id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
news-45518374
https://www.bbc.com/amharic/news-45518374
የአማዞን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ለቤት አልባ ድሆች 2 ቢሊየን ዶላር ሊለግሱ ነው
የአማዞን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጄፍ ቤዞስ ባቋቋሙት የግብረ ሰናይ ድርጅት አማካኘነት ቤት ለሌላቸው ድሆች መኖሪያ ቤት ለመስራት እና ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት 2 ቢሊየን ዶላር (55 ቢሊየን ብር ገደማ) ፈሰስ ሊያደርጉ ነው።
ባለጸጋው እቅዳቸውን በትዊተር ገጻቸው ላይ ይፍ ባደረጉበት ወቅት፤ የግብረ ሰናይ ድረጅቱ ስም 'ደይ ዋን ፈንድ' ይባላል ብለዋል። 164 ቢሊየን የሚገመት ሃብት እንዳለቸው የሚነገርላቸው ቤዞስ በበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ አይሳተፉም እየተባሉ ይወቀሱ ነበር። ቤንዞስ እአአ 1994 የመሰረቱት አማዞን ከጥቂት ሳምንታት በፊት በአሜሪካ ከሚገኙ በአክሲዮን ድርሻ ከተቋቋሙ ኩባንያዎች መካከል ከአፕል በመቀጠል 1 ትሪሊየን ዶላር የሚያወጣ ኩባንያ ለመሆን ችሏል። • 'በእኔ በኩል ሒሳቤን ዘግቻለሁ ' አቶ ታምራት ላይኔ • ቄሮ፣ ሴታዊት፣ ፋኖ…የትውልዱ ድምጾች ምንም እንኳ የአማዞኑ መስራች 2 ቢሊየን ዶላር ለበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ ለማዋል ቢያስቡም፤ በርካቶች ግን ከቢል ጌትስ እና ከማርክ ዙከርበርግ ጋር በማነጻጻር ሁለት ቢዮን ዶላሩ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም እያሉ ነው። ከማይከሮሶፍት መስራቾች መካከል አንዱ የሆኑት ቢል ጌትስ በራሳቸው እና ባለቤተቸው ስም በተቋቋመው ቢል ኤንድ ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን አማካኝነት ከ10 ቢዮን ዶላር በላይ ለበጎ አድራጎት ሥራዎች ፈሰሰ አድረገዋል። የፌስቡክ መስራቹ ማርክ ዙከርበርግ ከማህበራዊ ሚዲያዎች የሚያተርፈውን 99 በመቶ ያክሉን ለበጎ ሥራዎች ላይ እንደሚያውል ቃል ግበቷል። የዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ባለቤት የሆኑት የአማዞን መስራቹ ቤዞስ 'ብሉ ኦሪጅን' በተሰኝ የህዋ ፕሮጀክት ላይ እየሰሩ ይገናሉ።
news-56156447
https://www.bbc.com/amharic/news-56156447
ለኢትዮጵያውያንና ለአፍሪካውያን ፈር ቀዳጅ ድል ያስመዘገበችው ፋጡማ ሮባ
ፋጡማ ሮባ የመጀመሪያውን የሴቶች ማራቶን ፈር ቀዳጅ ድሏን እ.ኤ.አ. በ1996 በሞሮኮ ማራክሽ ነበር የተቀዳጀችው።
በመቀጠልም ከሁለት ወር በኋላ በሮም ማራቶን አሸናፊ ሆነች። ከሮም አሸናፊነት በኋላም በ1996 በአትላንታ አሜሪካ በሚደረገው የኦሊምፒክ ውድድር በ2:26:05 በሆነ ሰዓት አንደኛ በመሆን አጠናቀቀች። በወቅቱ ፋጡማን በመከተል ሁለት ደቂቃ ዘግይተው የሩሲያዋ ቫለንቲና ይጎሮቫና ጃፓናዊቷ ዩኩ አርሞሪ 2ኛና 3ኛ በመሆን ተከታትለው ገብተዋል። ከ1997 እስከ 1999 የተካሄዱ የቦስተን ማራቶን ውድድሮች በተከታታይ ያሸነፈችውን ፋጡማ የ'ቦስተኗ ንግሥት' የሚል ቅጽል ስም አግኝታበታለች። ለአትሌት አበበ ቢቂላ ትልቅ ፍቅር እንደላት የምትናገረው አትሌት ፋጡማ ሮባ "አቤን በደንብ እወደዋለሁ፤ አደንቀዋለሁ። አቤን እኔ ብቻ ሳልሆን መላው ዓለም ያደንቀዋል" ትላለች። ለዓመታት ከአገርና ከአትሌቲክሱ መድረክ ርቃ የቆችው የኦሊምፒኳ ኮከብ አትሌት ፋጡማ ከቢቢሲ ጋር ባደረገችው ቆይታ ስለ ህይወቷ እንዲህ ብላለች። [የተጠቀሱት ዓመታት በሙሉ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ናቸው] ስለ አትሌቲክስ ምንም የማውቀው ነገር የለኝም በ1970 ዓ.ም በአርሲ ዞን ሌሙና ቢልቢሎ ወረዳ፣ ሁሉሌ ካራ በሚባል ስፍራ ተወለድኩ። ገጠር ውስጥ ከአርሶ አደር ቤተሰብ ነው የወጣሁት። ኑሮዬና ትምህርቴም እንደ ማንኛውም የገጠር ልጅ ነበር። በገጠር እንዳደጉት ልጆች ከብቶችን ስጠብቅና ቤተሰብን ስረዳ ስለቆየሁ ቶሎ ትምህርት ቤት አልገባሁም። ትምህርት ቤቱም ከቤተሰቤ ርቆ ስለሚገኝ በደንብ ካደግሁ በኋላ በደርሶ መልስ 14 ኪሎ ሜትር በእግር ተጉዤ እማር ነበር። ያደግኩበት ገጠር ቴሌቪዥንም ሆነ ሬዲዮ አልነበረም። ስለዚህ ስለአትሌቲከስ የማውቀው ነገር አልነበረም። ይሁን እንጂ በትምህርት ቤት ውስጥ እኣወዳደሩ ነጥብ ይይዙልን ነበር። አስተማሪያችን መሃረብ ይዞልን "ማን ቀድሞ ይነካል" እያለ ያወዳድረን ነበር። እኔ ከሴቶች ጋር ተወዳድሬ አሸንፋለሁ። ወንዶችንም ቢያመጡ አሸንፍ ነበር። ከዚያ በኋላ ከትምህርት ቤቴ ተመርጬ በወቅቱ አውራጃ ወደሚባለው፣ ከዚያ ደግሞ ክፍለ አገር ለሚባለው ተወክዬ መወዳደር ጀመርኩኝ። በዚሁ ነው እንግዲህ ወደ አዲስ አበባ መጥቼ የተለያዩ የስፖርት ቡድኖች መኖራቸውን ያወቅኩት። ክፍለ አገርን ወክዬ በተወዳደርኩበት ጊዜ የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ቡድን አይቶኝ ሃጂ ቡልቡላ የሚባለል ሰው ላከብኝ። እርሱም ቡድኑ እንደሚፈልገኝ፣ ትምህርቴንም እንድማር፣ ደሞዝም እንደሚከፍሉኝ ነገረኝ። እኔም ቤተሰቤን ሳማክር ብዙም ደስተኛ ስላልነበሩ ሊከለክሉኝ አሰቡ። ይሁን እንጂ ሃጂን ካዩ በኋላ ፈቀዱልኝ፤ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ መጣሁ። ተስፋ መቁረጥና ወደ ስኬት ጉዞ በ1994 እኤአ ቤልጂየም አገር ነበርኩኝ። እዚያም በአገር አጭር ውድድሮች ላይ በመሮጥ ተሳተፍኩኝ። ቤልጂየም በቆሁበት ወቅት አንድ ማራቶን የምትሮጥ ሴትን በፓሪስ ማራቶን ለምን ካንቺ ጋር አልሮጥም ብዬ ጠየቅኳት። እርሷም ነይ አብረን እንሂድ አለችኝ። ከዚያም በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1994 በተካሄደው የፓሪስ ማራቶን ሳልዘጋጅ ተወዳደርኩ። ውድድሩ ሲጀመር ከሌሎች አትሌቶች ጋር መሮጥ አቃተኝ። ጥለውኝ ሄዱ፤ ይሁን እንጂ ወደ 35ኛው ኪሎ ሜትር ላይ ደረስኩባቸው። ከእነርሱ ጋር ግን መቀጠል አልቻልኩም ጥለውኝ ሄዱ። በጣም ደክሞኝ ስለነበር ውሃ ጠጣሁ። ውሃውም ሆዴን ወጥሮ ያዘኝ። ውድድሩንም ብጨርስም ሁለተኛ አልሮጥም ብዬ ነበር። ወደ አገር ቤት ስመለስ ግን ዶ/ር ወልደ መስቀል ኮስትሬ ማራቶን እንድሮጥ ጠየቁኝ። ከዚያ በኋላ ስልጠና ወስጄ እንዴት ማራቶን እንደምሮጥ ተማርኩ። ወደ ሞሮኮ ሄጄም ማራካሽ ላይ ማራቶን ተወዳደርኩ። ከሞሮኮ ሞሮኮሽ እስከ ቦስተን በ1996 የማራካሽ ማራቶን ላይ ብዙም ስልጠናና ልምምድ ሳላደርግ ነበር የተሳተፍኩት። በውድድሩም 'ቢ ካታጎሪ' የሚባለውን አምጥቼ ተመለስኩ። ከሁለት ወር በኋላ በሮም ማራቶን ተወዳድሬ፣ 'ኤ ካታጎሪ' የሚባለውን ውጤት አምጥቼ በኦሊምፒክ ውድድር ለመሳተፍ የሚያስችለኝን ነጥብ አገኘሁ። በዚሁ ልምምድ አድርጌ በ1996 በተካሄደው የአትላንታ ኦሊምፒክ ለመሳተፍ ሄድኩኝ። ኦሊምፒክ ትልቅ ውድድር ነው። የአትላንታ ኦሊምፒክ ለእኔ ከተሳተፍኩባቸው ሁሉ ትልቁ ውድድር ነበር። ለውድድሩ በበቂ ተዘጋጅቼ ነበር። ግን ፍርሃት በውስጤ ስለነበረ አሸንፋለሁ የሚል ግምት አልነበረኝም። ካሸነፍኩ በኋላ ግን ትልቅ ደስታ ነው የተሰማኝ። አሰልጣኞቼም በውድድሩ ታሸንፋለች ብለው አልጠበቁም ነበረ። በኦሊምፒክ ማራቶን ውድደድር ላይ በማሸነፍ የመጀመሪያዋ ሴት አፍሪካዊት መሆኔ በጣም አስደሰተኝ። የሚረሳም አይደለም። ከአትላንታ በኋላ በ1997፣ 98፣ 99 በቦስተን ማራቶን ውድድሮች በተከታትዬ ለሦስት ጊዜ አሸንፌያለሁ። ሩጫ ማቆምና ቤተሰብ በ2004 ነበር ሩጫ ያቆምኩት። በዚያ ጊዜ ለመውለድ ብዬ ነበር ሩጫ ያቆምኩት፤ ከዚያ በኋላ ግን አልተመለስኩበትም። አሁን የሁለት ልጆች እናት ነኝ። የመጀመሪያው ልጄ 15 ዓመት ሁለተኛዋ ደግሞ 13 ዓመቷ ናቸው። ሩጫ ካቆምኩ በኋላ ምንም እየሰራሁ አልነበረም። ልጆቼን እያሳደኩ ነበር። ይሁን እንጂ እነርሱ ካደጉልኝ በኋላ አንደንድ ሥራዎችን ለመስራት እያሰብኩ ነው። የአሁኑን አትሌትክስ ብዙም አልከታተልም። ይሁን እንጂ በተለያዩ ውድድሮች ላይ ስመለከት ጠንካራ አትሌቶች አሉ። እኛ ስንገባበት የነበረውንም ሰዓት እያሻሻሉ ነው። ከአሰልጣኞቻቸው ጋር ከተስማሙ እና በደንብ ከሰሩ ከዚህ የበለጠ ነጥብ ማምጣት እንደሚችሉ ተስፋ አደርጋለሁ።
48545499
https://www.bbc.com/amharic/48545499
እግር ኳስ ተጫዋቹ ወንድወሰን ዮሐንስ እንዴት ተገደለ?
ትናንት ህይወቱ ያለፈው የነቀምት ከነማ ተጫዋች ወንድወሰን ዮሐንስ አሟሟት አጠያያቂ ሆኗል።
የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት ኃላፊው አቶ አዲሱ አረጋ ትናንት ምሸት በነቀምት ከተማ በአንድ ሆቴል ላይ በተወረወረ ቦንብ አንድ ሰው ተገደለ ቢሉም ሟቹን በቅርብ የሚያውቁ እና የሆስፒታል ምንጮች ደግሞ ወጣቱ የተገደለው በጥይት ተመትቶ ነው ይላሉ። አቶ አዲሱ አረጋ ትናንት ከምሽቱ 1 ሰዓት አካባቢ ነቀምት ከተማ 'ፋክት' በሚባል ሆቴል ላይ በተወረወረ ቦምብ ሶስት ሰዎች መቁሰላቸውንና አንድ ሰው መገደሉን በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አስፈረዋል። አቶ አዲሱ የሟቹንም ሆነ በቦንብ ፍንዳታ ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር አልጠቀሱም። • የደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ስጋት ላይ ነን ይላሉ • ስለ ግንቦት 27፤ 1983 የጎተራው ፍንዳታ ምን ያስታውሳሉ? • ድምጻዊ ዳዲ ገላንን ገድሏል የተባለው የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት አቶ ቾምቤ ገ/ህይወት የነቀምት ከነማ አሰልጣኝ ሲሆኑ፤ ትናንት የተገደለው ወጣት የቡድናቸው ተጫዋች መሆኑን አረጋግጠዋል። አቶ ቼምቤ እንደሚሉት ሟች ወንድወሰን ዮሐንስ ህይወቱ ያለፈው በቦንብ ፍንዳታ ሳይሆን ከፍንዳታው በኋላ በተተኮሰበት ጥይት መሆኑን ያስረዳሉ። ''እራት ለመብላት አምስት ሆነን ወጣን። እነሱ የፈረንጅ ምግብ መብላት ፈልገው 'ፋርም ላንድ' ወደሚባል ሆቴል ገቡ። እኔ ደግሞ እነሱ ካሉበት ጎን ወደሚገኘው 'ፋክት' ሆቴል ገባሁ። ቦምቡ የፈነዳው እኔ የነበርኩበት ሆቴል ውስጥ ነው'' የሚሉት አቶ ቾምቤ፤ በፍንዳታው ጉዳት ባይገጥማቸውም፤ ከተፈጠረው ግርግር ለማምለጥ ሲሞክሩ የመፈነካከት ጉዳት እንደደረሰባቸው ያስረዳሉ። ''ቦምቡ ከፈነዳ በኋላ እነ ወንደሰን ደውለው ደህን መሆኔን ጠይቀውኝ ነበር'' የሚሉት አቶ ቾምቤ፤ ተጫዋቾቹ በፍጥነት ከሚገኙበት ሆቴል ወደ መኖሪያ ቦታቸው እንዲሄዱ እንደነገሯቸው አቶ ቾምቤ ያስታውሳሉ። ''ህክምና ለማግኘት ወደ ግል ክሊኒክ ሄጄ ነበር። እዛ እያለሁ አንድ የጸጥታ ኃይል አስከባሪ የሆነ ሰው ስልክ ደውሎ ወንድሰን በጥይት ተመትቶ ሆስፒታል እንደሚገኝ ነገረኝ'' በማለት ትናንት የነበረውን ሁኔታ ያስረዳሉ። አቶ ቾምቤ ሆስፒታል ሲደርሱ ተጨዋቹ ህይወቱ አልፎ ነበር። በነቀምት ሆስፒታል ሃኪም የሆኑት ዶ/ር ዳምጠው ጋረደው ተጨዋቹ በጥይት ተመትቶ ህይወቱ ማለፉን ያረጋግጣሉ። ''በስተቀኝ በኩል ከብብቱ ስር የተመታ ሲሆን ጥይቱ በግራ በኩል ወጥቷል'' ያሉት ዶ/ር ዳምጠው፤ ወንድወሰን ወደ ሆስፒታል የመጣው ከምሸቱ ሁለት ሰዓት አከባቢ እንደሆነ እና ሆስፒታል ሲደርስም ህይወቱ አልፎ እንደነበረ ይናገራሉ። ወንድወሰን ለምን እና ማን በተኮስው ጥይት እንደተገደለ የታወቀ ነገር የለም። ስለጉዳዩ ማብራሪያ ለመጠየቅ ፖሊስን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። 'ፋክት' በሚሰኘው ሆቴል ላይም ማን እና ለምን የቦምብ ጥቃት እንደሰነዘረ ባይገለጽም፤ አቶ አዲሱ ትናንት በፌስቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ ቦምቡን የወረወሩ ተጠርጣሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ገልጸዋል። 'ፋክት' ሆቴል በነቀምት ከተማ በርካታ ተጠቃሚ ካላቸው ታዋቂ ምግብ ቤቶች መካከል አንዱ መሆኑን ለመረዳት ችለናል። በተጨማሪም የምስራቅ ወለጋ ዞን ፖሊስ ጽ/ቤት፣ ፍርድ ቤት እና የዞኑ አስተዳደር ቢሮዎች 'ፋክት ሆቴል' በሚገኝበት አቅራቢያ ይገኛሉ።
news-56797850
https://www.bbc.com/amharic/news-56797850
ሱፐር ሊግ፡ 'ታላላቆቹ ስድስት' የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በሱፐር ሊግ ለመሳተፍ ተስማሙ
አርሰናል፣ ቼልሲ፣ ማንቸስተር ዩናይትድ፣ ማንቸስተር ሲቲ፣ ሊቨርፑል እና ቶተንሀም በአውሮፓ ሱፐር ሊግ ለመሳተፍ ተስማሙ።
የአውሮፓ እግር ኳስን ባልተጠበቀ መልኩ የነቀነቀው ይህ ውሳኔ በርካቶችን ያስገረመ ሲሆን ከጣልያን ኤሲ ሚላን፣ ኢንተር ሚላን እና ጁቬንቱስ በሱፐር ሊግ ለመሳተፍ ወስነዋል። ከስፔን ደግሞ ሪያል ማድሪድ፣ ባርሴሎና እና አትሌቲኮ ማድሪድ ይቀላቀላሉ። የአውሮፓ ሱፐር ሊግ እንደገለጸው መስራች ቡድኖቹ የሳምንቱ ግማሽ ላይ ጨዋታዎቹን ለማድረግ የተስማሙ ሲሆን የአገራቸው ሊግ ጨዋታ ላይ ግን መሳተፋቸውን አያቆሙም። የአውሮፓ ሱፐር ሊግ አክሎም' "እቅዱ ተግባራዊ መደረግ ሲችል የመጀመሪያው የውድድር ዓመት ወዲያውኑ ይጀመራል። ሶስት ተጨማሪ ቡድኖች ደግሞ ሊጉን እንደሚቀላቀሉ ይጠበቃል'' ብሏል። ከዚህ በተጨማሪም የወንዶቹ የአውሮፓ ሱፐር ሊግ ውድድር ከተጀመረ በኋላ የሴቶች ሱፐር ሊግም እንደሚጀመር ተገልጿል። እሁድ ዕለት የአውሮፓ ሱፐር ሊግ ዜና መሰማቱን ተከትሎ የዩናይትግ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን፣ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር እና የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ውሳኔውን አውግዘውታል። የዓለም እግር ኳስ አስተዳዳሪው ፊፋ በበኩሉ ቀደም ብሎ ለመሰል ውድድሮች እውቅና እንደማይሰጥና በውድድሩ የሚሳተፉ ተጫዋቾች በዓለም ዋንጫ ላይ ላይሳተፉ እንደሚችሉ አስታውቋል። የአውሮፓ ሱፐር ሊግ ዜና ከተሰማ በኋላ ፊፋ "ለእግር ኳስ ሲባል በዚህ ውሳኔ ላይ የተሳተፉት አካላት በሙል የተረጋጋ፣ ጠቃሚና ሁሉንም የሚጠቅም ውይይት ሊያደርጉ ይገባል" ብሏል። የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበርም ትናንት ባወጣው መግለጫ በአውሮፓ ሱፐር ሊግ የሚሳተፉ ተጫዋቾች ከሁሉም የአገር ውስጥ ውድድሮች ሊታገዱ እንደሚችሉ ያስታወቀ ሲሆን በአውሮፓም ሆነ በዓለም መድረክ ከብሔራዊ ቡድን ውጪ ሊሆኑ እንደሚችሉ ገልጿል። የአውሮፓ ሱፐር ሊግ ደግሞ በመግለጫው "ወደፊት መስራች ክለቦቹ ከአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር እና ፊፋ ጋር አብሮ መስራት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ውይይት ያደርጋሉ'' ብሏል። ሊጉ 20 ተሳታፊ ብድኖችን የሚያካትት ሲሆን 12ቱ መስራች ክለቦች እና እስካሁን ስማቸው ያልተጠቀሰው ሶስት ክለቦች በፍጥነት ይቀላቀላሉ። ከአገር ውስጥ የሊግ ውድድሮች ደግሞ አምስት ቡድኖች ተወዳድረው የአውሮፓ ሱፐር ሊግን ይቀላቀላሉ። በእቅዱ መሰረት የአውሮፓ ሱፐር ሊግ በየዓመቱ ነሀሴ ወር ላይ የሚመጅር ሲሆን ጨዋታዎቹም የሳምንቱ አጋማሽ ላይ ይደረጋሉ። ተሳታፊዎቹ 20 ቡድኖችም በሁለት ምድቦች ተከፍለው በደርሶ መልስ ጨዋታ ይፋለማሉ። ከሁለቱ ምድቦች ከአንድ እስከ ሶስት ሆነው የሚጨርሱት ቡድኖች ለእሩብ ፍጻሜ የሚያልፉ ሲሆን አራተኛና አምስተኛዎቹ ደግሞ እርስ በርስ ተጋጥመው አሸናፊው እሩብ ፍጻሜውን ይቀላቀላሉ። የአውሮፓ ሱፐር ሊግ እንደሚለው ይህ ውድድር ከአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ በተሻ መልኩ ገንዘብ የሚያስገኝ ሲሆን ተሳታፊ ክለቦችም ጠቀም ያለ ትርፍ ያገኙበታል።
43644589
https://www.bbc.com/amharic/43644589
እነ እስክንድር ነጋ ከእሥር ተፈቱ
ያለፉትን አስራ ሁለት ቀናት በእስር ያሳለፉት እስክንድር ነጋና ተመስገን ደሣለኝን ጨምሮ 11 ፖለቲከኞች፣ ጦማሪያንና ጋዜጠኞች ዛሬ ከእሥር መለለቃቸው ተሰማ።
ከተፈችዎቹ መካከል አንደኛው የሆነው ተመስገን ደሣለኝ ወንድም ታሪኩ ደሣለኝ ለቢቢሲ እንደተናገረው ግለሰቦቹ አመሻሽ ገደማ ነው ከእስር የተለቀቁት። ታሳሪዎቹ ሰኞ ማታ ፍርድ ቤት በጠራቸው ጊዜ ለመቅረብ የራስ ዋስትና ሞልተው ቢፈርሙም እንዳልተፈቱ መዘገባችን የሚታወስ ነው። በድጋሚ እሥሩ ምክንያትት ለጤና መታወክ ተጋልጦ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ ሆስፒታል ገብቶ ህክምና ካገኘ በኋላ ወደ እስር ተመልሶ ነበር። ታሪኩ እንደሚለው የተመስገን ጤና መሻሻል ቢያሳይም አሁንም ማስታገሻ መድሃነት እየወሰደ ይገኛል። የተለቀቁት 11 ግለሰቦች እስክንድር ነጋ፣ ተመስገን ደሳለኝ፣ አንዱዓለም አራጌ፣ አዲሱ ጌታነህ፣ ዘላለም ወርቅ አገኘሁ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ በፍቃዱ ኃይሉ፣ ወይንሸት ሞላ፣ ይድነቃቸው አዲስ፣ ስንታየሁ ቸኮል እና ተፈራ ተስፋዬ ናቸው። በተመሳሳይ ዘገባ በባህር ዳር ከተማ ታስረው የነበሩ ምሁራን፣ የፖለቲካ መብት አቀንቃኞች እና ፖለቲከኞች በትናንትናው ዕለት መፈታታቸው ይታወሳል። ከተፈችዎቹ መካከል አንደኛው የሆኑት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፍልስፍና መምሀሩ አቶ በለጠ ሞላ በእስር ቆይታቸው ወቅት ሲጎበኛቸው በነበረው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ መደነቃቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ካለፈው ወርሃ ሕዳር ጀምሮ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዕውቅናን አግኝተው ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ ለመመሥረት ሲንቀሳቀሱ እንደነበር ያስታወሱት አቶ በለጠ፤ ለእስር መዳረጋቸው እንቅስቃሴያቸውን እንደማይገድበው እና ይልቁንም ፓርቲውን የማወቀር እንቅስቃሴያችውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
news-55226710
https://www.bbc.com/amharic/news-55226710
ትግራይ፡ የተባበሩት መንግሥታት በትግራይ የሕግ የበላይነትን መመለስ አስፈላጊ ነው አለ
በትግራይ ክልል የሕግ የበላይነትን በአፋጣኝ መመለስ አስፈላጊ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ ገለጹ።
የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እንዳሉት መንግሥት በትግራይ ክልል ውስጥ "የሰብአዊ መብቶችን ባከበረ ሁኔታ በአፋጣኝ የሕግ የበላይነትን በፍጥነት መመለስ ያስፈልጋል" ብለዋል። ዋና ጸሐፊው በሰጡት አጭር መግለጫ ላይ ጨምረው እንዳሉት በክልሉ የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊትና በህወሓት ኃይሎች መካከል ውጊያ ከተካሄደ ከአራት ሳምንታት በኋላ "ያለው ወቅታዊው ሁኔታ በጣም አሳስቦኛል" ብለዋል ግጭቱን ተከትሎ ከ40 ሺህ በላይ ሰዎች ድንበር ተሻግረው ወደ ሱዳን የገቡ ሲሆን ሌሎች በርካቶች ደግሞ ቤት ንብረታቸውን ጥለው ሸሽተዋል ተብሏል። በትግራይ ክልል ውስጥ ጭምር ጥቂት የማይባሉ ሰዎች ሠብአዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን፤ ለዚህም ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ "ነጻ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መስመር" እንዲመቻች ጠይቀዋል። ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናት ለእርዳታ አቅርቦት ሠራተኞች የሚያገለግል መተላለፊያ መስመር እንደሚከፍቱ አስታውቀው ነበር። በአብዛኛው የትግራይ ክልል ውስጥ ለሳምንታት ተቋርጦ በቆየው የኮምዩኒኬሽን መስመር ምክንያት ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎችን ለማረጋገጥ አዳጋች ሆኗል። የትግራይ ክልልን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በቅርቡ እንደተናገሩት የፌደራል መንግሥቱ በትግራይ ክልል ውስጥ "ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር" እንዲሁም የህወሓት መሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየተሰራ ነው ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በድጋሚ ከህወሓት አመራሮች ጋር የሚደረግ ማንኛውም አይነት ድርድር እንደማይቀበሉት አሳውቀዋል። ከተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ በተጨማሪ የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይ ተወካይ ጆሴፍ ቦረል ፎንቴሌስም መንግሥት የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መስመር እንዲከፍት ጠይቀዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት "ሕግ ማስከበር" ያለውና ከሦስት ሳምንታት በላይ የቆየው ወታደራዊ ዘመቻ የክልሉ ዋና ከተማ ከተቆጣጠረ በኋላ እንዳበቃ ቢገልጽም የእርዳታ ድርጅቶች ድጋፍ የሚፈልጉ ሰዎችን በመድረስ እርዳታ ለማቅረብ እንዳልቻሉ እየተናገሩ ነው። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ትናንት ባወጣው መግለጫ ላይ የዜጎችን ደኅንነት መጠበቅ የፌደራል መንግሥቱ ቀዳሚ ትኩረት እንደሚሆን አመልክቶ፤ ከተባበሩት መንግሥታት ተቋማት ጋር በመሆን በግጭቱ ምክንያት ለችግር የተጋለጡ ዜጎችንና በትግራይ ክልለ ውስጥ ባሉ የስደተኞች መጠለያ ውስጥ የሚገኙትን ስደተኞች ጭምር ለመርዳት እየሰራ መሆኑን ገልጿል። በፌደራል መንግሥቱና የትግራይ ክልልን ሲያስተዳድር በነበረው ህወሓት መካከል ለወራት የቆየው አለመግባባት ወደ ወታደራዊ ግጭት ከተሸጋገረ በኋላ ግጭቱን በመሸሽ ከቀያቸው የሸሹና በአስር ሺዎች ወደ ጎረቤት አገር መሰደዳቸው የተነገረ ሲሆን በክልሉ ውስጥ ሆነው የሰብአዊ እርዳታ የሚፈልጉ በርካታ ሰዎች እንዳሉ የእርዳታ ድርጅቶች ገልጸዋል።
43340810
https://www.bbc.com/amharic/43340810
ኢትዮጵያና ሩሲያ የኒውክሌር ማበልፀጊያ ፕሮግራም በጋራ ለማካሄድ ተስማሙ
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።
ሚኒስትሮቹ ከውይይታቸው በኋላም የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም ሁለቱ ሃገራት የኒውክሌር ቴክኖሎጅ ማዕከል ግንባታ በኢትዮጵያ ውስጥ በጋራ ለማቋቋም መስማማታቸውን ገልፀዋል። የኒውክሌር ማበልፀጊያ ፕሮግራሙ በሁለቱ ሃገራት መካከል ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላ ወዲያውኑ እንደሚጀመር ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ተናግረዋል። ሁለቱ ሃገራት 120 ዓመታት የዘለቀ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዳላቸው የተናገሩት ሚኒስትሩ የምጣኔ ሐብት፣ ኢንቨስትመንት፣ በአፍሪካ ቀንድ የሰላም ሁኔታ እና በሌሎች ሁለቱ ሃገራት በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ መስማማታቸውን ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ተናግረዋል። የኒውክሌር ማበልፀጊያ ፕሮግራሙ ለሰላማዊ አገልግሎት መሆኑንም ገልፀዋል። በተጨማሪም ከአዲስ አበባ ወደ ሞስኮ በየቀኑ የቀጥታ በረራ ለመጀመር ስምምነት ላይ መደረሱም በዚሁ መግለጫ ላይ ተነግሯል።
news-47053067
https://www.bbc.com/amharic/news-47053067
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ሶማሊያ ውስጥ በአል-ሻባብ ይዞታ ላይ ጥቃት ፈፀምኩ አለ
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ሶማሊያ ውስጥ ባለው ጽንፈኛ እስላማዊ ቡድን አል-ሻባብ ይዞታ ላይ ባካሄደው የአየር ድብደባ ከባድ ጉዳት እንዳደረሰ አስታወቀ።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ላይ ጥቃቱን የፈጸመው ባለፈው ሳምንት ከባይደዋ ከተማ በስተምሥራቅ 75 ኪሎ ሜትሮች እርቆ በሚገኘውና ቡርሃይቤ በተባለ የአል-ሻባብ ይዞታ ላይ እንደሆነም አመልክቷል። ሐሙስ ዕለት ጥር 16 ቀን 2011 ዓ.ም አየር ኃይሉ ፈጸምኩ ባለው የአየር ጥቃት በጽንፈኛ እስላማዊ ቡድኑ ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱን ገልጾ፤ በተዋጊ ሄሊኮፕተሮች በተፈፀመው በዚህ ጥቃት 35 የአልሻባብ ታጣቂዎች ተገድለዋል ብሏል። • ለናይሮቢው የሽብር ጥቃት አልሸባብ ኃላፊነቱን ወሰደ • የኢትዮጵያ አየር ኃይል አልሸባብ ላይ ጥቃት ፈጸመ ከተገደሉት የአል-ሻባብ አባላት መካከልም የቡድኑ የዘመቻ ኃላፊና በፈንጂ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን የሚያቀናብረው ቡድን መሪ እንደሚገኙበት መረጋገጡን መግለጫው አመልክቷል። አየር ኃይሉ በአልሻባብ ላይ አካሄድኩት ባለው በዚህ ድብደባ አራት የሚደርሱ ተሽከርካሪዎችና አምስት ከባድ መትረየሶችን ማውደሙን ጨምሮ ገልጿል። ይህንን ጥቃት በተመለከተ ማረጋገጫ ለማግኘት የሶማሊያ መንግሥት ባለስልጣናትን ለማናገር ያደረግነው ሙከራ ያልተሳካ ሲሆን አልሻባብም ስለጥቃቱ ምንም ያለው ነገር የለም። ይህ ጥቃት አልሻባብ ሶማሊያ ውስጥ በሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ ለፈጸመው የደፈጣ ጥቃት አጸፋ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል። የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዜያትና ቦታዎች የአልሻባብ ይዞታዎችና ታጣቂዎች ላይ ጥቃት እንደፈጸመ ሲዘገብ ቆይቷል።
news-48343180
https://www.bbc.com/amharic/news-48343180
ኢኳዶር የዊክ ሊክስ መስራች ጁሊያን አሳንጅን እቃዎች ለአሜሪካ ማስረከብ ጀመረች
ኢኳዶር በለንደን ኤምባሲዋ የቀሩ የጁሊያን አሳንጅ እቃዎችን ለአሜሪካ ማስረከብ ጀመረች።
እቃዎቹ ኤሌክትሮኒክስ ፣ፅሁፎች ፣ የህግ ሰነዶችና የህክምና ሪፖርቶች ይገኙባቸዋል። የአሳንጅ ጠበቃ እርምጃውን በጥገኝነት የሂደት ታሪክ ፈፅሞ የማይጠበቅ ሲሉ አውግዘውታል። •"ማህበሩ የማያልፈው ቀይ መስመር የስራ ማቆም አድማ ነው"-ዶ/ር ገመቺስ ማሞ የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ፕሬዚዳንት •የታሪክ መማሪያ መጻሕፍት ለምን ይከለሳሉ? አሜሪካ የተለያዩ አገራት ሚስጥሮችን ያጋለጠው ዊኪሊክስ ድረ ገፅ መስራች አሳንጅ ከእንግሊዝ ተላልፎ እንዲሰጣት ትፈልጋለች። ዊኪ ሊክስ በርካታ የአሜሪካ ምስጢራዊ ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ መረጃዎች ይፋ ማውጣቱ የሚታወስ ነው። ትውልደ አውስትራሊያዊው አሳንጅ ኮምፒውተሮችን በመጥለፍ እንዲሁም በርካታ የመንግስት ምስጢሮችን በማሾለክ ተወንጅሏል። በዚህም እስከ አምስት አመት ሊፈረድበት ይችላል።
news-52683708
https://www.bbc.com/amharic/news-52683708
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 27 የፖለቲካ ፓርቲዎችን መሰረዙን አስታወቀ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአገሪቱ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች በድጋሚ ለመመዝገብ የሚጠበቅባቸውን መመዘኛዎች አላሟሉም ያላቸውን 27 ፓርቲዎችን መሰረዙን አስታወቀ።
ቀደም ሲል በነበረው አሰራር ተመስርተው በአገሪቱ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች እስከ መጋቢት ወር መጀመሪያ ድረስ በአዲሱ ህግ ላይ የተቀመጡ መስፈርቶችን እንዲያሟሉ ተጠይቀው እንደነበር ቦርዱ አመልክቷል። ቦርዱ እንዳለው በሕጉ መሰረት የሚጠበቅባቸውን ሰነድ ማቅረብ ያልቻሉና የሚያሟሉበት ጊዜ እንዲራዘም የጠየቁ የፓለቲካ ፓርቲዎች የነበሩ ሲሆን ከእነዚህ መካከል የ13ቱ አጥጋቢ ምክንያት ባለማቅረባቸው እንዲሰረዙ ተወስኗል። በተጨማሪም ሌሎች 14 ፓርቲዎች ከቦርዱ በተደረገው ጥሪ መሰረት የሚያስፈልጉ ሰነዶችን ያላቀረቡ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር መዋሃዳቸውን በመግለጻቸው መሰረዛቸው ተነግሯል። ከእነዚህ ባሻገር ከ106 የፖለቲካ ፓርቲዎች 76 የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰነዶችን ያቀረቡ ሲሆን በሕጉ መሠረት ተሟልተው የቀረቡ ስለመሆናቸው ምርመራ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል። ፓርቲዎቹ ያቀረቧቸው ሰነዶችና ማስረጃዎች ላይ የሚደረገው ምርመራ ሲጠናቀቅ የተቀመጡትን መስፈርቶች አሟልተው በእንቅስቃሴያቸው መቀጠል የሚችሉትን ቦርዱ ይፋ እንደሚያደርግ አመልክቷል። ከዚህ በተጨማሪ ሁለት ፓርቲዎች በውስጥ ችግር የተነሳ ሰነዶችን ማቅረብ አለመቻላቸው ስለታመነ ጠቅላላ ጉባኤያቸውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽን በሚያበቃበት ወቅት አንዲያከናውኑ ቦርዱ ወስኖ፤ ሌሎች ሰነዶቻቸው እየተገመገሙ እንደሆነ ተገልጿል። የተጨማሪ ጊዜ ጥያቄ አቅርበው ተቀባይነት ሳያገኙ የተሰረዙ ፓርቲዎች 1. የኢትዮጵያውን ዴሞክራሲያዊ አንድነት ንቅናቄ (ኢዴአን) - የመስራች አባላት ዝርዝር ያላቀረበ፣ ጉባኤ ያላካሄደ 2. የገዳ ስርአት አራማጅ ፓርቲ (ገሥአፓ) - የመስራች አባላት ዝርዝር ያላቀረበ 3. የየም ብሔረሰብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( የብዴን) - የመስራች አባላት ዝርዝር ያላቀረበ፣ ጉባኤ ያላካሄደ 4. የደንጣ ዱባሞ ክችንችላ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት - የመስራች አባላት ዝርዝርም ያላቀረበ፣ ጉባኤ ያላካሄደ 5. የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ኮንግረስ (ኮንግረስ) - የመስራች አባላት ዝርዝር ያላቀረበ 6. የትግሪ ወርጂ ብሔረሰብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ትወብዴድ) - ጠቅላላ ጉባኤ ያላካሄደ 7. የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት (መአህድ) - የመስራች አባላት ዝርዝር ያላቀረበ፣ ጉባኤ ያላካሄደ 8. የኢትዮጵያን አንድነት ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኢአዴድ) - ጠቅላላ ጉባኤ ያላካሄደ 9. የመላው አማራ ህዝብ ፓርቲ (መዐሕፓ) - የመስራች አባላት ዝርዝር ያላቀረበ 10. የኢትዮጵያውያን አገር አቀፍ ንቅናቄ (ኢሃን) - የመስራች አባላት ዝርዝር ያላቀረበ 11. የደቡብ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኮንግረስ (ደቡብ ኮንግረስ) - የመስራች አባላት ዝርዝር ያላቀረበ 12. የሸኮና አካባቢው ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ሸአሕዲድ) -ጠቅላላ ጉባኤ ያላካሄደ 13. ነጻነትና ሰላም ለኢትዮጵያ ህብረት ፓርቲ (ነጻነትናሰላም) - የመስራች አባላት ዝርዝር ያላቀረበ ሰነድ ባለማምጣታቸው እንዲሰረዙ የተሰወኑት ፓርቲዎች 1. የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ 2. መላው ኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ 3. የከምባታ ሕዝቦች ኮንግረስ 4. የሐድያ ብሔር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት 5. የኦሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ኅብረት 6. የዲል ወቢ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ 7. የቤንች ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት 8. የስልጤ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ 9. የአፋር ሕዝብ ነፃነት ፓርቲ 10. የሱማሌ አንድነት ፓርቲ 11. ነፃነት ለአንድነትና ለፍትሕ ፓርቲ 12. ብሔራዊ ተሀድሶ ለሰላም ልማት 13. የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ህብረት 14. የጋምቤላ ክልላዊ ንቅናቄ በልዩ ሁኔታ ሰነድ ካስገቡ ፓርቲዎች ጋር ሰነዶች እንዲታይላቸው የተደረጉ ፓርቲዎች 1. ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ( ኢዴፓ) 2. ወለኔ ህዝቦች ፓርቲ በኢትዮጵያ ውስጥ ከአንድ መቶ በላይ ክልላዊና አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች የነበሩ ሲሆን በሕግ የተቀመጡትን መስፈርቶች ባለማሟላታቸው በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰረዙት ፓርቲዎች ከዘርዝሩ ሲወጡ ቁጥሩን ዝቅ ቢያደርገውም፤ የቀሩት ፓርቲዎች ቁጥር ቀላል የሚባል አይደለም። ኢትዮጵያ በየአምስት ዓመቱ የሚደረገውን አጠቃላይ ምርጫ በመጪው ነሐሴ ወር ለማድረግ አቅዳ የነበረ ቢሆንም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ባስከተለው ስጋት ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ እንዲሸጋገር ተደርጓል።
news-53075792
https://www.bbc.com/amharic/news-53075792
የኢትዮጵያ 10ኛው ክልል ከደቡብ ክልል የስልጣን ርክክብ አካሄደ
በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ውስጥ አንድ ዞን በመሆን ለሦሰት አስርት ዓመታት ያህል የቆየው የሲዳማ ዞን የአገሪቱ አስረኛ ክልል ሆነ።
የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት ዛሬ ማካሄድ በጀመረው አስቸኳይ ጉባኤው የሲዳማ ዞን በሕዝበ ውሳኔ በክልል እንዲደራጅ በተገኘው ውጤት መሰረት የሥልጣን ርክክብ ርክክብ ተፈጽሟል። በዚህም መሰረት የደቡብ ክልል እና አዲሱ የሲዳማ ክልል በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት አባላት ፊት የዞኑን ስልጣን በማስረከብ ዞኑ ክልል መሆኑ ይፋ ሆኗል። የሲዳማ ሕዝብ በኅዳር ወር (ህዳር 10/2012 ዓ.ም) ባካሄደው ሕዝበ ውሳኔ ላይ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ድምጽ ሰጠ ሲሆን፤ ዞኑ ክልል እንዲሆን የሚያስችለውን ከፍተኛ ድምጽ በማግኘቱ ነው እዚህ ውሳኔ ላይ የተደረሰው። የሲዳማ ሕዝብ በከፍተኛ ድምጽ ራሱን ችሎ ክልል እንዲሆን መወሰኑን የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ያሳወቀው ደግሞ ኅዳር 13/2012 ነበር። የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው የሲዳማ ክልል ራሱን ችሎ በመውጣቱ በሌሎች ሕዝቦች ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ እንደማይኖር መናገራቸው ፋና ዘግቧል። የደቡብ ኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አሁን ያለው ፌደራላዊ አወቃቀር ተግባራዊ ከሆነ በኋላ የነበሩ አምስት ክልሎችን በማዋሃድ የተፈጠረ ከ50 በላይ ብሔርና ብሔረሰቦች የሚገኙበት ክልል ነው። የሲዳማ ዞን ራሱን የቻለ ክልል ለመሆን ለዓመታት ጥያቄ ሲያቀርብ ቆይቶ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አስተዳደር ከመጣ በኋላ ጥያቄው ተጠናክሮ በሕዝበ ውሳኔ እልባት አግኝቷል። ከሲዳማ በተጨማሪ በደቡብ ክልል ውስጥ ያሉ ከአስር የሚበልጡ ዞኖች የእራሳቸው ክልል እንዲኖራቸው ጥያቄ ማቅረባቸው በተደጋጋሚ ሲገለጽ ነበር። ማክሰኞ ሰኔ 2/2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከደቡብ ክልል የዞን እና የልዩ ወረዳ አስተዳዳሪዎች ጋር ተገናኝተው ከተነጋገሩ በኋላ የሲዳማ ዞንን ጨምሮ የደቡብ ክልልን በአራት የሚከፍል አዲስ አወቃቀር ለፌዴሬሽን ምክር ቤት እንዲተላለፍ ከስምምነት ላይ መደረሱ ተሰምቷል።
sport-45401975
https://www.bbc.com/amharic/sport-45401975
ከቻይና- አፍሪካ-ኢትዮጵያ ወዳጅነት ጀርባ ምን አለ?
"ቻይና ለአፍሪካ የቅርብ ወዳጅና ታማኝ ጓደኛ ነች" ብለዋል ፕሬዚዳንት ሺ ዢንፒንግ ትናንት በተከፈተው የአህጉሪቱና የአገራቸው የጋራ ጉባኤ መክፈቻ ላይ።
"አፍሪካን እንወዳለን፤ እንደግፋለን" ሲሉም ለተሰብሳቢዎቹ ምቾት የሚሰጡ ቃላትን አስተጋብተዋል። ለመሆኑ ከቻይና የአፍሪካ ወዳጅነት ጀርባ ምን አለ? አቶ ሀይለመለኮት ተከስተብርሃን የቢዝነስና ኢንቨስትመንት ባለሞያ ናቸው። ለዚህ ጥያቄ ምላሽ የሚሰጡት የቻይና አፍሪካ ወዳጅነት በገበያና በጥሬ ዕቃ የሚመራ መሆኑን አጽንኦት በመስጠት ነው። • ዘጠኝ አየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ታሰሩ • ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር የፍቅር ግንኙነት አለዎት? "የቻይና ሕዝብ ከ1 ቢሊዮን በላይ ነው። አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገሮች ሕዝባቸው ወጣት ነው። በዕድገት ላይ ናቸው። ትልቅ ሸማች እየተፈጠረ ነው። ይህ እውነታ የቻይናን ሞልቶ የሚፈስ ምርት ላያጓጓ አይችልም።" ይላሉ። ሁለተኛው የሚያቀርቡት ምክንያት የርካሽ ጥሬ ዕቃ ረሀብ ነው። ቻይና ተስፋፊ ፋብሪካዎቿ በጥሬ ዕቃ የከበረችውን አህጉር እንዲያማትሩ ያስገድዳቸዋል። "በርካሽ የሚያገኙትን ጥሬ ዕቃ እሴት ጨምረው ለራሳችንም ለተቀረው ዓለምም ያደርሱታል።" የአፍሪካ ኅብረት የወቅቱ ሊቀመንበር ፖል ካጋሜ ለሺ ጂንፒንግ የእስከዛሬው ድጋፍ ሞቅ ያለ ምስጋናን ካቀረቡ በኋላ ቻይና "እኩል ተጠቃሚነትን መሠረት የምታደርግ ወዳጃችን ናት" ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይም ተመሳሳይ ምስጋናን አቅርበዋል። በዚህ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት ብቻ የምጣኔ ሐብት ቀውስ ውስጥ ገብታ የቆየችው ዚምባብዌን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ መሪዎች የቤጂንግን ደጅ ጠንተዋል። ለመሆኑ የአፍሪካ መሪዎች ለምን ቀድመው ወደ ቻይና ያማትራሉ? አቶ ኃይለመለኮት ለዚህም ሁለት አበይት ምክንያቶችን ያቀርባሉ። አንዱ ቻይና የምትሰጠው ብድር በቅድመ ሁኔታዎች የተጀቦነ አለመሆኑ ሲሆን ይህ ለብዙ ከዲሞክራሲና ሰብአዊ መብቶች ለተኳረፉ የአፍሪካ መሪዎች ምቾትን የሚሰጥ ነው ይላሉ። ሌላው ደግሞ …የቻይና የተፍታታ ብድር ለመስጠት አለማቅማማቷ ነው። የብድር እፎይታዋና የወለድ ምጣኔዋ ከምዕራቡ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ሲነጻጸር ሻል ያለ ነው። የኢትዮጵያ እና ቻይና «ወዳጅነት» ከ80 በላይ የሚሆኑ ጥናቶችን በአፍሪካ-ቻይና ግኝኙነት ላይ ያጠኑት ጌዲዮን ገሞራ ጃለታ የኢትዮጵያ እና ቻይና ግንኙነት ጥንተ-መሰረት እንዳለው ያስረዳሉ። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በአውሮፓውያኑ በ1995 ወደ ቤጂንግ ማቅናታቸውን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቻይናን እንደ ፈጣን እድገት አብነት ማየቷ እንደጨመረ የሚያነሱት አጥኚው በቅርብ ዓመታት ውስጥ ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማግዘፍ የፈለገችበት ምክንያት ኢትዮጵያ ካላት ዲፕሎማቲክ እና የገበያ ጠቀሜታ አንፃር እንደሆነ ያብራራሉ። ምሁሩ እንደሚሉት ኢትዮጵያ በተለይ አዲስ አበባ የአፍሪካ ዲፕሎማቲክ መናገሻ መሆኗ እንዲሁም ያላት ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ጋር ተያያይዞ ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት በተለየ መንገድ እንደምታየው ነው። «።ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያደርጉት ነገር ሁሉ የመላው አፍሪካን ዐይን(ቪዚብሊቲ) እንደሚያገኝ ስለሚያውቁ ከኢትዮጵያ ጋር ወዳጅነታቸውን ለማጠንከር ፈልገዋል። ከዚህም በተጨማሪ ኢትዮጵያ ከ100 ሚሊየን በላይ ህዝብ አላት ፤ይሄ ለቻይና ትልቅ የገበያ መዳረሻ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ እየተሸጡ ያሉ ብዙ ሸቀጦች እየመጡ ያሉት ከቻይና ነው።» የሚሉት አቶ ጌዲዎን ከእነዚህ በተጨማሪ የመንገድ ስራን በመሳሰሉ ዘርፎች ያለውን የስራ ዕድል ቻይናዊያን በመልካም ማየታቸው ለሁለቱ ሀገራት ዕድገት መጠንከር እንደ ምክንያትነት ያነሳሉ። ይሄም ቢሆን ቅሉ ግኑኝነቱ በጥንቃቄ መከወን እንዳለበት አጥኚው ይመክራሉ፤ በተለይ ደግሞ ኢትዮጵያ ከቻይናዊያን ወደ ዜጎቿ የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖር መዋቅር እንዲኖራት፣ ተመጣጣኝ ያልሆነው የሁለቱ ሀገራት የንግድ ግንኙነት እንዲስተካከል፣የቻይና ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን ገሸሽ ያደረገ የኢኮኖሚ ስርዓትን ፍፁም ትክክል አድርጎ ከመቀበል ራስን ማቀብ እንደሚገባ ይመክራሉ። የብሔራዊ ባንክ አዲሱን ገዢና ሌሎች ቁልፍ የካቢኔ አባሎቻቸውን አስከትለው በጊዜ ቤጂንግ የገቡት ዐብይ አህመድ፣ ከትናንት በስቲያ ዕሑድ የቻይናን ፕሬዚዳንት አግኝተው በአበይት ምጣኔ ሐብታዊ ጉዳዯች ላይ ተነጋግረዋል። በውይይቱ ሺ ጂንፒንግ "የኢትዯጵያ ዕድገት ጎዳና ከቻይና ብሔራዊ ልማት ቅድመ ሁኔታ ጋር ስምምነት ነው" ብለዋል። ይህ ዲፕሎማሲያዊው ቋንቋ በትክክል ምን ማለት እንደሆነ ባይብራራም። ለመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከቤጂንግ ምን ጉዳዮችን አሳክተው መመለስ ይኖርባቸዋል? አቶ ሓይለመለኮት "ቢያንስ ሦስት ጉዳዮችን ይላሉ። ቀዳሚው ግን ይላሉ አቶ ኃይለመለኮት፣ "ቀዳሚው ኢኮኖሚያዊ ሳይሆን ፖለቲካዊ ጉዳይ ነው። "በኢትዮጵያ ባለፉት ወራት በተከሰቱ ፖለቲካዊ ኩነቶች ላይ የተፈጠረባቸውን ጥያቄ መመለስ፣ ከኢህአዴግ ጋር የነበረው የርዕዮተ ዓለም መጣጣም እምብዛምም ማፈግፈግ እንደሌለ ለቻይናዎቹ በአገሪቱ ላይ የነበራቸውን እምነት መመለስ ይኖርባቸዋል ይላሉ አቶ ኃይለመለኮት። • "አቶ በረከት ባለሐብቶችን ለቅመህ እሰር ብሎኝ ነበር" አቶ መላኩ ፈንታ • ከአንታርክቲካ በስተቀር ስድስቱን አህጉሮች ያዳረሰችው ኢትዮጵያዊት ይህን ፖለቲካዊ መደላደል በስኬት ካጠናቀቁ በኋላ ግን ሁለት ተጨማሪ ሥራዎች ይጠብቅዋቸዋል ባይ ናቸው አቶ ሀይለመለኮት። የመጀመሪያው በኢኮኖሚው ረገድ የሚከተለው ስራ ነው። ቻይና ከፍተኛ ብድሮችን ለኢትዮጵያ ስለሰጠች፤ በዋናነት እንደ ባቡርና ማዳበሪያ ፋብሪካዎች ያሉ ትላልቅ ሃገራዊ ፕሮጀክቶች ጋር በተያያዘ የብድሩ የመክፈያ ጊዜ ደርሷል። በመሆኑ የመክፈያ ጊዜውን እንዲያራዝሙላቸው ይጠይቃሉ ተብሎ ነው የሚገመተው። ሌላኛው የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን መሳብ ነው። አጠቃላይ ኢኮኖሚው በቂ የሆነ የውጭ ምንዛሬን ማመንጨት አልቻለም። አሁን እየተሄደበት ባለው አሰራር ትላልቅ የመንግስት ድርጅቶች በግሉ ዘርፍና በመንግስት ሽርክና ወይንም ለተለያዩ የሃገር ውስጥና የውጪ ድርጅቶች በሽያጭ መልክ ይተላለፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፤ ቻይናም በዚህ ሂደት ውስጥ ሚና እንዲኖራት ያደርጋሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።
news-48183256
https://www.bbc.com/amharic/news-48183256
በማይናማር ታስረው የነበሩት የሮይተርስ ጋዜጠኞች ተለቀቁ
በማይናማር ታስረው የነበሩት ሁለቱ የሮይተርስ ጋዜጠኞች መለቀቃቸው ተሰማ። ጋዜጠኞቹ የታሰሩት ማይናማር ውስጥ በሮሂንግያ ሙስሊሞች ላይ የደረሰውን በደል በማጋለጣቸው ነበር ተብሏል።
እነዚህ ጋዜጠኞች ከቀናት በፊት በኢትዮጵያ በተከበረው የፕሬስ ነፃነት ላይ በተወካያቸው አማካይነት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። የ33 ዓመቱ ዋ ሎን እና የ29 ዓመቱ ኪያው ሶኤ ሶ የተለቀቁት የሚያንማር ፕሬዝዳንት ባደረጉላቸው ይቅርታ ነው ተብሏል። ጋዜጠኞቹ ለ500 ቀናት ከማይናማር ዋና ከተማ ርቆ በሚገኘው ያንጎን ከተማ ነበር የታሰሩት። • ስራቸው ለሞት የዳረጋቸው ጋዜጠኞች ጋዜጠኞቹ ሮሂንግያ ሙስሊሞች ላይ የደረሰውን በደል በማጋለጣቸው ጥፋተኛ ተብለው እያንዳንዳቸው የሰባት ዓመት እስር ተፈርዶባቸው ነበር። የሁለቱ የሮይተርስ ጋዜጠኞች እስር በማይናማር የመገናኛ ብዙኃን ላይ እንደተቃጣ ጥቃት ተቆጥሮ የነበረ ሲሆን በሀገሪቱ ስላለው ዲሞክራሲም ጥያቄዎች ተነስተዋል። • ግጭትን ለማባባስ ፌስቡክ ጥቅም ላይ ውሏል ተባለ ጋዜጠኛ ዋ ሎን ከእስር እንደተለቀቀ ለቢቢሲ በሰጠው ቃል፤ በጋዜጠኛነት እንደሚቀጥልበት ተናግሯል። "ቤተሰቦቼንና ባልደረቦቼን ለማግኘት ናፍቄያለሁ፤ ወደ ዜና ክፍልም እስክሄድ ድረስ ጓጉቻለሁ" ብሏል። • ቦይንግ አደጋው ከመድረሱ በፊት ችግሩን አውቅ ነበር አለ ጋዜጠኞቹ የተለቀቁት ከሌሎች በርካታ እስረኞች ጋር ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ በየዓመቱ ለማይናማር አዲስ አመት ከሚደረግ ይቅርታ ጋር የተያያዘ ነው። የሮይተርስ ከፍተኛ ዋና አዘጋጅ ስለ ጋዜጠኞቹ ሲናገር፤ ለፕሬስ ነፃነት "ቀንዲል" የሆኑ ሲል አሞካሽቷቸዋል። አክሎም "ብርቱ ጋዜጠኞቻችንን የማይናማር መንግሥት በመልቀቁ በጣም ደስተኞች ነን" ብሏል። • "የአደገኛ ግለሰቦች" የፌስቡክ ገጽ መዘጋት ጀመረ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ሂይውመን ራይትስ ዎች በበኩሉ፤ ጋዜጠኞቹን እንኳን ደስ አላችሁ ካለ በኋላ "አሁንም በርካታ ጋዜጠኞች በማይናማር በእስር ላይ ይገኛሉ።" ሲል አስታውሷል። እነዚህ ጋዜጠኞች የማይናማር ዜግነት ያላቸው ሲሆን ለሮይተርስ ነበር የሚሰሩት። በቁጥጥር ስር ሲውሉም በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል በፀጥታ ኃይሎች ስለተገደሉ 10 ወንዶች መረጃ እየሰበሰቡ ነበር ተብሏል። በቁጥር ስር የዋሉት ዘገባው ከመውጣቱ በፊት ሲሆን፤ መረጃ አለን ብለው በአንድ ሆቴል የቀጠሯቸው እና መረጃ ያቀበሏቸው ሁለት የፖሊስ አባላት አሳልፈው እንደሰጧቸው በኋላ ላይ ለፍርድ ቤት ቃላቸውን ሰጥተዋል። • ጋዜጠኞች ስለ ለውጡ ማግስት ሚዲያ ምን ይላሉ? እነሱ በእስር ላይ እያለ እያጠናቀሩት የነበረው ዘገባ የወጣ ሲሆን፤ ዘገባው በርካታ መረጃዎችን በመያዙና የደረሰውን የሰብአዊ መብት ጥሰትና ሞት በማጋለጡ ተደንቆ ነበር።
news-51582937
https://www.bbc.com/amharic/news-51582937
አሠሪዎ እየሰለለዎ መሆኑን እንዴት ያውቃሉ?
ባርክሌስ ባንክ ሠራተኞቹ ምን ያህል ሰዓት ወንበራቸው ላይ እንደተቀመጡ የሚያሰላ የስለላ መረብ ዘርግቶ ነበር። ይህ መረጃ ይፋ ሲደረግ ወቀሳ የበዛበት ባርክሌስ ሠራተኞቹን መሰለል ቢያቆምም፤ ድርጊቱ አለቆች ተቀጣሪዎቻቸው ላይ መሰለል አለባቸውን? የሚል ጥያቄ አጭሯል።
ባርክሌስ ተቀጣሪዎቹ ለሥራ ከተመደበላቸው ሰዓት በላይ እንዳይሠሩ ለመከላከል እንዲሁም ውጤታማነታቸውን ለማሳደግ የኮምፒውተር ሥርዓት ዘርግቶ እንደነበረ ተናግሯል። ድርጅቱ የተጠቀመውን መተግበሪያ የፈጠረው ሳፒየንስ የተባለ ድርጅት ነበር። ሠራተኞች ኮምፒውተራቸው ላይ ምን እንደሚያደርጉ፣ መቼ የኢንተርኔት አገልግሎት መጠቀም እንደሚያቆሙም የሚመዘግብ አሠራርም ፈጥሯል። ባርክሌስ ሠራተኞቹ ላይ እየሰለለ እንደሆነ ይፋ ሲደረግ መተግበሪያው ሠራተኞች እረፍት እንዳያደርጉ እና በቂ ጊዜ እንደሌላቸው እንደሚጠቁም ተገልጿል። በእርግጥ ባርክሌስ ሠራተኞቹን ሲሰልል ይህ የመጀመርያው አይደለም። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ2017፤ ሠራተኞች ከዴስካቸው መነሳት አለመነሳታቸውን በሙቀት እና በእንቅስቃሴ የሚለካ መሣሪያ አስገጥሞ ነበር። ተቋሙ ድርጊቱን "የቢሮ አጠቃቀምን ለመረዳት ያለመ ነው" ሲል ገልጾት ነበር። • ሥራ ቀጣሪና አባራሪ እየሆነ የመጣው ሮቦት • ሴት ተመራቂዎች ለምን ሥራ አያገኙም? ድርጅቶች ተቀጣሪዎቻቸውን እንዴት ይሰልላሉ? በርካታ ድርጅቶች በዘልማዳዊ መንገድ ሠራተኞቻቸውን ይሰልላሉ። የተቀጣሪዎቸን ኢሜል ማየት፣ ኮምፒውተር ላይ ያሳለፉትን ጊዜ መለካት እና ሠራተኞች ቢሮ ውስጥ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ መከታተል ዘልማዳዊ የስለላ ዘዴዎች ናቸው። ተቋሞች "የምንሰልለው የከፋ ነገር አስበን አይደለም" ቢሉም፤ አካሄዳቸው በስፋት ይተቻል። ቴሌግራፍ ጋዜጣ ሠራተኞቹ ዴስክ ላይ መቆጣጠሪያዎች ገጥሞ የነበረ ሲሆን፤ ወቀሳ ሲገጥመው እንደ ጎርጎሮሳውያኑ 2016 ላይ መሣሪያዎቹን አንስቷል። በተመሳሳይ አማዞን መጋዘኖቹ ውስጥ ሠራተኞችን መሰለሉ አስተችቶታል። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ 2013 ላይ የወጣ ጥናት እንደሚያሳየው፤ አማዞን የሠራተኞችን ፍጥነት ለመለካት መጋዘኖቹ ውስጥመሣሪያ አስገጥሟል። ሠራተኞችን መሰለል ይፈቀዳል? ዩናይትድ ኪንግደምን እንደምሳሌ ብንወስድ የሰዎች የግል መረጃ የሕግ ከለላ አለው። መረጃ መሰብሰብ ያለበት ግልጽና ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ሲሆን፤ መረጃን ያለምክንያት ማስቀመጥ ወይም ከተወሰነ ጊዜ በላይ በክምችት ክፍል ማቆየት ሕገ ወጥ ነው። በሕጉ መሰረት ሠራተኞች የግል መረጃቸው እየተሰበሰበ እንደሆነ ሊነገራቸው ይገባል። • ሥራ ቦታ ጋደም ማለት መፈቀድ አለበት? • ሥራ የማዘግየት ልማድን ለመቅረፍ የሚረዱ 8 ነጥቦች የሕግ ባለሙያው ማክስ ዊንትሮፕ እንደሚሉት፤ ቀጣሪዎች የሠራተኞቻቸውን ውጤታማነት ለመመዘን ወይም በሌላ ምክንይትም መረጃ መሰብሰብ ካስፈልጋቸው፤ ሂደቱን በሥራ ስምምነት ሰነድ ውስጥ ማካትተት እና ከተቀጣሪዎች ይሁንታ መጠየቅ ይገባቸዋል። ሠራተኞች ምን ይላሉ? አንድ የሠራተኞች ማኅበር እንደሚለው፤ ተቀጣሪዎች መጸዳጃ ቤት ሲሄዱ ጨምሮ አጠቃላይ እንቅስቃሴያቸውን መከታተል ተጠራጣሪነት እንዲሁም ፍርሀት ይፈጥራል። ሠራተኞች ላይ የሚደረግ ማንኛውም ክትትል በሠራተኞች ፍቃድ ሊደረግ እንደሚገባ ያክላሉ። ከሦስት ዓመታት በፊት የወጣ ጥናት እንደሚያሳየው፤ ወደ 2,000 የሚጠጉ ሠራተኞች የቀጣሪዎችን ስለላ በተለያየ መንገድ ያዩታል። ለምሳሌ የመሥሪያ ቤት ንብረት የሆነ መኪና፣ ስልክ ወይም ኮምፒውተር ላይ የሚደረግ ክትትልን የማይቀበሉ ጥቂቶች ናቸው። በሌላ በኩል ከሥራ ሰዓት ውጪ የተቀጣሪዎችን የማኅበራዊ ሚዲያ እንቅስቃሴ መከታተል እና የሠራተኞችን ፊት የሚለይ (ፌስ ሪኮግኒሽን) ቴክኖሎጂ መጠቀምን በርካቶች ተችተዋል። • ሰራተኞች በፈቀዳችሁ ሰዓት ሥራ ገብታችሁ ውጡ ተብለዋል • ሥራ እና ፍቅር፡ ከሥራ አጋርዎ ጋር የፍቅር ግንኙነት መጀመር ሊያስባርር ይገባል? የሠራተኞች ማኅበሩ እንደሚለው፤ ድርጅቶች ሠራተኞቻቸውን መከታተላቸው በበጎ የሚታይባቸው አጋጣሚዎች አሉ። ሠራተኞች ያሉበትን ቦታ ተቋሙ ማወቁ ተቀጣሪዎቹ ደህንንት እንዲሰማቸው ሊያደርግ ይችላል። ስልክ ላይ ክትትል ማድረግ፤ በመሥሪያ ቤቱ ስልክ ደውለው ቅሬታ ከሚያቀርቡ ደንበኞች ሠራተኞችን ለመጠበቅ የሚረዳም ይሆናል። የግለሰብ መረጃ ጥበቃ ላይ የሚሠሩት ኤድዋርድ ሆውተን በበኩላቸው፤ ሠራተኞችን መሰለል ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል ይላሉ። "ሠራተኞች፤ ቀጣሪያቸው እምነት እንዳልጣለባቸው ሊሰማቸው ይችላል" ሲሉ ያስረዳሉ።
57056780
https://www.bbc.com/amharic/57056780
ምርጫ 2013፡ የድምጽ መስጫ ቀን ላይ ለውጥ ሊኖር ይችላል ተባለ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ በርቱካን ሚደቅሳ የ2013 አጠቃላይ ምርጫ የመራጮች ድምጽ መስጫ ቀን ላይ ለውጥ ሊደርግ እንደሚችል ተናገሩ።
የምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ የቦርዱ ሰብሳቢዋ የስድሰተኛው ሃገራዊ ምርጫ የድምጽ መስጫ ቀን "አስፈላጊ ከሆነ የተወሰኑ ቀናት ወደፊት ወደ ኋላ ሊል" ይችላል ሲሉ ተናግረዋል። ሰብሳቢዋ ቦርዱ በጉዳዩ ላይ እስካሁን የወሰነው ምንም ዓይነት የቀን ለውጥ አለመኖሩን አረጋግጠው፤ በመራጮች ምዝገባ እና በድምጽ መስጫ ቀናት መካከል መከናወን ያለባቸው ተግባራት መኖራቸውን አስረድተዋል። ኢትዮጵያ በአንድ ዓመት የተራዘመውን አጠቃላይ ምርጫ ግንቦት 28 እና ሰኔ 5 ለማድረግ አቅዳለች። ባሳለፍነው ቅደሜ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት፤ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢዋ ብርቱካን ሚደቅሳ የሎጂስቲክ እና የደህንነት ጉዳዮችን እንደምክንያት በመጥቀስ፤ የድምጽ መስጫው ቀን "አስፈላጊ ከሆነ የተወሰኑ ቀናት ወደፊት ወደ ኋላ ሊል ይችላል ብዬ እገምታለሁ" ሲሉ ተናግረዋል። ቦርዱ እስካሁን ድረስ ከ31 ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸውን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። የምርጫ ቁሳቁሶችን ማከፋፈል፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች ምልመላ እና ስልጣና እንዲሁም የፓርቲዎች ግብዓት ማግኘት የሚሉት ተግባራት የመራጮች ምዝገባ ተጠናቆ እስከ ድምጽ መስጫ እለት የሚተገበሩ መሆናቸውን አስረድተዋል። "እነዚህን አይተን በሁለቱ መካከል ለማስገባት እንሠራለን። የሚያስፈልገው ነገር የሚወስደው ጊዜ ከታወቀ በኋላ አስፈላጊ ከሆነ የተወሰኑ ቀናት ወደፊት ወደ ኋላ ሊል ይችላል ብዬ እገምታለሁ" ብለዋል። በአዲስ አበባ እና በሌሎች ህዝብ በብዛት የሰፈረባቸው ቦታዎች የምርጫ ጣቢያ አለመኖሩን ያረጋገጡት የቦርዱ ሰብሳቡቢ "ይህ የአሰራር ክፍተት ነው። ችግር በመሆኑ ኃላፊነትም የወሰድንበትም ጉዳይ ነው" ብለዋል። የሕዝብ ቆጠራ አለመደረጉ እና ያለው መረጃ የቆየ መሆኑ የመራጮች ምዝገባ ግምት አስቸጋሪ ማድረጉን በምክንያትነት አስቀምጠዋል። ችግሩን ለመቅረፍ እየተሠራ መሆኑን በመጠቆም "አዲስ አበባ ላይ ብዙ ቦታዎች ላይ በተለይም ኮንዶሚኒየም አካባቢዎች ላይ ከህዝብ ቁጥር አንጻር ያለመመጣጠን ነበር። በቀረው ጊዜ ብዙ ሰው እንመዘገባል ብለን እንገምታለን። የተሻለ ምዝገባ እንጠብቃልን" ብለዋል። የመራጮች ምዝገባ የተራዘመባቸው ስፍራዎች የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢዋ ብርቱካን፤ በደህንነት ስጋት የመራጮች ምዝገባ ዘግይቶ በነበረባቸው አካባቢዎች የመራጮች ምዝገባ መጀመራቸውን ተናግረዋል። በኦሮሚያ በአራቱ የወላጋ ዞኖች፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ካማሺ እንዲሁም በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ምዝገባ መጀመሩን ተናግረዋል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን በተመለከተም "በመተከል ዙሪያ ቦርዱ በትኩረት እየተከታተለው ነው። የደህንነት እና የተፈናቃዮች ሁኔታን ከግምት በማስገባት ምዝገባ ለማስጀመር እያየነው እንገኛለን" በማለት እስካሁን መተከል ላይ የመራጮች ምዝገባ አለመጀመሩን ተናግረዋል። በሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ 3 የምርጫ ክልሎችም አሁንም ምዝገባ አልመጀመሩን ጠቅሰው ከአባቢው የተፈናቀሉ ወደቦታቸው ስላልተመለሱ እና የደህንንነት ስጋት በመሆኑ ምዝገባ አለመጀመሩን አስረድተዋል። በደቡብ ክልል ደግሞ የሱርማ ልዩ እና ዲዚ ልዩ እስካሁን ምዝገባ አለመጀመሩ እንዲሁም በሶማሌ ክልል የምርጫ ምዝገባ ግድፈት ተፈጸሞባቸዋል በተባሉ አካባቢዎች ቦርዱ ምዝገባውን መታገዱን አስታውቀዋል። የአውሮፓ ሕብረት ታዛቢዎቸን አልክም ስለማለቱ የአውሮፓ ሕብረት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር መግባባት በለመቻሉ የምርጫ ታዛቢዎቹን እንደማይልክ ባሳለፍነው ሳምንት ማስታወቁ ይታወሳል። የአውሮፓ ሕብረት ታዛቢዎችን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ "የውጭ ታዛቢዎች ሁለት ደረጃዎች አሉት። የመጀመሪያው ከመንግሥት ጋር የሚያልቅ ነው። . . . በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የሚጠናቀቅ ነው። [ሁለተኛው] በውጭ ጉዳይ ማረጋገጫ መሠረት ዕውቅና በመስጠት እናሰማራለን። አውሮፓ ህብረት ታዛቢዎችን ባለመላኩ ቦርዱ አዝኗል። ከእኛ በፊት ከመንግሥት ጋር ያለውን ግንኙነት ሳይጨርስ ነው ይህ ነገር የተፈጠረው። ቢመጡ እንደምንወድ ለሂደቱም የሚጨምረው ነገር እንዳለ አረጋግጠንላቸው ነበር። በእነሱም በኩል ተመሳሳይ ግምት እና እምነት ነበር። . . . ቢመጡ መልካም ነበር። ከዚህ ያለፈ ሃሳብ መስጠትል አልችልም" ብለዋል። ኢትዮጵያ ምርጫ ለመታዘብ ካቀደው የአውሮፓ ሕብረት ጋር ያልተስማማቸው ሕብረቱ ሉዓላዊነትን የሚጻረር ጥያቄን በማቅረቡ ነው ሲሉ የውጪ ጉዳይ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ መናገራቸው ይታወሳል። ሕብረቱ ኢትዮጵያ የሌላትን የኮሚኒኬሽን ስርዓት ወደ አገር ውስጥ ይዞ መግባትን እንደ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጡ እና የምርጫ ውጤትን ይፋ የማድረግ እኔ ነኝ ማለቱን ተከተሎ ከስምምነት መድረስ አለመቻሉን የውጪ ጉዳይ ቃል አቀባይ ተናግረዋል።
news-46450672
https://www.bbc.com/amharic/news-46450672
በብራዚል በሕይወት ከሌለች እናት በተለገሰ ማሕፀን የመጀመሪያዋ ህፃን ተወለደች
በህይወት ከሌለ ሰው ስለሚደረግ የአይን ብሌን ንቅለ-ተከላ ሰምተን እናውቅ ይሆናል። ከወደ ብራዚል የተሰማው ግን በሕይወት ከሌለች እናት በተለገሰ ማሕፀን ልጅ ወልዶ መሳም መቻሉን ነው።
በብራዚል በሕይወት ከሌለች እናት በተለገሰ ማህፀን ሙሉ ጤናማ ሴት ልጅ መወለዷ ተሰምቷል። • አሜሪካዊው ወታደር የወንድ መራቢያ አካል ንቅለ-ተከላ ተደረገለት በአውሮፓውያኑ 2016 በብራዚል ሳኦ ፓኦሎ ከተማ አንዲት የ32 ዓመት እናት 10 ሰዓት በፈጀ ቀዶ ሕክምናና ክትትል ካለማህፀን ልጅ መውለድ ችላ ነበር። እስካሁን እናት ለልጇ የለገሰችውን ጨምሮ በሕይወት ካለ ሰው በተለገሰ 39 የማህጸን ንቅለ ተከላ 11 ሕጻናት ተወልደዋል። ይሁን እንጂ በሕይወት ከሌለች እናት በተለገሰ 10 የማህፀን ንቅለ ተከላ በፅንስ መጨንገፍ ምክንያት አንዱ እንኳን ሳይሳካ ቀርቷል። አሁን ላይ የተሰማውና በሕይወት ከሌለች እናት የሚለገስ ማህፀን ልጅ ማፍራት በመቻሉ ለበርካታ ወላጆች ተስፋ የሰጠ ሆኗል። ለጋሿ በ40 ዎቹ የዕድሜ ክልል የምትገኝ የ3 ልጆች እናት ነበረች፤ ሕይወቷ ያለፈውም በጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ ሳቢያ ነው። የእርሷ ማህፀን የተለገሳት እናት ደግሞ ሜየር ሮኪታንስኪ ኩስተር ሁሰር የተባለ የሆርሞን መዛባት( syndrome) ችግር አለባት። ይህ ችግር በሴቶች ላይ የሚፈጠር ሲሆን የመራባት ሒደታቸውን የሚገታ ነው፤ ለዚህ የጤና ችግር የተዳረጉ ሴቶች የውጫዊ መራቢያ አካላቸውና ማህፀናቸው እድገቱን ያቆማል አሊያም ጭራሽ ሊጠፋ ይችላል። • ሃያ ልጆቿን በፅንስ መጨንገፍ በሞት የተነጠቀች እናት የተከለሰዉን ሕግ አወደሰች እርሷም ታዲያ ይሄው ከ4500 ሴቶች በአንዷ የሚከሰተውና ማህፀንንና የሴት ልጅ ውጫዊ የመራቢያ ክፍል የሚያጠቃ የጤና ችግር አጋጥሟታል። በዚህ ምክንያትም ማህፀኗ ፅንስ መሸከም አይችልም ነበር። ነገር ግን ዕንቁላል የሚሸከመው ክፍል ግን ችግር አልነበረበትም፤ ሐኪሞቹም እንቁላሉን ከግድግዳው ላይ ማስወገድና ከወንዱ ፈሳሽ (ስፐርም) ጋር በማዋሃድ ማቀዝቀዝ ችለው ነበር። ከዚያም እናትየዋ ንቅለ ተከላውን የሚከላከልና ለማስወገድ የሚያስችለውን በሽታ የመከላከል አቅሟን የሚያዳክም መድሃኒት ተሰጥቷል። • ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ስለተዘረፉ ቅርሶች ምን እናውቃለን? ከዚያም ከስድስት ሳምንት በኋላ የወር አበባ ማየት ጀመረች፤ ከሰባት ወራት በኋላ ደግሞ ከወንዱ የዘር ፈሳሽ ጋር የተዘጋጀው እንቁላል በማህፀኗ እንዲቀመጥ ተደረገ። ከዚያ በኋላ ጤናማ በሆነ እርግዝና 2.5 ኪሎ ግራም የምትመዝን ህፃን በቀዶ ሕክምና ለመገላገል ችላለች። በሳኦ ፓኦሎ ዳስ ክሊኒካስ ሆስፒታል ሐኪም ዶ/ር ዳኒ ኢጂዘንበርግ "መካንነት ላጋጠማቸው ሴቶች በሕይወት ካለች ሴት የማህፀን ንቅለ ተከላ ማድረግ የሕክምና መርቀቅን ያሳያል" ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ይሁን እንጂ በሕይወት ያሉ የማህፀን ለጋሾች ቁጥር በጣም አነስተኛ መሆኑን ይናገራሉ፤ ብዙ ጊዜ ፈቃደኛ የሚሆኑትም የቤተሰብ አባላትና የቅርብ ጓደኞች ናቸው ይላሉ - ዶ/ር ዳኒ። በእንግሊዝ ኢምፔሪያል ኮሌጂ ሐኪም የሆኑት ዶ/ር ስርጃን ሳሶ በቡላቸው አሁን የተገኘው ውጤት በጣም የሚያስደስት እንደሆነ ይናገራሉ። ይህም ብዙዎች ልጅ ወልደው መሳም እየፈለጉ በጤና ችግር ያልቻሉ ወላጆች ተስፋቸውን ያለመለመላቸው አጋጣሚ ሆኗል። በርካታ ለጋሾች ይመጣሉ የሚል ተስፋ እንዳላቸውም ገልፀዋል። "በሕይወት እያሉ ማሕፀናቸውን የሚለግሱ እናቶች በቀዶ ሕክምና ወቅት የሚያጋጥማቸውን አደጋም ያስወግዳል" ሲሉ በታየው ውጤት ተስፋቸው እንደለመለመ አስረድተዋል።
43876447
https://www.bbc.com/amharic/43876447
አሜሪካዊው ወታደር የወንድ መራቢያ አካሉን በንቅለ-ተከላ በማግኘት ፈር ቀዳጅ ሆነ
የአሜሪካ ዶክተሮች የመጀመሪያውን የወንድ የመራቢያ አካላት ንቅለ-ተከላ አከናወኑ።
ባልቲሞር ሜሪላንድ በሚገኘው የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ባለሙያዎች ንቅለ-ተከላውን ያደረጉት በአፍጋኒስታን ሲዋጋ በቦምብ ለቆሰለ ወታደር ነው። ንቅለ-ተከላውም የተከናወነው የወንድ ብልትና የመራቢያ አካላት እንዲሁም የሆድ አካባቢ ህዋሳትን ከሞተ ለጋሽ በመውሰድ ነው። ከአስራ አራት ሰዓት በላይ በወሰደው በዚህ ንቅለ-ተከላ ላይ አስራ አንድ ዶክተሮች ተሳትፈውበታል። በጦርነት ላይ ለተጎዳ ወታደር ሲከናወን የመጀመሪያው የሆነው ይህ ንቅለ-ተከላ፤ ከዚህም በተጨማሪ ከሆድ አካባቢ፣ ሙሉ በሙሉ የወንድ መራቢያ አካላትንና ህዋሳትን በመውሰዱ ፈር ቀዳጅ ነው ተብሏል። ዶክተሮቹ ጨምረውም ቆለጡ ሞራላዊ በሆነ ምክንያት ንቅለ-ተከላ መደረግ እንዳልተቻለም ተገልጿል። በጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ የፕላስቲክና መልሶ ጥገና ኃላፊ የሆኑት ዶክተር አንድሪው ሊ እንዳሉት "ፊት ለፊት የሚታዩ የተቆረጡ አካላት ጉዳታቸውም ይታያል፤ አንዳንድ የጦር ጉዳቶች ግን የተደበቁ በመሆናቸው ተፅኗቸውም በብዙዎች አይታዩም" ብለዋል። በመራቢያ አካላት ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችንም "የጦርነት ያልተነገረላቸው ጉዳቶች" ብለዋቸዋል። በአውሮፓውያኑ 2014 በጆንስ ሆፕኪንስ አስተባባሪነት "ግንኙነት ከጉዳት በኋላ" በሚል ርዕስ በተዘጋጀ ሲምፖዚየም "ከባለቤቶቻቸው፣ ከቤተሰቦቻቸውና ከሚንከባከባከቧቸው ግለሰሰቦች እንደሰማነው፤ በብልታቸው አካባቢ ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች በማንነታቸው ላይ፣ በራሳቸው ላይ ያላቸው እምነት እንዲሁም በግንኙነታቸው ላይ ከፍተኛ ማሽቆልቆል ያጋጥማቸዋል" ብለዋል። ስሙ እንዳይገለፅ የፈለገው ወታደርም ለዩኒቨርሲቲው እንደተናገረው "ዛሬ ከእንቅልፌ ስነቃ እንከን የሌለኝ መስሎ ተሰማኝ፤ በመጨረሻም ደህና ሆንኩኝ" ብሏል። ይህ ወታደር ጉዳቱም የደረሰበት አፍጋኒስታን ውስጥ በሚራመድበት ወቅት የተደበቀ ቦምብ ተረግጦ ነው። ይህ ንቅለ-ተከላ ቆዳ፣ አጥንት፣ ጡንቻዎችን እንዲሁም የደም ስሮችን ሁሉ ያካተተ ሲሆን የቀዶ ጥገና ባለሙያዎቹም ግለሰቡ ከ6-12 ወራት ሙሉ በሙሉ እንደሚያገግም ገልፀዋል። የንቅለ-ተከላው ፕሮግራም ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ሪክ ሬዴት በበኩላቸው ወታደሩ እያገገመ መሆኑንና በቅርቡም ከሆስፒታል እንደሚወጣ ተናግረዋል። "ንቅለ-ተከላው ሽንቱን በትክክል እንዲሸና እንዲሁም ሌሎች ግንኙነቶችን እንደሚያሻሽልለትና ጤናማ ህይወት ሊኖረው እንደሚችል ተስፋ እናደርጋለን" በማለት የሚናገሩት ዶክተሩ ለወደፊትም ለሌሎች ጉዳተኞች ተመሳሳይ የሆነ ንቅለ-ተከላ ሊያካሂዱ እቅድ እንደያዙ ተናግረዋል። የንቅለ-ተከላው ቡደን በበኩሉ የኒቨርስቲው 60 የሚሆኑ የመራቢያ አካላት ንቅለ-ተከላ እቅድ እንደያዘም ተግረዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያው የእስኪት ንቅለ-ተከላ የተደረገው በደቡብ አፍሪካ የቀዶ ጥገና ባለሙያዎች በአውሮፓውያኑ 2014 ነው።
sport-45180742
https://www.bbc.com/amharic/sport-45180742
የጀግና አቀባበል ለአትሌት ፈይሳ ሌሊሳ
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ሃገሩ ሲመለስ ደማቅ አቀባበል ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገለፁ።
አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በሪዮ ኦሎምፒክ አትሌት ፈይሳ ብራዚል ላይ በተደረገው የሪዮ ኦሊምፒክ በማራቶን ውድድር ሁለተኛ በመውጣት ሲያሸንፍ በወቅቱ የነበረውን የተቃውሞ ምልክት በማሳየት የዓለም መገናኛ ብዙሃን መነጋገሪያ ለመሆን ችሎ ነበረ። የኦሊምፒክ ኮሚቴና የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባወጡት መግለጫ በሪዮ ኦሊምፒክ እና በተለያዩ ውድድሮች ለሃገሩ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ሃገሩ ተመልሶ ለአትሌቲክሱ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል። • ፌስቡክ የስፔን ላ-ሊጋ ውድድሮችን ቀጥታ ሊያሳይ ነው • ለኑሮ ምቹ የሆኑ 10 ከተሞች ይፋ ሆኑ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን የኮሚኒኬን ቢሮ ሃላፊ የሆኑት አቶ ስለሺ ብስራት አትሌት ፈይሳ ወደ ሃገር የመመለስ ፍላጎት ካለው ሁለቱ ተቋማት የጀግና አቀባበል ሊያደርጉለት መዘጋጀታቸውን ጠቁመው አትሌቱ ወደ ሃገር የመመለስ ፍላጎት ይኑረው አይኑረው የምናውቀው ነገር የለም ብለዋል። የአትሌቲክስ ፌደሬሽኑ እና አትሌት ፈይሳ ከሪዮ ኦሎምፒክ በኋላ ግኑኘነት አድርገው እንደማያውቁም አቶ ስለሺ ጨምረው ተናግረዋል። በሌላ በኩል አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ሃገር የመመለስ ፍላጎት እንዳለው እና በቀርቡም ወደ ሃገር ለመመለስ ከውሳኔ እንደሚደርስ ለቢቢሲ ተናግሯል። አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በሪዮ ኦሎምፒክ በማራቶትን ውድድር በሁለተኝነት አጠናቆ እጆቹን አጣምሮ ከፍ በማድረግ የተቃውሞውን ምልክት ካሳየ በኋላ ወደ ሃገር ቤት ሳይመለስ ቀርቷል። ከዚያም ተከትሎ ወደ አሜሪካ በመጓዝ ኑሮውን እዚያ ካደረገ በኋላ ባለቤቱና ልጆቹ ከኢትዮጵያ ወደዚያው አቅንተው አብረውት መኖር ጀምረው ነበር። በወቅቱ የነበሩ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ፈይሳ ወደ ሃገር ቤት ቢመለስ ምንም አይነት ችግር እንደማይገጥመው ቢገልፁም እርሱ ግን ለመመለስ አልፈቀደም ነበር። ፈይሳ የዛሬ ዓመት ገደማ ለቢቢሲ በሰጠው ቃለ-ምልልስ ላይ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ ለሃገሩ ለመወዳደር ፍላጎት እንዳለው መግለፁ የሚታወስ ነው። •''አሁንም ኢትዮጵያን ወክዬ መሮጥ እፈልጋለሁ'' አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በኢትዮጵያ ውስጥ ከቅርብ ወራት ወዲህ እየታየ ያለውን ፖለቲካዊ ለውጥ ተከትሎ በርካታ ፖለቲከኞችና ሌሎችም ወደ ሃገርቤት እየተመለሱበት ባለበት በአሁኑ ወቅት አትሌት ፈይሳ ሌሊሳም አንዱ ሊሆን እንደሚችል እየተጠበቀ ነው። በዚህም መሰረትም የኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ኮሚቴና የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት በሆኑት አሸብር ወ/ጊዮርጊስ (ዶ/ር) እና አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በጋራ ተፈርሞ በወጣ ደብዳቤ ላይ ለፈይሳ ሌሊሳን የጀግና አቀባበል ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አሳውቀዋል።
news-53258123
https://www.bbc.com/amharic/news-53258123
በአምቦ የሃጫሉ አጎትን ጨምሮ አምስት ሰዎች መሞታቸው ተነገረ
ዛሬ [ረቡዕ] በአምቦ ከሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ እና የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ከሚፈጸምበት ቦታ ጋር ተያይዞ በተከሰቱ ግጭቶች የሟቹን ድምጻዊ አጎትን ጨምሮ 5 ሰዎች መገደላቸውን ከቤተሰብ፣ ከከተማው ነዋሪዎች እና ከሆስፒታል ምንጮች ቢቢሲ አረጋግጧል።
ሃጫሉ ሁንዴሳ ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪም ከ10 በላይ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውም ተነግሯል። የሃጫሉ ታናሽ ወንድም የሆነው ሃብታሙ ሁንዴሳ ለቢቢሲ ሲናገር “አጎታችን ተገድሏል። በእድሜ ትልቅ ሰው ነው። ያሳደገን ነው። የአባታችን ወንድም ነበር” ብሏል። ከሟቾቹ መካከል የአንዱ የሃጫሉ አጎት መሆናቸውን የኦሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ባልቻም ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ከሃጫሉ አጎት በተጨማሪ ሶስት የቤተሰብ አባላት በጥይት ተመተው የተለያየ ጉዳት እንደደረሰባቸው ሃብታሙ ሁንዴሳ ለቢቢሲ ተናግሯል። “የአጎታችን ሚስት እግሯን ተመታለች፣ የአጎቴን ልጅ የሚያገባም እጁን ተመቷል፣ የእህታችን ባል እግሩ ተመቷል” ብሏል። ሰዎቹ ላይ ጉዳት የደረሰው የድምጻዊ ሃጫሉን አስክሬን እንወስዳለን በማለት ወደ ቤት የመጡ ወጣቶች ጋር የመንግሥት ጸጥታ ኃይል አባላት መጋጨታቸውን ተከትሎ መሆኑ ተነግሯል። ሃብታሙ ሁንዴሳ ለቢቢሲ እንደተናገረው፤ ሃጫሉ አምቦ እንዲቀበር የቤተሰብ ፍላጎት ነው። የአምቦ ሪፈራል ሆስፒታል ምንጮች ለቢቢሲ እንደተናገሩት በጥይት ተመተው ሆስፒታል ከደረሱ በኋላ ወይም ሆስፒታል ሳይደርሱ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር አምስት መሆናቸውን ተናግረዋል። የከተማው ወጣቶች ወደ ምዕራብ ሸዋ ዞን አስተዳደር በመሄድ አርቲስቱ መቀበር ያለበት አዲስ አበባ ነው በማለት ድምጻቸውን ማሰማታቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም ከቤተሰቦቹ ፍላጎት ውጪ አስክሬኑን ወደ አዲስ አበባ እንወስዳለን በማለት ግርግር የፈጠሩ ሰዎች አንደነበሩም ከነዋሪዎች ተረድተናል። የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ቀብር ነገ በአምቦ ከተማ እንደሚከናወን ተነግሯል።
51867058
https://www.bbc.com/amharic/51867058
የኮሮናቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱ ተረጋገጠ
የኮሮናቫይረስ ያለበት አንድ ጃፓናዊ ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።
ሚኒስትሯ ዛሬ ከሰዓት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት የካቲት 25 2012 ዓ.ም ከቡርኪናፋሶ ወደ ኢትዮጵያ የመጣ ጃፓናዊ የኮሮናቫይረስ ተገኝቶበታል። የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ እንዳሉት ጃፓናዊ ትኩሳትና ማሳልን የመሳሰሉ የቫይረሱ ምልክቶችን የሚያሳይ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በለይቶ ማቆያ ውስጥ ይገኛል። የጤንነቱ ሁኔታም መጥፎ የሚባል አንዳልሆነ ጨምረው ገልፀዋል። ከጃፓናዊው ጋር ንክኪ የነበራቸው ከ25 በላይ ሰዎች ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑ በመግለጫው ላይ ተነግሯል። የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መግለጫ ከመስጠቱ ጥቂት ቀደም ብሎም የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ የሆኑት ኢንጂነር ታከለ ኡማ በትዊተር ገፃቸው ላይ አንድ ጃፓናዊ የኮሮናቫይረስ ተገኝቶበታል ሲሉ አስታውቀው ነበር። ከንቲባው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች መውሰድ ያለባቸውን ጥንቃቄ በመልዕክታቸው ላይ ጨምረው አስፍረዋል። በቅርቡ ኢትዮጵያ የነበረና ወደ አሜሪካ የተመለሰ አንድ አሜሪካዊ የኮሮናቫይረስ እንደተገኘበት ተገልጾ እንደነበር ይታወቃል። በጣሊያን አገር በበሽታው ህይወቱ እንዳለፈ ስለተነገረ አንድ "ኢትዮጵያዊ" በሰጡት ምላሽ እስካሁን በውጪ አገር በበሽታው ተይዘዋል ስለተባሉ ኢትዮጵያዊያን የሚያውቁት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን ብቻ እንደሆነና ስለጣሊያኑ መረጃ የለንም ብለዋል። ዶ/ር ሊያ ግለሰቡ ኢትዮጵያ ውስጥ ከየካቲት 9 እስከ የካቲት 13 2012 ዓ.ም እንደቆየና በሽታው ይዞታል ተብሎ ሆስፒታል የገባው የካቲት 30 2012 ዓ.ም እንደሆነ ገልጸዋል። ኮሮናቫይረስ፡ ጀርም ወይም ቫይረስ ከእጅ ወደ አፍ እንዴት ይተላለፋል? እንዴትስ እንከላከለዋለን? ኢትዮጵያ ውስጥ ሳለ ከግለሰቡ ጋር ንክኪ አድርገዋል የተባሉ ሰዎች እንደተመረመሩና እስካሁን ምንም እንዳልተገኘባቸው ተናግረዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት እስካሁን ድረስ ለዜጎች አስፈላጊውን የጥንቃቄ መልዕክት ከማስተላለፍ በዘለለ ምን ዓይነት እርምጃ ለመውሰድ እንዳልተዘጋጀ በመግለጫው ላይ ተጠቁሟል። ሕብረተሰቡ ከመንግሥት የሚሰጡ መረጃዎችን እየሰማ ተግባራዊ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል። ቫይረሱን ለመከላከል አለመጨባበጥ፣ ከቫይረሱ ከተጠቁ አገራት የመጡ እንግዶችን ማሳወቅ፣ ሳል ወይንም ትኩሳት ካለው ግለሰብ መራቅ፣ እጅን በአግባቡ መታጠብ፣ አይንና አፍንጫን አለመንካት እና ሌሎች መልዕክቶች ተላልፈዋል። ከንቲባ ታከለ ኡማ በትዊተር መልዕክታቸው ላይ "...ሁላችንም ከእጅ ንክኪና ከአላስፈላጊ ስብሰባዎች አንቆጠብ ለማለት እፈልጋለሁ" በማለት የጥንቃቄ መልዕክታቸውን ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች አስተላልፈዋል። መንግሥት ለቫይረሱ መከላከል ከ300 ሚሊየን ብር በላይ መድቦ እየሰራ መሆኑን ዶ/ር ሊያ ጨምረው ተናግረዋል። እስካሁን ድረስ ከ134 በላይ አገራት የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው ይታወቃል። ከ130ሺህ በላይ በዓለም ላይ በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ከ4ሺህ በላይ ደግሞ ሞተዋል። ዛሬ ማለዳ በኬንያም አንዲት ከአሜሪካ በለንደን በኩል አድርጋ የመጣች ሴት በቫይረሱ መያዟ ተነግሮ ነበር።
news-45894017
https://www.bbc.com/amharic/news-45894017
የመንገድ አቅጣጫ እንዳይጠፋብን የሚረዱ አንዳንድ ነጥቦች
ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለመሄድ አቅጣጫ መለየት ያስቸግሮታል? ወይስ ጠፍቼ ይሆን ብለው እራስዎን በተደጋጋሚ ይጠይቃሉ?
እንግዲያውስ እነዚህ ምክሮች ይጠቅሞት ይሆናል። • በዝምታ የምትጠማ ከተማ -ሐረር 1. ጉዞዎን ቀደም ብለው ያስቡት መሄድ የሚፈልጉበት ሃገር ወይም ማንኛውም ቦታ ከመሄድዎ በፊት የመንገዶቹን ምስሎች ማግኘት ከቻሉ በደንብ ይመልከቷቸው። እራስዎን በእነዚያ መንገዶች ላይ ሲንሸራሸሩ በጭንቅላትዎ ለመሳል ይሞክሩ። 2. ዘና ይበሉ ጠፋሁ አልጠፋሁ እያሉ የሚጨነቁ ከሆነ ተፈጥሯዊ የሆነውን አቅጣጫ የመለየት ችሎታዎን ያጠፋዋል። ጉዞ ከመጀመርዎ በፊት ቀድመው መዘጋጀትዎ ይህንን ጭንቀት ለመቀነስ ይረዳዎታል። 3. ትኩረት ይስጡ ጉዞ በሚያደርጉ ጊዜ ስልክ የሚያወሩ ከሆነ፣ የጽሁፍ መልዕክት የሚላላኩ ከሆነ አልያም ስለሌላ ነገር የሚያስቡ ከሆነ፤ አካባቢዎን ለማስተዋል ይቸገራሉ። • ኢትዮጵያዊያን በህጋዊ መንገድ ለሥራ መሄድ የሚችሉባቸው ሃገራት የትኞቹ ናቸው? ሙሉ ትኩረትዎን በአንድ ሥራ ላይ ብቻ ያድርጉ። ይሄ ደግሞ በጉዞ ወቅት ትኩረትዎ አካባቢዎ ላይ ብቻ ይሆናል ማለት ነው። 4. የተለዩ ምልክቶች ይፈልጉ እርሶ ከሚያውቁት ነገር ጋር የሚመሳሰል ወይም ለየት ብሎ የሚታይ ነገር በአካባቢዎ ይፈልጉ። በትልቅ ከተማ ውስጥ ከሆነ ያሉት በአካባቢው በጣም ትልቁን ህንጻ ለይተው በምልክትነት ይያዙት። እያንዳንዱ እንቅስቃሴዎን ከህንጻው አንጻር ያድርጉት። • በሥራ ቃለ መጠይቅ ወቅት ልንላቸው የማይገቡ 7 ነጥቦች 5. ወደ ኋላ ይመልከቱ ብዙ ጊዜ ሰዎች ትኩረታቸውን የሚያደርጉት ከፊታቸው ያሉት ነገሮች ላይ ብቻ ነው። ነገር ግን ወደ ኋላ መመልከት መግቢያና መውጫዎን ለመለየት ይረዳዎታል። ወደ ኋላ መመልከት የጥሩ አቅጣጫ አዋቂዎች መገለጫ ነው ተብሏል። በተለይ ደግሞ በተመሳሳይ መንገድ የሚመለሱ ከሆነ ወደ ኋላ መመልከት እጅግ ጠቃሚ ነው። 6. ትውስታዎን ከቦታዎች ጋር ያዛምዱ ይሄ ዘዴ የሄዱባቸውን ቦታዎች በትክክል ለማስታወስ እጅግ ጠቃሚ ነው። • ሞባይል ስልክዎ ላይ መከራን አይጫኑ በተንቀሳቀሱባቸው የተለያዩ ቦታዎች የሰሟቸው ዘፈኖች ቦታዎቹን በትክክል ለማስታወስ እንደሚረዱ ጥናቶች ያሳያሉ። በተለይ ደግሞ በሄዱበት መንገድ የሚመለሱ ከሆነ ሙዚቃ ጥቅም ይኖረዋል። 7. ማስታወሻ ምስል ያስቀሩ የጎበኟቸውን ቦታዎች ደግመው ለማየት የሚያስቡ ከሆነ በእያንዳንዱ ቦታ ማስታወሻ ምስሎችን ያስቀሩ። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከተንቀሳቃሽ ምስል በተሻለ መልኩ ምስል ማንሳት አቅጣጫዎችን ለመለየት ይረዳል። 8. ጉዞዎትን መለስ ብለው ያስቡት ጉዞዎን ካጠናቀቁ በኋላ መለስ ብሎ ማሰብ የማስታወስ ችሎታዎን ለመጨመር ይረዳል። ከላይ የተጠቀሱትን ነገሮች ሁሉ ካደረጉ በኋላ አሁንም የማስታወስ ችሎታዎ ካላስተማመንዎት ዘመነኛ ስልክዎን በመጠቀም መግቢያ መውጫዎን ማየት ይችላሉ። መልካም መንገድ!
news-46602672
https://www.bbc.com/amharic/news-46602672
በካሊፎርኒያ ኪዊቦት የተባለችዋ ምግብ አመላላሽ ሮቦት በእሳት ተያያዘች
ምግብ አመላላሿ ሮቦት ሰዎች በፈጠሩት ስህተት በእሳት ተያይዛ መውደሟን የሮቦቷ ፈጣሪ አስታውቋል።
ኪዊቦት የተሰኙት ራሳቸውን የሚቆጣጠሩት ምግብ አመላላሽ ሮቦቶች ላለፉት 2 ዓመታት በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ በርክሌይ ግቢ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ለተመጋቢዎች ምግብ በማመላለስ ስራ ተጠምደው ይውላሉ። ያለፈው አርብ ግን ለአንዷ ሮቦት ጥሩ ዜና ይዞ አልመጣም፤ አገር ሰላም ብላ የታዘዘችውን ምግብ ለማድረስ ተፍ ተፍ ስትል ነበር የእሳት አደጋ የገጠማት፤ በእሳት ተያይዛ የመውደሟ መርዶም በማህበራዊ ሚዲያዎች ናኘ። • ሳዑዲ ለሮቦት ዜግነት ሰጠች የሮቦቷ ሰሪ ኪዊ ለሮቦቷ እንደዚህ መሆን በስህተት የተገጠመባት ባትሪ ምክንያት እንደሆነ አስታውቋል። ደርጅቱ በሰጠው መግለጫ በሮቦቷ ላይ የተገጠሙት ባትሪዎች መለያየት እንደጀመሩና ከዚያም ቀስ በቀስ እየተቀጣጠለ የእሳት ነበልባልና ጭስ እንደታየ ገልጿል። "የግቢው ማህበረሰብ እሳቱን በፍጥነት ለመቆጣጠር በአቅራቢያ ያለውን የእሳት ማጥፊያ በመጠቀም ጥረት አድርገዋል" ሲሉ የነበረውን ሁኔታም አስረድተዋል። ምንም እንኳን ሮቦቶች እንደዚህ ዓይነት አደጋ ሲያጋጥማቸው የመጀመሪያው ባይሆንም በእርሷ ላይ የደረሰው ግን ያልተጠበቀ ነበር። • ሶፊያ ከአብይ አሕመድ ጋር የራት ቀጠሮ ይዛለች በተመሳሳይ ባለፈው ዓመት የአካባቢ ደህንነት ለመጠበቅ የምትንቀሳቀሰው ሮቦት 'ፋውንቴን' ውስጥ ወድቃ ሰጥማለች። በዚህ ዓመት ታህሳስ ወርም አንዲት ሮቦት የአማዞን የልብስ መሸጫ ህንፃ ጋር ተጋጭታ እዚያ ሲሰሩ የነበሩ ሰዎች ላይ ጉዳት ማስከተሏም ይታወሳል። ኪዊ እንደዚህ አልፎ አልፎ ለሚፈጠሩ አደጋዎች ድጋሜ እንዳይከሰቱ መፍትሔ ለመዘየድ ሮቦቶቹን በሙሉ ከስራ ያገደ ሲሆን የታዘዙ ምግቦችን በሰው ማመላለስ እንደጀመረ አስታውቋል። ድርጅቱ አክሎም እያንዳንዱ ሮቦቶች ላይ የሚገጠመውን ባትሪ የሚከታተል ሌላ ወስጠ-ስሪት (SoftWare) እንዳስገጠመ አስረድቷል። ኪዊ ፌሊፕ ቻቬዝ በተባለ ግለሰብ የተቋቋመ ሲሆን እስካሁንም ሮቦቶቹን በመጠቀም 10 ሺህ የሚደርሱ ምግቦችን ለተጠቃሚዎች ማድረስ ችሏል። • የሃምዛ ሃሚድ ገመድ አልባ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ
news-52405144
https://www.bbc.com/amharic/news-52405144
ኮሮናቫይረስ፡ "በኮሮና ተይዣለሁ ብዬ በመዋሸቴ ለእስር ተዳረግኩ"
ሚካኤል ሌን ብራንደን ፌስቡክ ላይ ሊፅፈው ያሰበው ነገር አወዛጋቢ ሊሆን እንደሚችል አልተጠራጠረም።
ነገር ግን ሥራዬን ያሳጣኛል፣ እከሰስበታለሁ፣ ለእስር እዳረጋለሁ የሚለውን ሃሳብ በጭራሽ ያልጠበቀው ነው። በባለፈው ወር ላይ የኮሮናቫይረስ ቢከሰት እንዴት መከላከል ይቻላል? የሚሉ ክርክሮችን በፌስቡክ ገፁ ላይ እየተመለከተ ድንገት አንድ ሃሳብ ብልጭ አለለት። ደብሮትም ነበር፤ እናም ለምን 'እስቲ በኮሮናቫይረስ ተይዣለሁ' ብዬ ልፃፍና ሰው የሚያደርገውን ልይ አለ። •"ሞትን ተሻገርኳት" ከኮሮናቫይረስ ያገገመች ሴት •ኬንያ ከለይቶ ማቆያ ያመለጡ ሰዎችን እያደነች ነው በኮሮናቫይረስ ተይዣለሁ ብሎም ፃፈ። በዚህም አላቆመም 'ያዳቆነ ሰይጣን . . ." እንደሚባለው ጭራሽ በቫይረሱ መያዙን ያረጋገጡት ዶክተሮች በአየር ላይ ወይም በትንፋሽ ቫይረሱ እንደሚተላለፍ ነግረውኛልም አለ። በቫይረሱ የተያዘ ሰው ድንገት በአቅጣጫዎ ቢያስነጥስ ወይም ቢያስል በአቅራቢያው ካሉ ሊያዙ ይችላሉ ብቻ ሳይሆን ቫይረሱ በአየር ላይ ስለሚቆይ በማንኛውም አጋጣሚ ይይዝዎታል ብሎም ፃፈ። ይህ ሁሉ ግን ውሸት ነበር። ብራንደን ዋናው ማስተላለፍ ፈለግኩ የሚለው ጉዳይ "ማንኛውንም የምታነቡትን ነገር በፍፁም ልቦናችሁ አትመኑ" የሚለውን መልዕከት ነው ይላል። ይህንንም ተከትሎ በርካታ ሰዎች በድንጋጤና በሃዘን መልዕክቶችን ያጎርፉለት ጀመር። ጓደኞቹ ደኅንነቱን ሲጠይቁት ግን "ውሸት ነው" የሚል ምላሽ ሰጣቸው። ብዙዎቹም ተበሳጩበት። ለምን እንዲህ እንዳደረገ ለጓደኞቹ ለማስረዳት እየታገለ ባለበት ወቅት በፌስቡኩ ላይ የፃፈው በኢንተርኔት ላይ ብቻ ሳይሆን በሚኖርባትም ቴክሳስ መነጋገሪያ ሆነ። ወቅቱም የቤት ውስጥ መቀመጥ አስገዳጅ ባልሆነበት ወቅት ነበር። ገና ስለ ቫይረሱ በርካታ መረጃዎች በሚናፈሱበት ወቅት ከመሆኑ ጋር ተያይዞም የአካባቢው ሰው ሆስፒታሎችንና የጤና ተቋማትን በስልክ አጨናነቀ። በትንፋሽ የሚተላለፍ በሸታን እንዴት መቆጣጠር እንችላለን የሚልም የረብሻ ዜናዎች መሰማት ጀመሩ። የእስር ትዕዛዝ የታይፐር ግዛት ፖሊስ ጣቢያም ጉዳዩን መስማቱን ተከትሎም ፅሁፉን እንዲያስተካክል ጠየቁት። ብራንደንም ፖሊስ ባዘዘው መሰረት አስተካከለ። ነገር ግን የፈሰሰ ውሃ አይታፈስ እንዲሉ ጉዳቱን መቆጣጠር አልቻሉም። ፖሊሶች በፌስቡክ ገፃቸው የ23 ዓመቱ ብራንደን ላሰራጨው የሐሰት መረጃ በወንጀል እንደሚጠየቅ ይፋ አደረጉ። በዚህ ብሔራዊ ቀውስ ወቅት ያሰራጨው መሰረት የሌለው መረጃ ረብሻን በመንዛቱ ሊጠየቅ ይገባዋልም አሉ፤ ብራንደንም እጁን ሰጠ። "ዳኛው በነገታው እስኪመጡ ድረስ አንድ ቀን በእስር ቤት ማደር አለብህ አሉኝ። ፍራቻዬ ከአቅሜ በላይ ነበር" ይላል ብራንደን። ከአንድ ቀን እስርም በኋላ በአንድ ሺህ ዶላር ዋስ ከእስር ወጣ፤ ፍርድ ቤትም ቀርቦ ክስ እንደሚጠብቀውም ተነገረው። •በሴቶች የሚመሩ አገራት ወረርሽኙን በተሳካ ሁኔታ እንዴት ተቆጣጠሩት? •ፌስቡክ ከእንግሊዛውያን የጤና መረጃ ሊሰበስብ ነው "የመጀመሪያ ዲግሪዬን የሰራሁት በኮሚዪኒኬሽን የትምህርት ዘርፍ ነው። ይህንንም ስፅፍ እንዴት ማንኛውም ሰው እውነትም ያልሆነ ነገር በመፃፍ ረብሻን ማነሳሳት እንደሚችል ለማሳየት ነበር" ያለው ብራንደን "ሰዎች የተፃፈውን ሁሉ ከማመናቸውም በፊት የራሳቸውን ምርመራ ማድረግ እንደሚገባቸው ለማስረዳት ነው" ብሏል። ሆኖም በዚህ ፅሁፉ ምክንያት ሥራውን አጥቷል፣ የጤና ኢንሹራንሱንም እንዲሁ፤ የድህረ ምረቃ ትምህርቱንም ገንዘብ ስላጠረው እንዲያዘገይ ተገዷል። "ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለቤተሰቦቼም ሸክም ነው የሆንኩት" ብሏል። ዓለም አቀፍ የወረርሽኝ ሐሰተኛ መረጃዎች የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት እንደሚለው ከወረርሽኙ ጋር በተያዘ የሚነዙ ሐሰተኛ መረጃዎችን ለመከላከል ባለስልጣናቱ ፈታኝ ሥራ እንደሆነባቸው ነው። በህንድ፣ በሞሮኮ፣ በታይላንድ፣ በሶማሊያ፣ ኢትዮጵያ፣ ሲንጋፖር፣ ቦትስዋና፣ ሩሲያ፣ ደቡብ አፍሪካና ኬንያ በመሳሰሉ አገራት ሐሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ከነዚህም ውስጥ አንዱ የ41 ዓመቱ ሮበርት አላይ ነው። ሮበርት በኬንያዋ የወደብ ከተማ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ተከስቷል የሚል መረጃን አስተላልፏል። የኬንያ መንግሥት በተደጋጋሚ ሕዝቡ ሐሰተኛ መረጃዎችን ከማሰራጨት እንዲቆጠብና ይህንን በማያደርጉ ሰዎች ላይ እስር እንደሚጠብቃቸው ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። እናም ይህንን ተከትሎም ሮበርት በአገሪቷ የመረጃ መረብ ሕግ መሰረት በወንጀል ተጠያቂ ሆኗል። ሐሰተኛ መረጃን ለማሰራጨትም ሆነ ሰዎችን ለማሳሳት ሃሳቡ እንዳልሆነ የሚናገረው ሮበርት በተጨናነቁ እስር ቤቶች ውስጥ መታሰሩም ስጋት ጥሎበት ነበር። "ሰዎች አይታሰሩ እያልኩ አይደለም ነገር ግን ፖሊሶች ምርመራቸውንና ሥራቸውን በደንብ ሊሰሩ ይገባል። መታሰር የሌለባቸው ንፁሃን ሰዎች ሊታሰሩ አይገባም" ብሏል። ሮበርት በቅርቡ በዋስ ተለቋል።
news-44963090
https://www.bbc.com/amharic/news-44963090
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ በጥይት ተመተው መኪናቸው ውስጥ ሞተው ተገኙ
ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ህይወታቸው ያለፈው በጥይት ተመተው ነው ሲሉ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል ዘይኑ ጀማል አስታወቁ።
ኮሚሽነሩ ጨመረውም እንደተናገሩት ከኢንጂነሩ አስክሬን ጎን ኮልት ሽጉጥ መገኘቱን ገልጸዋል። ዝርዝር የአሟሟታቸውን ሁኔታ በተመለከተ ፖሊስ ምርመራውን እያካሄደ እንደሆነ እና በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞችን እና ምስክሮች ላይ ምረመራ እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂኒየር ስመኘው በቀለ አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ላይ መኪናቸው ውስጥ ባልታወቀ ምክንያት ህይወታቸው አልፎ መገኘቱ ይታወሳል። ሐሙስ ሐምሌ 19/2010 ዓ.ም ጠዋት አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው ትልቁ አደባባይ የሰሌዳ ቁጥሯ ኢቲ ኤ 29722፣ ላንድክሩዘር ቪ8 መኪናቸው ውስጥ ተገኘ የተባለው አስከሬን ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የስነ-ምረዛ እና አስክሬን ምርመራ ክፍል ተወስዶ መምርመራ እየተደረገለት ነው። በአካባቢውም ፖሊስ ተሰማርቶ ምርመራ እያደረገ ሲሆን፤ ለሞታቸው ምክንያት ምን እንደሆነ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም። • በዳንጎቴ ሰራተኞች ግድያ ከ15 በላይ ጥይቶች ተተኩሰዋል • የአሜሪካው ኤፍ ቢ አይ በቦምብ ፍንዳታው ምርምራ ላይ መሰማራቱ ተገለፀ • በሰልፉ ላይ የታየው ክፍተት ምን ነበር? በአካባቢው የሚገኙት የህዳሴ ግድብ አስተባባሪ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ኃይሉ አብርሃም መኪናቸው በፖሊስ ምርመራ እየተደረገለት መሆኑና ብዙ ሰዎችም ተሰብስበው እንዳሉ ገልጸዋል። በትናንትናው ዕለት ቢቢሲ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን አስመልክቶ ኢንጅነር ስመኘውን ባነጋገረበት ወቅት ፕሮጀክቱ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳለ ገልጸው ነበር። ኢንጅነር ስመኘው ግድቡ የደረሰበትን ደረጃ በአካል ተገኘተን መመልከት እንደምንችል እና ከእሳቸውም ግድቡን በተመለከተ ማብራሪያ ለማግኘት በመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በኩል እንድናቀርብላቸው ጠይቀውን ነበር። ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በኢንጂነር ስመኘው ሞት የተሰማቸውን ከፍ ያለ ድንጋጤና ሐዘን በልዩ ረዳታቸው በኩል ገልጸዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ ከሰዓታት በፊት በትዊተር ገጻቸው እንደጻፉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዜናውን የሰሙት አሜሪካ ከደረሱ በኋላ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ለሟች ቤተሰቦችና ወደጃች መጽናናትን ተመኝተዋል። የኢንጅነር ስመኘው ሞት ከተሰማ በኋላ በርካቶች ሃዘናቸውን እየገለጹ ነው። የኢህአዴግ ምክር ቤትም ባወጣው የሃዘን መግለጫ ''ኢንጂነር ስመኘው በቀለ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዕውን እንዲሆን ከኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት የተሰጣቸውን ኃላፊነትንና አደራ ለመወጣት በከፍተኛ ቁርጠኝነት አገልግለዋል። ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ በተጨማሪ በሌሎች የኃይል ማመንጫ ግድቦችም አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡'' ያለ ሲሆን ምክርቤቱ ጨምሮም፤ ''ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ቢለዩም ትጋታቸውና ጽናታቸው በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ ታትሞ የሚኖር ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥትም ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከዳር ለማድረስ የሚያደርጉትን ርብርብ በማጠናከር የኢንጂነር ስመኘው በቀለን ህልምና ራዕይ ዕውን ያደርጋሉ'' ብሏል በመግለጫው። የኢንጂነሩን ሞት ተከትሎም የተቆጡ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጣቢያ ፊት ለፊት በመገኘት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። የተቃውሞ ሰልፈኞቹ ''ኢትዮጵያ ነጻ ትውጣ፣ ፍትህ ለኢንጂነር ስመኘ'' የሚሉ መፈክሮችን ሲያሰሙ ነበር። ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ማናቸው? ኢንጂነር ስመኘው በቀለ በጎንደር ማክሰኚት በ1957 ዓም ተወልዱ። ኢንጂነሩ በ1970ዎቹ መጨረሻ እና 80ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ በቀድሞው ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የቴክኒክ ስልጠና ማዕከል ውስጥ ተማሪ ሆነው መጡ። ከዚያም ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ከተመረቁ በኋላ እዚያው ማስተማር ጀመሩ። መምህር ሆነው የተወሰነ ጊዜ ከቆዩ በኋላ በተፈጠረ አለመግባባት መሥሪያ ቤቱን ለቅቀው የወጡ ሲሆን፤ ሲቪል ኢንጂነሪንግ አጥንተው ዳግመኛ በድርጅቱ ውስጥ ተቀጠሩ። ከዚያም በኋላ የጊቤ አንድ ምክትል ፕሮጀክት ኃላፊ በመሆን በተጨማሪም የጊቤ ሁለት ደግሞ የፕሮጀክቱ ኃላፊ በመሆን ሰርተዋል። ኢንጂነር ስመኘው የሦስት ልጆች አባት ሲሆኑ፤ ባለቤታቸው ከሃገር ውጪ ካናዳ ውስጥ እንደሚገኙ ለቤተሰባቸው ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ኢንጂነር ስመኘው በቀለ በ2007 ዓ.ም የበጎ ሰው ለተባለው ሽልማት መንግሥታዊ ኃላፊነትን በብቃት በመወጣት ዘርፍ ከቀረቡት ዕጩዎች መካከል አንዱ የነበሩ ሲሆን እስከ ህልፈተ- ህይወታቸው ድረስም የታላቁ ህዳሴ ግድብ የፕሮጀክት ኃላፊ በመሆን ለሰባት ዓመታት ያህል ሲሰሩ ቆይተዋል።
news-46471758
https://www.bbc.com/amharic/news-46471758
የኦሮሞ ፓርቲዎች የጋራ ፎረም ለማቋቋም ከስምምነት ላይ ደረሱ
ከ14 በላይ የሚሆኑ የኦሮሞን ጥያቄ ማዕከል ያደረጉ ፓርቲዎች የጋራ ፎረም ለማቋቋም ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።
ስምምነቱ የተደረሰው በዛሬው ዕለት 'የኦሮሚያ ተጨባጭ ሁኔታ እና የዲሞክራሲ ሽግግር'' በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ በኦሮሞ ባህል ማዕከል ውስጥ ምክክር ባደረጉበት ወቅት ነው። የኦዲፒ ምክትል ሊቀ መንበርና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ፣ የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ እና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀ መንበር ዶክተር መረራ ጉዲና በሰጡት መግለጫ በክልሉ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ፎረም እንዲቋቋም ከውሳኔ ላይ ደርሰዋል። •ሶሪያውያን ስደተኞች በአዲስ አበባ ጎዳናዎች •ፑቲን፡ አሜሪካ ስምምነቱን ጥላ ከወጣች ሩሲያ ሚሳዬል ትገነባለች •ጥቁር ለመሆን የሚጥሩት ነጭ እንስቶች ፎረሙ በፓርቲዎች መካከል ችግር ሲያጋጥም በመደማመጥ እና በውይይት ለመፍታት እንዲያስችልና ፓርቲዎቹ በተመሳሳይ ጉዳዮች ላይ አንድ መድረክን ሊፈጥሩ የሚችሉበት ሁኔታም እንዳለ ታምኗል። የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በመግለጫው ላይ "የህዝብ ጥያቄን መመለስ የሚቻለው አንድነት ሲኖረን ነው። መንግሥት የህግ የበላይነትን በሚያስከብርበት ጊዜ እኛም የሚጠበቅብንን ኃላፊነት እንወጣለን" በማለት ቃል ገብተዋል። የኦፌኮ ሊቀ መንበር ዶክተር መረራ ጉዲና በበኩላቸው "አሁን የተመዘገበው ድል በእልህ አስጨራሽ መስዋእትነት የተገኘ በመሆኑ፤ የወጣቱ እና የህዝቡ እንድነት ማጠናከር አለበት" ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም በውይይቱ ላይ ፕሮፌሰር ህዝቅኤል ገቢሳ 'የት ደረስን?' በሚል ርዕስ አንድ ንግግር አቅርበዋል። የኦሮሞ ህዝብ ሰላም እና ዲሞክራሲን መፈለጉ ህዝቡ ያለውን ጥንካሬ ማሳያ እንደሆነ ገልፀው ነገር ግን የፖለቲካ ክፍፍል እና የአመራር እጦት በኦሮሞ ፖለቲካው ውስጥ የሚታዩ ክፍተቶች ፈታኝ ችግሮች እንደሆኑ በንግግራቸው ዳስሰዋል። ውይይቱን የመሩት አቶ ለማ መገርሳ በበኩላቸው ሀገሪቱ እየሄደችበት ያለውን ለውጥ አድንቀው ''ይህች አገር እንደ አገር ለመቀጠል ትክክለኛው የሽግግር ሰዓት ይህ ነው'' ብለዋል። የክልሉ ፕሬዚዳንት ከውይይቱ በኋላ በሰጡት መግለጫ "የኦሮሚያ ክልልን የብጥብጥ አውድማ ለማድረግ ሴራዎች እየተጠነሰሱ ነው ያሉ ሲሆን ህዝቡም ይህን አይነት ተግባር በንቃት መከታተል አለበት" ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
news-52605103
https://www.bbc.com/amharic/news-52605103
የአሜሪካ የኮሮናቫይረስ መቆጣጠሪያ ግብረ-ኃይል ከፍተኛ ኃላፊዎች ራሳቸውን አገለሉ
በኮሮናቫይረስ ከታመመ ሰው ጋር ንክኪ ነበራቸው በሚል ሦስት የዋይት ሐውስ የኮሮናቫይረስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ግብረ ኃይል አባላት ራሳቸውን ለሁለት ሳምንት አግልለዋል ተባለ።
የዋይት ሐውስ ከፍተኛ የሕክምና አማካሪና የአሜሪካ የኮሮናቫይረስ ግብረ ኃይል ከፍተኛ ኃላፊ የሆኑት ዶክተር አንቶኒ ፋውቺ ከተጠቀሱት መካከል አንዱ ናቸው። አሜሪካ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ በምታደርገው ጥረት ፊት ለፊት ሲጋፈጡ የሚታዩት ዶክተር አንቶኒዮ ፋውቺ በበሽታው ከተያዘው ሰው ጋር የነበራቸው ንክኪ "ብዙ ለበሽታውም እንደማያጋልጣቸው" የሚመሩት ድርጅት የአሜሪካው ብሔራዊ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል። •ባራክ ኦባማ አሜሪካ ለወረርሽኙ የሰጠችውን ምላሽ "ቅጥ አምባሩ የጠፋው"ሲሉ ተቹ •በኮሮናቫይረስ ከተቀጠፉ ኢትዮጵያውያን መካከል ጥቂቶቹ የ79 አመቱ አንቶኒዮ ፋውቺ የኮቪድ 19 ምርመራ አድርገው ነፃ መሆናቸው ቢረጋገጥም ለተወሰኑ ጊዜያት ከሰው ተገልልለው በቤታቸው ሆነው እንደሚሰሩና በተከታታይም ምርመራ እንደሚደረግላቸው ኢንስቲትዩቱ ጨምሮ ገልጿል። የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ ፀሐፊ ኬቲ ሚለር፣ የቀዳማዊቷ እመቤት ሜላንያ ትራምፕ ረዳት ስቴፈን ሚለርም ከሰሞኑ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መያዛቸው ተረጋግጧል። የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አልባሽም በቫይረሱ ተይዘዋል ተብሏል። ራሳቸውን ያገለሉት እነማን ናቸው ? የአሜሪካ የበሽታዎች ክትትልና ቁጥጥር ማዕከል ዳይሬክተር ሮበርት ሬድፊልድና የአሜሪካ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ኮሚሽነር ስቴፈን ሃንም በኮሮናቫይረስ ከታመመ ሰው ጋር ግንኙነት ነበራቸው በሚል ራሳቸውን አግልለው ይገኛሉ። •ቤታቸው እስር ቤት የሆነባቸው ጥቃት የሚደርስባቸው ሴቶች የአሜሪካ የበሽታዎች ክትትልና ቁጥጥር ማዕከል ባወጣው መግለጫው የ68 አመቱ ዳይሬክተር የኮሮናቫይረስ ምልክቶች እንደማይታይባቸውና ጤንነታቸውም ጥሩ እንደሆነ አረጋግጦ በዋይት ሃውስ ውስጥ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ፈጥረዋል በሚልም በቤታቸው ሆነው ይሰራሉ ተብሏል። ንክኪ ከማን ጋር እንደነበራቸው አልተገለፀም። የአሜሪካ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ለሮይተርስ እንደተናገረው የ60 አመቱ ኮሚሽነር ስቴፈን ሃንም በተደረገላቸው ምርመራ ነፃ ቢሆኑም ራሳቸውን ለሁለት ሳምንታት ያህል ለይተው እንደሚያቆዩ ቃለ አቀባዩ ገልፀዋል። የአሜሪካ የበሽታዎች ክትትልና ቁጥጥር ማዕከል ዳይሬክተር ሮበርት ሬድፊልድና የአሜሪካ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ኮሚሽነር ስቴፈን ሃንም ራሳቸውን አግልለዋል ሦስቱ የሥራ ኃላፊዎች የምክር ቤቱን አባላትም በሚቀጥለው ሳምንት ምክር ቤቱን ለማናገር ቀጠሮ ይዘው ነበር ተብሏል። የዶክተር አንቶኒዮ ፋውቺ ራሳቸውን የማግለል ዜና ይፋ ከመሆኑ በፊት፣ ከንቲባ ላማር አሌክሳንደር ሁለቱ የሥራ ኃላፊዎች በቪዲዮ ከምክር ቤቱ ጋር ይወያያሉ ብለው ነበር። እስካሁን ባለው መረጃ በአሜሪካ ውስጥ 1.3 ሚሊዮን ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን፣ 78 ሺህ 794 ሞቶች መከሰታቸውን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የተገኘው መረጃ ያሳያል። ይህም አሃዝ አሜሪካን ከአለም ቀዳሚ አድርጓታል። በርካታ የአሜሪካ ግዛቶች የቫይረሱን መዛመት ለመቆጣጠር አስገዳጅ የቤት ውስጥ መቀመጥን ጨምሮ እንቅስቃሴ የሚገድቡ መመሪያዎችን ባለፈው ወር ቢያስተላልፉም ብዙዎቹ መመሪያዎቹን አላልተው ሰዎች ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ ማድረጋቸው በጤና ባለሙያዎች ዘንድ ስጋትን ፈጥሯል። ቫይረሱን ለመቆጣጠር እያደረገች ያለችውን እርምጃም የቀድሞው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ "ቅጥ አምባሩ የጠፋው" ሲሉ ክፉኛ ተችተውታል።
news-47931891
https://www.bbc.com/amharic/news-47931891
ኢቫንካ ትራምፕ አዲስ አበባ ናቸው
የዶናልድ ትራምፕ የመጀመሪያ ሴት ልጅና የዋይት ሃውስ አማካሪ ኢቫንካ ትራምፕ የሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ ላይ ትኩረት ያደረገ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን በአዲስ አበባ ጀምረዋል።
ኢቫንካና የሙያ ባህል አልባሳት ማምረቻ ማዕከል መስራች ሳራ አበራ ኢቫንካ ለሁለት ቀናት በሚቆየው ጉብኝታቸው የመጀመሪያ ውሎ የባህላዊ አልባሳት ማምረቻ ማዕከልን ጎብኝተዋል። በአሜሪካ መንግሥት የሚደገፍው እና በሥራ ቦታ ላይ የሴቶችን ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ የሚሰራው ፕሮጄክት እ.ኤ.አ 2025 ድረስ እያደጉ ባሉ ሃገራት ውስጥ የሚኖሩ 50 ሚሊዮን ሴቶችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል። የዶናልድ ትራምፕ ልጅ በመጀመሪያ ቀን ውሏቸው በሴት የሚመራ የአልባሳት ማምረቻ ተቋምን ጎብኝተዋል። • የዓለማችን ሃብታም ሴቶች • ሰዎች ለምንድነው ምትሃት የሚወዱት? • "ኢትዮጵያ የከሸፈች ሀገር እየሆነች ነው" ሻለቃ ዳዊት የትራምፕ አስተዳደር ፖሊሲ አፍሪካን በተመለከተ በሁለት ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጓል፤ ሽብርን መዋጋት እና የቻይናን ተጽእኖ በቅርብ መከታተል። ትራምፕ አፍሪካን በሚመለከት ዘግየተው ይፋ ያደረጉት ይህ ፖሊሲ በበርካቶች ዘንድ ተቀባይነትን አላገኘም። ከዚህ ቀደም አሜሪካ ስታደርገው እንደቆየችው በአፍሪካ ዴሞክራሲ እንዲዳብር፣ ነጻ እና ተዓማኒነት ያለው ምርጫ እና የሰብዓዊ መብት እንዲጠበቅ ትኩረት መሰጠት አለበት ይላሉ። ከሁለት ወራት በፊት ይፋ የተደረገው 'ዓለም አቀፍ የሴቶች እድገት እና ብልጽግና' የተሰኘው ፕሮጄክት፣ ለሴቶች ዘረፈ ብዙ ስልጠናዎችን በመስጠት ጥሩ ገቢ የሚያስገኙ ስራዎችን እንዲያገኙ ይሰራል ተብሏል። ኢቫንካ በመጀመሪያ ቀን ውሏቸው ሙያ ኢትዮጵያ የተሰኘ የአልባሳት ማምረቻ ድርጅትን ጎብኝተዋል። ድርጅቱ ከ16 ዓመታት በፊት የተመሰረተ ሲሆን ኢቫንካ ትራምፕን የድርጅቱ መስራት ሳራ አበራ አስጎብኝተዋቸዋል። ይህ ፕሮጀክት 'በዩ ኤስ አይ ዲ' የ50 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ይደረግለታል። ኢቫንካ ትራምፕ በኢትዮጵያ በቆይታቸው ከፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል። ኢቫንካ ከኢትዮጵያ ጉብኝታቸው በመቀጠል ወደ አይቮሪኮስት በማቅናት የሴቶችን ኢኮኖሚ በማጠንከር ዙሪያ በሚዘጋጅ ጉባዔ ላይ ይሳተፋሉ።
news-52571169
https://www.bbc.com/amharic/news-52571169
“በከሸፈው መፈንቅለ መንግሥት ተሳትፈናል” የአሜሪካውያኖቹ ኑዛዜ በቬንዙዌላ ቴሌቪዥን
አሜሪካውያኖቹ የቬንዙዌላውን ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮን ለመጣል መፈንቅለ መንግሥት የማካሄዳቸውን ኑዛዜ የቬንዙዌላው ቴሌቪዥን አሳይቷል።
ፕሬዚደንት ኒኮላስ ማዱሮ( በስተግራ) እና ሉኬ ደንማን እና ኤራን ቤሪ (በስተቀኝ) ፕሬዚዳንት ኒኮላስን መገልበጥ ብቻ ሳይሆን ይዘውም አሜሪካ እንዲያመጧቸው ትዕዛዝ መተላለፉንም ተናዘዋል። በባለፈው ሳምንት ቬንዙዌላ ከሽፏል ያለችው መፈንቅለ መንግሥትን ተከትሎ አስራ ሶስት ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውላለች። ከነዚህም ውስጥ አንዱ አሜሪካዊው ሉክ ዴንማን ነው። ቬንዙዌላ “ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮች” ስትል የጠራቻቸውን ሲሆን “እቅዳቸውም አልተሳካም” ብላለች። ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮ በተደጋጋሚ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ከስልጣን ሊገለብጧቸው እንደሚያሴሩና ሃገራቸውንም ለመውረር እንደሚያቅዱ ሲናገሩ ይሰማሉ። በዚህም ሳምንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ አልተሳተፈችም ሲሉ ውንጀላውን ውድቅ አድርገውታል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኃላፊ ማይክ ፖምፔዮ በበኩላቸው መንግሥታቸው ዜጎቹን ደህንነታቸው በተጠበቀ መልኩ እንዲመለሱ “የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም” ብለዋል። የቬንዙዌላ ቴሌቪዥን ምን አለ? በትናንትናው ዕለት የ34 አመቱ ሉክ ደንማን ለመፈንቅለ መንግሥቱ የሚሆኑ ቬንዙዌላውያንን እንዲመለምልና ወደ ኮሎምቢያ ወስዶ ስልጠና እንዲሰጣቸው ትእዛዝ ተሰጥቶኛል ብሏል። በመቀጠልም የሃገሪቱን አየር መንገድ በቁጥጥራቸው ስር እንዲያውሉና ፕሬዚዳንቱም ተይዘው ከሃገር እንዲወጡ አቅጣጫ መሰጠቱን ጠቁሟል። • በህዋ ላይ ፊልም ለመቅረጽ ቶም ክሩዝ እና ናሳ ተጣመሩ • ደቡብ ኮርያ ኪም የልብ ቀዶ ህክምና ስለማድረጋቸው 'ምንም ምልክት የለም' አለች • በእንቅስቃሴ ገደቡ ወቅት በርካታ አፍሪካውያን የምግብ እጥረት ያጋጥማቸዋል “ቬንዙዌላውያን ሃገራቸውን መልሰው እንዲቆጣጠሩ እየረዳሁ ነበር” ያለው ሉክ ደንማን የቀድሞ የልዩ ኃይል ተልእኮ አባል ነበር። ሉክና የ41 አመቱ አሪያን ቤሪ የተባለው ሌላ አሜሪካዊ ሲልቨርኮፕ በተባለ ኩባንያ መቀጠራቸውንም ግለሰቡ አጋልጧል። ኩባንያውን መቀመጫውን ፍሎሪዳ ያደረገ ሲሆን፤ ተልዕኮውንም የሚመሩት ጆርዳን ጎድሩ የተባሉ የአሜሪካ የጦር ኃይል አባል የነበሩ ግለሰብ ናቸው ብሏል። ቬንዙዌላ ጆርዳን ጎድሩ ተላልፈው እንዲደሰጡ እጠይቃለሁ ያለች ሲሆን፤ ግለሰቡም በመፈንቅለ መንግሥት ተልዕኮው ላይ ተሳትፎ እንደነበራቸው አምነዋል። ሲልቨርኮፕ የተባለው ኩባንያ በበቬንዙዌላ ውስጥ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ የሆኑትና በአውሮፓውያንና በአሜሪካውያን ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው ጁዋን ጉዋይዶ ጋር ስምምነት እንዳላቸው ፕሬዚዳንቱ ኒኮላስ ማዱሮ ገልፀዋል። “የወረራው ጠንሳሽ ዶናልድ ትራምፕ ናቸው” በማለት ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮ ከአሜሪካዊው ኑዛዜ በኋላ በሰጡት መግለጫ ወርፈዋቸዋል። ፕሬዚዳንቱ አክለውም አሜሪካውያኖቹ ፍትሃዊ ፍርድ ይጠብቃቸዋል ከማለት ውጭ ግለሰቦቹ የት እንደታሰሩ፣ ጠበቃ አግኝተው እንደሆነና ሌሎች መረጃዎች ከመስጠት ተቆጥበዋል። ስለ አሜሪካውያኖቹ የቀደመ ታሪክ ዝርዝር መረጃ ባይገኝም ቬንዙዌላ የአሜሪካ የፀጥታ ኃይል አባላት ናቸው ስትል፤ የአሜሪካ ሚዲያዎች በበኩላቸው የቀድሞ አባላት ናቸው ብለዋል። ከአሜሪካ መንግሥት ግን ስለማንነታቸው የተሰጠ መረጃ የለም። ጆርዳን ጎድሩ ከዚህ ቀደምም ከቬንዙዌላው ፖለቲከኛ ጁዋን ጉዋይዶ ጋር ግንኙነት አለኝ ሲሉ በተደጋጋሚ ተሰምተዋል። ፖለቲከኛው በበኩላቸው በመግለጫቸው የጦር ኃይል አባሉን እንደማያውቋቸውና “ከተፈፀሙት ነገሮችም ጋር ምንም አይነት ንክኪም ሆነ ኃላፊነት የለኝም” ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ ፕሬዚዳንቱን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ የመጡ ግድያዎችና ግጭቶችን ለማዘናጋት የፈጠሩት ዘዴ ነው በሚልም ፖለቲከኛው ተችተዋቸዋል። የከሸፈው መፈንቅለ መንግሥትን ተከትሎ 11 ሰዎች ሲታሰሩ፣ ስምንት ሰዎች ደግሞ ተገድለዋል።
news-52208070
https://www.bbc.com/amharic/news-52208070
እስራኤል ዜጋዬን ለኢራን ሲሰልል ደረስኩበት አለች
እስራኤል አንድ ዜጋዋ ዋነኛ ጠላቴ ለምትላት ኢራን ሲሰልል ደርሼበታለው ስትል በቁጥጥር ስር እንዳዋለችው ገልጻለች።
ግለሰቡ ለኢራን ጠቃሚ መረጃዎችን ሲያቀብል ነበር ተብሏል ግለሰቡ ለኢራን ከመሰለሉም በተጨማሪ የሽብር ጥቃት እያቀነባበረ ነበር ተብሏል። ሺን ቤት የሚባለው የእስራኤል የአገር ውስጥ የደኅንነት መስሪያ ቤት ሹም እንዳሉት ግለሰቡ ከኢራን የደኅንነት መሥሪያ ቤት ጋር ሌሎች አረብ-እስራኤላዊያን አሸባሪዎችን መመልመል በሚቻልበት ሁኔታ እየተወያየ ነበር። ግለሰቡ የእስራኤልን ደኅንነት አደጋ ላይ በመጣል ክስ ተመሥርቶበታል። ተጠርጣሪው ማንነቱ በስም አልተጠቀሰም። ሺን ቤት እንደሚለው ግለሰቡ ባለፈው ወር በቁጥጥር ሥር ሲውል በእጁ የመረጃ ቋት ማጠራቀሚያ ሃርድ ዲስክ እንዲሁም መልዕክትን ከተቀባይ እስከ ላኪ በምሥጢር የሚተበትብ መላን የያዘ ሁነኛ መረጃን ይዞ ነበር። ግለሰቡ በእስራኤል አደጋ ሊጣልባቸው የሚቻልባቸውን ቁልፍ ቦታዎች ለኢራን በመጠቆም ክፍያ ይቀበል ነበር ተብሏል። የክስ ዶሴው እንደሚያስረዳው ግሰለቡ በቅርብ ጊዜ ፖፑላር ፍሮንት ፎር ሊብሬሽን ከተባለ የሊባኖስ ቡድን አባል ጋር ሁለት ጊዜ ምሥጢራዊ ግንኙነት አድርጓል ተብሏል። ሁለቱ የተገናኙት በሁለት የተለያዩ ቦታዎች ነበር። ከዚህም ሌላ በሃንጋሪ ቡዳፔስት ውስጥ ከኢራን የደኅንነት መሥሪያ ቤት አባላት ጋር ተገናኝቶ ነበር። እስራኤላዊው ሰው ወደ ውጭ ባደረጋቸው ጉዞዎች መረጃን ስለመተብተብ፣ ስለመቆለፍና ስለመተንተን ስልጠና ተሰጥቶታል። ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ የቀድሞ የካቢኔ ሚኒስትር ጎነን ሴጎቭ ለኢራን ይሰልሉ ነበር በሚል ዘብጥያ መውረዳቸው ይታወሳል።፡
news-48442244
https://www.bbc.com/amharic/news-48442244
የሶማሌ ላንድ መስጊዶች ድምፅ እንዲቀንሱ ተጠየቁ
የራስ ገዝ አስተዳዳር በሆነችው ሶማሌ ላንድ የሚገኙ መስጊዶች ሌሊቱን ሙሉ በሚያካሂዱት የፀሎት ሥነ ሥርዓት ድምፅ እንዲቀንሱ አሊያም ሙሉ በሙሉ እንዲያጠፉ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው።
የሃይማኖት ጉዳዮች ጀኔራል ዳይሬክተር አዳን አበዲላሂ አባዳሌ ለቢቢሲ እንደገለፁት ኢማሞችና የመስጊዶቹ ባለሥልጣናት ጎረቤቶቻቸውን በማክበር በተለይ ግዴታ ያልሆነውንና ከእኩለ ሌሊት በኋላ የሚደረገውን የታሃጁድ ፀሎት እንዲተዉ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ብለዋል። ታሃጁድ ከኢንሻ ሶላት በኋላ የሚደረግ የፀሎት ሥነ ስርዓት ነው። • ሶማሊላንድ አስገድዶ መድፈርን በተመለከተ የመጀመሪያ ሕግ አወጣች • በፆም ወቅት ሰውነታችን ውስጥ ምን ይካሄዳል? • የጄል ኦጋዴን እስር ቤት ኃላፊ ተይዞ ለኢትዮጵያ ተሰጠ በመስጊዶቹ አቅራቢያ የሚኖሩ ሰዎች ከመስጊዶቹ ከተገጠሙት የድምፅ ማጉያ የሚወጡት ድምፆች ከእንቅልፋቸው እንደሚረብሻቸው ቅሬታቸውን እቅርበዋል። በተለይ ድምፁ ለአዛውንቶችና በህመም ላይ ላሉ ሰዎች ከባድ ነው ብለዋል። ሌሎች ደግሞ መስጊዶች አዛን በማድረግ የእምነቱን ተከታዮች ማንቃትና መጥራት መብታቸው ነው ሲሉ ይከራከራሉ። አክለውም መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገባ አስጠንቅቀዋል። በሶማሌ ላንድ የሚኖሩት አብዛኞቹ የእስልምና እምነት ተከታዮች ሲሆኑ ግዛቷ ራሷን የምታስተዳድር ቢሆንም በዓለም አቀፍ ደረጃ አንደ አንድ ራሷን እንደቻለች አገር እውቅና አልተሰጣትም።
news-49725564
https://www.bbc.com/amharic/news-49725564
ለሰው ልጅ ምርጡ ምግብ እንቁላል ይሆን?
የሰው ልጅ ከሚበላቸው ምግቦች መካከል እጅግ ፍጹም የሆነውን ማግኘት ከባድ ሊሆን ይችላል፤ እንቁላል ግን ለፍጹምነት የቀረበ የምግብ አይነት እንደሆነ ይነገርለታል።
እንቁላል በቀላሉ መገኘት ይችላል፣ በቀላሉ መብሰል ይችላል፣ ዋጋውም ርካሽ የሚባል ሲሆን ለሰውነታችን በጣም አስፈላጊ የሆነው ፕሮቲንንም በብዛት ይዟል። በዩኒቨርሲቲ ኦፈ ከነቲከት የሥነ ምግብ ሳይንስ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ክሪስቶፈር ብሌሶ እንደሚሉት እንቁላል ሁሉም አይነት አስፈላጊ ንጥረ ነገሮች ያሉት ሲሆን፤ አንድን ፍጥረት በተገቢው ሁኔታ ለማሳደግ ብቻውን በቂ ሊሆን እንደሚችል ይናገራሉ። • ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን? ከዚህ በተጨማሪ እንቁላልን ከሌሎች ምግቦች ጋር ቀላቅሎ መመገብ ሰውነታችን ቫይታሚኖችን በቀላሉ ለመሰብሰብ ያስችለዋል። ለምሳሌ አንድ ጥናት እንደጠቆመው እንቁላልን ከአትክልት ጋር መመገብ በአትክልቱ ውስጥ ያለውን ቫይታሚን ኢ የመሰብሰብ ሥራን ቀላል ያደርገዋል። ነገር ግን በእንቁላል ውስጥ ያለው የኮሌስትሮል መጠን ከፍተኛ በመሆኑ ለብዙ ዓመታት መከራከሪያ ሆኖ ቆይቷል። ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠን ደግሞ ለልብ በሽታዎች ያጋልጣል። በእንቁላል ውስጥ የሚገኘው አስኳል እስከ 185 ሚሊግራም የሚደርስ ኮሌስትሮል በውስጡ ይይዛል። ይህ ማለት እንቁላል ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል ማለት ነው? ኮሌስትሮል በጉበታችንና በጨጓራችን ውስጥ የሚመረት ቢጫ ቀለም ያለው 'ፋት' (ጮማ) ሲሆን በእያንዳንዱ የሰውነታችን ሴሎች ውስጥ ይገኛል። ብዙዎቻችን መጥፎ ነገር እንደሆነ እናስባለን። ነገር ግን ኮሌስትሮል ሴሎቻችንን ሸፍኖ ከተለያዩ ነገሮች ይጠብቃቸዋል። ከዚህ ባለፈም ቫይታሚን ዲ ለማምረትና እንደ ቴስቴስትሮን እና ኦስትሮጅን ያሉ ሆርሞኖችን ለማማንጨት ይረዳል። ምንም እንኳን ሰውነታችን ኮሌስትሮልን በራሱ ማማረት ቢችልም ከተለያዩ የእንስሳት ምርቶችም ሊያገኝ ይችላል። ለምሳሌ የበሬ ሥጋ፣ እንቁላል፣ አይብ እና ቅቤን መጥቀስ ይቻላል። • ምግብ ወሲብን የተሻለ ያደርጋል? መርሳት የሌለብን እንደ ልብ በሽታ ላሉ ከፍተኛ የጤና እክሎች የሚያጋልጠን ኮሌስትሮል በተፈጥሯዊ መንገድ የሚመረተው ሳይሆን፤ ሰው ሰራሽ የሆነው በተጠበሱ ምግቦች፣ ኬኮችና ሌሎችም ውስጥ የሚገኙት ናቸው። በእንቁላል ውስጥ የሚገኘው የኮሌስትሮል መጠን ከተለያዩ የእንስሳት ምርቶች የበለጠ ቢሆንም የስብ (ፋት) ክምችቱ ግን በጣም አነስተኛ ነው። ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ደግሞ ይህ የስብ ክምችት የደም ቧንቧችንን በመድፈን ለልብ በሽታ ሊያጋልጠን ይችላል። በቦስተን ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ኤሊዛቤት ጆንሰን እና ባልደረቦቻቸው በሰሩት ጥናት መሰረት ከቀጥተኛ የእንስሳት ተዋጽኦ የምናገኘው ኮሌስትሮል ለልብ ህመም እንደሚያጋልጥ ማረጋገጫ ማግኘት አልተቻለም። ሰውነታችን ኮሌስትሮልን እንደ እንቁላል ካሉ ምግቦች ማግኘት ከቻለ በራሱ የሚያመርተውን መጠን መቀነስ ይችላል። ይህ ማለት ደግሞ ተፈጥሯዊው ኮሌስትሮል መቼም ቢሆን በሰውነታችን ውስጥ መኖር ካለበት መጠን አያልፍም ማለት ነው። • እውን እንጀራ ሱስ ያስይዛል? የምርምርና ስርፀት ሥራዎች በኢትዮጵያ የዘርፉ ባለሙያዎች በቅርቡ በሰሩት ጥናት እንቁላል ምንም አይነት የጤና እክል እንደማያስከትል አረጋግጠናል እያሉ ነው። ተመራማሪዎቹ ባለፉት 17 ዓመታት 30 ሺህ ሰዎች ስለተመገቧቸው ምግቦች የሚያትቱ መረጃዎችን ሲያሰባስቡ ነበር። በጥናቱም መሰረት በየቀኑ እንቁላል የሚመገቡ ሰዎች በተለያዩ የልብ በሽታዎች የመሞት እድላቸው 18 በመቶ የቀነሰ መሆኑን የደረሱበት ሲሆን በደም ግፊት የመያዝ እድል ደግሞ እንቁላል ከማይመገቡት ጋር ሲነጻጸር 28 በመቶ የቀነሰ ነው። ምንም አንኳን እርግጠኛ ሆኖ መደምደም ባይቻልም እንቁላል ከጉዳቱ ጥቅሙ እንደሚጎላ መገመት ቀላል ነው። በእንቁላል ውስጥ የሚገኘው ኮላይን የተባለው ንጥረ ነገር የመርሳት በሽታን ለመከላከልና ጉበታችን ከጎጂ ነገሮች ለመከላከል ይረዳል።
news-55610110
https://www.bbc.com/amharic/news-55610110
ቻይና የትራምፕን ማዕቀብ ለመቋቋም አዲስ ሕግ ይፋ አደረገች
ቻይና ኩባንያዎቿን "ትክክለኛ ካልሆኑ" ሕጎች የሚከላከሉ አዳዲስ ሕጎችን በማውጣት የአሜሪካ ማዕቀብን ለመከላለከል እየሠራች መሆኗ ተነገረ።
በሳምንቱ መጨረሻ ይፋ የተደረጉት ለውጦች የቻይና ፍርድ ቤቶች እንደዚህ ያሉ ገደቦች የሚመለከታቸው ኩባንያዎችን እንዲቀጡ ያስችላቸዋል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለአሜሪካ ደኅንነት ስጋት ናቸው ያሏቸው የቻይና ኩባንያዎች ላይ ማነጣጠራቸውን ቀጥለዋል። እርምጃዎቹ በጥቁር መዝገብ ላይ ከሰፈሩ ድርጅቶች ጋር የሚሠሩት መቅጣትን ያካትታሉ። ሰኞ ዕለት በኒው ዮርክ የአክሲዮን ገበያ (NYSE) የተዘረዘሩ ሦስት ትልልቅ የቻይና የቴሌኮም ኩባንያዎች ከአገሪቱ ወታደራዊ ኃይል ጋር ግንኙነቶች አላቸው በሚል የአክሲዮን ድርሻቸውን እንዳይሸጡ ይከለከላል ተብሎ ይጠበቃል። ትራምፕ ባስተላለፉት ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ መሠረት የኒው ዮርክ የአክሲዮን ገበያ ቻይና ሞባይል፣ ቻይና ቴሌኮም እና ቻይና ዩኒኮም ሆንግ ኮንግ የተባሉት ድርጅቶች እያሰናበተ ነው። በቅርብ ወራት እንደቲክቶክ፣ ሁዋዌ እና የማይክሮቺፕ አምራች የሆነው ሴሚኮንዳክተር ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርናሽናል ኮርፖሬሽን ጨምሮ በቻይና ኩባንያዎች ላይ የተወሰዱ እርምጃዎችን ተከትሎ የመጣ ነው። ትራምፕ ባለፈው ሳምንት ታዋቂ የክፍያ ዘዴዎቹን አሊፔይን እና ዌቻት ፔይን ጨምሮ ከስምንት የቻይና መተግበሪያዎች ጋር ግብይቶችን ለማድረግ የሚያግደውን ትዕዛዝ ፈርመዋል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት መሰል የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች መረጃዎችን ከቻይና መንግሥት ጋር እንደሚያጋሩ ቢገልጹም ኩባንያዎቹ ክሱን ውድቅ ያደርጋሉ። የቻይና ንግድ ሚኒስቴር ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ የውጭ ሕጎችን "ተገቢ ያልሆነ የክልከላ አተገባበርን በመቃወም" ላይ አዲሱን ሕግ አስተዋውቋል። በሲንጋፖር ዩኒቨርሲቲ የምሥራቅ እስያ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር የሆኑት በርት ሆፍማን "በውጭ ሕግ ምክንያት የተጎዱ ሕጋዊ አካላት በፍርድ ቤት ጉዳያቸውን በማቅረብ ለደረሰው ጉዳት ካሳ መጠየቅ ይችላሉ። መንግሥትም ሌሎች የመከላከያ እርምጃዎችን መውሰድ ይችላል" ብለዋል። የመልስ ምት ቻይና በአሜሪካ ማዕቀብ እና በንግድ ላይ እገዳዎች ዙሪያ ለረዥም ጊዜ ቅሬታዋን ብትገልፅም ወደ ተግባር የገቡት እርምጃዎች በቀጥታ አሜሪካን አይጠቅሱም። የሕግ ባለሙያዎች አዲሱ ሕግ እንዴት እንደሚተገበር ግልፅ አለመሆኑን ይናገራሉ። የሕግ ባለሙያው ኒኮላስ ተርነር "ግልጽ መሆን የሚገባው አንድ ነጥብ ሕጉ በቻይና ላይ በተጣሉ ማዕቀቦች ላይ ያነጣጠረ ነው ወይስ እንደ ኢራን ወይም ሩሲያ ባሉ በሦስተኛ አገራት እና ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድም ቻይናን በሚነኩ ማዕቀቦችም ላይ ተግባራዊ የሚሆን ነው የሚለው ነው" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በቻይና ከፍተኛ የንግድ ፍላጎት ያላቸው ኩባንያዎች በጥንቃቄ መመልከት ሊያስፈልጋቸው ይችላል። በሆንግ ኮንግ ዩኒቨርሲቲ የቻይና የሕግ ፕሮፌሰር የሆኑት አንጄላ ዣንግ "አንድ ሁኔታን እናንሳ፤ አንድ የአውሮፓ ባንክ በአሜሪካ ማዕቀብ የተጣለበትን የቻይና ባለሥልጣን ንብረት እንዳይንቀሳቀስ ቢያደርግ፣ የቻይና ሕግ ባለሥልጣኑ የደረሰበትን ኪሳራ ለማስመለስ ባንኩን የመክሰስ መብት ይሰጠዋል" ብለዋል። እንደተርነር ከሆነ ትራምፕ በዚህ ወር መጨረሻ ከዋይት ሐውስ ከመውጣታቸው በፊት ሊያመጡዋቸው ከሚችሏቸው የወደፊት ማዕቀቦች ቻይና ራሷን እየተከላከለች እንደሆነ ያምናሉ። "ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በተሰጡ መግለጫዎች ላይ በመመስረት በጥቂት ቀናት ውስጥ ተጨማሪ እርምጃዎች ይወሰዳሉ ብዬ እጠብቃለሁ። የቀሩትን ቀናት ሁኔታውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ማንኛውንም አዲስ እገዳ ማወጣት መቻላቸው የሚታሰብ አይደለም" ብለዋል።
46232660
https://www.bbc.com/amharic/46232660
በቤንሻንጉል ክልል ካማሺ ዞን በሚገኙ 5 ወረዳዎች የመንግስት ሥራ ከተቋረጠ ሁለት ወር እንዳለፈው ተገለፀ
በቤንሻንጉል ክልላዊ መንግሥት በካማሺ ዞን በሚገኙ ወረዳዎች በነበረው ግጭት ምክንያት ላለፉት ሁለት ወራት የመንግሥት ስራ በመስተጓጎሉ ሰራተኞች ደመወዝ፣ የአካባቢው ነዋሪዎችም መሰረታዊ አገልግሎቶችንም እያገኙ አለመሆኑን ከክልሉ ኃላፊዎች ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ካማሺ ዞን በካማሺ ዞን ስር በሚገኙ አምስት ወረዳዎች፣ ከአሶሳ ዞን ደግሞ ኦዳ ወረዳ እንዲሁም ማኦ ኮሞ ወረዳዎች የመድሃኒት አቅርቦት ችግር እንደገጠማቸው የክልሉ የጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሐብታሙ ታዬ ለቢቢሲ ገለፀዋል። እንደ ኃላፊው ገለፃ በካማሺ ዞን 69 ቀበሌዎች ያሉ ሲሆን በሁሉም ቀበሌዎች የጤና ኬላዎች አሉ፤ በተጨማሪ ደግሞ 8 ጤና ጣቢያዎች ቢኖሩም በአሁኑ ሰዓት ሁሉም የመድሀኒት አቅርቦት ችግር ገጥሟቸዋል። • የካማሼ ዞን አመራሮች በታጣቂዎች ተገደሉ • በነቀምት የሚገኝ አንድ ቤተሰብ ለ1000 ተፈናቃዮች ድጋፍ እያደረገ ነው • የካማሼ ዞን ተፈናቃዮች አሁንም ስጋት ላይ እንደሆኑ ገለፁ በዞኑ የሚኙ ወረዳዎች ቆላማ በመሆናቸው ምክንያት የወባ ስርጭት እንዳለ ያስታወሱት ኃላፊው፤ በተለይ በሶስት ወረዳዎች ላይ በአንድ ሳምንት ብቻ ከ600 ሰዎች በላይ በወባ ታምመው ወደ ጤና ኬላዎች መምጣታቸውን መረጃ እንደደረሳቸው ተናግረዋል። ካማሺ ዞን ውስጥ ትልቅ ሆስፒታል የለም ያሉት ኃላፊው እስከ ቀዶ ጥገና የሚያስፈልገው ህክምና ሲኖር ከዚህ በፊት ኦሮሚያ ውስጥ በሚገኙ ሆስፒታሎች በመሄድ ህክምና እንዲያገኙ ይደረግ እንደነበር አስታውሰዋል። አሁን በፀጥታው ምክንያት የተሻለ ህክምና የሚያስፈልጋቸው እናቶች ወደ ኦሮሚያ ሄደው መታከም ባለመቻላቸው አምስት እናቶች በዞኑ በህክምና እጦት ምክንያት መሞታቸውን መረጃ እንዳላቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። የጤና ቢሮ ኃላፊ እንደሚሉት ከሆነ በካማሺ ዞን በነበረው ግጭት ምክንያት በዞኑ ስር ከሚገኙ አምስቱም ወረዳዎች የለቀቁ ባለሙያዎችም አሉ። ከዚህ በፊት ወደ ካማሺ ዞን መድሃኒት ይደርስ የነበረው ከነቀምት ወይንም ከአሶሳ እንደነበር አስታውሰው በአሁኑ ሰዓት ወደ ካማሺ ዞን የሚወስዱት ሁለቱም መንገዶች በፀጥታ ችግር ምክንያት በመዘጋታቸው መድሃኒት ማቅረብም ሆነ የተሻለ ህክምና የሚፈልጉ ሰዎችን ወደ አጎራባች ክልል የሕክምና ተቋማት መውሰድ አልተቻለም ብለዋል። አልፎ አልፎ በክልሉ በምትንቀሳቀሰው ሄሊኮፕተር መድሃኒት ለመላክ መሞከራቸውን የተናገሩት የጤና ቢሮ ኃላፊው በአሁኑ ሰአት ግን በወባ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እጨመረ መሆኑንና የወባ መድሃኒትም አለመኖሩ ስጋታቸውን ጨምሮታል። በዞኑ የሚሰሩ የጤና ቢሮ ሰራተኞች ደሞዝ ከተከፈላቸው ሁለት ወር እንዳለፋቸውም ጨምረው አስረድተዋል። የግብርናና የእንስሳት ኃብት ኃላፊ የሆኑት አቶ አባበክር ሐሊፋ መንገድ በመዘጋቱ ምክንያት የግብርና ባለሙያዎች በማህበረሰቡ ውስጥ በነፃነት መንቀሳቀስ እና መስራት አልቻሉም ብለዋል። ባለሙያ ቀበሌ ላይ የለም የሚሉት ኃላፊው ደሞዝም ባንክ የገንዘብ እጥረት ስለገጠመው መክፈል አለመቻላቸውን አስረድተዋል። ወደ አሶሳ ከተማ ተፈናቅለው የመጡ ባለሙያዎች እንዳሉ ያስረዱት ኃላፊው ሁሉም ችግር ውስጥ መሆናቸውን ተናግረዋል። ወደ ህዝቡ መሄድ የነበረባቸው ነገሮችም እንዳልደረሱ የሚያስረዱት ኃላፊው "በአሁኑ ሰዓት መሰብሰብ የነበረበት እህል መሰብሰብ አልተቻለም፣ የሰሊጥ ምርቱም ዝም ብሎ ማሳ ላይ ባክኖ ቀርቷል" ይላሉ። በዞኑ የነበሩ የምርጥ ዘር ስራዎች በፌደራል፣ በክልሉና ባለሀብቶች የሚሰሩ ስራዎች ባክነው መቅረታቸውን ተናግረዋል። ወደ ዞኑ መሄድ ስለማይቻልም የተፈጠረውንና ያለውን ችግር ለመፍታት አለመቻላቸውን አስረድተዋል። የግብርና ኃላፊው በካማሺ ዞን ጋር ከተቆራረጡ ሁለት ወር እንደሆናቸው አስረድተው ከማኦ ኮሞ ወረዳ ጋርም ከተገናኙ ስድስት ወር እንዳለፋቸው ተናግረዋል። ወረዳው 32 ቀበሌዎች ያሉት ሲሆን እስከ ትናንትና ድረስ ቀበሌ ውስጥ መንቀሳቀስ አደገኛ ነው የሚሉት ኃላፊው ወደ ድንበር አካባቢ የምትገኝ ላቂ የምትባል ቀበሌ በዝናብ እጥረት ምክንያት 960 ሰዎች ተፈናቀለው ወደ ማኦ ኮሞ ከተማ መምጣታቸውን መስማታቸውን ተናግረዋል። የክልሉ የሰው ሀብት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ሐሸሪፍ ሀጅ አኑር ደግሞ የካማሺ ዞን አምስት ወረዳዎች እንዳሉት አስታውሰው ከእነዚህ ወረዳዎች አራቱ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ አለመግባታቸውን ገልፀዋል። ሰዳል የሚባለው ወረዳ ከመጀመሪያውም ግጭት ስላልነበረበት የመንግስት ስራ በአግባቡ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል። የመንግስት ስራ በተቋረጠባቸው ስፍራዎች ትምህርትም መስተጓጎሉን ገልፀው ማኦ ኮሞ ላይ ከካማሺ ዞን አንፃር የተሻለ ሁኔታ አለ በማለት አስረድተዋል። የቤንሻንጉል ክልል የኮሙዩኑኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑት አቶ ዘላለም ጃለታ በበኩላቸው ካማሺ ዞን ያለውን ችግር ለመፍታት የክልሉ አስተዳደር ከኦሮሚያ አመራሮች ጋር በመነጋገር ላይ መሆኑን ነግረውናል።
news-51440554
https://www.bbc.com/amharic/news-51440554
''ባልሽን በጥንቆላ አሳብደሸል አሉኝ፤ እኔ ግን እስካሁን ከጎኑ አልተለየሁም''
ኤስተር ኪያማ በኬንያዋ 'ንዬሪ' ከተማ በመምህርነት በመስራት ላይ ሳለች ነበር ያልጠበቀችውን ዜና በስልክ የሰማችው።
ባለቤቷ ዴቪድ መታመሙን ደዋዩ ከነገራት በኋላ የአእምሮ ህመም እንደሆነ አስረዳት። በጎርጎሳውያኑ 2005 ኤስተር ከአንድ ዓመት በላይ ለሆነ ጊዜ ባለቤቷን አልተመለከተችውም ነበር። ምክንያቱ ደግሞ አንድ የንግድ ስራ ለማከናወን በሚል ወደሌላ ከተማ በመሄዱ ነው። እሷ ልታገኘው በሄደችባቸው ጊዜያት በሙሉ ምንም አይነት ህመም አላስተዋለችም ። ነገር ግን አንዴ መታመሙን በሰማች ጊዜ ሳታቅማማ ወዳለበት ቦታ መሄዷን ታስታውሳለች። ''ቤት ውስጥ ብቻውን ያወራ ነበር፤ እጆቹን እያወናጨፈ በተመስጦ ሃሳቡን ያብራራል። ምንም እንኳን ብቻውን ቢሆንም የሚያወራው፤ አጠገቡ ብዙ ሰዎች ተሰብስበው እንደሚያዳምጡት ነበር የሚያስበው።'' • 'ቅሽለት' ስለሚባለው የአእምሮ ጤና ችግር ያውቃሉ? • የአልኮል ችግር ያለባቸው ወንዶች ጥቃት የመፈጸም እድላቸው ከፍ ያለ ነው የኤስተር ባለቤት ወደ ህክምና ቦታ ከተወሰደ በኋላ 'ባይፖላር ዲስኦርደር' የሚባል የአእምሮ እክል እንደዳጋጠመው ተደረሰበት። '' ወደቤት ሲመለስ እንደውም ጭራሽ ባሰበት። እቤት ውስጥ ትቼው ከሄድኩኝ በጣም ነው የምሳቀቀው። አንድ ቀን ትቼው ሄጄ ስመለስ የቤቱን ጣራ አቃጥሎት ደረስኩኝ።'' ኤስተር ለረጅም ዓመታት የምታውቀው ባለቤቷ የማታውቀው ሰው ሲሆንባት ምን እንደምታደርግ ግራ ገባት። እየሆነ ያለውን ነገር ለመረዳትም እጅግ አስቸጋሪ ሆኖባት ነበር። በቃ የፈጀውን ይፍጅ ብላ ወደህክምና ቦታ ለመውሰድ ስትሞክር ግን የባለቤቷ ቤተሰቦች ይከለክሏታል። እንደውም ልጃችንን 'በመተት' ያሳበድሽው አንቺ ነሽ ብለው ይወነጅሏት ጀመሩ። ''አባቱ መጥተው ሊወስዱት እንደሆነ ነገሩኝ። 'ልጄን በጥንቆላ ያሳበድሽው አንቺ ነሽ፤' ሲሉኝ በጣም ደነገጥኩ። ለ 15 ዓመታት በትዳር አብሯት ከቆየው ግለሰብ በእንደዚህ አይነት አሳዛኝ ሁኔታ መለየት ቢከብዳትም ከእሷ በበለጠ እጅግ አስቸጋሪ የነበረው በትዳራቸው ያፈሯቸው ልጆች ነበሩ። ዴቪድ ወደቤተሰቦቹ ቤት ከሄደ በኋላ የጤናው ሁኔታ ከቀን ወደቀን እየባሰበት መምጣት ጀመረ። ነገር ግን ቤተሰቦቹ ጤናው የታወከው 'በጥንቆላ' ምክንያት ነው ብለው ስላመኑ ወደ ህክምና ቦታ ለመውሰድ አልፈቀዱም። በኬንያ በርካታ የጤና እክሎች ከጥንቆላ እና ከእርግማን ጋር የተገናኙ እንደሆነ ማህበረሰቡ ያምናል። ምንም እንኳን እነዚህ የጤና እክሎች በቀላል ህክምና መዳን የሚችሉ ቢሆኑም ታማሚዎች ከሰው ተደብቀው በቤት ውስጥ እንዲቆዩ ይደረጋሉ። የኬንያ ጤና ሚኒስትር እንደሚለው በርካታ ኬንያውያን የጤና እክል ሲያጋጥማቸው ባለሙያዎች ጋር ሄዶ ከመታከም ይልቅ ባህላዊ ህክምናዎችን ይመርጣሉ። የኤስተር ባለቤት ለሶስት ዓመታት ከቤተሰቦቹ ጋር የቆየ ሲሆን በተለይ ደግሞ በእድሜ ለገፉት እናቱ እጅግ አስቸጋሪ ሆኖባቸው ነበር። ልጃቸው አቅሉን ስቶ መመልከት የከበዳቸው እናት እሳቸውም ታመው ነበር። አንዳንድ ጊዜ የቤተሰቦቹ ጎረቤቶች ወደ ኤስተር በመደወል ስለባለቤቷ ሁኔታ ይነግሯታል። '' አንዳንድ ጊዜ ደውለው በመንገድ ላይ እየጮኸ እንደሆነ ይነገሩኛል፤ ወዲያው ሄጄ መኪና እከራይና ወደ ቤተሰቦቹ ቤት እመልሰዋለው። አንዳንድ ጊዜም ጥሩ ምግብ ሰርቼ አበላዋለው።'' ምንም እንኳን ባለቤቷ ጤናው እንዲመለስ የቻለችውን ሁሉ ብታደርግም ተወቃሽ ከመሆን ግን አላመለጠችም። እንደውም ባለቤቷም ጭምር ጥፋተኛ አድርጎ ቆጠራት። • ማልቀስ ጠቃሚ ነው ወይስ ጎጂ? ''አንድ ቀን ቆንጨራ ይዞ 'አንቺ ነሽ በጥንቆላ ያሳበድሽኝ' እያለ አባረረኝ። እንደምንም ብዬ አረጋጋሁትና እኔን ከገደልከኝ ማን ምግብህን ያበስልልሀል? ስለው ቆንጨራውን ወርውሮት ሄደ።'' ምንም እንኳን ዘመዶቿና ጓደኞቿ ባለቤቷን እንድተረሳው ቢነግሯትም፤ እሷ ግን አሻፈረን ብላ ቆይታለች። '' ስንጋባ የገባነው ቃል አለ፤ መቼም ቢሆን ከአንዱ ጎን ላለመለየት። ገና ወጣቶች እያለን ነበር ትዳር የመሰርተነው። እውነቱን ለመናገር በጣም ነበር የምንዋደደው። አራት ልጆችንም አፍርተናል።'' ከሶስት ዓመታት በኋላ ኤስተርና ልጆቿ ከአእምሮ ጤና ባለሙያ ጋር በመሆን ዴቪድን ከቤተሰቦቹ ለመውሰድ ወሰኑ። ሰርቀው ለማምጣትም ተስማሙ። '' ቤተሰቦቹ ሳይሰሙ ወደ እኛ ቤት ስናመጣው የእጅና የእግር ጥፍሮቹ በጣም አድገውና ቆሽሸው ነበር። እሱን ለማጽዳት ቀናት ነበር የፈጀብን። ጺሙም ቢሆን በጣም አድጎ ስለነበር አስፈሪ ገጽቶ ሰጥቶታል።'' በአሁኑ ሰአት ዴቪድ በሆስፒታል ህክምናውን እየተከታተለ ሲሆን ሁለተኛ ወሩን አስቆጥሯል። ቤተሰቡም በመጨረሻ አንድ ላይ ለመሆን በቅቷል።
53046817
https://www.bbc.com/amharic/53046817
ሻንጣ ሙሉ ወርቅ ባቡር ላይ ረስቶ የወረደን ሰው ፖሊስ እያፈላለገ ነው
ብዙ ወንዶች የኪስ ቦርሳ ታክሲ ላይ ይጥላሉ፡፡ የድምጽ ማዳመጫ (ሄድፎን) መርሳትም የተለመደ ነው፡፡ 'ስዝረከረክ ቻርጀሬን ባቡር ውስጥ ረስቼው ወረድኩ' ብሎ ጸጉሩን የሚነጭም ብዙ ነው፡፡
አንድ ፌስታል ሙሉ ሙዝ ታክሲ ላይ ጥለን በመወርዳችን ሕይወት አዳለጠችኝ ብለን ራሳችንን ረግመንም ይሆናል፡፡ አንድ ሻንጣ ሙሉ ወርቅ ባቡር ላይ ረስቶ የሚወርድም አለ። እንግዲህ ሁሉም ሰው እንደ አኗኗሩ ነው፡፡ ይህ የስዊዘርላንድ ሰው አንድ ሻንጣ ሙሉ ወርቅ ባቡር ውስጥ ረስቶ ነው የወረደው፡፡ ግን ለምን ወንድ ነው ብለን አሰብን? እርግጥ ነው ወንዶች ከሴቶች ይልቅ ዝንጉ ናቸው፡፡ ሙሉ ሻንጣ ወርቁን ዘንግታ የወረደችው ሴት ልትሆንም ትችላለች፡፡ ሰው እንዴት ሻንጣ ሙሉ ወርቅ በባሩር ውስጥ ረስቶ ይወርዳል? ወርቁን ከመርሳት ራስን መርሳትስ አይቀልም ያሉ ብዙ ናቸው፡፡ ይህ ወርቅ ረስቶ/ረስታ የወረደው ሰው (የወረደችው ሴት) ቢፈለግ ቢፈለግ (ብትፈለግ ብትፈለግ) አልገኝ ስላለ/ስላለች ፖሊስ ፍለጋውን ለማቆም ተገዷል፡፡ ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ ነበር 3 ኪሎ ግራም የሚመዘዝን ወርቅ ተረስቶ ባቡር ውስጥ የተገኘው፡፡ ባቡሩ ይጓዝ የነበረው ከቅዱስ ጋለን ወደ ሉሰርን ነበር ተብሏል፡፡ የወርቁ ዋጋ እንዲያ በገደምዳሜ ወደ 200ሺህ ዶላር አካባቢ ያወጣል ተብሏል፡፡ የዚህ ሙሉ ወርቅ የሞላበት ሻንጣ ባለቤት ነኝ የሚል ወይም የምትል በአምስት ዓመት ውስጥ የሉሰርን አቃቢ ሕግ ቢሮ ቀርባችሁ ንብረታችሁ ተረከቡ ብሏል ፖሊስ፡፡ ነገሩ በይፋ 'ወርቅ ባቡር ውስጥ የጣለችሁ ኑ እና ውሰዱ' መባል የተጀመረው ፖሊስ ባለቤቶችን በራሱ መንገድ ሊደርስባቸው ሙከራ አድርጎ ስላልተሳካለት ነው፡፡ ፖሊስ በሚቀጥሉት ቀናት እኔ ነበርኩ ባቡር ውስጥ ወርቅ ረስቼ የወረድኩት በሚሉ ሰዎች ሊጨናነቅ ይችል ይሆናል፡፡ ሀቀኛውን ሰው እንዴት ለይቶ ይህንን አዱኛ ሊያስረክብ እንደሚችል የታወቀ ነገር የለም፡፡
news-54527534
https://www.bbc.com/amharic/news-54527534
ለሁለተኛ ጊዜ በኮቪድ-19 የተያዘው ከመጀመሪያው በባሰ በጠና ታመመ
አሜሪካ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በኮሮናቫይረስ የተያዘው ሰው፤ ከመጀመሪያው በባሰ ሁኔታ በጠና መታመሙን ሐኪሞች ተናገሩ።
የ25 ዓመቱ ግለሰብ ከሳምባው በቂ ኦክስጅን ወደ ሰውነቱ መዘዋወር ስላልቻለ ሆስፒታል ገብቷል። በድጋሚ በቫይረሱ የመያዝ እድል አነስተኛ ሲሆን፤ ግለሰቡም እያገገመ ይገኛል። የኔቫዳ ነዋሪ የሆነው ግለሰብ በተለየ ሁኔታ ለኮቪድ-19 ተጋላጭ የሚያደርገው ህመም ወይም በሽታ የመቋቋም ኃይል ውስንንነት የለበትም። ግለሰቡ ከመጋቢት እስከ ሰኔ ድረስ ያሳየው የበሽታው ምልክቶች ቀጣዮቹ ናቸው፦ ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ግለሰቡ ሁለት ጊዜ በቫይረሱ ተይዟል። መጀመሪያ የያዘው ቫይረስ ተደብቆ በድጋሚ አላገረሸበትም። የሁለቱ ቫይረሶች የዘረ መል ቅንጣት የተለያየ ነው። በኔቫዳ ዩኒቨርስቲ መመህር የሆኑት ዶ/ር ማርክ ፓንዶሪ “ቀደም ያለ ኢንፌክሽን ለሁለተኛ ጊዜ በበሽታው ከመያዝ እንደማያድን ግኝታችን ይጠቁማል። ለሁለተኛ ጊዜ በቫይረሱ የመያዝ እድል መኖሩ በሽታን ስለመከላከል አቅም ያለንን አመለካከት ይለውጣል” ብለዋል። ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ፣ እጃቸውን አዘውትረው መታጠብ እና አካላዊ ርቀት መጠበቅ እንዳለባቸውም ዶክተሩ መክረዋል። ሳይንቲስቶች ገና ያልመለሷው ጥያቄዎች ሁሉም ሰው በሽታውን የመከላከል አቅም ያዳብራል? መጠነኛ ምልክት ያሳዩ ሰዎች በሽታውን መከላከል ይችላሉ? በሽታውን የመከላከል አቅም ለምን ያህል ጊዜ ይቆያል? የሚሉት ገና መልስ ያልተገኘላቸው ጥያቄዎች ናቸው። በሽታው በጊዜ ሂደት የሚያሳድርብንን ተጽዕኖ ለመረዳት እንዲሁም ክትባት ለማግኘትም እነዚህን ጥያቄዎች መመለስ ያሻል። እስካሁን በቫይረሱ ከተያዙ ከ37 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ዳግመኛ በሽታው የያዛቸው እጅግ ጥቂቶቹ ናቸው። ከሆንግ ኮንግ፣ ቤልጄም እና ኔዘርላንድ የተገኘ መረጃ እንደሚያሳየው፤ ለሁለተኛ ጊዜ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ከመጀመሪያው በበለጠ አልታመሙም። ኢኳዶር ውስጥ ግን ከመጀሪያው በላቀ የታመመ ሰው ነበር። ሰውነት ቫይረሱን የመቋቋም አቅም ስለሚያዳብር ለሁለተኛ ጊዜ በሽታው ሲከሰት ቀለል ይላል የሚል መላ ምት ነበር። አሜሪካ ያለው ግለሰብ በሁለተኛው ዙር ለምን በሽታው እንደጠናበት አልታወቀም። ምናልባትም ከመጀመሪያው በላቀ ከፍተኛ መጠን ላለው ቫይረስ ተጋልጦ ሊሆን ይችላል። ለመጀመሪያው ቫይረስ የዳበረው በሽታ የመከላከል አቅም ሁለተኛውን ዙር ከባድ አድርጎት እንደሆነም ይገመታል። የኢስት አንጅሊያው ፕ/ር ፖል ሀንተር “በሁለቱ ህመም መካከል ያለው ጊዜ አጭር መሆኑና ሁለተኛው ዙር ከመጀመሪያው መባሱ አሳሳቢ ነው” ይላሉ። የአሜሪካውን ግልሰብ የተመለከተው ጥናት ምን ይጠቁማል? ለሚለው ምላሽ ለመስጠት ገና ነው ብለዋል ፕ/ር ፖል።
49148532
https://www.bbc.com/amharic/49148532
በአስር ወራት አማርኛ ማንበብና መፃፍ የቻለው ጀርመናዊው ዳዊት
ቱሪስት ሆቴልን ያውቁታል? የአራት ኪሎውን ሳይሆን፤ የአርባምንጩን። የከተማይቱ ዘመናይ እና ፈር ቀዳጅ ሆቴል። ፊታቸውን ለአረንጓዴ ተፈጥሮ [ለእግዜር ድልድይ] ሰጥተው በርካታ ሆቴሎች [ሎጆች] ከመሰደራቸው በፊት የነበረ።
የተለመደ አርብ፤ በአርባ ምንጭ ጎዳና፤ በቱሪስት ሆቴል። ጎብኚ ብርቋ ያልሆነው አርባ ምንጭ ደርሶ ይህንን ሥፍራ ሳይጎበኝ የመጣ ተፈልጎ የሚገኝ አይመስልም። እዚህ ሥፍራ የውጭ ኃገር ዜጎችን በተለይም ነጮችን ማየትም የተለመደ ነው። እኔና ባልደረባዬም ቡና እየጠጣን ቀና ስንል በዙሪያችን ካሉ ሰዎች መካከል ግማሽ ያህሉ ነጮች ሆነው ብናገኝ አልተደናገጥንም፤ ስሙስ ቢሆን ቱሪስት ሆቴል አይደል። • "እናቴ ካልመጣች አልመረቅም" ኢዛና ሐዲስ ከማንችስተር ዩኒቨርስቲ ነገር ግን አንድ ሰው ቀልባችንን ገዛው፤ አንድ ወጣት ነጭ። አስተናባሪውን 'ማነህ ወዳጄ፤ የበግ ወጥ አላችሁ?' ብሎ ሲያዝ ስንሰማ ከተተከልንበት የሞባይል ስክሪን ቀና ልንል ግድ ሆነ። 'ጆሮዬ ነው ወይስ. . .?' የሁለታችንም ፊት ላይ የሚነበብ ጥያቄ። ትንሽ ቆይቶም የእጅ ስልኩን አንስቶ 'ሃሎ' ማለት ነው። አሁን ይለያል ጉዱ. . . 'ሃሎ? ሰላም ነው?. . .አለሁ፤ ደህና ነኝ።' አሁን ጠጋ ብዬ ላናግረው ቆረጥኩኝ። ልክ ስልኩን ከመዝጋቱ ከፊት ለፊቱ ቆሜ ለሰላምታ እጄን መዘርጋት። ፊቱ ላይ ትንሽ መደናገጥ ቢነበብም እጅ አልነሳኝም። "እንደው አማርኛ አቀላጥፈህ ስትናገር ስሰማ ጊዜ ነው. . .።" ለአንደዚህ ዓይነት ክስተት አዲስ ያልሆነው ዳዊት ወንበር ስቦ አስቀመጠኝ፤ በሰው ድግስ እኔም ጓደኛዬን ጠርቼ ቁጭ ማለት። • ኢትዮጵያ ወደ አውሮፓና እስያ ሠራተኞችን ልትልክ ነው ዴቪድ ቢሆንም ስሙ ኢትዮጵያን ባወጡለት ዳዊት ነው የሚጠራው፤ ጀርመናዊ ነው። ኢትዮጵያ መኖር ከጀመረ 10 ወራት ሆኖታል። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተልዕኮ የሶሲዮሎጂ እና የፖለቲካ ሳይንስ ተማሪ ነው። እንዳው 10 ወሩን ከሰዎች ጋር በምን ቋንቋ ተግባብቶ ቆየ? ብለው ቢጠይቁ በአማርኛ ነዋ. . .መልሱ። አማርኛን ቋንቋ በደንብ አድርጎ መናገር ይችላል፤ ይፅፋል፣ ያነባል፣ ያደምጣል። ከኢትዮጵያዊያን ጓደኞቹ ጋር በስልክ የሚያወራው በአማርኛ ነው፤ የፅሑፍ መልዕክት የሚለዋወጠውም እንዲሁ በአማርኛ። «አማርኛ መጀመሪያ እራሴን ያስተማርኩት ጀርመን ውስጥ ነው። አንድ መፅሐፍ ገዝቼ ማጥናት ጀመርኩኝ። ያንን መፅሐፍ ሙሉውን ጨረስኩት። በተጨማሪ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመጣሁ በኋላ ማጥናት ጀመርኩኝ። አማርኛ ለውጭ ዜጎች የሚል ኮርስ አለ።» ጀርመን እያለ ለ6 ወራት ገደማ አማርኛ አጥንቷል። ኢትዮጵያ መኖር ከጀመረ ደግሞ 10 ወራት። በጠቅላላው ወደ 1 ዓመት ተኩል ገደማ ነው አማርኛ ለመናገርና ለመፃፍ የፈጀብኝ ይላል። «እውነት ለመናገር ዋናው ጥረት ነው። ቀን በቀን እለማመዳለሁ። ሌላው ደግሞ ለእኔ ቋንቋን ለማወቅ ዋናው መሠረታዊ ነገር ፊደላቱን ማወቁ ይመስለኛል።» «አማርኛ ማውራት ስጀምር ለቡና ይጋብዙኛል» ዳዊት በደህና ጊዜ በተማራት አማርኛ ብዙ ነገር አይቶባታል። አማርኛ አይሰማም ብለው ከሚያሙትና ከሚዘልፉት ጀምሮ፤ አማርኛ መስማቱን ሲያውቁ ተደናግጠው የሚገቡበት እስከሚጠፋባቸው ሰዎች ድረስ። «አማርኛ ቋንቋን ማወቄ በጣም ጠቅሞኛል። መንገድ ላይ አግኝተውኝ በእንግሊዝኛ ሊያናግሩኝ ሲሞክሩ እኔ ደግሞ በአማርኛ አናግራቸዋለሁ፤ ብዙዎቹ ይደነግጣሉ። ከዚያ ቡና እንጠጣ ብለው ይጋብዙኛል። ብዙዎች ደጋጎች ናቸው።» እኔም 'የበግ ወጥ አለ?' ሲል አይደል የደረስኩበት፤ ብዙ ጊዜ ምግብ ቤት ውስጥ እነሱ በእንግሊዝኛ ሊያወሩኝ ሲሞክሩ እኔ በአማርኛ ሳወራቸው ግራ ይጋባሉ ይላል ዳዊት። «ለምሳሌ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ገብቼ አንድ ጉዳይ ላስፈፅም በእንግሊዝኛ ሳናግራቸው ማንም ምላሽ አይሰጠኝም። ነገር ግን በአማርኛ ማውራት ስጀምር ሁሉም ሊተባበሩኝ ወደ'ኔ ይመጣሉ።» ይላል ዳዊት አርባ ምንጭ የተገኘው ጓደኛውን ፍለጋ ነበር፤ ጀርመናዊ ጓደኛውን። ጓደኛው ከሞያሌ ወደ አርባ ምንጭ እየመጣ ነው። ከእርሱ ጋር ተያይዘው አንድ ምሽት አርባ ምንጭ፤ አንድ ምሽት ደግሞ ሻሸመኔ አሳልፈው አዲስ አበባ መግባት ነው ዕቅዳቸው። ነገር ግን ጓደኛው የውሃ ሽታ ሆኖበት ቱሪስት ሆቴል ምሳ እየበላ ሊጠብቀው ጎራ ይላል። • "ኦሮሞ እና ማዳጋስካርን የሚያገናኝ ፖለቲካ እንዳለ አላውቅም" የትነበርሽ ንጉሤ ታድያ ግራ ተጋብቶ ወዲያ ወዲህ ሲል የተመለከተው አንድ ሰው 'ይህ ደግሞ የማን ቀውላላ ነው?' ሲለው ይሰማል። ግን ይህ ለእርሱ አዲስ አይደለም። «በየቀኑ ያጋጥመኛል [ሳቅ. . .] አማርኛ እንደማልሰማ ስለሚያስቡ ስለእኔ የሆነ ነገር ይናገራሉ፤ መልካምም ይሆን ክፉ። ብዙ ጊዜ ስለእኔ የሚያወሩት ይገባኛል። ባይገባኝ እንኳ ስለእኔ እያወሩ እንደሆነ እረዳለሁ።» ምን ቋንቋ ብቻ ዳዊት ቋንቋችንን ብቻ አይደለም በርካታ ታሪካዊ ቦታዎችንና ከተማዎችን ያውቃል። «ላሊበላ፣ አክሱም፣ መቀሌ፣ ጎንደር፣ ባህርዳር፣ ጥቁር አባይ ፏፏቴ፣ ላንጋኖ፣ ሐይቅ ሐረር. . .» ኧረ በቃ። እኔ ኢትዮጵያዊው እንኳን እንደሱ አልተጓዝኩም። ምግብና መጠጡንስ. . .? «የበዓል ምግብ በጣም ነው የምወደው፤ ዶሮ ወጥ በጣም ይጣፍጣል። ግን ደግሞ ሸክላ ጥብስ በጣም ነው የምወደው። አንድ የወንድ ማሕበር አለን። ከእኔ በቀር ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ናቸው። ቅዳሜ ቅዳሜ እንገናኛለን። ሥጋ ለመብላት፤ ቢራ ለመጠጣት [ሳቅ. . .]።» «ከኢትዮጵያዊያን መጠጥ ደግሞ ጠጅ በጣም እወዳለሁ።» «አውሮፓ ውስጥ ቡና እንጠጣ ብሎ ነገር የለም» ጀርመናዊው ዳዊት አውሮፓ ውስጥ በርካታ ሃገራትን ተዛዋውሮ ተመልክቷል። እዚያ የሌለ ኢትዮጵያ ውስጥ ያስተዋልኩት አንድ ትልቅ ነገር አለ ይላል። «አውሮፓ ውስጥ፤ በተለይም ጀርመን ሃገር ሰው ሁልጊዜ ሩጫ ላይ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ሰዎች ቁጭ ብለው ቡና እየጠጡ ይጫወታሉ። ቁጭ ብሎ ቡና መጠጣት የሚባል ነገር እዚያ የለም። አረፍ ብሎ ቡና እየጠጡ መጫወት በጣም አሪፍ ነገር ነው። ተቀራርበህ ማውራት ደስ ይላል።» • "በጎጃም ማርያም ቤተክርስቲያን ለመስጊድ 3ሺ ብር ረድታለች' ተባልኩኝ" ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ይሁን እንጂ ዳዊት እንደዚያ ተቀራርባችሁም የማታወሯቸው ነገሮች ይበዛሉ ይለናል። ክርኔን ጭኔ ላይ አስደግፌ፤ የጀበና ቡናዬን ፉት እያልኩ እየሰማሁት ነው። «ለምሳሌ እኔ ከአባቴ ጋር ቢያንስ በሳምንት አንድ ሁለቴ በስልክ ልናወራ እንችላለን፤ በዚህ ወቅትም ሁሉን ነገር እነግረዋለሁ። እያሳለፍኩት ስላለሁት ሕይወት፤ ስለ ፍቅር ሕይወቴ ሳይቀር. . .ኢትዮጵያዊያን ግን ምናልባት ለጓደኞቻቸው እንጂ ከቤተሰቦቻቸው ጋር አብረው ቁጭ ብለው ቢበሉም ብዙ በግልፅ ሲያወሩ አላስተዋልኩም ይላል።» ዳዊት ስለኢትዮጵያ ለማወቅ ካለው ጉጉት የተነሳ በርካታ በአማርኛ የተፃፉ መፃሕፍትን እንዳነበበ ነግሮኛል። ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያን ታሪክ የሚተነትኑ የፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ [Oromo Democracy: An Indigenous African Political System]ና ሌሎችንም። እና ወደፊት ኢትዮጵያ የመኖር ሃሳብ አለህ? መቼስ አሁንስ ጨቀጨቀኝ ይለኝ ይሆናል። «አንድ ምክንያት ካለኝ በጣም። ለምሳሌ ፍቅር ሊሆን ይችላል ወይም ሥራ . . .ግን ሃሳብ አለኝ።»
news-53583748
https://www.bbc.com/amharic/news-53583748
እምነቱን በማዋረድ የተከሰሰው ፓኪስታናዊ ፍርድ ቤት ውስጥ በአንድ ግለሰብ በጥይት ተገደለ
እምነትን በማዋረድ ችሎት ፊት ቀርቦ የነበረው ፓኪስታናዊ በፍርድ ቤቱ ውስጥ በአንድ ግለሰብ በተተኮሰበት ጥይት ህይወቱ አልፏል። ግለሰቡ በሰሜናዊ ፓኪስታን በምትገኘው ፔሽዋር የፍርድ ሂደቱን ሲከታተል ነበር የተተኮሰበት።
ግለሰቡን ፍርድ ቤት ውስጥ ገድሏል የተባለው ካሊድ ታሂር አህመድ ናሲም የተባለው ይህ ግለሰብ ነብይ ነኝ ብሏል በሚል ነበር ክስ የተመሰረተበት፤ በዚህም ሁኔታ እምነቱን ዝቅ አድርጓል ተብሏል። ሃይማኖትን መሳደብ፣ ወይም ማዋረድ በህጉ መሰረት የሞት ቅጣት የሚያስፈርድ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ይሄ ተግባራዊ የሆነበት ሰው የለም። ነገር ግን እምነታቸውን አዋርደዋል ተብለው የተወነጀሉ ሰዎች ክፉኛ ጥቃት ይድርስባቸዋል። ታሂር ክሱ የተመሰረተበት ከሁለት አመት በፊት አንድ ታዳጊ እምነቱን አዋርዷል ብሎ መወንጀሉን ተከትሎ ነው። በትናንትናው ዕለት ፍርድ ቤት በጥይት ሲተኮስበት ተዝለፍልፎ ወንበሩ ላይ እንደወደቀም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የወጣው ቪዲዮ ያሳያል። ታሂርን በመግደል የተጠረጠረው ግለሰብ እዚያው እጅ ከፍንጅ ተይዟል። በወቅቱም በእጅ ሰንሰለት ታስሮ ታሂርን "የእስላም ጠላት" እያለም ሲጮህ ታይቷል። ታሂር ናሲም እምነቱን በመስደብ የተከሰሰው አዋይስ ማሊክ የሚባል የእስልምና እምነት ተማሪ ነበር። በወቅቱ በአሜሪካ ይኖር የነበረው ታሂር፣ ከአዋይስ ጋር በኢንተርኔት ስለ እምነት አውርተው ነበር። ወደ ፓኪስታንም ከመጣ በኋላ አንድ የመገበያያ መደብር ውስጥ አግኝቶት ስለ እምነቱ ያለውን አስተያየት በመጠየቅ ታሂር የሚለውን ሰምቶ ለፖሊስ ማሳወቁንም ይሄው ታዳጊ ለቢቢሲ ተናግሯል። ታዳጊው ፍርድ ቤት እንዳልቀረበና ስለ ተኩሱም የሚያውቀው ነገር እንደሌለ ተናግሯል። ታሂርን በመግደል የተጠረጠረው ካሊድ ሽጉጥ ወደ ፍርድ ቤቱ ማስገባት እንዴት እንደቻለ የተባለ ነገር የለም። ታሂር መናፍቃን ተብለው ከሚወነጀሉት የአህማዲ ቡድን ተከታይ የነበረ መሆኑን ቃል አቀባዩ ተናግረው፣ ነገር ግን ከጊዜያት በኋላ ይህንን ትቶ ራሱን ነብይ ብሎም ይጠራ ነበር ብለዋል። የአካባቢው ማህበረሰብ መሪ እንዲሁ ታሂር የአዕምሮ ህመምተኛ እንደነበርና ራሱንም የአምላክ መልዕክተኛ ነኝ በማለት በዩቲዩብ የቪዲዮዎች መልእክት ያስተላልፍ ነበር ብለዋል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በበኩላቸው ፓኪስታን እምነትን በመስደብ ያላት ህግ በአገሪቱ ውስጥ ያሉ አናሳ ማህበራት ላይ ያነጣጠረና ለደቦ ጥቃትም በር የሚከፍት ነው ይላሉ። በርካታ ፓኪስታናውያንም እምነታቸውን አዋርደዋል በሚል በተቆጡ ቡድኖች እንዲሁም በፀጥታ ኃይሎች ተገድለዋል።
news-53719602
https://www.bbc.com/amharic/news-53719602
አሜሪካ፡ የዶናልድ ትራምፕ፡ ጋዜጣዊ መግለጫ በተኩስ ምክንያት ተቋረጠ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዕለታዊውን የኮቪድ-19 ማብራሪያ በመስጠት ላይ ሳሉ ከዋይት ሐውስ ደጅ በተሰማ ተኩስ ምክንያት ጋዜጣዊ መግለጫውን አቋርጠው በጠባቂዎቻቸው ታጅበው መውጣታቸው ተነገረ።
የፕሬዝዳንቱን ደኅንነት የሚጠብቀው የልዩ ጥበቃ ዘብ መኮንን ድንገት ጋዜጣዊ መግለጫውን አቋርጦ ወደ መድረክ በመውጣት ዶናልድ ትራምፕን ከክፍሉ ውሰጥ እንዲወጡ ተደርገዋል። በጋዜጣዊ መግለጫ ክፍል ውስጥ የነበሩ ጋዜጠኞችም ምን እንደተከሰተ ለማወቅ ካሜራቸውን ወደ ደጅ በማድረግ ሲከታተሉ ነበር። ከአፍታ ቆይታ በኋላ ወደ ጋዜጣዊ መግለጫ ክፍል የተመለሱት ትራምፕ "ተፈጥሮ የነበረው ችግር በአስተማማኝ ሁኔታ በቁጥጥር ሥር ውሏል" ብለዋል። "አንድ ሰው እዚህ ደጅ ተተኩሶበት ነበር፤ ለዚያ ነው መግለጫዬ የተቋረጠው" ብለዋል ለሪፖርተሮች። ፕሬዝዳንቱ ውዝግብ በማይጠፋው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሳሉ ነበር አንድ የልዩ ጥበቃ ዘብ መኮንን ወደ መድረኩ ፈጠን ብሎ በመውጣት ዶናልድ ትራምፕን በጆሯቸው አንዳች ነገር ሹክ ካላቸው በኋላ ቀልጠፍ ብሎ ወደ ጓሮ ይዟቸው የሄደው። ትራምፕ ክፍሉን ሲለቁ "ነው እንዴ?" "ምን ተፈጠረ?" የሚሉ ቃላትን ሲናገሩ በክፍሉ የነበሩ ካሜራዎች ቀርጸው አስቀርተዋቸዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ በልዩ ጥበቃ ዘብ ታጅበው ገለል የተደረጉት ለስምንት ደቂቃዎች ያህል ነበር። ሲመለሱ ምን እንደተከሰተ የተጠየቁት ትራምፕ "የልዩ ጥበቃ አባል አንድን ተጠርጣሪ ተኩሶ እንደመታውና ወደ ሆስፒታል እንደተወሰደ" እንደሚያውቁ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ትራምፕ አያይዘውም ለደኅንነታቸው ጠብ እርግፍ ያሉትን ጠባቂዎቻቸውን ቅልጥፍናና ሙያዊ ሥነምግባር አወድሰው አመስግነዋል። ትራምፕን በነገር መተንኮስ ከሚወዱት ጋዜጠኞች አንዱ "ክቡር ፕሬዝዳንት፣ ወደ ጓሮ ሲወሰዱ በጣም ደንግጠው ነበር ወይ?" ብሎ የጠየቃቸው ሲሆን፣ "እርሳቸውም ቆጣ ብለው፣ የደነገጥኩ እመስላለሁ?" ሲሉ መልሰውለታል።
news-53366789
https://www.bbc.com/amharic/news-53366789
ገንዘብ በማጭበርበር ተጠርጥሮ በኤፍቢአይ ከዱባይ ‘የተጠለፈው’ ናይጄሪያዊ ማነው?
ሬመን ኦሎሩናዋ ይባላል። ናይጄሪያዊ ነው። 2.5 ሚሊዮን የኢንስታግራም ተከታዮቹ ሬይ ሀሽፓፒ በሚለው ስሙ ያውቁታል። 37 ዓመቱ ነው።
ሬይ ሀሽፓፒ በርካታ ሚሊዮን ዶላር በማጭበርበር እና ሕገ ወጥ ገንዘብን ወደ ሕጋዊነት በማስገባት በመጠርጠሩ ኤፍቢአይ ከዱባይ አግቶ እንደወሰደው ጠበቃው ተናግረዋል። የአሜሪካው የምርመራ ተቋም ኤፍቢአይ ሬመንን እንዲሁም በበይነ መረብ የገንዘብ ምዝበራ የተጠረጠረውን ኢላልኬን ጃኮብ ፖንሌ ይዟል። ኢላልኬን፤ ሚስተር ውድቤሪ በሚባል ቅጽል ስም ይታወቃል። ግለሰቦቹ ከዱባይ የተያዙት ሰኔ ላይ ነበር። ሐምሌ 3 በቺካጎ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ዩናይትድ አረብ ኤሚሬትስ እና አሜሪካ የወንጀል ተጠርጣሪን አሳልፎ የመስጠት ስምምነት የላቸውም። የዱባይ ፖሊሶች እንደሚሉት ግን ከዚህ ቀደምም ተጠርጣሪዎች ለአሜሪካ ተላልፈው ተሰጥተዋል። የአሜሪካ የፍትህ ተቋም ለቢቢሲ እንደተናገረው ሀሽፓፒ ከዱባይ ተባሯል እንጂ ለአሜሪካ ተላልፎ አልተሰጠም። ጠበቃው ጋል ፒስተኪ በበኩላቸው ደንበኛቸው ኢንስታግራም ላይ ቅንጡ ሕይወቱን ከማሳየት ውጪ ወንጀለኛ አይደለም። ሀብቱን ያካበተውም በሕጋዊ መንገድ ነው ይላሉ። “ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ተጽዕኖ ፈጣሪ ነው። ብዙ ሚሊዮን ተከታዮች አሉት። ይወዱታል፤ ያከብሩታል። በዚህ ዘመን ይሄ [የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪነት] ንግድ ነው” ብለዋል ጠበቃው። ኤፍቢአይ ክሱን የመሠረተው ‘ቢዝነስ ኢሜል ኮምፕሮማይዝ’ በመባል በሚታወቀውና በሌሎችም በይነ መረብን ባማከሉ ማጭበርበሮች ነው። በመቶ ሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር ሕገ ወጥ ገንዘብን ወደ ሕጋዊ መስመር ለማስገባት ሞክሯልም ይላሉ። አሜሪካ የያዘችው በሕገ ወጥ መንገድ ነው? ጠበቃው እንደሚሉት አሜሪካ ግለሰቡን ከዱባይ የመውሰድ ሥልጣን አልነበራትም ይላሉ። “ኤፍቢአይ ከዱባይ ያገተው በሕገ ወጥ መንገድ ነው፤ በወንጀል የተጠረጠረ ሰው ልውውጥ አልተደረገም። የፍርድ ቤት ሰነድም አልገባም። አሜሪካዊ አይደለም። አሜሪካ እሱን የመውሰድ ሥልጣን የላትም” ብለዋል። የዱባይ ፖሊስ ሁለቱን ተጠርጣሪዎች አሳልፎ በመስጠቱ ከኤፍቢአይ ዳይሬክተር ምስጋና እንደደረሰው በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል። የአሜሪካ የፍትህ ተቋም ቃል አቀባይ ግን፤ የዱባይ ፖሊስ ለምን ጉዳዩን “የወንጀል ተጠርጣሪን አሳልፎ መስጠት” እንዳለው መናገር ያለበት ራሱ የዱባይ ፖሊስ ነው ብለዋል ለቢቢሲ። ጠበቃው ግን ነገሩ አልተዋጠላቸውም። “ዱባይ ልታባርረው ከፈለገች መሄድ የነበረበት ወደ ናይጄሪያ ነበር” ብለዋል። ሀሽፓፒ የተከሰሰው በምንድን ነው? ሬይ ሀሽፓፒ ቅንጡ አኗኗሩን በኢንስታግራም በማሳየት ዝናን አትርፏል። ከታሰረ በኋላ 100,000 ተጨማሪ ተከታዮች አፍርቷል። የዱባይ ፖሊስ እንደሚለው፤ ናይጄሪያዊው ሲታሰር 40 ሚሊዮን ዶላር፣ 13 እጅግ ዘመናዊ መኪኖች (6.8 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ)፣ 21 ኮምፒውተር፣ 47 ተንቀሳቃሽ ስልክ እንዲሁም ወደ ሁለት ሚሊዮን የሚሆኑ ምዝበራ ሊካሄድባቸው እቅድ የተያዘ ሰዎች አድራሻ ተይዟል። ጥቃት ሊሰነዘርባቸው ነበር ከተባሉት መካከል የአሜሪካ የጠበቆች ተቋም፣ ባንክ እና የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ እግር ኳስ ክለብ ይገኙበታል። ድንበር ዘለል የኮምፒውተር መረጃ መዝባሪዎች መሪም መሆኑንም በክሱ ተመልክቷል። እነዚህ መዝባሪዎች የሰዎችን የግል መረጃ በመስረቅ፣ ሐሰተኛ የንግድ ድርድር በመፍጠር ወይም ሰዎች ወደተሳሳተ የባንክ ቁጥር ገንዘብ እንዲልኩ በማድረግ ይታወቃሉ። በናይጄሪያ የወጣ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግን ተከትሎ፤ ወንጀለኞቹ ‘419 ስካመርስ’ በሚል ቅጽል ስም ይጠራሉ። 419 ምንድን ነው? በተለያየ መንገድ የሚከናወን ማጭበርበር ነው። ለምሳሌ አንድ ሰው ገንዘብ ለማስተላለፍ እርዳታ እንዲያደርጉለት የሚጠይቅ ኢሜል ሊልክልዎ ይችላል። ባለበት አገር ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ ወይም ተፈጥሯዊ አደጋ ገንዘብ መላላክን አዳጋች እንዳደረገበትም ይነግርዎታል። የባንክ ቁጥርዎን ከላኩለት ገንዘቡን እንደሚያስተላልፍልዎም ይገልጻል። ከዚያም ቁጥሩን ተጠቅሞ ገንዘብዎን ይዘርፋል። የሀሽፓፒ ክስ እንደሚያሳየው፤ ሕገ ወጥ 14.7 ሚሊዮን ዶላር ወደ ሕጋዊነት ለማስገባት ከኮምፒውተር መረጃ መዝባሪዎች ጋር ተመሳጥሯል። ማልታ የሚገኝ ባንክ የተጠቀሰው ያህል ገንዘብ እንደጠፋበት ሪፖርት አድርጓል። ኤፍቢአይ እንደሚለው ባለፈው ዓመት ብቻ 1.7 ቢሊዮን ዶላር ከግለሰቦችና ከተቋሞች ተሰርቋል። ዐቃቤ ሕግ ኒክ ሀና እንዳሉት፤ ክሱ በመላው ዓለም የዘራፊዎችን መንገድ የሚያዘዋውር ግለሰብን ይመለከታል። የሀሽፓፒ ጠበቃ እንደሚሉት ከሆነ ግን ደንበኛቸው ገንዘቡን ያሰባሰበው ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ያለውን ዝና ተጠቅሞ ነው፤ የፍርድ ሂደቱ ወራት ወይም ዓመትም ሊወስድ እንደሚችል አክለዋልል። ሚስተር ውድቤሪ ሌላኛው ተጠርጣሪ ‘ሚስተር ውድቤሪ’ ሌላኛው በቁጥጥር ስር የዋለው ናይጄሪያዊ ኢላልኬን ጃኮብ ፖንሌ (ሚስተር ውድቤሪ) ነው። ጠበቃው ማይክል ቢ ናሽ ከደንበኛቸው ጋር ለመነጋገር ጊዜ እንዳልተሰጣቸው ለፍርድ ቤት ተናግረዋል። የ29 ዓመቱ ተጠርጣሪ ኢንስታግራም ላይ ‘ሚስተር ውድቤሪ’ የሚል ገጽ አለው። ኤፍቢአይ እንደሚለው፤ ኢሜል የሚልከው ማርክ ኬይን በሚል ስም ሲሆን፤ በበይነ መረብ ገንዘብ በማጭበርበር ክስ ተመስርቶበታል። አንድ ቺካጎ የሚገኝ ድርጅትን 15.2 ሚሊዮን ዶላር ማጭበርበሩ በክሱ ተመልክቷል። ከገንዘቡ ጥቂቱን በቢትኮይን በማስቀመጥ እንዳይደረስበትም ጥረት አድርጓል ተብሏል።
51410602
https://www.bbc.com/amharic/51410602
በቴፒ ከሞቱት መካከል የልዩ ኃይል አባል ይገኙበታል ተባለ
በደቡብ ክልል ቴፒ ከተማ ሰሞኑን የጸጥታ መደፍረስ አጋጥሞ የሰዎች ሕይወት ጠፍቷል። በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውም ተነግሯል።
የመዋቅር አደረጃጀት ጥያቄን መሠረት አድርጎ አለመረጋጋት ውስጥ በነበረችው ቴፒ ከተማ፤ ጥር 26/2012 ዓ.ም የልዩ ኃይል አባል መገደላቸውን ተከትሎ በተቀሰቀሰው ግጭት ቢያንስ 8 ሰዎች መሞታቸውን ቢቢሲ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። አንድ ስሙን የማንጠቅሰው የቴፒ ከተማ ነዋሪ ረቡዕ ከሰዓት በኋላ በተከሰተው ግጭት 8 ሰዎች መሞታቸውን እና ቢያንስ 12 የሚሆኑ ነዋሪዎች ደግሞ የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ይናገራል። ፋና ብሮድካስቲንግ የደቡብ ክልል የፀጥታ እና አስተዳደር ቢሮን ጠቅሶ ባለፉት 2 ሳምንታት ቴፒ ከተማን ጨምሮ በተፈጠረው ግጭት የ7 ሰዎች ሕይወት አልፏል ሲል ዘግቧል። ሌላኛው የቴፒ ነዋሪ ደግሞ ለቢቢሲ እንደተናገረው ረቡዕ ዕለት ለተፈጠረው ችግር "ዋነኛ መንስዔው ከአንድ ወር በፊት በአካባቢው የተፈጠረው የጸጥታ ችግር ነው" ይላል። "ከአንድ ወር በፊት 1 ልጅ በአካባቢው ተገድሏል። ይህንን ተከትሎ በቴፒ የአገልግሎት ተቋማትና መንገዶች ለ21 ቀናት ተዘጋግተው ነበር" የሚለው ይህ የቴፒ ነዋሪ ረቡዕ ዕለት ግን የተዘጉት አገልግሎቶች እንደ አዲስ ተከፍተው ሰውም ወደ መደበኛ እንቅስቃሴው መግባት ጀምሮ ነበር። ነገር ግን ከቀኑ 10 ሰዓት አካባቢ የአካባቢው የልዩ ኃይል አዛዥና አንድ ሌላ የልዩ ኃይል አባል ወደ አንድ ምግብ ቤት በማምራት፤ ምግብ በመመገብ ላይ የነበረን ወጣት 'ትፈለጋለህ' በማለት ይጠሩታል። "በዚህ መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ ልጁ ሲቪል ወደ ለበሰው የልዩ ኃይል አዛዥ በማምራት በስለት ወግቶት ሸሸቶ አመለጠ" በማለት የግጭቱን መነሻ ያስረዳሉ። በስለት የተወጋው ጸጥታ አስከባሪ ኃይል አባል ሕይወቱ ማለፉን እና ከዚያ በኋላ በተወሰደ እርምጃ የተቀሩት ሰዎች ሕይወት ማለፉን እና ሰዎች መቁሰላቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል። የሸካ ዞን ፕሬስ ሴክሬታሪያት አቶ አስማማው ኃይሉ ለቢቢሲ ሟች የሃምሳ አለቃ ዘማች ቁንሲል መሆናቸውን እና በደረሳቸው ጥቆማ መሰረት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል በሚንቀሳቀሱበት ወቅት በጥይት ተመትተው ተግድለዋል ብለዋል። እንደ ፕሬስ ሴክሬታሪያቱ ከሆነ የሃምሳ አለቃው የተገደሉት ቆጫ በር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ አደባባይ ላይ ነው። ጸጥታ አስከባሪ ሲገደሉ የተኩስ ልውውጥ እንደነበረም አስረድተዋል። አቶ አስማማው ጭመረው እንደተናገሩት፤ ክልሉ የመዋቅር ጥያቄን እንሁን ላይ አልቀበልም ብሎ ምላሽ ሰጥቶ እንደነበረ ተናግረዋል። 'የዞን አስተዳደር ጥያቄያችን ይመለስልን' የሚለው የነዋሪው ጥያቄ ለጸጥታ መደፍረስ ዋነኛ ምክንያት መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ። ጥያቄው ለዓመታት የዘለቀ ነው የሚሉት ነዋሪዎቹ በቴፒ ወረዳ ዙሪያ ያሉትን 22 ቀበሌዎች ጨምሮ የአስተዳደር መዋቅሩ ወደ ዞን ከፍ እንዲል የነዋሪዎች ጥያቄ መሆኑን ተናግረዋል። ከቅርብ ወራት በፊትም የሰላም ሚንስትሯና የክልሉ ገዥ ፓርቲ ሊቀ መንበር በሥፍራው ተገኝተው ከሕዝቡ ጋር ተወያይተው ምላሽ እንደሚሰጥበት ቃል ገብተው ቢሄዱም እስካሁን ምላሽ አለማግኘታቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ይናገራሉ። የደቡብ ክልል የጸጥታና አስተዳደር ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ እስካሁን 68 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው የተወሰኑት ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት በማድረግ እርቅ ፈጽመው መለቀቃቸውን የተቀሩት ደግሞ ጉዳያቸው በሕግ እየታየ መሆኑን ለፋና ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት በአከባቢው ያለው የጸጥታ ስጋት ተከትሎ የጤና ባለሙያዎች፣ የባንክ ሰራተኞች እና ነጋዴዎች የመሳሰሉ ሠራተኞች አከባቢውን ጥለው እየሸሹ መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ።
news-54920167
https://www.bbc.com/amharic/news-54920167
የኢትዮጵያ ቀይመስቀል ማሕበር በዳንሻ አካባቢ አምቡላንሶቹ በታጣቂዎች መመታታቸውን ገለፀ
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማሕበር ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም ከሁመራ ዳንሻ ባለው መስመር ሶስት አምቡላንሶች በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ተኩስ ተከፍቶባቸው ጉዳት እንደደረሰባቸው ገለፀ።
ዶ/ር ሰለሞን አሊ በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የሰብዓዊ ዲፕሎማሲ እና የግንኙነት ጉዳዮች ኃላፊ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ በጥቃቱ አምቡላንሶቹ በጥይት ቢመቱም በበጎ ፈቃደኞቹ እና በሠራተኞቹ ላይ የደረሰ ጉዳት የለም። የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በሰሜን ጎንደር በኩል የአምቡላንስና የመጀመሪያ ሕክምና እርዳታ ለመስጠት ከጥቅምት 24 ጀምሮ ከ10 በላይ አምቡላንሶችን ማሰማራቱን ዶ/ር ሰለሞን ለቢቢሲ ጨምረው ገልፀዋል። በአገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ተፈጸመ የተባለውን ጥቃት ተከትሎ ለወራት በውዝግብ ውስጥ የቆዩት የፌደራል መንግሥት እና የትግራይ ክልል አስተዳደር ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ወደ ግልጽ ጦርነት መግባታቸው ይታወሳል። በአሁኑ ሰዓት ወደ ጦርነት የተሸጋገረው በፌደራል መንግሥቱና በትግራይ ክልል መስተዳደር በኩል የነበረው ቅራኔ እየተባባሰ የመጣው ባለፈው ዓመት ሊካሄድ የታቀደው ምርጫ በኮሮናቫይረስ ስጋት ምክንያት እንደማይካሄድ ከታወቀ በኋላ በትግራይ የተናጠል ምርጫ በመደረጉ ሳቢያ ነው። ይህንንም ተከትሎ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምርጫውን ሕገወጥና ተፈጻሚነት የሌለው እንደሆነ መወሰኑን ተከትሎ ማዕከላዊው መንግሥት ከክልሉ መስተዳደር ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳያካሂድና የበጀት ድጋፍ እንዳይሰጥ ከወሰነ በኋላ ነገሮች እየተካረሩ መሄዳቸው ይታወሳል። ምክር ቤቱ ስልጣኑን የሕገ መንግሥት ትርጉም በመስጠት ማራዘሙ ሕገ መንግሥታዊ መሰረት እንደሌለውም የትግራይ ክልል ይጠቅሳል። በፌደራልና በትግራይ ክልል መንግሥት መካከል በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት የተጎዱ ሰዎችን ለመርዳት የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማሕበር ሰሜን ጎንደር ቅርንጫፍ ከ20 በላይ በጎ ፈቃደኞችንም በማሰማራት ወደ ሆስፒታል ለማመላለስ እና የመጀመሪያ ሕክምና እርዳታ በመስጠት መሰማራታቸውን ዶ/ር ሰለሞን ገልፀዋል። ማሕበሩ በአካባቢው ግጭት ከተቀሰቀሰበት ጥቅምት 24 ጀምሮ አምስት አምቡላንሶችን በመመደብ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የመጀመሪያ ሕክምና እርዳታ እየሰጠ፣ እንዲሁም ሕክምና ወደሚያገኙባቸው ሆስፒታሎች እያመላለሰ መሆኑን ኃላፊው ጨምረው አስረድተዋል። ዶ/ር ሰለሞን በግጭት ቀጠናው እስካሁን ድረስ ለምን ያህል ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ሕክምና እንደሰጡ ተጠይቀው የተጠናቀረ መረጃው እንደሌላቸው ገልፀዋል። ማህበሩ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች በአካባቢው በሚገኙ አራት ሆስፒታሎች የሚያደርስ መሆኑን የተናገሩት ዶ/ር ሰለሞን፣ የባሰ ጉዳት የገጠማቸውን ደግሞ ወደ ጎንደር ሆስፒታል እንደሚያመላልሱ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በሰሜን ወሎ ቆቦ አካባቢም በጎ ፈቃደኞቹን አምስት አምቡላንሶችን እንዲሁም ሁለት ትልልቅ ድንኳኖችን በማሰናዳት በተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኙ ይናገራሉ። የኢትዮጵያ ቀይመስቀል ማህበር በትግራይ ክልል የጤና ቢሮውን ጨምሮ 100 ያህል አምቡላንሶች እንዳሉት ጨምረው ተናግረዋል። ከክልሉ የቀይ መስቀል ቢሮ ጋር የስልክ መስመር በመቋረጡ ምክንያት እንደማይገናኙ ገልፀዋል። የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማሕበር በመላ አገሪቱ ከ550 በላይ አምቡላንሶች እንዳሉት ኃላፊው ይናገራሉ።
news-53089289
https://www.bbc.com/amharic/news-53089289
አሜሪካ "ቻይና የኢንተርኔት ምስጢሬን ልትመዘብር" ትችላለች አለች
አሜሪካና ሆንግ ኮንግን የሚያገናኘው ከውቂያኖስ ስር የተዘረጋው የኢንተርኔት መስመር ከቻይና በኩል ለሚኖር የመረጃ ምዝበራ ያጋልጠኛል ስትል አሜሪካ ላትፈልገው እንደምትችል ተገለጸ።
የኢንተርኔት ሥርጭት ገመዶች የሚያልፉት በብዛት በውቅያኖስ ሥር ነው። አሜሪካና ሆንግኮንግን በኢንተርኔት የሚያገናኘው ገመድም በፓስፊክ በኩል ተዘርግቶ ነበር። ይህ ረዥም ርቀት የተዘረጋው የኢንተርኔት ገመድ ሥራ እንዲጀምር ከአሜሪካ መንግሥት ፍቃድ ማግኘት ይኖርበታል። አሜሪካ ከዚህ በኋላ ቻይና መረጃ ልትሰርቀኝ ስለምትችል በዚያ ውቅያኖስ ሥር የሚያልፍ የኢንተርኔት ገመድ ይቅርብኝ ብላለች። ዘ ፓስፊክ ላይት ኬብል ኔትወርክ የተሰኘው ይህ የኢንተርኔት ገመድ ዝርጋታ በጉጉልና በፌስቡክ ኩባንያዎች ይደገፍ የነበረ ሲሆን የኢንተርኔት ፍጥነትን ከፍተኛ ለማድረግ እጅግ አስፈላጊ እንደነበር ታምኖበት ነው ወደ ሥራ የተገባው። ሆኖም ቲም ቴሌኮም በሚል የሚጠራውና የአሜሪካ መንግሥት ያቋቋመው ልዩ ኮሚቴ ይህንን ከአሜሪካ ወደ ሆንግ ኮንግ የተዘረጋውን የኢንተርኔት ገመድ መስመር ሊያጸድቀው አልፈለገም። ስጋቱ ደግሞ ቻይና በዚያ የሚያልፈው የኢንተርኔት መረጃን ትሰርቀናለች የሚል ነው። ይህ ክስተት ቻይናና አሜሪካ እያደረጉት ያለው የንግድ ጦርነት በባሕር ውስጥም መቀጠሉን አመላካች ነው ተብሏል። በባሕር ስር የሚያልፍ የኢንተርኔት ገመድ ለደኅንነት ስጋት ነው በሚል እንዲቀር ሲደረግ ይህ የአሜሪካ ውሳኔ በዓለም የመጀመርያው ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ በባሕር ውስጥ የሚዘረጉ በሺህዎች የሚቆጠሩ ገመዶች ኢንተርኔትን ያቀባብላሉ። ይህ በፓስፊክ ውቅያኖስ ሊያልፍ የነበረው የኢንተርኔት የባሕር ውስጥ ገመድ በጉግል፣ በፌስቡክና በሌሎች ኩባንያዎች ሲደገፍ የነበረ ፕሮጀክት ነው። የተጀመረውም በየ2016 እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ነበር። ጉጉል እንዳለው ዝርጋታው 12 ሺህ 800 ኪሎ ሜትር የሸፈነ ነበር። "በሌላ ቋንቋ ይህ መስመር ቢዘረጋ ለ80 ሚሊዮን ሆንግ ኮንጋዊያን በከፍተኛ ጥራት ከሎስ አንጀለስ አቻዎቻቸው ጋር የቪዲዮ ጥሪ በተመሳሳይ ሰዓት ማድረግ የሚያስችላቸው አቅም ይኖረው ነበር" ብሏል ጉግል። ይህ መስመር ከአሜሪካና ከሆንግ ኮንግ ሌላ አሜሪካንን ከታይዋንና ከፊሊፒንስ የሚያገናኝም ተቀጽላ ገመድ ነበረው ተብሏል። የውስጥ ለውስጥ ገመድ ዝርጋታው ብዙ ሚሊዮን ዶላሮች የፈሰሰበት እንደነበር ተዘግቧል።
news-49336569
https://www.bbc.com/amharic/news-49336569
የተጎሳቆሉት የባቢሌ ዝሆኖች ህልውና አደጋ ላይ ነው
ዝሆን በኢትዮጵያ ውስጥ በደቡብ፣ በኦሮሚያ፣ ጋምቤላ እና ትግራይ ክልሎች ጨምሮ በተለያዩ 10 ሥፍራዎች ይገኛል።
ከእነዚህ ሥፍራዎች መካከል በስፋት የሚገኘው በምስራቅ ሃረርጌው የባቢሌ የዝሆን መጠለያ ውስጥ ነው። አቶ ገዛኸኝ ፍቃዱ የመጠለያ ጣቢያው የቱሪዝም ባለሙያ ናቸው። እሳቸው እንደሚሉት የባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ የተቋቋመው ዝሆኖችን ለመጠበቅ በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት በ1962 ዓ.ም. ነበር። ባለሙያው እንደሚሉት መጠለያ ጣቢያው በንጉሡ ዘመን ከመመስረቱ በፊት ቦታው ዝሆን እና አንበሳ የሚታደኑበት ሥፍራ ነበር። በዚህም ሳቢያ የዝሆኖች ቁጥር እየተመናመነ ሲመጣ ነበር መጠለያው የተቋቋመው። • ከአዕዋፍ እስከ አንበሳ ያሉ እንስሳት በግለሰቦች እጅ ለስቃይና ለጉዳት እየተዳረጉ ነው። ይህ መጠለያ በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች መካከል የሚገኝ ሲሆን በውስጡ እስከ 350 የሚገመቱ ሎክሶዳንታ አፍሪካና የሚባል ዝርያ ያላቸው ዝሆኖችን ይዟል። ይሁን እንጂ በባቢሌ የዝሆን መጠለያ ውስጥ የሚገኙት ዝሆኖች በተጋረጡባቸው ፈተናዎች ምክንያት ሙሉ በሙሉ ከአካባቢው ሊጠፉ እንደሚችሉ የተለያዩ ጥናቶች ይጠቁማሉ። በአካባቢው ከሚገኙ ባለሙያዎች እንደሰማነው እና እኛም በቦታው ተገኝተን እንደታዘብነው ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ በሆኑ ምክንያቶች የዝሆኖቹ ህልውና አደጋ ላይ ወድቋል። የዝሆኖቹን ህልውና አደጋ ላይ ከጣሉ ግንባር ቀደም ምክንያቶች አንዱ ሕገ-ወጥ አደን እንደሆነ አቶ ገዛኸኝ ይናገራሉ። ከዚህም ባሻገር ሕገ-ወጥ ሰፈራ፣ እርሻ፣ በመጠለያ ውስጥ የቤት እንስሳትን ለግጦሽ ማሰማራት እና ከሰል ማክሰል ተጨማሪ ችግሮች መሆናቸውን የባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ ጠባቂ አቶ ሀሰን አሕመድ ነግረውናል። "ዝሆን በባህሪው ጸጥታ የሚፈልግ እንስሳ ነው። ረብሻ አይወድም። በሕገ-ወጥ መንገድ በአካባቢው የሰፈሩ ሰዎች ዝሆኑን እየረበሹት ነው" ይላሉ አቶ ሀሰን። እኛም ዝሆኖቹን ለመመልክት ወደ መጠለያ ጣቢያው በሄድንበት ወቅት እረኞች ድምጻቸውን ከፍ አድርገው እየተጯጯሁ ከብቶቻቸውን ለግጦሽ ሲያሰማሩ ተመልክተናል። አቶ ሀሰን አሕመድ (ቀኝ) ከባልደረባቸው ጋር በባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ሥፍራ የመጠለያው ጥበቃዎች እንደነገሩን ዝሆን ረብሻ ስለማይወድ የጩኸት ድምጽ ከሰማ አካባቢውን ለቅቆ ይሄዳል። በዚህም እረኞቹ ያለ ስጋት ከብቶቻቸውን አሰማርተው ወደ ቀያቸው ይመለሳሉ። "የአካባቢው ማህበረሰብ ከዝሆኖቹ የሚያገኙት ጥቅም ስለሌለ አይወዷቸውም" የሚሉት ደግሞ አቶ ገዛኸኝ ናቸው። ይህንን በዝርዝር ሲያስረዱም፤ የዝሆን መጠለያ ሥፍራው የተዘጋጀው ዝሆኖቹን ለመጠበቅ ብቻ ነው። • ከምድረ-ገጽ የመጥፋት ሥጋት በሰውነት መጠን ይወሰናል በአካባቢው ያለው ነባራዊ ሁኔታ ጎብኚዎችን የሚስብ ስላልሆነም የአካባቢው ነዋሪዎች ዝሆኖቹን ከመጠበቅ ይልቅ እየተስፋፋ ያለው በረሃማነት ወደ መጠለያው ዘልቀው እንዲገቡ እያስገደዳቸው ነው ይላሉ። አቶ ገዛኸኝ አክለውም መንግሥት በአካባቢው መሠረተ ልማትን በማጠናከር የጎብኝ ፍሰት እንዲኖር በማድረግ የአካባቢ ህዝብ ተጠቃሚ የሚሆንበት ሁኔታ መፈጠር አለበት ሲሉ እንደ ባለሙያ ሃሳባቸውን ሰንዝረዋል። የመጠለያው ጠባቂ አቶ ሀሰን በበኩላቸው ዝሆኖቹን እየገደሉ ጥርሱን ወደ ውጪ የሚወስዱት ሰዎች የተደራጁ እና ዘመናዊ መሳሪያዎችን የሚታጠቁ ናቸው ይላሉ። ይህ ብቻም ሳይሆን በዝሆን ግድያ እና በዝሆን ጥርስ ንግድ የተሰማሩት ቡድኖች ከጎረቤት ሃገራት ጭምር እንደሚመጡ እናውቃለን ሲሉ አቶ ሀሰን ነግረውናል። "ሕገ-ወጥ አዳኞችን ለማስወገድ ብንንቀሳቀስ በመቶ የሚቆጠሩ ዘመናዊ መሳሪያዎችን ይዘው ይወጡብናል። እኛ በቁጥር አነስተኛ ነን። የታጠቅነው መሳሪያው ኋላ ቀረሽ ነው" ሲሉም ያለባቸውን ተግዳሮት ያስረዳሉ። • ከአዕዋፍ እስከ አንበሳ ያሉ እንስሳት በግለሰቦች እጅ ለስቃይና ለጉዳት እየተዳረጉ ነው። በባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ በነበረን ቆይታ እንዳስተዋልነው፤ በጥብቁ መጠለያ ውስጥ የሰዎች እንቅስቀሴ እጅግ ከፍተኛ ነው። ሰፋፊ እርሻዎች፣ የቤት እንስሳት፣ የመኖሪያ ቤቶች እና የጫት ገበያ ጭምር ተመልክተናል። መጠለያው በዚህ ሁኔታ የሚቀጥል ከሆነ ምናልባትም ከሁለት እና ከሦስት ዓመታት በኋላ ዝሆኖቹን በፎቶ እንጂ በአካል መመልከት እንደማንችል የመጠለያው ጣቢያ የቱሪዝም ባለሙያ አቶ ገዛኸኝ ስጋታቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል። በመጠለያው ከዝሆኖች በተጨማሪ፣ 31 አጥቢ እንስሳት እና ከ191 በላይ አእዋፋት ይገኛሉ።
news-53967065
https://www.bbc.com/amharic/news-53967065
ኖርዌይ ፡ በአንድ ዋሻ ውስጥ ሲዝናኑ የነበሩ ሰዎች በጭስ ታፍነው ሆስፒታል ገቡ
በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ ውስጥ በሚገኝ በአንድ ከመሬት በታች ባለ ዋሻ ውስጥ ተሰባስበው እየተዝናኑ ከነበሩ ሰዎች መካከል ከ20 የሚበልጡት በካርበን ሞኖክሳይድ ጭስ ታፍነው በመመረዛቸው ሆስፒታል መግባታቸው ተነገረ።
ግለሰቦቹ ሊገኙ የቻሉት በአካባቢው ቅኝት ሲያደርጉ የነበሩ ፖሊሶች በዋሻው ውስጥ ከነበሩት መካከል የተወሰኑት ራሳቸውን ስተው ወደ ጎዳና በመውጣት ወዲያ ወዲህ ሲሉ ካገኟቸው በኋላ ነው። ከዚህም በኋላ ሌሎቹ ጓደኞቻቸው በጭሱ ታፍነው ከዋሻው ውስጥ በመውጣታቸው አምቡላንስ ተጠርቶ ወደ ሆስፒታል እንዲወሰዱ ተደርጓል። ባለስልጣናቱ የፓርቲው ታዳሚዎችን ለመመረዝ ያበቁት ወደ ዋሻው ይዘው ከገቡት አነስተኛ ጄኔሬተር በሚወጣ ጭስ ምክንያት ነው ብለው ያምናሉ። በጭሱ የመመረዝ ጉዳት ካጋጠማቸው 25 ሰዎች መካከል ሁለቱ በዋሻው ውስጥ የነበሩትን ሰዎች ለማውጣት ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ ፖሊሶች ናቸው። ግለሰቦቹ አሁን ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተም "እድለኞች ናቸው፤ የሁሉም የጤና ሁኔታ እየተሻሻለ ነው። በጤናቸው ላይ ምንም የሚያሰጋ ነገር የለም" ሲሉ በኦስሎ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል ዋና ሐኪም ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ከ20 በላይ ሰዎች በጭስ በታፈኑበት በዚህ ዝግጅት ላይ 200 የሚደርሱ ሰዎች ታድመውበት እንደነበር የኦስሎ ፖሊስ አስታውቋል። በተጨማሪም ታምመው ወደ ሆስፒታል ከገቡት የፓርቲው ታዳሚዎች ውጪ ያሉት ማቅለሽለሽ፣ የራስ ምታት፣ ራስን የመሳት ስሜት ካጋጠማቸው ወደ ሐኪም ቤት እንዲሄዱ ፖሊስ መክሯል። ፖሊሶች በአደጋው ስፍራ ከመድረሳቸው በፊት ከዋሻው ወጥቶ የሄደ የዝግጅቱ ታዳሚ እንዳለው በስፍራው በነበረው የታፈነ አየር ምክንያት በተደጋጋሚ ወደ ውጪ እየወጣ አየር ሲወስድ ነበር። የኦስሎ ፖሊስ በዋሻው ውስጥ ስለተካሄደው ዝግጅት ቀድሞ ጥቆማ የደረሰው ቢሆንም በወቅቱ ለምን እርምጃ መውሰድ እንዳልቻለ ምርመራ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።
57019300
https://www.bbc.com/amharic/57019300
አርሰናል ለአውሮፓ ሊግ ፍጻሜ ማለፍ ሳይችል ቀረ
አርሰናል በአውሮፓ ሊግ የፍጻሜ ተፎካካሪ ለመሆን ሲያደርገው የነበረው ግስጋሴ ትናንት ምሽት ተቋጭቷል።
ከቪላሪያል ያደረገው የግማሽ ፍጻሜ ያለምንም ግብ አቻ ተጠናቆ ቪላሪያል 2 ለ 1 በሆነ የደርሶ መልስ ውጤት አርሰናልን ማሸነፍ ችሏል። ሊጠናቀቅ ጥቂት ጨዋታዎች በቀሩት የፕሪሚየር ሊግ ሰንጠረዥ ላይ 9ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው አርሰናል፤ አርሰናል ከ25 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚቀጥለው የውድድር ዓመት በየትኛውም የአውሮፓ ውድድሮች ላይ ላይሳተፍ የሚችልበትን እድል ከፍ አድርጎታል። ስፔን ተካሂዶ በነበረው የዚህ ጨዋታ የመጀመሪያ ዙር ቪላሪያል ሁለት ለአንድ አሸንፎ የነበረ ሲሆን በመልሱ ጨዋታ አርሰናል ከሜዳው ውጪ ያስቆጠረውን ግብ ይዞ በሜዳው ጥሩ እንቅስቃሴ እንደሚያደርግ ተገምቶ ነበር። በአርቴታ የሚመሩት አርሰናሎች ግን በትናንቱ ጨዋታ ጥሩ ቢንቀሳቀሱም ግብ ማስቆጠር ሳይችሉ ቀርተዋል። ጋቦናዊው የፊት መስመር ተጫዋች ፒዬር ኤምሪክ ኦባምያንግ ሁለት ጊዜ የጎሉን አግዳሚ ያገኘባቸው አጋጣሚዎች ለአርሰናል አስቆጪ አጋጣሚዎች ሆነው አልፈዋል። በቀድሞው የአርሰናል አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሪ የሚመሩት ቪላሪያሎች ጨዋታውን አሸንፈው ወደ ፍጻሜ ማለፋቸው ደግሞ ትለቅ ድል እንደሆነ ገልጸዋል። ኤምሪ በአውሮፓውያኑ 2019 ላይ ነበር ከ18 ወራት ቆይታ በኋላ ከአርሰናል አሰልጣኝነታቸው የተባረሩት። ሌላኛው የእንግሊዝ ክለብ ማንችስተር ዩናይትድ ደግሞ በመጀሪያው ዙር በሜዳው ኦልድትራፎርድ ሮማን 6 ለ2 ማሸነፉን ተከትሎ በሮማ የተካሄደው የመልሱ ጨዋታ ብዙም አልከበደውም ነበር። ዩናይትዶች በጨዋታው ሶስት ለሁለት ቢሸነፉም በድምር ውጤት ግን ለአውሮፓ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። የፍጻሜው ጨዋታ ግንቦት 18 በፖላንድ ዳስክ ስታዲየም ይከናወናል። ለማንችስተር ዩናይትድ ሁለቱን ግቦች ያስቆጠረው ኡራጋያዊው ኤዲሰን ካቫኒ ሲሆን አሰልጣኝ ሶልሻየር አጥቂው በዚህ አቋሙ የሚቀጥል ከሆነ ዋንጫውን የማናናነሳበት ምንም ምክንያት የለም ብለዋል። በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ሁለቱ የእንግሊዝ ክለቦች ማንቸስተር ሲቲና ቼልሲ ለፍጻሜ ማለፋቸውን ተከትሎ በአውሮፓ ሊግም ሁለቱ እንግሊዝ ክለቦች አርሰናልና ዩናይትድ ለፍጻሜ እንደሚደርሱ ተገምቶ ነበር። ነገር ግን የአርሰናል ከውድድሩ ውጪ መሆንን ተከትሎ ሁለቱም ዋንጫዎች እንግሊዝ መግባታቸው እንዲረጋገጥ ማንችስተር ዩናይትድ የፍጻሜውን ጨዋታ ማሸነፍ አለበት። አርሰናል ከአውሮፓውያኑ 1996/97 የውድድር ዓመት ጀምሮ ከአውሮፓ ውድድሮች ውጪ ሆኖ አያውቅም። በቀድሞው አሰልጣኝ አርሰን ዌንገር እየተመራ በርካታ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ውድድሮችን አድርጓል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ደግሞ በአውሮፓ ሊግ መሳተፍ ጀምሯል። ነገር ግን ከትናንቱ ውጤት በኋላ በሚቀጥለው የውድድር ዓመት በአውሮፓ መድረክ የመሳተፍ እድላቸው በከፍተኛ ሁኔታ ጠቧል። አራት ጨዋታዎች በቀሩት የውድድር ዓመት ሁሉንም ጨዋታዎች ቢያሸንፍ እንኳን በአውሮፓ ሊግ ላይሳተፍ ይችላል። ምከንያቱም ከላይ ያሉት እነ ሊቨርፑል፣ ዌስትሀም፣ ቶተንሃምና ኤቨርተን በቀላሉ ነጥብ ይጥላሉ ብሎ ማሰብ ከባድ ነው።
news-50963121
https://www.bbc.com/amharic/news-50963121
ፕሬዝዳንት ትራምፕ፤ "ኢራን የእጅሽን ታገኛለሽ" ሲሉ ዛቱ
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራቅ ውስጥ የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ በደረሰው ጥቃት ኢራን ዋጋዋን ታገኛለች ሲሉ ዛቱ።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት እንደሚሉት ኢራቅ ውስጥ የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ በደረሰው ጥቃት ኢራን እጇ አለበት። በኢራቅ የሚገኘው አሜሪካ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ላይ በተናደዱ፣ በተቆጡ የተቃውሞ ሠልፈኞች ጥቃት የደረሰው በአሜሪካ የአየር ጥቃት የኢራቅ ወታደራዊ አባል መገደሉን ተከትሎ ነው። ፕሬዝዳንት ትራምፕ በአዲስ አመት ዋዜማ የትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ላይ እንዳስታወቁት በኤምባሲው ላይ በደረሰው ውድመትና በጠፋው የሰው ሕይወት ምክንያት ኢራን "በትልቁ የእጇን ስራ ውጤት ታገኛለች" ብለዋል። • በምዕራብ ቨርጂንያ የማረሚያ ቤት እጩ ጠባቂዎች ባሳዩት የሰላምታ አይነት ተባረሩ • አሳሳቢ እየሆኑ የመጡት አዳዲሶቹ የአባላዘር በሽታዎች አክለውም "ይህ ማስጠንቀቂያ አይደለም፤ ዛቻ ነው" ሲል ስሜታቸውን ገልፀዋል። የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ማርክ ኤስፐር ወዲያውኑ እንደተናገሩት በቀጠናው 750 ወታደሮች እንዲሰማሩ ተደርጓል። "አሜሪካ ዜጎቿንና ጥቅሟን በየትኛውም የዓለም ክፍል ቢሆን ትከላከላለች" ሲሉ በትዊተራቸው ላይ አስፍረዋል። ባለፈው እሁድ አሜሪካ በኢራንና ኢራቅ ድንበር ላይ ካደረሰችው የአየር ጥቃት ጋር ተያይዞ በባግዳድ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በተቆጡ የአገሬው ተቃዋሚዎች ጥቃት ደርሶበታል። በምላሹ የአሜሪካ ወታደሮች ወደግቢው ለመግባት የሚሞክሩ ሰልፈኞችን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ የተጠቀሙ ሲሆን አካባቢው ከባድ ውጥረት ነግሶበታል ተብሏል። ለግቢው ጠባቂዎች የተሠራ አንድ ማማ በተቃዋሚዎቹ በእሳት መቀጠሉም ታውቋል። በባግዳድ የሆነው ምን ነበር? ባለፈው እሁድ የአሜሪካ ወታደሮች ከካታይብ ሄዝቦላህ ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ የጦር ካምፖችን በአውሮፕላን ከደበደቡ በኋላ በትንሹ 25 ተዋጊዎች ሞተዋል። አሜሪካ ካታይብ ሄዝቦላህ የተባለው ቡድን በአንድ የኢራቅ ኪርኩክ ውስጥ በሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ ላይ ባለፈው አርብ ባደረሰው ጥቃት አንድ ወታደሬ ተገድሎብኛል ብላለች። የኢራቁ ጠቅላይ ሚኒስትር አደል አብዱል ማህዲ ''አሜሪካ የፈጸመችው የአየር ጥቃት የአገሪቱን ሉአላዊነት የሚጥስና ከአሜሪካ ጋር ያለንን ግንኙነት እንድንመረምረው ያስገድደናል'' ብለዋል። የካታይብ ሄዝቦላህ አዛዥ አቡ ማህዲ አል ሙሃንዲስ በበኩሉ ቡድኑ በኢራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ወታደሮች ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል። ኢራቅ የአሜሪካን እርምጃ ''ጥርት ያለ የሽብር ምሳሌ'' ነው ብላለች። • የኤርትራና ኳታር ቅራኔ • የቢላል መስጂድንና ራጉዔል ቤተ ክርስትያንን የሚያሰሩት ካህን የትናንትናውን ተቃውሞ የተቀሰቀሰው በአሜሪካው የአየር ጥቃት የሞቱ የቡድኑ አባላት የቀብር ስነ ሥርዓት በሚደረግበት ወቅት ነው። ከፍተኛ ወታደራዊና የሚሊሻ ኃላፊዎችን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ሀዘንተኞች 'አረንጓዴው ክልል' ወደሚባለውና በርካታ ኢራቅ መንግሥት መሥሪያ ቤቶችና ኤምባሲዎች ወደሚገኙበት ቦታ አቅንተዋል። ኢራቅ የጸጥታ ኃይሎች ሰልፈኞቹ ወደ ክልሉ እንዲገቡ ሲፈቅዱላቸው በቀጥታ ያመሩትም ወደ አሜሪካ ኤምባሲ ነበር። ተቃዋሚዎቹ የካታይብ ሄዝቦላህ እና ሌሎች የሚሊሻ ባንዲራዎችን ሲያውለበልቡ የተስተዋለ ሲሆን አሜሪካ ላይ ደግሞ ከፍተኛ ተቃውሞ ይሰነዘር ነበር። በርካቶችም በዋናው በር ላይ ድንጋይ በመወርወር፣ የቪዲዮ ካሜራዎችን በመስበርና ለጥበቃ አገልግሎት የሚውሉ ማማዎችን በማጥቃት ተቃውሟቸውን ገልጸዋል። • በኢራቅ ጎዳናዎች ከፍ ያሉት ሴቶች • ስለ ወሲብ እንዲያስቡ የማይፈቀድላቸው ኢራናውያን በመቀጠልም ሰልፈኞቹ ከዋናው በሮቹ መካከል አንደኛውን ሰብረው መግባት ችለዋል። የፈረንሳዩ የዜና ወኪል እንደዘገበው በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች በሩን ሰብረው አምስት ሜትር ያህል እንደተጓዙ የአሜሪካ ወታደሮች በአስለቃሽ ጭስ በመታገዝ እንዲመለሱ አድርገዋቸዋል። ሁኔታው ሲከሰት በኤምባሲው ውስጥ ምን ያህል ሠራተኞች እንደነበሩ የታወቀ ነገር የለም። ማረጋገጥ ባይቻልም አምባሳደሩ ቀደም ብለው እንዲሸሹ ተደርገዋል የሚሉ ዘገባዎችም እየወጡ ነው።
51166092
https://www.bbc.com/amharic/51166092
ውሉ ያልታወቀው ቻይና የተከሰተው ቫይረስ በርካቶችን ሳይበክል አልቀረም
ቻይና ውስጥ የተከሰተው ቫይረስ ባለሥልጣናት ከሚሉት ቁጥር በላይ ሰዎችን ሳይበክል እንዳልቀረ የሕክምና ባለሙያዎች ለቢቢሲ ገልፀዋል።
የቻይና መንግሥት በገዳዩ ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 60 ነው ቢልም የእንግሊዝ የሕክምና ባለሙያዎች ግን 1700 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል እያሉ ነው። የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቃው ይህ ቫይረስ የተከሰተው 'ዉሃን' የተሰኘ ግዛት ውስጥ ሲሆን እስካሁን ሁለት ሰዎች መሞታቸው ይፋ ተደርጓል። ከሕክምና ባለሙያዎቹ አንዱ የሆኑት ፕሮፌሰር ኒል ፈርጉሰን ሁኔታው እጅግ እያሳሰባችው እንደመጣ አሳውቀዋል። ምርምሩን ያከናወኑት የእንግሊዝ ሐኪሞች ሌሎች ተቋማትና ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን ነው። ሲንጋፖር እና ሆንግ ኮንግ ከቻይና ውሃን ግዛት የሚመጡ ተጓዦችን መርምረው ማስገባት ጀምረዋል። ዩናይትድ ስቴትስም ብትሆን በሳን ፍራንሲስኮ፣ ሎስ አንጀለስ እና ኒው ዮርክ በሚገኙ አውሮፕላን ማረፊያዎች በኩል የሚያልፉ መንገደኞች እንዲመረመሩ ትዕዛዝ አሳልፋለች። ምንም እንኳ ቫይረሱ መጀመሪያ ዉሃን ግዛት ላይ ይታይ እንጂ ታይላንድ ውስጥ ሁለት፤ ጃፓን ውስጥ ደግሞ አንድ ሰው በቫይረሱ መጠቃታቸው ተሰምቷል። አሁን ላይ የቫይረሱ ተጠቂዎች ትክክለኛ ቁጥር ምን ያክል እንደሆነ መገመት አዳጋች ነው፤ ነገር ግን በሽታውን የመቆጣጠር ኃላፊነት የተሰጠው አካል ከአውሮፕላን ማረፊያዎች የሚገኙ መረጃዎች ቁጥሩን ሊጠቁሙ ይችላሉ ተብሏል። የዉሃን አውሮፕላን ማረፊያ 19 ሚሊዮን ሰዎችን እንዲያስተናግድ ተብሎ የተገነባ ሲሆን የዓለም አቀፍ በረራ ተጠቃሚዎች ቁጥር ግን 3400 ብቻ ነው። የቻይና መንግሥት ቫይረሱ ከሰው ሰው ተላላፊ መሆኑን የሚያሳይ ምልክት እስካሁን አልታየም ብሏል። በሽታው ከተበከለ የባሕር ውስጥ እንስሳ ሳይመጣ እንዳልቀረም ግምት አለ። ቫይረሱ የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቃ ሲሆን በፈረንጆቹ 2002 ቻይና ውስጥ ከተከሰተውና ሳርስ ተብሎ ከሚታወቀው ቫይረስ ጋር ተመሳሳይነት አለው ተብሏል።
news-50869135
https://www.bbc.com/amharic/news-50869135
ሶማሊያዊያን የአንበጣውን መንጋ ለምግብነት በማዋል እየተዋጉት ነው
በሰሜናዊ የኢትዮጵያ ክፍል እንደተስተዋለው ሁሉ ጎረቤት ሃገር ሶማሊያም በ25 ዓመታት ውስጥ አይታ የማታውቀው ከፍተኛ የአንበጣ መንጋ ወረራ አጋጥሟታል።
በሃገራችን የአንበጣውን መንጋን ከፍተኛ ድምጽ በማውጣት ነበር ህዝቡ ከአካባቢው ሲያባረው የቆየው። የጎረቤት ሃገር ሶማሊያ ዜጎች ግን መፍትሄ ያሉትን ሌላ መላ ዘይደዋል። ይህም፤ የአንበጣ መንጋውን መያዝ፣ በውሃ መዘፍዘፍ፣ አጠንፍፎ በዘይት ጠብሶ መመገብ። በሶማሊያ አዳዶ ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች አንበጣን ጠብሰው ከሩዝ እና ከፓስታ ጋር ለምግብነት እያዋሉት ነው። አንዱ የከተማዋ ነዋሪ "አንበጣው ከአሳ በላይ ልዩ ጣዕም አለው" ያለ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የአንበጣው የንጥረ ነገር ይዘት ፍቱን የሆነ መድሃኒት እንደያዘ እንደሚያምን ይናገራል። ይሄው ግለሰብ ዩኒቨርሳል ሶማሊያ ለተሰኘ የቴሌቪዥን ጣቢያ አስተያየቱን ሲሰጥ፤ አንበጣው ውስጥ የሚገኘው ንጥረ ነገር የደም ግፊቱን እንደሚያስተካክልለት እና የጀርባ ህመሙን እንደሚያሽልለት ተስፋ አድርጓል። ዩኒቨርሳል ሶማሊያ ቴሌቪዥን ነዋሪዎች በምን አይነት መልኩ አንበጣውን አብስለው ለምግብነት እንደሚያቀርቡት አስመልክቷል። አንበጣው በቅድሚያ ተሰብስቦ ከተያዘ በኋላ በእቃ ውስጥ ተከድኖበት ይቆያል። ከዚያም በውሃ ይዘፈዘፋል። ውሃ ውስጥ ተዘፍዝፎ እንዲቆይ የተደረገው አንበጣ ይጠነፈፋል ከዚያም በዘይት ይጠበሳል። አንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች በአካባቢው የሚገኙ ምግብ ቤቶች ከአንበጣ የሚሰሩ ምግቦችን በምግብ ዝርዘሮቻቸው ውስጥ እንዲያካትቱ እየጠየቁ ነው። በሶማሊያ አንበጣን በምንም አይነት መልኩ የመመገብ ልምድ ከዚህ ቀደም ታይቶ እንደማይታወቅ ተነግሯል። በምዕራብ አፍሪካ፣ መካከለኛው ምስራቅ እና በኢሲያ የሚገኙ አንዳንድ ሃገራት አንበጣን ለምግብነት የማዋል ባህል አላቸው።
news-56616312
https://www.bbc.com/amharic/news-56616312
የቡድን 7 አባላት በትግራይ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች 'በእጅጉ ያሳስበናል' አሉ
ቡድን ሰባት (ጂ7) የሚባሉት የዓለማችን የኢኮኖሚ ኃያል አገራት በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ግጭት ውስጥ የሚከሰቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰትን በሚመለከት የሚወጡ ሪፖርቶች "በእጅጉ እንዳሳሰበቸው" ገለጹ።
ያለተገደበ አስቸኳይ የእርዳታ አቅርቦት እንዲመቻች ጠይቀዋል ይህ ቡድን ሰባት የሚባለው የአገራት ስብስብ ዩናይትድ ኪንግደምን፣ አሜሪካንን እና የአውሮፓ ሕብረት ያሉበት ሲሆን በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ እየተዘገቡ ያሉትን ወንጀሎች በተመለከተ ምርመራ እንዲደረግና አጥፊዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርቧል። ጨምረውም ትግራይ ውስጥ ከኢትዮጵያ ሠራዊት ጎን ሆነው እየተዋጉ ይገኛሉ ያሏቸውን ወታደሮቿን ኤርትራ እንድታስወጣ ጠይቋል። የሁለቱም አገራት ወታደሮች በግጭቱ ውስጥ ተፈጽመዋል በተባሉ በርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ይከሰሳሉ። የቡድን ሰባት አገራት በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ መውጣትን በተመለከተ ያስታወቁትን ውሳኔ እንደሚቀበለው ገልጿል። ይህም ሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸሙ የጅምላ ግድያዎችን፣ ወሲባዊ ጥቃቶችን፣ ዘረፋና ስደተኞችን መጎሳቆልን የሚጨምር ነው። የቢቢሲ 'አፍሪካ አይ' ምርመራ 15 ሰዎች በኢትዮጵያ ወታደሮች መገደላቸውን የሚያመለክት መረጃን ማውጣቱ ይታወሳል። የህወሓት ኃይሎች ትግራይ ውስጥ በሚገኘው የፌደራሉ መንግሥት ሠራዊት ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ካዘዙ በኋላ ነበር ግጭቱ የተጀመረው። በዚህ ግጭት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች የሞቱ ሲሆን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ተፈናቅለዋል። በግጭቱ ውስጥ የህወሓት ኃይሎችም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በመፈጸም ይከሰሳሉ። የቡድን ሰባት አባል አገራት ባወጡት መግለጫ ላይ "በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎችን፣ ጾታዊ ጥቃቶችን፣ ኢላማ ያልለየ የከባድ መሳሪያ ድብደባዎችና ነዋሪዎችንና ኤርትራውያን ስደተኞችን በኃይል ማፈናቀልን እናወግዛለን" ብለዋል። "ተፈጸሙ በተባሉት ወንጀሎች ላይ ግልጽና ገለልተኛ ምርመራ ተደርጎ የሰብአዊ መብት ጥሰቶቹ ፈጻሚዎች ተጠያቂ ማድረግ አስፈላጊ ነው" በማለት አክለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በቅርቡ በአገሪቱ ፓርላማ ውስጥ ባደረጉት ንግግር በትግራይ ክልል ውስጥ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን የሚያመለክቱ ሪፖርቶች እንዳሉ ተናግረው፤ መንግሥታቸው አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ አጥፊዎችን ተጠያቂ እንደሚያደረግ መግለጻቸው ይታወሳል። በቡድኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችና በአውሮፓ ሕብረት ከፍተኛ ተወካይ የወጣው መግለጫ ጨምሮም በግጭቱ አካባቢ "እየተባባሰ ያለ የምግብ ዋስትና ችግር" እንደሚያሳስባቸው በመግለጽ "አስቸኳይና ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት" እንዲመቻች ጠይቋል። በትግራይ ክልል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ከ70ሺህ በላይ ሰዎች ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን መሰደዳቸውን የእርዳታ ድርጅቶች ይናገራሉ። የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እንደሚለው አስካሁን ድረስ ከሁለት ሚሊዮን ሰዎች በላይ ሰዎች በክልሉ ውስጥ የተፈናቀሉ ሲሆን፤ ከአራት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑትን ደግሞ የሰብዓዊ እርዳታ ይፈልጋሉ።
52555290
https://www.bbc.com/amharic/52555290
መኪና ለመግዛት የወላጆቹን መኪና እስነስቶ የሄደው የ5 ዓመት ህጻን ተያዘ
አንዳንድ ህፃናት አጣፍጠው የሰሩላቸውን አልበላም ብለው ወላጆቻቸውን ያስቆጣሉ፤ ያስጨንቃሉ፤ የድመት ጭራ እየጎተቱ በመጫወት ራሳቸው ለአደጋ ይጋብዛሉ።
ላምበርጊኒ ለመግዛት የቤተሰቡን መኪናና ሶስት ዶላር ይዞ ወደ ካሊፎርንያ ያመራው ህፃን የአምስት ዓመቱ አንድርያን ግን የቤተሰቦቹን መኪና አስነስቶ ሲያሽከረክር ፖሊስ አስቁሞ በቁጥጥር ስር አውሎታል። ይህ የሆነው በአሜሪካ ዩታህ ግዛት ነው። ፖሊስ በዋና ጎዳና ላይ ዝግ ብሎ የሚሄድ መኪና ወዲያና ወዲህ ሲዋልል አስተዋለ። ከዚያም አሽከርከካሪው ጥጉን ይዞ እንዲያቆም ተጠየቀ። አሽከርካሪው የፖሊስን ትዕዛዝ አክብሮ አቆመ። • አቅመ ደካሞችን እያማለለ የሚገኘው የማፊያዎች ገንዘብ ፖሊስ ግን የተመለከተው እጅጉን እንዳስደነገጠው ተናግሯል። ልጁ ወዴት እንደሆነ ሲጠየቅም ላምበርጊኒ ለመግዛት እየሄደ መሆኑን አስረድቷል። ጉዳዩን የልጅ ነገር ብለው ንቀው የሚተዉት አልሆነም። ምክንያቱም ልጁ ከወላጅ እናቱ ጋር በዚሁ ጉዳይ እሰጥ አገባ ውስት ገብቶ ነበር ተብሏል። እናቱን ይህንን ቅንጡ መኪና ግዢልኝ ሲል ፈትሮ ይዟት ነበር ተብሏል። የመኪናው ዋጋ ደግሞ አይቀመስም። ዝቅተኛው እንኳ 180ሺህ ዶላር ነው የተተመነው። የዩታህ ፖሊስ መርምሬ ደረስኩበት እንዳለው የአምስት ዓመቱ ህፃን መኪና አስነስቶ ወደ ካሊፎርኒያ ለመሄድ የወሰነው ላምበርጊኒውን ገዝቶ ለመምጣት ነው። አሁንስ የልጅ ነገር እንበል ይሆን? • 7 ፓርቲዎች አሁን ላይ ላለው ችግር ምላሽ የሚሆነው 'ፖለቲካዊ መፍትሄ ነው' አሉ እስቲ ምን ያህል ገንዘብ ይዞ ወደ ካሊፎርኒያ ጉዞ እንደጀመረ ፖሊስ ያለውን አናንብብ። በአምስት ዓመቱ ህፃን ኪስ ውስጥ ሶስት ዶላር ተገኝቷል። ገንዘብ እንኳ ትንሽ ያጥረው ነበር ይላሉ ፖሊሶች። ፖሊስ በአሽከርካሪ ወንበር ላይ ተቀምጦ ያገኘውን ማሙሽ ሲመለከት መጀመሪያ የአካል ጉዳተኛ መስሎኝ ነበር ብሏል፤ በኋላ ግን እድሜውን ሲጠይቅ 'ጉድ ሳይሰማና ሳይታይ መስከረም አይጠባም' ብለው ሳይተርቱ አልቀሩም። ልጁ እድሜውን ሲጠየቅ አምስት አለ። • በስልጤ ዞን ኮቪድ-19 ያለባቸው ሴት እንዴት ሊገኙ ቻሉ? ይህ ልጅ መኪና የመግዣ ገንዘብ ብቻ ሳይሆን የማሽከርከሪያም እድሜ ያጥረዋል። ልጁ እግሩ ነዳጅ መስጫው ላይ እንዲደርስለት የአሽከርካሪ ወንበሩ ጫፍ ላእ ተቀምጦ ያሽከረክር እንደነበር ፖሊስ ገልጿል። የአካባቢው አቃቤ ሕግቤተሰቡን ለመክሰስ እያሰቡ መሆናቸው ታውቋል። ቤተሰቦቹ ሁለቱም ሥራ ነበሩ የተባለ ሲሆን መኪናውን አስነስቶ ሲሄድ ከወንድም እህቶቹ ጋር ቤት ትተውት መሄዳቸው ተገልጿል። ፖሊስ የመኪና ቁልፍ ልጆች በማይደርሱበት ይቀመጥ ሲል አስጠንቅቋል።
news-45422735
https://www.bbc.com/amharic/news-45422735
የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የሶማሊያ መሪዎች አሥመራ ላይ ይመክራሉ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከቻይና መልስ ወደ ኤርትራ ለሁለተኛ ጊዜ አቅንተው አሰብ ላይ በሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በተመሳሳይም በዛሬው እለት ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ የጭነት መርከብ በምፅዋ ወደብ ላይ ምልህቋን በመጣል ወደ ቻይና የሚላክ ጭነት እንደምታጓጉዝ ተነግሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በቅርቡ ለኢትዮጵያ የወጪና ገቢ ንግድ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል የተባለውን የአሰብ ወደብን ከኢትዮጵያ ድንበር ጋር የሚያገናኝ የየብስ መንገድ መንገድ ያለበትን ሁኔታ ጎብኝተዋል። • "የኤርትራ ማዕቀብ የመነሳት ጥያቄ በኤምሬትስ ተፅእኖ የተፈጠረ መሆኑን ጂቡቲ ታምናለች" ፕ/ር መድኃኔ ታደሰ • ስለ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ምን ያህል ያውቃሉ? ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሁለት ወራት ውስጥ በኤርትራ ጉብኝት ሲያደርጉ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን፤ ከአሰብ ወደ አሥመራ ከማቅናታቸው በፊት የምፅዋ ወደብንም ይጎበኛሉ ተብሏል። ለሁለት ቀናት በሚቆየው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የኤርትራ ጉብኝት ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ኢትዮጵያና ኤርትራ በቅርቡ የፈጠሩት ግንኙነትና ያስቀመጡት ዕቅድ ያለበትን ሁኔታን በተመለከተ እንደሚወያዩ ተነግሯል። በተያያዘ ዜና የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ወደ ኤርትራ እንደሚያቀኑ የሃገሪቱ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት አሳውቋል። መስሪያ ቤቱ እንዳመለከተው ፕሬዝዳንቱ ሃሙስና አርብ አሥመራ ውስጥ ይካሄዳል በተበላ የኤርትራ፣ ኢትዮጵያና ሶማሊያ የጋራ ትብብር ጉዳይ ላይ በሚያተኩር ስብሰባ ላይ ይሳተፋሉ ብሏል። ይህም የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የኤርትራ ጉዞ ይህንን የሦስት ሃገራት ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ያለመ እንደሆነም ይታመናል።
news-41522491
https://www.bbc.com/amharic/news-41522491
ካለሁበት 4፡ የሰው ሃገር የሰው ነው፤ ያለሁበት መጠለያ ጣቢያ እስር ቤት ውስጥ እንደ መኖር ነው
ስደት ህይወቴን ያትርፍልኝ እንጂ የስደተኝነት ኑሮ እጅግ መራራ ነው።
ካኩማ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ በረሃማ በሆነው ሰሜናዊ ኬንያ ይገኛል። ዱሬሶ ሞሲሳ እባላለሁ። ኬንያ ቱርካና ግዛት (ካውንቲ) ውስጥ ካኩማ በሚባል የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ነው የምኖረው። በዚህ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ከተለያዩ ሃገራት የመጡ ከ200 ሺህ በላይ ስደተኞች ይኖራሉ። በካኩማ መኖር እጅግ ከባድ ነው። አካባቢው በረሃማ ስለሆነ ሙቀቱ በአማካይ 30 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ይደርሳል። ወባን ጨምሮ በካኩማ ለተለያዩ በሽታዎች ተጋለጠናል። ከዚህም በላይ በካኩማ እንደ እባብ እና እፉኚት ያሉ መርዛማ ተሳቢ እንስሳት በብዛት ይገኛሉ። በእነዚህ መርዛማ ተሳቢ እንስሳት እየተነደፉ ብዙ የሚሞቱ ሰዎች አሉ። ወደዚህ የመጣሁት የኢትዮጵያን መንግሥት ሽሽት ነው። የኦነግ ደጋፊ ነህ ተብዬ 8 ዓመታትን በእስር ከተንገላታሁ በኋላ ተለቀኩኝ። ከእስር ቤት ከወጣሁም በኋላ ይከታተሉኝ ነበር። ክትትላቸው እረፍት ነሳኝ። በሄድኩበት ይከተሉኛል። ከዛም ህይወቴን ለማዳን ስል ሃገሬን ጥዬ ለመሰደድ ወሰንኩ። ከሃገሬ በቀጥታ ወደ ኬንያ ነበር የመጣሁት። ከሃገሬ ከወጣው 11 ዓመታት አለፉ። በስደት ለኑሮ በማይመቸው ካኩማ 11 ዓመታትን ማሳለፍ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ለማንም ግልፅ ነው። ካኩማ ሰፊ ከመሆኑ የተነሳ በውስጡ የተለያዩ መንደሮች አሉት። ካኩማ 1፣ ካኩማ 2 እና 3 በመባል ይታወቃሉ። እኔ የምኖረው ካኩማ 1 ውስጥ ነው። በካኩማ 1 ውስጥ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች የመጡ ስደተኞች በብዛት ይኖራሉ። እኛ የምንኖርበት መንደር ከሌሎች በተሻለ መልኩ ዛፎች አሉት። ከኛ በፊት የነበሩ ስደተኞች የተከሏቸው ናቸው። ዛፎቹ የአካባቢውን ሙቀት ጋብ ስለሚያደርጉልን ሁላችንም በተቻለን መጠን ለመጠጥ ከሚታደለው ውሃ በመቀነስ ዛፎቹን በማጠጣት እንከባከባለን። በካኩማ የስደተኞች ጣቢያ ውስጥ በርካታ ኢትዮጵያውያን ይገኛሉ። ከሃገር ቤት ከሁሉ በላይ የሚናፍቁኝ ቤተሰቦቼ ናቸው። ለዓመታት ከደረሰብኝ ስቃይ በላይ ከቤተሰቤ ሳልፈልግ መለየቴ ሁሌም ያሳዝነኛል። እንደ ኢትዮጵያ እስር ቤት የሚደርስብኝ ስቃይ እና ድብደባ የለም አንጂ በዚህም መንቀሳቀስ ስለማልችል እስር ቤት እንዳለሁ ነው የሚሰማኝ። በህይወቴ መልካም ነገር ተፈጠረ የምለው ከሶስት ዓመት በፊት የሴት ልጅ አባት መሆኔ ነው። የልጄን ዓይን ስመለከት ደስታ እና ሠላም ይሰማኛል። በህይወቴ የገጠመኝን ችግር እና ስቃይ የምረሳው ልጄን ሳስባት ነው። ወደፊትም የተሻለ ህይወት ሊገጥመኝ እንደሚችል አስባለሁ። በመጠለያ ጣቢያው ውስጥ ባለ ድርጅት ውስጥ የተለያዩ ስራዎችን በመስራት በማገኝው አነስተኛ ገንዘብ ልጄን አሳድጋለሁ። ብዙ እንደመቆየቴ መጠን የኬንያን ምግብ በደንብ ተላምጄዋለሁ። ኡጋሊ በጎመን ምርጫዬ ነው። እንደው ቢቻል እና በአንድ ተዓምር አምቦ ካሉት ቤተሰቦቼ መሃል ከልጄ ጋር እራሴን ባገኘው ደስታዬ ወደር አይኖረውም ነበር። ለጫሊ ነጋሳ እንደነገረው የ'ካለሁበት' ቀጣይ ክፍሎችን ለማግኘት ፦ ካለሁበት 5፡'ኑሮዬን ቶሮንቶ ያደረግኩት በአጋጣሚ ነበር' ካለሁበት 6 ''ከሀገር ቤት የስደት ኑሮዬ ይሻለኛል''
news-44312634
https://www.bbc.com/amharic/news-44312634
ሰባኪው የአንድ ቢሊዮን ብር አውሮፕላን ግዙልኝ አለ
በአሜሪካ እውቅ ከሆኑ የቲቪ ሰባኪዎች (ቴሌቫንጀሊስት) አንዱ የሆነው ነብይ ጀሴ ዱፕላንቲስ ተከታዮቹን የግል ጄት እንዲገዙለት በይፋ ጠየቀ። ምክንያቱም "ኢየሱስ አህያ ሊጋልብ አይችልም" ብሏል።
በሰሜን አሜሪካ የግል ጄት ያላቸው ሰባኪዎች ቁጥር በርካታ ነው አስገራሚ የሆነው ታዲያ ይህ ሰባኪ ሦስት የግል አውሮፕላኖች ያሉት ሲሆን ምዕመኑን መዋጮ እየጠየቀ ያለው ለ4ኛ አውሮፕላን (ጄት) ግዢ ነው። ሰባኪ ዱፕላንቲስ እንደሚለው ከሆነ ጌታ ግዛ ያለው ጄት ፋልኮን 7X የተባለውን ሲሆን ዋጋው ደግሞ 54 ሚሊዮን ዶላር ነው። ይህ ገንዘብ በብር ሲመነዘር 1.5 ቢሊዮን ብር ይጠጋል። ነብይ ዱፕላንቲስ ጨምሮ እንዳለው መጀመርያ ጌታ ይህን የግል ጄት ግዛ ሲለው "ትዕዛዙን ለመቀበል አቅማምቼ ነበር" ካለ በኋላ ጌታም ማቅማማቴን አይቶ "'አንተን ክፈል አላልኩህም፤ ይኖረኛል ብለህ እመን ነው ያልኩህ ሲል ጌታ ገሰጸኝ" ብሏል። ምንም እንኳ የግል አውሮፕላን ያላቸው ሰባኪዎች በአሜሪካን ምድር ማየት አዲስ ባይሆኑም ይህ የሰባኪ ዱፕላንቲስ ለ4ኛ ጊዜ "የጄት ግዙልኝ" ጥያቄ ማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃንን በስፋት እያነጋገረ ነው። በተለይ የትዊተር ተጠቃሚዎች የሰባኪውን ድርጊት ማመን ተስኗቸዋል። አንዳንዶቹም የመጽሐፍ ቅዱስ አንቀጾችን እየጠቀሱ እየሞገቱት ይገኛሉ። "ሐሳዊ ነብይ" ያሉትም አልጠፉም። "ምናለ ይህን የሚያህል ገንዘብ ለእርሱ መንደላቀቂያ ከሚሆን ለድሆች እርዳታ ቢውል" ያሉም አሉ። የ68 ዓመቱ እውቅ ሰባኪ ነብይ ዱፕላንቲስ በቪዲዮ ባስተላለፈው መልእክት እንዲህ ብሏል፦ "እንደምታውቁት ጄት ለኔ ብርቅ አይደለም። ከዚህ በፊት ሦስት የግል ጄቶች ነበሩኝ። ተጠቅሜባቸው ለኢየሱስ ክርስቶስ ስል አቃጥያቸዋለሁ።" ነብይ ዱፕላንቲስ እንደሚለው የጌታን ቃል ለዓለም ለማድረስ በተራ መኪና ወይም በባቡር ወይም በመርከብ የማይሆን ነገር ነው። ይህን ለማድረግ የቀረኝ ዕድሜ በቂ ካለመሆኑም በላይ አሰልቺም ነው። አንድ ጊዜ ነዳጅ ተሞልቶ ውቅያኖስ የሚያሻግርና ያለ ዕረፍት ረዥም ርቀት የሚጓዝ ዘመናዊ ጄት ያስፈልገኛል ብሏል። በ2015 ሰባኪ ዱፕላንቲስ ኬኔት ኮፕላንድ ከሚባል ሌላ ሰባኪ ጋር ሆኖ በቪዲዮ ባስተላለፈው አንድ መልዕክት እንደርሱ ያለ ትልቅ ሰባኪ ከሕዝብ ጋር በአውሮፕላን መሳፈር አሳፋሪ መሆኑን ለመግለጽ "በሕዝብ አውሮፕላን መጓዝ በትቦ ውስጥ ከአጋንንት ጋር እንደመሳፈር ያለ ነው" ብሎ ነበር።
news-44165279
https://www.bbc.com/amharic/news-44165279
ጥቃት የተፈጸመበት ታዳጊ ባህር ዳር ደርሷል
ባሳለፍነው ሰኞ ግንቦት 6 2010 ዓ.ም በመተከል ዞን፤ ድባጤ ወረዳ እድሜው አስራ ሦስት እንደሆነ በሚገመት ሕፃን ልጅ ላይ በስለት በተፈጸመ ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል።
ጥቃቱን በተመለከተ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ብዙ መረጃ እየወጣ ሲሆን፤ ጉዳዩን ለመማረጋገጥ የታዳጊው የቅርብ ቤተሰብ የሆኑት አቶ አያሌው አበረን ቢቢሲ አነጋግሯቸው ነበር። እንደ አቶ አያሌው ምስክርነት ከሆን ታዳጊው ጥቃቱ በተፈጸመ ወቅት የመራቢያ አካሉ የተቆረጠ ሲሆን፤ ፊቱም ላይም በካራ ከፍተኛ መቆራረጥ ተፈፅሞበታል። ሦስት የፊት ጥርሶቹም ረግፈዋል። ታዳጊው በደረሰበት ጉዳት ራሱን ስቶ የቆየ ሲሆን ከሁለት ቀናት በፊት ግን መናገር እንደጀመረ እና ጥቃቱን ያደረሰበት ግለሰብ በወቅቱ ጫት እየቃመ እንደነበረ ታዳጊው ነግሮናል ሲሉ አቶ አያሌው ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ አያሌው ጨምረው እንደተናገሩት፤ ግለሰቡ ሲያጫውተው እንደቆየና ድንገት ማጅራቱን ሲመታው መሬት ላይ በመውደቅ ራሱን ስቷል። ታዳጊው ሲያግዳቸው የነበሩት ከብቶች ከምሽቱ 12 ሰዓት አካባቢ ብቻቸውን ወደ ቤት ሲመለሱ ልጁ 'ያለ ወትሮው ከብቶቹን እንዴት ብቻቸውን ላከ' ብለው የቤተሰቡ አባላት ፍለጋ መውጣታቸውን ይናገራሉ አቶ አያሌው። ፍለጋ የወጣውም ቤተሰብ በአካባቢው የታዳጊውን ስም በመጥራት ሲፈልጉት ቆይተው በመጨረሻም ጥሪውን የሰማው ታዳጊ ድምጹን በማሰማቱ ከቦታው ሲደርሱ ወድቆ እንዳገኙትና ተረባርበው ወደ ህክምና ቦታ እንደወሰዱት አቶ አያሌው ለቢቢሲ ተናግረዋል። አሁን ታዳጊው በሚገኝበት ፓዌ ሆስፒታል ከደረሰበት ቀን ጀምሮ በነጻ ህክምና እየተደረገለት መሆኑን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ግርማ በየነ ገልጸውልናል። ታዳጊው ለተሻለ ህክምና ወደ ባህር ዳር መላክ የነበረበት ቢሆንም ወላጆቹ የትራንስፖርት እና ተያያዥ ወጪ መሸፈን ሳይችሉ በመቅረታቸው በፓዌ ሆሰፒታል ውስጥ ለቀናት እንዲቆይ ተደርጎ ነበር፤ ሲሉ በሆስፒታሉ ሃኪም የሆኑት ዶክተር ግርማ ይናገራሉ። ትናንት ማምሻውን ግን የሆስፒታሉ ሰራተኞች ገንዘብ በማሰባሰብ ታዳጊውን ወደ ባህር ዳር የላኩት ሲሆን፤ ዛሬ ጠዋት ከቤተሰብ አባላት እንደሰማነው በባህር ዳር ፈለገ ህይወት ሆስፒታል ይገኛል። ''በሆስፒታሉ በቆሁባቸው 2 ዓመታት እንደዚህ አይነት አሳዛኝ ሁኔታ ገጥሞኝ አያውቅም'' ያሉት ዶክተር ግርማ፤ የተቻለንን ህክምና አድርገንለታል ብለዋል። ለተሻለ ህክምና ግን ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል ሪፈር ስለተባለ ዛሬ ወደ ባህር ዳር ሆስፒታል መላኩንና ከባህ ርዳር ደግሞ ወደ አዲስ አበባ እንደሚጓዝ ጨምረው ተናግረዋል። በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ደግሞ ስለ ታዳጊው በማህበራዊ ሚዲያ ከሰሙ በኋላ ጉዳዩን በቅርበት ሲከታተሉ እንደቆዩ ይናገራሉ። ዶክተር ደሳለኝ ታዳጊው ባህር ዳር ከደረሰ በኋላ ሄደው የጎበኙት ሲሆን ''ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ይገኛል'' ሲሉ የታዳጊውን ሁኔታ ገልፀዋል። ከዶክተር ደሳለኝ እና ከሌሎች ምንጮቻችን እንደሰማነው ከሆነ አቶ በላይነህ ክንዴን ጨምሮ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የታዳጊውን የህክምና ወጪ ለመሸፈን ቃል ገብተዋል።
news-55401208
https://www.bbc.com/amharic/news-55401208
የእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የጤና ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ሃኪማቸው ገለፁ
እነ ጃዋር መሐመድ በረሃብ አድማ ላይ ለረዥም ቀናት በመቆየታቸው የተነሳ የጤና ችግር እየተስተዋለባቸው መሆኑን የጤና ክትትል ከሚያደርጉላቸው ሐኪሞች መካከል አንዷ የሆኑት ዶ/ር ኢሊሊ ጀማል ለቢቢሲ ገለፁ።
ከድምጻዊ ሃጫሉ ግድያ በኋላ በቁጥጥር ስር የዋሉት እና ክስ ተመስርቶባቸው በእስር የሚገኙት እነ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ፣ ሸምሰዲን ጠሃ እና ሃምዛ አዳነ በፖለቲከኞች እና በቤተሰብ አባላቶቻቸው ላይ የሚደርሰውን እስር እና ወከባ በመቃወም የረሃብ አድማ ማድረግ ከጀመሩ ከ13ት ቀናት በላይ እንዳስቆጠሩ ጠበቆቻቸው ይናገራሉ። ጃዋር እና ሌሎች በረሃብ አድማ ላይ የሚገኙ እስረኞችን የጤና ሁኔታ የሚከታተሉት ዶ/ር ኢሊሊ ጀማል፣ እስከ ማክሰኞ ድረስ ክትትል ሲያደርጉላቸው እንደነበር ለቢቢሲ ገልፀዋል። ነገር ግን ረቡዕ ዕለት የተለመደውን ሕክምና ለመስጠት ወደ ማረሚያ ቤቱ ቢያመሩም "ባላወቅኩት መንገድ በር ላይ ማዘግየቶችና ማመላለሶች ሲኖሩ ማግኘት አቅቶን ወጥተናል" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። እነ አቶ ጃዋር መሐመድ የረሃብ አድማውን እያደረጉ ያሉት በፖለቲከኞች ላይ የሚደርሰውን እንግልት እና እስር፣ እነሱን ለመጠየቅና የችሎት ሂደታቸውን ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት በሚመጡ ሰዎች ላይ የሚፈጸም እስር እና ወከባ እንዲቆም ለመጠየቅ እንደሆነም ቢቢሲ ከጠበቆቻቸው ለመረዳት ችሏል። እነ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ፣ ሸምሰዲን ጠሃ እና ሃምዛ አዳነ በተጨማሪ በአቶ ጃዋር መሐመድ የክስ መዝገብ ሥር የሚገኙት የአቶ ጃዋር መሐመድ ጠባቂዎች እና የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋዜጠኛ መለሰ ዲሪብሳ የረሃብ አድማውን መቀላቀላቸው ይታወሳል። እነ አቶ ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባን ጨምሮ በርካታ ፖለቲከኞች የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ከተፈጠረው ሁከት ጋር ተያይዞ እጃችሁ አለበት ተብለው ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው የሚታወስ ነው። ከእነ አቶ ጃዋር በተጨማሪ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከፍተኛ አመራሮች በተመሳሳይ የረሃብ አድማ ላይ እንደሚገኙ የተገለፀ ሲሆን አቶ ሚካኤል ቦረን እና ኬነሳ አያና ፍርድ ቤት የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ጉዳያቸው ከውጪ ሆነው እንዲከታተሉ ቢፈቅድላቸውም ፖሊስ እስረኞቹን አልለቅም በማለቱ የረሃብ አድማ ላይ እንደሚገኙ ጠበቃቸው አቶ ቱሊ ባይሳ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የጤንነታቸው ሁኔታ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል? ዶ/ር ኢሊሊ እነ አቶ ጃዋር ያሉበትን የጤና ሁኔታ ለቢቢሲ ሲያስረዱ "የመድከም፣ አቅም የማጣት. . . ሰውነታቸው ላይ መጎሳቆል" በጉልህ ይታያል ብለዋል። በየዕለቱ ደም በመውሰድ ምርመራዎችን እንደሚያደርጉ የገለፁት ዶ/ር ኢሊሊ የስኳር መጠናቸው ከሚገባው በታች መውረዱን ማረጋገጣቸውን ይገልጻሉ። አቶ ሸምሰዲን ጠሃ ከሁሉም በተለየ የስኳር መጠናቸው በጣም በመውረዱ፣ ሆስፒታል ገብተው የህክምና ክትትል እንዲያደርጉ መደረጉንም ጨምረው አስረድተዋል። እነ አቶ በቀለ ገርባም ሆኑ ሌሎች ደም ግፊት ስላለባቸው የኩላሊታቸው ሁኔታ ላይ ምርመራ መደረጉን የገለፁት ዶ/ር ኢሊሊ በዚህም ከረሃብ አድማው በኋላ የተፈጠሩ የኩላሊት መጎዳቶች መስተዋላቸውን ገልፀዋል። በረሃብ አድማ ውስጥ ያሉት ታሳሪዎች በአጠቃላይ ለረዥም ቀናት ምግብ ባለመመገብ የተነሳ የሚመጡ ችግሮች በሽንታቸው እና በደማቸው ውስጥ መስተዋሉን ዶ/ር ኢሊሊ ጨምረው አስረድተዋል። አቶ ጃዋር በረሃብ አድማው የመጀመሪያ ቀናት ላይ ውሃ ሳይወስድ በመቅረቱ ኩላሊቱ ላይ ጉዳት መስተዋሉን ገልፀዋል። ዶ/ር ኢሊሊ በየዕለቱ በረሃብ አድማ ላይ ከሚገኙት በሙሉ ደምና ሽንት ናሙና በመውሰድና በመመርመር ውጤታቸውን በማየት ሰውነታቸው ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት ምን እንደሆነ እንደሚነግሯቸው ገልፀው፣ እነርሱ 'የሚመጣውን ነገር እናውቃለን፤ ነገር ግን ወስነን ነው እያደረግን ያለነው' ማለታቸውን ገልፀዋል። ሰውነታቸው ላይ ከደረሰው ጉዳት አንጻር ሆስፒታል ተኝቶ መታከም ያስፈልጋቸው ነበር ያሉት ዶ/ር ኢሊሊ፣ ነገር ግን ተከሳሾቹ 'አንፈልግም' ማለታቸውን ተናግረዋል። እነ አቶ ጃዋር አሁን እያደረጉ ያሉት ሙሉ የረሃብ አድማ መሆኑን የገለፁት ዶ/ር ኢሊሊ፣ ምግብ ሳይወስዱ በመቅረታቸው ውሃ የመውሰድ ፍላጎታቸውም መቀነሱንና ይህም የተለያዩ የጤና እክሎች እንዲታይ ምክንያት መሆኑን አስረድተዋል። ከ13 ቀናት በላይ በረሃብ አድማ ላይ የሚገኙት እነ አቶ ጃዋር መሐመድ የረሃብ አድማውን እንዲያቆሙ በትናንትናው ዕለት በሃይማኖት አባቶች እና ፖለቲከኞች ቢጠየቁም ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የረሃብ አድማው ተከሳሾችን የከፋ አደጋ ላይ እንዳይጥል የቅርብ ክትትል ማድረግ እንደሚያስፈልግ መግለጻቸውን ኮሚሽኑ ባሳለፍነው አርብ ባወጣው መግለጫ አስነብቧል። "ለታሳሪዎች ምክንያታዊ የሆኑ ጥያቄዎች ተገቢውን አፋጣኝ ምላሽ መስጠትና የእስረኞችን ጠያቂዎች በማረሚያ ቤቱም ሆነ በፍርድ ቤቶች በአግባቡ ማስተናገድ ይገባል" ስለማለታቸው በመግለጫው ሰፍሯል። የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በቁጥጥር ሥር የዋሉት እነ አቶ ጃዋር ከቀረቡባቸው ተደራራቢ አስር ክሶች ስድስቱ እንዲቋረጡ ፍርድ መወሰኑ ይታወሳል። የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ፤ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል አዋጅ፤ የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ የመተላለፍ ክሶች ከተመሰረቱባቸው ክሶች መካከል ሲሆኑ፤ እንዲቋረጡ የተደረጉት ክሶች የጦር መሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ 1177/2021 ጋር የተያያዙ ናቸው።
55706104
https://www.bbc.com/amharic/55706104
ኮሮናቫይረስን ፈርቶ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ 3 ወር የተደበቀው ግለሰብ ታሰረ
አዲታ ሲንግ የተባለ ግለሰብ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ይይዘኛል ብሎ ፈርቶ ለሦስት ወራት የቺካጎ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ተደብቆ እንደነበር የአሜሪካ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ።
የ36 ዓመቱ ግለሰብ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ለሦስት ወራት ሲደበቅ ማንም አላስተዋለውም ነበር። ነገር ግን ቅዳሜ እለት አንድ የአውሮፕላን ማረፊያው ሠራተኛ የጉዞ ሰነድ እንዲያሳይ ጠይቆት ተጋልጧል። በቁጥጥር ስርም ውሏል። ግለሰቡ ማንነቱን የሚያሳይ ሰነድ እንዲያሳይ ሲጠየቅ ያቀረበው አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ የሚሠራ ግለሰብን መታወቂያ ነበር። ይህ ሠራተኛ ጥቅምት ላይ መታወቂያው እንደጠፋ አመልክቶ ነበር። ፖሊስ እንዳለው አዲታ ጥቅምት 19 ከሎስ አንጀለስ፤ ቺካጎ ከገባ በኋላ ከአውሮፕላን ማረፊያው አልወጣም። የአውሮፕላን ማረፊያው ሠራተኛን መታወቂያ አግኝቶ እንደወሰደ ተናግሯል። ኮሮናቫይረስ ሊይዘኝ ይችላል ብሎ ፈርቶ ወደ ቤቱ እንዳልተጓዘም ተገልጿል። ቺካጎ ትሪቢውን የዓቃቤ ሕግ አባል ካትሊን ሀግርቲን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ግለሰቡ ከተጓጓዦች እርዳታ እየጠየቀ 3 ወር ኖሯል። ጉዳዩን የተመለከቱት ዳኛ ሱዛና ኦርቴዝ መገረማቸውን ገልጸው "የአውሮፕላን ማረፊያው ሠራተኛ ያልሆነ ግለሰብ ከጥቅምት 19 እስከ ጥር 16 ድረስ ማንም ሳይደርስበት አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ኖረ ማለት ነው?" ሲሉ ዐቃቤ ሕግን ጠይቀዋል። ግለሰቡ የሎስ አንጀለስ ነዋሪ ነው። ከዚህ ቀደም ምንም ወንጀል እንዳልሠራ ተገልጿል። ለምን ወደ ቺካጎ እንዳቀና ግን ግልጽ አይደለም። ከውሮፕላን ማረፊያ ሠራተኞች ውጪ ክልክል በሆነ ቦታ በመገኘትና በአነስተኛ ስርቆት ክስ ተመስርቶበታል። በ1,000 ዶላር ዋስ ከእስር እንደሚለቀቅና ከዚህ በኋላ ወደ አውሮፕላን ማረፊያው መግባት እንደማይችል ተዘግቧል። ዳኛዋ፤ ተጓጓዦች ደህንነት እንዲሰማቸው የአውሮፕላን ማረፊያዎች ጥበቃ አስተማማኝ መሆን አንዳለበት ተናግረዋል። "ግለሰቡ የፈጸመው ተግባር ለማኅበረሰቡ አደገኛ ያደርገዋል" ሲሉም ተደምጠዋል። የቺካጎን አውሮፕላን ማረፊያዎች የሚቆጣጠረው አቪየሽን ክፍል "ጉዳዩን እየመረመርን ቢሆንም ግለሰቡ በተጓዦችም ይሁን በአውሮፕላን ማረፊያው ላይ የጸጥታ ችግር እንዳልፈጠረ አረጋግጠናል" ሲል መግለጫ አውጥቷል።
news-54702903
https://www.bbc.com/amharic/news-54702903
አየርላንድ፡ ከ40 ዓመታት ትውውቅ በኋላ በ80ዎቹ እድሜያቸው የተጋቡት ጥንዶች
በ80ዎቹ እድሜ ያሉ የእድሜ ባለ ፀጋ አየርላንዳውያን ከአርባ አመት ትውውቅ በኋላ ከሰሞኑ ተጋብተዋል።
የ86 አመቱ ጆን በርሚንግሃምና የ83 አመቷ ሜሪ ሎንግ ከሰሞኑ በአየርላንድ በሚገኝ የቱላሞር የጤና ማዕከል ጋብቻቸውን መፈፀማቸው ታውቋል። "ልባችን አያረጅም" ያሉት ጥንዶች ጋብቻቸውን ለመፈፀም ለረዥም አመት አቅደው የነበረ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ሲያራዝሙት ቆይተዋል። በአሁኑ ወቅት የተከሰተው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የበለጠ ጋብቻቸውን እንዲያራዝመው አልፈቀዱም። የጆን በርኒንግሃም ልጅ ካሮላይን ለቢቢሲ ጉድ ሞርኒንግ ፕሮግራም እንደተናገረችው መጋባታቸውን እንደ ትልቅ ድል እንደሚያዩት ነው። ካሮሊን እንደምትለው ጥንዶቹ ቆየት ያሉ ባህላዊ እሴቶችም ስላሉዋቸው ነው መጋባትን እንደ አማራጭ ያዩት ብላለች። ጥንዶቹ ትውውቃቸው በጎሮጎሳውያኑ 1976 ሲሆን በአንድ ሆቴል ውስጥ ነው። ከዚያም ለጥቂት ዓመታት በኋላ አልተገናኙም። እንደገና ሲገናኙም ሜሪ "ወንዶች በቃኝ" ያለችበት ጊዜ ነበር፤ ነገር ግን በመጨረሻ ቡና አብራው ልትጠጣ ተስማማች። ሆኖም በመጀመሪያው ቀን ምንም እንደማይፈጠር አሳውቃው ነበር ቡና አብራው ልትጠጣው መስማማቷን ለአይሪሹ ሚዲያ አርቲኢ ተናግረዋል። ከዚያ በኋላ ያለው ታሪክ ነው። "በእድሜ ባለ ፀጋ እንደሆኑ ሰዎች ዓለምን አያይዋትም፤ ለየት ባለ መልኩ ነው ነገሮችን የሚረዱት" ትላለች ካሮላይን ጋብቻቸውን ላለመፈፀም በርካታ ችግሮች ተደቅነውባቸው እንደነበር የምትናገረው ካሮላይን ዋነኛው ጉዳይም በአየርላንድ እስከ ጎሮጎሳውያኑ 1996 ድረስ ፍቺ መፈፀም ባለመቻሉ ነው። ጆን በርኒንግሃም ከሌላ ሴት ጋር በጋብቻ ተሳስረው የነበረ ቢሆንም መፍታት ቢፈልጉም በህጉ ምክንያት አልተቻለም ነበር። ሜሪም በበኩላቸው ከቤተ ክርስቲያንና ከግዛቲቷ የፍቺ ፈቃድ ማግኘት ነበረባቸው። እነዚህ ችግሮች ከተቀረፉ በኋላም ሁለቱም በእድሜ እየገፉ በመሄዳቸውና ዛሬ ነገ ሲሉም ጊዜው ማለፉን ካሮላይን ትናገራለች። "ሁለቱም ማርጀታቸውን ያውቁታል እነሱም ይህንኑ ደጋግመው ይናገራሉ። ከመጋባታቸው በፊት አንዳችን እንሞታለን የሚልም ፍራቻ ነበራቸው። እናም ይህንኑ ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው የሰርጉን ዝግጅት ለማድረግ የወሰንኩት" ብላለች ካሮላይን። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያትም ሰርጋቸው የደመቀ ባይሆንም የተወሰኑ ቤተሰቦችና ጓደኞቻቸው ሰርጋቸውን መታደም ችለዋል።
49041982
https://www.bbc.com/amharic/49041982
ቦይንግ በ 737 ማክስ ምክንያት አምስት ቢልየን ዶላር ማውጣቱ ተገለጸ
የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን በመላው ዓለም እንዳይበር መደረጉን ተከትሎ ቦይንግ ወጪዎቹን ለመሸፈን 4.9 ቢልየን ዶላር አውጥቷል።
የዓለም ትልቁ አውሮፕላን አምራች ቦይንግ፤ በሚቀጥለው ሳምንት የስድስት ወር ሪፓርት ሲያቀርብ ወጪው ከገቢው እንደሚበልጥም ተገልጿል። ቦይንግ ባወጣው መግለጫ፤ አውሮፕላኖቹ በዚህ ዓመት መጨረሻ ሦስት ወራት ወደ ሥራ ይመለሳሉ ብሎ ተስፋ እንደሚያደርግ ይፋ አድርጓል። 737 ማክስ ኢትዮጵያና ኢንዶኔዥያ ውስጥ ተከስክሶ 346 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል። ቁጥር አንድ አውሮፕላን አምራች የነበረው ቦይንግ ታይቶ የማይታወቅ ውጥንቅጥ ውስጥ ገብቷል። አደጋዎቹን ተከትሎ አሁን ላይ አውሮፕላኖቹ በመላው ዓለም ታግደዋል። • ኢንዶኔዥያ፡ የሟቾች ቤተሰቦች በቦይንግ ካሳ ተጭበርብረናል አሉ አደጋውን የመረመሩ ባለሙያዎች ችግሩ የነበረው የአውሮፕላኑ መቆጣጠሪያ ላይ እንደነበረ መናገራቸውን ተከትሎ፤ ቦይንግ ሶፍትዌሩን እያሻሻለ መሆኑን ተናግሯል። አውሮፕላኖቹ እንዲበሩ ይለፍ በመሰጠቱ እየተወቀሰ ያለው አውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ፤ አየር መንገዶች ምርቶቹን እየገዙ ስላልሆነ ወርሀዊ የምርት መጠኑን ከ52 ወደ 42 ለመቀነስ ተገዷል። ቦይንግ 4.9 ቢልየን ዶላር ያመጣው የበረራ ሰዓት ለተስተጓጎለባቸው ደንበኞቹ ካሳ እንዲሁም ለዘገዩ አውሮፕላኖች ማካካሻ ነው። የቦይንግ የፋይናንስ ኃላፊ ግሬግ ስሚዝ ድርጅታቸው ነገሮችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል እየሠራ መሆኑን ተናገረዋል። • ቦይንግ 737 ማክስ ሌላ ችግር ገጥሞታል የቦይንግ ሊቀ መንበር ዴኒስ ሙለንበርግ "ቅድሚያ የምንሰጠው ለተሳፋሪዎቻችን እና የበረራ ሠራተኞች ደህንነት ነው" ብለዋል። ድርጅቱ የገጠመው ችግር በገቢው ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩንም አክለዋል። ቦይንግ 737 ማክስን ወደ በረራ ለመመለስ ከአቪየሽን ባለ ሥልጣኖች ጋር እየሠራ መሆኑን ይፋ አድርጓል። በያዝነው ዓመት ማገባደጃ አካባቢ አውሮፕላኖቹ በረራ እንደሚጀምሩም ተስፋ አድጓል። ቦይንግ ባቀደው ጊዜ ማክስ 737 ካልበረረ የባሰ ኪሳራ ውስጥ እንደሚገባም ተናግሯል። ባለፈው ሀሙስ የአሜሪካ የትራንስፖርት አመራር ቦይንግ በዚህ ዓመት በረራ ስለመጀመሩ እርግጠኛ እንዳልሆኑ ገልጸዋል። • ቦይንግ "ችግሩ ተፈቷል" እያለ ነው የፌደራል አቪየሽን አድሚንስትሬሽን ወይም ኤፍኤኤ ሂደቱን በአንክሮ እየተከታተለ መሆኑን ኤሌን ኤል ቻዮ ተናግረዋል። አውሮፕላኑ የደህንነት ስጋት እንደሌለበት ሲገራገጥ እግዱ እንደሚነሳለትም አስረድተዋል።
47966985
https://www.bbc.com/amharic/47966985
ሰላሳ ሰባት ማዳበሪያ ዕፀ ፋርስ ወደ ውጭ ሊወጣ ሲል በያቤሎ መቆጣጠሪያ ላይ ተያዘ
በትናንትናው ዕለት 37 ማዳበሪያ ዕፀ ፋርስ ከሀገር ሊወጣ ሲል ያቤሎ መቆጣጠሪያ ላይ መያዙን በገቢዎች ሚኒስትር የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ አዲሱ ይርጋ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
የሰሌዳ ቁጥር 57519 ET ኮድ 3 የሆነ የግንባታ ጠጠር የጫነ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ ላይም ዕፀ ፋርሱ ተጭኖ እንደነበር ተገልጿል። ዕፀ ፋርስ የጫነው መኪና የተነሳበትን ትክክለኛ ቦታ ለማወቅ ፖሊስ ምርመራ ላይ እንደሆነ የገለፁት አቶ አዲሱ ወደ ውጭ ሊወጣ እንደነበር ግን ተረጋግጧል። አብዛኛውን ጊዜ በቁጥጥር ላይ ሲውሉ አሽከርካሪዎቹ መኪኖቹን ትተው የሚጠፉ ሲሆን በዚሁም አጋጣሚ አሽከርካሪው መኪናውን አቁሞ እንዳመለጠ ይናገራሉ። •"ዕፀ ፋርስ በመሸጥ ልጆቼን አሳድጋለሁ" የሌሴቶዋ አምራች በተደጋጋሚ ከሀገር ሊወጣ ሲል ዕፀ ፋርስ የሚያዝ ሲሆን፤ ባለፈው ሳምንት ቶጎ ጫሌ ላይ የተያዘውም ተጠቃሽ ነው። የጉምሩክ ስርአቱ አደረጃጀቱና ላይ ከፍተኛ መሻሻል እንዳለ የሚናገሩት አቶ አዲሱ በየኬላው የሚገኙ ፈታሾች አጥብቀው እንደሚቆጣጠሩ ይገልፃሉ። • አሜሪካዊው ዶክተር ለአራት አመት ህፃን ዕፀ ፋርስ አዘዘ ከዚህ በፊት የፌደራል ፖሊስ በአገሪቱ የሚገኙትን 94 ኬላዎች ይቆጣጠሩ የነበረ ሲሆን ነገር ግን በቦታው ላይ ተመድበው የሚሰሩት በተጨማሪ ስራነት በመሆኑ ግዳጅ በሚሄዱበት ጊዜ ኬላዎች ክፍት ስለሚሆኑ እሱን ክፍተት ለመሙላትም ራሳቸውን የቻሉ የጉምሩክ ፖሊሶች እንዲቋቋሙ ተደርጓል። •የካናዳ ፓርላማ ዕፀ-ፋርስን ለመዝናኛነት ህጋዊ አደረገ ሙሉ ጊዜያቸውን ለኮንትሮባንድና ለየጉምሩክ ስራ የሚያውሉ ለእያንዳንዱ ኬላ 1400 የጉምሩክ ፖሊሶች የሚያስፈልጉ መሆኑን የጠቀሱት አቶ አዲሱ ተጠሪነታቸውም ለፌደራል ፖሊስ ነው። ከነዚህም ውስጥ የተወሰኑትም ወደ ስራ እንደገቡ አቶ አዲሱ ይናገራሉ።
news-51102376
https://www.bbc.com/amharic/news-51102376
'ወንድ ያገቡት' ኡጋንዳዊ ኢማም ከኃላፊነታቸው ታገዱ
'ሴት ናት' ሲሉ በማሰብ ወንድ ያገቡት ኡጋንዳዊው ኢማም ከኃላፊነታቸው መታገዳቸውን ዘ ዴይሊ ሞኒተር ጋዜጣ ዘገበ።
ሼህ ሞሃመድ ሙቱምባ ለሁለት ሳምንታት አብራቸው የቆየችውና 'ሴት ናት' ሲሉ ያገቡት ሂጃብ ለባሹ 'ሚስታቸው' ስዋቡላህ ናቡኬራ፤ ወንድ እንደነበረ ባወቁ ጊዜ በድንጋጤ ደርቀዋል። • የሠርጋቸው ቀን ምሽት ለትዳራቸው መፍረስ ምክንያት የሆነባቸው ሴቶች • ለማጭበርበር የሞተ ያስመሰለው አባት ሚስቱንና ልጆቹን አጣ የአሁኗ 'ሙሽሪት' የቀድሞ ስሙ ሪቻርድ ቱሙሻቤ እንደነበር ተዘግቧል። እውነታው የተረጋጋጠው 'ባለቤታቸው' ቱሙሻቤ፤ አዲስ ትዳር በመሰረተችበት ቤት አካባቢ ከሚኖሩ ጎረቤቶቿ የቴሌቪዥን ማስቀመጫና ልብሶችን በመስረቅ ተጠርጥራ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ከዋለች በኋላ ነበር። "በተለመደው የፖሊስ ሥራ መሠረት፤ ሴት ፖሊስ እርሷን ወደ እስር ቤት ክፍል ከማስገባቷ በፊት ፍተሻ አድርጋ ነበር፤ ከዚያ ግን የሆነው ፖሊሷንም ድንጋጤ ውስጥ የከተተ ነበር፤ ተጠርጣሪው ጡት እንዲመስል በጡት መያዣ ጨርቆችን በመጠቅጠቅ ለብሶ ተገኝቷል" ሲል ጋዜጣው አትቷል። ከአገሪቷ ዋና መዲና ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ክያምፒሲ በተባለች መንደር በሚገኝ መስጊድ ኢማም የሆኑት ሼህ ሙቱምባ፤ በነበሩት ጊዜያት 'ከሙሽራቸው' ጋር ወሲባዊ ግንኙነት አልነበራቸውም። እንዴት ከሙሽራቸው ጋር ወሲባዊ ግንኙነት አልፈፀሙም ይሉ ይሆናል። ምክንያቱ ወዲህ ነው "ሙሽሪት የወር አበባ ላይ ነኝ" በማለቷ ነበር ግንኙነት ሳያደርጉ የቆዩት። ጋዜጣው እንዳስነበበው 'ግለሰቡ' ያለፆታው ሴት ለመምሰል በመሞከር፣ በስርቆት እና በማስመሰል የተለያዩ ቁሳቁሶችን በመቀበል ክስ ተመስርቶበታል። የአካባቢው ካዲ [የእስልምና ዳኛ] ሼህ አብዱል ኑር ካካንዴ በበኩላቸው አጋጣሚው ያልተጠበቀ ሲሆን በኢማሙ ላይ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን ገልፀዋል። ጋዜጣው ሼህ ሙቱምባ በሚያስተምሩበት መስጊድ ዋና ኢማም የሆኑትን ሼህ ኢሳ ቡሱልዋን ጠቅሶ እንደዘገበው የእስልምና ኃይማኖትን ለመጠበቅ ሲባል ኢማሙ ከኃላፊነታቸው ታግደዋል። አክሎም ሼህ ሙቱምባ ላለፉት አራት ቀናት ቤታቸው አልነበሩም ብሏል- ጋዜጣው። "በተፈጠረው ስሜታቸው በጣም ተጎድቷል፤ በመሆኑም የምክር አገልግሎት ያስፈልጋቸዋል" ሲሉ አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ግለሰብም ተናግረዋል።
44220837
https://www.bbc.com/amharic/44220837
"ትጥቅ ትግል ወደ ዴሞክራሲ አያመራም" አቶ ሌንጮ ለታ
የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር አምስት አባላትን የያዘ ልኡካን ቡድን ወደ አዲስ አበባ ዛሬ ገብቷል።
የቀድሞ የኦነግ አመራርና የኦዴግ ሊቀ-መንበር አቶ ሌንጮ ለታ ከመንግሥት ጋር ለመወያየት ሙከራ ሲያደርጉ ስድስት ዓመታት እንደፈጀባቸው ተናግረው አሁን ያለውን ለውጥ ተከትሎ ጥሪ ሲደረግላቸው መምጣታቸውን በቦሌ አየር ማረፊያ በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል። ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር አብሮ ለመስራት መወሰናቸውንም ተከትሎ መንግሥት አሸባሪ ብሎ ከፈረጀው ከግንቦት 7 ጋር ያላቸው ስምምነት የወደፊት ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን ተብሎ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ኦዴግ በሰላማዊ መንገድ የሚታገል ፖርቲ መሆኑን አፅንኦት በመስጠት የተናገሩ ሲሆን ታጣቂ ኃይሎች ጋር ግንኙነት እንዳላቸውም ተናግረዋል። "እኛ በሰላማዊ መንገድ የምንንቀሳቀስ ኃይል ነን። አንዳንድ ስለ ትጥቅ ትግል ከሚያወሩ ኃይሎች ጋር ግንኙነት አለን። ይህ ደግሞ ለአገር እንዲበጅ ለማለት ነው። እንደ ድልድይ እናገለግል ይሆን ወይ ብለን በማሰብ ነው እንጂ ትጥቅ ትግልን ለማበረታታት አይደለም" ብለዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ መጥቷል ብለው የሚያምኑት አቶ ሌንጮ የትጥቅ ትግል አስገዳጅ የሆነበት ሁኔታ እንደሌለ ጠቀሰዋል። "ትጥቅ ትግል ወደ ዴሞክራሲ አያመራም፤ በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎች አገራት ታሪክ ዴሞክራሲን አመንጭቶ አያውቅም" ያሉት አቶ ሌንጮ እርሳቸውም ትጥቅ ትግል ውስጥ እንደነበሩና ምንም ዓይነት ለውጥ እንዳልመጣ ገልፀዋል። "ዴሞክራሲን እፈልጋለሁ የሚል ማንኛውም ኃይል በሰላማዊ መንገድ መታገሉን ቢቀበል ይሻላል፤ ሁኔታው አስገድዶኝ ነው ሊል ይችላል፤ ሁኔታው እየተቀየረና እየተሻሻለ ከመምጣቱ አንፃር ትጥቅ ትግል አስፈላጊ እንዳልሆነ መረዳት አለባቸው።" ብለዋል። ፓርቲውም ሆነ መስራቾቹ ለዓመታት መቀመጫቸውን በውጭ አገራት ከማድረጋቸው አንፃር የወደፊቱን የፖለቲካ አቅጣጫ ለመቀየስ እንዲሁም ተሳትፏቸው ምን መልክ እንደሚኖረው ለማወቅ ጥናት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። "አገሪቱ በኢኮኖሚም፣ በፖለቲካው ሆነ በማህበረሰቡ በአፋጣኝ ሁኔታ እየተቀየረች ነው። ካጠናን በኋላ ነው ወደ ስራ ዕቅድ ማውጣት የምንሸጋገረው" ብለዋል። ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ ከመንግሥት ጋር የደረሱባቸው የድርድር ነጥቦች ይኖሩ ይሆን ወይ ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄም ያደረጉት ድርድር አመጣጣቸው ብቻ ላይ እንዳተኮረ ገልፀዋል። ወደ አገሪቷም ለመመለስ መፈታት የነበረባቸው ችግሮች እንደነበሩም ጨምረው ተናግረዋል። " ሰፋፊና አነታራኪ የፖለቲካ ጉዳዮች አልተነሱም፤ እነሱን እዚህ አንስተን እንወያይባቸዋለን " ብለዋል ከመንግሥት ጋር ጠለቅ ያለ የፖለቲካ ውይይት ለማካሄድ እንደሚያስቡ የተናገሩት አቶ ሌንጮ የፖለቲካ አቅጣጫቸውንም ለመቀየስ ያለውንም ለውጥ ደካማና ጠንካራ ጎኑን መፈተሽ ከቀዳሚ ስራዎቻቸው መካከል እንደሆነ ተናግረዋል። "ያለውን ለውጥ ደካማና ጠንካራ ጎን ከፈተሽን በኋላ እንዲሁም ከመንግሥት ጋር ውይይት ካደረግን በኋላ እኛ አስተዋፅኦ የምናደርገው በምን መልክ ነው የሚለው ላይ እንወስናለን" ብለዋል። ከመጡ በኋላስ አቀባበል ይጠብቁ እንደሆነ ለተጠየቁት ጥያቄ "እኛ ከሀገር ከወጣን አንድ ትውልድ ተወልዷል። አያውቀንም አቀባበል እንጠብቃለን ብየ አላስብም" ብለዋል። የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባርን (ኦነግ) ጨምሮ ግንቦት ሰባት፤ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር እና ሌሎች ፓርቲዎች በኢፌዴሪ መንግስት አሸባሪ ተብለው መፈረጃቸው የሚታወስ ነው። የግንባሩ ፕሬዚዳንት አቶ ሌንጮ ለታ እና አንዳንድ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር የአመራር አባላት የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር አባላት እንደነበሩ ይታወሳል።
news-51338564
https://www.bbc.com/amharic/news-51338564
አሜሪካ ኤርትራን ጨምሮ በስድስት አገራት ላይ የቪዛ እገዳ ጣለች
አሜሪካ ኤርትራን ጨምሮ ለስድስት አገራት ዜጎች የምትሰጠው የስደት ቪዛ ላይ እገዳ ጣለች።
እገዳው ከተጣለባቸው አገራት መካከል አራቱ ከአፍሪካ ሲሆኑ እነሱም ኤርትራ፣ ናይጄሪያ፣ ታንዛኒያና ሱዳን አሜሪካ አሜሪካ ከምትሰጣቸው የተወሰኑ የቪዛ አይነቶችን እንዳያገኙ እገዳ ጥላባቸዋለች። ከአፍሪካ ውጭ ደግሞ ኪርጊዝስታን እና ሚያንማር በእገዳው የተጠቃለሉ አገራት ናቸው። • ኤርትራ ኳታር ባለስልጣኖቼን ለመግደል ዕቅድ አላት ስትል ከሰሰች የእነዚህ አገራት ዜጎች የተወሰኑ አይነት ቪዛዎችን ለማግኘት እንደማይችሉ ቢገለጽም የቱሪስት ቪዛ ግን ለማግኘት ይችላሉ ተብሏል። በ2018 አሜሪካ አሁን እገደ ከጣለችባቸው ሌሎች አምስት ዜጎች ካገኙት ቪዛ ከሁለት ዕጥፍ በላይ የስደተኞች ቪዛዎችን ለናይጄሪያ ሰጥታለች። በዚሁ ዓመት አሜሪካ ከ8 ሺህ በላይ ቪዛ ለናይጄሪያዊያ፣ 2 ሺህ ለሱዳናዊያን፣ 290 ለታንዛኒያዊያንና 31 ደግሞ ለኤርትራዊያን ሰጥታለች። • እንቅስቃሴ አልባዋ ምጽዋ አንድ ባለስልጣን እንደተናገሩት እነዚህ አገራት እገዳው የተጣለባቸው የአሜሪካን የጸጥታ ሕግና የመረጃ መጋራት ደረጃን (ስታንዳርድ) ማሟላት ባለመቻላቸው ነው። "እነዚህ አገራት በብዙ መልኩ ጠቃሚ አገራት ናቸው፤ ነገር ግን ከእነርሱ የምንፈልገውን ዝቅተኛውን መስፈርት እንኳ ማሟላት ባለመቻላቸው እገዳው አስፈላጊ ሆኗል" በማለት ተጠባባቂ የአገር ውስጥ የደህንነት ሚንስትር ቻድ ዎልፍ አርብ ዕለት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። እሳቸው ጨምረው እንደተናገሩትም የአሜሪካ ባለስልጣናት ከአገሮቹ ጋር በመነጋገር የጸጥታ ሁኔታቸውን እንዲያሻሽሉና በሂደትም ከእገዳ ዝርዝሩ እንዲወጡ ይደረጋል ብለዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለመጀመሪያ ጊዜ የጉዞ እገዳ ያደረጉት በ2017 ነው። ያኔ በተረቀቀው መመሪያ መሰረትም ሰባት የሙስሊም አገራት የአሜሪካን ቪዛ እንዳያገኙ ክልከላ ተደርጎባቸው ይገኛሉ። አሜሪካ ከዚህ ቀደምም በ2017 ለኤርትራዊያን የተወሰኑ የቪዛ ዓይነቶችን ከልክላ ነበር። ለመሆኑ አዲሱ መመሪያ ምንድን ነው? በአዲሱ መመሪያ መሰረት ከናይጄሪያ፣ ኤርትራ፣ ኪርጊዝስታንና ሚያንማር ለሚመጡ ዜጎች ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ይዘት ያለው ቪዛ አይሰጣቸውም። ታንዛንያና ሱዳን ደግሞ የዲቪ ሎተሪ እድላቸው ይሰረዝባቸዋል። • ኤርትራ፡ "ሲአይኤ መፈንቅለ መንግሥት አሲሮብኝ ነበር" በአዲሱ መመሪያ መሰረት ለጎብኝዎች፣ የንግድ ሥራ ለሚሰሩና ሕክምና ለሚያደረጉ ሰዎች የሚሰጠው ጊዜያዊ ቪዛ ግን ከእገዳው ጋር እንደማይገናኝ ባለስልጣኑ አረጋግጠዋል። አሁን የተደረገው እገዳ እንደ ከዚህ ቀደሙ የሙስሊም አገራትን ብቻ ኢላማ ያደረገ አይመስልም። እገዳው ከተጣለባቸው አገራት መካከል ኪርጊዝስታን እና ሱዳን በአብዛኛው ሙስሊሞች ሲሆኑ ናይጄሪያና ኤርትራ ግን ሙስሊሙ ህዝባቸው ከጠቅላላ ህዝባቸው ግማሽ ብቻ የሚሸፍን ነው። የጉዞ እገዳው ምንድን ነው? ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስልጣን ላይ በወጡ በሰባተኛ ቀናቸው ነበር አወዛጋቢውን የጉዞ እገዳ የሚያትት መመሪያ የፈረሙት። እሳቤው የአሜሪካን ደህንነት ለመጠበቅ የግድ አስፈላጊ ነው በሚል ነበር። እገዳው ሰባት በአብዛኛው የእስልምና እምነት ተከታይ ባላቸው አገራት ላይ ያነጣጠረ ሲሆን ከፍርድ ቤትም ብርቱ ሙግት ገጥሞት ነበር። • የሱዳን የቀድሞ የመረጃና ደህንነት ኃላፊ አሜሪካ እንዳይገቡ ታገዱ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ባረቀቁት አወዛጋቢ መመሪያ መሰረትም የኢራን፣ ሊቢያ፣ሶማሊያ፣ ሶሪያ፣ የመን፣ ቬኒዙዌላ እና ሰሜን ኮሪያ የእገዳው ሰለባ ሆነዋል። ከእነዚህ አገራት ወደ አሜሪካ ለሚመጡ ዜጎች የቪዛ እገዳው ቢጣልም ለተማሪዎችና አለፍ ሲልም ከአሜሪካ ጋር የተለየ ቁርኝት አላቸው ለተባሉ ግለሰቡች እገዳው የተጣለባቸው አገራት ዜጎች ቢሆኑም ቪዛ የማግኘት ልዩ እድል እየተመቻቸላቸው ነው።
news-50027271
https://www.bbc.com/amharic/news-50027271
ኢሊዩድ ኪፕቾጌ ማራቶንን ከ2 ሰዓት በታች አጠናቀቀ
ኢሊዩድ ኪፕቾጌ ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች በመሮጥ የመጀመሪያው አትሌት ሆነ። ኪፕቾጌ ሩጫውን ለመጨረስ አንድ ሰዓት ከ59 ደቂቃ ከ40 ሰከንድ ፈጅቶበታል።
የ34 ዓመቱ ኬኒያዊ አትሌት 42.2 ኪሎ ሜትር ለመሮጥ የፈጀበት ሰዓት እንደ ዓለም ክብረ ወሰን እንደማይመዘገብለት የተገለጠ ሲሆን፣ ለዚህም ምክንያት ነው የተባለው የተጠቀማቸው አሯሯጮች፤ እየተፈራረቁ የሚያሯሩጡት አትሌቶች መሆናቸውና ለሁሉም ክፍት የሆነ ውድድር ባለመሆኑ ነው። ኪፕቾጌ ውጤቱን አስመልክቶ ሲናገር "ይህ የሚያሳየው ማንም ሰው ሊያሳካው እንደሚችል ነው" ብሏል። "አሁን እኔ አሳክቸዋለሁ፤ ከአሁን በኋላ ሌሎችም እንዲያሳኩት እፈልጋለሁ" ብሏል። • ኪፕቾጌን በሩጫ ይገዳደሩታል? • ከባህር ዳር - አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ ዛሬም አልተከፈተም • ነገ በአዲስ አበባ የሚደረግ ሠልፍም ሆነ ስብሰባ የለም-የአዲስ አበባ ፖሊስ ይሀ የኦሎምፒክ ሻምፒዮና የአለም አቀፉን የማራቶን ክብረወሰን በአውሮፓዊያኑ 2018 ጀርመን በርሊን ላይ በሁለት ሰዓት ከ01 ደቂቃ 39 ሰከንድ በእጁ አስገብቶ ነበር። የለንደን ማራቶንን አራት ጊዜ በማሸነፍ ስሙን የተከለው ኪፕቾጌ፤ ከድሉ በኋላ ባለቤቱ ግሬስን ተጠምጥሞ በመሳም የሀገሩን ባንዲራ ለብሶ በአሯሯጮቹ ተከብቦ ደስታውን ገልጧል። ኪፕቾጌ በሚሮጥበት ወቅት ከፊት ከፊቱ በመሆን ሰዓቱን የሚጠቁመው መኪና የነበረ ሲሆን 100 ሜትሩን 17 ደቂቃ ከ08 ሰከንድ በመሮጥ ለስኬት በቅቷል። ኪፕቾጌን 42 አሯሯጮች ያሯሯጡ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የ1500 ሜትር ሻምፒዮናው ማቲው ቹንትሮ ዊትዝ፣ የ5000 ሜትር የመዳብ ባለቤቱ ፓል ቼሊሞና ኖርዌጂያን ወንድማማቾቹ ጃኮብ፣ ፍሊፕና ሄንሪክ ይገኙበታል። እነዚህ አሯሯጮች እያረፉ ያሯሯጡት ሲሆን የ1500 እና የ5000 ዓለም ሻምፒዮና የሆነው በርናንርድ ላጋት የመጨረሻዎቹን ርቀቶች አሯሩጦታል። ኪፕቾጌም "እነዚህ በዓለም አሉ የሚባሉ ዝነኛ አትሌቶች ናቸው፤ አመሰግናለሁ" በማለት፤ አክሎም "ይህንን ሥራ ስለተቀበሉ አመሰግናለሁ። ያሳካነው በጋራ ነው" ብሏል። • "የማራቶን ሯጮቹ ላይ የተላለፈው እገዳ አይደለም" ዱቤ ጂሎ • 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና፡ የእኛ ሠው በዶሃ የኪፕቾጌ አሰልጣኝ አትሌቱ ልክ እንደ ሌላ ጊዜው የሚጠጣው ውሃ ከጠረጴዛ ላይ አንስቶ ከሚጠቀም ይልቅ በብስክሌት በመሆን ውሃና ኃይል ሰጪ ጄል ሲያቀብሉት ነበር። እንዲህ ዓይነት እገዛ ግን በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕግ መሰረት አይፈቀድም። ኪፕቾጌ የሮጠበት ሥፍራ የተመረጠው የአየር ጠባዩ ምቹ ስለሆነ መሆኑ ተነግሯል። ይህንን ሰዓት ለማሻሻል የተደረገውን ጥረት በገንዘብ የደገፉት እንግሊዛዊው ባለሀብት ሰር ጂም ራትክሊፍ በኩባንያቸው ፔትሮ ኬሚካልስ ስም ነው። ናይክም አምስት የዓለማችን ፈጣን የማራቶን ሯጮች ብቻ ያደረጉት አዲስ ሞዴል ጫማ አበርክቶለታል። የመጨረሻዎቹን ኪሎ ሜትሮች ያጠናቀቀበት ፍጥነት "አስደማሚ ነበር" ያሉት ራትክሊፍ ሲሆኑ የኪፕቾጌ አሰልጣኝ በበኩላቸው " በዚህ ሙከራችን ሁሉም ነገር እንዳሰብነው ሄዷል" ብለዋል። "ሁላችንንም ነው ያነቃቃው፤ በሕይወታችን አቅማችንን በመለጠጥ መፈተሽ እንደምንችል አሳይቶናል" ካሉም በኋላ "በስፖርቱ ዓለም ለሌሎች አትሌቶች ከሚያስቡት በተሻለ መሮጥ እንደሚችሉ ያሳየ፤ በሌላ ሕይወት መስክ ደግሞ ሌላ ከፍታ መውጣት እንደሚችል ያስተማረ ነው" በማለት ድሉን አሞካሽተውታል። "በአጠቃላይ ታሪክ ተሠርቷል፤ የማይታመን ነገር ነው" ብለዋል።
news-54975264
https://www.bbc.com/amharic/news-54975264
ኮሮናቫይረስ ፡ በቻይና የኮቪድ-19 ወረርሽኝን የዘገበችው ጋዜጠኛ እሥራት ይጠብቃታል ተባለ
በቻይናዋ ዉሃን ከተማ የተከሰከሰውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን የዘገበቸው ቻይናዊት ጋዜጠኛ አምስት ዓመት እሥር እንደሚጠብቃት አዲስ የወጣ መረጃ አመለከተ።
ዣንግ ዣን የቀድሞ ጠበቃ የሆነችው የ37 ዓመቷ ዣንግ ዣን ባለፈው ግንቦት ነው ለእሥት የበቃችው። ዣንግ 'ጠብ በመቀስቀስና በማነሳሳት' ወንጀል ነው የተከሰሰችው። ይህ ክስ ብዙ ጊዜ የመብት ተሟጋቾች ላይ ሲመዘዝ ይታያል። ዣንግ ወደ ዉሃን ከተማ በማቅናት ስለ ቫይረሱ የዘገበች ብቸኛዋ ቻይናዊት ጋዜጠኛ አይደለችም። ነገር ግን ከባለፈው የካቲት ጀምሮ ቢያንስ ሦስት ጋዜጠኞች ጠፍተዋል። ሊ ዜሁዋ የተባለ ጋዜጠኛ ሚያዚያ ላይ 'ራሴን አግልዬ ነበር' በማለት ከጠፋበት ብቅ ብሏል። ቼን ክዊሺ የተባለው ጋዜጠኛ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር እንዳለ ሲታወቅ የሦስተኛው ጋዜጠኛ ፋንግ ቢን የት አንዳለ አድራሻው አይታወቅም። የቻይና ባለሥልጣናት የመብት ተሟጋች ነን የሚሉ ሰዎች ላይ ጫና በማሳደር ይታወቃሉ። በጋዜጠኛዋ ላይ የቀረበውን ክስ የሚያሳየው አንድ መዝገብ እንደሚያመለክተው፤ ዣንግ የካቲት ላይ ስለቫይረሱ ለመዘገብ ወደ ዉሃን እንዳቀናች ይተቅሳል። የቻይና ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ጋዜጠኛዋ በወቅቱ በመንግሥት ታግተው ስለነበሩ ጋዜጠኞችም ጭምር ዘግባ ነበር ይላል። ነገር ግን ባለፈው ዓመት ግንቦት አጋማሽ ላይ ውሃን ውስጥ ሳለች አድራሻዋ ጠፋ። በነጋታው ግን 640 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሻንግሃይ ባለሥልጣናት ቁጥጥር ሥር እንዳለች ታውቋል ይላል ቡድኑ። ጋዜጠኛዋ ክስ የተመሠረተባት ሰኔ ላይ ነው። ከክሱ መመሥረት 3 ወራት በኋላ መስከረም ላይ ጠበቃዋ እንዲያገኛት ፈቃድ ተሰጠው። የመብት ተሟጋች ቡድኑ ጋዜጠኛዋ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር መሆኗን በመቃወም የረሃብ አድማ መትታ እንደነበር አሳውቋል። ባፈለው አርብ ጠበቃዋ፤ ደንበኛው በይፋ እንደተከሰሰች የሚጠቁም ስልክ እንደተደወለለት ታውቋል። የክስ መዝገቧ እንደሚያሳየው ጋዜጠኛዋ ሐሰተኛ መረጃ 'በፅሁፍ፣ በተንቀሳቃሽ ምስልና በሌሎች መንገዶችና ማኅበራዊ ድር አምባዎች አስተላልፋለች' ይላል። አልፎም ከውጭ አገራት መገናኛ ብዙሃን ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች ሲል የክስ መዝገቧ ያትታል። ጋዜጠኛዋ ከአራት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ እሥር ልትቀጣ እንደምትችል መዝገቡ ይናገራል። ጋዜጠኛዋ ከዚህ በፊትም ሆንግ ኮንግ ውስጥ ያሉ የመብት ተሟጋቾችን በመደገፏ ምክንያት ቃሏን ለመርማሪዎች እንድትሰጥ ተደርጋ ነበር።
54546131
https://www.bbc.com/amharic/54546131
ለንደን ማራቶን፡ አትሌት ሹራ ቂጣታ ከኬንያዊው ኪፕቾጌ የማራቶን ድል እንዲነጥቅ የረዳው ምንድን ነው?
ኤሉድ ኪፕቾጌን ለማሸነፍ እንዴት ያለ ወኔ ይበቃ ይሆን? ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች የሮጠውን ብርቱ አትሌት ለማሸነፍ ምን ሲደረግ ይቻላል?
ጥብቅ ልምምድ ወይስ ተሰጥኦ? ለለንደን ማራቶን አሸናፊው ሹራ ቂጣታ ግን ጥሩ ቁርስ በቂ ነው። ባለፈው ዓመት በዩኬ ዋና ከተማ አራተኛ በመሆን ነው ያጠናቀቀው። ያኔ ኬኒያዊው ኪፕቾጌ ነው ያሸነፈው። በወቅቱ ሹራ በትዊተር ሰሌዳው ላይ ባዶ ሆዱን መሮጡን፣ ለቁርስ ፍራፍሬ ብቻ መመገቡን ገልጾ ነበር። ሹራ በወቅቱ 35 ኪሎ ሜትሮች ከሮጠ በኋላ የተሰማውን ሲያሰፍር "ሆዴ ከጀርባዬ ጋር የተጣበቀ መስሎኝ ነበር፤ ሞርሙሮኝ ነበር" ብሏል። በዚህ ዓመት ከስህተቱ የተማረው ሹራ ውድድሩ ከመጀመሩ በፊት ጥሩ ምግብ ወሳስዷል። ለቢቢሲ ስፖርት አፍሪካ " ሁሉንም ነገር ተመግቤያለሁ" ብሏል። "ሾርባ፣ ዳቦ፣ እንቁላል እና እርጎ ወስጃለሁ፤ አቅም የሚሆነኝንና ውድድሩን በጥሩ ጉልበት መፎካከር የሚያስችለኝን ሁሉ ወስጃለሁ።" ውድድሩ ደግሞ ከ2014 ጀምሮ በማራቶኑ መስክ አልበገር ያለውን ኬንያዊ ማንበርከክን ያካተተ ነበር። ኪፕቾጌ የዋዛ አትሌት አይደለም። በኦሎምፒክ መንደር ስሙ በደማቅ ተጽፏል። የዓለም ክብረ ወሰን በእጁ ነው። የ35 ዓመቱ ኪፕቾጌ በለንደን ለአምስተኛ ጊዜ ድልን ለመቀዳጀት ጉልበቱን አበርትቶ ሞራሉን አደርጅቶ ነው የተገኘው። የዓለም መገናኛ ብዙኃንም ስሙን ደጋግመው ያነሳሉ። ምስሉን ደጋግመው ያሳያሉ። ጋዜጦች የፊት ገጻቸው ላይ አትመውታል። ለንደን ለኪፕቾጌ፣ ኪፕቾጌም ለለንደን መሃላ ያላቸው ይመስላል። ኪፕቾጌና ለንደን ግን ያላቸው ቃል ኪዳን ፈረሰ። መፍረስ ብቻ ሳይሆን ስምንተኛ ወጣ። ከፊት የፈለጉት ከኋላ አገኙት። በኋላም ጆሮውን አሞት እንደነበር አስረዳ። ለረዥም ርቀት ሩጫ እርጥበታማ አየርና ቅዝቃዜ ምቹ አይደለም። ሹራ የገባበት ሰዓትም፣ ሁለት ሰዓት ከአምስት ደቂቃ ከ41 ሰከንድ የሚያሳየው ይህንኑ ነው። ሹራ ግን እንደውም አየሩ ረድቶኛል ሲል ያምናል። እኤአ ከ2013 ወዲህ የለንደን ማራቶንን ሲያሸንፍ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የሆነው ሹራ "ሲዘንብ በጣም ደስ አለኝ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ በከባድ ዝናብ ውስጥ ነው ልምምድ ስሰራ የነበረው" ይላል። "አንድ ቀን ሶደሬ ለልምምድ ሄድኩኝ፣ ከባድ ዝናብ እየዘነበ ከተማው በጎርፍ ተጥለቅልቋል። አሰልጣኜ እኔን ለማዳን መምጣት ሁሉ ነበረበት" ሲል የነበረውን የልምምድ ሁኔታም ያስታውሳል። "የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሲከሰት፣ ቤት አልተቀመጥኩም። ለአምስት ወራት ያህል ከአሰልጣኜ ጋር ልምምድ ስሰራ ነበር። ይህን ድል ኪፕቾጌን ማሸነፌ ልዩ አያደርገውም፤ ጠንክሬ መስራቴ ነው ልዩ የሚያደርገው።" ቀነኒሳ በቀለ ባጋጠመው ጉዳት የተነሳ ከውድድሩ መውጣቱን ካሳወቀ በኋላ በኪፕቾጌና በቀነኒሳ መካከል ይኖራል ተብሎ የታሰበው ፍልሚያ ሳይሳካ ቀረ። ስለዚህ ማንም የቀነኒሳን አገር ልጅ፣ ሹራን ከኪፕቾጌ ጋር አነጻጽሮ ለማወዳደርና የዜና ፍጆታ ለማድረግ ፍላጎት አላሳየም። ሹራም ቢሆን "ሁሉም ትኩረቱ የነበረው ኪፕቾጌ እና ቀነኒሳ ላይ ነበር፤ እኔን ዞርም ብሎ ያየኝ አልነበረም" ሲል ይገልጻል። "ለራሴ ለዓለም ሌላ ሻምፒዮን መኖሩን አሳያለሁ ብዬ ነገርኩት፤ እናም ይህ ስሜት ነው እስከመጨረሻው ድረስ በራስ መተማመንና በሙሉ አቅም እንድቀጥል የረዳኝ።" ሹራ በበርካታ የስፖርቱ አድናቂዎች ዘንድ የሚታወቅ ስም አይደለም። ነገር ግን በለንደን ሁለት ጊዜ ሁለተኛ ሆኖ አጠናቅቋል፣ በ2018 ደግሞ በኒውዮርክ ሁለት ሰዓት ከአራት ደቂቃ ከ49 ሰከንድ በመግባት የራሱን ምርጥ ሰዓት አስመዝግቧል። በዙሪያው ያሉ አትሌቶች የ24 ዓመቱን ሹራ ዝምተኛ ግን በራስ መተማመን ያለው ሲሉ ይገልፁታል። የሹራ ወኪል ሁሴን ማኬ ለቢቢሲ ስፖርት አፍሪካ፤ " በጣም መልካም፣ የሚፈልገውን የሚያውቅ፣ ቤተሰቡን የሚያስቀድም ሰው ነው። እናም የእርሱ ምርጥ ነገሩ በራስ መተማመኑ ነው" ሲል ምስክርነቱን ሰጥቷል። "በለንደን በራሱ በብርቱ ተማምኖ ነበር፤ እናም ወደ ውድድር ሲገባ ውድድሩ ውስጥ ስላሉት አትሌቶች ግድ አልሰጠውም፤ ያም አሁን ላገኘው ሻምፒዮናነት ረድቶታል። ተስፋ አደርጋለሁ በዚሁ ይቀጥላል።" ሹራ አትሌቲክስን የተዋወቀው በትምህርት ቤት ውስጥ ነው። ኋላም እኤአ ከ2015 ጀምሮ አሰልጣኝ ሃጂ አዲሎ በአዲስ አበባ እያሰለጠኑት ይገኛሉ። "በጣም ደፋር አትሌት ነው፤ እናም ሁልጊዜ አቅሙን እስከቻለ ድረስ ይጠቀማል" ይላሉ አሰልጣኙ። አሰልጣኝ ሃጂ ወደ እንግሊዝ ለመሄድ ቀናት ሲቀራቸው የኮሮናቫይረስ እንዳለባቸው በምርመራ በመረጋገጡ ድሉን በአካል ተገኝተው ለማጣጣም አልታደሉም። ቢቢሲ ሹራን እንዴት ማሰልጠን እንደጀመሩ ሲጠይቃቸው "ሹራ ከመጣበት አካባቢ የሆነ ሰው ከኔ ጋር አብሮ ይሮጥ ነበር። እናም እኔ ወዳለሁበት ካምፕ አምጥቶት እስቲ እየው አለኝ። ሞከርነው፤ ጥሩ ነበር ግን ፅናቱንና ፍጥነቱን ማሻሻል ነበረበት" በማለት ሁኔታውን ያስታውሳሉ። "በሶስት ወር ውስጥ፣ በጣም በርካታ ነገር አሻሻለ፤ እናም የመጀመሪያውን ማራቶን እንዲካፈል ወደ ሻንጋይ ላክነው።" ሹራ የተገኘው ሰባት ልጆች ካሏቸው ገበሬ ቤተሰቦች ነው። "ትምህርት በጣም እወድ ነበር፤ ዶክተር አልያም ፓይለት ነበር መሆን የምፈልገው። ነገር ግን ከድሃ ቤተሰብ ስለሆነ የተገኘሁት ቤተሰቦቼን ለመርዳት ትምህርቴን ማቋረጥ ነበረብኝ" በማለት ልጅነቱን ያስታውሳል። "አንድ ቀን ዝነኛ እሆናለሁ፤ አለምን እዞራለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም" በማለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ስለ እርሱ እና ስለድሉ በትዊተር ሰሌዳቸው ለመጀመሪያ ጊዜ መጻፋቸውን በመግለጽ፤ "አስቤ የማላውቀውን ህይወት ነው እየኖርኩ ያለሁት" ይላል። የሁለት ልጆች አባት የሆነው ሹራ ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ በወንዶች ማራቶን ለሁለት አስርታት ያጣችውን ድል መመለስ ይፈልጋል። "ለአገሬ እና ለልጆቼ ጥሩ ትዝታ እንዲሆን የወርቅ ሜዳሊያ ማምጣት እፈልጋለሁ። ከዚያም 'አባታችን የኦሎምፒክ ሜዳሊያ አሸናፊ ነው' ይላሉ።"
news-56648759
https://www.bbc.com/amharic/news-56648759
ሱዳን የኢትዮጵያ ጦር ከአብዬ ግዛት እንዲወጣ የተባበሩት መንግሥታትን ጠየቀች
በአወዛጋቢው የአብዬ ግዛት ውስጥ በሠላም አስከባሪነት የተሰማራው የኢትዮጵያ ሠራዊት በሌላ አገር ጦር እንዲተካ ሱዳን የተባበሩት መንግሥታትን መጠየቋ ተነገረ።
የሱዳን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት "የኢትዮጵያ ሠራዊት በምሥራቃዊ የሱዳን ድንበር አካባቢ እየተጠናከረ ባለበት ጊዜ ስትራተጂክ በሆነው የሱዳን ማዕከላዊ ስፍራ ላይ የኢትዮጵያ ኃይሎች እንዲኖሩ መፍቀድ ምክንያታዊ አይሆንም" ማለቱን ዜና ወኪሉ ዘግቧል። የሱዳን ዜና ወኪል የአገሪቱን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪያም አል ሳዲቅ አል መሐዲ ይህንን ተናግረውታል ያለው በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ሲደረግ የነበረው ድርድር ውጤት ሳያመጣ ከተጠናቀቀ በኋላ ከአንድ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው። ሱዳንና ኢትዮጵያን ለዓመታት በይገባኛል ጥያቄ ሲያወዛግብ የነበረውን የድንበር አካባቢ ከአምስት ወራት በፊት ሰራዊቷን አሰማርታ በቁጥጥሯ ስር ማስገባቷን የገለጸች ሲሆን፤ ኢትዮጵያም እርምጃውን አውግዛ ችግሩ በውይይት እንዲፈታ በተደጋጋሚ ስትጠይቅ ቆይታለች። ኢትዮጵያና ሱዳን ከድንበር ውዝግቡ በተጨማሪ ግንባታው ወደ መጠናቀቁ በተቃረበው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያም ያላቸውን አለመግባባት ለመፍታት በተደጋጋሚ ሲያደርጉት የቆየው ድርድር ምንም ውጤት ሳያስገኝ ቆይቷል። ሱዳን ከግብጽ ጋር በመቆም ሁለቱ አገራት በግድቡ የውሃ አሞላልና ቀጣይ ሥራ ዙሪያ በሚደረገው ድርድር ላይ ብሔራዊ ጥቅማቸውን ለማስከበር ጥረት እያደረጉ ሲሆን፤ 85 በመቶ የወንዙን ውሃ የምታመነጨው ኢትዮጵያም ጠንካራ አቋም በመያዝ "ብሔራዊ ጥቅሟን የሚጎዳ ስምምነት ውስጥ እንደማትገባ" አሳውቃለች። በዚህም የሱዳኗ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኪንሻሳ ላይ በተካሄደው ውይይት ወቅት ኢትዮጵያ "ተቀባይነት የሌለው ግትርነትን" በማሳየት "ከዓለም አቀፍ ሕግ በተጻረረ ሁኔታ" የግድቡን ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ለማከናወን ወስናለች ሲሉ ወቀሳ ሰንዝረዋል። በግድቡ ድርድር ስምምነት ባለመደረሱና ከሱዳን ጋር ባለው የድንበር ጥያቄ ምክንያት "የተባበሩት መንግሥታት አብዬ ውስጥ ያሰማራውን የኢትዮጵያን ጦር በሌላ እንዲተካ ሱዳን ጥያቄ አቅርባለች" ሲሉ ሚኒስትሯ ተናግረዋል። የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ ጨምረውም ሱዳን ጨምረውም አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የግንኙነትና የትብብር ስምምነቶችን መለስ ብላ እየመረመረች መሆኑን ገልጸው፤ ነገር ግን ይህ ስደተኞችን ጨምሮ በአገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን የሚመለከት አይደለም ብለዋል። የተባበሩት መንግሥታት መረጃ እንደሚያመለክተው ከ3300 በላይ የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት በድርጅቱ ዕዝ ስር በአብዬ ግዛት ውስጥ ተሰማርተው የሠላም ማስከበር ተግባር እያከናወኑ ይገኛሉ። በግዛቲቱ የመቆያ ጊዜው ባለፈው ኅዳር ወር የተጠናቀቀው የሠላም አስከባሪው ሠራዊት አሁን ያለው በተራዘመለት የስድስት ወር ጊዜ ሲሆን ይህም በመጪው ግንቦት ወር የሚያበቃ ይሆናል።
news-45715890
https://www.bbc.com/amharic/news-45715890
በኢራን በቤት ውስጥ የተመረዘ መጠጥ የጠጡ 42 ኢራናውያን ሞቱ
በኢራን የተመረዘ መጠጥ የጠጡ 41 ግለሰቦች መሞታቸውን የሐገሪቱ የመንግስት ቃል አቀባይ ተናገሩ።
የጤና ሚኒስትር ቃል አቀባይ የሆኑት ኢራጅ ሐሪርቺ እንዳሉት 16 ሰዎች የአይን ብርሃናቸውን ሲያጡ 170 ሰዎች ደግሞ ይህንን የተመረዘ መጠጥ ከጠጡ በኋላ ወደ ኩላሊት እጥበት ሄደዋል። ባለፉት ሶስት ሳምንታት በአምስት አውራጃዎች የሚኖሩ 460 ሰዎች ወደ ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን ከነዚህም መካከል የ19 ዓመት ሴት ትገኝበታለች። • ያልተጠበቁ ስሞች በአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ምርጫ • በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት • ኢትዮጵያ 8.5 በመቶ ዕድገት ታሥመዘግባለች፡ አይ.ኤም.ኤፍ. በኢራን የአልኮሆል መጠጦች ሕገወጥ ቢሆኑም በቤት ውስጥ ኢታኖል ተጨምሮበት የሚዘጋጅ መጠጥ ግን ተስፋፍቶ ይገኛል። ይህ ኢታኖል ተደባልቆበት በቤት ውስጥ የሚዘጋጅ መጠጥ አደገኛ ሜታኖል ተቀላቅሎበትም ይዘጋጃል። ፖሊስ በደቡባዊ ኢራን በምትገኘው የባንዳር አባስ ከተማ በቤት ውስጥ ይህንን መጠጥ የሚያዘጋጁ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሎ ነበር። ይሁን እንጂ አሜሪካ በኢራን ላይ ማዕቀብ ከጣለች በኋላ በተፈጠረ የዶላር እጥረት ምክንያት የአልኮል መጠጦችን የሚጠቀሙ ግለሰቦች ርካሽ እና በቤት ውስጥ ወደሚዘጋጁ ፊታቸውን ሳያዞሩ እንዳልቀሩ ይገመታል። የኢራን ፀረ አደንዛዥ ዕፅ ባለስልጣናት በየዓመቱ 730 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ 80 ሚሊየን ሊትር አልኮሆል ወደ ኢራን በህገወጥ መልኩ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል። ኢራን ከ1979ኙ እስላማዊ አብዮት ወዲህ አልኮሆልን የከለከለች ቢሆንም ሙስሊም ያልሆኑ የሀገሪቱ ዜጎች ለተለያየ ተግባር በቤታቸው አልኮሆል ማዘጋጀት እንዲችሉ ተፈቅዷል።
news-55391881
https://www.bbc.com/amharic/news-55391881
ኮሮናቫይረስ፡ በርካታ የአውሮፓ አገራት በታላቋ ብሪታኒያ ላይ የጉዞ እቀባ እያደረጉ ነው
በርካታ የአውሮፓ አገራት በታላቋ ብሪታኒያ ላይ የጉዞ እቀባ እያደረጉ ነው። ምክንያቱ ደግሞ በዚያች አገር አዲስ ዓይነት የኮቪድ ዝርያ መገኘቱ ነው።
አዲሱ ዝርያ ገና በስፋት ያልተጠና ቢሆንም ከቁጥጥር ውጭ በሆነ መንገድ ከሰው ወደ ሰው ይዛመታል የሚለው ፍርሃት በርካታ አገራትን ድንጋጤ ውስጥ ከቷቸዋል። እስከ አሁን ባለው ብቻ ጀርመን፣ አየርላንድ፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያንና ኔዘርላንድስ እንዲሁም ቤልጂየም ሁሉም ወደ ታላቋ ብሪታኒያ የአየር በረራን አቋርጠዋል። ዛሬ ሰኞ የአውሮፓ ኅብረት መሪዎች ስብሰባ ስለሚቀመጡ ከዚህ የባሰ የእቀባ ውሳኔ ሊኖር እንደሚችል እየተጠበቀ ነው። አዲሱ ኮቪድ-19 ዝርያ በለንደንና በደቡብ ምሥራቅ ኢንግላንድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ነው በስፋት የተሰራጨው። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ቅዳሜ በሰጡት አስቸኳይ ትእዛዝ ደረጃ 4 የጥንቃቄ ደንቦች እንዲከበሩ አዘዋል። ለፈረንጆች ገናና አዲስ ዓመት የእንቅስቃሴ ገደቦች ይላላሉ ተብሎ ታስቦ የነበረውን ሐሳብ ሰርዘዋል። የጤና ባለሙያዎች አዲሱ የተህዋሲው ዝርያ ይበልጥ ገዳይ ስለመሆኑም ሆነ ለክትባት እጅ የማይሰጥ ስለመሆኑ ገና እርግጠኛ አልሆኑም። ሆኖም ግን ከለመድነው የኮሮናቫይረስ በ70 በመቶ በይበልጥ የመሰራጨት አቅም አለው መባሉ ማን ይተርፋል እንዲባል አድርጓል። የታላቋ ብሪታኒያ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ይህ አዲስ ዝርያ ቫይረስ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖብናል፤ በቁጥጥራችን ልናውለው ይገባል ብለዋል። ታላቋ ብሪታኒያ አዲሱን የቫይረስ ዝርያ ይፋ ባደረገች በሰዓታት ውስጥ ኔዘርላንድ ማንኛውም በረራ ከታላቋ ብሪታኒያ እንዳይመጣብኝ ብላለች። ፈረንሳይ በተመሳሳይ ከባድ መኪና ተሽከርካሪ፣ መርከብ፣ ጀልባዎች፣ እግረኛና በበራዎችን ከእንግሊዝ በኩል ወደ አገሯ እንዳይገቡብኝ ብላለች። አየርላንድና ጀርመንም ተመሳሳይ ውሳኔን አሳልፈዋል። ጣሊያን እስከ ጃንዋሪ 6 ማንም ከታላቋ ብሪታኒያ አይምጣብኝ ብላለች። በአዲሱ የቫይረስ ዝርያ የተጠቃ አንድ ሰው በጣሊያን መገኘቱም ድንጋጤን ፈጥሯል። ቱርክ፣ ቡልጋሪያና ኦስትሪያም ከታላቋ ብሪታኒያ ጉዞ እቀባ አድርገዋል። የዓለም ጤና ድርጅት አዲሱን የኮሮናቫይረስ ዝርያ በተመለከተ ከዩናይትድ ኪንግደም ባለሥልጣናት ጋር በቅርበት እየተነጋገረ እንደሆነ በትዊተር ገጹ አስታውቋል። ድርጅቱ እንዳለው ዩናይትድ ኪንግደም አዲሱን የቫይረስ ዝርያ በተመለከተ እየተካሄዱ ስላሉ ጥናቶች መረጃዎችን ስታጋራ እንደነበር ጠቅሶ፤ ድርጅቱ ስለአዲሱ ቫይረስ ባሕርይ እና አደጋው የደረሰበትን ለአባል አገራቱ እና ለሕዝብ እንደሚያሳውቅ ገልጿል። ምንም እንኳን የተረጋገጠ ነገር ባይኖርም፤ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን አዲሱ የቫይረስ ዝርያ ከቀድሞው እስከ 70 በመቶ ያህል የመዛመት እድሉ ከፍተኛ ነው ብለዋል። ይሁን እንጂ ባለሥልጣናት አዲሱ የቫይረስ ዝርያ ከፍተኛ ሞት ስለማስከተሉ አሊያም እስካሁን በተዘጋጁት የኮሮናቫይረስ ክትባቶች እና ሕክምናዎች ሊበገር ስለመቻሉ የሚያሳይ መረጃ እንደሌለ ተናግረዋል። ዩናይትድ ኪንግደም እና አሜሪካ ፋይዘርና በባዮንቴክ የበለጸገውን የኮሮናቫይረስ ክትባት ለዜጎቻቸው መስጠት መጀመራቸው ይታወሳል። 95 በመቶ ኮሮናቫይረስን ይከላከላል የተባለለት ይህንን ክትባት ለዜጎች በመስጠት ዩናይትድ ኪንግደም ቀዳሚዋ አገር ሆና ነበር።
news-57298241
https://www.bbc.com/amharic/news-57298241
ቤላሩስ አውሮፕላን አስገድዳ በማሳረፍ የያዘችው ጋዜጠኛ ማን ነው?
ከሰሞኑ የአውሮፓ ህብረት የቤላሩስ አየር መንገድ በአውሮፓ ሰማይ ላይ እንዳይበር ማዕቀብ ጥሏል።
ሮማን ፕሮታሴቪች የ27 አባላቱ ህብረት ለዚህ መነሻ የሆነው ቤላሩስ ጋዜጠኛውን ሮማን ፕሮታሴቪችን ለመያዝ በሚል የተሳፈረበትን አውሮፕላን አቅጣጫ ቀይሮ በመዲናው ሚኒስክ ተገዶ እንዲያርፍ መደረጉን ተከትሎ ነው። የመንግሥት ጠለፋ የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ድርጊት የቤላሩስ መንግሥት የጦር አውሮፕላን በመላክም ነው አውሮፕላኑ ተገዶ እንዲያርፍ ያደረገው። ለመሆኑ መንግሥት የጦር አውሮፕላኑን ልኮ ያሳረፈው ጋዜጠኛ ማን ነው? የ26 አመቱ ሮማን ፕሮታሴቪች በአሁኑ ወቅት በሚኒስክ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ነው ያለው። ሮማን እስከ ህዳር ወር ድረስ እንደሱ ተቃዋሚ በሆነው ስቴፓን ፑቲሎ በተመሰረተውና በቴሌግራም በሚሰራጨው የተቃዋሚው ኔክስታ ቻናል አዘጋጅ ነበር። ኔክስታና ኔክስታ ላይቭ የተባሉት ሚዲያዎች የጎዳና ላይ ተቃውሞዎችን በማዘጋጀት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክተዋል። ከፍተኛ ቁጥጥርና ክትትል ከመንግሥት ቢደረግባቸውም ሁለት ሚሊዮን ተከታይ አላቸው። ሮማን በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ክሶች ይጠብቁታል ተብሏል። እሱና ስቴፓን በቤላሩስ መንግሥት በሽብር ድርጊቶች የተሳተፉ በሚል የስም ዝርዝራቸው ባለፈው አመት ወጥቶ ነበር። በአገሪቱ ውስጥ ህዝባዊ አለመረጋጋት ማነሳሳት እስከ አስራ አምስት አመት ድረስ እስር ያስቀጣል። ሬናናይር በተባለው የአውሮፕላን መንገድ ተሳፍሮ እየበረረ እያለ አውሮፕላኑ አቅጣጫውን ወደ ሚኒስክ ሲያደርግ ሮማን ተደናገጠ ትላለች ሞኒካ ሲምኪየኔ የተባለችና አብራ ተሳፍራ የነበረች መንገደኛ። "ወደ መንገደኞቹም ዞሮ የሞት ቅጣት ይጠብቀኛል ብሎ ተናገረ" ብላለች ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪል። የ23 አመቷ የሮማን የሴት ጓደኛ ሶፊያ ሳፔጋም አውሮፕላኑ በሚኒስክ እንዲያርፍ ከተገደደ በኋላ በቁጥጥር ስር ውላለች። ዜግነቷ ሩሲያዊ ሲሆን በሉውቴንያ በሚገኘው የአውሮፓ ሂውማኒቲስ ዩኑቨርስቲ የህግ ተማሪ ናት። ትንሽ ሰራተኛ ያለው ኔክስታ የተመሰረተው በፖላንድ ሲሆን በጎረቤት አገር ሉውቴንያ ካሉ የቤላሩስ ተቃዋሚዎችም ጋር በቅርበት ይሰራል። የቤላሩስ ተቃዋሚ መሪ ሲቬትላና ቲካኖቭስካያ የሚኖሩት በሉውቴንያ ነው። ሉውቴንያ የኔቶ እንዲሁም አውሮፓ ህብረት አባል አገር ናት። በባለፈው አመት የተነሱ ከፍተኛ ተቃውሞዎችን ተከትሎ በቤላሩስ ነፃ ሚዲያና የተቃውሞ ድረገፆች ተዘግተዋል። በዚህ ሁኔታ ደግሞ ለቤላሩስ አማራጭ መቃወሚያ መንገድ እንዲሁም ዜናዎችን ማስተላለፊያ መንገድ የሆነው ቴሌግራም ነው። ኔክስታ ላይቭ ወይም ኔክታ ተብሎ የሚጠራው ሚዲያ በቤላሩስ ቋንቋ "አንድ ሰው" የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን በኔክስታ ቻናሎች ውስጥ በርካታ ተከታዮች አሉት። ኔክስታ ላይቭ ከሚያወጧቸው ፖስቶች መካከል የፖሊስ ጭካኔን የሚያሳዩ ፎቶዎችና ቪዲዮዎች እንዲሁም የተቃውሞ ሰልፎችና ስራ ማቆም አድማዎችን በተመለከተ መረጃ ያስተላልፋል። አምና ነሐሴ ወር በተደረገው ምርጫ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ አሸንፌያለሁ ማለታቸውን ተከትሎ ምርጫው ተጭበርብሯል በሚል ቤላሩስ በተቃውሞ እየተናጠች ነበር። ጨቋኝ ናቸው የሚባሉት ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ለባለፉት 27 አመታት ቤላሩስን አስተዳድረዋል። የአገሪቱ መሰረተ ልማቶችም በመንግሥት ቁጥጥር ስር ያሉ ሲሆን ከፍተኛ የሆነ ክትትል እንዲሁም ጥሰቶች እንደሚፈፀምም ይነገራል። ሮማን እንዳለው የኔክስታ ፕሮጀክት ከውጭ አገራት ድጋፍ የለውም ገንዘቡን የሚያገኘው ከማስታወቂያዎች ገቢ ነው። መስራቹ ስቴፓን ፑቲሎ ይህንን ሚዲያ ያቋቋመው በአውሮፓውያኑ 2015 በዩቲዩብ ቻናልነት ነበር። በኋላም ነው ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው መረጃዎችን ወደማስተላለፍ የተሸጋገረው። በአሁኑ ወቅት በእስር ላይ ያለው ሮማን ቤላሞቫ ለሚባል የቴሌግራም ቻናል ይሰራል። የቤላሞቫ ጦማሪ ኢጎር ሎሲክ ባለፈው አመት ሰኔ ወር ላይ መታሰሩን ተከትሎ ነው ሮማን በዚህ ሚዲያ ላይ መፃፍ የጀመረው። አንዳንድ ተችዎች ኔክስታ የሚያቀርባቸው መረጃዎች ያልተረጋገጡ ናቸው ይላሉ። ለምሳሌም ያህል በአንድ ወቅት የሩሲያ ልዩ ኃይል ቤላሩስ መግባታቸውን የሚያሳይ መረጃ ፅፎ የነበረ ሲሆን በኋላም ስህተት ነው በሚል ከቻናሉ እንደተወገደ ቢቢሲ ሞኒተሪንግ ዘግቧል። ባለፈው አመት ነሐሴ ወር ላይ ተቃውሞው በከፍተኛ ሁኔታ በተጋጋለበት ወቅት ኔክስታ በሰዓት ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ መልዕክቶች ከቤላሩስ ዜጎች ይደርሰው እንደነበር ሮማን ለቢቢሲ በአንድ ወቅት ተናግሯል። ኔክስታ የተቃውሞ ማዕከል ወይስ ሚዲያ ነው ተብሎ ሮማን ከቢቢሲ ሩሲያ ጥያቄ በቀረበለት ወቅት "ይሄንን ነን ማለት አስቸጋሪ ነው። ነገር ግን በዋነኝነት የቤላሩስ ዜጎች የሆንን በአገራችን አምባገነንነት እንዳይሰፍን የምንፈልግና በነፃነት አገራችን ተመልሰን መኖር የምንፈልግ ነን" ብሎ ነበር። ከሁለት አመት በፊት ከቤላሩስ የወጣው ሮማን በባለፈው አመትም የፖላንድ ዜግነት ለማግኘት ጥያቄ አቅርቧል። በባለፈው አመትም ቤተሰቦቹንም ወደ ፖላንድ አምጥቷል። አባቱ ዲሚትሩ በቤላሩስ የጦር አካዳሚ ውስጥ መምህርና ተጠባባቂ የጦር ኃላፊ ናቸው። ሮማን የፕሬዚዳንት አሌክሳንደርን አገዛዝ መቃወም የጀመረው በአውሮፓውያኑ 2011 ሲሆን በወቅቱም የተቃውሞ ሰልፍ ተሳትፈሃል ተብሎ ከትምህርት ቤት ተባሮ ነበር። በኋላም በቤላሩስ የመንግሥት ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት ትምህርቱን ለመከታተል ቢገባም ከዚያም ተባሯል። ሮማን ወደ ፖላንድ የሄደው ሌላኛው ተቃዋሚ ቭላድሚር ቹዴንስቶቭ መታሰሩን ተከትሎ ነው። "በቁጥጥር ስር መዋሉን የሰማሁት የመጀመሪያ ሰው እኔ ነኝ። መረጃውንም ያጋራሁት እንዲሁም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎችም ስለ እሱ እስር ተቃውሜ ተናግሬያለሁ" ብሏል።
42532607
https://www.bbc.com/amharic/42532607
ዘርፈ ብዙዋ ወጣት ጥበበኛ
ወጣት ናት። ከቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት "ወጣት የልማት ጀግና" በሚል የሜዳሊያ ሽልማት ተቀብላለች። በኪነ ጥበብ ዘርፍ፣ የዕደ ጥበብ እና የሥዕል ሥራዎች ላይ በመትጋት በዘርፉ የራሷን አስተዋጽዖ እያበረከተች ትገኛለች።
'ቃተኛ' የግጥምና የስዕሎች መድብል በታህሳስ 2007 ዓ.ም በሰሜናዊቷ ኮኮብ መቐለ ከተማ "ራሄል አርት ጋለሪ" በማለት የከፈተችው በትግራይ ብቸኛ የሆነው ጋለሪ፤ ወጣቶች ጥሩ ጊዜ የሚያሳልፉበት፣ የሚወያዩበት መድረክ በመሆን ሦስት ዓመታትን አስቆጥሯል። ከዚህ በተጨማሪ መድረኩ፤ አጫጭር ግጥሞች እና የተለያዩ የሥነ-ፅሑፍ ሥራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ወጣቶችን መጽሐፍ እስከማሳተም ደርሷል። በራሄል አርት ጋለሪ ውስጥ ያሉት ሥዕሎች እና የዕደ-ጥበብ ሥራዎችም ጥልቅ ምናባዊ መልዕክት የሚሸጋገርባቸው ናቸው። የድርጅቱን ባለቤት ጨምሮ ሌሎች በአርት ጋለሪው ሥዕሎቻቸውን የሚያስተዋውቁና ለገበያ የሚያቀርቡ ወጣቶች ሥራዎቻቸውን በጋለሪው ለእይታ ያቀርባሉ። አርት ጋለሪው ሥራ ሲጀምር፤ ከአሁን በፊት ያልተለመደ ስለነበር አትራፊ ያለመሆን፣ ሰዎች ጊዜያቸውን የሚያሳለፉበት የመዝናኛ ቦታ አድርጎ ለመውሰድ እና ሌሎች ችግሮች የነበሩ ቢሆንም፤ በአሁኑ ጊዜ ግን ይህ አመለካከት እየተለወጠ መሆኑን ራሄል ትናገራለች። በሰፊው የአትክልት ስፍራ ውስጥ በኪነ-ጥበብ ሥራዎች ያሸበረቀው የጥበብ ማዕከል ጊዜያቸውን የሚያሳልፉ ሰዎች በነፃ መጻሕፍት ያነባሉ። ነፃ የኢንተርኔት አገልግሎትን ያገኛሉ። ከዚህ ባለፈ ደግሞ የዕደ-ጥበብ ውጤቶች እና ባህላዊ ይዘት ያሏቸው ዕቃዎች በማዕከሉ ይሸጣሉ። ሳምንታዊ የሥነ-ጽሑፍ መድረክም ይዘጋጃል። ከዚህ ባሻገር ጋለሪው የጥበብ ትምህርት ቤት በመሆንም በማገልገል ይገኛል። ሕፃናት እና ወጣቶች አጫጭር የክረምት ሥልጠናዎች ያገኛሉ። "ይህ አርት ጋለሪ ለእኔ ኢንቨስትመንት ነው። በአስተሳሰብ ደረጃ ሰዎች የሚታነጹበት እና ብዙዎች የማንበብ እና የመጻፍ ችሎታቸውን የሚያሳድጉበት እየሆነ መጥቷል። ስለዚህ ጥበብ የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣት የሚደረግ ኢንቨስትመንት ነው" ትላለች ራሄል ብሉፅ። በርካታ ፈተናዎችን ያለፈችው ራሄል አሁን አርት ጋለሪው "ለጥበብ የነበረ የተሳሳተ አመለካከት ቀይሯል" ትላለች። ጋለሪዉ ምን ጠቀመ? በራሄል አርት ጋለሪ ዘወትር ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ በሚዘጋጀው የሥነ-ጽሑፍ መድረክ ላይ ሲቀርቡ የነበሩ አጫጭር ጽሑፎችና ግጥሞች የሚያነሷቸው ሃሳቦች የብዙዎች መነጋገርያ እየሆኑ እንደመጡ ከመድረኩ የማይጠፉ ታዳሚዎች ይናገራሉ። ሦስተኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን ያከበረው 'ራሄል አርት ጋለሪ' ባለፉት ዓመታት መድረኩ ላይ ሲቀርቡ ከነበሩት ግጥሞች፤ በገላጭ ሥዕሎች ታጅበዉ በአንድ መጽሐፍ ታትመዋል። በዚህ መጽሐፍም ላይ 40 ገጣሚያን እና 20 ሠዓሊያን ተሳትፈዋል። ከሠዓሊዎቹ መካከል አንዷ የሆነችው ምንያ ይህ መድረክ ሴቶችና ወጣቶች የሚሳተፉበት፣ አቅማቸውን የሚያሳድጉበት እንደሆነ ትናገራለች። "በቀጣይ የሥዕል ጥበብ በሴቶች እንዲያድግ እፈልጋለሁ። ሁላችንም በመተጋገዝ ጥበቡ እንዲያድግና ተጨማሪ አርት ጋለሪ እንዲኖረን ደግሞ እመኛለሁ" ትላለች ምንያ። በዕለተ ቅዳሜ በሚዘጋጀው የሥነ-ጽሑፍ መድረክ ላይ ባህላዊ ትዉፊቶችን በማቅረብ የሚታወቀዉ አስገዶም ተወልደ ደግሞ ጋለሪው ከተከፈተ ጀምሮ ብዙ ጸሐፊያን ሥራዎቻቸውን ማምጣት መጀመራቸውን ይገልጻል። "ማሕበራዊ ችግሮችን የሚዳስሱ የሥነ-ጽሑፍ ሥራዎች በድፍረት ይቀርቡ ነበር። ባህላዊ ትውፊቶች፣ ሥነ-ቃሎች እና ሌሎችንም በማቅረብ ሰዎች እንዲቀራረቡ አድርጓል" ይላል። ራሄል ብሉጽ ዘርፈ ብዙዋ ራሄል የልብስ ስፌትና ዲዛይን፣ ኢንጅነሪንግ፣ አርክቴክቸር እና አርባን ፕላኒንግ ራሄል በዲግሪ ፕሮግራም የተማረቻቸው መስኮች ናቸው። የስምንት ዓመት ልጅ ሆና ዲዛይን የጀመረችው ራሄል፤ እየሠራችው ላለችው ሥራ በያንግ አፍሪካ ሊደር ሺፕ ኢኒሽየቲቭ (ያሊ) በኬንያ ለሦስት ወራት ሥልጠና ወስዳለች። የአሜሪካ ኤምባሲም እውቅና የሰጣት ሲሆን የኦባማ ማንዴላ ፕሮጀክትም አባል ነች። ሴቶች እራሳቸው እንዲችሉ የሚደግፍ ፕሮጀክት ተግባራዊ በማድረግም በማሽን የማይሠሩ የሸክላ ሥራዎችን በማምረት እንዲያቀርቡላት በማድረግ የገበያ ትስስር እየፈጠረችላቸው ትገኛለች። በቀጣይም የጀመረችውን ሥራ በማሳደግ የዕደ-ጥበብ ሥራዎች እንዲሰፋፉ የሙዚቃ መድረኮች የሚዘጋጅበት፣ ሰፊ አረንጓዴ ቦታ፣ ቤተ መጻሕፍት፣ የቲያትር አዳራሽና ሌሎችንም ያሟላ ማዕከል እንዲኖር በመሥራት ትገኛለች።
news-51617819
https://www.bbc.com/amharic/news-51617819
የሌሴቶው ጠቅላይ ሚኒስትር በቀድሞ ባለቤታቸው ግድያ ያለመከሰስ መብቴ ይከበርልኝ እያሉ ነው
የሌሴቶው ጠቅላይ ሚኒስትር በቀድሞ ባለቤታቸው ግድያ ሊጠየቁ እንደማይችሉ ከሰሞኑ ጠበቆቻቸው አስረድተዋል።
ለዚህም እንደ መከራከሪያ ያነሱት ጉዳይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባላቸው ስልጣን ያለመከሰስ መብት ስላላቸው ነው። ሁኔታውም ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተመርቷል፤ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ የአሁኑ ባለቤታቸው ማሳየህ ታባኔ በግድያው ክስ ተመስርቷባቸዋል። • የሌሴቶ ቀዳማዊት እመቤት የባሏን የቀድሞ ሚስት በመግደል ተያዘች • የሌሴቶው ጠቅላይ ሚኒስትር በሚስታቸው ግድያ ተከሰሱ የቀድሞ ባለቤታቸው ሊፖሌሎ ታባኔ በሽጉጥ የተገደሉት ከሦስት ዓመታት በፊት ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፖለቲካዊ ባልሆነና ከቤት ውስጥ ግድያ ጋር በተያያዘ ፍርድ ቤት መቅረባቸው በስልጣን ላይ ያሉ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ያደርጋቸዋል። ሁኔታው በደቡብ አፍሪካ ተከባ የምትገኘውን ትንሿን ሌሴቶ ያስደነገጠ ሆኗል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠበቃ ኳሌሃንግ ሌትሲካ እንዳሉት "ደንበኛዬ በስልጣን ላይ እያሉ ሊከሰሱ አይችሉም። ይህ ማለት ግን ከሕግ በላይ ናቸው ማለት አይደለም" ብለዋል። የሕገ መንግሥት ትርጓሜን የሚሰጠው ፍርድ ቤት ያለመከሰስ መብታቸውን በተመለከተ ውሳኔ ሊያስተላልፍ ይገባል በማለትም ጠበቃቸው ተከራክረዋል። ጉዳያቸውን ሲያይ የነበረው ፍርድ ቤትም ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳያቸውን ይይ ሲል አስተላልፎታል። • "ዕፀ ፋርስ በመሸጥ ልጆቼን አሳድጋለሁ" የሌሴቶዋ አምራች • በአምቦ ለድጋፍ ሰልፍ በወጡ ሰዎች ላይ ቦምብ ተወርውሮ በርካቶች ቆሰሉ የ80 ዓመቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ባለፈው ሳምንት ፍርድ ቤት መቅረብ ቢኖርባቸውም ደቡብ አፍሪካ ለህክምና በመሄዳቸው ምክንያት ሳይቀርቡ ቀርተዋል። ይህንንም ተከትሎ ከአገር ኮብልለው ነው ቢባልም እሳቸው ግን አስተባብለዋል። በጥር ወር ፖሊስ የአርባ ሁለት ዓመት እድሜ ያላቸውን የአሁኗን ባለቤታቸውን ጠርጥሬያለሁ ማለቱን ተከትሎ፤ ቀዳማዊቷ እመቤቷ ጠፍተው ነበር። ፖሊስም በምላሹ የእስር ማዘዣ አውጥቶ ደቡብ አፍሪካ በመሄድ ከጠበቃዎቻቸውና ከፓሊስ ጋር በተደረገ ድርድር እጃቸውን መስጠታቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል። ባለፈው ወር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከግድያው ጋር በተያያዘ በፖሊስ መጠየቃቸውን ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ የተቃዋሚ ደጋፊዎች በመዲናዋ ማሴሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን እንዲለቁ በሰልፍ ጠይቀዋል። የተቃዋሚዎች ግፊት በመጨመሩም ስልጣን እንደሚለቁ ቢያሳውቁም መቼ ሊሆን እንደሚችል አላሳወቁም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለቤታቸውም ሆነ እሳቸው የተወነጀሉበትን ወንጀል ከማንሳት ተቆጥበው በጡረታ ራሴን አገልላሁ ብለው ነበር። የጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀድሞ ባለቤት ሊፖሌሎ ታቤን በሌሴቶ መዲና ማሴሮ በሚገኘው ቤታቸው ጥይት ተተኩሶባቸው የተገደሉት ከሦስት ዓመት በፊት ነበር። በወቅቱም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለበዓለ ሲመታቸው ሁለት ቀናት ሲቀራቸው ነበር ግድያው የተፈጸመው ተብሏል፤ መረር ያለ የፍች ሂደትም ላይ ነበሩ። በወቅቱም ከአሁኗ ባለቤታቸው ጋር አብረው ይኖሩ ነበር ተብሏል። ነገር ግን ሊፖሌሎ በወቅቱ ቀዳማዊት እመቤት ማን ተብሎ ይጠራ የሚለውንም ጉዳይ ወደ ፍርድ ቤት ወስደውት፤ የቀዳማዊ እመቤት ለሳቸው ይገባል በሚል ተወስኗላቸው ነበር። ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለበኣለ ሲመታቸው ሁለት ቀን ሲቀራቸው በመገደላቸው ምክንያት የአሁኗ ባለቤታቸው በክብረ በዓሉ ላይ ተገኝተዋል። ከሁለት ወራት በኋላም ከአሁኗ ባለቤታቸው ጋር በሮማውያን ካቶሊክ ስነ ስርአት መስረት ጋብቻቸውን ፈፀሙ። ቀዳማዊቷ እመቤት ማሳየህ ታባኔ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀድሞ ባለቤት ክስ ተመስርቶባቸው በ2ሺ ብር ዋስ ወጥተዋል። ከዚህም በተጨማሪ ቀዳማዊቷ እመቤት የቤተሰቡ ቅርብ የሆነውን ታቶ ሲቦላን በመግደል ሙከራም ክስ ተመስርቶባቸዋል። ታቶ ሲቦላ በወቅቱ የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ሲገደሉ የአይን እማኝ ነበርም ተብሏል። ማሳየህ እስካሁንም የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ አልተጠየቁም።
news-49800232
https://www.bbc.com/amharic/news-49800232
በወለደች በ30 ደቂቃ ውስጥ የተፈተነችው ተማሪ ስንት አስመዘገበች?
ልጇ ሦስት ወር ሆኖታል። የደከምሽበት ነውና ስም የማውጣቱ እድል ላንች ተሰጥቶሻል ስለተባለች 'ይዲዲያ' ብለዋለች። እሷ እንዳለችው 'ይዲዲያ' የመፅሐፍ ቅዱስ ስም ሲሆን 'እግዚአብሔር ይመስገን' ማለት ነው።
ስሙ የተወለደበትን ሁኔታ ገልጦልኛል ትላለች። በእርግጥ የአካባቢው ሰው፤ ጎረቤቱም የተለያዩ መጠሪያ ስሞችን አውጥተውለታል። ከእነዚህ መካከል በተማረችበት ትምህርት ቤት ስም 'አብዲ ቦሪ' ብላችሁት ጥሩት ያሏቸውም ነበሩ። 'አብዲ ቦሪ' ማለት የኦሮምኛ ቃል ሲሆን 'የነገ ተስፋ' ማለት ነው ብሎናል የሕፃኑ አባት አቶ ታደሰ ቱሉ። ሌሎችም ስሞች ወጥተውለታል። ግን እናቱ ያወጣችለት ይበልጣል ብለው እርሱ ቢፀድቅም 'አብዲ ቦሪ' ሁለተኛ መጠሪያው ሆኗል። • ከወለደች ከ30 ደቂቃዎች በኋላ ለፈተና የተቀመጠችው እናት አልማዝ ደረሰ ባሳለፍነው ዓመት በ10ኛ ክፍል ማጠቃለያ ሃገር አቀፍ ፈተና ወቅት ከወለዱ ሴት ተማሪዎች መካከል አንዷ ናት። አልማዝ ከወለደች ከ30 ደቂቃ በኋላ ነበር ፈተና ላይ የተቀመጠችው። የኢሉአባቦራ ዞን፤ መቱ ከተማ ነዋሪ የሆነችው አልማዝ ደረሰ ነፍሰጡር ሆና ትምህርት ቤት ተመላልሳ፤ ከወለደች ከ30 ደቂቃ በኋላ ሆስፒታል ውስጥ ሆና ፈተና ላይ ብትቀመጥም ያመጣችው ውጤት ግን ለመላው ቤተሰቡ ደስታን የሸለመ ነበር። አልማዝ 3.0 ውጤት በማስመዝገብ ወደ 11ኛ ክፍል አልፋለች። "ስፈተን ሕመም ላይ ስለነበርኩ ይህንን ውጤት አልጠበቅኩም ነበር፤ ቢሆንም አሁን ላይ ውጤቴን ሳይ በጣም ደስ ብሎኛል" ትላለች አልማዝ። አልማዝ እንደምትለው በፈተና ወቅት ምጥ ባይፈትናት ከዚህ በላይ ውጤት ልታስመዘግብ እንደምትችል ትናገራለች። • ወላጆች ለልጆቻቸው የሚመኟቸው ኢትዮጵያዊ መምህር ፈተናው ብቻ ሳይሆን ሙሉውን የትምህርት ጊዜም ነፍሰጡር ሆና ነው ትምህርቷን የተከታተለችው። የእርግዝናዋ የመጀመሪያዎቹ ወራት ፈታኝ ቢሆኑም ፅንሱ እየገፋ ሲመጣ መነሳት፣ መቀመጥ፣ መተኛት ቢቸግራትም አልተሸነፈችም። እንዲያውም "ማታ ማታ ለመተኛት ስለማይመቸኝ፤ ቁጭ ብየ አጠና ነበር" ስትል አለመመቸትን ወደ ውጤት መለወጥ እንደቻለች ታስረዳለች። አልማዝ በትዳር 4 ዓመታትን አስቆጥራለች። እስከ ሰባት ዓመቷ ድረስ ከወላጆቿ ጋር ሆና ብታሳልፍም፤ የሚኖሩት ገጠር በመሆኑ ከሰባት ዓመቷ በኋላ እናስተምራታለን ያሉ ዘመዶቿ ጋ ወደ ከተማ ሄዳ እንደነበር ታስታውሳለች። በወቅቱም በቤት ውስጥ የሥራ ጫና ነበረባት። በመሆኑም ትምህርቷን በተለያየ ጊዜ ለማቋረጥ ተገዳ ነበር። በዚያ የተነሳ ትዳር ወደ መመስረቱ እንዳዘነበለች እና ትዳር ከመሰረተች በኋላም ትምህርቷን እንደቀጠለች ከዚያም ሳታቋርጥ እዚህ እንደደረሰች ትናገራለች። "ባለቤቴ እንድማር ብቻ ነበር የሚፈልገው፤ ተማሪ በርቺ እያለ ሁሉንም እያሟላ ይደግፈኝ ነበር" ስትል ስለባለቤቷ ያልተቆጠበ ድጋፍ ታስታውሳለች። ወደፊት መሐንዲስ መሆን እንደምትፈልግ የምትናገረው አልማዝ አሁንም ትምህርቷን ጠንክራ እንደምትቀጥል ትናገራለች። "ልጅ እያደገ ሲመጣ ያጓጓል" የምትለው አልማዝ ልጇን ባየች ቁጥር፤ ያኔ የነበረባትን ጭንቅ፣ ፈተናው፣ ነፍሰጡር ሆና ወደ ትምህርት ቤት መመላለሷ ትውስ እንደሚላት ትገልጻለች። አልማዝ ከባላቤቷ ባሻገር በትምህርት ቤቱ ያሉ መምህራንና ተማሪዎች ድጋፍ እና እንክብካቤ ያደርጉላት እንደነበር ግን ሳትጠቅስ አላለፈችም። የእንጨት ሥራ ባለሙያ የሆነው ባለቤቷ አቶ ታደሰ ቱሉ በወቅቱ አልማዝ በምጥ ተይዛ ሆስፒታል ውስጥ ጭንቅ ላይ እያለች፤ በሠላም እንደምትወልድ እርግጠኛ በመሆኑ ፈተናዋ እንዳያልፋት ለማመቻቸት ላይ ታች ይል ስለነበር በሠላም የመገላገሏ ዜና የተነገረውም በስልክ ነው። ከዚህ ቀደም በፈተና ወቅት እንዲህ ዓይነት አጋጣሚዎች ሊኖሩ እንደሚችሉና መፈተን እንደሚችሉ ግንዛቤው ስለነበረው፤ ባለቤቱ የደከመችበት በከንቱ አይቀርም በማለት ከልጁን በሰላም የመወለድ ዜና ባሻገር የፈተናዋን ጉዳይ በቅርበት ይከታተል ነበር። "ባለቤቴ ነፈሰጡር ሆናም በጣም ጠንካራ ነበረች፤ ስትንቀሳቀስ የነበረው ነፍሰጡር እንዳልሆነች ሴት ነበር። በቤት ውስጥ እኔና እሷ ብቻ ስለነበርን እኔንም ለመርዳት ጥረት ታደርግ ነበር" ይላል። ታዲያ እሱም ቢሆን ከጎኗ ነበር። ጥንዶቹ በእርግዝናዋ ጊዜም ቢሆን ትምህርቷን ስለማጠናቀቅ እንጂ አንድም ቀን ስለማቋረጥ በጭራሽ አስበውትም፤ ተነጋግረውበትም አያወቁም። • 28 የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች በፈተና ወቅት ወለዱ "ፈተናው ከተጀመረ በኋላ ምጥ ይመጣባታል የሚል ፍራቻ ነበረኝ፤ ግን ቀደም ብሎ ነው ምጥ የመጣው፤ ከፈተናው በፊትም አስቀድማ ወለደች፤ እኔም በጣም ደስ አለኝ'" ይላል። አቶ ታደሰ እንደሚለው ባለቤቱ ፈተና ላይ ምጥ ባይገጥማት ከዚህ በላይ ውጤት እንደምታስመዘግብ እርግጠኛ ነበር- በትምህርቷ ከፍተኛ ውጤት የምታስመዘግብ ተማሪ እንደነበረችና ከክፍሏም የደረጃ ተማሪ እንደነበረች በመጥቀስ። ቢሆንም ግን ያንን ሁሉ ፈተና ተቋቁማ ይህንን ነጥብ በማስመዝገቧ መደሰቱን ገልጿል። ወደ 11ኛ ክፍል መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ ለመደበኛ፣ ለማታ እና ለግል ተፈታኝ ተማሪዎች ለወንድ 2.00 እና ከዚያ በላይ ለሴት ደግሞ 1.86 እና ከዚያ በላይ መሆኑን የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ማስታወቁ ይታወሳል። በ10ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ወቅት በመላ አገሪቱ 28 ሴት ተማሪዎች መውለዳቸው ይታወሳል፤ ነገር ግን ምን ያህሎቹ ወደ የሚቀጥለው ደረጃ እንደተሻገሩ ከኤጀንሲው ለማወቅ በተደጋጋሚ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
news-42007591
https://www.bbc.com/amharic/news-42007591
ስለ ጠልሰም ወይም በተለምዶ የአስማት ጥበብ ተብሎ ስለሚጠራው ምን ያህል ያውቃሉ?
ጠልሰም አስማታዊ ጥበብ ነው ፤ ትርጉሙ ደግሞ አምሳል፣ውክልና እንዲሁም ማስዋብ ማለት ነው።
ጠልሰም የተለየ ኀይል ያለው ጥበብ ነው። ኢትዮጵያውያን ከሁለተኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ይሰሩት የነበረ ጥበብ መሆኑም ይነገራል። ይህም ጥበብ በየገዳማቱ በብራናዎች ላይ አርፏል። የጠልሰም ጥበብ ኃይል ያላቸውን ቃላት፣ዕፅዋት እንዲሁም ምልክቶችን ይይዛል። ጠልሰም የመፈወስ ኃይል አለው ስለሚባል በክታብነት የሚጠቀሙበት አሉ። ይህ ጥበብ በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ አካባቢዎች ብቻ ተወስኗል። የጠልሰም ስዕልም እነዚህን ኃይል ያላቸውን ቃላቶች፣ ምልክቶችና ዕፅዋት በመጠቀም የሚሳል ነው። ጠልሰም ከመፈወስ በተጨማሪ ሰውን የመሰወር፤ ግርማ ሞገስን መስጠት፤ በሰዎች ጫንቃ ላይ ለመስፈር የሚዳዳውን ሰይጣን ጋሻና ጦር በመሆን መከላከልና ማስጣል የሚያስችል ኃይል አለው ተብሎ ይታመናል፤ ይህም ዓቃቤ ርዕስ ተብሎ ይጠራል። ለዛሬም ከአንድ ኢትዮጵያዊ ጠልሰምን የሚጠቀም ሰዓሊ እናስተዋውቃችሁ። ተወልደብርሃን ኪዳነ አስመራ ከተማ ውስጥ ማይ ጃሕጃሕ በተባለ ልዩ ስፍራ ነው የተወለደው። የአንድ ዓመት ህፃን ልጅ ሆኖም ወደ ኢትዮጵያ መጣ። በመቐለ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስትያን ውስጥ የአብነት ትምህርቱን የተማረው ከመርጌታ አርአያ ሲሆን በተጨማሪም ጥንታዊና እየጠፋ ያለውንም የጠልሰምን ዕውቀት አስተምረውታል። የመደበኛ ትምህርቱን 8ኛ ክፍል ከደረሰ በኃላ ሁሉንም ነገር ጥሎ ወደ ጐጃም ጣና ቂርቆስ ገዳም ገባ። ገዳሙ ውስጥ ለሦስት ዓመታት ያህል የጠልሰም ጥበብን ከሊቃውንት አባቶች ተማረ። የጠልሰምን ጥበብ ከአፈር፣ ከዕፅዋት፣ከቅጠልና ከአበባ እንዴት መሳል እንደሚቻልም ለዓመታት አጠና። ወደ ሰሜን ወሎ በማቅናትም በአቡነ ይምርሃነ ክርስቶስ ገዳም ውስጥ ስለ ጠልሰም አንድ ዓመት ተምሯል። ከዚያም በኃላ ሰሜን ሸዋ በሚገኘው የደብረ ሊባኖስ ገዳም በመሄድ የጠልሰምን ጥበብ ለአንድ ዓመት ተኩል ያህል አጥንቷል። ተወልደብርሃን በዚህ አላበቃም ወደ ቢሾፍቱም በመሄድ በቤተ ሩፋኤል ገዳም ውስጥ አንድ ዓመት ከሦስት ወር በመቆየት በጠልሰም ዙሪያ ላይ ቁፋሮና ምርምር አካሂዷል። ወጣቱ በነዚህ የምርምርና የጥናት ጊዜው ጠልሰም ትልቅ የኢትዮጵያውያን ስልጣኔ መሆኑን እንደተረዳ ይናገራል። "የመጀመርያው ሰዓሊ ራሱ ፈጣሪ ነው፤የሰው ልጅ የፈጣሪ የጠልሰም ጥበብ ውጤት ነው። የሰው ልጅም ከፈጣሪው የወረሰውን የጥበብ ኅይል ተጠቅሞ የጠልሰምን ጥበብ መከወን ችሏል። በዚሁ ዘዴ ከመላዕክት ጋር ይነጋገራል። ሲያሰኘው ደግሞ ጥበቡ እየረቀቀ በሄደ ቁጥር ከአጋንንት ጋርም ያወራል" በማለት ተወልደብርሃን ስለ ጠልሰም አፈጣጠርና መንፈሳዊ ግንኙነት ይገልፃል ። በኢትዮጵያ የጠልሰም ጥበብና ሐረግ በየገዳማቱ ብራና ላይ ይገኛሉ። ተወልደብርሃን በጠልሰም ምርምር ዘልቆ የገባ ሲሆን የራሱን የፈጠራ ውጤት በማከል የተለያዩ ስዕሎችን ያዘጋጃል። እስከ አሁን ድረስ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ሰዓሊያን ጋር በመሆን በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ፣ብሔራዊ ቴአትር፣ነፃ አርት ቪሌጅ፣ሸራተን ሆቴል፣እንዲሁም በመቐለ ከተማ፣ በዓዲ ግራትና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች በተለያየ ጊዜ የጠልሰም ስዕሎች ዓውደ ርእይ አቅርቧል። በመቶዎች የሚቆጠሩ የጠልሰም ስዕሎችንም ሰርቷል። "ኢትዮጵያውያን ከጠልሰም በፊት የነበረውና 'ርስተ ጌታ' በሚል ይታወቅ የነበረው የጥበብ ጸጋ አጥተነዋል። 'ርስተ ጌታ' በስነ ፍጥረት ዙሪያ የሚያጠነጥን የስዕል ጥበብ ነበረ። በአሁኑ ሰዓት የዚህ ጥበብ አሻራ በደብረ ዳሞ ገዳም (ትግራይ) እንዲሁም በይምርሃነ ክርስቶስ ገዳም (ላልይበላ) ይገኛል" በማለት ተወልደብርሃን ይናገራል። ይህንን ጥበብ ወደ ቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ዕቅድ ያለው ተወልደብርሃን ትግራይ ክልል ውስጥ ከክልሉ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር በአምስት አካባቢዎች በጠልሰም ጥበብ ዙሪያ ለወጣቶች ስልጠና ለመስጠት አቅዶ እንዳልተሳካለት ይናገራል። "ጠልሰም ደግሞ ምንድን ነው? አሉኝ። ብራና ላይ ስዬ አሳየሁዋቸው፤ሊቀበሉት አልቻሉም፤ይኸው ቤቴን ዘግቼ እስላለሁ" ሲል ሁኔታው ምን ያህል እንዳልተመቻቸለት ገልጿል። ተወልደብርሃን ማታ እስከ እኩለ ሌሊት ሲስል ሻማ ማብራትና ዕጣን ማጨስ ይወዳል። ባለፈው ዓመት ዘጠኙን ቅዱሳን ለመሳል 78 ሻማዎችን አብርቷል። በኢትዮጵያ የጠልሰም ጥበብ ውስጥ ሴቶች አይሳተፉበትም ምክንያቱም ይህ ጥበብ የአስማት ነው ተብሎ ስለሚታወቅ ከባድ ተፅዕኖ ስለሚደርስባቸው ነው በማለት ተወልደብርሃን ይገልፃል። ተወልደብርሃን በአሁኑ ሰዓት መቐለ በሚገኝ አንድ የሥነጥበብ ጥምህርት ቤት ዘመናዊ የስዕል ጥበብ ያስተምራል። በቀጣይ አንድ ትልቅ የጠልሰም ጥበብ ውጤቶችን የሚያሳይ ዓውደ ርዕይ ለማዘጋጀት አቅዷል። "ኢትዮጵያ ውስጥ ጠልሰም አደጋ ላይ ነው፤ሌላው ቀርቶ በውል ተጠንቶ አልተሰነደም። እኔ ያጠናሁትና የሰበሰብኩትን ዕውቀት በመፅሃፍ አሳትሜ ወደ ህዝቡ እንዳላቀርብ አጋዥ በማጣት ይኸው አቋረጥኩት" ሲል ተወልደ ብርሃን በምሬት ይናገራል።
news-56359827
https://www.bbc.com/amharic/news-56359827
ትግራይ፡ ኢትዮጵያ በአንቶኒ ብሊንከን የተሰነዘረውን 'የዘር ማጽዳት' ክስ አጥብቃ ተቃወመች
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን የሰነዘሩት በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል 'የዘር ማጽዳት' ድርጊት ተፈጽሟል የሚለው ክስ በፍጹም "ተጨባጭ ያልሆነና ሐሰተኛ" ነው ሲል የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውድቅ አደረገው።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ብሊንከን ባለፈው ረቡዕ ለአሜሪካ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ በሰጡት ማብራሪያ ወቅት ትግራይ ውስጥ "የዘር ማፅዳት ወንጀል" ተፈጽሟል ያሉ ሲሆን ድርጊቱን ከማውገዝ በተጨማሪ "ሙሉ ተጠያቂነት" እንዲኖር ጥሪ አቅርበው ነበር። ለዚሁ ክስ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ ላይ ምላሽ ሲሰጥ "በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የተሰነዘረ ተጨባጭነት የሌለውና ሐሰተኛ ክስ ነው" ብሎታል። መግለጫው ጨምሮም መንግሥት በትግራይ ክልል ውስጥ ያካሄደው ዋነኛው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ወቅትና ከተጠናቀቀ በኋላ ሆን ተብሎ በክልሉ ውስጥ ማንንም ኢላማ ያደረገ "ዘር ማጽዳት" ተብሎ የሚጠቀስ ድርጊት አልተጸመም በማለት ክሱን የኢትዮጵያ መንግሥት አጥብቆ እንደሚቃወመው ገልጿል። አንቶኒ ብሊንከን በትግራይ ክልል ተከሰተ ስላሏቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና ግድያዎች ተአማኒ መረጃዎች እንዳሉ አመልክተው የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንን እንዲያስቆም ጠይቀዋል። በትግራይ ክልል ስላለው ሁኔታ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም ሲልም በመስሪያ ቤታቸው በኩል መግለጫ ያወጡ ሲሆን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር መወያየታቸው ይታወሳል። የኢትዮጵያ መንግሥት ከአካባቢያዊና ዓለም አቀፋዊ አጋሮች ጋር በመሆን ጥልቅ ምርመራ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አቋሙን ግልጽ ባደረገበት ጊዜ "ነገሮችን ከሚገባቸው በላይ ማግዘፍ ጉዳዩን በማያስፈልግ ሁኔታ ፖለቲካዊ ከማድረግ ውጪ ፍትሕ ለማስፈን አይጠቅምም" ብሏል። መግለጫው አክሎም የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብአዊ መብት ጥሰቶችና ወንጀሎችን በተመለከተ የሚቀርቡ ክሶችን ትኩረት እንደሚሰጥ ጠቅሶ፤ ለዚህም ነው አጥፊዎችን ለፍርድ ለማቅረብ በቀረቡ ክሶች ዙሪያ አስፈላጊው ምርመራ እንዲደረግ አፋጣኝ እርምጃ የወሰደው ሲል ገልጿል። ለዚህም እንደማሳያ ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የተወከሉ መርማሪዎች ወደ ትግራይ ክልል ሄደው ምርመራ እያደረጉ መሆናቸውን አመልክቷል። በተጨማሪም መንግሥት ከተለያዩ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ድርጅቶች ጋር በመሆን ትግራይ ክልል ውስጥ ተፈጽመዋል ስለተባሉት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ለመመርመርና በሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ በትብብር ለመስራት አስፈላጊውን ሁሉ እያደረገ መሆኑን ገልጿል። ባለፈው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ "ተፈፅመዋል የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለመመርመር መንግሥታቸው እርምጃዎችን መውሰዱን" በመግለጽ ከአፍሪካ ሕብረት ጋር በጋራ ለመስራት በራቸው ክፍት መሆኑን ገልጸው ነበር። አምነስቲና ኢንተርናሽናልና ሂዩማን ራይትስ ዋች እንዲሁም ሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በትግራይ ክልል ውስጥ የኤርትራ ወታደሮች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ግድያዎችን፣ አስገድዶ የመድፈር ድርጊቶችንና ሌሎች የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ፈጽመዋል በማለት ሪፐፖርቶችን ማውጣታቸው ይታወሳል። ከዚህ በተጨማሪም የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኃላፊ ሚሼል ባሽሌት በክልሉ እየተፈፀመ ያለው ጥሰት "የጦር ወንጀልና በሰብዓዊነት ላይ የተፈፀመ ወንጀል" ተደርጎ ሊቆጠር እንደሚችል መናገራቸው የሚታወስ ነው። በዚህም የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በትግራይ ክልል ተፈጸሙ የተባሉትንና እንደ ጦር ወንጀል ሊቆጠሩ የሚችሉ ሪፖርት የተደረጉ የጅምላ ግድያዎችን፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችንና ወሲባዊ ጥቃቶችን ለመመርመር እንዲችል ፈቃድ እንዲሰጠው ጠይቋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በትግራይ ክልል ግጭት ወቅት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችንና ግድያዎችን በተመለከተ መንግሥት ምርመራ በማድረግ በሚገኘው ውጤት መሠረት ጥፋተኞችን ወደ ፍትህ እንደሚያቀርብና በምርመራው ላይ ተጨማሪ እርዳታ ካስፈለገ መንግሥት የውጭ አካል ሊጋብዝ እንደሚችል ገልጸዋል። ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚገኘው የሰሜን ዕዝ ላይ በህወሓት ኃይሎች ጥቃት በመፈፀሙ መንግሥት "ሕግ የማስከበር" ወታደራዊ ዘመቻን ማካሄዱን ገልጿል። የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት በኅዳር ወር አጋማሽ ላይ መቀለን ከተቆጣጠረ በኋላ በትግራይ ያካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ መጠናቀቁን ቢገልጽም በአንዳንድ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ወታደራዊ ግጭቶች እንዳሉና ነዋሪዎች ጉዳትና መፈናቀል እንዳጋጠማቸው በተለያዩ ጊዜያት የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
news-51534369
https://www.bbc.com/amharic/news-51534369
ዝነኛው ሩዋንዳዊ ዘማሪ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ሳለ ሕይወቱ ማለፉ ቁጣን ቀሰቀሰ
ኪቲቶ ሚሂጎ በመባል የሚጠራው ዝነኛው ዘማሪ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ሳለ ሕይወቱ ማለፉ በሩዋንዳ ቁጣን ቀስቅሷል።
የሩዋንዳ መንግሥትን በመተቸት የሚታወቀው ኪቲቶ ከሦስት ቀናት በፊት ቡሩንዲ ድንበር አቅራቢያ በሩዋንዳ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ውሎ እንደነበር ተነግሯል። ፖሊስ ዘማሪው በቡሩንዲ የሚገኙ የሩዋንዳ መንገሥትን የሚወጉ አማጺ ቡድኖችን ለመቀላቀል ሊሄድ ሲል ነው በቁጥጥር ሥር ያዋልኩት ብሏል። ኪቲቶ ከዚህ ቀደም ተመሥርቶበት በነበረው ክስ መሠረት አገር ጥሎ እንዳይወጣ ተበይኖበት ነበር። ፖሊስ ባወጣው የጽሑፍ መግለጫ ዘማሪው በቁጥጥር ሥር ውሎ በነበረበት እስር ቤት የተለመደው ቁጥጥር ሲደረግ በእስር ክፍሉ ውስጥ ሕይወቱ አልፎ ተገኝቷል ከማለት ውጭ በኪቲቶ አሟሟት ላይ ዝርዝር መረጃ ሳይሰጥ ቀርቷል። የሩዋንዳ መገናኛ ብዙኃን ኪቲቶ ሚሂጎ በሙስና እና በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማቋረጥ በሚል ክስ ተመሥርቶበት እንደነበር ዘግበው ነበር። ከቀናት በፊት ከቲቶ ሚሂጎ በቁጥጥር ሥር ሲውል የተመለከቱ የዓይን እማኞች ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ዘማሪው ምንነቱ ባልታወቀ ነገር የተሞላ ቦርሳ ይዞ ወደ ቡሩንዲ ድንበር ሊሻጋር ሲል በቁጥጥር ሥር ውሎ ነበር። የዘማሪው አድናቂዎች የመሞቱን መንስዔ መንግሥት እንዲያስረዳ እየጠየቁ ይገኛሉ። እአአ 2015 ዘማሪው ፕሬዝደንት ፕል ካጋሜን ለመግደል በማሴር እና በመንግሥት ላይ የጥላቻ ዘመቻ በመክፈት የ10 ዓመት እስራት ተፈርዶበት ነበር። ከሁለት ዓመት በፊት በፕሬዝደንቱ ምሕረት ተደርጎለት የነበረ ሲሆን፤ ከአገር መውጣት የሚችለው ከፍርድ ቤት ፍቃድ ሲያገኝ ብቻ ነበር።
53813963
https://www.bbc.com/amharic/53813963
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ነው የተባለ የእንስሳት አምቡላንስ ስራ ጀመረ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ሕክምናና ግብርና ኮሌጅ ለአገራችን ግንባር ቀደም የተባለውን የእንስሳት አምቡላንስ ሥራ አስጀምሯል።
አምቡላንሱ በሬ ወይም ግመል ሲታመም እንስሳቱ ያሉበት ድረስ ሄዶ ሕክምና ይሰጣል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የእንስሳት ሕክምናና ግብርና ኮሌጅ ኮሌጅ ዲን የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር ሒካ ዋቅቶላ ስለ አምቡላንሱ ሲናገሩ፣ "በአገሪቱ እስካሁን የነበረው የሰው አምቡላንስ ነው። ይህ የመጀመሪያ የእንስሳት አምቡላንስ ነው" ብለዋል። አክለውም አምቡላንሱ በቢሾፍቱ ከተማ እንዲሁም በከተማው ዙሪያ ባሉ የገጠር ከተሞች ለሚታመሙ እንስሳት አገልግሎት እንደሚሰጥ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አምቡላንሱ ማንኛውንም ሕክምና መስጠት የሚያስችል መሣሪያ የተገጠመለት ሲሆን እንስሳት በጠና ሲታመሙ ያሉበት ድረስ የህክምና ባለሙያ ይላካል ሲሉ ገልፀዋል። እስካሁን ሥራ የጀመረው አንድ አምቡላንስ ብቻ መሆኑን የተናገሩት ፕሮፌሰር ሂካ፣ ከቢሾፍቱና አካባቢው በስተቀር አገልግሎት መስጠት አይችልም ብለዋል። በተጨማሪም "ይህ ጥሩ ጅማሮ ስለሆነ ለወደፊትም ተጨማሪ የእንስሳት አምቡላንሶች የመጨመር እቅድ አለ።" ኢትዮጵያ በቀንድ ከብት ብዛት በዓለም አምስተኛ በአፍሪካ ደግሞ አንደኛ ናት። እንደ ረዳት ፕሮፌሰር ሒካ ከሆነ በአሁን ወቅት የተሻሻለ ዝርያ ያላት ላም እስከ 50 ሺህ ብር ድረስ ስትሸጥ ግመል ደግሞ ከዚያ በላይ ያወጣል። በቀላሉ መዳን የሚችሉ እንስሳት ሲሞቱ አርሶ አደሮች ከፍተኛ ችግር ውስጥ መውደቃቸውም አይቀርም የሚሉት ረዳት ፕሮፌሰሩ፣ "ስለዚህም የአምቡላንሱ ስራ መጀመር ለአርሶ አደሩ መልካም ዜና ነው።" ብለዋል። ከዚህ በፊት እንስሳት ሲታመሙ ወደ ኮሌጁ ጤና ተቋም ይሄዱ ነበር። ከዚህ በኋላ ግን ባሉበት ህክምና እንደሚያገኙ ተባባሪ ፕሮፌሰር ሒካ ገልጸዋል። "ምጥ ላይ ያለችን እንስሳ ወይም የታመመን እንስሳ ረዥም ርቀት ይዞ መሄድ ያስቸግራል። ስለዚህ አምቡላንሱ ላይ ባለው ስልክ ቁጥር አርሶ አደሮቹ ሲደውሉልን ያሉበት ድረስ ባለሙያዎች እንልካለን።" የቢሾፍቱ የጤናና ግብርና ኮሌጅ ከዚህ ቀደም የፈረስ ሆስፒታል መክፈቱ ይታወሳል። በዓመት ከ6 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ፈረሶች ነጻ ህክምና የሚሰጠው የፈረሶች ክሊኒክ
news-56304118
https://www.bbc.com/amharic/news-56304118
የኮቪድ-19 ክትባት ወደ ኢትዮጵያ በነገው ዕለት እንደሚገባ ተገለፀ
የኮቪድ-19ን ለመከላከል የሚውለው የመጀመሪያ ዙር ክትባት በነገው እለት፣ 28/6/2013 ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
ክትባቱ ኮቫክስ ከተሰኘው አለም አቀፍ ጥምረት የተገኘ ሲሆን መጠኑም 2.2 ሚሊዮን ዶዝ እንደሆነም ከጤና ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት የተገኘው መረጃ ያስረዳል። ክትባቱ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው የጤና ሰራተኞችን ጨምሮ ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመለየት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውም ተገልጿል። ከዚህ ቀደም የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለክትባቱ በዋናነት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ዜጎች ተጋላጭ ይሆናሉ ተብለው የተለዩ የማህበረሰብ ክፍሎች እንደሆኑ አስታውቀዋል። በዚህ መሰረት የጤና ባለሙያዎች፣ የማህበራዊ ጤና ሰራተኞች፣ የህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አካላት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል ያሉ ሲሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቋቋመው ግብረ ሀይልም የተሳለጠ የክትባት አሰጣጥና ቁጥጥር እንዲኖር ያደርጋል ማለታቸው የሚታወስ ነው። ከዚህም ጋር ተያይዞ ከተለያዩ ተቋማት የተዋቀረው ሃገራዊ የኮቪድ-19 ክትባት የበላይ አስተባባሪ ኮሚቴ ክትባቱን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባትና ለማሰራጨት እየተደረገ ያለውን አጠቃላይ ዝግጅት በተመለከተ በትናንትናው ዕለት፣ የካቲት 26፣ 2013 ዓ.ም ውይይት ተደርጓል። በዚህ ውይይት ላይም በዋነኝነት የኮቪድ-19 ክትባት አቅርቦትና ስርጭት አስመልክቶ በታቀደው መሰረት የተከናወኑ ዝርዝር ተግባራትና ዝግጅቱን መገምገሙንም ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዪት የተገኘው መረጃ ያስረዳል። ከዚህም በተጨማሪ ክትባቱ ጥራቱን በተጠበቀ መልኩ የሚደርስበትን፣ በተቆጣጣሪ አካል እየተከወኑ ስላሉ ስራዎች፣ ክትባቱን የሚከተቡትን የተለዩ አካላትም አስመልክቶና በህዝቡ ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር የተሰሩ ስራዎችን በተመለከተ ውይይቶች ተደርገዋል። በተጨማሪም አገሪቷ ከኮቪድ-19 ክትባት ጋር በተያያዘ ልታከናውናቸው የሚገቡ ጉዳዮችን በተመለከተም የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ አቅጣጫ መስጠታቸውም ተገልጿል። በውይይት መድረኩ ላይ የጤና ሚኒስትር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ፣ የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አጄንሲና የተለያዩ የልማት አጋር ድርጅቶች ኃላፊዎችና ተወካዮች ተሳትፈዋል። ኮቫክስ ምንድነው? የኮሮናቫይረስ ክትባት ሥራ ላይ መዋል ከጀመረ ወዲህ ሃብታም የሚባሉቱ አገራት ናቸው ክትባቱን በገፍ እየገዙ ዜጎቻቸውን እየከተቡ ያሉት። በዶክተር ቴድሮስ መሥሪያ ቤት አማካይነት የተዘረጋው ኮቫክስ የተሰኘው ማዕቀፍ ደሃ አገራት ክትባቱን ለማግኘት ብዙ እንዳይጠብቁ ለማድረግ ቆርጦ ተነስቷል። ኮቫክስ (COVAX) ምጣኔ ኀብታቸው ደካማና መካከለኛ ለሆኑ አገራት ክትባቱን ለማቅረብ ያለመ፣ በዓለም ጤና ድርጅት እና በሌሎች ዓለም አቀፍ የጤና ተቋማት የተመሰረተ ኢኒሼቲቭ ነው። ሁሉም የአፍሪካ አገራት ይህንን ኢኒሼቲቭ ተቀብለውታል። በዚህ ማዕቀፍ መሠረት ሃብታሞቹ አገራት አቅም የሌላቸውን አገራት በገንዘብ እንዲያግዙ ይደረጋሉ። በአንድ ዓመት ብቻ በ190 አገራት ሁለት ቢሊዮን ክትባቶችን ለማሠራጨት ታልሟል። በተለይ ደግሞ 92 ደሃ የሚባሉ አገራት ከሌሎች 98 አቅም ካላቸው አገራት እኩል ክትባቱን እንዲቀበሉ ይደረጋል። ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ ሃገራት የዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚዎች ናቸው። ይህም ማለት አፍሪካ በዚህ ኢኒሼቲቭ በኩል፣ 220 ሚሊዮን ክትባቶችን ታገኛለች። ነገር ግን እንደ ሴኔጋል ያሉ ጥቂት አገራት ከዚህ ማዕቀፍ ውጭ ክትባት ማግኘት ችለዋል። ፕሮግራሙ እስካሁን ድረስ ለክትባት የሚሆን 6 በሊየን ዶላር ማሳበሳብ ችሏል። ቢሆንም ተጨማሪ 2 ቢሊየን ዶላር ያስፈልጋል እየተባለ ነው። ምንም እንኳ ፕሮግራሙ ቀርፋፋ ነው እየተባለ ቢተችም የዓለም ጤና ድርጅትና ዩኒሴፍ አሁን ጋና የደረሰው ክትባት የመጀመሪያው ዙር ነው ብለዋል። እኤአ በ2021 መጨረሻ ላይ ኮቫክስ 2 ቢሊዮን የኮቪድ-19 ክትባቶችን ለመግዛት እቅድ ይዟል። አፍሪካ ለአህጉሩ የሚሰራጭ ለጊዜው 270 ሚሊዮን 'ዶዝ' (መጠን) የኮቪድ-19 ክትባት በአፍሪካ ሕብረት በኩል ማግኘቷ ተገልጿል። አጠቃላይ የተገኘው ክትባት በዚህ ዓመት ጥቅም ላይ እንደሚውል የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ ቃል ገብተው ነበር። ይህ ክትባት ከዚህ ቀደም ቃል ከተገባው 600 ሚሊየን 'ዶዝ 'ተጨማሪ ቢሆንም አሁንም ግን ሙሉ አህጉሩን ለመከተብ በቂ አይደለም። በዚህም የዓለማችን ድሃ አገራት ከሃብታም አገራት ይልቅ ክትባቱን ለመከተብ ረዥም ጊዜ ሊጠብቁ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ። የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ኢትዮጵያና መሰል ሀገራት ከኮቫክስ የክትባት ትብብር ተቋም ጋር በመሆን እስከ ፈረንጆቹ 2021 መጨረሻ 20 በመቶ የሚሆነውን ህዝባቸውን ለመከተብ እየሰሩ ነው ማለታቸው የሚታወስ ነው። ምንም እንኳን በአፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ እና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በንፅፅር ዝቅተኛ ቢሆንም በአንዳንድ አገራት በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በድጋሜ እየጨመረ ነው። በኢትዮጵያም ወረርሽኙ ከተከሰተባት እለት ጀምሮ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ ጭማሬ እያሳየ ሲሆን እስካሁንም ባለው 164 ሺህ 73 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ ከነዚህም ውስጥ 137 ሺህ 431 ሲያገግሙ 2 ሺህ 404 ሞተዋል።
news-43505319
https://www.bbc.com/amharic/news-43505319
የታኘከ ማስቲካ ዳግም ነብስ ሲዘራ
እንግሊዛዊቷ ዲዛይነር አና ቡሉስ የታኘከ ማስቲካን ድጋሚ ጥቅም ላይ በማዋል አዲስ ፈጠራ ከማምጣቷም ባሻገር መንገዶችን ፅዱ እንዲሆኑ በማገዝ ላይ ነች።
ጫማ ከማስቲካ የማስቲካ ገበያ በየዓመቱ በዓለም ዙሪያ ከ14 ቢሊዮን ፓውንድ በላይ ቢያወጣም ብዙ ማስቲካ ግን መጨረሻ ግን አካባቢን ማቆሸሽ ነው። ይህ ደግሞ ማስቲካን ከሲጋራ ቀጥሎ ሁለተኛው መንገድ የሚያቆሽሽ ነገር እንዲሆን ያደርገዋል። የእንግሊዝ መንግሥት በየዓመቱ ለመንገድ ፅዳት ብቻ 50 ሚሊዮን ፓውንድ ያወጣል። ይህን ያስተዋለችው ዲዛይነር አና ቡሉስ አንድ ሃሳብ መጣላት። እነዚህ የሚጣበቁና አካባቢ የሚያቆሽሹ ነገሮች በድጋሚ ጥቅም ላይ መዋል ቢችሉስ? የሚል። የዛሬ 10 ዓመት ገደማ ነው አና ማስቲካን ድጋሚ ጥቅም ላይ ማዋል ላይ የሚያተኩረው ፕሮጀክቷን ጀመረች። ለፕሮጀክቷ መሳካት የሚያግዟትን እንደ ሲጋራ፣ ስፖንጅና የድንች ጥብስ ማሸጊያ የመሰሳሉ ናሙናዎችን ይዘት ማጥናትም ተያያዘች፤ የትኞቹን ዳግም ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚቻልም ማጣራት ቻለች። ''ቆሻሻ ተብለው ከሚጣሉ ነገሮች መካከከል ማስቲካን ለምን ድጋሚ ጥቅም ላይ ማዋል እንዳልተቻለ ሳስበው በጣሙን ደነቀኝ'' ትላለች አና። ጥናቱንም ባካሄደችበት ወቅት ማስቲካ ከሰው-ሠራሽ ጎማ የተሠራ በመሆኑ ከፕላስቲክ ጋር የሚያመሳስለው እንደ ፖሊመር ዓይነት ይዘት እንዳለው ተረዳች። ''ፖሊሶቡቲሌን ይባላል'' ትላለች አና ''ለብስኪሌት ጎማ የውስጥ ክፍል የምንጠቀመው ዓይነት ነው''። ልክ እንደ ፕላስቲክ ከድንጋይ ከሰል ወጥቶ ከፔትሮኬሚካል የተጣራ ነው። ማስቲካ መሰብሰብ "ሰዎች ያኘኩትን ማስቲካ መሬት ላይ ከሚጥሉት ለእኔ እንዲሰጡኝ እንዴት ማድረግ ይቸላል?" 'ጋምድሮፕ' የተሰኙ ደማቅ ሮዝ ቀለም ያላቸውን የቆሻሻ መጣያዎች በየመንገዱ እንዲታዩ በሆነ መልኩ አስቀመጥኩት ትላለች ቆሻሻ መጣያዎቹ እራሳቸው ከታኘኩ ማስቲካዎች የተሠሩ ናቸው። በመጣያው አጠገብ የሚለጠፍ መልዕክት ደግሞ ማስቲካዎቹ በድጋሚ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ተደርገው እንደሚሠሩ ያሳውቃል። ደማቅ ሮዝ ቆሻሻ መጣያወቹ ከታኘኩ ማስቲካዎች የተሠሩ ናቸው ማስቲካ የሚያኝኩ ሰዎች ይጠቀሟቸው ይሆን? ዊንቼስተር ዩኒቨርሲቲ እነዚህን ቆሻሻ መጣያዎች ለመጠቀም ከተስማሙት የመጀሪያዎቹ ናቸው። በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የሚሠሩና የሚኖሩ ወደ 8000 ሰዎችን መጣያዎቹን እንዲጠቀሙ ማድረግ ያስፈልግ ነበር። ''ተማሪዎቹ ከማስቲካ የተሰሩ መጠጫዎችን እንደተቀበሉ ያሸቷቸው ነበር'' የዩኒቨርሲቲው የአካባቢ ደህንነት ኃላፊ የሆኑት ሊዝ ሃሪስ ሲናገሩ። በከተማው የሚሸጡ ማስቲካዎች በሙሉ ከፖሊመር የሚሠሩ ስለሆነ ዳግም አዳዲስ ዕቃዎችን ለመሥራት መጠቀም ይቻላ ነበር። ዩኒቨርሲቲው ይህንን ሥራ ላይ ማዋል በጀመረ በ18 ወራት ጊዜ ውስጥ በቅጥር ጊቢው ውስጥ የሚጣሉ ማስቲካዎች ቁጥር መቀነስ ያዘ። አንድ መጠጫ ለመሥራት እስከ 42 ታኘኩ ማስቲካዎችን ይፈጃል ሂትሮው የአይሮፕላን ማረፊያም ለሦስት ወራት ሙከራ ቆሻሻ መጣያዎቹን አስገባ፤ አልፎም ለፅዳት የሚወጣውን ገንዘብ በ6000 ፓውንድ ቀነሰ። ግሬት ሬልዌይ ስቴሽን የተሰኘውም ባቡር ጣቢያ 25 ቆሻሻ መጣያዎች አስገብቶ ብዙ መሻሻየያዎችን አመጣ። እነዚህ ቆሻሻ መጣያዎች በመኖራቸው ቆሻሻን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ ባይቻል እንኳ ሰዎች ማስቲካን መንገድ ላይ የመጣል ልምዳቸውን እንዲቀንሱ በእጅጉ አግዟል። ለማስቲካ ቅርጽ መስጠት ለአና ሌላው ከባድ ፈተና የሆነባት የታኘኩ ማስቲካዎችን በድጋሚ ሥራ ላይ ለማዋል ፈቃደኛ የነበረ ፋብሪካን ማግኘት ነበር። ምክንያቱም ሃሳቡ በጣም አዲስ ነበር። በስተመጨረሻም አንድ ፋብሪካን አሳምና ሥራው ተጀመረ። ቆሻሻ መጣያዎቿን ተቀብሎ የማይፈለጉትን ቆሻሻዎች ማለትም ወረቀትና ሌሎች ፕላስቲኮችን ይለይና ማስቲካውን ለከሌላ ፕላስቲክ ጋር በማቀላቀል ይፈጭላታል። ማስቲካው እንዲሞቅ ይደረግና ወደ ቅርጽ ማውጪያው ይገባል በዚህ ፋብሪካ ውስጥ የታኘከው ማስቲካ በቅርጽ ማውጪያ ውስጥ ይከተታል። መጀመሪያ ይሞቅና ከዚያ እንደ ፈሳሽ እንዲወጣና በቅርጽ ማውጪያዎቹ ውስጥ ይደረግና እስኪቀዘቅዝ ይጠበቃል። ''ከዚህ ቀደም ከምንጠቀምባቸው ከፖሊፕሮፔን ይዘቶች ምንም ልዩነት የለውም'' ይላሉ የፋብሪካው ሥራ አስኪያጅ ብሬት ኒክሰን። የእንግሊዝ ፓርላማ የማስቲካ አምራቾች ለቆሻሻው መፍትሔ የማያመጡ ከሆነ ግብር እንዲከፍሉ ሊያስገድዳቸው ነበር። ነገር ግን ሪግሊ የተሰኘው የማስቲካ አምራች ለአና ሥራ የገንዘብ ድጋፍ ለገሰ። ፋብሪካዎችም ተረፈ ምርቶቻቸውን ለአና ይለግሱ ያዙ። በሰው-ሠራሽ ጎማ የሚሠራው ማስቲካ በተለያየ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል ከአና ብልሃት በተጨማሪ ማስቲካ አካባቢ ላይ የሚያደርሰውን ብክለት ለመቀነስ ሌሎች መፍትሔዎችም ይፈለጉ ጀመር። ተመራማሪዎች ሰው-ሠራሽ፣ የሚበስበስና በቀላሉ የሚፀዳ ማስቲካ ለመሥራት መላ ማፈላገጉን ተያያዙት። አሁን ላይ ገበያ ውስጥ ያሉ ማስቲካዎች ባብዛኛው ከሰው-ሠራሽና ከማይበሰብስ ንጥረ-ነገር የተሰሠሩ ናቸው።
news-52197193
https://www.bbc.com/amharic/news-52197193
ኮሮናቫይረስ በአሜሪካ ከነጮች ይልቅ በጥቁሮች ላይ ለምን ጨከነ?
ኮሮናቫይረስ ዘር፣ ቀለም፣ ሃብት፣ ጾታና ሃይማኖት አይለይም ይባላል። ታዲያ በአሜሪካ ከነጮች ይልቅ በጥቁሮች ላይ ምነው ክንዱ በረታ?
በቅርብ ከወደ አሜሪካ የወጡ መረጃዎች አስገራሚ ሆነዋል። ይህ ዘገባ ሲጠናቀር በአሜሪካ 370 ሺህ ሰዎች በወረርሽኙ ተጠቅተዋል። 11ሺህ ሰዎች ደግሞ ሞተዋል። ከዚህ አሐዝ የጥቁሮች ድርሻ ከፍተኛ ነው። ለምሳሌ ቺካጎን እንመልከት። በቺካጎ ከጠቅላላው ነዋሪ የጥቁሮች ብዛት 30 ከመቶ ብቻ ነው። ወደ ኮሮናቫይረስ ስንመጣ ግን በቺካጎ ከሞቱት ሰዎች 70 ከመቶ ጥቁሮች ናቸው። በቫይረሱ ከተያዙት ደግሞ ግማሹ ጥቁሮች ናቸው። ከኤፕሪል 5 ወዲህ ያለውን ቁጥር እንኳ ብንመለከት በቺካጎ 4ሺህ 680 ሰዎች ቫይረሱ ይዟቸዋል፡፡ 1824ቱ ጥቁሮች፣ 847ቱ ነጮች፣ 478 ሂስፓኒክ እና 126 ኢሲያዊ ዝርያ ያላቸው ናቸው። ወደ ኢሊኖይ ግዛት እንሂድ። ተመሳሳይ ነገር እናገኛለን። እዚያ የጥቁሮች ብዛት 14 ከመቶ ብቻ ነው። 41 ከመቶ ሟቾች ግን ጥቁሮች ሆነው ተገኝተዋል። የቺካጎ የኅብረተሰብ ጤና ኮሚሽነር ዶ/ር አሊሰን በቺካጎ ጥቁሮች በኮሮና እያለቁ ነው ብለዋል። ማኅበራዊ ጥግግታቸው ከሆነ ብለን ወደ ሱቆቻቸው እየሄድን ይህንኑ ለመከታተል አስበናል ሲሉም አስታውቀዋል። የቺካጎ ከንቲባ በበኩላቸው ጥቁሮች በሚበዙባቸው መጠጥ ቤቶች አካባቢ ሰዓት እላፊ ለማሳለፍ አስበናል ብለዋል። በአገር አቀፍ ደረጃስ ጥቁሮች በብዛት እየሞቱ ነው? ሚቺጋን ሌላኛዋ ግዛት ናት። በሚቺጋን ከጠቅላላው ነዋሪ የጥቁሮች ብዛት 14 ከመቶ ብቻ ነው። በኮሮና ከሞቱት ውስጥ ግን 41 ከመቶ ጥቁሮች መሆናቸው አነጋጋሪ ሆኗል። በሚቺጋን በኮሮና የሞቱት ነጮች 28 ከመቶ ብቻ ናቸው። በሚቺጋን ግዛት ውስጥ ትልቁ ከተማ ዴትሮይት ነው። በዚያ ከተማ በኮሮናቫይረስ ከተያዙት 80 ከመቶዎቹ ጥቁሮች መሆናቸው አስገራሚ ነው፡፡ በዊስኮንስን ግዛት ትልቁ ከተማ ሚልዎኪ ነው፡፡ በዚያ የጥቁሮች ብዛት 26 ከመቶ ብቻ ቢሆንም በኮሮና የሞቱት ጥቁሮች ግን 81 ከመቶ ሆነዋል፡፡ እነዚህን ከተሞች ናሙና ወሰድን እንጂ በመላው አገሪቱ ቁጥሮች ለጥቁሮች የበለጠ ሞትን አመልካች ሆነዋል። ባዷቸውን ከቀሩት የቺካጎ ጎዳናዎች አንዱ ለምን ኮሮናቫይረስ በጥቁሮች ላይ ክንዱ በረታ? የጤና ባለሞያዎች ነገሩ ሰፊ ጥናት እንደሚፈልግና በዚህ ደረጃ እንዲህ ነው፤ እንዲያ ነው ማለት እንደማያስፈልግ ከተናገሩ በኋላ የሚያነሷቸው መላምቶች ግን አሉ። የጥቁሮች ማኅበራዊ ሕይወት በጥግግት ላይ የተመሰተ መሆኑ አንዱ ነው። የኮሮናቫይረስ ቁጥርን ለመቀነስ ደግሞ መራራቅንና ራስን ማግለል እጅግ ወሳኝ ዘዴ ነው። ይህ ለጥቁሮች በቀላሉ የሚሳካ ነገር አይደለም። በብዙ ምክንያት. . . አንዱ ባሕል ነው፤ ሌላው ድህነት ያመጣው የአኗኗር ዘይቤ። የማኅበረሰብ ጤና ባለሞያዎች ሌላ የሚያነሱት የጥቁሮች ጤና ሁኔታ ቀድሞስ ቢሆን መቼ በጎ ሆኖ ያውቃል የሚለውን ነው። ከመጠን ያለፈ ውፍረት፣ ደም ግፊት እንዲሁም ስኳር ከብሔራዊ አማካይ ቁጥሩ በላይ ጥቁሮች የተጠቁባቸው በሽታዎች ናቸው። የቺካጎ ከንቲባ እንደሚሉት ወትሮም ጥቁር ነዋሪዎቻችን ከነጮች ይልቅ በልብ ህመምና የመተንፈሻ አካላት ጤና መቃወስ የተጎዱ ሕዝቦች ነበሩ። ኮሮናቫይረስ ደግሞ በሽታ ያለበት ሰው ላይ ይጨክናል። ዶ/ር ካሜሮን ዌብ ቨርጂኒያን ወክለው ለኮንግረስ ወንበር የሚወዳደሩ አፍሪካ-አሜሪካዊ ናቸው። ምነው ኮሮናቫይረስ በጥቁሮች ላይ ጨከነ ተብለው ለተጠየቁት የመለሱት የሚከተለውን ነው። "ወረርሽኙ ያጋለጠው ነገር ቢኖር በአሜሪካ የገቢ ልዩነትና የኑሮ ሁኔታ እንዴት በቀለም ላይ መሠረት እንዳደረገ መሆኑን ነው።"
news-56495524
https://www.bbc.com/amharic/news-56495524
ምርጫ 2013፡ ለስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ማን በመራጭነት መመዝገብ ይችላል?
በዛሬው ዕለት፣ መጋቢት 16/2013 ዓ.ም ለስድስተኛው አገራዊ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ በመላው አገሪቱ ይጀመራል።
ምርጫ ቦርድ ግንቦት 28 እና ሰኔ 5/2013 ዓ.ም ለሚካሄደው አገራዊ ምርጫ 50 ሚሊዮን መራጮች ይሳተፋሉ ብሎ እንደሚጠብቅ ከዚህ ቀደም አስታውቆ ነበር። በስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ለመወዳደር 47 የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕጩዎቻቸውን ማስመዝገባቸውን ምርጫ ቦርድ ይፋ ያደረገ ሲሆን እንዲሁም 125 ግለሰቦች በግል ለመወዳደር ተመዝግበዋል። 10 ሳምንት ብቻ በቀረው ስድስተናው አገራዊ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ እስካሁን 8209 እጩዎችን ለክልል እና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መመዝገባቸው ታውቋል። በመራጭነት ለመመዝገብ ምን ያስፈልጋል? እንደ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መረጃ ከሆነ በምርጫ ሕጉ አንቀጽ 18 አዋጅ ቁ. 1162/2011 መሠረት አንድ ሰው በመራጭነት መመዝገብ የሚችለው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ከሆነ እና በምዝገባው ዕለት እድሜው 18 ዓመትና ከዚያ በላይ ከሆነ ነው። በተጨማሪም ለምዝገባ በቀረበበት የምርጫ ክልል ቢያንስ ለ6 ወራት የኖረ መሆን ይኖርበታል። ምርጫ ቦርድ በድረ ገፁ የመራጮች ምዝገባን በማስመልከት ባስቀመጠው መረጃ መሰረት በተለያየ ምክንያት ራሳቸውን ችለው መመዝገብ የማይችሉ ሰዎች በረዳቶቻቸው አማካኝነት በአካል ተገኝተው መመዝገብ እንደሚኖርባቸው አስታውቋል። ለመራጭነት ለመመዝገብ ምን ምን ማሟላት ያስፈልጋል? እንደ ምርጫ ቦርድ መረጃ ከሆን በመራጭነት ለመመዝገብ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወደ ምርጫ ጣቢያው ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ይዞ በአካል መቅረብ ይኖርበታል። የቀበሌ መታወቂያ ካርድ የሌለው ግለሰብ ደግሞ ያልታደሰም ቢሆን ፓስፖርት ይዞ መቅረብ እንደሚችል ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው መረጃ ላይ ተገልጿል። የቀበሌ መታወቂያ ካርድ ማቅረብ ያልቻሉ ተመዝጋቢዎች በቅርቡ ፎቶግራፍ ተደርጎበት የተሰጠ የመንጃ ፈቃድ፣ የመኖሪያ የምስክር ወረቀት፣ ከውትድርና የተገለሉበት ሰነድ፣ የትምህርት ቤት መታወቂያና የመሳሰሉ የመለያ ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። እነዚህ ሁሉ ማስረጃዎች በማይኖሩበት ወቅት መዝጋቢዎች የምርጫ ጣቢያው ለረዥም ጊዜ መኖራቸው የተረጋገጠ ሦስት ነዋሪዎች በሚሰጡት ምስክርነት ማስረጃ አልባውን ተመዝጋቢ ለመለየት ከተቻለ ቃለ ጉባኤ ተይዞ ምዝገባ ይከናወናል። በገጠር አካባቢ በባህላዊና ልማዳዊ ዘዴ ተመዝጋቢውን ለመለየት የሚቻልበት ሁኔታ ካለ እንዲሁ ቃለ ጉባኤ በመያዝ ምዝገባው መከናወን እንደሚቻል ምርጫ ቦርድ አመልክቷል። ማን ለመራጭነት ሊመዘገብ አይችልም? ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዕምሮ ህመም ምክንያት የመወሰን አቅም የሌለው መሆኑ ስልጣን ባለው አካል ወይም በበቂ ማስረጃ የተረጋገጠበት ሰው ለመራጭነት መመዝገብ እንደማይችል በሕግ ተደንግጓል። እንዲሁም የመምረጥ መብቱ በሕግ ወይም አግባብ ባለው ሕግ መሠረት በፍርድ ቤት ውሳኔ የተገደበባቸው ሰዎች በመራጭነት ሊመዘገብ አይችሉም። ለመራጭነት የት መመዝገብ ይቻላል? አንድ መራጭ መመዝገብ የሚችለው በአንድ የምርጫ ጣቢያ ላይ ብቻ ነው። ይህም በሚኖርበት ቀበሌ ላይ በተሰየመ የምርጫ ጣቢያ ላይ መሆኑ በምርጫ ቦርድ ተገልጿል። ከዚያ ባሻገር በአርብቶ አደር አካባቢዎች የምርጫ ጣቢያ ሊኖር የማይችልባቸው አጋጣሚዎች ሲኖሩ እንደ አስፈላጊነቱ አዳዲስ የምርጫ ጣቢያዎች በማቋቋም የመራጮች ምዝገባ ሊከናወን እንደሚችል ምርጫ ቦርድ ይገልጻል። በዚህ ምርጫ በመላው አገሪቱ ድምጽ የሚሰጡባቸው ከ50 ሺህ በላይ የምርጫ ጣቢያዎች፣ ከ152 ሺህ በላይ የመራጮች ምዝገባን የሚያከናውኑ ባለሙያዎችና ከ254 ሺህ በላይ ምርጫ አስፈጻሚዎ እንደሚሰማሩ ተነግሯል። ዛሬ የተጀመረውና ለአንድ ወር ያህል የሚቆው የመራጮች ምዝገባ የሚጠናቀቀው ሚያዚያ 15/2013 ዓ.ም መሆኑን የምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ ያሳያል። ምርጫ 2013 ባለፈው ዓመት ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ወደዚህ ዓመት ከተሸጋገረ በኋላ፤ በመጪው ግንቦት ማብቂያና በሠኔ ወር መጀመሪያ ላይ ለማካሄድ የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶለት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስፈላጊውን ዝግጅት እያካሄደ መሆኑ ይታወቃል። ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ከትግራይ ክልል በስተቀር በሌሎቹ የአገሪቱ ክፍሎች ይካሄዳል በተባለው በዚህ ምርጫ 50 ሚሊዮን መራጮች ማለትም ከአገሪቱ ሕዝብ ወደ ግማሽ የሚጠጋው ድምጽ በመስጠት ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ምርጫ ቦርድ ገልጿል። በምርጫው ከሚሳተፉት 47 የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል በርካታ ቁጥር ያላቸውን ዕጩዎች በማቅረብ በኩል ገዢው ፓርቲ ብልጽግና 2432 ዕጩዎችን በማስመዝገብ ቀዳሚው መሆኑ በመግለጫው ላይ ተመልክቷል። ከዚህ አንጻር ከብልጽግና በመከተል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ዕጩዎች በማስመዝገብ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) 1385 ዕጩዎችን እንዲሁም እናት ፓርቲ ደግሞ 573 ዕጩዎችን አስመዝግበዋል። ሦስቱን ፓርቲዎች ጨምሮ በምርጫው ለመወዳደር በፓርቲና በግል ለመወዳደር ከስምንት ሺህ ሁለት መቶ በላይ ዕጩዎች መመዝገባቸውን ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።
news-42348625
https://www.bbc.com/amharic/news-42348625
'ምስራቅ እየሩሳሌም የፍልስጤም መሆን አለባት'
የአምሳ ሰባት የሙስሊም ሃገራት ስብስብ የሆነው ቡድን መሪዎች ዓለም 'ፍልስጤምን እንደ ራስ ገዝ አስተዳደር እንዲሁም ምስራቅ እየሩሳሌምን እንደ ዋና መዲና' እውቅና እንዲሰጥ አሳስበዋል።
የእስላማዊ ሃገራት ጥምረት ባወጣው መግለጫ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ትራምፕ እየሩሳሌም የእስራኤል መዲና ናት ማለታቸው እርባና ቢስ ትርጉም አልባ ነው ሲሉ ይወቅሳሉ። አልፎም የአሜሪካ ውሳኔ በፍልስጤምና እስራኤል መካከል ስትጫወት ከነበረው የዳኝነት ሚና ጋር የሚጣረስና ከዚህ በኋላም ሊሆን የማይችል ነው ይላል መግለጫው። የፍልስጤሙ መሪ ማሕሙድ አባስ በቅርቡ የተባበሩት መንግሥታት በጉዳዩ ጣልቃ መግባት እንዳለበት ተናግረው እንደነበር ይታወሳል። ጥምረቱ በቱርክ መዲና ኢስታንቡል ባካሄደው ስብሰባ ላይ ድምፃቸውን ያሰሙት አባስ "አሜሪካ ከዚህ በኋላ እንደ ገላጋይ መቀበል አይቻልም፤ ለእስራኤል መወገኗን በግልፅ አሳይታለችና" ብለዋል። "ፍልስጤም ለጉዳዩ ፍትሃዊ መፍትሄ ለማበጀት ከአሜሪካ ጋር ስትሰራ ብትቆይም ትራምፕ ግን የክፍለ ዘመኑን አስደናቂ ድርጊት ፈፅመዋል" ሲሉም ተሰምተዋል አባስ። መግለጫው የትራምፕን ውሳኔ ውድቅ ከማድረጉም በላይ የአሜሪካ ውሳኔ ፍልስጤማውያን ላይ የተፈፀመ ጥቃት ነው ሲል ያትታል። "አሜሪካ ሆን ብላ የእስራኤል-ፍልስጤም የሰላም ሂደት ፉርሽ የሚያደርግ ድርጊት ከመፈፀሟም በላይ ለፅንፈኝነትና ሽብርተኝነት መንገድ እየከፈተችም ነው" ይላል የጥምረቱ መግለጫ። ዋሽንግተን በወሰነችው ውሳኔ ምክንያት ለሚደርሱ ጥፋቶች ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ መሆኗ እንደማይቀርም ጥምረቱ ባወጣው የአቋም መግለጫ አስታውቋል። የዓለም ሃገራት ፍልስጤም እንደ ሃገር መቀበል አለባቸው የሚለው የእስላማዊ ሃገራት ጥምረት የተባበሩት መንግሥታት ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣና ምስራቅ እየሩሳሌምን የፍልስጤም መዲና አድርጎ እንዲያውጅም ያሳስባል። የቢቢሲው ማርክ ሎዌን የጥምረቱ እርምጃ የትራምፕን ውሳኔ ተቃውሞ ከመንገድ ላይ ሰልፎች ላቅ ያለ ቢያደርገውም አሁንም አንዳንድ ሙስሊም ሃገራት የአሜሪካ አጋር በመሆናቸው ተፅዕኖ ፈጣሪነቱ ይህን ያህል ነው ይላል። ምንም እንኳ የቱርኩ ጣይብ ኤርዶዋን ቢገኙም ሳዑዲ አረቢያና ግብፅ ሚኒስትሮቻቸውን ብቻ ነው ወደ ስብሰባው የላኩት ይህም በእስላማዊ ሃገራት ጥምረት መካከል መከፋፈል እንዳለ ማሳያ ነው ይላል ማርክ በትንታኔው። ዋይት ሃውስ የማሕሙድ አባስ የመሰሉ ንግግሮች ናቸው ሁኔታዎችን እያባባሱ ያሉት እንጂ የአሜሪካ ውሳኔ የእስራኤልና የፍልስጤም ሕዝቦችን የሚጠቅም ነው ብሏል። ቤንጃሚን ኔታንያሁ በበኩላቸው የጥምረቱ ስብሰባ እንዳልማረካቸው በመግለፅ "ፍልስጤማውያን እውነታውን በመቀበል ለሰላም ተግተው ቢሰሩ እንደሚሻል" ተናግረዋል።
news-53973218
https://www.bbc.com/amharic/news-53973218
የትግራይ ምርጫ፡ ከ2.7 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ድምፅ ለመስጠት ተመዝግበዋል
በትግራይ ክልል ለሚካሄደው ክልላዊ ምርጫ ከ2.7 ሚሊዮን በላይ ሰዎች መመዝገባቸው ተነገረ።
ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም የትግራይ ክልል ምርጫ ኮሚሽን ኮሚሽነር [ከቀኝ ወደ ግራ የመጀመሪያው] ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በተካሄደው የትግራይ መራጮች ምዝገባ 2,740,888 ሰዎች መመዝገባቸውን የትግራይ ክልል የምርጫ ኮሚሽነር አቶ ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም ገልጸዋል። ባለፈው ሳምንት መመዝገብ ያልቻሉ ሰዎች ቅዳሜ እና እሑድ እንዲመዘገቡ የተደረገ ሲሆን፤ አሁን የመራጮች ምዝገባ መጠናቀቁም ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። የምርጫ ቅስቀሳው ደግሞ አርብ ይገባደዳል ተብሏል። ኮሚሽነሩ እንዳሉት፤ እስካሁን ሦስት የምርጫ ክርክሮች ተካሂደዋል። የመጨረሻው ክርክር ደግሞ በቀጣዩ ሐሙስ ይከናወናል። ምርጫውን ለማስፈጸም አስፈላጊ ግብዓቶች ወደ ምርጫ ጣቢያዎች እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ አቶ ሙሉወርቅ ተናግረዋል። 29 ሺህ 600 የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ቅሬታ ሰሚዎች እና ታዛቢዎች እንደተዘጋጁም አክለዋል። በተጨማሪም ምርጫውን ለመታዘብ ከውጪ የሚመጡ ሰዎች የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር በተቋቋመው ግብረ ኃይል በኩል እንደሚያልፉ ኮሚሽነሩ አስረድተዋል። በትግራይ ክልል 2,672 የምርጫ ጣቢያዎች አለ። በክልላዊው ምርጫ አምስት ፓርቲዎችና አራት የግል ተወዳዳሪዎች ይሳተፋሉ። ምርጫው የሚከናወነው ጷግሜ 4 ቀን 2012 ዓ. ም. ነው።
news-50709913
https://www.bbc.com/amharic/news-50709913
ፊንላንድ በዓለም በእድሜ ትንሿን ጠቅላይ ሚኒስትር መረጠች
የሠላሳ አራት አመቷ የፊንላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳና ማሪን በዕድሜ የዓለም ትንሿ መሪ ሊሆኑ ነው።
በሴቶች የሚመራ ጥምረት መሪ የሆኑት ሳና ማሪን ጠቅላይ ሚኒስትር አንቲ ሪኔ መልቀቃቸውን ተከትሎ ነው ወደሥልጣን የመጡት። የትራንስፖርት ሚኒስትር የነበሩት ሳና ማሪን በፓርቲያቸው ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ ነው የተመረጡት፤ በዚህ ሳምንትም ቃለ ሲመታቸውን ይፈፅማሉ ተብሏል። •ለዓመቱ ምርጥ የታጨችው ኢትዮጵያዊት •ከብራና ወደ ኮምፒውተር . . . በሴቶች የሚመራ የአምስት ፓርቲዎችንም ጥምረት ይመራሉ ተብሏል። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አንቲ ሪኔ ስልጣን የለቀቁት የፖስታ ቤቶች ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማን ተከትሎ ሁኔታውን የተቆጣጠሩበት መንገድ አንዳንድ የጥምረቱ አባላት መተማመን በማጣታቸው ነው ተብሏል። በመቶዎች የሚቆጠሩ የፖስታ ቤት ሰራተኞችን ደመወዝ እቀንሳለሁ ማለታችውን ተከትሎ ሃገር አቀፍ የስራ ማቆም አድማ መትተዋል። ሳና ማሪን ስልጣናቸውን ሲረከቡ የዓለም በዕድሜ ትንሿ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሆኑ፤ እስካሁን ባለው የጠቅላይ ሚኒስትሮች እድሜ የዩክሬኑ ጠቅላይ ሚኒስትር በሰላሳ አምስት አመታቸው፤ የኒውዚላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርን ደግሞ በ39 አመታቸው ይከተላሉ። ጥምረቱ፤ ስልጣን ከተረከቡ በኋላ የነበረውን የሃገሪቱን ፕሮግራሙን እንደሚያስቀጥል ከመስማማቱ አንፃር አዲሷ ጠቅላይ ሚኒስትር ስር ነቀል የፖሊሲ ለውጥ ያመጣሉ ተብሎ አይታሰብም። በጠባብ ልዩነት መንበረ ስልጣኑን ያሸነፉት ጠቅላይ ሚኒስትሯ ግን ሃገሪቷን በተለመደው መልኩ እንደማይመሩ አሳውቀዋል። •አምስቱ ተስፋ የተጣለባቸው አፍሪካውያን ሙዚቀኞች "የነበረውን እምነት ለመገንባት ከፍተኛ ስራ ያስፈልገዋል" በማለት ለሪፖርተሮች ተናግረዋል። ከጋዜጠኞች እድሜያቸውን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄም "እድሜዬም ሆነ ፆታዬ ትዝ ብሎኝ አያውቅም፤ ወደ ፖለቲካ የገባሁበትን ምክንያቶች ነው የማስበው፤ በነሱም ምክንያቶች ማሸነፍ ችለናል" ብለዋል። አዲሷ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳና ማሪን ያደጉት ያለአባት ሲሆን ዩኒቨርስቲም ሲገቡ ለቤተሰቡ የመጀመሪያ ናቸው ተብሏል። በፓርቲያቸው ሶሻል ዲሞክራት የስልጣን እርከን በፍጥነት ወደላይ የወጡት ጠቅላይ ሚኒስትሯ በ27 አመታቸውም ታምፐሬ የምትባለው ከተማ አስተዳዳሪ ለመሆን በቅተዋል። ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣን ከመምጣታቸው በፊትም የትራንስፖርትና ኮሚዩኒኬሽን ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል።
54298119
https://www.bbc.com/amharic/54298119
የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ዘረኛ ሃውልቶች መገርሰሳቸውን ደገፉ
የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጨቋኝ የሚባለውን የነጮች አፓርታይድ አገዛዝን የሚያንፀባርቁ ሃውልቶች እንዲገረሰሱ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል።
ፕሬዚዳንቱ እንዳሉት "ዘረኝነትን ከፍ የሚያደርግ የትኛውም ምልክትም ሆነ ሃውልት እንዲሁም ያንን አስጠሊታ የታሪክ ዘመናችንን የሚያስታውስ ማንኛውም ድርጊት በዲሞክራሲያዊቷ ደቡብ አፍሪካ ቦታ የለውም" በማለት ተናግረዋል። "ያንን የተከፋፈለ የታሪክ ጊዜን ከፍ አድርገው የሚያሳዩ ሃውልቶች ሊነሱ ይገባል" በማለትም በትናንትናው ዕለት አገሪቷ ሄሪቴጅ የተባለውን በዓሏን በምታከብርበት እለት ተናግረዋል። ሄሪቴጅ የተባለው ክብረ በዓል በአገሪቷ ውስጥ ያሉትን የተለያዩ ባህሎችን ቦታ በመስጠትም የሚከበሩበት እለት ነው። የነዚህ ሃውልቶች መገርሰስ ታሪክን የማጥፋት ወይም የመደምሰስ አካል ተደርጎ መታየት እንዳለበት ያስታወሱት መሪው ነገር ግን "በአገሪቱ ውስጥ የተጨቆኑ ህዝቦች ያለፉበትን ሁኔታ ቦታ መስጠትና ለነሱ ማሰብ ያስፈልጋል" ብለዋል። አክለውም "ሃውልቶቹን ለመገርሰስ ማሰባችን ይቅርታ የምንጠይቅበት አይደለም ምክንያቱን የምንተባበርባት አገርን መፍጠር ስለምንፈልግ ነው" ብለው አፅንኦት ሰጥተዋል። ዘረኛውንና ጨቋኙን የአፓርታይድን አገዛዝ የሚወክሉ ሃውልቶችን ለመገርሰስ በባለፉት አመታት ከፍተኛ ዘመቻ እየተካሄደ ነው። ከዚህ ቀደም በደቡብ አፍሪካዋ ኬፕታውን የእንግሊዛዊውን ቅኝ ገዥ ሰሲል ሮድስ ሃውልት ጭንቅላት መቆረጡ ይታወሳል።። በነጭ ፖሊስ ተደፍቆ የተገደለውን ጥቁር አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎይድን ሞት ተከትሎ የበርካታ ባርያ ፈንጋዮች፣ ጨፍጫፊዎችና ዘረኞች ሃውልት ተገርስሷል። ከዚህም በተጨማሪ በመላው አለምም ከፍተኛ ተቃውሞንም አቀጣጥሏል። ነጭ ፅንፈኛውና ዘረኛው ሮድስ የእንግሊዝን ቅኝ ግዛት በ19ኛው ክፍለ ዘመን የመራ ሲሆን፤ ደቡብ አፍሪካንም እንደ ሰም አቅልጦ በመግዛት ማዕድኗን በዝብዟል፤ ሃብትንም አፍርቷል። በርካቶችም የኢምፔሪያሊዝምና የዘረኝነትም ሃውልት ስለሆነ ሃውልቱ ይገርሰስ በሚልም ዘመቻ ተደርጓል። የሮድስ ማስታወሻ ሃውልት በኬፕታውን የቆመው በጎርጎሳውያኑ 1912 ነበር። ሃውልቱ መጀመሪያ ላይ ጉዳት የደረሰበት በጎርጎሳውያኑ 2001 ሲሆን ቀይ ቀለምም ተደፍቶበት ነበር። ከሶስት አመት በፊትም አፍንጫው ተቆርጦ እንደገና ታድሷል። በኬፕታውን ዩኒቨርስቲ የሚገኘው የቀድሞው ቅኝ ገዥ ሃውልት በጎርጎሮሳውያኑ 2015 "ጨፍጫፊዎችና ቅኝ ገዥዎች መውደቅ" አለባቸው የሚለውን ከፍተኛ ተቃውሞ እንዲገረሰስ ተደርጓል። በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ታሪክ ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠው ጨካኙ ሮድስ በስሙም የአሁኗን ዚምባብዌ የቀድሞዋን ሮዴዥያ በሚልም ገዝቷል። እንግሊዛውያን ከሁሉም ዘሮች የተመረጡ ናቸው የሚልም ጭፍንና ጠባብ ነበርም ይባላል። ደቡብ አፍሪካና ዚምባብዌ በነጭ አናሳዎችም ለዘመናት ተገዝተዋል፤ ተጨፍጭፈዋል። ከዚህ በተጨማሪ በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ የሚገኘው ሃውልትም ይገርሰስ ጥያቄዎች በርክተዋል።
news-56697410
https://www.bbc.com/amharic/news-56697410
ሕዳሴ ግድብ፡ ኢትዮጵያ የውሃ ሙሌት ከመጀመሯ በፊት ግብጽና ሱዳን ባለሙያ እንዲሰይሙ ጠየቀች
ሁለተኛው ዙር የታላቁ የሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ከመጀመሩ በፊት መረጃ ለመለዋወጥ እንዲቻል ሱዳንና ግብጽ ባለሙያዎችን እንዲሰይሙ የኢትዮጵያ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጠየቀ።
በመጀመሪያው ዙር የውሃ ሙሌት ወቅት ተነሳ የሳተላይት መስል ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ (ዶ/ር፣ ኢንጂ.) ለአገራቱ የውሃ ጉዳዮች ሚኒስቴሮች በጻፉት ደብዳቤ ላይ ቀጣይ ግድቡን በውሃ የመሙላት ሥራው በመጪው የክረምት ወራት ውስጥ እንደሚከናወንና ከዚህ በፊት በተደረሰው ስምምነት መሰረት አስፈላጊውን መረጃ ለመስጠት እንዲቻል ባለሙያዎቻቸውን እንዲያሳውቁ ጠይቀዋል። ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በታላቁ የሕዳሴው ግድብ የውሃ አሞላልና ቀጣይ ሂደት ላይ ለዓመታት ሲያካሂዱት የነበረው ድርድር ቀጣይ ዙር ተካሂዶ ያለውጤት ከተጠናቀቀ ከቀናት በኋላ ነው ኢትዮጵያ ግብዣውን ያቀረበችው። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ለሦስት ቀናት የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበር በሆነችው በዲሞክራቲክ ኮንጎ ሰብሳቢነት ኪንሻሳ ውስጥ የተካሄደው ድርድር ያለ ውጤት ከተጠናቀቀ በኋላ ኢትዮጵያ ስለሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት ሱዳንና ግብጽ መረጃ ለመለዋወጥ እንዲያመች ባለሙያዎቻቸውን እንዲያሳውቁ ጠይቃለች። ከኢትዮጵያ በኩል የቀረበው ጥሪ የሦስቱ አገራት ገለልተኛ ብሔራዊ የሳይንስ ቡድን አማካይነት በተደረሰው ስምምነት በወጣው ግድቡን በውሃ የመሙላት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት መሆኑን ገልጾ፤ የውሃ ሙሌቱም በሐምሌና በነሐሴ ወር የሚከናወን ሲሆን የዝናቡን ሁኔታ ከግምት በማስገባትም የመስከረም ወርን ሊጨምር እንደሚችል አመልክቷል። የሕዳሴ ግድብ የደረሰበትን ግንባታ ሂደትና የውሃ ሙሌቱ የሚካሄድበት የኢትዮጵያ ክረምት ወቅት መቃረቡን በመጥቀስ ተግባራዊ ጉዳዮች ዙሪያና በአስፈላጊ የግንኙነት መስኮች ላይ በጋራ የመሥራትን አስፈላጊነትን የኢትዮጵያ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር በደብዳቤው ላይ ጠቅሷል። ሱዳንና ግብጽ ለመረጃ ልውውጥ አስፈላጊ የሆኑ ባለሙያዎችን መሰየማቸው በአፍሪካ ሕብረት ጥላ ስር የሚካሄደው የሦስትዮሽ ድርድር መቋጫ አስኪያገኝ ድረስ አስፈላጊ የመረጃ ልውውጥ መስመርን ለማመቻቸትና መተማመንን ለመገንባት ይጠቅማልም ብሏል ሚኒስቴሩ። ከዚህ ቀደም ሱዳንና ግብጽ ኢትዮጵያ ሁለተኛውን ዙር የግድቡን ውሃ ሙሌት ከማከናወኗ በፊት ሕጋዊና አሳሪ ስምምነት ላይ መደረስ እንዳለበት ሲጠይቁ ቢቆዩም ይህ በኢትዮጵያ በኩል ተቀባይነትን አላገኘም። ባለፈው ማክሰኞ ካለውጤት ከተጠናቀቀው የኪንሻሳው ድርድር በኋላ የኢትዮጵያ ውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የግድቡን አሞላል፣ ውሃ አያያዝ እንዲሁም አለቃቀቅን በተመለከተ ከስምምነት ለመድረስ ኢትዮጵያ ዝግጁ እንደሆነች ጠቅሶ ነበር። ነገር ግን ግብጽና ሱዳን "ድርድሩ የኢትዮጵያን የውሃ ድርሻ የሚገድብና አለን የሚሉትን የውሃ ክፍፍል የሚያፀ አስገዳጅ ስምምነት ካልተደረሰ የሚል አቋም በመያዛቸው" ከውጤት አለመደረሱን ገልጿል። ጨምሮም ግብጽና ሱዳን በተደጋጋሚ ሲሉት የነበረውን አስገዳጅ ስምምነት ሳይደረግ የግድቡ ሙሌት መከናወን የለበትም የሚለው ሃሳብ "የሕግ መሠረት የሌለውና ኢትዮጵያ የላትን የተፈጥሮ ሃብት የመጠቀም መብት የሚጋፋ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም" በሚል ውድቅ አድርጋጎታል። ግንባታው ከተጀመረ አስረኛ ዓመቱን የያዘው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውሃ አሞላልና ቀጣይ የሥራ ሂደትን በተመለከተ በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በግብጽ መካከል ለዓመታት ሲካሄድ የቆየው ድርድር ውጤት ሳያስገኝ እስከአሁን ዘልቋል። የአፍሪካ ሕብረት የሚያሸማግለው ይህ ድርድር ቀደም ሲል በአዲስ አበባ፣ በካርቱም፣ በካይሮና በዋሽንግተን ላይ የሦስቱ አገራት ልዑካን ተገናኝተው ሲካሄድ የቆየ ሲሆን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ ተቋርጦ ከቆየ በኋላ በበይነ መረብ አማካይነት ቀጥሎ ነበር። ኢትዮጵያ አምስት ቢሊየን የሚጠጋ ዶላር አውጥታ እየገነባችው ያለው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሊጠናቀቅ 20 በመቶ ያህል የቀረው ሲሆን፤ የግድቡ ግንባታ ሲጠናቀቅ በአፍሪካ ካሉ ግዙፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎች ሁሉ ቀዳሚው ይሆናል ተብሏል። ግድቡ ተጠናቅቆ ሙሉ ለሙሉ ሥራውን ሲጀምር ከ5 ሺህ ሜጋ ዋት በላይ ኤሌክትሪክ የማመንጨት አቅም አለው። ግድቡ ባለፈው ዓመት የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት ያደረገ ሲሆን ሁለተኛውን ዙር ደግሞ በመጪው ክረምት እንደሚከናወን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል። ወደ 80 በመቶ የሚጠጋው የግድቡ የግንባታ ሥራ መከናወኑ የተነገረ ሲሆን በመጪው ዓመትም በተወሰነ ደረጃ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ይጀምራል። ግብጽና ሱዳን ግድቡ የውሃ አቅርቦታችንን በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሰዋል በሚል ከግንባታው መጀመር አንስቶ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ቢቆዩም፤ ከግማሽ በላይ ለሚሆነው ሕዝቧና እያደገ ላለው የኢንዱስትሪ ዘርፏ ኤሌክትሪክ ለማቅረብ ዋነኛ ግቧ አድርጋ የተሳችው ኢትዮጵያ በግንባታውና ቀጥላ ወደ ማጠናቀቁ ተቃርባለች። የግብጽና የሱዳን መንግሥታት ከፍተኛ ባለስልጣናት በተለያዩ አጋጣሚዎች ኢትዮጵያ እየገነባችው ባለው ግድብ ሳቢያ አገሮቻቸው ከወንዙ በሚያገኙት የውሃ መጠን ላይ የሚፈጠርን ማንኛውም ተጽእኖ እንደማይቀበሉት ሲገለጹ ቆይተዋል። የግብጹ ፕሬዝዳንት አቡዱል ፋታህ አል ሲሲም በዚህ ሳቢያ 'የከፋ አካባቢያዊ ችግር' ሊፈጠር ይችላል ሲሉ መስጠንቅቃቸው ይታወሳል። ፕሬዝዳንቱ "ማንም ከግብጽ ውሃ ላይ አንዲት ጠብታ መውሰድ አይችልም፤ ይህ ከሆነ ደግሞ ከሚታሰበው በላይ አደገኛ አለመረጋጋት በአካባቢው ይፈጠራል" ብለው ነበር። ኢትዮጵያ ግድቡን የምትጠቀመው ውሃውን በግዛቷ ውስጥ ለሚያስቀሩ ፕሮጀክቶች እንዳልሆነ በተደጋጋሚ ብታስረዳም ሱዳን በተለይም ግብጽ የትኛውም አይነት በውሃው ላይ የሚከናወን ሥራ የእነሱን ስምምነት ሳያገኝ መካሄድ እንደሌለበት ሲገልጹ ቆይተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ በአገሪቱ ምክር ቤት ላይ ባደረጉት ንግግር "ውሃ አሞላሉን በተመለከተ ተደራድረን ስናበቃ እንሙላ ካልን ክረምቱ ያልፍና በዓመት 1 ቢሊየን ዶላር እናጣለን" ሲሉ የውሃ ሙሌቱን ማዘግየት እንደማይቻል አመልክተዋል። የኢትዮጵያ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር የሆኑት ስለሺ በቀለ (ዶ/ር፣ ኢንጂ.) ኢትዮጵያ ወደ መጠናቀቁ የተቃረበውን የሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በምንም ዓይነት መልኩ እንደማታራዝመውና ለዚህም የሚያበቃ አሰራርና ምክንያትም እንደሌለ ተናግረዋል።
news-51019598
https://www.bbc.com/amharic/news-51019598
በ23 ዓመቱ የህክምና ትምህርቱን ያጠናቀቀው ዶ/ር አቤኔዘር ብርሃኑ
ጓደኞቹ 'ጢቆ' ይሉታል- ትንሽ እንደማለት። አንዳንዶች ደግሞ ያንግ [Young] የሚል ቅፅል አክለው 'ዶ/ር ያንግ' እያሉ ይጠሩታል። እናቱ በቤት ስሙ 'ቤቢ' ነው የሚሉት።
የህክምና ዶክትሬቱን ያጠናቀቀው በ23 ዓመቱ ነው። በተለመደው የእድሜ አሰላል እዚህ ማዕረግ ላይ ከሚደረስበት በሦስት ዓመታት ያንሳል። ዶክተር አቤኔዘር ብርሃኑ። • ወገኖቹን ለመርዳት ጠመኔ የጨበጠው ኢትዮጵያዊው ሐኪም • የራሱን ዘር ተጠቅሞ ታካሚዎቹን ያስረገዘው ዶክተር እናቱ መምህር፤ አባቱ ደግሞ የህክምና ባለሙያ ናቸው። ወላጆቹ ሥራ ላይ ስለሚውሉ በርካቶች የሚፈተኑበት ሁነኛ የልጆች ሞግዚት እጦት የእነርሱንም ቤት አልዘለለም። ይሁን እንጅ እናቱ ሥራቸውን ለመልቀቅም ሆነ፤ ልጃቸውን ለጎረቤት አደራ ብለው መተው አልተዋጠላቸውምና ከእርሳቸው ጋር ትምህርት ቤት ይዞ ለመሄድ መፍትሔ ሻቱ። ለቤተሰቡ ሦስተኛ ልጅ የሆነው አቤኔዘር ያኔ የ4 ዓመት ህፃን ነበር። አቤኔዘርም ከእናቱ ጋር እየሄደ የፊደልን ገበታ በጠዋቱ መቁጠር ጀመረ። በእርግጥ ታላላቆቹም እንደ እርሱ አይሁን እንጅ፤ አንደኛ ክፍልን የጀመሩት በ5 እና 6 ዓመት እድሜያቸው ነው። ታናናሾቹም እንዲሁ። ታዲያ ቤተሰብ ከፍተኛ ክትትልና ቁጥጥር ያደርግላቸዋል። በተለይ እናቱ መምህር በመሆናቸው ከእርሱ አስተማሪዎች ጋር በመነጋገር፤ ድክመቱን በመረዳት ለሚከብዱት የትምህርት ዓይነቶች አጋዥ መፅሐፍ በመግዛት፣ ከፍ ያሉ ጎበዝ ተማሪዎች እንዲያስተምሩት በማድረግ ይደግፉት ነበር። ምክራቸውም አይለየውም። "የምትፈልጉትን ነገር መሆን ትችላላችሁ፤ ሁሉም ነገር ተሰጥቷችኋል" እያሉ ያበረታቷቸው ነበር። ይህ በሁሉም ልጆች ሕይወት ውስጥ ውጤት አሳይቷል። • የሙያውን ፈተና ለመጋፈጥ ከከተማ ርቆ የሄደው ሐኪም አቤኔዘር የህልሙን ነው የሆነው። ፍላጎቱ በህክምና ሙያ ላይ መሰማራት ነበር። አቤኔዜር ባደገባት ከሚሴ ከተማ በተለይ በወቅቱ የጤና መሠረተ ልማት የተሟላ አልነበረም። የህክምና ባለሙያዎችም እጥረት እንደዚያው። ታዲያ በዚያ የህክምና ባለሙያዎች ብርቅ በሆኑበት ወቅት፤ በአካባቢው የሚያያቸው ዶክተሮች ቀልቡን ይይዙት ነበር። እኔም የእነርሱን ፈለግ መከተል አለብኝ አለ፤ ምሳሌዎቹም እነርሱ ሆኑ። በእርግጥ ይህ ምኞት የእናቱም ይመስላል። አቤኔዘር እንዳጫወተን እናቱ ባለቤታቸው ሐኪም በመሆናቸውም ይመስላል ጥሎባቸው ሐኪም ይወዳሉ። እርሱም ዶክተር በመሆኑ እጅግ ደስተኛ ናቸው። የፊዚክስና የሂሳብ ትምህርቶችን አብዝቶ የሚወደው አቤኔዘር፤ በህክምና ሙያ ላይ ባይሰማራ ራሱን መካኒካል መሀንዲስ ሆኖ ሊያገኘው እንደሚችል ይናገራል። ግኝቶችን መፍጠር፣ ለሰዎች አስተዋፅኦ ማድረግን ይመኝ ነበር። ተግባር ለሚበዛባቸው ሙያዎች የተሰጠ ነው። ይሁን እንጅ ህልሙ ተሳክቶለት ራሱን የህክምናው ሙያ ላይ አግኝቶታል። "የልጅነት ጊዜ ጨዋታ. . ." የልጅነት ጊዜ ጨዋታ አይጠገብም። እንኳንስ ልጅ ሆነውና አዋቂም ሆኖ ትዝታው አይለቅም። እድሉ ከተገኘ እርጅናም አያስቀረው። አቤኔዘር የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን የጀመረው በአራት ዓመቱ ነው- ጉልበቱ ሳይጠና፣ በመዋዕለ ህፃናት ትምህርትን ሳይለማመድ። ታዲያ ልቡ ወደ ጨዋታው ያመዝን ነበር። በተለይ እግር ኳስን የሚያህልበት የለም። በሰፈራቸው ባቋቋሙት የእግር ኳስ ቡድን ጎል ጠባቂ ነበር። "ለቡድኑ እጅግ አስፈላጊ ሰው ነበርኩ" ይላል። ቡድኑ በብቃቱ ስለሚተማመንበት፤ ከየትም ተፈልጎ ይመጣል እንጅ የእርሱን ምድብ የሚይዝ አልነበረም። በመሆኑም ራሳቸው ከቆርኪና ሽቦ የሰሩትን ዋንጫ በተደጋጋሚ አንስተዋል። በእግር ኳስ ቡድናቸው ውስጥ የነበሩት ጓደኞቹ በትምህርታቸው ለስኬት የበቁ ናቸው። ትምህርቱን አቋርጦ አልባሌ የሕይወት መንገድ ላይ የቆመ እምብዛም የለም። ይህ መሆኑም ለትምህርቱ ያለው ትኩረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ብርታት ሆኖታል። ከዚህም በተጨማሪ ከቤተሰብ ጠበቅ ያለ ቁጥጥር ይደረግበት እንደነበር ያስታውሳል። "ጊዜህን በማይሆን ቦታ አታሳልፍ" የሚነገረው የዘወትር ምክር ነው። በትምህርቱ ጠንክሮ በ10ኛ ክፍል ትምህርቱ 4 ነጥብ ነበር ያስመዘገበው። 12ኛ ክፍልም ላይ ያስመዘገበው ውጤት ከፍተኛ ነበር። ጂማ ዩኒቨርሲቲ ተመድቦ ሲገባ የ16 ዓመት ታዳጊ ነበር። በዚህ እድሜው ከቤተሰብ ተነጥሎ ሲወጣ የመጀመሪያ ጊዜው በመሆኑ ውስጡን ፍርሃት ገብቶት ነበር። ይሁን እንጅ ቀደም ብሎ ታላቅ ወንድሙ እዚያው ዩኒቨርሲቲ ተመድቦ ስለነበር ጭንቀቱን አቅልሎለታል፤ በእያንዳንዱ እንቅስቃሴው ከጎኑ አይጠፋም። እንደ ህፃን ነበር የሚንከባከበው። በተለይ ተማሪዎች፣ መምህራን እና የጥበቃ ሠራተኞቹ እንደ ተማሪ ስለማያምኑት በወጣ በገባ ቁጥር እነርሱን ማስረዳቱም ሌላ ጣጣ ነበር። • "የሚያክሙን ሙዚቃዎች እንዳሉ ሁሉ የሚያውኩንም አሉ" ዶ/ር መልካሙ ይህ ብቻም ሳይሆን መንገዱን የሚያስቱ አሉታዊ የአቻ ግፊቶች እዚያም አልጠፉም፤ ነገር ግን ራሱን በመቆጠቡና ጓደኞቹን በመምረጡ መሰናክሎቹን አልፎ ከዓላማው እንደደረሰ ያስረዳል። "ሰውን በገፁ መፅሐፍትን በሽፋናቸው. . ." ሰዎችን በአለባበሳቸው፣ በሰውነት አቋማቸው፣ በመልካቸው፣ ባላቸው የሐብት መጠን፣ እንዲሁም በእድሜያቸው ማንነታቸውን የመለካት ግምታዊ አስተሳሰብ በማህበረሰብ ዘንድ ሰርጎ የገባ አጉል ልማድ ይመስላል። በተለያዩ ጊዜያትም በተለይ ወጣት አመራሮች ከሚያነሱት ችግር አንዱ ለሥራ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ አመኔታ መነፈጋቸው ነው። አቤኔዘርም የዚሁ አስተሳሰብ ዳፋ ከሚያርፍባቸው ወጣቶች አንዱ ነው። ለዚህ ማሳያ በርካታ ገጠመኞች ቢኖሩትም፤ ለአብነት አንዱን ያስታውሳል። ነገሩ እንዲህ ነው። አንዲት ታማሚ ለሕክምና ክትትል ወደ ሐኪም ቤት ትሄዳለች። በወቅቱ አቤኔዘር ከአንድ ጓደኛው ጋር በመሆን ሥራው ላይ ተሰይሟል። ወደ ጤና ተቋሙ ለመጣችው ታማሚ ባልደረባው ምርመራውን ካደረገ በኋላ፤ መድሃኒት እንዲፅፍላት ለእርሱ ይነግረዋል። ታማሚዋ ግን በእርሱ ላይ እምነት አልጣለችበትም ነበር። "ህፃን እኮ ነው! ሊሳሳት አይችልም ወይ?" ስትል አመነታች። ያኔ ሴትዮዋን ለማሳመን በርካታ ጥረቶች እንዳደረገ የሚዘነጋው ጉዳይ አይደለም። እርሱ እንደሚለው የሰውን ማንነት መረዳት የሚቻለው በሚሰራው ሥራ፣ ባለው እውቀት እና በሙያው መሆን አለበት። በተለይ እርሱ በተሰማራበት የሕክምና ሙያ ከህሙማን ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት በመተማመን ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት። ህክምናው የሚጀምረውም በመተማመን ላይ በመመስረት ነው። አመኔታ ከሌለ ውጤቱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ስለሚያሳድር ሰዎች በአካል፣ በቁመና እና በዕድሜ ሳይሆን በተሰጣቸው ሙያ፣ በሚሰሩት ሥራ ሰውን መመዘን እንደሚገባ ያስረዳል። "ወደፊትም መሰል ፈተናዎች ሊገጥሙኝ ይችላሉ" የሚለው አቤኔዘር፤ ፈተናዎቹን ለመጋፈጥ ግን መዘጋጀቱን ያስረዳል። ቀጣይ ጉዞ ከአንድ ወር በኋላ በሕክምና ዶክትሬቱን የሚቀበለው የ23 ዓመቱ አቤኔዘር፤ ወደፊት በቀዶ ህክምና ስፔሻላይዝ የማድረግ ፍላጎት አለው። ቀዶ ህክምና የተለየ ክህሎት የሚጠይቅ በመሆኑና ክህሎትን የሚጠይቁ ሥራዎች ላይ ፍላጎት ስላለው ለዚህ ዘርፍ ከፍተኛ ፍላጎት አለው። ጅማ ዩኒቨርሲቲ በሚሰራበት ወቅትም በዘርፉ ላይ የሰዎች እጥረት መኖሩን በመረዳቱ፤ የበኩሉን ለማበርከት የተቻለውን እንደሚያደርግ ሃሳብ ሰንቋል።
news-50669175
https://www.bbc.com/amharic/news-50669175
ህንድ፡ የአስገድዶ መደፈር ጉዳዩዋን ለመከታተል ፍርድ ቤት የሄደችው ወጣት በእሳት ተቃጠለች
የአስገድዶ መደፈር ጥቃት እንደደረሰባት ገልጻ ጉዳይዋን በፍርድ ቤት ስትከታተል የነበረችው የ23 ዓመቷ ህንዳዊት ወጣት በመንገድ ላይ በእሳት መቃጠሏ ተሰምቷል።
በሰሜናዊ ህንድ ኡታር ፕራዴሽ በምትባለው ግዛት ውስጥ የምትኖረው ወጣት ባለፈው መጋቢት ወር ነበር ሁለት ወንዶች አስገድዶ የመድፈር ጥቃት አድርሰውብኛ ብላ ክስ የመሰረተችው። ጉዳይዋን ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት በመሄድ ላይ እያለች ጥቃት ፈጻሚዎች በእሳት እንድትቃጠል በማድረግ ወጣቷ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባት በሞትና በህይወት መካከል እንደምትገኝ ተገልጿል። • በህንድ በቡድን ተደፍራ የተገደለችው ዶክተር ጉዳይ ከፍተኛ ቁጣን ቀሰቀሰ • ሺህ ቃላት ከሚናገረው ፎቶ ጀርባ ያለው እውነታ ፖሊስም ከጥቃቱ በኋላ ወጣቷን መንገድ ላይ ጠብቀው በእሳት አቃጥለዋል ተብለው የተጠረጠሩ አምስት ግልሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የገለጸ ሲሆን፤ ከተጠርጣሪዎቹ መካከል አንደኛው በአስገድዶ መድፈር ክስ የቀረበበት ግለሰብ ነው ብሏል። የአካባቢው መገናኛ ብዙሃ እንደዘገቡት ወጣቷ ወደ ፍርድ ቤት ለመሄድ ባቡር ልትሳፈር ስትል ነው ተጠርጠሪዎቹ እየገተቱ ወደ አንድ የሰብል ማሳ ወስደው በእሳት ያቃጠሏት። ይህ አሳዛኝ ዜና ሲሰማ ብዙ ህንዳውያን ቁጣቸውን የገለጹ ሲሆን ባለፈውም ሳምንት በተመሳሳይ በደቡባ ህንድ የምትኖር አንዲት የ27 ዓመት ወጣት ተገዳ ከተደፈረች በኋላ በእሳት መቃጠሏም ተነግሯል። • በህንዷ ዴልሂ በአየር ብክለት ምክንያት 5 ሚሊየን ማስኮች እየተከፋፈሉ ነው በህንድ በፈረንጆቹ 2012 አንዲት ሴት የህዝብ ማመላለሻ ውስጥ ተገደድዳ ከተደፈረች በኋላ አስገድዶ መድፈርና ሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃት ከፍተኛ ትኩረት እያገኙ ቢመጡም ወንጀሎቹ ግን እየቀነሱ አልመጡም። በመንግሥት የወንጀል መረጃ መሰረት እ.አ.አ. በ2017 ህንድ ውስጥ ፖሊስ 33 ሺህ 658 የአስገድዶ መድፈር ክሶችን ተቀብሏል፤ ይህ ደግሞ በእያንዳንዱ ቀን 92 ሴቶች ተገደው ይደፈራሉ ማለት ነው።
news-49246184
https://www.bbc.com/amharic/news-49246184
በሶማሌና በኦሮሚያ ክልል የውይይት መድረክ ላይ ምን ተነሳ?
ባለፉት ጥቂት ዓመታት በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልል አጎራባች ቀበሌዎች በተፈጠሩ ግጭቶች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸው ይታወሳል። ግጭት ተፈጥሮ የነበረባቸው አካባቢዎች ወደ መረጋጋት መመለሳቸውን ተከትሎ፤ ቀላል የማይባሉ የሁለቱም ክልል ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ተመልሰዋል።
የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በሁለቱ ክልሎች አጎራባች አካባቢዎች ተከስቶ በነበረው ግጭት የተፈጠረውን ቁስል የማዳን እና የሁለቱን ሕዝቦች ግንኙነት ወደ አዲስ ምዕራፍ የማሸጋገር ኃላፊነት የእነሱ እንደሆነ ይናገራሉ። ባለፉት ሦስት ዓመታት በግጭቶች ሳቢያ ተዘግተው የነበሩት መንገዶች መከፈታቸውን የሚያስረዱት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፤ "ተፈናቅለው የነበሩ ሰዎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ አድርገናል። በተለየ መልኩ ደግሞ በሁለቱ ሕዝቦች መካከል የነበረው የንግድ እንቅስቃሴዎች ወደ ቀድሞ ሁኔታዎች ተመልሰዋል" ብለዋል። • "የክልሎች ልዩ ኃይልን በተመለከተ ውይይት ያስፈልጋል" የሶማሌ ክልል ም/ፕሬዝደንት • ቴክቫህ ኢትዮጵያ፡ የፀረ ጥላቻ ንግግር የወጣቶች እንቅስቃሴ ምክትል ፕሬዝደንቱ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ሥራው በፍላጎት ላይ የተመሰረት መሆኑን አስምረው ይናገራሉ። "ተፋናቃዮችን እንዲመለሱ ያደረግናቸው በሙሉ ፍላጎታቸው ላይ በመመስረት ነው። ማንም ያለ ፍላጎቱ እንዲመለስ አልተደረገም፤ ነገር ግን ለመመለስ ያልፈለጉ አሉ" ሲሉ ተናግረዋል። ወደ ቀያቸው የተመለሱ ተፈናቃዮችን ለመደገፍ መንግሥት የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ ነው የሚሉት ምክትል ፕሬዝደንቱ፤ "ምርጥ ዘር እያቀረብን ነው። ከብድር አገልግሎት በተጨማሪ አስፈላጊ ፍላጎቶችን እያሟላን ነው" በማለት እነዚህ ድጋፎች ወደ ሁለቱም ክልሎች ለተመለሱ ተፈናቃዮች እየተደረጉ መሆኑን ገልፀዋል። ምንም እንኳ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ቢመለሱም ከዚህ ቀደም ወደነበራቸው የኑሮ ዘይቤ መመለሱ ግን ጠንከር ያለን ሥራ ይጠይቃል ብለዋል። የድንበር ይገባኛል ግጭቶች በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ ለሚከሰቱ ግጭቶች እንደ ምክንያትነት ተደርገው ሲቀርቡ ከነበሩት መካከል የድንበር ይገባኛል ጥያቄ አንዱ እንደሆነ ይነገራል። ከድንበር ጋር ተያይዞ ለሚነሱ ጥያቄዎች ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ሕዝበ ውሳኔ ይካሄዳል ተብሎ ነበር። ሕዝበ ውሳኔውን ለማካሄድ የኦሮሚያ ክልል ምን እየሠራ ነው የተባሉት ምክትል ፕሬዝደንቱ "ግጭቶችን ለመፍታት መፍትሄ የሚሆነው ህዝበ ውሳኔ ማካሄድ ወይም ድንበር ማካለል አይደለም። ከዚህ ቀደም ለተከሰቱ ችግሮች ምክንያቱ ድንበር አይደለም" ሲሉ ተናግረዋል። ተመሳሳይ ጥያቄ ቀርቦላቸው የነበሩት የሶማሌ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሙስጠፌ ሙሐመድም በተመሳሳይ መልኩ ከዚህ ቀደም ለተከሰቱት ግጭቶች ምክንያቱ የድንበር ጉዳይ አለመሆኑን ተናግረው ነበር። • "ህዝብ ከህዝብ ሊጋጭ አይችልም" አቶ ሽመልስ አብዲሳ "በመጀመሪያ ደረጃ ባለፉት ዓመታት ለተከሰቱት ግጭቶች ምክንያቱ የግጦሽ መሬት ወይም የድንበር ጉዳዮች አልነበሩም። የመንግሥት መዋቅር ያለበት አሻጥር ነው ሕዝቡን ክፍተኛ ችግር ውስጥ የከተተው እና ያፈናቀለው።" በማለት ምክትል ፕሬዝደንት ሙሰጠፌ ለቢቢሲ ገልፀው ነበር። ምክትል ፕሬዝደንት ሽመልስ በተመሳሳይ መልኩ ለግጭቶቹ መቀስቀስ እንደ ምክንያትነት የሚያቀርቡት "የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚፍጨረጨሩ የፖለቲካ ደላሎች" ያሏቸውን ነው። በመሆኑም በሶማሌ እና በኦሮሞ ሕዝቦች መካከል ለተከሰተው ግጭት ዘላቂ መፍትሄ የሚሆነው የሕዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ጥያቄ ምላሽ መስጠትና የሁለቱን ሕዝቦች አንድነት ማጠናከር መሆኑን ያነሳሉ። "ይህ ቢሆን አይደለም ለሁለቱ ክልሎች ለአፍሪቃ ቀንድም ይተርፋሉ" ብለዋል -አቶ ሽመልስ። የሞያሌ ነገር ኢትዮጵያን ከኬንያ የምታዋስነዋ ከተማ- ሞያሌ፤ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች መካከል በተደጋጋሚ የይገባኛል እሰጥ አገባዎች አልፎ አልፎም ግጭቶችን አስተናግዳለች። በዚህም የተነሳ የሰው ሕይወት ጠፍቷል፤ ንብረት ወድሟል። ለዚህ ችግር መፍትሄ ለማበጀት ምን እየተሰራ ነው በማለት ለሶማሌ ክልል ፕሬዝደንት ጥያቄ በቀረበላቸው ወቅት "ቅድሚያ የምንሰጠው ለሰላም ነው . . . በአሁኑ ወቅት ግጭቶች የሉም። በሞያሌ ከተማ ዙሪያ ከአካባቢው ነዋሪዎች፣ ኦሮሚያ እና ከፌደራል መንግሥት ጋር በመወያየት መፍትሄ እንሰጣለን እንጂ፤ በአሁን ላይ መፍትሄው ይህ ነው ብዬ ለመናገር ይከብደኛል" ብለው ነበር። የኦሮሚያ አቻቸው አቶ ሽመልስ አብዲሳ በበኩላቸው፤ "በሶማሌ ክልል የአስተዳደር ሪፎርም ከተካሄደ ወዲህ በሞያሌ ከተማ ሰላም ሰፍኗል" ካሉ በኋላ አክለውም "ትኩረታችን በአካባቢው ያለው የንግድ እንቅስቃሴን ማስቀጠል ነው። የተቀረው ግን በጊዜ ሂደት መፍትሄ የሚያገኝ ይሆናል" በማለት ተመሳሳይ ምላሽ ሰጥተዋል። • ለዓመታት የተጠፋፉት የወላይታ ሶዶዋ እናትና የኖርዝ ኬሮላይናዋ ልጃቸው በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች መካከል ከፍተኛ የሆነ የንግድ ልውውጥ እንደሚደረግ ምክትል ፕሬዝደንት ሽመልስ ይናገራሉ። ጫት፣ እህል እና የቁም ከብት ከኦሮሚያ ወደ ሶማሌ ክልል የሚላኩ ሲሆን፤ በተቃራኒው ሸቀጦች፣ ዘይት እና በፋብሪካ የተቀነባበሩ እንደ ፓስታ እና መኮሮኒ ያሉ የታሸጉ ምግቦች ከሶማሌ ወደ ኦሮሚያ ከሚገቡ ምርቶች መካከል ይጠቀሳሉ። ተከስቶ በነበረው ግጭት መንገዶች በመዘጋታቸው በሁለቱ ክልሎች መካከል የነበረው ንግድ እጅጉን ተቀዛቅዞ እንደነበረ የሚናገሩት ምክትል ፕሬዝደንቱ፤ የንግድ እንቅስቃሴውን አጠናክሮ ለማስቀጠል፤ ምርቶች የሚገቡበት እና የሚወጡባቸውን የንግድ መስመሮች ለይቶ የማዘጋጀት ሥራዎችን ጨምሮ የተለያዩ እንቅስቃሴች እየተካሄዱ እንደሆነ ተናግረዋል።
news-55883438
https://www.bbc.com/amharic/news-55883438
ትምህርት፡ አራት ሜዳሊያ እና ዋንጫ የተሸለመችው ቆንጂት
ቆንጂት ሐብታሙ ትባለላች። ተወልዳ ያደገችው በሰሜን ሸዋ ጊዳ ሲሆን የከፍተኛ ትምህርቷን ያጠናቀቀችው ዘንድሮ ነው። ቆንጂት በመቱ ዩኒቨርስቲ ቆይታዋ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገቧ ሶስት ሜዳሊያ እና አንድ ዋንጫ ለመሸለም በቅታለች።
ቆንጅት ሐብታሙ ለስኬቷ ምክንያት የሆነውንና የወደፊት እቅዷን በማስመልከት ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ባደረገች ወቅት " ፊደል ካልቆጠሩ የገጠር ቤተሰብ መገኘቴ ለስኬቴ እንቅፋት አልሆነብኝም" ብላለች። "ተወልጄ ያደግኩት ገጠር ነው። ቤተሰቦቼም ፊደል የቆጠሩ አይደሉም። እኔ እንድማር ግን አብረውኝ ለፍተዋል። ከተማረ ቤተሰብ ይልቅ ተምሬ ትልቅ ሰው እንድሆንላቸው ያስቡልኛል" በማለት ቤተሰቦቿ ያደረጉላትን ትገልጻለች። ቆንጂት ከመቱ ዩኒቨርስቲ በአፕላይድ ባዮሎጂ የትምህርት ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገቧ የተለያዩ ሽልማቶችን ለማግኘት በቅታለች። "ያስመዘገብኩት ውጤት 3.96 ነው" የምትለው ቆንጂት፣ በመቀጠልም "እንደ ኮሌጅ አንደኛ በመውጣቴ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸልሜያለሁ። እንዲሁም ከሴቶች አንደኛ በመሆን ሌላ ተጨማሪ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸለምኩ" በማለት ታስረዳለች። ሶስተኛ ወርቅ ያገኘችው ደግሞ ከአጠቃላይ መቱ ዩኒቨርስቲ ሴት ተማሪዎች አንደኛ በመውጣት መሆኑን ገልጻለች። ከዚህ በተጨማሪ ከአጠቃላይ ዩኒቨርስቲው በሶስተኛ ደረጃ በመገኘቷ የነሐስ ሜዳሊያ እና በአጠቃላይ በዩኒቨርስቲው ካሉ ተማሪዎች በመላቋ ደግሞ ዋንጫ አግኝታለች። በዩኒቨርስቲ ቆይታዋ ከፍተኛ ውጤት ለማስመዝገብ ያበቋትንም ነገሮች ስታስረዳ " ዩኒቨርስቲ እንደገባሁ እቅድ በማውጣት ጊዜዬን በአግባቡ ተጠቅሜ ነበር። ክፍልም በአግባቡ እከታተል ነበር። አጠቃላይ ትኩረቴ በትምህርቴ ላይ በማድረግ ነበር ስከታተል የነበረው" ትላለች። በመቀጠልም "የተማርነውን መከለስ ብቻም ሳይሆን ወደ ፊት ልንማራቸው የምንችላቸውን ቀድሜ በማንበብ እዘጋጅ ነበር።" በማለት ልምዷን መለስ በማለት ታስታውሳለች። የዩኒቨርሰቲ ቆይታ በራስ ሕይወት ላይ ትኩረት በማድረግ ከተሰራ የወደፊት ሕይወት መስመር የሚይዝበት ነው የምትለው ቆንጂት፣ ይህ ሳይሆን ቀርቶ የተወጣበት ዓላማ ከተዘነጋ ግን የወደፊት ሕይወት የሚጠፋበት ስፍራም መሆኑን ታስረዳለች። "እኔ ዩኒቨርስቲ እንደገባሁኝ ከኔ በፊት የነበሩትን ሰዎች ምክር አግኝቼ ነበር። ለምሳሌ በዩኒቨርስቲ ሕይወት ምን ማድረግ እንዳለብኝና እንደሌለብኝ አስመልክቶ ከኔ በፊት ከነበሩት ተማሪዎች ጥሩ ምክር አግኝቻለሁ" በማለት የቀድሞ ተማሪዎች የሰጧት ምክር ለዛሬ ውጤቷ ማማር ድርሻ እንዳለው ትናገራለች። ሕይወት በርካታ እንቅፋቶች አለው የምትለው ቆንጂት " ያጋጠሙኝን እንቅፋቶችና ፈተናዎች በትዕግሥትና በዓላማዬ ላይ ትኩረቴን በማድረጌ ስኬታማ ለመሆን በቅቻለሁ" ትላለች። " እኛ ሴቶች በዓላማችን ላይ ጠንክረን ከሰራን ላንደርስበት የምንችለው ስፍራ የለም። በሴትነት የሚደርሱብን ፈተናዎችን ደግሞ በትዕግሥት ማለፍ በጣም አስፈላጊ ነው በማለት ምክሯን ትለግሳለች። በዩኒቨርስቲ ሕይወት ሴት ተማሪዎች በተለያዩ ነገሮች ሊታለሉ ይችላሉ በማለትም፣ ይኹን እነጂ ለወጡለት ዓላማ ቅድሚያ መስጠት ለወደፊት ዓላማ መመቅናት ወሳኝ ነው በማለት ሃሳቧን ታካፍላለች። ተማሪዎእ ዩኒቨርስቲ መግባትን የዓለም መጨረሻ አድርጎ መውሰድ እንደሌለባቸውም ትናገራለች። "ሌሎች ሕይወቶች የወጣንበትን ዓላማ ካሳካን በኋላ የሚደረሱ ናቸው።" ቆንጂት ስለወደፊት ሕይወቷ ስትናገር የከፍተኛ ትምህርቷን በመቀጠል አቅም ሲኖራት ደግሞ ለሴቶች ድጋፍ የሚያደርግን ተቋም አቋቁማ ለመስራት እቅድ እንዳላት ገልጻለች።
news-54009092
https://www.bbc.com/amharic/news-54009092
ዝነኛው ተዋናይ ዲዋይን እርሱና መላው ቤተሰቡ በኮቪድ-19 ተይዘው እንደነበር አስታወቀ
‘ዘ ሮክ’ በሚለው መጠሪያ የሚታወቀው ዝነኛው ተዋናይ ዲዋይን ጆንሰን እርሱን ጨምሮ መላው ቤተሰቡ በኮሮናቫይረስ ተይዘው እንደነበረ ይፋ አደረገ።
የቀድሞ የነጻ ትግል ስፖርተኛ እና የአሁኑ ከፍተኛ ገንዘብ ተከፋይ ተዋናዩ፤ የኮሮናቫይረስ መመሪያዎችን አጥብቀን ብንከተልም እኔን ጨምሮ ባለቤቴ እና ሁለት ሴት ልጆቼ በቫይረሱ ተይዘን ነበር ብሏል። በአሁኑ ወቅት ከቫይረሱ ማገገማቸውን እና ወደ ሌሎች ሰዎች ቫይረሱን እንደማናስተላልፍ ማወቃችን ትልቅ የአእምሮ እረፍት ሰጥቶናል ብሏል ዘ ሮክ። የ48 ዓመቱ ጆንሰን እንዳለው፤ የ35 ዓመቷ ባለቤቱ ሎውራ፣ የ4 እና የ2 ዓመት ሴት ልጆቹ በቫይረሱ መያዛቸውን የተረዱት ከሁለት ሳምንታት በፊት ነበር። ቫይረሱ “ከቅርብ የቤተሰብ አባል ጓደኞች” እንደያዛቸው የገለጸው ዘ ሮክ፤ የቤተሰብ አባላት ጓደኛ ያላቸው ሰዎችም በቫይረሱ ተይዘው እንደነበረ አላወቁም ብሏል። “አንድ ልነግራችሁ የምችለው ነገር፤ ይህ እንደ ቤተሰብ ያሳለፍነው እጅግ በጣም ከባዱ ነገር ነው” ብሏል ተዋናዩ በኢንስታግራም ገጹ ላይ። ከምንም ነገር በላይ ለቤተሰቤ ደህንነት ቅድሚያ እሰጣለሁ ያለው ዘ ሮክ ቫይረሱ በቤተሰብ አባላቱ ላይ ክፉ ጉዳት አለማስከተሉ መልካም አጋጣሚ እንደሆነ ገልጿል። እንዳንድ ሰዎች እና ፖለቲከኞች የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ እና ያለማደረግን ጉዳይ ፖለቲካዊ አጀንዳ ሲያደርጉት ያስደንቀኛል ያለው ዲዋይን፤ “ጭምብል ማድረግ ከፖለቲካ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም። ጭምብል አድርጉ። የበሽታውን ስርጭት ይቀንሳል። ይህ እውነታ ነው” ሲል በኢንታግራም ገጹ ላይ በለጠፈው ቪፊዮ ተናግሯል።
51813026
https://www.bbc.com/amharic/51813026
ኮሮናቫይረስ፡ ጣልያን 60 ሚሊየን ሕዝቧ በር ዘግቶ እንዲቀመጥ አዘዘች
የኮሮናቫይረስ ስርጭት እየተፋጠነባት ባለችው ጣልያን መንግሥት በመላ አገሪቱ ጉዞዎች እንዳይደረጉ፤ ምንም ዓይነት ስብሰባዎችም እንዳይካሄዱ ትእዛዝ ገደብ ጥሏል።
ትናንት የጣልያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ ጣልያናዊያን ቤታቸው እንዲቀመጡና የግድ አስፈላጊ ነው የሚሉት ጉዞ ካላቸው ደግሞ የመንግሥትን ፍቃድ እንዲጠይቁ ትእዛዝ አስተላልፈዋል። እርምጃው የተወሰደው በጣም ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን ለመጠበቅ እንደሆነ በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ባደረጉት ንግግራቸው የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ምንም ጊዜ የለም" በማለት ችግሩ አሳሳቢ እንደሆነ አስረድተዋል። በትናንትናው እለት በጣልያን በኮሮናቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ366 ወደ በከፍተኛ ደረጃ ወደ 463 ጨምሯል። • የኮሮናቫይረስ በአዲስ አበባ ሆቴሎች ላይ ያጠላው ስጋት • ኮሮና ቫይረስ ከየት መጣ? • ኮሮናቫይረስ፡ ምን ያህል አሳሳቢ ነው? ይህ ደግሞ ቫይረሱ ከተቀሰቀሰባት ቻይና ቀጥሎ ጣልያንን በኮሮናቫይረስ ክፉኛ የተጎዳች አገር አድርጓታል። የጣልያን መንግሥት ከትናንት በስቲያ ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም በ24 በመቶ የጨመረ ሲሆን በ20 ዎቹም የጣልያን ክልሎች ቫይረሱ ተሰራጭቷል። "በቫይረሱ የሚያዙም የሚሞቱም ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ ነው። እገዳዎች እንዲጠነክሩ ውሳኔ ያስተላለፍኩትም ለዚሁ ነው። ለጣልያን ስንል ሁላችንም የሚበጀውን ማድረግ አለብን" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ኮንቴ ዜጎች ማድረግ ያለባቸው ተገቢ ነገር ከቤታቸው አለመውጣት እንደሆነ ገልፀዋል። የጣልያን መንግሥት እንዳለው ለመንቀሳቀስ የሚፈቀድላቸው አሳማኝ የስራና የቤተሰብ ምክንያት ያላቸው ሰዎች ብቻ ሲሆን ከጣልያን የሚወጡም ሆኑ የሚገቡ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ የጉዞ ምክንያታቸውን ማስረዳት ግድ ይላቸዋል። የባቡር ተጓዦችም የሙቀት መጠን የሚለካ ሲሆን በጣልያን የተለያዩ የባህር ዳርቻዎች መርከቦች እንዳያርፉም እገዳ ተጥሏል።
news-53935477
https://www.bbc.com/amharic/news-53935477
ኮሮናቫይረስ፡ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከ20 በላይ ተለማማጅ ሐኪሞች በኮሮናቫይረስ ተያዙ
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል እና የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሁለት ሐኪሞችና 20 ተለማማጅ ሐኪሞች [ኢንተርኖች] በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተገለፀ።
ቢቢሲ ከዩኒቨርስቲው ምንጮች ባገኘው መረጃ መሰረት እስከ ማክሰኞ 17፣ ረቡዕ አራት እና ሐሙስ ደግሞ አንድ፤ በአጠቃላይ 22 ሐኪሞች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከእነዚህ መካከል ሰባቱ ሴቶች መሆናቸው ታውቋል። ይህንንም ተከትሎ ሁሉም ተለማማጅ ሐኪሞች ሥራ እንዳይገቡ እንደተነገራቸውና ሐሙስ ጀምሮ ሥራ አለመግባታቸውን ያነጋገርነው ስሙ አዳይጠቀስ የጠየቀ አንድ ተለማማጅ ሐኪም ለቢበሲ ገልጿል። በሽታው እንደተገኘባቸው ካወቁ ሐኪሞች መካከል ቢቢሲ ያናገራቸው ባለሙያዎች ለቫይረሱ ሊጋለጡ የቻሉት ወደ ሆስፒታሉ የሚመጡ ታካሚዎች በቅድሚያ ከእነርሱ ጋር እንደሚገናኝና በእነርሱ ከታዩ በኋላ ወደ ሌሎች ምርመራዎች እንደሚላኩ ገልጸው፤ ይህ የሥራቸው ሁኔታ ሳይሆን እንዳልቀረ ይገምታሉ። ነገር ግን ሥራቸውን በሚያከናውኑበት ጊዜ አስፈላጊ የመከላከያ አልባሳትና ሌሎች አቅርቦት በበቂ ሁኔታ አለመቅረባቸው ተጋላጭነታቸውን ከፍ አድርጎታል ሲሉ ይጠቅሳሉ። "ሰርጂካል ማስክ' እና አልኮል ተሰጥቶናል። በ15 ቀናት አስር የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ነው የሚሰጠን። አንድ ጭምብልን በአማካይ ከ24 ሰዓታት በላይ ነው የምንጠቀምበት" ሲል የመከላከያ ቁሶች በበቂ ሁኔታ እንደሌሉ ከተለማማጅ ሐኪሞቹ መካከል አንዱ ተናግሯል። ለቫይረሱ ከተጋለጡት ሰባት ሴት ተለማማጅ ሐኪሞች መካከል አንዷ የሆነችው ለቢቢሲ እንዳረጋገጠችው እርሷን ጨምሮ 22 ተለማማጅ ሐኪሞች በቫይረሱ መያዛቸውን ገልፃ፤ በበሽታው የተያዘችበትን ምክንያት ወይም አጋጣሚ ግን በውል እንደማታውቀው ተናግራለች። በሆስፒታሉ ውስጥ በኮቪድ-19 ሕክምና ማዕከል ሳይሆን በመደበኛ የሕክምና አገልግሎት ክፍል ውስጥ እንደምትሰራ የገለፀችው ሐኪም እንዳለችው "በሽታው እንዳለባቸው ሳይታወቅ የሚመጡ ሰዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ፤ ለበሽታው የተጋለጥነው ምናልባት ከዚያም ሊሆን ይችላል" ስትል ግምቷን አስቀምጣለች። ይህችው ተለማማጅ ሐኪም እንዳለቸው በሆስፒታሉ ውስጥ የእጅ ጓንትና ሌሎች ከቫይረሱ የመከላከያ ግብዓቶች እጥረት መኖሩንም ግምቷን ገልፃለች። "ብዙ ጊዜ በባዶ እጄ ነው የምንሰራው። በአብዛኛው ታማሚዎች የእጅ ጓንት እንዲገዙ እናደርጋለን። መግዛት የማይችሉትን ግን ካለጓንት በባዶ እጃችን እናክማለን፤ የግድ ጓንት የሚያስፈልገው ሕክምና ካለም ከሌላ ክፍል እንበደራለን" ስትል ያለውን ሁኔታ ታስረዳለች። እስካሁን በበሽታው ከተያዙ ተለማማጅ ሐኪሞች ውስጥ በፅኑ የታመሙ እንደሌሉና አብዛኞቹም የበሽታው ምልክት እንዳልታየባቸው ተናግራለች። ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ቢቢሲ ያናገራቸው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል እና የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ዶ/ር አሸናፊ ታዘበው፤ ሁለት ሲኒየር ሐኪሞች እና 20 ተለማማጅ ሐኪሞች በቫይረሱ መያዛቸውን አረጋግጠዋል። በቫይረሱ የተያዙት ተለማማጅ ሐኪሞች በኮሮናቫይረስ ሕክምና ማዕከል ውስጥ የሚሰሩ እንዳልሆኑ ገልፀው፤ በቫይረሱ ሊያዙ የቻሉት በሥራ ቦታ አሊያም በግል በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ወቅት ሊሆን እንደሚችል፤ ነገር ግን በሐኪሞቹ ላይ ከፍተኛ የሆነ የጥንቃቄ ጉድለት እንደሚስተዋል ተናግረዋል። በሆስፒታሉ ለባለሙያዎች የሚያስፈልጉ የበሽታው መከላከያ አቅርቦቶች እጥረት መኖሩን በተመለከተ ከቢቢሲ የተጠየቁት ሥራ አስኪያጁ፤ ተለማማጅ ሐኪሞች በቀን ስምንት ሰዓት እንደሚሰሩ ጠቅሰው፤ በወር 22 ቀን ይሰራሉ ተብሎ ታስቦ በቀን አንድ ማስክ እንደሚሰጣቸው፤ ነገር ግን በሳምንት ሁለት እና ሦስት ቀን ብቻ እንደሚሰሩ ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም ዶ/ር አሸናፊ አስፈላጊ የሚባሉት የበሽታው መከላከያ አልባሳት (ፒፒኢ) በአገር አቀፍ ደረጃ እጥረት መኖሩን ግን ገልፀዋል። የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብልን በተመለከተ ግን ሆስፒታሉ በተለማማጅ ሐኪሞቹ ተወካዮች አማካይነት ኤን -95 የተሰኘው ጭምብል ሳይቀር እንደሚሰጣቸው ጠቅሰው 'አይሰጠንም' የሚሉ ካሉ ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ ብለዋል። የተለማማጅ ሐኪሞቹ በበሽታው መያዝ ግራ ያጋባቸው ሥራ አስኪያጁ ዶ/ር አሸናፊ ከሆስፒታሉ ውጪ ጭምብል ሳያደርጉ የሚንቀሳቀሱ መኖራቸውን በመናገር "በሆስፒታሉ በርካታ ሐኪሞችና ተለማማጅ ሐኪሞች አሉ። እነዚህ ያውም ደግሞ የኮሮናቫይረስ ህክምና ማዕከል ውስጥ የማይሰሩት እንዴት ተያዙ?" ሲሉ ይጠይቃሉ። ዶክተር አሸናፊ አክለውም የሕክምና ባለሙያዎችም ሆኑ ማንኛውም ሰው ከቤት ውጪ በሚሆንበት ጊዜ የአፍን የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል በማድረግ እራሱንም ሆነ ሌሎችንን ለወረርሽኙ ከመጋለጥ ሊታደግ ይችላል ብለዋል። ዶ/ር አሸናፊ ከዚህ ቀደም በሆስፒታሉ የኮቪድ-19 ህክምና ማዕከል ውስጥ የሚሰሩ አንድ ሐኪምና አንድ የፅዳት ሠራተኛ በቫይረሱ መያዛቸውን አስታውሰው፤ ሌላ ተጨማሪ በቫይረሱ የተያዙ ባለሙያዎች እንዳልነበሩ ገልፀዋል። የዓለም የጤና ድርጅት እንደሚለው ለኮሮናቫይረስ ተጋላጭ ከሆኑት መካከል የሕክምና ባለሙያዎች ከፊት መስመር ላይ ይገኛሉ እንደሚገኙ አመልክቶ፤ በዓለም ዙሪያ በኮቪድ-19 ከተያዙት ሰዎች መካከል 10 በመቶዎቹ የጤና ሠራተኞች ናቸው ብሏል። በኢትዮጵያ ውስጥም ወረርሽኙ መኖሩ ከታወቀ በኋላ ባሉት ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ የጤና ተቋማት ውስጥ የጤና አገልግሎት የሚሰጡ ሠራተኞች ላይ ቫይረሱ እንደተገኘ ተነግሯል።
news-56439797
https://www.bbc.com/amharic/news-56439797
ፊንላንድ የደስተኞች አገር በመሆን ከዓለም ቀዳሚ ሆናለች፤ ኢትዮጵያስ?
ፊንላንድ ለአራት ዓመታት በተከታታይ የደስተኛ ሰዎች መኖሪያ መሆኗን ስታረጋግጥ ኢትዮጵያ ደግሞ በ133ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሚደገፈው በዚህ ዓመታዊ የዓለም አገራት ሕዝቦችን ደስተኝነት በሚለካው ጥናት መሠረት፤ ከመጀመሪያው ረድፍ ላይ የሚገኙት የአውሮፓ አገራት ናቸው። የ149 አገራት ሕዝቦችን የደስተኝነት ደረጃን ባስቀመጠው ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያ 133ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ከአፍሪካ አገራት በተሻለ ደረጃ ላይ የሚገኙት ሊቢያ [80ኛ]፣ ኮንጎ ብራዛቪል [83ኛ] እና አይቮሪ ኮስት [85ኛ] ናቸው። የኢትዮጵያ ጉረቤቶች ከሆኑት አገራት መካከል በዝርዝሩ ውስጥ የተካተተችው ኬንያ ስትሆን በ121ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ከዓለም አገራት በተለያዩ መለኪያዎች ደስተኛ ሕዝብ ያላት ቀዳሚዋ አገር ፊንላንድ ስትሆን ዴንማርክ ሁለተኛ፣ ስዊትዘርላንድ ሦስተኛ፣ አይስላንድ አራተኛ እና ኔዘርላንድስ አምስተኛ በመሆን ተከትለዋታል። ጥናቱ ደስተኛ የሆኑ ዜጎች እንዳሏቸው የመሰከረላቸውና ከአንደኛ እስከ አስረኛ ደረጃ ከያዙት አገራት ውስጥ አውሮፓዊ አገር ያልሆነችው ኒው ዚላንድ ብቻ ናት። ይህ ውጤት የተገኘው ጋሉፕ በተባለው የመረጃ ተንታኝ አማካይነት ደስተኛነታቸውን ለማወቅ ከ149 የዓለም አገራት በተሰበሰበ መረጃ መሠረት ነው። ይህ የሰዎች የደስተኝነት ሁኔታ የተለካው የሚያገኙት ማኅበራዊ ድጋፍ፣ ግለሰባዊ ነጻነት፣ ጠቅላላ አገራዊ ምርት (ጂዲፒ) እና በአገራቱ ውስጥ ባለው የሙስና መጠንን ጨምሮ ሌሎችንም መመዘኛዎች በመመልከት ነው። በዚህ ዓመቱ ጥናት ከዓለም አገራት ውስጥ ደስተኛ ያልሆኑ ሕዝቦች ይኖሩባቸዋል የተባሉት አፍጋኒስታን፣ ሌሶቶ፣ ሩዋንዳ እና ዚምባብዌ ናቸው። የጥናቱ አዘጋጆች እንዳሉት ዓለምን ባጠቃት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሰበብ አንድ ሦስተኛ በሚሆኑ አገራት ውስጥ "አሉታዊ የሆኑ ስሜቶች በተደጋጋሚ የመከሰታቸው ሁኔታ ከፍተኛ ነበር" ብለዋል። ቢሆንም ግን ባለፈው ዓመት በ22 አገራት ውስጥ ነገሮች መሻሻል አሳይተዋል። በርካታ የእስያ አገራት ባለፈው ዓመት ከነበራቸው ደረጃ መሻሻልን ሲያሳዩ ቻይና ቀደም ባለው ዓመት ከነበራት የ94ኛ ደረጃ ወደ 84ኛ ከፍ ብላለች። አጥኚዎች እንዳሉት በአንደኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ፊንላንድ በወረርሽኙ ወቅት የሰዎችን ህይወትና ኑሮ በመንከባከብ በኩል ከሁሉም አገራት በላቀ ሁኔታ ከፍተኛ ነጥብን አግኝታለች። የስካንዴኔቪያን አገር የሆነችው ፊንላንድ 5.5 ሚሊዮን ሕዝብ ያላት ሲሆን ከሌሎቹ የአውሮፓ አገራት በተሻለ ሁኔታ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር ችላለች። በጆንስ ሆፕኪንስ መረጃ መሠረት በአገሪቱ ከ70,000 ሰዎች በላይ በበሽታው የተያዙ ሲሆን 805 ሰዎች ለሞት ተዳርገዋል። በወጣው ሪፖርት መሠረት አስሩ የደስተኛ ሰዎች መኖሪያ የሆኑት አገራት ፊንላንድ፣ ስዊትዘርላንድ፣ አይስላንድ፣ ኔዘርላንድስ፣ ኖርዌይ፣ ስዊዲን፣ ሉክሰንበርግ፣ ኒው ዚላንድና ኦስትሪያ ናቸው።
news-47607901
https://www.bbc.com/amharic/news-47607901
አምስት ነጥቦች ስለጌዲዮ ተፈናቃዮች
ጉጂ ኦሮሞዎች እና የጌድዮ ማህበረሰብ ለዘመናት በጉርብትና አብረው ኖረዋል። እነዚህ ሁለት ማህበረሰቦች በንጉሡ ጊዜ በሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት ስር በአንድ ላይ ይተዳደሩም ነበር። በደርግ ዘመንም እንዲሁ በሲዳሞ ክፍለ ሃገር ስር መተዳደራቸውን ቀጥለው ነበር።
ሁለቱ ማህበረሰቦች፤ አሁን ወደሚገኙባቸው ክልሎች የተካለሉት ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ሲመጣ ባዋቀረው የፌደራል አከላለል መሰረት ነው። በዚህም ጉጂዎች በኦሮሚያ ክልል፤ ጌዲዮዎች ደግሞ በደቡብ ክልል ውስጥ ተካተው የየራሳቸው ዞኖች እንዲኖራቸው ተደርጓል። • ደቡብ ክልል አዲስ ለተፈናቀሉ 54 ሺህ ጌድዮዎች የፌደራል መንግሥትን ድጋፍ ጠየቀ በጉጂዎችና በጌዲዮዎች መካከል ቀደም ባሉት ጊዚያትም ቢሆን ማህበረሰባዊ ግጭቶች እንደነበሩ ይገለጻል። ነገር ግን በየትኞቹም አጎራባች ማህበረሰቦች መካከል እንደሚያጋጥመው፤ ከተፈጥሮ ሃብት ጋር የተያያዙ ግጭቶች እንደነበሩ አጥኚዎች ጽፈዋል። የመፈናቀሉ መንስዔ ምንድን ነው? ለአሁኑ ሰብአዊ ቀውስ ምክንያት የሆነው መፈናቀል የጀመረው፤ ባለፈው ዓመት በጉጂ እና በጌዲዮ ተወላጆች መካከል ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ ነው። ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር ላይ፤ በሁለቱም ማህበረሰቦች መካከል በተነሳ ግጭት ሰዎች መሞታቸው፣ ቤቶች መቃጠላቸው እና በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቀዬያቸውን ጥለው መሰደዳቸው ተዘግቦ ነበር። ለተወሰኑ ሳምንታት ግጭቱ ጋብ ብሎ ቢቆይም እንደገና በግንቦት ወር ያገረሸው ግጭት ችግሩን አባባሰው። ብዙዎች መሞታቸው፣ መኖርያ ቤቶችና የንግድ ተቋማት እንዲሁም ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸው በዜና ተነግሯል። • በጉጂ እና ጌዲዮ ግጭት ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቀሉ ይህን ተከትሎም ሰዎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው ተሰደዱ። ብዙ የጌዲዮ ተወላጆችም ከምዕራብ ጉጂ ዞን ተፈናቅለው ጌዲዮ ዞን ወደሚገኙ አካባቢዎች ገብተው መጠለል ጀመሩ። ከጉጂዎች በኩልም የተፈናቀሉ እንዳሉም ይነገራል። ተፈናቃዮቹ ምን ያህል ናቸው? ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) ከግጭቱ በኋላ ባወጣው መግለጫ፤ በምዕራብ ጉጂና በጌዲዮ አዋሳኝ አካባቢዎች በተቀሰቀሰው ግጭት 970 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች መፈናቀላቸውን ገልጾ ነበር። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በበኩሉ፤ በግጭቱ ምክንያት የተፈናቀሉት ሰዎች ቁጥር 818 ሺህ እንደሆነ ይጠቅሳል። ከእነዚህም መካከል 642,152 ተፈናቃዮች በጌዲኦ ዞን የሚገኙ መሆናቸውን፤ 176,098 ያክሉ ደግሞ በምዕራብ ጉጂ ዞን እንደሚገኙ ተገልጾ ነበር። • በተፈናቃዮች ብዛት ኢትዮጵያ ከዓለም ቀዳሚ ሆነች የኢትዮጵያ መንግሥት የብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ባለፈው ሳምንት ለቢቢሲ እንደገለጸው 800 ሺህ ከሚበልጡት ተፈናቃዮች መካከል አብዛኞቹ ወደ መጡበት ሲመለሱ 208 ሺዎቹ በመጠለያ ካምፕ ውስጥ ቀርተዋል። የሰብአዊ ቀውሱ አስከፊነት ምን ይመስላል? ለእነዚህ ተፈናቃዮች ተገቢው የሰብአዊ እርዳታ ምላሽ እየተሰጣቸው አይደለም የሚለው እሮሮ የጀመረው ገና ከመነሻው ነበረ። ባለፈው ሃምሌ ወር ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ይህን ቀውስ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎታል ሲል የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማኀበር ወቀሶ ነበር። ተፈናቃዮቹ ያሉበት ሁኔታ ሰብአዊ ክብራቸውን ለማስጠበቅ እንኳ የሚመች እንዳልሆነና በትምህርት ቤቶች፣ በቢሮዎች፣ በአብያተ-ክርስቲያናት ወለሎች ላይ እየተኙ ነው፤ የሚለብሱት ነገር እንኳን የላቸውም ብለው ነበር። • "የጌዲዮና ጉጂ ተፈናቃዮች ቸል ተብለዋል" የዓለም ቀይ መስቀል ማኀበር ተፈናቃዮቹ ምግብና ንጹሕ ውሃ ማግኘት እንዳልቻሉም ተገልጾ ነበር። ሰሞኑን ደግሞ፤ ሰብኣዊ ቀውሱ ተባብሶ ተፈናቃዮቹ ተርበው ለሞትና ለበሽታ መዳረጋቸውን በመገናኛ ብዙሃን እና በማህበራዊ መገናኛዎች ጭምር ሲገለጽ ሰንብቷል። የጀርመን ድምጽ ራዲዮ በጌዲዮ ዞን ተጠልለው ከሚገኙት ተፈናቃዮች መካከል በየቀኑ ከ 3 እስከ አራት ሰው እንደሚሞት ከአካባቢው አንድን የሃይማኖት መሪ በመጥቀስ የዘገበ ሲሆን፤ ዘ ጋርድያን በበኩሉ መንግሥት ተፈናቃዮቹ ወደ መኖርያቸው ወደ ምዕራብ ጉጂ እንዲመለሱ ሲል ሰብአዊ ድጋፍ እስከማቋረጥ መድረሱን አስነብቧል። ይህም ለሰብአዊ ቀውሱ መባባስ ምክንያት እንደሆነ ተፈናቃዮቹን እርዳታ ባለማግኘታቸው ለረሃብ መጋለጣቸው ሲገለጽ ሰንብቷል። እነዚህን አስተያየቶች ተከትሎም፤ የሰላም ሚኒስትርዋ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል "ለተፈናቃዮቹ ምንም አይነት ሰብአዊ እርዳታ እንዳልደረሳቸው የሚሰጠው አስተያየት ስህተት" ነው የሚል መግለጫ ሰጥተዋል። ቢሆንም፤ ሰብአዊ ቀውሱን መንግሥት ችላ ብሎታል የሚለው ወቀሳ በርትቶ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድም ተፈናቃዮቹን እንዲጎበኙ ግድ ብሏቸዋል። ተፈናቃዮቹ ለምን ወደቀያቸው መመለስ አልፈለጉም? አይኦኤም ህዳር ወር ላይ ያወጣው ሪፖርት እንዳመለከተው ተፈናቃዮቹ ወደቀያቸው ላለመመለሳቸው በተደጋጋሚ የሚቀርበው ምክንያት ቤታቸው መውደሙን ነው። ቤቶች በእሳት ቃጠሎ ወድመዋል። • የብሔር ግጭት የሚንጣት ሀገር ሌላኛው ምክንያት ደግሞ የደህንነት ስጋት ነው። በርካቶች ወደቀያቸው የሚመለሱ ከሆነ ለህይወታቸው እንደሚያሰጉ ተናግረዋል። ለምን መንግሥት ትችት ይቀርብበታል? ዘጋርዲያን በጌዲዮ ውስጥ ያለውን ቀውስ ሲገልጸው "በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አስተዳደር ላይ ጥቁር ነጥብ ነው" ሲል አስፍሯል። በርካቶችም መንግሥት ለችግሩ ምላሽ ለመስጠት በጣም ዘግይቷል ሲሉ ይተቻሉ። አንዳንዶች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ጌዲዮ በመጓዝ ጉብኝት ያደረጉት ጉዳዩ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ዋነኛ ርዕስ ከሆነ በኋላ ነው ይላሉ። በተጨማሪም የሰብአዊ እርዳታ እንዲቋረጥ የተደረገው ተፈናቃዮቹ ወደ መጡበት እንዲመለሱ ጫና ለመፍጠር ነው ሲል ዘ ጋርዲያን ጠቁሟል። የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ለዚህ ክስ በሰጡት ምላሽ ላይ "ይህ የመገናኛ ብዙሃን ፕሮፓጋንዳ ነው። ሰብአዊነትና ፖለቲካ ሁለት የተለያዩ ነገሮች ናቸው" ብለዋል። አክለውም ሃገሪቱን ለማናጋት የሚፈልጉ ኃይሎች ይህንን አጋጣሚ እየተጠቀሙበት እንደሆነም ገልጸዋል።
news-54008910
https://www.bbc.com/amharic/news-54008910
አሜሪካ ለኢትዮጵያ ‘ልትሰጥ የነበረውን 100 ሚሊዮን ዶላር ልትከለክል’ ነው
አሜሪካ በአጨቃጫቂው የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ምክንያት ለኢትዮጵያ ለመስጠት አቅዳ የነበረውን ወደ 100 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ የእርዳታ ገንዘብ ልትከለክል መሆኑ ተነገረ።
በሕዳሴ ግድበ ላይ እየተገነባ የሚገኘው ታላቁ ሕዳሴ ግድበ አሜሪካ ከዚህ ውሳኔ የደረሰችው ኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ግንባታን በተመለከት ከሱዳን እና ግብጽ ጋር ከስምምነት ሳትደርስ የግድቡን ውሃ ሙሊት በማስጀመሯ መሆኑን የአሜሪካ መንግሥት ምንጭ ለሬውተርስ ተናግረዋል። “እስከ 100 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ቅነሳ ሊደረግ ይችላል” ሲሉ የአሜሪካ የኮንግረስ አባል ለሬውተርስ ተናግተዋል። ዩናይትድ ስቴትስ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ የግደቡ ደህንነት ሁኔታዎች ሳይጠኑ የውሃ ሙሌት መጀመር የለበትም የሚል አቋም ይዛ እንደነበረ ይህ የኮንግረስ አባል ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም 'ፎሬይን ፖሊሲ' የተባለው መጽሔትም አሜሪካ ለኢትዮጵያ ለመስጠት የመደበችውን 130 ሚሊዮን ዶላር ላለመስጠት መወሰኗን የውስጥ ምንጮቹን ጠቅሶ ከቀናት በፊት ዘግቦ ነበረ። መጽሔቱ አሜሪካ ለደረሰችበት ለዚህ የእርዳታ ገንዘቡ እገዳ ውሳኔ ምክንያቱ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባች ካለው የታላቁ የህዳሴ ግድብ ጋር ተያይዞ እንደሆነ በዘገባው አስነብቧል። በሌላ በኩል በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አቶ ፍጹም አረጋ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ልትሰጥ አቅዳው የነበረው የገንዘብ ድጋፍ እንዳይሰጥ የተደረገው "በጊዜያዊነት" ነው ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረው ነበር። አምባሳደሩ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻቸው ላይ እንዳሰፈሩት የገንዘብ ድጋፉ የተያዘው ለአጭር ጊዜ መሆኑን ከሚመለከታቸው የአሜሪካ መንግሥት ኃላፊዎች እንደተረዱ ጠቅሰዋል። አምባሳደር ፍጹም አሜሪካ ለኢትዮጵያ የመደበችው 130 ሚሊዮን ዶላር እንዳይሰጥ መወሰኗ ከተሰማ በኋላ ስለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸውን ገልጸው የነበረ ሲሆን፤ በዚሁ መሰረት ነው ገንዘቡ በጊዜያዊነት እንዳይሰጥ መደረጉን እንደተረዱ ያመለከቱት። ግብጽ የአባይ ውሃ መጠን ይቀንስብኛል በሚል ስጋት ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለችውን የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ስትቃወም መቆይቷ ይታወቃል። ኢትዮጵያ በበኩሏ ግንባታው የአገሪቱ ዜጎች የሚፈልጉንት የኃይል መጠን ለማቅረብ የማደርገው ጥረት ነው ትላለች። የሕዳሴ ግደብ ግንባታ ተጠናቆ ግድቡ በሙሉ አቅሙ ኃይል ማመንጨት ሲጀምር እስከ 65 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የአሌክትሪክ አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል።
news-53758758
https://www.bbc.com/amharic/news-53758758
ብልጽግና ፡ የአቶ ሽመልስ አብዲሳ ንግግር "የግለሰብ እንጂ የብልጽግና አቋም አይደለም"
አማራ ብልጽግና ፓርቲ ላለፉት ሁለት ቀናት በክልሉና በአገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ሲያካሂድ ቆይቷል። ውይይቱን መጠናቀቅ ተከትሎ ትላንት ምሽት የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አገኘሁ ተሻገር መግለጫ ሰጥተዋል።
የሕግ የበላይነት፣ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ፣ የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ አደረጃጀት፣ የክረምት ሥራዎች ግምገማ፣ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ስለተፈጠሩት ጉዳዮችና የአቶ ሽመልስ አብዲሳ ንግግር በውይይቱ መነሳታቸውን አስታውቀዋል። የሕግ የበላይነትን በማስከበር ረገድ በክልሉ በሕገ ወጥ አደረጃጀት ስር የነበሩትን እንዲፈርሱ መደረጉን ተናግረዋል። በዚህም በሕግ የሚፈለጉ ሰዎችን ለህግ እንዲቀርቡ የተደረገ ሲሆን በአጠቃላይ የክልሉ ሠላም በጥንካሬ ተነስቷል ብለዋል አቶ አገኘሁ። "ክልሉ የተሟላ ሠላም ላይ ነው" ያሉት ኃላፊው "ሠላሙ ወደ ኋላ እንዳይመለስ ከሕዝቡ ጋር በጋራ እንሠራለን" ሲሉ ተናግረዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት በክልሉ እየጨመረ መሆኑን ጠቅሰው የምርመራ አቅምን ከማሳደግ ጀምሮ ሥራዎች መከወናቸውን አስታውቀዋል። ሆኖም እየታየ ያለው መዘናጋቱ ዋጋ እንዳያስከፍል የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። ግድያና መፈናቀል የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የተፈጸመውን ግድያና መፈናቀል በጉባኤው ላይ ተነስቶ መወገዙን አመልክተዋል። "ማንም ሰው እንዲሞት አንፈልግም" ያሉት አቶ አገኘሁ "ለሞቱት እና ለፍትህ ነው የምንታገለው" ሲሉ አስረድተዋል። የድርጊቱ ተሳታፊዎችን ለሕግ በማቅረብ ረገድ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ላደረገው ሥራና ችግሩ እንዳይባባስ ለሠሩ ወጣቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የሐይማኖት አባቶች ፓርቲው ባደረገው ውይይት ላይ እውቅና መሰጠቱንም ጠቁመዋል። በቀጣይም አጥፊዎች ወደ ሕግ እንዲቀርቡና አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድባቸው ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ጋር በጋራ እንደሚሠሩ አስታውቀዋል። የተፈናቀሉና ቤት ንብረት የወደመባቸውን ሰዎች ለማቋቋም የጀመርነውን ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አውስተዋል። የፓርቲው ጉባኤ ቀደም ሲል ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረትም ከክልሉ ውጪ የሚኖሩ የአማራ ብሔር ተወላጆች በሚኖሩበት አካባቢ እንዲወከሉ፣ በቋንቋቸው እንዲማሩና እንዲዳኙ ለመሥራት ባቀደው መሠረት ይህንን ለማሳካት ከሌሎች ክልሎች ጋር በጋራ እንሠራለንም ብለዋል። የአቶ ሽመልስ አብዲሳ ንግግር አቶ አገኘሁ በፓርቲው ጉባኤ ላይ በቅርቡ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ቀደም ባላ ጊዜ አደርገውታል በተባለ ንግግር ዙሪያ በኮንፈረንሱ ላይ ውይይት ተደርጎበታል። "አንደኛ ጉዳዩ የተነገረው መቼም ይሁን መቼ ለምን አሁን ማውጣት አስፈለገ? የሚለው አነጋግሮናል። የሁለተኛ ንግግሩ በይዘቱ ስህተት ነው" ሲሉ ገልጸዋል። ጨምረውም በርዕሰ መስተዳደሩ ንግግር ላይ የተንጸባረቀው ሃሳብ "የግለሰብ አቋም ነው። የፓርቲያችን የብልጽግና አቋም አይደለም" ሲሉ ተናግረዋል። በውይይቱም የንግግሩ ይዘት በብልጽግና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ደረጃ በዝርዝር መገምገም እንዳለበትና የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ አቅጣጫ መቀመጡንም አመለክተዋል። "ኮንፈረንሱ የተሰጠው መግለጫው ትክክል አለመሆኑን፤ በይዘት ደረጃ ስህተት መሆኑን ገምግሟል። የይቅርታ መጠየቅ የግለሰብ ጉዳይ ነው። የፓርቲ አቋም ግን አይደለም" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል አቶ አገኘሁ። በክልሉ የአመራር መከፋፈል አለመኖሩን እና አንድነቱ የጠነከረ ለአማራ ህዝብ እየሠራ ያለ አመራር መኖሩን ጠቅሰው "በንግግሩም ላይ ምንም ዓይነት የሃሳብ ልዩነት የለም" ሲሉ በጉዳዩ ላይ የአማራ ክልል አመራሮች ልዩነት አላቸው ይባላል ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሻቸውን ሰጥተዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሕር ዳር መገኘት ረቡዕ በውይይቱ የመጨረሻ ዕለት በባሕር ዳር ከተማ የተገኙት የፓርቲው ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በኮንፈረንሱ ላይ ቀደም ሲል በተያዘ ፕሮግራም እንደተገኙ አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የ5 ቢሊዮን ችግን ተከላ ፕሮግራምን መጠናቀቅ ከማብሰር በተጨማሪ የኮንፈረንሱን የማጠቃለያ አቅጣጫና የሥራ መመሪያ አስቀምጠዋል ብለዋል። የትግራይ ክልል ምርጫ የትግራይ ክልል ምርጫ ለማካሄድ ወስኖ መንቀሳቀሱ ፀረ ሕገ መንግሥት እንቅስቃሴ ነው ያሉት አቶ አገኘሁ "ሕገወጥ ምርጫ በመሆኑ ፌደራል መንግሥት እርምጃ ይውሰድ ነው የእኛ አቋም" ብለዋል። "የአማራ ክልል የትግራይ ክልልን ለምን ምርጫ ታካሂዳለህ ማለት አይችልም። የፌደሬሽን ምክር ቤትና ምርጫ ቦርድ እውቅና ስለነፈገው የፌደራል መንግሥት ማድረግ የሚችለውን ያደርጋል።" "የራያና ወልቃይት ሕዝቦች አማራ ማንነት ያላቸው ሲሆኑ ምርጫወንም አልደገፉትም። ባለመደገፋቸውም በአሁኑ ሰዓት እየታሰሩና እየተሰደዱ ተፈናቃዮችን እያስተናገድን ነው" ብለዋል። "የእነዚህን ሰዎች ጥያቄ የፌደራል መንግሥቱ መስማት አለበት። ጣልቃ ገብቶም ማስተካከልም አለበት። ከዚያ ውጪ የትግራይ ክልል ምርጫ ስላካሄደ ብለን እኛ አንተነኩስም። እኛ ከትግራይ ህዝብ ጋር በሰላም ነው መኖር የምንፈልገው" ሲሉ አስረድተዋል። ጨምረውም ከትግራይ ወንድም ሕዝብ የአማራን ሕዝብ ህወሐት ሊነጥለው አይችልም በማለት ገልጸዋል። "የአማራን ሕዝብ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር ለማጋጨትና ለመነጠል የሚሰሩ ህወሓት እና ኦነግ-ሸኔን የመሳሰሉ ኃይሎችን ከሌሎች ወንድም ሕዝቦች ጋር በመተባበር መታገል እንደሚገባም ተግባብተናል" ሲሉ ሃሳባቸውን አጠናቀዋል።
news-55255843
https://www.bbc.com/amharic/news-55255843
ትግራይ፡ በህወሓት ኃይሎች ታግተው የነበሩ 1 ሺህ መኮንኖች መለቀቃቸው ተነገረ
በህወሓት ኃይሎች ታግተው የነበሩ ወደ 1 ሺህ የሚጠጉ የሰሜን ዕዝ መስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖች መለቀቃቸውን የአገር መከላከያ አስታወቀ።
ሜ/ጀነራል መሐመድ ተሰማ በህወሓት ኃይሎች ታግተው ከነበሩት እና ከተለቀቁት መካከል የሰሜን ዕዝ ምክትል አዛዥ ብርጋዲየር ጀነራል አዳምነህ መንግስቴ እንደሚገኙበት ኢዜአ የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል መሐመድ ተሰማን ጠቅሶ ዘግቧል። የአገር መከላከያ እና የፌደራል ፖሊስ ባደረጉት የጋራ ኦፕሬሽን የተለቀቁት 1 ሺህ ያክሉ የጦር አባላት የመስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖች ናቸው ተብሏል። ሜጀር ጀነራል መሐመድ ተሰማ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የአገር መከላከያ አባላቱ ጥቅምት 24 ቀን ምሽት ላይ የእራት ግብዣ ተብለው ከተጠሩ በኋላ ታፍነው የተወሰዱ ናቸው። የህወሓት ኃይሎች በሸሹባቸው ቦታ ሁሉ በቁጥጥራቸው ሥር ይገኙ የነበሩ የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላቱን ይዘው ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸውን ተገልጿል። የአገር መከላከያ ሠራዊትና የፌዴራል ፖሊስ ባደረጉት ኦፕሬሽን መስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖቹ ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው ከህወሓት ኃይሎች መለቀቃቸውን ሜጀር ጀነራል መሐመድ ለኢዜአ ተናግረዋል። ሜ/ጀ መሐመድ የህወሓት አባላትን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የሚደረገው ጥረት መቀጠሉን ጨምረው ገልጸዋል። በተመሳሳይ በትግራይ ልዩ ኃይል ተይዘው ከነበሩት መካከል በመቶዎች የሚቆጠሩ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ከቀናት በፊት ተለቀው ወደ አማራ ክልል መግባታቸው ይታወሳል። ከእነዚህ መካከል በዋግ ኽምራ በኩል የተከዜ ሰው ሰራሽ ሐይቅን ተሻግረው ሰቆጣ ከገቡትን የሠራዊቱን አባላት መካከል ቢቢሲ የተወሰኑትን አነጋግሮ ነበር። የ31ኛ አድዋ ክፍለ ጦር ውስጥ የክፍለ ጦር አባል የሆነው አምሳ አለቃ አብርሐም ባየ 22 ቀናትን በትግራይ ልዩ ኃይል አባላት ቁጥጥር ስር ቆይቶ ነበር። አምሳ አለቃ አብረሐም በህወሓት ኃይሎች ቁጥጥር ሥር በነበሩበት ወቅት ወደተለያዩ ስፍራዎች ይዘዋቸው ሲንቀሳቀሱ እንደነበረ ለቢቢሲ ተናግሯል። ምርኮኛ ሆነው በቆዩባቸው ቀናትም በሚሊሻ እና በማረሚያ ቤት ጠባቂዎች ሲጠበቁ መቆየታቸውን የሚናገረው አምሳ አለቃ አብርሃም፣ "ምንም አይነት ንግግር አልነበረንም። በተለይ አብይ አዲ በነበርንበት ወቅት ሚሳኤሎች ሲተኮሱ በቦታው ሆነን እየተመለከትን ነበር። ከባድ መሳሪያዎች ወደ ስፍራው ሲጓጓዙ ስንመለከት በቀሪው የአገራችን ክፍል ውስጥ ምን እየተከናወነ እንደሆነ ስለማናውቅ በጣም ጭንቀት ውስጥ ነበርን፤ እንቅልፍም አልነበርንም" በማለት የነበራቸውን ቆይታ ገልጿል። ሌላኛው የሠራዊቱ አባል አስር አለቃ ኢብራሂም ሃሰን በተመሳሳይ ምርኮኛ ሆነው በቆዩባቸው ጊዜያት የህወሓት ኃይሎች ከቦታ ወደ ቦታ ሲንቀሳቅሷቸው እንደነበረ ያስታውሳል። ኢብራሂም ተይዘው የቆዩባቸው ቀናት እጅግ አስቸጋሪ እንደነበሩ በመግለጽ ይራቡ እንደነበረም ያስታውሳል "ጠዋት አንድ ዳቦ ይመጣል። ለምሳም አንድ ዳቦ ነው የሚሰጠን። አንዳንዴ ጠዋት ከበላን ምሳ ላይሰጠን ይችላል" ሲል ተናግሯል። የህወሓት ኃይሎች ይዘዋቸው ከነበሩ የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት መካከል ከ1ሺህ 200 በላይ ተለቀው ወደ አማራ ክልል መግባታቸውን በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ጳውሎስ በላይ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልልን ሲያስተዳድር በነበረው ህወሓት መካከል ለረዥም ጊዜ የዘለቀው አለመግባባት ተካሮ የህወሓት ኃይሎች የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል በማለት ጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ የፌደራሉን ጦር ወደ ትግራይ ማዝመታቸው ይታወሳል። መንግሥት "ሕግ የማስከበር" ባለውና ከአንድ ወር በላይ በተካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ ቁጥሩ በትክክል ባይታወቅም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን ተሰደዋል። የትግራይ መዲና የሆነችው መቀለ በፌደራል መንግሥት ሠራዊት ቁጥጥር ስር ከዋለች በኋላ ወታደራዊ ዘመቻው መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ተናግረው ነበር።
55349591
https://www.bbc.com/amharic/55349591
ድንበር አካባቢ የተከሰተው ግጭት "የሱዳን መንግሥት የታችኛው እርከን ችግር ነው"- ኢትዮጵያ
በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ሱዳንና ኢትዮጵያ በሚዋሰኑበት የድንበር አካባቢ የተከሰተው ግጭት በስፍራው ባለ የሱዳን መንግሥት መዋቅር ውስጥ በተከሰተ ችግር ምክንያት መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥት ገለጸ።
በድንበር አካባቢ ስለተከሰተው ጉዳይ በቢቢሲ የተጠየቁት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፤ "የተወሰኑ የሱዳን ታጣቂዎች ድንበር ተሻግረው የአርሶ አደሩን ንብረት ለመውሰድ ሙከራ በሚያደርጉበት ወቅት ለመከላከል የተደረገ ክስተት ነው" ሲሉ ግጭቱን ገልፀውታል። ማክሰኞ ታህሣሥ 6/2013 ዓ.ም ምሽት ላይ የሱዳን ወታደሮች በድንበር አካባቢ ቅኝት አድርገው ሲመለሱ "ወደ ሱዳን ግዛት ገብተው አድፍጠው በነበሩ የተወሰኑ የኢትዮጵያ ሚሊሺያዎች ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል" ሲሉ የሱዳን መገናኛ ብዙሃንን በመጥቀስ ሮይተርስ ዘግቦ ነበር። ማምሻውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በትዊተር ገጻቸው ላይ መንግሥት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር አካባቢ ከሚሊሻ ጋር የተፈጠረውን ክስተት በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ገልፀዋል። አምባሳደር ዲና ስለክስተቱ ጨምረው እንደተናገሩት ታጣቂዎቹ "የአርሶ አደር ማሳ ውስጥ ገብተው አንዳንድ ነገሮችን የመውሰድ፣ ወደዚያ የማስፋፋትና ከሕግ አግባብ ውጪ የመሄድ ሁኔታ ስለታየ ይህንን ነገር መመለስ ስለሚያስፈልግ እርምጃ ተወስዷል" ብለዋል። ግጭቱን ተከትሎ የሱዳን መገናኛ ብዙሃን በጥቃቱ አንድ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንን ጨምሮ አራት የሱዳን ወታደሮች መሞታቸውን ዘግበዋል። የሱዳን ሚኒስትሮች ምክር ቤት ከጦሩ ጎን መሆኑን እና ድጋፍ እንደሚያደርግ የዘገቡት መገናኛ ብዙሃኑ፤ የሱዳን ታጣቂ ኃይሎች የአገሪቱን ዳር ድንበር የመጠበቅ እና ማንኛውንም ጥቃት የመከላከል አቅም እንዳለው እምነታቸውን ገልጸዋል ብለዋል። አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በበኩላቸው ሁለቱ አገራት በጉዳዩ ላይ በመንግሥት ደረጃ ግንኙነት ማድረጋቸውን ገልፀው፤ ግጭቱን "ይህ የሱዳን መንግሥት ፍላጎት አይደለም" ብለዋል። እንደ ሱዳን መገናኛ ብዙሃን ዘገባ ከሆነ ጥቃቱን በፈፀሙት ታጣቂዎች ላይ የሱዳን ሠራዊት እርምጃ እንደሚወስድ የተገለጸ ሲሆን፤ የሱዳን ብሔራዊ ዜና ወኪል የሆነው ሱና፤ መከላከያ ኃይሉ "የሱዳንን ድንበር ከማንኛውም ጥቃት ለመከላከል ወታደር እንደሚመደብ" መግለፁን ዘግቧል። የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ባለፈው እሁድ በኢትዮጵያ የተሳካ ጉብኝት ማድረጋቸውን የገለፁት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ይህ ችግር "የሱዳን መንግሥት የታችኛው እርከን ችግር ነው" ሲሉ ተናግረዋል። ይህንን ችግር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት በአጭር ጊዜ የሁለቱ አገራት ከፍተኛ አመራሮች ለመነጋገር ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ገልፀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዶክ እሁድ እለት ኢትዮጵያ ውስጥ በነበራቸው አጭር ቆይታ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚነስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ከተነጋገሩባቸው ጉዳዮች አንዱ የድንበር ጉዳይ ነው። ሱዳን ትሪቡን ረቡዕ ዕለት፤ በሱዳን መከላከያ እና በኢትዮጵያ ታጣቂዎች መካከል ግጭት እንደነበር ዘግቦ ግጭቱ የተካሄደው በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ስደተኞችን በሚቀበል ጣብያ አቅራብያ ነበር ብሏል። ግጭቱ በምሥራቅ ሱዳን አል ቀዳሪፍ ግዛት ቁራይሻ መንደር፣ ዋድ አሩድ ከተማ አቅራብያ መከሰቱን አክሎ ዘግቧል። አምባሳደር ዲና ግጭቱ የተፈጠረው የመንግሥት ትኩረት ሌላ ቦታ ላይ መሆኑን ከግምት በማስገባት ነው ካሉ በኋላ፤ ከዚህ ቀደምም ድንበሩ አካባቢ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ፣ ከኢትዮጵያም ወደ ሱዳን እንቅስቃሴ እንደነበር ተናግረዋል። ኢትዮጵያና ሱዳን በድንበር አካባቢዎቻቸው ያሉ ጉዳዮችን በተመለከተ መፍትሄ የሚሰጥ የጋራ የድንበር ኮሚሽን ያላቸው ሲሆን በተለያዩ ጊዜያት በአዲስ አበባና በካርቱም እተገናኙ ሲመካከሩ መቆየታቸው ይታወቃል።
news-56359822
https://www.bbc.com/amharic/news-56359822
"ህወሓት ጦርነት እንደሚጀምር አውቀን ስንዘጋጅ ነበር" አቶ አገኘሁ ተሻገር
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘው ተሻገር ከህወሓት በኩል ጥቃት ሊሰነዘር እንደሚችል በማሰብ ክልሉ አስፈላጊውን ዝግጅት ሲያደርግ እንደነበር ተናገሩ።
ርዕሰ መስተዳደሩ ይህንን ያሉት ለአማራ ክልል ምክር ቤት የመስተዳደሩን የስድስት ወራት የሥራ ክንውን በተመለከተ ባቀረቡት ሪፖርት ላይ ነው። አቶ አገኘሁ ተሻገር እንዳሉት "ጦርነቱን ህወሓት መቼ እንደሚጀምረው ባናውቅም ወደማንፈልገው ጦርነት ሊያስገባን እንደሚችል በመገንዘብ ስንዘጋጅ ቆይተናል" ብለዋል። ይህንን መነሻ በማድረግ "የክልሉ መንግሥት የይሆናል ዕቅድ አዘጋጅቶ ራስን ለመከላከል ስንዘጋጅ ስለቆየን ጦርነቱ በተጀመረበት ወቅት መከላከል ችለናል" በማለት ለምክር ቤቱ አስረድተዋል። ምንም እንኳን ጥቃት ሊፈጸም ይችላል በሚል ተዘጋጅተው እንደነበር ገለጹት ርዕሰ መስተዳደሩ ጦርነቱ ጥቅምት መጨረሻ ላይ ይሆናል ተብሎ እንዳልተጠበቀ ተናግረዋል። አክለውም ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የህወሓት ኃይሎች በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት የሠሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን ተከትሎ በአማራ ክልል በማዕከላዊ ጎንደር በኩል ወረራ መፈጸሙን ርዕሰ መስተዳድሩ ለምክር ቤቱ አባላት አስረድተዋል። በተለይ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን፣ ቅራቅር እና ሶሮቃ በኩል የአገር መከላከያ ሠራዊት ለዘመቻው የሚያስፈልጉትን የተለያዩ አቅርቦቶችን እስኪያጓጉዝ ድረስ የክልሉ ልዩ ኃይል ጥቃቱን መመከት መቻሉን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል። አቶ አገኘሁ ትኩረት ሰጥተው ከተናገሩባቸው ጉዳዮች መካከል ከክልሉ ውጪ የሚኖሩ የአማራ ብሔር አባላት ደኅንነት ጉዳይ አንዱ ነው። ርዕሰ መስተዳደሩ በተለይም በኦሮሚያ፤ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በደቡብ ክልሎች ውስጥ "የአማራ ተወላጆች ጥቃት የሚደርስባቸው ህወሓት በሠራው የረጅም ጊዜ ሸፍጥ ነው። ይህም ምንም ጥናት የማያስፈልገው ነባራዊ እውነታ ነው" በማለት "በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች አማራ በማንነቱ ለሚደርስበት መፈናቀልና ግድያ" ህወሓትን ተጠያቂ አድርገዋል። ከዚህ ባሻገርም የአማራ ክልል ከሚዋሰናቸው ክልሎች ጋር የሚፈጠሩ ግጭቶችን ለማስቆም መስተዳደሩ እየሰራ መሆኑን አመልክተው፤ በተለይ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጋር በተያያዘ በርካታ የክልሉ ተወላጆች የሚደርስባቸውን ጥቃት በቋሚነት ለመከላከል ሁለቱ ክልሎች በጋራ የሚሰሩበት ቻርተር ተሰናድቶ ወደ ሥራ ለመግባት ዝግጅት ላይ መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር የምትዋሰንበት የአማራ ክልል አካባቢን በተመለከተም ርዕሰ መስተዳድሩ በሰጡት ማብራሪያ በጥቅምት ወር በትግራይ ውስጥ የተፈጠረውን ቀውስ እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም በምዕራብ ጎንደር አካባቢዎች የሱዳን መንግሥት ወረራ መፈጸሙን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል። በሱዳን ኃይል የተወረሩት አካባቢዎች አሁንም በሱዳን ቁጥጥር መሆናቸውን አቶ አገኘሁ የተናገሩ ሲሆን፤ በእዚህም ሰፊ የእርሻ ቦታዎችና ካምፖች መወሰዳቸውን ተናግረዋል። "ይህ ሲሆን ብዙ ጥፋት ደርሷል" ያሉት አቶ አገኘሁ፣ "በቀጣይም የበለጠ ጥፋት ሊደርስ እንደሚችል አመላካች ነገሮች በመኖራቸው የፌደራል መንግሥት አፋጣኝ ርምጃ እንዲወስድ ጠይቀናል" ብለዋል። ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘው ተሻገር የክልሉን መስተዳደር የግማሽ ዓመት የሥራ ክንውንን በተመለከተ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት ላይ የሥራ እድልን በመፍጠር፣ ኢንተርፕራይዞችን ማሳደግ፣ ዜጎችን የቤት ባለቤት ለማድረግ፣ አዳዲስ እና ነባር የመስኖ ሥራዎችን በመጠገንና በመገንባት የክልሉን ኢኮኖሚ ለማሳደግ የተሰሩ ሥራዎችንና ሌሎች ተግባራት አንስተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።