id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
55945225
https://www.bbc.com/amharic/55945225
ምዕራባዊያኑ በትግራይ ጉዳይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ምን መከሩ?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሰሞኑ ከአንዳንድ ምዕራባዊያን መሪዎች ጋር መምከራቸውን የሚዘክር ፅሑፍ በማሕበራዊ ድር አምባ ገፆቻቸው አስታውቀዋል።
ከእነዚህ መሪዎች መካከል የጀርመኗ መራሂተ-መንግሥት አንግላ ሜርክልና የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑዔል ማኽሮ ይጠቀሳሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ጠዋት ደግሞ ከአዲሱ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ጋር ውይይት ማድረጋቸውን አሳውቀዋል። የዩናይትድ ስቴትስ አዲሱ የጆ ባይደን አስተዳደር አባል የሆኑት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር መምከራቸውን ገልፀዋል። ሚኒስትር ብሊንከን በትዊተር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት ከጠ/ሚ ዐቢይ ጋር መነጋገራቸውን አስታውቀው በትግራይ ክልል ያለውን ቀውስ እንዳሳሰባቸው ተናግረዋል። ጨምረውም በትግራይ ክልል ምንም ዕክል የሌለው የሰብዓዊ እርዳታ ፍሰት እንዲኖር ጥሩ አቅርበዋል። 'ነገር ግን ተግዳሮቶች ቢኖሩም ዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ለውጥ እንዲቀጥልና ሰላማዊ ለውጥ እንዲኖር ድጋፍ እንደምታደርግ' ገልፀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይም ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን ለውጥ ለመደገፍ ላላቸው ቁርጠኝነት አመስግነዋል። አክለው በዩኤስ እና ኢትዮጵያ መካከል የሚኖር ጠንካራ ግንኙነት ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ግንባታ አስፈላጊ እንደሆነ አስምረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው በፃፉት መልዕክት ትግራይ ክልል ስላለው ሁኔታ ምንም ያሉት ነገር የለም። በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጀርመኗ መራሂተ መንግሥት ጋር ባደረጉት የስልክ ልውውጥ ስለሃገራዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች እንዲሁም ስለ ኮቪድ-19 እና ምጣኔ ሃብታዊ ግንኙነቶች ማውራታቸውን በትዊተር ገፃቸው አሳውቀዋል። በኢትዮጵያ የጀመርን ኤምባሲ የትዊተር ገፅ በበኩሉ መራሂተ-መንግሥት ሜርክል ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በነበራቸው ቆይታ ሰብዓዊ እርዳታ አቅራቢ ድርጅቶቸና መገናኛ ብዙሃን በትግራይ ክልል በነፃ እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ ማቅረባቸውን አስታውቋል። በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ጋር በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ስለማጠናከር እንዲሁም ሃገራዊና ቀጣናዊ ጉዳዮችን በተመለከተ መምከራቸውን አስታውቀዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑዔል ማኽሮ ስለዚህ ጉዳይ በማሕበራዊ ድር አምባዎቻቸው ያሉት ነገር ባይኖርም የፈረንሳይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ባወጣው መግለጫ ፈረንሳይ በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ እንዳሳሰባትና የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች ፈቃድ እንዲሰጥ መጠየቋን አስታውቋል። በሌላ በኩል በአስመራ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ የኤርትራ መንግሥት ወታደሮቹን ከትግራይ ክልል በአስቸኳይ እንዲያስወጣ አሜሪካ ጥሪ አቅርባለች ብሏል። ኤምባሲው በፌስቡክ ገፁ የአሶሺዬትድ ፕሬስ ዘገባን አጋርቷል። በዘገባው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ 'የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ክልል የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየፈፀሙ እንደሆነ የሚጠቁም መረጃ አሜሪካ እንዳላት' ተናግረዋል ብሏል። የኤርትራ መንግሥት በትግራይ ክልል ስላለው ጦርነት ብዙም ያለው ነገር ባይኖርም ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ጦርነት አልተሳተፉም ሲል በተደጋጋሚ አስተባብሏል። በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉ አምባሳደሮች በቅርቡ ትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ አሳስቦናል ብለው ግልፅ ደብዳቤ ፅፈው ነበር። የኤርትራ መንግሥት ማስታወቂያ ሚኒስትር ለዚህ ግልፅ ደብዳቤ ምላሽ መስጠቱ አይዘነጋም።
news-54459888
https://www.bbc.com/amharic/news-54459888
አትሌቲክስ፡ ለተሰንበት ግደይ የ5 ሺህ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰንን ሰበረች
ኢትዮጵያዊቷ ሯጭ ለተሰንበት ግደይ በትናንትናው ዕለት የአምስት ሺህ ሜትር ርቀት ክብረ ወሰን ሰብራለች።
ቫለንሺያ በተደረገው በዚህ ውድድር በጥሩነሽ ዲባባ ለአስራ ሁለት አመታት ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን አሻሽላለች ተብሏል። የ22 ዓመቷ ሯጭ የገባችበትም ሰዓትም 14 ደቂቃ ከ6.62 ሰኮንዶች ሲሆን የጥሩነሸ ደግሞ 14 ደቂቃ ከ11.15 ሰኮንዶች ነበር። በትናንትናው ዕለት ከሷ በተጨማሪ ኡጋንዳዊው ጆሹዋ ቼፕተጊ በቀነኒሳ በቀለ ለአስራ አምስት ዓመታት ተይዞ የነበረውን የ10 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን በስድስት ሰኮንዶች በማሻሻልም ሰብሯል። የ24 ዓመቱ ሯጭ የገባበትም ሰዓት 26 ደቂቃ ከ11 ሰኮንዶች ነው ተብሏል። በስፔኗ ቫለንሺያ ከተማም ሁለት ክብረ ወሰኖች የተሰበሩበት እለትም ሆኗል። "በጣም ተደስቻለሁ" በማለትም ለተሰንበት ከሩጫው በኋላ ተናግራለች። ከዓመት በፊት በዶሃ ተካሂዶ የነበረውን የአለም ሻምፒዮና በ10 ሺህ ሜትር ብር አግኝታ የነበረ ሲሆን " ለረዥም ጊዜ ሳልመው የነበረ ነው። ለኔ በጣም ትልቅ ነው" በማለትም ተናግራለች በቀነኒሳ በቀለ ተይዞ የነበረው 26፡ 17፡53 ሰዓት በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ለረዥም ጊዜ በመያዝ ታሪካዊ የተባለ ክብረ ወሰን ነው። ጆሹዋ በአስር ወራትም ውስጥ አራት የአለም ክብረ ወሰኖችን መጨበጥ ችሏል። በታህሳስ ወር የ10 ኪሎ ሜትር የመንገድና በየካቲት ወር እንዲሁም የ5 ኪሎ ሜትር የመንገድ ክብረ ወሰኖችን ይዟል። ነሐሴ ወር ላይ በነበረው የሞናኮ ዳይመንድ ሊግም በቀነኒሳ በቀለ ለ16 አመታት ተይዞ የነበረውን የ5 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰንም በሁለት ሰኮንዶች በማሻሻል ሰብሯል። 'የዓለም ሬኮርድ (ክብረ ወሰን) ቀን' በተባለው በዚህ ውድድርም በቫለንሺያ ቱሪያ ስታዲየም 400 ሰዎች በተገኙበት ተካሂዷል።
news-49356157
https://www.bbc.com/amharic/news-49356157
አሜሪካ ውስጥ አንድ ታጣቂ ስድስት ፖሊሶችን አቆሰለ
አንድ ታጣቂ በአሜሪካዋ ፊላደልፊያ ከተማ ውስጥ ከፖሊሶች ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርጎ ስድስቱን ካቆሰለ በኋላ መያዙ ተዘገበ።
የተኩስ ልውውጡ የተጀመረው ፖሊሶች ፊላዴልፊያ ከተማ ውስጥ ኒስታውን ቲያጎ ተብሎ በሚታወቅ አካባቢ ከዕፅ ጋር የተያያዘ የመጥሪያ ወረቀት ለመስጠት በመጡበት ጊዜ ነው ተብሏል። ታጣቂው በፖሊሶች ላይ ተኩስ ከፍቶ የተኩስ ልውውጡ ለሰባት ሰዓታት ያህል ከተካሄደ በኋላ ግለሰቡ እጅ በመስጠቱ ፍጥጫው አብቅቷል። • በቴክሳሱ ጅምላ ጥቃት 20 ሰዎች ሞተዋል • የኦሃዮው ታጣቂ እህቱንና ስምንት ሰዎችን ገደለ ሞውሪስ ሂል የተባለው የ36 ዓመቱ ጎልማሳ እጁን ወደላይ አንስቶ ከቤቱ ሲወጣ የሚያሳዩ ምስሎች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የታዩ ሲሆን የተጠርጣሪው ጠበቃም ግለሰቡ እጁን እንዲሰጥ እንዳግባቡት ተናግረዋል። በአካባቢው የደረሱት ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ አባላት ከግለሰቡ ቤት መውጫ አጥተው የነበሩ ሁለት የፖሊስ ኣባላትንና ሦስት ሌሎች ሰዎችን ነጻ ማውጣታቸው ተገልጿል። ተጠርጣሪው በርካታ ሽጉጦችና ከፊል አውቶማቲክ ጠመንጃ ታጥቆ እንደነበር ፖሊስ ገልጾ፤ ታጣቂው በአካባቢው በነበሩ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ አባላት ላይ ከቤት ውስጥ ሆኖ ሲተኩስ እንደነበረ ተብሏል። የአካባቢው መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ግለሰቡ ከፖሊሶች ጋር ያደርግ የነበረውን የተኩስ ልውውጥ ክስተት በፌስቡክ ላይ በቀጥታ ያስተላልፈው ነበር። በተኩስ ልውውጡ ለህይወት አስጊ ያልሆነ የመቁሰል ጉዳት የደረሰባቸው ስድስት የፖሊስ መኮንኖች ህክምና ተደርጎላቸው ከሆስፒታል መውጣታቸውም ታውቋል። የአካባቢው የፖሊስ ባለስልጣን እንደተናገት "በዚህ የተኩስ ልውውጥ በርካታ የፖሊስ መኮንኖች አለመገደላቸው እንደተአምር የሚቆጠር ነው" ሲሉ ተናግረዋል። • ከክራይስትቸርች የመስጊድ ጥቃት በተአምር የተረፈው ኢትዮጵያዊ በፍጥጫው ወቅት በመኪና የተገጨ አንድ ሌላ ፖሊስ ግን ህክምና እየተከታተለ ሆስፒታል ውስጥ እንደሚገኝም ተገልጿል። የዋይት ሃውስ ፕሬስ ክፍል ኃላፊ ሆጋን ጊድሊ እንደገለጹት ፖሊሶች ስለቆሰሉበት ስለዚህ ክስተት ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንደተነገራቸው ገልጸዋል። ይህ የተኩስ ልውውጥ ያጋጠመው በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች ውስጥ ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው በርካታ ሰዎችን ከገደሉና ካቆሰሉ ከጥቂት ሳምንት በኋላ በጦር መሳሪያ ላይ የሚደረግ ቁጥጥርን በተመለከተ የሚደረገው ክርክር እየጠነከረ በመጣበት ጊዜ ነው።
50010591
https://www.bbc.com/amharic/50010591
ስቶርምዚ በካምብሪጅ የጥቁር ተማሪዎች ቁጥር እንዲጨምር አስተዋፅኦ አድርጓል ተባለ
የብሪታኒያዊው ራፐር ስቶርምዚ "በጎ ተፅዕኖ" በርካታ ጥቁር ተማሪዎች ዩኒቨርስቲ ኦፍ ካምብሪጅ እንዲገቡ ማስቻሉ ተገለፀ።
ስቶምዚ በየዓመቱ ወደ ካምብሪጅ ለሚገቡ ጥቁር ተማሪዎች ወጪያቸውን ይሸፍናል ዩኒቨርስቲው ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት ከሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአጠቃላይ ተማሪዎቹ 3 በመቶ የሚሆኑ ጥቁር ተማሪዎችን ለመጀመሪያ ዲግሪ ተቀብሏል። ስቶርምዚ በየዓመቱ ወደ ዩኒቨርስቲው ለሚገቡ ሁለት ጥቁር ተማሪዎች ወጪያቸውን ለመሸፈን ቃል ገብቶ ነበር። ዩኒቨርስቲው ይህ ቁጥር የአጠቃላዩን የዩኬ ማህበረሰብ የሚያሳይ ነው ብሏል። • "የሞራል ባቢሎን ውስጥ ነን፤ በጎና እኩይ መለየት አቅቶናል" ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ • የከተማው ትምህርት ቢሮ 300ሺህ ተማሪዎችን ለመመገብ እየተዘጋጀ ነው ዘንድሮ ወደ ዩኒቨርስቲው 91 ጥቁር ተማሪዎች የገቡ ሲሆን በ 2018 በመስከረም ወር ትምህርት ከጀመሩት ከግምሽ በላይ የሚሆኑት ጥቁሮች ናቸው ተብሏል። ዩኒቨርስቲው አክሎም ስቶርምዚ የሁለት ተማሪዎችን ወጪ እችላለሁ ማለቱ ከተሰማ በኋላ ከዩኒቨርስቲው ውጪ የማህበረሰብ አገልግሎት የሚፈልጉና ስለተለያዩ ኮርሶች የሚጠይቁ ጥቁር ተማሪዎች ቁጥር ጨምሯል። በዩኒቨርስቲው ለሚማሩ ጥቁር ተማሪዎች ቁጥር መጨመር ሌላው ምክንያት ተደርጎ የተወሰደው በርካታ ተማሪዎች በራሳቸው ተነሳሽነት ዩኒቨርስቲውን ለማስተዋወቅ የወሰዱት ርምጃ ነው። ዩኒቨርስቲው በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ዘንድሮ ከ200 በላይ ጥቁር ተማሪዎችን ተቀብሎ ያስተምራል። በዩኒቨርስቲው ውስጥ የትምህርት ጉዳዮች ምክትል ቻንስለር የሆኑት ፕሮፌሰር ግርሃም ቪርጎ " ይህ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ጥቁር ተማሪዎች የተመዘገቡበት ዓመት ሲሆን በራሳቸው በተማሪዎችና በዩኒቨርስቲው ጥረት የተሳካ ነው ። እኛ የመግቢያ ነጥባችንን አልቀነስነም" ብለዋል። በዩኒቨርስቲው የአፍሪካ ካሪቢያን ማህበረሰብ ፕሬዝዳንት የሆኑት ዋኒፓ ንድሎቩ እንደሚገልፁት የተማሪዎቹ ቁጥር መጨመሩ " ጥቁሮችና ካሪቢያኖች የዩኒቨርስቲው የቀደመ ባህልን ለመስበር ጠንክረው በመስራታቸው ነው" ብለዋል። "ለሌሎች ጥቁር ተማሪዎች በካምብሪጅ ቦታ እንዳላቸውና ስኬታማ እንደሚሆኑ ጥሩ ማሳያ ይሆናል" ሲሉም አክለዋል።
news-57264681
https://www.bbc.com/amharic/news-57264681
ኮሮናቫይረስ፡በኦሃዮ ግዛት የኮቪድ ክትባት ሎቶሪ አሸናፊዋ 1 ሚሊዮን ዶላር ተሸለመች
የአሜሪካ ግዛት ኦሃዮ ለኮቪድ ተከታቢዋ 1 ሚሊዮን ዶላር ሸለመች፡፡
ኦሃዮ ይህን ያህል ገንዘብ ለኮቪድ ተከታቢ የሸለመችው ነዋሪዎቿ ክትባቱን እንዲወስዱ ለማበረታታት ባዘጋጀችው የሎቶሪ መርሐ ግብር ነው፡፡ ኦሃዮ ይህ የኮቪድ ሎቶሪ የመጀመርያ እንጂ የመጨረሻ እንደማይሆን ቃል ገብታለች፡፡ አሸናፊዋ አቤጌል በጀነስኪ የምትባል ሲሆን ከሲልቨርስተን፣ ሲንሲናቲ ሰፈር አንድ ሚሊዮን ዶላሩን ተረክባለች፡፡ በፍጹም አሸናፊ እሆናለሁ ብላ ያልጠበቀችው አቢጌይል ለእናቷ ሊዛ በመደወል ደስታ የምታደርገው እንዳሳጣት ተናግራለች፡፡ ክትባቱን የወሰደችውም በጭራሽ ሎቶሪ የማሸነፍ ዕድልን አስባ እንዳልሆነ ተናግራለች፡፡ በሌላ የሎተሪ መርሐግብር አዳጊ ጆሴፍ ካስቴሎ ከዳይተን አካባቢ የመጀመርያውን የኮቪድ ስኮላርሺፕ አሸንፏል፡፡ በዚህ መርሐግብር የታቀፉ ወጣቶች ክትባት በመውሰዳቸው የኮሌጅ ስኮላርሺፕ የማሸነፍ ዕጣ ውስጥ ይገባሉ፡፡ ይህ የኮቪድ ሎቶሪ የተጀመረው የኮቪድ ክትባትን ለማበረታታት ነው፡፡ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ለሌሎች አራት ሳምንታት ሎቶሪው እንደሚወጣ የተገለጸ ሲሆን በአራቱም ሳምንታት አራት የተለያዩ ዕድለኞች እያንዳንዳቸው አንድ ሚሊዮን ዶላር አሸናፊ እንደሚሆኑ ይጠበቃሉ፡፡ ሌሎች አራት አዳጊዎች ደግሞ የኮሌጅ ስኮላርሺፕ አሸናፊ ይሆናሉ፡፡ በዚህ ሎቶሪ ለመታቀፍ 2.7 ሚሊዮን ነዋሪዎች ክትባት ወስደው ተመዝግበዋል፡፡ መቶ ሺህ አዳጊዎች ደግሞ የአራት ዓመታት ነጻ የትምህርት ዕድል ለማግኘት በእጣ መርሐግብር ተካተዋል፡፡ ሪፐብሊካኑ የኦሃዮ ገዥ ማይክ ድዋይን ይህን ሎቶሪ ያስጀመሩት በግንቦት 12 ነበር፡፡ የሎቶሪው መርሐግብር መጀመር በርካታ ዜጎች የኮቪድ ክትባት እንዲወስዱ እንዳበረታታ የገዥው ቢሮ በአሐዝ አስደግፎ ይፋ አድርጓል፡፡ የባይደን አስተዳደር የሎቶሪውን ሐሳብ ያደነቀ ሲሆን አንዳንድ የሕዝብ እንደራሴዎች ግን አላስፈላጊ የገንዘብ ብክነት ነው ሲሉ ተችተውታል፡፡ ይህ የኮቪድ ሎቶሪ ሐሳብ አሁን ከኦሃዮ ሌላ በኒውዮርክ፣ በሜሪላንድ፣ በኦሪገን እና ኮሎራዶ እንዲጀመር ሆኗል፡፡
news-47520891
https://www.bbc.com/amharic/news-47520891
"የሞተው የኔ ያሬድ ነው ብዬ አላሰብኩም" የካፕቴን ያሬድ የ11 አመት ጓደኛ
ከትናንት በስቲያ የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ET 302 ዋና አብራሪ የነበረው ያሬድ ጌታቸው ለአስራ አንድ ዓመታት የሚያውቀው ኡጋንዳዊ ጓደኛው ሃሰን ካቴንዴ ያሬድ ራግቢ በጣም ይወድ እንደነበር ይናገራል።
ያሬድና ሃሰን የሚተዋወቁት ከዓመታት በፊት ቦሌ አካባቢ በሚገኝ አንድ ህንፃ ፀጉር ቤት ያሬድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ የበራሪ ፅሁፍ ወረቀት ይዞ ሃሰን [ፓይለት ነህ] ብሎ ያሬድን በጠየቀበት አጋጣሚ ነበር። ያሬድ ኬንያ እንደተወለደ ነግሮት ለመጀመሪያ ጊዜ ሲገናኙ ያወሩት በስዋሂሊ እንደነበር ሃሰን ያስታውሳል። •ስለ አደጋው እስካሁን የምናውቀው ሃሰን እንደሚለው ያሬድ ስፖርት የሚወድ አይነት ሰው የነበረ ሲሆን ለራግቢ ግን ልዩ ፍቅር ነበረው። ያሬድና ሃሰን አዘውትረው ይገኛኙ የነበረው ግእዝ የሚባል የፈረንሳይ ሬስቶራንት ተገናኝተው ነበር ራግቢ የሚመለከቱት። መጀመሪያ አካባቢ ሀሰንም መኪና ስላልነበረው አብዛኛውን ጊዜ ያሬድ ያሽከረክር የነበረውን የአባቱን አሮጌ መኪና እየሾፈረ ብዙ ቦታዎች መሄዳቸውንም ሃሰን ያስታውሳል። ያሬድና ሃሰን ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት ከሁለት ሳምንት ገደማ በፊት የነበረ ሲሆን በሎሜ ስካይ አየር መንገድ ስራ ስላገኘ ጓደኛቸው ነበር ያወሩት። •ቻይና በቦይንግ 737 ማክስ 8 የሚደረጉ በረራዎችን አገደች ያሬድ የተወለደው ኬንያ ውስጥ ሲሆን እናቱ ኬንያዊ ሲሆኑ አባቱ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ናቸው። የልጅነት ጊዜውን በኬንያ ያሳለፈ ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ኢትዮጵያ ውስጥ ተከታትሎ የኢትዯጵያ አየር መንገድ አቬሽን ትምህርት ቤትን ተቀላቅሏል። ሃሰን እንደሚለው ያሬድ ኢትዮጵያዊም ኬንያዊም ማንነቱን ይወድ ነበር። ያሬድ አማርኛ ፣ ስዋሂሊና እንግሊዝኛ ቋንቋዎችን ጥርት አድርጎ ይናገር እንደነበር ሀሰን ገልፆልናል። "ብዙ ጊዜ ማንነቱን የሚያውቁ ኢትዮጵያዊያን ኢትዮጵያዊ ነህ ሲሉት [ኢትዮጵያዊና ኬንያዊ]ብሎ ይመልስ ነበር] በማለት ነገሩ አንዳንድ ጊዜም ያሬድን ያስቆጣው እንደነበር ሃሰን ይናገራል። ሃሰን የአደጋውን ዜና የሰማው ከማህበራዊ ሚዲያ ሲሆን መጀመሪያ ላይ ጓደኛው በአደጋው ስለመሞቱ ያወቀው ነገር አልነበረም። "የአደጋውን ዜናና የአውሮፕኑን ሰራተኞች ስም ዝርዝር ስመለከት ያሬድ የሚል ስም ባይም የተለመደ ስም ስለሆነ ሌላ ያሬድ ነው ብዬ አሰብኩ። የኔ ያሬድ ነው ብዬ አላሰብኩም። ቆይቶ ማታ ሁለት ሰዓት ላይ ሌላ ጓደኛችን ስለ ያሬድ ሰማህ ወይ? ምንድነው ምንትለው? ያሬድ ምን ሆነ ነው ያልኩት። በጣም አሰቃቂ ነው" ብሏል ሃሰን። ከዚያም ጓደኛው የተከሰከሰው አውሮፕላን አብራሪ የእነሱ ጓደኛ ያሬድ እንደሆነ ሲነግረው ለማመን በጣም እንደከበደውና ሊሆን አይችልምም የሚል ስሜት እንደተሰማው ይናገራል። " ለማመን የሚከብድ ነገር ነው ።መተኛት አልቻልኩም እስካሁን ድንጋጤ ውስጥ ነኝ" እሱ ብቻ ሳትሆን የሀሰን እናትም በድንጋጤ ውስጥ እንዳሉ ይናገራል። ያሬድ የአውሮፕላን አደጋ ምርመራ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ይመለከት እንደነበር የሚናገረው ሃሰን "በሚገባ የሰለጠነ አብራሪ ነው። እርግጠኛ ነኝ እስከመጨረሻዋ ሰዓት ብቃቱን እንደተጠቀመ" በማለት ጓደኛው ያሬድ እንደ ጀግና እንዲታወስ እንደሚፈልግ ይናገራል።
news-53243001
https://www.bbc.com/amharic/news-53243001
"በሦስቱ ሰኔዎች ጉዟችንን የማደናቀፍና ደም የማፍሰስ ሙከራዎች ተደርገዋል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ማምሻውን በአገሪቱ የቴሌቭዢን ጣብያ ላይ ቀርበው በድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን በመግለጽ ለአገሪቱ ሕዝብ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሃጫሉ ሁንዴሳን ሞት ከዚህ ቀደም ሰኔ 16/2010 እንዲሁም ሰኔ 15/2011 ካጋጠሙት ክስተቶች ጋር በማዛመድ "በሦስቱ ሰኔዎች ጉዟችንን የማደናቀፍና ደም የማፍሰስ ሙከራዎች ተደርገዋል" ብለዋል። በመቀጠልም በዚህኛው ሰኔ ከሁለቱ ሰኔዎች በተለየ መንገድ በቀጥታ ጉዳዩ የማይመለከተው ሰው እንዲገደል ተደርጎ ከፍተኛ ድንጋጤ፣ ከፍተኛ ጥርጣሬ እና የእርስ በእርስ ግጭት እንዲፈጠር ሙከራ ተደርጓል ሲሉ ገልፀዋል። "መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲገነዘብ የሚያስፈልገው ሃጫሉ የእኛ መታወቂያ ባይኖረውም ዩኒፎርም ባይለብስም ታጋይ ነው" ካሉ በኋላ "ታጋይ መሆኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ ይገነዘባል" ሲሉ አድናቆታቸውን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጨምረውም በሃጫሉ መስዋዕትነት የኢትዮጵያ አንድነት፣ የኢትዮጵያ ሰላም፣ የኢትዮጵያ አጠቃላይ ጉዞ በአንጸባራቂ መንገድ ዳግም የሚመዘገብ እንጂ የሚቆም አይደለም በማለት፤ "የጠላቶቻችን መሻትና ፍላጎት እንዳይሳካ ሕዝቡ የዚህን እኩይ ተግባር አላማ በመረዳት ግብ እንዳይመታ" ከመንግሥት ጎን እንዲቆም ጠይቀዋል። የሃጫሉ ሁንዴሳ ገዳዮች ጉዳይ በፍጥነት ተጣርቶ ፍትህ እንዲገኝ፣ የሕግ የበላይነት በአገር ደረጃ እንዲረጋገጥ እንዲሁም ሠላም የማስከበር ሂደቱ እንዳይደናቀፍ ሕዝቡ ከመንግሥት ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል። በተጨማሪም መንግሥት የዚህችን አገር ሉአላዊነት፣ ሠላም፣ ዘላቂ ፍላጎቷን ለማሳካት በእጅጉ እንደሚጥር አመልክተዋል። ሰኞ ዕለት የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት በአትዮጵያና በጎረቤቶቿ ጉዳይ ላይ እየመከረ ባለበት ሰዓት መንግሥትን ሙሉ በሙሉ ትኩረቱን አድርጎ የከፋ ውሳኔ እንዳይወሰን በሚጥርበት ሰዓት ሃጫሉ ሁንዴሳ በጥይት መገደሉን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሃጫሉን ". . .በቅርብ ለረዥም ዓመታት የማውቀው ወዳጄ . . ." በማለት ሃዘናቸው ጥልቅ መሆኑን ገልፀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ "ጠላቶቻችን" ያሏቸውን አካላት ሲገልፁ "የጠላቶቻችን ፍላጎት የጀመርነው እንዳይሳካ። የኦሮሞ ሕዝብ ከሌሎች ብሔሮች ጋር በዚሁ ምክንያት ደም እንዲቃባ" እንደሚፈልጉ በመግለጽ ይህንንም ለማሳካት በተደጋጋሚ ሙከራ መደረጉን ጠቅሰዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አክለውም "በሰኔ ወር አዲስ አበባ ላይ ጀምረን አዲስ አበባ ጦርነቱን እንጨርሰዋለን፤ የሚያሰጋን የአሮሚያ ጉዳይ ነው" በማለት ሲቀሰቀስ እንደነበር በማስታወስ፣ ከዚያም "ገዳይ ቡድኖችን እያደራጁ ሲያሰማሩ እንደነበር መንግሥትም ሲያከሽፍ መቆየቱን" ገልፀዋል። የእነዚህ ቡድኖች ፍላጎት ሃጫሉን ብቻ መግደል ሳይሆን ሌሎች የኦሮሞ ታዋቂ ሰዎችን ጭምሮ በመግደል "በብሔሮች መካከል ቁርሾንና ግድያን ለመፍጠር፣ አንድነታችን እንዲናጋ፣ ሠላማችን እንዲደፈርስ፣ ያሰብናቸው ጉዳዮች እንዳይሳኩ የውስጥና የውጪ ጠላት በመቀናጀት ይህንን እኩይ ተግባር ፈጽመዋል" ብለዋል። በዛሬው ዕለትም የሃጫሉ አስከሬን ወደ ትውልድ ቀዬው አምቦ ሲሄድም እነዚሁ አካላት እንዲስተጓጎል በማድረግ በርከት ያሉ ሰዎች ሕይወታቸው እንዳለፈ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በህልፈተ ህይወታቸውም የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልፀዋል።
news-53996768
https://www.bbc.com/amharic/news-53996768
በምስራቅ ጎጃም ዞን በአዋበል ወረዳ የመሬት መንሸራተት ጉዳት አስከተለ
በምስራቅ ጎጃም ዞን በአዋበል ወረዳ በሰባት ቀበሌዎች በደረሰው የመሬት መንሸራተት ሰብሎችን ለውድመት ህብረተሰቡን ደግሞ ለችግር ዳርጓል፡፡
በመሬት መንሸራተቱ 135 ቤቶች ሲፈርሱ 336 አባውራዎች በቤተሰብ ደረጃ ደግሞ 1260 ሰዎች ለችግር ተጋልጠዋል። ጉዳቱ የደረሰባቸው አካባቢዎች ሚዛን፣ ጡረት፣ ለጋ የጠረብና፣ ጅት ባህር፣ ወጀል አንቅራቅ፣ እነቢ ጭፋር እና አዲስ አምባ ጨሊያ መሆኑ ታውቋል። መምህር ተመስገን አጥናፉ የሚዛን ነዋሪ ሲሆኑ እያቄም የምትባለውና እና ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባትን ጎጥ በቦታው በመሄድ መመልከታቸውን ለቢቢሲ አስታውቀዋል። የመሬት መንሸራተቱ ነሐሴ 22/2012 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 አካባቢ መከሰቱን አስታውቀው ከ100 በላይ ቤቶች የፈረሱ መሆኑን ገልጸዋል። "አንዳንዶች 'ቤታችሁ የት ነው?' ተብለው ሲጠየቁ ራሱ ቤታቸው የት እንደሆነ የት አካበቢ እንደሆነ ራሱ አያውቁትም" ሲሉ የነበረውን ሁኔታ አስታውሰዋል። ቤቶቹ ከእነ ሙሉ ዕቃቸው መፍረሳቸውን ገለጸው አብዛዎቹ ነዋሪዎች ቤት ዘግተው ሥራ ላይ እንደነበሩ እና አደጋው አስከፊ መሆኑን መመልከታቸውን አስታውቀዋል። በቦታው በደረሱበት ወቅትም ዛፎች እተንሸራተቱ ሲወድቁ መመልከታቸውንም ገልጸውልናል። "ላይ ነበረው መሬት ወደታች ሄዶ እፈርሳል ይሰነጣጠቃል" ብለዋል። በሰዎች ላይ ጉዳት ስለመድረሱ ባይሰሙም ከብቶች እና ፍየሎች ላይ ግን ጉዳት ማድረሱን ገልፀዋል። የፍየል ግልገሎች ላይ ቤት ፈርሶባቸው መመልከታቸውንም ጠቅሰዋል። አካባቢው አትክልት እና ፍራፍሬ በብዛት የሚለማበት መሆኑን ጠቅሰው የደረሰውን አደጋ "እኔ እንዲህ አይነት አስከፊ ሁኔታ ገጥሞኝም አይቼም አላውቅም በህይወቴ" ሲሉ ገልጸውታል። በአዋበል ወረዳ ሰባት ቀበሌዎች ከነሀሴ 22/2012 ጀምሮ የመሬት መንሸራተት መከሰቱን ደግሞ የወረዳው የአደጋ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ምላሽ ቡድን መሪ አቶ አቶ አስማማው አሰፋ ለቢቢሲ ገልጸዋል። የደረሰው ጉዳት ሙሉ ለሙሉ ተለይቶ አለመጠናቀቁን አስታውቀው በመሬት መንሸራተቱ 336 አባወራዎች ጉዳት ሲደርስባቸው 135 ቤቶች ደግሞ ፈርሰዋል ብለዋል። ስልሳ የሚጠጉ ተጨማሪ ቤቶች የመፍረስ አደጋ የተደቀነባቸው ሲሆን ከ125 እስከ 135 ሄክታር የሚደርስ መሬት ላይ ያለ ሰብል እና 135 ሔክታር ላይ ያለ አትክልትና ፍራፍሬ ጉዳት ሲደርስበት ከብቶች እና ፍየሎችም ሞተዋል ብለዋል። ሚዛን ዋሻ ቱሉ በምትባል ቀበሌ ጉዳቱ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው በተለይ እያቄም በምትባል ጎጥ የነበሩ ቤቶች፣ ሰብል፣ አትክልታና ፍራፍሬ እንዲሁም በገተራ ውስጥ ነበረ እህል ሙሉ ለሙሉ መውደሙን አስታውቀዋል። አደጋው ነሐሴ 22 የጀመረ ቢሆንም ዛሬም ድረስ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ እንደተከሰተ አስታውቀዋል። "አደጋው እየሰፋ ነው። እስከ ትላንት 119 ቤቶች ነበር ጉዳት የደረሰባቸው። ትላንት ከሰዓት እና ዛሬ ነው ቁጥሩ 135 ደረሰው። የመሬት መንሸራተቱ አሁንም አለ እየቀጠለ ነው። ወደ አካባቢው ሄደን ባናጣራም ዛሬ ሌሎች 2 ቀበሌዎች ተጨምረዋል የሚል ነገር አለ" ብለዋል። የመሬት መንሸራተቱ በዝናብ መብዛት ምክንያት ከፍተኛ ውሃ መሬት ውስጥ ስለላ ነው የተከሰተው ያሉት አቶ አስማማው ቤቶችን እስከ 15 ሜትር ድረስ በመውሰድ ከጥቅም ውጭ አድርጓል ብለዋል። ቤት ንብረታቸውን ያጡ ሰዎችን በዘመዶቻቸው፣ ጎረቤቶቻቸው እና እንደ ትምህርት ቤት ባሉ የመንግስት ተቋማት መጠለላቸውን ጠቁመዋል። እስካሁን ከህብረተሰቡ ድጋፍ ሲደረግላቸው መቆየቱን እና የወረዳው የቴክኒክ ኮሚቴ ቦታው ድረስ ሄዶ ችግሩን በመመልከት ተጎጂዎችን ጋር መነጋገሩን ጠቁመዋል። ኮሚቴ የምግብ እና አልባሳት ቁሳቁስ ድጋፍ ለመስተት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጸው መንግስት እና ተቋማት ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ጥሪ አቅርበዋል።
news-54776071
https://www.bbc.com/amharic/news-54776071
ኮሮናቫይረስ፡ የስፔን ቀብር አስፈጻሚዎች የሥራ ማቆም አድማ አደረጉ
በስፔን የሚገኙ የቀብር አስፈጻሚ ድርጅቶች ሰራተኞች በኮሮረናቫይረስ የሚሞሩ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ የሰራተኛ ቁጥር ይጨመርልን በማለት የሥራ ማቆም አድማ ማድረጋቸው ተሰምቷል።
የሰራተኞች ማህበራት እንደገለጹት ወረርሽኙ መጀመሪያ ላይ በአገሪቱ ሲከሰት ቀብር አስፈጻሚዎቹ ከአቅማቸው በላይ ስለሆነባቸው የአንዳንድ ሰዎችን ቀብር ሳይፈልጉ እንዲያራዝሙ ተገድደዋል። በአሁኑ ሰአት ደግሞ አውሮፓ በሁለተኛ ዙር የቫይረሱ ስርጭት እየተፈተነች ትገኛለች። በርካታ አገራት ቫይረሱ እንደ አዲስ መሰራጨት መጀመሩን ተከትሎ የሰአት እላፊዎችና የእንቅስቃሴ ገደቦችን ተግባራዊ ለማድረግ እየሞከሩ ሲሆን የሟቾችም ቁጥር ቢሆን እያንሰራራ መጥቷል። ቅዳሜ ዕለት ኦስትሪያ እና ፖርቹጋል አዳዲስ መመሪያዎችን ማስተዋወቃቸው ይታወሳል። በመላው ስፔን የሚገኙ የቀብር አስፈጻሚ ድርጅቶች ሰራተኞች ዕሁድ ዕለት አድማውን መትተዋል። አድማው የተካሄደው ደግሞ ፈረንሳያውያን የሞቱባቸውን ሰዎች መቃብር ስፍራ በሚጎበኙበት ቀን ነው። አንድ በዋና ከተማዋ ማድሪድ የሚገኝ የቀብር አስፈጻሚ ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል ሲናገር በአሁኑ ሰአት እየጨመረ የመጣውን የሟቾች ቁጥር ከግምት ውስጥ በማስገባት ከ15 እስከ 20 ሰራተኞች እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። አርብ ዕለት ብቻ በስፔን 239 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። ባሳለፍነው መጋቢት ወር ላይ የበርካታ ሰዎች አስክሬን ሳይቀበር ለተጨማሪ አንድ ሳምንት እንዲቆዩ የተገደዱ ሲሆን የቀብር ስነስርአቱም ቢሆን ከከተማዎች አካባቢ ራቅ ባሉ ቦታዎች ነበር የሚካሄደው። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተበት ዕለት ጀምሮ ስፔን እስካሁን ከ1.1 ሚሊየን በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ያስታወቀች ሲሆን 35 ሺ 800 ደግሞ የሟቾች ቁጥር ነው። በሌሎች የአውሮፓ አገራትም ቢሆን የሁለተኛ ዙር ስርጭቱን ተከትሎ በርካታ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው። ፈረንሳይ ባለፉት 24 ሰአታት ብቻ 46 ሺ 290 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የገለጸች ሲሆን ትናንት ከትናንት በስቲያ ደግሞ 35 ሺ 641 ሰዎች መያዛቸውን አስታውቃ ነበር። በአጠቃላይ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 37 ሺ 19 ደርሷል። ጣልያን ደግሞ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር አዳዲስና ውጤታማ እርምጃዎችን መውሰድ ጀምሪያለው ብላለች። የአገሪቱ የጤና ሚኒስትሩ ሮቤርቶ ስፔራንዛ በጣልያን ያለውን ስርጭት ለመቆጣጠር ሙሉ በሙሉ እንቅስቃሴን መገደብ አማራጭ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
news-48349481
https://www.bbc.com/amharic/news-48349481
ኤምአርአይ ምንድነው?
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተወሳሰቡና ቀደም ሲል ለመለየት እጅግ አስቸጋሪ የነበሩ በሽታዎችንና የሰውነት እክሎችን ለመለየት 'ኤምአርአይ' የተባለ የህክምና መሳሪያ በጥቅም ላይ መዋል ጀምሯል።
ኤምአርአይ በራዲዮዌቭና በማግኔት የሚሰራ ለህክምና አገልግሎት የሚውል ማሽን ነው። ማሽኑም በሰውነታችን ውስጥ ያለውን በሽታ በቀላሉና በጠራ መልኩ የሚያሳይ የህክምና መሳሪያ ነው። • በርካቶች ከምጥ ይልቅ በቀዶ ህክምና መውለድን እየመረጡ ነው ይህም ደግሞ የጎንዮሽ ጉዳት በሌለው መልኩና በቀላል መንገድ በሽታውን ለመለየት የሚያግዝ እንደሆነ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ራዲዮሎጂስት የሆኑት ዶክተር ሳምሶን አሽኔ ይናገራሉ። በዚህ ምክንያት ከሌሎች ለህክምና አገልግሎት ከሚውሉ ማሽኖች የተሻለ ነው። በህክምና ዘርፉ ውስጥ በሽታዎችን በቀላሉ በመመርመርና በማወቅ ሂደት ውስጥ ያሉ ግድፈቶችን ለማቃለልም ከፍተኛ ሚና እንዳለው ባለሙያው ያብራራሉ። • የሚያስወርዱ ሴቶች ቁጥር ከሚወልዱ ሴቶች የሚበልጥባት ሀገር ማሽኑ ትልልቅ በማግኔት የሚሰሩ ቱቦዎች ያሉት ሲሆን የህክምና ባለሙያዎች በአይናቸው ሊያዩዋቸው የማይችሏቸውን የሰውነታችንን ክፍሎችና በሽታዎችን በቀላሉ ለመለየት ያግዛል። ኤምአርአይን ለምን አይነት ምርመራዎች እንጠቀምበታለን? መሳሪያው ገና ለብዙ ዓመታት ጥቅም ላይ አለመዋሉን በዚሁ ዙሪያ ብዙ ምርምሮች እየተደረጉ ስለሆነ ለወደፊቱ አሁን እየሰጠው ካለው አገልግሎት በላቀ መልኩ ጥቅም ላይ እንደሚውል ዶክተር ሳምሶን ጠቅሰዋል። አሁን ባለበት ደረጃ ግን ኤምአርአይ በአጠቃይ ለአንጎል ችግሮች፣ የአከርካሪ አጥንት፣ ሆድ፣ ካንሰር እንዲሁም ለመገጣጠሚያ በሽታዎችና ሌሎችም ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን የዘመኑ እጅግ ጠቃሚ መሳሪያ ነው። • ወንዶች የማያወሯቸው አምስት አሳሳቢ ነገሮች በተለይ ደግሞ በአንጎል ውስጥ የሚገኙ ችግሮችንም ሆነ እጢዎች ለመለየት ለዘመናት ትልቅ ችግር ነበር የሚሉት ባለሙያው፤ ከዚህ በፊት ሲቲ ስካን የሚባል መሳሪያ በጥቅም ላይ ይውል ነበር። ሲቲ ስካንን ተከትሎ ደግሞ ኤምአርአይ መጣ። ''ይህ መሳሪያ ለምሳሌ አንጎልን ብንወስድ በመጀመሪያ አንጎላችን ውስጥ እጢ አለ ወይስ የለም? የሚለውን ይነግረናል። ከዚህ ባለፈም እጢው ምን አይነት ባህሪዎች አሉት? ይዘቱ ምንድን ነው? እንዲሁም ህክምናው ምን መሆን አለበት የሚሉት ጥያቄዎች ለመመለስ በእጅጉ ይረዳል'' ይላሉ ዶክተር ሳምሶን። ''ተገቢው ህክምና ከተደረገ በኋላ እንኳን ህክምናው ውጤታማ ነበር ወይ? የሚለውን ለማወቅ ይህ መሳሪያ እጅግ ጠቃሚ ነው። '' በኤምአርአይና በሲቲስካን መካከል ያለውን ልዩነት ሲያስረዱ ባለሙያው ሲቲስካን በሽታዎችንና የሰውነት ክፍሎቻችን ላይ የተፈጠሩ ችግሮችን ለመለየት ጨረር የሚጠቀም ስለሆነ ብዙ ጊዜ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል ብለዋል። • ከ27 ዓመታት በኋላ ከ'ኮማ' የነቃችው ሴት የሲቲስካን ምርመራ በሚደረግበት ወቅት በተለይ ህጻነት ለከፍተኛ ጨረር እንዳይጋለጡ ጥንቃቄ መደረግ አለበት። ''ኤምአርአይ ግን ለምርመራው የማግኔት ኃይልን ስለሚጠቀም የጎንዮሽ ጉዳት የለውም። ምናልባት ታካሚዎች በሰውነታቸው ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች ብረት ነክ መሳሪያዎች ካሉ ግን በጣም ከባድ ነው። እኛም ብንሆን ምርመራው ከመደረጉ በፊት ተገቢውን ማጣራት አካሂደን ነው ወደ ኤምአርአይ የምንመራው።'' ከዚህ በተጨማሪ በሰውነታችን ውስጥ ያለውን ነገር ጥርት አግርጎ ከማሳየት አንጻር ኤምአርአይ የተሻለ ነው። እንደውም ባለሙያው የሲቲስካንና ኤምአርአይ ልዩነትን ለማስረዳት በድሮና ዘመን አመጣሽ ካሜራዎች መካከል ያለውን ይጠቅሳሉ። ኤምአርአይ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ ቦታዎችን ጥርት ባለና ለውሳኔ በሚቀል መልኩ የሚያቀርብ ሲሆን ሲቲስካን ግን የምስሎቹ ጥራት ከኤምአርአይ ጋር ሲወዳደር በጣም ዝቅተና ነው። • ጫት የአእምሮ ጤናን እንደሚጎዳ ጥናት አመለከተ ነገር ግን ይላሉ ባለሙያው፤ ''ሁሉም ኤምአርአይ መሳሪያዎች እኩል የሆነ አገልግሎት የላቸውም። በውስጣቸው ባለው የማግኔት ቱቦ መጠንና የማጉላት አቅም መሰረት ሁሉም የየራሳቸው አይነት ጥቅምና አሰራር አላቸው።'' በሌሎች አጋጣሚዎች ግን ሲቲስካን የሚመረጥበት ጊዜ እንዳለ ዶክተር ሳምሶን ያስረዳሉ። ለምሳሌ ድንገተኛ አደጋዎች ሲያጋጥሙና ታካሚዎች አስቸኳይ ምርመራ ሲያስፈልጋቸው ሲቲስካን ተመራጭ ነው። ምክንያቱም ሲቲስካን በፍጥነት ውጤቱን ያደርሳል። ኤምአርአይ ግን በትንሹ 30 ደቂቃ ሊፈጅ ይችላል።
news-54093179
https://www.bbc.com/amharic/news-54093179
ኮሮናቫይረስ፡ የኮሮና ክትባትን በዓለም ለማሰራጨት 8ሺህ ግዙፍ አውሮፕላኖች ያስፈልጋሉ
ይበለውና የኮሮና ክትባት ቢሳካ በነገታው እንወጋዋለን ማለት አይደለም፡፡ በመላው ዓለም ማሰራጨቱ በራሱ ሌላ ትልቅ ፈተና ነው ሲል የአቪየሽን ኢንደስትሪ ማኅበር ተናግሯል፡፡
ምናልባትም በአውሮፕላን የካርጎ ታሪክ እጅግ ከባዱ ፈተና፣ እጅግ ከባዱ ኃላፊነት ይሆናል ተብሏል፡፡ የዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር (IATA) እንደሚለው ምናልባት ክትባቱ ቢሳካ እያንዳንዳቸው የቦይንግ 747 አውሮፕላኖች አይነት ግዝፈትና ፍጥነት ያላቸው 8ሺህ ግዙፍ የካርጎ አውሮፕላኖች ያስፈልጋሉ ብሏል፤ ክትባቱን ለማዳረስ፡፡ ምንም እንኳ ለጊዜው ክትባት ባይፈበረክም፣ መሳካቱ አይቀርም በሚል የአየር ትራንስፖርት ማኅበሩ ነገሮችን ለማቀናጀት ከወዲሁ ተፍ ተፍ እያለ ነው፡፡ ማኅበሩ በጤና ዙርያ ከሚሰሩት በርካታ ድርጅቶች፣ ከዓለም ጤና ድርጅት፣ ከመድኃኒት አምራቾች፣ ከመድኃኒት አቀባባዮች፣ አከፋፋዮች፣ ከአውሮፕላን ካርጎ ሥራ ተሳታፊዎች ጋር በጥምረት መስራት ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ ይህ 8ሺህ ቦይንግ ያስፈልጋል የተባለው ታዲያ አንድ ሰው በሕይወት ዘመኑ አንድ ጊዜ ብቻ፣ አንድ ጠብታ ክትባት ብቻ ነው የሚያስፈልገው በሚል የተሰላ ሲሆን ይህ ግምት ለምሳሌ በእጥፍ ቢጨምር እጥፍ ካርጎ አውሮፕላን ያሻል ማለት ነው፡፡ የአየር ትራንስፖርት ማኅበሩ ሥራ አስፈጻሚ አሌክሳንደር ዴ ጁኒያክ እንዲህ ተናግረዋል፣ ‹‹የኮቪድ 19 ክትባትን በጥንቃቄ ማጓጓዝ የዚህ ክፍለ ዘመን ትልቁ የካርጎ ኢንዱስትሪ ግብ ነው፡፡ ነገር ግን እንዲሁ በዘፈቀደ የሚጓጓዝ አይደለም፤ ከፍተኛ ዝግጅት ይፈልጋል፡፡ ለዝግጅቱ ትክክለኛው ጊዜ ደግሞ አሁን ነው›› በርካታ አየር መንገዶች በወረርሽኙ ጊዜ የሰዎች ከቦታ ቦታ እንቅስቃሴ በመታቀቡ ወደ ካርጎ ሥራ ገብተው ቆይተዋል፡፡ በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድም ይጠቀሳል፡፡ ነገር ግን ማንም እቃ የሚያጓጉዝ አየር መንገድ ክትባትን ማጓጓዝ ይችላል ማለት አይደለም፡፡ ክትባት ለማጓጓዝ ካርጎው ከ2 እስከ 8 ሴንትግሬድ የሙቀት መጠን ሊኖረው ይገባል፡፡ አንዳንድ ክትባቶች ደግሞ እጅግ ቀዝቃዛ (ከዜሮ በታች) የሆነ የሙቀት መጠንን ሊፈልጉ ይችላሉ፡፡ ይህን ማሟላት ለብዙ አየር መንገዶች ፈተና ሊሆን ይችላል፡፡ ዝግጅት ከወዲሁ የተጀመረውም ለዚሁ ነው፡፡ ይህንን ክትባት የማጓጓዙን ፈተና ለመቀነስ አንዱ መንገድ አገራት በየራሳቸው ክትባቱን እንዲያመርቱት ማድረግ ቢሆንም ይህ ለብዙ የዓለም አገራት የሚቻል አይሆንም፡፡ በተለይ በርካታ የካርጎ በረራዎች ወደ ደቡብ ምሥራቅ ኢሲያ ይደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በርካታ ሕዝብ ስለሚገኝና ክትባት የማምረት አቅም ያለው አገርም ባለመኖሩ ነው፡፡ ክትባቱን በቀላሉ ወደ አፍሪካ ለማጓጓዝም የሚቻል አይደለም ብሏል ማኅበሩ፡፡ ይህም በቂ የካርጎ አቅም ስለሌለ፣ አፍሪካ ሰፊ አህጉር በመሆኗና የድንበር ውስብስብነት መኖሩ ነው፡፡ የካርጎ ሥራው ልክ ወታደራዊ ጥንቃቄን የሚፈልግ ነው፤ ከተጓጓዘ በኋላም ቢሆን የሚቀመጥበት ቦታ መድኃኒቱን ለማስቀመጥ የሚሆን መሆን አለበት፡፡ ይህ ደግሞ ለበርካታ የአፍሪካ አገሮች ፈተና ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በዓለም ደረጃ 140 ቤተ ሙከራዎች ክትባት ለመሥራት ተፍ ተፍ ማለት ጀምረው ነበር፡፡ አሁን 24 የሚሆኑት በሰዎች ላይ ሙከራ ጀምረዋል፡፡ ከነዚህ ሁሉ ትልቅ ተስፋ የተሰጠው የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲው የክትባት ሙከራ ነው፡፡. ሩሲያ ክትባቱ በእጄ ገብቷል ብትልም ዓለም በአገሪቱ ላይ እምነት በማጣቱ ይመስላል እምብዛምም የራሺያ ክትባት አይወራም፡፡ የጤና ባለሙያዎች የሩሲያ ክትባት ሳይንሳዊ ሂደትን የተከተለ አይደለም፣ ብሔራዊ ኩራተን ከጤና አስበልጧል ሲሉ ይተቹታል፡፡
news-57127671
https://www.bbc.com/amharic/news-57127671
‹‹ባል›› የብዙዎችን ሕይወት ይቀይራል የተባለለት የአፍሪካ አዲሱ የቅርጫት ኳስ ሊግ
‹‹አፍሪካ፤ መጥተናል፤ ጨዋታው ይጀመር›› በሚሉት ቃላት ነበር ለአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የቅርጫት ኳስ ሊግ ወይም ባል ሴኔጋላዊ ፕሬዘዳንቱ አማዱ ጋሎ ፋል ያስጀመሩት፡፡
የመጀመሪያው የሊጉ ጨዋታ እሁድ በናይጄሪያ እና በሩዋንዳ መካከል ተካሂዶ ናይጄሪያ የመጀመሪያውን ጎል በማስቆጠር ታሪካዊ ብትሆንም ሩዋንዳ ጨዋታውን 83 ለ 60 ረትታለች፡፡ በሜዳዋ እና በደጋፊዎቿ ፊት የተጫወተችው ሩዋንዳ ክፍተኛ ድጋፍ እንደነበራትም ተዘግቧል፡፡ ‹‹ይሄ የብዙዎችን ህይወት ይቀይራል፡፡ በመላው አህጉሩ ላሉ ሰዎች ቤተሰቦቻቸውን ለመመገብ የሚያስችል እና ሌሎች በርካታ እድሎችን የሚፈጥር ነው›› ሲል የቀድሞው የኤን.ቢ.ኤ ተጫዋች እና አሁን ለናይጄሪያ ተሰልፎ የሚጫወተው ቤን ኡዞ ለቢቢሲ ስፖርት ተናግሯል፡፡ ‹‹ይህ የአፍሪካ ኤን ቢኤ ነው፣ እናም በዚህ አህጉር ለሚያድጉ ልጆች ይህ የራሴ ብለው የሚጠሩት እና የመጪውን ግዜ ተጫዋቾች የምናፈራበት ነው›› ሲልም አክሏል፡፡ የሊጉ ጨዋታዎች ከአንድ አመት በፊት እንዲጀመሩ እቅድ ተይዞላቸው የነበረ ቢሆንም በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለ14 ወራት ዘግይቶ ተጀምሯል፡፡ በዚህ የመጀመሪያው የውድድር አመት ከ12 አገራት የሚወጣጡ ቡድኖች የሚወዳደሩ ይሆናል፡፡ አንጎላ፣ ግብጽ፣ ሞሮኮ፣ ናይጄሪያ፣ ሴኔጋል እና ቱኒዚያ እንደሚሳተፉ ታውቋል፡፡ ቀሪ ስድስት ቡድኖች የማጣሪያ ጨዋታዎችን አድርገው ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የዚህ አመት የሊጉ ጫዋታዎች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በሩዋንዳዋ ዋና ከተማ በሚገኛው እና 10 ሺህ ሰው በሚይዘው የኪጋሊ አሬና ይካሄዳል፡፡ በእያንዳንዱ ጨዋታም 1ሺህ500 አካባቢ ታዳሚዎች እና ተጋባዥ እንግዳዎች ይከታተሉታል፡፡ በሊጉ 26 ጨዋታዎች የሚደረጉ ሲሆን እስከ ፍፃሜው ጨዋታ ድረስ ሁለት ሳምንታትን የሚፈጅ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
news-53243002
https://www.bbc.com/amharic/news-53243002
አቶ ጃዋር መሐመድን ጨምሮ 35 ሰዎችን መያዙን ፖሊስ አስታወቀ
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አባል የሆነው ጃዋር መሐመድ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደሚገኝ የፌደራል ፖሊስና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሸን በጋራ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽንር ጀነራል እንደሻው ጣሰው በዛሬው ዕለት ማክሰኞ ምሽት በብሔራዊው ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው በሰጡት መግለጫ ጃዋር መሐመድን ጨምሮ 35 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ብሏል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በጋራ በሰጡት በዚህ መግለጫ ላይ የጃዋር ጠባቂዎች ይዘውት የነበረው የጦር መሳሪያዎች እና መገናኛ ሬዲዮችም መያዛቸውን አመልክተዋል። በዚህም መሰረት 8 ክላሽ፣ 5 ሽጉጥ እና 9 የሬዲዮ መገናኛዎች ከጃዋር ጠባቂዎች ላይ ፖሊስ መያዙን ተገልጿል። ቀን ላይ ቀደም ሲል በጃዋር መሐመድ ዋና ዳይሬክተርነት ይመራ የነበረው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ጃዋርና ሌሎች ሰዎች በፖሊስ መያዛቸውን የዘገበ ቢሆንም ከሚመለከተው አካል ማረጋገጫ ሳይሰጥ ቆይቶ ነበር። ነገር ግን ምሽት ላይ የኦሮሚያና የፌደራል ፖሊስ እንዳስታወቁት ጃዋር መሐመድ በቁጥጥር ስር እንደዋለ ተገልጿል። በመግለጫው ላይ "ማንም ሰው ከሕግ በላይ አይደለም" ያሉት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራሉ "ሕግ ለማስከበር የጸጥታ አካል በሚወስደው እርምጃ ሁሉም ሰው ተባባሪ መሆን አለበት" ብለዋል። ኮሚሽነሩ አክለውም "አንዳንድ የኅብረተሰብ ክፍል በተሳሳተ አረዳድ እነዚህ ሰዎች የታሰሩበት ሁኔታ ትክክል አይደለም ብሎ በተለያየ መንገድ ተሰልፎ ዳግም ጥፋት እንዳያጠፋ አስፈላጊውን ማሳሰቢያ ፖሊስ እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል። አያይዘውም ስለጉዳዩ ፖሊስ በየጊዜው የሚደርስበትን መረጃ በደንብ አጠናክሮና አደራጅቶ ለኅብረተሰቡ የሚያሳውቅ መሆኑን ኮሚሽነር ጄነራሉ እንደሻው ጣሰው ተናግረዋል። የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አራርሳ መርዳሳ በበኩላቸው "በጃዋር መሐመድ የሚመራው ቡድን የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ አስከሬን ወደ አምቦ እንዳይሄድ አድርጓል" ብለዋል። ኮሚሽነሩ "በጃዋር መሐመድ የሚመራው ቡድን አስክሬኑ በቤተሰቡ ጥያቄ መሰረት ከጳውሎስ ሆስፒታል ወጥቶ ወደ አምቦ እየተሸኘ ሳለ፤ ከቤተሰቡ ፍቃድ ውጪ ቡራዩ ሲደርስ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ አደርጓል" ሲሉም ተናግረዋል። በተጨማሪም አስክሬኑ ወደ አዲስ አበባ ከተመለሰ በኋላ የብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ጽህፈት ቤት ውስጥ እንዲገባ እንደተደረገ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር ተናግረዋል። ከዚህ በኋላም "በኃይል ሰብረው በመግባት በጥበቃ ላይ የነበረ የኦሮሚያ ፖሊስ በጥይት በመምታት ገድለዋል። አስክሬኑን ካስገቡ በኋላም አስክሬኑን ይዞ ለማቆየት ጥረት ተደርጓል" ሲሉ ገልጸዋል። በጸጥታ ኃይሉ ግድያ እና አስክሬኑ ወደ ቤተሰብ እንዳይሄድ በመከልከል አቶ ጃዋርን ጨምሮ በዚህ ውስጥ ተሳትፎ አላቸው የተባሉ ወደ 35 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር አመልክተዋል። የፖሊስ ኃላፊዎቹ በአጠቃላይ 35 ሰዎች መያዛቸውን ይግለጹ እንጂ ከጃዋር መሐመድ ውጪ የሌሎቹን ማንነት እንዲሁም ቀጣይ ዝርዝር ሁኔታዎች አልገለጹም።
news-49848879
https://www.bbc.com/amharic/news-49848879
ሙጋቤ በተወለዱበት ከተማ እንዲቀበሩ መንግሥት ወሰነ
የዚምባብዌ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ የቀብር ስፍራ ካጨቃጨቀ በኋላ የመጨረሻ ውሳኔ አግኝቶ በትውልድ ከተማቸው እንዲቀበሩ ተወስኗል።
በ95 ዓመታቸው የሞቱት ሙጋቤ ከፍተኛ የአህጉሪቱ ሹማምንት በተገኙበት በሀገሪቱ መናገሻ ከተማ ሀራሬ ሽኝት የተደረገላቸው በቅርብ ነበር። ቤተሰቦቻቸው በትውልድ ስፍራቸው ዝቪምባ አፅማቸው ይረፍ ብለው ቢጠይቁም የዚምባብዌ መንግሥት ግን አሻፈረኝ በማለት በሀራሬ የጀግኖች መካነ መቃብር ቀብራቸው እንደሚፈፀም ተናግሮ ነበር። በዚህም የተነሳ ቤተሰቦቻቸው ተቃውሞዋቸውን ደጋግመው አሰምተዋል። የዚምባብዌ መንግሥት ቀብራቸውን ይፈፀምበታል ባለው ስፍራ ለስማቸው መጠሪያ ሐውልት አቆማለሁ፣ በትውልድም ሲታወሱም ይኖራሉ በማለቱ አስከሬናቸው በቤታቸው ተቀምጦ ቆይቶ ነበር። • የትራምፕን ስልክ ማን 'ጠለፈው'? • የትራምፕ የስልክ ጥሪ ሲተነተን በመጨረሻም ሐሙስ ዕለት መንግሥት የቤተሰቡን የማያቋርጥ አቤቱታ ሰምቶ ፈቃዳቸው ይፈፀም ዘንድ ውሳኔ አሳልፏል። መንግሥት በመጨረሻ የሀሳብ ለውጥ ለምን እንዳደረገ የታወቀ ነገር የለም። የሀገሪቱ ኮሙኑኬሽን ሚኒስትር መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ ውሳኔው የተላለፈው "በክብር ያለፉ ጀግኖቻችን ቤተሰቦችን ፍላጎትና ምኞት ከማክበር" መሆኑን ጠቅሷል። ሙጋቤ ሕይወታቸው ያለፈው የካንሰር ህክምና እየተከታተሉበት በነበረው ሲንጋፖር ነበር። • ደቡብ አፍሪካውያን መጤ ጠልነትን ማስቆም ይችሉ ይሆን? ዜና እረፍታቸው ከተሰማ በኋላ ቤተሰቦቻቸው ቀብራቸው ስለሚፈፀምበት ስፍራ መንግሥት እንዳላማከራቸው ተናግረው ነበር። ቤተሰቡ ባወጣው መግለጫም ላይ የመንግሥት እቅድ ተችተው " ከሙጋቤ ፍላጎት ውጪ" በጀግኖች መካነ መቃብር መቀበር የለባቸውም ሲሉ እርምጃውን ኮንነዋል። ቤተሰቡ እንዳለው ለባለቤታቸው ግሬስ ሙጋቤ የተናገሩት የመጨረሻ ቃል ስርዓተ ቀብሩ እስኪፈፀም ድረስ ከአጠገባቸው እንዳትርቅ ነበር። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር 2017 ላይ የዚምባብዌ መከላከያ ኃይል፤ ሮበርት ሙጋቤ ለሦስት አሥርት ዓመታት ይዘውት ከነበረው መንበረ ሥልጣን ማስነሳቱ ይታወሳል። በ1980 በዚምባብዌ የተካሄደውን የመጀመሪያ ምርጫ አሸንፈው ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው የነበሩት ሙጋቤ፤ 1987 ላይ ፕሬዘዳንት ሆነዋል።
news-51240546
https://www.bbc.com/amharic/news-51240546
የእግር ኳስ አፍቃሪዎች ለከባድ ጭንቀትና የልብ ህመም ተጋላጭ ናቸው ተባለ
አንድ የጥናት ተቋም ባወጣው መረጃ መሰረት የእግር ኳስ አፍቃሪዎች ለከባድ ጭንቀት ይጋለጣሉ፤ የሚደግፉት ቡድን ሲሸነፍ የሚሰማቸው ስሜትም ለልብ ህመም ያጋልጣቸዋል ተባለ።
በምሳሌነት ደግሞ በ 2014 ቱ የዓለም ዋንጫ ብራዚል በጀርመን 7 ለ 1 በተሸነፈችበት ወቅት በርካታ ብራዚላውያን ለከባድ የጤና እክሎች መጋለጣቸውን ጥናቱ ጠቅሷል። ጥናቱ እንደጠቆመው በወቅቱ የብራዚል ደጋፊዎች ብሄራዊ ቡድናቸው በሰፊ የግብ ልዩነት መሸነፉን ተከትሎ ለጭንቀት የሚያጋልጡ ሰውነት የሚያመርታቸው ሆርሞኖች መጠን መጨመር ታይቶባቸዋል። • አሠልጣኝ አብርሃም መብራህቱ፡ "የመጣውን በጸጋ መቀበልና መዘጋጀት ነው" • ከኮከብ እግር ኳስ ተጫዋችነት - ፖለቲካ - ወደ ታክሲ ሹፌርነት ይህ ደግሞ አደጋ አለው ይላሉ ተመራማሪዎቹ፤ የደም ግፊታቸው ጨምሯል፤ እንዲሁም ልባቸው ተጨንቃ ልትፈነዳ ደርሳም ነበር ብለዋል። ምንም እንኳን በርካቶች ወንዶች ለእግር ኳስ የበለጠ ፍቅር ስላለቸው ለበለጠ ጭንቀት ይጋለጣሉ ብለው ቢያስቡም፤ ተመራማሪዎቹ አገኘነው ባሉት መረጃ መሰረት ግን በሴትና በወንድ እግር ኳስ ደጋፊዎች የጭንቀት መጠን ላይ ልዩነት አልተገኘም። ''ለረጅም ዓመታት ድጋፋቸውን ለአንድ ቡድን ብቻ አድርገው እግር ኳስን የሚመለከቱ የኳስ አፍቃሪዎች ደግሞ ለበለጠ አካላዊ መዛልና ጭንቀት የተጋለጡ ናቸው'' ይላሉ የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የጥናቱ ተሳታፊ ዶክተር ማርታ ኒውሰን። እሳቸው እንደሚሉት አልፎ አልፎ ቡድናቸውን ለመደገፍ እግር ኳስን የሚመለከቱ ሰዎች ጭንቀት ቢያጋጥማቸውም እንደ ቋሚ ደጋፊዎቹ ከፍተኛ አይደለም። ለረጅምና ተከታታይ ጭንቀት የሚጋለጡ ሰዎች ተከታዩቹ ችግሮች ያጋጥሟቸዋል፡ ከባድ የእግር ኳስ ፍቅር ያለባቸው ደጋፊዎች ቡድናቸው ሲሸነፍ ወይም ግብ ሲቆጠርበት የሚያጋጥሙ የልብ ድካም በሽታዎች ከጊዜ ጊዜ እየጨመሩ መምጣታቸውንም ጥናቱ ጠቁሟል። • "በአንድ ጨዋታ ሰባት ግቦችን በማስቆጠር ታሪክ መስራቴ አስደስቶኛል" ሎዛ አበራ የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎቹ ለማስረጃነት እንዲጠቅማቸው በእግር ኳስ ፍቅር ያበዱ 40 ሰዎችን ከመረጡ በኋላ ከዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች በፊትና በኋላ ምራቃቸውን በመውሰድ መርምረዋል። ባገኙት መረጃ መሰረትም በተለይ ደግሞ ከግማሽ ፍጻሜ በኋላ የደጋፊዎቹ የጭንቀት መጠን በእጅጉ ከፍ ብሏል።
news-50864749
https://www.bbc.com/amharic/news-50864749
ከአለቃ ጋር አንድ ሁለት ማለት ያዋጣል?
የ28 ዓመቱ ሪኮ ኪታማውራ ከኮሌጅ ከተመረቀ በኋላ የገበያ ጥናት በሚያደርግ ተቋም ውስጥ ነበር የተቀጠረው።
ጃፓናዊው ሪኮ የተቀጠረበት መሥሪያ ቤት ሠራተኞች ከሥራ በኋላ ሰብሰብ ብለው መጠጥ የመቀማመስ ልማድ ነበራቸውና ሪኮም ይቀላቀላቸው ጀመር። ከሥራ ባልደረቦቹ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ የጠጣበትን ቀን አይረሳውም። "ብዙ ለመጠጣት ተገድጄ ነበር፤ ከእነሱ እኩል ለመሆን በፍጥነት ስጠጣ ቶሎ ሰከርኩ" ጃፓን ውስጥ ከሥራ በኋላ መጠጣት የተለመደ ነው። ከሥራ ባልደረቦች ጋር መጠጣት 'ኖሚኬይ' ይባላል። ማኅበራዊ መስተጋብርን እንደሚያጠናክርም ይታመናል። ይህ ልማድ ቀጣሪዎች ሥልጣናቸውን ያላግባብ እንዲጠቀሙ መንገድ ከፍቷል ስለተባለ ቀስ በቀስ እየተሸረሸረ መጥቷል። • ሥራ የማዘግየት ልማድን ለመቅረፍ የሚረዱ 8 ነጥቦች • ሥራ ቦታ ጋደም ማለት መፈቀድ አለበት? ሥልጣንን ያላግባብ መጠቀም፤ አንዳንድ ተቀጣሪዎችን ከመነጠል አካላዊ ጥቃት እስከማድረስ ይሄዳል። የማኅበረሰብ ጥናት ባለሙያው ኩሚኮ ንሞቶ እንደሚሉት፤ አንድ ሠራተኛ ከሌላው ጋር አብሮ እንዲጠጣ ማስገደድ እንደ ብዝበዛ ይታያል። "ቀደም ባለው ዘመን አንድ የሥራ ቦታ ልማድ ነበር፤ አሁን ግን ሥልጣን የመበዝበዣ መንገድ ተደርጎ ይወሰዳል" ሲሉ ያስረዳሉ። የጃፓን መንግሥት፤ ቀጣሪዎች ሥልጣናቸውን ያላግባብ እንዳይጠቀሙ በሚቀጥለው ዓመት አዲስ ሕግ የመተግበር እቅድ አለው። ጃፓን ለሰዓታት የሚሠሩ፣ በሥራ ጫና ሳቢያ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎችም ያሉባት አገር ናት። የአገሪቱ መንግሥት መሰል ችግሮችን ለመቅረፍ ሕጉ እንደሚረዳው ተገልጿል። አሁን አሁን ቀጣሪዎች፤ ሠራተኞቻቸው አብረዋቸው እንዲጠጡ የመጋበዝ ፍላጎታቸው እየቀነሰ መጥቷል። ሪኮ ኪታማውራ እንደሚናገረው፤ ባለፉት ሦስት ዓመታት ከአለቆች ጋር መጠጣት ግዴታ አይደለም ተብሏል። የ47 ዓመቱ ታትስ ካቱስኪ፤ የአንድ የንግድ ተቋም ኃላፊ ናቸው። ሠራተኞቻቸው በጋራ እንዲጠጡ እንደማያስገድዱ ይናገራሉ። • ሥራ ቀጣሪና አባራሪ እየሆነ የመጣው ሮቦት • በጃፓን ሴት ሠራተኞች መነጽር እንዳያደርጉ መከልከላቸው ጥያቄ አስነሳ ባለፉት አምስት ዓመታት የአመለካከት ለውጥ እየመጣ እንደሆነ ያስረዳሉ። እሳቸው የዛሬ ሀያ ዓመት ሥራ ሲጀምሩ ከነበረው የአሁኑ የተለየ እንደሆነም ያክላሉ። ያኔ በሳምንት ቢያንስ ለአራት ቀን ገደማ ከሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር ይጠጡ ነበር። "አለቃህ ና እንጠጣ ሲል 'አምቢ' ማለት አይቻልም።" እስከ እኩለ ሌሊትና ከዚያም በላይ ይጠጡ ስለነበረ በነጋታው ይታመሙም ነበር። ሆኖም ግን አለቃቸውን የተሻለ የሚያውቁበት አጋጣሚ እንደሆነ ይሰማቸዋል። ጃፓን ውስጥ ከሥራ ጋር በተያያዘ መጠጥ መቀማመስ እየቀረ መጥቷል። አለቆች 'ሠራተኞቻቸውን እየበዘበዙ ነው' መባል ስለሚያስፈራቸውም፤ ተቀጣሪዎችን መጠጥ መጋበዝ ቀንሰዋል። በሌላ በኩል አዳዲስ ተቀጣሪዎች ነገሩ እንደተጋነነ ያስባሉ። ታትስ ካቱስኪ እንደሚሉት፤ አዳዲስ ተቀጣሪዎች 'እንጠጣ' አለመባላቸው ቅያሜ ይፈጥርባቸዋል። "ተቀጣሪዎቹ እንደተተዉ ይሰማቸዋል። መጠጥ ማኅበራዊ ግንኙነትን ያጠነክራል፤ ከአለቃ ጋር ለመቀራረብም ይረዳል። አንዳንድ ተቀጣሪዎች አለቆቻቸው ለምን አብረን እንጠጣ እንዳላሏቸው ይጠይቃሉ።" • የሥራ ቦታ ወሲባዊ ትንኮሳ የቱ ነው? • ሥራ እና ፍቅር፡ ከሥራ አጋርዎ ጋር የፍቅር ግንኙነት መጀመር ሊያስባርር ይገባል? የሶፊያ ዩኒቨርስቲው ፓሪሳ ሀግሂሪያን እንደሚሉት፤ አብሮ በመመገብ እና በመጠጣት ማኅበራዊ መስተጋብርን ማጠናከር ይቻላል። "ጃፓን ውስጥ ሰዎች መጠጣት ይወዳሉ፤ መጠጥ እና ሲጋራ እንደሚያዝናኑ ይታመናል፤ በጋራ የሚደረጉ ነገሮች አካል መሆን መልካም ነው" ሲሉም ያስረዳሉ።
news-46263458
https://www.bbc.com/amharic/news-46263458
የነጻነት ቅርጫት፡ ባለ ረዥም ተረከዝ ጫማ
በርካታ ጥናቶች ባለ ረዥም ተረከዝ ጫማዎችን መጫማት የሰውነት ጡንቻ እና አጥንት ላይ ጉዳት እንደሚያደርስ ይጠቁማሉ። ጫማዎቹ ምቾት ስለሚነሱ ተጨማሪ የጫማ ሶል እና ሌሎች ምርቶችን ለመግዛት ያስገድዳሉ።
ምናልባትም ባለ ረዥም ተረከዝ ጫማ አለመጫማት የተሻለ ይሆን? በአሁኑ ሰዓት ሴቶች ባለ ረዥም ተረከዝ ጫማዎችን ለመዘነጫነት ቢጫሟቸውም በቀድሞው መጠሪያዋ ፐርሺያ በአሁኗ ኢራን ባለረዥም ታኮ ጫማ ይጫሙ የነበሩት ወንዶች እንጂ ሴቶች አልነበሩም። የኢራን ፈረሰኛ ወንድ ወታደሮች በጦርነት ወቅት የጫማቸው ታኮ ሚዛናቸውን እንዲጠብቁ ይረዳቸው ነበር። ከእነዚህ ምርጫዎች መካከል የሚፈልጉትን ዕቃ ይምረጡና እንዴት የጭቆና መሣሪያ እንደሆነ ይመልከቱ። መዋቢያ ቁሳቁስ "ወንዶች ፊታቸውን ሳያስውቡ ቢወጡ ምንም ነገር አይባሉም" ምቾች የሌለው ፋሽን "ሰዎች ለምን እንደሚያደርጓቸው አይገባኝም። ያማሉ፣ አይመቹም ደግሞም ቋሚ የሰውነት በሽታ ያስከትላሉ" ቤት ውስጥ የተዘጋጀ ምግብ "ሴት ልጅ ማብሰያ ክፍል ውስጥ ብቻ ነው መሆን ያለባት የሚለው ሃሳብ ሰልችቶኛል" - ኤማ የቤት ውስጥ ሥራዎች "እኩልነት ከቤት ስለሚጀምር ወንዶች ተነስታችሁ ቤት አፅዱ።" ጡት መያዣ "መዋብ ግዴታዬ አይደለም። ያለእሱ ቆንጆም አዋቂም ነኝ̃።" - ሊዛ ዝነኛ ሰዎችን የማድነቅ ባህል "ሁሉም የቁንጅና ሞዴሎች ሰውነት አንድ ዓይነት ነው፤ ደግሞም ደስተኛ አይመስሉም። ይሰለቻል።"- ዌንዲ ጋብቻ "እንደኔ እንደኔ የቃልኪዳን ቀለበቶች በሴት መብት ተሟጋቾች ዘንድ የስድብ ያህል ናቸው። ምክንያቱም ቀለበት ያደረገች ሴት የሌላ ሰው ንብረት መሆኗን ስለሚያመለክት።" ማቲልድ ማህበራዊ ድረ ገፆች "ለታዳጊ ወጣቶች አዕምሮ ሰላም በጣም አደገኛ ነው። በተለይ ለሴቶች። ምክንያቱም ከእውነታ የራቁና አደገኛ በሆኑ አመለካከቶች ተከበዋል።" - ሮሻን በፆታ የተለዩ መጫወቻዎች "በፆታ የተከፋፈሉ መጫወቻዎች በሙሉ ወንዶችንም ሴቶችንም ልጆች የተወሰኑላቸውን ነገሮችን ብቻ እንዲወዱ ያደርጋሉ።" - አና ተጨማሪ ዕቃ የጭቆና መሣሪያዎች ምንድን ናቸው? 'የፀረ-ነፃነት ቆሻሻ መጣያ' የተሰኘውን አመላከከት ምን እነዳስጀመረው ለማየት የራስዎን መሣሪያ ያጋሩን። 2016 ላይ የአንድ ተቋም እንግዳ ተቀባይ ባለ ረዥም ተረከዝ ጫማ እንድትጫማ በአሰሪዎቿ ብትታዘዝም ፍቃደኛ ሳትሆን ሥራዋን በገዛ ፍቃዷ ለቃለች። ከዚያም የእንግሊዝ መንግሥት ሰራተኞች ባለ ረዥም ተረከዝ ጫማ መጫማት ግዴታ እንዳይሆን ህጉ እንዲቀየር ጠይቃ ነበረ። የእንግሊዝ መንግሥት ግን ህጉን ባይቀይረውም በስራ ቦታዎች ላይ የሰራተኞችን የአለባበስ ስርዓት በተመለከተ ማስተካከያዎችን አደርጋለሁ ብሎ ነበር።
news-48718888
https://www.bbc.com/amharic/news-48718888
የሰኔ 16ቱ ጥቃትና ብዙም ያልተነገረላቸው ክስተቶች
ወደ መሪነት መንበሩ ከመጡ ሦስት ወራት ያልሞላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ስልጣን ከተረከቡበት እለት ጀምሮ ባደረጓቸው ንግግሮችና በአጭር ጊዜ በወሰዷቸው ቁልፍ እርምጃዎች የበርካታ ኢትዮጵያዊያንን ድጋፍ ማግኘት ችለዋል።
ይህንንም አደባባይ ወጥቶ ለመግለጽ አንድ ኮሚቴ ተሰባስቦ ቅዳሜ ሰኔ 16/2010 ዓ.ም ሕዝባዊ ሰልፍ በመስቀል አደባባይ ለማድረግ ማቀዱን በመገናኛ ብዙሃን ያሳወቀው ሰልፉ ሊደረግ ቀናት ሲቀሩት ነበር። አንዳንዶች የጥድፊያ ዝግጅት በመሆኑ ላይሳካ ይችላል የሚል ጥርጣሬ አሳድረው ነበር። • ዐብይ አሕመድ ለኖቤል ሽልማት ታጭተዋል? ነገር ግን የሰልፉ አስተባባሪዎች ባደረጉት ርብርብ ከሰልፉ ቀን ቀደም ብሎ የአዲስ አበባና የአካባቢዋ ነዋሪዎች ለሰልፉ በስፋት እየተዘጋጁ መሆናቸውን የሚያሳዩ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ተስተዋሉ። የጠቅላይ ሚኒስትሩን ምስሎች የያዙ ካኒቴራዎችና የተለያዩ ህትመቶች የመዲናዋ ጎዳናዎች ላይ በስፋት ተሸጡ። በሰልፉም ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚገኙ ስለተነገረ ቅዳሜ ሰኔ 16 በማለዳ ነበር የሰልፉ ታዳሚዎች ከተለያዩ የከተማዋ አቅጣጫዎች ወደ መስቀል አደባባይ መትመም የጀመሩት። በዚህም ከዝግጅቱ መጀመሪያ ሰዓት ቀደም ብሎ መስቀል አደባባይና አካባቢው በመቶ ሺዎች በሚቆጠሩ ሰዎች ተጥለቀለቀ። በአደባባዩ ከተሰበሰበው የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊ አብዛኛው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስል ያለበት ከነቴራና ምስላቸውን እንዲሁም እየወሰዷቸው ያሉትን እርምጃዎች የሚደግፉና ሚያሞግሱ ጽሁፎችን ይዞ ነበር። • የዶክተር ዐብይ አሕመድ ፊልም ጠቅላይ ሚኒስትሩም ዘወትር ከሚታዩበት ልብስ ውጪ ቀለል ያለ ልብስ ለብሰው ባርኔጣ ደፍተውና ጥቁር መነጽር አድርገው ከሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ጋር በመሆን አደባባዩ ሲደርሱ ተሰብሳቢው በሆታና በፉጨት ነበር የተቀበላቸው። እሳቸውም ከመድረክ ላይ ወደተለያየ አቅጣጫዎች እየተዘዋሩ ምስጋናቸውን አቀረቡ። ከማለዳው ጀምሮ እየተካሄደ የነበረውን ይህንን ሰልፍ በሃገሪቱ የሚገኙ አብዛኞቹ የመገናኛ ብዙሃን የቀጥታ ሽፋን ሰጥተው በየሰከንዱ በመስቀል አደባባይ የሚከናወነውን ነገር ያቀርቡ ስለነበር፤ በርካታ ሰዎች ሰልፉን እንዲከታተሉ አስችሏል። መስቀል አደባባይ ካስተናገዳቸው ሕዝባዊ ሰልፎች አንዱ የሆነው የዚህ ሰልፍ ታዳሚ ዋነኛ ጉዳይ የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይም በደማቅ ሆታና ጭብጨባ የታጀበውን ሕዝቡን በማመስገንና የወደፊት ዓላማቸውን በማመላከት ላይ ያተኮረውን ንግግራቸውን ፈጽመው ወደመቀመጫቸው ከተመለሱ በኋላ አስደንጋጩ ነገር ተከሰተ። ፍንዳታ የመድረኩ አጋፋሪ መነጋገሪያውን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ተረክቦ በአማርኛ የተናገረውን በእንግሊዝኛ እየደገመ ሳለ እምብዛም ጉልህ ያልሆነ የፍንዳታ ድምጽ ጠቅላይ ሚኒስትሩና ባለስልጣኖቻቸው ካሉበት መድረክ አቅራቢያ ተሰማ። ነገር ግን በዚያው ቅጽበት ፍንዳታው ቦንብ መሆኑን ያወቁት በመድረኩ ላይና እዚው አቅራቢያ የነበሩት ብቻ ናቸው። የፍንዳታው ድምጽ ወደተሰማበት አቅጣጫ ለመመልከት ጠቅላይ ሚኒስትሩና በዙሪያቸው የነበሩ ሰዎች ከመቀመጫቸው ተነስተው የነበረ ሲሆን በዚያው ቅጽበትም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠባቂዎች መሪውን ዙሪያቸውን በመክበብ እያጣደፉ ከመድረክ ይዘዋቸው በመውረድ ወደ መኪናቸው ወስደው ወደ ጽህፈት ቤታቸው አቀኑ። ቦንቡ በፈነዳበት የመድረኩ አቅራቢያ ትርምስ በመፈጠሩ የጸጥታ ሰራተኞች ተሰማርተው ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ለመርዳት ጥረት ያደርጉ ነበር። ይህም ሆኖ ከመድረኩ እርቀው የነበሩ የሰልፉ ታዳሚዎችና በቴሌቪዥን ሲከታተሉ የነበሩ ሰዎች ግን ምን እንደተከሰተ አላወቁም ነበር። በመድረኩ ላይ ይካሄድ የነበረውን ሥነ ሥርዓት በቀጥታ ሲያስተላልፉ ከነበሩት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች መካከል ቀዳሚው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የነበረ ሲሆን ከፍንዳታው መከሰት በኋላ ያቀርባቸው የነበሩት ምስሎች ከመድረኩ የራቁትን ብቻ ነበር። • የዶክተር ዐብይ አሕመድ 'ፑሽ አፕ' የፍንዳታው ክስተት በማህበራዊ ሚዲያዎችና በሌሎች መገናኛ ብዙሃን በኩል ከተገለጸ በኋላ በአጠቃላይ በሕዝቡ ላይ በተለይ ደግሞ በአደባባዩ ታድመው በነበሩ ሰዎች ላይ ድንጋጤና ቁጣን ቀሰቀሰ። አንዳንዶችም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ጉዳት የደረሰ ስለመሰላቸው ስሜታዊ እስከመሆን ደርሰው ነበር። ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ጽህፈት ቤታቸው በተመለሱ በደቂቃዎች ውስጥ በብሔራዊው ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው ደህና መሆናቸውንና በቦንብ ጥቃቱ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን በማሳወቃቸው ወዳልታወቀ አቅጣጫ ሊያመራ የነበረው ቁጣ ጋብ ብሏል። ቢሆንም ግን በታዳሚው መካከል የተወሰኑት ከጥቃቱ ጋር ሊገናኙ ይችላሉ ባላቸው ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት አድርሰዋል። ከፍንዳታው በኋላ ከቀናት በኋላም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት እንዳለው "የሰልፉ ሂደት እንዲስተጓጎል መብራት እንዲጠፋ እና የቴሌኮም ኔትወርክ የማቋረጥ ተግባር ተከናውኗል" ሲል ድርጊቱ የታሰበብት እንደሆነ አመልክቷል። • በ2018 ጎልተው የታዩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ • የጌታቸው ረዳ ዕይታ፤ ስለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በዚህ ዓመት ኅዳር ወር መጀመሪያ ላይም የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ ይፋ እንዳደረጉት የቦምብ ጥቃቱ በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የቀድሞ ኃላፊ የተመራ ነው። አቃቤ ሕጉ ጨምረውም ጥቃቱ ሃገር ውስጥና በውጭ ሃገር ባሉ ኃላፊዎች በቅንጅት መፈጸሙንና ኬንያ ውስጥ ያለችና ያልተያዘች አንዲት ግለሰብም በጥቃቱ ቁልፍ ሚና እንደነበራት ጠቅሰዋል። በወቅቱ በትንሹ ለሁለት ሰዎች መሞትና ለበርካታ ሰዎች የአካል ጉዳት ምክንያት ለሆነውና በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ጉዳት ቢደርስ ኖሮ ከባድ ምስቅልቅልን ሊያስከትል ይችል በነበረው የሰኔ 16ቱ የቦንብ ጥቃት በርካታ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ይገኛል።
49274611
https://www.bbc.com/amharic/49274611
አስራ አምስት ወጣቶችን ያጣችው ኢሮብ ወረዳ
ብዙዎች የተሻለ ህይወትን ፍለጋ፣ በረሃ አቋርጠው፣ ወንዙን ተሻግረው፤ ለሰው ልጅ አእምሮ ከባድ የሚመስሉ ውጣ ውረዶችን አልፈው ነገን ተስፋ አድርገው ይጓዛሉ።
ለዓመታትም ብዙ ኢትዮጵያዊያን ረሃብ ሳይበግራቸው፤ ቁር ሳይፈትናቸው በሊቢያ በኩል ወደ አውሮፓ የሚያደርጉት ጉዞ አሁንም በአደገኛ ሁኔታ እንደቀጠለ ነው። በቅርብ ጊዜያትም ይህን ያህል ኢትዮጵያዊያን በቀይ ባህር ሰምጠው ሞቱ፤ ድንበር ሊያቋርጡ ሲሉ ተያዙ፤ በተለያዩ ሃገራት እስር ቤቶች እየተሰቃዩ ነውና ሌሎችም ዜናዎች ይሰማሉ። •አፍጋናዊቷ ስደተኛ በኢትዮጵያ •የአንዱ እርግማን ለአንዱ ምርቃን፡ ኢትዮጵያን መጠጊያ ያደረጉ የስደተኞች ታሪክ በቅርቡም ከትግራይ ክልል ኢሮብ ወረዳ ከሊቢያ ተነስተው ሜዲትራንያንን ሊያቋርጡ የነበሩ 15 ወጣቶች ህይወታቸው አልፏል። ወጣቶቹ በኢሮብ ወረዳ እንዳልገዳ በሚባል ቀበሌ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የነበሩ ሲሆኑ በህገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች ተታልለው ወደ ስደት እንዳመሩ የቀበሌው አስተዳዳሪ ብርሃነ አውአላ ተናግረዋል። ሥርዓተ ቀብራቸውም ከትናንት በስቲያ ሐምሌ 30፣ 2011 ዓ.ም በቀበሌያቸው ተፈፅሟል። ወጣቶቹ የእንዳልገዳን መንደር መቼ እንዳቋረጡም ይሁን እንዲሁ ስለ ሞቱበት ቀን የተሰጠ መረጃ የለም። የአካባቢው ማህበረሰብ መርዶውን የተረዳው ከአደጋው ከተረፉ ግለሰቦች ሰኞ እለት ሲሆን ዘጠኝ ሴቶችና ስድስት ወንድ ታዳጊዎች አደገኛውን የሜድትራንያን ባህር ሊያቋርጡ ሲሉ መሞታቸው ታውቋል። አብረው የተጓዙት ተማሪዎች 19 የነበሩ ሲሆኑ ለወሬ ነጋሪ የተረፉት አራቱ ብቻ እንደሆኑ አስተዳዳሪው ገልፀዋል። •በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን ፌስቲቫል፡ ሙዚቃ፣ ኳስ፣ ፍቅርና ቡጢ.. በሊቢያ ውስጥ በነበሩበት ቀናት ታግተው እንደነበር የቀበሌው አስተዳዳሪ ገልፀው ዘመዶቻቸው እነርሱን ለማስለቀቅ እስከ 300 ሺህ ብር መክፈል ነበረባቸው ሲሉ ያስረዳሉ። በ1994 ዓ.ም ከኢሮብ ተነስተው ጂቡቲን አቋርጠው ወደ የመን ለመግባት ሲሞክሩ 14 ወጣቶች ባህር ላይ ሞተዋል። በዚህ ዓመት መጋቢት ወር ላይ ከጂቡቲ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ሰጥማ ከስልሳ በላይ ከአፅቢ ወረዳ የመጡ ሰዎች ህይወት መቀጠፍ ምክንያት መሆኑ ይታወሳል።
news-55033395
https://www.bbc.com/amharic/news-55033395
ትራምፕ ምርጫውን አስመልክቶ ያቀረቡት ክስ ውድቅ ተደረገ
የአሜሪካዋ ፔኒሲልቫኒያ ግዛት ዳኛ የፕሬዝደንት ትራምፕ ጠበቆች በፖስታ የተላኩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ድምፆች ውድቅ ይደረጉ ብለው ያቀረቡትን ክስ ውድቅ አደረጉ።
ዳኛ ማቲው ብራን የምርጫ ድምፅ ቆጠራው የተዛባ ነበር ተብሎ የቀረበው ክስ 'ጭብጥ አልባ' በማለት ውድቅ አድርገውታል። ይህ ማለት በሚቀጥለው ሳምንት የፔኒሲልቫኒያ ግዛት የጆ ባይደንን አሸናፊነት ውድቅ ያደርጋል ማለት ነው። ባይደን በግዛቲቱ ዶናልድ ትራምፕን በ80 ሺህ ድምፆች እየመሩ ይገኛሉ። ዶናልድ ትራምፕ በአውሮፓውያኑ ኅዳር 3 የተደረገውን ምርጫ ውጤት አልቀበልም በማለት ክስ ቢመሠርቱም በበርካታ ግዛቶች ድል እየቀናቸው አይደለም። ፕሬዝደንቱ በፖስታ የተላኩ ድምፆች መቆጠር የበላቸውም፤ የተጨብረበሩ ናቸው ሲሉ ማስረጃ አልባ ክስ በማሰማት ላይ ይገኛሉ። ለወትሮው የአሜሪካ ፕሬዝደንቶች ከምርጫው ጥቂት ቀናት በኋላ ውጤት አምነው የሚቀበሉ ቢሆንም ትራምፕ ግን እስካሁን አሻፈረኝ ብለዋል። ጆ ባይደን ትራምፕን 306 ለ232 በሆነ ኢሌክቶራል ኮሌጅ ድምፅ እየመሩ ይገኛሉ። በአሜሪካ ምርጫ ሕግ መሠረት የማሸነፊያው ድምፅ 270 ነው። የትራምፕ ጠበቆች በተለይ ግዙፍ የሚባሉ ግዛቶች የጆ ባይደንን አሸናፊነት እንዳያውጁ በመጎትጎት ላይ ናቸው። ግዛቶች የጆ ባይደንን አሸናፊነት አወጁ ማለት ዶናልድ ትራምፕ ኦፊሴላዊ በሆነ መንገድ አበቃላቸው ማለት ነው። ከወሳኝ ግዛቶች አንዷ የሆነችው ፔኒሲልቫኒያ ዳኛ የሆኑት ብራን የትራምፕ ምርጫ ቅስቀሳ ቡድን ሰባት ሚሊዮን የሚጠጉ ድምፆችን ሕጋዊ ያልሆኑ ለማድረግ ጥረት አድርገዋል ብለዋል። 'ፍርድ ቤት የቀረበለት ክስ ጭብጥ አልባ እና ማስረጃ የሌለው ወቀሳ ነው' ሲሉ ነው ዳኛው ጉዳዩን ውድቅ ያደረጉት። የትራምፕ ጠበቆች ነጋ ጠባ ሳንል ይግባኝ እንጠይቃለን ብለዋል። እስካሁን ድረስ ጥቂት የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት ናቸው ፕሬዝደንቱ የምርጫውን ውጤት እንዲቀበሉ በይፋ የወተወቱት። ጆርጂያ በተባለችው ግዛት ድምፅ ድጋሚ ይቆጠር ብለው ያመለከቱት ትራምፕ ቅሬታቸው ተሰምቶ ድምፅ ድጋሚ ቢቆጠርላቸውም ተሸናፊ ከመሆን አላዳናቸውም። ፕሬዝደንቱ ለሶስተኛ ጊዜ ድምፅ ድጋሚ ይቆጠር ሲሉ በጠበቆቻቸው አማካይነት አመልክተዋል። በሌላኛዋ ወሳኝ ግዛት ሚሺጋን የጆ ባይደን ማሸነፍ በይፋ ከመታወጁ በፊት ሁለት ሳምንት ያስፈልጋል ቢባልም የግዛቲቱ አስተዳዳሪዎች ይህ ሕገ ወጥ ነው ብለዋል። በዊስኮንሲን ደግሞ የትራምፕ ምርጫ ቡድን ታዛቢዎች ድጋሚ ቆጠራው እንዲዘገይ ጥረት እያደረጉ ነው ሲሉ የምርጫ አስተባባሪዎች ከሰዋል። ግዛቶች የአሸናፊዎችን ውጤት ይፋ የሚያደርጉበት ቀነ ገደብ እየቀረበ ነው። በአሜሪካ ምርጫ አሸናፊዎችን ይፋ የሚያደርጉት ግዛቶች ሲሆኑ ይህ ተደምሮ በሃገር ደረጃ ውጤቱ ይፋ የሚሆነው።
news-44642107
https://www.bbc.com/amharic/news-44642107
"ነዳጅ የማውጣት ስራውን ለማስቆም የቻልነውን ሁሉ እናደርጋለን" የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር
ኢትዮጵያ በሙከራ ደረጃ ትላንት በሶማሌ ክልል ነዳጅ ማውጣት መጀመሯን ተከትሎ የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ተግባሩን እንደሚቃወመው አስታወቀ።
ነዳጅ የማውጣት ስራውን ለማስቆምም የቻሉትን ሁሉ እንደሚያደርጉ የግንባሩ ቃል አቀባይ አብዱልቃድር ሃሳን አዳኒ ከቢቢሲ ሶማልኛ አገልግሎት ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል። ''የሶማሌ ክልል ህዝቦች ራስን በራስ የማስተዳደር ነጻነት እስካላገኙ ድረስና ለረጅም ጊዜ የቆየው የሶማሌ ህዝብና የኢትዮጵያ መንግስት አለመግባባት እስካልተፈታ ድረስ፤ የነዳጅ ማውጣት ስራው የህዝቡን ሃብት ያለአግባብ እንደመጠቀም ነው'' ብለዋል ቃል አቀባዩ። የኢትዮጵያ ፖለቲካና ኢኮኖሚ አካል ስላልሆንን፤ ምንም አይነት ባህላዊ ቁርኝት የለንም፤ ስለዚህ የሶማሌ ህዝብን የተፈጥሮ ሃብትና መሬት ለሌላው ጥቅም ማዋል የማንቀበለው ነው በማለት ግንባሩ አቋሙን ገልጿል። ''መሬታችን በሃይል የተወሰደብን ሲሆን፤ እሱን ለማስመለስና የተጀመረውን ነዳጅ የማውጣት ስራ ለማስቆም የምንችለውን ነገሩ ሁሉ እናደርጋለን። ምክንያቱም በክልሉ ያለው ሃብት ለክልሉ ህዝቦች ብቻ ነው መሆን ያለበት፤ ማንም ሊጠቀመው አይችልም ሲሉ ቃል አቀባዩ ጨምረዋል። ምንም እንኳን ግንባሩ በይፋ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ባይነጋገርም፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሁሉም ቡድኖች ያቀረቡትን የውይይት ሃሳብ ግን በበጎ ጎኑ እንደሚመለከተው ገልጿል። አቶ አብዱልቀድር አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የግጭት ዋና ምንጭ የሆኑት ጉዳዮች ላይ በማተኮር አዲስ ምዕራፍ የመጀመር አጋጣሚው እንዳላቸውም ጨምረው ተናግረዋል። ግንባሩ ኤርትራን ዋና መቀመጫው ያደረገ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ መንግስት አስመራ አማጺዎችን ትደግፋለች ሲከስ ነበር፤ የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባርንም አሸባሪ ብሎ ፈርጆታል። በቅርቡ የኢትዮጵያ መንግስት ከለቀቃቸው የፖለቲካ እስረኞች መካከል የግንባሩ አመራሮች ይገኙበታል። ከሌሎች ቡድኖች በተለየ የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ከ1976 ጀምሮ የሶማሌ ራስ ገዝ አስተዳደር መኖር አለበት ብሎ የትጥቅ ትግል ሲያካሂድ ነበር። በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ውስጥ የቻይናው ነዳጅ አፈላላጊ ድርጅት ላይ ግንባሩ በ2001 ጥቃት ፈጽሞ 74 ኢትዮጵያውያንና ዘጠኝ ቻይናውያን መሞታቸው ይታወሳል። በዛው ዓመት የኢትዮጵያ መንግስት ከአካባቢው የተውጣጣ ግንባሩን የሚዋጋ ልዩ የፖሊስ ቡድን አቋቁሞ ነበር። በዚህ ምክንያት ግንባሩ ከአካባቢው ለቅቆ እንዲሄድ ተገዶ የነበረ ሲሆን፤ አብዛኛዎቹ አባላት በአሁኑ ሰአት በውጪ ሃገራት ይገኛሉ።
news-52103781
https://www.bbc.com/amharic/news-52103781
ከኮሮናቫይረስ ስርጭት ጋር በተያያዘ አስገራሚ ሕግ ያወጡ አምስት አገራት
ኮቪድ-19 ብዙ እያሳየን ነው። ሀብታም አገራት ጭምር ቀውስን የመሸከም አቅማቸው እስከምን ድረስ እንደሆነ ፍንጭ ሰጥቷል።
ውሻን በምሽት ማንሸራሸር የተለያዩ አገራት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመቀልበስ ከልል እስከ ጥብቅ መመሪያ አውጥተዋል። የሚከተሉት አምስት አገራት ግን መመሪያቸው ለይት ያለ ሆኖ አግኝተነዋል።ት 1. ሰርቢያ ሰርቢያ አንድ ሰሞን ለውሾች የሽርሽር ሰዓት ወስና ነበር። ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ 3 ሰዓት ብቻ። የውሻ ባለቤቶች ግን ይህንን ተቃውመው አቤት በማለታቸው መመሪያው ተሸሯል። አንድ የእንሰሳት ሐኪም እንዳለው የምሽቱን የሽርሽር ሰዓት ማሳለፍ ለውሾች ፊኛ ጤና መልካም አይደለም። 2. ኮሎምቢያ በአንዳንድ የኮሎምቢያ ከተሞች ወደ ውጭ የሚወጣው በመታወቂያ ቁጥር መሰረት ነው። ለምሳሌ መታወቂያ ቁጥራቸው በዜሮ፣ በ4 እና በ7 የሚጨርሱ ሰኞ ሰኞ ደጅ ወጥተው ሽር ማለት ይችላሉ። በ1 በ8 እና በ5 የሚጨርሱ ደግሞ ማክሰኞ የግላቸው ናት። ጎረቤት ቦሊቪያም ተመሳሳይ ዘዴን ተከትላለች። 3. ፓናማ የመካከለኛው አሜሪካ አገር ናት። አንድ ሺህ ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተይዘውባታል። ወረርሽኙን ለመቀልበስ ከቤት አትውጡ ብላለች። ሆኖም ግን ለተወሰነ ሰዓት ወጣ ብሎ መናፈስ ይቻላል። ታዲያ ይህ ፈቃድ ግን በጾታ ተለይቶ ነው። ከረቡዕ ጀምሮ ዜጎች ለ2 ሰዓት ብቻ ከቤት ወጥተው መመለስ ይችላሉ። ወንዶች የሚናፈሱበት ቀንና ሴቶች የሚናፈሱበት ቀን ግን የተለያየ ነው። ነገር ግን ፓናማ ለምን ይህን እንዳደረገች ይፋ አላደረገችም። ሆኖም እሑድ እሑድ ወንድም ሆነ ሴት ከቤት አይወጣም። ይሄን መመሪያ ያወጣነው የራሳችሁን ሕይወት ለመታደግ እንጂ ለእኛ ብለን አይደለም ብለዋል የአገሪቱ የደኅንነት ሚኒስትር ሁዋን ፒኖ። 4. ቤላሩስ እንደ ቤላሩስ ፕሬዝዳንት በኮሮናቫይረስ ላይ የተሳለቀ መሪ የለም። አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ይባላሉ። በቲቪ ቀርበው "የምን ኮሮና ነው የምታወሩት? እኔ ቫይረሱ አይታየኝም" ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት የበረዶ የገና ጨዋታ ከሕዝብ ጋር እየተመለከቱ ነው ታዲያ። ጨምረውም "የሚባለው ቫይረስ ካለም ይሄ በረዶ ድራሹን ያጠፋዋል" ሲሉ ቀልደዋል። አገር ቤት በአንዳንድ ግለሰቦች አረቄ ፍቱን መድኃኒት ነው እየተባለ እንደሚቀለደው ሁሉ አሌክሳንደር ሉካሼንኮም "ለኮሮናቫይረስ መድኃኒቱ ቮድካ ነው፤ ቮድካ ጠጡበት›› ብለዋል። ከአውሮፓ አገሮች በተለየ ቤላሩስ የስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት እንዳልዘጋች መዘገባችን ይታወሳል። 5. ቱርከሚስታን ቱርከሚስታን በበኩሏ የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታት ከሁሉ የተለየ መንገድን መርጣለች። ይህም "ኮሮናቫይረስ" የሚለው ቃል ላይ ክልከላን መጣል ነው። በቱርኬሚስታን "ኮሮናቫይረስ" ማለት አይፈቀድም። መንግሥት የጤና መረጃ ከያዙ በራሪ ወረቀቶች ላይ "ኮሮናቫይረስ" የሚለውን ቃል አስወግዷል። ባለቤትነቱ የመንግሥት የሆነ ሬዲዮ ጣቢያ የፊት ማስክ የሚያደርጉ እና "ኮሮናቫይረስ" የሚለውን ቃል የሚጠቀሙ ዜጎች እስር ሊጠብቃቸው ይችላል ሲል ዘግቧል። በቫይረሱ ክፉኛ የተመታችው ኢራን ጎረቤት የሆነው የቱርከሚስታን መንግሥት እስካሁን ኮሮና የሚሉት በሽታ በአገራችን አልተገኘም እያለ ነው።
news-47852379
https://www.bbc.com/amharic/news-47852379
የዓለማችን ሃብታም ሴቶች
የዓለማችን ሃብታሙ ግለሰብ ከባለቤቱ ጋር ፍቺ ሲፈጽም የሚካፈሉት ገንዘብ ከፍተኛ ሊሆን እነደሚችል ማሰብ አይከበድም። ባለፈው ሳምንት አማዞን የተባለው የበይነ መረብ መገበያያ መስራችና ባለቤት ጄፍ ቤዞስ ከባለቤቱ ማኬንዚ ጋር ፍቺ ሲፈጽም የሆነውም ይሄው ነው።
ማኬንዚ ቤዞስ • የሴቶችና ወንዶች የኢኮኖሚ እኩልነት እንዴት ይስፈን? በስምምነታቸው መሰረት ማኬንዚ የአማዞንን 4 በመቶ የሃብት ድርሻ የምትወስድ ሲሆን ድርሻዋ እስከ 35.6 ቢሊየን ዶላር የሚደርስ ዋጋ ይኖረዋል። ይህ ደግሞ ብቻውን የዓለማችን ሦስተኛዋ ሃብታም ሴት ያደርጋታል ማለት ነው። በአጠቃላይ ግን ከዓለማችን 24ኛዋ ሃብታም ሰው መሆን ችላለች። ነገር ግን በዓለማችን ላይ ያሉት የናጠጡ ሃብታም ሴቶች እነማን ናቸው? • ብቻቸውን ወደ መዝናኛ ስፍራ የሚሄዱ ሴቶች ፈተና 1) ፍራንሷዝ ቤተንኩር ሜየርስ ፍራንሷዝ ቤተንኩር ሜየርስ የተጣራ ሃብት: 49.3 ቢሊየን ዶላር ሲሆን እንደ ፎርብስ መጽሄት ከሆነ የዓለማችን 15ኛ ሃብታም ሴት ነች። ይህች የ65 ዓመት ፈረንሳያዊት 'ሎሪያል' የተባለው የመዋቢያ እቃዎች አምራች ድርጅት ወራሽ ስትሆን የድርጅቱን 33 በመቶ ድርሻ የግሏ ማድረግ ችላለች። ፍራንሷዝ ቤተንኩር ሜየርስ በፈረንጆቹ 2017 ነበር የ94 ዓመት እናቷ ሊሊየን ቤተንኩር ህይወቷ ሲያልፍ ድርጅቱን የወረሰችው። ፍራንሷዝ ቤተንኩር ሜየርስ የታወቀች ምሁር ስትሆን በብዙ ኮፒ የተሸጡ ሁለት መጽሃፎችንም ማሳተም ችላለች። 2) አሊስ ዋልተን አሊስ ዋልተን የተጣራ ሃብት: 44.4 ቢሊየን ዶላር ባለቤት ስትሆን በዓለማችን 17ኛ ሃብታም ነች። የ69 ዓመቷ አሜሪካዊት 'ዋልማርት' የተባለው ታዋቂ ሱፐርማርኬት መስራች ሳም ዋልተን ልጅ ነች። ነገር ግን ከሁለቱ ወንድሞቿ በተለየ መልኩ የቤተሰቡን የንግድ ሥራ ወደ ጎን በማለት ወደ ጥበብ ሥራዎች ፊቷን አዙራለች። በአሁኑ ሰዓትም 'ክሪስታል ብሪጅስ ሚዩዚየም ኦፍ አሜሪካን አርትስ' የተባለ ድርጅት ዋና ኅላፊ ሆና እየሰራች ነው። • በአለም ላይ በየቀኑ 137 ሴቶች በህይወት አጋሮቻቸውና በቤተሰቦቻቸው ይገደላሉ 3) ማኬንዚ ቤዞስ ጄፍና ማኬንዚ ቤዞስ የተጣራ ሃብት : ቢያንስ 35.6 ቢሊየን ዶላር የሚሰደርስ ሃብት እንዳላት የሚገመት ሲሆን ከባለቤቷ ጋር ፍቺ ስትፈጽም ከአማዞን ድርሻ ያገኘችው ነው። ምናልባትም ከዚህ በኋላ ሃብት ሊኖራት እንደሚችል ይገመታል። የ48 ዓመቷ ማኬንዚ ከባለቤቷ ጄፍ ቤዞስ አራት ልጆችን ያፈራች ሲሆን በፈረንጆቹ 1993 ነበር ትዳራቸውን የመሰረቱት። 4) ጃከሊን ማርስ ጃከሊን ማርስ የተጣራ ሃብት:በ23.9 ቢሊየን ዶላር የዓለማችን 33ኛ ሃብታም ሰው ነች። የ79 ዓመቷ ቢሊየነር ማርስ የተባለው ድርጅት አንድ ሦስተኛ ድርሻ ባለቤት ስትሆን በድርጅቱ ውስጥ ለ20 ዓመታት አገልግላለች። • ለሴቶች የተከለከለ ተራራን የወጣችው የመጀመሪያ ሴት 5) ያን ሁዊያን የተጣራ ሃብት: 22.1 ቢሊየን ዶላር። በቻይና አንደኛ ሴት ቢሊየነር፣ የዓለማችን 42ኛ ባለሃብትና በሴቶች 5ኛ ሃብታም ሴት ነች። የ37 ዓመት ጎልማሳ የሆነችው ያን የቻይና በግንባታ ዘርፉን ወደ ላቀ ደረጃ አሸጋግሯል ተብሎ የሚጠራው 'ካንትሪ ጋርደን ሆልዲንግስ' አብዛኛው ድርሻ ባለቤት ነች። የኦሃዮ ዩኒቨርሲቲ ምሩቋ ያን 57 በመቶ የሚሆነውን የድርጅቱን ድርሻ ከአባቷ ነው የወረሰችው። 6) ሱዛን ክላተን ሱዛን ክላተን የተጣራ ሃብት: 21 ቢሊየን ዶላር ሲሆን የዓለማችን 46ኛ ሃብታም ነች። የ56 ዓመቷ ሱዛን ክላተን ጀርመናዊ ዜግነት ያላት ሲሆን በመኪና ማምረትና የመድሃኒት ምርቶችን በመሸጥ ላይ የተመሰረተ የንግድ ዘርፍ ውስጥ ነው ተሰማርታ የምትገኘው። • የሴት ልጅ ግርዛት ምንድነው? የት እና ለምን ይፈጸማል? የድርጅቱ መስራች የሆኑት ቤተሰቦቿ ህይወታቸው ሲያልፍ 50 በመቶ የሚሆነውን የመድሃኒት ድርጅት ድርሻ መውረስ ችላለች። ከዚህ በተጨማሪ እሷና ወንድሟ የታዋቂው መኪና አምራች ድርጅት 'ቢኤምደብልዩ' 50 በመቶ ድርሻም አላቸው። 7) ላውረን ፖወል ጆብስ ሎሪን ፖወል ጆብስ የተጣራ ሃብት: 18.6 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ሃብት ያላት ይህች ሴት በዓለማችን 54ኛ ሃብታም ሰው ናት። የአፕል ፈጣሪ ስቲቭ ጆብስ ባለቤት የነበረችው ላውረን ባለቤቷ ህይወቱ ካለፈ ወዲህ የድርጅቱን ጥቂት የማይባል ድርሻ በመውረስ 20 ቢሊየን ዶላር የግሏ ማድረግ ችላለች። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የ55 ዓመቷ ጎልማሳ በጋዜጠኝነትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ስትሰራ ቆይታለች።
news-53831248
https://www.bbc.com/amharic/news-53831248
ሰሜን ኮርያ፡ ኪም ጆንግ ኡን ለእህታቸው ዮ ጆንግ 'በርካታ ኃላፊነቶችን" ሰጡ
የሰሜን ኮርያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን፣ ለታናሽ እህታቸውና ለቅርብ ረዳታቸው በርካታ ኃላፊነቶችን መስጠታቸውን የደቡብ ኮርያ የስለላ ኤጀንሲ ገለፀ።
ኪም ዩ ጆንግ የሰሜን ኮርያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ታናሽ እህት ናቸው ኪም በሰሜን ኮርያ ውስጥ አሁንም "ፈላጭ ቆራጩ" ቢሆኑም ያለባቸውን የሥራ ጫና ለመቀነስ በሚል የተለየዩ የፖሊሲ ጉዳዮችን ለሌሎች መስጠታቸውን የደቡብ ኮርያ ስለላ ኤጀንሲ ጨምሮ ገልጿል። ብሄራዊ የደህንነት አገልግሎቱ አክሎም ኪም ጆንግ ኡን " አጠቃላይ የአገሪቱን ጉዳይ የሚያስኬዱት ራሳቸው ናቸው" ብሏል። ይሁን እንጂ የደቡብ ኮርያ የስለላ ድርጅት ከዚህ ቀደም ስለ ሰሜን ኮሪያ በሚያወጣቸው ሪፖርቶች ስህተት ይሰራ ነበር። የደቡብ ኮርያ ብሄራዊ ጉባዔ ሐሙስ እለት ዝግ ስብሰባ ካደረገ በኋላ የወጣው ሪፖርት እንደሚያሳው፣ የሰሜን ኮርያው ፕሬዝዳንት ለታናሽ እህታቸውና ለቅርብ ረዳታቸው የተለያዩ ትልልቅ የሚባሉ ኃላፊነቶችን ሰጥተዋል። የሕግ አውጪዎች ይህንን ሪፖርት ተከትሎ ከጋዜጠኞች ጋር ተወያይተዋል። " ኪም ጆንግ ኡን አሁንም የፈላጭ ቆራጭነቱን ስፍራ እንደያዙ ነው፣ ነገር ግን የተወሰነውን ስልጣናቸውን ቀስ በቀስ ለሌሎች እያስረከቡ ነው" ኤጀንሲው ማለቱ ተዘግቧል። ታናሽ እህታቸው ወይዘሪት ኪም ፒዮንግያንግ አሜሪካ እና ደቡብ ኮርያ ላይ የምትከተለውን ፖሊስ እንዲሁም ሌሎች የፖሊሲ ጉዳዮችን ጨምራ በበላይነት ትመራለች። በተጨማሪም ምንም እንኳ ፕሬዝዳንቱ የሚተካቸውን በይፋ ያልመረጡ ቢሆንም የፕሬዝዳንቱ ቀኝ እጅ እና "ሁለተኛዋ መሪ" ሆና እንደምትታይ ተገልጿል። ፕሬዝዳንት ኪም እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት " ያለባቸውን ጫና ለመቀነስ እንዲሁም ፖሊሲዎች ባይሳኩ ከተጠያቂነት ራሳቸውን ገለል ለማድረግ" እንደሆነ ተገልጿል። ነገር ግን የደቡብ ኮርያ ደህንነት መሥሪያ ቤት መረጃን ደረት ተነፍቶ እምነት የሚጣልበት ነው ማለት ለስህተት ያጋልጣል የሚሉ ወገኖች አሉ። እንደውም ከመሾም ይልቅ በዚህ ወር ሁለት ወሳኝ ስብሰባዎች ላይ አለመገኘቷን በመጥቀስ፣ ከነበራት ኃላፊነትም ዝቅ ብላ እንድትሰራ ሳይደረግ አይቀርም የሚሉ የሰሜን ኮርያን ጉዳይ በቅርበት የሚከታተሉ ታዛቢዎች አሉ። ኪም ዮ ጆንግ ማን ናት? ኪም ጆንግ ኡን እና ኪም ዮ ጆንግ በጣም ቅርብ መሆናቸው ይነገራል የኪም ጆንግ ኡን ታናሽ እህት ሆነችው ኪም ዮ ጆንግ፣ የፕሬዝዳንቱ በጣም ቅርብ እና ተሰሚነቷ ጠንካራ የሆነ አጋሩ ናት ትባላለች። እኤአ በ1987 የተወለደች ሲሆን ከፕሬዝዳንት ኪም በአራት ዓመት ታንሳለች። ሁለቱ ወንድምና እህት በተመሳሳይ ሰዓት በስዊዘርላንድ በርን ትምህርታቸውን ተከታትለዋል። ወይዘሪት ኪም የዓለም አቀፉ ማህበረሰብን ትኩረት ውስጥ የገባችው በ2018 ሲሆን ከቤተሰቦቿ መካከል ደቡብ ኮርያን በመጎብኘት የመጀመሪያዋ ናት። ደቡብ እና ሰሜን ኮርያ በጋራ የተሳተፉበት የክረምት ኦሎምፒክ ላይ የልዑካን ቡድኑ ወደ ደቡብ ኮርያ ሲያመራ አባል ነበረች። ከወንድምዋ ጎን በመሆንም የተለያዩ ዓለም አቀፍ ጉባዔዎች ላይ ተሳትፋለች፣ ይህ ስብሰባ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የቻይናውና የደቡብ ኮርያው አቻዎቻቸው ወንድሟን ያገኙበትንም ወቅት ያካትታል። የደቡብ ኮርያ የስለላ ድርጅት ምን ያህል ይታመናል? ሰሜን ኮርያ ሁሉ ነገሯ ምስጢር የሆነ አገር ናት። የደቡብ ኮርያ ደህንነት ተቋም ከማንኛውም አገር በተሻለ ስለ ሰሜን ኮርያ መረጃ ሊኖረው እንደሚችል ይታወቃል። ነገር ግን እስካሁን ድረስ ሁለት መልክ ያለው ታሪክ ነው ያለው። ለምሳሌ በ2016 የደቡብ ኮርያ መገናኛ ብዙኀን በደህንነት ተቋሙ ያገኙትን መረጃ ተጠቅመው የጦር ኃይል ኢታማዦር ሹሙ ሪ ዮንግ ጊል ተገደሉ ብለው ዘገቡ። ከሶስት ወር በኋላ፣ የደቡብ ኮርያ መንግሥት በሕይወት መኖራቸውን አረጋግጫለሁ ብሎ ተናገረ። በ2017 ደግሞ ደቡብ ኮርያ የ2012 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤት ለመለወጥ ሙከራ አድርጋ እንደነበር ገልጿል።
news-49157025
https://www.bbc.com/amharic/news-49157025
በፍጥነት እየመጣ ወደነበረ ባቡር በኤርትራዊው የተገፈተረው ታዳጊ ህይወቱ አለፈ
የስምንት ዓምት ታዳጊ እና ወላጅ እናቱ በፍጥነት እየመጣ ወደነበረ ባቡር ተገፍትረው ልጁ ህይወቱ ወዲያው ሲልፍ እናቲቱ ደግሞ ጉዳት ደርሶባት ወደ ሆስፒታል ተወሰዳለች።
በፍራንክፈርት ታዳጊውን የገጨው ባቡር በጀርመን ፍራንክፈርት ሁለቱን የቤተሰብ አባላት ገፍትሯል ተብሎ የተጠረጠረው ግለሰብ የ40 ዓመት ጎልማሳ ኤርትራዊ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል። ግለሰቡ እናትን እና ልጅን በፍጥነት እየመጣ ወደነበረ ባቡር ለምን እንደገፈተራቸው ባይታወቅም፤ ድርጊቱን ፈጽሞ በሩጫ ሊያመልጥ ሲል በባቡር ጣቢያው አከባቢ የነበሩ ሰዎች አሯሩጠው እንደያዙት እና ለፖሊስ አሳልፈው እንደሰጡት ሬውተርስ ዘግቧል። • የጠቅላይ ሚኒስትሩ 200 ሚሊዮን ችግኞች • አምባሳደር ሬድዋን የሹመት ደብዳቤያቸውን ለምን ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ አላቀረቡም? የዓይን እማኞች እንዳሉት ግለሰቡ በግልጽ ሆነ ብሎ እናት እና ልጅን ወደ ባቡር ሃዲዱ ገፍትሯቸዋል። በተጨማሪም ሶስተኛ ሰውን ለመገፍተር ሙከራ አድርጎ እንደነበር የዓይን እማኞች ተናገረዋል። የፖሊስ ቃል አቀባይ ሲናገሩ፤ "እናት እና ልጅ በፍጥነት እየተቃረበ ወደነበረ ባቡር ተገፍትረዋል። እናቲቱ እራሷን ማዳን ችላለች" ብለዋል። ፖሊስ ጨምሮም በግድያ ወንጀል ምረመራ መጀመሩን አስታውቋል። መርማሪ ፖሊሶች እንዳሚሉት ግለሰቡን ድርጊቱን ለመፈጸም ምን እንዳነሳሳው እስካሁን ግልጽ ባይሆንም፤ ተጠርጣሪው ከእናት እና ልጅ ጋር ትውውቅ አለው ብዬ አላስብም ብለዋል። ለህክምና ወደ ሆስፒታል የተወሰደችው እናት የደረሰባት የጉዳት መጠን አልታወቀም። እረፍት ላይ የነበሩት የሃገር ውስጥ ሚንስትሩ ከዜናው በኋላ ወደ ሥራ የተመለሱ ሲሆን፤ በጉዳዩ ላይ ከከፍተኛ የደህንነት ኃላፊዎች ጋር እወያያለሁ ብለዋል። የሃገር ውስጥ ሚንስትሩ ሆረስት ሲሆፈር "የዚህ ጭካኔ የተሞላበት ወንጀል ጀርባ ያለው ምን እንደሆነ እስካሁን ግልጽ አይደለም" ብለዋል።
news-47907300
https://www.bbc.com/amharic/news-47907300
መሞነጫጨርን አንድ የሥዕል ስልት ያደረገው ሙያተኛ
መርሃፅዮን ጌታቸው ይባላል፤ በሙያው የኪነ ሕንፃ ባለሙያ ሲሆን በዓይነቱ የተለየ የሥዕል ተሰጥዖውን በእራሱ ጥረት በልምምድ አዳብሯል።
ልጆች ሥዕል በሚስሉበት ወቅት ከመስመር ትንሽ ወጣ ሲሉ እንዲያስተካክሉ ማድረግ የተለመደ ቢሆንም ለመርሃፅዮን ግን ይሄ ከመስመር የመውጣትም ሆነ የመሞነጫጨር ስልት እንደ አንድ የጥበብ መገለጫ ዘዴ ሆኖ ታይቶታል። • ጥበብን ከቆሻሻ የኪነ ሕንፃ ትምህርት መማሩ አሁን ለደረሰበት ደረጃ ትልቅ አስተዋፅዖ እንዳደረገለት የሚናገረው መርሃፅዮን ምንም እንኳን የሥዕል ትምህርትን ባይማረውም ሁለቱ ዘርፎች አብረው መሄዳቸው ተሰጥዖውን ለማዳበር ረድቶታል። ሥዕል ለመሳል ያነሳሳው አጋጣሚ አስረኛ ክፍል በነበረበት ወቅት በፎቶግራፎች ተማርኮ እንደሆነ ይናገራል። "ጥቁርና ነጭ ፎቶግራፎች ቀልቤን ይስቡታል፤ እነሱን እያስመሰሉ በመሳል ነው የጀመርኩት" ይላል። • ከ'ሶፍትዌር' ቀማሪነት ወደ ሥነ-ጥበብ ባለሟልነት በፎቶዎች የብርሃንና ጨለማ መስተጋብር ልዩ ስሜት የተማረከው መርሃፅዮን ሰዎችን የሥዕሎቹ ዋና ገፀባህርይ ለማድረግ ጊዜ አልወሰደበትም። ዓይን የነፍስ መስኮት ነው እንደሚባለው መርሃፅዮንም "በሰዎች ፊት ላይ ምሉዕነት አያለሁ፤ በተለይ ደግሞ የሰዎች ዓይን በቃላት መግለፅ የማልችለው ስሜት ይፈጥርብኛል" ይላል። ብዙ ንግግር እንደማይችል የሚናገረው መርሃፅዮን ቃላትን ለማውጣት በሚቸገርበት ወቅትና ስሜቱን ለመግለፅ በሚከብደው ጊዜ ሥዕል ሃሳቡን መተንፈሻ መንገድ ብቻ ሳይሆን የሥዕል ኃያልነት መገለጫም እንደሆነ ያስባል። "የዚህ ዓይነት የአሳሳል ዘዴ ደግሞ ለጣቶቼ ነፃነት ይሰጠኛል" ይላል መርሃፅዮን። "እየሞነጫጨሩ መሳል ምስቅልቅል ባለ መልክ ላይ ሥርዓትን ማሳየት ይችላል፤ ይህ ተቃርኖ የእራሱ የሆነ ውበት ይፈጥራል። መስመሮቹ አቅጣጫ ስለሌላቸው በፈለጉት መንገድ ይወረወራሉ።" • የሩስያ የአብዮት ፖስተሮች የሚከተለው የሥዕል አሳሳል ስልት 'ስክሪብል' የሚባል ሲሆን "ስክሪብል የተባለው የሥዕል ስልት ሐቀኛ ነው፤ መስመሮቹ የሥዓሊው ጣቶች ሙሉ ጉዞ ሕትመት ናቸው" በማለት ስለ አሳሳል ዘዬው ያስረዳል። "በተለይ ደግሞ ሲመለከቱት የቆመ ሥዕል አይደለም፤ ጉልበት አለው፣ ይንቀሳቀሳል።" ከሥዕሎቹ ውስጥ ልዩ ስሜት የሚፈጥርበት የአዳም ረታ ሥዕል ሲሆን ሥራው የአዳምን ሥነ-ጽሑፍ ጥልቀት፣ ውስብስብነትና እውነታን እንደገለፀለት ያስረዳል። በፌስቡክና በኢንስታግራም ገፆቹ ቃላትን ከሥዕሎቹ ጋር አዛምዶ የሚጠቀም ቢሆንም አንዳንዴ ግን ሥዕሎቹ የሚገልፁትን ሃሳብ በቃላት ለመግለፅ እንደሚቸገርና ስለዚህም በእራሳቸው ለብቻቸው እንደሚያስቀምጣቸው ያስረዳል። ከስዕሎቹ መካከል ልዩ ስሜት የሚፈጥርበት ስዕል በዋናነት የታዋቂ ሰዎችን የፊት ገፅ የሚስል ሲሆን ይህንንም የመረጠበት ምክንያት ግለሰቦቹ የሚወክሉት ሃሳብ እንደሆነ ይናገራል። "ሰዎች ከሚያውቁት ነገር ጋር እራሳቸውን አዛምደው መረዳት ይችላሉ፤ ሃሳብ ለብቻ ከሚቀርብ ይልቅ ሰዎች ከሚያውቁት ነገር ጋር ሲቀርብ ለመረዳት አይቸገሩም" ይላል። ወደ መጀመሪያ አካባቢ ሥዕሎቹን ለመሳል እርሳስ በብዛት የሚጠቀም ቢሆንም በቅርብ ጊዜ ግን ቀለሞችን መጠቀም ጀምሯል። ሥዕሎቹን ወረቀትና እንጨት ላይ የሚስል ቢሆንም አሁን የተለያዩ ቁሶች ላይ ለመሳል ሙከራን እያደረገ ነው። • የዳቪንቺ ስዕል ክብረወሰንን ሰበረ የጥበብ ሥራ ሂደት እንደሆነ የሚናገረው መርሃፅዮን መማር እንደማያቆም ያስረዳል "አሁንም እየተማርኩ ነው፤ የእራሴ የሆነ የሥዕል ስልት አግኝቻለው ብዬ አላስብም። ሥነ-ሥዕል ውስጥ ገና ብዙ የምማራቸው ነገሮች አሉ" ይላል። መርሃፅዮን ለወደፊቱ ግን ከኪነ ሕንፃው ይልቅ ወደ ሥነ-ሥዕል ለማዘንበል አስቧል።
news-55084166
https://www.bbc.com/amharic/news-55084166
ኮሮናቫይረስ ፡ 'ለ25 ዓመታት የተሰራበትን የሴቶች እኩልነት ኮቪድ-19 እየናደው ነው'' ተመድ
ላለፉት 25 ዓመታት በጾታ እኩልነት ዙሪያ ሲሰራ የነበረውን ሥራ የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ ሙሉ በሙሉ ሊያጠፋው እንደሚችል አንድ በቅርቡ የተሰራ የተባበሩት መንግሥታት ጥናት አመለከተ።
በወረርሽኙ ምክንያት ሴቶች የቤት ውስጥ ሥራዎችን እንዲሰሩና ቤተሰብ ያላቸው ደግሞ ልጆቻቸውን እነሱ ብቻ እንዲንከባከቡ ተገድደዋል ይላል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሴቶች ተቋም ያወጣው መረጃ። "ላለፉት 25 ዓመታት ስንሰራበት የቆየነው የጾታ እኩልነት በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ ክፍኛ ሊደናቀፍ ይችላል" ብለዋል የተባበሩት መንግሥታት የሴቶች ቀቋም ምክትል ዋና ዳይሬክተሯ አኒታ ብሃሺያ። እኩል የሥራ እድል እና የትምህርት አጋጣሚዎች ሊጠፉ ይችላሉ፤ በዚህም ምክንያት ሴቶች ከባድ የሆነ ሥነ አእምሯዊ እና አካላዊ ጉዳት ሊደርስባቸው ይችላል ተብሏል። ሴቶች በቤት ውስጥ ሲውሉ በአብዛኛው ልጆችን የመንከባከብና ቤትን የመቆጣጠር ኃላፊነት የሚጣልባቸው ሲሆን ከኮሮናቫይረስ በኋላ ደግሞ ሥራቸውንም ሊያጡ የሚችሉ ብዙዎች ናቸው። ልክ ኮሮናቫይረስ በመላው ዓለም መሰራጨት ሲጀምርና ተቋማት ሠራተኞቻቸው ከቤታቸው ሆነው ሥራቸውን አንዲያከናውኑ ማድረግ ሲጀምሩ፤ ብዙዎች ምናልባት የቤት ውስጥ ሥራዎች እኩል በሆነ ሁኔታ ሊከወኑ ነው የሚል ግምታቸውን አስቀምጠው ነበር። 'ባሌ ፀጉሬን ይዞ ከግድግዳ ጋር ያጋጨኛል . . . ' ነገር ግን በበርካታ አገራት በተሰሩ ጥናቶች መሰረት እውነታው የተገላቢጦሽ ነበር። በርካታ ሴቶች ከዚህ ቀደም ከነበረው በበለጠ ልጆቻቸውን የመንከባከብና ምግብ የማብሰል ኃላፊነት ተጭኖባቸዋል። በአሜሪካ ቦስተን ተመራማሪዎች በሦስት ሺህ ሰዎች ላይ ባደረጉት የዳሰሳ ጥናት በቤት ውስጥ ከሚውሉ ሰዎች ውስጥ ሴቶቹ ከወንዶች በበለጠ ሁኔታ በሳምንት ተጨማሪ 15 ሰዓታትን በቤት ውስጥ ሥራና ልጆችን በመንከባከብ ያሳልፋሉ። ምንም እንኳን በበርካታ አገራት በተለይም በአውሮፓ የእንቅስቃሴ ገደቦቹ እየላሉ ቢሆንም ኮረሮናቫይረስ ያስከተለው ጫና በቀላሉ የሚጠፋ እንዳልሆነ ባለሙያዎቹ ይገልጻሉ። ከኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ በፊት እንኳን በዓለማችን በእያንዳንዱ ቀን ያለ ምንም ክፍያ በሥራ ከሚያልፉ 16 ሚሊዮን ሰዓታት መካከል ሦስት አራተኛውን ሥራ የሚሰሩት ሴቶች ናቸው። በሌላ አገላጽ ከኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ በፊት በእያንዳንዱ ያለክፍያ ወንዶች በሚሰሩት አንድ ሰዓት ሴቶች ደግሞ ሦስት ሰዓት ይሰራሉ ማለት ነው። ምንም እንኳን የተባባሩት መንግሥታት ድርጅት ስር በዓለም ዙሪያ የሴቶችን ጉዳይ የሚከታተለው ተቋም (UN Women) ያካሄዳቸው 38 የዳሰሳ ጥናቶች ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው አገራት ላይ ያተኮረ ቢሆንም ባደጉት አገራትም ጭምር ያለው መረጃ ግን ተመሳሳይ ነገር ያሳያል። ስዊድናዊቷ አና ዣቪዬር የሁለት ልጆች እናት ስትሆን በአሁኑ ጊዜ ደግሞ የስምንት ወር ነፍሰጡር ነች። ምንም እንኳን ባለፉት ወራት ከቤተሰቦቿ ቤት በመውጣት የራሷን ቤት በማፈላለግ ላይ የነበረች ቢሆንም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ነገሮችን እንዳመሰቃቀለባት ትናገራለች። ከወረርሽኙ በፊትም ለብዙ ዓመታት የሰራችበትን የውበት መጠበቂያዎች አምራች ኩባንያ በመልቀቅ ስቶክሆልም ውስጥ የራሷን የህጻናት መገልገያዎች ማምረቻ ድርጅት ለመክፈት በዝግጅት ላይ ነበረች። ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በኋላ እሷና ባለቤቷ ከቤት መስራት የጀመሩ ሲሆን፤ በቤት ውስጥ ያለው የሥራ ክፍፍል ግን የሥራ ሰዓቷን ጭምር እንደሚሻማባት ትናገራለች። ምንም እንኳን በቤት ውስጥ ለሚያስፈልጉ ነገሮች በየወሩ እኩል የሆነ ገንዘብ አዋጥተው የሚኖ ቢሆንም፤ እሷ ከባለቤቷ በበለጠ መልኩ ልጆችን የመንከባከብ፣ ምግብ ማብሰልና ቤት የማጽዳት ኃላፊነት አለባት። "በውይይታችን ወቅት ባለቤቴ የህክምና መሳሪያዎችን ለሚያመርት ድርጅት ስለሚሰራና የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በሚደገው ጥረት መንግሥትን ስለሚረዳ ሙሉ ጊዜውን መሰዋት እንዳለበት ተስማማን።" ነገር ግን ሥራውን ከጨረሰ በኋላ ያሉበትን ቀላል የሚባሉ ኃላፊነቶች እንኳን አሁንም ቢሆን ለመወጣት ፍላጎት አልነበረውም ትላለች አና። ነፍሰጡርነት፣ የወረርሽኝ ስጋትና የቤት ውስጥ ሥራ ተደማምረው ሕይወትን ከባድ እንዳደረጉባት የምትናገረው አና፤ ልጇን ከመውለዷ በፊት ለመጨረስ አስባቸው የነበሩ በርካታ ነገሮች እስካሁን እንዳልተጀመሩ ትገልጻለች። "ነገሮችን ይበልጥ አሳሳቢ የሚያደርጋቸው ደግሞ ሴቶቹ ከወረርሽኙ በኋላ እንኳን ተመልሰው ሥራ መጀመር መቻላቸው አለመረጋገጡ ነው" ይላሉ አኒታ ብሃሺያ። አክለውም "በመስከረም ወር ብቻ አሜሪካ ውስጥ እስከ 850 ሺህ የሚደርሱ ሴቶች ከሥራቸው የተቀነሱ ሲሆን በተመሳሳይ ከሥራቸው የተቀነሱ ወንዶች ቁጥር ግን 200 ሺህ ብቻ ነው" ሲሉ ያስረዳሉ። ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በፊት ጃፓን ውስጥ ከወንዶች ጋር ሲነጻጸር ሴቶች ተጨማሪ አምስት ሰዓታትን ያለክፍያ ሥራ እየሰሩ እንደሚያሳልፉ አንድ ጥናት ያመለክታል። በሌላ በኩል ደግሞ ከዚህ በፊት አብዛኛውን ሰዓታቸውን በሥራቸው ምክንያት ውጪ ያሳልፉ የነበሩ አባቶች የቤት ውስጥ ሥራዎችን በአግባቡ መስራት የጀመሩበትና ልጆቻቸውን መንከባከብ እያዘወተሩ ይገኛሉ። ምንም እንኳን አሁንም ቢሆንም ሴቶች ከቤት ውስጥ ሥራ የአንበሳውን ድርሻ ቢወስዱም ከነጭራሹ ምንም ነገር ሰርተው የማያውቁ አባቶች ወደ ኩሽናዎች ሲገቡ መታየታቸው እንደ ትልቅ የለውጥ ጉዞ መቆጠር አለበት የሚሉም አልጠፉም። አንድ ካናዳ ውስጥ በተሰራ ጥናት መሰረት ደግሞ 40 በመቶ የሚሆኑ አባቶች ከዚህ በፊት ከሚያደርጉት በተሻለ ምግብ እያበሰሉና ልጆቻቸውን እየተንከባከቡ እንደሆነ የገለጹ ሲሆን፤ 30 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ልብስ ማጠብና ቤት ማጽዳት መጀመራቸውን ተናግረዋል። ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት የተባበሩት መንግሥታት የዓለም መሪዎችና ትልልቅ ኩባንያዎች በርካቶች ያለክፍያ ሥራ እንደሚሰሩ እንዲረዱና በተለይ ደግሞ ሴቶች በዚህ ተጎጂ መሆናቸውን አውቀው ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ አሳስቧል።
news-53400207
https://www.bbc.com/amharic/news-53400207
በብሩንዲ ሙሽራው በደረሰበት የሞተር አደጋ ምክንያት ጥንዶቹ ሰርጋቸውን በሆስፒታል አደረጉ
በሰሜናዊቷ ብሩንዲ ኪሩንዶ ግዛት የሚኖሩ ሁለት ጥንዶች ሙሽራው ከቀናት በፊት በሞተር አደጋ ጉዳት ቢደርስበትም ሰርጋቸውን አንሰርዝም ማለታቸው ብዙዎችን አስደንቋል።
ቻርሎቴ ሙካንትዋሪና ጋቢን ንዳይዚጊየ የተባሉት ጥንዶችም የሰርጋቸውን ስነ ስርአት በሆስፒታል አከናውነዋል ተብሏል። አደጋው ከደረሰ በኋላ ጓደኛው የአሁኑ ባለቤቱ ከጎኑ ያልጠፋች ሲሆን ህክምናውን እየተከታተለ ባለበትም ወቅት ሰርጋቸውን ፈፅመዋል። ሰርጋቸውን የሚያስፈፅሙት ቄስ ሙሽሪትን ቀለል ያለ ልብስ እንድትለብስ ቢመክሯትም ነጭ ቬሎ ለብሳ እንደመጣች ተገልጿል። "ይህችን የሰርጌን ቀን በጉጉት ስጠብቃት ነበር። በዚህች ቀን እንዲህ አይነት ችግር ማጋጠም ማለት ሰይጣን እየተፈታተነኝ እንደሆነ ነው የማስበው። ህይወቴን ያለዚች ቀን ማሰብም አልችልም" በማለት ቻርሎቴ ሊቢሲ ተናግራለች። በርካታ የአካባቢው ሰዎች አደጋ ያልፈተናቸው ተጋቢዎችን ሰርግ ለመታደም ወደ ሆስፒታሉ እንደተመሙም ተገልጿል። ሙሽራው ጋቢንም ሰርጉ መካሄድ አለበት በማለት በሃሳቧ በፀናችው ሙሽሪት ልቡ እንደተነካ የገለፀ ሲሆን በተለይም ሙሽሪት በአደጋው ምክንያት እንደገና ይራመድ አይራመድ ሳታውቅ መሆኑም አግራሞት መፍጠሩን አልደበቀም። ሙሽራው ቃለ መሃላቸውን ሊፈፅሙ ሲሉ ለአጭር ጊዜ ቢገኝም ወዲያው ወደ ሆስፒታል አልጋው እንዲመለስ ተደርጓል ተብሏል።
news-41548915
https://www.bbc.com/amharic/news-41548915
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን እህቱን ለፖሊት ቢሮ ሾመ
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን የእህቱን ስልጣን በማሳደግ፤ በአገሪቷ ላይ ከፍተኛ የመወሰን ሃላፊነት ወዳለው ፖሊት ቢሮ አባል እንድትሆን ሾሟታል።
ከወንድሟ አካባቢ የማትጠፋው ኪም ዮ ጆንግ ከጀርባ ያለችው ናት ኪም ዮ ጆንግ የ ቀድሞው መሪ ኪም ጆንግ ኢል የመጨረሻ ልጅ ስትሆን አሁን ያለውንም የስልጣን ቦታም የተቆጣጠረችው የሰራተኞች ፓርቲን በመወከል የፖሊት ቢሮ አባል የነበረችውን አክስቷን በመተካት ነው። የ 30 አመት ዕድሜ ያላት ኪም ዮ ጆንግ ወደ ከፍተኛ ስልጣን ቦታ መቆናጠጥ የጀመረችው ከሦስት ዓመታት በፊት ነበር። አጠቃላይ ቤተሰቡ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ማግስት አንስቶ ሰሜን ኮሪያን በመምራት ላይ ነው። በተለያዩ አጋጣሚዎች ከወንድሟ ጋር በአደባባይ የምትታየው ኪም ዮ ጆንግ፤ በአደባባይ ላይ ላለውም እይታ ከፍተኛ ተፅዕኖን የፈጠረች ሲሆን የፕሮፓጋንዳ ክፍልን እንዲሁም ቀውሶች በሚፈጠሩበትም ጊዜ የሚመራው ክፍል ምክትል ሃላፊ ነች። ከሰብአዊ መብት ጥሰት ጋርግንኙነት አላት በሚል በአሜሪካ መንግሥት በጥቁር መዝገብ ከሰፈሩት ውስጥ አንዷ ናት። ይህ ሹመት የተነገረው ቅዳሜ በነበረው የፓርቲው ስብሰባ ላይ ሲሆን በዚህም ስብሰባ ላይ ከፍተኛ የሚባሉ የባለስልጣናት ሽግሽግ ተደርጓል። በባለፈው ዓመት በመሪው ፓርቲ ኮንግረስ ቁልፍ የሚባል ስልጣን ሲሰጣት በሃገሪቷም ላይ ከፍተኛ ስልጣን እንደምትቆናጠጥ ተጠብቋል። ኪም ዮ ጆንግ ማናት? ቅዳሜ ዕለት ሌላኛው ሹመት የተሰጣቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዮንግ ሆ ሲሆኑ፤ ባለፈው ወር የአሜሪካ ፕሬዚዳንትን ዶናልድ ትራምፕን በተባበሩት መንግሥታት ስብሰባ ላይ "መጥፎው ፕሬዚዳንት" በሚል ንግግር መወረፋቸው ይታወሳል። በፖሊት ቢሮው ውስጥ በሙሉ ድምፅ የመሳተፍንም ሹመት አግኝቷል። በኒዉክሌር መሳሪያ ላይ ጠንካራ አቋም ያለው ኪም አሁንም ግልፅ ያደረገው ምንም አይነት ማዕቀብ ይሁን ማስፈራራት ከእቅዳቸው እንደማያሰናክላቸው ነው። ይህ አስተያያየት የተሰጠው ትራምፕ ከሰዓታት በፊት በትዊተር ገፃቸው " ከፒዮንግያንግ ጋር ለመደራደር አንድ ነገር ብቻ ነው የሚሰራው'' ያሉ ሲሆን ከዓመታት ንግግርም በኋላም ውጤቶች ማምጣት አልተቻለም ብለዋል።
50390647
https://www.bbc.com/amharic/50390647
ኢትዮጵያ ወይስ ናይጄሪያ? የትዊተር አለቃ ለስድስት ወራት ሊኖርባት ያጫት ሃገር
ትዊተር የተሰኘው ማሕበራዊ ድር-አምባ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆነው ጃክ ዶርሲይ ከሰሞኑ ወደ አህጉረ አፍሪካ ዓይኑን ጥሏል።
የትዊተር ተባባሪ ፈብራኪው ጃክ፤ በሚቀጥለው ዓመት ለስድስት ወራት ያክል ወይ ኢትዮጵያ አሊያም ናይጄሪያ መኖር እፈልጋለሁ ማለቱን ተከትሎ የማሕበራዊ ድር አምባ ተጠቃሚዎች ግምታቸውን ማስፈር ጀምረዋል። አለቃ ጃክ ለስድስት ወራት ከሁለት ሃገራት በአንዷ መቆየት የሻተው የትዊተርን በአፍሪካ ተደራሽነት ለማስፋት ነው። ናይጄሪያ ከአፍሪካ ቀዳሚዋ በርካታ ሕዝብ ያላት ሃገር ስትሆን ኢትዮጵያ ደግሞ ሁለተኛ ላይ ትገኛለች። በናይጄሪያ የብሪታኒያ አምባሳደር የሆኑት ካትሪዮና ሌይንግ ጃክ ናይጄሪያ ወይ ኢትዮጵያ ቆይታ ለማድረግ መወሰኑ ብዙም አያስገርምም ይላሉ። የተለያዩ የአፍሪካ ሃገራትን እየተዘዋወረ በመጎብኘት ላይ የሚገኘው ጃክ የቀድሞ የናይጄሪያ የገንዘብ ሚኒስቴር ጠርተው እራት በጋበዙት ወቅት ነው ይህንን ዜና ይፋ ያደረገው። ዜናውን ተከትሎ በተለይ ኢትዮጵያውያን እና ናይጄሪያውን የማሕበራዊ ድር-አምባ ተጠቃሚዎች ክርክር ገጥመዋል። ዛሬ [ማክሰኞ] ጋና ከተማ አክራ የሚገኘው ጃክ የጋናውያን እንዲሁም የምዕራብ አፍሪካውያን ተወዳጅ ምግብ የሆነውን ጆሎፍ ሊመገብ ሲሰናዳ የሚያሳይ ፎቶ በትዊተር ገፁ ለጥፏል። ለአንድ ወራት ያክል በአህጉረ አፍሪካ ዝውውር የሚያደርገው ጃክ ዶርሲ ከጋና በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ያቀናል። የ42 ዓመቱ አሜሪካዊ የኮምፒውተር ጠቢብ እና ሥራ ፈጣሪ 4.1 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ገቢ እንዳለው ይገመታል።
news-55335595
https://www.bbc.com/amharic/news-55335595
የአንበጣ መንጋ፡ ምስራቅ አፍሪካ ሁለተኛ ዙር የአንበጣ ወረርሽኝ ስጋት ተደቅኖበታል
ለዓመት ያህል ለመቆጣጠር ጥረት ቢደረግም አዲስ የበረሃ አንበጣ ወረርሽኝ በሚሊዮን የሚቆጠሩ በየመንና በአፍሪካ ቀንድ የሚኖሩ ሕዝቦችን ሕይወት ላይ አደጋ መደቀኑን የተባበሩት መንግሥታት አስታወቀ።
ምስራቅ አፍሪካ ባለፉት ዓመታት ከ70 ዓመታት በላይ ያልታየ የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝን አስተናግዷል የተባበሩት መንግሥታት በምስራቅ ኢትዮጵያ እና ሶማልያ እንዲሁም ኬንያን ጨምሮ ለአንበጣ መራባት ምቹ ሁናቴ አለ ብሏል። በቀይ ባሕር ሁለቱም አቅጣጫዎች እየተራባ የሚገኘው አንበጣ በኤርትራ፣ ሳዑዲ አረቢያና የመን ላይ አደጋ መደቀኑን አክሎ ገልጿል። ምስራቅ አፍሪካ ባለፈው ዓመት ከ70 ዓመታት በላይ ያልታየ የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝን አስተናግዷል። "ለኬንያ አደጋው የማይቀር ነው፤ ከአሁን ጀምሮ በማንኛውም ወቅት ሊደርስ ይችላል" ያሉት የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና እርሻ ድርጅት ከፍተኛ የአንበጣ ወረርሽኝ ትንበያ ባለሙያ የሆኑት ኪት ክሬስማን ናቸው። ስለ ስጋቱ መጠን ሲያስረዱም " ባለፈው ዓመት እንዳየነው የከፋ ሊሆን ይችላል ምክንያቱም በእነዚህ አገራት አንበጣው እየተራባባቸው የሚገኙት ስፍራዎች 350,000 ስኬይር ኪሎ ሜትር ድረስ ስፋት አላቸው።" በዚህ ዓመት ከታሕሳስ እስከ ነሐሴ ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ምስራቅ አፍሪካ በቢሊዮን የሚቆጠሩ የበረሃ አንበጣዎች በቀጠናው ሰብሎችን ሲያወድሙ ይመለከታሉ ብለዋል። "በርካታ የግጦሽ ሳር እና ተክሎችን በበረሃ አንበጣው የተነሳ አጥተናል፤ በዚህም የተነሳ ቀላል ቁጥር የማይሰጣቸው የእንስሳት ሀብቶቻችን እየሞቱ ነው" ያሉት ደግሞ በሰሜን ኬንያ የሚኖሩት አርብቶ አደሩ ጎንጆባ ጉዮ ናቸው። "በበረሃ አንበጣው ወረርሽኝ የተነሳ 14 ፍየሎቸን፣ አራት ላሞች፣ ሁለት ግመሎች አጥቻለሁ። አሁን ደግሞ ተመሳሳይ ነገር ይገጥመናል የሚል ጽኑ ፍርሃት አለን" የተባበሩት መንግሥታት ምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) አገራት ከዚህ ቀደም ከደረሰው ወረርሽኝ በተሻለ የመከላከል ዝግጅት አላቸው ሲል ተናግሯል። እንደ ድርጅቱ ከሆነ ቅኝት የማድረግም ሆነ በምድርና በአየር የፀረ ተባይ ርጭት ለማድረግ ያለው ዝግጁነት እጅጉን የተሻለ ነው። በ10 አገራት በላይም ከአንድ ሚሊዮን ሄክታር በላይ ከአንበጣ ወረርሽ እንዲያገግሙ ተደርጓል። ወረርሽኙ ትልቅ ከሆነ ግን ማሕበረሰቦች በአንበጣ መንጋው ሊጥለቀለቁ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ። የበረሃ አንበጣው እንዲህ አስጊ በሆነ መልኩ እንዴት ሊራባ ቻለ? ምቹ የአየር ጠባይ ባለሙያዎች እንደሚሉት ማዕከላዊ ሶማልያ እና ምስራቅ ኢትዮጵያ ከመስከረም እስከ ሕዳር ወር ድረስ ወትሮ ከሚያገኙት መደበኛው የዝናብ መጠን ከፍያ ያለ አግኝተዋል። ይህም ማለት መሬቱ የተሻለ ለምለም እጽዋት ማብቀል የቻለ ሲሆን ይህም በስፋት ይገኛል። "ይህ ለበረሃ አንበጣው ምቹ የመራብያ ስፍራ ሆኖታል" ያሉት ክሪስማን " እነዚህ አካባቢዎች ደግሞ በጣም ሰፊ የመራብያ ቀጠናዎች ናቸው" ሲሉ አክለዋል። ይህ ምቹ ሁኔታ ባለበት በሁለት ወራት ውስጥ እንድ ነፍሳት የነበረው በቡድን የሚንቀሳቀስ የበረሃ አንበጣ ሆኖ ሰብሎች ላይ ውድመት ያደርሳል ሲሉም ያብራራሉ። እንደ ተባበሩት መንግሥታት እና የዓለም ሜቲዎሮሎጂ ድርጅት ሪፖርት ከሆነ የበረሃ አንበጣዎች በፍጥነት ሊራቡ እና በዓመት ውስጥ 160 ሺህ እጥፍ በመሆን ጥፋት ሊያደርሱ ይችላሉ። ሳይክሎን ጋቲ ሰሜን ሶማሊያ ያለው የመልከዓ ምድር አቀማመጥ አንጻር ለበረሃ አንበጣ መራባት ሁኔታዎችን አስቸጋሪ ሊያደርገው ይችላል ሲሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ነገር ግን በሕዳር ወር ሳይክሎን ጌቲ በአካባቢው ላይ በመድረስ ተቃራኒውን አደረገ። በሁለት ቀናትም ውስጥ አካባቢው በሁለት ዓመት የሚያገኘውን ዝናብ በማዝነብ ለበረሃ አንበጣ መራብያነት እንቅፋት የነበረውን አካባቢ ምቹ አደረገው። ከጎርፉ በኋላ እርጥበታማው አፈር አንበጣዎች እንቁላላቸውን እንዲጥሉ እና እንቁላላቸው ሲፈለፈል የሚመገበው የአረንጓዴ ተክል ፍሪዳ አዘጋጀላቸው። ሶማሊያ በዚህ ዓመት በአንበጣ ወረርሽኝ ክፉኛ ከተጎዱ አገራት መካከል አንዷ ናት። ግጭት ባለሙያዎች እንደሚሉት በአንበጣ ወረርሽኝ በተጠቁ በርካታ አገራት ቅኝት የማድረግ አቅም ማደጉ ለመከላከል እጅጉን ጠቅሟል። ነገር ግን በአካባቢዎቹ ያለው የፀጥታ ስጋት እስካልተወገደ ድረስ የአንበጣ መከላከሉን ሙሉ በሙሉ ማሳካት አይቻልም። "ለምሳሌ በሰሜን ሶማልያ ምንም ዓይነት የቅኝት ሥራ አልተሰራም" ይላሉ ክሪስማን። ለበረሃ አንበጣ መራቢያነት በርካታ ምቹ ስፍራዎች ካሏቸው አገራት መካከል አንዷ የመን ናት። ነገር ግን በአገሪቷ በውስጥ ያለው ግጭት በበርካታ አካባቢዎች ቅኝት ለማካሄድ ፈተና ሆኗል። ባለሙያዎች አክለውም የበረሃ አንበጣዎች ከየመን ተነስተው ወደ ሳዑዲ አረቢያ በመጓዝ ላይ ናቸው። እነዚህ የበረሃ አንበጣዎች 300 ኪሎ ሜትር ተሻግረው ቀይ በሃርን ማቋረጥ እንዲሁም አየር ላይ ለረዥም ጊዜ መቆየት ይችላሉ። የፀረ ተባይ መድሃኒት ርጭት በቀጠናው የሚገኙ አገራት በምድርም ሆነ በአየር የፀረተባይ ርጭት ለማካሄድ ተዘጋጅተዋል። "በእነዚህ በምግብ እህል እጥረትና በድህነት በተጎዱ አገራት ከዚህ ቀደም የተደረጉ የመድሃኒት ርጭቶች ዋጋው ወደ 800 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት፣ 2.7 ሚሊዮን ቶን እህልን ከአንበጣ መንጋጋ ማትረፍ ተችሏል።" ያለው የተባበሩት መንግሥታት የምግብና የእርሻ ድርጅት ነው። ባለሙያዎች ግን ከፊት አፍጥጦ እየመጣ ያለውን ተግዳሮት ለመቋቋም በርካታ ድጋፍ ያስፈልጋል ይላሉ። በሰሜን ኬንያዋ መርሳቤት የአካባቢ ጥበቃ ተመራማሪ የሆነውና በአንበጣ ወረርሽኝ ቅኝት ላይ የተሰማራው ጄርሜያህ ሌኮሊ " ቅኝቱን እያካሄድን ነው፤ ነገር ግን ምንም አይነት መሳሪያም ሆነ የምንረጨው ፀረ ተባይ አልተሰጠንም" ሲል ተናግሯል። አክሎም "እነዚህ ነገሮች አሁን ቢኖሩን ጥሩ ነው፤ አለበለዚያ መሳሪያዎቹ የሚደርሱት የበረሃ አንበጣው መጥቶ ውድመቱን አድርሶ ከሄደ በኋላ ይሆናል።" የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በበረሃ አንበጣ ወረርሽኝ በተጠቁ አገራት ከ35 ሚሊዮን ሕዝቦች በላይ በምግብ እጥረት ክፉኛ ተጎድተዋል ሲል አስጠንቅቋል። አሁን የሚከሰተውን ወረርሽኝ መቆጣጣር ካልተቻለ ይህ ቁጥር በ3.5 ሚሊዮን ሊጨምር ይችላል ሲልም ተናግሯል።
news-43638050
https://www.bbc.com/amharic/news-43638050
በመቅደላ ውጊያ ከኢትዯጵያ የተዘረፉ ቅርሶች በውሰት ለመለሱ ነው
የእንግሊዙ ቪክቶሪያና አልበርት ሙዚየም ከ150 ዓመታት በፊት በነበረው የመቅደላ ውጊያ በእንግሊዝ ወታደሮች ተዘርፈው የተወሰዱ በወርቅ የተንቆጠቆጠ ዘውድ፣ የሰርግ ቀሚስና የወርቅ ዋንጫዎችን በውሰት ሊመልስ ነው።
ከእነዚህ ቅርሶች መካከል የተወሰኑት እንደ አውሮፓውያኑ በ1868 የተካሄደው የመቅደላ ጦርነት አመታዊ በአል ሲዘከር ለእይታ መቅረባቸው ጥያቄዎችን አስነስቷል። የእንግሊዝ ሃይል ቅርሶቹን ከመቅደላ ለመውሰድ 15 ዝሆኖችንና 200 በቅሎዎችን ለማጓጓዣነት ተጠቅመው እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ። በ1860 የተሰራው ይህ የሰርግ ቀሚስ የንግስት ጥሩነሽ እንደሆነ ይታመናል። በ2008 ኢትዮጵያ ከመቅደላ የተዘረፉና በሚሊዮን ዶላር የሚገመቱ ቅርሶቿ እንዲመለሱላት ለተለያዩ የእንግሊዝ ቅርስ ተቋማት ጥያቄ አቅርባ ነበር። የቪክቶሪያና አልበርት ሙዚየም ዳይሬክተር ትሪስትራም ሀንት ግን ቅርሶቹ የእንግሊዝ ሆነው እንደሚቀጥሉ ነገር ግን ለረዥም ጊዜ መቆየት ይችሉ ዘንድ በውሰት ወይም በብድር መልክ ለኢትዮጵያ ሊሰጡ እንደሚችሉ አስታወቁ። መቅደላ 1868 የሙዚየሙ ዳይሬክተር ሚስተር ሃንት ለአንድ የኪነጥበብ ጋዜጣ እንደገለፁት ሙዚየሙ ቅርሶቹን ለኢትዮጵያ ማዋስ እንደሚፈልግ በለንደን ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቀዋል። አምባሳደሩ ሃይለሚካኤል አበራ አፈወርቅም "ከሙዚየሙ ጋር በተፈጠረው አጋርነት ተደስተናል ለጋራ ጥቅማችን አብሮ የመስራት ፍላጎትም አለን"ሲሉ ለጋርዲያን ተናግረዋል። ሙዚየሙ እንዳስታወቀው ለዕይታ የቀረቡት እነዚህ ቅርሶች ታዳሚዎች የዕጅ ጥበብን ውበትና የብረታ ብረት ስራና የጥልፍ ዲዛይን ረቂቅነትን እንዲሁም ከቅርሶቹ ጋር የተያያዘውን አወዛጋቢ ታሪክ እንዲያስተውሉ እንደሚያደርግ ገልጿል። የንግስት ጥሩነሽ የአንገት ጌጥና ሙሉ በሙሉ ከወርቅ የተሰራ ዋንጫም ለእይታ ይቀርባሉ። ለዘመናዊ ፎቶግራፍ መሰረት ነበሩ የተባሉ የጦር የእንግሊዝ ጦር ሃይል ፎቶግራፎችም ለእይታ እንደሚቀርቡም ሙዚየሙ አስታውቋል። ይህ በመቅደላ የሚገኝ ቤተክርስትያን ፎቶ የተነሳው በእንግሊዝ ንጉሳዊ መሃንዲሶች ነው።
news-45623495
https://www.bbc.com/amharic/news-45623495
አኳሪየስ፦ ከሊቢያ ወደ አውሮፓ የሚገቡ ስደተኞችን የምትታደገው መርከብ ፈቃዷን ተነጠቀች
አኳሪየስ ትባላለች፤ በሜድትራኒያናን ባህር ላይ በመንሸራሸር ስደተኞችን የመታደግ ሥራ በመሥራት ነው የምትታወቀው።
ከሊቢያ ወደ አውሮፓ የሚሸጋገሩ ስደተኞችን የመታደግ ሥራ የምትሠራው አኳሪየስ ፈቃዷን በመነጠቋ ምክንያት ሌላ ፈቃድ እስኪሰጣት ድረስ መንቀሳቀስ አትችልም። በሜድታራንያን ባህር ላይ በመንቀሳቀስ መሰል ስደተኞችን የመታደግ ሥራ ከሚሰሩ የግል መርከቦች የመጨረሻዋ ነበረች አኳሰሪየስ። የመርከቧ ባለቤት የሆነው የተራድዖ ድርጅት የጣልያን መንግሥት ነው የአኳሪየስ ፈቃድ እንዲነጠቅ ያደረገው የሚል ክስ በማቅረብ ላይ ይገኛል። • ሚሊዮን ዶላር አጭበርባሪው ስደተኛ • አፍጋናዊቷ ስደተኛ በኢትዮጵያ መርከቧ በፓናማ ባንዲራ ስር ሆና ነበር ሜድትራኒያን ባህር ላይ በመንቀሳቀስ ስደተኞችን ትታደግ የነበረው። የፓናማ መንግሥት መርከቧ ፖለቲካዊ ችግር እያስከተለች በመሆኗና የጣልያን መንግሥት ፈቃዷን እንድንሰርዝ በወተወተን መሠረት ነው ይህን ልናደርግ የተገደድነው ሲሉ ተደምጠዋል። የጣልያን የሃገር ውስጥ ሚኒስትር ማቴዎ ሳልቪኒ ግን እኛ የፓናማ መንግሥትን ጫና ውስጥ አልከተትንም ብለዋል። ምንም እንኳ አንድ ሰሞን መርከቧን 'የስደተኞች ታክሲ' ሲሉ መጥራታቸው ባይዘነጋም። • ለአፍሪካውያን ስደተኛ ልጆች አደገኛ የሆነው መጠለያ ሚኒስትር ማቴዎ በስደተኞች ጉዳይ ጠንካራ ቀኝ ዘመም አቋም በማፀባረቅ ይታወቃሉ። ከአኳሪየስ ጋር ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ስደተኛ ታደጊ መርከበኞች ጋር እሰጥ-አገባ በመግባትም ይታወቃሉ። የተባበሩት መንግሥታት መረጃ እንደሚያሳየው በአውሮፓውያኑ 2018 ብቻ 1700 ገደማ ስደተኞች ወደ አውሮፓ ለመጋባት በሚደረግ ሙከራ ህይወታቸውን አጥተዋል። አኳሪየስ ከወራት በፊት ከሊቢያ ወደ አውሮፓ ሲሸጋገሩ የነበሩ በርካታ አፍሪቃዊ ስደተኞችን በመታደጓ ምክንያት የዜና መክፈቻ ሆና እንደነበር አይዘነጋም።
53488248
https://www.bbc.com/amharic/53488248
በዱከም በአንድ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ከተገኙ ሰዎች 44ቱ በኮሮናቫይረስ ተያዙ
ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው የዱከም ከተማ ውስጥ ጥንቃቄ በጎደለው ሁኔታ በኮሮናቫይረስ በተያዘ ግለሰብ በቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙ 44 ሰዎች በኮሮናቫይረሰ መያዛቸው ተነገረ።
በኮሮናቫይረስ ስርጭት ወቅትም በርካቶች በቀብር ሰነ-ሰርዓት ላይ ሲገኑ ይስተዋላል ለቫይረሱ ተጋላጭ ከሆኑት ከአርባ በላይ ሰዎች መካከል በሐዘን ላይ ያሉ የሟች የቤተሰብ አባላትን እንደሚጨምር የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ደረጄ አብደና ለቢቢሲ ተናግረዋል። ለወረርሽኙ መተላለፍ ምክንያት የሆነው ግለሰብ ህይወቱ ያለፈው ባለፈው ሳምንት ባጋጠመው የመኪና አደጋ ሲሆን በአስክሬኑ ላይ በተደረገ ምርመራ ነበር የኮሮናቫይረስ እንደነበረበት የታወቀው። ቢሆንም ግን በትራፊክ አደጋ የሞተው ወጣት የምርመራ ውጤቱ ከመታወቁ በፊት አስከሬኑ ለቤተሰብ ተሰጥቶ አስፈላጊው ዝግጅትና ሥነ ሥርዓት ተከናውኖ እንዲቀበር ከተደረገ በኋላ ሟች አስከሬን ላይ የኮሮናቫይረስ መገኘቱ ታወቋል። ይህንንም ተከትሎ የሟች ቤተሰብ አባላት፣ ጎረቤቶች እና በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙና ንክኪ ሊኖራቸው ይችላል የተባሉ ሰዎችን የመለየት እና ምርመራ የማድረግ ሥራዎች ሲከናወኑ እንደቆዩ የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል። በዚህም መሰረት እስከ ሰኞ ድረስ በንክኪ ምክንያት ለቫይረሱ ሊጋለጡ ይችላሉ በተባሉ ሰዎች ላይ በተደረገው ልየታና ምርመራ መሠረት በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች ቁጥር 44 መድረሱን አቶ ደረጄ አብደና ተናግረዋል። የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ፤ በተለያዩ ምክንያቶች ህይወታቸው ላለፉ ሰዎች በሚከናወን የቀብር ሥነ ሥርዓቶች አማካይነት የሚከሰተው የኮሮናቫይረስ መስፋፋት ለበሽታው መዛመት አመቺ አጋጣሚዎች እየሆኑ እንደመጡ አመልክተዋል። በወረርሽኙ ሳቢያ ህይወታቸው ካለፉ ሰዎች አስከሬን ጋር ከሚደረግ የቀጥታም ሆነ የተዘዋዋሪ ንክኪ ባሻገር በቀብር ሥነ ሥርዓቶች ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ስለሚገኙ ከሐዘኑ ታዳሚ ጋር በሚኖረው መቀራረብ ቫይረሱ ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ ለመተላለፍ እድል እንደሚያገኝ ኃላፊው ገልጸዋል። በተጨማሪም በቀብር ሥነ ሥርዓትና በማስተዛዘን ወቅት ከተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ሰዎች የሚታደሙ ከመሆናቸው ባሻገር ርቀትን መጠበቅና የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል መጠቀም አምብዛም ስለሆነ ለቫይረሱ የመጋለጥ እድልን ከፍ እያደረገ ነው ብለዋል አቶ ደረጄ። ከዚህ ቀደምም በተመሳሳይ በኦሮሚያ ክልል በጉጂ ዞን፣ ምዕራብ ሸዋ ዞን ሜታ ወረዳ እንዲሁም በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ አካባቢ በጥንቃቄ በጎደለው የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ የተሳተፉ በርካታ ሰዎች ለኮሮናቫይረስ መጋለጣቸው ይታወሳል። በኮቪድ - 19 የሞተ ሰው የቀብር ሥነ- ሥርዓት እንዴት መፈጸም አለበት? በጣልያን በኮሮናቫይረስ የሞተ ሰው ሥርዓተ ቀብር 1. አዘገጃጀት በአገራችን በሁለት ዓይነት ሁኔታ አስክሬን ለቀብር ይዘጋጃል፤ ይህም በህክምና ተቋማት እና ከህክምና ተቋማት ውጪ የሚከናወን መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ። በቅድሚያ አንድ ግለሰብ ሕይወቱ እንዳለፈ በአቅራቢያ ለሚገኝ የጤና ተቋም ማሳወቅና የጤና ተቋሙ በአስከሬን አያያዝ ያሰለጠናቸውን ሰዎች በመላክ አስክሬኑ በጥንቃቄ መዘጋጀት አለበት። በመሆኑም አስክሬኑን የሚያዘጋጀው ሰው የእጅ ጓንቶች፣ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) እንዲሁም ገዋን ማድረግ ይጠበቅበታል። አካባቢውንም በጸረ ተህዋስ ኬሚካል በመርጨት ማጽዳት ያስፈልጋል። ሟች የተጠቀመባቸው ቁሳቁሶችና አልባሳት በበረኪና ወይም ኬሚካል ማጠብና መልሶ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ። ሌሎች ዕቃዎች ወይም ቁሳቁሶች በተመሳሳይ መልኩ ከጸዱ ማቃጠል ላያስፈልግ ይችላል። 2. አሸኛኘት በኮቪድ-19 የሞተን ሰው አስክሬን ከማዘጋጀት በተጨማሪ የአስክሬን አሸኛኘት ዋናው ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው። ምክንያቱም ሰዎች ሳያውቁ ከአስክሬኑ ጋር የቀጥታም ሆነ የተዘዋዋሪ ንክኪ ሊፈጠሩ ይችላሉ። ከዚህም ባሻገርም በቀብርና በሐዘን ሥነ ሥርዓት ወቅት ሰዎች ስለሚሰበሰቡ በሽታው ከአንድ ሰው ወደ ሌላው ሊተላለፍ ይችላል። በመሆኑነም አስክሬን የሚሸኙ ሰዎች ቁጥር እጅግ ማነስ ያለበት ከመሆኑ በተጨማሪ አካላዊ ርቀትን መጠበቅና ጭምብል መጠቀም ያስፈልጋል። 3. የግብዓተ መሬት አፈጻጸም አንድ በኮቪድ-19 የሞተ ሰው አስክሬን ከተዘጋጀና ከተሸኘ በኋላ ግብዓተ መሬቱ ሲፈጸም ቀብሩን የሚከናውኑት ሰዎች ከሌሎች ጥንቃቄዎች ባሻገር ቢያንስ ጓንት ማድረግ አለባቸው። በሐይማኖታዊም ሆነ በሌላ ምክንያት አስክሬኑ በሳጥን የማይቀበር ከሆነ በወረርሽኙ የሞተ ሰው በአስክሬን ሻንጣ (በላስቲክ ተጠቅልሎ )መቀበር አለበት። በዚህ ሁኔታም ከሟቹ በድን አካል ላይ የሚመነጭ ፈሳሽ ለኖር ስለሚችል ጓንት፥ ተደራቢ ጋዎን እና ማስክና ማድረግ ሊያስፈልግ ይችላል።
50922707
https://www.bbc.com/amharic/50922707
ቡርኪናፋሶ፡ 'ተዋዶ ያለበት እስላም ክርስቲያኑ'
የፈረንጆች ገና ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ የቤተክርስቲያን ጥቃት የዓለም ሚዲያ ካሜራውን ቡርኪናፋሶ ላይ እንዲያጠምድ አድርጎታል። የቡርኪናፋሶ ታሪክ ግን ይህ አልነበረም።
አፎሳቶና ዴኒስ ልጃቸውን አቅፈው እንዲያውም ያቺ አገር ይበልጥ የምትታወቀው በሙስሊም-ክርስቲያን አብሮ የመኖር የዳበረ ልምዷ ነበር። ቡርኪናፋሶ ሙስሊሞች የሚበዙባት አገር ናት። ከክርስቲያን ወንድሞቻቸው ጋር የሚተቃቀፉ፣ ክርስቲያን እህቶቻቸውን የሚወዱ ሙስሊሞች የሚበዙባት አገር። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ጽንፈኞች እያመሷት ነው። • "በጎጃም ማርያም ቤተክርስቲያን ለመስጊድ 3ሺ ብር ረድታለች' ተባልኩኝ" ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ለምሳሌ ሰሞኑን እንኳ በገና ዋዜማ 30 ሰዎች እጅግ በሚዘገንን ሁኔታ ተገድለዋል። ያውም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ። ብዙዎቹ ታዲያ ሴቶች ናቸው። ይህን ጥቃት የፈጸሙት ጽንፈኛ ጂሃዲስቶች እንደሆኑ እየተነገረ ነው። ከዚያ ቀደም ብሎ ከሁለት ወራት በፊት በአንድ መስጊድ ላይ ጥቃት ተፈጽሞ 15 ሰዎች ተገድለው ነበር። መገናኛ ብዙኀን በነዚህ ጥቃቶች ዜና ተጋርደዋል። "የቡርኪናፋሶ እውነተኛ መልክ ግን ይህ አልነበረም" ትላለች ኡጋዱጉን የጎበኘቸው ባልደረባችን ክሌር ማክዱጋል። እንዲያውም ቡርኪናፋሶ ታሪኳ የሚያስቀና ነበር። ሙስሊምና ክርስቲያን በፍቅር አንድ ማዕድ የሚቋደስባት፣ በፍቅር የሚወዳጁበት ብሎም ሦስት ጎጆ የሚመሠረትባት አገር ነበረች። ልጃቸው አይሪስ የገና አባትን ፎቶ ይዛ "እንዲያው..." ትላለች ክሌር... "ከቡርኪናፋሶ ሕዝብ 23 ከመቶው ከሙስሊምና ክርስቲያን አማኞች በተፈጠረ ጋብቻ የተገኘ ነው።" ክሌር ይህንን የቡርኪናፋሶን የሃይማኖት አብሮነት ለማሳየት አንድ ኦጋዱጎ የሚገኝ ቤተሰብን መጎብኘት ብቻ በቅቷታል፤ እንዲህ ታስቃኘናለች። የአምስት ዓመቷ አይሪስ ኦስኒያ ኦታራ ያደገችው በካቶሊክ እምነት ተከታዩ አባቷ ዴኒስ ኦታዋ እና በሙስሊሟ እናቷ አፎሳቶ ሳኖ እየታቀፈች ነው። ገናን በድምቀት ታከብራለች። ኢድ ሲደርስ ደስታዋ ወደር የለውም። • ቤተ-ክርስቲያን ላይ በተፈፀመ ጥቃት በርካቶች ተገደሉ እንዲያውም ኡጋዱጉ በሚገኘው ቤታቸው ከተሰቀሉት ፎቶዎች አንዱ እሷ ትንሽዬ ልጅ ሳለች አባቷ የገና አባት ጋር ቆሞ የሚያሳይ ምስል ነው። አባቷ የክርስትና አስተምህሮትን ሊያሰርጽባት ሲሞክር እናቷ በበኩሏ ስለ ኢስላም መሠረታዊ ቀኖናዎች ታብራራላታለች። "ወደ መስጊድ ስሄድ አብራን ነው የምትሄደው፤ እሁድ እሁድ ደግሞ ከአባቷ ጋር ቤተክርስቲያን ትሳለማለች" ትላለች እናት አፎሳቶ። አፎሳቶ በቀን አምስት ጊዜ ሶላት ትሰግዳለች እናት አፎሳቶ በቀን አምስት ጊዜ ሶላት ትሰግዳለች። ጁምአ ጁምአ ግን ሁልጊዜም ከልጇ አይሪስ ጋር መስጊድ ይሄዳሉ። ልጇ አይሪስ ዘወትር ጠዋት ጠዋት የማለዳ ጸሎት ለማድረስ (ሱብሂ ሶላት) በጊዜ ከእንቅልፏ ትነሳለች። ይህ የሶላት ጊዜ ለብዙዎች ቀላል የሚባል አይደለም። • ቤተ ክርስቲያኒቱ 'አጭር ቀሚስ ለብሳችሁ ባትመጡ ደስ ይለኛል' አለች "ኢስላም የታጋሾች ሃይማኖት ነው፤ የመቻቻል እምነት ነው፤ ሌሎች ሰዎችን ባሉበት ሁኔታ መቀበል የሚችል እምነት ነው" ትላለች። ቤት ውስጥ አይሪስ ኢስላማዊ መጻሕፍትን ታነባለች። ከእነዚህ ኢስላማዊ መጻሕፍት ጎን ታዲያ መዝሙረ ዳዊት ተቀምጧል። ዴኒስና አፎሳቶ ላለፉት ስድስት ዓመታት አብረው ኖረዋል። የተገናኙት ከቡርኪና ፋሶ 2ኛ ከተማ ቦቦ ዲላሶ 55 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኝ ገጠራማ ቀበሌ ነበር። በተገናኙ በዓመቱ ለመጋባት ወሰኑ። ሠርጉ ታዲያ ኢስላማዊም ክርስቲያናዊም ነበር። "ልንጋባ ስንወስን ተቃውሞ አልደረሰብንም አልልሽም" ይላል ዴኒስ። የዴኒስ አባት መጀመርያ አካባቢ ነገሩን ተቃውመውት ነበር። በኋላ ግን ይሁና አሉት። አፎሳቶ፣ ዴኒስና ልጃቸው አይሪስ ቤታቸው በር ላይ "መጀመርያ አካባቢ ነገሩ በጣም የተወሳሰበ ነበር። እንዲያውም አባቴ ብዙም ችግሩ አልታየውም፤ ከእርሱ በላይ እናቴ ናት የተንገበገበችው" ትላለች እናት አፎሳቶ። በተለምዶ ወንዱ ክርስቲያን ከሆነና ሚስት ሙስሊም ከሆነች የሴቷ ቤተሰቦች ተቃውሞ ያነሳሉ። ለዚህም ይመስላል ዛሬም ድረስ የፎሳቶ እናት ጋብቻቸውን ያላጸደቁላቸው። • ሁለት እምነቶችን በአንድ ጣራ ለአስርታት ያሳደሩ ጥንዶች በርካታ የቡርኪናፋሶ ቤተሰቦች ከክርስቲያንና ሙስሊም ጋብቻ የተገኙ ናቸው። በዚያች አገር በአመዛኙ ሙስሊሞች ቤተክርስቲያን፤ ክርስቲያኖች መስጊድ ለመግባት አይከለከሉም። ቡርኪናፋሶ በዚህ በሃማኖት ተከባብሮና ፍቅር በመኖር እንደ ተምሳሌት የምትታይ አገር ናት። አፎሳቶ ለምሳሌ በርካታ ክርስቲያን ጓደኞች አሏት። በገና ቤተክርስቲያን ባትሄድም ቅሉ ከእናትና አባቷ ጋር ገናን ማክበሯ አልቀረም። ኡጋዱጉ ለምትገኘው የቢቢሲ ጋዜጠኛ እንደተናገረችው "እኔ ረማዳንንም፣ ኢድ አል-አድሃንም፣ ገናንም ግጥም አድርጌ ነው የማከብረው።" ቡርኪናፋሶ በሃይማኖት መቻቻል መልካም ስም ነበራት በገና ዕለት የካቶሊክ ካቴድራል በአጥቢያው ምዕመናን ይሞላል። እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ ወታደሮች ታዲያ ቤተ ክርስቲያኒቱ በር ላይ ዘብ ይቆማሉ። ምክንያቱ ደግሞ ጽንፈኛ ጂሃዲስቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አብያተ ክርስቲያናትንና አንዳንድ ሙስሊሞችን ጭምር ዒላማ ማድረጋቸው ነው። ይህን ስጋት ተከትሎ ከሰሞኑ ቀሳውስት ለምዕመኖቻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል። • በሞጣ የተፈጠረው ምንድን ነው? ትልልቅ ቦርሳ ይዛችሁት አትምጡ። አንዳች የተለየ እንቅስቃሴ ስታስተውሉ ለፖሊስ ሹክ በሉ ብለዋል። ከካቴድራሉ አቅራቢያ በርካታ ሰዎች የገና ዛፍ ላይ የውሸት በረዶ የሚመስል ፕላስቲክ እየጠመጠሙበት ይታያሉ። በገና ዕለት ክርስቲያኑ ዴኒስ ልጁን አይሪስን ወደ ኪንግ ክራይስት ቤተክርስቲያን ይዞ ይሄዳል። "ሃይማኖቴ የሚያስተምረኝ ፍቅርንና ሕዝቦችን ከነፍጥርጥራቸው መቀበልን ነው" ይላል የክርስትና አማኙ ዴኒስ። "በዚህ ድርጊቴ ሊዳኘኝ የሚችለው ፈጣሪ ብቻ ነው።" የሆነስ ሆነና የልጃቸው ሃይማኖት ምን ሊሆን ነው? የአይሪስ ወላጆች እንደሚሉት ልጃቸው አይሪስ ስታድግ የመረጠችውን ሃይማኖት እንድትከተል መብቷ የእርሷና የእርሷ ብቻ ነው። እስከዚያው ግን ሁለቱንም ሃይማኖቶች ማየት፣ ከቤተሰቧ ፍቅርን መመገብ አለባት። አባቷ ዴኒስም ሆነ እናቷ አፎሳቶ በልጃቸው ማንኛውም የወደፊት ውሳኔ ደስተኞች ለመሆን ዝግጁ ናቸው። ምክንያቱም ዴኒስ እንደሚለው "ፍቅር እኮ ከሁሉም ሃይማኖት በላይ ነው።"
41806712
https://www.bbc.com/amharic/41806712
ተዓምራዊቷ ቅድስት ማርያም ውቕሮ ገዳም
የትግራይ ምድር አቅፎ ከያዛችው ከ120 በላይ የሆኑት ከአለት ተፈልፍለው የታነፁት አብያተ ክርስትያን ለዛሬ አንዱን እናስተዋውቃችሁ።
የቅድስት ማርያም ውቕሮ ገዳም፤ ትግራይ ቅድስት ማርያም ውቕሮ ትባላለች። ወደ አካባቢው ለመድረስ በጣም አስቸጋሪ የጠጠር መንገድና ወንዝ መሻገር የግድ ነው። መኪናችን ወንዙን መሻገር አቅቷት ስትንገዳገድ የተመለከቱት የአከባቢው አርሶ አደሮች ተጠራርተው መንገዱን አስተካክለው አሻግረውናል። ወደ ገዳሙ ቅጥር ግቢ ከተገባ በኋላ መጀመርያ ከአለት የተሰራው ሙዳዬ ምጽዋት ይገኛል። የገዳሙ አስተዳዳሪ ቄስ ዘሚካኤል ወልደጊዮርጊስ ሙዳዬ ምጽዋቱን ከማለፋችን በፊት ጫማችንን እንድናወልቅ ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፉ። በሰንሰለት ዙርያ ጥምጥም የተቆለፈው የገዳሙን በር ከፍተው አስገቡን። የበሩ መዝጊያ ከአንድ የዛፍ እንጨት ብቻ እንደተዘጋጀ ለመረዳት አይከብድም። ቄስ ዘሚካኤል፤ ገዳሟ መቼና እንዴት እንደተቆረቆረች ይናገራሉ። "ይህች ገዳም ንግሥት ማርያም በ333 ጐንደር ላይ ሆነው በህልም ተገልፆላቸው ነበር የታነፀው። ደግሞ የሰው ልጅ በዶማ ቆፍሮ ነው ያነፀው በሉና እመኑ" ሲሉ አፌዙብን። ብታምኑም ባታምኑም 'አብ ሃነጸ ወልድ መንፈስ ቅዱስ' ራሱ መንፈስ ቅዱስ ነው ያነፃት ብለን ነው የምናምነው" ይላሉ። ገዳሟ ውስጥ የአንድ ትልቅ የጥድ ዛፍ ቁመት ያላቸው 44 ዓምዶች ይገኛሉ። በሌሎች ገዳማትና አድባራት እንደሚደረገው ሁሉ በቅድስት ማርያምም ወንዶችና ሴቶች ተለያይተው ነው የሚቀመጡት። በጣሪያው ላይ ሦስት እምነ አድማስ ነበሩ። አንደኛው ወድቆ እንድያውም ጣልያን ለመውሰድ ሞክሮ አልተሳካለትም። ሁለቱ እስከ አሁን ድረስ አሉ። ድንጋዩ ላይ በእብራይስጥ ቋንቋ የተፃፈ ፅሑፍም ይታያል። እምነ አድማስ ድንጋይን ለመቁረጥና ለመጥረብ ኃይል የተሰጠው የድንጋይ ዘር ነው። ገዳሟ ውስጥ ከሚታወቅ ይልቅ የማይታወቀው ስለሚበዛ ቄስ ዘሚካኤል ያስታወሱትንና የነገሩንን ብቻ አሳጥሬ ልንገራችሁ። በአንድ የገዳሟ ጓዳ ውስጥ ልጅ መውለድ የዘገየባችው እንስቶች ተቀምጠው ፈጣርያቸውን የሚለምኑበት ከአለቱ ተፈልፍሎ የተዘጋጀ ወንበር ይታያል። ከፊት ለፊቱ ደግሞ መባ የሚያስቅምጡበት መደርደርያ አለ። በአንደኛው የገዳሟ ክፍል የቅድስት ማርያም መንበረ ታቦት አለ። መንበረ ታቦቱ ራሱ ሙሉ ለሙሉ ከአለት ተፈልፍሎ ነው የተሰራው። ከመንበረ ታቦቱ አናት ላይ 4 ጉልላት ይታያል። ወደ መንበረ ታቦቱ ከካህንና ከዲያቆን ውጪ ምዕመን እንዲገባ አይፈቀድለትም። ገዳሟ ውስጥ የሚገኘው የጨለመው በር ፈለገ ኦር ይባላል። ሊቃውንቱ ጉድጓዱ ቀጥ አድርጐ እስራኤል ነው የሚያስገባው ብለው ያምናሉ። ድሮ ነው አሉ 5 ካህናት ማሾና ጧፍ ይዘው ገብተው በዛው አልተመለሱም ብለውናል። መሪጌታ ቁጭ ብሎ ወደ ታቦቱ እያየ የሚጸልይበት ዙፋንም ተቀርጾ ይታያል። ዙፋኑ ከላይ ዘውድ አለበት፤ ይህም ከአለት ተፈልፍሎ ነው የተዘጋጀው። ገዳሟ ውስጥ የተለያየ ትርጉም ሊሰጣቸው የሚገቡ 5 ጉልላት አሉ፤ የኮከቦች ተምሳሌት ብለው የሚጠሩዋቸው ቅርፆችም አሉ። የገዳሟ የበር መዝጊያዎች ከእየሩሳሌም በቀስተ ደመና ተጠፍረው እንደመጡ ይነገራል። ገዳሟ በር የሌላቸው 12 መስኮቶችም አሉት። ልክ እንደ መንበረ ታቦቱ ከካህንና ዲያቆን ውጪ ሌላው ምዕመን የማይገባበት ቤተልሔምም አለ። በአንድ ትልቅ አለት ላይ ሆኖ ከቅድስት ማርያም በተጨማሪ የቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም አለ። ገዳሟ መወጣጫ አልነበራትም። በቅርቡ አንድ ምግባረ ሰናይ ግለሰብ ከብረት የተዘጋጀ መሰላል አሰርቶላታል። ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም የሚያስወጣ መሰላል የቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም መስኮተ አብርሃምን ጨምሮ 6 መስኮቶች አሉዋት። በመስኮተ አብርሃም በኩል አሻግሮ የቅድስት ማሪያም መንበረ ታቦትን ማየት ይቻላል። ሁለቱ ገዳማት ተአምራዊ የጥበብ ሥራ እንዳረፈባቸው ፍንትው ብሎ ይታያል። እነኝህን ታሪካዊ ገዳማት በእንግዶች እንዳይጐበኙ ወደ አከባቢው የሚወስደው የመኪና መንገድ አይመችም። ሌላው ቀርቶ ወንዙን በቀላሉ ለመሻገር እንኳን ድልድይ አልተሰራለትም። የወረዳው አስተዳደር ድልድዩን ለመስራት ሽርጉድ ሲል ተመልክተናል። ትግራይ ምድር ውስጥ የሚገኙት አብዛሃኛዎቹ ገዳማት በየተራራውና ሸንተረሩ ስለሚገኙ መሰረተ ልማት ካልተሟላላቸው በእንግዶች ሊጐበኙ አይችሉም። መንግሥት በዚህ ዙርያ ብዙ መስራት ይጠበቅበታል። ሌላው ቀርቶ ገዳማቱን ለማየት የሚሄዱት እንግዶች የሚያርፉበት መጠለያ እንኳን የላቸውም። ባለሃብቶችም መዋዕለ ንዋያቸውን በዚሁ ዙርያ እንድያውሉ ማበረታትና ሁኔታውን ማመቻቸት ይጠበቃል። ገደማቱም ጥገናና እንክብካቤ ይሻሉ። ከዚህ ውጭ የቅድስት ማሪያም ውቕሮ ተአምራዊ ናት ከማለት ባለፈ የተሰነደ ማስረጃ እንኳን የላትም።
news-52328126
https://www.bbc.com/amharic/news-52328126
ኮሮናቫይረስ፡ ኢኳዶር በአንድ ቀን ከ5ሺህ በላይ ሞት ያስመዘገበችው አገር
በኮሮናቫይረስ ክፉኛ ከተጠቁት አንዷ የኢኳዶሯ ግዛት ጉዋያ ናት፤ የሞት ጥላም ከቧታል። በአንድ ምሽት አምስት ሺህ ሰዎች ሞተዋል።
በከተማዋ መንገድ ላይ የተጣለ አስከሬን በዚህ በያዝነው ወር በሁለት ሳምንት ብቻ 6700 ሰዎች ሞተዋል። በግዛቷ ውስጥ በቀደመው ጊዜ በየወሩ ከሚመዘገበውም የሟች ቁጥር በአምስት ሺ ይበልጣል ተብሏል። ይህም ቁጥር ግዛቲቱን በአገሪቷ ብቻ ሳይሆን በላቲን አሜሪካ ውስጥ ቀዳሚ አድርጓታል። እነዚህ ሞቶች ግን በኮቪድ-19 ምክንያት ብቻ አይደለም። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የጤና ሥርዓቷ ፍርስርሱ ሲወጣ በሌሎች በሽታዎች በጠና ታመው የነበሩ ህሙማን የጤና ማዕከላትን እርዳታ ሳያገኙ ህይወታቸውን አጥተዋል። ጉያኩል፤ የሞት ከተማ በጉዋያ ግዛት ያለችውና የኢኳዶሯ ትልቅ ከተማ ጉያኩል ለቅሶ፣ ሃዘን፣ ግራ መጋባት ወሯታል። "የሞቱ ሰዎችን በመኪኖች፣ በአምቡላንስ፣ በቤታቸቸው፣ በየጎዳናው፣ በየቦታው ተረፍርፈው አግኝተናል" ይላሉ የቀብር አስፈፃሚዋ ካቲ መካ። "ሆስፒታል በነበረ የአልጋ እጥረት ምክንያት ተኝተው መታከም አልቻሉም። የግል ክሊኒኮችም ወጪ ከፍተኛ ነው። ሁሉም ሰው መክፈል ይችላል ማለት አይደለም" ይላሉ። 2.5 ሚሊዮን ሕዝብ በሚኖርባት ግዛት ያሉ መካነ መቃብሮችም ሆነ የቀብር አስፈፃሚዎች አስከሬኖቹን የመቅበር ሥራ ከአቅማቸው በላይ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ ቫይረሱ ይይዘኛል የሚልም ስጋት አለ። ተስፋ የቆረጡና የቤተሰቦቻቸውን አስከሬን ምን ውስጥ እንደሚያስገቡት ጭንቅ ጥብብ ያላቸው በየቤታቸው በር ላይ አስቀምጠዋቸዋል። አስከሬኖች በሚያሰቅቅ ሁኔታ ከሞቱበት እልጋ ለቀናት ያህል ተጣብቀው ይገኛሉ። ለከተማዋ ታይቶ ተሰምቶ በማያውቅ ሁኔታ ይህን ያህል ሰው በመሞቱ የመካነ መቃብር እጥረትም አጋጥሟል። ወደ ጎረቤት ከተሞችም አስከሬኖች ለቀብር ተልከዋል። በከተማዋ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው ህይወቱ አልፏል ቦታ ብቻ ሳይሆን የአስከሬን ሳጥንም ችግር በማጋጠሙ በከርቶን ውስጥ አስከሬኖቹን ተደርገው ለመቅበር ተገደዋል። እስረኞችም ጣውላ በመጥረብ የአስከሬን ሳጥን እየሰሩ ነው። የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሌኒን ሞሬኖ አገራቸው ያጋጠማትን ድንገተኛ የጤና ቀውስ ሳትወጣ ቀርታለች ብለዋል። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ መንግሥት በአጠቃላይ በአገሪቱ በኮሮናቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 400 ነው እያለ ነበር። ነገር ግን በመንግሥት ስር ያለው የኮሮናቫይረሰ ጥምር ግብረ ኃይል ሁሉንም መረጃዎች ሲሰበስብ መንግሥት ከሚለው ጋር በፍፁም ተቃራኒና፤ የሰማይና የምድር ያህል የተራራቀ ነበር። "ከተለያዩ መስሪያ ቤቶች እንዲሁም ከመካነ መቃብሮች ያገኘነው መረጃ የሚያሳየው 6ሺ703 ሰዎች በሁለት ሳምንት መሞታቸውን ነው" ይላሉ ጆርጅ ዋትድ የጥምሩ ግብረ ኃይል ኃላፊ። "ቀድሞ በከተማዋ በየወሩ የሚሞተው ሰው ቁጥሩ 2 ሺህ ነበር። ስለዚህ 5700 ሰዎች ከነበረው በተጨማሪ ሞተዋል" ይላሉ። ሁሉም የሞቱት በኮሮናቫይረስ አይደለም፤ በልብ ድካም፣ በኩላሊት ህመም እንዲሁም በሌሎች በሽታዎች የሞቱ ሰዎች አሉ። ይፋዊ የሆነው ቁጥርና መሬት ላይ ያለው እውነታ ክፍተት አሰቃቂ ሐቆችን ፍንትው አድርጎ አውጥቷል። በተጨማሪም ይሄንን ያህል ቁጥር ያለው ሰው መሞቱም በርካታ ጥያቄዎችን አጭሯል። በተለያዩ ላቲን አሜሪካ አገራትስ እንዲሁም የጤና ሥርዓታቸው ደካማ በሆነባቸው አገራት እንዲህ አይነት አሰቃቂ ክስተት ይከሰት ይሆን? የሚለውም አስደንጋጭ ሆኗል። የቫይረሱ መነሻ የሆነችው ዉሃንም ቀደም ሲል በበሽታው ሞተውብኛል ያለቻቸው ሰዎች አሃዝ ላይ 1290 በመጨመር በ50 በመቶ ከፍ ብሏል። የከተማዋ ባለስልጣናት እንዳሉት ይህ አሃዝ ሊጨምር የቻለው አዲስ በተገኙ ቁጥሮችና ከሆስፒታል ውጪ የሞቱ ሰዎችን በማካተቱ ነው። በቫይረሱ ክፉኛ በተጠቃችበት ስፔንም በብሔራዊ ደረጃ የሚነገሩ አሃዞችና ከተለያዩ አካባቢዎች የሚሰብስቡ መረጃዎች ላይ ከፍተኛ ልዩነት አለ። "የኢኳዶር የጤና ሥርዓት ደካማ ነው። መንግሥት ትኩረት ያልሰጠበት ዘርፍ ነው" በማለት ዶክተር ካርሎስ ማውይን ለቢቢሲ ተናግረዋል። በኢኳዶር ላይም ያለውን የኮቪድ-19 ቀውስንም ማዕበል ብለውታል። "በደከመ የጤና ሥርዓት ይህንን ያህል ቁጥር ያለው በሽተኛ ሲመጣ፤ የአገሪቱን የጤና ሥርዓት አሽመድምዶታል። የፅኑ ህሙማን ህክምናንም አፈራርሶታል" ብለዋል። ኢኳዶር ቫይረሱን ለመቆጣጠር የሰዓት እላፊን ማወጅ እንዲሁም በርካታ ህመምተኞችን እመረምራለሁ ብትልም፤ የሚወዷቸው ሰዎች ከአይናቸው ለተነጠቁባቸው የግዛቷ ነዋሪዎች ይህ ምንም የሚፈይደው ነገር የለም እየተባለ ነው።
news-52913218
https://www.bbc.com/amharic/news-52913218
የኮቪድ-19 ክትባት ለድሃ አገሮች በፍጥነት እንዲደርስ የ2 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈረመ
ግዙፉ መድኃኒት አምራች አስትራዜኔካ ሁለት አዳዲስ ስምምነቶችን ተፈራርሟል፡፡ ስምምነቶቹ ኩባንያው በአንድ ጊዜ ለኮሮናቫይረስ ክትባት 2 ቢሊዮን ጠብታዎችን ለማምረት የሚያስችለው ነው ተብሏል፡፡
ባለፈው ወር አስትራዜኒካ በአንድ ጊዜ 1 ቢሊዮን ጠብታዎችን ማምረት እንደሚችል ተናግሮ ነበር፡፡ ይህም በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ለተያዘውና ተስፋ ለተጣለበት የኮቪድ-19 ክትባት ምርምር የተደረገ ዝግጅት ነው፡፡ ትናንት ሐሙስ ግን ተጨማሪ ሁለት አዳዲስ ስምምነቶችን የተፈራረመ ሲሆን ከዚህም ውስጥ አንዱ በቢለጌትስ የሚደገፍ ነው፡፡ የእንግሊዙ አስትራዜኒካ በቅልጥፍና ያመርተዋል የተባለው ይህ የኮሮናቫይረስ ክትባት መድኃኒት በዋናነት እንዲደርስ የታሰበው ደግሞ መካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው አገሮች ነው፡፡ አስትራዜኒካ በበኩሉ ለፍጥነት እንዲረዳው ከሌሎች ሁለት ኩባንያዎች ጋር ስምምነት አድርጓል፡፡ ከነዚህ ውስጥ የመጀመርያው ሴሩም ኢንዲያ ጋር ሲሆን ይህ መድኃኒት አምራች በዓለም ላይ መድኃኒትን በከፍተኛ መጠን በማምረት አቅሙ ተስተካካይ የለውም፡፡ ሁለተኛውም ስምምነት የተደረገው ደግሞ ከቢል እና ሚሊንዳ ጌትስ ጋር በቅንጅት ከሚሰሩ ሌሎች ሁለት ድርጅቶች ጋር ነው፡፡ ይህም የ750 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ማዕቀፍ ነው፡፡ ሁለቱ ቢል እና ሚሊንዳ ጌትስ የሚደገፉት በጎ አድራጎት ድርጅቶች ጋቪ እና ሴፒ የሚባሉ ሲሆን 300 ሚሊዮን ብልቃጥ ክትባት የማምረት ሂደቱን እንዲያሳልጡና የምርት ግብአቶችን እንዲያቀርቡ ያስችላቸዋል፡፡ የክትባት መድኃኒቱ በዚህ ዓመት መጨረሻ ይደርሳል ተብሎ በከፍተኛ ጉጉት እየተጠበቀ ነው፡፡ የአስትራዜኔካ ሥራ አስፈጻሚ ፓስካል ሶሪዮት ለመገናኛ ብዙኃን እንደገለጹት በነሐሴ መጨረሻ ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ እየሞከረው ያለው ክትባት ውጤታማነት ይረጋገጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የሴፒ ሥራ አስፈጻሚ በበከላቸው ይህ ክትባት ላይሰራም የሚችልበት ዕድል እንዳለ መገንዘብ ያሻል ብለዋል፡፡ አስትራዜኔካ ከህንዱ ግዙፍ መድኃኒት አምራች ‹‹ሴሩም ኢንዲያ›› ጋር ያደረገው ስምምነት በአንድ ጊዜ አንድ ቢሊዮን የክትባት ብልቃጥ የማምረት ስምምነት ሲሆን ይህም በዋናነት ለመካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው አገራት የሚሆን ነው፡፡ በዚህ ስምምነት ማእቀፍ ውስጥ ሴሩም ኢንዲያ 400 ሚሊዮን የክትባት ጠብታ የፈረንጆቹ 2020 ከመጠናቀቁ በፊት ማድረስ ግዴታ ይኖርበታል፡፡ የአስትራዜኒካ ሥራ አስፈጻሚ ሚስተር ሶሪዮት እንደተናገሩት በቅድሚያ 300 ሚሊዮን የክትባት ጠብታዎች የሚላኩት ወደ አሜሪካ ሲሆን 100 ሚሊዮን ደግሞ ለዩናይትድ ኪንግደም የተያዘ ነው፡፡ ይህም በመስከረም እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ እርሳቸው ጨምረው እንዳስገነዘቡት ድርጅታቸው አስትራዜኒካ በወረርሽኙ ወቅት ለሚፈበረኩ የክትባት ጠብታዎች ምንም ዓይነት ትርፍ የማጋበስ ዓላማ አልተያዘም፡፡ ‹‹ ይህ በመላው ዓለም የመጣ መቅሰፍት ነው፤ ለሰው ልጆች ሁሉ ፈተናን የደቀነ ነው፤ በዚህ ወቅት ስለ ትርፍ ልናስብ አንችልም ብለዋል፡፡ ይህ ክትባት ፍቱንነቱ ከተረጋገጠ ለዘመናት የሰው ልጆች የሚወስዱት ክትባት ስለሚሆን ምናልባት በዚህ የመጀመርያ የወረርሽኙ ወቅት ኩባንያዎች ትርፍን ታሳቢ ላያደርጉ የሚችሉበት እድል ሰፊ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ በዚህ ላይ የዓለም መንግሥታት ለዚህ በጉጉት ለሚጠበቀው የኮቪድ-19 ክትባት ማግኛ እና ማምረቻ የሚሆን ቢሊዮን ዶላሮችን ለማዋጣት ቃል ገብተዋል፤ እያዋጡም ነው ያሉት፡፡ በተመሳሳይ በርካታ ቤተ ሙከራዎች እና መድኃኒት አምራቾች ውጤታማውን ክትባት ቀድሞ ለማግኘት በከፍተኛ እሽቅድምድም ላይ ናቸው፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬ ትናንት ሐሙስ ባስተላለፉት መልእክት ‹‹ እየጠበቅነው ያለነው ክትባት መታየት ያለበት ለሁሉም የሰው ልጆች በእኩል የሚደርስ የሕዝብ ክትባትን ነው›› ካሉ በኋላ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በየአቅሙ ርብርብ እንዲያደርግም ተማጽነዋል፡፡
news-47250806
https://www.bbc.com/amharic/news-47250806
አብዱል ፋታህ አልሲሲ እስከ 80 ዓመታቸው ግብጽን ሊገዙ ይችላሉ
የግብጽ ምክር ቤት አልሲሲን ለሚቀጥሉት 12 ዓመታት በርዕሰ ብሔርነት እንዲቀጥሉ የሚያስችላቸውን ረቂቅ በፍጹም አብላጫ ድምጽ ደገፈ። ይህ የሕገ መንግሥት ለውጥን የሚያስከትለው ረቂቅ ውሳኔ ከ596 የግብጽ ሸንጎ እንደራሴዎች 485 የሚሆኑት ደግፈውታል።
አብዱል ፋታህ አል-ሲሲ እንደ ጎርጎሮሲያዊያኑ በ2022 ሁለተኛ ምዕራፍ የሥልጣን ዘመናቸው እንደሚያበቃ ይጠበቅ ነበር። ሕግ አውጪው ሸንጎ ግን ለጊዜው ሁለት ዓመት ጨምሮላቸዋል። ከዚያ በኋላ ባሉ ዓመታትም በሥልጣን እንዲቆዩ ለሚያስችለው ረቂቅም ድጋፉን ሰጥቷል። • ''የተፈጥሮ ሃብታችንን ለመጠቀም የማንንም ይሁንታ አንጠብቅም'' በርካታ የግብጽ ሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች ውሳኔውን ክፉኛ ኮንነውታል። ይህ ረቂቅ ሕግ በድጋሚ ለፓርላማ ከቀረበ በኋላ ጸድቆ ይሁንታን ካገኘ ሕዝበ ውሳኔ እንደሚደረግበት ይጠበቃል። ረቂቅ ሕጉ ምን አዲስ ነገር አለው? በ2014 በሕዝበ ውሳኔ ጸድቆ የነበረው የግብጽ ሕገ መንግሥት 'አንቀጽ-140' ተመራጩ ርዕሰ ብሔር ከሁለት የአራት ዓመት የአገዛዝ ምዕራፍ በላይ በሥልጣን እንዳይቆይ ያስገድዳል። ነገር ግን አሁን በቀረበው ረቂቅ ርዕሰ ብሔሩ ከዚያም በላይ በሥልጣን እንዲቆይ ያስችለዋል። በዚህም መሠረት የ64 ዓመቱ አልሲሲ እንደ ፈረንጆቹ እስከ 2034 መንበራቸው አይነቃነቅም። በዚያን ጊዜ ዕድሜያቸው ወደ ሰማንያ ይጠጋል ማለት ነው። • ግብጻዊቷ ዘፋኝ አባይ ላይ ቀልደሻል ተብላ እስር ተፈረደባት በረቂቅ ሕጉ መሠረት የአልሲሲ የሥልጣን ዕድሜ ዘለግ ባለ ዓመታት መለጠጡ ብቻ ሳይሆን ዳኞችና አቃቤ ሕጉን የመሾም ልዩ ሥልጣንንም ያጎናጽፋል። ረቂቁ ከአል-ሲሲ ባሻገር ለመከላከያ ሠራዊትም ተጨማሪ ኃላፊነቶችን ይሰጣል። አዲሱ ረቂቅ አዲስ የታችኛው ምክር ቤት እንዲቋቋም፣ የፓርላማው መቀመጫ 25 እጅ ለሴቶች እንዲሰጥ፣ ተገቢ ውክልና ለኮፕቲክ ክሪስቲያን አማኞች እንዲቀርብ ያደርጋል። ሕዝቡ ምን አለ? በምክር ቤቱ የአልሲሲ ደጋፊዎች እንደሚሉት የሥልጣን ዕድሜ መራዘሙ ሲሲ የጀመሯቸውን የምጣኔ ሀብት ማሻሻያዎችን ከዳር እንዲያደርሱ ያስችላቸዋል። ተቃዋሚዎች በበኩላቸው ረቂቁ ለዲሞክራሲ አደጋ ነው ይላሉ። አስራ አንድ የሚሆኑ የሰብአዊ መብት ተቋማት በጋራ በሰጡት መግለጫ ረቂቁን 'አምባገነንነትን በወርቅ የመለበጥ ሙከራ' ሲሉ ተችተውታል። • ሴቶችን ከመንቀሳቀስ የሚያግደው መተግበሪያ ሊመረመር ነው ጥቂት ቢሆኑም የሕግ አውጪው ሸንጎ አባላትም ድምጻቸውን አሰምተዋል። "ሁሉንም ሥልጣኖች በአንድ ሰው መዳፍ እያስጨበጥን ነው። ይህ እየሆነ ያለውም ሕዝባችን ዳቦ፣ ነጻነትና ማኅበራዊ ፍትህን እንድናቀርብለት እየጠበቀን ባለበት ጊዜ መሆኑ ያሳዝናል" ብለዋል አሕመድ ታንታዊ የተባሉ የሕዝብ እንደራሴ። አልሲሲ እንደ ጎርጎሮሲያዊያኑ በ2013 በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን ከያዙ በኋላ የተቃውሞ ድምጾችን ሁሉ በመደምሰስ የድጋሚ ምርጫን 97 በመቶ ድጋፍ አግኝቼ አሸንፊያለሁ ብለው ካወጁ ጥቂት ዓመታት ተቆጥረዋል።
news-50258997
https://www.bbc.com/amharic/news-50258997
አይኤስ አል ባግዳዲን የሚተካውን አዲስ መሪ ይፋ አደረገ
እስላማዊው ቡድን አይኤስ መስራቹና መሪው አቡባካር አል ባግዳዲ መገደሉን ለመጀመሪያ ጊዜ አረጋግጦ ቡድኑን በመምራት የሚተካውን ሰው ስም ይፋ አድርጓል።
የአይኤስ መልዕክት ማስተላለፊያ በሆነው የቴሌግራም መድረክ ላይ ቡድኑ እንዳስታወቀው አዲሱ መሪና "ካሊፋ" አቡ ኢብራሂም አል ሐሼሚ አል ቁራሺ መሆኑን ገልጿል። የአሜሪካ ልዩ ኃይሎች ባለፈው እሁድ በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ ውስጥ አል ባግዳዲ ያለበትን ካወቁ በኋላ ባካሄዱት ዘመቻ ነበር የአይኤስ መሪው እንደሞተ የተገለጸው። • የአይ ኤስ መሪ አቡ ባካር አል ባግዳዲ ማነው? • የአይኤሱ መሪ አቡ ባክር አልባግዳዲ እንዴት ተገደለ? አል ባግዳዲ የአሜሪካኖቹን ክትትል በመሸሽ ከመሬት በታች ወዳለ መተላለፊያ በመግባት ነበር የታጠቀውን ቦንብ አፈንድቶ ራሱን ያጠፋው። ኢራቃዊው አልባግዳዲ አይኤስን መስርቶ ጥቃቶችን በማድረስ እውቅናን ካገኘበት ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ አሜሪካና አጋሮቿ ያለበትን ለጠቆመ 25 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ለማበርከት ቃል ገብተው ሲፈልጉት ቆይተው ነበር። አይኤስ ሐሙስ ዕለት የቃል አቀባዩ አቡ አል ሐሰን አል ሙሐጂርን ሞት አረጋግጧል። የሳኡዲ አረቢያ ዜጋና አልባግዳዲን ሊተካ ይችላል ተብሎ ይታሰብ የነበረው አል ሙሐጂር በሰሜናዊ ሶሪያ በአሜሪካና በሶሪያ የኩርድ ኃይሎች በተካሄደውና አል ባግዳዲን ኢላማ ካደረገው ጥቃት ከሰዓታት በኋላ ነበር የተገደለው። አዲሱ የአይኤስ ቃል አቀባይ አቡ ሐምዛ አል ቁራሺ፤ ሁሉም ሙስሊሞች ለአዲሱ የአይኤስ መሪ አቡ ኢብራሂም አል ሐሼሚ ታማኝነታቸውን እንዲያረጋግጡ ጥሪ አቅርቧል። • ኡጋንዳ የጠፉት ኤርትራውያን ኳስ ተጫዋቾች ስጋት ላይ ነን አሉ • ትዊተር የትኛውንም የፖለቲካ ይዘት ያለው ማስታወቂያ ሊያግድ ነው የአል ባግዳዲ ምትክ እንደሆነ የተነገረው የሐሼሚ ስም በደህንነት ተቋማት የማይታወቅ ሲሆን፤ ምናልባትም በቡድኑ ውስጥ ያለው መለያው ሊሆን እንደሚችል ይታመናል። አይኤስ ስለአዲሱ መሪው ሐሼሚ ዝርዝር መረጃንም ሆነ ማንነቱን የሚያሳይ ፎቶም ይፋ አላደረገም። ነገር ግን "በጂሃዳዊ እንቅስቃሴው ውስጥ ዋነኛ ሰው" እንደሆነ ተገልጿል። ከቡድኑ በወጣው መግለጫ፤ ሐሼሚ ቀደም ሲል አሜሪካንን በመዋጋት ልምድ ያለው የጂሃድ ተዋጊ እንደሆነ ተገልጿል።
news-52357580
https://www.bbc.com/amharic/news-52357580
የ68 ዓመቷ ናይጄሪያዊት አዛውንት መንታ ልጆች ተገላገሉ
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዜና የመገናኛ ብዙሃንን ባጨናነቀበት በአሁኑ ወቅት ከወደ ናይጄሪያ የተሰማው ዜና ብዙዎችን እያነጋገረ ነው።
ክስተቱ አዲስ ባይሆንም ብዙም የተለመደና የሚጠበቅ አይደለም፤ አንዲት ወደ 70 ዓመት የተቃረቡ አዛውንት ለወራት አርግዘው ጨቅላ ህጻናትን ታቅፈዋል። በዚህም የናይጄሪያው የሌጎስ ግዛት ዩኒቨርሲቲ መማሪያ ሆስፒታል አንዲት የ68 ዓመት እናትን መንታ ልጆች በሰላም እንዲገላገሉ ማድረጉን አስታቋል። የዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሉ የህክምና አማካሪዎች ቡድን ሊቀ መንበር የሆኑት ፕሮፌሰር ዋሲኡ አዲዬሞ እንዳሉት የ68 ዓመቷ እናት በተሳካ ሁኔታ መንታ ህፋናትን የወለዱት ትናንት እሁድ ነው። አዛውንቷ እናት መንታ ልጆቻቸውን የወለዱት በ37ኛ የእርግዝና ሳምንታቸው በቀዶ ህክምና መሆኑንም ዩኒቨርስቲው ጨምሮ ገልጿል። ከተሳካው የቀዶ ህክምና ማዋለድ በኋላ አራሷ የ68 ዓመቷ እናት እና ልጆች በጥሩ የጤንነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙም ተነግሯል። መውለድ አይቻልም በሚባልበት የዕድሜ ክልል የሚገኙት እናት ቀደም ሲል ምንም ልጅ ያልነበራቸው ሲሆን ትናንት የተገላገሏቸው መንታ ህጻንት የመጀመሪያ ልጆቻቸው ናቸው ተብሏል። ይህንንም ፕሮፌሰር ዋሲኡ አዲዬሞ የእኚህ እናት እርግዝና የመጀመሪያቸው መሆኑን ለናይጄሪያ የዜና የዜና አገልግሎት ተናግረዋል።
news-53135326
https://www.bbc.com/amharic/news-53135326
"የቻይናና የአሜሪካ ቀዝቃዛው ጦርነት ከኮሮናቫይረስ በላይ ለዓለም ያሰጋል"
በመጪዎቹ ዓመታት በአሜሪካና በቻይና መካከል ሊከሰት የሚችለው ቀዝቃዛ ጦርነት ዓለምን ከኮሮናቫይረስ በላይ ሊያስጨንቅ እንደሚገባ ዕውቁ የምጣኔ ሀብት ሊቅ ጄፍሪ ሳክስ ተናገሩ።
የኮሎምቢያው ዩኒቨርስቲ ዕውቅ ፕሮፌሰር ጄፍ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ዓለም ወደ አንዳች መደነቃቀፍ እያመራች ነው፤ መሪ አልባም ሆናለች ብለዋል። እንዲሁም የዓለም ሁኔታ መልክ ባልያዘበት ሁኔታ በሁለቱ የዓለም ኃያላን መካከል ያለው ቁርሾና ቅራኔ እየባሰ ከሄደ ሁኔታዎችን ያባብሳል፤ ጦሱም ለተቀረው ዓለም ይተርፋል ብለዋል። እኚህ ፕሮፌሰር ለዚህ ሁሉ ተጠያቂዋ አሜሪካና አመራሯ ነው ብለዋል። • አገራዊ መድረክ ማዘጋጀት እንጂ ከህወሓት ጋር በድብቅ የሚደረግ ውይይትን አንቀበልም፡ ደብረፅዮን (ዶ/ር) • "አባላቶቻችን በአካባቢው ይህን የደንብ ልብስ መልበስ ካቆሙ ስድስት ወራት አልፈዋል" የኦሮሚያ ፖሊስ አሁን ያለው የአሜሪካ አመራር ከትብብር ይልቅ ክፍፍልን የሚያፋፍም ነው ሲሉም ለቢቢሲ ተናግረዋል። "አመራሩ አዲስ ቀዝቃዛ ጦርነት ከቻይና ጋር ለመፍጠር እየሞከረ ነው። ይህ ከሆነ ደግሞ ዓለምን ዳግም ወደ ሰላም ለመመለስ በጣም ይቸገራል" ብለዋል ፕሮፌሰሩ። የፕሮፌሰር ጄፍሪ ሳክስ አስተያየት የመጣው ሰሞኑን ቻይናና አሜሪካ ከምጣኔ ሀብት ጦርነት ጋር ብቻም ሳይሆን ፖለቲካዊ መቆራቆዝ ውስጥ እየገቡ ስለመሆኑ ምልክቶች መታየታቸውን ተከትሎ ነው። በያዝነው ሳምንት ለምሳሌ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ በቻይና ባለሥልጣናት ላይ ማዕቀብ የሚጥለው ሰነድ ላይ ይፈርማሉ ተብሏል። ማዕቀቡን የሚጥሉት በዢንጂያንግ ግዛት የቻይና ሙስሊሞችን ለርዕዮተ ዓለም ጥምቀት ማጎርያ ውስጥ መከተታቸውን ተከትሎ ነው። ያም ሆኖ የዶናልድ ትራምፕ የቀድሞው የደኅንነት አማካሪ ሰሞኑን ለአንባቢዎች ያደርሱታል በተባለው አዲስ መጽሐፋቸው እንደጠቀሱት፤ ፕሬዝዳንቱ ቻይና ይህንን የሙስሊሞች ማጎርያ እንድትገነባ አበረታተው ነበር። ዶናልድ ትራምፕ ከሰሞኑ ከዎልስትሪት ጆርናል ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ቻይና ኮሮናቫይረስን ለዓለም ያቀበለችውና ብሎም ያሰራጨችው ሆን ብላ የአሜሪካንን ምጣኔ ሀብት ለማንኮታኮት ነው ሲሉ ተናግረዋል። የቻይናና የአሜሪካንን የኢኮኖሚ ጦርነት ካመላከቱ ነገሮች አንዱ አሜሪካ በቻይናው ግዙፍ የቴሌኮም ኩባንያ ሁዋዌ ላይ የጣለችው እቀባ ነው። አሜሪካ እንደምትለው ሁዋዌ የደንበኞችን መረጃ ለመሰለል የተቋቋመ ነው። ቻይና ይህንን ክስ ታስተባብላለች። አሜሪካ በቻይናው ተቋም ሁዋዌ ላይ ጥርጣሬ አላት የቀድሞው የዶናልድ ትራምፕ ከፍተኛ የደኅንነት አማካሪ ጆን ቦልተን አዲስ በጻፉት መጽሐፍ እንዳጋለጡት ከሆነ ዶናልድ ትራምፕ ህዋዌ ላይ እቀባ ያደረጉት በድጋሚ የመመረጥ ዕድላቸውን ለማስፋት ብቻ ነው። • ትራምፕ እንዳይታተም ባሉት መጽሐፍ ይፋ የሚደረጉ 6 ምስጢሮች • በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የሚደረገው ድርድር፡ የግብፅ ፍላጎትና የኢትዮጵያ ውሳኔ ፕሮፌሰር ጄፍሪ ሳክስም በዚህ የቦልተን ሐሳብ ይስማማሉ። ሁዋዌን ትራምፕ ያገዱት የምርም የደኅንነት ጉዳይ አሳስቧቸው ሊሆን አይችልም። "አሜሪካ በ5ጂ የሞባይል ቴክኖሎጂ ተቀድማለች። ሁዋዌ ደግሞ የዓለምን የገበያ ድርሻ ተቀራምቶታል፤ ይህ ነው አሜሪካንን የረበሻት" ይላሉ። ከቻይና ጋር ፍጥጫ ላይ ያለችው አገር አሜሪካ ብቻ አይደለችም። ቻይና ባለፈው ሳምንት ከሕንድ ጋር የድንበር ግጭት ውስጥ ገብታ 20 የሕንድ ወታደሮችን መገደላቸው አይዘነጋም። ይህ በእንዲህ እናዳለ ቻይና በፓኪስታን፣ በምያንማር፣ በሲሪሊንካና በኔፓል በርካታ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን እያገዘች ነው። እነዚህ አገራት ደግሞ የሕንድ ጎረቤቶች ናቸው። ሕንድ ቻይና የአካባቢው ተጽእኖ ፈጣሪ አገር የመሆኗን ጉዳይ ማስቆም ትፈልጋለች። ፕሮፌሰር ሳክስ እንደሚያምኑት ቻይና በአካባቢው አገራት ላይ የትብብር መንፈስ ካሳየች ነገሮች የተሻሉ ይሆናሉ። ቻይና እድሏ ያለው በእጇ ነው። ቻይና ተባባሪ ከሆነች፣ በዲፕሎማሲ ችግሮችን ለመፍታት ከፈለገችና የትብብር መንፈስ ካሳየች ጉልበት ያላት አገር ስለሆነች ብዙ ነገር መቀየር ትችላለች፤ የእሲያ አህጉርም የተሻለ መጻኢ እድል ይኖረዋል።
44544720
https://www.bbc.com/amharic/44544720
"የኢትዮጵያ ህዝብ ከኤርትራ ጋር ሰላም እንዲኖር መፈለጉ አዲስ ነገር አይደለም" ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ
ኢትዮጵያ የአልጀርስ ስምምነት መቀበሏን ተከትሎ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ አንድ የልዑካን ቡድን ወደ አዲስአበባ እንደሚልኩ ገልፀዋል።
ፕሬዚዳንቱ ይህንን ያሉት ዛሬ በኤርትራ ቴሌቪዥን የሰማዕታት ቀንን አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር ሲሆን ጉዳዩን በቀጥታና በጥልቀት ለማወቅና ቀጣይ የስራ እቅድ ለማውጣት እንደሆነም ጨምረው ተናግረዋል። "የሁለቱ ህዝቦችና ሀገራት ተደጋጋፊነት፣ የሁለትዮሽ ጥቅም እና እድገት ከሁለት ትውልዶች በላይ የተደከመበት እና የተሰዋንለት ዓላማም ስለሆነ ቀዳሚነት ሰጥተን የምንሰራው ስራ ነው" ያሉት ፕሬዚዳንቱ "ለይስሙላና ለህዝብ ግንኙነት ስራ ሳይሆን የህዝቡን ፍላጎት ለሟሟላት ነው" ብለዋል። "የኢትዮጵያ ህዝብ ከኤርትራ ጋር ሰላም እንዲኖር መፈለጉ አዲስ ነገር አይደለም" ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ጦርነት ሲታወስ ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ የኤርትራና የኢትዮጵያ ህዝብ ለአምሳ ዓመታት ያህል ዓለም አቀፍ አጀንዳን ለማስፈፀም እንደተሰቃየ ገልፀው ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት ታግለው ነፃ ለመውጣትና አዲስ ምዕራፍ ሊጀምሩ ቢሽቱም ሊሳካ አልቻለም እንዳልቻለም ገልፀዋል። "ይህ ጥሩ ጅማሮ ሳይሳካ መስመሩን የሳተ ዓለም ዓቀፍ ፖሊሲ ምክንያት የህይወት መጥፋት፣ መስዋዕትነት አስከፍሎናል። በጣም ፈታኝ ነው"ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ በቅርብ ጊዜ በቀጠናው በተለይም በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ ሂደቶች አስፈላጊ የሆነ ምልከታ ያስፈልገዋል ያሉት ፕሬዚዳንቱ በተለይም የኢትዮጵያ ህዝብ በቀጥታ እንደተጎዱና በተለይም ህወሐት ከሚያወጣቸው ፖሊሲዎች ጋር ተያይዞ ህዝቡ ገፈት ቀማሽ እንደሆነ አስምረውበታል። ከሁለቱ ኃገራት መቃቃር ጋር ተያይዞም የሁለቱን ህዝቦች ግንኙነት ማሻከሩ እንዲሁም የሁለቱ ኃገራት ህዝቦችና መዋዕለ-ሀብት በቀጠናው ላይ ሊያመጡት የሚችለውን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ኪሳራ አምጥቷል ያሉት ፕሬዚዳንቱ በዚህም ኢትዮጵያን ተወቃሽ አድርገዋል። የኢትዮ-ኤርትራ ግጭት ጦስ በሶማሊያ? "በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የደረሰውን ግፍም ህዝቡ በቃኝ በማለቱ ኢትዮጵያ አዲስ የለውጥ ጎዳና ላይ ናት። ይህ መጨረሻው ምንድን ነው? እንዴትስ ይሳካል? የሚሉት ጥያቄዎች አንገብጋቢ ጥያቄዎች ስለሆኑ መመለስ አለባቸው" ብለዋል። ኢትዮጵያውያን ከኤርትራውያን ጎረቤቶቻቸው ጋር በሰላም መኖር እንደሚፈልግ የገለፁት ፕሬዚዳንቱ "የኢትዮጵያ ህዝብ ከኤርትራ ጋር ሰላም እንዲኖር መፈለጉ አዲስ ነገር አይደለም" በማለት ተናግረዋል። ኤርትራ ፖሊሲ ስታረቅ የሀገሪቱንና የአለም እውነታ ከግምት ውስጥ እንደሚያስገቡ ጠቅሰው አጎራባች ሀገሮችን ባጠቃላይና በዋነኛነት ኢትዮጵያን ከግምት እንደሚያስገቡም ገልፀዋል።
44564369
https://www.bbc.com/amharic/44564369
ካለሁበት 37፡ ''አብረን ጥሩ ነገር የምንሠራበት ዕድል አልተፈጠረም''
መንግስተአብ ገብረገርግስ እባላለሁ። የምኖረው በዋሺንግተን ዲሲ በሲልቨር ስፕሪንግ ከተማ ነው። ከአራት ዓመታት በፊት ነበር ለትምህርት ወደዚህ አገር የመጣሁት።
ሲልቨር ስፕሪንግ ኢትዮጵያውያንን እና ኤርትራውያንን ጨምሮ በአሜሪካ ብዙ ስደተኞች የሚኖሩባት ከተማ ናት። እኔ መጀመሪያ ወደዚህ ስመጣ ብዙ በረዶ የነበረበት ጊዜ ስለነበር በጣም ከባድ ነበር። በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ያለ መኪና መንቀሳቀስ የማይታሰብ ነው። በዚህ ምክንያት በመጀመርያዎቹ ሁለት እና ሦስት ወራት ከቤት ወደ ትምህርት ቤት በመመላለስ ብቻ ነበር ያሳለፍኩት። አብዛኛውም ሰው ሥራ ስለሚውል ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረኝን ማህበራዊ ሕይወት እዚህ ላገኘው ባለመቻሌ ከብዶኝ ነበር። የአሜሪካ ኑሮ ሃገር ቤት ሆነን እንደምናስበው አይደለም። መጀመሪያ ስመጣ ኢትዮጵያ እያለሁ ስሰማው እንደበር ሆኖ አላገኘሁትም። ወደ አገሬ ልመለስ ያልኩበት ጊዜም ነበር። ከጊዜ በኋላ ግን የአገሪቱን አሠራር እየለመድኩት ስመጣ፣ ወንድሞቼም እዚህ በመሆናቸው በሕይወቴ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል ብዬ በማሰብ እዚህ እየኖርኩኝ ነው። ''አሜሪካ ሥራ ካልመረጥክ የምትኖርባት፣ ካማረጥክ ደግሞ እንደ ቆሻሻ የምትጣልባት አገር'' የአሜሪካ ኑሮ እንደምናስበው አይደለም። ሁሉም ነገር በቀላሉ የሚገኝበት አገር አይደለም። ገንዘብ በብዙ ጥረት ነው የሚገኘው። አሜሪካ ሥራ ካልመረጥክ የምትኖርባት፣ ሥራ ካማረጥክ ግን እንደ ቆሻሻ የምትጣልባት አገር ናት። መንግስተአብ በሥራ ገበታው ላይ እዚህ ሥራ አጥተው ኑሮ ከብዷቸው ጎዳና ላይ ወጥተው የሚለምኑ ብዙ ሰዎች አሉ። የዚህ ምክንያት አገራቸው እያሉ የነበራቸውን የአኗኗር ዘይቤ ሲያጡት አሊያም የዚህን አገር የኑሮ ሁኔታ መቀበል ሲያቅታቸው ይመስለኛል እንደዚህ ዓይነት ሁኔታ የሚፈጠረው። ሰዎችን ጎዳና ላይ ማየት ደግሞ በጣም ያሳዝናል። ኢትዮጵያ እያለሁ ለኤፍ ኤም መቀሌ ራድዮ ጋዜጠኛ ነበርኩኝ። ከዚያ በተጨማሪም በንግድ፣ በሙዚቃ እና በትወና እሠራ ነበር። አሜሪካን አገር በሙያዬ መቀጠል ከባድ ነው። ወደ ምፈልገው ደረጃ ለመድረስም ዝቅ ብዬ መጀመር ነበረብኝ። ይህንን መቀበል መጀመሪያ ላይ ከብዶኝ እንደነበር አልክድም። አብረን ጥሩ ነገር የምንሠራበት ዕድል አልተፈጠረም ሌላኛው የአሜሪካ ከባዱ ነገር ማህበራዊ ኑሮ አለመኖሩ ነው። አብዛኛው ሰው በዕለት ተዕለት ሕይወቱ የተጠመደ ነው። እኔ ግን አጋጣሚ ሆኖ እንደመጣሁ ከሁለት ወራት በኃላ 'አያ ማህበር' የሚባል ማህበር በዋሺንግተን ዲሲ ተቀበለኝ። ይህ ማህበር በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች በየዓመቱ ጉዞ በማድረግ የሚመካከሩበት እና እንደ በዓል የሚያዩት ነው። በዚህ መድረክ ትምህርት ቤት አብረውኝ የተማሩ እና አስተማሪዎቼን ያገኝሁበት አጋጣሚ ነበር። በአሜሪካ ምንም እንኳን እንደነዚህ ዓይነት ማህበሮች ቢኖሩም አጋጣሚዎች ከሌሉ የሚፈለገውን ያህል ግን ሕብረት የለም። እነዚህ ማህበራት በሰሜን አሜሪካ የምንኖር ኢትዮጵያውያን በየዓመቱ እንድንገናኝ መድረክ ቢያዘጋጁም፤ ከመዝናናት እና ብር ከማዋጣት ውጪ ባለፈ ዓላማው አይገባኝም። በኢትዮጵያና በተለያዩ የዓለም ክፍል የሚገኙ ኤርትራውያን ወንድሞቻችን በስደት ሆነው የሚሠሩት የጥበብ ሥራዎች ሳይ መንፈሳዊ ቅናት ያድርብኛል። እዚህ አገር የምንኖር ኢትዮጵያውያን አብረን የምንሠራበት ጥሩ ዕድል አልተፈጠረም። የፒዛ ቦሊስ መሸጫ ሱቅ አሁን ፒዛ ቦሊዝ በሚባል የ'ፒዛ ስቶር' ውስጥ ነው የምሠራው። ይህ ድርጅት በዲሲ እና አካባቢው ከሰማንያ አምስት በላይ ቅርንጫፎች ያሉት ነው። የፒዛችን ስም ደግሞ 'ፒዛ ቦሊስ' ነው። ዝቅተኛ ሊባል የሚችል ሥራ ሰርቼ ነው እዚህ የደረስኩት። ከአሁን በፊት ኢትዮጵያ እያለሁ ፒዛ እንዴት እንደሚሠራ እንኳን አላውቅም ነበር። አሜሪካ ብዙ ሙያ የምታስተምር አገር በመሆኗ ከዚህ በፊት ሠርቼው የማላውቀውን የፒዛ ሥራ ተያያዝኩት። የምኖርበት አካባቢ የመኖሪያና የሥራ ቦታ በመሆኑ አብዛኞቹ እንደ ባህር ዳርቻ ያሉ ተፈጥሯዊ የመዝናኛ ቦታዎች ከዲሲ እና አካባቢዋ ወጣ ብለው ነው የሚገኙት። ከዚያ ውጪ ግን ፓርክላንድ የሚባል የመዝናኛ ቦታ አሉት። ፓርክላንድ እንደ ቴንስ፣ ቮሊቦል እና የኳስ ሜዳ መጫወቻ ስፍራዎች አሉት። እናም አልፎ አልፎ ኢትዮጵያ ውስጥ ከጓዶኞቼ ጋር የምጫወታቸው ነገሮች ትዝ ሲሉኝ ወደዚህ የመዝናኛ ቦታ በመሄድ እራሴን አዝናናለው። ሲልቨርስፕሪንግ የሚገኘው ፓርክላንድ የመዝናኛ ቦታ የኢትዮጵያ ጋዜጠኝነት የተገደበ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ጋዜጠኛ በነበርኩበት ጊዜ ጎን ለጎን አዳዲስ ነገሮች መሞከር እወድ ነበር። ይህ ደግሞ እዚህ በጣም ረድቶኛል። በእርግጥ ጋዜጠኝነት እና የፒዛ ነጋዴ መሆን የሚገናኙ አይደሉም። ዕድሎች ሲጠፉ ግን ሕይወት መቀጠል ስላለባት በሌላ ዘርፍ ገብቼ በመሥራት ላይ ነኝ። ለጋዜጠኝነት ልዩ ፍቅር ነው ያለኝ። በኢትዮጵያ ጋዜጠኝነት ሙሉ በሙሉ ለሕብረተሰብ ለመሥራት ስታስብ ግን ብዙ የሚገድቡህ ነገሮች አሉ። መሥራት የምትፈልጋቸው ብዙ ነገሮች ቢኖሩም ብዙ ፈተናዎች ይጋረጡብሃል። እዚህ ሃገር ካለው የጋዜጠኝነት ሽፋን በጭራሽ የሚገናኝ አይደለም። በሙያው ብዙ የማልረሳቸው ትዝታዎች አሉኝ። በተለይም ዓመት በዓል ሲመጣ ጋዜጠኛ ከቤተሰቦቹ ተለይቶ ከአድማጮቹ ጋር የሚያሳልፈው ጊዜ ነው የሚበዛው። በፒዛ ስቶር ሚዘጋጀው ፒዛ ቦሊስ ለዓላማ የሚከፈል መስዋትነት ገና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁ ለጥበብ ልዩ ፍቅር ስለነበረኝ በተለያዩ ክለቦች የትወና፣ ፀረ-ኤድስ እና የሚኒ ሚድያ ክለቦች እሳተፍ ነበር። አሁን ሕይወቴን መስመር በማስያዝ ላይ ነኝ። ቀጥዬ ወደ ሃገሬ ተመልሼ የፕሮሞሽን ድርጅት በመክፈት በጣም በምወዳቸው የጋዜጠኝነት እና የፊልም ሙያ በትግርኛ ቋንቋ ከሌሎች የጥበብ ባለሞያዎች ጋር በመሆን ለሕብረተሰቡ ጥሩ ምሳሌ መሆን የሚችል ሥራ ለመስራት ዕቅዱ አለኝ። በአሁኑ ሰዓት ካለሁበት እራሴን በቅጽበት ወደ ኢትዮጵያ መላክ ብችል ተወልጄ ባደኩባት፣ ወደ ውቧ ከተማ መቀሌ ልኬ እራሴን ከምወዳቸው ቤተሰቦቼ እና ፍቅረኛዬ ጋር ባገኘው ምንኛ ደስ ባለኝ። ለላየን ፅጋብ እንደነገራት
48933118
https://www.bbc.com/amharic/48933118
የታገዱት ሞተረኞች እሮሮ እያሰሙ ነው
አሸናፊ አህመድና ግርማይ ሞተር በመንዳት የራሳቸውንና የቤተሰባቸውን ሕይወት ለማሻሻል ይታትራሉ። አሸናፊ እንደሚለው ባለፉት አስር ዓመታት በሞተሩ በእያንዳንዱ የከተማ ጥግ እየተንቀሳቀሰ ሰዎች ያዘዙትን ያመላልስ ነበር።
"ገንዘብም ሆነ እቃ አድርስ ያሉኝን በታማኝነት አደርስ ነበር" ያለው አሸናፊ የሁለት ልጆች አባት ነው። አሸናፊም ይሁን ግርማይ ሕይወታቸው ሙሉ በሙሉ የተመሰረተው ሞተር መንዳት ላይ ነበር። አሁን ግን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሰኔ 30 ቀን 2011 ዓ. ም. ጀምሮ ፈቃድ የሌለው ሞተር ከተማ ውስጥ ማሽከርከር ስለከለከለ፤ ሥራ አቁመው ቀን የሚያመጣውን ይጠብቃሉ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለከተማው ሰላም ስጋት ናቸው ያላቸውን ሞተር ብስክሌቶች ከሰኔ 30 ቀን 2011 ዓ. ም. ጀምሮ እንዳይንቀሳቀሱ ያገደው ሰኔ 13 ቀን 2011 ዓ. ም. ነበር። • የሞተር ብስክሌቶች እና ሕገወጥነት በአዲስ አበባ በ15 ቀን ውስጥ አስፈላጊውን ምዝገባና ተያያዥ ጉዳዮች በትራንስፖርት ቢሮ እንዲፈፅሙና ሕጋዊ እንዲሆኑ የከተማ አስተዳደሩ አስታውቆ ነበር። እነ አሸናፊን የከተማ አስተዳደሩ ተደራጅታችሁ ሥሩ ብሏል ምን እያሰባችሁ ነው? ተብለው ሲጠየቁ አማራጮችን ለመፈለግ ጊዜው አጭር መሆኑን ግርማይ ይናገራል። የእለት ጉሮሯቸውን ከሚደፍኑበትን ሥራ ማፈናቀል ተገቢ አለመሆኑን በመቃወም ሞተር አሽከርካሪዎች ተሰብስበው ሰልፍ ማድረጋቸውንም ያስታውሳል። ሰልፉን ሰኔ 26 ቀን 2011 ዓ. ም. ቢያደርጉም ምላሽ የሚሰጣቸው አካል ባለማግኘታቸው እንዳዘነ የሚናገረው ግርማይ፤ "ነገሩ ተስፋ ያለው አይመስልም" ይላል። አሸናፊም ጉዳዩን ወደሚመለከተው አካል ለመውሰድ ፍላጎት የለውም። • “የመከላከያው በአደባባይ ሚዲዎችን እከሳለሁ ማለት አስፈሪ ነው” ዶ/ር አብዲሳ ዘርዓይ አሸናፊ፤ ሞተር ከማሽከርከር ውጪ ሥራ ለመቀየር ባያስብም፤ "ባሉት ስራ አጦች ላይ ሌላ ሥራ አጥ ሆኜ ተደምሬያለሁ" ይላል በቁጭት። ሞተር በማሽከርከር በሚያገኙት ገቢ ቤት ተከራይተው ሦስትና አራት ልጅ የሚያሳድጉ፣ ወላጆቻቸውን የሚጦሩም አሉ የሚለው አሸናፊ፤ በእርግጥ አዲስ አበባ ውስጥ ወንጀል ስለተበራከተ መንግሥት ወንጀልን ለመከላከል እርምጃ ቢወስድም በርካቶችን ሥራ አጥ ማድረግ ደግሞ ተገቢ አይደለም ይላል። በከተማዋ ሌሎች የትራንስፖርት አገልግሎቶች ወንጀል ለመፈጸም ቢውሉም፤ ሞተር ላይ ብቻ እርምጃ መወሰዱ አስገርሞታል። አሸናፊ፤ ደንቡ ሰኔ 30 ይተገበራል ቢባልም፤ ከሰኔ 15 ጀምሮ ሥራ እንዳስቆማቸው ይጠቅሳል። ግርማይ በበኩሉ ከሰኔ 28 ጀምሮ ሥራ እንዳስቆሟቸው ይጠቅሳል። የ"ዘ ሞል ዴሊቨሪ" አገልግሎት ባለቤት አምባዬ ሚካኤል ተስፋዬም በመንግሥት እርምጃ ሥራቸው መጎዳቱን ይናገራል። "ሞተሮቻችን ቆመዋል" የሚለው አምባዬ፤ ሥራ ሙሉ በሙሉ ማቆማቸውን ይገልጻል። • ሲፒጄ ለኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች መስጋቱን ገለጸ የጥርስ ሀኪም የሆኑት ዶ/ር ሰብለ ማሞ ድርጅታቸው በቤተ ሙከራ ውስጥ የሚያመርታቸውንና ለተለያዩ የጥርስ ክሊኒኮች የሚያቀርቧቸውን ትዕዛዞች በሞተር ያመላልሱ እንደነበር ይናገራሉ። አሁን ግን ማቅረብ ባለመቻላቸው ደንበኞቻቸው እየተማረሩ መሆኑን ይገልጻሉ። አምባዬ፤ ደንቡ ይፋ እንደተደረገ የተለያዩ የመንግሥት ኃላፊዎችን ለማነጋገር መሞከራቸውን አስታውሶ፤ ደንቡን ያወጡትን አካላት ቢያነጋግሩም ምዝገባ የጀመሩት ባለፈው ሳምንት መሆኑን ይጠቅሳል። የከተማ አስተዳደሩ ያቀረበውን መስፈርት ሙሉ በሙሉ ማሟላታቸውን አምባዬ ገልጾ "ሞተሩ ላይ ጂፒኤስ ማስገጠም፣ ሞተረኛውን የደንብ ልብስ ማልበስ የሚሉትን አሟልተን ብናቀርብም በምንፈልገው ፍጥነት ጉዳያችን እየተስተናገደ አይደለም" ይላል። ማንን ማነጋገር እንዳለባቸው፣ ወይም የሚመለከተው ኃላፊ ማን እንደሆነ ግልፅ ያለ ነገር እንደሌለ የሚናገረው አምባዬ፤ በዚህም የተነሳ የተለያዩ ቢሮዎች ለመሄድና ደጅ ለመጥናት መገደዳቸውን ያክላል። የዘ ሞል ዴሊቨሪ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ተመስገን ገብረሕይወት፤ በከተማዋ ያለውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ በርካታ አማራጮችን መኖር አለባቸው ይላሉ። "በአሁኑ ሰአት ሞተር ብስክሌቶች ቀልጣፋ፣ አስተማማኝና ርካሽ አገልግሎት እየሰጡ ነው" በማለትም ስለ አገልግሎቱ ሀሳባቸውን አካፍለውናል። • በኻሾግጂ ግድያ የአሜሪካ ዝምታ 'መፍትሄ አይሆንም'፡ የተባበሩት መንግሥታት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ሰኔ 12 ቀን 2011 ዓ. ም. በሰጡት መግለጫ፤ በከተማዋ ሞተር በመጠቀም በተደራጀ መንገድ ቅሚያ፣ ስርቆትና አልፎ አልፎ ዝርፊያ እየተፈጸመ መሆኑን ተናግረው ነበር። ሰሌዳቸው የአዲስ አበባ ያልሆኑ ሞተር ብስክሌቶች ዋነኛ የችግሩ ምንጭ መሆናቸውን በማመልከት ነው የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ከሰኔ 30 ቀን 2011 ዓ. ም. ጀምሮ ሞተሮች እንዳይንቀሳቀሱ መታገዳቸውን ያስታወቁት።
news-53525202
https://www.bbc.com/amharic/news-53525202
በስፔን ወረርሽኙ ሊያገረሽ ይችላል የሚል ስጋት ተፈጥሯል
ቀደም ካለው ሰፋ ያለ የኮሮናቫይረስ መልሶ "ሊያገረሽ ይችላል" ብላ ስጋት ውስጥ ያለችው ስፔን አዳዲስ እርምጃዎችን እየወሰደች ነው።
በአገሪቱ ሰሜን ምሥራቅ ውጪ በሚገኙ ከተሞች ውስጥ የበሽታው መስፋፋት እየታየ ሲሆን የካታሎኒያ ግዛት ደግሞ ለሁለት ሳምንታት የምሽት መዝናኛ ቦታዎችን እንዲዘጉ አድርጋለች። ስፔን ጥላው የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ካበቃ ከወር በኋላ ዋና ከተማዋን ማድሪድን ጨምሮ ባርሴሎናንና ዛራጎዛን በመሳሰሉ ከተሞች በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ላይ ከፍተኛ ጭማሪ በመታየቱ መንግሥት ወረርሽኙ ለሁለተኛ ጊዜ ሊያገርሽ እንደሚችል እያስጠነቀቀ ነው። የአገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴርም በሠራዊቱ ውስጥ ሊከሰት የሚችል ወረርሽኝን ለመለየትና ለመከላከል የሚያስችል የቅድመ ማስጠንቀቂያ ምላሽ ሥርዓት ተግባራዊ እያደረገ ነው። የጤና ሚኒስቴር ባለፈው አርብ ከ900 በላይ አዲስ ህሙማን መገኘታቸውን ያረጋገጠ ሲሆን፤ በሁለተኛ ዲቪዚዮን የሚጫወት አንድ የእግር ኳስ ቡድን 28 አባላቱ በበሽታው ተይዘውበታል። ዩናይትድ ኪንግደም ከዛሬ ጀምሮ ከስፔን የሚመለሱ ሰዎች እራሳቸውን ለ14 ቀናት ለይተው እንዲቆዩ ያዘዘች ስታዝ፤ ኖርዌይም ተመሳሳይ እርምጃ እንደምትወስድ አሳውቃለች። ፈረንሳይ ደግሞ ወደ ስፔን ለሚደረጉ ጉዞዎች ማስጠንቀቂያ አውጥታለች። ቤልጂየም ወደ ተወሰኑ የስፔን ግዛቶች የሚደረጉ ጉዞዎችን ስትከለክል፤ ዜጎቿ ወደ ሌሎች የስፔን ከተሞች ጉዞ እንዳያደርጉ እየመከረች ነው። የስፔን ጤና ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ግን አገራቸው ውስጥ ያለው የወረርሽኙ ችግር በተወሰኑ ቦታዎች የተለየና በቁጥጥር ስር ያለ በመሆኑ ምንም የሚያሰጋ ነገር እንደሌለ ተናግረዋል። ከስፔን ባሻገር አውሮፓ ውስጥ ያሉ አገራት አዲስ በበሽታው የሚያዙ ሰዎችን ለመቆጣጠርና ምጣኔ ሃብታዊ እንቅስቃሴዎችን መልሶ ለመክፈት ጥረት እያደረጉ ባሉበት ጊዜ በፈረንሳይና በጀርመን እየጨመረ የመጣ የህሙምን ቁጥር እየተመዘገበ ነው። በአውሮፓ ውስጥ የታየው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመር በሌሎችም አካባቢዎች ከታየው ጋር የሚያያዝ ሲሆን፤ ባለፉት ሁለት ቀናት በመላው ዓለም ከፍተኛ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር ተመዝግቧል። 280 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ከተመዘገበ በኋላ "በዓለም ላይ በበሽታው ያልተጠቃ አገር ባይኖርም፤ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ባላቸው የአህጉረ አሜሪካና የእስያ አገራት ውስጥ የታየው ጭማሪ ቁጥሩን ከፍ አድርጎታል" ሲል የዓለም ጤና ድርጅት ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ ከ15.7 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወረርሽኙ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን ከ640 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን ማጣታቸውን የጆንስ ሆፕኪንስ መረጃ ያመለክታል።
43638047
https://www.bbc.com/amharic/43638047
"ህልም አለኝ":-በቀለ ገርባ
'ህልም አለኝ' ወይም አይ ሀቭ ኤ ድሪም በሚለው ታሪካዊ ንግግራቸው የሚታወቁት የጥቁር መብት ተሟጋቹ ማርቲን ሉተር ኪንግ ከተገደሉ 50 ዓመት ሞላው።
በአንደበተ ርዕቱነታቸው የሚታወቁት ማርቲን ሉተር ኪንግ ጥቁሮች ይደርስባቸውም ከነበረው የምእተ ዓመታት ጭቆና ነፃ የሚወጡበት መንገድ በሰላማዊ ትግል ላይ የተመሰረተ ሊሆን ይገባዋል በሚል እቅዶችን ነድፈዋል። ምንም እንኳን ብዙዎች ሰላማዊ ትግል ሲባል ኮሽ ሳይል የሚደረግ ትግል በሚል ቢረዱትም ማርቲን ግን በነጮች የበላይነት የተመሰረተውን ተቋማዊ፣ እምነታዊ ዘረኝነትና ጭቆናን ለመታገል ተቃውሞዎችን ማካሄድ፣ ዘረኛ ህጎችን መጣስንም ያካትታል። ህይወቱም ይሁን የትግሉ መንገድ ለብዙዎች እንደ ምሳሌነት የሚያዩት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ-መንበር አቶ በቀለ ገርባ ናቸው። በተደጋጋሚ ለእስር የተዳረጉት አቶ በቀለ ገርባ በአውሮፓውያኑ 1963 ማርቲን ያደረገውን (አይ ሀቭ ኤ ድሪም) የሚለውን ታዋቂ ንግግር 'ሙለታን ቀባ' (ህልም አለኝ) በሚል ወደ ኦሮምኛ ቋንቋ ተርጉመውታል። ይህንን መፅሀፍ ለመተርጎም ያነሳሳቸው ቃሊቲ ማረሚያ ቤት በነበሩበት ወቅት ሲሆን ይህም መፅሀፍ እጃቸው እንደገባ ይናገራሉ። በወቅቱም አንዷለም አራጌም አብሯቸው በእስር ላይ ነበር። ሀሳባቸውም የነበረው አንዷለም አራጌ ይህንን ታሪካዊ ፅሁፍ ወደ አማርኛ እንዲተረጉመውና እሳቸውም ወደ ኦሮምኛ በመተርጎም ሰፊው ህዝብ እንዲያነበው ማድረግ እንደነበር ይናገራሉ። "ህዝቦች በሰላማዊ መንገድ እንዴት መብቶቻቸውን ማስከበር እንደሚችሉ የሚያስተምር ነውና እኛም የድርሻችንን መወጣት አለብን" በሚል ስሜት እንደተነሳሱ የሚናገሩት አቶ በቀለ በአጋጣሚ ግን ሳይጨርሱት እንደተለያዩ ይናገራሉ። ከእስር ከተለቀቁ በኋላ ትርጉማቸውን አጠናቅቀው ጥቂት ኮፒዎችን ያሳተሙ ሲሆን እንደገና ለእስር በመብቃታቸው በብዛት ባያሳትሙም ከተፈቱም በኋላ መፅሀፉ የተወሰኑ ሰዎች እጅ እንዲገቡ እንዳደረጉ ይገልፃሉ። የማርቲን ሉተር ኪንግ የሰላማዊ ትግል በኢትዮጵያ ምን ያህል አዋጭ ነው ተብሎ ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ በቀለ ሲመልሱ "ያዋጣል ብቻ ሳይሆን አዋጭ እሱ ብቻ ነው። ወንድምን ወይም የራስን ወገን በመግደል የሚያዝ ስልጣን ዘላቂ ነው የሚል ዕምነት የለኝም" በማለት አቶ በቀለ ይናገራሉ። ይህ ጥያቄ በብዙዎች ዘንድ ተደጋግሞ እንደሚነሳ የሚገልፁት አቶ በቀለ ለማርቲን ሉተር ኪንግም ቀርቦለት ነበር። "እነዚህ ነጮች ነፃነታችንና መብታችንን እንዲሁ የሚሰጡን አይደሉም። መብታችንን ማስከበር የምንችለው በመሳሪያ ብቻ ነው። ነፃነታችንን መጎናፀፍ የምንችለው በዚሁ መንገድ ብቻ ነው" ብለው የተሟገቱ እንዳሉና ከዚህም አለፍ ሲል የግድያ ሙከራ እንደደረሰበት ያወሳሉ። ለአዋጭነቱም ማሳያዎች ብለው የሚጠቅሷቸውም የስራ ማቆም አድማ፣ ምርቶችና አንዳንድ ተቋማትን ያለመገልገል ማእቀብ ኢኮኖሚያዊ ተቃውሞዎችን ነው "እነዚህ አድማዎች በሰላማዊ መንገድ የተካሄዱ ናቸው። ለውጥም የሚያመጡ ናቸው። ትልቅ የፖለቲካ አንድምታ ነበራቸውም" ይላሉ።
news-53060110
https://www.bbc.com/amharic/news-53060110
ሰሜን ኮሪያ በድንበር የሚገኘውን ጊዝያዊ አገናኝ ቢሮ አጋየች
ሰሜን ኮሪያ ከደቡብ ጋር የሚያቀራርባትንና ድንበር ላይ የሚገኘውን ጊዝያዊ ቢሮ በቦንብ አጋየች፡፡
ቢሮው ከሁለት ዓመት በፊት ነበር የተከፈተው ካዮሶንግ የድንበር ከተማ ይገኝ የነበረው ይህ ቢሮ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ሥራ አቁሞ ለአገልግሎት ዝግ ሆኖ ቆይቶ ነበር፡፡ ሰሜን ኮሪያ ይህንን ቢሮ ስለማጋየቷ ደቡብ ኮሪያ ባለሥልጣናትም አረጋግጠዋል፡፡ ሰሜን ኮሪያ ሰሞኑን በተደጋጋሚ "ተናድጃለሁ፤ ደቡብ ኮሪያ አናዳኛለች" ስትል አስታውቃ ነበር፡፡ ትናንት የኪም እህት ለሰሜን ኮሪያ የጦር ኃይል በተጠንቀቅ ላይ ሁኑ ብላ ትእዛዝ ሰጥታ ነበር፡፡ በሰሜን ኮሪያ ግዛት ድንበር ላይ ይገኝ የነበረው ቢሮ የተከፈተው ከ2 ዓመት በፊት ነበር፡፡ የጊዝያዊ ቢሮው አገልግሎትም ሁለቱን ወንድም ሕዝቦች ማቀራረብ ነበር፡፡ በዚህ የድንበር ከተማ ግንኙነት ለማደስ በሚል በ2003 ሁለቱ አገራት ግዙፍ የኢንዱስትሪ መንደር ከፍተው ነበር፡፡ በዚህ ኢንዱስትሪ መንደር 120 ፋብሪካዎች ተከፍተው 50ሺ ሰራተኞች ከሰሜን ኮሪያ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሥራ አስኪያጆች ደግሞ ከደቡብ ኮሪያ ሆነው ምርት ያመርቱ ነበር፡፡ ኢንዱስትሪ መንደሩ በ2016 ሁለቱ አገራት ወደ ጦርነት ሊያመሩ ነው በሚል ፍርሃት ተዘግቶ ከሁለት ዓመት በኋላ በድጋሚ እንዲከፈት ተደርጎ ነበር፡፡ በዚህ የድንበር ከተማ የሚገኘው የአገናኝ ቢሮ ታዲያ ሁለቱ አገራት በየጊዜው እየተገናኙ እንዲማከሩ የሚያግዝ ሆኖ ከ440 በላይ ሰራተኞች የነበሩት ቢሮ ነው፡፡ ሰራተኞቹ ግማሾቹ ደቡብ ኮሪያዊያን ሲሆኑ ቀሪዎቹ የሰሜን ተወላጅ ናቸው፡፡ ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ታዲያ ሰሜን ኮሪያ ከዶናልድ ትራምፕ ጋር የታሰበው ንግግር ባለመሳካቱ ቢሮውን እዘጋዋለሁ ብላ ስታስፈራራ ነበር፡፡ ይህ አገናኝ ቢሮ በጊዝያዊነት የተዘጋው ባለፈው መስከረም የኮሮና ወረርሽኝ ተፈርቶ ነበር፡፡ የሁለቱ አገራት ግንኙነት ድሮም ቋፍ ላይ የነበረ ሲሆን ፒዮንግያንግ ከአሜሪካ ጋር ንግግር ከጀመረች ወዲህ ግን የሁለቱን ወንድም-ሕዝቦች ጠላት መንግሥታት ለማቀራረብ አንዳንድ እንቅስቃሴዎች ፍሬ እያፈሩ ነበር፡፡ ሰሜን ኮሪያ ደቡብ ኮሪያ እያበሳጨችኝ ነው ማለት የጀመረችው አገሪቱን ከድተው በደቡብ ኮሪያ የተጠለሉ ዜጎቿ ፊኛ ወደ አገር ውስጥ መላክ ከጀመሩ ወዲህ ነው፡፡ በደቡብ ኮሪያ የወንድም ሕዝቦች ግንኙነት ሚኒስትር እንዳረጋገጡት ዛሬ በአገሬው አቆጣጠር ለ9 እሩብ ጉዳይ ላይ ፍንዳታ ተሰምቷል፡፡ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የኪም እህት ኪም ዮ ጆንግ ወታደሮቿን ወደ ድንበር ለማስጠጋት ስትዝት ነበር፡፡ የኪም ጆንግ እህት ኪም ዮ ጆንግ በኢውሃ ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ሌይፍ ኤሪክ የዚህ አገናኝ ቢሮ መውደም በሰሜንና ደቡብ ኮሪያ እየተሸሻለ የነበረው ግንኙነት ማክተሙን የሚያረዳ ነው ብለዋል፡፡ ፖለቲካ አዋቂዎች እንደሚሉት ሰሜን ኮሪያ በዚህ መንገድ አካባቢውን ለማመስ በቀጣይነት ሌሎች እርምጃዎችንም ልትወስድ ትችላለች፤ ዋንኛ ፍላጎቷም በአሜሪካ የተጣለባትን ማዕቀብ እንዲላላላት መጠየቅ ነው፡፡ ሰሜንና ደቡብ ኮሪያ በ1953 ጦርነት ሲያበቁ የሰላም ስምምነት ስላላደረጉ አሁንም ደረስ ጦርነት ላይ እንዳሉ ነው የሚታሰቡት፡፡
news-44920809
https://www.bbc.com/amharic/news-44920809
በእንግሊዝ የሶስት ዓመት ጨቅላ ላይ አሲድ የደፉ ሶስት ግለሰቦች ታሰሩ
የሶስት ዓመት ጨቅላ ላይ አሲድ በመድፋት አሰቃቂ ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ ሶስት ግለሰቦችን የእንግሊዝ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር አውለዋል።
ፖሊሶች ጥቃቱ የደረሰበትን ቅጽበት በመገበያያ ማዕከሉ በተቀረጸ ቪድዮ ተመልክተዋል የማዕከላዊ እንግሊዝ ዎርሲስተር ግዛት ፖሊሶች እንደተናገሩት ሶስቱ ተጠርጣሪዎች ሆነ ብለው ጨቅላውን አጥቅተዋል። ጥቃቱ የተፈጸመው ቅዳሜ እለት ሆም ባርጌንስ በተባለ መገበያያ መደብር አቅራቢያ ነበር። የጨቅላው ቤተቦች በህጻናት ጋሪ ውስጥ ልጃቸውን አስቀምጠው በነበረበት ወቅት የ 22፣ የ 25 እና የ 26 እድሜ ያላቸው ተጠርጣሪዎች ጨቅላው ላይ አሲድ ደፍተዋል። • አሲድን እንደ መሳሪያ • የተነጠቀ ልጅነት • ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር የተለቀቁ ግለሰቦች ለዳግም እስር እየተዳረጉ ነው ተባለ ጨቅላው ፊቱና ክንዱ ላይ ጉዳት ደርሶበት ወደ ህክምና መስጫ ተወስዷል። ለጊዜው ወደቤቱ ቢመለስም የአሲድ ጥቃቱ ለዘለቄታው የሚያስከትልበት ጉዳት አልታወቀም። ተጠርጣሪዎቹ አሰቃቂ አካላዊ ጉዳት ለማድረስ በመመሳጠር በሚል ክስ ለንደን ውስጥ ታስረዋል። ሶስቱ ግለሰቦች ጨቅላው ላይ አሲድ የደፉበት ምክንያት እስከአሁን አልታወቀም። ቶኒ ጋርነር የተባሉ መርማሪ እንዳሉት የጥቃቱ ዜና ከተሰማበት ቅጽበት አንስቶ የአካባቢው ማህበረሰብ መረጃ በማቀበል ተጠርጣሪዎቹ እንዲያዙ ተባብሯል። • አሥመራ፡ የአዛውንቶች ከተማ • አብረሃም መብራቱ፡ «ቡድኑን ስኬታማ የማድረግ ሕልም አለኝ» በርካቶች ኢሰብአዊውን ጥቃት እየኮነኑ ይገኛሉ። "ጨቅላ ላይ እንዲህ ያለ ጥቃት መፈጸም ያስጸይፋል። ጥቃቱ መላው አለምን የሚያስደነግጥም ነው" ሲሉ መርማሪውን ሀዘኔታቸውን ገልጸዋል።
news-46093868
https://www.bbc.com/amharic/news-46093868
''ከመቼውም ጊዜ በላይ ጠንካራ'' የተባለለትና አሜሪካ በኢራን ላይ የተጣለችው ማዕቀብ ተግባራዊ ሊደረግ ነው
''ከመቼውም ጊዜ በላይ ጠንካራ'' የተባለለት ማዕቀብ በነዳጅ ሃብቷ በበለጸገችው ኢራን ላይ ተግባራዊ ሊደረግ ነው።
የትራምፕ አስተዳደርን የተቃወሙ ኢራናውያን በቀድሞ የአሜሪካን ኤምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል ከሶስት ዓመታት በፊት አሜሪካ እና ኢራን ያደረጉትን የኒውክሌር ስምምነት ተከትሎ ተነስተው የነበሩት ማዕቀቦች እንደገና ተግባራዊ እንዲደረጉ የትራምፕ አስተዳደር እየሠራ ነው። ይህ የባንክ፣ ነዳጅ እና የመርከብ ትራንስፖርት አገልግሎትን የሚመለከተው ማዕቀብ ኢራን እና የንግድ አጋሮቿ ጭምር ላይ ያነጣጠረ ነው። በትራምፕ አስተዳደር የተበሳጩ በርካታ ኢራናውያን ''ሞት ለ አሜሪካ'' የሚሉ መፈክሮችን በአደባባይ ሲያሰሙ ነበር። • ኢራን አሜሪካ ማዕቀብ እጥላለሁ ማለቷን አወገዘች • ኢራን አሜሪካ ዳግም የጣለችውን ማዕቀብ አወገዘች የኢራን የጦር ኃይልም የሃገሪቱን የመከላከያ ብቃት ለማስመስከር ሰኞና ማክሰኞ አየር ኃይሉ ልምምዶችን ያደርጋል ሲል ተሰምቷል። ፕሬዚዳንት ትራምፕ ''ኢራን ላይ የሚጣለው ማዕቀብ በጣም ጠንካራ ነው። እስካሁን ከጣልናቸው ማዕቀቦች ሁሉ ጠንካራው ነው። ኢራን የምትሆነውን አብረን እናያለን፤ የማረጋግጥላችሁ ግን አካሄዳቸው ጥሩ አይደለም።'' ብለው ነበር። የትራምፕ አስተዳደር ኢራን የሳይበር ጥቃቶችን፣ የሚሳዔል ሙከራዎችን እና በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ሚሊሻዎችን እና የሽብር ቡድኖችን መደገፍ ማቆም አለባት ይላል። ይህ በኢራን ላይ የተጣለው ማዕቀብ በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚኖረው ታምኖበታል። ከ70 በላይ ግለሰቦች፣ ድርጅቶች፣ መርከቦች እና አውሮፕላኖች በማዕቀቡ ዝርዝር ውስጥ ይካተታሉ። ማዕቀቡ የሃገሪቱን ዋነኛ ባንኮች፣ ነዳጅ ላኪ ኩባንያዎች እና የመርከብ ትራንስፖርት ኩባንያዎችን ዒላማ አድርጓል። የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፔዎ ከ100 በላይ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ማዕቀቡን ተከትሎ ራሳቸውን ከኢራን አግልለዋል ብለዋል። ፖምፔዎ ጨምረው እንደተናገሩት ኢራን የምትልከው የነዳጅ ብዛት በቀን በአንድ ሚሊዮን በርሜል ቀንሷል። • እንግሊዝ፦ 'ከኢራን ጎን ነኝ' • ትራምፕ፡ የኢራን የኑክሊዬር ስምምነትን አቋርጣለሁ እንግሊዝ፣ ጀርመን እና ፈረንሳይ ማዕቀቡን ተቃውመዋል። ሃገራቱ ከኢራን ጋር ህጋዊ ንግድ መፈጸም የሚፈልጉ አውሮጳዊ ኩባንያዎች የአሜሪካ ማዕቀብ ተጽዕኖ እንዳያሳድርባቸው የተለያዩ የክፍያ ስርዓቶችን እንደሚዘረጉ ቃል ገብተዋል። የትራምፕ አስተዳደር በስም ያልጠቀሳቸው ሰምንት ወዳጅ ሃገራት ከኢራን ነዳጅ እንዲያስገቡ ፈቀዷል። ተንታኞች ከእነዚህ አገራት መካከል ጣሊያን፣ ቻይና፣ ህንድ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ቱርክና ጃፓን ይገኙበታል ይላሉ።
news-52197191
https://www.bbc.com/amharic/news-52197191
ኮሮናቫይረስ፡ ዶናልድ ትራምፕ በእግር-በፈረስ እየፈለጉት ያለው መድኃኒት
የህንዱ ሞዲና የአሜሪካው ትራምፕ በፍቅር ክንፍ ብለው ነበር ከወራት በፊት.
ትራምፕ ድንገት ከሰሞኑ ሞዲን አስጠነቀቁ። ህንድ ያከማቸችውን ሀይድሮክሲክሎሮኪን ካልሸጠችልን እርምጃ እንወስዳለን ሲሉም ተናገሩ። የህንዱ ሞዲ ትንሽ ጊዜ ስጡኝ ላስብበት ብለው ነበር ትናንት። ዛሬ ከጥቂት ሰዓታት በፊት የትራምፕን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ "መድኃኒቱን ልንልክላችሁ ወስነናል" ብለዋል። ህንድ መድኃኒቱን በኮሮናቫይረስ ለተጎዱ አገሮች ለመስጠት ወስናለች ብለዋል ሞዲ። ይህ ንግግራቸው የትራምፕን የቅጣት ዛቻ ተከትሎ እንደሆነ ተዘግቧል። የሕክምና አዋቂዎች ይህ የወባ መድኃኒት ኮሮናን ስለመፈወሱ የሚታወቅ ነገር የለም ሲሉ አስጠንቅቀዋል። አሜሪካና ህንድን ያገናኘው መድኃኒት ትራምፕ በተደጋጋሚ በሕዝብ ፊት ይህ መድኃኒት ማርሽ ቀያሪ ነው እያሉ ተናግረዋል። እሑድ ዕለት ደግሞ ወደ ናሬንድራ ሞዲ ደውለው ቶሎ ይሄን መድኃኒት ይላኩልኝ ብለዋል። የህንዱ ሞዲ ደግሞ ጥቂት ቀደም ብሎ ማንኛውም የሕንድ ኩባንያ ይህን መድኃኒት ወደ ውጭ ቢልክ ወዮለት ብለው ነበር። ወዲያውኑ የትራምፕ ዛቻ ውሳኔያቸውን ሳያስቀይር አልቀረም። የሚገርመው ይህ የሞዲ ውሳኔ በህንድ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ ባለበት ሰዓት መደረጉ ነው። ሆኖም ከአሜሪካ ጋር የሚነጻጸር አይደለም። አሜሪካ የተያዦች ቁጥር አራት መቶ ሺህ እየተጠጋ ነው፡። ሟቾች 10 ሺህ አልፈዋል። ይህንን መድኃኒት ትራምፕ ለምን አጥብቀው ፈለጉት? ሃይድሮክሲክሎሮኪን ልክ እንደ ክሎሮኪን ያለ መድኃኒት ነው። ብዙ ዘመን ያስቆጠረና ወባን በመፈወስ የሚታወቅ መድኃኒት ሲሆን በኮሮናቫይረስ ጉዳይ ስሙ እየገነነ መጥቷል። ይህ መረጃ ኢትዮጵያ በመግባቱም በአዲስ አበባ በርካታ መድኃኒት ቤቶች በዚህ መድኃኒት ፈላጊዎች ተጨናንቀው እንደነበር የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ሲዘግቡ ቆይተዋል። ትራምፕ እንደሚሉት የአሜሪካ የምግብና መድኃኒት አስተዳደር ይህንን መድኃኒት ለኮሮና መጠቀምን ፈቅዷል። ትራምፕ ይህን ይበሉ እንጂ የመድኃኒት አስተዳደሩ እኔ አልወጣኝም ሲል አስተባብሏል። በኋላ ትራምፕ ቃላቸውን ለውጠው እኔ የተናገርኩት የመድኃኒት አስተዳደር ይህን መድኃኒት እንደው ከርህራሄ በመነጨ ሐኪሞች ለኮሮናቫይረስ በሽተኞች ቢጠቀሙት አልቃወምም ስለማለቱ ነው ብለዋል። "ከርህራሄ በመነጨ" ማለት አንድ ሐኪም ከመሞት ውጭ አማራጭ ለሌለው በሽተኛ ይህን መድኃኒት ቢሰጥ ክፋት የለውም ማለት ነው። ሐኪሞች በዚህ አውድ ውስጥ ይህን መድኃኒት ማዘዝ ይፈቀድላቸዋል። ምክንያቱ ደግሞ መድኃኒቱ በይፋ በምግብና መድኃኒት አስተዳደር የተመዘገበና የሚታወቅ ስለሆነ ነው። ምንም እንኳ የሚታወቀው በኮሮናቫይረስ ፈዋሽነቱ ባይሆንም። በህንድ ይህ መድኃኒት ውድ ያልሆነና ያለ ሐኪም ማዘዣ ሁሉ በየመድኃኒት ቤቱ የሚገኝ ነው። ሆኖም ኮሮናን ይፈውሳል የሚለው ወሬ መናፈሱን ተከትሎ መድኃኒቱ ላይ ህንድ ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ ጀምራለች። የሆነው ሆኖ ሐኪም ብዙም የማይሰሙት ትራምፕ እንደ ቅጠል እየረገፈ ላለው ሕዝባቸው "እጅግ አስፈላጊው መድኃኒት ይኸው ነው" ብለው የደመደሙ ይመስላል።
news-46040930
https://www.bbc.com/amharic/news-46040930
ኢትዮጵያ ጂ-20 ኮምፓክት የተባለውን ቡድን ተቀላቅላለች
ጂ-20 ይሉታል በእንግሊዝኛው አጠራር፤ ቡድን 20 የአማርኛ አቻ ፍቺው ነው፤ 20 የዓለም ሃገራትን ያቀፈው ቡድን።
ልዕለ ሃያላኑ አሜሪካ፣ ቻይና እና ጀርመንን ጨምሮ ሌሎች 16 የዓለማችን ሃገራትን እና አውሮፓ ሕብረት የቡድኑ አባላት ናቸው። በአውሮፓውያኑ 2008 ምሥረታውን ያደረገው ይህ ቡድን የየሃገራቱን ማዕከላዊ ባንኮች በማስተባበር ለምጣኔ ሃብታዊ መጠናከር የሚሠራ ነው። • የፖለቲካ አለመረጋጋት ለኢንስትመንት ደንቃራ ሆኖ ነበር ሃገራቱ ከራሳችን አልፎ ለመላው ዓለም የምጣኔ ሃብት መረጋጋትም እንሠራለን ይላሉ። ካናዳ እና አሜሪካ ከሰሜን፤ ሜክሲኮ፣ አርጀንቲናና ብራዚል ከደቡብ አሜሪካ፤ ቻይና፣ ኢንዶኔዢያ፣ ህንድ፣ ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ ከእስያ፤ ፈረንሳይ፣ ቱርክ፣ ጀርመን እና ጣልያን ከአውሮፓ፤ ብቸኛዋ የአፍሪቃ ተወካይ ደቡብ አፍሪቃና አውስትራሊያ አባል ሃገራት ናቸው። እኒህ የምድራችን ሁለት ሦስተኛ ህዝብ የሚኖርባቸው 19 ሃገራት የዓለማችንን ጠቅላላ ምርት 85 በመቶ እንዲሁም የዓለም ንግድን 80 በመቶ ይይዛሉ። ኢትዮጵያ እና ጂ-20 ኢትዮጵያ እና ጂ-20 ወዳጅነታቸው የሩቅ ዘመድ ዓይነት ነበር፤ አልፎ አልፎ ኢትዯጵያ ስብሰባውን በእንግድነት ከመታደም ያለፈ ሚና አልነበራትም። የዘንድሮ መዳረሻውን ከአባላቱ አንዷ በሆነችው ጀርመን ዋና ከተማ በርሊን ያደረገው የቡድኑ ስብሰባ ግን አንድ ሃሳብ ብልጭ ብሎለታል። ለምን የጂ-20 የአፍሪካ ክንፍ አናቋቁምም? የሚል። • ከኢትዮ- ቻይና ወዳጅነት ጀርባ በጀርመኗ መራሂተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል የተጠነሰሰው ይህ ውጥን ጂ-20 ኮምፓክት ከአፍሪቃ ጋር የተሰኘ ስያሜ ተሰጥቶታል። አላማውም የግል ኢንቨስትመንትን አህጉረ አፍሪካ ውስጥ ማነቃቃትና እና ማስተዋወቅ ይሆናል። ማዕቀፉ፤ አፍሪካ ውስጥ የጋራ ንግድ ቢበረታታ እና የገንዘብ ተቋማት ራሳቸውን ቢችሉ ትልቅ ለውጥ ይመጣል የሚል እምነትን አንግቦ ተነስቷል። ለውጥ ለማምጣት ቆርጠው የተነሱ የአፍሪካ ሃገራት ከዋናው የጂ-20 አባላት ጋር ምጣኔ ሃብታዊ ትስስራቸውን የሚያጠናክሩበት መንገድ እንደሚሆንም ታምኖበታል። ኢትዮጵያ፣ ቤኒን፣ ኮትዲቯር፣ ግብፅ፣ ጋና፣ ጊኒ፣ ሞሮኮ፣ ሩዋንዳ፣ ሴኔጋል፣ ቶጎ እና ቱኒዚያ የክንፉ የመጀመሪያ አባልነት መታወቂያ የተሰጣቸው ሃገራት ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በአውሮፓ አውሮፓ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድም ከፈረንሳይ ጉብኝታቸው በኋላ ያቀኑት ወደ ጀርመን ነው፤ በዚህ የምሥረታ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ። «የጂ-20 ሃገራት ውስጥ ያለው ዓይነት ኢንቨስትመንት እኛም ማየት እንሻለን፤ ይህ ክንፍ በዚህ ረገድ ጉልህ ሚና እንደሚኖረውም ተስፍ እናደርጋለን» ብለዋል በዝግጅቱ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ፍፁም አረጋም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ኮንፈረሱ ላይ ተገኝተው ስለኢትዯጵያ ንግግር እንዳደረጉ በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል። ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይኤምኤፍ እና የዓለም ባንክን የመሳሰሉ ግዙፍ ተቋማት የተገኙበት የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ኢትዮጵያ ለኢንቨስተሮች ምን ልታቀርብ እንደምትችል ያሳየችበት ነበርም ተብሏል። «ኢትዮጵያ ተወዳዳሪ የሆነ የኢንቨስትመንት አማራጭ አላት፤ ይህን ዕድል ተጠቅሜ ስትራቴጂክ የሆኑ አማራጮችን ማቅረባችንን ልገልፅላችሁ እወዳለሁ» ብለዋል መንበረ ሥልጣን ከጨበጥ መንፈቅ ያለፋቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ። በየቦታው የሚነሱ ግጭቶች እየናጧት የምትገኘው ኢትዮጵያን ጨምሮ የዚህ ክንፍ አባል የሆኑ ሃገራት በበርከታ መንገዶች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ እየተነገረ ይገኛል። • እውን የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ለኢትዮጵያ ይጠቅማል? ከጥቅሞቹ አንዱ ኢንቨስትመንትን በተመለከተ የጂ-20 አባል ሃገራት ከሌሎች ሃገራት በበለጠ ለክንፉ አባላት ቅድሚያ መስጠታቸው ነው። አልፎም የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይኤምኤፍ ቴክኒካዊ እርዳታ ሁሌም ከጎናቸው እንደሆነ ማዕቀፉ በግለፅ ያስቀምጣል። ከ20ዎቹ ሃገራት ኢንቨስት ለማድረግ የሚንቀሳቀሱ የግል ባለሃብቶች ወደእነዚህ 11 የአፍሪካ ሃገራት እንዲሄዱ መበረታታቸው ደግሞ ሌላኛው ጥቅም ተደርጎ ተቀምጧል። 2017 ላይ የተመሠረተው ይህ ክንፍ ምንም እንኳ አስካሁን ይህ ነው የሚባል ለውጥ ባያመጣም ለሃገራቱ ምጣኔ ሃብት መጠናከር የበኩሉን እንደሚያበረክት እምነት ተጥሎበታል። ከኢንቨስትመንት በፊት ሰላም ይቀድማል የሚል ትችት ያላጣት ኢትዮጵያስ ከዚህ ክንፍ አባልነት የምታተርፈው ምን ይሆን?. . . በጊዜ ሂደት የሚታይ ይሆናል።
news-46190743
https://www.bbc.com/amharic/news-46190743
ፈረንሳያዊ እናት ልጇን ለሁለት አመት ያህል ኮፈን ውስጥ በመደበቋ ተከሰሰች
ፈረንሳያዊቷ እናት ልጇን በመኪናዋ ኮፈን ውስጥ በመደበቅ ተከሰሰች።
ህፃኗ የተገኘችው መኪናዋ ጋራዥ ልትጠገን በመጣችበት ወቅት አንድ መካኒክ ድምፅ በመስማቱ ነው። እናቷም በህፃኗ ላይ ጥቃትን በማድረሷና ለእድሜ ዘላቂ የሆነ የአካል ጉዳት በማድረስ እስከ 20 አመት እስራት ይጠብቃታል። እርግዝናዋንና እንዲሁም መውለዷን ከህይወት አጋሯና ከሶስት ልጆቿ እንደደበቀችም ተገልጿል። •የሴት ልጅ ግርዛት በከፍተኛ ደረጃ ቀነሰ •"ቀጣዩን ምርጫ ከዳር ሆኜ ባልታዘብም ተወዳዳሪ ግን አልሆንም" ብርቱካን ሚደቅሳ ሮዛ ማሪያ ዳ ክሩዝ የተባለችው ይህቺ ግለሰብ ቱሌ በምትባለው ከተማ ክስ የቀረበባት ሲሆን፤ ልጇን በአንድ ክፍል በመደበቅና በኮፈን ውስጥ ታቆያት ነበር ተብሏል። በአውሮፓውያኑ 2013 የተገኘችው ይህች ህፃን ልጅ የሁለት ዓመት ዕድሜ ያላት ሲሆን በምግብ እጥረትና በመቀንጨር ላይ እንደነበረች ሪፖርቶች ያሳያሉ። ህፃኗን ያገኛት መካኒክ በበኩሉ የመኪናውን ኮፈን ሲከፍት መጥፎ ጠረን እንዳወደውና፣ ግርጥት ያለች፣ የተራቆተችና በሰገራ የተጨማለቀች ህፃን ልጅ እንዳገኘ ተናግሯል። የ50 ዓመት ዕድሜ ያላት ፖርቹጋላዊቷ እናት ፖሊስ በጠየቃት ወቅት "ልጅ እንዳልሆነችና ቁስ እንደሆነች ገልፃለች። የሰባት ዓመት እድሜ ያላት ይህች ህፃን በአሁኑ ወቅት በማደጎ ውስጥ ነው ያለችው። ሁለት ወንድሞቿና እህቷ ለጥቂት ጊዜ በማደጎ ውስጥ ቆይተው ወደ ቤተሰቦቻቸው ቤት ተመልሰዋል። የህይወት አጋሯ በበኩሉ ስለ ህፃኗም ሆነ ስለ እርግዝናው ምንም ባለማወቁ በነፃ ተሰናብቷል። የፍርድ ሂደቲ ከ5 እስከ 7 ቀናት ይወስዳል ተብሏል።
42770878
https://www.bbc.com/amharic/42770878
ሴት እስረኞችና የማዕከላዊ ምርመራ
ወ/ሮ ነበቡ ደሳለኝ የሶስት ሴት ልጆች እናት ነች። ጥር 22/2009 ዓ.ም መንገድ ላይ ነበር ድንገት የደህንነት አባላት የያዟት። ሲይዟት ለጥያቄ 'እንፈልግሻለን፣ ትመለሻለሽ' ቢሏትም እሷ ግን አላመነቻቸውም።
ስለዚህ መኪና ውስጥ ለመግባት ፈቃደኛ ሳትሆን ቀረች። ይህ ግን የደህንነት አባላቱን አላስደሰተም። ስለዚህ መኪና ውስጥ አንስተው ወረወሯት። በዚህ ምክንያትም የመኪናው ወንበር ሆዷ ላይ መቷት ጉዳት እንደደረሰባት ትናገራለች፤ ጀርባዋንም ያማታል። ማዕከላዊ ከገባች በኋላ ሕክምና ለማግኘት የጠየቀች ቢሆንም ለሁለት ወር ያህል ተከልክላ እንደቆየች ለቢቢሲ ተናግራለች። መጀመሪያ የተወሰደችው ወደ ማዕከላዊ እንደነበር የምትናገረው ነበቡ ስልኳን ከተቀበሏት በኋላ ስልኳ ላይ የሰፈሩ ሰዎችን ማንነት እንድትናገር ምርመራው እንደጀመረ ታስታውሳለች። ቤተሰቦቿ መታሰሯን ያወቁት መርማሪዎች ቤቷን ለመበርበር በሄዱበት ወቅት እንደሆነ የምትናገረው ነበቡ "ቤተሰቦቼ ጠፍታለች በሚል ፍለጋ ላይ ተሰማርተው ነበር" ብላለች። በብርበራው ወቅት ቤት ውስጥ የተገኙ ማንኛውም ሰነዶች ብርን ጨምሮ መወሰዳቸውን ታስታውሳለች። ''ማዕከላዊ ሰቆቃ የበዛበት ቦታ ነው" የምትለው ነበቡ በተለይ ደግሞ በምርመራው ሂደት ሴትነቷንና እናትነቷን የሚመለከቱ ዘለፋዎች እንደደረሰባት ትናገራለች። በምርመራ ወቅት በተለያዩ ንግግሮች አእምሮዋን ለመጉዳት ደጋግመው እንደሞከሩ የምትናገረዋ ነበቡ "ሌባ፣ ቅጥረኛ፣ ሽብርተኛ የምታደራጂ" እያሉ ይሰድቧት ነበር ትናገራለች። ከዚህ የከፋው ደግሞ "ልጆችሽ በረንዳ ነው የሚወጡት፣ ለወደፊቱ ሴተኛ አዳሪዎች ነው የሚሆኑት፣ ልጆችሽን ቁጭ አድርገን ስለሰራሽው እንነግራቸዋለን፣ ስለዚህ አንቺ ደግሞ እዚሁ ነው የምትበሰብሽው" የሚሉና ሌሎች አፀያፊ ስድቦች ይሰነዘሩባት እንደነበር ታስታውሳለች። በማዕከላዊ የሥነ-ልቦና ቀውስ ደርሶብኛል የምትለው ነበቡ በምርመራ ወቅት ብቻ ሳይሆን በኑሮም ጉዳት ይደርሳል ትላለች። በእስር ቤት እሷን ለመጠየቅ የሚሄዱ ቤተሰቦቿ ሳይቀሩ ተንገላተው እንደሚገቡም ታስታውሳለች። "ሲፈልጉ ምግብ፣ ሲፈልጉ ቤተሰቤን የሚፈልጉትን ነገር ብለው ይመልሳሉ" ይህ ሁሉ ሥነ-ልቦናዊ እና ማህበራዊ ጉዳት አለው ትላለች ነበቡ። ነበቡ ደሳለኝ በማዕከላዊ ምርመራ ወቅት ስለደረሰባት እንግልት ለሊሴ ባህሩ ክሳቸው ተቋርጡ በፌደራል መንግሥት ከተለቀቁ አምስት ሴት እስረኞች መካከል አንዷናት። የሁለት ልጆች እናት የሆነችው ለሊሴ ሰኔ ስምንት 2008 ዓም ከምትኖርበት ሸጎሌ አካባቢ ሦስት ማንነታቸውን የማታውቃቸው ሰዎች በኃይል አስገድደው ወደ ማዕከላዊ በመኪና እንደተወሰደች ታስታውሳለች። ''አሞኝ ስለነበር ከሐኪም ቤት ወደቤት ተመልሼ ብዙም ሳይቆይ ቤቴ ተከበበ። ከዚህ በፊትም ይመጡ ስለነበር ልጆቼ ፊት እንዳይዙኝ በማለት ከቤት ወጣሁ፤ ከዛ በመኪና ተከተሉኝ። በኋላም በኃይል ወደ መኪና አስገቡኝ።" ብላ የተያዘችበትን ሁኔታ ታስታውሳለች። ለሊሴ በተያዘችበት ቀን አይኗን ታስራ ከተማ ውስጥ ሲያሽከረክሯት ከቆዩ በኋላ ማታ ላይ ወደ ማዕከላዊ እንደወሰዷትና ለሶስት ቀን ከቤተሰቦቿ ደብቀው እንዳቆይዋት ትናገራለች። ሕይወት በእስር ቤት ነበቡ ስለታሰረችበት ስፍራ ስትናገር "የሴቶች ክፍል ያለው ሁለት ነው። አራት በአራት ወይም ሶስት በሁለት ይሆናሉ ክፍሎቹ። 20 እና 30 እስረኛ ተፋፍገን ነው የምንኖረው" ብላለች። እስር ቤት ሳለች እፈታለሁ ብላ አስባ እንደማታውቅ የምትናገረው ነበቡ "እዚሁ በስብሰሽ ትቀሪያለሽ' የሚለው ንግግር ስለነበር የሚመጣውን ነገር ሁሉ ለመቀበል ከመወሰን ውጭ ሌላ የማስበው ነገር አልነበረም" ትላለች። ነበቡ በደህንነቶች በቁጥጥር ስር ከዋለች በኋላ ለተከታታይ አምስት ወራት በየወሩ ፍርድ ቤት እየሄዱ የ28 ቀን ቀጠሮ ተቀብሎ ከመምጣት ውጪ ጉዳይዋ ታይቶ ፍትህ አገኛለሁ የሚል ተስፋ እንዳልነበራት ታስታውሳለች። "እኔ ንፁህ ነኝ ብልም በንፅህናዬ አላምንበትም ነበር" የምትለው ነበቡ ለዚህ ደግሞ ምክንያቷ ከሌሎች እህቶቼ እንዳየሁት እስከፈለጉት ድረስ በእስር ቤት ስለሚያቆዩ እኔም ለዚህ ራሴን አዘጋጅቼ ነበር ትላለች። ነበቡ እንደምትለው ለመፈታታቸው ምክንያት በሃገሪቱ የተለያዩ ስፍራዎች የተነሱት ተቃውሞዎች መንግሥት አካሄዱ ትክክል እንዳልሆነ እንዲረዳ ስላደረገው ነው ትላለች። ለአራት ወር በማዕከላዊ እንደቆየች የምትናገረው ለሊሴ የማዕከላዊ ቆይታዋ በጣም አስቸጋሪ እንደነበር ትናገራለች። እንደ ነበቡ ሁሉ ለሊሴም በማዕከላዊ ስቃይ ተፈፅሞባታል ''የሚፈልጉትን እንዳምን ድብደባ፣ የተለያዩ ማስፈራሪያዎችን ያደርሱብኝ ነበር።" በኋላም ከኦነግ ገንዘብ በእርሷ በኩል ይደርሰው እንደነበር ድሪብሳ በተባለ ግለሰብ ላይ መስክሪ ተብላ በተደጋጋሚ ተጠይቃ እንቢ በማለቷ ክፉኛ መደብደቧን ትናገራለች። ''ከግራና ከቀኝ በጥፊ ያጣድፉኝ ነበር። ጣቶቼ መካከል ማስመሪያ አስገብተው ይጨምቋቸዋል። በእስክርቢቶ አይኔን ለመውጋት በተደጋጋሚ ሞክረዋል" ትላለች። የማታውቀውን ነገር ወረቀት ላይ በመፃፍ ፈርሚ በማለት እንደተደበደበች እንዲሁ ትናገራለች። በማዕከላዊ መረገጥ፣ በጥፊ መመታት፣ አስተኝተው ጀርባ ላይ መሄድ፣ ስፖርት ማሰራት እና እርቃን በወንድ መርማሪዎች ፊት እንዲቆሙ በማድረግ የተለያዩ እንግልቶች ይደርስባቸው እንደነበር ታስታውሳለች። ከአራት ወር የማዕከላዊ ቆይታ በኋላ ወደ ቃሊቲ መዛወሯን የምትናገረው ለሊሴ፤ እዚያ ድብደባ ባይኖርም በፖለቲካ ምክንያት የታሰረ ሰው ከሌሎች እስረኞች እኩል መብት የላቸውም ትላለች። እርሷን ጨምሮ ሦስት ሰዎች የቀረበባቸው ምስክርም ሆነ የሰነድ ማስረጃ ስላልተገኘ፤ ስታወሩ የተቀዳ ነው ተብሎ ከቴሌ በመጣ የድምፅ ቅጂ በአሸባሪነት መከሰሷን ትናገራለች። የልጆች እናት የሆኑት ነበቡ ደሳለኝ እና ለሊሴ ባህሩ በማዕከላዊ የምርማራ ማዕከልና በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ ከቆዩ በኋላ መንግሥት በሰጠው ውሳኔ መሰረት ክሳቸው ተቋርጦ ከተለቀቁ እስረኞች መካከል በመሆን ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል።
news-49196476
https://www.bbc.com/amharic/news-49196476
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ፡ "ሰኔ 15 አደገኛ ክስተት ነበር"
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ዛሬ ከሰዓት በሰጡት መግለጫ የሰኔ 15ቱ ግድያ እና 'መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ'፣ ቀጣዩን ምርጫ እና የሰብዓዊ ምበት አያያዝን በሚመለከት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የሰኔ 15ቱን ሁኔታን አቅልሎ ማየት ልክ አይደለም ያሉ ሲሆን መንግሥታቸው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውን በፍጥነት መቆጣጣር ባይችል ኖሮ አስከፊ ነገር ይዞ የሚመጣ አደገኛ ክስተት ነበር ብለዋል። ጀኔራል ሰዓራ መኮንንን ገድሏል ተብሎ የተጠረጠረው ግለሰብ ስለሚገኝበት ሁኔታ ጥያቄ የቀረበላቸው ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ተጠርጣሪው በህይወት እንደሚገኝ እና አንገቱ ላይ ለደረሰበት ጉዳት የህክም እርዳታ እያገኘ ሲሆን በጉዳቱ ምክንያት መናገር ባለመቻሉ ከእርሱ ይገኝ የነበረ መረጃ ማግኘት አለማቻሉን አስረድተዋል። ይሁን አንጂ ጀኔራሉን በመግደል የተጠረጠረው ግለሰብ በስልክ ሲገናኛቸው የነበሩ ሰዎች በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ መደረጉን እና ከእነርሱም ብዙ መረጃዎች መሰብሰባቸውን ገልጽዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ተጨማሪ ጀኔራሎችን ለመግደል እንቅስቃሴ ሲደረግ እንደነበር መረጃ አለንም ብለዋል። መንግሥት የሰኔ 15ቱን ክስተት መሰረት አድርጎ የግለሰቦች እና የመገናና ብዙሃንን ድምጽ ለማፈን ሙከራ አድርጓል የሚል ቅሬታ ይቀርብበታል ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ ሲመልሱ ፤ ይህ እውነት አይደለም መንግሥት የሰዎችን ደምጽ የማፈን ፍላጎት የለውም እንደውም ከዚህ ቀደም በመንግሥት ተዘግተው የነበሩ መገናኛ ብዙሃን እንዲከፈቱ ተደርጓል ብለዋል። የኢንተርኔት አገልግሎትን በተመለከተ፡ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል፤ የጸጥታ ችግር በተከሰተ ቁጥር ለምን የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ ይደረጋል? የሚል ይገኝበታል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ለዚህ ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ፤ እራሳችንን ከበለጸጉት ሃገራት ጋር ማወዳደር የለብንም፤ በበለጸጉ ሃገራት ሰዎች ኢንተርኔትን በመጠቀም ብሔርን ከብሔር የሚያጋጭ ምልዕክት አያስተላልፉም፣ በበለጸጉት ሃገራት ሰዎች ኢንተርኔትን ለበጎ ነው የሚጠቀሙት ያሉ ሲሆን፤ የሰዎችን ህይወት እና ንብረት ከጥቃት ለማትረፍ አስፈላጊ ሆኖ እስከተገኘ ድረስ ለሳምንት ሳይሆን እስከ ወዲያኛው ኢንተርኔት ሊዘጋ ይችላል ብለዋል። የሰብዓዊ መብት አያያዝን በተመለከተ፡ የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ መንግሥት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የሰብዓዊ መብት አያያዝን በተመለከተ ቅሬታዎች እየተነሱበት እንደሆነ በመጠቀስ መንግሥታቸው በዚህ ረገድ የነበረው አቋሙ ስለመቀየሩ ጥያቄ የቀረበላቸው ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ አሁንም ጭለማ ቤት የታሰረ የለም፣ ሰው አይገረፍም፣ ጥፍር አይነቀልም ያሉ ሲሆን በሰብዓዊ መብት አያያዝ ያለን አቋም አልተቀየረም፤ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲስፋፋ ነው ፍላጎታችን ብለዋል። የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግነኙነትን በተመለከተ ከኢትዮጵያ መልካም ግነኙነት ከኤርትራ ጋር መመስረቷን በማስታወስ፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የኤርትራ ህዝብ እና መንግሥት ከኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግሥት ጋር አብሮ ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ተናግራዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ሁለቱ ሃገራት ግኑኝነታቸውን አድሰው ወደስራ ሲገቡ ግን በርካታ የባህል እና የኢኮኖሚ መዛባቶች መስተዋላቸውን አልሸሸጉም። ይህ የሁለቱን ሃገራት ግነኙነትም ስርዓት ለማስያዝ እየተሰራ መሆኑን እና ይህም ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል ጠቁመዋል። የሲዳማ ዞን የክልል እንሁን ጥያቄን በተመለከተ፡ የትኛውም ህዝብ ፖለቲካዊ መብቱን የመጠየቅ እና የማስከበር መብት አለው ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ፤ የክልልነት ጥያቄው ከፖለቲካ መብት በተጨማሪ የሃብት ክፍፍል እና ህጋዊ ሂደቶች ያስፈልጉታል በማለት፤ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ህዝበ ውሳኔው እንደሚከናወን ተናግረዋል። የአዴፓ እና የህወሃት የቃላት ጦርነትን በተመለከተ፤ ከሰሞኑን በህወሃትና በአዴፓ መካከል የተፈጠረው የቃላት ጦርነት በፖለቲካ አለም የሚያጋጥም መሆኑን የሚናገሩት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ሁለቱ ፓርቲዎች ለህዝብ ጥቅም ሲባል አብራው ሲታገሉ መቆየታቸውን አስታውሰዋል። ሁለቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለረጅም ዓመታት ለህዝብ ጥቅም ሲሉ አብረው ታግለዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክትር አብይ፤ በዚህ ሁሉ ጊዜ ውስጥ ግን እንዲህ አይነት ንትርኮች ሊያጋጥሙ ይችላሉ ብለዋል። ሁለቱ የኢህዴግ እህት ድርጅቶች ችግሮቻቸውን በውይይት እንዲፈቱ መድረክ እንደሚዘጋጅ ተናግረዋል።
42503300
https://www.bbc.com/amharic/42503300
የስልክዎን ባትሪ ለረዥም ጊዜ ለመጠቀም የሚያግዙ ነገሮች
የስማርት ስልኮች ባትሪ ቶሎ ቶሎ ማለቅ የቴክኖሎጂው ትልቁ ድክመት ሆኗል። አፕል ከቀናት በፊት የባትሪዎችን እድሜ ለማርዘም ሲባል የስልኮቹን የአሰራር ሥርዓት (ኦፕሬቲንግ ሲስተም) ዝግ እንዲል ማድረጉን ይፋ አድርጓል።
ምንም እንኳ ኩባንያው ምርቶቹን እያሻሻለ ቢሆንም በአሜሪካ ብዙ ክሶች ተመስርተውበታል። ሞባይል ስልኮች የሚጠቀሙት በቶሎ የሚሞሉ ሊቲየም አየን ባትሪዎችን ሲሆን ዲዛይናቸውም ባትሪዎቹ ተጠጋግተው እንዲቀመጡ የሚያደርግ ነው። የስማርት ስልኮች ግፅታና ዲዛይን ቶሎ ቶሎ መቀያየር ማሻሻያውን እንዳከበደውም እየተነገረ ነው። በርግጠኝነት ይህ ነው የሚባል ነገር ባይኖርም የስማርት ስልኮችን እድሜ ለማርዘም የሚረዱ ነገሮች አሉ። 1.ደካማ በይነ መረብ ስልኮዎ በየሄዱበት ጥሩ የበይነ-መረብ (ኢንተርኔት) መስመርን ለማግኘት ይሞክራል። በተለይም ደካማ የበይነ-መረብ አገልግሎት ባለበት ወይም አንድ ቦታ ላይ ብዙ ሰዎች የገመድ አልባ ኢንተርኔትን (ዋይ ፋይ) ለመጠቀም ሲሞክሩ ስልክዎ ሙከራውን ያከረዋል። ምርጥ የሚባል መፍትሄ ባይሆንም ስልክዎን ኤርፕሌን ሞድ ላይ ማድረግ ጥሩ ኢንተርኔት ለማግኘት እየታገለ ያለው ስልክዎ ባትሪ እንዳይጨርስ ይረዳዋል። 2. አንዳንድ መተግበሪያዎች (አፕልኬሽኖች) አንዳንድ መተግበሪያዎች ባትሪ ይጨርሳሉ። ስለዚህ የማይፈልጓቸውን መተግበሪያዎችን መዝጋት የባትሪን እድሜ ያረዝማል። በተጨማሪም ባትሪ የሚለው ክፍል ውስጥ በመግባት በከፍተኛ ሁኔታ ባትሪ እየጨረሰ ያለውን መተግበሪያ መለየት ያስፈልጋል። 3. ያሉበትን ቦታ አመልካች (ጂፒኤስ) የቦታ አመልካችን (ጂፒኤስ) ማብራትም ባትሪ የሚጨርስ ነገር ነው። እንደ ትዊተር ያሉ አፕልኬሽኖች ደግሞ እርስዎ ሳያውቁት ሁሉ ያሉበትን ቦታ መዝግብው ይይዛሉ። ስለዚህ ያሉበትን ቦታ የሚመዘግቡ መተግበሪያዎችን ቁጥር ለመቀነስ የማይፈልጓቸውን እንዳይሰሩ ማድረግ ይቻላል። 4.ከፍተኛ ሙቀት ሊቲየም ባትሪዎች ለከፍተኛ ሙቀት ከተጋለጡ በደንብ አይሰሩም። ምክንያቱም በውስጣቸው ያለው አየን ባትሪው ቶሎ ቶሎ ቻርጅ እንዲደረግ ያስገድዳልና። ስለዚህ ስልክዎ ለከፍተኛ ሙቀት ወይም ለከፍተኛ ቅዝቃዜ እንዳይጋለጥ ማድረግ አይነተኛ መፍትሄ ነው። 5. ትልልቅ ስክሪኖች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስልኮች ትልልቅ ስክሪኖች እንዲኖራቸው እየተደረገ ነው። ይህ ትልቅ ስክሪን ሲከፈትና ሲበራ ባትሪ ይጨርሳል። ስለዚህም የስክሪኑን የብርሃን መጠን መቀነስ ጠቃሚ ነው። ስክሪኑን ማጥፋትና ቶሎ ቶሎ ስልክዎን አለመመልከትም ሌላው መፍትሄ ነው። 6. ከፍተኛ ድምፅ የመተግበሪያዎች ወይም የስልክ ጥሪዎች ድምፅ ከፍተኛ ከሆነ ባትሪ ይጨርሳል። አብዛኛውን ጊዜ የድምፅ ነገር ስልክዎ ባለው ስፒከር የሚወሰን ይሆናል። የጆሮ ማዳመጫ መጠቀምና በሚያዳምጡበት ወቅት የሌሎች መተግበሪያዎችን ድምፅ ማጥፋትም ጥሩ ነው። 7. ቶሎ ቶሎ ቻርጅ ማድረግ በፊት በፊት ስልክዎ ባትሪ እስኪጨርስ ከተጠቀሙ በኋላ ቻርጅ ማድረግ ነበር ተመራጩ። አሁን ግን ማድረግ የሚጠቅመው ተገላቢጦሹን ነው። ይህ ማለት ደግሞ ከስር ከስር ባትሪ ሳይጨርስ ስልክን ቻርጅ ማድረግ መልካም ነው። ባትሪዎ መጠን ከግማሽ በታች ዝቅ እንዳይል ቻርጅ ቢያደርጉ የባትሪዎን እድሜ እንደሚያረዝም የሞባይል ስልኮች ባለሙያዎች ይመክራሉ። እርግጠኛ መፍትሄዎች ሁሉም የሞባይል አምራቾች የሚስማሙበት ዋነኛ መፍትሄ ስልክዎን ባትሪ ሃይል ቆጣቢ ሞድ ላይ ማድረግን ነው። ይህ ማለት ደግሞ የስልክዎ ስክሪን ብርሃን ይቀንሳል፣ ስልክዎ ንዝረት ያቆማል፣ ብዙ ማሳወቂያዎች (ኖቲፊኬሽን) አይደርስዎትም። ያሉበትን ቦታ አመልካች አገልግሎት አይሰጥም። ነገር ግን ባትሪዎ በአሁኑ ወቅት የደከመ ከሆነ እነዚህ ነገሮችን ማድረግ ብዙም ለውጥ አያመጣም፤ ያለው አማራጭ የስልክዎን ባትሪ መቀየር ብቻ ነው።
news-53379801
https://www.bbc.com/amharic/news-53379801
በደቡብ አፍሪካ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አጋቾች ባደረሱት ጥቃት አምስት ሰዎች ተገደሉ
በደቡብ አፍሪካ አንድ ቤተክርስቲያን ላይ አጋቾች ባደረሱት ጥቃት አምስት ሰዎች መገደላቸው ተገለፀ። የጥቃቱ መነሻ የሆነው ከቤተክርስቲያኒቱ አመራር ጋር በተፈጠረ ውዝግብ ነው ተብሏል።
የደቡብ አፍሪካ ፖሊስም ጥቃቱ ደረሰበት በተባለበት ከጆሃንስበርግ ወጣ ብሎ በሚገኘው ቤተ ክርስቲያን ህፃናትን ጨምሮ በርካታ ምዕመናንን ከአጋቾች ነፃ ማውጣታቸውን አሳውቋል። ከዚህም በተጨማሪ አርባ የሚሆኑ ግለሰቦችንና የጦር መሳሪያዎችን በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ተገልጿል። አለም አቀፍ ፔንጤቆስጣል በተሰኘው በዚህ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ምዕመናኑን ያገቱት ግለሰቦች በቤተክርስቲያኒቷ አመራር ላይ ጥያቄ ያነሱ ተገንጣይ ቡድን እንደሆኑ የአይን እማኞች አሳውቀዋል። የቤተ ክርስቲያኗ መሪ ከአራት አመታት በፊት መሞታቸውን ተከትሎ የግጭት መነሻም ሆኖ ነበር ተሏል። ከሁለት አመታት በፊትም በምዕመናኑ መካከል የተኩስ ልውውጥ መፈጠሩን ተከትሎ ፖሊስም ተጠርቶ እንደነበር አይኦኤል የተባለው ሚዲያ ዘግቧል። ከአመት በፊትም እንዲሁ 6.5 ሚሊዮን ዶላር ከቤተክርስቲያኗ መዛግብት ጠፍቷል በሚልም ውዝግብ ተፈጥሮ እንደነበርም እንዲሁ ሶዌታን የተባለው ጋዜጣ ዘግቧል። ቅዳሜ እለት ዘጠኝ ሰአት አካባቢ ነው ሲሆን ጥቃቱ የደረሰው፤ የብሔራዊ ፖሊስ ቃለ አቀባይ ብርጋዲየር ቪሽ ናይዱ እንዳሳወቁት አጋቾቹ የቤተ ክርስቲያኗን ግቢ ለመቆጣጠር እንደመጡ ተናግረዋል። አራት ሰዎች በተተኮሰባቸው ጥይት ተገድለው በመኪናቸው ውስጥ የተቃጠሉ ሲሆን አንድ የጥበቃ ሰራተኛም እንዲሁ ለመካለከል ሲሞክር ተገድሏል። ከሰላሳ በላይ የተለያያዩ ጦር መሳሪያዎችም በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ እንደተያዘም ተገልጿል። ፖሊስ እንዳሳወቀው በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ የጆሃንስበርግ ፖሊስና የማረሚያ ቤት ፖሊሶች ይገኙበታል ተብሏል። አለም አቀፉ የጴንጤቆስጣል ቤተክርስቲያን ሶስት ሚሊዮን ያህል አባላት አሉት።
50848549
https://www.bbc.com/amharic/50848549
ዶናልድ ትራምፕ የቀረበባቸውን ክስ ለመከላከል ሴኔት ፊት ሊቀርቡ ነው
የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሴኔት ፊት ቀርበው የቀረበባቸውን ክስ እንዲከላከሉ በትናንትናው ዕለት ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምጽ ወስኗል።
ዶናልድ ትራምፕ በተወካዮች ምክር ቤት ሴኔቱ ፊት ቀርበው ክሳቸውን እንዲከላከሉ ሲደረግ በታሪክ ሶስተኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ናቸው። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሴኔት ፊት ቀርበው ክሳቸውን ሲከላከሉ የሚሰጠው ውሳኔ በስልጣናቸው ላይ መቀጠል አለመቀጠላቸውን ለመወሰን ይረዳል። • እሷ ማናት፡ ከሊስትሮነት እስከ ከተማ አውቶቡስ አሽከርካሪነት በትናንትናው ዕለት ምክር ቤቱ በፕሬዝዳንቱ ላይ በቀረቡ ሁለት ክሶች ላይ ድምጽ ሰጥቷል። አንደኛው ክስ ፕሬዝዳንቱ ስልጣናቸውን ያላአግባብ ተጠቅመዋል የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የምክር ቤቱን ስራ አደናቅፈዋል የሚል ነው። ሁለቱንም ክሶች ዲሞክራቶች ሲደግፉት ሪፐብሊካን ግን ተቃውመውታል። ድምጽ አሰጣጡ እየተካሄደ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሚችጋን የምረጡኝ ቅስቀሳ ላይ የነበሩ ሲሆን፣ ለተሰበሰበው ደጋፊያቸው" ስራ እየፈጠርንና ስለሚቺጋን እየተሟገትን ባለበት ሰዓት የምክር ቤቱ አክራሪ ኃይሎች በቅናት፣ በጥላቻና በቁጣ ተሞልተው ምን እያደረጉ እንደሆነ እያያችሁ ነው" ብለዋል። ከምክር ቤቱ ውሳኔ በኋላ ዋይት ሐውስ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳለው፣ ፕሬዝዳንቱ በሴኔቱ ችሎት " ነጻ እንደሚወጡ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ናቸው" ብሏል። የፕሬዝዳንት ትራምፕ መከሰስ ጉዳይ በምክር ቤቱ ለ10 ሰዓታት ያህል አከራክሯል። • 'የአልባኒያ ተቃዋሚዎች' በትግራይ • የኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጁ በዋጋ የሚያንራቸው ምርቶች በኋላም ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ትራምፕ የዩክሬን አቻቸውን የምርጫ ተቀናቃኛቸውን፤ ጆ ባይደን፤ ላይ ምርመራ እንዲጀምሩ ጫና አድርገዋል በሚል፣ ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም በሚል የቀረበባቸውን ክስና ሁለተኛው ፕሬዝዳንቱ ለሚደረግባቸው ምርመራ መረጃዎችን ለመስጠት ተባባሪ ባለመሆናቸው የምክር ቤቱን ስራ በማደናቀፍ በሚለው ክስ ላይ ድምጽ ሰጥተዋል። በሁለቱም ክሶች ዲሞክራቶች አብላጫውን የድጋፍ ድምጽ በመስጠት አሳልፎታል። ከዚህ በፊት በአሜሪካ ታሪክ ሴነት ፊት ቀርበው ክሳቸውን የተከላከሉ ፕሬዝዳንቶች አንድሪው ጆንሰንና ቢል ክሊንተን ሲሆኑ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሶስተኛው ይሆናሉ።
news-50031930
https://www.bbc.com/amharic/news-50031930
በቡርኪና ፋሶ መስጅድ ላይ በተሰነዘረ ጥቃት 15 ሰዎች ተገደሉ
በሰሜን ቡርኪና ፋሶ በአንድ መስጅድ ላይ በተሰነዘረ ጥቃት ቢያንስ 15 ሰዎች መገደላቸው ተገልጿል።
ከተፈጸመው ጥቃት በኋላ የመንግሥት ጸጥታ አስከባሪዎች ወደ ስፍራው ተሰማርተዋል ታጣቂዎች ሳልሞሲ ተብላ በምትጠራ መንደር መስጅድ ውስጥ ጸሎት ሲያደርሱ በነበሩ ሰዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ ነው 15 ሰዎች የተገደሉት። በዚህ ጥቃት የተደናገጡ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ወደ ጎረቤት ሃገር ማሊ መሸሽ ጀምረዋል። በማሊ በምትገኝ አንድ መንደር ውስጥ '100 ሰዎች ተገደሉ' የአይ ኤስ መሪ ከአምስት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ታየ በማሊ 37 ሰዎች ገደማ በታጣቂ ተገደሉ በቡርኪና ፋሶ መሰል ጥቃቶች ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ተከስተው የነበረ ሲሆን፤ ጥቃቶቹ የሚፈጸሙት ደግሞ በጽንፈኛ እስላማዊ ቡድኖች እንደሆነ ይነገራል። ጥቃቱ ከተሰነዘረባት መንደር አቅራቢያ በምትገኘው ጎሮም-ጎሮም ከተማ ነዋሪ የሆኑ አንድ ሰው ለኤኤፍፒ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት፤ ''ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ ሰዎች አከባቢውን ለቅቀው እየወጡ ነው"። እስካሁን ለጥቃቱ ኃላፊነቱን የወሰደ አካል የለም። ከጎርጎሳውያኑ 2015 ወዲህ በቡርኪና ፋሶ የጽንፈኛ ቡድኖች የሚያደርሱት ጥቃቶች የተበራከቱ ሲሆን፤ በዚህም ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል። የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን እንደሚለው ከሆነ በቡርኪና ፋሶ ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ ሩብ ሚሊዮን ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል።
news-48431584
https://www.bbc.com/amharic/news-48431584
የምልክት ቋንቋ በብዛት የሚነገርባት መንደር
ቤንግካላ በምትባለው ትንሽ የኢንዶኔዢያ መንደር የሚወለዱ ሰዎች አብዛኛዎቹ መስማት የተሳናቸው ናቸው። ከስድስት ትውልዶች በላይ ያስቆጠረው ይህ አጋጣሚ በአካባቢው ሰዎች ዘንድ ከእርግማን የመጣ እንደሆነ ይታመናል።
ሳይንቲስቶች ግን በጤና እክል ምክንያት የሚመጣና ከወላጅ ወደ ልጆች የሚተላለፍ ችግር እንደሆነ ያስረዳሉ። በዚህች መንደር መስማት የተሳናቸው ሰዎች የሚናገሩት ካታ ኮሎክ የተባለ የምልክት ቋንቋ አለ። ካታ ኮሎክ በኢንዶኔዢያኛ መስማት የተሳናቸው ሰዎች ቋንቋ እንደማለት ነው። • "አካል ጉዳተኛ መሆኔ ጥሩ ደረጃ እንድደርስ አድርጎኛል" • ሙዚቃ ሳይሰሙ መወዛዋዝ ይችላሉ? ሲወለዱ ጀምሮ መስማት የተሳናቸው የዚህች መንደር ነዋሪዎች ከሌሎች መስማት የተሳናቸው ሰዎች የተሻለ ሕይወት ነው የሚመሩት። ምክንያቱም መስማት የሚችሉትም ግማሾቹ ነዋሪዎች ካታ ኮሎክ የተባለውንና በመንደሪቷ ብቻ የሚታወቀውን የምልክት ቋንቋ መናገር ይችላሉ። ለብዙ ዘመናት በመንደሪቱ የኖሩት መስማት የተሳናቸው ሰዎች ስለሆኑና ጎረቤትም ሆነ አንድ የቤተሰብ አባል መስማት ስለማይችል ግማሽ የሚሆኑት ነዋሪዎች ለመግባባት ሲሉ የምልክት ቋንቋውን መማር ግዴታቸው ነው። ዊንሱ የመንደሯ ነዋሪ ሲሆን ወጣት እያለ የባሊ ደሴትን ለቱሪስቶች በመስጎብኘትና የማርሻል አርትስ ጥብበ በማሳየት ሕይወቱን ይመራ ነበር። ለሥራ በተንቀሳቀሰባቸው የተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎችን ብዙ መስማት የተሳሳናቸው ሰዎችን የመተዋወቅ እድል አጋጥሞታል። እሱ እንደሚለው አብዛኛዎቹ መስማት የተሳናቸው ሰዎች በጣም ቅርብ ከሚሏቸው የቤተሰብ አባላት ውጪ ከማንም ጋር አይነጋገሩም። ቋንቋቸውንም ለመማር ጥረት የሚያደርግ ሰው የለም። በኢንዶኔዢያ መስማት የተሳናቸው ጥምረት ተወካይ የሆኑት ኬቱት ካንታ መስማት የተሳናቸው ሆነው ለሚወለዱ ሰዎች ከዚህች መንደር የተሻለ ቦታ የለም ብዬ አላምንም ብለዋል። በዚህች ትንሽ መንደር መስማት የሚችሉት ሰዎች 'ኢግኔት' ተብለው የሚጠሩ ሲሆን መስማት ከተሳናቸው የመንደሪቱ ነዋሪዎች ጋር ተቀላቅለው የሆድ የሆዳቸውን ሲያወሩ መመልከት የተለመደ ነው። ከመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እስከ ሃይማኖት ተቋማት፣ ከገበያ ቦታዎች እስከ መዝናኛ ስፍራዎች ሁሉም ቦታ ለይ መስማት የተሳናቸውና ያልተሳናቸው ተቀላቅለው ነው የሚኖሩት። • በዓይነ ስውሯ የተሠራው የሚያይ ሻንጣ • ''እግሬን ባጣም ትልቁን ነገር አትርፌ ለትንሹ አልጨነቅም'' በካታ ኮሎክ የምልክት ቋንቋ መሰረት ሁሉም ነገር በቀላሉ ለመረዳት እንዲቻል ተደርጎ ነው የተሰራው። ረጅም ለማለት እጅን ወደላይ በመስቀል ቁመትን ማሳየት እንዲሁም ትልቅ ለማለት ደግሞ እጆችን ሰፋ አድርጎ ምልክት ማሳየትን የመሳሰሉ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ። በዚህ ምክንያት ማንኛውም ቋንቋውን የማይናገር ሰው እንኳን በቀላሉ መግባባትና የምልክት ቋንቋውን በአጭር ጊዜ መልመድ ይችላል። በቤንግካላ መንደር መስማት የተሳናቸውን ያልተሳናቸው ለሚሰሩት ማንኛውም ዓይነት ሥራ እኩል ክፍያ ነው የሚፈጸመው። ነገር ግን ከመንደሯ ወጣ ብለው ሥራ ማግኘት የሚፈልጉ መስማት የተሳናቸው ሰዎች ብዙ ፈተናዎች እንደሚገጥሟቸው ይናገራሉ።
news-50317390
https://www.bbc.com/amharic/news-50317390
የኢትዮጵያዊቷ ህክምና መቋረጥ በደቡብ አፍሪካ አነጋጋሪ ሆነ
ለአስር ዓመታት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የኖረችው ኢትዮጵያዊት አሳሳቢ የጤና ችግር አጋጥሟት ሆስፒታል ገብታ ህክምና ማግኘት ከጀመረች በኋላ በፍርድ ቤት ውሳኔ እንድትወጣ መደረጉ ሌላ የፍርድ ቤት ሂደት ቀሰቀሰ።
በስደት ወደ ደቡብ አፍሪካ ገብታ፤ ለስድስት ወራት በሚታደስ የመኖሪያ ፈቃድ ለረዥም ዓመታት የግል ሥራ እየሠራች የቆየችው ኢትዮጵያዊት ዓለም ኦርሲዶ፤ ከባድ የኩላሊት ህመም አጋጥሟት ሆስፒታል ከገባች በኋላ ደቡብ አፍሪካዊ ዜግነት ወይም መደበኛ የጥገኝነት ወረቀት የላትም በሚል ህክምና አቋርጣ እንድትወጣ መደረጉ ተነግሯል። • ደቡብ አፍሪካ በወሮበሎች ላይ የጦር ሠራዊቷን አዘመተች • በደቡብ አፍሪካ እስር ላይ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ተለቀቁ በድንገተኛ ህመም ሆስፒታል ተወስዳ የኩላሊት እጥበት (ዳያሊስስ) እንደሚያስፈልጋት ተነግሯት፤ የህክምና እርዳታ ሲደርግላት የቆየችው ዓለም፤ አስፈላጊው የመኖሪያ ሰነድ እንደሌላት ተነግሯት ህክምናዋን አቋርጣ እንድትወጣ በመታዘዟ ጉዳይዋ ፍርድ ቤት ሄዶ ነበር። ዓለም ከደቡብ አፍሪካ መንግሥት በጥገኝነት እንድትቆይ የተሰጣት ሰነድ በየስድስት ወሩ የሚታደሰ የመኖሪያ ወረቀት መሆኑን የሚናገሩት የኢትዮጵያዊቷን ጉዳይ በቅርበት የሚከታተሉት አቶ ዳዊት አስገዶም ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚህ የጥገኝነት ወረቀት በርካታ ኢትዮጵያዊያን ደቡብ አፍሪካ ውስጥ እንደሚገኙ የሚናገሩት አቶ ዳዊት ዓለም ሆስፒታል እያለች ያጋጠማት ነገር ሁሉንም ማስደንገጡን ና ማሳዘኑን ገልጸዋል። • ደቡብ አፍሪካውያን መጤ ጠልነትን ማስቆም ይችሉ ይሆን? • ወንድማማቾች አግብተው የነበሩ ፓኪስታናውያን በጋራ ራሳቸውን አጠፉ ዓለም ያላት በየስድስት ወሩ የሚታደሰው የመኖሪያ ፈቃድ የጤና ችግር አጋጥሟት ሆስፒታል በቆየችበት ጊዜ የአገልግሎት ጊዜው በማብቃቱ መታደስ የነበረበት ሲሆን፤ በህክምና ላይ በቆየችበት ጊዜ አስፈላጊው የመኖሪያ ሰነድ ስላልነበራት ህክምናዋ እንዲቋረጥ ተደርጓል። ጉዳዩም ወደ ፍርድ ቤት አምርቶ፤ ፍርድ ቤቱም ዓለም የሚያስፈልጋትን ህክምና ለማግኘት የሚያስችላት የመኖሪያ ሰነድ እንደሌላት በመግለጽ ከሆስፒታል እንድትወጣ መወሰኑ ተገልጿል። ደቡብ አፍሪካ የሚኖሩት ኢትዮጵያዊ አቶ ዳዊት አስገዶም እንደሚሉት፤ ዓለም ወደ ደቡብ አፍሪካ ከሄደች አስር ዓመት የሆናት ሲሆን፤ በነዚህ ዓመታት ውስጥ የመኖሪያ ሰነዷን በየስድስት ወሩ እያሳደሰች ስትኖር ቆይታለች። የስድስት ወር የመኖሪያ ፈቃድ ለአጭር ጊዜ የሚሰጥ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ዳዊት፤ "ከዚህ ፈቃድ ተከትሎ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ መስጠት ሲኖርባቸው፤ ለዓመታት በአጭር ጊዜ የጥገኝነት ሰነድ እንድትቆይ ማድረጋቸው የነሱ ችግር ነው" በማለት ጠቅሰዋል። በዚህም ምክንያት ዓለም የሚያስፈልጋትን ህክምና እንዳታገኝ መደረግ የለባትም በሚል አቶ ዳዊትና ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ከሰብዓዊ መብት ቡድኖች ጋር በመሆን ገዳዩን መልሰው ወደ ፍርድ ቤት መውሰዳቸውንም ተናግረዋል። • የአጋላጩ መረጃ የቦይንግ ኦክስጅን አቅርቦት ላይ ጥያቄ አስነሳ • በቃፍታ-ሸራሮ ብሔራዊ ፓርክ በተከሰተው ሰደድ እሳት 1,500 ሄክታር ደን ወደመ ዓለም የግድ የኩላሊት እጥበት በሳምንት ሦስት ጊዜ ማድረግ እንዳለባት በሃኪሞች የተነገራት ቢሆንም፤ ከሆስፒታል እንድትወጣ ከተደረገች በኋላ ላለፉት አስር ቀናት አድርጋ እንደማታውቅ አቶ ዳዊት ተናግረዋል። ዓለም የሚያስፈልጋትን የህክምና ድጋፍ እንድታገኝ ለማድረግም አቶ ዳዊትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በኢንተርኔት በኩል በጎ አድራጊ ኢትዮጵያዊያንና ሌሎችም ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበው መዋጮ እኣሰባሰቡ እንደሚገኙም ለማወቅ ችለናል። ዓለም አሁን ያለችበት ሁኔታ ከቀን ወደ ቀን አሳሳሲ ወደ ሆነ ደረጃ እየደረሰና ምግብ ለመመገብም እየተቸገረች መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ጤንነቷ እንዲስተካከል የኩላሊት እጥበቱን ማድረግ መጀመር እንዳለባትና በመደበኛነት መከታተል እንደሚያስፈልግ ሃኪሞች መክረዋል። ለረዥም ዓመታት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መኖሯና በተገቢው ሁኔታ የጥገኝነት ሰነድ አለማግኘቷ ጉዳዩ የሚመለከተው የደቡብ አፍሪካ መንግሥት አካል ችግር መሆኑን በመግለጽ፤ የጀመረችው ህክምና እንድታገኝ እንዲደረግ ለፍርድ ቤት የቀረበው ጥያቄ ጊዜ የሚፈልግ ሰለሆነ በዙሪያዋ ባሉ ሰዎች በሚደረገው ጥረት ብቻ ነው በሕይወት እንድትቆይ ማድረግ የሚቻለው ሲሉ አቶ ዳዊት ተናግረዋል። እጅግ አስፈላጊ የሆነውን የኩላሊት እጥበት አቋርጣ ከሆስፒታሉ እንድትወጣ በፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ በደቡብ አፍሪካ በሚገኙ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪዎች በኩል ከባድ የሰብዓዊነት ጥያቄ ያስነሳ ሲሆን፤ ጉዳዩ ተመልሶ ወደ ፍርድ ቤት እንዲሄድ ያደረጉትም ለዚህ እንደሆነም ተነግሯል። ደቡብ አፍረካዊ ባለመሆኗና የመኖሪያ ፈቃድ ለዓመታት ማግኘት ባለመቻሏ በሕይወት ለመቆየት እጅግ አስፈላጊ የሆነውን ህክምና አቋርጣ እንድትወጣ በመደረጓ፤ ሕይወቷ አደጋ ላይ እንዲወድቅ እንዳደረገ በመግለጽ ደቡብ አፍሪካ ውስጥና በሌሎችም ቦታዎች የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ለዓለም ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። ዓለም ኦርሲዶ ከአስር ዓመት በፊት ወደ ደቡብ አፍሪካ ሄዳ የግል ሥራ በመሥራት እራሷን በማስተዳርና ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ቤተሰቦቿን ትደግፍ እንደነበር በአሁኑ ወቅት አስጠግተዋት ህክማና እንድታገኝ ጥረት እያደረጉ የሚገኙት አቶ ዳዊት ለቢቢሲ ተናግረዋል።
news-55767355
https://www.bbc.com/amharic/news-55767355
በትግራይ ክልል ስለሚያስፈልገው ሰብአዊ እርዳታ ምን ተባለ?
በትግራይ ክልል ምግብ እና መድኃኒትን ጨምሮ የተለያዩ ሰብአዊ እርዳታዎች በአፋጣኝ እንደሚያስፈልጉ የአገር ውስጥና የውጪም የተራድኦ ድርጅቶች አስታውቀዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ኦክስፋም እንዲሁም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በተለያዩ የትግራይ ክልል አካባቢዎች አስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታ እንደሚያስፈልግ መግለጫ ካወጡ ተቋሞች መካከል ይጠቀሳሉ። በክልሉ ውስጥ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ እርዳታ እንደሚያሻቸውና በተለያዩ መጠለያዎች የሚገኙት ዜጎች ላይ ወሲባዊ ጥቃት እየደረሰ መሆኑ ሪፖርት እንደተደረገም ተመልክቷል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፤ ከትግራይ ክልል እየደረሱኝ ያሉት ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች እጅጉን አሳስቦኛል ብሏል። ዓለም አቀፉ የግብረ ሰናይ ድርጅት ኦክስፋም በበኩሉ ትናንት ባወጣው መግለጫ፤ በትግራይ ክልል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ብሏል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን፤ ጦርነት በተካሄደባቸው የትግራይ ክልልና አዋሳኝ አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች ደህንነትና ከመኖሪያ አካባቢያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑንና ሰብአዊ ቀውስ ሊያስከትል እንደሚችልም አሳሰቧል። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፤ በግጭት ወቅት የሚደርስ ወሲባዊ ጥቃትን የሚከታተሉ ትፕርሚላ ፓተን፤ "የቤተሰብ አባላቸውን ተገደው እንዲደፍሩ የተደረጉ ግለሰቦች ስለመኖራቸው የሚረብሹ ሪፖርቶች ደርሰውናል" ብለዋል። ፕራሚላ፤ መሠረታዊ ቁሶችን ለማግኘት ሲባል ከወታደሮች ጋር ወሲብ ለመፈጸም የሚገደዱ ሴቶች ስለመኖራቸው፣ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ መድኃኒቶችን የሚፈልጉ ሴቶች ቁጥር ስለመጨመሩ እንዲሁም በመጠለያ ጣቢያዎችም በሴቶች እና ሕጻናት ላይ የሚደርሱ ጾታዊ ጥቃቶችን የሚያትቱ ሪፖርቶች ስለመናራቸው ገልጸዋል። በጉዳዩ ላይ የመንግሥት ባለሥልጣናት ምላሽ እንዲሰጡን ያደረግነው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል። ዓለም አቀፉ የግብረ ሰናይ ድርጅት ኦክስፋም በትግራይ ክልል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ሲል ትናንት መግለጫ አውጥቷል። ኦክስፋም በመግለጫው፤ በትግራይ የተከሰተው ግጭት ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና ከአንበጣ መንጋ ወረራ ጋር ተያይዞ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ጠባቂ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ብሏል። ኦክስፋም ከግጭቱም በፊት ቢሆን በደቡብ እና ምዕራብ ትግራይ እንዲሁም በሰሜን አማራ ክልል የሚኖሩ ሰዎች ድጋፍ ይሹ ነበር ብሏል። የኦክስፋም የኢትዮጵያ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ገዛኀኝ ከበደ፤ "በደቡብ ትግራይ የሚኖሩ ነዋሪዎች ግጭቱን በመሸሽ ወደ ሌሎች ስፍራዎች ሸሽተው ሲመለሱ ቀያቸው ወድሞ አልያም ተዘርፎ እንደጠበቃቸው ነግረውናል" ብለዋል። ኦክስፋም ከግጭቱ በፊትም በትግራይ ከአንድ ሚሊዮን ሕዝብ በላይ እርዳታ ጠባቂ ነበር ብሏል። በግጭቱ ወቅት በርካታ ሰዎች በቋሚነት ያገኙ የነበረውን የምግብ እርዳታ መቀበል ሳይችሉ ቀርተዋል። እንደ የተባበሩት መንግሥታት አሐዝ ከሆነ፤ በትግራይ ከ4.5 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ አስቸኳይ ሰብአዊ አርዳታ ያስፈልጋቸዋል። የብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ግን የተመድ አሐዝ የተጋነነ ነው ብሏል። የብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ባለፈው ሳምንት በሰጡት መግለጫ፤ "በትግራይ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር 4.5 ሚሊዮን ሳይሆን 2.5 ሚሊዮን ነው" ብለዋል። ኮሚሽነሩ፤ 2.5 ሚሊዮን ሕዝብ ለመርዳት መንግሥት በቂ ዝግጅት አድርጓልም ብለዋል። ለትግራይ ክልል 311 ሺህ 526 ኩንታል እንደቀረበና ይህም ከ2.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን መመገብ እንደሚችል አቶ ምትኩ ገልጸዋል። "በአቅርቦት ረገድ ክፍተት የለብንም። በአሁን ሰዓት ከ20 በላይ የጭነት መኪናዎች አቅርቦቱን እያደረሱ ይገኛሉ" ሲሉም አክለዋል። እርዳታ የሚሹ ሰዎች ቁጥር ወደ 4.5 ሚሊዮን ገደማ እንደሆነ የሚጠቁም መረጃ መውጣቱን በተመለከተ፤ ይህንን አሐዝ "የፌደራል መንግሥት አላጸደቀውም" ብለዋል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዶ/ር ሙሉ ነጋ በበኩላቸው፤ የሰብአዊ እርዳታ እንዳልቀረበ ተደርጎ የሚነገረው የፖለቲካ ጥቅም ለማግኘት በሚፈልጉ አካላት ነው ሲሉ ለኢዜአ ተናግረዋል። ዶ/ር ሙሉ፤ "ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር፤ ሰብአዊ ድጋፍ እንዲሰጥ በመንግሥት በኩል ምንም ወደኋላ የተባለበት ጊዜ የለም" ብለዋል። ጉዳዩን "ለፖለቲካ ፍጆታ" የሚያውሉ መገናኛ ብዙሀን እንዳሉ ጠቅሰውም "የተዛባ መረጃ እያሰራጩ ነው። ይህ ትክክል አይደለም" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። መንግሥት የሚፈናቀል ሰው ሊኖር እንደሚችልና ሰብአዊ እርዳታ ሊያስፈልግ እንደሚችል ከመጀመሪያውም እንደተገነዘበ ጠቅሰው፤ "ከመጀመሪያው ጀምሮ ይህ ታሳቢ ተደርጎ ሥራ ተጀምሯል" በማለት ገልጸዋል። አቶ ምትኩ አሁን ላይ 1.8 ሚሊዮን ዜጎች እርዳታ እየቀረበላቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል። ይህ ቁጥር መንግሥት ሕግ የማስከበር እርምጃ ካለው በኋላ ሳይሆን ቀድሞውንም የነበረ መሆኑን አክለዋል። "700 ሺህ ተጨማሪ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ ብለን ግምት ወስደን በአሁን ሰዓት ለ2.5 ሚሊዮን ዜጎቻችን እርዳታ ለማቅረብ በቂ ዝግጅት አድርገናል" ብለዋል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ፤ የችግሩ ተጎጂዎች በቂ ያልሆነ ወይም ምንም እርዳታ እንዳላገኙ በማስታወቅ፤ "በአካባቢዎቹና በሠላማዊ ሰዎች ላይ የደረሰው ጉዳት ከሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ከፍተኛና አፋጣኝ ርብርብ የሚጠይቅ ነው" በማለት መግለጻቸው ይታወሳል። በትግራይ ክልል የተከሰተውን ግጭት በመሸሽ ወደ ሱዳን የሄዱ ዜጎች ከ55 ሺህ በላይ ሲሆኑ በአገር ውስጥ የተፈናቀሉ ደግሞ 2 ሚሊዮን እንደሚጠጉ መረጃዎች ያሳያሉ።
56539800
https://www.bbc.com/amharic/56539800
በግብጽ በደረሰ የባቡር አደጋ ቢያንስ የ32 ሰዎች ሕይወት አለፈ
በግብጽ ባጋጠመ የባቡር አደጋ ቢያንስ 32 ሰዎች ሲሞቱ ከ100 በላይ ደግሞ መጎዳታቸውን የአገሪቱ የባቡር ትራንስፖርት ባለስልጣን አስታወቀ።
አደጋው ተከሰተው ሁለት የመንገደኛ ባቡሮች በተጋጩበት ጊዜ ሁለት ፉርጎዎች ከሃዲዳቸው ወጥተው በመገልበጣቸው ነው። የትራንስፖርት ባለስልጣኑ እንዳለው ከሆነ፤ ከፊት የነበረው ባቡር የአደጋ ጊዜ ፍሬን "ማንነታቸው ባልታወቀ ግለሰቦች" በመያዙ ከኋላ የነበረው ባቡር ከፊተኛው ባቡር ጋር ሊጋጭ ችሏል። የአገሩቱ ባለስልጣናት በአደጋው ዙሪያ ተጨማሪ ምርመራዎችን እያካሄዱ ይገኛሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ለአደጋው ተጠያቂ ሆኖ በሚገኝ አካል ላይ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወሰድ ፕሬዝደንት አብዱልፋታህ አልሲሲ ተናግረዋል። "በቸልተኝነት፣ በሙስናም ሆነ በማናቸውም ምክንያት ለዚህ አደጋ መንስዔ የሆነ ሰው፤ ያለ አንዳች መዘግየት ከፍተኛውን ቅጣት መቀጣት አለበት" ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ላይ ፕሬዝደንት ሲሲ ጽፈዋል። የደረሰውን አደጋ የሚያሳዩ ፎቶግራፎች ሁለት ፉርጎዎች የውሃ አካል አቅራቢያ ተገልብጠው አሳይተዋል። የአገሪቱ ጤና ሚንስቴር በአደጋው ከሞቱት ባሻገር በ108 ሰዎች ላይ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት ማጋጠሙን አስታውቋል። ከባቡሩ ፉርጎ ሥራ መውጣት ያልቻሉ ሰዎችን ለማግኘት ክሬኖች እንደሚያስፈልጉ እና ሰዎችን በፍጥነት ከአደጋው ቦታ ማንሳት ባለመቻሉ የሰዎች ሕይወት ስለማለፉ ሬውተርስ በስፍራው የነበሩ የዓይን እማኞች ጠይቆ ዘግቧል። የግብጽ መገናኛ ብዙሃን የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ሙስጠፋ ማድባውለይ አደጋው ወደ አጋጠመበት ስፍራ እየተጓዙ እንደሆነ ዘግበዋል። ግብጽ ለባቡር መስመሮቿ ጥብቅ ጥገና ባለማድረጓ በባቡር መስመሮቿ ላይ ተደጋጋሚ አደጋ ያጋጥማታል። እአአ 2002 ወደ ደቡባዊ ካይሮ እየተጓዘ በነበረ ባቡር ላይ ባጋጠመ የእሳት አደጋ 373 ሕይወታቸውን አጥተው ነበር።
news-54662206
https://www.bbc.com/amharic/news-54662206
ልጁን ጨምሮ 160 የወሲባዊ ጥቃቶችን በማድረስ ሲፈለግ የነበረው ጣልያናዊ ተያዘ
ከ160 በላይ መድፈርና ወሲባዊ ጥቃቶችን አድርሷል ብላ ጀርመን ስትፈልገው የነበረው የ52 አመቱ ጣልያናዊ በቁጥጥር ስር ዋለ።
ግለሰቡ በተለይም ታዳጊ ህፃናትን ሲደፍር እንደነበር የተገለፀ ሲሆን የፈረንሳይ ድንበርንም ሲያቋርጥ ነው የተያዘው። የፈረንሳይ የወንጀለኞች አዳኝ ቡድን ቢኤንአርኤፍ ግለሰቡን ባለፈው ሳምንት አርብ ሩመርሺም ለ ሃውት በሚባል ቦታ ይዞታል። ግለሰቡ ወሲባዊ ጥቃቱን በአብዛኛው ያደረሰው የፍቅር አጋሮቹ ታዳጊ ልጆች ላይ ሲሆን ለበርካታ አመታትም ሲፈፅመው የነበረ ነው ተብሏል። መረጃውም እንደሚያሳየው ከጎሮጎሳውያኑ 2000-2014 ድረስ ነው ይህንን ተግባር ሲፈፅም የነበረው። በጀርመን 122 ክሶች እንደተከፈቱበት ገልጿል። ግለሰቡ ከተጠረጠረባቸው ወንጀሎች መካከል በልጁ ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት በማድረስ ነው። ለአመታትም ያህል ልጁን በመድፈር ተጠርጥሮም ክስ እንደቀረበበት የፈረንሳይ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ተጠርጣሪው ወደ ፈረንሳይ የገባው ከሶስት ሳምንት በፊት መሆኑን መረጃ የሰሙት የጀርመን ባለስልጣናት ለፈረንሳይ አሳወቁ። በመጨረሻም ያለበት ትክክለኛ ቦታ የታወቀ ሲሆን ከሳምንት በኋላም በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል። በአሁኑ ወቅት ኮልማር በሚባል የፈረንሳይ ግዛት የሚገኝ ሲሆን ወደ ጀርመንም ተላልፎ ይሰጣል ተብሏል።
news-53511870
https://www.bbc.com/amharic/news-53511870
ፌስቡክ አፍሪካ ውስጥ ርካሽ የኢንተርኔት አገልግሎት ሊያቀርብ ነው
የአሜሪካው ግዙፍ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረክ የሆነው ፌስቡክ በአፍሪካ ውስጥ የኢንተርኔት ትስስርን ለማሻሻል በሚያፈሰው መዋዕለ ነዋይ የአህጉሪቱ ምጣኔ ሃብት እድገት ላይ አስተዋጽኦ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገለጸ።
የኢንተርኔት ትስስር ላይ በሚደረገው ለውጥ በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ውስጥ በአህጉሪቱ ምጣኔ ሃብት ላይ ወደ 60 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ እድገትን ያመጣል ተብሏል። ፌስቡክ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው የኢንተርኔት ተደራሽነት በጨመረ ቁጥር በአህጉሪቱ የሚኖረው የኢንተርኔት ዋጋ ላይ ከፍተኛ ቅናሽ እንደሚኖረው ገልጿል። ፌስቡክ በአፍሪካ ውስጥ በሚመድበው መዋዕለ ነዋይ የኢንትርኔት ዳታ ማዕከላት፣ የባሕር ውስጥ ማስተላለፊያ ገመዶችና የዋይ ፋይ መሰረተልማቶችን በመዘርጋት ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት ውስጥ ያሉ በርካታ ሰዎች የኢንተርኔት ተጠቃሚ እንዲሆኑ አቅዷል። እንዲሁም በኢንተርኔት አማካይነት የሚደረጉ የንግድ ልውውጦችንና የሥራ ማመልከቻዎችን ለማበረታታትም ያግዛል ተብሏል። አስካሁንም ፌስቡክ በሰባት አገራት ውስጥ የዋይፋይ አገልግሎትን የጀመረ ሲሆን በኡጋንዳና በናይጄሪያ ደግሞ የ3ጂ ሽፋንን አስፋፍቷል። ከሰሃራ በታች ባለው የአፍሪካ ክፍል ውስጥ ከሚገኘው ሕዝብ ከግምሽ የሚበልጡት የኢንተርኔት አገልግሎትን አያገኙም። በተጨማሪም በአገራቱ ውስጥ ያለው አገልግሎት ከሌላው ዓለም ጋር ሲወዳደር ውድ ነው። በርካሽ ኢንተርኔት አቅርቦት ላይ የተደረገ አንድ ጥናት እንዳመለከተው በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ለአንድ ሚጋ ባይት የኢንትርኔት አገልግሎት የሚወጣው ወጪ ከአማካይ ገቢ 8 በመቶን የሚጠይቅ ሲሆን በአሜሪካ 2.7 በመቶ በአስያ ደግሞ 1.5 በመቶ ብቻ ነው። በአፍሪካ ውስጥ 20 በመቶ የሚሆነው የኢንተርኔት ግልጋሎት የሚውለው የፌስቡክ መተግበሪያዎች የሆኑትን ኢንስታግራምና ዋትስአፕን ለመጠቀም ነው። ዋነኛው የማኅበራዊ መገናኛ መድረክ የሆነው ፌስቡክ እንዳስታወቀው ከሁለት ዓመት በፊት አፍሪካ ውስጥ 139 ሚሊዮን ሰዎች አገልግሎቶቹን ይጠቀማሉ።
41482922
https://www.bbc.com/amharic/41482922
ስለምን የሰው ሕይወት የቀጠፈው የላስ ቬጋስ ጥቃት 'ሽብርተኝነት' አልተባለም?
59 ሰዎች በአንድ ታጣቂ የተገደሉበት ጥቃት በአሜሪካ ዘመናዊ ታሪክ አስከፊ ክስተት እነደሆነ ቢነገርም፤ የሽብር ጥቃት ነው አልተባለም። ለምን?
እሁድ ዕለት የሙዚቃ ድግስ በታደሙ ሰዎች ላይ በ64 ዓመቱ ስቴፈን ፓዶክ ተፈፅሞ የ59 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈውና ከ500 በላይ ሰዎችን ያቆሰለውን ጥቃት የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ድርጊቱን የሽብር ጥቃት ብለው እንደማይጠሩት ለማሳወቅ ጊዜ አላጠፉም ነበር። ነገር ግን ብዙ ሰዎች፤ ይህ በአሜሪካ ታሪክ የከፋ ሆኖ በርካታ ሰዎችን የገደለ ጥቃት ከሽብር ድርጊት ውጪ ምን ተብሎ ሊጠራ ይችላል? በማለት ይጠይቃሉ። ፓዶክን ሽብርተኛ ብሎ ከመጥራት ይልቅ እንዲሁ እንደቀላል 'ብቸኛው ጥቃት ፈፃሚ' ፣ 'ተኳሹ' ወይም 'ታጣቂው' ተብሎ መጠራቱን በመቃወም በርካቶች በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ላይ ትችትን እንዲሰነዝሩ አድርጓቸዋል። ሌሎች እንዲያውም 'ሽብርተኛ' የሚለው ስያሜ ለሙስሊሞችና ነጭ ላልሆኑ ሰዎች ብቻ ጥቅም ላይ እየዋለ፤ ዘርንና ፖለቲካን መሰረት እንዲያደርግ ሆኗል እስከማለት ደርሰዋል። ስለዚህ ሽብርተኝነት ትርጉሙ ምንድን ነው? አብዛኞቹ የሽብርተኝነት ትርጓሜዎች የሚያተኩሩት ድርጊቱ ባስከተለው ውጤት ላይ ሳይሆን ድርጊቱ እንዲፈፀም ያነሳሳው ምክንያት ላይ ነው። የአሜሪካ ፌደራል ህግ ስለሽብር ባስቀመጠው ብያኔ 'ፖለቲካዊ ወይም ማህበራዊ ዓላማዎችን ለማሳካት ሲባል በሰዎች ወይም በንብረት ላይ ህገ-ወጥ ኃይልና ድርጊትን በመጠቀም ማስፈራራትና መንግሥትን ማስገደድ' ይለዋል። ስለዚህም ምንም እንኳን ይህ ጥቃት በአሜሪካ ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ እጅግ አደገኛው ቢሆንም፤ የጥቃቱ ፈፃሚ አላማ ነው ትኩረት የተሰጠው። ሰኞ ዕለት የላስ ቬጋስ ፖሊስ ኃላፊ እንደተናገሩት "በዚህ ጊዜ የጥቃቱ ፈፃሚ የሚከተለው እምነት ምን እንደሆነ አናውቅም" ብለዋል። የኤፍቢአይ ልዩ ወኪል የሆኑት አሮን ሩስ በበኩላቸው እንዳሉት መሥሪያ ቤታቸው በጥቃቱ ፈፃሚና በዓለም አቀፍ የሽብር ቡድኖች መካከል ግንኙነት እንዳለ የሚያሳይ ነገር አላገኘም። በዚህ መሰረትም ፓዶክ ሽብርተኛ ተብሎ አይጠራም ማለት ነው። ነገር ግን የላስ ቬጋስ ከተማ ግዛት ውስጥ የምትገኘው ኔቫዳ ሽብርተኝነትን በተመለከተ የተለየ ትርጓሜ አላት። 'ሽብርተኝነት በህዝብ ላይ ከፍ ያለ አካላዊ ጉዳት ወይም ሞትን ለማድረስ ታስቦ ማስገደድና ኃይልን መጠቀም ወይም ለመጠቀም የመሞከር ማንኛውም ድርጊት ነው'' ይላል። ይህም ደግሞ አሁን ከተፈፀመው ጥቃት አንፃር በማያሻማ መልኩ ተግባራዊ ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ሪፐብሊካንና ዴሞክራት ፖለቲከኞች ግን ድርጊቱን የሽብር ተግባር ነው ብለው ለመጥራት አላንገራገሩም። በእርግጥም በዚም አለ በዚያ ዋናው ነገር ድርጊቱ በስሙ መጠራቱ ነው።
51225315
https://www.bbc.com/amharic/51225315
ሶማሊያ የዓለማችን ሙስና የተጠናወታት አገር ተባለች
ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የተባለው ዓለማቀፍ ድርጅት ሶማሊያ ሙስና የተጠናወታት አገር ናት ሲል ፈረጃት።
ሙስናን የሚዋጋው ድርጅት ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሶሪያ የዓለማችን ሙሰኛ አገራት ናቸው ሲል በቅድመ ተከተል አስፍሯቸዋል። ሙስና የራቃቸው አገራት ዝርዝር ላይ ደግሞ ኒውዚላንድ፣ ዴንማርክ፣ ፊልላንድ፣ ሲንጋፖር እና ስዊድን ተቀምጠዋል። ከሰሃራ በታች የሚኙ አገራት ሙስና የተንሰራፋባቸው አገራት መሆናቸውን ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የገለጸ ሲሆን፤ ኢትዮጵያም ከ180 አገራት 96ኛ ደረጃን ይዛለች። • የብር የመግዛት አቅም መቀነስ አንድምታዎች • ቤት ለመከራየት ግማሽ ሚሊዮን ብር ቀብድ የሚጠየቅባት ከተማ ድርጅቱ አገራት ሙስናን በመዋጋት ረገድ ያሳዩት ለውጥ እጅግ ዘገምተኛ ነው ብሏል። ባለፉት ስምንት ዓመታት ሙስናን ማቃለል ከቻሉ ጥቂት አገሮች መካከል ግሪክ እና ሰሜን አውሮፓዊቷ ኢስቶኒያ ተጠቃሽ ሆነዋል። ጥናቱን ይፋ ያደረገው ቡድን እንደሚለው ከሆነ ሙስና በስፋት የሚነሰራፋው ለምርጫ ቅስቀሳ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ፈሰስ ሲደረግ እና መንግሥታት ለባለጸጎች ብቻ ጆሯቸውን ሲሰጡ ነው። 180 አገራትን ያሳተፈው ጥናት የተለያዩ መለኪያዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለአገራቱ ከዜሮ እስከ 100 ድረስ ነጥብ ሰጥቷል። ዜሮ ማለት እጅግ ሙስና የበዛበት አገር ሲሆን 100 ደግሞ ከሙስና የጸዳ ማለት ነው። • "ኢስላማዊ ባንክ ለኢትዮጵያ ምን ይፈይዳል?" ኒው ዚላንድ እና ዴንማርክ 87 ነጥብ ሲያስመዘግቡ፤ ሱማሊያ 9፣ ደቡብ ሱዳን 12 እና ሲሪያ ደግሞ 13 አስመዝገበዋል። ኢትዮጵያ በበኩሏ ከ 100 ሀገራት ተወዳድራ ከአጠቃላይ 100 ነጥብ 37 ማግኘት ችላለች። በዚህም ከጠቅላለው 180 አገራት ሁለት ሶስተኛው ያገኙት ነጥብ ከ50 በታች ሆኗል።
news-55485496
https://www.bbc.com/amharic/news-55485496
ጣሊያን ውስጥ ታዋቂ የሆነችውን ኢትዮጵያዊት መግደሉን ሠራተኛዋ ለፖሊስ አመነ
በጣሊያን ውስጥ ከፍየል ወተት በምታዘጋጀው አይብና ለስደተኞች መብት ተቆርቋሪነቷ የምትታወቀው ኢትዮጵያዊቷ ስደተኛ አጊቱ ጉደታ ቤቷ ውስጥ ተገድላ መገኘቷን ፖሊስ ማሳወቁን በጣሊያን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለቢቢሲ አረጋገጠ።
የኤምባሲው ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ሠራተኛ የሆኑት አቶ ደሳላኝ መኮንን እንደተናገሩት ትናንት ግድያው ከተፈጸመ በኋላ ፖሊስ ባደረገው ማጣራትና ምርመራ በአጊቱ ተቀጥሮ ይሰራ የነበረ ተጠርጣሪ ስደተኛ ወንጀሉን መፈጸሙን እንዳመነ ገልጸዋል። በሮም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲም የአጊቱ ጉደታን ሞት በተመለከተ በፌስቡክ ገጹ ላይ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጾ፤ ግድያውን በተመለከተም ኤምባሲው ከጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን በቶሎ ተጣርቶ ይፋ እንዲደረግና ወንጀለኛው ለፍርድ እንዲቀርብ በትኩረት የሚሰራ መሆኑን አመልክቷል። የአጊቱ ግድያ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ብቻ ሳይሆን በጣሊያኖችም ላይ ትልቅ ድንጋጤና ሐዘን የፈጠረ መሆኑን የገለጹት አቶ ደሳለኝ በተለይ በስደት ወደ ጣሊያን የሚመጡ ኢትዮጵያውያንና ሌሎች አፍሪካውያንን በመርዳት ስለምትታወቅ ወንጀሉ በስደተኞች ዘንድ ታላቅ ሐዘንን አስከትሏል ብለዋል። ፖሊስ እንዳለው አጊቱ ጉደታ ትሬንቲኖ ውስጥ በሚገኘው ፍራሲሎንጎ በተባለው ስፍራ ባለው መኖሪያ ቤቷ ውስጥ ጭንቅላቷ ላይ ጉዳት ደርሶባት አስከሬኗ አግኝቷል። ምርመራ እያደረገ እንደሆነ የገለጸው ፖሊስ የአጊቱ ጉደታ ሞት ጭንቅላቷ ላይ በመዶሻ በመምታት የተፈጸመ የግድያ ወንጀል ሳይሆን እንዳልቀረ ገልጿል። ከአስር ዓመት በፊት በስደት ወደ ጣሊያን የገባችው አጊቱ ጉደታ በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት አርብ ዕለት 43 ዓመት ይሆናት ነበር። የዘረኝነት ጥቃት ይደርስባት ነበር ጣሊያን ከጀርመን ጋር በምትዋሰንበት በተራራማዋ ትሬንቲኖ ግዛት ውስጥ ለዓመታት የኖረችው አጊቱ፣ ዘረኝነት ላይ የተመሰረቱ ጥቃቶች ያጋጥሟት እንደነበር ለፖሊስ አመልክታለች። አንዳንዶች በቆዳዋ ቀለም የተነሳ "አስቀያሚ ጥቁር እያሉ ይሰድቡኛል፤ ያለሁበትም ቦታ አገሬ እንዳልሆነ ይነግሩኛል" በማለት በግልጽ ያገጠሟትን የዘረኝነት ጥቃቶች ስትገልጽ ነበር። ነገር ግን 'ላ ሪፐብሊካ' የተባለው የጣሊያን ጋዜጣ እንደዘገበው ፖሊስ በግድያው ዙሪያ የሚያደርገው ምርመራ በአንድ ወጣት አፍሪካዊ ላይ ያተኩራል ብሏል። ወጣቱ ከዚህ በፊት በአጊቱ ላይ ጥቃትና ማስፈራሪያ ከሰነዘሩት ሰዎች መካከል እንዳልሆነ የተገለጸ ሲሆን፤ ምናልባት በገንዘብ ጉዳይ አለመግባባት ሊኖራቸው እንደሚችል ተገምቷል።. አጊቱ የሚገጥማትን የዘረኝነት ጥቃት ይፋ ባወጣችበት ጊዜ የግዛቲቱ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ኡጎ ሮሲ ድርጊቱን ተቃውመው ከጎኗ ቆመው ነበር። ፕሬዝዳንቱ በወቅቱ "አጊቱ ስደተኛ ሆና የእንስሳት እርባታ ሥራዋን በግዛታችን ውስጥ ማከናወን መጀመሯ የትሬንቲኖን እንግዳ ተቀባይነትና ደጋፊነትን ያሳያል" ብለው ነበር። አጊቱ በምትኖርበት ግዛት ውስጥ ሊጠፉ ተቃርበው ነበር የተባሉ የፍየል ዝርያዎችን በማርባት ከወተታቸው የተለያዩ ተዋጽኦዎችን እያመረተች ምርቷ ተወዳጅነትን እሷም ታዋቂነትን አትርፋ ነበር። አዲስ አበባ ውስጥ ተወልዳ ያደገችው አጊቱ ጉደታ ለስደት የተዳረገችው፣ በትላልቅ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ይካሄድ የነበረውን የመሬት ነጠቃ በመቃወም በምትሰጠው አስተያየት፣ የግድያ ዛቻ ይደርሳት ስለነበረ ነው። አጊቱ ጉደታ ከአስር ዓመት በፊት በመንግሥት የሚደርስባትን ጫና ሸሽታ ወደ ጣሊያን ከገባች በኋላ የስደተኝነት ፈቃድ አግኝታ የእንስሳት እርባታና የወተት ተዋጽኦ ምርት ሥራን በመጀመር በአጭር ጊዜ ስኬታማ በመሆን ለበርካታ ስደተኞች ምሳሌ ለመሆን ችላ ነበር። በሥራዋ ዝናን ያተረፈችውን የአጊቱን ሞት በተመለከተ በርካታ የጣሊያን ጋዜጦች ጽፈዋል። ሁሉም አጊቱ በትሬንተን ግዛት ውስጥ ወደ ደረሰችበት ስኬት ለመብቃት ከባድ ፈተናዎችን ማሳለፏን የጠቀሱ ሲሆን፤ ባላት ጥንካሬና ቆራጥነት የዘረኝነት አመለካከቶችን ተጋፍጣ በምትኖርበት አካባቢ ተወዳጅነትን እንዳተረፈች ሁሉም መስክረዋል። በአጊቱ ላይ በተፈጸመው ግድያ ተጠርጥሮ ከተያዘ በኋላ ምርመራ የተደረገበት ጋናዊ ስደተኛ ለፖሊስ በሰጠው ቃል ወንጀሉን እንደፈጸመ ማመኑን ኮሪየር ዴላ ሴራ የተባለው የጣሊያን ጋዜጣ ምርመራውን ያካሄዱ መኮንኖችን ጠቅሶ ዛሬ ዘግቧል። አጊቱ በምትሰራው የፍየል እርባታና የወተት ተዋጽኦ ምርት ሥራ ውስጥ ለበርካታ አፍሪካውያን ስደተኞች የሥራ ዕድል እንደፈጠረች የተገለጸ ሲሆን፤ ግድያውን መፈጸሙን ያመነው ስደተኛም ለሦስት ዓመታት ተቀጥሮ መስራቱ ተነግሯል። ተጠርጣሪው ከግድያው በኋላ በነበረው ምሽት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ለሰዓታት በሰጠው ቃል ግድያውን መፈጸሙን አምኗል። የግድያው ምክንያት ምን እንደሆነ ግልጽ ባይሆንም በመጀመሪያ ላይ ከገንዘብ ጋር የተያያዘ ሳይሆን እንደማይቀር ተገምቷል። አጊቱ እዚያው ጣሊያን ውስጥ ሶሲዮሎጂ ተምራ ዲግሪ ያገኘች ሲሆን በተገደለችበት ዕለት የግብርና ሥራዋን ለማስፋፋት ከቅየሳ ባለሙያዎች ጋር ቀጠሮ ነበራት። በወቅቱ በቀጠሮዋ መሰረት ባለመገኘቷ በሰዓት አክባሪነቷ የሚያውቋትን ሰዎችን አሳስቧቸው እንደነበር ተዘግቧል። ከጎረቤቶቿ አንደኛዋም "ምን ሆና ነው የጠፋችው" በሚል ወደ ቤቷ በመሄድ ወደ መኝታ ቤቷ ሲገቡ ወድቃ እንዳገኟት ጋዜጣው ዘግቧል። ከዚህ በኋላ ነበር ፖሊስ በስፍራው ደርሶ ምርመራውን የጀመረው።
news-53580508
https://www.bbc.com/amharic/news-53580508
ኮሮናቫይረስ፡ 350 ህሙማንን ከኮቪድ-19 ፈወስኩ የምትለው አወዛጋቢዋ ዶክተር
ዶክተር ስቴላ ኢማኑኤል 350 ያህል የኮሮናቫይረስ ህሙማንን በአወዛጋቢው የወባ መድኃኒት አማካይነት መፈወሷን በባለሙያዎች ፊት ስትናገር የሚያሳው ቪዲዮ ይፋ በተደረገ በአጭር ጊዜ ውስጥ በወረርሽኙ በተጨነቀው በሚሊዮን በሚቆጠር የዓለም ሕዝብ ታይቷል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕም ስለዚህ መድኃኒት ፈዋሽነት ደጋግመው ቢናገሩም ከህክምና ባለሙያዎች ዘንድ የሚሰማቸው ካለማግኘታቸው በተጨማሪ ለትችት ተዳርገው ቆይተዋል። አሁን የእሳቸውን አቋም የምትጋራ ዶክተር በይፋ ወጥታ ስለመድኃኒቱ ስትናገር እጅጉን ነው የተደሰቱት። ስለዚህም ዶክተር ስቴላ ኢማኑኤል በትራምፕ ተወድሳለች። ያለምክንያት አይደለም። ዶናልድ ትራምፕ እጅግ አድርገው ስለ ፈዋሽነቱ የሚሰብኩለትን ለአፍ ጥሪ እንኳ የማይመች ሀይድሮክሲክሎሮኪይን የሚባል መድኃኒትን እርሷም 'ፈዋሽ ነው' ስላለች ነው። ሀይድሮክሲክሎሮኪይን ወትሮ ለወባ በሽተኞች የሚሰጥ መድኃኒት ነው። ዶናልድ ትራምፕ ግን ለኮሮናቫይረስም ይሆናል ይላሉ። ትናንትና እንዲያውም "በዚህ መድኃኒት ዙርያ ጥልቅ ንባብ አድርጊያለሁ፤ ፈዋሽነቱ አሌ አይባልም፤ እመኑኝ፤ መቼም እኔ ያልኩትን ነገር ማጣጣል ትወዳላቸሁ" ለጋዜጠኞች ሲሉ ነበር። ለወባ ህክምና ሲሰጥ የቆየው ሀይድሮክሲክሎሮኪይን በዚህች ካሜሮናዊት ሐኪም የተዘመረለትን የዚህን የወባ መድኃኒት የኮሮናቫይረስ ፈዋሽነት የሚመሰክረውን የዶ/ር ስቴላን ቪዲዮ ዶናልድ ትራምፕ ስላጋሩት እነፌስቡክና ትዊተር ቶሎ ብለው ከገጻቸው አንስተውታል። ምክንያቱ ደግሞ ሐሰተኛ መረጃን ይዟል፣ ሰውን ያሳስታል በሚል ነው። ቪዲዮውን ፌስቡክ ከገጹ ከማንሳቱ በፊት የትራምፕ የበኩር ልጅም ለዓለም አጋርቶት ሚሊዮኖች ተመልከተውታል። ከዚህ በኋላ ነው ዶ/ር ሴቴላ ዝነኛ የሆነችው። ዶ/ር ስቴላ ኢማኑኤል ማን ናት? ዶ/ር ስቴላ የተወለደችው ካሜሮን ውስጥ ነው። አሁን የምትኖረው በበአሜሪካዋ ሂዩስተን ቴክሳስ ነው። ዶናልድ ትራምፕ ስለ ዶ/ር ስቴላ ሲናገሩ፣ "እጹብ ድንቅ የሆነች ሐኪም ናት" ብለዋል። "በመቶዎች የሚቆጠሩ በሽተኞችን መፈወሷን ተናግራለች፤ የእርሷ ንግግር እውነት ነው፤ እኔ ግን በግል አላውቃትም" ብለዋል ትራምፕ። ዶ/ር ስቴላ ኢማኑኤል ሐኪም ብቻ ሳትሆን የፕሮቴስታንት ፓስተርም ናት። ባለፈው ሰኞ በአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በር ላይ በሚገኘው ደረጃ ላይ ቆማ ሰው በተሰበሰበበት ስብከት ስታደርግ ነበር። ያ ቪዲዮ ነጭ አክራሪዎች በሚያስተዳድሩት አንድ ድረ ገጽ ላይ ታትሟል። በዚህ ስብክቷ ዶ/ር ስቴላ አሜሪካዊያን ፈውስ የሚያገኙበትን መድኃኒት ተከልክለዋል ስትል ይህን የወባ መድኃኒት ታሞካሽ ነበር። "ማንም ሰው ከኮቪድ-19 መፈወስ ይችላል። ይህ ቫይረስ መድኃኒት አለው። መድኃኒቱም ሀይድሮክሲክሎሮኪይን ይባላል። እኔ ብቻ 350 ሰዎችን ፈውሼበታለሁ። አንድም ሰው አልሞተብኝም" ብላለች ዶ/ር ስቴላ። ይህ ምስክርነት ለዶናልድ ትራምፕ ሠርግና ምላሽ ሆኖላቸዋል። ዶናልድ ትራምፕ ሀይድሮክሲክሎሮኪይን ፈዋሽ ስለመሆኑና እርሳቸውም ለሁለት ሳምንት ያህል እንደወሰዱት በተደጋጋሚ ሲናገሩ ቆይተዋል። ያም ሆኖ የዓለም ጤና ድርጅትም ሆነ የእራሳቸው መንግሥት የጤና አማካሪዎች መድኃኒቱ ለኮቪድ ፈዋሽነቱ ምንም ማረጋገጫ አልተገኘም ይላሉ። እንዲያውም ለከፍተኛ የልብ ሕመም ስለሚያጋልጥ ጥንቃቄ ይደረግ ነው የሚሉት። ዶ/ር ስቴላ ግን ይህ መድኃኒት ምንም የጎንዮሽ ጣጣ አያመጣም፤ "በአገሬ ካሜሮን ብዙ ሰው ወባ ሲታመም ይወስደው የለም እንዴ?" ትላለች። ዶ/ር ስቴላ ስለመድኃኒቱ ፈዋሽነት ማብራሪያ በሰጠችበት ወቅት ሰባኪዋ ዶክተር እንደ አውሮፓዊያኑ በ1965 በካሜሮን የተወለደችው ዶ/ር ስቴላ ኢማኑኤል ሕክምና ያጠናቸው በናይጄሪያ ካላባር ዩኒቨርስቲ ነው። የቴክሳስ የህክምና ቦርድ እንዳረጋገጠው ዶ/ር ስቴላ የህክምና ፍቃድ አላት። ከህክምናው ጎን ለጎን ዶ/ር ስቴላ ፓስተር ናት። በሂዩስተን ፋየር ፓወር ሚኒስትሪ ቤተ ክርስቲያንን አቋቁማለች። ስብከቶቿ በዩትዩብ ላይ በብዛት ይገኛሉ። ከአምስት ዓመት በፊት በስብከቶቿ መካከል ትናገራቸው የነበሩ ነገሮች ግን የሐኪም አይመስሉም። አስደንጋጭም ናቸው። ለምሳሌ በአንድ ቪዲዮዋ ላይ "ሳይንቲስቶች ከመናፍስት ዲኤንኤ ናሙና ወስደው አዲስ ክትባት እየቀመሙ ነው። የክትባቱ ዋንኛ ዓላማ ታዲያ ሰዎች ሐይማኖት እንዳይኖራቸው የሚያደርግ ነው" ብላለች መናፍስትና ሰይጣኖችን በምድር ላይ እየተከሰተ ላለው ምሰቅልቅል ተጠያቂዎች እንደሆኑ በመግለጽ ወደ ፊት የከፋ ነገር እንደሚያስከትሉም ዶ/ር ስቴላ ትናገራለች። እየሱስ ፌስቡክን ሊዘጋው ነው በዚህ ማክሰኞ ዕለት የዓለም ሚዲያ ትኩረትን ባገኘላት ቪዲዮ ላይ ዶ/ር ስቴላ ከኮቪድ-19 የፈወሰቻቸው ሰዎች ወደ መድረክ እንዲመጡ ስትጠይቃቸው ይታያል። "እናንተ ካልመሰከራችሁ ሰዎች እኛን ይሰድቡናል" ስትል ፈወስኳቸው የምትላቸውን ሰዎች በኢንተርኔት ራሳቸውን እንዲገልጹ አበረታታለች። ይህ የእርሷ የትዊተር መልዕክት 27 ሺህ ሰዎች አጋርተውት ሚሊዮኖች ተመልክተውታል። ዶናልድ ትራምፕ ያጋሩትና እርሷም ከአሜሪካ ፍሮንትላይ ዶክተርስ ከተባለው ቡድን ጋር ሆና የምትታይበትን ቪዲዮ ፌስቡክ ሐሰተኛ ብሎ ካስወገደው በኋላ ዶ/ር ስቴላ ተቆጥታ መጣች። እንዲህም ስትል ተናገረች። "ፌስቡክ የእኔን ቪዲዮ በአስቸኳይ ወደ ቦታው ካልመለሰ፤ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የፌስቡክን ሰርቨር ድምጥማጡን አጠፋዋለሁ ብሎኛል።" ነገር ግን ፌስቡክ ቪዲዮዋን መልሶ አልለጠፈውም፤ ሰርቨሩም እስካሁን ምንም አልሆነም።
news-54643712
https://www.bbc.com/amharic/news-54643712
ጆን ማጉፉሊ፡ ኮሮናቫይረስን ከአገር አባረዋለሁ ያሉት መሪ
የታንዛንያው ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ የኮሮረናቫይረስን በተመለከተ በሚሰጧቸው አስተያየቶችና በሚያስተላልፏቸው ውሳኔዎች የዓለምን ትኩረት መሳብ የቻሉ መሪ ናቸው። በአሁኑ ወቅት ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ ፕሬዚዳንት ሆነው ለመመረጥ እየሰሩ ነው።
ኮቪድ-19 ታንዛኒያ ሲደርስ ፕሬዚዳንቱ ሰዎች በቤታቸው መቆየት የለባቸውም ብለው አጥብቀው ይከራከሩ ነበር። እንዳውም ቫይረሱ እንዲጠፋ ቤተክርስቲያን እና መስጂድ ሄደው እንዲጸልዩ አበረታትተዋል። ''ኮሮናቫይረስ እርኩስ መንፈስ ነው፤ በክርስቶስ ሰውነት ውስጥ ሊቆይ አይችልም. . . . . ወዲያውኑ ይቃጠላል'' ሲሉም ተደምጠዋል አጥባቂ ክርስቲያኑ መሪ ጆን ማጉፉሊ። ፕሬዚዳንቱ ከዚህ በተጨማሪ ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅና የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ስለማድረግ በተመለከተ ሲናገሩ ምንም አይጠቅመንም ብለዋል። አክለውም የምርመራው እውነተኛነት ላይ ጥርጣሬ እንዳለቸው በመግለጽ በተለያዩ ፍራፍሬዎችና አንዲት ፍየል ላይ ምርመራ ተደርጎ ቫይረሱ በፓፓዬና በፍየሏ ላይ መገኘቱን ገልጸዋል። ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ ጎረቤት አገራት የእንቅስቃሴ ገደብ መጣላቸውን በመተቸትም እሳቸው ግን በዚህ መልኩ ኢኮኖሚውን መጉዳት እንደማይፈልጉ በተደጋጋሚ ገልጸዋል። ፕሬዚዳንቱ በርካታ አወዛጋቢና አነጋጋሪ ውሳኔዎችንም በማሳለፍ ይታወቃሉ። በአገሪቱ ታሪክ ከ54 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የነጻነት ቀን ብዙ ገንዘብ እያስወጣን ስለሆነ በህዝባዊ በአል አናከብረውም ማለታቸው የሚታወስ ነው። በአሉን በማክበር ፋንታም ህዝቡ ወጥቶ አካባቢውን እንዲያጸዳ ኣደረጉ ሲሆን እራሳቸውም በመንገድ ላይ በመውጣት በእጃቸው ቆሻሻ ሲሰበስቡ ውለዋል በነጻነት ቀን ላይ። ጆን ማጉፉሊ ፕሬዚዳንቱ በሆኑበት የመጀመሪያ ዓመት ላይ የሚወስዷቸው እርምጃዎች በበርካቶች ዘንድ ሙገሳን አስገኝቶላቸው ነበር። እንዳውም ታንዛንያውያን በትዊተር በኩል ማጉፉሊ ቢሆኑ ምን ያደርጉ ነበር እያሉ የተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮችን በማንሳት ሲጋሩት ከርመዋል። ጉዳዩን ወደ ቀልድ የወሰዱት በርካቶች ቢሆንም ለጊዜውም ቢሆን ፕሬዚዳንቱ የአገሬውን ዜጋ መነጋገሪያ ጉዳይ ሰጥተውት ነበር። ከአገራቸው አልፎም በጎረቤት አገራት ከፍተኛ ተጽዕኖ መፍጠር ችለው ነበር። በአውሮፓውያኑ 2017 አንድ ኬንያዊ ፕሮፌሰር በዳሬሰላም ዩኒቨርሲቲ ንግግር ሲያደርጉ አፍሪካ በማጉፉሊ አስተሳሰብ መቃኘት አለባት ሲሉ ተደምጠው እንደነበር የሚታወስ ነው። ነገር ግን ቀስ በቀስ ፕሬዚዳንቱ የነበራቸው ድጋፍና ተቀባይነት እየተሸረሸረ መጥቷል። የማጉፉሊ አስተዳደር ያልተለመዱና በድፍረት የሚወሰዱ በርካታ ሕጎችንና መመሪያዎችንም ሲያወጣ ነበር። በተለይ ደግሞ ከዓለምአቀፍ የማዕድን አውጭ ተቋማት ከፍተኛ ገቢ ለመሰብሰብ ያለሙ ሕጎች ተጠቃሽ ናቸው። 2017 ላይ 'አኬሺያ ማይኒንግ' የተባለው ዓለምአቀፍ የማዕድን አውጭ ድርጅት 190 ቢሊየን ዶላር ግብር እንዲከፍል ተጠይቆ የነበረ ሲሆን ከብዙ ክርክር በኋላ ግን ድርጅቱ 300 ሚሊየን ዶላር ለመክፈል ተስማምቷል። በመቀጠልም የታንዛንያ መንግሥት በድርጅቱ 16 በመቶ ድርሻ እንዲኖረውና ወደፊት ለሚገኙ ትርፍና መሰል ጥቅማትቅሞች እኩል ለመካፈል ተስማምተዋል። ፕሬዚዳንቱን በእጅጉ ከሚያስተቿቸው ውሳኔዎች መካከል ደግሞ ሴት ተማሪዎች በትምሀርት ላይ እያሉ ካረገዙ ተመልሰው ወደ ትምህርት ቤት መግባት አይችሉም የሚለው ነበር። ኢኮኖሚውን ከማነቃቃት አንጻር ደግሞ ፕሬዚዳንቱ በርካታ ስራዎችን መስራት ችለዋል። ታንዛንያን ከጎረቤት አገራት የሚገናኘው የባቡር መስመርን ጨምሮ በአገሪቱ አሉ የሚባሉ ትልልቅ ፕሮጀክቶች እንዲሰሩ አድርገዋል። በመንግሥት ቁጥጥር ስር የሚገኘው ብሄራዊ አየር መንገድም ከእዳው ተላቆ በአዲስ መልክ እንዲዋቀርና ወደ ገበያ እንዲገባም የሰሩ ሲሆን በአገሪቱ በመንግሥት ትምህርት ቤቶች እስከ አራተኛ ዓመት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ድረስ ትምህርት በነጻ እንዲሰጥ አድርገዋል። ነገር ግን ፕሬዝዳንቱ ኮሮረናቫይረስን በመቆጣጠር ረገድ ለወራት ይወስዷቸው የነበሩ እርምጃዎች ከአገሬው ዜጋም ሆነ ከዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ከፍተኛ ትችትን አስከትሎባቸዋል። ምንም እንኳን አገሪቱ የመጀመሪያውን የኮሮረናቫይረስ ምልክት ካየች በኋላ ትምህርት ቤቶችን በመዝጋትና ገደቦችን ማስቀመጥ ብትጀምርም የዓለም ጤና ድርጅት ግን ታንዛንያ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የወሰደችው እርምጃ የዘገየና ውጤታማ ያልነበረ ነው ብሏል። በወቅቱ ገበያዎችና የስራ አካባቢዎች ክፍት የነበሩ ሲሆን የእምነት ቤቶችም ቢሆኑ ለአማኞች ክፍት ሆነው እንዲቆዩ ተደርገው ነበር። ''በአገራችን በርካታ በቫይረስ የሚተላለፉ በሽታዎች አሉ፤ እንደ ኤችአይቪ ኤድስ ያሉትን መጥቀስ ይቻላል። ሁሌም ቢሆን ኢኮኖሚያችን መቅደም አለበት። ኢኮኖሚው እንዲተኛ መፍቀድ የለብንም፤ ሕይወትም መቀጠል አለባት'' ብለው ነበር ፕሬዚዳንቱ። በተጨማሪም ''ሌሎች የአፍሪካ አገራት ኢኮኖሚያቸውን ቸኩለው በመዝጋታቸው ከፍተኛ ችግር ውስጥ ስለሚገቡ በቅርብ ዓመታት ምግብ ከእኛ ለመግዛት መምጣታቸው አይቀርም'' ሲሉም ተደምጠው ነበር። በአሁኑ ሰአት ታንዛንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ስትሆን ፕሬዝዳንቱም በድጋሚ ለመመረጥ እንደሚፈልጉ እየገለጹ ነው። ዋነኛ ተቀናቃኞቻቸው ደግሞ የቻዴማ ፓርቲ ተወካዩ ቱንዱ ሊሱ ናቸው። ሰውዬው በአውሮፓውያኑ 2017 ላይ የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው የነበረ ሲሆን ላለፉት ሶስት ዓመታት በውጪ አገር በሕክምናና ማገገም ላይ አተኩረው ቆይተዋል። በአገሪቱ ታሪክ ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ የሚመሩት ፓርቲ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተሸንፎ አለማወቁ እሳቸውም በድጋሚ ሊያሸንፉ እንደሚችሉ በርካቶች ግምታቸውን እያስቀመጡ ነው። ተቀናቃኛቸው ቱንዱ ሊሱ ደግሞ በአገሪቱ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ለውጥ እንደሚያደርጉና ሰብአዊ መብት እንዲከበር እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል። ሌላኛው ተፎካካሪ በርናርድ ሜምቤ ደግሞ የቀድሞ ሚኒስትር ሲሆኑ እሳቸውም በምርጫው ካሸነፉ በርካታ ለውጦችን እንደሚያደርጉ እየገለጹ ነው። ጆን ማጉፉሊ በምርጫው የሚያሸንፉ ከሆነ በአገሪቱ ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ግንባታ ላይ እንደሚያተኩሩና የዜጎችን ኑሮ ለመቀየር በርካታ ፖሊሲዎች ማርቀቅና ተግባራዊ ማድረግ ላይ ትኩረት እንደሚሰጡ ተናግረዋል።
news-46691386
https://www.bbc.com/amharic/news-46691386
ፈረንሳይ ስለሩዋንዳው ፕሬዚዳንት አሟሟት ጀምራ የነበረውን ምርመራ አቋረጠች
የፈረንሳይ ፍርድ ቤት ስለቀድሞው የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ጁቬናል ሀቢሪማናን አሟሟት ያደርግ የነበረውን ምርመራ ማቋረጡን ይፋ አደረገ።
እንደ አውሮፓውያኑ በ1994 ፕሬዚዳንት ጁቬናል ሀቢሪማና በአውሮፕላን እየተጓዙ ሳለ ሚሳኤል ተተኩሶባቸው ሕይወታቸው አልፏል። ሞታቸው ሩዋንዳ ውስጥ የነበረውን የዘር ጭፍጨፋ አስከትሏል። • ሩዋንዳ 700 አብያተ ክርስትያናትን ዘጋች • ሩዋንዳ ስደተኞችን ከእስራኤል እንዳትቀበል ጥሪ ቀረበላት የፈረንሳይ መንግሥት ሚሳኤሉን ማን እንደተኮሰ ለማወቅ ምርመራ የጀመረው በአውሮፕላኑ ውስጥ በነበሩ ሠራተኞች ቤተሰቦች ጥያቄ ነበር። የፈረንሳይ ፍርድ ቤት ተጠያቂ ያደረገው በአሁኑ የሩዋንዳ ፕሬዘዳንት ፖል ካጋሜ የሚመሩ የቱትሲ አማጽያንን ነው። የፕሬዚዳንቱ የቅርብ የሚባሉ ሰዋች ላይም የእስር ማዘዣ ወጥቶ ነበር። ሆኖም ክሱ ባለፈው ሳምንት መቋረጡ ተሰምቷል። የፈረንሳይ አቃቤ ሕግ ለክሱ በቂ ማስረጃ ባለመገኘቱ ክሱ እንዲቋረጥ የጠየቀው ባለፈው ወር ነበር። ፕሬዘዳንት ጁቬናል ሀቢሪማና እየተጓዙበት የነበረው አውሮፕላን በሚሳኤል ተመቶ መውደቁን ተከትሎ በተነሳው የዘር ጭፍጨፋ 800,000 ቱትሲዎችና በርካታ ሁቱዎች ተገድለዋል። • ሩዋንዳ በሊቢያ 'በባርነት' የተያዙትን ስደተኞች እንደምትቀበል አሳወቀች • እስራኤል ከ35 ሺ በላይ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ልታዘዋውር ነው ከሁቱ ጎሳ የሆኑት ፕሬዚዳንቱ ከቱትሲ አማጽያን ጋር የሰላም ስምምነት አድርገው ወደ ሩዋንዳ መዲና ኪጋሊ እያቀኑ ሳለ ነበር ሚሳኤሉ የተተኮሰባቸው። በአውሮፕላኑ ተሳፍረው የነበሩ ሰዎች ባጠቃላይ ሕይወታቸው አልፏል። እንደ አውሮፓውያኑ በ2006 ፈረናሳዊው ዳኛ ዣን-ልዊስ ብሩጊዬሬ፤ ፕሬዘዳንት ፖል ካጋሜ የሚሳኤል ተኩሱን እንዳዘዙ ተናግረው፤ የፕሬዚዳንቱ አጋሮች እንዲታሰሩ ጠይቀው ነበር። የፍርድ ቤት ሂደቱ በፈረንሳይና በሩዋንዳ መካከል ያለውን ግንኙነት አሻክሯል። ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ፈረንሳይን የሁቱ አስተዳደርን ትደግፋለች፤ በዘር ጭፍጨፋውም እጇ አለበት ብለው ይከሳሉ። በ2012 ጉዳዩን ከዳኛ ዣን-ልዊስ ብሩጊዬሬ የተረከቡት ሌላ ፈረንሳዊ ዳኛ በሚሳኤል ተኩሱ የሁቱ አክራሪዎች ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ማለታቸውን ተከትሎ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መሻሻል አሳይቷል። የፖል ካጋሜ መንግሥት የምርመራ ውጤት የሚያሳየው ሚሳኤሉ የተተኮሰው ከሁቱ ካምፕ እንደነበር ነው።
news-55030280
https://www.bbc.com/amharic/news-55030280
ትግራይ ፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለህወሓት ኃይሎች የመጨረሻ ያሉትን ቀነ ገደብ አስቀመጡ
የአገሪቱ ሠራዊት ወደ መቀለ እየተጠጋ ባለበት በአሁኑ ሠዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በክልሉ ዋና ከተማ ውስጥ ያሉ አመራሮችና ኃይሎች በሰላም እጃቸውን እንዲሰጡ የመጨረሻ ያሉትን የሦሰት ቀናት ቀነ ገደብ አስቀመጡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመጨረሻው ምዕራፍ ነው ያሉትና የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ወደ ክልሉ ዋና ከተማ በሚያደረገው ወታደራዊ ዘመቻ ምክንያት በሰው ላይና በንብረት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት በከፍተኛ ደረጃ ለመቀነስ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ለህወሓት አመራሮች፣ ለልዩ ኃይሉና ለሚሊሻ አባላት ጥሪ አቅርበዋል። ጨምረውም በዘመቻው ነዋሪው ከሠራዊቱ ጋር በመተባበር ሊደርስ የሚችል ጉዳትን እንዲከላከል ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፤ የህወሓት አመራሩና የትግራይ ኃይል እጃቸውን በሰላም እንዲሰጡ የ72 ሰዓታት የመጨረሻ የጊዜ ገደብ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስቀምጠዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከሳምንት በፊት ለልዩ ኃይሉ እና ሚሊሻ አባላት ተመሳሳይ ቀነ ገደብ አስቀምጠው የነበረ ሲሆን ቀነ ገደቡ ሲጠናቀቅ መንግሥት በቀናት ውስጥ የመጨረሻውን ሕግን የማስከበር እርምጃ እንደሚወስድ መግለጻቸው ይታወሳል። ይህ አሁን ያስቀመጡት ቀነ ገደብ ሠራዊቱ ወደ ዋና ከተማዋ መቀለ መቃረቡን ተከትሎ መሆኑን አመልክተው በከተማዋና በነዋሪው ላይ ሊደርስ የሚችልን ጉዳት ለመቀነስ እንደሆነ ገልጸዋል። በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊትና በትግራይ ክልል ኃይሎች መካከል ለሳምንታት የዘለቀው ወታደራዊ ግጭት ወደ ሦስተኛው ምዕራፍ መሸጋገሩን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ "በትግራይ ክልል የጀመርነው ሕግን የማስከበር እርምጃ ሁለተኛ ምዕራፍ ተጠናቅቋል" በማለት የመጨረሻውና ወሳኝ ባሉት በሦስተኛው ምዕራፍ ላይ እንደሚገኙ አመልክተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት በሁለተኛ ምዕራፍ ዘመቻ የክልሉን የተለያዩ ቦታዎችን በማስለቀቅ "አመራሩ የመሸገባትን ዋና ከተማዋን መቀለን መክበብ ነበር" በማለት፤ በዚህም ሠራዊቱ ዕቅዱን በማሳካት ወደ ቀጣይ ምዕራፍ መሸጋገሩን ገልጸዋል። በጥቅምት ወር የመጨረሻ ሳምንት በትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኘው የሠሜን ዕዝ ላይ በትግራይ ክልል ኃይሎች ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ በፌደራል መንግሥቱ መውሰድ በጀመረው ወታደራዊ ዘመቻ በርካታ የትግራይ አካባቢዎችን መቆጣጠሩን ገልጾ ሠራዊቱ ወደ መቀለ ከተማ እያመራ መሆኑ ተነግሯል። ይህንንም ተከትሎ የዘመቻው ሦስተኛው ምዕራፍ በመቀለ የሚካሄድ እንደሆነና "ሕግ የማስከበር የመጨረሻው እርምጃ ነው" በማለት፤ ይህ ዘመቻ ከፍተኛ ጥበብ፣ ጥንቃቄና ትዕግሥት የሚፈልግ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። በፌደራል መንግሥቱና የትግራይ ክልልን በሚያስተዳድረው በህወሓት መካከለው ለወራት የቆየው አለመግባባት ከማይታረቅበት ደረጃ ላይ ደርሶ ወደ ወታደራዊ ግጭት ተሸጋግሮ የመንግሥት ኃይሎች የክልሉን ቁል ከተሞች ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ እንደተቆጣጠሩ እየተነገረ ነው። ሦስተኛ ሳምንቱን ሊደፍን በተቃረበው ወታደራዊ ግጭት ከፍተኛ መጠን ያለው ሞትና ጉዳት እንዳጋጠመ ቢነገርም በትግራይ ክልል ያሉ የስልክና የኢንተርኔት የግንኙነት መስመሮች በመቋረጣቸው ትክክለኛውን መረጃና አሃዝ ለማግኘት አዳጋች ሆኗል። በተጨማሪም ቁጥራቸው ከ30 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ግጭቱን በመሸሽ ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን መሰደዳቸውና በችግር ላይ እንደሚገኙ የእርዳታ ድርጅቶች እያሳወቁ ሲሆን፤ መንግሥትም በበኩሉ እነዚህን ሰዎች ወደ ቀያቸው ለመመለስ ጥረት እያደረገ እንደሆነ አመልክቷል።
54308127
https://www.bbc.com/amharic/54308127
ዐቃቤ ሕግ፡ ከሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ ከነበረው ሁከት ጋር በተያያዘ ከ5 ሺህ በላይ ሰዎች ላይ ክስ ተመሰረተ
የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ከተፈጠረው ሁከት ጋር በተያያዘ ከ5ሺህ 700 በላይ ሰዎች ላይ ክስ መመስረቱን ጠቅላይ ዐጨቃቤ ሕግ አስታወቀ።
ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የአርቲስቱን ግድያ ተከትሎ በተፈጸሙ ወንጀሎች ዙሪያ ሲያካሂድ የነበረው ምርመራ ማጠናቀቁን አስታውቋል። በዚህም መሠረት አቃቤ ሕግ በ5 ሺህ 728 ሰዎች ላይ ማንነትን መሰረት ያደረገ የእርስ በእርስ ግጭት በመቀስቀስ በሚል ወንጀል ክስ መመስረቱን ዛሬ ከኦሮሚያ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጋር በጋራ በሰጡት መግለጫ አስታውቋል። በወንጀል ምርመራው የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ እና የኦሮሚያ ፖሊስ ተሳታፊ ሆነው መቆየታቸውን ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ፍቃዱ ጸጋ በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተናግረዋል። ክስ ከተመሰረተባቸው መካከል 3 ሺህ 377 በፌዴራል መንግሥት ስልጣን ስር የሚወድቅ እንዲሁም 2 ሺህ 351 በኦሮሚያ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሥር ክስ እንደተመሰረተባቸው ተገልጿል። በፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተከሳሾች በ114 በኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ደግሞ በ374 የክስ መዛግብት ክሱ መደራጀቱ ተጠቁሟል። የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ ከተፈጠረው ሁከት ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሰዎች ምርመራ ተጠናቆ ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ ክስ መመስረት እንደሚጀመር ከትናንት በስቲያ መግለጻቸው ይታወሳል። ከተፈጸመው የወንጀል ስፋት አንጻር በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው አንዳንዶች ከጅምላ እስር ጋር ቢያያይዙትም በወንጀሉ የተሳተፉ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ በርካቶች በቁጥጥር ሥር ሊውሉ እንደቻሉ አብራርተዋል። በቁጥጥር ሥር ከሚገኙት መካከል ፖለቲከኞች መኖራቸው ያስታወሱት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ፤ ፖለቲከኞቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ግን በፖለቲካ ተሳትፏቸው አይደለም ብለዋል። ከተጠርጣሪዎች ብዛት እና ከወንጀሉ ስፋት አንጻር የምርመራ ጊዜው ረዥም ጊዜ እንደወሰደ የፌደራል ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ አቶ ፍቃዱ ጸጋ ጨምረው የተናገሩ ሲሆን፤ አነስተኛ የወንጀል ተሳትፎ የነበራቸው ሰዎችም ጉዳያቸው እየታየ ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ በዋስትና እንደሚለቀቁ ተናግረዋል። ከአርቲስት ሃጫሉ ግድያ በኋላ በኦሮሚያ በተከሰተው ሁከት የ167 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል። ከዚህ በተጨማሪም 360 ሰዎች የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከ4.67 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ደግሞ መወድሙ በመግለጫው ተጠቅሷል።
news-56755325
https://www.bbc.com/amharic/news-56755325
'የኤርትራ ወታደሮች ስለመውጣታቸው ምንም ማረጋገጫ የለም'
የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ስለመውጣታቸው የሚያመለክት ምንም አይነት ማስረጃ እንደሌለ የተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ የሰብአዊ እርዳታ ባለስልጣን ለጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ተናገሩ።
ማርክ ሎውኮክ በግጭት ከተጎዳው የሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል "የኤርትራ ወታደሮች መውጣታቸውን የሚያመለክት ነገር የተባበሩት መንግሥታት ተቋማትም ሆኑ ሌሎች ከእኛ ጋር አብረው የሚሰሩ የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች አላዩም" ብለዋል። በጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት የአሜሪካ መልዕክተኛ የሆኑት ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድም በዚሁ ጊዜ የአስገድዶ መድፈርና ጾታዊ ጥቃቶችን የተመለከቱ ሪፖርቶችን ተከትሎ የኤርትራ ወታደሮች "በአስቸኳይ" ከኢትዮጵያ ለቀው እንዲወጡ ጠይቀዋል። መልዕክተኛዋ በጽህፈት ቤታቸው በኩል ውይይቱን በተመለከተ ባወጡት መግለጫ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተፈጸሙ ከተባሉት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ጥቃቶችና ግድያዎች አንጻር ድርጊቱን የፈጸሙትን በሙሉ ተጠያቂ እንደሚያደርጉ ያሳዩትን ቁርጠኝነት አድንቀዋል። የኤርትራ መንግሥትም ተመሳሳይ አቋም መያዝ አለበት ብለዋል። "በተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽንንና በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አማካይነት ትግራይ ውስጥ የሚካሄደው ምርመራ በበጎ የምንመለከተው ሲሆን በፍጥነትና በዝርዝር እንዲከናወን እንጠይቃለን" ብለዋል። የሊንዳ ቶማስ መግለጫው ጨምሮም "ከታማኝ ምንጮች የሚወጡ ዘገባዎች የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያ ሠራዊት ልብስን በመልበስ ትግራይ ውስጥ ለመቆየት እየሞከሩ እንደሆነ" አመልክተው ክልሉን ለቀው እንዲወጡ ጠይቀዋል። ኤርትራ ኢትዮጵያ ውስጥ በወታደሮቿ ተፈጽመዋል የተባሉትን የመብት ጥሰቶች የፈጠራ ክስ በማለት ቀደም ሲል ውድቅ ማድረጓ ይታወሳል። ትግራይ ውስጥ የተከሰተውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ ድንበር ተሻግረው ገብተዋል የተባሉት የኤርትራ ወታደሮች የተለያዩ ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን በተመለከተ ክስ ሲቀርብባቸው ቆይተዋል። ኢትዮጵያና ኤርትራ ግን ለወራት ወታደሮቹ ወደ ትግራይ ክልል መግባታቸውን በተመለከተ ይወጡ የነበሩትን ሪፖርቶች ሲያስተባብሉ የቆዩ ሲሆን፤ በመጨረሻም በመጋቢት ወር ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኤርትራ ወታደሮች መኖራቸውን ለአገሪቱ ፓርላማ ተናግረው ነበር። ከቀናት በኋላም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ኤርትራ ተጉዘው ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከተናጋገሩ በኋላ ወታደሮቹ ከኢትዮጵያ የድንበር አካባቢዎች ለቀው በመውጣት የኢትዮጵያ ሠራዊት ስፍራዎቹን እንዲቆጣጠር ከስምምነት መድረሳቸውን ገልጸው እንደነበር ይታወሳል። በትግራይ ክልል ውስጥ ወታደራዊ ግጭት ከተከሰተ አምስት ወራት የተቆጠሩ ሲሆን በዚህ ጊዜ የተባበሩት መንግሥታት በጉዳዩ ላይ ለመምከርና መግለጫ ለመውጣት ምክር ቤቱ የትናንቱን ጨምሮ ለአምስት ጊዜ ተሰብስቦ ተወያይቷል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት ማርክ ሎውኮክ ግጭቱ እንዲቆምና የበለጠ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መስመር እንዲመቻች ጥያቄ አቅርበዋል። ትግራይ ውስጥ ግጭቱ የተቀሰቀሰው ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የህወሓት ኃይሎች በመንግሥት ጦር ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ካዘዙ በኋላ ነበር። በትግራይ ክልል ውስጥ በተካሄደው ወታደራዊ ግጭት ሳቢያ ምን ያህል ሰዎች እንደሞቱ የሚታወቅ ነገር ባይኖርም አሃዙ በበርካታ ሺዎች ሊሆን እንደሚችል የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ይናገራሉ። ከዚህ ባሻገርም በግጭቱ ውስጥ ተሳታፊ በሆኑ ኃይሎች ግድያዎች፣ ጾታዊ ጥቃቶች፣ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ዘረፋና የንብረት ውድመቶች መፈጸማቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ባወጧቸው ሪፖርቶች ላይ አመልከተዋል። በተጨማሪም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዳለው በግጭቱ ሳቢያ ከሁለት ሚሊዮን ሰዎች በላይ ለመፈናቀል የተዳረጉ ሲሆን፤ ከአራት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ የሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ናቸው።
48591305
https://www.bbc.com/amharic/48591305
የሴቶች ዓለም ዋንጫ፡ ሴት እግር ኳሰኞች ስንት ይከፈላቸዋል? ዓለም ዋንጫ ላይ የሚሳተፉ ሃገራትስ?
የሴቶች እግር ኳስ ከጊዜ ጊዜ እያደገ የመጣ ይመስላል፤ ትኩረት መሳብም ጀምሯል። የዘንድሮውን የዓለም የሴቶች ዓለም ዋንጫ ጨዋታ 1 ቢሊዮን ተመልካቾች ይታደሙታል የሚል ግምት አለ።
ወደ ክፍያው ስንመጣስ? የሉሲዎቹ አምበል የሆነችው ሎዛ አበራ ከወንዶች ጋር ሲነፃፀር የሴቶች ክፍያ እዚህ ግባ የማይባል ነው ትላለች። በዓለም አቀፍ ደረጃስ? የባለፈው ዓለም ዋንጫ አሸናፊ የአሜሪካ አጥዊ የሆነችው ሆፕ ሶሎ የሴቶች እና የወንዶች ክፍያ ልዩነት ፊፋ ውስጥ ያለውን 'የወንድ የበላይነት' ያሳያል ስትል ትወቅሳለች። እስቲ ክፍያውን በቁጥር ከፋፍለን እንመልከተው። • እግር ኳስ ተጫዋቹ ወንድወሰን ዮሐንስ እንዴት ተገደለ? ፈረንሳይ እየተካሄደ ባለው የዘንድሮው የሴቶች የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ላይ አሸናፊ የምትሆነው ብሔራዊ ቡድን 4 ሚሊዮን ዶላር [115 ሚሊዮን ብር ገደማ] ታገኛለች። ከባለፈው ዓለም ዋንጫ ክፍያ እጥፍ ማለት ነው። እያንዳንዳቸው ተሳታፊ ቡድኖች ደግሞ ከ750 ሺህ ዶላር [22 ሚሊዮን ብር ገደማ] ጀምሮ በነብስ ወከፍ ይቀበላሉ። ከሽልማት ወጪው በተጨማሪ ለዝግጅት በሚል እያንዳንዷ ቡድን 800 ሺህ ዶላር ከፊፋ ትቀበላለች። በጠቅላላው ፊፋ ለዘንድሮው ዓለም ዋንጫ 30 ሚሊዮን ዶላር ያወጣል። ወደ ወንዶቹ ስንመጣ. . . ሩስያ አዘጋጅታ ፈረንሳይ በወሰደችው የ2018ቱ የወንዶች ዓለም ዋንጫ ፊፋ ለሽልማት ብሎ ያዘጋጀው ጠቅላላ ገንዘብ 400 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ ነው፤ ከሴቶቹ ከአስር እጥፍ በላይ ማለት ነው። ለዝግጅት ተብሎ ለእያንዳንዱ ቡድን በነብስ ወከፍ የተሰጠው ደግሞ 1̋ሚሊዮን ዶላር ነው፤ ከሴቶቹ እጥፍ በላይ ማለት ነው እንግዲህ። አጀብ! የሚያስብል ሆኖ እንዳገኙት እንጠራጠርም። የወንዶቹ ክፍያ ከሴቶቹ በልጦ የመገኘቱ ጉዳይ ከሚያመጡት ገቢ ጋር መገናኘቱ ነው ብለው የሚከራከሩ አልጠፉም። ቢሆንም በፊፋ ሕግ መሠረት ከሴቶች እግር ኳስ የሚገኘው ገንዘብ ለሴቶች እግር ኳስ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ወጪዎች የሚውል ነው። ለሃገራት የሚከፈለውን ዶላር ተጫዋቾች ያገኙታል? ፊፋ ለሃገራት የሚከፍለው ገንዘብ የተጨዋቾች ኪስ ሳይሆን ወደ ፌዴሬሽን ካዝና የሚገባ ነው። የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ድርሻ ቆንጠር አድርጎ ለተጨዋቾች መስጠትና የቀረውን ደግሞ ሌሎች መስኮች ላይ በተን በተን ማድረግ ይሆናል። ታድያ በፌዴሬሽኖች እና በእግር ኳስ ተጨዋቾች ማሕበር መካከል የሚደረግ ድርድር አለ። • «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ የአውስትራሊያ ሴቶች እግር ኳስ ቡድን የትኛውንም ገንዘብ በሽልማት መልክ ሲያገኝ ተጨዋቾች 30 በመቶ እንዲያገኙ ተደራድሯል። ወደ ክለቦች ስንወርድ ደግሞ የተሻለ ክፍያ የሚያገኙት [ከወንዶች ሲነፃፀር ቁጥሩ እጅግ አናሳ ቢሆንም] በምዕራብ አውሮፓ የሚጫወቱቱ ናቸው። ገንዘቡ ደግሞ ከ1 ሺህ እስከ 2 ሺህ ዩሮ ይደርሳል፤ ጨዋታ ባለ ቁጥር ደግሞ የላብ መተኪያ የሚሆን ከ50-100 ዩሮ ያገኛሉ። እርግጥ ነው ስም ያላቸው ተጨዋቾች ከዚህ የተሻለ ይከፈላቸዋል። እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሃገራት ክፍያው ምን ያህል ዝቅ ያለ እንደሆነ መገመት አያዳግትም። ፊፋ የሴቶች ዓለም የዋንጫ አሸናፊ ሽልማትን ከባለፈው ዓለም ዋንጫ እጥፍ ማድረጉ አንድ እርምጃ ወደፊት ነው የሚሉ ባይጠፉም 'አሁንም ትንሽ ነው' ብለው የሚከራከሩ አልጠፉም። በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ፊፋ የሴቶች እግር ኳስ ላይ ከ400-500 ሚሊዮን ዶላር አፈሳለሁ ይላል። ድምፃችን ይሰማ! የአሜሪካ ሴቶች እግር ኳስ ቡድን የሃገሪቱን እግር ኳስ ማሕበር እኩል ክፍያን እውን አላደረገም በሚል ከሶታል። የአውስትራሊያ እግር ኳስ ተጫዋቾች ማሕበር ፊፋ የሴቶች እና የወንዶች የዓለም ዋንጫ ሽልማት እኩል መሆን አለበት ሲል እየሞገተ ነው። 2016 ላይ የአፍሪካ ዋንጫን የበላችው የናይጄሪያ ሴቶች ቡድን በክፍያ ጉዳይ ከፌዴሬሽን ጋር በነረው እሰጥ-አገባ አድማ አድርጋ ነበር። የኒው ዚላንድ ወንዶች እና ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አባላት ከ2018 ጀምሮ ማንኛውም ዓይነት ክፍያ እኩል እንዲያገኙ የሚያደርግ ውል ደርሰዋል፤ በኖርዌይም እንዲሁ። ምንም እንኳ ልዩነቱ አሁንም የሰማይና ምድርን ያክል [የሎዛ አበራን አገላለፅ ለመጠቀም] ቢሆንም ከጊዜ ጊዜ ግን ለውጥ መምጣቱ አይካድም። የሴቶች እግር ኳስ የዓለም ዋንጫ ከየት ተነስቶ የት ደረሰ?
news-53469670
https://www.bbc.com/amharic/news-53469670
ጥያቄን ያጫረው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የሳዋ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ጉብኝት
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ፤ በኤርትራ የሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ሳዋ በመባል የሚታወቀውን የኤርትራ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል መጎብኘታቸው ተገለጸ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከኤርትራው ፕረዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በመሆን ሳዋ ሲደርሱ፤ ለምርቃታቸው ልምምድ ሲያደርጉ የነበሩ የ33ኛው ዙር የኤርትራ ብሔራዊ አገልግሎት ሰልጣኞች ወታደራዊ አቀባበል አድርገውላቸዋል። የሳዋ ማሰልጠኛ ማዕከል በአውሮጳውያኑ በ1994 የተቋቋመ ሲሆን፤ ባለፉት 26 ዓመታት የኤርትራ ዋና ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል በመሆን እያገለገለ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ፤ ቀደም ሲል ወደ ኤርትራ በተደጋጋሚ ያቀኑ ቢሆንም ሳዋን ሲጎበኙ ይህ ለመጀመርያ ጊዜያቸው ነው። ከዚህ ባሻገርም ይህንን ብዙ ተባለለትን ወታደራዊ መሰልጠኛ የሌላ አገር መሪ በይፋ ሲጎበኝ የተለመደ አይደለም፤ በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ መሪ ናቸው። የኤርትራው የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል፤ መሪዎቹ ሳዋን የጎበኙት "እግረ-መንገዳቸውን' እንደሆነ በትዊተር ገጻቸው ላይ አመልክተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በኤርትራ በቆዩባቸው ሁለት ቀናት፤ የተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎችን ጎብኝተዋል። ቅዳሜ፤ በአገሪቱ ደቡባዊ ዞን የሚገኘውን የ 'ገርገራ' ግድብን በመዘዋወር በአካባቢው ያለውን የመስኖ እርሻ መጎብኘታቸውን የአገሪቱ ቴሌቪዥን ዘግቧል። እሁድ ጠዋት ደግሞ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በጋሽ ባርካ ግዛት የሚገኙትን እርሻዎችንና የ 'ከርከበት' ግድብን ተመልክተዋል። የኤርትራው ፕረዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ፤ በተዳጋገሚ እየተገናኙ ውይይቶችን ያካሄዱ ቢሆንም፤ "በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ" ከሚል መግለጫ የዘለለ ዝርዝር መረጃ ከየትኛውም መንግሥት እስካሁን ተሰጥቶ አያውቅም። በተመሳሳይም ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ለሥራ ጉብኝት ወደ አሥመራ ያቀኑት ከፕሬዝደንት ኢሳያስ ጋር በሁለቱ አገራት ጉዳዮችና ቀጠናዊ ትብብሮችን በማጠናከር ላይ የተኮረ ውይይት እንደሚያካሂዱ የኤርትራው ማስታወቂያ ሚንስትር በትዊተር ካሰፈሩት መልእክት ውጪ የተባለ ነገር የለም። የፖለቲካ ተንታኞች፤ ሁለቱም መሪዎች በሁለት ዋና ጉዳዮች ላይ በትብብር እየሰሩ ነው የሚል ግምታቸውን ሲያስቀምጡ ቆይተዋል። የመጀመሪያው በአገራቱ በቅርብ ያደረጉትን ጉብኝት በመጥቀስ በህዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ ፕረዝደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ በግብጽ፣ ኢትዮጵያና ሱዳን መካከል ይፋዊ ያልሆነ የማሸማገል ሚናን እየተጫወቱ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አላቸው። ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ ፕረዝደንት ኢሳይያስ አፈወርቂና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ብዙ ያልተባለለትንና መቋጫ ያላገኘውን የድንበር ጉዳይ ፍጻሜ ለመስጠት ሊሆን እንደሚችል በመጥቀስ ከዚሁ ጋር ያለውን ፖለቲካዊ ጉዳይንም እንደሚነጋገሩበት ግምታቸውን ያስቀምጣሉ። የኤርትራው ፕሬዝደንት የካቲት ወር ላይ ከአገራቸው ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተከናወኑ ባሉት ፖለቲካዊ ክስተቶች ላይ "እጃችንን አጣምረን ቁጭ አንልም" ማለታቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ይህም በሁለቱ መንግሥታት መካከል ያለው ወዳጅነት እየጠነከረ ለመሆኑ እንደማሳያ ይቀርባል። በተለይ ከትግራይ ክልል እና ከክልሉ ገዢ ፓርቲ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው በመሆኑ አሁን በህወሓትና በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፓርቲ ብልጽግና መካከል ያለው አለመግባባትና እየጠነከረ የመጣው መወነጃጀል የድንበሩን ጉዳይ መፍትሄ ለመስጠት አመቺ ጊዜ አይመስልም። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) እሁድ ዕለት በሰጡት መግለጫቸው 'ፖለቲካዊ ጫናዎች' እየደረሱብን ነው በማለት አሁን ፓርቲያቸው ያለበትን ሁኔታ አብራርተዋል። ከዚህ በተጨማሪም ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ ከዚህ በፊት "ወደ ምርጫ ከገባችሁ ትቀጠቀጣላችሁ" የሚሉ ዛቻዎች እንደነበሩ ጠቅሰው፤ ምርጫውን ለማደናቀፍና ክልሉ ላይ ጫና ለመፍጠር "በውህደት እየሰሩ ነው" ያሏቸውን ኃይሎች በግልጽ ከስሰዋል። በዚህም መሰረት ከክልላቸው አንጻር ተባብረውብናል ያሏቸውን ኃይሎች "ሻዕቢያ አለ፤ ብልጽግና አለ፤ ባንዳዎችም አሉ" በማለት የሦስት ወገን ጫና እንዳለ አመልክተዋል። ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና ሌሎች የኤርትራ ባለስልጣናት በተለያዩ ጊዜያት በይፋ እንደሚናገሩት ለህወሓት በጎ አመለካከት እንደሌላቸው ግልጽ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ በህወሓት በዋነኝነት ሲዘወር የነበረው ኢህአዴግ ከስሞ ብልጽግና ሲመሰረት ከጥምረቱ እራሱን ካገለለ በኋላ በማዕከላዊው መንግሥት ውስጥ የነበረው ሚና ከመዳከሙ በላይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ፓርቲ ጋር በተለያዩ ምክንያቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ፍጥጫ ውስጥ ገብቷል። ስለዚህም በሁለቱ መሪዎች መካከል ያለው የጠበቀ ወዳጅነት ያለውን ስጋት ያጎላዋል። ጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አህመድ ለሥራ ጉብኝት ወደ አሥመራ ያቀኑት ከፕሬዝደንት ኢሳያስ ጋር በሁለቱ አገራት ጉዳዮችና ቀጠናዊ ትብብሮችን በማጠናከር ላይ ያተኮረ ውይይት ለማካሄድ እንደነበረ የማስታወቂያ ሚንስትሩ የማነ ገ/ መስቀል አስታውቀው ነበር። ጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ ወደ አሥመራ ያቀኑት ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እና አሁን የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ከፍተኛ ባለስልጣንና ቀደም ሲል በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር ከነበሩት ከአቶ ሬድዋን ሁሴን ጋር ነበር።
41665521
https://www.bbc.com/amharic/41665521
የመጀመሪያው ጥቁር የኦክስፎርድ ተማሪ ክሪስትያን ኮል
ኦክስፎርድ የመጀመሪያው ጥቁር ተማሪ ሆኖ በዩኒቨርሲቲው የተመዘገበውን ሴራሊዮናዊ ክሪስትያን ኮልን ሰሞኑን አስታውሷል።
ነገር ግን ክሪስትያን ኮል ማነው? ጥቁር ሆኖ ዩኒቨርሲቲ መቀላቀል 'አስደናቂ' በሚባልበት ወቅት ይህንን እንዴት ማድረግ ቻለ? የክላሲክ ሙዚቃ ስልትን ሊያጠና ወደ ኦክስፎርድ ብቅ ያለው ጥቁሩ ኮል ቅጥር ግቢውን ሲረግጥ የወሬ ርዕስ መሆኑ አልቀረም። ጊዜው በአውሮፓውያኑ 1873 ነበር። የ21 ዓመቱ ኮል ከሴራሊዮን ዋተርሉ ከተማ በመምጣት በወቅቱ አቅም ያላቸው እንግሊዛውያን የሚማሩበትን ትምህርት ቤት ተቀላቀለ። ይህም ዩኒቨርሲቲው የመጀመሪየውን የሴቶች ትምህርት ቤት ከማቋቋሙ ስድስት ዓመታት ቀደም ብሎ ነው። "ከተማዋ አስፈሪ ነገር ሆና ሳትጠብቀው አትቀርም" ይላሉ የዩኒቨርሲቲው የማሕደር ባለሙያ ዶ/ር ሮቢን ዳርዋል ስሚዝ። "በዚያን ጊዜ ለነበሩ ተማሪዎች ኮል፤ በሕይወታቸው ያዩት የመጀመሪያው ጥቁር ሠው ሳይሆን አይቀርም" ይላሉ ዶ/ር ሮቢን። 'የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር ተማሪዎች ያልተነገረ ታሪክ' የሚል መጽሓፍ ያሳተሙት ታሪክ አጥኚዋ ፓሜላ ሮበርትስ እንደሚያምኑት፤ ለኮል ከሴራሊዮን ወደ ብሪታኒያ የእንግሊዝኛ አነጋገር ዘይቤውን መቀየር በራሱ ፈታኝ ነገር ነበር። እርግጥ ኮል ሴራሊዮን እያለ ምን ዓይነት ሕይወት ይመራ እንደነበር ብዙ የሚታወቅ ነገር የለም። ቢሆንም ትምህርት የመቀበል ልዩ ችሎታው ከሌሎች ነጥሮ እንዲወጣ ምክንያት እንደሆነው ፓሜላ ይናገራሉ። ኮል ሴራሊዮን ውስጥ የእንግሊዝ ቤተክርስትያን ቄስ የነበሩ ሠው የማደጎ ልጅ ነበር። በሴራሊዮን ዋና ከተማ ፍሪታውን ባለ ታዋቂ ትምህርት ቤትም ተማሪ ነበር። በኦክስፎርድ ቆይታውም የመክፈል አቅም የሌላቸው ተማሪዎች በሚረዱበት ሥርዓት ውስጥ ነበር የተማረው። ከአጎቱ የሚላክለትን መጠነኛ ገንዘብን በትርፍ ጊዜ የሙዚቃ ትምህርት በማስተማር ከሚያገኘው ጋር አድርጎ ራሱን ይደጉምም ነበር። እንዲህ ራሱን ለመደጎም ላይ ታች ቢልም በኦክስፎርድ ሕይወቱ ሰኬትን ከማጣጣም አላገደውም ነበር ሲሉ ዶ/ር ሮቢን ይተርካሉ። በዩኒቨርሲቲው የመከራከሪያ መድረክ ላይ ንግግር ያደርግ የነበረው ሲሆን፤ በኦክስፎርድ የተማሪዎች ሕብረትም የነቃ ተሳትፎ አድርጓል። ታዋቂነትንም አትርፎ እንደነበረም ይወሳል። በስተመጨረሻም ዩኒቨርሲቲው የክብር ድግሪ በሚሰጥበት ሥነ-ሥርዓት ላይ የክርስቲያን ኮል ስም ሲጠራ የነበረውን ጩኸት እና ጭብጨባ ዩኒቨርሲቲው በታሪክነት አስቀምጦታል። "ሥነ-ሥርዓቱን ለመታዘብ የመጡ ሠዎች ማነው ይህ እንዲህ የሚጨበጭብለት ሲሉ 'ክሪስትያን ኮል ነው። ከሴራሊዮን ነው የመጣው' ብለው ሲናገሩ ይታሰበኛል" ሲሉ ዶ/ር ሮቢን ያወሳሉ።
news-57265516
https://www.bbc.com/amharic/news-57265516
እነ አቶ ጃዋር ከዚህ በኋላ ፍርድ ቤት መቅረብ እንደማይፈልጉ አስታወቁ
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አመራር የሆኑት አቶ ጃዋር መሃመድና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ከ20 በላይ ተከሳሾች ጉዳያቸውን ፍርድ ቤት ቀርበው እንደማይከታተሉ በትናንትናው ዕለት ግንቦት 18፣ 2013 ዓ.ም አስታውቀዋል።
ተከሳሾቹ አቤቱታቸውን በአምስት ገፅ ደብዳቤ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የጸረ-ሽብር እና ህገ መንግሥታዊ ጉዳዮች እንዳቀረቡም ቢቢሲ ከጠበቆቻቸው አንዱ ከሆኑት አቶ ከድር ቡሎ ሰምቷል። ትናነት በዋለው ችሎት ላይ በዋነኝነት ያነሱትም የፍርድ ቤት ውሳኔ በማይከበርበትና በተደጋጋሚ በህግ አስፈፃሚው አካል በሚጣስበት ሁኔታ የነሱ ችሎት መምጣት ትርጉም እንደሌለው ማስረዳታቸውንም አቶ ከድር ይናገራሉ። ፍርድ ቤቱ ነፃ ቢለቃቸውም ህግ አስፈፃሚው አካል "ከህግ በላይ ሆኖ ስለማይለቀንና ፍርድ ቤቱም ውሳኔው በማይከበርበት ሁኔታ ችሎቱ የክብር ነው እንጂ መቀለጃ መሆን የለበትም" ብለዋል ይላሉ። ለዚህም በርካታ ማጣቀሻዎች ማቅረባቸውን የሚናገሩት አቶ ከድር ከነዚህም መካከከል ፍርድ ቤት በነፃ ያሰናበታቸው እነ ኮሎኔል ገመቹ አያናና ሌሎች ግለሰቦች ፖሊስ ለመልቀቅ ፈቃደኛ አይደለም፤ እንዲሁም ያሉበት አይታወቅም። የጂማ ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰሮች እንዲሁ ፍርድ ቤቱ በነፃ ቢለቃቸውም ከቤተሰብም ሆነ ከጠበቆቻቸው ጋር መገናኘት አልቻሉም፤ እስከዛሬ የት እንዳሉም አይታወቅም። የኦነግ ስራ አስፈፃሚ የነበሩ አመራሮችም እንዲሁ ፍርድ ቤቱ ነፃ ቢያወጣቸውም ያለ ፍርድ ቤቱ እውቅና ታስረው እንዳሉና ያሉበት ቦታም ግልፅ እንዳልሆነ ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል። ከዚህም በተጨማሪ በባለፉት ሶስት ወራት ወደ አስር የሚጠጉ ግለሰቦች ከኦነግ ጋር በተገናኘ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በኦሮሚያ ፖሊስ ታስረው ይገኛሉ ብለዋል። "ይህ የሚያሳየው የፍትህ መዛባትን ነው። የህግ አስፈፃሚው አካል ህግ አለማክበሩን ነው የሚያሳየው"ነው ማለታቸውን አቶ ከድር ያስረዳሉ። አቶ ከድር እንደሚናገሩት ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ አለመከበር በተጨማሪ ግለሰቦች ያለ ፍርድ "በሚገደሉበት ሁኔታ"ን እንደ ምክንያትነት መጥቀሳቸውን አውስተዋል። የትናንትና የፍርድ ቤት ውሎ የተጀመረው በህሊና ፀሎት ሲሆን እነ አቶ ጃዋር መሃመድና ተከሳሾቹ በዶምቢዶሎ ከተማ "በአደባባይ ላይ በቤተሰቦቹ ፊት" የተረሸነው አማኑኤል ወንድሙ እንዲሁም በትግራይ ጦርነት እየደረሰ ስላለው ግድያና ጥሰት የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት እነ ጃዋር አከናውነዋል። ቢቢሲ ከአማኑኤል ቤተሰቦች እንደተረዳው አማኑኤል ሲገደል በቦታው እንዳልነበሩና በኋላ ግን አስከሬኑን ወስደው እንዳሳዩዋቸው ገልፀዋል። በትግራይ ካለው ጥሰት ጋር በተያያዘ የትግራይ ህዝብ ፆም (የረሃብ አድማ) እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው እነሱም የህዝቡ አካል ስለሆኑና ስለሚመለከታቸው ለሶስት ቀናት ከትግራይ ህዝብ ጋር የረሃብ አድማ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። በትግራይ ክልል ከገዳማት አባቶች በታወጀው መሰረት ከግንቦት 17-19 ድረስ ፆመ-ትግራይ በሚል የፆም፣ ፀሎትና የአርምሞ ቀናት እየተካሄደ ነው። በትግራይ የተለያዩ ከተሞችም የንግድ ከተሞች ተዘግተውና ከእንቅስቃሴ ታቅበው እንደነበር ቢቢሲ ከነዋሪዎች የተረዳ ሲሆን በትግራይ ክልል ውስጥ በግጭቱ "የተገደሉ ዜጎችንና ካህናትን፣ የተደፈሩ ሴቶችን እንዲሁም የተቃጠሉ አብያተ ክርስቲያናትን" በማስታወስና ይሄም እንዲቆም ለማድረግ መሆኑ ተነግሯል። በፀረ-ሽብር አዋጅ የተከሰሱት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮቹ እነ ጃዋር መሃመድ በተጨማሪም ጠበቆቻቸው ጭምር ለእንግልት እየተዳረጉ መሆናቸውንም ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል። የጠበቆቻቸው መኪኖች እንደተሰበሩና አካላዊ ድብደባም ደርሶባቸዋል በማለት "ህግ በማይከበርበት ሁኔታ ችሎት መቅረብ የለብንም" ማለታቸውንም አቶ ከድር ያስረዳሉ። ከዚህ ቀደምም ግንቦት 12፣2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት የፍርድ ቤት ቀጠሯቸው ከሁለት ዓመት በኋላ እንዲሆን ጥያቄ አቅርበው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ውድቅ ማድረጉ የሚታወስ ነው። ከዚህ ቀደምም በነበረው ችሎትም ሆነ በአሁኑ የአቤቱታ ደብዳቤ ከምርጫውና አገር ከተረጋጋ በኋላ ወደ ፍርድ ቤቱ እንደሚመጡ ችሎቱን አስረድተዋል።
news-44249246
https://www.bbc.com/amharic/news-44249246
ኬንያዊያን ፍየል አርቢ ቤተሰቦች የአውሮፓ ህብረትን ሊከሱ ነው
ፍየል በማርባት የሚተዳደሩ ኬንያውያን ቤተሰቦች የአውሮፓ ሕብረትን ፍርድቤት ሊያቆሙ ነው።
ቤተሰቦቹ ሕብረቱን የከሰሱት ከአየር ንብረት መዛባት ሊጠብቃቸው ባለመቻሉ ቤታቸውና መተዳደሪያ ንብረቶቻቸው ላይ አደጋ በመጋረጡ እንደሆነ ገልፀዋል። በሰሜን ኬንያ የኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ የሚኖሩት የጉዩ ቤተሰቦች ከበርካታ ከሳሾች መካከል አንዱ ናቸው። ጉዩ ለኤ ኤፍ ፒ እንደተናገሩት የአካባቢያቸው ሙቀት በጣም ከፍተኛና ተደጋጋሚ በመሆኑ ለአምስት ልጆቻቸው ጤናና የትምህርት ሁኔታ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል ብለዋል። "በአካባቢያችን ከፍተኛ ሙቀትን እያስተናገድን ነው፤ ይህም ህይወታችንን በተለያየ መልኩ እየተፈታተነው ነው" ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል። "የምንጠጣውም ሆነ ለከብቶቻችን የሚሆን ውሃ እየጠፋ ነው፤ በተለይ የልጆቼ ጤና አደጋ ላይ ነው" ሲሉም ይገልፃሉ። በአካባቢው ያለው የሙቀት መጠን ከ40 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ ይሆናል ያሉት እኝህ አባት ፤ ልጆቻቸው ወደ ትምህርት ቤት ሄደው ትምህርታቸውን ለመከታተል ከባድ ሆኖባቸዋል ይላሉ። የከሳሾቹ ቡድን 10 ቤተሰቦችን የያዘ ሲሆን ከፈረንሳይ የመጡ የወይን አምራች ገበሬዎችን እንዲሁም በሳሚ ማህበረሰብ የደጋ አጋዘንን የሚጠብቁ አርብቶ አደሮችን ይጨምራል። የአውሮፓ ህብረት በአውሮፓውያኑ 2030 በአገር ውስጥ ያለውን የግሪን ሃውስ ጋዝ ልቀት 40 በመቶ ለመቀነስ የገባው ቃል መሰረታዊ መብቶቻችንን ሊያስጠብቅልን አልቻለም የሚል ቅሬታ አላቸው።
news-57303944
https://www.bbc.com/amharic/news-57303944
አሜሪካ ከዴንማርክ ጋር በማበር የአውሮፓ ፖለቲከኞችን ሰልላች ተብላ ተወቀሰች
የዴንማርክ የስለላ ድርጅት አሜሪካ የጀርመኗ መራሂተ መንግሥት አንግላ ሜርክልን ጨምሮ በአውሮፓ ፖለቲከኞች ላይ ስለላ እንድትፈፅም ረድቷል ሲሉ የዴንማርክ መገናኛ ብዙሃን ዘግቡ።
የጀርመኗ መራሂተ መንግሥት አንግላ መርክል መገናኛ ብዙሃኑ እንደሚሉት ስለላው የተፈፀመው በፈረንጆቹ ከ2012 እስከ 2014 ባለው ጊዜ ነው። የዴንማርክ መከላከያ ደህንነት መሥሪያ ቤት ከአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት ኤጀንሲ ጋር በመተባበር መረጃ ሰብስበዋል ብሏል የዴንማርክ ብሔራዊ ራድዮ ጣቢያ። ስለላው ተካሄደ የተባለው እንደ ጀመርን፣ ፈረንሳይ፣ ስዊድን እና ኖርዌይ ባሉ ሃገራት ባለሥልጣናት ላይ ነው። ተመሳሳይ ወቀሳዎች በፈረንጆቹ 2013 ቀርበው እንደነበር ይታወሳል። በወቅቱ የአሜሪካ ስለላ ሚስጢሮችን ለዓለም ይፋ ያደረገው ኤድዋርድ ስኖውደን የአሜሪካው ስለላ ድርጅት የጀመርኗ መራሂተ መንግሥት አንግላ ሜርክልን ስልክ ጠልፏል ብሎ ነበር። ይህ ወቀሳ በቀረበ ወቅት ዋይት ሃውስ መረጃውን በቀጥታ አላስተባበለም፤ ነገር ግን የሜርክል ስልክ አልተጠለፈም ወደፊትም አይጠለፍም ብሎ ነበር። ጀርመር አውሮፓ ውስጥ ካሉ የአሜሪካ ቅርብ ወዳጆች ቀንደኛዋ ናት። አሁን በበርካታ የአውሮፓ መገናኛ ብዙሃን ዘንድ እየተሰራጨ ያለው ዜና የአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት ኤጀንሲ የበርካታ ፖለቲከኞችን የፅሁፍ መልዕክት ልውውጥና የስልክ ልውውጥ ሰምቷል ይላል። ይህን ለማድረግ ደግሞ ከዴንማርክ ስለላ ድርጅት ጋር ተባብሯል ሲሉ መገናኛ ብዙሃን ይዘግባሉ። "ኦፕሬሽን ደንሃመር" የተሰኘ ስም ተሰጥቶት ነበር የተባለው ይህ የስለላ ተግባር አሜሪካ በስልክ መስመር አማካይነት መረጃዎችን እንድትሰበስብ ረድቷል ብሏል የዳኒሽ ራድዮ ጣቢያ። ራድዮ ጣቢያው የሠራው የምርመራ ዘገባ ከዴንማርክ ስለላ ድርጅት ጋር ግንኙነት ያላቸው ዘጠኝ የመረጃ ምንጮችን ተጠቅሞ ነው። ከአንግላ ሜርክል በተጨማሪ የያኔው የጀመርን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንክ ዋልተር እና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ፒር ስታይንብሩክም ስልካቸው ተጠልፎ ነበር ተብሏል። የዴንማርክ መከላካያ ሚኒስቴርም ሆነ የስለላ ድርጅቱ እስካሁን በቀረበው ወቀሳ ላይ ያሉት ነገር የለም። ዘገባዎቹን ተከትሎ ኤድዋርድ ስኖውደን የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን "በወቅቱ በስላለው ላይ ተሳትፎ ነበራቸው" ሲል ወቅሷቸዋል። ባይደን በወቅቱ ምክትል ፕሬዝደንት እንደነበሩ አይዘነጋም። የአሜሪካው ስለላ ድርጅት [ሲአይኤ] የቀጠረው ድርጅት ውስጥ ይሰራ የነበረው ስኖውደን አሜሪካ ሕዝቧን በስልክ ትሰልላች ሲል መረጃ አጋርቶ ሃገር ጥሎ መጥፋቱ ይታወሳል። አሜሪካ ሰውዬውን የመንግሥት ንብረት በመስረቅ፣ ያልተፈቀደለትን የደህንነት መረጃ በማጋራት እንዲሁም ምስጢራዊ መረጃዎችን ይፋ በማድረግ ወንጀል ከሳዋለች። ስኖውደን በአሁን ወቅት ሩስያ ውስጥ በጥገኝነት ይኖራል።
news-55226427
https://www.bbc.com/amharic/news-55226427
ባይደን የቀድሞውን ጄኔራል ለመከላከያ ሚኒስትርነት አጩ
ተመራጩ የዩናይት ስቴትስ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ጡረት የወጡትን ጀኔራል ሎይድ ኦስቲንን ለመከላከይ ሚኒስትርነት ማጨታቸው ተሰምቷል።
ጀኔራል ሎይድ ኦስቲን ጄኔራል ሎይድ ኦስቲን ሹመታቸው ከፀደቀ ፔንታጎን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚመሩ ጥቁር አፍሪካዊ አሜሪካዊ ይሆናሉ። በፕሬዝደንት ባራካ ኦባማ ዘመነ መንግሥት የአሜሪካ ማዕከላዊ ኮማንድ አዛዥ ሆነው ያገለገሉት ጄኔራል ኦስቲን ጡረታ ከወጡ ሰባት ዓመት ስላልሞላቸው ከኮንግረሱ ፈቃድ ማግኘት ይኖርባቸዋል። ባይደን ከሁለት ሳምንት በፊት የብሔራዊ ደህንነት ሹም ይሆናሉ የተባሉት ዕጩዎችን ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል። ባይደን ጄኔራሉን ማጨታቸውን የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ይዘግቡት እንጂ ባይደንም ይሁኑ ጄኔራል ኦስቲን እስካሁን አስተያየት አልሰጡም። የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ጆ ባይደን ነባሯ የፔንታጎን ባለሥልጣን ሚሼል ፈሎርኖይ የመከላከያ ሚኒስትር ይሆናሉ የሚል ግምት አለ ብለው ዘግበው ነበር። ሚሼል ዕጩ ሆነው ቀርበው ሹመታቸው ቢፅድቅ ኖሮ የመጀመሪያ ሴት የመከላከያ ሚኒስቴር ይሆኑ ነበር። በፈረንጆቹ ኅዳር 3 አሜሪካ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ አካሂዳ ጆ ባይደን አሸናፊ መሆናቸው ይታወሳል። የዴሞክራት ፓርቲው ዕጩ በሚቀጥለው ጥር በኦፊሴላዊ በዓለ ሲመት መንበረ ሥልጣኑን ከፕሬዝደንት ትራምፕ ይረከባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ነገር ግን ፕሬዝደንት ትራምፕ እስካሁን ድረስ የምርጫውን ውጤት አምነው አልተቀበሉም። እስካሁን ድረስ ማስረጃ ማቅረብ ባይችሉም ምርጫው ተጭበርብሯል ሲሉ ያማርራሉ። ጄኔራል ኦስቲን ማናቸው? ፖለቲኮ የተሰኘው ጋዜጣ ነው ጄኔራል ኦስቲን የመከላከያ ሚኒስትር ለመሆን ታጭተዋል ሲል የዘገበው። ጄኔራል ኦስቲን ይህንን ቦታ ያገኛሉ ብሎ ብዙ ሰው እንዳልጠበቀ ጋዜጣው ይናገራል። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የሰውየው ስም በጉልህ መሰማት ተጀምሯል። የቢቢሲ የአሜሪካ አጋር የሆነው ሲቢኤስ ደግሞ ከበርካታ ሰዎች አጣርቻለሁ ሲል ዘግቧል። ሰውዬው ለዚህ ቦታ ሊታጩ የቻሉት ቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ለከፍተኛ የሥልጣን እርከኖች ጥቁር አሜሪካዊያን፣ እስያዊያንና ላቲን አሜሪካዊያን እንዲያጩ ከመብት ተሟጋቾች ተደጋጋሚ ጥሪ ስለቀረበላቸው ይሆናል ብሏል። ሲኤንኤን በበኩሉ ደግሞ ውስጥ አዋቂ ነገረኝ ብሎ ባወጣው ዘገባ ባይደና ባለፈው ቅዳሜና እሁድ ነው ጄኔራል ኦስቲን የመከላከያ ሚኒስትር እንዲሆኑ የጠየቋቸው እሳቸውም እሺታቸውን ሰጥተዋል ብሏል። ባለ አራት ኮከቡ ጄኔራል ከ2013 እስከ 2016 ባለው ጊዜ የአሜሪካ ማዕከላዊ ኮማንድ ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል። በወቅቱ መካከለኛው ምስራቅ፣ እንዲሁም ማዕከላዊና ደቡባዊ እስያን ይመለከቱ ነበር ተብሏል። ከዚህ ኃላፊነታቸው በፊት የአሜሪካ ወታደር ምክትል ጠቅላይ አዛዥና በኢራቅ የአሜሪካ ወታደሮች አዛዥ ሆነው አገልግለዋል። በእነዚህ ዓመታት ከያኔው ምክትል ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ጋር በቅርበት ይሰሩ እንደነበርም ይነገርላቸዋል።
news-54641714
https://www.bbc.com/amharic/news-54641714
ኮሮናቫይረስ፡ በኦክስፎርዱ የክትባት ሙከራ ላይ አንድ ሰው ቢሞትም የደህንነት ስጋት የለበትም ተባለ
በአስትራዜኔካ እና ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ በጥምረት እየበለጸገ የሚገኘው የኮሮናቫይረስ ክትባት ላይ ሙከራ በሚደረግባት ብራዚል የአንድ በጎ ፈቃደኛ ሕይወቱ ማለፏን ተከትሎ ክትባቱ ምንም አይነት የድህንነት ስጋት እንደሌለበት ተገለጸ።
የብራዚል ጤና ባለስልጣን ከሙከራው ጋር በተያያዘ ሕይወቱ ስላለፈው በጎ ፈቃደኛ ምንም አይነት መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል። የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ቡድን በበኩሉ በጉዳዩ ላይ ጥንቃቄ የተሞላበት ምርመራ እንደሚደረግና ክትባቱ ግን ምንም አይነት የደህንነት ስጋት እንደሌለበት አስታውቋል። ቢቢሲ ባገኘው መረጃ መሰረት ደግሞ በጎ ፈቃደኘው ክትባቱን አልወሰደም። በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እየተሰራ የሚገኘው ክትባት ላይ ከሚሳተፉት በጎ ፈቃደኞች መካከል ግማሽ የሚሆኑት ብቻ ሲሆን ክትባቱን እንዲወስዱ የተደረገው ቀሪዎቹ ደግሞ ማረጋገጫ የተሰጠው የማጅራት ገትር ክትባት ነው የተሰጣቸው። የሙከራው ተሳታፊ በጎ ፈቃደኞችም እራሳቸው የሚሰጣቸው የኮሮረናቫይረስ ክትባት ይሁን የማጅራት ገትር የሚያውቁት ነገር የለም። ይህ የሚደረገውም በገዛ ፈቃዳቸው ነው ተብሏል። ግዙፉ የመድሀኒት አምራች አስትራዜኔካ በበኩሉ በእያንዳንዱ የግለሰብ የሙከራ ሂደት ላይ አስተያየት እንደማይሰጥና ሙከራው ሲካሄድ ግን አስፈላጊው ጥንቃቄና የደህንነት እርምጃዎች መወሰዳቸውን አስታውቋል። ''ሁሉም ወሳኝ የጤና ሁኔታዎች በጥንቃቄ ተመርምረዋል፤ ከግምት ውስጥም ገብተዋል። ሙከራውም ሆነ የምርምር ሂደቱ ምንም አይነት አሳሳቢ ነገር አልተገኘባቸውም፤ የሚመለከታቸው ኃላፊዎችም ሂደቱን እንዲከታተሉት አድርገናል'' ብሏል። በአሁኑ ሰአት ከፍተኛ ተስፋ ከተጣለባቸው የክትባት ሙከራዎች መካከል ይሄኛው በቀዳሚነት የሚጠቀስ ሲሆን በቅርቡ ለገበያ እንደሚበቃም ይጠበቃል። እስካሁን ደረጃ አንድና ደረጃ ሁለት የሙከራ ሂደቶችን በስኬታማነት ያጠናቀቀው ይኸው ክትባት ደረጃ ሶስትን ለማጠናቀቅ ደግሞ በዩኬ፣ ብራዚልና ሕንድ በበጎ ፈቃደኞች ላይ ሙከራውን እያካሄደ ይገኛል። ባሳለፍነው ወር በዩኬ ይካሄድ የነበረው ሙከራ የጎንዮሽ ጉዳት ሊኖረው ይችላል በሚል ተቋርጦ የነበረ ሲሆን ከቀናት በኋላ ግን ሙከራውን ለማከናወን ምንም ስጋት እንደሌለ በመገለጹ ሂደቱ በድጋሚ እንዲጀመር ሆኗል። የብራዚል ጤና ባለስልጣን በጎ ፈቃደኛው ሕይወቱ ስለማለፉ ከትናንት በስትያ መስማቱን አስታውቋል። የብራዚል መገናኛ ብዙኃን በበኩላቸው ሕይወቱ ያላፈችው ግለሰብ የ28 ዓመት የህክምና ባለሙያ እንደሆነና ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ሕይወቱ እንዳለፈች ዘግበዋል። ይህ ክትባት ሙሉ ፈቃድ የሚያገኝ ከሆነ ብራዚል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ብልቃጦችን ለመግዛት ወስናለች። በአገሪቱ እስካሁን 5.3 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ከአሜሪካና ሕንድ በመቀጠል በዓለማችን ሶስተኛው ከፍተኛ ቁጥር ነው። የሟቾች ቁጥር ደግሞ እስካሁን 155 ሺ መድረሱ ተረጋግጧል።
news-47084924
https://www.bbc.com/amharic/news-47084924
የሱዳኑ ፕሬዝዳንት አልበሽር በማህበራዊ ሚዲያ የተቀሰቀሰባቸውን ተቃውሞ ተቹ
የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር አልባሽር ማህበራዊ የመገናኛ መድረኮችን በመጠቀም በመንግሥታቸው ላይ እየተካሄደ ያለውን ተቃውሞ በቀሰቀሱት ተቃዋሚዎቻቸው ላይ ተሳለቁ።
"መንግሥትን ወይም ፕሬዝዳንቱን በምርጫ ብቻ ካልሆነ በዋትስአፕ እና በፌስቡክ መፈታተን አይቻልም" በማለት ለደጋፊዎቻቸው ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ ይህንን የተናገሩት እንደ አዲስ የተቀሰቀሱ የተቃውሞ ሰልፎች በዋና ከተማዋ ካርቱም ከተካሄዱ በኋላ ነው። • ወደ ካናዳ መሄድ አስበዋል? ከአጭበርባሪዎች ይጠንቀቁ • ሱዳን ውስጥ የዳቦና የነዳጅ ዋጋ ንሮብናል ያሉ ዜጎች ከፖሊስ ጋር ተጋጩ ሰልፎቹ የተጀመሩት ህዳር ላይ መንግሥት በዳቦ ላይ የሚያደርገው ድጎማ ማንሳቱመን በመቃወም ሲሆን ኋላ ላይ ቁጣው ወደ ፕሬዝዳንቱ ዞሯል። ፕሬዝዳንት አልባሽር በምሥራቃዊ ሱዳን በምትገኘው ከሰላ ከተማ በደጋፊዎቻቸው በተካሄደ ሰልፍን ላይ ነበር በተቃዋሚዎቻቸው ላይ የተሳለቁበትን ንግግር ያደረጉት። በንግግራቸው ተቃዋሚዎች የመንግሥት ለውጥ ማምጣት የሚችሉት በምርጫ ብቻ ነው ብለዋል። "ይህ በሱዳን ሕዝብ ፊት የምንገባው የማይለወጥ ቃላችን ነው። ውሳኔው የብዙሃኑ የሱዳን ሕዝብ መብት ነው" ሲሉ ተናግረዋል። በተቃውሞው ወቅት የሱዳን መንግሥት ባለስልጣናት የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን መድረኮችን ለመዝጋት ሞክረው ነበር። ነገር ግን ሱዳናዊያን ያሉበትን ስፍራ የሚደብቅ ዘዴን በመጠቀም የመንግሥትን እገዳ በማለፍ ሲጠቀሙ ቆይተዋል። በተጨማሪም ፕሬዝዳንቱ ከኤርትራ ጋር በምትዋሰነው የከሰላ ከተማ ባደረጉት ንግግር ለአንድ ዓመት ገደማ ተዘግቶ የነበረው ድንበርም እንደሚከፈት ተናግረዋል። • የቮልስ ዋገን መምጣት የመኪና ዋጋን ይቀንስ ይሆን? ሱዳን በምሥራቅ በኩል ያለውን ድንበሯን የዘጋችው ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመግታት በሁለት ግዛቶቿ ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ስትደነግግ ነበር። የተቃውሞ ሰልፎቹ መካሄድ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ 30 ሰዎች እንደተገደሉ የሱዳን መንግሥት ቢናገርም፤ የሰብአዊ መብት ቡድኖች ግን የሟቾቹን ቁጥር ከ40 በላይ ያደርሱታል።
45469071
https://www.bbc.com/amharic/45469071
ስለ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በጥቂቱ
1997 ላይ በተደረገው የኢትዮጵያ ሃገር አቀፍ ምርጫ ቅንጅት ለአንድነት እና ዴሞክራሲ ፓርቲን ወክለው የአዲስ አበባ ከንቲባ ሆነው መመረጥ ችለዋል ነበር። ሥልጣን ከመያዛቸው በፊት ለእሥር ተዳረጉ፤ ለጥቆም ስደት።
የአርበኞች ግንቦት 7 ፓርቲ ዋና ሊቀመንበር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከ11 ዓመታት የስደት ሕይወት በኋላ ጵጉሜ 4/2010 ወደሃገራቸው ተመልሰዋል። • ፓርላማው የኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7 የሽብርተኝነት ፍረጃ መነሳትን አፀደቀ • ዶክተር ብርሃኑ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር ምን ተወያዩ? • "ወትሮም ቢሆንም የትጥቅ ትግል ፍላጎት የለንም" ግንቦት 7 ለመሆኑ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ማን ናቸው? ከአዲስ አበባ ጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቃ በምትገኘው ቢሾፍቱ ከተማ እትብታቸው የተቀበረው ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፤ የመጀመሪያ ድግሪያቸውን ያገኙት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነው። በዩኒቨርሲቲው በነበራቸው ቆይታ የወቅቱን ወታደራዊ አገዛዝ (ደርግ) በፅኑ በመቃወምም ይታወቃሉ። የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲን (ኢሕአፓ) በግልፅ ነቅፈዋል በሚል ክስ ለወራት ከታሠሩ በኋላ ወደ ሱዳን አመሩ፤ እዚያም ለሁለት ዓመት ያክል ቆይተው የጥገኝት ጥያቄያቸውን ወደ ተቀበለችው አሜሪካ አመሩ። እዚያም 'ከስቴት ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ኒው ዮርክ' በኢኮኖሚክስ ትምህርት ድግሪ አገኙ፤ 'ኒው ስኩል ፎር ሶሻል ሪሰርች' ከተሰኘው ተቋም ደግሞ የዶክትሬት ድግሪያቸውን በተመሳሳይ የትምህርት ዘርፍ ማግኘት ቻሉ። ከዚያ ቀጥሎ ባክኔል ዩኒቨርሲተን በመቀላቀል ኢኮኖሚክስ ትምህርት ለሶስት ዓመታት አስተማሩ። ወደ ሃገር ቤት በ1986 ዓ.ም. ብርሃኑ (ፕ/ር) ባለቤታቸው ዶ/ር ናርዶስ ምናሴ፣ ኖህ ብርሃኑ እና እያሱ ብርሃኑ የተሰኙ ሁለት ልጆቻቸውን ይዘው ወደ ሃገር ቤት የተመለሱት። የንግዱን ዓለም በመቀላቀልም የማዳበሪያ ፍብሪካ አቋቁመው መሥራት ያዙ፤ ጎን ለጎን ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ማስተማራቸውን ተያያዙት። ፕ/ር ብርሃኑ ሲነሱ ሁሌም አብሯቸው ከሚጠቀሱ ክስተቶች መካከል የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ ማሕበር አንዱ ነው። በእርሳቸው መሪነት የተቋቋመውን ይህን ማህበር ከ1988 - 92 ድረስ በፕሬዚዳንትነት መርተውታል። በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ውስጥም በአማካሪነት ይሠሩ ነበር፤ ፕ/ር ብርሃኑ። መጋቢት 30፤ 1993 ዓ.ም. ፕ/ር ብርሃኑ እና ፕ/ር መሥፍን ወልደማርያም በብሐራዊ ሎተሪ አዳራሽ የትምህርት ዓለም ነፃነትን በተመለከተ አንድ ቀን የፈጀ ውይይት አካሄዱ። በቀጣዩ ቀን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ባነሱት ግርግር ተናጠች፤ ምሁራኑም ለዚህ ግርግር መነሾ ናቹ በሚል ለእሥር ተዳረጉ፤ ከቀናት በኋላም ተፈቱ። ምርጫ 97 በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ በጉልህ ተፅፎ ባለፈው ምርጫ 97 ላይ ከፍተኛ ተሣትፎ የነበራቸው ፕ/ር ብርሃኑ ፓርቲያቸው ቅንጅት ለአንድነት እና ዴሞክራሲ ወክለው ቅስቀሳ መካሄድ ተያያዙ። ከወቅቱ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋርም ፊት ለፊት ክርክር አካሄዱ፤ ከ138 የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መቀመጫዎች 137 በማግኘት ፓርቲያቸው መዲናዋን መቆጣጠር ቻለ። ፕ/ር ብርሃኑም አዲስ አበባን በከንቲባነት እንዲያስተዳድሩ በፓርቲያቸው ተመረጡ፤ ዶ/ር አድማሱ ገበየሁ ምክትል ከንቲባ፤ አሰፋ ሃብተወልድ ደግሞ አፈ ጉባዔ በመሆን ተሾሙ። ነገር ግን ምርጫውን ተከትሎ የተነሳው ግርግር ፕ/ር ብርሃኑ ለእሥር እንዲዳረጉ ምክንያት ሆነ። ፕሮፌሰሩ ብቻ ሳይሆኑ የፓርቲ አጋሮቻቸው፤ በርካታ የመብት ተሟጋቾችና ጋዜጠኞችም ለአሥር እንዲዳረጉ ሆነ። ፕ/ር ብርሃኑ 'የነፃነት ጎህ ሲቀድ' የተሰኘውን መፅሐፋቸውን የፃፉት ቃሊቲ ሳሉ ነበር፤ መፅሐፉ በኡጋንዳ ከተማ ካምፓላ 1998 ላይ ሊታተም ችሏል። ድህረ ቃሊቲ ፕ/ር ብርሃኑ ለ21 ወራት ያክል እሥር ላይ ከቆዩ በኋላ 1999 ላይ ወደ አሜሪካ በመመለስ በክኔል ዩኒቨርሲቲ ማስተማራቸውን ቀጠሉ። አሜሪካ ሳሉም ግንቦት 7 የተሰኘ የፖለቲካ ፓርቲ ማቋቋማቸውን፤ ፓርቲው በተገኘው አማራጭ ሁላ ሥርዓቱን በመቋቋም ለውጥ ለማምጣት እንደሚጥርም ይፋ አደረጉ። ሚያዝያ 16፤ 2001 ዓ.ም.፤ ኢህአዴግ ግንቦት 7 መፈንቅለ መንግሥተ ሊያካሂድ ቢሞክርም አክሽፊያለሁ ሲል አስታወቀ፤ ከዚሁ ጋር ተያይዞም 35 ሰዎች ለእስር ተዳረጉ። በዚያው ዓመት የሃገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሮፌሰር ብርሃኑ በሌሉበት የሞት ብይን ወሰነባቸው፤ ከእርሳቸው ጋር ሌሎች 4 ግለሰቦች በሌሉበት የሞት ፍርድ የተበየነባቸው ሲሆን 33 ግለሰቦች ደግሞ የዕድሜ ልክ እሥራት ሰለባ ሆኑ። ፕሮፌሰር ብርሃኑ 2007 ላይ ሙሉ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ከበክኔል ዩኒቨርሲቲ ተቀበሉ። በተመሳሳይ ዓመት ወርሃ ሐምሌ ላይ ፕሮፌሰሩ ወደ ኤርትራ በማቅናት መሬት ላይ ያሉ የፓርቲው 'የናፃነት ታጋዮችን' በይፋ መቀላቀላቸውን አስታወቁ። በፈረንጆቹ 2016 መባቻ ላይ ግን የፓርቲውን ደጋፊዎች ለማበረታታትና የገንዘብ ድጋፍ ለማሰባሰብ በሚል ወደ አሜሪካ መመለሳቸውን አሳወቁ። የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፓርቲ ግንቦት 7 በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ ተከትሎ ትጥቅ በመፍታት ወደ ሃገር ቤት ለመመለስ እንዳሰበ ያሳወቀው በቅርቡ ነበር። ግዜው ደርሶም ፕሮፌሰሩን ጨምሮ ሌሎች የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ከዓመታት የውጭ ሃገራት ቆይታ በኋላ ጳጉሜ 4/2010 ወደ ሃገር ቤት ተመልሰዋል።
44369772
https://www.bbc.com/amharic/44369772
የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ የአልጀርስ ስምምነትን ተግባራዊ ለማድረግ ወሰነ
የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ለሃያ ዓመታት ኢትዮጵያና ኤርትራን በጦርነት ውስጥ ተፋጠው እንዲቆዩ ላደረጋቸው የድንበር ፍጥጫ መፍትሄ ይሰጣል የተባለውን የአልጀርስ ስምምነትን እንደሚቀበል አሳውቋል።
ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ከዚህ በተጨማሪም ወሳኝ የሚባሉ ኢኮኖሚያዊና ውሳኔዎችን አሳልፏል። በዚህም መሰረት ለሦስት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ በመንግሥት ብቸኛ ቁጥጥር ስር የነበሩ እና በግንባታ ላይ ያሉ ማምረቻ እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ወደ ግል ባለቤትነት እንዲዘዋወሩ ወስኗል። በዚህም መሰረትም የኢኮኖሚ ዕድገቱ ዜጎችን አካታች ሆኖ እንዲቀጥል የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች በትላልቅ ፕሮጀክቶች ላይ የአክስዮን ድርሻ እንዲኖራቸውም ወስኗል። በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም እውቀትና የውጭ ምንዛሪ ካፒታል ያላቸው የውጭ ባለሃብቶች ተገቢውን አዎንታዊ ሚና እንዲጫወቱ ለማስቻል • በመንግሥት ይዞታ ሥር ያሉ በማምረት ወይም አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙትም ሆነ በግንባታ ላይ የሚገኙ የባቡር፣ የስኳር ልማት፣ የኢንዱስትሪ ፓርክ፣ የሆቴልና የተለያዩ የማኑፋክቸሪንግ ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በአክሲዮን ሽያጭ ወደ ግል ዘርፍ እንዲተላለፉ • እንዲሁም የኢትዮ ቴሌኮም፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎች እና የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ድርጅት ትልቁን የአክስዮን ድርሻ መንግሥት ይዞ ቀሪው አክሲዮን ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ባለሃብቶች እንዲተላለፍ የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮ-ኤርትራ ወቅታዊ ሁኔታን በጥልቀት በመገምገም በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ተፈጥሮ የቆየው አለመግባባት እንዲያበቃና በሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች መካከል ዘላቂ ሰላም እንዲፈጠር ጥሪ አቅርቧል። የኢትዮጵያ መንግሥት የአልጀርሱን ስምምነት እና የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ ሙሉ ለሙሉ ተቀብሎ ተግባራዊ ለማድረግ የወሰነና ለተግባራዊነቱ ያለማመንታት በቁርጠኝነት የሚሰራ መሆኑንም ገልጿል። የኤርትራ መንግሥትም ተመሳሳይ አቋም በመውሰድ ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ የሰላም ጥሪውን ተቀብሎ ከዚህ በፊት የነበረውን አብሮነትና ሰላም ወደነበረበት ለመመለስና በቀጣይም ዘላቂነቱን ለመጠበቅ ለተግባራዊነቱ ያለማመንታት በቁርጠኝነት እንዲሰራ ጥሪ አቅርቧል።
41438844
https://www.bbc.com/amharic/41438844
የአይ ኤስ መሪ ባግዳዲ ድምፁ ተሰማ
የአይ ኤስ ታጣቂዎች የመሪያቸው የአቡበከር አል ባግዳዲ ነው ያሉትን የተቀዳ ድምፅ በድረ-ገፅ ለቀቁ።
የአይ ኤስ መሪ አቡበከር አል ባግዳዲ በዚህ በተቀዳው ድምፅ ላይ ተናጋሪው የአይ ኤስ መሪን በሚመስል ድምፅ፤ የሰሞኑን ሰሜን ኮሪያ ጃፓንን እንዲሁም አሜሪካንን እንዳስፈራራች ይጠቅሳል። ከዚህም በተጨማሪም የአይ ኤስ ጠንካራ ይዞታ የነበረቸው ሞሱልን ለማስመለስ የጦርነትን አስፈላጊነት ያወራል። ሞሱል በሐምሌ ወር በኢራቅ ኃይሎች እጅ ተመልሳ መግባቷ የሚታወስ ነው። በአደባባይ ከታየ ሦስት ዓመት ያለፈውን ባግዳዲን አድኖ ለመያዝ የሚደረገውን ጥረት ለተባበረ የ25 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ይሰጣል ተብሎ የታወጀ ሲሆን፤ በዕጣ ፈንታው ላይ ብዙ መላምቶች እየተነገሩ ነው። ለመጨረሻ ጊዜ አቡበከር አል ባግዳዲ የታየው ሞሱል በሚገኘው ታላቁ የአል ኑሪ መስጊድ ላይ በሰብከበት ወቅት ሲሆን፤ አይ ኤስ ከተማዋን ተቆጣጥሮ የኢስላማዊ መንግሥት አካል መሆኗን ባወጀበት ወቅት ነበር። ይህንን ድምፅ አስመልክቶ አይ ኤስን እየተዋጋ ያለው የአሜሪካ ኃይል ቃል አቀባይ ራያን ዲሎን ሲጠየቁ "ስለሞቱ ምንም የተጣራ መረጃ በሌለበት ሁኔታ፤ በህይወት እንዳለ ነው የምናስበው" በማለት ተናግረዋል። ከሱኒ ሙስሊም ጎራ የሚፈረጀው የአይ ኤስ ታጣቂ ቡድን ሰላማዊ ህዝብ ላይ ባነጣጠረው ከፍተኛ ጭካኔ በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ ሥጋትን ፈጥሯል። ባለፈው ዓመትም ከባድ ሽንፈት ገጥሞት ወደ ኢራቅና ሶሪያ ተገፍቷል። ይህ የ45 ደቂቃ ርዝማኔ ያለው ድምፅ የወጣው ከአይኤስ ቡድን ጋር ግነኙነት ባለው ድረ-ገፅ ላይ ሲሆን፤ ከባለፈው ኅዳር ወር ወዲህ እንደዚህ አይነት መረጃ ሲወጣ የመጀመሪያው ነው። ይህንንም ተከትሎ ባግዳዲ በአይ ኤስ ቁጥጥር ስር ባለው በኢራቅና ሶሪያ ድንበር አካባቢ አሁንም ተደብቆ ይሆናል የሚሉ ግምቶች እየተሰጡ ነው። በዘርፉ ላይ ያሉ አጥኚዎች እንደሚሉት አቡበከር አል ባግዳዲ ያለበትን የሚያውቁ እፍኝ የማይሞሉ ሰዎች ናቸው። ይህ ክስተት ልዩ ኃይልን አደራጅታ እያደነችው ላለችው አሜሪካ አስቸጋሪ ሁኔታን እየፈጠረ ነው።
news-52883363
https://www.bbc.com/amharic/news-52883363
የሊቨርፑል ተጫዋቾች የአሜሪካውን ግድያ ተቃወሙ
የሊቨርፑል ተጫዋቾች በአፍሪካ አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎይድ ላይ በፖሊስ የተፈጸመውን ግድያ በመቃወም በልምምድ ሜዳቸው ማሃል ላይ ክብ ሰርተው በጉልበታቸው ተንበርክከው አጋርነታቸውን አሳዩ።
የሊቨርፑል ተጫዋቾች የፍሎይድ ግድያን በመቃወም ተነሱት ፎቶ 29 የሊቨርፑል ተጫዋቾችን ተንበርክከው የሚያሳየው ፎቶግራፍ የወጣው "አንድነት ኃይል ነው" ከሚል የፎቶ መግለጫ ጋር ነው። ተጫዋቾቹ ፎቶውን የተነሱት ዛሬ ሰኞ በነበራቸው ልምምድ ላይ ሲሆን፤ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾቹ ማርከስ ራሽፎርድ እና ጃደን ሳንቾም በዓለም ዙሪያ እየተስተጋባ ባለው ጸረ ዘረኝነት ተቃውሞ ላይ ድምጻቸውን በማሰማት ተሳትፈዋል። የማንችስተር ዩናይትድ እና የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቹ ማርከስ ራሽፎርድ በበኩሉ ክስተቱ ለመቀበል እንደተቸገረ እንዲህ ሲል ተናግሯል "በምድራችን ላይ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ለመረዳት እየሞከርኩ ነው።" ጨምሮም "ሰዎች አንድ ላይ እንዲሆኑ፣ አብረው በመስራት ህብረት እንዲፈጥሩ በሚጠየቅበት ጊዜ፤ ከሌላው ጊዜ በበለጠ ተከፋፍለን እንገኛለን። "በዚህም ሰዎች እየተጎዱ ነው ምላሽን ይሻሉ። ስለጥቁሮች ሕይወት ግድ ይለናል። ስለጥቁሮች ባሕል ያገባናል። ስለጥቁሮች ማኅበረሰብ ግድ ይለናል። እኛም ድርሻ አለን። [ብላክ ላይቭስ ማተርስ]" ብሏል። ከሳምንት በፊት ጆርጅ ፍሎይድ ሚኒያፖሊስ ውስጥ ዴሪክ ቾቪን የተባለ ፖሊስ መሬት ላይ በደረቱ እንዲተኛ አድርጎት በጉልበቱ አንገቱ ላይ ለደቂቃዎች በመጫን ትንፋሽ እንዲያጥረው በማድረግ ካሰቃየው በኋላ ህይወቱ በማለፉ አሁን ድረስ መላዋን አሜሪካ ያናወጠ ተቃውሞ እየተካሄደ ነው። የፖሊስ መኮንኑ በዚህ ድርጊቱ ከሥራው የተባረረ ሲሆን በግድያ ወንጀልም ክስ ተመስርቶበታል።
news-49737850
https://www.bbc.com/amharic/news-49737850
በምዕራብ ወለጋ መንዲ በመከላከያ ካምፕ ላይ የተወረወረ ቦምብ አንድ ሰው ገደለ
በምዕራብ ወለጋ መንዲ ከተማ በሚገኝ የሃገር መከላከያ ሠራዊት ካምፕ ላይ የተወረወረ ቦምብ አንድ ሰው ሲገድል በርካቶችን አቁስሏል።
የመንዲ ከተማ የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለሙ ጉዲና ለቢቢሲ እንደተናገሩት ትናንት ጠዋት (ማክሰኞ) የተወረወረው ቦምብ የአንድ ሰው ህይወት ከመቅጠፉም በላይ በርካቶችን አቁስሏል። የመንዲ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር አዳም ኦልጂራ "በቅድሚያ ሶስት ሰዎች ቆስለው ወደ ሆስፒታላችን መጡ። ከዚያ ደግሞ ህይወቱ ያለፈ ሌላ ሰው መጣ" በማለት ይናገራሉ። "ህይወቱ ያለፈውም ሆነ ጉዳት የደረሰባቸው ከቦምብ ፍንጣሪ ይመስላል" ያሉት ሜዲካል ዳይሬክተሩ ቆስለው ወደ ሆስፒታሉ የመጡት ህክምና ተደርጎላቸው ከሆስፒታል እንዲወጡ ተደርጓል። • በምዕራብ ኦሮሚያ የጉሊሶ ከተማ ከንቲባ ግድያ የነዋሪውን ስጋት አባብሷል ከቦምብ ፍንዳታው ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር የዋለ ተጠርጣሪ እንዳለ የተጠየቁት አቶ አለሙ "እስካሁን አልታወቀም። እያጣራን ነው።'' ሲሉ መልሰዋል። በምዕራብ ወለጋ የምትገኘው የጉሊሶ ከተማ ከንቲባ አቶ አበበ ተካልኝ እሁድ ዕለት ማታ በመኖሪያ ቤታቸው ደጃፍ ላይ በታጣቂዎች መገደላቸው ይታወሳል። ቅዳሜ ከምሽቱ 1 ሰዓት ገደማም በቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ከተማ ሁለት ሰዎች በጥይት ተመትተው መገደላቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በምዕራብ ኦሮሚያ በዚህ መሰሉ ግድያ ምክንያቶች የነዋሪው ሕይወት ዕለት በዕለት ሰቆቃ የተሞላ መሆኑን ቢቢሲ ያነጋገራቸው ግለሰቦች አስረድተዋል። በምዕራብ ኦሮሚያ ይህን መሰሉ በነዋሪዎችና በመንግሥት ኃላፊዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችና ግድያ ሲፈጸም ወራት የተቆጠሩ ሲሆን ለጥቃቱ በይፋ ኃላፊነት የሚወስድም ሆነ ተጠያቂ የሆነ አካል አልተገኘም። • የምዕራብ ኦሮሚያ ነዋሪዎች ስጋትና ሰቆቃከአንድ ዓመት በፊትም በዚሁ ጉሊሶ ከተማ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ እና አዋሽ ባንክ በታጣቂዎች መዘረፋቸው ይታወሳል። በወቅቱ መንግሥት የኦነግ ሠራዊት አባላት ዝርፊያውን መፈጸማቸውን አሳውቆ ነበር። በተያያዘ ዜና በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሄር አስተዳደር ልዩ ዞን ባቲ ከተማ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ካምፕ ላይ ቅዳሜ ዕለት ቦምብ ተወርውሮ እንደነበር የዞኑ ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሑሴን አህመድ ለቢቢሲ ገልፀዋል ። ቦምቡን ማን እንደወረወረ የታወቀ ነገር የለም ያሉት አቶ ሁሴን፤ የተወረወረው ቦምብ በሰው ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለማድረሱንም ጨምረው ተናግረዋል።
news-55570563
https://www.bbc.com/amharic/news-55570563
የኢትዮጵያውያን ድምጽ ከሪያድ እና ጅዳ እስር ቤቶች ውስጥ
በተለያዩ የሳዑዲ አረቢያ እስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ እንግልት እንደሚደርስባቸው በመግለጽ መንግሥት ወደ አገር ቤት እንዲመልሳቸው ተማጽኗቸውን አቀረቡ።
በእስር ቤት ያሉ ስደተኞች (ቆየት ያለ ፎቶ) ጂዳ ውስጥ በሚገኝ እስር ቤት የሚገኙ ሦስት ኢትዮጵያውያን ስለሚደርስባቸው ስቃይ ለቢቢሲ የገለፁ ሲሆን፣ በየጊዜው በፖሊስ ድብደባ እንደሚደርስባቸው፣ በቂ ምግብ እንደማይሰጣቸው እና መታረዛቸውንም ጨምረው ገልፀዋል። ወደ አገራችን መልሱን የሚሉት እነዚህ ኢትዮጵያውያን ከኢትዮጵያ ቆንስላ መጥቶ የሚጠይቃቸው ማንም እንደሌለ፣ በአንድ ወቅት ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ቅጽ ቢሞሉም ከዚያ በኋላ ግን ማንም እንዳላነገራቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በበኩላቸው በየሳምንቱ ከሳዑዲ አረቢያ፣ ከኩዌይት፣ ከሌባኖስ እና ከሌሎችም የአረብ አገራት ኢትዮጵያውያን እየተመለሱ መሆኑን ገልፀው እስር ቤት ያሉና ቆንስላው ያላገኛቸው ኢትዮጵያውያን ወደ ኋላ እንደቀሩና እነርሱም በጊዜ ሂደት ወደ አገራቸው እንደሚገቡ አስረድተዋል። ከየመን ወደ ሳዑዲ ከገባ በኋላ ተይዞ እስር ቤት መግባቱን የሚናገረው ጀማል አሁን ያለበትን ሁኔታ ሲያስረዳ "ልብስ የለንም፤ ወደ አገራችን ይልኩናል በሚል ምግብ አንበላም ስንል ወታደሮች እየመጡ ይደበድቡናል" ይላል።። "ከትናንት ወዲያ በአንድ እግራችን አቁመው እየደበደቡን አረፈዱ። ከዚያ በኋላ እንድንበላ ሆንን። የሚመጣውም ምግብ ዝም ብሎ ነው። እንዳንሞትም እንዳንድንም ሆነን ነው ያለነው" ብሏል። እስር ቤት ከገባ ስምንት ወር እንደሆነው የሚገልፀው ጀማል፣ "ሪያድ ከርጅ የሚባል ስፍራ ታስረን ከርመናል። ከዚያ አስወጥተው ሃየር በሚባል እስር ቤት ከወሰዱን በኋላ ወደ ጂዳ አምጥተውናል" በማለት ከሁለት ወር በፊት ከሪያድ ወደ ጅዳ መዛወሩን እና ሪያድ ውስጥ መያዙን ገልጿል። በዚያው እስር ቤት የሚገኘው ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አሚን፣ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ እንደሚፈልግ ይናገራል። "ተስፋ ቆርጠናል" የሚለው አሚን ድምጻቸው ተሰምቶ ወደ ኢትዮጵያ መንግሥት እንዲመልሰው ይፈልጋል። አሚን ሪያድ ለአንድ ወር ከሪ ከርጅ እስር ቤት መታሰሩን ከዚያ በኋላም ሪያድ ውስጥ ሃይር በሚባል እስር ቤት ለአራት ወር ያህል ከታሰሩ በኋላ አሁን ወዳለበት መዘዋወሩንና ባለበት እስር ቤት ውስጥም ለሦስት ወር እንደቆየ ገልጿል። የእስር ቤቱ ጠባቂ ፖሊሶችን የታመሙ ታሳሪዎች ወደ ህክምና እንዲወሰዱ በሚጠይቁበት ጊዜ እንደሚደበደቡ፣ ወደ አገር ቤት እንዲመልሷቸው በሚጠይቁበት ጊዜ "መንግሥታችሁ አይፈልጋችሁም" የሚል ቅስምን የሚሰብር ምላሽ እንደሚሰጧቸው ያስረዳል። ጀማል በበኩሉ ሪያድ እስር ቤት ውስጥ ሳሉ "ከአስከሬን ጋር እንውላለን እናድራለን። አስከሬን እንኳ የማይነሳበት ወቅት ነው የነበረው። በሦስት ቀናችን ነበር አስከሬን ይነሳ የነበረው። ሰው ሆኖ መፈጠር ያስጠላ ነበር" በማለት የቆይታቸውን አስከፊነት ለቢቢሲ ገልጿል። ሌላው ከታሰረ ስምንት ወር እንደሆነው ለቢቢሲ የተናገረው አማረ ከኢትዮጵያ ከወጣ ሁለት ዓመት እንደሆነው ይገልጻል። በየመን አድርጎ ሳዑዲ አረቢያ ሲገባ ጧይት የሚባል ስፍራ ነው የተያዘው። እርሱ ባለበት እስር ቤት ውስጥ በአንድ ክፍል ከአንድ መቶ በላይ እስረኞች እንዳሉም ይናገራል። "በጣም አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው። በየጊዜው ፖሊሶች እየገቡ ይደበድቡናል። ምግብም በአግባቡ አይገባልንም።" ወደ ሳዑዲ ከጓዶኞቹ ጋር ሰርተን እንለወጣለን በሚል መምጣታቸውን የሚናገረው አበራ ደግሞ እስር ቤት ገብተው መቅረታቸውን እና በጣም ችግር ላይ መሆናቸውን በመግለጽ ወደ ኢትዮጵያ መልሱን ሲል የተማጽኖ ጥሪ ያሰማል። "የሚጠይቀን፣ የሚጎበኘን የለም፤ ተዘግተን ቀረን" ሲል ያሉበትን ሁኔታ ያስረዳል። ከኤምባሲ ወደ አገር ቤት ትሄደላችሁ በሚል ቅጽ መሙላታቸውን የሚናገረው አበራ ከዚያ ወዲህ የጠየቀን የለም በማለት ሁኔታውን ያስታውሳል። ከአንድ ወር በፊት ገንዘብ እየከፈለ የሚሄድ ካለ በሚል መጠየቃቸውን የሚናገረው አበራ፣ ገንዘብ ስለሌላቸው ግን እስር ቤት ውስጥ መቅረታቸውን ይገልጻል። ዓለም አቀፎቹ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች አምነስቲ ኢንተርናሽናልና ሂዩማን ራይትስ ዋች በሳዑዲ እስር ቤቶች ውስጥ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ የሚደርሰውን እንግልትና ስቃይ ላይ ባደጓቸው ማጣራቶች የስደተኞቹ ህይወት አደጋ ላይ መሆኑን አመልክተው የነበረ ሲሆን፣ የሞቱ ኢትዮጵያዊያን መኖራቸውንም በእስር ቤቶቹ ካሉ ስደተኞች መስማታቸውን ገልጸው ነበር። የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶቱ ጨምረውም የሳዑዲ መንግሥት ስደተኞቹ ያሉበት አደገኛ ሁኔታ እንዲያሻሽል እንዲሁም ነጻ እንዲወጡ የጠየቁ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ መንግሥትም የስደተኞቹ አያያዝ እንዲስተካከል ግፊት እንዲያደርግና ፈቃደኛ የሆኑትም ወደአገራቸው እንዲመለሱ የሚደረግበትን መንገድ እንዲፈልግ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል። የአውሮፓ ሕብረት ምክር ቤትም በሳዑዲ አረቢያ እስር ቤቶች በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ የሚፈጸመውን አስከፊ አያያዝና የሰብአዊ መብት ጥሰት በጽኑ የሚያወግዝ የውሳኔ ሐሳብ አስተላልፎ ነበር።
44558118
https://www.bbc.com/amharic/44558118
ኢትዮጵያና ኤርትራ የት ድረስ አብረው ይራመዳሉ?
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ስልጣን ሲረከቡ ፓርላማ ቀርበው ባደረጉት ንግግር ከኤርትራ ጋር ሰላም ለማውረድ እንደሚፈልጉ አስታውቀው ነበር።
በወቅቱ ከኤርትራ በኩል የተሰጠው ምላሽ ኢትዮጵያ ሰላም ማውረድ ከፈለገች የአልጀርሱን ስምምነት ተግባራዊ ማድረግ ቀዳሚው እርምጃ ነው የሚል ነበር። ኢትዮጵያ የአልጀርሱን ስምምነት ተግባራዊ እንደምታደርግ ስታስታውቅ በአገር ውስጥ ውሳኔውን የመቃወም ድምፆች ተሰምተው ነበር። በኤርትራ በኩል ግን ምንም የተባለ ነበር አልነበረም። ዛሬ ግን ዝምታው ተሰብሮ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ አዲስ አበባ ልኡካን እንደሚልኩ አስታውቀዋል። በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህር የሆነው መኃሪ ዮሃንስ ዘላቂ ሰላምን ያመጣል የሚለው ጉዳይ ዛሬ ላይ የሚመለስ ባይሆንም እርምጃው ግን በራሱ ትልቅ ነው ይላል። እርምጃው ትልቅ ነው የሚለው የእስከዛሬውን የሁለቱ አገራት ግንኙነት ከግምት በማስገባት ነው። የሁለቱ አገራት መንግስታት ላለፉት ሃያ ዓመታት ደረቅ አቋም ይዘው የኢትዮጵያ መንግስት የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ በመርህ ደረጃ ተቀብለነዋል ነገር ግን ትግበራው ውይይት ይፈልጋል ፤ የኤርትራ መንግስት ደግሞ ውሳኔው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፈፀም አለበት ሲሉ ከመቆየታቸው አንፃር እርምጃው የፖሊሲ ለውጥ ነውም ይላል። ከፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ንግግር እንደተረዳው ዋናው ችግር የነበረው በኤርትራው ገዥ ፓርቲና በህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ(ህወሃት) መካከል እንደነበርና አሁን ግን በኢትዮጵያ የአመራር ለውጥ መምጣቱ ፕሬዝዳንቱን ለውሳኔው አብቅቷቸዋል። ይህን "በሁለቱ አገራት መሪዎች መካከል መናበብ ያለ ይመስላል"በማለት ይገልፀዋል መኃሪ። የኤርትራ መንግስት ልኡክ ለመላክ በመወሰን የወሰደው እርምጃ ምን ያህል ጉልህ ነው የሚለው የሚመዘነው ልኡካኑ መጥተው በሚያደርጉት ውይይት እንደሆነ መኃሪ ያስረዳል። ልኡካኑ ከኢትዮጵያ አቻዎቻቸው ጋር የሁለቱ አገራት መሪዎችን ለማገናኘት ነገሮችን ለማመቻቸት ወይስ በድንበር ጉዳዩ ላይ ለመነጋገር የሚለውን ማወቅ እርምጃውን ለመመዘን ወሳኝ እንደሆነ ያምናል። "እርምጃው ዘላቂ ሰላምን ያመጣል አያመጣም የሚለው ጊዜው ደርሶ የውይይቱን ርእሰ ጉዳዮች ማወቅ ይጠይቃል"ብሏል። ከሁለት አስርታት በላይ በአገራቱ መካከል የዘለቀውን ዝምታ ለሰበሩት ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ትልቅ ዋጋ እንደሚሰጡ የሚናገሩት ኤርትራዊው የህግ ባለሙያና ግጭት አፈታት ኤክስፐርት አቶ ኤልያስ ሃብተስላሴ የኤርትራ መንግስት ወደዚህ ነገር የገባው ተገዶ ነው ይላሉ። ቢሆንም ግን ለንግግር በር መክፈቱ ትልቅ ግምት የሚሰጠው እንደሆነ ያምናሉ። እርምጃው ምን ድረስ የሚዘልቅ ነው የሚለውን ለማወቅ ጊዜ እንደሚጠይቅ "ምን ያህል ነው በሩን ክፍት ያደረገው የሚው በጊዜው የሚታይ ነው"በማለት በመኃሪ ሃሳብ ይስማማሉ። እሳቸው እንደሚሉት ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የኤርትራ መንግስት ወጣቱን በብሄራዊ ግዳጅ ሲያስገድድና ህዝቡ ላይ የተለያዩ ተፅእኖዎችን ሲያሳደር ኢትዮጵያ የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ ተግባራዊ ላለማድረግ እንቢተኛ ሆናለች በሚል ነበር። በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ መንግስት ባደረጋቸው ውሳኔዎች ምክንያት የኤርትራ መንግስት በቀደመው አቋሙ እንዳይቀጥል ሆኗል የሚል እምነት አላቸው። በሁለቱ አገራት ግጭት በደረሱ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ምክንያት ግን ጅማሮውን ከዳር ማድረስና በሁለቱ አገራት መካከል ሰላም ማስፈን ብዙ ስራ የሚጠይቅ እንደሚሆን አቶ ኤልያስ ይገልፃሉ። እንደ እሳቸው አገላለፅ በሁለቱ አገራት መንግስታት ምክንያት ሞት፣አካል ጉዳት፣መፈናቀል በአጠቃላይ ማህበራዊና ኢኮኖሚ ቀውሶች በሁለቱም ህዝቦች ላይ ደርሰዋል።በተለይም በሁለቱም በኩል ድንበር ላይ ያሉ ህዝቦች ይበልጥ ተጎድተዋል። ስለዚህም በሁለቱ አገራት ሰላም የማስፈን ነገር በመሪዎች ስምምነት ብቻ የሚጠናቀቅ ጉዳይ እንዳልሆነ አቶ ኤልያስ ያስረዳሉ። ይልቁንም የተጎጅዎች ካሳ ፣ሁለቱን ህዝብ የማገናኘትና ወደ ቀደመ ዝምድናው የመመለስ ጉዳይ ሊተኮርበት እንደሚገባ ያምናሉ። ለዚህ ደግሞ ስምምነቱ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ገፅታ ሊኖረውና ሲቪል ማህበራትን ፣ የሃይማኖት ተቋማትንና በሁለቱም አገራት በኩል የሚመለከታቸውን እንዲሁም አህጉራዊና አለም አቀፍ አካላትን ሊያሳትፍ እንደሚገባ ያስረዳሉ። ይህ ካልሆነ ግን አዎንታዊው ጅማሮ ግቡን አይመታም የሚል ስጋት አላቸው።
49030116
https://www.bbc.com/amharic/49030116
በሐዋሳ ውጥረት ነግሷል ተባለ
ዛሬ ረፋድ ላይ በሐዋሳ ከተማ የተኩስ ድምጽ መሰማቱን ተከትሎ፤ ስጋትና ውጥረት መንገሱን ቢቢሲ ያነጋገራቸው በከተማዋ የተለያዩ ክፍሎች የሚኖሩ ሰዎች ተናገሩ።
ቢቢሲ ያነጋገራቸው የከተማው ነዋሪዎች እንዳረጋገጡትም ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ በከተማዋ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ተቋርጧል። ቀድሞውኑም በዛሬው ዕለት (ሐምሌ 11/2011 ዓ. ም) የሲዳማን ክልልነት ይታወጃል በሚል ከነበረው እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ የከተማው ነዋሪዎች ዘንድ ስጋት የነበረ ሲሆን፤ ረፋድ ሦስት ሰዓት ገደማ በአንዳንድ ስፍራዎች ላይ በከተከሰተ ተቃውሞና በተሰማ የተኩስ ድምጽ ሳቢያ አብዛኛው የከተማዋ ክፍል ከተለመደው እንቅስቃሴ ውጪ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል። • "ነገ ክልል መሆናችንን እናውጃለን" የኤጀቶ አስተባባሪ የሲዳማ ክልል የመሆን ጥያቄን በተመለከተ ምርጫ ቦርድ ያቀረበውን ሃሳብ በተመለከተ የአገር ሽማግሌዎችና የዞኑ መስተዳደር ተወያይተው፤ ሕዝቡ ያቀረበውን ሃሳብ ተቀብሎ ሕዝበ ውሳኔውን እንዲጠብቅ መስማማታቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ሰዎች ቢቢሲ ለማወቅ ችሏል። ነገር ግን ወጣቶች ውሳኔውን በመቃወም ዛሬ ረፋድ ላይ ጉዱማሌ ወደተባለው ስፍራ ተሰብስበው በሚሄዱበት ጊዜ መንገድ መዝጋታቸውንና መኪኖች ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ በቦታው ነበርኩ ያለ የከተማዋ ነዋሪ ለቢቢሲ ተናግሯል። በዚህም ጊዜ የጸጥታ ኃይሎች ወጣቶቹ እንዲበተኑ ማድረጋቸውንም ተናግሯል። • 'ከሕግ ውጪ' የተዋሃዱት አምስቱ ክልሎች ይህንንም ተከትሎ ስጋት ውስጥ የነበረው የከተማዋ ነዋሪ ከመደበኛ ተግባሩ መቆጠቡንና ሱቆችና ሌሎች የንግድ ተቋማት በራቸውን መዝጋታቸውን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል። በአንዳንድ የከተማዋ ክፍሎች ተኩስ መሰማቱን አንድ ነዋሪ ለቢቢሲ ቢናገርም፤ ሌላ ነዋሪ ግን የከተማዋ እንቅስቃሴ ተገቶ ጭር ማለቱን ተናግራ፤ ባለችበት አካባቢ ግን ተኩስ አለመስማቷን ገልጻለች። ውጥረቱን ተከትሎ በሕዝብ እንቅስቃሴ የሚታወቁ የከተማዋ ክፍሎች መቀዛቀዛቸውን ያናገርናቸው ሰዎች የተናገሩ ሲሆን፤ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ይታዩ የነበሩት የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሠራዊት አባላት ከክልሉ የጸጥታ ኃይሎች ጋር በዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ እንደሚታዩም ተናግረዋል። አቶቴ ተብሎ በሚታወቀው የከተማዋ አካባቢ ያሉ የንግድ ተቋማት መዘጋታቸውንም አንዳንዶች እየተናገሩ ነው። • ኢትዮጵያ ከገባችበት የፖለቲካ ቅርቃር እንዴት ትውጣ? በተጨማሪም አላሙራ በተባለው አካባቢ ወጣቶች ከጸጥታ ኃይሎች ጋር ተፋጠው አንደነበረና እነሱን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ መጠቀማቸውንና ወጣቶቹም ድንጋይ ሲወረውሩ መመልከቱን አንድ የዓይን እማኝ ለቢቢሲ ተናግሯል። ይህንንም ተከትሎ በሰዎች ላይ ጉዳት እንደደረሰ አንዳንድ ሰዎች ቢናገሩም እስካሁን የተረጋገጠ ነገር የለም። የሲዳማ ዞን አስተዳደር፣ የአገር ሽማግሌዎችና የፖለቲካ ቡድኖች ህብረተሰቡ የቀረበውን መፍትሄ እንዲቀበልና በትዕግስት እንዲጠባበቅ ጥሪ እያቀረቡ ነው።
news-52880986
https://www.bbc.com/amharic/news-52880986
በአማራ ክልል ሁለት አመራሮች እና አንድ የፖሊስ አባል ተገደሉ
በአማራ ክልል በሁለት የተለያዩ ቦታዎች ላይ ትናንት እሁድ ሁለት የወረዳ ባለስልጣናትና አንድ የፖሊስ አባል በጥይት መገደላቸውን ቢቢሲ አረጋገጠ።
አቶ ስዩም መስፍን እና አቶ መንገሻ ሞላ ግድያዎቹ የተፈጸሙት ትላንት ግንቦት 23/2012 ዓ.ም የአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ወረዳ እና በክልሉ መዲና በባህር ዳር ውስጥ ነው። የራያ ቆቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ስዩም መስፍን እና የወረዳው የሕዝብ ሠላምና ደኅንነት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መንገሻ ሞላ ህይወታቸው ያለፈው ሕግ ለማስከበር ጥረት ሲያደርጉ መሆኑን የወረዳው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት የቡድን መሪ አቶ አየነ አማረ ለቢቢሲ ገልጸዋል። አመራሮቹ በወልዲያ ከተማ የነበራቸውን ሥራ አጠናቀው ወደ ቆቦ ከተማ በመመለስ ላይ እያሉ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በሚጻረር እና ለኮሮናቫይረስ ስርጭት በሚያጋልጥ መልኩ አንድ የባጃጅ አሸከርካሪ ስድስት ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ ተመልክተው ሕግን ለማስከበር መሞከራቸውን ገልጸዋል የቡድን መሪው። ይህንንም ተከትሎ ከሮቢት ከተማ ወጣ ብላ በምትገኝ መንጀሎ 036 ቀበሌ አካባቢ ሁለቱ አመራሮች ከመኪና ወርደው የተመለከቱትን ሕግን የተላለፈ ድርጊት ለማስቆም ሲጥሩ ከሁለት ሰዎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው ወዲያው ሕይታቸው ማለፉን ተናግረዋል። በክስተቱ ሟቾቹ በነበሩበት አሽከርካሪ ውስጥ የነበሩ ሌሎች ሰዎች በጥቃቱ ምንም ጉዳት ያልደረሰባቸው ሲሆን ግድያውን ተከትሎ የጸጥታ ኃይሎችን ከሮቢት ከተማ ይዘው በመመለስ ተጠርጣሪዎቹ ለመያዝ ጥረት መደረጉን አመልክተው፤ የድርጊቱ ፈጻሚዎች ይዘዋት የነበረችውን ባለጎማ ተሽከርካሪ (ባጃጇ) ጢሻ ውስጥ ደብቀው መሰወራቸውን አስታውቀዋል። ከግድያው በኋላ ፖሊስ ምርመራ በማካሄድ ድርጊቱን ፈጽመዋል ተብለው የተጠርጠሩትን ሰዎች ማንነት ለመለየት የቻለ ቢሆንም ቢሆንም እስካሁን በቁጥጥር ስር አለመዋላቸው ታውቋል። የወረዳ አመራር አባል የሆኑት ሁለቱም ሟቾቹ አቶ ስዩምና አቶ መንገሻ ባለትዳር እና የአንድ አንድ ልጆች አባት ነበሩ። የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው መፈጸሙንም ቢቢሲ ከቤተሰቦቻቸው ለማወቅ ችሏል። የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኮማንደር መሠረት ደባልቄ ለክልሉ መገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ ፖሊስ ከአካባቢው ሕብረተሰብ ጋር በመተባበር እየሠራ መሆኑን አስታውቀዋል። በተመሳሳይ በትላንትናው ዕለት ሻምበል አዛዥ የነበረው ምክትል ኢንስፔክተር ጀግኔ ዋሱ የተባለ የፖሊስ አባል ባህር ዳር በተከተኮሰበት ጥይት ህይወቱ ማለፉንም ኮማንደር መሠረት አስታውቀዋል። እንደ ኮማንደር መሠረት ከሆነ ባህርዳር ከተማ ሰባታአሚት በሚባል ቦታ በለቅሶ ሥነ ሥርዓት ወቅት ጥይት የሚተኩሱ ሰዎችን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥረት በሚያደርግበት ጊዜ ተተኩሶበት የጸጥታ ኃይል አባሉ ህይወቱ እንዳለፈ ገልጸዋል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን እንዳለው ድርጊቱን ተከትሎ በግድያው እጃቸው አለበት የሚባሉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል እያደረገ እንደሆነ አመልክቷል።
news-51232629
https://www.bbc.com/amharic/news-51232629
የዱባይ ማራቶን በኢትዮጵያውያን አትሌቶች የበላይነት ተጠናቀቀ
ትናንት ሌሊት በተከናወነው የዱባይ ማራቶን በሁለቱም ጾታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በበላይነት አጠናቀዋል።
አትሌት ኦሊቃ አዱኛ ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቋል። በወንዶች አትሌት ኦሊቃ አዱኛ ቢቂላ ሲያሸንፍ በሴቶች ደግሞ ወርቅነሽ ደገፋ የመጀመሪያ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። አትሌት ኦሊቃ ውድድሩን በአንደኝነት ለማጠናቀቅ 02፡06፡15 የፈጀበት ሲሆን፤ ሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከሦስተኛ እስከ 10 ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል። ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ኬኒያዊው ኤሪክ ኪፕታኑ ነው። በሴቶች በተካሄደው ውድድር አትሌት ወርቅነሽ ደገፋ 02፡19፡37 በመግባት በአንደኝነት ስትጨርስ፤ ሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከሁለተኛ እስከ ዘጠነኛ ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል። አትሌት ጉተኒ ሾኔ ሁለተኛ ስትሆን አትሌት በዳቱ ሂርጳ ደግሞ ሦስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። አትሌት ወርቅነሽ ደገፋ የ2017ቱን የዱባይ ማራቶንን ማሸነፏ ይታወሳል። አትሌት ወርቅነሽ ትናንት ከውድድሩ በፊት ለቢቢሲ ለዚህ ውድድር ከፍተኛ ዝግጅት ማድረጓን ተናግራለች። አትሌት ወርቅነሽ "የዱባይ አቀማመጥ ለኔ በጣም ምቹ ነው አሸንፋሁ" ብላ ነበር። አትሌት ወርቅነሽ ደገፋ የ2017ቱን የዱባይ ማራቶን ማሸነፏ ይታወሳል። ሁለተኛ ደረጃን የያዘችው አትሌት ጉተኒ ሾሜ 02፡20፡11 የገባች ሲሆን አትሌት በዳቱ ደግሞ 02፡21፡54 በሆነ ሰዓት አጠናቃለች። የዱባይ ማራቶን መዘጋጀት ከጀመረ ወዲህ ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች 15 ጊዜ በወንዶች ደግሞ 14 ጊዜ አሸንፈዋል።
news-53440865
https://www.bbc.com/amharic/news-53440865
ሪያል ማድሪድ ለ34ኛ ጊዜ ላ ሊጋውን ማሸነፉን አረጋገጠ
ሪያል ማድሪድ ትናንት ምሽት ቪላሪያልን ማሸነፉን ተከትሎ የላ ሊጋውን ዋንጫ ማንሳቱን አረጋግጧል።
ሪያል ማድሪድ ለ34ኛ ጊዜ ላ ሊጋውን ማሸነፉን አረጋገጠ የሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን ከሶስት ዓመት በኋላ ላ ሊጋውን ማሸነፉ የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ከማንሳት በላይ ደስታ እንደፈጠረለት ተናግሯል። ማድሪድ የላ ሊጋውን ዋንጫ ማንሳቱን ያረጋገጠው ካሪም ቤንዜማ ባስቆጠራቸው ሁለት ግቦች ቪላሪያልን ማሸነፉን ተከትሎ ነው። በኮሮናቫይረስ ስርጭት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የስፔን ሊግ ከተመለሰ በኋላ ማድሪዶች ያደረጓቸውን 10 ጨዋታዎች በሙሉ ማሸነፍ ችለዋል። በዚህም ሁለተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ባርሴሎና በ7 ነጥቦች እርቀው ነው ዋንጫ ማንሳታቸውን ያረጋገጡት። "ዛሬ ለእኔ ልዩ ቀን ነው። ብዙ ነገር ካሳለፍን በኋላ፣ ለሦስት ወራት ሊጉ ተቋርጦ ቆይቶ ተመልሰን ያሳካነው ነገር ድንቅ ነው" ብሏል ዚዳን። ሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም በእድሳት ላይ ስለሚገኝ ማድሪዶች ያለፉትን ጥቂት ጨዋታዎች ሲያካሂዱ የነበረው በሁለተኛው ስታዲየማቸው ነው። በኮሮናቫይረስ ስርጭት ስጋት እንደተለመደው ተጫዋቾች ከድል በኋላ በክፍት አውቶብስ ላይ ሆነው በማድሪድ ከተማ ከደጋፊዎቻቸው ጋር ተሰባሰበው ድላቸውን ማጣጣም እንደማይችሉ ከአሁኑ ግልጽ ተደርጓል። "ለሁላችንም ያልተለመደ ነገር ነው" ያለው ዚዳን "ከደጋፊዎቻችን ጋር በአንድ ላይ ሆነን ደስታችንን ብንገልጽ ደስ ይለኝ ነበር። ይሁን እንጂ እርግጠኛ ነኝ ሁሉም ደጋፊ በየቤቱ ደስተኛ ነው" ሲል ተናግሯል።
53089269
https://www.bbc.com/amharic/53089269
ቻይና የአፍሪካ ሲዲሲ ዋና መሥሪያ ቤትን በአዲስ አበባ ልትገነባ ነው
ቻይና የአፍሪካን የበሽታ መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከል-ሲዲሲ ዋና መሥሪያ ቤትን በአዲስ አበባ እንደምትገነባ ፕሬዚዳንት ዢ ዢንፒንግ ተናገሩ።
ፕሬዝደንት ዢ ዢንፒንግ የማዕከሉ ግንባታ ከታቀደው ጊዜ በፊት በዚህ ዓመት እንደሚጀመርም ፕሬዝደንቱ ጨምረው ተናግረዋል። የቻይናው ፕሬዝደንት ዢ ዢንፒንግ ይህንን የተናገሩት ትናንት በቻይና-አፍሪካ ኮቪድ-19 ስብሰባ ላይ ሲሆን በጎርጎሳውያኑ 2020 መከፈል የነበረባቸው ከወለድ ነጻ ብድሮችን ለአፍሪካ አገራት እንደምትሰርዝም አስታውቀዋል። በኮሮናቫይረስ ክፉኛ ለተጎዱ የአፍሪካ አገራትም የብድር መክፈያ ጊዜ ይራዘምላቸዋል ብለዋል። "የአፍሪካን ፍላጎት መሠረት ባደረገ መልኩ፤ በአፍሪካ ኮቪድ-19ን ለመዋጋት ቻይና ከተባበሩት መንግሥታት፣ የዓለም ጤና ድርጅት እና ከሌሎች አጋሮች ጋር በጥምረት ተሰራለች" ሲሉ ፕሬዝደንቱ ተናግረዋል። ዢ ዢንፒንግ ለቫይረሱ ክትባት ሲገኝ ከቻይና ሰራሹ ክትባት ቀድመው ተጠቃሚ የሚሆኑት አፍሪካውያን ናቸው ብለዋል። ቻይና በመላው አፍሪካ የሆስፒታል ግንባታ ማድረግ እንደምትቀጥልም ፕሬዝደንቱ አስታውቀዋል። "በመላው አፍሪካ የቻይና-አፍሪካ ወዳጅነት ሆስፒታሎች ግንባታ ይከሄዳል" ብለዋል ዢ ዢንፒንግ። በዚህ ቻይና-አፍሪካ ኮቪድ-19 ሰብሰባ ላይ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝን ጨምሮ፣ የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጀነራል ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም፣ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ሙሳ ፋኪ ማሃመት እና የበርካታ የአፍሪካ አገራት መሪዎች ተሳታፊ ነበሩ።
57111329
https://www.bbc.com/amharic/57111329
ፕሬዝደንት ባይደን ማስካቸውን አውልቀው ይህ "ለአሜሪካ ታላቅ ቀን ነው" አሉ
በአሜሪካ የኮቪድ-19 ክትባት የወሰዱ ሰዎች የአፍ እና አፍንጫ ጭምብል የማድረግ ግዴታ የለባቸውም መባሉን ተከትሎ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ማስካቸውን አውልቀው ይህ ለአሜሪካ ታላቅ ቀን ነው ብለዋል።
ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ባለስልጣናት በአሜሪካ የኮሮናቫይረስ ክትባትን የወሰዱ ሰዎች ከውስን ቦታዎች በስተቀር ያለጭምብል መንቀሳቀስ ይችላሉ ብለዋል። አካላዊ ርቀትን መጠበቅም አይጠበቅባቸውም ተብሏል። ከዚህ ውሳኔ በኋላ "ኦቫል" ቢሮ ከሪፐብሊካን ሕግ አውጪዎች ጋር ፕሬዝዳንቱ ራሳቸው ያለጭምብል ታየተዋል። ይሁን እንጂ እንደ አወቶብስ፣ አውሮፕላንና ሆስፒታል ባሉ መሰባሰብን በሚጠይቁ ከበር መለስ አገልግሎቶች የሚሰጡባቸው ቦታዎች ላይ ግን ክትባት የተከተቡትም ቢሆኑ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ ግዴታቸው ነው። ሙሉ በሙሉ ክትባቱን ላገኙ ሰዎች የኮቪድ ክልከላዎች እንዲነሱላቸው በባይደን አስተዳደር ላይ ጫና ሲደረግበት ቆይቷል። በሌላ በኩል ደግሞ የአሜሪካ የመምህራን ፌዴሬሽን ለፕሬዝዳንት ባይደን ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ እንዲከፈቱ ጥሪ አቅርቧል። ይህ ጥሪ የተላለፈው ፋይዘር ያመረተውን ከትባት ዕድሜያቸው ከ12 እስከ 15 ያሉ ህጻናት መከተብ እንዲችሉ ፍቃድ ከተሰጠ በኃላ ነው። አሁን ላይ በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ተሰምቷል። የአሜሪካ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል (ሲዲሲ) ክትባቱን የወሰዱ ሰዎች አካላዊ ርቀትን መጠበቅም ግዴታቸ እንዳልሆነ አስታውቋል። በቲውተር ገጻቸው ያልተከተቡ ሰዎች 'ማስክ' ማድረጋቸውን እንዲቀጥሉ ያሳሰቡት ባይደን "ህጉ ቀላል ነው መከተብ ወይም እስከትከተቡ ጭምብል ማደረግ። ምርጫው የእናንተ ነው" ብለዋል። በአሜሪካ 35 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ክትባት ያገኘ ሲሆን የ ጆ ባይደን አስተዳደር ይሄ ቁጥር እስከ ሀምሌ ደረስ በእጥፍ አሳድጎ 70 በመቶ ለማደረስ አቅዷል።
news-48211244
https://www.bbc.com/amharic/news-48211244
አሜሪካ፡ የዘር ልዩነት ለእናቶች ሞት ምክንያት ሆኗል
በአሜሪካ ከእርግዝና ጋር በተያያዘ የሚሞቱ እናቶች ቁጥር ማሻቀቡን የበሽታ ቁጥጥር ማዕከል (ሲ ዲ ሲ) በጥናቴ ደርሸበታለሁ ብሏል፤ ምከንያቱ ደግሞ ጥቁር መሆን ነው ሲል አመላክቷል።
ጥናቱ እንዳመለከተው ጥቁር አሜሪካውያን፣ የአላስካ ነባር አሜሪካውያን፣ እና ነባር አሜሪካውያን እናቶች ሞት ቁጥር ከነጭ አሜሪካውን በሦስት እጥፍ ይበልጣል። በየዓመቱ 700 ገደማ የሚሆኑ ሴቶች ከእርግዝና ጋር በተያያዘ እንደሚሞቱም ጥናቱ ይፋ አድርጓል። 60 በመቶ የሚሆነው የሞት ምክንያትም ቀድሞ መከላከል የሚቻል ነው ሲል ጥናቱ ጠቅሷል። በአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል (Centers for Disease Control) ዳይሬክተር የሆኑት አን ሹቻት "በጣም በርካታ ሴቶች ቀድሞ መከላከል በሚቻልና ከእርግዝና ጋር በተያያዘ ይሞታሉ" ብለዋል። እነዚህን ችግሮችም ለመለየትና ለመፍታት ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ተናግረዋል። • በሕይወት ከሌለች እናት የተወለደችው ሕፃን ከዚሁ ጋር በተገናኘም በዚህ ጥናት ያልተካተቱት የአሜሪካ የፅንስና ማህፀን ሐኪሞች ኮሌጅ ባለፈው ሳምንት አንድ መግለጫ አውጥቶ ነበር፤ በመግለጫቸውም ላይ በጤና ጥበቃው ስርዓትና በጤና ተቋማት የዘር መድሎ እንደሚፈፀም ገልፀዋል። "ለእናቶች ሞት ምክንያት ዋናው ዘረኝነት ነው" ሲሉም በመግለጫቸው አስፍረዋል። "ችግሩ በጤና ተቋማትና በጤና ጥበቃ ሥርዓቱ ያለው ጥግ የነካ ዘረኝነት ዋናው ምክንያት እንደሆነ አስታውቋል። ሲ ዲ ሲ በጥናቱ ከአውሮፓውያኑ 2011-2017 ድረስ ያለውን የእናቶች ሞት የተመለከተ ሲሆን ባለፉት አምስት ዓመታት ከእርግዝና ጋር በተያያዘ 3400 ሞት መመዝገቡን አስታውቋል። በነጭ ሴቶች፤ ከሚወለዱ 100 ሺዎቹ 13 እናቶች ሲሞቱ፤ ይህ በጥቁር እናቶች ሲታይ ደግሞ ቁጥሩ በሦስት እጥፍ አድጎ ከ100 ሺዎቹ 42 እናቶች ሕይወታቸው ያልፋል። • አራት ልጆች የወለዱ እናቶች ከግብር ነፃ ሊሆኑ ነው በነባር አሜሪካውያን እና በአላስካ ሴቶች ሲታይ ቁጥሩ 32.5 ሲሆን ኢሲያ እና ፓስፊክ ሴቶች 14.2 ሆኖ ተመዝግቧል። በጣም ዝቅተኛ ቁጥር የሚያሳው ሂስፓኒክ ሴቶች ሲሆን ከ100 ሺዎቹ የሚሞቱት 11 እናቶች ብቻ ናቸው። ዋነኛው በእርግዝና ወቅት ለሞት ከሚዳርጉ ምክንያቶች የተጠቀሰው ከልብ ጋር የተያያዙ ችግሮች ሲሆኑ፤ የልብ ህመምና ስትሮክ ሞቱን በሦስት እጥፍ ይጨምሩታል። በዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት መሠረት በአሜሪካ የእናቶች ሞት ቁጥር መጨመሩ ከሌላው ዓለም ጋር ሲነፃፀር ያልተጠበቀ ቢሆንም በዓለም ከአውሮፓውያኑ 1990 እና 2015 መካካል ባሉት ዓመታት የእናቶች ሞት በ44 በመቶ እንደቀነሰ ታውቋል።
news-44450369
https://www.bbc.com/amharic/news-44450369
አሜሪካ ከጥገኝነት ጋር በተያያዘ ዐብይ ውሳኔ አሳለፈች
የአሜሪካው ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በቤት ውስጥ ጥቃት የተፈፀመባቸውና የቡድን ጥቃት ደርሶብናል ማለት በአሜሪካ ጥገኝነት ለመጠየቅ ብቁ አለመሆኑን የሚያትት ጉልህ ውሳኔን አስተላልፈዋል።
ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ጄፍ ሴሽንስ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ጄፍ ሴሽንስ ያስተላለፉት ውሳኔ በ2014 በገዛ ባሌ የመደፈር ጥቃት ደርሶብኛል በማለት በአሜሪካ ምድር የጥገኝነት ጥያቄ ያረበችውን ኢል ሳልቫዶራዊት ሴት የከለላ ይሰጠኝ ጥያቄ ውሳኔ የሚቀለብስ ነው። በአሜሪካ የቤት ውስጥ አልያም የቡድን ጥቃት ደርሶብኛል በሚል ብቻ ጥገኝነት መጠየቅ ወዲያዉኑ ከለላን የሚያስገኝ ጉዳይ መሆን የለበትም ያሉት ዐቃቤ ሕጉ፤ መንግሥታት በአገራቸው የሚፈጸም ወንጀልን ማስቆም አልቻሉም ማለት የአሜሪካ ፍርድ ቤት ለዚያች አገር አመልካቾች ሁሉ የከለላ ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ እንዲሰጥ የሚስገደድው አይሆንም ሲሉ በጻፉት የፍርድ ውሳኔ ሐተታ ላይ አብራርተዋል። የሰብዓው መብት ተሟጋቾች በበኩላቸው እርምጃው በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ከለላ ፈላጊዎች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል ሲሉ የአቃቢ ሕጉን አዲስ ውሳኔ ተችተውታል። "አገራቱ እንደዚህ ዓይነት ወንጀሎችን የፈፀሙ ሰዎችን ለመቅጣት የሕግ ክፍትት ሊኖርባቸው ይችላል፤ ነገር ግን ብቻውን ጥገኝነት ለመጠየቅ በቂ ምክንያት አይደለም ሲሉ ተናግረዋል። ሴትየዋ ተደረሰባት ጥቃት ግለሰባዊ የወንጀል ድርጊት እንጂ አገራዊ አይደለም ሲል ለሴትየዋ የተመለሰው መልስ አግባብ አልነበረም ሲሉ በፍርድ ውሳኔያቸው ላይ ጠቅሰዋል። ምንም እንኳን በዓለም ላይ የሚኖሩ ሰዎች በየቀኑ የሚያጋጥሟቸው ብርቱ ችግሮች ቢኖሩም ጥገኝነት መጠየቅ ለእነዚህ ሁሉ ችግሮች መፍትሔ አይደለም ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል። ይህ የጠቅላይ አቃቢ ሕጉ ዋነኛ ውሳኔ ከዚህ ቀደም በታችኛው ፍርድ ቤት በገዛ ባሏ የመደፈር ጥቃት ደርሶባት የነበረችውንና ይህንኑ ተከትሎ ጥገኝነት አግኝታ የነበረችውን የኤልሳል ቫዶር ሴት ውሳኔ የሚቀለብስ ነው። ይህ ውሳኔ ምን ያህል የጥገኝነት አመልካቾ ላይ ተጽእኖ ይኖረዋል የሚለው በግልጽ ባይታወቅም የመብት ተሟጋቾች ግን ቢያንስ በየዓመቱ 10ሺህ ስደተኞች የቤት ውስጥና የቡድን ጥቃትን እንደ ዋና ምክንያት በማቅረብ ጥገኝነት ያገኙ እንደነበር ገልጸዋል።
news-45243838
https://www.bbc.com/amharic/news-45243838
የግብፅ ኦርቶዶክስ ኮፕቲክ ቤተክርስትያን መነኮሳት በግድያ ተከሰሱ
የግብፅ ኦርቶዶክስ ኮፕቲክ ቤተክርስትያን ሁለት መነኮሳት በግድያ የተከሰሱት የቤተክርስትያኗ የበረሃ ገዳም ሃላፊ ተገድለው መገኘታቸውን ተከትሎ ነው።
መነኮሳቱ ሃላፊውን የገደሏቸው ፀሎት ለማድረግ በመዘጋጀት ላይ ሳሉ ነበር። በምእራብ ግብፅ በርሃ የሚገኘው ማካሪየስ ገዳም ሃላፊ ጳጳስ ኢፒፋነስ ሰውነት በደም ተነክሮ የተገኘው እንደ አውሮፓውያኑ ባለፈው ወር መጨረሻ ላይ ነበር። አሁን በግድያ የተጠረጠሩት ሁለቱ መነኮሳት ከጳጳሱ ጋር ቀድም ሲል የአቋም ልዩነት ነበራቸው በሚል መነሻ መጠርጠራቸውም ተገልጿል። ሁኔታው የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያንን እጅግ አስደንግጧል። . ልዩ ፖሊስን ማን መሰረተው? . በታንዛንያ የአንድ ሰፈር ነዋሪዎች በሙሉ በቁጥጥር ስር ዋሉ . የባለዳንቴሏ የክር ጫማዎች የግብፅ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ቢሮ እንዳስታወቀው ከተከሳሾቹ መነኮሳት አንዱ ዋለ አለ ሳድ ጳጳሱን 90 ሴ.ሜ ርዝበት ባለው የቧንቧ ብረት ጭንቅላታቸውን መትተዋቸዋል። እኚህ መነኩሴ ግድያውን ተከትሎ ከገዳሙ ተባረው የነበረ ሲሆን ቀደም ሲልም ከሃላፊዎች ጋር በመጋጨትና የገዳሙን ህግ በመጣስ ጉዳያቸው ሲታይ መቆየቱ ተጠቁሟል። መቼ እንደሆነ በግልፅ ባይታወቅም አሁን ሁለቱም መነኮሳት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ። ይህን ተከትሎ ቤተክርስትያኗ አዳዲስ ህገ ደንቦችን አውጥታለች። ከእነዚህም ለአንድ አመት ያህል አዲስ መነኩሴ አለመቀበል ፣ ቀሳውስት ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙና መነኮሳት ያለ ፍቃድ ከገዳም እንዳይወጡ የሚሉት ይገኙበታል።
news-48264656
https://www.bbc.com/amharic/news-48264656
ኢንዶኔዥያ፡ እናት አልባዎቹ መንደሮች
በምስራቃዊ ኢንዶኔዢያ በሚገኙ መንደሮች አብዛኛዎቹ ወጣት እናቶች ለተሻለ ስራና ህይወት ፍለጋ ልጆቻቸውን ትተው ወደውጪ ሃገራት ተሰድደዋል።
የሃገሬው ሰውም እነዚህን አካባቢዎች 'እናት አልባዎቹ መንደሮች' ይላቸዋል። ኤሊ ሱሲያዋቲ እናቷ ጥላት ስትሄድ ገና የ11 ዓመት ልጅ የነበረች ሲሆን አያቷ ናቸው የሚያሳድጓት። የኤሊ እናት ማርቲያና ከባለቤቷ ጋር ከተፋታች በኋላ ልጇን በተሻለ ሁኔታ ለማሳደግና ቤተሰቦቿን ለመርዳት በማሰብ ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ በቤት ሰራተኝነት ለመቀጠር ወሰነች። • ቄሮ፣ ሴታዊት፣ ፋኖ…የትውልዱ ድምጾች ኤሊ በአስራዎቹ እድሜ ክልል ውስጥ የምትገኝ ሲሆን እናቷ አብራት አለመኖሯ ብዙ ነገር እንዳጎደለባት ትናገራለች። ''ትምህርት ቤት ውስጥ ቤተሰብ ያላቸው ጓደኞቼን ስመለከት እጅጉን አዝናለሁ። እናቴ መቼ ነው የምትመጣው እያልኩ በጣም እጨነቃለሁ።'' ትላለች። ኤሊ የምትኖርባትና በምስራቃዊ 'ሎምቦክ' የምትገኘው መንደር 'ዋናሳብ' ትባላለች። በዚች መንደር እናቶች የልጆቻቸውን ፍላጎት ለማሟላትና የተሻለ ህይወት ለመምራት ወደ ውጪ ሃገራት መሄድ የተለመደና የሚበረታታ ነገር ነው። አብዛኛዎቹ ወንዶች ደግሞ በግብርና ስራ የሚተዳደሩ አልያም በቀን ስራ ህይወታቸውን የሚገፉ ናቸው። ገቢያቸው ሴቶቹ ወደውጪ ሃገራት ሄደው ከሚልኩት ገንዘብ ጋር ሲወዳደር ደግሞ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። በመንደሯ እናቶች ወደውጪ ሃገራት ሲሄዱ ቤተዘመድ ሰብሰብ ይልና ልጆቻቸውን እንዴት እንደሚያሳድጉላቸው ይመክራል። ሁሉም የቤተሰብ አባል ልጆቹን የመንከባከብ ሃላፊነት አለበት። ነገር ግን እናቶቻቸውን ለሚሰናበቱት ልጆች ምን ያህል ከባድ ሊሆን እንደሚችል መገመት አይከብድም። ካሪማቱል አዲቢያ እናቷ ጥላት ስትሄድ ገና የአንድ ዓመት ልጅ የነበረች ሲሆን እንደገና የተገናኙትም የ12 ዓመት ታዳጊ እያለች ነው። '' ልክ እንዳየኋት ግራ ተጋባሁ። ማን እንደሆነች አላውቅም። እናቴ ስታለቅስ አስታውሳለሁ። ለምን የእኔ ልጅ እንደሆነች አትረዳም እያለች አያቴን ትጠይቅ ነበር።'' ትላለች። ካሪማቱል እናቷን ለመጀመሪያ ጊዜ እስከምታያት ድረስ ፎቶዋን እንኳን ተመልክታ አታውቅም። ሙሉ እድሜዋን ያሳለፈችው በአክስቷ ባይቅ ቤት ነው። ባይቅ በቤቷ ውስጥ ዘጠኝ ልጆችን ታሳድጋለች። ከዘጠኙ ግን የእርሷ የሆነው አንድ ልጅ ብቻ ነው። ካራማቱልን ጨምሮ ስምንቱ ስራ ፍለጋ ወደሌላ ሃገር የሄዱ የእህቶቿ ልጆች ናቸው። • ሜድ ኢን ቻይና- የሀገር ባህል አልባሳቶቻችን • በአንዳንድ ሃገራት ጉርሻ መስጠት እንደ ስደብ እንደሚቆጠር ያውቃሉ? የኢንዶኔዢያ ሴቶች ወደተለያዩ ሃገራት ስራ ፍለጋ መሄድ የጀመሩት በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር 1980ዎቹ ውስጥ ሲሆን አብዛኛዎቹ ለጥቃትና ሌሎች ተዛማጅ ችግሮች የተጋለጡ ናቸው። ስራ ፍለጋ ዘመድ አዝማድ ተሰናብተው፤ ልጆቻቸውን ለቤተሰብ አደራ ሰጥተው ወደ ውጪ ሃገራት የሄዱና በሬሳ ሳጥን የተመለሱ ብዙዎች መሆናቸውን 'የዋናሳብ' መንደር ነዋሪዎች ይናገራሉ። ጾታዊ ጥቃት ይደርስባቸዋል፤ ይደበደባሉ አንዳንዴም የሰሩበት ደመወዝ ሳይከፈላቸው ይባረራሉ። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ አንዳንዶቹ ደግሞ ሌሎች ልጆች ወልደው ይመጣሉ። ብዙ ጊዜ በአሰሪዎቻቸው ጾታዊ ጥቃት ደርሶባቸው ነው ልጆቹን የሚወልዷቸው። የተሻለ ስራ ፍለጋ በተለይ ወደ አረብ ሃገራት ከሚሄዱት ኢንዶኔዢያውያን መካከል ሁለት ሶስተኛውን ቦታ የሚይዙት ሴቶች ሲሆኑ የሚልኩት ገንዘብ ደግሞ ተተኪው ትውልድ ወደ ትምህርት ቤት የመሄዱንና ያለመሄዱን እድል እስከመወሰን ይደርሳል። ኤሊ እናቷን ለዘጠኝ ዓመታት አላየቻትም፤ ነገር ግን የሚላከው ገንዘብ ቤተሰቡ ምግብ በልቶ ማደሩን ከማረጋገጥ አልፎ ዩኒቨርሲቲ የገባች የመጀመሪያዋ የቤተሰብ አባል መሆን አስችሏታል። • የምግብ ምርጫዎ ስለማንነትዎ ይናገራል? በአሁኑ ወቅት ኢስላማዊ የገንዘብ አስተዳደር በማጥናት ላይ የምትገኘው ኤሊ እናቷ ያደረገችላትን ነገር መገንዘብ የጀመረች ትመስላለች። ''እሷ ወደ አረብ ሃገር ባትሄድ ኖሮ ቤተሰባችን ምን ይውጠው እንደነበር አላውቅም። ትምህርቴንም መከታተል እንደማልችል ይሰማኛል'' ትላለች። '' ቤተሰቦቻችን የተማሩ ስላልነበሩ ይህንን መንገድ መርጠዋል። እኛ ደግሞ ተምረን የተሻለ ህይወት እንደምንመራ ተስፋ አደርጋለሁ። ጥሩ ህይወት ለመኖርና ፍላጎቶቻችንን ለማሟላት ወደውጪ ሃገራት የግድ መሄድ የለብንም።''