id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
49685478
https://www.bbc.com/amharic/49685478
ኔታንያሁ እስራኤል ዋይት ኃውስን ትሰልላለች የሚለውን ዘገባ አስተባበሉ
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ፤ አገራቸው አሜሪካን ትሰልላለች ተብሎ የወጣውን ዘገባ ሙሉ በሙሉ አስተባበሉ።
እስራኤልን አሜሪካን በመሰለል የሚወነጅለው ዘገባ በአሜሪካ በሚገኝ 'ፖለቲኮ' በተሰኘ የዜና ድረገፅ ላይ የወጣው ሐሙስ ዕለት ነበር። 'ፖለቲኮ' የተሰኘው ይህ የዜና ድረገፅ፤ ሦስት የቀድሞ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናትን ጠቅሶ፤ ዋይት ኃውስ አቅራቢያ ተገኘ ካለው የመከታተያ መሣሪያ ጀርባ እስራኤል ትኖርበታለች ሲል ዘግቧል። ነገር ግን ከጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ቢሮ የወጣው መግለጫ እንደሚያስረዳው ውንጀላው "ነጭ ውሸት ነው"። • "ስተዳደር የቆየሁት በዋናነት ለመለስ በሚሰጠው የጡረታ ገቢ ብቻ ነው" ወ/ሮ አዜብ መስፍን • “ጭኮ እወዳለሁ” ወ/ሮ አዳነች አቤቤ "በአሜሪካ በየትኛውም የስለላ ተግባር ላለመሳተፍ ረዥም ጊዜ ፀንቶ የቆየ መግባባት እና አሠራር አለ" ይላል መግለጫው አክሎ። ሐሙስ ዕለት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጋዜጠኞች ስለ ሪፖርቱ ሲጠየቁ፤ እስራኤል አሜሪካን ትሰልላለች ብለው እንደማያምኑ ተናግረው ነበር። "እጅጉን ለማመን ተቸግሬያለሁ፤ ከእስራኤል ጋር ያለኝ ግንኙነት በጣም ጥሩ ነው" ያሉት ፕሬዝዳንት ትራምፕ፤ ከኢራን ጋር ያለው የኒውክሌር ስምምነት ማብቃቱንና አሜሪካ በእስራኤል የሚገኘውን ኢምባሲዋን ወደ እየሩሳሌም ለማዞር የወሰነችበትን አወዛጋቢ ውሳኔ በአስረጅነት ጠቅሰዋል። "ይህንን ወሬ አላምነውም፤ አይሆንም ማለት አልችልም፤ ግን አላምንም" ብለዋል። 'ፖለቲኮ' የተሰኘው ድረገፅ በዘገባው ላይ እንዳስቀመጠው፤ የእስራኤል ሞባይል ኔትወርክ አቅራቢ ስቲንግሬይስ፣ ንብረት የሆነ መሣሪያ በፕሬዝዳንቱ መኖሪያ አቅራቢያ የተገኘ ሲሆን፤ ከዚህ በፊትም በትራምፕ አስተዳደር ዘመን ዋሺንግተን ዲሲ አቅራቢያ ሌላ ተመሳሳይ መሣሪያ መገኘቱን ጠቅሷል። ይህ መሣሪያ እንደ ሞባይል ኔትወርክ ማማ የሚመስል ሲሆን፤ ስልኮችን በመጥለፍ ያሉበትን ሥፍራ፣ የማን እንደሆኑ፣ እንዲሁም መደወልና ዳታቸውን መጠቀም ያሰችላል። ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የቀድሞ ባለስልጣን ለዜና ተቋሙ እንዳሉት፤ ስቲንግሬይስ ይህንን መሣሪያ የሠራው ሆን ብሎ ፕሬዝዳንት ትራምፕን ለመሰለል ነው። ነገር ግን ይሳካላቸው አይሳካላቸው ማረጋገጥ አለመቻላቸውን ጠቅሰዋል። • "ኢትዮጵያዊነቴን ያገኘሁት ሙዚቃ ውስጥ ነው" አቨቫ ደሴ • "ፍቅር እስከ መቃብርን አልረሳውም" ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም የአሜሪካው የፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ) ፀረ ስለላ ቡድን መሣሪያው ከየት እንደመጣ ማጥናቱን የጠቀሱት የአሜሪካ የስለላ መሥሪያ ቤት የቀድሞ ባለስልጣን፤ "የእስራኤል እጅ እንዳለበት ግልፅ ነው" ብለዋል ለ'ፖለቲኮ'። እኚሁ ባለስልጣን የትራምፕን አስተዳደር የተቹ ሲሆን፤ የእስራኤል መንግሥትን በይፋም ይሁን በግል ስለላ በማካሄዳቸው አለመውቀሳቸውን ኮንነዋል። "ማንም ተጠያቂ ስለመደረጉ አልሰማሁም" ብለዋል እኚህ የቀድሞ ባለስልጣን። የኔታንያሁ ማስተባባል እንዳለ ሆኖ፤ እስራኤል ከዚህ ቀደም አሜሪካን ሰልላ ታውቃለች። ራፊ ኢታን፣ በ1960 ናዚ አዶልፍ ኢችማንን በቁጥጥር ሥር ያዋለው የሞሳድ ወኪል፣ በ1980 በርካታ ከፍተኛ ሚስጥር የያዙ የአሜሪካ ሰነዶችን ለእስራኤል ማስተላለፉን ይፋ አውጥቶ ተናግሮ ነበር። በ2006 ደግሞ የአሜሪካ መከላከያ ኃይል ተቀጣሪ የነበረው ሎውረንስ ፍራንክሊን የአሜሪካን ጥብቅ ሚስጥር የያዙ ሰነዶችን ለእስራኤል አሳልፎ በመስጠቱ የ13 ዓመት እስራት ተፈርዶበታል። በኋላ ላይ እስሩ በአስር ወር የቁም እስር ተቀይሮለታል።
50470329
https://www.bbc.com/amharic/50470329
የብልጽግና ፓርቲ ከአማርኛ በተጨማሪ ኦሮምኛና ሌሎችም ቋንቋዎች የሥራ ቋንቋ እንዲሆኑ ወሰነ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባለፉት ሦስት ቀናት አዲሱን የብልጽግና ፓርቲ ለመመስረት የነበረውን ሂደት አስመልክተው መልዕክት አስተላለፉ።
የኢሕአዴግን ውሕደት በተመለከተ፣ አዲሱ ሕገ ደንብ እና ፕሮግራም ላይ መወያየታቸውና ውሳኔዎችን ማሳለፋቸውን ገልፀዋል። • "ኢትዮጵያ የኢህአዴግ አባት እንጂ፤ ኢህአዴግ የኢትዮጵያ አባት አይደለም" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዚሁ መልዕክታቸው የአዲሱን ፓርቲ ስያሜ አስመልክተው "የብልጽግና ፓርቲ" መባሉን በመግለጽ፤"ብልጽግና በቁስ ብቻ ሳይሆን፣ በክብርም በነጻነትም ማረጋገጥ የሚችል ፓርቲ" ለመመስረት መወሰኑን ገልጸዋል። የፌደራል ሥርዓቱ እስካሁን የነበረበትን ስህተቶች ለማረም በሚያስችል መልኩ የሚደራጅ እንዲሆን መስማማታቸውን በመግለጽም፤ ከአማርኛ በተጨማሪ ኦሮምኛ፣ ትግርኛ፣ ሶማልኛ እና አፋርኛ የፌደራል የሥራ ቋንቋ እንዲሆን መወሰኑን ገልፀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት በዚህ መልዕክት ፓርቲያቸው የፌደራል መንግሥቱ የሥራ ቋንቋ እንዲሆን ጠንክሮ እንደሚሠራም ተናግረዋል። ይህ ኢትዮጵያውያን አንዳቸው ከአንዳቸው ተምረው፣ በጋራ የጋራ አገራቸውን ለመገንባት ያላቸውን ፍላጎት ይበልጥ የሚያጠናክር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እርምጃው "እስካሁን ከነበረው በእጅጉ የላቀ እድገት ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል" ብለዋል። ከእዚህ ባሻገር እያንዳንዱ ሕዝብ በልኩ የሚሳተፍበትና ሌላውን የሚያከብርበት የዲሞክራሲ አውድ ለመፍጠር መግባባት ላይ መደረሱን ተናግረዋል። • "ኢትዮጵያ የኢህአዴግ አባት እንጂ፤ ኢህአዴግ የኢትዮጵያ አባት አይደለም" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ኢትዮጵያን በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ወደ ብልጽግና ለማሻገር የነበረውን ትልም ለማሳካት በእጅጉ የሚረዳን ነው በማለትም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ግንባሩን በማዋሃድ ወጥ ፓርቲ ለመመስረት በቀረበለት የውህደት ዝርዝር ጥናት ላይ ተወያይቶ በስድስት ተቃውሞ በአብላጫ ድምፅ ከስምምነት ላይ መድረሱ እሁድ ዕለት መዘገባችን ይታወሳል። በስብሰባው ላይ ከተሳተፉት የግንባሩ አባል ድርጅቶች መካከል የቀረበውን ሃሳብ ተቃውመው ድምጽ የሰጡት የህወሓት አባላት ሲሆኑ ከቀድሞው የደህንነት ተቋም ኃላፊ ከአቶ ጌታቸው አሰፋ በስተቀር የህወሓት አባላት መሳተፋቸውን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አባል አቶ አስመላሽ ወልደሥላሴ በወቅቱ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
47931824
https://www.bbc.com/amharic/47931824
በሰሜን ተራሮች ፓርክ በሄሊኮፕተር ውሃ እየተረጨ ነው
በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በድጋሚ የተከሰተውን እሳት ለማጥፋት ከደቡብ አፍሪካ የመጣችው ሄሊኮፕተር ትላንት ሥራ ጀምራለች።
ሄሊኮፕተሯ በደቡብ አፍሪካ የተመዘገበች ሲሆን ንብረትነቷ የኬንያ መሆኑን በሰሜን ተራሮች ፓርክ የህብረተሰብ እና የቱሪዝም ኃላፊ አቶ ታደሰ ይግዛው ለቢቢሲ አስታውቀዋል። ዛሬ ማለዳ የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ገዛኸኝ አባተ ለቢቢሲ እንደገለፁት በትናንትናው እለት ከኬኒያ የመጣችው እሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተር አምስት ጊዜ በመመላለስ ርጭት አካሂዳለች። 9 አባላት ያሉት የእስራኤላውያን የእሳት አደጋ ሰራተኞች ቡድንም በትናንትናው እለት በስፍራው የደረሰ ሲሆን ከሄሊኮፕተር አብራሪው ጋር እሳቱን በተሻለ መልኩ እንዴት ማጥፋት ይቻላል የሚለውን ይመካከራሉ ብለዋል። • እሳቱን ለማጥፋት ከኬኒያ መንግሥት ሄሊኮፕተር ተጠየቀ • በሰሜን ተራሮች በድጋሚ የተነሳውን እሳት ለመቆጣጠር ጥረቱ ቀጥሏል • የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከለከለ ሰሞኑን በድጋሚ የተቀሰቀሰውን እሳት ለማጥፋት በተደረገው ሥራ፣ ጓሳ ሳር ያለበትን የላይኛውን ክፍል በህብረተሰቡ ርብርብ ጠፍቷል ያሉት ኃላፊው ገደላማው የፓርኩ ክፍል አስቸጋሪ በመሆኑ ከትላንት ጀምሮ በሄሊኮፕተር የማጥፋት ሥራው ተጀምሯል ብለዋል። ሄሊኮፕተሯ ውሃ የምትቀዳው ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ አቅራቢያ ከሚገኘው አፈራ ወንዝ ነው ያሉት አቶ ታደሰ፣ ነዳጅ ለመሙላት ደግሞ ጎንደር እንደምትመላለስ አስረድተዋል። በየበረራው መካከል የሚደረገው የቴክኒክ ፍተሻ እንዳለ ሆኖ በቀን ከስምንት እስከ አስር ጊዜ የውሃ ርጭት ታደርጋለች ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ ያለውን ሂደት ያስረዳሉ። በዛሬው ዕለት የእሳቱ መጠን በከፍተኛ መጠን መቀነሱን የተናገሩት አቶ ታደሰ፤ እስራኤላውያን የእሳት አደጋ ሰራተኞች ዛሬ ጠዋት ቅኝት አከናውነው እሳቱ ቀላል መሆኑን እንደተናገሩ ገልጸዋል። እንደ አቶ ገዛኸኝ ከሆነ ባለሙያዎቹ እሳቱን በተሻለ ሁኔታ እንዴት መቆጣጠር ይቻላል የሚለው ላይ የሚሰሩ ሲሆን ከዚህ በኋላም በፓርኮች ተመሳሳይ የእሳት አደጋ እንዳይደርስ መከላከል የሚቻልበት መንገድ ላይ ይሰራሉ ብለዋል። መንግሥት በሰሜን ተራሮች የተከሰተው የእሳት አደጋ ሰዎች እንደለኮሱት አምኗል ያሉት አቶ ገዛኸኝ አባተ እነማን ናቸው የሚለው በምርመራ ላይ ያለ ነው ብለዋል። እሳቱ በፓርኩ ላይ ያደረሰው ጉዳት እስካሁን ያልታወቀ መሆኑን የገለፁት ቃል አቀባዩ "እስካሁን ድረስ ከብርቅዬ እንስሳቶቻችን መካከል አንድም እንዳልሞተ ነው የምናምነው" ሲሉ ተናግረዋል።
47493182
https://www.bbc.com/amharic/47493182
ሩሲያ ባለስልጣኖቿ እንዳይሰደቡ የሚከለክል ህግ አወጣች
ሩሲያ በተለይ የባለስልጣናቴን ስብዕና የሚያንቋሽሽና በአጠቃላይ የሩሲያን ክብር የሚነካ ነገር እያየሁ አልታገስም ለዚህም የመከላከያ ህግ ያስፈልገኛል ብላለች።
ህጉም በረቂቅ ደረጃ ተዘጋጅቶ የፕሬዝዳንት ፑቲንን ፊርማ ብቻ እየጠበቀ ነው። በሌላ በኩል የሀሰት መረጃዎችን ማሰራጨትና ማጋራትም ሩሲያን ያሳሰበ ጉዳይ በመሆኑ ሌላ ህግ እንዲዘጋጅለት ተደርጓል። ሁለቱንም ረቂቅ ህጎች የሩሲያ የላይኛው ምክር ቤት ከተወያየባቸው በኋላ በሚቀጥለው መጋቢት 13 ፕሬዝዳንት ፑቲን ፈርመውባቸው ህግ ሆነው እንደሚወጡ ይጠበቃል። •ዕጣ የወጣባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች በኦሮሚያ ተቃውሞን ቀሰቀሱ በሁለቱም ህጎች ተላልፎ የሚገኝ ማንኛውም ዜጋ ከፍተኛ ቅጣት የሚጠብቀው ሲሆን ስም በማጉደፍ የተጠረጠረ ግለሰብ እስከ 15 ቀናት እስራት ሊቀጣ ይችላል። ህጉን ተላልፎ ባለስልጣናትን ያጥላላ ወይም ስብዕናቸውን የሚነካ ጽሁፍ ወይም ንግግር ያሰራጨ ግለሰብ 100000 ሩብል ወይም 1500 ዶላር ሊቀጣ ይችላል።በድጋሚ ተመሳሳይ ችግር ከፈጸመ ደግሞ ቅጣቱ ሁለት ወይም ሶስት እጥፍ ይሆናል። የሃሰት ዜና ያሰራጨ ደግሞ ግለሰብ ፣ ባለስልጣንና የቢዝነስ ተቋማት ተብሎ የተከፋፈለ ሲ ሆን በቅደም ተከተል 300000 ፣600000 እና 1 ሚሊዮን ሩብል እንደሚቀጡ ረቂቅ ህጉ ያትታል። •"በራሷ ገቢ የምትተማመንና መቆም የምትችል ሀገር መፍጠር እሻለሁ"ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በህጉ መሰረት ከሀገሪቱ ፍትህ ሚኒስቴር ፈቃድ ወስደው የሚሰሩ የብሮድ ካስት ሚዲያዎች ፍቃድ እስከመነጠቅ ገደብ ሲጣልባቸው የዜና መረቦች ደግሞ ያለቅድመ ማሰጠንቀቂያ ሊዘጉ ይችላሉ። •የጋራ መኖርያ ቤቶቹ በዕጣ መተላለፋቸውን የኦሮሚያ ክልል ተቃወመ ይህንን ተከትሎም ጋዜጠኞች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና ሚንስትሮችም ጭምር ረቂቅ ህጉን በመቃወም ድምጻቸውን እያሰሙ ይገኛሉ። ኒኮላይ ስቫኒድዜ የተባለው ጋዜጠኛ ለቢቢሲ ሲናገር "ይህ አረመኔ የሆነ ምክር ቤት ጋዜጠኞች እንዳይናገሩና እንዳይጽፉ አንደበታቸውን ሊዘጋቸው ነው" ብሏል። የድረገፅ ዘጋቢዎችም የመንግስትን ድክመት የሚናገሩ የሌሎችን ሰዎች ሃሳብ እንዳንወስድ ለማሸማቀቅ ታሰቦ የተሰራ ነው እያሉ ነው። የፓርላማ አባሉ ፓቬል ክራሸኒኒኮቭ እንደገለጹት ግን ህጉ "በድረ ገጽ የተከፈተን ሽብርተኝነት ለመከላከል ነው"። ሌላኛው የፓርላማ አባል አናቶላይ ቪቦርኒ እንደገለጹት ደግሞ ህጉ የተዘጋጀው "ስነ ምግባር ያለው ዜጋን ለመፍጠርና ተጠያቂነትን ለማስፈን ነው"።
news-56886036
https://www.bbc.com/amharic/news-56886036
በክብረ ወሰን የተንበሸበሸው የዘንድሮው የኦስካር ሽልማት
ኖማድላንድ የተሰኘው የድራማ ዘውግ ያለው ሲኒማ ሦስት የአስካር ሽልማቶችን በማግኘት የዘንድሮው አነጋጋሪ ፊልም ሆኗል።
ዳንኤል ካሉያ፣ ሰር አንተኒ ሆፕኪንስ እና ክሎዊ ዣዎ የዘንድሮው ኦስካር 'የመጀመሪያው' እና 'የመጀመሪያዋ' በሚሉ ቅጥያዎች የደመቀና በክብረ-ወሰን የተንበሸበሸ ነው ብንል ማጋነን አይሆንም። ጥቁር እንግሊዛዊው ዳንኤል ካሉያና ሰር አንተኒ ሆፕኪንስ በትወና ዘርፍ አሸናፊ ለመሆን ችለዋል። ዳይሬክተሯ ክሎዊ ዣዎ በምርጥ ሴት ዳይሬክተር ዘርፍ የኦስካር ሽልማት በማግኘት የመጀመሪያዋ እስያዊት ሆናለች። የ83 ዓመቱ ሰን አንተኒ ሆፕኪንስ ምርጥ ተዋናይ በመባል በዕድሜ ትልቁ ተሸላሚ ሲሆን ዳንኤል ካሉያ ደግሞ በምርጥ ረዳት ተዋናይ ዘርፍ ኦስካር ያገኘ የመጀመሪያው ጥቁር ብሪታኒያዊ ሆኗል። ፍራንሲስ ማክዶርማን 'ኖማድላንድ' ላይ ባሳየችው ትወና ምርጥ ሴት ተዋናይት ተብላ የኦስካር ሽልማት አግኝታለች። በሴት ረዳት ተዋናይ ዘርፍ ደግሞ ደቡብ ኮሪያዊቷ ዩህ-ጁንግ ናት ሽልማቱን መውሰድ የቻለችው። የዘንድሮው ኦስካር ሽልማት ሎስ አንጀለስ ውስጥ ባለ አንድ ግዙፍ አዳራሽ ውስጥ ሰዎች ዘርዘር ብለው ተቀምጠው ነው የተከናወነው። በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ያሉ ዕጩዎች ደግሞ ለንደን ውስጥ በሚገኝ አዳራሽ ነው የሽልማት ሥነ-ሥርዓቱን የተከታተሉት። በሁለቱም አዳራሾች ውስጥ ያልታየው ሰር አንተኒ ሆፕኪንስ 'ዘ ፋዘር' በተሰኘው ፊልም ነው ሽልማት ያገኘው። 'ሳይለንስ ኦፍ ዘ ላምብስ' በተሰኘው ቀደምት ፊልሙ ከ25 ዓመታት በፊት የኦስካር ሽልማት ያገኘው ሆፕኪንስ አንድ የማስታወስ ችግር ያለበት አባት ሆኖ በተወነበት ፊልሙ ሁለተኛ ኦስካሩን አግኝቷል። ማያ ኔል፣ ጃሚካ ዊልሰን እና ሰርጂዮ ሎፔዝ ሪቬራ የፊልም ሜካፕና የጸጉር ሥራ አሸናሪ ሆነዋል ምርጥ ወንድ ተዋናይ በተሰኘው ዘርፍ ሟቹ ተዋናይ ቻድዊክ ቦስማን ያሸንፋል ተብሎ ተጠብቆ ነበር። የዌልስ ዜግነት ያለው ሆፕኪንስ ማሸነፉ ብዙዎች ያልጠበቁት ነበር። ለዚህም ይሆናል ተዋናዩ በሁለቱም አዳራሾች ያልተገኘው። ሌላኛው የምሽቱ መነጋገሪያ የነበረው 'ኖማድላንድ' ዳይሬክት የተደረገው ቻይና ተወልዳ፣ እንግሊዝ ተምራ አሜሪካ በምትኖረው ዣዎ ነው። ዣዎ በታሪክ ኦስካር ያሸነፈች ሁለተኛዋ ሴት ዳይሬክተርና የመጀመሪያዋ ነጭ ያልሆነች ሴት በመሆን ታሪክ ፅፋለች። በምሽቱ ኖማድላንድ 3 ሽልማቶችን፣ ዘ ፋዘር፣ ጁዳስ ኤንድ ዘ ብላክ መሳያህ፣ ማ ሬይኒ፣ ማንክ፣ ሶል እንዲሁም ሳውንድ ኦፍ ሜታል እያንዳንዳቸው 2 ሽልማቶችን አሸንፈዋል። የ32 ዓመቱ የለንደን ነዋሪ ዳንኤል ካሉያ ጁዳስ ኤንድ ዘ ብላክ መሳያህ በተሰኘው ፊልም ላይ ባሳየው ብቃት ነው ኦስካር የተቀዳጀው። ዩህ-ጁንግ ዩን ኦስካር ያገኘች የመጀመሪያዋ ደቡብ ኮሪያዊት ሆናለች። በወጣትና ተስፋ ያላቸው የሲኒማ ሴቶች ዘርፍ እንግሊዛዊቷ ኤሜራልድ ፌኔል አሸናፉ ሆናለች። የዘንድሮው የኦስካር ሽልማት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከወትሮው በሁለት ወራት ዘግይቶ ነው የተከናወነው። ተዋንያኑ በአዳራሾቹ ዘርዘር ብለው ይቀመጡ እንጂ አብዛኛዎቹ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ አላደረጉም ነበር።
news-53018870
https://www.bbc.com/amharic/news-53018870
ፊልም ለመቅረጽ ሲል የጎዳና ተዳዳሪዎችን መርዝ ያበላው ሰው በቁጥጥር ሥር ዋለ
በአሜሪካ ካሊፎርኒያ አንድ ግለሰብ ስምንት የጎዳና ተዳዳሪዎችን አፍዝ አድንግዝ እጽ በምግብ ለውሶ ሰጥቷቸዋል፡፡
ዊሊያም ሮበርት ኬብል የ38 ዓመት ጎልማሳ ሲሆን ይህን አደንዛዥ መርዝ ለጎዳና ተዳዳሪዎቹ ከሰጣቸው በኋላ ሲሰቃዩ እርሱ ይቀርጻቸው ነበር ተብሏል፡፡የጎዳና ተዳዳሪዎቹ በተመገቡት የተመረዘ ምግብ የተነሳ ሆስፒታል ነው የሚገኙት፡፡ ተከሳሹ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ 19 ዓመት ዘብጥያ ይወርዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡የኦሬንጅ ወረዳ የሕግ ጠበቃ ቶድ ስፒዘር እንደተናገሩት ተከሳሹ እነዚህን ሰዎች የመረጣቸው ድህነታቸውን ተጠቅሞ ነው፡፡ የነርሱን ስቃይ በካሜራ ቀርጾ እርሱ ለመዝናኛነት ሊያውለው ነው ያሰበው፤ ይህ ጭካኔ ነው ብለዋል ቶድ፡፡በካሊፎርኒያ የኦሬንጅ ወረዳ አቃቢ ሕግ እንዳብራራው ተከሳሹ የጎዳና ተዳዳሪዎችን ያገኛቸው በሀንቲግተን የባሕር ዳርቻ ሲሆን ምግብ እንደሚፈልጉ ከጠየቃቸው በኋላ አዎ ሲሉት የተመረዘ ምግብ አቀብሏቸዋል። አንዳንዶቹ የጎዳና ተዳዳሪዎች ተከሳሹ የሚያቃጥል ምግብ ውድድር እያደረኩ ነው፣ ቶሎ የጨረሰ ይሸለማል በሚል አታልሎ እንደቀረጻቸው ተናግረዋል፡፡ ያቀረበላቸው የተመረዘ ምግብ በአደገኛ በርበሬና ቃሪያ የተሰነገና እጅግ የሚያቃጥል ነው ተብሏል፡፡ምግቡን ከቀመሱ በኋላ የጎዳና ተዳዳሪዎቹ ግማሾቹ ራሳቸውን የሳቱ ሲሆን ቀሪዎቹ ለመተንፈስ ተቸግረው ታይተዋል፡፡ ሌሎች ደግሞ ሲያስመልሳቸው ነበር፡፡ ተከሳሹ አሁን በግማሽ ሚሊዮን ዶላር ዋስ የተለቀቀ ሲሆን ባፈለው ወር ነበር በቁጥጥር ሥር የዋለው፡፡አቃቢ ሕግ በሰውየው ላይ 8 ክሶችን አቅርቦበታል፡፡ ከጎዳና ተዳዳሪዎቹ አንዱ ሽማግሌ ሲሆኑ ትንንሽ ልጆችም ይገኙበታል፡፡ ይህም ክሱን ያጠናክርበታል፡፡ ባለፈው ዓመት አንድ ስፔናዊ የዩቲዩብ አሰናጅ በተመሳሳይ የጎዳና ተዳዳሪዎችን አትታሎ ኦሪዮ ብስኩት እያስበላ ቀርጻ ሲያደርግ ነበር፡፡ ብስኩቱ ተለውሶ የነበረው ደግሞ በጥርስ ሳሙና ፈሳሽ ነበር፡፡ይህ ሰው 15 ወራት ተፈርዶበት ዘብጥያ ወርዷል፡፡
news-54958646
https://www.bbc.com/amharic/news-54958646
ከቤተሰቧ ጋር የሞተችው የ12 ዓመት ታዳጊ አሳዛኝ ቪድዮ
ባለፈው ወር ከቤተሰቧ ጋር የእንግሊዝ ሰርጥን ለመሻገር ስትሞክር የሞተች ኢራናዊት-ኩርድ ታዳጊን የሚያሳይ ቪድዮ ተሰራጭቶ ነበር።
አኒታ ኢራንጃድ በቪድዮው የ12 ዓመቷ ታዳጊ እየሳቀችና እያለቀሰች "ስሜ አኒታ ኢራንጃድ ነው። የተወለድኩት ሳራዳሳሀት ነው" ትላለች። ቪድዮው በትውልድ አገሯ ለሚዘጋጅ የአጭር ፊልም ውድድር የተዘጋጀ ነው። ቪድዮው ላይ አባቷ ከኋላ ሆኖ ሲያበረታታት ይሰማል። "ተዋናይ መሆን እፈልጋለሁ" ትላለች አኒታ በቪድዮው። ቪድዮው ቤተሰባዊ መደጋገፍ፣ ተስፋ ይታይበታል። አባቷ ራሱል ልጁ ህልሟን እንድታሳካ ይመኛል። ግን ቀዬያቸው የተጨቆነና በግጭት የሚናጥ ነው። በምዕራብ ኢራን ኩርዶች በብዛት የሚኖሩባት ሳራዳሳሀት ነው የተወለዱት። ታዳጊዋ ቪድዮውን ለውድድር ካስገባች ከዓመት በኋላ አባቷና እናቷ ከሦስት ልጆቻቸው ጋር ወደ አውሮፓ ጉዞ ጀመሩ። አኒታ፣ የስድስት ወሩ አርሚን እና የ15 ወሩ አርቲን ከቤተሰቦቻቸው ጋር የጀመሩት አደገኛ ጉዞ ነበር። ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ይጓዝ የነበረው አነስተኛ መርከብ ጥቂት እንደተጓዙ ተገለበጠ። ተሳፋሪዎቹ ነፍስ አድን ጃኬት አላደረጉም ነበር። የትውልድ መንደራቸው በሕይወት ለመቆየት ከሚደረግ ትግል ባለፈ ህልም የሚሳካበት አይደለም። ብዙዎች ሥራ አጥ ናቸው። ወደ ኢራቅ ኩርዲስታን ድንበር በሕገ ወጥ መንገድ ቁሳቁስ በማዘዋወር የሚተዳደሩም ብዙ ናቸው። ትርፋማ ግን አይደሉም። ባለፉት ጥቂት ዓመታት በርካቶች በኢራን ድንበር ጠባቂዎች ተገድለዋል፤ የቆሰሉም አሉ። "ሀዘን ልቤን ቢሰብረውም ኩርዲስታንን ትቼ ከመሄድ ውጪ አማራጭ የለኝም" እአአ ከ1979ኙ የኢራን አብዮት ወዲህ በኢራን የጸጥታ ኃይሎች እና በታጣቂዎቹ ኩርዶች መካከል ግጭት አልቆመም። ኩርዶች ለመብታችን እየታገልን ነው ሲሉ ኢራን ደግሞ በውጪ ኃይሎች የሚደገፉ ተገንጣዮች ትላቸዋለች። ከኢራን 10 በመቶው ኩርዶች ናቸው። የተባበሩት መንግሥታት እንደሚለው፤ አብላጫውን ቁጥር የያዙት እስረኞች እነሱ ናቸው። አምና ጸረ መንግሥት ተቃውሞ ከተካሄደ በኋላ ከፍተኛ እርምጃ እየተወሰደ ነው። የአኒታ አባት ከእስር ለማምለጥ ነበር ጉዞውን የጀመረው። ንብረታቸውን ሸጠው፣ ገንዘብ ከጓኞቻቸው ተበድረው፤ ወደ አውሮፓ ለሚያሻግሩ ሰዎች ከፍለው ነበር። ህልማቸው ዩናይትድ ኪንግደም ደርሶ ጥገኝነት መጠየቅ ነበር። የራሱል ጓደኞች ለቢቢሲ የላኩት ቪድዮ ላይ ራሱል እየሰጠመ ሳለ በኩርድኛ ሲዘፍን ይታያል። "ሀዘን ልቤን ቢሰብረውም ኩርዲስታንን ትቼ ከመሄድ ውጪ አማራጭ የለኝም" እያለ ሲዘፍን ልጁ አርሚን ይስቅ ነበር። ጨቅላ ልጁ አርቲን ደግሞ ወደአባቱ እየዳኸ ይሄድ ነበር። "ከተራራዎቹ ውጪ ወዳጅ የለንም" ኩርዶች "ከተራራዎቹ ውጪ ወዳጅ የለንም" የሚል አባባል አላቸው። የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት አክትሞ፤ የኦቶማን ግዛት ከወደቀ በኋላ ኩርዶች ነጻ እንደሚወጡ በውጪ ኃይሎች ቃል ሲገባላቸው ነበር። በግዛቲቱ ግን ተቀባይነት አላገኘም። እንዲያውም የትውልድ ቀዬያቸው በሦስት የመካከለኛው ምሥራቅ ግዛቶች ተከፋፈለ። ቤተሰቡ ከዚያ በኋላ በኢራን፣ በቱርክ፣ በሶርያ እና በኢራቅ የሚኖሩ ኩርዶች የነጻነት ትግል ፍሬ አላፈራም። ራሱል እና ባለቤቱ ሺቫ ወደ አውሮፓ ለመሻገር 24,000 ዩሮ ከፍለዋል። ሦስት ልጆቻቸውን ይዘው ከቱርክ ወደ ጣልያን ከዚያም ወደ ሰሜን ፈረንሳይ መሻገር ነበር እቅዳቸው። ሺቫን በዱንኪክ የእርዳታ መስጫ ያገኘቻት በጎ ፍቃደኛ አድራ "በጣም ቀና ሰው ናት። ትንሽ ኩርድኛ አዋርቻት ስትስቅ ነበር" ስትል ታስታውሳታለች። ሺቫ እና ባለቤቷ በፈረንሳይ ጉዟቸው ሀብት ንብረታቸውን በአጠቃላይ ተዘረፉ። ያኔ ለጓደኛዋ በላከችው የጽሁፍ መልዕክት፤ ለቀጣዩ የጉዟቸው ክፍል ለጭነት መኪና የሚሆን ገንዘብ እንደሌላቸው ገልጻ ነበር። ከራሱል ጋር የነበረ ጓደኛው እንደሚለው፤ አዘዋዋሪዎቹ በቀጣዩ ቀን ጉዞ እንደሚቀጥሉ ነገሯቸው። ያ ቀን ከፍተኛ ንፋስ ስለነበር ጓደኛው ላለመሄድ ወሰነ። "ራሱልም እንዳይሄድ ለምኜው ነበር" ሲል ያስታውሳል። አብሯቸው የነበረ ዘጋቢ ፊልም ሰሪ ኢብራሂም ሞሐመድ ኑር እንደሚለው፤ ጀልባው ለስምንት ሰው ብቻ የተዘጋጀ ነበር። ከጭነቱ ጋር ግን 23 ሰዎች ነበሩ። በጀልባው የነበረው የ16 ዓመቱ ያሲን፤ ከእሱና ሌሎች ሁለት ሰዎች ውጪ ነፍስ አድን ጃኬት ያደረገ ሰው እንዳልነበረ ይናገራል። 22ቱም ተጓዦች የአንድ መንደር ነዋሪዎች ነበሩ። ሺቫና ልጆቿ በመስታወት የተሸፈነ ቦታ ላይ ነበሩ። ቦታው ሙቀት የሚሰጣቸው ይመስል ነበር። ግን አደጋው ሲከሰት አልታደጋቸውም። ስምንት ኪሎ ሜትር ከሄዱ በኋላ ጀልባው በውሃ መሞላቱን ኢብራሂም ይናገራል። "ውሃውን ለማፍሰስ ሞክረን ነበር። አልተሳካም" ይላል። ተሳፋሪዎቹ ደንግጠው መንቀሳቀስ ሲጀምሩ ጀልባው ተገለበጠ። የዩኒቨርስቲ ተማሪው ፒሻው ሺቫ እና ልጆቿ የነበሩበት መስታወት ሰብሮ ሊያድናቸው ቢሞክርም አልተሳካም። ራሱል ውሃው ውስጥ ገብቶ ሊያወጣቸው ሞክሮ ነበር። እርዳታ ለማግኘት እየጮኸም ነበር። ራሱል አርቲንን ካወጣ በኋላ ሁለቱን ልጆቹና ባለቤቱን ለማውጣት ተመልሶም ነበር። ኢብራሂም ይህ ሁሉ ሲሆን፤ አኒታ ውሃው ላይ ስትንሳፈፍ እንዳየ ያስታውሳል። እያለቀሰ "በአንድ እጄ ጀልባውን ይዤ በሌላ እጄ ታቀፍኳት። በሕይወት ያለች መስሎኝ ነበር። ግን ሞታለች። ራሴን ይቅር አልለውም" ይላል። ራሱል ከውሃው ሲወጣ እያንዳንዱን የቤተሰቡን ስም እየጠራ እያነባ ነበር። ከዚያም በውሃው ተወሰደ። የፈረንሳይ ባለሥልጣናት እንደሚሉት ሰዎቹን ለመታደግ የመጀመሪያው መርከብ የደረሰው ከአደጋው ከ17 ደቂቃ በኋላ ነበር። ከአደጋው የተረፉት እንደሚሉት፤ ራሱል፣ ሺቫ፣ አኒታ እና አርሚን ሞተዋል። ጨቅላው አርቲን እየተፈለገ የነበረ ቢሆንም እንደሞተ ይታመናል። 15 ሰዎች ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። የመርከቡ ካፒቴኔን የሆነ ኢራናዊ በነፍስ ማጥፋት እንደሚከሰስ የፈረንሳይ መርማሪዎች ተናግረዋል። በዚህ መንገድ ወደ አውሮፓ የሚገቡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው። 2018 ላይ 297 ሰዎች በአነስተኛ ጀልባ ዩናይትድ ኪንግደም ደርሰዋል። 2019 ላይ 1,840 በዚህ ዓመት ደግሞ ወደ 8,000 ገደማ ሰዎች ተጉዘዋል። አብዛኞቹ ጥገኝነት ጠያቂዎች ኢራናውያን ናቸው።
news-46997615
https://www.bbc.com/amharic/news-46997615
የህንድ ፊልም አፍቃሪዎች ወተት እየሰረቁ ነው
በደቡባዊ ህንድ ታሚል ናዱ ግዛት የሚገኙ ወተት ሻጮች መጠነ ሰፊ የወተት ዝርፊያ እየተካሄደባቸው መሆኑን ለፖሊስ ገልጸዋል።
ህንድ ውስጥ በአንዳንድ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ላይ ለመልካም ዕድል እየተባለ አማልክት ላይ ወተት ማፍሰስ የተለመደ ነው። ታዲያ ይህንን ባህል በመከተል በግዛቲቱ የሚገኙ የፊልም አፍቃሪዎች የሚወዱት ፊልም ስኬታማ እንዲሆን በማለት ግዙፍ ማስታወቂያዎች ላይ ወተት ማፍሰስ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ወተቱን የሚያመጡት ደግሞ ከሻጮች በመስረቅ መሆኑ ነገሩን ትንሽ ለየት ያደርገዋል። የወተት ሻጮቹ በፊልም አፍቃሪዎቹ ምክንያት ከባድ ኪሳራ እንደደረሰባቸው በምሬት ለፖሊስ አስታውቀዋል። • በረከት ስምኦን ከየት ተነስተው እዚህ ደረሱ • መስታወት መፃዒውን ለማየት እንደሚያስችል ያውቁ ኖሯል? የወተት ሻጮች ማህበሩ ፕሬዝዳንት ደግሞ ይህ ሥነ ሥርዓት የሚካሄደው ለአማላክት እንጂ ለፊልም ተዋናዮች አይደለም ሲሉ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። ፖሊስ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ማህበሩ የጠየቀ ሲሆን ፖሊስም አታስቡ እርምጃ እወስዳለሁ ብሏቸዋል። 'ፓላቢሼካም' በመባል የሚታወቀው ሥነ ሥርዓት የሚካሄደው ፊልሙን ለማስተዋወቅ በተሰቀሉ ግዙፍ ማስታወቂያዎች ላይ እና የፊልም ተዋናዮቹ ትንንሽ ምሥሎች ላይ ወተት በማፍሰስ ነው። ይህ ለ20 ዓመታት ሲደረግ ነበር ሥነ ሥርዓት አድናቂዎቹ የወደዱት ፊልም ስኬታማ እንዲሆን ያደርገዋል ተብሎ ይታመናል። በታሚል ናዱ ግዛት የሚገኙት የወተት አከፋፋዮች በትልልቅ መኪናዎች የሰበሰቧቸውን ወተቶች በየሱቆቻቸው ደጃፍ ላይ በማስቀመጥ ነው የሚሸጧቸው። እነዚህ ለማዳ የተባሉት የወተት ቀበኞች ታዲያ አሳቻ ሰዓት በመጠበቅና ባለሱቆቹ ሲዘናጉ የቻሉትን ያህል ወተት ተሸክመው ይሮጣሉ፤ አልያም በመኪናቸው ይዘው ይሰወራሉ። • ታማሚዋን ያስረገዘው ነርስ በቁጥጥር ስር ዋለ ታዋቂው የቦሊዉድ ፊልም ተዋናይ ሲላምባርሳን አዲስ የለቀቀው ፊልሙ ተወዳጅ እንዲሆንለት አድናቂዎቹ በየመንገዱ የተሰቀሉ ማስታወቂያዎችን ወተት በወተት አድርገዋቸዋል። እሱም ወተት እንዲያፈሱለት የተማጽኖ መልእክት አስተላልፎ ነበር። ታዲያ ታዋቂው ፊልም ተዋናይ የለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምሥል በታሚል ናዱ ግዛት ብዙ ተቀባዮችን ማግኘቱ የወተት ሻጮችን ሕይወት ከባድ አድርጎታል እየተባለ ነው።
news-50542198
https://www.bbc.com/amharic/news-50542198
ቻይናዊው ቢሊየነር ጃክ ማ በአዲስ አበባ
ቻይናዊው ጉምቱ የቢዝነስ ሰው ጃክ ማ አዲስ አበባ ገብተው ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ጋር መክረዋል።
አሊባባ የተሰኘው ግዙፉ የቻይና 'ኦንላይን' መገበያያ መድረክ አጋር መሥራች የሆኑት ጃክ ማ ትላንት ምሽት ነው ለሁለት ቀናት ጉብኝት ኢትዮጵያ የገቡት። አይሲቲ ፓርክ የተገኙት ጃካ ማ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ጋር በመሆን 'ኤሌክትሮኒክ ዎርልድ ትሬድ ፎረም' [ኢደብልዩቲፒ] የተሰኘ ፕሮጀክት መርቀዋል። ፕሮጀክቱ በዓለም ዙሪያ ምርቶቻቸውን ማስተዋወቅ እና መገበያየት ለሚፈልጉ አነስተኛ ቢዝነሶች ዕድል ይሰጣል ተብሎለታል። ኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን ኮሚዪኒኬሽን ቴክኖሎጂ [አይሲቲ] የኢንቨስትመንት አማራጭ እንዲሆን ደፋ ቀና በማለት ላይ ትገኛለች። አይሲቲ ፓርክም የተገነባው ኢትዮጵያን የአፍሪካ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል ለማድረግ እንደሆነ መንግሥት ይናገራል። ባለፈው ሚያዚያ ቻይና አቅንተው የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፤ ሃንግዡ የሚገኘውን የአሊባባ ዋና መሥሪያ ቤት መጎብኘታቸው አይዘነጋም። የጃክ ማ አሊባባና የኢትዮጵያ መንግሥት በኤሌክትሮኒክስ የታገዘ ዓለም አቀፍ የንግድ መገናኛ ማዕከል ለመገንባት የፊርማ ስምምነት አድርገዋል። በስምምነቱ መሠረት ኢትዮጵያዊያን ምርቶች በቻይና እና በቻይና ጎረቤት ሃገራት ገበያዎች ላይ እንዲተዋወቁ ይደረጋል። ቻይናዊው የቢዝነስ ሰው ጃክ ማ በ33 ዓመታቸው ነው የመጀመሪያ ኮምፒውተራቸውን ገዝተው ወደ 'ኦንላይን' ወይም በይነመረብ ቢዝነስ የገቡት። በግሪጎሪያዊያን አቆጣጠር 2017 ላይ ፎርብስ የተሰኘው መፅሔት ባወጣው መረጃ መሠረት ጃክ ማ 36.6 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ሃብት አላቸው። አሊባባ በተሰኘው እጅግ ግዙፍ 'ኦንላይን' መገበያያ ላይ ያላቸው 9 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ 420 ቢሊዮን ዶላር ይገመታል። ባለፈው ሳምንት ናይጄሪያ የነበሩት የትዊተር አጋር መሥራችና ዋና ኃላፊ የሆኑት ጃክ ዶርዚ ለቀናት ጉብኝት ኢትዮጵያ ገብተዋል።
news-57313043
https://www.bbc.com/amharic/news-57313043
ኮሮናቫይረስ፡ የዓለም ጤና ድርጅት ለአዲሶቹ የኮቪድ ዝርያዎች የግሪክ ስያሜዎችን ሰጠ
የዓለም ጤና ድርጅት ለአዳዲሶቹ የኮቪድ-19 ዝርያዎች ስም ለመስጠት የሚያስችል ስርአት ማዘጋጀቱን አስታወቀ።
ከዚህ በኋላም ድርጅቱ የቫይረሱን አይነቶች ለመለየት የግሪክ ፊደላትን የሚጠቀም ሲሆን በዩናይትድ ኪንግደም፣ ደቡብ አፍሪካና ሕንድ ውስጥ የታዩት አዳዲስ ዝርያዎች መጀመሪያ ስያሜ ይሰጣቸዋል። ለምሳሌም በዩናይትድ ኪንግደም የታየው አዲሱ ቫይረስ ዝርያ 'አልፋ' የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። የደቡቡ አፍሪካው 'ቤታ' የተባለ ሲሆን በሕንድ በርካቶችን ያጠቃው የቫይረስ አይነት ደግሞ 'ዴልታ' ተብሎ እንደሚጠራ የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። የዓለም ጤና ድርጅት ስያሜዎቹን ያስተዋወቅኩት አንደኛ በንግግር ወቅት ቀላል ለማድረግና በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በቫይረሱ ዙሪያ የሚኖሩ የተለያዩ ማግለሎችን ለማስቀረት ነው ብሏል። ባሳለፍነው የፈረንጆቹ ወር መጀመሪያ አካባቢ የሕንድ መንግሥት በአገሪቱ የተገኘውን የኮቪድ-19 አዲስ ቫይረስ 'ቢ.1.617.2' የሚል ስያሜ መስጠቱን ተከትሎ በርካታ ትችቶችን አስተናግዶ ነበር። ''የትኛውም አገር አዲስ የቫይረሱ አይነቶችን ሪፖርት በማድረጉ መገለል ሊደርስበት አይገባም'' ብለዋል የዓለም ጤና ደርጅት ቴክኒካል መሪ የሆኑት ማሪያ ቫን ኬርኮቭ። አክለውም አገራት አዲሶቹ ቫይረሶች ላይ ጠበቅ ያለ የክትትልና የምርመራ ስራ እንዲያከናውኑ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። አዲሱ የቫይረሶቹ ስያሜ ከተለያዩ ነገሮች አንጻር ከግምት ውስጥ እንደገባ የተገለጸ ሲሆን የሁሉም ቫይረሶች ስም ዝርዝር በዓለም ጤና ድርጅት ድረገጽ ላይ ይፋ ተደርጓል። እነኚህ የግሪክ ፊደላት አሁን በጥቅም ላይ እየዋሉ የሚገኙትን ሳይንሳዊ ስሞች የሚተኩ አይደለም። አዲሶቹ የኮሮናቫይረስ አይነቶች ከ24 የሚበልጡ ከሆነ የተዘጋጀው ስርአት ፊደላት ያልቁበታል። በዚህም መሰረት አዲስ ስያሜ የመስጠት ስርአት ይዘረጋል ብለዋል ማሪያ ቫን ኬርኮቭ። ''እኛ እያልን ያለነው እንደ ቢ.1.617.2 ያሉ ሳይንሳዊ ስያሜዎችን ሙሉ በሙሉ መቀየር ሳይሆን ሁሉም ሰው የሚረዳው አይነት ስያሜ እንስጠው ነው። ስያሜው ቀለል ሲል ማህበረሰቡ በዕለት ተዕለት ግንኙነቱ ይጠቀማቸዋል'' ብለዋል። ሰኞ ዕለት የዩናይትድ ኪንግደም መንግስትን የሚያማክሩ ተመራማሪዎች አገሪቱ በሶስተኛው ዙር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የመጀመሪያ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ገልጸዋል። በዋነኛነት ሰዎችን እያጠቃ የሚገኘውም 'ዴልታ' የሚል ስያሜ የተሰጠው የሕንዱ ዝርያ ነው። ይህ ዝርያ 'አልፋ' የሚል ስያሜ ከተሰጠው የዩኬው ዝርያ በበለጠ መልኩ በቶሎ መሰራጨት የሚችል ሲሆን በዩኬ ለጨመረው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ምክንያት ነው። በሌላ በኩል በቬትናም የተስተዋለው አዲሱ የቫይረስ አይነት በሕንድ እና ዩናይትድ ኪንግደም ከታዩት የቫይረሱ ዝርያዎች የተቀላቀለ ሲሆን በቀላሉ በአየር መተላለፍ የሚችል ነው።
news-55761780
https://www.bbc.com/amharic/news-55761780
ሪፐብሊካኖች የትራምፕ 'የፍርድ ሂደት ፍትሃዊ ለማድረግ' እንዲዘገይ ጠየቁ
የአሜሪካ ሪፐብሊካን የህግ መምሪያ ምክር ቤት እንደራሴዎች የተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ክስ እስከሚቀጥለው ወር እንዲራዘም ዲሞክራቶችን ጠይቀዋል።
ሪፐብሊካኖቹ ይህንን ጥያቄ ያቀረቡት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለፍርዱ ሂደት ዝግጅት ጊዜ እንዲያገኙ ነው። የቀድሞው ፕሬዚዳንት በቅርቡ የተከሰተውን የካፒቶሉን ነውጥ አነሳስተዋል በሚል እንዲከሰሱ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል። ከስልጣን ሊለቁ ጥቂት ቀናት በቀራቸው ወቅት ያለመከሰስ መብታቸው እንዲገፈፍና በአመፅና ሁከት እንዲከሰሱም ለማስቻል እንደራሴዎቹ በአብላጫ ድምፅ መወሰናቸው የሚታወስ ነው። ለሪፐብሊካን አቻቸው ጥሪ ያደረጉት ሚክ ማኮኔል ዲሞክራት እንደራሴዎች የመጀመሪያ ሂደት ክሱን ከማቅረብ እንዲዘገዩና ትራምፕም ለዝግጅት ሁለት ሳምንት ያህል እንዲኖራቸው ጠይቀዋል። የክሱ ሂደት በአውሮፓውያኑ የካቲት አጋማሽ ላይ ቢጀመር ለትራምፕ በቂ ጊዜ ይኖራቸዋል ብለዋል። ከትናንት ጀምሮ ሪፐብሊካኖች በምክር ቤቱ አብላጫ ወንበር መኖሩን ማቆም ተከትሎ የዲሞክራቶች መሪ ቹክ ሹመር በሃሳቡ ላይ ይስማማ ዘንድ ግድ ይላል ተብሏል። የዲሞክራት እንደራሴዎች በበኩላቸው ክሱን ለምክር ቤቱ ለማቅረብ ዝግጅታቸውን ጨርሷል ተብሏል። በትናንትናው ዕለት ይፋዊ የስልጣን ዘመናቸው ያበቃው የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የተከታያቸውን ጆ ባይደንን በዓለ ሲመት ሳይታደሙ ወደ ፍሎሪዳ አቅንተዋል። የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከወር በፊት ነበር በዋይት ሃውስ አቅራቢያ ለነበሩ ሰልፈኞች "በሰላማዊና በአርበኝነት" ድምፃቸው እንዲሰማ እንዲያደርጉ ጥሪ ያስተላለፉት። ነውጠኛ ሰልፈኞቹ ወደ አሜሪካው ካፒቶል ህንፃ እየተቃረቡ ነበር ተብሏል። የቀድሞው ፕሬዚዳንት አክለውም "በእልህ እንዲታገሉም" ለደጋፊዎቻቸው ተናግረዋል። ነውጠኛ ደጋፊዎቻቸውም ወደ ካፒቶል ሂል ህንፃ ሰብረው ገቡ፤ ከፍተኛ ሁከት ተነሳ። በወቅቱም በህንፃው የምክር ቤቱ እንደራሴዎች ተመራጭ የነበሩትን የጆ ባይደንን ፕሬዚዳንታዊ ድል ይፋዊ ለማድረግ ስብሰባ ላይ ነበሩ። በተነሳውም ሁከት አራት ተቃዋሚዎች ሲገደሉ በቦታው የነበረ የካፒቶል ፖሊስም ተገድሏል። ሁከቱና ነውጡ ከተነሳ ከሳምንት በኋላ በስልጣን ላይ እያሉ ሁለት ጊዜ እንዲከሰሱ የተወሰነባቸው ወይም ኮንግረሱ በወንጀሎች የጠየቃቸው የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ሆኑ። ከስልጣን ከተገለሉ በኋላ የፍርድ ሂደታቸው በምክር ቤቱ የሚታይ የመጀመሪያ ሰው አድርጓቸዋል። ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙም እስከ ወዲያኛው ድረስ መቼም ቢሆን በስልጣን ቦታ ላይ እንዳይቀመጡ ይደረጋል።
news-43819632
https://www.bbc.com/amharic/news-43819632
ዚምባብዌ በሺህ የሚቆጠሩ ነርሶችን አባረረች
ባለፈው ሰኞ አድማ አድርገው የነበሩትን ከ 10ሺ በላይ የሚሆኑ ነርሶች ዚምባብዌ ከሥራ ገበታቸው አባረረች።
የዚምባብዌ ነርሶች ማህበር ውሳኔውን መከታተላቸውንና በአድማው ግን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል ምክትል ፕሬዚዳንት ኮንስታንቲኖ ቺዌንጋ ነርሶቹ ደምወዛቸውን ለመጨመር ታስቦ 17 ሚልዮን ዶላር ከተለቀቀም በኋላ ወደ ሥራ ገበታቸው ለመመለስ ፈቃደኛ እንዳልነበሩ ተናግረዋል። ነርሶቹ ''የሰውን ሕይወት ለማዳን'' ወደ ሥራ ገበታቸው ስላልተመለሱ ምክትል ፕሬዝደንቱ ኮንነዋቸዋል። ወኪሎች እንደሚናገሩት ከሆነ ይህ ነርሶቹን ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ ግፊት ማድረጊያ ዘዴ ነው ይላሉ። ለፕሬዘዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ የጤናውን ዘርፍ መሻሻል ፈተና ሆኖባቸዋል። በቅርቡም የዶክተሮችን የሥራ አድማ ለማስቆም ክፍያቸውን ለመጨመር ተስማምተው ነበር። ቀድሞው የወታደራዊ ኃይል ኃላፊ የነበሩትና ሮበርት ሙጋቤን ከስልጣን ለማውረድ ይታገሉ የነበሩት ጄን ቺዌንጋ በሰጡት መግለጫ ላይ ''መንግሥት አድማ ያደረጉትን ነርሶች ከሥራ ለማባረር የወሰነው የታመሙ ሰዎችን ሕይወት ለማዳን ባለው ፍላጎት ነው'' ብለዋል። ቀጥለውም ሥራ አጥ የሆኑና ጡረታ የወጡ ነርሶች የተባረሩትን ነርሶች እንዲተኩ እንደሚደረግ ተናግረዋል። በምላሹም የዚምባብዌ ነርሶች ማህበር የምንግሥትን ውሳኔ እያጤኑት እንደሆነ እና በአድማው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
news-45179431
https://www.bbc.com/amharic/news-45179431
ለኑሮ ምቹ የሆኑት ቀዳሚዎቹ 10 ከተሞች ይፋ ሆኑ
የኦስትሪያ መዲና ቬይና ቁጥር አንድ የዓለማችን ለኑሮ ምቹ ከተማ ተብላ ተሰይማለች። ቬይና ከዚህ ቀደም ቁጥር አንድ ለኑሮ ምቹ ከተማ ተብላ የነበረችው የአውስትራሊያዋ ሜልበርን ከተማን ተሽላ በመገኘት ነው ለዚህ ማዕረግ የበቃችው።
ቬይና ምቹ ከተማ ተብላለች በኢኮኖሚስት ኢንተለጀንስ ዩኒት የዓለም ከተሞች የዳሰሳ ጥናት መሰረት፤ በአውሮፓ የሚገኝ ከተማ በዓለም ቁጥር አንድ ምቹ ከተማ ተብሎ ሲሰየም ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። የዳሰሳ ጥናቱ በ140 ከተሞች ሲካሄድ የመጠነ ሀብትና ማህበራዊ መረጋጋት፣ የወንጀል መጠን፣ የትምህርትና የጤና አገልግሎቶች እንዲሁም መሰል መስፈርቶችን ከግምት በማስገባት ነው። በዳሰሳ ጥናቱ ውስጥ የእንግሊዟ ማንችስተር ከተማ 16 ደረጃዎችን በማሻሻል 35ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን፤ ይህም በጥናቱ ከተካተቱ ከተሞች የተሻለ መሻሻል ያሳየች ከተማ አስብሏታል። የአውስትራሊያዋ ሜልበርን ከተማ ላለፉት ሰባት ዓመታት በአንደኝነት ስትመራ ቆይታ ነበር ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በዳሰሳ ጥናቱ ላይ የተካተቱት ሁሉም ከተሞች ለነዋሪዎች ምቹ በመሆን መሻሻል አሳይተዋል። በዘንድሮው የዳሰሳ ጥናት ሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው የአውስትራሊያዋ ሜልበርን ከተማ ላለፉት ሰባት ዓመታት በአንደኝነት ስትመራ ቆይታ ነበር። ሰሜን አሜሪካዊቷ ሃገር ካናዳና አውስትራሊያ እያንዳንዳቸው ለኑሮ ምቹ የሆኑ ሶስት ከተሞችን አስመርጠዋል። • በምስራቅ ሐረርጌ 37 ሰዎች ተገደሉ • በኢትዮጵያ የመንጋ ፍትህ የሰው ህይወት እየቀጠፈ ነው • ደቡብ ሱዳን ለበጎ ፍቃደኞች አስጊ ሃገር ተባለች ለኑሮ ምቹ ያልሆኑ ከተሞች በሚለው ዘርፍ ደግሞ ከቀዳሚዎቹ አስር ከተሞች አራቱ በአፍሪካ የሚገኙ ናቸው። በጦርነት እየተመሰቃቀለች የምትገኘው የሶሪያዋ ደማስቆ ከተማ ፈጽሞ ለኑሮ የማትመች ተብላለች። ዘ ኢኮኖሚስት እንደሚለው ከሆነ ''ለኑሮ ምቹ ያልሆኑ ከተሞች'' በተባሉት ከተሞች ውስጥ ወንጀል፣ ማህበራዊ አለመረጋጋት፣ ሽብርተኝነት እና ጦርነት በስፋት ይስተዋላሉ ። ደማስቆ በዓለም የማትመቸው ከተማ ተብላለች የ2018 አስሩ ለኑሮ ምቹ የሆኑት ከተሞች 1. ቬይና፣ ኦስትሪያ 2. ሜልበርን፣ አውስትራሊያ 3. ኦሳካ፣ ጃፓን 4. ካልጋሪ፣ ካናዳ 5. ሲደኒ፣ አውስትራሊያ 6. ቫንኮቨር፣ ካናዳ 7. ቶኪዮ፣ ጃፓን 8. ቶሮንቶ፣ ካናዳ 9. ኮፐንሃገን፣ ዴንማርክ 10. አደሌይድ፣ አውስትራሊያ የ2018 አስሩ ለኑሮ ምቹ ያልሆኑት ከተሞች ደረጃ 1. ደማስቆ፣ ሶሪያ 2. ዳካ፣ ባንግላዴሽ 3. ሌጎስ፣ ናይጄሪያ 4. ካራቺ፣ ፓኪስታን 5. ፖርት ሞሬስቤይ፣ ፓፓኦ ኒው ጊኒ 6. ሃራሬ፣ ዚምባብዌ 7. ትሪፖሊ፣ ሊቢያ 8. ዶኡላ፣ ካሜሮን 9. አልጀርስ፣ አልጄሪያ 10. ዳካር፣ ሴኔጋል
news-56441608
https://www.bbc.com/amharic/news-56441608
አልጀሪያውያኑ ለሳምንታት ኑሯቸውን በፓሪስ አየር ማረፊያ አድርገዋል ተባለ
ከዩናይትድ ኪንግደም መነሻቸውን ያደረጉ ሃያ ስድስት አልጀሪያውያን ከፓሪስ አየር ማረፊያ መውጣት አልቻሉም ተብሏል።
በፖሪሱ ቻርለስ ደ ጎል አየር ማረፊያም ውስጥ ለሶስት ሳምንታት ያህል መኖሪያቸውን አድርገዋል ተብሏል። ከእንግሊዝ የተነሱት እነዚህ አልጀሪያውያን ውስጥ ሁለት ህፃናትና አንዲት የ75 አዛውንት አሉበት ተብሏል። መንገደኞቹ ፓሪስ ሲደርሱ አሳፍሯቸው የነበረው የአልጀሪያ አየር መንገድ ኤይር አልጀሪያ በኮቪድ-19 መመሪያዎች ምክንያት ጉዟቸውን መቀጠል እንደማይችሉ ተነገራቸው። ከዚያም በኋላ አለም አቀፍ መንገደኞች መሻገሪያ በሆነው ተርሚናል 2 ውስጥ መኖሪያቸውን አድርገዋል ተብሏል። በፓሪስ ተቀማጭነቱን ያደረገው የአልጀሪያ ኤምባሲ ለቢቢሲ እንደተናገረው ከበረራቸው በፊት ቲኬታቸውን መሰረዙን ለመንገደኞች አስታውቋል። በአልጄሪያ ውስጥ የዩኬ-ኬንት ኮቪድ ዝርያ መገኘቱንም ተከትሎ ነው መንገደኞቹ እንዳይገቡ የተደረገው። ከመንገደኞቹ መካከል አንደኛው እንደተናገረው አንዳንዶቹ የእንግሊዝ ፓስፖርት ያላቸው ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ በእንግሊዝ ነዋሪነታቸውን ያደረጉ ወይም የእንግሊዝ ቪዛ ያላቸው ናቸው። የአንዲት ሴት ቪዛም ጊዜው አልፎበታል ተብሏል። ሌላኛው ደግሞ "ህገ ወጥ ስደተኛ' ነህ በሚል ወደ አልጀሪያ የሚመለስ መንገደኛ ነው ተብሏል። ሁሉም መንገደኞች ቢሆን ወደ አልጀሪያ የሚመለሱበት አፋጣኝ ምክንያት እንዳላቸው ነው። አንዳንዶቹም የታመመዙ ዘመዶች አሏቸው ተብሏል። አየር ማረፊያው ላይ ከደረሱ በወለሎች ላይ እንዲሁም በወንበሮች ላይ እየተኙ እንደሆነ የተነገረ ሲሆን ምግብ የሚያገኙት ከበጎ ፈቃደኞች ነው ተብሏል። ሌላኛው መንገደኛ በሆስፒታል ውስጥ ህክምና እየተደረገለት መሆኑ ተነግሯል። የመንግሥት ንብረት የሆነው ኤይር አልጀሪያ መጀመሪያ አካባቢ ለመንገደኞቹ ነፃ ምግብ እየሰጠ የነበረ ቢሆንም ወደ ለንደን ልመልሳችሁ ሲል እምቢ በማለታቸው ምግብ መስጠቱን አቁሟል ተብሏል።
news-54090720
https://www.bbc.com/amharic/news-54090720
የሴቶች ጥቃት፡ የ86 አመት የእድሜ ባለፀጋ አያት መደፈር መላ ህንድን አስደንግጧል
የመደፈር ጥቃት ከፍተኛ በሆነባት ህንድ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች በየአመቱ ይደፈራሉ።
አንዳንድ ጥቃቶች ደግሞ ጎልተው ይወጡና በርካቶችን ያስደነግጣሉ። ከሰሞኑም በህንዷ መዲና ደልሂ የ86 አመት እድሜ ባለፀጋ አያት መደፈራቸውን ህንድን አንቀጥቅጧታል። የእድሜ ባለፀጋዋን በመድፈር በ30ዎቹ ዕድሜ የሚገኝ ግለሰብ ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሏል። ግለሰቧ በዚህ ሳምንት ሰኞ እለት ወተት የሚያመጣላቸውን ሰው እየጠበቁ ባለበት ወቅት ጥቃት እንደደረሰባቸው የደልሂ የሴቶች ኮሚሽን ስዋቲ ማሊዋል ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ጥቃት አድራሹ ወተት የሚያመጣላቸው ግለሰብ እንደማይመጣና ወተት የሚመጣበት ስፍራ ልውሰድዎት አላቸው" ብለዋል። አያቲቷ ምንም ባለመጠራጠር ግለሰቡን ተከትለውት የሄዱ ሲሆን ቀረብ ወዳለ እርሻ ቦታም በመውሰድ እንደደፈራቸው ስዋቲ አስረድተዋል። "እያለቀሱም እንዲተዋቸው ለመኑት። አያቱ ማለት እንደሆነም ተማፀኑት። ግን ልመናቸውም ሆነ መማፀናቸው ትርጉም አልነበረውም። ራሳቸውን ለመካለከልም ሲታገሉ ክፉኛ ድብደባ ፈፅሞባዋቸዋል። ከዚያም ደፈራቸው" ብለዋል። በአካባቢው ሲዘዋወሩ የነበሩ ነዋሪዎች ለቅሷቸውን ሰምተው እንዳዳኗቸው ተነግሯል። ግለሰቡንም በቁጥጥር ስር በማዋል ለፖሊስ አሳልፈው ሰጥተዋል። ስዋቲ ማሊዋል ጥቃት የደረሰባቸውን የእድሜ ባለፀጋ ማክሰኞ እለት በቤታቸው ሄደው የጎበኟቸው ሲሆን፤ ካዋሯቸውም በኋላ ሁኔታቸውን"ልብ የሚሰብር" ብለውታል። "እጃቸው ተላልጧል። ያለፉበትን ለሰማ በጣም የሚያስደነግጥ ነው። ፊታቸው አባብጧል፤ ሰውነታቸው ቆስሏል። ብልታቸውም እየደማ ነበር። ከፍተኛ የሆነ ድብደባም ተፈፅሞባቸዋል። የደረሰባቸውን ሰነ ልቦናዊ ጉዳት በቃላት መግለፅ ይከብዳል" በማለትም ኃዘናቸውን ገልፀዋል። ስዋቲ ጥቃቱን ያደረሰው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣም ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን " ሰው አይደለም" በማለት ጠንከር ባለ ቃል ተናግረዋል። "በደልሂ ለሚገኙ የፍትህ ቢሮ ኃላፊዎች፣ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የከተማዋ አስተዳዳሪዎች ግለሰቡን በስድስት ወራት ውስጥ በስቅላት እንዲቀጡትም ደብዳቤ ፅፌያለሁ" በማለት የሚገባውን ቅጣትም ገልፀዋል።
news-52916925
https://www.bbc.com/amharic/news-52916925
ስዊድንን ጎረቤቶቿ ለምን ይሆን ያገለሏት?
ስዊድን በኮቪድ-19 ላይ የተከተለችውን ፍልስፍና በዓለም ላይ የትኛውም አገር አልተከተለውም። ይህ የቫይረሱ የመጨረሻው ምዕራፍ ከሆነ እውነትም ስዊድን ፍልስፍናዋ ዋጋ ሳያስከፍላት አልቀረም።
ስዊዲናዊያን አካላዊ ርቀትን እንዲጠብቁ እንጂ ከቤታቸው እንዳይወጡ አልታዘዙም ለምሳሌ ዴንማርክና ኖርዌይ ውድ ጎረቤቶቿ ናቸው። የብልጽግና ቁንጮ ተደርገው የሚታዩት እነዚህ ሦስቱ አገሮች እንደ ወንድምና እህት ያህል ይቀራረባሉ ማለት ይቻላል። በብዙ መንገድ መመሳሰል አላቸው። በኮሮና ተህዋስ ዙርያ የተከተሉት መመርያ ግን ለየቅል ነው። የወረርሽኙን መከሰት ተከትሎ ስዊድን እጅግ ልል የሆነ መመርያን ነው ለሕዝቧ ያስተላለፈችው። ጎረቤቶቿ ወለም ዘለም የማይባልበትን ሁሉን አቀፍ የጉዞና የእንቅስቃሴ እቀባ ሲያደርጉ ስዊድን ግን "አዋቂ አይመከርም፤ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እያደረጋችሁ ኑራችሁን ቀጥሉ" የሚል መልዕክት ነው ያስተላለፈችው ለሕዝቧ። "ከዚህ ሌላ ትንሽም ቢሆን ሕመም ከተሰማችሁ ከቤት አትውጡ" ብላለች ዜጎቿን። ታመው ቤት የዋሉ ዜጎች ደመወዛቸው ሳይቀነስ ይከፈላቸዋል። በስዊድን ከተሞች ለሚዘዋወር በዓለም ላይ እጅግ አደገኛ ወረርሸኝ ስለመከሰቱ እምብዛምም ላይሰማው ይችላል። የሰዎች እንቅስቃሴ ከወትሮው ብዙም አልተለየም ነበር። ካፌዎችና ሬስቶራንቶች ሥራቸውን ቀጥለዋል። ሰዎች ርቀታቸውን ጠብቀው ይዝናናሉ። የሕዝብ ትራንስፖርት አልተቋረጠም። ይህ ሁኔታ ስዊድንን ጎድቷታል የሚሉ አሉ። እነ ዴንማርክና ኖርዌይ ታዲያ ከሰሞኑ ድንበራቸውን ሲከፍቱ፤ ጎረቤታቸው ስዊድንን ገሸሽ ያደረጉበት አንዱ ምክንያትም ይኸው ነው። እርግጥ ነው ስዊድን ከመጀመርያውም ቢሆን ከቤት እንዳትወጡ ብላ እንደ ሌሎች የአውሮፓ አገራት ዜጎቿን አላስጨነቀችም። በጣሊያንና ስፔን ሰዎች እንደ ቅጠል ሲረግፉ ስዊድኖች በየካፌው ሰብሰብ ብለው ድራፍታቸውን ይጨልጡ ነበር። ዶ/ር አንደርስ ተግኔል ከዚህ ልል ፍልስፍና ጀርባ ያለ ሰው ነው። በድርጊቱ መጠነኛ ጸጸት የተሰማው ይመስላል። ግን ደግሞ ተሳስተን ነበር ለማለትም ጊዜ ገና እንደሆነ ይናገራል። ዶ/ር አንደርስ ተግኔል "ከዚህ ልል የመከላከል ፍልስፍናችን የተነሳ ከፍ ያለ ቁጥር ያለው ዜጋ ሳይሞትብን አልቀረም" ብሏል ትናንት ከስዊድን ራዲዮ ጋር በነበረው ቆይታ። ስዊድን እስከ ትናንት ድረስ 40 ሺህ 800 ሰዎች በኮሮና ተህዋስ ሲያዙባት፣ 4 ሺህ 542 ሰዎች ደግሞ ሞተውባታል። ይህ ከነጣሊያን፣ ስፔንና ዩናይትድ ኪንግደም ጋር ሲነጻጸር ትንሽ ቢመስልም ለስካንዲኒቪያን አገሮች ግን አስደንጋጭ ቁጥር ነው። እነ ዴንማርክ፣ ፊንላንድና ኖርዌይ ጠበቅ ያለ መመርያን ለሕዝባቸው በማስተላለፋቸው ከዚህ በጣም ያነሰ የሟች ቁጥር ነው ያስመዘገቡት። ለምሳሌ ዴንማርክ 580 ዜጎች ብቻ ናቸው የሞቱባት፤ ኖርዌይ በበኩሏ 237 ሰዎች ሞተውባታል። ፊንላንድ 321 ዜጎቿን አጥታለች። 10 ሚሊዮን ሕዝብ ያላት ስዊድን ከተጠቀሰው አሃዝ በተጨማሪ ትናንት ረቡዕ ተጨማሪ 74 ሰዎች ሞተውባታል። ዶ/ር አንደርስ ተግነል በስዊድን የኅብረተሰብ ጤና ኃላፊና የኮቪድ-19 ጉዳዮች ዋናው ተጠሪ ናቸው። ባለፈው ሚያዚያ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ አገራቸው ስዊድን የምትከተለው ፍልስፍና ላላ ያለ መሆኑ ችግር እንዳላስከተለ ተናግረው ነበር። ለጊዜው የሟቾች ቁጥር ከፍ ያለውም የአዛውንቶች ማረፊያ የሆኑ የእንክብካቤ ማዕከላት ቫይረሱን ለመመከት በመዘግየታቸው እንደሆነ ነበር የተናገሩት። ትናንት ግን ዶ/ር ተግነል ለስዊድን የሕዝብ ራዲዮ እንዳመኑት "ከዚህ ወዲህ እንዲህ ዓይነት ወረርሽኝ ቢመጣ ምላሻችን እንዳሁኑ ይሆናል ብዬ አላምንም። ያኔ ፍልስፍናችን የሚሆነው አሁን እኛ በተከተልነውና ሌላው ዓለም በተከተለው ጥብቅ መመርያ መሀል የሚሆን ይመስለኛል" ብለዋል። በተከተልነው ልል መመሪያ ምክንያት በርካታ ዜጎቻችንን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጥተናል ማለት ይቻላል ወይ? ተብለው ሲጠየቁም "አዎ! ይህ ምንም ጥርጥሬ የለውም" ብለዋል። ነገር ግን ስዊድን በትክክል ምን ማድረግ ነበረባት በሚለው ዙሪያ አሁንም ግልጽ ምላሽ አልሰጡም። ትናንት ረቡዕ በነበረው ሌላ ጋዜጣዊ መግለጫ ለምሳሌ "ስዊድን ቫይረሱን ለመከላከል የተከተለችው ፍልስፍና ትክክል ነበር" ብለዋል። "በመሠረተ ሐሳብ ደረጃ ስዊድን ትክክለኛውን የመከላከል ዘዴ ነው የተከተለችው ብለን ነው አሁንም የምናምነው" ሲሉ ተደምጠዋል ዶ/ር አንደርስ ተግነል። "ልዩነታችን ሌሎች አገሮች በአንድ ጊዜ ድንበራቸውን ዘጋግተው ዜጎቻቸውን በቤታቸው ውስጥ ሲቆልፉ እኛ የተከተልነው ዘዴ ግን ቁጥጥሩን ቀስ በቀስ ማጥበቅ ላይ ነበር።" "አሁንም ቢሆን የእኛ አካሄድ ችግር ነበረበት ለማለት ጊዜ ገና ነው" ብለዋል። "ከታሪክ እንደምንረዳው እንዲህ ያሉ ወረርሽኞች ዳግም ሲመጡ የከፋ ጉዳት ያደርሳሉ" ሲሉ ለድምዳሜ ጊዜው ገና እንደሆነ ጠቁመዋል። ዴንማርክ የእንቅስቃሴ ገደቦችን አንስታ የእግር ኳስ ውድድር በዝግ ስታዲም እንዲካሄድ ፈቅዳለች ልል የተባለው የስዊድን መመሪያ እንዴት ያለ ነበር? በርካታ አገራት በሕዝባቸውን ላይ ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብ ሲጥሉ ስዊድን ይህንን አላደረገችም። እርግጥ ነው ስዊድን በሕዝቧ መልካም ፈቃድ ላይ የተመሰረተ የማኅበራዊ መራራቅን አበረታታለች። ከ50 ሰዎች በላይ በአንድ ቦታና ጊዜ መሰብሰብን ከልክላለች። ይህም ወደ በኋላ የሆነ ነው። በእድሜ የገፉ ዜጎችን መጎብኘትንም ከልክላ ነበር። ስዊድን እጅግ አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ጉዞ ማድረግን አላበረታታችም። ሆኖም ጥንቃቄ ባለው ሁኔታ ጉዞ ማድረግን ስዊድን አልከለከለችም። ዘመድ ወዳጅ ጥየቃ በእድሜ የገፉ ሰዎች ጋር እስካልሆነ ድረስ ክልከላ አልነበረውም። ዴንማርክና ኖርዌይ ይህ የስዊድን አካሄድ ብዙም ስሜት የሰጣቸው አይመስልም። የኖርዌይ የኅብረተሰብ ጤና ኃላፊ ፍሮድ ፎርላንድ እንደተናገሩት ስዊድን በይበልጥ ትኩረት ያደረገችውና የተከተለችው ታሪካዊ የቫይረሶችን የሥርጭት ሞዴልን ነው። እኛ በአንጻሩ ጠርቅመን በራችን መዝጋት ነው የመረጥነው" ብለዋል። የስዊድን የቀድሞው የኅብረተሰብ ጤና ኃላፊ አኒካ ሊንድ አገሪቱ የተከተለችው የመከላከል ፍልስፍና ትክክል እንዳልነበረ ፊት ለፊት ተናግረዋል። በሦስት ነገሮች ላይ ልዩ ትኩረት መስጠት ሲገባ ይህ እንዳልተደረገ ነው ያብራሩት። የቀድሞ የኅብረተሰብ ጤና ጉዳዮች ኃላፊ ይህ እንዳልተደረገ ጠቅሰው አገራቸው ስዊድን በተከተለችው ልል መመሪያ ምክንያት የደረሰውን ጥፋት ተችተዋል። የስዊድን መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ከሆነ የዚህ ስዊድን የተከተለችው ልል ፍልስፍና አመንጪና መሪ ለሆኑት ዶ/ር አንደርስ ተግነል በቅርቡ ካልታወቁ ሰዎች የግድያ ዛቻ በኢሜይል ደርሷቸዋል። ያም ሆኖ በስዊድን በመንግሥት፣ በሕዝብና በተቋማት መካከል ከፍተኛ መተማን እንዳለ ይነገራል። ዶ/ር ተግነል በቅርቡ ለአሜሪካ ዴይሊ ሾው አሰናጅ ትሪቨር ኖዋ እንደገለጹት የሕዝባቸው 70 እና 80 ከመቶው ስዊድን የተከተለችው ልል የመከላከል እርምጃ ተገቢ ነው ብሎ ያምናል።
news-49534094
https://www.bbc.com/amharic/news-49534094
የአማዞን እሳት ሕይወታቸውን ያሳጣቸው ጥንዶች
የኢዲ ሮድሪገስ እና የባለቤቷ ሮሚልዶ ቤት እንዳልነበር ሆኗል። እነሱም እስከወዲያኛው አሸልበዋል።
ኢዲ ሮድሪገስ እና ባለቤቷ ሮሚልዶ የዛሬን አያድርገውና ጥንዶቹ ቤታቸውን በአማዞን በሚገኝ መንደር የሠሩት በኩራት ነበር። ማቻዲንሆ ዴኦስቴ የምትባለው መንደር በደቡብ ምዕራብ ብራዚል ትገኛለች። በአካባቢው በተደጋጋሚ የሚነሳው እሳት ጥንዶቹን ያሰጋቸው ነበር። • 'የዓለም ሳምባ' የሚባለው አማዞን ጫካ በአስፈሪ ሁኔታ እየነደደ ነው በተለይም ዝናብ በሌለበት ወቅት በአቅራቢያቸው እሳት ሲነሳ 'አንድ ቀን እኛ ጓሮ ይደርስ ይሆን' ብለው ይፈሩ ነበር። ነሐሴ 13 ቀን ጥንዶቹ የፈሩት ደረሰ፤ ቤታቸው በእሳት ጋየ፤ እነሱም ሕይወታቸውን አጡ። የጥንዶቹ ቤት ጥንዶቹ የሞቱት ቤታቸውን ለማዳን ሲጣጣሩ ነበር። ከኢድ ልጆች አንዷ ጄግስሌን ካርቫልሁ ለቢቢሲ እንዲህ ብላለች፦ "እዚ አካባቢ እሳት በመጠቀም መሬት ይመነጠራል፤ ያን ቀን ግን ንፋሱ ከቁጥጥር ውጪ ስለነበር እሳቱን ማጥፋት አልተቻለም፤ ሮጠው የሚያመልጡበት ጊዜ እንኳን አላገኙም።" • 'የዓለም ሳምባ' የሚባለው አማዞን ጫካ በአስፈሪ ሁኔታ እየነደደ ነው የአማዞን ደን በእሳት መጋየት ከጀመረ ቀናት ተቆጥረዋል። እሳቱ እየጨመረ መምጣቱን የሳተላይት ምስሎች ያሳያሉ። ካለፈው ዓመት ጀምሮ በአካባቢው የሚነሳው እሳት 76 በመቶ ጨምሯል። ጥንዶቹ ይኖሩበት በነበረው አካባቢ ብቻ 6,500 የአማዞን ቦታዎች እሳት ተነስቷል። የአማዞን ደን በእሳት መንደድ የዓለም መነጋገሪያ ከመሆኑም በላይ፤ የተለያዩ አገራት መሪዎች የብራዚል ፕሬዘዳንት ጃይር ቦልሶናሮ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ እየጠየቁ ነው። የቡድን 7 አገራት ለብራዚል የ 22 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለመስጠት መስማማታቸውን የፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ቢናገሩም የብራዚሉ ፕሬዘዳንት አልተቀበሉም። የብራዚል አመራሮችም የውጪ ኃይሎች በብራዚል ፖለቲካ እጃቸውን ለማስገባት ጥረት እያደረጉ ነው ብለዋል። • "የከተማ መስፋፋት የኢትዮጵያን ብዝሀ ሕይወት አደጋ ላይ ጥሏል" ዶ/ር መለሰ ማርዮ ኢዲ ሮድሪገስ እና ባለቤቷ ሮሚልዶ ቤት የሠሩበትን መሬት የገዙት ለ10 ዓመት ብር አጠራቅመው ነበር። ጎረቤቶቻቸው ለፖሊሶች እንደተናገሩት፤ ቤታቸው በእሳት ሲያያዝ ጨክነው ጥለውት መሄድ አልቻሉም ነበር። እንደሌሎቹ የመንደሩ ነዋሪዎች እሳቱን ለማጥፋት ጥረት እያደረጉም ነበር። በመንደሩ ይገኙ የነበሩ ዛፎች ተመንጥረው ስላለቁ እሳቱ ለመሰራጨት ጊዜ አልወሰደበትም። ከኢድ ልጆች አንዷ የሆነችው ጄግስሌን እንደተናገረችው፤ ጥንዶቹ በቅርቡ የገዙትን የጣሪያ ንጣፍ ለማዳን ብዙ ደክመዋል። "እቃቸውን እያወጡ እሳት ወዳልደረሰበት አካባቢ እየወሰዱ እንደነበር ጎረቤቶቻቸው ነግረውኛል።" እሳቱ ከሁለት አቅጣጫ መጥቶ ቤቱን አውድሞታል እሳቱ ከሁለት የተለያየ አቅጣጫ እየተቀጣጠለ ስለነበር ጥንዶቹ ራሳቸውን ማዳን አልቻሉም። አንድ የአይን እማኝ ለፖሊስ እንደተናገሩት፤ እሳቱ ከቁጥጥር ውጪ ቢሆንም የአካባቢው ነዋሪዎች የእሳት አደጋ ተከላካይ ሠራተኞችን አልጠሩም። "ሠራተኞቹን ያልጠሩት በደን ጭፍጨፋ ተጠያቂ እናደረጋለን ብለው ስለፈሩ ነው" ሲሉም አስረድተዋል። • ኢትዮጵያ ሀይቆቿን መጠበቅ ለምን ተሳናት? የእሳት አደጋ ተከላካይ ሠራተኞች በአካባቢው የደረሱት ጥንዶቹ ሞተው በማግሥቱ (ነሐሴ 14) ነበር። ጥንዶቹ ሕይወታቸው ያለፈው በካርቦን ሞኖክሳይድ ታፍነው ነው ተብሏል። ጥንዶቹ ዶሮና እሳማ ያረቡ ነበር የጥንዶቹ ጎረቤቶች ከእሳቱ ተርፈዋል። ጉዳዩን እያጣሩ ያሉት መርማሪ ስሌሶ ኮንድገስክ "እሳቱን ያስነሱት ሰዎች በግድያ ተጠያቂ ይደረጋሉ" ብለዋል። ከኢድ ልጆች አንዷ የሆነችው ጄግስሌንም "ፍትህ እንሻለን" ብላለች።
55914561
https://www.bbc.com/amharic/55914561
ቢሊየነሩ ጄፍ ቤዞስ ከአማዞን ሥራ አስፈጻሚነቱ ሊለቅ ነው
የአማዞን መሥራችና ባለቤት ጄፍ ቤዞስ ከኩባንያው ሥራ አስፈጻሚነት እንደሚለቅ አስታወቀ።
ቤዞስ ከ30 ዓመት ዕድሜው ጀምሮ አምጦ የወለደውን ድርጅቱን የሚለቀው ሌሎች ሥራዎች ላይ ለማተኮር በማሰቡ ነው። ሆኖም ከአማዞን የዕለት ተዕለት ሥራ አስፈጻሚነት ቢለቅም የበላይ ጠባቂ ሆኖ መሥራቱን አይተውም። 'እዚህ ውሳኔ ላይ የደረስኩት ጊዜዬንና ጉልበቴን ሌሎች ሥራዎች ላይ ለማድረግ ስለፈለኩ ነው' ብሏል ቢሊየነሩ ጄፍ ቤዞስ። የዓለም ቢሊየነሩን ቤዞስን በሥራ አስፈጻሚነት የሚተኩት አንዲ ጄሲ ይሆናሉ። አንዲ የአማዞንን ክላውድ ኮምፒውቲንግ ቢዝነስ ክፍል ኃላፊ ሆነው የቆዩ ናቸው። ጄፍ ቤዞስ ከሥራ አስፈጻሚነቱ በይፋ የሚለቀው በዚህ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት አጋማሽ ይሆናል። 'የአማዞን ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ መሥራት ፋታ የለውም። ጊዜና ጉልበትን ያሟጥጣል። እንዲህ ዓይነት ኃላፊነት ላይ መሆን ሌሎች ነገሮች ላይ ለማተኮር ጊዜ አይሰጥም' ይላል ቤዞስ በይፋ በጻፈው የመልቀቂያ ደብዳቤ። 'እንደ በላይ ጠባቂ ሆኜ በዋና ዋና የአማዞን ጉዳዮች ብቻ እየተሳተፍኩ ትኩረቴን ግን ለሌሎች ድርጅቶቼ መስጠት እፈልጋለሁ' ብሏል በዚሁ ደብዳቤ ቤዞስ። ቢሊየነር ቤዞስ አሁን ትኩረት ሊያደርግበት የፈለጋቸው የሥራ ዘርፎች በህዋ ትራንስፖርት ላይ የሚያተኩረው ብሉ ኦሪጂን እንዲሁም ዋሺንግተን ፖስት ጋዜጣ ህትመት እና ሌሎች የግል ፍላጎቶቹ ላይ ነው። 'በፍጹም ጡረታ እየወጣሁ አይደለም፤ ጉልበቴና የመንፈስ ጥንካሬዬ አሁንም እንዳለ ነው፤ ነገር ግን ትኩረቴን ሌሎች ነገሮች ላይ ለማዋል ስለፈለኩ ብቻ ነው' ብሏል ቤዞስ በዚሁ ደብዳቤው። ቢሊየነሩ ቤዞስ አሁን 57 ዓመቱ ነው። የአማዞን የበይነ መረብ ገበያን የጀመረው በ1994 ሲሆን ያን ጊዜ መጽሐፍ በበይነ መረብ የሚሸጥ ትንሽ ድርጅት ሆኖ ነበር አማዞን የተመሰረተው። አሁን አማዞን በመላው ዓለም 1.3 ሚሊዮን ሰራተኞች አሉት። በ2020 ዓ/ም ብቻ የአማዞን ጠቅላላ ሽያጭ 386 ቢሊዮን ዶላር አልፏል። ይህም የሆነው በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት የበይነ መረብ ገበያው ስለደራ ነው። ጄፍ ቤዞስ በፎርብስ የሀብት ዝርዝር ውስጥ የተጠቀሰለት ሀብቱ 192 ቢሊዯን ዶላር ደርሷል።
news-53526233
https://www.bbc.com/amharic/news-53526233
ማኅበረሰቡ ከኮቪድ-19 ራሱን ከመጠበቅ ተዘናግቷል፡ የተለያዩ ከተማ ነዋሪዎች
ማኅበረሰቡ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ተገቢውን ጥንቃቄ እያደረገ እንዳልሆነና ከጊዜ ወደ ጊዜ ቸልተኝነት እየጨመረ መምጣቱን የተለያዩ ከተሞች ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ።
ከሦስት ቀናት በፊት በ24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ 704 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ከተገለጸ በኋላ፤ የጤና ሚንስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ማኅበረሰቡ እራሱንና ቤተሰቡን ከወረርሽኙ ለመከላከል ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ በትዊተር ገጻቸው አሳስበዋል። ኮሮናቫይረስ በኢትዮጵያ ሪፖርት በተደረገበት ወቅት፤ በሕዝቡ ዘንድ አሁን ካለው በተሻለ ሁኔታ ጥንቃቄዎች ይደረጉ እንደነበረ በርካቶች ይስማማሉ። አካላዊ ርቀት ይጠበቅ ነበር፤ ሰዎች ወደ ንግድ እና የመንግሥት ተቋማት ከመግባታቸው በፊት እጃቸውን እንዲታጠቡ ይገደዱም ነበር። አሁን በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ በመጣበት ወቅት የበርካቶች መዘናጋት እስጨናቂ መሆኑን የተለያዩ ከተሞች ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ነዋሪዎች ምን ይላሉ? የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዋ አስቴር ቶላ “ሰዉ ተዘናግቷል፤ መጀመሪያ አካባቢ ጥንቃቄ ይደረግ ነበር። አሁን ግን እንዲያም ሰው እየተላመደው መጥቷል ማለት ይቻላል” ትላለች። ሰው እየተዘናጋ መምጣቱን ያስተዋለችው አስቴር፤ በበሽታው የተያዙ ሰዎችን ቁጥር ብቻ ከመግለጽ ይልቅ፤ ህሙማንን በቴሌቭዥን ማቅረብ ሰው ለበሽታው ትኩረት እንዲሰጥ ያግዛል ብላ ታምናለች። “ሰዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አድርገው በቴሌቭዥን ቢታዩ፣ ታመው የተኙ ሰዎችም ቢታዩ ጥሩ ነው። ሰው ከቁጥር ይልቅ ሁኔታውን በአይኑ ማየት ያሳምነዋል” ስትልም ታስረዳለች ሌላው የአዲስ አበባ ነዋሪ አክሊሉ ዓለማየሁም የአስቴርን ሀሳብ ይጋራል። “ዳቦ ቤት፣ አውቶብስ ላይ፣ ቀበሌ ስኳር ስንገዛም ተቃቅፈን ነው” ይላል። በርካቶች አካላዊ ርቀት መጠበቅን እየዘነጉ መሆኑን ይናገራል። ቀድሞ እጅ መታጠቢያ በየመንገዱ እንዲሁም በምግብ ቤቶች መግቢያ ላይ ይቀመጥ የነበረ ቢሆንም፤ አሁን ግን ውሃና ሳሙና ማስቀመጥ መቅረቱን አክሊሉ ታዝቧል። የምዕራብ ሃረርጌ ነዋሪው አቶ አፈንዲ መሐመድ በሐረር እና አከባቢዋ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ሕዝቡ ከጤና ባለሙያዎች የሚሰጠውን ምክር እየተገበረ እንዳልሆነ ይናገራሉ። "ከአንድ ወር ወዲህ 'መንግሥት ኮሮናቫይረስን የፖለቲካ አጀንዳ አድርጎታል' የሚል አመለካከት በመምጣቱ ሕዝቡ ከዚህ ቀደም ያደርግ የነበረውን ጥንቃቄ ትቶታል" ይላሉ። አቶ አፈንዲ እንደሚሉት፤ አሁን ላይ ሰዎች ሰላምታ ሲለዋወጡ እጅ መጨባበት ጀምረዋል። ይህ ልማድ ወረርሽኙ ከተቀሰቀሰ ወዲህ ቀንሶ ነበር። የአምቦ ከተማ ነዋሪው አቶ መረራ ፋና፤ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ባለበት ወቅት በሕብረተሰቡ ዘንድ የጥንቃቄ እርምጃዎች እየላሉ መምጣታቸው አሳሳቢ እንደሆነ ይናገራሉ። "የትራንስፖርት ዋጋ በእጥፍ ቢጭምርም በአንድ መኪና የሚጫነው ቁጥር አልቀነሰም። የሚቆጣጠር ሰው የለም። የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የወጣው አዋጅ አምቦ ከተማ ላይ ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚ እየሆነ አይደለም ማለት ይቻላል" ይላሉ። የቢቢሲ ሪፖርተር በአደማ፣ በዱከም እና በቢሾፍቱ ከተሞችም በተመሳሳይ ሁኔታ የጥንቃቄ ጉድለቶች መኖራቸውን ታዝቧል። በአዳማ ከተማ በቡድን ሆኖ መዝናናት፣ መጠጥ መጠጣት እና በስጋ ቤቶች ጥሬ ስጋ መመገብ በስፋት ይታያል። በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 11 ሺህ 933 ደርሷል። 197 ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸው አልፏል።
news-55036275
https://www.bbc.com/amharic/news-55036275
ትግራይ፡ ግጭቱን ሸሽተው ወደ ሱዳን የገቡ ተፈናቃዮች ከ40 ሺህ ማለፉ ተነገረ
ሦስት ሳምንት ባስቆጠረው የፌደራል መንግሥት ሠራዊትና በትግራይ ክልል ኃይሎች መካከል እየተካሄደ ባለው ግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን ከ40 ሺህ በላይ መድረሱን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር፣ ዩኤንኤችሲአር አስታወቀ።
ኢትዮጵያን በትግራይ ክልል በኩል ከሱዳን ጋር የሚያዋስነው ድንበር የሚገቡ ተፈናቃዮች በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ያስታወሰው ድርጅቱ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻም 5 ሺህ ተፈናቃዮች በምሥራቃዊ ሱዳን በኩል እንደገቡም ዩኤንኤችሲአር በድረገፁ ባወጣው መረጃ አስፍሯል። ዩኤንኤሲአርም ሆነ አጋር ድርጅቶቹ ምግብን ጨምሮ ህይወት አድን እርዳታዎችን እያደረጉ ቢሆንም የተፈናቃዮች ቁጥር በመጨመሩ የሰብዓዊ የእርዳታ የቁሳቁስ ችግርን ጨምሮ ሌሎች እክሎች ገጥሟል ብሏል። እየጨመረ የመጣውንም ተፈናቃይ ለማስተናገድ በቂ መጠለያም የለም ተብሏል። በምግብ እጥረት ለተጎዱ ህፃናት፣ ለነፍሰጡሮችና ለሚያጠቡ 300 የሚሆኑ ተፈናቃዮች የሚያስፈልጋቸውን ተጨማሪ ምግብም እየለገሰ ሲሆን፤ ከዚህም በተጨማሪ ተጋላጭ የሆኑ ለማኅበረሰብ ክፍሎችም የሚያስፈልጋቸውን አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑንም አስታውቋል። የተፈናቃዮቹን ደኅንነት ለማስጠበቅ ከድንበር አካባቢ እያራቀ ያለው ድርጅቱ ያለው ቁሳቁስ ውስን መሆን እንዲሁም ወደ ሱዳን መግባት ያለባቸው ርቀት መወሰንም እክል ሆኖብናል ብሏል። እስካሁን ባለውም በሱዳን ውስጥ 70 ኪሎሜትር ርቀት ባለችው ኡም ራቁባ ግዛት ድረስ ማስፈር መቻሉንም አስታውቋል። ከሰኞ ጀምሮ ባለውም አስከ 8 ሺህ የሚጠጉ ተፈናቃዮች መስፈራቸውም ተገልጿል። በኢትዮጵያ ውስጥ የሰላማዊ ዜጎች ደኅንነት እንዲሁም በግጭቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችና የእርዳታ ድርጅት ሠራተኞች እንዳሳሰበውም ዩኤንኤችሲአር አስታውቋል። ዩኤንኤችሲአርም ሆነ የተባበሩት መንግሥታት አጋሮች ሁለቱም ወገኖች የዓለም አቀፍ ሕግን አክብረው ንፁሃን ዜጎችን የመጠበቅ ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። ነፃ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀና እክል በሌለበት ሁኔታ የሰብዓዊ እርዳታ የሚደርስበት ሁኔታ እንዲመቻችም ጠይቋል። በኢትዮጵያ፣ በትግራይ ክልል ያሉ 100 ሺህ ኤርትራውያንም ተፈናቃዮች በግጭቱ ምክንያት አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ መግባታቸውንም ድርጅቱ ገልጿል። ምግብ፣ ውሃ፣ መድኃኒትን የመሳሰሉ መሰረታዊ የሚባሉ አቅርቦቶችን ማድረስ አስቸጋሪ በመሆኑም ለስደተኞቹ ያለው ክምችትም በሳምንት ውስጥ ሊያልቅ መቻሉ ከፍተኛ ስጋት ሆኖብኛል ብሏል ድርጅቱ። ሁለቱም አካላት ነፃና ደኅንነቱ በተጠበቀ መልኩ ዜጎች እርዳታ ወደሚያገኙበት ቦታ የመንቀሳቀስ መብታቸውን እንዲያከብሩ ዩኤንኤችሲአር ጠይቋል። ድርጅቱ አክሎም ተፈናቃዮች በብሔር ልዩነት ሳይደረግባቸው ደኅንነት ወደሚሰማቸው ቦታ አንዲንቀሳቀሱ የአገር ውስጥም ሆነ የዓለም አቀፍ ድንበሮችን እንዲያቋርጡም ሁለቱም ወገኖች ማመቻቸት አለባቸው ብሏል። በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊትና ትግራይ ክልል ኃይሎች መካከል ተቀስቅሶ ለሦስት ሳምንታት በዘለቀው ወታደራዊ ግጭት ሳቢያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ እተነገረ ሲሆን፤ ግጭቱን በመሸሽም በአስር ሺዎች ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን መግባታቸውን ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ገልጸዋል።
news-53762527
https://www.bbc.com/amharic/news-53762527
የህፃናት ጥቃት፡ የናይጄሪያ ፍርድ ቤት የ12 ዓመቷን ታዳጊ የደፈረውን ግለሰብ ሞት ፈረደበት
በናይጄሪያዋ ካኖ ግዛት የአስራ ሁለት ዓመቷን ታዳጊ የደፈረው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ እስላማዊው ፍርድ ቤት በይኖበታል።
የካኖ ግዛት የፍትህ ቢሮ ቃለ አቀባይ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የላይኛው ሻሪያ ፍርድ ቤት የ61 ዓመቱን ግለሰብ ጥፋተኛ ሆኖ አግኝቶታል። ታዳጊዋንም ከከተማ ወጣ ባለ ፋርሳ በተባለ የገጠር መንደር ውስጥ በሚገኝ ገላጣ ስፍራ ከዓመት በፊት ግለሰቡ ደፍሯታል ተብሏል። በደፋሪዎች ላይ ያልተለመደ በተባለው በዚህ ብያኔም መሰረት የእስልምና ሕግጋትን ተከትሎ ግለሰቡ በድንጋይ ተወግሮ እንዲሞት ነው ተፈረደበት። ግለሰቡ ባለ ትዳር እንደሆነም ተገልጿል። ደፋሪው ይግባኝ የመጠየቅ ሰላሳ ቀናት ጊዜ አለው። በቅርብ ሳምንታት ውስጥ በናይጄሪያ የሚደፈሩ ህፃናትና ሴቶች መበራከታቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ተቃውሞዎች ሲካሄዱ ነበር። በዚህ ሳምንት ውስጥ በካኖ ከተማ የእስልምና ፍርድ ቤቶች የሞት ቅጣት ሲፈርዱ ሁለተኛቸው ነው። ሰኞ ዕለትም አንድ ዘፋኝ የነብዩ መሐመድን ስም በግጥሞቹ አንቋሻል በሚልም የሞት ፍርድ ተበይኖበታል። በሰሜን ናይጄሪያ ውስጥ የሸሪያ ሕግ ተግባራዊ ካደረጉ በርካታ ግዛቶች መካከል ካኖ አንዷ ናት። በባለፉት ሁለት አስርት ዓመታትም ከሌሎች አገሪቷ ሕጎች ጋር ሆኖም እጅ ለእጅ ሆኖ ይሄዳል። ምንም እንኳን በርካታ ሰዎች የሞት ፍርድ ቢፈረድባቸውም እስካሁን ተግባራዊ የሆነው አንድ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።
news-47743562
https://www.bbc.com/amharic/news-47743562
የቀድሞው የፈረንሳይ ሰላይ ሞቶ ተገኘ
የቀድሞው የፈረንሳይ የደኅንነት መሥሪያ ቤት ክንፍ ባልደረባ እንደነበረ የሚጠረጠረው ዳኒኤል ፎረስቲር ሬሳው ከጄኔቫ ኃይቅ ራቅ ብሎ በሚገኝ የመኪና ማቆምያ ጋራዥ ውስጥ ተጥሎ መገኘቱን ፖሊስ ገለጸ።
ጭንቅላቱም በአምስት ጥይት ተበሳስቷል። ዳኒኤል ለፈረንሳይ የስለላ መሥሪያ ቤት በደኅንነት መኮንንነት ማገልገሉ ይገመታል። የፈረንሳይ ፖሊስ እንዳለው የዳኒኤል ፎረስቲር ግድያ የተጠናና በጥንቃቄ የተፈጸመ ነው። ባለፈው መስከረም ዳኒኤል የቀድመውን የኮንጎ ብራዛቪል ፕሬዝዳንት ልዩ ዘብ ጄኔራል የነበሩትን ፈርዲናንድ አምባኦን አሲሮ በመግደል ተጠርጥሮ ነበር። ጄኔራል ፈርዲናንድ አምባኦ ያን ጊዜ የፕሬዚዳንት ዴኒስ ሳሳኦ ነጉሶ ተቀናቃኝ እንደነበሩ ይነገራል። ጄኔራል አሞባኦ በፈረንሳይ ለ20 ዓመታት ኖረዋል። • እስራኤል የቀድሞ ሚኒስትሯን በኢራን ሰላይነት ፍርድ ቤት አቆመች • የቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት ትውስታዎች በኢትዮጵያውያን ዓይን • የዐቢይ ለውጥ፡ በመስቀለኛ መንገድ ላይ? ዳኒኤል በእርግጥ ሰላይ ነበር? ዳኒኤል በርካታ የስለላ መጻሕፍትን የጻፈ ሰው ነው። ነገር ግን አንድም ጊዜ ቢሆን በጄኔራል ፈርዲናንድ አምባኦ ግድያ እጁ እንዳለበት አምኖ አያውቅም። ፖሊስ ግን የቀድመውን ሰላይ ዳኒኤልን ሞት ከዚሁ የጄኔራል ፈርዲናድ አምባኦ አወዛጋቢ ግድያ ጋር እንደሚያያዝ ይጠረጥራል። ዳኒኤል በጄኔራሉ ግድያ ክስ ተመሥርቶበት ክሱን በመከታተል ላይ ነበር። የዳኒኤል ጠበቃ በዳኒኤል ላይ ክሱ ከተመሰረተበት በኋላ የዳኒ ሕይወት አደጋ ላይ እንደሆነ ጠቁመው ነበር። በተለይም የዳኒኤል ማንነት በማኅበራዊ ትስስር መድረኮች ከተዘዋወረ በኋላ ሕይወቱ በሰው እጅ ሊጠፋ እንደሚችል ግምት ተይዞ ነበር። ዳኒኤል የሚኖርባት ሉሲንገስ የምትባል ከተማ ከንቲባ ዣን ሉክ ሶላ በአንድ ወቅት ስለ ዳኒኤል ሲናገሩ "ብዙ የስለላ መጻሕፍት የደረሰ ሰው ነው፤ እሱ ምን እንደፈጸመ ግን አንድም ቀን ነግሮን የሚያውቅ አይመስለኝም" ብለው ነበር። "በከተማችን የተረጋጋ ኑሮ መስርቶ ሲኖር ነበር። በቀደም ለታ እንኳ አዳራሽ ምረቃ ሥራ ሲያግዘኝ ነበር" ብለዋል ከንቲባው። የፈረንሳዩ ጋዜጣ ሉ ሙንድ እንደዘገበው ከሆነ ደግሞ ዳኒኤል ጄኔራል ሞባኦን ለመግደል ከተዋቀረው መቺ ኃይል ውስጥ አንዱ እንደነበር አምኖ ያውቃል።
news-52179743
https://www.bbc.com/amharic/news-52179743
ኮሮናቫይረስ፡ ተስፋ ቢኖርም ይህ ሳምንት ለአሜሪካ አደገኛው ይሆናል ተባለ
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ክፉኛ ባጠቃቸው ቦታዎች ላይ ለውጦች መታየታቸውን ተከትሎ በሽታውን ለማስቆም ተስፋ እንዳለ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ተናገሩ።
በበሽታው የተያዘ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው የሚገኘው በአሜሪካ ትናንት እሁድ በአሜሪካ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ዋነኛ ማዕከል በሆነችው የኒው ዮርክ ከተማ ውስጥ በበሽታው የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር መቀነሱም ተነግሯል። ምንም እንኳን ፕሬዝዳንቱ ይህ የቁጥር መቀነስ "ጥሩ ምልክት" እንደሆነ ቢናገሩም፤ ወረርሽኙ በአሜሪካ ከፍተኛው ደረጃ ላይ እየደረሰ በመሆኑ ተጨማሪ ሞት ሊያጋጥም እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። "በመጪዎቹ ቀናት አሜሪካ የዚህን ወረርሽኝ ከፍተኛው ጉዳት ሊያጋጥማት ይችላል" ሲሉ በጽህፈት ቤታቸው በየዕለቱ በኮሮናቫይረስ ላይ በሚሰጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል። • በኮሮና ዘመን የትኞቹ ፊልሞች ቀን ወጣላቸው? የአፍና ፊት መሸፈኛ ጭንብልና የመተንፈሻ መሳሪያዎችን ጨምሮ የህክምና ባለሙያዎችና መገልገያዎች በበሽታው ክፉኛ ወደ ተጠቁትና ከፍተኛ ድጋፍን ወደሚፈልጉት ግዛቶች እንደሚላኩ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። የፕሬዝዳንቱ የኮሮናቫይረስ ግብረ ኃይል አባል የሆኑት ዴብራ ቢርክስ እንዳሉት በወረርሽኙ የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በቅርብ ቀናት ውስጥ እየቀነሰ ባለባቸው ጣሊያንና ስፔን ውስጥ የሚታየው "ወደፊት በሚኖረው ሁኔታ ላይ ተስፋን የሚሰጥ ነው" ብለዋል። በፕሬዝዳንቱ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተናገሩት ዶክተር ቢርክስ "ከበርካታ ሳምንታት በፊት ወረርሽኙ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ያለው የበሽታው መስፋፋት በሚቀጥለው ሳምንት ሊረጋጋ እንደሚችል ተስፋ" መኖሩን ተናግረዋል። ቀደም ሲል ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ወረርሽኝ "በጣም መጥፎ ነው" ያሉት የፕሬዝዳንቱ ዋነኛ የጤና አማካሪ ዶክትር አንተኒ ፋውቺ እንዲሁም ሌሎች ባለሙያዎች የፕሬዝዳንቱና የዶክተሯ የታያቸውን ተስፋ ጋር አይስማሙም። ነገር ግን ዶክትር አንተኒ ፋውቺ እንዳስጠነቀቁት "ይህ ሳምንት በአብዛኞቹ አሜሪካዊያን ህይወት ውስጥ ከባዱና አሳዛኙ ሳምንት ይሆናል።" "ይህ ሳምንት በታሪካችን ከባድ ጉዳት እንደደረሱበት የፐርል ሃርበርና የመስከረም 11ዱ ጥቃቶች ያህል ይሆናል" በማለት ለፎክስ ኒውስ የተናገሩት ደግሞ ዋነኛው ሐኪም ጄሮም አዳምስ ናቸው። አሜሪካ እስካሁን ድረስ ከ337 ሺህ በላይ ሰዎች በበሽታው መያዛቸውንና 9,619 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው ማለፉን ሪፖርት አድርጋለች። ይህም በዓለም ላይ ከፍተኛ በኮቪድ-19 የተያዙና የሞቱ ሰዎች ቁጥር ነው።
news-46388412
https://www.bbc.com/amharic/news-46388412
ኢትዮጵያ፡ ሕንዳውያን የግንባታ ሠራተኞች ከታገቱ ቀናት ተቆጠሩ
የሃገረ ሕንድ የሆነው አይኤል እና ኤፍኤስ (IL&FS) ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በኢትዮጵያ ላለፉት ሶስት ዓመታት የተለያዩ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ሲያካሄድ ቆይቷል።
በቅርቡም ከነቀምት-ጊዳ እና ከአጋምሳ-ቡሬ ያሉ የመንገድ ግንባታዎችን ሲያካሂድ ነበር። ይሁን እንጂ ኩባንያው ባጋጠመው የፋይናንስ ቀውስ የመንገድ ግንባታ ስራውን ማከናወን ተስኖታል። ይህም ብቻ አይደለም፤ ለሰራተኞች ደሞዝ፣ ለተቋራጮችና ለአቅራቢዎች የሚከፍለው ገንዘብ አጥሮታል። ያነጋገርናቸው ተቋራጮች ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስደው ክፍያው እንዲፈጸምላቸው ቢፈረድላቸውም ኩባንያው ግን ክፍያዎችን መፈጸም ተስኖታል። • ኢትዮጵያ በዲፕሎማቶቿ ላይ ሽግሽግና ለውጥ ልታደርግ ነው • "ፓስፖርት መስጠት አልተከለከለም" የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች ተቋም አቶ ሃብታሙ ካላዩ ከዚህ ኩባንያ ጋር ለሰራተኞች መኖሪያ የሚሆን ተገጣጣሚ ቤቶችን ለመገንባት ከሁለት ዓመታት በፊት ውል ወስዶ ነበር። በውሉ መሰረት መፈጸም የነበረበት 220 ሺህ ብር ክፍያ ስላልተፈጸመላቸው ሥራውን ለማቋረጥ መገደዳቸውን ይናገራሉ። አቶ ሃብታሙ ክፍያው እንዲፈጸምላቸው ፍርድ ቤት ቢወስንላቸውም ኩባንያው ግን የተጠየቀውን ክፍያ መፈጸም አልቻለም ይላሉ። ኩባንያው ለሌሎች ተቋራጮች፣ የመኪና እና የተለያዩ ማሽነሪዎች አከራዮችም ያልተከፈለ ውዝፍ እዳ እንዳለበት አቶ ሃብታሙ ነግረውናል። ደሞዛቸው ከሶስት እስከ አምስት ወራት የዘገየባቸው የነቀምት፣ ወሊሶ እና ቡሬ ሳይት ሰራተኞች ግን ሕንዳዊ የሆኑ የኩባንያውን ሰራተኞች በማገት ክፍያ እንዲፈጸምላቸው ጠይቀዋል። በዚህም የተነሳ በቡሬ ሳይት 4፣ ወሊሶ 2 እንዲሁም ነቀምት ላይ 1 በድምሩ 7 ሕንዳውያን ላለፉት ስድስት ቀናት ታግተው ይገኛሉ። ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸውንና የሚገኙበትን ሳይት የማንጠቅሰው አንድ ታጋች ''ኩባንያችን ባጋጠመው የፋይናንስ ችግር ምክንያት ለሰራተኞች ደሞዝ መክፈል አልቻለም፤ ላለፉት ስድስት ቀናት ከመጠለያ ጣቢያ እንዳንወጣ በአካባቢው ሰዎች ታግተናል፤ የኤሌትሪክ ኃይል አቅርቦት እና የመጠጥ ውሃ እጥረት ችግር አጋጥሞናል። ያለንበት ሁኔታ በጣም አስቸጋሪ ነው'' ሲሉ ያሉበትን ሁኔታ ያስረዳሉ። ይህ ታጋች እንደሚሉት ከሆነ ለሰራተኞች ለወራት ያክል ያልተከፈለ ደሞዝ፣ ለተቋራጮች እና አቅራቢዎች መፈጸም የነበረበት ክፍያ አለ። በአጠቃላይ ኩባንያው ወደ 60 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ክፍያ መፈጸም አለበት ይላሉ። • የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እና የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር ተዋሃዱ • ''የአንድ ቤተሰብ አባላት ግድያ'' በቤኒሻንጉል ክልሏ ያሶ ከተማ ''ሰራተኞቹ ያልተረዱት ነገር፤ ፤ እኛም ከ3-5 ወራት ድረስ ደሞዝ ያልተከፈለን እንደነርሱ ቅጥረኞች ነን፤ የሚለየን ነገር ቢኖር እኛ ሕንዳውያን እነርሱ ደግሞ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ነው።'' ይላሉ ታጋቹ። እኝህ ግለሰብ እንደሚሉት ለሕንድ መንግሥት እና በኢትዮጵያ የሕንድ ኤምባሲ ለጉዳዩ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጥያቄ አቅርበዋል። ''ኤምባሲው መፍትሄ እንደሚሰጠን ቃል ቢገባልንም እስካሁን መልስ አላገኘንም፤ ምላሻቸውን እየተጠባበቅን ነው'' ሲሉ ይናገራሉ። የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የህዝብ ግነኙነት ኃላፊው አቶ ሳምሶን ወንድሙ በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የሚጠበቅበትን ክፍያ ሁሉ መፈጸሙን አስታውሰው፤ የኩባንያው ሰራተኞች የታገቱት ለሰራተኞቹ ክፍያ መፈጸም ባለመቻላቸው መሆኑን ይናገራሉ። ''ለሰራተኞቹ ክፍያ መፈጸም እንዳለበት እናምናለን፤ በሌላ በኩል ደግሞ ሕንዶቹ በእንዲህ ዓይነት አያያዝ መቆየት እንደሌለባቸው እንረዳለን፤ እኛም ችግሩን ለመፍታት ከሕንድ ኤምባሲ፣ አዲስ አበባ ከሚገኙ የኩባንያው የሥራ ኃላፊዎች እና ከሚመለከተው አካል ጋር በጉዳዩ ላይ እየመከርን ነው።'' ብለዋል። በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ለመጠየቅ በኢትዮጵያ የሕንድ ኤምባሲን ለማነጋገር ብንሞክርም አልተሳካልንም።
46134515
https://www.bbc.com/amharic/46134515
መምህራን የበለጠ ክብር የሚያገኙት የት ሀገር ነው?
መምህራን በተማሪዎቻቸው ዘንድ መከበርን ከፈለጉ ቻይና፣ ማሌዢያ ወይም ታይዋን ቢያስተምሩ ይበጃቸዋል። ምክንያቱም አንድ ዓለም ዓቀፍ ጥናት እንደሚያሳየው በእነዚህ ሶስት ሀገራ የሚማሩ ተማሪዎች ናቸው ለመምህራን ክብር ያላቸው።
በተገላቢጦሽ በብራዚል፣ እስራኤልና ጣሊያን መምህራን ከተማሪዎቻቸው ክብርን ለማግኘት እንኳ ቢናፍቁ ምኞታቸውን ውሃ ይበላዋል እንጂ አያገኟትም። እንግሊዝ ከአሜሪካ ከፈረንሳይና ከጀርመን ተሽላ በደረጃ ከተቀመጡት 35 ሀገራት ዝርዝር ውስጥ መካተት ችላለች። • ጡረተኛው የፍቅር አጋር ለማግኘት በማሰብ እድሜውን ለማስቀነስ ፍርድ ቤት ሄደ • ትራምፕ ጠቅላይ አቃቢ ሕጉን አባረሩ ተማሪዎች ለመምህራኖቻቸው ያላቸው ክብርን በተመለከተ ከተጠየቁ 35 ሺህ ሰዎች መካከል በርካቶች ከሁሉም አናት ላይ ቁጭ ያደረጓት ቻይና ናት። በአውሮጳና በደቡብ አሜሪካ "በአጠቃላይ ተማሪዎች መምህራኖቻቸውን አያከብሩም የሚል አመለካከት አለ" ይሁን እንጂ ተማሪዎች ለመምህራኖቻቸው ያላቸው ክብር እንደ ደቡብ ኮሪያና ሲንጋፖር ባሉ የኤዢያ ሀገራት ጠንካራ ነው። በእነዚህ ሀገራት የሚገኙ ተማሪዎችም ዓለም አቀፍ ፈተናዎች ላይ ሲቀመጡ ተፎካካሪዎቻቸውን ሲዘርሩ ነው የሚስተዋለው። ጥናቱን ያካሄዱት ባለሙያዎችም እንዳሉት ለመምህርነት ክብር ባለበት ስፍራ ብቃቱ እና ተሰጥኦው ያላቸውን መምህራን በማምጣት የተማሪዎቹን ተወዳዳሪነት ከፍ ማድረግ እንደሚያስችል ያሳያል ብለዋል። የመምህርነት ሙያን ተወዳጅ መሆኑን ለማሳየት ከተጠየቁት ጉዳዮች መካከል ወላጆች ለልጆቻቸው መምህርነትን እንደሙያ እንዲቀበሉት ይነግሯቸዋል ወይ የሚለው ነው። በቻይና፣ ሕንድና ጋና ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወላጆች ልጆቻቸው መምህር እንዲሆኑ ይነግሯቸዋል። ወላጆች ለመምህራን ያላቸው አመለካከትም በጥናቱ ተካትቷል። በጥናቱ ከተካተቱ ሀገራት መካከል በርካታ ወላጆች የመምህራን የስራ ሰዓትን ዝቅ አድርገው ይመለከታሉ። ይህ መምህራን ረጅም ሰዓት በሚሰሩበት ኒው ዚላንድም ሆነ ዝቅተኛ ሰዓት በሚሰሩበት ፓናማና ግብፅ ተመሳሳይ ነው። በትምህርት ስርዓታቸው የላቁ በተባሉት ካናዳና ፊንላድ የሚገኙ መምህራን ትንሽ ሰዓት ቢሰሩም ወላጆች ግን ረጅም ሰዓት እንደሚሰሩ ያስባሉ። መምህራን የሚከበሩባቸው ሃገራት በደረጃ 1. ቻይና 2. ማሊዢያ 3. ታይዋን 4. ሩሲያ 5. ኢንዶኔዢያ 6. ደቡብ ኮሪያ 7. ቱርክ 8. ህንድ 9. ኒውዚላንድ 10. ሲንጋፖር
53188955
https://www.bbc.com/amharic/53188955
ከኮሮናቫይረስ ያገገሙት የ114 ዓመቱ የዕድሜ ባለፀጋ ማን ናቸው?
ሐሙስ እለት ከኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ዳይሬክተር የፌስቡክ ሰሌዳ ላይ የተገኘው መረጃ አንድ የ114 ኣመት አዛውንት ከኮሮና ማገገማቸውን የሚያበስር ነበር።
ግለሰቡ ከኮሮናቫይረስ ቢያገግሙም ለተጨማሪ ሕክምና ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል መላካቸው በዚሁ መልዕክት ላይ ሰፍሯል። የካቲት 12 ሆስፒታልም የጀመሯቸውን ሕክምናዎች ጨርሰው ያለመሳርያ እገዛ መተንፈስ በመጀመራቸው ወደ ቤታቸው መሄዳቸውን ትናንት ያነጋገርናቸው የሕክምና ተቋሙ ባለሙያዎች አረጋግጠውልናል። እንዲሁም የልጅ ልጃቸው ቢንያም ለቢቢሲ እንዳረጋገጠው በሙሉ ጤንነት ላይ ሲሆኑ ሆነው በቤታቸው ይገኛሉ። ለመሆኑ እኚህ የ114 ዓመት አዛውንት ማን ናቸው? ከኮሮና ያገገሙት የእድሜ ባለፀጋ አባ ጥላሁን ይባላሉ። ወደ እርሳቸውጋር ስንደውል ገና ከሆስፒታል መውጣታቸው ስለነበር ቃለምልልስ ለማድረግ በሚያስችል ሁኔታ አልጠነከሩም። ስለዚህ ከጎናቸው ሆኖ የሚንከባከባቸው የልጅ ልጃቸው ቢንያም ልኡልሰገድም ስለእርሳቸው አጫውቶናል። አባ ጥላሁን የተወለዱት በቡልጋ ሲሆን ወደ አዲስ አበባ የመጡት በልጅነታቸው ነው። በአሁን ሰዓት የሚኖሩት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 25 ። አባ ጥላሁን ወደ አዲስ አበባ በመጡበትና ኑሯቸውን በመሰረቱበት ወቅት በተለያዩ ስራዎች በመሰማራት ሕይወታቸውን መግፋታቸውን ቢንያም ይናገራል። የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ጥገናዎችን መስራት፣ ቀለም በመቀባት የእለት ገቢያቸውን ማግኘት ብቻ ሳይሆን ነየተካኑበት ሙያቸው ነበር። በርግጥ ጊዜውን በውል ባያስታውሱትም ከባድ የሆነ የኤሌክትሪክ አደጋ አጋጥሟቸው ስራውን ማቆማቸውንም ቢንያም ለቢቢሲ ጨምሮ አስረድቷል። ከዓመታት በኋላ ባለቤታቸው ሲሞቱና የልጅ ልጃቸው ሲወለድ አባ ጥላሁን መነኮሱ። በአሁን ሰዓት አብሯቸው የሚኖረው የልጅ ልጃቸው በቅርብ እንክብካቤም የሚያደርግላቸው መሆኑን ይናገራል። አባ ጥላሁን ሳል ይዟቸው መኖሪያ ሠፈራቸው በሚገኘው ጤና ጣብያ ሲታከሙ እነደነበር የሚገልፀው ቢንያም፣ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ሲደረግላቸው በቫይረሱ በመያዛቸው በመታወቁ ወደ ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል በመወሰድ ህክምና ክትትል ጀመሩ። ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የተለያዩ ሕሙማን ማረፊያ ክፍሎች እንዳሉት ይናገራል። አባ ጥላሁን ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ ሕሙማን የሚታከሙበት ክፍል የነበሩ ሲሆን በሆስፒታሉ የሚገኙ የሕክምና ባለሙያዎች የቅርብ ክትትልና እገዛ እንዳደረጉላቸው ይመሰክራል። በሆስፒታሉ ገብተው ቤተሰቦቻቸውን ማስታመም የማይፈቀድላቸው ግለሰቦች የቤተሰቦቻቸውን ዜና የሚያቀብል፣ የሚያመጡላቸውን ምግብና የሚጠጣ ነገር ተቀብሎ የሚያደርስ ሰው መመደቡንም ያስረዳል። የህክምና ክትትል ያደረጉላቸው ባለሙያዎች ምን ይላሉ? አባ ጥላሁንን በቅርበት ካከሟቸው የሕክምና ባለሙያዎች መካከል አንዱ ዶ/ር ሕሉፍ አባተ ነው። ዶ/ር ሕሉፍ ፣ አባ ጥላሁን እድሜያቸው 114 መሆኑን የሚያሳይ መረጃ ማግኘት ይከብዳል ሲል ለቢቢሲ ገልጿል። በእርሳቸው እድሜና ትውልድ ውስጥ የሚገኝ ግለሰብ የልደት ሰርተፍኬት እንዲሁም ሌሎች የእድሜ ማረጋገጫዎችን ማቅረብ ስለማይችል በሰነድ ማረጋገጥ ከባድ ነው ሲልም ሃሳቡን ያጠናክራል። ነገር ግን ይላል ዶ/ር ሕሉፍ በእርሳቸው እድሜ የሚገኝ ሰው የእጅና እግር መገጣጠሚያዎች እና ጡንቻዎች በማየት እድሜያቸው ከ100 በላይ መሆኑን እርግጠኛ እንደሚሆን ይመሰክራል። አባ ጥላሁን በቲቢ ተጠቅተው ስለነበር ተደጋጋሚ ምርመራ ተደርጎላቸው ከኮሮናቫይረስ ነጻ ከሆኑ በኋላ ወደ ካቲት 12 በመሄድ የቲቢ ህክምና ክትትል ተደርጎላቸዋል። ከኮሮናቫይረስ አገግመው ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል ለተጨማሪ ሕክምና ተልከው የነበሩት የ114 ዓመት አዛውንት ሕክምናቸውን ጨርሰው መውጣታቸውን ለቢቢሲ ያረጋገጡት በየካቲት ሆስፒታል የውስጥ ደዌ ህክምና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር ሊያ ፋንታሁን ናቸው። ዶ/ር ሊያ በየካቲት ሆስፒታል ለግለሰቡ ሕክምና ሲያደርጉ እንደነበር ገልፀው፣ ግለሰቡ ያለ መሳሪያ ድጋፍ መተንፈስ በመቻላቸውና የነበሩባቸውን ኢንፌክሽኖች በመታከማቸው ከሆስፒታል መውጣታቸውን ገልፀዋል። ግለሰቡ እድሜያቸው 114 ይሆናል ተብለው የተጠየቁት ዶክተሯ " የ114 ዓመት አዛውንት ናቸው። ልጆቻቸውም የልጅ ልጆቻቸውም አብረዋቸው አሉ" ሲሉ መልሰዋል። በኢትዮጵያ እስካሁን የተደረገው የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ 232,050 ሲሆን 5,175 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። 81 ሰዎች ከቫይረሱ ጋር በተገናኘ ህይወታቸው ሲያልፍ 1,544 ሰዎች ደግሞ ማገገማቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ይገልፃል። በአሁን ሰዓት ቫይረሱ ያለባቸው 3 ሺህ 548 ሰዎች ሲሆኑ 30 ሰዎች በፀና ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የጤና ሚኒስቴር ሪፖርት ጨምሮ ያሳያል።
news-57075420
https://www.bbc.com/amharic/news-57075420
አየር መንገዶች ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን እንዳያበሩ ዳግም ታገዱ
ከሁለት የመከስከስ አደጋ በኋላ ዳግም እንዲበር ፍቃድ አግኝቶ የነበረው የቦይንድ 737 ማክስ አውሮፕላን ዳግም አጣብቂኝ ውስጥ ገባ።
የኢትዮጵያ እና የኢንዶኔዢያው ላየን አየር መንገድ ንብረት የሆኑት የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች የመከስከስ አደጋ ካጋጠማቸው በኋላ በመላው ዓለም አውሮፕላኑ እንዳይበር እግድ ተጥሎበት እንደነበረ ይታወሳል። ከስድስት ወራት በፊት ግን የአሜሪካ የበረራ ደህንነት ተቋማት አውሮፕላኑ ዳግም እንዲበር ፈቃድ ሰጥተው ነበር። ይሁን እንጂ አውሮፕላኑ ሌላ የኤሌክትሪክ ችግር እንዳለበት በመታወቁ ዳግም ሌላ አጣበቂኝ ውስጥ መግባቱ ተነግሯል። አውሮፕላኑ ዳግም ለማብረር የወሰኑ በመላው ዓለም የሚገኙ 24 አየር መንገዶች አውሮፕላኑን እንዳያበሩ ተነግሯቸዋል። ይህም ብቻ ሳይሆን ቦይንግ ያመረታቸውን አውሮፕላኖች ከማከፋፈል ተቆጥቧል። ቦይንግ እና የአሜሪካ የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር (ኤፍኤኤ) ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት እየሰራን ነው ብለዋል። በአውሮፕላኑ ላይ የኤሌክትሪክ ችግር መገኘቱ ቀድሞውኑ አውሮፕላኑ ጥብቅ የደህንነት ፍተሻ ሳይካሄድበት ለበረራ ብቁ ነው መባሉ ሲተቹ ለነበሩ ሌላ የመከራከሪያ ነጥብ ሆኖላቸዋል። ቦይንግን አጥቦቆ በመተቸት የሚታወቁት የቀድሞ የቦይንግ አስተዳዳሪ ኤድ ፒርሰን፤ በቦይንግ ፋብሪካ ያለው ደካማ የምርት ጥራት የኤሌክትሪክ ችግር እንደምክንያት በማንሳት የበርካቶችን ህይወት ለቀጠፉት አደጋዎች ምክንያቱ ይህ ሊሆን ይችላል ይላሉ። ቦይንግ እና ኤፍኤኤ አውሮፕላኑ ላይ የተገኘው ችግር የኤሌክትሪክ ኃይል በሚያመነጨው ስርዓት ላይ ነው ብለዋል። ለዚህ መንስዔው የኤሌክትሪ ግነኙነቶች ሥራ ጥራት ደካማ መሆኑ ነው ይላሉ። ኤፍኤኤ እንደሚለው የአሌክትሪክ ችግር፤ “መሠረታዊ የሆኑ የአውሮፕላኑ ስርዓት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ይኖረዋል።” ኤፍኤኤ ይህ የአውሮፕላኑ የኤሌክትሪክ ችግር ሳይቀረፍ አውሮፕላኑ አገልግሎት መስጠት የለበትም በማለት ከሁለት ሳምንት በፊት "አውሮፕላኑ ለመበረር የደህንነት ስጋት አለበት" የሚል መመሪያ አውጥቶ እንደነበረም ተጠቅሷል። ቦይንግን 737 ማክስ አውሮፕላን የበረራ ቁጥር ኢቲ302 ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ናይሮቢ ሲበር ተከስክሶ ሁሉም ተሳፋሪዎች መሞታቸው ይታወሳል። ተመሳሳይ የኢንዶኔዥያ ላየን ኤር ንብረት የሆነ አውሮፕላን ከኢንዶኔዢያ ተነስቶ ባህር ውስጥ መከስከሱ ይታወሳል። በሁለቱ አደጋዎች በአጠቃላይ 346 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል።
news-50153833
https://www.bbc.com/amharic/news-50153833
በኦሮሚያ የተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎችን ተከትሎ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት አጋጠመ
ትናንት ሌሊት በአክቲቪስት ጀዋር መሃመድ መኖሪያ ቤት አጋጠመ የተባለውን ክስተት ተከትሎ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች በርካታ ሰዎች ለተቃውሞ ሰልፎች አደባባይ ወጥተዋል።
በአምቦ ግጭቱን ተከትሎ በከተማው የንግድ እንቅስቃሴ መቆሙን እና ከተማውን አቋርጦ የሚያልፈው መንገድ ዝግ መሆኑን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። የተቃውሞ ሰልፍ ከተደረገባቸው ከተሞች መካከል አምቦ፣ አዳማ እና ሻሸመኔ ከተሞች ይጠቀሳሉ። በዚህም በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ቢቢሲ ያነጋገራቸው መንጮች ጠቁመዋል። አምቦ በአምቦ በተቀሰቀሰው ግጭት ቢያንስ ስድስት ሰዎች በጥይት የተመቱ ሲሆን ሦስቱ ህይወታቸው አልፏል። ዛሬ ጠዋት በአምቦ በተቀሰቀሰው ግጭት ነዋሪዎች አምስት ሰዎች በጥይት መመታታቸውን ለቢቢሲ ተናግረው የነበረ ሲሆን፤ የሆስፒታል ምንጮች በበኩላቸው ሦስት ሰዎች ለሕክምና ወደ አምቦ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠው ነበር። የአምቦ ከተማ ነዋሪዎች ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ሌሊቱን በአክቲቪስት ጀዋር መሃመድ መኖሪያ ቤት ተፈጸመ የተባለውን ክስተት ተከትሎ ተቃውሟቸውን ለመግለጽ አደባባይ ወጥተው ነበር። ለተቃውሞ የወጡትን ሰዎች ለመበተን የጸጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጭስ ከተኮሱ በኋላ ተቃዋሚዎች ፖሊሶች ላይ ድንጋይ መወርወር እንደጀመሩ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ያስረዳሉ። ዛሬ ጠዋት የነጋገርናቸው የአምቦ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ ደበበ ፈጠነ ሦስት ሰዎች በጥይት ተመተው ለህክምና ወደ ሆስፒታላቸው መምጣታቸውን ነግረውን ነበር። ዛሬ ከሰዓት በስልክ ደግመን ያገኘናቸው የአምቦ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ዛሬ ረፋድ ላይ በጥይት ተመተው ህይወታቸው ያለፈ የሦስት ሰዎች አስክሬን ወደ ሆስፒታላቸው መምጣታቸውን ነግረውናል። አቶ ደበበ ጠዋት ላይ በጥይት ተመተው ለህክምና ስለመጡት ሰዎች ሲያስረዱ፤ "እድሜያቸው ከ17-28 የሚገመቱ ሦስት ወጣቶች ወደ ሆስፒታላችን በጥይት ተመተው መጥተዋል። አንዱ ሆዱ ላይ የተመታ ሲሆን ከፍተኛ ጉዳት አጋጥሞት የቀዶ ህክምና ተደርጎለታል። ሁለተኛው መራቢያ አካሉ ላይ ጉዳት የደረሰበት ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የቀዶ ህክምና እየተካሄደለት ነው። ሦስተኛው ትከሻው አካባቢ ቀላል የሚባል ጉዳት የደረሰበት ሲሆን ለእርሱም ህክምና ተደርጎለታል" በማለት አስረድተዋል። ግጭቱ የተከሰተው ከኦሮሚያ ፖሊስ ጋር መሆኑን ያስረዱት ነዋሪዎቹ፤ አንድ የፖሊስ መኪና ሙሉ ለሙሉ በቃጠሎ መውደሙን ጨምረው ተናግረዋል። ግጭቱን ተከትሎ በከተማው የንግድ እንቅስቃሴ መቆሙን እና ከተማውን አቋርጦ የሚያልፈው መንገድ ዝግ መሆኑን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። አዳማ በተመሳሳይ መልኩ በአዳማ ከተማ የተቃውሞ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው። ሰልፎቹ ባህርያቸውን በመቀየር በሁለት ጎራ በተከፈሉ ሰዎች መካከል ግጭት መከሰቱን በሥፍራው የሚገኘው ሪፖርተራችን ተመልክቷል። "ቄሮ ሌባ" በሚል ቡድን እና ለጀዋር መሐመድ ድጋፍ ለማሳየት በወጡ ወጣቶች መካከል ግጭት እንደተፈጠረ ሪፖርተራችን ከሥፍራው ዘግቧል። የሃገር መከላከያ ሠራዊት እና ኦሮሚያ ፖሊስ በሁለት ቡድን ተከፍለው ወደ ግጭት ባመሩ ኃይሎች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ዘጋቢያችን ተመልክቷል። እስካሁን በአዳማ በተከሰተው ግጭት በሰው እና በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት በግልጽ ማወቅ ባይቻልም የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን የከተማው ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የአዳማ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ራውዳ ሁሴን የአንድ የዱቄት ፋብሪካ ጥበቃ ተኩሶ ሁለት ሰዎችን መግደሉን እና በዚህ የተበሳጩ ሰልፈኞ በፋብሪካው ቅጥር ግቢ ውስጥ የነበሩ 15 መኪኖችን ማቃጠላቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ግልጽ ባልሆነ ምክንያት የአፍሪካ ዱቄት ፋብሪካ ጥበቃ ሰልፈኞች ላይ ተኩሶ ሁለት ሰዎች ገድሏል። ጥበቃው ስለሚገኝበት ሁኔታ ምንም መረጃ የለኝም" ያሉት የከተማው ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ፤ የሃገር መከላከያ ሠራዊት በስፍራው ደርሶ ነገሮችን በቁጥጥር ሥር እንዳለዋለ ለቢቢሲ አስረድተዋል። ከዚህ በተጨማሪም በሥፍራው የሚገኘው ሪፖርተራችን በከተማዋ የተቃውሞ ሰልፉን ተከትሎ ሱቆችን የመዝረፍ፣ የሥርዓት አልበኝነት ተግባራት ሲፈጸሙ ታዝቧል። ይህንን ተከትሎም የንግድ እንቅስቃሴዎች የቆሙ ሲሆን ወደ ከተማዋ የሚያስገቡ መንገዶች ዝግ መሆናቸውን መረዳት ችለናል። ሻሸመኔ በሻሸመኔ ከተማም በተመሳሳይ ሁኔታ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል። የተቃውሞ ሰልፉ ተሳታፊ የሆነ አንድ ወጣት ለቢቢሲ "በጀዋር መሃመድ ላይ የሚደረገው ማስፈራሪያ መቆም አለበት" በማለት ተናግሯል። ይህ ወጣት የተቃውሞ ሰልፉ ከሌሊቱ 10፡30 ጀምሮ ሲካሄድ እንደነበረ ያስረዳል። ምንም እንኳን ወደ ሻሸመኔ የሚያስገቡ መንገዶች ሙሉ ለሙሉ ተዘግተው ቢገኙም፤ የተቃውሞ ሰልፉ በሰላም እየተከናወነ እንደሆነ ሌሎች የተቃውሞ ሰልፉ ተሳታፊዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። አወዳይ በምስራቅ ሃረርጌ የአወዳይ ከተማ ነዋሪ የነበረ ወጣት በጥይት ተመትቶ ስለመገደሉም የአወዳይ ከተማ ክንቲባ ጃፋር ሙሐመድ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከንቲባው ወጣቱ የተገደለው አወዳይ እና ሃረር ከተሞች መካከል ሃማሬሳ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ከመከላከያ ሠራዊት አባል በተተኮሰ ጥይት መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል። በጀዋር መኖሪያ ቤት አቅራቢያ በርካታ ደጋፊዎቹ ያላቸውን ድጋፍ ለመግለጽ ተሰባስበዋል። ጀዋር ምን ይላል? ጃዋር እንደሚለው ከሆነ ማክሰኞ ዕኩለ ሌሊት አቅራቢያ ሁለት መኪኖች ወደሚኖርበት ቤት አካባቢ በመምጣት ጥበቃዎቹን "እኔ ሳላውቅ እቃቸውን ይዘው ቤቱን ለቀው እንዲወጡ" እንደተነገራቸው በፌስ ቡክ ገጹ ላይ አስፍሯል። በጥበቃዎቹ ላይ ግፊቱ ሲበረታ ከእንቅልፉ ቀስቅሰው ሁኔታውን እንደነገሩትና እሱም ወደ ጥበቆቹ አዛዥ ጋር ደውሎ ማብራሪያ እንደጠየቀና በመጀመሪያ ላይ "የተለመደው ጥበቃዎችን የመቀየር ሂደት መሆኑን" እንደተነገረው፤ ከዚያም ኃላፊው የተሰጠውን ትዕዛዝ ብቻ እያስፈጸመ መሆኑን ጽፏል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽር እንደሻው ጣሰው ፌደራል ፖሊስ ምን አለ? የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽር እንደሻው ጣሰው፤ ጃዋር መሀመድ ለተከታዮቻቸውና ለደጋፊዎቻቸው ልታሰር ነው፣ ጥቃት ሊደርስብኝ ነው በማለት ያስተላለፉት መልዕክት ስህተት ነው ብለዋል። "በፖሊስ ተወሰደብኝ ያሉት እርምጃ ስህተት ነው" ካሉ በኋላ "በመንግሥትም በፖሊስም በኩል ምንም ዓይነት እርምጃ አልተወሰደባቸውም" ሲሉ ተናግረዋል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር፤ ለውጡን ተከትሎ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ፖለቲከኞችና አክቲቪስቶች በሚንቀሳቀሱበትና በሚኖሩበት ስፍራ ችግር እንዳያጋጥማቸው የጥበቃ ከለላ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰው "የግል ጥበቃዎችን የማንሳት ሥራ ስንሰራ ቆይተናል" ብለዋል።
news-44490688
https://www.bbc.com/amharic/news-44490688
የወባ በሽታ ያለ ደም ምርመራ ሊታወቅ ነው
አንድ ኡጋንዳዊ የፈጠራ ባለሙያ የወባ በሽታን ያለደመ ናሙና የሚመረምር መሳሪያ በመፍጠሩ ትልቅ ሽልማት አሸነፈ።
የፈጠራው ባለቤት ጊታ የ24 ዓመቱ ወጣት ጊታ ሮያል አካዳሚ ኦፍ ኤንጂነሪንግ ከተባለ ተቋም፤ የበሽተኛው ጣት ላይ ቀይ መብራት በማብራት ብቻ የወባ በሽታ መኖር አለመኖሩን የሚመረምር መሳሪያ በመፍጠሩ የአፍሪካ ተሸላሚ ሆኗል። ውድድሩን ያሸነፈው ጊታ የ25 ሺህ ዶላር ሽልማትን ሲሆን፤ በአዲሱ መሳሪያ የተደረገው ምርመራ ውጤት ከደቂቃ በኋላ በተንቀሳቃሽ ስልክ ላይ ማየት እንደሚቻል ገልጿል። ኡጋንዳዊው የሥራ ፈጣሪ የወባ ምርመራ ለማድረግ ወደ ህክምና ቦታ ሄዶ በጊዜው ደሙን የሚመረምረው መሳሪያ ውጤቱን ማሳየት ስላልቻለ፤ ይህንን ''ማቲባቡ'' የተባለውን የፈጠራ ውጤት ለመስራት እንደተነሳሳ ተናግሯል። በኡጋንዳ የወባ በሽታ ገዳይ ከሚባሉት አንዱ ሲሆን፤ የመሳሪያው ፈጣሪ ጊታ ደሙ አራት ጊዜ ተመርምሮ ነበር ውጤቱን ማወቅ የቻለው። የ'ማቲባቡ' ፈጠራ ቡድን አባል የሆነው ሴኪቶ እንደሚለው በኮምፒዩተር ምህንድስና ያገኘነውን እውቀት ለምን አንድን ሰው ደሙ ሳይፈስ ወባን ለመመርመር አንጠቀምበትም በማለት ጊታ ሃሳቡን እንዳቀረበ ይናገራል። ሽልማቱን ለመስጠት በነበረው ውድድር የተሳተፉት አንደኛው ዳኛ ''ምህንድስና የህይወት ችግሮችን ለመፍታት ቁልፍ መሆኑን ማሳያ ነው'' ብለዋል። 'ማቲባቡ' በስዋሂሊ ቋንቋ ህክምና ማለት ሲሆን፤ በሽታውን ለመመርምር የግድ የህክምና ባለሙያ አያስፈልግም። መሳሪያው የነጭ ደም ሴሎች እንቅስቃሴንና የደም ቀለምን በመመልከት ታካሚው በበሽታው መያዝ አልያም አለመያዙን ያመለክታል። ጊታ እና የቡድን አጋሮቹ የመሳሪያው መፈጠር ለአፍሪካ ፈተና የሆነውን የወባ በሽታ ለመቆጣጠር እንደሚረዳ ተስፋ አድርገዋል። የወባ መመርመሪያ መሳሪያው ወደ ገበያ ከመቅረቡ በፊት ብዙ የደረጃ ምዘና ፈተናዎችን ማለፍ እንዳለበት ጨምረው ተናግረዋል።
news-53410880
https://www.bbc.com/amharic/news-53410880
ቱኒዚያዊቷ ፌስቡክ ላይ ባሰፈረችው ጽሁፍ የስድስት ወር እሰር ተፈረደባት
ቱኒዚያዊቷ ጦማሪ የኮሮናቫይረስን በተመለከተ ቅዱስ ቁርዓን በሚጻፍበት መንገድ ባሰፈረችው ምጸታዊ ጽሁፍ የተነሳ የስድስት ወር እስር ተፈረደባት።
የ28 ዓመቷ ወጣት ኤምና ቻርኪ ባለፈው ግንቦት ወር በፌስቡክ ላይ ሕዝቡ የኮሮናቫይረስ በሽታን ለመከላከል የንጽህና አጠባበቅ ደንቦችን እንዲከተል ባሰፈረችው መልዕክት ነው የተከሰሰችው። ነገር ግን ኤምና መልዕክቷን የጻፈችው የእስልምና ቅዱስ መጽሐፍ ቁርዓን በሚጻፍበት መንገድ መሆኑ ነው የስድስት ወር እስር ያስፈረደባት። ኤምና በቅርቡ በሰጠችው ቃለ መጠይቅ ላይ እንዳለችው በዚህ መንገድ የጻፈችው ሰዎችን ለማስደንገጥ ሳይሆን መልዕክቱን ዘና የሚያደርግ እንዲሆን በማለት እንደሆነ ተናግራለች። ለዚህ ድርጊቷም ፍርድ ቤት ቀርባ "በሐይማኖቶች መካከል ጥላቻን በመፍጠር" ጥፋተኛ ተብላ እስር ተወስኖባታል። ነገር ግን ኤምና ይግባኝ ለመጠየቅ እያሰበች ስለሆነ አስካሁን እስር ቤት አልገባችም። ኤምና በማኅበራዊ መገናኛ መድረክ ላይ ባሰፈረችው ጽሑፍ የቅዱሱ መጽሐፍ አንቀጾች በተጻፉበት መንገድ መሆኑ እንጂ ይዘቱ የጤና መልዕክት እንደሆነ ነው የተገለጸው። የጽሑፉ ይዘት ሕዝቡ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል እጁን እንዲታጠብ እንዲሁም አካላዊ ርቀትን እንዲጠብቅ የሚመክር ነው። ጽሑፉ የሰፈረበት መንገድ በመጀመሪያ የተዘጋጀውና ዲዛይን የተደረገው ፈረንሳይ ውስጥ በሚኖር በአንድ ኢአማኒ አልጄሪያዊ ነው ተብሏል። ኤምና ይህንን ጽሑፍ በፌስቡክ ላይ ያወጣችው የሙስሊሞች የጾም ወቅት በሆነው በረመዳን ጊዜ ሲሆን፤ በወቅቱ ቱኒዚያ በወረርሽኙ ምክንያት በአብዛኛው በእንቅስቃሴ ገደብ ውስጥ ነበረች። ጽሑፉ ከወጣ በኋላ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን አንዳንዶች ኤምና እንድትቀጣ ጥሪ ሲያቀርቡ ነበር። ከቀናት በኋላም በፖሊስ ምርመራ ተደርጎባታል። ይህንንም ተከትሎ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባለስልጣናት ቀደም ሲል የነበሩትን ጨቋኝ ህጎችን በመጠቀም የመናገር ነጻነትን እየተጫኑ ነው በማለት ኤምና ላይ የተመሰረተው ክስ ውድቅ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቦ ነበር።
news-54144046
https://www.bbc.com/amharic/news-54144046
እስያ፡ አዲሱ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ዮሺሒዳ ሱጋ ማን ናቸው?
ዮሺሒዳ ሱጋ ይባላሉ፡፡ ማን ናቸው ደግሞ እሳቸው ካላችሁ ሺንዞ አቤን የሚተኩት ቁልፍ ሰው ናቸው እንላለን፡፡
ዛሬ ሰኞ ሺንዞ አቤን ለመተካት 3 ተወዳዳሪዎች ቀርበዋል፡፡ አሸናፊው ዮሺሒዳ ሱጋ እንደሚሆኑ ግን ብዙም አጠራጣሪ አልሆነም፡፡ ምክንያቱም ደግሞ ፓርቲያቸው ቀዳሚ እጩ ስላደረጋቸው ነው፡፡የተወለዱት በ1948 እንደነሱ አቆጣጠር ነው፡፡ ቤተሰባቸው እንጆሪ አምራች ገበሬዎች ነበሩ፡፡ ዮሺሒዳ ሱጋ ወደ ፖለቲካ የገቡት ድሮ የፓርላማ አባላት ምርጫን በማስተባበር ሥራ ካገኙ በኋላ ነበር፡፡ ያን ጊዜ እሳቸው ገና ከሆሴይ ከተባለ የግል ዩኒቨርስቲ መመረቃቸው ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ ለሊበራል ዲሞክራቲክ ፓርቲ ተወካይን በጸሐፊነት አገልግለዋል፡፡ ከዚያ በኋላ ነው እንግዲህ ወደ ፖለቲካ ጭልጥ ብለው የገቡት፡፡መጀመርያ ለዩኮሓማ ከተማ ተመራጭ ሆነው ቀረቡ፡፡ ይህ 1987 አካባቢ ነበር፡፡ ከዚያ ለጃፓን ምክር ቤት ተመረጡ፡፡ በ2005 ጠቅላይ ሚኒስትር ጁኒቺሮ ኩዊዙሚ የአገር ውስጥ ጉዳይና የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዴኤታ አድርገው ሾሟቸው፡፡በቀጣይ ዓመት የሚስተር ኮይዙሚ ተተኪ ሺንዞ አቤ ዋና ሚኒስትር አድርገው ሹመት ደረቡላቸው፡፡ እስከ 2007 በዚሁ ቦታ አገልግለዋል፡፡ የሺንዞ አቤና የርሳቸው ግንኙነት እየተጠናከረ ሄዶ ሺንዞ አቤ በ2012 ወደ ሥልጣን ሲመለሱ የካቢኔ ጉዳዮች ዋና ጸሐፊ አድርገው ቁልፍ ቦታ ሾሟቸው፡፡ ላለፉት 8 ዓመታት ታዲያ ሰውየው የሺንዞ አቤ ቀኝ እጅ ሆነው አገልግለዋል፡፡በየቀኑ ሁለት ጊዜ ለሚዲያ መግለጫ ይሰጣሉ፤ የጃፓንን ውስብስብ ቢሮክራሲ አብጠርጥሮ በማወቅም ዝናን አትርፈዋል፡፡ ጃፓናውያን የሳቸውን ፊት ያህል የማንንም ፊት በቴሌቪዥን ደጋግመው አይተዋል ማለት ይከብዳል፡፡ሺንዞ አቤ በነሐሴ 28 በጤና ምክንያት ሥልጣን በቃኝ ሲሉ በርካታ ጃፓናዊያን አቤን ማን ሊተካቸው እንደሚችል በትክክል ገምተው ነበር፡፡ ሚስተር ሱጋ፡፡ በመስከረም 2 ሺንዞ አቤ በይፋ ከሥልጣን ለመሰናበት ሲያስታውቁ በጃፓን ታሪክ የካቢኔ ጉዳዮች ጸሐፊነት ቦታ ላይ ረዥም ዘመን በመሥራት የሚታወቁት ሰው ቀጣዩ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሆኑ ውስጥ ውስጡን መግባባት ላይ ተደርሶ ነበር፡፡ አዲሱ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሚስተር ሱጋ ኮቪድ-19 የበጠበጠውን ግዙፉን የጃፓን ኢኮኖሚ ለማነቃቃት ቅድሚያ ሰጥተው እንደሚሰሩ ይጠበቃል፡፡ የጃፓን ኢኮኖሚ የዓለማችን 3ኛው ግዙፉ ኢኮኖሚ ነው፡፡ ሚስተር ሱጋ ጃፓን ከአሜሪካ ጋር ያላትን ጥብቅ ግንኙነት አጠናክረው ለመቀጠል ይፈልጋሉ፡፡ ከቻይናም ጋር ጤናማ ግንኙነትን ይሻሉ፡፡ ሚስተር ሱጋ ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋር ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመገናኘት መፍቀዳቸው ልዩ ያደርጋቸዋል፡፡ በ1970ዎቹና 80ዎቹ ሰሜን ኮሪያ አፍና የወሰደቻቸው ጃፓናዊያንን ጉዳይ እልባት መስጠት ፍላጎት አላቸው፡፡ ዮሺሒዳ ሱጋ አሁን 71 ዓመታቸው ነው፡፡
47314977
https://www.bbc.com/amharic/47314977
ናንሲ ፒሎሲን ሊገድል የነበረው አሜሪካዊ ወታደር
የአሜሪካ ድንበር ጠባቂ አባል የሆነው ግለሰብ የሽብር ጥቃት ለማድረስ በማሰብ ተብሎ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተሰማ።
ይህ የፖሊስ ባልደረባ ክሪስቶፈር ፖል ሐሶን የሚባል ሲሆን መኖሪያ ቤቱ ሲበረበር የተለያዩ የጦር መሣሪያዎች ስብስብ ተገኝቷል። ይህ የነጭ የበላይነትን አቀንቃኝ እንደሆነ የሚናገረው የፖሊስ ባልደረባ ጥቃቱን የሚፈፅምባቸውን ታዋቂ ዲሞክራት ፖለቲከኞችን ጨምሮ ሌሎች ግለሰቦችን ለይቶ የጨረሰ መሆኑን አቃቢ ሕግ ተናግሯል። ግለሰቡ ይህንን ሐሳብ ያገኘው ከኖርዌጂያዊው የጭምላ ግድያ ፈፃሚ አንደርስ ብሬቪክ እንደሆነ ገልጿል። "ግለሰቡ ንፁሐን ዜጎችን በዚህ ሀገር ከዚህ በፊት እምብዛም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ለመግደል አስቦ ነበር" ያሉት ደግሞ የሕግ ባለሙያው ሮበርት ሁር ናቸው። • ዶናልድ ትራምፕ ተከሰሱ • ዓለም ሁሉ የሚያወራለት ክሪይፕቶከረንሲ ምንድነው? አቃቤ ሕግ እንደሚለው ከሆነ በ2017 ጽፎ ባልላከው የኢሜል መልእክት ላይ " በምድር ላይ ያለን የመጨረሻውን ግለሰብ ሳይቀር የምገልበትን መንገድ እያለምኩ ነው። መቅሰፍት የሚያስከትል ነገር በጣም ጥሩ ሳይሆን አይቀርም፤ ነገር ግን እንደ ስፔን ጉንፋን፣ አንትራክስ እና ቦቱሊዝምን እንዴት ማግኘት እችላለሁ? እስካሁን እርግጠኛ ባልሆንም አንድ ነገር እንደማገኝ ግን እርግጠኛ ነኝ። " ሲል አስፍሯል። የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ግለሰቡ 49 ዓመቱ መሆኑን ጠቅሰው በድንበር ጠባቂ ፖሊስ ውስጥ የሌተናል ማዕረግ ያለው መሆኑን ዘግበዋል። የድንበር ጠባቂው ቢሮም የሥራ ባልደረባቸው በቁጥጥር ሥር መዋሉን አረጋግጠው ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል። 15 የጦር መሳሪያዎች፣ 1ሺህ ቦንቦች ከተለያዩ ሕገወጥ ዕጾች ጋር በግለሰቡ መኖሪያ ምድር ቤት ውስጥ ተገኝቷል። ሊገድላቸው በዕቅድ ውስጥ ከያዛቸው ግለሰቦች መካከል የዲሞክራቲክ ፖርቲ አባሏ ናንሲ ፒሎሲ፣ ቻክ ሹመር እና የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ባልደረቦች ይገኙበታል።
news-56229474
https://www.bbc.com/amharic/news-56229474
ትግራይ፡ ለህይወታችን እንሰጋለን ያሉት የኢትዮጵያ የተመድ ሰላም አስከባሪዎች
ባለፈው ሳምንት ሰኞ በደቡብ ሱዳን ተሰማርተው የነበሩት የሰላም አስከባሪ ኃይሎች ወደ ኢትዮጵያ ለመብረር በተዘጋጀ አውሮፕላን አንሳፈርም ብለው ነበር።
የትግራይ ተወላጅ የሆኑት የሰላም አስከባሪ ኃይሎች ወደ ኢትዮጵያ ብንመለስ እስር እና ክስ ይገጥመናል በሚል ይሰጋሉ። የተባበሩት መንግሥታት ቃል አባይ "የትግራይ ተወላጅ የሆኑት የሰላም አስከባሪ ኃይል አባላት በጁባ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በኢትዮጵያ ወታደሮች ታስረው አካላዊ ጥቃት ደርሶባቸዋል" ብለዋል። ባሳለፍነው ማክሰኞ የአገር መከላከያ ሚንስትር ቃል አቀባይ ሜጀር ጀነራል ሞሐመድ ተሰማ በሰላም አስከባሪ ኃይል አባላቱ ላይ ደረሰ ስለተባለው እስር እና አካላዊ ጥቃት ያሉት ነገር ባይኖርም፤ በቁጥር 15 የሆኑት ወታደሮች "በጁባ አየር ማረፊያ መሬት እየተንከባለሉ እና እየጮሁ ሁከት ፈጥረው ነበር" ሲሉ ከስሰዋል። በአሁኑ ወቅት 15 የሰላም አስከባሪ ኃይሉ አባላት በተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን እና በደቡብ ሱዳን መንግሥት ጥበቃ ስር ይገኛሉ። ከ15ቱ ወታደሮች አንዱ የሆነው ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ ኮሎኔል ለቢቢሲ እንደተናገረው ባሳለፍነው ሕዳር ወር በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ፤ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ወታደሮች ኢላማ እንደሚደረጉ እና መገለል እንደሚደርስባቸው ተናግሯል። ይህ ኮሎኔል እንደሚለው ከሆነ ጥገኝነት እየጠየቁ የሚገኙት የትግራይን ጦርነት በመቃወማቸው፣ የኤርትራ ሠራዊት ከትግራይ እንዲወጡ እና በክልሉ የምግብ እጥረት መኖሩ እንዳሳሰባቸው መናገራቸውን ተከትሎ ነው። "የትግራይ ቀውስን ተከትሎ ኢላማ ውስጥ ገብተን ነበር፤ በጦሩ ውስጥ ያሉ ባልደረቦቻችንም መታሰራቸውን አውቀናል። እና ምንም በማይመለከተን ጉዳይ ነው መንግሥት የሚከስሰን። ከዚህ የሰላም ማስከበር ዘመቻ በኋላ የተመለሱ በተለያዩ እስር ቤቶች ታስረው ይገኛሉ። ይህ ሁሉ ነገር ነው እንድንሰጋ ያደረገን" በማለት ይህ ኮሎኔል ይናገራል። "ትጥቅ አስፈቱን፣ ምሽት 4 ሰዓት የሚጀምር ሰዓት እላፊ አወጁ እንዲሁም የአማራ እና የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ባልደረቦቻችን በአይነ ቁራኛ ይመለከቱናል" በተባበሩት መንግሥታት ጥበቃ ሥር ያለ ሌላ ሳጅን በትግራይ ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ እንቅስቃሴያቸው በክትትል ሥር እንደነበረ ይናገራል። "በማንነታችን እንደጠላት ታይተናል ማለት እችላለሁ። እንቅስቃሴያችን ተገድቦ ለወራት በክትትል ሥር ቆይተናል። ከሌሎች እንድንለይ ተደርገን ከሌሎች ወታደሮች ጋር እንዳንገናኝ ተደርገናል። ከኢትዮጵያ መንግሥት መገናኛ ብዙሃን ውጪ ሌሎች መገናኛ ብዙሃንን እንድንመለከት አይፈቀድም። ሙሉ በሙሉ ነጻነታችን ተገፈን ነበር" በማለት ይከስሳል። በትግራይ ክልል ግጭቱ የተቀሰቀሰው ሕወሓት በክልሉ የሚገኘውን የፌዴራል ጦር ሠፈር በማጥቃቱ ነው። ይህ የሕወሓት እርምጃ የፌዴራል መንግሥቱ የአፀፋ ምላሽ እንዲሰጥ አድርጎታል። በፌዴራል መንግሥቱ በክልላዊው አስተዳደር መካከል ያለው ውጥረት የጦዘው የኢትዮጵያ ምርጫ በኮሮናቫይረስ ምክንያት መራዘሙን ተከትሎ ነው። ከቀናት በፊት ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የተባበሩት መንግሥታት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪክ 15 የትግራይ ተወላጅ ሰላም አስከባሪዎች አሁን በተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት ጥላ ሥር ይገኛሉ ብለዋል። "ሊሰመርበት የሚገባው ነገር ማንኛውም ሰው ከለላ ሲፈልግ ጥገኝነት የመጠየቅ መብት አለው። ዓለም አቀፍ ከለላ የሚያስፈልጋቸው መሆኑ ከታመነበት ማንኛውም ሰው ነፃነቱን አሊያም ሕይወቱን ወደሚያጣበት ሃገር መመለስ የለበትም። ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተልነው ነው።" ጥገኝነት የጠየቁ ግለሰቦች አሁን ደህንነታቸው በተጠበቀ ቦታ እንዳሉ ተዘግቧል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ደቡብ ሱዳን ያሉ 15 የሰላም አስከባሪ አባላቱ ወደ ሃገር ቤት ላለመለስ መወሰናቸውን አረጋግጧል። ሰላም አስከባሪዎቹ በተባበሩት መንግሥታ የደቡብ ሱዳን ሚሽን መሠረት በሌሎች አዳዲስ ወታደሮች መተካት ነበረባቸው። ባለፈው ማክሰኞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ኢንዶክትሪኔሽን ኃላፊ ሜጀር ጄኔራል ሞሐመድ ተሰማ 15ቱን ወታደሮች "የሃገራቸውንና የወታደሮችን ስም ያጠፉ ናቸው" ሲሉ ወቅሰዋቸዋል። "ጁባ አየር ማረፊያ እየጮሁና መሬት ላይ እየተኙ ግርግር ሲፈጥሩ ነበር" ብለዋል ሜጀር ጄኔራሉ። ጄኔራሉ አክለው ለወታደሮቹ ከለላ የሰጠው የተመድ ስደተኞች ተቋምን [ዩኤንኤችሲአር] "የተዛባ መረጃ አሰራጭቷል" ሲሉ ወቅሰዋል። እንደ ኮሎኔሉ ከሆነ ከ200 በላይ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ወታደሮች ደቡብ ሱዳን ውስጥ በሰላም ማስከበር ተሰማርተው ከ18 ወራት በላይ አገልግለዋል። የተባበሩት መንግሥታት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪክ እንደሚሉት 15 ወታደሮች ከኢትዮጵያ ከመጡ 169 የተባበሩት መንግሥታት የደቡብ ሱዳን ሰላም አስከባሪ ሚሽን አባላት መካከል ናቸው። ወታደሮቹ በሚሽኑ መሠረት በሌሎች ወታደሮች ሊተኩ ነበር። ቃል አቀባዩ አክለው በሚሽኑ ውስጥ ካሉ 17 ሺህ 200 ወታደሮች መካከል 2 ሺህ 100 ኢትዮጵያዊያን ወታደሮችና ሲቪሎች ይገኛሉ። በአሁኑ ወቅት የተባበሩት መንግሥታት የአስራ አምስቱን ጥገኝነት የተቀበለ ሲሆን ሌሎች አራት "በደረሰብን ጥቃት" ጉዳት ገጥሞናል ያሉ ሰዎች ሆስፒታል ውስጥ እርዳታ እያገኙ ይገኛሉ።
news-55040028
https://www.bbc.com/amharic/news-55040028
ትግራይ፡ አምነስቲና የተባበሩት መንግሥታት ለመቀለ ሰላማዊ ዜጎች ጥንቃቄ እንዲደረግ ጠየቁ
የኢትዮጵያ ሠራዊት ወደ መቀለ በተቃረበበት ጊዜ በሚቀጥሉት ቀናት በሚደረጉ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ወቅት ለከተማዋ ነዋሪዎች ደኅንነት ጥንቃቄ እንዲደረግ ተጠየቀ።
መቀለ ከተማ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ለህወሓት አመራሮች እና ተፋላሚዎች የ72 ሰዓታት የመጨረሻ ጊዜ ገደብ መስጠታቸውን ተከትሎ በመቀለ ሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ ሊደርስ የሚችለው አደጋ እንዳሳሰባቸው የተበባሩት መንግሥታት እና አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታውቀዋል። ሦስት ሳምንት ለመድፈን በተቃረበው ግጭት የፌዴራሉ መንግሥት አሁን በትግራይ ዋና ዋና የሚባሉ ከተሞችን መቆጣጠሩን እና ወደ ክልሉ መዲና መቃረቡን አስታውቋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴንም ትናንት በነበራቸው መግለጫ መቀሌ በመከላከያ ሠራዊት ከ50-60 ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ ተከባ እንደምትገኝ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለህወሓት መሪዎች በሰጡት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ በንሑሃን እና በንብረት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ከዚህ በኋላ ብቸኛው አማራጭ እጅ መስጠት መሆኑን አስገንዝበው ነበር። የጠቅላይ ሚንስትሩ ማስጠንቀቂያ ተከትሎ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ለሚገመቱ የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች አስፈላጊው ከለላና ጥበቃ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል። በተመሳሳይ ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናልም ሁለቱ ኃይሎች ለሰላማዊ ዜጎች ደኅንነት ቅድሚያ እንዲሰጡ ጠይቋል። በክልሉ የሰብዓዊ እርዳታ የሚደርስበትን ሁኔታ እንዲያመቻቹም አስገንዝቧል። የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ዳይሬክተር ዴፕሮስ ሙቼና፤ "በሁለቱም ወገን ያሉ የጦር አዛዦች ዓለም አቀፍ የሰብዓዊነት ሕጎችና መርሆችን እንዲያከብሩ እጠይቃለሁ። በሰላማዊ ሰዎችና ወታደራዊ ባልሆኑ መሠረተ ልማቶች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የሚቻለውን ጥንቃቄ ሁሉ እንዲያደርጉ፤ ሰላማዊ ሕዝብ በሚበዛባቸው ሰፈሮች የወታደራዊ ቁሳቁሶች ክምችትን እንዲያስወግዱ፣ የወታደሮች እንቅስቃሴም በሰላማዊ ነዋሪዎች መኖርያ አካባቢ እንዳይሆን ጥሪ አቀርባለሁ" ብለዋል። በተጨማሪም ተዋጊዎች ሰላማዊ ዜጎችን ጋሻ ከማድረግ እንዲቆጠቡ አምነስቲ ጠይቋል። ከመቀለ ከተማ ባሻገርም በመላው ትግራይ ክልል ለደረሰው ሰብአዊ ቀውስ እርዳታ እንዲደርስ ለማስቻል ተራድኦ ድርጅቶች እንደልብ መንቀሳቀስ እንዲችሉ ለማገዝ ዕድሉን እንዲመቻች፣ የግንኙነቶች መስመሮች ወደነበሩበት እንዲመለሱ የስልክና የኢንተርኔት ግንኙነቶች ክፍት እንዲደረጉ አምነስቲ አሳስቧል። አስተማማኝ መረጃ መግኘት አስቸጋሪ በሆነበት በትግራይ እየተካሄደ ባለው ግጭት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወታቸውን ሳያጡ እንደማይቀር የእርዳታ ድርጅቶች ይገምታሉ። በተጨማሪም ከ30ሺህ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎችም ግችቱን በመሸሽ ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን እንደተሰደዱ እተነገረ ነው። በፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልልን በሚመራው ህወሓት መካከል ለወራት የቆየው አለመግባባትና መካሰስ ባለፈው ዓመት ማብቂያ ላይ በትግራይ ክልል በተናጠል የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ መባባሱ ይታወሳል። በጥቅምት ወር ማብቂያ ላይ በትግራይ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ ላይ በክልሉ ኃይሎች ጥቃት መፈጸሙን በመግለጽ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ማዘዛቸውን ተከትሎ ፍጥጫው ወደ ግጭት አምርቶ ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ የአገሪቱ ሠራዊት ወደ ክልሉ ዋና ከተማ መቃረቡ ተነግሯል።
news-50926124
https://www.bbc.com/amharic/news-50926124
በመስጅዶች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት የሚያወግዙ ሰልፎች ተካሄዱ
በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች በመስጅዶች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት የሚያወግዙ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሄዱ።
ባሳለፍነው ሳምንት በሞጣ ከተማ በአራት መስጅዶች ላይ የደረሰውን ጥቃት ለማውገዝ ከተደረጉት ሰልፎች አብዛኛዎቹ የተካሄዱት በአማራ ክልል በሚገኙ ከተሞች ነው። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እውቅና አልሰጠሁትም ያለው የተቃውሞ ሰልፍ ከተካሄደባቸው ከተሞች መካከል አዲስ አበባ፣ ሀዋሳ፣ አሰላ፣ ጅማ፣ ደሴ፣ መርሳ፣ ወልዲያ፣ ባሌ እና በደሌ ከተሞች ተጠቃሽ ናቸው። በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ በመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች እንዲበተን መደረጉን በስፍራው የሚገኘው ሪፖርተራችን ዘግቧል። በአማራ ክልል የተደረጉት ሰልፎች በሰላም መጠናቀቃቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ለአማራ ብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ አስታውቋል። በምሥራቅ ጎጃም ሞጣ ከተማ አራት መስጅዶች ላይ ጥቃት አድርሰዋል ተብለው የተጠረጠሩ 27 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ መሆኑ መገለጹ ይታወሳል። ለተቃውሞ ሰለፍ አደባባይ የወጡ ነዋሪዎች "የኃይማኖት ተቋማት መቃጠል መንግሥት የሚያሳየውን ቸልተኝነት ያሳያል"፣ "ለሁሉም የእምነት ተቋማት ጥበቃ ይደረግላቸው" እንዲሁም "ሚዲያዎች ያለ አድልዎ በሃይማኖት ተቋማት ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ይዘግቡ" የሚሉ መፈክሮችን ይዘዋል። በደሴ ከተማ የተካሄደውን ሰልፍ ሲያስተባበሩ ከነበሩት መካከል አቶ ከማል ሁሴን አንዱ ናቸው። አቶ ከማል "ይህ ድንገተኛ ጥቃት አይመስልም። ያን ያክል ቁጥር ያለው ህዝብ እየጨፈረ መስጅድ ሲወድም የሚያስቆም መንግሥት የለም ወይ? ይሄ ሆነ ተብሎ ድንገተኛ አደጋ ለማስመሰል ተሞክሯል። እዚህ ያለው ህዝብ የክልሉ መንግሥትን ጥፋተኛ ያደረገው" ይላሉ። አቶ ከማል ጨምረውም በጥቃቱ ንብረታቸው ለወደመባቸው ግለሰቦች የክልሉ መንግሥት ካሳ እንዲከፍላቸው መጠየቁን ተናግረዋል። ስሟ እንዳይጠቀስ የጠየቀች ሌላኛዋ በደሴ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተሳተፈችው ወጣት፤ የተካሄደው ሰላማዊ ሰለፍ በሰላም መጠናቀቁን ከተናገረች በኋላ፤ "ጥቃቱ ሲፈጸም መንግሥት ባፋጣኝ እርምጃ መውሰድ ለምን ተሳነው?" የሚለው የበርካቶች ጥያቄ ነው ብላለች። በሞጣ ከተማ የሚገኘው ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ጭስ መታየቱን ተከትሎ፤ በከተማዋ በሚገኙ አራት መስጅዶች ላይ ጥቃት የተሰነዘረው ከሳምንት በፊት ነበር።
news-53846433
https://www.bbc.com/amharic/news-53846433
ማሊ፡ተመድን ጨምሮ የተለያዩ አገራት መሪዎች የማሊን መፈንቅለ መንግሥት አወገዙ
በዚህ ሳምንት በማሊ የተደረገው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥትን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ጨምሮ የተለያዩ አገራት እያወገዙት ይገኛሉ።
መፈንቅለ መንግሥቱን ተከትሎም ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ባውባካር ኬታ ከስልጣናቸው እንዲለቁ ተገደዋል። የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤትና የቀጠናው ድርጅቶች በወታደራዊው ሃይል በቁጥጥር ስር ያሉት ፕሬዚዳንቱ እንዲለቀቁና ህገ መንግሥታዊው ስርዓት መስፈን እንዳለበት ጥሪ እያደረጉ ይገኛሉ። ወታደሮቹ በበኩላቸው አገሪቷ የባሰ ጦስና ቀውስ ውስጥ እንዳትገባ ለመከላከልም ነው እያሉ ይገኛሉ። የሲቪል አስተዳደር በቅርቡም እንደሚመሰርቱና አዲስ ምርጫም እንደሚካሄድ ቃላቸውን ሰጥተዋል። ሰፊ የቆዳ ሽፋን ያላት ማሊ ግዛቷ የሰሃራ በረሃንም የተወሰነ የሚሸፍን ሲሆን በተደጋጋሚም ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥቶችን አስተናግዳለች። በአሁኑም ወቅት አገሪቷ የአክራሪ ፅንፈኞች ጥቃትና የብሄር ግጭቶችንም ለማረጋጋት እየጣረች ትገኛለች። ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ባውባካር ኬታ ከሁለት አመት በፊት ለሁለተኛ ጊዜ ምርጫን አሸንፈው በስልጣን ላይ ይገኛሉ። ነገር ግን ከጥቂት ወራት በፊት በሃገሪቱ ውስጥ ባለው ሙስና፣ የምጣኔ ኃብት ኢ-ፍትሃዊ ክፍፍልና አወዛጋቢ የምርጫ ህግን በተመለከተ በርካቶች ተቃውሟቸውን በጎዳናዎች እያሰሙ ይገኛሉ። ከዚህም በተጨማሪ የሃገሪቱ ሰራዊት ፅንፈኛ አክራሪዎች ጋር በሚያደርገው እልህ አስጨራሺ ትግል የሚከፈላቸው ክፍያ ትንሽ መሆኑ ቁጣን ፈጥሯል። መፈንቅለ መንግሥቱን ተከትሎ ማሊ ከአፍሪካ ህብረት አባልነቷ ታግዳለች። "ይህ ያረጀ ያፈጀ ነው ተቀባይነት የለውም" ብሏል "ምንም አይነት ቀውስ በአገሪቷ ውስጥ ሲፈጠር የህዝቡን ፈቃድ ለመፈፀም ነው በሚል ወታደራዊ መፈቅለ መንግሥቶች ይካሄዳሉ። እንዲህ አይነት ምላሽ ተቀባይነት የለውም" በማለት የአፍሪካ ህብረት የሰላምና ፀጥታ ኮሚሸነር ስማይል ቸርጉ ለቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ፕሮግራም ተናግረዋል። አስራ አምስት አባላት ያሉት የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ) በበኩሉ መፈንቅለ መንግሥቱን በመቃወም አገራት ድንበሮቻቸውን እንዲዘጉ አድርጓል። ከዚህም በተጨማሪ ማንኛውንም የገንዘብ እንቅስቃሴም የገደበ ሲሆን ከማህበረሰቡም የውሳኔ ሰጭነት ቦታ እንድትገለል ወስኗል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ማይክ ፖምፔዮ በትዊተር ገፃቸው አውግዘውታል። የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮንም ወደ ሲቪል አስተዳደር እንድትመለስ ጠይቀው "ሽብርተኝነትን መዋጋትና ዲሞክራሲና የህግ የበላይነት የማይነጣጠሉ ናቸው" ብለዋል።
45099861
https://www.bbc.com/amharic/45099861
አብዲ ሞሃመድ ኡመር በቁጥጥር ስር ዋሉ
የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አብዲ ሞሃመድ ኡመር በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ።
አብዲ ሞሃመድ ኡመር ትናንት ከክልሉ ፕሬዚዳንትነታቸው መነሳታቸው ቢገለጽም የኢትዮጵያ ሶማሌ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) መሪ ሆነው ይቀጥላሉ ተብሎ ነበር። የቀድሞው የክልሉ ፕሬዝዳንት በመከላከያ ሠራዊት አባላት በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ከተደረጉ በኋላ ጅግጅጋ ከሚገኘው ቤተ-መንግሥት እንደተወሰዱ ምንጮች ለቢቢሲ ሶማልኛ ገልጸዋል። ከቅዳሜ አንስቶ በጂግጂጋ እና በሌሎች የክልሉ ከተሞች የተከሰተውን ሁከት ተከትሎ የሃገር መከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ ወደ ክልሉ ገብቶ ሰላም እንዲያስከብር መታዘዙ የታወሳል። አህመድ አብዲ ሞሃመድ የቀድሞውን ፕሬዝዳንት በመተካት መሾማቸውም ይታወሳል። • አብዲ ሞሃመድ ኡመር ከስልጣናቸው ወረዱ • መከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ ሶማሌ ክልል ገብቶ ሰላም እንዲያስከብር ታዘዘ አዲሱ የክልሉ ፕሬዚዳንት አህመድ አብዲ ሞሃመድ የሶማሌ ክልል ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሃላፊ በመሆን አገልግለዋል። አህመድ አብዲ ሞሃመድ ከቢቢሲ ሶማልኛ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ስልጣናቸውን አስረክበው በሰላም የስልጣን ሽግግር መካሄዱን ተናግረው ነበር። አህመድ አብዲ ሞሃመድ ''አብዲ ሞሃመድ ሥልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ የክልሉ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አዲስ መሪ መርጧል። የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ጂግጂጋ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ እየኖሩ ይገኛሉ'' ሲሉም ትናንት ተናግረው ነበር። • በሶማሌ ክልል ከ10 የሚበልጡ አብያተ ክርስትያናት ጥቃት ደረሰባቸው • በድሬዳዋ ከተማ በተከሰተ ግጭት የ10 ሰዎች ህይወት ጠፋ • በጅግጅጋ ግጭት ሸሽተው የተሸሸጉ ሰዎች በከፋ ችግር ላይ ናቸው ተባለ
54790647
https://www.bbc.com/amharic/54790647
መከላከያ ሠራዊት በሕወሃት ላይ የኃይል እርምጃ እንዲወስድ መታዘዙ ተሰማ
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ የአገር መከላከያ ሠራዊት በሕወሃት ላይ የኃይል እርምጃ እንዲወስድ ትዕዛዝ መሰጠቱን ይፋ አደረጉ።
ጠቅላይ ሚንስትሩ በአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው "ይህንን ጡት ነካሽ ኃይል ለማሳፈር እና ለመደምሰስ አስፈላጊውን ሁሉ የምናደርግ መሆኑን እገልጻለሁ" በማለት ጦርነት መከፈቱን አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ መከላከያ ሠራዊት አገር የማዳን ግዳጅ እንደተሰጠውም አስረድተዋል። ከዚህም በተጨማሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ "ሕወሐት በትግራይ በሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ላይ ጥቃት አድርሷል። ሰሜን ዕዝንም ለመዝረፍ ሙከራ አድርጓል" ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ሠራዊቱ ከሃያ ዓመታት በላይ የትግራይን ሕዝብ ሲጠብቅ የቆየ መሆኑን ገልፀው በቦታው የሚገኘውም የትግራይን ሕዝብ ከጥቃት ለመከላከል ነው። "ሕወሐት ግን እንደ ባዕድና እንደ ወራሪ ሀገር ሠራዊት ቆጥሮ፤ የመከላከያ ሠራዊቱን ለመምታትና ለመዝረፍ ተነሥቷል። በዳልሻሕ በኩልም ጦርነት ከፍቷል" ብለዋል። አክለውም "የመከላከያ ሠራዊታችን በኮማንድ ፖስት እየተመራ ሀገሩን የማዳን ተልዕኮውን እንዲወጣ ትእዛዝ ተሰጥቶታል። ቀዩ መሥመር የመጨረሻው ነጥብ ታልፏል። ሀገርና ሕዝብ ለማዳን ሲባል ኃይል የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል" በማለት ገልፀዋል። ከፌደራሉ መንግስት ጋር ውጥረት ላይ የሚገኘው የትግራይ ክልል መንግሥት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ መንግስት "በትግራይ ላይ የኃይል እርምጃ ወደ መውሰድ እየተሸጋገረ ነው" ሲል መግለጫ የሰጠው ሰኞ እለት ነበር የትግራይ ክልል መሪ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶክተር) ሰኞ ዕለት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ መንግሥት በትግራይ ላይ የሃይል እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል በመግለጽ 'ሕብረተሰቡ ዝግጅቱን አጠናክሮ ይቀጥል' ብለዋል። "ብዙ ጫናዎች ብዙ የሚድያ ዘመቻዎች ብዜ የኢኮኖሚ ዱላዎች ያደረሰብን ሳይበቃው፤ አሁን ደግሞ በኃይል እጨፈልቃለሁ ብሎ እየተንቀሳቀሰ ነው። ብዙ ምልክቶችም አሉ" ሲሉ ተናግረው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በቅርቡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ሲናገሩ ከትግራይ ክልል ጋር የተከሰተው አለመግባባት "በሕግ እና ሕግ ብቻ የሚመለስ ይሆናል" በማለት መናገራቸው ይታወሳል። ሰሞኑን፤ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አደረጃጀት ላይ ለውጥ መደረጉን ተከትሎ የትግራይ ክልል መንግሥት እርምጃውን ተቃውሞ መግለጫ ማውጣቱም የሚታወስ ነው። "የፌደራሉ መንግስት ስልጣኑ መስከረም 25/ 2013 ዓ.ም ላይ ያበቃ በመሆኑና ሕጋዊ ተቀባይነት ስለሌለው በመከላከያ ሰራዊት አደረጃጀት ላይ ለውጥ ሊያደርግ አይችልም" ብሏል በመግለጫው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በበኩሉ ይህን የትግራይ ክልል መግለጫ "ኢ-ህገመንግስታዊ" በማለት ተቃውሞ መግለጫ አውጥቷል። ዶ/ር ደብረጽዮን፤ የፌደራሉ መንግሥት ትግራይ ላይ የሓይል እርምጃ ለመውሰድ እየተዘጋጀ መሆኑን "የሚያሳዩ ምልክቶች አሉ" ሲሉ ነበር የተናገሩት። በወቅቱ ለክልሉ ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ወቅት "ምልክቶች፣ ዝግጅቶች አሉ። አንዱ ምልክት፤ ሰራዊቱ በተጠንቀቅ ላይ እንዲሆን ተነግሮታል" ያሉ ሲሆን ዝርዝር መረጃ ግን አልሰጡም። አክለውም፤ የትግራይ ክልል መንግሥት የመጀመርያው ፍላጎት ሰላም መሆኑን በመግለጽ "ቢሆንም፤ እኛም ሰራዊት አዘጋጅተናል፤ ሚሊሻችንን አዘጋጅተናል፤ ልዩ ኃይላችንን አዘጋጅተናል። ጦርነት ለማስቀረት ነው የተዘጋጀነው። መዋጋት ካለብን ግን፤ ድል ለማድረግ ተዘጋጅተናል" ሲሉ ተናግረው ነበር። የትግራይ ክልል የጸጥታ ቢሮም በፌስቡክ ገጹ ላይ "ጸረ ህልውናችን የተሰለፉ ኃይሎች ግልጽ መሰባሰብ እያደረጉ ነው" ሲል ጽፎ ነበር። ዶክተር ደብረጽዮን በሰኞ መግለጫቸው ላይ "የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ መንግሥትና የኤርትራው መንግስት በትግራይ ላይ አብረው እያሴሩ ነው" ሲሉ ከስሰው ነበር።
news-54165432
https://www.bbc.com/amharic/news-54165432
ሞዛምቢክ ፡ መንግሥት አንዲት ሴት ስትገደል የሚያሳየውን ቪዲዮ አጣራለሁ አለ
የሞዛምቢክ ባለስልጣናት በነዳጅ ሀብቷ በታወቀችው የካቦ ዴልጋዶ ግዛት ወታደራዊ የደንብ ልብስ የለበሱ ግለሰቦች ራቁቷን ያለች ሴት ደብድበው ሲገድሉ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል መውጣቱን ተከትሎ ምርመራ እንደሚካሂድ ገለፁ።
የመከላከያ ሚኒስትሩ በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ የሚታየውን ድርጊት "ጭካኔ የተሞላበት" በማለት "እውነተኛነቱን እንደሚያጠሩ" ተናግረዋል። የመብት ተሟጋቾችም ግድያውን አውግዘዋል። ሞዛምቢክ ላለፉት ሦስት ዓመታት በሰሜናዊ የአገሪቱ ክፍል ከእስላማዊ ታጣቂ ቡድኖች ጋር ፍልሚያ ላይ ነች። የሞዛምቢክ ጦርም ከአማፂያኑ ጋር በሚያደርገው ፍልሚያ በሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚወነጀል ሲሆን፣ መንግሥት ግን የሚቀርብበትን ክስ ያስተባብላል። ተንቀሳቃሽ ምስሉ የሁለት ደቂቃ ርዝማኔ ያለው ሲሆን በተለያዩ የመብት ተሟጋቾች ሰኞ ዕለት በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን ላይ ተጋርቷል። የወታደሩን ደንብ ልብስ የለበሱ ሰዎች አንዲት ራቁቷን ያለች ሴት ከበው በዱላ ከደበደቧት በኋላ በጥይት ተኩሰው ገድለዋታል። እንደ ሮይተርስና ኤኤፍፒ ዘገባ ከሆነ ግለሰቦቹ "ግደላት" እያሉ በፖርቹጋል ቋንቋ ሲነጋገሩ እንዲሁም "አልሸባብ ነሽ" ሲሏት ይሰማል። የሞዛምቢክ መከላከያ ኃይል ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ እንዲህ አይነት ጭካኔ የተሞላበትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት የታየበትን ተግባር እንደሚያወግዝ አስታውቋል። እንደ ሮይተርስ ዘገባ አልሸባብ በአገሪቱ ሰሜናዊ ግዛት ከሦስት ዓመት በፊት ጀምሮ በሰነዘረው ጥቃት 1ሺህ 500 ሰዎች ሲሞቱ 250 ሺህ ያህሉ ደግሞ ተፈናቅለዋል። ባለፈው ሳምንት አምንስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው መግለጫ አረጋገጥኩት ባላቸው ተንቀሳቃሽ ምስሎች ላይ ወታደራዊ ኃይሉ ከእስላማዊ ታጣቂ ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ እስረኞችን ሲያጉላላ፣ እንዲሁም ሲገድል እንደሚታይ ገልጿል። መንግሥት ግን ውንጀላውን አስተባብሎ፣ ታጣቂዎቹ የወታደሩን ልብስ በመልበስ እንደሚያጭበረብሩ ገልጿል። ካቦ ሌልጋዶ በአፍሪካ ትልቁ ነው የተባለ የተፈጥሮ ጋዝ የሚገኝባት ስፍራ ነች። በዚህች ግዛት ኤክሶን ሞቢል 60 ቢሊየን ዶላር በማውጣት የተፈጥሮ ጋዙን ለማልማት እየሰራ ነው።
news-53118425
https://www.bbc.com/amharic/news-53118425
ውዝግብ የፈጠረው የሌኒን ሐውልት ጀርመን ውስጥ ቆመ
ጀርመን ውስጥ የሚገኘው ግራ ዘመም የፖለቲካ ፓርቲ ውዝግብ የፈጠረውን የሶቪየት ኮሚኒስት መሪ ቭላድሚር ሌኒንን ሐውልት አቆመ።
ብዙም ደጋፊ የሌለው የጀርመን ማርክሲስት ሌኒኒስት ፓርቲ ሐውልቱን ያቆመው በምዕራባዊዋ የጀርመን ከተማ ጌልሰንኪርቸን ውስጥ በሚገኘው ዋና ጽህፈት ቤቱ ፊት ለፊት ነው። የከተማዋ ባለስልጣናት ፖርቲው የሌኒንን ሐውልት ለማቆም የሚያደርገውን ጥረት እንዲተው ለማድረግ በማኅበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ "ለሌኒን ቦታ የለንም" በሚል መለያ ርዕስ ዘመቻ አካሂደው ነበር። በተጨማሪም ጉዳዩን ወደ ሕግ በመውሰድ ሐውልቱ እንዳይቆም ለማሳገድ ቢጥሩን ፍርድ ቤት የሌኒን ሐውልት ቅዳሜ ዕለት ተመርቋል። የከተማዋ ከንቲባ ፍራንክ ባራኖወስኪ የሐውልቱን መቆም ተቃውመው ባሰራጯቸው የቪዲዮ መልዕክቶች ላይ በበርካታ አገራት ውስጥ ለዘመናት ቆመው በነበሩ ሐውልቶች ዙሪያ ክርክሮች እየተካሄዱ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ጨምረውም "የቅርብ ዘመን አምባገነንን ሐውልት የመታሰቢያ ሐውልትን ማቆም ከባድ ድርጊት ነው። ምንም እንኳን በሚያሳዝን ሁኔታ ፍርድ ቤት ቢፈቅድም ውሳኔውን የምንቀበለው ቢሆንም ጥያቄ ግን አለን" ብለዋል። የጀርመን ማርክሲስት ሌኒኒስት ፓርቲ ሊቀ መንበር ጋቢ ፌችነር ግን ሌኒንን "ነገሮችን ቀድሞ የሚረዳ በዓለም ታሪክ ተጠቃሽ የነጻነትና የዴሞክራሲ ታጋይ" ሲሉ መግለጻቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል። ሌኒን በጎርጎሳውያኑ 1917 የተካሄደው የሩሲያ አብዮት መሪ የነበረ ሲሆን በ1924 ህይወቱ እስኪያልፍ ድረስ አገሪቱን መርቷል። ሌኒን ከህልፈቱ በኋላ በመላው ዓለም በደጋፊዎቹና በተቃዋሚዎቹ ዘንድ የኮሚኒዝም ሥርዓት መለያ ሆኖ ለዘመናት ዘልቋል። የሁለተኛውን የዓለም ጦርነትን ተከትሎ ጀርመን ለሁለት ተከፍላ የበርሊን ግንብ ከ30 ዓመታት በፊት እስኪፈርስ ድረስ ምሥራቃዊው ክፍሏ በሶቪየት ኅብረት በሚደገፈው የኮሚኒስት ሥርዓት ስትተዳደር ቆይታለች። እንደ ጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር በ1957 የቀድሞዋ ቼኮዝላቫኪያ ውስጥ ተሰርቶ ጌልሰንኪርቸን ውስጥ በቆመው የሌኒን ሐውልት ዙሪያ የተነሳው ውዝግብ በቅርብ ሳምንታት ውስጥ በተለያዩ አገራት የጸረ ዘረኝነት እንቅስቃሴዎች ከባሪያ ንግድ ጋር የተያያዙ ሐውልቶች እንዲገረሰሱ ካቀረቡት ጥያቄ ጋርም ተያይዞ ነበር።
43722158
https://www.bbc.com/amharic/43722158
ካለሁበት 28፡ "ያደግኩበት አካባቢና የሰፈሬ ልጆች በጣም ይናፍቁኛል"
ስሜ ሙሴ ርዕሶም ይባላል። ከኤርትራ የወጣሁት ሃገሬን ጠልቼ ሳይሆን እንደ አብዛኛው ኤርትራዊ ማለቂያ የሌለውን የውትድርና ልምምድ በመቃወም ነው።
በረሃውንና ባህሩን አቋርጬ፣ ከብዙ ፍዳ በኋላ 2002 ላይ እንግሊዝ መግባት ቻልኩ። እንግሊዝ ውስጥ የመኖሪያ ፈቃድ ማግኘት እጅግ የከበደ እና ብዙ ውጣ ውረድ ያለው ቢሆንም የምፈልገውን ከማድረግ አልገታኝም። አሁን ላለሁበት ስኬት ለመድረስ ብዙ ፈተናዎችን ማለፍ ነበረኝ። ያሳልፈኳቸው ተዘርዝረው የማይልቁ ውጣ ውረዶች ነገሮችን በትዕግስት ማድረግ እንዳለብኝ እንድማር አግዘውኛል። እንግሊዝ ከገባሁ በኋላ አስፈላጊውን መመዘኛ በማሟላት የኤሌክትሪክ ምህንድስና ትምህርቴን ተከታትዬ አጠናቀቅኩኝ። ከዚያም ከፍቅር ጓደኛዬ ጋር ትዳር ከመሠረትን በኋላ ወደ ኖርዌይ ገባሁ፤ እርግጥ ነው የኖርዌይን ቋንቋ ለመማር ትንሽ ጊዜ ወሰዶብን ነበር። ኖርዌይ መኖር ከጀመርን ከጥቂት ጊዜያት በኋላ በአንድ የነዳጅ ማጣሪያ ኩባንያ በትምህርቴ የቴክኒክ ባለሙያ ሆኜ መሥራት ጀመርኩ። ከጥቂት ዓመታት በኋላ ደግሞ እሠራበት ከነበረው መሥሪያ ቤት ለቅቄ ኦስሎ ከተማ ውስጥ 'ዱባይ ጠቅላላ አገልግሎት' የሚባል ሱቅ ከፍቼ የንግድ ሥራን ተቀላቀልኩ። ኖርዌይ ውስጥ የሌላ ሃገር ዜጋ ሆኖ እንደዚህ ዓይነት ሥራ መሥራት በጣም ከባድ ቢሆንም ህልሜ ትልቅ በመሆኑ ማድረግ ችያለሁ። የምኖርበት አካባቢ ለዓይን በሚማርኩ ተራራዎች የተከበበ በመሆኑ ሁልጊዜ ከቤተሰቦቼ ጋር በመስኮት አሻግሬ የማየው አስደናቂ ተፈጥሮን ቢሆንም በኦስሎ ሱቄ ውስጥ ሆኜ አሻግሬ የማየው ግን መጪውን ዕድሌንና እድገቴን ነው። ተራራዎች ኤርትራና ኖርዌይን የሚያመሳስሏቸው ቢሆንም አጥንት በስቶ የሚገባው የኖርዌይ ብርድና በረዶ ከሃገሬ ሙቀት ጋር የሰማይና ምድር ያህል ልዩነት እንዳላቸው እንዲሰማኝ ያደርገኛል። በማሕበራዊ ኑሮም ኤርትራ እና ኖርዌይ ሰፊ ልዩነት አላቸው። ዋነኛ ምክንያቱ ደግሞ የኖርዌይ ሰዎች የግላዊ የሕይወት አዙሪት ውስጥ ያሉና ብዙም ከሰው ጋር ቁጭ ብሎ የማውራት ባህል የሌላቸው መሆኑ ነው። ጮክ ብለው እንኳን አይናገሩም። የቅርብ ጎረቤት መተዋወቅ በራሱ ከባድ ነው፤ ሁልጊዜ የቤታቸው በር ዝግ ነው። በሥራም ሆነ በትምህርት የሚያውቁት ሰው ከእነዚያ ቦታዎች ውጪ እንግዳ ነው፤ አትኩሮ ብቻ ይመለከትዎታል። መጀመሪያ በጣም ይከብደኝና ያናድደኝ ነበር፤ ሳስበውም ያስገርመኝ ነበር፤ አሁን ግን ለምጄዋለሁ። እዚህ የምንኖር ኤርትራውያን እርስ በራሳችን መልካም የሚባል ግንኙነት አለን፤ በደስታም ሆነ በሐዘን እንረዳዳለን። በቤታችን ውስጥ አንዳንድ ጊዜ እንጀራና ሌሎች ሃገራዊ ምግቦችን እናዘጋጃለን። ቢሆንም ግን እንደ ሃገር ቤት በፍፁም አይሆንም። ብዙ ጊዜ ግን ጨው ጨው የሚልና ደርቆ ለብዙ ጊዜ የሚቆይ የኖርዌይ ምግብ ነው የምንመገበው። ከዓሣ፣ አትክልትና ሥጋ የተሠራ ፓስታ በጣም ነው የምወደው። ከልጅነቴ ጀምሮ እግር ኳስ መጫወት እወዳለሁ። " ምድላው መግቢ" ለሚባል እግር ኳስ ቡድን እጫወትም ነበር። ይሄና ሌሎች ትዝታዎች አንድ ላይ ሆነው ያደግኩበትን አካባቢና የሰፈሬን ልጆች በጣም እንድናፍቅ ያደርጉኛል። ወደ ሃገር ቤት የመሄድ ዕድል ቢያጋጥመኝ ተወልጄ ባደግኩባት ውቢቷ አስመራ ከተማ ከቤተሰቦቼ ጋር ጥሩ ጊዜ ማሳለፍ እፈልጋለው። ለኤደን ሃብተሚካኤል እንደነገራት የ'ካለሁበት' ቀጣይ ክፍል ለማግኘት ፦ ካለሁበት 29 ፡ ''እዚህ ሰው በሰውነቱ ብቻ ትልቅ ክብር አለው'' ካለሁበት 30፡ መስቀል እና አረፋን ሳስታውስ ውስጤ ይረበሻል
news-50080787
https://www.bbc.com/amharic/news-50080787
እንግዳ ሰዎችን በመርዳት ላይቤሪያ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆነች
ላይቤሪያ እንግዳ የሆኑ ሰዎችን በመርዳት በዓለማችን ካሉ አገራት ግንባር ቀደም መሆኗን 'ወርልድ ጊቪንግ ኢንዴክስ' አመለከተ።
ተቀማጭነቱን በእንግሊዝ ያደረገው ግብረ ሰናይ ድርጅት ለጋሽ ሰዎችን አስመልክቶ ላካሄደው ጥናት ከተጠቀማቸው መስፈርቶች መካከል እንግዳ የሆኑ ሰዎችን መርዳት የሚለው ይገኝበታል። • የዓለማችን ለኑሮ ምቹ የሆኑ 10 ከተሞች እነማን ናቸው? • ከአንታርክቲካ በስተቀር ስድስቱን አህጉሮች ያዳረሰችው ኢትዮጵያዊት በተጨማሪም ሰዎች ምን ያህል ገንዘብ ለግብረ ሰናይ ድርጅት ይለግሳሉ፤ ምን ያህል ጊዜስ በበጎፈቃደኝነት ሥራ ላይ ያውላሉ የሚለውንም ተመልክቷል። ጥናቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ 1.3 ሚሊየን ሰዎችን ያሳተፈና ከ10 ዓመታት በፊት የተሠራ ጥናትን መሰረት አድርጓል። በአጠቃላይ ዝርዝሩ ውስጥ ኬንያ በአፍሪካ ካሉ ለጋሽ አገራት ቀዳሚ፤ በዓለም ደግሞ በ11ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ላይቤሪያ በ17ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ፤ ሴራሊዮን በ20ኛ እንዲሁም ናይጄሪያ በ22 ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል። ላይቤሪያን ጨምሮ፤ ሰባት የአፍሪካ አገራት እስከ አስር ባሉት ደረጃዎች ላይ ተቀምጠዋል። ሴራሊዮን ሁለተኛ፣ ኬንያ አራተኛ፣ ዛምቢያ አምስተኛ፣ ኡጋንዳ ስድስተኛ ፣ ናይጄሪያ ሰባተኛ እና ማላዊ አስረኛ ደረጃን ይዘዋል። ደረጃው እንግዳ የሆኑ ሰዎችን በመርዳት የተዘረዘረ ነው።
news-55464023
https://www.bbc.com/amharic/news-55464023
ኮሮናቫይረስ፡ ትራምፕ ለአሜሪካዊያን በነፍስ ወከፍ 600 ዶላር እንዲሰጥ ፈቀዱ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በኮሮናቫይረስ ምክንያት አቅማቸው ለደከመ አሜሪካዊያን የሚሆን ድጎማና ሌሎችም ወጪዎች የተካተቱበት ማዕቀፍ ላይ ፊርማቸውን አሳርፈዋል።
ፕሬዝደንቱ አልፈረምም ማለታቸውን ተከትሎ የአሜሪካ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ይዘጋሉ ተብሎ ተሰግቶ ነበር። ትራምፕ ለአሜሪካ ሕዝብ 600 ዶላር አይበቃውም 2 ሺህ እንጂ ብለው ላለመፈረም ቃል ገብተው ነበር። በዚህ ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሥራ አጥ አሜሪካዊያን ያለምንም ጥቅም ቀናት ለማሳለፍ ተገደው ነበር። የአሜሪካ ኮንግረስ ለወራት ከመከረና ከዘከረ በኋላ ባለፈው ሳምንት 900 በሊዮን ዶላር የያዘ ድጎማ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል። ድጎማው ከ2.3 ትሪሊዮን ዶላር በጀት የተቀነጨበ ሲሆን 1.4 ትሪሊዮን ዶላር ደግሞ ለመንግሥት ወጭ ይሆናል ተብሏል። ትራምፕ ሰኞ እኩለ ለሊት ፊርማቸውን ባያሳርፉ ኖሮ የአሜሪካ መንግሥት ይዘጋ ነበር። 14 ሚሊዮን ገደማ ሥራ የሌላቸው አሜሪካዊያን ፊርማው በመዘግየቱ ምክንያት ከመንግሥትሌምንም ዓይነት ደጎማ ሳያገኘዑ ከርመዋል። አሁን ግን ከመንግሥት ጥቅማ ጥቅም ማግኘት ይጀምራሉ። ለእያንዳንዱ አሜሪካዊ 2 ሺህ ዶላር ይሰጠው የሚል ማዕቀፍ ካለመጣችሁ 'አንገቴን ለካራ' ብለው የነበሩት ዶናልድ ትራምፕ በምን ምክንያት ሐሳባቸውን እንደቀየሩ አልታወቀም። ትራምፕ፤ ኮንግረስ ውስጥ ካሉ የሁሉቱም የአሜሪካ አውራ ፓርቲዎቻ አባላት ጫና ሲደርስባቸው ነበር። ሪፐብሊካኑ ሴናተር ሚት ሮምኒ በስተመጨረሻም ማዕቀፉ ሕግ ሆኖ በመፅደቁ 'እፎይታ' እንደተሰማቸው ተናግረዋል። ተመራጩ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ተሰናባቹ ፕሬዝደንት ትራምፕ ፊርማቸውን የማያሳርፉ ከሆነ 'አደጋው የከፋ' ሊሆን እንደሚችል ሲያስጠነቅቁ ነበር። ጠንከር ያሉ ቃላት ያዘለ መግለጫ የለቀቁት ባይደን ትራምፕ ፊርማን ለማሳረፍ አሻፈረኝ ማለታቸው 'ኃላፊነት የጎደለው' ሲሉ ዘልፈዋቸው ነበር። የኮሮናቫይረስ ድጎማና ሌሎችም በርካታ በጀቶች የተካተቱበት የገንዘብ ማዕቀፍ ወደ አሜሪካ ኮንግረስ ቀርቦ በአብላጫ ድምፅ ቢፀድቅም ትራምፕ ይህ "ውርደት" ነው ሲሉ ገልፀውት ነበር። አልፎም ማዕቀፉ "በአላስላፈጊ በጀቶች የተሞላ ነው" ሲሉ ትራምፕ አጣጥለውታል። ማዕቀፉ በዓመት ከ75 ሺህ ዶላር በታች ለሚያገኙ አሜሪካዊያን 600 ዶላር ይሰጣቸው ይላል። ትራምፕ ደግሞ 2 ሺህ ነው የሚገባው ለአሜሪካ ሕዝብ ይላሉ። ነገር ግን ይህ ሐሳባቸው ከሳቸው ፓርቲ ሆነ ከዴሞክራቶች ተቀባይነት አላገኘም። ትራምፕ ሐሳብ በርካታ ፖለቲከኞችን አስደንቋል፤ አስደንግጧል። ተንታኞች ፕሬዝደንቱ በኮሮናቫይረስ ምክንያት አቅማቸው ለደከመ አሜሪካዊያን እንዲሆን ድጎማ ይሰጥ ተብሎ ክርክር ሲደረግ አንዳችም ሐሳብ አላነሱም፤ አሁን ደርሰው ይህን ማድረጋቸው ተገቢ አይደለም ሲሉ ይተቻሉ። የዶናልድ ትራምፕ አጋር የሆኑት የገንዘብ ሚኒስትሩ ስቲቨን መኑቺን 600 ዶላሩን ደግፈው ከጥቂት ሳምንታት በፊት አስተያየት ሲሰጡ ነበር።
news-52576828
https://www.bbc.com/amharic/news-52576828
ኬንያ ሶማሊያ እና ሩዋንዳ በከባድ ጎርፍ ተመቱ
በምስራቅ አፍሪካ በጣለ ከባድ ዝናብ ምክንያት በተከሰተ ጎርፍ ከ 260 በላይ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል።
በጎርፉ ክፉኛ የተጎዳችው ኬንያ ስትሆን 194 ሰዎች ሕይወታቸን ማጣታቸው ታውቋል። • ለስምንት ልጆቿ ድንጋይ የቀቀለችው ኬንያዊት • አሳሳቢው የአንበጣ መንጋ ስጋት በኢትዮጵያና በአካባቢው አገራት በሩዋንዳ ደግሞ በዚሁ ጎርፍ ምክንያት 55 ሰዎች የሞቱ ሲሆን በሶማሊያ 16 ሰዎች ሞተዋል። በኡጋንዳ ጎርፉ ባስከተለው መጥለቅለቅ 200 የሚሆኑ ታካሚዎች ከአንድ ሆስፒታል ውስጥ መውጣት አቅቷቸው እስካሁን እዛው መሆናቸው ተዘግቧል። የምስራቅ አፍሪካ አገራት በአሁኑ ሰአት የኮቪድ-19፣ የአንበጣ መንጋ እና የጎርፍ አደጋ እየፈተኗቸው ነው። ይህ ጎርፍ እስካሁን ከ3000 ሄክታር በላይ መሬት ላይ የነበረ ሰብልም ሙሉ በሙሉ አጥፍቷል። የአየር ትንበያ ባለሙያዎች እንደሚሉት ዝናቡ ከዚህም በላይ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይችላል። በሩዋንዳ ከጎርፉ በተጨማሪ በርካቶች በመሬት መንሸራተት ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን መኖሪያ ቤቶች፣ ዋና ዋና መንገዶችና የእርሻ ማሳዎች ከጥቅም ውጪ ሆነዋል። በምዕራባዊ ዩጋንዳ ደግሞ አንድ ወንዝ ሞልቶ ወደ ውጪ በመፍሰሱ በርካቶች ማቄን ጨርቄን ሳይሉ ተሰደዋል። በዚህም ምክንያት ቤት አልባ የሆኑ ሰዎች መንግስት ድረስልን እያሉ ይገኛሉ። • የአንበጣ መንጋው አሁንም ሊቀጥል ይችላል በቅርብ ሳምንታት በአፍሪካ ትልቁ የሆነው ቪክቶሪያ ሐይቅ ከሚገባው በላይ በመሙላቱ በዙሪያ የነበሩ ነዋሪዎች ቤታቸውን ትተው ሸሽተዋል። ከባድ የአፈር መሸርሸርም አስከትሏል።
44531247
https://www.bbc.com/amharic/44531247
ካናዳን በጥበብ ሥራው ያስዋበው ኢትዮጵያዊ
ጊዜው በአውሮፓውያኑ 2000 ዓ.ም.፤ ለአራት ዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሥነ ጥበብና ዲዛይን የተማረው ሲሳይ ሽመልስ ህይወትን አንድ ብሎ ጀመረ።
ሲሳይ ከሳለው 'የሰንበት ቀለማት' የተሰኘው የአዳም ረታ መጽሐፍ ሽፋን ጋር ዕድል ፈገግ ያለችለት ሲሳይ በጀርመኗ ሃኖቨር ከተማ በተዘጋጀ ዓውደ ርዕይ ላይ ኢትዮጵያን ወክሎ ከሌሎች አርቲስቶች ጋር እንዲሳተፍ ሆነ። ኑሮውንም በጀርመን ተያያዘው፤ በግራፊክስ ዲዛይን ሙያም ተመረቀ ''ከዚህ ወዲህ ነው ሕይወቴ አዲስ መልክ የያዘው'' ይላል ሲሳይ። ለጥቆም መኖሪያውን ከአውሮፓ ካልጋሪ ወደተሰኘችው የካናዳ ከተማ ቀየረ። ሥራዎቹ ኢትዮጵያዊ ሠዓሊነቱን እንዲያንፀባርቁ ብሎም ሕዝቡን እንዲወክሉ ከማድረግ ወደኋላ እንደማይል የሚናገረው ሲሳይ፤ "ፋይዳ ያላቸው' ሥራዎችን መሥራት እመርጣለሁ"ይላል። በተለያዩ ዝግጅቶች ላይ በ15 ደቂቃ ውስጥ የሰዎችን ፊት በመሳል እራሱንና ሥራውን ያስተዋውቃል። "ብዙውን ጊዜ ከሥራዬ ይልቅ የቆዳዬን ቀለም ወይም አመጣጤ ላይ የሚያተኩሩ ሰዎች ያጋጥሙኛል" የሚለው ሲሳይ "አንዳንዴ አዝናለሁ ... 'በዚህ እንለካካ?' ያስብለኛል" ሲል ቁጭቱን ይገልፃል። ከሁሉም በበለጠ ግን እንደ አፍሪካዊነቱ በምዕራቡ ዓለም ማንነቱን የሚገልጹ ሥራዎች ለሕዝብ ማቅረብ በመቻሉ ደስታ እንደሚሰማውም ይናገራል። «ፋይዳ ያለው ሥዕል». . . ? የቀሰመውን የግራፊክስ ዲዛይን ትምህርት ሥራ ላይ በማዋል በካልጋሪ ፖሊስ ጣቢያ ግድግዳዎች ላይ ሥራዎቹ በቋሚነት ተሰቅለውለታል። አብዛኛውን ጊዜ የግራፊክስ ዲዛይን ሲባል የማስታወቂያ ሥራን ተኮር ያደረጉ ሥራዎች የሚቀርብበት ነው የሚለው ሲሳይ፤ የእርሱ ፍላጎት ግን የሥዕሎቹን የጀርባ ማንነት ማጥናት እንደሆነ ያስረዳል። ለዚህም ነበር የመመረቂያ ሥራውን 'የሕይወት አዕማዶች' በማለት ፍቅር፣ ተስፋ፣ እምነት፣ ትህትና፣ ምህረትና ምስጋና ላይ ያተኮረው። ከእነዚህም መካከል 'እምነትና ተስፋ የተሰኙት' ሥዕሎቹ ተመርጠው በካልጋሪ ፖሊስ ጣቢያ ለመሰቀል በቅተዋል። የተገነቡበት መንፈስም አብሮ የመሥራትን፣ በተስፋ አብሮ የማደግን፣ ለአዳዲስ ነገሮችና ለለውጥ መዘጋጀትን እንዲያመላክቱ እሳቤ ውስጥ በማስገባት ነበር። ሥዕሎቹ ከሌላው ተለይተው የተመረጡበት ምክንያትም "በሃገሪቱ ያለውን የፖሊሱንና የስደተኛውን ሕይወት እንዲያቆራኙ እና የሁለቱን አብሮ የመሥራት ፍላጎት እንዲያነሳሱ ተደርገው በመሠራታቸው" እንደሆነ ይገልፃል። በተለያዩ ቦታዎች እንደሚሰማው በፖሊሱና በስደተኛው ሕብረተሰብ መካከል ያለው የሃሳብና የድርጊት አለመገጣጣም ብዙ ችግሮችንና ሕፀፆችን እንዳስከተለ ይናገራል። ለሲሳይ እነዚህ ሥራዎቹ በፖሊስ ጣቢያው መሰቀላቸው ከዚህም ያለፈ ትርጉም አለው። "እኛም በተሻለ መንገድ እራሳችንን ማሳየት እንችላለን፤ 'በበኩላችን የምናደርገው አስተዋጽዖ አለ' የሚለውን ሀሳብ የሚወክሉ ሥራዎች ናቸው ብዬ አምናለሁ" ይላል። ለካልጋሪ ማሕበረሰብ ትርጉም ሰጪ ሥራዎች በመሆናቸው ፋይዳ ያላቸው ሥዕሎች እንደሆኑም ይናገራል። 'የሕይወት አዕማዶች' ከተሰኘው የሲሳይ ሥራ ከፊሉ የኩራት ምሳሌ በካልጋሪ ነዋሪዎች ዘንድ ተቀባይነት ያገኙት ሥራዎቹ "ለአሁኑም ሆነ ለወደፊቱ ትውልድ እንደ ምሳሌ ሊቀርቡ የሚችሉ እንደሆኑ እምነቴ ነው» ይላል ሲሳይ። «የመጪውን ትውልድ የሚያነቃቁና የወጣቱን የወደፊት ተስፋ ብሩህ የሚያደርጉ ሥራዎች ናችው» በማለት ያስረዳል። «እስቲ ሥራዎችህን አቅርብልን» የሚሉ ጥሪዎች ከተለያዩ ተቋማት እንደሚደርሱት የሚናገረው ሲሳይ፤ ወጣቶች ሥራዎቹን ሲመለከቱ «የመነሳሳትና የኩራት መንፈስ ሲፈጥር አስተውላለሁ» ይላል። «እዚህ ሃገር በተለምዶ 'ኢንዲጂነስ አርት' ብለው የሚጠሩትን ዓይነት ሥራ እየሠራሁ ነው፤ አልፎም ሥራዎቼ የማሕበረሰባችንን ማንነት እያንፀባረቁና ለየት ያለ ሚና እየተጫወቱ እንደሆነ ይሰማኛል።» «ይህን በማድረጌ ደግሞ እጅጉን ደስተኛ ነኝ፤ ምክንያቱም ብዙዎች 'ድምፃችን ሆነሃል' ይሉኛል» ይላል የሚሰማውን ኩራት ሲገልፅ። «በባህላችን 'ምልሶች' ነን፤ ብዙውን ጊዜ ኢትዮጵያውያን እራሳቸውንም ሆነ ችሎታቸውን ገፍተው ሄደው አያቀርቡም፤ ጨምሮም በምንኖርበት ሕብረተሰብ ውስጥ ለውጥ መፍጠር የሚለው ሃሳብ ገዥ አይደለም። በተሰማራንበት በማንኛውም ሙያና ችሎታ ይህን የምናደርግበት ዕድሉም ጠባብ ነው።» ሆኖም ግን ሲሳይ ከሃገሩ ልጆች በተለየ ይህ ዕድል ለእርሱ በመከፈቱ ይህን ተልዕኮ የመወጣት ግዴታም እንዳለበት ይሰማዋል። በተለይ የሚሠራቸውን ሥዕሎች ለሕዝብ በሚያቀርብበት ጊዜ «አፍሪካዊያንም ይህን መሠራት ይችላሉ» የሚለውን ስሜት በምዕራባውያን ላይ መፍጠር እንደሚፈልግ ይናገራል። «ከዚያ ባለፈም በውጪው ዓለም የሚወለዱና የሚያድጉ በብዛት ከወላጆቻቸው ወይም ከማንነታቸው ጋር የሚያስተሳስራቸው ሰንሰለት ልል በመሆኑ ሥራዎቼን በመመልከት ''እኛም እንችላለን'' የሚለውን ስሜት እንዲፈጥርባቸው እፈልጋለሁ።» ይህን ለማሳካት ደግሞ እስካሁን የሠራቸውና ለሕዝብ ያቀረባቸው ሥዕሎች ጥርጊያ መንገድ እንደሆኑ የሚሰማው ሲሳይ፤ ወደ ፊት ለመጪው ትውልድ «የተለያዩ ታሪካዊና ባህላዊ እሴቶቻችንን ማስተማርን ከግምት ውስጥ ያስገባ በሥነ-ጥበብ የተደገፈ «እራስን የማወቅ ትምህርታዊ ጉዞ» እንደሚያቅድ ይናገራል። በካልጋሪ ከተማ መንገዶቸ የተለያዩ ቦታዎች ላይ በቋሚነት የቀረቡት የሲሳይ ሥራዎች በቀለማት የተዋቡ መንገዶች ከዚህ ቀደም ሥራዎቹን በተለያዩ ቦታዎች ለዕይታ የሚያቀርብ በመሆኑ እራሴን 'ስቱድዮ አርቲስት' ከሚባሉት ነው የምፈርጅው የሚለው ሲሳይ፤ አሁን የተሰማራበት ዘርፍ ያልተለመደ እንደሆነ ያስረዳል። የካልጋሪ ከተማ አስተዳደር ለሕዝብ ዕይታ ለሚቀርቡ የጥበብ ሥራዎች ባለው ትኩረት ምክንያት የከተማው ነዋሪዎች እራሳቸውን የሚገልጹበትና ችሎታቸውን የሚያዳብሩበትም ሆነ የሚያንፀባርቁበት ዕድል ሰፊ ነው። ሲሳይ እነዚህን ዕድሎች ከተጠቀሟቸው ሰዎች መካከል አንዱ ነው። ለሁለት ዓመታት 'የተቀባች ከተማ' በተሰኘ ሃሳብ የተለያዩ ሠዓሊዎችን ባዋቀረ የከተማው ተነሳሽነት ከሌሎች ሠዓሊዎች ጋር ተመርጦ በከተማው ማስዋብ ሥራ ላይ ተሳትፏል። የካልጋሪን ከተማ ከሚያስውቡት ሥራዎቹ መካከል የምስራቅ አፍሪካ ውዳሴ በሚል ርዕስ ዙሪያ 'የነፃነት ክብረ በዓል' የተሰኘ ቁመቱ 3 ሜትር በ 5 ሜትር የሆነ ሥራው 'ኢንተርናሽናል' በተሰኘው ጎዳና ላይ በቋሚነት ተሰቅሏል። ከዚያ ውጪ የተለያዩ የከተማው ማስታወቂያዎች፤ በመብራት ዘንጎች እንዲሁም የመብራትና የስልክ ጋኖች ወይም መቁጠሪያዎችን በማስዋብ ሥራ ላይ እንደተሳተፈም ይናገራል። እነዚህም ሥራዎቹ ከሕዝቡ ጋር በይበልጥ እንዲተዋወቅ ያደረጉት መሆኑን ይገልፃል። የሲሳይ ስልት ደግሞ ለየት ያለ ነው። የምዕራቡን የሥዕል ዘይቤ ከአፍሪካ ወይም ከኢትዮጵያ ጋር በማደባለቅ የእራሱን ዱካ በከተማው ላይ እንዳስቀመጠ ይሰማዋል። በተጨማሪም ይህን የመሳሰሉ ዕድሎች በመከፈታቸው «ለሕዝቤና እኔን ለሚመስሉ ሌሎች ድምፅ እንደሰጠሁ ያህል ነው የሚሰማኝ» የሚለው ሲሳይ፤ ማንነቱንና አመጣጡን ከማንፀባረቅ ወደ ኋላ እንደማይል ይናገራል። ይህ ሁሉ ስኬት ግን በቀላሉም ሆነ ያለፈተና አይመጣምና አልፎ አልፎ የሥዕሎቹ ፈጣሪ እርሱ መሆኑን የሚያውቁ ሰዎች በቆዳው ቀለምም ሆነ በአፍሪካዊነቱ እንደሚገረሙ ይነግረናል። «ቆዳዬ ይለቅ አይለቅ ለማየት እሰከመንካት የደረሱ መደበኛ የሆኑ ሰዎች አጋጥመውኛል» ቢልም ሙያውን የሚረዱት ደግሞ ለሥራው፣ ለችሎታውና ለብቃቱ ታላቅ አክብሮት እንዳላቸውና በተለያዩ ቦታዎች ላይ ሥራውን እንዲያቀርብም ሆነ እንዲያስተምር እንደሚጋበዝ ይናገራል።
41678617
https://www.bbc.com/amharic/41678617
በኬንያ የሚገኙ ኦሮሞ ስደተኞች ፖሊስ እገዳ እንዳበዛባቸው ይገልጻሉ
የኬንያ ባለስልጣናት በኢትዮጵያ መንግሥት ግፊት በሃገራቸው የሚገኙ ስደተኞች ላይ እገዳ እየጣሉባቸው መሆኑን የስደተኞች ቡድንና ሂውማን ራይትስ ዋች ገለጹ።
በኬንያ ናይሮቢ በ2008 የተከበረው የኢሬቻ በዓል የኦሮሞ ስደተኞች መስከረም 22/2010 ዓ.ም የኢሬቻ በዓልን በይፋ ለማክበር ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ መሆኑን ተከትሎ ጥቅምት 5/2010 በዓሉን በግል ይዞታ ላይ አክብረዋል። እነሱ እንደሚሉት ይህ በተከታታይ በኬንያ ባለስልጣናት ከሚጣሉባቸው ገደቦች አንዱ ነው። ዲሪርሳ ቀጄላ በኬንያ የሚገኘው የኦሮሞ ስደተኞች ማህበር የህዝብ ኮሙኒኬሽን ኃላፊ ነው። ዲሪርሳ እንደሚለው ችግሩ የጀምረው እ.አ.አ በ2015 በእድሜ ባለጸጋው የባህል እና የታሪክ አዋቂው ዳበሳ ጉዮ የት እንደደረሱ ከጠፉ በኋላ ነው። ግለሰቡ ከናይሮቢ ቤታቸው የጠፉት በዚያ ዓመት ከተካሄደው ኢሬቻ ክብረ በዓል በኋላ ነበር። በ2016 የተከበረው የኢሬቻ ክብረ በዓል ከመጀመሩ በፊትም 42 ኦሮሞዎች በኬንያ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለዋል። ናይሮቢ ውስጥ ህገወጥ የኦሮሞ ማህበረሰብ ሊያቋቁሙ ነው በሚል ነው የተያዙት። "የኢትዮጵያ መንግሥትን ሊያስቆጣ ይችላል" "ባለፉት 15 ዓመታት ኢሬቻን እያከበርን ብንቆይም ዘንድሮ ለማክበር ያቀረብነው 'ህጋዊ ጥያቄ' ውድቅ ተደርጎብናል" ሲል ዲሪርሳ ለቢቢሲ ተናግሯል። የዓመታዊውን ክብረ በዓል ዓላማ እና እስከ 200 የሚደርሱ ሰዎች እንደሚሳተፉበት በመጥቀስ በናይሮቢ ሲቲ ፓርክ ለማክበር የጽሑፍ ጥያቄ ቀርበው ነበር። የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን ጥያቄውን ለጊጊሪ ፖሊስ ጣቢያ ቢመራውም ጥያቄያቸው ውድቅ መደረጉን ዲሪርሳ አስታውቋል። ማህበሩ ስለጉዳዩ ናይሮቢ ከሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፈቃድ መጠየቅ እንዳለበት ተገልጾላቸዋል። ፖሊስ ፈቃዱን የሚሰጠው ከኤምባሲው ፈቃድ ከተገኘ በኋላ ነው ተብለዋል። "የፖሊስ ጣቢያው አዛዥ 'በፖለቲካዊ ምክንያቶች' ኦሮሞዎች እንዲሰበሰቡም ሆነ በዓል እንዲያከብሩ ፈቃድ እንደማይሰጡ ገልጸውልናል። ሆኖም እነዚህ 'ፖለቲካዊ ምክንያቶች' ምን እንደሆኑ ግልጽ አላደረጉልንም" ሲል ዲሪርሳ አስታውቋል። እንደዲሪርሳ አገላለጽ ከሆነ ኤምባሲውን ሳያማክሩ ክብረ በዓሉ እንዲካሄድ ቢፈቅዱ "የኢትዮጵያ መንግሥትን ሊያስቆጣ ይችላል" ተብለዋል። ዳበሳ ጉዮ በ2008 ኬንያ በተከበረው የኢሬቻ በዓል ላይ የስደተኖች ጉዳይ በኬንያ የህዝብ ሥነ-ምግባር ህግ አንቀጽ 56 እንደሰፈረው ከሆነ ለማህበራዊ፣ ባህላዊ እና ለበጎ ፈቃድ አገልግሎት መሰባሰብ ፈቃድ አያስፈልገውም። በዚህ መሠረት ኢሬቻ እንዳይከበር የሚከለክል ምክንያት አልነበረም። ኢሬቻ ባህላዊ ክብረ በዓል ቢሆንም ኦሮሞ አክቲቪስቶችን ጨምሮ የተለያዩ ወገኖች ክብረ በዓሉን ፖለቲካዊ ተቃውሞዎች የሚሰሙበት ሲያደርጉ ቆይተዋል። የማህበሩ አባላት ስደተኞች በመሆናቸው ከኤምባሲው ጋር ግንኙነት መፍጠር አለመቻላቸውን ለቢቢሲ አስታውቀዋል። "ስደተኞች በመሆናችን ስለጉዳዩ ኤምባሲውን ለመጠየቅ መብት የለንም" ይላል ዲሪብሳ። ብዙዎቹ ስደተኞች ኢትዮጵያን ለቀው የወጡት በፖለቲካ ምክንያት ነው። "ደህንነት አይሰማኝም" ይላል። "እታሰራለሁ ወይንም ታፍኜ ወደ ኢትዮጵያ ልመለስ እችላለሁ የሚል ፍራቻ አለኝ። እስከማውቀው ድረስ የኬንያ ፖሊስና ኢትዮጵያ መንግሥስት ይህንን በተደጋጋሚ ሲያደርጉት ቆይተዋል" ብሏል። "ይህንንም እንደስደተኞች ጉዳይ እና ለተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ላሉ ድርጅቶች በተደጋጋሚ መረጃ ሰጥቻለሁ" ሲል ይገልጻል። ተደጋጋሚ እገዳዎች የሂውማን ራይትስ ዋች የምሥራቅ አፍሪካ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ፌሊክስ ሆርን በኬንያ ፖሊስ እና በኢትዮጵያ ኤምባሲ መካከል ጠንካራ ግንኙነት መኖሩን ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ሁለቱ አካላት በጋራ በመሆን ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችንና ጥገኝነት ጠያቂዎችን በተደጋጋሚ ጊዜ ሲያንገላቱ፣ ሲያስፈራሩ ወይንም በዘፈቀደ ሲያስሩ እንደነበር ሂውማን ራይትስ ዋች መረጃዎች አሉት" ይላሉ። "የኦሮሞ ማህበረሰብ አባላት ተሰባስበው ኢሬቻን እንዳያከብሩ መከልከሉ፤ ስደተኞችን የማስፈራራትና የማንገላታት አዲሱ ስትራቴጂ ነው" ሲሉ ያስረዳሉ። ድሪብሳ የሂውማን ራይትስ ዋች ጥናት ትክክል ነው ይላል። እሱ እንደሚለው የመሰብሰብ መብታቸውን ለኢሬቻ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች ላይም ለመገናኘት ተቸግረዋል። "ማህበራችንን በኬንያ የማህበረሰብ ህግ መሠረት አስመዝግበን ፈቃዱን በየወቅቱ ብናድስም የመሰባሰብ መብታችንን ተከልክለናል" ይላል ድሪብሳ። የኃላፊዎች ምላሽ የኢሬቻ በዓልን ለማክበር ከየትኛውም ድርጅት ጥያቄ እንዳልቀረበላቸው በኬንያ የኢትዮጵያ አምበሳደር ዲና ሙፍቲ ለቢቢሲ አስታውቀዋል። የኬንያ ፖሊስ ፈቃድ ስለመከልከሉ ምንም እንደማያውቁም ገልጸዋል። በቅርቡ ሂውማን ራይትስ ዋች የኬንያ ባለስልጣናትና ኢትዮጵያ መንግሥት በጋራ በመሆን ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ከማንገላታት ባለፈ ለኢትዮጵያ አሳልፈው ይሰጣሉ ለሚለው ሪፖርት አምባሳደሩ ምላሽ ሰጥተዋል። "እኛ ማንንም ከኬንያ አልወሰድንም፤ ለኬንያም አሳልፈን አልሰጠንም። በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት አጠናክረን ለመቀጠል እንሰራለን። ይህ ልብወለድ ነው" ብለዋል። የናይሮቢ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የጊጊሪ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊና ብሔራዊ የፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊን ለማናገር ሙከራ ቢደረግም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።
news-41995962
https://www.bbc.com/amharic/news-41995962
''ሮበርት ሙጋቤ በቁጥጥር ስር ውለዋል፤ ደህንነታቸውም ይጠበቃል'' ሲል የዛኑ ፒኤፍ ፓርቲ ይፋዊ የትዊተር ገጽ አስታውቋ።
ሮበርት ሙጋቤ በቁጥጥር ስር ውለዋል፤ ደህንነታቸውም ይጠበቃል ሲል የዛኑ ፒኤፍ ፓርቲ ይፋዊ የትዊተር ገጽ አስታውቋ።
ሮበርት ሙጋቤ እና የዚምባብዌ ጦር አባል መግለጫ ሲያነቡ የዚምባብዌ ጦር የሃገሪቱን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ከተቆጣጠረ በኋላ በሰጠው መግለጫ ''ይህ መፈንቅለ መንግሥት አይደለም። የጦሩ ተልዕኮም ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ማዋል እንጂ ሙጋቤን አይደለም'' ብሎ ነበር። ጦሩ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያን ከተቆጣጠረ በኋላ ጣቢያው የትግል ሙዚቃዎችን እያጫወተ ይገኛል። በሃራሬ የምትገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ ግን ''የጦሩ እንቅስቃሴ መፈንቅለ መንግሥት ነው የሚመስለው'' ትላለች። • ጦሩ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያን ከተቆጣጠረ በኋላ ''መፈንቅለ መንግሥት አይደለም'' ብሏል በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር የነበሩት ሳማንታ ፓወር ''ግሬስ ሙጋቤ የሚፈጽሙት ተግባር ነው ጦሩ ይህን አይነት እርምጃ ለመውሰድ እንዲገደድ ያደረገው'' ሲሉ ተናግረዋል። በከፍተኛ ደረጃ የታጠቁ የሃገሪቱ የጦር ኃይል አባላት በሃራሬ ጎዳናዎች ላይ ዛሬ ጠዋት በብዛት ታይተዋል። ጦሩ የሃራሬ ጎዳናዎችን የትራፊክ እንቅስቃሴ ሲመራ የሚያሳዩ ፎቶዎችም ታይተዋል። ኒውስ 24 የተሰኘ የደቡብ አፍሪካ የቴሌቪዥን ጣቢያ ሮበርት ሙጋቤ ሥልጣን ለመልቀቅ ዝግጅት እያደረጉ ነው ሲል ተጨማሪ መረጃ ሳይሰጥ ዘግቧል። ሙጋቤ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩትን ኤመርሰን ምናንጋግዋን ከስልጣን ካባረሩ በኋላ በዙምባብዌ የፖለቲካ ውጥረት ነግሶ ቆይቷል። • ሙጋቤ ታማኝ አይደሉም ያሏቸውን ምክትላቸውን ከስልጣን አነሱ ሙጋቤ ምክትላቸውን ታማኝ አይደሉም በማለት ከሥልጣን ካባረሩ በኋላ የሮበርት ሙጋቤ ባለቤት የሆኑት ግሬስ ሙጋቤ ባለቤታቸውን በመተካት ቀጣይ የዚምባብዌ መሪ ይሆናሉ ተብሎ ነበር። ግሬስ ሙጋቤ እና ኤመርሰን ምናንጋግዋ የቀድሞው የደህንነት ሹም የነበሩት ምናንጋግዋ ፕሬዝዳንት ሙጋቤን የመተካት ተስፋ የተጣለባቸው መሪ ነበሩ። ኤመርሰን ምናንጋግዋ ከሥልጣን ከተባረሩ በኋላ ለሕይወቴ ሰግቻለው ብለው ከሃገር ሸሽተው ወጥተው ነበር። ዛሬ እየወጡ ያሉ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ከሆን ኤመርሰን ምናንጋግዋ ወደ ሃገር ተመልሰዋል።
news-41041313
https://www.bbc.com/amharic/news-41041313
በመዲናችን የሚገኙ ጥንታዊ ቤቶችና የነዋሪዎቻቸው ህልውና አደጋ ላይ ነው
አዲስ አበባ ከተማ ከተመሰረተችበት ጊዜ አንስቶ ባሳለፈቻቸው ዘመናት የበርካታ ታሪካዊ ቅርሶች ባለቤት ሆናለች። ከእነዚህም መካከል በከተማዋ የሚገኙት ጥንታዊና ታሪካዊ ቤቶች ተጠቃሽ ናቸው።
በዚህ በአፈ-ንጉሥ ነሲቡ መስቀሎ ቤት ውስጥ በርካቶች ይኖራሉ በማንኛውም ሰዓት ቤቱ ሊደረመስ እንደሚችል ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተገኙ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ በከተማዋ ውስጥ ከ230 ያላነሱ በቅርስነት የተመዘገቡ ቤቶች ያገኛሉ። እነኚህ ጥንታዊ ቤቶች ባላቸው ታሪክ፣ የሥነ-ህንፃ ውበት፣ ማህበራዊ ጠቀሜታዎችና ካላችው ረጅም እድሜ አኳያ በቅርስነት የተመዘገቡ ናቸው። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የባህልና ቱሪዝም ቢሮም በከተማዋ ውስጥ የሚገኙትን ቅርሶችን የመጠበቅ፣ የመንከባከብና የማሳወቅ ስልጣንና ሃላፊነት ተሰጥቶታል። ነገር ግን ተዘዋውረን እንደተመለከትነው በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ የበርካታ ጥንታዊና ታሪካዊ ቤቶች ህልውና አደጋ ላይ ይገኛል። ከነዚህም መካከል ፈረንሳይ ለጋሲዮን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው የልዑል ራስ ሥዩም መንጋሻ ቤትና ሳንፎርድ ት/ቤት ጀርባ የሚገኘው የአፈ-ንጉሥ ነሲቡ መስቀሎ ቤት ያሉበት ይዞታ እጅግ አሳሳቢ ነው። በአሁኑ ወቅት በሁለቱም ቤቶች ውስጥ በርካታ ሰዎች እየኖሩ ይገኛሉ። ከዚህም በላይ አስቸኳይ ጥገና ካልተደረገላቸው የቤቶቹም ሆነ የነዋሪዎቹ ህልውና አደጋ ላይ ይገኛል። የአምስት ልጆች እናት የሆነችው ወ/ሮ መሰረት ቶላ በአፈ-ንጉሥ ነሲቡ መስቀሎ ቤት ውስጥ ከሰላሳ ዓመትታ በላይ እንደኖረች ትናገራለች። ደርግ ሥልጣን ላይ በነበረበት ወቅት ለወላጆቿ የቤቱ የኋለኛ ክፍል እንደተሰጣቸውና ከዛን ጊዜ ጀምሮ በቤቱ ውስጥ ስትኖር እንደቆየች የምትናገረው ወ/ሮ መሰረት፤ አሁን አሁን ''ዝናብ ሲዘንብ እንቅልፍ የለኝም! ቤቱ በእኔና በልጆቼ ላይ አንድ ቀን ይደረመሳል በሚል ሥጋት ነው የምኖረው'' ትላለች። በመዲናችን የሚገኙ ጥንታዊ ቤቶችና የነዋሪዎቻቸው ህልውና አደጋ ላይ ነው በልዑል ራስ ሥዩም መንጋሻ ቤት የሚኖሩ ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሆነ፤ ለወረዳቸውና ለአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ተቀያሪ ቤት እንዲሰጣቸው ማመልከታቸውን፤ ይሁን እንጂ እሰካሁን ምንም ነገር እንዳልተፈጸመ ነግረውናል። ነዋሪዎቹ ቤቱ ብዙ ታሪክ እንዳለው ይረዳሉ፤ ቅርሱም ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ይፈልጋሉ። ይሁን እንጂ እዚህ የሚኖሩት ሌላ አማራጭ ስላጡ እንደሆነና አማራጭ ካገኙ ታሪካዊውን ቤት ለመልቀቅ ፍቃደኛ ናቸው። የሥነ-ህንፃ ባለሙያና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ፋሲል ጊዮርጊስ እንደሚሉት ''ጥንታዊ ቤቶቹ የተገነቡት ከእንጨትና ከጭቃ ነው። ከእድሜያቸውና ከአስራራቸው አንጻር ቤቶቹ ብዙ መሸከም አይችሉም። ይሁን እንጂ አሁን በቤቶቹ ውስጥ በርካታ አባዎራዎች እየኖሩ ይገኛሉ። ይህ ማለት ደግሞ በማንኛውም ሰዓት ቤቶቹ ሊደረመሱና ጉዳት ሊያደረሱ ይችላሉ'' በማለት ሥጋታቸውን ይገልፃሉ። ስለዚህ ነዋሪዎቹን ወደ ሌላ ቦታ በማዘዋወር የቤቶቹን ታሪካዊነት መጠበቅ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። ፋሲል ጊዮርጊስ ስለ ጥንታዊ ቤቶች ይናገራሉ በሌላ በኩል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የባህልና ቱሪዝም ቢሮ የቅርስ ቁጥጥርና ኢንቨንተሪ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ደርጄ ሥዩም እንደሚሉት ቢሮው በከተማዋ ለሚገኙ ቅርሶች ጥበቃና ጥገና እንደሚያደርግ፤ ይሁን እንጂ ከብዛታቸው የተነሳ ለሁሉም በአንድ ጊዜ ጥበቃና እንክብካቤ ማድረግ አለመቻሉን ይናገራሉ። አቶ ደረጄ እንደሚሉት ቢሮው ከፍተኛ ጉዳት ላይ የሚገኙ ቤቶችን ለመጠገን የዲዛይን ሥራው እየተጠናቀቀ መሆኑን ተናግረዋል። ቤቶቹን ለማደስ ሥራ ከመጀመሩ በፊት ግን የማጣራትና ለነዋሪዎቹ ተለዋጭ ቤት በማስፈለጉ ረጅም ጊዜ መጠየቁን ገልፀዋል።
news-52393655
https://www.bbc.com/amharic/news-52393655
ኢትዮጵያን የቢጫ ወባ ወረርሽኝ እንደሚያሰጋት የዓለም ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ
በኢትዮጵያ የቢጫ ወባ ወረርሽኝ ሊከሰት እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ።
ድርጅቱ እንዳለው በመጋቢት ወር በበሽታው ተይዘዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች ቁጥር ሦስት እንደነበረ አመልክቶ ባለንበት የሚያዝያ ወር ግን የተጠርጣሪዎችቹ አሃዙ ወደ 85 ከፍ ማለቱን ገልጿል። በሽታው አለባቸው ተብለው ከተጠረጠሩት ሰዎች መካከልም ስምንቱ በምርመራ በሽታው እንደተገኘባቸው ተረጋግጧል። የቢጫ ወባ ክትባት ተመልሶ እንዲጀመር መደረጉን ያመለከተው የዓለም ጤና ድርጅት፤ ከሚኖሩበት አካባቢ እርቀው የመሄድ የጉዞ ታሪክ በሌላቸው ሰዎች ላይ መታየቱ እንዳሳሰበው አመልክቷል። "በአገር ደረጃ ያለው የበሽታው ስጋት በከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የተደረሰበት" መሆኑን ድርጅቱ ጠቅሶ፤ በተለይ በደቡብ ክልል ውስጥ በሚገኘው የጉራጌ ዞን ገጠራማ አካባቢዎች ውስጥ የቢጫ ወባ በሽታው የመስፋፋት መጠን ፈጣን መሆኑን ተገልጿል። አክሎም "በሕዝብ ውስጥ በሽታውን ለመከላከል የሚያስችል ዕድል ባልተፈጠረበት ሁኔታ፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው በበሽታው የተጠረጠሩ ሰዎች መገኘታቸው በጣም አሳሳቢ ነው" ሲል ድርጅቱ ስጋቱን ገልጿል። በኢትዮጵያ ለቢጫ ወባ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን በተለይ ትኩረት በማድረግ የበሽታው መከላከያ ክትባት ለሰዎች ሲሰጥ ቆይቷል። በዓለም ዙሪያ የኮሮናቫይረስ ዋነኛ የጤና ችግር በሆነበትና ትኩረት ሁሉ ወደዚህ ወረርሽኝ በዞረበት በዚህ ጊዜ ተጨማሪ በሽታዎች የሚከሰቱ ከሆነ የሚያስከትሉት ጉዳት የከፋ እንደሚሆን ባለሙያዎች ይናገራሉ።
56520047
https://www.bbc.com/amharic/56520047
ሰሜን ኮሪያ ሁለት የባሊስቲክ ሚሳኤሎችን ወደ ጃፓን ባሕር አስወነጨፈች
ሰሜን ኮሪያ ጆ ባይደን የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ከሆኑ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት የባሊስቲክ ሚሳኤሎችን በጃፓን ባህር ላይ እንደተኮሰች አሜሪካ እና ጃፓን ገለጹ።
በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ መሠረት ፒዮንግያንግ አስጊ መሳሪያዎች ተደርገው የሚቆተሩትን የባሊስቲክ ሚሳኤሎችን ከመሞከር ታግዳለች። ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ ሙከራውን አውግዘዋል። የአሁኑ ሙከራ ሰሜን ኮሪያ ባሊስቲከው ያልሆኑ ሁለት ሚሳኤሎችን መተኮሷ ከተዘገበ ከጥቂት ቀናት በኋላ ነው። ጃፓን በግዛቷ ውስጥ በሚገኝ የውሃ አካል ውስጥ ምንም ስብርባሪ እንዳልተገኘ ገልጻለች። በእስያ-ፓስፊክ አካባቢ የሚገኙ ወታደራዊ ኃይሎችን በበላይነት የሚቆጣጠረው የአሜሪካ የፓስፊክ እዝ ሙከራው "የሰሜን ኮሪያ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ መርሃ ግብር ለጎረቤቶቿ እና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚያደርሰውን ሥጋት" አጉልቶ ያሳያል ብሏል። ይህን ሙከራ ተከትሎ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በጉዳዩ ላይ እስካሁን ያሉት ነገር የለም። ባይደን ከቀናት በፊት ሰሜን ኮሪያ ያከናወነችውን ባሊስቲክ ያልሆነ ሚሳኤል የማስወንጨፍ ሙከራ አሜሪካ እንደነገር ቀስቃሽ አትቆጥረውም ብለው ነበር። በዕለቱ ሰሜን ኮሪያ ያስወነጨፈቻቸው የአጭር ርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳኤሎች፤ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔዎች ያልታገዱ እንደሆኑ ይቆጠራል። የሀሙስ ሙከራም የተከናወነው ማሌዥያ ሙን ቾል ሚዩንግ ተብሎ የሚጠራ የሰሜን ኮሪያ ዜግነት ያለው ነጋዴን ለአሜሪካ አሳልፈ ከሰጠች ከቀናት በኋላ ነው። ሙን የአሜሪካን የገንዘብ ስርዓት ተጠቅሞ ገንዘብ በሕገ-ወጥ መንገድ በማዘዋወር የቅንጦት መገልገያዎችን ወደ ሰሜን ኮሪያ አስገብቷል የሚል ክስ ቀርቦበታል። ክስተቱ ሰሜን ኮሪያን ያስቆጣ ሲሆን ከማሌዥያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትም እንድታቋርጥ አድርጓል። የጃፓን ባለሥልጣናት ሰሜን ኮሪያ ሁለቱን ሚሳኤሎች ሐሙስ እንዳስወነጨፈች ተናግረዋል። ከጃፓን ብቸኛ የኢኮኖሚ ቀጠና ውጭ ባሉ ውሃዎች ውስጥ ከመድረሳቸው በፊት 420 ኪ.ሜ. በላይ ተጉዘው አርፈዋል። በመርከቦች ወይም በአውሮፕላኖች ላይ የደረሰ ጉዳትም የለም። በተያያዘ ዜና የባይደን አስተዳደር ከሰሜን ኮሪያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማድረግ ያደረገው ሙከራ አለመሳካቱን አስታውቋል። ፕዮንግያንግ ለባይደን ፕሬዝዳንትነት እውቅና ያልሰጠች ሲሆን ሁለቱ አገራት በሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር እና የባሊስቲክ ሚሳኤል መርሃግብሮች ላይ አልተግባቡም።
news-56425429
https://www.bbc.com/amharic/news-56425429
ዝማሬዋ የጠፋባት ወፍ በአውስትራሊያ
አውስትራሊያ ውስጥ በዝማሬዋ ትታወቅ የነበረች ብርቅዬ የወፍ ዝርያ በድንገት ዝማሬዋ ጠፍቶባት የተምታታና ለዛ የሌለው ዜማ እያሰማች ነው።
አሁን በዚህ 'ሬጀንት ሐኒ ኢተር' ዝርያ ውስጥ ከሚገኙ ወፎች ተደምረው በሕይወት የቀሩት 300 ብቻ ናቸው 'ዘ ሬጀንት ሐኒ ኢተር' ተብላ የምትጠራዋ ወፍ በዓለም ለመጥፋት ከተቃረቡ የወፍ ዝርያዎች መካከል አንዷ ናት። ከዘመናት በፊት የእሷ ዝርያ ወፎች በደቡብ ምሥራቅ አውስትራሊያ በብዙ ቁጥር ይኖሩ ነበር። አሁን ግን ከዛሬ ነገ ዝርያቸው ለዘላለሙ ይጠፋል ተብለው ከተሰጋላቸው ወፎች መካከል ሆናለች። አሁን በዚህ 'ሬጀንት ሐኒ ኢተር' ዝርያ ውስጥ ከሚገኙ ወፎች ተደምረው በሕይወት የቀሩት 300 ብቻ ናቸው። "ይህች ወፍ ለጊዜው ከዝርያዎቿ ጋር አብሮ ጊዜ ለማሳለፍ ዕድሉን አላገኘችም ነበር፤ ለዚያ ይሆናል ዝማሬዋን የዘነጋችው" ብለዋል ዶ/ር ሮዝ ክሬተስ። ዶ/ር ሮዝ በአውስትራሊያ ካንቤራ ዩኒቨርስቲ አንድ የወፍ ዝርያዎች የጥናት ቡድን ውስጥ የሚሠሩ ሲሆን ዝማሬ የጠፋባትን ወፍ የዘመዶቿን የዝማሬ ቅኝት እያስተማሯት ይገኛሉ። እነዚህ የወፍ ዝርያዎች በምድር ላይ ጥቂት የቀሩ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን በአንድ አካባቢ አለመገኘታቸው ፈተና ሆኗል። በጉዞ የሚሸፍኑት ቦታ ስፋት የታላቋ ብሪታኒያን ሦስት እጥፍ ይሆናል፤ ከዚህ ሁሉ ሰፊ ቦታ እነዚህን ዝርያዎች መፈለግ ግመልን በመርፌ ቀዳዳ የማሳለፍ ያህል ከባድ ሆኗል። ወፎች ዝማሬ የሚማሩት የሰው ልጆች ቋንቋን በሚማሩበት መንገድ ነው። "ገና ትንሽ ወፍ ሳሉ የወፍ ጎጇቸውን ጥለው ይወጡና ከዝርያዎቻቸው ጋር መዋል ይጀምራሉ። ታላላቆቻቸው ሲዘምሩ ይሰሙና ያንን ይደግማሉ፤ ዝማሬ የሚማሩትም በዚህ መንገድ ነው" ይላሉ ዶ/ር ሮዝ። አሁን ትልቁ ፈተና የሚዘምሩ ወፎች በተመሳሳይ ስፍራ ባለመሆናቸው አንዱ ከሌላኛው ዝማሬ ሰምቶ መቅዳትና መማር አልሆንላቸው ማለቱ ነው። ወፎችን ዝማሬን በክፍል ውስጥ ማስተማር ሳይንቲስቶች አሁን ከወፎች የቀዷቸውን ዝማሬዎች ዜማ ለተቃወሰባቸው ወፎች እያስደመጡ 'መሠረተ ዜማን' እያስተማሩ ይገኛሉ። ዝርያቸው እየተመናመኑ ያሉትን ወፎች በቤተ ሙከራ እያባዙ ወደ ጫካ መልቀቅ ፕሮጀክት በሙከራ ላይ ሲሆን ይህም ምናልባት የወፎቹን ዝርያ ጨርሶውኑ ከመጥፋት ይታደጋል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል። ነገር ግን ወፎቹ ዜማቸው ማራኪ ካልሆነ ሴት ወፎች ከእነሱ ጋር መገናኘት አይፈልጉም። እነ ዶ/ር ሮዝ ወፎቹን መሠረተ ዜማ እያሰለጠኑ የሚገኙትም ይህን ችግር ለመቅረፍ ነው። ከዓለማችን ላይ ሊጠፉ የተቃረቡ 5ቱ እንስሳት የትኛዎቹ ናቸው?
45279887
https://www.bbc.com/amharic/45279887
ታዋቂው ተከታታይ ፊልም ቢግ ባንግ ቲዎሪ ሊጠናቀቅ ነው
አሜሪካዊው ታዋቂ የቲቪ ተከታታይ ፊልም ቢግ ባንግ ቲዎሪ በአውሮፓውያኑ ቀጣይ አመት ይጠናቀቃል። በአሜሪካ ሲት ኮም ታሪክ ረዥም ክፍል ያለው ተብሏል።
የፊልሙ 12ኛና የመጨረሻ ክፍል በመስከረም ወር ተጀምሮ በመጋቢት ወርም ይጠናቀቃል ተብሏል። መቼቱን በካሊፎርኒያ ፓሴዴና ያደረገው ይህ ፊልም በሁለት ዶክተሮችና የፊልም ተዋናይት ለመሆን በምትጥር ገፀ-ባህርያት ላይ የሚያጠነጥን አስቂኝ ፊልም ነው። በአውሮፓውያኑ 2012 ስድስተኛው ክፍል መውጣቱን ተከትሎ 18 ሚሊዮን ተከታታዮችን ማፍራት ችሏል። በያንዳንዷ ክፍልም 18.6 ሚሊዮን ተመልካቾች መኖሩን ያስመዘገበ ሲሆን፤ በአሜሪካም ትልቅ ተመልካችን ማፍራት የቻለ የቲቪ ፊልምም መሆን ችሏል። የፊልሙ አዘጋጆች በጋራ በሰጡት መግለጫ "ለወዳጆቻችን ምስጋናን እናቀርባለን" ብለዋል። ተከታታይ ፊልሙ ለአርባ ስድስት ግራሚዎች የታጨ ሲሆን ሼልደን ኩፐርን ወክሎ የሚጫወተው የፊልሙ መሪ ተዋናይ ጂም ፓርሰን አራት ሽልማቶችንም ተቀብሏል። የሼልደን ገፀ-ባህርይ ታዋቂነትን ከማግኘቱ በተጨማሪ "ህፃኑ ሼልደን" (ያንግ ሼልደን) የሚል ተከታታይ ፊልም እንዲሰራ መነሻ ሆኗል። የፊልሙ ሌሎች ተዋናዮች ጆኒ ጋሌስኪ፣ ሲሞን ሄልበርግ፣ ኩናል ናያርና ኬሊ ኩዎኮ ናቸው። ከሁለት አመታት በፊትም ዋናዎቹ ተዋናዮች በአንድ ክፍል ትወና ብቻ አንድ ሚሊዮን ዶላር ተከፍሏቸዋል። ለተዋናዮቹ ከሚፍለውና ብዙ አመትም ከመታየቱ አንፃር ለማዘጋጀት በጣም ውድ ስለሆነ ነው 13ኛውን ክፍል ማዘጋጀት የተሳናቸው የሚሉ ግምቶችን ያስቀመጡ ሚዲያዎች አሉ። የፊልሙን መቋጨት አስመልክቶ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተለያዩ ስሜቶችን አስተናግዷል።
news-54367501
https://www.bbc.com/amharic/news-54367501
ታኩ ሴኪን፡ ጃፓናዊው ሼፍ የቀረበበትን ወሲባዊ ትንኮሳ ውንጀላ ተከትሎ ራሱን አጠፋ
ዝነኛው ጃፓናዊው ሼፍ ታኩ ሴኪን በፈረንሳይ ሁለት እውቅ ምግብ ቤቶች አሉት።
በምግብ አቅርቦታቸውም ሽልማትን ተቀዳጅተዋል። ምርጥ ምግብ ቤት የሚል ስያሜም አግኝተዋል። 'ደርሶ' የሚል ስያሜ ያለው መግብ ቤቱ ከአራት ዓመታት በፊት ነበር የተከፈተው። 'ዘ ቤስት ኢን ፍራንስ' የተሰኘውን ሽልማት ያገኘውም በዚያው ዓመት ነው። ባለፈው ዓመትም ' ቼቫል ዲኦር' የተባለ የተለያዩ የእስያ አገራት ምግቦች የሚዘጋጁበት ምግብ ቤት የከፈተ ሲሆን፤ ይህም ሽልማትን ተቀዳጅቷል። የ39 ዓመቱ ታኩ፤ ከፈረንሳዩ እውቅ ሼፍ አሌን ዱካሴ ጋር በቶክዮ እንዲሁም በፓሪስ በሚገኘው አቴኔ ፕላዛ አብረው ሰልጥነዋል። ታዲያ አሁን የመሞቱ ዜና ተሰምቷል። ጃፓናዊው ሼፍ የቀረበበትን ወሲባዊ ትንኮሳ ውንጀላ ተከትሎ ሰኞ ዕለት ራሱን ማጥፋቱን ቤተሰቦቹ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። በእርግጥ በታኩ ላይ የቀረበ ይፋዊ ክስም አልነበረም ፤ በፖሊስም ምርመራ እየተደረገበት አልነበረም። እርሱ ግን የቀረበውን ውንጀላ አስተባብሏል። ነገሩ ወዲህ ነው። ታኩ የተወነጀለው ባሳለፍነው የፈረንጆቹ በጋ ወራት፤ በርካታ ሴቶች ላይ ወሲባዊ ትንኮሳ ፈፅሟል የሚል ነው። በኋላ ላይ አንዲት ሴት ስሙን ባልጠቀሰችው እንድ ጃፓናዊ ዝነኛ ሼፍ ወሲባዊ ትንኮሳ ደርሶባት እንደነበር በኢንስታግራም ገጿ ላይ አሰፈረች። ይህንን ተከትሎም በዘርፉ ያሉ ሴቶችም ለዚች ሴት ድጋፋቸውን ማሰማት የጀመሩ ሲሆን፤ 'ሚቱ' የሚል እንቅስቃሴም መጀመሩን የምግብ የዜና ድረ ገፁ- ኢተር ዘግቧል። እንደ ኤኤፍፒ የዜና ወኪል ከሆነ፤ ምግብ ላይ ትኩረት የሚያደርገው 'አታቡላ' የተሰኘው የፈረንሳይ ድረ ገፅ ባሳለፍነው ነሃሴ ወር ላይ በፈረንሳይ ምግብ ቤቶች ኩሽና ስለተፈፀመ ወሲባዊ ጥቃትና ትንኮ ዘለግ ያለ የምርመራ ፅሁፍ አትሞ ነበር። በፅሁፉ ስሙ ያልተገለፀው ዝነኛው ጃፓናዊ ሼፍ ለመድፈር ወንጀሉ ተጠያቂ እንደሚሆን አስፍሯል። ሼፍ ታኩም ይህ ሰው ማን እንደሆነ እንደሚያጣራ ተናግሮ ነበር። በኋላ ላይ ግን ይሄው ድረ ገፅ የተለያዩ ምንጮችን ዋቢ በማድረግ የሼፉን ስም ይዞ ወጥቷል። ሼፍ ታኩ ይህ ውንጀላ ከተመሰረተበት በኋላ ቁጡ እና እረፍት የለሽ እየሆነ መምጣት መጀመሩን ቤተሰቦቹ ተናግረዋል። ይህ ችግር እያደገ ሄዶም ለከፍተኛ የአዕምሮ ጤና ችግር - ድብርት ተዳረገ ይላሉ ቤተሰቦቹ። "በራሱ ክብርና ፅናት ላይ የተፈፀመው ጥቃት ጥልቅ ነበር፤ ለድብርት ችግር ከተዳረገም በኋላም፤ ታኩ ከዚህ ችግር እንዴት ሊወጣ እንደሚችል ግራ ገብቶት ነበር" ብለዋል ቤተሰቦቹ ባወጡት መግለጫ። የሼፉን መሞት ተከትሎ የጥቃቱን ዘገባ ያወጣው ምግብ ላይ ትኩረት የሚያደርገው 'አታቡላ' የተሰኘው የፈረንሳይ ድረ ገፅ ያቀረበውን ሪፖርት ተከላክሏል።
47550358
https://www.bbc.com/amharic/47550358
አቶ ተወልደ አየር መንገዶች ሁሉ ለጊዜው ቦይንግ 737-8 ማክስን እንዳይጠቀሙ ጠየቁ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም አስተማማኝነታችው እስኪረጋገጥ አየር መንገዶች ሁሉ ቦይንግ 737-8 ማክስ አውሮፕላኖችን ለጊዜው መጠቀም እንዲያቆሙ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
አቶ ተወልደ ይህን ያሉት ዛሬ ጠዋት ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው። እሁድ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ቦሌ አለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ ወደ ናይሮቢ ያመራ የነበረው ቦይንግ 737-8 ማክስ አውሮፕላን ከተነሳ ከስድስት ደቂቃዎች በኋላ የተከሰከሰው ቢሾፍቱ አቅራቢያ ኢጄሬ በተባለ ቦታ ነው። • ለ60 ዓመታት የዘለቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድና የቦይንግ ግንኙነት የአደጋው መንስኤ ገና መጣራት ያለበት ቢሆንም አውሮፕላኑን ግን ለጊዜው ከአገልግሎት ውጭ ማድረግ ያስፈልጋል ይላሉ አቶ ተወልደ። በምክንያትነት የሚያስቀምጡት እሁድ ያጋጠመው አደጋ ከአምስት ወራት በፊት በላየን አየር መንገዱ ተመሳሳይ አውሮፕላን ቦይንግ 737-8 ማክስ በኢንዶኔዥያ ጃካርታ ካጋጠመው አደጋ ጋር መመሳሰሉን ነው። ሁለቱም አውሮፕላኖች በተነሱ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ነው የተከሰከሱት። የአሜሪካው የፌደራል አቪየሽን ባለስልጣን ምንም እንኳ በአሜሪካ ሴናተሮችና የሰራተኛ ማህበራት ግፊት ቢኖርም ቦይንግ 737-8 ማክስን አገልግሎት እንዳይሰጥ የማድረግ ፍላጎት እንደሌለው አስታውቋል።
news-52266796
https://www.bbc.com/amharic/news-52266796
ነዳጅ አምራች አገራት በታሪክ ከፍተኛ የተባለለት ስምምነት ላይ ደረሱ
በኮሮናቫይረስ ምክንያት የፍላጎት መቀዛቀዝ የታየበትን የነዳጅ ምርት እንዲያንሰራራ ለማድረግ ሲባል የነዳጅ አምራች አገራት ኅብረት ኦፔክና አጋሮቹ ታሪካዊ የተባለ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
ስምምነቱ በዋናነት የዓለም የነዳጅ ምርትን በ10 እጅ መቀነስ ላይ ያተኮረ ነው። ትናንት እሑድ በቪዲዮ ስብሰባ የተቀመጡት የነዳጅ አምራች አገራት ኅብረትና አጋሮቻቸው የደረሱበት ይህ ስምምነት በታሪካቸው ትልቁ ነዳጅ ምርትን ለመቀነስ ያደረጉት ስምምነት ተብሏል። አገራቱ ስምምነት ላይ ደርሰው የነበረው ቀደም ብሎ ቢሆንም ሜክሲኮ ግን ስምምነቱን ሳትደግፍ ቆይታለች። አሜሪካ ሜክሲኮ እንድትቀንስ የሚጠበቅባትን ያህል የነዳጅ ምርት በሜክሲኮ ፈንታ ለመቀነስ ቃል በመግባቷ ስምምነቱ ሊፈረም ችሏል። • ትራምፕ ጨረቃ ላይ ማዕድን ቁፋሮ እንዲጀመር ለምን ፈለጉ? • ኮሮናቫይረስን ለመቆጣጠር የፈጠራ ሥራዎቹን ያበረከተው ወጣት • የኮሮናቫይረስ ተጽዕኖ በቻይናና በዓለም ምጣኔ ሃብት ላይ ስምምነቱ ተግባራዊ ሲሆን ወደ 10 ሚሊዮን በርሜል የነዳጅ ምርት በየቀኑ ሳይመረት ይቀራል ማለት ነው። ይህ ስምምነት ታሪካዊ የሚያስብለው ከፍተኛ ምርትን ለመቀነስ በመወሰኑ ብቻ ሳይሆን በስምምነቱ የተካተቱ አገራት ብዛት ጭምር ነው። የኦፔክ አገራትና አጋሮቻቸውን ጨምሮ ሌሎች እንደ ኖርዌይ፣ አሜሪካ፣ ብራዚልና ካናዳ ጭምር የሚፈርሙት መሆኑ ነው። ምርት የመቀነስ ስምምነቱ ሊዘገይ የቻለው ሳኡዲ አረቢያና ሩሲያ እልህ ተጋብተው ስለነበረ ነው ተብሏል። በስምምነቱ መሰረት ከግንቦት 1 ጀምሮ አገራቱ ምርታቸውን በ10 እጅ ይቀንሳሉ። ይህም ማለት በቀን 10 ሚሊዮን በርሜል ነው፤ አሜሪካ፣ ካናዳ፣ ኖርዌይና ብራዚል ሌላ 5 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ከዕለታዊ ምርታቸው ይቀንሳሉ። ከሐሌ ጀምሮ ግን ምርት እየጨመሩ ሄደው ምርት ቅነሳው በቀን ከ10 ሚሊዮን በርሜል ወደ 8 ሚሊዮን በርሜል እየወረደ ይመጣል። ከወር በፊት የነዳጅ ዋጋ በ18 ዓመት ታሪክ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ አሽቆልቁሎ ነበር።
news-53924177
https://www.bbc.com/amharic/news-53924177
ኮሮናቫይረስ፡ በሚሊኒየም አዳራሽ የሚገኘው የኮቪድ-19 ጽኑ ህሙማን ክፍል እየሞላ ነው
በአዲስ አበባ በሚሌኒየም አዳራሽ በኮቪድ-19 ለተያዙ የሕክምና አገልግሎት የሚሰጠው ማዕከል የጽኑ ሕሙማን ክፍል አልጋዎች ሙሉ በሙሉ በሕሙማን ሲያዙ፤ ከፊል ጽኑ ሕሙማን ክፍልን የሚያስተናግደው ክፍልም እየሞላ መሆኑን ዳይሬክተሩ ተናገሩ።
ማዕከሉ በኮቪድ-19 የታመሙ እና የሕክምና ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች ሕክምና እንዲያገኙበት በሚል የተደራጀ ነው። በሚሊኒየም አዳራሽ ለይቶ ማቆያ ከሁለት መቶ በላይ ታካሚዎች መኖራቸውን የማዕከሉ ዳይሬክተር ዶ/ር ውለታው ጫኔ ለቢቢሲ ገልፀዋል። በአሁኑ ሰዓት ሕክምና ማዕከሉ በቀን በአማካኝ በጽኑ የታመሙ 20 ሕሙማንን እየተቀበለ እያስተናገደ እንደሚገኝ የገለፁት ዳይሬክተሩ፤ በአሁኑ ሰዓት ከ210 በላይ ታካሚዎች አልጋ ይዘው እያታከሙ እንደሚገኙ አብራርተዋል። ከእነዚህ ታካሚዎች መካከል ወደ 118 የኦክስጅን ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው መሆናቸውን ጨምረው ገልፀዋል። የማዕከሉ የሕክምና ክፍሎች በአራት ደረጃ ተከፍለው መደራጀታቸውን ዳይሬክተሩ ይገልጻሉ። የመጀመሪያው የጽኑ ሕሙማን ክፍል በከፍተኛ ግፊት ኦክስጅን ማግኘት ያለባቸው ታካሚዎች የሚታከሙበት ክፍል፣ ሁለተኛው ክፍል በኦክስጅን ድጋፍ የሚታከሙበት ክፍል፣ ሦስተኛው መጠነኛ የሆነ የኦክስጅን ድጋፍ የሚፈልጉ ታካሚዎች የሚታከሙበት ክፍል፣ የመጨረሻው ተጓዳኝ ችግር ኖሮባቸው በቤታቸው ራሳቸውን መለየት የማይችሉ እና የባለሙያ ክትትል የሚፈልጉ ሕሙማን የሚታከሙበት ክፍል ነው። ሁሉም ክፍሎች አለመሙላታቸውን የተናገሩት ዳይሬክተሩ፤ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማም ሆነ በአገር ደረጃ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን በመግለጽ፤ በጽኑ የሕክምና ክፍል ካሉ አልጋዎች አብዛኛዎቹ በሕሙማን መያዛቸውን ይገልፃሉ። ለዳይሬክተሩ ቃለ መጠይቅ ባደረግንላቸው ዕለት (ነሐሴ 20 ቀን 2012 ዓ. ም.) በከፍተኛ ግፊት የኦክስጅን ድጋፍ የሚፈልጉ ሕሙማን ክፍል አምስት አልጋዎች ብቻ ክፍት መሆናቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። መጠነኛ የኦክስጅን ድጋፍ በሚፈልጉ ታካሚዎች ክፍል ግን ከዚያ በላይ አልጋዎች ክፍት መሆናቸውን ገልፀዋል። በአሁኑ ወቅት አልጋዎች ሙሉ በሙሉ የሞሉ ባይሆንም “ሂደቱ ያስፈራል፤ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የማንጠነቀቅና መከላከሉ ላይ በርትተን የማንሰራ ከሆነ የኦክስጅን ፍላጎት ያላቸው ታማሚዎች አልጋ ሊያጡ ይችላሉ” ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል። አሁን ባለው ሁኔታ የሚቀጥል ከሆነ ማዕከሉ በጽኑ ታምመው የሚመጡ ሰዎችን የመቀበል አቅሙ ፈተና ውስጥ ሊወድቅ እንደሚችል ይናገራሉ። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ማዕከሉ ያሉት የአልጋ ቁጥሮች ብቻ ሳይሆን በጽኑ ታምመው የሚመጡ ሰዎች በቶሎ አልጋ ለቅቀው የሚሄዱ ባለመሆናቸው ጭምር መሆኑን ተናግረዋል። ሕሙማኑ ለማገገም ጊዜ ስለሚወስድባቸው ቢያንስ ለሁለት ሳምንት አልጋው ይዘው ይቆያሉ በማለት በማዕከሉ ያለውን ልምድ የሚያስረዱት ዳይሬክተሩ፤ ስለዚህ የኦክስጅን ድጋፍ የሚፈልጉ ሕሙማንን በዚህ መልክ ለሳምንታት ተቀብሎ መቀጠል እንደማይቻል ይናገራሉ። እንደ ባለሙያ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ከሕክምና ባለሙያዎችና ተቋማት አቅም ውጪ እንዳይወጣ ስጋት አለን ያሉት ኃላፊው፤ የመከላከልና የጥንቃቄ ስራው ላይ ጠንክሮ መስራት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል። ማዕከሉ የመቀበል አቅሙ 670 ሕሙማንን ሲሆን፤ ተጨማሪ ነገሮች ተደራጅተውበት 1000 ድረስ መቀበል እንደሚችል ይናገራሉ። ማዕከሉ በኤሌትሪክ የሚሰሩ መጠነኛ ኦክስጅን የሚፈልጉ ሕሙማን ለመቀበል የሚያስችል ስራ እየሰራ መሆኑን ገልፀው፤ ከፍተኛ የኦክስጅን ድጋፍ የሚፈልጉ ሰዎችን ለመቀበል ግን የሚያስችል ስራ ለመስራት ከፍተኛ ኢንቨስትመንት እንደሚጠይቅ ያስረዳሉ። እንደ ጤና ሚኒስቴር ገለጻ፤ ከ42 ሺህ በላይ ሰዎች በኮቪድ-19 የተያዙ ሲሆን፤ ከዚህ መካከልም ከፍተኛው ቁጥር የሚገኘው በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ነው።
news-55495519
https://www.bbc.com/amharic/news-55495519
ሶሪያ ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ 28 ሰዎች ተገደሉ
በምሥራቃዊ ሶሪያ በአውቶብሶች ላይ በተፈጸመ ድንገተኛ ጥቃት ቢያንስ 28 ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረና ሁሉም ወታደሮች ሊሆኑ እንደሚችሉ ተገለጸ።
የሶሪያ ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ እንደገለጸው አውቶብሶቹ ዴር አል ዘር ተብሎ በሚታወቀው ግዛት ረቡዕ እለት ነው ኢላማ የተደረጉት። በጥቃቱም በርካታ ዜጎች ተገድለዋል ብሏል ጣቢያው። ነገር ግን አንዳንድ ምንጮችና ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ አውቶብሱ ውስጥ ወታደሮች እንደነበሩ እና የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ከፍ ሊል እንደሚችል አስታውቀዋል። ከጥቃቱ በኋላ ወዲያው ኃላፊነቱን የወሰደ ቡድን አልነበረም። መቀመጫውን ዩናይትድ ኪንግደም ያደረገው የሶሪያ ሰብአዊ መብቶች ተቆጣጣሪ ድርጅት ጥቃቱን የፈጸመው ኢስላሚክ ስቴት (አይኤስ) እንደሆነ በመግለጽ የሟቾች ቁጥር ደግሞ 37 ነው ብሏል። ድርጅቱ በቦታው ላይ የነበሩ ምንጮችን በመጥቀስ ''ጥቃቱ በተቀናጀ መልኩ በኢስላሚክ ስቴት አባላት የተካሄደ ነው። መንግስትን የሚደግፉ ታጣቂዎችና ወታደሮችን የጫኑ ሶስት አውቶብሶች ላይ ጥቃት ተፈጽሟል'' ሲል መግለጫ አውጥቷል። ሌሎች ምንጮች ለሮይተርስ የዜና ወኪል ሲናገሩ አውቶብሶቹ የሶሪያ ወታደሮችን ጭነው ነበር። የአይኤስ ተዋጊዎች እና ለሶሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አል አሳድ መንግስት ታማኝ የሆኑ ወታደሮች በጥንታዊቷ ፓልሚራ ከተማ አካባቢ በተደጋጋሚ ይዋጋሉ። በአውሮፓውያኑ 2014 አይኤስ በሚሊየኖች በሚቆጠሩ ዜጎች ላይ ከባድ አስተዳደራዊ መዋቅር ጭኖ የነበረ ሲሆን በአንድ ወቅት 88 ሺ ስኩዌር ኪሎሜትር የሚደርስ ድንበር ያስተዳድር ነበር። ከአምስት ዓመታት ውጊያ በኋላ የአካባቢው ወታደሮች በአሜሪካ በመታገዝ ቀስ በቀስ በአይኤስ ተይዘው የነበሩ አካባቢዎችን ማስለቀቅ ችለዋል። በዚህም ምክንያት አይኤስ የሚያስተዳድረው ሰፊ ግዛት እንደሌለው ታውጆ የነበረ ሲሆን 2019 ላይ ሶሪያ እና ኢራቅ ላይ በዚህ ረገድ ተሸንፏል ተብሎ ነበር። ነገር ግን አሁንም ድረስ የቡድን እንቅስቃሴ ሶሪያን ያምሳታል።
news-53929600
https://www.bbc.com/amharic/news-53929600
አሜሪካ፡ ፖሊሶች ጄኮብ ብሌክ ላይ መተኮሳቸውን በመቃወም ቴኒስ ተጫዋቿ ኦሳካ ራሷን ከውድድር አገለለች
ጃፓናዊቷ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ናዮሚ ኦሳካ ፖሊሶች ጄኮብ ብሌክ ላይ መተኮሳቸውን በመቃወም ከታላቁ የኒው ዮርክ ቴኒስ ውድድር ራሷን አገለለች።
“ጥቁር ሴት እንደመሆኔ እኔ ቴኒስ ስጫወት ከማየት በበለጠ ቅድሚያ የሚሰጣቸው አንገብጋቢ ጉዳዮች እንዳሉ አምናለሁ” ብላለች በትዊተር ገጿ። ምንም መሣሪያ ያልታጠቀው ጥቁር አሜሪካዊው ጄኮብ ላይ ፖሊሶች ከጀርባው ተኩሰውበታል። እሁድ በኪኖሻ ግዛት ከተተኮሰበት በኋላ በመላው ዊስኮንሰን ተቃውሞ ተቀጣጥሏል። በፖርትላንድ፣ ሚኒሶታና ሌሎችም ግዛቶች ተቃውሞው ቀጥሏል። ከወራት በፊት ጆርጅ ፍሎይድ በፖሊስ መገደሉን በመቃወም በመላው አገሪቱ የ ‘ብላክ ላይቭስ ማተር’ [የጥቁሮች ሕይወት ዋጋ አላት] ሰልፎች መካሄዳቸው አይዘነጋም። ደብሊውቲኤ የተባለው የሜዳ ቴኒስ ውድድር አዘጋጆች እስከ አርብ ድረስ ጨዋታው እንደተሰረዘ አስታውቀዋል። “የዘር መድልዎና ኢፍትሐዊነትን የቴኒስ ስፓርት እንደሚቃወም ማሳየት እንፈልጋለን” የሚል መግለጫም አውጥተዋል። ናዮሚ ኦሳካ ከግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ መውጣቷን መግለጿን ተከትሎ ነበር ይህ መግለጫ የወጣው። በጃፓንኛና በእንግሊዘኛ በጻፈችው ትዊት “ቴኒስ ስላልተጫወትኩ ትልቅ ነገር ይፈጠራል ብዬ አልጠብቅም። ነገር ግን ነጭ ተጫዋቾች በሚበዙበት ስፖርት ውስጥ አንዳች ውይይት እንዲጀመር ምክንያት ከሆንኩኝ ወደ ትክክለኛ አቅጣጫ እየተራመድን ነው” ብላለች። ናዮሚ አያይዛም “ጥቁሮች በፖሊሶች እየተገደሉ መሆኑን ሳይ ያመኛል” ስትል ሀዘኗን ገልጻለች። ጃፓናዊና የሄይቲ ውህድ የሆነችው ናዮሚ፤ ጃፓን ውስጥ የዘረኝነት ሰለባ ናት። ማስታወቂያዎች ላይ የቆዳ ቀለሟን ሲያነጡ፤ ቆዳዋን ነጭ ማድርግ አለባት እያሉ የሚሳለቁ ኮሜዲያኖችም አሉ። በስፓርቱ ዓለም ጄኮብ ብሌክ ላይ መተኮሱን የተቃወሙ ሌሎችም አሉ። የቅርጫት ኳስ ቡድኑ ሚልዋኪ ባክስ ከውድድር መውጣታቸውን ተከትሎ ኤንቢኤ ሦስት ግጥሚያዎች ሰርዟል። ሁለት የቤዝቦል ጨዋታዎችም ተሰርዘዋል። ፖሊሶች ጄኮብ ላይ የተኮሱት ያሳለፍነው እሁድ ሦስት ልጆቹ ወደ ነበሩበት መኪና ሲገባ ነው። አሁን ሆስፒታል ውስጥ እያገገመ ሲሆን፤ ጠበቃው ከዚህ በኋላ መራመድ ከቻለ ተዓምር ነው ብለዋል። ፖሊሶች ጄኮብ ላይ ሰባት ጊዜ መተኮሳቸውን ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ ሁለት ሰዎች ተገድለዋል።
55547000
https://www.bbc.com/amharic/55547000
የጉግል ሠራተኞች የመጀመሪያውን የሠራተኛ ማኅበር መሠረቱ
የጉግል እህት ኩባንያ በሆነው አልፋቤት የሚሠሩ ከ 200 በላይ ሠራተኞች ለአሜሪካ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ውስጥ ባልተለመደ መልኩ የሠራተኛ ማኅበር ለማቋቋም እርምጃዎችን ወስደዋል።
ለማኅበሩ መመስረት ምክንያት የሆነችው ትምኒት ገብሩ ማኅበሩ በድርጅቱ ውስጥ ያሉ አድሎአዊ አሠራሮችን እና የጥላቻ ንግግርን የመሰሉ ጉዳዮች ስለሚፈቱበት መንገድ ለሠራተኞቹ የበለጠ አቅም ይሰጣቸዋል ብለዋል። እርምጃው ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማ እና ሌሎች እርምጃዎችን ተከትሎ የመጣ ነው። ጉግል "ከሁሉም ሠራተኞቻችን ጋር በቀጥታ መስራቱን እንቀጥላለን" ሲል አስታውቋል። የሠራተኞች ኦፕሬሽን ዳይሬክተር ካራ ሲልቨርስተይን በሰጡት መግለጫ "ለሠራተኞቻችን ደጋፊ እና የሚመች የሥራ ቦታ ለመፍጠር ሁሌም ጠንክረን እንሰራለን" ብለዋል። "በእርግጥ ሠራተኞቻችን የምንደግፋቸውን የሠራተኛ መብቶች አስጠብቀዋል። ሁሌም እንደምናደርገው ግን በቀጥታ ከሠራተኞቻችን ጋር መስራታችንን እንቀጥላለን" ሲሉም አክለዋል፡፡ የአልፋቤት ሠራተኞች ሕብረት እውን ሆነው ጉግል አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና የሥነ ምግባር ተመራማሪ የሆነቸው ትምኒት ገብሩን ማባረሩን ተከትሎ ተቃውሞ ከቀረበበት ከሳምንታት በኋላ ነው። የአሜሪካ ብሔራዊ የሠራተኞች ግንኙነት ቦርድም በቅርቡ ድርጅቱ ሠራተኞች ማኅበር ለማደራጀት በመሞከራቸው ሠራተኞቹን በሕገወጥ መንገድ የማባረር ውሳኔ አስተላልፏል ብሏል። ሠራተኞቹም ከመከላከያ የሥራ ክፍሉ እና ከኩባንያው የወሲብ ትንኮሳ ቅሬታዎች አያያዝ ጋር በተያያዘ የድርጅቱን "ፕሮጀክት ማቨንን" ሥራ በመቃወም እንቅስቃሴ ጀምረዋል። "ይህ ማኅበር ለዓመታት በጉግል ሠራተኞች በተደራጀ ደፋርነት ላይ የተመሠረተ ነው" ሲሉ የፕሮግራሙ ሥራ አስኪያጅ ኒኪ አንሴልሞ ተደምጠዋል። "አርእስተቶች ከጠፉም በኋላም ቢሆን አዲሱ ሕብረታችን እንደ አልፋቤት ሠራተኞች የጋራ እሴቶቻችን መከበራቸውን የሚያረጋግጥ ዘላቂ መዋቅርን ያቀርባል" ብለዋል። ማኅበሩ በሶፍትዌር መሐንዲሶች የተደራጀ ቢሆንም ጊዜያዊ ሠራተኞችን ጨምሮ በኩባንያው የአሜሪካ እና የካናዳ ሥር ላሉ ለሁሉም ተቀጣሪዎች ክፍት ነው ተብሏል። ማኅበሩን የሚቀላቀሉ አባላት ከሚያገኙት ካሳ አንድ በመቶ ያህሉን ያበረክታሉ።
55827241
https://www.bbc.com/amharic/55827241
"በኢትዮጵያ በየዓመቱ ቢያንስ 5 ሺህ ሴቶች በማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ሳቢያ ይሞታሉ"
ኢትዮጵያ ውስጥ በየዓመቱ ቢያንስ 5000 ሴቶች በማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ሳቢያ ሕይወታቸው እንደሚያልፍ በጤና ሚንስትር የእናቶችና የህጻናት ጤና እንዲሁም የሥርአተ ምግብ ዳይሬክቶሬት ዳይዴክተር ዶ/ር መሠረት ዘላለም ገለጹ።
በማህጸን በር ጫፍ ካንሰር የሚያዙ ሴቶች ቁጥርን በተመለከተ የተሟላ መረጃ ባይኖርም፤ በየዓመቱ እስከ 7ሺህ የሚደርሱ ሴቶች በበሽታው እንደሚያዙ ተናግረዋል። በሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ አማካይነት የሚከሰተውን የማህጸን በር ጫር ካንሰር ለመከላከል ከጥር 17 እስከ 23 ቀን 2013 ዓ. ም. አገር አቀፍ የክትባት ዘመቻ እየተካሄደ ነው። ዶ/ር መሠረት እንዳሉት፤ ዘንድሮ ለሦስተኛ ጊዜ እየተካሄደ ባለው የክትባት ዘመቻ 14 ዓመት የሞላቸው ሴቶች እንዲከተቡ እየተደረገ ነው። ከጡት ካንሰር ቀጥሎ ሁለተኛው አስጊ የሆነውን የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር በክትባት መከላከል ይቻላል። "የግብረ ስጋ ግንኙነት ከመጀመራቸው በፊት ክትባቱን መውሰድ ስላለባቸው 14 ዓመት ለሞላቸው ሴቶች ክተባቱን እየሰጠን ነው። ክትባት ቅድመ መከላከል ይሰጣል" ሲሉ አስረድተዋል። የሚሰጠው ሁለት ጠብታ ክትባት ሲሆን የመጀመሪያው ከተሰጠ ከስድስት ወር በኋላ ሁለተኛው ይሰጣል። "ሴቶች ይህንን ክትባት ሁለት ጠብታ ከወሰዱ በኋላ በድጋሚ መውሰድ አያስፈልግም። ነገር ግን ኤችአይቪ ላለባቸው ክትባቱ በድጋሚ ሊሰጥ ይችላል" ይላሉ ዶ/ር መሠረት። ከዚህ በፊት በነበሩት ሦስት ዓመታት ከትምህርት ሚንስትር ጋር በመሆን 14 ዓመት ለሞላቸው ሴቶች ክትባቱ መሰጠቱን ይናገራሉ። "በየዓመቱ 1. 2 ሚሊዮን ልጃገረዶች እንደርሳለን ብለን እናስባለን" የሚሉት ዶ/ር መሠረት ዘንድሮም በየትምህርት ቤቱና በጤና ጣቢዎች አማካይነት ቅስቀሳ ማድረጋቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። አምና የመጀመሪያው የክትባት ጠብታ ከተሰጠ በኋላ በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ሁለተኛውን ዙር ማዳረስ ባለመቻሉ፤ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ክትባት ከሚወስዱ ጋር አንድ ላይ እንደሚሰጥ ገልጸዋል። ዘንድሮ የመጀመሪያውን የክትባት ጠብታ የሚወስዱ ታዳጊ ሴቶች ሐምሌ ላይ ወይም በቀጣዩ ዓመት ጥቅምት አካባቢ ሁለተኛውን ጠብታ ይወስዳሉ። ትግራይ ክልል ውስጥ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ክትባቱን መስጠት እንደማይቻል፤ የገለጹት ዶ/ር መሠረት ክትባቱን ማዳረስ ላልተቻለባቸው አካባቢዎች ቀጣይ እቅድ እንደሚወጣ ተናግረዋል። በትምህርት ሚኒስትር በኩል ትምህርት ቤት የገቡ ታዳጊ ሴቶችን እንደሚያገኙና በተለያየ ምክንያት ትምህርት ላይ ያልሆኑትን ደግሞ በጤና ተቋሞች እንዲሁም ቤት ለቤት በመዘዋወርም ክትባቱን እንደሚሰጡ አስረድተዋል። ዶ/ር መሠረት "የማህጸን በር ጫፍ ካንሰርን በተመለከተ ሴቶች ክትባቱን እንዲወስዱ በመገናኛ ብዙሀንም እንቀሰቅሳለን። አንደኛ ዙር ክትባት የወሰዱ ሁለተኛውንም ዙር እንዲወስዱም ቅስቀሳ እናደርጋለን" ብለዋል። በኢትዮጵይ ላለፉት በርካታ ዓመታት ኩፍኝን ጨምሮ የተለያዩ በሽታዎችን ለመከላከል አገር አቀፍ የክትባት ዘመቻዎች ተካሂደዋል።
news-55068596
https://www.bbc.com/amharic/news-55068596
ትግራይ፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ ዓለም አቀፉ ማህብረሰብ በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገባ አሳሰቡ
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ለህወሓት መሪዎችና ኃይሎች የሰጡት ጊዜ ገደብ ሊጠናቀቅ በተቃረበበት በአሁኑ ጊዜ ዓለም አቀፉ ማኅብረሰብ በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገባ አሳሰቡ።
ጠቅላይ ሚንስትሩ ዛሬ ባወጡት መግለጫ "የወዳጆቻችን ስጋት እና ምክረ ሃሳብ ከግምት እያስገባን፤ በውሳጣዊ ጉዳዮች ላይ ጣልቃ ለመግባት የሚደረግን ጥረትን አንቀበልም። ስለዚህም ዓለም አቀፉ ማኅብረሰብ ተቀባይነት ከሌላው እና ሕጋዊ ካልሆነ ጣልቃ ገብነት እንዲቆጠብ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ጣልቃ-አለመግባት መሠረታዊ ምርሆዎችን እንዲያከብር በአክብሮት እናሳስባለን" ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህን ያሉት የአገር መከላከያ ሠራዊት ወደ መቀለ መቃረቡን ተከትሎ በሰው እና ንብረት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የህወሓት አመራሮች እና ተዋጊ ኃይሎች እጃቸውን እንዲሰጡ የሰጡት የ72 ሰዓታት ሊገባደድ በተቀረበበት ወቅት ነው። ጠቅላይ ሚንስትሩ የሰጡት ቀነ ገደብ ሲጠናቀቅ በሚኖረው ወታደራዊ ዘመቻ በርካቶች ስጋት ገብቶናል እያሉ ነው። የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች በተቀመጠው ቀነ ገደብ እጃቸውን እንዲሰጡ የቀረበላቸውን ጥሪ እንደማይቀበሉት መግለጻቸው ይታወሳል። የህወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ " ክልላችንን እራሳችን ለማስተዳደር መስዋትነት እንከፍላለን" ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በትግራይ በኩል ላሉ ኃይሎችና ለህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ያስቀመቱት የጊዜ ገደብ ዛሬ ረቡዕ አመሻሽ ላይ የሚያበቃ ይሆናል። ይህ ተከትሎ ነው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የመጨረሻ ይሆናል ባለው ዘመቻ በመቀለ ሊከሰት የሚችለው ሁኔታ ከወዲሁ አሳስቦኛል ያለው። ድርጅቱ የጦር ወንጀል ሊፈጸም ይችላል የሚል ስጋት እንዳለውም ከወዲሁ አስታውቋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ግን በመግለጫቸው "ሕግ በማስከበሩ ሥራ" ንሑሃን ዜጎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ጥንቃቄ እንደሚደረግ ጠቅሰዋል። ከዚህ ቀደም የተለያዩ አገራት መንግሥታት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት የፌደራል መንግሥቱ እና የህወሓት ኃሎች ግጭቱን አብርደው ልዩነቶቻቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈቱ ሲጠይቁ ቆይተዋል። ከዚህ በተጨማሪም የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ሊወያይ እንደሚችል የሚጠቁሙ ሪፖርቶች እየወጡ ይገኛሉ። የጠቅላይ ሚንስትሩ ከፍተኛ አማካሪ ማሞ ምህረቱ ግን ለቢቢሲ ሲናገሩ፤ "ከወንጀለኞች ጋር አንመካከረም . . . ለፍትሕ እናቀርባቸዋለን። በጠረጴዛ ዙሪያ ከእነርሱ ጋር የሚደረግ ድርድር የለም" ብለው ነበር። ጠቅላይ ሚንስትሩም በመግለጫቸው "የዓለም አቀፍ የሕግ ሥርዓት መሠረት በሉዓላዊ አገር ውስጣዊ ጉዳይ ላይ ጣልቃ አለመግባት" መሆኑን አስታውሰው፤ ይህም በተባበሩት መንግሥታት መቋቋሚያ ቻርተር ላይ መስፈሩን ጠቅሰዋል። በዚህም መሠረት ባለፉት ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ግንባታ ላይ እክል ሆኖ ቆይቷል ባሉት ቡድን እና በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት በሰነዘረው ኃይል ላይ የሚወሰደውን እርምጃ፤ "ሕግን የማስከበር እና ጥፋተኞችን ወደ ሕግ የማቅብ ነው" ብለዋል። "ኢትዮጵያ በግዛቷ ውስጥ ሕግን የማስከበር ሙሉ መብት አላት - እያደረግን ያለውም ይህው ነው" ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሩ በመግለጫቸው። በፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልልን በሚመራው ህወሓት መካከል ለወራት የቆየው አለመግባባትና መካሰስ ባለፈው ዓመት ማብቂያ ላይ በትግራይ ክልል በተናጠል የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ መባባሱ ይታወሳል። በጥቅምት ወር ማብቂያ ላይ በትግራይ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ ላይ በክልሉ ኃይሎች ጥቃት መፈጸሙን በመግለጽ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ማዘዛቸውን ተከትሎ ፍጥጫው ወደ ግጭት ማምራቱ ይታወሳል። ባለፉት ሳምንታት በተካሄዱት ወታደራዊ ዘመቻዎች የመንግሥት ኃይሎች የተለያዩ ከተሞችን መያዛቸው የተነገረ ሲሆን በክልሉ ዋና ከተማ መቀለ አቅራቢያ መድረሳቸውም ተገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ መቀለ የአገሪቱ ሠራዊት ከመንቀሳቀሱ በፊት ሊደርስ ይችላል የተባለ ጉዳትን ለማስቀረት የትግራይ ክልል ኃይሎችን የህወሓት አመራሮች እጃቸውን እንዲሰጡ ዛሬ ረቡዕ ምሽት የሚያበቃ የ72 ሰዓታት የጊዜ ገደብ አስቀምጠዋል።
news-54415190
https://www.bbc.com/amharic/news-54415190
ሩሲያና ቻይና በአሜሪካ ምርጫ ማን እንዲያሸንፍ ነው የሚፈልጉት?
እውን ክሬምሊን "ዳግም አሜሪካን ታላቅ ማድረግ" የሚለው የትራምፕ ሕልም ነው የሚስማማት? ለዚህም ተግታ ትሰራለች?
እውን ቻይና ለባይደን ያላሰለሰ ድጋፍ እየሰጠች ነው? ትራምፕ አንገት ላይ ገመድ እያስገባች ነው? በመጪው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ ሦስት አገሮች ስለአሜሪካ ከአሜሪካኖች በላይ ሊጨነቁ ይችላሉ። ቻይና፣ ሩሲያና ኢራን። እነዚህ አገሮች የሚፈልጉት ሰው እንዲመረጥ በይፋም በህቡዕም፣ በቀጥታም በእጅ አዙርም የሚችሉትን ሀሉ ከማድረግ አይቆጠቡም። ምክንያቱም በአሜሪካ ወደ ዋይት ሐውስ የሚዘልቀው ሰው ጎሮሯቸውን ሊከፍተው ወይም ሊዘጋው ስለሚችል ነው ወራት ብቻ በቀሩት የአሜሪካ ምርጫ የትኛው አገር ማን እንዲመረጥ ይሻል? ለምን? የሚለውን በአጭሩ እንቃኝ። ለጊዜው ኢራንን እናቆያት። ሩሲያ ሩሲያ በባለፈው የ2016ቱ የአሜሪካ ምርጫ ዶልታለች፣ ፈትፍታለች የሚለው የአደባባይ ምስጢር ነው። ትራምፕና ወዳጆቻቸው ቢክዱትም። ፍርድ ቤት በቂ መረጃ አላገኘሁም ቢልም። የአሜሪካ ደኅንነት መሥሪያ ቤት እንደሚያምነው ሩሲያ ዶናልድ ትራምፕን የዛሬ 4 ዓመት ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት እጃቸውን ይዛ አስገብታቸዋለች። የትራምፕ ሰዎችና የሩስያ ሰዎች አብረው ሻይ ቡና ሳይሉ አይቀርም። የሳይበር ጥቃት በማድረግም ሒላሪን አሳጥተዋታል። ዲሞክራቶችን አሽመድምደዋል። የአገሬውን መራጭ ወደ ትራምፕ እንዲያጋድል በበይነ መረብ ጠልፈው ጥለውታል። አባብለውታል። ሩሲያ ይህን ለማድረግ በቂ አቅም ፈጥራለች። ባለፈው ወር ሪፐብሊካኖች የመሩት የሴኔት ጉባኤ ሩሲያ ትራምፕ እንዲመረጡ ስለመፈለጓ ተጨማሪ መረጃን ሰጥቶ ነበር። ሆኖም ይህ ወንጀል ሆኖ ትራምፕን በሕግ የመጠየቁን ነገር አልገፋበትም። በ2020 ሒላሪ በባይደን ተተክተዋል። ሩሲያም ሒላሪን እንዳበሻቀጠች ባይደንን ነክሳ ይዛለች። የአሜሪካ የብሔራዊ ደኅንነትና ስለላ ክፍል ኃላፊ ዊሊያም ኢናቪና እንደሚሉት ምክትር ፕሬዝዳንት ባይደንን ለማደናቀፍ ሩሲያ ሁሉን አቀፍ ዘመቻ ከፍታለች። በሰሞኑ መደማመጥ በራቀውና የሰፈር ጎረቤታሞች ብሽሽቅ ይመስል በነበረው የቀጥታ የቴሌቪዥን ክርክር ባይደን ዶናልድ ትራምፕን "የፑቲን አሻንጉሊት" ሲሉ የገለጽዋቸው ወደው አይደለም። ትራምፕ ለፑቲን በይፋም በጓዳም አድናቆት አላቸው። ምናልባትም ከፖለቲከኛ እንደ ፑቲን የሚያስቀናቸው ሰው የለ ይሆናል። የኤፍቢአይ ዳይሬክተር ክሮስቶፎር ሬይ እንደሚያምኑት ሩሲያ መቼም ቢሆን በአሜሪካ ምርጫ ውስጥ መፈትፈቷን ትታ አታውቅም። ከሁለት ዓመት በፊት በነበረው የሕዝብ ተወካዮች ምርጫ ሳይቀር ሩሲያ እጇን ማስገባቷን በመጥቀስ ክርስቶፎር ሬይ ክስተቱን "ለ2020 ተውኔት ቃለ ተውኔት ልምምድ ላይ ያለች ትመስል ነበር" ብለዋል። ሩሲያ በበኩሏ እኔ በውጭ አገር ምርጫ ምን ጥልቅ አደረገኝ ስትል ድርጊቱን እንደካደች ነው። በዚህ የፈረንጆች ዓመት መጀመርያ የክሬምሊን ቃለ አቀባይ አሜሪካኖች የሚያቀርቡትን ክስ "ደንብረው የሚዘላብዱት ነገር ነው" ሲሉ ተሳልቀውበታል። ሩሲያ ዶናልድ ትራምፕ ለ2ኛ ዙር ዋይት ሐውስ ቢቆዩላት ምርጫዋ ሲሆን ከዚህ በላይ የምትፈልገው ግን በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ ትርምስን መፍጠር ነው ይላሉ የደኅንነት ጉዳይ አጥኚዎች። ለምሳሌ የአውሮፓ ኅብረት አንድ ሰነድ እንደሚያስረዳው ከሆነ ሩሲያ ከአብዛኛዎቹ ኮሮናቫይረስን ከሚመለከቱ ሐሳዊ ዜናዎች ጀርባ ያለች አገር ናት። ይህን የምታደርገውም ትርምሱ ፖለቲካዊ ትርፍ ስለሚያስገኝላት ነው። ጆ ባይደን ምን አሉ? ባይደን ሩሲያን ጠንከር ባለ ቃል አስጠንቅቀዋል። ሩሲያ በሉአላዊት ልዕለ ኃያል አሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ እጇን አስገብታ መፈትፈቷን በቶሎ ካልገታች የምትከፍለው ዋጋ ይኖራል ብለዋል። የፑቲን አሻንጉሊት የሚሏቸው ዶናልድ ትራምፕም ከጠላት አገር ጋር መሞዳሞዳቸውን እንዲተዉ አሳስበዋል። ባይደን በሩሲያ ላይ ያላቸው አቋም ይህን ሲመልስል ዶናልድ ትራምፕ ግን ራሺያ በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ እጇ አለበት የሚለውን ነገር እንዳጣጣሉት ነው የቆዩት። ትራምፕ በዚህ ረገድ የራሳቸው የደኅንነት አለቆች ከሚያቀርቡት ሪፖርት ይጣረሳሉ። እንኳን ከባለሥልጣናት ጋር ከራሳቸው ንግግርም ጋር ለሚቃረኑት ትራምፕ ይህ እምብዛምም አስገራሚ ነገር ላይሆን ይችላል። ቻይና ማን ቢመረጥ ምኞቷ ነው? አሁን በአሜሪካ የሚወጡ የደኅንነት ሰነዶች እንዲሚደመድሙት ከሆነ አሁን ለአሜሪካ ምርጫ ስጋትና ውጋት የምትሆነው ከሩሲያ ይልቅ ቻይና ናት። ጠቅላይ ዐቃቢ ሕግ ዊሊያም ባር የቻይና ከሩሲያ በላይ ስጋት መሆን ምንም የሚያጠራጥር አይደለም፤ በሰነዶች የተደገፈ ነው ይላሉ። በምክር ቤቱ የደኅንነት ጉዳዮች ኮሚቴ ሊቀመንበር ዲሞክራቱ አዳም ስኪፍ አቃቢ ሕግ ዊሊያም ባርን ቀጣፊ ይሏቸዋል። ሚስተር ኢቫኒና እንደሚሉ የአሜሪካ ደኅንነት መሥሪያ ቤት "ቻይና ዶናልድ ትራምፕ ዳግም እንዲመረጡ አትፈልግም" ምክንያቱ ደግሞ ትራምፕ የሚጨበጡ ሰው አለመሆናቸው ነው። ይህንንም ለማሳካት ቻይና በይነ መረብን ተጠቅማ በአሜሪካ ምርጫ እጇን ማስገባት ከፍተኛ ፍላጎት አላት። ቻይና በበኩሏ በሌሎች አገሮች ጉዳይ ገብቶ ለወሰን ፍላጎት የለኝም ብላለች። ዶናልድ ትራምፕ የቻይና እሳቸው እንዲመረጡ አለመፈለግ የተስማማቸው ይመስላል። ለምሳሌ ብሪትባርት በተባለ ድረገጽ የወጣውን አንድ ዜና ትራምፕ በትዊተር ሰሌዳቸው አጋርተዋል። ዜናው የሚያትተው ቻይና ባይደን እንዲመረጡ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ነው። የሚገርመው ግን ይህ ድረ ገጽ ጭልጥ ያለ የትራምፕ ደጋፊ መሆኑ ነው። "ታዲያሳ! ቻይናዎች ባይደንን እንደሚፈልጉ ምን ጥርጥር አለው። ቢሊዮን ዶላር ወስጄባቸዋለኋ! ከቻይና ወስጄ ለአሜሪካ ገበሬዎች ሰጥቼዋለኋ! ከቻይና ወስጄ ለአሜሪካ ግምጃ ቤት ገቢ አድርጊያለኋ። ባይደን ካሸነፈማ ቻይና አሜሪካንን ኪሷ ጠቅልላ ከተተቻት ማለትም አይደል?" ብለዋል ትራምፕ። የአሜሪካና የቻይና ግንኙነት አሁን ላይ መሬት ነክቷል። በሁሉም ነገር ቅራኔ ውስጥ እየገቡ ነው ያሉት። ኮሮናቫይረስን 'የቻይናው ጉንፋን' እያሉ ነው የሚጠሩት ትራምፕ። ሆንግኮንግን እየሰለቀጠቻት ያለቸው ቻይና አሜሪካንን ብቻም ሳይሆን አውሮፓን በሙሉ አስቆጥታለች። ቲክቶክንና ሁዋዌን እየተነኮሱ አስቸግረዋታል። ቻይና ትራምፕን ብትጠላ ከበቂ በላይ ምክንያት አላት።
news-53610864
https://www.bbc.com/amharic/news-53610864
ቤላሩስ፡ ፕሬዚዳንቱን ለማውረድ ተጣምረው እየተፋለሙ ያሉት ሶስቱ ሴቶች
በፕሬዚዳንትነት ለመመረጥ በሁሉም ነገር መስዋዕትነት ለመክፈል የቆረጡ ሦስት ሴቶችን እናስተዋውቃችሁ።
ከግራ ወደ ቀኝ ማሪያ ኮሌስኒኮቫ፣ስቬትላና ቲካኖቭስካያ፣ ቬሮኒካ ትሴፕካሎ ስቬትላና ቲካኖቭስካያ፣ ቬሮኒካ ትሴፕካሎ እና ማሪያ ኮሌስኒኮቫ የተባሉት የቤላሩስ ሴቶች በመጣመር ታሪክ ለመስራት እየጣሩ ነው። በሚቀጥለው ወር በሚደረገው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫም ለማሸነፍ ቆርጠው ተነስተዋል። የእነሱ ዘመቻም ከተሳካ ስቬትላና ቲካኖቭስካያ ቀጣይዋ ፕሬዚዳንት ትሆናለች። ስቬትላና ቲካኖቭስካያ የባለቤቷንም ዘመቻ በማስቀጠልም ስፍራውንም ወስዳለች። ባለቤቷ ሰርጌይ ቲካኖቭስካያ ፖለቲከኛና ፀሐፊ ሲሆን ለእስር ተዳርጎ ነበር፤ ለምርጫም ሆነ በፕሬዚዳንትነት እንዳይወዳደር ተከልክሏል። እሷም ብትሆን ከፕሬዚዳንትነት ምርጫ ዘመቻው እንድትታቀብና ልጆቿን ይዛ ወደሌላ አገር እንድትሄድ የአገሪቱ ባለስልጣናት ቢያስፈራሯትም እሷ ግን ከቁብ የቆጠረችው አትመስልም። በእምቢተኝነቷ በመቀጠልም ለመወዳደር ወስናለች። የስቬትላና ባለቤት ብቻ ሳይሆን የቬሮኒካ ትሴፕካሎ ባለቤትም እንዲሁ በፕሬዚዳንትነት ምርጫ እንዳይሳተፍ እግድ ተጥሎበታል። ማሪያ ኮሎስኒኮቫ ደግሞ በእስር ላይ ያለው ፖለቲከኛና እጩ ተወዳዳሪ ቪክቶር ባባርይኮ ቃለ አቀባይ ናት። ተልዕኳቸው ምንድነው ብትሉ? ነሐሴ 3/2012 ዓ.ም በሚደረገው ምርጫ ማሸነፍና፤ በዚህም ለ26 ዓመታት ያህል በስልጣን ላይ የቆየቱን የፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮን የስልጣን ማብቂያን ማብሰር ነው። 'ሚስቶች፣ እናቶችና የቤት አስተዳዳሪዎች' የሦስቱን ሴቶች ጅማሮ አዲስና አስደናቂ የሚያደርገው ዋናው ነገር በወንዶች በከፍተኛ የበላይነት በተያዘው የቤላሩስ ፖለቲካ ውስጥ ሰብረው ለመግባት የሚያደርጉት ጥረት እንደሆነ የቢቢሲ ሞኒተሪንግ ተንታኝ የሆኑት ያና ልዩሽኔቭስካያ ያስረዳሉ። ለሦስት አስርታት ያህል በስልጣን ላይ የቆዩት ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር በተደጋጋሚም በቤላሩስ የሴቶች ሚና "ሚስትነት፣ እናትነትና የቤተሰብ አስተዳዳሪነት" ብቻ ነው በማለት የበላይነት መልዕክትን ሲያስተላልፉም ተሰምተዋል። በጎርጎሳውያኑ 1994 መንበረ ስልጣኑን የተቆጣጠሩት ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ለስድስተኛ ጊዜም ለመመረጥ አኮብኩበዋል። የቤላሩስ ዜጎች "ሴቶችን ለመምረጥ ዝግጁ አይደሉም"፣ "ሕገ መንግሥቱ ለሴቶች አይደለም" እያሉም እየቀሰቀሱ ነው። ነገር ግን ፕሬዚዳንቱ ለአስርት ዓመታት የመሩትን ሕዝብ የሚያውቁት አይመስልም ምክንያቱም ይህ አስተያየታቸው በበርካቶች ዘንድ ውግዘት እንዲደርስባቸው አድርጓቸዋል። በኋላም ፕሬዚዳንቱ ንግግራቸውን ለማረም በሚመስል መልኩ "ፆተኛ ለመሆንና የሴቶችን ክብር ዝቅ ለማድረግ" ያለመ እንዳልሆነ አስረድተዋል። "ሕገ መንግሥታችን የተፃፈበት መንገድ ለወንድም ቢሆን ሸክሙ ከባድ ነው። እዚህ ቦታ ላይ ሴትን ብናስቀምጣት፤ ከብዷት ትወድቃለች፤ ምስኪን" በማለት ፕሬዚዳንቱ ለማብራራት ሞክረዋል። ለቤላሩስ አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ ይሆን? ስቬትላና ቲካኖቭስካያ፣ ቬሮኒካ ትሴፕካሎ፣ ማሪያ ኮሌስኒኮቫ በጥምረት የሚያደርጓቸው የምረጡኝ ቅስቀሳዎች በቤላሩስ በታሪክ ሰሪነት እንዲመዘገቡ አድርጓቸዋል። ሦስቱ ሴቶች ዘመቻቸውን ሲያካሂዱ የተነሱዋቸው ፎቶዎችም ፕሬዚዳንት አሌክሳንደርን የሚፋለም አዲስ መንፈስ ምልክትም ተደርጎ እየተወሰደ መሆኑንም ተንታኝዋ ያና ይናገራሉ። ምንም እንኳን በጥምረት መምጣታቸው እንደ መጤ ቢያስቆጥራቸውም፤ የሦስቱንም ህይወት በምናጤንበት ወቅት ለዓመታት ያህል በፖለቲካው ውስጥ ከፍተኛ ተሳትፎ የነበራቸውና በተለያዩ ተቋማትም ያገለገሉ ናቸው። "ባለቤቴ ሰርጌይ ቲካኖቭስካያ ሕዝቡን ወደ አንድ ማምጣት ችሎ ነበር እኛም ሕዝባችንን በማስተባበር አንድነትን መፍጠር ዋና አላማችን ነው" በማለት ስቬትላና የመጀመሪያ የምረጡኝ ቅስቀሳ ላይ ተናግራለች። ሰርጌይ ታዋቂ ፀሐፊና ፖለቲከኛ ሲሆን ከፍተኛ ሁከት በማነሳሳት ለእስር ተዳርጓል፤ በፕሬዚዳንትነት እንዳይወዳደርም እገዳ ተጥሎበታል። ስቬትላና ፍትሃዊና ሚዛናዊ ምርጫ ተደርጎ ካሸነፈችም ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች እንደሚፈቱ ቃል የገባች ሲሆን፤ ከዚህም በተጨማሪ የፕሬዚዳንት ስልጣንና የስልጣን ዘመኑን የሚገድብ ሕገ መንግሥታዊ ለውጥ አመጣለሁ ብላለች። የወደፊቱ ተስፋ ቬሮኒካ ትሴፕካሎም በስቬትላና ሃሳብ ትስማማለች። የእሷም ባለቤት ቫለሪ ትሴፕካሎ በአሜሪካ አምባሳደርነት አገልግሏል፤ በአንድ ወቅትም በፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ቀንደኛ ጠላት ተደርጎ ነበር። በቤላሩስ ማዕከላዊ የምርጫ ኮሚሽንም ለፕሬዚንዳንትነት አይመጥኑም ተብለው ከተገለሉ ዘጠኝ እጩዎችም አንዱ ነው። ሚንስክ በተባለችው ከተማም ቬሮኒካ ባደረገችው የምርጫ ቅስቀሳ ላይ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደርን የሕዝቡን ቁጥር በመቀነስ ወንጅላቸዋለች። "ወጣቱ ክፍል አንዳንዴም መላው ቤተሰብ ለተሻለ ህይወት እየተሰደደ ነው። ቤላሩስ ነፃነታቸውን ስለገፈፋቻቸው ነው መሸሽን የመረጡት" ብላለች። "የመናገር ነፃነት፣ የተሻለ ገቢ፣ ከዚህም በላይ ተስፋን ቤላሩሳውያን ቢፈልጉትም የላቸውም። እነዚህን ሁኔታዎች መቀየር እንፈልጋለን" በማለት ቬሮኒካ ትናገራለች። የማሪያ ኮሌስኒኮቫ ልምድ ከእነሱ ትንሽ ለየት ይላል። የፕሬዚዳንትነት እጩ ለነበረው ቪክቶር ባባርያኮ ቃለ አቀባይ ነበረች። በባንኩ ዘርፍ ስመ ጥር ሲሆን የፕሬዚዳንቱም ቀንደኛ ተፎካካሪ ነበር። እጩው ፕሬዚዳንት ገንዘብ በመመዝበርና በማጭበርበር ለእስር የተዳረገ ሲሆን ከውድድሩም እንዲወጣ ተገዷል። ይህንንም ተከትሎ ነው ማሪያ በሴቶች ብቻ የሚመራውን ዘመቻ የተቀላቀለችው። የቪክቶር ከምርጫው መወገድን ተከትሎ የአውሮፓ ሕብረት መልዕክተኞች የምርጫ ኮሚሽኑ ውሳኔ የአገሪቱን የዲሞክራሲ ሂደትን የሚቀለብስና ምርጫውንም ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው በማለት አስጠንቅቀዋል። ሦስቱ ሴቶች ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተውጣጡ ሲሆን ሁሉም ቢሆን ቁልፍ በሚባሉት ፖሊሲዎች፣ ፖለቲካዊ ማሻሻያዎች፣ ፀረ-ሙስናና የንግግር ነፃነትን በተመለከተ ተመሳሳይ አቋም አላቸው። ከባድ ፈተና የቢቢሲ ሞኒተሪንግ ባልደረባ ያና ልዩሽኔቭስካያ እንደሚሉት የሦስቱ ሴቶች ጥምረት ፖለቲካው ላይ የነበረውን ድባብ በመለወጥ በርካቶች እንዲነሳሱ አድርጓል። በአስርት ዓመታት ውስጥ በነበረው የምርጫ ማጭበርበርና ለውጥ አያመጣምም በሚል በርካታው ሕዝብ ተሰላችቶ ነበር። "ይህ የጨለምተኝነት ስሜት የመጣው ዝም ብሎ አይደለም አገሪቱ ስታካሂደው በነበረው ኢ-ዲሞክራሲያዊ የምርጫ ውጤት ከዚህም በተጨማሪ ፕሬዚዳንቱ በተቀናቃኞቻቸው ላይ የሚያደርጉት ጫና ነው" ትላለች ያና። ከዚህም በተጨማሪ ለዋናው ተፎካካሪ ፓርቲም የሴቶቹ አንድ ላይ መምጣት እንደ አደጋም መታየቱን ያና ያስረዳሉ። የምርጫው ውጤት ምንም ይሁን ምን የሦስቱ ሴቶች ጥምረት በቤላሩስ ፖለቲካ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ አንድነትን ማምጣት ችሏል። ፕሬዚዳንት አሌክሳንደርም በበላይነት አሸንፍበታለሁ ብለው እንዳሰቡት ምርጫም እንዳልሆነም እየታየ ነው።
news-45520904
https://www.bbc.com/amharic/news-45520904
በአዲስ አበባ ለሚደረገው ሥነ-ሥርዓት ፖሊስ መዘጋጀቱን አስታወቀ
ፖሊስ በአዲስ አበባና በዙሪያዋ የተከሰተውን ውጥረት ማርገቡንና ነገ በሚካሄደው ሥነ-ሥርዓት ላይም ምንም አይነት የፀጥታ ችግር እንዳይከሰት አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።
ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል እንዳሉት በተለያዩ ቦታዎች ላይ አጋጥመው የነበሩ ፍጥጫዎችንና ውጥረቶችን ፖሊስ አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ ማርገቡንና ጉዳት እንዳይደርስ እየሰሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል። በቡራዩ በኩል ወደ ከተማዋ ለመግባት ጥረት እያደረጉ የነበሩ በርካታ ወጣቶች ወደ ከተማዋ ዘልቀው እንዳይገቡ በፖሊስ በመታገዳቸው ከፍተኛ ውጥረት ተከስቶ ነበር። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል ለቢቢሲ እንደተናገሩት ወጣቶቹ ወደ ከተማው እንዳይገቡ እንዳልተከለከሉ ነግር ግን በተጠቀሰው አካባቢ በወጣቶች መካከል ፍጥጫ በመፈጠሩ ፖሊስ በመሃል ገብቶ ለማረጋጋት ጥረት ሲያደርግ እንደነበር ገልፀዋል። • ጉዳት ለማድረስ የሚሞክሩትን እንደማይታገስ ፖሊስ አስጠነቀቀ • የአዲስ አበባን የአርብ ውሎ የሚያሳዩ የፎቶ ስብስቦች ጨምረውም በፍጥጫው ምክንያት ወደ አዲስ አበባ ሳይገቡ የቆዩ ሰዎች እንዲገቡ አመቺ ሁኔታ እንዲፈጠር ፖሊስ አስፈላጊው ነገር ማድረጉን ተናግረዋል። ውጥረቱ በቀዳሚነት ተከስቶበት በነበረው ዊንጌት አካባቢ የሚገኙ ሱቆችና ሌሎች ንግድ ቤቶች አሁንም ዝግ ሲሆኑ፤ በዊንጌት፣ በጳውሎስና በመድሃኒዓለም አካባቢዎች ጥቂት የሕዝብ ትራንስፖርት መኪኖች ብቻ ናቸው እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት። ነገ ቅዳሜ የኦነግ አመራር አባላትን ለመቀበል በሚደረገው ሥነ-ሥርዓት ወቅትም ችግርና ግጭት ሊከሰት ይችላል የሚል ስጋት በበርካታ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ዘንድ የተፈጠረ ሲሆን ኦፌኮና ሰማያዊ ፓርቲ በጋራ ባወጡት መግለጫ ችግሩ ከቁጥጥር እንዳይወጣ መንግሥት እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ዘይኑ ጀማል ግን ፖሊስ ሥነ-ሥርዓቱ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ሁሉ ዝግጅት ማድረጉን ተናግረዋል። "ችግር ለመፍጠር የሚሞክር ካለ ለመቆጠጠር የሚስችል ተገቢ ዕቅድ አውጥተን ተዘጋጅተናል" ብለዋል። • 'በእኔ በኩል ሒሳቤን ዘግቻለሁ ' አቶ ታምራት ላይኔ • ቄሮ፣ ሴታዊት፣ ፋኖ…የትውልዱ ድምጾች የፊታችን ቅዳሜ ወደ ሃገር ቤት የሚመለሱትን የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮችን ለመቀበል በደጋፊዎቻቸው ከሚደረገው ዝግጅት ጋር በተያያዘ በአንዳንድ የአዲስ አበባ አካባቢዎች ያጋጠመውን ውጥረትና ግጭት ተከትሎ ስጋት ተከስቷል። የቢቢሲ ዘጋቢ ውጥረትና ግጭት አጋጥሞባቸው ወደነበሩ አካባቢዎች ተዟዙሮ ተመልክቷል። ዛሬ ጠዋት ላይ የመረጋጋት ምልክት ሲያሳዩ የነበሩ አካባቢዎች ዛሬ ከሰዓት ላይ እንደገና የግጭት ስጋት እንደሰፈነባቸው ዘጋቢያችን መታዘብ ችሏል። በዚህም ዛሬ ከሰዓት በፒያሳ፣ አዲሱ ገብያ እና ቡራዩ ውጥረት ሰፍኗል። በአካባቢውም የሚታዩ በርካታ ሰዎች ትራንስፖርት በማጣታቸው ምክንያት በእግራቸው ሲጓዙ ዘጋቢያችን ተመልክቷል። ጳውሎስ አካባቢ ባሉ አንዳንድ ሕንፃዎች ላይ የኦነግ ሰንደቅ አላማ ተሰቅሎ የሚታይ ሲሆን፤ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ የያዙ በርካታ ወጣቶችን ዘጋቢያችን በተዘዋወረባቸው ቦታዎች ተመልክቷል። ይህ ቢሆንም ጠዋት ላይ በየትኛውም ቦታ ፍጥጫና ግጭት ሳያጋጥም ቆይቶ እኩለ ቀን ላይ ውጥረቱ በተለያዩ ቦታዎች ላይ አገርሽቷል። ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው ከቡራዩ የመጡ ግለሰብ በነበረው ግጭትና ውጥረት ሳቢያ ወደመኖሪያቸው የሚወስድ ትራንስፖርት አጥተው መቅረታቸውንና ዛሬም ሊያገኙ እንደማይችሉ ስጋት እንደገባቸው ተናግረዋል። ዘጋቢያችን በተዘዋወረባቸው አካባቢዎች በሙሉ በርካታ የፖሊስ አባላት ተሰማርተው ተመልክቷል። ዕሮብ ዕለት ተከስቶ በነበረው ግጭት የአንድ ሰው ህይወት ማለፉንና ሌሎች ላይ ደግሞ አካላዊ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ ማስታወቁ ይታወሳል።
news-53885872
https://www.bbc.com/amharic/news-53885872
ጎንደር፡ ጥንታዊው የጉዛራ ቤተ መንግሥት ጉዳት ደረሰበት
በዘንድሮው ክረምት የሚጥለውን ከፍተኛ ዝናብ ተከትሎ በዓለም ቅርስነት የተመዘገበው የጉዛራ ቤተ መንግሥት ጉዳት ደረሰበት።
በዝናብ አማካኝነት ጉዳት የደረሰው ነሐሴ 4 ከምሽቱ 4 ሰዓት አካባቢ ነው ሲሉ የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አባይ ምላሹ ጌቱ በተለይ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ጉዳት የደረሰበት በ1998 ጥገና የተደረገለት የቤተመንግስቱ መወጣጫ ደረጃ መሆኑን ኃላፊው ጠቁመዋል። ጥገናው ሙሉ ለሙሉ አለመሆኑ እና ደረጃው ሲጠገንም በአፈር እና ኖራ ቅልቅል መሆኑ ለአደጋው መከሰት ምክንያት ነው ብለዋል። ዝናቡ አፈሩን በመጥረጉ መወጣጫ ደረጃው መደርመሱን አቶ አባይ አስታውቀዋል። ከ400 ዓመታት በላይ የቆየው ቅርስ ዝናብ እና ፀሐይ እየተፈራረቀበት አደጋ እንዳንዣበበት በመናገር ኃላፊው ስጋታቸውን ገልጸዋል። በዓለም አቀፉ የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ተቋም ዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት የተመዘገበው የጉዛራ ቤተመንግሥት የደረሰበት አደጋ ከዓለም ቅርስነት መዝገብ እንዳይወጣ ስጋት ይፈጥራል ወይ ተብሎ ጥያቄ የቀረበላቸው ኃላፊው "ሙሉ ለሙሉ አይደለም የፈረሰው። መወጣጫ ደረጃው ብቻ ነው። ስለዚህ ከዓለም ቅረስነት የሚያሰርዘው አይደለም የተደረመሰው። በነበረው ልክ አስተካክሎ መስራትም ይችላል። ደረጃውም ቢሆን ሙሉ ለሙሉ ሳይሆን ግማሹ ነው የፈረሰው። ስለዚህ ለመስራት የሚያዳግት ስላልሆነ የሚያሰርዘው አይደለም" ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል። በዚህ ሃሳብ የሚስማሙት የኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥገና ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አበበው አያሌው (ረዳት ፕሮፌሰር) ቅርሱ በዓለም ቅርስነት የተመዘገበው የጎንደር አብያተ መንግስታትን ጨምሮ ከሌሎች ስምንት ቅርሶች ጋር መሆኑን ጠቁመዋል። አደጋው የደረሰው በቅርቡ መለስተኛ ጥገና የተደረገለት የዋናው መግቢያ መወጣጫ መሆኑንም ጠቁመዋል። በቅርሶቹ ላይ የሚደረጉት ጥገናዎች ሙሉ ጥገና ሳይሆን የተናደ ወይም ያዘመመን የግንብ ክፍል የመደገፍ ዓይነት ሥራ ብቻ እንጂ ተጠቃሎ ሁሉንም የሚያጠቃልል የጥገና ስራ አልተካሄደም ብለዋል። ለዚህ መፍትሔ ያሉት ደግሞ ሙሉ ጥናት በማካሄድ የጥገና ሥራ ማከናወን ነው። "የተወሰነውን ክፍል የመጠገን ሥራ አንሠራም። ጥናት ተካሂዶ ሲጠናቀቅ በቅደም ተከተል መሠረት ለሚቀጥሉት ከ50-70 ዓመታት የማያሳስብ ጥገና እንሠራለን። ያንን ለማድረግ ጥናት የሚያደርጉትን አወዳድረን በዋጋም በልምድም ጥሩ የሆኑትን መርጠናል። ልምድ ያላቸው ናቸው። የጥገና ጥናት ውል አዘጋጅተን በሚቀጥለው ሳምንት እንፈራረማለን። መስከረም ጋማሽ ላይ ጥናት ጀምረው በሦስት ወር ያጠቃልላሉ። ያንን ይዘን ወደ ገንዘብ ሚኒስቴር እንሄዳለን ማለት ነው" ብለዋል። አበባው አያሌው፤ ጉዛራ ቤተመንግስት ላይ ስለደረሰው ጉዳት በተመለከተ "የፈረሰውን ለመሥራት ግን ጥናቱ እስኪያልቅ አንጠብቅም። አንድ ቡድን ወደ ቦታው ይሄዳል። ያለውን የጉዳት መጠንን እና በአፋጣኝ የሚያስፈልገውን አጥንቶ ይመጣል እንጂ ጥናቱ እስኪያልቅ አንተወውም። ከክልሉ ባህልና ቱሪዝምም ጋር እየተነጋገርን ነው" ሲሉ ምላሻቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። የጉዛራ ቤተ መንግሥት ኢትዮጵያን ከ1556-1589 ዓ.ም ድረስ በመሯት በአፄ ሰርፀ ድንግል የታነፀ ነው።
news-55608008
https://www.bbc.com/amharic/news-55608008
ካፒቶል ሒልን ጥሰው የገቡ አመጸኞችን ለመያዝ የኤፍቢአይ አደን
በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ በካፒቶል ሒል ሕንጻ ላይ የትራምፕ ደጋፊዎች የተቃውሞ ግርግር ከፈጠሩ በኋላ ኤፍቢአይ አመጸኞቹን ለፍርድ ለማቅረብ ሕዝቡ እንዲጠቁመው ጠይቋል።
የካፒቶል ሕንጻን የትራምፕ ደጋፊዎች ሲወርሩ ነውጠኞቹ ባለፈው ረቡዕ የትራምፕ ደጋፊዎች በካፒቶል ሒል ሕንጻ ተሰብስበው ጥሰው በመግባት የጆ ባይደንን የምርጫ አሸናፊነት በመቃወም የሕዝብ እንደራሴዎችን ስብሰባ አወከዋል። በዚህም በሕንጻው ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን የአፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ረዳትም ላፕቶፓቸው መሰረቁ ታውቋል። ከአመጸኞቹ መካከል የ60 ዓመቱ ሪቻርድ ባርኔት ወደ ካፒቶል ሒል ሕንጻ ከገቡት ሰዎች መካከል አንዱ ሲሆን አሁን በፖሊስ ተይዞ እስር ላይ ነው። ባርኔትን ለመለየትና ለመያዝ አስቸጋሪ ስላልነበረ ነው በቀላሉ የተያዘው። ሪቻርድ ባርኔት ባርኔት በግርግሩ ውስጥ ወደ ካፒቶል ሒል ገብቶ በአፈ ጉባኤዋ ናንሲ ፔሎሲ ቢሮ ውስጥ እግሩን ጠረጴዛ ላይ ሰቅሎ የተነሳው ፎቶግራፍ ወዲያውኑ ነበር በዓለም ዙሪያ በስፋት ተሰራጭቷል። ግለሰቡ ከሌሎች ጋር በመተባበር የሕዝብን ንብረት በመዝረፍ ክስ ተመስርቶበታል። የምዕራብ ቨርጂኒያ ሕግ አውጭ አባል የሆኑት ዴሪክ ኢቫንስም በተቃውሞው ወቅት በቦታው ተገኝተው ከተቃዋሚዎች ጋር በመሆን የቀረጹትን ቪዲዮ በኦንላየን በማጋራታቸው ክስ ተመስርቶባቸዋል። የፌደራል የሕግ አስፈጻሚ አካላት እንደገለጹት በአሁኑ ወቅት በርካታ ሰዎች ረቡዕ ላይ በነበረው ግርግርና ጥፋት ምክንያት ክስ ተመስርቶባቸዋል። በሚቀጥሉት ቀናት ተጨማሪ በዛ ያሉ እስራቶች ይኖራሉ ተብሎም ይጠበቃል። እስካሁን በተካሄደው ምርመራ የተገኘው ውጤት ተስፋ ሰጪ ቢሆንም የሕዝቡ ጥቆማ አስፈላጊ መሆኑ ተገልጿል። በተጠርጣሪዎቹ ላይም ተቀጣጣይና ሌሎች የጦር መሣሪያዎችን ይዞ አመጽ በማነሳሳት ወንጀል ከከባድ እስከ ቀላል ክስ ይመሰረትባቸዋል ተብሏል። ምናልባትም በእዚሁ ክስ በርካታ ዓመታትን በእስራት እንዲቆዩ የሚያደርግ ቅጣት ሊበየንባቸው እንደሚችል ይጠበቃል። በአሁኑ ጊዜ የኤፍቢአይ መርማሪዎች የተጠርጣሪዎችን ፎቶ ይዘው ሰዎች እንዲጠቁሟቸው እየጠየቁ ነው። ይህንን መነሻ በማድረግም ረቡዕ ዕለት በካፒቶል ሕንጻ የተሳተፉ ሰዎችን ለማደን እየሠሩ ነው። አደኑ ደግሞ በመላው ከተማ [ዋሽንግተን ዲሲ] እና አለፍ ሲልም በመላዋ አሜሪካ ሊሆን ይችላል ተብሏል። እስካሁን ያሉት እውነታዎች ምንድን ናቸው? ያም ሆኖ ግን ከሕዝቡ የሚመጡ ጥቆማዎችን ለመለየት ተጨማሪ ሥራዎች ያስፈልጋሉ። ምናልባት አንዳንድ ጊዜ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ከዜጎች የሚመጡ መረጃዎች ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው ሊያመዝን ይችላል ተብሏል። በ2013 (እአአ) የቦስተን ቦምብ ፍንዳታ ከተከሰተ በኋላ ከቦስተን ማራቶን አቅራቢያ ላይ የተነሳ ሁለት የጉዞ ሻንጣ የያዙ እና የሚያወሩ ሰዎች ምስል በኦንላይን ይዘዋወር ነበር። እናም ሌላው ሰው እነዚህን ሰዎች "ወንጀለኞቹ ናቸው" ይላቸው ነበር። እውነታው ግን እነዚህ ሰዎች ከጥቃቱ ጋር ምንም ግንኙነት አልነበራቸውም። በተመሳሳይም የካፒቶል ሒል ግርግር ተሳታፊዎችንም በትክክል ያልጠቆመ መረጃ ሊሰጥ ይችላል የሚል ስጋት አለ። ለምሳሌ አንዳንድ የትራምፕ ደጋፊዎች አመጹን ከአንቲፋ ወይም ከብላክ ላይቭስ ማተር ጋር ሲያገናኙት ነበር፤ ነገር ግን ይህንን የሚያረጋግጥ መረጃ ግን እስካሁን አልተገኘም። ይህ በእንዲህ እንዳለ በርካታ አሜሪካውያን ይህን አመጽ የቀሰቀሱ ሰዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ይፈልጋሉ። በአሜሪካ ፍትህ ሚንስቴር ውስጥ የወንጀል ዘርፍ ጋር የሚሰሩት የጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የሕግ ፕሮፌሰሩ ስቴፈን ሳልዝበርግ፣ ሕብረተሰቡ የወንጀል ተጠርጣሪዎችን ለመጠቆምና ኤፍቢአይን ለመተባበር ከፍተኛ መነሳሳት እያሳየ መሆኑን ገልጸዋል። "ሰዎች ስለዲሞክራሲ ይጨነቃሉ፣ አጥፊዎች ተገቢውን ቅጣት አግኝተው ማየት ይፈልጋሉ፣ ፍትህ ሰፍኖ ማየት ይሻሉ" ብለዋል።
news-46601692
https://www.bbc.com/amharic/news-46601692
አስር ኢትዮጵያዊያን ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲጓዙ ዛምቢያ ላይ በቁጥጥር ስር ዋሉ
በህገወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲያቀኑ ዛምቢያ ላይ የተያዙት አስር ኢትዮጵያዊያን በእስር ላይ ይገኛሉ።
ስደተኞቹ ባለፈው ሳምንት አርብ ፍርድ ቤት ቀርበው እያንዳንዳቸው ሦስት መቶ ዶላር እንዲከፍሉ ካልሆነ ግን እንደሚታሰሩ እንደተገለፀላቸው ችሎቱ ላይ የኢትዮጵያዊያኑ አስተርጓሚ የነበረችው ብርቱካን ገረመው ለቢቢሲ ገልፃለች። • ሶሪያውያን ስደተኞች በአዲስ አበባ ጎዳናዎች አስሩም ወንዶች ሲሆኑ ከ18 እስከ 38 የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው። ብረቱካን እንደገለፀችው ስደተኞቹ ከታንዛንያ ጋር ዛምቢያን በምታዋስነውና ከዋና ከተማዋ ሉሳካ 750 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ቺንሳሊ በተሰኘችው ትንሽ ከተማ ውስጥ ሲሆን ኢትዮጵያዊያኑ ለቀናት ምግብ ሳያገኙ ልብሳቸው እላያቸው ላይ ተቀዳዶ በከፍተኛ አካላዊ ጉስቁልና ላይ ሆነው ነው የተገኙት። ከተያዙት ስደተኞች መካከልም አንዱ በፅኑ መታመሙ ተነግሯል። • አሜሪካ የመናዊቷ እናት በሞት አፋፍ ላይ ያለ ልጇን እንዳታይ ከለከለች "በኮንቴነር ከኬንያ ታንዛንያ ፤ ከታንዛያ ደግሞ ወደ ዛምቢያ ክልል እንደገቡ ነበር በቁጥጥር ስር የዋሉት" የምትለው ብርቱካን መንገድ ላይ ፖሊስ ሲያስቆማቸው ሾፌሩ እንዳመለጠና ከዚያም ሾፌሩ መኪናውን ነድቶ ወደ ጫካ በመውሰድ ገንዘብ እንደጠየቃቸው እንደነገሯት ገልፃለች። ብርቱካን ከጉዳዩ ጋር የሚያገናኛት ምንም ነገር ባይኖርም በአካባቢው ኢትዮጵያዊ ሆና በመገኘቷ በማስተርጎም እንድትረዳቸው በአካባቢው የዛምቢያ የፀጥታ ሃላፊዎች በአለቃዋ በኩል መጠራቷን ተናግራለች። ኢትዮጵያዊያኑ በአስራ አራት ቀናት ውስጥ የተጣለባቸውን የገንዘብ ቅጣት ካልከፈሉ በውሳኔው መሰረት እስሩ እንዲፀናባቸው እንደሚደረግ በፍርድ ቤት ተገልፆላቸዋል። • ብሄራዊ ባንክ ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ጋር የግሉን ዘርፍ ለማገዝ ስምምነቶችን አደረገ የተወሰኑት ስደተኞች ደቡብ አፍሪካ ዘመዶች ስላሏቸው እነሱን እንዳነጋገረችና ገንዘብ ከፍሎ ለማስለቀቅ መስማማታቸውን እንዲሁም እራሷ የተቻላትን አድርጋ በቀሩት ጥቂት ቀናት ከእስር እንዲለቀቁ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰች መሆኑን ትናገራለች። ከዚህ ቀደምም በተመሳሳይ ኢትዮጵያዊያን አካባቢው ላይ በቁጥጥር ስር ውለው ሁለት ባልደረቦቿ በተለያየ ጊዜ ተደውሎ ፍርድ ቤት መሄዳቸውን ብርቱካን አስታውሳለች።
48768238
https://www.bbc.com/amharic/48768238
"የጋምቢያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ያህያ ጃሜህ ደፍረውኛል"
የ23 ዓመቷ የቀድሞ የጋምቢያ የቁንጅና ንግሥት፣ ፋቱ ጃሎው በ2015 በቀድሞው የጋምቢያ ፕሬዝዳንት ያህያ ጃሜህ መደፈሯን ተናገረች።
ይህንን ቃሏን የሰጠቸው ሂውማን ራይትስ ዎች እና ትራያል ኢንተርናሽናል ባደረጉት ምርመራ ፕሬዝዳንት ያህያ ጃሜህ ፈፀሟቸው በተባለው ጾታዊ ትንኮሳና መደፎሮችን ባጋለጠው ዝርዝር ሪፖርት ላይ ነው። ፋቱ ጃሎው ፕሬዝዳንቱን ስታገኛቸው የቁንጅና ውድድሩን በበላይነት አሸንፋ የነበረ ሲሆን እድሜዋም 18 ነበር። ይህንን ውድድር ባሸነፈችበት ወር ፕሬዝዳንቱ እንደ አባት እየመከሩ የተለያዩ ስጦታዎችን እና ገንዘብ እየሰጧት አክለውም ቤተሰቦቿ በሚኖሩበት አካባቢ ውሃ እንዲገባ በማስተባበር ቅርበታቸውን አጠናከሩ። • ሳፋሪኮም የተጠቃሚዎችን መረጃ በማውጣት ተከሰሰ • “የኢህአፓና መኢሶን ነገር አማራ ክልል ላይ ሊከሰት ይችላል ብዬ ነበር” • ዶ/ር አምባቸው በሌሎች አንደበት ከዛም ትላለች ፋቱ ለፕሬዝዳንቱ ድጋፍ ለማሰባሰብ በተዘጋጀ በአንድ የእራት ግብዣ ላይ የጋብቻ ጥያቄ አቀረቡላት። ፋቱ ግን ጥያቄውን በመቃወም በእራት ግብዣው ላይ ለመስራት የወሰደቻቸውን ኃላፊነቶችን ሰረዘች። በ2015 ሰኔ ወር ላይ ግን በፕሬዝዳንቱ ቤተመንግሥት በተካሄደ ሀይማኖታዊ ፕሮግራም ላይ እንድትገኝ ተጠየቀች። ቤተመንግሥቱ እንደደረሰች ግን የተወሰደችው ወደ ፕሬዝዳንቱ የግል መኖሪያ ነው። "ምን እንደሚፈጠር ግልፅ ነበር" ትላለች ፋቱ፤ ፕሬዝዳንቱ የጠየቁትን እምቢ በማለቷ መናደዳቸውን በማስታወስ። ከዛም በጥፊ እንደመቷትና መርፌ እንደወጓት ታስታውሳለች። ቀጥሎም ደፈሯት። ቢቢሲ ያህያ ጃሜህን በስደት በሚኖሩበት ኢኳቶሪያል ጊኒ ስለቀረበባቸው ክስ ለማነጋገር ሞክሮ ነበር። የፓርቲያቸው ቃል አቀባይ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ላይ የቀረበውን ክስ በአጠቃላይ ክደዋል። ቃል አቀባዩ ኡስማን ራምቦ ጃታ ለቢቢሲ በላኩት መግለጫ "እንደፓርቲ እና እንደ ጋምቢያ ህዝብ በቀድሞው ፕሬዝዳንት ላይ በሚቀርቡ መሠረተ ቢስ ውንጀላዎች ተሰላችተናል" ብለዋል። "የቀድሞው ፕሬዝዳንት ለእንዲህ አይነቱ ውሸትና የጥላቻ ዘመቻ መልስ ለመስጠት ጊዜ የላቸውም። የተከበሩ፣ ፈጣሪያቸውን የሚፈሩ፣ አማኝ ለጋምቢያ ሴቶች ክብር ያላቸው ናቸው" ሲሉ የተናገሩት ደግሞ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ናቸው። ጃሎ ለቢቢሲ ፕሬዝዳንቱን ፍርድ አደባባይ ለማቆም እንደምትፈልግ ተናግራለች። "ይህንን ታሪኬን ለመደበቅ፣ ለማጥፋት ሞክሬያለሁ፤ የታሪኬ አካል እንዳልሆነ ለማድረግ ጥሬያለሁ" "እውነታው ግን አልቻልኩም፤ አሁን ለመናገር የወሰንኩት ታሪኬን በመናገር ያህያ ጃሜህ የሰሩትን እንዲሰሙ ስለፈለኩ ነው።" አክላም በጋምቢያ ሀቅና እርቅ አፈላላጊ ኮሚሽን ፊት ቀርባ ለመመስከርም ፈቃደኛ መሆኗን ተናግራለች። ይህ የሀቅና እርቅ አፈላላጊ ኮሚሽን የተቋቋመው በ2016 በፕሬዝዳንት አዳማ ባሮው ሲሆን በያህያ ጃሜህ የ22 ዓመት አስተዳደር ወቅት የተጸፀሙ ጥፋቶችን ይመረምራል።
40960174
https://www.bbc.com/amharic/40960174
ሰው ሰራሽ ልህቀት፦ ከመፃኢ የዓለም ፈተናዎች አንዱ! ሌሎቹስ?
እ.አ.አ በ2050 እጅጉን የሚያሳስቡን ነገሮች ምን ይሆኑ? እርግጥ እቅጩን መናገር ይከብዳል። ቢሆንም አሁን እየሄድንበት ካለው መንገድ በመነሳት የዓለማችን ሳይንቲስቶች አስርቱ አበይት ፈተናዎችን አስቀምጠዋል።
የአየር ንብረት ለውጥ የዛሬ አረባ ዓመት የዓለማችን አበይት የራስ ምታት አንደሚሆን ይገመታል። 1. የሰው ልጅን ዘረ-መል ማሻሻል በሳይንሳዊ አጠራሩ 'ክሪስፐር' እየተባለ የሚጠራው መላ የሰው ልጅን ዘረ-መል ወይም ዲኤንኤ በማሻሻል ካንሰርን የመሳሰሉ በሽታዎች የሚከላከል ትውልድ ለመፍጠር የሚተጋ ዘዴ ነው። ሀሳቡ ባልከፋ። ነገር ግን ዘዴውን ያሰበውን ሳያሳካ ቀርቶ በዚህ ንድፍ መሰረት የተወለዱ ልጆች ልቀት ወይም ኢንተለጀንሳቸው እንዲሁም የሰውነት ቅርጻቸው ከተለመደው ወጣ ያለ እንዳይሆን ያሰጋል። ነገሩ ትልቅ አደጋ ነው ብሎ ለማሰብ ጊዜው ገና ቢሆንም መዘዙ የከፋ ሊሆን ስለሚችል መጠንቀቅ አለብን ባዮች ናቸው ሳይንቲስቶቹ። ''ቴክኖሎጂው በፍጥነት እያደገ ባለበት በዚህ ዘመን ስለመዘዙ የምናስብበት ጊዜ ዘሁን አይደለም የሚባለው ነገር እርባና ቢስ።" ነው ይላሉ በኒውዚላንድ ዌሊንግተን ዩኒቨርሲቲ የስነ-ምግባር ፕሮፌሰር የሆኑት ኒኮላስ አጋር። 2. ዕድሜው የገፋ ትውልድ ከጊዜ ወደጊዜ ቁጥሩ እየጨመረ የመጣው የዓለማችን ሕዝብ እዚች ምደር ላይ የሚኖርበት የዕድሜ ገደብም እያሻቀበ እንዳለ መረጃዎች ይጠቁማሉ። "ኧረ ዕድሜ ጨምሮ ጨማምሮ ይስጠን" ሊሉ ይችላሉ። አሳሳቢው ጉዳይ ወዲህ ነው። ወደ እርጅና ዘመን የሚሻገሩ ሰዎች እንክብካቤ እንደሚያሻቸው የሚያከራክር ጉዳይ አይደለም። አንድ ጥናት እንደሚያሳው መቶ ዓመትን የሚሻገሩ ሰዎች ቁጥር አሁን ካለበት አምስት መቶ ሺህ ሀምሳ እጥፍ በማደግ እ.አ.አ. በ2100 ሃያ ስድስት ሚሊዮን ይደርሳል። ይህም ለኣዛውንቶች የሚሆን ከባቢ አየር እንድንፈጥር ግድ ይለናል። እንደውም ጃፓን ሮቦቶችን በዚህ መስክ ለማሰማራት ዕቅድ ላይ ነች። 3. የሚዋጡ ከተሞች ሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ብዙ ለውጦችን ያየንበት ዘመን ነው። የጎርፍ አደጋ የዕለተ ዕለት ክስተት እየሆነ ወደ መምታት ደርሷል። የአየሩ ሁኔታም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተቀያየረ መጥቷል። በዚህ ምክንያትም የአሜሪካዋ ማያሚ ከተማ ሕንጻዎች ሲገነቡ ምድር ቤቱን ከፍ አድርገው እንዲገነቡ ትዕዛዝ አውጥታለች። ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ እንደባለሙያዎች ትንበያ ውቅያኖስ እና ሀይቅ አካባቢ የሚኖሩ ከተሞች፥ ደሴቶች እንዲሁም ባንገላዲሽን የመሳሰሉ ዝቅ ባለ ስፍራ የሚገኙ ከተሞች መጥፍያቸው ሩቅ አይደለም። የሚሆነው ባይታወቅም ወደፊት የስደት አንዱ መንስኤ ይሄ ሊሆን እንደሚችልም ይገመታል። 4. የማህበራዊ ሚድያ ዝግመተ ለውጥ ማህበራዊ ሚድያ የእርስ በርስ መገናኛ መንገዳችንን መቀየር ከጀመረ እነሆ አስር ዓመት ሞላው። ከዛም አልፎ ዋነኛ የዜና ምንጭም ሆኖ መቆጠር ከጀመረም ሰንበትበት ብሏል። ይሄም ሰዎችን ለውሸት ዜና እንዲጋለጡ አርጓዋቸዋል። ሰዎች የዜና ምንጫቸውን ማሕበራዊ ሚዲያ ካደረጉ በጊዜ ሂደት ዕውቀታቸውም ላይ ትልቅ ተጽዕኖ እንደሚያመጣም ይተነበያል። ማህበራዊ ሚድያው ካመጣቸው አሉታዊ ተጽዕኖዎች ሳይበር ቡሊይንግ ወይም በማሕበራዊ ሚድያ የሚደርስ ጥቃት ደግሞ ሌላኛው ነው። ከተፈጠረ ገና አስራ ሶስት ዓመት የሆነው ፌስቡክን ጨምሮ ማህበራዊ ሚድያዎች በሚቀጥሉት ሰላሳ ዓመታት ምን ሊያጋጥማቸው እንሚችል መተነቤይ ቢያዳግትም ቀላል ፈተና እንደማይጠብቅን ግን እሙን ነው። ሳይበር ቡሊይንግ ወይም በማሕበራዊ ሚድያ የሚደርስ ጥቃት አንዱ የማህበራዊ ሚድያ አሉታዊ ተጽዕኖ። 5. ጄኦፖለቲካዊ ውጥረት የሰሜን ኮሪያ የሚሳኤል ጥቃት፥ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች፥ በሰው ሀገር ምርጫ የሚገቡ የቤይነመረብ ጠላፊዎች ወይም ሀከሮች ጉዳይ፥ የታላቋ ብሪታንያ ከአውሮፓ ሕብረት ራሷን ማግለል፥ እያደገ የመጣው የብሔርተኝነት አስተሳሰብ. . . እኚህ ሁሉ እ.አ.አ. 2016ን ጨምሮ በያዝነው 2017 ዓ.ም አጀንዳ የነበሩ ኹነቶች ናቸው። ታዲያ በዚህ ከቀጠለ የኣለማችን ጄኦፖለቲካዊ ውጥረት መርገቢያው ምን እና መቼ እንደሆነ ለማሰብ ይከብዳል። 6. የተሽከርካሪ ነገር እያደገ በመጣው የከተሜነት ዑደት ውስጥ እንደ ጥይት የፈጠኑ ባቡሮች እንዲሁም ሃይፐርሉፕ እየተባሉ የሚጠሩ በጣም ፈጣን መጓጓዣዎችን ማየት እየተለመደ መጥቷል። ነገር ግን መኪና ቦታውን የሚለቅ አይመስልም። እንደውም በሚቀጥሉት ጥቂት አስርት ዓመታት የመኪኖች ቀጥር እየጨመረ እንደሚመጣ ይታሰባል። አሽከርካሪ አልባ መኪኖችም ቁጥር እጀጉን በፍጥነት እያደገ ነው። መካከለኛ ደረጃ ያለው ማሕበረሰብ እየሰፋ በመታባት ቻይና እና መሰል ሀገራት አሽከርካሪ የመጠቀም ፍለጎት እጅጉን አሻቅቧል። አደጋ የማይበዛበት፥ እንዲሁም በካይ ያልሆነ የመንገድ ስርዓት እንዴት ይዘርጋ የሚለው ደግሞ ሌላው የዓለማችን መጻኢ ራስ ምታት ነው። የአሽከርካሪ አልባ መኪኖች ነገር እንዳለ ሀኖ። 7. የተፈጥሮ ሀብታችን የ21ኛው ክፍለ ዘመን መለያ የሆኑት የቴክኖሎጂ ውጤቶች አንዳቻው እንኳ ያለ ተፈጥሮ ሀብት እገዛ እውን መሆን ባልቻሉ ነበር። አንድ ዘመናዊ ስልክ በውስጡ እስከ ስልሳ የሚሆኑ ከተፍጥሮ ሀብት የተሰሩ ክፍሎች እንዳሉት ልብ ይሏል። እየተመናመኑ ከመጡ የዓለማችን ተፈጥሯዊ ሀብቶች ዘጠና በመቶውን የያዘችው ቻይና ያሏት ምዕድኖች በሚቀጥሉት ሁለት አስርት ዓመታት ሊጠፋ እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ። በምን ሊተኩ እንደሚችሉ ግን እስከ አሁን አልታወቀም። 8. ሌላ ዓለም ማመቻቸት ታዋቂው የፊዚክስ ምሁር ስቴፈን ሀውኪንግ ሰዎች ሌላ ዓለም በቶሎ ካላመቻቹ ነገሮች እንዳልሆኑ እንደሚችሉ ያስጠነቅቃል። የውጭኛው ዓለም ሙሉ በመሉ የምንተማመንበት ባይመስልም ፊት የምንነሳው ጉዳይ እንዳልሆነም ሳይንቲስቶች ይናገራሉ። አሁን ላይ የሕዋ ኩባንያዎች እና ቢሊየነሮች ብቻ የሚረግጡት የሚመስለን ሌላኛው ዓለም ወይም ሕዋ ወደፊት ለሁሉም ተደራሽ እንደሚሆን ይገመታል። ያን ጊዜ የመጓጓዥ ነገር፥ ደህንነታችን እንዲሁም ዲፕሎማሲ አሳሳቢ ጉዳዮች እንደሚሆን ኑ ግልጽ ነው። 9. የሰው ልጅ ጭንቅላት አቅም ቡናም ሆነ ጠንከር እንደ ሞዳፊኒል ያሉ ነገሮች በመውሰድ ጭንቅላትን ማገዝ የተለመደ ነገር። ከዛም በዘለለ ያደጉ የሚባሉ ሀገራት ዘመናዊ ስልኮችን እንደ ውጫዊ መረጃ ማስቀመጫ በመጠቀም ጭንቅላታቸውን ያግዛሉ። ቤተ-ሙከራዎች አሁን ላይ በፍጥነት እንድናስብ የሚያግዙን እንዲሁም ትኩርታችንን እንድንቆጣጠር የሚረዱ መድሃኒቶችን በማምረት ላይ ናቸው። ጥያቄው እነኚህን መድሃኒቶች የመግዛት አቅም የሌላቸው ሰዎች ምን ያደርጋሉ የሚለው ነው። ከዛም አልፎ የስነ-ምግባር ጥያቄውም ሌላ አሳሳቢ ጉዳይ ነው። 10. ሰው ሰራሽ ልህቀት መጪውን ዓላሚው ሬይ ኩርዝዌል እንደሚያምነው ሰው ሰራሽ ልህቀት ወይም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ወደፊት ከተፈጥሯዊው ልህቀት በብዙ እጥፍ በመብለጥ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይደርሳል። እርግጥ አሁን ጊዜው ለጋ ቢሆንም ስለወደፎቱ ማሰብ እንደማይጎዳ ግን ብዙዎች ይስማሙበታል። ሰው ሰራሽ ልህ ቀት ለብዙ ነገሮች እንዲጠቅም ሆኖ ከመሰራቱ ባለፈ ባልሆነ መንገድ ተጉዞ የሰው ልጅ አደጋ ላይ እንዳይጥል ማስጋቱ ግን አልቀረም።
news-53044858
https://www.bbc.com/amharic/news-53044858
ኢራን የሕዝብ ቁጥሯን ለማሳደግ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎትን ማቅረብ አቆመች
ኢራን የሕዝብ ቁጥሯን ከፍ ለማድረግ በሚል በመንግሥት ሆስፒታሎች ውስጥ ይቀርብ የነበረው የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት አቅርቦትን ውስን አደረገች።
በዚህም በመንግሥት በሚተዳደሩ ሆስፒታሎች ውስጥ እርግዝና በጤናቸው ላይ እክል ለሚያስከትልባቸው ሴቶች ብቻ የእርግዝና መከላከያዎች የሚሰጥ ሲሆን፤ በወንዶች ላይ ይደረግ የነበረው ቫሴክቶሚ የተባለው ቀዶ ህክምና እንዳይካሄድ ተደርጓል። ነገር ግን የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎቶቹ በግል ሆስፒታሎች ውስጥ እንደሚሰጡ ታውቋል። የኢራን መንግሥት በአገሪቱ ውስጥ የሚመዘገበው ዝቅተኛ የወሊድ መጠንና እየጨመረ የመጣው እድሜያቸው እየገፋ የሚሄድ ሰዎች ቁጥር አሳስቦታል። የኢራን አመታዊ የሕዝብ ቁጥር እድገት በአንድ በመቶ እየቀነሰ ሲሆን፤ በቶሎ ርምጃ ካልተወሰደ አገሪቱ በሚቀጥሉት 30 ዓመታት ውስጥ በርካታ በእድሜ የገፉ ዜጎች ካላቸው አገራት ተርታ ውስጥ እንደምትገባ የአገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል። ከሁለት ዓመት በፊት ኢራን የሕዝብ ብዛቷ 1.4 በመቶ ማስመዝገቧ ተገልጾ ነበር። ይህ አሃዝ በጎረቤቷ ኢራቅ ውስጥ 2.3 በመቶ ሲሆን ባላንጣዋ ሳኡዲ አረቢያ ደግሞ 1.8 በመቶ የሕዝብ ቁጥር እድገት ማስመዝገባቸውን የዓለም ባንክ መረጃ ያመለክታል። የአገሪቱ መንግሥት የዜና ተቋም የሆነው ኢርና እንደዘገበው ጋብቻ እና በጋብቻ ውስጥ የሚወለዱ ልጆች ቁጥር ቀንሷል፤ ለዚህም ምክንያቱ ኢኮኖሚያዊ ጫና እንደሆነ አመልክቷል። ግንቦት ወር ላይ የጤና ጥበቃ ምክትል ሚኒስትሩ ሰይድ ሐሚድ ባራካቲ እንደተናገሩት በኢራን ውስጥ ያለው የጋብቻ መጠን በአስር ዓመት ውስጥ በ40 በመቶ ቀንሷል። "በዚሁ የምንቀጥል ከሆነ በሚቀጥሉት 30 ዓመታት ውስጥ በዕድሜ የገፉ በርካታ ሕዝብ ካላቸው አገራት አንዱ እንሆናለን" ብለዋል ምክትል ሚኒስትሩ። እንደ አውሮፓዊያኑ በ1979 የተካሄደው እስላማዊ አብዮትን ተከትሎ የሕዝብ ቁጥሯ በከፍተኛ መጠን ጨምሮ ነበር። ነገር ግን ከዚያ በኋላ ውጤታማ የሕዝብ ብዛት መቆጣጠሪያ ፖሊሲ በመከተሏ አሁን የታየው ውጤት መመዝገቡ ተገልጿል። የአገሪቱ የበላይ መሪ የሆኑት አያቶላህ አሊ ኻሚኒ ሕዝቡ በርካታ ልጆች እንዲኖሩት ሲያበረታቱ ቆይተዋል። እንደ እሳቸው ፍላጎት ኢራን አሁን ካላት 80 ሚሊዮን ሕዝብ ወደ ግማሽ የሚጠጋ ጭማሪ አድርጋ ቁጥሩ ወደ 150 ሚሊዮን ከፍ እንዲል ይሻሉ።
news-47382340
https://www.bbc.com/amharic/news-47382340
የፈረንሳዩ ኩባንያ በደረሰበት ጫና ሂጃብ መሸጥ አቆመ
የፈረንሳዩ የስፖርት ትጥቅ አከፋፋይ ኩባንያ ለስፖርተኞች ሂጃብ ማቅረቤን አቁሜያለሁ አለ።
ዲካትሎን የተባለዉ ትጥቅ አምራችና አከፋፋይ ኩባንያ ዛቻዎችና የገበያ ማስፈራሪያዎች ስለደረሱብኝ የስፖርተኞች ሂጃብ ማቅረቡን ለጊዜው ትቼዋለሁ ብሏል። ኩባንያዉ የሚያመርተው ሒጃብ ሴት ስፖርተኞች በጨዋታዎች ጊዜ የሚለብሱት ነው። ነገር ግን ይህን አንቀበልም ያሉ ወገኖች በኩባንያዉ ላይ ጫና አሳድረዋል። • ዴንማርክ ሙሉ የፊት ገጽታን የሚሸፍን 'ሂጃብ' አገደች ከዚህም በተጨማሪ መንግሥት ሂጃብ ማድረግ የሃገሪቱ መንግሥት ከሃይማኖት ጋር የተለያየ መሆኑን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው የሚል አስተያየት ሲሰጥ፣ የሕግ ባለሞያዎች ደግሞ ምርቱ እንዳይሸጥ ቅስቀሳ እናደርጋለን የሚል ተቃውሞ መሰንዘራቸው ዲካትሎን ምርቱን እንዲያቆም ካደረጉት ምክንያቶች መካከል ናቸው። የኩባንያዉ ቃል አቀባይ ዣቬየር ሪቮየር "ዉሳኔ አሳልፈናል. . . በዚህ ሰዓት ፈረንሳይ ውሰጥ መሸጥ የለበትም" ብለዋል። ነገር ግን ካሁን በፊት ቃል አቀባዩ ለኤኤፍፒ በሰጡት ቃለ መጠይቅ "ሂጃብ ገበያ ላይ የምናቀርበው ሁሉንም የዓለም ሴቶች በስፖርት ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ ነዉ" ብለው ነበር። ጸጉርን ብቻ የሚሸፍነዉ ሂጃቡ ከባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ጀምሮ በ49 ሃገራት በስፋት ይሸጥ ነበር። ነገር ግን ይህ በመሆኑ ተቋሙ ባለፉት ወራት የተቃውሞ ይዘት ያላቸው ከ500 በላይ የማስጠንቀቂያ የስልክ ጥሪዎችና የኢሜይል መልዕክቶች ደርሰውኛል ብሏል። • ሂጃብ ለባሿ የሕግ ብቃት መመዘኛ ፈተና ላይ እንዳትቀመጥ ተከለከለች የሀገሪቱ የጤና ሚኒስትር አግነሰ በዚን "ይህ ልጋራው የማልፈልግ የሴቶች ምርጫ ነው። የፈረንሳይ ኩባንያም ይህን ምርት ባያስተዋውቀው እመርጣለሁ" የሚል ሃሳብ መስጠታቸዉም ሌላኛው ጫና ተደርጎ ተወስዷል። በተመሳሳይ የፈረንሳይ መንግሥት ቃል አቀባይ አውሮር በርጌ "እንደሴትነቴና እንደ ፈረንሳያዊ ዜጋ እሴቶቻችንን የማያከብር ምርት ላይ እምነት አለመጣልን እመርጣለሁ" የሚል መልዕክት በትዊተር ገጻቸው ማስፈራቸው ኩባንያዉን ምርቱ ወደ አለመሸጥ ውሳኔ መርቶታል። ፈረንሳይ መንግሥትን እና ሃይማኖትን የሚለያይ ጠንካራ ሕግ ያላት በመሆኗ ምንም አይነት ሃይማኖታዊ መገለጫ ያላቸዉ አልባሳት በትምህርት ቤቶችና በመንግሥት ተቋማት እንዳይለበሱ ከልክላለች። ፈረንሳይ በ2010 ሙሉ ፊትን መሸፈንን የከለከለች ሲሆን የመብት ተሟጋች ነን የሚሉ ቡድኖች "ፈረንሳይ ሙስሊም ሴቶችን ታገልላለች፣ እስልምናንም ትጠላለች" በማለት እየከሰሱ ነው።
news-49718702
https://www.bbc.com/amharic/news-49718702
አምነስቲ ኤርትራ ለ18 ዓመታት ያሰረቻቸውን 28 ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች እንድትለቅ ጠየቀ
የኤርትራ መንግሥት ከ18 ዓመት በፊት የሃገሪቱን ፕሬዝዳንት በመተቸታቸው ምክንያት ለእስር የዳረገቻቸውን 11 ፖለቲከኞችንና 17 ጋዜጠኞችን እንድትለቅ አምነስቲ ኢንትርናሽናል ጥሪ አቀረበ።
ብርሀነ አብረኸ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪው አምነስቲ እንዳለው እነዚህ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች የታሰሩት በ1994 ዓ.ም ላይ ነበር። ከዚያ በኋላም ግለሰቦቹ ላይ ይፋዊ ክስ ያልተመሰረተባቸው ሲሆን ታይተውም ሆነ ስላሉበት ሁኔታ ምንም የተሰማ ነገር የለም ብሏል። አምነስቲ የህሊና እስረኞች ያላቸውን እነዚህን ታሳሪዎች የተያዙበትን 18ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ እንዲለቀቁ ለመጠየቅ ለ18 ቀናት የሚቆይ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ መጀመሩንም ገልጿል። • በፕሮቴስታንት እምነት ተከታይነቱ ለእስር ተዳርጎ የነበረው ኤርትራዊ ህይወቱ አለፈ • ኤርትራ፡"እያስተማሩን ሳይሆን ባሪያ እያደረጉን ነው" አስራ አንዱ ፖለቲከኞች የታሰሩት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ምርጫ በማካሄድና ለሕግ የበላይነት በመገዛት ሕገ መንግሥቱን እንዲያከብሩ የሚጠይቅ ግልጽ ደብዳቤ በመጻፋቸው ሲሆን 17ቱ ጋዜጠኞች ደግሞ ፖለቲከኞቹ ስለጻፉት ደብዳቤ በመዘገባቸው ነው ተብሏል። የአምነስቲ ኢንትርናሽናል የምሥራቅ አፍሪካ፣ አፍሪካ ቀንድና የግሬት ሌክስ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ሰይፍ ማጋንጎ እንዳሉት "ለታሳሪዎቹ ፍትህ ሲጠየቅ ሁለት አስርት ዓመታት ሊሆን ነው፤ ምጸት የሚሆነው ደግሞ ኤርትራ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት አባል መሆኗ ነው።" "ይህ ከሕግ ውጪ የሆነው እስር የፕሬዝዳንት ኢሳያስ መንግሥት ተቃዋሚዎቹን ለመጨፍለቅ ምን ያህል እርቀት እንደሚሄድ የሚያመላክት ነው። በብዙ መቶዎች እንደሚቆጠሩት ሌሎች የህሊና እስረኞች ሁሉ እነዚህ 28 ታሳሪዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ መለቀቅ አለባቸው" ሲሉ አክለዋል። • ኤርትራ፡ ''እናቶች ከህጻናት ልጆቻቸው ጋር ታስረዋል'' • ኤርትራ የደብረቢዘን ገዳም መነኮሳትን አሰረች ዛሬ የሚጀምረውና አምነስቲ ለ18 ቀናት የሚያካሂደው የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ የኤርትራ የቀድሞ የገንዘብ ሚኒስትር የነበሩት ብርሐነ አብረሃ ከተያዙበት አንደኛ ዓመት ጋር በማያያዝ ነው። አቶ ብርሐነ በቁጥጥር ስር የዋሉት ሕዝቡ ለዲሞክራሲ ሰላማዊ ትግል እንዲያደርግ የሚቀሰቅስ መጽሐፍ ካሳተሙ በኋላ የዛሬ ዓመት ነበር። እንደ ሌሎቹ የህሊና እስረኞች አቶ ብርሐነ ከውጪው ዓለም ጋር ምንም አይነት ግንኙነት በሌለው ምስጢራዊ ስፍራ ውስጥ ተይዘው እንዳሉ ይታመናል። ቤተሰባቸውም ስላሉበት የጤንንት ሁኔታና የት እንደሚገኙ ምንም አይነት መረጃ እንደሌላቸውም አምነስቲ ገልጿል። አምነስቲ አክሎም ፕሬዝዳንት ኢሳያስና መንግሥታቸው በእነዚህና በሌሎች የህሊና እስረኞች ላይ እየፈጸሙት ያለው ኢፍትሐዊነት እንደሚያሳስበውና "ዓለምም ከታሳሪዎቹና ከቤተሰባቸው ጎን በመቆም የኤርትራ ባለስልጣናት ያለቅድመ ሁኔታ በቶሎ ከእስር እንዲለቋቸው መጠየቅ አለበት" ብለዋል ሰይፍ ማጋንጎ። ባለፈው ዓመት ቢቢሲ የ13 ዓመት ታዳጊ እያለ ወላጆቹ ከ18 ዓመታት በፊት ከታሰሩት ሰዎች መካከል አንዱ የሆነውን ኢብራሒም ሸሪፎን አናግሮ ነበር። እናቱ አስቴር ፍስሃጽዮን እና አባቱ ማህሙድ አህመድ ሸሪፎ ታዋቂ ከሆኑ ኤርትራዊያን ፖለቲከኞች መካከል ነበሩ። "ከ18 ዓመታት በፊት በዕለተ ማክሰኞ የተከሰተው ነገር እስካሁን ከህሊናዬ አልጠፋም። ያቺ ዕለት ህይወቴን እስከወዲያኛው ቀይራዋለች" ሲል ነበር የተናገረው። "ከእንቅልፌ የነቃሁት ጎህ ከመቅደዱ በፊት ባልተለመደ የሰዎች እርምጃና ትዕዛዝ በሚሰጥ ድምጽ ነበር። ሮጬ ስወጣ እናቴ ከቤታችን በወታደሮች እየተጎተተች ስትወጣ ተመለከትኩ" ሲል ክስተቱን ያስታውሳል።
news-49457662
https://www.bbc.com/amharic/news-49457662
ብራዚል የአማዞን እሳትን ለማጥፋት ወታደር ልትልክ ነው
የብራዚል ፕሬዘዳንት ጃዬር ቦልሶናሮ፤ በአማዞን ደን የተነሳውን እሳት ለማጥፋት በሚደረገው ጥረት የአገሪቱ ወታደራዊ ኃይል ድጋፍ እንዲሰጥ ትዕዛዝ አስተላለፉ።
በፕሬዘዳንቱ ውሳኔ መሰረት በጥብቅ ተፈጥሯዊ ሥፍራና በድንበር አካባቢ ወታደሮች ይሰማራሉ። ውሳኔው ይፋ ከመደረጉ አስቀድሞ የአውሮፓ መሪዎች ብራዚል ላይ ከፍተኛ ጫና እያደረጉ ነበር። "ወታደር እንደመሆኔ የአማዞን ጫካን እወደዋለሁ፤ ልታደገውም እፈልጋለሁ" ሲሉ ፕሬዘዳንቱ ንግግር አድርገዋል። ወታደሮቹ ይሠማራሉ የተባለው ለአንድ ወር ሲሆን፤ የመከላከያ ሚንስትሩ ፈርናንዶ አዜቬዶ ኤ ሲልቫ ሂደቱን ያስፈጽማሉ ተብሏል። • 'የዓለም ሳምባ' የሚባለው አማዞን ጫካ በአስፈሪ ሁኔታ እየነደደ ነው ብራዚል በአማዞን ጫካ የተከሰተውን እሳት ለማጥፋት ያላሰለሰ ጥረት ካላደረገች ፈረንሳይና አየርላንድ ከሰሜን አሜሪካ ጋር ሊያደርጉት የነበረውን የንግድ ስምምነት እንደማያጸድቁ ተናግረዋል። የብራዚል ፕሬዘዳንት በበኩላቸው መሪዎቹ "በአማዞን ደን የተነሳውን እሳት አስታከው ማዕቀብ መጣል አይችሉም" ሲሉ ተችተዋል። በአሁን ወቅት የአውሮፓ ሕብረት ካውንስል መሪ የሆነችው ፊንላንድ የገንዘብ ሚንስትር፤ የአውሮፓ ሕብረት የብራዚል የሥጋ ምርት ላይ ማዕቀብ እንዲጥል ጠይቀዋል። የተፈጥሮ ጥበቃ ላይ የሚሠሩ ቡድኖች ባሳለፍነው አርብ በመላው ብራዚል ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው ነበር። በተለያዩ አገሮች የሚኖሩ ብራዚላዊያንም ተቃውሟቸውን እያሰሙ ይገኛሉ። • አከራካሪው የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ ካርታ የዓለም ግዙፉ ደን እንዲሁም "የዓለም ሳምባ" እየተባለ የሚሞካሸው አማዞን የሙቀት መጠን መጨመር ጋብ እንዲል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል። አማዞን የአንድ ሚሊየን ሰዎች መኖሪያ ከመሆኑ በተጨማሪ ከሦስት ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ እጽዋትና እንስሳት መገኛም ነው። የጀመርኗ መራሔተ መንግሥት አንግላ መርኬል፣ የፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን እሳቱን "ዓለም አቀፍ ቀውስ" ብለውታል። አንግላ እና ኢማኑኤል በ ጂ-7 ውይይት ላይ የአማዞን ደን እሳት ለውይይት መቅረብ እንዳለበትም ገልጸዋል። • ከሶማሌላንድና የመን የመጣው አንበጣ በአምስት ክልሎች ተከስቷል የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሀፊ አንቶንዮ ጉቴሬዝ በትዊት ገጻቸው ላይ "ዓለም በአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ውስጥ በምትገኝበት በዚህ ወቅት፤ ቀዳሚ የኦክስጅን ምንጫችን የሆነው የአማዞን ደን አደጋ ውስጥ መውደቅ አይገባውም" የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል። የብራዚሉ ፕሬዘዳንት ጃዬር በበኩላቸው፤ የፈንሳዩ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤልን ጨምሮ በርካታ መሪዎች በአማዞን ጉዳይ ጣልቃ የሚገቡት "ለፖለቲካ ጥቅም ነው" በማለት ትችት ሰንዝረዋል። ብራዚል የአማዞን ደንን ለመጠበቅ በቂ ጥረት እያደረገች አይደለም የሚለውን አስተያየት "መሰረተ ቢስ ወሬ" በማለት ፕሬዘዳንቱ አጣጥለዋል። አገሪቱ ጫካውን ለመጠበቅ "አዳዲስ ሕጎች አውጥታለች" ሲሉም ተደምጠዋል። አገሪቱ ሞቃታማ የአየር ሁኔታ በምታስተናግድበት ወቅት ሁሉ እሳት እንደሚነሳም ተናግረዋል። ከብሔራዊ የህዋ ምርምር የወጣ የሳተላይት መረጃ እንዳመለከተው የእሳት ቃጠሎው 85 በመቶ ጨምሯል። ፕሬዘዳንቱ ግን "ወቅቱ አርሶ አደሮች አዲስ ሰብል ለመትከል መሬት የሚያቃጥሉበት ወቅት ስለሆነ ነው" ብለው ቁጥሩን አልተቀበሉም። የተፈጥሮ ጥበቃ ባለሙያዎች እንደሚሉት፤ የብራዚል ፕሬዘዳንት አርሶ አደሮች የአማዞንን ደን እንዲመነጥሩ ያበረታታሉ። የምረጡኝ ቅስቀሳ ባካሄዱበት ወቅት፤ ደኑ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ግለሰቦች የሚጣልባቸውን ቅጣት እንደሚያለዝቡ ተናግረው ነበር። የአገሪቱን የአካባቢ ጥበቃ ተቋም ለማዳከምም ቃል ገብተው ነበር።
news-55581630
https://www.bbc.com/amharic/news-55581630
ትግራይ፡ አቶ ስብሐት ነጋና ሌሎችም በመከላከያ ሠራዊት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ
በፌደራል መንግሥቱ ሲፈለጉ ከቆዩት ከፍተኛ የህወሓት አመራሮች መካከል አቶ ስብሐት ነጋ (አቦይ ስብሐት) እና ሌሎች ወታደራዊ መኮንኖች በአገሪቱ ሠራዊት ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ።
ስብሐት ነጋ (ፎቶ ከፋይል) የህወሓት መስራች ከሆኑት ሰባት ሰዎች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ስብሐት ነጋ ተደብቀውበት ነበር በተባለው ቦታ ላይ ሠራዊቱ ባካሄደው ዘመቻ ከሌሎች ተፈላጊ ሰዎች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የመከላከያ ሠራዊት የስምሪት መምሪያ ኃላፊ ብርጋዲየር ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ ገልጸዋል። ኃላፊው ጨምረው እንደገለጹት አቶ ስብሐት ነጋ ለመንቀሳቀስ እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ስፍራ ውስጥ ተደብቀው ቆይተው በሠራዊቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አመልክተዋል። የመያዣ ትዕዛዝ ወጥቶባቸው የሚፈለጉትን ከፍተኛ የህወሓት ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራሮችን ለመያዝ የመከላከያ ሠራዊቱና የፌዴራል የፀጥታ አካላት በጋራ ባደረጉት ፍተሻና አሰሳ አቶ ስብሐትና ሌሎች ተፈላጊዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉና ሌሎች ደግሞ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ብርጋዲየር ጀነራል ተስፋዬ ገልጸዋል። በዚህም ከአቶ ስብሐት በተጨማሪ የቀድሞ የአገሪቱ መከላከያ ሠራዊት አባላት የነበሩና የከዱ ሌሎች የህወሓት ወታደራዊ መኮንኖችም በቁጥጥር ስር ውለዋል ተብሏል። በቁጥጥር ስር የዋሉት ወታደራዊ መኮንኖች የቡድኑን ኃይል በማሰልጠንና በማዋጋት ሚና የነበራቸው መሆኑን ጠቁመው፤ በመጨረሻም የአመራር ጥበቃ ሲያስተባብሩ ቆይተው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከፍተኛ ኃላፊው ገልጸዋል። በቁጥጥር ስር መዋላቸው ከተገለጹት ከአቶ ስብሐት ነጋ በተጨማሪ ባለቤታቸው ሌተናል ኮሎኔል ፀአዱ ሪች፣ ኮሎኔል ክንፈ ታደሰ፣ ኮሎኔል የማነ ካህሳይ የተባሉ የቀድሞ የመከላከያ ሠራዊት አባላት የነበሩ ናቸው ተብሏል። ከተጠቀሱት በተጨማሪ ሎችም ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ከዚህ ባሻገር ደግሞ በዙሪያቸው የነበረ ታጣቂ ኃይል ላይ እርምጃ እንደተወሰደበት ብርጋዲየር ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ገልፀዋል። ሐሙስ ዕለት መከላከያ ሠራዊቱ በሕግ ከሚፈለጉ ከፍተኛ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል አራቱ መገደላቸውንና ዘጠኙ ደግሞ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ማሳወቁ ይታወሳል። ከእነዚህም የህወሓት አመራሮች መካከል የአቶ ስብሐት ነጋ እህት የሆኑትና የቀድሞ የትግራይ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ ይገኙበታል። በእርምጃው ከተገደሉት መካከል አቶ ሴኩቱሬ ጌታቸው፣ የህወሓት ቀደምት ታጋይና የቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘርዓይ አስገዶም፣ የህወሓት የመገናኛ ብዙሃን ተቋም የሆነው ድምጺ ወያኔ ኃላፊ አቶ አበበ ገብረመድኅን፣ የትግራይ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳንኤል አሰፋ ከተገደሉት ከፍተኛ አመራሮች መካከል እንደሆኑ ተገልጿል። ከተገደሉት አራት ሰዎች ባሻገር ሌሎች ዘጠኝ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጀነራሉ ተናግረዋል። ቀደም ሲል የተያዙ ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይም በተመሳሳይ የጸጥታ ኃይሉ ባደረገው አሰሳ የተገደሉና በቁጥጥር ስር የዋሉ የህወሓት ወታደራዊ መኮንኖችና ሲቪል አመራሮች የስም ዝርዝር ይፋ መደረጉ ይታወሳል። እስካሁን ድረስ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር የነበሩት ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤልም ሆኑ ሌሎች ከፍተኛ ሹማምንቶች ያሉበት ሁኔታ በዚህ መግለጫ ላይ አልተጠቀሰም። ከጥቂት ሳምንት በፊት የመከላከያ ሠራዊቱ ከፍተኛ የህወሓት አመራሮች ያሉበትን ለጠቆመ የ10 ሚሊዮን ብር ሽልማት ማዘጋጀቱን መግለጹ ይታወሳል። በዚህ መግለጫ የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ዓርብ ታኅሳስ 23 ቀን 2013 ዓ. ም. በሰጠው መግለጫ፤ የቀድሞ የትራንስፖርት ሚኒስትር ደኤታ ወ/ሮ ሙሉ ገብረእግዚአብሔርና በርካታ ወታደራዊ መኮንኖች መማረካቸውን እንዲሁም በርካቶች መደምሰሳቸውን አስታወቆ ነበር። መንግሥት በቁጥጥር ስር ውለዋል ወይም ተገድለዋል ያላቸውን የህወሓት ወታደራዊ መኮንኖችና ሲቪል አመራሮችን በተመለከተ ከቡድኑም ሆነ ከሌላ ገለልተኛ ወገን የተሰማ ነገር የለም። የክልሉ ዋና ከተማ መቀለ በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ቁጥጥር ስር ስትገባ የህወሓት አመራሮች ውጊያውን እንደሚቀጥሉ ከገለጹ በኋላ ስላሉበት ሁኔታና ወቅታዊ ጉዳዮች በይፋ የሰጡት መግለጫ የለም። እስካሁን መገደላቸው እንዲሁም መያዛቸው ከተገለፁ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ሌላ የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንትና በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት አዲስዓለም ባሌማንና የቀድሞዋን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ ኬርያ ኢብራሂም ጨምሮ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙ የተለያዩ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የቀድሞ ባለሥልጣናት ይገኛሉ። ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ምሽት የህወሓት ኃይሎች በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ተከትሎ በትግራይ ክልል ወታደራዊ ግጭት ተቀስቅሶ ክልሉን ይመራ የነበረው ህወሓት ከሥልጣን መወገዱ ይታወሳል። በትግራይ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር በተያያዘ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና የፌደራል ፖሊስ በበርካታ የህወሓት ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራሮች ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣታቸው ይፋ አደረገው ነበር። ለእስር ማዘዣውም ዋነኛ ምክንያቶቹ ህወሓትን በበላይነት በመምራት፣ በትግራይ ክልል በሚገኘው በአገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈፀም፣ የአገር ክህደት ወንጀል ፈጽመዋል፣ የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አባላት እንዲታገቱ አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው ነው። በተጨማሪም የቀድሞው የአገሪቱ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም የነበሩት ሜጀር ጄኔራል ጻድቃን ገብረተንሳይን ጨምሮ፣ ከፍተኛ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ኃይል፣ የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አመራሮችም በአገር ክደትና በሠራዊት አባላት ላይ በተፈጸመ ተጠርጥረው የመያዣ ትዕዛዝ ወጥቶባቸዋል።
news-56714545
https://www.bbc.com/amharic/news-56714545
ሶልሻዬር፡ "ይህን ያደረገው ልጄ ቢሆን ኖሮ ምግብ አልሰጠውም ነበር"
የማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ኦሌ ጉናር ሶልሻየር ቡድኑ በአጨቃጫቂ ሁኔታ ቶተንሃም ሆትስፐርን 3-1 ከረታ በኋላ "የጨዋታ ውበት ጠፍቷል" ሲሉ ተደምጠዋል።
የዩናይትዱ ኤዲሰን ካቫኒ ያስቆጠረው ጎል ዳኛው ጎሉ ከመግባቱ በፊት ጥፋት ተፈፅሟል ብለው የቪድዮ ማስረጃውን ካዩ በኋላ እንዲሻር ወስነዋል። የቶተንሃሙ ሶን የዩናይትዱ ስኮት ማክቶሚናይ በጣቱ ፊቴን ጭሮኛል ብሎ መሬት ላይ ወድቆ ሳለ ነው ጎሉ የተቆጠረው። "ልጄ ይሄን ቢያደርግና የቡድኑ አጋሮቼ መጥታችሁ ካላነሳችሁ ቢል ምግብ ነበር የምቀጣው፤ ምክንያቱም ይህ አሳፋሪ ድርጊት ነው" ሲሉ ሶልሻዬር በድህረ ጨዋታ አስተያየታቸው ምሬታቸውን ገልፀዋል። "ጨዋታው ውበቱ ጨርሶ እየጠፋ ነው።" የቶተንሃሙ ሶን ከአጨቃጫቂው ክስተት በኋላ ዩናይትድ ላይ አስቆጥሮ የመጀመሪያው አጋማሽ 1-0 ተጠናቋል። በሁለተኛው አጋማሽ ፍሬድ፣ ካቫኒ እንዲሁም ግሪንውድ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ዩናይትድ 3-1 ረትቷል። ሶልሻዬር ሶን ላይ የተፈፀመው ጥፋት ግልፅ ቢሆን ኖሮ ዳኛው ቢመለከተው አይገርመኝም፤ ጎሉ ግን መፅደቅ ነበረበት ብለዋል። "እኛ በሶን አላታለልንም። ዳኛው ግን ተሸውደዋል።" የቶተንሃሙ ጆዜ ሞውሪንሆ በበኩላቸው "በመጀመሪያ አንድ ነገር ልንገራችሁ። ሶልሻዬር ስለ ሶኒ ያንን አስተያየት ከሰጠ በኋላ እኔን አለመጠየቃችሁ ገርሞኛል" ብለዋል። "እኔ ብሆን ኖሮ አንድ ተጨዋች ይህንን አድርጓልና እራት አልሰጠውም ያልኩት ምን ሊፈጠር ይችል ነበር? እጅግ በጣም ነው የሚያሳዝነው። ሌሎችን በምታዩበት ዓይን እኔን አለማየታችሁ እጅግ ያሳዝናል።" "ስለ ሶን ከጠየቃችሁኝ ኦሌ አባቱ አለመሆኑ ዕድለኛ ነው። እኔ አባት ነኝ። አባት ሁሌም ልጁን ሊመግብ ይገባል። ለልጅህ መስረቅ ካለብህ ትሰርቃለህ" ብለዋል ጆዜ። የቶተንሃሙ ሶን ሄውንግ-ሚን በስኮት ማክቶሚናይ ከተነካ በኋላ ለደቂቃዎች መሬት ላይ ወድቆ ቆይቷል። የስፐርሱ ጆዜ ሞውሪንሆ የቪድዮ እገዛ [ቪኤአር] ቀንደኛ ተቃዋሚ ናቸው። "ለሁሉም ከባድ ነው። ለኛ፣ ለተጨዋቾች፣ ለዳኞች። በርካታ የሚጋጩና የማይገቡ ውሳኔዎች እየተስተዋሉ ነው። ይህ የኔ ችግር አይደለም። ላስተካክለው አልችልም።" የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ጨዋታዎች በአጨቃጫቂ የቪኤአር ውሳኔዎች የታጀቡ ሆነዋል። አርብ ምሽት ዎልቭስ ፉልሃምን ሲያሸንፍ ፉልሃሞች ያስቆጠሩት ጎል ከጨዋታ ውጭ ተብሎ መሰረዙ አነጋጋሪ ሆኖ ነበር። ቅዳሜ ከሰዓት ደግሞ ሊቨርፑል አስተን ቪላን ባሸነፈበት ጨዋታ አንድ ጎል ከጨዋታ ውጭ ተብሏል። ሞውሪንሆን የፉልሃምን ጨዋታ ስመለከት ነበር ብለዋል። "እኔም ምንም እየገባኝ አይደለም። አንዳንዴ ታገኛለህ። አንዳንዴ አታገኝም። ጎል አስቆጥረህ ለመደሰት ትፈራለህ።" ሞውሪንሆ ከዩናይትድ ጋር በነበረው ጨዋታ ስፐርስ ሊሸነፍ አይገባውም ነበር ሲሉ ተደምጠዋል። በሌላ በኩል የእግር ኳስ ተንታኞች ስለ አጨቃጫቂው ጨዋታ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ ተጨዋች ሮይ ኪን ስካይ ስፖርት ላይ በሰጠው አስተያየት "ይሄ ጥፋት ከሆነ ወደ ቤታችን ብንሄድ ነው የሚሻለው" ብሏል። የቀድሞ አየርላንዳዊው አጥቂ ክሊንተን ሞሪሰን ቢቢሲ ራድዮ 5 ላይ በሰጠው አስተያየት "ይሄ በፍፁም ጥፋት ሊሆን አይችልም" ሲል የሶንን ድርጊት አጣጥሏል። ተንታኙ እንደሚለው ዳኛው ይሄ ጥፋት ነው ብለው ካመኑ ቀድሞ አንድ ቢጫ ላየው ስኮት ማክቶሚናይ ሁለተኛ ቢጫ አሳይው ከሜዳ ሊያሰናብቱት ይገባ ነበር። "ጨዋታው ቅጥ እያጣ ነው። ተመሳሳይ ውሳኔዎች አይስተዋሉም" ብሏል ተንታኙ።
news-45054704
https://www.bbc.com/amharic/news-45054704
በረዷማ ተራራ ላይ ለ7 ቀናት ጠፍቶ የነበረው አውስትራሊያዊ በህይወት ተገኘ
ተራራ መውጣት የሚያዘወትረው የ29 ዓመቱ አውስታራሊያዊ ለሰባት ቀናት በረዷማ ተራራ ላይ ቆይቶ ህይወቱ አለማለፉ ብዙዎችን አስገርሟል።
አውስትራሊያዊው የተገኘበት ተራራ ኒውዚላንድ ውስጥ የሚገኝ አስፕሪንግ የተባለ ተራራ ላይ ብቻውን ከወጣ በኋላ የት እንደደረሰ አልታወቀም ነበር። የበረዶው ቅዝቃዜ ለህይወት አስጊ ቢሆንም ያለ ማንም ሰው ድጋፍ ለሰባት ቀናት በህይወት ቆይቷል። ከሰባት ቀናት በኃላ የታደጉት ነፍስ አድን ሰራተኞች ለሰባት ቀናት በረዷማው ተራራው ላይ ቢቆይም ያለ የሌለ ሀይሉን አሰባስቦ የነፍስ አድን ሄሊኮፕተር መጥራቱ አስገራሚ ነው ብለዋል። የነፍስ አድን ሰራተኞቹ ግለሰቡ ከዚህ ቀደም ወታደራዊ ስልጠና መውሰዱ በህይወት ለመቆየት ሳይግዘው አልቀረም ብለዋል። • "የኤርትራ ማዕቀብ የመነሳት ጥያቄ በኤምሬትስ ተፅእኖ የተፈጠረ መሆኑን ጂቡቲ ታምናለች" ፕ/ር መድኃኔ ታደሰ • "ያለፉት 27 ዓመታት ብዙ ቆሻሻ ነገሮች የተሰሩበት ዘመን ነው'' ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የነፍስ እን ሰራተኞቹ፤ አውስትራሊያዊው የተራራውን ግግር በረዶ ቆፍሮ ዋሻ በመስራትና ውስጡ በመሆን ራሱን እንዳተረፈ ይገምታሉ። ተራራው ላይ በረዶ የቀላቀለ ንፋስ በሰአት 600 ኪሎ ሜትር ይነፍሳል። አውስትራሊያዊው በበረዶው ቅዝቃዜ ሳቢያ ሰውነቱ ከመሸማቀቁ ባለፈ የከፋ ጉዳት አልደረሰበትም። አውስትራሊያዊው ለነፍስ አድኖች የአደጋ ጊዜ ምልክት ከሰጠ በኃላ ከፍተኛ ንፋስ ስለነበረ በቶሎ ሊደርሱለት አልቻሉም ነበር። • የኢትዩጵያውያን አካል ጉዳተኞች ፈተናዎች ምን ድረስ? • ጀዋር እና ዐብይ ምን ተባባሉ? አውስታራሊያዊው ተራራ መውጣት እንደማዘውተሩ ለሁኔታው አመቺ ቁሳቁሶች አንግቦ ነበር። ሆኖም ተራራውን ከወጣ በኃላ ከፍተኛ ንፋስ ስለነበረ ለሰባት ቀናት ያህል ለመውጣት ተቸግሮ ነበር።
news-47703594
https://www.bbc.com/amharic/news-47703594
የኢትዮጵያዊያን እርጅና በስንት ዓመት ነው የሚጀምረው?
ፓፓ ኒው ጊኒ በተባለችው ሃገር የሚኖር አንድ የ45 ዓመት ጎልማሳ ፈረንሳይ ወይም ሲንጋፖር ውስጥ ካለ የ76 ዓመት ሽማግሌ ጋር ተመሳሳይ የእርጅና ስሜትና ድካም ያጋጥመዋል።
ከዓለም የዕድሜና የእርጅና ደረጃ ጋር ሲወዳደር ደግሞ ይህ ግለሰብ በአማካይ የ65 ዓመት ሰው ሊሰሙት የሚገቡ ስሜቶችን ነው የሚያስተናግደው። ይህ ውጤት የተገኘው በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎችን ያካተተ የጥናት ቡድን ባሳተመው የምርምር ውጤት ላይ ነው። • ጌዲዮ በዐቢይ ጉብኝት ማግስት • የምግብ ምርጫዎ ስለማንነትዎ ይናገራል? ተመራማሪዎቹ ከጉዳዩ ጋር የተያያዙ የ195 ሃገራት መረጃዎችን ያሰባሰቡ ሲሆን አንድ ሰው በአማካይ 65 ዓመት ሲሞላው እርጅና ምልክቶችን ማሳየት ይጀምራል ይላሉ። በጥናቱ መሠረትም ከእርጅና ጋር ተያይዘው የሚመጡ የልብ ህመም፣ የመስማት ችግር፣ ከመውደቅ ጋር ተያይዝው የሚመጡ ጉዳቶችና አጠቃላይ የጤና እክሎች የማጋጠም እድላቸው እንደምንኖርበት ሃገርና አካባቢ ይወሰናል። ስለዚህ በትክክል በሚያረጁና ያለ ዕድሜያቸው በሚያረጁ ሰዎች መካከል እስከ 30 ዓመት የሚሆን ልዩነት ሊፈጠር ይችላል ይላል ጥናቱ። ጥናቱ ከዚህ በተጨማሪ እርጅናን ከዕድሜ ጋር ብቻ ሳይሆን ከአጠቃላይ ጤንነት አንጻርም ተመልክቶታል። ይህ ደግሞ ከእርጅና ጋር ተያይዘው ከሚመጡ በሽታዎች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው። በጥናቱ ዋና ተሳታፊ የነበሩት ዶክተር አንጌላ ዋይ ቻንግ እንደሚሉት ረጅም ዕድሜ መኖር ጥሩ አጋጣሚ የመሆኑን ያክል ይዞት የሚመጣው አደጋም አለ። ''በተለይ ደግሞ ባላደጉት ሃገራት የሚኖሩና ያልተመቻቸ ሕይወት ያላቸው በዕድሜ የገፉ ሰዎች ከራሳቸው አልፈው ለአጠቃላዩ ኅብረተሰብ አስጊ በሽታዎችን ይዘው ሊመጡ ይችላሉ።'' • የዓለማችን ውድ እና ርካሽ ከተሞች ይፋ ሆኑ ተመራማሪዎቹ የሰውን ልጅ አካላዊና አእምሯዊ አሠራር የሚያውኩ 92 ችግሮችን ለይተው ያስቀመጡ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ደግሞ ካንሰርና ከልብ ጋር የተያያዙ በሽታዎች ቀዳሚውን ቦታ ይይዛሉ ብለዋል። በጥናቱ ላይ የእርጅና ስሌቶቹ የሚሠሩት ማኅበራዊ ጉዳዮችንና የሕዝብ ብዛትን ባማከለ መልኩ ሲሆን ለእያንዳንዱ ሃገር የተለያየ መለኪያ አስፈልጎ ነበር። በዚህም መሠረት አጠቃላይ የገቢ ደረጃ፣ የትምህርት ደረጃና አማካይ የተዋልዶ ምጣኔም ቢሆን ከግምት ውስጥ ገብተዋል። እነዚህ ማሳያዎችን ከግምት ውስጥ አስገብቶ የተሠራው ጥናቱ እንደሚለው የእርጅናን ከባድ ምልክቶች ቶሎ ማስተዋል የሚጀምሩት በማደግ ላይ ባሉና ባላደጉ ሃገራት የሚኖሩ ዜጎች ናቸው። የሃገራት ደረጃ ምን ይመስላል በዚህ ጥናት መሠረት ኢትዮጵያ ከዓለም ሀገራት ጋር ስትነጻጸር ሰዎች ያለዕድሜያቸው አያረጁም። እንደውም ከፍተኛ ከሚባሉት ሃገራት ተርታ ነው የምትመደበው። የጥናት ዕትሙ ያካተታቸው ከዕድሜ ጋር የሚያያዙ የጤና እክሎች በዓለም ላይ ካሉ ሰዎችን ከሚገድሉ በሽታዎች ግምሹን ይይዛሉ። • ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን? • እውን እንጀራ ሱስ ያስይዛል? ከዕድሜ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች ሁሌም ቢሆን ያለ ጊዜ ጡረታ መውጣትን ስለሚያስከትሉ የሃገራት ሠራተኛ ኃይል ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራሉ። ይህ ደግሞ ለከፍተኛ የጤና አገልግሎት ወጪና አላስፈላጊ ብክነት ይዳርጋል። ስለዚህ የሃገራት መሪዎችና የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ የእርጅና አሉታዊ ተጽእኖዎችን ለመቀነስ የተቻላቸውን ሁሉ ማድረግ አለባቸው ይላል ጥናቱ። ተመራማሪዎቹ የእርጅና ምልከቶችን ከተቻለ ማስቀረት አልያም ዘግይተው እንዲመጡ የሚያስችሉ መንገዶችን ወደ ማፈላለጉ ፊታቸውን አዙረዋል። መደረግ አለባቸው ብለው ካስቀመጧቸው ነገሮች መካከል ደግሞ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ እንደ ሲጋራ ያሉ ሱሶችን ማስወገድና የተደራጅ የህክምና አገልግሎት መፍጠር ይገኙባቸዋል።
news-49030135
https://www.bbc.com/amharic/news-49030135
አቶ ቶማስ ታማ፡ «እኔ አዞዎችን እንደቤት እንሰሳ ነው የማያቸው»
ቶማስ ታማ ይባላሉ፤ የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪ ናቸው። አዞ ማለት ለእርሳቸው የቤት እንሰሳ ነው። ለአዞ ፍቅር አላቸው፤ አዞዎችም ያውቋቸዋል፤ ይወዷቸዋል።
ለኢትዮጵያ ብርቅዬ የሆነው የአርባምንጭ አዞ እርባታ ጣብያ የተመሠረተው በ1976 ነው፤ አቶ ቶማስ ድርጅቱን የተቀላቀሉት ደግሞ 1981 ላይ፣ ድርጅቱ ገና የአምስት ዓመት ታዳጊ ሳለ ነበር። የእርባታ ጣብያው መመሥረት ዋነኛ ዓላማ በሕገ-ወጥ መንገድ አዞ እየገደሉ ቆዳ እና ስጋውን የሚሸጡ ሰዎችን ለመከላከልና በሕጋዊ መንገድ የአርባንምጭ አዞን ለመጠበቅ ነበር። ምንም እንኳ አሁን አሁን የአዞ ገበያ ቢቀዛቃዝም የአዞ እርባታ ጣብያው ሌላኛው ዓለም የውጭ ምንዛሪ ማስገኘትም ነበር፤ ከጉብኝት የሚገኘው ገቢ ሳይረሳ። • የኢትዮጵያ አዞ ቆዳና ሥጋ ገበያ አጥቷል «81 ታኅሳስ ላይ ነበር መጀመሪያ በጊዜያዊነት የተቀጠርኩት። ከዚያ 1993 ላይ በቋሚነት ተቀጠርኩ፤ ይኸው እስከዛሬ በተለያዩ ዘርፎች እያገለገልኩ አለሁኝ » ይላሉ አቶ ቶማስ፤ ጣብያውን የተቀላቀሉበትን ጊዜ ሲያስታውሱ። ታድያ በእነዚህ 30 ዓመታት አቶ ቶማስ በአዞ እርባታ ጣብያው ያላዩት ጉድ የለም። ከአዞ ጋር ውሎ ማምሸት ምን ይመስላል? «እጅግ በጣም ደስ ይላል። ከተፈጥሮ ጋር ኑሮ እጅግ ማራኪ ነው። እርግጥ ነው መጀመሪያ ላይ በጣም አስፈሪ ነበር። ኋላ ላይ ግን እየለመድነው መጣን። አሁን ሰዉ ከኦዘዎች ጋር ተስማምተን ሲያየን ይገረማል፤ ወይም ፍራቻ ያድርበታል፤ ነገር ግን እኛ ከአዞዎች ጋር ያለን ቁርኝት ደስታ ይሰጠናል።» «እኔ አዞዎችን እንደቤት እንሰሳ ነው የማያቸው» በጣም ከሚፈሩና የከፋ አደጋ ማድረስ ከሚችሉ የውሃ ውስጥ እንስሳት አዞ አንዱ መሆኑን መናገራችን አዲስ ነገር የፈጠረን ላያስመስለን ይችል ይሆናል። አዞ የቤት እንሰሳ መሆን ይችላል ብለን አፍ ሞልተን ማውራቱም አያዋጣንም። አቶ ቶማስ ግን ይላሉ. . . «አዞ እንደቤት እንሰሳ ነው።» • ወንዶች አዞ ለመምሰል ቆዳቸውን የሚበሱባት ሃገር «ሰዎች ሁሌም የሚሉን ነገር ቢኖር አዞ እኮ ጨካኝ ነው። እንዴት ከአዞ ጋር ትሠራላችሁ ነው። እኔን ጨምሮ እዚህ 'ራንች' ውስጥ ለምንሠራ ሠራተኞች ግን አዞ እንደቤት እንሰሳ ነው። እየተንከባከብን ስለምናሳድጋቸው፤ ቀናቸውን ከእኛ ጋር ስለሚያሳልፉ በጣም ይለምዱናል፤ ልክ እንደቤት እንሰሳ። በጣም የሚቀርቡና ፍቅር ያላቸው ናቸው።» አርባምንጭ አዞ እርባታ ውስጥ የሚገኙ አዞዎች ገና ከእንቁላላቸው እንተደፈለፈሉ ነው ወደ መጠበቂያ ጣብያው የሚመጡት። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የሚያስፈልጋቸው እንክብካቤ እየተደረገላቸው እንደ እድሜያቸው በመከፋፈል አንድ ላይ እንዲያድጉ ይደረጋሉ። አቶ ቶማስ እና ባልደረቦቻቸውም አዞዎቹን ከጨቅላ ዕድሜያቸው ጀምሮ ነው የሚያውቋቸው፤ አዞዎቹም እንዲሁ። «ስጋዬ ተቦጭቆ ሆስፒታል ገብቼ ነበር» ጊዜው 1989፤ የዚያኔ አዞ እርባታው አሁን ከሠፈረበት አካባቢ ፈንጠር ብሎ የሚገኝ ቦታ ላይ ነበር የተገነባው። የቀድሞው ሥፍራ የአዞዎች ሰፊ መኖሪያ ለሆነው የአባያ ሐይቅ እጅጉን የቀረበ ነበር። ታድያ ክረምት ሲገባ በአዞ እርባታ ታላቅ ሰቀቀን ይሰፍናል፤ አባያ ሐይቅ እየሞላ የአዞዎቹን ገንዳ ይጎበኛል። አንዳንዴም ሞልቶ ሲፈስ አጋጣሚውን የተጠቀሙ አዞዎች ወደ ጥልቁ ሐይቅ ይጠልቃሉ። «. . . እና ሐይቁ ሲሞላና ግቢውን ሲያጥለቀልቀው በጀልባ እየቀዘፍን ነበር የምንሠራው። ያኔ እኔ የአዞዎቹን ውሃ እየቀየርኩ ነበር። የቀድሞው ግቢ ሰው እንዲረማመድበት ተብሎ የተሠራ የእንጨት ድልድይ ነበር። ከድልድዩ ላይ ወደነሱ ለመውረድ ቀኝ እግሬን ስሰድ ከሥር ተደብቆ የነበረ አንድ አዞ ዘሎ ያዘኝ። ይሄኔ በድንጋጤ እግሬን ብድግ ሳደርግ እግሬን እንደያዘ ተነሳና ስጋዬን ቦጭቆ ጣለው። ከዚያ ስጮህ የሰሙ ጓደኞቼ መጥተው በጨርቅ ጉዳት የደረሰበትን ቦታ ጠምጥመው ወደ ሆስፒታል ወሰዱኝ።» «ከፍተኛ ጉዳት ነበር የደረሰብኝ። እርግጥ ነው አጥንቴ አልተነካም ግን ከጉልበቴ በታች ስጋዬን ቦጭቆብኛል።» እና ተመልሰው ወደ አዞዎች ጋር መጠጋት አላስፈራዎትም? «ሰፈር ውስጥ ያሉ ሰዎች፣ ጎረቤቶችም እንደዛ ነበር ያሉኝ፤ 'ሁለተኛ ይሄን ሥራ ብለህ ወደ እርባታ ጣብያው እንዳትመለስ፤ ሕይወትህን ሁላ ልታጣ ትችላለህ' ነበር ያሉኝ። ቢሆንም ቁስሉ ሲሽርልኝ ተመልሼ መጣሁ።» የአዞ ስጋ እርግጥ ኢትዮጵያ በርካታ ሥፍራዎች የአዞ ስጋ መመገብ ከባሕል እንደማንፈንገጥ ይቆጠር እንጂ ሌሎች ሀገራት በሰልፍ እንኳ የማይገኝ ምግብ መሆኑን ሰምተናል። ቅርጥፍ አድርገው የበሉም ሞልተዋል። ለአቶ ቶማስ፤ የአዞ ስጋ ቀምሰው ያውቃሉ? የሚል ጥያቄ ስናቀርብላቸው በፈገግታ በመታጀብ ነበር የመለሱልን። «እንግዲህ በኃይማኖታችንም ይሁን በባሕል የአዞ ስጋ መብላት ብዙ አይመከረም። ቢሆንም እኔ ቀምሼ አውቃለሁ። ያው ጣዕሙ እንደ ዓሳ ነው፤ በተለይ ተጠብሶ በጥሩ ሁኔታ ሲቀርብ። መልኩም ቢሆን ነጣ ያለ ነው። ግን ጥርስ ላይ ትንሽ ጠንከር ይላል። በጥሩ ሁኔታ ከተሠራ ይጣፍጣል። እና ቀምሻለሁ ውሸት መናገር አያስፈልግም. . .[ሳቅ]» ከእርሳቸውና ባልደረቦቻቸው ውጭ ወደ ጣብያው ለጉብኝት የሚመጡ ኢትዮጵያውያን የአዞ ስጋ ለመብላት እንደማይደፍሩ አቶ ቶማስ ሹክ ብለውናል። ነገር ግን በዓላትን አስታከው የሚመጡ የውጭ ሃገር ዜጎች፤ በተለይ ደግሞ ቻይናውይንና እና ጣልያናውያን አልፎ አልፎ መጥተው አዞ ገዝተው ካስበለቱ በኋላ ስጋውን አስጠብሰው እንደሚመገቡ አልደበቁንም። አንድ ጫማውን ለአዞ የገበረው ጎብኝ ክብሩ ይስፋ በጎብኝዎች አካል ላይ የደረሰ ጉዳት እኔ እስካማስታውሰው ድረስ አጋጥሞ አያውቅም ይላሉ አቶ ቶማስ። ነገር ግን አንዳንድ ዕቃዎች ከእጃቸው ከወደቁ የመመለሳቸው ዕድል ኢምንት መሆኑን ነግረውናል። «ለምሳሌ አንድ ጎብኝ አንድ ጊዜ ኦዞዎቹ ሲንቀሳቀሱ ማየት ፈልጎ እግሩን ሲያወዛውዝ ጫማው ወደ ገንዳው ውስጥ ይወድቅበታል። ይሄኔ ኦዘዎቹ ተረባርበው ጫማውን ይዘው ውሃው ውስጥ ገቡ። አንድ ነገር ከያዙ ደግሞ አይለቁም። እና ጎብኚው በአንድ እግር ጫማ መመለሱን አልረሳም [ፈገግ]።» «ከዚህ ውጭ ተንቀሳቃሽ ስልኮች እና ካሜራዎች ወድቀውባቸው ከጥቅም ውጭ የሆኑባቸው ጎብኝዎች አውቃለሁ። አንድ ጎብኝ ደግሞ ሸሚዙን አውልቆ ሲያውለበልብ ዘለው ነጥቀውታል። ምንም እንኳ እኛ ጎብኝዎች እነዚህን ነገሮች እንዳያደርጉ በፅሑፍም በቃልም ብናስጠነቅቅም።» ታድያ የአቶ ቶማስ ሥራ አዞዎችን መንከባከብ ብቻ አይደለም። ለእርድ የደረሱ አዞዎችን አርዶ መበለትንም ተክነውበታል። የአዞ ቆዳን ፍቆ በጨው ዘፍዝፎ ለጥቅም እንዲውል ማድረግም ጥርሳቸውን የነቀሉበት ሙያ ነው። አቶ ቶማስ የስድስት ልጆች አባት ናቸው። ከአዞ መንጋ ጋር ተጋፍጠው በሚያገኙት ገቢ ቤተሰቦቻቸውን ያስተዳድራሉ። ጎብኝዎች አቶ ቶማስና ባልደረቦቻቸው ከአዞዎች ጋር እየተጋፉ ገንዳ ሲያፀዱ እና ሲንከባከቡ ሲመለከቱ በአድናቆት ይመለከታሉ። አቶ ቶማስ ግን ከቤት እንሰሳዎቻቸው ጋር በፍቅር 30 ዓመት ኖረዋል። ታድያ ይህ ፍቅራቸው በቅርቡ የሚያበቃም አይመስልም።
news-56087617
https://www.bbc.com/amharic/news-56087617
በተቃውሞ በምትናጠው ሚየንማር አን ሳን ሱቺ ተጨማሪ ክስ ቀረበባቸው
ከስልጣን በኃይል የተገረሰሱትና በእስር ላይ የሚገኙት የሚየንማር መሪ አን ሳን ሱቺ አዲስ ክስ ቀርቦባቸዋል።
በትናንትናው ዕለት በበይነ መረብ አማካኝነት ቀርበው ክሳቸው በቪዲዮ ተነቦላቸዋል። በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ ህገ -ወጥ የመገናኛ ዘዴዎች እንደ ዋኪ ቶኪ በመያዝ ክስ ተከሰው የነበረ ሲሆን በትናንትናው ዕለት ደግሞ የአገሪቱን የተፈጥሮ አደጋዎች ህግ በመጣስ ወንጀል ተከሰዋል። ምንም እንኳን የተፈጥሮ አደጋዎች ህግ ጥሰዋል ቢባልም ዝርዝር መረጃ እስካሁን አልቀረበም። አገሪቷ መፈንቅለ መንግሥት ከተከሰተባት እለት ጀምሮ በአደባባይ ተቃውሞዎች እየተናጠች ሲሆን ጦሩም አዲስ ምርጫ እንደሚያካሂድ ቃል ገብቷል። ሆኖም ተቃዋሚዎቹ አን ሳን ሱቺን ጨምሮ በምርጫ ያሸነፉ መሪዎቻችን ይፈቱ በሚለው ጥያቄ ፀንተውበታል። በባለፉት ሳምንታት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአደባባይ ተቃውሞ አንስተዋል።ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር መመለስ አለበት በማለት ጥሪያቸውን እያሰሙ ነው። ተቃዋሚዎቹ በቀድሞዋ በርማ በአሁኗ ሚየንማር የተላለፈውን የስብሰባ እግድ በመጣስ ነው ተቃውሟቸውን እየገለፁ ያሉት። ስልጣን በኃይል የተቆጣጠረው ጦር ያንጎንና ማንዳላይ በመሳሰሉ ከተሞች ከአምስት ሰዎች በላይ መሰብሰብ አይቻልም የሚል ትዕዛዝ ከማስተላለፍ በተጨማሪ የሰዓት እላፊ አዋጅ ጥሏል። ስልጣን በኃይል ከጨበጠ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ጦሩ ባካሄደው ጋዜጣዊ መግለጫ ቃለ አቀባዩ ብርጋዲየር ጄነራል ዛው ሚን ቱን እንዳሉት ወታደራዊው ኃይል በስልጣን ለረዥም ጊዜ እንደማይቆይ ተናግረዋል። በሚመጣው ምርጫ "ለአሸናፊው ፓርቲ ስልጣን እናስረክባለን" ሲሉ ቃል ገብተዋል። ነገር ግን ምርጫው መቼ እንደሚካሄድ ትክክለኛ ቀን አልተሰጠም። በዚሁ ቀን እንዲሁ በርካታ የጦሩ አባላት በተደጋጋሚ እንደሚናገሩት ቃለ አቀባዩም አገሪቱ ባለፈው ህዳር ያደረገችው ምርጫ የተጭበረበረ ነው ብለዋል። ለዚህ ንግግራቸው አባሪ አቅርበው ያደረጉት መረጃ የለም። የአን ሳን ሱቺ ፓርቲ ናሽናል ሊግ ፎር ዲሞክራሲ ፓርቲ በከፍተኛ ድምፅ አሸንፎ መንግሥት መመስረት የቻለ ሲሆን ጦሩ በበኩሉ ተጭበርብሯል ከማለት አልፎ ለመፈንቅለ መንግሥቱንም እንደ ምክንያትነት ያቀርበዋል። የአን ሳን ሱቺን ክስ አስመልክቶ ብሪታንያና አሜሪካ ትችታቸውን ሰንዝረዋል። የብሪታንያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ክሱ "የተፈጠረና ሰብዓዊ መብቷን የሚጥስ" ያሉት ሲሆን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃለ አቀባይ በበኩላቸው "የሚረብሽ ነው" ብለውታል። በቅርቡም የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በሚየንማር መፈንቅለ መንግሥት አመራሮች ላይ ማዕቀብ መጣል የሚያስችላቸውን ትእዛዝ አስተላልፈዋል። ጆ ባይደን ያሳለፉት እቀባ የጦሩ አመራሮች፣ ቤተሰቦቻቸውና ከነሱ ጋር የንግድ ሽርኪያ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉት ሁሉ ላይ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በአሜሪካ ተቀማጭ የሆነ የሚየንማር 1 ቢሊዮን ዶላር ገንዘብ ጦሩ እንዳያገኘው ለማድረግ እግድ ለመጣል በሂደት ላይ ነው ተብሏል። ጆ ባይደን መፈንቅለ መንግሥቱ እንዲቀለበስና መሪዋን አንግ ሳን ሱቺን ጨምሮ በእስር ላይ ያሉት የሲቪል አመራሮች እንዲፈቱ ጠይዋል።
46698729
https://www.bbc.com/amharic/46698729
የቴክኖሎጂ ተቋማት ግላዊ መረጃዎትን ያለአግባብ እንደሚጠቀሙበት ያውቃሉ?
ግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋማት የተጠቃሚዎቻቸውን ግላዊ መረጃ ያለአግባብ እየተጠቀሙበት መሆኑ የቴክኖሎጂን በጎ ገጽታ እያጠለሸው እንዳለ የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽነር ማርጋሬት ቬስታጋር ይገልጻሉ።
ማርጋሬት ቬስታጋር ሊገባደድ ጥቂት ቀናት የቀሩትን 2018 ወደ ኋላ መለስ ብለው ሲቃኙ፤ የቴክኖሎጂ ተቋማት የመረጃ አጠቃቀምን ይተቻሉ። እነዚህ ተቋማት የተጠቃሚዎችን መረጃ ያለአግባብ በመጠቀም የግለሰቦችን ነጻነት እየገፈፉ ነው። • ፌስቡክ የተጠቃሚዎችን ግላዊ መረጃ መበርበሩን አመነ • ፌስቡክ የትራምፕን ክስ ውድቅ አደረገ ተቋማቱ አወንታዊ ሚና ሊኖራቸው ቢገባም፤ ሚናቸው ተሸርሽሮ የተጠቃሚዎችን መረጃን ያለ ፈቃድ በማግኘት ያለአግባብ ተጠቅመዋል። ማርጋሬት ቬስታጋር "ለሰዎች ግላዊ መብት ዋጋ አልተሰጠም። መብታቸው እየተጣሰ ነው" ብለው አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። እንደ ማጣቀሻ በ2018 የተጠቃሚዎች መረጃ የተመዘበሩባቸው አጋጣሚዎችን እንመልከት። የ2018 የቴክኖሎጂ ተቋሞች ቅሌቶች የእነዚህ ተቋማት ተግባር፤ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በማኅበረሰቡ ዘንድ ያላቸውን ቦታ እያሳጡ መጥተዋል። • የፌስቡክ ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ ጨመረ • ግጭትን ለማባባስ ፌስቡክ ጥቅም ላይ ውሏል ተባለ የአውሮፓ ኅብረት የመረጃ ጥበቃ ሰነድ የሆነው 'ጄነራል ዳታ ፕሮቴክሽን'፤ የሰዎች ግላዊ ነጻነት እንዲጠበቅ እንዲሁም መረጃዎቻቸውም እንዳይጋለጡ የሚያስችል ማዕቀፍ አውጥቷል። ሆኖም ማርጋሬት ቬስታጋር የበለጠ መሥራት እንደሚያሻ ይናገራሉ። ግለሰቦች በቴክኖሎጂያዊ መሳሪያዎች ከሚጭኗቸው፣ አስተያየት ከሚሰጡባቸው ወይም ከሚጋሯቸው ነገሮች መረጃ በመሰብሰብ እየተጠቀሙ የሚገኙ የቴክኖሎጂ ተቋማት አሰራራቸውን ግልጽ የሚያደርጉበት መንገድ መፈለግ ይኖርባቸዋል ይላሉ። ስለ መረጃና መረጃን ለሌላ ወገን የማስተላለፍ ሂደት ግልጽ አሰራር ከሌለ፤ ጥቂት ግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋማት የግለሰቦች መረጃ መቆጣጠራቸው አይቀርም። ማርጋሬት ቬስታጋር፤ የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ትልልቅ የቴክኖሎጂ ተቋማት መረጃ የሚያገኙበትን መንገድ መፈተሽ ጉልበታቸውን መገደብ ይችላል ሲሉ መፍትሄ ያስቀምጣሉ።
news-50731121
https://www.bbc.com/amharic/news-50731121
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት፡ "የአማራ ሕዝብ የወሰንና ማንነት ጥያቄዎች የክልሉ መንግሥትም ጥያቄዎች ናቸው"
ከአስተዳደር እና ማንነት ጉዳዮች ጋር የሚነሱ ጥያቄዎች በሠላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ጥረት እንደሚያደርግ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስታወቀ።
ከሠላም እና ደኅንነት፤ ወቅታዊ የግብርና ተግባር እና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት መግለጫ ሰጥቷል። መግለጫውን የሰጡት የጽህፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌትነት ይርሳው እንዳሉት "የአማራ ህዝብ ከወሰን እና ማንነት ጋር ተያይዞ ጥያቄዎችን ያነሳው ዛሬ ብቻ አይደለም። ለዘመናት የነበሩ ጥያቄዎች ናቸው። የክልሉ መንግሥትም ጥያቄዎች ናቸው" ብለዋል። • ከ20 ዓመት በኋላ የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆናል? • "አሸባሪዎችና ጽንፈኞች በአፍሪካ ቀንድ ጠንካራ መሰረት ለመጣል እየጣሩ ነው" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ • የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የኖቤል ሽልማትን በመቃወም ኤርትራውያን በኦስሎ ሰልፍ ወጡ በዚህም የክልሉ መንግሥት ከአስተዳደር ወሰንና ማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ጋር በመሆን በእውነት ላይ ተመስርቶ የሕብረተሰቡን ጥያቄ እስከ መጨረሻው ለመፍታት ጥረት እንደሚያደርግ ገልጸዋል። "ክልሉ ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ መፈታት አለባቸው የሚል ጽኑ እምነት አለው" ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ጥያቄዎቹን በሠላማዊ መንገድ ለመፍታት ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ተሳትፎ ያደርጋል ብለዋል። በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶችን ለመፍታት ደግሞ ውይይቶች እና እርቆች መካሄዳቸውን በመጠቆም የሠላምና ደኅንነት ሥራው ባለፉት ጊዜያት በተሻለ ሁኔታ ክልሉን ሠላማዊ ለማድረግ የተሻሉ ሥራዎች ተከናውነዋል። 130 የቅማንት የማንነት ኮሚቴ አባላት የተደረገላቸውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው መግባታቸውን በመግለፅ፤ በአካባቢዎቹ እንቅስቃሴዎች በተለመደው ሠላም እንዲቀጥሉ በመደበኛነት እንደሚሠራም አስታውቀዋል። በክልሉ በሚገኙ 10 ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ተማሪዎች በሠላማዊ መንገድ እንዲማሩ ጥረቶች እየተካሄዱ መሆኑን አቶ ጌትነት ጠቁመው "ሊማሩ የሚመጡ ልጆች ወደ ክልሉ ከመጡ በኋላ የራሳችን ልጆች ናቸው። ተማሪዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ሁሉም ሊያወግዘው ይገባልም" ብለዋል። በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልለዊ መንግሥት የሚማሩ የክልሉ ተማሪዎች ደህንነታቸው እንዲጠበቅ በጋራ እየሠራን ነው ብለዋል። የአንበጣ መንጋ እና ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በደረሱ ሰብሎች ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ የተቀናጀ ሥራ በመከናወን ላይ መሆኑንም በመግለጫቸው ጠቁመዋል።
news-44948969
https://www.bbc.com/amharic/news-44948969
የኤምሬትስና የአፍሪካ ቀንድ የገንዘብ ፖለቲካ?
ትናንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መዲና አቡዳቢ ተገናኝተዋል።
መሪዎቹ ከአልጋ ወራሹ ልዑል ሼክ መሃመድ ቢን ዘይድ ጋር በሁለትዮሽ ስምምነቶችና በቀጠናው ጉዳይ መወያየታቸውን እንዲሁም የሁለቱ ሃገራት መሪዎች በመካከላቸው ሰላም እንዲወርድ በማድረጋቸው ልዑሉ የሃገራቸውን ከፍተኛ ሜዳልያ እንደሰጧቸው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል። •ኢትዮጵያ በዱቤ ተጨማሪ ነዳጅ ከሳኡዲ አረቢያ ጠየቀች •"ኢህአዴግ ተዳክሟል ብላችሁ እንዳትሳሳቱ" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በጉዞ በተጨናነቀው አጭር የስልጣን ዘመናቸው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስን ሁለት ጊዜ እንዲሁም ሳዑዲ አረብያን መጎብኘታቸው ይታወሳል። የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጉብኝት ተከትሎ የተባበሩት ኤምሬትስ በቀጥታ ወደ ማእከላዊ ባንክ የሚገባ እንዲሁም በውጭ የቀጥተኛ ኢንቨስትመንት መልክ ለኢትዮጵያ በጥቅሉ 3 ቢሊዮን ዶላር ለመስጠት መስማማቷም ይታወቃል። የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በአጠቃላይ የባህረ ሰላጤው አገራት ከአፍሪካ ቀንድ አገራት ጋር ግንኙነታቸውን እያጣደፉ መሆኑ ምን ያሳያል? በአካባቢው ፖለቲካ ላይስ ምን አይነት ተፅእኖ ያሳድራል? •ዶላር በጥቁር ገበያ ለምን ቀነሰ? •የዲያስፖራው አንድ ዶላር የባህረ ሰላጤው አገራት ፍላጎት ለምን ናረ? በመልክአ ምድር ሲታይ የአፍሪካ ቀንድ ለመካከለኛው ምሥራቅ እጅግ ቅርብ የሚባል ነው። ይህ ሁኔታ አካባቢውን ቁልፍ ቦታ አድርጎታል። ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የባህረ ሰላጤው የአፍሪካ ቀንድ ቅርምት ፍላጎት እየጋመ መጥቷል። ለምን? በኬል ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህር የሆኑት ዶ/ር አወል አሎ ሁለት አካባቢያዊና ዓለም አቀፋዊ ምክንያቶችን ያነሳሉ። በኢራን የሚመራው የሺዓ ሃይማኖታዊ ቀኖና ቡድን እና በሳኡዲ ከሚመራው የሱኒ ጥምረት ጋር ያለው ፖለቲካዊ ልዩነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ መጥቷል። የዚህ ልዩነት ነጸብራቅ የመን ላይ እየተካሄደ ያለው የውክልና ጦርነት በይበልጥ ይገልጸዋል። እነ ሳኡዲ ኤርትራና ጅቡቲ ወርደው ወደቦችን ሲያለሙ ለሸቀጥ ማራገፊያ ብቻ እንዳልሆነ የሚናገሩት ዶ/ር አወል" አንድ አገር የሌላ አገር ሄዶ ወደብ ሲያለማራ ትልቅ ኢንቨስትመንት ነው። በዚህ አካባቢ ደግሞ የወደብ ልማቶቹ የኮኖሚያዊ ብቻ ሳይሆን ፖለቲካዊ እንድምታ አላቸው"ይላሉ። ታዲያ እነዚህ በበርካታ ሪያል ወደብ የተሠራላቸው አገሮች ውለታ ሲጠየቁ እምቢ የሚሉበት እድል እምብዛም እንደሆነ ያመለክታሉ። ከፖለቲካ አንጻር ጫና ውስጥ እንደሚከታቸውም ዶ/ር አወል አክለው ይናገራሉ። ከዚህም ባሻገር ጦርነቱ አድማሱ እየሰፋ መምጣቱና የአካባቢው ፖለቲካ እየተቀየረ መሆኑ የባህረ ሰላጤው የአፍሪካ ቀንድን ቸል እንዲሉት አልሆነም። •የዶክተር ዐብይ አሕመድ 'ፑሽ አፕ' የሪያል ፖለቲካ ዶ/ር አወል በአፍሪካ ቀንድና በባህረ ሰላጤው አገሮች ያለውን ግንኙነት ጥቅል ባሕሪያቸውን በመግለጽ ይጀምራሉ። አብዛኛው የባህረ ሰላጤው አገሮች ሊሰጡ የሚችሉትና አፍሪካ አገሮች የሌላቸው ጥሬ ገንዘብ ነው። ለሶማሊያና ለኤርትራ ቀጥተኛ የሆነ የበጀት ድጎማ እስከማድረግ የደረሱትም ለዚሁ ነው። በምላሹ ታዲያ የባህረ ሰላጤው አገሮች ፍጹማዊ የፖለቲካ ታማኝነት መጠበቃቸው አልቀረም። ለዚህም ነው ግንኙነቱ "የሪያል ፖለቲካ" የሚለውን ስያሜ የያዘው። " የባህረ ሰላጤው ፖለቲካ ትራንዛክሽናል ነው" የሚሉት ዶ/ር አወል ግንኙነቱ ከዲፕሎማሲ ይልቅ ይሄን አድርጌልኻለሁና ያንን አድርግልኝ በሚል የገንዘብ ውለታ መቀፍደዱ የራሱ አሉታዊ ጎን እንደሚኖረው አልሸሸጉም። የአፍሪካ ቀንድ አገሮች ከዚህ ግንኙነት ምን ያተርፋሉ? ምን ያጣሉ የሚለው ጥያቄም የሚመለሰው በዚሁ የግንኙነት መርህ ነው። ሁለቱም ወገኖች አገራዊ ጥቅም ላይ የተመሠረተ ዘላቂ ግንኙነትን ካስቀደሙ ሁለቱም ወገኖች ይጠቀማሉ። ነገር ግን የአፍሪካ ቀንድ አገራት ፖለቲካዊ ተቋማት ያለባቸው ድክመት ሲታይና የባህረ ሰላጤ አገራት ላይ ያለው የፖለቲካ ባህል ሲታይ የሕዝቦቻቸውን ጥቅም የሚያስጠብቅ ግንኙነት ላይሆን እንደሚችል ምሁሩ ይገምታሉ። ያም ኾኖ ግንኙነቱ አሉታዊ ነው ብለው አይደመድሙም። "አዲስ ግንኙነት (ኢንጌጅመነት) ነው፤ ገና ጊዜ ወስዶ ማየት ያስፈልጋል።" ይላሉ። የተባበሩት ኤምሬትስ አዲስ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ? በለንደን የሚገኙት ኤርትራዊው የፖለቲካ ተንታኝ አቶ አብዱራህማን ሰኢድ ከባህረ ሰላጤው አገራት አንዷ የሆነችው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ካለፉት ጥቂት ጊዜአት ወዲህ አዲስ የውጭ ሃገር ፖሊሲ እየተከተለች መሆኗንና በዚህም ባለችበት አካባቢ ከፖለቲካ ገለልተኝነት ወደ ፖለቲካዊ ተሳትፎ እየመጣች መሆኑን በቀዳሚነት ይጠቅሳሉ። ቀጥለውም የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አገራት ከሳኡዲ አረብያ ጋር በመሆን የመን ውስጥ እያካሄዱት ያለውን ጦርነት፣ ኤምሬቶቹ እንደ ኤርትራ ባሉ የአፍሪካ ቀንድ አገራት የባህር ሃይል ጣቢያ መገንባትን በማሳያነት ያነሳሉ። እሳቸው እንደሚሉት የእነዚህ የባህረ ሰላጤው ቡድን አገራት በሌላኛው ወገን ካለው ኢራንና ኳታር ምድብ አገራት ጋር ከፍተኛ እሰጥ አገባና የፖለቲካ ተፅእኖ መገፋፋት ላይ መሆናቸው ወሳኝ ሁነት ነው። "ከእነዚህ አገራት ጋር የሚፈጠር ወታደራዊ ግንኙነት አደጋ ይኖረዋል።አደጋው እነዚህ አገራት ወደ ጦርነት ሲገቡ የአፍሪካ ቀንድ አገራትም በተዘዋዋሪ ጦርነቱ ውስጥ መግባታቸው ነው" በማለት ወታደርም ባትልክ በየመን ጦርነት የኤርትራ እጅ አዙር ተሳትፎን በምሳሌነት ይጠቅሳሉ። ይህን የባህረ ሰላጤው አገራት የፖለቲካ ፍትጊያ ታሳቢ በማድረግ ለአፍሪካ ቀንድ አገራት ኤርትራ ፣ ኢትዮጵያ ፣ ሶማሊያና ጅቡቲም ሆነ ኬንያና ሱዳን ከአገራቱ ጋር የሚደረግ ጥብቅ ግንኙነት ጊዜያዊ እንጂ ዘለቄታዊ ጥቅም እንደሌለው ይደመድማሉ። የአፍሪካ ቀንድ ሃገራት የግንኙነቱን አደጋ በመቀነስ ተጠቃሚነታቸውን ሊያረጋግጡ የሚችሉበት መንገድ ለሳቸው አንድና አንድ ነው። አገራቱ በተናጠል ሳይሆን እንደ ምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ድርጅት ኢጋድ አባልነት አንድ ላይ በመቆም ከባህረ ሰላጤው አገራት ሊመጣባቸው የሚችለውን ተፅእኖ ሊገቱት እንደሚችሉ ያምናሉ።
news-49317094
https://www.bbc.com/amharic/news-49317094
በጥይት ተመትተው የነበሩት ጄነራል ስብሐት ኤፍሬም ወደ ኤርትራ ተመለሱ
ባለፈው ታኅሳስ ወር ላይ ማንነቱ ባልተገለጸ ግለሰብ በጥይት ተመትተው ውጪ ሃገር በህክምና ላይ የቆዩት የኤርትራው ኃይልና ማዕድን ሚኒስትር ጄነራል ስብሐት ኤፍሬም ወደ ሃገራቸው እንደተመለሱ ተገለጸ።
ጉዳዩን በተመለከተ ከመጀመሪያው አንስቶ በጄኔራሉ ላይ ስለደረሰው ጥቃት በትዊተር ገጻቸው ላይ መረጃ ሲሰጡ የነበሩት በጃፓን የኤርትራ አምባሳደር አቶ እስጢፋኖስ አፈወርቅ እንዳሰፈሩት ጄነራል ስብሐት ኤፍሬም ህክምናቸውን አጠናቀው ተመልሰዋል። • የኤርትራውን ሚኒስትር በጥይት ያቆሰለው መያዙ ተነገረ • ኤርትራ በሳዋ ባደረገችው ወታደራዊ ትዕይንት ምን እያለች ይሆን? አምባሳደር እስጢፋኖስ በትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት "ጄነራል ስብሐት ኤፍሬም በውጪ ሃገር ሲከታተሉ የነበረውን ህክምና በተሳካ ሁኔታ አጠናቀው ከሚወዱት ቤተሰባቸው ጋር ወደ አሥመራ መመለሳቸውን በመስማቴ ደስተኛ ነኝ" ብለዋል። የኤርትራ መንግሥት በጄነራሉ ላይ ስለተፈጸመው ጥቃትም ሆነ አሁን ህክምናቸውን ጨርሰው ስለመመለሳቸው በይፋ እስካሁን ያለው ነገር የለም። ጄነራል ስብሐት ኤፍሬም ላይ ደረሰ የተባለው ጥቃት በመኖሪያ ቤታቸው አካባቢ አድብቶ በነበረ አንድ ግለሰብ መፈፀሙንና ግለሰቡም በቁጥጥር ስር እንደዋለ በወቅቱ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ከአሥመራ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። • ኤርትራ፡ ''እናቶች ከህጻናት ልጆቻቸው ጋር ታስረዋል'' • መስመር ያልያዘው የኢትዮ-ኤርትራ የንግድ ግንኙነት ወዴት ያመራል? ጄነራሉ ጥቃቱ ከተፈጸመባቸው በኋላ የተባበሩት አረብ ኤምሬት ውስጥ የሚገኝ ነገር ግን ስሙ ያልተጠቀሰ ሆስፒታል ውስጥ ከፍተኛ ህክምና እንዲያገኙ መወሰዳቸው ሲገለጽ ቆይቷል። ጄኔራል ስብሐት የኃይልና ማዕድን ሚኒስትር ከመሆናቸው ቀደም ብሎ ለ19 ዓመታት የመከላከያ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩ ሲሆን፤ ከዚያ በፊት ደግሞ የአሥመራ ከተማ አስተዳደርና የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ነበሩ። ጄኔራል ስብሐት ኤፍሬም ከሕዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ ከፍተኛ አመራሮች አንዱ ሲሆኑ የፖለቲካ ጽህፈት ቤት አባልም ናቸው።
news-41715264
https://www.bbc.com/amharic/news-41715264
በቡኖ በደሌ የተከሰተው ምንድን ነው?
ባሳለፍነው ሳምንት መገባደጃ በኦሮሚያ ክልል በቡኖ በደሌ ዞን የተደረገ ሰልፍን ተከትሎ በተከሰተው ሁከት እና ግጭት በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ ከተለያዩ ምንጭች እየወጡ ያሉ መረጃዎች እስካሁን ድረስ አወዛጋቢ ሆነዋል።
ቢቢሲ ጉዳዩን ለማጣራት እና ተጨባጭ መረጃ ለማግኝት የተለያዩ አካላትን አነጋግሯል። የበደሌን ከተማን ጨምሮ በዞኑ በተለያዩ ስፈራዎች ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ቀናት ላይ ሰልፎች ተካሂደው ነበር። ሰልፉን ተከትሎ በተነሳ ግርግር በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን አረጋግጠናል። ከኦሮሚያ እና አማራ ክልል ሃላፊዎች የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው በግጭቱ ምክንያት እስካሁን የጠፋው የሰው ህይወት ቁጥር አስራ አንድ ሲሉ፤ ያልተረጋገጡ ምንጮች ግን ቁጥሩን ከዚያ በላይ ያደርጉታል። ክስተቱን ተከትሎ ነዋሪዎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው ወደ ተለያዩ ቦታዎች በመሸሽ በፖሊስ ጣቢያ እና በእምነት ተቋማት ተጠልለው እንደሚገኙ ያነጋገርናቸው ግለሰቦች ገልፀዋል። በጥቃቱ ንብረታቸው የወደመ እና ለህይወታቸው ሰግተው በዲጋ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ከሚገኙ ሰዎች መካከል ቢቢሲ ያናገራቸው ግለሰቦች የትግራይ ተወላጆችም ከሞቱት መካከል ናቸው ቢሉንም፤ የፖሊስ ጣቢያው ምክትል ኮማንደር ሳጅን ኢተፋ መዝገቡ ግን ሟቾቹ ከኦሮሞና አማራ ወገን መሆናቸውን ተናግረዋል። ሳጅን ኢተፋ ጨምረው እንደገለፁት በዲጋ ወረዳ ብቻ የ9 ሰዎች ህይወት መጥፋቱን ተናግረዋል። በተጨማሪም ሰባት መቶ የሚሆኑ የትግራይና የአማራ ተወላጆች በፖሊስ ጣቢያው ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኝ ገልፀዋል። ከአቶ ተመስገን አያና የቡኖ በደሌ ዞን የፀጥታና አስተዳደር ጉዳዮች ሃላፊ እንዲሁም ከዞኑ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ሃላፊን አቶ ሌይኩን ተካልኝ ጋር ባደረግነው ቆይታ በበደሌ ከተማ፣ በጮራ እና ዴጋ ወረዳዎች ማን እንደጠራቸው የማይታወቁ ያሏቸው ሰልፎች ተካሂደው እንደነበር አረጋግጠውልናል። ከፀጥታ ቢሮ እና ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊዎች መረዳት አንደቻልነው በሰልፉ ምክንያት የተፈጠረው ሁከት ወደ ዘረፋ እና ንብረት ማውደም መሸጋገሩን ተናግረዋል። አቶ ተመሰገን እንደሚሉት ግለሰቦች ንብረታቸውን ከዝርፊያ እና ከጥፋት ለመጠበቅ ሲሉ በከፈቱት ተኩስ አንዲሁም በዞኑ በተለያዩ አከባቢዎች በተፈጠሩ ሁከቶች የ11 ሰዎች ህይወት አልፏል። የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ በቡኖ በደሌ ዞን ጮራ እና ዴጋ ወረዳዎች በተከሰተው ሁከት 8 የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች እና 3 የአማራ ብሔር ተወላጆች መሞታቸውን አረጋግጠዋል። ''ይህን አስነዋሪ ድርጊት እናወግዛለን የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እየገለፅን ለተጎጂ ቤተሰቦች መፅናናትን እንመኛለን'' ብለዋል። አቶ አዲሱ ይህን ጥቃት የሚፈፅሙት እናማን እንደሆኑ በግልፅ ባያስቀምጡም ''የኦሮሚያ ክልል የህዝብን ጥቅም ለማስከበር እየወሰደ ያለው ተግባር ያላስደሰታቸው አካላት ናቸው'' ሲሉ ይገልጿቸዋል። በተመሳሳይ መልኩ የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በፌስቡክ ገፃቸው በቡኖ በደሌ የተከሰተውን ግጭት የክልሉ መንግሥት በቅርበት እየተከታተለው እንደሆነ አመልክተው ሟቾቹን በተመለከተ ከአቶ አዲሱ ጋር ተመሳሳይ መረጃ ሰጥተዋል። አቶ ንጉሱ ጨምረውም ግጭቱን የብሔር መልክ በማስያዝ እውነታውን በማዛባት የሚደረገው ዘገባ የበለጠ ጉዳት እንጂ ሌላ ጥቅም የለውም ብለዋል። የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ ጥቅምት 11/2010 ለኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ በሰጡት መግለጫ ''በክልሉ እየተስተዋሉ ያሉት ግጭቶችን እናወግዛለን። እንዲህ አይነቱ ድርጊት የኦሮሞን ህዝበ የሚጠቅም አይደለም፤ ፈፃሚዎቹም የኦሮሞ ህዝብ ጠላት የሆኑ ቡድኖች ናቸው'' ብለዋል። ችግሩን ለመፈታት የክልሉ መንግሥት የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሆነ አቶ ለማ ጨምረው ተናግረዋል።
news-48815869
https://www.bbc.com/amharic/news-48815869
ሲሪላንካ የሞት ፍርድን ለማስፈፀም ከአርባ ሶስት አመታት በኋላ ሁለት አናቂዎች ቀጠረች
ሲሪላንካ ከአርባ ሶስት አመት በኋላ አራት ሰዎችን በሞት ልትቀጣ ዝግጅት ላይ ስትሆን ይህንንም ተግባር እንዲያከናውኑ ሁለት አናቂዎችን ቀጥራለች።
የኃገሪቱ ፕሬዚዳንት ከአደንዛዥ ዕፅ ጋር በተገናኘ የታሰሩ አራት ግለሰቦች ላይ የሞት ፍርድ መወሰናቸውን ካወጁ በኋላ ነው ሁለቱ ሰዎች የተፈለጉት። በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር 1976 ተቋርጦ የነበረው የሞት ቅጣትም በነዚህ ግለሰቦችም ይጀመራል ተብሏል። •ኢትዮጵያ ከገባችበት የፖለቲካ ቅርቃር እንዴት ትውጣ? •"ከጄ/ል አሳምነው ጋ በምንም ጉዳይ ያወራሁበት አጋጣሚ የለም" እስክንድር ነጋ •ራሱን አጥፍቷል የተባለው የጄነራል ሰዓረ ጠባቂ ሆስፒታል እንደሚገኝ ተገለፀ የሁለቱ አናቂዎች የስራ ማስታወቂያ የወጣው በየካቲት ወር ሲሆን ተፈላጊዎች ተግባሩን ለማከናወን ማሟላት ካለባቸውም መስፈርቶች መካከል "ጠንካራ የግብረገብ ባሕርይን የተጎናፀፉ፣ ዕድሜያቸው ከ18-45 የሚሆን፣ ወንድና "የአዕምሮ ጥንካሬ" የሚሉ ይገኙታል። የኃገሪቱ ሚዲያ ዴይሊ ኒውስ እንደዘገበው ከመቶ በላይ ሰዎች ለስራው ያመለከቱ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ሁለት ሴቶች እንዲሁም ሁለት አሜሪካውያን ይገኙበታል። የእስር ቤቶች ቃል አቀባይ እንደተናገሩት የተመረጡት ሁለቱ አናቂዎች የመጨረሻ ስልጠና መውሰድ የሚጠብቃቸው ሲሆን ይህም ሁለት ሳምንታትን ይፈጃል ተብሏል። የመጨረሻው አናቂ የማነቂያውን ስፍራ ሲመለከት በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ተዘፍቆ ከአምስት አመታት በፊት የለቀቀ ሲሆን ሌላ አናቂ ከአመት በፊት ቢቀጠርም ስራው ቦታ ሳይመጣ ቀርቷል። በሲሪላንካ መድፈር፣ አደንዛዥ እፅ ማዘዋወርና ነፍስ ማጥፋት በህጉ መሰረት የሞት ቅጣት የሚያስቀጡ ቢሆንም ከጎርጎሳውያኑ 1976 ጀምሮ ተግባራዊ ሳይደረግ ቆይቷል። ፕሬዚዳንት ማይትሪፓላ ሲርሴና እንደገለፁት የሞት ፍርድን እንደገና ማምጣት ያስፈለገው በሃገሪቷ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ የመጣውን የአንደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ለመቆጣጠር ነው። የፖለቲካ ተንታኞች በበበኩላቸው በዚህ አመት መጨረሻ ለሚደረገው ምርጫ ያላቸውን ተቀባይነት ለመጨመር ነው ይላሉ። "አራት ግለሰቦች በሞት እንዲቀጡ የሚያስተላልፈውን ውሳኔ ፈርሜያለሁ" በማለት የተናገሩት ፕሬዚዳንት ሲርሴና "እስካሁን ድረስ ግለሰቦቹ የሞት ቅጣት ተፈፃሚ እንደሚደረግባቸው አልተነገራቸውም፤ የግለሰቦቹን ማንነት በአሁኑ ሰዓት መግለፅ የማንፈልገው በእስር ቤቶች ውስጥ ሊነሳ የሚችለውን መበጣበጥ ለማስቀረት ነው" ብለዋል ፕሬዚዳንቱ እንደሚሉት በሃገሪቷ ውስጥ 200 ሺ ግለሰቦች በአደንዛዥ ዕፅ ሱስ የተጠቁ ሲሆን፤ በሃገሪቷ ካሉ እስር ቤቶች ውስጥ 60%ቱ እስረኞች ከአደንዛዥ ዕፅ ጋር በተያያዘ ክስ ነው። ይህ ውሳኔያቸው በብዙዎች ዘንድ 'ኢሰብአዊ ድርጊት' ነው እየተባለ በመኮነን ላይ ሲሆን ሲሪላንካውያንም ውሳኔውን አደባባይ በመውጣት ተቃውመውታል። እንግሊዝ፣ ፈረንሳይና ኖርዌይን ጨምሮ የአውሮፓ ህብረት የሞት ፍርድን እንደገና የማምጣት ውሳኔዋን አውግዘውታል።
news-54424934
https://www.bbc.com/amharic/news-54424934
ሹራ ቂጣታ፡ “የለንደን ማራቶንን ያሸነፍኩት በቀነኒሳ ምክር ነው”
ከትናንት በስቲያ እሁድ ዕለት በተካሄደው የለንደን ማራቶንን በማሸነፍ ዓለምን ያስደነቀው አትሌት ሹራ ቂጣታ የድሉ ምክንያት የአትሌት ቀነኒሳ በቀለ ምክር መሆኑን ለቢቢሲ ተናገረ።
ሹራ ከውድድሩ በፊት ከአትሌት ቀነኒሳ በቀለ ጋር ልምምድ ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሶ፤ ቀነኒሳ እግሩ ላይ ባጋጠመው ጉዳት በውድድሩ ሳይሳተፍ መቅረቱን ያስታውሳል። "ከውድድሩ በፊት ቀነኒሳ ብዙ ምክር ለግሶኛል። ቀድመህ ወጥተህ እንዳትመራ፣ እራስህን እየጠበክ እሩጥ፣ ከፊት ሆነህ ከንፋስ ጋር አትጋፈጥ፣ ውሃም በደንብ ውሰድ፣ ውሃ ልታነሳ ስትል ደግሞ ከሌሎች ሯጮች ጋር እንዳትጋጭ ተጠንቀቅ ብሎ መክሮኛል" በማለት ከአትሌት ቀነኒሳ ያገኘውን ምክር ያስረዳል። • ቀነኒሳ በቀለ በጉዳት ምክንያት ከለንደን ማራቶን ራሱን አገለለ • ኢትዮጵያዊው ሹራ ቂጣታ በለንደን ማራቶን ማሸነፍ ዓለምን አስደመመ • ''ምን እንደተፈጠረ አልገባኝም" አትሌት ሃጎስ ገ/ሕይወት "እኔም እሱ እንዳለኝ ነበር ያደረኩት። ወደፊትም የወጣሁት እሱ በነገረኝ ኪሎ ሜትር ላይ ነው። በዚህ ምክንያት ነው ውድድሩን ማሸነፍ የቻልኩት" በማለት አትሌት ሹራ ውድድሩን በድል ለማጠናቀቅ የአትሌት ቀነኒሳን ምክር ወሳኝ እንደነበር ለቢቢሲ ተናግሯል። የዚህ ዓመቱ የለንደን ማራቶን ላይ በኢትዮጵያዊው ቀነኒሳ በቀለና በበኬንያዊው ኢሉድ ኪፕቾጌ መካከል የሚደረገውን ፉክክር ዓለም በጉጉት እየተጠባበቀ በነበረበት በመጨረሻው ሰዓት ላይ ቀነኒሳ ባቱ ላይ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት በውድድሩ ዋዜማ ከውድድሩ መውጣቱ ይታወሳል። ከውድድሩ በፊት የለንደን ማራቶንን ያሸንፋል ተብሎ በስፋት ተጠብቆ የነበረው የርቀቱ የክብረ ወሰን ባለቤት ኬኒያዊው ኤሊዩድ ኪፕቼጌ ነበር። ይሁን እንጂ የተጠበቀው ሳይሆን ቀርቶ ኪፕቼጎ 8ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል። "ሚዲያው ሲያወራና ሲያስተላልፍ የነበረው ስለ እነኪፕቾጌ ነበር" ያለው ሹራ፤ ይህን ውድድር ለማሸነፍ እልህ አስጨራሽ ዝግጅት ሲያደርግ እንደነበረ ለቢቢሲ ገልጿል። "ወድድሩ ከባድ ነበር። የአየር ሁኔታውም ዝናባማ ነበር። ጠንካራ አትሌቶችም ነበሩበት፤ ይሁን እንጂ 80 በመቶ ውድድሩን እንዳሸንፍ የሚያስችለኝን ጠንካራ ዝግጅት አድርጌ ስለነበረ ለድል በቅቻለሁ" ሲል አትሌት ሹራ ቂጣታ ያደረገውን ዝግጅት ተናግሯል። ኬኒያዊው አትሌት ኪፕቾጌ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ በውድድሩ ለመሸነፉ ዋነኛ ምክንያት በውድድሩ ላይ እያለ በጆሮው ላይ ባጋጠመው እክል ምክንያት መሆኑን አስፍሮ ነበር። "ከ25ኛው ኪሎ ሜትር በኋላ ጆሮዬ ተደፍኖ አልከፈት አለኝ። ስፖርት እንዲህ ነው። ሽንፈትን ተቀብለን በቀጣይ ለማሸነፍ ማተኮር አለብን" ያለው አትሌት ኪፕቾጌ ለተደረገለት ድጋፍ ምስጋናውን አቅርቧል። አትሌት ኪፕቾጌ በውድድሩ ለመሸነፉ ዋነኛው ምክንያት ጆሮው መደፈኑ መሆኑን በገለፀበት ጽሁፉ አስተያየት መስጫ ሥር በአትሌት ሹራ ስም በተከፈተ ገጽ ምክንያቱን የሚያጣጥል ምላሽ ተሰጥቶ በርካቶች ሲጋሩት ነበር። ይህንን በተመለከተ በቢቢሲ የተጠየቀው አትሌት ሹራ፤ ውድድሩ ከተጠናቀቀ በኋላም ከኪፕቾጌ ጋር እንዳልተገናኙ እንዲሁም ከኪፕቾጌ የፌስቡክ ጽሑፍ ሥር በስሙ የተሰጠው አስተያየት የእርሱ አለመሆኑን ተናግሯል። የ2018 ለንደን ማራቶን በ2ኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው አትሌት ሹራ ቂጣታ የዚህ ዓመቱ የማራቶን ድል "ትልቅ ደስታ እና መነሳሳትን ፈጥሮልኛል" ብሏል። "በሽልማት በኩል ለውድድሩ አሸናፊው የተሰጠው ከነበረው የሽልማት መጠን የዘንድሮ በ50 በመቶ ቀንሷል። 30 ሺህ ዶላር አካባቢ ነው የተሸለምኩት። ሌሎች ሽልማቶችም ይኖራሉ" ሲል አትሌት ሹራ ቂጣታ ለቢቢሲ ተናግሯል። በሹራ ቂጣታ አሸናፊነት የተጠናቀቀው የለንደኑ የወንዶች ማራቶን ውድድር ላይ ኢትዮጵያውያን ሯጮች በበላይነት አጠናቀዋል። በዚህም መሰረት በውድድሩ ሁለተኛ ከወጣው ኬንያዊው ቪንሰንት ኪፕቹምባ ውጪ ከአንድ አስከ ስድስተኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ ያጠናቀቁት ኢትዮጵያውያን ናቸው። አሸናፊው ሹራ ቂጣታ፣ ሦስተኛ ሲሳይ ለማ፣ አራተኛ ሞሰነት ገረመው፣ አምስተኛ ሙሌ ዋሲሁን እና ስድስተኛ ታምራት ቶላ ተከታትለው በመግባት አሸናፊ መሆናቸው ይታወቃል።
41805701
https://www.bbc.com/amharic/41805701
በምድር ሽንቁር ውስጥ የሚገኘው የካርቦን ዳይኦክሳይድ ክምችት በታሪክ እጅግ ልቆ ተገኘ
የ2016 አሃዝ ከዚያ በፊት ከታዩ የካርቦን ዳይኦክሳይድ ክምችቶች በ50 በመቶ የላቀና በ8 ሺህ ዓመታት ጊዜ ውስጥ ያልታየ ነው ተብሏል።
አጥኚዎች እንደሚሉት ሰው ሠራሽ እና እንደ ኤልኒኖ የመሳሰሉ ተፈጥሯዊ ክስተቶች ለካርቦንዳይኦክሳይድ መጨመር ምክንያቶች ናቸው። ዓለም አቀፉ የሜትዮሮሎጂ ድርጅት የካርቦንዳይ ኦክሳይድ፤ ሚቴን እንዲሁም ኒትርየስ ኦክሳይድን ልቀት አካቶ ጥናቱን በ51 የዓለማችን ሃገራት ነው ያከናወነው። ዓለም አቀፉ የሜትዮሮሎጂ ድርጅት አባል የሆኑት ዶ/ር ኦክሳና ታራሶቫ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ድርጅቱ መሰል ጥናቶች ማካሄድ ከጀመረ ጊዜ አንስቶ የአሁኑ አሃዝ እጅግ ከፍተኛው ነው። ቀደም ያለው ከፍተኛው በምድር ከባቢ ሽፋን ሽንቁር ውስጥ የሚገኝ የካርቦን ዳይኦክሳይድ ክምችት የተመዘገበው በ1997ቱ የኤልኒኖ ክስተት ወቅት ነበር። የአሁኑ ግን ባለፉት አስር ዓመታት ከተመዘገበው በ50 በመቶ ልቆ ተገኝቷል። በጥናቱ መሠረት መሰል የካርቦን ዳይኦክሳይድ ክምችት መጨመር ድንገተኛና አስከፊ ለሆኑ የተፈጥሮ አደጋዎች አጋላጭ ነው። በዘርፉ ብዙ ልምድ ያላቸው ሰዎች የጥናቱ ውጤት ለምድራችን መፃኢ ዕጣ ፈንታ እጅግ አስጊ እንደሆነ ያስረዳሉ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተፈጥሮ ጥበቃ ሃላፊ ኤሪክ ሶልሄይም "ቁጥሮች አይዋሹም። ይህንን አደጋ ለመመከት ብዙ መፍትሄዎች በእጃችን አሉ። የሚያስፈልገን ፖለቲካዊ ፈቃደኝነት ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
54734867
https://www.bbc.com/amharic/54734867
በፈረንሳይ ሦስት ሰዎች በስለት ተወግተው ተገደሉ
በፈረንሳይ ኒስ ከተማ ሦስት ግለሰቦች በስለት ተወግተው መገደላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።
የከተማዋ ከንቲባ ክርስችን ኤስቶርሲ "ሁሉም ነገር የሚጠቁመው የሽብር ጥቃት እንደሆነ ነው" ብለዋል። ፖሊስ እንዳለው፤ በጥቃቱ አንድ ሴት አንገቷ በስለት ተቆርጧል። ጥቃቱን አድርሷል ተብሎ የተጠረጠረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉም ተዘግቧል። በፈረንሳይ ጸረ ሽብር ላይ አተኩሮ የሚሠራው የዓቃቤ ሕግ ክፍል በግድያ ወንጀል እንደሚጠይቀው ተገልጿል። ከንቲባው እንዳሉት "ጥቃት አድራሹ በተደጋጋሚ 'አላሁ አክበር' ይል ነበር"። . በሶማሊያ ፀረ-ፈረንሳይ ሰልፍ ተካሄደ . ፕሬዚዳንት ማክሮን በፈረንሳይ ሁለተኛ ዙር ብሔራዊ የእንቅስቃሴ ገደብ አወጁ . ቱርክ ፕሬዚዳንቷን አዋርዷል ያለችውን የፈረንሳይ መፅሄት ልትከስ ነው በጥቃቱ ከተገደሉት አንዱ ባሲሊያ ውስጥ ይሠራ ነበር ተብሏል። ጥቃቱ በደረሰበት ወቅት አማኞች ሕንፃ ውስጥ እንደነበሩና አንድ የዐይን እማኝ ለአደጋ ጊዜ በተገጠመ መሣሪያ ጥቆማ መስጠቱ ተነግሯል። የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትሩ ጄራልድ ደርሜን ፓሪስ ውስጥ የአስቸኳይ ጊዜ ውይይት እያደረጉ እንደሆነ ገልጸው ዜጎች ጥቃት ከደረሰበት አካባቢ እንዲርቁ አሳስበዋል። ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አካባቢውን እንደሚጎበኙ ተገልጿል። ጠቅላይ ሚንስትር ዣን ካስቴክስ ኮቪድ-19ን ለመግታት ስለሚታወጀው የእንቅስቃሴ ገደብ መግለጫ ሲሰጡ፤ የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት ተደርጓል። "ጉዳዩ አገራችንን የገጠማት አዲስ ፈተና መሆኑ ጥያቄ የለውም" ብለዋል። የፈረንሳይ የእስልምና ካውንስል ጥቃቱን አውግዞ፤ በጥቃቱ ከተጎዱ ሰዎችና ቤተሰቦቻቸው ጎን እንደሚቆም አስታውቋል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት ከተማዋ ውስጥ ጥቃቶች በተደጋጋሚ እየተሰነዘሩ ነው። ከአራት ዓመታት በፊት የ31 ዓመት ቱኒዝያዊ በዓል ለማክበር የተሰበሰቡ ሰዎች ላይ በጭነት መኪና ጥቃት አድርሶ 86 ሰዎች ሞተዋል። ከቀናት በኋላ ጃክዊስ ሀሜል የተባሉ ቄስ ጸሎት እየመሩ ሳለ አንገታቸውን ተቀልተዋል። በዚህ ወር መባቻ ላይ በሰሜን ምዕራብ ፓሪስ ሳሙኤል ፓቲ የተባለ የታሪክ መምህር መገደሉ ይታወሳል። መምህሩ ከመገደሉ ከቀናት በፊት የነብዩ መሐመድን የካርቱን ሥዕል ለተማሪዎቹ አሳይቶ ነበር። ጥቃቱ ፈረንሳይ ውስጥ ውጥረት ከማስከተሉ ጎን ለጎን፤ የአገሪቱ መንግሥት አክራሪነትን ለመግታት የሚያደርገው ጥረት ከቱርክ እና ከሌሎች አገሮች መንግሥታት ጋር አጋጭቶታል። የቱርኩ ፕሬዘዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን የፈረንሳይ ምርቶች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ጠይቀዋል። የፕሬዘዳንቱ ምስል በፈረንሳዩ የስላቅ መጽሔት ቻርሊ ሄብዶ ላይ መታተሙን ተከትሎ ነገሮች ተካረዋል።
news-54841982
https://www.bbc.com/amharic/news-54841982
በትግራይ ክልል የተወሰደው እርምጃ በስኬት መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታወቁ
ከሶስት ቀናት በፊት በፌደራል መንግሥት ትግራይ ላይ የተጀመረው እርምጃ በስኬት መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት በብሔራዊ ቴሌቪዥን ቀርበው በሰጡት መግለጫ ህወሃት በትግራይ የሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ላይ ያደረሰው ጥቃት ድንገተኛ መሆኑን ገልፀው የመጀመሪያው ዙር ዘመቻ ብለው የጠሩት የሃይል እርምጃ ሙሉ ለሙሉ ተሳክቷል ብለዋል። የፌደራል መንግሥቱ የተለያዩ እቅዶችን ይዞ እንደተነሳ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በመጀመሪያም ጥቃትን መግታት እንደነበር አስረድተዋል። "በሰራዊቱ፣ በፖሊስ ላይና በአንዳንድ ወሳኝ የመሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርሰውን በሁሉም አቅጣጫ የሚሰነዘር ጥቃት መግታት ተችሏል" ብለዋል። የክልሉ ኃይል ጥቃት የሚሰነዝርባቸው አካባቢዎች የመከላከያ ኃይሉ በብዛት ያልሰፈረበት እንደነበር ገልፀው የሰራዊቱ አባላትንም ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በማንቀሳቀስ ጥቃት መሰንዘር ወደማይቻልበት ደረጃ ላይ መደረሱን ተናግረዋል። ከዚህም በተጨማሪ በባድመ፣ በፆረና እና በዛላንበሳ የሚገኙ የሰራዊት አባላት፣ ወሳኝ የጦር መሳሪያዎችን እና ትጥቆች በሙሉም "ከክልሉ ኃይል ውጭ መደረጋቸውንም" ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው ጠቅሰዋል። በተጨማሪም በዳንሻ ግንባር ላይ የነበረውን የክልሉን ጦር ሙሉ በሙሉ ተደምስሶ አካባቢው መቆጣጠር ተችሏል ብለዋል። የአማራን ክልል በሚያዋስነው የምዕራብ ትግራይ ድንበር በኩል ግጭቶች እንዳሉና ውጊያው መቀጠሉን የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) በትናንትናው እለት ገልፀዋል። ደብረፅዮን (ዶ/ር) ውጊያው የአማራ ክልል በሚያዋስነው ድንበር አካባቢ ቀጥሏል ከማለታቸው ውጭ የትኛው ግዛት (ግዛቶች) እንደሆኑ አልጠቀሱም። የአማራ ልዩ ኃይልና የፌደራል ሰራዊቱ በጥምረት በመሆን የትግራይ ኃይል ጋር መዋጋታቸውን ተናግረዋል። የትግራይ ኃይል በክልሉ የሚገኙትን የመከላከያ ሰሜን ዕዝ ጦር መሳሪያም ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር አውሏል ብለዋል።
news-55399198
https://www.bbc.com/amharic/news-55399198
አሜሪካውያን በነፍስ ወከፍ 600 ዶላር ሊሰጣቸው ነው
ከወራት ጭቅጭቅ በኋላ የአሜሪካ ሕግ አውጭዎች በወረርሽኙ ምክንያት አቅማቸው ለተዳከመ አሜሪካውያን መደጎሚያ የሚሆን 900 ቢሊዮን ዶላር በጅተዋል።
በጀቱ በወረርሽኙ ምክንያት ሥራቸውን ላጡና ንግዳቸው ለተደካመ ይሆናል ተብሏል። ከዚህ በተጨማሪ የመንግሥት ሥራዎችን የሚያግዝ 1.4 ትሪሊየን ዶላር በጀትም ተለቋል። ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ተለቀው የነበሩ ድጎማዎች ማብቂያቸው የያዝነው ወር ነበር። 12 ሚሊዮን አሜሪካዊያን የጤና ሽፋናቸውን ሊያጡ ይችላሉ የሚል ፍራቻ አለ። የሕዝብ እንደራሴዎችና የሴናተሮች ምክር ቤት አባላት በአዲሱ የድጎማ መርሃ ግብር ላይ ክርክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከዚያ በመቀጠል ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የመጨረሻ ፊርማቸውን ያሳርፉበታል። በርካታ አሜሪካውያን ከአዲሱ ድጎማ በነፍስ ወከፍ 600 ዶላር ይደርሳቸዋል። ሥራ አጥ አሜሪካውያን ደግሞ በሳምንት ተጨማሪ 300 ዶላር ያገኛሉ። ከድጎማው 300 ቢሊዮን ዶላር የሚሆነው ለንግድ ቤቶች የሚሰጥ ነው። የተቀረው ደግሞ ክትባት ለማከፋፈል፣ ለትምህርት ቤትና የቤት ኪራይ መክፈል ላልቻሉ ነው ተብሏል። ድጎማውን ይፋ ያደረጉት ሪፐብሊካኑ የሴኔት አፈ ጉባዔ ሚች ማክኮኔል ናቸው። ዴሞክራቷ የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲና የፓርቲ አጋሯ ቻክ ሹመር ድጎማው አቅም ለሌላቸው አሜሪካውያን 'አስፈላጊ ነው' ሲሉ ተደምጠዋል። ዴሞክራቶች እንደሚፈልጉት ግን አልሆነላቸውም። የዴሞክራቶች ምኞት የነበረው ከድጎማው ቀንጨብ ተደርጎ ለክፍለ ግዛት አስተዳዳሪዎች እንዲሰጥ ነበር። ሹመር፤ ድጎማው በሚቀጥለው ዓመት ኮሮናቫይረስን ለመከላከል ለምናደርገው ርብርብ 'መሠረቱን ገነባ እንጂ ጣራ የለውም' ሲሉ ተችተውታል። ዴሞክራቶች ጆ ባይደን ሥልጣን እስኪጨብጡ ቸኩለዋል። በፈረንጆቹ ጥር 20 መንበሩን ከትራምፕ የሚረከቡት ባይደን ተጨማሪ ድጎማ ያፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። የአሜሪካ ኮንግረስ ባለፈው አርብ ድጎማውን ያረቃል ተብሎ የነበረ ቢሆንም የፖለቲከኞች ክርክር ቅዳሜና እሁድ ቀጥሎ ውሏል። ክርክሩ ለበርካታ ወራት በመቆየቱ የዶናልድ ትራምፕ መንግሥት ድጎማ ሳያፀድቅ ይህን የፈረንጆች ዓመት ያገባድዳል ተብሎ ተፈርቶ ነበር። ባፈለው መጋቢት የአሜሪካ መንግሥት ለዜጎቼ ይሆናል ብሎ 1.4 ትሪሊየን ዶላር መድቦ ነበር። በወቅቱ አሜሪካውያን 1200 ዶላር በነፍስ ወከፍ ተከፍሏቸዋል። ሥራ አጦች ደግሞ በሳምንት 600 ዶላር አግኝተዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ አሜሪካን ማናወጥ ከጀመረ ወዲህ 20 ሚሊዮን አሜሪካውያን የዕለት ጉርሳቸው ምንጭ ከሆነው የሥራ ገበታቸው ተፈናቅለዋል። ነገር ግን ከዚያ በኋላ ባለው ጊዜ ግማሽ ያህሉ መልሰው ሥራቸውን አግኝተዋል። ባለፉት 5 ወራት አሜሪካ ውስጥ የድህነት መጠኑ 11.7 ደርሷል። በአሁኑ ወቅት ከ8 ሚሊዮን በላይ አሜሪካውያን በድህነት ይኖራሉ። አሜሪካ ባለፉት 60 ዓመታት ይህን የመሰለ የድህነት አዘቅት አይታ አታውቅም።
news-49061654
https://www.bbc.com/amharic/news-49061654
የብሪታኒያ አየር መንገድ ወደ ካይሮ የሚያደርገውን በረራ አቋረጠ
የብሪታኒያ አየር መንግድ (ብሪቲሽ ኤርዌይስ) ''ለደህንነት ሲባል'' ወደ ካይሮ ግብጽ የሚደርገውን በረራ ለአንድ ሳምንት ያክል አግጄያለሁ ሲል አስታወቀ።
በረራው የተሰረዘባቸው ተሳፋሪዎች በረራው የተቋረጠበትን ምክንያት የሚያስረዳ ደብዳቤ ከአየር መንገዱ ተቀብለዋል። ተጓዦች ለንደን ሂትሮ አየር ማረፊያ ከደረሱ በኋላ የብሪታኒያ አየር መንገድ ወደ ካይሮ የሚያደርገው በረራ መሰረዙ እና ለአንድ ሳምንት ያክል ተለዋጭ በረራ እንደሌላ ተነግሯቸዋል። አየር መንገዱ በረራውን ለአንድ ሳምንት ለመሰረዝ ያደረሰው የደኅንነት ስጋቱ ምንነት በዝርዝር አልገለጸም። የካይሮ አየር ማረፊያ ቃል አቀባይ ከአየር መንገዱ ማብራሪያ እየጠበቁ እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የብሪታኒያ አየር መንገድ ቃል አቀባይ በሰጡት መግለጫ ''በመላው ዓለም በሚገኙ መዳረሻ አየር ማረፊያዎች ላይ የደኅንነት ምርመራ እናደርጋለን። ወደ ካይሮ የምናደርገውን በረራም ለአንድ ሳምንት ያክል የሰረዝነው አስፈላጊውን የደኅንነት ምርመራ ለማድረግ ጊዜ ለማግኘት ነው። የደንበኞቻችን እና የሥራተኞቻችን ደኅንነት ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው። ደኅንነት እስካልተረጋገጠ ድረስ በረራ አናደርግም'' ብለዋል። የጀርመኑ አየር መንገድ የሆነው ሉፍታንዛ በተመሳሳይ መልኩ ወደ ካይሮ የሚያደርገውን በረራ ትናንት ሰርዞ የነበረ ሲሆን ከዛሬ እሑድ ጀምሮ ግን በረራዎቹ እንደሚቀጥሉ አስታውቋል። • ከነመንገደኞቹ የጠፋው አውሮፕላን ሳይገኝ ቀረ • ልብ የረሳው አውሮፕላን • ሰባኪው አውሮፕላን ግዙልኝ አለ የዩናይትድ ኪንግደም የውጪ ጉዳይ ቢሮ ወደ ግብጽ ለሚጓዙ እንግሊዛውያን የጉዞ ደኅንነት መረጃን አውጥቷል። በውጪ ጉዳዩ ቢሮ ገጽ ላይ ''በአቪዬሽን ላይ ለመፈጸም የታቀደ ሽብር ስለመኖሩ ከፍተኛ ጥርጣሬ አለ። ከግብጽ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም በሚደረጉ በረራዎች ላይ ከፍተኛ ምረመራ ይካሄዳል'' የሚል መልእክትን አሰፍሯል። 2015 ላይ የሩሲያ አየር መንገድ አውሮፕላን ከግብጽ ከተነሳ በኋላ አየር ላይ ሳለ በውስጡ የነበረ ቦምብ ፈንድቶ በርካቶች መሞታቸው ይታወሳል። ይህን ጥቃት ተከትሎም የብሪታኒያ አየር መንገድን ጨምሮ በርካታ አየር መንገዶች ወደ ግብጽ የሚያደርጉትን በረራ አቋርጠው ነበር። በብሪታኒያ አየር መንገድ ወደ ካይሮ ለመብረር ትኬት ቆርጠው ከአየር ማረፊያ የተገኙ ተሳፋሪዎች በረራው በመሰረዙ እና ከአየር መንገዱ የተሰጣቸው አገልግሎት ደካማ መሆኑ እጅጉን እንዳበሳጫቸው ቃላቸውን ለቢቢሲ የሰጡ ተሳፋሪዎች ተናግረዋል። የ70 ዓመቷ ክርስቲን ሼልቦርን ከልጅ ልጇ ጋር ወደ ካይሮ ለመጓዝ ከበረራው ጥቂት ሰዓታት ቀድም ሂትሮ አየር ማረፊያ እንደደረሰች ትናገራለች። አውሮፕላን ለመሳፈር የሚያስችላት የይለፍ ወረቀት (ቦርዲንግ ፓስ) ማግኘት ብትችልም የአየር ማረፊያ መተላለፊያ በሮችን አልከፍት እንዳላት ታስረዳለች። ክርስቲን ሼልቦርን ''የአየር መንገዱ ሠራተኞች የተፈጠረውን ነገር የሚያውቁ አይመስለኝም'' የምትለው ክርስቲን ቀጣዩ በረራ ከአንድ ሳምንት በኋላ እንደሚደረግ ሲነግሩኝ 'በጣም ተበሳጫሁ' ትላለች። ሌለኛው ተሳፋሪ ማይክል ካህሊል የማልቀርበት ጉዳይ ስላለኝ በሌላ አየር መንገድ ከለንደን ወደ ካይሮ ለመብረር £1200 (43 ሺህ ብር በላይ) ለመክፍል ተገድጄያለሁ ይላል።
news-47147638
https://www.bbc.com/amharic/news-47147638
በደቡብ ወሎ ሙሽራና ሚዜውን የገደለው ቦምብ የማን ነበር?
በደቡብ ወሎ ዞን ቦረና ወረዳ በታ መንደጋ ቀበሌ የሰርግ ሥነ ሥርዓታቸውን ፈፅመው በጫጉላ ሥነ ሥርዓታቸው ላይ በፈነዳ ቦምብ ሙሽራውን ጨምሮ የሁለት ሰዎች ሕይወት አልፏል።
• ሙሽሪት እጮኛዋ መቃብር ላይ ድል ባለ ሠርግ ተሞሸረች የቦረና ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን ባለሙያ የሆኑት አቶ ሲሳይ ክፍሉ በሌሎች 3 ሰዎች ላይም ጉዳት መድረሱን እንደሰሙ ለቢቢሲ የገለፁ ሲሆን ቦምቡ ሙሽራውና ሚዜው ሲነካኩት ሊፈነዳ እንደቻለ ተናግረዋል። በወቅቱ ሙሽራዋ ወደ ቤተሰቦቿ ጋር ሄዳ ስለነበር ከአደጋው ልትተርፍ እንደቻለች ባለሙያው ጨምረው አስረድተዋል። የበታ ቀበሌ ምክትል ሊቀመንበር አቶ አበበ ጌቶ የአካባቢው ማኅበረሰብ እጅግ ማዘኑን ገልጸው፤ "ሕብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግና ህገወጥ መሳሪያ ያላቸው እንዲያጋልጡ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ እየሰራን ነው" ብለዋል። • ለማጭበርበር የሞተ ያስመሰለው አባት ሚስቱንና ልጆቹን አጣ የቦረና ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ንጋቱ ታመነ በበኩላቸው ጋብቻው ጥር 14፣ 2011 ዓ.ም የተፈፀመ ሲሆን ከሠርጉ ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በጫጉላ ከቆዩ በኋላ በአካባቢው ባህል መሰረት አስርት (ልብስ አጠባ) የሚባለውን ስርዓት ጨርሰዋል። ከዚያም ሙሽሮቹ ወደ ቤተሰቦቻቸው ተቀላቅለው በሙሽራው ቤተሰቦች ቤት መኖር ጀምረው እንደነበር ኮማንደሩ ያስረዳሉ። ጥር 26፣ 2011 ዓ.ም ከቀኑ ስምንት ሰዓት አካባቢ F1 የተሰኘ የእጅ ቦምብ ከሚዜው ጋር በመሆን ከቤት በስተጀርባ ሲቀጠቅጡ ፈንድቶ የሁለቱም ሕይወት ወዲያወኑ ሊያልፍ እንደቻለ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ኮማንደሩ አንዲት ህፃን በፍንጣሪው ቀላል የሚባል ጉዳት እንደደረሰባት አክለዋል። ሟቾቹ በሃያዎቹ መጀመሪያ የእድሜ ክልል የሚገኙ ሲሆን የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ጥር 27/2011 ዓ.ም መፈፀሙን ኮማንደር ንጋቱ ገልፀዋል። "ከመንግስት ታጣቂዎች ውጭ ህብረተሰቡ በሠርግ፣ በኃይማኖት ተቋማትና፣ ሠዎች በሚበዙባቸው ቦታዎች የጦር መሳሪያን ይዞ መንቀሳቀስ መመሪያው የሚከለክል ቢሆንም ህብረተሰቡ ግን የጦር መሳሪያ ይዞ የመንቀሳቀስ ልምድ አለው" የሚሉት ኮማንደሩ ይህንንም ልማድ ለመለወጥ የግንዛቤ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል። የፈነዳው ቦምብ ሙሽራው በህገ ወጥ መንገድ ያስቀመጠው መሆኑን መረጃ በማግኘታቸው ሌላ በህግ የሚጠየቅ አካል እንደሌለ ለቢቢሲ ጨምረው ተናግረዋል። የጫጉላ ሥነ- ሥርዓት የወረዳው ኮሚዩኒኬሽን ባለሙያ እንደገለፁልን በአካባቢው ባህል የጫጉላ ሥነ ሥርዓት፤ ከሠርጉ ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ሙሽራው፣ ሙሽሪትና የወንድ ሚዜዎች ከሙሽራው ቤተሰብ ቤት በተዘጋጀላቸው 'መጨጉያ' ጊዜያዊ ቤት በእንክብካቤ የሚቆዩበት ሥርዓት ነው፤ በአስራ ሁለተኛው ቀን የልብስ አጠባ ሥነ ሥርዓት ከተከናወነ በኋላ ሽልማትና ስጦታ ተበርክቶላቸው ወደ ቤተሰብ ይቀላቀላሉ። በባህሉ መሰረት የሴት ሚዜዎች ከሠርጉ ቀን በኋላ ወደየራሳቸው ቤት ይመለሳሉ እንጂ ከሙሽሮቹ ጋር አይቆዩም።
46670041
https://www.bbc.com/amharic/46670041
"ሕዝብ እንዲጠይቅ አድርገናል፣ በተቋሙ ላይ እምነት ማሳደር እንዲችልም ሞክረናል" ዋና ኦዲተር
የፌደራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ዋና ኦዲተር የሆኑት አቶ ገመቹ ዱቢሶ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ የመሥሪያ ቤቱ እንቅፋት ካሏቸው መካከል ብቃት ያለው ባለሙያ ፍልሰት ይገኝበታል።
"የቁጥር ችግር ባይኖርብንም፤ ብቁ የሰው ሀብት እጥረት ፈተና ሆኖብናል" የሚሉት ዋናው ኦዲተሩ፤ በኦዲት ሙያ የተካነ ብቁ ሰው አለመገኘቱና ከተገኘም መሥሪያ ቤቱን ቶሎ መልቀቁ ፈተና እንደሆነባቸው በአፅንኦት ገልጸዋል። ብቃት ያለው ባለሙያ ፍልሰት በሥራው ላይ ተፅዕኖ እንዳሳደረ ያስረዱት ዋና ኦዲተሩ፤ የሚሰማራው የሰው ሀይል በሚፈልጉት የብቃት ደረጃ ላይ ያለመሆኑን ችግር ለመቅረፍ የራሳቸውን ማሰልጠኛ ለማቋቋም እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ ተናግረዋል። ዋና ኦዲተሩ፤ ከሕግ ማዕቀፍና ከደረጃ አንጻር የተሟላ የሕግ ማዕቀፍና ደረጃ እንዳላቸው በመግለጽ፤ "ሥራችንን እንዳንሠራ የከለከለን መሰረታዊ ነገር የለም" ብለዋል። • ብዙ ስላነጋገረው ኮሚሽን ማወቅ የሚገባዎ 5 ነጥቦች • "ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ ተስፋና ስጋት አለ" ኦባንግ ሜቶ • ኢትዮጵያ 8.5 በመቶ ዕድገት ታሥመዘግባለች፡ አይ.ኤም.ኤፍ. በአቶ ገመቹ ገለጻ፤ የመሥሪያ ቤቱ ሪፖርት ውጤት ላይ የማይውልበት ጊዜ መኖሩ ሌላው መሰናክል ነው። "ሥራችን ኦዲት አድርጎ ሪፖርት ማቅረብ ብቻ አይደለም" ብለው፤ ሪፖርታቸው ተፅዕኖ ፈጣሪ መሆን እንዳለበት ያብራራሉ። መሥሪያ ቤቱ የሚያቀርበው የኦዲት ሪፖርት አሰራር ላይ፣ ሀብት አጠቃቀም ላይ እንዲሁም አፈፃፀም ላይ ውጤት ማምጣት እንዳለበት ይገልጻሉ። "በኦዲት ሪፖርቱ መሰረት የማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ ረገድ እኛ በምንፈልገው መልኩ እየሄደ አይደለም። ይህ መሰረታዊ ችግር ነው። ሥራችን ውጤት ካላመጣ እርባና የለውም።" ሪፖርትን ውጤታማ ማድረግ ከኦዲት መሥሪያ ቤቱ አቅም ውጪ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ገመቹ፤ ችግሩ በምክር ቤትና በመንግሥት ደረጃ መፈታት እንዳለበት ይመክራሉ። ውጤታማ መሆን ለሥራቸው ማበረታቻና ማትጊያ መሆኑን ገልጸው፤ የኦዲት ሪፖርታቸውን ተመርኩዘው የማስተካከያ እርምጃ በማይወስዱ ተቋማት ላይ እርምጃ እንዲወሰድም ያሳስባሉ። "እርምጃ ካልተወሰደ ሌሎች ተቆሞችን ተመሳሳይ መንገድ ካለመከተል የሚገድባቸው ነገር የለም፤ ምክንያቱም ማንም ተጠይቆ አላዩም።" ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መንግሥት እየወሰዳቸው ያሉ እርምጃዎች ጥሩ መሆናቸውን የሚናገሩት ዋና ኦዲተሩ፤ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ኃላፊዎች ሲገመገሙ አንዱ የመገምገሚያ ነጥብ ተደርጎ የተወሰደው የኦዲት ማስተካከያ እርምጃ መውሰድ መሆኑና ማስተካከያ ያላደረጉ ከፍተኛ ነጥብ እንዲያጡ መደረጉ ተስፋ ሰጭ ነው ይላሉ። "መንግሥት እየወሰደው ያለው ተጠያቂነትን የማረጋገጥ እርምጃ ተስፋ ሰጪ ነው። እስካሁን የነበረው ጫጫታ ነበር። አሁን ግን ተግባራዊ እርምጃ እየተወሰደ ነው። ስለዚህ እስካሁን ፈተና የሆኑብን ነገሮች ሊቀረፉ ይችላሉ ብዬ ነው የማስበው" ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት ተመሳሳይ ሪፖርት ማቅረባቸውን የሚያስረዱት ዋና ኦዲተሩ፤ ከዓመት ዓመት ለውጥ አለመታየቱን ያስገርጣሉ። ሆኖም በ2011 በጀት ዓመት ሂሳብ ሪፖርት መሰረታዊ ለውጥ ይመጣል ብለው ተስፋ ያደርጋሉ። "መንግሥት አሁን እያሳየ ያለውን ቁርጠኛ አቋም የሚቀጥልበት ከሆነ በሁሉም ደረጃ መሰረታዊ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል" ብለው አቶ ገመቹ ተስፋቸውን ገልጸዋል። እስካሁን መሰረታዊ የሚሉት ለውጥ ባያዩም፤ ተቋማት ላይ የተጠያቂነት ፍራቻ ማየታቸውን ጥሩ ጅማሮ ነው ይሉታል። "እስካሁን ለውጥ አልታየም። ለውጥ ነው ማለት ቢከብደኝም ትንሽ ፍራቻ አያለሁ። ይህንን ሁለት ዓመት ገደማ 'ተጠያቂነት ወደ እኛ እየመጣ ነው' የማለት ፍራቻ አለ። ይህ ለውጥ ባይሆንም ወደ ለውጥና መሻሻል ይወስደናል" በማለት ለውጥ ለማድረግ የሚጣጣሩ ግለሰቦች መበረታታት እንዳለባቸው ይናገራሉ። የተወካዮች ምክር ቤት በተደጋጋሚ የሂሳብ ኦዲት ሪፖርት ላይ ክፍተት የተገኘባቸውን ጠርቶ እያነጋገረ ነው ያሉት ዋና ኦዲተሩ፤ ምን እርምጃ እንደወሰዱና እያከናወኑ ያሉትን እየተከታተለ ነው በማለት እየታየ ያለውን ለውጥ ያስረዳሉ። ኦዲተሩ አክለውም፤ "ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ የኦዲት ጉዳይ እየተነሳ እየተመከረ፣ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር መርሃ ግብር አዘጋጅቶ እርምጃ መውሰዳቸውን አጣርቶ ሪፖርት እንዲያቀርብላቸው የሚኒስትሮች ምክር ቤት እየጠየቀ ነው። ይህ የሚያበረታታ ቢሆንም፤ በተጨባጭ መሬት ላይ እርምጃ መውሰድ ላይ ያለው ነገር ዘገምተኛ ነው" ብለዋል። ዋናው ኦዲተር መስሪያ ቤት፤ ለዜጎች እሴት ጨማሪ ሪፖርት የሚያቀርብና በአፍሪካ ደረጃ ምርጥ ከሚባሉት ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤቶች አንዱ መሆን እንደሚፈልግ አቶ ገመቹ ይናገራሉ። መሥሪያ ቤቱ የሚያደርገው ኦዲት ወደ ጠንካራ የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ስርዓት እንዲያደርስ እንደሚፈልጉም አክለዋል። በተጨማሪም ግልፅነትና ተጠያቂነት ወደ መልካም አስተዳደር ግንባታ እንዲሁም ወደ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ግንባታ እንዲወስድ እንደሚፈልጉ የሚናገሩት ዋና ኦዲተሩ፤ መሥሪያ ቤቱ ለዚህ ጉልህ አስተዋፅኦ የሚያደርግ ነፃና ገለልተኛ፣ ንቁና ሙያዊ ስነ ምግባሩን የጠበቀ ተቋም ሆኖ እንዲገነባ ያላቸውን ፍላጎት ለቢቢሲ አስረድተዋል። "መሥሪያ ቤቱ ይህን ራዕይ ይዞ እየሰራ ነው" የሚሉት ዋና ኦዲተሩ፤ ይሳካል የሚል እምነትም አላቸው። "አሁን ሕዝብ እንዲጠይቅ አድርገናል" ብለውም፤ ሕዝብ በተቋሙ ላይ እምነት ማሳደር እንዲችል እየሠሩ መሆኑን ጠቁመዋል። ሥራቸው ተጠናክሮም ሕዝብ የኔ ብሎ የሚተማመንበት ተቋም ሆኖ ማየት እንደሚሹ ተናግረዋል።
45251399
https://www.bbc.com/amharic/45251399
ለ10 ሰዓታት ባህር ውስጥ የቆየችው ሴት
ለ10 ሰዓታት በባህር ላይ ህይወትዋን ማቆየት የቻለችውነ ሴት የባህር ዳርቻ ጠባቂዎች ህይወቷን ሊታደጓት ችለዋል።
ካይ ሎንግስታፍ የተባለችው እንግሊዛዊት ከክሮሺያ ባህር ዳርቻ ከተነሳው መርከብ ላይ ነበር አድዓቲክ በተሰኘ ባህር ላይ የወደቀችው። • ታላቁ ዲፕሎማት ኮፊ አናን ሲታወሱ • የጅግጅጋ ተፈናቃዮች በአዲስ አበባ ጎዳና ላይ ወድቀዋል • የሳምንቱ ምርጥ 11! በሳምንቱ የጋሬት ክሩክስ ቡድን ውስጥ እነማን ተካተዋል? የአካባቢው ባለስልጣናት እንደተናገሩት፤ የ46 ዓመቷ ሴት ባህር ውስጥ ከወደቀች ከ10 ሰዓታት ቆይታ በኋላ ነበር የባህር ዳርቻ ጠባቂዎች የታደጓት። ወደ ሆስፒታል ከተወሰደች በኋላ ''ከመውደቄ በፊት በመርከቡ ጫፍ ላይ ተቀምጬ ነበር። ህይወቴ በመትረፏ በጣም እድለኛ ነኝ'' ብላለች። ኤችአርቲ ለተባለ የክሮሺያ መገናኛ ብዙሃን ጨምራ እንደተናገረችው ''የባህር ዳርቻው ጠባቂዎች እኔን ከመታደጋቸው በፊት፤ ለ10 ሰዓታት በቀዝቃዛው ባህር ውስጥ ነበርኩኝ'' ብላለች። ዘሰን የተባለው ጋዜጣ ካይ ሎንግስታፍ ከታደጓት የባህር ዳርቻ ሰራተኞች አንዱ እንደነገረኝ ብሎ እንደዘገባው ካይ ''ዮጋ መስራቴ ለረዥም ሰዓታት መንሳፈፍ እንድችል ረድቶኛል እንዲሁም ቅዝቃዜውን ለመርሳት ስዘፍን ነበር'' ብላለች ብሏል። ካይ 291 ሜትር ርዝመት ካለው መርከብ ላይ የወደቀች ሲሆን የባህር ዳርቻው ጠባቂዎች ካይን ከመርከቧ 2 ኪ.ሜ. እርቀት ላይ ነበር ያገኟት። ባህር ጠላቂዎች እንደሚሉት ከሆነ ካይ 291 ሜትር ርዝመት ካለው መርከብ ላይ ስትወድቅ ቢያንስ እስከ 4 ሜትር ድረስ ልትሰምጥ ትቻላለች። በባህሩ ላይ የነበረውን ማዕበል ተቋቁማ ህይወቷን ማትረፏ በርካቶችን አስገርሟል።
news-43111401
https://www.bbc.com/amharic/news-43111401
ማንበብ ስፓ ከመግባት ይሻላል?
ስለ ዮጋና ስፓ የእረፍት ቦታዎች ሰምተን እናውቅ ይሆናል በተጨማሪም ለሥነ-ጽሑፍና ለሥዕል ተብለው የተዘጋጁም አሉ። ለንባብ ብቻ ተብሎ የተዘጋጀ የእረፍት ቦታስ?
(ከግራ ወደ ቀኝ) ኒንክ, ሔለን, ናኒ እና አኒ በቅርቡ ወደ ንባብ የእረፍት ቦታ የሄዱ ኤማ ጄን መጽሐፍቶቻቸውን ይዘው እረፍት የወጡ ሰዎችን ለማግኘት ወደዚህ የእረፍት ቦታ አምርታ ነበር። ክሬሲዳ ዳውኒንግ እራት ለአምስት ደቂቃ መተላለፉን አሳወቀች። እሱም አኒ የጀመረችውን ምዕራፍ እስክትጨርስ ነው በማለት መብራሪያ ሰጠች። ቢሆንም ግን ማንም ልብ ያለ አልነበረም። ሔለንና ኒንክ ስለሚያነቡት መጽሐፍ የአጻጻፍ ዘይቤ እየተነጋገሩ ነው፤ በሌላ በኩል ደግሞ ኒና እና ፔኒ 'ማዳም ቦቫሪ' የተሰኘው መጽሐፍ ልጅነታቸውን ምን ኣህል እንደቀየረው እየተወያዩ ነው። ሮቢ ግን የጀመረውን መጽሐፍ ማስቀመጥ አቅቶት እራት በመኝታ ቤቱ እንዲቀርብለት ጠይቋል። የንባብ የእረፍት ቆይታ ይህን ይመስላል። የሚመጡት እንግዶች ለሦስት ሌሊት እስከ 450 ፓውንድ ከፍለው እራሳቸውን በመኝታ ቤት ዘግተው ሳይረበሹ በሰላም የሚያነቡበት ቦታ ነው። 'ለእራሴ መብት እየሰጠሁት ነው' በትርፍ ጊዜዋ አርታዒ የሆነችው ክሬሲዳ የዚህ የንባብ እረፍትን ከመሰረቱት መካከል ናት እሷም ''ሃሳቡ የመጣልኝ በጣም ከባድ ወቅት ላይ በነበርኩበት ጊዜ ባለቤቴ 'ለምን ስፓ አትሄጅም' ሲለኝ ነበር። ስፓ ብሄድ ደስ እንእደሚለኝ ግን መጽሐፎቼን ይዤ ብሄድ ግን እንደሚረጥቡብኝ አስቤ ነው'' ትላለች። ''በጣም አስፈልጎኝ የነበረው ያለ ረብሻ ማንበብ ነበር። ግን ለንባብ ተብሎ የተዘጋጀ ቦታ ማግኘት ሲያቅተኝ የንባብ እረፍት ፈላጊ ብቸኛዋ ሰው ልሆን አልችልም ብዬ አስብኩ።'' ስለዚህ ሣራ ኖኤል ከተሰኘችው በሙያዋ ፎቶግራፈር ከሆነችው የሥራ አጋሯ ጋር በመሆን ጊዜያዊ የሆነ የንባብ ብቻ እረፍት ቦታ አቋቋመች። ይህ የንባብ እረፍት ቦታ ከከተማ ራቅ ያለ ሲሆን፤ በዚያም አንድ ሕግ ብቻ ነው ያለው እሱም የንባብ ክፍል ውስጥ በማንኛውም ሰዓት ፀጥታ መጠበቅ ብቻ ነው። አኒ የተሰኘችው እንግዳ የዩኒቨርስቲ የቅሬታ ክፍል ኃላፊ ስትሆን በንባብ እረፍት ላይ ስትሳተፍ ይህ የሁለተኛ ጊዜዋ ነው። ኤማ ጄን፤ አኒ ቤቷን ዘግታ ብታነብ ገንዘብ ታተርፍ እንደነበር ስትነግራት ከት ብላ ሳቀች። ''ይሄ እኮ ለንባብ ቅድሚያ መስጠት እንድችል ለእራሴ እየፈቀድኩኝ ነው'' ብላ በመቀጠልም '' ቤት ብሆን ኖሮ ሌሎች ስለሚሠሩ ነገሮች ማሰቤ አይቀርም። ጓደኞቼን ማግኘት፣ መጻፍ፣ ማፅዳትና ሸራብ መሥራት'' አለችኝ። ''እዚህ ግን እሳቱ አጠገብ ቁጭ ብዬ ለሰዓታት ያለምንም ረብሻ መጽሐፌ ውስጥ መጥፋት እችላለሁ።'' ለአኒ ክሬሲዳ ናት የምታነባቸውን መጽሐፍት ሃሳብ ያቀረበችላት እንግዶች ግን የፈለጉትን መርጠው ማንበብ ይችላሉ። አንባቢዎች በቤቱ ውስጥ በፈለጉበት ቦታ መጽሐፋቸውን ይዘው መቀመጥ ይችላሉ ከዲጂታል መፅዳት ጊዜ እያጠረ በመጣበት ዓለም ውስጥ ለንባብ ብቻ ተብለው የሚዘጋጁ የእረፍት ቦታዎች በቁጥር እየበዙ መጥተዋል። የተለያዩ ድርጅቶችም የተለያዩ የኪስ አቅምን ያገናዘቡ አቅርቦቶች ማሰናዳት ጀምረዋል። አንዳንድ የንባብ እርፍት ቦታዎች ለጥሞናም አመቺ ናቸው። አንዳንዶቹ ቤተ-መንግሥት የሚመስሉ ቦታዎች ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ የምንኩስና ሕይወትን የሚያስታውሱ ራቅ ያሉ ቦታዎች ናቸው። ሁሉም ግን ዓላማቸው አንድ ነው። አንባቢያን በሕዝብ ማመላለሻ ላይ ለ20 ደቂቃ ብቻና በሚያገኙት አጋጣሚ ከሚያነቡ፤ ሙሉ ሃሳባቸውን ሰብስበውና ጊዜ ሰጥተው እንደፈለጉ ማንበብ እንዲችሉ ነው። ሔለን የሥነ-ልቦና ባለሙያ ስትሆን አጋታ ክሪስቲ የተሰኘችውን ደራሲ በጣም ስለምትወዳት የሌሊት ልብሷን ሳትቀይር ሙቅ ውሃ ታቅፋ በመጽሐፏ ውስጥ ሰምጣለች። እዚህ ስትመጣ በመኝታ ቤቷ ተቆልፋ የምትውል መስሏት ነበር። ሆኖም ግን ከሌሎች አንባብያን ጋር በአንድ ክፍል ውስጥ በፀጥታ ማንበቡን ወዳዋለች። ''ይህ የሳምንት መጨረሻ የቅንጦት ነው'' ብላ በሳቅ ፈነደቀች። በመቀጠልም ''ሆቴል ውስጥ ቢሆን ደስ አይለኝም ነበር። ምክንያቱም ብቸኝነት የሚሰማኝ ይመስለኛል። እዚህ ግን ስፈልግ ፀጥታ ስፈልግ ደግሞ እራት እየበላን ስለተለያዩ መጽሐፍት መወያየት እንችላለን'' ትላለች ሔለን። እ.አ.አ በ2014 የተደረገ የመንግሥት ጥናት እንደመዘገበው 41% የሚሆኑ ከ25 እስከ 39 ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ በውዴታ የሚያነቡት ሰዎች ቁጥር እንደቀነሰ ይናገራሉ። ባለፈው ዓመት ውስጥም በእንግሊዝ ሃገር ካሉ ሰዎች መካከል እሩብ የሚያክሉት መጽሐፍ በውዴታ እንዳላነበቡ ተጠቅሷል። ሱዛን ሂል እና ሃዋርድ ጃኮብሰን የተሰኙት ታዋቂ ደራስያን እንዳስጠነቀቁት እየበዛ የመጣው የዲጂታል ሱስ ያለንን የትኩረት አቅም እየቀነሰ በመሄዱ ረዘም ያሉ ጽሑፎችን የማንበብ አቅማችንን እየቀነሰ ነው። በዚህ የንባብ እረፍት ላይ ስልኮችና ታብሌቶች ባይከለከሉም እንኳን፤ ክሬሲዳና ሣራ እንግዶቻቸው ከረብሻ ነፃ እንዲሆኑ ወስደው አንዲቆልፉበት ያበረታታሉ። አንባቢያኑም አይናቸው ችግር እንዳይገጥመው በየተወሰነ ጊዜ ወጣ እያሉ ነፋስ እንዲቀበሉም ይበረታታሉ። ሔለን ዘና ብላ እያነበበች 'ከስፓ የተሻለ' የሮቢ ባለቤት ይህን የንባብ እረፍት ለገና ነበር እንደ ስጦታ ያበረከተችለት። እሱም ሁሌም ማንበብ የሚመኛቸውን መጽሐፍት አምጥቶ በእራስጌው ደርድሯቸዋል። ''ቤት ስሆን ተዘግቼ ባነብ ቤተሰቤን ትቼ ለእራሴ ብቻ የማስብ ያህል ነው የሚሰማኝ። እዚህ የተለየ አስተሳሰብ ነው፤ ምክንያቱም እየከፈልኩበትም ነው። ከሰው ጋር የመገናኘት ግዴታም የለብኝም'' እንደውም ገበታ ላይ እራሱ ማንበብ ይቻላል። ''ለምን አይቻልም'' ትላለች ክሬሲዳ። ''ዋናው ነጥብ እኮ ማንም ከጓደኛውና ከሥራ ባልደረባው ጋር ስለማይመጣ 'ይቅርታ ባነብ ቅር አይላችሁም አይደል' ማለት አያስፈልግም። እዚህ ምን ጊዜም የማንበብ ፈቃድ አለን።'' እራት ቀርቦም ገበታ ላይ ውይይቱ ባንድ ጊዜ ተቋረጠና ከቀረቡት ጣፋጮች መካከል የትኛውን እንደሚወስዱ መነጋገር ጀመሩ። አኒ ስለ ንብ ጀምራ ነበረውን መጽሐፍ ለመጨረስ ሹልክ ብላ ወጣች። ሔለንና ሣራ ከአጋታ ክሪስቲ መጽሐፍት መካከል የትኛው እንደሚበልጥ ይከራከራሉ። ቀጥላም ''ንባብ እኮ በደመነፍስ የሚደረግ አይደልም። ንባብ ተሳትፎና ከመጽሐፉም ጋር መቆራኘትን ይጠይቃል። ደግሞ ሳይንቲስቶች እንደደረሱበት ንባብ ለአዕምሮና ለዕድሜ ርዝመትም አስተዋጽዖ ያደርጋል ስለዚህ ከስፓ የተሻለ የእረፍት ጊዜ ነው።'' በማግስቱም ለቁርስ የወረደችው የቢቢሲዋ ኤማ ጄን ብቻ ነበረች። ሌሎቹ በጠቅላላ መጽሐፍ ውስጥ ተደብቀው ነበር።
news-55212134
https://www.bbc.com/amharic/news-55212134
ሚኒስትሩ የእርዳታ ቁሳቁሶችን ከሚያቀርቡ ድርጅቶች ጉቦ በመቀበል ተከሰሱ
የኢንዶኔዢያ ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስትር በኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለተቸገሩ ሰዎች ከሚከፋፈል እርዳታ ጋር በተያያዘ ጉቦ ሲቀበሉ ነበር በሚል ክስ ቀረበባቸው።
ሚኒስትሩ ጁሊያሪ ባቱባራ ለተቸገሩ ዜጎች የምግብና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ከሚያቀርቡ ድርጅቶች ገንዘብ በመቀበል ነው ክስ የቀረበባቸው። የአገሪቱ የጸረ ሙስና መስሪያ ቤት በሚኒስትሩ መኖሪያ ቤት ባደረገው ፍተሻ 14.5 ቢሊየን ሩፒያ ወይም 1 ሚሊየን ዶላር በሳምሶናይት እና ሌሎች ማሸጊያዎች ተከማችቶ አግኝተዋል ተብሏል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም ቅዳሜ ዕለት በተደረገው ድንገኛ ኦፐሬሽን አራት ተጠርጠሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ትናንት ደግሞ ሚኒስትሩ ጁሊሪያ ባቱባራ እጃቸውን ለፖሊስ ሰጥተዋል። ''ገንዘቡ በሰባት ሳምሶናይቶች ውስጥ ተደርጎ ነበር። በተጨማሪም በሶስት የጀርባ ሻንጣዎች እና በፖስታ ማሸጊያዎች ጭምር ተቀምጧል'' ሲሉ የአገሪቱ የጸረ ሙስና ኮሚሽን ኃላፊ ፊርሊ ቡሃሪ በመግለጫው አስታውቀዋል። ኤኤፍፒ የዜና ወኪል አገኘሁት ባለው መረጀ መሰረት ደግሞ የጸረ ሙስና ሰራተኞቹ በድንገት ፍተሻ በሚያደርጉበት ወቅት ሚኒስትሩ ከእያንዳንዱ የእርዳታ ካርቶን 10 ሺ ሩፒያህ እንደሚሰጧቸውና ለማንም እንዳይናገሩ ጠይቀዋል። የማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስትሩ ጥፋተኛ ሆነው የሚገኙ ከሆነ እስከ 20 የሚደርስ እስርና አንድ ቢሊየን ሩፒያህ ቅጣት ይጠብቃቸዋል ተብሏል። በቁጥጥር ስር ከዋሉት ሰዎች መካከል ሁለቱ መንግስት ኃላፊዎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ሰዎች ግን ተራ ዜጎች መሆናቸው ተገልጿል። የኢንዶኔዢያው ፕሬዝዳንት ጆኮ ዊዶዶ ደግሞ እሁድ ዕለት በሰጡት መግለጫ ሚኒስትሮች ከእንደዚህ አይነት የሙስና ወንጀል እንዲርቁ በተደጋጋሚ ማስጠንቀቃቸውንና ሙሰኞችን እንደማይታገሱ አስታውቀዋል። ''ይህ የህዝቡ ገንዘብ ነው፤ በኮቪድ-19 ጉዳት ለደረሰባቸው ድጋፍና ኢኮኖሚያዊ መነቃቃትን ለመፍጠር ተብሎ የታቀደ ነው' ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።
news-57222410
https://www.bbc.com/amharic/news-57222410
አሜሪካ በውስጥ ጉዳይዋ ጣልቃ መግባቷን ከቀጠለች ግንኙነቷን ለማጤን እንደምትገደድ ኢትዮጵያ አስታወቀች
አሜሪካ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባቷን የምትቀጥል ከሆነ መንግሥት ከአገሪቱ ጋር ያለውን ግንኙነት መለስ ብሎ ለማጤን እንደሚገደድ አስታወቀ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በትግራይ ክልል ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ላይ የቪዛ እገዳ መጣሉን ተከትሎ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ላይ ነው ይህንን ያለው። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በትግራይ ክልል ያለው ቀውስ መፍትሔ እንዲያገኝ የተደረጉት ጥረቶች ውጤት ባለማስገኘታቸው በኢትዮጵያ፣ በኤርትራ፣ በአማራ ክልል ባለስልጣናትና በህወሓት አባላት ላይ የቪዛ ዕገዳ መጣሉን እሁድ ሌሊት ማሳወቁ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአሜሪካ መንግሥት በዚህ እርምጃው "በኢትዮጵያ ላይ ተገቢ ያልሆነ ጫናን ማድረግ መቀጠሉን" በመጥቀስ ተቃውሞውን አሰምቷል። ይህ ውሳኔ የተሰጠው የኢትዮጵያ መንግሥት ከአሜሪካ አስተዳደር ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ ገንቢ የሆነ ግንኙነት እያደረገ ባለበት ጊዜ መሆኑን ጠቅሶ፤ አገሪቱ ምርጫ ለማካሄድ እየተዘጋጀት ባለችበት በዚህ ወቅት መሆኑ ደግሞ የተሳሳተ መልዕክትን የሚያስተላለፍ ነው ብሎታል። ጨምሮም አሜሪካ የጣለችው የቪዛ ዕቀባና ቀደም ሲል የወሰደቻቸው ሌሎች ተያያዥ እርምጃዎች የሁለቱ አገራትን የረጅም ጊዜ ግንኙነት በከፍተኛ ሁኔታ ይጎዳዋል ብሏል። ይህ የአሜሪካ የጉዞ ዕቀባ ውሳኔ በትግራይ ክልል የተከሰተውን ቀውስ እንዲፈጠር ያደረጉ ወይም የቀረበውን የመፍትሔ ሐሳብ እንዳይሳካ ያደናቀፉ የአገራቱን የደኅንነት ኃይል አባላትን ወይም የአማራ ክልልና ኢመደበኛ ኃይሎችንና ሌሎች ግለሰቦች እንዲሁም የህወሓት አባላትን የሚያካትን መሆኑ ተገልጿል። ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፤ እዚህ ውሳኔ ላይ የተደረሰው በትግራይ ክልል ውስጥ የሚካሄደው ግጭት እንዲቆምና የኤርትራ ወታደሮች ከክልሉ እንዲወጡ፣ የሰብአዊ ዕርዳታ አቅርቦት እንዲሻሻል እንዲሁም በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑት ኃይሎች ወደ ድርድር እንዲመጡ ያደረገችው ጥረት ተቀባይነት ባለማግኘቱ ነው ብሏል። የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ መግለጫ ከዚህ አንጻር ከሁሉ የከፋ ብሎ የጠቀሰው የአሜሪካ መንግሥት ከሁለት ሳምንታት በፊት በአገሪቱ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ቡድን ተብሎ የተሰየመውን ህወሓት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በእኩል የመመልከት ዝንባሌ ነው ብሏል። የኢትዮጵያ መንግሥት ብሔራዊ ውይይት የሚያደርገው ከውጭ በሚደረግበት ግፊት ሳይሆን የአገሪቱን የወደፊት ተስፋ በተሻለ መንገድ ላይ ለመምራት ብሔራዊ መግባባት ትክክለኛው መንገድ ነው ብሎ ስለሚያም እንደሆነ ገልጿል። ነገር ግን "ሽብርተኛ ተብሎ ከተሰየመው ህወሓት ጋር ድርድር ማድረግ እንደማይቻል ከግንዛቤ ሊገባ ይገባል" በማለት ቡድኑ መልሶ እንዲያንሰራራ የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ አሉታዊ ውጤት የሚኖረውና የማይሳካ መሆኑን መግለጫው ጠቅሷል። ጨምሮም "የኢትዮጵያ መንግሥት በተደጋጋሚ ግልጽ እንዳደረገው፤ የአሜሪካ አስተዳደር በውስጣዊ ጉዳዩ ላይ ጣልቃ ለመግባት የሚያደርገው ሙከራ ተገቢ ያልሆነ ብቻ ሳይሆን ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ነው" ብሏል። ትግራይ ውስጥ ተፈጸሙ የተባሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተም የኢትዮጵያ መንግሥት አጥፊዎችን ተጠያቂ ለማድረግ ግዴታውን እየተወጣ መሆኑን በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፣ በሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እንዲሁም በአፍሪካ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እየተከናወኑ ያሉትን ተግባራት በመግለጫው ላይ አመልክቷል። የሰብአዊ እርዳታን በተመለከተም የኢትዮጵያ መንግሥት ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር በመተባበር ባልተገደበ ሁኔታ እርዳታ እንዲቀርብ ከማድረጉ በላይ መንግሥት ያለውን ውስን አቅም በመጠቀም እርዳታ እያቀረበ እንደሚገኝ ገልጿል። የአሜሪካ መንግሥት በትግራይ ክልል ውስጥ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ መፍትሔ እንዲገኝ በከፍተኛ ባለሥልጣናቱ በኩል ጥረት ሲያደርግ የቆየ ሲሆን፤ የአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናትና ልዩ መልዕከተኞች በተደጋጋሚ ኢትዮጵያን መጎብኘታቸው ይታወሳል። አሜሪካ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ያለውን ቀውስና የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ጉዳይን በቅርበት እንዲከታተሉላት አንጋፋውን ዲፕሎማት ጄፍሪ ፊልትማንን በልዩ መልዕክተኝነት ሰይማ ከሳምንታት በፊት በአካባቢው ጉብኝት አድርገዋል። ባለፈው ሳምንትም የአገሪቱ ሴኔት በትግራይ ግጭት ላይ ተሳታፊ በሆኑ ወገኖች ላይ የተለያዩ እርምጃዎች እንዲወሰድ የሚጠይቅ የውሳኔ ሐሳብ አሳልፎ ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥትም በተደጋጋሚ በውስጥ ጉዳዩ ውስጥ ጣልቃ በመግባት ተጽእኖ ለመሳደር የሚሞክሩ መንግሥታትን ጫና እንደማይቀበለው በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል። በትግራይ ክልል ውስጥ ስላለው ሁኔታ እና ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ምዕራባውያን በተለይም አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ተጽእኖ ለማሳደር የሚያደርጉትን ጥረት የሚቃወም ንቅናቄ በአዲስ አበባ ከተማ ተካሂዶ ነበር። በትግራይ ክልል ውስጥ ከስድስት ወራት በፊት በተቀሰቀሰው ግጭት ምን ያህል ሰዎች እንደሞቱ እስካሁን የሚታወቅ ነገር ባይኖርም አሃዙ በሺዎች የሚቆጠር ሊሆን እንደሚችል አንዳንዶች ግምታቸውን ያስቀምጣሉ። በጥቅምት ወር ማብቂያ ላይ የህወሓት ኃይሎች የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ በተጀመረው ወታደራዊ ግጭት ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም ኃይሎች በርካታ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በመፈጸም ሲከሰሱ ቆይተዋል።
news-48659573
https://www.bbc.com/amharic/news-48659573
የቀድሞ የሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር አል-በሽር ከወራት በኋላ ታዩ
ከሥልጣን የተወገዱት የሱዳኑ ኦማር ሃሰን አል-በሽር ከወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አደባባይ ታይተዋል።
በሽር ከታሠሩበት ሥፍራ በመኪና ወደ ሱዳን መዲና ካርቱም የመጡበት ምክንያት በሙስና ወንጀል የተከሰሱበትን ክስ ለመስማት ነው። በጥበቃ ኃይሎች ተከበው የነበሩት የ75 ዓመቱ በሽር ባሕላዊ ነጭ ኩታቸውን ደርበው ከጭንቅላታቸው በማይለየው ጥምጣም ደምቀው ነበር ብቅ ያሉት። • በደቡብ ሱዳን የምሽት ክለቦች ታገዱ ከሳሾቻቸው በሽር ከሥልጣን በተወገዱበት ወቅት በርከት ያለ ጥሬ ገንዘብ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ተገኝቷል ይላሉ። እሁድ ዕለት ክሳቸውን ለመስማት ካርቱም የተገኙት አል-በሽር ከመኪናቸው እስከ አቃቤ ሕጉ ቢሮ እስኪደርሱ ድረስ ከሌላው ጊዜ በተለየ ጠደፍ ጠደፍ ሲሉ ተስተውለዋል። ከደቂቃዎች በኋላ ሲመለሱ ደግሞ ንዴት ቢጤ ፊታቸው ላይ ይታይ ነበር ይላል በሥፍራው የነበረው የሮይተርስ ወኪል። ዓለም አቀፉ የወጀለኞች ፍርድ ቤትም [አይሲሲ] በሽርን በፅኑ ይፈልጋቸዋል፤ በዳርፉር ግዛት ለተፈፀመው የጦር ወንጀል ተጠያቂ ናቸው በማለት። በሌላ በኩል የጊዜያዊው ወታደራዊ አገዛዝ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ሞሐመድ ሐማድ 'ሄሜቲ' በቅርቡ የሲቪል ነፍስ ያጠፉ ሰዎችን ለሕግ አቅርባለሁ ሲሉ ተደምጠዋል። • አልበሽር በማህበራዊ ሚዲያ የተቀሰቀሰባቸውን ተቃውሞ ተቹ ተቃዋሚዎች በሰኔ ወር መባቻ ላይ ብቻ 100 ሰዎች በወታደሮች ተገድለዋል ሲሉ የሃገሪቱን ወታደራዊ ኃይል ይኮንናሉ። ሄሜቲ 'ጃንጃዊድ' በተሰኘ ቅፅል ስም የሚታወቀውን ልዩ ኃይል አድንቀዋል፤ ምንም እንኳ ልዩ ኃይሉ ከዳርፉር ጀምሮ እስከ አሁኑ አመፅ በፈፀማቸው ግፎች ቢወቀስም። የበሽርን ከሥልጣን መወገድ ተከትሎ መንበሩን የተረከበው ወታደራዊ ኃይል ሰላማዊ ሰዎች ላይ ኃይል በመጠቀሙ እየተወቀሰ ይገኛል፤ ሱዳንም ለጊዜው ከአፍሪቃ ሕብረት አባልነቷ ተሰርዛለች። •ኦማር አል-በሽር: ከየት ወደየት?
54627452
https://www.bbc.com/amharic/54627452
አሜሪካ፡ በትናንቱ ምሽት ክርክር ትራምፕ እና ባይደን ምን ተባባሉ?
ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እና ተቀናቃኛቸው ጆ ባይደን በመጨረሻው የፊት ለፊት ክርክራቸው በኮቪድ-19፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና በዘር ጉዳዮች ላይ ብዙ ተመላልሰዋል።
የትናንት ምሽቱ ክርክር ከመጀመሪያው ዙር የተሻለ እርጋታ የታየበት ነው ተብሏል። እንደዛም ሆኖ ሁለቱ ፖለቲከኞች ግላዊ ጉዳዮችን እያነሱ ሲተቻቹ ነበር። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዙሪያ ጆ ባይደን አሁንም በአሜሪካ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ጥብቅ ክልከላዎች መጣል አለባቸው ሲሉ ፕሬዝደንት ትራምፕ በበኩላቸው አሜሪካን ክፍት ማድረግ አለብን ሲሉ ተከራክረዋል። ትራምፕ "ይህ ግዙፍ ምጣኔ ሃብት ያለው ትልቅ አገር ነው" ያሉ ሲሆን "ሰዎች ሥራቸውን እያጡ ነው። ድብርት አለ። ሰዎች ራሳቸውን እያጠፉ ነው" ብለዋል። ባይደን ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ለሞቱት ከ220ሺህ በላይ አሜሪካውያንን ትራምፕን ተጠያቂ አድርገዋል። "ለዚሁ ሁሉ ሰው ሞት ተጠያቂ የሆነው ሰው ፕሬዝደንት ሆኖ መቆየት የለበትም" ብለዋል። በዘር ጉዳይ ላይ ትራምፕ "እዚህ ክፍል ውስጥ ካለን ሰዎች መካከል ዝቅተኛ ዘረኛ ያልሆንኩት እኔ ነኝ" ሲሉ ተደምጠዋል። ትራምፕ እአአ 1994 ላይ የወጣውን የወንጀል መመሪያ በማስታወስ ጆ ባይደን ይህ መመሪያ ሲወጣ ተሳትፎ አድርገዋል ብለዋል። ጥቁር አሜሪካውያን ይህ መመሪያ የጥቁሮችን መብት ይጋፋል ሲሉ ይተቻሉ። ባይደን በበኩላቸው በአሜሪካ የቅርብ ዘመን ታሪክ ውስጥ ከተመለከትናቸው ዘረኛ ፕሬዝደንቶች መካከል አንዱ ትራምፕ ነው ብለዋል። ባይደን ዘረን መሠረት አደርገው በሚነሱ አለመግባባቶች ላይ ትራምፕ በሚሰጧቸው አስተያየቶች ወይም በሚወስዷቸው እርምጃዎች ነገሮችን እንደሚያባብሱ ተናግረዋል። ትራምፕ ተቀናቃኛቸው ጆ ባይደን ከልጃቸው ሃንተር የንግድ ሥራ ተጠቃሚ ሆኖዋል ሲሉ ጆ ባይደን በበኩላቸው ትራምፕ የሚጠበቅባቸውን ግብር አይከፍሉም ብለዋል። ስደተኞችን በተመለከተ ትራምፕ አስተዳደራቸው በደቡብ አሜሪካ የመኖሪያ ፍቃድ የሌላቸው ሰዎች ከልጆቻቸው እንዲነጠሉ ስላደረገው ፖሊሲያቸው ተጠይቀው ነበር። ትራምፕ በኦባማ ዘመን ወላጆች ብቻ ሳይሆኑ ልጆችም ታስረው ነበር ብለዋል። የቀድሞ ምክትል ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በበኩላቸው የትራምፕ አስተዳደር ወላጆች እና ልጆችን መለየቱ ጭካኔ ነው ካሉ በኋላ ወላጆችን እና ልጆችን መለየት "የወንጀል ተግባር ነው" ሲሉ ትራምፕን ድርጊት ኮንነዋል። የአየር ንብረት ለውጥ ሁለቱ አጩዎች አሁንም በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ተመላልሰዋል። ትራምፕ ጆ ባይደንን "የነዳጅ ኢንደስትሪውን ሙሉ በሙሉ ትዘጋዋለህ?" ሲሉ ጠይቀዋል ባይደን በበኩላቸው "አዎ ከነዳጅ ኢንደስትሪው መላቀቅ አለብን። ምክንያቱም የነዳጅ ኢንደስትሪው ከፍተኛ ብክለት ያስከትላል ብለዋል። ትራምፕ በበኩላቸው ከነዳጅ ኢንደሰትሪው እንውጣ ቢባለ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ሰው ከሥራ ውጪ ይሆናል ብለዋል። ሌሎች የተነሱ ጉዳዮች ባይደን በአሜሪካ አንድ ሰራተኛ በሰዓት የሚከፈለው መጠን ከ15 ዶላር ያላነሰ እንዲሆን አደርጋለሁ ብለዋል። ወረቀት የሌላቸው 11 ሚሊዮን ሰዎች የአሜሪካ ዜግነት እንዲያገኙ በሩን እከፍትላቸዋሁ ብለዋል ጆ ባይደን። የአፍ እና አፍንጫ ማድረግን ግዴታ አደርጋለሁ ሲሉም ጆ ባይደን ተናግረዋል። ፕሬዝደንታዊ ክርክሩን የመራችው ጋዜጠኛ ክሪስተን ዎከር ማን አሸነፈ? በትናንት ምሽት ክርክር ማን ተሽሎ ተገኘ ለሚለው ቁርጥ ያለ ምላሽ የሚሰጥ የተገኘ አይመስልም። እንደ ሲኤንኤን ከሆነ በክርክሩ ላይ ትራምፕ ለ41 ደቂቃዎች የተናገሩ ሲሆን ባይደን በበሉላቸው 38 ደቂቃዎች ያክል ተናግረዋል። በመጨረሻው ፕሬዝደንታዊ ክርክር ላይ ትራምፕ ያሳዩት እርጋት እና የሰነዘሯቸው መከራከሪያ ሃሳቦችን በርካቶችን አስደንቋል። የክርክሩ አሸናፊ፡ አከራካሪዋ! ፕሬዝደንታዊ ክርክሩን ለመራችው ለኤንቢሲ ጋዜጠኛዋ አድናቆት እየቀረበላት ይገኛል። የ44 ዓመቷ ክሪስተን ዎከር አስፈላጊ ሲሆን እጩ ፕሬዝዳንቶቹን ታቋርጥ ነበር። ክርክሩ ከተጀመረበት ቅጽበት እስከ መጠናቀቂያው ድርስ ክርክሩን መቆጣጠር ችላ ነበር ተብሏል። 12 ቀናት በቀሩት ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ጆ ባይደን ሊያሸንፉ እንደሚችሉ ቅድመ ምርጫ ግምቶች ይጠቁማሉ። እስካሁን ከ46 ሚሊዮን በላይ አሜሪካውያን ድምጻቸውን ሰጥተዋል። የምርጫ ቅድመ ግምቶች ግን ትክክለኛው የምርጫውን ውጤታ ላያሳዩ ይችላሉ። ከአራት ዓመት በፊት በተካሄደው ምርጫ የቅድመ ምርጫ ውጤቶች ሂላሪ ክሊንተን እንደሚያሸንፉ የሚጠቁሙ ነበሩ።
54672468
https://www.bbc.com/amharic/54672468
ኮሮናቫይረስ፡ ቻይና በአንድ ሰው ምክንያት የአንድ ከተማ ነዋሪዎችን በጠቅላላ እየመረመረች ነው
ቻይና በዢንዣንግ ግዛት በኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው መገኘቱን ተከትሎ ለግዛቲቱ ነዋሪዎች በአጠቃላይ የኮሮናቫይረስ ምርመራ እያደረገች ነው።
እስካሁን ድረስ 4.7 ሚሊዮን የሚጠጋ የካሽጋር ነዋሪዎች የተመረመሩ ሲሆን፤ 138 ምልክቱን የማያሳዩ ነገር ግን ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ተገኝተዋል ተብሏል። ቻይና የቫይረሱን ስርጭት በመቆጣጣር ረገድ ውጤታማ ብትሆንም ነገር ግን አልፎ አልፎ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች እየተገኙ ነው። ዢንዣንግ በርካታ ሙስሊም ቻይናውያን የሚገኙ ሲሆን፤ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ቤይዢንግ የመብት ጥሰት ትፈጽምባቸዋለች ሲሉ ይከስሳሉ። በካሽጋር ትምህርት ቤቶች የተዘጉ ሲሆን ነዋሪዎቿም ቢሆኑ ነጻ መሆናቸውን የሚያሳይ ምስክር ወረቀት ካልያዙ በስተቀር ወዴትም መሄድ እንደማይችሉ ተነግሯቸዋል። በካሽጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ቫይረሱ እንዳለባት የተረጋገጠችው ሴት ምንም ዓይነት ምልክት የማታሳይ የነበረች ሲሆን፤ በከተማዋ ዳርቻ በሚገኝ አንድ ፋብሪካ ውስጥ ሰራተኛ ናት ተብሏል። የቻይና መገናኛ ብዙኀን "ተከታታይነት ያለው ምርመራ" ሲሉ በጠሩት የኮቪድ-19 ምርመራ መሰረት የተመረመረችው ይህች ሴት በቻይና ከ10 ቀን በኋላ የተገኘች የመጀመሪያዋ በቫይረሱ የተያዘች ሴት ሆናለች። ቅዳሜ እለት የተጀመረው አጠቃላይ ምርመራ እስካሁን ድረስ 138 ምልክቱን የማያሳዩ ነገር ግን ቫይረሱ ያለባቸውን ሰዎችን አግኝቷል። በቻይና እስከ አሁን ድረስ 85,810 በቫይረሱ መያዛቸው ቢመዘገብም ምልክቱን የማያሳዩ ሰዎች ግን በዚህ ቁጥር ውስት አይካተቱም። እስካሁን ድረስ ቻይና የ4,634 ሰዎችን ህይወት በቫይረሱ ምክንያት አጥታለች። የከተማዋ ባለስልጣናት እሁድ ከሰዓት በካሽጋር ከ2.8 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የኮሮናቨይረስ ምርመራ እንደተደረገላቸው ገልፀው፣ ቀሪዎቹ ነዋሪዎች ደግሞ በሁለት ቀናት ውስጥ ተመርምረው ይጠናቀቃል ብለዋል። በቻይና ሰዎች ወደ መደበኛ ህይወታቸው የተመለሱ ቢሆንም አሁንም ግን አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው እየተገኙ ነው። ቻይና በፍጥነት ሰፊ እና አጠቃላይ ምርመራ በማካሄድ ቫይረሱን ለመቆጣጣር እየሞከረች ትገኛለች። ከዚህ ቀደም ብሎ ቂንግዳኦ ከተማ 9 ሚሊዮን ነዋሪዎቿን በአጠቃላይ መርምራለች። በግንቦት ወር ደግሞ ለመጀመሪያ ገዜ የኮሮናቫይረስ የተገኘባት ዉሃን ከተማ 11 ሚሊዮን ነዋሪዎቿን መርምራለች።