id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
news-53803610
https://www.bbc.com/amharic/news-53803610
የሶማሊያ ልዩ ኃይል በሞቃዲሾ የሆቴል አጋቾቹን ደመሰስኩ አለ
አልሸባብ በትናንቱ ጥቃት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ገደለ።
copyrightREUTERS አልሻባብ በሞቃዲሾ አንድ ሆቴል ውስጥ ትናንት ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ የአገሪቱ ልዩ ኃይል እገታውን አክሽፊያለው ብሏል፡፡ ትናንት እሑድ አልሸባብ ባደረገው ጥቃት በትንሹ 10 ሰዎች ተገድለዋል፡፡ ጥቃቱና እገታው የተደረገበት ሆቴል ኤሊት ሆቴል የሚሰኝ ሲሆን በሊዶ የባሕር ዳርቻ የሚገኝ ነው፡፡ ጥቃት አድራሾቹ መጀመርያ በሆቴሉ መግቢያ ላይ በተሸከርካሪ የተጠመደ ቦምብ ካፈነዱ በኋላ ወደ ሆቴሉ ዘልቀው በመግባት እንግዶቹን አግተዋል፡፡ ይህ በቅርብ ጊዜ ተመረቀ የተባለው ሆቴል የተገነባው በአንድ የሶማሊያ የምክር ቤት አባል በሆኑ ሰው ሲሆን ትልልቅ የአገሪቱ ባለሥልጣናት ይዘወተራል ተብሏል። የጸጥታ ኃይሎች አካባቢውን ካጠሩ በኋላ ከአጋቾቹ ጋር የተኩስ ልውውጥ ውስጥ ገብተዋል፡፡ ከአራት ሰዓታት የተኩስ ልውውጥ በኋላ የመንግሥት ቃል አቀባይ የሆኑት ኢስማኤል ሙክታር ኡመር በትዊተር ሰሌዳቸው እገታው መክሸፉን ይፋ አድርገዋል፡፡ በዚህ የትዊተር መግለጫቸው ቃል አቀባዩ እንዳሉት አጋቾቹ ሁሉም 'ተደምስሰዋል'፡፡ እስካሁን ምን ያህል አጋቾች በዚህ ጥቃት እንደተሳተፉ የወጣ መረጃ የለም፡፡ ከሟቾቹ መካከል ከማስታወቂያ እና ከመከላከያ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሥልጣናት ይገኙበታል፡፡ ሌሎች በርካቶች በጥቃቱ ቆስለዋል፡፡ አንድ የግል የሶማሊያ የዜና አገልግሎት የሚሰጥ ድረገጽ እገታው የተካሄደበት ሆቴል በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ጥበቃና ፍተሻ የሚደረግበት እንደሆነ ጽፏል፡፡ የአልሸባብ እንደሆነ ከሚገልጽ አንድ የኢንተርኔት መልእክት ‹‹ሠራዊታችን አንድ ዘመቻ ላይ ነው። በምክር ቤት አባሉ የተገነባው ኤሊት ሆቴል ውስጥ የተሰዉ አባሎቻችን አሉ፡፡ ጥቃት እየዳረስንባቸው ያለነው ፈጣሪን የካዱትና የጥመት መንገድን የተከተሉት ላይ ነው›› ይላል፡፡ ከአልቃኢዳ ጋር በጥምረት የሚሰራው አልሸባብ በሶማሊያና አጎራባች አገራት ውስጥ ጥቃት ሲያደርስ ዐሥር ዓመት አስቆጥሯል፡፡ አልሸባብ በመንግሥት ኃይልና በአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል ትብብር ከፖለቲካው ገለል የተደረገ ቢሆንም አሁንም አልፎ አልፎ በአገሪቱ ላይ ጥቃቶችን የመሰንዘር አቅሙን አላጣም፡፡ በተለይም ባለፉት ሁለት ወራት የአልሸባብ ጥቃት በርትቷል፡፡ ባለፈው ሳምንት ለምሳሌ በአንድ ታሳሪ በነበረ የአልሸባብ አባልና በእስር ቤት ጠባቂዎች መካከል በነበረ መታኮስ 20 ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸው አይዘነጋም፡፡ እስር ቤት ሳሉ የጦር መሣሪያ ማግኘት የቻሉ የአልሸባብ አባላት ከፍተኛ ጥበቃ ይደረግለታል ከሚባለው እስር ቤት ተታኩሰው ሊያመልጡ ሲሉ ነበር አደጋው የደረሰው።
news-54178624
https://www.bbc.com/amharic/news-54178624
በኢትዮጵያ ከ1.8 ሚሊዮን በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተገለፀ
ኢትዮጵያ ውስጥ ከ1.8 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አስታወቀ።
በያዝነው ወር የወጣውና ከኢትዮጵያ መንግሥትም እውቅና እንደተሰጠው በተገለጸው የድርጅቱ ሪፖርት መነሻ ያደረገው ከሰኔ እስከ ሐምሌ የተሰበሰበ መረጃን ነው። መረጃው የተገኘው ከ1200 የተፈናቃዮች መጠለያዎች እንዲሁም ከሌላ 1200 ተፈናቅለው የነበሩ ሰዎች የተመለሱባቸው መንደሮች ነው። ሰዎች በዋነኛነት እየተፈናቀሉ የሚገኙት በግጭት ሳቢያ ሲሆን፤ በመላው አገሪቱ 1,233,557 ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል ። ሁለተኛው ምክንያት ድርቅ ሲሆን 351 ሺህ 62 ሰዎችን አፈናቅሏል። በጎርፍ ሳቢያ የተፈናቀሉ ደግሞ 104 ሺህ 696 ናቸው። ድርጅቱ በደቡብ እና ሲዳማ ክልሎች በሰበሰበው መረጃ መሠረት፤ ባጠቃላይ 93 ሺህ 982 ተፈናቅለዋል። 66,994ሰዎች (71 በመቶ ያህሉ) የተፈናቀሉት በግጭት ምክንያት ሲሆን፤ 26,988ሰዎች (29 በመቶው) በጎርፍ ሳቢያ ቤት ንብረታቸውን አጥተዋል። ከደህንንት፣ የመሠረተ ልማት ውስንነት እና የአየር ንብረት ለውጥ አንጻር በተለያዩ ክልሎች የተሠራው ዳሰሳ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚለያይ ነው። ሆኖም ግን በሁሉም ክልሎች በመዘዋወር መረጃ ተጠናቅሯል። የድርጅቱ ሪፖርት ተፈናቃዮች አሁን ከሚገኙባቸው መጠለያዎችና በተለያየ ጊዜ የተፈናቀሉ ሰዎች በመልሶ ማቋቋም ከሚኖሩባቸው መንደሮች የተሰባሰበ ነው። መልሶ ማቋቋሚያ ሂደትን በተመለከተ ምን ያህል የመሠረተ ልማት አቅርቦት አለ? ተፈናቃዮችን ወደ ቀድሞ ሕይወታቸው ለመመለስ የሚደረገው ጥረትስ ምን ይመስላል? የሚለው ተፈትሿል። መንግሥት ካለፈው ዓመት ግንቦት አንስቶ ተፈናቃዮችን የመመለስ ሥራ ጀምሯል። አምና ሚያዝያ ላይ የተፈናቃዮች ቁጥር 3.04 ሚሊዮን ደርሶ ነበር። በአገሪቱ ባጠቃላይ1,400,892 ተፈናቃዮች ወደ መንደራቸው ተመልሰዋል። ከተመላሾች መካከል 1,328,652 (95 በመቶ ገደማው) በግጭት ምክንያት ነበር የተፈናቀሉት። ድርጅቱ ከጎርጎሮሳውያኑ 2016 ጀምሮ በተፈናቃዮች መጠለያዎች፣ ከ2019 ወዲህ ደግሞ ተመላሾች በሚኖሩባቸው መንደሮች ዳሰሳ ያካሂዳል። የድርጅቱ የኢትዮጵያ ጊዜያዊ አስተባባሪ ሳራ ቾንግ “ተፈናቃዮችና ተመላሾችን በተመለከተ ጥልቅና አስተማማኝ መረጃ በመስጠት እንቀጥላለን” ብለዋል። መረጃው ሰብዓዊ እርዳታ ለማድረግና ፖሊሲ ለመቅረጽ ይውላል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉም አክለዋል። በድርጅቱ የሚወጡ ሪፖርቶች በአገራዊ ደረጃ እንዲሁም በቀጠናውም የሰዎችን እንቅስቃሴ ለመቃኘት ይረዳሉ። ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) ከአገራዊው አደጋ መከላከልና ዝግጁነት እንዲሁም ከሠራተኞችና ማኅበራዊ ጉዳይ ጋር በቅርበት ይሠራል። መረጃው ከመንግሥት በተጨማሪ ለኢ-መንግሥታዊ ድጋፍ አድራጊዎችና የመብት ተሟጋቾችም ይሰጣል።
news-54581878
https://www.bbc.com/amharic/news-54581878
እምቦጭን ለማጥፋት በጣና ሐይቅ ዘመቻ ሊጀመር ነው
በጣና ሐይቅ ላይ የተከሰተውን የእምቦጭ አረም በአንድ ወር ዘመቻ ለማጥፋት ከነገ ሰኞ ጀምሮ ወደ ሥራ እንደሚገባ ተገለጸ።
ጣና ሐይቅ ባለፉት ዓመታት የተለያዩ ፈተናዎች እየገጠሙት ነው የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ እንዳሉት ዘመቻው የሚከናወነው ከጥቅምት 09 እስከ ህዳር 09/2013 ዓ.ም ነው። "የጣና ሐይቅን መጠበቅ እና ከአደጋ ነጻ መሆን አለበት" የሚል እምነት ክልሉ አለው ያሉት ዳይሬክተሩ የዘመቻው ዓላማ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ጣናን ከእምቦጭ በመታደግ ወደነበረበት መመለስ እና የህዳሴ ግድብንም ከእምቦጭ አረም ስጋት ነጻ ማድረግ ነው ብለዋል። በሦስት ዞኖች፤ 9 ወረዳዎች እና አንድ የከተማ አስተዳደርን ጨምሮ በ30 ቀበሌዎች ላይ የእምቦጭ አረሙ ተስፋፍቶ 4ሺህ 300 ሄክታር የሚሆነው የሐይቁን ክፍልም አረሙ ወሯል። ክልሉ ሐይቁንና ሌሎች የውሃ ውስጥ አካላትን የማልማት እና የመጠበቅ ኃላፊነት የተሰጠው ኤጄንሲ ከማቋቋም ባለፈ በበጀት እና የሰው ሃይል በመመደብ በተለያየ ጊዜ ሐይቁን ከእምቦጭ ለመከላከል መሥራቱን አስታውቀዋል። በዚህም አረሙ እንዳይስፋፋ ማድረግ መቻሉን አስታውቀው ሆኖም እምቦጭን ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት በአካባቢው ማህበረሰብ እና ክልል ብቻ ማሳካት አይቻልም ብለዋል። በዘመቻው ከሁሉም ክልሎች እና ከሁለቱ የከተማ መስተዳደሮች መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ የምርምር ማዕከላት፣ የሲቪክ ማኅበራት እና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ይሳተፋሉ ተብሏል። እምቦጭ የሚገኝባቸውን ቀበሌዎች እና ወረዳዎች በመከፋፈል በቀን ከ250 እስከ 300 ሰው በየቀበሌው የሚሠማራ ሲሆን ይህንን የሚያስፈጽም ኮሚቴም ተቋቁሟል። ክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮችም ተከፋፍለው ሊያስወግዱት የሚችሉት ድርሻ እንደሚሰጣቸው ለማወቅ ተችሏል። ለዘመቻው 106 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ እና ይህንም ከተለያዩ አካላት ለማሰባሰብ መታቀዱም ተገልጿል።
news-55403162
https://www.bbc.com/amharic/news-55403162
የሚበሩ መኪኖች እየመጡ ነው - ዓለምን ሊቀይሩ ተዘጋጅተዋል
በፈረንጆቹ 1982 የተሠራው ብሌድ ራነር የተሰኘው ፊልም ሎስ አንጀለስ የተሰኘችውን የአሜሪካ ብርቅርቅ ከተማ መቼቱ አደርጎ ነው የተሠራው።
ፊልሙ 82 ላይ ሆኖ 2019 ተሻግሮ ይመለከታል። ፊልሙ ላይ መኪናዎች ሲበሩ፤ ሰዎች እርስ በርስ ሲባረሩ ይታያል። ከዚህ ሲኒማ በኋላ ዓለም በሳይንሱ ዘርፍ አድጋለች፤ ተመንድጋለች። ሆሊውድ 2019 የማይደርስ መስሎታል፤ እነሆ ደረሰ። ደርሶም አለፈ። እርግጥ ነው በራሪ መኪናዎች ጣራችንን ታከው ሲያልፉ አላየን ይሆናል። ነገር ግን መምጫቸው ቅርብ እንጂ ሩቅ አይደለም። በራሪ መኪናዎች የምንኖርባትን ዓለም እስከወዲያኛው ሊቀይሩ ይችላሉ። የመኪና አንቀሳቃሽ ባትሪ፤ ቁሳቁስ እና ኮምፒውተር ሳይንስ ዕለተ'ለት በፍጥነት እየተለወጡ ነው። በቅርቡ ሰማይ ላይ የምናያቸው መኪናዎች ልክ 'ብሌድ ራነር' እንደተሰኘው ፊልም ላይሆኑ ይችላሉ። ቅርፃቸውን ቀይረው መምጣታቸው ግን አይቀሬ ነው። ከትናንሽ አውሮፕላኖችም ያነሱት በራሪ መኪናዎች ክንፍ የላቸውም፤ ቸርኬ እንጂ። ይህ ደግሞ ሲነሱና ሲያርፉ እንዲያመቻቸው ታስቦ የተደረገ ነው። ቸርኬዎቹ አስፋልት መንገድ ላይ እንደምናያቸው መኪናዎች ቀጥ ያሉ አይደሉም። ጋደል ያሉ ናቸው። በራሪ መኪናዎች ያስፈለጉበት ምክንያት ግለፅ ነው። ሕይወትን ለማፍጠን። ከቤት ወደ ሥራ፤ ከሥራ ወደቤት የምንሄድበትን ጊዜ ለማሳጠር ያለሙ ናቸው። ቀጠሮ ቦታችን ከች በኮሮኮንች ቀርቶ ከላይ እንደ ድንገቴ ዝናብ ዱብ እንድንል ያደርጉናል። በተለይ ደግሞ ትራፊክ ለሚጨናነቅባቸው ከተማዎች በራሪ መኪና ወደር የለሽ መድኃኒት ነው። በአሁኑ ወቅት በራሪ መኪና ለማምረት ወዲያ ወዲህ የሚሉ በርካታ ፋብሪካዎች አሉ። 1.5 ትሪሊየን ዶላር መድቦ በራሪ በፈረንጆቹ 2040 መኪና ለማምረት እየጣረ ያለውን ኡበር የተሰኘውን የታክሲ ኪራይ ድርጅት ጨምሮ በርካቶች ከቀን ቀን እመርታ እያሳዩ ነው። የአቪዬሽን ተቆጣጣሪ ድርጅቶች ደግሞ ይህን ከግምት ውስጥ ያስገባ አዲስ ፖሊስ ለማርቀቅ ምክክር ላይ ናቸው። ጀርመን ውስጥ የሚገኘው ቮሎኮፕተር የተሰኘው ፋብሪካ ቮሎሲቲ የተባለ ያለ አብራሪ የሚበር የሰማይ ታክሲ ሰርቷል። የድርጅቱ ምክትል ሊቀ መንበር ፋቢዬን ኔስትማን 'እኛ የመጀመሪያዎቹ ነን' ይላሉ። ለጊዜው ቮሎሲቲ ለአንድ ሰው ብቻ የሚሆን ጋቢና ተበጅቶለታል። ይህ ማለት ደፍሮ የሚሳፈር ኪሶ ወፈር ያለ መሆን አለበት ማለት ነው። ነገር ግን ድርጅቱ ለተጠቃሚዎች በዋጋም በደህንነትም ምቹ የሆነ በዘጠኝ ባትሪዎች የሚሠራ በራሪ መኪና ለመፈብረክ አልሟል። ይህ በራሪ መኪና ልክ እንደ አውሮፕላን ተቆጣጣሪ ያለው መንደርደሪያ ይዘጋጅለታል። በሰዓቱ ይነሳል፤ በሰዓቱ ያርፋል። ቮሎሲቲ በራሪ መኪናዎች በመጪው የፈረንጆቹ 2022 የሙከራ በረራ ለማድረግ ተልመዋል። የመጀመሪያዎቹ በረራዎች ቲኬት 300 ፓውንድ [140 ሺህ ብር] ናቸው ተብሏል። ነገር ግን ቀስ በቀስ ዋጋቸውን ተመጣጣኝ እናደርጋለን ይላሉ ኔስትማን። ሌሎች ኩባንያዎችም ከመኪና [መሬት ላይ ከሚበረው] አምራች ፋብሪካዎች ጋር ተጣምረው በሰማይ በራሪ መኪና ለመሥራት እየተንደፋደፉ ነው። ስካይድራይቭ የጃፓን ኩባንያ ነው። ይህ ኩባንያ ከቶዮታ ጋር ተጣምሮ በኤሌክትሪክ የሚሠራ የሰማይ ታክሲ ሠርቶ ለመሞከር አቅዷል መኪናዋ በዓለም ትንሿ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ትሆናለች ይላሉ። ድርጅቱ ከወራት በፊት ኤስዲ-03 ሲል የሰየመውን አብራሪ ያለው መኪና በተሳካ ሁኔታ ሞክሯል። የበራሪ መኪናዎችን ዕድገት ተከትሎ ተያያዥ ቴክኖሎጂዎችም እያደጉ ነው። የሞተር ድምፅ መቀነሻ፤ ረዥም ዕድሜ ያለው ባትሪና የመሳሰሉት ጥቅም ላይ መዋል ጀምረዋል። ነገር ግን በራሪ መኪናዎችን እንዲሁ ሠርቶ ሰማይ መስቀል ቀላል አይደለም። የመጀመሪያው ነገር የመኪናዎቹ ደህንነት ምን ያክል ነው የሚለው ነው። ቀጥሎ ሰዎች እንዲሳፈሯቸው ማሳመን ይጠይቃል። ደህንነታቸው ስለተረጋገጠ ብቻ ሰዎች ይሳፈራሉ ማለት አይደለም። በራሪ መኪናዎች የወደፊቱ ዓለም ዜማ መቃኛ ናቸው ብሎ ሰዎችን ማሳመን ቀላል አይሆንም። አሁን ከአድማስ አድማስ የምንፈላሰስባቸው አውሮፕላኖች ቁጥጥር የሚደርግላቸው መሬት ላይ ካለ ማማ የተሰቀሉ ተቆጣጣሪዎች ናቸው። በራሪ መኪናዎች ግን ሰው አልባ በሆነ ቴክኖሎጂ ነው ወጥተው የሚገቡት። ይህ ቴክኖሎጂ ሰማይ ላይ ያለውን ሁሉ ያውቃል። ስንት ሰዓት መነሳት፤ መቼ ማረፍ እንዳለበት ይረዳል። ቅድሚያ ለሚሰጠው ቅዳሚያ ይሰጣል። ሰማይ ላይ 'ዜብራ' የእግረኞች ማቋረጫ ቢኖር እንኳ ቆሞ ለማሳለፍ የሚሰንፍ አይደለም ይሉለታል። በራሪ መኪናዎች መሬት ላይ የሚተራመሱ ተሽከርካሪዎችን ቁጥር ሊቀንሱ ይችላሉ። ሰዓት ይቆጥባሉ። ችግሩ ግርግሩ ከመሬት ወደ ሰማይ እንዳይሸጋገር ነው። ይህን የሰማይ ትራፊክ የሚቆጣጠር ቴክኖሎጂ ማዳበር የግድ ነው። አልፎም መሬት ላይ ያሉ ሰዎች በበራሪ መኪናዎች አደጋ እንዳይቀጠፉ ማረጋገጫ መኖር አለበት። በራሪ መኪናዎች ወደ ሰማይ ምን ያክል ጫማ ከፍ ብለው ነው መብረር ያለባቸው የሚለው ሌላው አከራካሪ ጉዳይ ነው። ይህን የተመለከቱ ሕጎች ከወዲሁ አሜሪካና አውሮፓውያን ሃገራት ማርቀቅ ጀምረዋል። በጠቅላላው በራሪ መኪናዎችን ቀና ብለን እንድናይ ወይም እንድንሳፈር በርካታ ኢንዱስትሪዎች ተባብረው መሥራት እንዳለባቸው መረዳት አያዳግትም። በራሪ መኪናዎች ከወፎች ጋር እየተጋፉ መብረር ጀመሩ ማለት ከተሞች ቅርፃቸውን መቀየር አለባቸው ማለት ነው። ሕንፃዎች አደግ አደግ ብለው ለበራሪ መኪናዎች ማረፊያ የሚሆን ደረቱ ሰፋ ያለ ጣራ ሊኖራቸው ይገባል። መሬት ያሉ መኪናዎች ቁጥራቸው ቀነሰ ማለት ደግሞ ለአረንጓዴ መስክ የሚሆን ትርፍ ቦታ ተገኘ ማለት ነው። ብሌድ ራነር እንደተነበየው በ2019 መኪናዎች መብረር አልጀመሩ ይሆናል። ከአስርና ሃያ ዓመታት በኋላ ግን የመኪናዎችን ብልት ቀና ብለን ማየታችን አይቀሬ ይሆናል።
49327880
https://www.bbc.com/amharic/49327880
የኢቦላ መድሃኒት ላይ የተደረገ ሙከራ 90 በመቶ ውጤት አሳየ
ኢቦላን ማከምና መፈወስ የሚያስችሉ መድሀኒቶች ላይ እየተደረጉ ካሉ ምርምሮች መካከል ሁለቱ በከፍተኛ ሁኔታ ውጤት በማሳየታቸው ወረርሽኙን "መከላከልና ማከም" ያስችላል ሲሉ ተመራማሪዎች ተናገሩ።
የኢቦላ ወረርሽኝ በከፍተኛ ሁኔታ በተስፋፋበት ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አራት መድሃኒቶች በሕሙማን ላይ ሲሞከሩ ቆይተዋል። እንደጥናቱ ውጤት ከሆነ ከአራቱ መድሐኒቶች ሁለቱ በከፍተኛ ሁኔታ በሽታውን በመከላከል ከፍተኛ ውጤት አሳይተዋል። እንደ ሕክምና ባለሙያዎች ከሆነ መድሐኒቶቹ አሁን በዲሞክራቲክ ኮንጎ በበሽታው የተያዙ ሕሙማንን ለማከም ይውላሉ። • ኢቦላን የሚያክሙ የጤና ባለሙያዎች የሞት ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው ነው • ምግብ ወሲብን የተሻለ ያደርጋል? • ብጉርን እንዴት መከላከል ይቻላል? የምርምር ስራውን ካገዙት መካከል አንዱ የሆነው የአሜሪካው ብሔራዊ የአለርጂና የኢንፌክሽኖች ተቋም (NIAID) ውጤቱን ኢቦላን በመዋጋት ረገድ "በጣም መልካም ዜና" ሲል ገልጾታል። መድሐኒቶቹ አርኢጂኤን-ኢቢ3 እና ኤምኤቢ114 ተብለው የተሰየሙ ሲሆን የኢቦላ ቫይረስ አንቲቦዲዎችን በማጥቃት ይሰራሉ፤ ይህም በሽታው የሰው ልጅ ሕዋስ ላይ የሚኖረውን ተፅዕኖ ነፃ ማድረግ ያስችላል። የኤንአይኤአይዲ ዳይሬክተር የሆኑት አንቶኒ ፋውቺ እንዳሉት ከሆነ "በሳይንሳዊ መንገድ ሞትን በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ውጤት ያሳዩ መድሀኒቶች" ናቸው። ዜድኤምኤፒፒ እና ሬምዴሲቪር የተባሉ ሌሎች ሁለት መድሀኒቶች ውጤታማነታቸው ስላልታየ ከሙከራ ተወግደዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ከአለም አቀፍ ተመራማሪዎችን በማስተባበር የኢቦላ መድሀኒቶች ላይ ሙከራ መደረግ የተጀመረው ሕዳር ወር ላይ ነበር። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ አራት መድሀኒቶች በ700 ሰዎች ላይ ውጤታማነታቸው የተፈተሸ ሲሆን የ499 ሰዎች ቅድመ ውጤት አልታወቀም ነበር። ሁለቱ ውጤታማ መድሀኒቶቹ ከተሰጧቸው ግለሰቦች መካከል አርኢጂኤን-ኢቢ3 የወሰዱ 29 በመቶ ኤምኤቢ114 የወሰዱ ደግሞ 34 በመቶ መሞታቸውን የአሜሪካው የምርምር ድርጅት አስታውቋል። በተቃራኒው ዜድኤምኤፒፒ የተሰጣቸው 49 በመቶ ሰዎች እንዲሁም ሬምዴሲቪርን የወሰዱ 53 በመቶ መሞታቸውን ድርጅቱ ገልጿል። በደማቸው ውስጠጥ አነስተኛ የኢቦላ ቫይረስ መጠን ያለ ግለሰቦች አርኢጂኤን-ኢቢ3 ሲሰጣቸው የመዳን እድላቸው 94 በመቶ መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን ኤምኤቢ114ን የወሰዱ ደግሞ 89 በመቶ የመዳን እድል እንዳላቸው በምርምሩ ተረጋግጧል። እንደ ምርምሩ ውጤት ከሆነ የጤና ባለሙያዎች ሰዎች በቫይረሱ እንደተያዙ ቀድመው ሕክምና ከጀመሩ የመትረፍ እድላቸው ከፍተኛ ስለሆነ "90 በመቶ የመትረፍ እድል ያላቸው ሰዎች ላይ አፅንኦት ሰጥተው ይሰራሉ" ሲሉ የጥናቱ አባል የሆኑት ሳቡኤ ሙላንጉ ተናግረዋል። "ያለምንም ጥርጥር ሕይወትን ይታደጋል" ሲሉ የምርምር ስራውን ውጤት ያሞካሹት ደግሞ ትረስት ግሎባል ሔልዝ ቻሪቲ የተሰኘው ድርጅት ዳይሬክተር ጀርሚ ፋራር ናቸው። የምርምሩ ውጤት የሚያሳየው ይላሉ ሚስተር ፋራር ተመራማሪዎች ኢቦላን "መከላከልና ማከም " ወደሚቻል በሽታነት ለመቀየር ቅርብ መሆናቸው ነው። አክለውም "ኢቦላን ፈፅሞ ልናጠፋው አንችልም። ነገር ግን ይህንን ወረርሽኝ የብሔራዊም ሆነ የዓለም አቀፍ ስጋት ከመሆን ልናቆመው እንችላለን።" • በኮንጎ ሦስት ዶክተሮች የጤና ባለሙያዎችን በመግደል ተጠርጥረው ተያዙ ኢቦላ ሊድን የሚችል በሽታ አለመሆኑና በሕክምና ባለሙያዎች ላይ ከተፈጠረ ጥርጣሬ ጋር ተደምሮ በዲሞክራቲክ ኮንጎ በሽታውን ለማቆም የሚደረገውን ጥረት ጎድቶት ነበር። ዶ/ር ፋኢቺ ሕሙማን የመድሀኒቱን ውጤታማነት ሲያዩ "ሕክምና ፈልገው ለመምጣት ፍላጎት ያሳያሉ" ሲሉ ያላቸውን ተስፋ ገልጠዋል። ወረርሽኙን ለማቆም ግን "ውጤታማ ክትባት" ማካሄድ የያስፈልጋል በማለት ክትባቱ ለወረርሽኙ ተጋላጭ የሆኑ ማህበረሰቦችን የመከላከል አቅም ከፍ በማድረግ የሚሰራ መሆኑን አስታውሰዋል። ባለፈው ዓመት ብቻ 1ሺህ 800 ሰዎች በኢቦላ ተይዘው የሞቱ ሲሆን የበሽታውን ሥርጭት ለመግታት የሚደረገውን ጥረት የታጠቁ አማፂያንና የውጪ የሕክምና ድጋፍ ላይ ያለው ጥርጣሬ እያደናቀፈው ይገኛል። በአሁን ሰዓት በምስራቃዊ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ የጀመረው ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ላይ ሲሆን በሽታው ለመጀመሪያ ጊዜ በሃገሪቱ ውስጥ ከተገኘበት ከአውሮፓዊያኑ 1976 ወዲህ ይህ በስፋቱ 10ኛ ደረጃን ይዟል። ከዚህ በፊት በምዕራብ አፍሪካ ከአውሮፓዊያኑ 2014-16 ድረስ ተከስቶ በነበረው የኢቦላ ወረርሽኝ 28ሺህ 616 ሰዎች የተያዙ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 11ሺህ 310 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። አብዛኞቹ የኢቦላ ወረርሽን ተጠቂዎች የጊኒ፣ ላይቤሪያ፣ ሴራሊዮን ሃገራት ዜጎች ነበሩ።
news-52240987
https://www.bbc.com/amharic/news-52240987
ነዳጅ አምራች አገራት በኮሮናቫይረስ ምክንያት ምርታቸውን ሊቀንሱ ነው
የነዳጅ አምራች አባል አገራት (ኦፔክ) እና አጋሮቹ በኮሮናቫይረስ ምከንያት አገራት በጣሉት የእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት የተፈጠረውን የፍላጎት መውረድ ተከትሎ የነዳጅ ምርታቸውን በአምስት እጅ ለመቀነስ ተስማሙ።
ቡድኑ በግንቦትና በሰኔ በ10 ሚሊዮን በርሜል በመቀነስ ዋጋው እንዲያንሰራራ እንደሚያደርግ ገልጿል። ከዚያ በኋላም ቀስ በቀስ እአአ እስከ 2022 ድረስ የተቀነሰው ምርት እንዲጨምር ይደረጋል ተብሏል። ሩሲያን የሚያካትተው ኦፔክ፤ የነዳጅ አምራች አባል አገራትና አጋሮቹን ያቀፈ ሲሆን ሐሙስ ዕለት በቪዲዮ ኮንፍረንስ ስብሰባ ተቀምጦ ነበር። ሩሲያና ሳኡዲ አረቢያ በዚህ ውይይት ላይ አለመግባባቶች ስለነበሯቸው ፈታኝ ነበር ተብሏል። ቡድኑና አጋሮቹ 10 ሚሊዮን በርሜል በቀን ወይንም የዓለማችንን አቅርቦት 10 እጅ ለመቀነስ ተስማምቷል። ተጨማሪ 5 ሚሊዮን በርሜል በሌሎች ነዳጅ አምራች አገራት እንደሚቀነስ ይጠበቃል። በሐምሌና ኅዳር ወራት መካከል የሚቀነሰው ምርት ወደ 8 ሚሊዮን ዝቅ ሊል ይችላል ተብሏል። ከዚያም እአአ በታህሳስ 2021 እና ሚያዚያ 2022 መካከል የሚቀነሰው የነዳጅ ምርት ወደ 6 ሚሊዮን ዝቅ እንደሚል ተገልጿል። የዓለማችን የነዳጅ ዋጋ የነዳጅ አምራች አገራቱ ስምምነት ላይ መድረስ ባለመቻላቸው ምክንያት ባለፈው መጋቢት ወር ወድቆ ነበር። መጋቢት ላይ በነበረው ስብሰባ ሳኡዲ አረቢያና ሩሲያ ምንም እንኳ የዓለም የነዳጅ ፍላጎት ቢወድቅም የገበያ ድርሻቸውን ለማሳደግ በማሰብ ምርታቸውን ከፍ አድርገው ነበር። በዚህ ላይ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ካስከተለው የነዳጅ ፍላጎት መውረድ ጋር ተጨምሮ በመጋቢት ወር የመጨረሻ ሳምንት ላይ ከ18 ዓመት ወዲህ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የነዳጅ ዋጋ ወርዷል። በርግጥ ከዚያ ወዲህ ዶናልድ ትራምፕ ሩሲያና ሳኡዲ አረቢያ ጠባቸውን እንዲያበርዱ ከገሰጹ በኋላ የነዳጅ ዋጋ መጠነኛ መሻሻል አሳይቷል። ሐሙስ ዕለት የተደረገው የቪዲዮ ኮንፍረንስ አርብ እለት የቡድን 20 አባል አገራት የኃይል ሚኒስትሮች ካደረጉት ስብሰባ ተከትሎ የተካሄደ ነው። ይህንን ጉባዔ ያስተናገደችው ሳኡዲ አረቢያ ናት። የሞስኮ ከፍተኛ የነዳጅ ዘይት ተደራዳሪ እና የሩሲያ ዌልዝ ፈንድ የበላይ ኃላፊ ኪሪል ዲሚትሪቭ ለሮይተርስ እንደተናገሩት "ከነዳጅ አምራች አባል አገራት ውጪ ያሉ ይህንን ውሳኔ እንዲቀላቀሉን እንጠብቃለን፤ ይህ ምናልባት ነገ በሚካሄደው የቡድን 20 አባል አገራት ስብሰባ ላይ ይሆናል" ብለዋል። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሳኡዲ አረቢያ የነዳጅ ምርቷን የማትቀንስ ከሆነ ማዕቀብ እንደሚጠብቃት አስጠንቅቀው ነበር። አሜሪካ ምንም እንኳ ያላት የነዳጅ ምርት እየቀነሰ መሆኑን ብትናገርም የነዳጅ ምርትን የመቀነስ ውሳኔው ግን ተገዥ አይደለችም።
news-54351590
https://www.bbc.com/amharic/news-54351590
ኮሮናቫይረስ፡ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሆስፒታል ገቡ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኮሮናቫይረስ እንዳለባቸው ከተገለጸ በኋላ ሆስፒታል መግባታቸው ተነገረ።
ትራምፕ ወደ ሆስፒታሉ ሲደርሱ ፕሬዝዳንቱ ትኩሳት አላቸው። ዋይትሐውስ ትንሽ ድካም ተሰምቷቸው ነው እንጂ መንፈሳቸው ጠንካራ ነው ብሏል። ትራምፕ አሁን በሆስፒታል ሆነው ገና ሙከራ ላይ ያለው መድኃኒት እየወሰዱ እንደሆነ ተሰምቷል። ባለቤታቸው ሜላኒያ ትራምፕ አብረዋቸው ናቸው። ትራምፕ ወደ ሆስፒታል በሄሊኮፕተር ከነጩ ቤተ መንግሥት ሲወሰዱ ቀድሞ ይሳለቁበት የነበረውን የአፍና የአፍንጫ ጭምብልን ግጥም አድርገው ለብሰው ታይተዋል። ዶናልድ ትራምፕ የተወሰዱት ከዋሽንግተን ዲሲ ወጣ ብሎ ወደሚገኘው የዋልተር ሪድ ብሔራዊ የወታደራዊ ህክምና ማዕከል ነው። ወደ ሄሊኮፕተሩ ሲያቀኑ እጃቸውን አውለብልበዋል። በአውራ ጣታቸውም የደህና ነኝ ምልክት አሳይተዋል። በዝምታ ሄሊኮፍተር ውስጥ የገቡት ትራምፕ በትዊተር ሰሌዳቸው ቀደም ብሎ የተቀረጸ ቪዲዮ መልዕክት አስተላልፈዋል። 'ደህና ነኝ ብዬ እገምታለሁ። ነገሮች በጥሩ ሁኔታ ይሄዳሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ባለቤቴም ደህና ናት። ስለሁሉም እናመሰግናችኋለን" ብለዋል። የትራምፕ ልጆች ኢቫንካ እና ኤሪክ በትዊተር ሰሌዳቸው አባታቸውን "ጀግና፣ እጅ የማይሰጠው፣ ተፋላሚው" ብለው ካወደሷቸው በኋላ "እንወድሀለን" ብለዋቸዋል። ትራምፕ አሁን የገቡበት የዋልተር ሪድ ሆስፒታል የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች በብዛት የጤና ምርመራ የሚያደርጉበት ስፍራ ነው። ትራምፕ ከልዩ ረዳታቸው ጋር በኤይርፎርስ ዋን አውሮፕላን ለነበረባቸው የፕሬዝዳንታዊ ክርክር ወደ ኦሃዬ አቅንተው ከተመለሱ በኋላ ነው ረዳታቸው ሆፕ ሒከስ በተህዋሲዋ መጠቃቷን ተከትሎ ምርመራ ያደረጉት። የዋይት ሐውስ ቃል አቀባይ ኬይሊ ማካነኒ "ትራምፕ በጣም ደህና ናቸው። የተወሰነ የጉንፋን ምልክት ከማሳየታቸው ውጪ እንዲያውም በሥራ ላይ ናቸው" ብላ ነበር። አሁን ሆስፒታል የተወሰዱትም "እንደው ለከፍተና ጥንቃቄ ሲባልና ሐኪሞቻቸውም ይህ እንዲሆን ስለጠየቁ እንጂ…ደህና ናቸው" ብላለች ቃል አቀባያቸው። ሆኖም ሌሎች ትራምፕ ደህና እንዳልሆኑ መገመት ይቻላል ይላሉ። በተለይም እድሜያቸው መግፋቱና ክብደታቸውም አሳሳቢ በመሆኑ ትራምፕ ክፉ እጣ ሊያጋጥማቸው እንደሚችል የሚገምቱም አልጠፉም። ፕሬዝዳንቱ አሁንም ሥራ ላይ ናቸው። ሥልጣናቸውን ወደ ምክትላቸው ማይክ ፔንስ አላስተላለፉም። ማይክ ፔንስ ምርመራ ያደረጉ ሲሆን ለጊዜው ነጻ መሆናቸው ተረጋግጧል። ትራምፕ በትዊተር ላይ በለቀቁት ቪዲዮ መጠነኛ መገርጣት ይታይባቸዋል። በሙከራ ላይ ያለ መድኃኒት መውሰዳቸው፣ እድሜያቸው 74 መድረሱና ከፍ ያለ ክብደት ያላቸው መሆኑ ነገሩ አሳሳቢ እንዲሆን አድርጎታል። ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ከባይደን ጋር በነበራቸው የቀጥታ የቴሌቪዥን ክርክር ተቀናቃኛቸው ጆ ባይደን ጭምብል አዘውትረው ማልደረጋቸው ላይ ሲሳለቁ ነበር። ጆ ባይደን ኮሮናቨዓይረስ ምርመራ ወዲያውኑ አድርገው እሳቸውም ሆኖ ባለቤታቸው ነጻ እንደሆኑ ተነግሯቸዋል። ጆ ባይደን ለትራምፕና ለባለቤታቸው ሚላኒያ ጤንነትን ተመኝተዋል። ዶናልድ ትራምፕ ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተራ ጉንፋን ነው፣ በራሱ ጊዜ ይጠፋል በሚል ተገቢውን ክብደት አልሰጡትም ሲሉ ተቀናቃኞቻቸው ይተቿቸዋል። ትራምፕ ለወባ በሽታ ፈዋሽነቱ የሚታወቀውን ሀይድሮክሲክሎሮኪውን መድኃኒትን በተደጋጋሚ ሰዎች እንዲወስዱ ሲወተውቱ ነበር። ከዚህ በፊት ይህንኑ መድኃኒት እንደወሰዱትና ጥሩ እንደሆነም ተናግረው ያውቃሉ። አሁን እርሳቸው ሀይድሮክሲክሎሮኪውንን ወስደው ይፈወሱ ይሆን ወይ የሚለው የጠላትም የወዳጅም ጥያቄ ሆኗል። ትራምፕ አሁን የሚወስዱት መድኃኒት ረምዴስቪር የተባለ ጸረ-ቫይረስ መድኃኒት ነው። ይህ መድኃኒት በኢቦላ ፈዋሽነቱ ይታወቃ። የትራምፕ በተህዋሲው መያዝን ተከትሎ ሴናተሮችና ከፍተኛ የአሜሪካ ባለሥልጣናት እንዲሁም ረዳቶቻቸው ምርመራ ማድረግ ጀምረዋል። እስከአሁን ምክትል ፕሬዝዳንቱና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተህዋሲው እንደሌለባቸው ተረጋግጧል። ሆኖም የቀድመው የፕሬዝዳንቱ አማካሪ ኬሌያን ኮንዌይ፣ ሁለት የሪፐብሊካን ሴናተሮች ማይክ ሊ እና ቶም ቲሊስ ቫይረሱ ተግኝቶባቸዋል። የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ጉዳዮች ሥራ አስኪያጅ ቢል ሰቴፒን በተመሳሳይ ተህዋሲው ተገኝቶበታል።
45481918
https://www.bbc.com/amharic/45481918
በደቡብ አፍሪካ የግድያ ወንጀል አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል
ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በየዕለቱ የሚገደሉ ሰዎች ቁጥር 57 መድረሱን የሃገሪቱ ፖሊስ ለፓርላማ ባቀረበው በቁጥር በተደገፈ ማስረጃ ይፋ አደረገ።
የፖሊስ ሚኒስትሩ በሄኪ ቼሌ የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ሚኒስትር በሄኪ ቼሌ የቁጥሩን ከፍተኛ መሆን በተመለከተ ሲናገሩ የግድያው መጠን በጦርነት ቀጠና ከሚያጋጥመው ጋር የተቀራረበ ነው ብለዋል። ለግድያ ወንጀሎች መበራከት እንደ ዋነኛ ምክንያት የቀረቡት ከወሮበላ ቡድኖች ጋር የተያያዙ የበቀል ድርጊቶች፣ የቡድንና ፖለቲካዊ ግድያዎች ናቸው። • ማንዴላን ውትድርና ያሰለጠኑት ኢትዮጵያዊ • 6 ሚሊዮን ብር፡ በማንዴላ እሥር ቤት ለማደር ከዚህ ጋር ተያይዞ የፖሊስ ሚኒስትሩ በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ያለው ወንጀልን የመዋጋት፣ የመከላከልና የደህንነት ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ሚኒስትሩ ጨምረውም ግድያንና አስገድዶ መድፈርን የመሳሰሉ የወንጀል ድርጊቶች እየጨመሩ መጥተዋል። ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ሦስት ሺህ የሚጠጉ ሴቶች የተገደሉ ሲሆን፤ ገዳዮቻቸውም የሚያውቋቸው ሰዎች ናቸው። የጦር መሳሪያና ስለት በግድያዎቹ ውስጥ በስፋት ጥቅም ላይ የዋሉ ሲሆን ግማሽ ያህሉ ግድያዎች የተፈፀሙት በእነዚህ መሳሪያዎች ነው። በአንድ የበጀት ዓመት ውስጥ ከ20 ሺህ የሚልቁ ሰዎች በደቡብ አፍሪካ ውስጥ የተገደሉ ሲሆን፤ ከእነዚህ ውስጥ 62ቱ ብቻ ናቸው በእርሻ ስፍራዎች ላይ የተገደሉት። የፖሊስ ሪፖርት እንደሚያመለክተው ምንም እንኳን የግድያ ወንጀሎች በደቡብ አፍሪካ ውስጥ እየጨመሩ ቢሆንም ድብደባ እና ተራ የዝርፊያ ወንጀሎች በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ መቀነሳቸው ተገልጿል። የፖሊስ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በሀገሪቱ ውስጥ የሚፈፀሙት ወንጀሎች ቁጥር ባለፉት ስድስት ተከታታይ ዓመታት ጨምሯል። በደቡብ አፍሪካ ፓርላማ ውስጥ ፖሊስን የሚቆጣጠረው ኮሚቴ ሰብሳቢ ፍራንሲስ ቡክማን የሁኔታውን አሳሳቢነት ሲገልፁ "ፍፁም ተቀባይነት የሌለውና አሳሳቢ" ብለውታል። የፖሊስ ሚኒስትሩ ይህንን ሁኔታ ለመቀየር ጠንክረው እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።
news-42200770
https://www.bbc.com/amharic/news-42200770
''የአውደ ዓመት ግርግር ሁልጊዜ ይናፍቀኛል''
ፍሬሕይወት ወንድሙ (ዶክተር) እባላለሁ ፤ እኔ ደግሞ ባለቤቷ ቴዎድሮስ አክሊሉ (ዶክተር) ነኝ። ከስድስት ዓመታት በፊት ነበር በኒውዮርክ ከተማ ውስጥ በምትገኘው ሲራክዩዝ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ዕድል አግኝተን ወደ አሜሪካ የመጣነው።
መጀመሪያ የትምህርት ዕድሉን ያገኘችው ባለቤቴ ፍሬ ነበረች። እኔ ደግሞ በጥገኝነት እርሷን ተከትዬ ብመጣም እድል ቀናኝና ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የእኔም ማመልከቻ ተቀባይነት አግኝቶ ትምህርቴን ጀመርኩኝ ። ሁለታችንም በግንቦትና በሐምሌ በ2009 ከዚሁ ዩኒቨርሲቲ በዶክትሬት ዲግሪ ተመርቀናል። አሁን ደግሞ ሁለታችንም በትልቅ ተቋም ውስጥ በካንሳስ ግዛት ዊቺታ ከተማ የማስተማርና ሌላም የቢሮ ሥራ ዕድል አግኝተን ከሁለት ወራት በፊት በዚሁ ከተማ መኖር ጀምረናል። በፊት የነበርንባት ኒውዮርክ ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ የምታስተናግድ ከተማ በመሆኗ መርካቶን ታስታውሰኝ ነበር። ለኑሮም ቢሆን በጣም የምትመች ከተማ ናት። ሰው ሁሉ ኑሮው በጥድፊያ የተሞላ ስለሆነ ማህበራዊ ግንኙነቱ በጣም ደካማ ነው። እኛ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ግን በጣም ደስ የሚል ግንኙነት ነበረን፤ በደስታም ሆነ በሃዘን ጊዜ በደንብ እንተጋገዝ ነበር፤ ቤተክርስቲያንም በጋራ እናገለግል ነበር፤ ትንሿ ኢትዮጵያ እንደሆነች ነበር የሚሰማኝ። ሆኖም ሲራኪዩስ መልክዓምድሯና አየረንብረቷ በጣም ከባድ ነበር። በአሜሪካ በረዶ ክፉኛ ከሚጥልባቸው ከተሞች አንዷ ስለሆነች በዓመት እስከ ሰባት ወር ድረስ በረዶ አይጠፋባትም። በዓመት ውስጥ በአማካይ እስከ 100 ኢንች (200 ሴ.ሜ) ድረስ በረዶ ከመጣሉ የተነሳ እጅግ ቆፈናማ ነበር። ይህም ብቻ አልነበረም ለእኔም ሆነ ለባለቤቴ እየተማርን እና እየሠራን አንድ ወንድና አንድ ሴት ልጆችን ስላፈራን እነርሱን መንከባከቡ ጥንካሬያችንን ይፈትን ነበር። ያኔ ደግሞ ልጆቻችን ወደማቆያ የመውሰድ አቅም ስላልነበረን የግድ ሁለታችንም ድካሙ ቢኖርም ጊዜውን እንደምንም አመቻችተን በፈረቃ ነበር የምንንከባከባቸው። ቴዎድሮስ፦ እኔ ካህን ነኝ፤ ቤተክርስቲያን በቄስነት አገለግላለሁ። አስታውሳለሁ ሁለተኛ ልጃችን ስትወለድ በምናገለግልበት የቅድስት አርሴማ ገዳም ዓመታዊ ንገስ ነበር። ለወትሮው አብረውኝ የሚሰሩ አገልጋዮች በተለያዩ ምክንያቶች ስላልነበሩ ሙሉ ኃላፊነቱ እኔ ላይ ነበር የወደቀው። ከዚያ በበዓሉ ዋዜማ ፍሬ ምጧ መጣና ሆስፒታል ገባች። በአቅራቢያችን የነበረው ሰው ሁሉ በዝግጅት ላይ ስለሆነ ቤት ማንም አልነበረም፤ ማንን እንደምጠራ ግራ ገባኝ። የጭንቁ ጊዜ አልፎ 10 ሰዓት ገደማ ስትገላለገል እርሷን ለሰዎች አደራ ብዬ ወደ አገልግሎቴ ሄድኩ፤ ነገር ግን ልቤን ቅር እያለውና እያመነታሁ ነበር የሄድኩት። በኋላ ግን ማህበራችን በጣም ጠንካራ ስለነበረ ጓደኞቻችን የሆኑ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ሳይሰለቹ በየጊዜው እየተመላለሱ በደንብ አረሱልኝ፤ ስሟንም አርሴማ አልናት። የሀገር ልጅ የማር እጅ ከሲራኪዩስ አንጻር ዊቺታ ከገባን በኋላ በጣም የሚጎልብኝ ነገር (ፍሬሕይወት) ልጆቼ ሮጥ ብለው፣ ጓደኛዬ ብለው የሚሄዱበት ቦታ አለመኖሩ ነው፤ ኒውዮርክ እያሉ ብዙ ጓደኞች ነበሯቸው። ቋንቋችንን በተቻለን መጠን ለማስተማር እንሞክራለን። ነገር ግን ቤት ብቻ የሚሆን ነገር ስላልሆነ እና ከአካባቢው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጋር ገና ስላልተዋወቅን የሚያወሩት ሰው አለመኖሩ ትንሽ ሆድ ያስብሰኛል። እኛ አዋቂ ስለሆንን በሕይወታችን በምንወስናቸው ውሳኔዎች የሚመጡ ነገሮችን ለመቀበል ራሳችንን አዘጋጅተናል። ሕጻናቱ ግን በቀድሞ ከተማችን አብረው የነበሩትን ጓደኞቻቸውን ይናፍቃሉ። ሃገር ቤትን የማስበው ይህን ጊዜ ነው። ሀገራችን ቢሆን እኛ እንኳን ባንኖር ጎረቤትም ዘመድም አይጠፋም ነበር። እዚህ ግን በአንጻራዊነት ቅርብ ነው የሚባለውን የኢትዮጵያ ምግብ ቤት እንኳ ለማግኘት ሁለት ሰዓት ተኩል መንዳት ይጠበቅብናል። ስለዚህ ያለንን አማራጭ ለመቀጠም እንጀራ ቤት ውስጥ እንጋግራለን። ብዙ ጊዜ የምንመገበውም እንጀራ ነው። ከዚያ ውጭ በፍስክም ሆነ በጾም ሩዝ በአትክልትና በስጋ ስልስ እንመገባለን። እኔ በአትክልት ሲሆን ይበልጥ እወደዋለሁ። እኔ ግን (ቴዎድሮስ) ያው መቼም መብላት ስላለብኝ እንጂ እንጀራ ከሌለ ፆሜን ላድር ሁሉ እችላለሁ፤ እሱ እንኳን ባይኖር መጠባበቂያ ድርቆሽ ከቤታችን አይጠፋም ። ለነገሩ በየቀኑ ከሥራ እየተመላለስን ምግብ መሥራት ስለሚከብደን በአንድ ጊዜ ለሶስት ለአራት ቀን ነው ምግብ የምናበስለው። ለዚህ አይነት አመጋገብ ደግሞ እንጀራ በደንብ ይመቻል። ባናዘወትረውም ፓስታ፣ ሩዝ ፣አትክልት፣ ዓሣና ሌሎች ጥብሳ ጥብሶችንም እንሠራለን። ከኢትዮጵያ የሚናፍቃችሁ ነገር አለ? እኔ ካህንም ስለሆንኩ ኢትዮጵያ ሆኜ የምሰማቸው የቤተክርስቲያን የኪዳን፣ የቅዳሴ ድምጽ፣ ደውሉ ሁልጊዜ እንደናፈቀኝ ነው። ምክንያቱም አሜሪካ እንዲህ ያለ ነገር የለም። አንድ ቀን መኖሪያ ቤታችን አቅራቢያ ወደሚገኘው ኦክልሃማ ስሄድ አሜሪካ ከመጣሁ ለመጀመሪያ ጊዜ ቀይ አፈር አየሁ። ያኔ ታዲያ ጉለሌ ሰፈሬ ትዝ አለኝ። ሌላ ደግሞ (ፍሬህይወት) ኒውዮርክ ባሉ መኖሪያ ቤቶች ምንም አይነት የውጭ አጥር አልነበረም። እዚህ ግን እንደሃገር ቤት ባይረዝሙም አብዛኞቹ ቤቶች የእንጨት አጥር ስላላቸው ሰፈሬንም የክፍለሃገር ጉዞዬንም ያስታውሱኛል። ግን እስካሁንም እንደናፈቅኩት የቀረሁትን በዓይኔ የሚዞርብኝ የዓመት በዓል ግርግር ነው፤ ከሳምንት ጀምሮ ገበያው ዋዜማው የጎረቤት ዘመድ አዝማድ ስብስቡ በጣም ይናፍቀኛል። የምንኖርበት ቤት በጣም ብዙ መስታወት አለው። በዚህ ውስጥ አሻግረን የምናየው በመኖሪያ ህንጻዎች መሃል የተንጣለለ በንጽህና የሚጠበቅ አረንጓዴ ለምለም ቦታ አለ። ልጆቻችን ይጫወቱበታል። ድመትና ውሻዎችም ይዝናኑበታል። ልጆቻችንም እነርሱን እያዩ ሲዝናኑ በአንድ እይታ ሁለት ውብ ነገር እንመለከታለን። ሁሉንም ነገር የመቀየር አቅም ቢኖረን ኖሮ በቅርቡ በሞት ያጣናትን እናታችንን እቴቴን ሕይወት ለማትረፍ የሆነ ነገር እናደርግ ነበር፤ በዚህ አስቸጋሪ ጊዜም ከቤተሰባችን ጋር እንሆን ነበር። በዊቺታ ያሉ ሐበሻ ወንድምና እህቶቻችን ብዙዎቹ ባያውቁንም በሃዘናችን ጊዜ አጠገባችን ሆነው አጽናንተውናልና በዚህ አጋጣሚ ምስጋናችን ይድረስልን። ለክሪስቲን ዮሐንስ እንደነገረቻት የ'ካለሁበት' ቀጣይ ክፍሎችን ለማግኘት ፦ ካለሁበት 13፡ ''ለእኔ ስኬት ማለት ገንዘብ ማግኘት ብቻ አይደለም'' ካለሁበት 14፡ "ብርዱ ሲከፋ፣ ቀኑም ሲያጥር የሀገሬ አየር በስንት ጣዕሙ እላለሁ።"
49239675
https://www.bbc.com/amharic/49239675
በእነብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ መዝገብ ፖሊስ የጠየቀው የግዜ ቀጠሮ ውድቅ ተደረገ
በእነብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ የክስ መዝገብ የተከሰሱ ተጠርጣሪዎች ላይ ፖሊስ የጠየቀውን የግዜ ቀጠሮ ፍርድ ቤት ውድቅ አደረገ።
ሰኔ 15 በአማራ ክልል ተሞከረ ከተባለው 'መፈንቅለ መንግስት' ጋር በተያያዘ የጸጥታ ኃላፊዎችን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ግለሰቦች ጉዳይ ዛሬ ሃምሌ 29 ቀን 2011ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ታይቷል። • በእነብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ የክስ መዝገብ ፍርድ ቤት የቀረቡት ተጠርጣሪዎች ለሀምሌ 29 ተቀጠሩ ፖሊስ ተጨማሪ የ28 ምስክሮችን እና የተወሰኑ የሰነድ ማስረጃዎችን ማየቱን ለፍርድ ቤት አስታውቋል። ተጨማሪ የምስክሮችን ቃል ለመቀበል እየሰራ መሆኑን እና የፎሬንሲክ እና የስልክ ምርመራ ውጤቶች ያልደርሱ መሆናቸዉን በመጥቀስ ተጨማሪ የ14 ቀን የግዜ ቀጠሮ እንዲሰጠቀው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል። የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው በደንበኞቻቸው ላይ ምስክሮች አለመገኘታቸውን፤ ደንበኞቻቸው ቢወጡ በቴክኒክ እና በስልክ ምርመራ ላይ ምንም ተጽህኖ የማያሳድሩ መሆናቸውን እንዲሁም የሰው ማስረጃ ፣የቴክኒክ እና የሰነድ ማስረጃዎች ጎን ለጎን መካሄድ ነበረባቸው በሚል የግዜ ቀጠሮው ውድቅ እንዲሆን ጠይቀዋል። • የሥራ ኃላፊነታቸውን "ከባድና የሚያስጨንቅ... ነው" ያሉት ዶ/ር አምባቸው ማን ነበሩ? ግራ ቀኙን ያዳመጠው ፍርድ ቤት የፖሊስን ተጨማሪ ግዜ ቀጠሮ ጥያቄ ውድቅ አድርጎ እስከ ነሐሴ 13 ቀን 2011 ዓ.ም ፖሊስ ክስ እንዲመሰርት ትዕዛዝ በመስጠት የዛሬውን ችሎት አጠናቋል። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ 218 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው የነበረ ሲሆን 160 የሚሆኑት በተለያየ ግዜ ተለቀዋል።
news-43041270
https://www.bbc.com/amharic/news-43041270
ኤ ኤን ሲ -ጃኮብ ዙማ ከስልጣን መውረድ አለባቸው
ፕሬዚዳንት ዙማ ከስልጣን ለመውረድ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የደቡብ አፍሪካ ገዢ ፓርቲ ኤ ኤን ሲ በህጉ መሰረት ከስልጣን እንዲወርዱ እንደሚጠይቅ የሚዲያ ዘገባዎች ያስረዳሉ።
ገዢው ፓርቲ በይፋ እቅዱን ያላሳወቀ ሲሆን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ለደቡብ አፍሪካ መገናኛ ብዙሃን እና ለሮይተርስ ተናግረዋል። ከፍተኛ የፓርቲው አመራሮች ከ ዙማ ጋር ረዥም ሰአት የፈጀ ንግግር ቢያደርጉም መቋጫ ላይ ባለመድረሳቸው ነው ወደዚህ ውሳኔ የመጡት። የ 75 አመቱ ዙማ ሀሳባቸውን ካልቀየሩ የሕዝብ እንደራሴው የመተመመኛ ድምፅ እንዲሰጣቸው መጠየቁ አይቀርም፤ ያ ደግሞ የመሆን እድሉ አናሳ ነው። ከ 2009 ጀምሮ በስልጣን ላይ የነበሩት ዙማ በከፍተኛ ሙስና ተጠርጥረው በተደጋጋሚ ተወንጅለዋል። ራማፎሳ የፓርቲ ሊቀመንበርነት ስልጣኑን ከያዙ ጀምሮ ዙማ ከፕሬዚዳንትነት ይውረዱ የሚለው ግፊት ቢያይልባቸውም እርሳቸው ግን በእንቢተኝነታቸው ፀንተዋል። ዙማ ዛሬ በስርአቱ መሰረት ለሚቀርብላቸው ከስልጣን ይልቀቁ ጥያቄ እንዴት ምላሽ እንደሚሰጡ አይታወቅም። ደቡብ አፍሪካው ገዢ ፓርቲ ኤ ኤን ሲ የፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማን የወደፊት ዕጣፈንታ ለመወሰን በቅርቡ ስብሰባ የሚያደርጉ ሲሆን ከስልጣን አንዲወርዱ እንደሚጠይቋቸውም እየተነገረ ነው። በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ሲሪል ራማፎሳ "ይህ ጉዳይ በፍጥነት እንዲቋጭ እንደምትፈልጉ እናውቃለን" ሲሉ የኔልሰን ማንዴላን 100ኛ የልደት በአል ለማክበር ለተሰበሰበው ሕዝብ መናገራቸው ይታወሳል። ከዚህ በፊት ከፕሬዝዳንቱ ጋር "ውጤታማ እና ገንቢ ውይይት" ማድረጉን ፓርቲው አስታውቆ ነበር። የቀረቡባቸውን የሙስና ውንጀላዎች ተከትሎ የኤ ኤን ሲ አባላት ዙማ ከስልጣን እንዲለቁ ግፊት በማሳደር ላይ ናቸው። የሃገሪቱ ፓርላማ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ሊደረግ የነበረውን ብሔራዊ መግለጫ ባልተለመደ መልኩ ወደ ሌላ ቀን እንዲተላለፍ ወስኗል። የደቡብ አፍሪካው ታይምስ ላይቭ ድረ-ገጽ ስማቸው ያልተገለጹ ሰዎችን ጠቅሶ ትክክለኛ ድርድር ከተካሄደ ዙማ ስልጣን ለመልቀቅ ተዘጋጅተዋል ብሏል። ከፍተኛው የአመራር ቡድን ያለ ፕሬዝዳንቱ ስምምነትም ቢሆን ከስልጣናቸው ሊያነሳቸው ይችላል። የ75 ዓመቱ ዙማ ባለፈው ታህሳስ ነው ከፓርቲ መሪነታቸው ተነስተው ምክትላቸው በነበሩት ራማፎሳ የተተኩት። ባለፈው ሳምንት የኔልሰን ማንዴላ ፋውንዴሽን ፕሬዝዳንቱ ከስልጣን እንዲለቁ ምክሩን አስቀምጧል። የኤ ኤን ሲ ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ በሚያደርገው ስብሰባው በፕሬዝዳንቱ ዕጣ ፈንታ ላይ ይወስናል። ፓርቲው ድጋፉን ሙሉ ለሙሉ የሚነፍጋቸው ከሆነ ዙማ በፓርላማው ላይ ከፍተኛ ድጋፍ ስለማይኖራቸው ከስልጣን ለመልቀቅ ይገደዳሉ። ባለፈው እሁድ የፓርቲው ስብሰባ በጆሃንስበርግ የተካሄደ ሲሆን፤ የስብሰባው ተሳታፊዎች እንዳስታወቁት ከሆነ ሙሉ ለሙሉ ባይሆንም በአብዛኛው ከስምምነት ላይ ተደርሷል። ስልጣን ላይ በሚገኙት ፕሬዝዳንት የሚደረገው ብሔራዊ መግለጫ በደቡብ አፍሪካ በዓመቱ ውስጥ ከሚደረጉ ዋነኛ የፖለቲካ ጉዳዮች አንደኛው ነው። እንደ ብሄራዊ ጉባኤው ቃል አቀባይ ባሌካ ምቤቴ ከሆነ ፓርላማው ብሔራዊ መግለጫው እንዲቀር የወሰነው "ረብሻ እንዲፈጠር ጥሪ ሊቀርብ ይችላል" በሚል ስጋት ነው። "ፕሬዝዳንቱ ጊዜው እንዲራዘም የጠየቁት በአንዳንድ ጉዳዮች ለውጥ ነው" ሲል የዙማ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
53836095
https://www.bbc.com/amharic/53836095
ከማሊው መፈንቅለ መንግሥት ጀርባ ያሉት እነማን ናቸው?
በትናንትናው ዕለት የማሊ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ባውባካር ኬታ መፈንቅለ መንግሥት ተካሂዶባቸው ከስልጣን ተወግደዋል። ለመሆኑ ከዚህ መፈንቅለ መንግሥት ጀርባ እነማን አሉ?
መፈንቅለ መንግሥቱን ካቀነባበሩት መካከል አንድ የወታደራዊ ማሰልጠኛ አካዳሚ ምክትል ኃላፊና በፈረንሳይ ወታደራዊ ስልጠና የወሰዱ ጄኔራሎች አሉበት ። በዚህ መፈንቅለ መንግሥት ቁልፍ ሚናን ከተጫወቱት መካከል የሶስቱን ማንነት እነሆ ካቲ የተባለ የጦር አካዳሚ ምክትል አሰልጣኝ ሲሆኑ፤ መፈንቅለ መንግሥቱም እዚህ ቦታ ነው የተጀመረው። ስለ ኮሎኔሉ ጥልቅ የሚባል መረጃ ባይኖርም በቅርቡ ከሩሲያ ወታደራዊ ስልጠና ወስደው እንደተመለሱ ሪፖርቶች ወጥተዋል። የአየር ኃይል ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ኢስማኤል ዋጌ በዛሬው ዕለት የአገሪቱን ስልጣን ወታደራዊ ኃይሉ እንደተቆጣጠረ መግለጫውን ሲያነቡ ኮሎኔል ማሊክ ከጎናቸው ቆመው ነበር። "ኮሎኔል ማሊክ ከመዲናዋ ባማኮ 15 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የካቲ ወታደራዊ ማሰልጠኛ አካዳሚ ላይ የተነሳው አመፅን መሪ ናቸው። ፕሬዚዳንቱ ከስምንት ሰዓት በፊት ስልጣናቸውን እንዲያስረክቡም ትእዛዝ ያስተላለፉት እኚሁ ኮሎኔል ናቸው" በማለት ኮሎኔሉ ስለነበራቸው ሚና የወጡ መረጃዎች ያስረዳሉ። የካቲ ወታደራዊ ማሰልጠኛ አካዳሚ የቀድሞ ዳይሬክተር ነበሩ ኮሎኔል ሳዲዮ በማሊ ደቡባዊ ክፍል ኩሊኮሮ ግዛት፣ በካቲ በጎርጎሳውያኑ 1979 መወለዳቸውን ማሊ ትሪቡን ድረገፅ አስነብቧል። ከኮሊኮሮ ወታደራዊ ማሰልጠኛ አካዳሚም በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቀዋል። በሰሜናዊ ማሊም ተመድበው በጄኔል ኤል ሃጂ ጋሙ ስር እስከ ጎርጎሳውያኑ 2012 ድረስም አገልግለዋል፥ በኋላም በካቲ ወታደራዊ ማሰልጠኛ አካዳሚ ዳይሬክተር የሆኑ ሲሆን እስከያዝነው አመት ጥር ወር ድረስ፣ ለሩሲያ ወታደራዊ ስልጠና እስከሄዱበት ወቅት በዚሁ ኃላፊነታቸው እያገለገሉ ነበር። ከሩሲያ የተመለሱት በዚህ ወር ሲሆን ለአንድ ወርም ያህል ፈቃድ ላይ እንደነበሩ ማሊ ትሪቡውን ዘግቧል። "ኮሎኔል ሳዲዮ በሁሉም ዘንድ የተከበሩ፣ የሚሞገሱና የተወደዱ ናቸው ። በስራቸው ላሉት ወታደሮችም ቀጥተኛነትን፣ ፅናትንና ቁርጠኝነት ተምሳሌት ናቸው" በማለትም ድረ ገፁ ስለባህርያቸው መረጃን አስፍሯል። ጄኔራል ሼክ ፋንታ ማዲ ዴምቤሌ አሊዩኔ ብሎንዲን ቤዬ የተባለ የሰላም አስጠባቂ ተቋም ዳይሬክተር ጄኔራል ናቸው። ከሁለት አመታት በፊት የብርጋዲየር ጄኔራል ማዕረግን ያገኙት ሼክ ፋንታ የተቋሙም መሪ የሆኑት በዚሁ ወቅት ነው። ጄኔራሉ በዚህ ተቋም ከመሾማቸው በፊት በአፍሪካ ህብረት የሰላምና ፀጥታ ኮሚሽን ግጭት አፈታት ስልታዊ ዕቅድን የተመለከተውን ቢሮ ይመሩ ነበር ተብሏል። በዚህ ወቅትም መቀመጫቸው አዲስ አበባ ነበር። ጄኔራል ዴምቤሌ በፈረንሳይ የሚገኝ ሴይት ሲር የጦር አካዳሚ ምሩቅ ናቸው። በማሊ በሚገኘው ኮውሊኮሮ ኮሌጅም ትምህርታቸውን ተከታትለዋል። ከዚህም በተጨማሪ ከፓሪስ ዩኒቨርስቲ በታሪክ ትምህርት ዲግሪ ያላቸው ሲሆን፣ ከጀርመኑም ፌደራል አርሚ ዩኒቨርስቲም በሲቪል ምህንድስና የማስተርስ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።
45649052
https://www.bbc.com/amharic/45649052
«አዲስ አበባ የሁሉም ናት» አርበኞች ግንቦት 7
የአርበኞች ግንቦት 7 የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑት አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ድርጅታቸውን የሚመለከቱ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ከቢቢሲ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎቸ ምላሽ ሰጥተዋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከ3 ሺህ በላይ ወጣቶችን በወንጀል ምክንያት ከሰሞኑ ማሰሩ ይታወቃል። ከእነዚህ እሥረኞች መካከል የአርበኞች ግንቦት 7 አቀባበል ኮሚቴ አባል የነበረው ብርሃኑ ተክለያሬድ እና ሌሎችም የፓርቲው አባላት እና ደጋፊዎች እንደሚገኙበት አቶ ኤፍሬም አረጋግጠዋል (ከቃለመጠይቃችን ጥቂት ሰዓታት በኋላ ብርሃኑ ከእስር ተፈትቷል)። • «ኦሮሞ እና አማራን የሚነጣጥሉ አይሳካላቸውም» • የአርበኞች ግንቦት 7 አቀባበል ኮሚቴ አባል ፍርድ ቤት ቀረበ «የእኛ ፓርቲ አባላት ብቻ አይደሉም የሌሎች ፓርቲ አባላትም ለእሥር ተዳርገዋል» የሚሉት አቶ ኤፍሬም በጉዳዩ ዙርያ ከመንግሥት ጋር ተደጋጋሚ ውይይት እያደረጉ እንደሆነ ነግረውናል። «አባሎቻችን እየተደረገባቸው ያለው ምርመራ እየተጠናቀቀ ነው፤ አሁን ጥሩ መንፈስ ላይ ነው ያሉት» ሲሉ አቶ ኤፍሬም ታሣሪ አባሎቻቸው ያሉበትን ሁኔታ ያስረዳሉ። «ሂደቱ በአጭር ጊዜ አልቆ አባሎቻችን ቶሎ ይፈታሉ የሚል እምነት አለኝ» ይላሉ አቶ ኤፍሬም። «በመንግሥት ደረጃ የምንታገለው መንግሥት የለም» ምነው ግንቦት ሰባት በታሰሩ አባላቱ ዙርያ ዝምታን መረጠ? ብለን ለጠይቅናቸው ጥያቄ አቶ ኤፍሬም ሲመልሱ «ከዚህ በፊት አንድ ክስተት ሲከስተ መግለጫ እንሰጥ ነበር፤ የዚያ ምክንያት ደግሞ ከሃገር ቤት ውጭ ሆነን መንቀሳቀሳችን ነው፤ ትግላችን ከአገዛዙ ጋር ነበር። አሁን ግን ሃገር ቤት ነን፤ በመንግሥት ደረጃ የምንታገለው መንግሥት የለም አብረን የምንሠራው እንጂ» ሲሉ የፓርቲያቸውን አቋም ነግረውናል። «የምናስቀድመው የተፈጠረው ነገር ምንድነው ብለን ከመንግሥት ጋር መወያየት እንጂ አስቀድመን መግለጫ የምንሰጥበት ሁኔታ ላይ አይደለንም።» አቶ ኤፍሬም አክለውም «መግለጫ ሳናወጣ ከመንግሥት ጋር የሰራናቸውን ሥራዎች ሕዝቡ በአጭር ጊዜ ያየዋል» ብለውናል። ግንቦት 7 ከመንግሥት ጋር ያደረገውን ውይይት እና የውይይቱን ውጤት አሁን ባለበት ሁኔታ ለሚድያ ሊያሳውቁ እንደማይችሉ ነው አቶ ኤፍሬም ያስረዱት። «አዲስ አበባ የሁሉም ናት» አምስት የኦሮሞ ፖለቲካ ድርጅቶች ማክሰኞ ዕለት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ባለ አምስት ነጥብ አቋም መግለጫ አውጥተዋል። መግለጫው በተለይ በማሕበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል። ድርጅቶቹ ካወጧቸው አቋሞች መካከል «አዲስ አበባ የኦሮሞ ሕዝብ ናት፤ ነግር ሁሉም ሊኖርባት ይችላል» የሚለው ብዙዎች ጎራ ከፍለው እንዲነጋገሩ ያደረገ ሆኗል። • "ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ተገንጥሎ የሚወጣ አካል የለም"-ኤፍሬም ማዴቦ • «የሠራዊታችን አባላት በክብር ይሸኛሉ» ግንቦት 7 ሌሎች ደግሞ መግለጫው ግንቦት 7 ላይ የተሰነዘረ ዱላ ይመስላል ይላሉ። አቶ ኤፍሬም ግን «መግለጫው እኛ ላይ የተሰነዘረ ነው ብዬ አላምንም» ባይ ናቸው። አክለውም «ድርጅቶቹ አዲስ አበባ ላይ የኦሮሞ ሕዝብ አለኝ የሚለውን ጥያቄ አንስተዋል፤ እርግጠኛ ነኝ ወደፊት ይህንን ጥያቄ ኢትዮጵያዊያን ተመካክረው የሚፈቱት ይሆናል» ሲሉ ያስረዳሉ። «እስከዛሬ ድረስ ያለውን ብናወራ ግን አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ናት፤ አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ህዝብ ከየአቅጣጫው መጥቶ ላለፉት 120 ዓመታት የገነባት ከተማ ናት። የአንድ አካባቢ ሕዝብ የገነባው ቦታ አይደለችም፤ የሁሉም እንጂ።» አቶ ኤፍሬም ከመግለጫው መካከል ሚድያ ላይ የተሰነዘረው ጥቃት እንዳላስደሰታቸው አልሸሸጉም። «የትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ሆነ ግለሰብ ሚድያ ጠላቴ ነው የሚል ከሆነ እርሱ ነው የሚድያ ጠላት። ኢሳት የኦሮሞ ሕዝብ ጠላት ነው ተብሎ የተሰጠውን መግለጫ በግሌ አወግዛለሁ።» አቶ ኤፍሬም አርበኞች ግንቦት 7 ኢትዮጵያ ውስጥ በዜግነት ላይ የተመሠረተ ፖለቲካ ከሚያራምዱ ኃይሎች መካከል አንዱ ነው ይላሉ። «ኢትዮጵያ ውስጥ ለላፉት 27 ዓመታት የነገሰውን የጎሳ ፖለቲካ ወይም የማንነት ፖለቲካ የምንለውን ማራማድ የሚፈልጉ ኃይሎች ሁሉ የእኛ እዚህ መምጣትና የጠፋ የመሰላቸውን ኢትዮጰያዊነት እንደ አዲስ ማቆጥቆጥ ያስፈራቸው ኃይሎች ናቸው» ሲሉ ይገልፃሉ። አቶ ኤፍሬም «ግንቦት 7 ለሁት ተከፍሏል ተብሎ በተደጋጋሚ የሚነገረው ጉዳይ ርካሽ ፖለቲካ ነው፤ ግንቦት 7 አሁንም አልተከፈለም» ሲሉ አስረግጠዋል።
news-53751582
https://www.bbc.com/amharic/news-53751582
ጥንታዊ መገልገያ ፡ ከፈረስ አጥንት የተሠሩ የጥንታዊ ሰው መገልገያዎች ተገኙ
በአውሮፓ የቅሪተ አካል ጥናት (አርኪዎሎጂ) ዘርፍ ጥንታዊ የተባሉ ከአጥንት የተሠሩ መገልገያዎች ተገኙ።
መገልገያዎቹ በአውሮፓውያኑ በ1980ዎቹ እና 90ዎቹ አካባቢ ሰዎች ጥለውት የወጡት ምዕራብ ሰሴክስ አካባቢ ነው የተገኙት። ጥንታዊ ሰዎች ይጠቀሙባቸው የነበሩት መሣሪያዎች የተዘጋጁት ከፈረስ አጥንት ነበር። ፈረሱ ታርዶ ስጋው ለምግብነት ከዋለ በኋላ አጥንቱ መገልገያ ለመሥራት ውሏል። በአካባቢው የተገኘው እንስሳ ቅሪተ አካል ዙርያ የነበረው የድንጋይ ክምር፤ መሣሪያውን ለማዘጋጀት ቢያንስ ስምንት ሰዎች መሳተፋቸውን ያሳያል። በአካባቢው ወጣት ወይም በእድሜ የገፉ የማኅበረሰቡ አባላት እንደነበሩም ተመራማሪዎች ደርሰውበታል። በብሪታኒያ በተካሄደው ቁፋሮ ወደ መቶ የሚጠጉ የድንጋይ መገልገያዎችና ወደ 500 ሺህ ዓመታት ገደማ ያስቆጠሩ የእንስሳት ቅሪተ አካሎች ተገኝተዋል። መገልገያዎቹ የዘመናዊ ሰው እንዲሁም የኒያንደርታልስ ቅድመ ዝርያ በነበሩት ሆሞ ሄይድልበርገንሲስ እንደተሠሩ ይታመናል። በቁፋሮ የተገኘው የሰው ቅልጥም ቅሪተ አካል ከብሪትን የሰው ቅሪተ አካሎች በእድሜ ትልቁ ነው። የምርምር ሂደቱን የመሩት ዶ/ር ማቲው ፖፕ “አሁን ዝርያው የጠፋ ማኅበረሰብ የኖረበትን አካባቢ እንዳለ ማግኘት ትልቅ እድል ነው” ብለዋል። ተቀራርበው ይኖሩ የነበሩ ጥንታዊ ሰዎችን ማኅበራራዊ ትስስር መገንዘብ እንደቻሉም አክለዋል። ተመራማሪው እንደሚናገሩት፤ ፈረስ እንዴት ወደዛ አካባቢ እንደደረሰ አልታወቀም። “ፈረሶች ጥብቅ ማኅበራዊ ትስስር ያላቸው እንስሳት ናቸው። ስለዚህም ቅሪተ አካሉ የተገኘው ፈረስ የመንጋ አባል እንደነበረ መገመት ይቻላል። ግን በአንዳች ምክንያት ከመንጋው ተለይቶ እዛ አካባቢ ሕይወቱ አልፏል።” ምናልባትም ፈረሱ እየታደነ ነበር የሚል መላ ምት አለ። የፈረስ ቅሪተ አካል ላይ የተሠራው ጥናት፤ ፈረሱ ከምግብነት ባሻገር አጥንቱ መገልገያ ለመሥሪያነትም እንደዋለ ይጠቁማል። የለንደን ዩኒቨርስቲ ኮሌጁ ተመራማሪ ሳይመን ፓርፊት፤ “በሰው ልጅ ዝግመተ ለውጥ ሂደት የተገኙ እድሜ ጠገብ ከድንጋይ ያልተዘጋጁ መገልገያዎች ናቸው” ብለዋል። ዶ/ር ሲልቪያ ቤሎ በበኩላቸው፤ ግኝቱ ጥንታዊ ሰው ከአንድ ቁስ እንዴት ሌላ ቁስ ማዘጋጀት እንደሚቻል መገንዘቡን ይጠቁማል ሱሉ አስረድተዋል። በአዕምሮ፣ በማኅበራዊ ትስስር እንዲሁም በባህልም የመጠቁ መሆናቸውን እንደሚያሳየም አክለዋል። ተመራማሪዎቹ ቅሪተ አካሉን ባገኙበት ስፍራ አቅራቢያ ከ30 እስከ 40 የሚሆኑ ሰዎች ይኖሩ እንደነበር ገምተዋል። ምናልባትም አደኑን ተቀላቅለው ፈረሶች ገድለው ሊሆን እንደሚችል መላ ምት ተቀምጧል። ሰዎች ከፈረስ አጥንት መቅኒና ፈሳሽ ያገኙ እንደነበርም መረጃ ተገኝቷል። ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት፤ አደን እና እንስሳትን ማረድ ለጥንታዊ ሰዎች ማኅበራዊ ክንውኖች ነበሩ።
48280312
https://www.bbc.com/amharic/48280312
ጫት የአእምሮ ጤናን እንደሚጎዳ ጥናት አመለከተ
ጫት ለተለያዩ የአእምሮ ጤና ችግሮች እንደሚያጋልጥ አጥኚዎች እንደደረሱበት ባለፈው ሳምንት ኬንያ ውስጥ ለህትመት የበቃ የሳይንሳዊ ምርምር መጽሄት አስታወቀ።
"ጥናቱ በተደረገባቸው ጫት የሚጠቅሙ ሰዎች የአእምሮ ጤና ችግር ምልክቶች ከፍ ብሎ ታይቷል" ሲል ባለፈው ማክሰኞ የታተመው ቢኤምሲ ሳይኪያትሪ የምርምር መጽሄት አስፍሯል። • "ልዩ ነዳጅ መኖሩን አልደረስንበትም" የማዕድን፣ የፔትሮሊየምና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር ሪፖርቱ እንደሚለው፤ ጫት መቃም ካልተለመዱ ክስተቶችና ከቅዠት ጋር በከፍተኛ ደረጃ የሚያያዝ ሲሆን እነዚህም የአእምሮ ጤና ችግር ጠቋሚ ምልክቶች ናቸው። ተመራማሪዎቹ ይፋ ያደረጉት ከኬንያ መንግሥት ባገኙት የገንዘብ ድጋፍ በሁለት አካባቢዎች ላይ በሚገኙ 831 ሰዎች ላይ ባደረጉት ጥናት ላይ ተመስርተው ያገኙትን ውጤት ነው። ከ831 የጥናቱ ተሳታፊዎች መካከል 306ቱ ወይም 37 በመቶው ጫት ቃሚዎች ሲሆኑ ከግማሽ በላዩ ወንዶች ናቸው። • "ጫትን ማገድ ፈፅሞ የሚቻል አይደለም" ዶ/ር ዘሪሁን መሃመድ እድሜያቸው ከ10 - 17 ያሉ ታዳጊ ልጆችም ጫት እንደሚቅሙ በጥናቱ የተገኘ ሲሆን፤ ይህም በአእምሮ ጤና ላይ የሚኖረው ተጽእኖ ከፍተኛ እንደሚሆን ተገልጿል። አጥኚዎቹ ይህ የታዳጊዎች ጫትን የመጠቀም ልማድ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን አመልክተው፤ በለጋ እድሜ እንዲህ አይነት ሱስ አስያዥ ነገሮችን መጠቀም ከዕፅ ጋር ተያያዥነት ባላቸው በሽታዎች የመጠቃት እድልን ከፍ ያደርጋል ብለዋል። በዚህ ጥናት ላይ የተሳተፉ ሰዎች አልኮልና ሲጋራን ይጠቀሙ እንደሆነ የተጣራ ሲሆን፤ ጥናቱ እንዳመለከተው ከጫት መቃም ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ የአእምሮ ጤና ችግሮች አመላካች ምልክቶች ከአልኮልና ከሲጋራ አንጻር ከሚከሰቱ ችግሮች ጋር ተያያዥነት የላቸውም። • ጫትን መቆጣጠር ወይስ ማገድ? ቀደም ሲል በጫት ላይ በተደረገ ጥናት አወንታዊ ውጤቶች እንዳሉት የተገለጸ ቢሆንም፤ አዲስ ይፋ በተደረገው ጥናት መሰረት ግን ጫት በወሲባዊ ግንኙነት፣ በምግብ ፍላጎት እንዲሆም ከውፍረት አንጻር ስለሚኖረው ውጤት አንዳች የተጠቀሰ ነገር የለም። ጫትን በተመለከተ ይፋ በተደረገው ጥናት ላይ ከተሳተፉት ተመራማሪዎች በተጨማሪ ከሦስት የተለያዩ የኬንያ ዩኒቨርሲቲዎች የተወጣጡ አጥኚዎችም ተሳትፈውበታል።
news-55270484
https://www.bbc.com/amharic/news-55270484
ኮሮናቫይረስ፡ የፋይዘር ክትባት በአሜሪካ ጥቅም ላይ እንዲውል ምክር ሃሳብ ቀረበ
የአሜሪካ የምግብና መድሃኒት አስተዳደር መሠሪያ ቤትን (ኤፍዲኤ) የሚያማክሩ ባለሙያዎች በፋይዘር/ባዮንቴክ የበለጸገው የኮሮረናቫይረስ ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ሀሳብ ማቅረባቸው ተገለጸ።
ባለሙያዎቹ ይህን ምክረ ሃሳብ የሰጡት 23 አባላት ያሉት የባለሙያዎች ቡድን ክትባቱ ሊፈጥረው የሚችለው ስጋት ከሚሰጠው ጥቅም አንጻር ምን ሊመስል እንደሚችል ምክክር ካደረጉ በኋላ ነው ተብሏል። የፋይዘር/ባዮንቴክ ክትባት እስካሁን በዩናይትድ ኪንግደም፣ ካናዳ፣ ባህሬን እና ሳኡዲ አረቢያ ጥቅም ላይ ለመዋል ፍቃድ አግኝቷል። በፋይዘር/ባዮንቴክ የተመረተው ክትባት በአሜሪካ ጥቅም ላይ እንዲውል የኤፍዲኤ ይሁንታ ማግኘት ያለበት ሲሆን በሚቀጥሉት ቀናት ይሄው ይሁንታ እንደሚገኝ ይጠበቃል። አሜሪካ ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ ከ3 ሺ በላይ ሰዎች በኮሮረናቫይረስ ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉን አስታውቃለች። ይህ ደግሞ በአገሪቱም ሆነ በዓለም እስካሁን በአንድ ቀን ውስጥ ከፍተኛው የሟቾች ቁጥር መሆኑ ተገልጿል። የአሜሪካ የጤና ሚንስትር አሌክስ ረቡዕ ዕለት ''በሚቀጥሉት ቀናት ክትባቱ በእጃችን ሊገባ ይችላል፤ በሚቀጥለው ሳምንት ደግሞ እጅግ ተጋላጭ የሆኑትን ዜጎች መከተብ ልንጀምር እንችላል'' ብለዋል። የትራምፕ አስተዳደር 'ራፕ ስፒድ' ብሎ በሚጠራው የክትባት ማከፋፈል ፕሮግራም መሠረት ክትባቱ ፈቃድ ባገኘ በ24 ሰዓታት ውስጥ ማከፋፈል ይጀምራል ተብሏል። ፋይዘር በያዝነው የፈረንጆቹ ታህሳስ ወር መጨረሻ አካባቢ 6.4 ሚሊየን የክትባት ብልቃጦችን ለማቅረብ እቅድ ይዟል። ሁለት ብልቃጦች በሁለት ሳምንት ልዩነት ለአንድ ሰው ስለሚሰጡ ይህ 6.4 ሚሊዮን ክትባት ለ3.2 ሚሊየን ሕዝብ መከተብ የሚቻለው። አሜሪካ ደግሞ ያላት የሕዝብ ቁጥር 330 ሚሊየን ነው። የአሜሪካ በሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማዕከል እንዳለው በአገሪቱ የሚገኙ 3 ሚሊየን የእድሜ ባለጸጋዎች እና 21 ሚሊየን የሚሆኑ ጤና ላይ የሚሰሩ ሰዎች ቅድሚያ ክትባቱን ያገኛሉ። በመቀጠል ደግሞ 87 ሚሊየን የሚሆኑ ወሳኝ የስራ ሂደቶች ላይ የተሰማሩ ሰዎች ክትባቱን እንደሚያገኙ የተገለጸ ሲሆን የትኛው የስራ ዘርፍ ቅድሚያ ይሰጠው የሚለውን ግን እያንዳንዱ ግዛት የራሱን ውሳኔ ያስተላልፋል። በሞደርና እና በብሄራዊ የጤና ኢንስቲትዩት የተሰራው ሌላኛው ክትባትም ቢሆን አሜሪካ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዲውል ተጠይቋል። ይህም ክትባት ልክ እንደ ፋይዘር ሁለት ጊዜ ነው የሚወሰደው።
news-48619236
https://www.bbc.com/amharic/news-48619236
በተበከለ ደም አራት ወንድሞቹ የሞቱበት እንግሊዛዊ
ጆን ኮርኔስ የተባለው እንግሊዛዊ ከአምስት ወንድሞቹ ውስጥ አራቱ በተበከለ ደም እንዴት እንደሞቱ ሰሞኑን ለአጣሪው ኮሚቴ አስረድቷል።
ደም ያለመርጋት ችግሩን ለመታከም በሄደበት ወቅት በተነካካ ደም ምክንያት በጉበት በሽታ እንደተያዘ ይናገራል። የ58 ዓመቱ ጆን ኮርኔስ ለአጣሪው ኮሚቴው እንደገለፀው ሶስቱ ወንድሞቹ ጥንቃቄ በጎደለው በተበከለ ደም ምክንያት በኤች አይ ቪ ቫይረስ ተጠቅተው በ1990ዎቹ ሞተዋል። •የኤድስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ •ሳይንቲስቱ መንትዮች ኤች አይ ቪ እንዳይዛቸው ዘረ መላቸውን አስተካከለ የ26 አመቱ ጌሪ በ1992፣ ሮይ በ26 አመቱ በ1994ና ጎርደን በ40 አመቱ በ1995 ህይወታቸው በኤች አይ ቪ ያለፈ ሲሆን፤ ሌላኛው ወንድሙ በጉበት በሽታ ከሁለት አመት በፊት ሞቷል። ቤተሰቡን ቤተሰብ እንዳይሆኑ የማይሽር የህሊና ጠባሳ ባደረሰው በዚህ የደም መበከል ቀውስ በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር ከ1970-1980 ባሉት አስር አመታት ውስጥ 4ሺህ 800 የደም መርጋት ችግር ያለባቸው ሰዎች በሄፐታይተስ እንዲጠቁ ተደርገዋል። ከነዚህም ውስጥ ከ2ሺዎቹ በላይ ሞተዋል። በእንግሊዝ ሃገር በጤናው ላይ ከተከሰቱት ቀውሶች አስከፊው ተብሏል። ጆን እንደሚናገረው ወንድሙ ሮይ ባለማወቅ አንዲት ሴት ላይ ኤችአይቪ እንዳስተላለፈባትና የሱ ህይወት ከማለፉ በፊት እንደሞተች ነው። "የሀገሪቱ ሚዲያ ዜናውን ከሰሙ በኋላ ለአመታትም "ተውሳኮቹ" "ባለኤድሳሞቹ ቤተሰቦች" በሚል ቅጥያ ስም ሚዲያው ሲያሸማቅቃቸው እንደነበር የሚናገረው ጆን ወንድሙ ጌሪ በሞተበት ወቅት አምሳ ሪፖርተሮች ተደብቀው የቀብር ስርአቱን ፎቶ ሲያነሱ እንደነበር ያስታውሳል። •ዚምባብዌ ኤች አይ ቪ እፈዉሳለሁ ያለዉን ፓስተር ቀጣች •ኮንዶም መጠቀም እያቆምን ይሆን? የጌሪ ባለቤትም ባለቤቷ ከሞተ ከአምስት አመት በኋላ በኤችአይቪ ሞተች። ከዚህም ጋር ተያይዞ "ብዙ አባት ወይም እናት የሌላቸው የወንድምና የእህት ልጆች አሉኝ" ይላል። "ቢያንስ ከ30 የማያንሱ ቤተሰቦቼ ቀጥታ ተጎድተዋል፤ እዚህ የመጣሁት የተጠቁትን ወክየ ሳይሆን ተፅእኖ የደረሰባቸውንም እንጂ" ብሏል። ቤተሰቦቹ ላይ የደረሰውን ጉዳት በጎርጎሳውያኑ 1974 በርሚንግሃም ላይ የደረሰውን የቦምብ ፍንዳታ ተከትሎ በአየርላንድ ማህበረሰብ ላይ የደረሰውን ጭቆና ያስታውሰዋል። " አየርላንዳዊ ከሆንክ መንገድ ላይ ከተገኘህ ትደበደባለህ፤ የሚሰቀጥጥ ጉዳይ ነበር" የሚለው ጆን " በቤተሰባችን ላይ የደረሰው ተመሳሳይ ነው፤ "ባለኤድሳሞቹ" ቤተሰቦች እንባል ነበር። የነሱ ስህተት እንዳልነበረው በኛም ላይ የተፈጠረው የኛ ስህተት አልነበረም፤ ተጠቂዎች ነን" ይላል። በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር በ1970ዎቹ ለደም አለመርጋት ችግሩ ህክምና ሲከታተል የነበረው ጆን "ህፃን እያለን ደሙን ለማቆም ደም በመለገስ ነው" መደረግ ስለሚገባው ጥንቃቄም ሆነ ስለ ህክምናው ችግሮች ተነግሮት እንደሆነ የተጠየቀው ጆን ምንም ነገር እንደማያውቅና " ስለ ቫይረሱም ምንም አይነት እውቀት አልነበረንም" ብሏል።
news-56142076
https://www.bbc.com/amharic/news-56142076
ሱዳን በኢትዮጵያ ለቀረበባት ክስና ወቀሳ ምላሽ ሰጠች
ሱዳን ባለፈው ሐሙስ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ላይ የቀረበባትን ክስና ወቀሳ በመቃወም ምላሽ ሰጠች።
የሱዳን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቅዳሜ ዕለት ባወጣው መግለጫ ከኢትዮጵያ በኩል የተሰነዘረውን ክስ አጥብቆ የተቸ ሲሆን፤ ከኢትዮጵያ በኩል የወጣውን መግለጫ "በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል ያለውን ግንኙነትና የሁለቱን አገር ሕዝቦች ትስስር የካደ ነው" ማለቱን የአገሪቱ ዜና ወኪል ሱና ዘግቧል። በጥቅምት ወር ማብቂያ ላይ ሁለቱ አገራት በሚዋሰኑበት ድንበር አካባቢ ኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች ሰፍረው ይገኙባቸው የነበሩ ለም የእርሻ ቦታዎችን የግዛቴ አካል ናቸው በማለት ሱዳን ከተቆጣጠረች በኋላ ውዝግብ ላይ መቆየታቸው ይታወሳል። ወራት ያስቆጠረው የሁለቱ አገራት የድንበር ውዝግብ ከተከሰተ በኋላ የኢትዮጵያ የውጭጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው ጠንካራ መግለጫ በድንበር ይገባኛል ሰበብ "ሁለቱ አገራት ወደ ጦርነት እንዲገቡ የሱዳን የመከላከያ ኃይል በጠብ አጫሪነት የሦስተኛ ወገን መጠቀሚያ ሆኗል" ሲል ከሶ ነበር። ይህ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል የወጣው መግለጫ ከዚህ ቀደም የድንበር ጉዳዩን በተመለከተ ከተሰጡ መግለጫዎች መካከል ጠንካራ መሆኑ የተነገረ ሲሆን "ሱዳንን ዝቅ የሚያደርግና ይቅር የማይባል ስድብ ነው" ስትል ሱዳን ተቃውሞዋን ገልፃለች። የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በምላሹ ባወጣው መግለጫ ላይ በሁለቱ አገራት መካከል ስላለው ታሪካዊ ትስስር በመጥቀስ፤ ይህንን ግንኙነት በማስቀጠል ለሕዝቦቹ ደኅንንት፣ መረጋጋትና ምጣኔ ሐብታዊ ልማት እንዲውል ለመስቻል ከፍ ያለ ፍላጎት ሱዳን እንዳላት አመልክቷል። በሁለቱ አገራት መካከል የተከሰተውን የድንበር ውዝግብ መካረርን ለማርገብና ችግሩ መፍትሔ እንዲያገኝ በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ይሁንታን ያገኘ የአፍሪካ ሕብረት ልዑካን ካርቱም ውስጥ መሆናቸውን መግለጫው ጨምሮ ገልጿል። ይህ በእንዲህ እንዳለም የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ያወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ያላትን ታሪካዊ ግንኙነት "የካደ ነው" በማለት "ሱዳን ላይ ይቅር የማይባል ስድብ" ሰንዝሯል ሲል አጽንኦት ሰጥቷል። የሱዳን መግለጫ ጨምሮም አወዛጋቢው የድንበር አካባቢ የሱዳን ሉዓላዊ ግዛት መሆኑን አጠንክሮ በመግለጽ፤ ኢትዮጵያ ጉዳዩን ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ወደ ሆኑ ሕጋዊ አማራጮችን ልትወስደው ትችላለች ብሏል። ኢትዮጵያ ባለፈው ሐሙስ ባወጣችው መግለጫ የትኛውም ግጭት የሁለቱን አገራት ደኅንነት የሚጎዳና ከባድ ጉዳትን የሚያስከትል መሆኑን እንደምትገነዘብ ጠቁሞ፤ በሱዳን መንግሥት ወታደራዊ ክንፍ እየተበረታታ ያለው ግጭት "በሱዳን ሕዝብ ኪሳራ የሦስተኛ ወገንን ፍላጎት የሚያስፈጽም ነው" ብሎ ከሶ ነበር። ጨምሮም የድንበር ጥያቄው ሊስተናገድባቸው የሚችሉ በቂ መንገዶች ቢኖሩም "የሱዳን ሠራዊት ዓለም አቀፍ ሕጎችን በመጣስ በኢትዮጵያ ላይ ወረራ ፈጽሟል" ብሏል። እንዲሁም በሁለቱ አገራት መካከል ካለው የትብብርና የወዳጅነት መንፈስ በተቃራኒ "የሱዳን ሠራዊት ንብረቶችን ዘርፏል፣ ካምፖችን አቃጥሏል፣ በሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን በማጥቃት እንዲፈናቀሉ ያደረገ ሲሆን ባዷቸውን የነበሩ የኢትዮጵያ ሠራዊት ካምፖችን ተቆጣጥሯል" ሲል ከሷል። ሱዳንም በበኩሏ በየካቲት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ማብቂያ ላይ የኢትዮጵያ ሠራዊት ወደ ግዛቴ ዘልቆ በመግባት ወረራ አካሂዷል በማለት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል መክሷ ይታወሳል። የሁለቱ አገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት በድንበር ውዝግቡ ምክንያት ወደ ጦርነት የመግባት ፍላጎት እንደሌላቸው በተደጋጋሚ የገለጹ ሲሆን በድንበር አካካቢ ያለው ሁኔታ ግን በውጥረት ውስጥ መሆኑን ቢቢሲ ያናገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል። ባለፈው ሳምንት ሱዳን በአዲስ አበባ የሚገኙትን አምባሳደሯን ለምክክር በሚል ወደ ካርቱም የጠራች ሲሆን ይህም ከድንበር ውዝግቡ ጋር የተገናኛ ስለመሆኑ የታወቀ ነገር የለም። ሱዳን ባለፈው ጥቅምት ወር ማብቂያ ለረጅም ጊዜ ይገባኛል ስትላቸው የነበሩትን በርካታ የድንበር አካባቢዎችን ሠራዊቷን በማሰማራት የተቆጣጠረች ሲሆን፤ ባለስልጣናቷም በቁጥጥራቸው ስር ያስገቡት ሕጋዊ ግዛታቸው መሆኑን በመግለጽ ይዞታቸውን ሲያጠናክሩ ቆይተዋል። የሱዳንን እርምጃ ተከትሎ ኢትዮጵያ የድንበር አካባቢው ይዞታ ወደነበረበት እንዲመለስና ሁለቱ አገራት ችግሩን ቀደም ሲል ጀምረውት በነበረው የድንበር ኮሚሽን በኩል በውይይት እንዲፈቱት በተደጋጋሚ መጠየቋ ይታወሳል።
news-51382235
https://www.bbc.com/amharic/news-51382235
የሌሴቶ ቀዳማዊት እመቤት የባሏን የቀድሞ ሚስት በመግደል ወንጀል ፍርድ ቤት ልትቀርብ ነው
የሌሴቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ባለቤት ቀዳማዊት እመቤት ሜይሳያህ ታባን የባሏን የቀድሞ ባለቤት በመግደል ወንጀል ፍርድ ቤት ልትቀርብ ነው።
ከሰሞኑ ቀዳማዊቷ እመቤት ሜይሳያህ ታባን በደቡብ አፍሪካ ለፖሊስ እጇን ሰጥታለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ቶማስ ታቤንም በግድያው ዙሪያ ከፖሊስ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር። • ኮሮናቫይረስና የነዳጅ ዘይት ምን አገናኛቸው? • "የደባ ፖለቲካውን ማስቆም ፈተና ሆኗል፤ ግን ኢትዮጵያን የምናስቀጥል መሆኑን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ" የጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀድሞ ባለቤት ሊፖሌሎ ታቤን በሌሴቶ መዲና ማሴሮ በሚገኘው ቤቷ በጥይት ተተኩሶባት የተገደለችው ከሦስት ዓመት በፊት ነበር። በወቅቱም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለበዓለ ሲመታቸው ሁለት ቀናት ይቀራቸው ነበር ግድያው የተፈጸመው ተብሏል፤ መረር ያለ የፍች ሂደትም ላይ ነበሩ። ግድያውን የፈፀሙት ያልታወቁ ታጣቂዎች ነበር ቢባልም በቅርቡ የፖሊስ ኮሚሽነር ሆሎሞ ሞሊቤ ለፍርድ ቤት ያቀረቧቸው አዳዲስ መረጃዎች ጥያቄዎችን አጭረዋል። ፖሊስ የአርባ ሁለት ዓመት እድሜ ያላትን የአሁኗን ባለቤታቸውን ጠርጥሬያለሁ ማለቱን ተከትሎ፤ ቀዳማዊቷ እመቤት ጠፍታ ነበር። ፖሊስም በምላሹ የእስር ማዘዣ አውጥቶ ደቡብ አፍሪካ በመሄድ ከጠበቃዎቿና ከፓሊስ ጋር በተደረገ ድርድር ራሷን አሳልፋ መስጠቷን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪል ዘግቧል። የፖሊስ ኮሚሽነር ሆሎሞ ሞሊቤሊ ለቢቢሲ እንዳሳወቁት በአሁኑ ሰዓት በፓሊስ ቁጥጥር ስር እንዳለችና በዛሬው እለትም ፍርድ ቤት እንደምትቀርብ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፍርድ ቤት ሄደው የዋስ መብቷ እንዲከበር ይጠይቃሉ የሚለው ግልፅ ባይሆንም፤ ፖሊስ ኮሚሽነሩ ግን ቀዳማዊት እመቤቷ ልትሰወር ስለምትችል የዋስ መብቷ እንዳይከበር እንደሚሟገቱ ጨምረው አስረድተዋል። የቀዳማዊቷ እመቤት ጠበቃ ሬታቢሌ ሴትሎጆአኔ በበኩላቸው ምንም አይነት አስተያያት አልሰጥም በማለት ለቢቢሲ ገልፀዋል። • ሴቶች ቆመው እንዲሸኑ የሚያስችለው ቱቦ • ካሜሮናዊው በኮሮናቫይረስ በመያዝ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሆነ ባለፈው ወር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከግድያው ጋር በተያያዘ በፖሊስ መጠየቃቸውን ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ የተቃዋሚ ደጋፊዎች በመዲናዋ ማሴሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን እንዲለቁ በሰልፍ ጠይቀዋል። የተቃዋሚዎች ግፊት በመጨመሩም ስልጣን እንደሚለቁ ቢያሳውቁም መቼ ሊሆን እንደሚችል አላሳወቁም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለቤታቸውም ሆነ እሳቸው የተወነጀሉበትን ወንጀል ከማንሳት ተቆጥበው በጡረታ ራሴን አገልላሁ ብለዋል። አገሪቷን እያስተዳደረ ያለውና ተቃዋሚው ፓርቲ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቀድሞ ባለቤታቸው ግድያ ወንጀል ምርመራ እንቅፋት ሆነዋል ይሏቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆነ የአሁኑ ባለቤታቸው ምንም አይነት አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል።
48424921
https://www.bbc.com/amharic/48424921
ምርጫው በተያዘለት ጊዜ እንደሚካሄድ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለፀ
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቀጣይ ለሚደረገው ምርጫ ያስፈልገኛል ያለውን 3.7 ቢሊዮን ብር ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የበጀት ኮሚቴ መጠየቁን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።
ወጪው ከህዝብ ቁጥር መጨመርና አንዳንድ ምክንያቶች ጋር ተያይዞ ከዚህ በፊት ከነበሩት ምርጫዎች ጋር ሲወዳደር ከፍተኛ መሆኑን የተናገሩት ወ/ት ብርቱካን ከዚህም ውስጥ 900 ሚሊዮን ብር ከአጋር ድርጅቶች ለማግኘት ታቅዷል። •የቦርዱ ማሻሻያና የብርቱካን ሹመት ምንና ምን ናቸው? ከቀጣዩ ምርጫ ጋር ተያይዞ በተለያዩ አካላት ዘንድ የፀጥታ ችግር በተለያዩ ቦታዎች የሚነሱ የማንነትና ራስን የማስተዳደር ጥያቄዎች ስጋቶች ጋር ተያይዞ በቀጣዩ ምርጫ ላይ ፈታኝ ሁኔታዎች ሊደቀኑ እንደሚችሉ የተለያዩ አካላቶች እየገለፁ ሲሆን ይህንን የቦርዱ ኃላፊ ጉዳዩን እንደሚረዱት ገልፀዋል። በተለይም ከጥቂት ወራት በፊት መካሄድ የነበረበት ኃገራዊ የህዝብና የቤቶች ቆጠራ በተለያዩ ምክንያቶች ካለመከናወኑ ጋር ተያይዞ፤ ቀጣዩ ምርጫ እንዴት ሊካሄድ ይችላል የሚሉ ጥያቁ የተጠየቁት የቦርድ ኃላፊዋ በኢትዮጵያ ባለው የምርጫ አሰራር አወቃቀር መሰረት የመራጮች ምዝገባ ከቤትና ከህዝብ ቆጠራው ጋር ቀጥታ የሚመሰረት እንዳልሆነ ነው። ነገር ግን ምርጫውና የህዝብ ቆጠራው ቢደጋገፉ ጠቃሚ መሆኑንም አልደበቁም። •"ቀጣዩን ምርጫ ከዳር ሆኜ ባልታዘብም ተወዳዳሪ ግን አልሆንም" ብርቱካን ሚደቅሳ በተለይም አገሪቱ ካለችበት የፀጥታ ስጋቶች ጋር ተያይዞ ምንም እንኳን ምርጫው ሊራዘም ይችላል የሚሉ አስተያየቶች ከተለያዩ አካላት ቢሰሙም ምርጫ ቦርዱ ማንኛውንም ስራ እያከናወነ ያለው ምርጫው በህገ መንግሥቱ በተያዘለት ቀነ ቀጠሮ ይከናወናል በሚል እሳቤ እንደሆነና፤ በተለያዩ ምክንያቶች ግን ጊዜው ሊቀየር እንደሚችል ጠቆም አድርገዋል። "እስካሁን ባለው ሁኔታ እኛ እየሰራን ያለነው ምርጫው በተያዘለት ጊዜ እንደሚከናወን ታሳቢ አድርገን፤ በዛን ጊዜ ለመድረስ ነው።" ብለዋል።
news-53119133
https://www.bbc.com/amharic/news-53119133
ሕንድ ከቻይና ጋር የሚያዋስናትን ድንበር በወታደራዊ ኃይል እጠብቃለሁ አለች
የሕንድ እና የቻይና ወታደሮች ሰኞ ዕለት መጋጨታቸውን ተከትሎ 20 ሕንዳውያን ወታደሮች ተገድለዋል። ሕንድም አስፈላጊ ከሆነ ድንበሬን በወታደራዊ ኃይል እከላከላለሁ ብላለች።
ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ እንዳሉት፤ አንድም የውጪ ወታደር ወደ አገራቸው አልገባም። ከድንበር ወሰናቸው የተወሰደ መሬት እንደሌለም ተናግረዋል። በቻይና እና በሕንድ የሄማልያ ድንበር ላይ በተከሰተው ግጭት ምን ያህል ወታደሮቿ እንደሞቱ ቻይና አልተናገረችም። አገራቱ ድንበር በመጣስ ጸብ በማጫር አንዳቸው ሌላቸውን ይከሳሉ። ከቀናት በፊት ላዳክህ በሚባለው ግዛት በሚገኘው ጋልዋን ወንዝ አቅራቢያ ነበር የቻይና እና ሕንድ ወታደሮች የተጋጩት። ጠቅላይ ሚንስትር ሞዲ እንዳሉት በሁለቱም ወገን ጉዳት ደርሷል። “የሕንድ ኃይሎች ድንበር ለማስጠበቅ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸዋል” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስተር ሞዲ በቴሌቪዥን በተላለፈ መግለጫቸው። ቻይና በወሰደችው እርምጃ መላው ሕንድ ተቆጥቷል ሲሉም ተደምጠዋል። “ሕንድ ሰላምና ወዳጅነት ትፈልጋለች፤ ነገር ግን ለሉአላዊነቷ ቅድሚያ ትሰጣለች” ብለዋል። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር 1996 ላይ በተደረሰነ ስምምነት መሠረት በአካባቢው የጦር መሣሪያም ሆነ ፈንጂ መጠቀም አይቻልም። የሰኞ ዕለት በተከሰተው እና 20 የሕንድ ወታደሮችን ህይወታቸውን ባጡበት ግጭትም አንድም ጥይት አልተተኮሰም ነበር። በግጭቱ ወደ 76 የሕንድ ወታደሮች መጎዳታቸውም ተዘግቧል። በዚህም ምክንያት ሐሙስ የወጡ ዘገባዎች እንዳመለከቱት በሁለቱ አገራት ወታደሮች መካከል በነበረው ግጭት ላይ ሚስማር የተበየደባቸው የብረት ዘንጎች ወቅት ጥቅም ላይ ውለው ጉዳቱን አድርሰዋል። በግጭቱ ወቅት የቻይና ወታደሮች በሕንድ ወታደሮች ላይ ጥቃት ሰነዘሩበት የተባለው ቢስማር የተበየደበት ብረት በሕንድ እና በቻይና ድንበር ያሉ የሕንድ ከፍተኛ የጦር ኃላፊ ለቢቢሲ የብረት ዘንጎቹን የሚያሳይ ፎቶ ሰጥተዋል። ዘንጉን የተጠቀሙበት የቻይና ወታደሮች መሆናቸውንም ገልጸዋል። የእነዚህ መሣሪያዎች ፎቶግራፍ በሕንድ በትዊተር መሰራጨቱን ተከትሎ ሕዝቡ ተቆጥቷል። የቻይናም ይሁን የሕንድ ባለሥልጣናት ስለ ጉዳዩ ያሉት ነገር የለም። መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት፤ ወታደሮቹ የተጋጩት 4,300 ሜትር ከፍታ ላይ ስለነበር ጋልዊን ወንዝ ውስጥ የገቡ ወታደሮች አሉ። በአካባቢው ለምን መሣሪያ ተከለከለ? ጋልዊን ወንዝ የሚገኘው በላዳካህ ተራራማ አካባቢ ሲሆን፤ የአየር ሁኔታው አስቸጋሪ ነው። አካባቢው ሁለቱም አገራት የእኔ ነው በሚሉት አክሲ ቺን አቅራቢያ የሚገኝ ወንዝ ነው። በአካባቢው መሣሪያ ቢታገድም፤ ሕንድ እና ቻይና ከተለመደው የሽጉጥና ፈንጂ መሣሪያ ውጪ በመጠቀም ሲጋጩ የአሁኑ የመጀመሪያቸው አይደለም። ለመጨረሻ ጊዜ የተጋጩት በ1975 አራት ሕንዳውያን ወታደሮች ሲገደሉ ነበር። 1966 ላይ ሁለቱም አገሮች መሣሪያ ላለመማዘዝ ተስማምተዋል። “በድንበሩ በሁለት ኪሎ ሜትር ርቀት ጦር መሳሪያ ወይም በፈንጂ ተጠቅሞ ጥቃት ማድረስ ወይም እንስሳት ማደንም አይቻልም” ሲሉም ተፈራርመዋል። ነገር ግን የድንበር አካባቢው በውጥረት የተሞላ ነው። ግንቦት ላይ የቻይና እና ሕንድ ወታደሮች ተደባድበው ነበር። ሕንድ፤ ቻይና በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ድንበር ላይ አሰማርታች፣ 38 ሺህ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ይዛለች ስትል ትከሳለች። ባለፉት ሰላሳ ዓመታት ሁለቱን አገራት ለማሸማገል የተደረገው ጥረት አልተሳካም።
54529035
https://www.bbc.com/amharic/54529035
በባሌ በፖሊስ ተገደለ የተባለው ወጣት ጉዳይ እየተመረመረ መሆኑ ተገለጸ
ባለፈው እሑድ ጥቅምት 1 ቀን 2013 ዓ. ም. ባሌ ሮቤ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ በነበሩ ወጣቶች ላይ ፖሊስ በወሰደው እርምጃ አንድ ወጣት ከተገደለ በኋላ ጉዳዩ እየተመረመረ መሆኑ ተገለጸ።
ቢቢሲ ያነጋገራቸው የዓይን እማኞች እንዲሁም የሮቤ ከተማ ከንቲባ አቶ ገዛኸኝ ደጀኔ ወጣቱ መገደሉን አረጋግጠዋል፤ ክስተቱ ሰልፍ ሳይሆን በከተማው ረብሻ ለመፍጠር የተደረገ ሙከራ ነው ሲሉ ከንቲባው ተናግረዋል። ሰልፉ ላይ ከተሳተፉት አንዱ የሆነና ስሙ እንዲገለጽ ያልፈለገ ወጣት ለቢቢሲ እንደገለጸው፤ ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ 4 ሰዓት ገደማ ከ15-20 የሚጠጉ ወጣቶች በሮቤ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ሲያካሂዱ ነበር። "ሰልፉ ላይ ጀዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባ ይፈቱ የሚልና በኦሮሚያ ግድያ መቆም አለበት የሚሉ መፈክሮቸን እያሰማን ነበር" ብሏል ወጣቱ። ሰላማዊ ሰልፉ ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ግሪን ካፌ ተብሎ በሚጠራ ቦታ ላይ "የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ከኋላ መጥቶ ከበበን። ከዚያም ተኩስ ከፈቱብን። ሰልፉን በተኑ። ልጁ የተገደለው ያኔ ነው። ይሄን ልጅ መግደላቸው ሕብረተሰቡ ውስጥ ከፍተኛ ቁጣና ሀዘን ፈጥሯል" ሲልም የተከሰተውን አስረድቷል። ሌላው ስሜ አይጠቀስ ያለን የዓይን እማኝ፤ ወጣቱ በተገደለበት ወቅት እሱም ግራ እጁን በጥይት መመታቱን ተናግሯል። በቦታው ከ10 እስከ 15 የሚሆኑ ወጣቶች እንደነበሩ የገለጸው ወጣት "ፖሊሶች ከኋላችን መምጣታቸውን አየን። ከአውራሪስ ሰፈር ተነስተን፣ በአረጎው መናሀርያ ጋር አልፈን ግሪን ካፌ ጋ ደረስን። እዛ ስንደርስ ነው ፖሊሶቹ ከኋላችን መምጣታቸውን ያየነው" ሲል ክስተቱን ተናግሯል። "ፖሊሶቹ ተኩስ ሲጀምሩ መሮጥ ጀመርን። እኔም ሮጬ ዘልዬ የሆነ ሱቅ ውስጥ ገባሁ። ግራ እጄን፣ ከክንዴ በላይ በጥይት መመታቴን የተረዳሁት ያኔ ነው" ሲልም አክሏል። የሮቤ ከተማ ከንቲባ አቶ ገዛኸኝ ደጀኔ አንድ ወጣት መገደሉን አምነው፤ ጉዳዩ በምርመራ ላይ እንደሚገኝ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ሁኔታውን ሰልፍ ብሎ ለመጥራት ያስቸግራል። ምክንያቱም ቁጥራቸው ከ10 እስከ 15 ቢሆን ነው" ያሉት አቶ ገዛኸኝ ደጀኔ፤ "ረብሻ ለመፍጠር ሙከራ እንዳደረጉ ነው የምንረዳው። እነዚህ ወጣቶች ተደራጅተው ድምጽ እያሰሙ ለረብሻ ቅስቀሳ እያደረጉ ነበር። በወቅቱ የጸጥታ ኃይል በቦታው ስለነበር ቶሎ ማስቆም ችሏል" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተሰራጨ አጭር ቪዲዮ ፖሊስ ሲተኩስ እንደሚያሳይ በመጥቀስ፤ የጸጥታ ኃይል ሁኔታውን አረጋጋ የሚባለው እንዴት ነው? ወጣቶቹ ቁጥራቸው ትንሽ ሆኖ ሳለ ለምን ተኩስ መክፈት አስፈለገ? ተብለው የተጠየቁት ከንቲባው፡ "በቦታው የጸጥታ ኃይል ስላለ የሕግ የበላይነትን ለማስከበርና ሁኔታውን ለማረጋጋት እርምጃ ወስዷል። በዚህም የደረሰ ጉዳት አለ። የችግሩን ክብደት የሚወስነው በቦታው የነበረው የጸጥታ አካል እንጂ እኔም ሆንኩ ሌላ አይደለም" ሲሉ አቶ ደጀኔ መልሰዋል። ከንቲባው አያይዘውም፤ "ምናልባት ሊመጣ ይችል የነበረውን ችግር ለማስቀረት እርምጃ ወስዶ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ሁኔታው ምርመራ ላይ ስለሆነ ከዚህ በላይ ለመናገር አሁን ይከብዳል። ምርመራው ሲያልቅ ለሕዝብ ግልጽ እናደርጋለን" ብለዋል። በደገም የተከሰተው ምንድን ነው? በሌላ በኩል በኦሮሚያ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ደገም ወረዳ ውስጥ ትናንት ማታ ከምሸቱ 6 ሰዓት አካባቢ አንድ ሾፌር ባለታወቁ ሰዎች መገደሉ ተሰምቷል። በተጨማሪም ሦስት ሰዎች መቁሰላቸውን የዞኑ አስተዳደርና ጸጥታ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አጥናፉ በቀለ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ከአዲስ አበባ ወደ አማራ ክልል በመሄድ ላይ የነበሩ የከባድ መኪና ጭነት አሽከርካሪዎች ላይ አደጋው መድረሱን የምተናገሩት ኃላፊው፤ የተወሰኑት ተጎጂዎች ደግሞ ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ በመሄድ ላይ ነበሩ ናቸው ብለዋል። አቶ አጥናፉ እንዳሉት፤ ጥቃቱ የደረሰው ከምሽቱ 6 ሰዓት አካባቢ ነው። "የሞተው አንድ ሾፌር ሲሆን ሌሎች 3 ሾፌሮች ደግሞ በዱላ ተደብድበዋል። በጥይትም የተመቱ አሉ። ይህ ክስተት ከዚህ ቀደም አጋጥሞን አያውቅም። አሁን ሕዝቡ መንገድ እየጠበቀ ነው ያለው" ሲሉ አስረድተዋል። ኃላፊው አያይዘውም፤ "ጥቃቱን ያደረሰው አካል ለጊዜው አይታወቅም። ፖሊስ ጉዳዩን እያጣራ ነው። ሆኖም ግን አጥቂዎቹ ዝርፊያ ለማካሄድ ጥቃቱን እንደፈጸሙ የሚያመለክቱ ነገሮች አሉ" ብለዋል።
news-50330519
https://www.bbc.com/amharic/news-50330519
የኮንጎ አማጺያን መሪው ቦስኮ ንታጋንዳ የ30 ዓመት እስር ተፈረደበት
የቀድሞ የኮንጎ የአማጺያን መሪው ቦስኮ ንታጋንዳ ፈጽሞታል ለተባለው የጦር ወንጀል እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የ30 ዓመት እስራት ተበየነበት።
ለቦስኮ ንታጋንዳ ታማኝ ናቸው የተባሉ ታጣቂዎች በንጹሃን ዜጎች ላይ አሰቃቂ ድርጊቶችን መፈጸማቸውን የዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ሐምሌ ወር ላይ አሳውቆ ነበር። "ተርሚኔተር" በሚል ቅጽል ስሙ የሚታወቀው ንታጋንዳ በ18 የክስ መዝገቦች ጥፋተኛ የተባለ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ግድያ፣ አስገድዶ የመድፈር፣ ሴቶችን የወሲብ ግዞተኛ ማድረግ እና ህጻናትን ለውትድርና መመልመል የሚሉ ይገኙበታል። ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት እስካሁን ካስተላለፋቸው ቅጣቶች ይህ ረዥሙ መሆኑም ተነግሯል። ትውልደ ሩዋንዳዊው ቦስኮ ንታጋንዳ የ46 ዓመት ጎልማሳ ሲሆን በሩዋንዳ እና በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በተፈጸሙ በርካታ ግድያዎች እና ግጭቶች ተሳታፊ ነበር። እአአ 2013 ላይ ሩዋንዳ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ እጅ መስጠቱ ይታወሳል። ቦስኮ ንታጋንዳ ማነው? አቃቢ ሕጎች ባቀረቡት ክስ ንታጋንዳ የኮንጎ አርበኞች ሕብረት የተረሰኘው ፓርቲ የጦር ሠራዊት ክንፍ ዘመቻዎች እና እቅዶችን ይመራ ነበር። ይህ አማጺ ቡድን የሄማ ጎሳ አባል አይደሉም በተባሉ ግለሰቦች ላይ የጭካኔ እርምጃ ይወስድ ነበር ሲል የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ያትታል። በአንድ የሙዝ እርሻ ላይ በተፈጸመ ጥቃት 49 ሰዎች መገደላቸው የተረጋገጠ ሲሆን ሰዎቹ በዱላ፣ በቢላዋ እና በገጀራ ተደብድበው እና ተቆራርጠው እንዲገደሉ ተደርጓል ይላል የፍርድ ቤቱ መዝገብ። • "በብሔር ግጭት ወደ 900 ሰዎች ገደማ ተገድለዋል" "የወንዶች፣ ሴቶች እና ህጻናት አስከሬን በሙዝ እርሻው ላይ ተገኝቷል። አንዳንዶቹ አስክሬኖች እርቃናቸውን ነበሩ። የአንዳንዶቹ እጃቸው የፊጥኝ ታስሯል፤ የአንዳንዶቹ ጨንቅላት ፈርጧል" ሲሉ የፍርድ ቤቱ ዳኛ ፍሬመር ተናግረዋል። የቦስኮ ንታጋንዳ አማጺ ቡድን በሚንቀሳቀስበት ቀጠና ከ1999 ጀምሮ ከ60 ሺህ በላይ ሰዎች ተገድለዋል። የፍርድ ቤቱ ዳኞች ቦስኮ ንታጋንዳ አንድ የካቶሊክ ቄስ ገድሏል ሲሉም ማስረጃ አቅርበውበታል።
news-56702737
https://www.bbc.com/amharic/news-56702737
ህዳሴ ግድብ፡ ሱዳንና ግብጽ የኢትዮጵያን ጥሪ ሳይቀበሉት ቀሩ
ኢትዮጵያ ሁለተኛውን ዙር የታላቁ የሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ከመጀመሯ በፊት መረጃ ለመለዋወጥ እንዲቻል ግብጽና ሱዳን ባለሙያዎችን እንዲሰይሙ ያቀረበችው ጥሪ አገራቱ ሳይቀበሉት እንደቀረ ተዘገበ።
ኢትዮጵያ ቀደም ሲል በያዘችው መርሃ ግብር መሠረት ሁለተኛውን ዙር የግድቡን የውሃ ሙሌት በመጪው የክረምት ወር እንደምታካሂድ ገልጻ ነው አገራቱን ባለሙያዎቻቸውን እንዲያሳውቁ የጠየቀችው። ግብጽና ሱዳን ኢትዮጵያ እየገነባቸው ያለውን ግዙፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫን በተመለከተ አስገዳጅ ሕጋዊ ስምምነት ላይ ሳይደረስ የውሃ ሙሌት እንዳይካሄድ አጥብቀው ሲወተውቱ መቆየታቸው ይታወቃል። ኢትዮጵያ የሱዳንና የግብጽን ጥያቄ በተደጋጋሚ ውድቅ ያደረገችው ሲሆን ግድቡን ውሃ እንዲይዝ የማድረጉ ሥራ በአገራቱ መካከል የሚደረገው ድርድር እየተካሄደም ቢሆን የማይቀር እንደሆነ ስትገልጽ ቆይታለች። ባለፈው ሳምንት የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበር በሆነችው በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሰብሳቢነት ኪንሻሳ ላይ የተካሄደው ድርድር ያለ ውጤት ከተጠናቀቀ በኋላ ኢትዮጵያ ስለሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት ከሱዳንና ግብጽ ጋር መረጃ ለመለዋወጥ እንዲያመች ባለሙያዎቻቸውን እንዲያሳውቁ ጠይቃለች። ሮይተርስ የዜና ወኪል ከካይሮ እንደዘገበው ግብጽና ሱዳን ከኢትዮጵያ የቀረበላቸውን ጥሪ ተከትሎ አገራቱ ሲያቀረቡ የቆየው ሕጋዊና አሳሪ ስምምነት ላይ ሳይደረስ መረጃ ለመለዋወጥ የሚያግዙ ባለሙያዎችን እንዲያሳውቁ የቀረበውን ጥያቄ አልተቀበሉትም። የሱዳን ዜና ወኪል የአገሪቱ የውሃ ሚኒስቴር መግለጫን ጠቅሶ እንደዘገበው በግድቡ ሙሌት ላይ የመረጃ ልውውጡ አስፈላጊ አካሄድ እንደሆነ ጠቅሶ ነገር ግን ከስምምነት ላይ ከተደረሰው ክፍል ውስጥ በተወሰኑት ላይ የሚያተኩር መሆኑ ጥርጣሬን እንደፈጠረ ገልጿል። አገራቱ ኢትዮጵያ አከናውነዋለሁ ያለችው ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በተመለከተ ስምምነት ሳይደረስ እንዳይካሄድ በተደጋጋሚ ተቃውሟቸውን ቢያሰሙም የማይቀር መሆኑን በመገንዘብ ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑ ታውቋል። በሱዳን በኩል 600 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የሚይዘውን የጀበል አወልያ የውሃ ማከማቻ ግድብን፣ ለመጠጥ ውሃና ለግብርና የሚያስፈልጋትን ውሃ መጠን ኢትዮጵያ ሁለተኛውን ዙር ሙሌት ከመጀመሯ በፊት እንደምትሞላ ሱና ዘግቧል። የግብጽ የመስኖ ሚኒስትርም ለአንድ የአገሪቱ ቴሌቪዥን ኢትዮጵያ የምታካሂደውን ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በግዙፉ የአሰዋን ግድብ ውሃ እንደሚያካክሱት ገልጸው፤ ዋና ስጋታቸው የድርቅ ወቅት እንደሚሆን ማመልከታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር የሆኑት ስለሺ በቀለ (ዶ/ር፣ ኢንጂ.) ኢትዮጵያ ወደ መጠናቀቁ የተቃረበውን የሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በምንም ዓይነት መልኩ እንደማታራዝመውና ለዚህም የሚያበቃ አሰራርና ምክንያትም እንደሌለ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድም መጋቢት ወር ላይ ለአገሪቱ ምክር ቤት ላይ እንዳስረዱት፤ ኢትዮጵያ የግድቡን ውሃ አሞላል በተመለከተ ከድርድሩ ማብቃት በኋላ ይከናወን የሚባል ከሆነ አገሪቱን "በዓመት አንድ ቢሊየን ዶላር ያሳጣታል" በማለት የውሃ ሙሌቱን ማዘግየት እንደማይቻል አመልክተዋል። ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ዙር የውሃ ሙሌት ያከናወነችው ተመሳሳይ የሆነ ጥያቄ ከሱዳንና ግብጽ እየቀረበ በነበረበት ጊዜ መሆኑ ይታወሳል። ኢትዮጵያ አምስት ቢሊየን የሚጠጋ ዶላር አውጥታ እየገነባችው ያለው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሊጠናቀቅ 20 በመቶ ያህል የቀረው ሲሆን፤ የግድቡ ግንባታ ሲጠናቀቅ በአፍሪካ ካሉ ግዙፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎች ሁሉ ቀዳሚው ይሆናል ተብሏል። ግድቡ ተጠናቅቆ ሙሉ ለሙሉ ሥራውን ሲጀምር ከ5 ሺህ ሜጋ ዋት በላይ ኤሌክትሪክ የማመንጨት አቅም አለው። ግድቡ ባለፈው ዓመት የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት ያደረገ ሲሆን ሁለተኛውን ዙር ደግሞ በመጪው ክረምት ሐምሌና ነሐሴ እንዲሁም አስፈላጊ ከሆነ በመስከረም ወር ላይ እንደሚከናወን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል። ወደ 80 በመቶ የሚጠጋው የግድቡ የግንባታ ሥራ መከናወኑ የተነገረ ሲሆን በመጪው ዓመትም በተወሰነ ደረጃ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ይጀምራል። ግብጽና ሱዳን ግድቡ የውሃ አቅርቦታችንን በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሰዋል በሚል ከግንባታው መጀመር አንስቶ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ቢቆዩም፤ ከግማሽ በላይ ለሚሆነው ሕዝቧና እያደገ ላለው የኢንዱስትሪ ዘርፏ ኤሌክትሪክ ለማቅረብ ዋነኛ ግቧ አድርጋ የተሳችው ኢትዮጵያ በግንባታውና ቀጥላ ወደ ማጠናቀቁ ተቃርባለች። የግብጽና የሱዳን መንግሥታት ከፍተኛ ባለስልጣናት በተለያዩ አጋጣሚዎች ኢትዮጵያ እየገነባችው ባለው ግድብ ሳቢያ አገሮቻቸው ከወንዙ በሚያገኙት የውሃ መጠን ላይ ተጽእኖ እንደሚኖረው ስጋታቸውን በተደጋጋሚ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ግድቡን የምትጠቀመው ውሃውን በግዛቷ ውስጥ ለሚያስቀሩ ፕሮጀክቶች እንዳልሆነ በተደጋጋሚ ብታስረዳም ሱዳን በተለይም ግብጽ የትኛውም አይነት በውሃው ላይ የሚከናወን ሥራ የእነርሱን ስምምነት ሳያገኝ መካሄድ እንደሌለበት ሲገልጹ ቆይተዋል። ግንባታው ከተጀመረ አስረኛ ዓመቱን የያዘው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውሃ አሞላልና ቀጣይ የሥራ ሂደትን በተመለከተ በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በግብጽ መካከል ለዓመታት ሲካሄድ የቆየው ድርድር ውጤት ሳያስገኝ እስካሁን ዘልቋል። የአፍሪካ ሕብረት የሚያሸማግለው ይህ ድርድር ቀደም ሲል በአዲስ አበባ፣ በካርቱም፣ በካይሮና በዋሽንግተን ላይ የሦስቱ አገራት ልዑካን ተገናኝተው ሲካሄድ የቆየ ሲሆን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ ተቋርጦ ከቆየ በኋላ በበይነ መረብ አማካይነት ቀጥሎ ነበር። ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በታላቁ የሕዳሴው ግድብ የውሃ አሞላልና ቀጣይ ሂደት ላይ ለዓመታት ሲያካሂዱት የነበረው ድርድር ቀጣይ ባለፈው ሳምንት ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዋና ከተማ ላይ ለሦስት ቀናት ተካሂዶ ያለውጤት ከተጠናቀቀ ከቀናት በኋላ ነበር ኢትዮጵያ አገራቱ ባለሙያዎቻቸውን እንዲሰይሙ ጥያቄ ያቀረበችው።
news-53930363
https://www.bbc.com/amharic/news-53930363
ሕንድ፡ 53 ሰዎች ብቻ ያሉት ጎሳ ኮሮናቫይረስ አስግቶታል
ሕንድ ውስጥ ባሉ ትናንሽ ደሴቶች ላይ የሚኖሩት አንዳማን የኮሮናቫይረስ ወረርሽን ስጋት ሆኖባቸዋል።
አራት የታላቁ አንዳማን ጎሳ አባላት ኮቨድ-19 ተገኝቶባቸዋል። ሁለቱ ወደ ሆስፒታል ገብተዋል። የተቀሩት ሁለቱ ደግሞ ለይቶ ማቆያ ናቸው። የታላቁ አንዳማን ጎሳ አባላት 53 ናቸው። ሕንድ ውስጥ ባሉ 37 ትናንሽ ደሴቶች ላይ ነው የሚኖሩት። ምስራቃዊ አንዳማንና ኒኮባር ውስጥ ባሉ ደሴቶች ላይ ከሞነሩ ሰዎች መካከል 2985 ሰዎች እስካሁን በበሽታው መያዛቸው ይፋ ሆኗል። 41 ሰዎች ደግሞ በበሽታው ሳቢያ ሞተዋል። እየጠፉ ያሉት የታላቁ አንዳማን ጎሳ አባላት የመጀመሪያውን የኮሮናቫይረስ ታማሚ የመዘገቡት ባለፈው ሳምንት ነው። 53ቱም የጎሳው አባላት ምርመራ እንደተደረገላቸው ለቢቢሲ የተናገሩት የጤና ባለሙያው ዶክተር አቪጂት ሮይ ናቸው። የሕንድ የአስቸኳይ ጊዜ የጤና ባለሙያዎች ለቀናት በመኪናና በጀልባ ተጉዞው ነው ወደ ደሴቶቹ የደረሱት። ምርመራውን ያጠናቀቁት በአንድ ቀን ነው። "ሁሉም ተባባሪዎች ነበሩ" ይላሉ ዶ/ር ሮይ። ዶክተሩ እንደሚሉት አብዛኛዎቹ የጎሳው አባላት ብሌር ወደተባለ ወደብ በየቀኑ ጉዞ ያደርጋሉ፤ ቫይረሱን ያገኙትም በዚህ ምክንያት ሳይሆን አይቀርም። ቫይረሱ እየተመናመኑ ወዳሉ ጎሳዎች ዘልቆ ገብቶ ጥፋት እንዳያደርስ እየተረባረቡ እንዳለ የጤና ባለሙያዎች ይናገራሉ። 'ለዚህም ነው አንዳንድ ጎሳዎችን ሙሉ በመሉ መመርመር የያዝነው።' አንዳማን አምስት ቁጥራቸው እየተመናመነ ያለ ጎሳዎች መገኛ ሥፍራ ነው። እነዚህም ጃራዋ፣ ሰሜን ሴንቲኔል፣ ታላቁ አንዳማን፣ ኦንጌ እና ሾምፔን ናቸው። ጃራዋና ሰሜን ሴንቲኔል የሚባሉት ጎሳዎች ከሌሎች የሕንድ ጎሳዎች ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የላቸውም። በተለይ ሰሜን ሴንቲኔል የተሰኙት ጎሳዎች ማንም ሰው ከውጭ እንዲመጣባቸው አይፈልጉም። ወደ ደሴታቸው የሚመጣ ፀጉረ ልውጥ አደጋ ሊደርስበት ይችላል። በፈንረጆቹ 2018 አሜሪካዊው ጆን አለን ቻው ወደ ደሴታቸው ሲቀርብ ተመልክተው ከርቀተ በቀስት ወግተው መግደላቸው አይዘነጋም። ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል የተባለ ተቋም በ1850ዎቹ ብሪታኒያ ሕንድን ስትወር የታላቁ አንዳማን ሕዝብ ቁጥር ከ5 ሺህ በላይ ነበር ይላል። በወረራው ወቅት በገባው በሽታ ምክንያት ነው ቁጥራቸው የተመናመነው ይላል። በፈረንጆቹ 2010 ታላቁ ቦዋ የተባሉ ሽማግሉ የጎሳው አባል በ85 ዓመታቸው መሞታቸው ይታወሳል። አዛውንቱ የጎሳውን ቋንቋዎች የሚናገሩ የመጨረሻው ሰው ነበሩ። በሌላ በኪል 476 አባላት ያሉት የጃራዋ ጎሳ አባላት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከመስፋፋቱ በፊት ቫይረሱአ እንዳይደርስባቸው በማሰብ ራቅ ወዳለው የደሴት ጫካ መዘዋወራቸውን ባለሥልጣናት ይናገራሉ። ከ115 በላይ አባላት እንዳሉት የሚገመተው የኦንጊ ጎሳ ደግሞ አንድ ደሴት ላይ ሰፍሮ ይኖራል። የጎሳውን አባላት ለመመርመር የጤና ባለሙያዎች ተልከዋል። የሾምፔን ጎሳ አባላትም ምርመራ ይደርግላቸዋል። 10 ደሴቶች ላይ ቫይረሱ መገኘቱን ዶክተር ሮይ ለቢቢሲ ይናገራሉ። በተመሳሳይ ብራዚልና ፔሩ ውስጥ የሚኖሩ ትንሽ ቁጥር ያላቸው ጎሳዎች በቫይረሱ ምክንያት ክፉኛ ተጠቅተዋል። በብራዚል አማዞን ጫካ ከሚኖሩ ቀደምት ጎሳዎች መካከል 280 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት መሞታቸው ተዘግቧል።
50900209
https://www.bbc.com/amharic/50900209
በቀጥታ ሥርጭት ላይ እያለች ደስታዋን መቆጣጠር ያልቻለችው ጋዜጠኛ ይቅርታ ጠየቀች
በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ላይ እያለች ሎተሪ እንደደረሳት ስታውቅ የሥራ ባልደረቦቿን 'ነገ ሥራ አልመጣም' ያለችው ስፔናዊት ጋዜጠኛ ይቅርታ ጠየቀች።
ናታልያ እስኩድሮ አርቲቪኢ ለተባለ የቴሌቪዥን ጣቢያ የምትሰራ ሲሆን፤ የቀጥታ ስርጭት ላይ እያለች ሎተሪ እንደደረሳት ስታውቅ በደስታ ተሞልታ እየጮኽች በነጋታው ወደ ሥራ ገበታዋ እንደማትመጣ ተናግራለች። ነገር ግን ቆየት ብላ የደረሳት ሎተሪ በጠቅላላ 4 ሚልዮን ዩሮ ከሚያስገኘው ዕጣ ናታልያ የደረሳት 5ሺህ ዩሮ ብቻ መሆኑን ተረድታለች። • ጃኖ ባንድ በኤርትራ እንዳይዘፍን የተደረገው ሙዚቃ አለ? • "በዓይን የሚታይ የእምቦጭ አረም ወደ ሚቀጥለው ዓመት እንዳይተላለፍ እናደርጋለን" • ቦይንግ ዋና ስራ አስፈፃሚውን ቢያሰናብትም በ737 ማክስ ላይ ስጋቶቹ እንዳሉ ናቸው የገና ሎተሪው ከፍተኛ ሽልማት 4 ሚሊዮን ዩሮ ቢሆንም ብሩ ግን ለበርካታ አሸናፊዎች የሚከፋፈል ነበር። ናታልያ ይህንን እንዳወቀች ለድርጊቷ ይቅርታ ጠይቃለች። ናታልያ እንዳለችው እንደዛ "ስሜታዊ" ሆና በመናገሯ እንደተፀፀተችና ባደረገችው ነገር ጥሩ ስሜት ላልተሰማቸው ተመልካቾቿም ስለሁኔታው እንደምታብራራ ገልፃለች። የናታልያ ምላሽ የመጣው የቴሌቪዥን ምስሉ በሰፊው ማህበራዊ መገናኛ ብዙኀን ላይ ሲሰራጭ 'ሙያዊ ስብዕና ይጎድላታል' የሚል ክስ ከቀረበባት በኋላ ነው። በሎተሪው ዕጣ የሽልማት ሥነ ሥርዓቱ ላይ ሻምፓኝ ተከፍቶ፣ ትልቁ የዕጣ መጠን በሚነገርበት ግዜ ናታልያ በደስታ ስትዘል በቀጥታ በቴሌቪዥን ተላልፏል። ተመልካቾችም ዳጎስ ያለ ገንዘብ እንዳሸነፈችና ሥራዋንም እንደምታቆም የገለፀችበት አኳኋንን እንደነቀፉት የስፔን መገናኛ ብዙኀን ዘግበዋል። ይህ የእርሷን ስሜት የያዘው ስርጭት ከተላለፈ በኋላ እስኩድሮ ዳግመኛ በቴሌቪዥን መስኮት ላይ ብትቀርብም ብዙም አላወራችም። ለቀረበባት ትችት ትዊተር ላይ የሰጠችው ምላሽ እንደሚለው በጊዜው ለወራት ያክል ግላዊ በሆነ ምክንያት ችግር ገጥሟት የነበረ ቢሆንም በ25 ዓመት ብቁ በሆነ የጋዜጠኝነት ህይወቷ በቅንነት ተግታ እንደሰራችና እንደምትኮራበትም ተናግራለች። "ናታሊያ እስኩድሮ አደናጋሪና ውሸታም የአርቲቪኢ ጋዜጠኛ" ተብላ ትዊተር ላይ ለተፃፈው ክስና ለተፈጠረው ግራ የሚያገባ ድርጊቷ ይቅርታ በመጠየቅ አሰትባብላለች።
news-50163995
https://www.bbc.com/amharic/news-50163995
የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የሦስት ቀናት ጸሎት እና ምሕላ አወጀ
ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ጥቅምት 13 ቀን 2012 ዓ. ም በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሰጠው መግለጫ የምሕላና የሰላም ጥሪ አስተላልፏል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በአገሪቷ እንኳንስ ሊደረግ ቀርቶ ሊታሰቡ የማይገባቸው ጎሳንና ሃይማኖትን መሠረት ያደረጉ መጠነ ሰፊ ግጭቶች በተለያዩ አካባቢዎች መስፋፋታቸው እንዳሳሰበው የገለፀው ቅዱስ ሲኖዶሱ፤ ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ቀናት የጸሎትና ምሕላ እንዲደረግ አውጇል። • የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በተለያዩ ከተሞች ሰልፍ አካሄዱ • ቅዱስ ሲኖዶስ የኦሮሚያ ቤተክህነት አደራጅ ኮሚቴ የጠራውን መግለጫ መንግሥት እንዲያስቆም ጠየቀ ከመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ጀምሮ ሁሉም አካላትና ዜጎች በየድርሻው ለአገራዊ ሰላም፣ አንድነት እና ተግባቦት የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ አድርጓል። ቅዱስ ሲኖዶሱ በመግለጫው በተለያዩ አካባቢዎች የሚነሱ ግጭቶች "ምክንያታዊ ባልሆኑ ጉዳዮች መነሻነት የተከሰቱ ናቸው" ብሏል። ከእውነታ የራቁ፣ የሕዝቡን የአንድነት እና የአብሮነት ባህል የሚጎዱ፣ ታሪክን የሚያፋልሱ ሐሰተኛ ትርክቶች ለግጭቶች መንስዔ እንደሆኑም ገልጿል። አክሎም የፖለቲካ ኃይሎች፣ የብዙኃን መገናኛዎች፣ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እንዲሁም ምሁራንና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ብሔርንና ኃይማኖትን መሠረት ካደረጉ የትንኮሳ ቃላት ተቆጥበው፤ ለአገራዊ አንድነትና ተግባቦት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪውን አቅርቧል። የጸጥታ እና የፍትሕ አካላት፣ ግጭቶች እና አለመግባባቶች ከመከሠታቸው በፊት ቀድሞ በመከላከል የሰው ሕይወት መጥፋትንና የንብረት ውድመትን በማስቀረት የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ቅዱስ ሲኖዶሱ ጠይቋል። "እስከ አሁን ድረስ በግጭቶች እየደረሱ ካሉት የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት ልንማር ባለመቻላችን ችግሩ ቀጥሎ በዚህ ሳምንትም በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ ክልልና በሌሎችም ክልሎች እየተሠከተ ያለው ግጭት እጅግ አሳሳቢ ነው" ሲል ገልጿል ሲኖዶሱ። ችግሩ ጊዜ የማይሰጥና ሁሉም ኢትዮጵያውያን በአንድነትና በሕብረት ችግሩን ካልቀረፍነው መጠነ ሰፊ ጉዳትን የሚያስከትል በመሆኑም ከሌሎች የመወያያ አጀንዳዎች በማስቀደም በጉዳዩ ላይ በስፋት መወያየቱን ገልጿል። ከውይይቱ በኋላም ባለ አስራ ሁለት ነጥብ የአቋም መግለጫ እና የሰላም ጥሪ አስተላልፏል። • ቅዱስ ሲኖዶስ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አደራጅ ኮሚቴ ጥያቄን አወግዛለሁ አለ ሲኖዶሱ በመግለጫው ማንኛውም የተለየ ሃሳብ ያለው ወገን በሰለጠነ እና በሰከነ መንገድ በውይይት ችግሮችን እንዲፈታ፣ የወደፊት የአገር ተረካቢ የሆነው ትውልድ አገራቸውንን ከጥፋትና ካልተገባ ድርጊት እዲታደጉ ጥሪ አቅርቧል። ልዩ ልዩ ፅሁፎችንና ዘገባዎችን በመገናኛ ብዙኃን አሊያም በማህበራዊ ሚዲያ የሚያቀርቡ የፖለቲካ ተንታኞች እና አክቲቪስቶች ከስሜት፣ ከብሔር፣ ከቋንቋና ከኃይማኖት ልዩነት በጸዳ ሁኔታ ለሰላም የበኩላቸውን እንዲያደርጉ፣ የመንግሥትም ሆነ የግል መገናኛ ብዙሃን ከተቋቋሙበት ዓላማ አንጻር ግጭትን ከሚፈጥሩ ነገሮችና ትንኮሳዎች እንዲቆጠቡና ሚዛናዊ የሆኑ መረጃዎችን ለሕዝቡ በማድረስ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጠይቋል። ምሁራን ለአገር እድገት ያላቸውን ሚና የሚጠቅሰው መግለጫው አሁን አሁን ግን አንዳንድ ምሁራን የሚያስተላልፏቸው የኢትዮጵያን ታሪክ መሠረት ያላደረጉ ትርክቶች ለግጭትና ላለመግባባት መንስዔ ሲሆኑ እንደሚስተዋሉ ጠቅሷል። በመሆኑም ምሁራን ለአገራዊ አንድነትና ሰላም ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጥሪ አስተላልፏል። በየደረጃው ያሉ የመንግሥት ኃላፊዎችም ግጭቶች ከመከሰታቸው በፊት ከሕዝብ ጋር ውይይት በማድረግ እና ከውይይቱ የሚገኙ ግብዓቶችን የእቅዳቸው አካል አድርገው ለትግበራው በመሥራት ኃላፊነታቸውን እዲወጡ ጠይቀዋል። መላው የኢትዮጵያ ሕዝብም እስከ አሁን ድረስ የኢትዮጵያን ሰላም በማይወዱ አካላት የሚከሠቱ ልዩ ልዩ አፍራሽና ግጭት ቀስቃሽ አጀንዳዎችን ወደ ጎን በመተውና በአርቆ አሳቢነትና በአገር ባለቤትነት መጠነ ሰፊ ትዕግሥት የተሞላበት አገራዊ አንድነትና ኅብረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ላበረከቱት የማይተካ ሚና የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም ምስጋና አቅርቧል። በመሆኑም አሁንም ለሰላምና አንድነት በዘር፣ ብሔርና ሃይማኖት ሳይለያዩ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ሲኖዶሱ የአደራ መልዕክት አስተላፏል። መግለጫው አክሎም ሌሎች የሃይማኖት ተቋማትም ለአገራዊ አንድነትና ለእምነት ነጻነት በአንድነትና በሕብረት ለመላው ሕዝባችን የሰላም ጥሪ በማስተላለፍ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጥሪ አድርገዋል። በመጨረሻም መላው ሕዝብ እንደየእምነቱና ሃይማኖቱ ሥርዓት ከዛሬ ጥቅምት 13 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለ3 ቀን ያህል በጾም፣ በጸሎትና በሐዘን ስለ ሀገር ሰላም በአንድነት ጥሪውን ለፈጣሪው ያቀርብ ዘንድ ጥሪውን አስተላልፏል።
news-50670465
https://www.bbc.com/amharic/news-50670465
የልጁን 'ድንግልና' በየዓመቱ የሚያስመረምረው ራፐር ውዝግብ አስነሳ
ታዋቂው አሜሪካዊ አቀንቃኝ ቲአይ የ18 ዓመት ልጁን በየዓመቱ የማህጸን ሐኪም ጋር እየወሰደ 'ድንግልና' ዋ መኖር አለመኖሩን እንደሚያረጋግጥ ከተናገረ በኋላ ተቃውሞና ውዝግብን እያስተናገደ ነው።
የራፕ ሙዚቃ አቀንቃኙ ቲ.አይ (ክሊፎርድ ሃሪስ) ራፐሩ ጨምሮም ምርመራውን ያደረገውን ዶክተር "ውጤቱን በፍጥነት ነበር" የሰጠኝ ሲል አድናቆቱን ገልጿል። • በማርገዛቸው ከትምህርት ቤት የተባረሩት ተማሪዎች ተመረቁ ይህንን ተከትሎም የኒው ዮርክ ግዛት ሕግ አውጪዎች፤ ሴቶች ቀደም ብሎ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጽመው እንደሆነ ለማወቅ የሚደረገው የ 'ድንግልና' ምርመራ እንዲከለከል ጥሪ እያቀረቡ ነው። ጾታዊ ጥቃት ነው ምርመራው እንዳይደረግ የሚከለክለው ሕግ እንዲወጣ ከሚጥሩት የኒው ዮርክ ምክር ቤት አባላት መካከል የዲሞክራቲክ ፓርቲ ወኪል የሆኑት ሚሼል ሶላጅስ "ድርጊቱ በሴቶች ላይ ከሚፈጸሙ ጥቃቶች መካከል አንደኛው ነው" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። • "ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ብወስድም አረገዝኩ" "ቲአይ በሴት ልጁ ላይ ያስደረገው የ 'ድንግልና' ምርመራና የሰጠው አስተያየት ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ነው። በዚህም ድርጊቱ ሴቶችን እንደ ቁስ የሚቆጥር የተሳሳተ መልዕክት አስተላልፏል" ብለዋል የምክር ቤት አባሏ። እንዲወጣ የተጠየቀውን ሕግ የሚደግፍ ተመሳሳይ ረቂቅ ለግዛቲቱ ምክር ቤት ቀርቦ ደንቦችን የሚመረምረው ኮሚቴ እንዲወያይበት እንደሚደረግ ይጠበቃል። ሕጉ ምን ይዟል? ሕጉ ተቀባይነት አግኝቶ ከጸደቀ በሴቶች ላይ የሚደረግ ማንኛውም አይነት የ 'ድንግልና' ምርመራ ሕገ ወጥ የሚደረግ ሲሆን፤ ምርመራውን ፈጽመው የተገኙ ሐኪሞችም የሥራ ፈቃዳቸው እንዲሰረዝ የሚያደርግ እርምጃ ይወሰድባቸዋል። በተጨማሪም ምርመራውን የፈጸሙ ሐኪሞች ላይ ቅጣትና የወንጀል ክስ የሚቀርብባቸው ሲሆን፤ ምርመራው ከህክምና ተቋም ውጪ ከተከናወነ ደግሞ ድርጊቱ እንደ ወሲባዊ ጥቃት ይቆጠራል። በአሁኑ ወቅት 'ድንግልና' ምርመራን በተመለከተ በመላዋ አሜሪካም ሆነ በየትኛውም ግዛት ውስጥ የሚከለክል ሕግ የለም። ቲ.አይ ከቤተሰቡ ጋር 'ምርመራው አስፈላጊ አይደለም' 'ድንግልና' ምርምራ ቢያንስ 20 በሚሆኑ አገራት ውስጥ የሚፈጸም ሲሆን፤ የዓለም የጤና ድርጅት ግን ድርጊቱ ምንም አይነት የጤና ጠቀሜታ የሌለው ከመሆኑ ባሻገር በአብዛኛው በሴቶች ላይ ህመምንና ስቃይን የሚያስከትል አዋራጅ ተግባር ነው ይላል። • ኢንስታግራም ለአዳዲስ ተመዝጋቢዎች እድሜን ሊጠይቅ ነው የጤና ባለሙያዎች ድርጊቱን ሳይንሳዊ ያልሆነ፣ ጎጂና የሴቶችን ሰብአዊ መብት የሚጋፋ ከመሆኑ ባሻገር ጥቅም አልባ ነው ይላሉ። አክለውም በምርመራው 'ድንግልና' መኖር አለመኖሩን ማረጋገጥ አይቻልም፤ ምርመራውም ጎጂ አካላዊና አዕምሯዊ ጉዳትን የሚያስከትል ውጤት ሊኖረው ይችላል። የዓለም የጤና ድርጅት፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብትና የሴቶች ተቋማት ድርጊቱን "በህክምና አስፈላጊ ያልሆነ" በሚል በዓለም ዙሪያ ክልከላ እንዲደረግበት ጥሪ አቅርበዋል። ዓመታዊ 'ድንግልና' ምርመራ ምርመራው በአባቷ አማካይነት እንዲደረግባት የተገደደችው የራፕ ሙዚቀኛው ቲአይ ሴት ልጅ፣ ዴይጃህ ሃሪስ ጉዳዩ ይፋ ከተደረገ በኋላ በተለያዩ ማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃኖች ላይ አባቷን መከተል አቁማ እራሷን እንዳራቀች ተዘግቧል። የ39 ዓመቱ ቲአይ ትክክለኛ ስሙ ክሊፎርድ ሃሪስ ሲሆን፤ ሦስት ግራሚ ሽልማቶችን አግኝቷል። በልጁ ላይ ያስደረገውን የ 'ድንግልና' ምርመራን በተመለተ አወዛጋቢውን ነገር የተናገረው በአንድ የፖድካስት ስርጭት ላይ ቀርቦ ነው። ዘፋኙ በውይይቱ ላይ ለልጆቹ ስለ ጾታዊ ጉዳዮች የሚሰጠውን ትምህርት በተመለከተ ተጠይቆ ሲመልስ "ግልጽ የሆነ ውይይት ብቻ ሳይሆን በየዓመቱ ሴት ልጄን ሃኪም ጋር በመውሰድ 'ድንግልና' አስመረምራለሁ። አብሪያት ነው የምሄደው 18 ዓመቷ ነው አስካሁን ምንም ለውጥ የለም" ብሏል። • እቴጌ፡ የጡት ካንሰርን በቀላሉ በስልክዎ መለየት እንደሚችሉ ያውቃሉ? ባለሙያዎች የሴቶች 'ድንግልና' መለያ ነው ተብሎ የሚነገርለት ተፈጥሯዊው ስስ አካል [ሃይመን] ከግብረ ሥጋ ግንኙነት ውጪ በሆኑ አጋጣሚዎች ሊጠፋ እንደሚችል ይናገራሉ። ዘፋኙ እንዳለው ዶክተሩ ብስክሌትና ፈረስ በመጋለብ፣ በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በሌሎች ከባድ ሥራዎች ሳቢያ 'ድንግልና' ሊጠፋ እንደሚችል ቢነግረውም "የተባሉትን ከባድ እንቅስቃሴዎችን አድርጋ አታውቅም። ስለዚህ ምርመራውን አድርጉና በቶሎ ውጤቱን ስጡኝ" እንዳለቸው ተናግሯል። በተጨማሪም ሁሉም ሴቶች ሲወለዱ 'ድንግልና' ን ያመለክታል የተባለው ስስ አካል በተፈጥሮ ይኖራቸዋል ተብሎ እንደማይጠበቅ አሜሪካው ውስጥ የሚገኝ አንድ ኮሌጅ ጠቅሷል። ከውዝግብ የማይርቀው ከሦስት ሴቶች ስድስት ልጆችን የወለደው ቲአይ በተለያዩ ጎዳዮች ላይ ውዝግቦችን በመቀስቀስ በኩል አዲስ እንዳልሆነ ዘገባዎች ያመለክታሉ። አቀንቃኙ ከዚህ ቀደም የጦር መሳሪያዎችንና ዕጾችን ይዞ በመገኘት ተይዞ ሁለት ጊዜ ለእስር ተዳርጓል። • የኮሌስትሮል መጠናችን ማወቅ ያለብን መቼ ነው? ቲኒ ተብላ የምትታወቀው አሜሪካዊት ዘፋኝና የሙዚቃ ጸሐፊ የሆነችው ባለቤቱ፤ ታማኝ ባለመሆንና አክብሮት የጎደለው ነው በሚል ክስ አቅርባበት ነበር። ከአራት ዓመት በፊት ሒላሪ ክሊንተን ለምርጫ በተወዳደሩበት ጊዜ በእጩዋ ላይ ተገቢ ያልሆነ አስተያየት በመሰንዘሩ ከፍተኛ ውዝግብና ውግዘት ገጥሞት ነበር።
news-53988778
https://www.bbc.com/amharic/news-53988778
ፈረንሳይ፡ ቻርሊ ሄብዶ መፅሄት አወዛጋቢውን የነብዩ መሐመድ ካርቱንን እንደገና አተመ
ቻርሊ ሄብዶ የተሰኘው የፈረንሳዩ ቧልት ቀመስ መፅሄት ከአምስት ዓመታት በፊት ለሽብር ጥቃት ያጋለጣቸውን የነብዩ መሐመድን ምስል በካርቱን እንደገና አውጥቷል።
የሽብር ጥቃቱን በዋነኝነት ያቀነባበሩት ሁለት ፅንፈኛ አክራሪዎችና እነሱንም በመርዳት አስራ አራት ግለሰቦች የፍርድ ሂደት በነገው እለት የሚጀመር ይሆናል። የመፅሄቷ ጋዜጠኞች ስብሰባ ላይ እያሉ በተሰነዘረው ጥቃት ታዋቂ ካርቱኒስቶችን ጨምሮ አስራ ሁለት ሰዎች ተገድለዋል። በዚያኑ ቀንም እንዲሁ በፓሪስ በደረሰ ሌላ ጥቃት አምስት ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። ይህንንም ተከትሎ ፀረ- ጂሃድ ተቃውሞዎች ፈረንሳይን አጥለቅልቀዋት ነበር። መፅሄቱ በፊት ገፁ ላይ በአሁኑ ወቅት ይዞት የወጣው የነብዩ መሃመድን የሚወክል አስራ ሁለት ካርቱኖችን ናቸው። እነዚህ ካርቱኖች በቻርሊ ሄብዶ መፅሄት ላይ ከመውጣታቸው በፊት አንድ የዴንማርክ ጋዜጣ ነበር መጀመሪያ ይዞት የወጣው። በአንደኛው ካርቱንም ላይ ነብዩ መሃመድ በተርባን ጥምጥም ፈንታ ቦምብ ጭንቅላታቸው ላይ ይታያል። በፈረንሳይኛም "ይሄ ሁሉ የደረሰው ለዚህ ነበር" የሚልም መልዕከትን አስፍሯል። መፅሄቱ በርዕሰ አንቀፁም ላይ እንዳሰፈረው ከአምስት አመት በፊት የደረሰውን ጥቃት ተከትሎም የነብዩ መሐመድን ተመሳሳይ ካርቱን እንዲያትሙ ከፍተኛ ጥያቄ እንደቀረበላቸው ነው። "ተመሳሳይ ካርቱኖች እንድናትም ከፍተኛ ፍላጎት ቢኖርም ፈቃደኛ አልነበርም። ህጉ ቢፈቅድልንም ምክንያት አልነበረንም። በአሁኑ ሰዓት ግን ጥቃቱን ያደረሱት ግለሰቦች የፍርድ ሂደት በሚጀመርበት ሳምንት መሆኑ እንደገና ማተሙ ትርጉም አለው" በማለት አስፍሯል። በፍርድ ሂደቱ ምን ይጠበቃል? የቻርሊ ሄብዶ የፓሪስ ቅርንጫፎቹን ጨምሮ፣ በአይሁዶች ባለቤትነት የሚገኝ መደብር ጥቃት ደርሶባቸዋል። አንድ ፖሊስ እንዲሁ የሽብር ጥቃቱ ኢላማ ሆኗል። ሶስቱ ተጠርጣሪዎች በሌሉበት ጉዳያቸው የሚታይ ሲሆን ወደ ሶሪያና ኢራቅ ሳይሄዱም አልቀሩም ተብሏል። በፍርድ ሂደቱ ላይ ከጥቃቱ የተረፉትን ጨምሮ፣ ወዳጅ ዘመድ ቤተሰቦቻቸውን ያጡ 200 የሚጠጉ ምስክሮች እንደሚሰሙበትም የፈረንሳዩ አርኤፍአይ ዘግቧል። ፍርዱ መጋቢት ላይ ይጀመራል ተብሎ ዕቅድ ተይዞለት የነበረ ቢሆንም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተራዝሟል። ሂደቱም እስከ ህዳር ድረስ ይቆያል ተብሏል። ቧልት ቀመስ የሆነው ቻርሊ ሄብዶ በቀኝ አክራሪዎች ላይ በመዘባበት በርካታ ስራዎችን የሚያቀርብ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ በካቶሊክ፣ ይሁዲና እስልምና እምነቶችም ላይ ፌዝና ቀልድ ማቅረቡ አወዛጋቢ አድርጎታል። ሆኖም ነብዩ መሃመድን በካርቱን ማሳየታቸው በተደጋጋሚ የሽብር ጥቃት ኢላማ አድርጓቸዋል። መፅሄቱም ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ነው በሚል ካርቱኑን ደግፎ አዘጋጁ ስቴፈን ቻርቦኒየር (ቻርብ) ተከራክሯል " ሙስሊሞች በስዕላችን ስላልሳቁ ምንም አልላቸውም። እኔ የምኖረው በቁርዓን ህግ ስር ሳይሆን በፈረንሳይ ህግ ነው" በማለት በ2012 መናገሩንም አሶሺየትድ ፕሬስ አስነብቦ ነበር። በ2015 ጥቃት በኋላም በርካቶች " እኔ ቻርሊ ነኝ" በሚልም ለመፅሄቱ ያላቸውን ድጋፍ አሳይተዋል። በአወዛጋቢነቱና በቆስቋሽነቱ በአለም የገነነው መፅሄቱም የሌሎችን እምነት እንዲያከብርም ከፍተኛ ትችት እንደደረሰበትም የጋዜጣው ስራ አስኪያጅ ጄራርድ ቢያር ለቢቢሲ ጥቃቱ ከደረሰ ከአመት በኋላ ተናግረው ነበር።
51813106
https://www.bbc.com/amharic/51813106
ወደ እስራኤል የሚገቡ መንገደኞች በሙሉ ለ14 ቀን ራሳቸውን ለይተው እንዲያቆዩ ተወሰነ
ማንኛውም ወደ እስራኤል የሚያቀና መንገደኛ ለ14 ቀን ራሱን ለይቶ እንዲያቆይ መወሰኑ ተሰምቷል።
ለቀጣዮቹ ሁለት ሳምንታት ከተለያዩ አገራት ወደ እስራኤል የሚገቡ መንገደኞች ራሳቸውን ለይተው እንዲያቆዩ ተወስኗል ይህ ውሳኔ የመጣው የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በሚል ሲሆን ውሳኔውንም የተናገሩት የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ናቸው። "ከተለያዩ አገራት ወደ እስራኤል የሚመጡ ሰዎች በለይቶ ማቆያ ውስጥ ይቀመጣሉ" ብለዋል በትዊተራቸው ላይ ባሰፈሩት የተንቀሳቃሽ ምስል መልዕክት። • በኮሮናቫይረስ ምክንያት በመላ ጣልያን እንቅስቃሴ እንዲገደብ ተደረገ • በኮሮናቫይረስ ተያዙ ከተባሉት ኢትዮጵያዊያን አንዱ ነጻ ሆነ ኮሮናቫይረስ፡ ጀርም ወይም ቫይረስ ከእጅ ወደ አፍ እንዴት ይተላለፋል? እንዴትስ እንከላከለዋለን? የእስራኤል የአገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር አርያ ዴሪ እርምጃው ከተለያዩ አገራት የሚመጡ እስራኤላውያን ላይም ወዲያውኑ ተፈፃሚ እንደሚሆን ገልፀዋል። ለውጪ አገራት ዜጎች ግን ከማክሰኞ ዕለት ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ሲሉ አስታውቀዋል። ይህ እርምጃ ተግባራዊ ሲሆን ከውጪ አገራት የሚመጡ የሌላ አገር ዜጎች ተነጥለው ሊያርፉ የሚችሉበት ቦታ እንዳላቸው ማረጋገጥ መቻል አለባቸው ማለት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ " ከረዥም ክርክር በኋላ ውሳኔውን አስተላልፈናል። ማንኛውም ወደ እስራኤል የሚመጣ ሰው ለ14 ቀን ተለይቶ መቆየት አለበት" ብለዋል በመግለጫቸው ላይ። "ይህ ውሳኔ አስቸጋሪ ውሳኔ ነው። ነገር ግን የሕዝብ ጤናን ለመጠበቅ ማኝኛውንም ነገር ማድረግ አለብን" በማለት ውሳኔው ለሁለት ሳምንት እንደሚቀጥል ተናግረዋል። ውሳኔው ተግባራዊ ሲሆን በባህር ማዶ የሚገኙ 268 ሺህ እስራኤላውያን ወደ አገራቸው ሲመለሱ ራሳቸውን ከሰው አግልለው ማቆየት ይጠበቅባቸዋል ማለት ነው። 9 ሚሊዮን ሕዝብ ባላት እስራኤል እስካሁን 42 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን የሞተ ግን የለም። እስራኤል ከተለያየ አገራት የሚገቡ መንገደኞች ላይ እገዳ የጣለች ሲሆን ከእነዚህም መካከል ጣሊያን አንዷ ናት። እስካሁን ድረስ በዓለም ላይ 111 ሺህ ሰዎች በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሲሆን 3890 ሞት ተመዝግቧል።
news-46678595
https://www.bbc.com/amharic/news-46678595
ሀውስ ኦፍ ካርድ ላይ ፍራንክ አንደርውድን ሆኖ የሚተውነው ኬቨን ስፔሲ በፆታዊ ትንኮሳ ክስ ተመሰረተበት
ሀውስ ኦፍ ካርድስ የተሰኘው ተከታታይ ፊልም ላይ ፍራንክ አንደርውድ በሚል ገፀ ባህርይ የሚታወቀው ታዋቂው አሜሪካዊ ተዋናይ ኬቨን ስፔሲ ማሳቹሴትስ በሚገኝ መጠጥ ቤት ውስጥ የ17 ዓመት ልጅ ላይ ፆታዊ ትንኮሳ በማድረሱ ክስ ተመስርቶበታል።
ይህንን ፈፅሟል ተብሏል የተጠረጠረው ከሁለት ዓመታት በፊት ሲሆን ታህሳስ 29 ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ቢዘገብም ተዋናዩ በምላሹ ሰኞ ዕለት ምንም ስህተት እንዳልሰራ በመናገርም መልዕክቱን በተንቀሳቃሽ ምስል (ቪዲዮ) አስተላልፏል። •"ገዳ የወደፊቱ የፖለቲካ ስርዓት መሆን ይችላል" ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ •የ "ጥርስ አልባው" ማዕቀብ መነሳት ፖለቲካ? •"በኢትዮጵያ ፖለቲካ የኦነግ ስም ቅመም ነው" የኦነግ የፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ "ምንም ባላጠፋሁት ጉዳይ ዋጋ ልከፍል አይገባም። ያለ ማስረጃ እንዴት ታምናላችሁ። እውነታውን ሳያገናዝቡ ለፍርድ መቸኮል አይገባም" ብሏል። ይህ 'ግልፅ ልሁን' የሚል መጠሪያ የተሰጠው ቪዲዮ የፆታዊ ትንኮሳ ውንጀላ ከቀረበበት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየበት ነው። በቪዲዮው ላይ በሴረኛው ፍራንክ አንደርውድ የአነጋገር ዘዬን በመጠቀም " አንዳንዶች ሁሉንም ነገር ያምናሉ። እንድናዘዝም በጉጉት እየጠበቁ ነው" ብሏል። ትንኮሳውን ይፋ ያደረገችው ጥቃቱ የደረሰባት ወላጅ እናት የቀድሞ የዜና አቅራቢ ሄዘር ኡንሩህ ስትሆን ጊዜውም ባለፈው አመት ነው። በዛን ጊዜ አስራ ስምንት አመት ያልሞላውን ልጇን መጠጥ ከመግዛት በተጨማሪ እንደጎነታተለው በማሳወቅ ወንጅላዋለች። በኔትፍሊክስ በሚተላለፈው ተከታታይ ፊልም ከስድስተኛው ክፍል ቀድሞ ከመገደሉ በፊት ፍራንክ አንደርውድ የተሰኘው ገፀባህርይ በሴረኛነቱ የሚታወቅ ሲሆን ጋዜጠኛንና ፖለቲከኛን ገድሏል። ይህ ውንጀላ ከቀረበበት በኋላ አንቶኒ ራፕ የተሰኘው ተዋናይም በአውሮፓውያኑ 1986 ፆታዊ ትንኮሳን በማድረስ የወነጀለው ሲሆን ሌሎች ፆታዊ ትንኮሳዎችም ይፋ በመሆን ላይ ናቸው። ተዋናዩ ምንም እንደማያስታውስ ቢናገርም እንደ ሌሎች ውንጀላዎች ፈፅሞ አልካደም ነገር ግን በይፋ ይቅርታ ጠይቋል። ውዝግቡ የሙያ ህይወቱን የጎዳው ሲሆን 'ሀውስ ኦፍ ካርድስ'ን ጨምሮ 'መኒ ኢን ዘ ወርልድ' የተሰኘው ፊልምም ያለ እሱ ተዋናይነት እንደገና እንዲቀረፅ ተደርጓል። እሱ የሚተውንበት ቢሊየነር ቦይስ ክለብ የተሰኘው ፊልም ነሀሴ ወር ላይ ሲኒማ ቤት በታየበት በመጀመሪያው ቀን 126 ዶላር ገቢ ብቻ በማስገባት የዝቅተኛ ገቢ ሬከርድ ሰብሯል።
news-49392249
https://www.bbc.com/amharic/news-49392249
ሐኪሞች ለቀዶ ህክምና የሚጠቀሙበት የናዚ መፅሐፍ
ዶክተር ሱዛን ማኪነን ቀዶ ጥገና ማድረግ ሲያሻት እጇን ወደ አንድ የቀደመ መፅሐፍ ትዘረጋለች፤ በ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ የተፃፈ መፅሐፍ።
መፅሐፉ የሰው ልጅ ሰውነትን ልክ እንደ አንድ የኤሌክትሮኒክስ እቃ ከፋፍሎ ያሳያል፤ ከቆዳ ጀምሮ እስከ አጥንት፤ ከጉበት እስከ አንጅት. . .መፅሐፉን ስስ ልብ ያላቸው እንዲያዩት አይመከረም። መፅሐፉ 'Pernkopf Topographic Anatomy of Man' የተሰኘ ርዕስ አለው። የሰው ልጅ መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥ ተብሎ በግርድፉ ሊተረጎም ይችላል፤ ወይም መልክዓ-ሰዋዊ አቀማመጥ። ይህን መፅሐፍ የቀዶ-ጥገና ሐኪሞች እንደ ቅዱስ መፅሐፍ ነው የሚያዩት ተብለው ይታማሉ። የሰው ልጅን ውስጣዊ አሠራር ብትንትን አድርጎ የሚያሳየው መፅሐፍ ኤድዋርድ ፐርንኮፕፍ በተሰኘ የኦስትሪያ ሰው የተፃፈ ነው። መፅሐፉ አሁን ከህትመት ውጭ ቢሆንም ማግኘት ግን ብዙ ድካም አይጠይቅም። በይነ-መረብ ላይ የተለያዩ የመፅሐፉ ዕትሞች ይገኛሉ። ከእርስዎ የሚጠበቀው ትንሽ ሺህ ፓውንዶች [ረብጣ ብር] መያዝ ነው። መፅሐፉ ያላቸው ሰዎች ግን በኩራት ሼልፋቸው ላይ ወይም ከመስታወት ሥር ሲያስቀምጡት አይታዩም፤ ምክንያቱ ወዲህ ነው። ይህን መፅሐፍ ለመፃፍ የሰው ሕይወት ተከፍሏል-የሺህዎች ሕይወት። መፅሐፉ ላይ ደም-ሥራቸው፣ አጥንታቸው እና ቆዳቸው እንደ ምስር ተለቅሞ የሚታዩ ሰዎች በናዚ ግፍ የተጨፈጨፉ ናቸው። ሐኪሞች ይህን መፅሐፍ በፍፁም ሊጠቀሙበት አይገባም የሚሉ በርካቶች ናቸው። ምክንያታቸውም 'መፅሐፉ ጥቁር ታሪክ አዝሏልና' ይላሉ። ዶክተር ሱዛን መፅሐፉን መጠቀሟ ሰላም እንደማይሰጣት ባትክድም ለሥራዋ እጅግ አጋዥ እንደሆነ ግን አትሸሽግም። ከናዚ የጅምላ ጭፍጨፋ (ሆሎኮስት) የተረፉት የጤና ፕሮፌሰሩ ዮሴፍ ፖላክ 'መፅሐፉ የሞራል ጥያቄ ያለበት ነው' ይላሉ። «የመፅሐፉ ሥረው-ግንድ ሠይጣናዊ ተግባር ቢጠናወተውም አሁን ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው ለበጎ ነው።» የመፅሐፉ ደራሲ ኤድዋርድ ፐርንኮፕፍ የናዚ ዶክተር ነበር፤ የአዶልፍ ሂትለር ቀንደኛ ደጋፊ። የሥራ ባልደረባዎቹ 'ሶሻሊስት' ሲሉ ይገልፁታል፤ ወደ ሥራ ሲመጣ የናዚ ምልክት ክንዱ ላይ የማይለየው ቀንደኛ ናዚ ነበር። ግለሰቡ በቪዬና ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ትምህርት ክፍል ኃላፊ ሆኖ ሲሾም የሎሪየትነት ሽልማት ያገኙትን ሳይቀር አይሁዶችን መርጦ ጠራርጎ ያባረረ ሰው። በወቅቱ በናዚ የተገደሉ የአይሁዶች ሬሣ ለሕክምና ትምህርት ወደ ዶክተሩ ይመጡ ነበር። ሰውዬው በቀን 18 ሰዓት የሰውን ልጅ አካል ሲቀድ እና ሲሰፋ፤ ሲከፋፍል ይውላል። አጋሮቹ ደግሞ ያዩትን በፎቶ እና በስዕል ያስቀራሉ። አንዳንድ ጊዜ ክፍሉ ሙሉ ከመሆኑ የተነሳ ሊገደሉ ተራ የተያዘላቸው አይሁዶች አንድ ቀን ይራዘምላቸው ነበር። መፅሐፎች የመጀመሪያ ዕትሞች የናዚ ምልክት [ስዋስቲካ] ያለባቸውና ፊርማ ያረፈባቸው ናቸው። 1964 [በግሪጎሪ አቆጣጠር] እንግሊዝ ውስጥ የታተመው ሁለተኛ ዕትምም ቢሆን ስዋስቲካ ያለበት ፊርማ ሰፍሮበታል። 90ዎቹ ላይ የሕክምና ተማሪዎች መፅሐፉ ላይ ያሉ ሰዎች እነማ ይሆኑ የሚል ጥያቄ ይጫርባቸውና መመርመር ይጀምራሉ። በኋላ ላይ የመፅሐፉ ያለፈ ምስጢር ሲጣራና ሲታወቅ እንዳይታተም እግድ ተጣለበት። መፅሐፉ በበርካታ ሃገራት ከጥቅም ውጭ እንዲሆን ተደርጓል። በታሪክነት እንዲቀመጥ እንጂ ሐኪሞች እንዲጠቀሙበት አይመከርም። ነገር ግን በቅርቡ የቀዶ ጥገና ሐኪሞች የተሳተፉበት ጥናት ተሠርቶ 59 በመቶ ያህሎቹ መፅሐፉን እንደሚያውቁት ሲናገሩ፤ 13 በመቶዎቹም እንደሚጠቀሙበት ይፋ አድርገዋል። ዶ/ር ሱዛን በቀዶ ጥገና ላይ ሳለች ዶ/ር ሱዛን የዚህን መዘዘኛ መፅሐፍን ያህል ቅንጣት ታክል እንኳ መረጃ የሚሰጥ ሌላ መፅሐፍ የለም ትላለች። በተለይ ደግሞ ከበድ ያሉ ቀዶ ህክምናዎችን ቀለል የሚያደርግ እንደሆነ ዶክተሯ ትመሰክራለች። ዶ/ር ሱዛን በአንድ ሰው ላይ የቀዶ ህክምና እያካሄደች ነበረች። እግሩ አካባቢ ጉዳት የደረሰበት ይህ ሰው ትክክለኛው ነርቭ ተገኝቶ ጥገና ካልተደረገለት እግሩ ሊቆረጥ ግድ ነበር። ዶክተሯ ወዲህ ብትል ወዲያ ትክክለኛው ነርቭ ሊገኝ አልቻለም። በስተመጨረሻ ግን እጇን ዘረጋች. . .ወደ መፅሐፉ። የሰውየውም እግሩ ከመቆረጥ ዳነ። • ለልጃቸው "ሂትለር" የሚል ስም የሰጡ እናትና አባት ተፈረደባቸው ፐርንኮፕፍ ናዚ ከተሸነፈ በኋላ ለእሥር ቢበቃም ከሦስት ዓመታት በኋላ ተለቀቀ። ምንም ዓይነት ክስ አልተመሠረተበትም ነበር። ሰውዬው ከእሥር ከወጣ በኋላ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ዕትም በማውጣት ቸብችቧል። አራተኛውን ዕትም ሊያወጣ በመዘጋጀት ሳለ ነበር ሞት የቀደመው። መፅሐፉ ከወጣ 60 ዓመታት ቢያልፉትም አሁንም የሰው ልጅ ሰውነትን ለማጥናት ወደር የማይገኝለት እየተባለ ነው። መፅሐፉን የመጠቀም ተገቢነት ግን አሁንም አከራካሪነቱ ቀጥሏል።
news-46806124
https://www.bbc.com/amharic/news-46806124
በፊሊፒንስ ጥቁሩን የኢየሱስ ሀውልት ለማክበር በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አደባባይ ወጡ
በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ፊሊፒናውያን ታሪካዊውንና ጥቁሩን የኢየሱስ ሀውልት ለማ ክበር በመዲናዋ ማኒላ በጎዳናዎች ላይ ወጥተው ነበር።
በዚህ አመታዊ ክብረ በዓል በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ፊሊፒናውያን ታሪካዊውን የናዝሬቱን እየሱስ ሀውልት ለማየት ወደ ጎዳናዎች ይወጣሉ። •ስለኢትዮጵያ የቤተ ክርስቲያን ስዕሎች ምን ያህል ያውቃሉ? ሀውልቱ የተቀረፀው በሜክሲኮ ሲሆን ወደ ፊሊፒንስ የመጣው 17ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ነው። በጊዜውም በመርከብ ላይ ከተነሳ እሳት ተርፏል። በፊሊፒንስ የተቀደሰና ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠው ይህ ሀውልት የእየሱስን ስቅለት የሚያሳይ ነው። ኩያፖ በምትባል የሀገሪቷ ግዛት በሚገኝ ቤተክርስቲያን ውስጥ መስቀሉ የሚቀመጥ ሲሆን፤ በየአመቱ ጥር ወር ላይ ግን የተመረጡ ሰዎች ተሸክመውት በመዲናዋ ማኒላ ለሰባት ኪሎ ሜትር ያህል ጉዞ ይደረጋል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አማኞች የስቅለቱን ሀውልት ለማየት የሚመጡ ሲሆን፤ ብዙዎችም ባዶ እግራቸውን ናቸው። ሀውልቱን መንካትም ሆነ መጠጋት ከበሽታም እንደሚፈውስና መልካም እድል እንደሚያመጣ ይታመናል። በፊሊፒንስ ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አጥባቂ የካቶሊክ አማኞች ያሉ ሲሆን የጥቁሩን የናዝሬቱ እየሱስን ሀውልት ለመንካትም ከፍተኛ አደጋ አይበግራቸውም። የፊሊፒንስ ቀይ መስቀል ድርጅት እንዳሳወቀው አረፋፈዱ ላይ ለስድስት መቶ ሰዎች ከመተንፈስ ችግር፣ አቅልን መሳትና ሰውነታቸው ላይ ብልዘት ጋር በተያያዘ ህክምና እንደሰጡ ነው። ሶስት ግለሰቦች ደግሞ ህመማቸው ጠና ያለ በመሆኑ ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። ጉዞው ከመጀመሩ በፊት ሀውልቱ በቤተክርስቲያኗ የሚባረክ ሲሆን ብዙዎችም ከሀውልቱ ጋር የሚመሳሰል የራሳቸውን ሀውልት ለማስባረክ ይዘው ይመጣሉ። የካቶሊክ እምነት አመራሮች ይህ ሰልፍ የሚያሳየው እምነቱ ምን ያህል እያደገና እየጠነከረ መሆኑን ነው ብለዋል።
news-50312930
https://www.bbc.com/amharic/news-50312930
በግድያ የተጠረጠሩት 22 ኢንች በምትሰፋ ቀዳዳ ሾልከው አመለጡ
ፖሊስ በካሊፎርኒያ በአስደናቂ መልኩ ከእስር ቤት ያመለጡ ሁለት ተጠርጣሪዎችን ምስል ይፋ አደረገ።
ሳንቶስ ሳሙኤል ፎንሴካ (ግራ) እና ጆናታን ሳላዛር (ቀኝ) ሳንቶስ ሳሙኤል ፎንሴካ እና ጆናታን ሳላዛር የ21 እና የ20 ዓመት ወጣቶች ሲሆኑ በግድያ ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ ይገኙ ነበር። ሁለቱ ተጠርጣሪዎች የእስር ክፍላቸውን ጣራ በመቦርቦር 22 ኢንች ስፋት ያለው ቀዳዳ ከፈጠሩ በኋላ ሾልከው አምልጠዋል። "በግድያ የተጠረጠሩ ሰዎች ከእስር ቤት ውጪ መሆናቸው በጣም አሳዛኝ ነው" በማለት የአከባቢው ፖሊስ አዛዥ ጆናታን ቶርንበርግ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። • 241 ዓመት የተፈረደበት ጎረምሳ • ኤል ቻፖ ዕድሜ ይፍታህ ተፈረደበት • ባለ አምስት ኮከቡ የኖርዌይ እስር ቤት ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ያመለጡት 22 ኢንች በሚሰፋው ቀዳዳ በኩል ነበር ባለሰልጣናት አደገኛ ናቸው፤ የጦር መሣሪያ ሳይታጠቁ አይቀርም የተባሉትን ሁለቱን ተጠርጣሪዎች ፍለጋ ላይ ይገኛሉ። ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ የሚገኙበትን ለጠቆመ 5ሺህ የአሜሪካን ዶላር ሽልማት እንደሚሰጥ አስታውቋል። ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ከእስር ቤት ሊያመልጡ የቻሉት የእስር ቤቱ ጠባቂዎች ሊመለከቷቸው በማይችሉበት የመጸዳጃ ክፍል ጣሪያ በኩል ነበር። 21 ኢንች ብቻ ስፋት ያለው ቀዳዳ ሁለቱን ተጠርጣሪዎች ማሾለክ መቻሉን ፖሊስ ተናግሯል። ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ከአንድ ዓመት በፊት ነበር በተለያዩ የግድያ ወንጀሎች ተጠርጥረው ነው በቁጥጥር ሥር የዋሉት። ሳንቶስ ሳሙኤል ፎንሴካ ሁለት ሰዎችን በመግደል ተጠርጥሮ የታሰረ ሲሆን፤ ጆናታን ሳላዛር ደግሞ የ20 ዓመት ወጣትን ተኩሶ ገድሏል የሚል ክስ ነበር የቀረበበት ግለሰብ ነው። ሁለቱም ተከሳሾች ጥፋተኛ አይደለንም ሲሉ እየተከራከሩ ነበር።
news-52734566
https://www.bbc.com/amharic/news-52734566
አቶ ታደሰ ካሳ ስምንት ዓመት ከአምስት ወር ጽኑ እስር ተፈረደባቸው
የባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአቶ ታደሰ ካሳ ላይ ስምንት ዓመት ከአምስት ወር ጽኑ እስር ፈርዷል።
ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ በእነ ታደሰ ካሳ የክስ መዝገብ ሥር የነበሩ ሰባት ተከሳሾችን ጉዳይ በተመለከተ ዛሬ ውሳኔ ሰጥቷል። በዚህም መሠረት 1ኛ ተከሳሽ አቶ ታደሰ ካሳ ስምንት ዓመት ከአምስት ወር ጽኑ እስራት እና 20 ሺህ ብር እንደተፈረደባቸው አማራ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። ፍርድ ቤቱ ግንቦት 11 በዋለው ችሎት በጥረት ኮርፖሬት የአክሲዮን ሽያጭ ዙሪያ ክስ የተመሠረተባቸው በእነታደሰ ካሳ የክስ መዝገብ የሚገኙ ዘጠኝ ሰዎች ጉዳይ ተመልክቶ የነበረ ሲሆን፤ ሁለት ተከሳሾቸን በነፃ አሰናብቶ፤ ሰባት ተከሳሾችን ደግሞ ጥፋተኛ ብሎ ነበር። የአማራ ክልል ፍርድ ቤት ከዚህ ቀደም ባለስልጣናቱ አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ በጥረት ኮርፖሬሽንን ከቦርድ ሰብሳቢነትና ከዋና ሥራ አስፈፃሚነት ሚናቸው ጋር በተያያዘ ወንጀል ፈፅመዋል በሚል ጥር 2011 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ መቆየቱ ይታወሳል። በዚሁ ክስ በ1ኛ እና 2ኛ የክስ መዝገቦች ላይ ጥፋተኛ በተባሉት በ1ኛ ተከሳሽ አቶ በረከት ስምኦን ላይ የስድስት ዓመት እስር እና የ10 ሺህ ብር ቅጣት ወስኗል። ከዚህም በተጨማሪ በ1ኛ፣ 2ኛ እና 4ኛ የክስ መዝገቦች ላይ ጥፋተኛ በተባሉት 2ኛ ተከሳሽ አቶ ታደሰ ካሳ ላይ ደግሞ የስምንት ዓመት የእስር ቅጣትና የ15 ሺህ ብር የቅጣት ውሳኔ መበየኑን የሚታወስ ነው።
news-44857829
https://www.bbc.com/amharic/news-44857829
ማንዴላን ውትድርና ያሰለጠኑት ኢትዮጵያዊ
ጊዜው በፈረንጆቹ ሐምሌ 1962፤ ኮሎኔል ፍቃዱ ዋኬኔ ለአንድ ከደቡብ አፍሪቃ ለመጣለ ግለሰብ ወታደራዊ ሥልጠና በመስጠት ላይ ናቸው። ድምፅ ሳያሰሙ ጠላት ቀጣና በመግባት ፈንጂ መቅበር የሥልጠናው አካል ነበር።
ሰውየው 'ኡምኮንቶ ዌ ሲዝዌ' በመባል የሚታወቀው የደቡብ አፍሪካ ሽምቅ ተዋጊ ቡድን የበላይ አዛዥ ነው። ዊኒ ማንዴላ -አልበገር ባይ እናት ቡድኑ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የሚገኙ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሰጪ ጣብያዎች ላይ የፍንዳታ ጥቃት ፈፀመ፤ ይህን ተከትሎም የጊዜው የአፓርታደይድ አገዛዝ አዛዡን ያፈላልግ ያዘ። ሰውየው ግን ማንም ሳያይ ሳይሰማ ኢትዮጵያ ገብተው ኖሯል። አልፎም በአፍሪካ ሃገራት እየተዘዋወሩ ለተዋጊ ቡድኑ አርዳታ ማሰባሰብን ሥራዬ ብለው ተያይዘውት ነበር። ኔልሰን ሮሊህላህላ ማንዴላ፤ ኢትዮጵያ የተገኙበት ዋነኛ ምክንያት ራሳቸውን በወታደራዊ ስብዕና ለማነፅ ነበር። 6 ሚሊዮን ብር፡ በማንዴላ እሥር ቤት ለማደር አዝናኙ ሰው «ማንዴላ በጣም ጠንካራና ምንም የማይበግራቸው ሰው ነበሩ፤ አመራር ሲከተሉ ደግሞ ለጉድ ነው» ይላሉ ኮሎኔል ፍቃዱ። «በዚያ ላይ ደግሞ እጅግ ተወዳጅ ሰው ናቸው።» ኮሎኔል ፍቃዱ በወቅቱ ኮልፌ የሚገኘው አድማ በታኝ ባታሊዮን ልዩ ኃይል አባል ነበሩ። «ደስተኛና ለመማር ዝግጁ የሆነ አንድ ደቡብ አፍሪካዊ ሲመጣ አስታውሳለሁ፤ በዚያ ላይ እጅግ ትሁትና ታጋሽ ነበሩ» ሲሉ ማንዴላን ይዘክራሉ። የኮሎኔል ፍቃዱ ድርሻ ለማንዴላ ፈንጂ ማፈንዳት እንዲሁም ድንገተኛ አደጋ መጣል የመሳሰሉ ወታደራዊ ሥልጠናዎች መስጠት ነበር። «አካለ-ጠንካራ ሰው ነበሩ፤ አንዳንድ ጊዜ እንደውም ከአቅማቸው በላይ የሆነ ነገር ሲያደርጉ አስተውላለሁ። ይህን ስመለከት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እመክራቸው ነበር፤ አንዳንድ ጊዜም አግዳቸው ነበር።» የኮሎኔል ፍቃዱ አዛዥ የነበሩት ጄኔራል ታደሰ ብሩ ነበሩ ማንዴላን የማሰልጠኑን ግዳጅ ለኮሎኔሉ የሰጡት። በፈረንጆቹ 1960 ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ላይ የተቃጣውን መፈንቅለ-መንግሥት ካከሸፉ ወታደራዊ መኮንኖች መካከል አንዱ የሆኑት ጀኔራል ታደሰ ብሩ ኋላ ላይ በደርግ እንደተገደሉ ይታወሳል። ትዕዛዙ የደረሳቸው ኮሎኔል ፍቃዱ መጀመሪያ አካባቢ ደቡብ አፍሪካዊው ሰው ብዙም ሊገባቸው አልቻለም ነበር። ዊኒ ማንዴላ ሲታወሱ «አንድ ከደቡብ አፍሪካ የመጣ እንግዳ እንዳለና ከእኛ ጋር የተወሰነ ጊዜ እንደሚያሳልፍ ብቻ ነበር እኔ የማውቀው። ሁሉም ነገር ምስጢር ነበር፤ ማንም እንዲያውቀው አልተፈለገም» ይላሉ ኮሎኔሉ። እህጉረ አፍሪቃ ከቅኝ አገዛዝ በፍጥነት እንድትላቀቅ ፅኑ ፍላጎት የነበራቸው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ናቸው ማንዴላ ኢትዮጵያ እንዲገቡ የፈቀዱት። በጊዜው ደግሞ ኢትዮጵያ አፍሪካ ውስጥ አለ የሚባል ጠንካራ ወታደራዊ ኃይል ነበራት፤ ጦርነት የተነሰባቸው የአህጉሪቱ ክፍሎችን ለማረጋጋት ማን እንደ ኢትዮጵያ ኃይል የተባለለት። ንጉሡ በይፋ «ነፃነት ለማምጣት የሚታገሉ የአፍሪካ ወንድሞቻችን ኢትዮጵያ መጥተው ወታደራዊ ሥልጠና መውሰድ ይችላሉ» ሲሉ አውጀዋል። ቀጣዩን የኤኤንሲ መሪ ለመምረጥ ሩጫ መሣሪያ መታጠቅ፣ ወታደራዊ ሳይንስ እና ጦር መምራት የመሳሰሉ ሥልጠናዎች የማንዴላ መዝገብ ውስጥ ተካተዋል። ከከተማዋ ወጣ ብለውም የበርካታ ሰዓታት የእግር ጉዞን የመሳሰሉ ፈታኝ ሥልጠናዎችን መውሰድ ተያያዙ። ማንዴላ 'ሎንግ ዎክ ቱ ፈሪደም' ወይም በግርድፍ ትርጉሙ 'ወደ ነፃነት የተደረገ ረዥም ጉዞ' ብለው በሰየሙት መፅሐፋቸው ላይ «ረዥም ጉዞ ማድረግ በጣም እወድ ነበር፤ መልክዐ-ምድሩ ግሩም ነበር። ሰዎች ከፍርግርግ እንጨት በተሰራ ቤት ያለ ሕይወት ሲመሩ ሳይ፤ ቀለል ያለ ምግብ ቤት ውስጥ በተጠመቀ ቢራ ሲያወራርዱ ስመለከት፤ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የማውቀውን ሕይወት ያስታውሰኛል» ሲሉ ጠቅሰዋል። ማንዴላ ወደሃገራቸው ሲመለሱ ድያ ከጀኔራል ታደሰ ብሩ በርካታ የጦር መሣሪያ ሽልማት ተደርጎላቸዋል። ንግግር የሚያበዛ ማንዴላ ኢትዮጵያ ውስጥ የነበራቸው ጊዜ በድብቅ እንዲያዝ የተፈለገ ቢሆንም እሳቸው ግን ዓይን በዛባቸው። በዚያ ላይ አብረዋቸው ሥልጠና ከሚወስዱ ሰዎች ረዘም እና ገዘፍ ያሉ መሆናቸው ለዓይን አጋለጣቸው። ተስፋዬ አበበ (ፋዘር) በጊዜው የኮልፌው ባታሊዮን ሙዚቃ እና ድራማ ክፍል ኃላፊ ነበሩ። «ትዝ ይለኛል፤ ግቢው ውስጥ የነበረውን ሰፊ ሜዳ ሮጠው አይጠግቡም ነበር፤ ይዘላሉ፣ ቁጭ ብድግ ይሰራሉ፤ በዚያ ላይ አንድ ቀን እንኳን ሳይሰሩ አይውሉም» ሲሉ ማንዴላን ያስታውሳሉ። አንድ ቀን ታዲያ ማንዴላ ከአሠልጣኛቸው ጋር ሆነው ማሰልጠናው ውስጥ ባለ ምግብ ቤት ውስጥ ሲመገቡ ከአቶ ተስፋዬ ጋር ይገናኛሉ። «በደህንነት ከመጠበቃቸው አንፃር፤ ከእሳቸው ጋር ተገናኝቶ ማውራት የማይታሰብ ነበር።» ኤ ኤን ሲ ዙማ ከስልጣን እንዲወርዱ ወሰነ የዚያን ቀን ግን አጋጣሚውን ያገኙት ፋዘር ከማንዴላ ጋር ወግ ጠረቁ፤ ስለ አፓርታይድ አወሯቸው። ፋዘር ማንዴላን «በጣም ሰው መቅረብ የሚወዱና ወሬ የሚያበዙ» ሲሉ ይገልጿቸዋል። ከዚያ በኋላ ታድያ የፋዘር ቡድን በመኮንኖች ክለብ የሙዚቃ ትርዒት በሚያቀርብበት ወቅት ማንዴላ መገኘት ጀመሩ። «ትርዒቱን በጣም ይዝናኑበት ነበር፤ ለእርሳቸው ስናዜምላቸው ደግሞ ይበልጥ ደስ ይላቸው ነበር።» ማንዴላ ኢትዮጵያ አንዲቆዩ የታሰበው ለስድስት ወራት ቢሆንም ፓርቲያቸው የአፍሪካዊያን ብሔራዊ ኮንግረስ (ኤኤንሲ) ከሁለት ሳምንታት ቆይታ በኋላ እንዲመለሱ ወሰነ። ማንዴላ ወደሃገራቸው ሲመለሱ ታድያ ከጀኔራል ታደሰ ብሩ በርካታ የጦር መሣሪያ ሽልማት ተደረገላቸው። በፈረንጆቹ ነሐሴ 5/1962 ማንዴላ በሕገ-ወጥ ወጥ መንገድ ከሃገር በመውጣት በሚል ለእሥር ተዳረጉ። ማንዴላ ከደቡብ አፍሪቃ ወጥተው ለስደስት ወራት ቆይተው ነበር የተመለሱት፤ ሁለቱን ሳምንታት ያሳለፉት ደግሞ ኮልፌ፤ አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ።
51813027
https://www.bbc.com/amharic/51813027
ዚምባብዌ ትምህርት የሚያቋርጡ ተማሪዎች ወላጆችን ልታስር ነው
የዚምባብዌ መንግሥት ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት የማይልኩ እና ልጆቻቸው ትምህርት የሚያቋርጡ ተማሪዎች ወላጆችን ሁለት ዓመት በሚደርስ እስራት ሊቀጣ እንደሆነ አስታወቀ።
መንግሥት እስከ 16 ዓመት እድሜ ድረስ ትምህርት ግዴታ እንዲሆን ያደረገው በአገሪቱ ትምሀርት የሚያቋርጡ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ስለመጣ ነው። መረጃዎች እንደሚያሳዩት በአንዳንድ የአገሪቱ ክፍሎች 20 በመቶ የሚሆኑ ህፃናት ወደ ትምህርት ቤት አይሄዱም። አሁን መንግሥት ያወጣው ህግ ተማሪዎች የትምህርት ክፍያ ባለመክፈላቸው ወይም እርጉዝ በመሆናቸው ማባረርንም ጭምር እንደ ጥፋት ቆጥሮ ይቀጣል። • "ትልቅ ዋጋ ተከፍሎበት ዋጋ ያላገኘሁበት ቢኖር ትምህርት ነው" • በሶማሌ ክልል የነዳጅ ማውጫ አካባቢ ያልተለመደ የጤና ችግር እያጋጠመ ነው ተባለ • የዓለም የሴቶች ቀንን ማን ጀመረው? እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ባለፈው ዓመት 60 በመቶ የሚሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች ክፍያ አልፈፀማችሁም በሚል ከትምህርት ቤት ተባርረው ነበር። ባለፈው ዓመት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የቀድሞ የአገሪቱ ፕሬዘዳንት ሮበርት ሙጋቤ አገሪቷ ነፃነቷን ማግኘቷን ተከትሎ በዘረጉት የትምሀርት ስርዓት አድናቆትን አግኝተው ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ የህዝብ ትምህርት ቤቶችን በመክፈት ሙጋቤ የዘረጉት የትምህርት ስርዓት ለጥቁር ዚምባብዌያን ትልቅ የትምህርት እድል ፈጥሮ ነበር። በዚህም ዚምባብዌ ከአፍሪካ ከፍተኛ የትምህርት ሽፋን ያላት አገር ሆና ነበር። ነገር ግን ነፃ ትምህርት በ1990ዎቹ እንዲቆም የተደረገ ሲሆን ከዚህ ቀጥሎ በነበሩት ዐሰርታት የአገሪቱ የትምህርት ስርዓት መፈራረስ ጀመረ። መንግሥት ትምህርት የሚያቋርጡ ተማሪዎች ወላጆችን ለመቅጣት የተገደደው በዚህ መልኩ የወደቀውን የአገሪቱ ትምህርት ለመታደግ በማሰብ ነው። ጥፋተኛ ሆነው የሚገኙ ወላጆች የሁለት ዓመት እስር ወይም የ260 ዶላር የገንዘብ ቅጣት ይጠብቃቸዋል። መንግሥት ራሱ ቃል የገባውን የነፃ የትምህርት እድል ማሟላት ሲያቅተው የዚህ ዓይነት ህግ ማውጣቱ ተገቢ እንዳልሆነ የሚገልፁ አሉ። እርግዝና፣ ያለ እድሜ ጋብቻ፣ የትምሀርት ቤቶች ተደራሽ አለመሆን፣ የትምህርት ፍላጎት አለመኖር በአገሪቱ እየታየ ላለው የትምሀርት ማቋረጥ በምክንያትነት የሚቀመጡ ናቸው።
49013422
https://www.bbc.com/amharic/49013422
በአዲስ አበባ 3.6 ሚሊየን ብር የሚያወጡ ትራንስፎርመሮች የሰረቁ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታወቀ
የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት ባለፈው አንድ ወር ገደማ ሰባት ትራንስፎርመሮች እንደተሰረቁበት አስታወቀ። ትራንስፎርመሮቹ በተደራጀ ሁኔታ በቀን ጭምር መሰረቃቸውን የአገልግሎቱ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታዬ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በየካ ክፍለ ከተማ የካ አባዶ ኮንዶሚኒየም እየተባለ በሚታወቀው አካባቢ ወደ ዘጠኝ ትራንስፎርመሮች መሰረቃቸውን የተናገሩት ደግሞ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካው ፋንታ ናቸው። በስርቆት ወንጀሉ ላይ የተሰማሩት አንዱ ሹፌር፣ ስልክ እንጨቱ ላይ ወጥቶ የሚፈታና ሌላ ይረዳ የነበረ ግለሰብ በአጠቃላይ ሦስት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮማንደር ፋሲካው ገልጠዋል። • 'ከሕግ ውጪ' የተዋሃዱት አምስቱ ክልሎች ኮማንደር ፋሲካው እንዳሉት በቁጥጥር ስር ከዋሉት ግለሰቦች መካከል አንዱ ለአስራ ሁለት ዓመት በመብራት ኃይል ውስጥ በቀን ሰራተኝነት ይሰራ የነበረ መሆኑ መታወቁን ተናግረዋል። የአገልግሎቱ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተርም ወንጀሉ በባለሙያ ታግዞ ለመፈፀሙ ምንም ጥርጣሬ እንደሌላቸው ተናግረው፤ በቁጥጥር ስር ከዋሉት ግለሰቦች መካከል ከዚህ ቀደም የድርጅቱ ሰራተኛ የነበረ እንደሚገኝበት አረጋግጠዋል። አክለውም ግለሰቡ ከአስራ አምስት ቀን በፊት ሽቦ ሲሰርቅ ተይዞ በዋስትና መለቀቁን ገልጠዋል። ትራንስፎርመሮቹ የተሰረቁባቸው አካባቢዎችንም ሲዘረዝሩ ወረገኑ አካባቢ፣ ገርጂ ማሪያም ቅጥር ግቢ ውስጥና መሪ ጎሮ ሚካኤል አካባቢ መሆኑን ጠቅሰው መብራት በጠፋበት ባለፈው አንድ ወር ብቻ በምሥራቅ አዲስ አበባ ላይ ወንጀሉ መፈፀሙን ተናግረዋል። • በኢትዮጵያ ካምፕ ውስጥ ባለ2 ፎቅ መኖሪያ የገነባው ስደተኛ በቁጥጥር ስር ከዋሉት ተጠርጣሪዎች መካከል አንዱ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ወንጀል ተከስሶ ጉዳዮ በፍርድ ቤት እየታየ የነበረና በዚህ መካከል ከመስሪያ ቤቱ የተባረረ ግለሰብ እንደሆነ የተናገሩት ኮማንደር ፋሲካው ግለሰቡ፣ ቀሪዎቹን ተጠርጣሪዎች ለተመሳሳይ ወንጀል በማነሳሳትና በማስተባበር ወንጀሉ ውስጥ መሳተፉን ገልጠዋል። ተጠርጣሪዎቹ ምርመራ ላይ ናቸው ያሉት ኮማንደር በሕብረተሰቡ ጥቆማና በፖሊስ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውንም አስረድተዋል። ለስርቆቱ ትልቅ ክሬን በመከራየት ተጠቅመዋል ያሉት ደግሞ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ ትራንስፎርመሩን እንዳለ አንስተው ሳይሆን የሚወስዱት ፈትተው ከውስጡ ያሉ ሽቦዎች፣ ጥቅሎችንና ኮፐሮችን እንደሆነ አስረድተዋል። ተጨማሪ ተጠርጣሪዎች እነማን ናቸው የሚለው በምርመራው ሂደት የሚታይ ነው የሚሆነው ያሉት ኮማንደር ፋሲካው ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ውስጥ አልፎ አልፎ ተመሳሳይ ስርቆት ይከሰት እንደነበር አስታውሰዋል። • የማትተነፍሰው ከተማ: አዲስ አበባ • የታገዱት ሞተረኞች እሮሮ እያሰሙ ነው ወንጀሉ የሚፈፀመው በቀን የመብራት ኃይል ሰራተኛ የደንብ ልብስ ለብሰው መሆኑን የተናገሩት ኮማንደር ፋሲካው ማህበረሰቡ በነበረው ጥርጣሬ ለፖሊስ ጥቆማ መስጠታቸውን ተናግረዋል። ሰርቀው ምን ያደርጋሉ? ለማን ይሻጣሉ? የሚለው ላይ ምርመራ እያደረጉ መሆኑን ገልጠዋል። የአንድ ትራንስፎርመር አማካይ ዋጋው 400ሺህ የኢትዮጵያ ብር ነው ያሉት የኮሙኑኬሽን ዳይሬክተሩ ውድ የሚባለው 2.5 ሚሊዮን የሚያወጣ ትልቅ ትራንስፎርመር እንዳለም ተናግረዋል።
51087786
https://www.bbc.com/amharic/51087786
የአውስትራሊያ ነባር ብሔረሰቦች ጫካ እንዲቃጠል የሚፈልጉት ለምን ይሆን?
ለሺህ ዘመናት የአውስትራሊያ ነባር ብሔረሰቦች ጫካ በማቃጠል ይታወቃሉ።
አውስትራሊያ በአውሮጳውያን ከመወረሯ በፊት የነበረ ባህል ነው፤ 'ባሕላዊ ቃጠሎ' ሲሉ ይጠሩታል። ነገር ግን በዕቅድ ነው የሚቃጠለው፤ የእሣቱም ቁመት ከጉልበት የሚበልጥ አይደለም። የተመረጡ ሥፍራዎችን ይዞ የሚቀጣጠል ነው። አሁን አውስትራሊያን በጭንቀት ሰቅዞ የያዛት ሰደድ እሣት አምና ሲጀምር ይህን ባሕላዊ መንገድ መጠቀም አስፈላጊ ነበር የሚሉ ድምፆች ከየቦታው መሰማት ጀመሩ። ነገር ግን ሃሳቡ መደመጥ የጀመረው ዘግይቶ ነበር። ሻኖን ፎስተር የተሰኙ የአቦርጅናሎችን ባሕል በማጥት የሚታወቁ ሴት «አጫጭር ዛፎች [ቡሽ] መቃጠል አለባቸው» ይላሉ። «ይህ መንገድ 'ሃገር ሳትቃጠል በቅጠል' ለመከላከል የሚደረግ ሙከራ ነው። እኛ አቦርጅናሎች በዚህ እንታወቃለን። ከሃገራችን ስለምንወስደው ብቻ ሳይሆን ለሃገራችን ስለምናበረክተውም እናስባለን።» አቦርጅናሎችና ሃገር በአቦርጅናሎች ዘንድ ሃገር እንደ ሰው ትመሰላለች። «መሬት እናታችን ናት። በሕይወት ታኖረናለች» ይላሉ አጥኚዋ ሻኖን። ቅድመ ቃጠሎ ደግሞ አደጋ ከመምጣቱ በፊት በአቦርጅናሎች የሚከወን መከላከያ መንገድ ነው። 'ዘመናዊ ነን' የሚሉ ሰዎች አደጋ ከመከሰቱ በፊት የሚያከውኑት ተግባር እየሠራ አይመስለኝም ይላሉ ምሁሯ። ሻኖን ፎስተር ጥበብን ከአያቶቻቸውን እንደቀዱ ይናገራሉ «ዘመናዊው መንገድ ሁሉን ነገር እያጠፋ ነው። በብልሃት እየተሠራ አይመስለኝም። ነባር ብሔረሰቦች ጫካውን የሚያውቁትን ያህል ከተሜዎች ያወቁት አልመሰለኝም።» «ንበረት አይተነፈስም፣ አይበላም፣ አይጠጣም። ያለ ሃገር የሰው ልጅ ከንቱ ነው።» ባሕላዊ ቃጠሎ የጫካውን ቅኝት ተከትሎ የሚደረግ ነው። በቃጠሎው ወቅት ከጫካው የሚሸሹ ተሳቢና ባለ አራት እግር እንስሳት የአቦርጅናሎች እራት ይሆናሉ። ቃጠሎው የሚፈጥረው አመድ ፖታሺዬም ወደ ተሰኘው ኬሚካል ተቀይሮ ለመሬቱ እንደ ማዳበሪያ ሆኖ እንደሚያገለግል የአካባቢው ሰዎች ይናገራሉ። ባሕላዊ ቃጠሎ ያልተካሄደለት ጫካ ማለት ፀጉሩ እንዳልተከረከመ ሕፃን ልጅ ማለት ነው' እንክብካቤ ይጠይቃል ይላሉ ሻኖን። አክለውም ታላላቆቿ ይህ ቀን ሊመጣ እንደሚችል ጥንቃቄ ቢሰጡም የሰማቸው የለም ይላሉ። አውስትራሊያ የተሰባጠረ ምድራዊ አቀማመጥ ያላት ሃገር ናት። ከቦታ ቦታ የተለያየ መልክ ያለው ምድር አላት። አንዳንድ ሥፍራዎች ባሕላዊውን የጫካ አያያዝ ከዘመናዊው ጋር አሳልጠው ይጠቀማሉ። ብዙዎች ግን ሃገር-በቀሉን መንገድ ለመጠቀም ዝግጁ አይመስሉም። «ሰሜናዊው የአውስትራሊያ ክፍል እንዴት አድርጎ ባሕላዊውን መንገድ እንደሚጠቀምበት ማየት ይቻላል። ደቡባዊው ክፍል ግን ወጣ ገባ ነው።» አውስትራሊያ ቅኝ ከተገዛችበት 1788 ጀምሮ ባሕላዊ ቃጠሎ እየጠፋ ቢመጣም አሁን አሁን እንደ አዲስ እያበበ ነው። እርግጥ ነው ባሕላዊው ቃጠሎ የራሱ የሆኑ ችግሮች አሉበት ብለው የሚያምኑ አሉ። ተግባራዊ መደረግ ያለበት ሁሉ ቦታ አይደለም ይላሉ። የአውስትራሊያ ሰደድ እሣት ከ10 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት ያቃጠለ ሲሆን 27 ሰዎችን ገድሏል፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዱር እንሳስትም ሰለባ ሆነዋል።
news-46381925
https://www.bbc.com/amharic/news-46381925
የዕፀ ፋርስ የገበያ እሽቅድምድም በሌሴቶ
ሌሶቶ በአለም ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ገበያ እያገኘ ያለውን ለመድኃኒትነት የሚያገለግለውን ዕፀ-ፋርስ ኢንዱስትሪ ለመቀላቀል እየጣረች ቢሆንም የቢቢሲው ቩማኒ ምክሂዜ በበኩሉ ግለሰቦች ህጋዊ ባልሆነ ንግድ ዕፀ ፋርስን ለመዝናኛነት እንደሚጠቀሙበት ዘግቧል።
ከነዚህም አምራቾች አንዷ ማምፖ ቱሎ ስትሆን ፤ የቢቢሲው ጋዜጠኛ በቦታው ላይ ሲደርስ የደረቀውን የዕፀ ፋርስ ቅጠሎች በእጇ እያፈሰች ቤቷ ወለል ላይ በተዘረጋው ትልቅ የላይነን ቦርሳ ውስጥ በማስገባት ላይ ነበረች። •ሳይንቲስቱ መንትዮች ኤች አይ ቪ እንዳይዛቸው ዘረ መላቸውን አስተካከለ •በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ወደ ፅዮን ውሰዱን ተማፅኖ •"ፓስፖርት መስጠት አልተከለከለም" የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች ተቋም ማፖቴንግ በሚባል መንደር ውስጥ ነዋሪነቷን ያደረገችው ማምፖ ለዘመናት ዕፀ ፋርስን ስታበቅል ነበር። ከመዲናዋ ማሴሩ በሰባ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው መሬቷ ሸለቋማ ሲሆን፤ ሀገሪቷ በምትታወቅበት ተራራም የተከበበ ነው። ይህ መንፈስን በሚሰርቀው አካባቢ ህጋዊ ባልሆነ መልኩ ዕፀ ፋርስ የሚበቅል ሲሆን ለአስርት አመታትም ለመዝናኛነት ይጠቀሙበታል። ቦታው በከፍተኛ ስፍራ መገኘቱ፣ ከመሬቱ ለምለምነት፣ በማዳበሪያ አለመበከሉ፤ የአካባቢውን አብቃዮች በዓለም ላይ የሚፈለግ ጥሩ ምርት እንዲያፍሱ አድርጓቸዋል። በተቃራኒው በመዲናዋ አካባቢ የተለያዩ ሰራተኞች ላብራቶሪ በሚመስል የአረንጓዴ ቤቶች ለመድኃኒትነት የሚያገለግለውን ዕፀ ፋርስን ለማብቀልና ከፍተኛ ገንዘብም ለማግኘት ኃገሪቷ እሽቅድምድም እያደረገች ነው። በባለፈው አመት ሌሴቶ ዕፀ ፋርስን ለመድኃኒትነት ለመጠቀም ህጋዊ በማድረግ የመጀመሪያዋ ቀዳሚ አፍሪካዊ አገር ብትሆንም ኢንዱስትሪ ገና በጅማሮ ላይ ነው። በትንሽ መሬት ዕፀ ፋርስን የሚያመርቱት ገበሬዎች ከመድኃኒት ዕፀ ፋርስ ጋር ሲወዳደር የቴክኖሎጂ አቅርቦትም ሆነ ንግዱ የሚያስፈልገው መነሻ ገንዘብ የላቸውም። የመድኃኒቱ ዕፀ ፋርስ በትልቅ ደረጃ የታሰበ ከመሆኑ አንፃር ጋር ሲወዳደር ያለውን ከፍተኛ የስራ እድል ለመፍጠርም ትግል ላይ ነው። ነገር ግን የአምስት ልጆች እናት የሆነችው ማምፖ ቱሎ ባላት ምርት ትተማመናለች። "የእለት ጉርሳችን የምናገኘው ዕፀ ፋርስን በመሸጥ ነው። ስራ ያለው ለተማሩ ሰዎች ነው እሱም እምብዛም ነው። ትምህርትም ስላልተማርን ኑሯችንን የምንደግፈው ዕፀ ፋርስን በመሸጥ ነው" በማለት ለቢቢሲ ተናግራለች። ምንም እንኳን ሌሴቶ ዕፀ ፋርስን ለመድኃኒትነት ለመጠቀም ህጋዊ ብታደርግም እንደነ ማምፖ ቱሎ ያሉት ግን አሁንም ምርታቸው ህገ ወጥ ነው።
news-55329582
https://www.bbc.com/amharic/news-55329582
ኮቪድ-19፡የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት በኮሮናቫይረስ ተያዙ
የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ፓሪስ የሚገኘው የፕሬዚዳንቱ ቢሮ አረጋግጧል።
የ42 አመቱ ፕሬዚዳንት የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ማሳያታቸውን ተከትሎ ምርመራ ማድረጋቸውንና ለሰባት ቀናትም ራሳቸውን ለይተው እንደሚቆዩ ፅህፈት ቤታቸው ኤሊዜ ቤተ መንግሥት በመግለጫው አሳውቋል። ፅህፈት ቤታቸው ፕሬዚዳንቱ አገሪቷን የመምራት ኃላፊነታቸውንም እንደሚቀጥሉበትና ራቅ ብለው ተግባራቸውንም እንደሚያከናውኑም አስታውቋል። ፕሬዚዳንቱ በቫይረሱ እንዴት እንደተያዙ ቢሯቸው እንደማያውቅ ገልፆ በቅርብ የተገናኟቸውንም ሰዎች ለመለየት ክትትል እያደረገ እንደሆነም አክሎ ገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር ጂን ካስቴክስም ከፕሬዚዳንቱ ጋር ቅርበት ነበራቸው በሚልም ራሳቸውን ለይተው እንደሚቆዩም ተገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአገሪቱን የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት ፖሊሲ ለምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት እንዲያስተዋውቁ እቅድ ተይዞ የነበረ ቢሆንም በምትኩ የጤና ሚኒስትሩ ኦሊቪየር ቬራን ይናገራሉ ተብሏል። ሆኖም ጠቅላይ ሚኒስትሩ እስካሁን ድረስ ምንም ምልክት እንዳላሳዩም ቢሯቸው ገልጿል። የስፔኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝም ከፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ጋር በዚህ ሳምንት ሰኞ ምሳ በልተው የነበረ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ራሳቸውን ለይተው እንደሚቆዩም ተናግረዋል ። በዚሁ የምሳ ስብሰባ ወቅት የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቻርልስ ሚቼልና ዋና ፀሃጊ አንጄል ጉሪያ ተገኝተዋል ተብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮም እመረመራለሁ ብለዋል። የማክሮን ባለቤት ብሪጄት በለይቶ ማቆያም ቢሆኑም ምልክት አልታየባቸውም። ከሳቸው በተጨማሪ የፓርላማው ቃለ አቀባይ ሪቻርድ ፌራንድም በለይቶ ማቆያ ናቸው። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ በርካታ የአለም መሪዎች በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሲሆን የማክሮንን ጨምሮ ከዚህ ቀደምም ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕና የዩኬው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን መያዛቸው ይታወሳል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሁለተኛ ዙር እያገረሸባት ያለችው ፈረንሳይ ከሰሞኑም የሰዓት እላፊ አዋጅ ጥላለች። ወረርሽኙ ከተከሰባት እለት ጀምሮ 2 ሚሊዮን ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 59 ሺህ 400 ዜጎቿን በኮሮናቫይረስ ማጣቷን ከጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።
news-56115859
https://www.bbc.com/amharic/news-56115859
ታዋቂው የግሪክ ተዋናይ ታዳጊ በመድፈር ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋለ
.ታዋቂው የግሪክ ተዋናይና ዳይሬክተር ዲሚትሪስ ሊግናዲስ ሁለት ታዳጊ ልጆችን ደፍሯል በሚል ክስ በቁጥጥር ስር ዋለ።
የ56 አመቱ ስመ ጥር ተዋናይ የ14 አመት ወንድ ደፍሯል የተባለው በአውሮፓውያኑ 2010 ሲሆን ሁለተኛውን ክስ አስመልክቶ ዝርዝሩ ለህዝብ ይፋ አልተደረገም። የግሪክ ብሔራዊ ቲያትር የቀድሞ ዳይሬክተር ዲሚትሪስ የተጠረጠረባቸውን የመድፈር ወንጀሎች አልፈፀምኩም እንዳለም ጠበቃው አሳውቀዋል። ለጥያቄ ተፈልጎ በፈቃደኝነት አቴንስ ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ አምርቶ የነበረው ተዋናዩ ከዚያ በኋላ በትናትናው እለት በቁጥጥር ስር መዋሉን ጠበቃው ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት በእስር ላይ የሚገኘው ተዋናዩ በቅርቡም ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ኢካቲሜሪኒ የተባለው ጋዜጣ ዘግቧል። ተዋናዩ ከብሄራዊ ቲያትር ዳይሬክተርነቱ ስልጣን ለቅቄያለሁ ያለው ባለፈው ወር ሲሆን ይህም በስራ ቦታው ላይ "አሉባልታዎች እየተነዙ ፤ እውነታ የሌላቸው መረጃዎች እየወጡ ስለሆነ ስራዬን ሊያሰራኝ አልቻለም" የሚል ምክንያት አቅርቦ ነበር። ከሰሞኑ ስመ ጥር ግሪካውያን ከወሲባዊ ጥቃት ጋር ተያይዞ ስማቸው እየተጠራ ሲሆን የቀድሞ የግሪክ ኦሎምፒክ አሸናፊ ሶፊያ ባካቶሩ የሄሊኒክ ሴይሊንግ ፌዴሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ጥቃት አድርሶብኛል ስትል አጋልጣለች። አትሌቷ የግለሰቡን ማንነት ባትጠቅስም ሁኔታው በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል፤ በርካቶችም ጉዳዩን ወደ ማህበራዊ ሚዲያ ወስደውታል። በባለፉት አመታት በአለም ላይ ወሲባዊ ጥቃትን አስመልክቶ በማህበራዊ ድረ ገፆች ሚቱ የሚለው ዘመቻ የተቀጣጠለ ሲሆን በግሪክም ይህ ሁኔታ መነሻ ሆኗል ተብሏል።
news-53044857
https://www.bbc.com/amharic/news-53044857
ፀሐይን ተጠግታ የምታልፈው መሣሪያ በሳይንቲስቶች ዘንድ ጉጉትን ፈጥራለች
የአውሮፓ ሥርዓተ ፀሐይ ጥናት ማዕከል (ሶሎ) ወደ ህዋ የላካት አነስተኛ የምርምር መሣሪያ ዛሬ ሰኞ ፀሐይን በቅርብ ርቀት ተጠግታ ታልፋለች ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡
ይቺ የምርመራ አንቴና ፀሐይን በቅርብ ርቀት ተጠግታ አለፈች የሚባለው 77 ሚሊዮን ኪሎ ሜትር ከፀሐይ ርቃ መሾር ስትችል ነው። መድር በምህዋሯ ላይ ፀሐይን እየዞረች ያለችው በአማካይ 149 ሚሊዮን ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሆና ነው፡፡ የዚህች አንቴና መሰል መሣሪያ ዓላማ የከዋክብትን ባህሪ ማጥናት ሲሆን፤ በተለይ ከዋክብት ከፀሐይ ጋር ያላቸውን መተስተጋብር ለመተንተን የሚያስችል መረጃ በመቃረም ወደ ምድር ታቀብላለች ተብሏል፡፡ በቬኑስና ሜርኩሪ መካከል ባለ ምህዋር ትሾራለች የተባለችው ይቺ መሣሪያ ወደ ህዋ የመጠቀችው ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ ነበር፡፡ ሶሎ የሚል ስም ያላት ይቺ መሣሪያ በጊዜ ሂደት ወደ ፀሐይ እየተጠጋች በመሄድ ከፀሐይ ጋር የሚኖራት ርቀት 43 ሚሊዮን ኪሎ ሜትር ብቻ የሚሆንበት አጋጣሚ ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በሥርዓተ ፀሐይ ውስጥ በዚህን ያህል ወደ ሥርዓተ ፀሐይ ጠልቆ ለመግባት ሶሎ አምስተኛዋ ናት፡፡ ከዚህ ቀደም ማሪነር 10፣ ሄሊዮስ 1 እና 2፣ ሜሴንጀር እና የሜሪካኑ ፓርከር ሶላር ፕሮብ ፀሐይን በመጠጋት ባህሪዋን ለማጥናት ሞክረዋል፡፡ ሶሎ የአውሮፓ የሥርዓተ ፀሐይ ኤጀንሲ ንብረት ስትሆን የተገጣጠመችውም በዩናይትድ ኪንግደም የኤሮስፔስ ኩባንያ በሆነው ኤርበስ ነው፡፡ ሶሎ ከመጠቀችበት ጊዜ ጀምሮ ባለፉት አራት ወራት ጠቅላላ አሰሳና ራሷንና የተገጠሙላት መሣሪያዎች ምን ያህል ጤናማ እንደሆኑ በመፈተሸ ላይ ቆይታለች፡፡ እንደዚህ ዓይነት ወደ ህዋ የሚመጥቁ መሣሪያዎች ወደፊት መሬታችን ምን ዓይነት የአየር ንብረት ይኖራታል፤ የፀሐይና ሌሎች በአካባቢው የሚገኙ ከዋክብት መስተጋብር ምንድነው ለሚለው እጅግ ወሳኝ ጥያቄዎች መረጃን ያቀብላሉ፡፡
news-46068742
https://www.bbc.com/amharic/news-46068742
ነዳጅ እንዳለ የሚያመላክት ጥናትን ተከትሎ ዚምባብዌ ነዳጅ ቁፋሮን ልትጀምር ነው
የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ በሰሜኑ የሀገሪቷ ክፍል በኩል የተፈጥሮ ዘይትና የጋዝ ክምችት እንዳለ ተናግረዋል።
የአውስትራሊያው የማዕድን ኩባንያ ኢንቪክተስ ኢነርጂ ከዚምባብዌ መንግሥት ጋር በጥምረት በመሆን የቁፋሮ ስራ አዋጭነትን በመመርመር ላይ ላይ ናቸው። ይህንን አስመልክቶ ፕሬዚዳንቱ እንደተናገሩት ኢንቪክተስ የተባለው ኩባንያ ሙዛራባኒ በሚባለው አካባቢ በዚህ ሁለት ዓመት ውስጥ ቁፋሮ ይጀምራል። ዚምባብዌ በአስር ዓመታት ውስጥ አጋጥሟት የማያውቅ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ተዘፍቃለች። •አዲሷ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ማን ናቸው? •የሴቶች መብት ታጋይዋ ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ማን ናቸው? •"ሌሎች ሴቶች ላይ የአሲድ ጥቃት ሳይ ይረብሸኛል፤ ህመሜን ያስታውሰኛል" ካሚላት መህዲ በዚምባብዌ የነዳጅ እጥረት በተደጋጋሚ የሚፈጠር ችግር ሲሆን መብራት መቆራረጥም ያጋጥማል። "በአካባቢያችን ኢንቪክተስ የተፈጥሮ ዘይትና የጋዝ ክምችት መኖሩን ነግሮን ነበር፤ ምክሮችንም ለግሶናል" በማለት ምናንጋግዋ ተናግረዋል። ጨምረውም " ውጤቱም ኢንቪክተስ እንደነገረን ሆኖ ለአገራችን የሚያስደስት ዜና ነው" ብለዋል። የማዕድን ሚኒስትሩ ዊንስተን ቺታንዶ በበኩላቸው ነዳጅ የሚወጣበት ጉድጓድ ከመዲናዋ ሐራሬ በ240 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ ለቁፋሮውም ወደ 20 ሚሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚገመትም ሮይተርስ ዘግቧል። ዚምባብዌ በማዕድን የበለፀገች ሀገር ብትሆንም እስካሁን የነዳጅ ምርት አልነበራትም።
news-51367631
https://www.bbc.com/amharic/news-51367631
ካሜሮናዊው ተማሪ በኮሮናቫይረስ በመጠቃት የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሆነ
የሃያ አንድ ዓመቱ ካሜሮናዊው ተማሪ በኮሮናቫይረስ በመያዝ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሆኗል።
ትምህርቱን በቻይና ያንግትዜ ዩኒቨርስቲ ይከታተል የነበረው ተማሪ ዉሃን ከተማ ለጉብኝት በሄደበት ወቅት በበሽታው መያዙን ከዩኒቨርስቲው የወጣው መግለጫ ያስረዳል። ከሁለት ሳምንት በፊት ወደሚኖርበት ከተማ ጂንግዙ ከተመለሰም በኋላ በበሽታው መያዙ ታውቋል። •ቻይና አሜሪካን ኮሮናቫይረስን አስመልክቶ ፍራቻ እየነዛች ነው ስትል ወነጀለች •በኮሮናቫይረስ ከተጠረጠሩ አራት አዲስ ሰዎች አንዱ በአክሱም እንደሚገኝ ተገለፀ የቢቢሲ ዘጋቢ ኪልያን ኒጋላ ከካሜሮኗ መዲና ያውንዴ እንደዘገበው ይህ ዜና መሰማቱ በካሜሮናውያን ዘንድ ከፍተኛ ስጋትን ፈጥሯል። 300 የሚሆኑ ካሜሮናውያን በዉሃን የሚገኙ ሲሆን ወደየትም መንቀሳቀስም ስለማይቻል የውሃ፣ ምግብና ሌሎችም ቁሳቁሶች እጥረትም በማጋጠሙ ችግር ላይ ናቸው ተብሏል። ዩኒቨርስቲው ለተማሪው ቤተሰቦች እንዲሁም ለኤምባሲው ማሳወቁንና ህክምናም እየተከታተለ ነው ተብሏል። በአሁኑ ሰዓት የሰውነት ሙቀቱ እየተስካከለ እንደሆነ፣ የምግብ ፍላጎቱም መመለሱን እንዲሁም በተረጋጋ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝም ዩኒቨርስቲው በመግለጫው አትቷል። •ከቻይና ውጪ የመጀመሪያው ግለሰብ በኮሮና ቫይረስ ሞተ •ቻይና ለኮሮና ቫይረስ ህሙማን በስምንት ቀናት ሆስፒታል ገነባች በሺዎች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ተማሪዎች በቻይና የሚገኙ ሲሆን፤ ኮሮናቫይረስ በከፍተኛ ሁኔታ መዛመቱን ተከትሎ በርካታ መንግሥታት ከቻይና በተለይም ከዉሃን እንዲያወጧቸው ቢማፀኑም ምላሽ አላገኙም። ባለፈው ሳምንት በዉሃን የሚገኙ ካሜሮናውያን ለፕሬዚዳንታቸው ፓውል ቢያ ቤጂንግ የሚገኘው ኤምባሲ ምንም እርዳታ እያደረገላቸው እንዳልሆነ እንዲሁም መሰረታዊ የሸቀጥ ፍጆታዎችም እጥረት አለ በማለት ደብዳቤ ፅፈው ነበር።
news-46548932
https://www.bbc.com/amharic/news-46548932
ታንዛኒያ የዓለም ቅርስ የተባለ ቦታ ላይ ግድብ ልትገነባ ነው
የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ በአፍሪካ ድንቅ ከሚባሉት ጥብቅ የእንስሳት ማቆያ አንዱ በሆነ አካባቢ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድብ ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት መፈራረማቸው ብዙ ትችት እያስነሳ ነው።
ሶስት ቢሊዮን ዶላር የሚፈጀው ሃይል ማመንጫው ግድብ የሚገነባው ሴለስ በተባለው ጥብቅ ማቆያ ውስጥ በሚገኘው ሩፊጂ ወንዝ ላይ ሲሆን፤ አካባቢው ደግሞ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ሳይንስና ባህል ድርጅት 'ዩኔስኮ' ዓለም ቅርስ ተብሎ ተመዝግቧል። ታንዛኒያ ግድቡ የሃገሪቱን የኤሌክትሪክ አቅርቦት በእጥፍ ይጨምርልኛል ብትልም፤ የአካባቢ ተቆርቋሪዎች ደግሞ ድንቅ የሆኑትን የዱር አራዊትና መኖሪያቸውን ያጠፋዋል የሚል ስጋት አላቸው። • ፈረንሳይ 'አላሁ አክበር' ብሎ ተኩስ የከፈተውን ግለሰብ በማደን ላይ ናት • ኻሾግጂ የዓመቱ ምርጥ ሰው ዝርዝር ውስጥ ተካተተ ፕሬዝዳንቱ ስምምነቱን የተፈራረሙት ከግብጽ ከመጡ ሁለት የግንባታ ድርጅቶች ጋር እንደሆነ ተገልጿል። የግድቡ ግንባታ ሲጠናቀቅ በአካባቢው የሚኖረው የውሃ ማጠራቀሚያ በአፍሪካ ትልቁ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ 1200 ስኩዌር ኪሎሜትር ቦታ ይሸፍናል ተብሏል። ታንዛኒያ ውስጥ አንድ ሶስተኛ የሚሆነው ዜጋ ብቻ ሲሆን የኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚያገኘው፤ የግድቡ ግንባታ ደግሞ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ሁነኛ መፍትሄ ተደርጎ ተወስዷል። የዓለማቀፉ የአካባቢ ተቆርቋሪ ድርጅት እንደሚለው የግድቡ ስራ ከእንስሳቱ ባለፈ እስከ 200 ሺ የሚደርሱ የአካባቢው ገበሬዎችና አሳ አጥማጆች ህይወትንም አደጋ ላይ ይጥላል። • የ7 ዓመቷ ህፃን መፀዳጃ ቤት አልሰራልኝም ስትል አባቷን ከሰሰች • ቴሬዛ ሜይ ሥልጣናቸውን እንዳያጡ ተሰግቷል ድርጅቱ ባለፈው ዓመት ባወጣው ሪፖርት መሰረት ግድቡ የታችኛው ተፋሰስ አካባቢዎችን አፈር ስለሚሸረሽር፤ ሃይቆች ሊደርቁ ይችላሉ። ይህ ደግሞ በውሃው ላይ ህይወታቸው መሰረት ያደረጉ አእዋፍና እንስሳት ከአካባቢው እንዲሰደዱ ያስገድዳቸዋል። የሴለስ ጥብቅ እስሳት ማቆያ ብዙ ብርቅዬ እስሳት የሚገኙት ሲሆን፤ ቁጥራቸው እጅግ እየተመናመነ የመጡት አውራሪና ዝሆንም ይገኙበታል።
news-53604862
https://www.bbc.com/amharic/news-53604862
በአፍጋኒስታን መኪና ላይ የተጠመደ ቦምብ ፈንድቶ ቢያንስ 17 ሰዎች ሞቱ
በአፍጋኒስታን ሎጋር ግዛት በመኪና ላይ የተጠመደ ቦምብ ፈንድቶ ቢያንስ 17 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ።
ታሊባን ጥቃቱን አላደረስኩም ሲል ተናግሯል ፍንዳታው ከባድ እንደነበር ተገልጿል። የቦምብ ፍንዳታው የደረሰው ታሊባን የኢድ በዓልን ለማክበር የተኩስ አቁም ካወጀ በኋላ ነው። ታሊባን በጥቃቱ እጄ የለበትም በማለት የተናገረ ሲሆን፣ እስካሁን አይኤስ የተባለው ቡድን ግን ያለው ነገር የለም። ጥቃቱ በአጥፍቶ ጠፊ የተፈፀመ ሊሆን እንደሚችል የሎጋር ግዛት አስተዳዳሪ ቃል አቀባይ፣ ዴዳር ላዋንግ፣ ለፈረንሳዩ ዜና ወኪል ተናግረዋል። ፍንዳታው የደረሰው ከግዛቱ አስተዳዳሪ ቢሮ አቅራብያ ሲሆን በርካታ ሰዎች ለኢድ በዓል ሸመታ ላይ እንደነበሩ ተገልጿል። ጥቃቱ የደረሰው በእግረኞች በሚጨናነቅ መንገድ ላይ ነው " አሸባሪዎቹ በድጋሜ ጥቃት አድርሰው በኢድ አል አድሃ ምሽት ዜጎቻችንን ገድለዋል" ያሉት የአገር ውስጥ ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ ታሪቅ አርያን ናቸው። የታሊባን ቃል አቀባይ፣ ዛቢሁላህ ሙጃሂድ፣ በበኩላቸው ጥቃቱ "ከቡድኑ ጋር አይያያዝም" ሲሉ ተናግረዋል። ታሊባንና የአፍጋኒስታን መንግሥት ከአርብ ጀምሮ የሚቆይ የሦስት ቀን የተኩስ አቁም ስምምነት አድርገዋል። በሁለቱ መካከል የሰላም ስምምነት ይደረሳል የሚል ተስፋ ቢኖርም ድርድሩ በእስረኛ ልውውጥ ምክንያት ዘግይቷል። መንግሥት ታሊባን በቁጥጥሩ ስር ያዋሉትን 1000 የአፍጋን ደህንነት ሰራተኞች ከለቀቀ 5000 የታሊባን እስረኞችን ለመልቀቅ ተስማምቷል። እስካሁን ድረስ የአፍጋን መንግሥት 4,400 የታሊባን አማፂያን እስረኞችን የለቀቀ ሲሆን፣ የታጣቂ ቡድኑ ቃል አቀባይ በበኩላቸው በአጠቃላይ 1,005 የመንግሥት ደህንነት ሰራተኞች መልቀቃቸውን ተናግረዋል።
news-48050416
https://www.bbc.com/amharic/news-48050416
በቻይና የተደረሱት ስምምነቶች የትኞቹ ናቸው?
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የተመራ ልዑክ በቤልት እና ሮድ ፎረም (Belt and Road Forum) ላይ ለመሳተፍ ቻይና ይገኛሉ።
ጠቅላይ ሚንስትሩ እና ልዑኩ ፎረሙ ከሚጀምርበት ቀን በፊት ቀደም ብሎ ወደ ቻይና በማቅናት ከሃገሪቱ ፕሬዝዳንት በተጨማሪ ከተለያዩ አካላት ጋር ውይይት አድርገዋል፤ ስምምነቶችንም ደርሰዋል። ከተደረሱት ስምምነቶች እና ከመወያያ ርዕሶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል። • "ቻይና በአፍሪካ ውስጥ የታይታ ፕሮጀክት የላትም" ፕሬዚዳንት ሺ ዢፒንግ ከወለድ ነጻ ብድር ስረዛ ጠቅላይ ሚንስትሩ ትናንት ሚያዚያ 16 ከቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ዥንፒንግ ጋር ከቤልት እና ሮድ ፎረም በፊት የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል። የውይይቱን ይዘት በማስመልከትም የጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ፤ ዢ ዥንፒንግ የጠቅላይ ሚንስትሩን አመራር እና ባለፈው አንድ ዓመት በኢትዮጵያ የተመዘገበውን የለውጥ ሂደት እንደሚያደንቁ ተናግረዋል ብሏል። ከዚህ በተጨማሪም የጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ ኢትዮጵያ ለቻይና በፈረንጆች አቆጣጠር 2018 ማብቂያ ድረስ መመለስ የነበረባትን ከወለድ ነፃ ብድሮች መሰረዙንም ገልጿል። ምንም እንኳ እስከ 2018 መጨረሻ ድረስ ከወለድ ነጻ ብድሮች ተሰረዙ ቢባልም፤ የዕዳው መጠን ግን በአሃዝ አልተጠቀሰም። • "ለዋጋ ግሽበት የውጪ ምንዛሪ ማሻሻያው ምክንያት ነው" ቻይና አፍሪካ ሪሰርች ኢንሼቲቭ የተሰኘ ድርጅት አደረኩት ባለው ጥናት፤ ኢትዮጵያ ለቻይና መክፈል ያለበትን ዕዳ 13.73 ቢሊዮን ዶላር ያደርሰዋል። ይህ ተቋም እንደሚለው ከሆነ ከአፍሪካ ሃገራት መካከል ከፍተኛ የቻይና እዳ ያለባት ሃገር በነዳጅ ሃብቷ የበለጸገችው አንጎላ ነች። አንጎላ ለቻይና መክፈል የሚጠበቅባት ዕዳ 42.8 ቢሊዮን ዶላር ነው። በ 9.8 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ ደግሞ ኬንያ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ኃይል ማሰራጫ እና ማከፋፈያ መስመር ዝርጋት ከጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ ባገኘነው መረጃ መሰረት፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ከቻይናው ስቴት ግሪድ ከተሰኘ ኩባንያ ጋር ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ ለኃይል ማሠራጫና ማከፋፈያ መስመር ዝርጋታ የ1.8 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ስምምነት ፊርማ እንዲፈረም አድርገዋል። በኢትዮጵያ በኩል ስምምነቱን ያኖሩት የፋይናንስ ሚንስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ናቸው። አቶ አህመድ ''ዕዳ ሳንፈጥር በቀጥታ ኢንቨስትመንት እድገታችንን ማስቀጠል የሚያስችል ግዙፍ ፕሮጀክት ነው።'' ሲሉ ከኩባንያው ጋር የተደረውን ስምምነት ገልጸውታል። ይህ ፕሮጀክት ለ16 የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኃይል አቅርቦት፣ ለሁለተኛው የአዲስ ጅቡቲ የባቡር መሥመርና ለተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል ለማዳረስ የሚያስችል ነው ተብሎለታል። ይህ የ1.8 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ያልተቋረጠ የኤሌክትሪክ ኃይል ከማቅረብ በተጨማሪ ሥራ ለመፍጠርም ይረዳል ተብሏል። ሸገርን የማስዋብ ፕሮጀክት ሸገርን [አዲስ አበባን] የማስዋብ ፕሮጄክት በጠቅላይ ሚንስትሩ የተጀመረ የሶስት ዓመት ፕሮጀክት መሆኑ ይታወቃል። የፕሮጀክቱን ዓላማ ለማሳካት በጠቅላይ ሚንስትሩ ጋባዥነት በሰው 5 ሚሊዮን ብር የሚያስከፍል የእራት ፕሮግራም እየተዘጋጀ እንደሆነ ተገልጿል። የቻይናው ፕሬዝዳንትም "የዚህን ፕሮጀክት ጠቀሜታ እንገነዘባለን፤ ለፕሮጀክቱ መሳካትም የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ መንግሥታችን እየሠራ ነው" ብለዋል ሲል የዘገበው የጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ ነው። • የቻይና የዕርዳታ ሚስጢር ሲገለጥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቻይና ሬልዌይ ኮንስትራክሽን ኩባንያ (ሲ.ረ.ሲ.ሲ) ኃላፊዎችንም አግኝተዋል። ሲ.ረ.ሲ.ሲ ኢትዮጵያን እና ጅቡቲን የሚያገናኘዉን የባቡር ፕሮጄክት ላይ ተሳታፊ ነበር። የ ሲ.ረ.ሲ.ሲ ኃላፊዎች የሸገርን ማስዋብ ፕሮጀክት ላይ ተሳትፎ እንደሚኖራቸው ለጠቅላይ ሚንስትሩ ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና ልዑካቸው ከቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኬኪያንግ ጋር የሁለቱን ሃገራት ትብብር የሚያጠናክሩ ስምምነቶች መድረሳቸው ተዘግቧል። ከእነዚህም መካከል የሸገርን ማስዋብና ፕላዛ ፕሮጀክት 12 ኪሎ ሜትር የሚሽፍን የፋይናንስ ስምምነት ይገኝበታል። በዚህ ስምምነት ዙሪያ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ የተሰጠ ዝርዝር ማብራሪያ የለም። አሊባባ ጠ/ሚር ዐቢይ የኢንተርኔት ንግድ ኩባንያ የሆነውን የአሊባባን ዋና መሥሪያ ቤት ጎብኝተዋል። በጉብኝታቸው ወቅትም ከአሊባባ ሊቀመንበር ጃክ ማ ጋር ተገናኝተዋል። ጃክ ማ በኢትዮጵያ እየተካሄዱ ባሉት ለውጦች መደነቃቸውንና ኢትዮጵያ ለኩባንያቸው ቁልፍ አጋር በመሆኗ በዚህ ዓመት መጨረሻ ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ የጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ ዘግቧል። • ኢትዮጵያ ከውጭ ምንዛሬ እጥረት አዙሪት እንዴት ትውጣ? ናዝራዊት አበራ ናዝራዊት አበራ በቻይና በአደገኛ እፅ ዝውውር ተጠርጥራ በእስር እንደምትገኝ ይታወሳል። በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና ቆንስላ ጽ/ቤት የናዝራዊትን ጉዳይ በቅርብ እየተከታተለ መሆኑን የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብያት ጌታቸው ለቢቢሲ ገልፀው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከቻይና ፕሬዝዳነት ጋር በነበራቸው ውይይት የናዝራዊት አበራ እስር እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።
52627588
https://www.bbc.com/amharic/52627588
ኮሮናቫይረስ፡ አሜሪካ በዳሬሰላም በቫይረሱ የመያዝ እድል "ከፍተኛ" ነው አለች
በታንዛንያ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ መንግሥት አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር መግለፁን ማቆሙን ተከትሎ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች "በከፍተኛ ሁኔታ ሊጨምር" ይችላል ሲል አስጠነቀቀ።
በተጨማሪም በዳሬሰላም በኮሮናቫይረስ የመያዝ እድሉ " እጅግ በጣም ከፍተኛ" መሆኑን አስታውቋል። የአሜሪካ ኤምባሲ በታንዛንያ የሚኖሩ አሜሪካውያንን በቤታቸው እንዲቆዩ እና አብረዋቸው ከሚኖሩ ውጪ ከሌሎች ሰዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲቀንሱ መክሯል። በዳሬሰላም የሚገኙ ሆስፒታሎች በሕሙማን መጨናነቃቸውን የገለፀው ኤምባሲው፣ የአገሪቱ ጤና ስርዓት አቅም ውስን በመሆኑ ሕሙማን ምናልባት አፋጣኝ ሕክምና ካለማግኘት የተነሳ ሕይወታቸው አደጋ ላይ ሊወድቅ እንደሚችልም ገልጿል። ቢቢሲ ኤምባሲውን በዚህ ጉዳይ ላይ ያለውን መረጃ የጠየቀ ሲሆን ከታንዛንያ ጤና ሚኒስቴር መውሰዱን ገልጿል። • በአፍሪካ ከ63 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮናቫይረስ ቢያዙም የተጣለው ገደብ እየላላ ነው • “በአፍሪካ በኤችአይቪ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በግማሽ ሚሊዮን ሊጨምር ይችላል” • ከጎረቤት አገራት ጋር የሚዋሰኑ ክልሎችና የኮሮና ወረርሽኝ ስጋት የታንዛንያ መንግሥት የአሜሪካ ኤምባሲ ላወጣው መግለጫ ያለውን አስተያየት ቢቢሲ ቢጠይቅም ምላሽ ማግኘት አልቻለም። ከዚህ ቀደም ፕሬዝዳንት ማጉፉሊ የጤናውን ቀውስ የአካባቢ ጤና ባለሥልጣናት እያጋነኑት መሆኑን ተናግረዋል። በታንዛንያ ለመጨረሻ ጊዜ በቫይረሱ የተያዘ ሰው መገኘቱ የተገለፀው ከአስራ አምስት ቀን በፊት ሲሆን በወቅቱ በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 509 ደርሶ ነበር። ከእነዚህም መካከል 21 ሰዎች መሞታቸው በወቅቱ ተገልጿል። የታንዛንያ ባለስልጣናት የወረርሽኙን መጠን ዝቅ አድርገው ቢያቀርቡትም፣ በማህበራዊ መገናኛ ብዙኃን ላይ በምሽት የሚደረጉ ቀብሮች መታየታቸውን ተከትሎ አንዳንዶች መንግሥትን እንዲጠይቁ አስገድዷቸዋል። ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ ለኮሮናቫይረስ የሰጡት ምላሽ እጅግ አነስተኛ ነው በሚል፣ እንዲሁም ቤተ እምነቶች እንዳይዘጉ እንዲሁም ፀሎት ቫይረሱን "ያሸንፈዋል" ማለታቸው በበርካቶች ትችት አስከትሎባቸዋል። ፕሬዝዳንቱ የማዳጋስካሩ ፕሬዝዳንት ኮቪድ-19 ሕሙማንን ይፈውሳል ሲሉ ያስተዋወቁትን ከእጽዋት የተቀመመ መድሃኒት ካዘዙ የአፍሪካ አገራት መሪዎች መካከል አንዱ ናቸው። ነገር ግን የዓለም ጤና ድርጅት ፍተሻ ያልተደረገበትን መድሃኒት እንዳይጠቀሙ አስጠንቅቋል። ከዚህ ቀደም ግን የታንዛንያ መንግሥት የሚቀርቡበትን ትችቶችና ክሶች ሁሉ ሲያጣጥል መቆየቱ ይታወሳል።
news-57133533
https://www.bbc.com/amharic/news-57133533
ጋዛ፡ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር 'በጋዛ የሚደረገው ጥቃት ይቀጥላል' አሉ
ዛሬ ንጋት ላይ እስራኤል ጋዛ ውስጥ በወሰደችው የአየር ድብደባ ሶስት ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የጤና ባለሙያዎች ገልጸዋል።
ጋዛ የፍልስጤም ታጣቂዎች ወደ ቴል አቪቭ በርካታ ሮኬቶችን የተኮሱ ሲሆን በዚህም ምክንያት ነዋሪዎች ለቦምብ መከላከያ ተብለው ወደተሰሩ መጠለያዎች ሸሽተዋል። የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁለቱም ወገኖች ግጭቱን ለማርገብ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪውን እያቀረበ ነው። ትናንት ቅዳሜ ዕለት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና ከፍልስጤም ፕሬዝደንት ማህሙድ አባስ ጋር በስልክ የተነጋገሩ ሲሆን እየተፈጠረ ያለው ነገር እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል። የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ደግሞ በጉዳዩ ላይ ዛሬ ስብሰባ ያካሂዳል። ሰኞ እለት ወደለየለት ግጭት በገባው የሁለቱ አገራት አለመጋባባት እስካሁን ቢያንስ 148 ሰዎች ጋዛ ውስጥ መገደላቸውን የፍልስጤም ኃላፊዎች የገለጹ ሲሆን እስራኤል ደግሞ ሁለት ህጻናትን ጨምሮ 10 ሰዎች ሞተዋል ብላለች። እስራኤል በጋዛ ከሞቱት ሰዎች መካከል አብዛኛዎቹ ታጣቂዎች ናቸው ብትልም የፍልስጤም ባለስልጣናት ግን ከሟቾች መካከል 41 ህጻናት እንደሚገኙ አስታውቀዋል። ቅዳሜ ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በቴሌቪዥን መስኮት ባስተላለፉት መልዕክት የአየር ጥቃቶቹን አስፈላጊ እስከሆኑ ድረስ እንደሚቀጥሉበት ገልጸዋል። ንሑሀን ዜጎች ጉዳት እንዳይደርስባቸውም የቻሉትን ሁሉ እያደረጉ እንደሆነም አስረድተዋል። ‘’አሁን ለተፈጠረው ፍጥጫ ጥፋተኞቹ እኛ አይደለንም፤ እኛ ላይ ጥቃት እየፈጸሙ ያሉት ናቸው’’ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። ባለፉት አምስት ቀናት በግጭት እየተናጠ ያለው ይህ ግዛት ካለፉት አመታት በቀጠናው ከተከሰተው የከፋ ነው ተብሏል። በምስራቅ ኢየሩሳሌም በእስራኤልና በፍልስጤማውያን መካከል ለሳምንታት የዘለቀው ውጥረት ወደ ግጭት ያመራው በያዝነው ሳምነት መጀመሪያ ሰኞ እለት ነው። በእስልምናና በአይሁድ እምነት ተከታዮች ዘንድ ቅድስት ተብላ የምትጠራው ስፍራ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ የሆነ መጋጋል ተፈጥሮ ነበር። ጋዛን የሚያስተዳድረው ታጣቂው ሃማስ እስራኤል ከቅድስቲቷ ስፍራ ለቃ እንድትወጣ ካስጠነቀቀ በኋላ ሮኬቶ ማስወንጨፉ ተገልጿል። እስራኤልም በምላሹ የአየር ጥቃቶችን ፈፅማለች። አሜሪካም ብትሆን በእስራኤልና ፍልስጤም መካከል ያለው ግጭት ከፍ ወዳለ ጦርነት ሊያመራ ይችላል በተባለበት ወቅት ግጭቶቹን ለማርገብ ለሚደረገው ውይይት ልዑኳን ልካለች። ሃዲ አሚር ከእስራኤል፣ ከፍልስጤምና ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከተውጣጡ ኃላፊዎች ጋር በሚደረገው ውይይት ይሳተፋሉ። ውይይቱም የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደረስ ተስፋ ተጥሎበታል። በእስራኤል የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ እንዳስታወቀው የልዑኩ ጉዞ "ዘለቄታዊ ሰላም እንዲመጣ የሚሰሩ ስራዎችን ለማገዝ" እንደሆነ ቢያትትም የእስራኤልና የፍልስጤም ባለስልጣናት ተኩስ እንዲያቆሙ የቀረበላቸው ተማፅኖ ፍሬ አላፈራም። ትናንት ቅዳሜ ላይ ደግሞ እስራኤል በፈጸመችው የአየር ድብደባ አልጀዚራ እና አሶሼትድ ፕረስ እንዲሁም ሌሎች ድርጅቶችና ነዋሪዎች ይጠቀሙበት የነበረ ህንጻ ሙሉ በሙሉ ፈርሷል። የእስራኤል መከላከያ ወዲያው ባወጣው መግለጫ ህንጻውን ጋዛን የሚያስተዳድረው የሀማስ ቡድን ታጣቂዎች ሲጠቀሙበት ነበር ብሏል። የህንጻው ባለቤት ግን ከዚህ ጋር በተያያዘ ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸው ገልጸዋል። የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የዓለማቀፍ መገናኛ ብዙሀን የሚጠቀሙበት ህንጻ ላይ በደረሰው ጥቃት በጣም መደንገጣቸውን አስታውቀዋል። ‘’ዋና ጸሀፊው በሁለቱም ወገኖች በከኩል ንጹሀን ዜጎች እና የመገናኛ ብዙሀን ላይ የሚደርሱ ትቃቶች በርካታ ዓለማቀፍ ሕጎችን የሚጥሱና በቶሎ መቆም ያለባቸው ጉዳዮች ናቸው’’ ብለዋል ሲል የዋና ጸሃፊው ቃል አቀባይ አስታውቋል።
news-52586656
https://www.bbc.com/amharic/news-52586656
ጥቁር አሜሪካዊውን በመግደል አባት እና ልጅ ክስ ተመሰረተባቸው
በአሜሪካዋ ጆርጂያ ግዛት የአካል እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረውን ጥቁር አሜሪካዊ ተኩሰው የገደሉት አባት እና ልጅ ክስ ተመስርቶባቸዋል።
ተከሳሾቹ የ64 ዓመቱ ጆርጅ ማክሚካኤል እና የ34 ዓመቱ ትራቪስ ማክሚካኤል ትናንት ነበር በቁጥጥር ሥር የዋሉት። ሟች የ25 ዓመቱ አህሙድ አርቤረይ በአባት እና ልጅ ጥቃት ሲሰነዘርበት አካላዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ በሩጫ ላይ ነበር። እንደ መርማሪ ፖሊስ ከሆነ ወንጀሉ የተፈጸመው የካቲት 23 ሲሆን፤ አባት እና ልጅ በታጠቁት ጦር መሳሪያ ወጣቱን ያስፈራሩት ሲሆን፤ አህሙደን ተኩሶ የገደለው ግን የ34 ዓመቱ ትራቪስ ነው። አባት እና ልጅ ለፖሊስ ቃላቸውብ ሲሰጡ፤ ሟች በተደጋጋሚ ቤት ሰብሮ ዘረፋ ይፈጽማል ተብሎ የተገለጸ ሰው ነው ብለው አምነዋል። ለአካላዊ እንቅስቃሴ በሩጫ ላይ የነበረውን ወጣት ሲመለከቱ በመኪናቸው መከታተል ጀመሩ። የ64 ዓመቱ ተከሳሽ እና የቀድሞ የፖሊስ አባል፤ ለፖሊስ በሰጡት ቃል ላይ “ቁም ቁም ልናነጋግርህ እንፈልጋለን አልነው። ከዛ ትራቪስን ማጥቃት ጀመረ። ከዛ የተኩስ ድምጽ ተሰማ” ብለዋል። ሟች አህሙድ አርቤረይ የወንጀሉን ድርጊት አፈጻጸም ያሳያል የተባለ የ36 ሰከንድ ተንቀሳቃሽ ምሰልም በማህብራዊ ገጾች ላይ በስፋት ተሰራጭቷል። በቪዲዮ ላይ አንድ ወጣት እየሮጣ ይታያል። ከዚያም የሁለቱ ተጠርጣሪዎች ተሽከርካሪ እየሮጠ ወደላው ወጣት ይጠጋል። ከዚያም እየሮጠ የነበረው ወጣት መሳሪያ ከታጠቀ ሰው ጋር ሲታገል ያሳያል። ከዚያም የተኩስ ድምጽ ይሰማል። ቀጥሎ በቪዲዮ ላይ የሚታየው የ64 ዓመቱ አባት ሽጉጥ ይዞ ነው። ወንጀሉ ከተፈጸመ በኋላ ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ሥር ሳያውል እና ክስ ሳይመሰረትባቸው ለበርካታ ሳምንታት መቆየቱ በጥቁር አሜሪካውያን ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሶ ነበር። የሟች እናት በበኩላቸው፤ ከክስተቱ በፊት ፖሊስ ልጃቸው በዘረፋ ወንጀል ተሳትፎ ነበር ሲል ነግሯቸዋል። ልጃቸው በወንጀል ድርጊቶች ተሳትፎ ነበረው የተባለው “ሐሰት ነው” ብለዋል።
news-55183434
https://www.bbc.com/amharic/news-55183434
ኮቪድ-19 ፡ ስለ ክትባቱ እየተሰራጩ የሚገኙ አራት ሐሰተኛ ወሬዎች
ተስፋ ሰጪ የኮሮናቫይረስ ክትባቶች መገኘታቸው ዓለምን ቢያስደስትም ስለ ክትባቶች የሚሰራጩ አሉባልታዎች መሰናክል መሆናቸው ግን አልቀረም።
ቢቢሲ ክትባቶችን በተመለከተ እየተሰራጩ ያሉ አራት ሐሰተኛ ወሬዎችን ለይቷል። ‘ክትባቱ የዘረ መል መዋቅር ያዛባል’ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ክትባቱ የሰዎችን ዘረ መል መዋቅር እንደሚያቃውስ ተነግሯል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሦስት ገለልተኛ ሳይንቲስቶች ግን ይህ ሐሰት ነው ብለዋል። ፋይዘርና ባዮቴክ የሠሩትን ክትባት ጨምሮ ብዙ ክትባቶች የተዘጋጁት ከቫይረሱ የዘረ መል ቅንጣት በመውሰድ ነው። የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲው ፕ/ር ጀፍሪ አልመንድ ክትባቶቹ የሰዎች ዘረ መል ላይ ምንም አይነት ጉዳት አያስከትሉም ይላሉ። ክትባት የሰው ሰውነት ቫይረሱ የተሸፈነበትን ፕሮቲን እንዲያመነጭ በማነቃቃት በሽታ የመከላከል አቅምን ያዳብራል። የኮሮናቫይረስ ክትባት የዘረ መል መዋቅር ያዛባል የሚለው አሉባልታ መሰራጨት የጀመረው ከግንቦት ወዲህ ነው። አርኤንኤ የሚባለው የክትባት ሂደት ከዚህ ቀደም እንዳልተሞከረ ያጣቅሳል። በእርግጥ አርኤንኤ የተባለው ሂደት ከዚህ ቀደም ፍቃድ ባያገኝም፤ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በሰዎች ላይ ተሞክሯል። ወረርሽኙ ከተቀሰቀሰ ወዲህ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ላይ የክትባት ሙከራ ተደርጓል። አስተማማኝነቱ የሚረጋገጠው ከጥብቅ ፍተሻ በኋላ ነው። በመጀመሪያውና በሁለተኛው ሙከራ ክትባቶች በጥቂት በጎ ፍቃደኛ ሰዎች ላይ ይሞከራሉ። ሂደቱ ስለክትባቱ አስተማማኝነት እና በምን ያህል መጠን መሰጠት እንደሚገባው መረጃ ይሰጣል። በሦስተኛው የሙከራ ደረጃ ክትባቱ በሺዎች በሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ተሞክሮ ውጤታማነቱ ይፈተሻል። የጎንዮሽ ጉዳት ያስከትል እንደሆነም ሙከራው ጠቋሚ ነው። ‘ቢል ጌትስ ማይክሮቺፕ ሊቀብሩብን ነው’ የኮሮናቫይረስ ክትባት በሰውነት የሚገባ የመረጃ መሣሪያ (ማይክሮቺፕ) ለመቅበር የተፈጠረ ሽፋን ነው የሚለው የሴራ ትንተና መሰራጨት ከጀመረ ሰነባብቷል። ከዚህ አጀንዳ ጀርባ ያሉት የማይክሮሶፍት ፈጣሪው ቢልጌትስ እንደሆኑም በስፋት ሲወራ ነበር። ሆኖም ግን ይህንን ወሬ የሚያረጋግጥ ተጨባጭ ማስረጃ የለም። የቢል እና መሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን የተወራው ነገር “ሐሰት ነው” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሚያዝያ ላይ ቢል ጌትስ ቃለ መጠይቅ ሲደረግላቸው “ከወረርሽኙ ያገገሙ ሰዎችን ለመለየት ዲጂታል የምስክር ወረቀት ይኖራል” ማለታቸውን ተከትሎ ነው ወሬው የተሰራጨው። በእርግጥ በቃለ ምልልሱ ወቅት ስለ ማይክሮቺፕ ምንም አልተናገሩም። የጌትስ ፋውንዴሽን ክትባት ሲሰጥ የሰዎችን የክትባት መረጃ የሚመዘግብ ስውር ቀለም ያለው ቴክኖሎጂን በገንዘብ ይደግፋል። ቴክኖሎጂው ገና ሥራ ላይ አልዋለም። ይህ ቴክኖሎጂ የሰዎችን የግል መረጃ አያሾልክም። ሰዎችን በስውር ለመከታተል እንደማይውልም በጥናቱ የተሳተፉት ሳይንቲስት አና ጃክሊንስ ተናግረዋል። አንድ ጥናት እንደሚያሳየው፤ 28 በመቶ የሚሆኑ አሜሪካውያን ቢል ጌትስ በክትባት ሰበብ ማይክሮቺፕ ሊቀብሩ እንደወጠኑ ያምናሉ። ከነዚህ ሰዎች 44 በመቶው ሪፐብሊካን ናቸው። ‘ክትባቱ የጽንስ ህዋስ ይዟል’ ሌላኛው ሐሰተኛ ወሬ ክትባቱ የጽንስ ሳንባ ህዋስ አለበት የሚለው ነው። የሳውዝሀምተን ዩኒቨርስቲው ዶ/ር ማይክል ሄድ “በየትኛውም ክትባት ውስጥ የጽንስ ህዋስ የለም” ይላሉ። ጸረ ክትባት መረጃ ከሚያሰራጩ የፌስቡክ ገጾች አንዱላይ የተለቀቀ ተንቀሳቃሽ ምስል ጥናት አጣቅሶ የአስትራዜኒካ እና የኦክስፎርድ ክትባት ይዘትን ይተነትናል። ሆኖም ግን በቪድዮው የሚጠቀሰው ጥናት ያተኮረው ቤተ ሙከራ ውስጥ ክትባቱ በሰዎች ህዋስ ላይ ሲሞከርምን ውጤት እንደሚያሳይ ነው። ክትባት ሲዘጋጅ በቤተ ሙከራ የተሠራ ህዋስ ጥቅምላይ መዋሉ ትክክለኛ የሂደቱ አካል ቢሆንም ቪድዮው ላይ የተገለጸበት መንገድ ግን ስህተት ነው። የብሪስትል ዩኒቨርስቲው ዶ/ር ዴቪድ ማቲውስ ክትባቶች በዚህ መንገድ እንደሚሠሩና ለሂደቱ ጽንስ እንዲወርድ ተደርጓል መባሉ ስህተት መሆኑን አስምረውበታል። ‘ሰው ከበሽታው የሚያገግም ከሆነ ክትባት አያስፈልግም’ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰራጩ አሉባልታዎች፤ ሰዎች በወረርሽኙ ሳቢያ የመሞት እድላቸው ጠባብ ከሆነክትባት ምን ይጠቅማል? ይላሉ። ከበሽታው የማገገም እድል 99.97% ነው ሲሉም ይከራከራሉ። ስለዚህም ክትባት ከመውሰድ ይልቅ በኮቪድ-19 መያዝ እንደሚመረጥ ይጠቁማሉ። በተቃራኒው ተመራማሪዎች እንደ ማስረጃ የተጠቀሰው አሐዝ ትክክል እንዳልሆነ ያስረዳሉ። በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ የሚሠሩት ጄሰን ኢኬ፤ በቫይረሱ ከሚያዙ ሰዎች 99.0% ያህሉ የመትረፍ እድል አላቸው ይላሉ። ይህ ማለት ደግሞ ከ10,000 ሰዎች 100 ያህሉ ይሞታሉማለት ነው። ከሚሞቱ ሰዎች በተጨማሪ በቫይረሱ ተይዘው ከፍተኛ የጤና ቀውስ የሚገጥማቸው፣ ለዓመታት ጤናቸው ላይ ጠባሳ የሚያድርባቸውም ብዙ ናቸው። በሌላ በኩል በኮሮናቫይረስ ሳቢያ የጤና ዘርፉ እየደረሰበት ካለው ጫና በቀላሉ ለማገገም መቸገሩ አይቀርም። ይህ ማለት ደግሞ ሌላ ህመም ያለባቸው ሰዎች ተገቢውን እንክብካቤ ለማግኘት ይቸገራሉ ማለት ነው። ፕ/ር ሊያም ስሚዝ፤ ክትባት በማኅበረሰብ ደረጃ ካልተወሰደ በግለሰቦች ብቻ ተወስኖ የሚፈለገውን ለውጥ አያመጣም በማለት የክትባትን አስፈላጊነት ያስረግጣሉ።
48361984
https://www.bbc.com/amharic/48361984
የሰዎችን ማንነት የሚለየው ቴክኖሎጂ እያከራከረ ነው
በአንድ ምስል ወይም ቪድዮ ላይ ያሉ ሰዎችን ማንነት የሚለየው የ 'ፌስ ሪኮግኒሽን' ቴክኖሎጂ አሁንም እያከራከረ ነው።
አማዞን 'ሪኮግኒሽን' በሚል ስያሜ የሠራው የ 'ፌስ ሪኮግኒሽን' ቴክኖሎጂ ለአሜሪካ ፖሊሶች መሸጥ አለበት ወይስ የለበትም የሚለው ጉዳይ የአማዞን ባለድርሻዎች መካከል አለመግባባት ፈጥሯል። ባለድርሻዎቹ በአማዞን ዓመታዊው ጉባኤ ላይ ምርጫ በማድረግ ውሳኔ እንደሚያሳልፉም ይጠበቃል። ባለድርሻዎቹ፤ አማዞን 'ሪኮግኒሽን'ን ለመንግሥት ተቋማት መሸጥ አለበት? ቴክኖሎጂው የሰዎችን ሰብአዊ መብት ስላለመጋፋቱ በገለልተኛ ወገን ይጠና? የሚሉ ሁለት ጉዳዮች ላይ ምርጫ ያደርጋሉ። አማዞን ምርጫው እንዳይካሄድ ለማድረግ ቢሞክርም የማስቆም መብት ስለሌለው አልተሳካለትም። ሜሪ ቤት ጋልጋር የተባሉ ባለሙያ ለቢቢሲ፤ " 'ሪኮግኒሽን' ለመንግሥት ተቋሞች መስጠት የሚያስከትለው ተጽዕኖ ሳይጠና እንዳይሸጥ እንፈልጋለን። ውሳኔውን ለማሳለፍም ባለሀብቶች እንደሚያግዙን እናምናለን" ብለዋል። • ሥራ ቀጣሪና አባራሪ እየሆነ የመጣው ሮቦት ቴክኖሎጂው መቶ በመቶ ትክክለኛ መረጃ እንደማይሰጥ ጠቅሰው፤ ጥቅም ላይ ሲውል የሰዎችን መብት ተጋፍቶ እንደሚሰልል ተናግረዋል። "ሰዎች፣ ፖሊሶች እያንዳንዱን እንቅስቃሴያቸውን እየተመለከቱና እየተከታሏቸው እንደሆነ ከተሰማቸው በነጻነት አይንቀሳቀሱም" ብለዋል። አማዞን በበኩሉ 'ሪኮግኒሽን' ያለአግባብ ጥቅም ላይ ውሏል የሚል ሪፖርት ቀርቦ ስለማያውቅ ባለድርሻዎች እንዲደግፉት ጠይቋል። ድርጅቱ በመግለጫው እንዳሳወቀው፤ ቴክኖሎጂው ወንጀለኞች በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ያግዛል። "የጠፉ ሰዎች እንዲገኙ ይረዳል። ወንጀል መከላከልም ይቻላል። ያለአግባብ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል ብሎ አዲስ ቴክኖሎጂ ማጣጣል ተገቢ አይደለም" ተብሏል። • አፕል ቲቪ ጀመረ ወደ 20 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች መረጃ ያለው ቴክኖሎጂው፤ በምስልና ቪድዮ ላይ የታየ ሰውን ማንነት ለማወቅ ያስችላል። የሰዎችን ጾታ ይለያል። ምስል ላይ ያለ ጽሁፍ እንዲተነተንም መረጃ ያቀብላል። ሆኖም በኤም አይ ቲና ዩኒቨርስቲ ኦፍ ቶሮንቶ የተሠሩ ጥናቶች፤ ቴክኖሎጂው ሰዎችን በጾታቸውና በቆዳ ቀለማቸው የሚያገል መሆኑን ይጠቁማሉ። ቴክኖሎጂው የነጭ ወንዶችን ማንነት በቀላሉ ለማወቅ ቢረዳም ስለጥቁር ሴቶች ትክክለኛ መረጃ አይሰጥም። አማዞን እነዚህ ጥናቶች የተሠሩት ቀድሞ በነበረው ቴክኖሎጂ እንደሆነና አሁን መሻሻሉን ይገልጻል። ቢሆንም የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና የአማዞን ሠራተኞችም ቴክኖሎጂውን ይቃወማሉ።
48014334
https://www.bbc.com/amharic/48014334
የጡት ካንሰር የያዛት የጡት ካንሰር ሀኪም
ዶ/ር ሊዝ ኦሪዮርዳን ትባላለች። የጡት ካንሰር የቀዶ ጥገና ሀኪም ነበረች። የጡት ካንሰር ይዟት ሥራዋን ለማቆም እስከተገደደችበት ጊዜ ድረስ በሙያዋ ብዙ ሴቶችን አገልግላለች።
ዶ/ር ሊዝ ኦሪዮርዳን ስለ ህመሟ ስትናገር፦ "እንደ አብዛኞቹ ሴቶች ጡቴን አልተመረመርኩም ነበር። የጡት ካንሰር ሀኪም ስለሆንኩ የጡት ካንሰር ይይዘኛል ብዬ አስቤ አላውቅም" • አስጊነቱ እየጨመረ ያለው ካንሰር ህክምና ስትማር ቢያንስ ለ20 ዓመት የጡት ካንሰር ሀኪም እሆናለሁ ብላ ነበር። ነገር ግን በሙያዋ መሥራት የቻለችው ሁለት ዓመት ብቻ ነበር። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2015 ጡቷ ላይ ቀዶ ጥገና ተደርጎ ነበር። ባለፈው ወር ካንሰር ዳግም አገርሽቶባታል። ዶ/ር ሊዝ ኦሪዮርዳን "ከሀኪምነት ወደ ታማሚነት ልሸጋገር ነው?" የጡት ካንሰር እንዳለባት ከማወቋ በፊት ጡቷ ላይ አንዳች ምልክት ታይቷት ነበር። ጡት በሚመረመርበት ኤክስሬይ 'ማሞግራም' ስትታይ ጡቷ ላይ ችግር እንደሌለ ተነገራት። ቢሆንም ምልክቱን በድጋሚ ስታይ እናቷ ካንሰር እንድትመረመር አደረጓት። በምርመራውም ካንሰር እንዳለባትም ታወቀ። የጡት ካንሰር ሀኪም በመሆኗ ምን እንደሚያስፈልጋት ለማወቅ አማካሪ አላስፈለጋትም። "ከሀኪምነት ወደ ታማሚነት ልሸጋገር ነው?" ብላ ትካዜ ቢገባትም፤ ኬሞቴራፒ እንደሚያስፈልጋት እንዲሁም ምን ያህል ጊዜ በሕይወት መቆየት እንደምትችል ታውቃለች። • በኢትዮጵያ ለካንሰር ተጋላጮች እነማን ናቸው? ዶ/ር ሊዝ አሁን 43 ዓመቷ ነው። ብዙ ዶክተሮች ህክምና በሚሰጡበት በሽታ አንደማይያዙ ትናገራለች። ዶክተሯ 'ሬድዮቴራፒ' (የጨረር ህክምና) ካደረገች በኋላ የክንዷ እንቅስቃሴ ተገደበ። ቀዶ ጥገና ማድረግም አልቻለችም። ህመሙ አካል ላይ የሚያደረሰውን ጉዳት እንጂ ሥነ ልቦናዊ ተጽዕኖው እስከሚደርስባት ድረስ አታውቅም ነበር። "የጡት ካንሰር ላለበትን ሰው መንገር እንጂ በበሽታው መያዝ ምን ማለት እንደሆነ አላውቅም ነበር።" ሀኪሟ ከቀዶ ጥገና በኋላ ትከሻዋን እንደቀድሞው ማዘዝ አልቻለችም "የራሴን ህመም ደጋግሞ ማስታወስ ነው የሆነብኝ" ካንሰር እንደያዛት ካወቀች በኋላ የቀዶ ጥገና አማካሪ ከሆነ ባለቤቷ ጋር ተመካክራ የትዊተር ገጿ ላይ ስለመታመሟ ጻፈች። ትዊተር ላይ 1,500 ተከታዮች ያሏት ሲሆን፤ እንደሷው የጡት ካንሰር ያለባቸው ሴቶች ማኀበራዊ ሚድያ ላይ ድጋፍ ይቸሯት ጀመረ። • "ወንዶች በጡት ካንሠር እንደሚያዙ አላውቅም ነበር" እንደሷው ሀኪም ሆነው የጡት ካንሰር ከያዛቸው ሴቶች ጋር የተገናኘችውም በማኀበራዊ ሚዲያ ነበር። የዋትስአፕ ቡድን ፈጥረው ተሞክሯቸውን ይጋራሉ። የጡት ካንሰር ከያዛት በኋላ ህመሙ ያለባቸውን ሰዎች በተሻለ ሁኔታ መርዳት እንደምትችል ገምታ ነበር። ሆኖም እንዳሰበችው ቀላል ሆኖ አላገኘችውም ። "ለእያንዳንዷ ሴት የጡት ካንሰር እንዳለባት መንገር ከባድ ነው። የራሴን ህመም ደጋግሞ ማስታወስ ነው የሆነብኝ" ትላለች ዶ/ር ሊዝ። ቀዶ ጥገና ከተደረገላት በኋላ ታካሚዎቿ ላይ ቀዶ ጥገና ማድረግ ተቸግራ ነበር "እኔና እሷ አንድ ነን" ትሠራበት በነበረው ሆስፒታል አንድ በሷ ዕድሜ ያለችና እንደሷው አይነት የጡት ካንሰር ያለባት ሴት ህክምና ትከታተል ነበር። ሰለታማሚዋ ከሌሎች ሀኪሞች ጋር እየተነጋገረች ሳለ "ያለችበት ሁኔታ እጅግ የከፋ ነው" ሲባል ልክ ስለሷ እንደሚወራ እንደተሰማት ትናገራለች፤ "እኔና እሷ አንድ ነን" ስትልም የተሰማትን ስብራት ትገልጻለች። • የካንሰር የደም ምርመራ "አሰደናቂ ውጤት" አስገኘ ዶ/ር ሊዝ ሰዎች ካንሰር ከያዛቸው በኋላ ወደሥራ ገበታቸው እንዲመለሱ ትመክራለች። በርካታ መሥሪያ ቤቶች ሠራተኞቻቸው ካንሰር ከያዛቸው በኋላ ወደሥራ የሚመለሱበትን መንገድ እንደማያመቻቹም ትናገራለች። አሁን የጡት ካንሰር ላለባቸው ሴቶች እገዛ ማድረግ በምትችልባቸው ማህበሮች ውስጥ ትሳተፋለች፤ ታማክራለችም። "አማካሪ ሆኜ በዓመት ቢያንስ ከ70 እስከ 100 ሴቶች እረዳለሁ። በመጽሐፌ ደግሞ መቶ ሺዎችን አግዛለሁ" ትላለች ዶክተሯ።
news-55278524
https://www.bbc.com/amharic/news-55278524
ዩኬ እና ሩስያ ክትባቶቻቸውን አጣምረው ሙከራ ሊያደርጉ ነው
የዩናይትድ ኪንግደም እና የሩስያ ሳይንቲስቶች የኮሮናቫይረስ ክትባቶቻቸውን አጣምረው ሙከራ ሊያደርጉ ነው።
የኦክስፎርድና አስትራዜኒካ ክትባት ከሩስያው ስፑትኒክ ጋር ቢጣመር ቫይረሱን በተሻለ ሁኔታ መከላከል ይቻል ይሆናል። ሁለት ተመሳሳይ ክትባቶችን ማዋሀድ የሰዎችን በሽታ የመከላከል አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ሊያሳድግ ይችላል። ሙከራው የሚካሄደው ሩስያ ሲሆን፤ ከ18 ዓመት በላይ በሆኑ ሰዎች ላይ ነው የሚሞከረው። ኦክስፎርድ የሠራው ጠብታ ሰዎች ላይ ተሞክሮ አስተማማኝ እና ውጤታማ መሆኑን በቅርቡ አስታውቋል። ተመራማሪዎች ክትባቱ ለአረጋውያን እንደሚሠራ ለማረጋገጥ መረጃ እየሰበሰቡ ነው። ዩኬ ውስጥ ፍቃድ እስኪሰጣቸው እየጠበቁም ነው። አስትራዜኒካ የተለያዩ የአድኖቫይረስ ክትባቶችን በማዋሀድ የተሻለ በሽታ የመከላከል አቅም ማዳበር ይችሉ እንደሆነ እየተመራመረ ነው። ክትባቶችን ማደባለቅ ዘለግ ላለ ጊዜ ሰውነት በሽታን እንዲከላከል እና በቫይረሱ ሳይያዙ ረዥም ጊዜ ለመቆየት ይረዳከል የሚል ተስፋ አለ። የኦክስፎርዱ እንዲሁም የሩስያው ስፑትኒክ ክትባትም ጉዳት አልባ ቫይረስን በመጠቀም ነው የተሠሩት። ይህም ሰውነት በሽታውን መቋቋም እንዲችል ያግዛል። የኦክስፎርድ ክትባት መጀመሪያ ላይ ግማሽ ጠብታ ከዛም አንድ ሙሉ ጠብታ ይሰጣል። ይሄ ሂደት በአንድ ጊዜ ሁለት ጠብታ ከመስጠት የተለየ ነው። የኦክስፎርድና አስትራዜኒካ ክትባት ከስፑትኒክ ጋር የሚመሳሰሉት ሁለቱም የሳርስ-ኮቭ-2 የዘረ መል መዋቅርን የያዙ በመሆናቸው ነው። የነዚህ ክትባቶች አሠራር ከፋይዘር እና ባዩቴክ ክትባቶች የተለየ ነው። እነዚህ ሁለት ክትባቶች በዩኬ፣ ካናዳ፣ ባህሬን፣ ሳኡዲ አረቢያ ፍቃድ አግኝተዋል። የጤና ባለሙያዎች ክትባቶቹ በአሜሪካም ፍቃድ እንዲሰጣቸው መክረዋል። የስፑትኒክ የመጨረሻ ሙከራ ደረጃ ላይ የተገኘው ቅድመ መረጃ ክትባቱ ተስፋ ሰጪ መሆኑን ይጠቁማል። ሩስያ የኮሮናቫይረስ ክትባትን በማስመዝገብ ከዓለም ቀዳሚ አገር ናት። አሁን ለዜጎች እየተሰጠም ይገኛል።
news-53983206
https://www.bbc.com/amharic/news-53983206
ኦሮሚያ፡ የታመመ ግመል ስጋ የበሉ ከ100 በላይ ሰዎች መታመማቸው ተሰማ
የታመመውን ግመል አርደው ስጋውን ተካፋፍለው የበሉ 110 ጎረቤታሞች ሰዎች መታመማቸው ተነገረ።
ባሳለፍነው ሳምንት የታመመ ግመል ስጋ ተመግበው ሕመም ያጋጠማቸው ሰዎች ቦርቦሪ ተብሎ በሚጠራ ጤና ጣቢያ ሕክምና እንደተደረገላቸው ተጠቁሟል። የመጨረሻዋ ታማሚም እሁድ እለት በጤና ጣቢያ ውስጥ የሚደረግላትን ሕክምና አጠናቃ ከማዕከሉ መውጣቷ ተነግሯል። የግመሉን ስጋ ተመግበው ከታመሙ ሰዎች መካከል አንዷ መሆናቸውን የሚናገሩት ወ/ሮ ቦሪ ጃርሶ፤ ስጋውን አብስለው ቢመገቡም ለህመም መዳረጋቸውን ተናግረዋል። “ባለ ግመሉ ሰውዬ ጎረቤታችን ነው። ግመሉ ሲታመም የተለያየ ባህላዊ መድሃኒት ሲያጠጡት ነበር። ግመሉ ግን ሕመሙ እየተባባሰበት ሲሄድበት ታረደ። ለእኛም ስጋው ተልኮልን ተካፍለን በላን” ይላሉ። ስጋውን አብስለው የተመገቡ ሰዎች ጨምሮ በሙሉ በሰዓታት ልዩነት ውስጥ መታመማቸውን ወ/ሮ ቦሪ ይናገራሉ። “ራስ ምታት እና ማስመለስ ያለው ከፍተኛ ህመም ነው ያስከተለብን። ፈጣሪ እና ሐኪም ነው ያዳኑን እንጂ ከፍተኛ ህመም ነበር ያጋጠመን። አሁንም ድረስ የሕመሙ ሰሜት ከውስጣችን አልወጣም” ብለዋል። በቦርቦር ጤና ጣቢያ ነርስ የሆኑት አቶ ኮከብ መሐዲ በቅድሚያ ወደ 20 የሚጠጉ ሰዎች ታመው መምጣታቸውን ይናገራሉ። “እንደ ተቅማጥ፣ ማስመለስ እና የሰውነት ሙቀት ያሉ ተመሳሳይ ምልክት ይታይባቸው ነበር” ያሉ ሲሆን፤ ተመሳሳይ የሕመም ምልክት የሚያሳዩ ሰዎች ወደ ጤና ጣቢያቸው በብዛት መምጣት መጀመራቸውን ይናገራሉ። “በአጠቃላይ 110 ሰዎች አክመናል” ብለዋል። በአጠቃላይ የታመመውን የግመል ስጋ በልተው የታመሙ ሰዎች በእድሜ ከ1 ዓመት እስከ 70 ድረስ እንደሆኑ ያስታወሱት አቶ ኮከብ ለታመሙ ሰዎች በተሰጠው ህክምና የሰዎች ህይወት እንዳለለፈ ተናግረዋል። በቦረና ዞን ዳሲ ወረዳ የእንስሳት ሐኪም የሆኑት ዶ/ር ፍራኦል ዋቆ ማህበረሰቡ የታመሙ እንስሳት ስጋ እና ጥሬ ስጋን መመገብ ማቆም ይኖርበታል ይላሉ። “የእንስሳት በሽታ በሰው ላይ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል። እንስሳት የሚታመሙት የተመረዘ ነገር በልተውም ሊሆን ይችላል ይህ ደገሞ በሰው ጤና ላይ ጉዳት ያስከትላል። እንስሳት መድሃኒት ወስደው ከሆነ ደግሞ ከማረዳችን በፊት መድሃኒቱ ከሰውነታቸው እስኪወጣ መጠበቅ ይኖርብናል” ይላሉ።
news-50204867
https://www.bbc.com/amharic/news-50204867
የሳውዝዌስት አብራሪዎች በአውሮፕላን መጸዳጃ ክፍል ውስጥ ድበቅ ካሜራ ገጥመዋል የሚል ክስ ተመሰረተባቸው
የሳውዝዌስት አየር መንገድ የበረራ አስተናጋጅ በአውሮፕላን መጸዳጃ ክፍል ውስጥ ድብቅ ካሜራዎችን ገጥመዋል ያለቻቸው ሁለት የአየር መንገዱ አብራሪዎች ላይ ክስ መሰረተች።
ሪኒ ስቲንከር የተባለችው የበረራ አስተናጋጅ ሁለቱ አብራሪዎች በመጸዳጃ ክፍል ውስጥ ካሜራ መግጠማቸውን አይቻለሁ ያለችው ከሁለት ዓመት በፊት ከሩሲያ ፒተርስበርግ ወደ ፊኒክስ በነበራት በረራ ነው። ዋና አብራሪ ቴሪ ግርሃም ወደ መጸዳጃ ክፍል ለመሄድ በማሰብ ከረዳት አብራሪው ራየን ራስል ጋር በመሆነ የበረራ መቆጣጠሪያ ክፍል ውስጥ አብራ እንድትቆየ ከጠየቃት በኋላ መጸዳጃ ክፍል ውስጥ እየሆነ ያለውን በቀጥታ የሚያስመለከት አይፓድ መመልከቷን የክስ መዝገቡ ያስረዳል። ጉግል የሰዎችን ፊት መለየት የሚችል ካሜራ ይፋ አድርጓል። በአየር መንገዱ መመሪያ መሰረት በማንኛው ሰዓት ቢያንስ ሁለት የአየር መንገዱ ባልደረቦች የበረራ መቆጣጠሪያ ክፍል ውስጥ እንዲሆኑ ያዛል። አብራሪዎቹ እና ሳውዝዌስት አየር መንገድ የበረራ አስተናጋጆችን እና መንገደኞችን መጸዳጃ ቤት ውስጥ በድብቅ የሚቀርጽ ካሜራ አለመተከሉን ይናገራሉ። የበረራ አስተናጋጇ ሪኒ ስቲንከር ስለ ካሜራው ዋና አብራሪው ለማንም ሰው እንዳትናገር እንዳስጠነቀቃት ተናግራለች። ሪኒ ስቲንከር ስለ ጉዳዩ ለአየር መንገዱ ሪፖርት ብታደርግም የአየር መንገዱ አስተባባሪ ስለጉዳዩ ከማንም ጋር መነጋገር እንደማትችል እንደገለጸላት በክስ መዝገቡ ላይ ሰፍሯል። • ሁሉንም በደህንነት ካሜራ የምትመለከተው ቻይና ክስ የተመሰረተባቸው ሁለቱ አብራሪዎች ምንም አይነት እርምጃ ሳይወሰድባቸው በሥራቸው እንደቀጠሉበት ተነግሯል። አየር መንገዱ በአውሮፕላን መጸዳጃ ክፍል ውስጥ ድብቅ ካሜራ ተገጥሟል መባሉን ተከትሎ ባደረኩት ፍተሻ ተገጥሞ የተገኘ ድበቅ ካሜራ የለም ብሏል። "ካደረግነው ምረመራ ማረጋገጥ የቻልነው በመጸዳጃ ክፍሎች ውስጥ የተገጠመ ካሜራ አለመኖሩን ነው" ይላል የአየር መንገዱ ምላሽ። በክሱ ላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ የሚያስተላልፍበት ጊዜ እስካሁን አልተቆረጠም።
49750897
https://www.bbc.com/amharic/49750897
በአሜሪካ የ'ወሊድ ቱሪዝም' በማጧጧፍ የተከሰሰችው ቻይናዊት
ቱጃር ቻይናውያን ልጆቻቸውን አሜሪካ እንዲወልዱ በማመቻቸት የተከሰሰችው ቻይናዊት ጥፋተኛ መሆኗን አመነች።
የሚወለዱት ልጆች የአሜሪካ ዜግነት እንዲያገኙ፤ እናቶቻቸው ወደ አሜሪካ እንዲጓዙ ያመቻቸችው ቻይናዊት ዶንግዩአን ሊ፤ ክስ የተመሰረተባት አሜሪካ ውስጥ ነበር። 'የወሊድ ቱሪዝም' የሚል ስያሜ ባለው ሂደት፤ አንዲት ሴት ወደ አሜሪካ ሄዳ ለመውለድ ገንዘብ ትከፍላለች። ቻይናዊቷ ዶንግዩአን ያቋቋመችው ድርጅት በኃብት የናጠጡ ቻይናውያን ልጆቻቸው የአሜሪካ ዜግነት እንዲያገኙ ያመቻች ነበር። ዶንግዩአን፤ ሴቶቹ እርጉዝ መሆናቸው ሳይታወቅ የአሜሪካን ኢሚግሬሽን እንዴት ማለፍ እንደሚችሉ ስልጠና ትሰጥ ነበር። ለአገልግሎቷ በጠቅላላው ከሦስት ሚሊየን ዶላር በላይ ሰብስባለች ተብሏል። • ፀረ-መውለድ ፍልስፍናን ያውቁታል? • በጂንስ የተሞሸሩት ጥንዶች ጥቅምት ላይ በዶንግዩአን ጉዳይ ብይን የሚሰጥ ሲሆን፤ የ15 ዓመት እሥር መከናነቧ እንደማይቀር ተገምቷል። የ 'ወሊድ ቱሪዝም' ለምን? እንደ ጎርጎሮሳያውኑ ከ2013 እስከ 2015 ድረስ፤ ቻይናውያን እርጉዝ መሆናቸው ሳይታወቅ የአሜሪካን ኢሚግሬሽን ማለፍ የሚችሉበትን መንገድ ለማሰልጠን ከ40,000 እስከ 80,000 ዶላር ታስከፍል እንደነበረ ዶንግዩአን አምናለች። 'ዩ ዊን ዩኤስኤ ቫኬሽን ሰርቪስ' የተባለው ድርጅቷ የቻይና ባለሥልጣኖችን ጨምሮ ለብዙዎች አገልግሎቱን ሰጥቷል። የድርጅቱ ድረ ገጽ ላይ የሚገኘው ማስታወቂያ ወደ 500 የሚደርሱ ደንበኞቹ፤ "አሜሪካዊነት ከሁሉም አገሮች በበለጠ የሚያስደስት ዜግነት ነው" ማለታቸውን ይገልጻል። የዶንግዩአን፤ ደንበኞቿ መጀመሪያ ከቻይና ወደ ሀዋይ ከበረሩ በኋላ ወደ ሎስ አንጀለስ እንዲጓዙ ትመክር ነበር። የአሜሪካ ኢሚግሬሽንን በቀላሉ ለማለፍ መዳረሻን ሀዋይ ማድረግ የተሻለው አማራጭ ሲሆን፤ ደንበኞቿ ከሀዋይ ወደ ሎስ አንጀለስ ከበረሩ በኋላ አፓርትመንት ውስጥ ያርፋሉ። • ከተለያየ አባት የተወለዱት መንትዮች • በሻንጣ ውስጥ ተጉዞ ስፔን የደረሰው ልጅ አባት ከእስር ነፃ ሆነ ዶንግዩአን፤ ደንበኞቿ ለቻይና ኢሚግሬሽን ሠራተኞች፤ አሜሪካ ውስጥ ለሁለት ሳምንት ብቻ እንደሚቆዩ መንገር እንዳለባቸው ታሰለጥናቸው እንደነበርም አምናለች። ቻይናውያኑ ሴቶች ቢያንስ ለሦስት ወር አሜሪካ ውስጥ ይቆያሉ። ቻይናዊቷ ቪዛ በማጭበርበር የቀረበባትን ውንጀላ ከተቀበለች በኋላ፤ ወደ 850,000 ዶላር፣ 500,000 ዶላር የሚያወጣ ቤቷን እንዲሁም መርሴደስ ቤንዝ መኪኖቿን ለማስረከብ ተስማምታለች። የአሜሪካ ሕግ፤ አገሪቱን መጎብኘትና እዛው ሳሉ ልጅ መውለድን አይከለክልም። ሆኖም በሀሰተኛ መረጃ ቪዛ ማግኘት በሕግ ያስቀጣል። ዶንግዩአን፤ ቻይናውያን ሴቶች አሜሪካ ውስጥ ልጅ ቢወልዱ፤ ቤተሰቦቻቸው ለስደተኞች በወጣ ድንጋጌ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ በመግለጽ ድርጅቷን ታስተዋውቅ ነበር። የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሌሎች አገራት ዜጋ ከሆኑ ቤተሰቦች አሜሪካ ውስጥ ለሚወለዱ ልጆች የአሜሪካ ዜግንት የሚሰጥበትን አሠራር የማገድ እቅድ እንዳላቸው መናገራቸው ይታወሳል።
news-53704705
https://www.bbc.com/amharic/news-53704705
ፍርድ ቤት፡ የኦነግ አመራሮች፣ አባላት እና የኬንያዊው ጋዜጠኛ የፍርድ ቤት ውሎ
ከፍተኛ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮች እና አባላትን ጭምሮ ሌሎች ተጠርጣሪዎች ትናንት ዓርብ ነሐሴ 1 ቀን 2012 ዓ.ም. የሱሉልታ ከተማ የወረዳ ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ከተጠርጣሪ ጠበቆች መካከል አንዱ የሆኑት ቶኩማ ዳባ (ዶ/ር) ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ሚካኤል ቦረን፣ ጫልቱ ታከለ እና ኬኒያዊው ጋዜጠኛ ያሲን ጁማ ትናንት ፍርድ ቤት የቀረቡት በኮሎኔል ገመቹ አያና መዝገብ ሥር የተካተቱ 11 ተጠርጣሪዎች ናቸው። ከእነዚህም መካከል የኦነግ ከፍተኛ አመራሮች እና አማካሪዎች ኮሎኔል ገመቹ አያና፣ ሽጉጥ ገለታ (ዶ/ር)፣ ሚካኤል ቦረን እና ሌሎች የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ይገኙበታል። ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ፤ የሰው ነብስ እንዲጠፋ፣ በንብረት ላይ ጉዳት እንዲደርስ፣ መንግድ እንዲዘጋ እና የንግድ እንቅስቃሴ እንዲቆም አድርገዋል ሲል ጠርጥሬያቸዋለሁ ስለማለቱ ጠበቃው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሥማቸውን ከላይ የተጠቀሰው የኦነግ ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ሥር ከዋሉ አንድ ወር ቢያልፋቸውም፤ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን እና ከቤተሰብና ከጠበቆቻቸውም ጋር ግነኙነት እንዳልነበራቸው ጠበቃ ቶኩማ ተናግረዋል። ዐቃቤ ሕግ ፖሊስ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ሲያካሂድ የነበረውን ምርመራ ማጠናቀቁን አስታውቆ፤ የምርመራ መዝገቡ ተዘግቶ ተጠርጣሪዎቹ ወደ ማቆያ እንዲያመሩ መጠየቁን ጠበቃ ቶኩማ አሳውቀዋል። ፍርድ ቤቱ፤ ዐቃቤ ሕግ በ15 ቀናት ውስጥ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ክስ እንዲመሰረት፤ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ግን ክስ የማይመሰረት ከሆነ ተጠርጣሪዎቹ በተጠቀሰው ጊዜ ፍርድ ቤት መምጣት ሳያስፈልጋቸው ከእስር ይውጡ ብሎ በማዘዝ የመርመራ መዝገቡ መዘጋቱን ጠበቃው ለቢቢሲ ተናግረዋል። በትናንቱ የፍርድ ቤት ውሎ የተጠርጣሪ ጠበቆች ደንበኞቻቸውን ከዚህ በፊት አግኝተው እንደማያውቁ ለፍርድ ቤቱ በመናገር፤ ደንበኞቻቸው ተይዘው የሚገኙበት ሁኔታ መብታቸውን የሚጠብቅ አለመሆኑን እና ለችግር ተዳርገው እንደሚገኙ ለፍርድ ቤት አስረድተዋል። በተለይ የስኳር እና ደም ግፊት ሕመሞች ተጠቂ የሆኑ ተጠርጣሪዎች የሚወስዷቸውን መድሃኒቶች ሊያገኙ አለመቻላቸውን ጠበቃው ለፍርድ ቤት ማመልከታቸውን ተናግረዋል። ከተጠርጣሪዎች መካከል የኦነግ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ኮሎኔል ገመቹ አያና ታስረው የሚገኙበት ስፍራ በቂ የጸሃይ ብርሃን እንደሌለው እንዲሁም በቂ ምግብ እያገኙ አለመሆኑን በመጥቅስ ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርበዋል። ጠበቃው ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ፍርድ ቤቱ የታሳሪዎች አያያዝ መብት እንዲከበር፤ መድሃኒት የሚያስፈልጋቸውም መድሃኒት እንዲቀርብላቸው፣ ከቤተሰብ እና ከጠበቆቻቸው ጋር እንዲገናኙ ማዘዙን ተናግረዋል። በሌላ በኩል ጫልቱ ታከለ ትናንት የሱሉልታ ከተማ የወረዳ ፍርድ ቤት መቅረቧን ጠበቃው ለቢቢሲ ተናግረዋል። የኦነግ አባል የሆነችው ጫልቱ ታከለ ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በቁጥጥር ሥር ከዋለች በኋላ የአራዳው ምድብ ችሎት በ4 ሺህ ብር የዋስ መብት ከእስር እንድትወጣ ካዘዘ በኋላ፤ ጫልቱ ዳግም በኦሮሚያ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ውላ ወደ ሱሉልታ መወሰዷ ይታወሳል። በትናንቱ ውሎ መርማሪ ፖሊስ ጫልቱ ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ የጠየቀ ቢሆንም የሱሉልታ ከተማ የወረዳ ፍርድ ቤት ግን ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ውድቅ በማድረግ በከዚህ ቀደሙ የዋስትና መብት ከእስር ትውጣ በማለት ማዘዙን ጠበቃው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሌሎች በሱሉልታ ተይዘው የሚገኙት የኦነግ መካከለኛ አመራር የሆኑት ለሚ ቤኛ እና ዳዊት አብደታ በተለያዩ ምክንያቶች ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን ጠበቃው ተናግረዋል። በሌላ በኩል የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ችሎት ትናንት ነሐሴ 1 2012 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ፖሊስ የጠየቀውን ይግባኝ ውድቅ በማድረግ ኬኒያዊውን ጋዜጠኛ ያሲን ጁማ ጨምሮ 11 ሰዎች የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ከእስር ይለቀቁ ሲል መበየኑን የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ አቶ አብዱለጢፍ አሜ ኤሌሞ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጋዜጠኛ ያሲን ጁማን ጨምሮ 11 ተጠርጣሪዎች ሐምሌ 29 የዋስትና መብት ተፈቅዶላቸው የነበረ ቢሆንም ፖሊስ ይግባኝ በመጠየቅ ከእስር ሳይለቀቁ ቆይተው ነበር።
news-55401207
https://www.bbc.com/amharic/news-55401207
እያወዛገበ ያለውን የኢትዮጵያና የሱዳን ድንበር በጨረፍታ
ከአንድ ምዕተ ዓመት በላይ ሁለት አገሮችን ያወዛገበ ድንበር፤ ከፍ ያለ የእርሻ ልማትና ተያያዥ ኢንቨስትመንቶች የሚደምቁበት አካባቢ ነው።
በሁለቱም አገሮች የሚገኙ የአካባቢው ነዋሪ ድንበርተኞች የይገባናል ጥያቄን ያነሱበታል፡፡ ይህ ለረዥም ዘመን የዘለቀ ጉዳይ ነው። ለመሆኑ የኢትዮ-ሱዳን ድንበር መልክ ምን ይመስላል? ባለፈው ሳምንት በርካታ የሱዳን ወታደሮች ከኢትዮጵያ በኩል በተሰነዘረ የሚሊሻ ጥቃት መገደላቸው ተዘግቧል። ካርቱም ክስተቱን "የደፈጣ ጥቃት" ስትል ጠርታዋለች፤ ድርጊቱ የተፈጸመው በሚሊሻዎች እንደሆነ ተጠቅሷል። በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በኩል ክስተቱ ያልተስተባበለ ሲሆን "ድንበር ጥሰው በገቡ ኃይሎች ላይ የተወሰደ ራስን የመከላከል አስፈላጊ እርምጃ ነው" ብለውታል። እንዲህ ዓይነት የድንበርተኞች ግጭት በተደጋጋሚ በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ላይ ይከሰታል። ግጭቱ ቦታው የእኛ ነው በሚሉ ኢትዮጵያዊያን አራሽ ገበሬዎች እና "የለም አካባቢው የእኛ ነው" በሚሉ የሱዳን ጎረቤቶቻቸው መካከል የሚከሰት ነው። ይህ ክስተት የተሰማው ደግሞ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በትግራይ ክልል የተካሄደው ሕግን የማስከበር ወታደራዊ እርምጃ መጠናቀቁን በገለጹ ማግስት መሆኑ ነገሩን ላልተረጋገጡ ፖለቲካዊ ትርጓሜና መላምቶች አጋልጦታል። የፌዴራል መንግሥት ወታደሮች መቀለን መቆጣጠራቸው እንዲሁም ጦርነቱን ተከትሎ 50ሺህ ዜጎች ወደ ሱዳን መሰደዳቸው የቅርብ ሳምንት ትኩስ ክስተት ነው። የድንበር ግጭቱን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በትዊተር ሰሌዳቸው፤ "እንዲህ ዓይነቱ ክስተት በሁለቱ አገሮች ያለውን ጥብቅ ቁርኝት አይበጥሰውም፤ እኛ ሁልጊዜም ችግሮቻችንን በውይይት ነው የምንፈታው" ብለዋል። ሁለቱ አገሮች ዛሬ ማክሰኞ ይህን ለዘመናት ያልተፈታውን የድንበር ችግር በተመለከተ ንግግር ይጀምራሉ ተብሏል። ይህንንም የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ጽሕፈት ቤት እሑድ ዕለት ነው ቀደም ብሎ ያስታወቀው። ለመሆኑ ከዚህ ድንበር ጋር በተያያዘ ያለው ታሪክ ምንድነው? ኢትዮጵያና ሱዳን የሚጋሩት ድንበር ርዝመት 750 ኪሎ ሜትር ያካልላል። ነገር ግን ይህ ድንበር አብዛኛው ርቀት ግልጽ በሆነ መንገድ መሬት ላይ አልተመላከተም። ይህን ለማሳካት ተደጋጋሚ ንግግሮች ተጀምረው በተደጋጋሚ ተቋርጠዋል። አሁን ኢትዮጵያና ሱዳን ያሉበት አካባቢ ታሪካዊ ሁኔታዎች ከብሉ ናይል እና አትባራ ወንዞች ጋር በአንድም በሌላም መልኩ የተጋመዱ ናቸው። እነዚህ ወንዞች ሁለቱ ሕዝቦች በንግድና በሌሎች መልኮች እንዲገናኙ ለዘመናት ምክንያት ሆነው የቆዩ ናቸው። ነገር ግን ንግድ ብቻ ሳይሆን ለተከታታይ ግጭቶችም መነሻ ናቸው፡፡ በተለይም ድንበር ላይ ለሚነሱ ግጭቶች። በ19ኛው ክፍለ ዘመን የቅኝ ገዢዎች ያበጇቸው ድንበሮች ሱዳንን፣ ግብጽንና ሌሎች የሰሜን ምሥራቅ አፍሪካ አገራትን የአሁን ቅርጽና መልክ ፈጥረውላቸዋል። ዶ/ር ወንድወሰን ተሾመ የተባሉ ተመራማሪ፤ "የአፍሪካ ቅኝ ግዛት ዘመን ድንበሮች በተለይም የሱዳንና ኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ" በተሰኘና በእንግሊዝኛ በተጻፈ ጥናታቸው እንደገለጹት የሁለቱ አገሮች ድንበር የአሁን ጊዜ ወሰን እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ1902 እና በ1907 የተደረጉ የአንግሎ-ኢትዮጵያ የካርታ ላይ ምልከታ ስምምነቶችን መሠረት ያደረጉ ናቸው። በቅኝ ግዛት ወቅት በሱዳንና በኢትዮጵያ መሬት ላይ ለተመላከቱ ድንበሮች ኃላፊነቱ ተሰጥቶት የነበረው ሁነኛ ሰው የአይሪሽ ተጓዥና አሳሽ የነበረው ቻርለስ ግዊይን ነበር። የሱዳን ገዳሪፍና ብሉ ናይል ግዛቶች ከአማራ ክልል ጋር ይዋሰናሉ። በ1908 ነበር በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ድንበር የተሰመረው። መልካሙ ዜና በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያና በሱዳን መንግሥታት መካከል ይበል የሚያሰኝ ግንኙነት ነው ያለው፡፡ ይህም ማለት ሁኔታዎች ከመካረራቸው በፊት በንግግር የመፍታት ሰፊ ዕድል ይሰጣል። የቀድሞው የሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር በ2001 ዓ.ም አዲስ አበባን ሁለት ጊዜ ጎብኝተዋል። የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊም በቀጣዩ ዓመት፤ ማለትም በ2002 (እ.አ.አ) ካርቱምን ጎብኝተዋል። ይህም በሁለቱ አገሮች መካከል የነበረው ግንኙነት መልካም እንደነበረ አንድ ማሳያ ነበር፡፡ ይህ ግንኙነት አሁንም መልኩን አልቀየረም። ቀረብ ባለው ዘመንም ቢሆን በሚያዚያ 2012 የቀድሞው የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሐመድ በሱዳን ጉብኝት አድርገው ነበር። ባለፈው ግንቦት ወር ደግሞ የሱዳን የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ኦማር በሽር ማኒስ ወደ አዲስ አበባ ልኡክ ይዘው ሄደው ነበር። በኢትዮጵያ በኩል ደግሞ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሚመራ ቡድን ለንግግር ተቀምጦ ነበር። ይህ ውይይት በግንቦት 10/2012 ሲጠናቀቅ የድንበር ንግግሩ የወሰን ማካለሉን ጉዳይ ወደተሻለ ደረጃ ሊያደርስ፣ የአካባቢው ሕዝቦችን ዘላቂ ተጠቃሚ ሊያደርግ የሚችል ደረጃ መድረሱን አቶ ደመቀ ጠቅሰው ነበር። አርሶ አደሮች ያለስጋት ወደ ግብርናቸው እንዲመለሱ፣ ተገቢነት የሌላቸው እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙ ሁለቱ አገሮች መስማማታቸውም ያን ጊዜ ተገልጾ ነበር። የአልፋሽቃ ማዕዘን ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በይገባኛል የምትወዛገብብት አካባቢ ረዥም የግዛት ድንበር ነው ያላት። ሁለቱም አገሮች ለም ነው የሚባለውን ፋሽቃ አካባቢን እጅጉኑ ይፈልጉታል። ይህ በሁለቱ አገሮች ዓይን ውስጥ ያለው አካባቢ የአልፋሽቃ ማዕዘን ወይም የአልፋሽቃ ጥግ ተብሎ ይጠራል። በዚህ ድንበር ሁለቱም አቅጣጫ የሚገኙ ገበሬዎች ባሻገራቸው ያሉ ለም መሬቶች ላይ ያማትራሉ። አልፋሽቃ ማዕዘን በደቡብ ምሥራቅ ሱዳን ምሥራቃዊ ገዳሪፍ የሚገኝ ለም መሬት ነው። አልፋሽቃ መሬት 250 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሸፍንና 600 ሺህ ኤክር ለም መሬትን የሚሸፍን ነው። ለለምነቱ ምክንያት የሆኑት እንደ አትባራ፣ ሰቲት እና ባስላም ወንዞችም በቅርብ ይገኛሉ። የሱዳን ባለሥልጣናት አልፋሽቃ የሱዳን ግዛት ነው ይላሉ። አሁን በኢትዮጵያን እጅ ለምን ሆነ ሲባሉ፣ "የሱዳን መንግሥት ከአገሪቱ ጋር ባለው የትብብርና የመግባባት ስምምነት መንፈስ ነው የኢትዮጵያ ገበሬዎች ቦታውን አሁን እያለሙት ያሉት" ይላሉ። ሁለቱ መንግሥታት ከዚህ ቀደም ይህንን አወዛጋቢ ድንበር በድጋሚ ለማስመር፣ የጋራ ፕሮጀክቶችን ለመጀመር እና የአካባቢው ሕዝብ ተጠቃሚ ለማድረግ ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር። ቀደም ካለው አስተዳደር ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግሥት በአገሬው ሕዝብ ሉአላዊ መሬቱን ቆርሶ እየሰጠ ነው በሚል ተደጋጋሚ ወቀሳ ሲቀርብበት ነው የቆየው። እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2014 የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እና የወቅቱ ሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር ሐሰን አልበሽር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸውን ድንበሩ መሬት ላይ የሚመላከትበትን የመጨረሻ ቀን እንዲያሳውቁ መመርያ አስተላልፈውላቸው ነበር። ሆኖም አወዛጋቢውን ድንበር መሬት ላይ የማመላከቱ ሥራ እስከዛሬም አልተሳካም፡፡ ይህ ዛሬ የሚጀመረው ንግግርስ ለውዝግቡ የመጨረሻ እልባት ይሰጣል ወይ? የሚለው በጊዜ ሂደት የሚታይ ነው የሚሆነው።
51625454
https://www.bbc.com/amharic/51625454
የኮቢ ብራያንት ባለቤት የተከሰከሰው ሄሊኮፕተር ባለቤትን ከሰሰች
ባለፈው ወር በሄሊኮፕተር አደጋ ባለቤቷ እውቁ ኮቢ ብራያንትን እና የ13 ዓመት ሴት ልጇን ያጣችው ቫኔሳ ብራያንት፣ በሄሊኮፕተሩ ባለቤት ላይ የመሰረተችው ክስ ጭብጥ በመጥፎ የአየር ሁኔታ ለመብረር መወሰኑ የአብራሪውን ግድየለሽነት ያሳያል የሚል ነው።
የሄሊኮፕተሩ ባለቤት አይላንድ ኤክስፕረስ ሄሊኮፕተሮችና አብራሪዎች የተሰኘ ድርጅት ሲሆን፣ ፓይለቱ አራ ጆርጅ ዞባያን ማንኛውም ጠንቃቃ አብራሪ ሊያደርግ የሚገባውን ጥንቃቄ መውሰድ ነበረበት ይላል የቀረበው ክስ። ክሱ እንደሚለው በሄሊኮፕተሩ አደጋ ከኮቢ ብራያንት እና ልጁ ጋር የሞተው የሄሊኮፕተሩ አብራሪ ዞባያን ለበረራ ሲዘጋጅ የአየር ሁኔታ ትንታኔን ከግምት አላስገባም። አብራሪው ሁኔታዎች ከባድ ሆነው እያለም በራራውን ለማቋረጥ አልወሰነም፤ ለበረራው የይለፍ ፍቃድ የሰጠው አይላንድ ኤክስፕረስም ሄሊኮፕተሩ አስቻጋሪ በሆነ የአየር ሁኔታ እንደሚበር እያወቀ ፍቃድ ሰጥቷል ሲል ክሱ ያትታል። ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ለጊዜው የተቀመጠ የገንዘብ መጠን ባይኖርም ቫኔሳ ብራያንት ከኩባንያው ካሳና ኩባንያው በወንጀል እንዲቀጣም ትፈልጋለች። • ታዋቂው አሜሪካዊ ስፖርተኛ ከነልጁ በሄሊኮፕተር አደጋ ሞተ • 2019 የአውሮፕላን አደጋ ተጎጂዎች ቁጥር የቀነሰበት ነው ተባለ • ከ33 ዓመት በፊት የተዘረፈው ዘውድ ለጨለቆት ሥላሴ ቤተክርስቲያን እንደሚመለስ ተገለጸ ኮቢ እና ልጁን ይዞ የነበረው ሄሊኮፕተር ካላባሳስ ከተሰኘች ከተማ ከከፍታማ ቦታ ቁልቁል ወርዶ መከስከሱ ቀደም ሲል ተገልጿል። ሄሊኮፕተሩ በተነሳበት ወቅት የአየሩ ሁኔታ ጭጋጋማ ነበር። ምንም እንኳ የአየር ሁኔታው ከባድ የነበረ ቢሆንም ፓይለቱ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎችን ልዩ ፍቃድ በመጠየቅ እና ፍቃዱን በማግኘት መብረሩም ተገልጿል። አይላንድ ሄሊኮፕተርስ በአሁኑ ወቅት በረራ አቋርጧል። ትናንት በርካታ ሥመ ጥር ሰዎች በተገኙበት ኮቢ እና ልጁ ጊያና ተዘክረዋል። መርሃግብሩን ቢዮንሴ ብያንት ይወደው ነበር ባለችው ዜማዋ ጀምራለች። እንደ ማይክል ጆርዳን፣ ማጅክ ጆንሰን እና የብራያንት የቀድሞ ክለብ ጓደኛ የሆነው ሻኪል ኦኒል ያሉ የቅርጫት ኳስ ኮከቦች በዝግጅቱ ላይ ተገኝተዋል።
news-56439796
https://www.bbc.com/amharic/news-56439796
ትግራይ ፡ ግጭት የተካሄደባት የትግራይ ሁኔታ በጨረፍታ
የሽረ ከተማ በየዕለቱ ቁጥራቸው በርከት ያሉ ተፈናቃዮችን ታስተናግዳለች።
እናቷንና ሁለት እግሮቿን ያጣችው ህጻን ቤተልሔም ተስፋዬ ከእነዚህም መካከል ከሽረ 50 ኪሎ ሜትር ርቃ ከምትገኘው አክሱም የመጣችው የስድስት ዓመቷ ቤተልሔም ተስፋዬ አንዷ ናት። ቤተልሔም በግጭቱ እናቷንና ሁለት እግሮቿን አጥታለች። አባቷ የቋጠረውን ጥሪትም ለእሷ ማሳከሚያ አውጥቶ ጨርሷል። አሁን ለቤተልሔም ሰው ሰራሽ እግር እንዲደረግላት የሚያስችለውን ገንዘብ ከየት እንደሚያገኝ ጨንቆታል። ሽረ እንደ ሌሎቹ የትግራይ ከተሞች ሁሉ የግፍ ግድያዎችና አስገድዶ መድፈርን ጨምሮ ሌሎችም የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተፈጽመውበታል በሚባለው ግጭት ሳቢያ ለተፈናቀሉ በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች መጠለያ ሆናለች። ነገር ግን በማዕከላዊ ትግራይ የምትገኘውና የ170,000 ሰዎች መኖሪያ የሆነችው ሽረ፤ ተፈናቃዮቹን ለማስተናገድ ከአቅም በላይ ሆኖባታል። ባለፉት አራት ወራት ምንም አይነት ዝግጅት ወዳላደረገችው ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው ተሰዷል።. በከተማዋ ያሉ ትምህርት ቤቶችና የዩኒቨርስቲ ግቢዎች የሰዎች ሰቆቃ የሚሰማባቸው ማዕከላት ሆነዋል። ተፈናቃዮች የተጠለሉበት ትምህርት ቤት፤ ሽረ የእርዳታ ድርጅቶች በከተማዋ ውስጥ ባሉት ጊዜያዊ መጠለያዎች በአሁኑ ጊዜ 200,000 ያህል ሰዎች እንደሚገኙ ይገምታሉ። ብዙዎቹም ሴቶችና ህጻናት ናቸው። የመጀመሪያዎቹ ተፈናቃዮች የመጡት ጦርነቱ በተቀሰቀሰበት በኅዳር ወር ላይ ነበር። ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ በግጭቱ ጅማሬ ላይ የውጊያ ማዕከል ከነበሩት ከደቡብ ምዕራብ ትግራይ አካባቢዎች የመጡ ናቸው። ግጭቱ የተከሰተው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን እስኪመጡ ድረስ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የበላይ በነበረውና የትግራይ ክልልን ሲያስተዳድር በቆየው ህወሓት እና በፌደራል መንግሥቱ መካከል ለረጅም ጊዜ ሲብላላ በቆየው አለመግባባት ሰበብ ነበር። ትግራይ ውስጥ በሚገኘው የአገሪቱ ሠራዊት ላይ ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ሲያዙ ግጭቱ በተለያዩ ግንባሮች የተለያዩ ኃይሎችን አሰልፎ ነበር የተቀሰቀሰው። በደቡብና በደቡብ ምዕራብ ትግራይ በኩል የአጎራባች የአማራ ክልል ኃይሎች የፌደራል ሠራዊቱን በማገዝ ከህወሓት ኃይሎች ጋር በሚደረገው ውጊያ ውስጥ ተሳታፊ ሆኑ። የ65 ዓመቷ ወ/ሮ አፀደ መብርሃቶም በእነዚያ ቀናት የተመለከቷቸውን አሰቃቂ ሁኔታዎችን ያስታውሳሉ። ወ/ሮ አፀደ በሁለት ሴት ልጆቻቸውና በቤተሰቦቻቸው እየተደገፉ ዳንሻ ውስጥ ይኖሩ ነበር። በአሁኑ ጊዜ ግን ወ/ሮ አፀደ፣ ልጆቻቸው፣ የልጆቻቸው ባሎች እና የልጅ ልጆቻቸው የሚኖሩት ሽረ ውስጥ ከሚገኙ መጠለያዎች በአንዱ ነው። ወ/ሮ አፀደ መብርሃቶም ቤታቸውን ትተው ወዴት እንደሚሄዱ እንኳን ሳያውቁ ሲሸሹ በእጃቸው የነበራቸው በጣም ጥቂት ገንዘብ ነበር። አስፈላጊ ሲሆን በእግራቸው እየተጓዙ፣ ሲችሉ እንደእነሱ የተፈናቀሉ ሰዎችን ከልክ በላይ ጭነው የሚጓዙ አውቶብሶችና የጭነት ተሽከርካሪዎችን ተጠቅመዋል። "ማረፍ እንኳን አልቻልንም" ይላሉ ወ/ሮ አፀደ። በጉዟቸው ላይ በረሃብና በውሃ ጥም ተሰቃይተዋል። "ቁራሽ ዳቦ ለምነን ለልጆቹ እንሰጣለን፤ ኩባያ ተውሰን ልጆቹን ውሃ እናጠጣለን።" ይላሉ። በመንገዳቸው ላይ ያልተቀበሩ አስከሬኖችን በየቦታው ወዳድቀው መመልከታቸውን ይናገራሉ። ይህንንም ለመርሳት አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል። ደስተኛ ባይሆኑም በህይወት መቆየታቸውን እንደ ትልቅ ነገር የሚያዩት ወ/ሮ አፀደ "ጊዜ ይመጣል ይሄዳል። እኛ ባለመሞታችን እድለኞች ነን" ይላሉ። በመጠለያ ካምፑ ውስጥ የተወሰነ እርዳታ የሚሰጥ ቢሆንም ቢቂ እንዳልሆነ ተፈናቃዮቹ ይናገራሉ። ህወሓት ከሥልጣን ሲወገድ በፌደራል መንግሥቱ የተሾመው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እንደሚለው ከትግራይ ክልል ነዋሪ ውስጥ ከግማሽ በላይ ወይም አራት ሚሊዮን ያህል ሰዎች የእርዳታ ድጋፍ ይፈልጋሉ። ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች ደግሞ ተፈናቅለዋል። የአስተዳደሩ ቃልአቀባይ የሆኑት እቴነሽ ንጉሠ እንደሚሉት ለጋሾችና የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች በችግር ላይ ያለውን ሕዝብ ለመርዳት የሚያደርጉትን ጥረት የበለጠ ማጠናከር አለባቸው። በክልሉ ውስጥ ያልተገደበ የእርዳታ አቅርቦት መንገድ እንዲመቻች ዓለም አቀፋዊ ጥሪ ሲደረግ መቆየቱ ይታወሳል። "አሁን የእርዳታ ድርጅቶች ገብተው ድጋፍ እንዲያደርጉ ተፈቅዶላቸዋል። ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው" ይላሉ እቴነሽ ቀደም ሲል የህወሓት መሪዎች መቀመጫ በነበረውና ከዕምነ በረድ ከተገነባው ህንጻ ፊት ለፊት ቆመው። "በመንግሥት ከሚቀርበው እርዳታ በተጨማሪ የእርዳታ ድርጅቶች ሕዝቡን ለመታደግ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉልን እንጠብቃለን።" ብለዋል ቃል አቀባይዋ። ለተብርሐን አሰፋ ሽረ 450 ኪሎ ሜትር ርቃ ከምትገኘውና ኢትዮጵያ ከሱዳንና ከኤርትራ ጋር ከምትዋሰንባት ትንሽ ከተማ ሁመራ ነው የመጣችው። ግጭቱ ከመጀመሩ በፊት ልጇ በቀዶ ህክምና ወልዳ ተኝታ ነበር። መኖሪያቸውን ጥለው ሲሰደዱ እናት አራስ ልጇንና አዲስ የተወለደውን ጨቅላ መንከባከብ ነበረባት። ሽረ መጠለያ ውስጥ ከገቡ በኋላ ደህንነት ቢሰማቸውም የሚያስፈልጋቸውን ነገር ግን እያገኙ እንዳልሆነ ትናገራለች። በመጠለያው ያለው ሁኔታ አስቸጋሪ ቢሆንም አሁንም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተጨናነቁ አውቶብሶች፣ የጭነት መኪኖችና በፈረስ ጋሪ እየተጓዙ ወደ ሽረ እየመጡ ነው። ለዚህም ምክንያቱ ምንም እንኳን የፌደራል መንግሥቱ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ አብዛኛውን የትግራይ ክልል አካባቢዎችን መቆጣጠሩን ቢገልጽም፤ በአንዳንድ አካባቢዎች አልፎ አልፎ ውጊያዎች እንዳሉ ስለሚነገር የደኅንነት ሁኔታው አሁንም ድረስ ሙሉ ለሙሉ አስተማማኝ ባለመሆኑ ነው። በክልሉ ላይ የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አሁንም ተግባራዊ ሲሆን፤ ከምሽት እስከ ንጋት የሚቆይ የሠዓት እላፊ ገደብ አለ። በመንገዶች ላይ በርካታ የፍተሻ ኬላዎችም ይገኛሉ። የተደረገው ወታደራዊ ግጭት የተቋጨ ቢመስልም ያስከተለው ቁስል ግን እስኪሽር ድረስ ዓመታትን ሊወስድ ይችላል። ለአንዳንዶች ደግሞ ጠባሳው እስከመጨረሻው አብሯቸው የሚኖር ይሆናል።
news-53879111
https://www.bbc.com/amharic/news-53879111
አሜሪካ፡ በዘረ መል ምህንድስና የተሻሳሉ 750 ሚሊዮን ትንኞችን ልትለቅ ነው
በአሜሪካ፣ ፍሎሪዳ ግዛት በዘረ መል ምህንድስና የተሻሻሉ 750 ሚሊዮን ትንኞች እንዲለቀቁ ባለስልጣናቱ ፍቃድ ሰጥተዋል።
የተሻሻሉት ትንኞች በአየር ላይ የሚለቀቁት በሽታን የሚያስተላልፉ ተፈጥሯዊ ትንኞች ቁጥርንም ለመቀነስ ነው ተብሏል። ከነዚህም መካከል የደንጊ፣ የወባና፣ ዚካ ቫይረስ የሚያስተላልፉ ትንኞች ይገኙበታል። ፕሮጀክቱ የተጠነሰሰው ከአመታት በፊት ቢሆን በርካታ የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋቾች ያልተጠበቀ አደጋ ሊያስከትል ይችላል በሚልም ሽንጣቸውን ገትረው በመከራከራቸው ከመተግበር ዘግይቶ ነበር። አንደኛው ቡድንም በህዝቡ ላይ ጁራሲክ ፓርክን መፍጠር ነው ብሎታል። (በስቲቨን ስፒልበርግ የተሰራው ጁራሲክ ፓርክ ፊልም ዳይኖሰሮች ብቻ የሚኖሩበት ደሴትን ሊጎበኙ የሄዱ ሳይንቲስቶችን ታሪክ ያስቃኛል)። ፕሮጀክቱ ፈቃድ ቢያገኝም የከባቢ ጥበቃ መብት ተሟጋቾች አሁንም ቢሆን ተፈጥሮን ሊያዛባ ይችላል እያሉም እያስጠነቀቁ ነው። ለምሳሌም ያህል በዘረ መል ምህንድስና ከተሻሻሉት ትንኞችና የተፈጥሮ ትንኞች ቢዳቀሉ የሚፈጠሩት ትንኞችና ፀረ ተባይን የሚቋቋሙ ትንኞች መሆናቸው ከሚያነሷቸው ስጋቶች መካከል ይገኙበታል። ይህንን የሚቃወሙ ሰዎችም ተግባራዊ መሆን የለበትም በሚልም 240 ሺህ ፊርማን አሳባስበዋል። ሆኖም ፕሮጅክቱን የሰራው በእንግሊዝ ተቀማጭነቱን ያደረገው ኦክዚቴክ ኩባንያም ለአከባቢም ሆነ ለሰው ልጅ ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት የለውም፤ ፕሮጀክቱም ሲጀመር በመንግሥት ድጋፍ የተደረገባቸውን በርካታ ጥናቶች ተከናውነዋልም ብሏል። ትንኞቹም በሚቀጥለው አመት ለሁለት አመታት በሚፈጅ ጊዜ በፍሎሪዳና አቅራቢያው ባሉ ደሴቶች ይለቀቃሉ ተብሏል። በዚሁ አመት ግንቦት ወር የአሜሪካ አካባቢ ጥበቃ ኤጀንሲ ለኦክዚቴክ ኩባንያ 'አደስ አጀብቲ' የሚል መጠሪያ ያላቸውን ትንኞችን በዘረ መል ምህንድስና እንዲያሻሽላቸው ፈቃድ የሰጠው። አደስ አጀብቲ የተባሉት ትንኞች የወባ በሽታን ጨምሮ፣ ዚካ፣ ደንጊ፣ ቺኩንጉንያን የመሳሰሉ አደገኛ በሽታዎችን በማስተላለፍ ይታወቃሉ። እነዚህን በሽታ የሚያስተላልፉት ሴት ትንኞች የሰውን ልጅ በመንደፍ ሲሆን እንቁላል ለማምረት ደም ስለሚያስፈልጋቸው ነው። እቅዱም ወንድ ትንኞችን በዘር መል ምህንድስና በማሻሸል ከሴት ትንኞች ጋር እንዲራቡ ማስቻል ነው። ሆኖም ወንድ ትንኞች ፅንሱ ከማደጉ በፊት በእንጭጩ የሚገድል ፕሮቲን ያመርታሉ። ሆነም ቀረም የነዚህን ትንኞች ቁጥር በመቀነስ ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎችን መግታት ነው። ኦክዚቴክ በድረገፁ እንዳሰፈረው በብራዚል ባካሄዱት ሙከራ አመርቂ ውጤት ማሳየታቸውን ነው።
50922706
https://www.bbc.com/amharic/50922706
ዶናልድ ትራምፕን ከዝነኛው ፊልም ማን ቆርጦ ጣላቸው?
በፈረንጆች ገና ዙርያ ከሚያጠነጥኑና በሚሊዮኖች ዘንድ ከማይረሱ ፊልሞች አንዱ 'ሆም አሎን' የተሰኘው ፊልም ነው። ፊልሙ የ8 ዓመት ሕጻን በቤተሰቦቹ ተዘንግቶ ለብቻው በፍርሃት ውስጥ ሆኖ የቆየባቸውን ቀናት የሚተርክ ነው።
ትራምፕ ጎልማሳ ሳሉ ሆም አሎን ላይ ተውነዋል ታዲያ በዚህ ሆም አሎን 2 በተሰኘው ፊልም ላይ የአሁኑ አወዛጋቢ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ይተውኑበት ነበር። ትራምፕ የአገር ቤት ፊልም ጥበበኞች አስተኔ ገጸ ባሕሪ የሚሉትና ፈረንጆቹ (cameo appearance) ብለው የሚጠሩት በአንድ ፊልም ላይ ውልብ ብሎ የመታየት ያህል ኢምንት ሚና ያለው ቦታ ነበራቸው። ታዲያ የካናዳው ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሲቢሲ ይህን ፊልም ከሰሞኑ ሲያስተዋውቅ እርሳቸው የሚታዩበት ቦታ ላይ ቆረጥ ሳያደርጋቸው አልቀረም። • "አሜሪካ ምኞቷ ሞላላት"፡ ዶናልድ ትራምፕ • ዶናልድ ትራምፕ ተከሰሱ • ኢቫንካ ትራምፕ አዲስ አበባ ናቸው የጣቢያው ቃል አቀባይ ቸክ ቶምሰን እንደሚሉት 120 ደቂቃዎች በሚረዝመው ፊልም 8 ደቂቃ ያህሉ ተቆርጦ ወጥቷል። ይህ የተደረገው ግን ዛሬ ሳይሆን በፈረንጆቹ 2014 ነው። ያን ጊዜ ደግሞ ትራምፕ ገና ወደ ሥልጣንም አልመጡም ብለዋል። ዶናልድ ትራምፕ ተቆርጠው አልተጣሉም፤ የፖለቲካ ትርጉም ሊሰጠውም አይገባም ብለዋል። ይህ አርትኦት የተሠራበት ፊልም በያዝነው የፈረንጆች የመጨረሻ ወር ላይ ለዕይታ ቀርቧል። ሆኖም የትራምፕ አድናቂዎች የካናዳ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያን ሲወርዱበት ነው የከረሙት። የትራምፕ የበኩር ልጅ ትራምፕ ጁኒየር ትናንት ሐሙስ ለት በትዊተር ሰሌዳው ላይ ድርጊቱን "ቀሽም" ሲል አውግዞታል። በትንሽ በትልቁ አወዛጋቢ አስተያት በመስጠት የሚታወቁት ትራምፕ በበኩላቸው ሐሙስ በድርጊቱ ተሳልቀዋል። "እኔ የሌለሁበት ሆም አሎን ፊልም መቼም አይጥምም" ሲሉ። ከዚህም አልፈው ከካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር የነበራቸውን አለመግባባት መዘው በማውጣት ለማሾፍ ሞክረዋል። የርሳቸው ሚና በፊልሙ ከተቆረጠ በኋላ ትራምፕ እንዲህ ጽፈዋል። "ይሄ ጀስቲን ቲ ለናቶና ለንግድ ገንዘብ ስላስከፈልኩት (የተወንኩበትን ክፍል እየቆረጠ) እየተበቀለኝ ሳይሆን አይቀርም" ትራምፕ ከሰሞኑ በጉዳዩ ላይ ዘርዘር ያለ አስተያየት ሲሰጡ እንዲህ ብለዋል። "እውነት ነው ሆም አሎን 2 ላይ ተውናለሁ። በየዓመቱ ብዙ ሰዎች ይህን ነገር ያነሱታል። በተለይ በክሪስማስ ሰሞን። በተለይ ትንንሽ ልጆች ሲያገኙኝ በፊልም አውቅኻለሁ ይሉኛል። እነሱ በፊልም እንደሚያውቁኝ በቴሌቪዥን አያውቁኝም" ትራምፕ ይቀጥላሉ፦ "ነገር ግን ፊልሙ ምርጥ ፊልም ነበር። ያን ጊዜ ወጣት ነበርኩ። በዚያ ፊልም ላይ በመታየቴ ኩራት ይሰማኛል" ትራምፕ አስተኔ ገጸ ባሕሪ (የውልብታ ሚና) ባላቸው ፊልሞች ሲተውኑ ሆም አሎን 2 ብቸኛው አይደለም። 'ዙላንደ'ር እና 'ጎስትስ ካንት ዱ ኢት' በተሰኙ ሌሎች ፊልሞችም ውልብ ብለው የመጥፋት ያህል ይተውናሉ። በዚህ ሆም አሎን 2 ፊልም ላይ ትራምፕ በኒውዮርክ ፕላዛ ሆቴል ትንሹን ልጅ (ዋና ገጸ ባሕሪውን) አቅጣጫ ሲያመላክቱት ይታያሉ። ፊልሙ በሚቀረጽበት በዚያ ዘመን ትራምፕ የሆቴሉ ባለቤት ነበሩ።
41573566
https://www.bbc.com/amharic/41573566
ህወሓትና የትግራይ ወጣቶች፡ ሆድና ጀርባ?
ከሰባት ቀናት በኋላ ሰኞ አመሻሹ ላይ መግለጫ የሰጠው ማዕከላዊ ኮሚቴው፤ በጥልቀት መታደሱን፣ የህዝብ ጥያቄ እየመለሰ መሆኑን እና ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር የነበረውን ግንኙነት ማሻሻሉን በድል አድራጊነት ይገልፃል።
ከህወሓት 12ኛ ጉባኤ ላይ የተወሰደ ፎቶ የፓርቲው ልሳን በሆነው ወይን መፅሔት፤ ሐምሌ-ነሐሴ በወጣው እትም ላይ "ከአሁን በኋላ ፓርቲያችንን ከአደጋ ለመታደግ ሰፊ ጊዜና ዕድል የለንም" በማለት ፓርቲው አብዮታዊ መገለጫዎቹን ሊያጣ እንደሚችልና የትግራይ ህዝብ በተለይም ደግሞ ወጣቱ ተስፋ ሊቆርጥበት እንደሚችል ስጋቱን ገልፆ ነበር። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አባዱላ ገመዳ በፈቃዳቸው ስልጣን እለቃለሁ ማለታቸውን ጨምሮ፤ በክልሎች መካከል የሚፈጠር ግጭት እየተባባሰ በሄደበት በአሁኑ ወቅት፤ የገዢው ፓርቲ መስራች ድርጅት የሚያካሂደው ስብሰባ የትግራይ ወጣቶችን ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያዊ ትኩረትን ይስብ ነበር፤ ይላሉ የሃገሪቱ ፖለቲካ ታዛቢዎች። ለየቅል ታድያ የፓርቲው ስብሰባ የትግራይ ህዝብን በተለይ ደግሞ የወጣቶችን ትኩረት ያጣበት ምክንያት ምን ይሆን? ፓርቲውን የሚያሰጋው ተስፋ መቁረጥ ላለመፈጠሩስ ምን ዋስትና ይኖራል? ቢቢሲ በፌስቡክ ገፁ ላይ ወጣቶችን "ከስብሰባው ምን ትጠብቃላችሁ?" በማለት ጥያቄ አቅርቦ ነበር። ከመቶ በላይ ሰዎች አስተያየታቸውን ያስቀመጡ ሲሆን፤ 95 በመቶዎቹ የሚጠብቁት አዲስ ነገር እንደሌለ ሲገልፁ ጥያቄውን ማቅረባችንን ራሱ የተቹም ነበሩ። በርግጥ ጥቂቶቹም ፓርቲው ስብሰባውን በድል እንደሚያጠቃልል ገልፀዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌደራሊዝም ትምህርት ተቋም መምህር ናሁሰናይ በላይ "የፓርቲው ስብሰባ ሚስጢራዊነት የበዛበትና ዝግ ቢሆንም፤ ቀድም ሲል አንዳንድ መረጃዎች ይወጡና አነጋጋሪ ይሆኑ ነበር" ይላል። "ዛሬ ግን ያገኘነው መረጃ የለም" ይላል። ተስፋኪሮስ አረፈ በፌስቡክ ከሚፅፉና ከሚቀሰቅሱ ታዋቂ ወጣቶች መካከል አንዱ ነው። "የማሌሊት አስተሳሰብ እስካልጠፋ ድርጅቱ አይታደስም" በሚል በተደጋጋሚ አቋሙን ያንፀባርቃል። "ይህም አዲስ ነገር የለውም፤ የወጣቱና የፓርቲው አጀንዳዎች ተለያይተዋል" ሲል ሃሳቡን ይገልፃል። "ከአሁን በኋላ ማን መጣ፤ ማንስ ሄደ የሚለው አያስጨንቀኝም። ጭራሽ መርሳት ነው ያለብን" ይላል ለውጥ እንደማይመጣ ተስፋ በመቁረጥ። "ነገሩ የወንበራቸው ጉዳይ ይመስለኛል። የውስጣቸው አጀንዳ እንጂ የህዝብ ጉዳይ እያስጨነቃቸው አይመስልም።" "ምን ሊያጣላቸው እንደሚችል ቀደም ብለው ነግረውናል። ጉዳያቸው የግል ጥቅምና የስልጣን ቆይታቸው ነው" የሚለው ደሞ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር መሓሪ ዮሃንስ ነው። ፓርቲውን በመተቸት የሚታወቀው መሓሪ "ድርጅቱ ምን አጀንዳ ላይ ይወያይ እንደነበር አላወቅኩም" ይላል። ለማወቅም ብዙ ጉጉት እንደሌለውም ይናገራል። "ለትግራይ ህዝብ የሚበጅ ነገር እንደማይገኝበት አውቃለሁ። በክልሉም ሆነ በሃገሪቱ ስላለው መሠረታዊ ችግር መረዳት አልቻሉም። መሠረታዊ መፍትሔ ማምጣትም አይችሉም" ይላል መሓሪ። እሱ እንደሚለው ወጣቶች የሚያቀርቡት ጥያቄ በህወሓት ዘንድ ቀልድ ነው። አልያም የጤና አይደለም። በተለይ ስለ ፍትሕና አስተዳደር፣ ሰላምም ጦርነትም የሌለበት ሁኔታ፣ የልማት እጦት፣ ስለ ዴሞክራሲ ጥያቄ የሚያነሳ እንደጠላት ነው የሚቆጠረው። አሉላ ሰለሞን በዋሺንግተን የሚኖር የኮሚዩኒቲ መሪ ነው። በማህበራዊ ገፆች በንቃት የሚሳተፍ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ፓርቲውን ደግፎ በሚያቀርባቸው ፅሑፎቹ ይታወቃል። አሉላ የወጣቱን ተስፋ መቁረጥ ውድቅ አላደረገም። "በአጠቃላይ በስብሰባው ውስጥ ምን እየተካሄደ እንደሆነ የመረጃ እጥረት አለ" ይላል። "ከዚህ ጋር በተያያዘ መታየት ያለበት ግን በፌደራል ደረጃ ያለውን ሁኔታ ለመለወጥ የኢህአዴግ በተለይም ደግሞ የህወሓት አቅም ውስንነት አለ" ሲልም ሃሳቡን ይሰጣል። የፓርቲው ልሳን "አብዮታዊና ዴሞክራሲያዊ መገለጫዎቻችን እየተሸረሸሩ፤ የግል ጥቅሞቻችንን ለማሟላት ስንሯሯጥ ነው ፓርቲያችን ስጋት ላይ የሚወድቀውና በጥርጣሬ የተሞላው" ይልና፤ ቀጥሎም በተለይ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚንቀሳቀሱ ወጣቶች "ከጥፋት ሃይሎች" ጋር በመተባበር እየሰሩ እንደሆነ ይገልፃል። "ውጤቱም የርዕዮተ-ዓለም ጉዳይ አይደለም፤ በተግባር እየተጀመረ ያለ የጥፋት መንገድ ነው" በማለት ያስቀምጣል። ከህወሓት 12ኛ ጉባኤ ላይ የተወሰደ ፎቶ "ስራውን ጨርሷል" አሉላ ስብሰባው የወጣቱን ትኩረት ያልሳበበት ምክንያት የመረጃ እጥረት በመኖሩ ነው ይበል እንጂ፤ ናሑሰናይ ግን ዋናው ምክንያት ሌላ እንደሆነ ይሞግታል። ከሁለት ዓመት በፊት በተካሄደው 12ኛው ጉባኤ ላይ "ከውስጥም ከውጭም የተፈጠረው ተፅዕኖ የት ገባ?" በማለት ናሁሰናይ ይጠይቃል። ሂደቱን አድንቆ በውጤቱ ግን የወጣቱን ተስፋ ለመጨረሻ ጊዜ ያስቆረጠ አጋጣሚ እንደነበር ይናገራል። "በመጨረሻም እንደወትሮው ነው የሆነው። ትልቅ ያመለጠ ዕድል አድርጌ እቆጥረዋለሁ" ይላል። አረና (መድረክ) እና ኋላ ላይ ድርጅቱን የተቀላቀለው አብርሃ ደስታ እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያ በትኩረት ድርጅቱን ሲተቹ የነበሩ ወጣቶች ለዚህ መነቃቀትና ተስፋ አድርሰውት ነበር። "በቃ ድርጅቱ አልቻለም፤ ሌላው ቀርቶ የቁርጥ ቀን ደጋፊ የሚባለው እንኳን ፀጥ ብሏል" በማለት ድርጅቱ ማህበራዊ መሠረቱን እያጣ ስለመሆኑ አመላካች ነው ይላል ናሁሰናይ። የኢህአዴግ ዋና መስራችና በሃሳብ አመንጪነት የሚታወቀው ህወሓት፤ ምናልባት የሊቀመንበሩ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የመለስ ዜናዊ ድንገተኛ ህልፈት ከፈጠረበት መደናገር የወጣ አይመስልም። ህወሓት አገራዊ ሚናውንም በዚያው ልክ እየተወጣ አይደለም የሚለው ናሁሰናይ፤ የመሪነት ቁመናውን በሌሎች ምናልባትም በኦህዴድ ሊወሰድ እንደሚችል ይገምታል። መገማገምና መነቃቀፍ የድርጅቱ ባህሪ ነበር። አሁን አሁን ግን የፍትህ እጦት፣ የመልካም አስተዳደር ችግር እየበዛ በመጣ ቁጥር የድርጅቱ ህዝባዊነት እየተሸረሸረ፤ የታገለለትን ዓላማ እየዘነጋ መምጣቱ ይነገራል። በእርግጥ ድርጅቱም "በውስጣችን ያለው የዛገ ነገር መቀየር አለበት" በማለት በልሳኑ ላይ አምኗል። "ትግራይ ውስጥ ያለው የመልካም አስተዳደርና የፍትህ እጦት ከሌላ አካባቢ የባሰ እንጂ የተሻለ አይደለም" የሚለው መሓሪ፥ ነጻ ሚድያና ተቃዋሚዎች፥ ህዝቡንና ድርጅቱን የአለመለየት ችግር እንዳለባቸው ይናገራል። አሉላ እንደሚለው፤ ህወሓት እንደ ሌሎች እህት ድርጅቶች የመተካካትና አዲስ አመራር የመፍጠር ሥራ አልሰራም የሚል ስሜት ወጣቱ እንዳለው ይቀበላል።
news-54486905
https://www.bbc.com/amharic/news-54486905
የስፔኗ ካናሪ ደሴት በርካታ የምዕራብ አፍሪካ ስደተኞች እየጎረፉባት ነው ተባለ
በርካታ የምዕራብ አፍሪካ አገራት ስደተኞች ወደ ስፔኗ ካናሪ ደሴቶች እየጎረፉ እንደሆነ ቀይ መስቀል አስታውቋል።
በባለፉት አርባ ስምንት ሰዓትም 1 ሺህ ስደቶች መድረሳቸውን ያስታወቀው የቀይ መስቀል መረጃ በአስር አመታት ውስጥ ያልታየ ቁጥርም ነው ተብሏል። በደሴቲቷ ጉብኝት ያደረጉት የስፔን የስደተኞች ሚኒስትር ጆሴ ሉይስ ኤስክሪቫ "የተቀናጀ ምላሽ እንሰጣለን" በማለትም ቃል ገብተዋል። ከምዕራብ አፍሪካ አገሮች አንስቶ ደሴቲቱ የሚያደርሰው መስመርም ከ2018 ጀምሮ እውቅናን አትርፏል። ከዚህ ቀደምም ከፍተኛ የስደተኞች ቁጥር የታየው በጎሮጎሳውያኑ 2006 ሲሆን 35 ሺህ የሚቆጠሩ ስደተኞች በስፔን የባህር ዳርቻ ደሴቶች ላይ መድረሳቸውን የተባበሩት መንግሥታት አስታውቋል። ከምዕራብ አፍሪካዋ ሴኔጋል የተነሱት በርካታ ስደተኞችም ከ1 ሺህ 600 ኪሎ ሜትር በላይ በውሃ መጓዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን በዚህ ሳምንትም 186 ሰዎች የተሳፈሩባቸው ሁለት ጀልባዎች በሴኔጋል የባህር ኃይል መያዛቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል። በነዚህ ሁለት ቀናት የደረሱት ስደተኞችም ከሴኔጋልና ከጋምቢያ መሆናቸውም ተገልጿል። ስደተኞቹ በ37 ጀልባዎችም ወደ ደሴቲቷ መድረሳቸውንም የስፔን የዜና ወኪል ኢፌኢ ዘግቧል። የስፔን የቀይ መስቀልም ጊዜያዊ መጠለያ በማዘጋጀት እንክብካቤም እያደረገላቸው ይገኛል። የቀይ መስቀል ቃለ አቀባይ ለኤኤፍፒ እንደተናገሩት አንዳንድ ቀለል ካለ በሽታ በስተቀር ሁሉም በሙሉ ጤንነት ላይ የሚገኙ እንደሆኑና የኮሮናቫይረስ ምርመራም ተደርጎላቸዋል ብለዋል። የስደተኞቹ ሚኒስትር ሁኔታውን ለመረዳት ሶስቱን ዋነኛ የስፔን ደሴቶችን ጎብኝተዋል። ሆኖም ስደተኞቹ በቋሚነት የሚኖሩበትን ቤት አላመቻቹም በሚልም የምክር ቤት አባሉ ብላስ አኮስታ መተቸታቸውን ኤልሙንዶ ጋዜጣ ዘግቧል። ከጥር እስከ ሃምሌ ባሉት ወራት 3 ሺህ 269 ስደተኞች ከምዕራብ አፍሪካ ተነስተው ካናሪ ደሴቶች የደረሱ ሲሆን ይህም ቁጥር በዚሁ ወቅት ከነበረው ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር 600 በመቶ መጨመሩን አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይ ኦ ኤም) አስታውቋል። በዚህ አመትም ደሴቶቹ ለመድረስ ሲሉ የ250 ሰዎች ህይወት መቀጠፉንም እንዲሁ አይ ኦ ኤም አክሎ ገልጿል።
news-45917870
https://www.bbc.com/amharic/news-45917870
ፖሊስ: አብዲ ሞሐመድ ዑመር ከእስር ቤት ለማምለጥ ሞክረዋል
የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሐመድ ከእስር ቤት ለማምለጥ ሙከራ አድርገዋል ሲል ፖሊስ ለፍርድ ቤት ተናገረ።
አቶ አብዲ ዛሬ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቀጠሯቸው መሰረት በቀረቡበት ወቅት ፖሊስ የታሰሩበትን ቢሮ መስታወት በመስበርና የጥበቃ አባልን በማነቅ ለማምለጥ ሙከራ አድርገዋል ሲል ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል። አቶ አብዲ በበኩላቸው ድርጊቱን እንዳልፈጸሙ እና ሆን ተብሎ ስማቸውን ለማጥፋት የተደረገ ሴራ ነው ብለዋል። • አብዲ ሞሃመድ ያለመከሰስ መብታቸው ተገፈፈ • አብዲ ሞሃመድ ኡመር በቁጥጥር ስር ዋሉ • በ96 ሰዎች ግድያ የ'ሄጎ' ቡድን አባላት እጅ አለበት፡ ፖሊስ አቶ አብዲ ጨምረውም ምቹ ባልሆነ እስር ቤት መታሰራቸውን፣ የአዕምሮ ህመምተኛ የሆነ ታራሚ የታሰሩበትን ክፍል በር ገንጥሎ በመግባት ሁለት ቀን ጉዳት ሊያደርስባቸው እንደሞከረና ይህም በደህንነቴ ላይ ስጋት ፈጥሮብኛል በማለት ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዱ ኢቲቪ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን ጠቅሶ ዘግቧል። ፖሊስ በአቶ አብዲ መሐመድ የክስ መዝገብ ተጨማሪ መረጃ ለማሰባሰብ የ10 ቀናት የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን የጠየቀ ሲሆን፤ ፍርድ ቤቱም ፖሊስ የምርመራውን ውጤት ለጥቅምት 19 ቀን 2011 ዓ.ም. ይዞ እንዲቀርብ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
news-55177235
https://www.bbc.com/amharic/news-55177235
መረጃ ሰርሳሪዎች የኮቪድ-19 ክትባት ዝውውርን ለማደናቀፍ አሲረዋል?
ዓለም አቀፉ የኮቪድ-19 ክትባት ዝውውር መስመር በኮምፒውተር መረጃ ሰርሳሪዎች ኢላማ መደረጉን የአሜሪካው ግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋም አይቢኤም አስታውቋል።
ኢላማ የተደረገው ክትባቶች ሲጓጓዙ በቀዝቃዛ ቦታ እንዲቀመጡ የሚያስችለው መሣሪያ ነው። መረጃ ሰርሳሪዎቹ እነማን እንደሆኑ ባይታወቅም፤ ለምዝበራ የተጠቀሙት መንገድ የተራቀቀ መሆኑ ምናልባትም ከምዝበራው ጀርባ ያሉት አገራት ሊሆኑ እንደሚችሉ አመላክቷል። ዩናይትድ ኪንግደምን ጨምሮ የተለያዩ አገሮች የኮቪድ-19 ክትባት ምርምር በመረጃ ሰርሳሪዎች ኢላማ ተደርጓል ብለው ማስጠንቀቂያ መስጠታቸው ይታወሳል። የተጭበረበሩ ኢሜሎች አይቢኤም እንደሚለው፤ መረጃ ሰርሳሪዎቹ እንቅስቃሴ የጀመሩት መስከረም ላይ ነው። ሐሰተኛ ኢሜሎች በስድስት አገሮች ለሚገኙ ተቋሞች ተልከዋል። ተቋሞቹ ጋቪ በመባል ከሚታወቀው ዓለም አቀፍ የክትባት አምራቾች ጥምረት ጋር ትስስር ያላቸው ናቸው። ከጥምረቱ አባሎች መካከል የዓለም ጤና ድርጅት፣ ዩኒሴፍ፣ የዓለም ባንክ እንዲሁም የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ይገኝበታል። እነዚህ ድርጅቶች ክትባት በድሃ አገሮች እንዲደርስ የሚሠሩ ናቸው። ክትባቶች ሳይበላሹ ከቦታ ቦታ እንዲጓጓዙ ለማስቻል ‘ኮልድ ቼን’ የተባለ ቀዝቃዛ መሣሪያ እንዲሁም ሂደት አለ። መረጃ መዝባሪዎች ኢላማ ያደረጉትም ይህንን ነው። የመረጃ ሰርሳሪዎቹ መረብ የፋይዘር እና ባዮቴክ ክትባቶች ሲጓጓዙ ከዜሮ በታች በ70 ሴንቲ ግሬድ መቀመጥ አለባቸው። መረጃ ሰርሳሪዎቹ ኢሜል የሚልኩት አንድ የቻይና የንግድ ተቋም ዋና ኃላፊን አስመስለው ሲሆን፤ ተቋሙ በክትባት ዝውውሩ ተሳታፊ ከሆኑ አንዱ ነው። ኢሜሉ የተላከው ለመጓጓዣ ድርጅቶች ሲሆን፤ ሐሰተኛ ኮዶች በውስጡ ይዟል። ኢሜሉን የሚመልሱ ድርጅቶች በሚሰጡት መረጃ አማካይነት ክትባቶችን እንዴት ለማዘዋወር እንደታቀደ ማወቅ ይቻላል። አይቢኤም እንደሚለው፤ መረጃ ሰርሳሪዎቹ ክትባቶችን ለማዘዋወር የወጣውን ውጥን ካወቁ በኋላ ጥቃት ይሰነዝራሉ። ጥቃቱ ካነጣጠረባቸው መካከል የአውሮፓ ኮሚሽን የግብር ድርጅት ዋና ኃላፊ እና ከጸሐይ ኃይል የሚያመነጭ መሣሪያ የሚያመርቱ ተቋሞች ይጠቀሳሉ። እነዚህ ተቋሞች የሚሠሩት መሣሪያ ክትባቶችን ቀዝቃዛ ቦታ ለማስቀመጥ ያስችላል። የደቡብ ኮርያ መተግበሪያ አምራች እና የጀርመን ድረ ገጽ አምራች ሌሎቹ የጥቃቱ ኢላማ ናቸው። ድረ ገጽ አምራቹ ለመድኃኒት ሠሪዎች፣ አጓጓዦች እና ሌሎችም ድጋፍ ይሰጣል። ጥቃቱ እንዴት ታወቀ? አይቢኤም ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ የሚሰነዘሩ የኮምፒውተር መረጃ ምዝበራዎችን ለማምከን የደህንት ቡድን አዋቅሮ ነበር። የኮቪድ-19 ክትባት ዝውውር መስመር በኮምፒውተር መረጃ ሰርሳሪዎች ኢላማ መደረጉን የደረሰበትም በዚህ ቡድን አማካይነት ነው። “መረጃ መዝባሪዎቹን የሚደግፉ አገራት ባይኖሩ ከፍተኛ ጊዜና ገንዘብ አውጥተው ጥቃቱን አይወጥኑም ነበር” ብሏል አይቢኤም ባወጣው መግለጫ። አይቢኤም የምዝበራው ኢላማ ለተደረጉ ድርጅቶችና ለጸጥታ ኃይሎች መረጃውን አቀብሏል። የአሜሪካ የሳይበር ደህንነት ኤጀንሲ ጥቃቱን በተመለከተ ማስጠንቀቂያ አውጥቷል። በማስጠንቀቂያው ክትባት አጓጓዥ ድርጅቶች ጥበቃ እንዲደረግላቸው አሳስቧል። ሐምሌ ላይ ዩናይትድ ኪንግደም፤ ኦክስፎርድ የሚሠራውን ክትባት ሩስያ ኢላማ አድጋለች ስትል ከሳ ነበር። አሜሪካ ደግሞ ቻይና መረጃ ለመመዝበር እየሞከረች ነው ማለቷ አይዘነጋም። በተያያዥ፤ ሰሜን ኮርያ እና ሩስያ የኮቪድ-19 ክትባት ምርምርን ሊሰርቁ እንደነበር ማይክሮሶፍት በቅርቡ አስታውቋል።
news-41925360
https://www.bbc.com/amharic/news-41925360
አሽከርካሪ አልባዋ አውቶብስ በመጀመሪያ ቀኗ ግጭት ገጠማት
በርከት ያሉ ሰዎችን አሣፍራ በላስ ቬጋስ ከተማ ስትጓዝ የነበረችው አሽከርካሪ አልባዋ አውቶብስ በመጀመሪያ ቀን ሥራዋ ከአንድ ሌላ ተሽከርካሪ ጋር ነው የተጋጨችው።
የተጎዳ ሰው እንደሌለ ያሳወቁት ባለሥልጣናቱ ጥፋቱ በተቃራኒ አቅጣጫ ሲያሽከረክር የነበረ ሹፌር ነው ሲሉ ገልፀዋል። አሽከርካሪ አልባዋ አውቶብስ በአሜሪካ በሕዝብ መመላለሻ መንገድ ላይ ጥቅም በመስጠት የመጀመሪያዋ መሆን ችላለች። አውቶብሷ እስከ 15 ሰው ድረስ የማሣፈር አቅም ሲኖራት በሰዓት እሰከ 45 ኪሎ ሜትር መጓዝ ትችላለች። የላስ ቬጋስ ቃል-አቀባይ ጄስ ራድኬ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ገጭቱ ቀላል የሚባል ስለሆነ በቅርብ ቀናት ውስጥ አውቶብሷ ወደ መደበኛ ሥራዋ ትመለሳለች ሲሉ ገልጸዋል። "አሽከርካሪ አልባዋ አውቶብስ አደጋው ሲያጋጥማት ማድረግ ያለባትን ነው ያደረገችው እሱም መቆም ነው። ነገር ግን የጭነት መኪና አሽከርካሪው ሊያቆም አልቻለም" በማለት ጄስ ገልጸዋል። አሽከርካሪ አልባ ተሽከርካሪዎች ከዚህ በፊትም ግጭት አጋጥሟቸው የሚያውቅ ሲሆን በሁሉም አጋጣሚዎች ስህተቱ የሰው ልጅ ሆኖ ተገኝቷል። ባለሙዎች እንደሚሉት ከሆነ አሽከርካሪ አልባ ተሽከርካሪዎች ሰው ከሚያሽከረክራቸው ተሽከርካሪዎች የበለጠ ደህንነታቸው የተጠበቀ ነው።
news-47900312
https://www.bbc.com/amharic/news-47900312
"የአማራ ልዩ ኃይል ሕዝብን የሚጎዳበት ምክንያት የለውም" የአማራ ክልል ደህንነት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ገደቤ
ሰሞኑን በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደርና ሰሜን ሸዋ ዞን ለተከሰተው ግጭት ተጠያቂው ማን ነው የሚለውን በተመለከተ የተለያዩ እርስ በርስ የሚቃረኑ ሃሳቦች እየተሰነዘሩ ነው።
የአካባቢው የአስተዳደር፣ ነዋሪዎችና የአማራ ክልል የጸጥታ ኅላፊዎች የችግሩ ፈጣሪና ጥቃት ፈጻሚው ኦነግ ነው ይላሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ኦነግ እዚያ አካባቢ ወታደር የለኝም ጥቃቱን አላደረስኩም ብሏል። • በሰሜን ሸዋ በተከሰተ ግጭት ህይወት ጠፍቷል ንብረት ወድሟል በመከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ አዛዥ ሜ/ጀኔራል ጌታቸው ጉዲና ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ ደግሞ "በክልሉ የጸጥታ መዋቅር የሚመራው የጸጥታ ኃይል ነው በዋናነት ችግር ያደረሰው" ብለዋል። የአማራ ክልል የሰላም ግንባታና የህዝብ ደህንነት ቢሮ ምክትል ኅላፊ አቶ ገደቤ ኃይሉ "ልዩ ኃይሉም ሆነ የጸጥታ መዋቅሩ ተልዕኮውን በሚገባ የሚያውቅና የአማራ ክልል ህዝብን ደህንነት የሚጠብቅ እንጂ መልሶ የአማራን ህዝብ የሚጎዳበት ምክንያት የለውም" ብለዋል። አቶ ገደቤ እንዲህ አይነቱ ሃሳብ በጣም የተሳሳተና የአማራን ህዝብ መብትም ታሳቢ ያላደረገ ነው በማለት "እዚያ አካባቢ የሚንቀሳቀስ ኃይል መኖሩ ይታወቃል ማስረጃዎችም አሉን። የተፈጸመው ጥቃትም በአማራው ህዝብ ላይ እና በንጹሃን ላይ ነው። ይህን የፈጸመው ልዩ ኃይል ነው ማለት ምን ማለት ነው?" ሲሉ ይጠይቃሉ። • አወዛጋቢው ግጭት በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር እሳቸው እንደሚገምቱት ይህን የሚሉ አንድም ይህንን የፈጸመው አካል በህግ እንዳይጠየቅ ለማድረግ ወይም ደግሞ የክልሉን ህዝብ ሰላምና ደህንነት የሚጠብቀውን የፖሊስ አካል ህዝባዊ አመኔታ እንዳይኖረው ለማድረግ ሊሆን ይችላል። ታዲያ በመከላከያ ሠራዊት ሰሜን እዝ አዛዥ የተሰጠውን መግለጫ አንቀበለውም እያሉ ነው? በሚል ለተነሳላቸው ጥያቄ "እኔ አልሰማሁትም ነገር ግን በዚህ መልኩ ተላልፎ ከሆነ ትክክል ነው ብዬ አላምንም። ተቀባይነትም የለውም" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል አቶ ገደቤ ። በሌላ በኩል ሜ/ጀኔራል ጌታቸው "ግጭቱ በአካባቢው በሁለቱም ወገን ባሉ የታጠቁ ኃይሎች መካከል የተፈጠረ ነው። ከሌላ አካባቢ በመጣ አካል ነው ችግሩ የተፈጸመው የሚባለው መሰረተ ቢስ ነው" ቢሉም በአማራ ክልል መንግሥት በኩል ደግሞ በተለያዩ የአስተዳደር መዋቅሮች በተደጋጋሚ ጥቃት ፈጻሚው ኦነግ ስለመሆኑ ይነገራል። ጥቃቱ በኦነግ ለመፈፀሙ አቶ ገደቤ ሦስት ምክንያቶችን እንደ ማስረጃ ያስቀምጣሉ። "አንደኛ ቤት ለቤት እየዞረ የኦሮሞ አርሶ አደሮችን አማራ እምነታችሁን ለማስቀየርና ማንነታችሁን ሊነጥቅ እየተንቀሳቀሰ ነው በማለት ቅስቀሳ ማድረጉን የኦሮሞ አርሶ አደሮች ራሳቸው ነግረውናል፤ ሁለተኛ ከአካባቢው የጸጥታ መዋቅር አቅም በላይ የሆነ፣ የቡድን መሳሪያ የተጠቀመና የተቀናጀ ነው፤ ሦስተኛ አሰላለፉና ስምሪቱንም መመልከት ይቻላል። አማራውና ኦሮሞው ተሰባጥሮ የሚኖርበት ነው። ነገር ግን ጥቃቱ የተፈጸመው አማርኛ ተናጋሪዎች በሚኖሩበት አጣዬና ማጀቴ ነው ይህንንም ያደረገው የጸጥታ አካሉ ማረጋጋት ሲጀምር በሌላ ቦታ ሄዶ ነው" ይላሉ። • ኦማር አል-ባሽር: ከየት ወደየት? አቶ ገደቤ ይህን ይበሉ እንጂ ሜ/ጄኔራል ጌታቸው "እኛ ደርሰን አካባቢውን ካረጋጋን በኋላ በሌላ አካባቢ ሂዶ የክልሉ የጸጥታ መዋቅር ጥቃት ያደርሳል" ሲሉ ክልሉን ተጠያቂ ያደርጋሉ። ከወራት በፊት በምሥራቅ አማራ ወታደራዊ ስልጠና የሚሰጥ ቡድን መኖሩን የአማራ ክልል መንግሥት በተለይ ለቢቢሲ ገልጾ ነበር። ይህን መቆጣጠር ያልቻልነው በሁለት ምክንያት ነው ብለዋል ምክትል ቢሮ ኀላፊው። "አንደኛ ይህ አይነት ስልጠናው የተካሄደው በአፋር አማራና ኦሮሞ አዋሳኝና ድንበር አካባቢዎች በመሆኑ ከስልጣናችን ውጭ ነው። ሁለተኛ ጉዳዩን ራሱ ለማጥናት ጊዜ ያስፈልግ ነበር" ብለዋል። የሰሜን እዝ አዛዡ ሜ/ጀኔራል ጌታቸው ግን "የአካባቢው ማህበረሰብ ኑሮው ከትጥቅ ጋር የተቆራኘ ነው። ከዚያ ውጭ እስከ ቀበሌ ድረስ ያለ የጸጥታ አካል ካልሆነ በስተቀር ሌላ የታጠቀ አካል የለም" የሚል ሃሳብ ሰንዝረዋል። ታስቦ የተቀነባበረና ጥቃት አድርሶ የመደበቅ እርምጃ ስለሆነ አስካሁን የተያዘ ጥቃት ፈጻሚው ቡድን አባል እንደሌለ የገለፁት ምክትል ቢሮ ኅላፊው የሞቱና የቆሰሉ ሰዎችን የሚመለከት መረጃም ተጠናቅሮ አላለቀም ብለዋል።
43153036
https://www.bbc.com/amharic/43153036
"ሕገ-መንግሥቱ ተተኪ ጠቅላይ ሚኒስትርን በሚመለከት ክፍተት አለበት" ውብሸት ሙላት
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄያቸውን ካቀረቡበት ማግሥት ጀምሮ እሳቸውን የሚተካቸው ማነው? ለሚለው ጥያቄ ብዙዎች ግምቶቻቸውን እየሰነዘሩ ነው።
አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር በተለያዪ ምክንያቶች ከስልጣን በሚወርድበት ወቅት ስለ ተተኪው ግለሰብ ሕገ መንግሥቱ ምን ይላል? በሚል የህግ ምሁሩን አቶ ውብሸት ሙላትን ቢቢሲ ጠይቆ ነበር። ሕገ መንግሥቱንም ጠቅሶ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል መሆን እንዳለባቸው ውብሸት ይናገራል። የፓርላማ ሥርዓትን በሚከተሉ ሃገራት መካከል አሸናፊው የፖለቲካ ፓርቲ መንግሥት የሚመሰርት ሲሆን ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማፅደቁን ተግባር ያከናውናል። በዚህም መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪነታቸው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመሆኑ የግድ የተወካዮች ምክር ቤት አባል ሊሆኑ እንደሚገባም አቶ ውብሸት አፅንኦት ያስረዳል። ሰሞኑን በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እና በማህበራዊ ድረ ገፆች ላይ በተደጋጋሚ ስማቸው እየተጠቀሰ ከሚገኙት ግለሰቦች መካከል አንዳንዶቹ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ካለመሆናቸው ጋር ተያይዞ ሌላ አማራጭ አለ ወይ ለሚለው ጥያቄ የህግ ባለሙያው ሲመልስ፤ "መንግሥት ካልፈረሰ፤ ተጠባባቂ ወይም የሽግግር መንግሥት እስካልተመሰረተ ድረስ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ያልሆነ ግለሰብ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ ሊቀርብ አይችልም፤ ምክንያቱም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪነታቸው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስለሆነ" ይላል። ሌላው የህግ ባለሙያው አማራጭ ብሎ የሚያስቀምጠው የማሟያ ምርጫ ማድረግ ነው። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ያልሆነ ግለሰብ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆን ከተፈለገ ተቃዋሚዎችም ሆነ ሌሎች ግለሰቦች ተወዳድረው ምርጫውን ማሸነፍ የቻለ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሆን እንደሚችል ውብሸት ይገልፃል። ነገር ግን ይሄ ረዥም ጊዜ ሊወስድ እንደሚችልም ይናገራል። ይህም ሆኖ ሕገ መንግሥቱ ክፍተት እንዳለው የሚናገረው አቶ ውብሸት፤ ይህንን ክፍተቱንም ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት በኋላ ትምህርት መውሰድ ይገባ እንደነበር ይገልፃል። "እሳቸውም ሲሞቱ ተተኪያቸውን ሕገ-መንግሥቱ በግልፅ አላስቀመጠውም" ይላል። ሕገ መንግሥቱ እንደሚያትተው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማይኖሩበት ጊዜ ተክተው ይሰራሉ እንዲሁም ተጠሪነታቸውም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው። "በማይኖሩበት" ማለት በጊዜያዊነት፣ ለሥራ ጉብኝት በሚሄዱበት ወቅት፣ ቢታመሙ፣ እረፍት ላይ ቢሆኑ ማለት እንደሆነና ከስልጣን ቢለቁ፣ ቢባረሩ ወይም ቢሞቱ ማን ሊተካቸው ይችላል ለሚለው ሕገ-መንግሥቱ በግልፅ ባለማስቀመጡ ችግር እንደፈጠረም ጨምሮ ይናገራል። "በየትኛውም ሃገር ጠቅላይ ሚኒስትር በሚለቅበት ጊዜ በጣም በአፋጣኝ መተካት አለበት፤ በአፋጣኝ ካልተተኩ ስልጣን ይገባናል የሚሉ በርካታ ተቀናቃኞች ሊፈጠሩ ስለሚችል ሃገሪቱን አደጋ ላይ ሊጥላት ይችላል ተብሎ ይታሰባል" ይላል። በቀድሞው የነገሥታት ሥርዓት ወራሾችንም ያዘጋጁ እንደነበር የሚናገረው ውብሸት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት በኋላ ይህ ክፍተት መሞላት እንደነበረበትም ይናገራል። በቅርብ ጊዜ የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ አባይ ወልዱ በለቀቁበት ወቅት ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የክልሉ ምክር ቤት አባል ባይሆኑም የሟሟያ ወይም ሌላ ሙሉ ምርጫ እስከሚደረግ ድረስ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው የርዕሰ መስተዳድር ሥራ እንዲሰሩ ቢያደርጓቸውም ይህ ሁኔታ በፌዴራል መንግሥቱ መድገም ከባድ እንደሆነም ውብሸት ይገልፃል። "ጠቅላይ ሚኒስትሩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ካልሆኑ ተጠሪነት ሊኖራቸው አይችልም፤ ምክር ቤቱም ሊቆጣጠራቸው አይችልም" የሚለው ውብሸት "ብዙ ምስቅልቅሎችን ያስከትላል" ይላል። በአሜሪካ ጆርጂያ ጉኔት ኮሌጅ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር የሆኑት ዶክተር ዮሐንስ ገዳሙ በቀጣይ ጠቅላይ ሚኒስትር ማን ሊሆን ይችላሉ? ለሚለውም ጥያቄም ሲመልሱ ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ከብአዴን ወይም ከኦህዴድ ውስጥ በአመራር ላይ ያሉ አቶ ደመቀ መኮንን ወይም ዶክተር አቢይ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይገምታሉ። ዶክተር ዮሀንስ ኢህአዴግ እስካሁን እየሰራበት ያለውን አሰራር በማየትም አራቱ ፓርቲዎችም ሆነ መሪዎቻቸው የተለያዩ ቁልፍ የሚባሉ የስልጣን እርከኖችን ተከፋፍለው እንደሚጨብጡ ይናገራሉ። ''የፓርላማው አፈ-ጉባኤ ከኦህዴድ፣ ፕሬዚዳንቱ እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ናቸው'' የሚሉት ዶክተር ዮሀንስ ከዚያ አንፃር ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከኦህዴድ ላይሆን ይችላል የሚል ግምት አላቸው። "ይህ ሁኔታ ከተቀየረና ዶክተር አብይ ልዩ ዕድል የሚኖራቸው ከሆነ አመራሩ ላይ ያለው የስልጣን ክፍፍል ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ይቀያየራል"ይላሉ። ያለውን ሁኔታ በማየትም ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ሊሆኑ እንደሚችሉ ግምታቸውን ያስቀምጣሉ።
sport-44920775
https://www.bbc.com/amharic/sport-44920775
«ሳሸንፍ ጀርመናዊ ስሸነፍ ስደተኛ» ሜሱት ኦዚል
ጀርመናዊው የአርሴናል እግር ኳስ ተጫዋች ሜሱት ኦዚል ከቱርኩ ፕሬዝደንት ሬሴፕ ጣይብ ኤርዶዋን ጋር በአካል መገናኘቱን ተከትሎ ከደረሰበት ወቀሳ በኋላ ራሱን ከበሔራዊ ቡድን ማግለሉን አስታውቋል።
ከግራ ወደ ቀኝ ጎንዶጋን፣ ኦዚል፣ ፕሬዝደንት ኤርዶዋን እና ሴንክ ቶሱን ውሳኔውን አስመልክቶ በሰጠው ረዘም ባለ መግለጫ ላይ የ29 ዓመቱ ኦዚል «ከጀርመን እግር ኳስ ማሕበር የደረሰኝ ምላሽ የብሔራዊ ቡድኑን ማልያ ድጋሚ መልበስ እንዳልሻ አድርጎኛል» ሲል አስታውቋል። በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ደካማ አቋም አሳይቷል ተብሎ የተወቀሰው ኦዚል «ጀርመን በሩስያው የዓለም ዋንጫ ላይ ላሳየችው የወረደ አቋም ሁሉ እኔ ተጠያቂ እየሆንኩ ነው» በማለት ምሬቱን አሰምቷል። «ሳሸንፍ ጀርመናዊ ስሸነፍ ስደተኛ» ሲልም የተሰማውን ስሜት በፅሑፍ ገልጿል። • አብረሃም መብራቱ፡ «ቡድኑን ስኬታማ የማድረግ ሕልም አለኝ» • አብረሃም መብራቱ፡ የየመንን ብሔራዊ ቡድን ለትልቅ ውድድር ያበቃ ኢትዮጵያዊ ወርሃ ግንቦት ላይ ከቱርኩ ፕሬዝደንት ሬሴብ ጣይብ ኤርዶዋን ጋር ፎቶ ተነስተዋል በሚል ኦዚል እና የቡድን አጋሩ ኢካይ ጉንዶጋን ወቀሳ ሲዘንብባቸው እንደነበረ አይዘነጋም። ኦዚል «እኔና ጉንዶጋን ከፕሬዚዳንቱ ጋር የመከርነው ስለ እግር ኳስ እንጂ ስለፖለቲካ አይደለም» ይላል። ኋላ ላይ የቱርክ ገዥው ፓርቲ ሁለቱ እግር ኳስ ተጫዋቾች ከፕሬዚዳንቱ ጋር የተነሱትን ፎቶ ለምርጫ ቅስቀሳ ተጠቅሞበታል። ከክስተቱ በኋላ በርካታ የጀርመን ፖለቲከኞች «ተጫዋቾቹ ለጀርመን ያላቸው አተያይ ጥያቄ የሚያጭር ነው» ሲሉ ተደምጠዋል። • ኤርትራ የሃይማኖት እሥረኞችን ፈታች • ኢትዮጵያ በዱቤ ተጨማሪ ነዳጅ ከሳኡዲ አረቢያ ጠየቀች • ''የኤርትራ ኢኮኖሚያዊ ዕቅድ የተነደፈው በኢትዮጵያ ሃብት ላይ ነበር'' አምባሳደር አውዓሎም ወልዱ • ኢትዮጵያ በዱቤ ተጨማሪ ነዳጅ ከሳኡዲ አረቢያ ጠየቀች የጀርመን መንግሥት የጣይብ ኤርዶዋን አገዛዝ ላይ የተፈፀመውን መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ ቱርክ የወሰደችውን እርምጃ በፅኑ እንደሚቃወም አሳውቆ ነበር። ከቱርካዊያን ቤተሰቦች የተወለደው ሜሱት ኦዚል «ከቱርክ ፕሬዝደንት ጋር ፎቶ አልነሳም ብል የአያቶቼን አምላክ እንደናቅኩ ነበር የምቆጥረው ሲል» አቋሙን ግልፅ አድርጓል። ኦዚል ክስተቱን ተክትሎ ከእርሱ አልፎ ቤተሰቦቹ ማስፈራራት እና ዛቻ እየደረሰባቸው እንደሆነም አልሸሸገም።
57024494
https://www.bbc.com/amharic/57024494
ምርጫ 2013: 28 ሚሊዮን ተመዝግበዋል ለተባለው ምርጫ ምዝገባው ለተጨማሪ ቀናት ተራዘመ
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አዲስ አበባ እና ድሬ ዳዋን ጨምሮ በክልሎች የመራጮች ምዝገባ ለተጨማሪ 7 ቀናት እንዲራዘም ማድረጉን አስታወቀ።
ቀደም ብሎ ይፋ በተደረገው ቀነ ገደብ መሠረት የመራጮች ምዝገባ ከአፋር እና ከሶማሌ ክልል በስተቀር የሚጠናቀቀው ዛሬ ነበር። ይሁን እንጂ ባለፉት ቀናት በተደራራቢ ብሔራዊ የበዓል ቀናት ምክንያት በርካታ የመራጮች መመዝገቢያ ጣቢያዎች ዝግ ሆነው መቆየታቸው እና ንኡስ ጣቢያዎችን ለማደራጀት ጊዜ መውሰዱን በመጥቀስ ምዝገባውን ማራዘም ማስፈለጉን ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። ቦርዱ ተቀዛቅዞ የነበረው የመራጮች ምዝገባ በከፍተኛ ሁኔታ ተሻሽሎ በአሁኑ ወቅት በጊዜያዊነት በተሰበሰበው መረጃ ከ28 ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸውን አስታውቋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከዚህ ቀደም በቀጣዩ አገራዊ ምርጫ እስከ 50 ሚሊዮን የሚደርሱ መራጮች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል ብሎ ነበር። በአሁኑ ወቅትም በ41,798 ምርጫ ጣቢያዎች ምዝገባ እየተከናወነ እንደሚገኝ ቦርዱ አስታውቋል። ቦርዱ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር፣ በድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር፣ በአማራ ክልል፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል፣ በጋምቤላ ክልል፣ በሃረሪ ክልል፣ በኦሮሚያ ክልል እና በሲዳማ ክልል የመራጮች ምዝገባ እስከ አርብ ግንቦት 06 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ለተጨማሪ 7 ቀናት እንዲከናወን ወስኗል። ቦርዱ የመራጮች ምዝገባ በተከናወኑባቸው ስፍራዎች ነዋሪዎች በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን፤ የቦርዱ አስፈጻሚዎች እና አስተባባሪዎች ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ግንቦት 06 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ የመራጮች ምዝገባን እንዲያከናውኑ አስታውቋል።
news-53544128
https://www.bbc.com/amharic/news-53544128
በትግራይ ምርጫ ለመሳተፍ የሚፈልጉ በሦስት ቀናት ውስጥ እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀረበ
ከቀሪው የአገሪቱ ክፍል በተለየ ስድስተኛውን ዙር ምርጫ ለማካሄድ በተወሰነበት በትግራይ ክልል ውስጥ በሚካሄደው ምርጫ ለመወዳደር የሚፈልጉ የፖለቲካ ድርጅቶችና ግለሰቦች እንዲመዘገቡ ጥሪ እንደቀረበ ተገለጸ።
በቅርቡ በክልሉ ምክር ቤት የተቋቋመው የትግራይ ምርጫ ኮሚሽን ጽህፈት ቤት በመጪው ነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ ሊካሄድ በታቀደው ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ፓርቲዎች ጥሪ አቅርቧል። በዚህም መሰረት ኮሚሽኑ ነሐሴ መጨረሻ ላይ በሚካሄደው ምርጫ ላይ ለመወዳደር የሚፈልጉ በሙሉ ቀርበው እንዲመዘገቡ ይፋዊ ጥሪ አቅርቧል። በጥሪው መሰረት በምርጫው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ የፖለቲካ ድርጅቶችና የግል ተወዳዳሪዎች ከማክሰኞ (ሐምሌ 21/2012) እስከ ሐሙስ (ሐምሌ 23/2012) ባሉት ሦስት ቀናት ውስጥ ሊመዘገቡ እንደሚችሉ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር መምህር ሙሉወርቅ ኪዳነ ማርያም ለቢቢሲ ገልጸዋል። ኮሚሽኑ በምርጫው መሳተፍ ለሚፈልጉ ወገኖች ቀርበው እንዲመዘገቡ ጥሪ ከማቅረብ ውጪ ለምርጫው አፈጻጸም ስለሚያስፈልጉ የጊዜ ሰሌዳና ሌሎች ወሳኝ ነገሮች እስካሁን ያለው ነገር የለም። ምርጫው ሊካሄድበት ይችላል ስለተባለው ትክክለኛ ቀንም እስካሁን የተገለጸ ነገር ባይኖርም ቢቢሲ ኮሚሽነሩን ስለዚሁ ጉዳይ ጠይቆ፤ ምርጫው የሚካሄድበት ቀንን ከሚመዘገቡ ድርጅቶችና ግለሰቦች ጋር በመወያየት እንደሚወሰን መምህር ሙሉወርቅ ተናግረዋል። ኮሚሽኑ በክልላዊ ምርጫው የሚሳተፉ ፓርቲዎችን ለምዝገባ ከመጥራት ውጪ፣ ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ዝርዝር ነገሮች ምን ምን እንደሆነ አልገለፀም። የትግራይ ክልል ሊያካሂድ ያሰበው ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዳሉ ሁሉ ላለመሳተፍ የወሰኑ ድርጅቶችም አቋማቸውን አሳውቀዋል። በተናጠል ይካሄዳል እየተባለ ባለው ክልላዊ ምርጫ ላይ እንደሚሳተፉ ካሳወቁት የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል የክልሉ ገዢ ፓርቲ ህወሓት፣ ሳልሳይ ወያኔ ትግራይ፣ ባይቶና ትግራይና የትግራይ ነጻነት ድርጅት የተባሉት ይገኙበታል። ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ አረና ትግራይ እና የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ በክልሉ ሊካሄድ የታቀደው ምርጫ ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት በሂደቱ ላለመሳተፍ መወሰናቸውን አሳውቀዋል። ምርጫው የሚካሄድ ከሆነ፤ ያለው ጊዜ ከአንድ ወር ብዙም ያላለፈ በመሆኑ፤ ከገንዘብና አስፈላጊው አቅርቦት ባሻገር ሌሎችም ዝግጅቶችን ለማከናወን አዳጋች እንደሚሆን እየተገነረ ነው።
news-56945591
https://www.bbc.com/amharic/news-56945591
ከነጭ ሴቶች ይልቅ ጥቁሮች ስለምን ጽንስ አልረጋ ይላቸዋል?
በቅርብ የተደረገ አንድ ጥናት ጥቁር ሴቶች ከነጮች 40 ከመቶ በበለጠ ለጽንስ ማቋረጥ የቀረቡ ናቸው ይላል።
ይህ ጥናት በላንሴት አማካኝነት የተካሄደ ነው። ወደ 5 ሚሊዮን እርግዝናዎችን በሰባት አገራት ክትትል በማድረግ ጥናቱ መደረጉ ልዩ ያደርገዋል። እንዳለመታደል ሆኖ ዩናይትድ ኪንግደምን ጨምሮ በርካታ አገራት የጽንስ ማቋረጥ ላይ መረጃ አይሰበስቡም። ነገር ግን ይህ ጥናት እንደተነበየው 15 % እርግዝናዎች በጽንስ ማቋረጥ ይደመደማሉ። 1% ሴቶች ደግሞ ከአንድ በላይ ጽንስን ያቋርጣሉ። ጥናቱ በተጨማሪ እንዳረጋገጠው ጽንስ ያቋረጡ ሴቶች ለበርካታ ሥነልቡናዊ ምስቅልቅሎች ይጋለጣሉ። ይህም ብቻ ሳይሆን የደም መርጋት፣ የልብ ሕመም እና ድብታ ይከተላቸዋል። ዶሪን እና ሪጌ ባልና ሚስት ናቸው። ዶሪ 7 ጊዜያት ያህል ጽንስ አቋርጣለች። "ለመጀመርያ ጊዜ እርጉዝ የሆንኩ ጊዜ በደስታ ሰክሬ ነበር" ትላለች። ደስታዋን ለራሷ ደብቃ ማስቀረት አልቻለችም ነበር። ጓደኞቿንና ቤተሰቧን አበሰረቻቸው። ለሚጠበቀው ልጅም ስም እንዲያወጡ አሳሰበቻቸው። ነገር ግን እርጉዝ መሆኗን ባወቀች በ2ኛው ወር ላይ አስወረዳት። "ስለማስወረድ ብዙ እንሰማለን። በኛ የሚከሰት ግን አይመስለንም" ትላለች። በድጋሚ ሞከረች። አልሆነም። በሦስተኛ ጊዜ ስትሞክር አልሆነም። ተመሳሳይ ችግር ገጠማት። ከዚህ በኋላ ነበር ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ብሔራዊ የጤና አገልግሎት ምክር ፍለጋ ያመራችው። ሆኖም ለምን በተከታታይ እንዳስወረዳት መልስ አላገኘችም። የትኞቹ ሁኔታዎች በይበልጥ ለጽንስ አለመጽናት ያጋልጣሉ? ምን ዓይነት መፍትሄዎች ይሰጣሉ? አብዛኛው ጥናት የተደረገው በስዊድን፥ ፊንላንድ እና ዴንማርክ ሲሆን እነዚህ አገሮች የጽንስ መቋረጥ አሐዞችን በየፈርጁ በማደራጀት ይታወቃሉ። ሆኖም በዚህ እምብዛምም የሆኑት ዩናይትድ ኪንግደም፣ አሜሪካ፥ ካናዳና ኖርዌይም በጥናቱ ተሳትፈዋል። "ማወቅ የቻልነው አንድ ነገር ቢኖር ጥቁር ሴቶች ከነጮች በብዙ እጥፍ በጽንስ ማቋረጥ የመሞት ዕድላቸው ሰፊ መሆኑን ነው" ይላሉ ፕሮፌሰር ሲዮብሃን ኩዩንቢ። እኚህ ፕሮፌሰር በዩኒቨርስቲ ኦፍ ዎርዊክ መምህርና በጥናቱም ተሳታፊ የነበሩ ናቸው። "ጥቁር ሴቶች በጽንስ ማቋረጥ እንደሚሞቱ ከቀድሞ ጥናቶችም እናውቅ ነበር። የገረመኝ ጥቁር ሴቶች ከነጭ ሴቶች ይልቅ ለውርጃ መጋለጣቸው ነው" ይላሉ ፕሮፌሰሩ። ጥቁር ሰዎች ከነጮች የበለጠ ለስኳር በሽታ (ዓይነት 2) እና የልብ ሕመም ተጋላጭ ናቸው። ይህ ሀቅ ምናልባት ለጽንስ ያለጊዜው ማስወረድ ምክንያት እንደሆነ ይታመናል። ለዶሪን ይህ የጥናት ውጤት እጅግ የሚያሳዝን ሆኖ ነው ያገኘችው። "እንዲህ ዓይነት የጥናት ውጤቶችን ስሰማ አዝናለሁ' ምናልባት ይህ የጥቁሮች ፍዳ እንዲበዛ ተቋማዊ ምክንያቶች ይኖሩ ይሆን? ለምን ጥቁር ሴቶች ጽንስ አይጸናላቸውም? ያ ከሆነ ደግሞ ከነጭ ሴቶች እኩል እንድንሆንና ለጤና ምስቅልቅል እንዳንዳረግ ተቋማዊ እኩልነት ያሻናል" ትላለች። የአኗኗር ለውጦችን ማድረግ ጽንስ መውረድ ከሚያጋጥማቸው ሴቶች መካከል 75 ከመቶዎቹ በድጋሚ የማርገዝ ዕድል አላቸው። ይህ በመሆኑም ነው ሐኪሞች ሴቶችን ደጋግመው እንዲሞክሩ የሚመክሩት። ፕሮፌሰር ኩዊንቢ "የጽንስ መጽናት እንዲኖር አንዳንድ የምንረዳቸው ነገሮች አሉ" ይላሉ። ፕሮፌሰሯ የጽንስ ክትትል ሕክምናን የሚሰጥ ክሊኒክ ባለቤትም ናቸው። አንዱ ምክር የአኗኗር ዘዬ ለውጦችን ማድረግ ነው። እሷ ዘንድ ከመጡ 30 ከመቶ የሚሆኑት ጽንስ አልረጋ ካላቸው ታካሚዎች ውስጥ የስኳር ታማሚዎች፣ አጫሾች። የተጋነነ የሰውነት ክብደት የላቸውና የደም ግፊት የሚያሰቃያቸው ሆነው ተገኝተዋል። ይህ ሁኔታ በአኗኗር ዘዬ ለውጥ፥ አዘውትሮ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በመሥራትና ጤናማ አመጋገብን በመከተል በድጋሚ መጸነስ የሚችሉበትን ዕድል ማስፋት ተችሏል።
news-57053671
https://www.bbc.com/amharic/news-57053671
በኮሎራዶ አንድ ግለሰብ ፍቅረኛውን ጨምሮ ስድስት ሰዎችን ተኩሶ ገደለ
በአሜሪካ ኮሎራዶ ግዛት አንድ የታጠቀ ግለሰብ ትላንት እሁድ በተካሄድ የልደት ድግስ ላይ ስድስት ሰዎችን ከገደለ በኋላ ራሱን አጠፋ።
"ከሟቾቹ መሃል የገዳዩ የፍቅር ጓደኛ ትገኝበታለች። መጀመሪያ እያሽከረከረ ወደ ቦታው መጣ። ራሱን ከማጥፋቱ በፊት በልደት ዝግጅቱ ላይ እየታደሙ የነበሩ ሰዎች ላይ በዘፈቀደ ተኩስ ከፈተ" ሲል የኮሮሎራዶ ስፕሪንግ ፖሊስ ገልጿል። ገዳዩ ይህንን ድርጊት ለመፈጸም ምን እንዳነሳሳው እስካሁን የታወቀ ነገር የለም። የጥቃቱ ሰለባዎች በሙሉ አዋቂዎች ቢሆኑም በድግሱ ላይ ግን ህፃናትም ታድመው ነበር። ፖሊስ የሟቾች ማንነትን እስከ አሁን ድረስ ይፋ አላደረገም። "በድግሱ ላይ ህጻናት ታድመው የነበረ ቢሆንም ከመሃላቸው ማንም አልተጎዳም። ነገር ግን በዚህ አሰቃቂ ተግባር የስድስት ሰዎች ህይወት ተቀጥፏል" ሲሉ አንድ የአካባቢው ፖሊስ ገልፀዋል። ፖሊስ የድረሱልኝ የሰልክ ጥሪ ሲደርሰው ወደ ቦታው ቢያመራም የስድስት ሰዎች ህይወት ካለፈ በኋላ መድረሱ ታውቋል። እንዲሁም አንድ ሰው ከባድ ጉዳት ደርሶበት ወደ ሆስፒታል ሲወሰድ ህይወቱ አልፏል። የከተማዋ ከንቲባ ድርጊቱን "ትርጉም አልባ ጥቃት" ሲሉ ገልፀውታል። "ዛሬ ስለሞቱት ሰዎች በከባድ ሃዘን ውስጥ ሆነን እንዲሁም ቤተሰባቸውን ላጡ እና ጉዳት ለደረሰባቸው እየፀለይን እንገኛለን" ሲሉ ተናግረዋል። በተመሳሳይ ግዛት ቡልደር ከተማ ከሁለት ወራት በፊት የ10 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈ ጥቃት በአንድ መደብር ውስጥ ተፈጽሞ ነበር። ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ውሎ በ 10 የግድያ ወንጀሎች ተከሷል።
news-53216688
https://www.bbc.com/amharic/news-53216688
የአሜሪካው ዩኒቨርስቲ ለመረጃ መዝባሪዎች 1.14 ሚሊዮን ዶላር ለመክፈል ተገደደ
ለኮሮናቫይረስ መድኃኒት ለማግኘት ጥረት እያደረጉ ካሉ ቀደምት የምርምር ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው ዩኒቨርስቲ ያሉትን መረጃዎች ለማዳን ሲል ለኢንትርኔት የመረጃ መዝባሪዎች (ሐከርስ) በድብቅ ከተደረገ ድርድር በኋላ 1.14 ሚሊዮን ዶላር መክፈሉን አመነ።
የካሊፎርኒያው ሳንፍራንሲስኮ ዩኒቨርስቲ የምዝበራ ጥቃቱ የተሰነዘረበት በፈረንጆቹ የሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ 'ኔትዎከር' በተባለው የወንጀለኛ ቡድን ነው። የዩኒቨርስቲው የኮምፒውተር ባለሙያዎች ለመረጃ ምዝበራው የተለቀቀው ቫይረስ በዩኒቨርስቲው ኮምፒውተሮች ላይ ከመሰራጨቱ በፊት ለማስቆም ጥረት አድርገው ነበር። ከዚህ ክስተት በኋላ ዩኒቨርስቲው ከመረጃ ሰርሳሪዎቹ ጋር በድብቁ የበይነ መረብ ክፍል እየተደራደረ መሆኑን ማንነቱ ያልታወቀ ሰው መረጃውን ለቢቢሲ በማቀበሉ ቢቢሲ ድርድሩን ለመከታተል ችሏል። ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ ይህ 'ኔትዎከር' የተባለው የመረጃ መዝባሪ ቡድን ቢያንስ በሌሎች ሁለት ዩኒቨርስቲዎች ላይ ለገንዘብ ሲል የመረጃ መረብ ጥቃቶችን ፈጽሟል። የመረጃ መዝባሪዎቹ ከተቋማት እጅግ ጠቃሚ መረጃዎችንና በገንዘብ የማይተመኑ የምርምር ስራዎችን በመስረቅ በቁጥጥራቸው ስር በማድረግ ከባለቤቶቹ ጋር በድብቁ የኢንተርኔት ዓለም ላይ በሚያስቀምጡት የጊዜ ገደብ የሚፈልጉትን ገንዘብ ይጠይቃሉ። በዚህም የተቀመጠው ጊዜ ሲያበቃ የጠየቁት የገንዘብ መጠንን በዕጥፍ ያሳድጉታል ወይም የሰረቁትን መረጃ ያወድሙታል። ዩኒቨርስቲው በድብቅ መረጃ ከመዝባሪዎቹ ጋር ባደረገው ድርድር ተቋሙ በዓመት በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገቢ እንዳለው የተረዱት ተደራዳሪዎች በመጀመሪያ ላይ መረጃውን ለመመለስ የ3 ሚሊዮን ዶላር ክፍያን ጠይቀው ነበር። ዩኒቨርስቲውም በተደራዳሪው በኩል የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በዩኒቨርስቲው ገቢ ላይ ከባድ የሆነ የገንዘብ ተጽእኖን መፍጠሩን ለመዝባሪዎቹ በማስረዳት 780 ሺህ ዶላር እንዲቀበሉት ጠይቆ ነበር። ለአንድ ቀን በተደረገው ድርድር ዩኒቨርስቲው ያለውን ገንዘብ በሙሉ አሰባስቦ 1.02 ሚሊዮን ዶላር ለመክፈል ቢስማማም ወንጀለኞቹ ግን ከ1.5 ሚሊዮን ዶላር በታች እንደማይቀበሉ አሳወቁ። ከሰዓታት በኋላም ዩኒቨርስቲው ቀድሞ በሰጠው የገንዘብ መጠን ላይ ጭማሪ በማድረግ በመጨረሻ መክፈል የሚችለውን ገንዘብ መጠን 1,140,895 ዶላር በማሳደግ መረጃውን ለዘረፉበት ወንጀለኞች ለመክፈል ተስማማ። በቀጣዩ ቀንም በበይነ መረብ በኩል 116.4 ቢትኮይን ከዩኒቨርስቲው ወደ መረጃ መዝባሪው ቡድን 'ኔትዎከር' መተላለፉን የሚገልጽ መረጃ ደርሷቸዋል። የካሊፎርኒያው ሳንፍራንሲስኮ ዩኒቨርስቲ ክፍያውን ከፈጸመ በኋላ በመዝባሪዎቹ ጥቃት የተፈጸመበትን የኮምፒውተር ሥርዓቱንና መረጃዎቹን ወደ ነበሩበት የመመለስ ሥራውን እያከናወነ ኤፍቢአይ በወንጀል ድርጊቱ ላይ ለሚያደርገው ምርመራ ድጋፍ እየሰጠ ነው። ዩኒቨርስቲው ስለክስተቱ ለቢቢሲ በሰጠው ምላሽ "የተመዘበሩት መረጃዎች ዩኒቨርስቲው ሲያከናውናቸው የነበሩ ሕዝባዊ ጠቃሜታ ያላቸው የምርምር ሥራዎች ናቸው። በዚህም ምክንያት አስቸጋሪ ውሳኔ በመወሰን መረጃዎቻችንን ለማስለቀቅና ለማስመለስ 1.14 ሚሊዮን ዶላር ለመክፈል ተገደናል" ብሏል። የመረጃ ደኅንነት ባለሙያዎች እንደሚሉት የሕግ አስከባሪ አካላት ከሚሰጡት ምክር በተቃራኒው ተቋማት ከመረጃ መዝባሪዎች ጋር ድብቅ ድርድር እያደረጉ መሆኑን ይገልጻሉ።
news-57045743
https://www.bbc.com/amharic/news-57045743
ኮሮናቫይረስ: ሕንድ ውስጥ ከኮቪድ ያገገሙ ሰዎች ዓይነ ስውር በሚያደርግ በሽታ እየተጠቁ ነው
ሁለተኛው የኮሮናቫይረስ ማዕበል እጅግ ሕንድን እያመሳት ነው። በርካቶች በየቀኑ ይሞታሉ፤ በመቶ ሺዎች ይያዛሉ።
አሁን ደግሞ የሕክምና ባለሙያዎች ከኮቪድ-19 እያገገሙ ባሉና ባገገሙ ሕመምተኞች ላይ 'ብላክ ፈንገስ' የተባለ በሽታ እያዩ ነው። በሕክምና ቋንቋ ሙክሮሚኮሲስ የሚሰኘው ይህ በሽታ ሰው ለይቶ የሚያጠቃ ነው። ብዙ ጊዜ ይህ በሽታ የሚመጣው ከአፈር፣ ዕፅዋት፣ የከብቶች ኩበት አሊያም ከበሰበሰ ፍራፍሬና አትክልት ነው። በሽታው ወደ ሰውነታችን አየር የሚገባባቸው ቀዳዳዎችን እንዲሁም ሳንባን በማጥቃት በተለይ ደግሞ ተደራቢ በሽታ ያለባቸውን ሰዎች ሊገድል ይችላል። በተለምዶ የስኳር [ዳያቢቲስ] በሽታ ያለባቸው ሰዎች፣ የሰውነት የመከላከል አቅማቸው የደከመና የኤችአይቪና ካንሰር ተጠቂዎች በዚህ በሽታ የመሞት ዕድላቸው የሰፋ ነው። ዶክቶሮች ይህ የመግደል አቅሙ 50 በመቶ የሆነ በሽታ የተስፋፋው በኮቪድ-19 እጅግ የታመሙ ሰዎች የሚወስዱትን ኃይል ሰጪ መድኃኒት ተከትሎ ነው ይላሉ። ስቴሮይድስ አሊያም ደግሞ ሰው ሰራሽ ሆርሞን የሚባሉት ሳንባ እንዳይቆጣ በማድረግና የሰውነት መከላከል አቅምን በመጨመር ይታወቃሉ። ነገር ግን ዳያቢቲስ ያለባቸው እንዲሁም የለሌባቸው ሰዎችን የመከላከል አቅምን ሊያዳክሙም ይችላሉ። በዚህ ጊዜ ነው ይህ ሙኮርሚኮሲስ የተሰኘው በሽታ የሚቀሰቀሰው ሲሉ ዶክተሮች ያብራራሉ። በሁለተኛው ማዕበል እጅግ በተመታችው ሙምባይ ውስጥ ባሉ ሶስት ሆስፒታሎች የሚሠራው ዶክተር ናይር ከባለፈው ወር ጀምሮ ቢያንስ 40 ሰዎች በዚህ በሽታ ሲጠቁ ማየቱን ይናገራል። ከባፈለው ታህሣሥ እስከ የካቲት ባለው ጊዜ በአምስት ዋና ዋና ከተሞች 58 ሰዎች በዚህ በሽታ የተጠቁ ሰዎች ተገኝተዋል። አብዛኛዎቹ ሰዎች በዚህ የሚጠቁት ከኮቪድ-19 ካገገሙ በኋላ ከ12-15 ባሉት ቀናት ነው። የሙምባይ ሳዮን ሆስፒታል ባለፉት ሁለት ወራት 24 ሰዎች በዚህ ሰው ለይቶ በሚያጠቃ በሽታ መያዛቸውን ሪፖርት አድርጓል። ከእነዚህ ሰዎች መካከል አስራአንዱ አንድ ዓይናቸውን እንዲያጡ ሲሆኑ ስድስቱ ደግሞ ሕይወታቸውን አጥተዋል። በቤንጋሉሩ ከተማ የዓይን ቀዶ ጥገና ባለሙያ የሆኑት ዶክተር ራንጉራጅ ባለፉት ሁለት ሳምንታት 19 በሙኮርሚኮሲስ የተጠቁ ሰዎች ማየታቸውንና አብዛናዎቹ ደግሞ ወጣቶች መሆናቸውን ይናገራሉ። ዶክተሮች ይህ በፈንገስ የሚመጣው በሽታ በሁለተኛው ማዕበል እንዲህ በፍጥነት መስፋፋቱ እንዳስደገነጣቸው ይናገራሉ። ዶ/ር ናይር ባፈለው አንድ ዓመት ሙምባይ ውስጥ 10 በዚህ በሽታ የተያዙ ሰዎች ማግኘቱን ያስታውሳል። ነገር ግን በዚህ ዓመት እጅግ በፍጥነት መስፋፋቱን ይናገራል። በዚህ በሽታ የተያዙ ሰዎች አፍንጫቸው ይታፈናል፣ ይደማል እንዲሁም ዓይናቸው አካባቢ እብጠት ሕመም ይሰማቸዋል። ትንሽ ቆይቶ የማየት አቅማቸው እየተዳከመ ይመጣና በስተመጨረሻ ዓይነ ስውር ይሆናሉ። ይህን በሽታ ለመከላከል የሚረዳው መድኃኒት አንዱ 48 ዶላር የሚሸጥ ሲሆን ይህን መድኃኒት ለተከታታይ ስምንታት መውሰድ ግድ ይላል።
45675618
https://www.bbc.com/amharic/45675618
ጠቅላይ አቃቤ ህግ በሰኔው የቦምብ ጥቃት አምስት ግለሰቦች ላይ የሽብርተኝነት ክስ መሰረተ
ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ድጋፍ ለመግለጽ አዲስ አበባ ውስጥ በተካሄደ ሰልፍ ላይ ቦምብ በማፈንዳት ተጠርጥረው በተያዙ ግለሰቦች ላይ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የሽብርተኝነት ክስ መሰረተ።
በሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም በተፈፀመው ጥቃት የሙሳ ጋዲሳና ዮሴፍ አያሌው የተባሉ ግለሰቦች ህይወታቸው ማለፉንና ከ163 በላይ ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱ በክሱ ተገልጿል። •የብአዴን መግለጫ፡- ከስያሜ መቀየር እስከ ኢትዮ ሱዳን ድንበር •የተጠበቀውን ያህል የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች አልተመለሱም •የካማሼ ዞን አመራሮች በታጣቂዎች ተገደሉ ከተፈፀመው ከዚህ የቦምብ ጥቃት ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች በፖሊስ ተይዘው ምርመራ የተደረገባቸው ሲሆን ከእነዚህም መካከል አምስቱ ላይ በአቃቤ ህግ ዛሬ ክስ ተመስርቶባቸዋል። አቃቤ ሕግ ቦምብ በማፈንዳት የወንጀል ክሱ የተመሰረተባቸው አምስቱ ተጠርጣሪዎች ጌቱ ግርማ፣ ብርሃኑ ጃፈር፣ ጥላሁን ጌታቸው፣ ባህሩ ቶላ እና ደሳለኝ ተስፋዬ ናቸው። የጠቅላይ አቃቤ ህግ ክስ እንደሚያመለክተው አንደኛ ተከሳሽ ጌቱ ግርማ ከሁለተኛ ተከሳሽ ጋር ሱሉልታ ላይ በመገናኘት ሰልፉን የጠራው ገለልተኛ ወገን ሳይሆን ኢህአዴግ ነው ኤችአር 128 የተባለውን በአሜሪካ ኮንግረስ የተላለፈውን ውሳኔ ተግባራዊ እንዳይሆን ያደርጋል የሚል ምክንያቶችን በመግለጽ ቦምቡን በመወርወር እንዲበተን እናድርግ በማለት እንዲዘጋጁ አድርጓል። ለሦስተኛ ተከሳሽ ደውሎም ቦምብ የሚወረውር ሰው አንዲፈልግ ተልዕኮ መስጠቱ በክሱ ተገልጿል፡፡ ሌሎችም ተከሳሾች በቡድን በመደራጀት ለጊዜው በቁጥጥር ስር ባልዋሉ ግለሰቦች ጋር በመተባበር በተለያየ መንገድ ቦምቡን ለመወርወር ሰዎችን በመመልመልና በሌሎችም ጉዳዮች ተሳታፊ እንደሆኑ ክሱ አትቶ በሽብርተኝነት ድርጊትም ወንጅሏቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ የቦብ ፍንዳታውን የወንጀል ድርጊት ያቀነባበረችው በኬንያ ናይሮቢ የምትገኝ ገነት ታምሩ (ቶለሺ ታምሩ) የምትባል መሆኗን፣ ዓቃቤ ሕግ በክሱ አመልክቷል፡፡
50127054
https://www.bbc.com/amharic/50127054
ኤርትራ በዶይቼ ቬለ ዘገባ ሳቢያ የጀርመን አምባሳደር ማብራሪያ እንዲሰጡ ጠየቀች
የኤርትራ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር በዶይቼ ቬለ (የጀርመን ድምጽ ራዲዮ) ዘገባ ምክንያት በኤርትራ የጀርመን አምባሳደር ማብራሪያ እንዲሰጡ ጠየቀ።
የኤርትራ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር የማነ ገብረ መስቀል "ያልተቋረጠ የመረረ ትችት" ባሉት የዶይቼ ቬለ ዘገባ ምክንያት በኤርትራ የጀርመን አምባሳደር ቀርበው ማብራሪያ እንዲሰጡ መጠየቃቸውን በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። • የዛሬዋን ኤርትራ የሚገልጹ አስደናቂ እውነታዎች • አሥመራን አየናት፡ እንደነበረች ያለችው አሥመራ የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ በጀርመን መንግሥት ፈንድ የሚንቀሳቀሰው የዶይቼ ቬለ የአማርኛ እና የእንግሊዘኛ አርታኢዎች የኤርትራን ብሔራዊ አገልግሎት በተመለከተ እንዲሁም በኤርትራ እና በኢትዮጵያ መካከል ስለተደረሰው የሰላም ስምምነት የተሳሳተ መረጃን ያስተላልፋሉ ሲሉ ነቅፈዋል። የኤርትራን መንግሥት ያስቆጣው የዶይቼ ቬለ ዘገባ በትክክለ የቱ እንደሆነ ግልጽ ባይሆንም፤ በቅርቡ በድረ-ገጹ ላይ ይዞት የወጣው ጽሁፍ አንዱ ሳይሆን እንደማይቀር ተገምቷል። ይህ ከ10 ቀናት በፊት በአማርኛ ዴስክ ኃላፊ በሆነው ሉደር ሽዶመስኪይ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተጻፈው የግል አስተያየት፡ ''ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ የለውጥ አራማጅ ቢሆኑም ከኤርትራ ጋር በደረሱት ሰላም ምክንያት የኖቤል የሰላም ሽልማት እንዲሰጣቸው መወሰኑ ስህተት ነው'' የሚል ይዘት አለው። ሉደር በጽሁፉ የኤርትራውን ፕሬዝደንት "ብስጩና ፈላጭ ቆራጭ መሪ" ሲል የገለጻቸው ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ". . . ስልጣን ላይ ለመቆየት ጭካኔ በተሞላበት መልኩ ዜጎቹን በሰንሰለት ያስራል። . . . በዓለም ዓይን በግማሽ እድሜው በሚያንሰው መሪ መበለጥ የሚያስደስትው አይሆንም" በማለት ፕሬዝደንቱን ከጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ጋር አነጻጽሮም አስነብቧል። በጉዳዩ ላይ የጀመርን መንግሥትም ሆነ ዶይቼ ቬለ ያሉት ነገር የለም። • የኤርትራ ወጣቶችና ምኞታቸው የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ ጨምረውም፤ ቢቢሲን በተመለከተም ከዚህ ቀደም "ከአንድም ሁለቴ [በኤርትራ] የዩናይትድ ኪንግደም አምባሳደር በጉዳዩ ላይ የመንግሥታቸው አቋም እና አስተያየት ምን እንደሆነ" መጠየቃቸውን በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። "በዚህም አስፈላጊ እርምጃዎች የማይወሰዱ ከሆነ ሌሎች አማራጮች/ዘዴዎች እንከተላለን" ሲሉ የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፈረዋል።
42368446
https://www.bbc.com/amharic/42368446
በሀሰተኛ መድሃኒት ሰዎች እየሞቱ ነው
ልጅዎ በጠና ታሞቦታል እንበል። የሚታይበት ምልክት ሁሉ በቀዳሚነት ዓለም ላይ የልጆች ገዳይ የሆነው ወባ ነው። ቢሆንም መድሃኒት እሰጠዋለው ብለው ይፅናናሉ። መድሃኒቱንም ለልጅዎ ይሰጡታል።
መድሃኒቱ ልጅዎን እያሻለው አለመሆኑ ግን ያሳስብዎታል። ምክንያቱ ደግሞ የገዙት መድሃኒት ሀሰተኛ በመሆኑ ነው። ይህ ብዙዎች ሳያውቁ የተጎዱበት አሰቃቂ እውነታ ነው። ከዚህ ጀርባ ያሉት ደግሞ በብዙ ቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር የሚያንቀሳቅሱ ዓለም አቀፍ ተቋማት ናቸው። የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው አፍሪካ ውስጥ በዓመት 120ሺህ ሰዎች በሀሰተኛ የወባ መድሃኒት ሳቢያ ህይወታቸውን ያጣሉ። መድሃኒቶቹ ከደረጃ በታች ናቸው አልያም መያዝ ያለባቸውን ንጥረ ነገር ፈፅሞ አልያዙም። ሀሰተኛ መድሃኒቶች ብቻም ሳይሆኑ የጥራት ደረጃቸው የወረደ መድሃኒቶች እንኳን የመድሃኒት መላመድን ስለሚያስከትሉ ነገሩ በጣም አደገኛ ነው። መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሰሃራ በታች ባሉ አገራት ካሉት መድሃኒቶች አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ሀሰተኛ ናቸው። እነዚህ ሃሰተኛ መድሃኒቶች ደግሞ በየመድሃኒት ቤቱ፣ በየክሊኒኩ፣ በየመንገዱና በድረ-ገፆች ጭምር ይሸጣሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ውስን አቅም ያላቸው ተቋማት ይህን ለመከላከል እየተንቀሳቀሱ ነው። ቀላልና ርካሽ ለምሳሌ ስፕሮክሲል የተባለ ቴክኖሎጂ ኩባንያ ለችግሩ ቀላል መፍትሄ ፈጥሯል። ይህ ኩባንያ መድሃኒት አምራች ድርጅቶች እንዲመዘገቡና የሚያመርቷቸው መድሃኒቶች ማሸጊያ ላይ ኩባንያው የሚሰጣቸውን ስቲከር እንዲለጥፉ ያደርጋል። መድሃኒቶቹን የሚገዙ ሰዎች ስቲከሮቹን በመፋቅ የሚያገኟቸውን ቁጥሮች ለስፕሮሲስ ኩባንያ በስልክ መልዕክት ይልካሉ። ኩባንያውም መድሃኒቱ ትክክለኛ ስለመሆኑ በመልዕክት ማረጋገጫ ይሰጣል። ኩባንያው 24 ሰዓት የማረጋገጥ አገልግሎት ይሰጣል። እስካሁን 70 የሚሆኑ መድሃኒት አምራቾች የተመዘገቡ ሲሆን እስካለፈው የፈረንጆች ዓመት ድረስ 28 ሚሊዮን ማረጋገጫዎችንም ሰጥቷል። "ይህ ርካሽ የሆነ የደህንነት እርምጃ ነው"ይላሉ የስፕሮክሲል ቃል አቀባይ የሆኑት ጋባሞላዩን። ይህ የኩባንያው ሥርዓት በአፍሪካ በኬንያ፣ ጋና፣ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ታንዛኒያና ማሊ ተግባራዊ ሆኗል። ቢሆንም ግን ሥርዓቱ በአፍሪካ በደንብ ሊስፋፋ ይገባል። ምክንያቱም የሀሰተኛ መድሃኒቶች ገበያ አሁንም እንደደራ ነውና። ከአስር ዓመታት በፊት ተመሳሳይ "በሞባይል ያረጋግጡ" የሚል ሥርዓት የፈጠረ ኩባንያም ነበር። ይህ ሥርዓትም በተመሳሳይ መልኩ መድሃኒት ላይ የተለጠፉ ቁጥሮችን በስልክ መልዕክት በመላክ ለማረጋገጥ የሚረዳ ነው። ኩባንያው እንደሚለው ሥርዓቱ በናይጄሪያ ከመድሃኒት ምርትና ሽያጭ ሰንሰለት ጋር በተያያዘ ማረጋገጫዎችን በመስጠት ለቅኝትና ቁጥጥር አመቺ ሁኔታን ፈጥሯል። ይህ ደግሞ ተቆጣጣሪዎችንና አምራቾችንም ጠቅሟል። ይህ ኩባንያ በ12 የአፍሪካና የእስያ አገራት የሚንቀሳቀስ ሲሆን በተለይም በአፍሪካ ሃሰተኛ መድሃኒቶች በመያዛቸው 75 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰወች መጠቀማቸውን ድርጅቱ ይገልፃል። በስልክ መልእክት የመድሃኒቶችን እውነተኝነት ለማረጋገጥ ከመሞከር ባሻገር የመድሂኒት ተቆጣጣሪ አካላትን ብቃት የመገንባት እርምጃዎችም በዓለም አቀፍ መድሃኒት ተቆጣጣሪ ድረጅቶች ተሰጥቷል። የመድሃኒት ቁጥጥር ህጎችን ጨምሮ የተለያዩ ጥረቶች የተደረጉ ቢሆንም ዛሬም ሰዎች በሀሰተኛ መድሃኒቶች ህይወታቸውን እያጡ ነው። ጥረቶቹ ለምን አልተሳኩም? የተለያዩ የቁጥጥር ሥርዓቶችን የዘረጉ ኩባንያዎች እያሉና ብዙ ጥረቶች እየተደረጉ ሰዎች ለምን በሀሰተኛ መድሃኒቶች ይሞታሉ የሚለው አሁንም የብዙዎች ጥያቄ ነው። ከኩባንያዎቹ አንዱ እንደሚለው ብዙዎቹ ሃሰተኛ መድሃኒቶች የሚሰሩት እስያ ውስጥ ነው። የሃሰተኛ መድሃኒቶቹ ገበያ ስፋት ከቁጥጥር ሥራው ጋር ሲነፃፀር ገበያው በጣም ጠንካራ ነው። ይህ ማለት ደግሞ ቁጥጥሩ ላይ በጣም ሊሰራ ይገባል። የትልልቅ ዓለም አቀፍ መድሃኒት አምራች ኩባንያዎች የቁጥጥር ሥርዓቱን ለመቀላቀል መዘግየታቸውም ለችግሩ መባባስ በምክንያትነት ይጠቀሳል። በተጠቃሚዎችና በአምራቾች ዘንድም ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን የስፕሮክሲል ሥራ አመራሮች ይገልፃሉ። አመራሮቹ እንደሚሉት ሙስና ደግሞ ችግሩን ያባባሰ ሌላው ጉዳይ ነው። በዚህ ምክንያት ሃሰተኛ መድሃኒቶች መረጃው እያለና እየታወቀ እርምጃ ሳይወሰድባቸው እንዲያልፉና ገበያ ላይ እንዲውሉ ይደረጋል። ስለዚህ ከቁጥጥር ጎን ለጎን ተጠያቂነት ሊኖርና ቅጣቶች ሊጠብቁ እንደሚገባ ይገልፃሉ። ደካማ የመድሃኒት ቁጥጥር ህግና ደካማ ተቆጣጣሪ አካል ባለባቸው አገራት ዛሬም የሃሰተኛ መድሃኒቶች ገበያ እየደራና ለአንቀሳቃሾቹ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እያስገኘ ነው። ይህ የሚያሳየው ሃሰተኛ መድሃኒቶችን ለማስወገድ ቴክኖሎጂ ብቻውን ምንም የሚፈይደው ነገር አለመኖሩን ነው። ይልቁንም የህብረተሰብን ግንዛቤ መጨመር፣ የቁጥጥር ሥርዓትን ማጠናከርና ህጎችን ማጥበቅ የግድ ይላል።
news-53550068
https://www.bbc.com/amharic/news-53550068
በአፍሪካ በኮቪድ-19 የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር አነስተኛ መሆን ምን ያህል ይታመናል?
በደቡብ አፍሪካ የኮሮናቫይረስ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየተዛመተ ይገኛል። በአገሪቱ ውስጥ ለቫይረሱ ስርጭት መስፋፋት ሰበብ የሆኑና ሌሎች አፍሪካውያን ሊማሩባቸው የሚችሏቸው ነጥቦች ግን አሉ።
ቁጥሮች ሁሉን አይናገሩም ደቡብ አፍሪካ በአህጉሪቱ ከሚገኙ አገራት ሁሉ የተሻለ የመረጃ አሰባሰብና አደረጃጀት ልምድና ተሞክሮ አላት። ግን ቁጥሮችን ማመን ከባድ ነው። ቁጥሮችን ብቻ ሳይሆን እንደማሳያ የሚወሰዱ መረጃዎችን ማመኑም አዳጋች ነው። አንዳንድ ታዛቢዎች በአገሪቱ በኮቪድ-19 ተይዘው የሞቱ ሰዎች ቁጥር አነስተኛ መሆኑን በማየት ብቻ የአገሪቱን ስኬት ለማንቆለጳጰስ ይሮጣሉ። ይህ የሆነው በአገሪቱ ውስጥ የወጣቶች ቁጥር ከፍተኛ ስለሆነ ነው? ወይስ አፍሪካውያን የተለየ የመከላከል ብቃት፣ ተፈጥሮ ወይም ሌላ ምስጢር ስላላቸው ነው? መልሱ አጭርና ግልጽ ነው። አይደለም። ደቡብ አፍሪካ በኮቪድ-19 ምክንያት እየተጋፈጠች ያለውን ሞት ለመናገር ጊዜው ገና ነው። ለምሳሌ በደቡብ አፍሪካ ትልልቅ ሆስፒታሎች በኮቪድ-19 ተይዘው የሞቱ ሰዎችን ቁጥር ከጣልያን እና ዩናይትድ ኪንግደም ጋር ሲነጻጸር እጅጉን ተቀራራቢ ነው። ነገር ግን ይህንን ቁጥር ወደ ሆስፒታል መጥተው ሕክምና እርዳታ ከሚፈልጉ ሰዎች ውጪ መመልከት በተለያዩ አገራት የተለያየ መረጃ ይሰጣል። ይህ ደግሞ የሆነበት ምክንያት አገራት በመሰረታዊነት በኮቪድ-19 ምክንያት የተከሰተ ሞትን ሲመዘግቡ የተለያየ መስፈርትና ስልት ስላላቸው ነው። ፕሮፌሰር ሻቢር ማድሂ በዊትዋተርስራንድ ዩኒቨርስቲ የክትባት ባለሙያ ናቸው ስለሞት ምዝገባ ሲያስረዱም "እርባና የለውም" በማለት ነው። ለዚህ ደግሞ ምክንያታቸው በአህጉሪቱ በአጠቃላይ በጣም አነስተኛ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን በመጥቀስ ለማነፃፀርም ሆነ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ እንደማይቻል በመግለጽ ነው። የሆስፒታል ፍራቻ ደቡብ አፍሪካውያን ተመራማሪዎች ባሳተሙት አንድ ጥናት ላይ በኮቪድ-19 ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉ የሚጠረጠር ነገር ግን ያልተመዘገቡ 17 000 ሞቶች ማግኘታቸውን ጠቅሰዋል። ይህ ጥናት እንደሚያሳየው ዜጎች ወደ ሕክምና ተቋማት ለመሄድ ያላቸው ፍራቻ፤ በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ ተቋማቱ በቅርብ አለመገኘታቸው ተጨምሮበት ሳይታወቁ ለሚከሰቱ ሞቶች ሰበብ ሆኖ ሊሆን ይችላል ተብሏል። ይህም ማለት ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች በቤታቸው ውስጥ ያለምንም ሕክምና እርዳታ እየሞቱ ነው ማለት ነው። በደቡብ አፍሪካ ኮቪድ-19 ከተከሰተ በኋላ ቲቢ ለመመርመር ወደ ሆስፒታል የሚሄዱ ሰዎች ቁጥር በግማሽ፣ ለክትባት የሚመጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ በ25 በመቶ ቀንሷል። የሕክምና ቁሳቁስ እጥረት በደቡብ አፍሪካ ፖርት ኤልዛቤጥ በባለሃብቶች ትልቅ የኮሮናቫይረስን ለማከም የሚውል "የመስክ ሆስፒታል" ተገንብቷል። ነገር ግን ባለፉት ሳምንታት ካሉት 1200 አልጋዎች 30 ብቻ ነው በሕሙማን ተይዞ የነበረው። ለዚህ ደግሞ እንደምክንያት የተጠቀሰው የኦክስጅን አለመኖርና የባለሙያዎች እጥረት ነው። ፕሮፌሰር ማድሂ እንዲህ አይነት ሆስፒታሎች ሲገልጿቸው "አእምሮ የሌላቸው" ይሏቸዋል። ይህ ግን በደቡብ አፍሪካ ብቸኛው ማሳያ አይደለም። በርካታ ሆስፒታሎች የባለሙያ እጥረትና የኦክስጅን አለመኖር የኮቪድ-19 ህሙማንን በማከሙ ረገድ እግር ተወርች እንዳሰራቸው ይናገራሉ። ለዚህም በጎ ፈቃደኞችንና ለጋሾችን በመማፀን ያለውን እጥረት ለማሟላት እየጣሩ ነው። "ኦክስጅን ዋናው ነገር ነው" የሚለው በእነዚህ ሆስፒታሎች የሚሰራው ዶክተር፣ የባለሙያም ሆነ የኦክስጅን እጥረት እንዳለ እየታወቀና ለመግዛትም ሆነ ለመቅጠር ሙከራ ሳይደረግ፣ ለጤና ተቋማቱ ተጨማሪ የሕሙማን አልጋዎች ማስገባትና መዘርጋት የገንዘብም ሆነ የጊዜ ብክነት መሆኑን ያስረዳል። የኮሮናቫይረስ ወጀብ አብሮን ነው የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በቅርቡ ባደረጉት ንግግር ላይ እንደጠቀሱት "አሁንም ወጀቡ አብሮን አለ።" ይህ ንግግር ኮሮናቫይረስ ገና ድል አለመመታቱን ለመግለጽ የተጠቀሙበት ዘይቤ ነው። የፕሬዝዳንቱ ንግግር ለደቡብ አፍሪካም ሆነ ለቀሪው የአህጉሪቱ ክፍሎች እውነትነት እንዳለው የሚጠቅሱ ባለሙያዎች ምክራቸውን ይለግሳሉ። ክትባት ባልተገኘበት፣ ተፈጥሯዊ የወል መከላከያ ባልጎለበተበት ወይንም መሰረታዊ የባህሪ ለውጥ ባልመጣበት ሁኔታ ደቡብ አፍሪካ ኮሮናቫይረስን መመልከት ያለባት እንደ ቲቢና ኤች አይቪ አብሯት እንደሚቆይ ነው። ይህም ልክ ሁለቱን በሽታዎች ለማከም፣ ለመቆጣጠር የወሰደቻቸውን እርምጃዎችና የዘረጋቻቸውን ሥርዓቶች ለመተግበር ያስችላታል ይላሉ። ለዚህ ደግሞ ምክንያታቸው ቫይረሱ ለረዥም ጊዜ አብሮን እንደሚቆይ በማንሳት ነው። የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎች በየትኛው ስፍራ፣ መቼና በማን መደረግ አለባቸው የሚለው ወረርሽኙ ከተከሰተ ጊዜ አንስቶ ሲያነጋግር ነበር። አሁን ግን በርካታ አገራት ሕዝብ በሚሰበሰብባቸው ስፍራዎች መሸፈኛዎቹ መደረግ እንዳለባቸው ደንግገዋል። ደቡብ አፍሪካውያ ይህንኑ መመሪያ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ናቸው። በእርግጥ የደቡብ አፍሪካ ምግብ ቤቶች፣ ሆቴሎችና መዝናኛ ስፍራዎች የኮሮናቫይረስን ስርጭት ለመግታት በሚል መንግሥት በጣለው ገደብ የተነሳ መጠጥ እንዳይሸጡ መከልከላቸው አስቆጥቷቸዋል። ባለፈው ሳምንትም የምግብ ቤቶች ባለቤቶች ባዶ ወንበሮቻቸውን ይዘው አደባባይ ለተቃውሞ ወጥተው ነበር። አሁንም ቢሆን ግን ሃኪሞች በየትኛውም ስፍራ ሁል ጊዜና በአግባቡ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛን ማድረግ ኮሮናቫይረስን ለመከላከል እንደሚረዳ ይመክራሉ። በደቡብ አፍሪካ የተስተዋሉ ሌሎች ሁለት ነገሮች አሉ። የኮሮናቫይረስን ስርጭት ለመከላከል ትልልቅ ሆስፒታሎችና ተቋማት ብቻ ሳይሆኑ አነስተኛ ድርጅቶችና የግለሰቦች ጥረትም ወሳኝ በመሆናቸው ሊደገፉ እንደሚገባ ነው። ሌላው የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የሚታዩ ሙስናዎችን ማጋለጥ ቁልፍ ተግባር ሊሆን እንደሚገባም ተስተውሏል። በዚህ ወቅት የመከላከያ ቁሳቁስ ግዢ፣ የእርዳታ አቅርቦት ላይ የሚኖሩ ሙስናዎችን የመከላከል ሥራውንም ሆነ የቫይረሱ ስርጭት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖራቸዋል ሲሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
news-54984267
https://www.bbc.com/amharic/news-54984267
ትግራይ ፡ የኢትዮጵያ ሠራዊት ወደ መቀለ እያመራ መሆኑ ተነገረ
የኢትዮጵያ መንግሥት ሠራዊት በትግራይ ልዩ ኃይል ላይ ባለፉት ቀናት የበላይነት በመያዝ የተለያዩ ቦታዎችን ተቆጣጥሮ ወደ ክልሉ ዋና ከተማ እያመራ መሆኑን አሳወቀ።
የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳደር የሆኑት ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ለድምጺ ወያኔ ቴሌቪዥን እንደተናገሩት የፌደራሉ ሠራዊት ሽረንና ራያን መቆጣጠሩን አረጋግጠው ይህ "ጊዜያዊ ድል ነው" ብለዋል። ከመንግሥት የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው የመከላከያ ሠራዊቱ ወደ ዋና ከተማዋ እያመራ ባለበት በአሁኑ ጊዜ የህወሓት ኃይሎች "በሁሉም አቅጣጫ ወደ መቀሌ በሚወስዱት መንገዶች ላይ የሚገኙ አራት ድልድዮችን አፍርሰዋል" ብሏል። ከመንግሥት በኩል የሚወጡ መረጃዎችን ይፋ የሚያደርገው የአስቸኳይ ጊዜ መረጃ ማዕከል እንዳለው ሠራዊቱ በትግራይ በምሥራቅና በምዕራብ ግንባሮች "ወሳኝ ድሎችን ተቀዳጅቷል።" በዚህም መሰረት ሠራዊቱ በምሥራቅ በኩል ጨርጨር፣ ጉጉፍቶና መሖኒን ጨምሮ የራያ አካባቢን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ ወደ መቀለ እያመራ መሆኑን ገልጿል። በተጨማሪም በምዕራብ በኩል በአዲ ነብሪድና በአዲ ዳእሮ የነበሩ ከባድ ምሽጎችን በማፍረስ ሽሬን በመቆጣጠር ወደ አክሱም ከተማ እያመራ መሆኑን አመልክቷል። በተጠቀሱት አካባቢዎችም በተደረጉ ውጊያዎች በርካታ መሣሪያዎች መማረካቸውን ገልጾ፤ በውጊያው ተሰልፈው የነበሩ የትግራይ ልዩ ኃይል አባላት በቁጥጥር ሥር ውለዋል ብሏል። የመረጃ ማዕከሉ በተጨማሪም የሽሬ ከተማ በአገሪቱ ሠራዊት መያዟን ተከትሎ በሽሬና በአኩስም መካከል የሚገኘው የአስፓልት መንገድ "በግሬደር ተቆፍሮ ወደ ጉድጓድነት ተቀይሯል" ሲል አመልክቷል። ሁለት ሳምንታት ያስቆጠረው በፌደራል መንግሥቱና በትግራይ ልዩ ኃይሎች መካከል እየተደረገ ያለው ግጭት ከተቀሰቀሰ ጀምሮ በክልሉ ውስጥ ያለው የግንኙነት መስመር በመቋረጡ ዝርዝር መረጃዎችን ለማግኘት አዳጋች ሆኗል። የፌደራል መንግሥቱ የትግራይ ክልልን ከሚያስተዳድረው ህወሓት ጋር የነበረው አለመግባባት ተካሮ ወደ ጦርነት የተሸጋገረው በክልሉ በሚገኘው የሠሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መሰንዘሩ ከተገለጸና ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ሕግን ማስከበር" ያሉት ወታደራዊ እርምጃ መወሰድ ከጀመረ በኋላ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በትግራይ ክልል ተሰልፈው ያሉ የልዩ ኃይልና ሚሊሻ አባላት ለአገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት በሠላም እጃቸውን እንዲሰጡ የተቀመጠው የሦስት ቀናት ቀነ ገደብ መጠናቀቁን አስመልክቶ ትናት፤ "በቀጣይ ቀናት ውስጥ የመጨረሻው ሕግን የማስከበር ወሳኝ እርምጃ በትግራይ ውስጥ ባሉ ኃይሎች ላይ ይወሰዳል" ማለታቸው ይታወሳል።
news-52635909
https://www.bbc.com/amharic/news-52635909
"ምዕራባውያን ለአፍሪካ ሃገር በቀል መድኃኒቶች ንቀት አለባቸው" ሲሉ የማዳጋስካሩ ፕሬዚዳንት ተቹ
ከሰሞኑ የማዳጋስካሩ ፕሬዚዳንት አንድሪ ራጆይሊና ለኮሮናቫይረስ ፈውስ ከተለያዩ አገር በቀል ዕፅዋት አግኝተናል ማለታቸውን ተከትሎ፤ ያልተፈተነ መድኃኒት ነው እንዲሁም በተለያዩ ሙከራዎች አላለፈም የሚሉ ትችቶች እየተሰሙ ነው።
ባለፈው ሳምንት የአለም ጤና ድርጅት ያልተፈተነ መድኃኒቶችን አትውሰዱ ብሎ ማስጠንቀቁንም ተከትሎ የማዳጋስካሩ ፕሬዚዳንት በሁኔታው ደስተኛ አልሆኑም። ድርጅቱ ሃገር በቀል መድሃኒቶችን በሚጠቀሙበት ወቅት ተገቢ የሆኑ ሙከራዎችን ማለፋቸውን መረጋገጥ አለባቸው ብሏል። •በኮሮናቫይረስ ከተቀጠፉ ኢትዮጵያውያን መካከል ጥቂቶቹ •“ያልተፈተነ መድኃኒት አትውሰዱ” የአለም ጤና ድርጅት የአለም ጤና ድርጅትም ሆነ የምዕራቡ አለም ሃገር በቀል የኮሮናቫይረስ መድሃኒትን የሚተቹት "ለአፍሪካ ሃገር በቀል መድሃኒት ንቀት ስላላቸውና የበላይ ነን ብለው ስለሚያስቡ ነው" በማለት ፕሬዚዳንቱ ትችታቸውን ለፈረንሳዩ ሚዲያ ፍራንስ 24 ተናግረዋል። "መድኃኒቱን ያገኘቸው ማዳጋስካር ባትሆንና አንዷ አውሮፓዊ ሃገር ብትሆን በፈዋሽነቱ ላይ ጥርጣሬ ወይም ጥያቄ የሚነሳ ይመስላችኋል? በጭራሽ አይመስለኝም" ብለዋል ፕሬዚዳንቱ ይህንን ይበሉ እንጂ መድኃኒቱ ፈዋሽ ስለመሆኑ በቂ መረጃ የለም ተብሏል። የአፍሪካ ህብረት መድኃኒቱ "ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑና አዳኝነቱን" በተመለከተ ሳይንሳዊ ድጋፎችን እንዲቀርቡለት ጠይቋል። ይሁን እንጂ ጊኒ ቢሳው፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ታንዛንያና ላይቤሪያ ከዕፅዋት የተቀመመውን መድኃኒት ወደ ሃገራቸው እንዲመጣ አዘዋል፤ የተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት መድሃኒቱን ወደ ሃገራቸው በማስገባት ላይ ይገኛሉ። ናይጄሪያም መድኃኒቱን እንደምትፈልግ አስታውቃለች። የናይጄሪያ የኮሮናቫይረስ መቆጣጠሪያ ግብረ ኃይል እንዳስታወቀው ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ መድኃኒቱ ወደ ናይጄሪያ እንዲገባ ፈቃድ ሰጥተዋል ብሏል። ሆኖም መድኃኒቱ ለኮሮና ህሙማን ከመሰጠቱ በፊት የማረጋገጫ ሂደቶች እንደሚከናወኑ አስታውቀዋል። መድኃኒቱ የተሰራው የወባ በሽታንና ለሌሎችም በሽታዎች መድኃኒት ከሆነው የአሪቲ ቅጠል (አርቲሚዥያ)ና ሌሎችም ዕፅዋት መሆኑ ተነግሯል። ከተለያዩ ዕፅዋት የተቀመመው መድኃኒት በባለፉት ሶስት ሳምንታት በሃያ ሰዎች ላይ ሙከራ መደረጉን የፕሬዚዳንቱ አማካሪ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይህም የአለም አቀፉ ጤና ድርጅት ካወጣው መመሪያ ጋር ይጣረሳል ተብሎም እየተተቸ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ሰዎች የቫይረሱን መዛመት ለመቆጣጠር የሚያደርጓቸውን ጥንቃቄዎች ችላ በማለት ራሳቸውን ሊያጋልጡ ይችላሉ እንዲሁም "ሃሰተኛ ተስፋን" ይሰጣል እየተባለ ነው። ከሰሞኑም በአፍሪካ የአገር በቀል መድኃኒቶች ላይ ሰባ ባለሙያዎችን ያሳተፈ አንድ ስብሰባ የተደረገ ሲሆን፤ ባለሙያዎቹም የአገር በቀል መድኃኒቶች በተለያየ ሙከራ ሊያልፉ እንደሚገባ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የአለም አቀፉ ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቅርንጫፍ በትዊተር ገፁ አስፍሯል።
news-52690047
https://www.bbc.com/amharic/news-52690047
የኮሮናቫይረስ ክትባት ለዓለም ሕዝብ በነጻ እንዲቀርብ ግፊት እየተደረገ ነው
ከ140 በላይ የዓለም መሪዎች፣ ባለሙያዎችና ታዋቂ ሰዎች የኮሮናቫይረስ ክትባትና መድኃኒት ለሁሉም የዓለም ሕዝብ በነጻ እንዲቀርብ ጥያቄ አቀረቡ።
ከዚህ ቀደም ባልታየ ሁኔታ እነዚህ ተሰሚነት ያላቸው ሰዎች በጋራ ባወጡት ደብዳቤ ላይ ማንም ከማንም ሳይለይ ወረርሽኙን ለመመርመር፣ ለመከላከልና ለማከም የሚያስፈልጉ መገልገያዎች ሲገኝ ለሁሉም በነጻ እንዲቀርብ ነው ጥያቄ ያቀረቡት። የኮቪድ-19 ክትባትን ለማግኘት እየተደረጉ ያሉት ምርምሮች ውጤታማ ወደ መሆን በተቃረቡበት በአሁኑ ወቅት ሐብታም አገራት ቀድመው በተናጠል ምርቱን በማግኘት ለዜጎቻቸው ለማቅረብ ሽሚያ መጀመራቸውን ተከትሎ ነው ታዋቂዎቹ ሰዎች ደብዳቤውን የጻፉት። የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንትና የአፍሪካ ሕብረት የወቅቱ ፕሬዝዳንት የሆኑትን ሲሪል ራማፎሳ፣ የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የሴኔጋሉና የጋና ፕሬዝዳንቶች፣ የአፍሪካ ሕብረት ዋና ጸሐፊን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ ያሉ 140 ታዋቂ ፖለቲከኞችና ባለሙያዎች ደብዳቤው ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል። በተባበሩት መንግሥታት የጸረ ኤድስ ድርጅትና በኦክስፋም አስተባባሪነት የተዘጋጀው ይህ ደብዳቤ ከኮሮናቫይረስ የሰዎችን ህይወት ለመታደግ የሚረዱ መከላከያዎችና መድኃኒቶችን ለመቆጣጠር የሚደረገው ፉክክር ከባድ ጉዳትን ሊያስከትል እንደሚችል አስጠንቅቋል። ደብዳቤው የዓለም መሪዎች የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያስፈልገውን ክትባት፣ መድኃኒትና መመርመሪያን ማንም በባለቤትነት እንዳይዛቸውና በስፋት ተመርተው በአግባቡ ለሁሉም አገራት ዜጎች በነጻ እንዲቀርቡ እንዲያደርጉ ጠይቋል። "በአሁኑ ጊዜ ወረርሽኙ እንዲያበቃ ቢሊዮኖች ክትባትን ተስፋ አድርገው እየጠበቁ ነው" ያሉት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ የአፍሪካ አገራት ክትባቱ ከባለቤትንት ነጻ ሆኖ በቶሎ እንዲቀርብ ይፈልጋሉ በማለት ማንም ቀዳሚ ማንም ከኋላ መሆን የለበትም ብለዋል። በርካታ አገራት የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት ጥረት እያደረጉና ተስፋ ሰጪ ውጤት እያገኙ ሲሆን በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በአውሮፓ ሕብርት አነሳሽነት በተካሄደው የገንዘብ ማሰባሰቢያ ላይ 8 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለምርምርና ለምርት ቀርቧል። አሜሪካ ክትባቱን ሊያመርት ይችላል የተባለውን የፈረንሳይ የመድኃኒት አምራች ኩባንያ ሳኖፊ የኮቪድ-19 ክትባትን መስራት ከጀመረ ለአሜሪካ ገበያ ቀድሞ መስጠት አለበት በማለት ግፊት እያደረገች ነው። ለዚህ ጥያቄዋ ተቀባይነትም "የአሜሪካ መንግሥት ምርምሩ ላይ ቀድሞ ኢንቨስት በማድረጉ በብዛት ቀድሞ የማዘዝ መብት አለው" የሚል ነው። ይህንንም ተከትሎ አንድ ከፍተኛ የፈረንሳይ ባለስልጣን ጥያቄው "ተቀባይነት የለውም" ሱሉ ተቃውመውታል። የኮሮናቫይረስ ህመም ምልክቶችና እንዳይዘን ማድረግ ያለብን ጥንቃቄ
50474994
https://www.bbc.com/amharic/50474994
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ ከህወሓት አመራሮች ጋር ያደረጉት ውይይት ውጤታማ ሆኖ ይሆን?
ቅዳሜ ኅዳር 7/ 2012 ዓ.ም በተካሄደው የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ግንባሩ ወደ ውህደት እንዲያመራ በአብላጫ ድምጽ ሲወሰን ስድስት የህወሓት ተወካዮች የተቃውሞ ድምጽ ሰጥተው ነበር።
በቀጣዩ ቀን ዕሁድም በተካሄደው ስብሰባ ላይ የህወሓት አባላት ያልተሳተፉ ቢሆንም ከኢህአዴግ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ጋር የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አባላት ተገናኝተው ሊወያዩ እንደሆነ ቢቢሲ የህወሓት ከፍተኛ አመራር አባል የሆኑትን አቶ አስመላሽ ወልደሥላሴን ጠቅሶ ዘግቦ ነበር። • የብልጽግና ፓርቲ ከአማርኛ በተጨማሪ ኦሮምኛና ሌሎችም ቋንቋዎች የሥራ ቋንቋ እንዲሆኑ ወሰነ • የተቀዛቀዘችው ሐዋሳ: በሕዝበ ውሳኔው ዋዜማ • የሲዳማ ሕዝበ ውሳኔ ውጤት ሐሙስ እንደሚታወቅ ይጠበቃል እንደተባለውም ጠቅላይ ሚኒስትሩና የህወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በኢህአዴግ የውህደት ሂደት ላይ በተፈጠረው የአቋም ልዩነት ላይ መወያየታቸውን ለግንባሩ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ቢቢሲ ዛሬ ማክሰኞ ከህወሓት ጽሕፈት ቤት ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የግንባሩን ውህደት በተመለከተ የህወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር እሁድ ዕለት ያደረጉት ውይይት ውጤታማ ሳይሆን እንደቀረ ያመለክታል። በውይይቱ ላይም በኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ቅዳሜ ዕለት ከተሳተፉት ስምንት አባላት መካከል አንደኛው በሥራ ጉዳይ ወደ መቀሌ በመሄዳቸው ምክንያት ሰባቱ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በተደረገው ውይይት ላይ እንደተሳተፉ ተነግሯል። ምን ተወያዩ፤ ውጤቱስ? ቢቢሲ ውይይቱን በተመለከተ ከህወሓት ጽህፈት ቤት ያገኘው መረጃ የህወሓት አባላት በጉዳዩ ላይ ደግመው እንዲያስቡበትና ከግንባሩ ጋር አብረው እንዲሰሩ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጥያቄ ቀርቦላቸው እንደነበረ ያመለክታል። ይሁን እንጂ በቅዳሜው ስብሰባ ላይ የተሳተፉት የህወሓት ሥራ አሰፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ቀደም ሲል በውህደቱ ጉዳይ ላይ ከያዙት አቋም ውጪ የሚቀይሩት ነገር እንደሌለ በመግለጽ በውሳኔያቸው ስለጸኑ ውይይቱ የተጨበጠ ፍሬ ሳይገኝ ማብቃቱ ተገልጿል። እስከ ትናንት [ሰኞ] ድረስ ለሦስት ቀናት የቀጠለው ኢህአዴግና የአጋር ድርጅቶቹ የግንባሩን ውህደት በተመለከተ ሲያካሂዱት የነበረውን ስብሰባ አጠናቀው ጉዳዩን ለድርጅቱ ምክር ቤት እንዲቀርብ መወሰናቸው ተገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድም በማህበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ እንዳሰፈሩት በሚዋሃደው ፓርቲ ሕገ ደንብ ላይ እንደተወያዩና እንዳጸደቁት ጠቅሰው ሰንወያይ "ወደ ምክር ቤቱ እንዲመራ ወስነናል" ብለዋል። አክለውም "የሦስቱም ቀናት ውይይታችን ግልጽና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ ተካሂዷል። ውይይቱ ይበልጥ አመራሮቹን ያቀራረበ ሆኖ በመጠናቀቁ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል" ሲሉ ውይይታቸው በመግባባት መጠናቀቁን ጠቅሰዋል። ከዚህ በኋላ ህወሓት፣ ቀሪዎቹ የግንባሩ አባላትና አጋር ድርጅቶች በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በኩል ሂደቱ ስላለቀ በቀጣይ በሚካሄደው የኢህአዴግ ምክርቤት መድረክ በውህደቱ ላይ ሊወያዩ እንደሚችሉ ይጠበቃል። ለረዥም ግዜ ሲመከረበትና ሲጠና የቆየው የኢህአዴግ የውህደት ጉዳይ ላይ ሌሎቹ የግንባሩ አባላትና አጋር ድርጅቶች የደገፉት ሲሆን፤ ህወሓት ግን በነበረው የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ፕሮግራም መቀጠል አለብን በማለቱ ነው ልዩነቱ የተፈጠረው። ህወሓት ግንባሩን የማዋሃዱ ጥረት "አሃዳዊ ሥርዓት ለመፍጠር እና በስልጣን ላይ ለመቆየት የሚደረግ መሆኑ ሲናገር" ውህደቱን የሚፈልጉት ደግሞ "ከለውጡ ጋር የሚሄድ አዲስ ፕሮግራም አስፈላጊ" መሆኑን ይጠቅሳል። ጠቅላይ ሚኒስተር ዐብይ አህመድ እና ሌሎች የውህደቱ ደጋፊ የደርጅቶች አመራሮች በበኩላቸው ውህደቱ አሀዳዊ ሥርዓትን የማያመጣና ሕብረ ብሔራዊ ፌደራሊዝሙን የሚያስቀጥል እንደሚሆን በመጥቀስ የውህደቱ ጠቀሜታ ይጠቅሳሉ። ቢቢሲ የኢህአዴግ ሊቀመንበር በሆኑት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድና በህወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት መካከል የነበረውን ውይይት በተመለከተ መረጃ ለማግኘት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤትን ቢጠይቅም ጉዳዩ የግንባሩ ጽህፈት ቤት መሆኑ ተገልጾለታል። በተጨማሪም ከኢህአዴግ ጽህፈት ቤት መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካልንም።
news-45557292
https://www.bbc.com/amharic/news-45557292
ጨረቃን የሚረግጠው የመጀመሪያው ጎብኚ ታወቀ
ስፔስ ኤክስ የተሰኘው ኩባንያ ቱሪስት ሆኖ በመጀመሪያ ወደ ጨረቃ የሚሄደው ደንበኛው የ42 ዓመቱ ጃፓናዊ ቢሊየነር ያሱካ ማዚዋ እንደሆነ አስታወቀ።
ቢሊየነሩ ስምነት የሚሆኑ አርቲስቶች አብረውት እንዲጓዙ ይጋብዛል ያሱካ ማዚዋም "ወደ ጨረቃ መሄድን መርጫለሁ"ብሏል። ጨረቃን የሚጎበኘው ይህ ጃፓናዊ ቱሪስት ወደ ጨረቃ የሚመጥቀው ኩባያው እንደ አውሮፓውያኑ በ2016 ይፋ ባደረገ መርሃግብር መሰረት መሆኑ ተገልጿል። ይህ የጨረቃ ጉዞ የታቀደው ለ2023 ሲሆን የናሳዋ አፖሎ 17 እንደ አውሮፓውያኑ በ1972 ጨረቃ ላይ ካረፈች ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰው ልጅ ጨረቃን የሚረግጥበት አጋጣሚ ይሆናል ተብሏል። • ስለተፈፀመው ጥቃት እስካሁን የምናውቀው • አቶ ዳውድ ኢብሳ ማናቸው? • ረሃብ የቀሰቀሰው ፈጠራ ይህ ጉዞ ይፋ የተደረገው ዛሬ ኒዮርክ ላይ ሲሆን ኩባንያው "ወደ ህዋ የመጓዝ ህልም ላላቸው በየእለቱ መሄድ እንዲችሉ ለማድረግ ይህ ወሳኝ እርምጃ ነው" ብሏል። ሚስተር ማዚዋ ባለፈው ዓመት ኒውዮርክ ላይ ተደርጎ በነበረ ጨረታ ለአንድ የስዕል ሥራ 110.5 ሚሊዮን ዶላር መክፈሉን ተከትሎ የመገናኛ ብዙሃን ርዕስ ሆኖ ነበር። ቢሊየነሩ ወደ ህዋ በሚያደርገው ጎዞ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተውጣጡ ስድስት ወይም ስምንት አርቲስቶች አብረውት እንዲጓዙ እንደሚጋብዝም አስታውቋል። "ወደ መሬት ሲመለሱ የሆነ ነገር እንዲሰሩ ይጠየቃሉ። እነዚህ የሚሰሩ ምርጥ የጥበብ ውጤቶች ለሁላችን መነሳሳትን ይፈጥራሉ" በማለት ቢሊየነሩ ለጋዜጠኞች ተናግሯል።
news-53498009
https://www.bbc.com/amharic/news-53498009
አሜሪካ የኮቪድ-19 ክትባት ምርምሮችን ‘ሰልለዋል’ ያለቻቸውን ቻይናውያን ከሰሰች
ቻይና የኮቪድ-19 ክትባት ምርምር የሚያካሂዱ ቤተ ሙከራዎች ላይ ስለላ እያደረገች ነው ሲል የአሜሪካ የፍትህ ተቋም ወነጀለ።
በኮሮናቫይረስ ላይ የሚደረግ ምርምርን ሰልለዋል የተባሉ ሁለት ቻይናውያን ክስ ተመስርቶባቸዋል። ክሱ የተመሰረተው አሜሪካ ቻይናን በበይነ መረብ ስለላ አምርራ መተቸቷን ተከትሎ ነው። ባለፈው ሳምንት አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ካናዳ፤ ሩስያ የኮቪድ-19 ምርምር ለመስረቅ ሞክራለች ብለው ነበር። አሜሪካ የከሰሰቻቸው ቻይናውያን የቀድሞ የኤሌክትሪክ ምህንድስና ተማሪዎቹ ሊ ዢያዩ እና ዶንግ ጂአዚ ናቸው። የንግድ ሚስጥር በመስረቅና ለበይነ መረብ የገንዘብ ምዝበራ በመመሳጠር ተወንጅለዋል። አሜሪካ የከሰሰቻቸው ቻይናውያን የቀድሞ የኤሌክትሪክ ምህንድስና ተማሪዎቹ ሊ ዢያዩ እና ዶንግ ጂአዚ ናቸው። ክሱ ምንድን ነው? ዐቃቤ ሕግ እንደሚለው ከሆነ ሁለቱ ቻይናውያን መጋቢት ላይ የማስቹሴትስ የባዮቴክኖሎጂ ተቋምን ሰልለዋል። በተቋሙ ለኮቪድ-19 ክትባት ለማግኘት ጥናት እየተደረገ ይገኛል። ሜሪላንድ የሚገኝ ድርጅት ኮሮናቫይረስ ላይ ምርምር እያደረገ መሆኑን አስታውቆ በሳምንቱ ቻይናውያኑ የድርጅቱን በይነ መረብ ሰርስረው እንደገቡም ተገልጿል። ተጠርጣሪዎቹ አብዛኛውን ጊዜ በግላቸው በበይነ መረብ መረጃ ቢሰርቁም፤ አልፎ አልፎ የቻይና ሰላዮች ድጋፍ ያደርጉላቸዋል ተብሏል። ድጋፍ አድርገዋል ከተባሉት መካከል የቻይና የብሔራዊ ደህንነት ኃላፊ ይገኙበታል። ከጎርጎሮሳውያኑ 2009 ወዲህ በመቶ ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የንግድ ሚስጥር እና አዕምሯዊ ንብረት መስረቃቸውን ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል። ቻይና የሚኖሩት እነዚህ ግለሰቦች፤ ስለ ኮሮናቫይረስ ክትባት፣ ህክምና እና ምርመራ መረጃ ለማግኘት የባዮቴክ ተቋማትን የመረጃ መረብ ደህንነት ጥሰዋል። ከአሜሪካ በተጨማሪ አውስትራሊያ፣ ቤልጄም፣ ጀርመን፣ ጃፓን፣ ሊቱኒያ፣ ኔዘርላንድስ፣ ስፔን፣ ስዊድን እና ዩናይትድ ኪንግደም ኢላማ ተድገዋል። ቻይናውያኑ የዩኬን ሰው ሰራሽ ክህሎት (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ) ተቋም፣ የስፔንን የመከላከያ ተቋም እና አውስትራሊያን የፀሐይ ብርሃን ሀይል ተቋም ሰረስረው መግባታቸው በክሱ ተመልከቷል። ቻይና ለምን ስለላውን ትደግፋቸዋለች ተባለ? ዐቃቤ ሕግ እንደሚናገረው፤ ግለሰቦቹ ለግል ጥቅማቸው የሚሠሩበት ጊዜ አለ። ከዚህ በፊት አንድ ድርጅት ሚስጥሩን እንዳያጋልጡበት ገንዘብ እንዲከፍላቸው መጠየቃቸው እንደ ምሳሌ ተጠቅሷል። ከግል ጥቅም ባሻገር ግን ለቻይና መንግሥትም ያገለግሉ ነበር ተብሏል። ወታደራዊ መረጃ ሰርቀው ለቻይና መንግሥት መስጠታቸው በክሱ ተገልጿል። በተጨማሪም የሆንግ ኮንግ የዴሞክራሲ አቀንቃኝ እንዲሁም የቀድሞ የቲያናመን አደባባይ ተቃዋሚን የይለፍ ቃል ለቻይና መንግሥት አሳልፈው ሰጥተዋል ተብሏል። ተባባሪ ዐቃቤ ሕግ ጆን ደምረስ “ቻይና ለበይነ መረብ ወንጀለኞች ከለላ በመስጠት አሳፋሪ የሆኑትን የሩስያ፣ የኢራን እና የሰሜን ኮርያን ጎራ ተቀላቅላለች። ግለሰቦቹ በድካም ያገኘነውን አዕምሯዊ ንብረት ለቻይና ኮምኒስት ፓርቲ ያስተላልፋሉ” ብልዋል። የቻይና የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ቃል አቀባይ ሁዋ ቹንያንግ፤ ቻይና አሜሪካ ላይ የበይነ መረብ ጥቃት ከፍታለች የሚለውን ክስ አጣጥለዋል። ኮቪድ-19ን የተመለከቱ ምርምሮችን ለመስረቅ ተሞክሯል የሚለውን ውንጀላም “የማይመስል” ሲሉ አስተባብለዋል። በያዝነው ወር መባቻ የአሜሪካ የምርመራ ተቋም ኤፍቢአይ ዳይሬክተር ክሪስቶፈር ዋሪ፤ ቻይናን “የዓለም ብቸኛዋ ፈርጣማ አገር ለመሆን የማትፈነቅለው ድንጋይ የለም” ማለታቸው ይታወሳል። ድርጅቱ አሁን ላይ በየአስር ሰዓቱ ከቻይና ጋር የተያያዙ የደህንት ሥራዎች እንደሚያከናውን ተናግረዋል። በተቋሙ ሥር ካሉት ወደ 5,000 የሚጠጉ የደህንነት ጥበቃ የምላሽ ስለላዎች (ካውንተርኢንተለጀንስ) መካከል ግማሹ ቻይና ላይ ያነጣጠሩ መሆናቸውንም አክለዋል።
news-44825756
https://www.bbc.com/amharic/news-44825756
የኤርትራ ኤምባሲ የማደስ ሥራ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ ተገለፀ
የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ከነገ ጀምሮ በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉብኝት ተከትሎ፤ ኤርትራ ኤምባሲዋን ዳግም ልትከፍት ነው።
የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሚንስትር አቶ አህመድ ሽዴ ለኃገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ በአዲስአበባ ከተማ ስታዲየም ፊት ለፊት የሚገኘው የቀድሞ ኤርትራ ኤምባሲ እድሳት እየተደረገለት እንደሆነም ገልፀዋል። የቢቢሲ ዘጋቢዎች በቦታው ተገኝተው እንደታዘቡት መቶ የሚሆኑ ሰራተኞች እድሳቱን ለማጠናቀቅ በመረባረብ ላይ መሆናቸውን ነው። የ "ጥርስ አልባው" ማዕቀብ መነሳት ፖለቲካ? የግንባታው ሰራተኞች ለቢቢሲ እንደገለፁት እድሳቱን ለማጠናቀቅ 48 ሰዓት እንደተሰጣቸውና ከትናንትና ጀምሮም በመስራት ላይ መሆኑን ነው። ቦታው የቀድሞ የወጣቶችና ስፖርት ፌዴሬሽን ሆኖ ሲያገለግል የነበረ መሆኑን ገልፀው ጫካውን በመመንጠርም ስራ እንደጀመሩ በተጨማሪ ገልፀዋል። ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በአዲስ አበባና ሃዋሳ ጉብኝት ያደርጋሉ በመቶ ሺዎች ህይወት መቀጠፍ ምክንያት የሆነውን የሁለቱን ሀገራት ጦርነት ተከትሎ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸው የተቋረጠ ሲሆን፤ በየመዲናቸው ያሉትን ኤምባሲዎቻቸውንም ለሁለት ዓስርታት መዝጋታቸው የሚታወስ ነው።
news-46386919
https://www.bbc.com/amharic/news-46386919
ትዊተር በሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ስም የተከፈተውን ሀሰተኛ ገጽ ዘጋ
ትዊተር በፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ስም ተከፍቶ በእንግሊዝኛ ቋንቋ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረን ሀሰተኛ ገጽ ዘጋ።
በፕሬዚዳንቱ ስም የተከፈተው ሀሰተኛ አካውንት ማን እንደሚያስተዳድረው በግልፅ የታወቀ ነገር የለም ከማህበራዊ ሚዲያዎች አንዱ የሆነው ትዊተር፤ @putinRF_eng የተባለውን ሀሰተኛ ገጽ ለመዝጋት የተገደደው ከሩሲያ ባለስልጣናት በደረሰው ይፋዊ ሪፖርት እንደሆነ አስታውቋል። • ትዊተር 70 ሚሊዮን ሃሰተኛ ገጾችን ዘጋ • የትራምፕ ትዊተር ገጽ በኩባንያው ሠራተኛ ተዘጋ • የማህበራዊ ድረ-ገፅ ዘመቻዎች ይሄው በአውሮፓውያኑ 2012 የተከፈተው ሀሰተኛ ገጽ ብዙ ጊዜ ፕሬዚደንቱ በአደባባይ የሚያስተላልፏቸው መልዕክቶች ይቀርቡበት ነበር። ገጹ ባለፉት ስድስት ዓመታት ጊዜ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ተከታዮችን ማፍራት ችሏል። በርካታ የገጹ ተከታዮችም ገጹ እውነተኛና በሌሎች አንጋፋ ሚዲያዎችም ማጣቀሻ የሚሆን አድርገው ያስቡታል። ከሩሲያ ባለስልጣናት ቅሬታ እንደቀረበለት የሚገልፀው ትዊትር "ገጹ አንድን ግለሰብ መስሎ መቅረብን የሚመለከተውን የትዊተር ህግ የሚጥስ ነው፤ በሚያምታታና በሚያታልል መልኩ፣ ሌላን ሰው በመምሰል የትዊተር ገጾችን መጠቀም በዘላቂነት ለመዘጋት ይዳረጋል" ሲል አሳስቧል። ምንም እንኳን ከፕሬዚዳንቱ ሀሰተኛ ገጽ ጀርባ ማን እንዳለ በግልፅ የታወቀ ነገር ባይኖርም የትዊተር ተጠቃሚዎች በሀሰተኛ ገጾች ሲጭበረበሩ ግን ይህ የመጀመሪያው አይደለም ብለዋል። በዚህ ዓመት ብቻ በአሜሪካው ባለሃብት ዋረን ቡፌት ስም በተከፈተ ሀሰተኛ ገጽ ለወጣቶች አነቃቂ መልዕክት ተለጥፎ 2 ሚሊዮን ውዴታ(like) ማግኘቱን ለንግግራቸው ዋቢ አድርገዋል። ነገር ግን ገጹ ሰማያዊ መለያ የሌለውና ስሙ ላይ የፊደላት ስህተት መገኘቱ እንዳባነናቸው ገልጸው ሀሰተኛ መሆኑን ጊዜ ሳይወስድባቸው ይፋ እንዳደረጉ አስታውሰዋል።
news-54565663
https://www.bbc.com/amharic/news-54565663
በመተከል ዞን ተጨማሪ የሚሊሻ ምልመላ እየተካሄደ መሆኑ ተጠቆመ
በቤንሻንጉል ዞን መተከል ዞን ስር ባሉ ሰባት ወረዳዎች የሚሊሻ ስልጠና መሰጠቱን የክልሉ ኮሙኑኬሽን ኃላፊ አቶ መለሰ በየነ ለቢቢሲ ገለፁ።
አቶ መለሰ እንደገለፁት ከሆነ በቤንሻንጉል ክልል መተከል ዞን አካባቢ አሁን በተደጋጋሚ የሚፈጠሩ የፀጥታ ችግሮችን በመደበኛ የሕግ ማስከበር የሚቻል ስላልሆነ ከመስከረም 11፤ 2013 ዓ. ም ጀምሮ ለሶስት ወራት የሚቆይ የኮማንድ ፖስት ታውጇል። የኮማንድ ፖስቱ በመከላከያ ሰራዊት የሚመራ ሲሆን፣ የፌደራል እና የክልሉ ፖሊስ በጋራ ሰላም የማስከበሩን ስራ እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል። በዞኑ ከዚህ ቀደም የነበሩ የሚሊሻ አባላት እንዲሁም አዲስ ምልመላ ተካሂዶ ስልጠናው ላለፉት ሶስት ቀናት መሰጠቱን ኃላፊው ጨምረው ተናግረዋል። በዞኑ ከሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች የተመለመሉት እነዚህ የሚሊሻ አባላት ከሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች መመልመላቸውን የሚገልፁት ኃላፊው፣ ከስልጠናውም በኋላ በቂ ትጥቅ አስታጥቆ የፀጥታ መዋቅሩን እንዲደግፉ እንደሚደረግ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም የሚሊሻ አባል የነበሩና እድሜያቸው ያልገፉ አባላት በአሁኑ ስልጠና ላይም መካተታቸውን የገለፁት አቶ መለሰ፣ እንደየቀበሌው ስፋት ከ15 እስከ 20 የሚሆኑ አዳዲስ አባላት መመልመላቸውን ተናግረዋል። ምልመላው የብሔር ብሔረሰቦችን ተዋፅኦ የጠበቀ መሆኑንም የገለፁት ኃላፊው፤ ስልጠናው ለተከታታይ ሶስት ቀናት በመከላከያ ሠራዊት አባላት እና ፖሊሶች መሰጠቱን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት በመተከል ዞን እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው የኮማንድ ፖስቱ ከክልሉ እንዲሁም ከፌደራል ፖሊስ ጋር በጥምረት የሚሰራ ሲሆን፤ ለአካባቢው ሰላም መደፍረስ ዋነኛ ምከንያት ናቸው ተብለው የሚጠረጠሩ ሰዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑን አስረድተዋል። ክልሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በተገኙበት በአካባቢው የሚፈጠረውን የሰላም መደፍረስ ለመፍታት ምን መደረግ አለበት የሚለውን በተደጋጋሚ ውይይት ማካሄዱንም ኃላፊው ጨምረው ገልፀዋል። ኮማንድ ፖስቱ ሁለት ዓይነት ሥራዎችን እንደሚሰራ የተናገሩት ኃላፊው፣ ቀዳሚው የሕዝብ ግንኙነት ሥራ መሆንኑ አስረድተዋል። በሕዝብ ግንኙነት ሥራው የክልል፣ ዞንናወረዳ ከፍተኛ አመራሮች፣ ተሰሚነት ያላቸው ታዋቂ ግለሰቦች፣ የአገር ሽማግሌዎች የሃይማኖት አባቶች፣ ወጣቶች፣ እንዲሁም ሴቶች የተሳተፉበት መድረክ መካሄዱን ገልፀዋል። በክልል ደረጃ የጦር መሳሪያ እጥረት አለ ያሉት ኃላፊው ፤ ነገር ግን በጣም ተጋላጭ የሆኑ ቀበሌዎችና፣ ጎጦችን በመለየት ለሰልጣኝ ሚሊሻ አባላት መሳርያ ማስታጠቅ መታቀዱንም አክለው ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም ማንነታቸው በማይገለጽ አካላት ተደጋጋሚ ጥቃቶች እየተፈጸሙ በርካታ ንጹሃን ዜጎች በመተከል ዞን ውስጥ ተገድለዋል። በዞኑ በሚከሰተው የፀጥታ ችግር እጃቸው አለበት የተባሉ እና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ባለመወጣት የተጠረጠሩ ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮች ላይ ፖለቲካዊ እርምጃ መወሰዱን ይታወሳል።
news-47520888
https://www.bbc.com/amharic/news-47520888
የጋብቻ ቃልኪዳናቸውን በአደባባይ በማድረጋቸው የታሰሩት ኢራናዊ ጥንዶች በዋስ ተለቀቁ
በሰሜናዊ ኢራን አራክ ከተማ በሚገኝ አንድ የገበያ ማእከል ነው ወንድየው ድንገት የ (ታገቢኛለሽ) ጥያቄን ያቀረበው።
የሴቷ እሽታ ለግብይት ቦታው ላይ በነበሩ በርካታ ሰዎች ጭብጨባና እልልታ ታጀበ የቃል ኪዳን ቀለበትም ታሰረ። ነገር ግን ጥንዶቹ የእስልምና መርህን ጥሰዋል በሚል ወዲያው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ። • ሁለት እምነቶችን በአንድ ጣራ ለአስርታት ያሳደሩ ጥንዶች በአደባባይ ሴቶችና ወንዶች አንድ ላይ መታየት ወይም ፍቅርን በአደባባይ መግለፅ በኢራን እስላማዊ ህግ በጥብቅ የተከለከለ ነው። •የቱኒዚያው ጤና ጥበቃ ሚኒስትር በ11 ህፃናት ሞት ምክንያት ስልጣን ለቀቁ የአካባቢው ፖሊስ ኮማንደር ሞሃመድ ካላጂ ለኢራኑ ፋርስ ኒውስ እንደገለፁት ጥንዶቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት 'በህዝብ ጥያቄ' ነው። •በኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም የተቀሰቀሰው ውዝግብ ኮማንደሩ ነገሩ 'በምእራባዊያን የባህል ተፅእኖ ህዝባዊ ጨዋነትን መጣስ ነው' ብለውታል። የመታሰራቸው ምክንያትም ይህው ነው ብለዋል።
news-51396027
https://www.bbc.com/amharic/news-51396027
ኢራን የአሜሪካ ሰላይ ነው ባለችው ግለሰብ ላይ ሞት ፈረደች
የኢራን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለሲአይኤ ይሰልል ነበር ተብሎ የተወነጀለውን ግለሰብ ሞት ፈረደበት።
የሞት ፍርድ የተፈረደበት አሚር ራሂምፖር የኢራንን የኒውክሊየር ፕሮግራም መረጃ ለሲአይኤ በማቀበል ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ተቀብሏል በማለት የፍርድ ቤቱ ቃል አቀባይ ጎላምሆሴይን እስማኤል ተናግረዋል። ሰላዮች ናቸው ተብለው የተወነጀሉ ሁለት አሜሪካውያንም በመሰለል ወንጀል አስር ዓመት እንዲሁም በተጨማሪ ብሔራዊ ጥቅምን በመተላለፍና ደህንነትን አደጋ ላይ በመጣል ሌላ አምስት ዓመት ተፈርዶባቸዋል። • በጀነራሉ ቀብር ላይ ከ35 በላይ ሰዎች ተረጋግጠው ሞቱ • ቴህራን ጥቃት ከፈፀመች በሚል አሜሪካ 52 የኢራን ተቋማት ላይ መሳሪያዋን አነጣጥራለች ቃል አቀባዩ የሁለቱን ግለሰቦች ማንነት ከመግለፅ ተቆጥበዋል፤ በዚህ ጉዳይ ላይም ከአሜሪካም ሆነ ከሲአይኤ የተሰማ ነገር የለም። ነገር ግን በሐምሌ ወር ኢራን ለሲአይኤ ሲሰልሉ ነበር ያለቻቸውን አስራ ሰባት ሰዎች የሞትና ሌሎችም ቅጣቶች ወስኘባቸዋለሁ ብትልም አሜሪካ ጥርጣሬ አላት። "መዋሸት የአያቶላህ ባህርይ ነው" በማለት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ የኢራኑን ታላቁን መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒን ወርፈዋቸዋል። ከወር በፊት ለኢራን መከላከያ ሚኒስትር ተቀጥሮ ይሰራ የነበረው ጃላል ሃጂዛቫር በስለላ ወንጀል ጥፋተኛ ተብሎ በሞት ፍርድ ተቀጥቷል። ጃላል ከሲአይኤ ከፍተኛ ገንዘብ ተቀብያለሁ ሲል ተናዞ ነበር። •እውን ሶስተኛው የዓለም ጦርነት ተቀስቅሶ እናየው ይሆን? እነሆ ምላሹ •ከአንደኛ ክፍል ዲግሪ እስኪጭኑ ከልጃቸው ጋር የተማሩት አባት ኢራን እንደ ጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር በ2016 የኒውክሊየር ሳይንቲስቷን ሻሃራም አሚሪን ለአሜሪካ ይሰልላል በሚል ገድላዋለች። ሳይንቲስቱ ከኢራን አምልጦ ወደ አሜሪካ በ2009 ሄዶ የነበረ ሲሆን፤ በዓመቱ ታፍኜ ያለፈቃዴ ነው የተወሰድኩት በማለት ወደ ኢራን ተመልሶ የነበረ ቢሆንም ከሞት አላደነውም። የሳይንቲስቱ ሞት በኢራንና በዋሽንግተን መካከል ያለውን የተበላሸ ግንኙነት የበለጠ አካሮታል። ከወራት በፊት በፕሬዝደንት ትራምፕ ትዕዛዝ በሰው አልባ አውሮፕላን ተተኩሰው የተገደሉት የጀነራል ቃሲም ሱለይማኒ ጉዳይ ሁለቱን አገራት የበለጠ አይንና ናጫ አድርጓቸዋል። በምላሹ ኢራን የአሜሪካ ይዞታ ነው በሚባል የጦር ሰፈር ላይ በባሌስታይክ ሚሳይል ጥቃት መፈጸሟ ይታወሳል።
news-51716794
https://www.bbc.com/amharic/news-51716794
ሳዑዲ አረቢያ፡ አረብ አገር የለፋችበትን አገባሻለሁ ባለሰው ተጭበርብራ ባዶዋን የቀረችው ሻሼ
ህይወታቸውን ለመቀየር ከአገራቸው ውጪ በተለያዩ ሥራዎች ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ሴት ኢትዮጵያዊያን ለቀጣይ ዕቅዳቸው ማሳኪያ የቆጠቡት ገንዘብ በፍቅር ጓደኞቻቸው አሊያም በቤተሰብ አባላቸው ተወስዶ ወይም ባክኖ ባዷቸውን ቀሩ ሲባል መስማት እየተለመደ የመጣ ነገር ሆኗል።
በተለይ በአረብ አገራት ውስጥ ህይወታቸውንና ጤናቸውን ለአደጋ በሚያጋልጥ ከባድ ሁኔታ ውስጥ በመሥራት ወደ አገራቸው ሲመለሱ የራሳቸውን ሥራና ህይወት ለመመስረት ያስችለናል ያሉት ገንዘብ ጠፍቶ ወይም ባክኖ ሲያገኙት የሚፈጠርባቸው ስሜት ከባድ ከመሆን አልፎ አንዳንዶችንም ለሥነ ልቦና ጫና እንደዳረጋቸው የሚሰሙ ታሪኮች ይጠቁማሉ። በውጪ አገር ሰርተው ያጠራቀሙትና ወደ አገር ቤት የላኩት ገንዘብ ባመኑት ሰው ከተበላባቸው በርካታ ኢትዮጵያዊያን እህቶች መካከል ሻሼ አንዷ ናት። ሻሼ፤ የተወለደችው በምዕራብ ሸዋ ኮቲቤ በምትባል አካባቢ ነው። ሳዑዲ የምትኖረው ሻሼ በትውልድ ቀዬዋ ከሚኖር ከአንድ ግለሰብ ጋር ወደ አገሯ ስትመለስ ለመጋባት አቅደው ለወደፊት ህይወታቸው የሚሆኑ ነገሮችን እንዲያሟላ የላከችለትን ገንዘብ እንዳጭበረበራት ትናገራለች። ሙሉ ታሪኳን እነሆ . . . ሻሼ ለሥራ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ነበር የሄደችው «ሳዑዲ አራቢያ ከሄድኩ በኋላ የቀጠረቻት ሴት እህት መንቀሳቀስ አትችልም። የምትበላው የምትጸዳዳውም በተኛችበት ነበር። ልብሷን መቀየር፣ ማጽዳትም የዘወትር ሥራዬ ነበር» ትላለች። ሻሼ፤ ለአራት ዓመት እሷን ስትንከባከብ በወር የሚከፈላት 700 ሪያል የነበረ ሲሆን ደመወዟ ደግሞ በጊዜ አይሰጣትም ነበር። «ብዙ መከራ አሳልፌ ከዚያ ቤት ወጥቼ ሌላ ቤት በ900 ሪያል ተቀጠርኩ።» «አዲስ የገባሁበት ቤት ተቆልፎብኝ ይውላል፣ ያድራል። በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ለሁለት ዓመት ቆየሁ። ለ24 ሰዓታት ስለሚቆለፍብኝ፣ መስኮትም ስለማይከፈት ፀሐይ መውጣትና መግባቷን እንኳ አላውቅም ነበር።» ሻሼ፤ በከፍተኛ ሙቀት ሳቢያ ሰውነቷ ተጎድቶ እንደነበርም ትናገራለች። ከተቀጠረችበት ቤት ሥራ ስትጨርስ ቀጣሪዋ እህት ቤት ተወስዳ ደግሞ ሌላ ሥራ እንደትሰራ ትደረግ ነበር። በዚህ መልኩ እየሰራች ለስድስት ዓመት ያገኘችውን ብር ለማጠራቀም ሞክራለች። ሻሼ ሳዑዲ ውስጥ በከባድ የቤት ውስጥ ሥራ ዓመታትን ካሳለፈች በኋላ ወደ አገሯ ተመልሳ የምታሳካው ዕቅድ እንደነበራት ትናገራለች። «አገር ቤት ፍቅረኛ ነበረኝና ስመለስ ለመጋባት ተስማምተን ነበር። ስልክ ስላልነበረኝ የምደውልለት ከአሰሪዬ ስልክ እየለመንኩ ነበር። አሰሪዎቼን ከፍቅረኛዬ ጋር ለመጋባት ወደ አገር ቤት ስለምሄድ ስልክ ግዙልኝ ብዬ ለመንኳቸው።» አሰሪዎቿ ስልክ ከገዙላት በኋላ ኢሞ የተሰኘ መደዋወያ ስልኳ ላይ ትጭናለች። ከዚያም በአንድ አጋጣሚ አንድ የተወለደችበት አካባቢ እንደሆነና በስም የምታውቀው ልጅ ስልክ ይደውልላታል። ቢሆንም ግን ከልጁ ጋር በአካል አይተዋወቁም ነበር። ከቤተሰቦቿ ጋር ቅርበት ያለው የግለሰቡ ወንድም ደውሎ ልጁ የቤተክርስቲያን አገልጋይና መልካም ሰው እንደሆነ በመግለፅ እንድታገባው ሃሳብ ሰነዘረላት። «ፍቅረኛ እንዳለኝ ነገርኩት። ማነው ሲለኝ የፍቅረኛዬን ሙሉ ስም ነገርኩት። 'እሱማ ወለጋ ሄዶ አግብቶ ሚስቱን ትቶ እዚህ ተመልሷል። እዚህም አግብቶ ሁለት ልጅ ወልዷል' አለኝ። 'በሰው አገር ይህን ያህል ለፍተሽ ያገኘሽውን ብር ባገባ ሰው ላይ ማጥፋት የለብሽም' አለኝ። በፍቅረኛዬ በጣም አዘንኩ። ከዚያ ከአዲሱ ጓደኛዬ ጋር ተቀራረብንና ለመጋባት ተስማማን።» ጓደኛዋ፤ ቤት ሰርቶ እንዲጠብቃት መሬት መግዣ ብር እንድትልክለት ይጠይቃታል። 'የእግዚአብሔር ሰው ስለሆንኩ ብርሽን አልበላም' ሲልም ቃለ ገባ። እሷም መልካም ሰው ነው ብላ ብዙ ደክማ የቆጠበችውን ብር ሙሉ በሙሉ ላከችለት። መጀመሪያ 10 ሺህ ሪያል በባንክ አስገባች። ከዚህ በኋላ እሱ ደግሞ መሬት እንደገዛ ነገራት። ትንሽ ቆይቶ መንግሥት መሬቱን ወስዶብኝ ነበር አሁን ግን መልሶልኛል እንዳላትም ታስታውሳለች። በማስከተል ደግሞ መንግሥት መሬቱን መልሶ እንዳይወስደው በሽቦ ለማጠር ብር ላኪልኝ አላት። እሷም እጇ ላይ የነበረ ብር ላይ ከቀጣዩ ወር ደመወዟ ተበድራ በመጨመር 4500 ሪያል ላከችለት። ከዚህ ቀጥሎ የሆነው ግን ፈፅሞ ያልጠበቀችው ነበር። «እሁድ ልኬለት ሰኞ ደረሰ ወይ ብዬ ስደውልለት 'ብሎክ' አድርጎኛል። ደጋግሜ ብሞክርም ላገኘው አልቻልኩም» «ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ራሴን አላውቅም። ለሦስት ወር ያህል ምግብ በአግባቡ አልበላም ነበር። ደም በአፍና አፍንጫዬ ይወጣል። በቀን ሦስቴ ሆስፒታል ሄጄ 'ግሉኮስ' እየወሰድኩ ወደስራ እመለሳለሁ። ስድስት ዓመት የሰራሁበትን በሙሉ አጥቻለሁ» ትላላች ፍጹም በተሰበረ ሁኔታ። ሻሼ በኋላ ላይ እንደደረሰችበት የቀድሞ ፍቅረኛዋ እንዳላገባ ሰማች፤ ይህም ሃዘኗን የበለጠ አጠነከረባት። ሻሼ ወደ ሳዑዲ አረቢያ የሄደችው አባትና እናቷ በተመሳሳይ ጊዜ በሞት በተለይዋት ወቅት ስለነበረ «በከባድ ሃዘን ተሰብሬ ነበር» ትላለች። ስለዚህም የምትሰራው ከባድ የቤት ውስጥ ሥራ ሃዘኗ የበለጠ አጠንክሮባት የነበረ ሲሆን አብሯት ለረጅም ጊዜ ቆይቷል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆና ያጠራቀመችው ገንዘቧ የወደፊት የህይወት አጋሬ ይሆናል ባለችው ግለሰብ ስትጭበረበር የገጠማት መረበሽ ተስፋ እስከመቁረጥ እንዳደረሳት «ሃዘኑ፣ የሥራ ጫናውና መጭበርበሬ በአንድ ላይ ተደማምሮ ራሴን ስለማጥፋት ሁሉ አስብ ነበር» ትላለች። ከዚህ ሁሉ በኋላ የሻሼ ወንድም በእህቱ ላይ የተፈጸመውን ማጭበርበር ለፖሊስ ቢያመለክትም ያጭበረበራት ግለሰብ ገዛው የተባለውን መሬት ሸጦ ከአካባቢው መሰወሩን ፖሊስ እንደገለጸለት ትናገራለች። ሻሼ የወደፊት ህይወቷን ለማሳካት ስድስት ዓመታትን ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ በከባድ የቤት ውስጥ ሥራ አሳልፋለች፤ ይህም ሳያንስ ባርነት በሚመስል ልፋት ያጠራቀመችው ገንዘቧ የህይወት አጋሬ በመሆን ሸክሜን ያቀልልኛል ባለችው ግለሰብ ተጭበርበርራ ባዶ እጇን ቀርታለች። ዙሪያዋም ገደል ሆኖባታል።
news-52962025
https://www.bbc.com/amharic/news-52962025
የሚኒያፖሊስ ከተማ ምክር ቤት የከተማውን ፖሊስ ለመበተን ቃል ገባ
የሚኒያፖሊስ ከተማ ምክር ቤት የአካባቢውን ፖሊስ ጣቢያ ለመበተን ቃል ገቡ።
በጆርጅ ፍሎይድ ሞት ምክንያት በአሜሪካና በመላው ዓለም የተቀሰቀሰውን ከባድ ተቃውሞ ተከትሎ አብዛኛዎቹ የሚኒያፖሊስ ከተማ ምክር ቤት አባላት የከተማውን ፖሊስ እንዲ በተን ጠየቁ። ከአስራ ሦስቱ የምክር ቤት አባላት ዘጠኙ በዚህ ሀሳብ የተስማሙ ሲሆን “አዲስ የማኅበረሰብ ደኅንነትን የሚያስጠበቅ ሞዴል’’ ይፈጠራል ብለዋል። ተመሳሳይ እርምጃዎች መወሰድ አለባቸው ብለው ለዓመታት ሲከራከሩ የነበሩ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ደግሞ ውሳኔውን "ወሳኝ ጅማሮ ነው" ብለውታል። በፖሊስ እጅ የጆርጅ ፍሎይድ ሕይወት ማለፉ ከተሰማበት ጊዜ አንስቶ የፖሊስ ጭካኔ ይቁም ያሉ በርካታ አሜሪካውያን ከባድ የተቃውሞ ሰልፍ ሲያካሂዱ ቆይተዋል። የተቃውሞ ሰልፎቹ ቀስ በቀስ መቀዛቀዛቸውን ተከትሎ ተቀምጠው የነበሩት ጥብቅ የደኅንነት እርምጃዎች ከእሁድ ዕለት ጀምሮ እንዲነሱ ሆኗል። ዛሬ ደግሞ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የጆርጅ ፍሎይድን አስክሬን ለመሰናበት በሂውስተን እንደሚሰባሰቡ ይጠበቃል። ፍሎይድ ወደ ሚኒሶታ፣ ሚኒያፖሊስ ከመሄዱ በፊት መኖሪያ ቤቱ የሚገኘው ቴክሳስ ሂውስተን ነበር። ነገ ማክሰኞ ደግሞ ቤተሰብ ብቻ በተገኘበት የቀብር ሥነ ሥርዓቱ እንደሚፈጸም ታውቋል። የጆርጅ ፍሎይድ የመጨረሻ ሰዓት ትንቅንቅ በቪዲዮ ተቀርጾ ማኅበራዊ ድር አምባው በከፍተኛ ፍጥነት ከተጋራው በኋላ በአሜሪካ አብዛኞቹ ግዛቶች ለቀናት የዘለቀ ተቃውሞን ቀስቅሶ ቆይቷል። ተቃውሞቹን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስጋትም ሆነ የሰዓት እላፊ ገደብ ሊያቆማቸው አልቻለም ነበር። ለጆርጅ ፍሎይድ ደማቅ የሽኝት ሥነ ሥርዓት የተደረገለት ደግሞ ቅዳሜ ዕለት ሲሆን በርካታ ስመ ጥር የጥቁር መብት ተሟጋቾች በሥነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር አድርገዋል። የጆርጅ ፍሎይድ ቤተሰብ ጠበቃ "ደንበኛዬን ለሞት ያበቃው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ነው ይላሉ፤ በዘረኝነት ወረርሽኝ መሞቱን ማን በነገራቸው. . ." ሲል ስሜታዊ ንግግር አሰምቷል። በሟች ጆርጅ ፍሎይድ የሽኝትና መታሰቢያው ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙ ሁሉ ተነስተው እንዲቆሙና ለ8 ደቂቃ ከ46 ሴኮንዶች የሕሊና ጸሎት እንዲያደርጉ የተደረገ ሲሆን፤ ይህም ነጩ የፖሊስ ባልደረባ ዴሪክ ሟች ፍሎይድ አንገት ላይ በጉልበቱ ቆሞ ትንፋሹን እስኪያጣ የቆየበትን ጊዜን ለመዘከር የተደረገ ነበር። "አሁን ያለንበት ሁኔታ ላይ እራሳችንን ያገኘንበት ምክንያት በሚኒያፖሊስና በአጠቃላይ አሜሪካ የተዘረጋው የፖሊስ መዋቅር የሕዝቡን ደኅንነት ማስጠበቅ ባለመቻሉ ነው" ብለዋል የከተማ ካውንስሉ ፕሬዝደንት ሊሳ ቤንደር። ፕሬዝዳንቷ አክለውም የፖሊስ ጣቢያውን እንዴት እንደ አዲስ ማዋቀር እንደሚቻል በቅርቡ እቅድ እንደሚዘጋጅ የገለጹ ሲሆን፤ ለፖሊስ ይመደብ የነበረ ገንዘብ ወደ ማኅበረሰብ ተኮር ሥራዎች ለማዞር እንደሚጥሩም ተናግረዋል። ባሳለፍነው ሳምንት የሚኒሶታ ግዛት የሚኒያፖሊስ የፖሊስ ክፍል ላይ ምርመራ እንዲጀመር አድርጓል። የከተማዋ ገዢ ቲም ዋልትዝ በበኩላቸው በተጠና መልኩ የሚደረጉ የዘረኝነት ተግባራትን ማስወገድ እንደሚፈልጉ በመግለጽ ምርመራውን እንደሚቀበሉት ገልጸዋል። በተጨማሪም የከተማ ምክር ቤት በፖሊስ ተግባራት ላይ በርካታ ለውጦች እንዲኖሩ የወሰነ ሲሆን፤ በዋነኛነት ተጠርጣሪዎችን ማነቅና አንገት ላይ በጉልበት መቆምን ከልክሏል። በሚኒያፖሊስ ተግባራዊ የሚሆነው ሕግ በመላው አሜሪካ ፖሊስ እስከ ምን ድረስ ነው ኃይሉን መጠቀም አለበት የሚለውን ጥያቄ በድጋሚ አስነስቷል። በሚኒሶታ አንድ ምግባረ ሰናይ ድርጅት የሚመሩት ካንዲስ ሞንትጎመሪ "ውሳኔው እስኪታላለፍ ድረስ ይህን ያክል ጊዜ መቆየት አልነበረበትም፤ የታጠቁና ተጠያቂነት የሌለበት እርምጃ የሚወስዱ ፖሊሶች ባሉበት ጥቁር አሜሪካውያን ደህንነት አይሰማቸውም" ብለዋል።
news-48905189
https://www.bbc.com/amharic/news-48905189
ስፔን ውስጥ ከኮርማዎች ጋር በተደረገው ሩጫ ሦስት ሰዎች ተጎዱ
ከነውጠኛ ኮርማ ጋር ሲሯሯዙ የነበሩ ሦስት ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት ደረሰባቸው።
ሦስት ሰዎች የተጎዱበት ከኮርማዎች ጋር የተደረገ ሩጫ በስፔን በሚካሄደው ከነውጠኛ ኮርማዎች ጋር የመሯሯጥ ዓመታዊው ሳን ፌርሚን ፌስቲቫል ላይ 2 አሜሪካዊያንና የስፔን ዜጋ ላይ ጉዳት መድረሱን ባለስልጣናት አስታወቁ። • የኢትዮ ቴሌኮም 49 በመቶ ድርሻ ለሽያጭ ይቀርባል ተባለ በቀይ መስቀል ህክምና የተደረገላቸው በጠቅላላው ቀላል ጉዳት ያስተናገዱ ሰዎች ቁጥር ወደ 48 እንደሚጠጋ ባለስልጣናቱ ጨምረው አስታውቀዋል። ፌስቲቫሉ እስከ የፊታችን እሁድ የሚቀጥል ሲሆን ከኮርማው ጋር መሯሯጡ ጠዋት ጠዋት ላይ ይካሄዳል። በፌስቲቫሉ ላይ የሚሳተፉት ሰዎች ነጭ ልብስ እና ቀይ ስካረፍ በማድረግ በጠባብ ጎዳና ላይ ለ850 ሜትር ከበሬ ፊት በመሮጥ ለኮርማዎች ወደ ተከለለው ቦታ ድረስ ከኮርማው ጋር ይሯሯጣሉ። • ጥሩ ሰው ምን አይነት ነው? በየቀኑ ስድስት ኮርማዎች ይለቀቃሉ በዚህም በርካቶች ጉዳት ይደርስል። ይህ ጥንታዊ ፌስቲቫል ከ1910 ጀምሮ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን እስካሁን 16 ሰዎች በኮርማዎች ተወግተው ህይታቸው አልፏል። ለመጨራሻ ጊዜ አንገቱ ላይ ተወግቶ ህይወቱ ያለፈው ዳኒኤል ሮሜሮ 2009 ላይ ነበር። ትናንት ጉዳት ያስተናገደው የ46 ዓመቱ አሜሪካዊም አንገቱ ላይ እንደተወጋና ቀዶ ህክምና እንደተደረገለት አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል። በዚህ ፌስቲቫሉ ላይ ለመሳተፍ በርካቶች ከመላው የዓለማችን ክፍል ወደ ስፔን ያቀናሉ። ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ሁሉ በፌስቲቫሉ ላይ መሳተፍ የሚችል ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ተሳታፊ ሆነው የሚታዩት ግን ወንዶች ብቻ ናቸው። ከኮርማዎች ፊት የመሯሯጥ ፌስቲቫል በእንስሳት መብት ተሟጋቾች ከፍተኛ ተቃውሞ ይቀርብበታል።
news-41719256
https://www.bbc.com/amharic/news-41719256
''ቤትና ንብረታችን ወድሟል፤ የምንበላውም ሆነ የምንለብሰው የለንም''
በኦሮሚያ ክልል በቡኖ በደሌ ዞን ውስጥ ሰሞኑን ተከስቶ የነበረውን ግጭት በመሸሽ ከቤታቸው ተፈናቅለው በፖሊስ ጣቢያ ተጠልለው ከሚገኙት መካከል አቶ አቢ አዝመራው ይገኙበታል።
በተፈጠረው ግጭት 14 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋልወ አቶ አቢ እንደነገሩን በስልክ እና በቃል የሚደርስባቸውን ማስፈራሪያን ተከትሎ ነበር ሀሙስ ዕለት ከነቤተሰባቸው ወደ ጫካ ሸሽተው የገቡት። እሳቸው እንደሚሉት በአካል የሚያውቁት ግለሰብ ተገድሏል፤ ሌላኛው ደግሞ ጉዳት ደርሶበት ህክምና ላይ ይገኛል ሲሉ ነግረውናል። ከኮቼ ኩሳዬ ቀበሌ የተፈናቅልን 91 ሰዎች በፖሊስ ድጋፍ ከጫካ ወጥተን አሁን በወረዳው ፖሊስ ጣቢያ ውሰጥ እንገኛለን ብለውናል። ወ/ሮ ፋጤ እንድሪስም በዛው ፖሊስ ጣቢያ ተጠልለው የሚገኙ ናቸው። እሳቸው እንደሚሉት ችግሩን መቋቋም የማይችሉ ህፃናት፣ እናቶች እና አቅመ ደካሞች አሉ። ምግብ፣ አልባሳት እና መጠለያ ያስፈልገናል መንግሥት ደግሞ ምንም አይነት ድጋፍ እያደረገልን አይደለም ይላሉ። እስከ አሁን ድረስም በርካታ ሰዎች ጫካ ውስጥ እንደሚገኙ ያነጋገርናቸው ሰዎች አረጋግጠውልናል። ጥቃት ያደረሱት እነማን ናቸው? ''የአካባቢው ወጣቶች እና ሌሎች የማናውቃቸው ሰዎች ናቸው ቤቶቻችንን እየለዩ ያቃጠሉት እንዲሁም ንብረት ያወደሙት። ውጡልን ይሉን ነበር'' ይላሉ አቶ አቢ። የ1977 ድርቅን ተከትሎ ከአማራ ክልል ወደ አካባቢው በሰፈራ እንደመጡ የሚናገሩት አቶ አቢ፤ እንደዚህ አይነት ችግር እየተፈጠረ ያለው ካለፉት 5 ዓመታት ወዲህ መሆኑን ያስረዳሉ። ''በአንድ በኩል የአካባቢው ወጣቶች ማንም አይነካችሁም እያሉ ጥበቃ ያደርጉልናል በሌላ በኩል ደግሞ ጥቃት ይፈፀምብናል። ማንንም ማመን አይቻልም። እኛ እየተሳቀቅን መኖር ስለማንሻ መንግሥት ከዚህ ቦታ እንዲያነሳን እንፈልጋለን'' ሲሉ በምሬት ይናገራሉ። በመንግስት መሰሪያ ቤት ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮች የክልሉና እና የአካባቢው ባለስልጣናት ምን ይላሉ? በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጡን የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ሃላፊ የሆኑት አቶ አዲሱ አረጋን እና የቡኖ በደሌ ዞን የገጠር ግንባታ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ሃላፊ የሆኑትን አቶ ሞሲሳ ለሜሳን በስልክ አነጋግረናል። አቶ አዲሱ አረጋ፤ በቡኖ በደሌ ዞን የሟቾች ቁጥር 14 መድረሱን እና ከነዚህም መካከል 9 የክልሉ ተወላጆች መሆናቸውን ገልፀው በርካታ የሌላ ብሔር ተወላጆች በሚደርስባቸው ዛቻ እና ማስፈራሪያ ሳቢያ ቤት ንብረታቸውን ጥለው እየሸሹ እንደሆነ ተናግረዋል። ከአሁን በኋላ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይከሰት ኦሮሚያ ፖሊስ አስፈላጊ ጥበቃ እንደሚያደርግ ገልፀዋል። አቶ አዲሱ አክለውም ከኦሮሚያ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚሆን ምግብ እና አልባሳት የጫኑ መኪኖች ወደ ቦታ እየተጓዙ እንደሆኑ ነግረውናል። አቶ ሞሲሳ ደግሞ ''እውነት ነው የሰው ህይወት ጠፍቷል፣ የተቃጠሉ ቤቶች እና እርሻዎች አሉ። ይህ አይነት ጥቃት ደግሞ በአማራ እና በትግራይ ተወላጆች ላይ ብቻ ሳይሆን በኦሮሞ ላይም ጥቃት ተፈፅሟል'' ይላሉ። ችግሩን ለመፍታት እየሰራን ነው ያሉት አቶ ሞሲሳ እሳቸው የሚመሩት በዞን ደረጃ የተቋቋመው ኮሚቴ የተፈናቀሉ እና ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች መልሶ ለማቋቋም መንግሥት፣ የሃገር ሽማግሌዎች እና ፖሊስ የተለያዩ ሥራዎችን እየሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም ኮሚቴው ተፈናቃዮቹ የምግብ፣ የህክምና እና የአልባሳት ድጋፍ እንዲያገኙ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ ነው ብለዋል። ጥቃት ፈፃሚዎቹ እነማን ናቸው? ''አዲሱ የኦሮሚያ ክልል አመራር እርምጃ የወሰደባቸው ኪራይ ሰብሳቢዎች ናቸው ድራማ እየሰሩ የሚገኙት። የመጀመሪያው ክፍል የድንበር ጦርነት መቀስቀስ ነበር ሁለተኛው ክፍል ደግሞ የብሔር ግጭት መፍጠር ነው'' ይላሉ አቶ አዲሱ። በአማራ እና ኦሮሞ ህዝቦች መካከል የተፈጠረውን አንድነት ለመናድ ፍላጎት ያላቸው ናቸው ይላሉ አቶ አዲሱ። የእነዚህን ግለሰቦች ማንነት አስፈላጊውን ማጣራት ካደረግን በኋላ ለህዝብ ይፋ እናደርጋለን ብለዋል። ለአቶ ሞሲሳም ይህን ድርጊት የፈፀሙት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ እንደሆነ እና ከሃገር ሸሽተው የወጡም እንዳሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
news-54612584
https://www.bbc.com/amharic/news-54612584
ኢትዮጵያ፡ ማንነትን ማሳያ የሆኑት የባህል አልባሳት
በርካቶች በባሕል አልባሳቶቻቸው ተውበው ለመታየት ዳተኛ የነበሩበት ዘመን ሩቅ አይደለም። ለዚህ ደግሞ የተለያየ ምክንያት ቢሰጡም ዋናው ግን አልባሳቶቹ ለሥራ ምቹ ተደርገው አለመሸመናቸው አንዱ ነው።
የኦሮሞ ባሕል አልባሳትም ተዘውትረው ሲለበሱ ከማይታዩ በርካታ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች አልባሳት መካከል ውስጥ ነበሩ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የብሔር ማንነት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ማእከላዊ ማጠንጠኛ እየሆነ ሲመጣ እና የፋሽን ኢንዱስትሪው አልባሳቱን በተለያየ ስልት ሸምኖ ሲያቀርብ በርካቶች እንደ ፍላጎቶቻቸውና እነደምርጫቸው መልበስ ጀምረዋል። በቅርቡም በዓመታዊው የኢሬቻ ክብረ በዓል ላይ በእነዚህ ባሕል አልባሳት ተውበው የታዩ የተለያዩ ግለሰቦች ተስተውለዋል። አልባሳቱን በማዘመን ረገድ ከሚጠቀሱት መካከል አንቲኮ ዲዛይን አንዱ ነው። ቀይ፣ ጥቁርና ነጭ ቀለማት ያላቸው አልባሳት በአንድ ላይ በህብር ሆነው ሲመጡ በፍጥነት ለኢትዮጵያዊ ተመልካች የኦሮሞ ባህል አልባሳት ቀለማትን ምስል ይከስታሉ። እነዚህ ሶስት ቀለማት በተለያዩ አልባሳት ላይ በአንድ ላይ ተጋምደውና ውበት ሰርተው ይገኛሉ። የባሕል አልባሳቱን ለማጀብ የሚያገለግለው ሌላው ደግሞ ሲንቄ የተሰኘው ባህላዊ በትር ነው። እነዚህ በኩሽ ዲዛይን የተሰሩ አልባሳት ደግሞ የኦሮሞ ባህላዊ አልባሳት ላይ ተዘውትረው የሚታዩ ቀለማትና መስመሮችን በአዲስ መንገድ ያስቀመጡ ናቸው። እነዚህ መስመሮች በልብሱ ወርድና ቁመት ላይ በመሆን ለባሱን በቁመትና በዙሪያው ተጨማሪ ግርማ ሞገሥ እንዲላበስ ያደርጉታል። ይህንን ምስል ያነሳው ባለሙያ ኤልያስ በሻዳ ለቢቢሲ ሲያስረዳ "የሌሎች ባሕሎች በምስል ተሰንደው ሲቀሩ አስተውላለሁ፤ የእኛ [የኦሮሞ] ግን በአግባቡ አልተሰነደም" ይላል። "ስለዚህ ራሴን ስለምን ባህላችንን አናስተዋውቅም ስል መጠየቅ ጀመርኩ? በአፍሪካ ቀንድና ከዚያም ባሻገር እንድንታወቅ ፈለግሁ" ሲል ያክላል። የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የህዝብ ብዛት ያለው ሲሆን በባሕልም እንዲሁ ዝንቅ የሆነ ማህበረሰብ ነው። ከላይ የሚታው ምስል ሴቶች እርቦ ጭንቅላታቸው ላይ ይዘው የሚታይ ሲሆን፣ የለበሱት ቀሚስ ደግሞ የምስራቅ አገሪቱ ክፍል የሚኙትን የሀረር ኦሮሞዎች ይወክላል። በርግጥ ቀሚሱ እና ጭንቅላታቸው ላይ ያስቀመጡት እርቦ የምስራቁን የአገሪቱ ክፍል የሚወክል ቢሆንም ወገባቸው ላይ ያሰሩት መቀነት ግን የደቡብ የአገሪቱን ክፍል ባህል እነደሚወክል ዩሚዮ የባህል አልባሳት ይናገራል። የኢሬቻ ፌስቲቫል በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚሳተፉበት በዓል ቢሆንም፣ በዚህ ዓመት ግን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት በውስን ሰዎች ብቻ እንዲከበር ተደርጓል። በኦሮሞ ባህል አልባሳት ላይ በተደጋጋሚ የሚስተዋለው የኦዳ ዛፍ ምልክት ነው። ይህ የኦዳ ዛፍ ምልክት በቀሚሶች፣ ሱሪዎችና ኮቶች ላይ በሕትመት መልክ ገብቶ ተጨማሪ ፈርጥ በመሆን ሲያገገለግልም ይስተዋላል። ከአራት ዓመታት በፊት በቢሾፍቱ የኢሬቻ ዓመታዊ ክብረ በዓል ላይ በነበረ ተቃውሞ ፖሊስና ተቃዋሚ ሰልፈኞች አለመግባበት ተፈጥሮ በደረሰ መረጋገጥ ቢያንስ 55 ሰዎች ሞተዋል። የመብት ተሟጋች ድርጅቶች የሟቾቹን ቁጥር ወደ መቶዎች ያስጠጉታል። በተደጋጋሚ የኦሮሞ ወጣቶች በፖለቲካ እና ምጣኔ ሀብት መገለላቸውን በማንሳት ተቃውሞ ካሰሙ በኋላ ለውጥ ተደርጎ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን መጥተዋል። ነገር ግን አሁንም ውጥረቱ በአንዳንድ ሥፍራዎች ይታያል። ስለ ኦሮሞ ሕዝብ መብት የሚከራከሩ ወገኖች አሜሪካን ጨምሮ በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ይገኛሉ። ይህ ምስል የተወሰደውም በአሜሪካዋ የሚኒሶታ ግዛት በሬድፎክስ አፓረል (RedFox Apparel) ነው። የ27 ዓመቷ ዲዛይነር ሴናክቤኪ ግርማ በኦሮሞ ባህል አልባሳት ላይ ያየችውን ለውጥ "ማይታመን" ስትል ትገልፀዋለች። "ሰዎች የበለጠ በማንነታቸው እየኮሩ መምጣት ጀምረዋል' ስትልም ታክላለች። እነዚህ ባህል አልባሳትም ከበዓላት ቀናት ውጪ ሰርክ የሚለበሱ እንዲሆኑ ምኞቷ ነው። All images subject to copyright.
news-54435796
https://www.bbc.com/amharic/news-54435796
ኢትዮጵያ፡ በምስራቅ አፍሪካ በጎርፍ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ስድስት እጥፍ መጨመሩ ተገለፀ
በምስራቅ አፍሪካ በጎርፍ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር በስድስት እጥፍ መጨመሩን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያወጣው ሪፖርት ያሳያል።
ሪፖርቱ የአምስት አመታትን መረጃም ያጠናቀረ ነው። በዘንድሮው ጎርፍ ስድስት ሚሊዮን ሰዎች የተጠቁ ሲሆን፣ ከነዚህም መካከል 1.5 ሚሊዮን ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል። በቀጠናው የሚገኙ አንዳንድ አገራትም በክፍለ ዘመኑ አጋጥሞ የማያውቅ ከፍተኛ ዝናብና ጎርፍ እንዳጋጠማቸውም ተዘግቧል። የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ በጎርፉ ጉዳት ለደረሰባቸው አካባቢዎች ድንገተኛ እርዳታ እያደረገም ይገኛል። በቀጠናውም ላይ ያጋጠመው ጉዳት አስከፊነት የተባበሩት መንግሥታትን አስጊ ነው ብሎታል። በጎሮጎሳውያኑ 2016 ከሚሊዮን ሰዎች በላይ በጎርፍ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ይህ ቁጥርም በ2019 ወደ አራት ሚሊዮን አሻቅቧል። በተለይም በአንዳንድ አካባቢዎች በህዳር ላይ የሚጠበቀው ዝናብ የበለጠ ጉዳት ያስከትላልም ተብሏል። ከሐምሌ ጀምሮ በሱዳን ከፍተኛ ጎርፍ የተከሰተ ሲሆን በኢትዮጵያና በደቡብ ሱዳንም እንዲሁ ጎርፍ ሚሊዮኖችን ቤትና ንብረት አልባ አድርጓቸዋል። የህንድ ውቅያኖስ በከፍተኛ ሁኔታ መሞቅ ለከፍተኛ ዝናቡ ምክንያት እንደሆነ ሳይንቲስቶችም ገልፀዋል።
news-45949212
https://www.bbc.com/amharic/news-45949212
የዓለማችን ረዥሙ ቻይናን ከሆንግ ኮንግ የሚያገናኘው ባህር አቋራጭ ድልድይ ተከፈተ
የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ግንባታው 9 ዓመታትን የፈጀውን የዓለማችንን ረዥሙን ባህር የሚያቋርጥ ድልድይ መርቀው ከፈቱ።
ቻይና ላለፉት 9 ዓመታት ድልድዩን ስትገነባ ቆይታለች። የድልድዩ አካል የሆኑ መንገዶችን ጨምሮ ርዝመቱ 55 ኪ.ሜ ሲሆን ሆንግ ኮንግን ከማካኡ እንዲሁም የቻይናዋን ዡሃይ ከተማን ያገናኛል። የድልድዩ ግንባታ የተጠናቀቀው ከተያዘለት ጊዜ ዘግይቶ ሲሆን 20 ቢሊየን ዶላር ወጪንም ጠይቋል። • ኦብነግ እዚህ እንዴት ደረሰ? • የመንገድ አቅጣጫ እየጠፋብዎ ተቸግረዋል? ጠቃሚ ነጥቦች እነሆ • በአላማጣ ግጭት ቢያንስ 5 ሰዎች መገደላቸው ተነገረ • በዝምታ የምትጠማ ከተማ -ሐረር በግንባታው ወቅት ቢያንስ 18 ሰራተኞች ህይወታቸውን ቢያጡም ቻይናውያኑ ድልድዩን እውን ከማድረግ አልሰነፉም። የቻይናው ፕሬዚዳንት ከማካኡ እና ሆንግ ኮንግ መሪ ጋር በመሆን የምረቃው ሥነ-ስርዓት ላይ ተገኝተዋል። ድልድዩ ነገ ለትራፊክ ክፍት ይደረጋል ተብሏል። ድልድዩ የመሬት መንቀጥቀጥን እና አውሎ ንፍስን እንዲቋቋም ተደርጎ የተሰራ ሲሆን፤ 400 ሺህ ቶን ብረት ለግንባታው ጥቅም ላይ ውሏል። የብረቱ መጠን የፈረንሳዩን ኤፍል ማማ አይነት 60 መገንባት ያስችላል ተብሎለታል። ድልድዩ የመርከቦችን እንቅስቃሴ እንዳይገታ በሚል 6.7 ኪ.ሜ የሚሆነው አካሉ በሰው ሰራሽ ዋሻ መልክ ከባህሩ ስር ተገንብቷል። የፕሮጀክቱ አካል የሆኑ ቢሊየን ዶላሮች ፈሰስ የተደረገባቸው ሁለት ሰው ሰራሽ ደሴቶች በባህሩ ላይ ተገንብተዋል። ከዡሃይ እስከ ሆንግ ኮንግ ይደረግ የነበረው ጉዞ 4 ሰዓት ይፈጅ ነበር። ድልድዩ ግን የጉዞውን ርዝመት ወደ 30 ደቂቃ አሳጥሮታል። በድልድዩ ላይ ለመጓዝ ክፍያ የሚጠይቅ ሲሆን የአካባቢው ባለስልጣናት ቀደም ብለው ድልድዩ በቀን እስከ 9200 ተሽከርካሪዎችን ያስተናግዳል ብለው ገምተው ነበር። የባህር እንስሳት ላይ ጉዳት ያስከትላል በሚል የድልድዩን ግንባታ የነቀፉ አልጠፉም። ከምድር ገጽ ላይ እየጠፉ የሚገኙ እንደ ነጫጭ የቻይና ዶልፊን መሰል እንስሳቶች ላይ ከፍተኛ አደጋ ደቅኗል ይላሉ።