id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
news-53041154
https://www.bbc.com/amharic/news-53041154
በዛፍ ላይ ተሰቅለው የተገኙት ጥቁር አሜሪካውያን አሟሟት ላይ ዳግም ምርመራ ሊጀመር ነው
የአሜሪካ ፌደራል ባለስልጣናት በቅርቡ በዛፍ ላይ ተንጠልጥለው የተገኙት ሁለት ጥቁር አሜሪካውያን አሟሟት ላይ የተደረገውን ምርመራ ሊገመገም እንደሆነ አስታውቀዋል።
ግለሰቦቹ ሞተው የተገኙት በካሊፎርኒያ ሲሆን፤ ከአሟሟታቸውም ጋር በተያያዘ የተቀጣጠለውንም ተቃውሞ ተከትሎ ነው ምርመራው እንደገና እንዲጀመር የተወሰነው። የአካባቢው ፖሊስ ሮበርት ፉለርና ማልኮልም ሃርሽ የተባሉት ጥቁር አሜሪካውያን ግድያ አይደለም ብሏል። በካሊፎኒያ ግዛት በተለያየ ከተማ በዛፍ ላይ ተንጠልጥለው የተገኙት ጥቁር አሜሪካውያኑ በሁለት ሳምንታት ልዩነት ነው የሞቱት። ብዙዎች ራሳቸውን አጥፍተው ሳይሆን ተገድለው ነው በሚልም ምርመራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው። የ24 አመቱ ሮበርት ፉለር ፓልሜድ በምትባለው አካባቢ ከሚገኝ ዛፍ ላይ ተሰቅሎ የተገኘው ሰኔ 3፣ 2012 ዓ.ም ነው። ምንም እንኳን የአካባቢው ባለስልጣናት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ራሱን አጥፍቶ ነው ቢሉም፤ ብዙዎች አልተቀበሉትም። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም ምርመራ እንዲካሄድ ፊርማቸውን አሰባስበዋል። ቤተሰቦቹም ቢሆኑ ራሱን ነው የገደለው የሚለው ፅንሰ ሃሳብ ሊዋጥላቸው አልቻለም "የሚነግሩን ነገር በሙሉ ስህተት ነው፤ በምንም መንገድ ተቀባይነት የለውም። ወንድሜ ራሱን ማጥፋት አይፈልግም ነበር" በማለት የሮበርት ፉለር እህት ዳይመንድ አሌክሳንደር ተናግራለች። ሌላኛው ሟች ማልኮልም ሃርሽም ግንቦት 23፣ 2012 ዓ.ም ቪክቶርቪል በምትባል አካባቢ በዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ ነው የተገኘው። ባለስልጣናቱም የ37 አመቱ ማልኮልም ራሱን አጥፍቷል የሚል ግምት ቢኖራቸውም አሟሟቱን በተመለከተ ይፋዊ መረጃ ገና አልወጣም። "አሟሟቱን በተመለከተ በርካታ ጥያቄዎች አሉን፤ ምላሾችም እየጠበቅን ነው። ወንድሜ ሁሉን ወዳጅ ነበር። ለቤተሰቦቹ ብቻ ሳይሆን ለሁሉ ቀና ነበር። እንዲህ አይነት ሰው ራሱን ያጠፋል ማለት አያሳምንም" በማለት አህቱ ሃርሞኒ ሃርሽ ለሚዲያዎች ተናግራለች። የአሜሪካ የፌደራል ምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ)፣ ጠቅላይ አቃቤ ህግ፣ የካሊፎርኒያ ግዛት ምርመራ ቢሮ፣ የአሜሪካ የሲቪል መብቶች የፍትህ ዘርፍ ክፍል ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በላኩት መመግለጫ ግለሰቦቹ ላይ የተከናወኑትን ምርመራዎች እየተገመገሙና እንደገናም ምርመራ ሊጀመር መሆኑን ነው። የመጀመሪያ ምርመራው የተከናወነው በሎስ አንጀለስና ሳንበርናርዲኖ ፖሊስ ቢሮዎች ሲሆን ለግምገማውም እንደሚተባበሩ አስታውቀዋል። የጆርጅ ፍሎይድን ግድያ ተከትሎ የተነሳው ተቃውሞ የሁለቱ ግለሰቦች አሟሟት ላይም ምርመራ እንዲካሄድ ጫና አሳርፏል።
news-56980751
https://www.bbc.com/amharic/news-56980751
ትዳራቸውን ያፈረሱ አምስት ቢሊየነሮች
አሜሪካዊው ቢሊየነር ቢል ጌትስ ከ27 ዓመታት በኋላ ከሚሊንዳ ጌትስ ጋር መስርተውት የነበረውን ትዳር ለማፍረስ መስማማታችውን ገልጸዋል።
ሁለቱ ጥንዶች የተገናኙት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር 1980ዎቹ ውስጥ ሚሊንዳ የቢል ጌትስን ማይክሮሶፍት ተቋም በተቀላቀለችበት ወቅት ነበር። ''ከብዙ ማሰብና ግንኙነታችንን ለማሻሻል ከሰራን በኋላ ትዳራችንን ማፍረሱ የተሻለ አማራጭ አድርገን ወስደናል'' ብለዋል በትዊተር ገጻቸው ላይ ባስቀመጡት መልዕክት። ቢሊየነሮቹ ጥንዶች በ27 ዓመታት የትዳር ዘመናቸው ሦስት ልጆችን ያፈሩ ሲሆን፤ በተለያዩ ዘርፎች ድጋፍ የሚያደርገውን 'ቢል ኤንድ ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን' አቋቁመዋል። ድርጅታቸውም የተለያዩ አይነት ተላላፊ በሽታዎችን ለመዋጋትና ለህጻናት ክትባቶችን ለማድረስ በቢሊየኖች የሚቆጠር ዶላር ፈሰስ አድርጓል። ቢል ጌትስ በፎርብስ መጽሄት መረጃ መሠረት የዓለማችን አራተኛው ቢሊየነር ሲሆን የተጣራ ሀብቱም 124 ቢሊየን እንደሆነ ተነግሯል። የጥንዶቹ ትዳር ማፍረስ ዓለምን ያነጋገር ትልቅ ዜና ቢሆንም ያልተለመደ ነገር ግን አይደለም። ከዚህ በፊትም በርካታ ቢሊየነር ጥንዶች ትዳራቸውን አፍርሰው ሀብት ንብረታቸውን ተካፍለዋል። እስቲ ጥቂቶቹን እንመልከት። ጄፍ ቤዞስ እና ማኬንዚ ቤዞስ የአለማችን ቀንደኛ ሃብታም ጄፍ ቤዞስ እና ባለቤቱ ማክኬንዚ ትዳራቸውን ለማፍረስ የተስማሙት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ሚያዝያ 2019 ላይ ነበር። ። ጄፍ ቤዞስ ፍቺውን ለህዝብ ይፋ ያደረገው በቲውተር ገፁ ላይ ሲሆን ጉዳዩም በመስማማት መከናወኑን ጠቅሷል። ፍቺው ግን እንዲሁ በቀላሉ የሚወጡበት አልሆነም። ባለቤቱ የድርሻዋ ነው የተባለውን 35 ቢሊየን ዶላር ተካፍላለች። 35 ቢሊዮን ዶላር ድርሻዋን የምትቀበለው ማክኬንዚን ከዓለማችን ሃብታም ሴቶች ዝርዝር ውስጥ ያካትታታል። ይህ ብቻ ሳይሆን ባለቤቷ ከዛሬ 25 አመት በፊት ከመሰረትውና በአለማችን ቁጥር አንድ ከሆነው የኢንተርኔት የችርቻሮ ግብይት ድርጅት አማዞን የአራት በመቶ ድርሻ ይኖራታል። ቢሊየነሯ ማኬንዚ በአሁኑ ሰአት ልጆቿ በሚማሩበት ትምህርት ቤት ሳይንስ የሚያስተምር ግለሰብ አግብታለች። ቢሊየነሯ የሳይንስ አስተማሪው ዳን ጄዌትን ማግባቷ ይፋ የሆነው 'ጊቪንግ ፕሌጅ' በተሰኘው የእርዳታ ድረ-ገፅ ላይ ነው። አሌክ ዊልደንስቲን እና ጆሰሊን ዊልደርስቲን እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር 1999 እነዚህ ጥንዶች ትዳራቸውን ለማፍረስ ሲስማሙ ዓለም ጉድ ብሎ ነበር። በወቅቱ ከፍቺ በኋላ ከፍተኛ ወጪ ያስከተለ ትዳር ሆኖ ተመዝግቦ ነበር። በንግድ ስራውና የጥበብ ስራዎችን በመሰብሰብ የሚታወቀው አሜሪካ ፈረንሳያዊው አሌክ ዊልደንስቲን ከ21 ዓመታት በኋላ ትዳራቸውን እንደሚያፈርሱ ገልጾ ነበር። ባለቤቱ ጆሰሊን ዊልደርስቲን ደግሞ ከፍቺው በኋላ መጀመሪያ ላይ 2.5 ቢሊየን ዶላር እንደምታገኝ ተገልጾ ነበር። በወቅቱም በየዓመቱ ለሚቀጥሉት 13 ዓመታት ተጨማሪ 100 ሚሊየን ዶላር እንደሚሰጣት ተገልጿል። በዚህም በአጠቃላይ ያገኘችው ገንዘብ ወደ 3.8 ቢሊየን ዶላር ይደርሳል። ቢል እና ሱ ግሮስ ቢል ግሮስ እና ሱ ግሮስ በአውሮፓውያኑ 2016 ትዳራቸውን ሲያፈርሱ ክፍያው በኋላ በርካታ ያልተጠበቁ ነገሮች ተከስተው ነበር። ቢል በዓለማችን ታዋቂ አሜሪካዊ ቢሊየነር ሲሆን የመንግሥት ቦንድ በመግዛት ከፍተኛ ትርፍ በማግኘት ይታወቃል። የጥንዶቹ የፍቺ ሂደት ደግሞ ሁለት ዓመታትን የፈጀ ነበር። ፍቺያቸውን ሳይጠናቀቅ በፊት ቢል ግሮስ 31 ሚሊየን የሚያወጣውን የባለቤቱን መኖሪያ ቤት ከጥቅም ውጪ አድርጎት መውጣቱን እና ተክሎችን ጭምር ገድሎ እንደሄደ ባለቤቱ ለፍርድ ቤት ተናግራ ነበር። ከፍቺው መጠናቀቅ በኋላ ደግሞ ሱ ግሮስ 1.3 ቢሊየን ዶላር እንዲሁም 31 ሚሊየን የሚያወጣውን መኖሪያ ቤት እንዲሰጣት ፍርድ ቤት ወስኗል። በተጨማሪም ጥንዶቹ የገዟቸው በሚሊየኖች የሚያወጡ የጥበብ ስራዎችን እኩል እንዲካፈሉም ተወስኗል። ሩፐርት መርዶክ እና አና ቶርቭ በሚዲያ ቢዝነስ የሚታወቀው ቢሊየነሩ ሩፐርት መርዶክ እና አና ቶርቭ ለ31 ዓመታት የቆየ ትዳር የነበራቸው ሲሆን ሶስት ልጆችንም ማፍራት ችለዋል። ነገር ግን ቢሊየነሩ ሩፐርት መርዶክ ከሁሉም ነገር ራሱን ለማግለል ሲያቅድ በአውሮፓውያኑ 1998 ላይ አብረው ትዳራቸውንም ለማፍረስ ተስማምተዋል። ከፍቺው ጋር ተያይዞም አና ቶርቭ እስከ 1.7 ቢሊየን ዶላር የሚደርስ ገንዘብ እንደተሰጣት ተገልጿል። ፍቺያቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ጥንዶቹ ወደ ሌላ ትዳር ለመሄድ ብዙም አልፈጀባቸውም ነበር። ሩፐርት መርዶክ ትዳሩን ባፈረስ በ17ኛው ቀን ዌንዲ ዴንግ የተባለች ሴት አግብቶ ትዳር መስርቷል። አና ቶርቭ ደግሞ ከስድስት ወራት በኋላ ዊሊያም ማን የተባለ ግለሰብ አግብታለች። ሀሮልድ ሀም እና ሱ አን አርኖል በነዳጅ እና ጋዝ ንግድ ላይ የተሰማራው አሜሪካዊው ቢሊየነር ሀሮልድ ሀም እስከ 14 ቢሊየን ዶላር የሚደርስ ሀብት እንዳለው ይነገር ነበር። ከባለቤቱ ሱ አን አርኖል ጋር በአውሮፓውያኑ 2015 ትዳራቸውን ለማፍረስ ሲስማሙ 1 ቢሊየን ዶላር ለባለቤቱ እንዲሰጥ ፍርድ ቤት ወስኗል። በአሁኑ ሰአት ሀሮልድ ሀም የተጣራ ሀብቱ 9 ቢሊየን ዶላር እንደሆነ ተገልጿል።
news-54341613
https://www.bbc.com/amharic/news-54341613
የታይላንድ ሆቴልን አንቋሿል የተባለው አሜሪካዊ ሊታሰር ይችላል ተባለ
በታይላንድ ቆይታው ወቅት ስላረፈበት ሆቴል አሉታዊ ነገሮችን መፃፉን ተከትሎ አንድ አሜሪካዊ ግለሰብ የሁለት ዓመት እስር ሊጠብቀው ይችላል ተብሏል።
ያረፈበት ሪዞርትም ጥብቅ በሚባለው የአገሪቱ ስም ማጥፋት ወንጀል ከስሶታል። በታይላንድ ነዋሪ የሆነው አሜሪካዊው ዌስሊ ባርንስ በተለያዩ ድረገፆችም ላይ ሪዞርቱን "ዘመናዊ ባርነት የሚካሄድበት" በማለት ወንጅሎ ፅፏል። ዘ ሲ ቪው ሪዞርት በበኩሉ እንግዳው ያቀረበው ትችት "መሰረት የሌለው፣ ሃሰትና የሆቴሉንም ስም በማጥፋትም ጉዳት አድርሷል ብለዋል። በትሪፕ አድቫይዘር ድረገፅ ላይ ሆቴሉን አስመልክቶ የወጣው ፅሁፍ ፍትሃዊ እንዳልሆነ በማስመልከት ክስ የሆቴሉ ባለቤት መመስረቱንም ፖሊስን ዋቢ አድርጎ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል። ይህን ሁሉ ክስና ውዝግብ ያስነሳው ኮህ ቻንግ በምትባለው ደሴት ውስጥ የሚገኘው ሪዞርት ውስጥ ያረፈው ዌስሊ የራሴን መጠጥ ማስገባት አለብኝ በሚል ከሆቴሉ አስተዳደር ጋር እሰጣገባ በመግባቱ ነው። ግለሰቡ የሆቴሉን ተስተናጋጆች እንደረበሸና መጠጥ የሚያስገባም ከሆነ ክፍያውን ፈፅም ቢባልም እምቢተኝነት ማሳየቱን ሆቴሉ ባወጣው መግለጫው አትቷል። ሆቴሉን ለቅቆ ከወጣም በኋላ በተደጋጋሚ አሉታዊ ነገሮችን ስለሆቴሉ መፃፉንም ተከትሎ ሆቴሉም በስም ማጥፋት ወንጀል ከሶታል። ግለሰቡም በቁጥጥር ስር ውሎም ለሁለት ምሽቶች በእስር ቤት ያሳለፈ ሲሆን በዋስም ተለቅቋል። አሜሪካዊው ግለሰብ በስም ማጥፋት ክስ ወንጀል ጥፋተኛም ሆኖ ከተገኘ እስከ ሁለት አመት የሚቆይ እስር ይጠብቀዋል ተብሏል። ከዚህም ጋር በተያያዘ ስራውን ያጣው ግለሰብ ጉዳዩ የበለጠ ከገፋም ሌላ ስራ ለማግኘት እንደሚቸገር ለቢቢሲ ተናግሯል። የፍርድ ሂደቱም ጥቅምት ወር ላይ ይጀምራል ተብሏል።
news-57065443
https://www.bbc.com/amharic/news-57065443
ከ400 ዓመት በፊት የተነገሩ አምስት ጠቃሚ የሕይወት ምክሮች
ራስን ለመለወጥ የሚረዱ ምክሮችን ስናስብ ምናልባት ገበያውን የሞሉት አዳዲሶቹ መጽሐፍት ጠቃሚ ሊመስሉን ይችላሉ። ሁሌም ቢሆን ማንም ሰው ዘመናዊና አዲስ የሆኑ ነገሮችን በመጠቀም ራሱን መቀየር ይፈልጋል።
ነገር ግን ከብዙ ዘመናት በፊት የተጻፉ መጻሕፍት አሁን ላለንበት ዓለም ተግባራዊ መሆን ይችላሉ። 'ዘ አናቶሚ ኦፈ ሜላንኮሊ' የተባለው መጽሐፍ በአውሮፓውያኑ 1621 እንደተጻፈ ይነገራል። የዘመናዊውን ሰው አኗኗርና አስተሳሰብ ከዚህ መጽሀፍ በላይ የሚገልጽ ግን አልተገኝም። በርተን እንግሊዛዊ ቄስና ምሁር ሲሆን ከ2 ሺ ዓመታት በላይ ግሪክ ውስጥ ጥቅም ላይ ይውሉ የነበሩ ሕክምናዎችና እና ፍልስፍናዎችን አጠናቅሯል። ይህ እንግሊዛዊ ምሁርና ቄስ ከፍተኛ ድብርትን ያውቀዋል። በዚህ ጉዳይ ዙሪያም በርካታ ሃሳቦችን አስቀምጧል። ነገር ግን የበርተን የሕይወት ስራዎች በዘመናዊው ሰው ሕይወት ውስጥ ድብርትና ሀዘንን እንዴት ይረዱታል? ስኮትላንዳዊቷ ጋዜጠኛ ኤሚ ሎፕትሮት የበርተንን ስራዎች አጠናቅራ በድጋሚ በማዘጋጀት ለ21ኛው ክፍለዘመን ሰው በሚመች መልኩ አቅርባዋለች። እሷ እንደምትለው በ1620ዎቹ ሰዎች ከድብርትና ሀዘን ለመላቀቅ ይወስዷቸው የነበሩ የመፍትሄ እርምጃዎች አሁንም ድረስ ጥቅም ላይ መዋል የሚችሉ ናቸው። 1. የራሳችንን የስሜት መለዋወጥ በአንክሮ መከታተል በድብርት አልያም በሀዘን ለሚሰቃይ ሰው የሚሰሙት ስሜቶች ምናልባት ያለምንም ምክንያት የሚሆኑ መስለው ሊታዩ ይችላሉ። ነገር ግን የሚሰሙን ስሜቶች የራሳቸው አካሄድ አላቸው። ድብርት ተላላፊ በሽታ እንደሆነና ምልክቶቹም ሆነ የሚያሳርፉት ጫና ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተወረስ እንደሚሄድ በርተን ያስብ ነበር። ምናልባት ነገሮችን የተመለከተበት መንገድ የተለየ ሊመስል ቢችልም በዘመናዊው ህክምናም ብቸኛው ምክንያት ባይሆንም ድብርት ከቤተሰብ የሚተላለፍ እንደሆነ ተረጋግጧል። "አንድ የቤተሰብ አባል በከባድ የድብርት በሽታ የሚሰቃይ ከሆነ መላው ቤተሰብ አብሮት ህክምናውን አብረውት እንዲከታተሉና ለራሳቸውም ነገሮችን እንዲያስተውሉ እፈልጋለሁ'' ይላሉ በቤተሰብ ጉዳዮች ላይ የሚሰሩት ዶክተር ፍራንሲስ ራይስ። ነገር ግን ድብርት ከቤተሰብ ብቻ የሚመጣ ጉዳይ አይደለም። የተለያዩ ውጪያዊ ምክንያቶችም የራሳቸው አስተወዋጽኦ አላቸው። በርተን መጽሐፉን በሚያዘጋጅበት ወቅት ራሱ ላይ ያስተዋላቸውን ነገሮች ከግምት ውስጥ አስገብቷል። በየጊዜው የሚቀያየር የደስታና ሀዘን ስሜቶች በዘመናዊው የህክምና ዓለም 'ባይፖላር ዲስኦርደር' የሚባል ሲሆን በርካቶችን የሚያጠቃ ነው። በአሁኑ ጊዜ ሰዎች የሚሰሟቸውን ስሜቶች በአግባቡ መከታተልና ለምን እንደሚለዋወጡ ማወቅ ለድብርት ፍቱን መድሀኒት ተደርጎ ይወሰዳል። ምን ሲገጥመን የስሜት መለዋወጥ ውስጥ እንደምንገባ ማወቅ ከቻልን እነዚያን ነገሮች ማስወገድ ቀላል ነው። 2. የቀዝቃዛ ውሃ ጥቅም በርተን በመጽሐፉ ላይ ከብዙ ዓመታት በፊት በሌሎች ሰዎች የተጻፉ የተለያዩ ሀሳቦችን አስፍሯል። ንጹህ በሆነ ቀዝቃዛ ወንዝ ውስጥ ገላችንን መታጠብ ደግሞ በርተን ካስቀመጣቸው መፍትሄዎች መካከል አንደኛው ነው። ማንኛውም ሰው ረጅም ህይወት መኖር ከፈለገ በጣም በሚያምር ተፈጥሮአዊ ቦታ ላይ ገላን መታጠብ አንደኛው መንገድ ነው ይላል። '' በቀዝቃዛ ውሀ ምክንያት ሰውነታችን የሚሰማውን ጭንቀት መቋቋም ካስለመድነው ሌሎች አስጨናቂ ነገሮችንም መቋቋም ይማራል'' ይላሉ በዩናይትድ ኪንግደም በሚገኘው ፖርትስማውዝ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ማይክ ቲፕተን። 3. ከተፈጥሮ አለመራቅ ተፈጥሮ ለበርተን ከፍተኛ ድብርትን ለማባረር ቁልፍ ሚና የሚጫወት ነገር ነበር። በተለይ ደግሞ በተፈጥሮአዊ ጫካ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ አይነት እጽዋት ጭንቅላታችን ዘና እንዲል እና የሚያስጨንቁትን ነገሮች እንዲረሳ የማድረግ ከፍተኛ አቅም አላቸው። በኦክስፎርድ ቦታኒክ ጋርደን ዳይሬክተር የሆኑት ፕሮፌሰር ሳይመን ሂሰኮክ እንደሚሉ አንዳንድ ተክሎች ድብርትን ለማከም ጭምር ጥቅም ላይ ይውላሉ። በርተን ደግሞ አንዳንድ ተክሎች ስንመገባቸው ጭምር ድብርትና የማባረር አቅም ያላቸው ቢሆንም ተክሎቹን መመልከት በራሱ ድብርትን እና ጭንቀትን የማባረር አቅም አለው ይላል። እንግሊዛዊው የእጽዋት ተንከባካቢ ሞንቲ ዶን እንደሚለው በከፍተኛ ሁኔታ በድብርትና ጭንቀት ተሰቃይቶ ነበር። ነገር ግን እጽዋትን መትከልና መንከባከብ ከጀመረ በኋላ ግን ነገሮች እየቀለሉ መምጣታቸውን ያስታውሳል። ''አንድ ተክል ከተተከለበት ጊዜ ጀምሮ እድገቱን መመልከትና መንከባከብ ለጭንቅላት የሚሰጠው ትልቅ እረፍት አለ'' ይላል። 4. ችግራችንን ለሌሎች ማጋራት ''በውስጣችን የሚሰማንን ጭንቀትና ድብርት ለራሳችን ብቻ ይዘነውና ተሸክመነው ከመቆየት ይልቅ ለሌሎች ማጋራትና አብሮ መፍትሄ መፈለግን የመሰለ ነገር የለም'' ብሎ ነበር በርተን ከ400 ዓመታት በፊት። ጭንቀትና ድብርት የሚያጋጥማቸው ሰዎች ሁሌም ቢሆን ራሳቸውን ከሰዎች ለይተው መቀመጥ ይመርጣሉ። ነገር ግን መሰል ነገሮች እንደውም ጭራሽ ስቃዩን ያበዙታል። በቤተሰብ ጉዳዮች ላይ የሚሰሩት ዶክተር ፍራንሲስ ራይስ እንደሚሉት ጭንቀት ሲገባን ከምንወዳቸውና ከሚወዱን ሰዎች ጋር ዘና የሚያደርግ ነገር ማድረግና ችግራችን በዚያው ለእነርሱ ማጋራት በጣም ወሳኝ ነው። ''ምናልባት ከሰዎች ጋር ብዙም ማውራት የማንወድ እንኳን ቢሆን ከሰዎች ጋር ለየት ያለ ነገር ማድረግ ጭንቅላታችን ትኩረቱን ወደ ሌሎች ነገሮች እንዲያደርግ ያግዘዋል'' ጭንቀትና ድብርት አሰቃየኝ ብሎ አንድ ሰው ሐኪም ጋር ቢሄድ ምናልባት ድብርትን የሚያስወግዱ በርካታ አይነት መድሀኒቶች ሊታዘዙ ይችል ይሆናል። ነገር ግን በአሁኑ ሰአት እንደ ዴንማርክ፣ ካናዳ እና ዩኬ ባሉ አገራት መሰል ችግር የሚያጋጥማቸው ሰዎች ከመድሀኒት ይልቅ ከሰዎች ጋር እንዲገናኙ፣ አዲስ ክህሎቶችን እንዲማሩ አልያም ተፈጥሮአዊ ቦታዎችን እንዲጎበኙ ነው የሚታዘዝላቸው። 5. ስራችንን እና ሕይወታችንን ማጣጣም ምናልባት በርተን ቃል በቃል ስራችንን እና ሕይወታችንን ማጣጣም ብሎ ላይሆን ይችላል። ነገር ግን አዲስ ነገር የመማር ፍቅር በሚል ገልጾታል። እንደውም ይህ የመማር ፍቅር በራሱ ከበዛ ችግር ሊሆን እንደሚችልም አስቀምጧል። በርተን እንደሚለው ሕይወታችንን የምንመራበት ስራን ለማሳካት አልያም ምርምር ለማድረግ ይሁን ሙሉ ትኩረታችንን እና ጭንቅላታችንን በሙሉ እዛ ላይ ባደረግን ቁጥር ራሳችን ላይ ተጨማሪ ጭንቀትና ድብርት እንጨምራለን። ሰዎች ስለስራቸው አብዝተው ሲጨነቁ እና ነገሮችን ለማስተካከል ሙሉ ጊዜያቸውን እዚያ ጉዳይ ላይ ባዋሉ ቁጥር ከሰዎች ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት እየቀነሰ ይመጣል። የሚያስደስታቸውን ነገር ማድረግም ቢሆን ያቆማሉ። ምናልባት በርተን የሰዎችን አስተሳሰብ የተመለከተበትና ያጠናበት መንገድ ያረጀ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን እርሱ ተውሶ ያመጣቸው የግሪክ ፈላስፋዎች አስተሳሰብና ህክምናዎች አሁንም ድረስ ጥቅም ላይ መዋል የሚችሉ ናቸው። ራስን ማወቅ፣ መዋኘት፣ ተፈጥሮ፣ ማህበረሰብ እና ማንበብ ከዛሬ 400 ዓመት በፊት ከሰሩ አሁን ላይ ለእኛስ የማይሰሩበት ምክንያት አለ?
news-53749528
https://www.bbc.com/amharic/news-53749528
ፊልም ፡ በዚህ ዓመት በሆሊውድ ብዙ ሚሊዮን ዶላሮች የተከፈላቸው ተዋናዩች ታወቁ
በዚህ ዓመት የትኞቹ ተዋናዮች ብዙ ሚሊዮን ዶላሮች ተከፈሏቸው? ብሎ ለሚጠይቅ ዘንድሮ ድዋይን "ዘ ሮክ" ጆሐንሰንን በክፍያ የሚያህለው አልተገኘም አጭሩ መልስ ነው።
ድዋይን ጆሐንሰንን የሐብታም የገንዘብ መጠን አደባባይ በማስጣት የሚታወቀው ፎርብስ የአዱኛ ዝርዝር መጽሔት ትናንት እንዳስነበበው ከሆነ ድዋይን ጆሐንሰን በዚህ ዓመት ብቻ 87 ሚሊዮን ተኩል ዶላር አጋብሷል። ይህም ካለፈው ዓመት ሰኔ እስከ ዘንድሮ ሰኔ መሆኑ ነው፤ በፈረንጆች አቆጣጠር። ደግሞም የድዋይን ከፍተኛ ተከፋይነት ዘንድሮ ለተከታታይ ሁለተኛ ዓመት መሆኑ አስገራሚ ሆኗል። የቀድሞው የነጻ ትግል ተወዳዳሪና የአነቃቂ ዲስኩርተኛ ጆሐንሰን ዘ ሮክ በተመሳሳይ ባለፈው ዓመት የምድራችን ትልቅ ገንዘብ ተከፋይ ተዋናይ ተብሎ መሰየሙ ይታወሳል። ድዋይን ዘ ሮክ ጆሐንሰን ይህ ክፍያው ኔትፍሊክስ ላይ በቅርብ መታየት ለሚጀምረው "ሬድ ኖቲስ" (Red Notice) ለተሰኘው ፊልም ማስታወቂያና ትወና የተከፈለውን 23 ሚሊዮን ዶላር ተኩል ይጨምራል። በፊልሙ ላይ ድዋይን ራሱ መሪ ሆኖ ይተውንበታል። ሬድ ኖቲስ በቅርብ በኔትፍሊክስ የሚቀርብ አንድ ኢንተርፖል በጥብቅ በሚፈልገው የዓለማችን የሥዕል ቀበኛ ላይ የሚያጠነጥን 'አክሽን ኮሜዲ' ዘውግ ያለው ፊልም ነው። ከዚህ ባሻገር የስፖርታዊ እንቅስቃሴ አልባሳት ማምረቻ የሆነውና "ፕሮጀክት ሮክ" የሚል ስም ያለው ድርጅቱ ለድዋይን ዘ-ሮክ ጠቀም ያለ ገንዘብ ያስገኝለታል። ከድዋይን 'ዘ-ሮክ' ጆሐንሰን ጋር 'በሬድ ኖቲስ' ፊልም ላይ አብሮት የሚሰራው ሌላኛው ተዋናይ ራየን ሬይኖልድ 2ኛው ከፍተኛ ተከፋይ ነው፤ በፎርብስ መጽሔት መረጃ መሰረት። ራየን ሬይኖርልድ 71 ሚሊዮን ዶላር ተኩል ወደ ኪሱ አስገብቷል በዚህ ዓመት። ይህ ገንዘብ 'ሬድ ኖቲስ' ላይ ለሚተውንበት የተከፈለውን 20 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ሲክስ አንደርግራው (Six Underground) ለተሰኘው ፊልም ደግሞ ሌላ 20 ሚሊዮን የተከፈለውን ይጨምራል። ፎርብስ የዓለማችን ሦስተኛው ከባድ ተከፋይ ተዋናይና ፕሮዲዩሰሩ ማርክ ዋልበርግ እንደሆነ አስታውቋል። 58 ሚሊዮን ዶላር በዓመት ገቢ አግኝቷል ማርክ። በአራተኛና በአምስተኛ ደረጃ የተቀመጡት ቤን አፍሌክ እና ቪን ዲዝል ናቸው። ከዚህ ሌላ የቦሊውዱ ኩማር እስከ 10 ከገቡ ከፍተኛ ተከፋዮች ብቸኛው ሆኗል። በዚህ ዝርዝር ውስጥ ሚራንዳ፣ ዊል ስሚዝ እና አዳም ሳንድለር ይገኙበታል። ጃኪ ቻንም እስከ 10 ባለው ዝርዝር ቦታ አላጣም። ፎርብስ የወንድ ተዋናይንን ዝርዝ ነው ለጊዜው ይፋ ያደረገው። በቀጣይ ሴት ተዋንያንን እንዲሁ ይፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል። ባለፈው ዓመት በዚህ የከፍተኛ ተከፋዮች ዝርዝር ከሴት ተዋንያን ሁሉ ልቃ የተገኘችው ስካርሌት ጆሐንሰን ነበረች፤ 56 ሚሊዮን ዶላር በማፈስ። ይህ ገንዘብ መጠን ባለፈው ዓመት ከወንዶች ዝርዝር ሰባተኛ ደረጃን የሚያስቀምጥ ነበር።
50450883
https://www.bbc.com/amharic/50450883
ሺህ ቃላት ከሚናገረው ፎቶ ጀርባ ያለው እውነታ
ሃይድርባድ የተሰኘችው የደቡባዊ ሕንድ ግዛት ነዋሪ የሆነችው የአምስት ዓመቷ ሕፃን ፎቶ ሰሞኑን የሃገሬውን ሰው ጉድ አሰኝቷል
ፎቶው ይህች ሕፃን ትምህርት ገበታ ላይ ያሉ እኩዮችዋን ከውጪ አጮልቃ ስትመለከት ያሳያል። ዲቭያ አሁን በመንደሩ ታዋቂ ሆናለች፤ ዕድሜ ከሺህ ቃላት በላይ ለተናገረው ፎቶ። ዓይን-አፋሯ ዲቭያ በአንድ የመንግሥት ትምህርት ቤት በኩል ስታልፍ ነው እኩዮችዋ ሲማሩ አጮልቃ ስትመለከት የነበረው። በአንድ እጇ ጎድጓዳ ሳህን ይዛለች። ይህ ፎቶ ቴሉጉ በተሰኘው ጋዜጣ የፊት ገፅ ላይ ከወጣ ወዲህ መነጋገሪያ ሆነ። ርዕሱ ደግሞ የተጠማ ዕይታ ይላል። ለጥቆ የማሕበራዊ ድር-አምባው አፍ ሟሟሻ ሆነ። የሕፃናት መብት ተሟጋች ነን ያሉ ድምፃቸውን በፎቶው በኩል አሰሙ። ይሄኔ ነው ትምህርት ቤቱ ዲቪያን በነፃ ለማስተማር የወሰነው። የዲቪያ አባት ግን ፎቶው ባመጣው ዕድልም ሆነ ጩኸት ደስተኛ አይደሉም። «እኔና የፅዳት ሠራተኛ የሆነችው እናቷ ከፍቶናል» ይላል። «ፎቶውን ባየሁት ጊዜ አዘንኩኝ። ዲቫያ ቀን ተሌት ተራሩጠው መፃኢ ሕይወቷን የሰመረ ለማድረግ የሚሮጡ እናት እና አባት አሏት። ጋዜጣው ግን ወላጅ አልባ አስመስሎ ነው ያቀረባት።» አባት፤ ዲቪያ 6 ዓመት እስኪሆናት እየጠበቅኩ ነበር እንጂ የማስተማር አቅም አለኝ ይላሉ። ዲቪያ ታላቅ ወንድም እንዳላትና ሁለተኛ ደረጃ ጨርሶ ኮሌጅ ለመግባት እየተጠባበቀ እንዳለ አባት ይናገራሉ። ዲቪያና ወላጆቿ በአንድ ክፍል ቤት ውስጥ ይኖራሉ፤ ትምህርት ቤቱም ከቤታቸው በቅርብ እርቀት ላይ ይገኛል። አካባቢው ዝቅተኛ ኑሮ ያላቸው ሕንዳዊያን የሚኖሩበት ነው። የዲቪያ እናትና አባት ደፋ ቀና ብለው በወር 10 ሺህ ሩፒ ያገኛሉ፤ 4 ሺህ ብር ገደማ ማለት ነው። እርግጥ ትምህርት ቤቱ የመንግሥት እንደመሆኑ ለሕፃናት ትምህርት በነፃ ስለሚሰጥ መክፈል አይጠበቅባቸውም። የዲቪያ አባት እሷና ወንድሟን ጨምሮ የሟች ወንድሙን አምስት ልጆች ያሳድጋል። «እኔ ያለፍኩበትን ስለማውቅ የፈለገ ቢሆን ልጆቼ ትምህርት እንዲነፈጉ አልፈግም» ይላል። የመንደሩ ሕፃናት ምሳ ሰዓት ሲደርስ ወደ ትምህርት ቤቱ ያቀናሉ። ብዙዎቹ ጎድጓዳ ሳህን ከእጃቸው አይጠፋም። ምክንያታቸው ደግሞ በመንግሥት የሚደገፈው ት/ቤት ምሳ ለተማሪዎች ስለሚያቀርብ ከዚያ ቢደርሰን በሚል ነው። «ዲቪያ አልፎ አልፎ ምሳ ሰዓት ወደዚያ ትምህርት ትሄዳለች። ድንገት ፎቶ ተነሳችና መነጋገሪያ ሆነች።» ምሳ ከቤታቸው ቋጥረው የሚመጡ ስላሉ የተረፈውን የመንግሥት ምሳ ተማሪ ባይሆኑም እንኳ ዲቪያና ጓደኞቿ ይጋሩታል። በአካባቢው በመንግሥት የሚተዳደር የሕፃናት ማቆያ ባለመኖሩ ሕፃናት መንደር ውስጥ ሲዞሩ ይውሉና ምሳ ሰዓት ላይ ወደ ት/ቤቱ ያቀናሉ። አባት ላክሽማንና የአካባቢው ሰዎች የዲቪያ ፎቶ እንዲህ መነጋገሪያ መሆኑ በአንድ በኩል አስከፍቷቸዋል። ምክንያታቸው ደግሞ ምንም ቢሆን ልጆቻችንን ማስተማር አያቅተንም ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ለመንግሥት ማንቂያ ደወል ነው ይላሉ። በአካቢው አንድ እንኳ የሕፃናት ማቆያ ቢኖር ዲቪያና እኩዮቿ ሳህን ይዘው የመንግሥት ት/ቤት ደጃፍ ባልረገጡ ነበር በሚል።
news-55301089
https://www.bbc.com/amharic/news-55301089
ባሕል፡ መጠሪያ ስምን መቀየር እድል ያስተካክል ይሆን?
እውን መጠሪያ ስምን መቀየር የተሻለ ዕድል ያመጣ ይሆን? አንዳንድ የቻይና ማህበረሰቦች በዚህ ሀሳብ በእጅጉ ይስማማሉ።
በአንድ የሚያዝያ ከሰአት ላይ ማንዲ ፓንግ በጣም የምትፈራው ነገር ተፈጠረ። የስራ አለቃዋ በዙም ስብሰባ ላይ በድንገት እንድትካፈል አጭር ትዕዛዝ ሰጧት። የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ በኢኮኖሚው ላይ ባደረሰው ጫና ምክንያት ከስራ መቀነሷ ተነገራት። ነዋሪነቷን በሆንግ ኮንግ ያደረገችው የ29 ዓመቷ ማንዲ በጣም ተናደደች፤ አዘነች። ትንሽ ወደኋላ መለስ በማለትም ከዚህ በፊት ስላጋጠሟት መጥፎ ነገሮችና ዕድሎች ማስታወስ ጀመረች። ከስራዋ ከተቀነሰች አንድ ወር በኋላ አሁንም ስራ አጥ ነበረች። ከዚህ በኋላ ነበር ምን ማድረግ እንዳለባት እርግጠኛ የሆነችው። በእሷ አጠራር መጥፎ ዕድል እያመጣብኝ ነው ያለችው ሕጋዊ መጠሪያ ስሟን መቀየር ነበር የመጨረሻ አማራጭ ያደረገችው። ''አንዲት የእናቴ ጓደኛ መጠሪያ ስሜን ብቀይር መጥፎ እድልን ማባረር እንደምችልና ስለእኔ መትፎ የሚያስቡ ሰዎችን መራቅ እንደምችል ነገረችኝ'' በቻይና ባህል መሰረት የሰዎች መጠሪያ ትርጓሜ ትልቅ ቦታ ያለውና ብዙ ነገሮችን መወሰን ሚችል እንደሆነ ይታመናል። በሰሜናዊ እስያ የሚገኙ ቻይናውያን ደግሞ የሰዎች ስም ሕይወታቸውን፣ ጤናቸውን፣ ስኬታቸውን፣ የፍቅር ሕይወታቸውን እንዲሁም ዕድላቸውን የመወሰን ኃይል አለው ብለው ያምናሉ። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በኢኮኖሚዎች ላይ ያሳደረው ጫና እየበረታ ሲሄድ ደግሞ እንደ ማንዲ ፓንግ ያሉ በርካቶች እራሳቸውን ስራ አጥ ሆነው ያገኛሉ። ታዲያ ስራ ለመፈለግ ሲቪያቸውን ማሰማመር ብቻ ሳይሆን የወደፊቱን እንተነብያለን ወደሚሉ ሰዎችም ፊታቸውን እንዲያዞሩ አስገድዷቸዋል። አብዛኛዎቹ ምክር ደግሞ ለምን መጠሪያ ስማችሁን አትቀየሩም? ነው። ''ቻይናውያን ሕይወታቸውን የመወሰን አቅም ያላቸው 10 ነገሮች አሉ ብለው ያምናሉ'' ይላል በሆንግ ኮንግ አሉ ከሚባሉት የወደፊቱን ከሚተነብዩ ሰዎች መካከል አንዱ የሆነው ሊ ሺንግ ቻክ። አክሎም ''ሰዎች ከሚወለዱበት ቀን እና ጥሩ ነገር ከመስራት በተጨማሪ መጠሪያ ብዙ ነገሮችን የመቀየር አቅም ያለው ነው'' ብሏል። ማንዲ ፓንግም ብትሆን ስሟን መቀየሯ እያጋጠማት ያለውን መጥፎ ዕድል እንደሚቀይርላት በጽኑ ታምናለች። በዚህ ጥንታዊ ባህል መሰረት አንድ ሕፃን የተወለደበትን ትክክለኛ ጊዜ በጥንቃቄ ከተመረመረ በኋላ ወሳኝ ከሚባሉት የቻይናውያን መገለጫዎች (እሳት ፣ እንጨት ፣ ውሃ ፣ ብረት እና ምድር) መካከል በኮከብ ቆጠራ በየትኛው መሰየም አለበት የሚለው ይወሰናል። በተጨማሪም ደዲስ የሚወለደው/ የምትወለደው ልጅ፣ የሚሰጠው/ የሚሰጣት ስም ለጆሮ ተስማሚ የሆነና የወደፊት ዕድልን የሚያሳካ እንዲሆን ብዙ ነገሮች ከግምት ውስጥ ይገባሉ። ስለዚህ ሰዎች ካደጉ በኋላ በሕይወታቸው ደስተኛ ካልሆኑና መጥፎ ዕድል እያጋጠማቸው እንደሆነ ካመኑ ከላይ የተጠቀሱትን ነገሮች ከግምት ውስጥ አስገብተው ሌላ ጥሩ ዕድል የሚያመጣ ስም ይፈልጋሉ። ሁሉም የወደፊቱን እተነብያለው የሚል ሰው በርካታዎቹን መመዘኛዎች በተለያየ መንገድ መረዳቱን መተርጎሙ ደግሞ ብዙ የስም አማራጭ እንዲኖር ያደርጋል ይላል ሊ። በተመሳሳይ በቻይናዋ ጉዋንግዶንግ የሚኖረው ቺን ፎኩን ስሙን ከቀየረ አራት ዓመታት ማለፋቸውን ይገልጻል። በወቅቱ የመተንፈሻ አካላለት በሽታ ለወራት ያሰቃየው ነበር። ምንም እንኳን በርካታ የሕክምና ቦታዎች ቢሄድም ምንም ፈውስ ማግኘት አልቻለም። ''እናቴ ስሜን እንድቀይር ነገረችኝ። በወቅቱ በሽታው ለረጅም ጊዜ ሲያሰቃየኝ የነበረ ቢሆንም ልክ መጠሪያ ስሜን ከቀየርኩ በኋላ ግን ሙሉ በሙሉ ከሕመሜ ዳንኩኝ'' ይላል። ነገር ግን የ24 ዓመቱ ቺን አሁንም ቢሆን ስሙን መቀየሩ ብቻ ከህመሙ እንዳዳነው ሙሉ በሙሉ አያምንም። ''ምናልባት እድሜዬ እየጨመረ ሲመጣ ሰውነቴ የመከላከል አቅሙን አዳብሮ ሊሆን ይችላል'' ምንም እንኳን መጠሪያ ስምን መቀየር በሕይወታችን ብዙ ለውጦችን ስለማምጣቱ በሳይንሳዊ መንገድ ምንም የተረጋገጠ ነገር ባይኖርም በርካቶች ግን በስፋት የሚያምኑበት ጉዳይ ነው። በሲንጋፖር ናሽናል ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዛንግ ያን በእንደዚህ አይነት ጉዳዮች ዙሪያ በርካታ ምርምሮችን አካሂደዋል። ''ሰዎች ሁሉንም ነገር መቆጣጠር ይፈልጋሉ፤ በተለይ ደግሞ እየሆኑ ስላሉ ነገሮች እርግጠኛ መሆን ሲያቅታቸው። ሰዎች ስማቸውን ሲቀይሩ በሕይወታቸው የሚሆነውን ነገር እየተቆጣጠሩ እንደሆነ ይሰማቸዋል። ምናልባት ምንም የሚቀይሩት ነገር ላይኖር ይችላል፤ ነገር ግን ጭንቀቱ ስለሚቀንስላቸው እውነትም ነገሮች እየተስተካከሉ ይሄዳሉ'' ይላሉ። ሆንግ ኮንግ ውስጥ የሚኖረው የላውራ ዪፕ ቤተሰቦች የእነሱን ምክር ተቀብላ የ23 ዓመቷ ወጣት ስሟን ከቀየረች በኋላ ከሰዎች ጋር ያላት ግንኙነት መሻሻሉንና ነገሮች መቀየራቸውን ያምናሉ። ''መላው ቤተሰቤ ስሜን እንድቀይር ይፈልግ ነበር። አጎቴ ስሜን ከቀየርኩ በቶሎ ትዳር እንደምመሰርት የነገረኝ ሲሆን እናቴ ደግሞ ስሜን ከቀየርኩ እድሌ እንደሚሰምርልኝ ነገረችኝ። እኔም በዚህ ነገር አምናለሁ'' ላውራ ዪፕ በሕጋዊ መንገድ ስሟን ለመቀየር ቀላል የሚባል ወጪ አይደለም ያደረገቸው። 1 ሺ 930 ዶላር መክፈል ግድ ያላት ሲሆን የተቀየረውን ስሟን በአገሪቱ መዝገብ ላይ ለማስመዝገብ ደግሞ ተጨማሪ 500 ዶላር መክፈል ነበረባት። ይህ መጥፎ ነገር ሲያጋጥም ስምን የመቀየር ልምድ በቻይና ብቻ የሚታይ ነገር አይደለም። በአውሮፓውያኑ 2016 ላይ ደቡብ ኮሪያ ከፍተኛውን የስራ አጥ ቁጥር ባስመዘገበችበት ወቅት ብቻ 150 ሺ ሰዎች ስማቸውን ለመቀየር ጥያቄ አቅርበዋል። የሆንግ ኮንግ መንግስት ባወጣው መረጃ መሰረትም በርካታ ሰዎች ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት በኋላ ስማቸውን ለመቀየር ጥየቄ አቅርበዋል። በ2020 የመጀመሪያ ወራት ብቻ 1 ሺ 252 ሰዎች ስማቸውን ለመቀየር ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን በ2109 ደግሞ 1 ሺ 600 ሰዎች በተመሳሳይ ስማችንን መቀየር እንፈልጋለን ሲሉ ጥያቄ አቅርበዋል።
news-46450972
https://www.bbc.com/amharic/news-46450972
የአልበርት አንስታይን ደብዳቤ በ84 ሚሊዮን ብር ተሽጧል
አልበርት አንስታይን የከተበው ደብዳቤ ከግምቶች ሁሉ ልቆ በ2.9 ሚሊዮን ዶላር (84 ሚሊዮን ብር ገደማ) ሊሸጥ ችሏል።
በፈረንጆቹ 1954 ላይ የተጻፈው እና ''ጎድ ሌተር'' ተብሎ የሚታወቀው አንስታይን የጻፈው ደብዳቤ ኒውዮርክ ላይ በተካሄደው ጨረታ 1.5 ሚሊዮን ዶላር ያወጣል ተብሎ ተገምቶ ነበረ። በወቅቱ የ74 ዓመት የእድሜ ባለጸጋ የነበረው የኖቤል ሽልማት አሸናፊው አንስታይን ይህን ባለ አንድ ገጽ ከግማሽ ደብዳቤ የጻፈው ለጀርመናዊው ፈላስፋ ኤሪክ ጉትኪንድ ስራ ምላሽ በማለት ነበር። • አንስታይን ቻይኖችን "ቆሻሾች" ሲል ተሳድቧል ጽሑፉ በሃይማኖት እና ሳይንስ መካከል ስላለው ክርክር መሰረት ጥሎ ያለፈ ሃሳብ ነው ይባልለታል። ይህ ግልጽ እና ግላዊ ደብዳቤ የተጻፈው አንስታይን ከመሞቱ አንድ ዓመት ቀደም ብሎ የነበረው ሲሆን አንስታይን በሳይንስ እና ሃይማኖት ዙሪያ ያለውን አመለካከት በግልጽ ያሰፈረበት ተደርጎ ይወሰዳል። ደብዳቤው የተሸጠበት ዋጋ ከተጠበቀው በእጥፍ በልጦ ተገኝቷል። የአፍ መፍቻ ቋንቋው በሆነው በጀርመንኛ የተጻፈው ይህ ደብዳቤ በፈጣሪ ስለማመን ጉዳይ ያብራራል። ''ፈጣሪ ለእኔ ምንም ነው፤ የሰው ልጆች ድክመት መገለጫ እንጂ'' ሲል ጽፏል፤ ''መጽሐፍ ቅዱስ ማለት የቅዱሳን ስብስበ ነው፤ እኚህ ቅዱሳን ግን ጥንታዊያን ናቸው'' ሲልም ያክላል። ''ምንም አይነት ትርጓሜ ቢሰጠው፤ ምንም ያክል አሳማኝ ቢሆን፤ [ለእኔ] ስለ ጉዳዩ የሚለውጠው ነገር የለም'' በማለት ይቀጥላል። • የአይንስታይን ማስታወሻ በ1.6 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠ በራሱ አይሁዳዊ ማንነትም ላይም ''እንደ ሌሎች ሃይማኖቶች ሁሉ ጥንታዊ እና ፍርሃት ላይ የተመሠረተ እምነት ነው'' ሲል ጽፏል። የአንስታይን የእጅ ፅሁፍ ለጨረታ ሲቀርብ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። ባለፈው ዓመት አንስታይን ሊያገኘው ፍቃደኛ ላልሆነ ለአንድ ጣሊያናዊ የኬሚስትሪ ተማሪ የጻፈው ደብዳቤ 6100 ዶላር ተሽጧል። 2017 ላይ አንስታይን ደስተኛ ህይወት እንዴት መምራት እንደሚቻል ምክር የሰጠበት ጽሑፍ 1.56 ሚሊዮን ዶላር መሸጡም የሚዘነጋ አይደለም። በዚህ ደብዳቤ ላይ ''የተረጋጋ ህይወት መምራት ብዙ ደስታ ይሰጣል፤ ስኬትን ማሰስ ግን እረፍት ማጣት ነው" የሚል ምክር ጣል ያደርጋል። ያልተነገረላት
news-55899058
https://www.bbc.com/amharic/news-55899058
ዴሞክራቶች የትራምፕ ደጋፊ የሆኑትን ሴት ከኮንግረስ ለመፈንገል እያሴሩ ነው
በአሜሪካ ፖለቲካ ቁንጮ ከሆኑት ሁለት ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆኑት ዴሞክራቶች፤ የትራምፕ ደጋፊ የሆኑትን ሕግ አውጭ ከጨዋታ ውጭ ለማድረግ እየጣሩ ነው።
የሪፐብሊካን ፓርቲ አባል የሆኑት ወግ አጥባቂዋ ፖለቲከኛ በማሕበራዊ ድር አምባ ገፆቿ ላይ በጻፉት ጉዳይ ነው ከኃላፊነቷ ትነሳ እየተባለ ያለው። ማርጆሪ ታይለር ግሪን የተባሉት ሪፐብሊካን በሴራ ትንተና ያምናሉ። የመስከረም 9/11 የሽብር ጥቃት ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ነው ብለው ከሚያምኑ አሜሪካዊያን መካከልም አንዷ ናቸው። ጆርጂያ ግዛት ወኪል የሆኑት የኮንግረስ አባል ባለፈው ወር አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደንን ለመክሰስ ደፋ ቀና ሲሉ ነበር። ማርጆሪ ግሪን ባሳለፍነው ሰኞ በትዊተር ገጻቸው ላይ "ዴሞክራቶች ከተወከልኩበት ኮሚቴ ካባረሩኝ ቃል እገባላችኋለሁ እኛ በ2022 [በቀጣዩ የምክር ቤት ምርጫ] አብላጫ ድምፅ ስናገኝ አፀፋውን እጥፍ ድርብ አድርገን እንመልሳለን" ሲሉ ጽፈው ነበር። "አብላጫ ድምፅ ማግኘታችን የማይቀር ነው፤ እሱን እንዳትሳሳቱ" ሲሉም ዝተዋል። ባለፈው ኅዳር ወደ አሜሪካ ኮንግረስ የሚያስገባትን ድምፅ ያገኘችው ማርጆሪ በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የትምህርትና ሰው ኃይል እንዲሁም የበጀት ኮሚቴ አባል ሆነው ተመርጠዋል። የኮሚቴው አባል እንዲሆኑ የመረጧቸው በምክር ቤቱ የሪፐብሊካኖች መሪ የሆኑት ኬቪን ማካርቲ ናቸው። ዴሞክራቶቹ ለምን ሊያስወግዷቸው ፈለጉ? ዴሞክራቶች የትራምፕ ደጋፊ የሆኑት ግለሰብ ከዚህ በፊት የፈፀሟቸው ድርጊቶች የኮሚቴ አባል እንዲሆኑ የሚያደርጋቸው አይደለም ሲሉ ይከራከራሉ። በተለይ ደግሞ ከትምህርት ኮሚቴው እንዲፈነገሉ ነው ፍላጎታቸው። ሴትዬዋን ከኮሚቴው የመፈንገል ሂደቱን እየመሩ ያሉት ዴሞክራቷ ዴቢ ሹልትዝ "ሪፐብሊካኖች እሷን መተካት ካልቻሉ እኛ እንተካላቸዋለን" ሲሉ ተደምጠዋል። ትላንት [ሰኞ] በምክር ቤቱ አብላጫ ድምፅ ያላቸው ዴሞክራቶች መሪ የሆኑት ስቴኒ ሆዬር ለሪብሊካኖች መሪ 'ግለሰቧን ያውርዱልን' የሚል ጥሪ አቅርበዋል። ማርጆሪ ከኮሚቴዎቹ በ72 ሰዓታት ውስጥ ካልወረዱ ግን ዴሞክራቶች ይህንን ጉዳይ በራሳቸው እንደሚወጡ ዝተዋል። ዴሞክራቶች ግለሰቧ ከኮሚቴዎቹ ብቻ ሳይሆን በጠቅላላው ከኮንግረሱ እንዲባረሩ ይፈልፈጋሉ። ከወግ አጥባቂነታቸው አልፈው አክራሪ ሆነዋል ብለው የሚያምኑ ሪፐብሊካኖችም ጭምር ማርጆሪ ከኮንግረስ እንዲባረሩ ጥሪ እያቀረቡ ነው። በሴኔቱ አናሳ ድምፅ ያላቸው ሪብሊካኖች መሪ የሆኑት ሚች ማኮኔል ሴትዬዋ የምታምንባቸውን የሴራ ትንተናዎች 'ለሪብሊካን ፓርቲ ካንሰር ናቸው' ሲሉ ወርፈዋል። በፈረንጆቹ 2019 በኮንግረሱ የአዮዋ ግዛት ተወካይ የሆኑት ሰው በአንድ ቃለ መጠይቅ ወቅት የነጭ የበላይነትን አጣጥለው አስተያየት በመስጠታቸው ከሁለት ኮሚቴዎች መወገዳቸው አይዘነጋም። ነገር ግን ሪፐብሊካኖች አሁንም በፖርቲ አጋራቸው ላይ ይህን ዓይነት እርምጃ ይወስዳሉ ወይ የሚለው እርግጥ አይደለም። አንድ የኮንግረስ አባልን ከኮንግረሱ ሙሉ በሙሉ ለማስወገድ ሁለት ሶስተኛ ድምፅ ያሻል። በአሜሪካ ታሪክ ከኮንግረስ አባልነታቸው የተወገዱ ሰዎች ቁጥር አምስት ብቻ ነው። ማርጆሪ የኮንግረስ አባል ሆነው አነጋጋሪ አስተያየት የሰጡ የመጀመሪያዋ ሴት አይደሉም። በ2019 የሚኒሶታዋ ኢልሃን ኦማር ፀረ-አይሁድ ናቸው ተብለው በተፈረጁ አስተያየታቸው ምክንያት ብዙ ትችት ደርሶባቸው ነበር። በወቅቱ ኢልሃን ለሰጡት አስተያየት ይቅርታ ጠይቀው ነበር። የትራምፕ ቀንደኛ ደጋፊዋ ማርጆሪ ግሪን ግን በተደጋጋሚ አነጋጋሪ አስተያየት ከመስጠት ባለፈው በይፋ የሴራ ትንተና አማኝ መሆናቸው ነው ለየት የሚያደርጋቸው። ማርጆሪ፤ በ2016 የአሜሪካ ምርጫ የትራምፕ ተፎካካሪ የሆኑት ሂላሪ ክሊንተን ሕፅናትን ይገርዛሉ ብለው ያምናሉ። አልፎም በፈረንጆቹ 2001 የደረሰው የ9/11 አደጋ የአሜሪካ መንግሥት ሴራ ነው ብለው ነው የሚያምኑት። ይህም አልበቃ ብሏቸው ካሊፎርኒያ ውስጥ የተከሰተው የሰደድ እሳት ሆን ተብሎ ከሕዋ ላይ በተለቀቀ ጨረር የተነሳ ነው ይላሉ። በአንድ ወቅት 'ጥቁሮች የዴሞክራቲክ ፓርቲ ባሪያዎች ናቸው'፤ ነጭ ወንዶች ደግሞ አሜሪካ ውስጥ በጣም በደል የሚደርስባቸው ናቸው ሲሉ አስተያየት ሰጥተው ነበር።
news-45936975
https://www.bbc.com/amharic/news-45936975
በአሜሪካ ኢንዲያናፖሊስ አንበሳዋ የሶስት ልጆቿን አባት ገደለችው
አንበሳዋ የሶስት ልጆቿን አባት በመካነ አራዊት ውስጥ እንደገደለችው የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
ዙሪ የምትሰኘውና በነፍስ ግድያ የተጠረጠረችው 10 ዓመቷ ሲሆን የልጆቿ አባት ኒያክ ደግሞ የ10 ዓመት ጎረምሳ ነው። ከመሞቱ በፊት የመካነ አራዊቱ ባለስልጣናት ሊለያይዋቸው ባለመቻላቸው ታፍኖ መሞቱ ተዘግቧል። • ዛሚ ሬዲዮ ሊዘጋ ይሆን? እነዚህ ሁለት አንበሶች በአንድ ጣሪያ ስር ለስምንት ዓመታት አብረው በፍቅር የኖሩ ሲሆን እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2015 ዓ.ም 3 ደቦሎችን አፍርተዋል። የመካነ አራዊቱ ባልደረቦች በድርጅቱ ፌስቡክ ገፅ ላይ እንዳስቀመጡት በትክክል ምን እንደተፈጠረ "ጥልቅ ምርመራ" እናካሂዳለን ብለዋል። "ኒያክ ግርማ ሞገሱ የሚያስደምም አንበሳ ነበር፤ በእጅጉ ሞቱ ልብ ሰባሪ ነው" ሲሉም አክለዋል። የመካነ አራዊቱ ሰራተኞች ባልተለመደ መልኩ ከአናብስቱ መኖሪያ ማጓራት መስማታቸውንና በፍጥነት ወደስፍራው ማምራታቸውን ያስታውሳሉ። ሲደርሱም ዙሪ የኒያክን አንገት ጨምድዳ ይዛ የነበረ ሲሆን ሊያስለቅቋት በሞከሩ ቁጥር መንቀሳቀስ እስኪያቆም ድረስ ሳትለቀው መቆየቷን ተናግረዋል። • መስመር ያልያዘው የኢትዮ-ኤርትራ የንግድ ግንኙነት ወዴት ያመራል? • ሞባይል ስልክዎ ላይ መከራን አይጫኑ ከዚህ በፊት በሁለቱ መካከል እንዲህ ኃይል የተቀላቀለበት ተግባር አስተውለው እንደማያውቁ የተናገሩት ሰራተኞቹ " ከአንበሳው ጋር የተለየ ቅርበት ነበረን፤ በሞቱ እጅጉን አዝነናል" ብለዋል። የኢንዲያና ፖሊስ መካነ አራዊት ሃላፊ በበኩሉ "ለበርካቶቻችን እንደቤተሰብ ነበር" በማለት በመካነ አራዊቱ የሚገኙ አንበሶች አኗኗር ላይ ምንም አይነት ነገር ለመቀየር እቅድ እንደሌለ ጨምረው ገልፀዋል።
43722244
https://www.bbc.com/amharic/43722244
ዲግሪ ከማግኘትም በፊት ራስን ማግኘት
እኛ ወጣቶች ዲግሪ እንድንጭን የበዛ ጫና ነው ያለብን። ያውም ራስን እስከማጥፋት የሚያደርስ
አውቃለሁ፤ ይህን ጉዳይ ኅብረተሰቡ እንደዋዛ ሊመለከተው እንደሚችል፤ እውነታው ግን ይኸው ነው። ቤን እባላለሁ።ራሴን ለማጥፋት ስንት ጊዜ እንዳሰብኩ ብነግራችሁ አታምኑኝም። ከልጅነቴ ጀምሮ ጭምት ነበርኩ። ዩኒቨርስቲ ስገባ ግን ነገሮቹ እየከፉ መጡ። ከሰው አልቀርብ፤ አልጫወት፥ አላጠና ትዝ ይለኛል መጀመርያ የተመደብኩበት ዩኒቨርስቲ ስደርስ፤ በሕዝብ አውቶቡስ ነበር የሄድኩት። ሌሎች ዘናጭ ተማሪዎች ግን በወላጆቻቸው በልዩ ክብካቤ፤ እንደ እንቁላል ተይዘው፤ በውል ውል የግል አውቶሞቢል፤ መዓት ሻንጣዎቻቸው ተጭኖላቸው ነበር የመጡት። እውነት ለመናገር የማየው ነገር ሁሉ እኔን ወደ መገለል ስሜት የሚከት ነበር። ቢጤዎቼን ለመምሰል ሩቅ ነበርኩ፤ የኔ ቤተሰቦች ከሰራተኛው መደብ ናቸው።ከወላጆቼ የሚደረግልኝ ድጋፍ ምንም ነበር። ኮርሶቼን መልክ አስይዞ በመረዳት ረገድ ነገሮች እንዳሰብኩት ቀላል አልሆኑልኝም። ሁሉም ነገር ለኔ ባዕድ ነበር። ብዙዎቹ ተማሪዎች እገዛን ሲሹ የሚያማክሩት የሆነ የቅርብ ሰው ነበራቸው፡።እኔ ግን በአመዛኙ ባይተዋር ሆኜ ነው የቆየሁት። አባቴ እንደሆነ ስለ ዩኒቨርስቲ ብዙም የሚያውቀው ነገር አልነበረውም። ድሮ ነው ትምህርት አቋርጦ ወታደር ቤት የገባው።እናትና አባቴ የተለያዩት ደግሞ ገና የ16 ዓመት ወጣት ሳለሁ ነበር። ከአባቴ ጋር ስኖር መልካም የሚባል ግንኙነት ነበረን ለማለት ይከብዳል።አንደኛ ሰካራም የሚባል ዓይነት ሰው ነው። ከፍተኛ የመጠጥ ሱስ ነው ያለበት። በዚያ ላይ ሞገደኛ የሚባል ዓይነት ነው። ምንም ልንግባባ አልቻልንም። መጀመርያ ዩኒቨርስቲ ስመደብ አባቴን ተገላገልኩት ብዬ ነበር። ⷎኖም ዩኒቨርስቲም የኔ የምለው ቦታ ሆኖ አላገኘሁትም። በፍፁም! ገና ዶርም እንደገባሁ እርኩስ ሐሳቦች አእምሮዬን ጨምድደው መያዝ ጀመሩ። ገና እኮ 6 ወርም አልሆነኝም። የፍቅር ግንኙነትም ጀምሬ ነበር። እንዲያ ከተባለ፤ እውነት ለመናገር ፍቅር ሳይሆን ጭቅጭቅና አለመግባባት የሞላው ነበር። ያን ሰሞን ትክክል አልነበርኩም። ስንለያይ ጊዜ ከአዲሱ ፍቅረኛዋ ጋር ተደባደብኩ። በፍፁም ትክክል አልነበርኩም። ይባስ ብሎ አብዝቼ መጠጣትና ክላስ መቅጣት ጀመርኩ። ሰካራምነቴ በመላው ዩኒቨርስቲ በመታወቁ የስነልቦና ባለሞያ እንድጎበኝ ተደረገ።ለእርዳታው ብዙም ዝግጁ አልነበርኩም። ለሚጠይቁኝ ጥያቄ ሁሉ አሉታዊ መልስ ነበር የምሰጣቸው። ብቻ አንድ ሴሚስተር እንዲሁ አለፈ። አንድም ፈተና አላለፍኩም ብላችሁ አታምኑኝም። ወደ ቤት መመለስ አሳፋሪ ነበር። ለአባቴ ምን ብዬ እንደምነግረው ግራ ገባኝ። ወደ ዩኒቨርስቲ እንደማልመለስ ሳልነግረው ሁለት ወራት አለፉ። እሱም ለነገሩ በቀን በቀን ነው የሚሰክረው። እኔም ክፍሌ ውስጥ ቆልፌ ነበር አብዛኛውን ሰዓት የማሳልፈው። ድንገት አዲስ ሐሳብ ተከሰተልኝ። እንዴት እስከዛሬ ሳላስበው ቀረሁ! ራስን ስለማጥፋት! ቤት የነበረ መዓት መድኃኒት መዋጥ ጀመርኩ።ከአንድ ሰዓት በኋላ ግን ምንድነው እያደረኩ የነበረው ብዬ ራሴን መጠየቅ ጀመርኩ። በአንቡላንስ ወደ ሆስፒታል ሄድኩኝ። ምን ብዬ ነው ለሐኪሞቹ የምነግራቸው? ግራ ገባኝ። የሆነ ዓይነት ከባድ ቅጣት እንደሚጥሉብኝ ስለተሰማኝ ከፍተኛ የራስ ውዝግብ ውስጥ ገባሁ። አታምኑኝም፤ ተሳፍሬ ወደ ቤት ተመለስኩ። ጭንቅላቴን ይደቃኛል።ነገሮች ድብልቅልቅ አሉብኝ። ደግነቱ አባቴ ቤት አልነበረም። ገብቼ ተኛሁ። ሆኖም ታመምኩ። ሌሊቱን ሙሉ እንዲሁ ታምሜ አደርኩ። እንደዚያም ሆኜ ስለሆነው ነገር ለማንም ትንፍሽ አላልኩም። እንደነገርኳችሁ ጭምት ሰው ነበርኩ፡። ለምን እንደሆን አላውቅም ከሌሎች ሰዎች እርዳታን መጠየቅ በፍርሃት የሚያንዘፈዝፈኝ ጉዳይ ሆኖ ነው የሚሰማኝ። እርዳታን ብጠይቅ ኖሮ ምናልባት ነገሮች እንዲህ አይከፉም ነበር። ራስን የማጥፋት ሐሳብ ሲፀናወት ነገሮችን በምክንያት አናስብም። የሆነ ግዙፍ እኩይ ስሜት እላያችሁ ላይ ይሰፍርና ሙሉ በሙሉ ይቆጣጠራችኋል።ለምሳሌ እኔ ከዚህ መንፈስ ለመላቀቅ ያልሞከርኩት ነገር፤ ያልፈነቀልኩት ድንጋይ አልነበረም። ወታደር ሆኖ ከመዝመት ጀምሮ ከባድ ወንጀል ሰርቶ በገዛ ፈቃድ እስር ቤት እስከመግባት ያለውን አማራጭ ሁሉ አስቤያለሁ። በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለሁ ክረምቱ መጨረሻ ላይ ከዩኒቨርስቲዬ ደብዳቤ ደረሰኝ። የደብዳቤው ይዘት ሁሉንም ፈተና ስለወደቅኩ ወደ ዩኒቨርስቲው በር ድርሽ እንዳልል የሚያትት ነበር። ስለሁኔታው አባቴን መንገር ነበረብኝ። እውነት ለመናገር አባዬ እንዲህ ዓይነት ነገር ለማውራት የሚመች ዓይነት ሰው አልነበረም። ሞገደኛ ነው ብያችሁ የለ! እንደፈራሁት አልሆነም። ስነግረው ሥራ ፈልጌ ማግኘት እንዳለብኝ ነገረኘ። ለአምስት ወራት እግሬ እስኪቀጥን ሥራ ፈለኩ። አልተሳካም። በድጋሚ ጥልቅ ድብታ ውስጥ ተዘፈቅኩ። ቤት ተዘፍዝፎ መዋል ሆነ ሥራዬ። ማኅበረሰቡን በሙሉ ጠምጄ ያዝኩት። ሰው ጠላሁ። ራሴን ጠላሁ። አካባቢዬን ጠላሁ። ዓለምን ጥምድ አድርጌ ያዝኳት። እንደኔው ዓለም ጀርባዋን የሰጠችው ጓደኛ አገኘሁ። ሁለታችንም በአገራችንና በኑሯችን የተሰላቸን ሰዎች ስለነበርን ለመግባባት ጊዜ አልወሰደብንም። ከአገር ለመሰደድ ወሰንን። ወደ ቡዳፔስት ጠፋን። ለአባቴ ግን ለሁለት ሳምንት ሽርሽር እየሄድኩ እንደሆነ ብቻ ነበር የነገርኩት። ለአንድ ዓመት አልተመለስኩም። አባቴ ሲጨንቀው ለፖሊስ ሪፖርት አድርጎ ኖሮ ከፖሊስ ጣቢያ የስልክ ጥሪ ደረሰኝ። ደህና እንደሆንኩና ከአባቴ ጋር ለማውራት ግን በፍፁም ፍቃደኛ እንዳልሆንኩ ነግሪያቸው ስልኬን ዘጋሁት። ወደ ቡዳቤስት የሄድነው እቅድ ኖሮን ሳይሆን በአቦሰጥ ነበር። ምን እንደምንሠራ እንኳ መረጃው አልነበረንም። ከቡዳፔስት ግሪክ፤ ከግሪክ ቱርክ፤ ከቱርክ የባልካን አገሮችን በሙሉ አዳረስን። ስፔንና ሞሮኮ ሁሉ አልቀሩንም። ምግብ ከሰው ቤት እየለመንን፤ መጓጓዣ ከመኪና ኋላ እየተንጠላጠልን ነበር ከአገር አገር የምንሄደው። በርግጥ ጉዞው ከገባሁበት ጥልቅ ድብታ መንጭቆ ባያወጣኝም ራስን ስለማጥፋት የማስበውን ነገር ቀንሶልኝ ነበር። አንደኛ ከኔ በባሰ አስቸጋሪ ሕይወት የሚኖሩ ሰዎች በሁሉም ሥፍራ እንደሚገኙ እንድረዳ አድርጎኛል፤ ሁለተኛ ደግሞ ከግል ፍርሃቴ ወጥቼ ከዓለም ጋር ለመጋፈጥ መንገድ ከፍቶልኛል። ወደ አገሬ ስመለስ ነገሮች እንዲለወጡ በፅኑ ፍላጎት አሳድሬ ነበር። በተለይም ሥራ ለማግኘት ቁርጠኛ ነበርኩ። ደግሞም ተሳካልኝ። 27 ዓመት ሲሞላኝ ሕይወቴ ቀስ በቀስ መልክ መያዝ ጀመረ። ሥራ አገኘሁ፤ ሚስት አገባሁ፤ ልጅ ወለድኩ። ከቤተሰባችን ይሁን ከአስተዳደጌ አላውቅም ብቻ ችግሬን ወደ ውስጥ እንጂ ለሌሎች የማጋራት ነገር አላውቅም። ማንኛውንም ጭንቀቴን በራሴው አፍኜ መቀመጤ በብዙ ጎድቶኛል። እንደኔው በብቸኝነት መቀመጤ ሳይጎዳኝ አልቀረም። ለረዥም ጊዜ ያህል ከዩኒቨርስቲ መባረር የዓለም መጨረሻ እንደሆነ አስቤ ነበር። ልክ እንዳልነበረ ያወቅኩት ግን ዘግይቼ ነው። ዋናው ነገር ራስን ተረድቶ የሰዎች እርዳታ በሚያስፈልግ ጊዜ ሁሉ ያን መሻት ነው። የዩኒቨርስቲ ዲግሪን መጫን የሞት ሽረት ጉዳይ መሆኑ መልካም ነገር አይመስለኝም። በዚህ ረገድ ማኅበረሰቡ የማይታይና የማይዳሰስ ጫናን ነው በወጣቶች ላይ የሚፈጥረው። በኔ ሕይወት የተረዳሁት ግን ዲግሪን አናታችን ላይ ከመጫንም በፊት ጤናማ ጭንቅላት እንዲኖረን ማስፈለጉን ነው።
53963765
https://www.bbc.com/amharic/53963765
ትራምፕ 7 ጥይት የተተኮሰበትን ጥቁሩን ጃኮብ ሆስፒታል ሄደው ሊጠይቁት ይሆን?
የአሜሪካውን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ ዊስኮንሰን ግዛት የምትገኘውን ኬኖሻ ከተማን ሊጎበኙ ነው፡፡
ባለፈው ሳምንት ጆኮብ ብሌክ የተባለ ወጣት ጥቁር በ7 ጥይት በፖሊስ ከፍተኛ ጥቃት ከደረሰበት በኋላ በኬኖሻ ከፍተኛ ቁጣ ተቀስቅሷል፡፡ ትራምፕ ወደ ኬኖሻ የሚሄዱት ከነገ በስቲያ ማክሰኞ እንደሆነ ዋይት ሐውስ ይፋ አድርጓል፡፡ ትራምፕ እዚያ ሄደው ምን እንደሚያደርጉ በዝርዝር ባይገለጽም ከጸጥታ አስከባሪ አካላት ጋር ይነጋገራሉ፤ የደረሰውን ጉዳት ይገመግማሉ ተብሏል፡፡ ጥቁሩ ጃኮብ ብሌክ 7 ጥይት በጀርባው ተተኩሶበት በሕይወት መትረፉ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ አከርካሪው ላይ አንዲት ጥይት በመሰንቀሯ ህብለሰረሰሩ ተጎድቷል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በኋላ ቆሞ መራመድ አይችልም ተብሏል፡፡ የጃኮብ ጉዳትን የሚያሳየው ቪዲዮ ማኅበራዊ ድራምባው ከተጋራ በኋላ በበርካታ የአሜሪካ ከተሞች ተቃውሞ ተቀስቅሷል፡፡ በኬኖሻ ዊስኮንሰን የነበረው ተቃውሞ ግን በዝርፍያና በነውጥ የታጀበ ሲሆን የሰዎች ሕይወትም ጠፍቷል እየተባለ ነው፡፡ በርካታ መኪናዎችም ወድመዋል፣ ሱቆች ተዘርፈዋል፤ በእሳት ተያይዘዋል፡፡ ባለፈው ግንቦት ወር በሜኔሶታ፣ ሚኒያፖሊስ ከተማ ጆርጅ ፍሎይድ የተባለ አንድ ጥቁር በነጭ ፖሊስ ማጅራቱ ተቆልፎ እንዲሞት ከሆነ በኋላ የጥቁሮች የመብት እንቅስቃሴ በመላው ዓለም እየተፋፋመ ይገኛል፡፡ ዶናልድ ትራምፕ ጃኮንብ ይጎበኙታል? ፕሬዝዳንቱ በጉብኝታቸው ጃኮብን ይጎበኙት ይሆን የሚለው በጉጉት እየተጠበቀ ነው፡፡ አሁን ለጊዜው የታወቀው የከተማዋን ፖሊስ እንደሚያነጋግሩና በነውጡ የደረሰውን የጉዳት መጠን እንደሚብራራለቸው ነው፡፡ ይህን የተናገሩት የዋይት ሐውስ ቃል አቀባይ ጁድ ዲር ናቸው፡፡ ፕሬዝዳንቱ የጥቃቱን ሰለባ የሆነውን ጃኮብ ብሌክንና ቤተሰቦቹን ይጎበኛሉ ወይ በሚል ለቃል አቀባዩ ጥያቄ ቀርቦላቸው የነበረ ሲሆን ይህን ለመናገር ገና ዝርዝር የጉብኝት እቅድ መረጃ ያስፈልገኛል ብለዋል፡፡ ዶናልድ ትራምፕ በጥቁሮች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን በግልጽ ሲኮንኑ ብዙም አይሰሙም፡፡ እሁድ ለታ በጃኮብ ብሌክ የደረሰውን ጥቃትም በቀጥታ አላወገዙም፡፡ በጃኮብ ላይ የተኮሰው ፖሊስ መከሰስ አለበት ወይ በሚል አርብ ዕለት አንዲት ጋዜጠኛ ጥያቄ አቅርባላቸው ነበር፡፡ ‹‹ ገና ሪፖርት አልቀረበልኝም፤ ነገሩን ማጤን አለብኝ፡ ቪዲዮውን አይቼው ግን አልወደድኩትም›› ብለዋል፡፡ ትራምፕ በመጪው ኅዳር በሚጠብቃቸው ምርጫ ‹‹ሥርዓት ማስከበርን› እንደ አጀንዳ ይዘው እንደሚሰሩበት ተናግረዋል፡፡ ‹ዲሞክራቶች በሚበዙባቸው ከተሞች ሥርዓት አልበኝነት ነግሷል፣ ዙርፊያ ተጧጡፏል፣ ፖሊሶች እየተጎዱ ነው ፤ ስለዚህ ይህን ጋጠወጥ ሁላ ልክ አስገባዋለሁ› ብለው ሲዝቱም ነበር፣ በምረጡኝ ቅስቀሳ ወቅት፡፡ ከምርጫ ጋር በተያያዘ ዊስኮንሰን ግዛት ‹ወላዋይ› ከሚባሉ ግዛቶች አንዷ ናት፡፡ ግዛቷ ቀድሞ ባራክ ኦባማ ያሸነፉባት በመሆኑ የዲሞክራቶች ግዛት ብትመስልም ትራምፕ በ2016 በ20ሺ ድምጽ ብልጫ ሂላሪን ማሸነፋቸው ደግሞ ወላዋይነቷን የሚያሳይ ነው፡፡ በኬኖሻ ከአንድ ሺ በላይ ሰልፈኞች ‹የጥቁር ነፍስ ዋጋው ስንት ነው?› በሚል ቅዳሜ ሰልፍ ወጥተዋል፡፡ የጃኮብ አባት ሰልፈኞች ከነውጥ፣ ከጥቃትና ካያልተገባ ድርጊት ራሳቸውን እንዲያቅቡ አደራ ብለዋል፡፡ በኬኖሻ ከ1ሺ በላይ የብሔራዊ ጥበቃ ልዩ ኃይል እንዲገባ ተደርጓል፡፡ ብዙዎቹ ታዲያ ከሌላ ግዛት የመጡ የልዩ ጥበቃ አባላት ናቸው፡፡
news-55459259
https://www.bbc.com/amharic/news-55459259
ግብርና፡ አርሶ አደሮችን በሳተላይት የምታግዘው ኡጋንዳዊቷ የናሳ ሳይንቲስት
ለባድሚንተን ስፖርት ፍቅር ያላት ኡጋንዳዊቷ ካትሪን ናካሌምቤ ፍላጎቷ ዩኒቨርሲቲ ገብቶ የስፖርት ሳይንስ ማጥናት ነበር።
ነገር ግን የሚያስፈልገውን የመመዘኛ ነጥብ ባለማሟላቷ ምክንያት ይህን ማድረግ አልቻለችም። ቢሆንም የትምህርት ጉዞዋ በዚህ አልተቋጨም። አሁን በምድራችን ቀዳሚ ከሚባሉት የህዋ ምርምር ተቋማት አንዱ በሆነው የአሜሪካው ናሳ ውስጥ ሳይንቲስት ናት። ዶክተር ካትሪን በሰሜን ምሥራቅ ኡጋንዳ ውስጥ በምትገኘው ካራሞጆንግ በሚባለው አካባቢ ለሚኖሩ አርሶ አደሮች "የሳተላይት ምስል ተጠቅሜ የናንተን ግብርና ማሳደግ እችላለሁ" ስትላቸው ሳቅ ቀድሟቸው ነበር። ሳይንቲስቷ ከሳተላይት የተገኙ ጥራታቸው ከፍ ያሉ ምስሎችን ተጠቅማ አርሶ አደሮችንና መንግሥትን ማገዝ ነው ሕልሟ። ነገር ግን ይህን ለማድረግ አርሶ አደሮቹ ወደሚኖሩበት የገጠሩ ክፍል በመሄድ ማሳቸው ውስጥ መገኘት ግድ ይላታል። በሌላ አነጋገር ከህዋ ላይ በሚገኘው መረጃ ብቻ ሳርን፣ ከገብስ ወይም ከበቆሎ መለየት አይቻልምና። "አንዱን ገበሬ ያለኝን ምስል ሳየው አረንጓዴ ነገር እንጂ በውል ምን እንደሆነ መለየት አልቻልኩም ብዬ በአስተርጓሚ ነገርኩት" ትላለች። "አትሜ ያመጣሁትን ምስል ሳሳየው ገባውና 'ነይ ማሳየን ላሳይሽ' አለኝ" ስትል ለቢቢሲ ትናገራለች። አብዛኛዎቹ ገብሬዎች በአነስተኛ ማሳዎች ላይ ብቻ ወቅት ጠብቀው ነው የሚፈልጉት ሰብል የሚያመርቱት። በአሜሪካው ሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ የጂኦግራፊ ሳይንስ ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር የሆነችው ካትሪን (ዶ/ር) የሳተላይት ምስል ተጠቅማ ግብርና እና የአየር ንብረት ለውጥን ታጠናለች። ከሳተላይት የሚገኘው ምስል መሬት ካለው መረጃ ጋር ተዳምሮ የሰብሎችን ቀመር የሚያጠና ቴክኖሊጂ ለመሥራት ይውላል። ካትሪን (ዶ/ር) በዚህ ሥራዋ ነው እየተጠናቀቀ ባለው የ2020 'የአፍሪካ ፉድ ፕራይዝ' ሽልማትን ከቡርኪናፋሶው አንድሬ ባቲዮኖ (ዶ/ር) ጋር የተጋራችው። ካትሪን (ዶ/ር) በአሁኑ ጊዜ ናሳ ውስጥ የአፍሪካ ምግብና ግብርና ፕሮግራም ኃላፊ ናት። "ከሰማይ ላይ የትኛው አካባቢ የተገነባ እንደሆነ፣ የትኛው ደረቅ፣ ወይም ውሃ ያለው እንደሆነ መለየት ይቻላል" ትላለች ሳይንቲስቷ። "አልፎም የትኛው ቦታ ለሰብል የሚሆን መሬት ነው፤ ጫካ የሆነውስ የቱ ነው የሚለውን መለየት ችለናል። የ30 ዓመት ሰብል የማምረት ልምድ ስላለን የትኛው ጤናማ መሬት እንደሆነ የትኛው ደግሞ ሊሻሻል እንደሚገባው አውቀናል።" ካትሪን (ዶ/ር) አርሶ አደሮች ስለሰብላቸው መረጃን በሞባይል እንዲት መላክ እንደሚችሉ ስታሰለጥን መፍትሄ ለአርሶ አደሮች አጥኚዎች ከመሬት የሚያገኙትን ወይም አርሶ አደሮች የሚልኳቸውን መረጃዎች በመጠቀም ሳይንቲስቷ ካርታ ታዘጋጃለች። ካርታው የገበሬዎቹ ሰበል ከሌሎች አካባቢዎች ጋር ሲነፃፀር እያደገ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ለመለየት ያስችላል። ይህ መንገድ አሜሪካ ውስጥ ለትላልቅ በዘመናዊ የግብርና መሳሪያዎች ለሚካሄዱ እርሻ ሥራዎች ጥቅም ላይ ይውላል። መረጃው መቼ ሰብል መመረት እንዳለበትና መሬቱ ምን ያህል ዝግጁ እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ይህ መረጃ አነስተኛ ማሳ ላላቸው ኡጋንዳ ውስጥ ላሉ ወይም ለሌሎች የአህጉሪቱ አርሶ አደሮች እጅግ ጠቃሚ ነው። "ለምሳሌ በሚቀጥሉ ቀናት ዝናብ እንደሚዘንብ እርግጠኛ ከሆንን አርሶ አደሮች ማሳቸውን እንዲያዘጋጁ እንነግራቸዋለን። ዝናብ ከሌለም ጊዜያቸውን እንዲሁ እንዳያባክኑ እናስረዳቸዋለን።" በአፍሪካ አብዛኛዎቹ የእርሻ ማሳዎች ቁራሽ መሬት ናቸው። ሰብል ማምረትን በተመለከተም ይህን ያህል መረጃ የለም። ነገር ግን ከሳተላይት የሚገኘው መረጃ ወደ አካባቢው ቋንቋ ተተርጉሞ በስልክ የፅሁፍ መልዕክት፣ ወይም በሬዲዮ፣ አሊያም በግብርና ሠራተኞች አማካይነት ሊተላለፍ ይችላል። አልፎም መንግሥታት ይህንን መረጃ ተጠቅመው ተፈጥሯዊ አደጋ በሚመጣ ጊዜ ማኅበረሰቡ ከድርቅ እንዲጠበቅ አስፈላጊውን ሊያደርጉ ይችላሉ። አስካሁንም የካትሪን (ዶ/ር) ጥናት በካራሞጃ የሚኖሩ 84 ሺህ ገበሬዎች በአየር ለውጥ ሳቢያ በሚመጣ የዝናብ እጥረት እንዳይጎዱ መታደግ ችሏል። በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ሰብል ለሚያመርቱ ኡጋንዳውያን አርሶ አደሮች የሳይንቲስቷ ጥናት መፍትሄ ይዞ መጥቷል። ዝናብ በማይኖርበት ወቅት አርሶ አደሮች ትኩረታቸውን ወደ ሌላ ሥራ እንዲያደርጉና ቤተሰቦቻቸውን እንዲያግዙ ይደረጋል። ካትሪን (ዶ/ር) ለሥራዋ የተበረከተላት ያልጠበቀችው ሽልማት በድንገት የመጣ ሳይንቲስትነት ካትሪን (ዶ/ር) ከሜካኒክ አባቷና ምግብ ቤት ከምታስዳድረው እናቷ የተወለደችው በኡጋንዳዋ ዋና ከተማ ካምፓላ ነው። "ሥራዬ ከሳተላይት ጋር የተገናኘ ይሆናል ብዬ አንድም ቀን አስቤ አላውቅም" ትላለች። ከእህቶቿ ጋር ባድሚንተን መጫወት ታዘወትር ነበር። ሕልሟም በስፖርት ሳይንስ ዲግሪ መጫን ነበር። ነገር ግን ያለሽ ውጤት በታዋቂው የማኬሬሬ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ ክፍል ለመግባትና ለመማር አይበቃም ስትባል ወደ ኢንቫይሮንሜንታል [የአካባቢ] ሳይንስ ክፍል አቀናች። ትምህርቷን ለመማር ያግዛት ዘንድ ለኡጋንዳ ዱር እንስሳት ባለሥልጣን ለመሥራት አመለከተች። ካርታ ማጥናት እወድ ነበር የምትለው ካትሪን ለመጀመሪያ ጊዜ ካርታ ለማጥናት ተራራ ላይ ወጥታ የተሰማትን ሐሴት አትዘነጋውም። አሁን በአፍሪካ የተለያዩ አገራት ውስጥ እየተዘዋወረች ለመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ስለ ምግብ ዋስትና ምክር የምትለግሰው ካትሪን በወቅቱ የማስተርስ ድግሪዋን ለመማር ለጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ማመልከቻ አስገባችና እድሉን አገኘች። ሁለተኛ ዲግሪዋን እንደጨረሰች ደግሞ የዶክትሬት ድግሪዋን ለመከታተል እዚያው አሜሪካ ሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ ገባች። ሳይንቲስቷ ካትሪን (ዶ/ር) የእራሷን ተሞክሮ መሰረት አድርጋ ወጣት ጥቁር ሴቶች ወደ አካባቢ ሳይንስ ጥናት እንዲገቡ ምክር ትለግሳለች። የ2020 የአፍሪካ 'ፉድ ፕራይዝ' ሽልማት አሸናፊ ስትሆን የተሰማትን ደስታ መደበቅ አትችልም። ስልክ ተደውሎላት "የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝደንት ኦሌሴጉን ኦባሳንጆ ይፈልጉሻል፤ መሥመር ላይ ጠብቂ" ስትባል የአጭበርባሪዎች ስልት ይሆን ብላ ጠርጥራም ነበር። "አስቡት እስቲ፤ አሁን እኔ የዊኪፔዲያ ገፅ አለኝ።" አሁን አሁን ራሴን ለሰዎች ሳስተዋውቅ 'የ2020 የአፍሪካ ፉድ ፕራይዝ አሸናፊ ነኝ' ማለት ማስታወስ አለብኝ" ትላለች በፈገግታ። "አምስት ኪሎ ግራም የሚመዝን ሽልማት ተሰጥቶኛል። በሕልሜ እንዳልሆነ ማረጋገጫው ይሄ ነው።"
45243823
https://www.bbc.com/amharic/45243823
የጅግጅጋ ተፈናቃዮች በአዲስ አበባ ጎዳና ላይ ወድቀዋል
ከሁለት ሳምንታት በፊት በሶማሌ ክልል በተከሰተው ግጭት ጥቃት የደረሰባቸው ስደተኞች በአዲስ አበባ ስታዲየም አካባቢ ኦሮሚያ የባህል ማዕከል ፊት ለፊት ተጠልለዋል።
እስከመቶ የሚደርሱት እነዚህ ስደተኞች በዚሁ ጎዳና ላይ በሸራ በተከለለችው ስፍራ ከማረፍ ውጪ ምንም አይነት አማራጭ እንደሌላቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከስድስት ወር ህጻን ጀምሮ ሴቶች፤ አዛውንቶችና በጥቃቱ ድብደባ የደረሰባቸው ደካሞች ለአራት ቀናት በዚሁ ቦታ ላይ እየዋሉም እያደሩም ነው። ቤት ንብረታቸውም ሙሉ በሙሉ በጥቃቱ በመውደሙ የሚለበስም ሆነ እንዲህ ላሉ ክፉ ቀን የሚሆን ጥሪት አለመቋጠራቸውን ተናግረዋል። •በሶማሌ ክልል በተከሰተ ቀውስ ህይወት ሲጠፋ አብያተ-ክርስትያናት ተቃጠሉ •አብዲ ሞሃመድ ኡመር በቁጥጥር ስር ዋሉ •የጠቅላይ ሚኒስትሩ የጅግጅጋ ጉብኝት ፋይዳ እስካሁን የዕለት ጉርሳቸውንም እዛው አካባቢው ያሉ ወጣቶች ከመንገደኞች እየሰበሰቡ ከሚያቀርቡላቸው ምግብ እያገኙ ቢሆንም ከዚህ ውጭ ምንም አይነት የመንግስት ድጋፍ አለማግኘታቸውን ገልጸዋል። በዓመቱ መጀመሪያ በተመሳሳይ ጥቃት ሙሉ ቤተሰቡን እንዳጣ የሚናገረው አደም አህመድ በጅጅጋ 03 በሚባለው አካባቢ ነበር ኑሮውን ያደረገው። አሁን ሁኔታዎች ተቀይረው ሥምምነት ተፈጥሯል መባሉን ተከትሎ ወደጅግጅጋ ከተመለሰ ሰባት ወሩ ነው። "ባለፈው መስከረም ግርግሩ ሲፈጠር ሱቅ ውስጥ ነበርኩኝ፤ በበር በኩል ሲገቡብኝ በመስኮት ዘልዬ መኖሪያ ቤቴ ስሮጥ ሁለት ልጆቼ ፣ ሶስት እህቶቼና እናቴ ተገድለው ነበር ያገኋቸው፤ ተመልሼ ስሄድም ይኸው ግርግሩ ተፈጥሮ አሁንም ውጡልን ተባልን ፤ ወዲዚሁ መጣሁ፤ ግን ቤተሰቦቼ በሙሉ እንዳለቁ ስነግራቸው አንድም የተረዳኝ ሰው የለም።" ይላል። "እሰከዛሬ ድረስ ወደዛም ወደዚህም ስንል፣እኛ ጎዳና ተዳዳሪ ስንሆን አንድ ቀን መጥቶ አይዟችሁ እኛ አለን ያለን ሚዲያም የለም ህዝብ ነው እየተባበረን እሰከዛሬ እንድቆይ ያደረገን እንጂ የመንግስት አካል ሁሉ ወደእዚያው ተመለሱ እያሉን ነው፤ እኛ ለምንድነው እንደዚህ የምንሆነው ኢትዮጵያዊ አይደለንም አንዴ?" ቢቢሲና እንድ የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃንም ተፈናቃዯችን ለማናገር ሲሞክሩ በአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ አባላት እንዳይቀርጹ በመከልከላቸው ተፈናቃዮቹ ከፖሊሶቹ ጋር የቃላት እሰጥ አገባ ውስጥ ገብተው ነበር። ከቆይታ በኋላ ግን የጋዜጠኞቹን መታወቂያዎችን አረጋግጠው ክልከላውን አንስተዋል። በጅግጅጋ ከመርሲን አካባቢ የመጣችው በቀሉ ቶሎሳ በጥቃቱ ከ 80ሺ ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት እንደተዘረፈባት ተናግራለች። "ይኸው አስራ አምስት ቀናችን ምንም መፍትሄ አላገኘንም፤ የወደቅነው ጎዳና ላይ ነው። አሁን እዚህ ተኝተን ደካማ አሉ፤ ልጆች የያዙ እናቶች አሉ ፤በሽተኞች አሉ፤ ምንም መፍትሄ አላገኘንም። " ብላለች በቀሉ ጉዳያቸውን አቤት ለማለት ወደተለያዩ የመንግስት አካላት ቢሮ ቢቀርቡም ሰሚ ጆሮ እንዳላገኙ ነው የምትናገረው። "ወደ አስራ ምናምን ቦታ ጠየቅን፤ ያልገባንበትቢሮ የለም ፤ መፍትሔ አላገኘንም ይኸው ጎዳና ላይ ወደቅን፤ እሰከዛሬ እኔ የመንግስት ያለህ እያልኩኝ ነው። " በዕለቱ ጥቃት የተሰነዘረባቸው አይነስውሩ ባህታዊ ታምሩ ዘለቀም ከጉዳታቸው ሳያገግሙ በዚሁ ጎዳና ላይ ተመጽዋች ሆነዋል። " ኪዳነምህረት አስቀድሼ ወደሚካኤል ስመጣ ነዋይ ቅድሳት እየተቃጠለ ነበር፤ ተመልሼ ወደኪዳነምህረት ስንሄድ ለካ ኪዳነምህረትንም አቃጥለው ጨርሰዋታል ፤ ተመልሰን ወደ ሚካዔል ስንመጣ ጥርሴን አረገፉኝ፤ ወገቤንም መቱኝ" ለዚህ ህመማቸው በቂ የህክምና አግልግሎትት ባያገኙም ከአስተባባሪ ወጣቶች ባገኙት መድኃኒቶች ህመማቸውን ያስታግሳሉ። ከተፈናቃዮቹ ውስጥ 30 የሚሆኑት ከሁለት ቀናት በፊት ነበር ነፍሳችውን ለማዳን ከመሸጉባት ሃረር ወደ አዲስ አበባ የመጡት። ለአምስት ቀን የሃረር ህዝብ እየረዳን ቆየን፤ ልጆች አሉ፤ ደካማ አለ፤ አይነስውራን፤ የተደበደበ፤ በጥይት የተመታ ሁሉ ነበረ፤ እኛ እንዴት ነው የምንሆነው ? እንዳንመለስ ንብረታችን ተዘርፏል፤የመመለስም ህልውና የለንም ስንላቸው ወደ አዲስ አበባ ሂዱ ፤ መንግስትም ይረዳችኋል ሲሉን መጣን፤ ከእነዚህ ግማሹ ሴቶች ናቸው" ብሏል የተፈናቃዮችን ስም ሲመዘግብ ቢቢሲ ያገኘው ሞላ የተባለው ተፈናቃይ። " የሌሊቱ ብርድ ራሱ እኔ ከዱላው በላይ አድርጌ ነው የማየው፤ በጣም ነው የሚሰቃዩት፤ የሚለብሰው አጥቶ በብርድ የሚሰቃይ ሞልቷል።" ስታዲየም አካባቢ የሚሰራው ጋሻው ተወዳጅ ተፈናቃዮቹን ለመርዳት ከተሰባሰቡት ወጣቶች አንዱ ነው። ካለፈው አርብ ጀምሮ ጎዳናው ላይ የወደቁትን ተፈናቃዮች የማገዙ ሂደት አስቸጋሪ እንደሆነባቸው ይገልጻል። "እኛ ብቻ ነን አሁን እየረዳናቸው ያለነው ፤ መንግሥትም ሆነ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት እስካሁን የረዳቸው የለም፤ ህጻናት አሉ ፤የሚያጠቡ እናቶች አሉ፤ ሽማግሌዎችም አሉ፤ ብርድ ላይ ነው ያሉት ትንሽ ቢቀንሰውብለን ሸራ ገዝተን አጠርንላቸው።ምግብ አንዳንድ ሰው ይዞ ይመጣል፤ ካልሆነ ደግሞ አስተባብረን በምናገኘው ገንዘብ ምግብ ቤት ሄደን ገዝተን ነው የምናበላቸው፤ ጠዋት ጠዋት ደግሞ በየቦታው የሚያፈሉትን እያፈላለግን በፔርሙሶች እየሰበሰብን በቁርስ እናበላቸዋለን" ብሏል። ወጣቶቹ መንግሥትም ሆነ ድርጅቶች ተፈናቃዮቹን በመጎብኘት ለጊዜው ምግብና መኝታ የሚያገኙበትን መንገድ እንድሚያመቻቹ ጠይቀዋል። ተመልሶ ወደጅግጅጋ መሄዱ የዘላቂ መፍትሄው አካል እንደሆነ የተጠየቀችው በቀሉ ይህን ብላለች። "መመለስ አለልፈልግም፤ መንግሥት እዚህ ቢገድለኝ ሁሉ ይሻለኛል፤ በቃ እዚሁ ብሞት እመርጣለሁ፤ የዛሬ ዓመትም ሁለት ዓመትም እንደዚሁ ስለሆነ ወደዚያ የሚያስብ ቤተሰብ የለም" አስተባባሪ ወጣቶችም ችግሩ ከአቅማቸው በላይ እየሆነ በመምጣቱ መንግስትም ሆነ ለጋሾች እጃቸውን እንዲዘረጉላቸው ጠይቀዋል።
news-55950982
https://www.bbc.com/amharic/news-55950982
ኢሰመኮ በረሃብ አድማ ላይ ናቸው የተባሉትን እነ አቶ ጃዋርን መጎብኘቱን ገለፀ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የረሃብ አድማ ላይ ናቸው የተባሉትን በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ መዝገብ የተከሰሱ እስረኞች መጎብኘቱን ዛሬ፣አርብ ባወጣው መግለጫ ላይ ገለፀ።
በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በረሃብ አድማ ላይ የሚገኙ እስረኞችን አስመልክቶ፣ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ "የእስረኞቹ ጤንነትና ሕይወት የከፋ አደጋ ላይ እንዳይወድቅ የቅርብ ክትትል ማድረግ እንደሚያስፈልግ፣ ለታሳሪዎች ምክንያታዊ የሆኑ ጥያቄዎች ተገቢውን አፋጣኝ ምላሽ መስጠትና የእስረኞችን ጠያቂዎች በማረሚያ ቤቱም ሆነ በፍርድ ቤቶች በአግባቡ ማስተናገድ ይገባል" ማለታቸውም ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ ላይ ተመልክቷል። ኮሚሽኑ ጥር 25 ቀን 2013 ዓ.ም. በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እና በቂሊንጦ ጊዜያዊ ማቆያ በመገኘት እስረኞቹን መጎብኘቱን የገለፀ ሲሆን ከእነ አቶ ጃዋር መሐመድ በተጨማሪም፣ የኮሎኔል ገመቹ አያና እና የአቶ ጥላሁን ያሚ አያያዝ ላይም ክትትል ማድረጉን በመግለጫው ላይ አመልክቷል። እነ አቶ ጃዋር መሐመድ ከጥር 19 ጀምሮ በረሃብ አድማ ላይ እንደነበሩ የገለፀው ኮሚሽኑ፣ የረሃብ አድማው ዓላማ "መንግስት በሕዝብ እና በፓርቲያቸው ላይ እያደረሰ ያለውን አፈና እና የመብት ጥሰት ለመቃወም፣ የኮሎኔል ገመቹ አያናን አላግባብ የሆነ አያያዝ እና እንግልት እንዲቆም ለመጠየቅ እና የችሎት ሂደታቸውን ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት በሚመጡ እና እነሱን ለመጠየቅ ወደ ማረሚያ ቤት በሚመጡ ሰዎች ላይ የሚፈጸም እስር እና ወከባ እንዲቆም ለመጠየቅ" መሆኑን ለኮሚሽኑ ማሳወቃቸው ተመልክቷል። የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስተዳደር በበኩሉ እነ አቶ ጃዋር ያነሷቸው አብዛኞቹ ጉዳዮች እንደማይመለከቱት መግለፁን በመግለጫው ላይ ሰፍሯል። እነ አቶ ጃዋርን ለመጠየቅ ወደ ማረሚያ ቤት የሚመጡ ሰዎች ላይ ወከባ እንደማይፈፀምም ማረሚያ ቤቱ ማስታወቁ ተገልጿል። ከመካከላቸውም ሁለት እስረኞች የጤና ችግር ያለባቸው በመሆኑ በረሃብ አድማው ምክንያት የጤና እክል እንዳይገጥማቸው ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን መመልከቱን ኮሚሽኑ ገልጿል። አቶ ጃዋር መሃመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ሃምዛ አዳነ እና አቶ ሸምሰዲ ጠሃ በትናንትናው እለት በረሃብ አድማው በመዳከማቸው ችሎት ፊት ሃሳባቸውን ማስረዳት እንደተሳናቸው ከጠበቆቻቸው አንዱ የሆኑት አቶ መሐመድ ጅማ ለቢቢሲ መግለፃቸው የሚታወስ ነው። "ሰውነታቸው በጣም ስለተዳከመ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። እነሱ ብዙ መናገር ስላልቻሉ እኛ ሃሳባቸውን አስረድተናል።" ብለዋል። ተከሳሾቹም እንዲሁ "በጣም ተዳክመን፣ ራሳችንን ስተን የህክምና እርዳታ የሚያስፈልገን ከሆነ እኛ በመረጥነው ሃኪም ብቻ የህክምና ርዳታ ይደረግልን' ሲሉ ፍርድ ቤቱን እንደጠየቁም ጠበቃቸቸው አስረድተዋል። ከእነ አቶ ጃዋር በበተጨማሪም ኮሚሽኑ የኮሎኔል ገመቹ አያናን እና ጥላሁን ያሚን ደህንንት ማጣራቱንም አስታውቋል። "ሁለቱም ታሳሪዎች በመልካም ደህንነት ላይ ይገኛሉ" ያለው ኮሚሽኑ አካላዊ ጥቃትም እንዳልደረሰባቸው ማረጋገጡን አስታውቋል። አቶ ጥላሁን ዋሚ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከማረሚያ ቤት ተቀርጾ በተሰራጨ ተንቀሳቃሽ ምስል ጋር በተያያዘ ደህንነቱ አደጋ ላይ ወድቋል ተብሎ በስፋት ሲወራ ነበር። ጥላሁን ዋሚ በማሕበራዊ ሚዲያ የተሰራጨውን ቪዲዮ ተከትሎ ከማቆያ ቤቱ ቅጥር ግቢ እንዳይወጣ ከመደረጉ በስተቀር በቂሊንጦ ጊዜያዊ ማቆያ እያለ ድብደባም ሆነ ሌላ አይነት የመብት ጥሰት እንዳልተፈፀመበት ለኮሚሽኑ ማስረዳቱ ተገልጿል።
news-50709579
https://www.bbc.com/amharic/news-50709579
ሳዑዲ ምግብ ቤቶች በጾታ የተለየ መግቢያ በሮችን መጠቀም የለባቸውም አለች
የሳዑዲ መንግሥት ከአሁን በኋላ በምግብ ቤቶች ውስጥ ወንዶችና ሴቶች የተለያየ መግቢያ እንዲጠቀሙ የሚያስገድደውን ሕግ ማስቀረቱን አስታወቀ።
በሳዑዲ በምግብ ቤቶች ሴቶችና ወንዶች አንድ በር እንዳይጠቀሙ በሚያግደው ሕግ ምክንያት ወንዶችና ሴቶች በማክዶናልድ ለየብቻቸው ሲገበያዩ ከዚህ በፊት በምግብ ቤቶች ውስጥ ለሴቶችና ለቤተሰቦች አንድ በር፣ ለወንዶች ደግሞ ለብቻቸው ሌላ በር ማዘጋጀት የግድ ነበር። ይህ ዕገዳ በበርካታ ምግብ ቤቶች፣ ካፌዎች፣ እንዲሁም ሌሎች የሕዝብ መሰብሰቢያ ሥፍራዎች ከአሁን በኋላ ተግባራዊ አይሆንም ተብሏል። • «ካሾግጂ ወዲያው ነበር የታነቀው» ቱርክ • የሳዑዲ ሴቶች መሪ ጨበጡ በሳዑዲ አረቢያ የተለያዩ ለውጦች እየተካሄዱ ቢሆንም የተቃውሞ ድምጻቸውን የሚያሰሙ ዜጎችንም ማፈኑን ቀጥሏል ብለው የሞሞግቱ የመብት ተሟጋቾች አሉ። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ የሳዑዲ ሴት ያለ ወንድ ፈቃድ ወይም አጃቢነት ከሀገር ውጪ መሄድ እንደምትችል ንጉሡ ባስተላለፉት ትዕዛዝ አስታውቀው ነበር። እ.ኤ.አ. በ2018 ደግሞ በሴት አሽከርካሪዎች ላይ ለአስርታት ተጥሎ የነበረው የማሽከርከር እገዳ መነሳቱ ይታወሳል። አሁንም ግን የመብት ተሟጋቾች በርካታ ሴት አግላይ የሆኑ ሕጎች እንዳሉ መሆናቸውን በማንሳት የተቃውሞ ድምጻቸውን ያሰማሉ። መንግሥት ይህንን ለውጥ እያካሄደ ባለበት ወቅት እንኳ በርካታ የሴት መብት ተሟጋቾች በእስር ላይ እንደሚገኙ አክለው ተናግረዋል። እሁድ እለት የሳዑዲ ከተሞች ሚኒስትር ምግብ ቤቶች በጾታ የተለየ መግቢያ በሮችን መጠቀም እንደማይገባቸው ተናግረዋል። ይህን ውሳኔ የንግድ ተቋማቱ ራሳቸው እንዲወስኑ ተትቷል ሲሉም አክለዋል። • ፈጣን ለውጥና ጭቆና በሳኡዲ አረቢያ • ሳዑዲ ሴቶች እንዳያሽከረክሩ ጥላ የነበረችውን እገዳ ልታነሳ ነው መሐመድ ቢን ሳልማን በ 2017 የልዑሉነቱን ዘውድ ከደፉ በኋላ እጅግ ወግ አጥባቂ የሆነውን የሳዑዲ አረቢያ ማህበረሰብ ክፍት ለማድረግ የተለያዩ እርምጃዎች እየወሰዱ ናቸው። እያደረጉ ያሉት ለውጥ ከበርካታ የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ አድናቆትን ቢያገኝም አሁንም ግን ጭቆና እንዳለ የሚገልፁ አልጠፉም። እ.ኤ.አ. በ2018 ቱርክ በሚገኘው የሳዑዲ ኢምባሲ ውስጥ የተገደለው ጋዜጠኛ ጃማል ኻሾግጂ ጉዳይ የዓለም አቀፍ መንግሥታት በአንድነት ያወገዙት ተግባር ሆኖ ይጠቀሳል። ጃማል ኻሾግጂ የሳዑዲ መንግሥትን የሚተቹ ጽሑፎችን በመጻፍ ይታወቅ ነበር።
news-45028176
https://www.bbc.com/amharic/news-45028176
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በአሜሪካ ጉዟቸው ከጀዋር መሃመድ ጋር ተወያይተዋል
በጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ የተመራው የልዑካን ቡድን በሰሜን አሜሪካ ዋሽንግተን ዲ.ሲ፣ ሎስ አንጀለስ እና ሚኒያፖሊስ ከተሞች 'ግንቡን እናፍርስ፣ ድልድዩን እንገንባ' በሚል መሪቃል ያደረጉት ጉብኝት ተጠናቋል።
ከግራ ወደ ቀኝ ለማ መገርሳ፣ ጀዋር መሃመድ፣ ዐብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) እና ተሺቴ ዋቆ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር እና የጉዞው አዘጋጅ ኮሚቴ የጠቅላይ ሚንስትሩ ጉብኝት እጅግ የተሳካ ነበር እንደሆነ ገልፀዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ባደረጉት ጉብኝት ከአሜሪካ መንግሥት ባለስልጣናት፣ መቀመጫቸውን ከኢትዮጵያ ውጪ ካደረጉ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ ከጋዜጠኞች እና መብት ተሟጋቾች ጋር ፊት ለፊት ተገናኘተው ተወያይተዋል። ከእነዚህም መካከል አንዱ ጀዋር መሃመድ ነው። ጀዋር ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር የተወያዩባቸውን ርዕሰ ጉዳዮች ነግሮናል። . ዶክተር ብርሃኑ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር ምን ተወያዩ? . "ያለፉት 27 ዓመታት ብዙ ቆሻሻ ነገር የተሰራበት ዘመን ነው'' ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ . የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሜሪካ ጉዞ ተጠናቀቀ ጀዋር ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ባለስልጣን ወደ ሰሜን አሜሪካ ሲመጣ ይደረግለት የነበረውን አቀባበል እና አሁን ለጠቅላይ ሚንስትሩና ልዑካቸው የተደረገውን በማነጻጸር ይጀምራል። ''ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ባለስልጣን ወደዚህ ሃገር ሲመጣ በተበላሽ እንቁላል ይደበደብ ነበር። ዛሬ ላይ የተበላሽ እንቁላል ይወረውሩ የነበሩት ወጣቶች ናቸው የአቀባበል ሥነ-ስረዓቱን ያደመቁት'' ሲል ይናገራል። ''ይህ ብቻ ሳይሆን አንድ ቦታ ላይ ታይተው የማይታወቁት ባንዲራዎች ጎን ለጎን ሲውለበለቡ ለመታዘብ ችለናል'' ይላል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ከጀዋር ጋር ምን ተወያዩ? ከጀዋር እንደሰማነው ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል። ጀዋር በሃገሪቱ የሚፈለገው ለውጥ እንዲመጣ የተቻለውን አስተዋጾ እንደሚያበረክት ለጠቅላይ ሚንስትሩ የገለፀላቸው ሲሆን ፤ ''ጠቅላይ ሚንስትሩ የምንፈልጋትን ሃገር ለመገንባት ውጪ ያሉ እና ሃገር ውስጥ ያሉ ባለሙያዎችን ለማሳተፍ ፍላጎት እና ዝግጅቱ አለን'' ሲሉ ነግረውኛል ሲል ጀዋር ለቢቢሰ ገልጿል። . "ጠቅላይ ሚኒስትሩን አምባገነን እንዳያደርጉት እሰጋለሁ" ጃዋር መሀመድ ''አሁን ባለው ሁኔታ እና ሽግግር ላይ መንግሥትን፤ ጠቅላይ ሚንስትሩን እደግፋለሁ'' - ጃዋር ሞሃመድ
50385137
https://www.bbc.com/amharic/50385137
ሂላሪ ክሊንተን የሩስያ እጅ በእንግሊዝ ፖለቲካ ውስጥ ገብቷል አሉ
«እጅግ አሳፋሪ ነው፤ ቃላት የሚያሳጣ» ሂላሪ ክሊተን የሩስያ እጅ የእንግሊዝ ፖለቲካ ውስጥ መኖሩን የሚያሳየው ዘገባ አለመውጣቱን አስመልክተው ያሰሙት ንግግር ነው።
ከቢቢሲ ጋር ቆይታ የነበራቸው ሂላሪ ዘገባው ከሚቀጥለው የዩናይትድ ኪንግደም ምርጫ በፊት መውጣት አለበት ባይ ናቸው። የሩስያ እጅ የእንግሊዝ ፖለቲካ ውስጥ ደርሶ ይሆን አይሆን የሚያትተው ዘገባ ታኅሣሥ 2 ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል። ነገር ግን ሂላሪ ክሊንተን ሪፖርቱ ከምርጫው በፊት ቢወጣ ለመራጩ ሕዝብ ይጠቅማል ይላሉ። • ሚሼል ኦባማ በአሜሪካ እጅግ ተወዳጇ ሴት ተባሉ • ስፖርታዊ ፍልሚያ ለማየት ስታድየም የገቡት ትራምፕ ያላሰቡት ገጠማቸው • ትራምፕ በትልቁ ቡሽ ቀብር ላይ ይገኙ ይሆን? ከእንግሊዝ ሕዝብ እንደራሴዎች በተወከሉ መርማሪዎች የተሠራው ሪፖርት፤ ስለላ፣ ጣልቃ ገብነት እና ሕግን ያልተከተለ አሠራር የእንግሊዝ ፖለቲካ ውስጥ ተንፀባርቀው እንደሆንና የሩስያ እጇ ምን ያህል ረዝሟል የሚለውን አጣርቷል ተብሏል። እንግሊዝ ከአውⶂጳ ሕብረት ጋር ፍቺ ለመፈፀም ያደረገችው ሕዝበ ውሳኔና የዛሬ ሁለት ዓመት የተደረገው ጠቅላላ ምርጫ የሩስያ እጅ አለበት እየተባለ ነው። ባለፈው መጋቢት የተጠናቀቀው ሪፖርት የእንግሊዝ መንግሥት መቀመጫ ወደሆነው መንገድ ቁጥር 10 ቢመራም እስካሁን ይፋ አልተደረገም። የቦሪስ ጆንሰን መንግሥት ሪፖርት እንዳይወጣ ጫና አድርጓል በማለት የሕዝብ እንደራሴዎች ይወቅሳሉ። መፅሐፋቸውን ለማስተዋወቅ ወደ እንግሊዝ ያቀኑት ሂላሪ ክሊንተን ከቢቢሲ ራድዮ 4 ጋር ቆይታ አድርገዋል። «አገራችንም አይተነዋል። አውሮጳም እንዲሁ። እዚህ እንግሊዝም ቢሆን። ሩስያ የምዕራቡን ዓለም ፖለቲካ ለመቆልመም ቆርጣ ተነስታለች» ሲሉ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል። «የአገራችሁ መንግሥት ዘገባውን ማዘግየቱ እጅግ አሳፋሪ ነው፤ ቃላት የሚያሳጣ ነው» ሲሉ ነው ሂላሪ ቁጭታቸውን ለጋዜጠኛዋ የገለፁት። ሂላሪ፤ ሩስያ አሁንም በአሜሪካ የምርጫ ሂደት ውስጥ አለች ብለው ያምናሉ። እርሳቸው በተሸነፉበት ምርጫም እጃቸው እንዳለበት አይጠራጠሩም። «እኔም ልክ እንደሌላው ሰው ሪፖርቱ ምን እንዳዘለ አላውቅም። ነገር ግን በወር ጊዜ ውስጥ ድምፁን ለመስጠት የሚሄው ሰው መረጃ ሊደርሰው ይገባል።»
news-53386387
https://www.bbc.com/amharic/news-53386387
የኮቪድ-19 መድኃኒት አለኝ ባለችው ማዳጋስካር 2 ባለስልጣናት በበሽታው ሞቱ
ለኮሮናቫይረስ የሚሆን መድኃኒት ማግኘቷን በፕሬዝዳንቷ አማካይነት ለዓለም ስታስተዋውቅ የቆየችው ማዳጋስካር ሁለት የምክር ቤት እንደራሴዎቿ በወረርሽኙ መሞታቸው ተገለጸ።
ፕሬዝደንት ራጆሊን 'መድኃኒቱን' ሲያስተዋውቁ አንድ የአገሪቱ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባልና ሌላ የሕዝብ እንደራሴ ናቸው በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ በኋላ ህይወታቸው ማለፉ የተገለጸው። የምክር ቤት አባላቱ በበሽታው መሞትን በተመለከተ ትናንት ዕሁድ ይፋ ያደረጉት የአገሪቱ ፕሬዝደንት አንድሬይ ራጆሊን ናቸው። ፕሬዝደንቱ ከአርቲ የተቀመመ ነው የተባለውን የኮሮናቫይረስ 'መድኃኒት' በመገናኛ ብዙሃን ወጥተው በማስተዋወቅ ቀዳሚው እንደሆኑ ይታወቃል። ፕሬዝደን ራጆሊን ይፋ ካደረጉት የሁለት የምክር ቤት አባላት ሞት በተጨማሪ 11 የአገሪቱ ምክር ቤት የሕዝብ እንደራሴዎችና 14 የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት አባላት በተደረገላቸው የኮሮናቫይረስ ምርመራ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው መናገራቸውን ኤኤፍፒ የዜና ወኪል ዘግቧል። የማዳጋስካር መንግሥት ዋና ከተማዋ አንታናናሪቮ በምትገኝበት ዋነኛ ግዛቱ ውስጥ የኮሮናቫይረስ በከፍተኛ መጠን መስፋፋቱን ተከትሎ ቀደም ሲል አንስቶት የነበረውን ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብ ባለፈው ሳምንት ተመልሶ ተግባራዊ ማድረግ ተጀምሯል። ባለስልጣናት እንዳሉት ጥብቅ የሆነው የእንቅስቃሴ ገደብ የተጣለው በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ ያለውን ወረርሽኝ ለመግታት ነው ብለዋል። ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት በኋላ የአገሪቱ ፕሬዝደንት ማዳጋስካር ኮቪድ-19ን ሊፈውስ የሚችል መድኃኒት ማግኘቷን በመግለጽ በልበ ሙሉነት በመገናኛ ብዙሃን ላይ እየወጡ ሲያስተዋውቁ እንደነበር ይታወሳል። አንዳንድ የአፍሪካ አገራትም በእርግጥ መድኃኒቱ ፈዋሽ እንደሆነ ለማወቅ ወደ ሃገራቸው ማስገባታቸው የሚታወቅ ሲሆን እስካሁን ግን ስለመድኃኒቱ ውጤት ያሉት ነገር የለም። ከአሪቲ የተቀመመው "መድኃኒት" ስላለው ጠቀሜታ በህክምና ባለሙያዎች በኩል የተሰጠ ምንም ማረጋገጫ የሌለ ሲሆን ባለሙያዎችና የጤና ተቋማት ግን ስለመድኃኒቱ ፋዋሽነት የታወቀ ነገር ስለሌለ ሰዉ እንዳይዘናጋ ሲያስጠነቅቁ ቆይተዋል። አሁን ደግሞ በሽታው በአገሪቱ ከመስፋፋት አልፎ በወረርሽኙ ሰበብ ሁለት የምክር ቤት አባላት መሞታቸው የመድኃኒቱን ነገር ጥያቄ ውስጥ ከትቶታል ተብሏል። በዓለም ጤና ድርጅት መረጃ መሰረት ወረርሽኙ በመጀመሪያ በማዳጋስካር መኖሩ ከታወቀ ጀምሮ እስካሁን 4,578 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን 34 ሰዎች ደግሞ በበሽታው ሰበብ ህይወታቸውን አጥተዋል።
50357378
https://www.bbc.com/amharic/50357378
በጃፓን ሴት ሠራተኞች መነጽር እንዳያደርጉ መከልከላቸው ጥያቄ አስነሳ
አንዳንድ የጃፓን ተቋሞች ሴት ሠራተኞች ቢሮ ውስጥ መነጽር እንዳያደርጉ መከልከላቸው አነጋጋሪ ሆኗል።
ኒፖን ቲቪ እና ቢዝነስ ኢንሳይደር የተባሉ የጃፓን መገናኛ ብዙሀን እንደዘገቡት፤ አንዳንድ ተቋሞች ልዩ ልዩ ምክንያት በማቅረብ ሴት ሠራተኞች መነጽር እንዲያወልቁ ያስገድዳሉ። ይህም የጃፓን ማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች መነጋገሪያ ሆኗል። የአውሮፕላን ማረፊያ እና የውበት ሳሎን ሠራተኞች መነጽር ሳያደርጉ መሥራት ተጽዕኖ እንደሚያሳድርባቸው ከገለጹት መካከል ናቸው። በኮዮቶ ዩኒቨርስቲ የሶሾሎጂ መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር ኩሚኮ ኔሞቶ፤ ሴቶች ሥራ ቦታ መነጽር እንዳያደርጉ መከልከል "ያረጀ ያፈጀ የጃፓን አሠራር ነው" ብለው ሕጉ አግላይ መሆኑን ገልጸዋል። • ጃፓን ከቀበሌ መታወቂያ ያነሰች ሞባይል ሠራች • ዚምባብዌ 211 ሀኪሞችን ከሥራ አገደች • ተቃዋሚዎች የከንቲባዋን ጸጉር አስገድደው ላጩ "ተቋሞች ሴቶችን የሚመዝኑት በሥራቸው ሳይሆን በገጽታቸው ነው" በማለትም ተናግረዋል። ተዋናይትና ጸሀፊ ዩሚ ኢሺካዋ፤ በመሥሪያ ቤቶች ሴቶች "እንዲህ ይልበሱ" የሚል ድንጋጌ መኖሩን በመቃወም ፊርማ እያሰባሰበች ነው። ዩሚ የቀብር ሥነ ሥርዓት ስታስተባብር ታኮ ጫማ እንድታደርግ መገደዷን እንደ ምሳሌ ትጠቅሳለች። ብዙዎች ዩሚ የጀመረችውን እንቅስቃሴ እየደገፉ ነው። በተለይም የጃፓን አመራሮች፤ ተቋሞች ለሠራተኞቻቸው የአለባበስ ደንብ እንዲያወጡና እንዲያስፈጽሙ ማድረጋቸው ተቃውሞውን አባብሶታል። ፕሮፌሰር ኩሚኖ እንደሚሉት፤ ሴት ሠራተኞች ታኮ ጫማ እንዲያደርጉ የሚያስገድደውን ፖሊሲ በርካቶች እየተቃወሙ ነው።
55416249
https://www.bbc.com/amharic/55416249
ኮሮናቫይረስ፡ የአውሮፓ ሕብረት አገራት በዩኬ ላይ የጣሉትን የጉዞ እገዳ እንዲያነሱ አሳሰበ
የአውሮፓ ሕብረት 27 አባል አገራት ከዩናይትድ ኪንግደም ጋር በተያያዘ የተጣሉ ገደቦችን በተመለከተ የተባበረ ምላሽ ለመስጠት እንደሚሞክሩ አስታወቁ።
ይህን ያሉት በዩናይትድ ኪንግደም ከተገኘው አዲስ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ጋር ተያይዞ በርካታ አገራት የጉዞ እገዳ መጣላቸውን ተከትሎ ነው። ዛሬ ማክሰኞ የአውሮፓ ኮሚሽን፤ አገራት የጣሉትን የጉዞ እገዳ እንዲያነሱና ወሳኝ የሆኑ ጉዞዎችን እንዲጀምሩ ምክረ ሃሳብ ሰጥቷል። ይሁን እንጂ የአውሮፓ ሕብረት አባል አገራት በድንበር ቁጥጥር ላይ የራሳቸውን ሕግ ለማስቀመጥ ነጻ በመሆናቸው በራሳቸው ፖሊሲዎችም ይህንን ማድረግ ሊቀጥሉ ይችላሉ። አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ከነባሩ በበለጠ ይበልጥ ተስፋፊ ሲሆን፤ የበለጠ ገዳይ ስለመሆኑ ግን የሚያመላክት ማስረጃ የለም። የአውሮፓ ሕብረት አባል አገራት ሁሉም በሚባል ደረጃ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም የሚደረግ የጉዞ እገዳ እየጣሉ ነው። የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን፤ አባል አገራቱ የኮቪድ-19 ምርመራ እንዲያደርጉ ወይም ራሳቸውን እንዲያገሉ በማድረግ ሰዎች ወደ የሚኖሩበት አገራቸው እንዲሄዱ መፍቀድ አለባቸው ብሏል። ነገር ግን አስፈላጊ ያልሆነ ጉዞ ሊበረታታ እንደማይገባ ገልጿል። አክሎም እንደ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ያሉ መጓጓዣ አገልግሎት ላይ የሚሰሩ ሰራተኞች ከተጣለው የጉዞ እገዳ እና አስገዳጅ ምርመራ ሊካተቱ አይገባም ብሏል። የተሰጡት ምክረ ሃሳቦችም ለሕብረቱ አምባሳደሮች የሚቀርብ ሲሆን አባል አገራቱ የሚጥሏቸውን ገደቦች ከግምት ያስገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ምንም እንኳን ይህ ምክረ ሃሳብ ቢሰጥም፤ አገራት በራሳቸው ፖሊሲዎች እቀባውን የመቀጠል እድላቸው ሰፊ መሆኑን የቢቢሲው ጋቪን ሊ ከብራስልስ ዘግቧል። በሌላ በኩል የዓለም ጤና ድርጅት የድንገተኛ አደጋዎች ኃላፊ ማይክ ርያን "አዲሱ የቫይረስ ዝርያ የወረርሽኙ ዝግመተ ለውጥ መደበኛ አካል ነው። ከቁጥጥር ውጭም አልሆነም" ብለዋል። ይህ ንግግራቸው ግን ከዚህ ቀደም የዩኬው የጤና ሚኒስትር ማት ሃንኮክ ከተናገሩት ጋር የሚቃረን ነው ተብሏል። በዩኬ እየተሰጠ ያለውን የፋይዘር ክትባት አምራች የሆነው የባዮንቴክ ተባባሪ መስራች ኡጉር ሳሂን በበኩላቸው ብሩህ ተስፋን ሰንቀዋል። ኡጉር "በሳይንሳዊ መልኩ ከክትባቱ የሚገኘው የበሽታ መከላከያ ምላሽ አዲሱን የቫይረስ ዝርያ ሊቋቋም ይችላል" ብለዋል። አክለውም "ካስፈለገ አዲሱን ዝርያ የሚከላከል ክትባት በስድስት ሳምንታት ውስጥ ሊሰጥ ይችላል" ሲሉም ተናግረዋል።
news-48899946
https://www.bbc.com/amharic/news-48899946
ኤርትራ የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠናን ያልፈረመች ብቸኛዋ ሃገር ሆነች
የአፍሪካ የምጣኔ ሃብት ኃያል ሃገር ባለቤት ናይጄሪያ የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነትን ፈረመች። ይህም ኤርትራን ስምምነቱን ያልፈረመች ብቸኛዋ አፍሪካዊት ሃገር አድርጓታል።
የናይጄሪያው ፕሬዝደንት ሙሃመዱ ቡሃሪ በኒጄር በተካሄደው የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል። ነጻ የንግድ ቀጠናው ስምምነት ዓላማ በአባል ሃገራት መካከል በሚደረጉ የንግድ ልውውጦች ላይ ታሪፍን በማስቀረት አፍሪካውያን ሃገራት እርስ በእርሳቸው የንግድ ልውውጥ እንዲያደርጉ ለማበረታታት ያሰበ ነው ተብሏል። ይህ ስምምነት ወደ ሥራ የሚገባበት ቀን ለጊዜው አልተወሰነም። በአሁኑ ወቅት አፍሪካውን ሃገራት ምርት እና አገልግሎታቸውን እርስ በእርስ የሚነግዱት 16 በመቶ ብቻ ሲሆን አውሮፓውያን ሃገራት ግን ከሚያመርቱት ምርት እና አገልግሎት 65 በመቶ የሚሆነውን ለተቀረው አውሮፓ ሃገር ይሸጣሉ። የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ አህጉር ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነትን ተግባር ላይ ማዋል፤ እአአ በ2022 ላይ በአፍሪካ ሃገራት መካከል የሚደረገውን የንግድ ለውውጥ በ60 በመቶ ከፍ ያደርገዋል ሲል ግምቱን ያስቀምጣል። • እውን የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ለኢትዮጵያ ይጠቅማል? • የአሜሪካና ቻይና የንግድ ጦርነት ዓለምን ሊያደኽይ ይችላል • ህንድ አሜሪካን ይጎዳል የተባለ የንግድ ታሪፍ ልታስተዋውቅ ነው በተጨማሪም ስምምነቱ በዓለማችን ትልቁን ነጻ የንግድ ቀጠናን ይፈጥራል ተብሎለታል። የአፍሪካ ግዙፍ መጣኔ ሃብት ባለቤት ናይጄሪያ የነጻ ንግድ ቀጠና ስምምነት ላይ ፊርማዋን ማኖሯ የስምምነቱን ውጤታማነት ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረክታል ሲሉ ባለሙያዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ኤርትራ ለምን ብቻዋን ቀረች? ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በነበራት አለመግባባት እና በሌሎች ምክንያቶች በስምምነቱ ዙሪያ ውይይቶች ላይ ተሳታፊ ሳትሆን መቆየቷን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የንግድ እና ኢንዱስትሪ ኮሚሽነር አልበርት ሙቻንጋ ይናገራሉ። ኮሚሽነሩ ጨምረውም ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ሰላም ማውረዷን ተከትሎ በስምምነቱ ዙሪያ ከአፍሪካ ህብረት ጋር ለመወያየት ጥያቄ ማቅረቧን ተናግረዋል። ''በጊዜ ሂደት እነሱም የስምምነቱ አካል ይሆናሉ'' ብለዋል ኮሚሽነሩ።
51016544
https://www.bbc.com/amharic/51016544
እግራቸው አሜሪካ ልባቸው አፍሪካ ያለ የሆሊውድ ተዋንያን
አፍሪካ አሜሪካዊው ራፐር ሉዳ ክሪስ ሰሞኑን አፍሪካዊ ዜግነት አግኝቷል። በእውነተኛ ስሙ ክርስቶፈር ብሪያን ብሪጅስ በመባል የሚታወቀው ሉዳክሪስ አፍሪካዊ ዜግነት በቅርቡ ያገኘ የሆሊውድ ተዋናይ ነው።
ከግራ ወቀደኝ፤ ሉዳክሪስ፣ ኢድሪስ ኤልባ፣ ቲፋኒያ ሃዲሽ እና ሳሙዔል ኤል ጃክሰን። የሉዳክሪስ ውሃ አጣጭ ጋቦናዊት ስትሆን እናቱና ሁለት ሴት ልጆቹም ጋቦናዊ ዜግነት አግኝተዋል። በሆሊውድ ከፍ ካለ የዝና ማማ ላይ የሚገኘው ሉዳ ክሪስ፣ በነዳጅ ሐብቷ ከበለፀገችው ጋቦን ምን ፈልጎ ነው? የሚል ደፋር ጠያቂ ቢመጣ፣ የእርሱ መልስ 'ወደ አፍሪካዊ ማንነቴ መመለስ ፈልጌ' የሚል ይሆናል። ከሉዳክሪስ በፊት ግን በርካታ የሆሊውድ ተዋንያን አፍሪካዊ ዜግነት አግኝተዋል። ሳሙኤል ኤል ጃክሰን የጋቦንን ፓስፖርት ያገኘው የከየት መጣሁ ጥያቄን ለመመለስ በተሰራው ዘጋቢ ፊልም ላይ ተሳትፎ የዲኤን ኤ ምርመራ ካደረገ በኋላ ነበር። ታዲያ የዘር ግንዱ ወደኋላ ሲቆጠር በደሙ ውስጥ ጋቦን ገነን ብላ ስለተገኘች ጋቦንም ሳታቅማማ ፓስፖርቷን ጀባ ብለዋለች። ጋቦን ብቻ አይደለችም ለአፍሪካ አሜሪካዊያን ዜግነት የሰጠችው። በግንቦት ወር ኮሜዲያንና ተዋናይት የሆነችው ቲፋኒ ሐዲሽ ወደ ኤርትራ ተጉዛ ዜግነት አግኝታለች። በዚህ ተግባሯ አንዳንዶች የኤርትራን አምባገነን መንግሥት ትደግፋለች በሚል ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። ባለፈው ሕዳር ወርም ጋና ለ126 አፍሪካ አሜሪካውያን እንዲሁም አፍሮ ካሪቢያን ዜግነትን ሰጥታለች። ይህንን ያደረኩት አፍሪካውያን በባርነት ተወስደው ሰሜን አሜሪካ እግራቸው የረገጠበትን 400ኛ ዓመት በማሰብ ነው በማለት 'የመመለስ ዓመት' በሚል ስም ዜግነት መስጠቷን ይፋ አድርጋለች። እንግሊዛዊው ታዋቂ የፊልም ተዋናይ ኢድሪስ ኤልባም የሴራሊዮን ዜግነት ያገኘው ባለቀው የፈረንጆች ዓመት የመጨረሻ ወር ላይ ነበር። • ስለኢትዮጵያ የቤተ ክርስቲያን ስዕሎች ምን ያህል ያውቃሉ? የኤድሪስ ኤልባ አባት ሴራ ሊዮናዊ ሲሆኑ ዜግነቱን ያገኘው ለመጀመሪያ ጊዜ ሀገሪቱን በረገጠበት ወቅት ነበር። ኢድሪስ በወቅቱ "ከአገሬ ላገኘው የምችለው ትልቁ ክብር ነው" ሲል ነበር የተሰማውን ለቢቢሲ የገለፀው። ለአፍሪካ አዲስ ያልሆነው ኢድሪስ ስለአፍሪካ ፊልም መስራቱን አፍሪካ ውስጥ ፊልም መቅረፁን ከጠቀሰ በኋላ "ሴራሊዮን ግን በልቤ ውስጥ ትልቅ ቦታ አላት" በማለት የቤተሰቦቹ አገር መሆኗን ገልጿል። በዚህ ዓመት በጋና የተዘጋጀው አፍሮፌስት ክብረ በዓል ላይ ለመገኘት ታዋቂዋ ሞዴል ናኦሚ ካምቤል፣ ተዋናይቷ ሉፒታ ኒያንጎ፣ ድምጻዊ ኤኮን፣ የቢዮንሴ እናት ቲና ኖውልስ ላውሰን ቀጠሮ ይዘዋል።
news-49202443
https://www.bbc.com/amharic/news-49202443
ሳዑዲ አረቢያ ሴቶች ያለወንዶች ጥበቃ እንዲጓዙ ፈቀደች
ሳዑዲ አረቢያ ሴቶች ያለ ወንዶች ጥበቃና ፈቃድ ፓስፖርት እንዲያወጡና ከአገር ውጭ እንዲጓዙ ፈቀደች።
ባለፈው አርብ ይፋ የተደረገው አዲሱ ሕግ፤ እድሜያቸው ከ21 ዓመት በላይ የሆናቸው ሴቶች ያለወንድ ረዳቶቻቸው ወይም አጋሮቻቸው ፈቃድ ፓስፖርት ለማውጣት ማመልከት እንዲችሉ ይፈቅዳል። • ሳዑዲ ሴቶች ወደ ስታዲየም እንዲገቡ ልትፈቅድ ነው • ሳዑዲ ለሮቦት ዜግነት ሰጠች ማንኛውም አዋቂ የሆነ ሰው ፓስፖርት ኖሮት ከአንድ አገር ወደሌላ እንዲጓዝ የሚያደርገው ሕግም ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ መብት ረገድ ሴቶችን ከወንዶች እኩል አድርጓቸዋል። ሕጉ ጨምሮ እንዳስቀመጠው ሴቶች የውልደትን፣ ጋብቻንና ፍቺን ማስመዝገብ እንዲችሉም ተፈቅዷል። ከዚህም በተጨማሪም የሴቶችን የሥራ እድል የሚመለከተውን የሥራ ቅጥር ሕግ ተመልክቷል። በዚህ ሕግ ማንኛውም የአገሪቱ ዜጋ ያለምንም ልዩነት፤ ያለ ፆታ፣ የአካል ጉዳት ወይም እድሜ መድልዎ እኩል የመሥራት መብት እንዳላቸው አትቷል። እስካሁን ድረስ የሳዑዲ ሴቶች ፓስፖርት ለማግኘትና ወደ ሌላ አገር ጉዞ ለማድረግ ከትዳር አጋራቸው፣ ከአባታቸው አሊያም ከሌላ ወንድ ዘመዳቸው ፈቃድ ማግኘት ይጠበቅባቸው ነበር። ከዚህ ቀደም የሳዑዲ አረቢያው ልዑል ሞሐመድ ቢን ሰልማን ሴቶች ማሽከርከር እንዳይችሉ የሚከለክለውን ሕግ ማንሳታቸው ይታወሳል። ይህም በአገሪቷ ለሴቶች እድሎች እየተከፈቱ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው ተብሏል። ውሳኔው ሴቶች ከወንዶች እኩል ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ መብታቸውን የሚያስጠብቅ ነው • ሳዑዲ ልዕልቷን የአሜሪካ አምባሳደር አደረገች ልዑል ሞሐመድ ቢን ሰልማን የሴቶችን በሥራ ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ከነበረው 22 በመቶ ወደ 30 በመቶ ከፍ በማድረግ የአገሪቱን ኢኮኖሚ በ2030 ለማሳደግ ዓላማ ይዘው እየሠሩ መሆናቸውን ከሦስት ዓመታት በፊት አስታውቀው ነበር። ይሁን እንጂ በርካታ ከፍተኛ እውቅና ያላቸው ሴቶች የሚደርስባቸውን የፆታ መድልዎ ምክንያት በማድረግ በካናዳና በተለያዩ አገራት ጥገኝነት ይጠይቃሉ። ባለፈው ጥር ወር የ18 ዓመቷ ራሃፍ መሀመድ አልቁኑን በካናዳ ጥገኝነት ተሰጥቷታል። ራሃፍ ከሳዑዲ አረቢያ የተሰደደች ሲሆን ወደ አውስትራሊያ ለመግባት ሞክራ ነበር። በመጨረሻም በታይላንድ ባንኮክ አየር ማረፊያ ሆቴል ተይዛ ዓለም አቀፍ እርዳታ እንዲደረግላት ጠይቃለች። ይህች ሴት በአገሯ ላይ እንደሁለተኛ ዜጋ ተቆጥራላች ሲሉ የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ቅሬታቸውን ያሰሙ ነበር።
49561212
https://www.bbc.com/amharic/49561212
ድሬ ዳዋ ስለሚገኙት የለገ ኦዳ የዋሻ ሥዕሎች ያውቃሉ?
ከድሬ ዳዋ ከተማ 36 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የለገ ኦዳ ዋሻ ወደ 600 የሚጠጉ ጥንታዊ የዋሻ ሥዕሎች ይገኙበታል። በ1920ዎቹ አካባቢ በተመራማሪዎች ዕውቅና እንዳገኙ የሚነገርላቸው የዋሻ ሥዕሎች ከ7,000 ዓመታት በላይ እንዳስቆጠሩ ባለሙያዎች ይገልጻሉ።
የለገ ኦዳ ዋሻ በብዛት በቀይ፣ በቢጫና ግራጫ ቀለም ከተሠሩት ሥዕሎች መካከል የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳ ቁሶች እንዲሁም እንስሳት የሚያሳዩት ይገኙበታል። • "የዘረፉትን ቅርስ በውሰት እንመልስ ማለታቸው ተገቢ አይደለም" ሚኒስትር ሂሩት ካሳው • የመይሳው ካሳ የልጅ ልጆች • ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ስለተዘረፉ ቅርሶች ምን እናውቃለን? የድሬ ዳዋ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ባለሙያ የሆኑት አቶ ደረጄ ታደሰ፤ ሥዕሎቹ ጥንት በአካባቢው ይኖሩ በነበሩ ሰዎች እንደተሠሩና፤ የአኗኗር ዘይቤያቸውን እንደሚያሳዩ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ሥዕሎቹ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ አደጋም እንደተጋረጠባቸው አቶ ደረጄ ተናግረዋል። ዋሻ ሥር የሚገኙት ሥዕሎች በዝናብ ሳቢያ እየደበዘዙ መጥተዋል። በሰው ንክኪ ምክንያትም የቀድሞ ይዘታቸውን እያጡ ነው። አቶ ደረጄ እንደሚሉት፤ ቅርሱ በአግባቡ ባለመያዙ የአገር ውስጥና የውጪ ጎብኚዎች ቁጥር እየቀነሰ መጥቷል። ቅርሱን ከዝናብ ለመከላከል መጠለያ ቢሠራም፤ የበለጠ እንክብካቤ እንደሚያስፈልገው ባለሙያው ተናግረዋል። የቢቢሲ ባልደረባ ወደሥፍራው አቅንቶ ካነሳቸው ፎቶግራፎች የሚከተሉት ይገኙበታል። በለገ ኦዳ ዋሻ ከሚገኙት ጥንታዊ ሥዕሎች አንዱ በቢጫና ግራጫ ቀለም ከተሠሩት ሥዕሎች መካከል የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳ ቁሶች እንዲሁም እንስሳት የሚያሳዩት ይገኙበታል የዋሻ ሥዕሎቹ ከ7,000 ዓመታት በላይ እንዳስቆጠሩ ይነገርላቸዋል በዋሻው ውስጥ ወደ 600 ሥዕሎች ይገኛሉ ሥዕሎቹ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋም ተጋርጦባቸዋል ሥዕሎቹን ከዝናብ ለመከላከል የተሠራው መጠለያ የለገ ኦዳ ዋሻ የዋሻ ሥዕሎቹ በ1920ዎቹ አካባቢ በተመራማሪዎች እውቅና ማግኘታቸው ይነገራል
news-48607488
https://www.bbc.com/amharic/news-48607488
ለጎንደር ጥልቅ ፍቅር ያለው ኬንያዊ ቤተ መንግሥት ሊገባ ሲል ተያዘ
ጎንደር በመሄድ የማገልገል ጥልቅ ፍላጎት አለኝ የሚለው ኬንያዊ ቢላ ይዞ ወደ ፕሬዚዳንቱ ቤተ መንግሥት ጥሶ ለመግባት ሲሞከር በጠባቂዎቹ ተተኩሶበት ቆስሎ ተይዟል።
በፌስቡክ ገጹ ላይ በኬንያ መሪዎች ስር ከመተዳደር ጎንደር ውስጥ የቤት ውስጥ አገልጋይ ሆኖ መኖርን እንደሚመርጥ የሚናገረው ብሪያን ኪቤት ቤራ ሰኞ እለት ነበር ቤተ መንግሥቱ ውስጥ ለመግባት የሞከረው። በጆሞ ኬንያታ የግብርናና የቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ውስጥ የአምስተኛ ዓመት የሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ተማሪ የሆነው ብራያን፤ ቤተ መንግሥት ሊገባ ሲል ግራ ትከሻው ላይ በጥይት ከቆሰለ በኋላ ሆስፒታል ገብቷል። •እምቦጭ የጣና ቂርቆስ መነኮሳትን ከገዳሙ እያስለቀቀ ነው •"ማንም ቢሆን ኢትዮጵያን ለብቻዬ ሰራኋት ሊል አይቻለውም" ጠ/ሚ ዐብይ ፖሊስ እንዳለው የ25 ዓመቱ ብሪያን ኪቤት ወደ ቤተ መንግሥቱ ለመግባት ሲሞክር የተመለከተው የጥበቃ መኮንን ግለሰቡ የአእምሮ ህመምተኛ ሊሆን ይችላል በሚል ለሞት በማያበቃው ቦታ ላይ በጥይት እንደመታው ገልጿል። ብሪያን በተደጋጋሚ በፌስቡክ ገጹ ላይ ወደ ብሔራዊ ቤተ መንግሥቱ በመሄድ "ሌባ" የሚላቸውን ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታን እንደሚገድል ይጽፍ ነበር። ሰሞኑንም ይህንን ዛቻውን ለመፈጸም ሙከራ አድረጓል። የ25 ዓመቱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ በተደጋጋሚ መንግሥትን የሚጻረሩ በተለይ ደግሞ ፕሬዝዳንቱን በማጥላላት የተሞሉ ሃተታዎችን በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ያሰፍር ነበር። አቋሙን ለመደገፍም የመጽሃፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ያጣቅስ እንደነበር የተለያዩ የኬንያ ጋዜጦች ዘግበዋል። የተለያዩ የታሪክ መጽሃፍትን እንዳነበበ የሚገመተው ብሪያን ወደ ኢትዮጵያ በመሄድ ጎንደር ውስጥ መኖር እንደሚፈልግ ጠንከር ባለ ሁኔታ በተደጋጋሚ ሲጽፍ እንደነበረም ተነግሯል። በአንድ ጽሁፉ ላይም "ይህ መልዕክት መሬቴንና ርስቴን ለዘረፉኝ ለፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታና ለህዝባቸው እንዲደርስ ይሁን። ኬንያ ውስጥ መሪ ከምሆን ኢትዮጵያ ውስጥ አገልጋይ ብሆን ይሻለኛል" ሲል አስፍሯል። •ኢትዮ ቴሌኮም... ወዴት? ወዴት? ወደ ጎንደር የመሄድ ፍላጎቱን በተደጋጋሚ የሚጠቅሰው ተማሪው "ከጠላቶቼ ጋርም ጦርነት አውጃለሁ። ምክንያቴ ደግሞ ወደ ጎንደር የምሄድበትን ገንዘብ ለማግኘት ነው" ብሏል። "ሞኝ (ጨቋኝ) መሪ ከመሆን የብልሆች ባሪያ መሆንን እመርጣለሁ" የሚለው ብሪያን ጎንደር በመሄድ ብልህ ለሆኑት ህዝቦች አገልጋይ መሆን እንደሚፈልግ ጠቅሶ ለጉዞው የሚያስፈልገውን ገንዘብ አለማግኘቱ እንዳዘገየው አስፍሯል። ስለጎንደርና ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ በማህበራዊ ገጹ ላይ እንደሚጽፍ የተነገረው ይህ ወጣት በእያንዳንዱ ጽሁፉ ማብቂያ ላይ "ከኢትዮጵያዊው ልዑል፤ ቀድሞ ብሪያን ኪቤት ቤራ ተብሎ ይጠራ የነበረው" ሲል ያሰፍራል። ብራያን ወደ ቤተመንግሥቱ ለመግባት ካደረገው ሙከራ ቀደም ብለው ጽሁፎቹ በመመልከት በርካቶች የተለያዩ ሃሳቦች በመሰንዘር ድርጊቱን የተቃወሙ ሲሆን አንዳንዶች ደግሞ የአእምሮ ጤንነቱን ተጠራጥረዋል።
45725160
https://www.bbc.com/amharic/45725160
የፍስሀ ተገኝ የቤተሰብ ፍለጋ ጉዞ
ፓስፖርቱ ላይ የትውልድ ስፍራ የሚለው ክፍት ቦታ ላይ 'ሐረር' ተብሎ ተጽፏል። የተወለደው ግን ሐረር አይደለም። ታዲያ ለምን ሐረር ተብሎ ተጻፈ?
ፍስሀና አክስቱ በእርግጥ ሐረር አሳድጋዋለች። ቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመድ ሰጥታዋለች፤ ለፍስሀ ተገኝ። የፍስሀ ህይወት በጥያቄዎች የተከበበ ነው። 'ቤተሰቦቼ፣ ዘመዶቼ ወዴት አሉ?' የሚለውን ጥያቄ እንዳነገበ ከሐረር አዲስ አበባ፣ ከአዲስ አበባ እንግሊዝ ባዝኗል። የ1997 ዓ. ም ምርጫ የሚወደውን የስፖርት ጋዜጠኛነት ብቻ ሳይሆን ሀገሩንም አሳጥቶታል። ያኔ ኤፍኤም አዲስ 97̏. 1 እየሰራ ሳለ አዲስ አበባ በ97ቱ ምርጫ ማግስት ታመሰች። • በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት • ከጥንት ሮማውያን እስከ ትዊተር የደረሰው የ# ምልክት በወቅቱ ህይወታቸው ካለፉ ሰዎች አብዛኞቹ የተገደሉት ባንክ ለመዝረፍ ሲሞክሩ ነበር የሚል ዜና እንዲያነብ ተሰጠው፤ አሻፈረኝ አለ። ህሊናዬ የማያምንበትን ነገርስ አልናገርም ማለቱ ሥራውን አሳጣው። የኋላ ኋላ ከትውልድ ሀገሩ መሰደድ ግድ ሆነበት። የሥጋ ዘመዶቹን የማግኘት ፍላጎቱን እንዳነገበ ወደ እንግሊዝ አቀና። ለጥያቄው መልስ ሳያገኝ በዓመት ላይ ዓመት ተደረበ። በ2010 ዓ. ም ያልተጠበቀ ዜና ተሰማ። በተለያዩ ሀገሮች በፖለቲካ ጥገኝነት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ወደሀገራችሁ መመለስ ትችላላችሁ ተባሉ። ጥሪውን ተቀብለው ከአስርታት በኋላ ዳግም ኢትዮጵያን ለመርገጥ ከቻሉ አንዱ ፍስሀ ነው። 2011 ዓ.ም ለመቀበል ባትወልደውም ወዳሳደገችው ከተማ ወደ ሐረር አቀና። «ቤተሰቦቼን ማግኘት አለብኝ. . . » ያደገው ሐረር ኤስኦኤስ የህፃናት ማሳደጊያ ውስጥ ነው። የልጆች ማሳደጊያው ውስጥ ለአስር ህጻናት አንድ እናት ይሰጣል። ፍሰሀን ከሌሎች ዘጠኝ ልጆች ጋር ያሳደጉት እናት አሁን ጡረታ ወጥተዋል። «በጣም የምወዳት የማፈቅራት እናቴ እሷ ነች። የምወደው ቤትም ኤስኦኤስ ነው፤ አሳድጎኛል። ቤተሰብ ጎደለብኝ ሳልል አድጌያለሁ» የሚለው ፍስሀ አዲሱን ዓመት ከእናቱ ጋር ማሳለፉ እጅጉን አስደስቶታል። ሆኖም የዘመናት ጥያቄው ማቃጨሉን አላቆመም። «ቤተሰቤ የታሪኬ አካል ነው፤ የአብራኬ ክፋዮች ናቸው። መፈለግ አለብኝ። ማግኘት አለብኝ፤» ስደት ቤተሰቦቹን እንዳያፈላልግ አግዶት ነበር። ቤተሰቦቹን ሳይገኝ የባከኑ ዓመታት ቢቆጨውም ለማንነት ጥያቄው መልስ ለማግኘት ወደ ላሊበላ ተጓዘ። የተወለደው ላስታ አካባቢ እንደሆነ ቢያውቅም፣ እትብቱ የተቀበረበትን ቦታ በትክክል አያውቅም። የሥጋ ዘመዶቹ የት እንዳሉም መረጃው የለውም። እሱና እናቱ በ77ቱ ረሀብ ሳቢያ ወደ ወለጋ፤ ቄለም ተወሰዱ። ቄጦ የሚባል ሰፈራ ጣቢያ ይኖሩም ነበር። እናቱ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ ከአርባ ልጆች ጋር ወደ ኤስኦኤስ ተወሰደ። «እዚያ ስናድግ ቤተሰባችን፣ ወላጃችን፣ አሳዳጊያችን፣ እናታችን፣ አባታችን ኤስኦኤስ ነበር። ሙልቅቅ አድርጎ ነው ያሳደገን» ይላል ስለአስተዳደጉ ሲናገር። እድሜው እየጨመረ ሲሄድ ስለቤተሰቦቹ ማንነት ያለማቋረጥ ያሰላስል ጀመር። ለጥያቄው መልስ የሚሰጥ ኢሜል እጁ ሲገባ ለፍለጋው መንገድ ተቀየሰለት። ኢሜሉ ለኤስኦኤስ የተሞላ ቅጽ ሲሆን፤ የትውልድ ቦታውን እንዲሁም የእናቱን ስም ከነአያታቸው ይዟል። ከእንግሊዝ ከተመለሰ በኋላ በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን ቃለ መጠይቅ ሲደረግለት ስለቤተሰብ ፍለጋው ያወራ ነበር። ይህን የሰማ አንድ ሰው እናቱ የላስታ ሰው ስለሆኑ በፍለጋው ሊያግዙት እንደሚችሉ ይነግሩታል። «አባቴ አለ!» ወደ ላሊበላ በረረ። እኚያ ሴት ቤትም አረፈ። ደስታ ይባላሉ። ፍስሀ ወደ ላሊበላ ከመሄዱ በፊት የቤተሰቦቹን ማንነት እያጣሩለት ነበር። «ለመሆኑ የእናትህን አያት ስም ታውቃለህ?» አሉት። «ቢሰውር ይባላል፤ ሙሉ ስሟ ሸዋዬ ታገል ቢሰውር ነው» ሲል መለሰ። ደስታ ጊዜ ሳያጠፉ ወደ አንድ ሰው ደወሉ። የደወሉለት ሰው የነገራቸው ነገር እሳቸውንም ፍስሀንም በሀሴት የሞላ ነበር። «ሙጃ የሚባል ቦታ ለሚገኝ ተድላ ለሚባል ሰው ደውላ የእናቱ አያት ስም ቢሰውር ነው ስትለው፤ የቢሰውር ቤተሰቦችማ የኛ ቤተሰቦች ናቸው አለ። ከዛ በደስታ ጨፈረች፤ እኔንም አቀፈችኝ፤» • አይሸወዱ፡ እውነቱን ከሐሰት ይለዩ • በእራስ ውስጥ ሌሎችን ማየት በማግስቱ ከላሊበላ ወደ ሙጃ ሄደ። ከዚያማ የዘመድ ጎርፍ አጥለቀለቀው። «በእናቴም በአባቴም በኩል የተገኙ ሰዎች ነበሩ። እነሱን ካገኘን በኋላ እነሱ ሌሎችን ይዘው ማምጣት ጀመሩ። ቀጥሎም ሙጃ ውስጥ ወንድም አለህ ተባልኩ» ፍሰሀ ለእናቱ ብቸኛ ልጅ እንደሆነ ነበር የሚያውቀው። ታናሽ እህቱ ሞታለች። ወንድምህ የተባለው ሰው የአባቱ ልጅ ነበር። እዚያው ሙጃ ውስጥ የሚኖረውን ወንድሙን ሲያገኘው፤ አስቦትም አልሞትም የማያውቀውን ብስራት አሰማው። «አባታችን በህይወት አለ!» መላ ህይወቱን አባቱ እንደሞቱ ነበር የሚያስበው። ኢሜል የተደረገለት ቅጽ ላይም አባቱ መሞታቸው ተጽፏል። ወደ አባቱ ስልክ ደውሎ በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ድምጻቸውን ለመስማት በቃ። «የተወለድኩት ብርግነት ነው» ፓስፖርቱ ላይ 'ሐረር ተወለደ' ይባል እንጂ እትብቱ የተቀበረው ብርግነት ነው። ልጅ ሳለ እናቱን እና እሱን ከትውልድ ቀያቸው የሸኛቸው የእናቱ ታናሽ ወንድም ነበር። «እሽኮኮ አድርጎ ሸኘኝ» የሚለውን አጎቱን ዳግም አገኘ። ከበርካታ የእናቱ ወገኖች ጋርም አገናኘው። «የእናቴን እህቶች፣ አክስቶቼን አገኘሁ። የእነሱን ልጆች፣ የልጅ ልጆች አገኘሁ። የእናቴ ታናሽ ወንድም፤ አጎቴ ጋር ሄጄ አራት ቀን ቆየሁ። ስልክ የለ፣ ኤሌክትሪክ የለ፣ የገጠር ህይወትን ለመድኩ። በግ ታርዶልኝ ሲያሞላቅቁኝ ነበር።» የእናቱ ታላቅ እህት ትርንጎ ይባላሉ። አብዛኞቹ ዘመዶቹ 'ሞቷል' ብለው ቢያምኑም፤ እሳቸው ግን 'በህይወት አለ' ይሉ ነበር። ይጸልዩለት እንደነበርም ይናገራል። እንዳፋቸው ሆኖ በአይነ ሥጋ ሲያገኙት 'ትተኸኝ አትሂድ' ብለውት እንደነበር በትዊተር ገጹ ላይ አስፍሯል። እሱና አክስቱ የተነሱትን ፎቶ በትዊተር ገጹ ሲለጥፍ ተከታዮቹ በፍጥነት ነበር ምላሽ የሰጡት። የቤተሰብ ፍለጋ ጉዞውን ከጀመረበት እለት አንስቶ ትዊተር ገጹ ላይ ይጽፍ፣ ፎቶም ይለጥፍ ነበር። አብረውት ያሉ ያህል ጉዞውን በድረ ገጽ የተከታተሉ ወዳጆቹም መልካም ምኞታቸውን ይገልጹለት ነበር። የልጅነት ትውስታውን ከአክስቱ ከሰማ በኋላ በስልክ ድምጻቸውን የሰማውን አባቱን በአካል ለማግኘት ወደ ሳንቃ ሄደ። «አባቴ ካገኘኝ ጀምሮ ሲያለቅስ ነበር የዋለው» ይላል ፍስሀ። ሳንቃ ውስጥ ያገኘው አባት ብቻ ሳይሆን በአባት የሚገናኛቸው እህትና ወንድም ጭምርም ነበር። «ሙጃ አንድ ታላቅ ወንድም ነበረኝ። ከእሱ ተጨማሪ አንድ እህትና አንድ ወንድም አገኘሁ» ጉዞውን ሲጀምር አባት፣ እህት፣ ወንድም፣ አክስት፣ አጎት አገኛለሁ ብሎ አልነበረም። በስተመጨረሻ ግን ራሱን በዘመድ ተከቦ አገኘው። የሆነው ሁሉ ቢያስደስተውም እንደዘገየም ተሰምቶታል። እሱ ቤተሰቦቹን ለማግኘት በተቻለው ሁሉ ጥሯል። ነገር ግን 'እነሱስ ለምን ሊፈልጉኝ አልሞከሩም?' ብሎ ግን ይጠይቃል።
48048268
https://www.bbc.com/amharic/48048268
አሜሪካ፡ ታዳጊዋን ለ16 ዓመታት ያሰቃዩ ጥንዶች እስር ተፈረደባቸው
ለ16 ዓመታት የአንዲት ታዳጊን ጉልበት ይበዘብዙ የነበሩ ጥንዶች የሰባት ዓመት እስር ተፈርዶባቸዋል።
መሐመድ ቱሬ እና ባለቤቱ ዴኒስ ቱሬ መሐመድ ቱሬ እና ባለቤቱ ዴኒስ ቱሬ የተባሉት ጋያናውያን ጥንዶች ታዳጊዋን ከጋያና ወደ አሜሪካ የወሰዷት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2000 ነበር። • ለአካል ክፍላቸው ሲባል ህጻናት ተገድለው ተገኙ ቴክሳስ ውስጥ ይኖሩ የነበሩት ጥንዶች ታዳጊዋን ለ16 ዓመታት ያለምንም ክፍያ አሠርተዋታል። ወደአሜሪካ ስትወሰድ የአምስት ዓመት ልጅ የነበረችው ሴት፤ ቤት እንድታጸዳ፣ ምግብ እንድታበስልና ልጆች እንድትንከባከብ ትገደድ ነበር። • የአንዱ እርግማን ለአንዱ ምርቃን፡ ኢትዮጵያን መጠጊያ ያደረጉ የስደተኞች ታሪክ ጥንዶቹ ታዳጊዋን ይደበድቧት ነበር። ጸጉሯን ላጭተዋት፣ ቅጣት ብለው በቤታቸው አቅራቢያ በሚኝ ፓርክ ውስጥ ብቻዋን ያሳድሯትም ነበር። እንዳትማር ከመከልከላቸው ባለፈ ፖስፖርቷን ነጥቀዋትም ነበር። 2016 ላይ የጥንዶቹ የቀድሞ ጎረቤቶች ታዳጊዋ እንድታመልጥ ረድተዋታል። አቃቤ ሕግ የነበረችበትን ሁኔታ የገለጸው "ልጅነቷን ቀምተዋታል። ለዓመታት ጉልበቷን በዝብዘዋል። እሷ እየተሰቃየች እነሱ ሕይወታቸውን ያለችግር ገፍተዋል" በማለት ነበር። • በስዊድን ያሉ የስደተኛ ልጆች ሚስጥራዊ ህመም ባልየው የጋያና የመጀመሪያ ፕሬዘዳንት አህመድ ሶኩ ቱሬ ልጅ ሲሆን፤ ጥንዶቹ የአሜሪካ ዜግነታቸውን ሊቀሙ ይችላሉ ተብሏል። ፍርድ ቤት ጥንዶቹ 288,620 የአሜሪካ ዶላር እንዲከፍሉ ወስኗል። ባልና ሚስቱ፤ ስለኛ የተወራው ነገር "እጅግ ተጋኗል" በማለት አቤቱታ የማሰማት እቅድ አላቸው ተብሏል።
news-56506565
https://www.bbc.com/amharic/news-56506565
አሜሪካ፡ በኮሎራዶ ጥቃት የሟቾች እና ጥቃት አድራሹ ማንነት ይፋ ተደረገ
የኮሎራዶ ግዛት ባለስልጣናት በትናትናው ጥቃት የተገደሉ 10 ግለሰቦችን እና የጥቃት አድራሹን ማንነት ይፋ አደረጉ።
በገበያ ስፍራ የተገሉት ሰዎች እድሜ በ20 እና 65 መካከል የሚገኝ ሲሆን ከሟቾቹ መካከል የ7 ልጆች አባት የሆነ የፖሊስ አባል ይገኝበታል። ጥቃቱ የቆመው ፖሊስ ከጥቃት አድራሹ ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርጎ በቁጥጥር ሥር ካዋለ በኋላ ነው። ተኳሹ የ21 ዓመት ወጣት አሕመድ አል አሊዊ አል ኢሳ የሚባል ሲሆን በ10 ሰዎች ግድያ ክስ ይመሰረትበታል ተብሏል። ጥቃት አድራሹ አብዛኛውን ሕይወቱን በኮሎራዶ ግዛት በምትገኝ አርቫዳ መኖሩን ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል። ፖሊስ ተኳሹ ይህን ጥቃት ለመሰንዘር ምን እንዳነሳሰው እስካሁን ግልጽ አይደለም ብሏል። ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ከጥቃቱ በኋላ በሰጡት አጭር መግለጫ መሰል ጥቃቶችን ለማስቆም የጦር መሳሪያ ቁጥጥር መደረግ አለበት፤ የጦር መሳሪያ መግዛት በሚሹ ላይም የኋላ ማንነት ማጣራት አስፈላጊ ነው ሲሉ አሳስበዋል። ስለ ጥቃቱ ምን እናውቃለን በገበያ በደረሰው ጥቃት ፈጻሚው ቆስሎ መያዙ ተመልክቷል። የደረሰው ጥቃት በዩቲዩብ ቀጥታ መተላለፉም ታውቋል። ጥቃቱ የደረሰው በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር 8፡30 ቀን ላይ ሲሆን ግለሰቡ ወደ ገበያ አዳራሹ እንደገባ መተኮስ ጀምሯል። ጥቃቱ የደረሰበት አካባቢ፣ ቦውልደር ፖሊስ ከ20 ደቂቃ በኋላ በትዊተር ገፁ ላይ "በኪንግ ሱፐርስ የገበያ ስፍራ ተኩስ የከፈተ ግለሰብ አለ" ሲል ጽፎ ነበር። ከሁለት ሰዓት በኋላ ፖሊስ ሰዎች ከአካባቢው እንዲርቁ አስጠንቅቋል። በአከባቢው የነበሩት ሰዎች ሁኔታውን በተንቀሳቃሽ ምስል አስቀርተውት በማህበራዊ ሚዲያዎች አጋርተው ነበር። በአንዱ ቪዲዮ ላይ "ምን እንደተከሰተ አላውቅም. . . የተኩስ ድምጽ ሰማሁ። የሆነ ሰው ተመትቶ ወደቀ" ሲል ምስሉን የሚቀርጸው ይሰማል። በቪዲዮው ላይ ፖሊስ ደርሶ የገበያ አዳራሹን ሲከብ ይታያል።
news-53507160
https://www.bbc.com/amharic/news-53507160
ኮሮናቫይረስ፡ በበይነ መረብ የተካሄደው ታላቁ የአፍሪካ ሩጫ
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት በርካታ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን ከስረ መሰረቱ ቀይሯል። ከአሁን በፊት ልንጠቀምባቸው ያልመረጥናቸው መንገዶችን የቫይረሱ መከሰት አሁን እንድናጤናቸው ግድ ብሏል።
አምባሳደር አሪካና ቺሆምቦሪ ቃኦ፣ አትሌት ደራርቱ ቱሉ እና ዶ/ር ጋሻው አብዛ [ከግራ ወደ ቀኝ] በአሜሪካ ሜሪላንድ ግዛት ታውሰን ዩንቨርሲቲ በስፓርት ቢዝነስና ቴክኖሎጂ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ጋሻው አብዛ የኮሮናቫይረስ መከሰትን ተከትሎ ስራቸው በቤት ውስጥ ከሆነ ሰነባብቷል። ነገር ግን አንዳንድ ስራዎቻቸው የግድ በአካል መገኘትን የሚጠይቁ በመሆናቸው፣ ቅርጻቸውን መቀየር ግድ ብሏቸዋል። ዶክተር ጋሻው በሞያቸው ከኢትዮጵያውያን አትሌቶች ጋር በመገናኘት የተለያዩ ሥራዎች ይሰራሉ። ነገር ግን ኮሮናቫይረስ ይህንን ሥራቸውን በአካል ተገኝተው እንዳይሰሩ አግዷቸዋል። ከዚህም ባለፈ ኮሮናቫይረስ በተማሪዎቻቸው ላይ የጤና፣ የሥነ ልቦናና የኢኮኖሚ ጫና የሚያሳድር በመሆኑ "እንደ መምህር ያ ያሳስበኛል" ይላሉ። ከቤት ሳንወጣ እንድንሰራ መገደዳችንም ተጽዕኖ ያሳድራል ያሉት ዶ/ር ጋሻው፣ ከህዝብ ጋር መገናኘት አለመቻልና ውጪ ላይ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ አለመቻልም ሌላኛው ችግር መሆኑን ያብራራሉ። አገር ቤት መኖሪያቸውን ያደረጉ አትሌቶችን ማማከርና ማስተማር የተጓዳኝ ስራቸው ነው። በስፖርቱ ዘርፍ ያካበቱትን እውቀት አገር ቤት በመመላለስ ለኢትዮጵያውያን አትሌቶች ያካፍላሉ፤ ነገር ግን የኮሮናቫይረስ መከሰት ይህንን ከማድረግ አግዷቸዋል። በዚህም ምክንያት ወረርሽኙ በአትሌቲክሱ ዘርፍ ከፍተኛ ጫና ማሳደሩን ያብራራሉ። "አትሌቶች ከመላ አገሪቱ ተሰባስበው መቀመጫቸውን አዲስ አበባ በማድረግ ነው ልምምድ የሚያደርጉት" የሚሉት ዶ/ር ጋሻው፤ በቫይረሱ ምክንያት በመላው ዓለም ኦሊምፒክን ጨምሮ ሁሉም ውድድሮች በመሰረዛቸው የገቢ ምንጫቸው ተዘግቶ ከግማሽ ዓመት በላይ የቆዩ በመሆናቸው፤ የምጣኔ ሃብት ቀውሱ በቀላሉ የሚታይ አይደለም ይላሉ። እንደ እርሳቸው ገለጻ የአትሌቶች ዋነኛ የገቢ ምንጭ በመላው ዓለም ተዘዋውረው በሚያደርጓቸው ውድድሮች የሚያገኙት ሽልማት ነው። ያንን አሁን ባለው ሁኔታ ማድረግ ስለማይቻልም ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫና ውስጥ እየገቡ መሆናቸውን ይናገራሉ። ዶ/ር ጋሻው በተጨማሪም በየዓመቱ በአሜሪካ ዋሽንግተን የሚካሄድ "ታላቁ የአፍሪካ ሩጫን" ኢትዮጵያውያን እና ሌሎች ፍላጎት ያላቸውም የሚሳተፉበት ዝግጅት ከጓደኞቻቸው ጋር በመሆን ጀምረዋል። በፈረንጆቹ 2018 ሃሳቡ ተጠንስሶ ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ላይ የመጀመሪያ ውድድሩን ያካሄደው ታላቁ የአፍሪካ ሩጫ፤ በአዋቂዎች̀ 2 መቶ ሰዎች የተሳተፋበት የ5 ሺህ ሜትር እና 200 ታዳጊዎች የተሳተፉበት የህጻናት ውድድር መካሄዱን ይገልጸሉ። በዚህ ዓመትም ዝግጅቱን ሰፋ በማድረግ በተመሳሳይ ቦታ አሜሪካ ዋሺንግተን፣ በዚህ ወር ላይ ለማካሄድ ታስቦ የነበረ መሆኑን የሚገልጹት ዶ/ር ጋሻው፣ የወረርሽኙ መከሰት ግን ይህ እንዳይሳካ አድርጓል ይላሉ። በመሆኑም የኢንተርኔት አማራጭን በመጠቀም በተለያዩ የዓለም ክፍል የሚገኙ ታዋቂ ኢትዮጵያዊያንን በማሳተፍ በአይነቱ ለየት ያለ ሩጫ ማካሄዳቸውን ይገልጻሉ። "የኢትዮጵያ ቨርቹዋል ሩጫ" በሚል ደራርቱ ቱሉ፣ የዲባባ ቤተሰቦች፣ ቀነኒሳ በቀለ፣ ሚሊዮን ወልዴ፣ ፋጡማ ሮባ እና በላይነህ ዲንሳሞ የመሳሰሉት እውቅ አትሌቶች የተሳተፉበት የዙም ሩጫ ማካሄዳቸውን የተናገሩት ዶክተር ጋሻው፤ ተሳታፊዎቹም ከጀርመን፣ ከእንግሊዝ፣ ከዱባይ፣ ከኢትዮጵያ፣ ከደቡብ አፍሪካና ከተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች መሳተፋቸውን ገልጸዋል። በ'ዙም' የተደረገው ሩጫ፣ በተለያዩ ብዙሃን መገናኛዎችና የዩቲዩብ ቻናሎችም በቀጥታ መተላለፉን ዶ/ር ጋሻው ተናግረዋል። የሩጫው ዓላማም ኢትዮጵያውያን ወገኖችን በያሉበት "አይዟችሁ፤ ይህም ጊዜ ያልፋል" ለማለት እና ጎን ለጎን ደግሞ በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ ወገኖችን ማሰብ እና ለቫይረሱ መከላከያ የሚሆን ገቢ ማሰባሰብ ነበር ብለዋል። በማከልም ከዚህ ውድድር የተገኘውን ገቢም ቫይረሱን ለመከላከል እንዲያስችል ለሁለት በጎ አድራጎት ድርጅቶቾ ማበርከታቸውንም ገልጸዋል። በኮቪድ-19 ምክንያት ለወራት ያክል ከቤት ሆነው ሥራቸውን ሲያከናውኑ፣ኢንተርኔትን በመጠቀም ራት አብሮ መብላት፣ ስብሰባዎችን ማካሄድ፣ ልደት ማክበርና ሥራን በአግባቡ የትም ቦታ ሆኖ በኢንተርኔት መከወን እንደሚቻል ወረርሽኙ በደንብ አስተምሮናል ይላሉ። በወረርሽኙ ምክንያት ባለፈው ግማሽ ዓመት የተፈጠሩትን አዳዲስ ነገሮችንም "የማይመስል፣ ነገር ግን በኮቪድ-19 ምክንያት የመጣ እውነት ነው" ብለውታል። • ኢሰመኮ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚያጣራ ቡድን ማሰማራቱን ገለጸ "ኢንተርኔት ቴክኖሎጂ ብቻ አይደለም፤ የአኗኗር ዘይቤያችንን ስር ነቀል በሆነ መልኩ የሚቀይር ጉልበት እና ሃይል ሆኗል" በማለት የኢንተርኔትን ጠቀሜታ ያብራራሉ። "ኢንተርኔት የዘመናችን ልዩ ስጦታ፣ በአግባቡ ካልተጠቀምንበት ደግሞ አደጋ ነው" የሚሉት ዶክተር ጋሻው፣ ቴክኖሎጂው በሁሉም ዘርፍ አዲስ ነገር ለማበርከት ምቹ በመሆኑ፣ በተለያየ የሙያ ዘርፍ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የአተያይ አድማሳቸውን በማስፋት እና በመቀየር ለማህበረሰባቸው ፈጠራ የታከለበት አስተዋጽዖ ማድረግ ስለሚችሉ ይህንን ትኩረት እንዲያደርጉበት ይመክራሉ። በሚቀጥለው ዓመት ነገሮች ይስተካከላሉ በሚል ተስፋ ዘንድሮ የተቋረጠውን የታላቁ አፍሪካ ሩጫን ለማካሄድ አቅደዋል። በውድድሩም በርካታ ተሳታፊዎችና የኦሊምፒክ አሸናፊ አትሌቶች እንዲሳተፉ እቅድ መያዙን ዶክትር ጋሻው ገልጸዋል። በፈረንጆቹ 2021 ሰኔ ወር ላይ ዝግጅቱ እንዲካሄድ ጊዜያዊ እቅድ ተቀምጦለታል።
news-52369314
https://www.bbc.com/amharic/news-52369314
ኮሮናቫይረስ፡ ለሕክምና ከሄዱበት ሕንድ መመለስ ያልቻሉ ኢትዮጵያዊያን ችግር ላይ ነን አሉ
በሺዎች የሚቆጠሩ አፍሪካዊያን የተሻለ ህክምና ለማግኘት ወደ ሕንድ ይጓዛሉ።
ኒው ዴልሂ ከተማ በአሁኑ ሰዓት አገሪቱ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኘን ለመከላከል ከአንድ ነጥብ ሦስት ቢሊየን በላይ ሕዝቧ ከቤት እንዳይወጣ እና ማንኛውም እንቅስቃሴ እንዳይደርግ አግዳለች። ይህን ተከትሎም ለህክምና ወደ አገሪቱ የሄዱ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው መመለስ ባለመቻላቸው ከባድ ችግር ላይ እንደሚገኙ ለቢቢሲ ገልፀዋል። ዘውዲቱ ንጉሴ የመቅኔ ንቅለ ተከላ ወይም ‘ቦንማሮ ትራንስፕላንት’ የሚባል ህክምና ለማግኘት ነበር ለሁለት ሳምንታት ወደ ሕንዷ ዋና ከተማ ኒው ደልሂ ያቀናችው። • ኮሮናቫይረስ በአፍጋኒስታን ቤተመንግሥት • ዶ/ር ቴድሮስ ፖለቲካዊ አለመግባባት ህይወት ለማዳን የሚደረገን ጥረት እንዳያደናቅፍ አስጠነቀቁ • በምሥራቅ ሸዋ ዞን በአንድ ቤተክርስትያን ውስጥ ሰባት ወጣቶች ሞተው ተገኙ ዘውዲቱ የደርሶ መልስ የአውሮፕላን ትኬት ብትቆርጥም በሕንድ እንቅስቃሴ እንዳይኖር በመታወጁ ካሰበችው በላይ ለተጨማሪ ቀናት እንድትቆይ ተገዳለች። "የተወሰነ ገንዘብ ብቻ ነበር ይዤ የመጣሁት፤ ግን የእንቅስቃሴ ገደቡ ከታወጀ በኋላ መንቀሳቀስ ስላልተቻለ ካሰብኩት ጊዜ በላይ በቀን 1000 ሩፒ እየከፈልኩኝ እንድቆይ ተደርጌለሁ ፤ እጄ ላይ ያለው ገንዘብ አልቋል። አላስፈላጊ ወጪ እና እንግልት እየደረሰብኝ ነው" ትላለች። "አጋጣሚ ሆኖ ለትምህርት የመጡ የማውቃቸው ሰዎች በመኖራቸው አገር ቤት ስሄድ የምከፍላቸው ገንዘብ ሰጥተውኛል" በማለት ስላለችበት ሁኔታ ታስረዳለች። ከአንድ ቤተሰብ ለህክምና ሦስት ሆነው የመጡ ሌሎች ኢትዮጵያንም አሉ። እህቱንና እና አባቱን ለማሳከም የመጣው ጌታቸው ሹሜ ስላሉበት ሁኔታ፤ “እህቴ በጣም ብዙ መድሃኒት ነው የምትወስደው፤ ለዚያም ደግሞ በቂ ምግብ መመገብ አለባት። እዚህ ያለው ምግብ ብዙም የሚስማማ አይደለም፤ ብዙ መድሃኒት ወስዶ ምግብ አለመመገብ ከባድ ነው” ሲል ይገልጻል። ሌላኛው ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ ታካሚም “ምግብ ለማግኘት በጣም ተቸግረናል። የታሸገ ምግብ ለመግዛት እየፈራን ነው ወደ ውጭ የምንወጣው። ሁኔታው ከቀን ወደቀን እየከበደን ነው። በየቀኑ የቤት ኪራይ ብቻ ነው እያሰላን ያለነው” ሲል በፈተና ውስጥ እንዳሉ ይናገራል። እነዚህ ታካሚዎች የቀደመ የጤና እክል የነበረባቸው መሆኑ ደግሞ ለኮሮናቫይረስ ያላቸውን ተጋላጭነት ከፍተኛ ያደርገዋል። ይህም ሌላ ጭንቀት ሆኖባቸዋል። ዘውዲቱ “ያረፍንበት ሆቴል ያን ያህል ግድ ያለው አይደለም፤ ያለው ነገር በጣም የሚያስፈራ ነው። ህክምና ቢያስፈልገን ከሃኪም ቤት መኪና ካልተላከልን በስተቀር መሄድ አንችልም። የምንፈልገውን በቅርበትና በፈለግነው ሰዓት አናገኝም" ትላለች። ዘውዲቱ ጨምራ "ቢያንስ የመጀመሪያው የእንቅስቃሴ ገደቡ 21 ቀኑ እንዳለቀ ወደ አገር ቤት በረራ ይጀመራል ብለን ተስፋ አድርገን ነበር ተደጋግፈን ተጋግዘን ነገሮችን እያለፍን የነበረው። በድጋሜ ይራዘማል የሚል በፍጹም አልጠበቅንም። ይሄ ነገር ሲሆን ግን ለእኛ ዱብዳ ነው” ስትል ትናገራለች። እነዚህ በተለያዩ የሕንድ ግዛቶች በሚገኙ ሆስፒታሎች የሚታከሙ ኢትዮጵያውያን በኒው ዴልሂ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳውቀው መልስ እንዳላገኙ ነግረውናል። ሕንድ ለመጀመሪያ ጊዜ ለ21 ቀናት እንቅስቃሴ እንዳይኖር እገዳ በጣለችበት ወቅት በ56 በረራዎች 10,600 የሚሆኑ የውጭ ዜጎች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ አድርጋለች። ጃፓን፣ ኖርዌይ፣ ጀርመን፣ ሩስያና ፈረንሳይን የመሳሰሉ አገራት በእገዳው ምክንያት ሕንድ የቀሩ ዜጎቻቸውን ካስወጡ አገራት መካከል ናቸው። የኢትዮጵያ መንግሥትም ዜጎቹን ወደአገራቸው ለመመለስ ያደረገው ጥረት ካለ በማለት በሕንድ ወደሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ደውለን ነበር። ይሁን እንጅ በሃገሪቱ በታወጀው የእንቅስቃሴ እገዳ ምክንያት ኤምባሲው እስከ ቀጣይ ወር ዝግ እንደሆነ ስልካችንን ያነሱ የአገሬው ዜጎች ገልፀውልናል። በኤምባሲው የሚሰሩ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችም ስለጉዳዩ መረጃ ለመስጠት ፍቃደኞች አልሆኑም። በሰሜናዊ ሕንድ የሚኘውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥራ አስከያጅ የሆኑትን አቶ ክሩቤል ሽታሁን ግን ስለጉዳዩ፤ “አንዳንድ አገራት በቻርተር በረራ ዜጎቻቸውን እያስወጡ እንደሆነ እናውቃለን። እኛ ግን ከኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ ከሕንድ መንግሥት መንገደኛ ለማጓጓዝ የተሰጠን ፈቃድ ስለሌለ ምንም ማድረግ አልቻልንም። ለቻርተር በረራ እኛ እንደዚያ አይነት ጥያቄ አልቀረበልንም። ኤምባሲውም ወደ እናንተ የሚደውሉ ሰዎችን ዝርዝር ስጡን ብለውን ሰጥተናቸዋል። በሕንድ መንግሥት ምንም ዓይነት የኮሜርሻል (ንግድ) በረራዎችን ማድረግ እንዳይቻል ተዘግቷል። የተለየ በረራ ካስፈለገ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሳይሆን በመንገደኞች፣ በአገራት እና በኤምባሲዎች ነው የሚጠየቀው።” ሲሉ በዚህ ምክንያት ዜጎችን ወደ አገር ቤት ለመመለስ እንዳልተቻለ አብራርተዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለያዩ አገራት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት መንቀሳቀስ ያልቻሉ አሜሪካዊያንን ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ እያደረገ መሆኑ የሚታወስ ነው። ባሳለፍነው ሳምንትም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ማይክ ፖምፔዮ፤ በቫይረሱ ምክንያት በሌሎች አገራት የነበሩ አሜሪካዊያን ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ አገልግሎት መስጠቱን በመጥቀስ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አሕመድን ማመስገናቸው ይታወሳል።
news-52634062
https://www.bbc.com/amharic/news-52634062
ኮሮናቫይረስ፡ ዉሃን ለ11 ሚሊዮን ነዋሪዎቿ በሙሉ የኮቪድ-19 ምርመራ ልታደርግ ነው
የቻይናዋ ዉሃን ከተማ አስራ አንድ ሚሊዮን የሚደርስ ነዋሪዋን የኮሮናቫይረስ ምርመራ ልታደርግ ዕቅድ እያዘጋጀት መሆኑ ተነገረ።
ዕቅዱ ገና በመጀመሪያ ደረጃ ላይ ያለ ቢሆንም በከተማዋ ያሉ ሁሉም አካባቢያዊ አስተዳደሮች በአስር ቀናት ውስጥ ምርመራውን አድርጎ ለማጠናቀቅ የሚያስፈልገውን ዝርዝር እንዲያቀርቡ ታዘዋል። ይህ ሃሳብ የቀረበው የኮሮናቫይረስ መነሻ በሆነችው ዉሃን ከተማ ውስጥ ባለፈው ቅዳሜና እሁድ ስድስት ሰዎች ላይ ቫይረሱ ከተገኘባቸው በኋላ ነው። ከዚህ በፊት ለአንድ ወር ያህል አንድም በሽታው ያለበት አዲስ ሰው አልተገኘም ነበር። ዉሃን በወረርሽኙ ምክንያት ለአስራ አንድ ሳምንታት ጥብቅ በሆነ የእንቅስቃሴ ገደብ ውስጥ ቆይታ በሚያዝያ ወር ሁለተኛ ሳምንት ላይ ነበር የተከፈተችው። ለተወሰኑ ሳምንታትም ትምህርት ቤቶች ተከፍተው፣ የንግድ ተቋማት ሥራ ጀምረው እንዲሁም የሕዝብ መጓጓዣዎችም አገልግሎት መስጠት በመጀመራቸው ህይወት ወደ ነበረችበት መመለስ ጀምራ ነበር። ነገር ግን ከቅርብ ቀናት ወዲህ በተወሰኑ የመኖሪያ አካባቢዎች በርከት ያሉ አዳዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸው ከተማዋ ወደ ቀድሞ እንቅስቃሴዋ ለመመለስ እያደረገችው የነበረውን ጥረት ስጋት ላይ ጥሎታል። ዉሃን ሁሉንም የከተማዋን ነዋሪ ለመመርመር ባወጣችው ዕቅድ መሰረት ሁሉም የከተማዋ ከፍል በአስር ቀናት ውስጥ ምርመራው አድርጎ ለማጠናቀቅ የሚያስችለውን ዕቅድ እስከ ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ እንዲያርቡ ታዝዘዋል። ምርመራ ለማድረግ የተያዘውን ዕቅድ የሚተነትነው ዕቅድ "የ10 ቀናት ፍልሚያ" የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን፤ መርመራው በዕድሜ ለገፉ ሰዎችና ተጠጋግተው ለሚኖሩ ማኅበረሰቦች ቅድሚያ እንደሚሰጥም ተገልጿል። ነገር ግን የረጅም ጊዜ ልምድ ያላቸው በርካታ የጤና ባለሙያዎች የታቀደው ሁሉንም የከተማዋን ነዋሪ ለመመርመር የተያዘው ግዙፍ ዕቅድ ከፍተኛ ወጪን የሚጠይቅ ከመሆኑም በላይ አዋጪ እንዳልሆነ እየተናገሩ ነው። በዉሃን ዩኒቨርስቲ ዦንግናን ሆስፒታል ውስጥ የሚገኘው የጽኑ ህሙማን ክፍል ኃላፊ የሆኑት ፔንግ ዢዮንግ እንዳሉት፤ ምርመራው በተለይ የጤና ባለሙያዎችን፣ ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑና በበሽታው ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ባላቸው ሰዎች ላይ ቢያተኩር መልካም እንደሆነ መክረዋል። ሌላ የዉሃን ዩኒቨርስቲ ኃላፊ ደግሞ፤ እስካሁን ከ3 እስከ 5 ሚሊዮን የሚደርሰው የከተማዋ ነዋሪ በመመርመሩ የቀሩትን ከ6 አስከ 8 ሚሊዮን የሚደርሱትን ሰዎች በ10 ቀናት ውስጥ መርምሮ ለማጠናቀቅ እንደሚቻል አመልክተዋል።
news-53638909
https://www.bbc.com/amharic/news-53638909
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፡ በጉባ ወረዳ 3 ሰዎች በታጣቂዎች ታገቱ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ቅዳሜ ዕለት ሦስት ሰዎች በታጣቂዎች ታግተው መወሰዳቸውን አንድ የክልሉ ሠላም ግንባታና የጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ለቢቢሲ ተናገሩ።
አቶ አብዱላዚዝ መሐመድ፣ የቤንሻንጉል ሠላም ግንባታና የጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ለቢቢሲ እንደገለጹት ታጣቂዎቹ ሦስት የጉባ አካባቢ ነዋሪዎችን እንደወሰዱና እስካሁን የት እንዳሉ አለመታወቁን ገልጸዋል። እገታው የተፈጸመው ቅዳሜ ዕለት መሆኑን የሚናገሩት አቶ አብዱለዚዝ "ታጋቾቹ የጉሙዝ ብሔረሰብ አባላት" ናቸው በማለት የደረሱበት ባለመታወቁ ቤተሰቦቻቸው ለአካባቢው ባለስልጣናት ማመልከታቸውን ገልጸዋል። ታጋቾቹ የጉባ ወረዳ ነዋሪዎች ሲሆኑ ታጣቂዎቹ ያገቷቸውን ሰዎች ለመንግሥት መረጃ ትሰጣላችሁ ከማለት በተጨማሪ የቤተሰብ አባሎቻቸው ከአካባቢው መስተዳደሮች ጋር ያላቸውን ግንኙነት በመጥቀስ መታገታቸውን ቤተሰቦቻቸው እንደተናገሩ ኃላፊው ጠቅሰዋል። የታገቱትን ሰዎች በተመለከተ "ስላሉበት ሁኔታ የታወቀ ነገር የለም። ስላሉበት ሁኔታ እርግጠኞች አይደለምን። ነገር ግን ተይዘው በተወሰዱበት አቅጣጫ የመከላከያ ሠራዊት ተሰማርቶ ታጣቂዎቹን ለመያዝና ታጋቾቹን ለማስለቀቅ ጥረት እየተደረገ ነው" ሲሉ ገልጸዋል። ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላም መከላከያ እና ልዩ ኃይል ታጣቂዎቹ ተደብቀውባቸዋል በተባሉ አካባቢዎች ላይ አሰሳ በማድረግ ጥቂት የማይባሉት እንደተገደሉ የተናገሩት አቶ አብዱላዚዝ "[ታጣቂዎቹ] ተስፋ የመቁረጥ ሁኔታ ውስጥ ስለገቡ የቻሉትን ያህል ጥፋት መፈጸም ነው ፍላጎታቸው። ነገር ግን መውጫ የላቸውም. . . ሠራዊቱ ተሰማርቶ እያሰሰ ነው" ብለዋል። ከሳምንት በፊት ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በጉባ ወረዳ አቡጃር ቀበሌ ላይ ጥቃት ፈጽመው ቢያንስ 13 ሰዎች ተገድለው ሌሎች ሰዎች ደግሞ የመቁሰል ጉዳት እንደደረሰባቸው የሚታወስ ሲሆን የክልሉ ልዩ ኃይልና የአገሪቱ የመከላከያ ሰራዊት ታጣቂዎቹን ለመያዝ በከፈተው ዘመቻ በርካታ ታጣቂዎች መገደላቸውና መያዛቸው ተገልጿል። ይህንንም በተመለከተ አቶ አብዱላዚዝ መሐመድ በተለይ እንደገለጹት ቀደም ባለው ጥቃት ውስጥ ተሳትፈው ከነበሩት ታጣቂዎች መካከል 13ቱ ሲገደሉ 30ዎቹ ደግሞ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቀዋል። በታጣቂዎቹ እርምጃ የተወሰደው በመከላከያና በክልሉ ልዩ ኃይል በጋራ በተከታታይ በተደረጉ ዘመቻዎች መሆኑን አስረድተዋል። ጥቃት የደረሰባቸውን ሰላማዊ ሰዎችና ለፍቶ አዳሪ ዜጎች መሆናቸው የሚናገሩት ምክትል ኃላፊው "የታጠቁ ሽፍቶች" ሲሉ የገለጿቸው የጥቃት አድራሾቹ ዓላማ በአካባቢው ግጭት ማስነሳት መሆኑን ጠቁመዋል። አካባቢው አሁን ሠላማዊ እንቅስቃሴው በተለመደው መልኩ መቀጠሉን ተናግረው "የቀሩትን ጥቃት አድራሾች አድኖ ለመያዝ ጥረት እየተደረገ ሲሆን፤ ተበታተነው የሚገኙትን ሽፍቶች የመያዝ ሥራም እየተሠራ ነው" ብለዋል። ቤንሻንጉ ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሌ ሀሰን ለብሔራዊው ቴሌቪዥን ኢቢሲ እንደተናገሩት፣ ጥቃቱ የደረሰው በክልሉ አለመረጋጋት እንዲፈጠር በሚፈልጉ ኃይሎች ድጋፍ የሚደረግላቸውና በሱዳን ድንበር አካባቢ ስልጠና ሲወስዱ በነበሩ ቡድኖች አማካኝነት ነው ሲሉ ተናግረዋል። ታጣቂዎቹ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ከፈጸሙት ግድያ በኋላ በነበሩ ቀናት በጸጥታ ኃይሎች በተከታታይ በተወሰዱ እርምጃዎች ከ70 በላይ የሚጠጉት መያዛቸውንም ጠቁመዋል። ተያዙ ስለተባሉት ታጣቂዎች የቁጥር ልዩነትን በተመለከተ አቶ አብዱላዚዝ ሲናገሩ የተያዙት ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ቢሆንም 30ዎቹ ከጥቃቱ ጋር ቀጥተኛ ተሳታፊ ናቸው የተባሉ መሆናቸውን ጠቁመዋል። በተያያዘ ዜና በጉባ ወረዳ አልመሃል በሚባል ቦታ ሌላ ጥቃት ተፈጽሟል የሚል መረጃ እየወጣ መሆኑን የተጠየቁት አቶ አብዱላዚዝ "ችግር ተከሰተ የሚባለው ውሸት ነው። አጣርተን ትክክል አለመሆኑን ደርሰንበታል" በማለት በስጋት ከመኖሪያ ቦታቸው ሸሽተው የወጡ ሰዎች እንዳሉና የጸጥታ ኃይል ደርሶ በማረጋጋት ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን ኃላፊው አመልክተዋል። ቢቢሲ ያናገራቸው ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ አንድ የአካባቢው ነዋሪ ከሐምሌ 20 ጥቃት በኋላ የአካባቢው አመራሮችን ጨምሮ "በርካታ ሰዎች መታሰራቸውን" ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከክልሉና ከፌደራል መንግስት ከመጡ አመራሮች ጋር ከተደረገ ውይይት በኋላ ከኅብረተሰቡ የተሰጡ ጥቆማዎችን መሠረት አድርጎ ብዙዎች መያዛቸውን አስታውቀዋል። አካባቢው አሁን ሠላማዊ መሆኑን ጠቁመው ቤታቸው ትተው የሸሹ ሰዎችም ንብረታቸውን እያወጡ መሆኑን ተናግረዋል። አልመሃል አካባቢ ጥቃት ስለመድረሱ እና ታጣቂዎች ስለመያዛቸው ግን የሰሙት ነገሩ አለመኖሩን ጠቁመው ታጣቂዎቹ ከቦታ ቦታ እንደሚንቀሳቀሱ ተናግረዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኝ ሲሆን ከሱዳን ጋር የሚካለል አካባቢ ነው። በክልሉ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በነዋሪዎች ላይ በሚፈጸም ጥቃት በርካታ ሞት፣ የአካል ጉዳትና የንብረት መውደም አጋጥሟል።
49826386
https://www.bbc.com/amharic/49826386
ቻይና ግዙፉን አዲስ አየር ማረፊያዋን ከፈተች
አስራ አንድ ቢሊየን ዶላር የወጣበት አዲሱ የቻይና አየር ማረፊያ አገልግሎት ለመስጠት ተከፈተ።
ዳዢንግ፡ አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ በዋና ከተማዋ ቤይጂንግ ውስጥ የሚገኘው ይህ ዳዢንግ ተብሎ የሚጠራው ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዛሬ ተመርቆ የተከፈተው በሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ነው። አየር ማረፊያው 700 ሺህ ስኩየር ሜትር ስፋትን የሚሸፍን ሲሆን ይህም 98 የእግር ኳስ ሜዳዎችን እንደሚሸፍን የሃገሪቱ መንግሥት ዕለታዊ ጋዜጣ ቻይና ዴይሊ ዘግቧል። • ሁሉንም በደህንነት ካሜራ የምትመለከተው ቻይና የአየር መንገዶችን ደረጃ የሚመዘግበው ኤርፖርት ካውንስል እንደሚለው አሁን ቤይጂንግን እያገለገለ የሚገኘው አየር ማረፊያ ከአሜሪካው አትላንታ አየር ማረፊያ ቀጥሎ ብዙ አውሮፕላኖችን የሚያስተናግድ ነው። የቻይና ባለስልጣናት እንዳሉት አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ ያስፈለገው የነበረው አውሮፕላን ማረፊያ ያለበትን ከፍተኛ መጨናነቅ ለመቀነስ ነው። በታዋቂ አርክቴክት የታነጸው ዳዢንግ አየር ማረፊያ በታዋቂ አርክቴክት የታነጸው ዳዢንግ አየር ማረፊያ ይህ አዲሱ ዳዢንግ አውሮፕላን ማረፊያ በአንድ ህንጻ ውስጥ ትልቅ የመንገደኞች ማስተናገጃ በመያዙ ቀዳሚ ይሆናል ተብሏል። ይህ አውሮፕላን ማረፊያ ከአምስት ዓመት በኋላ ወደ ቤይጂንግ ይመጣሉ ተብለው ከሚጠበቁት መንገደኞች መካከል 170 ሚሊዮኖቹን ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቃል። ከትላልቆቹ ዓለም አቀፍ አየር መንገዶች በተጨማሪ ሰባት ያህል የሃገር ውስጥ አየር መንገዶች ከዛሬ ጀምሮ ከዚህ ከአዲሱ አየር ማረፊያ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ ተነግሯል። • ቻይና ሙስሊም ልጆችን ከቤተሰቦቻቸው እየነጠለች ነው መሃል ቤይጂንግ ከሚገኘው የታይናሚን አደባባይ በስተደቡብ 46 ኪሎ ሜትሮች እርቆ የሚገኘው የአዲሱ አየር ማረፊያ ንድፍ የተዘጋጀው በትውልድ ኢራቃዊ በዜግነት እንግሊዛዊ በሆነችው በእውቋ አርክቴክት ዛሃ ሃዲድ ነው። ይህ አየር ማረፊያ ሲከፈት ቤይጂንግ ለንደንና ኒው ዮርክን የሚገኙበትን ግዙፍ አቀፍ አየር ማረፊያ ካላቸው ዓለም ከተሞችን ተቀላቅላለች። እንደ አውሮፓዊያኑ በ1958 የተከፈተው ቤይጂንግ ካፒታል የሚባለው ነባሩ አውሮፕላን ማረፊያ ከ100 ሚሊዮን በላይ መንገደኞች ተጠቅመውበታል።
news-51232421
https://www.bbc.com/amharic/news-51232421
አሜሪካ ነፍሰ ጡር ቪዛ አመልካቾች ለመቆጣጠር አዲስ ሕግ አወጣች
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነፍሰ ጡር ሴቶች ለመውለድ ሲሉ ወደ አሜሪካ እንዳይሄዱ ለመቆጣጠር የሚያስችል አዲስ ሕግ አወጣ።
'የወሊድ ቱሪዝም' ተብሎ የሚጠራውን እና አሜሪካ ሄዶ ለመውለድ የሚደረግን ጉብኝት ለመከላካል የወጣው ፖሊሲ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል። ሕጉ ነፍሰ ጡር ሴቶች ለሥራ ወይም ለጉብኝት ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ቪዛ ሲያመለክቱ፤ ወደ አሜሪካ የሚሄዱበት ዋነኛ ምክንያት ለመውለድ አለመሆኑን የሚያሳይ ማረጋገጫ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ይላል። በአሜሪካ ሕግ መሠረት በአገሪቷ የሚወለዱ ልጆች በቀጥታ የአሜሪካ ዜግነት ያገኛሉ። ይህ ሕግ ግን በፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ሲተች ቆይቷል። የፕሬዚደንት ትራምፕ አስተዳደር አዲሱ የጉዞ ሕግ የአገሪቷን ብሔራዊ ደህንነትና የሕዝብ ጤና ለመጠበቅ አስፈላጊ እንደሆነ ተናግሯል። ትራምፕ ወደ አገሪቷ የሚገቡ ስደተኞችን ለመቀነስ ፍላጎት ያላቸው ሲሆን፤ ቀደም ብሎ "በአሜሪካ ለተወለዱና ለኖሩ የሌላ አገር ዜጎች" ዜግነት እንደሚሰጥ የሚገልፀው የአሜሪካ ሕገ መንግሥት መሻሻል እንዳለበት ጠይቀዋል። አዲሱ ሕግ ምን ይላል? አዲሱ ሕግ 'ቢ' ቪዛ የሚጠይቁ ሁሉንም አመልካቾች ይመለከታል። የቪዛ ኦፊሰሮች ዋነኛ አላማቸው ለመውለድ ወደ አሜሪካ የሚገቡ ሴቶችን ቪዛ እንዲከለክሉ ይፈቅዳል። "የወሊድ ቱሪዝም ኢንደስትሪ የዓለም አቀፉን የወንጀል መስፋፋት ጨምሮ ከወንጀል ድርጊቶች ጋር የተያያዘ ነው" ሲልም ሕጉ ያስረዳል። ከዚህም በተጨማሪ ሕጉ የተሻለ ሕክምና ለማግኘት ሲሉ ወደ አሜሪካ የሚገቡ ሰዎችም ላይ የሚደረገውን ቁጥጥርም ያጠብቃል። በመሆኑም ቪዛ አመልካቾች የህክምና ወጪያቸውን ለመሸፈን የሚያስችል የገንዘብ ምንጭና አቅም እንዳላቸው፤ እንዲሁም ህክምናውን ከሚሰጣቸው ዶክተር ጋር ቀጠሮ እንዳላቸው ለቪዛ ኦፊሰሩ በማቅረብ ማሳመን ይጠበቅባቸዋል። የፕሬዚደንቱ ፕረስ ሴክሬታሪ ስቴፋኒ ግሪሻም፤ በመግለጫቸው እንዳሉት "የወሊድ ቱሪዝም ኢንደስትሪው በሆስፒታሎች ወሳኝ ግብዓቶች ላይ ጫና ያሳደረ ሲሆን የወንጀል ድርጊቶችንም አባብሷል ብለዋል። በመሆኑም ሕጉ ይህንን አገራዊ የሆነ ችግር ለመከላከልና አሜሪካን በዚህ ምክንያት ከሚከሰቱ የብሔራዊ ደህንነት አደጋዎች መጠበቅ እንደሚያስችል ጨምረው ተናግረዋል። በወሊድ ቱሪዝም ምን ያህል ህፃናት ተወልደዋል? በየአመቱ ወደ አሜሪካ ከሚያቀኑ ሰዎች ምን ያህል ህፃነት እንደተወለዱ የሚያሳይ የተመዘገበ መረጃ ባይኖርም የተለያዩ አካላት ግን ግምታቸውን ያስቀምጣሉ። እንደ የአሜሪካ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠሪያ ማዕከል መረጃ በአውሮፓዊያኑ 2017 በአሜሪካ ከሚኖሩ የውጭ አገር ዜጎች 10 ሺህ የሚሆኑ ሕፃናት ተወልደዋል። ይህም የቅርብ ጊዜ መረጃ ነው። ይህ ቁጥር በአውሮፓዊያኑ 2007 ከነበረው 7,800 የህፃናት ቁጥር ጨምሯል። የስደተኞች ጥናት ማዕከል ደግሞ በ2016 እና 2017 መጀመሪያው አጋማሽ ጊዜያዊ የጉብኝት ቪዛ ካላቸው እናቶች 33 ሺህ ህፃናት መወለዳቸውን ያስረዳል። አሁን ላይ ነፍሰጡር ሴቶች እስከሚወልዱ ድረስ ለመቆየት ወደ አሜሪካ መግባት እንደሚችሉ የአሜሪካ የጉምሩክና ድንበር ጥበቃ መሥሪያ ቤት አስታውቋል። ይሁን እንጅ እናቶች ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ በመቆየት ለመቅረት ፍላጎት እንዳላቸው ከታመነ ጉዟቸው ሊከለከል ይችላል።
news-55458661
https://www.bbc.com/amharic/news-55458661
በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር ላይ ባለው ችግር ጉዳት መድረሱ ተነገረ
ሰሞኑን ወታደራዊ እንቅስቃሴ እየታየበት ባለው ኢትዮጵያን ከሱዳን ጋር በሚያዋስነው የድንበር አካባቢ በነዋሪዎች ጉዳት ሲደርስ በርካቶች ደግሞ መፈናቀላቸውን የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ገለጸ።
የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ለቢበሲ እንዳስታወቁት በግጭቱ አራት ሰዎች ላይ ጉዳት ሲደርስ ሁለቱ መሞታቸውን ጠቅሰው ከ1700 በላይ ሰዎች ከድንበሩ አካባቢ መፈናቀላቸውን ተናግረዋል። ጥቃቱን ተከትሎ እስከ 200 የሚጠጉ አርሶ አደሮች ለዘመናት ያፈሩት ከፍተኛ ግምት ያለው ንብረት በሱዳን ወታደሮች ወድሞባቸዋል ብለዋል። የሱዳኑ የማስታወቂያ ሚንስትር የአገራቸው ወታደሮች በሁለቱ አገራት አዋሳኝ የድንበር አካባቢ በኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች ተይዞ የቆየ ካሉት መሬት ውስጥ አብዛኛውን መቆጣጠራቸውን ባለፈው ቅዳሜ ዕለት መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። "ማንኛውም ችግር በውይይት ይፈታል ብለን እናምናለን" ብለዋል የማስታወቂያ ሚንስትሩ ፋይሳል ሳሊህ። "ነገር ግን ሠራዊታችን መሬታችንን ለማስመለስ ኃላፊነቱን ይወጣል። በዚህም በአሁኑ ጊዜ ከ60 አስከ 70 በመቶ የሚሆነውን የሱዳን መሬትን መልሶ ይዟል" በማለት ለሮይተርስ ተናግረዋል። በአወዛጋቢው የድንበር አካባቢ ያለው የምዕራብ ጎንደር አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ ለቢቢሲ እንደገለጹት፤ የሱዳን ሠራዊት በድንበር አካባቢ ባሉ ቦታዎች ላይ ጥቃት መሰንዘር የጀመሩት ከጥቅምት ወር ማብቂያ ጀምሮ ነበር። "ምንም እንኳን የሱዳኖች እንቅስቃሴ ጥቅምት 27 ጀምሮ የንብረት ጉዳትን ቢያደርስም በሰው ላይ ጉዳት ስላላደረሰ ነገሮችን ሳናሰፋና ሳናጋንን ለመያዝ ሞክረን ነበር" ብለዋል አስተዳዳሪው። ሆኖም የሱዳን ወታደሮች አንዳንድ ቦታዎችን መያዝ በመጀመራቸው ይህንንም ተግባር ማቆም እንዳለባቸው መነጋገራቸውን የሚጠቅሱት አቶ ደሳለኝ፤ "በኅዳር 3 እና 4 በነበሩት ቀናት አዳዲስ ቦታዎችን በመያዝ የአርሶ አደር ካምፖችን ማቃጠል እና ጉዳት ማድረስ እስከ ትላንትና ድረስም ቀጥሏል" ሲሉ ገልጸዋል። የምዕራብ ጎንደር አስተዳዳሪው እንደሚሉት የሱዳን ወታደሮች በአካባቢው ለተከታታይ ቀናት በወሰዱት እርምጃ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውና ንብረት መውደሙን አመልክተዋል። "የአርሶ አደሩ የተለያዩ ንብረቶች፣ ማሽኖች፣ መጋዘኖች እና እህል በማቃጠል ቀሪውን ደግሞ ሰብስበው ወስደዋል" በማለት ጨምረውም "የማሽላና የጥጥ ምርቶችን እየሰበሰቡ ወደ ቀጠናቸው አጓጉዘዋል" በማለት ሌሎች ንብረቶችን ማቃጠላቸውን ተናግረዋል። በተፈጸመው ጥቃት ሳቢያ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው፤ "ሠላም በር በምትባል መለስተኛ ቀበሌ ከ400 አስከ 500 የሚደርስ አርሶ አደር የሚኖርባት መንደራቸውን ለቀው እንዲወጡ ሆነዋል። በዚህም ወደ 1750 የሚሆኑ ቤተሰቦች ለመፈናቀል ታዳርገዋል" ሲሉ አስረድተዋል። በድንበር አካባቢው ግጭት እንደነበረ ለሮይተርስ የተናገሩት የሱዳን የማስታወቂያ ሚንስትር፤ ወታደሮቻቸው የመከላከል እርምጃ መውሰዳቸውን አመልክተው ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ግጭቶች ጋብ ማለታቸውን ተናግረው ነበር። ሳሊህ ጨምረውም "የሱዳን የደኅንነት ሪፖርት እንዳረጋገጠው ሠራዊቱ የገጠማቸው ኃይሎች ከአደረጃጀት፣ ከስልጠናና ከትጥቅ አንጻር መደበኛ ኃይል እንጂ ሚሊሻ አይደለም" በማለት ግጭቱ ከየትኛው ኃይል ጋር እንደሆነ አመልክተዋል። በድንበሩ አካባቢ በተለያዩ ጊዜያት ግጭቶች ያጋጥሙና በቀላሉ መፍትሔ ያገኙ እንደነበር የተናገሩት የምዕራብ ጎንደር ዞን እተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ የአሁኑ ግን ከዚህ ቀደም ከነበሩት የተለየ ነው ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "የአሁኑ የተደራጀ ሜካናይዝድ ሠራዊት በማሰለፍ በርከት ባለ ከባድ መሣሪያ ታገዞ የተካሄደ ጥቃት ነው። በተጨማሪም ከዚህ በፊት ደርሰውባቸው ወደማያውቁ አዳዲስ ቀጠናዎችን ጭምር ለመያዝ አላማ ያደረገ ነው" ብለዋል። የአካባቢው ማኅበረሰብ ወደ ግጭት አንዳይገባ ጥረት እያደረጉ መሆኑን የሚገልጹት የምዕራብ ጎንደር አስተዳዳሪ "ሕዝቡ እራሱን ለመከላከል ቢችልም ሁሉም ነገር ሕግና ሥርዓትን ተከትሎ እንደሚከናወን እያስረዳን ነው። ነገር ግን ይህ ሁኔታ በመንግሥት መፍትሔ ካላገኘ ነገሮች ሲበዙ ወደ ሌላ አቅጣጫ እንዳያመሩ ስጋት አለ" ብለዋል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ባለፈው ሳምንት ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ሁለቱ አገራት በጉዳዩ ላይ በመንግሥት ደረጃ ግንኙነት ማድረጋቸውን ገልፀው፤ ግጭቱን "የሱዳን መንግሥት ፍላጎት አይደለም" በማለት በስፍራው ባለ የሱዳን መንግሥት መዋቅር ውስጥ በተከሰተ ችግር ምክንያት የተከሰተ መሆኑን አመልክተዋል። በድንበር አካባቢ የተከሰተውን ችግር ተከትሎ የኢትዮጵያው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ደመቀ መኮንን ባለፈው ሳምንት ወደ ሱዳን በመሄድ ከአገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር መወያያታቸው ይታወሳል። ኢትዮጵያና ሱዳን በሚዋሰኑበት አካባቢ ያልተቋጨ የድንበር ይገባኛል ጥያቄ ያለ ሲሆን፤ በተለያዩ ጊዜም በድንበር አካባቢ ግጭቶች እንደሚከሰቱ ሲዘገብ ቆይቷል። የሁለቱ አገራት መንግሥታትም ለረዥም ጊዜ ለቆየው ለዚህ የድንበር ጉዳይ መፍትሔ ለመስጠት በሚል የጋራ የድንበር ኮሚሽን አዋቅረው ተከታታይ ውይይቶችን ቢያደርጉም የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ሳይደርስ እስካሁን ዘልቋል።
news-46679164
https://www.bbc.com/amharic/news-46679164
ማስጠንቀቂያ! 'የሶሻል ሚድያ' አጠቃቀምዎን ቢያስቡበት ይሻላል ይላሉ የዘርፉ ባለሙያዎች
ከዓለማችን ሕዝብ 40 በመቶ ያህሉ ማኅበራዊ ድር-አምባዎች ላይ ተተክሎ ይውላል። 3 ቢሊዮን ሕዝብ ማለት ነው።
አንድ ሰው በቀን ቢያንስ 2 ሰዓት ያህል ማኅበራዊ ድር-አምባዎችን እንደሚጠቀም ይነገራል፤ 'ላይክ' በማድረግ፣ በማጋራት እንዲሁም 'ትዊት' በማድረግ። አንድ ጥናት እንደሚጠቁመው 'ስናፕቻት' የተሰኘው ድር-አምባ ላይ ብቻ ግማሽ ሚሊዮን ፎቶዎች በአንድ ደቂቃ ውስጥ ይሸከረከራሉ። አጀብ! አይደል ታድያ? ነገሩ ይገደናል የሚሉ ሰዎች ግን አንድ ጥያቄ ያነሳሉ። ሕይወታችን ውስጥ እንዲህ ሰርፆ የገባው 'ሶሻል ሚድያ' በአዕምሮ እና አካላዊ ጤናችን ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ምን ያህል ነው? የሚል። • 'ሃሰተኛ ዜና '፡ የኢትዮጵያ የማሕበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ስጋት? ዘመኑ የሶሻል ሚድያ ነው። ምንም ጥያቄ የለውም። ክፉ ደጉን መመዘን ደግሞ የእኛ ሥራ ነው። ጥናቶችም ብቅ ብቅ ማለታቸውን ቀጥለዋል። እንዲያውም በዚህ ዘመን የማይነጥፍ ሥራ ቢኖር የ'ሶሻል ሚድያ' ትሩፋቶች ላይ ያተኮረ ጥናት መሆን አለበት። እርግጥ ነው 'ሶሻል ሚድያ' ገና ወጣት ነው። ፌስቡክ እንኳ ወደመንደራችን ከገባ አስራዎቹ ቢሆነው ነው። ጥናቶቹ በብርቱ ያተኮሩትም ከፌስቡክ በሚገኝ መረጃ ነው። ውጥረት የዛሬ ሦስት ዓመት ገደማ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኝ አንድ መሥሪያ ቤት የተሠራ ጥናት እንደሚያሳየው 'ሶሻል ሚድያ' ውጥረት ከማቃለል ይልቅ ጭራሽ ያባብሳል። 1800 ሰዎች የተሳተፉበት ይህ ጥናት ሴቶች ከወንዶች በላቀ ለውጥረት ተጋላጭ እንደሆኑ ይጠቁማል። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ፤ ጥናቱ ላይ የተሳተፉ ወንዶች ከሴቶች አነስ ባለ መልኩ ወደ ማኅበራዊ ድር-አምባዎች ብቅ ማለታቸው ነው። አንድ የማንካካደው ነገር አለ፤ የበይነ መረብ ግንኙነት ያላቸው ስልኮች ሰዎች እርስ በርስ የሚያደርጉትን ጭውውት እየገደቡ መሆኑ። 'ሙድ' ይህ ጥናት የተወሰደው በአውሮጳውያኑ 2014 ነው። ''እስኪ ስልካችሁን ምዘዙ'' ተባለ፤ "ግማሾቻችሁ ፌስቡካችሁን ከፍታችሁ ለ20 ደቂቃ ያህል አስሱ" የሚል ትዕዛዝ ተከተለ። የተቀሩቱ ደግሞ ወደ ፌስቡክ ድርሽ እንዳይሉ፤ ነገር ግን ሌላ ነገር ማሰስ እንደሚችሉ ተነገራቸው። ውጤቱ ይህንን ጠቆመ። ፌስቡክ የተጠቀሙት ሰዎች ፀባያቸው (ሙድ) ልውጥውጥ ይል ጀመር፤ ጊዜያቸውን እንዲሁ እንዳባከኑ እንደተሰማቸው አሳወቁ። የጥናቱ አንኳር ነጥብ ፌስቡክ እና መሰል ማኅበራዊ ድር-አምባዎች ላይ የምናያቸው ዜናዎች ይጋቡብናል የሚል ነው። ፌስቡካችንን ከዘጋን በኋላ እንኳ፤ ያየነውን ዜና እያሰብን ላልተገባ ጭንቀት እንጋለጣለን ይላሉ የዘርፉ ሰዎች። ሰዎች ደስታቸውን ሲያጋሩን ደስተኛ እንሆናለን፤ ሃዘንን የሚፈጥሩ 'ፖስቶች' ስናይ ደግሞ ሃዘን ይጋባብናል ነው ቀመሩ እንግዲህ። ጭንቀት ትኩረት ማጣት፣ መጨናነቅ፣ ድብርት. . . ከማኅበራዊ ድር-አምባ አጠቃቀማችን ጋር የሚያያዙ መሆናቸውን ደርሰንበታለን ይላሉ አጥኚዎች። ፌስቡክ፣ ትዊተር፣ ኢንስታግራም፣ ዋትስአፕ፣ ቴሌግራም. . . ብቻ ምኑ ቅጡ. . . እኒህን ማኅበራዊ ድር-አምባዎች አብዝተው የሚጠቀሙ ሰዎች 'ወዮላቸው!' ነው የሚለው የተገኘው የጥናት ውጤት። ምክንያቱም እኒህ ሰዎች ጭራሹኑ 'ሶሻል ሚድያ' ከማይጠቀሙት ወይም በመጠኑ ከሚጠቀሙ ሰዎች በላቀ ከላይ ለተጠቀሱት የአዕምሮ ጤንነት ጠንቆች ተጋላጭ ናቸው። እንቅልፍ ድሮ ድሮ 'በደጉ ዘመን'. . . (መቼም ድሮ ተብሎ 'ደጉ ዘመን' ካልታከለበት ለጆሮ አይጥምም በማለት እንጂ). . . ብቻ በቀደመው ጊዜ የሰው ልጅ በጊዜ ወደ መኝታው ያመራ ነበር። ለዚህ ደግሞ ትልቁ ምክንያት የመብራት ነገር ነው። መብራት እንደልብ ባልነበረበት ዘመን የሰው ልጅ በጊዜ ወደ መኝታው ይሄድ ነበር፤ አሁን ግን ሰው ሰራሽ መብራቶች ከመብዛታቸው የተነሳ ቀንና ሌሊቱ ይዛባ ይዟል። እስቲ ስንቶቻችን ነን ወደ መኝታችን ካቀናን በኋላ ትራሳችንን ተደግፈን ከፌስቡክ መንደር የተገኘ ወሬ የምንለቃቅም? • ፌስቡክ የምንጠቀምበት ሰዓት ሊገደብ ነው ሳይንቲስቶች ባደረጉት ጥናት መሠረት 'ሶሻል ሚድያ' እና እንቅልፍ ትልቅ ቁርኝት አላቸው። ይህ ግንኙነታቸው ታድያ ጤናማ አይመስልም፤ ማኅበራዊ ድር-አምባው እንቅልፍ አዛቢ ነውና። የአጥኚዎቹ ምክር "እነ ፌስቡክና ኢንስታግራምን ተጠቀሙ ችግር የለም፤ ነገር ግን እባካችሁ በእንቅልፍ ሰዓት አይሁን" ነው። ሱስ የምን ሱስ አለብዎ? የመጠጥ? የዕፅ? ወይስ. . .? ምንም እንኳ 'ሶሻል ሚድያ' በይፋ ከሱስ ተራ ባይመደብም ሱስ አስያዥ እንደሆነ ይነገራል። በእንግሊዝ አፍ 'ዲስኦርደር' ይባላል፤ መዛባት የሚለው የአማርኛ ፍቺ ሊገልፀው ይችላል። ሁለት አጥኚዎች በዚህ ዙሪያ የተሠሩ በርካቶች ጥናቶችን አዋህደው ከመረመሩ በኋላ የ'ሶሻል ሚድያ' ሱስ የሀኪም ክትትል የሚሻ የአስተሳሰብ መዛባት ያመጣል ሲሉ ይደመድማሉ። ከልክ ያለፈ የ'ሶሻል ሚዲያ' አጠቃቀም ከሰዎች ጋር ያለንን ግንኙነት ያውካል፤ የትምህርት አቀባበላችንን ይበክላል፤ የእውነተኛውን ዓለም ፈተና በፅኑ እንዳንጋፈጥ ይጋርደናል ሲሉ ሳይንቲስቶቹ ይከራከራሉ። በራስ መተማመን ፌስቡክና ኢንስታግራም ላይ ከወገባቸው ቀጠን፤ ከመቀመጫቸው ደልደል ብለው የሚታዩ ሴቶች በወጣት ሴቶች ራስ መተማመን ላይ አሉታዊ አስተዋፅዖ እንሚያመጡ ተደጋግሞ ይነገራል። ከ18-34 ዕድሜ ላይ የሚገኙ 1500 ወጣቶች የተሳተፉበት ጥናት ላይ እንደተመለከተው ታዳጊዎች ማኅበራዊ ድር-አምባ ላይ ከሚያይዋቸው ሰዎች ጋር ራሳቸውን አነፃፅረው የበታችነት ስሜት ይሰማቸዋል። የፍቅር ግኑኝነት "የፍቅር ጓደኛዎ ፌስቡክ ላይ ተቃራኒ ፆታ ጓደኛ ሲያደርጉ ምን ዓይነት ስሜት ይሰዋዎታል?" ከ17-24 ዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ወጣቶች የቀረበ ጥያቄ ነበር። አብዛኛዎቹ ምላሻቸው ተመሳሳይ ነበር፤ 'ምቾት አይሰጠንም' የሚል። ቅናት ቢጤ ይወረናል፣ ወደ ጭቅጭቅ እናመራለን እና መሰል መልሶች የመመለሻ ቅፁ ላይ ሰፍረው ታይተዋል። ስለ ቅናት ከተነሳ ደግሞ የፍቅር ግንኙነት ውስጥ ያሉ ብቻ ሳይሆኑ ላጤዎችም ራሳቸውን 'ሶሻል ሚድያ' ላይ ካሉ 'ስኬታማ' ሰዎች ጋር አነፃፅረው የሚሰማቸውን ስሜትም ይጠቀሳል። • ፌስቡክ ግላዊ መረጃን አሳልፎ በመስጠት ተከሰሰ ብቸኝነትም የሶሻል ሚድያ ሌላኛው አሉታዊ ጎን እንደሆነ መነገር ከጀመረም ሰንበትበት ብሏል። ማኅበራዊ ሚድያን አብዝተው የሚበዘብዙ ሰዎች ከማኅበረሰቡ እንደተገለሉ ይሰማቸዋል ይላል 7 ሺህ ሰዎች የተሳተፉበት ሌላ ጥናት። እስቲ እናጠቃለው. . . እርግጥ አብዛኛዎቹ ጥናቶች የተሠሩት አደጉ በሚባሉ ሀገራት ነው። ነገር ግን ሳይንቲስቶች መከራከሪያ ያስቀምጣሉ። እኒህ የ'ሶሻል ሚድያ' ትሩፋቶች ዓለም አቀፋዊ ናቸው። እያደጉ ባሉ ሀገራት አሁን ባይስተዋሉ እንኳ ትንሽ ቆይቶ መምጣታቸው አይቀርምና። "ዋናው ቁም ነገር". . . እንደ ሳይንቲስቶቹ ምክር. . . "ዋናው ቁም ነገር ማኅበራዊ ድር-አምባዎችን በአግባቡና በተመጠነ መልኩ መጠቀም ነው" አዎንታዊ ውጤታቸው የሚካድ አይደለምና።
news-53836089
https://www.bbc.com/amharic/news-53836089
ብራዚል፡ተደፍራ ያረገዘች ታዳጊ ፅንስ እንዳታቋርጥ በሚል መረጃዋ መውጣቱ ቁጣን ቀሰቀሰ
ወሲባዊ ጥቃት የደረሰባት የአስር አመት ታዳጊ ዝርዝር መረጃ በማህበራዊ ሚዲያና በተለያዩ ድረገፆች ላይ መውጣቱ በርካታ ብራዚላውያንን አስቆጥቷል።
የልጅቷ ስምና ዝርዝር መረጃ የወጣው ፅንስ ማቋረጥን በሚቃወሙ ቡድኖች እንደሆነም ተገልጿል። ታዳጊዋ በመደፈሯ ያረገዘች ሲሆን ፅንሱንም ለማቋረጥ ከሰሞኑ ቀጠሮ ተይዞላት ነበር። ፅንሱን ማቋረጥ የለባትም የሚሉት እነዚህ ቡድኖች መረጃዋን ከማውጣት በተጨማሪም ሆስፒታሉም ደጃፍ ላይ ለተቃውሞ ተሰባስበው ነበር። ታዳጊዋን የደፈራት ግለሰብ ከሰሞኑ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል። የታዳጊዋ መረጃ መውጣት በብራዚላውያን ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን ማቀጣጠሉን ተከትሎ ጉግል፣ ፌስቡክና ትዊተር የታዳጊዋን የግል መረጃ ከገፆቻቸው እንዲያጠፉ አንድ ዳኛም ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። ዳኛ ሳሙኤል ሚራንዳ ጎንካልቭስ ኩባንያዎቹ መረጃውን ለማጥፋት 24 ሰዓታት የሰጧቸው ሲሆን፤ ይህንን ተግባራዊ የማያደርጉ ከሆነ በቀን 9 ሺህ ዶላር እንዲቀጡም ወስነዋል። ፅንስ ማቋረጥ ላይ ጠበቅ ያለ ህግ ያላት ብራዚል በአንዳንድ ሁኔታዎች ግን ፍቃድ አለው። ለተደፈሩ፣ የእናቲቷ ህይወት አደጋ ውስጥ በሚገባበት ወቅት እንዲሁም ፅንሱ መወለድ የማይችልበት ህመም ካለው ፅንስ ማቋረጥ ይፈቀዳል። ታዳጊዋ ፅንሱን የማቋረጥ ህጋዊ ድጋፍ ቢኖራትም ይህንን የሚቃወሙ ቡድኖች በሆስፒታሉ ደጃፍ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። የሆስፒታሉን ሰራተኞችም "ነፍሰ ገዳዮች" እያሉም ሲጮሁባቸው የነበረ ሲሆን ወደ ሆስፒታሉ ውስጥ ለመግባት የሞከሩም እንዳሉ ተነግሯል። የፀጥታ ኃይሎችም ጣልቃ በመግባት በትነዋቸዋል ተብሏል። የፅንስ ማቋረጥን እንደ ምርጫ የሚያዩት ደጋፊዎች ታዳጊዋን በመኪና ደብቀው ያመጧት ሲሆን በሆስፒታሉም በኋላ በር እንዲሁ ደብቀው አስገብተዋታል። የቢቢሲ ደቡብ አሜሪካ ዘጋቢ ካቲ ዋትሰን እንደምትናገረው የታዳጊዋን መረጃ ይፋ ያደረገችው በፅንፈኝነቷ የምትታወቀው ሳራ ጂሮሚኒ የምትባል ግለሰብ መሆኗን ነው። ሳራ የታዳጊዋን መረጃ ይፋ በማድረጓ ክስ ይጠብቃት እንደሆነ እስካሁን ያልተገለፀ ሲሆን የህግ ባለሙያዎች ለቢቢሲ እንደተናገሩት ግጭትን በማነሳሳት ልትከሰስ እንደምትችል ጠቁመዋል። ሳራ ጂሮሚኒ "ኦስ 300 ዱ ብራሲል" የተባለ የቀኝ ክንፍ አክራሪ እንቅስቃሴ መሪ ስትሆን የፕሬዚዳንት ጄይር ቦልሶናሮም ቀንደኛ ደጋፊ ናት ተብሏል። በሰኔ ወር ላይ በጠቅላይ ፍርድ ቤት አካባቢ "ፀረ-ዲሞክራሲያዊ" ሰልፍ አስተባብራለች በሚልም ለአጭር ጊዜ በቁጥጥር ስር ውላ ነበር።
news-56228220
https://www.bbc.com/amharic/news-56228220
ትግራይ ፡ የኢትዮጵያ መንግሥት አሜሪካ በውስጥ ጉዳዬ ጣልቃ መግባት የለባትም አለ
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አሜሪካ በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ መግባት የለባትም ሲል ምላሽ ሰጠ።
የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር "አሜሪካ በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ማውጣቷ በተለይም የአማራ ክልል ኃይሎች ስምሪት በመግለጫው መጠቀሱ የሚያሳዝን ነው" ብሏል በመግለጫው። ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ይህን ያለው ትናንት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የኤርትራ ሠራዊት እና የአማራ ክልል ኃይል ከትግራይ ክልል መውጣት አለባቸው የሚል መግለጫን ማውጣቱን ተከትሎ ነው። የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ለዚህ በሰጠው ምላሽ "እንደ ሉዓላዊት አገር ይህ የኢትዮጵያ መንግሥት ብቻ ኃላፊነት ነው ያለ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ በግዛቷ ውስጥ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የትኛውንም የጸጥታ መዋቅር ማሰማራት የመንግሥት ኃላፊነት ነው" ብሏል በመግለጫው። "የፌደራሉ መንግሥት በሕገ-መንግሥቱ በተሰጠው ኃላፊነት መሠረት ሰላም እና ደኅንነትን በማረጋገጥ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓትን ያስከብራል" ያለው የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መግለጫ፤ ይህን ኃላፊነት ታሳቢ ባደረገ መልኩ "በትግራይ ክልል የሕግ ማስከበር ተልዕኮ መካሄዱን" አስታውቋል። የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር በትናንቱ መግለጫው የኤርትራ ሠራዊት በትግራይ ተሰማርቷል ስለመባሉ ምንም ያለው ነገር ባይኖርም፤ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥትም ሆነ የኤርትራ መንግሥት በትግራዩ ጦርነት ኤርትራ ተሳትፎ የላትም ብለዋል። ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጽ/ቤት የወጣው የአሜሪካ መግለጫ፤ "የኤርትራ እና የአማራ ክልል ኃይሎች ከትግራይ መውጣታቸው ወሳኝነት ያለወቅ ቀዳሚ እርምጃ ነው" ካለ በኋላ፤ "በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም አካላት እራሳቸውን ከኃይል እርምጃዎች ቆጥበው በትግራይ ክልል ውስጥ ድጋፍ የሚያሻቸው ሰዎች ሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲደርሳቸው መፍቀድ ይኖርባቸዋል" ብሏል። የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በበኩሉ፤ ከግጭቱ ጋር በተያያዘ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበር ድጋፍ እያደረገ መሆኑን እና 3 ሚሊዮን ሕዝብ ጋር መድረስ መቻሉን ገልጿል። ጨምሮም መንግሥት 70 በመቶ ድጋፍ በራሱ እያደረገ መሆኑ እና ቀሪውን 30 በመቶ ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ድጋፍ እያደረጉ ነው ብሏል። የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን በመግለጫቸው በትግራይ ክልል የተከሰተውን ቀውስ ማስቆም አስፈላጊነት ላይ፣ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦትን በተመለከተ፣ እንዲሁም ተፈጽመዋል የተባሉ ግፎችና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚመረምር የተሟላ፤ ገለልተኛ ዓለም አቀፍ መርማሪ ቡድን እንዲገባ መፍቀድን በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በተደጋጋሚ መነጋገራቸውን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ በትግራይ ክልል ያለው የጸጥታ ሁኔታ እየተሻሻለ በመሆኑ የሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ ተቋማት ያለገደብ ወደ ክልሉ ገብተው ድጋፍ እንዲያደርጉ ፈቅጃለሁ ብሏል። እንደማሳያም የዓለም የምግብ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር በትግራይ የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት መሻሻል ማሳየቱን እና ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መጠቆማቸውን በመግለጫው ተመልክቷል። ተፈጽመዋል ስለተባሉት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችም በተመለከተ መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት የማስጠበቅ ኃላፊነት እንዳለበት ገልጾ፤ አስፈላጊውን ምርመራ በማድረግ አጥፊዎች ለፍርድ ለማቅረብ ቁርጠኝነት እንዳለው አስታውቋል። የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር በመግለጫው መንግሥት "ዝርዝር ምርመራ አድርጎ" ተጠያቂዎችን ለፍርድ እንደሚያቀርብ ገልጿል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም መንግሥት ከዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ድጋፍን ከመቀበል በሻጋር፤ አግባብ ካለው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አካል ጋር በጥምረት ምርመራ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መግለጫ አመላክቷል። በመግለጫው ላይ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጥያቄዎች ሁለት መሆናቸው የተጠቀሰ ሲሆን ፤ እነዚህም፤ የሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ ያልተገደበ ፍቃድ መስጠት እና ተፈጽመዋል በተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በገለልተኛ አካል ይጣሩ የሚሉ ናቸው። እነዚህ ሁለት አበየት ጉዳዮች በአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የተነሱ መሆኑን ያስታወሰው ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ፤ መንግሥት አዎንታዊ እና ገንቢ በሆነ መልኩ ለእነዚህ ሁለት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ቁርጠኝነቱን አሳይቷል ብሏል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በትግራይ ያለውን ሁኔታ በሚመለከት መግለጫ ያወጣው አምነስቲ ኢንተርናሽናል በአክሱም ከተማ በኤርትራ ወታደሮች በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የሚገልጽ ሪፖርት ማውጣቱን ተከትሎ ነበር።
41911332
https://www.bbc.com/amharic/41911332
ሳዑዲ አረቢያ የጣለችው እገዳ ለየመን ጥፋት ነው
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና የዓለምአቀፉ ቀይ መስቀል ማሕበር በየመን ያለውን ሁኔታ ለሚሊዮኖች ሕይወት አደጋ ነው ሲሉ ገልፀውታል።
ሳዑዲ አረቢያ የየመን ሁቲ ታጣቂዎች በኢራን እየታገዙ ነው ስትል ትወቅሳለች፤ ቴህራን ከዚህ ተግባሯም እንድትቆጠብም አሳስበዋል። ኢራን በበኩሏ ለሁቲ ታጣቂዎች ምንም ዓይነት እርዳታ እያደርኩ አይደለም ስትል ክሱን ውድቅ ታደርጋለች። ዕለተ ቅዳሜ ወደ ሳዑዲ ዋና ከተማ ሪያድ የተተኮሰ ሚሳዔል በሳዑዲ ተመቶ እንደወደቀ ይታወሳል። የሳዑዲ ልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማን "ለአማፂያን የጦር መሣሪያ ማቅረብ ከጦርነት አይተናነስም" ሲሉ ተሰምተዋል። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአሜሪካ አማባሳደር ኒኪ ሄሊ ሚሳዔሎቹ የኢራን ሳይሆኑ አይቀሩም ብለዋል። ኢራን የመንግሥታቱ ድርጅትን ሕግ እየጣሰች ነው፤ ተጠያቂ ልትሆንና እገዳ ሊጣልባትም ይገባል ሲሉ ተድምጠዋል። ኢራን ወቀሳውን "የሚሳዔል ጥቃቱ አማፅያኑ በሳዑዲ እየደረሳበቸው ያለውን ወረራ ለመዋጋት ያደረጉት የተናጥል ትግል እንጂ የቴህራን እጅ የለበትም" ስትል አጣጥላዋለች። በሳዑዲ የሚመራው ጥምር ኃይል የሚሳዔል ጥቃቱን ተከትሎ ወደ የመን የሚያስገቡ በሮችን በጠቅላላ ላልተወሰነ ጊዜ ዘግቷል። ነገር ግን ሰብዓዊ እርዳታ በጥብቅ ፍተሻ አልፎ ሊሰጥ እንደሚችል አስታውቋል። ነገር ግን ጄኔቫ የሚገኘው የቢቢሲው ኢሞገን ፎክስ እርዳታ ድርጅቶች የድንበሮቹ መዘጋትን ተከትሎ ቁጣቸውን እየገለፁ እንደሆነ ዘግቧል። የዓለምአቀፉ ቀይ መስቀል ማሕበር 900 ሺህ ሰዎችን ያጠቃውን ኮሌራ ለመመከት ወደ የመን ያስጫነው የክሎሪን ክኒን ደንበር መሻገር እንዳልቻለ ተናግሯል። "እኚህ መግቢያ በሮች እስካልተከፈቱ ድረስ በየመን ያለው ቀውስ ሊፈታ አይችልም። ሃገሪቱ ከአሁን በፊት ታይቶ በማያውቅ ሁኔታ ትልቅ ችግር ውስጥ ነች" ሲሉ የቀይ መስቀሉ ጄንስ ላርክ ይናገራሉ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰባት ሚሊዮን የመናውያን የረሃብ አደጋ ላይ ናቸው ሲል ማስታወቁ አይዘነጋም። ሃገሪቱ ከውጭ በሚገባ ምግብ ላይ ሙሉ በሙሉ ጥገኛ ስትሆን አሁን ላይ ግን ነዳጅም ሆነ መድሐኒት ለማስገባት እጅግ አዳጋች ነው። በየመን ግጭት እስካሁን ደረስ 8 ሺህ 670 ሰዎች የሞቱ ሲሆን 49 ሺህ 960 ሰዎች በአየር ድብደባ ቆስለዋል፤ እንደተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ገለፃ።
news-53012387
https://www.bbc.com/amharic/news-53012387
አስገድዶ ሊደፍራት የሞከረውን የገደለችው ናይጄሪያዊት ታዳጊ ነጻ ተባለች
የናይጄሪያ አቃቤ ሕግ አስገድዶ ሊደፍራት የሞከረውን የ51 ዓመት ግለሰብ የገደለችው የ15 ዓመት ታዳጊ ክስ ሊመሰረትባት አይገባልም አለ።
በርካቶች ታዳጊዋ እራሷን ለመከላከል ስትል በወሰደችው እርምጃ መጠየቅ የለባትም ሲሉ ድምጻቸውን አሰምተዋል። ከሦስት ወራት በፊት የአባቷ ጓደኛ ወደ ሆነው ግለሰብ መኖሪያ የቤት ውስጥ ሥራ ለመስራት ከሄደች በኋላ ግለሰቡ አስገድዶ ሊደርፍራት ሲሞክር በስለት እንደወጋችው ፖሊስ አስታውቋል። አቃቤ ሕግ በእስር ላይ የነበረችው የ15 ዓመት ታዳጊ በ51 ዓመቱ ግለሰብ የግድያ ወንጀል ክስ ሊመሰረትባት የሚያስችል ማስረጃ ባለመኖሩ ክስ ሊመሰረትባት አይችልም ካለ በኋላ ታዳጊዋ ነጻ ወጥታለች። በእስር ላይ በነበረችበት ወቅት በርካቶች እራሷን ለመከላከል ስትል በወሰደችው እርምጃ መጠየቅ የለባትም ሲሉ ድምጻቸውን አሰምተዋል። በናይጄሪያ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች በተደጋጋሚ ይፈጸማሉ። በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችም ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች ይቁሙ ሲሉ በኢንተርኔት አማካኝነት ፊርማ ሲያስባስቡ ቆይተዋል። የታዳጊዋ ወላጆች በጉዳዩ ላያ ያሉት የለም። በተመሳሳይ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተቀሰቀሰ በኋላ በናይጄሪያ ጾታዊ ጥቃት እየደረሰባቸው ያሉ ሴቶች ቁጥር በፍጥነት መጨመሩ ተነግሯል። የናይጄሪያ የሴቶች ጉዳይ ሚንስትሯ ፖውሊን ታለን፤ በእንቅስቃሴ ገደቡ ወቅት ሴቶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት በአስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ ጭምሯል ብለዋል። "ሴቶች እና ህጻናት ከበዳዮቻቸው ጋር በአንድ ቤት ውስጥ ተቆልፎባቸዋል" ብለዋል። እ.አ.አ. 2019 ላይ ኤንኦአይ የተባለ ድርጅት ይፋ ያደረገው ጥናት እንዳሳየው፤ ከሦስት ናይጄሪያዊያን ሴቶች አንዷ 25 ዓመት እስኪሆናት ድረስ የተለያያ አይነት መልክ ካላቸው ጾታን መሰረት ካደረጉ ጥቃቶች መካከል ቢያንስ አንድ ጥቃት ይሰነዘርባታል ይላል። በናይጄሪያ በርካታ ሪፖርት ሳይደረጉ የሚቀሩ የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች ይኖራሉ። ጥቃት አድራሾቹ የቤተሰብ አባል መሆናቸው፣ አድሎ እና መገለልን በመፍራት ወይም በፍርድ ሂደት ላይ ዕምነት ማጣት ብዙ ጊዜ የሚጠቀሱ ምክንያቶች ናቸው።
news-56369843
https://www.bbc.com/amharic/news-56369843
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት በትግራይ ሁኔታ' ከፍተኛ ስጋት አድሮባቸዋል'-ዋይት ሐውስ
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በትግራይ ካለው ግጭት ጋር ተያይዞ "ከፍተኛ ስጋት እንዳደረባቸው" የዋይት ሐውስ የፕሬስ ሴክሬታሪ ጄን ሳኪ ተናገሩ።
የፕሬስ ሴክሬታሪዋ ይህንን የተናገሩት በትናንትናው ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው። "ፕሬዚዳንቱ በሁኔታው ከፍተኛ ስጋት ገብቷቸዋል፤ ጉዳዩንም በጥልቀት እየተከታተሉት ነው" በማለት ፕሬስ ሴክሬታሪዋ አስረድተዋል። ፕሬዚዳንቱ በክልሉ ላይ ያለውን የሰብዓዊ ቀውስ እንደተረዱትና አስተዳዳራቸውም በአካባቢው ያለው ነገር ተሻሽሎ ማየት ፍላጎት እንዳለው ተገልጿል። ለዚህም በክልሉ ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረስ እንዲቻል ያልተገደበ የእርዳታ ሠራተኞች መግባትንም አስፈላጊነትም እንደተነሳ ተጠቁሟል። በፌደራል መንግሥቱና በትግራይ ኃይሎች መካከል በተነሳው ግጭት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሞተዋል እንዲሁም በመቶ ሺዎች ደግሞ ከመኖያቸው መፈናቀላቸውን የረድኤት ድርጅቶች ገልጸዋል። በዚሁ በያዝነው ሳምንት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በትግራይ ሕዝብ ላይ "የዘር ማፅዳት ወንጀል" መፈጸሙን ተናግረዋል። የሰብዓዊ መብት ጥሰቶቹን ከማስቆም በተጨማሪ የጎረቤት አገር ኤርትራ ወታደሮችና የአጎራባቹ ክልል አማራ ሚሊሺያ እንዲወጡም ጠይቀዋል። "በትግራይ ክልል ውስጥ ከኤርትራ የመጡ የውጭ አገር ሠራዊት አባላት አሉ እንዲሁም ከአጎራባቹ ክልል አማራ ክልል የገቡ ወታደሮች አሉ። እነዚህ ኃይሎች ሊወጡ ይገባል" በማለት አፅንኦት ሰጥተዋል። ከዚህ ቀደም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የተጠቀሱት ኃይሎች ከትግራይ ክልል እንዲወጡና ተኩስ አቁም እንዲደረግ በመጠየቅ መግለጫ ማውጣቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምላሽ መስጠቱ ይታወሳል። የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በሰጠው ምላሽ "እንደ ሉዓላዊት አገር ይህ የኢትዮጵያ መንግሥት ብቻ ኃላፊነት ነው" ያለ ሲሆን፤ "ኢትዮጵያ በግዛቷ ውስጥ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የትኛውንም የጸጥታ መዋቅር ማሰማራት የመንግሥት ኃላፊነት ነው" ብሏል በመግለጫው። ከዚህም ጋር ተያይዞ "አሜሪካ በኢትዯጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት የለባትም" የሚሉና የመንግሥትን አቋም የሚደግፉ ሰልፎች በአሜሪካ የተካሄዱ ሲሆን፤ በተቃራኒው "ጦርነቱ የትግራይ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረ ነው" የሚሉ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል። በፌደራል መንግሥቱና በህወሓት ኃይል መካከል ያለው ቁርሾ ተባብሶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወታደራዊ ዘመቻ እንዲካሄድ ያዘዙት ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወታደራዊ ዘመቻውን ያዘዙት ህወሓት በክልሉ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ ጥቃት በመፈፀሙ እንደሆነ ተናግረዋል። ህወሓት በበኩሉ የሰሜን ዕዝን የተቆጣጠረውና ድንገተኛ ጥቃት ያደረሰው የፌደራል መንግሥቱ በክልሉ ያለውን ጣልቃ ገብነት በመፍራት እንደሆነ ይናገራል።
news-55314972
https://www.bbc.com/amharic/news-55314972
ኮሮናቫይረስ ፡ ኬንያ 24 ሚሊየን 'ዶዝ' ክትባት ማዘዟ ተነገረ
ኬንያ 24 ሚሊየን የኮቪድ-19 ክትባት ብልቃጦችን ማዘዟን የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴርን ጠቅሶ ዘ ስታር ጋዜጣ ዘገበ።
የኬንያ መንግሥት 10 ቢሊየን የኬንያ ሽልንግ (89 ሚሊየን ዶላር) ገንዘብ ለክትባቱ እንደሚያወጣም ጋዜጣው አስነብቧል። ይሁን እንጅ ምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር የትኛውን ክትባት እንዳዘዘች የተገለፀ ነገር የለም። እንደ ሪፖርቱ ከሆነ የጤና ሚኒስቴር ክትባቱን ለማግኘት በዓለም ዙሪያ ክትባትና የጤና አገልግሎት ማስፋፊያ ፕሮግራሞችን ለሚረዳው የዓለም አቀፍ ለጋሾች ጥምረት በእንግሊዝኛ ምህፃረ ቃሉ 'ጋቪ' ጥያቄ ያቀረበው ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። ኬንያ ያዘዘችው የክትባት መጠንም 20 በመቶ የሚሆነውን ሕዝቧን ለመከተብ በቂ ነው ብላለች። የዓለም ባንክ የኬንያ የሕዝብ ብዛት ከ52 ሚሊየን በላይ እንደሆነ ያስቀምጣል። ክትባቱን በቅድሚያ ከሚወስዱ ሰዎች ዝርዝር ውስጥም ግንባር ቀደም የጤና ባለሙያዎች፣ አረጋውያን እና ከባድ የጤና እክል ያለባቸው ሰዎች መሆናቸው ተገልጿል። በዚህ ዓመት አጋማሽ ላይ ጋቪ፤ እያንዳንዱ የኮቪድ-19 ክትባት 3 ዶላር ድረስ እንደሚያስወጣ መናገሩ ይታወሳል። ጋቪ ወደ ዘጠኝ ከሚጠጉ እጩ ክትባትን ከሚያመርቱ ተቋማት ጋር ስምምነቶችን ተፈራርሟል። እስካሁን በተደረጉ ምርምሮችና ሙከራዎች በርካታ ተስፋ ሰጪ የክትባት ውጤቶች መገኘታቸው ከመነገሩ ባሻገር፤ በሽታውን ለመከላከል ያስችላሉ የተባሉ ጥቂት ክትባቶችም ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ለበሽታው ተጋላጭ ናቸው ለተባሉ ሰዎች በአንዳንድ አገራት መሰጠት ተጀምሯል። በዚህ ረገድ ቀዳሚውን የተጠቃሚነት ዕድል ያገኙት ባለጸጋ አገራት ናቸው። የዓለም ጤና ድርጅትም ክትባቶቹ ለሁሉም እንዲዳረስ ጥረት እያደረገ መሆኑን አመልክቷል። ሌሎች አገራትም ክትባቱን ለማቅረብ ባላቸው አማራጮች ሁሉ እየሞከሩ እንደሆነ እየገለፁ ነው። ኢትዮጵያም ኮቫክስ ከተሰኘው ዓለም አቀፍ የክትባት ድጋፍ ሰጪና እቅራቢ በኩል ለአገልግሎት ከሚቀርቡት የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት ጥያቄ እንዳቀረበች የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ባለፈው ሳምንት ገልጸዋል። ሚኒስትሯ ጨምረውም ለአገልግሎት ብቁ ከሆኑ የክትባት ዓይነቶች መካከል ኢትዮጵያም እንድታገኝ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረው፤ በኮቫክስ በኩል ክትባቱን በፍጥነት ለማግኘትና በቅድሚያ መከተብ ለሚገባቸው ወገኖች እንዲደርስ እንደሚደረግ ገልጸዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ አንድ ዓመት ሊሞላው ተቃርቧል። በአፍሪካ ከ2.3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በበሽታው ሲያዙ ከ56 ሺህ በላይ ደግሞ ለሞት ተዳርገዋል። ከዚህ ውስጥ ደግሞ በኢትዮጵያ ከ117 ሺህ በላይ ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን ከ1 ሺህ 800 በላይ ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል። ከ72 ሚሊዮን በላይ የምድራችን ነዋሪዎችም በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን ከ1.6 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በወረርሽኙ ሰበብ ሕይወታቸውን ማጣታቸው የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ያሳያል።
42985380
https://www.bbc.com/amharic/42985380
ህንዳዊቷ ጥሎሽ ባለመክፈሏ ኩላሊቴን ሰርቆኛል ስትል ባሏን ወነጀለች
ጥሎሽ አልከፈልሽም በማለት የህንዳዊቷን ኩላሊት የሰረቁት ባለቤቷና የባለቤቷ ወንድምን ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል።
የሀገሪቱ ሚዲያ እንደዘገቡትም በምዕራብ ቤንጋል ነዋሪነቷን ያደረገችው ይህች ሴት ከሁለት ዓመታት በፊት በከፍተኛ ሆድ ህመም ትሰቃይ ነበርም ይህንንም ተከትሎ ባለቤቷ የትርፍ አንጀት ቀዶ ጥገና ለማድረግም ማመቻቸቱ ተዘግቧል። በአውሮፓውያኑ ባለፈው ዓመት መጨረሻም ላይ በተደረገላት ሁለት የህክምና ምርመራዎች አንደኛዋ ኩላሊቷ እንደሌለም ማረጋገጥ ተችሏል። ባለቤቷም ለዓመታት ያህልም "ጥሎሽ" ልትሰጠው እንደሚገባም ሲጨቀጭቃትም ነበር። በህንድ ባህል የጥሎሽ ክፍያ ከሴት ሙሽሪት ቤተሰብ ለወንድ ቤተሰብ የሚሰጥ ሲሆን ከተከለከለም ከአምስት አስርት ዓመታት በላይን አስቆጥሯል። ይህ ጥቃት የደረሰባት ሪታ ሳርካር ለህንድ ሚዲያ እንደተናገረችውም ለዓመታትም ያህል በጥሎሽ ምክንያት ከፍተኛ የሆነ የቤት ውስጥ ጥቃትም ባሏ ያደርስባትም እንደነበር ገልፃለች። "ባለቤቴ ኮልካታ በሚገኝ አንድ የግል ህክምና ወሰደኝ፤ እሱም ሆነ በሆስፒታሉ የሚሰሩ ሰራተኞች የትርፍ አንጀቴን በቀዶ ህክምና ባስወጣው እንደሚሻለኝ ነገሩኝ" በማለት ለሂንዱስታን ታይምስ ተናግራለች። "ባለቤቴም ኮልኮታ ላይ ስለተፈፀመው ቀዶ ጥገና ለማንም ትንፍሽ እንዳልልም አስጠነቀቀኝ" ትላለች። ከወራትም በኋላ ህመም ሲሰማት ቤተሰቦቿ ዶክተር ጋር ወሰዷት። በተደረገው ምርመራ የቀኝ ጎን ኩላሊቷ እንደጠፋም ታወቀ። ይህ የተረጋገጠውም በሁለተኛው ምርመራ ነው። "ለምን ስለ ቀዶ ህክምናው ለማንም እንዳልናገር ያደረገኝ ምክንያቱን አሁን ተረዳሁት" በማለት ለሂንዱስታን ታይምስ ተናግራለች። "ቤተሰቦቼ ጥሎሽ መክፈል ስላልቻሉ ባሌ ኩላሊቴን ሸጠው" ብላለች።
48523383
https://www.bbc.com/amharic/48523383
በአለም ከተዘነጉ መፈናቀሎች ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያ ተካታለች
የኖርዌጂያን የስደተኞች ካውንስል በአለማችን የተዘነጉ መፈናቀሎች በሚል ባወጣው አመታዊ ሪፖርት ላይ ኢትዮጵያ በዘጠነኛነት ተቀመጠች።
ሹቦ ቤክሶ ከምዕራብ ጉጂ ከተፈነቀሉት መካከል አንዷ ነች። የሀገራት ዝርዝሩ ያካተተው በ2018 የተከሰተውን መፈናቀል መሆኑን የጠቀሰው ሪፖርቱ በቀዳሚነት ካሜሮን፣ በማስከተል ኮንጎ የስደተኞች ጉዳይ ቸል የተባለባቸው ሀገራት በሚል ተቀምጠዋል። ባለፈው የፈረንጆች አመት ብቻ በኢትዮጵያ ውስጥ 2.9 ሚሊየን የተፈናቀሉ ወገኖች መኖራቸውን ያስታወሰው ሪፖርቱ ይህም ሀገሪቱን በአለም አቀፍ ደረጃ ቀዳሚ ያደርጋታል ብሏል። ተፈናቃይ ዜጎች በተጣበበ ስፍራ፣ በትምህርት ቤቶችና በቤተ ክርተስትያናት ለመኖር ተገድደዋል የሚለው የኖርዌጂያን የስደተኞች ካውንስል ሪፖርት በርካቶች ወደ ቀያቸው የተመለሱ ቢሆንም አሁንም ግን በመመለሳቸው ደህንነት አይሰማቸውም ሲል ያትታል። • የሱዳን ተቃውሞ፡ የሟቾች ቁጥር 60 ደርሷል • ''ወደ ኢትዮጵያ የምናደርገውን ጉዞ አንሰርዝም'' በኢትዮጲያ ውስጥ ባለፈው ዓመት ብቻ 8 ሚሊየን ሰዎች የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸው ነበር ያለው ሪፖርቱ ከዓለም አቀፍ ሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች የተገኘው እርዳታም ከተጠየቀው ግማሹ ብቻ መሆኑንም ያስታውሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ያመጡት ለውጥ፣ ከኤርትራ ጋር የፈጠሩት ሰላም በመገናኛ ብዙሃን ዘንድ በሰፊው ሽፋን ቢያገኝም የእነዚህ ተፈናቃይ ወገኖች ጉዳይ ግን የመገናኛ ብዙኀኑን አይንና ጆሮ ተነፍጎ ነበር ሲል ያስረዳል። የኖርዌጂያን የስደተኞች ካውንስል ሪፖርት እንደጠቀሰው የሰብዓዊ እርዳታ በፍላጎት ላይ የተመሰረተ ብቻ ቢሆንም አንዳንድ ቀውሶች ግን ከሌሎች በተለየ ትኩረትና ድጋፍ ያገኛሉ ብሏል። በአለማችን አንድ ጥግ በሚደርስ ሰብአዊና ተፈጥሯዊ ቀውስ ምክንያት የሚጎዱ ሰዎች ትኩረት አግኝተው የተለያዩ እርዳታና ድጋፎች ሲያገኙ ሌሎች ደግሞ ዞር ብሎ የሚያያቸው የማያገኙበት ምክንያት ምንድነው ሲል ይጠይቃል። ምናልባት ከጂኦ ፖለቲካዊ ፍላጎት የተነሳ ሊሆን ይችላል በማለት ግምቱን ያስቀመጠው ሪፖርቱ ምናልባትም ተጎጂዎች የሚገኙበት ስፍራ የራቀ መሆንና ተጎጂዎችን ለመለየት አዳጋች ሆኖ ሊሆን ይችላል ሲል መላምቱን ያስቀምጣል። ግብረ ሰናይ ድርጅቱ ይህንን የሀገራት ዝርዝር ያዘጋጀበትን ምክንያት ሲጠቅስ የአለም አቀፍ ማህበረሰቡን ትኩረት እምብዛም ትኩረት ያልሳቡት መፈናቀሎች ላይ፣ ፖለቲከኞች የዘነጓቸው ወይንም ትኩረት የነፈጓቸውን፣ የሚያስፈልጋቸውን ጥበቃ እና ድጋፍ ያላገኙ ሰዎች ላይ ብርሀን ለመፈንጠቅ እንደሆነ ያትታል። ለውጥ ለማምጣት ስለእነዚህ ሰዎችና ስለ ደረሰው ቀውስ በቂ መረጃ መኖር አስፈላጊ ነው ያለው ሪፖርቱ፣ ይህንን ጥናት ለማዘጋጀት ሶስት ማዕቀፎች ላይ መመስረቱን ያስረዳል። የፖለቲካ ፈቃደኝነት አለመኖር፣ የመገናኛ ብዙኀን ትኩረት ማጣትና የኢኮኖሚ ድረጋፍ አለማግኘት የሪፖርቱ ማዕቀፎች ሆነው ተቀምጠዋል። • የኬንያ ፖሊስ የልጇን አፍ የሰፋችውን እናት እያደነ ነው ሪፖርቱ የፖለቲካ ፈቃደኝነት ሲል የተፈናቃይ ዜጎች ደህንነትንና መብት በማስጠበቅ ረገድ የፀጥታ ኃይሉ ተነሳሽነት ማጣት እንደምክንያት ተጠቅሷል። አለም አቀፉ ማህበረሰብም ለእነዚህ ወገኖች ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት የነበረውን የፖለቲካ ቁርጠኝነት አናሳ እንደነበር ያስቀምጣል። ሌላው የተፈናቃይ ወገኖች ያገኙት የመገናኛ ብዙኃን ሽፋን በተለያየ ምክንያት እንዳነሰ የጠቀሰው ሪፖርቱ ሽፋኑ በቀውሱ ስፋት ልክ አይደለም ብሏል። መገናኛ ብዙኃን ግጭቶችን ሲዘግቡ እንኳን ስለጦር ስልት፣ የፖለቲካ ጥምረቶችና በአማፂያን መካከል በሚደረጉ ግጭቶች ዜናው ይሸፈናል ሲል ሪፖርቱ ያትታል። በሶስተኛ መስፈርትነት የቀረበው የተባበሩት መንግሥታት እና ሰብአዊ እርዳታ አጋሮቹ በሀገራት ለሚደርሱና ለደረሱ ቀውሶች የጠየቁትን ድጋፍ ነው። እነዚህ ጥያቄዎች ምን ያህሉ ፈጣን ምላሽ አገኙ የሚለው ከመስፈርቶቹ መካከል ነው። በኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ እና ኤርትራ መጥተው የተጠለሉ 900 ሺህ ስደተኞች ይገኛሉ።
news-52963784
https://www.bbc.com/amharic/news-52963784
ከባድ የጤና ችግር ኖሮባቸው ከኮቪድ-19 ያገገሙ ሰዎች ታሪክ
'ከባድ የጤና እክል ቢኖርብኝም ከቫይረሱ አገግሜያለ ሁ '
ሌሎች አሳሳቢ የጤና እክል ያለባቸው ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዝ በጣም አስፈሪ ነገር ሊሆንባቸው ይችላል። ምናልባትም ብዙዎች ስለዚህ ጉዳይ ሲያስቡ በጣም ሊጨነቁ ይችላሉ። ነገር ግን አስጊ የሚባል የጤና ሁኔታ ላይ ሆነው እንኳን ከቫይረስ እያገገሙ ያሉ ሰዎች አሉ። ብርዮኒ ሆፕኪንስም በከባድ የጤና ችግር ውስጥ ሆነው ቫይረሱን ማሸነፍ ከቻሉት መካከል አንዷ ስትሆን ታሪኳን እንዲህ ትናገራለች። አንድ ቀን በድንገት መተንፈስ ሲያቅተኝ ደረቴ አካባቢ ከባድ ጭንቀት ተሰማኝ። ምንም የተለየ ነገር እየሰራሁ አልነበረም፤ በቤቴ ውስጥ ደረጃ እየወጣሁ ነበር። ኮሮናቫይረስ ያዘኝ? ደረጃው እንዲህ ከባድ ነው? ሰውነቴ ምን ሆነ? ሳንባዬስ ምን ችግር ገጠመው? የሚሉ ጥያቄዎች ተመላለሱብኝ። ‘ክሮንስ ዲዚዝ’ የሚባል በሽታ ተጠቂ ነኝ። በሆዴ ውስጥ የሚገኘው የሥርዓተ ልመት እራሱን በራሱ ያጠቃል። በጣም ከባድ የጤና እክል እንደሆነ አውቃለው። • ዴክሳሜታሶን ኢትዮጵያ ውስጥ ጥቅም ላይ ስለሚውልበት ሁኔታ ባለሙያዎች ሐሳብ አቀረቡ • ዴክሳሜታሶን ምን ያህል አስተማማኝ ነው? ኢትዮጵያ ውስጥስ ይገኛል? ይህንን በሽታ ለማከም በዋነኛነት ጥቅም ላይ የሚውለው ህክምና ‘ኢሚዩኖሰፕረሲቭ ቴራፒ’ የሚባል ሲሆን መድኃኒቱ በሰውነቴ ውስጥ ያለውን የበሽታ መከላከል አቅም መቀነስ ነው ሥራው። ይሄ ደግሞ ለኢንፌክሽንና እንደ ኮሮናቫይረስ ላሉ የመተንፈሻ አካላትን ለሚያጠቁ በሽታዎች ተጋላጭ ያደርገኛል። መጀመሪያ አካባቢ እንደ ትኩሳትና የድካም ስሜትን የመሳሰሉ የመጀመሪያዎቹ የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ሲሰሙኝ ብዙም አላሳሰበኝም ነበር። ምልክቶቹ እየተባባሱ ሲመጡ ግን ጭንቅላቴ በጣም በሚያስፈሩ ሀሳቦች መሞላት ጀመረ። ያነበብኳቸው አስፈሪ የሞት ዜናዎችና የሆስፒታል መጨናነቆች ትዝ አሉኝ። ሆስፒታል መግባት ሊኖርብኝ ይሆን? የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ ያስፈልገኝ ይሆን? በቫይረሱ ምክንያት ሕይወቴ ታልፍ ይሆን? እያልኩ ብዙ ተጨነኩኝ። በወቅቱ ከነበረው ሁኔታ አንጻር ሆስፒታል ሄዶ መመርመር የማይታሰብ ነው። ሆስፒታሎች በእጅጉ ተጨናንቀው ነበር። ነገር ግን አንድ ዶክተር በተቻለ መጠን እንድመረመርና ሁኔታዎች እየባሱ ከሄዱ ድንገተኛም ክፍል ቢሆን እንድሄድ ነገረኝ። ነገር ግን ከስምንት ቀናት በኋላ ምልክቶቹ መቀነስ ጀመሩ። ከዚህ በፊት ባለብኝ የጤና እክል ምክንያት እንዲዳከሙም ተደርጎ የነበረው በሽታ የመከላከል አቅሜ ቫይረሱን ተዋግቶ አሸንፎታል። ይሄ ታሪክ የእኔ ብቻ እንዳልሆነ አስባለሁ፤ በርካቶች ተጓዳኝ አስጊ የጤና እክሎች እያሉባቸው እንኳን ቫይረሱን ማሸነፍ ችለዋል። "ምንም እንኳን ሁኔታው በጣም አስፈሪ ቢሆንም ጥሩ ጥሩውን እያሰብኩ አሳልፌዋለው።" ከድጃ እንግሊዝ ሊድስ ውስጥ የምትኖር የ25 ዓመት ወጣት ናት። ‘ታይፕ 1’ የሚባለው የስኳር በሽታ ታማሚ ነች። ጣፊያዋ ኢንሱሊን የሚባለውን ንጥረ ነገር ማምረት ስላቆመ በዶክተሮች አማካይነት ነው ኢንሱሊን ለሰውነቷ የሚሰጠው። "ልክ በቫይረሱ ከተያዙ የመሞት እድላቸው ከፍተኛ ከሆኑት ሰዎች መካከል መሆኔን ሳውቅ በጣም ነበር የፈራሁት። ኮሮናቫይረስ ሊይዘኝ ይችላል፤ ቢይዘኝስ ምን እሆናለሁ እያልኩ ብዙ እጨነቅ ነበር።" በሆስፒታል ውስጥ በነርስነት ከምታገለግል ከእናቷ ጋር የምትኖረው ከድጃ ለቫይረሱ የመጋለጥ እድሏ ከፍ ያለ ነበር። ከአራት ሳምንታት በፊትም አንዳንድ የቫይረሱን ምልክቶች ማሳየት ጀመረች። የአጥንት መቆረጣጠም፣ የትንፋሽ ማጠር፣ ደረት አካባቢ ከባድ ህመምና ትኩሳት ነበረባት። "ልክ ምልክቶቹን ሳስተውል በጣም ፈራሁ፤ ምክንያቱም በዜና የምሰማው ሁሉ ሞት ብቻ ነበር። በቫይረሱ ተይዘው ስላገገሙ ሰዎች እምብዛም አይወራም ነበር። በጭንቅላቴ ቫይረሱ ተገኝቶበት ወደ ሆስፒታል የሄደ ሰው በሙሉ እንደሚሞት ነበር የማስበው።" በመጀመሪያ የህክምና ባለሙያዎች ወደቤታችን ተልከው መጡ። ነገር ግን ወደ ሆስፒታል መሄድ እንደሌለብኝ ወስነው በቤት ለቤት ምርመራ እንደምካተት ነገሩኝ። ነገር ግን እሱም አልተሳካም። በሚያስገርም ሁኔታ ከድጃ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ተሻላት። ከቤት ባለመውጣቴም ደኅንነት ተሰምቶኛል ትላለች። ከነባለቤቱ በበሽታው ተይዞ የዳነው ጆ ጆ ጀስትነር ደግሞ ‘ኒፍሮቲክ ሲንድረም’ የሚባል የኩላሊት ችግር አለበት። በፈረንጆቹ 2000 ላይ የኩላሊት ንቀለ ተከላ እስከማካሄድም አድርሶታል ይሄው በሽታ። "ንቅለ ተከላ የተደረገላቸው ሰዎች ይበልጥ ተጋላጭ መሆናቸውን ስሰማ እራሴን መከላከል እንዳለብኝ ተሰማኝ። ወደቤት ገባሁና እራሴን ከሰዎች ንክኪ አራቅኩኝ" ይላል። ነገር ግን እራሱን ከሰዎች ቢለይም የኮሮናቫይረስ ምልክቶችን ግን ማሳየቱ አልቀረም። ምናልባትም በሽታው ከህክምና ባለሙያ ባለቤቱ ሳይዘው እንዳልቀረ ይገምታል። እሷም አንዳንድ ምልክቶችን ማሳየት ጀምራ ነበር። "ሁለታችንም ደረታችን አካባቢ መታፈን ይሰማን ነበር። ምናልባት ጭንቀቱ ሊሆን ይችላል ብለን ነበር። ነገር ግን በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ደረቅ ሳል ማሳል ጀመርኩ።" ጆ ትንሽ ቆይቶ ትኩሳትና ሌሎች የኮሮረናቫይረስ ምልክቶችን ለማሳየት ጊዜ አልፈጀበትም። "ለሚቀጥሉት ቀናት ጤናዬ ተቃወሰ፤ ማሳልና ማስነጠሱም እስከ አስረኛው ቀን ድረስ አልተወኝም ነበር። ቀስ በቀስ ግን እሱ እና ባለቤቱ የጤና ሁኔታቸው እየተስተካከለ መጣ። ሌላው ቀርቶ አስጊ የጤና ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሰዎች እንኳን በቫይረሱ ከተያዙ በኋላ ቀላል የሚባሉ ምልክቶችን ብቻ አሳይተው መዳን እንደሚችሉ ተገነዘብኩ ይላል ጆ።
52293148
https://www.bbc.com/amharic/52293148
ኮሮናቫይረስ፡ 300ሺህ አፍሪካውያን በኮቪድ-19 ምክንያት ሕይወታቸውን ሊያጡ ይችላሉ-የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን
የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ያለበቂ መከላከያ 300ሺህ አፍሪካውያን በኮሮና ምክንያት ህይወታቸውን እንደሚያጡ ይገመታል ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ ላይ አስታወቀ።
የኮሮና ቫይረስ በአፍሪካውያን ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት በገመመገመበት በዚህ መግለጫ ከሰው ህይወት በተጨማሪ የአህጉሪቷን ምጣኔ ኃብት እያሽመደመደው እንደሆነም አስፍሯል። በዚህ አመት የአህጉሪቱ ምጣኔ ሃብት በ3.2 በመቶ ያድጋል ተብሎ የተገመተ ቢሆንም ቫይረሱ ባደረሰው ጫና ምክንያት ምናልባት 1.8 በመቶ ሊያድግ ይችላል ብሏል። ይህም ሁኔታ 27 ሚሊዮን ህዝብን ለረሃብ እንደሚያጋልጥ የኮሚሽኑ መግለጫ ጠቁሟል። • መንግሥታት ከተሜውን ከኮሮናቫይረስ ኢኮኖሚያዊ ጫና እንዲታደጉ ጥሪ ቀረበ • ኢትዮጵያ ከኮሮናቫይረስ ምጣኔ ሐብታዊ ጫና ትተርፋለች? • አገራትን ጭምብል እስከመሰራረቅ ያደረሳቸው የኮሮናቫይረስ ዲፕሎማሲ ኮሚሽኑ ነገ ይፋ በሚያደርገው ሪፖርት ቫይረሱ ካስተለው ቀውስ ጋር ተያይዞም ደካማ የሚባለው የአህጉሪቷጤና ስርዓት ለተጨማሪ ወጪ እንደሚዳረግም አስገንዝቧል። እስካሁን ባለው መረጃ በአህጉሪቷ ውስጥ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 16 ሺ ሲሆን 800 ሰዎችም ህይወታቸውን አጥተዋል፤ ይህ ቁጥር እየጨመረ ሊሄድ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ የአህጉሪቱ የጤና ስርአትም ጥያቄ ውስጥ እንደሚገባ መግለጫው አመላክቷል። ይህንንም ለመታደግ የመንግሥታት ቁርጠኝነት እንዲሁም ድጋፍ እንደሚገባም የኮሚሽኑ ዋና ፀሐፊ ቬራ ሶንግዌ ገልፀዋል። " የአህጉሪቱን የጋራ ብልጽግና ለመከላከልና ለመንባት፤ መንግሥታት ለዜጎቻቸው በአስቸኳይ መሰረታዊ ፍላጎታቸውን ማቅረብ እንዲችሉ 100 ቢሊየን ዶላር ያስፈልጋል" ብለዋል " የወረርሽኙ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ቫይረሱ በቀጥታ ከሚያደርሰው ጉዳት የበለጠ ነው" ያሉት ፀሐፊዋ በአፍሪካ አገራት በአጠቃላይ ምጣኔ ሃብታቸው ቫይረሱ እንደተከሰተ መጎዳት መጀመሩን ገልጠዋል። "ወረርሽኙን ለመከላከል ተብሎ የተቀመጠው አካላዊ ርቀትን መጠበቅ የኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን እግር ተወርች አስሯል" ሲሉ አስረድተዋል የኮሚሽኑ ሪፖርት አክሎም አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ድጋፍ ካልተደረገላቸው በስተቀር ሙሉ በሙሉ እንደሚዘጉ አትቷል። የአፍሪካን ምጣኔ ሃብት 40 በመቶ የሚሸፍነው ዘይት በግማሽ ዋጋው መቀነሱን፣ በዋነኝነት አፍሪካ ወደውጪ የምትልካቸው የጨርቃ ጨርቅና አበባ ምርቶችም መውደቃቸውን ጠቅሷል። ቱሪዝም የአንዳንድ የአፍሪካ አገራት አጠቃላይ ብሔራዊ ምርትን 38 በመቶ ቢይዝም አየር መንገዶች ስራቸውን በማቋረጣቸው ምክንያት ሙሉ በሙሉ ቆሟል ሲል ያትታል። የአፍሪካ ምጣኔ ሃብት የተሳሰረ ነው ያለው ሪፖርቱ ለቀውሱም የምንሰጠው ምላሽ " ወደ አንድ ሊያመጣን ይገባል" ብሏል።
news-55321489
https://www.bbc.com/amharic/news-55321489
በትግራይ ለ2.3 ሚሊዮን ህፃናት እርዳታ ማድረስ አልተቻለም- ዩኒሴፍ
በትግራይ ክልል ባለው ግጭት ምክንያት 2.3 ሚሊዮን የሚሆኑ ህፃናት ከሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ውጪ መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት አስተታወቀ።
"ከእነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ ስደተኛና የተፈናቀሉ ናቸው። በአጠቃላይ ህፃናቱን መጠበቅ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ሥራ ነው" በማለት የተባበሩት መንግሥታት የዓለም አቀፉ የህፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) ኃላፊ አስታውቀዋል። ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የሰብዓዊ እርዳታዎችን ለማድረስ ስምምነት ላይ ቢደረስም ድርጅቶቹ በክልሉ የእርዳታ አቅርቦት ለማድረስ አልተቻለም እያሉ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ከትግራይ ኃይሎች ጋር የገባበት ግጭት የተቀሰቀሰው ጥቅምት 24/ 2013 ዓ.ም እንደነበር ይታወሳል። በዚህ ግጭት በሩካታ ሰዎች ተገድለዋል እንዲሁም ከ60 ሺህ በላይ የሚሆኑ ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን መሰደዳቸው ይነገራል። "ለህፃናቱ የሚሰጠው እርዳታ አቅርቦት በዘገየ ቁጥር፣ ምግብ፣ በችጋር ለተጋለጡት ህፃናትን ለማደስ የሚያስፈልጉ አልሚ ምግቦች፣ ህክምና፣ ውሃ፣ ነዳጅና እና ሌሎችም አስፈላጊ ነገሮች እያጠሩ ወደ ከፋ ሁኔታ ያመራሉ" ብሏል ዩኒሴፍ ባወጣው መግለጫ። አክሎም "አፋጣኝ፣ ዘላቂ፣ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ማንንም ባላገለለ መልኩ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ለየትኛውም ቤተሰብ በያሉበት እንዲመቻች እንጠይቃለን" ብሏል ድርጅቱ። ድርጀቱ አክሎም "ባለስልጣናቱ ለደኅንነታቸው ፈርተው የሚሸሹ ንፁህ ዜጎችን በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ መፍቀድ እንዳለበትና ይሄም ዓለም አቀፍ ጥበቃ ፈልገው ድንበር የሚያቋርጡትንም ያካትታል" ብሏል። የኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ ህወሓት በጉዳዩ ላይ የሰጡት አስተያየት የለም። ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሻከረ የመጣው የፌደራል መንግሥቱና የህወሓት ግንኙነት የማይታረቅ ደረጃ ደርሶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የትግራይ ልዩ ኃይል በክልሉ የሚገኘውን የመከላከያ ሰሜን ዕዝ ካምፕ ላይ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ማዘዛቸው ይታወሳል። ለሦስት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ በአገሪቱ መንግሥት ውስጥ ጉልህ ሚና የተጫወተው ህወሓት ከሦስት ዓመት በፊት በተነሳው ፀረ-መንግሥት ተቃውሞና የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ ከማዕከላዊው መንግሥት መራቁ የሚታወስ ነው።
45365303
https://www.bbc.com/amharic/45365303
እውን የኢትዮጵያ መንግሥት ጥቁር ገበያውን ማሸጉ መፍትሄ ይሆነዋል?
ጎረቤት ሃገር ኬንያ መዲና ናይሮቢ ነዋሪነቱን ያደረገው ሄኖክ አበራ ዘመድ ጥየቃ ወደ ተወለደባት አዲስ አበባ ከማምራቱ በፊት የሚያደርገው አንድ ነገር አለ፤ የኬንያ ሽንግልን ወደ ዶላር መቀየር።
ኢትዮጵያ ሆቴል አካባቢ የሚገኝ የውጪ ሃገራት ግንዘብ ህጋዊ ባልሆነ መልኩ ይመነዘርበታል ተብሎ የታሸገ ሱቅ። «ናይሮቢ ውስጥ ዶላር መግዛትም ሆነ መሸጥ እጀግ በጣም የቀለለ ነው፤ ሊያውም በሕጋዊ መንገድ። እኔ አዲሳ'ባ ላይ ዶላሩን ሞቅ ባለ ዋጋ ስለምሸጠው አዋጭ ነው» ይላል ሄኖክ። «ማድረግ ያለብህ መታወቂያህን ወይም ፓስፖርትህን ይዘህ ለውጭ ምንዛሪ ወደተዘጋጁ ወርደ ጠባብ ሱቆች መሄድ ብቻ ነው።» በእርግጥም ናይሮቢ ውስጥ በሕጋዊ መንገድ በፍጥነት ከሚከናወኑ ተግባራት አንዱ ዶላር መግዛት እና መሸጥ ነው፤ ከአዲስ አበባ እጅጉን በተለየ መልኩ። • ዶላር በጥቁር ገበያ ለምን ቀነሰ? • ''የጫት ንግድና የዶላር ጥቁር ገበያ. . .ለግጭቶች ምክንያት ሆነዋል'' በኢትዮጵያ ሕጋዊ ባልሆነው የውጭ ምንዛሬ ገበያ ወይም ጥቁር ገበያ የዶላር ዋጋ ማሽቆልቆላ ማሳየት ከጀመረ ሰንበትበት ብሏል። ከሰሞኑ ደግሞ መንግሥት ጥቁር ገበያ ላይ ሲያገበያዩ የተገኙ ሱቆችን እንዲሁም ሲያሻሽጡ ነበሩ ያላቸውን ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ተያይዞታል። ኢትዮጵያ ሆቴል አካባቢ በሰፊው ይንቀሳቀሱ የነበሩ የጥቁር ገበያ የደራባቸው አልባሳት መሸጫ ሱቆችም 'ታሽጓል' በሚል ምክልት ዝምት ለብሰው ታይተዋል። እውን ጥቁር ገበያውን ማሸግ ዘለቄታዊ መፍሄ ነው? የምጣኔ ሃብት ባለሙያ የሆኑት ዶክተር አየለ ገላን «ጥቁር ገበያ ሊሠራ የማይችል ነገር እንዲሠራ ያደርጋል፤ ወደ ሃገር ቤት የሚገቡ የካፒታልም ሆነ የጥሬ ዕቃ አቅርቦቶች የተሳኩ እንዲሆኑ ያደርጋል፤ ግለሰቦች ኢኮኖሚያዊ ችግራቸውን እንዲቀርፉ ያደርጋል። ለዚህ ነው ጥቁር ገበያው የሚጫወተው ሚና ቀላል አይደለም የምንለው» ሲሉ ባለሙያው ያስረዳሉ። «መንግሥት ጥቁር ገበያውን ሲዘጋ ሰዎች አማራጭ በማጣት ወደ ባንክ በመሄድ በኦፌሴላዊ መንገድ ይገበያያሉ የሚል እምነት አለው። ነገር ግን ጥቁር ገበያውን በእንዲህ ዓይነት መልኩ መግታት ይቻላል የሚል እምነት የለኝም።» «ዞሮ ዞሮ. . .» ይላሉ ዶክተር አየለ «ዞሮ ዞሮ ዶላሩ የሚመጣው ከውጭ ሃገር ነው። ሰዎች ካስፈለጋቸው ሕጋዊ መንገድ ሳይጠቀሙ ዶላሩን ብሩን በሰው በሰው ማዘዋወር ይችላሉ። ወጣም ወረደ በእንዲህ ዓይነት መልኩ ጥቁር ገበያውን ማሸነፍ አይቻልም።» ዶ/ር አየለ ብቻ ሳይሆን ሌሎች የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎችም መንግሥት ጥቁር ገበያውን በመሰል መልኩ ማሸነፍ እንደማይችል ሃሰብ እየሰነዘሩ ነው። የማክሮ እና ዓለም አቀፍ ኢኮኖሚክስ ባለሙያ የሆኑት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ጥቁር ገበያው የሚሸፍነውን ክፍተት መደበኛው ገበያ ሊሸፍነው አይችልም ሲሉ በትዊተር ገፃቸው ፅፈዋል። ወደ መፍትሄው. . . አሁን ትልቁን ጥያቄ ማንሳት ይቻላል። መንግሥት ጥቁር ገበያውን እንዴት ማሸነፍ ይችላል። «የመንግሥት ፖሊሲ አውጭዎች ማሸነፍ የማይችሉትን ጦርነት ከመጀመር እንዴት ባለ ፖሊሲ ነው ጥቁር ገበያውን ማስወገድ የሚቻለው የሚለው ላይ ማተኮር አለባቸው» በላመት ዶክተር አየለ ይተንትናሉ። «ይህ የሮኬት ሳይንስ አይደለም፤ ሌሎች ሃገራት አድርገውታል። ኢትዮጵያ አሁን ባለው ሁኔታ ዶላር ያስፈልጋታል፤ የዶላር እጥረት አለ። እንዲህ ባለ አስቸጋሪ ወቅት ከበድ ያለ እርምጃ መውሰድ ሊያስፈልግ ግድ ይላል።» ዶክተር አየለ እንደ መፍትሄ የሚያቀርቡት 'መልቲፕል ኤክስጄንጅ ሬት' የተሰኘውን ሃሳብ ነው። «'መልቲፕል ኤክስጄንጅ ሬት' ማለት ለተወሰነ ጉዳዮች ቋሚ የሆኑ የውጭ ምንዛሪ ዋጋን መጠቀም፤ ለምሳሌ ዕቃ ከውጭ ለሚያስመጡ እና ለሚልኩ። ጥሬ ገንዘብ ወደ ሃገር ቤት በሚገባበት ጊዜ ደግሞ ለእሱ የተለየ ምንዛሬ መጠቀም ይቻላል።» ሁለት የተለያዩ የውጭ ምንዛሬ ዋጋዎችን መጠቀም አስቸጋሪ አይሆንም ወይ ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ባለሙያው ሲመልሱ፤ «ይሄ እኮ አዲስ ነገር አይደለም» ይላሉ። «እንዲህ ባለ አስቸጋሪ ጊዜ 'መልቲፕል ኤክስጄንጅ ሬት'ን መጠቀም ይፈቀዳል፤ ሌሎች ሃገራትም አድርገውታል፤ ነገር ግን ይህ ለተወሰነ ጊዜ የሚሆን እንጂ ለዘለቄታው አይደለም።» ዶክተር አየለ ትንታኔያቸውን ሲቀጥሉ «በፍላጎት እና አቅርቦት ላይ የተመረኮዘ የገንዘብ ፍሰት ከተከናወነ ጥቁር ገበያው ቢያንስ እንዲህ እንደ አሁኑ አይንሰራፋም።» ዶክተር አየለም ሆነ ፕሮፌሰር አለማየሁ በአንድ ጉዳይ የተስማሙ ይመስላል፤ መንግሥት የተሻለ የምጣኔ ፖሊሲ እንደሚያስፈልገው። ዶክተር አየለ «መንግሥት ፈጠራ የተሞላቸው የምጣኔ ሃብት ፖሊሲዎችን በመቅረፅ ሊጠመድ እንጂ ከጥቁር ገበያው ጋር ትንቅንቅ ውስጥ ሊገባ አይገባም» በማለት ሃሳባቸውን ይቋጫሉ። • የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ቀጣይ ፈተናዎች
48559840
https://www.bbc.com/amharic/48559840
ሞ ሳላህ ለሊቨርፑል መፈረሙ በከተማዋ ሙስሊም ጠልነት ቀነሰ
ሞሃመድ ሳላህ ለሊቨርፑል መፈረሙን ተከትሎ በከተማዋ ሙስሊም ጠልነት መቀነሱን አንድ ጥናት ጠቆመ።
ስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ያደረገው ጥናት ሞሃመድ ሳላህ ለሊቨርፑል እግር ኳስ ክለብ መፈረሙ በሊቨርፑል ከተማ ሙስሊም ጠልነት በቀጥታ እንዲቀንስ ማድረጉን አረጋግጧል። ሳላህ ከሁለት ዓመት በፊት ለሊቨርፑል ከፈረመ በኋላ በሊቨርፑል ከተማ የሙስሊም ጠል የሆኑ የወንጀሎች ቁጥር በ18.9 በመቶ ቀንሰዋል። • በሞ ሳላህ ቅርጽ የተሰራው ሃውልት መሳቂያ ሆኗል • ሊቨርፑል ሞ ሳላህን ለፖሊስ አሳልፎ ሰጠ • ሞ ሳላህ የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ ተጫዋች ኾኖ ተመረጠ ታዋቂ ግለሰቦችን ማወቅ እና ማድነቅ ጭንፍን ጥላቻን ይቀንሳል ወይ? ሞሃመድ ሳላህ በሙስሊም ጠልነት በባሕርይ እና አመለካከት በመቀየር ረገድ የለው ተጽዕኖ ምን ይመስላል በሚል እርዕስ ነው ጥናቱ በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ የተሠራው። በእንግሊዝ ጥላቻን መሠረት ያደረጉ ወንጀሎች እና 15 ሚሊዮን የትዊተር መልዕክቶችን በጥናቱ ተንትነዋል። ጥናቱ ሊቨርፑል እግር ኳስ ቡድን በሚገኝበት ግዛት ውስጥ ሙስሊም ጠል የሆኑት ወንጀሎች ከመቀነሳቸው በተጨማሪ የሊቨርቱል ክለብ ደጋፊዎች ፀረ-እስልማና ይዘት ያላቸውን የትዊተር መልዕክት በግማሽ ቀንሷል። ጥናቱ ይህ አዎንታዊ ለውጥ የመጣው ሰዎች ስለ እስልምና ያላቸው እውቀት በመጨመሩ ነው ይላል።
news-54520360
https://www.bbc.com/amharic/news-54520360
ፔሩ ሰባት ወር ለጠበቀው ጃፓናዊ ታሪካዊ ስፍራዋን ብቻውን እንዲጎበኝ ፈቀደች
ፔሩ የኢንካ ህዝቦች ስልጣኔ ማሳያ የሆነውን የማቹ ፒቹን ታሪካዊ ስፍራ አንድ ጃፓናዊ ቱሪስት ብቻውን እንዲጎበኝ ክፍት አድርጋለች።
በኮሮናቫይረስ ምክንያት ከአለም ቅርስ አንዱ የሆነው የማቹ ፒቹ የፍርስራሽ ስፍራ ተዘግቶ የነበረ ሲሆን ጃፓናዊው ቱሪስትም ሰባት ወራት መጠበቅ ነበረበት። ጄስ ታካያማ ስፍራውን ለመጎብኘት አቅዶ የነበረው መጋቢት ወር ላይ የነበረ ቢሆንም በኮሮናቫይረስ ምክንያት ጉብኝት በመከልከሉም ሳይሳካለት ቀርቷል። በቱሪዝም ዘርፉ በርካታ ጎብኝዎች ያሉት ጥንታዊው የኢንካ ከተማ ፍርስራሽ በሚቀጥለው ወርም ላይ በጥቂት ሰዎች ለመክፈት ታቅዷል። ስፍራው የሚከፈትበት ትክክለኛ ቀን ግን አልተገለፀም። ጄስ ታካያማ መጋቢት ወር ላይ ወደ ፔሩ ሲመጣ ይህንን ቅርስ ለመጎብኘት የነበረ ቢሆንም በወረርሽኙ ምክንያት መውጣት መግባት ባለመቻሉም በአቅራቢያው ባለች አጉዋስ በተባለች ከተማም ለወራት ያህል ያለ ምንም መሄጃ ጠብቋል። በዚህም ምክንያት የባህል ሚኒስትሩ አሌሃንድሮ ኔይራ ብቻውን እንዲጎበኝ መፍቀዳቸውን ተናግረዋል። "ፔሩ የመጣው ስፍራውን የመጎብኘት ህልም ስለነበረው ነው" በማለትም ሚኒስትሩ በትናንትናው ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል። ጄስ ታካያማ ለሰባት ወር ጠብቆ ስፍራውን ሳይጎበኝ እንዳይመለስ በሚልም ቅዳሜ እለት የፍርስራሽ ስፍራውን እንዲጎበኝ ተደርጓል። በማቹ ፒቹ ተራራማ ስፍራም ላይ ሆኖ ለወራት የጠበቀውን ቦታ በመጎብኘቱ የተሰማውን ደስታም መግለፁንም በቀረፀው ቪዲዮ አስተላልፏል። "ጉብኝቱ በጣም አስገራሚ ነበር፤ አመሰግናለሁ" በማለትም ጄስ መልእክቱን አስተላልፏል። በአንደስ ተራራዎች የሚገኘው የማቹ ፒቹ ስፍራ የኢንካ ግዛት ማሳያ ሲሆን በጎሮጎሳውያኑ 1450 እንደተገነባም ይታመናል። በዩኔስኮ የአለም ቅርስነት የተመዘገበው ይህ ስፍራ አለም ካላት ሰባቱ አስደናቂ ቅርሶችም ዝርዝር ውስጥ ተካቷል። ወረርሽኙ ከተከሰተባት እለት ጀምሮ በፔሩ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 849 ሺህ ሲሆን 33 ሺህ መሞታቸውንም ከጆንስ ሆፕኪንስ የተገኘው መረጃ ያሳያል።
news-55729086
https://www.bbc.com/amharic/news-55729086
በታይላንድ ንጉሥን ተችተሻል የተባለች ሴት 43 ዓመት ተፈረደባት
አንዲት የታይ ሴት የንጉሣዊያኑን ቤተሰብ ተችተሻል በሚል 43 ዓመት እስራት ተፈርዶባታል።
በአገሪቱ ታሪክ ንጉሥን ለተቸ ይህ ትልቁ የእስር ውሳኔ ነው ተብሏል። አንቻን የሚል ስም ያላት ይቺ ሴት በማኅበራዊ ሚዲያ የድምጽ ፖድካስቶችን ነበር ከ7 ዓመታት በፊት ለሕዝብ ያጋራችው። እሷ እንደምትለው እነዚህን ንጉሡን የሚተቹ የድምጽ ፋይሎች ዝምብላ ከማጋራት ውጭ ያደረገችው ነገር የለም። የታይላንድ 'ልሴ ማጄስቴ' ሕግ በዓለም ላይ ጥብቅ ከሚባሉት ሕጎች የሚመደብ ሲሆን በፍጹም ንጉሣዊያን ቤተሰቡን በማንኛውም ሁኔታ፣ ምንም ቢያደርጉ መተቸት ወይም ማጥላላት ወይም ነቀፋ መሰንዘርን ይከለክላል። ታይላንድ የንጉሣዊ ዲሞክራሲ ሥርዓትን የምትከተል አገር ስትሆን ይህ እንዲለወጥ በቅርብ ጊዜ ወጣቶች አደባባይ ወጥተው በመቃወማቸው ከፖሊስ ጋር ተደጋጋሚ ግጭት ውስጥ ገብተው እንደነበር ይታወሳል። ተከሳሽ አንቻን ንጉሡን የሚተቹ ድምጾች ያሉበትን ይዘት ከ2014 እስከ 2015 በዩትዩብና በፌስቡክ ስታጋራ በመቆየቷ 29 ክሶች ተከፍቶባት ስትከራከር ነበር። አንቻም የማይከሰሱትን፣ የማይገረሰሱትን ፍጹማዊውን ንጉሥ ተዳፍራችኋል በሚል ከተከሰሱ 14 ሰዎች አንዷ ናት። አንቸም መጀመርያ ድርጊቱን በመፈጸሟ የተፈረደባት የ87 ዓመት እስር የነበረ ሲሆን የቅጣት ማቅለያ ተደርጎላት እስሩ በግማሽ ቀንሶላታል። ለብሔራዊ ደኀንነት በሚል የአንቻ ክሶች ይታዩ የነበረው በዝግ ችሎት ነበር።
news-55435608
https://www.bbc.com/amharic/news-55435608
እግር ኳስ፡ ዩናይትድ፣ አርሴናል፣ ቼልሲ . . . ምን አስበዋል?
የስፖርት ጋዜጦች ስለ እግር ኳስ ምን እያሉ ነው? በሚቀጥለው ጥር የሚከፈተው የዝውውር መስኮትስ ምን ያሳየን ይሆን?ዋና ዋናዎቹን በዚሀች አጭር ዘገባ እንዳስሳለን።
አላንድ አላንድ፡ የቦሩሲያ ዶርትመንዱ አጥቂ ኧርሊንግ ብራውት አላንድ ፈላጊው በዝቷል። አሁን ደግሞ ቼልሲዎች ተጫዋቹን ለማስፈረም ዕቅድ እንዳላቸው እየተነገረ ነው። ነገር ግን ማንቸስተር ሲቲዎች ተጫዋቹ የእኛ ነው እያሉ ነው። ይህን የዘገበው '90 ሚኒት' ጋዜጣ ነው። ቼልሲ አላንድንና የዌስትሃሙን ዴክሌን ራይስ ለማስፈረም ሰባት ተጫዋቾቹን ሊሸጥ እንደሚችል ስካይ ስፖርት ዘግቧል። ባርክሌይ፣ አሎንሶ፣ ሩዲገር፣ ክሪስቴንሰን፣ ጆርጊንሆ፣ ድሪንክዎተርና ሞሰስ ለገበያ ሊቀርቡ እንደሚችሉ ተነግሯል። በሌላ በኩል ማንቸስተር ዩናይትድም አላንድን ማስፈረም ይፈልጋል። ነገር ግን የተጫዋቹ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ከዩናትድ ጋር ያለው ግንኙነት ሰላማዊ ስላልሆነ ችግር ሊፈጥር ይችላል እየተባለ ነው ይላል ሚረር ባወጣው ዘገባ። ዩናይትድ አላንድን ማስፈረም ካልቻለ ፊቱን ወደ ኤቨርተኑን ዶሞኒክ ካልቨርት-ሌዊን ሊያዞር ይችላል። ሩዲገር፡ ቼልሲ ሊሸጣቸው ካሰባቸው ተጫዋቾች መካከል የሆነው ጀርመናዊው አንቶኒዮ ሩዲገር በፓሪስ ሴይንት ዠርሜይን ይፈለጋል። ይህን ያተመው የፈረንሳዩ 'ለ ፓሪዚያ' ነው። ሊቨርፑል፡ ቀያዮቹ የሪያል ማድሪዱን ብራዚላዊ ተከላካይ ኤደር ሚሊቶን ለማስፈረም አቅደዋል። አርጀንቲናዊው የ34 ዓመት ተጫዋች እዝቄል ጋሬይም በሊቨርፑሎች እየተፈለገ ነው። ይህን ዜና ያሰማው የስፔኑ ቶዶፊቻሄስ ነው። አርሴናል፡ የመድፈኞቹ አሠልጣኝ ማይክል አርቴታ የሪያል ማድሪዱን ብራዚላዊ አጥቂ ቪኒሺዬስ ጁኒዬርን ወደ ኤሜሬትስ ለማምጣት አቅደዋል። የ22 ዓመቱ አጥቂ ወደ ኤሜሬትስ በሚቀጥለው ጥር ወር በውሰት ሊመጣ ይችላል ተብሏል። አርቴታ ከወጣቱ አጥቂ በተጨማሪ የ28 ዓመቱን ስፔናዊ አማካይ ኢስኮ፤ ይፈልገዋል። ነገር ግን ተጫዋቹ ወደ ዩቬንቱስ መሄድን ይመርጣል - 'የደይሊ ስታር' እንደዘገበው። ባርሴሎና፡ የካታሎኑ ክለብ የአርሴናሉን ተከላካይ ሹከርዳን መስጣፊን ይፈልገዋል ይላል 'ስፖክስ' ጋዜጣ። የ28 ዓመቱ ሙስጣፊ ከአርሴናል ጋር ያለው ውል እየተገባደደ ነው። ጆንስ፡ የደርቢ ካውንቲ አሠልጣኝ የሆነው ዋይኒ ሩኒ የቀድሞ የቡድን አጋሩ ፊል ጆንስን ማስፈረም ይሻል። እንደ 'ሜትሮ' ዘገባ ከሆነ በማንቸስተር ዩናይትድ ቤት ዕድል ያጣው ጆንስ በዌስትብሮምም ይፈለጋል። የአውሮፓ እግር ኳስ የዝውውር መስኮት በሚቀጥለው የፈረንጆቹ ጥር ወር ይከፈታል። ማን ወደ የት ይሄዳል? ጊዜ ይፈታዋል።
50963338
https://www.bbc.com/amharic/50963338
የአንጎላ መንግሥት የቀድሞ ፕሬዝደንት ልጅ ዶስ ሳንቶስ ንብረት በቁጥጥር ሥር እንዲውል አዘዘ
የአንጎላ ፍርድ ቤት የቀድሞ የሃገሪቱ ፕሬዝደንት ሴት ልጅ ቢሊየነሯ ኢሳቤል ዶስ ሳንቶስ ንብረት እና ባንክ ያላቸው ገንዘብ በቁጥጥር ሥር እንዲውል አዟል።
ነዳጅ ጠገቧ ሃገር አንጎላ የሙስናን አከርካሪ እሰብራለሁ ብላ ቆርጣ ከተነሳች ሰንበትበት ብላለች። የፕሬዝደንት ጃዎ ሎሬንሶ መንግሥት በኢሳቤል ዶስ ሳንቶስ እጅ ውስጥ ያለ 1 ቢሊየን ዶላር አስመልሳለሁ እያለ ነው። • በባግዳድ የአሜሪካ ኤምባሲ ጥቃት ደረሰበት • ስለ ሀብት ማውራት ነውር የሆነባት አገር • ኢንጂነር አዜብ ላይ የተመሰረተው ክስ ከ5.1 ቢሊዮን ብር ውል ጋር የተያያዘ ነው ኢሳቤል ዶስ ሳንቶስ እኔ በአባቴ ዘመን የፈፀምኩት በደል የለም ንበረቴም በቁጥጥር ሥር ሊውል አይገባም ስትል ስሞታ አሰምታለች። ኢሳቤል በአፍሪካ ሃብታሟ ሴት የሚል ስያሜ የተሰጣት ግለሰብ ናት። ፎርብስ የተሰኘው የቱጃሮች ገንዘብ ቆጣሪ መፅሔት ኢሳቤል 2.2 ቢሊዮን ረብጣ ዶላር አላት ሲል የሃብት መጠኗን ይተነብያል። የ46 ዓመቷ ኢሳቤል ዶስ ሳንቶስ ሕይወቴ አደጋ ላይ እንዳይወድቅ በመስጋቴ ነው በሚል ምክንያት ኑሮዋን ከአንጎላ ውጭ አድርጋለች። ታላላቅ ኩባንያዎችን በማስተዳደር የምትታወቀው ኢሳቤል አንጎላ እና ፖርቹጋል ውስጥ ትልቅ ድርሻ ያላቸው ድርጅቶች አሏት። የአንጎላ መንግሥት ግለሰቧ አንጎላ ውስጥ በሚገኙ ትላልቅ ድርጅቶች ውስጥ ያላት የአክስዮን ድርሻ እና የባንክ ደብተሯ ነው በቁጥጥር ሥር እንዲውል ያዘዘው። ኢሳቤል፤ ድርጊቱ በፖለቲካ የተሟሸ ነው ስትል ንብረቷ በቁጥጥር ሥር እንዲውል መድረጉን በክፉ አውግዛለች። ዶስ ሳንቶስ በግሪጎሪ አቆጣጠር 2016 ላይ አባቷ የአንጎላ ነዳጅ አውጭ ኩባንያ ኃላፊ አደርገው ሲሾሟት ነበር ወደ እውቅና ጣራ የተመነጠቀችው። በቀጣዩ ዓመት ግን አባቷን ተክተው ወደ ሥልጣን በመጡት ፕሬዝደንት ጆሴ ፊሎሜኖ ዶስ ሳንቶስ ተባረረች።
news-45341285
https://www.bbc.com/amharic/news-45341285
ፍየሎችም «ከፍትፍቱ ፊቱ» ይሉ ይሆን?
ፍየሎች በተለይ ደስተኛ ገፅ ያለው የሰው ፊት ቀልባቸውን እንደሚገዛው በጥናቱ ተጠቁሟል።
የመርማሪዎች ቡድን ጥናቱን ለማካሄድ ከተጠቀመባቸው መንገዶች አንዱ የተለያዩ ስሜቶችን የሚያሳይ የአንድ ሰው የፊት ፎቶ በ1.3 ሜትር ርቀት አራርቆ በመስቀል ለፍየሎች ማሳየት ነው። ፍየሎችም ከሌሎች በተለየ ፈገግታ እና ደስታን በሚያሳየው ፎቶ ዙሪያ እንደተኮለኮሉ ተነግሯል። • አቶ ታደሰ ካሳ፡ "…ወሎዬ ነኝ፤ መታወቂያዬም አማራ የሚል ነው" • የደሞዙን 100 እጥፍ በስህተት የተከፈለው ሰው • የጦስ አውራ ዶሮ ወጣቶችን አሳሰረ በደስተኛው ገፅ ከመሳብ በተጨማሪ ከሌሎች ፎቶዎች በተለየ ከፍ ላለ ጊዜ እንዳጤኑት ተመስክሯል። ከጥናቱ አድራጊዎች መካከል አንዱ የሆኑት ዶ/ር አለን ማክኤልጋት ጥናቱ የሰው ልጅ የቅርብ ወዳጆች ከሆኑት ውሾች እና ፈረሶች በተጨማሪ ሌሎች እንስሳትም የሰውን ስሜት የማንበብ አቅም እንዳላቸው ፍንጭ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።
news-46875227
https://www.bbc.com/amharic/news-46875227
ከቤተሰቦቿ አምልጣ ካናዳ የገባችው የሳዑዲዋ ወጣት፡ 'ምንም የሚጎልብኝ የለም'
ከቤተሰቦቿ አምልጣ በካናዳ ጥገኝነት ያገኘቸው የሳዑዲዋ ወጣት ራሃፍ ሞሐመድ አል-ቁኑን ''የወሰድኩት እርምጃ አደገኛ ቢሆንም ትክክለኛ ውሳኔ ነው'' በማለት በካናዳ ነጻነት የሞላበት ህይወት እንደምትጀምር ተናግራለች።
ራሃፍ ሞሐመድ አል-ቁኑን ከሶስት ቀናት በፊት ካናዳ መግባቷ ይታወሳል የ18 ዓመቷ ወጣት ከቀናት በፊት ነበር ከቤተሰቦቿ ጋር በጉዞ ላይ ሳለች ወደ አውስትራሊያ ለማምለጥ በማሰብ ባንኮክ ከተማ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ እራሷ ላይ በመቆለፍ ወደ ሳዑዲ አልመሰም ያለችው። ራሃፍ በትዊተር ገጿ ላይ በምትለቃቸው ተንቀሳቃሽ ምስሎች የእስልምና ሀይማኖትን መካዷን እና ወደ ሳዑዲ ብትመለስ ጨቋኝ ናቸው የምትላቸው ቤተሰቦቿ ሊገድሏት እንደሚችሉ የተናገረችው። • የሳዑዲ ሴቶች መሪ ጨበጡ • በሳዑዲ 'አንድ ወንድ እኩል ይሆናል ሁለት ሴት' • ሳዑዲ ሴቶች ወደ ስታዲየም እንዲገቡ ልትፈቅድ ነው የወሰድኩት እርምጃ አደገኛ እንደሆነ ይገባኛል ይሁን እንጂ ትክክለኛ ውሳኔ ነው። ምንም የሚጎድልብኝ ነገር አይኖረም ስትል ቶሮንቶ ስታር ለተሰኘ ጋዜጣ ተናግራለች። ''የህይወት ታሪኬን እና የሳዑዲ ሴቶች የሚደርስባቸውን በደል በይፋ መናገር እፈልጋለሁ። እንደ እቃ ነው የምንቆጠረው፤ እንደ ባሪያ።'' ብላለች ራሃፍ። "ይህ ይሆናል ብዬ በጭራሽ አላሳብኩም ነበረ። የሰው ልጆች መብት በሚከበርባት ካናዳ ደህንነቴ እንደተጠበቀ ይሰማኛል።'' ስትልም ተናግራለች። ራሃፍ ከወላጆቿ ጋር ወደ ኩዌት እየተጓዘች ሳለ ነበር የአውስትራሊያ ቪዛ እንዳላት በመናገር በባንኮክ አድርጋ ወደ አውስትራሊያ ለመግባት ከወላጆቿ ያመለጠችው። ይሁን እንጂ ባንኮክ አየር ማረፊያ እንደደረሰች የሳዑዲ ዲፕሎማት ፓስፖርቴን ስለቀማኝ ጉዞዬን መቀጠል አልቻልኩም ብላ ነበር። ወንድሟና አባቷ ራሃፍን ወደ ሳዑዲ ለመመለስ ባንኮክ አየር ማረፊያ ድረስ ሄደውም ነበር። ራሃፍ ባንኮክ የሆቴል ክፍል ውስጥ እራሷ ላይ ቆልፋ፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና የተለያዩ ሀገራት መንግሥታት እንዲታደጓት ጥሪ አቅርባ ነበር። የወጣቷ ጉዳይ የበርካቶችን ቀልብ ስቦ ነበረ። የታይላንድ መንግሥት በባንኮክ እንድትቆይ ፍቃድ ሰጥቶ የነበረ ሲሆን፤ የተባበሩት መንግሥታትም የጥገኝነት ጥያቄዋን ሲያስፈጽምላት ነበረ። ካናዳ ለራሃፍ ጥገኝነት በመስጠቷ ወጣቷ ከሦስት ቀናት በፊት ቶሮንቶ ገብታለች። በቶሮንቶ አውሮፕላን ማረፊያ የካናዳ የውጪ ጉዳይ ሚንስትርን ጨምሮ በርካታ ደጋፊዎቿ አቀባበል አድርገውላታል። ራሃፍ አል-ቁኑን የሚለውን የቤተሰብ ስሟን ከዚህ በኋላ እንደማትጠቀምበት አስታውቃለች።
news-52589245
https://www.bbc.com/amharic/news-52589245
ኮሮናቫይረስ፡ በዓለም ላይ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች አሃዝ ከአራት ሚሊዮን በላይ ሆነ
ከወራት በፊት በቻይናዋ ዉሃን ከተማ የተቀሰቀሰውና የመተንፈሻ አካላትን እንደሚያጠቃ የተነገረለት የኮሮናቫይረስ ለዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት በተደረገ በአራት ወራት ውስጥ አራት ሚሊዮን ሰዎችን በበሽታው ተይዘዋል።
በሽታው በፍጥነት እየተዛመተ ባለበት በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች አሃዝ 4 ሚሊዮን 24 ሼህ ደርሷል። በዚህም መሰረት እጅግ በጣም ከፍተኛውን በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥርን ያስመዘገበችው አገር አሜሪካ ስትሆን ከ1,309,541 በላይ ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተረጋግጧል። በመከተለም በቅደም ተከተል ስፔን 223,578፣ ጣሊያን 218,268፣ ዩናይትድ ኪንግደም 216,525፣ ሩሲያ 198,676፣ ፈረንሳይ 176,782 እና ጀርመን 171,324 ከሁለተኛ እስከ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። በወረርሽኙ በተያዙ ሰዎች ቁጥር ቀዳሚ የሆነችው በሽታው በገደላቸውም አሃዝ የመጀመሪያው ረድፍ ላይ ትገኛለች በዚህም ከ77 ሺህ በላይ ዜጎቿ ለሞት ተዳርገዋል። ኮቪድ-19 ከአውሮፓዊያኑን ከዩናይትድ ኪንግደም፣ ከጣሊያን፣ ከስፔንና ከፈረንሳይም ከእያንዳንዳቸው ከ25 ሺህ በላይ የሚሆኑ የዜጎቻቸውን ህይወት ነጥቋል። ወረርሽኙ ከእስያ ወደ አውሮፓ ከዚያም ወደ ሰሜን አሜሪካ ተዛምቶ ሺህዎችን ያረገፈ ሲሆን በርካታ ድሃ አገራት የሚገኙባቸውን አፍሪካና ደቡብ አሜሪካንንም አልማረም። እስካሁን በእነዚህ አህጉራት ውስጥ ያደረሰው ጉዳት የጎላ ባይሆንም በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ ሊያስከትል የሚችለው ጉዳት ብዙዎችን አስግቷል። እስካሁን ባለው አሃዝ በአፍሪካ ውስጥ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች 60 ሺህ የደረሰ ሲሆን በየዕለቱ ከተለያዩ የአህጉሪቱ አገራት የሚወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው የበሽታው መስፋፋት ፍጥነት እየጨመረ በወረርሽኙ የሚያዙትም ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ መጠን እያደገ ነው። የኮሮናቫይረስ ከመስፋፋት ፍጥነቱና እስካሁን በመላው ዓለም ለሞት ከዳረጋቸው ከ277 ሺህ በላይ ሰዎች አንጻር ከፍተኛ ስጋትን የደቀነ ቢሆንም በየዕለቱ ከበሽታው የሚያገግሙ ሰዎችም እየጨመረ ነው። በዚህም መሰረት በዓለም ዙሪያ ከቫይረሱ ያገገሙት ሰዎች ቁጥር በአሁኑ ውቀት ከ አንድ ሚሊዮን 348 ሺህ በላይ ሰዎች ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ማገገማቸውን የጆንስ ሆፕኪንስ መረጃ ያመለክታትል። አህጉረ አፍሪካ በበሽታው ከተያዙ 60 ሺህ ሰዎች መካከል ከ20 ሺህ የሚልቁት ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን 2200 ያህ አፍሪካዊያን ደግሞ በወረርሽኙ ህይወታቸውን አጥተዋል። አስካሁን በተለያዩ የዓለም አገራት ውስጥ በሽታውን የሚከላከል ክትባትና የሚፈውስ መድኃኒት ለመስራት ያልተቋረጠ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም የተጨበጠ ውጤት ላይ ግን ገና አልተደረሰም። ባለሙያዎች እንደሚሉትም መድኃኒት ወይም ክትባት ለማግኘት ወራት መጠበቅ ሳያስፈልግ አይቀርም። ነገር ግን ከበሽታው ክስተት ጀምሮ በጤና ባለሙያዎች የሚመከሩና ውጤታማ የቫይረሱን መከላከያ መንገዶች ተግባራዊ ማድረግ በአሁኑ ወቅት ብቸኛው አማራጭ እንደሆነ ነው። በዚህም መሰረት የእጅን ንጽህና በውሃና በሳሙና በተደጋጋሚ በመታጠብ መጠበቅ፣ በርካታ ሰዎች ከሚሰበሰቡባቸው ስፍራዎች እራስን ማራቅና በየትኛውም ቦታ አካላዊ ርቀትን ሁሉንም ሳይነጣጥሉ ተግባራዊ በማድረግ እራስንም ሆነ ሌሎችን ከበሽታው ለመጠበቅ ያለ አማራጭ ነው።
news-56826760
https://www.bbc.com/amharic/news-56826760
ዴሪክ ሾቪን በጆርጅ ፍሎይድ የግድያ ወንጀል ጥፋተኛ ተባለ
የቀድሞ የፖሊስ አባል ዴሪክ ሾቪን በጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ጥፋተኛ ነው ሲል የዳኞች ቡድን ብይን ሰጠ።
የ45 ዓመቱ ዴሪክ ሾቪን ከወራት በፊት ጥቁር አሜሪካዊውን ጆርጅ ፍሎይድን በቁጥጥር ሥር ለማድረግ የተጠርጣሪው አንገት ላይ ከ9 ደቂቃዎች በላይ በጉልፈቱ አፍኖ ሲቆይ በተንቀሳቃሽ ምስል ተቀርጾ ነበር። ይህ የቀድሞ የፖሊስ አባል ተግባር በርካቶችን አስቆጥቶ የነበረ ሲሆን፤ የፖሊስ አባሉ አላስፈላጊ ኃይል ተጠቅሟል በሚል እና ዘረኝነትን በመቃወም በመላው ዓለም የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደው ነበር። ሾቪን በአገሪቱ የወንጀል ሕግ፤ በሦስት የግድያ ወንጀል ክሶች ነው ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘው። የቀድሞ የፖሊስ አባል የእስር ፍርድ እስኪሰጠው ድረስ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ይቆያል። ሾቪን ምናልባትም አስርት ዓመታትን በእስር እንዲያሳልፍ ሊፈረድበት ይችላል። 12 አባላት ያሉት የዳኞች ቡድን የቀድሞ የፖሊስ አባሉን ጥፋተኛ ለማለት ከአንድ ቀን ያነሰ ጊዜ ብቻ ነበር ያስፈለጋቸው። ዳኞቹ ከዚህ ብይን ከመድረሳቸው በፊት የ45 ምስክሮችን ቃል ያደመጡ ሲሆን በርካታ ተንቀሳቃሽ ምስሎችንም ተመልከተዋል። የተከሳሽ ጠበቆች እና ከሳሽ ዐቃቤ ሕግም ለሦስት ሳምንታት የዘለቀ ክርክር አድርገው ነበር። የተከሳሽ ጠበቆች ደንበኛቸው አካሉ ግዙፍ የሆነ እና ከሦስት የፖሊስ አባላት ጋር ሲታገል የነበረን ተጠርጣሪ በቁጥጥሩ ሥር ለማድረግ የወሰደውን እርምጃ የትኛውም የፖሊስ አባል ሊያደርገው የሚችለው ነው ሲሉ ተከራክረዋል። ጠበቆች ደንበኛቸውም የሚወስደው ተግባር በሙሉ በተንቀሳቃሽ ምስል እንደሚቀረጽ ስለሚያውቅ ተመጣጣኝ ያልሆነ እርምጃ ሆነ ብሎ አይወስድም ብለዋል። ከሳሾች በበኩላቸው ዴሪክ ሾቪን በጆርጅ ፍሎይድ አንገት ላይ ከ9 ደቂቃዎች በላይ በጉልበቱ ተጭኖ የሚያሳየውን ተንቀሳቃሽ ምስል በማጣቀስ "የምታዩትን እመኑ። ያያችሁትን አይታችኋል" የሾቪን ተግባር የፖሊስ ሳይሆን ግድያ ነው ብለውም ተናግረዋል ከሳሹ። ሁለቱ አካላት መከራከሪያቸውን ካቀረቡ በኋላ 12 አባላት ያሉት የዳኞች ቡድን ምስጢራዊነቱ በተጠበቀ መልኩ ውሳኔያቸውን አስተላልፈዋል። የዳኞቹ ውሳኔ እንደተሰማ ከፍርድ ቤቱ ውጪ ሆነው ዜናውን ሲጠባበቁ የነበሩት ሰዎች ደስታቸውን ገልጸዋል። የጆርጅ ፍሎይድ ቤተሰብ ጠበቃ፤ ይህ በአሜሪካ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ነው ብለዋል። ከውሳኔው በኋላ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን እና ምክትል ፕሬዝደንት ካማላ ሃሪስ የጆርጅ ፍሎይድ ቤተሰብ አባላት ጋር ስልክ ደውለዋል። ፕሬዝደንት ጆ ባይደን፤ ከቤተሰቡ ጋር በነበራቸው ንግግር፤ "ቢያንስ አሁን ፍትህ አለ" ሲሉ ተደምጠዋል። ሾቪን ውሳኔውን በተመለከት ይግባኝ እንደሚለው የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን በስፋት እየገለጹ ይገኛሉ።
news-54157746
https://www.bbc.com/amharic/news-54157746
አሜሪካ፡ ዶናልድ ትራምፕ "ሳይንስ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም" ሲሉ አጣጣሉ
በኅዳር ወር ለዳግም ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ቅስቀሳ ላይ ያሉት ዶናልድ ትራምፕ ማወዛገባቸውን ቀጥለዋል፡፡
ትናንት የሰደድ እሳት የበላውን ምዕራቡን የአሜሪካ ክፍል ለመጎብኘት ካሊፎርኒያ ነበሩ፡፡ የካሊፎርኒያ ሰደድ እሳት ሰፊውን የካሊፎርኒያ ግዛትን ብቻ ሳይሆን ኦሪጋንና ዋሺንግተን ግዛቶችን ጭምር ያካለለ በታሪክ ሰፊ ቦታን ከሸፈኑ ሰደድ እሳቶች አንዱ ነው፡፡ እሳቱ የበላው ጫካ ምን ያህል ይሰፋል ቢባል ከሎንዶን ወይም ከኒውዮርክ ከተሞች በእጅጉ የላቀ ነው፡፡ ሁለቱ ከተሞች ቢደመሩም ሰደድ እሳቱ ካካለለው ቦታ ያንሳሉ፡፡ ወይም ደግሞ 10 ኒውዮርክ ከተማዎችን ያክላል በመጠን፡፡ ወይም በሌላ አነጋገር በየ 24 ሰዓቱ ዋሺንግተን ዲሲን የሚያህል መሬት በእሳት ይበላል፡፡ በሌላ አሐዛዊ አነጋገር ሰደድ እሳቱ ያወደመው ቦታ ስፋት ከ2 ሚሊዮን ሄክታር በላይ ሆኗል፡፡ በእሳት አደጋው እስከ አሁን 35 ሰዎች ሞተዋል፡፡ የዚህ ሰደድ እሳት ዋንኛ ምክንያት አየር ንብረት ለውጥ እንደሆነ ሳይንስ ቢናገርም ትራምፕ በሳይንስ ተሳልቀዋል፡፡ ከካሊፎርኒያ ግዛት አስተዳዳሪዎች ጋር የተገናኙት ዶናልድ ትራምፕ ‹‹አይዟችሁ እሳቱ በራሱ ጊዜ ይጠፋል› ብለዋቸዋል፡፡ እሳቱ ከነሐሴ ወር መጀመርያ የጀመረ ዛሬም ድረስ አልጠፋም፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ ብሎ ነገር የለም የሚሉት ዶናልድ ትራምፕ ለሰደድ እሳቱ ዋናው ምክንያት የጫካ አስተዳደር ድክመት ስለሆነ እሱን ማጠናከር ነው ብለዋል፡፡ ዶናልድ ትራምፕ ዌስት ኮስትን ከጎበኙ በኋላ ከአካባቢው ኃላፊዎች ጋር በነበራቸው ውይይት አንድ ኃላፊ ሳይንስና የአየር ንብረት ለውጥ እስከነ አካቴው ገሸሽ መደረግ እንደሌለባቸው ሲያነሱ ዶናልድ ትራምፕ ሰውየውን አቋርጠው ‹‹ሳይንስ ምን ያውቃል? ሳይንስ ምንም የሚያውቅልህ ነገር የለም›› ብለዋቸዋል፡፡ ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ከፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት እንድትወጣ ያደረጉ መሪ ናቸው፡፡ ከዚህ ስብሰባ በኋላ አንድ ጋዜጠኛ ዶናልድ ትራምፕን ‹‹ለመሆኑ የሰደድ እሳት መልሶ መላልሶ የሚያጠቃን ጉዳይ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተያያዘ ይሆን ወይ ሲል ጠይቋቸው ነበር፡፡ ‹‹አይደለም፤ ዋናው የጫካዎችን አስተዳደር ማስተካከል ነው›› ብለውታል፡፡
news-49202442
https://www.bbc.com/amharic/news-49202442
ሊቢያ ሦስት የስደተኛ ማቆያ ማዕከላትን ልትዘጋ ነው
ሊቢያ በአገሪቱ ያሉ ሦስት ትላልቅ የስደተኛ ማቆያ ማዕከላትን ልትዘጋ መሆኑን የአገሪቷ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ፋቲ ባሻጋ አስታወቁ። ማዕከላቱ ሚስራታ፣ ታጆራ እና ኮምስ መሆናቸውም ተገልጿል።
ሚንስትሩ ይህን ያስታወቁት ባለፈው ስደተኞች ታጆራ ወደተባለው ማዕከል እንዲመለሱ መደረጋቸውን ተከትሎ ባጋጠማቸው ትችት ሲሆን ይህ ካምፕ በሐምሌ ወር በሚሳይል ተመትቶ ከ20 በላይ ስደተኞች ሕይወት አልፏል። ከሞቱት መካከል አብዛኞቹ አፍሪካውያን ስደተኞች ናቸው ተብሏል። • የትሪፖሊ አየር ማረፊያ የሮኬት ጥቃት ሙከራ ተሰነዘረበት • በኢትዮጵያ ስላሉ ስደተኞች አንዳንድ ነጥቦች ማዕከሉ በተባበሩት መንግሥታት የሚደገፈው መንግሥት እና ራሱን የሊቢያ ብሔራዊ ጦር ብሎ የሚጠራውን አማጺ ኃይል ለሚዋጉበት ቀጠና ቅርብ በመሆኑም እንደተዘጋ ተገልጿል። በሊቢያ ያለውን ሁኔታ የሚከታተሉ ድርጅቶች የእነዚህ ማዕከላት መዘጋት ሌሎች የስደተኛ ማዕከላት የተጨናነቁ እንዲሆኑ ያደርጋል ብለዋል። ከዚህ ባሻገርም በርካታ ስደተኞች በሕገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ እጅ ሊወድቁ እንደሚችሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል። ባለፈው ሳምንት ከሊቢያ ወደ ጣሊያን ለመጓዝ ሲሉ 150 ስደተኞች ባህር ላይ ሰጥመው ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል። በዚህ ዓመት በሜዲትራኒያን ባህር ላይ ሰጥመው ከሞቱት ይህ አደጋ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች ያለቁበት ነውም ተብሏል። ሊቢያ ለረዥም ጊዜ ሲያስተዳድሯት የነበሩት ሙአመር ጋዳፊ እ.ኤ.አ በ2011 ከሥልጣን ከወረዱ በኋላ በግጭት እየታመሰች ሲሆን የተለያዩ የጦር አበጋዞች በሚቆጣጠሯቸው ሥፍራዎችም ተከፋፍላ ትገኛለች።
44812417
https://www.bbc.com/amharic/44812417
"መኖር የምፈልገው ልጆቼን ለማየት ብቻ ነው"
ኢትዮጵያዊው ጋዜጠኛ አዲስዓለም ሀድጉ ለ16 ዓመታት ኤርትራ ውስጥ የሚገኙትን ባለቤቱንና ሁለት ሴት ልጆቹን አላያቸውም።
የአዲስ ዓለም ትንሿ ልጁ ወታደር ናት ከሁለት ዐሥርታት በላይ ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት ወደ ሰላም መመለሱና ጦርነቱንም ለማቆም የፈረሙት ስምምነት ተከትሎ የአዲስዓለም ተስፋ ታደሰ። ቤተሰቦቹን በዓይነ ሥጋ የማግኘት ተስፋው አንሰራራ። በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚጀመር የሚጠበቀው የአየር በረራ ብዙ ቤተሰቦች እንዲናፍቁት የኾነውም ለዚሁ ነው። • የኢትዮጵያና ኤርትራን የአብሮነት እርምጃ ምን ይፈትነዋል? ለዓመታት ተቋርጦ የነበረው የስልክ ግንኙነት መመለሱ ጋር ተያይዞ ብዙዎች ናፍቆታቸውን በስልክ ለመወጣት ቢሞክሩም በድንበሩ ጦርነት ትዳሩ የፈረሰዉና ቤተሰቡ ለሁለት የተከፈለው አዲስዓለም ግን አሁንም በጉጉት እየጠበቀ ነዉ። በሁለቱ አገራት ጦርነት ምክንያት ከመቶ ሺዎች በላይ ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል፤ ኢኮኖሚያዊ ኪሳራን አስከትሏል፤ ከዚህም በላይ በሕዝቦች መካከል መቃቃርን ፈጥሮ የጠላትነት ስሜት እንዲጎለብት አድርጓል። አዲስ ዓለም የደረሰበትን ሁኔታ በአንደበቱ እንዲህ ይተርከዋል። • ወደ አሥመራ ለመጓዝ ማወቅ የሚገባዎ 6 ነጥቦች ሁለት ወንድሞቼን በዚህ ጦርነት አጥቻለሁ። የጦርነቱ ጦስ ቤተሰቤንም አሳጥቶኛል። ከባለቤቴ ምፅላል ጋር የተጋባነው በ1972 ዓ.ም ነው። ሁለት ሴትና አንድ ወንድ ልጅም አፍርተናል። በ1994 ዓ.ም ወደ ኤርትራ ሁለት ሴት ልጆቼን ይዛ ከሄደች በኋላ ተያይተን አናውቅም። ኤርትራዊ በመሆንዋ ከምታስተምርበት ሥራ ስትባረር፤ ካገርም ሊያባርሯት ይችላሉ ብዬ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢትዮጵያዊ አግብታ እንደምትኖር ወረቀት አዘጋጅቼ ነበር። ከአንድ ዓመት በፊት ግን ኤርትራ ባካሄደችው ሕዝበ-ውሳኔ ላይ በኔ ተነሳሽነት ለነፃነት ድምፅ ሰጥታ ነበር። በወቅቱ እሷ ስጋት ቢኖርባትም ልጆቼ አባታቸው ከትግራይ መሆኑን እናታቸው ደግሞ ከኤርትራ መሆኗን እንዲያውቁ በማለት አደፋፍሬያት ድምፅ ሰጠች። ይህ ሕዝበ-ውሳኔም ሥራዋን እንድታጣና ኤርትራም እንድትሄድ ምክንያት ሆነ። ትዳራችንም አከተመ። የሞትኩ ያህል ነበር የመሰለኝ ትናንትና የተፈጠረ በሚመስል ሁኔታ የሆነውን በዝርዝር አስታውሰለሁ። ቀኑ ሮብ ነበር፤ ባለቤቴ አጎቷን ለመጠየቅ ሌላ ከተማ እንደምትሄድ ነገረችኝ። አጎቷም ቤት አልሄደች። ልጆቼን ይዛ ኤርትራ ገባች። ኤርትራ ለመሄድ አቅዳው የነበረ ቢሆንም ለኔ ግን ምንም ያለችኝ ነገር አልነበረም። ሰማይ የተደፋብኝ መሰለኝ፤ በሕይወት መኖሬ ትርጉሙ ጠፋኝ። ኤርትራ ውስጥ ይህ ነው የምትለው ቤተሰብ ባይኖራትም የስደተኞች መጠለያ ማዕከል ውስጥ ገባች። የሁለቱም ሀገራት ድንበር በመቋረጡ ተከትያትም መሄድ አልቻልኩም፤ የሞትኩ ያህል ነው የተሰማኝ። በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ከመቶ ሺዎች በላይ ህይወታቸውን አጥተዋል። ደብዳቤዬ ምላሽ አልነበረውም ባለቤቴ ሳትነግረኝ በድንገት መሄዷ ለቤተሰቦቼ አልተዋጠላቸውም። "አንድ ነገር ብታደርጋት ነው እንጂ እንዲህ ብን ብላ አትጠፋም ነበር" ይሉኝ ነበር። እኔ ግን ምንም እንዳልበደልኳት አውቃለሁ። በጣም የምንዋደድና የምንከባበር ባልና ሚስት ነበርን። ቤታችን ሳቅና ደስታ ተለይቶት አያውቅም ነበር። ስትሄድ ጎረቤቶቼ ጋር የተወችልኝ ደብዳቤ ሲሆን "መለያየት ከሞት በላይ እንደሚከብድ አውቃለሁ፤ ሆኖም ልጆቼን ይዤ ሄጃለሁ። ወንዱ ልጃችንን አንተ ጋር ትቼዋለሁ። አጋጣሚውን ካገኘሁ ደብዳቤ እጽፍልኸለሁ፤ ለማንኛውም እራስህን ጠብቅ" የሚል ነው። • የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት ኢኮኖሚያዊ ትርፍ? ለሳምንት ያህል ሐዘን ተቀምጫለሁ፤ ጎረቤቶቼም ሊያፅናኑኝ ቢሞክሩም ለኔ ሕይወት ያከተመች መስሎ ነበር የተሰማኝ። እንዳበደ ሰው በቁሜ የሞትኩ ያህል ይሰማኝ ነበር። የባለፉትን ዓመታት በቃላት ልገልጻቸው አልችልም። ሐዘኑን ለመርሳት ምርጫዬ የነበረው መጠጥ ብቻ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ወደ ኤርትራ ከመሄዳቸው በፊት፤ ሁለቱ አገራት የሰላም ስምምነት ይኖራቸዋል የሚል ሐሳብ አልነበረኝም። በፍፁም! • የትናንትናዋ እለት- በኢትዮ ኤርትራ ግጭት ቤተሰባቸው ለተለያየ? ባለቤቴም ሆኑ ልጆቼ እድሉን አግኝተው ወደ ውጭ ሀገር ቢሄዱ መገናኘት እንደምንችል ተስፋ አደርግ ነበር። በቀይ መስቀል በኩል በተከታታይ ደብዳቤ ብጽፍም ምላሽ አላገኘሁም። ተስፋ ስለቆረጥኩም የኋላ ኋላ መጻፍ አቆምኩ። ሁልጊዜም ግን ወደፊት አንድ ቀን ግን ባለቤቴን አግኝቻት ለምን ትታኝ እንደሄደች መጠየቅ እፈልግ ነበር። በኤርትራ የሚገኘው ይህ መካነ-መቃብር የጦርነቱ አሰቃቂነት ማስታወሻ ነው። ልጄ! ሴቶች ልጆቼን በፌስቡክ ለማግኘት እየሞከርኩ በነበርኩበት ወቅት ትንሿ ሴት ልጄ ዳናይት በፌስቡክ መልእክት ላከችልኝ። "በድምፅ ልናዋራህ አንችልም፤ ግን ሁልጊዜም ቢሆን እናስብኻለን" የሚል ነበር። እንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም። ናፍቆቴ ከቃላት በላይ ነበር። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ከቴክኒክ ኮሌጅ ተመርቃ ሳዋ ወታደራዊ ካምፕ ስትገባ ግንኙነታችን ተቋረጠ። ወታደር በመሆኗ ስልክ ስለማይፈቀድ መገናኘታቸንም የመይታሰብ ሆነ። ከዚህ በኋላ ሕይወት እንዴት ሸክሟ እንደከበደብኝ! ደግሞም ሁሉንም ልጆቼን ብወዳቸውም ለምን እንደሆነ አላውቅም ለትንሿ ልጄ ያለኝ ፍቅር ይለያል። እንዴት ብዬ እንደምገልፃት አላውቅም። አስተዋይ፣ ከዕድሜዋ በላይ አሳቢ፣ የራሷ ያልሆነ ነገር የማትወድ ንፁህ ልጅ ናት። ልጆቼን ማግኘት የየዕለት ምኞቴ ነው። አንድ ቀን ተገናኝተን የዚህ ሁሉ ዓመታት የልብ ናፍቆታኝንና ያሳለፍነውን መጥፎ ታሪክ በለቅሶ እንዲወጣልን እመኛለሁ። የስልክ አድራሻቸውንም እየፈለግኩ ነው። አሁን የ58 ዓመት ዕድሜ ባለፀጋ ነኝ። ከዚህ በላይ የመኖር ፍላጎቱ የለኝም። ልጆቼንና ባለቤቴን ዳግመኛ የማገኝበትን ቀን ለማየት ብቻ ነው መኖር የምፈልገው። • የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አዲስ ምዕራፍ • ሊገዳደሉ ከአንድ ጦር አውድማ የተገኙ ወንድማማቾች የአዲስዓለም አዲስተስፋ ልጆቼን በህልሜ አያቸዋለሁ። ባለፈው ዕሁድ ኤርትራውያን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን ሲቀበሉ ልጆቼንና ባለቤቴን ያየሁ ነው የመሰለኝ። ቤተሰቤንና የድሮ ጓደኞቼን አግኝቼ አዲስ ሕይወት ለመጀመር ወደ ኤርትራ መሄድ እፈልጋለሁ። ልጄም እናቱንና እህቶቹን እንዲያገኝ እፈልጋለሁ። የልጆቼን እጆች መንካት፣ ፀጉራቸውን መዳበስና ጠረናቸውን ማሽተት ይናፍቀኛል። አሁን ትልቅ ሰውም ስለሆንኩ "አባዬ አለንልህ!" እንዲሉኝ እሻለሁ። ይህቺ ቀን ከመጣች ለኔ ዳግም ውልደቴ ናት።
news-55036279
https://www.bbc.com/amharic/news-55036279
ዘ ዊኬንድ የግራሚ ሽልማት "ሙሰኛ" ነው ሲል ተናገረ
ካናዳዊው ሙዚቀኛ ዘ ዊኬንድ፣ አቤል ተስፋዬ በሙዚቃው ኢንዱስትሪ ዘንድ ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠውን የግራሚ ሽልማት ሙሰኛ ነው አለ።
ከዚህ ቀደም የግራሚ ሽልማቶችን ያሸነፈው ዘ ዊኬንድ ለዘንድሮው ዓመታዊ የግራሚ ሽልማትም አልታጨም። ሙዚቀኛው ያወጣው አልበም ከፍተኛ ተቀባይነትን ማግኘቱን ተከትሎ እንዲሁም በተለይም በአልበሙ የተካተተው 'ብላይንዲንግ ላይትስ' የተሰኘው ዜማው ተወዳጅ የሙዚቃ ሰንጠረዦችን በአንደኛ ደረጃ መምራቱን ተከትሎ ለግራሚ ሽልማት መታጨት ብቻ ሳይሆን በርካታ ሽልማቶችን ያሸንፋልም ተብሎ ተጠብቆ ነበር። "የግራሚ ሽልማት አሁንም ቢሆን ሙሰኛ ነው" በማለት በትዊተር ገፁ ላይ ያሰፈረው ሙዚቀኛው አክሎም "ለእኔም፣ ለአድናቂዎቼም ሆነ ለሙዚቃ ኢንዱስትሪው ሲባል ግልፅነትን እንጠብቃለን" ብሏል። የግራሚ ሽልማት ኃላፊዎች በበኩላቸው የሙዚቀኛውን ቅር መሰኘት እንደተሰማቸው ገልፀው ነገር ግን በየዓመቱ ድንቅ ችሎታ ያላቸው ሙዚቀኞችም ሽልማት ላያገኙ ይችላል በማለት ምላሽ ሰጥተዋል። 'አፍተር ሃወርስ' የተሰኘው አልበሙ ከፍተኛ ሽያጭ በማስመዝገብ የዓመቱን ክብረ ወሰን የጨበጠ ሲሆን 'ብላይንዲንግ ላይትስ' የተሰኘውና በዚህ አልበም የተካተተው ሙዚቃው በአሜሪካ የሙዚቃ ሰንጠረዥን ለረዥም ጊዜ በመቆጣጠር ከአስሩ ምርጥ ተካቷል። ከኢትዮጵያዊ ቤተሰቦች በካናዳ ተወልዶ ያደገው ዘ ዊኬንድ (አቤል ተስፋዬ) በቅርቡ በሙዚቃው ስፍራ ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸውን ኤምቲቪ፣ ቪኤምኤና የአሜሪካ የሙዚቃ ሽልማቶችን አግኝቷል። በየካቲት ወርም በአሜሪካውያን ዘንድ ከፍተኛ ስፍራ በሚሰጠው ሱፐር ቦውል የእግር ኳስ ጨዋታ በእረፍት ሰዓት ላይ ይዘፍናል ተብሎ ይጠበቃል። በርካታ የአሜሪካ ሚዲያዎችም ሪፖርት እንዳደረጉት ሙዚቀኛው ከሽልማቱ እንዲወጣ የተደረገው በሱፐር ቦውል በመዝፈኑ ነው ተብሏል። በሱፐር ቦውል እንዲዘፍን የተለያዩ ስምምነቶች ላይ መደረሱንና ገደብም ተቀምጧል ቢባልም የሽልማቱ አዘጋጆች በበኩላቸው የሙዚቀኛው ለግራሚ ያልታጨው ከእነዚህ ስምምነቶች ጋር በተያያዘ ነው የሚለውን አይቀበሉትም። የዚህን ዓመት የግራሚ ሽልማትን እጩነትን የምትመራው ቢዮንሴ በዘጠኝ ዘርፍ ሲሆን፤ ከእሷ በተጨማሪም ዱዋ ሊፓ፣ ቴይለር ስዊፍትና ሮዲ ሪችም በስድስት ዘርፎች ታጭተዋል።
news-55391890
https://www.bbc.com/amharic/news-55391890
ኮሮናቫይረስ፡ በፈረንሳይና በዩናይትድ ኪንግደም ድንበር ላይ የከባድ መኪኖች እንቅስቃሴ ተገታ
ከአንድ ሺህ አምስት መቶ በላይ ከባድ ጭነት መኪኖች ዩናይትድ ኪንግደምን ለቆ ለመውጣት የፈረንሳይ ድንበር ለንግድና ለጉዞ እስኪከፈት ድረስ በኬንት ከተማ መቆማቸው ተገለፀ።
ፈረንሳይ አዲሱን የኮሮናቫይረስ ዝርያ በመፍራት ከእሁድ ዕለት ጀምሮ ለ48 ሰዓታት ድንበሯን ዘግታለች። በአሁኑ ሰዓት ከ50 በላይ አገራት ከዩናይትድ ኪንግደም የሚመጡ ተጓዦች ወደ አገራቸው እንዳይገቡ ከልክለዋል። የከባድ መኪና አሽከርካሪዎቹ እንዲንቀሳቀሱ ለማድረግ የተለያዩ መፍትሔዎች እየታሰቡ ሲሆን አንደኛው አሽከርካሪዎቹ የኮቪድ-19 እንዲመረመሩ ማድረግ ነው ተብሏል። ይህ በእንዲህ እዳለ የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን አገራት የጣሉት የጉዞ ገደብ እንዲያነሱ ጠይቋል። ለአውሮፓ አባል አገራት በቀረበ ምክረ ሃሳብ ላይ የአውሮፕላን እና የባቡር ጉዞ ላይ የተጣለው ገደብ የአቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠር በሚል እንዲነሳ ተጠይቋል። ነገር ግን ኮሚሽኑ እንዳለው ከሆነ አስፈላጊ ያልሆኑ ጉዞዎች አሁንም ቢሆን መበረታታት የለባቸውም። የአውሮፓ ሕብረት አባል አገራት በሙሉ አዲሱን ቫይረስ በመፍራት ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ሆነ ከአገሪቱ የሚደረጉ ጉዞዎችን አቋርጠዋል። የአውሮፓ ሕብረትም የተባበረ ምላሽ መስጠት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እየመከረ ይገኛል። በአሁኑ ጊዜ ወደ ፈረንሳይ ከዶቨር ወደብም ሆነ ከዩሮታነል የሚነሳ ተሽከርካሪ የለም። የአገር ውስጥ ሚኒስትሩ ፕሪቲ ፓቴል እንዳሉት ከሆነ 650 ከባድ የጭነት መኪኖች በኤም 20 እንዲሁም ተጨማሪ 873 ደግሞ በከባድ ተሽከርካሪዎች ማቆሚያ ስፍራ ይገኛሉ። የአውሮፓ አገራት ድንበሮቻቸውን የዘጉት አዲሱ አይነት ቫይረስ መከሰቱን እና በፍጥነት መስፋፋቱን የዩናይትድ ኪንግደም ከፍተኛ ተመራማሪ ካስጠነቀቁ እና "በየትኛውም ስፍራ" እንደሚገኝ ካሳወቁ በኋላ ነው። ሰር ፓትሪክ ቫላንስ አክለውም በእንግሊዝ ተጨማሪ ክልከላዎች ያስፈልጋል ብለዋል። በእንግሊዝ 17 ሚሊዮን ሰዎች በጥብቅ የኮቪድ-19 ክልከላ ውስጥ ናቸው። ደረጃ አራት የእንቅስቃሴ ገደብ ከተጣለባቸው አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ሰዎችም በዌልስና በተወሰኑ የእንግሊዝ ከተሞች ሲደርሱ ራሳቸውን አግልለው እንዲቀመጡ ተደንግጓል። ፓቴል እንዳሉት የተስተጓጎለውን የተሽከርካሪዎቹን እንቅስቃሴ ለማስቀጠል በዩናይትድ ኪንግደም እና በፈረንሳይ መካከል "መፍትሔ ለመፈለግ" ንግግሮች እየተደረጉ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን እና የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማርኮን ሰኞ ዕለት የተነጋገሩ ሲሆን እንደመፍትሔ ከዩናይትድ ኪንግደም ወደ ፈረንሳይ የሚመጡ አሽከርካሪዎች ተመርምረው ከኮቪድ-19 ነጻ መሆናቸው መረጋገጥ አለበት ብሏል። ፓቴል የከባድ መኪና ሾፌሮቹን ኮሮናቫይረስ መመርመር "የንግግሩ አካል ነበር" ካሉ በኋላ "የምርመራ ውጤቱን በፍጥነት ማግኘትና ጉዞን ማቀላጠፍ በአንጻራዊነት ፈጣን ነው" ብለዋል። በቦሪስ ጆንሰን እና በማርኮን የተደረሰው ስምምነት ከረቡዕ ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል። በዩሮ ታነል ኃላፊዎች ማክሰኞ እለት 2500 የጭነት ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ተመሳሳይ ቁጥር ያለው መኪና ረቡዕ ዩናይደትድ ኪንግደም ይደርሳሉ ብለው እንደሚገምቱ ተናግረዋል። የድንበር መዘጋቱ በአውሮፕላን፣ በመርከብ እንዲሁም በባቡር ከዩናይትድ ኪንግደም ወደ ፈረንሳይ የሚጓዙ መንገደኞችን አስተጓግሏል። ዩሮታነል እንዳለው ከዩናይትድ ኪንግደም ወደ ፈረንሳይ የሚሄዱ መንገደኞች ስምምነት ላይ ከተደረሰ ረቡዕ እና ሐሙስ መፍትሔ ሊያገኙ ይችሏሉ። የብሪታንያ አየር መንገድም በአነስተኛ ቁጥር በረራ እንደሚጀምር አስታውቋል።
news-44150233
https://www.bbc.com/amharic/news-44150233
ኬንያ፣ ኡጋንዳና ታንዛኒያ ተጨባጭ ያልሆነ መረጃ ላይ ዘመቻ ጀመሩ
ለምስራቅ አፍሪካ አዲስ የሆነውና በኬንያ የወጣው አዋጅ ተጨባጭ ያልሆነ መረጃ የሚያሰራጩ ሰዎች ላይ እስራትን ያስከትላል።
ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ አዲሱ ህግ የሳይበር ጥቃት የሚያደርሱ ወንጀለኞችን በህግ ለመጠየቅ ያስችላል ብለዋል። አዋጁ 50000 የአሜሪካ ዶላር እና እስከ ሁለት ዓመት የሚደርስ ቅጣት ያስከትላል። አዋጁ በኮምፒውተርና በኢንተርኔት አማካኝነት የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለመቆጣጠር በሚል የወጣ ቢሆንም በኬንያ፣ በኡጋንዳ እና በታንዛኒያ የወጡት ህጎች ነጻ ሚዲያዎችን ለመቆጣጠር የተዘረጉ አዲስ ዘዴዎች መሆናቸውን ተቺዎች ይሞግታሉ። የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቾች ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ ያፀደቁት አዋጅ ሃሳብን በነፃ የመግለፅንና የፕሬስ ነፃነትን ይፃረራል ሲሉ ህጉን ተቃውመዋል። አዋጁ የሚድያ ነፃነትን ከመጋፋቱም በላይ ኬንያ ሚዲያን የተመለከተ ህግ እያላት ለምን ተጨማሪ አዋጅ ማውጣት አስፈለጋት ሲሉ ጠይቀዋል። ፕሬዚደንቱ በበኩላቸው አዋጁ የሳይበር ጥቃትን ለመከላከል፣ የህፃናት የወሲብ ፊልሞችን፣ የኮምፒውተር ጥቃትንና መረጃ ምንተፋን ለመቆጣጠር ይውላል ብለዋል። የኬንያ ሚዲያ አዲሱን ህግ ስራቸውን እንደሚቆጣጠር አዲስ ዘዴ አይተውታል በበርኒንግሃም ዩኒቨርሲቲ የዲሞክራሲ ፕሮፌሰር የሆኑት ኒክ ቺዝማን ተጨባጭ ያልሆኑ መረጃዎችን ለመቆጣጠር የፀደቀው አዋጅ በሌላ አጀንዳ ምክንያት የመጣ ነው ሲሉ ተናግረዋል። "ከፍተኛ የሆነ የተጋረጠ አደጋ አለ። ከዚህ በፊትም ከፀረ ሽብር ህጉ ጋር የተያያዘ ህግ ወጥቶ ነበር። መንግሥታት የራሳቸውን አቅም ለማጠናከር ያወጡት አዋጅ ነው" ብለዋል። ሌሎችም በበኩላቸው "ከዚህ ቀደም ወደወጣው የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ይወስደናል። መንግሥትን የሚያጣጥል እና የመንግሥት ባለስልጣናት የማይፈልጉትን ፅሁፍ የፃፉና በገፆቻቸው ላይ አስተያየት የሰጡ ጦማሪያንን ለእስር የዳረገ ነው። ይህም አዋጅ ከዚያ ተለይቶ አይታይም" ሲሉ ትችታቸውን ሰንዝረዋል። ፕሬዚደንት ጆን ማጉፋሊ አነጋጋሪ ህግ አውጥተዋል በቅርቡ በጎረቤት አገር ታንዛኒያም የወጣው ህግ ከዚህ የተለየ አይደለም። ህጉ ጦማሪያን ፅሁፋቸውን በኢንተርኔት አማካኝነት ሲያቀርቡ 920 የአሜሪካ ዶላር እንዲከፍሉ የሚያስገድድ ነው። "ምንም እንኳን ሃሳብን በነፃ ከመግለፅ መብት ጋር ይፃረራል የሚሉ ትችቶች ቢሰነዘሩም፤ ህጉን ለማውጣት የተፈለገበት ምክንያትም ምስራቅ አፍሪካን ተጨባጭ ካልሆነ የመረጃ ስርጭት ለመጠበቅ ነው" ሲል የአገሪቷ መንግሥት ገልጿል። ተጨባጭ ያልሆነ መረጃ ስርጭት በሽታ ነው ሲሉ የገለፁት ፕሬዜደንት ማጉፋሊ ዓላማው መረጃዎችን መርጦ ማስተላለፍ ነው ብለዋል። አዲሱ ህግ ጦማሪያን፣ ኢንተርኔት በመጠቀም መልዕክት የሚያስተላልፉ ግለሰቦች እንዲመዘገቡና ለሶስት ዓመት ፍቃድ 480 ዶላር እንዲከፍሉ በተጨማሪም በዓመት 440 የአሜሪካ ዶላር ክፍያ እንዲፈፅሙ የሚያዝ ነው። ህጉን የተላለፈም 2000 የአሜሪካ ዶላር እና ከአንድ ዓመት ባላነሰ እስር እንዲቀጣ ይደነግጋል። በኬንያ የሚገኙ አቀንቃኞች ሚዲያዎች መዘጋትን ባለፈው የካቲት ሲቃወሙ የታንዛኒያን ጦማሪያን ኔትወርክ ህጉ አባላቶቻቸውን እንዳይፅፉ ወይም የሚፅፉትንም እንዲያቋርጡ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል ከማለት ባለፈ ተቃዋሚ የሆኑ የሚዲያ ባለሙያዎችና ግለሰቦችን ለመቅጣት የተመቻቸ ነው ሲሉ ፕሬዚደንቱን ሞግተዋል። በሌላኛዋ ምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኡጋንዳም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የቀረጥ የሚጥል ረቂቅ ህግ የወጣ ቢሆንም የገንዘብ ሚኒስትሩ "እንዲህ ዓይነት የቀረጥ ህግ እንዴት ተፈፃሚ ሊሆን ይችላል?" ሲሉ ባቀረቡት ጥያቄ ምክንያት በጅማሮ ላይ ይገኛል። ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቭኒ ከማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰበሰበው የቀረጥ ገቢ የአገሪቷ ኢኮኖሚ ላይ አስተዋፅኦ ያበረክታል ሲሉ ገልጸዋል። ከዚህ በተጨማሪም በማህበራዊ ድረ ገፆች የሚለቀቁ የሃሰት መረጃዎችን መቆጣጠር አለብን ብለዋል በቅርቡ ከሚዲያ ባለቤቶችና ጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ስብሰባ ላይ እባካችሁ እየመረጣችሁ አስተላልፉ፤ ውሸት አታሰራጩ ሲሉ ተናግረዋል።
news-55246427
https://www.bbc.com/amharic/news-55246427
ልዑል አልጋ ወራሹ የማይወጧቸው ሦስት ፈተናዎች
አሁን ያለንበት ወቅት ለሳዑዲ መንግሥት በተለይ ደግሞ ለልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሰልማን ምቾት የሚፈጥር አይደለም።
ልዑል አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ሰልማን ምንም እንኳ ኤምቢኤስ በሚል መጠሪያ የሚታወቁት ልዑል አልጋ ወራሽ በአገራቸው ዜጎች ዘንድ ያላቸው ተቀባይነት እንዳለ ቢሆንም፤ በዓለም አቀፉ ማህብረሰብ ዘንድ በጎ ገጽታቸውን የሚያጠለሹ ክስተቶች መኖራቸው አልቀረም። ከሁለት ዓመት በፊት ኢስታንቡል በሚገኘው የሳዑዲ ቆንስላ ውስጥ የጋዜጠኛ ጀማል ካሾግጂ መገደል ዓለም ኤምቢኤስን በጥርጣሬ እንዲያያቸው ምክንያት ሆኗል። አሁን ላይ በአሜሪካ አዲስ ፕሬዝደንት መመረጡ የልዑሉ ሌላኛው ራስ ምታት ነው። ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶ ባይደን ገና ከአሁኑ አስተዳደራቸው በሳኡዲ አረቢያ አንዳንድ ጉዳዮች ላይ ጠንከር ያለ አቋም እንደሚይዝ አስታውቀዋል። ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሦስት ጉዳዮች በዋሽንግተን እና ሪያድ ወዳጅነት መካከል ነፋስ የሚያስገቡ ለሆኑ ይችላሉ። በቀጣይም የኤምቢኤስ ፈተናዎች ሆነው መዝለቃቸው አይቀርም። የየመን ጦርነት የየመን ጦርነት በጦርነቱ ለተሳተፉት ሁሉ መዘዝን ይዞ መጥቷል። ካልተገመተ ፈተና ውስጥም ከቷቸዋል። ሳኡዲ አረቢያ ጦርነቱን አልጀመረችውም። የየመንን የእስር በእርስ ጦርነት ያስጀመሩት ሁቲዎች ናቸው። እአአ 2014 ላይ የሁቲ አማጺያን ወደ የመን መዲና ሰነዓ ዘምተው ሕጋዊ መሠረት ያለውን መንግሥት ከጣሉ በኋላ አገሪቷን ወደ የእርስ በእስር ጦርነት አስገብተዋል። ሁቲዎች በየመን ሰሜናዊ ተራራማ ቦታ በስፋት የሚኖሩ ሲሆን ከአጠቃላይ የአገሪቱ ሕዝብ 15 በመቶውን ይወክላሉ። እአአ ሕዳር 2015 ላይ ሞሐመድ ቢን ሰልማን ሁቲዎችን ለመዋጋት የአረብ አገራትን ማስተባበር ያዙ። ልዑል አልጋ ወራሹ የበርካታ አረብ አገራትን የተባበረ ክንድ በማስተባበር በአየር ጥቃቶች የሁቲ አማጺያንን በጥቂት ወራት ውስጥ ማንበርከክን ዓላማ አድርገው ነበር የተነሱት። በጥቂት ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል የተባለው የጦር ኦፕሬሽን ግን ስድስት ዓመታት አስቆጥሮም መገባደጃው አልታወቀም። ለዓመታት በዘለቀው ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ተገድለዋል፤ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። በሁለቱም ጎራ የሚፋለሙት ኃይሎች የጦር ወንጀሎችን ፈጽመዋል። አሁንም ሳኡዲ መራሹ ኃይል የሁቲ አማጺያንን ከሰነዓ እና የበርካቶች መኖሪያ ከሆነው ምዕራብ የመን ማስወጣት አልተቻለውም። በኢራን የሚደገፉት የሁቲ አማጺያን የሚያስወነጭፏቸው ዒላማቸውን የጠበቁት ሚሳኤሎች እንዲሁም የድሮን ጥቃቶች የሳኡዲ አረቢያን ነዳጅ ማብላያ ጣቢያን በመምታት በሳኡዲ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ማድረስ ችለዋል። ሳኡዲ መራሹ ኃይል የሁቲ አማጺያንን ከሰነዓ ማስወጣት ተስኖት ቆይቷል። ሳኡዲ አረቢያ ራሷን ከዚህ ጦርነት ለማውጣት ጽኑ ፍላጎት አላት። የሁቲ ታጣቂዎች ሰነዓን እንደተቆጣጠሩ ከጦርነቱ መውጣት ግን ለሳኡዲ የማይሆን አማራጭ ነው። የሁቲ አማጺያን በስልጣን ላይ እንዲቆዩ መፍቀድ ማለት ኢራን በየመን ጠንካራ መሠረት እንዲኖራት መፍቀድ ማለት ነው። ይህን ደግሞ እንዲሆን ሳኡዲ ትፈቅዳለች ተብሎ አይጠበቅም። ሪያድ በየመን የእስር በእርስ ጦርነት በነበራት ተሳትፎ ከትራምፕ አስተዳደር የጠየቀችውን ድጋፍ ስታገኝ ቆይታለች። ይህ ድጋፋ ግን በባይደን አስተዳደር የሚቀጥል አይሆንም። ለኤምቢኤስ ጦርነቱን ጥሎ መውጣት አማራጭ አይደለም። ባካሄዱት የጦር ኦፕሬሽንም የጠበቁትን ድል ማምጣት ተስኗቸዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የኃያሏ አሜሪካን ድጋፍ የማግኘታቸው ጉዳይ ጥያቄ ላይ ወድቋል። በእስር የሚገኙ የሳዑዲ ሴቶች የመብት ተሟጋች ሴቶች እስር የሞሐመድ ቢን ሰልማን አስተዳደር በበጎ እንዳይታይ ካደረጉ ምክንያቶች መካከል አንዱ ነው። 13 ጠንካራ የሳኡዲ አረቢያ የመብት ተሟጋቾች ለእስር ከተዳረጉ ሰንበትበት ብለዋል። ሴቶቹ የታሰሩባቸው ምክንያቶች ደግሞ መኪና ማሽከርከራቸው እና የወንድ ፍቃድ ማግኘት የለብንም በሚል ድምጻቸውን ማሰማታቸው ነው። እንደ ሉወጄይን አል-ሃታሎለ ያሉ የመብት ተከራካሪዎች አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ። የሳኡዲ መንግሥት ሉወጄይን ከውጪ ኃይሎች ገንዘብ ተቀብላለች ሲሉ ይከሰቷል። ለዚህ ግን አሁንም ማስረጃ ማቅረብ አልቻሉም። ጓደኞቿ ግን ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ኮንፍረንስ ላይ ከመሳተፏ እና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለመቀጠር የሥራ ማመልከቻ ከማቅረቧ ውጪ ያደረገችው ምንም የለም ይላሉ። ሉወጄይን አል-ሃታሎለ የመብት ተከራካዊዎቹ እስር በባይደን አስተዳደር እንዲሁ በዋዛ የሚታለፍ አይሆንም። የቢቢሲው የመካከለኛው ምስራቅ ዘጋቢ ፍራንክ ጋርድነር፤ ምናልባትም የሳኡዲ መንግሥት ለዓመታት አስሮ ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻሉ፤ "ምህረት አድርጊያለሁ" በማለት የመብት ተሟጋች ሴቶቹን ከእስር ሊለቅ ይችላል ይላል። ኳታርን የማግለል ሴራ ኳታር በጎረቤት አገራት ተገላ ቆይታለች። ኳታር እንድትገለል ሴራውን ከጠነሰሱት መካከል ደግሞ ሳኡዲ ቀዳሚዋ ናት። ኩዌት ግን ችግሩን ለመፍታት ከመጋረጃው ጀርባ ጥረት ስታደርግ ቆይታለች። ይህ ግን በቀላሉ የሚፈታ ላይሆን ይችላል። እአአ 2017 ላይ ፕሬዝደንት ትራምፕ በሪያድ ጉብኝት ባደረጉ በቀናት ልዩነት፤ ሳኡዲ አረቢያ፣ ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ፣ ባህሬን እና ግብጽ ተባብረው የባህረ ሰላጤ ጎረቤት አገራቸው ኳታርን አገለሉ። ለዚህም ምክንያታቸው ኳታር ለጽንፈኛ እስላማዊ ቡድኖች ድጋፍ ታደርጋለች የሚል ነው። ይህም ከሽብር ይመደባል ይላሉ። ዩናይድ አረብ ኤሜሬትስ መኖሪያቸውን ኳታር ያደረጉ ናቸው ያለቻቸውን የአሸባሪዎች ዝርዝር አቅረባ ነበር። አገራቱ ኳታር ሽብርተኞችን መደገፏን ማቆም አለባት፣ የቱርክ ወታደሮች ከኳታር መውጣት አለባቸው፣ ከኢራን ጋር ያላትን ግንኙነት ታቁም ከሚለው ቅድመ ማስጠንቀቂያዎች በተጨማሪ የኳታሩ አልጀዚራ ይዘጋ የሚል ማሳሰቢያ ተሰጥቷት ነበር። ይህ ተፈጻሚ ካልሆነ ኳታር ላይ ኢኮኖሚያዊ ማዕቀቦች እንጥላለን ሲሉም አስጠነቀቁ። ልክ የሳኡዲ መራሹ ኃይል በየመን ጦርነት በወራት ውስጥ የተፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ ይቻላል የሚለው የተሳሳተ ስሌቱ በኳታርም ተደግሟል። አገራቱ አንድ ላይ በማበር ኳታርን ሲያገሉ፤ ኳታር ጫናውን መቋቋም ተስኗት እጅ መስጠቷ አይቀርም የሚል መላምት ይዘው ነበር የተነሱት። ይህ ግን አልሆነም። ኳታር ባላት የተፈጥሮ ሃብት፣ በዩናይትድ ኪንግደም ያላት ኢንቨስትመንት እንዲሁም ከቱርክ እና ኢራን ያገኘቻቸው ድጋፎች የአረብ አገረቱ ያሰቡት እንዳይሳካ ረድቷታል። በቅርብ ዓመታትም በመካከለኛው ምስራቅ ሁለት ጎራ ተፈጥሯል። የሱኒ ባህረ ሰላጤ አገራት ሳኡዲ አረቢያ፣ ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ እና ባህሬን ከግብጽ ጋር በአንድ ጎራ ሲሰለፉ፤ ኳታር፣ ቱርክ እና እንደ ሙስሊም ብራዘርሁድ እና ሃማስ የመሳሰሉ በርካታ ኢስላማዊ እንቅስቃሴዎች በሌላኛው ጎራ ተሰልፈዋል። የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ጃሬድ ኩሽነር በባህረ ሰላጤው አገራት መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት በድርድር ለመፍታት ወደ አገራቱ ተጉዘው ነበር። አሜሪካ በኳታር ግዙፍ ወታደራዊ ካምፕ እንዳላት ሁሉ መጪው የባይደን አስተዳደርም ችግሩን ለመፍታት ጥረት ማድረጉ አይቀርም።
news-55285686
https://www.bbc.com/amharic/news-55285686
ትግራይ ፡ ቀይ መስቀል ከወር በኋላ መድኃኒቶችና ሌሎች ድጋፎችን መቀለ አደረሰ
ቀይ መስቀል በትግራይ ክልል ወታደራዊ ግጭት ከተከሰተ ከአንድ ወር በኋላ የመጀመሪያውን የመድኃኒትና የእርዳታ አቅርቦት ወደ መቀለ ከተማ ማድረስ እንዳቻለ ገለጸ።
ግጭቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ የግንኙነት መስመሮች በመቋረጣቸው ሳቢያ ለሳምንታት መድኃኒቶችና መሠረታዊ የህክምና አቅርቦት ተቋርጦ ነበር። በዚህም ምክንያት መደበኛ ሥራቸውን ለማከናወን ከባድ ችግር ውስጥ የነበሩትን የህክምና ተቋማት ለመደገፍ ከዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ እና ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የተላኩ መድኃኒቶች እና የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦቶች ዛሬ መቀለ ደርሰዋል። የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ባሰራጨው መግለጫ፤ በህክምና ተቋማት ውስጥ ያጋጠመውን ችግር ለመቅረፍ በሰባት ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች የተላከው ድጋፍ ግጭቱ ከተከሰተ በኋላ መቀለ ከተማ የደረሰ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ እርዳታ እንደሆነ አመልክቷል። በከተማዋ ላሉና ከከተማዋ ውጪ ለሚመጡ ህሙማን አገልግሎት የሚሰጠው የመቀለው አይደር ሪፈራል ሆስፒታል ግጭቱ ከተከሰተ በኋላ ባሉት ሳምንታት ውስጥ በነዳጅ እጦትና በመድኃኒቶች አቅርቦት መቋረጥ ምክንያት የጽኑ ህሙማንና የቀዶ ህክምና ክፍሎቹ አገልግሎት ለማቆም ተገደው እንደበር ተገልጿል። ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ እንዳለው፤ ሆስፒታሉ ከጥቅምት ወር መጨረሻ ጀምሮ በግጭቱ ጉዳት የደረሰባቸውን በርካታ ሰዎች ተቀብሎ የህክምና አገልግሎት ይሰጥ ነበር። ከዚህ በተጨማሪ የከፋ ህመም ላለባቸውና መደበኛ ክትትል ለሚፈልጉ የስኳር በሽተኞች፣ የኩላሊት እጥበት ለሚደረግላቸውና ለወላዶች አገልግሎት በመስጠት የሚታወቅ የጤና ተቋም ሲሆን፤ ሆስፒታሉ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ለሚገመቱ የከተማዋ ነዋሪዎች ዋነኛው የጤና ተቋም ነው። ከሳምንታት በፊት ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ባወጣው መግለጫ ከመድኃኒት፣ ከውሃ፣ ከኤሌክትሪክና ከሌሎች መሠረታዊ አቅርቦቶች አንጻር የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል ያለበት ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን ጠቁሞ ነበር። ሆስፒታሉ በእጁ ላይ የነበረውን አቅርቦት በመጠቀም "ለሳምንታት ያለ ተጨማሪ የመድኃኒት አቅርቦት፣ ያለ ውሃ እና መብራት በመቆየቱ ዶክተሮችና ነርሶች የትኞቹን አገልግሎቶች ትተው የትኞቹን እንደሚያስቀጥሉ ለመምረጥ በጣም ተቸግረው ነበር" ሲሉ የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የአፍሪካ አህጉር ዳይሬክተር ፓትሪክ ዩሱፍ ተናግረዋል። ከአንድ ወር በኋላ ዛሬ ቅዳሜ ለሆስፒታሉ የደረሰው አቅርቦት ሆስፒታሉ ለሚያከናውነው የነፍስ አድን ሥራ ከማገዙም በተጨማሪ የህክምና ባለሙያዎቹ የነበረባቸውን ጫና እንደሚቀንስላቸው ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። በጣም አስፈላጊ የሆኑትን መሠረታዊ አቅርቦቶች ወደ መቀሌ በመላክ ከቀይ መስቀል በተጨማሪ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የበኩሉን እንዳበረከተ የተጠቀሰ ሲሆን፤ መድኃኒቶቹና እርዳታው በመቀለ ከተማ ከሚገኘው አይደር ሆስፒታል ባሻገር በክልሉ ጤና ቢሮ እና በቀይ መስቀል መድኃኒት ቤት አማካይነት ለአገልግሎት ይቀርባል ተብሏል። ዛሬ መቀለ ከተማ በቀይ መስቀል አማካይነት ከደረሰው የመድኃኒት አቅርቦት በተጨማሪ ብርድ ልብሶች፣ የፕላስቲክ መጠለያዎች፣ የማዕድ ቤት ቁሳቁሶች፣ አልባሳት እና ሳሙናዎች እንዲሁም የውሃ እና የንጽህና አገልግሎትን ለማግኘት የሚያስችሉ ቁሳቁሶች እንደደረሱ ተገልጿል። በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊትና በህወሓት ኃይሎች መካከል የተቀሰቀሰውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ በትግራይ ክልለ ውስጥ የእንቅስቃሴና የግንኙነት መስመሮች በመቋረጣቸው ሳቢያ የህክምናና የሰብአዊ እርዳታ ተቋማት ለሳምንታት የመሠረታዊ አቅርቦቶች እጥረት አጋጥሟቸው ቆይቷል። የክልሉ ዋና ከተማ በፌደራል ሠራዊቱ ቁጥጥር ስር ከገባች በኋላ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ወደ ክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች እያቀረበ መሆኑን መግለጹ ይታወሳል።
news-49188405
https://www.bbc.com/amharic/news-49188405
የኦሳማ ቢን ላደን ልጅ ፣ ሐምዛ ቢን ላደን፣ 'በአየር ጥቃት መገደሉ' ተነገረ
የአልቃይዳ መስራች የነበረው ኦሳማ ቢን ላደን ወንድ ልጅ፣ ሐምዛ ቢን ላደን፣ በአየር ጥቃት ወቅት መገደሉን የአሜሪካ የስለላ ባለስልጣናት ጠቅሰው የአሜሪካ መገናኛ ብዙኀን ዘገቡ።
ሐምዛ መቼና የት እንደሞተ የተነገረ ምንም ነገር የለም። ፔንታጎንም በጉዳዩ ላይ አስተያየቱን አልሰጠም። የካቲት ወር ላይ የአሜሪካ መንግሥት ሐምዛ የት እንዳለ ለጠቆመ የአንድ ሚሊየን ዶላር ጉርሻ እንደሚሰጡ ተናግረው ነበር። • በቦይንግ 737 ማክስ 8 አደጋ በሰው 800 ሚሊየን ዶላር ተጠየቀ ሐምዛ ቢን ላደን ዕድሜው 30 የሚገመት ሲሆን፣ አሜሪካና ሌሎች ሀገራት ላይ ጥቃት እንዲፈፀም የሚጠይቅ የቪዲዮና የድምፅ መልዕክት አስተላልፎ ነበር። ይህ ዘገባ መጀመሪያ ላይ የወጣው በኤንቢሲ እና በኒው ዮርክ ታይምስ ላይ ነው። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕም ሆኑ የኋይት ሐውስ የሀገር ደህንነት አማካሪ ጆን ቦልቶን በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየታቸውን ከመስጠት ተቆጥበዋል። ሐምዛ ቢን ላደን አባቱን በጎርጎሳውያኑ 2011 ግንቦት ወር ላይ የገደሉት አሜሪካኖች ላይ ጂሀዲስቶች ጥቃት እንዲፈፅሙ ጥሪ አቅርቦ ነበር። አክሎም የአረብ ሰላጤ ሀገራት እንዲያምፁ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ሳውዲ ዓረቢያ መጋቢት ወር ላይ ዜግነቱን ነጥቃዋለች። • በሱዳን ተማሪዎች መገደላቸውን ተከትሎ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ተወሰነ • ብሔራዊ አገልግሎት መንፈሳዊ ህይወቱን የነጠቀው ኤርትራዊው ዲያቆን በኢራን ውስጥ በቤት ውስጥ የቁም እስር ላይ እንዳለ ይታመን የነበረ ሲሆን ሌሎች ዘገባዎች ደግሞ አፍጋኒስታን፣ ፓኪስታን እና ሶሪያ መሆኑን ይጠቅሱ ነበር። ከአሜሪካ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ቢን ላዲን በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር 2011 ፓኪስታን አቦታዳድ ውስጥ ከተገደለ በኋላ፣ ሐምዛ የአባቱን ስፍራ እንዲወስድና አልቃይዳን እንዲመራ ታጭቶ ነበር። አባቱ ከተገደለበት ቤት ውስጥ ከተሰበሰቡ መረጃዎች መካከል የሐምዛ የሠርግ ስነስርዓትን የሚያሳይ ቪዲዮ የተገኘ ሲሆን በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ ሐምዛ ከሌላ የአልቃይዳ ከፍተኛ አመራር ልጅ ጋር ጋብቻውን ሲፈፅም ይታያል። የሠርግ ስነስርዓቱ ኢራን ውስጥ እንደተካሄደ ይታመናል። የሐምዛ አማች ይሆናሉ ተብለው የሚጠረጠሩት አብዱላህ አህመድ አብዱላህ ወይንም አቡ ሙሐመድ አል ማስሪ ሲሆኑ በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር 1998 በታንዛኒያና በኬኒያ የአሜሪካ ኢምባሲዎች ላይ ከተፈፀመው ጥቃት ጋር ግንኙነት አላቸው ተብሎ ይታመናል። አልቃይዳ በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር መስከረም 11 2001 በአሜሪካ ጥቃት ያደረሰ ሲሆን ከዚያ በፊት ግን ይህ እስላማዊ ቡድን እዚህ ግባ የሚባል ትኩረት ተሰጥቶት አያውቅም ነበር።
news-52560729
https://www.bbc.com/amharic/news-52560729
በኮሮና ዘመን በኒው ዚላንድ ታሪክ የተፈፀመው ትልቁ የመኪና ዘረፋ
የሁሉም ዘራፊ 'ምኞት' ሳይሆን አይቀርም። በአንድ የመኪና አከራይ ኩባንያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ጥሩ አቋም ያላቸው በርካታ ዘመናዊ መኪኖች ተሰልፈው ቆመዋል። የመኪኖቹ ቁልፍ ደግሞ መኪኖቹ ውስጥ ተንጠልጥሏል።
ኒው ዚላንድ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብን ጥላ ብትገኝም፤ ጥቂት ዘራፊዎች ግን ወደ ሥራ ተሰማርተዋል። ዘራፊዎቹ ኒው ዚላንድ ኦክላንድ ከተማ የሚገኘውን ጁሲ የተባለ የመኪና አከራይ ድርጅት ሽቦ ቆርጠው ይዘልቃሉ። ከዛም እያንዳንዳቸው የሰረቁትን መኪና እያሽከርከሩ ይሄዱሉ። ዘራፊዎቹ ዘረፋቸውን በመጀመሪያው ዙር አልቋጩትም። ደግመው ተመለሱ፤ እያሽከረከሩ ሄዱ። እንደገና ተመልሰው ተሰልፈው ከቆሙ መኪኖች እያመረጡ መውሰዳቸውን ቀጠሉ። 97 መኪኖች ከቆሙበት ተሰረቁ። በአገሪቱ የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉን ተከትሎ፤ የኒው ዚላንድ ጎዳናዎች ጸጥ እረጭ ብለው ነበር። ፖሊስ ግን ጎዳናዎች ላይ ቅኝት ማደረጉን ቀጥሏል። በዚህ መሃል ፖሊስ በርካታ የኪራይ መኪኖች ሲሽከርከሩ ማየቱ ጥርጣሬን ፈጠረበት። ፖሊስ መኪኖቹ መሰረቃቸው በማመኑ ለኩባንያው ያሳውቃል። ብዙም ሳይቆይ በርካታ የኩባንያው መኪኖች የመሰረቃቸው ዜና የአገሪቱ መገናኛ ብዙሃን መነጋገሪያ ሆነ። ዜጎችንም መኪኖቹ እንዲገኙ ጥቆማ እንዲሰጡ ተጠየቁ። ከተሰረቁት መኪኖች መካከል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው መኪኖች በኢንተርኔት አማካኝነት ለመሸጥ ሲተዋወቁ ነበር። በሰዎች ጥቆማ እና በፖሊስ ጥረት ብዙም ሳይቆይ ከተሰረቁት 97 መኪኖች 85 ያክሉ ለአከራይ ኩባንያው ተመልሰዋል። በአገሪቱ ታሪክ ትልቁ የመኪና ስርቆት ከተባለለት ወንጀል ጋር በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ግንኙነት አላቸው የተባሉ 29 ሰዎችም በቁጥጥር ሥር ውለዋል።
news-54179475
https://www.bbc.com/amharic/news-54179475
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፡ ኢሰመኮ አሳሳቢ መረጃዎች ከክልሉ እየደረሱት መሆኑን ገለጸ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች እየታዩ ያሉ የፀጥታ መደፍረሶችን ተከትሎ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ከተፈጸሙ ጥቃቶች ጋር በተያያዘ እጅግ አሳሳቢ መረጃዎች እየደረሱት መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ ላይ አመለከተ።
ኮሚሽኑ እንዳለው እነዚህ መረጃዎች እየደረሱት ያለው በክልሉ ውስጥ ከሚገኘው መተከል ዞን፣ ከቡለን ወረዳ አጳር ቀበሌ እንዲሁም ከወንበራ ወረዳ መልካን ቀበሌ መሆኑን ገልጿል። በዚህም ሳቢያ በተጠቀሱት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባሉ አንዳንድ ቦታዎች የሚያጋጥሙ ክስተቶችና በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶች በእጅጉ እንዳሳሰበው በመግለጫው ላይ ጠቅሷል። በመግለጫው ላይ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጳጉሜ 1/2012 ዓ.ም እንዲሁም ከመስከረም 4 አስከ መስከረም 10/2013 ዓ.ም መካከል ባሉት ቀናት ውስጥ ቢያንስ ሁለት ጥቃቶች ማጋጠማቸውን ከክልሉ መንግሥት ለማረጋጥ መቻሉን አመልክቷል። ይህንንም ተከትሎ ቢያንስ በሁለት ዙር በተፈጸሙ ጥቃቶች ባልታጠቁ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ግድያዎች መፈፀማቸውን እንዲሁም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸውን በስፍራው ከሚገኝ አንድ መንግሥታዊ ምንጭ መረዳት እንደቻለ ኮሚሽኑ ገልጿል። ስለሆነም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ባልታጠቁ ሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸሙትን ጥቃቶች፣ ግድያዎችና መፈናቀሎችን ሙሉ በሙሉ እንደሚያወግዝ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በመግለጫው ላይ አመልክቷል። በክልሉ ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር በመከላከያ ሠራዊት፣ በፌዴራል ፖሊስ እና በክልል የጸጥታ ኃይሎች ሰላምን ለማስጠበቅ እየተደረገ ያለውን ጥረት እንደሚያበረታታም አስታውቋል። እንዲሁም አገሪቱ በተቀበለቻቸው ሕጎችና ሰነዶች መሰረት የሰዎች በሕይወት የመኖር መብቶች እንዲከበሩ የጠየቀ ሲሆን፣ በክልሉ ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ ጥቃቶች በተደጋጋሚ ማጋጠማቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ ገለልተኛ፣ ፈጣን ምርመራዎችን በማካሄድ ግድያው በተከሰተባቸው ሁኔታዎች ላይ የጥፋተኞችን ተጠያቂነት እንዲያረጋግጡ አሳስቧል። በተጨማሪም የክልሉ መንግሥት አካላት ተጎጂዎችና ቤተሰቦቻቸው ወደ ቀደመ ሕይወታቸው የሚመለሱበትን መንገድ እንዲያመቻቹ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቦ፤ በተለይም የዜጎች በሕይወት የመኖር መብት ለማስከበር የሚመለከታቸው የክልሉ የመንግሥት አካላት እንዲሰሩ አሳስቧል። መግለጫው አክሎ እንዳለው የክልሉ መንግሥት ከተፈናቃዮቹ መካከል 300 ያህል የሚሆኑት ወደ ቀያቸው መመለሳቸውንና የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌደራል ፖሊስ እንዲሁም የክልሉ የፀጥታ ኃይሎች በጋራ አካባቢውን ለማረጋጋት እየሰሩ መሆናቸውን መገልጹን ጠቅሷል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በተለያዩ ጊዜያት ማንነታቸው ባልታወቁ ኃይሎች በሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ ጥቃቶችና እገታዎች ሲፈጸሙ መቆየታቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ከቀናት በፊት በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች ላይ በተፈጸሙ ጥቃቶች ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች መገደላቸው በስፋት እተገለጸ ነው።
news-46313414
https://www.bbc.com/amharic/news-46313414
ወ/ሪት ብርቱካን በወዳጆቻቸው አንደበት እንዴት ይገለፃሉ?
ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በምርጫ 97 ጎልቶ የወጣው የቅንጅት ለአንድነት እና ዴሞከራሲ ፓርቲ ተቀዳሚ ፕሬዚዳንት ነበሩ።
በሃገር ክህደት ወንጀል ተከሰው ወህኒ ማቀዋል፤ መንግሥት ይቅርታ አድርጌዎለታለሁ ብሎ ከሌሎች የፖለቲካ ሰዎች ጋር እስኪፈታቸው ድረስ። በይቅርታ ከተለቀቁ በኋላም አንድነት ለፍትህና ዴሞክራሲ የሚባል ፓርቲ ያቋቋሙ ሲሆን የመጀመሪያ ሊቀመንበርም ነበሩ። ይቅርታው ፖለቲከኞቹ ከእሥር ከወጡ በኋላ በሚያከናውኑት ድርጊት ላይ የተወሰነ በመባሉ ምክንያት ይቅርታው ተሽሮ እንደገና ለእሥሩ ተዳረጉ። ከወራት በኋላ እንደገና ተፈቱ፤ ወዳጆቻቸውም እልል አሉ፤ ወ/ሪት ብርቱካን ግን እንደቀድሞው ወደፖለቲካ ማዘንበሉን ቸል በማለት ወደትምህርት ዓለም መመለስ ይሻለኛል አሉ። ከተፈቱ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ወደአሜሪካ አቀኑ፤ በአሜሪካ ቆይታቸውም በሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ ስኩል ኦፍ ኬኔዲ በታዋቂው ጥቁር ምሁር ዱ ቦይ በተሰየመው የአፍሪካና የጥቁር አሜሪካውያን ጥናት ማዕከል ውስጥ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በህዝብ አስተዳደር (ፐብሊክ አድሚኒስትሬሽን) አግኝተዋል። ለባለፉት ሰባት ዓመታትም ነዋሪነታቸውን ያደረጉት በአሜሪካ ውስጥ ነው። በስደት እስከተመለሱበት ወቅት ድረስ ናሺናል ኢንዶውመንት ፎር ዴሞክራሲ በተባለ ድርጅት ውስጥ በተመራማሪነት ይሰሩ ነበር። አንዲት ቀንደኛ የቀድሞ የፖለቲካ ፓርቲ አባል የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አባል ይሆናሉ ብሎ የጠበቀ ማንም አልነበረም፤ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀር፤ ለዕጩነት ያቀረቧቸው እሳቸው ናቸውና። ኢትዮጵያም ይሁን አሜሪካ ሳሉ በቅርብ የሚያውቋቸው ወዳጆቻቸው ወ/ሪት ብርቱካን ለተሰጣቸው ሃላፊነት ትክክለኛዋ ሴት ናቸው ይላሉ። • የቦርዱ ማሻሻያና የብርቱካን ሹመት ምንና ምን ናቸው? ለሕትመት ዓለም ከተወገደች ዓመታት የሆናት የአዲስ ነገር ጋዜጣ አዘጋጅ የነበረው ታምራት ነገራ ስለወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ከመመስከር ወደኋላ አልልም ይላል። «ሃገሪቱ የተሻለች ሃገር እንድትሆን ወደፊት የሆነ ነገር እንደምታበረክት ታውቀዋለች፤ ፖለቲካው ውስጥ ሚና እንደሚኖራት ታውቀዋለች። አሜሪካ ትልቅ የወሰነችው ውሳኔ ከየትኛውም የዳያስፖራ ኮሚኒቲ ራሷን ማግለሏ ነው። በጣም ለሷ ቀላል ነበር፤ በጣም በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ይፈልጓት ነበር። ስብሰባ እንኳን አትሄድም ነበር። ራስን ለትልቅ ነገር ማጨት የሚባል ነገር ካለ ብርቱካን ትክክለኛዋ ሴት ነች።» ታምራት ብርቱካን ለዚህ ሥልጣን ብትበዛ ነው እንጂ አታንስም ባይ ነው፤ የተሳጣትን ነገር ማሳነሴ ግን አይደለም ይላል። «ብዙ ፖለቲከኞች ፓርቲ መሥርተው ወደሥልጣን መውጣት ነው የሚያስቡት፤ ብርቱካን ግን ከሥልጣን በላይ ማሰብ ችላለች። ጠቅላይ ሚኒስትሩንም በጣም የማደንቀው 'ሪስኩን' በውሰዳቸው ነው። ውለታ ውለውልኛል፤ ምናምን የሚባል ነገር የለም፤ ካልተስማማት አልተስማማትም ነው።» ከታምራት በተጨማሪ የዞን ዘጠኝ ጦማሪ የነበረችውና በቅርቡ በስደት ከምትኖርባት አሜሪካ የተመለሰችው ሶሊያና ሽመልስም ስለ ብርቱካን የምትለው አላት። «ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምርጫው ከመንግሥት ተፅዕኖ ለማውጣት ነው ይህን የማደርገው ያሉት ምንም የሚያጠራጥር አይደለም። መንግሥት የምርጫ ቦርዱን ራሱን እንደቻለ ተቋም እንዲቋቋም ፈልጓል ማለት ነው የሚለው ድምዳሜ ላይ እንድንደርስ ያደረገን ውሳኔ ነው።» • «ሃገሬን ሳላስብ የዋልኩበት፤ ያደርኩበት ቀን የለም» ብርቱካን ሚደቅሳ ሶሊያና ከትምህርትና ልምዷ ባለፈ የወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የግል ባህሪ ለቦታው ብቁ ሆና እንድትገኝ በጣም ያግዛል ትላለች። «ፖለቲካዊ ትርጉም ባለው መልኩም ብቻ ሳይሆን በሌሎች ጉዳዮችም ላይ፤ በማንኛውም ሁኔታ በፍርድ ቤትም ይሁን ባለፈችበት ሕይወት የግል ዕሴቶቿን በማስቀደም አይ ይህ አይደረግም በማለት ትቃወማለች፤ ለእውነት ትቆማለች።» ትላለች ለበርካታ ዓመታት ከፖለቲካ ሕይወት ፀድታ መኖሯ ደግሞ የበለጠ ለቦታው ብቁ ያደርጋትል ስትል ሶሊያና ሃሳቧን ታጠናክራለች። "በስደትም ሆና አብዛኛውን ጊዜ የፖለቲካ ተሳትፎ አላደረገችም። በግልፅ ራሷን ከፖለቲካ ካገለለች ዘጠኝ ወይም አስር ዓመታት ተቆጥረዋል፤ ከዚህ በፊት የነበረው ታሪኳም የሚያሳየው ለቦታው የሚመጥን ዕሴት ያላት መሆኑን ነው። የትኛውም ቦታ ብትሆን፤ ፍርድ ቤት ሊሆን ይችላል፤ የፖለቲካ ፓርቲ፤ በስደትም ውስጥ እኒህ ባህሪዎቿ አይቀየሩም።" ታምራትም ሆነ ሶሊያን ስለብርቱካን አውርተው የሚጠግቡ አይመስሉም፤ ምንም እንኳን ፤ ሹመቱን የተቃወሙ ባይጠፉም በርካታ ኢትዮጵያውያንም በማህበራዊ ትስስር ዘዴዎች ፎቶ እና ፅሁፎችን በማስፈር ደስታቸው ገልፀዋል • «ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የተሾሙት ለህግ ባላቸው ቀናኢነት ነው»
news-55557504
https://www.bbc.com/amharic/news-55557504
የአሜሪካ ምርጫ 2020 ፡ በጆርጂያ ለሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ምርጫ ለመጀመርያ ጊዜ ጥቁር እንደራሴ 'አሸነፉ'
ዲሞክራቶችና ሪፐብሊካኖች የሞት ሽረት ትግል እያደረጉ ባሉበት ደቡባዊ የአሜሪካ ግዛት ጆርጂያ ራፋኤል ዋርኖክ ድል ቀንቷቸዋል እየተባለ ነው።
ራፋኤል ዋርኖክ ዩኤስ ቲቪ እና አሶሺየትድ ፕሬስ የዜና ወኪል ራፋኤል ማሸነፋቸውን ይፋ አድርገዋል። ቆጠራው ለጊዜው መቶ በመቶ ባይጠናቀቅም ከ98 ከመቶ በላይ ድምጽ ተቆጥሮ ነው ራፋኤል ዋርኖክ አሸንፈዋል የሚለው መረጃ እየወጣ ያለው። ይህ መረጃ ከተረጋገጠ ራፌኤል ዋርኖክ ቀድሞ ባሪያ አሳዳሪ ከነበረችው ጆርጂያ ግዛት በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ግዛቷን የሚወክል ጥቁር ሰው ሆነው የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ሸንጎን ይቀላቀላሉ። ዋርኖክ ያሸነፉት ባለጸጋዋን የቀድሞዋን የሴኔት አባል ኬሊ ሊዮፍለርን በትንሽ ልዩነት በልጠው ነው ተብሏል። ይህ በጆርጂያ ግዛት እየተደገ ያለው ምርጫ የድጋሚ ምርጫ ሲሆን የድጋሚ ምርጫ እንዲካሄድ የተወሰነው ባለፈው ኅዳር አንድም እጩ 50 ከመቶ የመራጭ ድምጽ ባለማግኘቱ ነው። በግዛቲቱ የምርጫ ሕግና ደንብ መሰረት ተወዳዳሪ እጩዎች በምርጫ ከ50 ከመቶ በላይ ካላስቆጠሩ ለ2ኛ ዙር ድምጽ እንዲሰጥ ያዛል። በአሜሪካ ታሪክ አንድ ግዛት መላውን የአሜሪካ እጣ ፈንታ ሊወስን የሚችልበት አጋጣሚ ሲፈጠር ጆርጂያ ግዛት ምናልባትም የመጀመርያዋ ሳትሆን አትቀርም ይላሉ ተንታኞች። ምክንያቱም በአሜሪካ የመንግሥት አስተዳደር የሕግ መወሰኛ ምክር ቤትን የበላይነት መያዝ እጅግ ቁልፍ ጉዳይ በመሆኑ ነው። አሁን የበላይነቱን ዲሞክራቶች ለመያዝ የሚችሉት በጆርጂያ ራፋኤል ዋርኖክን ጨምሮ ሌላኛው የዲሞክራቲክ ዕጩም ካሸነፉ ብቻ ነው። ዋርኖክና ኬሊ ሎፍለር እጅግ ፈታኝ ውድድር ያደረጉ ሲሆን ዋርኖክ 50.5 በመቶ በማግኘት ኬሊን አሸንፈዋታል ነው የሚሉት፣ አሁን እየወጡ ያሉ መረጃዎች። ይህ ጊዜያዊ ውጤት ይፋ የሆነው እስከ አሁን 98 ከመቶ የሚሆነው የመራጮች ድምጽ ከተቆጠረ በኋላ ነው። አሁን በጉጉት እየተጠበቀ ያለው የዲሞክራቱ ጆን ኦሶፍ እና የሪፐብሊካኑ ዴቪድ ፐርዲዮ የፖለቲካ ፍልሚያ ውጤት ነው። ከሁለቱ ዕጩዎች ማን አሸናፊ ነው የሚለውን ለመለየት ቆጠራው ቀጥሏል። በጣም የተቀራረበ ድምጽ እያገኙ ስለሆነ ግን ይህ ዘገባ እስከሚጠናቀርበት ሰዓት ድረስ አሸናፊውን መለየት አልተቻለም። የ51 ዓመቱ ራፋኤል ዋርኖክ ጆርጂያ አትላንታ ውስጥ ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር ድሮ በሰባኪነት የሰራበት የኤቤኔዘር ቤተክርስቲያን ሰባኪ ሲሆን እንደ ማርቲን ሉተር ኪንግ ሁሉ ለጥቁሮች መብት ድምጹ በማሰማት ይታወቃሉ። ዛሬ ጆርጂያን አንድ ጥቁር በሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ሊወክላት መቻሉ ትልቅ ፈንጠዚያን በዲሞክራቶች ዘንድ ፈጥሯል። ራፋኤል ዋርኖክ የድሉን መታሰቢያ ለእናቱ ቬርሌኒ አድርጎታል። እናቱ ቬርለኒ በጆርጂያ ግዛት ገና በአፍላነታቸው በእርሻ ውስጥ የጉልበት ሠራተኛ ሆነው አስቸጋሪ ልጅነትን ያሳለፉ ናቸው። "ይህ አሜሪካ ስለሆነ በአንድ ወቅት ጥጥ ለቃሚ የነበሩ የእናቴ እጆች ለትንሹ ልጃቸው ድምጽ ሊሰጡ ምርጫ ጣቢያ ተገኙ" ሲል የ82 ዓመት እናቱን አሞካሽቷል። "ወደ ምክር ቤቱ የምገባው ለሁሉም የጆርጂያ ነዋሪ ለመሟገት ነው ብሏል ዋርኖክ ውጤቱን ተከትሎ። "ለእኔ ድምጽ የሰጣችሁኝም፣ ያልሰጣችሁኝም በእኔ ዘንድ እኩል ናቸው። ለናንተ ነው የምታገለው" ብሏል ራፋኤል ዋርኖክ። ዶናልድ ትራምፕ በዚህ ግዛት ተገኝተው የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ለጆርጂያዊያን ይህ ምርጫ የሪፐብሊካን የመጨረሻው የጦር ግንባር ነው ሲሉ ነበር የተናገሩት። ይህን ያሉበት ምክንያት እንደተፈራው ዲሞክራቶች በጆርጂያ 2 ዕጩዎቻቸው ከተመረጡ በሕግ መወሰኛው ምክር ቤት የሚኖራቸው የወኪል ብዛት 50 ይሆናል። ይህም ከሪፐብሊካን እንደራሴዎች ጋር እኩል ያደርጋቸዋል። ክርክር በሚደረግ ጊዜ ሴኔቱን በሊቀመንበርነት የሚመሩት ካምላ ሐሪስ ስለሚሆኑ ሁልጊዜም ዲሞክራቶች ያሉት ነገር እንዲሆን ሰፊ እድል ይሰጣቸዋል። በአሁኑ ጊዜ የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት በሪፐብሊካን እንደራሴዎች የበላይነት የተያዘ ነው። የታችኛው ምክር ቤት ደግሞ በዲሞክራቶች የበላይነት ይዘወራል። የራፋኤል ዋርኖክ ማሸነፍ ብቻውን ግን የዲሞክራቶችን በሴኔት የበላይነት አያስገኝም። ጆን ኦሶፍ ሪፐብሊካኑን ዕጩ ዴቪድ ፐርዲዮን ማሸነፍ ይኖርባቸዋል። ውጤቱ በጥቂት ሰዓታት ሊታወቅ ይችላል እየተባለ ነው።
news-57077652
https://www.bbc.com/amharic/news-57077652
የኢትዮጵያ ምርጫ፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓ ሕብረት ምርጫው ታዛቢ ይልካል አለ
የአውሮፓ ሕብረት ቀጣዩን 6ኛ አገራዊ ምርጫ እንዲታዘቡ ባለሙያዎቹን ይልካል ሲሉ የውጪ ጉዳይ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ።
ከአውሮፓ ሕብረት በተጨማሪ ከአሜሪካ እና ሩሲያ የተውጣጡ የባለሙያዎች ምርጫውን ለመታዘብ እንደሚመጡ የውጪ ጉዳይ ቃል አቀባዩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። የአውሮፓ ሕብረት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ከስምምነት መድረስ ባለመቻሉ ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ አስቦ የነበረውን የምርጫ ታዛቢ እንዲቀር መወሰኑን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። የአውሮፓ ሕብረት የቀደመ ውሳኔውን ሰርዞ ምርጫውን ለመታዘብ ስለመወሰኑ እስካሁን ያለው ነገር የለም። ሕብረቱ የሚልካቸው የምርጫ ታዛቢ ቡድን የሚሰማራበት ቁልፍ መለኪያዎች /ፓራሜትርስ/ ላይ ከመንግሥት ጋር ከስምምነት መድረስ አልተቻለም ብሎ ነበር። የአውሮፓ ሕብረት ይህን ካለ በኋላ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ከአንድ ሳምንት በፊት በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ ምርጫ ለመታዘብ ካቀደው የአውሮፓ ሕብረት ጋር ያልተስማማቸው ሕብረቱ ሉዓላዊነትን የሚጻረር ጥያቄን በማቅረቡ ነው ብለው ተናግረው ነበር። ቃል አቀባዩ በወቅቱ የአውሮፓ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑኩን ላለመላክ የወሰነው በሁለት ምክንያት ነው ብለዋል። ይህም ሕብረቱ አገሪቱ የሌላትን የኮሚኒኬሽን ስርዓት ማስገባትን አስገዳጅ ማድረጉ እንዲሁም የምርጫውን ውጤት ይፋ የማደርገው እኔ ነኝ ማለቱን ተናግረው ነበር። ይህም የአገሪቱን ሉዓላዊነት እና ደህንነት የሚጻረር ስለሆነ ከስምምነት ሳይደረስ ቀርቷል ሲሉ አስረድተው ነበር። ቃል አቀባዩ አምባሳደር ዲና ዛሬ በሰጡት መግለጫ የአውሮፓ ሕብረት ምርጫ ታዛቢ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ መንግሥት የያዘው አቋም እንዳልተቀየረ ተናግረው፤ ከአውሮፓ ህብረት ስድስት አባላትን የያዘ ቡድን፣ ከአሜሪካ ሁለት ተቋማት የተውጣጣ እንዲሁም ከሩሲያና የአፍሪካ ህብረት ምርጫውን የሚታዘቡ ባለሙያዎች ይመጣሉ ብለዋል።
news-50025474
https://www.bbc.com/amharic/news-50025474
"በርካታ አባላቶቻችን ስለታሰሩብን እነሱን ለማስፈታት እየተንቀሳቀስን ነው" እስክንድር ነጋ
የአዲስ አበባ ፖሊስ በነገው ዕለት በከተማዋ የሚደረግ ሠልፍም ሆነ ስብሰባ የለም ሲል አስታወቀ።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካው ፋንታ ለቢቢሲ እንደገለፁት፤ በማህበራዊ ሚዲያዎች እሁድ ጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ሰልፍ እንደሚደረግ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በሰልፉ ምክንያት የሚዘጉ መንገዶች መኖራቸውን ገለፀ በሚል የኮሚሽኑን አርማና የኃላፊዎችን ስም በመጠቀም የተላለፈው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን ገልፀዋል። • የአዲስ አበባ መስተዳደርና የባላደራው ምክር ቤት • በዛምቢያ ከካናቢስ እፅ ኬክ የጋገረው ተማሪ 50 ገጽ ሃተታ በመፃፍ ተቀጣ • 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና፡ የእኛ ሠው በዶሃ አክለውም በነገው ዕለት ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ ስብሰባ በመስቀል አደባባይ የሌለና ምንም የሚዘጋ መንገድ አለመኖሩን ተናግረዋል። 'የባላደራው ምክር ቤት' ትናንት በሰጡት መግለጫ ላይ ሕጋዊ መስፈርቶችን አሟልተው ለአዲስ አበባ መስተዳደር ጥያቄ ማቅረቡን ገልፀው ነበር። በዚሁ መግለጫ ሠላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ጥያቄ ቢያቀርቡም መከልከሉም መፈቀዱም እንዳልተገለፀላቸው ተናግረው የነበሩት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፤ ነገር ግን ሕጉ እንደተፈቀደ ለማሳወቅ አያስገድድም በማለት 'ዝም በማለታቸው እንደተፈቀደልን ይቆጠራል' ብለው ነበር። የአዲስ አበባ ባለ አደራ ምክር ቤት ጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ የጠራው "ተስፋ የተጣለበት የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ጅምር በመቀልበሱ ነው" ሲል አስታውቆ ነበር። ከዚህ በፊት በተለያየ መንገድ ነገሮች እንዲስተካከሉ ድምፃቸውን ማሰማታቸውን፤ ነገር ግን ሰሚ በማጣታቸው ሁለተኛውን የሰላማዊ ትግል ስልት ለመጠቀም መገደዳቸውን ገልፀው ነበር። በዚህም መፍትሄ ካላገኘን በቀጣይ መንግሥትን ወደሚያስገድዱ የሥራ ማቆም እና ሌሎች የትግል ስልቶች ለመግባት እንደሚገደዱም በመግለጫቸው ላይ ተናግረዋል። በጉዳዩ ላይ አስተያየቱን እንዲሰጠን የደወልንለት 'የባለ አደራው ምክርቤት' ሊቀመንበር እስክንድር ነጋ "በአሁኑ ሰዓት በየቦታው በርካታ አባላቶቻችን ስለታሰሩብን እነርሱን ለማስፈታት እየተንቀሳቀስኩ ነው በዚህ ጉዳይ ምላሽ ለመስጠት አልችልም" ሲል ተናግሯል። በሌላ በኩል የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድን የሰላም የኖቤል ሽልማትን በማስመልከት በነገው ዕለት በኦሮሚያ ክልል የደስታ መግለጫ ሰልፎች እንደሚካሄዱ የክልሉ መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ማስታወቁን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። በመሆኑም ነገ እሁድ ጥቅምት 2፣ 2012 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ዞኖች፣ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳዳሮች የደስታ መግለጫ ሰልፎች ይደረጋሉ ተብሏል። በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ለሚካሄደው ሰልፍም አስፈላጊው የፀጥታ ጥበቃ እንደሚደረግለት ተገልጿል።
news-56569253
https://www.bbc.com/amharic/news-56569253
ለቀናት ባሕር ላይ ቆመው የነበሩ መርከቦች በሱዊዝ ቦይ ማቋረጥ ጀመሩ
የዓለማችን ዋነኛው የንግድ መርከቦች መተላለፊያ የሆነው የሱዊዝ ቦይን ዘግታው የነበረችው ግዙፍ መርከብ እንድትነሳ ከተደረገ ከአንድ ቀን በኋላ ለቀናት ቆመው የነበሩ መርከቦች ጉዟቸውን ጀመሩ።
መተላለፊያውን ዘግታ የነበረችው መርከብ መንገድ ስትለቅ በአሁኑ መተላለፊያው በተዘጋበት ጊዜ ወደ ማቋረጫው ገብተው ባሉበት ቆመው የነበሩ 37 የጭነት መርከቦች ቅድሚያውን አግኝተው እንዲያልፉ የተደረገ ሲሆን፤ ሌሎች 70 መርከቦች ደግሞ ዛሬ ማክሰኞ በሱዊዝ ቦይ በኩል ያልፋሉ ተብሏል። የመተላለፊያው ባለስልጣናት የባሕር መስመሩ በተዘጋባቸው ባለፉት ቀናት ውስጥ ባሉበት ቆመው ለመጠበቅ ተገድደው የነበሩትን ከ300 በላይ መርከቦች አስተላልፎ ለመጨረስ ሦስት ቀን ተኩል ይፈልጋል ብለዋል። ከእነዚህ መርከቦች መካከል ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ከሞሮኮ ማዳበሪያና ከቱርክ ደግሞ የተለያዩ ሸቀጦችን የጫኑ ሁለት መርከቦች በሜዲትራኒያን ላይ ቆመው እንደቆዩ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ለቢቢሲ መግለጹ ይታወሳል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በመተላላፊያው የሚያቋርጡ መርከቦች ለባሕር ጉዞ ብቁ መሆናቸው በባለሙያዎች ይመረመራሉ ተብሏል። 400 ሜትር ርዝመትና 200 ሺህ ቶን የምትመዝነው ኤቨር ጊቭን የተባለችው መርከብ ባለፈው ማክሰኞ ጠዋት በመተላለፊያው በኩል እያቋረጠች ሳለ አሸዋ በቀላቀለ ከባድ ንፋስ ሳቢያ መስመሯን ስታ ነበር አግድም የባሕር ማቋረጫውን የዘጋችው። መስመሩ ከተዘጋ ከሰባት ቀናት በኋላ በአሸዋ መቆፈሪያ ከባድ መሳሪያዎችና በጎታች ጀልባዎች እየተረዳች ግዙፏ መርከብ ተቀርቅራበት ከነበረው የባሕሩ ዳርቻ አሸዋ ውስጥ ሰኞ ዕለት ለማውጣት ተችሏል። የሱዊዝ መተላለፊያ ቦይ በግብጽ ግዛት ውስጥ 193 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን፤ የዓለማችን 12 በመቶ የንግድ ጭነት የሚያልፍበት መስመር ነው። የባሕር ላይ መስመሩ የሜዲትራንያንና የቀይ ባሕርን በማገናኘት ከእስያ ወደ አውሮፓ የሚደረግን ጉዞ አጭር አድርጎታል። በመተላለፊያው ላይ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች እንዳሉት እስከ ማክሰኞ ጠዋት ድረስ 306 መርከቦች ለማለፍ እየተጠባበቁ ናቸው። ከእነዚህም ውስጥ 163 በቦዩ ደቡባዊ የቀይ ባሕር ክፍል ላይ ሲገኙ ቀሪዎቹ 137ቱ ደግሞ በሰሜን በኩል ሜዲትራኒያን ባሕር ላይ ይገኛሉ ተብሏል። በሱዊዝ መተላለፊያ ቦይ በኩል ለማለፍ ተሰልፈው እየተጠባበቁ ያሉትን መርከቦች በማስተናገድ እንዲያልፉ ለማድረግ ረጅም ሠዓት የሚጠይቅ ሲሆን ሁሉም አልፈው እስኪያበቁ ድረስ ከሦስት ቀን በላይ እንደሚፈጅ ይጠበቃል።
news-54388116
https://www.bbc.com/amharic/news-54388116
ትራምፕ በጠና ታመው አገር መምራት ቢሳናቸው ምን ይፈጠራል?
የአሜሪካ አጠቃላይ ምርጫ ሊከናወን ሳምንታት ሲቀሩት ትራምፕ በኮሮናቫይረስ ተይዘዋል።
ወደ ሆስፒታልም ተወስደዋል። ፕሬዝዳንቱ የበሽታውን ምልክትም ማሳየት ጀምረዋል፣ ትኩሳት አላቸው። ድካም እየተመሳቸውም ነው። በቅድሚያ ትራምፕ እራሳቸውን ለይተው በሚያቆዩበት ወቅት ምን ሊያመልጣቸው ይችላል የሚለውን እንይ። የአሜሪካ የመድኃኒትና ተዛማች በሽታዎች ቁጥጥር ባለሥልጣን በኮሮናቫይረስ መያዙ የተረጋገጠ ሰው እራሱን ለ10 ቀናት ለይቶ ማቆየት ይኖርበታል የሚል ምክር ሃሳብ አለው። የትራምፕ ውጤት የተሰማው መስከረም 21 ነው። በዚህ የሲዲሲ መመርያ መሠረት ቢያንስ እስከ ጥቅምት 1 ድረስ እራሳቸውን ለይተው ያቆያሉ። ይህ ማለት ትራምፕ ጥቅምት 5 ላይ ለማካሄድ ቀጠሮ በተያዘለት ሁለተኛው ፕሬዝደንታዊ የመድረክ ክርክር ላይ ሊገኙ ይችላሉ። የፊታችን አርብ በፍሎሪዳ ሊያደርጉ ያሰቡት የምርጫ ቅስቀሳ ላይ ግን መገኘት አይችሉም። በዚህም ምክንያት በአካል ይደረግ የነበረው የምርጫ ቅስቀሰው እንዲሰረዝ ተደርጓል። ትራምፕ እስከ ጥቅምት 1 ድረስ ለማካሄድ ያቀዷቸውን የምርጫ ቅስቀሳዎች ወይ ሰርዘዋል አልያም ወደ ሌላ ጊዜ አዘዋውረዋል። ምርጫው ሊራዘም የሚችልበት ሁኔታ አለ? ትራምፕ እራሳቸውን ለይተው ማቆየታቸው የምርጫ ቅስቀሳ ስራቸውን ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚያሳድር ጥርጥር የለውም። ይህ ግን የአሜሪካንን ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ለማራዘም በቂ ምክንያት ሊሆን አይችልም። የአሜሪካ ምርጫ የሚካሄድበትን ቀን የመቀየር መብት ያለው ሕግ አውጪው አካል እንጂ ፕሬዝደንቱ አይደሉም። የታችኛውና የላይኛው ምክር ቤት በአብላጫ ድምጽ ሊወስኑ ይገባል፡፡ ምርጫውን የማራዘሙ ነገር በተለይ በዲሞክራቶች በተሞላው የታችኛው ምክር ቤት ያልፋል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ ሆኖም በሁለቱም ምክር ቤቶች አብላጫ ቢጸድቅ ምርጫው ወደ ሌላ ቀን ሊሸጋገር ይችላል፡፡ የምርጫ ቀኑ እንኳ ቢቀየር የአሜሪካ ሕገ-መንግሥት አንድ ፕሬዝደንት ዳግም በምርጫ እስካላሸነፈ ድረስ የሥራ ዘመኑ ከአራት ዓመት በላይ ሊሆን አይችልም ስለሚል የትራምፕ የሥራ ዘመን እአአ ጄነዋሪ 20፣ 2021 ላይ ያበቃል። ስለዚህ የምርጫ ቀኑን የመቀየር ሃሳብ ካለ ቅድሚያ ሕገ-መንግሥታዊ ማሻሻያ ማድረግ ያስፈልጋል። ዶናልድ ትራምፕ ከምክትላቸው ማይክ ፔንስ ትራምፕ በጠና ታመው አገር መምራት ቢሳናቸው ምን ይፈጠራል? ለጊዜው ትራምፕ ቀላል ሊባል የሚችል የበሽታው ምልክት አሳይተዋል። ይሁን እንጂ እድሜያቸውን እና የሰውነት ክብደታቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ከዚህ ቀደም በእርሳቸው የእድሜ ክልል እና ክብደት ውስጥ የሚገኝ ሰው በኮሮናቫይረስ በጠና የመታመም እድሉ ከወጣቶች አንጻር ሲነጻጸር በብዙ እጥፍ ከፍ ይላል። ትራምፕ በጠና ታመው ኃላፊነታቸው መወጣት የማይችሉ ከሆነ ሥልጣናቸውን ለምክትል ፕሬዝደንቱ አሳልፈው ይሰጣሉ። ትራምፕ ወደ ቀደም አቋማቸው እስኪመለሱ ድረስ ማይክ ፔንስ ተጠባባቂ ፕሬዝደንት ሆነው ይቆያሉ ማለት ነው። ማይክ ፔንስም ኃላፊነታቸውን መወጣት የማይችሉበት ምክንያት ቢፈጠር ስልጣኑ ወደ ዲሞክራቷ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤዋ ናንሲ ፔሎሲ ይሸጋገራል ማለት ነው። ናንሲ ፔሎሲ ኃላፊነቱን ለመቀበል ካልቻሉ በአራተኛ ደረጃ ላይ ሆነው ሥልጣን ሊረከቡ የሚችሉት የሪፐብሊካን ሴናተሩ እና 87 ዓመት አዛውንቱ ቻርልስ ኢ ግራሰሌይ ናቸው።
news-46791204
https://www.bbc.com/amharic/news-46791204
በነፍስ ማጥፋት እድሜ ልክ የተፈረደባት አሜሪካዊት በነጻ ተሰናበተች
በአሜሪካዋ ቴነሲ ግዛት የምትገኝ አንዲት ሴት ጥቃት ሊያደርስባት የነበረን ግለሰብ በመግደሏ ከ15 ዓመታት የማረሚያ ቤት ቆይታ በኋላ በግዛቲቱ አስተዳዳሪ ትእዛዝ በነጻ እንድትሰናበት ተወሰነላት።
ሲንቶያ ብራውን በአውሮፓውያኑ 2004 ዓ.ም. በ16 ዓመቷ በቀረበባት ክስ ጥፋተኛ ተብላ የነበረ ሲሆን በሰላሳ አመቷ ደግሞ ጥፋተኛ አይደለችም ተብላለች። በወቅቱ የ16 ዓመት ታዳጊ የነበረችው ብራውን በህገወጥ የሴቶች ዝውውር ተጠቂ የነበረችና እራሷን ለመከላከል ስትል ግለሰቡን ተኩሳ እንደገደለችው ጠበቆቿ ቢገልጹም፤ ፍርድ ቤቱ ግን ጥፋተኛ ናት በማለት የእድሜ ልክ እስራት በይኖባት ነበር። • ወሲባዊ ትንኮሳን የሚከላከል ካፖርት ተፈለሰፈ • ሴቶች በሰሜን ኮሪያ ሠራዊት ውስጥ ''ወደቤቱ ከወሰደኝ በኋላ በሃይል ጥቃት ይሰነዝርብኝ ነበር፤ በመጨረሻም ከአልጋው ስር የሆነ ነገር ሊያወጣ ሲሞክር ሽጉጥ ሊሆን ይችላል ብዬ ስለፈራሁ እራሴን ለመከላከል ተኩሼ ገደልኩት'' ብላለች ብራውን ሁኔታውን ስታብራራ። የቴነሲ ግዛት ዋና አስተዳዳሪ ሰኞ እለት እንዳስታወቁት ብራውን ከመጪው ሃምሌ ወር ጀምሮ በነጻ እንድትሰናበት ማዘዛቸውን ገልጸዋል። • "ሌሎች ሴቶች ላይ የአሲድ ጥቃት ሳይ ይረብሸኛል፤ ህመሜን ያስታውሰኛል" ካሚላት መህዲ በማረሚያ ቤት ቆይታዋ ትምህርት በመከታተል የመጀመሪያ ዲግሪዋን ማግኘት የቻለችው ብራውን፤ ጥሩ ዜጋ በመሆን አስተዳዳሪውን ለማኩራት እንዳሰበችና ለእሷ መብት ሲታገሉ ለነበሩ በሙሉ ምስጋና ማቅረብ እንደምትፈልግ ገልጻለች።
news-44934227
https://www.bbc.com/amharic/news-44934227
በደብረ ማርቆስ ማረሚያ ቤት እሳት ተነሳ
ታራሚዎች ያስነሱትን አመፅ ተከትሎ የደብረ ማርቆስ ማረሚያ ቤት ለእሳት አደጋ መዳረጉን የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር አስታወቀ።
የደብረ ማርቆስ ማረሚያ ቤት እሳት አደጋ የማረሚያ ቤቱ ምክትል መምሪያ ሃላፊ እና የታራሚዎች አያያዝና አስተዳደር ቡድን መሪ የሆኑት ምክትል ኮማንደር ባንቴ ጥበቡ ስለሁኔታው ለቢቢሲ ሲያብራሩ፤ አመፁ የተጀመረው ትናንት ምሽት የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቢ ህጉ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ የምህረት አዋጅን በተመለከተ በቴሌቭዥን የሰጡትን ዝርዝር ተከትሎ እንደሆነ ተናግረዋል። ከምክትል ኮማንደር ባንቴ መረዳት እንደቻልነው ታራሚዎቹ በምህረት አዋጁ ተጠቃሚ አንሆንም የሚል ዕምነት አድሮባቸዋል። • በደሴ ከተማ የሸዋበር መስጂድ ላይ በደረሰ ጥቃት ሰዎች ተጎዱ • የቤተ ክርስትያኗ የክፍፍል እና የውህደት ጉዞ ትናንት ምሽት ቁጣቸውን ሲያሰሙ የነበሩ ታራሚዎችን ማረጋጋት ተችሎ እንደነበር የተናገሩት ም/ ኮማንደሩ ''ዛሬ ጠዋት ግን የታራሚዎች ማደሪያ በር ከተከፈተ በኋላ ታራሚዎች በሮችን ገነጣጠሉ ከዚያም የመሳሪያ መጋዘን ቤቶችን ለመስበር ጥረት አድርገዋል'' ሲሉ ስለተፈጠረው ሁኔታ አብራርተዋል። ቆየት ብሎም በተቀሰቀሰ እሳት የማረሚያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እና የማደሪያ ቤቶች በእሳት መያያዛቸውን ም/ኮማንደር ባንቴ ጥበቡ አክለው ነግረውናል። ቃጠሎው ከተፈጠረ በኋላ በስፍራ ከደረሱ የከተማው ነዎሪዎች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ማረው አበበ በበኩላቸው በቃጠሎው ወቅት የታራሚዎች ጩኸት እና የተኩስ ድምፅ ይሰማ እንደነበር ተናግረዋል። • በደብረማርቆስ 'ባለስልጣኑ አርፈውበታል' የተባለው ሆቴል ጥቃት ደረሰበት • ቀኝ እጇን ለገበሬዎች የሰጠችው ኢትዮጵያዊቷ ሳይንቲስት የማረሚያ ቤቱን ሁኔታ ለመከታተል የተሰበሰበው የከተማዋ ነዋሪ ቁጥር እየጨመረ በመጣ ወቅት ጠባቂዎች አስለቃሽ ጭስ በመተኮስ ህዝቡን ለመበተን ጥረት ማድረጋቸውን የዓይን ምስክሩ ያክላሉ። ከሰዓት በኋላ እሳቱ እንደቆመ በምትኩ ጭስ ብቻ ይታይ እንደነበር ያጋሩን አቶ ማረው፤ በህይወት ላይ ስለደረሰው ጉዳት እንደማያውቁ ሆኖም በማረሚያ ቤቱ ውስጥ ያለው የዕደ-ጥበብ ማስተማሪያ ክፍል በእሳት እንደተቃጠለ ሲነገር መስማታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። በሰው ህይወት ላይ ስለደረሰ ጉዳት ያገኘነው መረጃ የለም። የደብረ ማርቆስ ማረሚያ ቤት በተለያዩ ወንጀሎች ጥፋተኛ ናቸው የተባሉ እና ፍርዳቸውን የሚጠብቁ ከአንድ ሺ በላይ ታራሚዎችን እና ተጠርጣሪዎችን በውስጡ የያዘ ነው።
49603898
https://www.bbc.com/amharic/49603898
አሜሪካ፡ የስድስት ቀን ጨቅላ በቦርሳዋ ይዛ የተገኘችው ሴት ተከሰሰች
የስድስት ቀን ጨቅላን በቦርሳዋ ደብቃ ከፊሊፒንስ ልትወጣ ስትል በፖሊስ የተያዘችው አሜሪዊት በሕገ ወጥ የሰው ዝውውር ክስ ተመሰረተባት።
ጄኔፈር ታልቦት ጄኔፈር ታልቦት የተባለችው የ43 ዓመት ሴት በቁጥጥር ሥር የዋለችው ባለፈው ረቡዕ ፊሊፒንስ በሚገኝ የአውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ነበር። ወደ አሜሪካ የሚበር አውሮፕላን እየጠበቀች የነበረችው ጄኔፈር፤ ቦርሳዋ ውስጥ ከተወለደ ስድስት ቀን የሆነው ጨቅላ ቦርሳዋ ውስጥ መገኘቱን ፖሊስ አስታውቋል። • በስዊድን ያሉ የስደተኛ ልጆች ሚስጥራዊ ህመም • ኮሎኔል መንግሥቱ ለህፃናት አምባ ልጆች ደብዳቤ ላኩ • ፀረ-መውለድ ፍልስፍናን ያውቁታል? የኢሚግሬሽን ኃላፊዎች እንደተናገሩት ጄኔፈር ልጅ እንደያዘች አልነገረቻቸውም ነበር። የፊሊፒንስ የወንጀል ምርመራ ቡድን፤ ግለሰቧ ጨቅላውን ደብቃ ከአገር ለማስወጣት ሞክራለች ብሏል። የጨቅላው እናትና አባት፤ የልጆችን መብት በመጋፋት ክስ ተመስርቶባቸዋል። የስድሰት ቀን ልጃቸውን ማኅበራዊ ሠራተኞች ተረክበዋል። ጄኔፈር ታልቦት ጄኔፈር ታልቦት ክሱ ከቀረበባት በኋላ፤ ልጁን ወደ አሜሪካ ለመውሰድ ፍቃድ አግኝቼበታለሁ ያለችውን ሰነድ ብታቀርብም፤ ሰነዱ ላይ የልጁ እናት ፊርማ አልሰፈረም ተብሏል። ጥፋተኛ ሆና ከተገኘች የእድሜ ልክ እሥራት ይጠብቃታል።
news-55681378
https://www.bbc.com/amharic/news-55681378
ትግራይ፡ ከፍተኛ የህወሓት አመራሮች አዲስ አበባ ውስጥ ፍርድ ቤት ቀረቡ
ባለፈው ሳምንት ትግራይ ውስጥ ተይዘው ወደ አዲስ አበባ ከተወሰዱት ከፍተኛ የህወሓት አመራሮች መካከል አቶ ስብሐት ነጋንና ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂምን ጨምሮ በርካታ ግለሰቦች አርብ ዕለት ፍርድ ቤት ቀረቡ።
አቶ ስብሐት ነጋ፣ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ አቶ አባይ ወልዱ እና ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው ፍርድ ቤት የቀረቡት ሰዎች ሁለቱን ግለሰቦች ጨምሮ በትግራይ ውስጥ ከተከሰተው ቀውስ ጋር በተያያዘ ወንጀል የተጠረጠሩ 20 የህወሓት አመራሮች ናቸው። ግለሰቦቹ አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የቀረቡ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል የህወሓት ቀደምትና ከፍተኛ አመራሮች የነበሩት አቶ ስብሃት ነጋ፣ አቶ አባይ ወልዱ፣ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር)፣ ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ፣ ወ/ሮ ሙሉ ሙሉ ገብረእግዚአብሔር እና አቶ አባዲ ዘሞ እንደሚገኙበት ተገልጿል። ተጠርጣሪዎቹ በዋናነት ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ ሕገ ወጥ ቡድን አደራጅተው በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት እንዲፈጸም በማድረግ፣ ወጣቶች ለጦርነት እንዲዘምቱ በመቀስቀስ፣ የነዳጅ ማከማቻዎች እንዲዘረፉ በማድረግ፣ የበርካታ የመከላከያ ሠራዊቱ አባላት ህይወት እንዲጠፋ አድርገዋል በሚል መከሰሳቸውን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል። በተጨማሪም በሕግ ባልተሰጣቸው ስልጣን ከተለያዩ አገራት ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ ለጦርነት ገንዘብ መሰብሰብ፣ በጎንደርና በባሕር ዳር ከተሞች ውስጥ በሚገኙ አውሮፕላን ማረፊያዎች ላይ ሮኬት እንዲተኮስና የንጹሃን ህይወት እንዲጠፋ በማስደረግ እና በሌሎች ወንጀሎች መሳተፋቸውን የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቡድን ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል። እነዚህ ከፍተኛ የህወሓት አመራሮች በፖሊስ የቀረቡባቸውን የወንጀል ክሶች በሙሉ አልፈጸምንም ብለው ጉዳያቸውን ላደመጠው የፌደራል ፍርድ ቤት መግለጻቸው ተነግሯል። ፍርድ ቤት ጉዳያቸውን ከሰማው 20 ሰዎች መካከል የቀድሞው የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አባይ ወልዱና የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባና የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ሰለሞን ኪዳኔ (ዶ/ር) ህክምና ላይ በመሆናቸው በችሎቱ አለመገኘታቸው ተነግሯል። ጉዳዩን እየመረመረ ያለው መርማሪ ፖሊስ ፍርድ ቤት በቀረቡት 20 ተጠርጣሪዎች ላይ የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ጠይቆ ተፈቅዶለታል። በዕለቱ የፍርድ ቤት ውሎ መቅረባቸው በስም ከተጠቀሰው ቁልፍ የህወሓት አመራሮች በተጨማሪ የሌሎቹ ተጠርጣሪዎች እነማን እንደሆኑ በኢዜአ ዘገባ ላይ አልገለጸም። ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የህወሓት ኃይሎች በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ፈፅመዋል መባሉን ተከትሎ በትግራይ ክልል ወታደራዊ ግጭት ተቀስቅሶ ክልሉን ይመራ የነበረው ሕወሓት ከሥልጣን ከተወገደ በኋላ የተለያዩ የቡድኑ አመራሮች እየተፈለጉ ይገኛሉ። በትግራይ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር በተያያዘ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና የፌደራል ፖሊስ በበርካታ የህወሓት ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራሮች ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣታቸው ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል። ለእስር ማዘዣውም ዋነኛ ምክንያቶቹ ህወሓትን በበላይነት በመምራት፣ በትግራይ ክልል በሚገኘው በአገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈፀም፣ የአገር ክህደት ወንጀል ፈጽመዋል፣ የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አባላት እንዲታገቱ አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው መሆኑንም መንግሥት ገልጿል። በተጨማሪም የቀድሞው የአገሪቱ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም የነበሩት ሜጀር ጄኔራል ጻድቃን ገብረተንሳይን ጨምሮ፣ ከፍተኛ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ኃይል፣ የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አመራሮችም በአገር ክህደትና በሠራዊት አባላት ላይ ወንጀል ፈፅመዋል በሚል ተጠርጥረው የመያዣ ትዕዛዝ ወጥቶባቸዋል። ፍርድ ቤት የቀረቡት የሕወሓት አመራሮች የነበራቸው ኃላፊነት ምን ነበር? ፍርድ ቤት ከቀረቡት የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል የ86 ዓመቱ አዛውንት አቶ ስብሐት ነጋ፣ ቀደምት የሕወሓት መሪና በሕወሓት/ኢህአዴግ ውስጥ ከፍተኛ ተሰሚነት የነበራቸው እንዲሁም ኤፈርት የተባለውን የድርጅቱን ግዙፍ የምርትና የአገልግሎት ተቋም በበላይነት ሲመሩ የቆዩና በመጨረሻም የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ስትራተጂያዊ ጥናት ተቋምን ዋና ዳይሬክተር የነበሩ ናቸው። ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ የነበሩ ሲሆን በፌደራል መንግሥቱና በህወሓት መካከል የነበረው ውዝግብ ተካሮ ወደ ወታደራዊ ግጭት ከመግባታቸው ከጥቂት ወራት በፊት ስልጣናቸውን ለቀው ወደ ትግራይ ያቀኑ ሲሆን፤ በቀዳሚነት እጃቸውን መስጠታቸው ይታወሳል። ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር ደግሞ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ሆነው ሰርተዋል። አባይ ወልዱ ደግሞ የሕወሓት ቀደምት ታጋይ የነበሩና በህወሓት ውስጥ በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች ቆይተው የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሆነው ሰርተዋል። አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር) ደግሞ በ2010 በአገሪቱ ውስጥ እስከተካሄደው ለውጥ ድረስ የአገሪቱ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዲኤታ የነበሩ ሲሆን፤ ባለፉት ሁለት ዓመታት ወደ ትግራይ ሄደው የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ ነበሩ። የአቶ ስብሐት ነጋ ታናሽ እህት የሆኑት ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ ከቀደምት የህወሓት ሴት ታጋዮች መካከል አንዷ የነበሩ ሲሆን የፓርቲው ማዕከላዊና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል፣ የመቀለ ከንቲባ እና የትግራይ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ለበርካታ ዓመታት ሰርተዋል። ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል ከተባሉት ግለሰቦች በተጨማሪ በርካታ የህወሓት ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራሮች በቁጥጥር ሰር የዋሉ ሲሆን ጥቂት የማይባሉት መገደላቸውን የመከላከያ ሠራዊት መግለጹ ይታወሳል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እየተፈለጉ ያሉትን የሕወሓት ከፍተኛ አመራሮችን ጠቁሞ በመንግሥት ቁጥጥር ስር እንዲውሉ የሚያስችል መረጃዎችን ለሚሰጡ ሰዎች የአስር ሚሊዮን ብር ሽልማት እንደሚሰጥ ቃል መግባቱ ይታወሳል።
news-57065444
https://www.bbc.com/amharic/news-57065444
አቶ አሕመድ ሐሰን ሱካሬ፡ የ64 ዓመቱ አዛውንት የፈጠራ ባለሙያ
አቶ አሕመድ ሐሰን ሱካሬ ይባላሉ። የ64 ዓመት አዛውንት ናቸው። እስከ ስምንተኛ ክፍል ድረስ ነው የተማሩት። እኚህ አዛውንት ከሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አራት የፈጠራ ባለቤትነት መብት ያገኙባቸው ፈጠራዎች አሏቸው።
"እኔ ብዙ የተማርኩ ሰው አይደለሁም። የፈጠራ ሥራን ከጀመርኩ ግን አርባ ዓመት ሆኖኛል። ፈጠራን ችግር ነው ያስተማረኝ። አሁን ዩኒቨርስቲ ሄጄ ልምዴን እያካፈልኩ ነው" በማለት ለቢቢሲ ተናግረዋል። ትምህርታቸውን ካቋረጡ በኋላ ጋራዥ ውስጥ ሲሰሩ እንደቆዩ የተናገሩት አቶ አሕመድ፣ አሁን የጋራዡን ቦታ ወደ የፈጠራ ስራዎቻቸው ማምረቻ መለወጣቸውን ያስረዳሉ። ከፈጠራ ስራቸው መካከል አንዱ ቡና ማጠቢያ ማሽን ሲሆን በብዛት እያመረቱ ይሸጣሉ። አቶ አሕመድ በ2004 ዓ.ም. በአገር አቀፍ ደረጃ የፈጠራ ስራዎቻቸውን ካቀረቡ 5098 ሰዎች ጋር ተወዳድረው አንደኛ በመውጣት 150 ሺህ ብር፣ ወርቅ እንዲሁም የእውቅና ምስክር ወረቀት ማግኘታቸውን ያስታውሳሉ። የፈጠራ ባለቤትነት መብት ካገኙባቸው አራት ማሽኖች መካከል ሁለቱን ከልጃቸው ጋር በመሆን መስራታቸውንም ጨምረው አስረድተዋል። ከልጆቻቸው መካከል አንዱ የእርሳቸውን ፈለግ መከተሉን የሚናገሩት አቶ አሕመድ፣ ሁለት ማሽኖችን በጋራ በመሆን ሰርተው የፈጠራ ባለቤትነት መብት ከሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ማግኘታቸውን ይናገራሉ። "በእኔ ጊዜ ብረት የሚቀጠቅጥ ሰው ይናቃል። የእኛ ጎሳ ብረት የሚቀጠቅጥ ሰው የለውም። አሁን ግን ልጄ ስራዬን ወድዶ በመግባት ከእኔ ጋር እየተወዳደረ ነው" ይላሉ አቶ አሕመድ። አቶ አህመድ ሐሰን ማን ናቸው? የቡሌ ሆራ ነዋሪ የሆኑት አቶ ሐሰን ሱካሬ፣ የአካባቢያቸው ነዋሪዎች ሲጠሯች በአያታቸው ስም ሱካሬ በማለት ነው። አቶ ሐሰን የፈጠራ ስራውን ከጀመሩ አርባ ዓመት ቢሆናቸውም እውቅና ያገኙት ግን ከ12 ዓመታት ወዲህ ነው። የዛሬ ስምንት ዓመት ገደማ ደግሞ ሽልማት እንዳገኙበት ይናገራሉ። የፈጠራ ስራ እንዴት እንደጀመሩ ሲናገሩ ፊደል በቅጡ ባይቆጥሩም የማህበረሰቡን ችግር የሚፈታ ፈጠራን ራሳቸውን በራሳቸው ማስተማራቸውን ያስታውሳሉ። "እኛ አካባቢ ትምህርት ቤት አልነበረም፤ ትምህርቴን ስምንተኛ ክፍል አቋርጩ የመኪና ረዳት በመሆን ስራ ጀመርኩ። ከዚያም በኋላ ወደ ሹፍርና ገባሁ" በኋላም ከሹፍርና ወደ ጋራዥ ስራ መግባታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። በጋራዥ ውስጥ ረዳት ሆነው መሰራት የጀመሩት አቶ አህመድ ራሳቸውን ሙያ በማስተማር ወደ ሙሉ መካኒክነት ከዚያም ወደ ጋራዥ ባለቤትነት ተሸጋግረዋል። "የከፈትኩትን ጋራዥ ወደ ኋላ ላይ ወደ ማሽን ማምረቻ ነው ያሳደግኩት። አሁን ከውጪ የሚመጣውን እሸት ቡና መፈልፈያ በማሻሻል የፈጠራ ባለቤትነት መብት አግኝቻለሁ" የሚሉት አቶ አሕመድ በብዛት በማምረት ለገበያ እያቀረቡ እንደሚጠቀሙ ገልፀዋል። የአቶ አሕመድ የፈጠራ ስራዎች አቶ አህመድ እውቅና ካገኙበት የፈጠራ ስራዎቻቸው መካከል አንዱ የቡና ማጠቢያ ማሽን ነው። ሁለተኛው ደግሞ ለባህላዊ የወርቅ ፈላጊዎች የሚያገለግል፣ የወርቅ ድንጋይ መፍጫ ማሽንን በማሻሻል ሰርተዋል። የታጠበ ቡናን ከቦታው በማንሳት ወደ ማድረቂያ አልጋ የሚወስድ ማሽን ደግሞ ከፈጠራ ስራዎቻቸው መካከል ሶስተኛው ነው። ይህንን የወርቅ ድንጋይን የሚፈጭ ማሺን በጉጂ ዞን የሚገኙ በወርቅ ፍለጋ ላይ የተሰማሩ 16 የወጣት ማህበራት በመግዛት እየተጠቀሙበት መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል። አራተኛው የፈጠራ ባለቤትነት መብት ያገኙበት ደግሞ በአነስተኛ የኤሌትሪክ ጉልበት (5.5hp) የሚሰራ የእህል ወፍጮን በማሻሻል የሰሩት ነው። ከልጃቸው ካሚል አሕመድ ጋር ደግሞ ገብስ በመሸክሸክ ከገለባው የሚያፀዳ ማሽን በመስራት የፈጠራ ባለቤትነት መብት አስመዝግበዋል። አቶ አሕመድ በ2004 ዓ.ም 150 ሺህ ብር፣ መሬት፣ ወርቅ እና ቴሌቪዥን በሽልማት ማግኘታቸውን ይናገራሉ። ካገኙት የብር ሽልማት በላይ እውቅና እንደሚበልጥ የሚናገሩት አቶ አሕመድ በፈጠራ ስራዎቻቸው በገንዘብም ተጠቃሚ መሆናቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል። ስለ ስራዎቻቸው ሲያብራሩም "ከውጪ የሚገባው ማሽን በ1 ሰዓት 300 ኪሎ ግራም ይፈለፍላል፤ እርሱን አሻሽዬ 800 ኪሎ ግራም የሚፈለፍል ሰራሁ" የቡና ማጠቢያው ማሽን ደግሞ በአንድ ሰዓት ውስጥ 40 000 ኪሎ ግራም ማጠብ እንደሚችል አብራርተዋል። የአቶ አህመድን የፈጠራ ስራ የተመለከቱት ቡሌ ሆራ እና አዳማ ዩኒቨርስቲዎች አብረዋቸው ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል። አቶ አሕመድ በእነዚህ ዩኒቨርስቲዎች ለሚማሩ የምህንድስና ተማሪዎች ልምዳቸውን በማካፈል እና በማሳየት አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን ተናግረዋል። "እነዚህ ኢንጂነሮች የምሰራቸውን ስራዎች ያደንቃሉ፤ ከዚያም ይማራሉ፤ ያግዙኛል" አቶ አህመድ በአሁኑ ጊዜ እምቦጭ አረምን የሚያፀዳ ማሽን የመኪና መለዋወጫዎችን በመጠቀም መስራታቸውን ገልፀዋል። ወደፊትም ወደ አዲስ አበባም በመቅረብ የራሳቸውን ኢንደስትሪ ለመክፈት እቅድ እንዳላቸው ተናግረዋል።
news-49902873
https://www.bbc.com/amharic/news-49902873
የጥበብ እጆች ከዞማ ቤተ መዘክር ወደ ታላቁ ቤተ መንግሥት
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ ከገቧቸው ቃልኪዳኖች መካከል አንዱ ታላቁን ቤተ መንግሥት አድሰው ለሕዝብ ክፍት ማድረግ ነበር።
ኤሊያስና መስከረም በዚህ መሠረትም በቅርቡ የተለያዩ ግንባታዎች እና እድሳት የተካሄደበትን ቤተ መንግሥት የደረሰበትን ደረጃ ለማሳየት ራሳቸው መኪና እያሽከረከሩ ሲያስጎበኙ በመገናኛ ብዙሃን ታይተዋል። እድሳቱ ተጠናቆም ከመስከረም 30/2012 ጀምሮ ለጎብኝዎች ክፍት እንደሚደረግ ተገልጿል። • ባሕልና ተፈጥሮን ያጣመረው ዞማ ቤተ መዘክር • አደጋ የተጋረጠበት የአፄ ፋሲለደስ ቤተ መንግሥት በቤተ መንግሥቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የእድሳት እና የአረንጓዴ መናፈሻውን ሥራ ከሚሠሩት ባለሙያዎች መካከል አንትሮፖሎጂስቷ መስከረም አሰግድና የሥነ ጥበብ ባለሙያው ኤሊያስ ስሜ የሚመራው ቡድን ይጠቀሳል። የዞማ ቤተ መዘክርን ሃሳብ የጠነሰሱት መስከረም አሰግድ፤ ከሥራ ባልደረባቸው ኤሊያስ ስሜ ጋር በመሆን በርካቶችን ያስደመመውን የቅርጻ ቅርጽና የዞማ አፀድ ሠርተው ለሕዝብ ክፍት አድርገዋል። አሁንም እሱን የማጠናከር አላማ እንዳላቸው እና ቤተ መዘክሩ "በቅቶታል" የሚባል ደረጃ እንዳልደረሰ ይናገራሉ። እነዚህ የጥበብ እጆች ታዲያ በዚያው ተወስነው ብቻ አልቀሩም። አሻራቸውን ለማሳረፍ በጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ጥሪ ወደ ቤተ መንግሥትም አቅንተዋል። መስከረም ይህንን እድል ያገኙበትን አጋጣሚም "ጠቅላይ ሚንስትሩ ለጉብኝት ወደ ዞማ ቤተ መዘክር ጎራ ባሉበት ጊዜ በሥራችን በመደመማቸው የአዲስ አበባ የሥነ ጥበብ ትምህርት ቤትን ገጽታ እንድንለውጥላቸው ጥያቄ አቅርበውልን ሊያሳዩን ይዘውን ሄዱ።" ሲሉ ያስታውሳሉ። ከጉብኝታቸው በኋላ ሥራቸውን የጀመሩት ወዲያውኑ ነበር። እሱን በመሥራት ላይ ሳሉም ወደ ቤተ መንግሥቱ ሥራ እንዲሻገሩ በድጋሚ በጠቅላይ ሚንስትሩ ጥያቄ ቀረበላቸው። የሥነ ጥበብ ትምህርት ቤቱ ሥራ ሙሉ በሙሉ እንዳልተጠናቀቀ የሚናገሩት መስከረም "እሱን ካሳመርን በኋላ በቀጥታ ቤተ መንግሥቱን እንድናስውብ ጠየቁን፤ እኛ በማግስቱ ወደ ሥራው ገባን" በማለት ይናገራሉ። ቤተ መንግሥቱ ካረፈበት 40 ሺህ ካሬ ሜትር፤ 15 ሺህ ካሬ ሜትር የሚሆነው የግቢውን አካል እነ መስከረም እየተጠበቡበት ይገኛሉ። በእርግጥ መስከረም ለቤተ መንግሥቱ እንግዳ አይደሉም። በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ጊዜ በአውሮፓ ኅብረት አማካኝነት ከሌሎች አምባሳደሮች ጋር ለእራት ግብዣ ወደ ቤተ መንግሥት አቅንተው ነበር። ይሁን እንጅ የሄዱት በምሽት ስለነበር ግቢው ምን እንደሚመስል የማየት እድል አላገኙም። "ቀጥታ ወደ እራት ግብዣው ከዚያም ወደ መኪና ነበር" ይላሉ። ይሁን እንጅ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አስተዳደር፤ ከሌሎች አርቲስቶች ጋር ተጋብዘው፤ ግቢውን በሙሉ ዞረው ጎብኝተዋል፤ ጠቅላይ ሚንስትሩም ከባለሙያዎቹ አስተያየት እየጠየቁ ሲወያዩ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታቸው ነው። "አንድ መንግሥት ቤተ መንግሥት የሕዝብ ነው ብሎ ለመክፈት ማሰቡ ለእኔ ትልቅ ነገር ነበር፤ ለዘመናት አጥሩን ነበር እኮ የምናየው" ሲሉ በወቅቱ የተሰማቸውን ደስታ ይገልጻሉ። በመሆኑም ወደ ሥራው በደስታ እንደገቡ ይናገራሉ። እንዲያስውቡት የተሰጣቸው ቦታ የሌሎች ግንባታዎች ትራፊ ቁሳቁሶች የሚጣልበት፤ ምንም ያልለማ ተዳፋት መሬት በመሆኑ የመጀመሪያ ሥራቸው ፅዳት እንደነበር ይናገራሉ። የመጀመሪያ ዲዛይናቸውን የሠሩትም በእነዚሁ ከሌሎች ግንባታዎች በተራረፉና በተጣሉ ድንጋዮች ነበር። ይሁን እንጅ የቦታው አቀማመጥ ተዳፋት በመሆኑና ወቅቱ ክረምት ስለነበር ሥራቸውን ፈታኝ አድርጎባቸዋል። • የፈረሰው የደጃዝማች ዐምዴ አበራ ቤት ጠባቂ ምን ይላል? • ለአደጋ የተጋለጡ ሦስት የትግራይ ቅርሶች ቦታው የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ከግምት ውስጥ ያስገባ እና ለሁሉም ምቹ እንዲሆን ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል። የውሃ ተፋሰሱንና መሬቱን ካስታካከሉ በኋላ ወደ ግንባታ የገቡት ባለሙያዎቹ፤ እያንዳንዱ ድንጋይ በተለያዩ አገር በቀል በሆኑ እፅዋቶች፤ አበባ፣ በቅጠላ ቅጠል እንዲሁም በተለያዩ ቅርፆች አምሳያ እየተጠረቡ እንደተሠሩ ይናገራሉ። በባለሙያው ኤሊያስ እየተሳሉ፣ በጠራቢዎች እየተጠረቡ ከአገር በቀል እፅዋቶች በተጨማሪ የድንጋይ ቅርጾቹ ግቢውን አስውበውታል። የድንጋዩ ንጣፍ እንዳይፈነቀልና ለዘመናት እንዲቆይ ድንጋዮቹ እየተበሱና ከሥራቸው በብረት እየተሳሰሩ የተሠሩ ናቸው። የተለያዩ የዓለም ክፍሎችን የመጎብኘት እድል የነበራቸው መስከረም፤ "ሥራው ከዚህ የተቀዳ ነው፤ አልተቀዳም ብሎ መናገር አይቻልም" ይላሉ። ምናልባት ከአስተዳደጋቸው አሊያም ተዟዙረው ከጎበኟቸው የተከማቸ እውቀት ሊሆን ይችላል በማለት። "ዋናው የማምንበት ጉዳይ በጥራት በኩል ድርድር እንዳማይደረግ ነው፤ ለዘመናት የቆዩ እንደ ፋሲለደስ ያሉ ሃገራዊ ቅርሶችን ጥቃት ቢደርስባቸውም እስካሁን ድረስ ሊቆዩ የቻሉት ጥራት ስላላቸው ነው" ሲሉ ምሳሌ ያጣቅሳሉ። "ለነገ ተብለው ስለተሠሩ፤ ሲፈርሱ ቢውሉ ምልክታቸውን አልተውም" ሲሉ የሚሠሩት ሥራዎች ጥራት እንዲኖራቸው ያስገነዝባሉ። አገር በቀል እጽዋቶች ስለተተከሉ፣ አረንጓዴ በመሆኑ፣ በኢትዮጵያ ጥበብ በእጅ በመሠራቱ፣ ባለሙያዎቹ አገር ያፈራቸውና ከየገጠሩ የመጡ በመሆናቸው ሥራውን ለየት ያደርገዋል ብለዋል- መስከረም። "ያ እጅ የተረሳ እጅ ነው፤ ይህ ጥበብ እንዳለው ያልታወቀ ሕዝብ፤ ወደታች ሲታዩ የነበሩ ጠበብቶች ናቸው የሠሩት።" ይላሉ። ቅማመ ቅመም፣ መድሃኒት፣ አትክልትና ፍራፍሬ፤ እንደ ግራር፣ ወይራ እና የመሳሰሉት አገር በቀል ዛፎች መኖራቸውም ሌላው ልዩ የሚያደርገው ጉዳይ ነው። ጠቅላይ ሚንስትሩ በየቀኑ እንደሚጎበኟቸው የሚናገሩት መስከረም "ፍቅር፣ ድጋፍ ይሰጡናል፤ ባላቸው ደቂቃ ተሻምተው ብቅ ብለው ያዩናል፤ ሞራል ይሰጡናል። 'እጃችሁ ይባርክ!' እያሉ ነው የሚሄዱት፤ እኔ ስለ ፖለቲካ የማውቀው ነገር የለም፤ ግን እንደዚህ ዓይነት መሪ አለ እንዴ?" ሲሉ ይጠይቃሉ። በመሆኑም ቤተ መንግሥቱ ውስጥ የሚሠሩት ሥራ ዘመን ተሻጋሪ እንዲሆን እንደሚተጉ ይናገራሉ። እርሳቸው እንደሚሉት ስለ ክፍያ አስበውም፤ ተጨንቀውም አያውቁም "ጥሪ ሲቀርብልን እኔና ኤሊያስ ባንክ ያለንን ገንዘብ አይተን ብቻ ነው የገባነው" ይላሉ። "ስለ ገንዘቡ ጨርሶውኑ ማሰብ አልፈልግም፤ ሥራውን በጥራት ሠርተን ማስረከብ ብቻ ነው" ብለዋል። በሥራቸው ከ200- 250 የሚደርሱ ባለሙያዎች እንደተሳተፉ የሚገልፁት መስከረም "ከመንግሥት ክፍያ የሚፈጸመው ለእነርሱ ደመወዝ እንጂ፤ እኛ ሙያችንን በነፃ ነው የሰጠናቸው" ሲሉ ለሙያቸው የሚከፈላቸው ክፍያ እንደሌለ ነግረውናል። ሥራውን በራሱ እንደ ስጦታ ነው የሚመለከቱት። እስካሁን ሲሶ (1/3ኛው) የሆነው ክፍል እንደተጠናቀቀ እና ለመስከረም መጨረሻ ለጉብኝት ክፍት እንደሚሆን ገልጸዋል። የእጅ ሥራ በመሆኑና የጥበበኞች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ ሙሉ በሙሉ የማጠናቀቂያ ጊዜውን እንዲህ ነው ብሎ ማስቀመጥ እንደሚያስቸግር ነግረውናል። በጀቱም ቢሆን ሥራው ተጠናቆ ከስሌት በኋላ ካልሆነ በቀር አሁን እንዲህ ነው ማለት ተራ ግምት እንደሚሆን በመግለጽ ከመናገር ተቆጥበዋል። ባለሙያዎቹ መስከረምና ኤሊያስ ለሠሩት ሥራ በተለያየ ጊዜ ሽልማት አግኝተዋል። በዞማ ቤተ መዘክር የተባበሩት መንግሥታት ሽልማት አበርክቶላቸዋል። ሌሎችም የሚጠበቁ ሽልማቶች እንዳሉ ገልፀውልናል። ኤሊያስ ስሜ በዚህ ወር መጨረሻ ላይ የአፍሪካ አርት አዋርድ ከሁለት አሸናፊዎች አንዱ በመሆን አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከሚገኘው የስሚዝሶኒያን የአፍሪካ አርት ብሔራዊ ሙዚየም ሽልማት እንደሚበረከትለትም ይጠበቃል። ቤተመንግሥቱ ለጎብኚዎች ክፍት ሲሆን እያንዳንዱ ሰው 200 ብር እየከፈለ መጎብኘት እንደሚችል የተገለፀ ሲሆን፣ ሳይጋፉ እንደመጡ መግባት የሚፈልጉ ደግሞ 1,000 ብር እየከፈሉ መጎብኘት እንደሚችሉ ተዘግቧል።
news-52804685
https://www.bbc.com/amharic/news-52804685
ምዕራብ ኦሮሚያ፡ ለልጃቸው ስንቅ ለማድረስ ወጥተው አስከሬኑን መንገድ ላይ ያገኙት እናት እሮሮ
"ልጄ ታስሮ ወደሚገኝበት ቦታ እንጀራ ይዤለት ስሄድ አጣሁት . . . የልጄ አስክሬን በሸራ ተጠቅልሎ ሜዳ ላይ ተጥሎ አገኘሁ" ሲሉ በምዕራብ ኦሮሚያ ልጃቸው በጸጥታ ኃይል የተገደለባቸው እናት ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ወጣት ለሊሳ ተፈሪ በምዕራብ ወለጋ ዞን የገንጂ ወረዳ ነዋሪ ነበር። ከሁለት ሳምንት በፊት በአካባቢው ተሰማርቶ በሚገኘው የመንግሥት ኃይል በቁጥጥር ሥር ከዋለ ከሁለት ቀናት በኋላ ሞቶ መገኘቱን የለሊሳ ቤተሰቦች ይናገራሉ። ግንቦት 2/2012 ዓ.ም ከገበያ ስፍራ በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር የዋለው ለሊሳ ከሁለት ቀናት በኋላ ማለትም ግንቦት 4 አስክሬኑ ሜዳ ላይ ተጥሎ መገኘቱን ወላጅ እናቱ ወ/ሮ ጫልቱ ሁንዴሳ እና አባቱ አቶ ተፈሪ ዱጉማ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ለሊሳ ትዳር ለመመስራት በዝግጅት ላይ እንደነበረ እና እጮኛውን ለማግኘት በወጣበት ወቅት መያዙን የቤተሰብ አባላቱ ይናገራሉ። 'እንደወጣ ቀረ' የለሊሳ ተፈሪ እናት ወ/ሮ ጫልቱ ሁንዴሳ እንደሚሉት ከሆነ፤ ለሊሳ አዲስ አበባ ከተማ የምትገኝ እህቱ ጋር ይኖር እንደነበረ እና ወላጆቹ ወደሚኖሩበት አከባቢ ከተመለሰ ሁለት ወራት አልሆነውም። በቀጣዩ ዓመት ለማግባት አቅዶ የነበረው ለሊሳ፤ በጉዳዩ ላይ ከእጮኛው ጋር ለመመካከር ገንጂ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ባለ የገበያ ቦታ ቀጠሮ ይዞ እጮኛውን ለመግኘት እንደወጣ አለመመለሱን ይናገራሉ ወ/ሮ ጫልቱ ይናገራሉ። "ቀኑ ሰንበት ነበር። ከእሷ ጋር እያወራ ገበያ ላይ ያዙት። ታስሮ ይገኘበታል ወደተባለው ቦታ እንጀራ ይዤለት ስሄድ ከዚያ አጣሁት። 'ማንን ነው የምትፈልጉት?' ሲሉ ጠየቁኝ 'ለሊሳ ተፈሪ' ብዬ ስመልስላቸው 'እሱ ከዚህ ወጥቷል' አሉኝ።" ወ/ሮ ጫል ልጃቸው የት እንደተወሰደ ደጋግመው ሲጠይቁ በአንድ የጸጥታ አባል ተመነጫጭቀው እና 'አጸያፊ ስድብ' ተሰድበው መባረራቸውን ይናገራሉ። የለሊሳ ወላጆች "የልጄን አስክሬን በሸራ ተጠቅልሎ ሜዳ ላይ ተጥሎ አገኘሁ" ከዚያ በኋላ ለሊሳ ታስሮ ነበር የተባለበት አከባቢ ያሉ ሰዎች 'ጠዋት ላይ እጁን አስረውት [የለሊሳን] ወደ ጉደያ [በቅርበት ያለ ስፍራ] ወስደውታል እዚያ ፈልጉ' ይባላሉ። ከዘያ "ለእሱ ይዤ የወጣሁትን እንጀራ አስቀምጬ ፍለጋ ስወጣ፤ የልጄ አስክሬን በሸራ ተጠቅልሎ ሜዳ ላይ ተጥሎ አገኘሁ። የልጄን ሞት እዚያው ተረዳሁ" በማለት የለሊሳ እናት ተናግረዋል። ወላጆቹ እንደሚሉት የለሊሳ ህይወት ያለፈው በጥይት ተመቶ ነው። "ያለ ለሊሳ ማን አለኝ?" ሲሉ የሚጠይቁት ወ/ሮ ጫልቱ ለሊሳ አያቱን ጨምሮ ወላጆቹን ይረዳ የነበረው እሱ መሆኑን ይናገራሉ። ለሊሳ ለምን ታሰረ? ከዚህ ቀደም ለሊሳ ታስሮም ሆነ ጥፋተኛ ተብሎ ተከሶ እንደማያውቅ ወላጆቹ ይናገራሉ። አሁን ተይዞ በነበረበት ወቅትም ወደ ፍርድ ቤት አለመወሰዱን ይናገራሉ። ለምን እንደተሳረም ከሚመለከተው አካል የተነገራቸው ምንም መረጃ የለም ይላሉ። "ፍርድ ቤት ሳይቀርብ፣ ጥፋተኛ ሳይባል፣ ሞት ሳይፈረድበት በመንግሥት ጦር ተገደለ" ይላሉ ወላጅ አባቱ አቶ ተፈሪ ዱጉማ። እናቱ እንደሚሉት ለሊሳ 'ቻይና ካምፕ' ተበሎ በሚጠራው ቦታ ታስሮ እያለ፤ ለሊሊሳ ምግብ ይዘው የሄዱ ወጣቶችን "ወታደሮች 'እሱ ሸኔ ነው' ብለው አበረሯቸው።" ወላጅ እናቱ ግን ልጃቸው የሸኔ አባል ስለመሆኑ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ይናገራሉ። በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙ ዞኖች እንዲሁም በደቡብ ኦሮሚያ ጉጂ እና ቦረና አካባቢዎች ታጠቀው የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን መንግሥት 'ሸኔ' ሲል ይጠራቸዋል። እነዚህ ታጣቂዎች የቀድሞ የኦነግ ጦር አባላት ነበሩ ሲሆን መንግሥት እና የአገር ሽማግሌዎች የቡድኑ አባላት ትጥቅ ፈተው ወደ ሰላማዊ ህይወት እንዲመለሱ ለማስገባት ያደረጉት ተደጋጋሚ ጥረት ሳይሳካ መቅረቱ ይታወሳል። የምዕራብ እና ደቡብ ኦሮሚያ ጸጥታ መደፍረስ ባለፉት ሳምንታት በምዕራብ ኦሮሚያ ባሉ አካባቢዎች ያለው የጸጥታ ሁኔታ መደፈረሱን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በተለይ በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙት ገንጂ እና ላሎ አሳቢ በሚባሉ ወረዳዎች ግጭቱ ተባብሷል ይላሉ። በምዕራብ ኦሮሚያ ብቻ ሳይሆን ታጣቂዎች ይንቀሳቀሱበታል በሚባለው ደቡብ ኦሮሚያ ጉጂ አካባቢ በመንግሥት ኃይሎና በታጣቂዎች መካከል ግጭት መኖሩ ነዋሪዎችና የአከባቢው ባለስልጣናት ለቢቢሲ ባለፈው ሳምንት ገልፈው ነበረ። ከጥቂት ሳምንታት በፊት በጉጂ ዞን በተፈጠረ ግጭት 12 የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላት መገደላቸውን የዞኑን ምክትል አስተዳዳሪ ጠቅሰን ከቀናት በፊት መዘገባችን ይታወሳል። የለሊሳ ተፈሪ የቀብር ስፍራ የመንግሥት ምላሽ በወጣቱ ግዳያ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የምዕራብ ወለጋ አስተዳዳሪ አቶ ኤሊያስ ኡመታ "ይህ ጉዳይ የቆየ ነገር ነው። ለመገናኛ ብዙሃንም ማብራሪያ ስሰጥ ነበር። አሁን የልማት ሥራ ግምገማ እና የሥራ እድል የመፍጠር ጉዳዮች ላይ ተጠምደን ነው ያለነው። በእዚህ ጉዳዮች ላይ ብትጠይቀኝ ይሻላል" በማለት በጉዳዩ ላይ የሚሰጡት ምላሽ እንደሌለ በመናገር የእጅ ስልካቸውን ዘግተዋል። አቶ ኤሊያ በምዕራብ ወለጋ ዞን ላሎ አሳቢ ወረዳ ባለፉት ቀናት ተከስቶ ከነበረው የጸጥታ መደፍረስ ጋር በተያያዘ ለጀርመን ድምጽ "መንግሥት በአካባቢው የሕግ የበላይነት በማስከበር ላይ ይገኛል። የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ሕግን ከማስከበር ውጭጪ በነዋሪው ላይ ያደረሱት ጉዳት የለም። በመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች እና ሸማቂዎች መካካል በነበረው ግጭት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ነዋሪዎች ካሉ አጣርተን ይፋ እናደርጋለን" ማለታቸው ተዘግቧል። የጀርመን ድምጽ በዚህ ዘገባው በምዕራብ ወለጋ ዞን ላሎ አሳቢ ወረዳ ከማክሰኞ ግንቦት 11 ጀምሮ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ የአምስት ሰዎች ህይወት አልፏል ብሏል። የኦሮሚያ ክልል አስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ የሆኑት ኮሎኔል አበበ ገረሱን ስለጉዳዩ ብንጠይቅም "ከኃላፊቴ ተነስቻለሁ" ብለዋል። የኮሎኔል ገረሱ ከኃላፊነት መነሳት ግን በመንግሥት ይፋ አልተደረገም። ቢቢሲ ከጥቂት ወራት በፊት በምዕራብ እና ደቡብ ኦሮሚያ ስላለው የጸጥታ ችግር የአገሪቱ ጦር ሠራዊት ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላን በጠየቀበት ጊዜ በተወሰደው እርምጃ አካባቢዎቹ ከታጣቂዎች ነጻ ወጥቷል ብለው ነበር።
50612203
https://www.bbc.com/amharic/50612203
የወላይታ ዞን ተወካዮች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ሊወያዩ ነው
የወላይታ ዞን በክልል የመደራጀት ጥያቄን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከሕዝብ ተወካዮች ጋር ለመነጋገር ነገ ማለዳ በጽህፈት ቤታቸው እንደጠሯቸው ያነጋገርናቸው የተወካዮች አባላት ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የክልሉ ሕዝብ ተወካዮችን በዞኑ አስተዳደር በኩል ለስብሰባ እንደጠሯቸው ቢነገርም በምን ጉዳይ ላይ እንደሚወያዩ ግን የተገለፀ ነገር የለም። አቶ አሸናፊ ከበደ የወላይታ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር የወጣቶች ክንፍ አመራር ሲሆኑ፤ በስብሰባው ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ካቀኑት አባላት መካከል ይገኙበታል። • የክልል እንሁን ጥያቄ እዚህም እዚያም? • ክልልነት ለጠየቀው ሁሉ ቢሰጥ ችግሩ ምንድነው? • ሲዳማ: 10ኛው የኢትዮጵያ ክልል እርሳቸው እንደሚሉት፤ የወላይታ ዞን ክልል የመሆን ጥያቄውን ካቀረበ ታሕሳስ 10 አንድ ዓመት የሚሆነው ሲሆን፣ ከዚያ በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዚሁ ዙሪያ ሊያነጋግሯቸው እንደጠሯቸው እንደሚገምት ተናግረዋል። ጥያቄው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበው አርብ ዕለት መሆኑን በመግለጽም በዞኑ አመራሮች በኩል ጥሪው ደርሶናል ብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከዚህ በፊት ወደ ዞኑ በማምራት ከሕዝብ ተወካዮችና ከዞኑ አመራሮች ጋር በተወያዩበት ወቅት የክልል መሆን ጥያቄው መነሳቱን የሚያስታውሱት የሀገር ሽማግሌዎችን ወክለው ስብሰባው ላይ የሚገኙት አቶ ነጋ አንጎሬ በወቅቱ ከሕዝባችሁ ጋር ተወያዩ መባላቸውን በማንሳት፣ እነርሱ ግን ተወያይተው መጨረሳቸውን መናገራቸውን ያስታውሳሉ። አቶ አሸናፊም በበኩላቸው ይህንኑ ስብሰባ በመጥቀስ ይህ የዘመናት የወላይታ ሕዝብ ጥያቄ የሚወሰንበትን ቀን አስታውቁ በተባልነው መሰረት አሳውቀናል ሲሉ ታሕሳስ 10፣ 2011 ዓ. ም. ጥያቄያቸውን ማቅረባቸውን ይናገራሉ። • 'ከሕግ ውጪ' የተዋሃዱት አምስቱ ክልሎች አቶ ነጋ በበኩላቸው ክልሉ በኮማንድ ፖስት ስር መሆኑን በማስታወስ የወጣቶች ሕይወት ሳይቀጠፍና አካል ሳይጎዳ በመነጋገር የሚሆነውን ለመወሰን መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል። ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ለሚደረገው ስብሰባ ወደ አዲስ አበባ እያመሩ ያሉት እነማን መሆናቸውን ሲናገሩም፤ የሀይማኖት አባቶች፣ ምሁራን፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የተቃዋሚ መሪ ተወካዮች፣ የክልሉን ወጣት አደረጃጀት የሚመሩ አካላትና የዞኑ አመራሮች እንደሚገኙበት አቶ ነጋም ሆኑ አቶ አሸናፊ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። አቶ አሸናፊ ታሕሳስ 10 የወላይታ ሕዝብ የክልልነት ጥያቄውን የሚያውጅበት መሆኑን በማስታወስ፣ "መንግሥት ሪፍረንደም የሚካሄድበትን ቀን የማያሳውቅ ከሆነ፣ በምንም ዓይነት ሁኔታ የማይቀለበስ ቀን ነው" በማለት ለዚህም ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
news-55993316
https://www.bbc.com/amharic/news-55993316
በትግራይ ክልል ተጨማሪ ከተሞች የስልክ አገልግሎት መጀመራቸው ተገለፀ
በትግራይ ክልል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ተቋርጦ የነበረው የስልክ አገልግሎት በ363 ጣቢያዎች መጀመሩን ኢትዮ-ቴሌኮም አስታውቋል።
ድርጅቱ በሰሜን ሪጅን የቴሌኮም መሰረተ ልማት ጥገና እና አገልግሎትን በተመለከተ በሰጠው መግለጫ እስካሁን ድረስ የጥገናና የኃይል አቅርቦት ስራዎች በመጀመር በ363 ጣቢያዎች የሞባይል ድምፅና የመደበኛ ስልክ አገልግሎት ተጀምሯል ብሏል። በዚህም መሰረት አገልግሎት ማግኘታቸው ከተጠቆሙ ከተሞች መካከል መቀለ፣ አድዋ፣ አክሱም፣ አዲግራት፣ ሽረ እንዳስላሴ፣ ነጋሽ፣ ዲንሻ፣ ውቅሮ፣ አዳጋ ሃሙስን ጨምሮ በ26 ከተሞች የቴሌኮም አገልግሎት ማግኘት እንደጀመሩ ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ አመላክቷል። ቀደም ሲል የፌደራል መንግሥቱ መቀለን ከተቆጣጠረ ጥቂት ሳምንታት በኋላ በደቡብና ምዕራብ ትግራይ የሚገኙት አንዳንድ ከተሞች ተቋርጦ የቆየውን አግልግሎቱን መጀመሩ ይታወቃል። በተለይ ማእከላዊ የትግራይ ዞን ከማናቸውም የግንኙነት መስመሮች ተቋርጦ ስለ ነበር በርካታ ሰዎች ስጋታቸውን ሲገልፁ ነበር። በአሁኑ ወቅት በማእከላዊ ዞን የሚገኙት እንደ ዓድዋ፣ አክሱም፣ ሽረ እንዳስላሰ፣ ቤተመራ፣ ውቕሮማራይ እና ሰለኽለኻ የመሳሰሉት ከተሞች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መደረጋቸው ኢትዮ ቴሌኮም ገልጿል። ከዚህም በተጨማሪ በክልሉ ውስጥ የተቋረጠውን የባንክ አገልግሎት ለማስጀመር በሽረ እንዳስላሴ፣ በአክሱም እና በአድዋ ከተሞችና አካባቢዎች የሚገኙ የሚገኙ ባንኮች የብሮድ ባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ማግኘታቸውን አስታውቋል። ድርጅቱ ባሰፈረው መረጃ መሰረት በመቀሌና በአዲግራት የሚገኙ ባንኮች እንዲሁ የብሮድ ባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት እያገኙ ናቸው። ሆኖም በአብዛኛዎቹ አካባቢዎች አገልግሎት እንዲያገኙ የተደረገው ጊዜያዊ የስርጭት መስመሮችን በመዘርጋት በመሆኑ የአገልግሎት መቆራረጥና ጥራት ጉድለት ሊያጋጥም እንደሚችል ተጠቁሟል። በአጠቃላይ በሰሜን ሪጅን ያሉት የቴሌኮም መሰረተ ልማቶችን ሙሉ በሙሉ ለመጠገን እየተሰራ እንደሆነ ገልፆ በሙሉ አቅም አገልግሎቱ እስጂመር ነዋሪዎች እንዲታገሱ ኢትዮ-ቴሌኮም ጠይቋል። ቢቢሲ በአንዳንድ ከተሞች ስልክ በመደወልና የደወሉ ሰዎችን የጠየቀ ሲሆን ከከተሞች ውጪ በገጠር አካባቢዎች የሞባይል ስልክ መስመሮች እንደማይሰሩ ተናግረዋል። ቢቢሲ ወደ ሽረና ሰለኽለኻ ተቋርጦ የቆየው የሞባይል ስልክ መስራቱን በአካባቢዎቹ ከሚኖሩ ነዋሪዎች ጋር በመደወል ማረጋገት ችሏል። በውጭ አገራት ነዋሪዎች የሆኑና በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ የትግራይ ክልል ተወላጆች ከቤተሰቦቻው፣ ዘመድ አዝማዳቸውና ወዳጆቻቸው ጋር ከሶስት ወር በኋላ መነጋገራቸውን ለቢቢሲ አስረድተዋል። በርካቶች የስልክ ግንኑነት መቋረጡን ተከትሎ የቤተሰቦቻቸውን ደህንነት ሁኔታ ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ አለማወቃቸው እንዳስጨነቃቸው በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ሲገልፁ መቆየታቸው ይታወሳል። ግጭቱን ተከትሎ በተለያዩ ምክንያት ህይወታቸውን ያለፈ ቤተሰባቸውን ሞት በዚህ አጋጣሚ የተረዱም እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል። የስልክና የባንክ አገልግሎት ተቋርጦ መቆየቱ ቤተሰቦቻቸው መሰረታዊ የሚባሉ ሸቀጦችን ለመግዛት ተቸግረው እንደነበርና ለከፋ ችግርም እንዳይጋለጡ ስጋት እንደነበራቸው የገለፁት ነዋሪዎች በአሁኑ ወቅት የስልክ መስመሮች መከፈታቸው እንዳስደሰታቸው አክለው ተናግረዋል። የባለፉት 100 ቀናት ለበርካታ የክልሉ ነዋሪዎች አስቸጋሪው የፈተና ጊዜ እንደነበር ያስረዳሉ። አንድ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚ ከ97 ቀናት በኋላ ወላጅ ኣባት እና እናቱን ማነጋገር ቢችልም "እርስ በርስ ከመላቀስ ውጪ መነጋገር አልቻልንም" በማለት አስፍሯል። ሌላ ወደ ሽረ ከተማ ስልክ ደውሎ ቤተሰቡን ማናገር የቻለ በውጭ አገር የሚኖር የትግራይ ተወላጅ መኖርያ ቤታቸው ተደርምሶና ፈራርሶ እንደሆነ ለማወቅ መቻሉን ለቢቢሲ ተናግሯል። "በሰፈራችን በርካታ ቤቶች ወድሟል። ሰውም ሞቷል። የእኛም ቤት በከባድ መሳርያ መመታቱና የቤት መሰተዋቱን መሰባበሩን ነግረውኛል። ቤተሰቦቼ በህይወት ተርፈው ማነጋገር መቻሌ ግን ትልቅ ነገር ነው" ብሏል። አብዛኛዎቹ የቤተሰቡ ኣባላት ሽረ ላይ ጦርነት ከተጀመረበት ወቅት ጀምሮ ከከተማው ሸሽተው በገጠር ማሳለፈቻውን ይናገራል። በአሁኑ ወቅት መጠነኛ መረጋጋት እንዳለና ወደ ከተማ ተመልሰው ኑሯቸውን መጀመራቸውን እንደነገሩት ይኸው ግለሰብ ለቢቢሲ ያስረዳል። ሆኖም ሌሎች ቤተሰቦቹን ጨምሮ በርካታ የሰፈሩ ነዋሪዎች ከከተማ ወደ ገጠር እየተመላለሱ እንዳሳለፉትና አሁንም ባለባቸው ስጋት ምክንያት ያልተመለሱ እንዳሉ መስማቱን ለቢቢሲ ገልጿል። በትግራይ ክልል የሕወሓት ኃይሎች በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት መክፈታቸው ከተገለፀ ከተገለፀ በኋላ መንግሥት "የሕግ የማስከበር" የሚለውን ወታደራዊ ዘመቻ መውሰዱን ተከትሎ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦ መቆየቱ ይታወሳል። በክልሉ በተከሰተው ወታደራዊ ግጭት ሳቢያ ተቋርጠው የነበሩት የመብራት፣ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎቶች በመሠረተ ልማቶቹ ላይ በደረሰው ውድመት እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን፤ ለዚህም የፌደራል መንግሥት ህወሓት ተጠያቂ እንደሆነ መግለፁ የሚታወስ ነው።
news-56353674
https://www.bbc.com/amharic/news-56353674
የሚያንማሯ ፕሬዝዳንት ሳን ሱ ቺ 600 ሺህ ዶላርና ወርቅ በመውሰድ ተወነጀሉ
የሚያንማር ጦር ኃይል አመራሮች ከሥልጣን የተወገዱት ፕሬዝዳንት ሳን ሱ ቺ በሕገወጥ መንገድ 600 ሺህ ዶላር ተቀብለዋል ሲሉ ወነጀሉ።
ፕሬዝዳንቷ በፈረንጆቹ የካቲት 1 ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ ከቀረቡባቸው ውንጀላዎች በሙሉ ይህኛው ጠንካራ ነው ተብሏል። ጦር ኃይሉ ለውንጀላው ማስረጃ አላቀረበም። ብርጋዴር ጄነራል ዛው ሚን ቱን፣ ዊን ሚንት እና ሌሎች ሚኒስተሮችን በሙስና ወንጅለዋል። የሳን ሱ ቺ ፓርቲ ናሽናል ሊግ ፎር ዲሞክራሲ ባለፈው ዓመት የተደረገውን አገራዊ ምርጫ በአብላጫ ድምጽ ማሸነፉ ይታወሳል። የሚያንማር ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ግን ምርጫው የተጭበረበረ ነው ሲሉ አስታውቋል። ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች የጦር ኃይሉን የተጭበረበረ ምርጫ ነው የሚል ክስ የሞገቱ ሲሆን ምንም የታየ ስህተት የለም ብለዋል። ሳን ሱ ቺ ላለፉት አምስት ሳምንታት በወታደራዊ ኃይሉ ቁጥጥር ስር ቢሆኑም ያሉበት ስፍራ ግን እስካሁን ድረስ አይታወቅም። ወታደራዊ ባለሥልጣናት በሳን ሱ ቺ ላይ "ፍርሃትና ሥጋት በመቀስቃስ"፣ በሕገወጥ መንገድ የሬዲዮ መሳሪያዎችን በመያዝ እና የኮቪድ-19 እገዳዎችን በመጣስ ክሶች መስርተውባቸዋል። እስካሁን ድረስ ከቀረቡባቸው ክሶች መካከል ሐሙስ ዕለት የተሰማው ሕገወጥ ገንዘብ መቀበል ትልቁ ነው። ሳን ሱ ቺ ተቀብለውታል የተባለው ወርቅ በገንዘብ ሲሰላ 450 ሺህ ፓውንድ ይሆናል ተብሏል። ሚያንማር ሳን ሱ ቺ በቁጥጥር ስር ውለው ወታደሩ ሥልጣንን ከተቆጣጠረ ጀምሮ በጎዳና ላይ ነውጦች እየታመሰች ትገኛለች። ሐሙስ ዕለት ብቻ ሰባት ተቃዋሚ ሰልፈኞች መገደላቸውን ተከትሎ የሟቾች ቁጥር 60 ደርሷል። የዓይን ምስክሮች እንደሚሉት የተወሰኑ ተቃዋሚ ሰልፈኞች የሞቱት ግንባራቸውን በጥይት ተመተው ነው ። የተባበሩት መንግሥታት፣ አሜሪካ እና ሌሎች አገራት የተቃዋሚ ሰልፈኞቹን ግድያ ያወገዙ ሲሆን ባለስልጣናቱም ከኃይል እርምጃ እንዲቆጠቡ አሳስበዋል። የአገሪቱ ወታደራዊ ኃይል ግን የቀረበበትን ውንጀላ በሙሉ አጣጥሎ ጥፋቱ በሙሉ የሱ ቺ ነው ብሏል።
49342542
https://www.bbc.com/amharic/49342542
የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት የምግብ ምርት ከውጪ እንዳይገባ አዘዙ
የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ሙሃማዱ ቡሐሪ የሃገር ውስጥ የእርሻ ምርትን ለማሳደግ ሲሉ ማዕከላዊው ባንክ የምግብ ምርቶችን ከውጭ ለሚያስገቡ አስመጪዎች የውጭ ምንዛሪ እንዳይሰጥ አዘዙ።
ፕሬዝዳንቱ እንዳሉት የሃገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ኢኮኖሚውን ለማስፋፋት በሚጠቅም መንገድ በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል እንጂ "ጥገኝነትን በሚያበረታቱ ከውጭ የሚመጡ ምግቦችን ለመግዛት በሚደረግ ወጪ ላይ መዋል የለበትም" ብለዋል። • ናይጄሪያ ውስጥ 'ሰልፊ' ሲነሱ የነበሩ ሦስት ተማሪዎች ሞቱ ፕሬዝዳንቱ "ወደ ናይጄሪያ ምግብ ለሚያስመጣ ማንኛውም ሰው ሰባራ ሳንቲም አንሰጥም" ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። ናይጄሪያ በአፍሪካ ውስጥ ባለግዙፍ ኢኮኖሚ ስትሆን፤ 200 ሚሊዮን የሚጠጋውን ሕዝቧን ለመመገብም በአብዛኛው የምግብ ምርቶችን ከውጭ ታስገባለች። በዚህ ዓመት አጋማሽ ላይ በተካሄደው ምርጫ ለሁለተኛ ጊዜ ያሸነፉት ቡሐሪ፤ በመጀመሪያው የስልጣን ዘመናቸው የተዳከመውን የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሻሻል ቃል ገብተው ነበር። ናይጄሪያ በአፍሪካ ውስጥ ትልቋ የነዳጅ ዘይት አምራጭ ስትሆን ከምርቱ የምታገኘው ገቢና ግብር ለኢኮኖሚዋ ወሳኝ ሲሆን አብዛኛው ገቢም ከውጭ ምግብ፣ መሰረታዊ ቁሳቁሶችና ከባድ ማሽኖች ለማስገባት ታውለዋለች። • በረመዳን ፆም ምግብ የበሉ 80 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ በሃገሪቱ ብሔራዊ ስታትስቲክስ ጽህፈት ቤት መረጃ መሰረት ባለፈው የፈረንጆች ዓመት የመጀመሪያ ሦስት ወራት ውስጥ ናይጄሪያ የግብርና ምርቶችን ለመግዛት 503 ሚሊዮን ዶላር አውጥታለች። ይህ አሃዝም ባለንበት የፈረንጆች ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ላይ ከ25 በመቶ በላይ ጨምሯል። ፕሬዝዳንቱ በመጀመሪያው የስልጣን ዘመናቸው ወቅት የሃገሪቱ ሕዝብ ዋነኛ ምግብ የሆነውና በበርካታ ግዛቶቿ የሚመረተውን ሩዝ ለማስገባት የውጪ ምንዛሪ እንዳይሰጥ አግደዋል። ይህ እርምጃ ዓላማ ያደረገው የሃገር ውስጥ ምርትን ማበረታታት ቢሆንም በተቃራኒው በአብዛኛው ከጎረቤት ቤኒን ከፍተኛ መጠን ያለው ሩዝ በድብቅ በድንበር በኩል እንዲገባ ምክንያት ሆኗል። • ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ስለተዘረፉ ቅርሶች ምን እናውቃለን? ከሁለት ሳምንት በፊት ማዕከላዊው ባንክ ናይጄሪያ ውስጥ የሚመረተውን ወተት ለማበረታታት በማለት የወተት አስመጪዎች የውጪ ምንዛሪ እንዳይሰጣቸው ከልክሏል። የሃገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ ከመንግሥት ተጽዕኖ ነጻ በመሆኑ ራሱ ከሚወስደው ርምጃ ውጪ የፕሬዝዳንቱን ትዕዛዝ እንዴት እንደሚያስተናግደው እስካሁን ግለጽ አይደለም። ውሳኔው ተግባራዊ የሚሆን ከሆነ አስመጪዎች የውጪ ምንዛሬ በከፍተኛ ዋጋ ከሚሸጥበት ጥቁር ገበያን ከመሳሰሉ አማራጮች የውጪ ምንዛሪ ስለሚገዙ በምግብ ዋጋ ላይ ጭማሪ መከሰቱ አይቀርም ተብሏል።
news-47931841
https://www.bbc.com/amharic/news-47931841
ሱዳን የቀድሞ የመንግስት ባለስልጣናትን በቁጥጥር ስር አዋለች
የሱዳን የሽግግር ወታደራዊ ምክር ቤት የቀድሞ የሃገሪቱ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን በቁጥጥር ስር በማዋል የተቃውሞ ሰልፈኞችን እንደማይበትን ቃል ገባ።
የምክር ቤቱ ቃል አቀባይ ጨምረው እንዳስታወቁት ተቃዋሚዎች ቀጣዩን ጠቅላይ ሚኒስትር በፍጥነት እንዲመርጡ በማሳሰብ ፍላጎታቸውም እንደሚከበር ቃል ገብተዋል። ለወራት የቆየው የሱዳን ተቃውሞ ለሰላሳ ዓመታት ሲመሩ የነበሩትን ኦማር አል በሽርን ባለፈው ሐሙስ ከስልጣን እንዲሰናበቱ ያስገደደ ሲሆን ሰልፈኞቹ እስካሁንም ቢሆን ገለልተኛ መንግስት እስኪቋቋም ድረስ ከመንገዶች እንደማይንቀሳቀሱ ተናግረዋል። • ኦማር አል-በሽር: ከየት ወደየት? • የሱዳን ተቃዋሚ ሰልፈኞች ወታደሩ ያስቀመጠውን ሰዓት እላፊ ጣሱ በዋና ከተዋማ ካርቱም በሚገኘው የመከላከያ ሚኒስትር መስሪያ ቤት ውስጥ እየተደረገ ያለውም ውይይት እስካሁን እንደቀጠለ ነው። ጊዜያዊው ወታደራዊ ምክር ቤት ተቃዋሚ ፓርቲዎች በሚያቀርቡት ማንኛውም አይነት የመንግስት አስተዳደር ሃሳብ እንደሚስማማና ተግባራዊ እንደሚያደርግ ቃል አቀባዩ ማጀር ጀነራል ሻምስ አድ ዲን ሻንቶ እሁድ ዕለት ገልጸዋል። ''እኛ ጠቅላይ ሚኒስትር አንሾምም። ራሳቸው ናቸው የሚመርጡት'' ብለዋል ቃል አቀባዩ። አክለውም ወታደሮች ለተቃውሞ የወጡ ሰልፈኞችን ለመበተን ምንም አይነት እርምጃ እንደማይወስዱ ቃል በመግባት ሰልፈኞች ግን ወደ ቀድሞ ህይወታቸው እንዲመለሱና መንገድ መዝጋት እንዲያቆሙ ጠይቀዋል። በተጨማሪም ''የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስም ሆነ መጠቀም ተቀባይነት የለውም'' ብለዋል። በመግለጫው ላይም የወታደራዊ ምክር ቤቱ አዲስ የመከላከያና የፖሊስ ሃላፊዎች እንዲመረጡ፣ አዲስና ጠንካራ የደህንንት መስሪያ ቤት እንዲቋቋም፣ የሙስና ወንጀሎችን የሚመረምርና የሚከላከል ኮሚቴ ስራ እንዲጀምር፣ በመገናኛ ብዙሃን ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳና አፈና እንዲነሳ፣ ተቃዋሚዎችን በመደገፋቸው በእስር ላይ የነበሩ የፖሊስ አባላት እንዲፈቱ ፣ ዲፕሎማሲያዊ ለውጥ እንዲደረግ እንዲሁም በአሜሪካና በስዊዘርላንድ የሱዳን አምባሳደር ከስራቸው እንዲነሱ ወስኗል። ኦማር አል-በሽር ከስልጣን ተነስተው በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ስለመደረጋቸው በቴሌቪዥን መስኮት ቀርበው የተናገሩት የጦር አለቃ አዋድ ሞሐመድ አህመድ ኢብን ኡፍ ይሰኛሉ። • ሱዳን ውስጥ የዳቦና የነዳጅ ዋጋ ንሮብናል ያሉ ዜጎች ከፖሊስ ጋር ተጋጩ • የኢትዮጵያና አሜሪካ የተለየ ግንኙነት እስከምን ድረስ? ባለፈው ሐሙስም ለሰላሳ ዓመታት ያህል ሱዳንን ሲመሩ የቆዩት አል-በሽር ከስልጣን መነሳታቸውን የሃገሪቱ መከላከያ ሚንስትር አስታውቀዋል። የኑሮ ውድነት ወደ አደባባይ ያወጣቸው ተቃዋሚዎች፤ የአል-በሽርን ከስልጣን መነሳት አደባባይ በመውጣት ሲጠይቁ መሰንበታቸው ይታወሳል። ተቃዋሚዎች በአደባባይ ተሰቅለው የሚገኙ የፕሬዚዳንቱን ምስል ሲያነሱ ተስተውለዋል። በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች በመናገሻ ከተማዋ ካርቱም በፕሬዝዳንቱ መኖሪያ ቅጥር ግቢ ፊት ለፊት በመገኘት የይውረዱ ጥያቄያቸውን ሲያቀርቡ የነበረ ሲሆን ሰኞ ዕለት ከመከላከያ ኃይሉ ጋር የሽግግር መንግሥት መመስረት በሚቻልበት ጉዳይ ላይ መነጋገር የሚፈልግ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት ተቃውሞ አካሂዷል። ፕሬዝዳንት አል በሺር እ.ኤ.አ ከ 1989 ጀምሮ ሱዳንን ያስተዳደሩ ሲሆን 'ስልጣን ይብቃዎት፤ ይውረዱ' የሚል የሕዝብ ድምፅ በአደባባይ መሰማት ከጀመረ ወራት ተቆጥሯል።
51582956
https://www.bbc.com/amharic/51582956
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝና የአየር መንገዶች የገቢ ማሽቆለቆል ስጋት
እኤአ በ2019 መጨረሻ ላይ በቻይና የተከሰተው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ አየር መንገዶችን 29.3 ቢሊየን ዶላር ገደማ ያከስራቸዋል ሲል ዓለም አቀፉ የአየር መጓጓዣ ማህበር አስጠነቀቀ።
ዓለም አቀፉ የአየር መጓጓዣ ማህበር (IATA) ከአስርት ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፕላን ለመጓዝ ያለው ፍላጎት ሊቀንስ ይችላል ሲል ተንብይዋል። በዚህም በዋናነት የሚጎዱት በቻይና የሚገኙ አየር መንገዶችና በእስያ ፓሲፊክ አካባቢ የሚገኙ አገራት መሆናቸውን አስቀምጧል። • ወደቻይና የተጓዙና የኮሮናቫይረስ ምልክቶች የታዩባቸው ሰዎች ተገኝተው ነበር ተባለ • በኮሮናቫይረስ ምክንያት የግል አውሮፕላን ተፈላጊነት ጨመረ • አፍሪካ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል አቅሙ አላት? ይህ ትንበያ የተሰማው በርካታ አየር መንገዶች ወደ ቻይና የሚያደርጉትን በረራ ለመቀነስ ብሎም ለማቋረጥ በተገደዱበት በዚህ ወቅት ነው። እንደ ዓለም አቀፉ የአየር መጓጓዣ ማህበር ትንበያ ከሆነ፤ በአጠቃላይ እኤአ በ2020 በእስያ ፓሲፊክ የሚገኙ አገራት 27.8 ቢሊየን ዶላር ገቢ ኪሳራ እንደሚገጥማቸው ተተንብይዋል። ከእስያ ውጪ ያሉ አገራት ደግሞ 1.5 ቢሊየን ዶላር የገቢ ማሽቆልቆል ይገጥማቸዋል ተብሏል። የማህበሩ ዳይሬክተር የሆኑት አሌክሳንደር ዲ ጁኒያክ በመግለጫቸው ላይ እንዳስቀመጡት "አየር መንገዶች አንዳንዴ ሙሉ በሙሉ፣ አንዳንዴ ደግሞ የበረራውን ብዛት በመቀነስ ከባዱን ውሳኔ እየወሰኑ ነው። ይህ ዓመት ለአየር መንገዶች ፈታኙ ዓመት ይሆናል...።" ማህበሩ አክሎም ይህ ቢሆንም እንኳ የዚህ የገቢ ማሽቆልቆል በአየር መንገዶቹ ትርፋማነት ላይ ያለውን ተጽዕኖ ለመናገር ጊዜው ገና መሆኑን ገልጿል። ዓለም አቀፉ የአየር መጓጓዣ ማህበር እኤአ በ2003 የሳርስ ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅትም እንዲህ አይነት ትንበያ አስቀምጦ ነበር። በወቅቱ ወረርሽኙ ለስድስት ወራት ብቻ የዘለቀ ሲሆን በአውሮፕላን ለመጓዝ የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሶ ወረርሽኙ ሲያቆም ደግሞ በፍጥነት አንሰራርቷል። የሳርስ ወረርሽኝ ተከስቶ በነበረበት ዓመት፤ በእስያ ፓሲፊክ የሚገኙ አየር መንገዶች በ5.1 በመቶ የደንበኞች መቀነስ ገጥሟቸው ነበር። ምንም እንኳ የበሽታው ወረርሽኝ በቻይና ብቻ ተወስኖ ይቀራል የሚል ትንበያ ቢኖርም ተጽዕኖው ግን ሰፊ እንደሚሆን ተተንብዮ ነበር። ዓለም አቀፉ የአየር መጓጓዣ ማህበር (IATA) እስያ ፓሲፊክ ከ2015 እስከ 2035 ባለው ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ በአውሮፕላን ተጓዥ የሚኖርበት አካባቢ ነው ሲል መተንበዩ ይታወሳል። ይህም ማለት በአራትና በአምስት እጥፍ የሚያድግ የአየር መንገዶች ገበያ እንደሚኖር የተተነበየበት ነበር። በትናንትናው ዕለት የአውስትራሊያው ቃንታስ አየር መንገድ እና የአውሮፓው ኤር ፍራንስ ኬኤልኤም በኮሮና ቫይረስ ወረርረሽኝ ምክንያት በዚህ ዓመት የገቢ ማሽቆልቆል እንደሚገጥማቸው አስታውቀው ነበር።
43109491
https://www.bbc.com/amharic/43109491
በሄይቲ የኦክስፋም ቅሌት፡ተጠርጣሪዎች የአይን እማኞችን አስፈራርተዋቸዋል
ሄይቲ በሚገኘው ኦክስፋም ቅርንጫፍ በወሲብ ትንኮሳ ተከሰው የነበሩ ሶስቱ ሰራተኞች በአውሮፓውያኑ 2011 በነበረው ምርመራ የአይን እማኞችን እንዳስፈሯሯቸው ኦክስፋም አጋለጠ።
የእርዳታ ድርጅቱ ሰራተኞቹ ያደረሱትን "ብልግና" ድርጅቱ በደረሰበት የዓለም አቀፍ ግፊት ምክንያት ሪፖርቱን ለማሳተም እንደተገደደ ገልጿል። በአውሮፓውያኑ 2011 ኦክስፋም ባወጣው ሪፖርት ስርዓት ያጓደሉ ሰራተኞች በእርዳታ ድርጅቶች እንዳይቀጠሩ ብዙ መስራት እንደሚያስፈልግ ማሳሰቢያ ሰጥተው ነበር። ነገር ግን ይህ ማሳሰቢያ ችላ ተብሎ በወሲብ ጥቃት እንዲሁም ስርዓትን በማጓደል የተወነጀሉ ወንዶች በተለያዩ እርዳታ ድርጅቶች ለመስራት እንደ ተቀጠሩ ለመረዳት ተችሏል። በ90 አገራት ከ10ሺ በላይ ሰራተኞች ያሉት ኦክስፋም ስለሳለፉት ውሳኔዎቹ ግልፅ መሆን እንፈልጋለን በሚል በተቀባባ መልኩ ሪፖርቱን አውጥቶታል። ይህ 11 ገፅ ያለው ሪፖርት የሰዎችን ማንነት ላለመግለፅ ስማቸው የተሰረዘ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የአይን እማኞች ላይ ዛቻ ያደረሱት ሶስት ወንዶች ይገኙበታል። ዋናውን ሪፖርት ዛሬ ኦክስፋም ለሄይቲ መንግሥት የሚያቀርብ ሲሆን ለተፈፀሙ ስህተቶችም ይቅርታ እንደሚጠይቅ ተዘግቧል። የእርዳታ ድርጅቱ ሴተኛ አዳሪነት ጋር ግንኙነት አላቸው የሚላቸውን ሰራተኞቹን ምርመራ በደንብ አልተወጣም በሚል ከፍተኛ የሆነ አለም አቀፍ ግፊትም እየደረሰበት ነው። ማስፈራራያና ዛቻ በአውሮፓውያኑ 2011 ሰባት የኦክስፋም ሰራተኞች በባህርያቸው ምክንያት በሄይቲ ከሚገኘው የኦክስፋም ቅርንጫፍ እንደለቀቁ ሪፖርቱ ያሳያል። በኦክስፋም ግቢ ውስጥ ከሴተኛ አዳሪ ጋር በመገኘታቸው አንደኛው ሲባረር ሶስቱ ከስራ እንደለቀቁ ሪፖርቱ ያሳያል። ግንኙነታቸው ለአቅመ-ሔዋን ያልደረሱ ሴቶችም ጋር ይሁን አልታወቀም። ከዚህም በተጨማሪ ሁለቱ በማስፈራራትና ዛቻ ምክንያት የተባረሩ ሲሆን አንደኛው ፖርኖግራፊ በመጫንና አንደኛው ደግሞ ሰራተኞችን ባለመጠበቁ ከስራቸው ተባረዋል። ሪፖርቱም የኦክስፋም የስራ ሂደት ዳይሬክተርን ሮናልድ ቫን ሀዌርሜይረን ጠቅሶ እንደተናገረው በኦክስፋም ግቢ ውስጥ ከሴተኛ አዳሪዎች ጋር መገናኘታቸውን ዳይሬክተሩ በምርመራ ቡድኑ ሲጠየቁ አምነዋል። ከምርመራ ቡድኑ ጋር ተባብረዋል በሚልም በምላሹም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በተከበረ መልኩ ዳይሬክተሩ እንዲለቁ አድርገዋቸዋል። ተቀባብቶ በወጣው ይህ ሪፖርትም የአይን እማኞች ላይ ዛቻ በማድረስ በሚልም ስማቸው አልተጠቀሰም። ከፍተኛ የሆነ ቁጥጥር እንደሚያስፈልግ ትምህርት ተወስዷል የሚለው ኦክስፋም አጠቃላይ በእርዳታው ኢንዱስትሪ ውስጥ በዚህ ጉዳይ የተዘፈቁ ሰራተኞች ወደ ሌላ አገር ሲዛወሩ ማስረጃ መስጠት ያስፈልጋል ተብሏል። "ሰራተኞች ስርዓት በማጉደል ምክንያት ከአንድ ቦታ ሲባረሩ ለሌሎች ክልሎች፣ ኤጀንሲዎች ማሳወቅና ከፍተኛ የሆነ ቁጥጥር ያስፈልጋልም" ብለዋል። Mr Van Hauwermeiren worked in Chad from 2006-09 before going to Haiti in 2010 ከፍተኛ ቦታን የተቆናጠጡ ሰራተኞች ሪፖርቱ በስርዓት ማጉደል ምክንያት የተባረሩ ሰራተኞች ሌላ ቦታ እንዳይቀጠሩ የተሻለ ቁጥጥር እንደሚያስፈልግ ማስጠንቀቂያ ቢሰጥም በተቃራኒው የተባረሩ ሰራተኞች በተለያዩ እርዳታ ድርጅቶች እንዲሁም በኦክስፋም ተቀጥረዋል። ሮናልድ ቫን ሀዌርሜይረን ራሳቸው በባንግላዴሽ በሚገኝ "ሚሽን ፎር አክሽን ኤጌይንስት ሀንገር" በሚባል ድርጅት በከፍተኛ ኃላፊነት ቦታ ተቀጥረዋል። ምንም እንኳን ድርጅቱ በሰራተኛው ላይ ምርመራ አድርጌያለሁ ቢልም ከኦክስፋም ስርዓት በማጉደል እንደተባረሩ መረጃ አልደረሰኝም ብሏል።
46040928
https://www.bbc.com/amharic/46040928
አሜሪካዊው 'ጉደኛ ጋንግስተር' ጂሚ በልገር እሥር ቤት ውስጥ ተገደለ
የተወለደው በፈረንጆቹ 1929 ነው፤ የአሜሪካዊ እና የአይሪሽ ዝርያ ካላቸው ካቶሊክ ቤተሰቦች፤ ዕድገቱ ደግሞ ቦስተን ከተማ።
ቦስተን እያለ ነበር መኪና በመስረቅ የወንጀለኝነት ሕይወትን አንድ ብሎ የጀመረው፤ ለጥቆም ባንክ ወደ መዝረፍ ገባ። ገና በአስራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ሳለ ነበር ቀለል ባለ ወንጀል ለእሥር የተዳረገው፤ እያለ እያለ ግን ከበድ ወዳሉ ወንጀሎች ዘለቀ። በዝርፍያ እና ጠለፋ ክሶች ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ታዋቂ ወደሆነው የሳንፍራንሲስኮ ደሴት እሥር ቤት 'አልካትራዝ' ተላከ። በነጭ ፀጉሩ ምክንያት 'ዋይቲ' በልገር እየተባለ የሚጠራው ይህ ወንጀለኛ 'አልካትራዝ' ከተሰኘው እሥር ቤት ጋር ፍቅር ከመውደቁ የተነሳ ከተፈታ በኋላ ጎብኚ መስሎ በመምጣት ፎቶ ተነስቷል። • ባባኒ ሲሶኮ፦ 'ዓለም አቀፉ ምትሃተኛ' ከግድያ እና ዝርፊያ ባለፈ በሰሜን አየርላንድ ላሉ አማፅያን የመሣሪያ አቅርቦት ለማድረግ ይጥር እንደነበር ይነገርለታል፤ ጂሚ 'ዋይቲ' በልገር። ሁለት እንስቶችን በእጁ በማነቅ እንዲሁም አንድ ግለሰብ ለሰዓታት አሰቃይቶ ጭንቅላቱን በጥይት ማፍረስ፤ ጂሚ ባልገር ከሚታወቅባቸው እኩይ ተግባራት መካከል ናቸው። ከአሜሪካው የወንጀል ምርመራ መሥሪያ ቤት፤ ኤፍቢአይ ጋር አይንና ናጫ የነበረው በልገር በርካታ ጊዜ ታስሮ በርካታ ጊዜ አምልጧል። በስተመጨረሻም 2011 ላይ ካሊፎርኒያ ውስጥ ከፍቅር ጓደኛው ካትሪን ጋር ተደብቆ ሳለ በቁጥጥር ሥር ሊውል ችሏል። • የአፍሪካ እግር ኳስ ቅሌት በ11 ግድያዎች እንዲሁም በሌሎች በርካታ ከባድ ወንጀሎች ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘው በልገር የዕድሜ ልክ እሥራት ተፈርዶበት ጥብቅ በሆነው የፍሎሪዳ ማረሚያ ቤት ይገኝ ነበር። ነገር ግን ባልታወቀ ምክንያት ወደ ምዕራብ ቨርጂኒያ እሥር ቤት በተዘዋወረ የመጀመሪያ ቀን በሌላ ታራሚ ተገድሎ ተገኝቷል። ፖሊስ ጂሚ በልገር ለምን ከአንድ ወደ ሌላ ማረሚያ ቤት ሊዛወር እንዳስፈለገ ያለው ነገር ባይኖርም የስነ-ልቡና አማካሪው ከሆነችው ሴት ጋር ግንኙነት ሳይጀምር እንዳልቀረ ምንጮች ሹክ ብለዋል። • የሒጃብ ፋሽን ድዛይነሯ በማጭበርበር ወንጀል ለእስር ተዳረገች የበልገር ሕይወት በርካታ የሆሊዉድ ፊልሞች መነሻ ሃሳብም ሆኖ አገልግሏል፤ 'ዘ ዲፓርትድ' የተሰኘውና ኦስካር ያሸነፈው ፊልም የሚጠቀስ ነው። 2015 ላይ ስለግለሰቡ ሕይወት ማወቅ የፈለጉ ተማሪዎች ደብዳቤ ፅፈውለት ሲመልስ «ሕይወቴ ባክኗል፤ በሞኝነት አሳልፌዋለሁ» ሲሉ ምላሽ ሰጥቶ እንደነበር አይዘነጋም፤ ጂሚ 'ዋይቲ' በልገር።
news-54672464
https://www.bbc.com/amharic/news-54672464
በአማራ ክልል በባለፈው ዓመት ብቻ 1 ሺህ 700 ሕፃናት ያለ እድሜያቸው ተድረዋል
በአማራ ብሔራዊ ክልል በ2012 ዓ.ም ከ1 ሺህ 700 በላይ የልጅነት ጋብቻዎች መፈጸማቸውን የክልሉ ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ የሴቶች ንቅናቄና ተሳትፎ ማስፋፊያ ዳይሬክተር አቶ ስማቸው ዳኜ ለቢቢሲ ገለፁ።
በአማራ ክልል የልጅነት ጋብቻ በስፋት የሚፈጸም መሆኑን ለቢቢሲ የገለጹት አቶ ስማቸው ዳኜ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው ቁጥሩ ይበልጥ እንዲጨምር ማድረጉን አስረድተዋል። ይህ መረጃ የተገኘው ስለጉዳዩ የሚቆረቆሩ ሰዎች በሚሰጡት መረጃ መሆኑን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ፣ የተጠናከረ የመረጃ ስርዓት ስለሌለ ቁጥሩ ይህ ብቻ ነው ለማለት ያስችግራል ብለዋል። አብዛኛው የልጅነት ጋብቻ የህግ ተጠያቂነትን ለመሸሽ በድብቅ የሚፈጸም መሆኑን የሚናገሩት ኃላፊው በዚህ ምክንያት ይፋ ሳይደረግ የሚቀር እንዳለም ጠቁመዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የህጻናት መርጃ ድርጅት /ዩኒሴፍ/ እኤአ 2019 ባደረገው ጥናት መሠረት በኢትዮጵያ የልጅነት ጋብቻ በስፋት ከሚታይበቸው 50 ወረዳዎች ውስጥ 23ቱ በአማራ ክልል ይገኛሉ። እንደጥናቱ ከሆነ የልጅነት ጋብቻ ምጣኔ ሃብታዊ ተጽዕኖው ብቻ ቢታይ እንኳን የልጅነት ጋብቻ በማስቀረት 1.5 በመቶ ዓመታዊ የገቢ ጭማሪ ማግኘት ይቻላል። በትምህርት ረገድ ከታየ ደግሞ የልጅነት ጋብቻውን በማስቀረት ልጆቹ አንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ቢያጠናቅቁ በሃገር ኢኮኖሚ ውስጥ ከ10-20 በመቶ ሚና ይኖራቸዋል። ሁለተኛ ደረጃን ካጠናቀቁ ደግሞ 15-25 በመቶ ከፍ ይላል። ይህ ደግሞ በየዓመቱ 646 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ የሚጨምር ነው ተብሏል። የኮሮናቫይረስ በኢትዮጵያ መከሰቱን ተከትሎ ትምህርት ቤቶች ከተዘጉ በኋላ የልጅነት ጋብቻ በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩ በግልጽ ታይቷል። ኮቪድ-19 ከመከሰቱ በፊት የልጅነት ጋብቻ በአማራ ክልል እየቀነሰ ነበር ያሉት አቶ ስማቸው "ይህ በጥናትም የተረጋገጠ ነው። የመቀነሱ ሁኔታም ፈጣን እንደነበረ ነው የሚያሳየው። ግን ባለፈው በኮሮና ስርጭት ትምህርት ቤቶች በመዘጋታቸው ህብረተሰቡ ትምህርት ሳይጀመር ሊቆይ ይችላል በሚል ትዳር ይያዙ የሚለው ነው እንጂ ጥሩ መሻሻል ነው የነበረው" ብለዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ የልጅነት ጋብቻ ቁጥር ሲጨምር በሽታውን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ሲሠራ ነበረው ግብረሃይል ጎን ለጎንም ስለልጅነት ጋብቻ መረጃ ለህብረተሰቡ እንዲያደርስ መደረጉን ጠቁመዋል። ከክልል እስከ ታችኛው የመንግስት መዋቅር ድረስ ግንዛቤ ለመፍጠር በተደረገው ጥረት ውስጥ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችንም አሳታፊ ማድረግ ተችሏል። ከኮሮና በተጨማሪ የማህበረሰቡ የግንዛቤ ደረጃ፥ ሥራ አጥነት እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ለልጅነት ጋብቻ መኖር በተጨማሪነት በምክንያትነት ተነስተዋል። ትምህርት ቤቶ ች በድጋሚ መከፈት መጀመራቸውን ተከትሎ ባለፈው ዓመት ትምህርት ላይ የነበሩ ተማሪዎች በሙሉ ወደ ትምህርት ገበታ እንዲመለሱ ጥረት እየተደረገ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ ተማሪዎች ከተመለሱ በኋላ ደግሞ በልጅነት ጋብቻ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ እንደሚሰበሰብ አስታውቀዋል። የልጅነት ጋብቻ በክልሉ የሚበዛባቸው አካባቢዎችን ለመለየት ጥናት እንደሚያስፈልግ የገለጹት አቶ ስማቸው የቅርብ ጊዜ ጥናት ባይኖርም ባላቸው መረጃ መሠረት " ሰሜንና ደቡብ ወሎ ምስራቅ ጎጃም እና ደቡብ ጎንደር አካባቢዎች ላይ ሰፊ እንደሆነ ነው የሚያሳየው" ብለዋል። በምስራቅ ጎጃምም የልጅነት ጋብቻ ይበዛባቸው ተብለው ከተለዩት ወረዳዎች መካከል ደባይ ጥላት ወረዳ አንዷ ናት። በወረዳው የልጅነት ጋብቻ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየየጨመረ ነው ያለው ያሉት የደባይ ጥላት ወረዳ የሴቶች፣ ህጻናት እና ወጣቶች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ነጻነት ዘለቀ ለቁጥሩ መጨመር አንደኛው ምክንያት ህብረተሰቡ ውስጥ ያለው "የአመለካከት ክፍተት" መሆኑን ጠቅሰዋል። ቀደም ሲል በተማሪዎች እና መምህራን በኩል መረጃ ይገኝ እንደነበር ጠቁመው የትምህርት ቤቶች መዘጋት ተጽዕኖ እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል። የልጅነት ጋብቻ አንዳይፈጸም የግንዛቤ ማስጨበጫ በየጊዜው እየተሰጠ መሆኑን ጠቁመው በዚህም ቀደም ሲል ከነበረው አንጻር መቀነሱን አስታውቀዋል። ከህብረተሰቡ የሚደርሳቸውን መረጃ መሠረት በማድረግ እንዲቋረጡ እና ወደ ሌላ ጊዜ እንዲዘዋወሩ የተደረጉ ጋብቻዎች አሉ ብለዋል። በወረዳ በሚገኙ "ደጋማ ቀጠናዎች አካባቢ" የልጅነት ጋብቻ እንደሚበዛ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ከ2012 እስከ 2017 ዓ.ም ባሉት አምስት ዓመታት የልጅነት ጋብቻ እና የሴት ልጅ ግርዛትን ለማስቀረት በሃገር ዓቀፍ ደረጃ ብሔራዊ ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቷል። እንደአማራ ክልል ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ከሆነ በክልሉ በ2017 ዓ.ም የልጅነት ጋብቻን ለማስቀረት እየተሠራ ነው። ኮቪድ-19 ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ከተገለጸ በኋላ በአማራ ክልል 500 በላይ ጋብቻ ተቋረጠ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 350ቱ ከተፈጸመ በኋላ ነው እንዲቋረጥ ተደረገው።
41147066
https://www.bbc.com/amharic/41147066
"ኢትዮጵያ ውስጥ የስኳር እጥረት የለም "
ሰሞኑን የንግድ ሚኒስቴርን ጨምሮ ሁሉም የከተማና የክልል ንግድ ቢሮዎች ስኳር በኮታ እያደሉ ቢሆንም የኢትዮጵያ መንግስት ለኬንያ 44 ሺህ ኩንታል ስኳር መላኩ በብዙዎች ዘንድ አግራሞትን ፈጥሯል።
ስኳር ለመግዛት የተሰለፉ ሰዎች በሃገሪቷ በአብዛኛው አካባቢዎች ስኳር ለማግኘት ብዙ ሸማቾች ይንገላታሉ። በዓመታት ውስጥም የስኳር ዋጋ መናርና በቀላሉ አለመገኘት ለብዙዎች ፈተና ሆኗል። ቢቢሲ ያነጋገራት ቤቴል ቡና በማፍላትና በመሸጥ የምትተዳደር ሲሆን በዚህ ሁለት ሳምንት ውስጥ ስኳር በማጣቷ የንግድ ቦታዋን ለመዝጋት እንደተገደደች ትናገራለች። ለዓመታት ከንግድ ሚኒስቴር በተተመነው ሂሳብ መሰረት ቀበሌዎች ስኳር የማከፋፈሉን ሥራ ወስደው ቆይተዋል። ቤቴልም ይህንን መሰረት በማድረግ ጉዞዋን ወደ ቀበሌ ብታደርግም አሉታዊ መልስ እንዳገኘች ትናገራለች። ከቀበሌ ውጪ በአንዳንድ ሱቆች ስኳር ለመግዛት ብትሄድም የአንድ ኪሎ ዋጋ ከ 28- 30 ብር ይደርሳል። ቤቴል ብቻ ሳትሆን ብዙዎች ንዴታቸውንና መሰላቸታቸውን በተለያዩ የማህበራዊ ድረ ገጾች እየተናገሩ ነው። በተለይም የሃገር ውስጥ የስኳር ፍላጎት ባለተሟላባት ሁኔታ ወደ ውጭ መላኩ ለብዙዎች ጥያቄ አጭሯል። በግንቦት ወር በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የኬንያ መንግስት 100 ሺህ ኩንታል ስኳር ለመግዛ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት 44ሺህ ኩንታል መላኩን የስኳር ኮርፖሬሽን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ጋሻው አይችሉህም ገልጸዋል። "ሃገሪቱ ውስጥ የስኳር እጥረት የለም " የሚሉት አቶ ጋሻው ከንግድ ሚኒስቴር በሚቀርብለት ኮታ መሰረት ኮርፖሽኑ 569 ሺህ ኩንታል ለተጠቃሚዎች እንደሚያቀርብ ይናገራሉ። ማከፋፈሉ ደግሞ በሸማች ማሀበራት፣ በህብረት ሥራ ማህበራት፣ በኢትፍሩትና በቀድሞው ጅንአድ አማካኝነት ይካሄዳል። ለዓመታት ኢትዮጵያ ወደ ውጪ ስኳር ከመላክ ታቅባ የነበረ ሲሆን በዚህ ዓመት ግን ለመጀመሪያ ጊዜ ልካለች። አቶ ጋሻው እንደሚሉት በሃገሪቱ ውስጥ ያሉ የስኳር ፋብሪካዎች 3.5 ሚሊዮን ኩንታል የሚያመርቱ ሲሆን 2 ሚሊዮን ኩንታል ደግሞ ከተለያዩ ሃገሮች ይገባል። በሃገሪቱ ውስጥ ያለው የስኳር ፍለጎት 6 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል እንደሆነ የሚናገሩት አቶ ጋሻው ይህ ፍላጎትም እየጨመረ እንደሆነ አክለው ይገልጻሉ። "በዓለም ገበያ መርህ መሰረት ይህ የተለመደ አሰራር ነው፤ ገበያው ጥሩ ሲሆን ወደ ውጭ ሃገራት መላክ እጥረት ሲያጋጥም ደግሞ ከሌሎች ሀገራት ማስገባት በብዙ ሃገራት የሚሰራበት ነው" ይላሉ። አቶ ጋሻው የምርት እጥረት የለም ቢሉም በሃገሪቷ ውስጥ በተደጋጋሚ የሚከሰተውን እጥረትም ጠንቅቀው ያውቁታል። ኢትዮጵያ ስኳር ለዜጎቿ ሳይዳረስ ለኬንያ መሸጥ ጀምራለች የስኳር ኮርፖሬሽን የአቅርቦት ሥራ እንደማያከናውን የሚናገሩት አቶ ጋሻው፤ ለተጠቃሚው በሚደርስበት የገበያ ስርጭት በኩል ችግሮች እንደሚታዩ ይገልፃሉ። "በህገውጥ መንገድ ስኳር ወደ ሱዳንና ወደ ሌሎች ሃገራት ይላካል፤ ነጋዴዎችም ትርፍ ፍለጋ ያለአአግባብ በማከማቸት የስኳር እጥረት እንዲያጋጥም አድርገዋል" ይላሉ። በሃገሪቱ ውስጥ ስድስት የስኳር ፋብሪካዎች ሲኖሩ በቀጣዮቹ ዓመታትም ስምንት የስኳር ፋብሪካዎች እንደሚከፈቱና እያደገ የመጣውንም የህዝቡን የስኳር ፍላጎት ሊያሟላ እንደሚችል አቶ ጋሻው ገልጸዋል። መንግሥት የምርት እጥረት የለም በሚልበት ሁኔታ ገበያው ላይ እጥረት ይታያል። ታዲያ የስኳር እጥረት ለዓመታት እየተንከባለለ የመጣ ጥያቄ ሆኖ እያለ፤ የገበያው ስርጭት ላይ ችግር መኖሩ ከታወቀ መፍትሔ ለማግኘት እንዴት አልተቻለም የሚል ጥያቄ ያሰነሳል። የኢኮኖሚ ባለሙያውና የኢንቨስትመንት አማካሪው አቶ ጌታቸው ተክለማርያም የስኳር ኢንደስትሪው በአጠቃላይ ለዘመናት በቆዩ ፋብሪካዎች የሚሰራ በምርታማነት ረገድ መሻሻል ያልነበሩት እንደሆነ ይገልጻሉ። ከ2000 ዓ.ም በኋላ በተያዘው እቅድ መሰረት ቀዳሚ ለሚባሉት ፋብሪካዎች የማሻሻያ፣ የማስፋፊያና የማሽን አደረጃጀት ለውጥ ማድረግ እንደተጀመረ አቶ ጌታቸው ይናገራሉ። እንደዚያም ሆኖ ሃገሪቷ ወደ ውጭ ከምትልከውና ከሌሎች ሃገራት ከምታስገባው ጋር ሲወዳደር የምታስገባው ይበልጣል። ይህንንም ሁኔታ ለመቀየር መንግስት በከፍተኛ ሁኔታ እየሰራ እንደሆነ አቶ ጌታቸው ይናገራሉ። "መንግስት ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ የሚያፈሰው በተወሰነ መልኩ ወደ ውጪ እንዲላክና በሃገሪቱ ውስጥ በተወሰነ መልኩ መደጎም እንዲችል አላማው አድርጎ እየተንቀሳቀሰ ያለን የኢንደስትሪ ዘርፍ ነው" ይላሉ አቶ ጌታቸው። በሃገሪቱ በውስጥ ያለው ፍላጎት ሳይሟላ እንዴት ስኳር ወደ ውጭ ትልካለች ለሚለው ጥያቄም አቶ ጌታቸው ሲመልሱ "የአንድ ሃገር ምርትን ወደ ሃገር ውስጥ ማስገባት ወይም ወደ ውጭ ሃገር መላክ የሚታየው ከዓለም የገበያ አንጻርና ለሃገሪቷ ከሚሰጠው ጥቅም አኳያ ነው" በማለት የሌሎችን ሃገራት ሁኔታም "ምርቶቻቸውን ወደውጭ የሚልኩት ሞልቶ ስለተረፋቸው አይደለም" በማለት ይናገራሉ። እንደምሳሌም የሚጠቅሱት ኢትዮጵያ ለጅቡቲ የኤሌክትሪክ ኃይል የምትሸጠው ከጂኦ ፖሊቲካል ጥቅሙ በተጨማሪ የዋጋ ልዩነት እንዲሁም የውጭ ምንዛሬ ስለሚያመጣ ነው። ይሄም ሆኖ ግን እንደ አቶ ጌታቸው አባባል፤ እንዲህ ህብረተሰቡ በቀጥታ የሚጠቀምባቸውን ምርቶች ሃገሪቷ ወደ ውጭ ሃገር እየላከች ህብረተሰቡ ግን ያን ምርት ለማግኘት የሚከፍለው ዋጋ እጅግ ብዙ ከሆነ፤ ከገቢ አንፃር የሚገኘውን ጥቅም ትርጉም አልባ ያደርገዋል። "ኢትዮጵያ ስኳር ወደ ውጭ ላከች ሲባል ህብረተሰቡ ስኳር ለመግዛት የሚከፍለውን ዋጋ፣ ረዥም ሰልፍና እንግልቱ ነው የሚታየው'' ይላሉ። በአንዳንድ አካባቢዎች የስኳር ዋጋ 40 ብርና ከዚያም በላይ የሚሸጥበትና ከፍተኛ እጥረት የሚያጋጥምበት ሁኔታ እንዳለ የሚገልጹት አቶ ጌታቸው፤ ይህንን ሁኔታ ስኳር ወደ ውጭ ከመላኩ በፊት ሊፈተሽና የፖሊሲ አቅጣጫ ሊሰጠው ይገባል ይላሉ። "ባለፉት አምስት ዓመታት የስኳር ምርት ብቻ ሳይሆን የገበያ ሰንሰለቱ እንዲሁም አስተዳደር ዝብርቅርቅ ያለ ነው። በዚህም ለረጅም ጊዜ መፍትሄ ሳይገኝ በመቆየቱ ተጠቃሚው እየተጎዳ ነው። በዚህ ያልተረጋጋ ገበያ ላይ ደግሞ ወደ ውጪ የመለኩን ጉዳይ ምክንያታዊ ለማድረግ አስቸጋሪ ነው።" በማለት አቶ ጌታቸው ይገልጻሉ።
48392891
https://www.bbc.com/amharic/48392891
ኡጋንዳ፡ ለጎዳና ተዳዳሪዎች ገንዘብ ወይም ምግብ መለገስ ተከለከለ
በኡጋንዳ መዲና ካምፓላ ለሚገኙ የጎዳና ተዳዳሪዎች ገንዘብ ወይም ምግብ መስጠት የሚከለክል ሕግ ወጥቷል። ሕጉን የሚተላለፉ ሰዎች ደግሞ 11 ዶላር (300 ብር ገደማ) ይቀጣሉ።
ካምፓላ ውስጥ እድሜያቸው ከ7 እስከ 17 አመት የሆነ ወደ 15,000 የሚጠጉ የጎዳና ተዳዳሪዎች እንደሚኖሩ የአገሪቱ መንግሥት ያሳወቀ ሲሆን፤ የከተማዋ ከንቲባ ኤሪያስ ሊክዋጎ፤ ሕጉ ወሲባዊ ጥቃት እንዳይደርስባቸውና እንዳይበዘበዙ ለመከላከል ያግዛል ብለዋል። • ኡጋንዳ ስደተኞችን ከእስራኤል ለመቀበል ስምምነት ማድረጓን አስተባበለች ህፃናት ከመኖሪያ መንደራቸው ተሰርቀው ወደከተማ እየተወሰዱ እንዲለምኑና በጠባብ ክፍል እንዲኖሩ እንደሚገደዱ የቢቢሲዋ ዲር ጀኔ ዘገባ ይጠቁማል። መንግሥት ችግሩን ለመቅረፍ ለጎዳና ተዳዳሪዎችና በወሲብ ንግድ ለተሰማሩ ግለሰቦች ቤት ማከራየት ከልክሏል። ህፃናትን አስከትለው የሚለምኑት ጋርአኒ ካቱሬጌ የተባሉ የ60 ዓመት ሴት እንደሚናገሩት፤ ሰዎች ህፃናትን ሲያዩ ስለሚራሩ ገንዘብ ይሰጧቸዋል። ስለዚህም ከህፃናት ውጪ መለመን አይፈልጉም። "ቢያስሩንም ግድ የለንም" ሲሉ የሕጉ መውጣት ለውጥ እንደማያመጣ ገልጸዋል። • ኡጋንዳ የዋትስአፕ ተጠቃሚዎችን ቀረጥ ልታስከፍል ነው ከንቲባው ኤሪያስ ሊክዋጎ በበኩላቸው ሕጉ ልጆቻቸውን ተጠቅመው ገንዘብ የሚካብቱ ቤተሰቦችና ደላሎችን እንደሚያስቆም ይናገራሉ። በሕጉ መሰረት፤ ጎዳና ላይ የሚነግዱና የሚለምኑ ቤተሰቦች እንደሚታሰሩም ገልጸዋል። "እየተጧጧፈ የመጣውን ልጆችን ከተለያዩ ከተሞች ወደካምፓላ የመውሰድ ንግድ ማስቆም እንፈልጋለን" ሲሉ ተደምጠዋል።
news-51471727
https://www.bbc.com/amharic/news-51471727
የዓለማችን የደስተኞች አገር ዜጎች የደስታቸው ምንጭ ምንድን ነው?
ምንም እንኳን በተለያዩ ጊዜያት የተፈጥሮ አደጋዎች ቢደጋግሟትም በፓሲፊክ ውቂያኖስ ላይ የሚገኙ ደሴቶች ስብስብ የሆነችው አገር በዓለማችን እጅግ ደስተኛ ዜጎች የሚኖሩባት እንደሆነች ታውቋል።
ቫኑዋቱ የሀገሪቱ ስም ሲሆን በፓሲፊክ ውቂያኖስ መሀል ላይ ነው የምትገኘው። ከአውስትራሊያ በ2000 ኪሎሜትር ርቅት ላይ የሚገኙት ደሴቶች ብዛታቸው ከ80 በላይ ነው። • ደስታን ለመፍጠር የሚረዱ አምስት መንገዶች • ደስታን አጥብቀን ስለፈለግን ለምን አናገኘውም? 'ሃፒ ፕላኔት ኢንዴክስ' የተባለው ሪፖርት የዓለማችንን ደስተኛ አገራት ደረጃ ያስቀምጣል። በዚህም መሰረት በጣም ደስተኛ ናቸው ከተባሉት አራት አገራት መካከል ቫኑዋቱ መካተት ችላለች። ደረጃው የሚወጣው የአገሪቱን ደህንነት፣ የእድሜ ጣሪያ፣ የእኩልነት ደረጃ እንዲሁም በርካታ ተፈጥሯዊ ሀብቶችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው ተብሏል። ለመሆኑ ይህችን ትንሽ አገር ደስተኛ ያደረጋት ምንድነው? ቫኑዋቱ እ.አ.አ. በ 1980 ከእንግሊዝና ፈረንሳይ ጥምር ቅኝ ግዛት ነጻነቷን ካገኘች በኋላ ማንኛውንም የአገሪቱ ክፍል ለማንኛውም ግለሰብም ሆነ አገር መሸጥ ክልክል ሆኗል። የደሴቶቹም ብቸና ባለቤቶች ለቫኑዋቱ ነባር ህዝቦች መሆኑ ታውጇል። በአውሮፓውያኑ 2011 ዓ.ም የቫኑዋቱ ስታቲስቲክስ ቢሮ ያወጣው መረጃ በደሴቶቹ መሬት ያላቸው ዜጎች ከሌላቸው ጋር ሲነጻጸር የበለጠ ደስተኛ መሆናቸውን ያሳያል። በአሁኑ ጊዜ አገሪቱ ካላት 280 ሺ ዜጋ መካከል ሦስት አራተኛ የሚሆኑት በገጠራማ ክፍሎች ውስጥ የሚኖሩ ሲሆን ሁሉም በሚባል መልኩ የራሳቸው የእርሻ መሬት አላቸው። አብዛኛዎቹም የሚበሉትን ምግብ ከማሳቸው ያገኛሉ። ከዚህ በተጨማሪ እንደ አሳማ፣ ኮኮናት እና ጭንቀትንና ህመምን ለማስታገስ የሚጠቅመው 'ካቫ' የተባለው ተክል በደሴቲቱ በቀላሉ ማግኘት የሚቻሉና አብዛኛውን ጊዜ ያለምንም ክፍያ ሰዎች የሚለዋወጧቸው ነገሮች ናቸው። ሌላኛው ለደስተኝነታቸው ምንጭ ነው ተብሎ የተቀመጠው ነገር ዜጎች ከቀደመው ባህላቸውና እሴቶቻቸው ጋር ያላቸው የጠበቀ ቁርኝት ነው። ከቤተሰብ አመሰራረት እስከ ልጅ አስተዳደግ፣ ከምግብ አሰራር እስከ የዕለት ተዕለት ግንኙነታቸው ድረስ ሁሉም ነገር ከባህልና እሴቶቻቸው ጋር የተቆራኙ ናቸው። ቫኑዋቱ ከ80 በላይ ደሴቶች የተወጣጣች እንደመሆኗ በርካታ ተፈጥሯዊ ሀብቶች አሏት። እጅን አፍ ላይ የሚያስጭኑ ናቸው የሚባልላቸው የቫኑዋቱ ደሴቶች ለሀገሬው ዜጎች የእለት ተዕለት መዝናኛዎች ናቸው። • የዓለማችን ቁጥር አንድ ሃቀኛዋ ሃገር • ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን? ቫኑዋቱ 'ምድራችን ለዘላለም' እንደ ማለት ሲሆን በደሴቶቹ የሚኖሩት ህዝቦች 139 ቋንቋዎችን ይናገራሉ። ይህ ደግሞ እጅግ በርካታ ቋንቋዎች ከሚነገርባቸው የዓለማችን አገራት መካከል አንዷ ያደረግታል። 92 በመቶ የሚሆነው የቫኑዋቱ ዜጋ አገር በቀል ቋንቋዎችን በደንብ መናገር ይችላል። በተጨማሪም አብዛኛው የአገሬው ዜጋ ተክሎች መቼ መተከል እንዳለባቸው፣ መቼ መሰብሰብ እንዳለባቸው፣ የቤተሰብ ታሪክ እና የተፈጥሮ እንክብካቤ እውቀታቸው ከፍተኛ ነው። የቫኑዋቱ ዜጎች እነዚህና ሌሎች በርካታ ያልተጠቀሱ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ሀብቶች ምክንያት ደስተኛ ቢሆኑም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን እንደ የባህር ጠለል ከፍ ማለት ያሉ የተፈጥሮ አደጋዎች ስጋት ሆነውባቸዋል። የተባበሩት መንግሥታት ዩኒቨርሲቲ በ2014 ባወጣው ሪፖርት መሰረት የቫኑዋቱ ደሴቶች ለተፈጥሯዊ አደጋዎች እጅግ የተጋለጡ እንደሆነ ገልጿል።
news-50985717
https://www.bbc.com/amharic/news-50985717
የጋና እግር ኳስ ፌዴሬሽን የብሔራዊ ቡድን አሠልጣኞችን በጠቅላላ አባረረ
የጋና እግር ኳስ ፌዴሬሽን የወንዶችና ሴቶች እንዲሁም ታዳጊ ብሔራዊ ቡድኖች አልጣኞች ከሥራ አባሯል።
ሐሙስ ምሽት ውሳኔውን ይፋ ያደረገው ፌዴሬሽኑ የብሔራዊ ቡድኑ አሠልጣኝ ኩዊሲ አፒያህን ጨምሮ የሥራ አጋሮቹ መበተናቸውን አሳውቋል። ፌዴሬሽኑ ውሳኔውን ለምን እንዳሳለፈ ሲያስረዳ የጋናን እግር ኳስ ለማነቃቃትና ወደ ቅድሞ ክበሩ ለመመለስ ነው ሲል አትቷል። አፒያህና አጋሮቹ ብቻ ሳይሆኑ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኞች እንዲሁም ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድኖች አሠልጣኞችም እንዲበተኑ ተደርጓል። በሙስና ምክንያት ባለፈው ጥቅምት ተበትኖ እንደአዲስ የተቋቋመው የጋና እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአዲሱ አመራር ሥር በርካታ ለውጦችን እያከናወነ ይገኛል። ፌዴሬሽኑ ባወጣው መግለጫ፤ «የብሔራዊ ቡድኖቻችን አሠልጣኞች እስከዛሬ ላደረጉልን ሁሉ እናመሰግናለን። በሄዱበት ሁሉ እንዲቀናቸውም እንመኛለን» ሲል የስንብት ቃሉን አሰምቷል። በውጤት ቀውስ የነበሩት የጥቁር ኮከቦቹ አሠልጣኝ አፒያህ ከብሔራዊ ቡድኑ ሊባረሩ እንደሚችሉ ግምቶች ቢኖሩም በእንደዚህ መልኩ ይሆናል ብሎ የጠበቀ አልበረም። የሴቶችም ሆነ የወንዶች ከ17 ዓመታች፣ ከ20 ዓመት በታች እንዲሁም ከ23 ዓመት በታች አሠልጣኞችና የቴክኒክ ባለሙያዎች ጠቅላላ ተበትነዋል። የጋና እግር ኳስ ፌዴሬሽን እንደ አዲስ ከተቋቋመ ወዲህ በርካታ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል። የቀድሞው የጋና እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት በሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ ፌዴሬሽኑ ቀልጦ እንደ አዲስ መሠራቱ አይዘነጋም።
news-50557826
https://www.bbc.com/amharic/news-50557826
የህንድ ሐኪሞች ከአንድ በሽተኛ 7.4 ኪሎ የሚመዝን ኩላሊት አወጡ
የህንድ ሐኪሞች የሁለት አራስ ልጆች ክብደት ያለው 7.4 ኪሎ ግራም የሚመዝን ኩላሊት ከአንድ ታማሚ ላይ ማስወገዳቸው ተነገረ።
ይህ ከፍ ያለ መጠን ያለው ኩላሊት ህንድ ውስጥ ከሰዎች አካል እንዲወጣ ከተደረጉት ሁሉ ትልቁ እንደሆነ የተነገረ ሲሆን መጠኑም ከሰባት ኪሎ በላይ ነው። የአንድ ጤናማ ሰው ኩላሊት በአብዛኛው ከ120 እስከ 150 ግራም ብቻ የሚመዝን መሆኑ ይህንን ክስተት ልዩ አድርጎታል። • የኢትዮጵያዊቷ ህክምና መቋረጥ በደቡብ አፍሪካ አነጋጋሪ ሆነ • ፊደል ያልቆጠሩት ኢትዮጵያዊት የቀዶ ህክምና ባለሙያ ኩላሊቱ እንዲወጣ የተደረገለት በሽተኛ 'አውቶሶማል ዶሚናንት ፖሊሲስቲክ' በተባለና በኩላሊቱ ዙሪያ የመጠን መጨመር ባስከተለ የኩላሊት ህመም ሲሰቃይ መቆየቱ ተነግሯል። በቀዶ ህክምናው የተሳተፉ አንድ ሐኪም እንዳሉት በዚህ አይነቱ በሽታ የተያዙ ሰዎች ላይ የኩላሊት መተለቅ ችግር ማጋጠም የተለመደ ነው። ነገር ግን ዶክተሩ አክለውም እንዲህ አይነቱ ችግር ያጋጠመው ኩላሊት በተወሰነ ደረጃ በአካል ውስጥ ሆኖ የማጣራት ሥራውን ካከናወነና የመታመም አሊያም የመድማት ምልክቶች ካላሳየ እንዲወጣ አይደረግም። • በርካቶች ከምጥ ይልቅ በቀዶ ህክምና መውለድን እየመረጡ ነው ይህ በሽተኛ ግን በጸረ ተህዋሲያን ሊታከም ያልቻለ ህመም ስላጋጠመውና ከመጠን በላይ እየተለቀ የመጣው ኩላሊቱም የመተንፈስ ችግር በማስከተሉ አማራጭ በመታጣቱ እንዲወገድ መደረጉን ዶክተሩ ገልጸዋል። የቀዶ ህክምናውን ያደረጉት ዶክተሮች ይህን ያህል መጠን ያለው ኩላሊት ከበሽተኛው አካል ውስጥ እናገኛለን ብለው ባለመጠበቃቸው በክብደቱ መደነቃቸውን ተናገረዋል። ዶክትር ሳቺን ካቱሪያ፤ "በውስጥ አካላት የምርምር መጽሔቶች ላይ ከፍተኛ ክብደት ያላቸው ኩላሊቶች ቢመዘገቡም በጊነስ የዓለም ክብረ ወሰን መዝገብ ላይ በክብደቱ የተመዘገበው ኩላሊት 4.5 ኪሎ ግራም ነው። ከዚህ ቀደም ግን በአሜሪካ ውስጥ 9 ኪሎ፣ በኔዘርላንድስ ውስጥ ደግሞ 8.7 ኪሎ የሚመዝን ኩላሊት ተገኝቷል" ብለዋል። • ዛፎችና የአእምሮ ጤና ምን ያገናኛቸዋል? • አሜሪካ ሱስ ያለባቸውን በቀዶ ጥገና ልታክም ነው ዶክተሩ አክለውም ይህንን ኩላሊት በጊነስ የዓለም ክብረ ወሰን መዝገብ ላይ እንዲሰፍር ለማድረግ ውሳኔ ላይ እንዳልደረሱ አመልክተው ነገር ግን "እያሰቡበት" እንደሆነ ገልጸዋል። የእንግሊዝ ብሔራዊ የጤና አገልግሎት ድረ ገጽ እንደሚለው፤ ፖሊሲስቲክ የተባለው የኩላሊት በሽታ የተለመደ በዘር የሚተላለፍ ሲሆን፤ ህሙማኑ በ30 እና 60 የዕድሜ ክልል ውስጥ ሲሆኑ የጤና ችግርን የሚያስከትል ነው። በሽታው ቀስ በቀስ የኩላሊት ተግባርን በማዳከም በመጨረሻም ሥራ እንዲያቆም ሊያደርገው ይችላል።
news-41938445
https://www.bbc.com/amharic/news-41938445
እስያ የሚገኙት ትራምፕ ወደ ቪየትናም አቅንተዋል
የዚህ ዓመት የእስያ-ፓሲፊክ ምጣኔ ሃብታዊ ትብብር (አፔክ) ጉባዔ አስተናጋጅ በሆነችው ቪየትናም የሚገኙት ትራምፕ በጉባዔው መክፈቻ ላይ ያደርጋሉ የተባለው ንግግር እየተጠበቀ ነው።
አሜሪካ ወደፊት በቀጣናው ስለሚኖራት ሚና እንዲሁም በንግድ እና ምጣኔ ሃብታዊ ዕድገት ትብብሮች ዙሪያ ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። ትራምፕ 'ቅድሚያ ለአሜሪካ' በተሰኘው መርሃቸው መሠረት ከቀጣናው የንግድ ስምምነት መውጣታቸውና በጃፓንና ቻይና ተይዞ የሚገኘውን የኃይል ሚዛን ለመመለስ ቃል መግባታቸው የሚታወስ ነው። የእስያ-ፓሲፊክ ምጣኔ ሃብታዊ ትብብር (አፔክ) የ21 ሃገራት ስብስብ ሲሆን ከዓለማችን ጠቅላላ የሃገር ውስጥ ምርት ዕድገት 60 በመቶውን ይይዛል። ትራምፕ ስልጣን በያዙ ማግስት 'ትራንስ ፓሲፊክ ፓርትነርሺፕ' ከተባለው በአሜሪካና በ12 የእስያ ሃገራት መካከል ከነበረው ስምምነት ሃገራቸውን ማግለላቸው ይታወሳል፤ ምክንያታቸውም ስምምነቱ ለአሜሪካ የሚጠቅም አይደለም የሚል ነበር። በትራምፕ እና በሩስያው መሪ ፑቲን መካከል ሊደረግ የሚችለው ንግግር እውን ይሁን አይሁን እስካሁን የታወቀ ነገር የለም። ለ30 ዓመታት ያክል አሜሪካ 'በአፔክ' አማካይነት በአህጉረ እስያ ከሚገኙ እንደ ጃፓንና ቻይና ካሉ የዓለማችን ምጣኔ ሃበታዊ ማማዎች ጋር የጠበቀ ግንኙነት መሥርታ ቆይታለች። ነገር ግን ከትራምፕ በኋላ ነገሮች መንገዳቸውን ቀይረዋል። ለዘመናት ከእስያ ጋር የነበረው የንግድ ግንኙነት አሜሪካንን ጎድቷታል ሲሉ መደመጥ ጀምረዋል። ዶናልድ ዛሬ የሚያደርጉት ንግግር ከዚህ በኋላ አሜሪካ በቀጣናው የሚኖራት ሚና ምን ሊመስል እንደሚችል ይጠቁማል ሲሉ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ይናገራሉ። ነገር ግን የአፔክ አባል ሃገራት ቻይናንም ጨምሮ ከአባልነት በመሰረዝ የራሳቸውን ጥምረት ሊመስርቱ እያሰቡ እንደሆነም እየተነገረ ይገኛል።
news-52740284
https://www.bbc.com/amharic/news-52740284
የህንድ ሆስፒታል ኮሮናቫይረስ ከተገኘባቸው እናቶች ከ100 በላይ ህጻናትን አዋለደ
በህንዷ ሙምባይ ከተማ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል ከ100 በላይ የሚሆኑ ጤናማ ህጻናት በኮሮናቫይረስ ከተያዙ እናቶች ማዋለዱን አስታወቀ።
ሆስፒታሉ ባለፈው የሚያዝያ ወር ቫይረሱ ካለባቸው እናቶች ካዋለዳቸው 115 ህጻናት ውስጥ መጀመሪያ ላይ ሦስቱ ቫይረሱ እንደለባቸው የተነገሪ ቢሆንም በድጋሚ በተደረገ ምርመራ ከኮቪድ-19 ነጻ መሆናቸው መረጋገጡን ዶክተሮች ተናግረዋል። ለመውለድ ወደ ሆስፒታሉ ከመጡት በበሽታው ከተያዙ እናቶች መካከል ሁለቱ በሆስፒታሉ ውስጥ የሞቱ ሲሆን አንዷ ልጇን ከመገላገሏ በፊት ነበር ህይወቷ ያለፈው። የህንድ የገንዘብና የመዝናኛ ከተማ በሆነችው ሙምባይ እስካሁን ወደ 20 ሺህ የሚጠጉ ነዋሪዎቿ ላይ ቫይረሱ የተገኘ ሲሆን ከ730 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ህይወታቸው አልፏል። በሎክማኒያ ቲልካ በተባለው አጠቃላይ ሆስፒታል ውስጥ የኮሮናቫይረስ ካለባቸው እናቶች ከተወለዱት ህጻናት ከግማሽ የሚበልጡት በቀዶ ህክምና የተወለዱ ሲሆን የተቀሩት ግን በተፈጥሯዊ መንገድ መውለዳቸውን የሐኪም ቤቱ ኃላፊዎች ተናግረዋል። ከተወለዱት ህጻናት መካከል 56ቱ ወንዶች ሲሆኑ 59ኙ ድግሞ ሴቶች ናቸው። በሽታው ከተገኘባቸው እናቶች መካከል ሃያ ሁለቱ ወደ ሌላ ሆስፒታል የተላኩ ሲሆን በቫይረሱ እንዴት ሊያዙ እንደቻሉ አልታወቀም። "ቫይረሱ ከተገኘባቸው ወላዶቹ መካከል አብዛኞቹ የበሽታውን ምንም አይነት ምልክት ያላሳዩ ሲሆን አንዳንዶቹ ብቻ ናቸው ትኩሳትና ትንፋሽ ማጠር የታየባቸው ሲሉ ሐኪሞቹ ተናግረዋል።
news-53808306
https://www.bbc.com/amharic/news-53808306
ደላላ፡ ሚሊየነር የሆኑ ‹‹ኢንተርናሽናል የበይነ መረብ› አጭበርባሪ ደላሎች
ጋብሬል ቤልትረን ከኡራጓይ ወደ ማያሚ የመጣው እውቅ የከበሮ ተጫዋች ለመሆን ነበር፡፡ ከአምስት ዓመት በፊት የቤት ኪራይ መክፈል አይችልም ነበር፡፡
ተማሪ ከነበረችው ሴት ጓደኛው የምሳ ይበደርም ነበር፡፡ ከዚያ በድንገት ተተኮሰ፡፡ 20 ሚሊዮን ዶላር አገኘ፡፡ ነገሩ በበይነመረብ ንግድ ውስጥ በዕቃ አቅራቢና በደንበኛ መሀል የሚደረግ የድለላ ሥራ ነው፡፡ ‹‹ድሮፕሺፒንግ›› ይባላል፡፡ ድለላ ለማለት እንኳ ይከብዳል፡፡ ሥራው እንዴት ነው የሚሰራው የሚለውን ቆየት ብለን እንመለስበታለን፡፡ በርካታ ሰዎች ይህንን ትርፉ የሚያቋምጥ ሥራ በመሥራት ላይ ናቸው፡፡ ለዚህ ሥራ የሚያስልገው ቆንጆ ኢንተርኔትና ቆንጆ ላፕቶብ ብቻ ነው፡፡ ጠዋት ከብርድልብስ ሳይወጡ መሰራት ይችላል ይላሉ፣ ትርፍ ያጋበሱበት፡፡ እንዴት? ሻጮቹ እንዲያውም የሚሸጡትን ዕቃ አይዳስሱትም አይነኩትም፡፡ መጋዘን የላቸውም፡፡ ግን እየሸጡ ያተርፉበታል፡፡ ሂደቱ እንዴት እንደሆነ እንመልከት፡፡ ይሄ የበይነ መረብ ደላላ (dropshipper) ላፕቶፑን ይከፍትና ርካሽ የሆነ ዕቃ ከአንዱ የቻይና በይነመረብ ገበያ ይፈልጋል፡፡ ከዚያ ይኼ ደላላ ምን ያደርጋል? በቅመም ያበደ ሻይ እንደሚባለው በቀለም ያሸበረቀ ድረ ገጽ ያሰራና ይህንን ርካሽ ዕቃ በድረ ገጹ ይለጥፈዋል፡፡ ድረ ገጹ ግን ምርቱ 'ኦሪጅናሌ' አሜሪካ ሰራሽ ወይም ጀርመን ሰራሽ ሆኖ ነው የሚለጠፈው፡፡ ከዚያ ይኸው የበይነመረብ ደላላ ወደ ማኅበራዊ የትስስር መድረኮች ይሄድና ከፍሎ 'ያበደ' ማስታወቂያ ለዚህ እቃ ያሰራል፡፡ በፌስቡክ፣ ቴሌግራም ወይም ኢንስታግራም እጅግ ተጽእኖ ፈጣሪ ለሚባሉ ሰዎች ገንዘብ እየከፈለ ይህንን ምርት ያስተዋውቃል፡፡ ይህን የሚያደርገው ምርቱ ላይ ጥርጣሬ እንዳይፈጠር በማለም ነው፡፡ ስለዚህ አንድ ደንበኛ ይህንን ዕቃ በሚያዝበት ጊዜ ከገዥው መጀመሪያ ገንዘቡን ይቀበላል፡፡ ደላላው ከገዢው ገንዘቡ ሲደርሰው ነው ምርቱን ከቻይና የሚገዛው፡፡ ከዚያ ዕቃው በቀጥታ ወደ ገዢው ይጫናል፤ ከቻይና፡፡ የበይነ መረቡ ደላላ ዕቃውን አልነካውም፣ አልዳሰሰውም፡፡ ነገር ግን ገንዘብ ያገኛል፡፡ በሌላ ቋንቋ ይህ ደላላ በመንፈስ በገዥና በሻጭ መሀል ያለ ሰው ነው፡፡ የሚደንቀው ታዲያ ይህ ሥራ ወንጀል አለመሆኑ ነው፡፡ ምኑ ነው ወንጀል፡፡ ምናልባት ከሚገባው በላይ አዳንቆና አዳምቆ ማስታወቂያ መሥራት? ችግሩ በዚህ ሕጋዊ ሥራ ውስጥ የሚጨበጥ ነገር ስለሌለ አጭበርባሪዎች መኖራቸው ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደንበኞች ገንዘብ ከፍለው እቃቸው ግን አይላክላቸውም፡፡ ይህ በሕጋዊዎቹ የበይነ መረብ ደላሎች ዘንድ የሚፈጸም ሳይሆን በነሱ ስም የሚፈጸም ወንጀል ስለሆነ ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡ ጋብሬል በዚህ መንገድ ቻይና ስሪት የሆኑ የብሔራዊ አሜሪካ እግር ኳስ ሊግ (NFL) ምርቶችን ይቸበችባል፡፡ ሰዎች የሚገዙት የአሜሪካ ኦሪጅናሌ ምርት እየመሰላቸው ነው፡፡ በዚህ መንገድ በአንድ ወር $50,000 ዶላር አተረፈ፡፡ ከዚያ በኋላ ግን የተጭበረበረ እቃ ሸጬ አላውቅም ይላል፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሰዎች አንድ ጊዜ ጥሩ ገንዘብ ካገኙ በኋላ ይሰወራሉ፡፡ በወር ውስጥ ጥሩ ትርፍ ካገኙ በኋላ እቃ መላክ የሚያቆሙ ደላሎችም አሉ ብሏል ለቢቢሲ። አንዳንድ ጊዜ እቃዎቹ የተባሉት አይነቶች ይሆኑና ነገር ግን የአእምሮ ጥበቃ መብታቸው በማይጠበቅበት አገር ይመረታሉ፡፡ እነሱን ስንሸጥ ገንዘብ እናገኛለን፡፡ አንዳንድ ጊዜ ምርቶቹ የሌላ ሆነው ማሸጊያቸው የታዋቂ ድርጅት ስም ሊለጠፍበት ይችላል፡፡ ኬቨን ዴቪድ ሌላኛው የበይነ መረብ ደላላ ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት የተጭበረበረ ነገር ውስጥ ገብቼ አላውቅም ይላል፡፡ ሆኖም ጓደኞቹ ተመሳስለው የተሰሩ ምርቶችን በመሸጥ በመቶ ሺህ ዶላሮች አጋብሰዋል፡፡ በተለይ የአፕል ገመድ አልባ የጆሮ ማዳመጫዎች AirPods ተቸብችበዋል ይለል፡፡ ሐሳዊ ምርቶች ድሮፕሺፒንግ ለበይነመረብ ንግድ አዲስ ሐሳብ አይደለም፡፡ አሁን አዲስ ያደረገው ማኅበራዊ ሚዲያው ነው፡፡ እነዚህ ደላሎች የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪዎችን ስለሚጠቀሙ በቀላሉ የተትረፈረፈ ገበያ ማግኘት ችለዋል፡፡ ለዚህም ነው ትርፋቸው አስደንጋጭ የሆነው፡፡ ቀደም ብሎ እነዚህ ሰዎች ያልዳሰሱትን ምርታቸውን ያስተዋውቁ የነበረው በኢቤይ ወይም በተለመዱ መገናኛ ዘዴዎች ነበር፡፡ አሁን ነገሩ ሁሉ ተቀየረ፡፡ ሰፊ ተቀባይነት ያገኙ የማኅበራዊ ሚዲያ ዝነኞች ምርት አስተዋዋቂ ከሆኑ በኋላ ገበያው ደርቷል፡፡ ኮርተኒ ካርዳሺያን ሳራ መባርኪ ማግኔቲክ ኤስ ኤል ለሚባል ድሮፕሺፒንግ ድርጅት ውስጥ ሰርታለች፡፡ ይህ ድርጅት የሚሸጠው የራሱን ብራንድ ነው፡፡ ሆኖም ስለ ድሮፕሾፒንግ አስገራሚ ሚስጥሮችን ታውቃለች፡፡ ሳራ ለቢቢሲ ክሊክ እንደገለጸችው የዝነኞቹ የካርዳሺያን ቤተሰብ የሆነችው ኮርተኒ ካርዳሺያን ይህንን ምርት በኢኒስታግረም አስተዋወቀችው፡፡ ኮርተኒ ካርዳሺያን በኢኒስታግራም 100 ሚሊዮን ተከታይ አላት፡፡ ይህን የተጭበረበረ የውበት ምርት ለማስተዋወቅ ሁለት መቶ ሺህ ዶላር ተከፈላት፡፡ የተከፈላት ብዙ ቢመስልም ድርጅቱን ትርፍ በትርፍ አደረገችው፡፡ በገበያ ጎርፍ ተመታ፡፡ በተጽእኖ ፈጣሪዎች ማስተዋወቅ በአንድ ጊዜ እጅግ ዝነኛ ብራንድ (የንግድ መታወቂያ) ለማግኘት አቋራጭ መንገድ ሆኗል፡፡ ሳራ እንዲህ ትላለች፡- ብዙ ሰዎች እንደ ኮርተኒ ካርዳሺያን ያለ ከፍተኛ ዝና ያለው ሰው ምርትን እንዲያስተዋውቅ ምርቱ የግድ ኦርጂናሌና ያልተጭበረበረ መሆን እንዳለበት ያስባል፡፡ ያ ውሸት ነው፡፡ አንዳንድ እውቅ ሰዎች ብቻ ናቸው ሐሳዊ ምርት አስተዋውቁልን ሲባሉ እምቢ የሚሉት፡፡ ብዙዎቹ ችግር የለባቸውም፡፡
news-46361404
https://www.bbc.com/amharic/news-46361404
ምግብ ማብሰልና ማጽዳት የቤት ውስጥ ጥቃቶችን ለመቀነስ
ሩዋንዳ ውስጥ ወንዶችን የቤት ውስጥ ስራ እንዲሰሩ በማድረግ በቤት ውስጥ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመቀነስ የሚረዳ ፕሮግራም በሙከራ ላይ ነው።
ሙሆዛ ዣን ፒዬር ከዚህ በፊት ባለቤቱን ይደበድባት ነበር። የባለቤቱ ስራ ልጅ ለመውለድና እነሱን ለመንከባከብ ብቻ እንደሆነ ያስብም ነበር። '' የአባቴን ፈለግ ነበር የተከተልኩት። አባቴ በቤት ውስጥ ምንም አይነት ስራ አይሰራም ነበር።'' ይላል። " ልክ ወደ ቤት ስገባ የሆነ ያላለቀ ስራ ካለ ሁሌም ቢሆን እንጣላለን። ሰነፍ ነሽ እያልኩ እጮህባታለሁ። ለምን ወደ ቤተሰቦችሽ ተመልሰሽ አትሄጂም እላታለሁ።'' ነገር ግን በቤታችን ውስጥ ድንገት ትልቅ ለውጥ መጣ። ሙሆዛ ዣን ፒዬር ምግብ ማብሰልና ቤት ማጽዳት ተማረ። • በአለም ላይ በየቀኑ 137 ሴቶች በህይወት አጋሮቻቸውና በቤተሰቦቻቸው ይገደላሉ • ታሪክ እየቀየሩ ያሉት ሴቶች የፒዬር መንደር ምዉሊሬ የምትሰኝ ሲሆን የምትገኘው በምስራቃዊ ሩዋንዳ ነው ። በዚህች መንደር በመተዋወቅ ላይ ያለው የሙከራ ፕሮጀክት ምስጋና ይግባውና ወንዶች በቤት ውስጥ ምግብ እንዲያበስሉና ሌሎች ስራዎችም መስራት እየተበረታቱ ነው። ፕሮጀክቱ 'ባንደቤርሆ' ይባላል። እንደ ፒዬር ላሉ የአካባቢው ወንዶች ጥሩ ተሞክሮ እያስተማረ ነው። ፒዬር ትምህርት ቤት ገብቶ ምግብ ማብሰል፣ ቤት ማጽዳትና ልጆችን መንከባከብ የሚችልበትን መንገዶች ተምሯል። ''በክፍሉ ውስጥ ወንዶች ቤት ማጽዳት ይችላሉ ወይ ተብለን እንጠየቃለን፤ የሁላችንም መልስ አዎ ይችላሉ ነው።'' '' በመቀጠል ከእናንተ መካከል ማነው ቤቱን የሚያጸዳ ሲሉን፤ ማንም እንላለን።'' ምንም እንኳን ፒዬር የቤት ውስጥ ስራዎች ባለቤቱ ብቻ መስራት እንዳለባት ቢያስብም፤ የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎች ምግብ የማብሰልና ቤት የማጽዳት ስልጠና ሰጥተውታል። ''ትምህርት ቤት የተማርነውን ወደ ቤት ተመልሰን ተግባራዊ ለማድረግ እንሞክራለን።'' ይላል ፒዬር። ተማሪዎቹ ወደ ትምህርት ቤት ሲመለሱ ፈተና ኦለባቸው። በቤት ውስጥ የሰሩትን ምግብ ደግመው እንዲሰሩ ይጠየቃሉ። "አሁን ጣፋጭ ምግቦች መስራት ችያለው፤ የልጆቼንም ልብሰ የማጥበው እራሴ ነኝ። ጽዳቱንም ቢሆን ቀጥ አድርጌ ይዤዋለው።'' ሲል በደስታ ይናገራል ፒዬር። ነገር ግን እንዲህ ተለውጦ ቤቴ ቤቴ ማለቱ በብዙ ጓደኞቹ ዘንድ ነቀፌታንና ፌዝ አስከትሎበታል። በተለይም መጀመሪያ አካባቢ ነገሮች ሁሉ ከባድ እንደነበሩ ያስታውሳል። '' ትክክለኛ ወንድ ምግብ አያበስልም'' ይሉት ነበር። ''ቤተሰቦቼና ጓደኞቼ እንደውም ባለቤቴ የሆነ መድሃኒት ሳትሰጠው አይቀርም ብለው እስከማሰብ ደርሰው ነበር።'' በቤት ውስጥ ስራዎችን መስራት ከጀመረ ወዲህ፤ ከሌላ ጊዜው በተለየ ልጆቹ እሱን መቅረብ መጀመራቸውንና ባለቤቱ የሙዝ ንግድ መጀመሯን ይናገራል። በዚህ ምክንያትም የቤተሰባቸው ገቢ መጨመሩንና ልጆቹ በአግባቡ መመገብ መጀመራቸውን በኩራት ይናገራል። "ባለቤቴም ቢሆን እንደ ድሮው በቁጣ አትመልስልኝም። ቁጭ ብለን ተወያይተን በነገሮች ላይ እንወስናለን።'' • "ማንም መብታችንን ሊሰጠን ስለማይችል፤ ሴቶች ማንንም ሳይጠብቁ በራሳቸው መታገል አለባቸው" • የተነጠቀ ልጅነት ፍርሃትና ነጻነት የፒዬር ባለቤት ሙሳብዪማና ዴልፊን ከዚህ በፊት ትንሽ ነጻነትና ብዙ ፍራቻ እንደነበረባት ታስታውሳለች። ''በህይወቴ ስራ ሰርቼ ገንዘብ ማግኘት እቻላለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር። ምክንያቱም ስለ እንደዚህ አይነት ነገሮች ለማሰብ ጊዜውም አልነበረኝም። ሁሌም ቢሆን ቤት ውስጥ የሆነ ያላለቀ ስራ ይኖራል።'' ዴልፊን ሁሌም ቢሆን ሌሊት 11 ሰአት በመነሳት ወደ ሙዝ ገበያው ስትሄድ፤ ፒዬር ደግሞ ቤት ውስጥ አራት ልጆቻቸውን ይንከባከባል። ''ደክሞኝ ከስራ ስገባ ቤቱ ንጹህ ሆኖ፣ ቆንጆ ምግብ ቀርቦ ይጠብቀኛል።'' ትላለች። ሴቶችና ከሴቶች ጋር ተያይዘው የሚነሱ የተሳሳቱ ሃሳቦችን ለመቀየር አልሞ ደቡብ አሜሪካ ውስጥ የተቋቋመው ፕሮጀክቱ፤ ህጻናትን የመንከባከብና ሌሎች የቤት ውስጥ ስራዎችን ወንዶች 50 በመቶ ማከናወን ሲጀምሩ እውነትም እኩልነት ሰፍኗል ማለት ነው ብሎ ያምናል። አስተባባሪዎቹ በሰሩት የዳሰሳ ጥናት መሰረት ባለፉት ሁለት ዓመታት ሩዋንዳ ውስጥ ምግብ ማብሰልና ህጻናትን ስለመንከባከብ ስልጠና የወሰዱ አባቶች ሚስቶቻቸውን የመደብደብና ሁሉንም ስራ እነሱ እንዲሰሩ የመጠበቅ አስተሳሰባቸው በእጅጉ ቀንሷል። የፒዬርና የዴልፊን የተቀየረ አስተሳሰብ ለቤተሰባቸው ብቻ ሳይሆን ለመላ መንደሪቱ ትልቅ ትምህርት ሆኗል። ''በመኖሪያ መንደራችን የባልና የሚስት አለመስማማት ሲኖርም ሆነ ሌላ ግጭት ሲፈጠር ለማስታረቅ እኛ የምናቀርበው ሃሳብ ሁሌም ቢሆን ተቀባይነት ያገኛል።'' "ምክንያቱ ደግሞ እኛ በቤታችን ውስጥ ሰላማዊ ኑሮ ስለምንኖር ነው።''