍሪካ ሃገሮችና ከአረብ ሃገር በመጡ ሰዎች የሚሰራውን በተለይም "ዙርቢያ" የተባለውን መብላት እንወዳለን። ከዚህ በቅፅበት ወደ ሃገሬ የሚወስደኝ ነገር ቢኖር ደስ ይለኛል፤ በተለይ ደግሞ የትውልድ መንደሬ አጋርፋ ራሴን ባገኝ በጣም ደስ ይለኛል። ለጫሊ ነጋሳ እንደነገረው የ'ካለሁበት' ቀጣይ ክፍሎችን ለማግኘት ፦ ካለሁበት 12፡ ''የአውደ ዓመት ግርግር ሁልጊዜ ይናፍቀኛል'' ካለሁበት 13፡ ''ለእኔ ስኬት ማለት ገንዘብ ማግኘት ብቻ አይደለም''
47249337
https://www.bbc.com/amharic/47249337
ታዋቂ ኢትዮጵያዊያን አርቲስቶች ለመዋብ ምን ያህል ይከፍላሉ?
ኢትዮጵያ ውስጥ ታዋቂ አርቲስቶችን በትልልቅ መድረኮች እና ፕሮግራሞች ከማየት ባለፈ፤ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው አማካይነት የአኗኗር ዘይቤያቸዉን በተለይም አለባበሳቸዉንና መዋቢያ መንገዳቸዉን መመልከት ተለምዷል።
ፍቅር መዋቢያና ዮሐንስ ሲስተርስ ዲዛይን አርቲስቶች ወደ ፋሽን ኢንዱስትሪዉ እንዲያማትሩ ከሚያደርጓቸው ምክንያቶች መካከል የፊልም ሠሪዎች የሽልማት ፕሮግራሞች፣ ቃለ መጠይቆች፣ የአልበም ወይም የፊልም ምርቃቶችን እና የማህበራዊ ሚዲያ የፎቶ ስብስቦች ይጠቀሳሉ። የፍቅር ዲዛይን ድምጻዊት ፀደንያ ገብረማርቆስ ለአለባበስ እና አቀራረብ የሚሰጠውን ትኩረት ስትገልፅ፣ "ከማቀርበዉ ሙዚቃ ባሻገር ለመታየትም መዘጋጀት አለብኝ፤ ታዋቂ ስትሆኚ ደግሞ ሰዎች አንቺን ለማየት ይጓጓሉ፤ ዘንጠሽ እንድትወጪ ይጠብቃሉ" ትላለች። • እውነተኛ ውበትን ፍለጋ • በፍቅረኞች ቀን የፍቅር ስጦታ ለሴት ተማሪዎች ብዙዎቹ አርቲስቶች በትልልቅ ፕሮግራሞች ላይ ለልብሶቻቸዉ አይከፍሉም። ለምን? ቢከፍሉ ኖሮ ምን ያህል ገንዘብ ያወጡ ነበር? "የፋሽን ዘርፉ ገና ታዳጊ ስለሆነ አርቲስቶችን የምንጠቀማቸዉ እንደ ማስተዋወቂያ ነዉ። እነሱ አንድን ልብስ ከለበሱት በኋላ ብዙ ሰዎች ልብሱን ያዛሉ" በማለት ዲዛይነር ዮርዳኖስ አበራ ትናገራለች። እንቁ ዲዛይን ዲዛይነር ሊሊ (የዮሃንስ ሲስተርስ ዲዛይን መስራች) እንደምትናገረው፤ ለተለያዩ ፕሮግራሞች የሚዘጋጁ የሴት አርቲስቶች አልባሳት በትንሹ ከ20,000 ብር ጀምሮ ይቀርባሉ። ከፍ እያለ ሲመጣ ከ40,000 እስከ 60,000 ብርም ሊደርስ ይችላል። የወንዶች አልባሳት ዋጋ ከሴቶች ጋር ሲወዳደር "ሰማይ እና መሬት" ነዉ በማለት አክላም ታስረዳለች። ብዙ ጊዜ ባይሆንም ለሠርግ የወንድ ልብስ ለወራት ዲዛይን ተደርጎ በጣም ቢበዛ ከ15,000 እስከ 18,000 ብር ያወጣል። • የነጻነት ቅርጫት: ሊፕስቲክ ዲዛይነር እንቁጣጣሽ ክብረት (የእንቁ ዲዛይን መስራች) "እኔ ዲዛይን ያደረኳቸውን ልብሶች አርቲስቶችን ማልበስ አንዱ ስኬታማ የሆነ የማስታቂያ መንገዴ ነው" ትላለች። የፋሽን ዘርፉ ቅድሚያ የሚሰጠው ለሴቶች ነው በሚል ቅሬታ የሚያቀርቡ ወንዶች እንዳሉም ትገልጻለች። ዮርዲ ዲዛይን የማርዜል ሜካፕ ባለቤት የማሪያምወርቅ አለማየሁ ስለ ፊት መዋቢያ ዋጋ ስትገልጽ፣ "ዛሬ ዛሬ የፊት መዋቢያ በፋሽን ዘርፉ መታወቅ ጀምሯል። ብዙዎቹ ታዋቂ ግለሰቦች ዝግጅት ሲኖራቸው ለመዋብ ይመጣሉ" ትላለች። ብዙዎቹ አርቲስቶች ሲዋቡ ተፈጥሯዊ ዉበትን የሚያጎላ የፊት መዋቢያ እንደሚጠይቁ የምትናገረው የማርያምወርቅ "ብዙ ኢትዮጵያዊያን የተጋነነ የፊት መዋቢያ አይወዱም" በማለት ትገልፃለች። • የኬንያ ዳኞችን አለባበስ የቀየረች ኢትዮጵያዊት • “ከወጡት ስራዎቼ ይልቅ ገና የሚወጡት ናቸው ትልቅ ቦታ ያላቸው” አለማየሁ ገላጋይ ፊት ማስዋብ በሴቶች ዘንድ የተለመደ ሲሆን፤ ወንዶች አሁን አሁን ለሰርግ ፊታቸዉን መሰራት እየጀመሩ ነው። የፊት መዋብያ ከፀጉር፣ ከጥፍር እና ሌሎች መዋቢያዎች አንፃር ይወደዳል። በየማርያምወርቅ የተሠራ ቀላል የፊት መዋቢያ ከ5,000 ብር ጀምሮ የሚቀርብ ሲሆን፤ ዋጋው ተጠቃሚዎች እንደሚፈልጉበት ወቅት ይለያያል። ለምሳሌ በሰርግ ወቅት ሲሰራ ዋጋው ከፍ ይላል። በሰርግ ጊዜ እንደሚጠየቀው የጥቅል አይነት ለሙሽራ የአንድ ጊዜ የፊት መዋቢያ ከ7,000 ብር ጀምሮ እስከ 15,000 ብር ድረስ ይከፈላል። የማርያምወርቅ እንደምትለው ብዙዎች በሰርግ ወቅት ጥቅል አገልግሎት ይጠቀማሉ። ጥቅሉም ከሰርግ በፊት፣ በሰርግ ቀን እና መልስን ያጠቃልላል። የዚህ አይነት የመዋብያ አገልግሎት ከ25 ,000 ብር እስከ 30,000 ብር አካባቢ ያስከፍላል። በየማርያምወርቅ የተሠራ ብዙዎች ፊታቸውን ሲዋቡ ፀጉራቸውንም በዚያው ይሰራሉ። ሰው ሰራሽ ፀጉር (ሂውማን ሄር) እንደጥራቱ ከ 7,000 ብር እስከ 20,000 ብር ድረስ ይሸጣል። የሰው ሰራሽ ፀጉር ከሚመረትባቸው ሀገራት እውቅ የሆኑት ብራዚል እና ጣልያንን ትጠቅሳለች። • "ቤቶቹ በማንኛውም ሰዓት ሊደረመሱ ይችላሉ" የማርያምወርቅ "የቆዳ መዋዋቢያ አጠቃቀም ኢትዮጵያ ዉስጥ እንደ ፋሽን ቢመጣ ደስ ይለኛል። ብዙ ሰው ተፈጥሯዊ የመሰለ የፊት መዋቢያ ይፈልጋል። እንክብካቤ ያልተለየው ቆዳ ላይ የፊት መዋቢያ ሲጨመር ተፈጥሯዊ ይመስላል" በማለት እያደገ ያለዉን የፊት መዋብያ መጠቀም ልምድ ከቆዳ እንክብካቤ ጋር ታያይዘዋለች።
news-41857306
https://www.bbc.com/amharic/news-41857306
የሴቶች እኩልነት በመጪዎቹ 100 ዓመታትም አይረጋገጥም- የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም
በሴቶችና በወንዶች መካከል ያለውን የጾታ ልዩነት ለማጥበብ መቶ ዓመታት እንደሚፈጅ የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም አስታውቋል።
የፎረሙ መረጃ ከአውሮፓውያኑ 2006 ጀምሮ በየዓመቱ እየተባባሰ የመጣውን የጾታ ልዩነት የሚያሳይ ነው። ሪፖርቱ 144 ሃገራትን በኢኮኖሚ እድል፣ በትምህርት፣ በፖለቲካ ተሳትፎና በጤና ደረጃ አውጥቶላቸዋል። ሴቶች ወንዶች ከሚያገኙት ዕድልና ውጤት 68%ውን ብቻ እንደሚያገኙ ይገልጻል፤ ባለፈው ዓመት ግን 68.3% ነበር። እናም ባለፈው ዓመት ክፍቱን ለመሙላት ያስቀመጠውን የ83 ዓመታት ጊዜ ከፍ በማድረግ 100 ዓመታት አድርሶታል። በእርግጥ በጤናና ትምህርት ክፍተቱ እየጠበበ ቢሆንም በኢኮኖሚና በፖለቲካ ተሳትፎ ግን በጣም ከፍተኛ ክፍተት እንዳለ ጥናቱ አረጋግጧል። እናም ሴቶች በሥራ ቦታቸው ከወንዶች እኩል እንዲወከሉ ተጨማሪ 217 ዓመታትን መጠበቅ ግድ እንደሚል ነው የገለጸው። የኖርዲክ ሃገራት በጾታ እኩልነት የተሻለ ደረጃ ላይ ሲገኙ በአይስላንድ ያለው ክፍተት የ12% ብቻ ነው። ኖርዌይ፣ ፊንላንድና ስዊዲንም ከመጀመሪያዎቹ 5 ሃገራት ተርታ ተመድበዋል። በፓርላማ ከአምስት ወንበሮች ሶስቱ በሴቶች የሚወከሉባት አፍሪካዊቷ ሩዋንዳ በ18 በመቶ አራተኛ ደረጃን ይዛለች። የመን በሴቶች የፖለቲካና የትምህርት ተሳትፎ የመጨረሻውን ደረጃ ይዛለች በመካከለኛው ምስራቅና በሰሜን አፍሪካ የሚገኙ ሃገራት ግን ሁኔታው የተባባሰባቸው ናቸው። በጦርነት እየታመሰች ያለችው የመን በ52 በመቶ ክፍተት የመጨረሻውን ደረጃ ይዛለች። ሪፖርቱ ሴቶች ከወንዶች ያነሰ ደሞዝ እንደሚያገኙና ግፋም ሲልም ክፍያ በሌላቸውና በትርፍ ጊዜ ሥራዎች እንደሚሰማሩ ይዘረዝራል። ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ ሃገራት ደግሞ በሴቶች ጤና ከፍተኛ መሻሻል መታየቱን ይጠቅሳል። ሴት ሰራተኞችን በማሰማራት በመጀመሪያዎቹ 20 ደረጃዎች 9ኙ ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ ሃገራት የተያዙ ናቸው።