id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
news-46135515
https://www.bbc.com/amharic/news-46135515
ኦነግ እና መንግሥትን ለማግባባት ወደ ምዕራብ ኦሮሚያ ያቀኑት የሃገር ሽማግሌዎች ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ
በምዕራብ ኦሮሚያ ያጋጠመውን የጸጥታ መደፍረስ በሽምግልና ለመፍታት ወደ ስፍራው አቅንተው የነበሩ የሃገር ሽማግሌዎች ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ።
ወደ ምዕራብ ኦሮሚያ ካቀኑት የሃገር ሽማግሌዎች መካከል አንዱ የሆኑት ኢንጂነር መስፍን አበበ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ነጋዴዎች፣ አባ ገዳዎች እና የሃይማኖት አባቶች ከልዑኩ ቡድን አባላት መካከል ይገኙበታል። "አስቀድመን ከነቀምት፣ ጊምቢ እና ደምቢ ዶሎ ከተሞች ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገናል" የሚሉት ኢንጂነር መስፍን የሃገር ሽማግሌዎቹ ከነዋሪዎች የተነሱላቸውን ጥያቄዎች እና አስተያየቶች አድምጠዋል። • በኦነግ እና በመከላከያ ሠራዊት መካከል በምዕራብ ኦሮሚያ ግጭት እንደነበር ተነገረ ከዚያም ጊዳሚ ከሚገኝ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮች ጋር ውይይት መደረጉን ይናገራሉ። ''የውይይቱን ውጤት መንግሥት እና ኦነግ መግለጫ የሚሰጡበት ጉዳይ ስለሆነ እኔ በዚህ ላይ ሃሳቤን አልሰጥም'' ብለዋል። ኢንጅነር መስፍን ጨምረው እንደሚሉት ''ውይይቱ በአንድ ጊዜ የሚጠናቀቅ ሳይሆን በቀጣይነት ብዙ ወይይት ሊያስፈልግ ይችላል'' ብለዋል። ''በጉዟችንም ሆነ በቆይታችን ምንም አይነት ችግር ሳይገጥመን በሰላም ደርሰን ተመልሰናል'' ይላሉ ኢንጂነር መስፍን። ሌለው የልዑኩ ቡድን አባል የሆኑት የታሪክ መሁሩ ሼክ ሃጂ ኢብራሚም ይገኙበታል። ሼክ ሐጂ እንዳሉት ከተለያዩ የከተማ ነዋሪዎች ጋር በተደረጉት ውይይቶች ላይ በርካታ የመብት ጥያቄዎች ተነስተዋል ብለዋል። • “ትጥቅ መፍታት ለድርድር አይቀርብም”፡ መንግሥት ''መሰረተ ልማቶች እንዲገነቡ፣ የኦሮሞ ህዝብ መብት እንዲከበር፣ ኦሮሚያ ውስጥ የሚኖሩ የሌሎች ብሔሮች ተወላጆች መብቶች እንዲከበሩ ለመንግሥት መልዕክት አስተላልፉልን ሲሉ ጠይቀውናል'' ሲሉ ሼክ ሐጂ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በምዕራብ ኦሮሚያ ከሚገኙ የኦነግ ወታደሮች እና አመራሮች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን የሚያስታውሱት ሼክ ሐጂ፤ ''ከፍተኛ አመራሮቻችን አዲስ አበባ ነው ያሉት፤ ከእነሱ ጋር መወያየት ይኖርባችኋል'' የሚል ምላሽ ከኦነግ ወታደሮች እና አመራሮች እንደተሰጣቸው ይናገራሉ። በተጨማሪም 'የኦሮሞ ህዝብ መብት ለረዥም ዓመታት ሳይከበር ቆይቷል። የኦሮሞ መብት እንዲከበር እንሻለን። ይህንንም መናገር ያለበት እላይ ያሉት ከፍተኛ አመራሮቻችን ናቸው። ከእነሱ ጋር ተወያይታችሁ ከስምምነት መድረስ ትችላላችሁ'' እንደተባሉ ሼክ ሐጂ ኢብራሂምም ለቢቢሲ ተናግረዋል። • «ኦነግ ሀገር ለመገንጠል ነው የምሠራው ብሎ አያውቅም» ሽጉጥ ገለታ (ዶ/ር) ''ወደ ሃገር ውስጥ ሳንገባ በመሪዎቻችን እና በክልሉ ፕሬዚዳንት መካከል የተደረሰው ስምምነት ለምን ተግባራዊ አልተደረገም?'' የሚል ጥያቄ በኦነግ ወታሮች መነሳቱን ሽማግሌዎቹ ገልፀዋል። በሌላ በኩል የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ አድማሱ ዳምጠው ለክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሲናገሩ ወደ ምዕራብ ኦሮሚያ የሄዱት የሃገር ሽማግሌዎች ተደብድበው እና ተዘርፈው የሄዱበትም ዓላማ ሳይሳካ መመለሳቸውን ተናግረዋል። በቄለም ወለጋ ዞን ከሚገኙ ዘጠኝ ወረዳዎች ፖሊስ ጣቢያዎች ውስጥ የጦር መሳሪያ ተዘርፏል የሚሉት አቶ አድማሱ፤ ከአንድ ሺህ በላይ ቀበሌዎች ውስጥ የመንግሥት አስተዳደር እንዲፈርስ ተደርጎ በሌላ ሥርዓት እየተደራጀ ነው ብለዋል። ሼክ ሐጂ ኢብራሂም ግን ''የተደበደበም ሆነ የተዘረፈ ሰው አላየንም። በሰላም ሄደን በክብር ነው የተሸኘነው'' ይላሉ። ''ከውይይታችን መረዳት እንደቻልነው ሁለቱም ወገኖች የሚፈልጉት ሰላም እንዲሰፍን ነው'' የሚሉት ሼክ ሐጂ፤ ከጥቂት ቀናት በኋላም የኦነግ እና የመንግሥት ባለስልጣናትን አንድ ላይ በማምጣት እንደሚያወያዩ ተናግረዋል።
news-52230707
https://www.bbc.com/amharic/news-52230707
በኮሮናቫይረስ ምክንያት እየተፈለፈሉ ያሉት ሐሰተኛ መድኃኒቶች
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መዛመትን ተከትሎ በታዳጊ አገራት ሐሰተኛ መድኃኒቶች በከፍተኛ ሁኔታ መጨመራቸውን የዓለም አቀፉ ጤና ድርጅት አስታውቋል።
እነዚህን መድኃኒቶች መውሰድ የከፋ የጎንዮሽ ጉዳት ሊያስከትሉም እንደሚችሉ ድርጅቱ በተጨማሪ አስጠንቅቋል። ገበያው ላይ የተፈጠረውን ክፍተት በመጠቀም ሐሰተኛ መድኃኒቶች በአፍሪካ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ እየተቸበቸቡ መሆናቸውንም ቢቢሲ ባደረገው የምርምር መረዳት ችሏል። ይህንንም ሁኔታ በማየት አንድ የጤና ባለሙያ "ከኮሮናቫይረስ ወረርሽን ጎን ለጎን ደረጃቸውን ያልጠበቁና ሐሰተኛ መድኃኒቶች ሊያጥለቀልቁን ይችላል" ብለዋል። የኮሮናቫይረስ የዓለምን ሕዝብ ሰቅዞ በያዘበት ሁኔታ ብዙዎች በመስጋት መሠረታዊ የሚባሉ መድኃኒቶችን እያከማቹ ነው። በዓለም ላይ መድኃኒቶችን በማምረትና በማቅረብ የአንበሳውን ድርሻ የያዙት ቻይናና ህንድ ድንበራቸውን መዝጋታቸው ከፍተኛ ክፍተትን ፈጥሯል። ለመድኃኒቶች ያለው ከፍተኛ ፍላጎትና አቅርቦት አለመጣጣምም ለሐሰተኛ መድኃኒት አቅራቢዎች በርን ከፍቶላቸዋል። የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ነው ባለበት ሳምንት ዓለም አቀፍ ወንጀሎችን አድኖ የሚይዘው ኢንተርፖል ድንበር ዘለል የመድኃኒት ወንጀልን ለመከላከል ባደረገው 'ኦፐሬሽን ፓንጊያ' የሚል ስያሜ በሰጠው ዘመቻ በዘጠና አገራት ውስጥ 121 ሰዎችን ከሐሰተኛ መድኃኒት ዝውውር ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር አውሏል። ዓለም አቀፍ የመድኃኒት ሽያጭ ወንጀሎች በከፍኛ ደረጃ እየተፈፀሙ እንደሆነ አመልካች ነው የተባለለት ይህ እስር በአንድ በሳምንት ብቻ የተከናወነ ነው። በዚህም ዘመቻ 14 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ አደገኛ የሚባሉ መድኃኒቶችም በቁጥጥር ስር ውለዋል። ከዓለም ጫፍ እስከ ጫፍ፣ ከማሌዥያ እሰከ ሞዛምቢክ፣ የፖሊስ አባላት በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ሐሰተኛ የፊት ጭምብሎችን፣ ሐሰተኛ መድኃኒቶችን በቁጥጥር ስር አውለዋል። አብዛኞቹ መድኃኒቶችም ኮሮናቫይረስን ይፈውሳሉ እየተባሉ የሚሸጡ ናቸው። "የዓለም የጤና ሁኔታ እንዲህ ቀውስ ውስጥ ባለበት ጊዜ፤ እንዲህ አይነት ሐሰተኛ መድኃኒቶችን መሸጥ ለሰው ልጅ ህይወት ግድለሽ መሆን ነው" በማለት የኢንተርፖል ዋና ፀሐፊ ጄኔራል ጀርጅን ስቶክ ተናግረዋል። ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድኃኒቶችን ጨምሮ፣ የተሳሳተ ወይም የጎደለ ንጥረ ነገር የያዙ በአጠቃላይ ሐሰተኛ መድኃኒቶች በመካከለኛና ታዳጊ አገራት 30 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያወጡ ከዓለም ጤና ድርጅት የተገኘው መረጃ ያሳያል። •ዶናልድ ትራምፕን ከህንድ ጋር ያፋጠጠው መድኃኒት •በኮሮናቫይረስ ከተያዙት ኢትዮጵያዊያን ሦስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው እነዚህ መድኃኒቶች ያድናሉ የተባለውን በሽታ መፈወስ አይደለም፤ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት ሊያስከትሉ እንደሚችሉ የሚናገሩት በዓለም ጤና ድርጅት ውስጥ የሐሰተኛ መድኃኒቶች ቁጥጥር ላይ የሚሰሩት ፔርኔት ቦርዶሊዮን "እነዚህ መድኃኒቶች በአብዛኛው መርዛማ የሆነ ንጥረ ነገርን ስለሚይዙ ነው" ብለዋል። ዓለም አቀፋዊው የመድኃኒቶች ስርጭት የዓለም የመድኃኒት ምርት ዘርፍ አንድ ትሪሊዮን የሚገመት ኢንዱስትሪ ነው። ስርጭቱንም በምናይበት ወቅት ከፍተኛ አምራቾች ከሚባሉት ቻይናና ህንድ ወደ አውሮፓ፣ ደቡብ አሜሪካም ሆነ እስያ ወዳሉ ትልልቅ ማከማቻ ወዳላቸው ማሸጊያ ቦታዎች ይላካል፤ ከዚያም ወደተለያዩ ሃገራት ስርጭት ይደረጋል። ከመድኃኒት በላይ ዓለም አቀፋዊ የሆነ ነገር እንደሌለ የሚጠቅሰው የዓለም የጤና ድርጅት አገራት ድንበራቸውን መዝጋታቸውን ተከትሎ ያለው የመድኃኒቶች ስርጭት ሥርዓት ብጥስጥሱ እየወጣ ነው። በህንድ የሚገኙ በርካታ ቁጥር ያላቸው የመድኃኒት አምራች ኩባንያዎች መስራት የሚችሉበትን አቅም ቀንሰው ከ50 እስከ 60 በመቶ እያመረቱ መሆናቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል። በተለይም ህንድ መሰረታዊ የሚባሉ መድኃኒቶችን 20 በመቶ ብቻ ለአፍሪካ መላኳ ከፍተኛ ተፅእኖን አስከትሏል። በዛምቢያዋ መዲና ሉሳካ የሚገኝ ኤፍሬም ፊሪ የተባለ ፋርማሲስት የመድኃኒት እጥረት እያጋጠመ እንደሆነ ገልጿል። "ክምችት ክፍላችን ውስጥ ያለው መድኃኒት በማለቅ ላይ ነው፤ በምን እንደምንተካው አናውቅም። ምንም ማድረግ አንችልም። በተለይም የፀረ ወባ መድኃኒቶችንና የህመም ማስታገሻን የመሳሰሉ መሰረታዊ መድኃኒቶች አቅርቦት የለም" ብሏል። ፈተናው ለመድኃኒት ሻጮች ብቻ ሳይሆን ለመድኃኒት አቅራቢዎችና አምራቾችም ነው። በተለይም ለመድኃኒት ግብአቶች የሚውሉ ጥሬ እቃዎች ዋጋ አልቀመስ ከማለቱ ጋር ተያይዞ የመድኃኒት አምራች ኩባንያዎች እንደ ቀድሞው ማምረት የማይታሰብ ሆኗል። በፓኪስታን የሚገኝ አንድ አምራች እንደተናገረው ከዚህ ቀደም ለወባ መድኃኒትነት የሚውለውን የሃይድሮክሎሮኪን ጥሬ እቃ ለመግዛት 100 ዶላር በኪሎ ይከፍል የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት ግን 1150 ዶላር ደርሷል። አገራት ድንበሮቻቸውን መዝጋታቸውን ተከትሎ የምርት መቀነስ ችግር ብቻ ሳይሆን የተከሰተው፤ ብዙዎች በፍራቻ መድኃኒት በማከማቸታቸው እጥረት ተከስቷል። ይህ የአቅርቦትና የፍላጎት አለመጣጣምም ነው ከደረጃ በታች የሆኑ እንዲሁም በአጠቃላይ ለሐሰተኛ መድኃኒቶች ሽያጭ በር የከፈተው። ሐሰተኛ መድኃኒቶች በዓለም ላይ ያሉ ፋርማሲስቶችም ሆነ የመኃኒት አምራቾች ዓለም አቀፉ የወባ መድኃኒት ስርጭት አደጋ ላይ እንደወደቀ ይናገራሉ። በተለይም የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተደጋጋሚ በዋይት ሐውስ በሚሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የወባ መድኃኒት የሆነው ክሎሮኪን ለኮሮናቫይረስ መድኃኒት ነው ማለታቸውን ተከትሎ የተፈጠረው ፍላጎት ገበያው ማቅረብ ከሚችለው በላይ ጨምሯል። ምንም እንኳን የዓለም ጤና ድርጅት የወባ መድኃኒቶች ኮሮናቫይረስን ለመፈወሳቸው ምንም አይነት ማስረጃ የለም ቢልም ትራምፕ አሁንም ቢሆን "ምን ታጣላችሁ? ዝም ብላችሁ መድኃኒቱን ውሰዱ" ብለዋል። ሐሰተኛ የወባ መድኃኒት ሽያጭ በኮንጎ እንዲህ ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ በናረበት ሁኔታም በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከፍተኛ መጠን ያለው ሐሰተኛ ክሎሮኪን ቢቢሲ ለማግኘት ችሏል። በኒጀርም እንዲሁ ሐተኛ የወባ መድኃኒት በዓለም የጤና ድርጅት መገኘት እንደተቻለ ተገልጿል። አንድ ሺህ እንክብሎችን የሚይዘው ክሎሮኪን የሚሸጠው 40 ዶላር ቢሆንም በኮንጎ 250 ዶላር እየተሸጠ ይገኛል። መድኃኒቱ ቤልጅየም ያለው ብራውን ኤንድ በርክ የተባለው የመድኃኒት አምራች ኩባንያ ያመረተው ነው እየተባለ ቢሸጥም፤ ኩባንያው በበኩሉ ይህንን መድኃኒት እንዳላመረተና ሐሰተኛ እንደሆነ አሳውቋል። የኮሮና ቫይረስ እየተዛመተ ባለበት ባሁኑ ወቅት የሐሰተኛ መድኃኒቶች ሽያጭ በከፍተኛ ሁኔታ ሊጨምር እንደሚችል የሚያስጠነቅቁት በሐሰተኛ መድኃኒቶች ላይ ተመራማሪ የሆኑት የኦስክፎርዱ ምሁር ፖል ኒውተን፤ አገራት ከፍተኛ ቁጥጥር ሊያደርጉ እንደሚገባና መተባበርም እንደሚያስፈልግ ምክራቸውን ለግሰዋል። አገራት የመድኃኒቶቹን ጥራት በተመለከተ ክትትል እንዲያደርጉና የስርጭቱንም ሁኔታ እንዲቆጣጠሩ አሳስበዋል።
48701205
https://www.bbc.com/amharic/48701205
በጋሪሳ ዩኒቨርስቲ ጥቃት ለ148 ህይወት መጥፋት ተጠያቂ የተባሉ ሶስት ሰዎች ተፈረደባቸው
ሶስት ግለሰቦች የዛሬ አራት ዓመት በኬንያ ጋሪሳ ከደረሰው ጥቃት ጋር በተያያዘ ተከሰው ፍርድ ተበይኖባቸዋል።
ራሺድ ቻርልስ ምቤሬሶ፣ ሞሐመድ ዓሊ አቢካር እና ሃሳን ኤዲን ሃሳን የተሰኙት እኒህ ግለሰቦች የጋሪሳውን ጥቃት ካቀነባበሩ መካከል ናቸው ተብለው ነው ፍርድ የተሰጠባቸው። አራት የታጠቁ ሰዎች ጋሪሳ ዩኒቨርሲቲ ገብተው 148 ተማሪዎችንና ሠራተኞች ነፍስ ያጠፉት በጎርጎሳውያኑ 2007 ላይ ነበር። • ኬንያ ሺሻን አገደች ግለሰቦቹ የአል-ሸባብ አባል ናቸው በሚልም ነው ፍርድ የተሰጠባቸው። አራተኛው ተከሳሽ ግን ነፃ ሆኖ በመገኘቱ ሊለቀቅ እንደቻለ ታውቋል። ነፃ የወጣውን ግለሰብ ጨምሮ ሶስቱ ግለሰቦቹ ኬንያውያን ሲሆኑ ራሺድ ቻርልስ የተባለው ግለሰብ ታንዛኒያዊ እንደሆነ ታውቋል። ራሱን የአል-ቃይዳ ክንፍ አድርጎ የሚቆጥረው አል-ሸባብ በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር 2007 ላይ ለተከሰተው የጋሪሳው ጥቃት ኃላፊነት መውሰዱ አይዘነጋም። በጎርጎርሳውያኑ አቆጣጠር 1998 ላይ አል-ቃይዳ የአሜሪካን ኤምባሲ አጋይቶ 200 ሰዎች ካለቁበት ክስተት በኋላ ሁለተኛው አሰቃቂ ጥቃት ነው የጋሪሳው እልቂት። • ኬንያ ሜሪ ስቶፕስን አገደች የቢቢሲው ኢማኑዔል ኢጉንዛ ፍርዱ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረ ነው ይላል፤ ከጥቃቱ ለተረፉ ትልቅ ትርጉም እንዳለው በመጠቆም። ለአራት ዓመታት ያክል የቆየው የፍርድ ሂደት የኬንያውያንን በተለይ ደግሞ ከጥቃቱ የተረፉትን ልብ አንጠልጥሎ የቆዬ እንደነበር ነው ኢጉንዛ የሚያስረዳው። መጋቢት 24/2007 ላይ በጋሪሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሃገር አማን ብለው ሳለ የደረሰው ጥቃት ጥበቃዎችን፣ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችና ሠራተኞችን ጨምሮ የ148 ሰዎችን ነፍስ ቀጥፏል። 500 ገደማ ተማሪዎች ደግሞ ጥቃቱን በመሸሽ ማምለጥ ችለዋል። 97 ግለሰቦች ደግሞ ክፉኛ አደጋ ደርሶባቸዋል። • 22 ኢትዮጵያዊያን ናይሮቢ ውስጥ ተያዙ
news-48898981
https://www.bbc.com/amharic/news-48898981
የእንግሊዝ አምባሳደር የትራምፕ አስተዳደርን 'የፈረሰ እና የተከፋፈለ' ሲሉ ወረፉ
አፈትልከው የወጡ ኢሜይሎ በአሜሪካ የብሪታኒያ አምባሳደር የሆኑት ኪም ዳሮች የትራምፕ አስተዳደርን 'ደካማ፣ በራሱ የማይተማመን፣ ክህሎት የሌለው እና ተወዳዳሪ ያልሆነ' ሲሉ ወረፉ።
አምባሳደሩ አፈትልከው በወጡ ኢሜይሎች ላይ ዋይት ሃውስ በዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ስር ''የፈረሰ'' እና ''የተከፋፈለ'' ነው ብለዋል። የብሪታኒያ የውጪ ጉዳይ ቢሮ አፈትልከው የወጡት ኢሜይሎች ''ከባድ ችግር ፈጥረዋል'' በማለት ሃሰተኛ አለመሆናቸውን አረጋግጧል። ዋይት ሃውስ በጉዳዩ ላይ ያለው ነገር የለም። አምባሳደሩ በተለዋወጧቸው መልዕክቶች የትራምፕ አስተዳደር ኃላፊነቱን በትክክል መወጣት መቻሉ ላይ ጥርጣሬያቸውን አስቀመጠዋል። በአሜሪካ የዩናይትድ ኪንግደም አምባሳደር ሰር ኪም ዳሮች አምባሳደሩ ትራምፕ ከሳምንታት በፊት በዩናይትድ ኪንግደም ያደጉት የሥራ ጉብኝት ''ተደንቀዋል'' ያሉ ሲሆን፤ አሁንም አስተዳደሩ ለራስ ፍላጎት ብቻ ቅድሚያ የሚሰጥ ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ''ይህ ምድር አሁንም ቅድሚያ ለአሜሪካ የሚባልበት ነው'' ሲሉም አክለዋል። አሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደም ከብሬክግዚት በኋላ ስለሚኖራቸው የንግድ ልውውጥ በሚመለከት ለመድረስ ላሰቡት የንግድ ስምምነት፤ በአየር ጸባይ ለውጥ፣ የመገናኛ ብዙኃን ሪፎርም እና በሞት ቅጣት ላይ ያላቸውን ልዩነት የንግድ ስምምነቱን ከግብ ለማድረስ ችግር እንደሚሆን በጽሑፋቸው ገልጻዋል። ፕሬዝደንቱን ስታገኘው ''ጉዳይህ እንዲገባው ቀላል ማድረግ ይኖርብኃል'' በሚል አምባሳደሩ የትራምፕን አእምሮ ውስብስብ ነገሮችን ለመረዳት እንደሚሳነው የሚጠቁም አስተያየት ሰጥተዋል። ከአንድ ወር በፊት በተላከ መልዕክት ሰር ኪም ዳሮች፤ አሜሪካ በኢራን ላይ ያላትን ፖሊሲ ''ወጥ ያልሆነ፣ የተጣረሰ'' ሲሉ አጣጥለውታል። አፈትልከው የወጡት ኢሜይሎች ከ2017 ጀምሮ የነበሩ ልውውጦች መሆናቸው ታውቋል። የዩናይትድ ኪንግደም የውጪ ጉዳይ ቢሮ ቃል አቀባይ ''የዲፕማሎማቶች አስተያየት የሚንስትሮች ወይም የመንግሥት አቋሞች ናቸው ማለት አይደለም። ይሁን እንጂ እውነታውን የሚያመላክቱ እንደሆኑ አድርገን እንወስዳቸዋለን'' ብለዋል። ቃል አቀባዩ ጨምረው እንደተናገሩት ሚንስትሮች እና የመሚለከታቸው የመንግሥት ኃላፊዎች ምክሩን እና ምልከታውን ይቀበላሉ። አምባሳደሮችም ይህን መሰል አስተያየቶችን ሚስጢራዊነቱ በተጠበቀ መልኩ ማስተላለፍ አለባቸው ብለዋል።
news-46450673
https://www.bbc.com/amharic/news-46450673
አሜሪካ ከ28 ዓመታት በኋላ ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮዋን በሶማሊያ በድጋሜ ጀመረች
አሜሪካ ከሶማሊያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከሰላሳ ዓመታት በኋላ እንደገና ጀመረች።
ምንም እንኳን አልሻባብ አሁንም የጎን ውጋት ቢሆንም በሞቃዲሾ ያለው ፀጥታ መሻሻል አሳይቷል የአሜሪካ መንግስት እንዳስታወቀው አጋጣሚው የምስራቅ አፍሪካ አገራት ያሳዩትን እድገት የሚያመላክት ታሪካዊ ቀን ነው። ከዚህ ቀደም ተቀማጭነቱን በኬንያ ናይሮቢ ያደረገው ኤምባሲ አሁን በሞቃዲሾ በሚከፈተው ኤምባሲ ዶናልድ ያማማቶ አምባሳደር እንደሚሆኑ ታውቋል። • የአይኤስ ታጣቂዎች ኢትዮጵያዊያንን ገደሉ አሜሪካ በአውሮፓውያኑ 1991 ጥር ወር በሶማሊያ በአማፅያኑ ቡድኖችና በመንግስት መካከል በተፈጠረ ግጭት ኤምባሲዋን ዘግታ አምበሳደሩንና ሰራተኞቿን ማስወጣቷ ይታወሳል። የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ሒዘር ኖርት አሁን የተደረገውን ለውጥ አስመልክተው በሰጡት አስተያየት "ይህ ታሪካዊ ቀን የሶማሊያን እድገት ያሳየ ነው፤ አሜሪካ በአገሪቱ የምታደርገውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከርም ይህ አንድ እርምጃ ነው" ብለዋል። ኤምባሲያቸውንም ተመልሰው መክፈታቸው በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ዘላቂነት ያለው ዲሞክራሲያዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማጠናከር እንደሆነ ገልፀዋል። የፀጥታ ጉዳይን በተመለከተ ምንም እንኳን አልሻባብ አሁንም ችግር ቢሆንም የሞቃዲሾ የፀጥታ ሁኔታ እየተረጋጋ እንደመጣ ሳይገልፁም አላለፉም - ቃል አቀባይዋ። • የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ41 ዓመታት በኋላ ወደ ሶማሊያ በረራ ጀመረ አልሻባብ የሶማሊያን መዲና ሞቃዲሾን ለቆ እንዲወጣ በአፍሪካ ኅብረት ወታደሮች ግፊት የተደረገበት ከ7 ዓመታት በፊት ነበር፤ ይሁን እንጂ አሁንም በአገሪቱ ተለያዩ አካባቢዎች ተፅዕኖው እንዳለ ነው። ባለፈው ዓመት የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በመዲናዋ ፀጥታ ለማምጣት ዘመቻቸውን አስፋፍተው ነበር፤ በዚህ ዓመትም በሰው አልባ የጦር ጀት ድብደባን ጨምሮ በወታደሮቿ ከ24 ጊዜ በላይ የአየር ድብደባ ፈፅማለች። በአውሮፓውያኑ 1993 አሜሪካ በሶማሊያ ሞቃዲሾ ባደረገችው ውጊያ ወቅት 18 የልዩ ኃይል ወታደሮቿ መገደላቸውን ተከትሎ አሜሪካ ጣልቃ መግባት ሰግታ ነበር። ባለፈው ወር 700 የሚሆኑ ሽብርተኛ ወታደሮች ከአፍሪካ ማስወታጣት መቻሏን አሜሪካ አስታውቃለች፤ ይሁን እንጂ አሁንም በሶማሊያ እያከናወኑት ያለው ተግባር ሰፊ እንደሆነ ገልፀዋል።
news-53386385
https://www.bbc.com/amharic/news-53386385
በደቡብ አፍሪካ ሠዓት እላፊ ሲታወጅ የአልኮል ሽያጭ በድጋሚ ተከለከለ
ደቡብ አፍሪካ ከሳምንታት በፊት አንስታው የነበረውን የአልኮል ሽያጭ ክልከላ መልሳ ተግባራዊ ያደረገች ሲሆን የኮሮናቫይረስ መስፋፋትን ለመቆጣጠር አዳዲስ ገደቦችንም ይፋ አድርጋለች።
ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ አሁን በደቡብ አፍሪካ የምሽት የሰዓት ዕላፊ ገደብ የተጣለ ሲሆን በተጨማሪም ከቤት ውጪ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ማድረግ ግዴታ ሆኗል። ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ እንዳሉት ለሁለተኛ ጊዜ የተጣለው የአልኮል ሽያጭ ክልከላ በአገሪቱ የጤና አገልግሎት ላይ ያለውን ጫና ይቀንሰዋል። መንግሥት ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በአጠቃላይ በአገሪቱ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ250 ሺህ ማለፉን ተከትሎ ነው። በደቡብ አፍሪካ እስካሁን በቫይረሱ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች አሃዝ ከ4 ሺህ በላይ የደረሰ ሲሆን በመንግሥት ግምት እስከ ጥር ወር ድረስ ቁጥሩ እስከ 50 ሺህ ሊደርስ ይችላል ተብሏል። ደቡብ አፍሪካ በአህጉሪቱ ውስጥ በበሽታው ክፉኛ የተጠቃች አገር ስትሆን ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ከዚህ ቀደም ከታየው ሁሉ በበለጠ በአንድ ቀን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ህሙማን ተገኝተዋል። ፕሬዝዳናንቱ ባደረጉት ንግግር አብዛኛው የአገሪቱ ዜጋ በሽታውን ለመከላከል ማድረግ ያለበትን እያከናወነ ሲሆን "አንዳንዶች ግን እራሳቸውንና ሌሎችን ከበሽታው ለመጠበቅ ማድረግ ያለባቸው እየፈጸሙ አይደለም" ሲሉ ወቅሰዋል። ፕሬዝዳናቱ እንዳስታወቁት አዲስ የተጣሉት እገዳዎች እስከ ነሐሴ ወር አጋማሽ ድረስ ተግባራዊ ሆነው ይቆያሉ። ደቡብ አፍሪካ 28 ሺህ የሆስፒታል አልጋዎችን ለኮሮናቫይረስ ህክምና ዝግጁ አድርጋለች። ነገር ግን ፕሬዝዳንቱ "አሳሳቢ" ያሉት ነርሶችን፣ ዶክተሮችንና የፊዚዮቴራፒ ባለሙያዎችን ጨምሮ 12 ሺህ የሚደርሱ የጤና ባለሙያዎች እጥረት በአገሪቱ እንዳለ ተናግረዋል። የአልኮል መጠጥ ሽያጭ ክልከላው በድጋሚ ተግባራዊ የሆነው ጸብን፣ የቤት ውስጥ ጥቃትንና የቅዳሜና እሁድ ከልክ ያለፈ የመጠጥ ልማድን ለመቆጣጠር ሲሆን፤ ቀደም ሲል ለሦስት ወራት ተጥሎ የነበረው ተመሳሳይ ዕገዳ የተነሳው ከሳምንታት በፊት ነበር። ሐኪሞችና ፖሊሶች እንደሚሉት ቀደም ሲል ተጥሎ የነበረው ክልከላ በድንገተኛ ሁኔታ ወደ ሆስፒታል በሚገቡ ሰዎች ቁጥር ላይ ከፍተኛ ቅናሽ እንዲታይ አድርጎ ነበር። ነገር ግን በአገሪቱ የሚገኙ የቢራና የወይን አምራች ፋብሪካዎች በአልኮል መጠጦች ላይ ተጥሎ የነበረው ክልከላ ከሥራ ውጪ አድርጎናል በማለት ሲያማርሩ ቆይተዋል።
news-52030447
https://www.bbc.com/amharic/news-52030447
ኮሮናቫይረስ፡ ዶናልድ ትራምፕ በአንድ ወር ውስጥ ከአገራቸው ኮሮና ይጠፋል ብለው ተስፋ አድርገዋል
ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ በአንድ ወር ውስጥ የኮሮናቫይረስን አራግፋ ትጥላለች ሲሉ ተናገሩ።
ከአሜሪካ ግዛቶች በሙሉ ኒውዮርክ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዳች ሆናለች ፕሬዝዳንት ትራምፕ አሜሪካ እስከ ፈረንጆቹ ፋሲካ ድረስ ከኮሮና ነጻ ትሆናለች ብለው ቢናገሩም የኒዮርኩ አገረ ገዢ ግን ወረርሽኙ በግዛታቸው "እንደ ፈጣን ባቡር በፍጥነት እየተምዘገዘገ" መሆኑን ገልፀዋል። ፕሬዝዳንቱ በዋይት ሐውስ ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ ወቅት የሚቀጥለው ወር መጀመሪያ "መልካም ጊዜ" ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል። ይህ የፕሬዝዳንቱ ተስፋ የተሞላበት ንግግር የተሰማው የዓለም ጤና ድርጅት አሜሪካ ቀጣይዋ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ማዕከል ትሆናለች ብሎ ስጋቱን ካስቀመጠ በኋላ ነው። አሜሪካ እስካሁን ድረስ 55 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 800 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል። • የአፍሪካ አገራት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እየደነገጉ ነው በዓለማችን ላይ በአጠቃላይ 420 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 19 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለፎክስ ዜና ተቋም ማክሰኞ ዕለት እንደተናገሩት ከ20 ቀናት በኋላ፤ ለፈረንጆቹ ፋሲካ ነገሮች ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው ይመለሳሉ ብለዋል። "በቅርብ ጊዜ ውስጥ የተዘጉ ተቋማት እከፈታሉ... ለፋሲካ ሁሉ ነገር ተከፍቶ የሚታይባት አገር እንድትኖረኝ እፈልጋለሁ" ብለዋል። በዚሁ ቃለ ምልልስ ወቅት እንደተናገሩት "ፋሲካ ለእኔ ልዩ ቀኔ ነው። በመላ አገሪቱ ቤተክርስቲያናት በሰዎች ተሞልተው ይታያሉ" ሲሉ ተስፋቸውን ተናግረዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ አገራቸው ዳግም የተዘጉ የንግድ ተቋማት ተከፍተው ወደ ሥራ ካልገባች "ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ድቀት ወይንም ውድቀት ይገጥማታል" ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ በመቀጠልም "በርካታ ሰዎችን ልናጣ፣ በርካታ ሺህ ሰዎች ራሳቸውን ሊያጠፉ ይችላሉ። ሁሉም ነገር ሊከሰት ይችላል። አለመረጋጋት ሊከሰት ይችላል" ብለዋል። በጽህፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ ወቅትም "ከዋሻው መውጫ ላይ ብርሃን ይታየኛል" ሲሉ ተስፋቸውን ገልፀዋል። ከዚያም "ውሳኔያችን በጠንካራ እውነታ ላይና በመረጃ ላይ የተመሰረተ ይሆናል" ብለዋል። የትራምፕ አስተዳደር የኮሮናቫይረስ ግብረ ኃይል አባል የሆኑት ዶ/ር አንቶኒ ፋኡቺ ግን "በኒውዮርክ የሚሆነውን ነገር የሚያይ ሰው ጉዳዩን ቀለል አድርጎ ሊገምት አይችልም " ሲሉ ተናግረዋል።
50470322
https://www.bbc.com/amharic/50470322
ሥራ ቦታ ጋደም ማለት መፈቀድ አለበት?
አሜሪካ፤ ሠራተኞች ቢሮ ውስጥ ጋደም ማለት የለባቸውም የሚል አቋም ስታራምድ ቆይታለች። በቅርቡ ደግሞ ቢሮ ውስጥ አጠር ላለ ጊዜ መተኛት በሕግ ተከልክሏል።
ሜትሮናፕ በዩኒቨርስቲ፣ በአውሮፕላን ማረፊያ፣ በሆስፒታል ውስጥ ይገኛል ሕጉ፤ ያለ ኃላፊዎች ፍቃድ ቢሮ ውስጥ መተኛትን ያግዳል። ሕጉን ማውጣት ለምን እንዳስፈለገ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም። ሕግ አውጪዎቹም በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አይደሉም። ከዓመት በፊት ከካሊፎርንያ የወጣ ሪፖርት እንደሚያሳየው፤ ሞተር ነጂዎች በቀን ቢያንስ ለሦስት ሰዓት ጋደም ማለታቸው የሞተር ሳይክል ተቋምን ከ40,000 ዶላር በላይ አሳጥቶታል። • የሥራ ቦታ ወሲባዊ ትንኮሳ የቱ ነው? • ሥራ እና ፍቅር፡ ከሥራ አጋርዎ ጋር የፍቅር ግንኙነት መጀመር ሊያስባርር ይገባል? በእርግጥ በሥራ ቦታ ላይ ዘለግ ላለ ሰዓት መተኛት ሥራ ላይ ጫና ቢያሳድርም፤ አጭር ጊዜ ጋደም ማለት ውጤታማ ያደርጋል የሚሉ ተመራማሪዎች አሉ። በአሜሪካ የእንቅልፍ ህክምና ተቋም ፕሬዘዳንት የሆኑት ዶ/ር ሎረንስ ኤፕስቲን እንደሚሉት፤ 70 ሚሊዩን የሚደርሱ አሜሪካውያን የእንቅልፍ መዛባት ችግር አለባቸው። ከ150,000 ሰዎች መካከል በቀን ከሰባት ሰዓት እስከ ስምንት ሰዓት የሚተኙት 35.6 በመቶዎቹ ብቻ መሆናቸውን አንድ ጥናት አሳይቷል። ቁጥሩ በሁለት ዓመት ውስጥ ወደ 30.9 በመቶ ወርዷል። በቂ እንቅልፍ ከማያገኙት ሰዎች ገሚሱ ፖሊሶችና የህክምና ባለሙያዎች ናቸው። ዶ/ር ሎረንስ ኤፕስቲን እንደሚናገሩት፤ ይህንን ችግር ያስተዋሉ መሥሪያ ቤቶች ለውጥ ለማምጣት እየሞከሩ ቢሆንም መንግሥት ግን የድርሻውን እየተወጣ አይደለም። እንቅልፍ ማጣት የሰዎች ጤናና ኢኮኖሚ ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ዶ/ር ሎረንስ ያስረዳሉ። እንቅልፍ ማጣት ከመጠን ያለፈ ውፍረት፣ የልብ ህመም፣ ስትሮክ፣ ስኳር፣ ድብርትና ሌሎችም የአዕምሮ ህመሞች እንደሚያስከትል ባለሙያዎች ይናገራሉ። ከአራት ዓመት በፊት የወጣ ጥናት እንደሚያሳየው፤ እንቅልፍ ባጡ ሠራተኞች ሳቢያ በዓመቱ፣ በአሜሪካ ምጣኔ ሀብት ላይ የ411 ቢሊየን ዶላር ጫና ይደርሳል። ዶ/ር ሎረንስ ኤፕስቲን እና ሌሎቸም ተመራማሪዎች ሠራተኞች ቢሮ ውስጥ ለአጭር ጊዜ መተኛት ሊፈቀድላቸው ይገባል ይላሉ። • ሥራ የማዘግየት ልማድን ለመቅረፍ የሚረዱ 8 ነጥቦች • በጃፓን ሴት ሠራተኞች መነጽር እንዳያደርጉ መከልከላቸው ጥያቄ አስነሳ "በአግባቡ ያልተኙ ሰዎች ውጤታማ አይሆኑም፤ በሥራ ቦታ አደጋ አስከትለው ቀጣሪዎችን ለተጨማሪ ወጪ ሊዳርጉም ይችላሉ" ይላሉ። ሠራተኞች ጋደም እንዲሉ በመፍቀድ ረገድ ጃፓን ጥሩ ተሞክሮ አላት። ረዥም ሰዓት የሚሠሩ ሠራተኞች የሚተኙበት ክፍል ይዘጋጃል። ለሠራተኞቻቸው ምቹ ወንበርና ብርድ ልብስ የሚያቀርቡ ድርጅቶችም አሉ። ካናዳ ውስጥ 'ናፕ ኢት አፕ' የተባለ ለሠራተኞች በ25 ደቂቃ መተኛ ክፍል የሚያከራይ ድርጅት አለ። መስራቿ ለረዥም ሰዓት በባንክ ውስጥ ትሠራ የነበረችው ማህዝባን ራህማን ናት። 'ሜትሮናፕ' የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን እውቅናው እየጨረ መጥቷል። በተለይም 24 ሰዓት አገልግሎት የሚሠጡ እንደ ሆስፒታል፣ አውሮፕላን ማረፊያ እና ፋብሪካ ያሉ ተቋሞች ይህን አማራጭ ይጠቀማሉ። ማህዝባን ራህማን እንደምትለው፤ ሥራውን ሲጀምሩ ብዙ ደጋፊ አልነበራቸውም። "ስንጀምር፤ ብዙዎች ሥራ ቦታ መተኛትን የምናበረታታ መስሏቸው ነበር" ትላለች። አሁን ግን ሠራተኞቻቸው ጋደም ብለው ወደ ሥራ በመመለሳቸው ውጠታማ መሆናቸውን ያስተዋሉ ድርጅቶች ሀሳባቸውን እየቀየሩ ነው።
news-55882700
https://www.bbc.com/amharic/news-55882700
የሞስኮው ፍርድ ቤት አሌክሲ ናቫልኒ ይታሰር የሚለውን ክስ እያየ ነው
በሩሲያ ፖለቲካ ውስጥ ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠውና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ የሆነው አሌክሲ ናቫልኒ ጉዳይ በፍርድ ቤት መታየት ጀምሯል።
አሌክሴ ናቫልኒ በሩሲያ ከተመረዘ በኋላ በርሊን ህክምናውን ተከታትሎ ወደ ሩሲያ ሲመለስ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወቃል። በአሁኑ ወቅት የሞስኮው ፍርድ ቤት እያየው ያለው በጊዜያዊነት በቁጥጥር ስር ያለው አሌክሲ ናቫልኒ ወደ እስር ይቀየር የሚለውን ጉዳይ ነው። የተቃዋሚው እስር ከፍተኛ ተቃውሞ በሞስኮ ያስነሳ ሲሆን በዛሬው ዕለት ከፍርድ ቤት ውጭ በርካታ ፖሊሶች ተሰማርተዋል። አንዳንዶቹ ፖሊሶች በፈረስ የፍርድ ቤቱን ሁኔታ እየተቆጣጠሩ ነው ተብሏል። በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። የሩሲያ መረጃ መቆጣጠሪያ ቡድን ባወጣው መረጃ መሰረት ፍርድ ቤቱ አካባቢ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ቁጥር 120 አድርሶታል። የፕሬዚዳንቱ ከፍተኛ ተቺ ነው የሚባለው አሌክሲ ከፍተኛ ተቃውሞ ባስነሳው ክሱ ሶስት አመት ተኩል እስር ይጠብቀዋል ተብሏል። የ44 አመቱ ፖለቲከኛ የተከሰሰበትን የገንዘብ መመዝበርና ማጭበርበር ክስ የተፈበረከ ነው ይላል። ህይወቱ በተአምር የተረፈችው አሌክሲ ወደ ሩሲያ በድፍረት ከሁለት ሳምንታት በፊት ሲመለስ በርካታ ሰዎች ድጋፋቸውን ለማሳየት ሰልፈው ወጥተዋል። በርካታዎቹ ደጋፊዎቹ ወጣቶች ናቸው ተብሏል። አሌክሲ በአውሮፓውያኑ 2014 ቢከሰስም እስር አልተፈረደበትም ነበር። በየጊዜው ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግም የክሱ በይደር ይቆይ አካል ስምምነት ነበር። ፖሊስ ይህንን ስምምነት ጥሷል እያለ ቢሆንም ጠበቆቹ በበኩላቸው ትርጉም የሌለው ነው ይላሉ። ለዚህ እንደ ምክንያትነት የሚያቀርቡት ባለስልጣናቱ አሌክሲ በከፍተኛ የነርቭ መጎዳት በሞትና በህይወት መካከል ሆኖ በርሊን ውስጥ ህክምናውን እየተከታተለ እንደነበር ያውቃሉ ይላሉ። ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረው አሌክሲ "በፅኑ ህመም ታምሜ በሰመመን ውስጥ ነበር የነበርኩት። ከሆስፒታል ስወጣ ጠበቆቼን አናግሬ የነበርኩበትን ሁኔታ የሚያስረዳ መረጃ ልኬያለሁ። እውነት ነው ቤቴ አልነበርኩም! ከዚህ በላይ ግን ምን ማድረግ እችላለሁ?" ብሏል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከሳምንት በፊት በአሌክሲ የተለቀቀ አንድ የቪዲዮ ሪፖርት ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ያወጣል ተብሎ የሚገመት እጅግ ቅንጡና ግዙፍ መኖርያ ቤት ንብረትነቱ የፑቲን እንደሆነ የሚገልፅ ነበር። ቪዲዮው በመላው ሩሲያ መነጋገርያ ከመሆኑም በላይ በአጭር ጊዜ ውስጥ መቶ ሚሊዮን ሰዎች ተመልክተውታል፡፡ የቪዲዮውን መውጣት ተከትሎም ተቃውሞዎች ተበራክተው ነበር፡፡ የዚህ ቤተመንግሥት ቪዲዮ በሩሲያ የማኅበራዊ ሚዲያዎች ትልቅ መነጋገርያ ከሆነ በኋላ ተቃውሞዎች ፈንድተው ከ4ሺ በላይ ሰዎች ታስረዋል፡፡ ከአሌክሴ ጋር ግንኙነታ አላቸው የተባሉ ሚዲያዎችና ግለሰቦች ተለቅመው የታሰሩ ሲሆን በሰብአዊ መብት ዙርያ የሚሰሩ በርካታ ድርጅቶችም ተዘግተዋል፡፡
48305969
https://www.bbc.com/amharic/48305969
ፌስቡክ አፍሪካ ላይ የተቃጡ ገጾችን ዘጋ
ፌስቡክ በመቶዎች የሚቆጠሩና አፍሪካ ላይ አነጣጥረዋል ያላቸውን ገጾችና አንድ የእስራኤል ተቋምን ማገዱን ይፋ አድርጓል።
ፌስቡክ ሀሰተኛ ናቸው ያላቸው ገጾች በተለያዩ ሀገሮች ስለሚካሄዱ ምርጫዎችና ስለሌሎችም ፖለቲካዊ ጉዳዮች መረጃ የሚሰራጭባቸው ነበሩ ተብሏል። • ፌስቡክ የሞቱ ሰዎችን ገፅ ለማስተዳደር አዲስ አሰራር ቀየሰ ፌስቡክ ያስወገዳቸው 265 ገጾች መነሻቸው እስራኤል ሲሆን፤ በሴኔጋል፣ በቶጎ፣ በአንጎላ፣ በኒጀር፣ በቱኒዝያ እንዲሁም በላቲን አሜሪካና ደቡብ ምስራቅ እስያ ላይ ያተኮሩ መረጃዎች ያሰራጩ ነበር። ፌስቡክ የተሳሳተ መረጃን ከድረ ገጹ አያስወግድም በሚል በተደጋጋሚ ይተቻል። ከአራት ዓመታት በፊት የመረጃ ትክክለኛነት የሚጣራበት አሠራር መጀመሩ ይታወሳል። • ፌስቡክ የጽንፈኛ አመለካከት አራማጆችን ሊያግድ ነው ፌስቡክ ካገዳቸው ገጾች ጀርባ ያሉ ግለሰቦች ሀሰተኛ ገጽ በመጠቀም የተሳሳተ መረጃ ይነዙ እንደነበረ ፈስቡክ ባወጣው መግለጫ አትቷል። በሀሰተኛ ገጾቹ ይሰራጩ የነበሩ መረጃዎች በርካታ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ጋር እንዲደረሱም ተደርጎ ነበር። የፌስቡክ የደህንንት ፓሊሲ ኃላፊ ናትናዬል ግሌይቸር እንደተናገሩት፤ ግለሰቦቹ በተለያዩ ሀገራት የሚሠሩ መገናኛ ብዙሀንን በመምሰል ስለፖለቲከኞች ተደብቀው የነበሩ መረጃዎች "አጋልጠናል" እያሉ የያሰራጩ ነበር። • ፌስቡክ የተጠቃሚዎችን ግላዊ መረጃ መበርበሩን አመነ 'አርቺሜድስ ግሩፕ' የተባለ የእስራኤል ተቋም ከነዚህ እንቅስቃሴዎች ጀርባ እንዳለ በምርመራ እንደደረሱበትም ኃላፊው ተናግረዋል። የፌስቡክ ገጾቹን የፈጠሯቸው ሰዎች እንደ አውሮፓውያኑ ከ2012 እስከ 2019 ለማስታወቂያ ወደ 812,000 ዶላር ገደማ ከፍለዋል። ገንዘቡ የተከፈለው በብራዚል፣ በእስራኤልና በአሜሪካ መገበያያ ገንዘብ ነው። ኢላማ ከተደጉት ስድስት የአፍሪካ ሀገሮች አምስቱ በ2010 ሀገር አቀፍ ምርጫ ያካሄዱ ሲሆን፤ የቱኒዝያ ምርጫ በሚቀጥለው ዓመት ይካሄዳል። ፌስቡክ ምርጫ በሚካሄድበት ወቅት የሰዎች ውሳኔ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ የተሰሳቱ መረጃዎችን ባለማገዱ ሲተች ቆይቷል።
54521496
https://www.bbc.com/amharic/54521496
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ተፈታ
በትናንትናው ዕለት (ረቡዕ )በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረው የፍትህ መፅሄት ዋና አዘጋጅና ባለቤት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በዛሬው እለት መፈታቱን ቢቢሲ ከወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ መረዳት ችሏል።
በዛሬው ዕለት፣ ጥቅምት 5፣ 2013 ዓ.ም ጥዋት በእስር ላይ የነበረበት አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተመስገንን ለመጠየቅም ሲያመራ መግባት አይቻልም ተብሎ እንደነበረና ፍርድ ቤት ሊያቀርቡት ይችላሉ በሚል እሳቤም እዛው እየጠበቁ የነበረ ቢሆንም ተፈትቶ ማየቱን አስረድቷል። ከሱ በተጨማሪ የፍትህ መፅሄት አዘጋጁ ምስጋናው ዝናቤም መፈታቱን ታሪኩ አክሎ ገልጿል። ለምን በቁጥጥር ስር እንደዋለም ይሁን የተፈታተበትንም ምክንያት በተመለከተ ምንም አይነት መረጃ እስካሁን እንዳላገኙም ታሪኩ ያስረዳል። በትናንትናው ዕለትም ታሪኩ ለጥቂት ደቂቃዎች እንዳገኘውና ለምን እንደታሰረ በጠየቀው ወቅት "የሐሰት ወሬ በማሰራጨት ትፈለጋለህ ከሚል ውጪ የነገሩኝ ነገር የለም።" "እኔም ጠበቃዬ ሳይመጣ ቃል አልሰጥም ብዬ ቁጭ ብያለሁ። ይልቅ ብርድ ልብስ እንዲገባልኝ ሞክር" ማለቱንም ታሪኩ በፌስቡክ ገፁ አስፍሯል። ረቡዕ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ አዲስ አበባ ስምንት የሚሆኑ ፖሊሶች አቧሬ የሚገኘው የፍትህ ቢሮ መጥተው እንደነበርና በወቅቱም ቢሮ ያልነበረው ተመስገን የመፅሄቱ አዘጋጆች ደውለው ሁኔታውን እንዳስረዱት ከታሪኩ የተገኘው መረጃ ጠቁሟል። ተመስገን በስልክ ከፖሊሶቹ ጋር የተነጋገረ ሲሆን መጥሪያ ወይም የክስ ወረቀት ይዘው ከሆነ ቢሮው እንዲተዉለት ነግሯቸው እንደነበርም ተገልጿል። ፖሊሶቹ በበኩላቸው እሱን ማናገር እንደሚፈልጉና ያለበትን እንዲነግራቸው በጠየቁት መሰረት እራሱ ፖሊሶቹን በአካል ለማግኘት ወደ ቢሮው መመለሱን ታሪኩ ጠቅሷል። ፖሊሶችም መኪናቸው ውስጥ አስገብተው ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በተለምዶ ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዱንም አክሎ ገልጿል። የፍትህ መፅሄት አዘጋጅ ምስጋናው ዝናቤም ከተመስገን ጋር እንደተወሰደ ታሪኩ ለቢቢሲ ተናግሯል። ከሰሞኑ ተመስገን እታሰራለሁ የሚል ፍራቻ ነበረው ወይ ተብሎ ከቢቢሲ ለቀረበለት ጥያቄ ምንም አይነት ስጋት እንዳልነበረው ወንድሙ አስረድቷል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ስለጋዜጠኛው መታሰር ተጠይቆ ጉዳዩ የፌደራል ፖሊስን እንደሚመለከተው በመግለጽ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቧል። ቢቢሲ ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ፌደራል ፖሊስ ቢደውልም በተመሳሳይ መልኩ ምላሽ ማግኘት አልቻለም። በሳምንታዊው ፍትህ መጽሔት ላይ በቅርቡ የተሾሙትን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳናች አቤቤን በሚመለከት ከወጣው ጽሁፍ ጋር በተያያዘ መጽሔቱን በተመለከተ፤ ለኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የተጻፈ ደብዳቤ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲዘዋወር በመቆቱ እስሩ ከዚሁ ጉዳይ ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ተገምቷል። ከዚህ ቀደም ለሦስት ዓመታት በማረሚያ ቤት የቆየው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የእስር ጊዜውን አጠናቅቆ መውጣቱ ይታወሳል። ጋዜጠኛ ተመስገን በወቅቱ ለእስር የተዳረገው የፍትህ ጋዜጣ ላይ በጻፋቸውና ባሳተማቸው ጽሁፎች ምክንያት ነበር። በጋዜጠኛው ላይ የቀረቡት ክሶችም በሐሰት የመወንጀል፣ ስም የማጥፋት፣ የሐሰት ወሬዎች የመዘገብ እና ማሰራጨት፣ የሕዝብን አስተሳሰብ ማናወጥ እንደዚሁም ሕዝብ እንዲያምጽ መገፋፋት የሚሉ ነበሩ። ተመስገን ጉዳዩን በፍርድ ቤት ሲከታተል ቆይቶ በአንደኛው ክስ ብቻ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ለሦስት ዓመት እስራት ተፈርዶበት እንደነበር ይታወሳል
news-52829811
https://www.bbc.com/amharic/news-52829811
ዶናልድ ትራምፕ ፌስቡክን ሊዘጉት ይሆን?
ዶናልድ ትራምፕ በትዊተር ሰሌዳቸው ያሻቸውን ነገር ሲጽፉ ነው የኖሩት፡፡ በማኅበራዊ ገጻቸው ስለሚጽፉት ነገር ሃይባይ አልነበራቸውም።
ትዊተር ግን ትናንት ያልተጠበቀ ነገር አደረገ። የፕሬዝዳንቱ ሰሌዳ ላይ ከተጻፈው ሐሳብ ሥር ‹‹የትራምፕ መልዕክት እውነታነት ሊጤን ይገባዋል›› የሚል ምልክት አደረገ። ይህ የሚሆነው አንድ ተጠቃሚ የሐሰት ወይም ያልተረጋገጠ ሐሳብ ሲጽፍ ወይም ሲዘባርቅ ነው። ይህ የትዊተር ድርጊት ፕሬዝዳንቱን ሳያበግናቸው አልቀረም። እንዲያውም ዛሬ ዶናልድ ትራምፕ እነዚህ ማኅበራዊ 'አሳሳች ሊሆን ይችላል' አለ እርግጥ ፕሬዝዳንቱ ይህን ማድረግ የሚያስችል ሥልጣን አላቸው ወይ የሚለው አነጋጋሪ ጉዳይ ነው። የሕግ መወሰኛው ምክር ቤትና የሕግ መምሪያው ምክር ቤት በአንድ ሊደግፋቸው ይገባ ይሆናል። ስለዚህ ከእለታት አንድ ቀን ብድግ ብለው ፌስቡሚዲያ የተባሉትን ጠራርጌ እዘጋቸዋለሁ ሲሉ ዝተዋል። ሆኖም እርሳቸው እነ ፌስቡክን ለመዝጋት የማያዳግም ፍጹማዊ ሥልጣኔን እጠቀማለሁ እያሉ ነው። ‹‹ኤክዝኪዩቲቭ ኦርደር›› ይሉታል በነርሱ አገር። ይህንን ሲሉ ምን ማለታቸው እንደሆነ ማብራሪያ ለመጠየቅ ጋዜጠኞች ብዙ ሞክረዋል። ሆኖም ፕሬዝዳንቱም የነጩ ቤተ መንግሥት ቃል አቀባዮችም ታሪካዊዋ መንኮራኮር ስትመጥቅ ለማየት ኬኔዲ የሕዋ ማዕከል ፍሎሪዳ በማቅናታቸው በሚፈለገው ፍጥነት ምላሽ አልተገኘም። በኤይር ፎርስ ዋን ከፕሬዝዳንቱ ጋር ወደ ፍሎሪዳ ያቀኑ ጋዜጠኞችም ጥያቄውን ለማንሳት ሞክረው ምላሽ አላገኙም። ዶናልድ ትራምፕ ‹‹የማያዳግም ፍጹማዊ ፊርማዬን ፈርሜ›› አፈር ከድሜ አበላቸዋለሁ የሚሏቸውን እነ ፌስቡክን የሚከሱት የወግ አጥባቂ አመለካከቶችንና ሐሳቦችን ሳንሱር ያደርጋሉ በሚል ነው። በሌላ አነጋገር እነ ፌስቡክ የዲሞክራቶች ደጋፊ ናቸው ወይም ለነርሱ ያደላሉ ሲሉ ይከሷቸዋል። በዶናልድ ትራምፕ የትዊተር ሰሌዳ ላይ በድፍረት መጥቶ ‹‹እውነት ስለመሆኑ እጠራጠራለሁ›› የሚል ምልክት ያደረገው ትዊተር ቁጡውን ፕሬዝዳንት ይበልጥ እንዲቆጡ ሳያደርጋቸው አልቀረም። ለዚህም ይመስላል ፕሬዝዳንቱ ወደዚያው የትዊተር ገጻቸው ዳግም በመመለስ፤ ‹‹ማኅበራዊ ሚዲያዎች አሁንስ የሚሰራቸውን አሳጥቷቸዋል፤ ይህ እብደት ነው። የ2020ውን የአሜሪካ ምርጫ ሳንሱር ሊያደርጉት ይሻሉ። በ2016 ሞክረውት አልተሳካላቸውም። አሁንም ያን ሊያደርጉ ይፈልጋሉ። ምን እንደማደርጋቸው እኔ ነኝ የማውቀው፤ ጠብቁኝ›› የሚል ይዘት ያለው ዛቻ ጽፈዋል። ዶናልድ ትራምፕ በትዊተር ከ80 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ተከታይ አላቸው። የትዊተሩ አለቃ ጃክ ዶርሲ ለፕሬዝዳንቱ ትችት በትዊተር ሰሌዳው ምላሽ ሰጥቷል። ‹‹ለዚህ ኩባንያ ድርጊት ተጠሪ የሆነ ሰው አለ፤ ያ ሰው እኔ ነኝ። ሰራተኞቼን ለቀቅ ያድርጉ። ሐሰተኛ አምታች መረጃዎችን መመንጠሩን እንቀጥልበታለን›› ብሏል። ይህ የሚስተር ዶርሲ ምላሽ ዶናልድ ትራምፕን ይበልጥ ሊያቆስላቸው እንደሚችል ይጠበቃል። ዶናልድ ትራምፕ በትዊተር ሰሌዳቸው የ ‹‹ይጣራ›› ምልክት የተደረገባቸውን ሐሳብ ፌስቡክም ላይ ለጥፈውት የነበረ ሲሆን ፌስቡክ ግን ምንም እርምጃ አልወሰደባቸውም። ፌስቡክ በተለይ ወረርሽኙን በተመለከተ የሚነዙ ሐሰተኛ መረጃዎችን አጠፋለሁ እያለ ሲዝት ከርሞ ነበር። ፕሬዝዳንቱን ለምን ሃይ ለማለት እንዳልደፈረ ለጊዜው አልታወቀም። ፎክስኒውስ ላይ በዚህ ጉዳይ ቃለ መጠይቅ የተደረገለት የፌስቡኩ አለቃ ማርክ ዙከርበርግ ግን የፕሬዝዳንቱን ዛቻ አጣጥሎታል፡፡ ‹‹ በሳንሱር የሚከሰሰውን ማኅበራዊ ሚዲያ ሳንሱር ለማድረግ መነሳት በራሱ ይጣረሳል›› ሲል ተችቷል። ይህን የዶናልድ ትራምፕና የትዊተር እሰጣገባን ተከትሎ የፌስቡክና የትዊተር የስቶክ ገበያ ትናንት ተቀዛቅዞ ነበር ተብሏል። ቢቢሲ ለዚህ ዘገባ የፌስቡክ፣ የትዊተርና የጉግል ኃላፊዎችን ሐሳብ ለማካተት ያደረገው ሙከራ በጊዜው ምላሽ ሳያገኝ ቀርቷል።
news-51780953
https://www.bbc.com/amharic/news-51780953
በኮሮናቫይረስ ምክንያት የሴሪ አ ውድድሮች ካለተመልካች ሊካሄዱ ነው
በኮሮናቫይረስ በአውሮፓ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው በሞተባት በጣሊያን የሴሪ አ እግር ኳስ ግጥሚያዎችን ጨምሮ ሁሉም የስፖርት ውድድሮች ለአንድ ወር ያህል ለተመልካች ዝግ ሆነው እንደሚካሄዱ ተገለጸ።
በተጨማሪም መንግሥት በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ ያለውን ይህንን በሽታ ለመግታት ሲል ሁሉም ትምህርት ቤቶች ለ10 ቀናት እንዲዘጉ አዟል። በአውሮፓዊቷ ጣሊያን ውስጥ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መቀስቀሱ ከታወቀ በኋላ የሟቾች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ጨምሮ 197 መድረሱ ተነግሯል። የአገሪቱ ባለስልጣናት እንደገለጹት በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ 49 ሰዎች በበሽታው ህይወታቸውን አጥተዋል። በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከ4600 በላይ ደርሷል። በኅዳር ወር የበሽታው ወረርሽኝ ከተቀሰቀሰባት ቻይና ቀጥሎ ጣሊያን ብዙ ሰዎች በኮሮናቫይረስ የሞተባት አገር ሆና ተመዝግባለች። የዓለም የጤና ድርጅት እንዳለው እስካሁን ድረስ በሽታው በተገኘባቸው አገራት ውስጥ 100 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተይዘዋል። ከዚህ ሁሉ የባሰው ደግሞ በአራት ወር ውስጥ ከ3 ሺህ በላይ ሰዎች በበሽታው ሲሞቱ አብዛኛው ሞት ያጋጠመው ደግሞ ቻይና ውስጥ መሆኑ ነው። የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶክትር ቴድሮስ አድሃኖም የበሽታውን መስፋፋት "በጣም አሳሳቢ" በማለት የገለጹት ሲሆን ሁሉም አገራት ወረርሽኙን መግታት ቀዳሚና ዋነኛው ተግባራቸው እንዲሆን ጠይቀዋል። የጣሊያን ባለስልጣናት ከፍተኛውን የሟቾች ቁጥር ይፋ ያደረጉት ትናንት ነው። የጣሊያን ብሔራዊ የጤና ኢንስቲቲዩት እንዳለው የሞቱት ሰዎች አማካይ ዕድሜ 81 ሲሆን አብዛኞቹ ሌላ የጤና ችግር የነበረባቸው ነበሩ። ከሟቾቹ ውስጥም 72 ከመቶ የሚሆኑት ወንዶች ናቸው። ጣሊያን በዓለም ላይ በርካታ በዕድሜ የገፉ ሰዎች ከሚኖሩባቸው አገራት መካከል አንዷ ናት።
news-43482621
https://www.bbc.com/amharic/news-43482621
እስራኤል የሶሪያን ኒውክሌር ማብላያ መምታቷን አመነች
የእስራኤል ጦር ኃይል መዝገቦች ለመጀመሪያ ለሕዝብ ጊዜ ክፍት መደረጋቸውን ተከትሎ ሃገሪቱ በአውሮፓውያኑ 2007 ሶሪያ ውስጥ የሚገኝ የኒውክሌር መሣሪያ ማብላያ ማውደሟን ይፋ አድርጋለች።
በሶሪያ በስተምሥራቅ ባለ ዴይር አል ዙር በተሰኘ አካባቢ ላይ በሚገኝ የኒውክሌር ማብላያ ላይ ''ለእስራኤልም ሆነ ለአካባቢው ሃገራት አስጊ'' ሆኖ በመገኘቱ ነው የአየር ኃይል ጥቃት የተፈፀመው። በተጨማሪም ማብላያው ሥራውን እያጠናቀቀ እንደነበር የእስራኤል ወታደራዊ ኃይል አስታውቋል። ምንም እንኳ ጥቃቱን ያደረሰችወው እስራኤል እንደነበረች ቢታመንም ቴል-አቪቭ ጉዳዩን ስታስተባብል ነበር። ሶሪያ በበኩሏ ጥቃት የደረሰበት አካባቢ የኒውክሊዬር ማብላያ አይደለም በማለት ስትክድ ቆይታለች። እስራኤል ጥቃቱን ማድረሷን ለማመን የተገደደችው ስለጥቃቱ ማውራት ይከለክል የነበረው እገዳ በመነሳቱ ነው። ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ አካባቢው ከድሮም የኒውክሊዬር ማብላያ መሆኑ ''አያጠራጥርም ነበር" ይላል። አክሎም ማብላያው የተገነባው በሰሜን ኮርያ እገዛ ሊሆን እንደሚችልም ድርጅቱ ይገምታል። ሶሪያ 'ነን ፕሮሊፈሬሽን ትሪቲ' የተሰኘውና ኒውክሌር ማብላላ የሚያግደውን ስምምነት የተቀላቀለች ሲሆን ማብላያ የለኝም ብላ የካደችበት ዋነኛ ምክንያትም ይህ ሊሆን እንደሚችል ተነግሯል። የእስራኤል ወታደራዊ ኃይል ምን ይላል? ለሕዝብ ይፋ ከሆኑት ወታደራዊ መረጃዎች መካከል እስራኤል በሶሪያ አል ካቡር ላይ ያደረሰችውን ጥቃት የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽና ቋሚ የፎቶ ፊልሞች ይገኛሉ። ''በአውሮፓውያኑ መስከረም 2007 የእስራኤል አየር ኃይል ሥራ ላይ የነበረውን የሶሪያን ኒውክሌር ማብላያ ጣብያ በምሽት መምታቷን ወታደራዊ ኃይሉ የሰጠው መግለጫ ያትታል። እስራኤል '4 ኤፍ-ሲክስቲን' እና '4 ኤፍ-ፊፍቲን' የተሰኙ የጦር አውሮፕላኖችን በመጠቀም አካባቢውን ማፈንዳቷንም አሳውቀዋል። በመግለጫው ላይ ''ጥቃቱን ያካሄድነው የእስራኤልን ደህንነት ስጋት ላይ የሚጥል በመሆኑ የእስራኤልን ህልውና ሊፈትኑ የሚችሉ በመሆናቸው ነው'' የሚል አንቀፅ ሰፍሯል። የኢራን ወታደራዊ ኃይል ሶሪያ ከገባበት ጊዜ አንስቶ እስራኤል ቀጣናውን በንቃት ከመጠበቅና ማስጠንቀቂያዎች ከመሰንዘር አልተቆጠበችም።
news-44397983
https://www.bbc.com/amharic/news-44397983
ካለሁበት 35፡ አቧራ እንደ ዝናብ ሲዘንብ አይቼ ስለማላውቅ ሁሌም ያስገርመኛል
አምለሰት ሃይሌ እባላለው። ወደዚህ ሃገር ማለትም ኩዌት የመጣሁት በአጋጣሚ ነው። በጊዜው ልጅ ስለነበርኩ ስለ ስደት እንኳን የማውቀው ነገር አልነበረም።
በአንድ አጋጣሚ ከአስተማሪዬ ጋር መስማማት ስላልቻልኩኝ ለሳምንታት ትምህርት ቤት ሳልሄድ ቀረሁኝ። በዚህ ጊዜ ለእረፍት ከኩዌት የመጣች አንዲት ልጅ አግኝቼ በቃ ወደ ኩዌት መሄድ እፈልጋለው ስላት ልጅ መሆኔን ተመልክታ አልተቀበለችኝም ነበር። እኔ ግን የሷን ምክር ከምንም ሳልቆጥር ልቤ የፈቀደውን ለማድረግ ወሰንኩኝ። ኩዌትን ከኢትዮጵያ የተለየ የሚያደርጋት ሃብቷ ነው። እዚህ ያሉ ሰዎች ሲበዛ ሃብታሞች ናቸው። ኢትዮጵያ ግን የተፈጥሮ ሃብት ብቻ ነው ያላት። እዚህ ሃገር ከሚያስገርመኝ ነገር አቧራው ነው። እንደ ዝናብ ነው የሚወርደው። ከኢትዮጵያ በጣም ይለያል። እኔ አቧራ እንደ ዝናብ ሲዘንብ አይቼ ስለማላውቅ ሁሌም ያስገርመኛል። እዚህ ሃገር ስኖር ሁሌ የምናፍቀው ዓመት በዓልን ነው። ዓመት በዓል በደረስ ጊዜ ሁላችንም ተሰባስበን ነው የምናከብረው። ምክንያቱም ወደ ኋላ ወስዶ ያሳለፍነውን ማህበራዊ ህይወት፤ ልጅነታችን እና ኑሯችንን ስለሚያስታውሰን ነው። ለእኔ በጣም ትልቅ ነገር ስለሆነ እንዲያመልጠኝ አልፈልግም። እዚህ ሃገር በጣም የማዘወትረው ከእንጉዳይ እና ጥራጥሬ የሚሰራ ምግብ ነው። ከመጠጥ ደግሞ ከፍራፍሬ እና ቅጠላ ቅጠል የሚሰራ ጭማቂ እወዳለሁ። ከምኖርበት ከተማ የምወደው ባህሩን ነው። በመስኮት ወደ ውጪ ስመለከትም ይህን ባህር፣ መኪኖቹን እና ህንጻዎቹን ማየት ደስ ይለኛል። ለከተማዋ ልዩ ሞግስ ያጎናጽፏታል። እንደ ትልቅ ነገር ልጠቅሰው የምችለው ችግር እስካሁን ባያጋጥመኝም፤ መጀመሪያ አካባቢ የሃገሩን ቋንቋ አለማወቄ ትልቅ እክል ሆኖብኝ ነበር። አንድ አጋጣሚ ኖሮ ወደ ሃገሬ ብመለስ የምወዳት እና ሁሌም የምትናፍቀኝ ከተማ መቀሌ ሄጄ ማረፍ እፈልጋለው።
news-57305761
https://www.bbc.com/amharic/news-57305761
ቬትናም 13 ሚሊየን የሚገመተ የአንድ ከተማ ነዋሪዎችን በሙሉ ልትመረምር ነው
ቬትናም ያጋጠማትን አዲስ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ለመቆጣጠር በማሰብ ለሆ ቺ ሚኒ ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ የኮቪድ ምርመራ ለማድረግና አዲስ ጠበቅ ያለ የአካላዊ ርቀት መመሪያዎችን ተግባራዊ ልታደርግ እንደሆነ አስታወቀች።
ቬትናም የወረርሽኙን ስርጭት በመቆጣጠር ትልቅ ስኬትን ማግኘት የቻለች አገር ብትሆንም በቅርብ ሳምንታት ግን በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአሳሳቢ ሁኔታ መጨመሩ ተገልጿል። ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ላይ በአገሪቱ በጣም አስጊ የሆነ አዲስ የኮሮናቫይረስ አይነት መኖሩን ባስልጣናት አስታውቀዋል። መንግሥት እንደሚለው አዲሱ የቫይረስ አይነት በሕንድ እና ዩናይትድ ኪንግደም ከታዩት የቫይረሱ ዝርያዎች የተቀላቀለ ሲሆን በቀላሉ በአየር መተላለፍ የሚችል ነው። በአጠቃላይ ቬትናም እስካሁን ከ7 ሺ በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ያስታወቀች ሲሆን 47 ሰዎች ደግሞ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ሕይወታቸው አልፏል። ነገር ግን በቅርብ ሳምንታት የታየው ቁጥር ከአጠቃላዩ ቁጥር ግማሹን ይይዛል። በሆ ቺ ሚኒ ከተማ የተከሰተው አዲሱ የቫይረሱ አይነት በብዛት የሚገኘው በክርስትና እምነት ተከታዮች በሚያዘወትሯቸው አብያት ክርስቲያናት አካባቢ ሲሆን እስካሁንም 125 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በከተማዋም ከተመዘገቡ ቁጥሮች ይሄኛው በጣም ከፍተኛ ነው ተብሏል። ቫይረሱ በብዛት ተሰራጭቶ በተገኘባቸው የከተማዋ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች ሁሉም ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን በአሁኑ ሰዓትም እራሳቸውን አግልለው እንደሚገኙ ተገልጿል። ባለስልጣናትም በሆ ቺ ሚኒ ከተማ የሚኖሩ 13 ሚሊየን ሰዎችን በሙሉ ለመመርመር እቅድ ይዘው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። ነገር ግን በቀን 100 ሺ ሰዎችን መመርመር በሚያስችል አቅም ሁሉንም ሰው ለመመርመር ከአራት ወራት በላይ ሊፈጅ እንደሚችል ተጠቁሟል። በከተማዋ ከሚደረገው ነዋሪዎችን የመመርመር ተግባር በተጨማሪ ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ ለ15 ቀናት የሚቆይ ጠበቅ ያለ አካላዊ ርቀትን የመጠበቅ መመሪያ ተላልፏል። ሱቆች፣ ባርና ሬስቶራንቶች ሙሉ በሙሉ የተዘጉ ሲሆን ለጊዜው ደግሞ ማንኛውም አይነት ሀይማኖታዊ ስነ-ስርአቶች ታግደዋል። ''ከ10 ሰዎች በላይ የሚሰባሰቡበት ማንኛውም አይነት ህዝባዊ ሁነት በመላ ከተማዋ ተከልክሏል። ነገር ግን እንደውም ቁጥሩን ወደ 5 ዝቅ ለማድረግ እየታሰበ ነው'' ሲሉ የአገሪቱ ጤና ኃላፊ ተናግረዋል። ኮሮናቫይረስ ባሳለፍነው ዓመት ከቻይና ተነስቶ ዓለምን ሲያዳርስ ቀድመው እርምጃ ከወሰዱት አገራት መካከል አንደኛዋ የሆነችው ቬትናም፤ ፈጣንና ውጤታማ የመከላከል ስራዎችን ሰርታለች።
53747877
https://www.bbc.com/amharic/53747877
የጎርፍ አደጋ፡ በምዕራብ ሸዋ ዞን በአዋሽ ወንዝ ሙላት የተነሳ 500 አባወራዎች ተፈናቀሉ
በምዕራብ ሸዋ ዞን በአዋሽ ወንዝ ሞልቶ የነዋሪዎችን መኖሪያ ቤቶችና አካባቢ በማጥለቅለቁ የተነሳ 500 አባዎራዎች መፈናቀላቸውን የምዕራብ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ድሪብሳ ዋቁማ ለቢቢሲ ገለፁ።
አስተዳዳሪው አክለውም የጎርፍ አደጋው ከደረሰበት ሰዓት አንስቶ የሰው ሕይወት እንዳይጠፋ ከፍተኛ ርብርብ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ገልፀው "በዚህም ተሳክቶልናል" ብለዋል። ጀልባዎችን ከተለያዩ ስፍራዎች በማስመጣት የሰዎችን ህይወት መታደግና ንብረታቸው ላይ የሚደርሰውን አደጋ ለመቀነስ እየሰሩ እንደሆነም ጨምረው አስረድተዋል። "በዚህ የጎርፍ አደጋ አምስት መቶ አባወራዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፤ ለእነርሱም የጊዜያዊ መጠለያ አዘጋጅተናል። እንዲሁም የቤት እነስሳቶቻቸው በጎርፉ እንዳይጎዱ የማዳንና ሳር የማቅረብ ስራ እየሰራን እንገኛለን " ብለዋል አስተዳዳሪው። የደረሰው የጎርፍ አደጋ ከሚገመተው በላይ ቢሆንም እንኳ፣ ለችግር የተጋለጡትን ማህበረሰቦች እንዲያገግሙ ለማድረግ ከዞኑ አቅም በላይ እንደማይሆን ጨምረው ተናግረዋል። ባለፈው ዓመትም የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ በምዕራብ ደቡብ ሸዋ ዞን በኢሉ ወረዳ ከ 7900 በላይ ሰዎች ከቀያቸው ማፈናቀሉን አስተዳዳሪው ያስታውሳሉ። 'ለሦስት ቀንና ሌሊት በቆጥ ላይ ነው ያሳለፍነው' በየዓመቱ ክረምት የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ በመፍሰስ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ እንዲሁም በምዕራብ ሸዋ ዞኖች የሚገኙ ነዋሪዎች ላይ በተደጋጋሚ ጉዳት ያደርሳል። በዚህ ዓመትም በምዕራብ ሸዋ ዞን ኤጀሬ ወረዳ ዲቡ ቀበሌ ወንዙ ሞልቶ በመፍሰሱ የተነሳ፣ ቀበሌው ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ጉዳት እንደደረሰበት የቀበሌው አስተዳደር አቶ ከበደ ዲሳሳ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከዚሁ ቀበሌ በጎርፉ ምክንያት ቀያቸውን ጥለው በመጠለያ እየኖሩ መሆኑን የተናገሩት ወ/ሮ ጌጤ ቦርጋ፣ " ዘንድሮ በአገሪቱ ያልነበረ አደጋ ነው የመጣብን" ሲሉ የተፈጠረውን የጎርፍ አደጋ ይገልጹታል። " ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ነው ደራሽ ውሃው የመጣብን፤ ከሁለት ልጆቼና ከባለቤቴ ጋር ነበርን [ቤት ውስጥ]፤ ባለቤቴ አይነ ስውር ናቸው። ጎረቤት ነው ደርሶ ግድግዳ በመብሳት እንድንቆይበት ቆጥ የሰራልን፤ መያዝ የምንችለውን ይዘን እዚያው ቆጥ ላይ ነው የቆየነው" ይላሉ ወ/ሮዋ። ላለፉት ሶስት ቀናት የውሃው መጠን መቀነስ ስላልቻለ ሶስት ቀንና ሶስት ለሊት እዚያው ቆጥ ላይ ማሳለፋቸውን ጨምረው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከሶስት ቀን በኋላ ግን ጀልባ ደርሶላቸው ወደ ጊዜያዊ መጠለያ ስፍራ መወሰዳቸውን እና በአሁኑ ሰዓት እዚያ እንደሚገኙ ገልፀዋል። " አንድም ነገር ይዘን አልወጣንም፤ ነፍሳችንን ብቻ ይዘን ነው ከቤታችን የወጣነው" የቀበሌዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ እንደተናገሩት በቀበሌው ውስጥ የአዋሽ ወንዝ ሙላት ያላጠቃው ቤተሰብ በጣም ጥቂት መሆኑን ገልፀው፣ ከዚህ ቀደም በወንዙ ሙላት የተነሳ የሚደርስ የጎርፍ አደጋ በአካባቢው ብዙ ጊዜ የሚገጥምና የሚታወቅ ቢሆንም የዘንድሮው ግን ከገመቱት በላይ አደገኛ እንደነበር ነዋሪዎቹ ጨምረው ተናግረዋል። በኦሮሚያ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት አባዲር አብዳ የአዋሽ ወንዝ በየዓመቱ በማህበረሰቡ ላይ የሚያደርሰውን አደጋ ለመከላከል የወንዙን ስፋት የመጨመር ፕሮጀክት ተቀርጾ፣ በአምስት ወረዳዎች ውስጥ 52 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የወንዙን ተፋሰስ የማስፋት ስራ ቢሰራም አደጋውን ለማስቀረት አልተቻለም ይላሉ። ለዚህም ምክንያቱን ሲገልፁ የዘንድሮው የዝናብ መጠን ከመብዛቱ ጋር ተያይዞ ወንዙ ከተሰራለት መከላከያ አልፎ መፍሰሱን ይናገራሉ። ወንዙ በዘንድሮው ዓመት ከኤጀሬ ውጪ በሌሎች አራት ወረዳዎች ላይም ተመሳሳይ ጉዳት ማድረሱን ኮሚሽነሩ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በተከሰተው የጎርፍ አደጋ የሚደርሰውን አደጋ ለመቀነስም የችግሩ ተጠቂ የሆኑ ማህበረሰብ ክፍሎችን የሚያስፈልጋቸውን ነገር በማቅረብ ከችግሩ እንዲያገግሙ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ኮሚሽነር አባዲር ይናገራሉ። " በአሁኑ ወቅት ከአቅም በላይ የሆነ ነገር አልገጠመንም፤ ጀልባዎች ከተለያዩ ስፍራዎች በማሰባሰብ የማዳን ስራ እየተሰራ ነው፤ ከአቅም በላይ የሆነ ነገር መኖሩ ከተረጋገጠ ደግሞ የሂሊኮፕተር ድጋፍ ለማድረግ ይቻላል" ብለዋል።
news-53188956
https://www.bbc.com/amharic/news-53188956
የዴንማርክ ጠቅላይ ሚኒስትር በስብሰባ ምክንያት ሰርጋቸውን ለ3ኛ ጊዜ ሰረዙ
በመጪው ሳምንት የሚካሄደው የአውሮጳ ኅብረት ስብሰባ ነው የሙሽሪት ጠቅላይ ሚኒስትሯን ሰርግ ያስተጓጎለባቸው፡፡
በሐምሌ 17 እና 18 የሚካሄደው የአውሮጳ ኅብረት ስብሰባ በኮቪድ-19 የማገገምያ በጀት ላይ ስለሚወያይ ከዚህ ጉባኤ መቅረትና ሰርግ መደገስ ለጠቅላይ ሚኒስትሯ አልተዋጠላቸውም፡፡ ይህ ስብሰባ ወረርሽኙ ከተሰከሰተ በኋላ መሪዎች ለመጀመርያ ጊዜ በአካል ተገናኝተው የሚወያዩበት ጉባኤ ነው የሚሆነው፡፡ ወ/ት መቲ ፍሬድሪክሰን እጮኛቻውን ቦ ቴንግበርግን ድል ባለ ሰርግ ለማግባት የቆረጡት ቀን ደግሞ ከዚህ ወሳኝ ስብሰባ ጋር ተገጣጥሞባቸዋል፡፡ በፌስቡክ ገጽ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ባሰፈሩት መልእክት ‹‹የዴንማርክን ጥቅም ማስቀደም አለብኝ›› ብለዋል፡፡ ዴንማርክ በወረርሽኙ ለተጎዱ የአውሮጳ ኅብረት አባላት ማገገምያ ገንዘብ መስጠት የሚለውን ሐሳብ የምትቃወም አገር ናት፡፡ ዴንማርክ ብቻ ሳትሆን ስዊድን፣ ኦስትሪያና ኔዘርላንድስ ይህን 750 ቢሊዮን ዶላር የሚሆን ገንዘብ በወረርሽኙ እጅግ ለተጎዱ የአውሮጳ አባል አገሮች መስጠት አግባብ አይደለም ብለው ያምናሉ፡፡ ለአባል አገራት የሚሰጡ ማገገምያ ገንዘቦችም ቢሆን የሚመለሱ መሆን ይኖርባቸዋል ይላሉ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ጠንካራ ውሳኔ ይተላለፍበታል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ወሳኝ ስብሰባ የሚደረገው በብራስልስ ነው፡፡ የሰርግ ዕለታቸው በዚህ የብራስልስ ስብሰባ የተስተጓጎለባቸው የዴንማርክ ጠቅላይ ሚኒስትር ወ/ት መዲ ፍሬድሪክሰን በፌስቡክ ሰሌቻው ላይ የሚከተለውን ጽፈዋል፡፡ "ይህን ድንቅ የሆነውን እጮኛዬን የማገባበት የመሞሸሪያዬን ዕለት በጉጉት እየጠበቅኩት ሳለ የብራስልሱ ስብሰባ ለቅዳሜ እንዲሆነ ተወሰነ፡፡ ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡ እጮኛዬ ይህን ይረዳል፤ ታጋሽም ነው፡፡" የወ/ት ፍሬድሪክሰን እና የአቶ ቦ የሰርግ ሥነ ሥርዓት በፖለቲካ ኩነቶች ሲስተጓጎል ይህ ለ3ኛ ጊዜ ነው፡፡
news-53963767
https://www.bbc.com/amharic/news-53963767
ቁርዓንን የማቃጠል ዘመቻ መካሄዱ በስዊድን ቁጣን ቀሰቀሰ
በስዊድን ካለፈው አርብ ጀምሮ ተቃውሞ ተነስቷል፡፡ መነሻው ደግሞ ነጭ አክራሪዎች ቁርዓንን የማቃጠል ዘመቻ ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው፡፡
ድርጊቱን የተቃወሙ አደባባይ ወጥተው ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል፡፡ ተቃውሞው በዋናነት የተቀሰቀሰባት ከተማ የደቡባዊ ስዊድኗ ማልመ ከተማ ናት፡፡ ሱቆችና መኪናዎች በሰልፈኞች ነደዋል፡፡ ሰብአዊ ጉዳቶችም ደርሰዋል፡፡ አሁን ተቃውሞውን ፖሊስ በቁጥጥር እንዳዋለው ተዘግቧል፡፡ 10 ሰዎች ከተቃውሞ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ ቁርአን የማቃጠሉ ተግባር የተፈጸመው ባለፈው አርብ በማልመ ከተማ ሮዘንጋርድ አካባቢ ሲሆን ሙስሊምና ጥቁር ጠል የሆኑ አክራሪ ነጭ ብሔርተኞች የተሳተፉበት ነበር፡፡ የቀኝ አክራሪው ዴንማርካዊ ፖለቲከኛ ራስመስ ፓሉዳን የሚመራው ክንፍና ደጋፊዎች በማቃጠሉ ተግባር ተሳትፎ ያደረጉት ራስመስ በዕለቱ ንግግር እንዲያደርግ ሲጠበቅ ነበር፡፡ ሆኖም ሚስተር ራስመስ ከዴንማርክ ወደ ስዊድን ለመግባትና በመርሐግብሩ ለመታደም ሲሞክር ፖሊስ ከድንበር መልሶታል፡፡ የስዊድን ፖሊስ ቀኝ አክራሪውንና ዝነኛውን የሙስሊምና የጥቁር ስደተኛ ጠል ሚስተር ራስመስን ከድንበር የመለሰው ስዊድን እንዳይገባ የ2 ዓመት ገደብ ስለተጣለበት ነው፡፡ ቀኝ አክራሪው ሚስተር ራስመስ በፌስቡክ ገጹ ላይ ወዲያውኑ ባሰራጨው መልእክት ‹‹እኔ አውሮጳዊው እንዳልገባ ተደረኩ፤ ሴት ደፋሪዎችና ወንጀለኞች (ስደተኞች) ግን ሁልጊዜም እንክብካቤ ይደረግላቸዋል›› ሲል ጽፏል፡፡ በዴንማርክ የጥቁርና ሙስሊም ጠል አክራሪ ፓርቲ (ስትራም ኩርስ) ሊቀ መንበር የሆነውን ሚስተር ራስመስ በዚህ ዓመት ጥላቻን በመስበክ ክስ አንድ ወር እስር ተፈርዶበት ነበር፡፡ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ደግሞ ጸረ ኢስላም ቪዲዮዎችን በማጋራቱ ክስ ተመስርቶበታል፡፡
news-49386101
https://www.bbc.com/amharic/news-49386101
ፀረ-መውለድ፦ ልጆች እንዳይወለዱ የሚቃወመው ፍልስፍና
የሰው ልጅ መራባት የለበትም የሚል እምነት አላቸው። እነማን? መውለድን የሚቃወሙት የፀረ መውለድ ፍልስፍና ተከታዮች አላማቸውንስ ለማስፈፀም ምን ያህል ይጓዛሉ?
"መሬት ውስጥ አንድ ፍንዳታ ተፈጥሮ ሁሉንም ነገር ድምጥማጡ ቢጠፋ እንዴት ጥሩ ነበር" በምስራቃዊዋ እንግሊዝ የሚኖረው የ29 አመቱ ቶማስ መሬትን የማፈንዳቱ ጉዳይ እንዲያው በሃሳብ ደረጃ የሚመላለስ ቢሆንም፤ በአንድ ጉዳይ ግን እርግጠኛ ነው፤ የሰው ልጅ ዘሩን ሊተካ አይገባም የሚል ፅኑ አቋም አለው። ይህም ሁኔታ የሰው ልጅ ዝርያ እንዲያከትም ያደርገዋል ይላል። •ባሕር ላይ ያለምግብና መጠጥ 11 ቀናት ያሳለፈው ኢትዮጵያዊ ይህ ዝም ብሎ ሀሳብ ሳይሆን ፀረ-መውለድ (አንታይ ናታሊዝም) የተሰኘ ፍልስፍና ነው። ፅንሰ ሃሳቡ በጥንታዊዋ ግሪክም የነበረ ቢሆንም አሁን በማህበራዊ ሚዲያ ዘመን የበለጠ ታዋቂነትን አትርፏል። በፌስቡክም ሆነ በሬዲት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የፀረ-መውለድ ቡድን ያሉ ሲሆን አንዳንዶቹም በሺዎች የሚቆጠሩ አባላት አሏቸው። ሬዲት በተሰኘው ድረገፅ 'አር/አንታይናታሊዝም' የተሰኘ ቡድን ሰላሳ አምስት ሺ አባላት ያሉት ሲሆን በፌስቡክ ከሚገኙት አንዱ የሆነው 'ጀስት ዋን' ከስድስት ሺ በላይ አባላት አሉት። •"ወሎዬው" መንዙማ በአለማችን ውስጥ በተለያዩ ሃገራት ተሰባጥረው የሚገኙት እነዚህ ቡድን የሰው ልጅ ማክተም አለበት ለሚለውም እምነታቸው የተለያየ ምክንያትን ይሰጣሉ። ከነዚህም መካከል በዘር የሚተላለፍ ችግሮች፣ ህፃናት የዚህን አለም ገፈት ቀማሽ እንዳይሆኑ ለመከላከል፣ ህፃናት ለመወለድ ፈቃዳቸው ሊጠየቅ ይገባል የሚል ፅንሰ ሃሳብና አለም ላይ የህዝብ ቁጥር መጨመርና የከባቢ ደህንነት መውለድን ለመቃወም የሚያነሱዋቸው ምክንያቶች ናቸው። ምክያቶቻቸው ቢለያይም የሰው ልጅ መዋለድንም በመቃወም ተባብረው ቆመዋል። ምንም እንኳን ይህን ያህል ተሰሚ ቡድኖች ባይሆኑም መሬትና ሃገር ላይ ባላቸው እሳቤ ተፅእኖ መፍጠር እየቻሉ ነው። •“ከተማ አስተዳደሩ የወሲብ ንግድን በህግ ወንጀል የማድረግ ስልጣን የለውም” የህግ ባለሙያ ከዚህ ቡድን ጋር ባይያያዝም የሱሴክሱ የንጉሳዊ ቤተሰብ አባልና ባለቤታቸው ከከባቢ ደህንነት ጋር በተያያዘ የሚወልዷቸው ልጆች ከሁለት እንደማይበልጡ አሳውቀዋል። ፍልስፍናዊ ወጎች ቶማስ ያምንበት የነበረውን ጉዳይ "ፀረ-መውለድ' የሚል የፍልስፍና አካል መሆኑን ያወቀው ከጥቂት አመታት በፊት በዩ ቲዩብ በተሰጠ አስተያየት ምክንያት ነው። ከሰማበት እለት ጀምሮ ግን የፀረ ውልጃ ፌስቡክ ቀንደኛ ተሳታፊ ሆኗል። ምሁራዊ አስተያቶችን እንዲቃርም እንዲሁም ሃሳቦቹንም እንዲፈትሽ እድል ሰጥቶታል። "የህይወትን እውነተኛ እክሎች ላይ ነው እያወራን ያለነው፤ ይህ አስደናቂ ነገር ነው" የሚለው ቶማስ አክሎም "የሰው ልጅ ጠፋ እንበል፤ ተመልሶ ቢመጣስ? ችግሩ አልተቀረፈም ማለት ነው" ይላል። "በርካታ ውይይቶች አሉ፣ አንዳንዶቹ ልብ ይነካሉ" በማለት ይናገራል። የፀረ መውለድ ፍልስፍናው በፅንሰ ሃሳብ ላይ የተመሰረተ ብቻ አይደለም። የሰው ልጅ ህይወት ትርጉም አልባ ነው የሚለውን እምነቱንም በተግባር ለመለወጥ ዜጎችን የማምከን ተግባር እንዲከናወን የብሪቴይን የጤና ማዕከልን (ኤን ኤች ኤስ) አናግሮ ነበር። ምንም እንኳን ሃሳቡ ተቀባይነት ባያገኝም ምንም እንኳን ህይወት ትርጉም የለውም በማለት ማህበረሰቡ የሚቀበላቸውን ሞራላዊ፣ እምነታዊ፣ ባህላዊና ሌሎች እሴቶችን ባይቀበሉም ኃይልን ወይም አመፅን በመጠቀም የሰውን ልጅ እናጥፋ አይሉም። ስለ ሰው ልጅ ዘር መጥፋት የሚያወሩትም እንዲያው ለውይይት ነው። በየትኛውም ድረገፅ ላይ ሰለ መግደልም ሆነ ማስፈራራትም አይፈፅሙም። የቶማስ አለምን የማፈንዳት ፅንሰ ሃሳብ እሱ እንደሚያስበው አንድ ቀይ ቁልፍ ነገር ቢገኝና ያንን ተጭኖ የሰውን ልጅ ድምጥማጡ ቢጠፋ የሚል ነው። ይህ እሳቤ ከራሳቸው ፅንሰ ሃሳብ ጋር የሚቃረን ነው፤ ህፃናት ለመወለድ ፍቃድ ሊሰጡ ይገባል እንደሚሉት የሚሞትም ሰው ፍቃዱ ሊጠየቅ ይገባል የሚል ነው። በቴክሳስ ሳን አንቶኒዮ የሚኖረው ከርክ በአራት አመቱ እናቱን ለምን እንደወለደች ሲጠይቃት ምርጫ እንደሆነ በነገረችው ሰአት ግራ ያጋባው ጉዳይ እንዴት የሰው ልጅ በምርጫው ልጆች እንዲሰቃዩ ወደዚህ አለም ያመጧቸዋል የሚል ነው። የሰው ልጅ ምርጫው ተጠይቆ ወደዚህ አለም እስካልመጣ ድረስ መውለድን የሚቃወም ሲሆን እሱ ምርጫ ቢሰጠው እንደማይወለድ ይናገራል። ነገር ግን አለም እንደነሱ በጨለምተኞች የተሞላች ብቻ ሳትሆን አለም እንድትጠፋ በማይፈልጉና በኑሯቸውም ደስተኞች የሆኑ ብዙዎች ናቸው። ከፍልስፍናውና ከሞራል ውይይቶች በተጨማሪ ወላጆችን በማዋረድና ልጆችን በመሳደብም ይተቻሉ። "ያረገዘች ሴት ሳይ መጀመሪያ የሚሰማኝ ነገር መቀፈፍ ነው" በሚል አንድ አባል በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አስተያየት ከሰጡት አንዱ ነው። ይህ ማለት ግን ሁሉም ልጆች ይጠላሉ ማለት እንዳልሆነ ቢቢሲ ያናገራቸው የፀረ መውለድ ፍልስፍና ተከታዮች ተናግረዋል። ከዚህም በተጨማሪ በተጨማሪ በተለይ በጦርነት ቀጠና ያሉና ድሃ ቤተሰቦች በጭራሽ መውለድ የለባቸውም ብለው ሽንጣቸውን የሚከራከሩ ሲሆን ይህም የተመረጠ ዝርያን ያበረታታሉ የሚል ትችት እንዲቀርብባቸው ምክንያት ሆኗል።
news-46402967
https://www.bbc.com/amharic/news-46402967
የሰከረው ጃፓናዊ አብራሪ የ10 ወራት እስር ተበየነበት
ጃፓናዊው አብራሪ ከበረራ በፊት በተደረገበት የአልኮል ምረመራ በሰውነቱ ውስጥ ከተፈቀደው የአልኮል መጠን 9 እጥፍ በላይ ወስዶ በመገኘቱ የ10 ወራት እስር ተበየነበት።
የ42 ዓመቱ ጎልማሳ ካሱቶሺ ጂትሱካዋ የመንገደኞች አውሮፕላን አብራሪ ሲሆን፤ ከሎንዶን ወደ ጃፓን መዲና ቶኪዮ በረራ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ነበር። የጃፓን አየር መንገድ አብራሪው በቁጥጥር ሥር የዋለው ከሁለት ቀናት በፊት ሲሆን ከታቀደው በረራ 50 ደቂቃ በፊት የተደረገለትን የትንፋሽ ምረመራ ማለፍ ሳይችል ቀርቷል። በትንፋሽ ምረመራ ውጤትም በአብራሪው 100 ሚሊ ሊትር ደም ውስጥ 189 ሚሊ ግራም የአልኮል ምጠን የተገኘ ሲሆን ለአውሮፕላን አብራሪዎች የሚፈቀደው መጠን 20 ሚሊ ግራም ብቻ መሆኑም ተጠቅሷል። • ኢትዮጵያዊቷ ሰው አልባ አውሮፕላን • ያለአብራሪ በሚበረው የሰማይ ታክሲ ይጠቀማሉ? የ10 ወራት እስር የበየኑበት ዳኛ ''ብዙ ልምድ ያለህ አብራሪ ነህ፤ ይሁን እንጂ የበረራ ሰዓቱ እንኳን ተቃርቦ አልኮል ስትጎነጭ ነበር። ይህን ረዥም በረራ ሊያደርጉ ሲሰናዱ የነበሩ መንገደኞችን ህይወት አደጋ ላይ ጥለህ ነበር። በረራው ቢከናወን ኖሮ እጅግ አስከፊ አደጋ ይከሰት ነበር።'' በማለት ገልጸውታል። አብራሪው ከመጠን ያለፈ አልኮል መጠጣቱ የታወቀበት፤ አንድ የጸጥታ ኃይል አስከባሪ አብራሪው የጠጣው አልኮል ከሸተተው በኋላ ነበር። አብራሪው ዓይኑን መግለጥ እና ቀጥ ብሎ መቆም ተስኖት ነበር ተብሏል። ከፍርድ ሂደቱ በኋላ የጃፓን አየር መንገድ ምክትል ፕሬዚዳንት ይህ አይነቱ ባህሪ ዳግመኛ እንዳይከሰት እንሰራለን በማለት ይቅርታ ጠይቀዋል። ከፍርድ ሂደቱ በኋላ የጃፓን አየር መንገድ ምክትል ፕሬዚዳንት ይህ አይነቱ ባህሪ ዳግመኛ እንዳይከሰት እንሰራለን በማለት ይቅርታ ጠይቀዋል። አቃቤ ሕግ ግን የአየር መንገዱ ሰራተኞች አብራሪው የአልኮል መጠን በማለፉ ማብረር እንደማይችል ሲነግሩት ከዚያ ቀን ቀደም ብሎ በነበረው ምሽት ውስኪ መጠጣቱን እና የትንፋሽ ምረመራ አድርጎ ማለፉን ግልጾላቸው ነበር። • ሴቶችና ወጣቶች የራቁት የተቃውሞ ፖለቲካ ከዚያም አብራሪው ወደ መጸዳጃ ቤት በማቅናት የአፍ መታጠቢያ ሳሙና በመጠቀም ሲግሞጦሞጥ ነበር ብሏል። ሊያበረው የነበረው ቦይንግ 777 የበረራ አስተናጋጆቹን ጨምሮ 244 ተሳፋሪዎችን ይዞ የነበር ሲሆን፤ ከ69 ደቂቃዎች መዘግየት በኋላም ወደ ቶኪዮ በርሯል።
54617478
https://www.bbc.com/amharic/54617478
ጋዜጠኛዋን ገድሎ መነጋገሪያ የነበረው ከእስር ቤት ሊያመልጥ ሲል ተያዘ
የስዊድን ዜጋ የነበረችውን ጋዜጠኛ ኪም ዎልን ከገደለ በኋላ መነጋገርያ የነበረው ፒተር ማደሰን ከእስር ቤት ሊያመልጥ ሲል በቁጥጥር ሥር ዋለ።
ፖሊስ ከኮፐንሀገን አቅራቢያ ከእስር ቤት ሊያመልጥ የነበረውን ሰው በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ከሳወቀ በኋላ ማንነቱ ሳይገልጽ ቆይቶ ነበር. በኋላ ላይ ከእስር ቤት ለማምለጥ ሲል በቁጥጥር ሥር የዋለው ሰርጓጅ መርከብ ሰሪው ፒተር ማደሰን መሆኑን አረጋግጧል። ዴንማርካዊው ማደሰን ከእስር ቤት ሊያመልጥ በሞከረበት ወቅት በታጠቁ ፖሊስ አባላት ተከቦ የሚያሳይ ምሥል በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት ተሰራጭቷል። በስፍራው የነበረ አንድ ፎቶ አንሺ ማደሰን ወገቡ ላይ ቀበቶ ታጥቆ እና ግድግዳ ተደግፎ የሚያሳይ ምሥል በድረ-ገጹ ላይ አትሟል። ማደሰን ፖሊሶች እየቀረቡት ሲመጡ ቦምብ ታጥቂያለሁና አትጠጉኝ እያለ ማስጠንቀቂያ ሲሰጣቸው ነበር። ፖሊስ ቦምብ አምካኝ ባለሙያዎችን ወደስፋራው ያሰማራ ሲሆን ኋላ ላይ የማደሰን ማስፈራሪያ የሐሰት መሆኑ ሲረጋገጥ ወደ እስር ቤት ወስዶታል፡፡ ማደሰን በጋዜጠኛዋ ኪም ዎል ግድያ ጥፋተኛ መባሉን ተከትሎ የዕድሜ ልክ እስራት የተፈረደበት እንደ አውሮጳዊያኑ አቆጣጠር ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ነበር። ጋዜጠኛዋ የገባችባት ሳይታወቅ ቆይቶ ከጠፋች ከ11 ቀናት በኋላ አካሏ ተቆራርጦ ከባህር ዳርቻ አቅራቢያ ተገኝቶ ነበር። ጋዜጠኛ ቶም ዎል ኪም ዎል ማን ነበረች? የስዊድን ዜጋ የነበረችው ኪም ዎል በመላው ዓለም በመዘዋወር በምትሰራቸው ዘገባዎች እውቅናን አትርፋለች። ከዚያ በኋላ ግን ድንገት ተሰውራ ቆይታ ነበር፡፡ በመጨረሻም እአአ 2017 ላይ የፒተር ማደሰንን ሰርጓጅ መርከብ ከተሳፈረች ከ11 ቀናት በኋላ የሰውነት አካሏ ተቆራርጦ ተገኝቷል። በወቅቱ ማድሰን ጋዜጠኛዋ የሞተችው ባጋጠመ አደጋ ነው ቢልም ፍርድ ቤቱ መከራከሪያውን ውድቅ አድርጎበታል። ማድሰን የጥፋተኝነት ውሳኔ ከተላለፈበት በኋላ ለአንድ ሚዲያ በሰጠው ቃል ለጋዜጠኛዋ ሞት ኃላፊነቱን እንደሚወስድ ተናግሮ ነበር፡፡።
news-45366339
https://www.bbc.com/amharic/news-45366339
ሰራተኞች የፈለጉትን ያክል ሰዓት ብቻ ሰርተው የሚወጡበት ተቋም
ከዓለም ግዙፍ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው ፕራይስ ዋተር ሃውስ ኮርፖሬሽን (PwC) ሰራተኞቹ ፈታ ዘና ብለው ሥራቸውን እንዲከውኑ የሚያደርግ አሰራር የሥራ ሰዓት ይፋ አድርጓል።
ተቋሙ አዲሱ አሰራሩ የተሻሉ ሰራተኞችን ለመመልመል እንደሚረዳው ተስፋ ሰንቋል በአዲሱ የሥራ ሰዓት መሰረት ሰራተኞች በተለመደው ከ3 እስከ 11 ሰዓት ድረስ በቢሮ ውስጥ የመቀመጥ ግዴታ አይኖርባቸውም። በምትኩ ሰራተኞች ሊሰሩበት የሚፈልጉትን የሰዓት ርዝመት እንደ ግል ፍላጎታቸው እንዲወሰኑ ፈቅዷል። ከዚህ በተጨማሪ ሰራተኞች ከሙሉ ዓመት ውስጥ የተወሰኑ ወራትን ብቻ በስራ የሚያሳልፉበትን መብትም ሰጥቷል። በተቋሙ ለመቀጠር የሚፈልጉ አመልካቾች በማመልከቻ ቅጽ ላይ ተሰጥኦና ዝንባሌያቸውን ብሎም ለሥራ ምቹ የሚሆንላቸውን ሰዓት የሚሞሉበትን አሰራር ጀምሯል። በዓለማችን ከሚገኙ አራት ግዙፍ የሒሳብ ሥራ ኩባንያዎች ውስጥ የሚመደበው ራይስ ዋተር ሃውስ ኮርፖሬሽን (PwC)፤ ይህን አሰራር ይፋ ያደረገው 2000 ሰዎችን በጥናት ካሳተፈ በኋላ ነው። በጥናቱ ከተሳተፉ 46 በመቶ ያህሉ እንዳሻቸው የሚለዋውጡት የስራ ሰዓት እንዲሁም ጥሩ የሥራ እና የህይወት ምጥጥንን እንዲኖር መርጠዋል። የተቋሙ ሃላፊ ሎውራ ሂልተን ''ሰዎች በግዙፍ ኩባንያዎች ውስጥ መስራት ማለት በተለመደው የሥራ ሰዓት መግባት እና መውጣት ግድ የሚላቸው ይመስላቸዋል። ይህ ግድ መሆን የለበትም። ብቃት ያላቸውን ሰራተኞችን ለማግኘት በቅድሚያ የተወሰነ የሥራ ሰዓትን ማስቀረት ነበረብን'' ብለዋል። ''ሰራተኞች በተመቻቸው የሥራ ስዓት እንዲገቡ እና እንዲወጡ መፍቀዳችን፤ ለሰራተኛው ብቻ ሳይሆን ለተቋሙም እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል'' ብለዋል።
news-47729863
https://www.bbc.com/amharic/news-47729863
ቦይንግ "ችግሩ ተፈቷል" እያለ ነው
አጣብቂኝ ውስጥ የገባው አውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ችግሩን ፈትቼዋለሁ እያለ ነው። እጅግ ዘመናዊ ከሚባሉት የቦይንግ 737 ማክስ ስሪቶች ጋር በተያያዘ ኩባንያው ላለፉት ወራት የሚይዝ የሚጨብጠው ጠፍቶት ሰንብቷል።
በተለይም የኢንዶኒዢያው ላየን አየር መንገድ አውሮፕላን በተከሰከሰ በአምስተኛ ወሩ የኢትዯጵያ አየር መንገዱ አደጋ ሲደገም በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ አየር መንገዶች የ737 ማክስ ስሪቶችን ላለማብረር ወስነው ነበር። ይህም በቦይንግ ላይ የቢሊዮን ዶላሮች ኪሳራን ማድረሱ ሲነገር ቆይቷል። ዋናው የችግሩ ምንጭ እንደሆነ የሚጠረጠረውን "ኤምካስ" የተሰኘውን የመቆጣጠሪያ ሲስተም ቀይሬያለሁ ብሏል ቦይንግ። ያም ሆኖ እንዳይበሩ የተደረጉት የብዙ አገራት የማክስ ስሪቶች በቅርቡ ወደ ሥራ ይመለሳሉ የሚል ግምት የለም። • አቶ ተወልደ አየር መንገዶች ሁሉ ለጊዜው ቦይንግ 737-8 ማክስን እንዳይጠቀሙ ጠየቁ • በእርግጥ የአብራሪዎቹ ስልጠና ከአደጋው ጋር ይያያዛል? ይህም የሆነው ቢያንስ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተከሰከሰበትን ምክንያት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ የምርመራ ውጤት ስለሚጠበቅ ነው። ኤምካስ የተባለውን ሲስተም አድሻለሁ የሚለው ቦይንግ አሁን አውሮፕላኖቹ ተመሳሳይ ችግር ውስጥ ቢገቡ ማስጠንቀቂያ የሚልክ ዘዴን ቀይሻለሁ ይላል። ይህ ዘዴ ቀደም ሲል እንደ አማራጭ የነበረ እንጂ አስገዳጅና መደበኛ ሲስተም ሆኖ ከቦይንግ የቀረበበት ሁኔታ ጨርሶ እንዳልነበረ የአቪየሽን ባለሞያዎች ይናገራሉ። ይህ አሁን ተሻሽሎ ይገጠማል የሚባለው የቅድመ ጥንቃቄ ሰጪ ሲስተም በኢንዶኒዢያውም ኾነ በኢትዯጵያው አየር መንገድ ላይ ያልነበረ ነው። ይህ ሲስተም መገጠሙ አውሮፕላኑ የሚቃረኑ ምልክቶችን ሲሰጥ ለፓይለቶቹ ጥቆማን ይሰጣል ተብሏል። ቦይንግ ለደንበኞቹ ይህን ሲስተም የምገጥምላችሁ በነጻ ነው፤ አንዳችም ክፍያ አልጠይቃችሁም ብሏቸዋል። ተሻሻለ የተባለው ሶፍትዌር ምንድነው? ኤምካስ (ማኑቨሪንግ ካራክተርስቲክስ ኦግመንቴሽን ሲስተም) ለሚለው ምህጻረ ቃል ነው። ይህ ሲስተም አውሮፕላኑን የሞተሩ ክብደትና የተቀመጠበትን ቦታ ምክንያት አድርጎ እንዳይቆምና እንዳያጋድል ያደርገዋል። ይህም አውሮፕላኑ ሽቅብ በሚወጣ ጊዜ የሚያሳየውን ዝማሜ ተከትሎ ሚዛኑን እንዲያስጠብቀው ለማድረግ የተሠራ ነበር። ነገር ግን የኢንዶኒዢያው ላየን አውሮፕላን ምርመራ ውጤት እንዳመላከተው ይህ ሴንሰር አውሮፕላኑ በአፍጢሙ እንዲደፋ የሚያደርግበት ሁኔታ አለ። ይህም የሚሆነው ሚዛኑን ለመጠበቅ የሚልከው መልዕክት (ሲግናል) እርስበርሱ የሚጣረስ በመሆኑ ነው። • ኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬም ስኬታማ ነው ይህም ከአብራሪዎቹ ቁጥጥር ውጭ የሚሆን ነገር ነው። የተከሰከሰው የኢንዶኒዢያ አየር መንገድ ከ20 ጊዜ በላይ የአውሮፕላኑ አፍንጫ ቁልቁል እንዲያዘምና እንዲምዘገዘግ አድርጎታል። አሁን ቦይንግ አድሼዋለሁ የሚለው ሶፍትዌር በአውሮፕላኑ አፍንጫ የምትገኘው ሴንሰር እርስበርሱ የሚጣረስ ምልእክት ካስተላለፈ ኤምካስ የተሰኘውን መቆጣጠሪያ ልክ እንደ ኤሌክትሪክ ባልቦላ ራሱን በራሱ እንዲያጠፋ የሚያደርግ ነው። ተቆጣጣሪው ባለሥልጣን ሊከሰስ ይችላል? የአሜሪካ የአቪየሽን ቁጥጥር ባለሥልጣን ከአምስት ወራት በፊት በተከሰከሰው የኢንዶኒዢያ አውሮፕላንና በኢትዯጵያው አደጋ ምስስሎሽ እንዳለ አምኗል። ባለፈው ረቡዕ በአሜሪካ የሴኔት ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ለጥያቄ የቀረቡት የአሜሪካ የአቪየሽን ቁጥጥር ባለሥልጣን ተጠባባቂ ኃላፊ ዳንኤል ኤልወል መሥሪያ ቤታቸው በሕግ የተሰጠውን ሥልጣን ለአውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ አሳልፎ የሰጠበትን ሁኔታ በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጡ ሸንጎ አቅርቧቸዋል። ቦይንግ ያመረታቸው ማክስ ዘመነኛ አውሮፕላኖች እንዲህ ዓይነት መሠረታዊ የምሕንድስና ሕጸጽ እያለባቸው እንዴት በተቆጣጣሪ መሥሪያ ቤቱ የይለፍ ፍቃድ አገኙ የሚለው ዓለምን እያነጋገረ ቆይቷል። አንዳንድ የምርመራ ዘገባዎች እንዳመለከቱት ተቆጣጣሪ መሥሪያ ቤቱ ባለበት የበጀትና የባለሞያ እጥረት ምክንያት የአምራቹን ቦይንግ መሐንዲሶች ራሳቸው አውሮፕላኑን ፈትሸው እንዲያረጋግጡለት በከፊል ኃላፊነቱን አሳልፎ ሰጥቷቸው ነበር። ሴናተር ሪቻርድ ብሉሜንተል ይህንን ዝርክርክ አሠራር "ቀበሮ የአውራዶሮ ማደሪያ ቆጥ እንዲጠብቅ" ከማድረግ የማይተናነስ ሲሉ የሰላ ትቸት ሰንዝረውበታል። • ለ60 ዓመታት የዘለቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድና የቦይንግ ግንኙነት ከዚህም ባሻገር የኢትዮጵያው አደጋ ከደረሰ በኋላ በርካታ ዓለም አቀፍ አየር መንገዶች እርምጃ ሲወስዱ የአሜሪካ የአቪየሽን ቁጥጥር ባለሥልጣን ግን የማክስ አውሮፕላኖችን እንዳይበሩ ውሳኔ ለማስተላለፍ ዘገምተኛ ሆኗል በሚል ከሴናተሮች ተጨማሪ ወቀሳ ቀርቦበታል። የባለሥልጣኑ ተጠባባቂ ኃላፊ ግን ለሴናተሮች ትቸት እጅ አልሰጡም። "በኤምካስ ሶፍትዌር ላይ እምነት አለኝ። አብራሪዎችም ቢሆን አውሮፕላኑ ድንገት በአፍንጫው ሲደፋ ያንን ለመቀልበስ የሚያስችል በቂ ስልጠና ወስደዋል" ሲሉ ፍርጥም ብለው ለሸንጎው ምላሽ ሰጥተዋል። "እንዲያ የሚሉ ከሆነ ታዲያ የኢንዶኒዢያው አውሮፕላን በአንድ ደቂቃዎች ውስጥ 21 ጊዜ በአፍንጫው ሲደፋ ፓይለቱ ለምን ዝም አለ?" ሲባሉ " በጉዳዩ ዙርያ ለጊዜው በቂ ምላሽ የለኝም። መረጃ ይዤ እመለሳለሁ" ብለዋል። በቀጣይነት ምን ይጠበቃል? ቦይንግ አድሼዋለሁ፣ በነጻ ትወስዱታላችሁ ያለውን ሶፍትዌር በሚቀጥለው ሳምንት መጨረሻ ለአሜሪካ ፌዴራል የአቪየሽን ቁጥጥር ባለሥልጣን ያስረክባል። • ቻይና በቦይንግ 737 ማክስ 8 የሚደረጉ በረራዎችን አገደች ነገር ግን አዲሱ ሶፍትዌር ተቀባይነት እንዲያገኝ አውሮፕላኑ ሲስተሙ ላይ ተጭኖ፣ ስለ አፈጻጸሙ ፍተሻና ግብረ መልስ ከተገኘ በኋላ ፓይለቶች እንዲሰለጥኑበት ይደረጋል። ይህን ሁሉ ሂደት ካለፈ በኋላ ነው አውሮፕላኖቹ እንዲበሩ "የይብረሩ ሰርተፍኬት" ሊያገኙ የሚችሉት። አሁን ምርመራ ላይ ተሳትፎ እያደረጉ ያሉት የአሜሪካ የብሔራዊ ተራንስፖርት ደኅንነት ቦርድ፣ የፈረንሳይ የአቪየሼን ምርመራ ባለሥልጣን እና የኢትዮጵያ ትራንስፖርት ባለሥልጣን በዚህ ሳምንት መጨረሻ የመጀመርያ ዙር የምርመራ ውጤታቸውን ያሰማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
52088097
https://www.bbc.com/amharic/52088097
ኮሮናቫይረስ፡ ሁለት ሰዎች ከኮቪድ-19 መዳናቸው ተገለፀ
ኢትዮጵያ ውስጥ በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ 21 ሰዎች መካከል ሁለቱ ሙሉ ለሙሉ ከበሽታው መዳናቸው ተገለጸ።
ወረርሽኙ በአገሪቱ ውስጥ መከሰቱ ታውቆ ይፋ ከተደረገ በኋላ በነበሩት ሁለት ሳምንታት ውስጥ የህሙማኑ ቁጥሩ 21 መድረሱን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል። ከእነዚህ ውስጥም ሁለት ሰዎች የሚሰጠውን ህክምና በአግባቡ ተከታትለው ከበሽታው ሙሉ ለሙሉ የዳኑ መሆኑ ተገልጾ፤ ለጥንቃቄ ሲባል በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኙ ዶክተር ሊያ ታደሰ ጠቅሰዋል። • የህክምና ባለሙያዎቻቸውን ለመከላከል የሚተጉት ቱኒዚያውያን በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የኮቪድ-19 ህክምናና ለይቶ ማቆያ ማዕከል የሚሰሩ ሕክምና ባለሙያዎች በበኩላቸው በኢትዮጵያ ውስጥ የመጀመሪያው ሰው በቫይረሱ መያዙ ከታወቀ ጊዜ ጀምሮ እረፍት የለሽ ሳምንት ማሳለፋቸውን በሐኪም የፌስቡክ ገጽ ላይ አስፍረው፤ ቢያንስ ሁለት ሰዎች ተሽሏቸው ማየታቸው ተስፋ እንደሚሰጣቸውና ይህም " ከምን ጊዜውም የበለጠ ጠንክረን ለመስራት ተነሳስተናል" ማለታቸው ተዘግቧል። ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው በአሁኑ ጊዜ ቫይረሱ ለተገኘባቸው ሰዎች በተዘጋጀው የለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል ውስጥ 17 ህሙማን ሲኖሩ አንድ ታማሚ በጽኑ ህሙማን ከፍል ውስጥ ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተገልጿል። እስካሁን በሚመለከታቸው አካላት በበሽታው መያዛቸው ተረጋግጦ ኢትዮጵያ ውስጥ ከተመዘገቡት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ህሙማን መካከል ኢትዮጵያዊያን 14፣ ጃፓናዊያን 4፣ አንዲት እንግሊዛዊት፣ አንድ ኦስትሪያዊና አንድ ሞሪሸሳዊ ናቸው። በኢትዮጵያ ውስጥ ተመርምረው ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ከተረጋገጡት ሰዎች መካከል ሁለቱ ጃፓናዊያን ወደ አገራቸው የሄዱ ሲሆን ሁለት ኢትዮጵያዊያን ደግሞ ከበሽታው ሙሉ ለሙሉ ድነዋል። • የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የኢትዮጵያ ዝግጁነት ምን ይመስላል? ስለዚህም በኢትዮጵያ ውስጥ በሽታው እንደተገኘባቸው የተገለጸው ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር 21 ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 17 ነው። እስካሁን በኢትዮጵያ ውስጥ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል በጽኑ ከታመሙ አንድ የኮሮናቫይረስ ህመምተኛ በስተቀር በበሽታው ምክንያት የሞተ ሰው እንደሌለ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል።
news-51471899
https://www.bbc.com/amharic/news-51471899
አቶ ታዬ ደንደአ 2 ሚሊዮን ብር ተዘረፍኩ አሉ
የብልጽግና ፓርቲ አመራር የሆኑት አቶ ታዬ ደንደአ በቢሸፍቱ ከተማ ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው ብርና ሌሎች ንብረቶች ዝርፊያ እንደተፈጸመባቸው ለቢቢሲ ተናገሩ።
አቶ ታዬ ዘረፋው ያጋጠማቸው ለሥራ ጉዳይ ወደ ቢሾፍቱ በሄዱበት ወቅት መሆኑንና በዚህም ይጓዙበት ከነበረው መኪና ውስጥ ሁለት ሚሊዮን ብር እና ሌሎች ንብረቶች እንደተወሰደባቸው ገልጸዋል። ዝርፊያው የተፈፀመበት ሁኔታም ሲያስረዱም፤ ቢሾፍቱ ከተማ ውስጥ ቢን ኢንተርናሽናል በተባለ ሆቴል ምሳ ለመመገብ መኪናቸውን አቁመው በገቡበት ጊዜ "የመኪናቸው በር በማስተር ቁልፍ ተከፍቶ" የተጠቀሰው ገንዘብና የተለያዩ ንብረቶች እንደተዘረፈባቸው ተናግረዋል። • ኤርትራውያን ስደተኞች በድንበር በኩል ምዝገባ ተከልክለናል አሉ • ኮሮና ቫይረስ መጠሪያ ስሙን አገኘ • ሶማሊያ፡ ታዳጊዋን ደፍረው ለህልፈት የዳረጉት በጥይት ተደብድበው ተገደሉ ይህ ከፍተኛ መጠን ያለውን ገንዘብ በመኪናቸው ይዘው የነበረው በቢሾፍቱ ከተማ ስልጠና እየተከታተሉ ለነበሩ ለሰልጣኞች የሚከፈል አበል እንደነበር ጨምረው አስረድተዋል። ከገንዘቡ በተጨማሪ ላብቶፕ ኮምፒውተር እና ሁለት የሥራና የግል ጉዳዮችን የሚጽፉባቸው ማስታወሻ ደብተሮች እንደተሰረቁባቸው ተናግረዋል። ጨምረውም ስርቆቱ ከተፈፀመ በኋላ "የታዬ ማስታወሻ ደብተር እጄ ገብቷል" ብሎ የፌስቡክ ገፁ ላይ የጻፈ ግለሰብ መኖሩንና ጉዳዩን ወደ ሕግ መውሰዳቸውንም ያስረዳሉ። የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ ስለጉዳዩ ተጠይቆ ምርመራ እየተካሄደ ስለሆነ ተጣርቶ ሲያልቅ ይፋ እንደሚደረግ የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ደረጀ ሙለታ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የአቶ ታዬ ደንደአ የማስታወሻ ደብተር መሰረቁን ፌስቡክ ገፁ ላይ ጻፈ ያሉት ግለሰብ በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ በማህበራዊ ሚዲያዎች ሃሳብ በመስጠት የሚታወቀው ደረጀ ቤጊ የተባለ ግለሰብ ነው። በጉዳዩ ላይ ቢቢሲ ያነጋገራቸው አቶ ደረጀ "እንደማንኛውም ጊዜ በፌስቡክ የመልዕክት ሳጥኔ እንደተላከልኝ አስታውቄ ነው ማስታወሻዎቹ መሰረቃቸውን የፃፍኩት" ብለዋል። "በውስጥ መስመር ነው የተላከልኝ፤ የለጠፍኩትም [ኢንቦክስ] ብዬ ነው። ታዬ መዘረፉንም ሆነ ስለ እርሱ ምንም የማውቅው ነገር የለኝም" ብለዋል። አቶ ታዩ ደንደአ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ሲሆኑ በመገናኛ ብዙህን እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያዎች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የፓርቲያቸውንና የራሳቸውን አቋም በመግለጽ ይታወቃሉ።
news-45505802
https://www.bbc.com/amharic/news-45505802
የጀርመን ቄሶች ሕፃናት ላይ የፈፀሙት በደል ይፋ ሆነ
የጀርመን ሮማን ካቶሊክ ቤተክርስትያን ቀሳውስት ከፈረንጆቹ 1946-2014 ባለው ጊዜ 3600 ገደማ ሕፃናት ላይ ፈፅመውታል የተባለው ጭቆና ይፋ ሆኗል።
ጥናቱን ያካሄደው የጀርመን ሮማን ካቶሊክ ቤተክርስትያን ኦፊሴላዊ ውጤቱን መስከረም 25 ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ዘገባው እንደሚጠቁመው 1670 ገደማ የቤተክርስቲያኒቱ ሰዎች 3677 ሕፃናት ላይ ፆታዊ ጥቃት አድርሰዋል። • የ80 ሚሊየን ዶላር የሙስና ቅሌት ተጋለጠ የቤተክርስትያኒቱ ቃል አቀባይ የሆኑ ግለሰብ በውጤት 'እጅግ ማፈራቸውን እና ጭንቀት ውስጥ መግባታቸውን' ተናግረዋል። ጥናቱ 'ግፍ ፈፃሚ ቀሳውስት አሏት' እየተባለች ለምትታማው የሮማን ካቶሊክ ቤተክርስትያን ሌላ መዘዝ ይዞ ብቅ ብሏል። ከጥቃት አድራሽ ቀሳውስት መካከል 38 በመቶ ያህሉ ብቻ ናቸው ቅጣት የተጣለባቸው የሚል ዘገባም ብቅ ብሏል፤ ከስድስት አንድ ብቻ ናቸው ለፍርድ የሚቀርቡት። ጥቃት ከደረሰባቸው ሕፃናት መካከል በርካቶቹ ወንዶች እንደሆኑ ሲነገር ዕድሜያቸው ደግሞ ከ13 ዓመት በታች ነው ተብሏል። • የአፍሪካ እግር ኳስ ቅሌት ጥናቱን ያካሄዱት ሦስት የጀርመን ዩኒቨርሲቲዎች ሲሆኑ 38 ሺህ ያህል መዝገቦች አገላብጠዋል፤ በርካታ መዝገቦች እንደተደመሰሰ ቢጠረጠርም። የቤተክርስቲያኒቱ ቃል አቀባይ የሆኑት ቢሾፕ ስቴፋን አከርማን «የጥናቱ ዓላማ በቤትክርስትያናችን እየተፈፀመ ያለውን ግፍ ማስቆም ነው» ብለዋል። የሮማን ካቶሊክ ቤ/ክ ዋና መቀመጫ የሆነችው ቫቲካን ስለጉዳዩ እስካሁን ምንም ባትልም ሊቃ ጳጳሳት ፖፕ ፍራንሲስ ግን ስለጉዳዩ ለመምከር ለወርሃ የካቲት ቀጠሮ መያዛቸው እየተነገረ ነው። • በሄይቲ የኦክስፋም ቅሌት፡ ተጠርጣሪዎች የአይን እማኞችን አስፈራርተዋቸዋል
news-49909587
https://www.bbc.com/amharic/news-49909587
አራት የኤርትራ የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን አባላት ኡጋንዳ ውስጥ ጠፉ
አራት የኤርትራ የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን አባላት ኡጋንዳ ውስጥ መጥፋታቸው ታወቀ።
ከ20 ዓመት በታች የሴካፋ እግር ኳስ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ወደ ኡጋንዳ ካቀኑት ተጫዋቾች መካከል አራቱ ወደ ሆቴላቸው ያልተመለሱ ሲሆን፤ ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ በተዘጋጀው ልምምድ ላይም አልተገኙም ተብሏል። • አሥመራን አየናት፡ እንደነበረች ያለችው አሥመራ • የኤርትራ ወጣቶችና ምኞታቸው የቢቢሲ ትግርኛ ክፍል ከምንጮቹ ማረጋገጥ እንደቻለው ከሆነ አራቱም ተጫዋቾች በኡጋንዳ የጥገኝነት ጥያቄ አቅርበዋል። የውድድሩ አዘጋጅ ኮሚቴ ዋና ጸሃፊ የሆኑት ኤማብል ሃቢማና የተጫዋቾቹን መጥፋት ማረጋገጣቸውን የኡጋንዳ ሚዲያዎች የዘገቡ ሲሆን፤ እስካሁን የት እንደሚገኙ የታወቀ ነገር የለም ተብሏል። ዋና ጸሃፊው ''አራቱም ተጫዋቾች ከማረፊያቸው ጠፍተዋል። ከክስተቱ በኋላ በሆቴሉ አካባቢ ያለውን ጥበቃ አጠናክረናል። ውድድሩ በጥሩ መንፈስ ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ነው የምንፈልገው'' ማለታቸውን ደይሊ ሞኒተር የተባለው የኡጋንዳ ጋዜጣ ዘግቧል። የኤርትራ ብሔራዊ ቡድን እስካሁን ጥሩ እየተጫወተ የነበረ ሲሆን፤ ዛሬ ከሰአት ላይ በግማሽ ፍጻሜ ከኬንያ አቻው ጋር ተጫውቶ 1 ለምንም ተሸንፏል። በሴካፋ ውድድር ስድስት ግቦችን በማስቆጠር ኮከብ ጎል አግቢነቱን እየመራ የሚገኘው ኤርትራዊው ማወል ተስፋይ በጉዳት ምክንያት በጨዋታው ላይ እንደማይሰለፍ ታውቋል። ምናልባትም ጥገኝነት ከጠየቁት አራት ተጫዋቾች መካከል ሊሆን እንደሚችልም ተገምቷል። የተጫዋቾቹ መጥፋት ብሔራዊ ቡድኑ ላይ ምን አይነት ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችል እስካሁን ባይታወቅም በውድድሩ እንደሚቀጥሉ ይጠበቃል። • የዛሬዋን ኤርትራ የሚገልጹ አስደናቂ እውነታዎች ተጫዋቾቹ ሊጠፉ የቻሉት "ጉዳት አጋጥሞናል" ብለው በሆቴላቸው ከቀሩ በኋላ መሆኑንም ደይሊ ሞኒተር ዘግቧል። የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ በቀሪ 14 ተጫዋቾች ውድድሩን የሚጨርሱ ሲሆን፤ የቀሩት ተጫዋቾች ግን በህምም ምክንያት ሊገኙ አልቻሉም ሲሉ ተደምጠዋል። በተመሳሳይ እ.አ.አ. በ2015 አሥር የዋና ብሔራዊ ቡድኑ አባላት ወደ ቦትስዋና ከሄዱ በኋላ አንመለስም ማለታቸው ይታወሳል። በ2013ትም ዘጠኝ የሚሆኑ የቡድኑ አባላትና አሰልጣኙም ጭምር ኬንያ ውስጥ ተሰውረው ነበር።
news-50703980
https://www.bbc.com/amharic/news-50703980
መከራቸው የበዛው ቦስኒያ የሚገኙ ስደተኞች
በቦስኒያ ክረምት ገብቷል። በድንበር በኩል አቋርጠው ወደ ክሮሺያ ለመግባት ያሰቡ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችም እጅግ የሚበርደውን ክረምት በቦስኒያ ለማሳለፍ ተገደዋል።
ለአብዛኛዎቹ ስደተኞች ምሽት ላይ በተለይ ከዜሮ በታች የሚሆነውን ቅዝቃዜ መቋቋም የማይታሰብ ነው። ሁኔታው ለህይወታቸውም አስጊ የሚባል ደረጃ ላይ እንደደረሰ ተገልጿል። • ሕይወትን ከዜሮ መጀመር • በኢትዮጵያ ስላሉ ስደተኞች አንዳንድ ነጥቦች 'ቢራ' በሚባለው አካባቢ የዓለማቀፉ ስደተኞች ድርጅት ማዕከል የከፈተ ቢሆንም በርካታ ስደተኞች መጠለያ ፍለጋ እዚህም እዚያም ሲንጎራደዱ መመልከት የተለመደ ነገር ሆኗል። ከዚህ በፊት የማቀዝቀዣ (ፍሪጅ) ፋብሪካ የነበረው አዳራሽ በአሁኑ ሰአት እስከ 2000 በሚደርሱ ስደተኞች ተጨናንቋል። ማዕከሉ መተኛ ክፍሎች፣ የጤና አገልግሎት፣ መታጠቢያዎች ያሉት ሲሆን ትኩስ ምግቦችንም ያቀርባል። ነገር ግን የስደተኞቹ ቁጥር ከአቅም በላይ በመሆኑ በርካታ ስደተኞች ወደ ማዕከሉ መግባት አይችሉም። የማዕከሉ ሃላፊ የሆነችው አሚራ ሀድዚሜሜዶቪችም ሁኔታው በጣም የሚያሳዝን መሆኑን ትገልጻለች። '' በጣም መጥፎ ስሜት ውስጥ ነው የሚከተው። አንድን ሰው ልረዳህ አልችልም ብሎ በእንደዚህ አይነት ብርድ ውስጥ ውጪ እንዲያድር ማድረግ በጣም ከባድ ነው'' ብላለች። ምንም እንኳን የሀገሪቱ መንግሥት አዲስ ስደተኞች እንዳይገቡ ቢከለክልም እስከ 2000 የሚደርሱ ስደተኞች አሁንም ከበረዶ ጋር እየታገሉ በመንገዶች ግራና ቀኝ ይታያሉ። በአውሮፓ ሕብረት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር የሆኑት ዱንጃ ሚጃቶቪች የስደተኞች መጠለያውን ከጎበኙ በኋላ ሁኔታው ''ኢሰብአዊና ተቀባይነት የሌለው ነው'' ብለዋል። • ከመስመጥ አደጋ የተረፉት ሁለት ኤርትራዊያን ስደተኞች ''ስደተኞች ከበረዶና ጭቃ ጋር ተቀላቅለው ማየት ያሳምማል፤ በቂ የሆነ ውሀ አቅርቦት እንኳን የላቸውም፤ የስደተኞች ማቆያው ከነጭራሹ ሊከፈት አይገባም ነበር'' ብለዋል በሰጡት መግለጫ። አክለውም ስደተኞቹን ወደተሻለ ቦታ ማዘዋወርና ተገቢውን ሰብአዊ አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል።
news-55541613
https://www.bbc.com/amharic/news-55541613
በኢትዮጵያ የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ምርቶች ቀረጥ ላይ ከፍተኛ ቅናሽ ተደረገ
ኢትዮጵያ በመሰረታዊ የንጽህና መጠበቂያ ምርቶች ላይ የቀረጥና የታክስ ማሻሻያ ማድረጓን የአገሪቱ የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ እንዳለው በዚህ ውሳኔ መሰረት የሴቶች ወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ (ሞዴስ) እንዲሁም የህፃናት ንጽህና መጠበቂያ (ዳይፐር) በኢትዮጵያ ውስጥ የሚያመርቱ ፋብሪካዎች ለምርታቸው በሚያስፈልጉና ከውጭ በሚያስገቧቸው የጥሬ እቃ ግብዓቶች ላይ የነበረው ታክስ እንዲነሳ መወሰኑን አመልክቷል። በተጨማሪም እነዚህ የሴቶችና የህጻናት ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ከውጭ ተመርተው ሲገቡ ደግሞ ቀደም ሲል ተጥሎባቸው የነበረው የ30 በመቶ ከፍተኛ የታክስ ምጣኔ ተቀንሶ ወደ 10 በመቶ ብቻ እንዲሆን መደረጉን ሚኒስቴሩ ገልጿል። ይህ የመንግሥት ውሳኔ እነዚህ መሠረታዊ የንጽህና መጠበቂያ ምርቶች በተለይም በወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ምርቶች በአገር ውስጥ እንዲመረቱ ለማስቻልና የአገር ውስጥ አምራቾች እንዲበረታቱ የቀረጥና የታክስ ማሻሻያ መደረጉ ታውቋል። ሚኒስቴሩ በተጨማሪም ይህ የቀረጥና ታክስ ማሻሻያ፣ ሴቶች የንጽህና መጠበቂያን በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ በማድረግ ሴት ተማሪዎች ትምህርታቸውን ከወር አበባ ጋር በተዛመዱ ምክንያቶች እንዳያቋርጡና በትምህርት ቤት ወይም በሥራ ላይ የሥነ ልቦና ጫና እንዳይገጥማቸው ለማገዝ ነው ብሏል። በተጨማሪም እርምጃው የአገር ውስጥ ምርትን በማሳደግና ዋጋ እንዲቀንስ በማድረግ የንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን ችግር ዘላቂ በመሆነ መንገድ መፍታት እንዲሁም ጥራት ያላቸው ምርቶች እንዲቀርቡ ለማስቻል እንደሚያግዝ ተገልጿል። በሴቶች የንጽህና መጠበቂያ ምርቶች አቅርቦት ዙሪያ በኢትዮጵያ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በእነዚህ ምርቶች ላይ ባለው የዋጋ ውድነትና የአቅርቦት ችግር የተነሳ አብዛኞቹ ሴቶች የሚጠቀሙት በቤት ውስጥ የሚዘጋጁ የወር አበባ መጠበቂያ ዘዴዎችን ነው። ይህም በተለይ አብዛኛው ሕዝብ በሚኖርባቸው የገጠር አካባቢዎች የሚኖሩ ሴቶች ትምህርትና አጠቃላይ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽእኖን እንደሚያሳድር ይነገራል። ለሴቶች መብት የሚሰሩ ማኅበራት፣ ተቋማትና ግለሰቦች የሴቶችን ጤናና ሁለገብ ተሳትፎ ለማበረታታት መንግሥት የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን ዋጋ በእጅጉ የሚቀንሱ እርምጃዎችን እንዲወስድ ለዓመታት ሲወተውቱ መቆየታቸው ይታወሳል። ኢትዮጵያ በሴቶች የንጽህና መጠበቂያ ምርቶች ላይ ተጥሎ የቆየውን የቀረጥ ታክስ ለማንሳት እንዲሁም ለመቀነስ የወሰደችው እርምጃ በምርቶቹ ዋጋ ላይና አቅርቦት ላይ ጉልህ ውጤት እንደሚኖረው ይጠበቃል። የገንዘብ ሚኒስቴር እንዳለው በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ስምንት የሴቶች የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ (ሞዴስ) የሚያመርቱ ፋብሪካዎች አሉ።
news-46534984
https://www.bbc.com/amharic/news-46534984
ኬንያ ሳንቲሞቿ ላይ የነበሩ መሪዎችን በእንስሳት ቀየረች
ኬንያ ከዚህ በፊት የተለመዱ የነበሩትን የቀድሞ መሪዎቿን ምስል ከሳንቲሞች ላይ በማንሳት በእንስሳት ምስሎች መተካት ጀምራለች።
የቀድሞዎቹ ሶስት መሪዎች ማለትም፤ ጆሞ ኬንያታ፣ ዳንኤል አራፍ ሞይ እና ሙዋይ ኪባኪ ከዚህ በኋላ በሳንቲሞች ላይ ምስላቸው እንደማይኖር የተገለጸ ሲሆን፤ በወረቀት ገንዘቦችም ላይ ተግባራዊ ሊደረግ ይችላል ተብሏል። የመሪዎቹ ምስል በሳንቲሞች ላይ የሚታተመው እራሳቸውን ለማስተዋወቅና የመንግሥትን ስልጣን እንደ ግል ሃብታቸው ስለሚቆጥሩት ነው ብለው ብዙ ኬንያውያን ያስባሉ። አዳዲሶቹ ሳንቲሞች እንደ አንበሳ፣ ዝሆን፣ ቀጭኔና አውራስ ያሉ የሃገሪቱን ታዋቂ የዱር እንስሳት ምስል እንደሚያካትት ተገልጿል። • ካሾግጂ የዓመቱ ምርጥ ሰው ዝርዝር ውስጥ ተካተተ • በሳተላይቶች ዙርያ ሰባት አስደናቂ እውነታዎች የኬንያ የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ልጅ የሆኑ የአሁኑ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እንደተናገሩት አዲሶቹ ሳንቲሞች እንደ ትልቅ ለውጥ ሊታዩ የሚገቡና ሃገሪቱ የተጓዘችውን ረጅም ርቀት የሚያሳይ ነው ብለዋል። በሚገርም ሁኔታ በሳንቲሞቹ ላይ ያሉት የሶስቱም የቀድሞ መሪዎች ምስል ፕሬዚዳንቶቹ በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት በተሰጠ ትዕዛዝ የታተሙ ናቸው። ሙዋይ ኪባኪ በ2002 በምርጫ አሸንፈው ፕሬዚዳንት ሲሆኑ ምስላቸውን በወረቀት ገንዘብ ላይ እነደማያሰፍሩ ቃል ቢገቡም፤ በመጨረሻ ግን ምስላቸው በሳንቲምና በወረቀት ገንዘብ ላይ እንዲታተም አዝዘዋል። ከኬንያ ዜጎች በመጣ ከፍተኛ ጫና ምክንያት የሃገሪቱ ህገ መንግስት በ2010 እንዲሻሻል የተደረገ ሲሆን፤ የማንኛውም ሰው ምስል በወረቀት ገንዘብና ሳንቲሞች ላይ መታተም የለበትም የሚለው ደግሞ ከማሻሻያዎቹ መካከል አንዱ ነበር። • ሞዛምቢክ ሰላሳ ሺ የማይታወቁ ሰራተኞች አሏት የሃገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ ይህንን ህግ በሳንቲሞቹ ላይ ተግባራዊ ማድረግ የጀመረ ሲሆን፤ በቅርቡ ደግሞ በወረቀት ገንዘብ ላይ ተመሳሳይ እርምጃ እንደሚወስድ ይጠበቃል። ማዕከላዊ ባንኩ እንዳስታወቀው አዲሱ የእንስሳት ምስል የበለጸገችና በአዲስ መልክ እየተሰራች ያለችውን ኬንያ በተገቢው ሁኔታ ይገልጻል።
news-53987818
https://www.bbc.com/amharic/news-53987818
ፌስቡክና ትዊተር "የሩስያን መረብ በጣጠስን" አሉ
ፌስቡክ አነስተኛ የትስስር መረብ ያላቸውንና የሩስያ እጅ አለበት ያላቸውን አካውንቶችና ገፆች መዝጋቱን አስታወቀ።
ኩባንያው እነዚህ ገፆች የከፈቱት ዘመቻ በቀጥታ የሚገናኘው እኤአ በ2016 የአሜሪካ ምርጫ ላይ ጣልቃ ገብቷል ተብሎ የሚወነጀለውና ከሩስያ መንግሥት ጋር ቅርብ የሆነው የሩሲያ ኢንተርኔት ምርምር ኤጀንስ (IRA) ጋር ነው ብሏል። ትዊተርም በበኩሉ ከዚሁ ድርጅት ጋር ግንኙነት ያላቸው አምስት አካውንቶችን መዝጋቱን ገልጿል። ድርጅቱ ስራውን ያከናውን የነበረው መንግሥታዊ ባልሆነ ድርጅት ስም ተመዝግቦ ሲሆን በእንግሊዘኛ እና በአረብኛ የሚነበብ ድረ ገጽም አለው። ፌስቡክና ትዊተር እንዳሉት ከሆነ ድርጅቱ ከፍቶ የነበረው ዘመቻ በጣም አነስተኛ ውጤት ነበር ያገኘው። ከሩስያ መንግሥት ጋር ግንኙነት ያለው ድርጅት በዚህ ዓመት አሜሪካ ምርጫ ላይ ተጽዕኖ ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ መሆኑ የተሰማው ፕሬዝዳንት ትራምፕ እና ጆ ባይደን የሚፋለሙበት ምርጫ ሊደረግ ሁለት ወር ብቻ በቀረው ወቅት ነው። ፌስቡክና ትዊትር ከኤፍቢአይ ጋር አብረው ከሩስያ ጋር ንክኪ ያለውን ፒስዳታ የተሰኘ ድረገጽ ላይ እርምጃ ለመውሰድ ግብረ ኃይል አቋቁመው ሲሰሩ ነበር ተብሏል። ፌስቡክ በዚህ ዘመቻ 13 አካውንቶች፣ ሁለት ገጾችን ማስወገዱን ገልጾ " ትኩረታቸው በአሜሪካ የሚደረጉ ህዝባዊ ውይይቶች ነበሩ" ካለ በኋላ ድርጅቱ ዩናይትድ ኪንግደም እና ግብጽ ላይም አይኑን መጣሉን አስታውቋል። ነገር ግን የድርጅቱ ስኬት እዚህ ግባ የሚባል እንዳልነበር የገለፀው ፌስቡክ፣ 14 ሺህ ያህል አካውንቶች ከተወገዱት ገጾች መካከል አንዱን ወይንም ሁለቱንም ይከተሉ ነበር ብሏል። የእንግሊዝኛ ድረ ገፁ 200 ተከታዮች ነበሩት ሲልም አክሏል። የተሰረዙት አካውንቶች ሐሰተኛ ስም እና የፕሮፋይል ምስል ይጠቀሙ ነበር ተብሏል። ገጾቹ ላይ የሚጽፉት ለፒስዳታ ድረገጽ በነጻ የሚሰሩ ግለሰቦች ነበሩ። ትዊተር በበኩሉ አምስት አካውንቶችን ማቋረጡን ገልጾ፣ ገጾቹ ከሩሲያ ጋር እንደሚገናኙ አስታውቋል። በተጨማሪም በገጾቹ የሚወጡት መረጃዎች ይዘታቸው የወረደ መሆኑን ገልጾ፣ " በጣም በአነስተኛ ሰዎች ብቻ ይከተሏቸው፣ መረጃዎቻቸውንም ያዩ ያጋሩ ነበር" ሲል ገልጿል። አይ አር ኤ በአሜሪካ የፍትህ ቢሮ የ2016 ምርጫ ላይ እጃቸውን አስገብተዋል ከተባሉ እና ከሩሲያ መንግሥት ጋር ግንኙነት አላቸው ከተባሉ ሶስት የሩሲያ ኩባንያዎች እንዲሁም 13 ሰዎች መካከል አንዱ ነው።
news-53369062
https://www.bbc.com/amharic/news-53369062
በኢትዮጵያ ክረምቱ የኮቪድ-19 ስርጭትን ሊያባብስ ይችላል?
ክረምት የተለያዩ የመተንፈሻ አካላት ህመሞች የሚቀሰቀሱበት ወቅት እንደሆነ የጤና ባለሙያዎች ይናገራሉ። ወቅት ጠብቆ የሚመጣ ጉንፋንን ጨምሮ ሌሎችም ህመሞች የሚበረቱበት ጊዜ ነው።
ከዚህ ጋር በተያያዘ የኮቪድ-19 ስርጭት ሊጨምር ይችል ይሆን? ስንል በጎንደር ዩኒቨርስቲ የሚሠሩትን የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ዶ/ር ቴዎድሮስ ጸጋዬን ጠይቀናል። ባለሙያው እንደሚሉት፤ በቫይረስ ሳቢያ የሚከሰቱ የመተንፈሻ አካል ህመሞች በተቀረው ዓለም ቀዝቃዛ በሆነ ወቅት ይከሰታሉ። ይህም በእንግሊዝኛው ዊንተር በሚባለው (ከኅዳር እስከ መጋቢት) ባለው ጊዜ የሚታይ ህመም ነው። ወደ ኢትዮጵያ አውድ ስንመጣ በቂ ጥናት ባይኖርም፤ ዝናባማ በሆኑ የክረምት ወራት (ከግንቦት እስከ መስከረም) የመተንፈሻ አካል ህመም በብዛት ይስተዋላል። አብዛኞቹ የመተንፈሻ አካል ህመሞች የሚከሰቱት በቫይረስ ቢሆንም እንደ አለርጂና አስም ያሉ ያለ ቫይረስ የሚመጡ ህመሞችም አሉ። እነዚህ ህመሞች በቅዝቃዜ ወቅት የሚቀሰቀሱት በሦስት ምክንያቶች እንደሆነ ዶክተሩ ያስረዳሉ። አንደኛው በበሽታው ከሚያዙ ሰዎች ጋር የተያያዘ ምክንያት ነው። “ሰዎች ቀዝቃዛ ወቅት ላይ የመሰባሰብ ባህሪ አላቸው። ይሄ ደግሞ የበሽታዎችን [ኮቪድ-19ኝን ጨምሮ] የመተላለፍ እድል ይጨምረዋል። ቀዝቃዛ አየር ሲኖር የአየር ቧንቧችንም ስሱ ይሆናል” ይላሉ። የሁሉም ሰው በሽታ የመከላከል አቅም እኩል ስላልሆነ በቀላሉ በቀዝቃዛ አየር ሳቢያ አለርጂ የሚነሳባቸው ሰዎች አሉ። ሰውነት ከውጪ የሚመጣውን ወራሪ ለመከላከል የሙቀት መጠኑን ከፍ ስለሚያደርግ ትኩሳት ይፈጠራል። ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ለቫይረሶቹ የሚፈጠረው ምቹ ሁኔታ ነው። ቅዝቃዜ የመተንፈሻ አካልን ሊጎዳ ይችላል። የመተንፈሻ አካል ሲጎዳ ደግሞ ለቫይረስ ምቹ ሁኔታ ይፈጠራል። ሦስተኛው የከባቢ አየር ለውጥ ለበሽታ ማጋለጡ ነው። “ይህ ወቅት ቀዝቃዛና ደረቅ ነው፤ ቀዝቃዛና ደረቅ አየር በአየር ቧንቧ ሲያልፍ ጉዳት ይፈጥራል” ሲሉ ዶክተሩ ያብራራሉ። ክረምት የኮቪድ-19 ስርጭትን ያባብሳል? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ጥናት እንደሚያስፈልግ ገልጸው፤ ከዚህ ቀደም የታዩ ተመሳሳይ በሽታዎችን በመመርኮዝ ግን ለበሽታው ተጋላጭ የመሆን እድል እንዳለ ይናገራሉ። “ኮሮናቫይረስ እንደ ሌሎቹ አይነት በሽታዎች ያለ ባህሪ የሚያሳይ ከሆነ ይህ ዝናባማ ወቅት ለበሽታው በጣም አጋላጭ ነው።” ሌሎች አገሮች ላይ የታውን የቫይረሱን የስርጭት መጠን ብንመለት፤ በቀዝቃዛ ወራት (በሽታው በተከሰተበት ዊንተር ወቅት) ላይ የህሙማን ቁጥር ጨምሯል። ይህ በኢትዮጵያም ሊከሰት እንደሚችል ዶ/ር ቴዎድሮስ ይናገራሉ። የበሽታዎች ምልክት መመሳሰል ሌሎች የመተንፈሻ አካል በሽታዎችና ኮቪድ-19 መካከል የምልክት መመሳሰል አለ? ካለስ አንድ ሰው በምን ህመም እንደተያዘ ለማወቅ ምን ማድረግ ነው የሚጠበቅበት? ስንል ዶ/ር ቴዎድሮስን ጠይቀን ነበር። ባለሙያው እንደሚያስረዱት፤ ቅዝቃዜን ተከትሎ አንዳች የመተንፈሻ አካል ህመም ሲከሰት፤ ሰውነት ከውጪ የሚመጣውን ወራሪ ለመከላከል የሙቀት መጠኑን ከፍ ስለሚያደርግ ትኩሳት ይፈጠራል። ይህም ከኮሮናቫይረስ ምልክቶች አንዱ ነው። “አለርጂም ቢሆን፣ ኮቪድ-19ኝም ቢሆን፣ ሌላም አይነት ኢንፌክሽን ቢሆን፤ ሰውነት ራሱን ለመከላከል በሚያደርገው ጥረት እንደ ማፈን፣ ማሳል፣ ትኩሳትን የመሳሰሉ ምልክቶች ይፈጠራሉ።” የመተንፈሻ አካል ህመሞች ምልክት መመሳሰል ካለ፤ ሰዎች በሌላ የመተንፈሻ አካል ወይም በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን እንዴት መለየት ይችላሉ? ወደ ህክምና ተቋምስ መቼ ነው መሄድ ያለባቸው? ሌላው ጥያቄ ነው። “በሽታዎችን በምልክት ለመለየት መሞከር እንዲሁም ለበሽታዎች ምልክት የተጋነነ ግምት መስጠት ጥሩ አይደለም” ይላሉ ባለሙያው። የመተንፈሻ አካል ማንኛውም ከውጪ የገባ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል ነገር ሲገጥመው በአፋጣኝ ምላሽ ይሰጣል። የሰዎች የበሽታ መከላከል አቅም የተለያየ ስለሆነ አንዳንዱ በአፋጣኝ ሰውነቱ ላይ የህመም ምልክት ሲታይ ሌላው ሰው ግን ምልክት ላያሳይ ይችላል። አብዛኞቹ የመተንፈሻ አካል በሽታዎች መካከል መመሳሰል ቢኖርም ጉዳት ከሚያደርሱበት አካል አንጻር የተለያየ ምልክት ሊያሳዩ ይችላሉ። የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ሐኪሙ እንደሚያስረዱት፤ አንዳንድ ቫይረሶች የላይኛውን የመተንፈሻ አካል ብቻ ያጠቃሉ። ለምሳሌ ጉንፋን ከአፍንጫ አካባቢ የዘለለ ጉዳት የለውም። ኮቪድ-19 ደግሞ የታችኛውን የመተንፈሻ አካል ማለትም የሳንባ ክፍል እንደሚያጠቃ ታይቷል። ሳምባ ሲጎዳ ሳል፣ ትንፋሽ ማጠር የመሳሰሉት ምልክቶች ይከሰታሉ። ከዚያ ውጪ አንዳንዴ ኮሮናቫይረስ ከላይ ያለውን የመተንፈሻ አካል ጎድቶ የጉንፋን አይነት (ጉልህ ያልሆነ) ምልክት ብቻ የሚያሳዩ ሰዎችም አሉ። አንዳንዴ በሽታውን በምልክት ለመለየት አስቸጋሪ የሚሆነውም ለዚህ ነው። በሽታውን ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት በክረምት ለውጥ ያስፈልገዋል? በዚህ የክረምት ወቅት የወረርሽኙ መስፋፋት የሚጨምርበት እድል ሰፊ ከሆነ፤ በሽታውን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ላይ ማሻሻያ ወይም ለውጥ ማድረግ በተመለከተ ዶ/ር ቴዎድሮስ እንደሚሉት፤ የተወሰነ ለውጥ ማድረግ ቢያስፈልግም ጉዳዩ ከተለያየ አቅጣጫ መታየት አለበት። የመጀመሪያው ከግምት መግባት ያለበት ነጥብ ወቅቱ እንደ አለርጂ ያሉ የመተንፈሻ አካል ህመሞች የሚጨምሩበት እንደመሆኑ፤ የበሽታዎች ምልክት ተመሳሳይ ስለሚሆን የምርመራ መጠን ይጨመር ቢባል መመርመሪያ መሣሪያ እጥረት ማስከተሉ ነው። “በብዛት ምርመራ ተደርጎ ሰዎች የሚገኝባቸው ኮቪድ-19 ሳይሆን ሌላ የመተንፈሻ አካል ህመም ከሆነ የምርመራ አቅምን ማባከን ነው። ምልክት ያሳየውን ሁሉ እንመርምር ብንል አቅማችን ይፈቅዳል?” ሌላው ነጥብ እምብዛም ጉልህ ምልክት ለማያሳዩ ሰዎች ለኮቪድ-19 ብቻ ተብሎ የተለየ ህክምና ካልተሰጠ፤ መጠኑን መጨመር ያለውን የመመርመር አቅም ማባከን ይሆናል። በሌላ በኩል ግን ምርመራ ሳይደረግ በኮሮናቫይረስ ሳቢያ የሚጎዱ፣ ሕይወታቸውን የሚያጡ ሰዎችም አሉ። ዶክተሩ ከላይ የተቀመጡትን ነጥቦች በማጣቀስ፤ “በሽታው የሚያስከትለው ጉዳት በአንድ ወገን በሌላ ጎን ደግሞ ያለን አቅም ከግምት ገብተው አማካዩን መንገድ መከተል ያስፈልጋል” ሲሉ ሐሳባቸውን ይገልጻሉ። ወረርሽኙን በተመለከተ የሚሰጠው ትምህርት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ይመክራሉ። በተለይ በክረምት ወቅት ያለው መጠጋጋት የበሽታውን የመተላለፍ እድል ስለሚጨምር ጥንቃቄ መደረግ አለበት። ቀዝቃዛ አየር የሚጎዳው የመተንፈሻ አካል በወረርሽኙ በቀላሉ የመያዝ እድልን ስለሚጨምርም ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልጋል።
news-49875478
https://www.bbc.com/amharic/news-49875478
የሳዑዲው ልዑል ኢራን ለዓለም ነዳጅ ምርት ስጋት ናት አሉ
የሳዑዲ አረቢያው ልዑል ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ኢራን ከድርጊቷ እንድትታቀብ ማድረግ ካልቻለ የነዳጅ ዋጋ በማይታመን ሁኔታ ይጨምራል ሲሉ አስጠነቀቁ።
በሳዑዲ አረቢያና በኢራን መካከል የሚደረግ ጦርነት ዓለም አቀፉን የኢኮኖሚ ሥርዓትን ሊያቃውስ ይችላል ብለዋል መሃመድ ቢን ሳልማን። ለዚህም መነሻ የሆናቸው ከሁለት ሳምንት በፊት በሳዑዲ ሁለት የነዳጅ ማምረቻ ተቋማት ላይ ቴህራን ጥቃት አድርሳለች ብላ ከመወንጀሏ ጋር ተያይዞ ነው። • የሳኡዲ አረቢያው ንጉሥ ጠባቂ በጥይት ተገደለ • «ካሾግጂ ወዲያው ነበር የታነቀው» ቱርክ ልዑሉ ከሲቢኤስ የዜና ወኪል ጋር በነበራቸው ቆይታ በጋዜጠኛው ጀማል ኻሾግጂ ግድያም ላይም የተወሰነ ኃላፊነት እንደሚወስዱ ቢናገሩም ለግድያው ትዕዛዝ አልሰጠሁም ሲሉ ክደዋል። የሳዑዲ አረቢያ መሪ ተደርገው የሚታዩት ልዑሉ በሰላ ትችቱ የሚታወቀውን የሳዑዲ ጋዜጠኛ ጀማል ካሾግጂ ግድያ በቀጥታ ተሳትፈዋል ተብለውም ይጠረጠራሉ። ኻሾግጂ የተገደለው በቱርክ በሚገኘው የሳዑዲ ቆንስላ ውስጥ ባለፈው አመት ነው። የመካካለኛው ምሥራቅ ቀጠና በዓለም ላይ ያለውን 30 በመቶ ነዳጅ አቅራቢ ሲሆን 20 በመቶ የሚሆነው የዓለም አቀፉ ንግድ መተላለፊያ እንዲሁም 4 በመቶ የዓለም ሃገራት አጠቃላይ ምርት ድምርን የሚያበረክት ነው ብለዋል። • የሁቲ አማጺያን የፎከሩበትን የድል ቪዲዮ ለምን ማሳየት አልቻሉም? "እስቲ እነዚህ ሦስቱ ነገሮች ቀጥ ቢሉ ብላችሁ አስቡ፤ ዓለም አቀፉ ኢኮኖሚ ሙሉ በሙሉ ይወድቃል፤ የሚጎዱት ሳዑዲ አረቢያ ወይም የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ብቻ አይሆኑም" ብለዋል። ሳዑዲ አረቢያ እንደምትለው በ18 ሰው አልባ አውሮፕላኖችና በሰባት ሚሳይሎች አማካኝነት ከሁለት ሳምንታት በፊት በሁለት የነዳጅ ተቋማቷ ላይ ጥቃት እንደደረሰባት ነው። በኢራን የሚደገፈው የሁቲ አማፅያን ቡድን ከጥቃቱ ጀርባ መኖራቸውን ቢያሳውቁም ሳዑዲ አረቢያ ግን የዓለም 5 በመቶ ነዳጅ የሚያቀርበውን ስፍራ በማጥቃትና የዓለምን የነዳጅ ዋጋ በማዛባት ኢራንን በመወንጀል ፀንታለች። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው ለዚህ ምላሽ የሚሆን ብዙ አማራጭ እንዳላቸውና "የሚያስገድድ አማራጭ" ሊጠቀሙ እንደሚችሉም አስጠንቅቀዋል።
42191702
https://www.bbc.com/amharic/42191702
በኢትዮጵያ ስላሉ ስደተኞች አንዳንድ ነጥቦች
በኢትዮጵያ ውስጥ ከ847 ሺህ በላይ ስደተኞች አሉ። ይህ ቁጥርም ስደተኞችን በመቀበል ሃገሪቱን በአፍሪካ ሁለተኛ እንደሚያደርጋት የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽን መረጃ ያሳያል።
እነዚህ ስደተኞች አብዛኛውን ጊዜ ግጭትና አለመረጋጋት ካለባቸው እንደ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ኤርትራና ሱዳን ካሉ ሃገራት ቢመጡም በአጠቃላይ የ19 ሃገራት ዜግነት ያላቸው ስደተኞች ናቸው። ስደተኞቹ በአብዛኛው በትግራይ ክልል መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ያሉ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ በአፋር፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላና በሶማሌ ክልሎች ተጠልለው ይገኛሉ። ስደተኝነት እንዴት ተቀባይነት ያገኛል? ከተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽን የተገኘ መረጃ እንደሚያሳየው የኢትዮጵያ መንግሥት ከለላ ለሚፈልጉ ስደተኞች በሩ ክፍት እንደሆነ ነው። ይህንንም ለማድረግ ኢትዮጵያ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን ፈርማለች። ብዙዎቹ ስደተኞች ያለውጣ ውረድ ወዲያው የጥገኝነት ጥያቄያቸው ተቀባይነት ያገኛል። የእያንዳንዱም ስደተኞች ጉዳይ የሚወሰነው በኢትዮጵያ መንግሥት በተዋቀረ ኮሚቴ ሲሆን፤ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽንም በታዛቢነት ጉዳዩን ይከታተላል። ሃገሪቱ በስደተኝነት የተቀበለቻቸውንም ሆነ ጥገኝነት ጠያቂዎች መንግሥት በመደባቸው የመጠለያ ጣቢያዎች መቀመጥ የሚኖርባቸው ሲሆን፤ ቁጥራቸው ብዙ ባይሆንም በከተማ ውስጥ እንዲኖሩ ፍቃድ ያላቸውም አሉ። እነዚህም ከህክምና፣ ከደህንንት እንዲሁም ከሌሎች ችግሮች ጋር በተያያዘ ምክንያት መጠለያ ውስጥ መቆየት የማይችሉ ናቸው። በአዲስ አበባ ውስጥ 17345 ስደተኞች አሉ። ይህ የመንግሥት "ከመጠለያ ጣቢያ ውጭ" ከሚለው ፖሊሲ በተጨማሪ ኤርትራውያን ስደተኞች በአዲስ አበባም ይሁን በሌሎች ከተሞች ራሳቸውን ማስተዳደር ከቻሉ መኖር የሚችሉበት መንገድ ተመቻችቶላቸዋል። ህጻናት ስደተኞች በኢትዮጵያ ውስጥ ከ847 ሺህ በላይ ስደተኞች አሉ መንግሥት ከመጠለያ በተጨማሪ አትኩሮት የሚሰጥባቸው ጉዳዮች አሉ። እነዚህም ለህፃናት ስደተኞች ጥበቃ፣ ትምህርት፣ ወሲባዊም ሆኑ ፆታዊ ጥቃቶችን መከላከል ናቸው። በተለይም ከኤርትራ ከቤተሰብ እገዛ ውጭ ብቻቸውን የመጡ ህፃናት በሽረ አካባቢ ለመንግሥትም ሆነ ለተለያዩ መንግሥታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች አሳሳቢ እንደሆኑ እየተገለፀ ነው። የእርሻ መሬት መስጠት የ19 ሃገራት ዜግነት ያላቸው ስደተኞች በኢትዮጵያ ይገኛሉ የስደተኞች ቁጥር በየዓመቱ እየጨመረ ሲሆን በተለይም ከደቡብ ሱዳን ጦርነት ጋር ተያይዞ 200 ሺህ የሚገመቱ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል። በተለያዩ የመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ያሉ የስደተኞችን ህይወት ለማሻሻል የተለያዩ ፕሮጀክቶችም እየተቀረፁ ነው። ከእነዚህም መካከል ለወደፊት የተያዙት ዕቅዶች ከመጠለያ ውጭ ያሉ ቦታዎችን ማስፋፋትና ቢያንስ 10% ስደተኞች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ፤ ለስደተኞች የሥራ ፈቃድ መስጠት፤ የስደተኛ ልጆችን በተለያዩ የትምህርት ደረጃዎች እንዲሳተፉ ማድረግ፤ 10 ሺህ ሄክታር የሚታረስ መሬት 20ሺ ለሚሆኑ ስደተኞች መስጠትና የራሳቸውን እርሻ የሚያለሙበትን መንገድ መፈለግ እንዲሁም ከኢትዮጵያውያን ጋር በቀላሉ እንዲዋሃዱ የማስተሳሰር ፕሮግራም ይገኙባቸዋል።
news-54201253
https://www.bbc.com/amharic/news-54201253
ሩስያ፡ አሌክሴ የተመረዘባቸው ብልቃጦች ተገኙ
ቭላድሚር ፑቲን በነርቭ ኤጀንት መርዘውታል ተብሎ የሚጠረጠረው አሌክሴ ናቫልኒ እያገገመ ይገኛል፡፡
ወደ ሩሲያ ተመልሶ እንደሚሄድም ተወካዩ ተናግሯል፡፡ አሌክሴ የት ነው በትክክል የተመረዘው የሚለው ጉዳይ ሲያወዛግብ ነበር፡፡ እስከዛሬ ይታመን የነበረው አየር ማረፍያ ውስጥ ቡና ከጠጣ በኋላ ነው የታመመው ስለዚህ ቡናው ላይ መርዝ ተጨምሮበት ይሆናል የሚል ነበር፡፡ የሱ ደጋፊዎች ቡድን አሌክሴ የተመረዘባቸውን የፕላስቲክ ብልቃጦች አግኝቻለሁ ብሏል፡፡ አሁን የት እንደተመረዘ አውቀናል፤ አርፎበት የነበረው ሆቴል ውስጥ ነው ብለዋል የሱ ሰዎች በኢኒስታግራም ባሰራጩት መልዕክት፡፡ አሌክሴ ናቫልኒ በሩሲያ ውስጥ ፍርሃት ያልፈጠረበት የፑቲን ተቃዋሚ ሆኖ ነው የሚታየው፡፡ ሙስናዎችን በማጋለጥና የፑቲንን ገመና ለሕዝብ በመዘክዘክ ዝናን አትርፎ ቆይቷል፡፡ በጀርመን ዋና ከተማ በርሊን እውቅ ሆስፒታል ውስጥ ክትትል እየተደረገለት ያለው አሌክሴ አሁን ያለ ዘመናዊ መሣሪያ እርዳታ በራሱ መተንፈስ እንደጀመረ ተነግሯል፡፡ የክሬምሊን ቤት መንግሥት አሌክሴ ስለመመረዙ እኛ የምናውቀው ነገር የለም ብሏል፡፡ በመመረዙ ጉዳይም ምንም አይነት ምርመራ በሩሲያው ውስጥ አልተጀመረም፡፡ ሆኖም የአሌክሴ መመረዝ በበርሊንና በሞስኮ መሀል የዲፕሎማሲ ቅራኔ እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል፡፡ የአውሮፓ ፓርላማ ሐሙስ'ለት በአሌክሴ ጉዳይ ዓለም አቀፍ ምርመራ እንዲጀመር ሐሳብ አቅርቧል፡፡ አሁን በአሌክሴ የኢኒስታግራም አልበም የተለጠፈ ቪዲዮ እንደሚያሳየው በሰርቢያ ዋና ከተማ ቶክስክ እያለ ያረፈበት ሆቴል ውስጥ የፕላስቲክ የውሀ ብልቃጦች ተገኝተዋል፡፡ እነዚህ ብልቃጦች የተገኙት አሌክሴ መታመሙ ከተሰማ ከሰዓታት በኋላ የሱ ሰዎች የመርዙን መነሻ ለማወቅ ባደረጉት ጥረት ነው፡፡ አሌክሴ መመረዙ ሲታወቅ በምን እንደተመረዘ የሚገልጽ መረጃ ማግኘት ሕይወቱን ለማትረፍ ወሳኝ ስለነበረ የሱ ሰዎች ይህንኑ ፍለጋ የነበረባቸው ቦታዎችን ሁሉ በፍጥነት አዳርሰዋል፡፡ ይህንንም ተከትሎ አሌክሴ በነበረበት ሆቴል ውስጥ በርካታ የውሃ ብልቃጦች (እኛ በተለምዶ የሃይላንድ ላስቲክ የምንላቸው) ተደርድረው ተገኝተዋል፡፡ ቪዲዮው እነዚህ የውሃ ብልቃጦችን ጓንት የለበሱ ሰዎች ሲሰበስቧቸው ያሳያል፡፡ ኢኒስታግራም አልበሙ ላይ ይህንን ቪዲዮ ተከትሎ የተጻፈው ጽሑፍ እንደሚያትተው በዚህ ክፍል ውስጥ ሳለ በነዚህ ብልቃጦች ውስጥ ነበር መርዙ የተጨመረው፡፡ ሆኖም የሩሲያው ፕሮይክት ዜና አገልግሎት ገጽ ቭላድሚር ኡግሌቭ የተባለ የመርዝ ቀማሚ (ኖቪቾክ መርዝ ከሰሩት አንዱ) በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጥ አድርጎት ነበር፡፡ ሰውየው እንደሚለው በውሃ ላስቲኮች ውስጥ መርዙ ተቀምጦ ነበር የሚለው የሚያስኬድ አይደለም፡፡ ምክንያቱም መርዙ ውሃ ውስጥ ኖሮ ቢሆን አሌክሴ ዛሬ በሕይወት ሊኖር አይችልም፡፡ መትረፉ የሚያሳየው መርዙ ቆዳውን ብቻ በስሱ መንካቱን ነው፡፡የጀርመን ሐኪሞችም ሆኑ የጀርመን መንግሥት በዚህ ጉዳይ ላይ ገና አስተያየት አልሰጡም፡፡
45675456
https://www.bbc.com/amharic/45675456
የአሜሪካው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕጩ ብሬት ካቭና የፍርድ ቤት ውሎ
በአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ለሃገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኃለቃነት ከወራት በፊት የታጩት ዳኛ ብሬት ካቭና በወሲባዊ ጥቃት ተጠርጥረዋል።
ጉዳዩ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን አፍ ማሟሻ ከሆነ ቢሰነባብትም በስተመጨረሻ ወደ ሃገሪቱ ህግ መወሰኛ ምክር ቤት ደርሷል። ጥቃቱን አድርሰዋል የተተባሉት ዕጩ ብሬት እና ወሲባዊ ጥቃት ደርሶብኛል ያሉት ዶ/ር ክርስቲን ብላሲ ፎርድ በሴናቶሮች ፊት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል። ዳኛ ብሬት ካቭና ወሲባዊ ጥቃቱን አልፈፀምኩም ሲሉ ስሜታዊነት በተሞላበት መልኩ ክሱን አጣጥለዋል። •የሰሞኑ የአዲስ አበባ እስርና ሕጋዊ ጥያቄዎች ከሳሽ ዶ/ር ክርስቲን ፎርድ በበኩላቸው ሰውየው ከ30 ዓመታት በፊት ያደረሱባቸው ወሲባዊ ጥቃት ሕይወታቸውን ክፉኛ እንዳመሳቀለው አስረድተዋል። • የጎንደር ሙስሊሞች እና የመስቀል በዓል ፕሬዝደንት ትራምፕ ብሬት 'ሃቀኛ' ናቸው ሲሉ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት በዕጩነት ያቀረቧቸውን ሰው ደግፈው ታይተዋል። ፕሬዝደንት ትራምፕ የዴሞክራቲክ ፓርቲ ሴናተሮች 'አጥፊ' የሆነ ዕቅድ የኮነኑ ሲሆን የተከሳሽን መልካም ስም እያጎደፉ ነው ሲሉም ወቀሳ ሰንዝረዋል። የሴናተሮች ሕግ ተርጓሚ ኮሚቴ በብሬት ካቭና ዕጩነት ዙሪያ ድምፅ ለመስጠት ለዛሬ ቀጠሮ ይዟል፤ ምንም እንኳ ሪፐብሊካኑ ሙሉ በሙሉ ለሰውየው ድምፃቸውን መስጠታቸው ቢያጠራጥርም። ጠቅላላ ሴናተሮች በሚቀጥለው ሳምንት አጋማሽ ተሰባስበው በሰውየው ዕጣ ፈንታ ላይ ውሳኔ እንደሚያስተላልፉ ይጠበቃል። የ51 ዓመቷ ዶ/ር ክርስቲን ፎርድ እንባ እየተናነቃቸው ነበር ቃላቸውን ለምክር ቤቱ አባላት ያሰሙት። • በጋምቤላ የሟቾች ቁጥር ዘጠኝ ደርሷል ተባለ «እዚህ የተገኘሁት ወድጄ አይደለም» ሲሉ የተደመጡት ዶ/ር ክርስቲን «ፍራቻ ውስጥ ነኝ፤ እዚህ የተገኘሁት የዜግነት ግዴታዬን ለመወጣት ነው፤ ብሬት እና እኔ ትምህርት ቤት እያለን የገጠመኝን ለሁሉም ለማሳወቅ ነው» ሰሉ አክለዋል። ከሳሽ የ15 ዓመት ታዳጊ ሳሉ የ17 ዓመቱ ብሬት እና ጓደኛው መኝታ ቤት ውስጥ ቆልፈውባት ልብሷን በማወላለቅ ሊደፍሯት እንደሞከሩ እና እንደተሳለቁባት ቃላቸው ሰጥተዋል። ጉዳዩ ከበርካታ ዓመታት በፊት ስለሆነ ምናልባት ተሳስተው ከሆነ ተብለው ሲጠየቁ መቶ በመቶ እርግጠኛ ሲሉ ተናግረዋል። ተከሳሽ በበኩላቸው «እኔ ዶ/ር ክርስቲንንም ይሁን ሌላ ሰው ላይ ወሲባዊ ጥቃት አላደርስኩም» ሲሉ ክሱን ክደዋል። ከሳሽ ባስቀመጡት ቦታ ላይ አለመገኘታቸውን ነው ለሴናተሮቹ ያሳወቁት። • ቢል ኮዝቢ ወደ ዘብጥያ ወረዱ
news-44831308
https://www.bbc.com/amharic/news-44831308
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አዲስ አበባ ገቡ
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከሃያ ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰዋል።
ፕሬዝዳንቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ቦሌ ተገኝተው አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን፤ ከፍተኛ የፌደራል መንግሥት ባለሥልጣናት እንዲሁም የተለያዩ ክልል መሪዎችና ባለስልጣናት ተገኝተዋል። ይህ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጉብኝት በሁለቱ ሃገራት መካከል የተደረገው ደም አፋሳሽ ጦርነት ከተካሄደ በኋላ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ባለፈው ሳምንት በአሥመራ ጉብኝት ካደረጉ በኋላ በምላሹ የሚካሄድ ነው። የፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጉብኝት ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ በኤርትራ መሪ ወደ ኢትዮጵያ የተደረገ የመጀመሪያው ጉዞ ነው። ፕሬዝዳንቱ በዚህ ጉብኝታቸው ለሦስት ቀናት ያህል ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚቆዩም የጉብኝታቸው ዝርዝር መረሃ-ግብር ያመለክታል። • ስለ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ምን ያህል ያውቃሉ? • የኤርትራ ኤምባሲ የማደስ ሥራ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ ተገለፀ • የኢትዮጵያና ኤርትራን የአብሮነት እርምጃ ምን ይፈትነዋል? በዚህ ጉብኝት ለሃያ ዓመታት ተዘግቶ በኋላም ለወጣቶች ፌዴሬሽን ተሰጠጥቶ የነበረው የኤርትራ ኤምባሲ ፕሬዝዳንቱ እንደሚከፍቱት ይጠበቃል። ይህም በሁለቱ ሃገራት መካከል ተቋርጦ የነበረው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መታደሱን በይፋ ለማመልከት እንደሆነም ተገልጿል።ቦሌ
news-55478319
https://www.bbc.com/amharic/news-55478319
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፡ በመተከል ዞን በተፈፀመው ግድያ ተጠረጥረው የተያዙ የክልሉ ባለሥልጣናት ቁጥር ዘጠኝ ደረሰ
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ባለፈው ሳምንት በተፈፀመው ግድያ ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የዋሉ የክልልና የዞን አመራሮች ቁጥር ዘጠኝ ደረሰ።
እነዚህ የመንግሥት ባለሥልጣናት ታኅሣስ 13/2013 ዓ.ም በኩጂ ቀበሌ በደረሰው ጥቃት ወቅት የተሰጣቸውን የመንግሥት ኃላፊነት በአግባቡ ባለመወጣት እንዲሁም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳታፊ ናቸው በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የክልሉ ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ መለሰ በየነ ለቢቢሲ ገልፀዋል። ዛሬ [ማክሰኞ] ጠዋት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት በመተከል ዞን ከተፈጸመው የበርካታ ሰዎች ግድያ ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት የተባሉ አራት የምክር ቤቱ አባላትን ያለመከሰስ መብት ማንሳቱ ይታወቃል። የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ መለሰ በየነ ለቢቢሲ በተጨማሪም አንድ የፀረ ሽምቅ አባል በኩጂ ቀበሌ በተፈፀመው ግድያ ላይ እጁ አለበት በሚል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ተናግረዋል። አክለውም የመተከል ዞን አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ አትንኩት ዛሬ ረፋድ 3፡00 ላይ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ገልፀዋል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለወራት የዘለቀ ተከታታይ ጥቃት በነዋሪዎች ላይ ሲፈጸምበት በቆየው የመተከል ዞን ውስጥ በሚገኘው ቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ ታኅሣስ 13/2013 ዓ. ም ንጋት ላይ በታጣቂዎች በተጸፈመ ጥቃት ከ200 በላይ ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል። አቶ መለስ አክለውም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የተቋቋመው ግብረ ኃይል የመተከል ዞንን የፀጥታ ማስከበር ሥራን መረከቡን ተናግረዋል። ይህ ግብረ ኃይል ከፍተኛ የመንግሥት ባለሰልጣናትን፣ የመከላከያ ሠራዊት አመራሮችን ያቀፈ ሲሆን በመተከል ዞን የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ኃላፊነት እንደተሰጠው ተነግሯል። አቶ መለስ፣ በአሁኑ ሰዓት ችግሩን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት ግብረ ኃይሉ በዞኑ በንፁሃን ላይ ጥቃት በመፈጸም፣ ህይወት በማጥፋት ወንጀል የተሳተፉ ተጠርጣሪዎችን በማደን ላይ መሆኑ በመግለጽ፣ በወንጀሉ የተሳተፉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር አውሎ በሕግ ተጠያቂ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። በዞኑ በተደጋጋሚ የሚከሰቱ ጥቃቶችን ለመከላከል በተወሰደ እርምጃም ከ300 በላይ ታጣቂዎች መገደላቸውን፣ በውጊያውም ሂደት ከ200 በላይ የጦር መሳሪያዎች መማረካቸውን ኃላፊው ጨምረው ገልፀዋል። በተጨማሪም በተፈጸመው ጥቃት ውስጥ ተሳታፊ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ ከ60 በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አብራርተዋል። በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ ታኅሣስ 13/2013 ዓ.ም ንጋት ላይ በታጣቂዎች በተጸፈመ ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 207 መድረሱን የአካባቢው ባለስልጣናትና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቀው ነበር። በጥቃቱ ከተገደሉት 207 ሰዎች መካከል የ171ዱ ሥርዓተ ቀብር በጅምላ ታኅሣስ 15/2013 ዓ.ም ተፈጽሟል። ኮሚሽኑ የተፈፀመውን የጅምላ ግድያ ተከትሎ ባወጣው መግለጫ ላይ ከሟቾቹ መካከል አዋቂዎቹ 133 ወንዶችና 35 ሴቶች ሲሆኑ፤ አንድ የስድስት ወር ሕጻንን ጨምሮ 17 ሕጻናት፣ የቀሩት 20 ሰዎች ደግሞ አዛውንቶች ናቸው ብሎ ነበር። በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ካለፈው ዓመት ጳጉሜ ወር አንስቶ በንፁሃን ዜጎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት ሲፈፀም ነበር። በዚህም የተነሳ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቀያቸውን ጥለው ሲሰደዱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ሕይወታቸውን አጥተዋል።
news-56569256
https://www.bbc.com/amharic/news-56569256
በአሜሪካ የኒውክሌር ተቋም ትዊተር ላይ መልዕክት ያሰፈረው ታዳጊ ብዙዎችን አስደነገጠ
አንድ ታዳጊ የአሜሪካንን የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎች በሚቆጣጠረው ተቋም የትዊተር ገጽ ላይ ለመረዳት ግልጽ ያልሆነ መልዕክት በማስፈሩ ምክንያት ግራ መጋባትና ፍርሃት ተፈጥሮ እንደነበረ ተገለጸ።
ነገሩ የተከሰተው ከጥቂት ቀናት በፊት ሲሆን ታዳጊው ምስጢራዊ የሚመስሉ ምንም ትርጉም የማይሰጡ የእንግሊዝኛ ፊደላትና ሥርዓተ ነጥቦችን ያሉበትን መልዕክት ሳያስበው በትልቁ ተቋም የትዊተር ሰሌዳ ላይ በማስፈሩ ነበር ብዙዎች ስጋት የገባቸው። ይህን መልዕክት በርካቶች ከተመለከቱት በኋላ የተፈጠረው ስሜት የአገሪቱ ኒውክሌር ጦር መሣሪያዎችን የሚቆጣጠረው ወሳኝ ተቋም የመረጃ መረብ በኢንተርኔት ሰርሳሪዎች ቁጥጥር ስር ገብቶ ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት ነበር። ተቋሙ የአሜሪካ ኒውክሌር ጦር መሳሪያዎች ጥበቃ የሚደረግላቸው ወሳኝ የጦር መሳሪያ የዕዝ ማዕከል ሲሆን የመረጃ መረቡ ደኅንነት አደጋ ላይ ከወደቀ ብሔራዊ ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፋዊ ቀውስ ሊከስት ይችላል ተብሎ ይሰጋል። የድርጅቱ አንደኛው መድረክ የማኅበራዊ መገናኛ የሆነው የትዊተር ገጹ ላይ ያልተጠበቀ ነገር ወጥቶ ሲገኝ እንግዳ የሆነውን መልዕክት የተመለከቱ ሰዎች፣ በተቋሙ ላይ አንዳች የመረጃ መረብ ጥቃት ሳይደርስ እንዳልቀረ በመገመት ስጋታቸውን ሲገልጹ ነበር። ነገር ግን ክስተቱ እንደተሰጋው ሳይሆን የተቋሙን የሶሻል ሚዲያ ገጾች ከሚቆጣጠሩ ሠራተኞች መካከል የአንዱ ልጅ መነጋገሪያ የሆነውን መልዕክት ሳያስበው በድንገት እንዳሰፈረው በኋላ ላይ ታውቋል። በትዊተር ገጹ ላይ የወጣው ጽሁፍም ";l;;gmlxzssaw" የሚል ነበር። ትርጉም የሌላቸውን እነዚህ ፊደላትና ነጥቦች ምናልባት ምስጢራዊ ናቸው ብለው በርካቶች ቢጠረጥሩም ታዳጊው ሳያስበው ጣቶቹ የተጫናቸው ፊደላትና ምልክቶች ነበሩ። መልዕክቱ በርካቶች ጋር ደርሶ ግራ መጋባትን ከፈጠረ እና መነጋገሪያ ከሆነ ከደቂቃዎች በኋላ ከተቋሙ ገጽ ላይ እንዲሰረዝ ተደርጓል። የዜና ማሰራጫ ድረ ገጽ የሆነው "ዘ ዴይሊ ዶት" ተቋሙን ስለተፈጠረው ነገር ጠይቆ ክስተቱን ዘግቦታል። ከቤቱ ሆኖ ሥራውን እያከናወነ የነበረው የተቋሙ የትዊተር ገጽ ተቆጣጣሪ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ክፍት አድርጎት የተፈጠረ ስህተት መሆኑን በመግለጽ ድርጅቱ ስለክስተቱ ምላሽ ሰጥቷል። "የሠራተኛችን ታዳጊ ልጅ የመጻፊያ ቁልፎቹን እየተጫነች በምትጫወትበት ጊዜ ሳታስበው በድርጅታችን የትዊተር ገጽ ላይ መልዕክቱ ሊወጣ ችሏል" ሲል ተቋሙ ማብራሪያ ሰጥቷል። የተቋሙ ቃል አቀባይም አንዳንድ ሰዎች የድርጅቱ የመረጃ መረብ በጠላፊዎች ቁጥጥር ስር ገብቷል በማለት ስጋታቸውን የገለጹት ሐሰት መሆኑንና እንዲህ አይነት ችግር እንዳልገጠማቸው አስተባብሏል። የድርጅቱ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ በመረጃ መዝባሪዎች አለመጠለፉ ከታወቀ በኋላ በርካቶች እንዲህ ያለ ትልቅ ተቋም የማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ በህጻናት እጅ ሊገባ የሚችልበት ዕድል እንዳለ ማወቃቸው አሳሳቢ መሆኑን አስተያየት ሰጥተዋል።
news-55472949
https://www.bbc.com/amharic/news-55472949
ትግራይ ፡ "አገሬ ኢትዮጵያ ችግር ውስጥ ናት፤ ተጨንቄያለሁ" ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም
ኢትዮጵያዊው የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁኔታ እንደሚያሳስባቸው ተናገሩ።
ዳይሬክተሩ ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት የቀሩትን የፈረንጆች 2020 በተመለከተ ባደረጉት ንግግር ላይ "ኮቪድ አልበቃ ብሎ እኔ ደግሞ የግል ህመም አለብኝ። ስለ አገሬ እጨነቃለሁ" ብለዋል። "ከኮቪድ-19 በተጨማሪ 2020 ከባድ የሆነብኝ አገሬ ችግር ውስጥ ስለሆነች ነው" ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር ቴድሮስ፤ በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል። ዶ/ር ቴድሮስ ባደረጉት ንግግር፤ "አገሬ ኢትዮጵያ ችግር ውስጥ ናት። በእናት አገሬ ኢትዮጵያ፣ በትውልድ ቀዬዬ ትግራይ እየተካሄደ ያለው አስከፊ ጦርነት ያስጨንቀኛል" ሲሉ ተደምጠዋል። አያይዘውም ታናሽ ወንድማቸውን ጨምሮ ሌሎች የቤተሰብ አባሎች የት እንዳሉ እንደማያውቁ ዶ/ር ቴድሮስ ገልጸዋል። "የግንኙነት መስመሮች ስለተቋረጡ ታናሽ ወንድሜንና ዘመዶቼን አላገኘኋቸውም። ወንድሜና ዘመዶቼ የማኅበረሰቡ አካል ናቸው። ስለ ታናሽ ወንድሜና ስለ ዘመዶቼ ብቻ ልጨነቅ አልችልም። የምጨነቀው ስለመላው አገሪቱ ነው" ብለዋል። በአጠቃላይ በመጠናቀቅ ላይ ያለው የፈረንረጆቹ 2020 ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ ለሁሉም ሰው አስከፊና አሳዛኝ ዓመት እንደሆነ ጠቅሰው፤ እሳቸው ደግሞ የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ተጨምሮ ዓመቱን ከባድ እንዳደረገባቸው አክለዋል። ዶክተር ቴድሮስ በዓመቱ ውስጥ የድርጅታቸው ዋነኛ ተግባር ስለነበረው የኮረናቫይረስ ወረርሽኝን በተመለከተ ስላጋጠሙ ችግሮች፣ ቫይረሱን በተመለከተ ስለተደረጉ ጥረቶችና አሁን ስለተተደረሰባት ውጤት ማብራሪያ ሰጥተዋል። የቀድሞው የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩት ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በትግራይ ክልል በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊትና በህወሓት ኃይሎች መካከል ግጭት በሚካሄድበት ጊዜ ህወሓትን ለመደገፍ ጥረት አድርገዋል በሚል በከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ክስ ቀርቦባቸው ነበር። የአገሪቱ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታው አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በወቅቱ እንዳመለከቱት ዶክተር ቴድሮስ ከመንግሥት ኃይሎች ጋር ወታደራዊ ግጭት ውስጥ ገብቶ የነበረውን ህወሓት በመደገፍ "አንዳንድ በሮችን ማንኳኳታቸውን" በመግለጽ ከሰዋቸው ነበር። ዶ/ር ቴድሮስ ለቀረበባቸው ለዚህ ክስ በወቅቱ በትዊተር ገጻቸው ላይ በሰጡት ምላሽ ኢትዮጵያ ውስጥ እየሆነ ያለው ነገር ልባቸውን እንደተሰበረ አመልከተው "በዚህ ውስጥ አንድ ወገንን እንደደገፍኩ የሚገልጹ ዘገባዎች ሲወጡ ቆይተዋል። ነገር ግን ይህ እውነት አይደለም" ብለዋል። ጨምረውም "እኔ የምደግፈው አንድ ወገን ቢኖር ሠላም የሚመጣበትን መንገድ ብቻ ነው" ሲሉ ለሠላም ያላቸውን ድጋፍ ገልጸው ነበር።
news-46374271
https://www.bbc.com/amharic/news-46374271
የ'ሰከረው' ህንዳዊ ሐኪም በቀዶ ጥገና ሲያዋልድ እናትና ልጅ ህይዎታቸው እንዲያልፍ ምክንያት ሆነ
ጉጃራት በምትሰኝ የህንድ ግዛት ውስጥ ሰክሮ አንዲት እናትን በቀዶ ሕክምና ለማዋለድ የሞከረ ሐኪም በቁጥጥር ሥር መዋሉን የአካባቢው ፖሊስ ለቢቢሲ አስታወቀ።
እናትና አዲስ የተወለደው ጨቅላ ቀዶ ጥገናው ከተከናወነ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ህይወታቸው አልፏል። ቀዶ ጥገናው እንደተካሄደ አዲስ የተወለደው ጨቅላ ወዲያው ሲሞት እናቲቱም ከሰዓታት በኋላ ህይወቷ አልፏል። ፖሊስ እንደሚለው ከሆነ ሐኪሙ ላይ የተከናወነው የትንፋሸ ምረመራ ቀዶ ጥገናውን ሲያከናውን ሰክሮ እንደነበረ ተረጋግጧል። • ኦዴፓ እና ኦዴግ ተዋሃዱ • የጋና ቅንጡ የሬሳ ሳጥኖች ፖሊስ ጨምሮ እንደተናገረው የወላዷና የጨቅላው ሞት ምክንያት በሐኪሙ ቸልተኝነት ወይም በሌላ ሕክምናዊ ጉዳዮች ስለመሆኑ እያጣራሁ ነው ብሏል። በቁጥጥር ሥር የዋለው ዶክተር ላክሃኒ፤ ልምድ ያለው ሐኪም ስለመሆኑና በዚያው ሆስፒታል ከ15 ዓመታት በላይ እንዳገለገለ ተገልጿል። ካሚኒ ቻቺ የተባለችው እናት የምጥ ስሜት ከተሰማት በኋላ ነበር ስኞ ምሽት ወደ ሆስፒታሉ ያቀናችው። የእናቲቱን በሰላም የመገላገል ዜና ለመስማት በጉጉት ሲጠባበቁ ለነበሩት የቤተሰብ አባላት፤ ልጁ እንደተወለደ መሞቱንና እናቲቱም ከፍተኛ የሆነ የደም መፍሰስ እንዳጋጠማት ተነግሯቸው እንደነበር የአካባቢው መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። • ''የአንድ ቤተሰብ አባላት ግድያ'' በቤኒሻንጉል ክልሏ ያሶ ከተማ • "ነጭ የለበሰ 'መልአክ' በኦሮምኛ አናገረኝ"- የሬሳ ሳጥን ፈንቅለው የወጡት ግለሰብ የቤተሰብ አባላቱም እናቲቱን ወደ ሌላ ሆስፒታል ይዘው ሲያመሩ ሕይወቷ መንገድ ላይ አልፏል። አንድ የፖሊስ አባል ለቢቢሲ እንደተናገሩት ሐኪሙ ለፖሊስ ደውሎ የሟች ቤተሰቦች የወላዷን ሞት ከሰሙ ሊያጠቁት እንደሚችሉ ስጋቱን በመግለጽ የፖሊስን እርዳታ ጠይቋል። ''ጥሪውን ተከታትለን በቦታው ስንደርስ ሰክሮ አገኘነው፤ ከዚያም በቁጥጥር ሥር አዋልነው'' ሲሉ የፖሊስ አባሉ አስረድተዋል። ሆስፒታሉም የእናቲቱንና የጨቅላውን ሞት ምክንያት የሚያጣራ ኮሚቴ ማቋቋሙን አስታውቋል።
51905319
https://www.bbc.com/amharic/51905319
በኬንያ ስለኮሮናቫይረስ ሃሰተኛ መረጃ ያሰራጨው ግለሰብ ታሰረ
የኬንያ ፖሊስ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ በትዊተር ሃሰተኛ መረጃ አሰራጭቷል ያለውን የ23 ዓመት ወጣት በቁጥጥር ስር አዋለ።
ወጣቱ ኤላሻ ሙቱይ ኪቶኒዮ በምስራቅ ኬንያ ምዌንጊ ከተማ በቁጥጥር ስር የዋለው በአገሪቱ የተመዘገበውን የመጀመሪያ የኮሮናቫይረስ ኬዝ በተመለከተ መንግሥት የተዛባ መረጃ ሰጥቷል ሲል ባሰራጨው መረጃ እንደሆነ ተገልጿል። ሃሰተኛ ነው በተባለው የትዊተር አድራሻ የተላለፈው ሃሰተኛ መረጃ ቅዳሜና እሁድ በስፋት ሲዘዋወር የነበረ ሲሆን የመጀመሪያዋ የኮሮናቫይረስ ተያዥ መንግሥት እንዳለው በለንደን በኩል ከአሜሪካ ሳይሆን ከጣልያን ሮም የመጣች ነች የሚል ነበር። የግለሰቡን መታሰር የኬንያ የወንጀል ምርመራ በትዊተር ገፁ አረጋግጧል። ወጣቱ ህብረተሰቡን ድንጋጤ ውስጥ ሊከት የሚችል ሃሰተኛ መረጃ በማተም ክስ እንደሚመሰረትበት የተገለፀ ሲሆን ጥፋተኛ ከተባለ በ50 ሺህ ዶላር ወይም እስከ አስር ዓመት በሚደርስ እስራት ሊቀጣ ይችላል። ትናንት እሁድ ፕሬዘዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ኬንያዊያን ስለ ኮሮናቫይረስ ሃሰተኛ መረጃዎችን ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ አስጠንቅቀዋል። • አንድ የኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪ ኬንያ ውስጥ ተገኘ • አፍሪካ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል አቅሙ አላት? • የዓለም ጤና ድረጅት ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሊሆን እንደሚችል አስታወቀ
news-52437010
https://www.bbc.com/amharic/news-52437010
በኢትዮጵያ ከባድ ዝናብ ለስድስት ሰዎች ሞት ምክንያት ሆነ
ባለፈው ሳምንት ማብቂያ በነበሩ ቀናት በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በደረሰው የጎርፍ አደጋ የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ።
አርብ ዕለት በምሥራቅ ኢትዮጵያ በምትገኘው የድሬዳዋ ከተማ ላይ የጣለው ከባድ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ ለአራት ሰዎች ሞት ምክንያት ሲሆን ሌሎች ሁለት ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳትን አስከትሏል። ከዚህ በተጨማሪም በጎርፉ ምክንያት ከ30 በላይ ቤቶች የመፍረስ አደጋ የገጠማቸው ሲሆን በሌሎች ንብረቶች ላይም መጠኑ ያልተገጸ ውድመት አጋጥሟል። በተመሳሳይ በደቡብ ክልል ውስጥ በጋሞ ዞን ገረሴ እና ጋጮ ባባ ወረዳዎቾ ለቀናት በተከታታይ የጣለ ዝናብን ተከትሎ ባጋጠመ የመሬት መንሸራተት የሁለት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ሌሎች በሁለት ሰዎች ላይ ደግሞ ጉዳት መድረሱን የዞኑ መስተዳደር ገልጿል። በተጨማሪም በዚህ አደጋ 33 የቤት እንሳት የሞቱ ሲሆን 10 ቆርቆሮና 42 የሳር ቤቶች ከነሙሉ ንብረታቸው በመውደማቸው 2757 ሰዎች የመፈናቀል ችግር ላይ ወድቀዋል። እዚያው ደቡብ ክልል ውስጥ በጂንካ ከተማ የጣለ ከባድ ዝናብ ደግሞ በከተማዋ የሚገኝ ወንዝን እንዲሞላ በማድረግ በአካባቢው መሰረተ ልማቶችና ንብረት ላይ ውድመትን አድርሷል። በደቡብ ኦሞ ዞን ባለስልጣንት እንዳስታወቁት ከተማውን ከሌሎች አካባቢዎች ጋር የሚያገናኙ ሁለት ድልድዮች በጎርፍ ተወስደዋል። በተጨማሪም መኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ በጎርፍ አደጋው በሰብልና በቤት እንስሳት ላይ ጉዳት ደርሷል። የአየር ትንበያ ባለሙያዎች ቀደም ብለው እንዳስጠነቀቁት በኢትዮጵያና በአካባቢው አገራት ውስጥ ጉዳትን ሊያስከትል የሚችል ከባድ ዝናብ እንደሚጥል ገልጸዋል። ዝናቡ በተከታታይ ሳምንታት ውስጥ የሚቀጥል በመሆኑ ነዋሪዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉም መክረዋል።
news-48987776
https://www.bbc.com/amharic/news-48987776
አል ሻባብ የጎሳ መሪዎችን አስጠነቀቀ
የሶማሊያው ታጣቂ እስላማዊ ቡድን አል ሻባብ ለፓርላማ አባል የሚሆኑ እጩዎችን አቅርበዋል ያላቸውን የጎሳ መሪዎች "ከሃዲዎች" በሚል መግለጫ አወጣ።
"ለከሃዲው የሶማሊያ ምክር ቤት አባልነት እጩዎችን የሰየሙ የጎሳ መሪ የተባሉት ግለሰቦች ኢአማኒ መሆናቸውን በግልጽ በማስመስከር የእስልምና እምነታቸውን ዋጋ አሳጥተውታል" ሲል አፍቃሪ አልሻባብ በሆነው ድረ ገጽ ላይ ቡድኑ ያወጣው መግለጫ ያመለክታል። ከአል ቃኢዳ ጋር ትስስር እንዳለው የሚነገርለት አል ሻባብ ቀደም ሲል ሲቆጣጠራቸው ከነበሩ አብዛኞቹ ዋነኛ የሶማሊያ ከተሞች ተገፍቶ የወጣ ቢሆንም አሁንም ከፍተኛ የደህንነት ስጋት ነው። • የጋዜጠኛዋ መገደል ለምን የዓለም መነጋገሪያ ሆነ? • በሶማሊያ በአንድ ሆቴል ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 26 ሰዎች ሞቱ • የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይቅርታ ጠየቀ አል ሻባብ በመግለጫው የጎሳ መሪዎቹ ፈጸሙት ላለው ሐጢያት በ45 ቀናት ውስጥ 'ንስሐ' እንዲገቡ ካልሆነ ግን የጂሃዳዊ ቡድኑ ኢላማ በመሆን እንደሚገደሉ አሳውቋል። አልሻባብ ጨምሮም የጎሳ ሽማግሌዎች ክልላዊ አስተዳደርን በመመስረቱ ሂደት ውስጥ እንዳይሳተፉም አስጠንቅቋል። ይህ ማስጠንቀቂያ በእስላማዊ ቡድኑ የወጣው ጁባላንድና ጋልሙዱግ በተባሉት የሶማሊያ ግዛቶች ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ሊካሄድ በታሰበበት ጊዜ ነው። ቀደም ሲል በተካሄዱ የሶማሊያ ክልላዊ ምርጫዎች ላይ የቀረቡ በርካታ ዕጩዎች በአል ሻባብ መገደላቸው ይታወሳል። ታጣቂው እስላማዊ ቡድን በተባበሩት መንግሥታት የሚደገፈውን የሶማሊያ ማዕከላዊ መንግሥትን ለመጣል እየተፋለመ ሲሆን፤ በተለያዩ ቦታዎች ተከታታይ ጥቃቶችን ሲፈጽም ቆይቷል።
news-44776328
https://www.bbc.com/amharic/news-44776328
ትዊተር 70 ሚሊዮን ሃሰተኛ ገጾችን ዘጋ
ትዊተር ማንነታቸው የማይታወቁ፤ አጠራጣሪ መረጃዎችን ከተለያዩ ቦታዎች የሚያሰራጩና ትዊተርን ያለአግባብ የሚጠቀሙ ናቸው ያላቸውን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የትዊተር ገጾችን ዘጋ።
ትዊተር ከባለፈው ግንቦት ወዲህ ብቻ በውሸት የተከፈቱና አጠራጣሪ ናቸው ያላቸውን 70 ሚሊዮን የሚሆኑ ገጾችን መዝጋቱን ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ አስታውቋል። ይህ ገጾቹን የመዝጋትና የማገድ እንቅስቃሴ ድርጅቱ ለተጠቃሚዎች ምቹ ሁነታዎችን ለመፍጠርና ተአማኒነቱን ለመጨመር እንደሆነ ተገልጿል። አብዛኛዎቹ ገጾች ማንነታቸው የማይታወቁ፤ አጠራጣሪ መረጃዎችን ከተለያዩ ቦታዎች የሚያሰራጩና ትዊተርን ያለአግባብ የሚጠቀሙ ናቸው። ትዊተር በበኩሉ ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ያወጣው ዘገባ ላይ ለመጨመር ባይፈልግም ትልቅ የማሻሻያ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ግን ገልጿል። የትዊተር የደህንነትና ተያያዥ ጉዳዮች ሃላፊ የሆኑት ዴል ሃርቪ ለጋዜጣው ሲናገሩ ድርጅቱ የተጠቃሚዎቹን ደህንነት ከመጠበቅ ይልቅ ሁሉም ሰው በነጻነት የመሰለውን እንዲናገር ሲያደርግ እንደነበር ገልጸዋል። አሁን በትልቁ ለመቀየር እተንቀሳቀስን ያለነው ነገር ሰዎች በነጻነት ሃሳባቸውን ሲገልጹ እንዴት የማንንም ስሜት በማይጎዳና አላስፈላጊ የሆኑ መልእክቶችን እንዳያስተላለፉ ማድረግ ላይ ነው በማለት አክለዋል። በሌላ በኩል የድርጅቱ ቃል አቀባይ የሆኑ ሰው ደግሞ ዋሽንግተን ፖስት ይዞት የወጣው መረጃ አዲስ ነገር እንዳልሆነና አጠራጣሪ ገጾችን የመዝጋቱ ሂደት ትዊተር ለተጠቃሚዎቹ ምቹና ጤናማ የግንኙነት መስመር ለመፍጠር እያደረገው ያለው ስራ አካል መሆኑን ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪ ትዊተር 130 ሚሊዮን ደረጃቸውን ያልጠበቁና አጠራጣሪ መልእክቶችን ወደ ትዊተር ያስተላለፉ 142 ሺ የሚሆኑ መተግበሪያዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን ቃል አቀባዩ ጨምረዋል። ትዊተር በአለማቀፍ ገበያ ያለው ድርሻ 8.5 በመቶ መቀነሱ ዋሽንግተን ፖስት ይህንን ዘገባ ይዞት ከወጣ በኋላ መሆኑ እየተዘገበ ነው። ምክንያቱም ይህን ያክል ቁጥር ያለው ተጠቃሚ (70 ሚሊዮን) የውሸት ከሆነ የማስታወቂያ ገቢው ላይ ከፍተኛ መቀነስ ሊያሳይ እንደሚችል ተገምቶ ነው።
43709286
https://www.bbc.com/amharic/43709286
የአሜሪካዋ ሴናተር በስልጣን ላይ ሆነው ልጅ በመውለድ የመጀመሪያዋ ሆኑ
የአሜሪካዋ ሴናተር ታሚ ደክወርዝ በስልጣን ላይ ሆነው ሴት ልጅ በመውለድ የመጀመሪያዋ ሴናተር ሆነዋል።
የዲሞክራት ፓርቲ አባል ሜይል ፐርል ቦውልስቤይ በትዊተር ገፁ እንዳሰፈረው ጨቅላዋም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ነርስ ሆና ባገለገለችው የታላቅ አክስቷ ስም እንደተሰየመች ነው። ሴናተሯም በትዊተር ገፃቸው ቤተሰባቸውን እንዲሁም የህክምና ቡድኑን አመስግነዋል። ሜይል የተባለችው ሁለተኛዋ ሴት ልጃቸው በዋሽንግተን ዲሲ ሆስፒታል ሰኞ ተወልዳለች። ደክወርዝ የቀድሞ አየር ኃይል ፓይለት ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በአውሮፓውያኑም 2004 ኢራቅ ውስጥ በደረሰ ግጭት ሁለት እግሯቻቸው ተቆርጠዋል። ሴት የአካል ጉዳተኛ ሆነው ሴናተርም በመሆንም ከዚህ ቀደም ታሪክ ሰርተዋል። ከዚህ ቀደም በፌዴራል ቢሮ ተመርጠው የልጅ እናት ከሆኑት መካከል ደክወርዝን 10ኛዋ ሴት እንደሚያደርጋቸው የአሜሪካ ሚዲያ ዘግቧል። "ወላጅነት የሴቶች ጉዳይ ብቻ አይደለም። ሴት ሆነ ወንድ ወላጆችን የሚያሳትፍ ኢኮኖሚያዊ ጉዳይ ነው" በማለት በመግለጫቸው አብራርተዋል። "እናትነትና ሴናተርነት የሚያስፈልገውን የስራ ጫና እሸከማለሁ። እንደሚሰራ እናት የኔ ጉዳይ የመጀመሪያ አይደለም፤ የተለየሁ አይደለሁም። ልጆቼም ስራየን ጠንክሬ እንድሰራና በዓለም ላይ ላሉ ጠንክረው ለሚሰሩ ቤተሰቦችም እንድቆም ያደርጉኛል" ብለዋል። በባለፈው ወር የሁለቱም ፓርቲ ሴናተሮች ልጃቸውን ለመቀበል ዝግጅት አድርገው እንደነበር የቺካጎው ሰን ታይምስ ጋዜጣ ዘግቧል። በጥር ወር ላይ ደክወርዝ ለሚዲያ እንደተናገሩት የሁለተኛ ልጃቸው እርግዝና ፈታኝ እንደነበረም ተናግረዋል። ከታይላንዳዊ እናት የተወለዱት ደክወርዝ በኮንግረስም ለመመረጥ የመጀመሪያዋ እስያዊ ዝርያ ያላቸው አሜሪካዊ ናቸው። በዚህ ዓመት ደክወርዝ አዳዲስ እናቶችን የሚጠቅም አዳዲስ ህጎችን ረቂቅ ያቀረቡ ሲሆን ከነዚህም አየር ማረፊያዎች ለሴቶች ጡት ማጥቢያ እንዲሁም ማለቢያ ቦታዎችን ማመቻቸት የሚለው ይገኝበታል። ከዚህም በተጨማሪ በወታደርነት ዘርፍ እያገለገሉ ያሉ ባለሙያዎች በጉዲፈቻ ካመጧቸው ልጆች የመተዋወቂያ ጊዜ እንዲያገኙ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲ ካምፓሶች ውስጥ የልጆች መንከባከቢያ አገልግሎት አቅርቦት እንዲኖር ፖሊሲዎች እንዲሻሻሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
news-53082263
https://www.bbc.com/amharic/news-53082263
የቆመ አውሮፕላን የገጨው አብራሪ ምርመራ ሊደርግበት ነው
የአየር በረራዎች ቆመዋል በሚባሉበት በአሁኑ ወቅት ቆሞ የነበረን አውሮፕላን የገጨው ፓይለት ላይ ምርመራ ሊደረግ ነው።
ግጭቱ የተከሰተው ማክሰኞ ማምሻውን ነው። አበርዲን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተሰኘው የስኮትላንዱ ጣቢያ። አንድ አነስ ያለ አውሮፕላን መስመሩን ጠብቆ የቆሞ ተለቅ ያለ አውሮፕላን ይገጫል። የአነስተኛው አውሮፕላን አፍንጫ ተለቅ ካለው አውሮፕላን ክንፍ ሥር እንደ እርጎ ዝንብ ጥልቅ ይላል። አልፎም በአፍንጫው የትልቁን አውሮፕላን ክንፍ ወደ ላይ ከፍ ያደርገዋል። አገር ሰላም ብሎ የቆመው አውሮፕላን የሎጋንኤር ንብረት ነው። ነገር ተንኳሹ ደግሞ የፋልይቢ። ትልቁ አውሮፕላን ያሳፈራቸውን መንገደኞች ከነሻንጣቸው ወደ መዳረሻቸው ከሸኘ በኋላ ነው መስመሩን ጠብቆ የቆመው ተብሏል። የአገሪቱ የአውሮፕላን አደጋዎች መርማሪ ተቋም ጉዳዩን ለእኔ ተዉት እመረምረዋለሁ ብሏል። በግጭቱ ማንም አልተጎዳም። ሎጋንኤር አውሮፕላኔ በቆመበት ተገጭቷል ሲል መግለጫ አውጥቷል። "ኢምብራዬር 145 የተሰኘው ጄታችን መንገደኞችም ሆኑ የበረራ ሠራተኞች በሌሉበት ቆሞ ሳለ በፍላይቢ ቦምባርዲኤር Q400 ተገጭቷል። ገጪው አውሮፕላን ለበረራ እየተዘጋጀ እንደነበር ተረድተናል።" መግለጫው አክሎ "የገጭው አውሮፕላን አፍንጫ የእኛን አውሮፕላን የቀኝ ክንፍ ጭሮታል፤ ከመሬት ወደ ላይም ቀና አድርጎታል። ዋናው ነገር ማንም አለመጎዳቱ ነው። የፍላይቢው አውሮፕላን ሠራተኞች ሰላም መሆናቸው በጎ ዜና ነው።" አበርዲን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያም "አዎ እውነት ነው፤ ማክሰኞ ምሽት 12፡00 ገደማ ግጭቱ ተከስቷል" ሲል አረጋግጧል። አየር ማረፊያው አክሎም አደጋው ምርመራ እየተደረገበት እንደሆነ ጠቁሟል። አውሮፕላኖች በቆሙበት ሲጋጩ እምብዛም አይስተዋልም። ለዚህም ነው ዜናው ከአውሮፓ አልፎ በዓለም የናኘው። ዜናው ያስደነቃቸው የማኅበራዊ ድር-አምባ ተጠቃሚዎች በሁኔታው ሲያፌዙ ተስተውለዋል። አንድ ፌስቡከኛ "አውሮፕላኖች አካላዊ ርቀት መጠበቅ ተዉ እንዴ?" ሲል ፅፏል።
49806966
https://www.bbc.com/amharic/49806966
ኢራን የአውሮፓ አገራትን ውንጀላ አጣጣለች
ፈረንሳይ፣ ጀርመን እና ዩናይትድ ኪንግደም በጥምረት፤ በሳዑዲ ነዳጅ ማቀነባበሪያ ላይ ከደረሰው ጥቃት ጀርባ ያለችው ኢራን ናት ቢሉም፤ ኢራን ውንጀላቸውን አጣጥላዋለች።
ኢማኑኤል ማክሮን፣ አንግላ መርከልና ቦሪስ ጆንሰን በተባበሩት መንግሥታት ድረጅት ዋና ጽሕፈት ቤት የኢራን የውጪ ጉዳይ ሚንስትር የሦስቱን አገራት ክስ "የአሜሪካን ከንቱ ክስ ያስተጋባ" ሲሉ ውድቅ አድርገዋል። • ሳዑዲ፡ ጥቅም ላይ የዋሉት መሣሪዎች ኢራን ተጠያቂ መሆኗን ያረጋግጣሉ • አሜሪካ ጦሯን ወደ ሳዑዲ ልትልክ ነው የአውሮፓ አገራት መሪዎች እንዳሉት፤ ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ ከኢራን ውጪ ማንም ላይ ጣት መቀሰር አይቻልም። ኢራን የምትደግፈው የየመኑ የሁቲ አማጽያን ቡድን ጥቃቱን የሰነዘርኩት እኔ ነኝ ሲል ኃላፊነቱን ቢወስድም፤ አሁንም ተጠያቂ የተደረገችው ኢራን ናት። ስምንት ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና ሰባት ሚሳኤሎች የሳዑዲን የነዳጅ ማቀነባበሪያ ከመቱ በኋላ፤ ሳዑዲ እንዲሁም አሜሪካ ኢራንን ወንጅለዋል። ኢራን በበኩሏ በጥቃቱ እጄ የለበትም ማለቷ ይታወሳል። መሪዎቹ ምን አሉ? የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን፣ የፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና የጀርመኗ መራሔተ መንግስት አንግላ መርኬል በጋራ በሰጡት መግለጫ፤ ኢራን ለጥቃቱ ተጠያቂ ናት ብለዋል። እየተካሄደ ያለውን ምርመራ እንደሚደግፉም አሳውቀዋል። "ኢራን በኒውክሌር ፕሮግራሟ ላይ ለድርድር ዝግጁ መሆን የሚጠበቅባት ጊዜ ላይ ነን" ሲሉም መሪዎቹ ተናግረዋል። • ቦይንግ ለሟች ቤተሰቦች ካሳ ሊከፍል ነው • አልሲሲን ለመቃወም አደባባይ የወጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ግብፃውያን ታሰሩ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ 2015 ላይ የተደረሰውን የኒውክሌር ስምምነት (ጆይንት ኮምፕሪሄንሲቭ ፕላን ፎር አክሽን) በማክበር እንደሚቀጥሉም ገልጸዋል። የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከስምምነቱ አገራቸውን አውጥተው ኢራን ላይ ማዕቀብ ከጣሉ በኋላ ሁለቱ አገራት ተፋጠዋል። ፕሬዘዳንት ትራምፕ "የቀድሞው ስምምነት ብዙ ችግሮች አሉት። አዲስ እና ከቀደመው የተሻለ ስምምነት ለመፈራረም ዝግጁ ነኝ" ካሉ በኋላ ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን ሀሳቡን እንደሚደግፉ ተናግረዋል። ቦሪስ ከኢራኑ ፕሬዘዳንት ጋር እንደሚገናኙም ተነግሯል። ኢራን ምን ምላሽ ሰጠች? የኢራን የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሞሀመድ ዣቪድ ዛሪፍ፤ አዲስ የኒውክሌር ስምምነት እንደማይረቀቅ ገልጸዋል። አሜሪካ ከስምምነቱ በመውጣቷ ሦስቱ የአውሮፓ አገራትም ከስምምነቱ የሚጠበቅባቸውን እየተወጡ አለመሆኑንም አክለዋል። "አሁን ያለው ስምምነት ሳይከበር አዲስ ስምምነት አይረቀቅም" ብለዋል። አሜሪካ እና አጋር አገራት፤ የሳዑዲ ነዳጅ ማቀነባበሪያ ላይ ለደረሰው ጥቃት ወታደራዊ ምላሽ ለመስጠት ከቃጡ፤ ኢራን አጸፋውን እንደምትመልስም ተናግራለች።
news-45365298
https://www.bbc.com/amharic/news-45365298
ኡጋንዳዊው እንደራሴ እና የጥበብ ሰው ቦቢ ዋይን እንደገና ለእሥር ተዳርጓል
ከመንግሥት ጋር ዓይና እና ናጫ የሆነው ኡጋንዳዊው እንደራሴ እና የጥበብ ሰው ቦቢ ዋይን ከተፈታ ከቀናት በኋላ እንደገና ለእሥር ተዳርጓል።
ኡጋንዳዊው እንደራሴ እና የጥበብ ሰው ቦቢ ዋይን ቦቢ ዋይን ዕለተ ሰኞ ነበር በሃገር መክዳት ክስ ተከሶ ለፍርድ ከቀረበ በኋላ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶት በዋስ የተለቀቀው። ነገር ግን የግለሰቡ ጠበቃ ቦቢ ዋይን ሐሙስ ምሽት ለዳግም እሥር መዳረጉን ለመገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል። ጠበቃ ሮበርት አምስተርዳም ለቢቢሲ እንደተናገሩት «ምንም አንኳ ዳኛው ቦቢ ዋይን ፓስፖርቱን በእጁ እንዲይዝና ከሃገር ቢወጣም ምንም ጉዳት እንደሌለው ቢያሳውቁም ለሕክምና ለመሄድ ሲሞክር ነው አየር መንገድ ውስጥ የተያዘው።» አክለውም «እየገፈታተሩ ወደ ፖሊስ መኪና አስገቡት፤ የት እንደወሰዱትም አናውቅም፤ ስጋት ላይ አንገኛለን» ሲሉ ቃላቸውን ሰጥተዋል። በመዝገብ ስሙ ሮበርት ኪያጉላኒ በመባል የሚታወቀው ቦቢ ዋይን ሰኞ ዕለት ፍርድ ቤት በቀረበ ጊዜ በክራንች ድጋፍ ሆኖ ታይቷል። አጋሮቹ እንደሚሉት ፖሊስ ጣቢያ በነበረበት ወቅት ለፕሬዝደንቱ ቅርብ በሆኑ የጥበቃ ሰዎች ስቃይ ደርሶበታል። የሃገሪቱ የጦር ኃይል ግን ውንጀላው መሠረተ ቢስ ነው ሲል አጣጥሎታል። • 'ስቃይ የደረሰበት' ኡጋንዳዊ ፖለቲከኛ ተፈታ ለመሆኑ ቦቢ ዋይን ማን ነው? አፍሮቢት በተሰኘው የሙዚቃ ስልት ጨዋታ የሚታወቀው ቦቢ ዋይን በኡጋንዳውያን ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይንት ያለው ሲሆን ከሙሴቬኒ መንግሥት ጋር ዓይን እና ናጫ ከሆነ ዓመታት ተቆጥረዋል። የሙዚቃ ሕይወቱን ትቶ ወደ ሕዝብ ፖለቲካ ዓለም ከመጣ ወዲህም የሕዝብ እንደራሴ ሆኖ በመመረጥ ምክር ቤቱን ሲያስጨንቅ ቆይቷል። ከ75 ዓመት በላይ የሆነው ግለሰብ ለፕሬዝዳንትነት መመረጥ የለበትም በሚልም ሕገ-መንግሥቱ እንዳይነካ ቢታገልም አልተሳካላትም። የኡጋንዳ መንግሥት ፌስቡክና እና ዋትስአፕን የመሳሰሉ ማሕበራዊ ድር አማባዎች ሊቀረጡ ይገባል ብሎ ያወጣውን ሕግም በፅኑ ሲቃወም ቆይቷል። • ኡጋንዳዊው ሙዚቀኛ በሃገር ክህደት ተከሰሰ
53783107
https://www.bbc.com/amharic/53783107
ኮሮናቫይረስ፡ አፍሪካ ከገባ ግማሽ ዓመት የሞላው ወረርሽኝ ወዴት እያመራ ነው?
አህጉረ አፍሪካ የመጀመሪያው ሰው በኮሮናቫይረስ ተይዞብኛል ብላ ካወጀች እነሆ ግማሽ ዓመት ሆነ።
አህጉሪቱ ውስጥ የመጀመሪያ በቫይረሱ የተያዘ ሰው ይፋ የተደረገው ግብፅ ውስጥ ነው። ይህ ዜና ከተሰማ በኋላም ቢሆን ወረርሽኙ አፍሪካ ላይ ብርቱ ክርኑን ወዲያው አላሰረፈም ነበር። አውሮፓውያን እንደቅጠል ሲረግፉ፤ አሜሪካውያን ለሞት ሲሰለፉ፤ አፍሪካ ግን ሃገር ሰላም ብላ ነበር። ይህ ለምን ሆነ ብለው የተንገበገቡ ሰዎች ጥናት እናካሂድም ብለው ነበር። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአህጉሪቱ ሃገራት በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ነው። በቀን አንድና ሁለት ሰው የመዘገበችው ኢትዮጵያ እንኳ ትላንት [ነሐሴ 8/2012] በ24 ሰዓታት ብቻ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ይፋ አድርጋለች። ደቡብ አፍሪካ በበኩሏ ከአህጉር አልፋ በዓለም ደረጃ መወዳደር ይዛለች። በአሁናዊ አሃዝ መሠረት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኮሮናቨይረስ የተያዙባት ደቡብ አፍሪካ በዓለም አምስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ከደቡብ አፍሪካ በተጨማሪ ግብፅ፣ ናይጄሪያ፣ ጋና እና አልጄሪያ፤ በአፍሪካ በኮሮናቫይረስ ከተያዙ ሰዎች 75 በመቶ ገደማ የሚሆነውን ድርሻ ይይዛሉ። ምንም እንኳ ቁጥሩ ከጊዜ ጊዜ ቢጨምርም የዓለም ጤና ድርጅት ወረርሽኙ አፍሪካ ላይ መች እንደሚበረታ መገመት አልቻልኩም እያለ ነው። ድርጅቱ የአፍሪካ ሃገራት የኮሮናቫይረስ ምርመራቸውን በገጠራማ ሥፍራዎችም እንዲያከናወኑ በፅኑ ያሳስባል። በተለይ ደግሞ ድንበር አካባቢ ያሉ ከተማዎች የቫይረሱን ሥርጭት መጠን የሚያሳዩ ናቸው ይላል ድርጅቱ። አውሮፓና አሜሪካ በወረርሽኙ ሲደናገጡ የእንቅስቃሴ ገደብ ጥለው የነበሩ የአፍሪካ ሃገራት አሁን ወረርሽኙ ፊቱን ወደ አህጉሪቱ ቢያዞርም እንቅስቃሴዎችን ማላላት ጀምረዋል። ከ54ቱ የአህጉሪቱ ሃገራት 25ቱ ድንበራቸውን ዘግተዋል። 23 ደግሞ ወደ ሃገር ለሚገቡና ለሚወጡ ሰዎች የግዴታ የኮሮናቫይረስ ምርመራ እንዲያከናውኑና የምርመራ ውጤት እንዲያመጡ ያዛሉ። የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠር ማዕከል [ሲዲሲ] በላይቤሪያ፣ ሲዬራ ሊዮን፣ ዛምቢያ፣ ዚምባብዌ፣ ካሜሩንና ናይጄሪያ ውስጥ የበሽታ መከላከል [አንቲቦዲ] ምርመራ ላከናውን ነው ብሏል። ማዕከሉ ይህን ማድረግ ያስፈለገው በሽታው በምን ያክል ፍጥነት እየተጓዘ እንዳለ ለመረዳት ነው። የአንቲቦዲ ምርመራ ማለት ሰዎች ከዚህ በፊት በኮሮናቫይረስ ይሆን ወይ የሚለውን የሚለይ ነው።
news-47983244
https://www.bbc.com/amharic/news-47983244
የመን፡ በስለላ ወንጀል የተጠረጠረው ጥንብ አንሳ
ኔልሰን የተባለው ጥንብ አንሳ የመን ውስጥ በመብረር ላይ ሳለ ነበር ባላሰበው መልኩ በወታደሮች ተይዞ በቁጥጥር ስር የዋለው። ከተያዘ በኋላም ጠባብና ጨለማ ክፍል ውስጥ እንዲቆይ ተደርጓል። የተጠረጠረበት ወንጀል ደግሞ ወታደራዊ ስለላ ነበር።
ቲያዝ በተባለችው ትንሽ ከተማ ወታደሮቹ ሲያገኙት እንቅስቃሴውን የሚቆጣጠር መሳሪያ እግሩ ላይ ተገጥሞለት ነበር። መሳሪያውም ወታደሮቹ አይተውት የማያውቁትና እጅግ የተራቀቀ ሲሆንባቸው ጊዜ ወታደራዊ መረጃዎችን ማስተላለፊያ ሊሆን እንደሚችል በመገመት በቁጥጥር ስር አዋሉት። በየትኛውም አይነት ጦርነት ውስጥ በስለላ ወንጀል መከሰስ በጣም ከባድ ነው። እንደ ቲያዝ ባለች ትንሽ የየመን ከተማ ውስጥ ደግሞ ማንኛው ሰውም ሆነ እንሰሳት ሰላይ ተብሎ ሊጠረጠር ይችላል- ጥንብ አንሳም ቢሆን። • መጠቀም ያቆምናቸው ስድስት የአካል ክፍሎች • ከጦርነት ይልቅ ለብዙዎች ሞት ምክንያት የሆኑት አይጦች በሳኡዲ የሚደገፉት እነዚህ ሚሊሺያዎች የኔልሰን እግር ላይ ያለውን ዘመነኛ መሳሪያ እንደተመለከቱ ወዲያው ያሰቡት ሁቲ የተባሉት አማጺያን ቡድኖች ለስለላ የላኩት እንደሆነ ነው። ነገር ግን የኔልሰን እግር ላይ የተገጠመው መሳሪያ ለጥበቃ ስራ ሲባል የበራሪ እንስሳውን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ታስቦ ነበር። በተጨማሪም በሕይወት መኖር አለመኖሩንም ባለሙያዎች የሚቆጣጠሩት በዚሁ መሳሪያ ነው። ኔልሰን በአውሮፓዊቷ ሃገር ቡልጋሪያ ውስጥ ለምርምር ስራ በማሰብ የእንቅስቃሴ መቆጣጠሪያ ከተገጠመላቸው 14 ጥንብ አንሳዎች መካከል አንዱ ነው። ጉዞውንም አንድ ብሎ የጀመረው ከቡልጋሪያ ነበር። የህይወት አጋጣሚ ሆነ እራሱን በጦርነት በምትታመሰው የመን ውስጥ አግኝቶታል። ሊያውም በስለላ ወንጀል ተጠርጥሮ እስር ቤት ውስጥ። የኔልሰንን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ሲቆጣጠሩ የነበሩት በቡልጋሪያ የሚገኙት ባለሙያዎች ደብዛው የጠፋውን ግዙፍ በራሪ ማፈላለጋቸውን ቀጥለው ነበር። እነሱ እንደሚሉት ሳኡዲ አረቢያን ካለፈ በኋላ ወደ የመን ሲጠጋ ኔልሰን እግር ላይ ተገጥሞ የነበረው መቆጣጠሪያ መሳሪያ መልዕክት ማስተላለፍ አቆመ። በሚያስገርም ሁኔታ ቡልጋሪያውያን ተመራማሪዎቹ በመቶዎች የሚቆጠሩ መልዕክቶች ይደርሷቸው ጀመር። ለማንኛውም ብለው በኔልሰን እግር ላይ ባስቀመጡት የስልክና የኢሜይል አድራሻ በኩል ብዙ የቲያዝ ከተማ ነዋሪ የመናውያን የድረሱለት ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። አንዳንዶቹ እንደውም የኔልሰንን ምስል በተንቀሳቃሽ ስልኮቻቸው በማንሳት ለተመራማሪዎቹ ልከውላቸዋል። ከተመራማሪዎቹ አንዷ የሆነችው ናድያ ቫንግሎቫ እንደተናገረችው የከተማዋ ነዋሪዎች በጣም ሩህሩህና አስገራሚ ሰዎች ናቸው ብላለች። ''የራሳቸውን የጦርነት መከራና ጭንቀት ወደ ጎን ብለው የኔልሰንን ደህንነት ለማረጋገጥ ይህን ያክል መሰዋዕትነት መክፈላቸው እጅግ አስገራሚ ነገር ነው።'' በማለት አድናቆቷን ለቢቢሲ ገልጻለች። • ደቡብ ኮሪያ ትልቁን የውሻ 'ቄራ' ዘጋች • ወባን በማሽተት የሚለዩት ውሾች በመጨረሻም ተመራማሪዎቹ የመን በሚገኘው ኤምባሲ በኩል መልዕክታቸውን ማስተላለፍ ጀመሩ። ሙከራቸውም ፍሬ አፍርቶ ኔልሰንን የያዙት ወታደሮች እግሩ ላይ ያለው መሳሪያ ለስለላ ሳይሆን ለምርምር እንደሆነ መረዳት ቻሉ። በአሁኑ ሰአት ኔልሰን እግሩ ላይ፣ አንገቱ ላይ እንዲሁም ክንፉ አካባቢ ጉዳት የደረሰበት ሲሆን ክብደቱም ቀንሶ ወደ 4.8 ኪሎ ግራም ወርዷል። እራሱን ችሎ ለመብረርም ቢያንስ ከአምስት ኪሎ በላይ መመዘን አለበት። በአካባቢው ያሉ የእንስሳት መብት ተቆርቋሪዎችና ነዋሪዎቹ ኔልሰን ወደ ሙሉ ጤንነቱ እስኪመለስ ድረስ ስጋ እየመገቡት ነው። በጦርነት እየታመሰች በምትገኝውና ከፍተኛ የምግብ እጥረት ባለባት የመን ዜጎቿ እንዲህ አይነት ደግነት በማሳየት ለዓለም ምን አይነት ህዝቦች እንደሆኑ መልዕክት እያስተላለፉ ይመስላል።
48313343
https://www.bbc.com/amharic/48313343
የትራምፕ አሜሪካ በኢትዮጵያውያን ላይ እያደረሰ ያለው ተፅእኖ ምንድን ነው?
ከምርጫ ቅስቀሳቸው ጀምሮ የስደተኞችን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ ቃል እየገቡ የመጡት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከትላንት በስትያ ብዙዎች አግላይ ያሉትን ንግግር አድርገዋል።
በንግግራቸው ከዚህ በኋላ አሜሪካ የምትቀበላቸው ስደተኞች "ወጣት፣ የተማሩና እንግሊዝኛ ቋንቋ የሚችሉትን ነው" ብለዋል። የስደተኞች የጥገኝነት ጥያቄ ተቀባይነት የሚያገኘው አቅማቸው ታይቶ ሲሆን፤ የአሜሪካን የሥነ ዜጋ ትምህርት ተፈትነው ማለፍ እንደሚኖርባቸውም ገልፀዋል። • የኢትዮጵያና አሜሪካ የተለየ ግንኙነት እስከምን ድረስ? • የዓለምፀሐይ፣ የፍስሃ እና የካሳሁን አዲስ ተስፋ ብዙዎች ይህን ንግግራቸውን "ዘረኝነት የተሞላበት"፤ "ፀረ ስድተኛና ፀረ-ጥቁር ነው" ሲሉ ተደምጠዋል። በብዙ ሃገራት ተቀባይነት ያለው የተባበሩት የመንግሥታት የስደተኞች ድርጅት ኮንቬሽን፤ ጦርነት፣ መፈናቀል፣ ግድያንና ሌሎችም ችግሮችን ፈርተው የሚሰደዱ ሰዎች በሦስተኛ አገር ነፃነታቸው ተጠብቆ ሊኖሩ እንደሚገባ ቢያትትም፤ ፕሬዚዳንት ትራምፕ በንግግራቸው ይህንን ሰብአዊ መብት እየጣሱት መሆኑን ብዙዎች ይተቻሉ። ከነዚህም ውስጥ ትውልደ ሶማሊያዋ የኮንግረስ አባል ኢልሃን ኦማር ትገኝበታለች። "ጥገኝነት ለሚጠይቁ ግለሰቦች ጀርባችንን ልንሰጣቸው አይገባም። የትራምፕ ንግግር በጣም ተስፋ አስቆራጭ ነው። በተለይም ከፍተኛ ፈተናን አምልጠው፣ አዲስ ተስፋን ሰንቀው የሚመጡ ሰዎች ላይ እንዲህ አይነት ንግግር ማድረጋቸው ሀዘኔን የበለጠ ይጨምረዋል። ምክንያቱም እኔም ከነሱ አንዷ ነበርኩ" ብላለች። • "ውሳኔው የአሜሪካ እና የኢትዮጵያን የጋራ ጥቅም ከግምት ውስጥ ያስገባ አይደለም" ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ የኢልሃንን ሀሳብ ተጋርተው የፕሬዚዳንቱ ንግግር አግላይና ዘረኛ ነው የሚሉት በአትላንታ የኢሚግሬሽን የሕግ ባለሙያ የሆኑት አቶ ማንችሎት ገበየሁ ጓዴ ናቸው። ነገር ግን ይህ ንግግራቸው ፖሊሲ ወይም ሕግ ሳይሆን ለዋይት ሃውስ የሕግ አቅጣጫ ማሳያ የሚሆን ነው ይላሉ። የትራምፕ ንግግር ወደሕግነትና ፖሊሲነት የመቀየር አቅሙ ዝቅተኛ እንደሆነም የሕግ ባለሙያው ያስረዳሉ። ትራምፕ የስደተኞችን ቁጥር ለመቀነስ በተደጋጋሚ ውሳኔ ቢያሳልፉም በተለያዩ ምክንያቶች ሳይተገበሩ ቀርተዋል። እንደምሳሌ በርካታ ሙስሊሞች የሚኖሩባቸው ሀገራት ላይ ገደብ መጣል ይጠቀሳል። ምንም እንኳን አንዳንዶቹ ውሳኔዎች ኮንግረስ ላይ ቢቀርቡም፤ ኮንግረሱ ሳያሳልፋቸው እንደቀሩ የሕግ ባለሙያው ይናገራሉ። "በአስቸኳይ አዋጅ አውጀው ፍርድ ቤት የገደባቸው ውሳኔዎችም አሉ። ስለዚህ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ያወሯቸውን ነገሮች ለመተግበር ጥረት ቢያደርጉም፤ አፈፃፀሙን በተመለከተ ወደሕግነትና ፖሊሲነት ተቀይሮ ተግባር ላይ እንዳይውል በተለያየ መንገድ ውድቅ ሆኗል" ይላሉ። • "የእስላማዊ ፍርድ ቤቶች ኅብረትን እናጠፋለን ብለን አልሸባብን ፈጠርን" አቶ ማንችሎት ለዚህ እንደምክንያትነት የሚጠቅሱት በአሜሪካ የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ሴኔቱ ሪፐብሊካኖች ሲሆኑ፤ ኮንግረሱን የሚቆጣጠሩት ደግሞ ዴሞክራቶች መሆናቸውን ነው። "ሕጉን የማሻል አቅማቸው በጣም ደካማ ነው። ሪፐብሊካኖችንና ዴሞክራቶችን የማሳመን ሥራ መሥራት አልቻሉም። በአስቸኳይ ጊዜ እንዲሁም የሥራ አስፈፃሚነት ኃይላቸውን ተጠቅመው ሲያዙም፤ ፍርድ ቤቶች ወዲያው ስለሚያግዱባቸው ያን ያህል የተለየ ነገር ይመጣል ብዬ አልጠብቅም" ሲሉ ያስረዳሉ። • የታሪክ መማሪያ መጻሕፍት ለምን ይከለሳሉ? ሆኖም የፕሬዚዳንቱ ንግግር እንደቀላል መወሰድ እንደሌለበት አቶ ማንችሎት ይናገራሉ። በተለይም አሜሪካ ካላት የምጣኔ ሀብትና የጦር ኃያልነት ጋር ተያይዞ ስደተኞች የሚመጡባቸው አገሮችን መጠለያ ላፍርስ ቢሉ ተቀባይነት ሊኖራቸው እንደሚችል አቶ ማንችሎት አልደበቁም። በተለይም ዓለም አቀፉ ሕግ የሀብታም አገራት ፍላጎት ማስፈፀሚያ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ፤ ትራምፕም የሁለትዮሽ ግንኙነትን በመጠቀም ሀሳባቸውን ሊያሳኩ እንደሚችሉ የሕግ ባለሙያው ጠቆም አድርገዋል። የሕግ ባለሙያው እንደማስረጃ የሚያነሱት ፕሬዚዳንቱ በተደጋጋሚ ያደረጉት ንግግር ከነጭ ማኅበረሰቡ ውጭ ያለውን ጥቁርም ሆነ ሌሎች ማኅበረሰቦችን የሚቃወም ቢሆንም ከመተቸት አልፎ በፕሬዚዳንት ትራምፕ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ የሚወስድ መንግሥት እስካሁን አለማየታቸውን ነው። • ኢትዮጵያ ሀይቆቿን መጠበቅ ለምን ተሳናት? "ኬንያ የሚገኘውን የስደተኞች ካምፕ አፈርሳለሁ ቢሉ አቅም ከመኖር የሚመነጭ ስለሆነ የኬንያ መንግሥት ሊተባበራቸው ይችላል። ስለዚህ አንዳንድ አገሮች ከአሜሪካ የሚያገኙትን ድጋፍ ታሳቢ በማድረግ የፕሬዚዳንት ትራምፕን ንግግርና ተፅእኖ ተግባራዊ ሊያደርጉ ይችሉ ይሆናል" ይላሉ። ፕሬዚዳንቱ የሥራ አስፈፃሚነት ኃይላቸውን የሚጠቀሙ ከሆነ በተለያዩ አገራት ያሉ ስደተኞችን በዛው መገደብ እንዲሁም በመጠረዝ ሊመልሷቸው እንደሚችሉ በመጠቆም፤ በዚህ ሂደትም ብዙ ኢትዮጵያውያን ሊጎዱ እንደሚችሉ ይናገራሉ። • "ማህበሩ የማያልፈው ቀይ መስመር የስራ ማቆም አድማ ነው"-ዶ/ር ገመቺስ ማሞ የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ፕሬዚዳንት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ወደአሜሪካ የሚሄጡ ኢትዮጵያውያን ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እያደረሰ መሆኑንም አቶ ማንችሎት ያስረዳሉ። በብዙዎች ዘንድ እንደገነት ወደምትቆጠረው አሜሪካ ለመሄድ ግለሰቦች ከቤት ባለቤትነት ጀምሮ፣ ንብረታቸውንና ላለመቅረታቸው የተለያዩ ማስረጃዎች ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን፤ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከመጡ በኋላ 'ቬቲንግ' (የማጣራት ሂደቱ) ወይም ቪዛ የማግኘት ሂደቱ ጠበቅ ማለቱን አቶ ማንችሎት ገልፀዋል። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ቀጥተኛ ሕግ ባይኖርም የተለያዩ አገራትን ኤምባሲ የሚቆጣጠረው የፕሬዚዳንት ትራምፕ ዋይት ሃውስ መሆኑ ነው። በአጠቃላይ በተለያየ ምክንያት ወደአሜሪካ በሚሄዱ ሰዎች ላይ ክልከላው እንደጨመረ ነው። ትራምፕ ፕሬዚዳንት ከመሆናቸው በፊት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ግለሰቦች ወደአሜሪካ ያቀኑ የነበረ ቢሆንም አሁን ካለው አሠራር ጋር ተያይዞ ብዙ ገደቦች እንደተጣሉ ነው። አቶ ማንችሎት እንደ ምሳሌ የሚያነሱት በትራምፕ አሜሪካ በጋብቻ የሚሄዱ ሰዎች ጋብቻቸው የውሸት ነው ተብሎ ስለሚታሰብ ተጋቢዎች የተለየ ማስረጃ ማቅረብ እንደሚኖርባቸው ነው። • በደቡብ ሱዳን የምሽት ክለቦች ታገዱ "ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ ጋብቻዎች አንድ ሰው ሕጉ የሚፈቅደውን ማስረጃ ከማቅረብ በተጨማሪ ጋብቻው የእውነት መሆኑን የማስረዳት ሸክም ይኖርበታል" ይላሉ። በዚህም መሰረት ፕሬዚዳንት ትራምፕ ስልጣን ከያዙ በኋላ ቤተሰብን ማምጣት፣ ሚስት ማምጣት፣ ልጅ ማምጣት የሚባለው ሂደት በጣም ጥብቅ ስለሆነ አንድ ዓመት ይወስድ የነበረው ሂደት ሁለት ዓመት እንደሚወስድም ያስረዳሉ። • "የኢትዮጵያ የህክምና ታሪክ አልተጠናም" ዶክተር አሰፋ ባልቻ ከዚህ ሁሉ በላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እያደረሰ ያለው ፕሬዚዳንት ትራምፕ ስልጣን ከመቆናጠጣቸው በፊት በተለያየ ምክንያት የሚሄዱ ኢትዮጵያውያን የጥገኝነት ጥያቄያቸው በቀላሉ ተቀባይነት ያገኝ የነበረ ሲሆን፤ አሁን ግን የማጣራት ሂደቱ ረዥም ጊዜ እየወሰደ ስለሆነ ተቀባይነት የሚያገኙ ስደተኞች ቁጥር መመናመኑን አቶ ማንችሎት ገልፀዋል። "ብዙዎች ተጠርዘዋል፤ ወደአሜሪካ ትሄዳላችሁ የተባሉ ስደተኛች እንደገና የማጣራቱን ሥራ እያራዘሙባቸው ነው" ይላሉ።
51209352
https://www.bbc.com/amharic/51209352
አሠልጣኝ አብርሃም መብራህቱ፡ "የመጣውን በጸጋ መቀበልና መዘጋጀት ነው"
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን 2022 የሚካሄደው የኳታሩ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ድልድል ተጋጣሚዎች ታውቀዋል። በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ በምድብ 7 ከጋና፣ ደቡብ አፍሪካ እና ዚምባብዌ ጋር ተደልድላለች።
የምድብ ድልድሉ በግብጿ ዋና ከተማ ካይሮ ይፋ የተደረገ ሲሆን የየምድቦቹ አሸናፊዎች በዕጣ ድልድል እርስ በርስ ጨዋታ ያደርጋሉ። የደርሶ መልስ ጨዋታውን ማሸነፍ የቻሉ 5 ሃገራት በኳታሩ የዓለም ዋንጫ አፍሪካን ወክለው ይጫወታሉ። ዋልያዎቹ ባሳለፍነው መስከረም ወር ላይ በባህር ዳር ስታዲየም ከሌሴቶ አቻቸው ጋር ያለምንም ግብ ቢለያዩም የመልስ ጨዋታዋን በሌሴቶ አድርገው አንድ አቻ መለያየታቸው ይታወሳል። ከሜዳ ውጭ ባገባ በሚለው ህግ መሰረትም ኢትዮጵያ ወደቀጣዩ ዙር በማለፍ የምድብ ድልድል ውስጥ መግባቷን አረጋግጣ ነበር። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ የሆኑት አብራሃም መብራህቱ፤ ቡድኑ ያለበትን ደረጃ ስመለከትና ተጋጣሚዎቻችንን ስመለከት ቀለል ያሉ ሀገራት ቢደርሱን ብዬ አስቤያለው ይላሉ። ''ቀደም ሲል ለዓለም ዋንጫ በማለፍ ታሪክ ውስጥ ተደጋጋሚ ታሪኮችን ያስመዘገቡ ሀገራት ባይደርሱን ብለህ ታስባለህ፤ ነገር ግን የምድብ ድልድሉ በዕጣ የሚወጣና ከሰዎች ንክኪ ውጪ ስለሆነ የመጣውን በጸጋ መቀበልና መዘጋጀት ነው የሚጠቅመው'' ብለዋል። እንደ ጋና እና ደቡብ አፍሪካን የመሰሉ በዓለም ዋንጫ ጥሩ የሚባል ልምድ ካላቸው ሀገራት ጋር የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እንደሚመደብ ባያስቡም እንደ አሰልጣኝ ግን ለጥሩውም ለመጥፎውም ነገር ተዘጋጀውተው እንደነበር አሰልጣኙ አክለዋል። ''በተደጋጋሚ የዓለም ዋንጫን ከተሳተፈችው ጋና እና በአዘጋጅነት እንኳን ቢሆንም የዓለም ዋንጫ ልምድ ካላት ደቡብ አፍሪካ ጋር መመደባችን ጨዋታዎቹን ትንሽ ፈታኝ ያደርጋቸዋል። ያም ቢሆን ግን ውድድር ውስጥ እስከገባን ድረስ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እና ከምድባችን አንደኛ ሆኖ ለመጨረስ ምድቡን የሚመጥን ዝግጅት ማድረግ ይኖርብናል ብዬ አስባለሁ።'' ''የምድብ ድልድሉ ይፋ ከተደረገ በኋላ በርካታ መገናኛ ብዙሀን እድለኞች እንዳልሆንንና ከባድ ምድብ ውስጥ እንደገባን ሲዘግቡ ሰምቻለው፤ እኔ ግን እንደዛ አላስብም። የትኛውንም ምድብ መፍራት የለብንም፤ ከፈራን ደግሞ ከነጭራሹ ባንገባባት ነው የሚሻለው። ስለዚህ በልበ ሙሉነት ውድድሩን መጀመር ይኖርብናል።'' አሰልጣኙ አክለውም ''በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ኮትዲቯርን በባህርዳር ዓለማቀፍ ስቴዲየም ማሸነፋችን እንደዚህ አይነት ከባድ ቡድኖችን መቋቋም እንደምንችል ማሳያ ሊሆን ይችላል። ይህንን እንደ ሞራል ስንቅ ተጠቅመን በይቻላል መንፈስ መግባት ይኖርብናል'' ብለዋል። ''በተጨማሪነትም እነዚህን ሀገራት አሸንፎ ወደቀጣዩ ዙር ለማለፍ ለኮትዲቯር ካደረግነው ዝግጅት የተሻለ ዝግጅት ማድረግ ይኖርብናል። ሁሉም ባለድርሸ አካላት ሊረባረቡ ይገባል፤ ምድቡን የሚመጥን በቂ ዝግጅትና የአቋም መለኪያ ማድረግ ይኖርብናል።'' ከዋናው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጋር ለአስር ዓመታት የተጫወተው አዳነ ግርማ በበኩሉ '' የምድብ ድልድሉን ወረቀት ላይ ስታየው ከባድ ነው የሚመስለው። ነገር ግን በቅርቡ እንኳን ሳይታሰብ ኮትዲቯርን ማሸነፋችን ቡድኑ ምን ያክል ጠንካራ እንደሆነ ማሳያ ነው፤ ሊታለፍ ይችላል'' ይላል። በአዳነ ግምት በሜዳ ላይ ከደጋፊ ጋር የሚደረጉ ጨዋታዎች እጅግ ወሳኝ ናቸው። እሱ እንደሚለው ዋልያዎቹ በሜዳቸው የሚያደርጓቸው ጨዋታዎችን በጥንቃቄና ግብ ባለማስተናገድ መጨረስ አለባቸው። ወደተቃራኒ ቡድን ሀገራት በሚሄዱ ጊዜ ደግሞ በተቻለ መጠን ነጥብ ይዞ ለመውጣት መሞከር አለባቸው፤ ቡድኑም ሕብረት ሊኖረው ይገባል ብሏል። ከምድብ ተጋጣሚዎች ጥሩ የሆነ ዓለም አቀፍ ልምድና ብቃት ጋር በማነጻጸር የዋልያዎቹ ወቅታዊ አቋም ምን ይመስላል? የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው ዋና አሰልጣኙ፤ ''እንግዲህ የወቅቱ አቋም መለኪያ ሊሆን የሚችለው የፊፋ ወርሃዊ ደረጃ ነው። በዚህም መሰረት በተለይ ከሁለቱ ሀገራት ጋር ያለን ልዩነት በጣም የሰፋ ነው፤ በሌላ በኩል ከኮትዲቯር ያደረግነውን ጨዋታ ስንመለከትና እነሱ ያደረጓቸውን የመጨረሻ ጨዋታዎች ስንመለከት ጥሩ የሚባል አቋም ላይ እንዳለን ይሰማኛል'' የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። በአሁኑ ሰአት በፕሪምየር ሊጉ እየተሳተፈ በሚገኘው ወልቂጤ ከተማ በተጫዋችነትና በምክትል አሰልጣኝነት እየሰራ የሚገኘው አዳነ ግርማ ''የአሁኑ አሰልጣኝ በጣም ጥሩ ቡድን ሰርተዋል፤ ነገር ግን ተጫዋቾች ቶሎ ቶሎ ሲቀያየሩ አስተውላለሁ። አሰልጣኙና የስልጠና ቡድኑ ባጠቃላይ ይህንን ነገር ቢያስተካክሉ ቡድኑ ይበልጥ የመተዋወቅና በደንብ የተዋሀደ እንዲሆን ይረዳዋል ብዬ አስባለሁ'' ይላል። አሰልጣኙ በበኩላቸው ''የሀገራችን ሊግ ወጥ ካለመሆን ጋር ተያይዞ ተጫዋቾች አቋማቸው ሊዋዥቅ ይችላል፤ እኔ ደግሞ ወቅታዊ አቋሙ ጥሩ ያልሆነ ተጫዋች ለብሄራዊ ቡድኑ ልጠራ አልችልም። ነገር ግን ኮትድቯርን ያሸነፈውን ቡድን በተቻለ መጠን ጠብቆ ለማስቆየት ግን ጥረት እናደርጋለን'' ብለዋል።
news-46190680
https://www.bbc.com/amharic/news-46190680
ሐዘንተኛው ውሻ አሳዳጊው የሞተበት ቦታ ላይ ለ80 ቀን ያህል ጠብቆታል
ውሻ በታማኝነቱ ከእንስሳት ሁሉ የላቀ ነው ይባላል፤ ለታማኝነት ውሻን ተምሳሌት ሲደረግም ይደመጣል፤ ለዚህም በቻይና የሆነው አንዱ ማሳያ ነው።
የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ስለ ውሻው ደህንነት ትኩረት ሰጥተው ሃሳባቸውን ሲገልፁ ነበር በቻይና አንድ ውሻ አሳዳጊውን ከአራት ወራት በፊት በሞት ይነጠቃል። በአጋጣሚውም በሃዘን ልቡ ይሰበራል፤ ታማኝ ነውና እንደ እሳት የሚፈጀውን ሃዘኑን ችሎ እርሷን ካጣበት መንገድ ቁሞ መዋልን መርጧል- ትመጣ እንደሁ ብሎ። • ጠቅላይ አቃቤ ሕግ 63 ተጠርጣሪዎች ተይዘዋል አለ • እምቦጭ የጣና ቂርቆስ መነኮሳትን ከገዳሙ እያስለቀቀ ነው በመኪና መንገድ ላይ ቁጭ ብሎ ለ80 ቀናት ያህል ሳይሰለች ማዶ ማዶውን እያየ መጠባበቁን ቀጠለ። ድርጊቱ በቻይና የበይነ መረብ ተጠቃሚዎችን ቀልብ የገዛና ያሳዘነ ነበር። ውሻው በሞንጎሊያ ሆሆት መንገድ መካከል ላይ ሆኖ የተቀረፀው ተንቀሳቃሽ ምስልም 'ሲና ዌቦ ማክሮ ብሎግ' የተሰኘ ገፅ ላይ 1.4 ሚሊዮን ጊዜ ታይቷል። ተንቀሳቃሽ ምስሉ እንደሚያሳየው ውሻው አሳዳጊው ከሞተችበት ጊዜ አንስቶ በየቀኑ መንገዱ ላይ ይታይ ነበር። በአካባቢው የሚሰራ አንድ የታክሲ አሽከርካሪም ሰዎች ውሻውን ሊረዱት ቢፈልጉም ሮጦ እንደሚያመልጥ ተናግሯል። አሽከርካሪው "በመንገዱ የሚያልፉ አሽከርካሪዎች ምግብ ይሰጡታል፤ ነገር ግን ከመኪናው ወርደን ስናየው ጥሎት ይሄዳል" ሲል የታዘበውን አካፍሏል። ይህም አሳዳጊዋ ከውሻው ጋር ያላት ትስስር በጣም የጠበቀና ጥልቅ እንደነበር ያሳያል፤ እርሷ ከሞተች በኋላ ትንሹ ውሻ የእርሷ ጠባቂ ሆኖ ቀርቷል። "በየቀኑ ውሻውን መንገድ ላይ አየዋለሁ፤ በሁለቱ መካከል ያለው ፍቅር እውነተኛ እንደነበር ያስታውቃል" ይላል አሽከርካሪው። • እምቦጭ የጣና ቂርቆስ መነኮሳትን ከገዳሙ እያስለቀቀ ነው • ተፈጥሮን በብሩሽ የሚመዘግበው መዝገቡ በሐዘን የተጎዳው ውሻ ደህንነት በርካቶችን ሳያሳስብ አልቀረም ታዲያ። ተንቀሳቃሽ ምስሉ ሲና በተባለ ድረገፅ ከተለቀቀ ጊዜ አንስቶ ድረገፁ ከትዊተርና ፌስቡክ በላይ ሰዎች በውሻው ታማኝነት ላይ አስተያየታቸውን ሲሰጡ ነበር። አንድ ሌላ ግለሰብም "ይህ ትንሽ ውሻ በጣም ታማኝ ነው ፤ ቤተሰቦቼ ውሻ ነበራቸው ፤ ሁል ጊዜም ከትምህርት ቤቱ በር ላይ ይጠብቀኝ ነበር" ሲል የራሱን ተሞክሮ ያስታውሳል። ሌላኛው አስተያየት ሰጭም "ውሻው በመንገዱ መሃል መቆሙ በጣም አደገኛ ነው፤ የሆኑ ሰዎች በማደጎ እንደሚወስዱትና እንደሚያሳድጉት ተስፋ አደርጋለሁ" ሲል የውሻው ደህንነት እንደሚያሳስበው ገልጿል። ይሁን እንጂ ይህ አጋጣሚ በቻይና የመጀመሪያው አይደለም። ከዚህ ቀደም አንድ ሌላ ውሻም አሳዳጊው ከስራ ወጥቶ ወደ ቤቱ ሲሄድ የባቡር ጣቢያ ላይ ቆሞ ይጠብቀው ነበር። በጃፓንም ከመቶ ዓመታት በፊት ባቡር ጣቢያ እየቆመ አሳዳጊውን የሚቀበል ውሻ አሳዳጊው ከሞተ በኋላም ተግባሩን ለ9 ዓመታት ቀጥሎ ነበር።
57291560
https://www.bbc.com/amharic/57291560
ስኮትላንድ ነዋሪ አልባውን ደሴት የሚጠብቅ ሠራተኛ እያፈላለገች ነው
ስኮትላንድ ውስጥ የሚገኝ አንድ ነዋሪ አልባ ደሴትን የሚጠብቅ ሠራተኛ እየተፈለገ ነው።
አይል ማርቲን የተባለው ደሴት ውስጥ የሚኖር ሰው የለም። የሚቀጠረው ሠራተኛ ኃላፊነት ደሴቱን መንከባከብና ለጎብኚዎች ዝግጁ ማድረግ ይሆናል። ከሰዎች ራቅ ብለው በብቸኝነት መኖር ለሚሹ ሰዎች ይህ ሥራ ሁነኛ አማራጭ ይመስላል። ለዚህ ሥራ የሚያመለክቱ ሰዎች ብቻቸውን ወይም ከውሃ አጣጫቸው ጋር ደሴቱ ውስጥ መኖር ይፈቀድላቸዋል። በደሴቱ ውስጥ ሁለት የባህር ዳርቻዎች፣ ጎጆ ቤት ውስጥ የሚገኝ ሙዚየም እና ለአዕዋፍት ቅኝት የሚመች ተራራ ይገኛል። በየዓመቱ መስከረም ላይ ሰባት ቀናት የሚቆይ ፌስቲቫል በደሴቱ ይካሄዳል። በጎ ፍቃደኞች ጊዜያዊ ካፍቴሪያ ይከፍታሉም። አይል ማርቲን ትረስት የተባለ ማኅበር ደሴቱን በበላይ ጠባቂነት ይዞታል። እአአ በ1999 የተራድኦ ድርጅት የሆነው አይል ማርቲን ትረስት ደሴቱን ያገኘው በስጦታ ነው። ላለፉት 30 ዓመታት ደሴቱ ነዋሪ አልባ ነበር። አዲሱ ሠራተኛ ከ30 ዓመታት በኋላ በደሴቱ ለመኖር የመጀመሪያ ይሆናል። ደሴቱን ከፕላስቲክ መገልገያዎች ነጻ ለማድረግ ታቅዷል። የበላይ ጠባቂ ማኅበሩ ኃላፊ ቤኪ ቶምሰን ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ የሚቀጥሩት ሠራተኛ በደሴቱ ውስጥ የሚገኙትን የሕዝብ መጸዳጃዎችና መኖሪያ ቤቶች የማጽዳት፣ እንግዶችን ወደ ደሴቱ የመቀበልና እንግዶቹ የኮሮናቫይረስ መከላከያ መርሆችን እንዲተገብሩ ማስቻል ኃላፊነቱ ነው። ሥራው በቀን ውስጥ ወደ ሦስት ሰዓት ገደማ ይወስዳል። ሠራተኛው በነጻ ደሴቱ ውስጥ ከመኖር ባሻገር በሳምንት 150 ዩሮ ይከፈለዋል። 400 ኤከር ስፋት ያለው ደሴት ሌሎችም ደሴቶች በአቅራቢያው ያዋስኑታል። ከዚህ ቀደም በውስጡ ገዳምና የዱቄት ማምረቻ ነበረው። አሁን ደግሞ የአዕዋፍት ማቆያ ተብሎ ተከልሏል። ወደ ደሴቱ የሚያቀኑ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ የሚያሳልፉት ከቤት ውጪ ነው። ይህም ከተፈጥሮ ጋር ለመተሳሰር እድል ይሰጣቸዋል። በደሴቱ የሞቀ ውሃ የለም። የኤሌክትሪክ ኃይሉም ስልክና ላፕቶፕ ቻርጅ ከማድረግ የዘለለ አቅም የለውም። ደሴቱን ለመጠበቅ ለወጣው ሥራ የሚያመለክት ሰው ጀልባ መቅዘፍና ሌሎችም በደሴት ለመኖር የሚያስፈልጉ ክህሎቶችን ማወቅ ይጠበቅበታል። "ሠራተኛው በደሴቱ መኖር ካስደሰተው የአትክልት እርሻውን መንከባከብና ሌላም ሥራ መሥራት ይችላል። ቦታው ሰላማዊና የተረጋጋ ስለሆነ ይወደዳል። መኪና የለም፤ የመንገድ ዳር ጫጫታ የለም። ለማረፍ የተመቸ ነው" ብለዋል ቤኪ ቶምሰን።
56828900
https://www.bbc.com/amharic/56828900
ቲክቶክ ከህጻናት ላይ ከሚሰበስበው መረጃ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ክስ ቀረበበት
ቲክቶክ የህጻናት መረጃ የሚሰበስብበትንና የሚጠበቀምበትን መንገድ በተመለከ በቀድሞ የእንግሊዝ የህጻናት ኮሚሽነር አን ሎንፊልድ ክስ ቀረበበት።
ክሱ የቀረበው በዩናይትድ ኪንግደም እና አውሮፓ ሕብረት ውስጥ በሚገኙ በሚሊየኖች በሚቆጠሩ ህጻናት ስም ሲሆን ታዋቂው የማኅበራዊ ሚዲያ መተግበሪያ ትልቅ ጫና ሊደርስበት እንደሚችል ተገምቷል። ክሱ ተቀባይነት አግኝቶ ቲክቶክ ጥፋተኛ የሚባል ከሆነ እነዚህ ህጻናት በሺዎች የሚቆጠር ፓውንድ በካሳ መልክ ሊከፈላቸው ይችላል። ቲክቶክ በበኩሉ ክሱ መሰረት የሌለው እንደሆነና እስከ መጨረሻው እንደሚከራከር ገልጿል። ክሱን የመሰረቱት ጠበቆች እንደሚሉት ቲክቶክ እንደ ስልክ ቁጥር፣ ቪዲዮ፣ አድራሻ እና አሻራ ጭምር ያሉ የህጻናትን የግል መረጃ ያለእውቅናቸው አልያም ያለቤተሰቦቻቸው እውቅና ይወስዳል። መረጃውን ለምን እንደሚጠቀመውም ግልጽ አላደረገም ብለዋል። ይህንን ተከትሎ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን በማጋራት የሚታወቀው ቲክቶክ "የግል መረጃ እና ደኅንነት የድርጅታችን ቀዳሚ ኃላፊነት ነው። ይህንን ለመቆጣጠርም ጠንከር ያሉ ፖሊሲዎች፣ አሰራሮችና፣ ቴክኖሎጂዎች አሉን። ወጣቶችም ሆኑ አዋቂዎች የተጠቃሚዎቻችንን መረጃዎች እንጠብቃለን። የቀረበብን ክስ መሰረተ ቢስ ነው፤ እኛም እስከመጨረሻው እንታገለዋለን" ብሏል። ቲክቶክ በመላው ዓለም እስከ 800 ሚሊዮን የሚደርሱ ተጠቃሚዎች ያሉት ሲሆን፤ ቲክቶክን የሚያስተዳድረው 'ባይትዳንስ' የተባለው ድርጅት ባለፈው ዓመት ብቻ በቢሊዮን የሚጠሩ ዶላሮችን አትርፏል። አብዛኛው ትርፉ የተገኘው ደግሞ ከማስታወቂያ ነው። ክሱ የተመሰረተው ከአውሮፓውያኑ 2018 ጀምሮ መተግበሪያውን ሲጠቀሙ በነበሩ ህጻናት ስም ሲሆን በዚህ ክስ መሳተፍ የማይፈልጉ ህጻናት ያለመካተት መብት አላቸው ተብሏል። የቀድሞዋ የእንግሊዝ የህጻናት ኮሚሽነር አን ሎንፊልድ ለቢቢሲ ሲናገሩ ምንም እንኳን ሌሎች ማኅበራዊ ሚዲያዎች የሰዎችን መረጃ ቢሰበስቡም ቲክቶክ ግን በተለየ መልኩ በከፍተኛ ሁኔታ መረጃ ይሰበስባል ብለዋል። "በዚህ አስቸጋሪ የወረርሽኝ ወቅት ህጻናት ከጓደኞቻቸው ጋር ለመገናኘት ቲክቶክን በጣም ይጠቀሙ ነበር። ነገር ግን ከአዝናኞቹ ቪዲዮዎችና ዳንሶች ጀርባ ያልታወቀ ተግባር እየተከናወነ ነው።" የቀድሞዋ ሚኒስትር አክለውም ቲክቶክ የህጻናትን ቤተሰቦች ጭምር ሆን ብሎ እና በተሳካ መልኩ በማሳሳት መረጃ ሲሰበስብ ነበር ብለዋል። በአውሮፓውያኑ 2019 የቻይናው ድርጅት የህጻናትን መረጃ በአግባቡ ባለመያዝ በሚል ክስ ቀርቦበት በፌደራል የንግድ ኮሚሽን 5.7 ሚሊየን ዶላር ቅጣት ተላልፎበት ነበር። ከዚህ በተጨማሪ ቲክቶክ ደቡብ ኮሪያ እና ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ የህጻናትን መረጃ ከመሰብሰብ ጋር በተያያዘ ምርምራ ተደርጎበታል። በዩናይትድ ኪንግደም የመገናኛ ብዙሃንን የሚቆጣጠረው 'ኦፍኮም' የተሰኘው ተቋም በሰራው ጥናት መሰረት በአገሪቱ ቲክቶክን ከሚጠቀሙ ታዳጊዎች መካከል 44 በመቶ የሚሆኑት ከስምንት እስከ 12 ዓመት እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው። በቲክቶክ ፖሊሲ መሰረት ግን እድሜያቸው ከ13 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት መጠቀም አይችሉም።
news-53196194
https://www.bbc.com/amharic/news-53196194
የኢንስታግራም ተጽዕኖ ፈጣሪው 400 ሚሊየን ዶላር በማጭበርበር ወንጀል ታሰረ
'ሃሽፓፒ' በሚል ስም የሚታወቀው ናይጄሪያዊው የኢንስታግራም ዝነኛ ሰው ራይመንድ ሊግባሎዲይ፤ 435 ሚሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ በማጭበርበር ወንጀል መታሰሩን የዱባይ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
ፖሊስ 'ፎክስ ሃንት 2' ሲል በጠራው ልዩ የወንጀል ምርመራ ዱባይ ውስጥ በተመሳሳይ የማጭበርበር ወንጀል ሌሎች 12 ሰዎች በቁጥጥር ሥር አውሏል፡፡ በዚህ የማጭበርበር ወንጀል በተለያዩ ክፍለ ዓለማት የሚገኙ 2 ሚሊየን ገደማ ሰዎች ተጠቂዎች እንደሆኑ ተገልጿል፡፡ ነዋሪነቱን ዱባይ ያደረገው ናይጄሪያዊ የማህበራዊ ሚዲያው ሰው፤ 'ሃሽፓፒ' የተሳካለት የንግድ ሰው እንደነበር በተለያዩ ጊዜያት ይናገራል፡፡ በሌላ በኩል የአገሪቷ ባለሥልጣናት እስሩን ለመፈጸም ያደረጋቸውንና አራት ወራት የፈጀውን የወንጀል ምርመራ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በማህበራዊ ሚድያ ገጻቸው አጋርተዋል፡፡ ቪድዮው 'ሃሽፓፒ' እና አጋሮቹ ሆቴላቸው እንዳሉ ፖሊስ ሰብሮ ሲገባ እና በቁጥጥር ሥር ሲያውላቸው ያሳያል። ፖሊስ፤ 'ሃሽፓፒ' በሐሰተኛ ደረሰኞች የገንዘብ ማጭበርበር፣ የሳይበር ማጭበርበር፣ የመረጃ ምንተፋ፣ የባንክ ማጭበርበር፣ ሃሰተኛ ማንነት በመጠቀም ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ውጭ ወንጀሉን ይሰራበት የነበረውን ድብቅ የኦንላይን ኔትወርክ ደርሸበታለሁ ብሏል፡፡ ቡድኑ የድርጅቶችን ኢሜል በመጥለፍ እንዲሁም ድረ ገጾችን በመቅዳት ገንዘቦች ወደ ራሱ የባንክ ሒሳብ ቁጥር እንዲገባ በማድረግም ተወንጅሏል፡፡ የዱባይ ፖሊስ መቼ ክስ እንደሚመሰረትባቸው ያለው ነገር የለም፡፡
news-54836979
https://www.bbc.com/amharic/news-54836979
የአሜሪካ ሴኔት ምርጫ ትንቅንቅ እስከ ጥር ሊቀጥል ይችላል
በጆርጅያ ሁለተኛ ዙር ውድድር ሊደረግ ስለሚችል የአሜሪካ ሴኔት ምርጫ ትንቅንቅ እስከ ጥር እንደሚቀጥል ተጠቁሟል።
የትኛውም እጩ 50 በመቶ ድምጽ አላገኘም። ሕጉ ደግሞ 50% ድምጽ ያስፈልጋል ይላል። ሁለተኛው ዙር ውድድር ጥር 5 ሊካሄድ ይችላል።አሁን ላይ ሪፐብሊካኖች 53 ለ 47 በሆነ መቀመጫ የሴኔቱን የበላይነት ይዘዋል። ዴሞክራቶች አራት ድምጽ በማግኘት የበላይ ለመሆን ተስፋ ጥለዋል። በሪፐብሊካኖች ደጋፊነት በምትታወቀው ጆርጅያ ዴሞክራቶች ሁለቱንም ድምጽ ካገኙ ሴኔቱ እኩል 50-50 ይሆናል። ከሴኔት ተወዳዳሪዎቹ አንዱና አሁንም በሴኔቱ መቀመጫ ያላቸው ሪፐብሊካን ዴቪድ ፕሩድ፤ ከ50 በመቶ በታች ድምጽ ነው ያገኙት። ተፎካካሪያቸው ዴሞክራቱ ጆን ኦሶፍ እና የሊበሬሽን ፓርቲ ሼን ሀዝል ናቸው። እስካሁን 98% ድምጽ ተቆጥሯል። የዴቪድ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን መሪ ቤን ፌይ እንደሚያሸንፉ ተናግረዋል። የጆን ኦሶፍ ቡድን ሁለተኛ ዙር ውድድር ሲካሄድ ባለ ድል እንደሚሆኑ ገልጸዋል። በጆርጅያ ሌሎቹ የሴኔት ተወዳዳሪዎች ማለትም ዴሞክራቱ ራፋኤል ዋርኖክ 32.8% አግኝተዋል። በሁለተኛው ዙር 26% ካገኙት ሪፐብሊካን ኬሊ ሎፈር ጋር ይወዳደራሉ። ለውድድር ከቀረቡት 35 መቀመጫዎች 23ቱ በሪፐብሊካኖች፤ 12ቱ በዴሞክራቶች የተያዘ ነው። ዴሞክራቶች ብዙ መቀመጫ ለማግኘት ቢጠብቁም፤ ከኮልዶናዶ ሁለት ወንበር አንዱን ብቻ ነው ያገኙት። በሌላ በኩል ለዘብተኛ ሪፐብሊካኗ ሱዛን ኮለንስ ከዴሞክራቷ ሳራ ጊዶን ጋር ከፍተኛ ፉክክር ይጠብቃቸዋል። ዴሞክራቶች ላለፉት ስድስት ዓመታት ሴኔቱን መቆጣጠር አልቻሉም።
news-52103782
https://www.bbc.com/amharic/news-52103782
የኮሮናቫይረስ ስርጭትና አንዳንድ የኢትዮጵያ ሆስፒታሎች ያሉባቸው ተግዳሮቶች
የኮሮናቫይረስ ሥርጭትን ለመግታት እንዲችሉ ሆስፒታሎች ያሉባቸውን ጫናዎች ለማቅለል ያሰችላል ያሏቸውን እርምጃዎችን እየወሰዱ ነው።
ከእነዚህ መካከልም፤ መጨናነቆችን ለመቀነስ ተመላላሽ ታካሚዎችና ጊዜ የሚሰጡ ሕመም ያለባቸው ሰዎች ባሉበት አካባቢ ባሉ ጤና ጣቢያዎች አገልግሎት እንዲያገኙ፣ የአስታማሚ ቁጥሮችን መቀነስ፣ የእጅ ንፅህና መጠበቂያዎችን ማቅረብ እና ለይቶ ማቆያዎችን ማዘጋጀት ይገኙበታል። ይህንን በተመለከተም በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ሆስፒታሎች እያደረጉ ስላለው ዝግጅት ጠይቀናል። ፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተሩ ዶ/ር የሰውበላይ ምናለ ሆስፒታሉ ከዚህ በፊት ሲጠቀምባቸው የነበሩ የፊት መሸፈኛ ጭንብልና ጓንቶች መኖራቸውን ገልፀው፤ እስካሁን የእነዚህ ግብዓት ችግር እንዳልገጠማቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ በሆስፒታሉ ውስጥ በተዘጋጀ ለይቶ ማቆያ ውስጥ በቫይረሱ ተጠርጥረው የሚገቡ ሰዎችን ክትትል ለማድረግ ግን ቫይረሱን ለመከላከል ተብሎ የሚለበሰው ሙሉ የህክምና ልብስ እንደሌላቸው ገልፀዋል። ሆስፒታሉ ከዚህ ቀደም የኦክስጅን እጥረት እንደነበረበት ያነሳንላቸው ዶ/ር የሰውበላይ፤ የአማራ የኦክስጅን ማምረቻ በመኖሩ የሚያጋጥም ችግር ቢኖርም አሁን ባለው ሁኔታ ቶሎ ማዘጋጀት እንደሚቻል ገልፀው፤ ለወደፊቱ ግን ምርቱን መጨመር እንደሚገባ ጠቁመዋል። ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ኑርዬ ሀሰን እንደገለፁልን፤ የኮሮናቫይረስ ሥርጭትን ለመግታት የደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ካሳለፋቸው ውሳኔዎች መካከል፤ እድሜያቸው ከ55 በላይ የሆኑና የተለያዩ አባባሽ ህመሞች ያሉባቸው የጤና ባለሙያዎች ለሁለት ሳምንት እረፍት እንዲወስዱ ማድረግ ነው። ሜዲካል ዳይሬክተሩ እንደሚሉት የባለሙያ እጥረት እንዳይከሰትም የማሸጋሸግ ሥራዎች ተከናውነዋል። ይሁን እንጅ የንፅህና መጠበቂያ የሚውል አልኮል ቢኖርም፤ ለጤና ባለሙያዎች የሚሆኑ የፊት ጭንብሎች እጥረት ግን ከፍተኛ ነው ብለዋል። በመሆኑም ሆስፒታሉ ከዚህ በፊት ከመድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ የገዛቸውንና ከአንድ ጊዜ በላይ አገልግሎት ላይ የማይውሉ ጭንብሎችን ከባዶው ይሻላል በማለት በድጋሚ ለመጠቀም መገደዱን ዶ/ር ኑርዬ ገልጸዋል። መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል በመደወላቡ የኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል አጠቃላይ ሐኪምና መምህር የሆኑት ዶ/ር ኦላና ዋቆያ በሆስፒታሉ በኮሮናቫይረስ የተጠረጠሩ ሁለት ሰዎችን ውጤት እየተጠባበቁ መሆኑን ገልፀው፤ ለባለሙያዎች እንደ ጭምብልና ጓንት ያሉ የህክምና ቁሳቁስ እጥረት መኖሩን ለቢቢሲ አስረድተዋል። በቫይረሱ ከተጠረጠሩት ታካሚዎች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ላላቸው ባለሙያዎችም ሆነ በአጠቃላይ የሆስፒታሉ ባለሙያዎች ራሳቸውን ለመጠበቅ የሚያስችሉ ቁሳቁሶች የሉም ብለዋል። "አንዴ ተጠቅመን ማስወገድ ያለብንን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ (ጭንብል) ለሳምንት ያህል እየተጠቀምን ነው" ሲሉም ያለውን ችግር ገልጸዋል። ይህንንም አጥተው ያለምንም መከላከያ የሚሰሩ ባለሙያዎች መኖራቸው ትልቅ ስጋት ነው ብለዋል። አርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ተመስገን ተሾመ በሆስፒታሉ በኮሮናቫይረስ የተጠረጠሩ ሰዎች በከተማው ወደተዘጋጀው ለይቶ ማቆያ እስከሚገቡ ድረስ ለሁለት ሰዓታት ያህል የሚያቆዩበት ቦታ መኖሩን ገልፀውልናል። በሆስፒታሉ ሌሎች ታካሚዎች በመኖራቸው ተጠርጣሪዎቹ ከዚህ ሰዓት በላይ እንዲቆዩም አይደረጉም ብለዋል። በቫይረሱ የተያዘ ሰው ቢገኝና የመተንፈሻ ችግር ካለበት አጋዥ የመተንፈሻ መሳሪያ (ቬንትሌተር) የተወሰነ በሆስፒታሉ ቢኖርም፤ የታማሚ ቁጥር እየጨመረ ከመጣ ግን እጥረት ሊያጋጥም ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ነግረውናል። እነዚህ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል ለሕዝቡ የህክምና አገልግሎት የሚሰጡ ሆስፒታሎች የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ቢከሰት ህሙማንን ለማከምና ለመንከባከብ የሚያስፈልጉ መሰረታዊ ቁሳቁሶች እጥረት እንዳለባቸው አመልከተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በጽህፈት ቤታቸው በኩል ዛሬ ባወጡት መግለጫ ላይ እንዳመለከቱት "የመከላከያና የሕክምና ቁሳቁሶችን በየቦታው ለማዳረስ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ይገኛል" ብለዋል። ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፌደራልና የክልል አካላትም በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚያስፈልጉ መገልገልገያዎችንና መድኃኒቶችን ለማሟላት ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ቢናገሩም፤ ባለሙያዎቹ ግን አቅርቦቶቹን በአፋጣኝ ማግኘት ካልቻሉ ሊፈተር የሚችለው ችግር እያሳሰባቸው መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
news-54157836
https://www.bbc.com/amharic/news-54157836
ናይጄሪያ፡ በተቀደሰች ሥፍራ የወሲብ ፊልም የሠራው ግለሰብ ታሠረ
በደቡባዊ ናይጄሪያ በአንድ ቅድስት በተባለች ሥፍራ የወሲብ ፊልም የቀረፀው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ፖሊስ አሰታወቀ።
ኦሹን ኦሶግቦ የተባለችው ቅድስት ጫካ በተባበሩት መንግሥታት የዓለም ቅርስ ተብላ የተመዘገበች ሥፍራ ናት። ኦሹን የዮሩባ ጎሳ አማልክት እንደሆነች ይታመናል። ፖሊስ እንዳለው ቲበላክ ሆክ በተሰኘ ቅፅል ስሙ የሚታወቀው ቶቢሎባ ጆላሾ ጫካው ውስጥ የወሲብ ፊልም በመቅረፁ ነው ለእሥር የተዳረገው። ግለሰቡም ሆነ ጠበቃው እስካሁን ስለጉዳዩ አስተያየት አልሰጡም። ኦሹን ኦሶግባ ጫካ ኮሶግባ ከተማ ወጣ ብሎ የሚገኘ በሕብረተሰቡ ዘንድ ቅድስት ተደርጋ የምትቆጠር ሥፍራ ናት። በርካታ ተከታዮች ያሉት የወሲብ ፊልም ሠሪው ጆላሾ በማሕበራዊ ሚድያ ገፆቹ ላይ የለቀቀው ቅንጭብ ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ ኦሹን ለተሰኘችው አማልክት እንደሚሰግዱ ሰዎች ለብሶ ይታያል። ምንም እንኳ ወደ ጫካው ለመግባት ቀላል ቢሆንም ሰውዬው ምስሉን በየት በኩል ገብቶ መቼ እንደቀረፀው እስካሁን አልታወቀም። የፖሊስ ቃል አቀባይ ኦፓሎላ የሚሲ፤ ፊልም ሠሪው ፈፀመ በተባለው ወንጀል ላይ ምርመራ ከተጠናቀቀ በኋላ ፍርድ ቤት ይቀርባል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሰውዬው የአካባቢውን ሰላም አደጋ ላይ በመጣል ሊከሰስ ይችላልም ብለዋል። በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ አምላኪዎች ከናይረጄሪያና ከሌሎች አካባቢዎች ወደ ጫካው በመምጣት ለወንዝ አምላኳ ኦሹን ስጦታዎች ያበረክታሉ። ከኦሹን አምላኪዎች አንዷ የሆነችው የሚ ኤሌቢቦን ሰውዬው ጫካው ውስጥ የወሲብ ፊልም በመቅረፁ የሥፍራዋን ቅድስትነት አርክሷል ትላለች። ከፖሊስ ምርመራ በኋላ ጥንታዊ አምላኪዎች ሰውዬው ይገባዋል የሚሉትን ቅጣት እንደሚጥሉበት የሚ ለቢቢሲ ትናገራለች። በአውሮፓውያኑ 2003 ዓ.ም. በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ሆና የተመዘገበችው የኦሹን ኦሶግቦ ቅድስት የመቃብር ሥፍራ በምዕራባዊ ናይጄሪያ ጥንታዊ ከሚባሉ ጫካዎች አንዱ ነው። በዮሩባ ጎሳ አባላት እምነት መሠረት ኦሹን ሳንጎ ከተሰኘው አምላክ ሚስቶች መካከል አንዷ ናት። አማኞች በየዓመቱ ወደ ሥፍራው እየመጡ መስዋዕት የሚያቀርቡላት ይህ እምነት 600 ዓመት የዘለቅ እንደሆነ ይነገራል። ለሁለት ሳምንታት የሚቆየው ይህ ክብረ በዓል በዮሩባ ሰዎች ዘንድ ትልቁ በዓል ነው።
45109052
https://www.bbc.com/amharic/45109052
በአውስትራሊያ ከባድ ድርቅ አጋጠመ
ከአውስትራሊያ ግዛቶች በሕዝብ ብዛት ትልቋ የሆነቸው ኒው ሳውዝ ዌልስ ሙሉ በሙሉ በድርቅ መመታቷን ባለስልጣናት ተናገሩ።
ደረቃማው የበጋ ወቅት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በምሥራቃዊ አውስትራሊያ የከፋ የተባለውን ድርቅ አባብሶታል። የኒው ሳውዝ ዌልስ ግዛት በአውስትራሊያ ከሚገኘው የእርሻ ምርት ውስጥ አንድ አራተኛውን የምታቀርብ ሲሆን፤ የሃገሪቱ ባለስልጣናት ዛሬ እንዳስታወቁት ግዛቲቱ ሙሉ በሙሉ በድርቅ ተመትታለች። ይህንን ድርቅ ለመቋቋምም የግዛቲቱ አስተዳደርና የፌደራል መንግሥቱ 430 ሚሊዮን ዶላር የአስቸኳይ ጊዜ የእርዳታ ገንዘብ መድበዋል። • ጤፍ ሃገሩ የት ነው? ደቡብ አፍሪካ? አውስትራሊያ? . . . • ካለሁበት 18፡ አውስትራሊያ መጥቼ እርቃናቸውን የሚሄዱ ሰዎችን ሳይ በጣም ደነገጥኩኝ ይህ የተመደበው ገንዘብም በድርቁ ምክንያት ምርታቸውን አጥተው ለችግር ለተጋለጡ አርሶ አደሮች ድጋፍ፣ የውሃ እጥረትን ለመቋቋምና ለእንስሳት መኖ ለማቅረብ እንደሚውል ተገልጿል። ባለፈው እሁድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማልከም ተርንቡል አውስትራሊያ "ድርቅ የሚደጋገምባት ምድር" እየሆነች እንደሆነ አስጠንቅቀው ነበር። ባለፈው ሐምሌ ወር በኒው ሳውዝ ዌልስ ግዛት ውስጥ በጣም ዝቅተኛ የዝናብ መጠን መመዝገቡን ባለስልጣናት ተናግረዋል። በቀጣዮቹ ወራትም ከተለመደው የበለጠ ደረቅ የአየር ሁኔታ እንደሚኖርም የአየር ትንበያ አመልክቷል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት አርሶ አደሮች ተደጋግሞ የሚከሰተው ድርቅ "የአውስትራሊያ የአየር ንብረት አካል" መሆኑን እንደተገነዘቡ ነገር ግን ድጋፍ እንሚያስፈልጋቸው ገልፀዋል። በኒው ሳውዝ ዌልስ የሚገኙ አርሶ አደሮች ለአንድ የጭነት መኪና የእንስሳቶች መኖ እስከ 10ሺህ የአውስትራሊያ ዶላር እያወጡ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል። "እንደዚህ አይነት አስቸጋሪ ጊዜ ሲያጋጥም መንግሥት ማድረግ የሚጠበቅበት ለአርሶ አደሮቹ ድጋፍ ማድረግ ነው" ሲሉ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአውስትራሊያ ብሮድካስቲን ኮርፖሬሽን ተናግረዋል። ከኒው ሳውዝ ዌልስ ባሻገር አጎራባቿ የኩዊንስላንድ ግዛት ግምሽ ክፍልም በድርቅ ተመትቷል። በተጨማሪም የቪክቶሪያና ሳውዝ አውስትራሊያ ግዛቶች የተወሰኑ ክፍሎች ደረቅ የአየር ሁኔታ አጋጥሟቸዋል።
news-51627085
https://www.bbc.com/amharic/news-51627085
የቀድሞ የግብጽ ፕሬዝደንት ሆስኒ ሙባረክ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
የቀድሞ የግብጽ ፕሬዝደንት ሆስኒ ሙባረክ በ91 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
ሆስኒ ሙባረክ ህይወታቸው ያላፈው ግብጽ ካይሮ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ ህክምና እየተደረገላቸው ሳለ ነው። ሆስኒ ሙባረክ እ.አ.አ. 2011 ላይ በግብጽ የአረብ አብዮት ከተቀሰቀሰ በኋላ በአገሪቱ ጦር ከሰልጣናቸው እንዲነሱ ተደርገዋል። የቀድሞ ፕሬዝደንት ግብጽን ለሦስት አስርት ዓመታት መርተዋል። የአረብ አብዮት በተቀሰቀሰ ወቅት ለተቃውሞ በወጡ ሰልፈኞች ላይ በተወሰደው እርምጃ በተባባሪነት ተጠያቂ ተደርገው የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላልፎባቸው ነበር። ይሁን እንጂ ከሦስት ዓመት በፊት የተመሰረቱባቸው ክሶች ውድቅ ተደርገው ነጻ ወጥተው ነበር። የቀድሞ ፕሬዝደንት ህልፈተ ህይወትን ይፋ ያደረገው የግብጽ ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ነው። ሙባረክ ከአንድ ወር በፊት የቀዶ ህክምና ማድረጋቸውን እና በጽኑ ህሙማን ማቆያ ውስጥ መቆየታቸውን የቤተብ አባሎቻቸው ለግብጽ መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል። ሙባረክ ከልጅ ልጃቸው ጋር በሆስፒታል ሳሉ የተነሱት ፎቶግራፍ በርካቶች ተጋርተውት ነበር። ባሳለፍነው ቅዳሜ የሙባረክ የልጅ ልጅ የሆነው አላ፤ አያቱ በጽኑ ሕሙማን ማቆያ ውስጥ እንደሚገኙ አረጋግጦ ነበር። እአአ 1928 የተወለዱት ሙባረክ፤ በወጣትነት እድሜያቸው የግብጽ አየር ኃይልን የተቀላቀሉ ሲሆን፤ የአረብ-አስራኤል ጦርነት ወቅት ጉልህ ሚና ተጫውተዋል። ፕሬዝደንት አንዋር ሳዳት መገደላቸውን ተከትሎ ሙባረክ የግብጽ ፕሬዝደንት በመሆን መንበረ ስልጣኑን ይዘዋል።
news-44488852
https://www.bbc.com/amharic/news-44488852
ግራ መጋባትን የፈጠረው የህወሓት መግለጫ
ከእሑድ አንስቶ ለሦስት ተከታታይ ቀናት በር ዘግቶ የተሰበሰው የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ረቡዕ አመሻሽ ላይ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል።
ህወሀት የኢህአዴግ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በኢትዮ-ኤርትራ ጉዳይና ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች ጋር በተያያዘ የተወሰኑ ውሳኔዎች ወደ ኢሕአዴግ ምክር ቤት ሳይቀርቡ፣ አጋር ድርጅቶች ሳይሳተፉበትና ሳይወያዩበት እንደመጨረሻ ውሳኔ መወሰዱ እንደ ጉድለት እንደሚያየው አስታውቋል። ከዚህም በተጨማሪ ግንባሩ ህገ-ደንብ እና ተቋማዊ አሰራር ያልተከተሉ የአመራር ምደባዎችን እንዲያርም ጠይቋል። የመግለጫው አንቀጾች ታዲያ መልስ ከመስጠት ይልቅ ጥያቄን የሚጭሩ ሆነዋል ይላሉ ታዛቢዎች። በቅርቡ የኢትዮጵያዊያን ሃገራዊ ንቅናቄ (ኢሃን) የሚል አዲስ ፓርቲ የመሠረቱት አቶ ይልቃል ጌትነት (ኢንጂነር) በአራቱ ፓርቲዎች መካከል የነበረው የውስጥ ሽኩቻ ህወሓት ለመጀመሪያ ጊዜ "አደባባይ ይዞት ወጥቷል" ይላሉ። ነገር ግን የአራቱ ፓርቲዎች ፍቺ ቶሎ ሊፈጸም አይችልም የሚሉት አቶ ይልቃል ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ አንዳቸው አንዳቸውን ስለሚፈልጉ ነው በማለት ምክንያታቸውን ያስቀምጣሉ። በመቀጠልም "ዞሮ ዞሮ ግን እየተዳከሙ ይሄዳሉ። በአገር ደረጃም ጉዳት ካደረሱ በኋላ ግን መፈራረሳቸው አይቀርም። ሽኩቻውና መነታረኩ ይቀጥላል። ከሕዝብ ጥያቄ ጋር ተዳምሮ የኢህአዴግ ፍጻሜ ይሆናል" ይላሉ። ለአቶ ይልቃል እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ሦስቱ ፓርቲዎች ህወሓት ለክቶ በሚሰጣቸው ነጻነት መጠን ነበር ሲተነፍሱ የኖሩት። አሁን ግን እስከዛሬው የነበረው ዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት፣ የህወሓት ነጻ አውጪነትና የሌሎች ነጻነት ተቀባይነት ከሕዝብ ጥያቄ ጋር ጉልበት አግኝቶ እየተሸረሸረ መሆኑን ይገልፃሉ። ብአዴን በከፊል ኦህዴድም በሰፊው በሕዝብ ድጋፍ ወደፊት እንዲመጡና ህወሓትን እንዲገዳደሩት አስችሏቸዋል የሚሉት አቶ ይልቃል ውስጣዊ ሽኩቻው በሰፊው እንደሚቀጥልም ይጠብቃሉ፤ ለእርሳቸው የግንባሩ የመፈራረስ አደጋም ቅርብ ነው። የአብይ አህመድ አዲሱ ፈተና፤ህወሓት? "ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በቆራጥ እርምጃ ወደ ትግሉ ይገባሉ ብዬ አላስብም " ይላሉ አቶ ይልቃል። ለዚህም ምክንያት ነው ያሉትን ሲያስቀምጡ "ከልጅነታቸው ጀምሮ ሲያልሙት የነበረውን ሥልጣን ከህወሓት ጋር በመላተም ሊያጡት ስለማይሹ " በማለት መሞገቻ ሃሳብ ያቀርባሉ። "በእኔ ግምት ዶክተር አብይ ሥልጣናቸውን ማስረገጥ ስለሚወዱ ይቺን ሁለት ዓመት እንደምንም አመቻምቸው የሚቀጥለውን አምስት ዓመት ጠቅላይ ሚኒስትርነትን ማረጋገጥ ይሻሉ። በዚህም ምክንያት በአሁኑ ሰዓት ከህወሓት ጋር የለየለት መቆራቆዝ ውስጥ መግባት አይፈልጉም።" የቀድሞ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ ግርማ ሰይፉ በበኩላቸው ''የህወሓት ድምጹን ተነጥሎ ማሰማቱ ያልተለመደ ቢሆንም ክፋት የለውም'' ይላሉ፤ ''መለመድም አለበት'' ሲሉ ያስረግጣሉ። "ህወሓቶች በአሁኑ ሰዓት ተገፍተናል የሚል ስሜት አላቸው። ስለተገፉ ሳይሆን ከነበራቸው ከፍተኛ ተጠቃሚነት ገሸሽ ስለተደረጉ ነው። ሁሉን ነገር እኛ ካልያዝነው ልክ አይሆንም ብለው ነው የሚያስቡት። ግብጾች ይሄን ያህል ውሃ ያስፈልገናል ይላሉ። ሌላው ግን ምንም አያስፈልገውም ብለው ያስባሉ' ህወሃትም እንደዚያ ነው የሚያስበው" በማለት ሃሳባቸውን ያብራራሉ። ነባር አባላትና እውቅና አቶ ሰይፉ "ህወሓት ቢፈልግ ሜዳሊያ ይሸልማቸው። ነገር ግን ዕድሜያቸው የገፉ ሰዎችን ጡረታ የማውጣት ሥራ መንግሥታዊ አሠራር እንጂ የፓርቲ ሥራ አይደለም። ህወሓትም በዚህ ሊከፋው አይገባም" ይላሉ። ''እውነት ለመናገር አሁን ይቅር እንባባል እየተባለ ካልሆነ በስተቀር ብዙዎቹ የሌብነት ዕውቅና ነው ሊሰጣቸው የሚገባው'' ሲሉም ጉዳዩን የሚያዩበት መንገድ የተለየ መሆኑን ያስረዳሉ። በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህሩ አቶ መሃሪ ዮሃንስ በበኩላቸው ከመግለጫው ምንም የተለየ ነገር እንዳላገኙ በመጥቀስ፤ የብአዴን ተሞክሮን አንስተው ከዚህ በፊትም ቢሆን ከኢህአዴግ መግለጫ ጋር የማይስማሙ ሃሳቦችን ሌሎች ፓርቲዎች አንጸባርቀው ነበር ሲሉ ሃሳባቸውን ያጠናክራሉ። ይህን የህወሓት መግለጫ በማንሳትም ከዚህ በፊት ህወሓት ተገቢ ያልሆነ ቦታ ይዞ እንደነበረና ይህንን ለማስተካከል እንደሚደረግ እርምጃ ከሆነ ግን እንደሚቀበሉት ይገልፃሉ። አክለውም "ዶክተር አብይ እና ሌሎች የኢህአዴግ አባላት የህወሓት አባላትን የማጥቃት እርምጃዎች የሚወሰዱ ከሆነ እናሳስባቸዋለን የሚል አይነት መልዕክት ያለው ይመስለኛል'' ብለዋል። ''ኢህአዴግ ቀውስ ውስጥ እንደገባና ሃገሪቱንም ቀውስ ውስጥ እንደከተታት ይታወቃል'' ያሉት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀ-መንበር ዶክተር መረራ ጉዲና፤ ከዚህ ቀውስ ለመውጣት እየተደራጀ እንደሆነ ይታወቃል ይላሉ። የአቶ መሃሪን ሃሳብ የሚጋሩት ዶክተር መረራ፤ ከዚህ አልፎ ግን አንዱ ድርጅት እንዲህ ሆኗል፤ ሌላኛው ወዲህ ሄዷል የሚባል ነገር በእኔ እይታ ገና ነው ብለዋል ። ''የህወሓት መግለጫ ከዚህ በፊት ኢህአዴግ ሲሰራበት የነበረውን አሰራር የጣሰ ነው ብዬ አላምንም'' ያሉት ዶክተር መረራ፤ ''ፓርቲው ችግር ውስጥ ስለሆነ እንደድሮው የውስጥ ልዩነቶቹን ደብቆ ማቆየት ስላልቻለ ነው'' ይላሉ።
52306187
https://www.bbc.com/amharic/52306187
ኮሮናቫይረስ፡ "እናቴን በእናቶች ቀን በኮሮናቫይረስ አጣሁ"
የእናቶች ቀን ሳምንታት ሲቀሩት አያ (ለዚህ ጽሑፍ ሲባል ስሟ ተቀይሯል) ለእናቷ ስጦታ እያፈላለገች ነበር።
የ33 ዓመቷ አያ ለእናቷ ስጦታ ስትፈልግ፤ እናቷን በእናቶች ቀን እንደምታጣ ፈጽሞ አልገመተችም ነበር። የአያ እናት ግብፅ ውስጥ ኮሮናቫይረስ ከተገኘባቸው የመጀመሪያዎቹ አስር ሰዎች አንዷ ነበሩ። እስካሁን 2,000 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው 160ው ሞተዋል። "ላቅፍሽ እፈልጋለሁ፤ ግን አልችልም" የአያ እናት ለሳምንት ያህል ተዳክመው ነበር። ነገር ግን በነበሩበት ሁኔታ ሕይወታቸው ያልፋል ብላ አላሰበችም። መሞታቸውን ስትሰማ ራሷን ስታለች። "ወንድሜ እየተሻላት ነው ብሎኝ ነበር። ድና ለልደቷ ወደ ቤት እንደምትመለስ ተስፋ አድርገን ነበር። የእናቶች ቀንና ልደቷን አጣምረን ልናከብርላት አስበን ነበር። ወንድሜ መሞቷን ሲነግረኝ ውሸትህን ነው አልኩት።" የአያ እናት በደቡብ ካይሮ በሚገኘው ሄልዋን ግዣት ወዳለ ሆስፒታል የተወሰዱት ከህልፈታቸው አንድ ቀን በፊት ነበር። የ69 ዓመቷ እናት ከዚያ በፊት ለሳምንት ያህል በግል ህክምና መስጫ ውስጥ ነበሩ። መጀመሪያ ባደረጉት ምርመራ ኮሮናቫይረስ 'የለብዎትም' ተብለው ነበር። ከዚያ ግን ከሁለት ቀናት በኋላ በድጋሚ ተመረመሩ። አያ እናቷን ያዋራችው ማክሰኞ ቀን ነበር። "የዛን ቀን ከአባቴ ጋር ነበርኩ፤ እሁድ ዕለት የደም ስር ምርመራ አድርጎ ስለነበር አብሬው ነበርኩ" ትላለች። አያ እናቷን ሳትሰናበታቸው መሞታቸው እጅግ ጎድቷታል። ሕይወታቸው ባለፈበት ቀን በመላው ግብፅ መስጊዶች እንዲዘጉ ትዕዛዝ ተላልፎ ነበር። በመስጊዶች ፀሎት ማድረግም ተከልክሎ ስለነበር የቀብር ፀሎቱን ራሷ ማድረግ ነበረባት። የእናቷን አስክሬን ከሆስፒታል ለማውጣት ረዥም ሰዓት መጠበቅ ስለነበረባት ቀብሩ የተፈጸመው ማታ ነበር። "ጥቂት ቤተሰብ ብቻ ነበር የተገኘው፤ ሁላችንም ጭንብል እና ጓንት አጥልቀን ነበር። የወንድሜ ሚስት እጄን ጥብቅ አድርጋ ይዛ 'ላቅፍሽ እፈልጋለሁ፤ ግን አልችልም' አለችኝ። "የወንድሜ ሚስት እናትም በሀዘን ተሰብራ ነበር። ግን አንዳችን ሌላውን ማጽናናት አልቻልንም። አባቴም እናቴን አልተሰናበታትም። ቀብሩ ላይ ቢገኝም አንድ ሳምንት አላያትም ነበር።" የአያ እናት ከሞቱ በኋላ አባቷም ኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸው እናቷ ይታከሙበት ወደነበረው ሆስፒታል ገብተዋል። አባቷ አገግመው ወደ ቤት የተመለሱት ከሳምንት በፊት ነው። አያ እና ወንድሟ ኮሮናቫይረስ ባይገኝባቸው ራሳቸውን አግልለዋል። "እንደ ቤተሰብ አንዳችን ሌላውን መደገፍ እንኳን አልቻልንም" ትላለች አያ። "እናቴ ሰማዕት ናት" የ31 ዓመቷ መሐንዲስ ረና ሳሜህ በኮሮናቫይረስ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች የሚዘከሩበት የዋትስአፕ ቡድን ፈጥራለች። የሞቱት ሰዎች እንዲፀለይላቸው ስማቸው ተጽፎ ይሰራጫል። ረና፤ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሞቱ ሰዎችን ስም ትሰበስባለች። ወዳጅ ዘመድ የሞተባቸው ሰዎችም ያጡትን ሰው ስም ይሰጧታል። "ሰዎች እየሞቱ ነው። መስጊዶች ተዘግተዋል። ለእኛ ደግሞ የቀብር ሥነ ሥርዓት ትልቅ ዋጋ አለው" ትላለች። የእስልምና አስተምሮት በቀብር ላይ ብዙ ሰዎች ሲገኙ ዋጋ አለው ይላል። ረና የዋትስአፕ ቡድኑን እንደፈጠረችው 256 አባላት ተቀላቅለዋል። ዋትስአፕ ከዚህ በላይ ሰዎች በአንድ ቡድን እንዲሰባሰቡ ስለማይፈቅድም፤ የፌስቡክ ገፅ ተከፍቷል። የፌስቡክ ገፁን የከፈተው የ30 ዓመቱ ነጋዴ ራሚ ሳአድ፤ በኮሮናቫይረስ በሞተ ሰው ቀብር ላይ በጣት የሚቆጠሩ ሰዎች ፎቶግራፍ አይቶ ልቡ እንደተነካ ይናገራል። ቀድሞ መሰል ሥነ ሥርዓቶችን የሚታደሙ በርካቶች ነበሩ። "ያየሁት ነገር ያሳዝናል፤ ስለዚህም የፌስቡክ ገፁን ከፈትኩ" ይላል። ገፁ በአስር ቀን 4,000 ተከታይ አፍርቷል። አያ እንደምትለው፤ የዋትስአፕ እና የፌስቡክ ገፆቹ፤ በርካታ ሰው ለሟቾች እንዲፀልይ ይረዳሉ። "ብዙዎች በእናቴ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸውልኛል። መቼ ስለእናቴ ህልፈት እንደሰሙ እንኳን አላውቅም። አራተኛ ክፍል አብሮኝ ይማር የነበረ ልጅ ሳይቀር ደውሎልኛል።" እንዲህ አይነት ድጋፍ ማግኘቷ እያጽናናት እንደሆነ ትናገራለች። "እንዲህ አይነቱ ተግባር እናቴን ሰማዕት ያደርጋታል፤ የሰው ድጋፍ ብርታትም ይሰጠኛል። እንዲህ አይነት ብርቱ ሰው መሆኔን አላውቅም ነበር። እናቴ በሌላ ሁኔታ ብትሞት ኖሮ ከሀዘኑ ፈጽሞ አልተርፍም ነበር።"
news-50633121
https://www.bbc.com/amharic/news-50633121
ለ12 ቀናት በሰዋራ ሥፍራ የቆዩት አውስትራሊያዊት በሕይወት ተገኙ
በአውስትራሊያ ገጠራማ ቦታ አንድት ሴት ከከተማ ውጭ ባለ ጥሻ አቅራቢያ ከ12 ቀናት በኋላ በሕይወት መገኘታቸው ተዘገበ። ግለሰቧ ብስኩት እና ከውሃ ጉድጓድ ውሃ እየተጎነጩ እንደቆዩ ታውቋል።
• በማርገዛቸው ከትምህርት ቤት የተባረሩት ተማሪዎች ተመረቁ • በህንድ በቡድን ተደፍራ የተገደለችው ዶክተር ጉዳይ ከፍተኛ ቁጣን ቀሰቀሰ ታምራ ማክቢዝ የተሰኙት እኝህ አውስትራሊያዊት እና ሌሎች ሁለት ሰዎች ሲጓዙበት የነበረው መኪና በአንድ ወንዝ ውስጥ በመግባቱ መውጣት ተስኗቸው ቆይተዋል። ሁለቱ ግለሰቦች እርዳታ ለማግኘት ሲሉ ተከፋፍለው በየፊናቸው ተሰማሩ። በዚያው አቅራቢያ ለመቆየት የወሰኑት ታምራ ማክቢዝ ሪሊይ ግን ከመኪናቸው አቅራቢያ ሲገኙ ሌሎቹ ሰዎች አሁንም የደረሱበት አልታወቀም። የ52 ዓመቷ ሴት፣ ክሌር ሆክሪግ እና ፕሁ ትራን ጋር በመሆን ከአገሪቷ ሰሜናዊ ግዛት አልሴ ስፕሪንግስ ከተሰኘ ከተማ አቅራቢያ እያሽከረከሩ ሳለ ነበር ከአንድ ትልቅ ወንዝ ዳርቻ የተደነቀሩት። የታምራ ማክቢዝ ውሻም አብራቸው ነበረች። ማክቢዝ ከሆስፒታል ከወጡ በኋላ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ለመውጣት ሲታገሉ ለሦስት ቀናት ያህል በመኪናው አቅራቢያ ቆይተዋል። "ለመውጣት ብዙ ጊዜ ሞክረናል፤ ነገር ግን ወንዙ ትልቅ በመሆኑ ልንወጣ አልቻልንም" ይላሉ እኝሁ ነፍሳቸው የተረፈላቸው ሴት። በዚያ ቀን አየሩ በጣም ይሞቅ ስለነበር መኪና ውስጥ ገባን ፤ ምሽቱንም መኪናው ውስጥ መተኛት ቻልን" የሚሉት ማክቢዝ በመኪና ውስጥ የያዙትን ምግብና መጠጥ ረሃባቸውን እንዳስታገሰላቸው ይናገራሉ። ከዚያ በኋላ ግን እርዳታ ለማግኘት ሲሉ ተከፋፈሉ። ትራንና ሆክሪጅ ወደ መንገዱ ለመሄድ አቀዱ። ማክቢዝ ግን ውሻቸው አብራቸው በመሆኗ እዚያው አቅራቢያ ለመቆየት ወሰኑ። ታዲያ ይህንኑ የተመለከተ አንድ የአካባቢው ነዋሪ አንድ ተሽከርካሪ ማየቱን በመጠቆሙ የአገሪቷ ሰሜናዊ ግዛት ፖሊስ ሄሊኮፕተር አሰማርቶ መፈለግ ጀመረ። ማክቢዝ ከመኪናቸው 1.5 ኪሎሜትር በሚርቅ ሥፍራ ታዩ። ወደ ሆስፒታል ተወስደው እያገገሙ ይገኛሉ። በአቅራቢያቸው ያለውን የጉድጓድ ውሃ እየጠጡ መሰንበታቸውም ነፍሳቸውን አቆይቶላቸዋል። ውሻቸው ግን ይገኝ አይገኝ የታወቀ ነገር የለም። ፖሊስ ቀሪዎቹን ግለሰቦችም መፈለጉን ቀጥሏል።
news-57184356
https://www.bbc.com/amharic/news-57184356
የኢትዮጵያ ወታደሮች 'የህወሓት ተዋጊዎችን ፍለጋ ሆስፒታል መፈተሻቸው' ተነገረ
የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት ባለፈው እሁድ ትግራይ አክሱም ከተማ ውስጥ ወደሚገኝ ሆስፒታል ገብተው ፍተሻ ማድረጋቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገበ።
ወታደሮቹ በታሪካዊቷ ከተማ ውስጥ ወደሚገኘው ሆስፒታል የገቡት የህወሓት ተዋጊ አባላትን ለመፈለግ እንደሆነ የዜና ወኪሉ የጠቀሳቸው ሐኪሞች ተናግረዋል። በሆስፒታሉ ውስጥ የሚሰሩና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የጤና ባለሙያዎች ነገሩኝ ብሎ ኤኤፍፒ እንደዘገበው፤ ወታደሮቹ ዶክተሮች፣ ነርሶችና ቁስለኛ ታካሚዎች ላይ መሳሪያ በመደገን ጥያቄ ሲያቀርቡ ነበር። ኤኤፍፒ ዋቢ ያደረጋቸው የጤና ባለሙያዎች ወታደሮቹ "ታካሚዎቹ የተሰጣቸውን ጉሉኮስ እንደነቀሉና ቁስላቸው የተሸፈነበትን ጨርቅ አንስተዋል" ብለዋል። ወታደሮቹ የጦር መሳሪያ እንደደቀኑባቸው የህክምና ባለሙያዎቹ ጨምረው ተናግረዋል። ሆስፒታሉን የሚደግፈው የህክምና በጎ አድራጎት ድርጅት የሆነው የድንበር የለሽ ሐኪሞች ቡድን ኤምኤስኤፍ ክስተቱ ማጋጠሙን አረጋግጧል። ኤምኤስኤፍ ባወጣው መግለጫ ላይ እንደጠቀሰው ወታደሮቹ በሆስፒታሉ ውስጥ በሚገኙ ክፍሎች ውስጥ እየተዘዋወሩ "አስታማሚዎችንና የጤና ሠራተኞችን አስፈራርተዋል" ብሏል። አክሎም "የህክምና ተልዕኮዎችን ገለልተኝነት በሚጥስ ሁኔታ በተደጋጋሚ የሚከሰቱት የታጠቁ ቡድኖች ተደጋጋሚ ድርጊት በእጅጉ ያሰስበናል" ሲልም ኤምኤስኤፍ በመግለጫው ላይ አመልክቷል። የህክምና በጎ አድራጎት ድርጅቱ ከወራት በፊት ባወጣው ሪፖርት በትግራይ ክልል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በርካታ ቁጥር ያላቸው የህክምና ተቋማት ሆን ተብለው ጉዳት እንዲደርስባቸው መደረጉን ገልጾ ነበር። ባለፈው ጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ የህወሓት ኃይሎች ትግራይ ውስጥ በሚገኘው የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ካዘዙ በኋላ በክልሉ ውስጥ ወታደራዊ ዘመቻ መካሄዱ ይታወሳል። አሁንም የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በአንዳንድ አካባቢዎች ውጊያዎች የሚካሄዱ ሲሆን፤ ባለፉት ሰባት ወራት ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደሞቱ የሚገመት ሲሆን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ደግሞ በአገር ውስጥና በጎረቤት አገር ሱዳን ውስጥ ተፈናቅለው ይገኛሉ። ግጭቱ በተካሄደባቸው ስፍራዎች የኤርትራ ወታደሮችን ጨምሮ በጦርነቱ ተሳታፊ የሆኑ ኃይሎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ አስከፊ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን የሚያመለክቱ ሪፖርቶች የተለያዩ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ማውጣታቸው ይታወሳል።
news-42482496
https://www.bbc.com/amharic/news-42482496
እንግሊዝ የሩሲያ ጦር መርከቦች የውሃ ክልሌን እየተጠጉ ነው አለች
በፈረንጆች ገና በዓል እለት በእንግሊዝ ኖርዝ ሲ አቅራቢያ የሩሲያ የጦር መርከብ በመታየቱ እንግሊዝም የራሷን የጦር መርከብ ለማስጠጋት መገደዷን የእንግሊዝ ባህር ሃይል አስታወቀ።
እርምጃው ብሄራዊ ጥቅምን መሰረት ያደረገ ነውም ተብሏል። ሩሲያ በጉዳዩ ላይ ምንም አስተያየት ከመስጠት ተቆጥባለች። ባህር ሃይሉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሩሲያ መርከቦች የእንግሊዝን የውሃ ክልል መጣስ መጀመራቸውንም ገልጿል። በተመሳሳይ በቅርቡ የባህር ስር የኢንተርኔት መስመር ላይ ችግር ፈጥራለች በማለት እንግሊዝ ሩሲያን ማስጠንቀቋም ይታወሳል። ከአንድ ወር በፊት የእንግሊዝ አየር ሃይልና የሀገሪቱ መከላከያ ሃይል ሃላፊ የሆኑት ማርሻል ሰር ስቱዋርት ፒች እንግሊዝና የሰሜን አትላንቲኩ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት ኔቶ የመገናኛ መስመሮችን መጠበቅ ቅድሚያ ሊሰጡት የሚገባ ተግባር እንደሆነ ገልፀዋል። ሩሲያ ተሳክቶላት የባህር ስር የኢንተርኔት መስመሩን ማቋረጥ ብትችል ኖሮ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ በፍጥነት ከባድ ውድቀት ይደርስ እንደነበር ሃላፊው ተናግረዋል። "የባህር ሃይሉ ሩሲያ የባህር ላይ ጥቃት ለማድረስ ከሞከረች የውሃ ክልላችንን ለማስከበር ወደ ኋላ አንልም ምንም አይነት ፀብ አጫሪነትም አንታገስም" ብለዋል ሃላፊው። እንግሊዝ ህዝቧን ለመከላከልና ብሄራዊ ጥቅሟን ለማስከበር መቼም ወደ ኋላ እንደማትል ግልፀዋል።
news-46267329
https://www.bbc.com/amharic/news-46267329
የነጻነት ቅርጫት፡ የጋብቻ ቀለበቶች
በቀደመው ጊዜ ትዳር ይመሰረት የነበረው ለጎሳ እና ፖለቲካዊ ቁርኝነት ትርፍ ነበር። አሁን ግን በአብዛኛው ትዳር የሚመሰረተው ውድ የሰርግ ስነ-ስርዓትን ተከትሎ በፍቅር ላይ በመመርኮዝ ነው።
ለምሳሌ በእንግሊዝ ሃገር በአማካይ የአንድ የሰርግ ወጪ 39ሺህ ዶላር (ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ) ያስወጣል። ከእነዚህ ምርጫዎች መካከል የሚፈልጉትን ዕቃ ይምረጡና እንዴት የጭቆና መሣሪያ እንደሆነ ይመልከቱ። መዋቢያ ቁሳቁስ "ወንዶች ፊታቸውን ሳያስውቡ ቢወጡ ምንም ነገር አይባሉም" ምቾች የሌለው ፋሽን "ሰዎች ለምን እንደሚያደርጓቸው አይገባኝም። ያማሉ፣ አይመቹም ደግሞም ቋሚ የሰውነት በሽታ ያስከትላሉ" ቤት ውስጥ የተዘጋጀ ምግብ "ሴት ልጅ ማብሰያ ክፍል ውስጥ ብቻ ነው መሆን ያለባት የሚለው ሃሳብ ሰልችቶኛል" - ኤማ የቤት ውስጥ ሥራዎች "እኩልነት ከቤት ስለሚጀምር ወንዶች ተነስታችሁ ቤት አፅዱ።" ጡት መያዣ "መዋብ ግዴታዬ አይደለም። ያለእሱ ቆንጆም አዋቂም ነኝ̃።" - ሊዛ ዝነኛ ሰዎችን የማድነቅ ባህል "ሁሉም የቁንጅና ሞዴሎች ሰውነት አንድ ዓይነት ነው፤ ደግሞም ደስተኛ አይመስሉም። ይሰለቻል።"- ዌንዲ ጋብቻ "እንደኔ እንደኔ የቃልኪዳን ቀለበቶች በሴት መብት ተሟጋቾች ዘንድ የስድብ ያህል ናቸው። ምክንያቱም ቀለበት ያደረገች ሴት የሌላ ሰው ንብረት መሆኗን ስለሚያመለክት።" ማቲልድ ማህበራዊ ድረ ገፆች "ለታዳጊ ወጣቶች አዕምሮ ሰላም በጣም አደገኛ ነው። በተለይ ለሴቶች። ምክንያቱም ከእውነታ የራቁና አደገኛ በሆኑ አመለካከቶች ተከበዋል።" - ሮሻን በፆታ የተለዩ መጫወቻዎች "በፆታ የተከፋፈሉ መጫወቻዎች በሙሉ ወንዶችንም ሴቶችንም ልጆች የተወሰኑላቸውን ነገሮችን ብቻ እንዲወዱ ያደርጋሉ።" - አና ተጨማሪ ዕቃ የጭቆና መሣሪያዎች ምንድን ናቸው? 'የፀረ-ነፃነት ቆሻሻ መጣያ' የተሰኘውን አመላከከት ምን እነዳስጀመረው ለማየት የራስዎን መሣሪያ ያጋሩን። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአደጉ ሃገራት አዲስ የሚጋቡ ጥንዶች ቁጥር እየቀነሰ ሲሆን በተቃራኒው ጋብቻቸውን የሚያፈርሱ ጥንዶች ቁጥር እየጨመረ ነው። ለጋብቻ ቁጥር መቀነስ እንደምክንያትነት ከሚጠቀሱ ጉዳዮች መካከል ትደር ለመመስረት እና ሰርግ ለመደገስ የሚያስፈልገው ከፍተኛ ወጪ ነው።
news-56417950
https://www.bbc.com/amharic/news-56417950
ልደቱ አያሌው፡ አቶ ልደቱ ለሕክምና ከአገር እንዳይወጡ ለሁለተኛ ጊዜ ለምን ተከለከሉ?
የቀድሞው ኢዴፓ የብሔራዊ ምክር ቤት አባልና ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው ለሕክምና ወደ ውጪ አገር እንዳይሄዱ ለሁለተኛ ጊዜ መከልከላቸውን ለቢቢሲ ገለፁ።
አቶ ልደቱ እንደሚሉት፤ ባጋጠማቸው የልብ የደም ቧንቧ መዘጋት ችግር ምክንያት በአሜሪካ አትላንታ በሚገኝ ኢስት ሳይድ ሆስፒታል ሕክምና ያደረጉት ከዛሬ አንድ ዓመት ከስምንት ወር ገደማ በፊት ነበር። በወቅቱ በልባቸው ሦስት የደም ቧንቧዎች ላይ ችግር በመኖሩ ለአንዱ ሕክምና ተደርጎላቸውና ሁለቱ የሚገኙበት ቦታ አስቸጋሪ በመሆኑ መድኃኒት እየወሰዱ እንዲቆዩና ከስድስት ወር በኋላ እንዲመለሱ ነበር ሆስፒታሉ ቀጠሮ የሰጣቸው። ነገር ግን ለቀጠሯቸው ሰባት ቀናት ገደማ ሲቀራቸው በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ይናገራሉ። አቶ ልደቱ በቁጥጥር ሥር የዋሉት የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ አመፅ ለማስነሳት አስተባብረዋል በሚል ነበር። አምስት ወራትን በእስር ካሳለፉ በኋላም፤ ከሁለት ወራት በፊት በ30 ሺህ ብር ዋስ ከእስር መለቀቃቸው ይታወቃል። ፖለቲከኛው እንደሚሉት ያኔ በእስር ላይ ሳሉም ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ጤናቸው አስጊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ጠበቆቻቸውና የፓርቲያቸው ፕሬዚደንት አቤቱታ ሲያቀርቡ ነበር። ይሁን እንጂ የውጪ አገር የሕክምና ጥያቄያቸው ከቀረበባቸው ክሶች ነጻ ከተባሉ በኋላም መልስ አላገኘም። "በእስር ቤት አምስት ወራት፤ ከተፈታሁ ደግሞ ሁለት ወራት ተቆጥረዋል። ቀጠሮዬም ስምንት ወር አለፈው" ይላሉ። የታሰሩበትና በእስር ቤት የቆዩበት መንገድ ሕገ ወጥ እንደነበር የሚያስታውሱት አቶ ልደቱ፤ የቀረበባቸው ክስ ዋስትና የሚያስከለከል ባይሆንም ዋስትናቸውን ለማስከበር ውጣ ውረድ እንደነበረው ይናገራሉ። በእስር ላይ ሳሉም ከኮሮናቫይረስ ወረርሽን ጋር ተያይዞ ያለባቸው የጤና ሁኔታ አስጊ በመሆኑ ሐኪሞቻቸው ዝርዝር የሕክምና ማስረጃቸውን አቅርበው ዋስትና እንደተፈቀደላቸው አስታውሰዋል። 'ያልተፈቀደ መሳሪያ መያዝ' በሚል በቀረበባቸው ክስ የዋስ መብታቸው ሲጠበቅላቸው ፍርድ ቤት ለመቅረብ የሁለት ወር ቀጠሮ የተሰጣቸው፤ "ውጭ አገር ታክሜ እንድመለስ በቂ ጊዜ እንዳገኝ ነበር" ይላሉ። ከአገር እንዳይወጡ ለምን ተከለከሉ? አቶ ልደቱ እንደሚሉት የዋስትና መብታቸው ከተከበረላቸው በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ውጭ አገር ለመሄድ ወደ አየር ማረፊያ ሲሄዱ እንዲመለሱ ተደርገዋል። "የፍርድ ቤት እግድ አላችሁ ወይ?" ሲሉ ቢጠይቁም "የፍርድ ቤት እግድ የለንም። የብሔራዊ ደኅንነት ሠራተኞች ነን። የታዘዝነው ከመሥሪያ ቤታችን ነው። መውጣት አትችልም አሉኝ" ይላሉ። ከአገር እንዳይወጡ የከለከላቸው ፍርድ ቤት ካለ እንዲነግሯቸው ቢጠይቁም፤ "የምናውቀው ነገር የለም አለቆቻችንን አነጋግር" የሚል ምላሽ ብቻ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል። በዚህ ጊዜ 'ሕገ-መንግሥቱን እና ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን መናድ' በሚል የቀረበባቸው ክስ አልተዘጋም ነበር። ምን አልባት ሰበቡ ይህ ሊሆን ይችላል ብለው አስበው የነበረ ቢሆንም፤ ይህ የክስ መዝገብ ከተዘጋ በኋላም ለሁለተኛ ጊዜ ከአገር መውጣት አለመቻላቸውን ይናገራሉ። "ከቀረበብኝ ክስ ነጻ መሆኔን የሚያሳይ የፍርድ ቤት ውሳኔ አስተርጉሜ ይዤ ብቀርብም ከአለቆቻቸው ጋር ተነጋግረው 'አሁንም አልተፈቀደልህም' ብለው አሰናበቱኝ" ይላሉ። አቤቱታ ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አቶ ልደቱ እንደሚሉት መጀመሪያ ከአገር እንዳይወጡ ሲከለከሉ፤ ለሠላም ሚኒስቴር፣ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ለደኅንነት መሥሪያ ቤት እና ለሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በሕይወት የመኖር መብታቸው እንዲከበርላቸው ጥያቄ አቅርበው ነበር። በወቅቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጥያቄያቸውን ተቀብለው እንዳነጋገሯቸው፤ ሌሎቹ ግን ሊያነጋግሯቸው ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸውን አቶ ልደቱ አስታውሰዋል። ያነጋገሯቸውም "የራሳችንን ጥረት እያደረግን ነው፤ እስካሁን የተገኘ መፍትሔ የለም" የሚል መልስ እንደሰጧቸውም ይናገራሉ። አሁን ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ደብዳቤ ያስገቡትም ጥያቄዬን በጽሁፍ እንዳስገባ ስለተጠየቅኩ ነው ብለዋል። "አሁንም የራሳችንን ክትትል እናደርጋለን ነው ያሉኝ " ይላሉ። ነገር ግን አቶ ልደቱ እነዚህ መሥሪያ ቤቶች መፍትሔ ይሰጡኛል የሚል እምነት እንደሌላቸው ይናገራሉ። "ኢትዮጵያ ውስጥ መንግሥትም እንደ መንግሥት፤ ተቋም ወይም ባለሥልጣን የሚወስን ያለ አይመስለኝም። የሚወስነው አንድ ሰው ነው። በእኔ ጉዳይ የማየው ይህንን ነው" ሲሉም ምክንያታቸውን ያስቀምጣሉ። ባለሥልጣናት የሚወስኑ ቢሆንና ሕግ ተቀባይነት ቢኖረው፤ መንግሥትና ሕግ ባለበት አገር የአንድ ዜጋ መብት በዚህ መልኩ ሊጣስ እንደማይችልም ያክላሉ። "ባለሥልጣናትም፣ ተቋማትም፤ ሕግም የለም። ውሳኔ የሚሰጠው በግለሰቦች በጎ ፈቃድ ብቻ ነው። ከዚህ በኋላ ተስፋ አድርጌ የምጠይቀው አካል የለም። የሚሆነውን ማየት ነው" ብለዋል አቶ ልደቱ። "የቂም በቀል ጉዳይ እንደሆነ መረዳት ይቻላል" አቶ ልደቱ ጉዳያቸውን በተመለከተ የተለያዩ ባለሥልጣናትን ማናገራቸውን ይጠቅሳሉ፤ "መፍትሔ ይሰጡኛል ያልኳቸውን አካላት ሁኑ አናግሬያለሁ፤ ግን ፈቃደኛ አልሆኑም። የቂም በቀል ጉዳይ እንደሆነ ከአካሄዱ መረዳት ይቻላል" በማለት ምላሽ ሰጥተዋል። ለዚህም አያያዛቸው ሕገ ወጥ እንደነበር፣ አዲስ አበባ ተይዘው ኦሮሚያ መታሰራቸው እና የዋስትና መብታቸው ሲከበር መንግሥት ሊለቃቸው ፈቃደኛ እንዳልነበር ያነሳሉ። "የጤናዬን ጉዳይ እኮ ከሐኪሜ ቀጥሎ መንግሥት ያውቀዋል። እኔ በጤናዬ ጉዳይ የምላላከውን ኢሜይል መንግሥት ያውቀዋል። ነገር ግን በውንጀላ ምክንያት አላስኬደኝ ብሏል" ሲሉም በጤና ምክንያት ሕይወታቸውን እንዲያጡ ካልተፈለገ በስተቀር ፤ የሚያስከለክላቸው ሌላ ምክንያት እንደሌለ ይናገራሉ። አንዳንዶች ለክልከላው ከአገር ወጥተው ይቀራሉ የሚል ስጋት ሊሆን ይችላል ቢሉም አቶ ልደቱ ግን፤ "እንደዚህ እንደማላደርግ ያውቃሉ። ታክሞ ይድናል ነው እንጂ፤ ሄዶ ይቀራል ብለው አይደለም" ሲሉ ከአገራቸው ውጭ የመኖር ፍላጎት እንደሌላቸው ተናግረዋል። "የፖለቲካ ታጋይ ነኝ በሕጋዊ መንገድ ሄጃለሁ፤ ከዚህ በኋላ ማንንም ባለሥልጣን ልለምን ወይም ልማፀን አልችልም፤ እንደ ትግሉ አካል ነው የምቆጥረው። ሕይወቴን ካጣሁም እንደከፈልኩት ዋጋ ነው የምቆጥረው" ብለዋል። ለዚህ ሁሉ ችግር እንደምክንያት የሚተቅሱትም መንግሥትን ስለሚቃወሙ፣ የሽግግር መንግሥት ይቋቋም፤ ከመስከረም 30 በኋላ መንግሥት የለም ብለው በመናገራቸው በመንግሥት ቂም እንደተያዘባቸው ነው። ይህንን ተከትሎም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአደባባይ 'እርምጃ እንወስዳለን' ሲሉ መዛታቸውን ያስታውሳሉ። ከዚህ ባሻገር የብልፅግና ፓርቲ አባል እንዲሆኑ ተጠይቀው ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸውም ባለሥልጣናቱን ሊያስከፋቸው እንደሚችል ያስባሉ። "ይህ የእኔ የትግል አካል ነው። የሚያሳስበኝ አገሪቷ እንደ አንድ መንግሥትና ሥርዓት ሳይሆን እንደ አንድ ተንኮለኛና ቂመኛ ግለሰብ የሚያስብ ሥርዓት ውስጥ መውደቋ ነው" ብለዋል። አቶ ልደቱ እንደሚሉት አሁን ከእርሳቸው ጉዳይ ይልቅ፤ የአገራቸው ሁኔታ እንደሚያሳስባቸው ይናገራሉ። አገሪቷ ላይ የሚታየው ተስፋ አስቆራጭ ቢሆንም እርሳቸው ግን አሁንም አቅማቸው በፈቀደ መጠን አገራቸው ልትድን የምትችልበትን ትግል እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
news-55183181
https://www.bbc.com/amharic/news-55183181
በናሚቢያ አዶልፍ ሒትለር ምርጫ አሸነፈ
ሙሉ ስሙ አዶልፍ ሒትለር የተባለ አንድ ተቃዋሚ ፖለቲከኛ በናሚቢያ የአካባቢ ምርጫ ማሸነፉ እያነጋገረ ነው።
አዶልፍ ሒትለር ይህንን ምርጫ ያሸነፈው ማንንም ሳያስፈራራ ነው። አዶልፍ ሒትለር ውኑና ካውንስለር የአካባቢ ምክር ቤት አባል ሆኖ የተመረጠው ኦምፑንጃ በሚባል አካባቢ ተወዳድሮ ነው። ቢልድ ከተባለ የጀመርመን ጋዜጣ ጋር ቀለ ምልልስ ያደረገው አዶልፍ ሒትለር "እኔ ከናዚ የፖለቲካ ፍልስፍና ጋር አንዳችም ግንኙነት የለኝም" ሲል ኮስተር ብሎ መልሷል። አዶልፍ የሚለው ስም በናሚቢያ የተለመደ ስም ነው። ምክንያቱ ደግሞ አገሪቱ በአንድ ወቅት የጀመርን ቅኝ ስለነበረች ነው። የናሚቢያው አዶልፍ ሒትለር ስዋፖ የሚባል ፓርቲ አባል ነው። ይህ ፓርቲ ደግሞ በብዛት የሚታወቀው ጸረ ቅኝ ግዛት እንቅስቃሴን በማድረግ መሆኑ ሌላ ግርምት ፈጥሯል። ውኖና ለጋዜጣው እንዳመነው ከሆነ አባቱ አዶልፍ ሒትለር ብሎ ስም ያወጣለት ከ2ኛው የዓለም ጦርነት ቀስቃሽ የጀርመኑ ብርቱ አዶልፍ ሒትለርን ተከትሎ ነው። ሆኖም አባቱ ስለ ጨካኙ አዶልፍ ሒትለር ስም እንጂ ምንም መረጃ አልነበረው ይሆናል ብሏል። "በልጅነቴ ስሜ ምንም ችግር ያለበት ሆኖ አይታየኝም ነበር" ብሏል የናሚቢያው አዶልፍ ሒትለር። አዶልፍ ሒትለር የአካባቢ ምርጫውን ያሸነፈው "የናሚቢያ ደም አሪየን ደም ነው" ማለት ሳያስፈልገው፣ አይሁዳዊያንን ለችግሮች ሁሉ ምንጭ አድርጎ ሳይመለከት ነው። ምርጫውንም በ85 ከመቶ ብልጫ አሸንፏል። "አዶልፍ ሒትለር መባሌ ችግር እንደሚፈጥር ያወቅኩት ካደኩ በኋላ ነበር፤ እኔ ዓለምን የመጨቆን ምንም እቅድ የለኝም ብሏል የናሚቢያው አዶልፍ ሒትለር። አዶልፍ ሒትለር ሚስቱ አዶልፍ ብላ እንደምትጠራውና ወደፊትም ስሙን የመቀየር ሐሳብ እንደሌለው ተናግሯል። በፈረንጆች 1884 እስከ 1915 ናሚቢያ የጀርመን ግዛት ነበረች። ስሟም ሳውዝ ዌስት አፍሪካ ነበር የሚባለው። የጀርመን ኢምፓየር በሺ የሚቆጠሩ ለነጻነት የሚታገሉ ናሚቢያዎችን ጨፍጭፏል። በአንደኛው የዓለም ጦርነት አካባቢ ናሚቢያ በደቡብ አፍሪካ ሥር ሆና ቆይታለች። ነጻ አገር የሆነችው ግን በ1990 ዓ ም ነበር። ሆኖም በርካታ የናሚቢያ ከተሞች አሁንም ድረስ የጀርመን ስሞችን እንደያዙ ናቸው። አዶልፍ ሒትለር አባል የሆነበት ስዋፖ ፓርቲ አገሪቱን ከጀርመን ቅኝ ለማላቀቅ ሰፊ ተጋድዶን የመራ ድርጅት ነው።
news-43780145
https://www.bbc.com/amharic/news-43780145
እስራኤል ረጅሙን የጋዛ ዋሻ አፈረሰች
ከጋዛ ሰርጥ ወድ እስራኤል የሚወስድው እና በሽምቅ ተዋጊዎች የተቆፈርውን ዋሻ የእስራኤ ጦር ከጥቅም ውጪ ማድረጉን አስታወቀ።
የእስራኤሉ መከላከያ ሚኒስትር አቪጎር ሊበርማን እንዳሉት ይሄኛው እስራኣኤል ከደረሰችባቸው ሁሉ ረጅሙ እና በጣም ጥልቁ ዋሻ ነው። ዋሻው በ2014 ከተካሄደው የጋዛ ጦርነት ጀምሮ እንደተቆፈረ እና በጊዜውም እስራኤል ከ 30 በላይ የሚሆኑ ዋሻዎችን ማፈራረሷን አንድ የእስራኤል ወታደራዊ ቃል አቀባይ ተናግረዋል። እንደ ቃል አቀባዩ ኮሎኔል ጆናታን ኮንሪከስ ከሆነ፤ ዋሻው በሃማስ የተቆፈረ እንደሆነና በሰሜናዊ ጋዛ ሰርጥ ጃባሊያ አካባቢ የተጀመረ ነው። ዋሻው በናሆል ኦዝ አቅጣጫ ጠቂት የማይባሉ ሜትሮች ወደ እስራኤል እንደገባና መውጫ ግን ገና እንዳልተሰራለት ኮሎኔል ጆናታን አክለዋል። ዋሻው ወደ ጋዛ በብዙ ኪሎሜትሮች የተዘረጋ ሲሆን፤ ከሌሎች ዋሻዎችም ጋር የተገናኘና ጥቃት ለመፈጸም ምቹ ነበር ነው ብለዋል። እስራኤል በሳምንቱ መጨረሻ ነው ዋሻውን ከጥቅም ውጪ ያደረገችው። ቃል አቀባዩ ሲናገሩም ''ዋሻው ለረጅም ጊዜ ጥቅም እንዳይሰጥ በሚያደርግ መሳሪያ ሞልተነዋል'' ብለዋል። በቅርብ ወራት ውስጥ እስራኤል ካፈራረሰቻቸው የጋዛ ዋሻዎች መካከል ይህ አምስተኛው ነው። አንዳንዶቹ ዋሻዎች በፍልስጤም እስላማዊ ጂሃድ ታጣቂ ቡድን የተሰሩ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ ጋዛን በተቆጣጠረው የሃማስ እስላማዊ ቡድን የተቆፈሩ ናቸው። ከባለፈው አመት ጀምሮ እስራኤል ዋሻዎችን መለየት የሚችል ልዩ መሳሪያ እየተጠቀመች ሲሆን በአሁኑ ሰአት ደግሞ በአዋሳኟ ጋዛ በኩል የሚቆፈሩ ዋሻዎችን ለማስቆም በከፍተኛ ቴክኖሎጂ የተራቀቀ የምድር ውስጥ መከላከያ እየገነባች ነው።
news-45022403
https://www.bbc.com/amharic/news-45022403
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በአሜሪካ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሰጡት ምላሽ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በአሜሪካ ሚኒሶታ ግዛት የሚገኙ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንን በትልቅ መሰብሰቢያ ውስጥ አግኝተው ከነጋገሩ በኋላ በተዘጋጀ የእራትና የውይይት መረሃ ግብር ላይ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት ባለፉት አራት ዓመታት እንቅልፍ ተኝተው እንደማያውቁ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዳለፉ አስታውሰው በተለይ ከአራት ወራት በፊት የእስር ማዘዣ ወጥቶባቸው እንደነበርም ተናግረዋል። የእስር ማዘዣው ከየትኛው ወገን እንደመጣ በግልፅ ባይናገሩም ከሀገር እንዲወጡ የሚያስገድዱ ጫናዎች እንደነበሩም ጠቁመዋል። "እኛም አንወጣም ብለን እዚያው የሚመጠውን ሁሉ ለመጋፈጥ ቆርጠን ቆይተናል ምክንያቱም ከሃገር የወጡ አልተመለሱም። ለዚህም ነው እዚህ ቦታ ላይ ልንደርስ የቻለው" ብለዋል። • ዶክተር ብርሃኑ ነጋ መቼ አገር ቤት ይገባሉ? • 40 ታጣቂዎች በመቀሌ አውሮፕላን ማረፊያ ተያዙ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሜሪካ ጉዞ ተጠናቀቀ በውይይቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከታዳሚው ለቀረቡላቸው የተለያዩ ወቅታዊ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። የሶማሌ ክልልን በተመለከተ በኢትዮጵያ ያሉት ሶማሌዎች ብቻ ሳይሆን ሞቃዲሾ ያለውም ጭምር ዴሞክራሲን እንዲተገብርና ከኢትዮጵያዊያንና በተለይ ከኦሮሞ ህዝብ ጋር ተሳስሮ መኖር አለበት ብለን በጽኑ እናምናለን በማለት ጀምረዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። ክልሉ መሪ ያስፈልገዋል፤ ክልሉ የልብ አንድነት ያስፈልዋል። ብዙዎቻችሁ ላታስተውሉት ትችላላችሁ ግን አፍሪካ በብዙ ጅብ መንግሥታት የተያዘች አህጉር ናት። እነዚህን መንግሥታት ከጎረቤት አስቀምጠን ኢትዮጵያ ላይ ዴሞክራሲ፤ ኢትዮጵያ ላይ ሰላም ማምጣት አይቻልም። አፍሪካ የሚገባትን ክብር እንድታገኝ በጋራ መስራት ያስፈልጋል። ለዚህ ደግሞ ኢትዮጵያ በቂ ጭንቅላት አላት፤ 100 ሚሊዮን ምርጥ ጭንቅላት። ይህንን በማውጣት መስራት ያስፈልጋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም የሶማሌ ክልልን በተመለከተ በመንግስት በኩል ሪፎርም እየሰራ እንደሆነና ህዝቡ በትዕግስት እንዲጠብቅ ጠይቀዋል። ዶክተር ብርሃኑ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር ምን ተወያዩ? • ያልተነገረለት የኮንሶ ጥያቄ በኦሮሞና በሶማሌ መካከል የተነሳውን ግጭት በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ "ኦሮሞና ሶማሌ አንድ ቤተሰብ ናቸው፤ ስለዚህ ማንም ምንም አለ አብሮ ተጋግዞ መስራት ብቻ ነው የሚያዋጣው ብለዋል።" በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነትን በተመለከተ ''በመጀመሪያ ትኩረተ የሰጠነው ዋነኛው ነገር የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ማጠናከር ላይ ነው። ለዚህም ነው በፍጥነት የአውሮፕላን ጉዞ ያስጀመርነው፤ የሚያገናኙንን መንገዶች እየጠገንን ያለነው። ስለዚህ ህዝቡ ተገናኝቶ ሰላሙን መመስረት ከቻለ መንግሥት ደግሞ ይከተላል ማለት ነው።'' ''እንኳን ለመታረቅ ለመዋጋትም ከዚህ በፊት ውክልና አልሰጠንም። ስንዋጋም ሃገር የሚመራው ጠቅላይ ሚኒስትር ተዋጉ ሲል ተዋጋን እንጂ በውክልና አልተዋጋንም። የትግራይን ህዝብ ሳናካትት ምንም አይነት ለውጥም ሆነ እድገት ማሳካት አንችልም፤ አንፈልግምም።" "ከትግራይ ህዝብ ውጪ ኢትዮጵያን የመቀየር ሃሳብ የለንም። ህዝቡ ያሳዝነናል፤ ህዝቡ ይቆረቁረናል። የኢትዮጵያ ህዝብ የትግራይ ጉዳይ ግድ አይሰጠውም ማለት አንችልም ምክንያቱም በባድመ ጦርነት ከማንም በላይ የሞቱት የኦሮሚያ ልጆች ናቸው።" የሰላሙ ጉዳይ ለህዝባችን ስለሚጠቅም፣ የኤርትራ ህዝብ የሰላም ህዝብ ስለሆነ፣ የትግራይ ህዝብ ደግሞ የሚጠቀመው ከዚህ ሰላም ስለሆነ ሌላውን ትተን አንድ ሆነን እንስራ የሚለውን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ፀጉረ ልውጦች እነማን ናቸው? "ፀጉረ ልውጦች የተወሰኑ የአንድ ብሄር ተወላጆች ናቸው ብሎ ማሰብ በመሰረቱ የተሳሳተ ነው" በማለት የጀመሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የትግራይ ህዝብ ኦሮሚያ ወይም አማራ ክልል ውስጥ ፀጉረ ልውጥ ሊሆን አይችልም።" ብለዋል። "ኦሮሚያ ውስጥ ትግሬም ይሁን አማራ፤ ወላይታም ይሁን ጉራጌ፤ ህዝቡ ማንንም አቅፎ ለማኖር ፈቃደኛ ነው። እንደውም እኔና የወከልኩት ኦህዴድ ብዙ ችግር አለብን። የኦሮሞ ህዝብ ግን አቃፊ ነው። በእኛ መነጽር፤ በእኛ ልክ ህዝቡን አትለኩት። ህዝቡ እንደእኛ አይደለም፤ ህዝቡ ከእኛ የላቀ ብስለት ያለው ነው።" "ፀጉረ ልውጥ ያልኩት በፍጹም አንድን ቡድን በሚገልጽ መልኩ ሳይሆን፤ የሚሰማሩ ሃይሎች ስለነበሩ መረጃው ስላለኝ ነው እንጂ የሆነ ቡድን ፀጉረ ልውጥ ሌላኛው ደግሞ ንጹህ ለማለት አይደለም። አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ውጥረት ማንኛውም ነገር ለፖለቲካዊ ጥቅም ሊውል ይችላል።" ባለፉት 27 ዓመታት የተሰራው ጥፋት ወይስ ልማት? ''ያለፉት 27 ዓመታ ብዙ ቆሻሻ ነገር የተሰራበት ዘመን ነው። ልማት ማለት አስፓልት፤ ልማት ማለት ኮንዶሚኒየም የሚመስላቸው ሰዎች አሉ። መሰረተ ልማት ያለ ውስጣዊ ሥርዓት ምንም ጥቅም የለውም። ምክንያቱም እርስ በእርሱ የማይነጋገር ህዝብ፤ እርስ በእርሱ የማይግባባ ህዝብ ፈጥረን ስናበቃ አስፓልት ሰርተንልሃል የምንል ከሆነ ተገቢ አይደለም'' ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ለተገኘው ልማት፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ለተገኘው ሰላም ባለቤቱ ህዝብ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ለጠፋው ጥፋት ግን ተጠያቂው መንግሥት ነው። ጥሩ ነገር ሲሰራ ሃላፊነት የምንወስድ፤ ጥፋት ሲጠፋ ደግሞ የምንሸሽ አክራሪዎች አይደለንም እኛ፤ መንግሥት ነን። እስከ ዛሬ ለጠፉ ጥፋቶች በሙሉ ኢህአዴግ እንደ መንግሥት ሃላፊነቱን ወስዶ ህዝቡንም ይቅርታ ጠይቋል። ይሄ ሁሉ ግን በይቅርታ ብቻ የሚያልፍ አይደለም። ባለፉት 27 ዓመታት ለገረፍናችሁ፣ ላባረርናችሁ፣ ላስቸገርናችሁ ሰዎች እኔ እንደ ኢህአዴግ ከልብ ይቅርታ እጠይቃችኋለው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
news-44955171
https://www.bbc.com/amharic/news-44955171
ካለሁበት 41: አብዱልራሂም ከባሌ ገበሬዎችን እስከ ቻድ ሕዝቦች የመብት ጥያቄ ሲል ብረት አንስቷል
ስሜ አብዱልራሂም አብዱልዓዚዝ ይባላል። በባሌ ዞን ድሬ በምትባል ከተማ ውስጥ ነው ተወልጄ ያደኩት። በእርግጥ በልጅነቴ በሐረር ዘለግ ላለ ጊዜ ተቀምጫለሁ።
ከአገር ሽሽቼ የወጣሁት በንጉሡ ዘመን ነበር። ያኔ ባሌ ውስጥ የተጋጋለ ጦርነት ይካሄድ ነበር። በጦርነቱ ንብረት ወድሟል፣ ሰዎች ተገድለዋል፤ በርካቶች ቀያቸውን ጥለው ተሰደዋል። በዚያን ወቅት ታዲያ ገና የ12 ዓመት ልጅ ነበርኩ። ያም ኾኖ ዕድሜዬ ትግሉን ከመቀላቀል አልገደበኝም። በዚያን ወቅት የነበረውን ሥርዓት ለመጣል ነፍጥ አንስቼ ጫካ ገባሁ። ከዚያን ጊዜ በኋላ በሄድኩበት ሁሉ ትግል ይከተለኛል። ካለሁበት ልዩ መሰናዶ፡ ሎስ አንጀለስ ከዐብይ አህመድ በፊትና በኋላ "ካለ ቪዛ ወደ 127 አገራት መጓዝ እችላለሁ" ያኔ ትግሉን ስቀላቀል የትግሉ መሪ ዝነኛው ጄነራል ዋቆ ጉቱ ነበሩ። በዚያ የተሟሟቀ ትግል ምክንያት በአገር ውስጥ ባሌ፣ ሐረር፣ ወለጋ እና አዲስ አበባ ተዟዙሪያለሁ። ከአገር ውጪ ደግሞ በሶማሊያ እና በሱዳን የትግል ስልጠናዎችን ወስጃለሁ። ቻድ-ሊቢያ-ኔዘርላንድ ከሱዳን በኋላ ቀጣዩ መዳረሻዬ ቻድ ነበር። በቻድ በስደት ላይ በነበርኩበት ወቅት የሊቢያ መንግሥት ኡራ የሚባሉ የቻድ ሕዝቦችን ይበድል ስለነበረ ይህን በመቃወም አሁንም ተመልሼ ወደ ትግል ገባሁ። በትግል ላይ ሳለሁ በሊቢያ መንግሥት ተማርኬ ወደዚያው ተወሰድኩ። ሊቢያ ከአንድ ዓመት በላይ ጨለማ በሆነ ጉድጓድ ውስጥ ታስሬ ቆይቼ ነበር። እጅግ መራራ ጊዜን ነበር ያሳለፈኩት። ከተፈታሁ በኋላ በብዙ ጥረት ወደ አውሮፓ አቀናሁ፤ ወደ ኔዘርላንድ። አሁን የምኖረው ናይሜጋን በምትባል የሆላንድ ከተማ ውስጥ ነው። እጅግ ውብ ከተማ ናት ታዲያ። የዚህ አገር ሰው ሲበዛ ሥራ ይወዳል። በዚህም ምክንያት ለራሳቸው እንኳ የሚሆን ጊዜ የላቸውም። በኔዘርላንድ ተወዳጅ ከሆኑ ምግቦች መካከል አንዱ የሆነው ''ኢስታንፖት'' በኔዘርላንድ ተወዳጅ ከሆኑ ምግቦች መካከል የኔ ምርጫ የሆነው ''ኢስታንፖት'' የሚባለው ምግብ ነው። ይህ ምግብ ከድንች እና ከካሮት የሚሠራ ሲሆን የኔዘርላንዶች ባህላዊ ምግብ ነው። ካለሁበት 38፡ ''ሳላስበው ወደ ትምህርት ዓለሙ የመቀላቀሉን ሕልሜን አሳካሁኝ'' እዚህ ''ዋል'' የሚባል ሥፍራ መጎብኘት ያስደስተኛል። ይህ የወደብ ሥፍራ ሲሆን ሰዎች ከመርከብ ላይ ሲወርዱ፣ እንዲሁም መርከቦች ባህር ላይ ሆነው ከርቀት በማየት ነፍሴ ሐሴት ታደርጋለች። ወደዚህ አገር በመምጣቴ የአእምሮ እረፍት ማግኘት ችያለሁ። ያም ኾኖ ግን ብቸኝነቱ ከባድ ነው። ሰዎች በአንድ አካባቢ ይኖራሉ እንጂ አይተዋወቁም። ይህ ሥፍራ ገጠራማውን የትውልድ መንደሬን ይስታውሰኛል። በምኖርበት ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ "ኦይ" የሚባል ልምላሜ ሥፍራ አለ። ይህ ሥፍራ ገጠራማውን የትውልድ መንደሬን ይመስለኛል። አካባቢው በተለያዩ ዓይነት ተክሎች የተሸፈነ ነው። ወደዚህ አገር ስመጣ ከብዶኝ የነበረው የአገሬውን ባሕል እና የአኗኗር ዘይቤ መላመዱ ነበር። በተለይ በሙቀት ወቅት እርቃናቸውን የሚሄዱ ሰዎችን ስመለከት በጣም እደነግጥ ነበር። ለጫሊ ነጋሳ እንደነገረው የ'ካለሁበት' ቀጣይ ክፍሎችን ለማግኘት ፦ ካለሁበት 42 : ''የጠበቀ ቤተሰባዊ ፍቅራቸውና ትስስራቸው ከኢትዮጵያውያን ጋር ያመሳስላቸዋል'' ካለሁበት 43፡" የናይሮቢ ነዋሪ በጣም የዋህ ህዝብ ነው"
news-51472010
https://www.bbc.com/amharic/news-51472010
ቶምና ጄሪ፡ ከኢትዮጵያ እስከ ኢራን ታዋቂነትን ያተረፈው ፊልም እንዴት ተሰራ?
አንድ ቤት ውስጥ እንዲኖሩ የተገደዱት አይጧ ጄሪና ድመቱ ቶም ተስማምተው አያውቁም። ከባለቤቶታቸው በሚሰጣቸው አይብ [ቺዝ] ሁሌም እንደተፋለሙ ነው። አይጥ ብልሃ ናት። ብዘዉን ጊዜ በአሸናፊነት ሆዷን ሞልታ ነው የምትሄደው።
መቸም መጨረሻውን መገመት አያዳግትዎትም። ድመቱ ጄሪ በብስጭት ፊቱ ቀልቶ አይኑ በርቶ ሳለ ነው የሚጠናቀቀው። አብዛኛው ክፍል ተመሳሳይ ይዘት አለው። ምንም እንኳ ጄሪ አሸናፊ ቶም ተሸናፊ እንደሆኑ መገመት ባያዳግትም ይህ የካርቱን ፊልም እጅግ ተወዳጅ ነው። በርካታ ሽልማቶችንም አፍሷል። ቶምና ጄሪ አሁን የ80 ዓመት አዛውንት ናቸው። ፊልሙን መጀመሪያ ያለሙት ቢል ሃና እና ጆ ባርቤራ ነበሩ። ሌሎች የፊልም አምራቾች በካርቱን ፊልም ስኬት ሲንበሻበሹ እነርሱ የሚሠሩበት መሥሪያ ቤት ግን መሰል ስኬት አላገኘም። ድብርት ተጫጭኗቸው ቁጭ ብለው እያወጉ ሳለ ነው ሃሳቡ የተገለጠላቸው። ሁሉቱም በወቅቱ ዕድሜያቸው 30 ዓመት ገደማ ነበር። ባርቤራ ስለ ድመትና አይጥ ፍጥጫ ሲያስብ እንደው ድንቅ እንደሚለው ይናገራል። ይሄኔ ነው ለምን ይህን ሃሳብ ፊልም አናደርገውም የሚለው የተገለጠላቸው። የመጀመሪያ ክፍል በግሪጎሪ አቆጣጠር 1940 ላይ ለአየር በቃ። ከዚያማ ፊልሙ ተወዳጅነት አተረፈ። ሁሉም ስለ ቶምና ጄሪ ማውራት ያዘ፤ አልፎም ለኦስካር ሽልማት ታጨ። ቶምና እና ጄሪ የመጀመሪያ ስማቸው ጃስፐር እና ጂንክስ ነበር። የቶምና ጄሪ አንድ ክፍል ለማምረት ሳምንታት ይወስዳል፤ እስከ 50 ሺህ ዶላርም ሊያስወጣ ይችላል። ለዚያም ነበር በዓመት ጥቂት ክፍሎች ብቻ የሚመረቱት። በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅናን ያተረፈው ቶምና ጄሪ በእጅ በተሳሉ ካርቱኖች ላይ ተመሥርቶ የሚሠራ ነው። ለእያንዳንዱ ክፍልም የተለያየ ሙዚቃ ይሠራላታል። በ1950ዎቹ ቴሌቪዥን እንደጉድ ሲፈላ የቶምና ጄሪ ፊልም ሠሪዎች አዳዲስ ክፍሎችን ከምናመርት ለምን ቀድሞ የተሠሩትን አናድሳቸውም የሚል ሃሳብ መጣላቸው። ያንንም ማድረግ ጀመሩ። ፊልሙን መጀመሪያ ያለሙት ቢል ሃና [ግራ] እና ጆ ባርቤራ [ቀኝ] ቶምና ጄሪ ፊልም ብዙ ውጣ ውረዶችን አልፏል። በርካታ የፊልም ሰዎችም ተሳትፈውበታል። በ1970ዎቹ ለሕፃናት አይሆንም፤ ምክንያቱም ብዙ አመፅ ይስተዋልበታል ተብሎ በቴሌቪዥን እንዳይታይ ተከልክሎም ነበር። ይሄኔ ቶምና ጄሪ የሚስማሙባቸው ክፍሎች መመረት ጀመሩ። ተወዳጅነታቸው ግን ያን ያህል አልነበረም። ፊልሙ ሌላው የሚወቅስበት የነበረው ጉዳይ ከቆዳ ቀለም ጋር የተገናኘ ነበር። ፊልሙ ላይ አልፎ አልፎ የሚታዩ ሰዎች የቆዳ ቀለም መጥቆርና የገፀ-ባሕርያቱ አሳሳል ትችት አስተናግዷል። በቴሌቪዥን በሚተላለፉ ክፍሎች ላይ ግን መሰል ገፀ-ባሕርያት ተቆርጠው እንዲወጡ ተደርጓል። የድመትና አይጥ ግብግብ የሚያሳየው ቶምና ጄሪ ዘንድሮም ተወዳጁ የካርቱን ፊልም እንደሆነ ቀጥሏል። ከጃፓን እስከ ካናዳ፤ ከኢትዮጵያ እስካ ኢራን የሕፃናት ቴሌቪዥን ጣብያዎች ይህንን ፊልም ያስኮመኩማሉ። ቻይና ውስጥ ደግሞ ይህንን ፊልም መሠረት አድርጎ የተሠራ 'ጌም' 100 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ማፍራት ችሏል። 2016 ላይ አንድ የግብፅ ከፍተኛ ባለሥልጣን በመካከለኛው ምሥራቅ ለተነሳው አለመረጋጋት ተጠያቂው ቶምና ጄሪ የተሰኘው ፊልም ነው ማለታቸው አነጋጋሪ ነበር። የኢራኑ ጠቅላይ መሪ የሃገራቸውና የአሜሪካ ግንኙነት እንደ ቶምና ጄሪ ነው ሲሉ ከአንድም ሁለት ጊዜ ተደምጠዋል። በሕፃናትም ሆነ በአዋቂዎች ዘንድ እጅግ ተወዳጅነት ያተረፈው ቶምና ጄሪ 80 ዓመት ደፍኗል። የፊልሙን ባለቤትነት የያዘው ዋርነር ብራዘርስ የተሰኘው ግዙፍ ተቋም ፊልሙን ለየት ባለ መልክ ሠርቶ ለዕይታ እንደሚያበቃ አስታውቋል።
news-56901133
https://www.bbc.com/amharic/news-56901133
ከ6.7 ቢሊየን ብር በላይ የሆነ የህወሓት ሀብት መያዙን ዐቃቤ ሕግ ገለጸ
ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ህወሓት ሊጠቅምበት ይችል የነበረን ከ6 ነጥብ ሰባት ቢሊየን ብር በላይ የሚሆን ገንዘብ ቡድኑ እንዳያገኝ ማድረጉን አስታወቀ።
ከስድስት ወር በፊት በህወሓት ኃይሎች በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ በቡድኑ አማካይነት በተለያየ መልኩ ይንቀሳቀስ ነበረን ከፍተኛ መጠን ያለውን ገንዘብ "ለወንጀል መፈጸሚያነት እንዳይውልና እንዳይሸሽ ለማድረግ መቻሉን ገልጿል። የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እንዳለው በህወሓት ቡድን ላይ ባለፉት ወራት በተደረገው የሀብት ክትትልና ምርመራ ከ6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ መቆጣጠር የቻለ ሲሆን፤ በተጨማሪም 97 ሚሊዮን 573 ሺህ ብር በላይ የሆነ ሀብት በሕግ አግባብ የውርስ ውሳኔ እንዲሰጥበት ለሚመለከተዉ አካል ማቅረቡን ገልጿል። በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጽህፈት ቤት ውስጥ በወንጀል የተገኘ ሀብት ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ጀነራል የሆኑት አቶ ዓለምአንተ አግደው እንዳሉት ይህን ያህል መጠን ያለው ሀብት ሊገኝ የቻለው በቡድኑ ተቋማትና በአመራሮቹ ላይ በተደረገ ክትትል ነው። "የህወሓት ኃይሎች ጥቃት ከፈጸሙ ማግስት ጀምሮ ቡድኑ ሲቆጣጠራቸው በነበሩ፣ ገንዘብና ንብረታቸውን ለሕገ-ወጥ አላማው ሊጠቀምባቸው ይችላል ተብለው በተጠረጠሩ ድርጅቶች እንዲሁም በጦርነት በተሳተፉ የጦር መኮንኖችና ሌሎች ባለስልጣናት ላይ በተደረገ የሀብት ክትትልና ምርመራ የተገኘ ነው" ብለዋል። በዚህም መሠረት "ክህደት ፈጽመው ከህወሓት ጋር በመሰለፍ በጦርነት ከተሳተፉ ዋና ዋና ተጠርጣሪዎች 45 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብና ሀብት የተገኘ ሲሆን፤ በገዙት ሼር ደግሞ ወደ 10 ሚሊዮን ብር ተገኝቷል" ብለዋል ኃላፊው። በዚህም በአጠቃላይ ከ54 ሚሊየን 237 ሺህ ብር በላይ የተገኘ ሲሆን በተጨማሪም ሌሎች በርካታ ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲታገዱ መደረጋቸው ተገልጿል። ህወሓት የኢንዶውመንት ተቋም ነው በሚለው ኤፈርት ስር ከሚተዳደሩና ተያያዥ ከሆኑ ድርጅቶችም ከ3 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ እንዲሁም ሼር የተገዛበት 420 ሚሊየን የሚደርስ የገንዘብ መጠን ሲገኝ በአጠቃላይ ከ4 ቢሊየን 205 ሚሊየን ብር በላይ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንደታገደ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አመልክቷል። በተጨማሪም ግምታቸዉ ከሁለት ቢሊየን ብር በላይ የሆኑ 179 የደረቅና የፈሳሽ ጭት ማመላለሻ ከባድ ተሽከርካሪዎችን የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በማውጣትና የጋራ የሕግ ትብብር ጥያቄ ለጅቡቲ መንግሥት በማቅረብ ወደ አገር እንዲመለሱ መደረጉ ተገልጿል። በዚህም የኤፈርት ተቋማት ገንዘብና ንብረት "ለተጨማሪ የወንጀል ተግባር መፈጸሚያነት እንዳይውል የመከላከል ሥራ መስራቱን" ዐቃቤ ሕግ አመልክቶ፤ እየተደረገ ያለው የወንጀልና የሀብት ምርመራው ተጠናቆ ፍርድ ቤት የመጨረሻ ውሳኔ አስኪሰጥ የኤፈርት ድርጅቶች በፍርድ ቤት በተሾሙ ገለልተኛ ባለአደራ ቦርድ ስር ሆነው ሕጋዊ ሥራዎችን ብቻ እንዲያከናውኑ ክትትል እየተደረገ ይገኛል ተብሏል። ከዚህ ባሻገርም ዐቃቤ ሕግ በተመሳሳይ "በህወሓት ቡድን ውስጥ በነበሩ አመራሮች ቀጥተኛ ቁጥጥር ይደረግባቸው ነበሩ" በተባሉ ሦስት የሲቪል ማኅበራት ላይ በተደረገ ምርመራ ከ400 ሚሊየን ብር በላይ እና ሼር የተገዛበት ከ5 ሚሊየን ብር በላይ አግኝቶ በፍርድ ቤት እንዲታገድና ገለልተኛ አስተዳዳሪ ተሹሞ በማኅበራቱ ገንዘብ ላይ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል። የዐቃቤ ሕግ በወንጀል የተገኘ ሀብት ማስመለስ ዳይሬክቶሬት አማካይነት በተደረገው የሀብት ምርመራ የህወሓት የሆነ ከ97 ሚሊዮን ብር በላይ አግኝቶ በፍርድ ቤት አሳግዶ እንደነበር ገልጿል። ይህንንም ተከትሎ ቡድኑ ኃይልን መሠረት ያደረገ የአመጽ ተግባር ላይ መሳተፉን መነሻ በማድረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከምዝገባ የሰረዘው መሆኑን ተከትሎ፤ በሕግ በሚያዘው መሠረት ቡድኑ የነበረበት ዕዳውን ተሸፍኖ የተረፈው ገንዘብ ለሥነ ዜጋና ለመራጮች ትምህርት እንዲውል ለቦርዱ መተላለፉን አቶ ዓለምአንተ አግደው ገልጸዋል። ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የህወሓት ኃይሎች ትግራይ ውስጥ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ ላይ የሰነዘሩትን ጥቃት ተከትሎ የፌደራል መንግሥቱ ወታደራዊ እርምጃ ወስዶ ቡድኑን ከሥልጣኑ ማስወገዱ ይታወሳል። ከዚህም በኋላ የህወሓት ከፍተኛ ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራሮች ላይ የእስር መዘዣ ከመውጣቱም በተጨማሪ በቡድኑ ስር ይንቀሳቀሳሉ የተባሉ በርካታ የንግድና የአገልግሎት ተቋማት ላይ እግድ ተጥሎባቸው ተጥሎባቸው እንደተነበር ይታወቃል።
news-50364744
https://www.bbc.com/amharic/news-50364744
'ኑሮ ከበደኝ' ያለው ፈረንሳያዊ ወጣት እራሱን አቃጠለ
የ22 ዓመቱ ፈረንሳያዊ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ እራሱን ካቃጠለ በኋላ ህይወቱ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ገብታለች።
ወጣቱ በፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ምክንያት ከሚማርበት ዩኒቨርሲቲ ፊትለፊት እራሱን ያቃጠለ ሲሆን ከደርጊቱ በፊት በፌስቡክ ገጹ ላይ መልዕክት አስፍሮ ነበር። ወጣቱ በጽሑፍ 'የገደሉኝ' የአሁኑና የቀድሞ የፈርንሳይ ፕሬዝደንቶች፣ የአውሮፓ ህብረት እና ቀኝ ዘመም ፖለቲከኞች ናቸው ሲል ተጠያቂ አድርጓቸኋል። የሊዮን ዩኒቨርሲቲ ተማሪው በወር በ450 ዩሮ (15ሺህ ብር ገደማ) ብቻ ህይወትን መግፋት ከብዶኛል ብሏል። እራሱን ካቃጠለ በኋላ ወደ ህክምና የተወሰደው ወጣት 90 በመቶ የሚሆነው አካሉ ከባድ ቃጠሎ አጋጥሞታል። በዚህም ህይወቱ የመትረፉ ጉዳይ አጠራጣሪ ሆኗል። "አንድ ላይ በመሆን ፋሽዝምን ለመታገል ቆርጠን እንነሳ፤ ... ልዩነቶችን የሚፈጥሩ ስርዓቶችን እንታገል" ሲል ጽፏል። "ማኽሮን [የአሁኑ የፈረንሳይ ፕሬዝደንት]፣ ፍራንስዋ ኦላንድን እና ኒኮላስ ሳርኮዚን [የቀድሞ ፕሬዝደንቶች]፣ እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት ስለገደሉኝ ተጠያቂ የሚሆኑት እነሱ ናቸው። የወደፊት ህይወቴን አጨልመውታል" ሲል በፌስቡክ ገጹ ላይ አስፍሯል። ድርጊቱን ለመፈጸም ሰዎች የሚበዙበተን ስፍራ የመረጠውም ሆነ ብሎ መሆኑን ጠቁሟል።
news-56569255
https://www.bbc.com/amharic/news-56569255
የተባበሩት መንግሥታት ኢትዮጵያ ቅሬታ ያቀረበችባቸው ኃላፊው ከአገር እንዲወጡ ወሰነ
የኢትዮጵያ መንግሥት ቅሬታ ያቀረበባቸው የተባባሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት ምክትል ተወካይ የሆኑት ማቲጂስ ሌ ሩቴ ድርጅቱ ከአገሪቱ እንዲወጡ መወሰኑ ተሰማ።
ምክትል ተወካዩ ሩቴ ላለፈው አንድ ዓመት ከሁለት ወር በኢትዮጵያ የድርጅቱ ምክትል ኃላፊ ሆነው በማገልገል ላይ የነበሩ ሲሆን መንግሥት ባቀረበባቸው ቅሬታ ምክንያት ተቋማቸው ከኢትዮጵያ አንስቶ ወደሌላ አገር እንዲዘዋወሩ ማድረጉን ቢቢሲ ከድርጅቱ ሠራተኞችና ከመንግሥት ምንጮች ተረድቷል። ቢቢሲ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው የዲፕሎማቲክ ምንጮቹ እንደተረዳው የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ተቋም ከፍተኛ ኃላፊ የነበሩት ግለሰብን ጨምሮ ሌሎች የተቋሙ ሠራተኞች ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር በተያያዘ ቅሬታ ማቅረቡን ገልጸዋል። ከከፍተኛ ባለስልጣኑ በተጨማሪም አንዲት ሴት የተቋሙ ሠራተኛ ሌላዋ ቅሬታ የቀረባበቸው ግለሰብ ሲሆኑ ግለሰቧ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት ውስጥ በከፍተኛ ኃላፊነት ላይ ያሉ መሆናቸው ታውቋል። ቢቢሲ ከተቋሙ ሠራተኞችና ከሌሎች ምንጮች ባደረገው ማጣራት ግለሰቧ ተቋሙ በአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ዙሪያ በሚሰራቸው ሥራዎች ላይ ከፍተኛ አስተባባሪ ናቸው። ባላቸው ኃላፊነትም በድርጅቱ አምስተኛ የስልጣን እርከን ላይ ያሉ ሰው መሆናቸውን ለመረዳት ችሏል። በሌላ በኩል በኢትዮጵያ መንግሥት ቅሬታ የቀረበባቸው ምክትል ኃላፊው በተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ተቋም ውስጥ ከ25 ዓመት በላይ ማገልገላቸውን ቢቢሲ ያገኛቸው ይፋዊ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከዚህ ቀደምም በቡልጋሪያ የስደተኞች ተቋሙ ዋና ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል። "በአጠቃላይ በየተመድ የስደተኞች ድርጅት ውስጥ ያሉ በርከት ያሉ ሠራተኞች ላይ ቅሬታችንን ካስገባን ሰንብተናል። በዚህም ሠራተኞቹ የሚጠበቅባቸውን የፖለቲካ ገለልተኝነት አላሟሉም የሚል ሃሳብ አለን" ሲሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለልጣን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። እኚሁ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣን ጨምረውም በሠራተኞቹ ላይ የተነሳው የገለልተኝነት ጥያቄ በትግራይ ክልል ከተካሄደው ወታደራዊ ግጭት ጋር የተያያዘ መሆኑንም ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ቢቢሲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ የሆኑትን አምባሳደር ዲና ሙፍቲን የጠየቀ ሲሆን ስለተባለው ነገር መረጃ እንደሌላቸው ገልጸዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ድርጅት በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጥበት ከቢቢሲ ጥያቄ ቀርቦለት በተቋሙ ሠራተኛ ላይ ቅሬታ መቅረቡን አረጋግጧል። "የኢትዮጵያ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በአንድ ባልደረባችን ላይ አቤቱታቸውን አቅርበዋል" ሲል ድርጅቱ ለቢቢሲ በሰጠው የኢሜይል ምላሽ ላይ ገልጿል። አክሎም "ተቋሙ ግለሰቡን ወደ ሌላ ቦታ የመቀየር ሥራ ሰርቷል፤ ይህ ግን ቀድሞውንም እየሰራንበት ከነበረው የመዋቅር ማሻሻል ተግባር ጋር የሚገናኝ ነው" ሲል ድርጅቱ ስለእርምጃው አስረድቷል። ድርጅቱ በትግራይ ክልል ካጋጠመው ድንገተኛ ቀውስ በኋላ በክልሉ ያለውን ሥራ ለማጠናከር የውስጥ ምክክሮች ሲደረጉ እንደነበር እና የተቋሙን ሰው ኃይል በድጋሚ መልሶ ለማዋቀር እየተሰራ እንደበርም የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት ገልጿል። በተመሳሳይ መንግሥት ባቀረበው አቤቱታ መሠረት ከአገር እንዲወጡ ተወስኗል ሲሉ ምንጮቻችን የገለጿቸው የድርጅቱ የፕሮጀክት አስተባባሪ ጉዳይን በተመለከተ ግን ተቋሙ ምንም አይነት አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል። በትግራይ ውስጥ የተከሰተውን ወታደራዊ ቀውስ ተከትሎ ከ70 ሺህ በላይ ሰዎች ድንበር ተሻግረው ወደ ሱዳን የገቡ መሆኑን የእርዳታ ድርጅቶች የገለጹ ሲሆን፤ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩት ደግሞ በክልሉ ውስጥ ተፈናቅለው እንደሚገኙ ተገልጿል። የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት የክልሉን ዋና ከተማ ተቆጣጥሮ ጦርነቱ ማብቃቱን ካሳወቀ በኋላ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተቋማትና ሌሎች የእርዳታ ድርጅቶች በትግራይ ውስጥ ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መስመር እንዲከፈት ሲጠይቁ ቆይተዋል። መንግሥት በቀረበለት ጥያቄ መሠረት የረድኤት ድርጅቶች ወደ ክልሉ ገብተው ለነዋሪዎች ድጋፍ እንዲያደርጉ የፈቀደ ቢሆንም አስካሁን ድረስ ከፍተኛውን የእርዳታ አቅርቦት እየሰጠ እንደሚገኝና የረድኤት ድርጅቶቹ ድረሻ ዝቅተኛ መሆኑን ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣንት ገልጸዋል። በግጭቱ ለተለያዩ ችግሮች ከተጋለጡት የትግራይ ክልል ነዋሪዎች በተጨማሪ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት የሚደግፋቸው ኤርትራውያን ስደተኞች የሚገኙባቸው መጠለያዎች ትግራይ ውስጥ እንደሚገኙ ይታወቃል።
news-53536097
https://www.bbc.com/amharic/news-53536097
በቦረና የእንስሳት ሃኪሞች ከአንድ ላም ሆድ ውስጥ 50 ኪሎ የሚመዝን ፕላስቲክ አወጡ
በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን 6 የእንስሳት ሃኪሞች ከአንዲት ላም ሆድ ውስጥ 50 ኪሎ ግራም የሚመዝን ፕላስቲክ በቀዶ ህክምና አስወገዱ።
ከጤና ባለሙያዎቹ አንዱ የሆኑት ዶ/ር ፍራኦል ዋቆ፤ “ላሚቷ በጥሩ ሁኔታ ላይ ትገኛለች” ሲሉ ከቀዶ ህክምናው በኋላ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ዶ/ር ፍራኦል “ከብቶች የሚግጡት ሳር ሲያጡ ወይም በሰውነታቸው ውስጥ የንጥረ ነገር እጥረት ሲያጋጥማቸው ፕላስቲክ ሊበሉ ይችላሉ” ያሉ ሲሆን ጨምረውም፤ ሰዎች ፕላስቲክ የሚያስወግዱበት መንገድ ለቁም እንስሳት ጤና ችግር እየሆነ ነው” ብለዋል። ከላሚቷ ሆድ ውስጥ የወጣው 50 ኪ.ግ የሚመዝነው ፕላስቲክ 50 ኪሎ ግራም ፕላስቲክ የተወገደላት ላም ባለቤት የሆኑት አቶ አሬሪ ጨሪ በተመሳሳይ ከዚህ ቀደምም ፕላስቲክ የተመገበች ሌላ ላም ወደ ጤና ባለሙያዎቹ አምጥቶ 20 ኪሎ ግራም የሚመዝን ፕላስቲክ ከሆዷ ወጥቶ ነበር። “ከዚህ ቀደም ረድተነው ስለነበረ፤ ስለሚያምነን ነው ይህችን ላም ይዞ በድጋሚ የመጣው” ይላሉ ዶ/ር ፍራኦል። በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኙት የቦረና ሕዝብ አርብቶ አደሮች ሲሆኑ፤ መተዳደሪያቸው የተመሰረተው በእንስሳቶቻቸው ላይ ነው።
news-53101244
https://www.bbc.com/amharic/news-53101244
ኬንያ ጂቡቲን ረትታ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት መቀመጫን አገኘች
ኬንያ ጂቡቲን በድምፅ ብልጫ ረትታ አፍሪካን በመወከል የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት የተለዋጭ አባልነት አግኝታለች።
በድምፅ አሰጣጡም መሰረት ኬንያ 129 ድምፅ ያገኘች ሲሆን የጂቡቲ ደግሞ 62 ነው። በመጀመሪያ ዙር 128 ወይንም 2/3 ድምፅ ማግኘት ሃገራቱ ተስኗቸው ነበር። ከአራት አመታት በፊትም ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ያልሆነ አባልነትም ተመርጣ ነበር። በወቅቱም በ185 ድምፅ አሸንፋለች። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መስራች አባል የሆነችው ኢትዮጵያ በታሪኳ ውስጥ ሶስት ጊዜ የምክር ቤቱ ቋሚ ያልሆነ መቀመጫን አግኝታለች። ከዚህ ቀደም በአፄ ኃይለሥላሴ እና በደርግ ዘመነ መንግሥታትም ነው። የምስራቅ አፍሪካዋ ሃገር ኬንያ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ምክር ቤት ቋሚ ያልሆነ መቀመጫ የነበራትን ደቡብ አፍሪካንም ትተካለለች። የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ሃገራቸው ማሸነፏንም ተከትሎ "ሃገሪቷ እያደገችበት ያለውን እንዲሁም በአለም አቀፉ ማህበረሰብ በልማት አጋርነቷ እየፈጠረች ያለውን እመርታ አሳይ ነው" ብለዋል። ጂቡቲንም በጥሩ ተፎካካሪነቷ ያመሰገኗት ፕሬዚዳንቱ የአፍሪካ ህብረትም ድጋፍ ስለቸራቸው አመስግነዋል። ፕሬዚዳንት ኡሁሩ አፍሪካ እንደ አህጉር በፀጥታው ምክር ቤት ያላትን ተሰሚነት መጨመር እንዲሁም ለጉባኤው ምርጫ ሲንቀሳቀሱበት የነበረውን ባለ አስር ነጥብ አጀንዳም እንደሚያስተዋውቁ ተናግረዋል።
52470512
https://www.bbc.com/amharic/52470512
የኮሮናቫይረስ ስጋት በሆነበት ወቅት ቤቶችን ማፍረስ "ኢሰብአዊነት" ነው በማለት አምነስቲ ኮነነ
የአዲስ አበባ አስተዳደር ህጋዊ ይዞታ የላቸውም በማለት በርካታ ቤቶችን ማፍረሱ እንዲሁም ቤተሰቦች መፈናቀላቸውን አምነስቲ በዛሬው እለት ባወጣው መግለጫ ኮንኗል።
ፎቶው ለገጣፎ/ለገዳዲ የፈረሱ ቤቶችን የሚያሳይ ሲሆን በየካቲት ወር ላይ የፈረሱ ናቸው በባለፉት ሶስት ሳምንታት በአብዛኛው በግንባታ ስራ የተሰማሩ የቀን ሰራተኞች ይኖሩባቸው የነበሩ ቤቶች በመፍረሳቸው ቢያንስ አንድ ሺ የሚሆኑ ሰዎችን ቤት አልባ ማድረጉን የገለፀው መግለጫው በተለይም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት መሆኑ ደግሞ ነገሩን የከፋ አድርጎታል ብሏል። ብዙዎቹ ቤታቸው የፈረሰባቸው ግለሰቦች የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ባስከተለው ጫና ስራቸውን ያጡ ግለሰቦች መሆናቸውን ያስታወሰው የአምነስቲ መግለጫ ባለስልጣናቱ በዚህ ሳይገቱ ለማደሪያ እንዲሁም ራሳቸውን ከዝናብ ለመከላለከል ብለው የሰሯቸውንም የፕላስቲክ እንዲሁም ጊዜያዊ መጠለያዎች በማፍረስ እንቅልፍ እያሳጧቸውም ነው ብሏል። •ስለቫይረሱ ከሚናፈሱት በጥቂቱ፡ የአሪቲ መድኃኒትነት፣ የአለምን ህዝብ መቆጣጠሪያ መንገድ •ሞተዋል የተባሉት ሴት "አልሞትኩም እህቴ ጋር ደውሉልኝ" አሉ "ቤታቸው የፈረሰባቸውና መሄጃ ያጡ ቤተሰቦች ልጆቻቸው ሜዳ ላይ ዝናብ እየወረደባቸው በብርድ ውጭ እንደሚያድሩ በአሳዛኘኝ ሁኔታ ነግረውናል" ያሉት በምስራቅና በደቡብ አፍሪካ የአምነስቲ ዳይሬክተር ዴፕሮዜ ሙቼና ናቸው አክለውም "የኮቪድ-19 ስጋት በሆነበት ወቅት ቤት መኖር ራስን ለመጠበቅና ለማገገምም ወሳኝ ሁኔታ ነው። ባለስልጣናቱ ይህንን ተገንዝበው የኮሮናቫይረስ ስጋት በሆነበት ወቅት የሰዎችን ተጋላጭነት በመጨመር ቤት አልባ ሊያደርጓቸው አይገባም" ብለዋል። በቦሌ ክፍለከተማ የሚገኙ ባለስልጣናት የካቲት መጨረሻ ላይ የተጀመረው ቤት ማፍረስ ህጋዊ ይዞታ የሌላቸው ላይ ያተኮረ መሆኑን ቢናገሩም አምነስቲ በበኩሉ ያናገራቸው ቤት የፈረሰባቸው ግለሰቦች በበኩላቸው ቦታቸውን ከአስራሶስት አመታት በፊት ከአርሶ አደሮች በመግዛት ቤታቸውን እንደገነቡ ነው። ባለስልጣናቱ በበኩላቸው የቦታዎቹን ግዥ ህጋዊነት እንደማያውቁና ቤተሰቦቹም የያዟቸው የጨረቃ ቤቶች መሆናቸውን አረጋግጠው የመሬቱን ግዢ የሚመለከተው በቀጥታ የአዲስ አበባ አስተዳደር መሆኑንም አሳውቀዋልል። ሆኖም መጋቢት ወር ላይ ቤት ቤታቸው የፈረሰባቸው ግለሰቦች የተለያዩ ቁሳቁሶችን በመጠቀምና ፕላስቲኮችን በመወጠር ድንኳን በመስራት ጊዜያዊ መጠለያ ቢሰሩም ባለስልጣናቱ ቁሳቁሶቻቸውን በመውሰድ እንዲሁም መጠለያዎቻቸውም እንዳፈረሱባቸውም መግለጫው አመላክቷል። •በቺካጎ የኢትዮጵያውያን ማኅበር መስራች አቶ መንግሥቴ አስረሴ በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው አለፈ •"ሞትን ተሻገርኳት" ከኮሮናቫይረስ ያገገመች ሴት ቤት የማፍረሱ ሁኔታ በቀጣይነት የቀጠለ መሆኑንም ያስታወሰው መግለጫው ሚያዝያ 6፣ 2012ዓ.ም ሌላ ዙር የማፍረስ ሂደት እንደጀመረ አትቷል። "በአዲስ አበባ ውስጥ በተከታታይነት እየተደረገ ያለው የቤት ማፍረስ ሁኔታ አሰቃቂ ኢሰብአዊነትን የሚያሳይ ነው። ህዝብ በኮሮናቫይረስ ስጋት ተሰቅዞ በተያዘበት ወቅት፣ ስራ አጥነት በተደራረበት ወቅት እንዲህ አይነት ተግባር መፈፀሙ አሳዛኝ ነው። ቀጣዩ ምግባቸው መቼ እንደሆነ የማያውቁ ሰዎችን ቤት አልባ በማድረግ ባለስልጣናቱ ሁኔታውን ወደከፋ ሁኔታ እየወሰዱት ነው።" በማለት ዴፕሮዜ ኮንነውታል። አምነስቲ የሳተላይት ምስሎችን በመጠቀም ማረጋገጥ ችያለሁ እንዳለው ከመጋቢት 28፣ 2012 ዓ.ም ጀምሮ በቦሌ ክፍለ ከተማ አርባ በቅርብ የተሰሩ ቤቶች ከጥቅም ውጭ መሆናቸውን ወይም መፍረሳቸውን ነው። በአካባቢው ቤቶቹ ከመፍረሳቸው በፊትና በኋላ የነበረውንም ምስል አነፃፅሯል፣ በቤቶቹም ፈንታ የተተከሉ ድንኳኖችም እንዳሉ በመግለጫው ውስጥ በተካተቱ ፎቶዎች አሳይቷል። በአብዛኛው ቤታቸው የፈረሰባቸው ግለሰቦች በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩ የቀን ሰራተኞች ሲሆኑ በኮቪድ-19 ወረርሽኝም ጋር ተያይዞ ግንባታዎች በመቆማቸው ከስራ ውጭም እንደሆኑ መግለጫው አትቷል። አምነስቲ አናገርኳቸው ያላቸው ቤተሰቦች ያለምንም ማስጠንቂያ ቤቶቻቸው እንደፈረሱባቸውና፣ ባለስልጣናቱም መጥተው ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት አላማካሄዳቸውን አስረድተዋል። አምነስቲ በበኩሉ አለም አቀፉን ህግ በመጥቀስ ሰዎች ቤቶቹ የራሳቸው ይሁን፣ ኪራይ ወይም የያዙት ቦታ ቢሆን ከመፈናቀላቸው በፊት ደህንነታቸውን የሚያስጠብቁ መመሪያዎች መተግበር ነበረባቸው ይላል። አንዲት እናት ለአምነስቲ እንደተናገረችው መጋቢት 28፣2012 ዓ.ም ቤቷ ሲፈርስ በስራ ላይ የነበረች ሲሆን ጎረቤትም ደውሎ እንደነገራት ገልፃለች። "ቤቴ ከፈረሰ በኋላ አራት ልጆቼንም ሆነ ራሴን ከዝናብ ለመጠለል በፕላስቲክ ተጠቅልለን ነው የምንተኛው። ተቀያሪ ቤትም መስራት ኦልቻልንም ምክንያቱም ፖሊስ ድንኳናችን እየወሰደብን ስለሆነ" ብላለች ስሟ እንዳይገለፅ የጠየቀችው ይህች ግለሰብ የአካባቢው ባለስልጣናት ስለመፈናቀላቸውም ሆነ ለሚዲያ የተናገሩትን እያሰረ ነው ማለቷንም አምነስቲ በመግለጫው አካቷል። "ባለስልጣናቱ ከየቤታቸው የሚያፈናቅሏቸውን እንዲያቆሙ፤ ቤታቸውም ለፈረሰባቸው ተተኪ ቤቶች መሰጣታቸውን ማረጋገጥ አለባቸው። ለወደፊቱም ጉዳቱ ከደረሰባቸው ቤተሰቦች ጋር ውይይት እንዲደረግና ችግሩን ከስር መሰረቱ መቀረፍ አለበት። "በማለት ዴፕሮዜ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
news-48382822
https://www.bbc.com/amharic/news-48382822
ጌታባለው መኩሪያው፡ የብስክሌት ጀልባ የሠራው ወጣት
በውሃ ላይ የጀልባና የመርከብ ሽርሽር የተለመደ ነው፤ ኢትዮጵያዊው ወጣት ግን የጀልባ ቀዛፊ አሊያም የመርከብ ካፒቴን ሳያስፈልገን በራሳችን እጅ እየዘወርን፤ በእግራችን ፔዳሉን እየመታን ለምን አንንሸራሸርም ብሏል።
ጌታባለው መኩሪያው ይባላል። የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የሜካኒካል ምህንድስና የሦስተኛ ዓመት ተማሪ ነው። በቅርቡ በሞከረው የብስክሌት ጀልባ (Pedal Boat) በርካታ አድናቆቶች ተችረውታል። • በፀሐይ የሚሰራው የሕዝብ ማመላለሻ ጀልባ • አዲስ አበባ፡ የፈጠራ ማዕከል ለመሆን እየጣረች ያለች ከተማ መኖሪያው ደግሞ የጣና በለስ የስኳር ፕሮጀክት በሚገኝበት አዊ ዞን ጃዊ ከተማ ነው። በከተማው መግቢያ አካባቢ ለሚገኘው የስኳር ፋብሪካ ታስቦ የተገነባ ሰፊ የሸንኮራ አገዳ እርሻ በአካባቢው አለ። እርሻው ክረምት ክረምት በአካባቢው ከሚጥለው ዝናብ ውሃ የሚጠቀም ሲሆን በበጋ ወቅት ደግሞ ለዚሁ ሲባል ከተገነባው የመስኖ ግድብ ውሃ ያገኛል። ጌታባለውን ጨምሮ የአካባቢው ልጆች ከአካባቢው ሙቀት ራሳቸውን ለማቀዝቀዝም ሆነ እንደ መዝናኛ ግድቡ ቦታ በመሄድ ይዋኛሉ። "በዚህ ጊዜ ነው ለምን ጀልባ አልሠራም ብዬ ራሴን የጠየኩት" ሲል የብስክሌት ጀልባ ለመሥራት እንዴት እንዳሰበ ለቢቢሲ የገለጸው። ጌታ ባለው እንደሚለው መጀመሪያ ሊሠራ ያሰበው በብዙ ቦታዎች የሚገኘውንና የተለመደውን ባለመቅዘፊያ ጀልባ ነበር። በኋላ ላይ ግን ሐሳቡን በመቀየር የብስክሌት ጀልባ የመሥራት ሃሳቡ ሚዛን ደፋበት። "ቀስ በቀስ ነው ፔዳል የሚለው ሃሳብ የመጣልኝ"ይላል። ሆኖም የብስክሌት ጀልባውን ሠርቶ ለማጠናቀቅ ዓመታትን መጠበቅ ግድ ብሎታል። "የብስክሌት ጀልባውን ለመሥራት ብዙ ጊዜ አይፈጅም" የሚለው ጌታባለው ወጪው ብዙ በመሆኑ ምክንያት ችግር እንዳጋጠመው ምክንያቱን ያስረዳል። ይህንን ሁሉ ተቋቁሞ የብስክሌት ጀልባውን እውን ለማድረግ የተነሳው ጌታባለው መጀመሪያ ላይ ሙከራ ያደረገው እጅግ ብዙ ብረት እንዲኖረው አድርጎ ስለነበር ክብደቱ ከፍተኛ መሆኑ ለመንሳፈፍ አስቸጋሪ አድርጎበታል። በዚህ ወቅት ነው አገልግሎት ከሰጡ እና ክብደት ከሌላቸው ዕቃዎች ጀልባውን መሥራት ጥሩ መፍትሔ መሆኑን በማመን በዚሁ መሠረት መሥራት የጀመረው። ይህም ጀልባው በቀላሉ እንዲንሳፈፍ ከመርዳቱም በላይ በአነስተኛ ወጪ ሠርቶ ለማጠናቀቅም የሚያስችለው ሆኖ አግኝቶታል። "ሙሉ ለመሉ ሠርቼ ያጠናቀቅኩት በቅርቡ ቢሆንም ስለ ጀልባው ግን ማሰብ የጀመርኩት ከሁለት ዓመታት በፊት ነው" ሲል ያስረዳል። የብስክሌት ጀልባው አራት ቱቦዎች፤ አገልግሎት የሰጠ ብስክሌት እና የግራይንደር (የብረት መቁረጫ ማሽን) አናትን በዋናነት ተጠቅሞ ነው የተሠራው። • በፀሐይ የሚሰራው የሕዝብ ማመላለሻ ጀልባ ቱቦዎች ጀልባው እንዲንሳፈፍ የሚረዱ ናቸው። ብስክሌቱ ደግሞ ለመቀመጫነት የሚያገለግል ሲሆን ጀልባውን ለማንቀሳቀስ እና መሪውን ተጠቅሞ ወደ ተፈለገው አቅጣጫ ለመጓዝ የሚያስችል ነው። ከብስክሌቱ ፔዳል ጋር የሚገናኘው ተሽከርካሪ ደግሞ ውሃውን ወደኋላ በመግፋት ጀልባው ወደ ፊት እንዲንቀሳቀስ ያግዛል። የብስክሌት ጀልባዎች ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ ከመርዳታቸውም በላይ እንደ አንድ የመዝናኛ መንገድ ጥቅም ላይ የሚውሉ እና አካላዊ እንቅስቃሴ ለማድረግም የሚያግዙ ናቸው። እንደ ጌታባለው ከሆነ ሌሎች የብስክሌት ጀልባ ዓይነቶችን ከተለያዩ ድረ-ገጾች መመለከት ቢችልም የእሱ የብስክሌት ጀልባ በብዙ ምክንያት ይለያል ይላል። "ብዙ ዓይነት የብስክሌት ጀልባዎች ቢኖሩም ይሄ በቀላሉ እና አገልግሎት ከሰጡ ዕቃዎች ቤት ውስጥ መሠራቱ ለየት ያደርገዋል" ሲል ምክንያቱን ነግሮናል። ከዚህ በተጨማሪም በቀላሉ ተፈትቶ የሚገጣጠም ከመሆኑም በላይ ይዞ ለመንቀሳቀስም የሚያስችግር አይደለም። • የዕለት ከዕለት ኑሮን የሚለውጡ ፈጠራዎች ጌታባለው የብስክሌት ጀልባውን ሠርቶ ሲያጠናቅቅ ጋራዥ ውስጥ ካገዙት ሰዎች ጋር በመሆን ነው የሞከሩት። ሥራውን በሚሠራበት ወቅት ከቤተሰቦቹ ውጭ ድጋፍ ያደረገለት አካል ባይኖርም ጋራዥ ውስጥ የሚሠሩ ጓደኞቹ ያደረጉለት ድጋፍንም ግን ሳያነሳ አያልፍም። ይሁን እንጅ ስለ ብስክሌት ጀልባው በማህበራዊ ሚዲያ ብዙዎች ከተጋሩት በኋላ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ባልደረቦች አናግረውት የነበር ቢሆንም ምንም ድጋፍ እንዳላደረጉለት ገልጿል። "የፈጠራ ሥራው በብዙ መልኩ መሻሻል ይችላል" የሚለው ጌታባለው ተሻሽሎ በሞተር እንዲንቀሳቀስ ማድረግ እንደሚቻል ገልጾልናል። በአካባቢው ያለው ውሃ ለመስኖ አገልግሎት ተብሎ የተሠራ በመሆኑ ለመዋኘትም ሆነ በጀልባ ለመዝናኛት አይፈቀድም። ጀልባ ለመጠቀም ሴፍቲ ጃኬት መጠቀምም ግዴታ ነው። ይህንን ለማግኘት ባህርዳር ድረስ ሄዶ ቢጠይቅም ሊያገኝ እንዳልቻለ ይናገራል። • ከጋና የፈጠራ ሥራዎች ጀርባ ያለው ሥራ ፈጣሪ የግድቡ ውሃ ደግሞ አነስተኛ መሆኑ ሌላው ችግር ነው። ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባትም ጣና ሐይቅ ላይ አገልግሎት እንድትሰጥ የብስክሌት ጀልባዋን ወደ ባህርዳር ለመወሰድም አቅዶ ነበር። ነገር ግን ባህርድዳር ውስጥ የሚያውቀው ሰው ባለመኖሩ ጀልባውን የሚያስቀምጥበት ቦታ ማጣቱን ጌታባለው ይገልጻል። እነዚህ ችግሮች ግን ተስፋ አላስቆረጡትም። ይህ የመጀመሪያው ፕሮጀክት ቢሆንም ሌሎች የሚያስባቸው ሥራዎችም አሉት። "ብቻዬን መሥራት አልችልም፤ የሚያግዘኝ ተቋምም ሆነ ግለሰብ ሲኖር ነው ወደ ተግባር መግባት የምችለው" በማለት የሌሎች ተባባራ አካላት እርዳታ እንደሚያስፈልገው ያስረዳል። በዚህም ምክንያት እንዳሰበው ሌሎች ዕቅዶቹን ወደ ሥራ ለማስገባት አልቻለም፤ ዋናው ምክንያቱ ደግሞ የኢኮኖሚ ችግር ነው። "ተማሪ ነኝ፤ በኢኮኖሚ በኩል ተወስኜ ቆሜያለሁ፤ በብስክሌት ጀልባው ሠርቼ ገቢ ባገኝ ያሰብኩትን እሠራለሁ" ሲል በመጨረሻም ተስፋው ገልፆልናል።
news-54196679
https://www.bbc.com/amharic/news-54196679
ካናዳ፡ በሰዓት 150 ኪሎ ሜትር እየነዳ እንቅልፍ የጣለው ካናዳዊ ተቀጣ
ካናዳዊው ሰው የሚያሽከረክረው ዘመናዊውን ቴስላ መኪና ነው፡፡ መኪናው ያለ ሾፌር እርዳታ አንድን ሰው ከቦታ ቦታ የሚወስድ ነው፡፡
መኪናው በሰዓት 150 ኪሎ ሜትር እየከነፈ ሾፌሩ ግን እንቅልፉን ይለጥጥ ነበር፡፡ ፖሊስ እንደሚለው መኪናው ክንፍ አውጥቶ በዚያ ፍጥነት ሲበር የሾፌሩ ወንበር ወደ ኋላ ተለጥጦ ከወንበር ይልቅ አልጋ ይመስል ነበር፡፡ መኪና ዘዋሪውም ይሁን አብሮት አጠገቡ የነበረው ተሳፋሪ ወንበራቸውን ዘርግተው ተኝተው ነበር፡፡ አልበርታ አካባቢ ሲደርሱ ነው የነቁት፡፡ ኤስ የተሰኘው የቴስላ ቅንጡና ዘመነኛ መኪና 140 ኪሎ ሜትር በሰዓት ራሱን ያስኬዳል፡፡ ፖሊስ የነቃው መኪናው 150 በሰዓት መብረር ሲጀምር ነው፡፡ የ20 ዓመቱ የመኪናው አሽከርካሪ ጎረምሳ፣ ፍርድ ቤት ለታኅሣሥ ቀጥሮታል፡፡ የጎረምሳው አሽከርካሪ ክስ ከተፈቀደ ፍጥነት በላይ ማሽከርከር ሆኖ ለ24 ሰዓት መንጃ ፍቃዱ የተነጠቀ ሲሆን፣ ቀጥሎ ደግሞ በአደገኛ አነዳድ ክስ ተመስርቶበታል፡፡ ተመሳሳይ ክስተት በሐምሌ ወር ፖኖካ አካባቢ ደቡብ ኤድመንተን አጋጥሞ ነበር፡፡ ሳጅን ዳሪ ተርንበል ለካናዳው ሲቢሲ ዜና እንደተናገሩት መኪናው በዚያ ፍጥነት ሲምዘገዘግ ማንም ሰው ስፖኪዮም ይሁን የፊት መስታወቱን የሚመለከት አልነበረም፡፡ ይህም አስደንጋጭ ነው፡፡ ሳጅን ጨምረው እንዳሉት መኪናውን መከታተል ሲጀምሩ ፍጥነት እየጨመረ መጣ፡፡ ምክንያቱም ከፊቱ መንገዱ ክፍት መሆኑን ሲያይ መኪናው በራሱ ጊዜ ፍጥነት ይጨምር ነበር፡፡ ማንም ግን ይህን የሚከታተል አሽከርካሪ አልነበረም፡፡ አሽከርካሪው ተኝቶ ነበር፡፡ 23 ዓመታት በትራፊክ ፖሊስነት ሰርቻለሁ ያሉት ሳጅን ዳሪ እንዲህ ዓይነት ጉድ አይቼም ሰምቼም አላውቅም ብለዋል፡፡ በእርግጥ ሳጅን እንደዚያ ይበሉ እንጂ እሳቸው ትራፊክ ፖሊስ በነበሩባቸው ዓመታት ራሱን በራሱ የሚዘውር ዘመነኛ መኪና አልተፈጠረም ነበር፡፡ ቴስላ መኪናዎች አሁን ደረጃ-2 በሚባል ሁኔታ ነው የሚነዱት፡፡ ይህም ማለት መኪናዎቹ ራሳቸውን በራሳቸው ቢዘውሩም፤ ሾፌር መሪ ሳይጨብጥ የቅርብ ክትትል ሊያደርግላቸው ግዴታ አለበት፡፡ የቴስላ መኪናዎች ፈጣሪ ኤለን መስክ በዚህ ዓመት ያለ ምንም ሾፌር እርዳታ መኪናዎች ራሳቸውን በራሳቸው እንዲዘውሩ ይጠብቃል፡፡ ያን ጊዜ ምናልባት ሾፌሮች እየነዱ እንቅልፋቸውን መለጠጥ ይችሉ ይሆናል፡፡
news-54581877
https://www.bbc.com/amharic/news-54581877
ቻይናውያን የኮቪድ -19 ክትባት ተሰልፈው መውሰድ ጀመሩ
በምስራቅ ቻይና ዜሄንጂን ግዛት ውስጥ በምትገኘው ዪዉ ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቻይናውያን የኮሮናቫይረስ ክትባት ለመከተብ ከንጋት ጀምሮ ተሰልፈው ታይተዋል።
የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት የሚጠባበቁ ቻይናውያን በቻይና መንግሥት ሲበለጽግ የነበረው ይህ የኮሮናቫይረስ ክትባት የመጨረሻው የክሊኒካል ሙከራ ላይ ይገኛል እንጂ ሙሉ ክሊኒካል ሙከራዎችን አላጠናቀቀም። ለህዝብ ጥቅም ላይ እንዲውልም ገና ፍቃድ አላገኘም። በስፍራው የሚገኘው የቢቢሲ ጋዜጠኛ ሮቢን ብራንት ማንኛውም ገንዘብ ያለው ሰው የተጠየቀውን ከፍሎ እና ተሰልፎ ክትባቱን ሲወስድ ተመልክቻለሁ ብሏል። ክትባቱ 60 የአሜሪካ ዶላር ወይም 2200 ብር ገደማ ይከፈልበታል። "ንጋት 1 ሰዓት ላይ ሆስፒታሉ ከመከፈቱ በፊት በርካቶች ክትባቱን ለማግኘት ተሰልፈው ነበር። መኪናቸውን እያሽከረከሩ፣ በታክሲ እና በእግራቸው የሚመጡ በርካታ ሰዎችን ተመልክቻለሁ" ይላል ሮቢን። የተጠየቀችውን ገንዘብ ከፍላ ክትባቱን ለመከተብ ተሰልፋ የነበረች አንዲት ሴትን አነጋግሪያት ነበር ይላል ሮቢን። "ክትባቱ ክሊኒካል ሙከራዎችን አላለፈም። ደህንነቱ አልተረጋገጠም። ክትባቱን መውሰድ አላሳሰበሽም ወይ? ስል ጠየኳት። 'ዶክተሮቹን አምናችዋለሁ። ክትባቱንም አምናለሁ' ስትል መለሰችልኝ" ይላል። የቻይና መንግሥት ክትባቱ ለህዝብ የቀረበው የክሊኒካል ሙከራ አካል ሆኖ አይደለም ብሏል። የሚጠየቀውን ገንዘብ መክፈል የሚችል እና ፍላጎት ያለው ክትባቱን መውሰድ ይችላል ብሏል። ኮሮናቫይረስ ከ10 ወራት ገደማ በፊት በቻይናዋ ዉሃን ከተማ በቅድሚያ ሪፖርት መደረጉ ይታወሳል። ቻይና ከሌሎች አገራት በተሻለ መልኩ የቫይረሱን ስርጭት መቆጣጠር ችላለች። ይሁን አንጂ በቫይረሱ ምክንያት በመላው ዓለም ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ1.1 ሚሊዮን ተሻግሯል።
news-53796986
https://www.bbc.com/amharic/news-53796986
ኮሮናቫይረስ፡ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ በቫይረሱ የተያዙባት ደቡብ አፍሪካ መመሪያዎቿን አላላች
የደቡበ አፍሪካ ፕሬዚዳንት የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ያወጣቻቸውን መመሪያዎች ለማላላት ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን ባስታወቁበት እለት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ጣሪያው ላይ ደርሷል ብለዋል።
ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ እንዳሉት ከመጪው ሰኞ ጀምሮ መመሪያዎቹ ይላላሉ። በአገሪቱ አወዛጋቢ የነበረው የአልኮል መጠጦችና የሲጋራ ሽያጭ እገዳም ይነሳል። ከዚህም በተጨማሪም የአገር ውስጥ ጉዞዎች፣ ቁጥሩ የተወሰነ የቤተሰብ ስብስብ ተፈቅዷል፤ እንዲሁም ጥቃቅን የንግድ ተቋማትም እንዲከፈቱ ተወስኗል። ፕሬዚዳንቱ በትናንትናው ዕለት በአገሪቷ ቴሌቪዥን ቀርበውም የመመሪያዎቹ መላላት ዳሽቆ የነበረውን የአገሪቱን ምጣኔ ኃብት ያንሰራራዋል በማለት ተስፋቸውን ተናግረዋል። ሆኖም ደቡብ አፍሪካውያን እንዳይዘናጉ አሳሳስበዋል። አሁን ባለው ሁኔታ የተስፋ ፍንጣቂ ቢታይም በጥንቃቄ ካልታለፈ መጪው ጊዜ ሊጨልም እንደሚችል ጠቁመዋል። በአፍሪካ ቀዳሚ በሆነችው ደቡብ አፍሪካ 570 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፤ 11 ሺህ 500 ዜጎቿንም አጥታለች። ደቡብ አፍሪካ በአህጉሪቷ ብቻ ሳይሆን በአለምም አምስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። አሜሪካ፣ ብራዚል፣ ሩሲያና ህንድ በቫይረሱ በተያዙ ሰዎች ቁጥር የአለማችን አራቱ ቀዳሚ አገራት ሆነዋል። ሆኖም በደቡብ አፍሪካ በቀን ውስጥ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መሆኑም ተገልጿል። በባለፈው ሳምንትም የተገኘው መረጃ እንደጠቆመው ከ12 ሺህ ወደ 5 ሺህ መቀነሱን ነው። ከዚህም በተጨማሪ ከህሙማኑ መካከል 80 በመቶዎቹ ማገገማቸውንና በህክምና ላይ ያሉት ዜጎችም ቁጥር ወደ 105 ሺህ ማሽቆልቆሉን ፕሬዚዳንቱ አመላክተዋል። "የባለፉትን አምስት ወራት ስንገመግም ደቡብ አፍሪካ ጣሪያው ላይ እንደደረሰች ተረድተናል፤ ከዚህ በኋላ እያሽቆለቆለ ነው የሚሄደው" በማለት ፕሬዚዳንቱ አስረድተዋል። ደቡብ አፍሪካ ወረርሸኙን እንዴት ተቆጣጠረችው? በኮሮናቫይረስ የተጠቃ ሰው ከተገኘባት እለት ጀምሮ ደቡብ አፍሪካ ጥብቅ የሚባሉ መመሪያዎችን አስተላልፋለች። ከመጋቢት ወር ጀምሮም ድንበሮቿን፣ ትምህርት ቤቶችና የንግድ ተቋማትን ዘግታለች፤ የአልኮል መጠጦች ሽያጭ ታግዷል፤ ዜጎችም በቤታቸው ብቻ እንዲወሰኑ አድርጋለች። እነዚህ መመሪያዎች የኮሮናቫይረስ የማህበረሰብ ስርጭትን በፍጥነት እንዳይስፋፋ ያገቱት ሲሆን ይህም የጤናው ዘርፍ ለህሙማኑ የሚያስፈልጉ ግብአቶችን እንዲያቀርቡ አስችሎታል። ሆኖም የአገሪቱን ምጣኔ ኃብት አሽመድምዶታል ተብሏል። የአገሪቱን የምጣኔ ኃብትም ለመታደግ መንግሥት አንዳንድ የንግድ ተቋማትን በሰኔ ወር እንዲከፈቱ ቢወስንም በሐምሌ ወር እነዚህ ውሳኔዎች እንዲቀለበሱ ተደርጓል። አገሪቷም በትናንትናው ዕለት ያነሳችውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም አስተላልፋ ነበር። በደቡብ አፍሪካም ክፉኛ የተጠቃችው የንግድ ማዕከል የሆነቸው የጉዋተንግ ግዛት ናት። በወረርሽኙ ምክንያትም የአገሪቱ ጤና ማዕከላት እንደተዳከሙም ተገልጿል።
news-48774191
https://www.bbc.com/amharic/news-48774191
የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈፀመ
የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌ የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ ሰኔ 19 ቀን 2011 ዓ.ም በላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት በቤተ ጊዎርጊስ የቀብር ቦታ መፈፀሙን የላሊበላ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ማንደፍሮ ታደሰ ለቢቢሲ ገለፁ።
• የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው አስክሬን ላሊበላ ገባ • ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ መገደላቸው ተገለጸ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የላሊበላ ከተማ ነዋሪዎች የብርጋዴር ጄነራሉ ሕልፈት ከተሰማ አንስቶ በሁሉም የአካባቢው ነዋሪዎች ሃዘንና ድንጋጤ እንደነገሰ ነው ብለዋል። ትናንት የብርጋዴር ጄነራሉን አስክሬን አውሮፕላን ማረፊያ ድረስ በመገኘት አቀባበል ማድረጋቸውን የሚናገሩት የከተማው ነዋሪና የቀብር ሥነስርዓት አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል፤ አባይ ወዳጀ አስክሬኑ የእርሳቸው መሆኑን ሳጥናቸውን ከፍተው እንዳረጋገጡ ገልፀውልናል። አቶ አባይ የብርጋዴር ጄነራሉን አስክሬን አጅቦ የመጣ የመንግሥት አካል እንዳልነበርም አክለዋል። አስክሬኑ ከአውሮፕላን ማረፊያ ወደ ተዘጋጀለት ማረፊያ - አደባባይ ተብሎ በሚጠራ ሥፍራ ያረፈ ሲሆን ሌሊቱን ሙሉ ፀሎተ ፍትሃት ሲደረግላቸው፤ ነዋሪዎችም ሃዘናቸውን ሲገልፁ አድረዋል። ዛሬም ከተለያዩ አካባቢዎች በመኪና የመጡ ወጣቶችን ጨምሮ ፖሊስና ሚሊሻ፣ ከተማ አስተዳደሩ፣ ነዋሪዎች በጋራ በመሆን በደማቅ ሁኔታ ሥነ ስርዓቱን ለመፈፀም የተለያዩ ዝግጅቶችን ሲያደርጉ ቆይተዋል። "ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በተኩስ ከተማዋ ተናውጣለች [በሃዘን ወቅት በሚተኮስ ተኩስ]፤ ሁሉም ሃዘንተኛ ነው" የሚሉት አባይ፤ " 'አሳምነው ፅጌ እንዲህ ዓይነት ድርጊት አይፈፅምም፤ ይጣራልን. . . አማራ ክልል አንድነት እንዳይኖረው የተደረገ ሴራ ነው፤ የታሰሩት እነ ጀኔራል ተፈራ ማሞ ይፈቱልን' " የሚሉ መፈክሮች ሲሰሙ መዋላቸውን ነግረውናል። • ስለ'መፈንቅለ መንግሥት' ሙከራው እስካሁን የማናውቃቸው ነገሮች በአካባቢው እንዲህ ዓይነት ጥያቄዎች ይነሱ እንጂ በከተማው የተፈጠረ የፀጥታ ችግር አለመኖሩን አክለዋል። "ትናንት ከሰዓት ጀምሮ ዛሬም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ዝግ ነበሩ" ያለችን ደግሞ ስሟ እንዲገለፅ ያልፈለገች የከተማው ነዋሪ ናት። እርሷ እንደምትለው የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ደማቅ የነበረ ሲሆን የተለያዩ ጥያቄዎችም በህብረተሰቡ ይነሱ እንደነበር ነግራናለች። "ጄነራል አሳምነው ባለፈው ዓመት ለአሸንድዬ በዓል አከባበር ላሊበላ ተገኝተው ንግግር ሲያደርጉ 'ከዚህ በኋላ የምኖረው ለአማራ ህዝብ ነው' ብሎ ስለተናገረ 'አማራን ለማጥፋት የተደረገ ሴራ ነው' እያሉ ነዋሪዎች መንግሥትን እየኮነኑ፣ ጥይት እየተተኮሱ፤ በፉከራና ቀረርቶ ታጅቦ ሥነ ሥርዓቱ ተከናውኗል'' በማለት የነበረውን ድባብ ገልፃልናለች።
news-51542805
https://www.bbc.com/amharic/news-51542805
እነ አቶ በረከት ስምኦን ዛሬ በችሎት ውሏቸው ላይ የጤና ችግር እንዳለባቸው በመግለጽ አጭር ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠየቁ
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእነ አቶ በረከት ስምኦን የክስ መዝገብ በቀረቡ ማስረጃዎች ላይ የዓቃቤ ህግን አስተያየት ለመስማት ለየካቲት 26/2012 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጠ።
ፍርድ ቤቱ በአንደኛ ተከሳሽ አቶ በረከት ስምኦን እና በሁለተኛ ተከሳሽ አቶ ታደሠ ካሣ በቀረቡ ማስረጃዎች ላይ የዓቃቤ ህግን አስተያየት ለመስማት እና ተከሳሾች ይያያዙልን ያሏቸው የሠነድ ማስረጃዎች እንዲቀርቡ ነበር ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው። ተከሳሾች የኤሌክትሪክ ስማርት ቆጣሪ ማምረትን በተመለከተ ያቀረቡት የምስክር ማብራሪያ ላይ ዓቃቤ ህግ አስተያየት ለመስጠት አለመቻሉን ጠቅሶ ለዚህም ይሆን ዘንድ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል። • «ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ በረከት አናግረውናል» የአቶ በረከት ስምዖን ባለቤት • "በረከትና ታደሰ በሙስና መጠርጠራቸው አስደንቆኛል" አቶ ጌታቸው ረዳ • "...ባለሐብቶችን ለቅመህ እሰር ብሎኝ ነበር" አቶ መላኩ ፈንታ የተጠየቀው ተለዋጭ ቀጠሮ ደንበኞቻቸው እንደሚያንገላታ የገለጹት የአንደኛ እና ሁለተኛ ተከሳሽ ጠበቃ የኤልክትሪክ ስማርት ቆጣሪው ለማሳየት ብቻ ማቅረባቸውን በመግለጽ ተለዋጭ ቀጠሮው ውድቅ ይደረግ ብለዋል። የኤሌክትሪክ ስማርት ቆጣሪው ወደ ሌላ ቦታ ሄዶ እንዲፈተሽ ከዓቃቤ ህግ የቀረበው ጥያቄም የንግድ ሚስጥርን የማይጠብቅ ሊሆን ይችላል በሚል ውድቅ እንዲሆን ተከሳሾች ጠይቀዋል። ተከሳሾች ይቅረቡልን ካሏቸው ሠነዶች መካከል የተወሰኑት የቀረቡ ሲሆን ማብራሪያ የሚጠይቁ እና መረጃዎቹ የሚሰጡት በሌላ አካል በመሆናቸው ከሚመለከተው መሥሪያ ቤት እንዲጠየቅ የሚገልጹ ምላሾች ተሰጥተዋል። ፍርድ ቤቱ በኤሌክትሪክ ስማርት ቆጣሪው ጉዳይ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለሐሙስ ተለዋጭ ቀጠሮ ቢሰጥም አንደኛ እና ሁለተኛ ተከሳሽ በኤሌክትሪክ ስማርት ቆጣሪው ምከንያት የንግድ ሚስጥር ከሚወጣ እና የአገር ሃብት ከሚጎዳ ማስረጃ መሆኑ ይቅር ብለዋል። በጉዳዩ ላይ የመከላከያ ምስክር በመሆን የቀረቡት ግለሰብ ምስክርነትም ውድቅ ይሁን ብለዋል። በዚህም በጽሑፍ ያቀረቡት ማስረጃ እንዲያዝላቸው ጠይቀዋል። ዓቃቤ ህግ በበኩሉ ዛሬ በቀረቡት ሠነዶች ላይ አስተያየት ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ይሰጠኝ ብሏል። ግራ ቀኙን የተመለከተው ፍርድ ቤት ተከሳሾች በጠየቁት መሠረት ኤልክትሪክ ስማርት ቆጣሪውንም ሆነ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የቀረቡትን የመከላከያ ምስክር ቃል ውድቅ አድርጓል። የተጠየቁ ማስረጃዎች ይቅረቡ ያለው ፍርድ ቤቱ ዓቃቤ ህግም አስተያየቱን በጽሑፍ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ቀጣዩ ቀጠሮም የካቲት 26/2012 እንዲሆን ትዕዛዝ ሰጥቷል። ተከሳሾች ጉዳዩ እስካሁን ከወሰደው ጊዜ አንጻር እና በህመም ምክንያት አሁን የተሰጠው ቀጠሮ ረዥም መሆኑን በመጥቀስ አጭር ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። "ጤንነታችን አሳሳቢ ነው" ያሉት አቶ ታደሠ "በአካል መቅረብ የማንችል ሠዎች በመሆናችን አስከሬናችን ላይ ይፈረዳል" ብለዋል። ፍርድ ቤቱ ተገቢ ያለሆነ አስተያየት መስጠታቸውን መግለጹን ተከትሎም አቶ ታደሠ ወዲያው ይቅርታ ጠይቀዋል። ክትትል የሚያስፈልገው ህመም እንዳለባቸው የጠቀሱት አቶ በረከት ስምኦን በበኩላቸው ማረሚያ ቤት ከመግባታቸው በፊት ለቀዶ ህክምና ቀጠሮ ተሰጥቷቸው እንደነበር አስታውሰዋል። በዚህ ምክንያት በተደጋጋሚ ቀጠሯቸውን ማራዘማቸውን በመጥቀስ ቀጠሮ እንዲያጥርላቸው ጠይቀዋል። • ዩኒቨርስቲው በጸጥታ ችግር ምክንያት ተማሪዎችን ወደ ቤታቸው እየሸኘ ነው በመዝገቡ ሦስተኛ ተከሳሽ የሆኑት አቶ ዳንኤል ግዛውም በጤና እክል ምክንያት አጭር ቀጠሮ ይሰጠን ብለዋል። ፍርድ ቤቱ ካለበት የሥራ ጫና እና ነባራዊ ሁኔታዎችን ከግምት በማስገባት ቀጠሮ መስጠቱን አስታውቋል። አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሠ ካሣ የጥረት ኮርፖሬሽንን በቦርድ ሰብሳቢነትና በዋና ሥራ አስፈፃሚነት ሲመሩ ሥራን በማያመች ሁኔታ በመምራት የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል በሚል ጥር 2011 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ነው። ተከሳሾች ጉዳዩ እስካሁን ከወሰደው ጊዜ አንጻር እና በህመም ምክንያት አሁን የተሰጠው ቀጠሮ ረዥም መሆኑን በመጥቀስ አጭር ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
news-56884289
https://www.bbc.com/amharic/news-56884289
"የሰው ነገር በቃኝ" ብለው ለ32 ዓመት ብቻቸውን የኖሩት ሽማግሌ ከኖሩባት ደሴት ተባረሩ
ለሰላሳ ዓመታት በላይ በአንዲት የጣሊያን ደሴት ላይ ብቻቸውን ደስተኛ ህይወት ሲመሩ የነበሩት ሽማግሌ ከሚኖሩባት ደሴት ተባረሩ።
ማውሮ ሞራንዲ ማውሮ ሞራንዲ ይባላሉ። አሁን የ81 ዓመት ሽማግሌ ናቸው። የጣሊያ ዜጋ ሲሆኑ ወደ ቡዴሊ፣ ሰሜን ሳርዲኒያ የሄዱት እንደ በ1989 (እአአ) ነበር። ቡዴሊ በሜዲታራኒያን ባሕር ውብ ከሚባሉ ሰው አልባ ደሴቶች እንዷ ናት። ቡዴሊ በዚህች ደሴት የሚኖሩ ብቸኛው የሰው ልጅ ናቸው። ሌላው በሙሉ ውብ ተፈጥሮ ነው። ባለፈው ዓመት ግን የደሴቲቱ ባለቤቶች "ይልቀቁ" ብለዋቸው ትካዜ ገብቷቸው ቆይቷል። አማራጭ አልነበራቸውም። ለ32 ዓመታት በብቸኝነት ከኖረባት ደሴት መልቀቅ ግድ ሆኖባቸዋል። "ችግር የለም መልቀቁንስ እለቃለሁ። ቡዴሊ ደሴትን ለ32 ዓመታት እንደተንከባከብኳት አዲስ የሚመጡ ነዋሪዎችም እንደሚንከባከቧት ቃል ይቡልኝ" ሲሉ እሁድ ዕለት በፌስቡክ ገጻቸው የስንብት ቃላቸውን አስፍረዋል። ሽማግሌው ለእነዚህ ሁሉ ዓመታት ከሰው ጋር ተቆራርጠው ሲቆዩ ኤሌክትሪክ ያገኙ የነበረው ከሶላር [ፀሐይ ብርሃን የሚመነጭ ኃይል] ነበር። በክረምቱ ወቅት ከ30 እስከ 40 መጻሕፍትን ያነቡም ነበር። "እንዴት ያለ ጓደኛ ትኖራለህ ይሉኛል፤ ብዙ ጓደኛ ነበር ያለኝ። እነሱም መጻሕፍት ናቸው" ሲሉ በሕይወታቸው ዙርያ በተሠራ አንድ ዘጋቢ ፊልም ላይ ተናግረዋል። "ደግሞም ጓደኞቼ ክደውኝ አያውቁም…" በማለት ለመጻሕፍት ያላቸውን ፍቅር ገልጠዋል። የቡዴሊ ደሴት ከአራት ዓመት በፊት እኚሁ ግለሰብ ከቢቢሲ 'አውትሉክ' ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ አማጺና ያልተመለዱ ነገሮችን ማድረግ ይወዱ እንደነበር ጠቀስ አድርገው ነበር። ሚስተር ሞራንዲ በሙያቸው የስፖርት አስተማሪ ናቸው። በዚያ ቃለ መጠይቅም ለምን ዓለም በቃኝ ብለው ወደ ደሴቲቱ እንዳመሩ ተጠይቀው ነበር። "በኅብረተሰባችን የሞራል ዝቅጠት ተሰላቸሁ። ሕዝቡ ለብልጭልጭ ሕይወት ያለው መስገብገብ፣ እንዲሁም በተጨማለቀው የጣሊያን ፖለቲካ ተከፋሁ። አንገሸገሸኝ። ስለዚህ ከተፈጥሮ ጋር ይበልጥ ለመቀራረብና ከብልጭልጩ ዓለም ለመራቅ ወሰንሁ። ሰው አልባ ወደሆነው ደሴት የሄድኩትም ለዚያ ነው" ሲሉ ነበር ሞራንዲ ለቢቢሲ የተናገሩት። ከሰው ሁሉ ተለይቶ ለመኖር ሲያስቡ እሳቸውና ጓደኞቻቸው በቅድሚያ ላ ማዴላና ወደተባለው ስፍራ በመሄድ ሥራ በመሥራት ለተቀረው ጊዜ የሚሆን ገንዘብን ለመቋጠር ነበር የወሰኑት። ሆኖም ቡዴሊ ደሴት ሲደርሱ የደሴቲቱ ጠባቂዎች ከደሴቷ እየለቀቁ እንደሆነና ጡረታ እንደሚወጡ ሲያውቁ ሞራንዲ እዚያው እቀራለሁ አሉ። ብቻቸውን። አሁን ወደ ሕዝብ የተቀላቀሉት ከ32 ዓመታት የብቸኝነት ሕይወት በኋላ መሆኑ ነው። "በደሴቲቱ ከሰው ጋር ሳልገናኝ ለ32 ዓመታት ስኖር አንድም ቀን አሞኝ አያውቅም፤ በክረምቱ አንድም ቀን አስሎኝ አያውቅም፤ ውብ ሕይወት ነው ያሳለፍኩት" ብለዋል። ሞራንዴ ከዚህ ደሴት ሊባረሩ በነበረ ጊዜ ጣሊያናውያን እንዳይባረሩ የድጋፍ ፊርማ አሰባስበው ለመንግሥት ማቅረባቸው ይታወሳል። መንግሥት ሽማግሌውን እንዳያባርር ከ70ሺህ በላይ ሰዎች በድጋፍ ፊርማ ጠይቀው ነበር። እሁድ ዕለት ሚስተር ሞራንዴ ለጋርዲያን ጋዜጣ እንደተናገሩት የተቀረ ሕይወታቸውን በትንሽዬ አፓርትመንት ውስጥ እንደሚያሳልፉና ክፍሏም ወደ ባሕር የምታሳይ መስኮት ስላላት ባሕሩን እያዩ እንደሚውሉ ተናግረዋል።
51686709
https://www.bbc.com/amharic/51686709
በኢራን በኮሮናቫይረስ ምክንያት ከ200 ሰዎች በላይ ሞቱ
በኢራን ከ210 በላይ ሰዎች በኮሮናቫይረስ ምከንያት መሞታቸውን ቢቢሲ ከተለያዩ ሆስፒታሎች ያገኘው መረጃ አሳየ።
በርካቶቹ ሟቾች ቫይረሱ በኢራን መጀመሪያ በተከሰተባቸው ሁለት ከተሞች፣ በዋና ከተማዋ ቴህራን እንዲሁም ቆም የተሰኘችው ከተማ ነዋሪዎች መሆናቸው ታውቋል። የሟቾቹ ቁጥር መንግሥት ከተናገረው በስድስት እጥፍ እንደሚልቅ ሲሆን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር 34 ሰዎች ብቻ መሞታቸውን ማስታወቁ ይታወሳል። የጤና ሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ የሆኑት ኪያኖሽ ጃሃንፑር ሚኒስቴራቸው ግልጽ መሆኑን በመናገር ቢቢሲን ሀሰተኛ መረጃ እየነዛ ነው ሲሉ ወንጅለዋል። • በናይጄሪያ በኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው ተገኘ • የዓለም አክስዮን ገበያ በኮረናቫይረስ እየተቃወሰ መሆኑ ተገለፀ • የዓለም ጤና ድረጅት ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሊሆን እንደሚችል አስታወቀ የቆም ከተማ የሕዝብ እንደራሴ አባል መንግሥት እውነታውን እየሸፋፈነ ነው ብለው ከወነጀሉ በኋላ አሜሪካ እውነታውን የሚያሳይ መረጃ እየተሰጠ አይደለም በማለት ስጋቷን ተናግራለች። ማይክ ፖምፒዮ " "ለኢራን መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ጥሪ አቅርበናል" ብለዋል በትናንትናው ዕለት በዋሽንግተን በነበራቸው የምክር ቤት ስብሰባ ላይ። "የኢራን የጤና ተቋማት የሚገኙበት ሁኔታ ዘመናዊና የተደራጁ አይደሉም፤ በውስጥ እየተካሄደ ስላለውም ወቅታዊ መረጃም ማግኘት ፈታኝ ሆኗል።" ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል። የኢራን ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት አባስ ሙሴይቭ የአሜሪካ የእርዳታ እጅ መዘርጋትን አጣጥለውታል። "በኢራን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ድጋፍ ለማድረግ እጇን የዘረጋችው አገር፣ አገራችን ላይ ከፍተኛ ጫና የሚያሳድር ማዕቀብ የጣለች፣ የኢኮኖሚ ሽብርተኝነት በማካሄድ ለሕክምና ተቋማቶቻችን እንኳ መድሃኒትና ቁሳቁስ መግዛት እንዳንችል ያደረገችው አገር መሆኗ ያሳዝናል። የፖለቲካ የሥነልቦና ጨዋታ ለመጫወት መፈለጓ ነው" ብለዋል። ኢራን ያጋጠማትን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንዴት መቆጣጠር እንዳለባት ላታውቅ እንዲሁም የቫይረሱ ወረርሽኝ መጠን ልትደብቅ ትችላለች የሚል ስጋት አለ። ቢቢሲ በኢራን ከሚገኙ ሆስፒታሎች እስከ ሐሙስ ዕለት ድረስ በሰበሰበው መረጃ መሰረት እስካሁን 210 ሰዎች መሞታቸውን መረዳት ችሏል። በኢራን ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ሳይቀሩ በቫይረሱ መያዛቸው የተሰማ ሲሆን በርካታ ቁጥር ያላቸው ህሙማን የሚገኙትም ቴህራን መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። አርብ ዕለት የሚካሄድ የፀሎት ስነስርዓት የተከለከለ ሲሆን ትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርስቲዎች ዝግ ሆነው ውለዋል። ከኢራን የሚወጡም ሆነ ወደ ኢራን የሚገቡ በርካታ በረራዎች በመከልከላቸው በርካቶች በያሉበት ለመቆየት ተገድደዋል።
news-46257869
https://www.bbc.com/amharic/news-46257869
የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ እና የሌሎች ሃገራት ስደተኞች ሊቢያ ወደብ ላይ ከመርከብ አንወርድም እያሉ ነው
ሊቢያ ወደብ የደረሱ ስደተኞች ህይወታቸውን ካተረፈቻቸው የዕቃ ጫኝ መርከብ አንወርድም እያሉ ነው።
መርከቧ ሊቢያ ወደብ ከደረሰች ስምንት ቀን ሞላት ቀደም ሲል በአዘዋዋሪዎች ግፍ እንደደረሰባቸው የሚናገሩት ስደተኞቹ በአስገዳጅ ሁኔታ ከመርከቧ ከመውረድ መሞትን እንደሚመርጡ ተናግረዋል። ስደተኞቹ ከሳምንት በፊት ነበር ከሊቢያ ምዕራባዊ ወደብ ወደ ሚዝራታ ያቀኑት። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መግለጫን ጠቅሶ ኤ ኤፍ ፒ እንደዘገበው ስደተኞቹ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ፣ የደቡብ ሱዳን፣ የፓኪስታን፣ የባንግላዴሽ እና የሶማሊያ ዜጎች ናቸው። • ሚሊዮን ዶላር አጭበርባሪው ስደተኛ • ለአፍሪካውያን ስደተኛ ልጆች አደገኛ የሆነው መጠለያ • የአውሮፓ ኀብረት በስደተኞች ጉዳይ ከስምምነት ደረሰ ባለፈው ረቡዕ ህጻናትንና እና ልጅ የያዘች እናትን ጨምሮ 14 ሰዎች ከመርከቧ በመውጣት ወደ ሊቢያ የስደተኞች ማቆያ መግባታቸውን አልጀዚራ ጠቅሶ 77 ሰዎች እስከትላንት ድረስ ከመርከቧ ለመውጣት ፈቃዳኛ አለመሆናቸውን ዘግቧል። የዕርዳታ ድርጅት ሠራተኞች የህክምና ድጋፍ እየሰጧቸው ሲሆን መርከቧ ውስጥ የቀሩት "ተስፋ የመቁረጥ ምልክት እየታየባቸው ነው" ብለዋል። ስደተኞች የፓናማን ሠንደቅ ዓላማ በምታውለብልበውና ኒቪን በምትባለው መርከብ ላይ የተሳፈሩት ጥቅምት 29 ነበር። "እንዴት ከመርከቡ ውረዱና ሊቢያ ቆዩ ትሉናላችሁ?" ሲል የሚጠይቀው የ17 ዓመቱ ሱዳናዊ ቢክቶር ከሬውተርስ ለቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ "ከሊቢያ ውጭ ወደየትኛውም ቦታ ለመሄድ ዝግጁ ነን" ብሏል። እንደ ቢክቶር ከሆነ በደቡባዊ ትሪፖሊ በሚገኘው ባኒ ዋሊድ የስደተኞች ማቆያ ወንድሙ እና ጓደኛው በአዘዋዋሪዎች እጅ ህይወታቸው አልፏል። ሌሎቹ ስደተኞች የመርከብ ጉዞውን የጀመሩት ወደ ማልታ ለመሄድ በማሰብ እንደሆነ ለአልጀዚራ ገልጸዋል። ፈረንሳይ ስደተኞችን የተመለከተ ጥብቅ ሕግ አወጣች በተዓምር የተረፈው ሕጻን ወላጆች የት ነበሩ? "ሁሉም ሰው የሚለው እዚሁ እንሞታለን እንጂ ከመርከቧ አንወርድም ነው" ሲል የደቡብ ሱዳን ዜግነት ያለው የ18 ዓመቱ ካኢ አስታውቋል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል ስደተኞቹ ያለፍላጎታቸው ከመርከቧ እንዲወርዱ ተደርጎ "የተለያዩ እንግልቶችን ወደሚያስተናግዱባቸው የሊቢያ የስደተኞች ማቆያዎች" ሊገቡ አይገባም ብሏል። ሊቢያ በህገወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ የሚያቀኑ ስደተኞች መተላለፊያ ማዕከል ናት።
news-57053458
https://www.bbc.com/amharic/news-57053458
ምርጫ 2013-“ከዘንድሮ ምርጫ በመውጣታችን አይቆጨንም”
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ ፓርቲያቸው ከዘንድሮ ምርጫ በመውጣት 'አይቆጨንም' ሲሉ ተናገሩ።
ከተማሪዎች ንቅናቄ ጀምሮ ከ50 ዓመት በላይ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ተሳትፎ ሲያደርጉ የቆዩት ፕሮፌሰር መረራ፤ ፓርቲያቸው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ከስድስተኛው አገራዊ ምርጫ 'በመንግሥት ተጽዕኖ መውጣቱን' ይናገራሉ። ፕሮፌሰር መረራ፣ ፓርቲያቸው ከምርጫው ስለወጣበት መንገድ እና በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ያሳለፉትን ጉዞ በተመለከተ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል። "ከዚህ በፊት ሲደረጉ የነበሩ ድርድሮች መግባባት መፍጠር አልቻሉም" የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ከምርጫ ለመውጣት ከመወሰኑ በፊት ላለፉት ሶስት ዓመታት፣ ከገዢው ፓርቲ እና ከተለያዩ አካላት ጋር ድርድር ሲያደርግ እንደነበር ፕሮፌሰር መረራ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከእነዚህ ድርድሮች መካከል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ መሐመድ የተገኙበት ድርድር እንደነበር የሚያስታውሱት ፕሮፌሰሩ፣ ይኹን እንጂ ሲደረጉ የነበሩት ድርድሮች፣ አገራዊ መግባባትን መፍጠር አልቻሉም ብለዋል። "መንግሥት . . .በአገሪቷ ውስጥ የሚደረጉ ለውጦች በበላይነት እንዲመራ ነው የሚፈልገው። እርሱን አትንኩብን ነው የሚሉት። ይህችን አገር ቀጥለን እኛ ነን መምራት ያለብን ከሚለው ሕልማቸው መውጣት አልቻሉም፤ እኛ ደግሞ የታሰርንበት፣ ስቃይ ያየንበት፣ ትልቅ ዋጋ የከፈልንበት፣ የኦሮሞ ልጆች ደማቸው የፈሰሰበት ይህንን ስርዓት መለወጥ ነው ፍላጎታችን።" አገር በሚመራው ፓርቲ እና በኦፌኮ መካከል የተፈጠረው ልዩነት የፓርቲያቸው አባላት እንዲታሰሩ እና ቢሯቸው እንዲዘጋ ምክንያት መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል። "ለምርጫ የሚያስፈልግ ከቀድሞ የተለየ ነገር የለም። የተሻሻለ ነገር የለም" ያሉት ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፤ ምርጫ ሠላም ማምጣት፣ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲወለድ ማድረግ፣ እንዲሁም መልካም አስተዳደር ሠፍኖ የሕዝብ ስሜት የአገሪቷን ኢኮኖሚ ወደ ማሳደግ መሄድ አለበት ብለዋል። ስድስተኛ አገር አቀፍ ምርጫ ይህንን ሶስት ነገሮችን እስከ አላሳካ ድረስ ከዚህ በፊት ሲደረግ ከነበረው ምርጫ ምንም ልዩነት የለውም ይላሉ። በዚህም ምክንያት ፓርቲያቸው በዚህ ዓመት ምርጫ ላይ ባለመሳተፉ እንደማይቆጫቸው ተናግረዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የብልጽግና ፓርቲ ከስድስተኛ አገር አቀፍ ምርጫ ለመውጣት ፓርቲዎች ያቀረቡትን ምክንያት መሰረተ ቢስ ነው ማለቱ ይታወሳል። "ከፖለቲካ ለመውጣት ምንም ሃሳብ የለኝም" ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ ከሶስት ዓመት በፊት ከእስር ሲፈቱ፣ ከፖለቲካ ራሳቸውን ማግለል ይፈልጉ እንደነበር የተናገሩ ቢሆንም፣ አሁን ግን ከፖለቲካ ለመውጣት ምንም ዓይነት ፍላጎት እንደሌላቸው አረጋግጠዋል። "ከፖለቲካ ለመውጣት ተስፋ መቁረጥ አለብህ፤ ሁለተኛ ደግሞ በቃኝ ከዚህ በኋላ ምንም ትልቅ ለውጥ ማምጣት አልችልም የምትል እና ወደ ሌላ ማስተላለፍ እፈልጋለሁ የሚል ደረጃ ላይ መድረስ አለብህ፤ አሁን ሳየው እዚያ ደረጃ ላይ መድረስ አልቻልኩም።" አሁን ራሳቸውን ከፖለቲካ ማግለል እንደማይፈልጉ የሚናገሩት ፕሮፌሰር መረራ "የዚህች አገር ትግል መሃል መንገድ ላይ ነው" ያለው ይላሉ። "ወንዝ አልተሻገረም፤ አሁን የምንለያይበት ጊዜ አይደለም" ይህ በእንዲህ እንዳለ በአገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ተሳትፎ እንደነበራቸው ፓርቲያቸውም ለኦሮሚያ ክልልም ሆነ በአገር አቀፍ ደረጃ መልካም አስተዋጽኦ ሲያበረክት እንደነበረ ፕሮፌሰር መረራ ተናግረው። "እንደ ታጋይ ምንም አልልም፤ ይህን ያህል ዓመት በትግል ውስጥ የቆየሁበትን ጊዜ ሳስበው የሚቆጨኝ ነገር የለም። ለምን ይህን ያህል ዓመት ትግል ውስጥ ቆየሁ ብዬ ሳስብ የሚቆጨኝ ነገር የለም፤ የቻልኩትን ያህል ሳበረክት ነው እስካሁን የመጣሁት" ግማሽ ምዕተ ዓመት ያስቆጠረው የፕሮፌሰር መረራ የፖለቲካ ትግል ጉዞ፣ ወንዝ እንዳልተሻገረ ይናገራሉ። "ታጋይ ትግሉን ወንዝ ማሻገር ይኖርበታል፤ ትግሉ ግን አልተሻገረም፤ ምኞት፣ ተስፋ፣ ሕልም ከወንዙ ባሻገር ነው " ይላሉ። በዚህን ሰዓት ፓርቲያቸው ኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ የአቅሙን ያህል እየተንቀሳቀሰ እንዳለ ተናግረዋል። ስለ ኦሮሚያ ሪፐብሊክ መገንባት እና ዲሞክራቲክ ኢትዮጵያ መፍጠር ከዚህ በፊት በኦሮሞ ምሁራን መካከል ሪፐብሊክ ኦሮሚያን ወይንም ዲሞክራቲክ ኢትዮጵያን መገንባት አልያም ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር እንደ አገር መቀጠል የሚለው ሃሳብ ልዩነት ሲፈጥር ነበር። አሁንም እነዚህ ሃሳቦች ከተለያየ አቅጣጫ ይደመጣሉ። እነዚህ በኦሮሞ ምሁራን መካከል የሚታዩ የተለያዩ ሃሳቦች የሕዝቡን ፍላጎት ሲጎዳ ነበር አሁንም እየጎዳ ነው የሚሉት ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና አሁን ግን ልዩነቶቹ እየጠበቡ መጥተዋል ይላሉ። "እንደ ቀድሞው የተራራቁ አይደሉም። የኦሮሞ ሕዝብ እና የኦሮሞ ምሁራን በሁለቱም መንገድ የኦሮሞ ሕዝብ ነጻ እስከወጣ ድረስ በሁለቱም መንገድ ሃሳቡን መውሰድ የተዘጋጁ ነው የሚመስለኝ" ይላሉ። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ መመለስን በማንሳት፣ "በዚህች አገር ውስጥ እየተገነባ ያለውን የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ውስጥ እንሳተፋለን ብለው ነው የመጡት፤ ሃሳቦች እየተቀራረቡ መጥተው ነበር። መንግሥት በሩን ባይዘጋ ኖሮ ብዙ ርቀቶች መሄድ ይቻል ነበር" ሲሉ ይናገራሉ። ፕሮፌሰር መረራ ማን ናቸው? እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1948 በምዕራብ ሸዋ ዞን ቶኬ ኩታዬ የተወለዱት ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በፖለቲካ ውስጥ አስርት ዓመታት ቆይተዋል። ፕሮፌሰር መረራ በአፄ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግሥት ተማሪዎች ንቅናቄ ላይ ከተሳተፉበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ በፖለቲካ ውስጥ ጎልህ ድርሻ አላቸው። ወደ ኋላ ላይ መኢሶን ተቀላቅለው በደርግ ዘመን ሰባት ዓመት ታስረዋል። የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ ግብጽ ከሚገኘው አሜሪካ ዩኒቨርስቲ ፖለቲካ ሳይንስ አግኝተዋል። እንዲሁም ሶስተኛ ዲግሪያቸውን ኔዘርላንድስ ተምረዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለበርካታ አመታት በመምህርነት ያገለገሉት ፕሮፌሰር መረራ የኢትዮጵያ ፖለቲካን የተመለከቱ መጽሐፍት እና ጥናቶች አሳትመዋል። በተጨማሪም የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ እና የኦሮሞ ሕዝብ ኮንግረስን አሁን ደግሞ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ በሊቀመንበርነት መርተዋል። ፕሮፌሰር መረራ በ1997 ዓ.ም የተካሄደው ምርጫን አሸንፈው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመግባት ለአምስት ዓመታት ማገልገላቸው ይታወሳል።
news-50926127
https://www.bbc.com/amharic/news-50926127
ኢንጂነር አዜብ ላይ የተመሰረተው ክስ ከ5.1 ቢሊዮን ብር ውል ጋር የተያያዘ ነው
በቀድሞ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ በነበሩት ኢንጂነር አዜብ አስናቀ ላይ ከባድ የሙስና ክስ ተመሰረተባቸው።
የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ሕግ ህዝብ ግነኙነት ኃላፊ አቶ ዝናቡ ቱኑ ኢንጂነር አዜብ ላይ የተመሰረተው ክስ ከ5.1 ቢሊዮን ብር ውል ጋር የተያያዘ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ታላቁ የህዳሴ ግድብ ውሃ የሚያርፍበትን 123ሺህ ሄክታር በላይ ስፋት የሪዘርቨር ክሊሪንግ እና የባዮማስ ዝግጅት ሥራ፤ ደን የመመንጠር፣ የማጽዳት እና ከግድቡ ስፍራ የማጓጓዝ ሥራን ለማስፈጸም ከኢፌዲሪ ብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ጋር የተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር በብር 5.1 ቢሊዮን ብር የጋራ ውል ስምምነት ፈጽሞ እንደነበረ አቶ ዝናቡ ይናገራሉ። ይህ የስምምነት ውል በተገባበት የስምምነት ጊዜ እና ሂደት ባለመፈጸሙ በመንግሥት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ማድረሱን አቶ ዝናቡ ተናግረዋል። በዚህ መሰረት የቀድሞ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ሥራ አስፈጸሚ የነበሩት ኢንጅነር አዜብ አስናቀ እና ሌሎች የዚህ ወንጀል ድርጊት ተሳታፊ ናቸው የተባሉ 50 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ እንደተመሰረተባቸው አቶ ዝናቡ ገልፀዋል። ኢንጂነር አዜብ አስናቀ በአሁኑ ወቅት በቁጥጥር ሥር ስለመዋላቸው የተጠየቁት የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ሕግ ህዝብ ግነኙነት አቶ ዝናቡ ቱኑ፤ "በእሱ ላይ ምላሽ መስጠት አልችልም" ብለዋል። በኢንጂነር አዜብ እስናቀ የክስ መዝገብ የቀድሞ የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኮለኔል ሙሉ ወ/ገብርኤል እንደሚገኙበት አቶ ዝናቡ ተናግረዋል።
news-50798741
https://www.bbc.com/amharic/news-50798741
በኢራቅ ጎዳናዎች ከፍ ያሉት ሴቶች
ከጥቅምት ጀምሮ ኢራቅ መንግሥትን በሚቃወሙ ለውጥ ፈላጊዎች እየተናጠች ነው። ተቃዋሚዎቹ የተለያዩ የማህበረሰቡን ክፍል የሚወክሉ ቢሆንም፤ አባታዊ ስርአት በከፍተኛ ሁኔታ በሰፈነባት ኢራቅ ሴቶች ተቃውሞውን ሲመሩት ተስተውሏል።
• ኢራቅ ከአሜሪካ የበለጡ ሴት እንደራሴዎች አሏት • "ማርታ፣ ለምን ለምን ሞተች?" ያላቸውን አስተዋፅኦ ለማሳየት በመዲናዋ ባግዳድም የስዕል ስራዎች ተሰቅሎላቸዋል። የዓመፁ ማዕከል የሆነው የባግዳድ ታህሪር አደባባይም ፈጠራ በተሞላባቸው ስዕሎች ተሞልቷል። በተቃውሞቹ ላይ ከፍተኛ ስፍራ የነበራቸውን የኢራቅ ሴቶችን ጥንካሬና አይበገሬ መንፈሳቸውንም የሚወክሉ ስዕሎችም ተንፀባርቀዋል። ብዚዎቹ የጥበብ ስራዎች የተሰሩት በሴቶች ሲሆን፤ በሃገሪቱ ውስጥ ሴቶች ሊኖራቸው የሚችለውን ሚናም ጠቋሚ ነው ተብሏል። ተቃውሞዎቹም ሆነ እነዚህ የጥበብ ስራዎች የኢራቅ ሴቶች አንድ ላይ ተሰባስበው እንዲመጡ፣ በሃገራቸው ላይ ያላቸውን ቦታ እንደገና እንዲያጤኑትና ታሪክንም እንደገና እንዲፅፉ ማስቻሉም እየተነገረ ነው። ምንም እንኳን ብዙ ሴቶች ከቤተሰቦቻቸውም ሆነ ከባሎቻቸው ጫና ቢደርስባቸውም ይህንን በመቋቋም ተቃውሟቸውን አደባባይ ይዘውት ወጥተዋል። እስካሁንም ባለው አራት መቶ የሚሆኑ ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች ተገድለዋል። • "ማንም መብታችንን ሊሰጠን ስለማይችል፤ ሴቶች ማንንም ሳይጠብቁ በራሳቸው መታገል አለባቸው" በብዙ ፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ዘንድ ችላ ተብለው የነበሩት ሴቶች የራሳቸውንም አጀንዳ ለመቅረፅ ተቃውሞውን እየመሩ ነው። አብዛኛውን ጊዜ ሴቶችና ወንዶች አብረው በማይተጋገዙባቸው መድረኮች እንደነዚህ የተባበሩ እንቅስቃሴዎች ማየት ከፍተኛ ለውጥን የሚያመጣም ነው ተብሏል።
news-52103783
https://www.bbc.com/amharic/news-52103783
ኮሮናቫይረስ፡ ለኅዳር በሽታ ያልተበገሩት የ108 ዓመቷ አዛውንት ለኮሮና እጅ ሰጡ
የኅዳር በሽታ በድሮ ጊዜ የነበረ ነው። ፈረንጆቹ ስፓኒሽ ፍሉ ወይም ግሪፕ ይሉታል። በኦሮምኛ ተናጋሪዎች ዘንድ ደግሞ ዱ'ኩባ ቂሌንሳ ወይም የንፋስ በሽታ ይባል ነበር።
ወ/ሮ ሂልዳ ቸርች የአንደኛውን የዓለም ጦርነት ፍጻሜ ተከትሎ ዓለምን ጉድ ያደረገ መቅሰፍት ነው። ያን ጊዜ በሕይወት ነበሩ፣ እንግሊዛዊቷ ወ/ሮ ሂልዳ ቸርችል። የዓለምን ሕዝብ በሚሊዮኖች የቀጠፈው ይህን በሽታ በድል የተወጡት እኚህ አይበገሬ ሴትዮ በመጨረሻም ለኮሮናቫይረስ እጅ ሰጥተዋል። እማማ ሂልዳ የሞቱት በታላቋ ብሪታኒያ ኦክስፎርድ ከተማ በፎልድ ኬንዮን ሎጅ የጡረተኞች ማዕከል ውስጥ ቅዳሜ ዕለት ነው። እማማ ሂልዳ ለአራት ቀናት የኮቪድ-19 መለስተኛ ምልክቶች ታይተውባቸው በኮሮናቫይረስ ከተያዙ በኋላ ነው ሕልፈታቸው ማለፉ ድንገት የተሰማው። የልጅ ልጃቸው ሚስተር ዊል ሃድኮፍት "አያቴ ልበ-ቀናና የቤተሰባችን ዋልታና ማገር ነበሩ" ሲል በሐዘን ልብ ለቢቢሲ ተናግሯል። በ108 ዓመታቸው የሞቱት እማማ ሂልዳ ቅዳሜ ባይሞቱ ኖሮ 109 ዓመት ልደታቸው በነገታው እሑድ ሊከበርላቸው ዕቅድ ተይዞ ነበር። "በእውነቱ ልባችን ተሰብሯል፤ በተለይ ለልደቷ አንድ ቀን ሲቀራት መሞቷ ድርብ ሐዘን ነው፤ ለዘላለሙ እንናፍቃታለን›› ብሏል የልጅ ልጃቸው አቶ ዊል ሃድክሮፍት። የልጅ ልጃቸው ሃድክሮፍት ራሳቸው ዕድሜያቸው የዋዛ አይደለም። 50 ዓመታቸው ነው። እማማ ሂልዳ 4 ልጆች፣ 11 የልጅ ልጆች፣ 12 የልጅ ልጅ ልጆችና 3 የልጅ ልጅ ልጅ ልጆችን አይተዋል። እማማ ሂልዳ በሰፈር መኪና ሲያልፍ "እኒህ ሀብታም መሆን አለባቸው" ይባል በነረበት ዘመን የነበሩና፤ ለመጀመርያ ጊዜ አውሮፕላን ክንፍ አውጥቶ ሲበር እንደተመለከቱ የልጅ ልጃቸው መስክረዋል። እማማ ሂልዳ የአንደኛውንም ሆነ የሁለተኛውን የዓለም ጦርነት ተመልክተዋል። የኅዳር በሽታ በኢትዮጵያ የኅዳር በሽታ እንደ ጎርጎሮሲያዊያኑ ከ1918 ጀምሮ ለሁለት ዓመታት የዘለቀና በመላው ዓለም 50 ሚሊዮን ሰዎችን የፈጀ መቅሰፍት ነበር። ያኔ ድሮ የእማማ ሂልዳን ታላቅ እህትም የገደለው ይኸው ወረርሽኝ ነበር። በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1911 ይህ መቅሰፍቱ ወደ አገራችን በኅዳር ወር በመግባቱ በተለምዶ የኅዳር በሽታ በሚል ይታወቃል። ቸነፈር ብለው የሚጠሩትም አሉ። በወቅቱ በተለይ በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቀባሪ እስኪያጡ ድረስ በቀን እስከ 300 ሰዎች ይሞቱ እንደነበር በታሪክ ተጽፏል። በሽታው ከኅዳር 7-20 ድረስ ለ14 ቀናት ብቻ ቢዘልቅም በሺህ የሚቆጠሩ አዲስ አበባዊያንን ፈጅቷል። ከመኳንንቱ መካከልም ከንቲባ ወሰኔ ዘአማኑኤልም በዚሁ ወር እንደሞቱም ይነገራል። አንዳንድ ታሪክ ጸሐፍት ስለዚህ በሽታ ልዩ ነገር ሲዘግቡ "የተያዘው ሰው በ5ቀናት ውስጥ ወይ ይሞታል ወይ ይሽራል›› ሲሉ ጽፈዋል።
51569066
https://www.bbc.com/amharic/51569066
በጀርመን በተፈጸመ ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች ተገደሉ
በጀርመን የሺሻ ባር ላይ በተፈጸመ ጥቃት ስምንት ሰዎች መሞታቸውንና ጥቃት ፈጻሚዎቹ ማምለጠጣቸው ተነገረ።
መሣሪያ የታጠቁ ግለሰቦች ባደረሱት ጥቃት ከሞቱት ሰዎች ባሻገር ቢያንስ አምስት ሰዎች ሳይጎዱ እንዳልቀሩ የአካባቢው ፖሊስ ተናግሯል። ጥቃቱ የተፈፀመበት ስፍራ ሃናው የሚባል ሲሆን ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን እየፈለገ መሆኑን አስታውቋል። • የዘመኑ ህጻናት የወደፊት እጣ ፈንታ ጥያቄ ውስጥ ገብቷል ተባለ • "ትግራይ ላይ ያለው ጥላቻ ይስተካከል፤ ካልሆነ ትግራይ ራስዋን የቻለች አገር ናት ብላችሁ አውጁ" ዶ/ር ደብረፅዮን • የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አባላት በንስሐ እስኪመለሱ ክህነታቸው ተያዘ ከአካባቢው የሚወጡ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ ጥቃቱ የደረሰው በሁለት ስፍራዎች ሲሆን አንዱ በመሃል ከተማ ሌላኛው ደግሞ ከመሃል ከተማው ርቆ በሚገኝ ቦታ ነው። ፖሊስ በሁለቱም ስፍራዎች በሄሊኮፕተር በመታገዝ ተጠርጣሪዎቹን ለመያዝ አሰሳ እያደረገ መሆኑን ገልጿል። ጥቃቱ የደረሰው እኩለ ለሊት ላይ ሲሆን ቁጥራቸው የማይታወቅ ታጣቂዎች በሺሻ ባር ውስጥ የተቀመጡ ሦስት ሰዎች ከገደሉ በኋላ ወደ አሬና ባርና ካፌ በማምራት ሌሎች አምስት ሰዎችን መግደላቸው ተሰምቷል። ጥቃቱን ያደረሱበት ምክንያት አልታወቀም ሲል ፖሊስ ገልጿል። ጥቃቱ በተፈፀመበት ወቅት በአካባቢው አባቱና ወንድሙ እንደነበሩ የተናገረው የኪዮስክ ሠራተኛ "ልክ እንደ ፊልም ነው። የሆነ የማይጥም ቀልድ ዓይነት ነገር፣ የሆነ ሰው ሊቀልድብን የመጣ ነበር የሚመስለው" ብሏል ለሮይተርስ የዜና ወኪል በሰጠው ቃል። "በአጠቃላይ ምን እንደተከሰተ ገና አላብላላሁትም። አጠቃላይ የሥራ ባልደረቦቼ ቤተሰቦቼ እንደማለት ናቸው- እነርሱ እንኳ ምን አንደሆነ በውል አላወቁትም" ብሏል። ጥቃቱ የተፈፀመባት ሃናኡ ግዛት ከምሥራቃዊ ፍራንክፈርት 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ናት። ከአራት ቀን በፊት በበርሊን ቱርኮች በሚበዙበት አካባቢ በተከፈተ ተኩስ አንድ ሰው መሞቱ ይታወሳል።
news-55937229
https://www.bbc.com/amharic/news-55937229
በፈረንሳይ ሰልፍ ላይ ጥቃት ሊያደርስ ነበር የተባለው የኢራን ዲፕሎማት እስር ተፈረደበት
በግዞት ያሉ የኢራን ተቃዋሚ ቡድኖች በፈረንሳይ ባደረጉት ሰልፍ ላይ የቦንብ ጥቃት ለመፈፀም አሲሯል የተባለው የኢራን ዲፕሎማት የእስር ቅጣት ተበይኖበታል።
በወቅቱ ኦስትሪያ፣ ቪየና ይገኝ በነበረው የኢራን ኤምባሲ ይሰራ ነበር የተባለው አሳዶላህ አሳዲ የቤልጂየሙ ፍርድ ቤት የ20 አመት እስር ፈርዶበታል። ከአውሮፓውያኑ 1979 የኢራን አብዮት በኋላ በአውሮፓ ህብረት የተከሰሰ የመጀመሪያው የኢራን ባለስልጣን ሆኗል- የ49 አመቱ አሳዶላህ አሳዲ ከሱ በተጨማሪ ሶስት ሌሎች ተጨማሪ ሰዎችም ተፈርዶባቸዋል። ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት የጀርመን፣ ፈረንሳይና ቤልጂየም ፖሊሶች ጥምር ኃይል ባደረጉት ዘመቻ ነው። በአውሮፓውያኑ 2018 በፈረንሳይ ከፓሪስ ወጣ ብላ በምትገኝ ስፍራ በተደረገው ሰልፍ የዶናልድ ትራምፕን ጠበቃ ሩዲ ጁሊያኒን ጨምሮ በአስር ሺዎች የሚገኙ ሰዎች የታደሙበት ነበር ተብሏል። ፈረንሳይ ታስቦ የነበረው ጥቃት የተቀነባበረ ነው ከጀርባውም የኢራን ደህንነት ሚኒስቴር አለበት በማለት የምትወነጅል ሲሆን የሁለት ኢራናውያን ባለስልጣናትን ንብረትም እንዳይንቀሳቀስ አድርጋለች። ኢራን በበኩሏ የተባለው ጥቃት የተፈጠረ ሴራ ነው ትላለች። " ይህ ውሳኔ ሁለት ነገሮችን አሳይቷል። አንደኛው ለወንጀል ተግባራት ሲሆን ማንኛውም ዲፕሎማት ያለመከሰስ (ያለመጠየቅ መብቱ) እንደሚገረሰስና ሁለተኛው ደግሞ የበርካታ ሰዎች ህይወትን ሊቀጥፍ የሚችለውን ጥቃት የኢራን ኃላፊነት እንደሆነ" በማለት አቃቤ ህግ ሄንሪ ቢየውቲየር ለሮይተርስ ተናግረዋል። በጥቃቱ ኢላማ ነበሩ የተባሉትና በግዞት ላይ ያለው የናሺናል ካውንስል ኦፍ ሬዚስታንስ ኦፍ ኢራን (NCRI) መሪ ማርያም ራጃፊ ውሳኔውን "ለኢራን ህዝብና እየታገለ ላለው ትልቅ ድል ነው። ለኢራን መንግሥት ደግሞ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ኪሳራ ነው" ብለዋል። ኤንሲአርአይ በኢራን መንግሥት የሽብርተኛ ቡድን ተብሎ የተፈረጀ ሲሆን የእስላሚክ ሪፐብሊክ እንዲገረሰስ የሚሰራ ቡድን ነው።
53640749
https://www.bbc.com/amharic/53640749
ኮሮናቫይረስ፡ በኖርዌይ የአንዲት መርከብ ተሳፋሪዎችና ሠራተኞች በቫይረሱ ተያዙ
በኖርዌይ የመዝናኛ መርከብ ላይ ተሳፍረው የነበሩ ቢያንስ 40 መንገደኞችና ሠራተኞች በኮቪድ-19 መያዛቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ።
ኤምኤስ ሮልስ አሙንድሰን በተባለችው መርከብ ላይ ተሳፍረው የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሌሎች መንገደኞች ደግሞ ለይቶ ማቆያ ገብተው የምርመራ ውጤታቸውን እየተጠባበቁ እንደሆነ የመርከቧ ባለንብረት ተናግረዋል። ሁርቲግሩትን የተባለ የኖርዌይ ድርጅት ንብረት የሆነችው መርከብ በትሮምሶ ወደብ ያረፈችው ባሳለፍነው አርብ ነበር። በዚህም ሳቢያ ድርጅቱ ሁሉንም የመዝናኛ መርከቦቹን እንዳይንቀሳቀሱ አግዷል። የድርጅቱ ኃላፊ ዳንኤል ስካይልዳም "አሁን ትኩረት ያደረግነው ባልደረቦቻችንና እንግዶቻችንን ለመንከባከብ የምንችለውን ሁሉ በማድረግ ላይ ነው" ሲሉ በመግለጫቸው ተናግረዋል። አራት የመርከቡ ሠራተኞች የኮሮናቫይረስ ምልክት ታይቶባቸው አርብ ዕለት መርከቧ ወደብ ላይ ካረፈች በኋላ ሆስፒታል የገቡ ሲሆን በኋላ ላይ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከ158 ሠራተኞች መካከልም ሌሎች 32ቱ በቫይረሱ መያዛቸው የምርመራ ውጤታቸው አመላክቷል። ይሁን እንጂ 180 የሚሆኑ መንገደኞች ከመርከቧ እንዲወጡ የተፈቀደላቸው ሲሆን በባለሥልጣናት ቁጥጥር እንዲመረመሩ ተደርጓል። ሁሉም መንገደኞች ራሳቸውን እንዲለዩ መደረጉንም የጤና ባለሥልጣናት ተናግረዋል። ከሐምሌ አጋማሽ ጀምሮ በመርከቧ ጉዞ ላይ ከነበሩ 387 ተሳፋሪዎች መካካልም እስካሁን በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠው አምስት እንደሆኑ ተገልጿል። የጤና ባለሥልጣን የሆኑት ሊን ቮልድ ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደተናገሩት አሁን ከተከሰተው የቫይረስ ሥርጭት ጋር ተያይዞ በርካታ ሰዎች ቫይረሱ ሊገኝባቸው እንደሚችል ገልፀዋል። መርከቧ በአርክቲክ በሚገኘው ስቫልባርድ ለአንድ ሳምንት የቆየች ሲሆን በኢንግላንድና ስኮትላንድ የሚገኙ ወደቦችን ደግሞ መስከረም ላይ ለመጎብኘት እቅድ ይዛ ነበር ተብሏል። ይሁን እንጂ ኢንዱስትሪው በወረርሽኙ በመመታቱ ሁሉም የወደፊት ጉዞዎች ስለመኖራቸው የታወቀ ነገር እንደሌለ ተገልጿል። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ወረርሽኙ በመርከቦች ላይ በመዛመቱ በሺህዎች የሚቆጠሩ መንገደኞች በባሕር ላይ እንቅስቃሴያቸው ተገድቦ መቆየታቸው ይታወሳል።
news-53133220
https://www.bbc.com/amharic/news-53133220
ኮሮናቫይረስ፡ በብራዚል የሟቾች ቁጥር ከ50ሺህ ዘለለ
በኮሮና ቫይረስ የሟቾች ቁጥር በላቲን አሜሪካዋ ትልቅ ሕዝብ ባላት አገር ብራዚል እየገሰገሰ ነው፡፡ ትናንት 50ሺ ማለፉ ይፋ ሆኗል፡፡
አገሪቱ በቫይረሱ የተያዙባት ሰዎች ቁጥር አንድ ሚሊዮን አልፏል፡፡ የማኅበረሰብ ጤና ባለሞያዎች እንደሚሉት ደግሞ በብራዚል በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር የወረርሽኝ ጣሪያውን እስኪነካ ገና ሳምንታት ይቀራሉ፡፡ ብዙዉን ጊዜ በወረርሽኝ ከፍተኛው የቁጥር ጣሪያ ከተመዘበ በኋላ የተያዦች ቁጥር እየቀነሰ የመምጣት ዝንባሌ ያሳያል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት ትናንት በአንድ ቀን ብዙ ሰዎች በኮቪድ-19 የተያዙበት ዕለት ሆኖ መዝግቦታል፡፡ በአንድ ቀን መያዛቸው ከተመዘገቡ 183,000 የዓለም ሕዝቦች ውስጥ 60 ከመቶ የሚሆኑት ከሰሜን አሜሪካና ደቡብ አሜሪካ አገራት በተለይም ከአሜሪካና ብራዚል መሆናቸውን ድርጅቱ ይፋ አድርጓል፡፡ • ግሬታ፡ የአየር ንብረት ለውጥ እንደ ኮሮናቫይረስ ሊያሳስበን ይገባል • በኢትዮጵያ ዴክሳሜታዞን ጥቅም ላይ እንዲውል ተወሰነ • የዘር ጥላቻን የሚያራግቡ የፌስቡክ ጓደኞቻችንን ምን እናድርጋቸው? የሚገርመው ቫይረሱ በዚህ ፈጣን ግስጋሴው ውስጥ ሆኖም በብራዚል የአወዛጋቢው ፕሬዝዳንት ጃይ ቦልሴናሮ ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች አደባባይ መውጣታቸው ነው፡፡ የጃይ ቦልሴናሮ ተቃዋሚዎች ፕሬዝዳንቱ በብራዚል ሕዝብ ላይ ባደረሱት የጤና ምስቅልቅል ፍርድ ቤት መከሰስ አለባቸው ሲሉ ድምጻቸውን ያሰሙ ሲሆን ደጋፊዎቻቸው ደግሞ የሕግ መምሪያው ምክር ቤት እና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንታችንን ሊያሰሩት አልቻሉም፤ ሥልጣኑን እየገደቡ አስቸግረውታል ሲሉ ሰልፍ ወጥተዋል፡፡ ጃይ ቦልሴናሮ ዜጎች ወረርሽኙን ፈርተው ቤታቸው እንዳይቀመጡና ወጥተው መደበኛ ሥራቸው ላይ እንዲሰማሩ ሲቀሰቅሱ የአንዳንድ ከተማ ገዢዎች ግን ሐሳቡን በመቃወም የዜጎችን እንቅስቃሴ እየገደቡ ነው፡፡ ትናንትና እሑድ ብቻ በብራዚል የሞቱት 641 ሲሆኑ በዚያው ቀን ብቻ አዲስ የተያዙት 17ሺ ናቸው፡፡ ይህም በዚያች አገር በድምሩ የሞቱ ሰዎችን ቁጥር 50,617 አድርሶታል፡፡ በዓለም ላይ በቫይረሱ ምክንያት የሞቱ ቁጥርም ሆነ የተያዦች ቁጥር ብራዚልን የምትበልጥ አገር አሜሪካ ብቻ ናት፡፡ በዶናልድ ትራምፕ አገር አሜሪካ የተያዙት 2.2 ሚሊዮን ሲሆኑ የሞቱት ደግሞ 120,000 አልፈዋል፡፡ ፕሬዝዳንት ጃይ ቦልሴናሮ እንደሚከራከሩት በብራዚል የእንቅስቃሴ ገደብ ቢደረግ ከቫይረሱ ይልቅ ምጣኔ ሀብታዊው ምስቅልቅል የብራዚልን ሕዝብ ይገድላል፡፡ በዚህም የተነሳ በብራዚል በብሔራዊ ደረጃ ቤት ውስጥ የመቀመጥ ግዴታ አልተጣለም፡፡ ሆኖም ክፍለ ግዛቶችና ከተሞች የራሳቸውን መመሪያ እያወጡ ነው፡፡ አንዳንድ ከተሞች የእንቅስቃሴ ገደብ ካደረጉ በኋላ ቀስ በቀስ በራቸውን መክፈት ይዘዋል፤ ምንም እንኳ የሟቾችና የተያዦች ቁጥር እያሻቀበ ቢሆንም፡፡ በሳውፖሎ እና ሪዮ ዴ ጀኔሮ ከተሞች አሁንም የተቃውሞና የድጋፍ ሰልፎች እንደቀጠሉ ናቸው፡፡
news-55472950
https://www.bbc.com/amharic/news-55472950
ኮሮናቫይረስ ፡ የቻይና መንግሥት ያፈናቸው ድምጾች
ቻይና ውስጥ የኮሮናቫይረስ ከተገኘ ዓመት ሊደፍን ነው። ቻይናን ከቫይረሱ ባሻገር ያሳሰባት በድረ ገጽ ላይ ስለ ወረርሽኙ የሚሰራጩ መረጃዎች ናቸው።
አሁን ላይ መንግሥት የሚቆጣጠረው መገናኝ ብዙሃን ወረርሽኙንም መረጃውንም የተቆጣጠረ ይመስላል። ቻይና አሉታዊ ነው የምትለውን መረጃ በማፈን ትታወቃለች። መንግሥት ሳንሱር ሲያደርግ ይህ የወረርሽኝ ወቅት የመጀመሪያው አይደለም። ሕዝቡ ግን የፕሮፓጋንዳን ግድግዳ አፍርሶ እውነታውን አደባባይ ለማውጣት ታግሏል። ትችትን ሳንሱር ማድረግ ዓመቱ መባቻ አካባቢ የቻይና ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሕዝቡ መንግሥት ሳርስን የሚመስል ቫይረስን ለመሸፋፈን እየሞከረ እንደሆነ እሮሮ ያሰማ ነበር። መንግሥት ለወትሮው እንደ ዌቦ ባሉ የቻይና ማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ ትችቶችን ሳንሱር ያደርግ ነበር። ኮሮናቫይረስን በተመለከተ ይሰራጩ የነበሩ ቅሬታዎች እጅግ ብዙ ስለነበሩ ግን መንግሥት ሊደብቃቸው አልቻለም። በርካታ የሚዲያ ተቋሞች የምርመራ ዘገባ አትመዋል። ማኅበራዊ ሚዲያ ላይም ዜናዎቹ ተሰራጭተዋል። ቤይጂንግ ለዚህ ምላሽ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ጀመረችና ዘገባዎቹ ታፈኑ። አምና ጥር ላይ ፕሬዘዳንት ዢ ዢፒንግ ከሕዝብና መገናኛ ብዙሃን ርቀው ነበር። በጋዜጦች የፊት ገጽ የፕሬዝዳንቱ ምስል ማተምም ቆመ። ይህም ፕሬዝዳንቱ ከወቀሳ እየሸሹ ነው የሚል ትችት ቀሰቀሰ። ብዙም ሳይቆይ ግን የቻይና ከፍተኛ ባለሥልጣናት የየክልሉ አመራሮች ስለ ኮሮናቫይረስ ትክክለኛ መረጃ ካልሰጡ "ታሪካዊ ውርደት" ይጠብቃቸዋል አሉ። ከዚያም ወቀሳው ቫይረሱ የተነሳባት ዉሃን ከተማ ላይ ማነጣጠር ጀመረ። ዉሃን ስለወረርሽኙ ቀደም ብላ ማሳወቅ ነበረባት እየተባለ ተብጠለጠለች። በየካቲት ዢ ዢፒንግ ዳግመኛ ወደ ሕዝብ እይታ ሲመለሱ ቻይና ከወረርሽኙ በማገገም ላይ ነበረች። መረጃ አጋላጩ ዶክተር ሊ ዌንበርግ በመላው ዓለም እውቅና ያገኘ የቻይና ዶክተር ነው። ሐኪሙ ስለ ኮሮናቫይረስ መረጃ በማጋለጥና ለባልደረቦቹ ሳርስን የሚመስል ቫይረስ እንደተነሳ በመናገር ነው የታወቀው። ዶክተሩ የካቲት ላይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ከመሞቱ በፊት "በሐሰተኛ ዜና ማኅበራዊ መዋቅርን በመረበሽ" ምርመራ ሲደረግበት እንደነበረ ተደርሶበታል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የዌቦ ተጠቃሚዎች ዶክተሩን እንደሚደግፉ ቢናገሩም፤ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የለጠፉት መልዕክት ተሰርዟል። ይህ የመረጃ ድምሰሳ ሕዝቡን አስቆጥቷል። ኢሞጂና ጥንታዊ የቻይና ስውር መልዕክት መለዋወጫን በመጠቀም ለዶክተሩ ያላቸውን ድጋፍ በመግለጽም ገፍተውበታል። የታሰሩት ጋዜጠኞች የቻይና ባለሥልጣኖች የኋላ ኋላ ዶ/ር ሊ "ሰማዕት" ነው ብለው እውቅና ሰጥተዋል። ሆኖም ግን ብዙ የመብት ተሟጋቾች ከቻይና ታሪክ ተሰርዘዋል። ዉሃን ውስጥ ወረርሽኙ ሲቀሰቀስ ብዙ ዜጎች ዘገባ ሠርተው ለዓለም ሕዝብ መረጃ አድርሰዋል። ከእነዚህ መካከል ቺን ኪውሺ፣ ፋንግ ቢን እና ዛንግ ዛን በዋነኛነት ይጠቀሳሉ። ዩቲዩብ ላይ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ሰው የተመለከተው ቪድዮ ለቀዋል። ዉሃን ውስጥ ምን እንደተከሰተ የሚያሳዩ ምስሎችም አሰራጭተዋል። ቻይና እነዚህን የዜጋ ጋዜጠኞች አስራለች። የተሰወሩም አሉ። ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ሲፒጄ እንዳለው፤ ከቤጂንግ ከሚወጣው መረጃ ውጪ ዜና ያሰራጩ ብዙ ጋዜጠኞች ታስረዋል። ዩቲዩብ ቻይና ውስጥ ስለታገደ እነዚህ ጋዜጠኞች የሚያሰራጩት መረጃ ምን ያህል ሰው ጋር እንደደረሰ አያውቁም። መረጃ ከሚያስተላልፉት አንዱ ሊ ዢሃን፤ የካቲት ላይ ቪድዮ ከለቀቀ በኋላ ለሁለት ወር አድራሻው ጠፍቶ ነበር። ፖሊሶች በመኪና እያሳደዱት እንደሆነ ከገለጸ በኋላ ለሁለት ወራት ጠፍቶ ለይቶ ማቆያ እንደገባ የሚገልጽ ቪዲዮ ለቋል። ከዚያ በኋላ ድምጹ አልተሰማም። ለይቶ ማቆያ እንደገባ የሚገልጸውን ቪድዮ እንዲቀርጽ መንግሥት ጫና እንዳሳደረበትም ይገመታል። ድምጻቸው የታፈነ ወጣቶች ከመጋቢት ወዲህ ቻይና ቫይረሱን እያሸነፈች እንደሆነ ለማሳየት እየሞከረች ቢሆንም ሳንሱር የተደረጉ መረጃዎች መኖራቸው ጥያቄ አጭሯል። በተለይም ወጣት ቻይናውያን አፈናው ያስቆጣቸዋል። ነሐሴ ላይ ተማሪዎች ቢመለሱም ከዩኒቨርስቲዎች አቅም በላይ በመሆኑ ተቃውሞ ተነስቷል። ተቃውሞዎቹ በይፋ እንዳይሰሙ ቢደረግም የቻይና ወጣቶች ከተለመዱ ማኅበራዊ ገጾች ውጪ ሌሎች ገጾች በመፍጠር ቅሬታቸውን አስተጋብተዋል። ድምጻቸውን ካሰሙባቸው ድረ ገጾች መካከል ሙዚቃ ማሰራጫዎች ይገኙበታል። ቻይና የተጋነነ ተስፈኛ ምስል ለመፍጠር ሞክራለች። ሆኖም ግን ትክክለኛው መረጃ አልተገለጠም ብለው የሚያምኑ ብዙ ናቸው። ቻይናዊቷ ጸሐፊ ፋንግ ፋንግ ዉሃን ስላለው ሕይወቷ በጻፈችው ተመስግናለች። በተቃራኒው የቻይና ብሔርተኞች "ክፉ ትርክት ወዳጅ" ሲሉ አብጠልጥለዋታል። የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን አጉልተው የሚያሰሙት ድምጽ ስለ ቻይና በጎ ገጽታ የሚተርከውን ነው። እውነተኛ ታሪክ ላይ ተመርኩዞ እንደተሠራ የተነገረለት የመጀመሪያው የቴሌቭዥን ድራማ የሴቶችን ሚና ያንኳሰሰ በመሆኑ ተተችቷል። ቻይና የምትመርጠው ትርክት ቻይና ከኮሮናቫይረስ ጋር ተያይዞ ስሟ እንዳይነሳ ለማድረግ እየተጣረች ነው። ወረርሽኙን ማሸነፍ ከቻለች ፖለቲካዊ መዋቅሯ ከምዕራባውያኑ የተሻለ ስለመሆኑ ማስረጃ እንደሚሆን ታምናለች። 'የዉሃን ኮሮናቫይረስ' በሚል የተጠራው ወረርሽኝ በዚህ ስያሜ እንዳይጠራ እንቅስቃሴ አድርጋለች። የቻይና መገናኛ ብዙሃን የአሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደም መንግሥታት ቫይረሱን መቆጣጠር እንዳልቻሉ የሚጠቁሙ ዘገባዎች አስተላልፈዋል። እንዲያውም ኮቪድ-19ን 'የአሜሪካ ቫይረስ' ወይም 'የትራምፕ ቫይረስ' ብለው የሚጠሩም አልታጡም። በሌላ በኩል የአሜሪካ ፖለቲከኞች ከጤና ሥርዓቱ ይልቅ ለምርጫ ቅስቀሳ ቅድሚያ እንደሰጡ በመግለጽ የዘገቡ የቻይና ሚዲያዎች አሉ። ቻይና ወደ መጪው የፈረንጆች 2021 ስትሻገር ማስተጋባት የምትፈልገው ትርክት፤ 2020 በአንድነትና በብልጽግና መጠናቀቁን ነው። በተቃራኒው ሌሎች አገሮች የበለጠ አለመረጋጋት እና ክፍፍል ይመጣል ብለው ይጠብቃሉ።
news-45318952
https://www.bbc.com/amharic/news-45318952
ትራምፕ በማኬይን ቀብር ላይ አይገኙም
ታዋቂው አሜሪካዊ የፖለቲካ ሰውና የቀድሞ ወታደር ህይወታቸው ማለፋቸውን ተከትሎ የቀድሞ የሃገሪቱ መሪዎችን ጨምሮ አሜሪካውያን ሃዘናቸውን እየገለፁ ይገኛሉ።
በ81 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ጆን ማኬይን በቪየትናም ጦርነት ላይ የጦር አውሮፕላን አብራሪ በመሆን ሃገራቸውን አገልግለዋል። በአውሮፓውያኑ 2008 ላይ በተካሄደው የአሜሪካ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ከባራክ ኦባማ ጋር የተፎካከሩት ማኬይን ለሚቃወሟቸው ሁሉ የሚታገሉ ተብለው ይገለፃሉ። አቶ በረከት ስምኦን ከብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት ታገዱ የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውን አስከፊ ሁኔታ ላይ መሆናቸው ተገለፀ የመዋቢያ ምርቶች ውስጥ መርዛማ ንጥረ-ነገሮች ተገኙ ኦባማ «ከማኬይን ጋር ያሳለፍነው ጊዜ በቃላት የሚገለፅ አይደለም» ሲሉ ሰውየውን አሞግሰዋቸዋል። ጆርጅ ቡሽ በበኩላቸው «እርሱ እኮ የከፍተኛ ዓላማ አርበኛ ነበር» በማለት ነው ያንቆለጳጰሷቸው። በማኬይን ክፉኛ ወቀሳ ሲደርስባቸው የነበሩት የወቅቱ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በሰውየው ማለፍ የተሰማቸውን ሃዘን በመግለፅ ሃሳባቸውን ቋጭተዋል። የትራምፕ ባለቤት ቀዳማዊ እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ በበኩላቸው «ለሃገራችን ላበረከቱት እናመሰግናለን» ሲሉ ከባላቸው በሃሳብ ላቅ ያለ ፅሑፍ አስፍረዋል። እንደ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ከሆነ ዶናልድ ትራምፕ በማኬይን ግብዓተ መሬት መርሃ ግብር ላይ እንዲገኙ አልተጋበዙም። በምትካቸው ምክትል ፕሬዝደንት ማይክ ፔንስ ሊገኙ እንደሚችሉ ነው መገናኛ ብዙሃኑ እየጠቆሙ ያሉት። በተቃራኒው የቀድሞዎቹ ባራክ ኦባማና ጆርጅ ቡሽ በዝግጅቱ ላይ ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። በአይምሮ እጢ ምክንያት ለአንድ ዓመት ያህል በህክምና ሲረዱ የቆዩት የ81 ዓመቱ ማኬይን ህክምና በቃኝ በማለታቸው ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉን ቤተሰባቸው አስረድቷል።