id
stringlengths 8
14
| url
stringlengths 36
42
| title
stringlengths 8
90
| summary
stringlengths 6
505
| text
stringlengths 133
19.2k
|
---|---|---|---|---|
news-55478320 | https://www.bbc.com/amharic/news-55478320 | ኮሮናቫይረስ፡ በቻይናዋ ዉሃን 500 ሺህ ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘው ነበር ተባለ | ከቻይናዋ ከተማ ዉሃን ነዋሪዎች መካከል 5 በመቶ ያህሉ በኮሮናቫይረስ ተይዘው ነበር ሲል የቻይና በሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማዕከል ተመራማሪዎች ጥናት ይፋ አደረገ። | በዚህ ጥናት መረጃ መሰረት የዉሃን ሕዝብ ብዛት 11 ሚሊዮን ሲሆን ከእነዚህም መካከል 500,000 ያህሉ በቫይረሱ ተይዘው ነበር ማለት ነው። የዚህ ጥናት ውጤት እውነት ሆኖ ከተገኘ የዉሃን ግዛት ባለሥልጣናት በቫይረሱ ተይዘዋል በሚል ከገለፁት ቁጥር በ10 እጥፍ የሚበልጥ ሰው በኮሮና ተህዋሲ ተጠቅቶ ነበር ማለት ነው። ዉሃን እስካሁን ድረስ በቫይረሱ መያዛቸውን የተናገረችው 50,354 ሰዎችን ብቻ ነው። በቻይና ቫይረሱ ኖሮባቸው ነገር ግን ምንም ዓይነት ምልክት የማያሳዩ ሰዎች (Asymptomatic cases) አይቆጠሩም። ይህ ጥናት ይፋ የተደረገው የዓለም አቀፍ ተመራማሪዎች ቡድን የኮቪድ-19 መነሻ የሆነችውን ዉሃንን ለመጎብኘትና ምርመራ ለማድረግ ከመምጣታቸው ቀደም ብሎ ነው። የዓለም አቀፍ ተመራማሪዎችና ገለልተኛ አካልን ለመቀበል ዳተኛ ከነበረው ከቻይና መንግሥት ጋር ለረዥም ጊዜ ከተደረገ ድርድር በኋላ በሚቀጥለው ወር ምርመራቸውን ለመጀመር ወደ ግዛቲቱ ይመጣሉ። ቻይና በኮሮናቫይረስ የተያዙ ዜጎቼ በሚል ይፋ ያደረገችው ቁጥር ላይ ጥርጣሬ የገባቸው አካላት፣ አገሪቱ የኮሮናቫይረስ ቁጥሮች ላይ ግልጽነት ይጎድላታል በሚል ሲተቿት ነበር። ለዚህ ጥናት በዉሃን ከ34,000 ሰዎች እንዲሁም ከሁቤ፣ ቤይዢንግ፣ ሻንጋይ እንዲሁም አራት ሌሎች አውራጃዎች ናሙናዎች መወሰዳቸውን የበሽታ መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከሉ በዊቻት ላይ የለቀቀው መግለጫ ያስረዳል። ተመራማሪዎቹ በዉሃን ብቻ ከተወሰዱ ናሙናዎች 4.43% አንቲቦዲ ያገኙ ሲሆን፣ በ ሁቤይ ድንበር ከተማ ደግሞ የስርጭት መጠኑ 0.44% መሆኑን ደርሰውበታል። ጥናቱ አክሎም ከሁቤይ ውጪ ከተመረመሩ 12,000 ሰዎች መካከል ሁለቱ ብቻ አንቲቦዲ አዳብረው ተገኝተዋል ብሏል። ጥናቱ የተካሄደው ቻይና የመጀመሪያውን ዙር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተቆጣጠረች ከወር በኋላ ነው። ይህ ጥናት በማጠቃለያው ላይ እንዳስቀመጠው በኮሮና ተህዋሲ የተያዙ ቻይናውያን ቁጥር ከዉሃን ውጪ አነስተኛ ሲሆን ይህም ሊሆን የቻለው በግዛቲቱ የተደረገው ጠንካራ የመከላከል ሥራ ወረርሽኙ ወደ ሌሎች አካባቢዎች በስፋት እንዳይሰራጭ ስላደረገው ነው ብሏል። እየተጠናቀቀ ባለው በዚህ የፈረንጆች ዓመት መጀመሪያ ላይ በዉሃን የገበያ ስፍራ የኮሮናቫይረስ መገኘቱ ይታወሳል። ከዚያ ጊዜ ወዲህ በዚህ የገበያ ስፍራ የኮሮናቫይረስ ከእንስሳት ወደ ሰው ሳይተላለፍ አልቀረም የሚል መላምት ሲነገር ቆይቷል። ነገር ግን አሁን ባለሙያዎች ቫይረሱ ከዚያ አካባቢ መነሻውን አድርጎ ሳይሆን፣ በበርካታ ሰዎች ላይ በስፋት የተሰራጭቶ ሊሆን ይችላል እያሉ ነው። |
news-46608416 | https://www.bbc.com/amharic/news-46608416 | ለልጃቸው "ሂትለር" የሚል ስም የሰጡ እናትና አባት ተፈረደባቸው | ክላውዲያ ፓታታ እና አዳም ቶማስ አፍቃሪ ናዚ የሆነው ሕገ ወጥ ፓርቲ አባላት ናቸው። | ለአዶልፍ ሂትለር ያላቸውን ፍቅር ለመግለጽ የሄዱበት ርቀት እንግሊዛዊያንን አስደንግጧል። የልጃቸውን የመሐል ስም "ሂትለር" ሲሉ ነው የሰየሙት። አዳም 22 ዓመቱ ሲሆን ክላውዲያ ደግሞ 38 ዓመቷ ነው። የበርሚንግሐም ፍርድ ቤት ትናንት በሰጠው ብይን አባትና እናትን እያንዳንዳቸው በ6 ዓመት ጽኑ እስራት ቀጥቷቸዋል። መኖርያ ቤታቸው በተበረበረበት ጊዜም የናዚ አርማ የሆነው "ስዋስቲካ" በብዛት ተገኝቷል። • ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን? • ኢትዮጵያዊያን ዛምቢያ ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋሉ "በድርጊታችሁ፣ ቤታችሁ በተገኙት ቁሳቁሶችም ሆነ ለልጃችሁ በሰጣችሁት ስያሜ ድርጊታችሁና ማንነታችሁ ጎልቶ ወጥቷል" ብለዋቸዋል የመሐል ዳኛው። ሂትለር የሚል ስም የተሰጠው ብላቴና ወደፊት ምን ሊሰማው እንደሚችል ባይታወቅም ወላጅ እናቱ ልጇን የናዚ ሰላምታ ሳይቀር ታሰለጥነው ነበር ተብሏል። የናዚ አልባሳትና የሕጻናት መጫወቻዎችም ቤት ውስጥ ተገኝተዋል። ይኸው ፍርድ ቤት የአፍቃሪ ናዚ አባል ነበሩ ያላቸውን ሌሎች አባላትን በተመሳሳይ በእስራት የቀጣ ሲሆን ሕገ ወጥ ፓርቲያቸውንም አደገኛ ዓላማን ያነገበ ብሎታል። ከነዚህ ፍቅረኛሞች ጋር ፍርድ ቤት የቆመው ዳንኤል ቦጉዋንቪክ የአፍቃሪ ናዚ ፓርቲን ስትራቴጂና ፕሮፓጋንዳ በማቀናበሩ ተከሶ በተመሳሳይ ስድስት ዓመት ቅጣት ተበይኖበታል። ፍሌቸር የተባለው የፓርቲው አባል እጅግ አክራሪ ሲሉ ዳኛው የገሰጹት ሲሆን ቀጥለውም 6 ዓመት አከናንበውታል። • "ነጭ የለበሰ 'መልአክ' በኦሮምኛ አናገረኝ"- የሬሳ ሳጥን ፈንቅለው የወጡት ግለሰብ የቡድኑ የደኅንነት ጉዳዮች ኃላፊ የተባለው ራይኬ 5 ዓመት ከ10 ወር ተፈርዶበታል። "ናሽናል አክሽን" የተባለው ይህ ሕገ ወጥ ቡድን በጀርመን የሚገኙ ማናቸውም ስደተኞች አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ይፈልጋል። ቡድኑ በ2013 የተመሠረተ ሲሆን በ2016 በአሸባሪ ቡድንነት ተፈርጇል። አውሮፓም በናዚ ዘመን ወደነበረው አስተዳደር እንድትመለስ ይፈልጋል። |
46997794 | https://www.bbc.com/amharic/46997794 | የሂትለር ሥዕሎች ለምን አልተሸጡም? | ለናዚው መሪ አዶልፍ ሂትለር ሥዕል ነፍሱ ነበረች። አለመታደል ኾኖ ግን እርሷ አትወደመውም ነበር። ሂትለር ከአንዴም ሁለት ሦስቴ ከቪየና የሥነ ጥበብ ትምህርት ቤት አመልክቶ "አትመጥንም" በሚል ተባሯል። ይህ ነገር ያበሳጨው ነበር። | ወደ ፖለቲካው መንደር ከመንደርደሩ በፊት በኦስትሪያ ቪየና የጉልበት ሥራ እየሠራ በዚያውም ያሰማመራቸውን ፖስትካርድና የሥዕል ሥራዎቹን በየመንገዱ እያዞረ ይሸጥ ነበር። አንዳንድ ታሪክ ጸሐፊዎች ታዲያ ሰውየውን ጨካኝ ያደረገው ይኸው በሥዕል ለነበረው ፍቅር ዕውቅና የሚሰጠው ማጣቱ እንደሆነ ይገምታሉ። ከሰሞኑ በሂትለር የተሳሉ እንደሆኑ የተነገረላቸው ሦስት ውሃ ቅብ ሥዕሎች ለጨረታ መቅረባቸውን የዓለም መገናኛ ብዙኃን ሲቀባበሉት ነበር። የጀርመን ፖሊስ ግን ከሰዓታት በፊት ነገሩ 'ጭቦ' ሳይሆን አይቀርም፤ ተጠርጣሪዎቹንም በቁጥጥር ለማዋል አስቢያለሁ ብሏል። የመጀመርያው ሥዕል ወንዝ፣ መልከአምድርና ዛፍን የሚያሳይ ሲሆን ሂትለር የለየለት ጨፍጫፊ ከመሆኑ በፊት ሙኒክ ሳለ የሳላቸው እንደሆኑ ሲነገር ነበር። ለጨረታ ሊቀርቡ የነበሩት ሦስት ሥዕሎች በሥዕል ተቺዎች ዘንድ "ፈጠራ የማይታይባቸው፣ ግልብና መናኛ ሥዕሎች" እየተባሉ ሲተቹ ቆይተዋል። ያም ኾኖ ለእያንዳንዱ ሥዕል መነሻ ዋጋ 4ሺህ 500 ዶላር ገደማ ተመድቦ ነበር። በኦንላይን ተጫራቾች ከፍተኛ ዋጋ ሊቀርብባቸው እንደሚችልም ግምት ተሰጥቶ ቆይቷል። ለቢቢሲ ቃል የሰጡት የጀርመን ፖሊስ ቃል አቀባይ ፓትሪሺያ እንዳሉት ከሆነ ግን ሥዕሎቹ ሐሰተኛ ሳይሆኑ አይቀርም። ይኸው ጥቆማ ደርሶን ምርመራ ጀምረናል ብለዋል። እስካሁን ግን በቁጥጥር ሥር ያዋሉት ግለሰብ እንደሌለ ተናግረዋል። ጨረታውን ያሰናዳው ድርጅትም እስካሁንም በጉዳዩ ላይ ትንፍሽ አላላም። ሂትለር ሥልጣን ከጨበጠ በኋላ ለረዳቶቹ ሥዕሎቹን በያሉበት ፈልገው እንዲያቃጥሏቸው ቀጭን ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር። ያም ኾኖ ሁሉንም አግኝቶ ማቃጠል አልተቻለም። ያኔ ከቃጠሎ የተረፉት በግለሰቦች እጅ እንደሚገኙ ይገመታል። በአሜሪካ ጦር ኃይል የተወሰዱም በርካታ ናቸው። አዶልፍ ሂትለር በቀን ቢያንስ ሦስት ሥዕሎችን ይሥል እንደነበር ይገመታል። |
news-50583011 | https://www.bbc.com/amharic/news-50583011 | ኃይል የተቀላቀለበት ወሲብ መፈጸም ''እየተለመደ መጥቷል'' | በፈቃደኝነት ላይ በተመሰረተ የግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ኃይል የመጠቀም ዝንባሌ እየተለመደ መምጣቱን አንድ ጥናት አመላከተ። | በዳሰሳ ጥናቱ ላይ ከተሳተፉ 42 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች፤ በፈቃድ ላይ በተመሰረተ የግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ምቾት የሚነሳ ኃይል የተቀላቀለበት ወሲብ ቢያንስ አንድ ግዜ ፈጽመናል ብለዋል። የጥናቱ ተሳታፊዎች በተለያዩ ወቅቶች በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት በጥፊ መመታት፣ አንገት ታንቆ መያዝ፣ ጨርቅ አፍ ውስጥ መጠቅጠቅ እና ምራቅ እንደተተፋባቸው ገልጸዋል። ይህን መሰል ኃይል የተቀላቀለበት ወሲብ ከፈጸሙ ሴቶች መካከል 20 በመቶ የሚሆኑት ኃይል የተቀላቀለበት ወሲብ መፈጸማቸው ፍርሃት እንዲሰማቸው አድርጓል ወይም ብስጭት ውስጥ ከትቷቸዋል። • ወንዶች፤ የወሊድ መቆጣጠሪያ ክኒና ለመዋጥ ዝግጁ ናችሁ? • የሥራ ቦታ ወሲባዊ ትንኮሳ የቱ ነው? የ23 ዓመቷ ወጣት የሆነችው አና፤ በፍላጎቷ ከሶስት የተለያዩ ወንዶች ጋር በተለያዩ ጊዜያት ወሲብ ስትፈጽም ኃይል የተቀላቀለበት ወሲብ አጋጥሟታል። እርሷ እንደምትለው በወሲብ ወቅት ኃይል መጠቀም የጀመረው ፀጉሯን መጎተት እና በጥፊ በመመታት ነበር። ከወንዶቹ አንዱ አንገቷን በክርኑ አንቋት እንደነበር ትገልጻለች። "በጣም ተደናገጥኩ" የምትለው አና፤ "በከፍተኛ ሁኔታ ምቾት ነሳኝ፤ ፈራሁኝ። አንድ ሰው በመንገድ ላይ አንገትህን ቢያንቅህ ወይም በጥፊ ቢመታህ ወንጀል ነው" ስትል የተፈጠረባትን ስሜት ትገልጻለች። • "ሰውነቴ ወሲብ እንድፈጽም አይፈቅድልኝም'' የብዙ ሴቶች የጤና እክል አና ስለደረሰባት ነገር ከሴት ጓደኞቿ ጋር ስታወራ ነበር ይህ መሰል ተግባር ብዙዎችን እንደሚያጋጥም የተረዳችው። "ሁሉም ወንዶች ቢያንስ አንድ አይነት መልክ ያለው ኃይል የተቀላቀለበት ተግባር ለመፈጸም ይሞክራሉ" ትላለች። አና በወሲብ ወቅት በሚያጋጥማት ኃይል የተቀላቀለበት ተግባር ለቀናት ህመም እንደሚሰማት እና ፊቷ በልዞ የሚቀርበት ሁኔታዎች ተፈጥረው እንደነበረ ታስታውሳለች። "አንዳንድ ሴቶች ኃይል የተቀላቀለበት ወሲብ መፈጸም ሊያስደስታቸው እንደሚችል እገምታለሁ። ችግሩ ግን ወንዶች ሁሉም ሴቶች ሊያስደስታቸው እንደሚችል ማሰባቸው ነው" ትላለች አና። ሳቫንታ ኮምሬስ የተሰኘ አጥኒ ኩባንያ እድሜያቸው ከ18-40 በሆኑ እና በዩናይትድ ኪንግደም በሚኖሩ 2002 ሴቶች ላይ ነው የዳሰሳ ጥናት ያካሄደው። በዳሰሳ ጥናቱ ላይ ከተሳተፉ ሴቶች መካከል 8 በመቶ የሚሆኑት በፈቃደኝነት ላይ በተመሰረተ የግብረ ስጋ ግንኙነት ባደረጉ ቁጥር በወንድ አጋራቸው በጥፊ መመታት፣ መታነቅ፣ ጨርቅ አፋቸው ውስጥ በመጠቅጠቅ እንዲታፈኑ ማድረግ እና መረቅ እንደሚተፋባቸው ተናግረዋል። • ቲማቲም የወንዶችን የዘር ፍሬ ያበረታ ይሆን? 12 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ አብዛኛውን ጊዜ ይህን መሰል ኃይል የተቀላቀለበት ወሲብ እንደሚፈጽሙ የተናገሩ ሲሆን፤ 22 በመቶ የሚሆኑት አልፎ አልፎ ያጋጥመናል ብለዋል። 56 በመቶ በበኩላቸው ይህን መሰል ኃይል የቀላቀለበት ወሲብ ፈጽመው እንደማያውቁ የተናገሩ ሲሆን፤ 2 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ አስተያየታቸውን ከመስጠት ተቆጥበዋል። ሳቫንታ ኮምሬስ በጥናቱ ላይ የተሳተፉት ሴቶች እድሜና የሚኖሩበት አካባቢ መላው ዩናይትድ ኪንግደምን ይወክላል ብሏል። 31 በመቶ የሚሆኑ የጥናቱ ተሳታፊዎች ኃይል የተቀላቀለበት ወሲብ መፈጸም ፈጽሞ እንደማይፈልጉ የተናገሩ ሲሆን፤ 38 በመቶ የሚሆኑት ኃይል የተቀላቀለበት ወሲብ ሁሌም መፈጸም እንደማያስደስታቸው ገልጸዋል። የሴቶች ፍትህ ማዕከል የተሰኘ ተቋም የጥናቱን ውጤት በማስመልከት ለቢቢሲ "ይህ ቁጥር ወጣት ሴቶች ለሚያዋርዷቸው ድርጊቶች ፈቃዳቸውን እንዲሰጡ የሚደረግን ግፊት ያሳያል" ብሏል። በሰላሳዎቹ መጀመሪያ ላይ የምትገኘው ኤማ ለረዥም ዓመታት ከቆየችበት ግንኙነት በቅርቡ ተለያይታለች። "ወሲብ እየፈጸምን ሳለ ያለምንም ማስጠንቀቂያ ያንቀኝ ጀመር። በጣም ነበር የተደናገጥኩትና የፈራሁት። በወቅቱ ምንም ማድረግ አልቻልኩም ነበር፤ ምክንያቱም ይህ ሰው በጉልበት ይበልጠኝ ስለነበር ነው" ኤማ ይህ አይነት ኃይል የተቀላቀለበት ተግባር ልቅ የሆኑ የወሲብ ፊልሞችን ከመመልከት ሊመነጭ እንደሚችል ትገምታለች። ስቴቨን ፖፕ የስነ-አእምሮ ሃኪም ሲሆን ከወሲብ እና ግንኙነት ጋር የህክምና አገልግሎት ለታካሚዎቹ ይሰጣል። "ሰዎች ይህን ኃይል የተቀላቀለበት ተግባር የሚፈጽሙት የተለመደ ነገር እንደሆነ አድርገው ስለሚያስቡ ነው። ይህ ግን በጣሙን ጎጂ ልማድ ነው። የጥንዶችን ግንኙነት ዝቅ ከማድረጉም በላይ በግንኙነት ውስጥ ኃይል ተቀባይነት እንዲኖረው ያደርጋል" ይላል የስነ-አእምሮው ሃኪሙ ስቴቨን። |
news-53578112 | https://www.bbc.com/amharic/news-53578112 | ኮሮናቫይረስ፡ የህሙማን ቁጥር ከሆስፒታሎች አቅም እንዳያልፍ የሰጋችው ከተማ | በሆንክ ኮንግ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር እየናረ ይገኛል። የከተማዋ መሪ ካሪ ላም፤ የህሙማን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ የሆስፒታሎችን አቅም “ሊያንኮታኩት ይችላል” ብለዋል። | በከተማዋ የበሽታው ማሕበረሰባዊ ስርጭት ጫፍ ላይ እየደረሰ መምጣቱን መሪዋ ተናግረዋል። ነዋሪዎች ከቤታቸው እንዳይወጡም አሳስበዋል። የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ግዴታ ሆኗል። ምግብ ቤቶች መስተንግዶ እንዲያቆሙም ማሳሰቢያ ተሰጥቷል። • በሙምባይ በድሃ ሰፈሮች የሚኖሩ ከግማሽ በላይ ነዋሪዎች በኮቪድ ተይዘዋል ኮቪድ-19 መሰራጨት በጀመረባቸው ወራት ሆንክ ኮንግ በሽታውን በመቆጣጠር ረገድ ስኬታማ ነበረች። አሁን ግን በየቀኑ ከ100 በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው እየተነገረ ነው። ከአንድ ወር በፊት በ24 ሰዓት ውስጥ ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሰዎች ከዓሥር በታች ነበሩ። ካሪ ላም ምን አሉ? መሪዋ ካሪ ላም ትላንት በሰጡት መግለጫ፤ የሆንክ ኮንግ ማሕበረሰብ ውስጥ ቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰራጭበት ነጥብ ላይ ደርሷል ብለዋል። ይህም የጤና ሥርዓቱን እንደሚያቃውሰው፣ በተለይም የአረጋውያን ሕይወት እንደሚቀጠፍም ተሰግቷል። መሪዋ ነዋሪዎች አካላዊ ርቀት እንዲጠብቁና በተቻለው መጠን ከቤት እንዳይወጡ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። ካሪ ላም መግለጫ ከመስጠታቸው ቀደም ብሎ ሆንግ ኮንግ ውስጥ በ24 ሰዓት 106 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። በአንድ ቀን 23 ሰዎችም ሞተዋል። ምን ውሳኔ ተላለፈ? ከዛሬ ጀምሮ ምግብ ቤቶች መስተንግዶ እንዳይሰጡ ታግደዋል። በተጨማሪም ከአንድ ቤተሰብ ውጪ የሆኑ ሰዎች ሲገናኙ፤ ቁጥራቸው ከሁለት መብለጥ የለበትም። በዚህ ወር መባቻ ላይ እስከ 50 ሰዎች መሰብሰብ ይችሉ ነበር። ከዛም ቁጥሩ ወደ አራት አሁን ደግሞ ወደ ሁለት ተቀንሷል። • የጀርመን ባለስልጣናት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መባባስ "በጣም አሳስቧቸዋል" ሕዝብ በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ ግዴታ ነው። መጠጥ ቤቶች፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዘውተሪያዎችና የውበት ሳሎኖችም ይዘጋሉ ተብሏል። ሆንክ ኮንግ እስከዛሬ ከወሰደቻቸው እርምጃዎች የአሁኑ ጥብቁ ነው። ሆንክ ኮንግ ቫይረሱን መቆጣጠር ችላ ነበር? ቫይረሱ መሰራጨት በጀመረበት ወቅት ሆንክ ኮንግ በሽታውን መቆጣጠር ችላ ነበር። ወደ ቻይና ከተሞች የሚካሄዱ ጉዞች ተቀንሰው፣ በበሽታው ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸው በፍጥነት የሚለዩበት አሠራር ተዘርግቶ ነበር። ከተማዋ ውስጥ በኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው ሳይገኝ ሳምንታት ያለፉበት ወርም ነበር። ነገር ግን ሰዎች ወደ ቀደሞው አኗኗራቸው መመለስ ሲጀምሩ፤ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ጨመረ። • ለ3 ቢሊዮን እንስሳት" መጥፋት" ምክንያት የሆነው የአውስትራሊያ ሰደድ እሳት በየቀኑ በቫይረሱ የተያዙ ከዓሥር በታች ሰዎች ሪፖርት ሲደረግ ቢቆይም አሁን ግን ቁጥሩ 120 ደርሷል። በሆንክ ኮንግ ዩኒቨርስቲ የሚሠሩ ፕ/ር ጂን ዶንግያን እንዳሉት፤ ድንበር አካባቢ ተገቢው ቁጥጥር አለመደረጉ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል። “ቫይረሱን በማሕበረሰቡ ውስጥ እያሰራጩ የሚገኙት በበሽታው ተይዘው ወደ ሆንክ ኮንግ የገቡ የሌሎች አገራት ዜጎች ሊሆኑ የይችላሉ” ብለዋል። የቫይረሱ ስርጭት መባባስ ሆንክ ኮንግን እንደሚጎዳት ሳይንቲስቶች ተናግረዋል። ቫይረሱ ቢያንስ ለ22 ቀናት ሳይስፋፋ ቆይቶ እንደነበረ በመጥቀስ፤ ቫይረሱ ከሰዎች ጋር እንደተላመደና ይህም በቀላሉ እንዲሰራጭ እንደሚያደርገው ተናግረዋል። ምርጫ ይካሄዳል? አዲሶቹ የኮሮናቫይረስ መከላከያ የጥንቃቄ እርምጃዎች የተወሰዱት የሆንክ ኮንግ ምክር ቤት ምርጫ በአንድ ዓመት በተገፋበት ወቅት ነው። የሆንክ ኮንግ መገናኛ ብዙኃን እንደሚሉት፤ መንግሥት በከሮናቫይረስ ስጋት ምክንያት ገና ውሳኔውን በይፋ አልገለጸም። ምርጫ ይካሄዳል ተብሎ የነበረው መስከረም 6 ነበር። ተቃዋሚዎች በበኩላቸው፤ ምርጫው የተራዘመው አዲሱን የብሔራዊ ደህንነት ሕግ በተመለከተ የተነሳውን ቁጣ ለማርገብ ነው ይላሉ። |
news-53089292 | https://www.bbc.com/amharic/news-53089292 | የዘር ጥላቻን የሚያራግቡ የፌስቡክ ጓደኞቻችንን ምን እናድርጋቸው? | ሁላችንም ቢያንስ አንድ የሆነ ጽንፈኛና የዘር ጥላቻን የሚያራግብ የፌስቡክ ጓደኛ ይኖረናል። የሚጽፋቸው ነገሮች የሚያቆስሉ፣ የሚሰጣቸው አስተያየቶች የሚያበግኑ። | ቼሪ ዊልሰን ይህን ሰው እንምከረው ወይስ "እንቦልከው"? እኔን አሁን መከራ እያበላኝ ያለ አንድ አብሮ አደጌ አለ። የፌስ ቡክ ጓደኛዬ ነው። በዘር ጥላቻ የተለከፈ ነው። የእርሱን የፌስቡክ ሰሌዳ ጭራሽ ባላየው ደስ ይለኛል። ቶሎ ቶሎ ገረፍ አድርጌ ለማለፍ እሞክራለሁ። ይህ ሰው አሁን የጆርጅ ፍሎይድን ሞት ተከትሎ ዘረኝነቱ ብሶበታል። ብዙ ሰዎች ስለእርሱ ስነግራቸው "አንቺ ደግሞ ቀለል አድርጊው እስኪ፤ አታካብጂ" ይሉኛል። ለምን ቀላል ነገር አድርገው እንደሚያስቡት አይገባኝም። ለእኔ እጅግ ዘረኛ አስተያየቶችን ከፌስቡክ ጓደኞቼ ሰሌዳ ላይ ስመለከት የሆነ የማቅለሽለሽ ስሜት አለው። ከፌስቡክ ውጪም እንዲሁ ነው። ሰዎች በተለያየ መንገድ ነው ዘረኝነታቸውን የሚያንጸባርቁት፤ አውቀውም ሆነ ሳያውቁት። ለምሳሌ እዚህ እንግሊዝ ውስጥ ብዙ ሰዎችን ስተዋወቅ "የእኔ ቆንጆ ከየት ነሽ?" ይሉኛል፤ ልክ እንደ ብርቅዬ እንሰሳ እየተመለከቱኝ። "ከዚሁ ከእንግሊዝ" እላቸዋለሁ። "ማለቴ የምር ከየት ነሽ. . . ?" ይሉኛል። በሌላ ቋንቋ (የቆዳ ቀለምሽን አይተሽዋል? ፈረንጅ አይደለሽም እኮ፤ ይህ የፈረንጅ አገር ነው።) እያሉኝ ነው። ይህ ዓይነቱ አስተያየት እኔና እህቴ ድሮ ወደ አንደንዳንድ የለንደን ቡና ቤቶች መሄድ ለምን እንፈራ እንደነበር ያስታውሰኛል። ቡና ቤቶቹ ውስጥ ለመስተናገድ ስንገባ "የእኛ ደንበኞች እኮ በብዛት የአውሮፓ ጎብኚዎች ናቸው" ይሉናል። ምን ማለታቸው ነው? (ጥቁሮች እባካችሁ አትምጡብን እያሉን ነው) ሌላው ግርም የሚሉኝ ጸጉሬን የሚነካኩ ሰዎች ናቸው። እኔምለው? የሆነች የቤት ውስጥ ድመት ነው እንዴ የምመስላቸው? ዘረኝነት አንድን ጥቁር "አንተ ኔግሮ!" ብሎ መጥራት ብቻ የሚመስላቸው አሉ። ዘረኝነት እጅግ ውስብስብና ጥልቅ ጉዳይ መሆኑን ለምን አይረዱም? አሁን እዚህ ፌስቡኬ ላይ እየመጣ ዘረኛ አስተያየት የሚሰጠውን ጓደኛዬን ምን እንደማደርገው ግራ ገብቶኛል። ለእርሱ ዝቃጭ አስተያየት መልስ መስጠት በራሱ ጉልበትን መጨረስ ሆኖ ይሰማኛል። ግን ደግሞ እንዲህ ሲንዘባዘብ ዝም ማለትም አግባብ መስሎ አልተሰማኝም። ዝም ሲባል ትክክል የሆነ ቢመስለውስ? በመጨረሻ አንድ ነገር ለማድረግ ወሰንኩ። ከዚያ በፊት ግን አሁን የምፈልገው "አንፍሬንድ" የሚለውን ቁልፍ ልጫን ነው ወይስ ምላሽ ልስጠው? በሚል ከእራሴ ጋር ተሟገትኩ። የማኅበራዊ ሥነልቦና አዋቂ ዶክተር ኬዎን ዌስት እንዲህ ዓይነት ውሳኔዎች ግለሰቡ ምን ማሳካት ነው የፈለገው በሚለው ላይ የሚወሰኑ ነው የሚሆነው ይላል ለዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ምክሩን ሲለግስ። "ጤናሽን መጠበቅ ከፈለግሽ ለእንዲህ ዓይነት የፌስቡክ ጓደኞችሽ ባትመልሺ ይመረጣል። ለእነርሱ ምላሽ ብትሰጪ ጨጓራሽን ይበልጥ ይልጡታል።" ". . .ነገር ግን ዓላማሽ ነገሮችን ቀስበቀስ እንዲረዱና ባንቺ ጫማ ውስጥ ሆነው ሁኔታዎችን እንዲያገናዝቡ ከሆነ፤ መልስ መስጠቱ ክፋት የለውም።" ". . . እርግጥ ነው እንደነዚህ ዓይነት ዘረኞች ባንቺ አስተያየት ዘረኝነታቸውን እርግፍ አድርገው ይተዋሉ ማለት አይደለም። ነገር ግን መባል ያለበትንና መባል የሌለበትን ነገር እያወቁ እንዲመጡ ምክንያት ትሆኛቸዋለሽ።" ይህ የዶክተር ኬዎን ምክር ልክ ሊሆን ይችላል። እኔ ፌስቡክ ላይ አስተያየት ስሰጥ ሁልጊዜም "ጀመረሽ ደግሞ ይቺን የዘር ጨዋታ ልታመጫት ነው?" ይሉኛል። ሌሎች ጓደኞቼን በነገሩ እንዲያማክሩኝ ጠየቅኳቸው። "ኧረ ለመሆኑ ምንድነው የምታደርጉት? ዘረኛ ሰው ፌስቡክ ላይ ሲገጥማችሁ? አልኳቸው።" አንዷ ጓደኛዬ አሊሻ ስታንዲንግ 27 ዓመቷ ነው። አሊሻ "ለዘረኛ አስተያየቶች ምላሽ መስጠት ጀመሬ ነበር። የሚገርምሽ እየባሰባቸው ሄደ" አለችኝ። ቀጠለች፣ "ለምሳሌ ልንገርሽ። 'ብላክ ላይቭስ ማተር' በሚለው እንቅስቃሴ ዙርያ አስተያየት ለጥፌ አንዱ ምን ቢለኝ ጥሩ ነው? 'አንቺ ለዚህ አስተያየትሽ መደፈር ነበረብሽ' አለኝ። ከዚያ በኋላ ነው ሰዎችን "መደለትና መቦለክ" የጀመርኩት። ነገሩ መጀመርያ አካባቢ ያስፈራኝ ነበር። ኋላ ላይ ግን እየለመድኩት መጣሁ።" አሊሻ ይህን ታድርግ እንጂ ለሰዎች ምላሽ መስጠት አንዳንድ ጊዜ ነገሩን ደጋግመው እንዲያስቡት እንደሚያደርጋቸው ነግራኛለች። "ለምሳሌ እንደዚያ የሰደበኝ ቀን ከምቦልከው ጠንካራ ምላሽ ብመልስለት ወደቤቱ ሲመለስ ቢያንስ ነገሩ እየከነከነው ይሄድ ነበር" ብላ ተቆጭታለች። ካሲያ ዊሊያምስ ሌላኛዋ ወዳጄ ናት። ካሲያ ባሏ ዘረኝነት ብዙ ጊዜ ያጋጥመዋል። ይህን ስለምታውቅ ፌስቡክ ላይ ማንኛውም ዘረኛ ሰው ሲያጋጥማት በቻለችው ሁሉ ትፋለማቸዋለች። "ቸል ልላቸው አልችልም፤ ብዙ ሰዎች ምላሽ ከሰጠኋቸው በኋላ አመስግነውኛል። ነገር ግን ሁሉም ሰዎች እንደዚያ ናቸው ማለት አይቻልም። አንዳንዶች ምላሽ ስትሰጫቸው የሚሆኑትን ነገር ስታይ ጊዜሽን ማጥፋትሽ ያናድድሻል።" ዶ/ር ዌስት በዚህ ረገድ ምክር አላቸው። "ለአንድ ሰው ለዘረኛ አመለካከት ምላሽ ሲሰጥ ያንኑ ምሽት ዘረኝነታቸውን እርግፍ አድርገው እንዲተዉ ከጠበቃችሁ ሞኞች ናችሁ። በኢንተርኔት አንድ ሁለት ስለተባባላችሁ የሚለወጥ ነገር የለም። ነገር ግን ከዚያ በኋላ የሆኑ ሰዎች እነርሱ በሚጽፏቸው ነገሮች ስሜታቸው እንደሚጎዳ ማሰብ ይጀምራሉ።" ማቲው ኮሊንስ ደግሞ "ዘረኝነት በእኛ ይብቃ!" ወይም "ኖትሄት" የተባለ የጸረ ዘረኝነት ተቋም መሪ ነው። ዘረኝነት ከፍርሃትና ከግንዛቤ ማነስ የሚመነጭ ነገር ነው ይላል። ለምሳሌ ዘረኞች የብላክ ላይቨስ ማተርን እንቅስቃሴ ሲመለከቱ 'እኔ የሌለኝን ነገር እነርሱ እንዴት ይኖራቸዋል?' በሚል ነው መተናኮስ የሚጀምሩት። እንደዚህ አይነት እንቅስቃሴዎች እነርሱን የሚያጠፋቸው ስለሚመስላቸው ይፈራሉ ይላል። ማቲው እንደሚለው ማኅበረሰቡ ጠንካራ አመራር ይሻል። የእነዚህን ሰዎች ፍርሃት ሊገፍላቸው የሚችል ከእነርሱ ከእራሳቸው የወጣ ብዙ አመራር ቢኖር ነገሩ ጥሩ መልክ እየያዘ ይመጣ ነበር። "የጥቁር መብት ላይ ስንሰራ በርካታ ተቃውሞ እንደሚመጣብን መረዳት አለብን። የሚለው ማቲው እንቅስቃሴው ለብዙዎች የፍርሃት ምንጭ ነው። ዘረኛ ነጮች የሚያስቡት እንዲህ ዓይነት እንቅስቃሴዎች በተፋፋሙ ቁጥር ከእነርሱ ድርሻ የሆነ ነገር እየተወሰደባቸው እንደሆነ ነው" ሲል ያብራራል። ይህን ሁሉ ሐሳብ ተቀብዬ፣ አሰላስዬ አውጥቼና አውርጄ ወደ ፌስቡኬ አመራሁ። አሁንም ያ ዘረኛ ጓደኛው ጸያፍ ነገር ጽፏል። በአንድ ጥቁር ጓደኛዬ የፌስቡክ ጽሑፍ ሥር በጥቁሮች ላይ ለማላገጥ የሞከረውን ነገርም ተመለከትኩ። ልቤ ደከመብኝ። ተሰላቸሁ፤ ከዚህ ሁሉ ለምን አልገላገልም አልኩ። ያቺን ቁልፍ ተጫንኳት፡፡ "Unfriend!" ከጓደኝነት አሰናበትኩት። [የዚህ ጽሑፍ አሰናጅ ቼሪ ዊልሰን ናት። በሼፊልድ ጋዜጠኝነት አጥንታለች። ከቤተሰቧ ወደ ዩኒቨርስቲ በመግባት የመጀመርያዋ ናት።] |
news-52962757 | https://www.bbc.com/amharic/news-52962757 | በኢንዶኔዢያዋ የውሃ ጉድጓድ ውስጥ ወድቆ ስድስት ቀናት የቆየው ኢንግሊዛዊ በህይወት ተገኘ | በኢንዶኔዢያዋ ባሊ ደሴት የውሃ ጉድጓድ ውስጥ ወድቆ ለስድስት ቀናት የቆየው እንግሊዛዊ በስተመጨረሻ ሕይወቱን ማትረፍ ተችሏል። | ጄኮብ ከጉድጓዱ ሲወጣ የ29 ዓመቱ ጄኮብ ሮበርትስ በፔካቱ መንደር ውሻ ሲያሯሩጠው ለማምለጥ ሲሞክር ነው አራት ሜትር በሚጠልቀው ጉድጓድ ውስጥ የወደቀው። ከአደጋው በኋላ እግሩ እንደተሰበረ የአካባቢው ባለስልጣናት ገልጸዋል። ምንም እንኳን ጉድጓዱ ውሃ ባይኖርበትም እግሩ በመሰበሩ ምክንያት መውጣት ሳይችል ቆይቷል። በአካባቢው የነበሩ የአይን እማኞች እንደገለጹት በጉድጓዱ ውስጥ ትንሽ ውሃ በመኖሩ ለስድስቱ ቀናት የሚጠጣውን ማግኘት ችሏል። ጄኮብ ሮበርትስ ለስድስት ቀናት ያለመታከት የድረሱልኝ ጥሪውን ሲያሰማ ነበር። በመጨረሻም አንድ የአካባቢው ነዋሪ ድምጹን በመስማቱ ሕይወቱ ልትተርፍ ችላለች። እምብዛም ሰዎች በማይኖሩበት አካባቢ በሚገኘው የውሃ ጉድጓድ አቅራቢያ ከብቶቹን ሲጠብቅ የነበረው ግለሰብ ሁኔታውን ከተመለከተ በኋላ ወዲያው የአካባቢው ኃላፊዎችን ጠርቷል። ጃኮብ በግለሰቡ የተገኘው ባሳለፍነው ቅዳሜ ሲሆን ወዲያውኑ ከጉድጓዱ ወጥቶ ህክምና እንዲያገኝ ተደርጓል። ደሴቲቱ ውስጥ የምትገኘው የፔካቱ መንደር እንደ ጄኮብ ያሉ በርካታ ጎብኚዎች የሚያዘወትሯት ሲሆን እንዲህ አይነት አደጋ እምብዛም የተለመደ አይደለም ተብሏል። |
news-56729025 | https://www.bbc.com/amharic/news-56729025 | በነቀምት ሆቴል ላይ በተወረወረ ቦምብ የሰው ህይወት ሲጠፋ፣ አስር ሰዎች ቆሰሉ | በምዕራብ ኦሮሚያ በምትገኘው የነቀምት ከተማ ሚያዝያ 2/2013 ዓ.ም በአንድ ሆቴል ላይ በተወረወረ የእጅ ቦምብ የአንዲት ግለሰብ ህይወት ሲጠፋ አስር ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተነገረ። | ቦምቡ የተወረወረው ሆቴሉ ውስጥ በነበሩ የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ላይ መሆኑም ተገልጿል። የኦሮሚያ ልዩ ኃይል የነቀምት ሬጅመንት አዛዥ ኮማንደር ግርማ አብዲሳ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል አራቱ የፀጥታ ኃይል አባላት ሲሆኑ የተቀሩት ስድስቱ ደግሞ ሲቪሎች ናቸው ብለዋል። ኮማንደሩ እንደሚያስረዱት ጥቃቱ የተፈፀመው ሚያዝያ 2 ቀን ቅዳሜ ምሽት በአንድ ግለሰብ ንብረት በሆነ ሆቴል ላይ ነው። "የፀጥታ ኃይሎች ሲቪል ለብሰው እንደ ማንኛውም ተጠቃሚ በሆቴሉ ውስጥ እየተገለገሉ ነበር። በአጠቃላይ አስር ሰው ነው የተጎዳው፤ ከነዚህም መካከል አራቱ የኦሮሚያ ፖሊስና ልዩ ኃይል አባላት ናቸው" ብለዋል። በጥቃቱ ህይወቷ ያለፈው በሆቴሉ ውስጥ የነበረች ሲቪል ሴት መሆኗን ኃላፊው ገልፈዋል። ይህንን ጥቃት ስለፈፀመው አካል በተመለከተም ኮማንደር አብዲሳ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ናቸው ሲሉ ለቢቢሲ አስረድተዋል። "ሌላ የሚጠረጠር አካል የለም። በአሁኑ ወቅት የኦሮሞ ሕዝብ ጠላት ኦነግ-ሸኔ ነው። ይህንን በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ። ከዚህ ቀደምም ቦምብ እየወረወሩ፣ መሳሪያ እየተኮሱ ሰዎች ሲገድሉ የከረሙት ኦነግ ሸኔዎች ናቸው።" ኮማንደሩ ከሰሞኑ ጥቃቶች ጋብ ብለው የነበሩ ቢሆንም አሁን ግን እየተባባሰ መሆኑን ጠቁመዋል። "ኦነግ-ሸኔ የሚያደርሰው ጥቃት ትንሽ ጋብ ብሎ ነበር። አሁን ደግሞ እንደ አዲስ እየተነሳባቸው ነው" ብወለዋል። ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ በጸጥታ ኃይሎች በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉም አመልክተዋል። "ከቅዳሜ ምሽት ጀምረን ብዙ ሰዎች በቁጥጥር ስር አውለናል። ተይዘው የተለቀቁ ሰዎች አሉ። አሁንም የምንፈልጋቸው ሰዎች አሉ" ብለዋል። በሆቴሉ ላይ በተፈጸመው ጥቃት በሰው ላይ ከሰደሰው ሞትና የመቁሰል አደጋ በተጨማሪ በንብረትም ላይ ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። መንግሥትና የጸጥታ አካላት በምዕራብ ኦሮሚያ ለሚፈፈሙ ጥቃቶች ተጠያቂ የሚያደርጉት ኦነግ-ሸኔ እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራ ቡድን ሲሆን በአካባቢው በተደጋጋሚ በሠላማዊ ሰዎች ላይ ከሚፈጸሙ ጥቃቶች ጋር ስሙ ይነሳል። በቅርቡም በምዕራብ ወለጋ ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች በቡድኑ ተፈጸሙ በተባሉ ጥቃቶች በርካታ ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል። |
52477586 | https://www.bbc.com/amharic/52477586 | ኮሮናቫይረስ: “ለሴቶች ተብለው የተሠሩ የሀኪም መገልገያዎች እንፈልጋለን” | የህክምና ባለሙያዎች የሚጠቀሙባቸው እንደ ጓንት፣ ገዋን፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ያለ መሣሪያ (ፐርሰናል ፕሮቴክቲቭ ኢክዊፕመንት ወይም ፒፒኢ) ለሴቶች እንዲሆን ተደርጎ የማይሠራበት ጊዜ አለ የሚል ቅሬታ እየተሰማ ነው። | ከሦስት ዓመት በፊት የተሠራ ጥናት አብዛኞቹ በአውሮፓና በአሜሪካ ጥቅም ላይ የሚውሉ የሀኪሞች መገልገያዎች ወንድን ታሳቢ አድርገው እንደሚመረቱ ያሳያል እነዚህ ቁሳ ቁሶች ሀኪሞች ራሳቸውን ከኮቪድ-19 እንዲከላከሉ ይረዳሉ። የዩናይትድ ኪንግደም የጤና ክፍል በበኩሉ መሣሪያዎቹ ለወንዶችም ለሴቶችም ምቹ በሆነ መንገድ ነው የሚሠሩት ብለዋል። ሆኖም ግን የህክምና ባለሙያዎች እንደሚሉት፤ በስፋት አነስተኛ የሚባሉትን የሀኪም መገልገያዎች ሳይቀር ሴቶች ሊጠቀሙባቸው አልቻሉም። በዩኬ 77 በመቶ የሚሆኑት የህክምና ባለሙያዎች ሴቶች ናቸው። ሀኪሞች ራሳቸውን ለመከላከል የሚጠቀሙባቸው ቁሳ ቁሶች ከሚፈለገው ስፋት በላይ ሲኖራቸው ተገቢውን አገልግሎት መስጠት አይችሉም። የአገሪቱ የጤና ክፍል ባወጣው መግለጫ እነዚህ መገልገያዎች ሴቶችም ወንዶችም እንዲጠቀሙባቸው ታስበው ስለተዘጋጁ በተለያየ መጠን ይገኛሉ ብሏል። የሮያል ኮሌጅ ኦፍ ነርሲንግ በበኩሉ፤ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎች ለነርሶች ምቹ አይደሉም ብለዋል። አንዳንድ ሴት ሀኪሞች ፎቷቸውን ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በመለጠፍ፤ መገልገያዎቹ ምቹ እንዳልሆኑ ሲናገሩ ነበር። የስታንፎርድ ዩኒቨርስቲዋ ዶ/ር አርጋቫን ሴልስ “ኤን-95 ማስኮች ያሉት በሁለት መጠን ብቻ መሆኑ ያስገርማል” ይላሉ። ሌሎች መገልገያዎች ያለ አማራጭ፣ በሁለት መጠን ብቻ እንደማይቀርቡም ይናገራሉ። አንዲት የሥራ ባልደረባቸው ለሷ ፊት የሚሆን ጭንብል ስላላገኘች ወደ ቤት የተመለሰችበት ቀን እንደነበርም ያስታውሳሉ። አነስተኛ የሚባሉት ጓንቶችና መነጽሮችም ከመጠን በላይ ትልቅ እንደሆኑ በመጥቀስ “እጄ 6 ኢንች ቢሆንም 6.5 ኢንች ጓንት ነው የማደርገው” ይላሉ። ‘ኢንቪዝብል ውሜን’ ወይም የማይታዩ ሴቶች የተሰኘ መጽሐፍ ያሳተመችው ካሮላይን ክሪዶፔሬዝ፤ አብዛኞቹ የሀኪም መገልገያዎች ወንዶችን ታሳቢ በማድረግ ነው የተሠሩት ትላለች። “ትንሽ ሲባል ለወንድ የሚሆን በትንሽ መጠን የተሠራ ለማለት እንጂ ለሴት የሚሆን ትንሽ መጠን ያለው መገልገያ አይደለም” ስትል ታስረዳለች። የህክምና ባለሙያዎች ባጠቃላይ መገልገያ ለማግኘት በተቸገሩበት በዚህ ወቅት ሴት ሀኪሞች ደግሞ ተጨማሪ ፈተና ገጥሟቸዋል። የሴቶች እኩልነት ፓርቲ ነገሩ “እጅግ አሳፋሪ ነው” ሲል በትዊተር ገጹ አስፍሯል። ከሦስት ዓመት በፊት የተሠራ ጥናት አብዛኞቹ በአውሮፓና በአሜሪካ ጥቅም ላይ የሚውሉ የሀኪሞች መገልገያዎች ወንድን ታሳቢ አድርገው እንደሚመረቱ ያሳያል። |
news-52089669 | https://www.bbc.com/amharic/news-52089669 | ዓለም በወረርሽኝ በተጨነቀበት ጊዜ ሰሜን ኮሪያ የሚሳኤል ሙከራዋን ቀጥላለች | ሰሜን ኮሪያ "ግዙፍ" የተባለ ሮኬት ማስወንጨፊያ መሞከሯን ተከትሎ ዓለም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በተጨነቀችበት ጊዜ የጦር መሳሪያ ሙከራ ማድረግ "ተገቢ አይደለም" ስትል ደቡብ ኮሪያ አወገዘች። | ትናንት እሁድ ደቡብ ኮሪያ እንዳለችው ሰሜን ኮሪያ ሁለት የአጭር ርቀት ሚሳኤሎችን አስወንጭፋለች፤ ይህም በዚህ ወር ውስጥ እያደረገቻቸው ካሉት ሙከራዎች አንዱ ነው ተብሏል። ሰሜን ኮሪያ የኮሮናቫይረስ የዓለም ጭንቀት በሆነበት ወራት ውስጥ የሚሳኤል ሙከራዋን የቀጠለች ሲሆን ወረርሽኙ ከድርጊቷ እንድትቆጠብ አላደረጋትም ተብሏል። እስካሁን ድረስ ሰሜን ኮሪያ ምንም አይነት የኮሮናቫይረስ ክስተት ሪፖርት ያላደረገች ቢሆንም፤ ባለሙያዎች ግን ጥርጣሬያቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። የሰሜን ኮሪያ የአጭር ርቀት ተወንጫፊ የሚሳኤል ሙከራ ተደረገው ከአገሪቱ ምሥራቃዊ ከተማ ዎንሳን ሲሆን፤ አረሮቹ ባሕር ላይ ከመውደቃቸው በፊት በ50 ኪሎ ሜትር ከፍታ 410 ኪሎ ሜትሮችን መጓዛቸውን የደቡብ ኮሪያ ጦር ሠራዊት ገልጿል። ዛሬ የሰሜን ኮሪያ የመንግሥት መገናኛ ብዙኀን ተቋም አገሪቱ "ግዙፍ" ያለውን ሚሳኤሎች በማስወንጨፍ የተሳካ ሙከራ ማድረጓን ዘግቧል። ነገር ግን የሰሜን ኮሪያ መንግሥት ሙከራውን ከማሳወቁ በፊት ደቡብ ኮሪያ ድርጊቱን ጠንከር ባሉ ቃላት አውግዛው ነበር። "ዓለም በኮቪድ-19 ወረርሸኝ ምክንያት ከባድ ችግር ውስጥ በገባበት ሁኔታ ውስጥ የሰሜን ኮሪያ ወታደራዊ ድርጊት በጣሙን ተገቢ ያልሆነና በአስቸኳይ መቆም ያለበት ነው" ሲል የደቡብ ኮሪያ ጦር ኃይል አውግዞታል። አሁን ሰሜን ኮሪያ ያደረገችው ሚሳኤል የማስወንጨፍ ሙከራ በዚህ ወር ብቻ በአራት ዙሮች ውስጥ ከተተኮሱት ስምንተኛውና ዘጠነኛው መሆናቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። ይህም እስካሁን በሰሜን ኮሪያ በአንድ ወር ውስጥ ከተተኮሱት ሚሳኤሎች ከፍተኛው የተመዘገበበት መሆኑን ተንታኞች ተናግረዋል። |
news-53373057 | https://www.bbc.com/amharic/news-53373057 | የማሊ ተቃዋሚ ሰልፈኞች የአገሪቱን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ወረሩ | ማሊ ውስጥ ተቃዋሚ ሰልፈኞች ዋና ከተማዋ ባማኮ የሚገኘውን ብሔራዊውን የቴሌቪዥን ጣቢያ ተቆጣጠሩ። | ፖሊስ ሰልፈኞቹን ለመበተን ጥይትና አስለቃሽ ጭስ ተኩሷል። አብዛኛዎቹ ተቃዋሚዎች ወደ ብሔራዊው ምክር ቤት ጥሰው ለመግባት ሲሞክሩ ታይተዋል። ሰልፈኞቹ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ቦባካር ኬይታ ከሥልጣን ይወረዱ ብለው አመፅ ሲጠሩ ይህ በአንድ ወር ውስጥ ለሦስተኛ ጊዜ ነው። ተቃዋማዊች፤ የኬይታ መንግሥት እስላማዊ ታጣቂዎችን ማስወገድ አልቻለም፣ የምጣኔ ሃብት ቀውሱን አልፈታም እንዲሁም የምክር ቤት ምርጫው ተጭበርብሯል ሲሉ ይወቅሳሉ። ወግ አጥባቂው ኢማም፤ ማሓሜድ ዲኮ የሚመሩት አዲስ ተቀናቃኝ ፓርቲ በዚህ ሳምንት 'ኬይታ ከሥልጣን ይውረዱ የሚለውን ጥያቄዬን አንስቻለሁ' ሲል ተደምጧል። ቢሆንም በአገሪቱ አሁንም በርካታ ለውጦች ያስፈልጋሉ ይላል ፓርቲው። የፕሬዝዳንት ኬይታ አስተዳደር ከአዲሱ ፓርቲ ጋር ተጣምሮ የቅንጅት መንግሥት ለመመሥት ያቀረበውን ጥያቄ የኢማሙ ፓርቲ አልቀበልም ብሏል። በሺህዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚ ሰልፈኞች የባማኮን መንገዶች ዘግተው የፕሬዝደንት ኬይታ መንግሥት ሥልጣን ይልቀቅ የሚለውን ጥያቄያቸውን በማሰማት ላይ ይገኛሉ። ከእነዚህ ሰልፈኞች መካከል ነው የተወሰኑት ወደ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያው [ኦአርቲኤም] በኃይል ዘልቀው የገቡት። በዚህም ጣቢያው ለተወሰነ ጊዜ ሥርጭቱን ለማቋረጥ ተገዶ ነበር። የተወሰኑ ወጣቶች ንበረት ማውደማቸውም ተዘግቧል። ሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው ወደ ብሔራዊ ምክር ቤት ለመግባት ከሞከሩ ተቃዋሚ ሰልፈኞች መካከል ቢያንስ አንድ ሰው ተገድሏል። ማሊ ውስጥ ተቃውሞዎች መሰማት የጀመሩት መጋቢት ወር ላይ ሊካሄድ ዕቅድ ተይዞለት ከነበረው የምክር ቤት ምርጫ ውጤት ይዞ ከመጣው መዘዝ በኋላ ነው። ዋነኛው ተቃዋሚ ፓርቲ ፕሬዝዳንቱ ከሥልጣን ባይወርዱ እንኳ ለውጥ እስኪመጣ ድረስ ተቃውሟችሁን አሰሙ ሲል ለደጋፊዎቹ ጥሪ አቅርቧል። ፕሬዝዳንት ኬይታ ከሁለት ዓመት በፊት ነበር ለሁለተኛ ጊዜ አገሪቱን ለአምስት ዓመት ለማስተዳደር የተመረጡት። ነገር ግን በአገሪቱ የጂሃዲስት ኃይሎች ጥቃት እየበረከተ መምጣቱ እና የምጣኔ ሃብት ቀውስ መሰከቱን ተከትሎ ተቃውሞዎች እየበረቱባቸው ነው። በአሁኑ ጊዜ ጂሃዲስት ኃይሎች በማዕከላዊና ሰሜን ማሊ ጥቃት እያደረሱ ነው። ታጣቂዎቹ ይህን ተቃውሞ ተጠቅመው በአገሪቱ ብጥብጥ እንዲስፋፋ ሊያደርጉ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ። |
news-56529611 | https://www.bbc.com/amharic/news-56529611 | ቴክኖሎጂ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ዘልቆ ፊታችንን እያየ ነው | በፊት ገጽታ የሚከፈት ስልክ የያዙ ሰዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አድርጎ ስልክ መክፈት እንደማይሞከር ያውቁታል። | ምንም እንኳ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጨርቆች 'ፌሻል ሪኮግኒሽን' [የፊት ቅርፅን አይቶ ማንነት የሚለይ] ቴክኖሎጂን ቢፈታተኑትም አልቻሉትም። ይህ ጉዳይ ባዕድ ሊመስል ይችላል ግን ቴክኖሎጂ በኮቪድ-19 ምክንያት ፊታችንን ላይ የምናደርገውን መሸፈኛ ዘልቀው እየለየን ነው። የዓለም ሕዝብ ሳይወድ በግዱ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማጥለቅ የጀመረው በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ነው። ይሄኔ ነው የፌሻል ሪኮኒሽን ነቃፊዎች የደስታ ድምጻቸውን ያሰሙት፤ የቴክኖሎጂው ሰዎች ደግሞ በሐዘን አንገታቸውን የደፉት። የፊትን ገጽታና ቅርጽ አጥንቶ ማንነት የሚለየው ቴክኖሎጂ ማንነትን ለመለየት ሙሉ ፊትን ማየት ይፈልጋል። አንድ ተቋም 89 ለሕዝብ ጥቅም የሚውሉ ፌሻል ሪኮግኒሽን ቴክኖሎጂዎችን ተጠቅም ከ5 እስከ 50 በመቶ ስህተት አግኝቶ ነበር። ጥናቱ የተካሄደው በኮምፒውተር የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ የተደረገላቸው ፎቶዎችን በመጠቀም ነው። ነገር ግን አንዳንድ የፊት መለያ ቴክኖሎጂዎች አሁንም መሸፈኛውን ዘልቀው የሰዎችን ማንነት መለየት እየቻሉ ነው። ባለፈው ጥር የአሜሪካ መንግሥት የአገር ውስጥ ደኅንነት መሥሪያ ቤት አንድ 96 በመቶ ስኬታማነት ያለው ቴክኖሎጂ አግንኝቷል። መሥሪያ ቤቱ ባገኘሁት ጥናት መሠረት ፎቶ ተጠቅመው ሰዎች መሸፈኛ ቢያደርጉም ማንነትን መለየት እያቻሉ ነው ብሏል። የደኅንነት መሥሪያ ቤቱ ሰዎች መሸፈኛቸውን አድርገው ራሳቸውን ከኮቪድ-19 እየጠበቁ ማንነታቸውን መለየቱን እንደክፋት አላየውም። ማርክ ዛከርበርግ የፌስቡክን ለየት ያለ መነጽር ባስተዋወቀበት እርግጥ ነው እንደ ለንደን ሜትሮፖለቲን ፖሊስ ያሉ የደኅንነት መሥሪያ ቤቶች በኮቪድ-19 ምክንያት ቴክኖሎጂውን መጠቀም ቢያቆሙም ባለፈው ዓመት እንደ 'ብላክ ላይቭስ ማተር' ባሉ የጥቁሮች መብት ጠያቂ ሰልፎች ላይ ቴክኖሎጂው እየተሰለለበት ነው። የአምነስቲ ኢንተርናሽናሉ ማይክል ክሌይንማን "ቴክኖሎጂው አሁን ጥቅም ላይ እየዋለ አይደለም ማለት ወደፊትም ያቆማል ማለት አይደለም" ሲሉ ለቢቢሲ ይናገራሉ። "ማንኛውም ሰው ካሜራ ያለበት አካባቢና የደኅንነት መሥሪያ ቤቶች ግድም ከሄደ ማንነቱ ሊለይ ይችላል" ይላሉ ማይክል። "ይህ በጣም አስፈሪ ነው። " የግል መሥሪያ ቤቶች ይህን ቴክኖሎጂ መጠቀም ያቁሙ አያቁሙ በውል አይታወቅም፤ ተመዝግቦ የተቀመጠ መረጃም የለም። ባለፈው ሰኞ ዲዝኒ ዎርልድ የተሰኘው የመዝናኛ ኩባንያ ይህን ቴክኖሎጂ ለአንድ ወር ያክል ሊሞክረው እንደሚችል ይፋ አድርጓል። ኩባንያው ደንበኞች ወደ ግቢው ሲገቡ ፊታቸውን በካሜራ ይወስድና ልዩ ቁጥር ይሰጠዋል። ዲዝኒ ይህን የማደርገው "ደንበኞች ሰልፍ ላይ እንዳይጉላሉ ነው" ይላል። ታድያ ወደ ዲዝኒ መዝናኛ ፓርክ ሲገቡ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዎን ማውለቅ አይጠበቅብዎትም። ወረርሽኙ ከመከሰቱ በፊት እንኳ ቴክኖሎጂው ሰዎች ፊታቸውን ሸፍነው እንዴት ማንነታቸውን መለየት ይችላል የሚለውን ሲያጠና ቆይቷል። ጃፓን ውስጥ አንድ ድርጅቱ በአለርጂ ምክንያት ጭምብል የሚያደርጉ ሰዎችን ማንነት ለመለየት ጥናት ሲያደርግ ነበር። ድርጅቱ ባለፈው ጥር ጥናቱ 99.9 በመቶ ውጤት ማሳየቱን ይፋ አድርጎ ነበር። ቴክኖሎጂው ይህን የሚያደርገው በመሸፈኛ ያልተሸፈኑ [ዓይንና ግንባርን የመሳሰሉ] የፊት ክፍሎችን በማጥናት ነው። ኩባንያው ይህን ቴክኖሎጂ ለትላልቅ ሕንፃዎች ለመሸጥ አስቧል። ፌሻል ሪኮግኒሽን በሚቀጥለው ሐምሌ በጃፓን በሚካሄደው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ ጥቅም ላይ እንደሚውል ተነግሯል። ቴክኖሎጂው እነማን ላይ እንደሚተገበር ይፋ ባይሆንም ሰዎች ኦሊምፒክ ላይ መጮህና መዝፈን እንደማይፈቀድላቸው ታውጇል። ፌስቡክም በቅርቡ ይፋ በሚያደርገው 'ስማርት መነጽር ላይ' ይህን ቴክኖሎጂ ለመጠቀም እንዳሰበ ተናግሯል። ነገር ግን ብዙዎች ይህን ዕቅድ እየተቃወሙት ነው። ፌሻል ሪኮግኒሽን አሁንም አከራካሪነቱ ቀጥሏል። ወደድንም ጠላንም ቴክኖሎጂው ወደፊት እያደገ መምጣቱ አይቀርም። |
46396268 | https://www.bbc.com/amharic/46396268 | እስራኤል፦በዌስት ባንክ ዘጠኝ ሺህ ዓመት ያስቆጠረ ጭምብል ተገኘ | በዓይነታቸው የተለየዩና በአለም ላይ 15 ብቻ ከሆኑ የጭምብል አይነቶች አንዱ በዌስት ባንክ መገኘቱን እስራኤል አስታወቀች። | ዘመን ተሻጋሪው ጭምብል የተገኘው በእስራኤል ይዞታ ስር በሚገኘው የዌስት ባንክ ክፍል ሄብሮን በተሰኘ ቦታ ነው። ከብርቱካናማና ቢጫ ድንጋይ የተሰራው ጭምብል በአሁኑ ወቅት በእስራኤል ቅርስ ጥበቃ ተቋም እንዲገባ ተደርጓል። በቅርስ ተቋሙ የቅርስ ተመራማሪ የሆኑት ሮኒት ሉፑ "ጭምብሉ በጣም ተፈጥሮአዊ በሆነ መንገድ የተሰራ ነው" ብለዋል። • 'ቆሞ የቀረው' የተቃውሞ ፖለቲካ? • በአዲስ አበባ አፍላ ወጣቶች በከፍተኛ መጠን በኤች አይቪ እየተያዙ ነው ባለሙያዋ እንደሚገምቱት ጭምብሉ ምናልባትም ጥንት ከሃይማኖታዊ በአላት አከባበር ላይ ጥቅም ላይ ይውል የነበረ ነው። ጭምብሉ ላይ ያሉ ቀዳዳዎች ሲታዩ ደግሞ ለእይታ ይሰቀል እንደነበር ያመለክታል። ጭምብሉ የሰው ዘር አዳኝና ፍራፍሬ ለቃሚ በነበረበት ዘመን የይጠቀምበት እንደነበር ተመራማሪዋ ግምታቸውን ይናገራሉ። አለም ላይ ካሉት ከነዚህ 15 ጨምብሎች 13 የሆኑነት በግለቦች እጅ የሚገኙ መሆኑ የጭምብሎቹ ዓይነት ላይ በቂ ምርምር ማድረግ እንዳይቻል አድርጓል። እስካሁን የተደረጉ ምርምሮች ውጤት ግን በቀጣዩ ሳምንት በእየሩሳሌም የእስራኤል ሙዚየም ይፋ እንደሚሆን ተናግረዋል። |
news-50462681 | https://www.bbc.com/amharic/news-50462681 | የብዙ ኢትዮጵያዊያንን ህይወት እየቀየረ ያለው የተፈጥሮ ጥበቃ ሥራ | በሰሜናዊ ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ባለፉት አስር ዓመታት በሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ምክንያት ተጎድተው የነበሩ አካባቢዎች በእጽዋት እየተሸፈኑ ይገኛሉ። ይህ ደግሞ በቂ ውሃ እንዲኖር ከማድረግ ባለፈ የዱር እንስሳትም እንዲመለሱ አድርጓል፤ ንቦችንም ጨምሮ። | የቢቢሲው ጀስቲን ሮውላት ወደ ትግራይ ክልል በተጓዘበት ወቅት ብዙ አስገራሚ ነገሮችን እንደተመለከተ ይናገራል። የማይረሳው ነገር ግን የነደፉትን ንቦች እንደሆነ ገልጿል። '' በወቅቱ ያልጠበቅኩትና አስደንጋጭ ነገር ነበር'' ብሏል ስለንቦቹ ሲያስረዳ። በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ መሪነት የሚሰራው በዓለማችን እጅግ የተራቆቱ ከሚባሉት አንዱ የሆነውን አካባቢ መልሶ በደን የመሸፈን ስራ ትልቅ ራዕይ አንግቦ የተጀመረ እንደሆነ ጀስቲን ይገልጻል። • ወደ ጫካነት የተቀየረው ስታዲየም • ሳናውቀው እያለቁብን ያሉ ስድስት ነገሮች መልሶ የማልማት ስራውን ከሚቆጣጠሩ የስነ ደን ባለሙያዎች መካከል አንዷ የሆነችው ሳራ ተወልደብርሀን፣ ጀስቲንን ይዘው ወደ ጥብቅ ደኑ ሄደች። ''ይህንን የመሰለ ትልቅ ፕሮጀክት በአግባቡ እንኳን በአጥር አለመከለሉ እያስገረመኝ ተከትለኳት'' ይላል ጀስቲን። በሳራ መሪነትም ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የሚከፋፈሉ ችግኞች የሚዘጋጁበትን ቦታ ተመለከቱ። '' አካባቢው ደስ የሚልና ሰላማዊ ስሜትን ይፈጥራል። ወፎች ሲዘምሩ መስማት ደግሞ እጅግ ያስደስታል።'' '' በልጅነቴ ስለ ሰሜን ኢትዮጵያ እየሰማሁት ካደግኩት ታሪክ ጋር ሊጣጣምልኝ አልቻለም። እኤአ በ1980ዎቹ ውስጥ ተከስቶ የነበረው ረሃብ ስለዚህ አካባቢ የተለየ አስተሳሰብ እንዲኖረኝ ነበር ያደረገው።'' በድርቁ ወቅት ምግብ በመፈለግ ላይ የነበረ ህጻን በወቅቱ ለተከሰተው ድርቅ ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም መንግስት አካባቢዎቹን ችላ ማለቱ፣ ጦርነት እና የደን ጭፍጨፋ ተጠቃሽ ናቸው። በምድራችን እጅግ ከፍተኛ ከሚባሉ የደን ጭፍጨፋዎች ከተደረገባቸው ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ ቀዳሚውን ስፍራ ትይዛለች። ያለዛፎች ደግሞ ለም የሆነውን የአፈር ክፍል መጠበቅ ከባድ ነው። ነገር ግን ሳራ እና ጓደኞቿ እያከናወኑት ባለው የተፈጥሮ ጥበቃና መልሶ የማልማት ስራ አካባቢው አረንጓዴና እጅግ ማራኪ ቦታ ሆኗል። የስራቸውን ውጤት በቀላሉ መመልከት ይቻላል። '' ተፈጥሮ ራሷን መልሳ ማዳን ትችላለች'' በማለት ሳራ እንደነገረችው ጀስቲን ያስታውሳል። • የማዉ ጫካን ለማዳን 60 ሺ ኬንያውያን ከመኖሪያቸው ተባረሩ ደኑን ወደነበረበት መመለስ ለአካባቢው አዲስ ነገር ነው። ነገር ግን አካባቢው ነዋሪዎች ፕሮጀክቱን ለመደገፍ ከፍተኛ ፍላጎት አሳይተዋል። ''ከብቶች ለግጦሽ እንዳይጠቀሙትና ዛፎች እንዳይቆረጡ በትብብር ይሰራሉ'' ስትል ስለአካባቢው ነዋሪዎች ሳራ ታስረዳለች። በማህበረሰቡ ጋር በትብብር የሚሰራው አካባቢውን መልሶ በደን የመሸፈን ስራ፣ ውጤታማ በመሆኑ ምክንያት በትግራይ ክልል 15 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ቦታ ሙሉ በሙሉ በደን ተሸፍኗል። በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ ለብዙ ዓመታት ደርቀው የነበሩ ምንጮች ጭምር ተመልሰው ውሃ ማፍለቅ ጀምረዋል። ወንዞችም ቢሆን ዓመቱን ሙሉ መፍሰስ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። በቅርብ የሚገኙ ገበሬዎች ምርት በእጅጉ ጨምሯል። '' በደኑ ውስጥ ስንዘዋወር አንድ ነገር ቀልቤን ገዛው። አረንጓዴ ቀለም የተቀቡ የንብ ቀፎዎች በብዛት ይታያሉ፤ በቅርበት ለመመልከት ተጠጋን።'' ምንም እንኳን ሳራ በጥንቃቄ እንድንቀሳቀስ ብትነግረኝም ብዙም አላሳሰበኝም ነበር የሚለው ጀስቲን በድንገት ግን ያላሰበው ነገር አጋጥሞታል። '' ወዲያውኑ በእጄ አካባቢ በጣም የሚያቃጥል ስሜት ወረረኝ። ልብሴን ሰብስቤ ስመለከት ሁለት ንቦች ወደታች ሲወርዱ አየኋቸው። ሁለቱም ንቦች ከነደፉኝ አካባቢ አነስተኛ ደም ተቋጥሮ ይታይ ነበር።'' ''እርዱኝ!! ንቦቹ ነደፉኝ!! ብዬ ጮህኩኝ ሳራ ወደ ጀስቲን ስትሄድ እሷም በንቦች ተነደፈች። • የምድራችን ትልቋ ንብ ተገኘች • ሜድ ኢን ቻይና- የሀገር ባህል አልባሳቶቻችን ወዲያውም አካባቢያችን በሙሉ በንቦች ተከበበ። አስደንጋጭም አስቂኝም አጋጣሚ ነበር። ሁለታችንም ከንቦቹ ለማምለጥ እርስ በእርስ እየተገጫጨንና እየተረጋገጥን በሩጫ ለማምለጥ ሞከርን።'' ''ነገር ግን አጄን፣ ጆሮዬን፣ ከንፈሬን እና ጀርባዬን ንቦቹ ነድፈውኝ ነበር።'' '' በሩጫ በቅርብ ወደነበረው ቤት ገባን። ሳራም በሩን ከዘጋች በኋላ በድንጋጤ ተያየን። ትንሽ ትንፋሻችንን ከሰበሰብን በኋላ አብረን መሳቅ ጀመርን።'' '' እንደውም የሆነ ነገር አስታወስኩኝ አለች ሳራ። ጓደኛዬ ከጫካው ማር ይሰበስባል እኮ፤ ለምን አንድ ገንቦ አልሰጥህም? ብላ ወደ ውስጥ ገባች።'' ''በጣም ጣፋጭና ተፈጥሯዊ ማር ነበር። ወደድኩት።'' |
news-56769258 | https://www.bbc.com/amharic/news-56769258 | በድህረ-ኮቪድ ወቅት የቻይና ኢኮኖሚ 18.3 በመቶ አደገ | የቻይና ኢኮኖሚ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነፃፀር በ 2021 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 18.3 በመቶ አደገ፡፡ | ቻይና ከአውሮፓውያኑ 1992 ጀምሮ የሩብ ዓመቱን ዕድገት መመዝገብ የጀመረች ሲሆን ይህም ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) ትልቁ ዕድገት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ የሮይተርስ የምጣኔ ሃብት ጥናት የ 19 በመቶ ዕድገት እንደሚኖር በመተንበዩ የአሁኑ ቁጥር ከሚጠበቀው በታች ሆኗል፡፡ ካለፈው ዓመት ግዙፍ የኢኮኖሚ መቀነስ ጋር ሲወዳደርም የተዛባ እና ጠንካራ ዕድገትን የሚያመለክት አይደለም ተብሏል፡፡ እንደ መነሻም በቻይና የኮሮናቫይረስ ከፍተኛ በሆነበት እና ሃገር ዓቀፍ የእንቅስቃሴ እገዳ በተጣለበት የ2020 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የተመዘገበውን 6.8 በመቶ ዕድገት ወስዷል። የቻይና የስታቲስቲክስ ቢሮ የተለቀቁ ሌሎች ቁልፍ አኃዞችም ቀጣይ ዕድገትን ቢያመለክቱም ከነበረው ካለፈው ዓመት ጋር ስለሚነጻጸሩ ጥንካሬው እምብዛም ነው ተብሏል፡፡ በመጋቢት የኢንዱስትሪ ምርት ከአንድ ዓመት በፊት ከነበረው አንጻር በ 14.1 በመቶ ከፍ ሲል የችርቻሮ ሽያጭ ደግሞ 34.2 በመቶ አድጓል፡፡ "ተስፋ ሰጪ በሆነ መልኩ ወርሃዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በመጀመሪያዎቹ ሁለት ወሮች ድክመት ቢኖርም በመጋቢት ወር የኢንዱስትሪ ምርት፣ የፍጆታ እና ኢንቨስትመንት ዕወድገት አሳይተዋል" ሲሉ በኦክስፎርድ የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ሉሲ ኩይስ ገልጸዋል፡፡ ሁሉም ነገር ለቻይና ኢኮኖሚ አልጋ በአልጋ አልሆነም። የመንግሥት የበጀት እና የገንዘብ ማበረታቻ እርምጃዎች እየቀነሱ በመሆናቸው የአንዳንድ ዘርፎች ዕድገት እንደሚቀንስ ተንታኞች ተናግረዋል። የኢኮኖሚስት ኢንተለጀንስ ዩኒት ባልደረባው ዩ ሱ እንዳሉት የቅርብ ጊዜ አኃዞች የቻይና ኢኮኖሚያዊ ማገገሚያ ሰፊ መሠረት ያለው እንደሆነ ቢያሳዩም አንዳንድ የምርት እና የወጪ ንግድ እንቅስቃሴዎች ከመጀመሪያው ሩብ ዓመት በፊት "ሊሰጡ" ይችሉ ነበር የዕድገት መቀዛቀዝ መኖሩን ይጠቁማሉ፡፡ አሃዞቹ እንደሚያመለክቱት ቻይና በ 2020 የመጨረሻ ሩብ ዓመት የ 6.5 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት በማስመዝገብ ኢኮኖሚያዊ ዕድገቷን እንዳስቀጠለች ነው፡፡ በጥብቅ የቫይረሱ መከላከያ እርምጃዎች እና ለንግድ ድርጅቶች አስቸኳይ እፎይታ በመስጠት ወረርሽኙ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ ኢኮኖሚው በተከታታይ እያገገመ ነው፡፡ የዓመቱ አጀማመር ከባድ የነበረ ቢሆንም በ 2020 ዕድገትን በማስመዝገብ ቻይና ብቸኛዋ የትልቅ ኢኮኖሚ ባለቤት ነች፡፡ ከዓለም ግዙፍ የኢኮኖሚ ባለቤቶች ሁለተኛ ደረጃን የያዘችው ቻይና 2.3 በመቶ ዕድገት ብታስመዘግብም በአስርት ዓመታት ውስጥ ደካማው ነው፡፡ ቻይና ባለፈው ዓመት ዕቅዷን በመተው ለ 2021 የ 6 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ አቅዳለች፡፡ ኮሮናቫይረስ ግን አሁንም በቻይና ኢኮኖሚ ላይ ጥላው እንዳጠላ ነው፡፡ |
news-47355926 | https://www.bbc.com/amharic/news-47355926 | በኦነግ ሠራዊት ውስጥ የመሮ ምክትል የሰላም ጥሪውን ተቀብሎ ገባ | የ'ጓድ' መሮ ምክትል እና 'ዲነራስ' በሚለው የትግል ስም የሚታወቀው ሁንዴ ዴሬሳ ከቀናት በፊት የአባ ገዳዎችን ጥሪ ተከትለው የጦር አባላቱን ይዞ ወደ ተዘጋጀለት ስፍራ ገብቷል። | ሁንዴ ዴሬሳ የአባ ገዳዎችን የሰላም ጥሪ የተቀበለውና ወደ ተዘጋጀው ስፍራ የገባ የመጀመሪያው የኦነግ የጦር አዛዥ ነው ተብሏል። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የምዕራብ ኦሮሚያ ዞን ምክትል ጦር አዛዥ የሆነው ሁንዴ ዴሬሳ ወደፊትም ቢሆን በኦሮሞ እና የኦሮሚያ መብትን ለማስከበር መታገላችንን እንቀጥላለን ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። • ኦነግ እና መንግሥትን ለማግባባት የሃገር ሽማግሌዎች እየጣሩ ነው ቅዳሜ ዕለት በአባ ገዳዎች አቀባበል ተደርጎለት የነበረው የጦር አዛዡ ተከታዮቹ በአምቦ ሰንቀሌ የፖሊስ ማሰልጠኛ ቆይታ ካደረጉ በኋላ ዛሬ ወደ ጦላይ የወታደር ማሰልጠኛ ማዕከል መሄዳቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። የምዕራብ ኦሮሚያ ዞን የጦር አዛዥ የሆነው መሮ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ላይ ''ወደፊት መራራ ትግል ማድረጋችንን እንቀጥላለን። ብቻዬን ብቀር እንኳ ትግል ማድረጌን እቀጥላለሁ እቅዴም ይሄው ነው" ሲል መናገሩ ይታወሳል። ሁንዴ ዴሬሳ እንዴት የአባ ገዳዎችን ጥሪ ለመቀበል እንደቻለ ሲያብራራ ''ይህ የህዝብ ፍላጎት ነው። ህዝቡ የሚፈልገው ይህን ነው። 'በኦሮሞ ጉዳይ ላይ ኑ አብራን እንሥራ' ብለው ጥሪ ስላቀረቡልን ከሠራዊቱ ጋር ከተወያየን በኋላ ጥያቄያቸውን ተቀብለናል'' ብሏል። ''የኦነግ የምዕራብ ኦሮሚያ ዞን በሁለት ተከፍሎ ነው የሚተዳደረው። ከጊምቢ በታች መሮ ነው ትዕዛዝ የሚሰጠው። ከጊምቢ በላይ እንደ ነቀምቴ፣ ሻምቡ እና ምዕራብ ሸዋ ደግሞ ትዕዛዝ የምሰጠው እኔ ነኝ'' የሚለው ሁንዴ የዕዝ ተዋረዱን ሲያስረዳ ''መሮ ከሊቀመንበሩ [ዳውድ ኢብሳ] ትዕዛዝ ይቀበልና ለእኛ ያስተላልፋል'' ብሏል። • በምዕራብ ኦሮሚያ የኦነግ ጦር አዛዥ ስለወቅታዊው ሁኔታ ምን ይላል? የሁንዴ የትግል አጋር እና አዛዥ የሆነው ኩምሳ ዲሪባ ወይም መሮ "የእርቅ የተባለው ኮሚቴ እኔን በአካል አግኝተው ለማነጋገር ፍላጎት የላቸውም። ትኩረት ያደረጉት ጦሩን አንድ በአንድ እጁን እንዲሰጥ ማድረግ ላይ ነው" በሚል እና በሌሎች ምክያቶች ጥሪውን እንደማይቀበል አርብ ዕለት ለቢቢሲ ተናግሮ ነበር። በዚህ ላይ ሁንዴ አስተያየቱን እንዲሰጡ ጠይቀን ''ይህን ትግል ህዝቡ የሚፈልግ ከሆነ አንድ መቶ ዓመት እንኳ በትግል ላይ እንቆያለን። የምንታገለው ለህዝቡ እስከሆነ ድረስ ህዝቡ የምፈልገው ሰላማዊ ትግል ነው እስካለ ድረስ የህዝቡን ስሜት ማዳመጥ ይኖርብናል። እሱ [መሮ] የግል አቋሙ ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጂ ማዳመጥ ያለብን የግል ስሜታችንን ሳይሆን የህዝቡን ፍላጎት ነው'' በማለት ''የአባ ገዳዎችን ጥሪ ከሰማን በኋላ ከመሮ ጋር ተገናኝተን ተነጋግረን ነበር። የእርቅ ጥሪውን ከተቀበልን በኋላ ሃሳቡን ቀየረ'' ሲል የነበረውን ሁኔታ ገልጿል። • በኦነግ እና በመከላከያ ሠራዊት መካከል በምዕራብ ኦሮሚያ ግጭት እንደነበር ተነገረ የምዕራብ ኦሮሚያ ዞን የኦነግ ጦር አዛዥ ኩምሳ ድሪባ ወይም መሮ የመሮን ውሳኔ በተመለከተም ''ሽንፈት መሰለው፤ ሰው የሚለውን መቀበል ላይ ትንሽ ድክመት አለበት። ብቸኝነትም ያጠቃዋል፤ ከዚህ ውጪስ ሌላ ችግር የለበትም" ብሏል። መሮ ከቀናት በፊት ለቢቢሲ እንደተናገረው ''ከዚህ የተለየን ጦር 5 በመቶ እንኳ አይሆንም። 95 በመቶ አሁንም እንደታጠቀ ነው የሚገኘው" ብሎ ነበር። የመሮ ምክትል የሆነው ሁንዴ እንደሚለው ከሆነ ግን የእርቅ ጥሪውን ተቀብለው የወጡ የኦነግ ወታደሮች በጫካ ከሚገኙት ይበልጣሉ። • "ከ[እኛ] የተለየን ጦር 5 በመቶ እንኳ አይሆንም" መሮ የኦነግ ጦር አዛዥ ''በእኔ ስር የነበሩ የሠራዊት አባላት በሙሉ የእርቅ ጥሪውን በደስታ ተቀብለውታል፤ በጫካ የቀሩት አባላት 'የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ እስኪመለስ እንታገላለን የሚሉት ናቸው'' በማለት ተናግሯል። በኦነግ ጦር አባላት መካከል የእርቅ ጥሪውን እንቀበል፤ አንቀበል በሚል የሃሳብ ልዩነት ተፈጥሯል ወይ ብለን ለጠየቅነው ጥያቄ፤ ሁንዴ ሲመልስ ''ይህ በደንብ ያለ ነው። እኔ እንደማውቀው እንኳ ሦስት ቦታ ተከስቷል።'' |
news-55487923 | https://www.bbc.com/amharic/news-55487923 | አሜሪካን ለእስራኤል ሲሰልል የነበረው ከ30 ዓመት እስር በኋላ ቴል አቪቭ ገባ | ጆናታን ፖላርድ የተባለው አሜሪካን ለእስራኤል ሲሰልል የነበረው ግለሰብ፤ ከ30 ዓመታት እስር ተለቆ እስራኤል፣ ቴላ ቪቭ ገባ። | የ66 ዓመቱ ግለሰብ ለአንድ ወር ተጥሎበት የነበረው የጉዞ እገዳ ከተነሳ በኋላ ከባለቤቱ ኤስተር ጋር ወደ እስራኤል አቅንቷል። አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የተቀበሏቸው ሲሆን “አሁን አገራችሁ ናችሁ” ሲሉም ጠቅላይ ሚንስትሩ የእስራኤል ብሔራዊ መታወቂያ ሰጥተዋቸዋል። ጆናታን የታሰረው እአአ በ1985 ነበር። የአሜሪካን ሚስጥር ለእስራኤል መስረቁን አምኖ የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት ነበር። አሜሪካ ከአጋሯ እስራኤል መረጃ መደበቋ አስቆጥቶት እንደነበር ተናግሯል። መጀመሪያ ላይ ጆናታን ይሰልልላት እንደነበረ እስራኤል አላመነችም። ከሕገ ወጥ ባለሥልጣኖች ጋር እንደሚሠራም ተነግሮ ነበር 1995 ላይ ግን እስራኤል ዜግነት ሰጠችው። 3 ዓመት ቆይታ ደግሟ ሰላይ እንደሆነ አመነች። ከእስር እንዲለቀቅ እስራኤል ብትጠይቅም ከዚህ ቀደም የነበሩ የአሜሪካ ፕሬዘዳንቶች እስከ 2015 ድረስ አልፈቀዱም። 2015 ላይ ሲለቀቅ፤ ቢያንስ ለአምስት ዓመት ያለ ፍቃድ ከአሜሪካ ውጪ መጓዝ እንደማይችል ቅድመ ሁኔታ ተቀምጦ ነው። ባለፈው ወር የአሜሪካ የፍትሕ ተቋም የጉዞ ክልከላው እንደተነሳለትና እስራኤል መሄድ እንደሚችል አስታውቋል። አሜሪካዊው ቢልየነር ሸልደን አደልሰን እና ባለቤቱ ሚርያም ባመቻቹት የግል ጀት ከኒው ጀርሲ እስራኤል በሯል። ከባለቤቱ ጋር እስራኤል እንደደረሱ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ የተቀበሏቸውደ ቤንያሚን ኔታንያሁ “እንኳን ደህና መጣችሁ። በስተመጨረሻ አገራችሁ መምጣታችሁ መልካም ነው። እዚህ በነጻነትና በሀሴት አዲስ ሕይወት መጀመር ትችላላችሁ” ብለዋል። ጥንዶቹ እስራኤል ሲደርሱ ተንበርክከው መሬቱን ስመው የአይሁድ እምነት ፀሎት አድርሰዋል። ጆናታን “ከ35 ዓመት በኋላ አገራችን መመለስ እጅግ ያስደስታል። ሕዝቡና ጠቅላይ ሚንስትሩ አገራችን እንድንገባ ስላደረጉን እናመሰግናለን። በአገራችን እና በመሪያችን እንኮራለን። ውጤታማ ዜጎች ለመሆን ቆርጠን ተነስተናል” ሲል ስሜቱን ገልጿል። ለቀጣይ ሁለት ሳምንታት እየሩሳሌም ውስጥ ባለ አፓርትመንት ራሳቸውን ለይተው ያቆያሉ። እስራኤል ሃዮም የተባለው ጋዜጣ ባለቤት ሚርያም፤ ጆናታን ሞቅ ያለ አቀባበል እንዲደረግለት ጠይቃለች። “እስራኤል ውለታው አለባት። ተጎድቶ እንደመጣ ወታደር አገሪቱ የሚገባውን ሁሉ ልታመቻችለት ይገባል” ብላለች። 1998 ላይ ከአሶሽየትድ ፕረስ ጋር በነበረው ቆይታ፤ ጆናታን ለስለላ የከፈለው መስዋዕትነትና ያገኘው ዋጋ እንደማይመጣጠኑ ተናግሮ ነበር። “ምንም ውጤት አላገኘሁም። ሁለት አገሮች ለማገልገል ሞክሬያለሁ። ያ ደግሞ አይሠራም” ብሎ ነበር በቃለ ምልልሱ። |
news-45168230 | https://www.bbc.com/amharic/news-45168230 | ጃካርታ በውሃ እየተዋጠች ያለችው ከተማ | አስር ሚሊዮን የሚደርስ ሕዝብ የሚኖርባት የኢንዶኔዢያዋ ዋና ከተማ ጃካርታ በፍጥነት ውሃ ውስጥ እየሰመጠች መሆኑ ተነግሯል። | ይህም አፋጣኝ እርምጃ ተወስዶ መፍትሄ ካላገኘ ከሰላሳ ዓመታት በኋላ ከተማዋ ሙሉ በሙሉ በውሃ እንደምትዋጥ አጥኚዎች ተናግረዋል። እንደባለሙያዎቹ በረግረጋማ ስፍራ የተመሰረተችውና 13 ያህል ወንዞችን በውስጧ የያዘችው ጃካርታ በተደጋጋሚ በጎርፍ ትጠቃለች፤ አሁን ግን ሁኔታው በእጅጉ እየከፋ መሆኑንም ተገልጿል። • ኦብነግ የተኩስ አቁም አወጀ • ታይዋናዊ ቱሪስት ፎቶ ሊያነሳው በነበረው ጉማሬ ተነክሶ ሞተ በዚህም ሳቢያ ይህች ግዙፍ ከተማ በውሃ እየተዋጠች ከምድረ ገፅ እየጠፋች መሆኑም ተነግሯል። ላለፉት ሃያ ዓመታት በባንዱግ የቴክኖኢሎጂ ኢንስቲቲዩት ውስጥ የጃካርታን በውሃ መዋጥ ሲያጠኑ የቆዩት ሄሪ አንድሪያስ እንደሚሉት "የከተማዋ በውሃ የመዋጥ ነገር በዋዛ የሚታይ ነገር መሆን የለበትም" ብለዋል። የከተማዋ አንዳንድ አካባቢዎች በውሃ የመዋጥ ክስተት እየታየ ሲሆን በሰሜናዊ ጃካርታ 2.5 ሜትር የመሬት አካል በአስር ዓመታት ውስጥ በውሃ ተውጧል። ይህም በአንዳንድ አካባቢዎች በ25 ሴንቲ ሜትር በየዓመቱ እየሰመጠ ሲሆን በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ባሉ የባሕር ዳርቻዎች ካጋጠመው ጋር ሲነፃፀር ከእጥፍ በላይ የሆነ ክስተት ነው ተብሏል። ጃካርታ በየዓመቱ በአማካይ ከ አንድ አስከ 15 ሴንቲ ሜትር ድረስ እየሰመጠች ሲሆን በአሁኑ ጊዜ የከተማዋ ግማሽ ያህል ከባህር ጠለል በታች ይገኛል። በዝናብ እጥረት ምክንያት ኬፕታውን ከባድ የወሃ እጥረት ውስጥ ነች። |
news-46285745 | https://www.bbc.com/amharic/news-46285745 | ኢንዶኔዥያ ውስጥ ዌል የተባለው የባህር እንስሳ 6 ኪሎ ያህል ፕላስቲክ ውጦ ተገኘ | ነገሩ ወዲህ ነው፤ ዌል የተባለው የባህር ላይ ግዙፍ እንሰሳ ይሞትና በማዕበል ኃይል የተገፋው በድን ሰውነቱ ኢንዶኔዥያ በሚገኝ አንድ ባህር ዳርቻ ላይ ይገኛል። | አጋጣሚ ሆኖ የባህር ዳርቻው የአንድ ብሔራዊ ፓርክ አካል ነበርና የፖርኩ ሰዎች የዌሉን ሆድ በቀደዱ ጊዜ መዓት ኩባያ ያያሉ። 6 ኪሎ ያህል ይሆናል የተባለ የፕላስቲክ ዓይነት የተገኘበት ይህ ዌል 'ታይዋን ተራ' የሚል ቅፅል ስያሜ እየተሰጠው ነው። 115 ኩባያ፤ አራት የፕላስቲክ ጠርሙስ፤ 25 የፕላስቲክ ፌስታል እና ሁለት ነጠላ ጫማዎች። • ትላልቅ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድቦች "አዋጭ አይደሉም" 9.5 ሜትር ርዝመት ያለው ይህ እንሰሳ ሆዱ ውስጥ መዓት ፕላስቲክ መገኘቱ የአካባቢ ጥበቃ ሰዎችን እያስቆጣ ነው። ኢንዶኔዥያዊቷ የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያ ድዊ ሱፕራፕቲ ሁኔታውን «እጅግ ደስ የማያሰኝ» ሲሉ ይገልፁታል። ባለሙያዋ እንሰሳው ሊሞት የቻለው በፕላስቲኮች ምክንያት ነው ባንል የፕላስቲኮች አለመፈጨት ከጊዜ በኋላ ሕይወቱን ሊያሳጡት እንደሚችሉ እሙን ነው የሚል አመክንዮ ያስቀምጣሉ። • እምቦጭ የጣና ቂርቆስ መነኮሳትን ከገዳሙ እያስለቀቀ ነው በዚህ ግራፍ ላይ እንደሰፈረው እስያ ባህርን በመበከል ረገድ አቻ የሌላት ሲሆን፤ ኢትዮጵያ፣ ሩስያ ሌሎች ሃገራት እጃቸው ከደሙ ንፅሁ ነው ኢንዶኔዥያን ጨምሮ በሌሎች የእስያ ሃገራት መልሰው ጥቅም ላይ የማይውሉ ፕላስተኮች ጉዳይ አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል። የዓለማችን የውሃ አካላት ከጊዜ ጊዜ በፕላስቲክ ዕቃዎች እየተበከሉ ነው፤ ቻይና፣ ኢንዶኔዥያ፣ ፊሊፒንስ፣ ቪየትናም እና ታይላንድ ለዚህ ጥፋት 60 በመቶ ያህል ድርሻ ያዋጣሉ። ፕላስቲክ የባህር ላይ ፍጡራንን ሕይወት ከሚቀጥፉ ነገሮች እንደአንሱ መሆን ከጀመረ ሰንበትበት ብሏል። • ኢትዮጵያ ሳተላይት ማምጠቅ ለምን አስፈለጋት? |
news-47980285 | https://www.bbc.com/amharic/news-47980285 | ባንግላዴሽ፡ ወሲባዊ ትንኮሳን ሪፖርት በማድረጓ ተቃጥላ የተገደለችው | በባንግላዴሽ ኑስራት ጃሃን የተባለች ተማሪ ርዕሰ መምህር ፆታዊ ትንኮሳ እንዳደረሰባት ሪፖርት ማድረጓን ተከትሎ በነጭ ጋዝ አርከፍከው አቃጥለው ገድለዋታል። | የደረሰባትን ትንኮሳ በመናገሯ ድፍረቷን ብዙዎች ቢያደንቁትም ከቀናት በኋላ ግን ሰቅጣጭ የሆነው አገዳደሏ ብዙዎችን አስደንግጧል። ፆታዊ ትንኮሳን ሪፖርት የሚያደርጉ ሰዎች ምን ያህል ለጥቃት ተጋላጭ እንዳደረጋቸውም የሚያሳይ ነው ተብሏል። በትንሽ መንደር የተወለደችው የአስራ ዘጠኝ አመቷ ኑስራት ማዳራሳ ወይም የእስልምና ትምህርትን ትከታተል ነበር። •የተነጠቀ ልጅነት •"በወንድሜ ለአምስት ዓመታት ተደፍሬአለሁ" ከሁለት ሳምንት በፊትም የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ቢሮው አስጠርቷት በማይሆን መልኩ ሰውነቷን መነካካት ሲጀምር ሮጣ እንደወጣች ተናግራለች። በባንግላዴሽ በየትኛውም እድሜ ላይ የሚገኙ ሴቶች በቤተሰብና በማህበረሰቡ ሊደርስባቸውን የሚችለውን መሸማቀቅ በመፍራት ፆታዊ ጥቃቶችን ሪፖርት አያደርጉም። ኑስራትን ለየት የሚያደርጋት ግን በግልፅ መናገሯ ብቻ ሳይሆን በቤተሰብ እርዳታ ወደ ፖሊስ ሄዳ ሪፖርት ማድረጓ ነበር። •"ሌሎች ሴቶች ላይ የአሲድ ጥቃት ሳይ ይረብሸኛል፤ ህመሜን ያስታውሰኛል" ካሚላት መህዲ በፖሊስ ጣቢያውም ውስጥ ደህንነቷን በሚያስጠብቅ መልኩ ሳይሆን የተፈፀመባትን ነገር በዝርዝር በምታስረዳበት ወቅት ፖሊሱ በስልኩ እየቀረፃት ነበር። ተንቀሳቃሽ ምስሉ እንደሚያሳየው ኑስራት በተጨናነቀ መልኩ በእጇ ፊቷን ለመደበቅ ጥረት ብታደርግም፤ ፖሊሱ ግን የደረሰባትን ጥቃት "ትልቅ ነገር" አይደለም በማለት እጇን ከፊቷ ላይ እንድታነሳ ይነግራት ነበር። ተንቀሳቃሽ ምስሉም የኃገር ውስጥ ሚዲያዎች እጅ ውስጥ ገብቶ ለህዝብ እይታ በቃ። 'ትምህርት ቤት ልወስዳት ሞክሬ ነበር' ከወግ አጥባቂ ቤተሰብ የተወለደችው ኑስራት ምንም እንኳን ትንኮሳን ሪፖርት በማድረጓ ከማህበረሰቡ ሊከተላት የሚችለውን ነገር አደገኛ ሊሆን እንደሚችል ሳይታለም የተፈታ ቢሆንም እሷ ግን አይበገሬ ነበረች። የተለያየ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች ከማህበረሰቡ በአካል፣ በተለያዩ ድረገፆች ከቃል ዘለፋ ጀምሮ አካላዊ ጥቃት ይደርስባቸዋል። ኑስራትም ከዚህ አላመለጠችም። ለፖሊስ ሪፖርት ካደረገች በኋላ ርዕሰ መምህሩ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተከትሎ ለኑስራት የከፋ ነበር። ግለሰቡ እንዲለቀቅ የሚጠይቁ ሰዎች ጎዳናውን አጥለቀለቁት። ተቃውሞውን ያደራጁት ሁለት ወንድ ተማሪዎች ሲሆኑ የአካባቢውም ፖለቲከኞችንም ድጋፍ ማግኘት እንደቻሉ ተገልጿል። •"ማንም መብታችንን ሊሰጠን ስለማይችል፤ ሴቶች ማንንም ሳይጠብቁ በራሳቸው መታገል አለባቸው" ምንም እንኳን ተጠቂዋ እሷ ብትሆንም ብዙዎች እሷን መወንጀል ጀመሩ። ቤተሰቧም የደህንነቷ ሁኔታ እንዳስጨነቃቸውም መናገራቸው ተዘግቧል። ጥቃቱን ሪፖርት ካደረገች ከአስራ አንድ ቀናት በኋላ ፈተና ልትፈተን ትምህርት ቤት ሄደች። "እህቴን ትምህርት ቤት የወሰድኳት እኔ ነኝ። ወደ ግቢው ለመግባት ስጠይቅ እንደማይፈቀድልኝ ነገሩኝ" በማለት የሚናገረው ወንድሟ ማህሙዱል ሃሰን ኖማን " ከመግባት ባያስቆሙኝ ኖሮ እንዲህ አይነት ሰቅጣጭ ጉዳይ በእህቴ ላይ አይፈፀምም ነበር" ብሏል። የኑስራት ጃሀን ወንድም በቀብሯ ላይ ከመሞቷ በፊት ኑስራት በሰጠችው መግለጫ አንዲት ሴት ተማሪ አንድ ጓደኛዋ እንደተጎዳ ነግራት ጣራው ላይ ወሰደቻት። ጣራው ላይ ስትደርስ ግን አምስት ተማሪዎች እንደከበቧትና በርዕሰ መምህሩ ላይ ያቀረበችውን ክስ እንድትተው ጫና ሊያደርጉባት ሞክረዋል። እምቢ ስትልም በእሳት እንደለኮሷት ተናግራለች። የወንጀል መርማሪ ፖሊስ ኩማር ማጁምደር እንደገለፀው ገዳዮቿ ራሷን ያጠፋች ለማስመሰል ቢሞከሩም እቅዳቸው ሳይሳካም ለጥቂት ቀናትም ቢሆን በህይወት ተርፋ መግለጫ መስጠት ችላለች። • "የመከላከያ ሚኒስቴርን በተሻለ መልኩ መምራት ይቻላል" ኢንጂነር አይሻ መሀመድ "አንደኛዋ ገዳይዋ በእጆቹ ጭንቅላቷን ያስጎነበሳት ሲሆን፤ እጁም እንዳይነካ በሚል ጭንቅላቷ ላይ ነጭ ጋዝ ያላርከፈከፉባት ሲሆን በዚህም ምክንያት ጭንቅላቷ ከመቃጠል መትረፍ ችሏል" በማለት የወንጀል መርማሪው ፖሊስ ኩማር ተናግሯል። ነገር ግን ኑስራት ወደ አካባቢው ሆስፒታል ከተወሰደች በኋላ ግን 80% ሰውነቷ እንደተቃጠለና ለተሻለም ህክምና ወደ ሌላ ሆስፒታል ተልካለች። በአምቡላንስ ውስጥ እያለች በህይወት አልኖርም ብላ በመፍራት በወንድሟ ስልክ የደረሰባትን ነገር ቀድታዋለች። "መምህሩ ነክቶኛል፤ እስከ መጨረሻ እስትንፋሴም ቢሆን የደረሰብኝን ወንጀል እታገላለሁ"ስትልም ተሰምታ ነበር። ጥቃት ያደረሱባትም ግለሰቦችም እዛው የሚማሩ ተማሪዎች መሆናቸውንም ተናግራ ነበር። ሆስፒታልም በነበረችበት ጥቂት ቀናትም የባንግላዴሽ ሚዲያ በከፍተኛ ሁኔታ ሽፋን ሰጥተውት የነበረ ጉዳይ ሲሆን፤ ለቀብሯም በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደተወለደችበት መንደር መጥተዋል። እስካሁን ድረስ ፖሊስ አስራ አምስት ሰዎች በቁጥጥር ስር ያዋለ ሲሆን ሰባቱ በቀጥታ ከግድያዋ ጋር በተገናኘ ነው። ከነዚህም ውስጥ ለርዕሰ መምህሩ ድጋፍ ለማሰባሰብ የተቃውሞ ሰልፍ አደራጅተው የነበሩ ሁለቱ ግለሰቦች ይገኙበታል። ርዕሰ መምህሩ አሁንም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሲሆን፤ ኑስራት ለፖሊስ ሪፖርት ስታደርግ ሲቀርፃት የነበረው ፖሊስም ከኃላፊነቱ ተነስቶ ወደ ሌላ ዘርፍ እንደታዛወረ ተዘግቧል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ ሀሲና የኑስራትን ቤተሰብ ያገኙዋቸው ሲሆን ጥፋተኞቹ ሁሉ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ቃል ገብተውላቸዋል። "ጥፋተኛ የሆነ ሁሉ ከህግ አያመልጥም" ብለዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም በቀብሯ ላይ ተገኝተዋል የኑስራት ሞት ከፍተኛ ተቃውሞን የቀሰቀሰ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦችም ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ንዴታቸውን ገልፀዋል። "ብዙ ልጃገረዶች እንዲህ አይነት ጥቃት ሲደርስባቸው በፍራቻ ምክንያት ተቃውሟቸውን አያሰሙም። መሸፋፈን አይደለም ከብረት የተሰራ ልብስ ደፋሪዎችን አያስቆምም" በማለት አንድ አስተያየት ሰጪ ተናግሯል። "በህይወቴ ሁሉ የምፈልገው ሴት ልጅ እንድትኖረኝ ነበር፤ ነገር ግን በዚች ሀገር ላይ ሴት ልጅ መውለድ ማለት ጭንቀትና ፍራቻ የተሞላ ህይወት ማለት ነው" በማለት ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ ገልፃለች። "ሴቶች የደረሰባቸውን ፆታዊ ትንኮሳ ሪፖርት ማድረግ ማለት ሌላ ትንኮሳን ማስተናገድ ማለት ነው። ጉዳዩ ለአመታት ይንጓተታል፤ ማህበረሰቡ ያሸማቅቃቸዋል። ከፖሊስ በኩል ጉዳዩን ለመርመር ፍቃደኝነት አያሳዩም። ወንጀለኞቹም ሳይቀጡ ይቀራሉ፤ ተጠቂዎቹም ፍትህ አያገኙም" በማለት የሰብአዊ መብት ጠበቃና የቀድሞ የሴቶች የህግ ባለሙያ ማህበር ዳይሬክተር ሳልማ አሊ ተናግረዋል። ብዙዎችም አሁንም እየጠየቁ ያሉት ጥቃቷ ከሞተች በኋላ ለምን ትኩረት አገኘ? እንዲሁም የሷ ሁኔታ ማህበረሰቡ ፆታዊ ጥቃትን የሚመለከትበትን መንገድ ይቀይረው ይሆን የሚሉ ናቸው። ለኑስራት ቤተሰቦች ልባቸውን የሰበረ ሐዘን ነው |
news-56356832 | https://www.bbc.com/amharic/news-56356832 | ልዑል ሃሪና ሜጋን ከዚህ በኋላ የገቢ ምንጫቸው ምን ይሆናል? | ልዑል ሃሪ ንጉሣዊው ቤተሰቡ ለሱና ለባለቤቱ ይሰጡትን የነበረውን የገንዘብ ድጎማ ማቋረጣቸውን ይፋ አድርጓል። | ይህ የሆነው ልዑሉና ባለቤቱ ሜጋን ከነባር የንጉሣዊያን ቤተሰብ አባልነት 'ራሳቸውን አግልለው' ወደ ካሊፎርኒያ በማቅናታቸው ነው። እና አሁን የገቢ ምንጫቸው ምን ይሆናል? ልዑል ሃሪና ሜጋን ከንጉሣዊው ቤሰተብ ገንዘብ የሚያገኙበት መንገድ ይኖር ይሆን? የሰሴክስ ዱክና ደችስ በመባል የሚታወቁት ሜጋንና ሃሪ ባለፈው ዓመት ጥር ነበር የንጉሣዊ ቤተሰብ አባልነት በቃን ብለው የወሰኑት። በወቅቱ ራሳቸውን በገንዘብ ለመቻል ቃል ገብተውም ነበር። ነገር ግን በጊዜው ጥንዶቹ በገቡት ስምምነት መሠረት ከሃሪ አባት የገንዘብ ድጎማ ይደረግላቸው እንደነበር ይነገራል። የሃሪ አባት የሆኑት ልዑል ቻርልስ የሒሳብ መዝገብ እንደሚያሳየው ሃሪና ሜጋንን ጨምሮ የካምብሪጅ ዱክና ደችስ ተብለው ለሚታወቁት ጥንዶች የሚሆን 5.6 ሚሊዮን ዩሮ ወጪ ተደርጓል። ይህ ወጪ እስከ መጋቢት 2020 ያለውን ጊዜ የሚያሳይ ነው። ነገር ግን ልዑል ሃሪ ከዚህ ወቅት ጀምሮ የገንዘብ ድጎማ ተቋርጦብኛል ሲል ለጉምቱዋ አሜሪካዊት ቃለ-ምልልስ አድርራጊ ኦፕራ ዊንፍሬይ ነግሯታል። ቢሆንም ልዑሉ እያወራ ያለው ከአባቱ ኪስ ስለሚሰጠው ገንዘብ ይሁን አሊያም ከግብር ከፋዩ ማሕበረሰብ ወይም ከሁለቱ ግልፅ አይደለም። ከመጋቢት ጀምሮ ያለው የልዑል ቻርልስ ሒሳብ ዝርዝር መረጃ ይፋ አልደተረገም። ቤተ-መንግሥቱም በዚህ ጉዳይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል። ሃሪና ሜጋን ሃብታም ናቸው? የሰሴክስ ዱክና ደችስ በመባል የሚታወቁት ሃሪን ሜጋን የማይናቅ ሃብት አላቸው። ልዑል ዊሊያምና ልዑል ሃሪ በድምሩ 13 ሚሊዮን ዩሮ ከእናታቸው ልዕልት ዳያና ወርሰዋል። ጓዛቸውን ጠቅልለው ወደ አሜሪካ እንደመጡ ለኦፕራ የነገራት ሃሪ "እናቴ ትታልኝ የሄደችው ነገር ባይኖር ኖሮ ይሄን ማድረግ አንችልም ነበር" ብሏል። የቢቢሲው የንጉሣዊያን ቤተሰብ ተንታኝ ኒክ ዊቼል ደግሞ ልዑል ሃሪ ከአያቱ [ንግሥት ኤሊዛቤት] ሚሊዮን ፓውንዶች ወርሷል ይላል። በሌላ በኩል ሜጋን ተዋናይት በነበረችበት ወቅት ሱትስ በተሰኘው ተከታታይ ድራማ ላይ ስትተውን በአንድ ክፍል 50 ሺህ ዶላር ይከፈላት እንደነበር ይነገራል። ሜጋን ከዚህ በተጨማሪ 'የላይፍስታይል' መጦመሪያ [ብሎግ] እና ለአንድ የካናዳ ልብስ አምራች የሚሸጥ የፋሽን ዲዛይን አላት። ሌላ የገቢ ምንጫቸው ምንድነው? አሁን ጥንዶቹ ከንጉሣዊው ቤተሰብ ጋር ያላቸው ውል ስለተቀደደ ያሻቸውን ነገር መሥራት ይችላሉ። ጥንዶቹ ከኦፕራ ጋር ያደረጉት ቆይታ በክፍያ አልነበረም። ነገር ግን ኔትፍሊክስና ስፖቲፋይ ከተሰኙት ድርጅቶች ጋር ውል ገብተዋል። እነዚህ ስምምነቶች በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር እንደሚያስገቡላቸው ይታመናል። ሜጋንና ሃሪ አርችዌል የተሰኘ ተቋም አላቸው። ይህ ድርጅት ከአንድ ሌላ የእርዳታ ድርጅት ጋር ይሠራል። ጥንዶቹ ዩናይትድ ኪንግደም እያሉ ጥበቃ ይመድብላቸው ነበር። የጥበቃው ሒሳብ ምን ያክል እንደሆነ አይታወቅም። የካናዳ መንግሥት ለጥንዶቹ የሚያደርገውን ጥበቃ እንደሚያቆም ሲያሳውቅ ነው ሜጋንና ሃሪ ወደ አሜሪካ ያቀኑት። ይሄኔ አሜሪካዊው ቢሊየነር ታይለር ፔሪ እስኪደላደሉ ድረስ መኖሪያ ቤትና ጥበቃ እንዳበረከተላቸው ጥንዶቹ ተናግረዋል። "ለኔ ዋናው ነገር የቤተሰቤን ደህንነት ለመጠበቅ በቂ የሆነ ገንዘብ ማግኘት ነበር" ሲል ሃሪ ለኦፕራ ነግሯታል። ጥንዶቹ የንጉሣዊው ቤተሰብ ኃላፊነት ይብቃን ከማለታቸው በፊት 95 በመቶ የገቢያቸው ምንጭ የሃሪ አባት ልዑል ቻርልስ ነበሩ። ለምሳሌ በፈረንጆቹ 2018-19 ብቻ ለሜጋንና ሃሪ እንዲሁም ለካምብሪጅ ዱክና ደችስ ከ25 ሚሊዮን በላይ ዩሮ ፈሰስ ተደርጓል። ከግብር ከፋዩ የሚገኘው ገቢ ደግሞ 5 በመቶ የሚሆነው ወጪ ይሸንፋል። ጥንዶቹ ከቤተሰቡ በወጡ ጊዜ በታክስ ከፋዩ ገንዘብ አሳደሱት የተባለውን ቤት ወጪ 2.4 ሚሊዮን ዩሮ መመለሳቸው አይዘነጋም። |
news-51993761 | https://www.bbc.com/amharic/news-51993761 | ቻይና ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ያደረገችውን ፍልሚያ በቅርብ የተመለከተው የኢትዮጵያዊው ዶክተር ምልከታ | በቻይና ህክምና ለማጥናት ከአምስት ዓመታት በላይ ቆይቷል። በጥቅሉ በኢትዮጵያና በቻይና ህክምና በማጥናትና በዘርፉ በማገልገልም ጭምር አስር ዓመት ገደማ መቆየቱን ይናገራል። | ዉሃን ከታሕሳስ ወር አጋማሽ ጀምሮ እንቅስቃሴ ተገድቦ ነበር ምንም እንኳ እሱ የሚኖርበት የቻይና ከተማ በኮሮናቫይረስ ከተጠቁት የቻይና አካባቢዎች የተሻለ የሚባለው ቢሆንም መንግሥት በአጠቃላይ የወሰደው እርምጃ ቻይና የቫይረሱን ስርጭት መግታት እንድትችል አድርጓል ይላል። ስሙን መጥቀስ ያልፈለገው ይህ በቻይና የሚሰራው ኢትዮጵያዊ የህክምና ባለሙያ የሆነው ዶክተር የኮሮናቫይረስን ስርጭት በመቆጣጠር በኩል ኢትዮጵያ ከቻይና የምትማረው በርካታ ነገሮች አሉ ብሎ ያምናል። ለዚህም ኅብረተሰቡ እጁን ቶሎ ቶሎ እንዲታጠብ ማሳሰብ፣ የትምህርት ቤቶችን መዘጋት፣ በርካታ ሰው የሚገኝባቸውን ትላልቅ ስብሰባዎች አለመካሄድ ከተካሄዱም በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እውቅና እንዲሆኑ ማድረግና ሌሎችም የኢትዮጵያ መንግሥት በአግባቡ መውሰድና ተፈጻሚ ማድረግ ካለበት ወሳኝ እርምጃዎች መካከል ቀዳሚ መሆናቸውን ይጠቅሳል። ነገር ግን እሱ ቻይና ውስጥ ካስተዋለው ልምድ በመነሳት የኢትዮጵያ መንግሥት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛን መጠቀም ላይ ትኩረት ቢያደርግ ወረርሽኙን ለመከላከል እንደ አንድ ጥሩ አማራች ሊሆን ይችላል ይላል። ምንም እንኳን የዓለም የጤና ድርጅትና የአገራት የጤና ባለስልጣናት ሁሉም ሰው ጭምብል ማድረግ የለበትም ቢሉም እሱ ግን "ሃኪሞች፣ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችና አስታማሚዎች ብቻ ሳይሆኑ ይህን ሰፋ አድርጎ ብዙዎች እንዲጠቀሙ ማድረግ ያስፈልጋል" በማለት ጥቅም እንጂ ጉዳት እንደሌለው ያመለክታል። ዶክተሩ በቅርብ ከተመለከተው ልምዱ በመነሳት እንደሚለው ከሆነ ማኅበራዊ ርቀትን ለመጠበቅ በማያስችሉ ቦታዎች በተለይም በሕዝብ ትራንስፖርት ላይ፣ በገበያዎች፣ ቤተ እምነቶች ውስጥ እንዲሁም በርካታ ሕዝብ በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ላይ የሰዎች ጭንብል መጠቀም የቫይረሱን ስርጭት በተወሰነ መልኩ በመገደብ ረገድ ወሳኝ እንደሆነ በቻይና መመልከቱን ይናገራል። የህክምና ባለሙያው ደጋግሞ በአጽንኦት እንደሚለው ሰዎች በሚበዙባቸው አካባቢዎች ላይ ማስክ ማድረግ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ነገር አይደለም። የሞባይል ስልኮችን ማፅዳት እንዲሁም ሰዎች ከቤት ውጭ ሳሉ የነካኳቸውን ነገሮች ቤት ገብተው ማፅዳትም አስፈላጊ ነው። "ለምሳሌ በእጅ የተነካኩ አትክልቶችን በሚገባ ማጠብ ያስፈልጋል። ምንም እንኳ እጃችንን ብንታጠብም እንደ ስልክ ያሉ ነገሮችን ስንነካ መልሶ ያው ይሆናል።" በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የተገኙባቸው አካባቢዎችን ይፋ ማድረግና አካባቢው ላይ ያሉ ሰዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማድረግ ቻይና የተከተለችው አንድ መንገድ ነው። ይህን ማድረግ ምናልባትም በኢትዮጵያ ማግለል እና ሌሎች ያልተገቡ ነገሮችን ሊያስከትል ቢችልም ይህ ተገቢ እንዳልሆነ አስገንዝቦ ሰዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ መረጃውን መስጠት ይጠቅማል ይላል። • ልናውቃቸው የሚገቡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዝርዝር ይዘቶች • ኢትዮጵያ ከኮሮናቫይረስ ምጣኔ ሐብታዊ ጫና ትተርፋለች? የኮሮናቫይረስ ህሙማንን የሚያክሙ የህክምና ባለሙያዎች በየቀኑ ወደቤታቸውን ከሚመላለሱ ይልቅ በሚሰሩበት ሆስፒታል ወይም ቅርብ አካባቢ ጊዜያዊ መቆያ ቢዘጋጅላቸው በብዙ መልኩ መልካም እንደሆነም በመግለጽ፣ "የአገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ይህን እየሰራበት እንደሚሆን አምናለሁ" በማለት፤ ይህ በኅብረተሰቡ ውስጥ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት እንደሚረዳ ይጠቅሳል። ከጣልያን ጋር በማነፃፀር ቻይና እጅግ በሚያስገርም መልኩ የቫይረሱን ስርጭት ተቆጣጥራዋለች የሚሉት ባለሙያው የተያዙ ሰዎች የመሞት እድልም አነስተኛ እንደሆነ ይገልጻል፤ ባለሙያው አክሎም ምንም እንኳ በቻይና በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ቢሆንም የሟቾች ቁጥር ግን ትንሽ የሚባል አንደሆነ ያስረዳል። በበሽታው የተጠረጠሩ ወይም ቫይረሱ ካለባቸው ጋር ግንኙነት ነበራቸው በሚል ተለይተው እንዲቀመጡ የተደረጉ ሰዎችን በተመለከተም እነዚህ ሰዎች በሙሉ ቫይረሱ ላይገኝባቸው ስለሚችል አንድ ቦታ ላይ እንዲቆዩ ሲደረግ በኋላ ላይ በምርመራ ሊገኝ የሚችለውን ውጤት ታሳቢ በማድረግ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ ይገልፃል። በበሽታው ስጋት ሳቢያ ራሳቸውን አግልለው የሚቆዩ ሰዎች ንፅህናን መጠበቅና አስፈላጊውን ሁሉ ጥንቃቄ ማድረግ የሚገባቸው ሲሆን መንግሥትም እነዚህ ሰዎች የሚከታተልበት የራሱ ሥርዓት ሊኖረው ይገባል ሲል ይመክራል። ለዚህም በምሳሌነት የጠቀሰው ቀደም ብለው "ከቻይና ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱ ተማሪዎች ሌሎችን ለመጠበቅ ሲሉ በራሳቸው ወጪ እንግዳ ማረፊያ ይዘው ራሳቸውን አግልለው የቆዩበት መንገድ የሚመሰግን ነው" በማለት አንስቷቸዋል። • ስለኮሮናቫይረስ ሐሰተኛ መረጃ እንዳይስፋፋ ምን ልናደርግ እንችላለን? በረራዎችን በሚመለከት ማንኛውም ወደ አገር የሚገባ መንገደኛ ራሱን አግልሎ እንዲቆይ መደረጉ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ወሳኝ እርምጃ መሆኑን የሚጠቅሰው ይህ የህክምና ባለሙያ፤ ከመንገደኞች ጋር ግንኙነት ያላቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞች ጭንብል ማድረግ እንደሚያስፈልጋቸው ያምናል። በእምነት ተቋማት ላይም የበሽታውን መስፋፋት ለመግታት ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበት የሚያሳስበው ባለሙያው፤ በደቡብ ኮሪያ በአንድ ቤተ እምነት ውስጥ በሚሰባሰቡ ሰዎች መካከል ወረርሽኙ በመዛመቱ ብዙዎች በቫይረሱ መያዛቸውንና ለሞትም የተዳረጉ መኖራቸውን በመጥቀስ ቤተ እምነቶች ላይ ትልቅ ሥራ እንዲሰራ፤ ቁጥጥርም እንዲደረግ ያሳስባል። ዉሃን ከታሕሳስ ወር አጋማሽ ጀምሮ እንቅስቃሴ ተገድቦ ነበር በአገር ውስጥ ሊኖር የሚችለውን የአስፈላጊ ነገሮችን እጥረት በማሰብም በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እንደ የፊት መሸፈኛ ጭንብል እና ሳኒታይዘርን የመሳሰሉ ነገሮችን ቢለግሱ የበሽታውን መስፋፋት ለመግታት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ትልቅ አስተዋፅዖ ነው ይላል። ጭንብል ማድረግ አስፈላጊ በሆኑባቸው ቦታዎች ላይ የማግኘት ችግር ቢኖር እንኳን እንደ ስካርፍ ባሉ አልባሳት አፍና አፍንጫን መሸፈን ከምንም እንደሚሻል ባለሙያው ይመክራል። ስለዚህ በዚህ ወቅት "ጉንፋን እንኳን ላለመያዝ እያንዳንዱ ሰው ጥረት ማድረግ ይኖርበታል።" ባለሙያው እንደሚለው ቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ ተቀስቅሶባቸው በነበሩ አካባቢዎች ላይ መደበኛ የህክምና ባለሙያዎች እና ባህላዊ ህክምና ባለሙያዎች አንድ ላይ ያደረጉት ርብርብ ቻይና የቫይረሱን ስርጭት በሚገባ እንድትቆጣጠር ረድቷል ብሎ ያምናል። በተጨማሪም የህክምና ባለሙያዎች ችግሩ የእኔ ነው በሚል መንፈስ በትጋት መስራታቸውና ኅብረተሰቡም የሚተላለፍለትን ማሳሰቢያ ያለ አንዳች ቸልተኝነት መፈፀሙ እንዲሁም የአገሪቱ መንግሥት ኃላፊነቱን በትጋት መወጣቱ ቻይናን እንደታደጋት ይገልፃል። |
44598670 | https://www.bbc.com/amharic/44598670 | የኤርትራ ልዑካን ቡድን አባላት አዲስ አበባ ደርሰዋል | በኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳልሕና የፕሬዝዳንቱ አማካሪ በሆኑት የማነ ገብረ አብ የሚመራው ከፍተኛ የልዑካን ቡድን አዲስ አበባ ገብተዋል። | የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳልሕ እና የፕሬዝዳንቱ አማካሪ የሆኑት የማነ ገብረ አብ በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል ሲደረግላቸው ለልኡካን ቡድኑ በቦሌ አየር ማረፊያ በመገኘት አቀባበል ያደረጉላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)፣ ምክትል ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ፣ የኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር የሆኑት አቶ አህመድ ሽዴና አርከበ ዕቁባይ (ዶ/ር) ናቸው። የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ባለፈው ሳምንት በኤርትራ ቴሌቪዥን የሰማዕታት ቀንን አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር ስለአገራቱ የወደፊት ጉዞ የሚመክር አንድ የልዑካን ቡድን ወደ አዲስ አበባ እንደሚልኩ መግለፃቸው ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ መለስ አለም አርብ ዕለት በሰጡት መግለጫ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የሚኖር ሰላም ከሁለቱ አገራት ባለፈ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት በጣም ጠቃሚ እንደሆነ "ፋይዳው ከክልሉ በላይ ነው" በማለት ነበር የተናገሩት። ጨምረውም በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ለኤርትራ ልዑካን አቀባበል ለማድረግ ዝግጅት እንደሚኖር ተናግረው ነበር። ፕሬዚዳንት ኢሳያስ የሰማዕታት ቀንን አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር ላይ እንደገለፁት የልዑካን ቡድኖቹ ወደ አዲስ አበባ የሚያቀኑት ጉዳዩን በቀጥታና በጥልቀት ለማወቅና ቀጣይ የስራ እቅድ ለማውጣት እንደሆነም ጨምረው ተናግረዋል። የኤርትራን የልዑካን ቡድን ለመቀበል በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ የነበረው ድባብ ይህን ይመስላል። የግል እና የመንግሥት ሚዲያ ተቋማት ባለሙያዎች በቦሌ አየር ማረፊያ የሃይማኖት አባቶች የኤርትራ ልዑካን ቡድንን ለመቀበል በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ይገኛሉ |
49123865 | https://www.bbc.com/amharic/49123865 | ቻይናዊቷ የ118 ልጆች የጉዲፈቻ እናት የ20 ዓመት እሥር ተፈረደባት | 118 ልጆች በጉዲፈቻ በማሳደግ ስትሞገስ የነበረችው ቻይናዊ ሴት የ20 ዓመት እሥር ተፈረደባት። የ54 ዓመቷ ሊ ያንዢያ፤ ገንዘብ በማጭበርበር፣ በማታለል፣ ሀሰተኛ ሰነድ በመሥራትና ማኅበራዊ ሥርዓትን በማወክ ጥፋተኛ ተብላለች። 388,000 ዶላር ቅጣትም ተጥሎባታል | በአንድ ወቅት "የፍቅር እናት" በሚል ቅጽል ስም ትጠራ የነበረችው ሊ፤ የህጻናት ማሳደጊያ ነበራት። ከሷ በተጨማሪ የወንድ ጓደኛዋን ጨምሮ 15 ተባባሪዎቿም ጥፋተኛ ተብለዋል። • በባርነት ከመሸጥ የተረፉት 64 ኢትዮጵያዊያን • ኢትዮጵያ ወደ አውሮፓና እስያ ሠራተኞችን ልትልክ ነው • "እናቴ ካልመጣች አልመረቅም" ኢዛና ሐዲስ ከማንችስተር ዩኒቨርስቲ ከግብረ አበሮቿ ጋር በመሆን የህጻናት ማሳደጊያውን ጠቀም ያለ ገንዘብ ለማግኘት እንዳዋለችው ፍርድ ቤቱ ተናግሯል። የወንድ ጓደኛዋ ዡ ኪ 12 ዓመት እሥራት የተፈረደበት ሲሆን፤ ሌሎቹ ተባባሪዎቿ እስከ አራት ዓመት የሚደርስ እሥራት ይጠብቃቸዋል። "የፍቅር እናት" ማናት? ሊ ያንዢያ ዝነኛ የሆነችው በቻይና ሀይቤይ ግዛት በምትገኝ ውዋን በምትባል አነስተኛ ከተማ ውስጥ በርካታ ልጆች በጉዲፈቻ መውሰድ ስትጀምር ነበር። የቀድሞ ባለቤቷ ልጃቸውን ለሕገ ወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች እንደሸጠው ለመገናኛ ብዙሀን ተናግራ ነበር። ልጇን ካስመለሰች በኋላ ሌሎች ህጻናትንም ለመርዳት እንደወሰነችም ገልጻ ነበር። በጊዜ ሂደት በትውልድ ቀዬዋ ውዋን የናጠጠች ሀብታም ሆነች። እንደጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ1990ዎቹ አጋማሽ ላይ በማዕድን አውጪ ድርጅት ኢንቨስት ካደረገች በኋላ የድርጅቱ ባለቤት ሆናለች። "አምስት ወይም ስድስት ዓመት የሚሆናት ልጅ በማዕድን ቁፋሮው አካባቢ ስትሯሯጥ እመለከት ነበር። አባቷ ሞቷል፤ እናቷ ኮብልላለች፤ ስለዚህም ልጅቷን ለማሳደግ ወሰንኩ። በጉዲፈቻ የወሰድኳት የመጀመሪያ ልድ እሷ ናት" በማለት ለአንድ ጋዜጣ ቃሏን ሰጥታ ነበር። • ደኢሕዴን የሐዋሳና የሲዳማ ዞን አመራሮችን አገደ • የቱኒዚያ ፕሬዝዳንት በ92 ዓመታቸው አረፉ ብዙ ልጆችን በማደጎ ከወሰደች በኋላ "የፍቅር መንደር" የተባለ የህጻናት ማሳደጊያ ከፈተች። የቻይና መገናኛ ብዙሀን በተደጋጋሚ ሽፋን ሰጥተዋታል። ካንሰር ይዟት እንደነበረም ተነግሮ ነበር። 2017 ላይ "አንዳች የሚያጠራጥር እንቅስቃሴ አይተናል" ያሉ ግለሰቦች ለፖሊስ ጥቆማ አደረሱ። ፖሊስ 20,000 ዶላር ተቀማጭ ገንዘብ፣ ላንድ ሮቨርና መርሰዲስ ቤንዝ እንዳላት 2018 ላይ ደርሶበታል። ከ2011 አንስቶ ሕገ ወጥ ተግባሮች እንደፈጸመችም ታውቋል። የጉዲፈቻ ልጆቿ ላይ ብዝበዛ ታደርስ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን፤ አንዳንዶቹ ልጆች ሆነ ብላ የግንባታ ሥራ እንዲያስተጓጉሉ ካደረገች በኋላ የግንባታ ተቋራጮች እንዲከፍሏት ታስገድድ ነበር። "የፍቅር መንደር" የተባለውን የህጻናት ማሳደጊያ ለመገንባት በሚል በርካታ ገንዘብ አጭበርብራለች። በቁጥጥር ሥር በዋለችበት ወቅት ማሳደጊያው ውስጥ የተገኙት 74 ልጆች ብቻ ነበሩ። ልጆቹ ወደተለያዩ የመንግሥት ተቋሞችና ትምህርት መስጫዎች ተወስደዋል። ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ "የበግ ለምድ የለበሰች ነብር" ሲሉ ብዙዎች አውግዘዋታል። ዊቡ በተባለው የቻይና ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ከተሰጡ አስተያየቶች አንዱ "አጎቴ ለህጻናት ማሳደጊያዋ ድጎማ አድርጎ ነበር፤ በጣም አሳፋሪ ናት" ይላል። "በአንድ ወቅት 'የፍቅር እናት' ብዬ መጥራቴ ይጸጽተኛል። ስለ ፍቅር የምታውቀው ነገር የለም። ስሙም አይገባትም" በማለት የወቀሳት ግለሰብም ነበር። |
news-47702924 | https://www.bbc.com/amharic/news-47702924 | ቻይና 300 የኤርባስ አውሮፕላኖችን ልትገዛ ነው | ቻይና ኤርባስ ከተሰኘው አውሮፕላን አምራች ኩባንያ 300 አውሮፕላኖችን ለመግዛት ውል ፈፀመች። ግዥው 30 ቢሊዮን ዩሮ የሚገመት ነው። | የግዥው ውል የተፈፀመው የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂፒንግ ፓሪስን በጎበኙበት ወቅት ሲሆን ግዥው ባለፈው ሳምንት ፕሬዚዳንቱ አውሮፓን በጎበኙበት ወቅት ያደረጓቸው ስምምነቶች አካል ነው። ኤርባስ ይህን የመሰለ የሽያጭ ውል ያደረገው ሁለቱን ከባድ አደጋዎች ተከትሎ ተፎካካሪው ቦይንግ 737-8 ማክስ አውሮፕላኖቹን ከአገልግሎት ውጭ ባደረገ ማግስት ነው። • ለ60 ዓመታት የዘለቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድና የቦይንግ ግንኙነት ብዙ አገራት 737-8 ማክስ አውሮፕላኖቹ በአየር ክልላቸው እንዳይበር ላገዱበትና አጣብቂኝ ውስጥ ለገባው ቦይንግ ይህ የኤርባስ የግዥ ውል ዱብ እዳ እንደሚሆን እየተገለፀ ነው። የቻይና አቪዬሽን አቅርቦት ከኤርባስ ከሚገዛቸው ውስጥ 290 እና A320 አውሮፕላኖች እንዲሁም ዐሥር A350 XWB ጀቶች እንደሚገኙበት ታውቋል። የኤርባስ የንግድ አውሮፕላኖች ሽያጭ ዘርፍ ፕሬዝዳንት ጉይላም ፋውሪ ግዥውን በማስመልከት "ዘመናዊ በሆኑ አውሮፕላኖቻችን የቻይና ሲቪል አቪዬሽንን እድገት መደገፍ በመቻላችን ክብር ይሰማናል" ብለዋል። ይህ ከቻይና ጋር የፈፀሙት የግዥ ውል በቻይና ገበያ ላይ ያላቸውን መተማመን እንዲሁም እንደ ቻይና ላሉ አጋሮች ያላቸውን የአገልጋይነት ፅናት ደረጃ የሚያሳይ እንደሆነም ገልፀዋል። • ቦይንግ 737-8 ማክስ አውሮፕላኖቹ በሙሉ እስከ ግንቦት እግድ ተጣለባቸው |
news-47744591 | https://www.bbc.com/amharic/news-47744591 | አምስት ጉዳዮች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ | ኢትዮጵያን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የማስተዳደር መንበርን ከተረከቡ አንድ ዓመትን ሊደፍኑ ጥቂት ቀናት የቀራቸው ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በስልጣን ቆይታቸው ሁለተኛ የሆነውን ጋዜጣዊ መግለጫ ትናንት በጽህፈት ቤታቸው ሰጥተዋል። | ባለፉት ወራት በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች አነጋጋሪ ጉዳዮች በተከሰቱባቸው አጋጣሚዎች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካልሆነም በተለያዩ ስብሰባዎች ባገኙት አጋጣሚ በሕብረተሰቡ ለሚነሱ የተወሰኑ ጥያቄዎችና ጉዳዮች ውስን መልስና ማብራሪያ ሲሰጡ ቆይተዋል። በዚህም ምክንያት ከተለያዩ ወገኖች ትችት ሲሰነዘርባቸው ቆይቷል። ስለዚህም ይመስላል ለሁለተኛ ጊዜ በጠሩት ጋዜጣዊ ጉባኤ ላይ በርካታ ጉዳዮች ተነስተው ሰዓታት የወሰደ መብራሪያ የሰጡት። በመግለጫው ላይ የትኞቹ ቁልፍ ጉዳዮች ተነሱ? የአዲስ አበባ ባለቤትነት ጉዳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ሲጀምሩ አዲስ አበባ የእኛ ናት የሚል ክርክር በስፋት ይነሳል ነገር ግን አዲስ አበባ የሁላችን ናት፤ በመሠረቱ አዲስ አበባ የማን ናት የሚል ጥያቄ በእኛ ደረጃ አንስቶ መወያየት አሳፋሪ ነው ሲሉ ተናግረዋል። አዲስ አበባ የማን ናት? የማን አይደለችም? እያሉ የሚከራከሩ ሰዎች ከጭንቅላታቸው ጀርባ ምን አስቀምጠው ነው የሚነጋገሩት የሚለውን በራሳቸው አውድ መመልከት ያስፈልጋል፤ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ምን ታስቦ ነው የማናት የሚባለው? አዲስ አበባ የእኔ ናት ስል የአንተ አይደለችም ማለት ከሆነ ስቼያለሁ። የእኔ ሆና የአንተ እንዳልሆነች የምናገር ከሆነ ስህተት ነው፡፡ አዲስ አበባ የሁላችንም ናት። • ዐብይ አሕመድ ለኖቤል ሽልማት ታጭተዋል? የፌደራል ሥርዓቱ ሲዋቀር አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል ውስጥ ስለምትገኝ የኦሮሚያ አካል የማድረግ ፍላጎት ነበረ፤ በሌላ በኩል ደግሞ የቻርተርድ ፌደራል ከተማ መሆን አለባት ነገር ግን በዙሪያዋ ካለው አካባቢ ጋር ባላት ግንኙነት የተነሳ ክልሉ ልዩ ጥቅም ማግኘት አለበት የሚል በሕገ መንግሥቱ ተቀምጧል። የኢትዮጵያ ፖለቲካ አሁን ባለበት አቅጣጫ በትክክለኛ መንገድ እንዳይሄድ በአልባሌ ጉዳይ ጊዜ እንድናባክን የሚፈልጉ ሰዎች ናቸው ይህንን ሐሳብ የሚያንሸራሽሩት። ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ይህ አጀንዳ ሊሆን አይችልም። አዲስ አበባ የእኛ ናት ስንል መነሻችን ምንድነው? የዛሬ 20 ዓመት በአዲስ አበባ የአሁኑን ያህል ሰው አልነበረም፤ አዲስ አበባ ከፍቶትም ሆነ ተደስቶ የመጣውን ኢትዮጵያዊና የውጭ አገር ዜጎች አቅፋና ተሸክማ ኖራለች። ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ያላት ልዩ ጥቅም ሕገ መንግሥታዊ በመሆኑ፣ እንዴት ይተግበር የሚለው ላይ የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ክልል አስተዳደሮች በጋራ መምከር አለባቸው። በሕገ መንግሥቱ የተቀመጠው የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ላይ ያለው የልዩ ጥቅም መብት ግን ሊረጋገጥ ይገባል፤ የሚለውን ሀሳብ ኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ሰው ሊደግፈው የሚገባ ነው። • የዶክተር ዐብይ አሕመድ ፊልም ለኦሮሚያ ክልልም በሕገ መንግሥቱ የተሰጡ መብቶች ሲባሉ አላግባብ ከአዲስ አበባ እድገትና መስፋፋት ጋር ከኢንዱሰትሪዎች መስፋፋት ጋር ተያይዞ የሚወጡ በካይ ፍሳሾች የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞንን የሚጎዱ መሆን የለባቸውም እና የተለያዩ የመሰረተ ልማት ሥራዎችም ተጠቃሚ መሆን ይገባቸዋል በሚል እንጂ አንድ ኦሮሞ አዲስ አበባ ላይ ከሌሎች በተለየ መልኩ መብት አለው ማለት አይደለም ብለዋል። የኦሮሚያ ክልል በሚያቀርበው ግብዓት ልክ ይጠቀም የሚል ሀሳብ ሊነሳ ይገባል። 170 ሺህ ቤተሰቦች በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚከናወኑ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች መፈናቀላቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እነዚህን ዜጎች መርዳት ያስፈልጋል። መንግሥት ተዳክሟል የፌደራል መንግሥት ተዳክሟል ለማለት መለኪያው መሆን ያለበት ሀገር ስትወረር መመከት ሲያቅተው ዲፕሎማሲያዊ ሥራዎችን በብቃት መስራት አልችል ሲል ነው። አሁን ግን በዚህ መልኩ የሚገለፅ አንዳችም ተግዳሮት አልገጠመንም በክልሎች የሚፈጠሩ ችግሮች ላይ ጣልቃ የማንገባው ክልሎች በራሳቸው መፍታት አለባቸው ብለን ስለምናምን ነው፤ ይህ ደግሞ ተገቢ ነው። ኢህአዴግ ኢህአዴግ የቀድሞ ጥምረቱ አለ፤ ብዙዎች የተለያየን የሚመስላቸው የልዩነት ሀሳቦች ሲኖሩ አራቱ ፓርቲዎች በውስጣዊ ውይይት ብቻ ይገድቡት የነበረው ሂደት ቀርቶ ፓርቲዎቹ የልዩነት አቋማቸውን በአደባባይ መግለፃቸው ነው ጥምረቱ የሌለ የሚያስመስለው። • የዶክተር ዐብይ አሕመድ 'ፑሽ አፕ' በኦዲፒና በአዴፓ እንዲሁም በኦዲፒ በራሱ ውስጥ አንድነት እንጂ ምንም አይነት የተለየ ነገር የለም። ነገር ግን በመካከላቸው የልዩነት ሀሳቦች ይኖራሉ እነሱንም በመነጋገር እየፈታን ነው በገዢው ፓርቲ አባላት መካከል የተጀመረው መቀራረብ ተጠናክሮ ይበልጥ ወደ አንድ ለመወሃድ የጀመርነው ሂደትም ይቀጥላል። ኢኮኖሚ ከለውጡ በኋላ በኢኮኖሚው ላይ በሚፈለገው መጠን ውጤቶች ያልታዩት ችግር ውስጥ ሆኖ ስለተቀበልን ነው። እሱን የማስተካከል ሥራ እየሰራን ቆይተናል። በዚህም በርካታ ሀገራት ድጋፍ ስላደረጉ ውጤት ማግኘት ተችሏል። አሁን ላይ ኢኮኖሚው ከታመመበት ሁኔታ ወጥቶ ጤናማ ሆኗል። የሕግ የበላይነትን ከማስከበር ከዚህ በፊት መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማስከበር የሚወስዳቸው ጠንከር ያሉ እርምጃዎች ከሰብዓዊ መብት አንፃር ጥያቄ የሚያስነሱ ነበሩ፤ መንግሥት ይህን ከሰብዓዊ መብት ጥሰት አንፃር ተገቢ ያልነበሩ እርምጃዎችን ሲወስድ ህግ አስከበረ ሲባል እንደነበረና አሁን ግን ያ ዓይነት አሰራር ትክክል እንዳልሆነ በመረዳት በለውጡ ውስጥ ማሻሻያዎች እየተደረጉ በመሆኑ ሕግን በተከተለ መልኩ የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ ናቸው። በርካታ የፖለቲካ ሁነቶች የነበሩበት፣ በርካቶች ተስፋ የሰነቁበት፣ ሌሎች ደግሞ በፖለቲካ ሁኔታው ግራ መጋባት ውስጥ የገቡበት ነበር። • በ2018 ጎልተው የታዩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከዚህ ባለፈ በርከት ያሉ የዲፕሎማሲ ስኬቶች የተገኙበት ነበር። ይህም ከጎረቤት ሀገራት ጀምሮ ከሌሎች በርካታ ሀገራት ጋር የተከናወነውን የዲፕሎማሲ ሥራ በማንሳት ለውጡን ከገንዘብ ጀምሮ በሀሳብና በባለሙያዎች የደገፉበት እንደነበር ገልፀዋል። የመገናኛ ብዙሃንም ይህንን ኃላፊነታቸውን በመወጣት ኢትዮጵያን እንደ ኢትዮጵያ ለማስቀጠል የሚያስችሉ እና ወደ ከፍታ የሚያሸጋገሩ የተለያዩ ሀሳቦችን በማንሸራሸር ፅንፍ የያዙ የፖለቲካ ሀሳቦችን የሚያቀራርቡ መድረኮችን በመፍጠር የሃሳብ ልዩነትን የሚያስታርቅ እድልን ማመቻቸት አለባቸው። |
46905225 | https://www.bbc.com/amharic/46905225 | በኢትዮጵያ የሚጠለሉ ስደተኞች የመማርና የመሥራት መብት ሊኖራቸው ነው | የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ጥር 9፣ 2011 ዓ. ም. ማለዳ ባደረገው አስራ ዘጠነኛ መደበኛ ስብሰባ፤ የስደተኞች ጉዳይ ረቂቅ አዋጅን በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል። | የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዋጁ በተለያየ ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ ስደተኞች ልዩ ልዩ መብቶችን በማጎናፀፍ፤ ኢትዮጵያ ለምታስተናግዳቸው ስደተኞች የምታደርገውን እንክባካቤ ያስቀጥላል ተብሏል። አዋጁ በሦስት ተቃውሞና በአንድ ተዓቅቦ ፀድቋል። • እስራኤል አፍሪካዊያን ስደተኞች እንዲወጡ አዘዘች • ስደተኞች በየዓመቱ 8 ቢሊዮን ዶላር ለቤተሰቦቻቸው ይልካሉ በአዋጁ መሠረት ዕውቅና ያገኙ ስደተኞች ከመንቀሳቀስ መብት በተጨማሪ ትምህርትና ሥራ የማግኘት መብት ይኖራቸዋል። ኢትዮጵያ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች የሚገኙባት ስትሆን፤ ይህም በርካታ ስደተኞችን ከተቀበሉ የአፍሪካ አገራት ከቀዳሚዎቹ ተርታ ያስመደባታል። "በኢትዮጵያዊያን ሥራ ፈላጊዎች ላይ ተጨማሪ ፈተና ይደቅናል። ስደተኞችን የሚያስተናዱ የክልል መንግሥታት አልተማከሩበትም" የሚሉ ነቀፌታዎችን አዋጁ ላይ የሰነዘሩ የሕዝብ እንደራሴዎች ነበሩ። • የሰሀራ በረሐን በክራች ያቋረጡት ስደተኞች • በካሌ ስደተኞች ጣቢያ በተነሳ ግጭት ኤርትራውያን ስደተኞች ጉዳት ደረሰባቸው አዋጁን የተመለከተ ማብራሪያ ሲሰጡ የነበሩት የሕግ፣ የፍትሕ እና ዲሞክራሲ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፎዚያ አሚን፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ወኪል በመሆኑ፤ በጉዳዩ ላይ መወያየቱ የሕዝቦችን ድምፅ እንዳስተናገደ እንደሚቆጠር ተናግረዋል። በተጨማሪም በረቂቅ አዋጁ ላይ ሕዝባዊ ምክክሮች መደረጋቸውን አስረድተዋል። በአዋጁ መሠረት፤ ስደተኞች ለውጭ አገር ዜጎች የተፈቀዱ የሥራ መስኮች ላይ የመሰማራት ዕድል የሚኖራቸው ሲሆን፤ ይህም የኢትዮጵያዊያንን ዕድል የሚነጥቅ ሳይሆን ክፍተትን የሚሞላ ይሆናል ተብሏል። ከማርቀቅ እስከ ማስፀደቅ ከሁለት ዓመታት በላይ ጊዜ ወስዷል የተባለው አዋጅ፤ በዓለም አቀፍ ትብብር በሚቀረፁ ላይ ሰባ መቶ የሚሆነውን ድርሻ ኢትዮጵያዊያን እንዲይዙት ተደርጎ፤ የቀረውን ብቃት ባላቸው ስደተኞች እንዲያዝ የሚያስችል ይሆናል። ለስደተኞች ክፍት ይሆናሉ ተብለው ከሚጠበቁት እና ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ አጋሮቿ ጋር በጋራ ከምትከውናቸው ፕሮጀክቶች መካከል የኢንዱስትሪ ፓርኮች እና የመስኖ ልማቶች ይገኙበታል። |
42248089 | https://www.bbc.com/amharic/42248089 | አሁንም ኢትዮጵያ ዜጎቿን በመሰለል ተከሳለች | የኢትዮጵያ መንግሥት የገዛ ዜጎቹ ላያ የበይነ መረብ (ኢንተርኔት) ስለላ እያደረገ ነው ሲል ሂዩማን ራይትስ ዎች የተሰኘው የመብት ተሟጋች ድርጅት ወቀሰ። | የፖለቲካ መብት ተሟጋቾች እና ነፃ ድምፆች ላይ የሚያደርገውን ስለላም እንዲያቆም ድርጅቱ አሳስቧል። ኅዳር 27/2010 የወጣው ሪፖርት እንደሚያሳየው የኢትዮጵያ መንግሥት የፖለቲካ መብት ተሟጋቾችና ተቃዋሚ አካላት ላይ ስለላ እያደረገ እንደሆነ መቀመጫውን ቶሮንቶ ያደረገ 'ሲትዝን ላብ' የተሰኘ የቴክኖሎጂ ተቋምን ጠቅሶ ድርጅቱ ዘግቧል። የኢትዮጵያ መንግሥት መሰል ትችቶች ሲቀርቡበት የመጀመሪያው ባይሆንም አሁን ላይ ግን ስለላውን እጅግ አጠናክሮ ቀጥሏል ይላል ሪፖርቱ። "የኢትዮጵያ መንግሥት ሃሳቡን የሚተቹ ዜጎች ላይ በየትኛውም የዓለም ክፍል ይሁኑ ስለላ ከማድረግ አልተቆጠበም" ሲሉ የሂዩማን ራይትስ ዎች ከፍተኛ አጥኚ ሲንቲያ ዎንግ ይናገራሉ። "መሰል ስለላዎች የሰዎችን ሃሳብ የመግልፅ ነፃነት፣ ግላዊነት እንዲሁም የዲጂታል ደህንነት ይፈታተናሉ" ሲሉ ያክላሉ አጥኚዋ። ከ2016 ጀምሮ ሲደረግ የነበረው ጥናት እንደሚጠቁመው ስለላው በርካታ የፖለቲካ መብት ተከራካሪዎችን ዒላማ ያደረገ ሲሆን በተለይ ደግሞ የኦሮሞ መብት ተሟጋቾች የስለላው ትልቅ አካል መሆናቸውን ድርጅቱ ያስታውቃል። ከእነዚህም መካከል መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው የኦሮሚያ ሚድያ ኔትዎርክ ኃላፊ ጃዋር መሐመድ አንዱ መሆኑ ታውቋል። የኦሮሚያ ሚድያ ኔትዎርክን ለማገድ ብዙ ሙከራዎችን ማድረጉን ያወሳው ሪፖርት የኢትዮጵያ መንግሥት ዜጎቹ መረጃ እንዳያገኙ እገዳ እያደረገ ነው ሲል ይወቅሳል። የስለላው ተጠቂዎች በኤሌክትሮኒክ የመልዕክት መላላኪያ አድራሻቸው (ኢሜይል) በኮምፒውተራቸው ላይ የሚጫን ሶፍትዌር በመላክ የሰዎቹን የግል መልዕክት ማየት የሚያስችል ቫይረስ ተልኮላቸዋል። ሶፍትዌሩን ኮምፒዩተራቸው ላይ የጫኑ ግለሰቦች የቫይረሱ ተጠቂ ሆነው የተገኙ ሲሆን፤ እነዚህም አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ኤርትራ፣ ካናዳና ጀርመንን ጨምሮ በሃያ ሃገራት ያሉ ኢትዮጰያውያን መሆናቸውም ታውቋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ስለላውን ያከናወነው ከሃገር ቤትና መሠረቱን እስራኤል ካደረገ የሳይበር ደህንነት ኩባንያ ጋር በትብብር በመሆን እንደሆነም ታውቋል። 'ሳይበርቢት' የተሰኘው የእስራኤል ኩባንያው 'ኤልቢት ሲስተምስ' የተባለ ድርጅት አካል መሆኑም ተዘግቧል። በስለላው ተጠቂ የሆኑ ግለሰቦች በኮምፒውተራቸው የሚያከናውኗቸውን ማንኛውም ዓይነት ተግባራትን የኢትዮጵያ መንግሥት መከታተል የሚችል ሲሆን ከዚህ አልፎም የኮምፒውተሩን ካሜራ በመጠቀም ቀጥታ ስለላ እንደሚያደርግም ድርጅቱ አጋልጧል። ቴክኖሎጂው ወንጀልን በተለይ ደግሞ ሽብርተኝነት ለመከላከል ተብሎ የተፈበረከ እንደሆነ ታውቋል። ከአውሮፓውያኑ 2013 ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግሥት መሰል ስለላዎችን ሲያከናውን ለሶስተኛ ጊዜ መሆኑን ደርጅቱ አስታውሷል። ከዚህ በፊት ሂዩማን ራይትስ ዎችና 'ሲትዝን ላብ' የኢትዮጵያ መንግሥት ከጣልያን፣ እንግሊዝና ጀርመን ድርጅቶች ጋር በመተባበር ስለላዎችን ማከናወኑን ገልጿል። ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን ካዛኪስታን፣ ናይጄሪያ፣ ፊሊፒንስ፣ ሩዋንዳ ቬትናምና ዛምቢያም መሰል ስለላዎችን በማከናወን ድርጊት ተኮንነዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት በዚህ ብቻ ሳይወሰን የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚዎችንም እየሰለለ እንዳለ ያወሳው ሪፖርቱ ድርጊቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነው ሲል ይኮንናል። የፖለቲካ መብት ተሟጋቾች የሚያደርጉትን የስልክ ንግግር በመቅረፅና በምርመራ ወቅት በመጠቀም እንደ አፍ ማዘጊያ እየተጠቀመው ነው ሲልም ይወቅሳል። ምንም እንኳ መሰል ቴክኖሎጂ የሚያመርቱ ድርጅቶች ከመንግሥታት ጋር ሽብርተኝተን ለመዋጋት እንደሚሰሩ ቢታወቅም የኢትዮጵያ መንግሥት ግን መሣሪያውን ተቃዋሚዎችን ለመስለል እየተጠቀመበት ነው፤ ጋዜጠኞችን፣ ጦማሪዎችን፣ እንዲሁም ተሟጋቾችን እያስፈራራበት ነው ባይ ነው ሪፖርቱ። መንግሥት የግል ጋዜጦችን ከገበያው ገሸሽ ማድረጉን ተከትሎ ከ2010 ጀምሮ ቢያንስ 85 ጋዜጠኞች ሃገራቸውን ጥለው እንደተሰደዱ ድርጅቱ ያትታል። ሂዩማን ራይትስ ዎች የሲትዝን ላብን ጥናት አጣቅሶ ሳይበርቢት የተሰኘው ድርጅት በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጥና መሰል ድርጊቶች ሲፈፀሙ ቀጣዩ እርምጃ ምን እንደሆነ እንዲያሳውቅ መጠየቁን ዘግቧል። ሳይበርቢት ቴክኖሎጂውን ለመንግሥታት ብቻ የሚሸጥ ሲሆን ሽያጩን ሲፈፀም ከሚመለከተው ከፍተኛ የመንግሥት አካል ፊርማ እንደሚጠይቅም አስታውቋል። ሳይበርቢት በጉዳዩ ዙሪያ እንዲሰጥ ለተጠቀው አስተያየት ምላሽ ሲሰጥ ድርጊቱ መፈፀም አለመፈፀሙን አለማረጋገጡን አስታውቆ አስፈላጊውን ምርመራና እርምጃ ለመውሰድ ግን ዝግጁ መሆኑን ተናግሯል። እርምጃው ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ውሉን እስከሟቋረጥና ድርጊቱ ከተፈፀመ ደግሞ በይፋ ለሕዝብ ማሳወቅን ሊያካትት እንደሚችል ጠቁሟል። ሂዩማን ራይትስ ዎች እስራኤልን የመሰሉ ሃገራት ድርጅቶቻቸው መሰል ቴክኖሎጂዎችን ለሃገራት ሲሸጥ አስፈላጊው ምርመራ እንዲካሄድ በተለይ ደግሞ የሰብዓዊ መበት ጥሰት አለመፈፀሙን ማረጋገጥ እንዳለባቸው ይጠቁማል። "የእስራኤል መንግሥት እያወቀ ሳይበርቢት የተሰኘው ኩባንያ ኢትዮጵያን ለመሰሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለሚያከናውኑ ሃገራት ቴክኖሎጂውን ሲሸጥ ዝም ካለ እጅግ አደገኛ ነው" ሲሉ ሲንቲያ ዎንግ ይደመድማሉ። |
news-53866643 | https://www.bbc.com/amharic/news-53866643 | ሴኔጋል፡ በዳካር ወደብ ያለው አሞኒየም ናይትሬት እንዲነሳላት ጠየቀች | በቅርቡ የሊባኖሷን መዲና ቤይሩት ያናወጠው ከባድ ፍንዳታን ያስከተለው የአሞኒየም ናይትሬት ክምችት በዳካር ወደብም ስጋት ሆኗል። | ሴኔጋል ይህንን ኬሚካል የት ላድርገው? እያለች ነው። የሴኔጋል ባለሥልጣናት 2 ሺህ 700 ቶን የሚመዝነውን ይህን ኬሚካል ከዳካር ወደብ እንዲነሳላቸው ጠይቀዋል። በመኖሪያ አካባቢዎች አቅራቢያ ባለው ዳካር ወደብ ተከማችቶ የሚገኘው አሞኒየም ናይትሬት መጠን በቤይሩት ከነበረው ጋር የሚቀራረብ ነው ተብሏል። ባለሥልጣናት እንደሚሉት ኬሚካሉ ወደ ጎረቤት አገሯ ማሊ ሊጓጓዝ የታቀደ 3 ሺህ ሃምሳ ቶን ኬሚካል አካል ነው። ከዚህ ውስጥ 350 ቶን ወደ ማሊ እንደተጓዘ የወደቡ ባለሥልጣናት ተናግረዋል። መንግሥት በበኩሉ የኬሚካሉ ባለቤት ኬሚካሉን ከዳካር 30 ኪሎ ሜትር በምትርቀው ዲያምኒያዶ በሚገኝ መጋዘን እንዲያስቀምጥ መጠየቃቸውን ተናግሯል። ይሁን እንጅ የአካባቢ ሚኒስቴር በአካባቢና በማህበራዊ ሕይወት ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ ጨምሮ ቦታው ለተባለው ዓላማ የሚያስፈልገውን መስፈርት አያሟላም በሚል ጥያቄውን አልተቀበለም። የሚኒስቴሩ ባለሥልጣን ባባ ድራሜ "ኬሚካሉ ከሴኔጋል እንዲወጣ ሁኔታዎችን እንዲያመቻች ባለቤቱን ጠይቀናል" ሲሉ ለኤኤፍፒ ተናግረዋል። የኬሚካሉ ባለቤት ማን እንደሆነ ያልተገለፀ ሲሆን በማሊም ለምን ሥራ ሊጠቀሙበት እንደሚፈልጉ የታወቀ ነገር የለም። የወደቡ ባለሥልጣናትም ኬሚካሉ ተጭኖ ወደቡ ላይ የደረሰበትን ቀን አልገለፁም። በማሊ ፕሬዚደንት ኢብራሂም ባውባካር ኬታን ከሥልጣን ካወረደው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት በኋላ ባለው ፖለቲካዊ ቀውስ ኬሚካሉን ወደዚያ ማጓጓዙን ፈታኝ ያደርገዋል። የት ይደረግ? ወዴት ይላክ? መልስ ያላገኘ ጥያቄ ሆኗል። ቤይሩት በዚሁ ኬሚካል በተፈጠረ ፍንዳታ ሳቢያ ክፉኛ የወደመች ሲሆን ከ200 በላይ ሰዎችም ሞተዋል። በከተማዋ ዙሪያ የሚገኙ ህንፃዎችም ሳይቀሩ ወድመዋል። |
47235822 | https://www.bbc.com/amharic/47235822 | ኢትዮጵያ፡ በፍቅረኞች ቀን የፍቅር ስጦታ ለሴት ተማሪዎች | ከስምንት ዓመት በፊት ነበር። አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ውስጥ፤ የጾታ እኩልነት ጥያቄ ያነገቡ ተማሪዎች 'የሎ ሙቭመንት' (ቢጫ ንቅናቄ) የተሰኘ ቡድን የመሰረቱት። ተማሪዎቹ ጾታን መሰረት ያደረገ አድልዎን ለመታገል በተለያየ መንገድ እንቅስቃሴ ማድረጋቸውንም ገፉበት። | ቢጫ ንቅናቄን የሚወክል አበባ • የሳዑዲ ሴቶች መሪ ጨበጡ • ሴቶች የተቆጣጠሩት የስፔን ካቢኔ ሩት ይትባረክ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲውን የሎ ሙቭመንት ወደ መቐለ ዩኒቨረስቲ የወሰደችው የተቋሙ ተማሪ ሳለች ነበር። ወጣቶች አበባ በመሸጥ ላይ ከየሎ ሙቭመንት ተግባሮች አንዱ የሆነውን የፍቅረኞች ቀን የአበባ ሽያጭ በማስተባበር ላይ ሳለች አነጋግረናታል። እንዳለፉት ዓመታት ሁሉ ዘንድሮም አበባ በመሸጥና ለሰዎች የአበባና የቸኮሌት ስጦታ በማድረስ ገንዘብ እያሰባሰቡ ነው። ገንዘቡ ችግረኛ ለሆኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሴት ተማሪዎች ተሰጥቶ የንጽህና መጠበቂያ ሞዴስና ሌሎችም አስፈላጊ ነገሮች ለመግዛት ይውላል። ለአካል ጉዳተኛ ሴት ተማሪዎች የገንዘብ ድጎማም ያደርጋሉ። በፍቀረኞች ቀን የፍቅር ስጦታ ለሴት ተማሪዎች የፍቅረኞች ቀን የሚከበርበት ወቅት አበባ በብዛት የሚመረትበት ነውና አበባ እንደልብ ይገኛል። ዘንድሮ አራት አበባ አምራች ፋብሪካዎች ወደ 15 ሺህ የሚጠጉ አበቦች እንደለገሷቸው ሩት ትናገራለች። "ፍቅር ደግነት ከሆነና ሰዎች በዚህ ቀን አበባ መግዛታቸው ካልቀረ ለምን ለጥሩ ነገር አይውልም? ስንል የጀመርነው ንቅናቄ ነው" ትላለች። ወቅቱ ተማሪዎች እረፍት የሚያደርጉበት በመሆኑም ብዙ በጎ ፍቃደኛ ተማሪዎች ለማግኘትም ያመቻል። • ታሪክ እየቀየሩ ያሉት ሴቶች • የሴቶች ብቻ መጓጓዣዎች ትንኮሳን ይቀንሳሉ? አንድ ሰው የየሎ ሙቭመንት አባላትን "ለእከሌ አበባ ስጡልኝ" ብሎ መላክ ይችላል። ሩት ባነጋገርናት የፍቅረኞች ቀን ብቻ ለአምስት ሰዎች አበባ ማድረሷን ነግራናለች። በሰዎች መኖሪያ ቤት፣ በመሥሪያ ቤትና ለወለደች ሴት። አበባዎቹ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን፣ በአሜሪካ ኤምባሲ እና እፎይ ሬስቶራንትን ጨምሮ በለያዩ አካባቢዎች ይሸጣሉ። አንዲት ተማሪን ለአንድ ዓመት ስፖንሰር የሚያደርግ ትልቅ የአበባ እስር 2,000 ብር፣ አንድ አበባ ደግሞ 30 ብር ይሸጣል። ወጣቶች አበባ በመሸጥ ላይ ከገንዘብ ልገሳ ባለፈ የዘንድሮው የአበባ ሽያጭ ያስገኘው ገቢ ገና ባይሰላም አምና 216 ሺህ ብር ተሰብስቦ 186 ሴት ተማሪዎች መረዳታቸውን ሩት ትናገራለች። የሎ ሙቭመንት ለፍቅረኞች ቀን አበባ ሸጦ ገንዘብ ከማሰባሰብ በተጨማሪ፤ የጷግሜ ንቅናቄን ጨምሮ በማኅበራዊ ሚዲያ ንቅናቄዎችና 'ቴብል ደይ' በተባለው ሳምንታዊ የውይይት መድረክም ይታወቃል። መድረኩ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ አስተማሪዎች በጾታ እኩልነት ላይ ውይይት የሚያደርጉበት ነው። "በትንንሽና ቀጣይነት ባላቸው ድምጾች እናምናለን" የምትለው ሩት፤ ዘለቄታዊ ለውጥ የእንቅስቃሴዎቹ ድምር ውጤት መሆኑን ታስረዳች። ችግረኛ ሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ ሞዴስ እንዲያገኙ ከማድረግ በተጨማሪ ስለ ወር አበባ ያለውን የተዛባ አመለካከት መቅረፍም ግባቸው ነው። ሩት እንደምትለው፤ "የወር አበባ እንደ ቆሻሻ መታየቱ እንዲቀር እንፈልጋለን። በአንድ ወቅት በሰራነው ስሌት አንዲት ሴት በወር አበባ ምክንያት በወር ሦስት ቀን ከትምህርት ቤት ከቀረች በአንድ የትምህርት ክፍለ ዘመን 18 ቀን ትቀራለች ማለት ነው። ይህም ብቃት እያላትም ከእኩዮቿ ጋር እኩል እንዳትፎካከር ያደርጋታል" የተዛባውን አመለካከት ለማቅናት መሰል እንቅስቃሴዎች አጋዥ ናቸው። አበባ ለመሸጥ ሲያዘጋጁ አበባ በአማካይ ከሚሸጥበት ገንዘብ ጨምረው ከየሎ ሙቭመንት አባላት አበባ የሚገዙ ሰዎች ቁጥር ከዓመት ወደ ዓመት እየጨመረ መምጣቱ፤ ሰዎች አላማቸውን ተረድተው እየደገፉ ስለመሆኑ ማሳያ እንደሆነ ታምናለች። |
news-41417383 | https://www.bbc.com/amharic/news-41417383 | 'ዕውቀት ሳያገኙ ትምህርት ቤት መመላለስ' | ዕድሜያቸው በአስራዎቹ ውስጥ ከሚገኙ 10 ህጻናት መካከል ስድስቱ መሠረታዊ የትምህርት ክህሎት እንደሌላቸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሪፖርት ይፋ አደረገ። | ድርጅቱ ጥናቱን 'አስደንጋጭ' እና 'የትምህርትን ቀውስ' የሚያሳይ ብሎታል። በግጭት ውስጥ ባሉ ወይንም ከሰሃራ በታች በሚገኙ ደሃ ሃገራት ውስጥ በትምህርት ላይ ትኩረት በማድረግ የሚሰሩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ትምህርት ቤቶችን በማቋቋም ላይ አትኩረዋል። ሆኖም በዩኔስኮ የስታትስቲክስ ተቋም የተደረገው ጥናት እንደሚያሳው በትምህርት ቤቶቹ የትምህርት ጥራት ችግር ይስተዋላል። ለዚህ ደግሞ ማሳያ የሆነው 600 ሚሊዮን ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ልጆች መሠረታዊ የሂሳብም ሆነ የማንበብ ክህሎታቸው ዝቅተኛ መሆኑ ነው። ከፍተኛ ልዩነት እንደጥናቱ ከሆነ ከሰሃራ በታች ባሉ ሃገራት ከሚገኙ ህጻናትና ታዳጊዎች መካከል 88 በመቶ የሚሆኑት መሠረታዊ የማንበብ ክህሎት ሳይኖራቸው ወደ ጉርምስና ይሸጋገራሉ። ሱዳን ውስጥ ያለ ትምህርት ቤት ሪፖርቱ ማህበራዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የሚመጣው የተማሩ ሰዎች ቁጥር ሲጨምር መሆኑን ይገልጻል። "እነዚህ ልጆች ከመንግሥታቸው ወይም ከማህበረሰባቸው የተሸሸጉ አይደሉም። እንደውም በትምህርት ቤት ነው የሚገኙት" ሲሉ የዩኔስኮ የስታትስቲክስ ተቋም ዳይሬክተር ሲልቪያ ሞንቶያ ይገልጻሉ። የላኦስ ተማሪዎች የዓለም ባንክም ከሰሞኑ ባወጣው ሪፖርት "ዕውቀት ሳይገበዩ በትምህርት ቤት መገኘት" በሚል እያጋጠመ ስላለው ችግር ይፋ አድርኋል። እንደጥናቱ ከሆነ በኬንያ፣ ታንዛንያ እና ኡጋንዳ የሚገኙ ተማሪዎች ለዓመታት በትምህርት ቤት ቆይተውም ቀላል ቁጥሮችን መደመርም ሆነ ቀላል ዓረፍተ ነገሮችን ማንበብ ይቸገራሉ። ችግሩ ምንድን ነው? ብዙ ህጻናት ትምህርት ቤት የሚገኙት ለትምህርት ሚያስፈልጋቸውን በሙሉ አሟልተው አይደለም። የዓለም ባንክ ጥናት የችግሩን ምንጭም ለመለየት ሞክሯል፡ የዓለም ባንክ ዋና የኢኮኖሚ ባለሙያ ፖል ሮመር እንደሚሉት ብዙ ልጆች ትምህርት ቤት ገቡ ማለት ሙሉ ለሙሉ በቂ ዕውቀት እያገኙ ነው ብሎ መታመን የለበትም። |
news-53913040 | https://www.bbc.com/amharic/news-53913040 | ወሰንሰገድ ገብረኪዳን፡ "አዶኒስ አስካሁን ከሰራው በላይ ወደፊት ሊሰራ ያቀደው ነበር ያጓጓኝ" | በርካቶች አዶኒስ በሚለው ስሙ ያውቁታል። የገመና ቁጥር -1 እና የመለከት የቴሌቪዥን ድራማዎች ደራሲ እንዲሁም በበርካቶች ዘንድ ተወዳጅ የሆነውን የአና ማስታወሻን መጽሐፍ ተርጓሚው አድነው ወንድይራድ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል። | አዶኒስ ከነዚህ ሥራዎቹ በተጨማሪ የበርካታ መጽሐፍትን፣ የሕጻናት መዝሙሮችንና የበርካታ ፊልሞች፤ እንዲሁም የሌሎች የኪነ ጥበብ ሥራዎች ደራሲ እና ተርጓሚ ነው። ብዙ ጊዜ ሚዲያዎች ላይ ቀርቦ ለመታየት ፍላጎት ያልበረው አዶኒስ በሙያው አርክቴክት [የሥነ ሕንጻ ባለሙያ] ነበር። በዚህም መስክ የበርካታ ሕንፃዎችን ዲዛይን እንደሰራ ይነገርለታል። ለበርካታ ዓመታት በጓደኝነት ያሰላፈውና በርካታ የአዶኒስ ሥራዎችን በመተየብ የሚታወቀው የቀድሞው የኢትዮጵ ጋዜጣና መጽሔት ዋና አዘጋጅ ወሰንሰገድ ገብረኪዳን አዶኒስ "ኪነ ጥበብን ማሳደግ አለብን" ብሎ ሙሉ ጊዜውን ለጥበብ የሰጠ ሰው ነበር ይላል። ከ1993 ጀምሮ ከአዶኒስ ጋር እውቅና እንዳላቸው የሚናገረወው ወሰንሰገድ፤ አዶኒስ ከትርጉምና ከድርሰት ሥራዎቹ ባሻገርም ሠዓሊና የሙዚቃ መሳሪያ ተጨዋችም እንደነበር ይገልጻል። አዶኒስ እስካሁን ከሰራቸው በላይ "ወደፊት ሊሰራ ያቀደው ነበር ይበልጥ ያጓጓኝ" የሚለው ወሰንሰገድ "ለአንድ ዓመት የተሰራ ተከታታይ ድራማ ሰርቶ ጨርሶ ነበር፤ ከዚህም ሌላ የኢትዮጵያ ህፃናት ላይ መሰራት አለበት በሚልም ለህፃናት ራሱ ጊታር እየተጫወተ የሰራው መዝሙር ተጠናቆ ነበር፤ ይህንን ለሕዝብ ያበቃል ብዬ ስጠብቅ ነበር" ጓደኛው በድንገት መለየቱን መቀበል የተቸገረው ወሰንሰገድ። ጓደኛ የነበረውን ተለየ ችሎታን በተመለከተም "ነገሮችን የሚያይበት የተለየ ገጽ ይገርመኝ ነበር። ውስብስብና ከባድ የሆነውን ነገር ቀለል አድርጎ የማቅረብ ችሎታው አስደናቂ ነበር፤ እምቅም ትልቅም ችሎታ ነበረው" ሲልም ለአዶኒስ ያለውን አድናቆት ይገልፃል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ ከአዶኒስ ጋር ለወራት በአካል ተገናኝተው እንደማያውቁ የሚናገረው ወሰንሰገድ፤ ከአንድ ወር በፊት ደውሎለት "ይህ በሽታ ካልጠፋ ሳንተያይ ልንሞት ነው እንዴ?" እንዳለው በሐዘን ያስታውሳል። እንደ ወሰንሰገድ ከሆነ አዶኒስ ከራስ ምታትና ነስር በስተቀር ሌላ የጤና እክል አልነበረበትም። ነገር ግን ከ15 ቀናት በፊት ህመም አጋጥሞት ምኒሊክ ሆስፒታል ገብቶ እንደነበር መስማቱን ይናገራል። አዶኒስ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ሲሆን የብዕር ስሙ - [አዶኒስ] የመጀመሪያ ወንድ ልጁ ስም ነው። የአድነው ወንድይራድ (አዶኒስ) የቀብር ሥነ ሥርዓት ነሐሴ 20/2012 ዓ.ም አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ውስጥ ተፈጽሟል። |
news-54778481 | https://www.bbc.com/amharic/news-54778481 | የአሜሪካ ምርጫ፡ ምርጫውን በቀላሉ መረዳት የሚያስችሉ ነጥቦች | የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ከአሜሪካ ዜጎች በተጨማሪ የበርካቶችን ሕይወት የሚነካ ስልጣን አለው። | ጥቅምት 24 ደግሞ የምርጫ ካርዳቸውን የወሰዱ አሜሪካውያን ዶናልድ ትራምፕን አልያም ጆ ባይደንን ፕሬዝዳንታቸው አድርገው ለመምረጥ ድምጻቸውን የሚሰጡበት ቀን ነው። የምርጫው ውጤት ሁሉንም ይመለከታል። የአሜሪካ የፖለቲካ ስርአት በሁለት ፓርቲዎች የበላይነት የሚመራ ነው። ስለዚህ የሚመረጠው ወይም የምትመረጠው ፕሬዝዳንት ከሁለቱ ፓርቲ የአንዱ አባል መሆን አለባቸው። ሪፐብሊካኖች ወግ አጥባቂ የፖለቲካ ፓርቲ ሲሆኑ የዘንድሮው እጩ ደግሞ የአሁኑ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ናቸው። በአሁኑ ሰአት የሚወዳደሩትም ለሁለተኛ ዙር ፕሬዝዳንት ለመሆን ነው። ካሸነፉ ለተጨማሪ አራት ዓመታት አሜሪካን ይመራሉ ማለት ነው። . ነገ ጠዋት ስለ አሜሪካ ምርጫ ምን ዜና ልንሰማ እንችላለን? . የዶናልድ ትራምፕ ሕይወት፡ ከሆቴል እስከ ቤተ መንግሥት . ጆ ባይደን ማን ናቸው? በቅርብ ዓመታት ሪፐብሊካኖች ዝቅተኛ ግብር አንዲኖር፣ ከፍተኛ ቁጥጥር በጦር መሳሪያዎች ላይ አንዲደረግና ስደተኞችን በተመለከተ ጠበቅ ያለ ሕግ እንዲወጣ ሲሰሩ ነበር። ፓርቲውም በገጠራማ የአሜሪካ ክፍሎች ከፍተኛ ተቀባይነትና ድጋፍ ያለው ሲሆን እንደ ጆርጅ ቡሽ፣ ሮናልድ ሬገን እና ሪቻርድ ኒክሰንን የመሳሰሉ የቀድሞ ፕሬዝዳንቶችም በነዚህ አካባቢዎች ከፍተኛ ድጋፍ ነበራቸው። ዴሞክራቶች ደግሞ ተራማጅ የሚባል ፖለቲካዊ ርዕዮተ ዓለም የሚከተሉ ናቸው። በዘንድሮው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ደግሞ ፓርቲውን ወክለው ከዶናልድ ትራምፕ ጋር የሚወዳደሩት የብዙ ዓመታት ፖለቲካዊ ልምድ ያላቸውና የቀድሞው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ምክትል የነበሩት ጆ ባይደን ናቸው። ዴሞክራቲክ ፓርኪ ከሲቪል መብት፣ ኢሚግሬሽን እና የአየር ጸባይ ለውጥን በተመለከተ ባለው ተራማጅ አስተሳሰብ ይታወቃል። ፓርቲው መንግስት እንደ ጤና መድህን መሳሰሉ ነገሮችን በማሟላት የህዝቡ የእለት ተእለት ሕይወት ላይ ከፍተና ሚና መጫወት እንዳለበት ያምናል። ከሪፐብሊካኖች በተቃራኒው መልኩ ዴሞክራቶች በርካታ ደጋፊዎቻቸው የሚገኙት ከተማ ቀመስ በሆኑ የአሜሪካ አካባቢዎች ነው። እንደ ጆን ኤፍ ኬኔዲ እና ባራክ ኦባማን የመሳሰሉት ፕሬዝዳንቶችም በነዚሁ አካባቢው ድጋፍ ነበራቸው። በዘንድሮው ምርጫ ላይ የሚፎካከሩት እጩዎች ዕድሜያቸው 70 ዓመትን የተሻገረ ሲሆን፤ ትራምፕ ካሸነፉ በ74 ዓመታቸው ለፕሬዝዳንትነት ይዘጋጃሉ። ጆ ባይደን እድል ከቀናቸው ደግሞ በ78 ዓመታቸው ፕሬዝዳንት በመሆን በአሜሪካ ታሪክ በእድሜ የገፉት ፕሬዝዳንት ይሆናሉ። አሸናፊው እንዴት ነው የሚታወቀው? የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫን ለማሸነፍ ብዙ ድምጽ ማግኘት ብቻ በቂ አይደለም። በኢሌክቶራል ኮሌጅ የምርጫ ሥርዓት መሠረት ሁለቱም ተፎካካሪዎች ካሉት 538 ድምጾች ቢያንስ 270 ለማግኘት ነው እየታገሉ ያሉት። በአሜሪካ ምርጫ ለማሸነፍ ወሳኝ የሚባሉ ግዛቶች አሉ። ፕሬዝደንታዊ ዕጩዎች እነዚህን ግዛቶች ለማሸነፍ የሞት ሽረት ትንቅንቅ ያደርጋሉ። የአሜሪካ ግዛቶች የሕዝብ ብዛታቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት በአጠቃላይ 538 ድምፆች ተከፋፍለው ይዘዋል። ነገር ግን እኒህ ድምፆች ለ50ዎቹ ግዛቶች እኩል የተከፋፈሉ አይደሉም። የምርጫ አውድማ የሚባሉት እኒህ ግዛቶች ከሌሎች ግዛቶች የበለጠ ድምፅ አላቸው። እስካሁን ድረስ የተሰበሰቡት ድምፆች እንደሚጠቀሙት ባይደን በሚቺጋን፣ ፔንሲልቫኒያ እና ዊስኮንሲን ግዛቶች የተሻለ ተቀባይነት አላቸው። ትራምፕ ከእነዚህ ግዛቶች በሰበሰቡት ድምፅ ነው በጠባብ ውጤት ያለፈውን ምርጫ መርታት የቻሉት። ጆ ባይደን፤ በእነዚህ ግዛቶች ብቻ ሳይሆን ባለፈው ምርጫ የትራምፕ ናቸው ተብለው በነበሩት ኦሃዮና ቴክሳስ ግዛቶችም የተሻለ ተቀባይነት አግኝተዋል። በነዚህ ግዛቶች የሪፐብሊካን እና ዴሞክራት ደጋፊዎች እኩል በሚባል ደረጃ ይገኛሉ። ከዚህ በፊት የሪፐበሊካኖች ተደርገው ይቆጠሩ የነበሩት እንደ አሪዞና እና ቴክሳስ ያሉ ግዛቶች በዘንድሮው ምርጫ ከፍተኛ ትንቅንቅ እንደሚደረግባቸው ይጠበቃል። ምክንያቱም በዘኒህ ግዛቶች ዴሞክራቶችም ከፍተኛ ተቀባይነት እያገኙ በመምጣታቸው ነው። ማን መምረጥ ይችላል? እንዴትስ ይመርጣል? እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ማንኛውም ዜጋ በየአራት ዓመቱ በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ መሳተፍ ይችላል። ነገር ግን በርካታ ግዛቶች ዜጎች ከመምረጣቸው በፊት ማንነታቸውን መግለጽ የሚችል መታወቂያ እንዲያቀርቡ ያስገድዳሉ። እነዚህ ሕጎች በብዛት የተቀመጡት በሪፐብሊካኖች ሲሆን፤ ምክንያታቸውም የምርጫ መጭበርበርን ለመከላከል የሚል ነው። ዴሞክራቶች ደግሞ ደሃ እና ጭቁን የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ድምጽ ለማፈን ሆን ተብሎ የተቀመጠ ሕግ ነው በማለት ይከሳሉ። ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የዘንድሮው ምርጫ በርካታ የተዘበራረቁ ነገሮችን አስተናግዷል። አንዳንድ ፖለቲከኞች ህዝቡ በፖስታ ቤት በኩል የምርጫ ድምጹን እንዲሰጥ የጠየቁ ሲሆን ዶናልድ ትራምፕ ደግሞ በፖስታ ቤት መምረጥ ለመጭበርበር ያጋልጣል ሲሉ ተደምጠዋል። እስካሁን ከ90 ሚሊየን በላይ ሰዎች በፖስታ ቤት በኩል ከወዲሁ ድምጻቸውን የሰጡ ሲሆን፤ በአገሪቱ ታሪክ በፖስታ ይህን ያክል ቁጥር ያለው ዜጋ ሲመርጥ ይህ ከፍተኛው ነው። በዘንድሮው ምርጫ ፕሬዝደንት ብቻ ነው የሚመረጠው? በዘንድሮው ምርጫ ዶናልድ ትራምፕ እና ጆ ባይደን ብቻ አይደሉም የሕዝብ ድምጽ የሚሰጣቸው። ሁለቱም ፓርቲዎች (ሪፐብሊካን እና ዴሞክራት) የአሜሪካ ምክር ቤት ምርጫን በትኩረት ነው የሚከታተሉት። በአሁኑ ሰዓት በምክር ቤቱ ሪፐብሊካኖች ከዴሞክራቶች በሦስት ወንበር አብላጫ ወስደዋል። የትራምፕ ወዳጅ የሆኑት ሊንዚ ግራሃም በደቡብ ካሮላይና በሕይወታቸው አይተውት የማያውቁት ፖለቲካዊ ጦርነት ውስጥ ገብተዋል። ተቀናቃኛቸው ደግሞ ዴሞክራቱ ጄሚ ሃሪሰን ናቸው። ምንም እንኳን ሊንዚ ግራሃም ከ2003 ጀምሮ በምክር ቤቱ ወንበር ተቆናጥጠው የቆዩ ቢሆንም ለፕሬዝዳንት ትራምፕ ባላቸው ድጋፍ ምክንያት ግን የአንዳንድ መራጮችን ድምጽ አጥተዋል። በዘንድሮው ምርጫ ሌሎች ነገሮችም የሕዝብ ድምጽ ያስፈልጋቸዋል። ለምሳሌ የዕጸ ፋርሰ ጉዳይ ትልቅ መነጋገሪያ ነው። በአሪዞና፣ ሞንታና፣ ኒው ጀርሲ እና ሳውዝ ዳኮታ መራጮች ዕጸ ፋርስ ለመዝናኛ መፈቀድ አለበት በሚለው ላይ ድምጻቸውን ይሰጣሉ። በተመሳሳይ በሚሲሲፒ ደግሞ መራጮች ዕጸ ፋርስ ለሕክምና መፈቀድ አለበት ወይስ የለበትም በሚለው ላይ ድምጻቸውን እንደሚሰጡ ይጠበቃል። አሸናፊው በይፋ ስራ የሚጀምረው መቼ ነው? በምርጫው ጆ ባይደን የሚያሸንፉ ከሆነ ወዲያውኑ ወደ ስራ መግባት አይችሉም። ምክንያቱም አዲሱ ፕሬዝዳንት የካቢኔ ሚኒስትሮቻቸውን ለመሾምና እቅድ ለማዘጋጀት የሽግግር ጊዜ ያስፈልጋቸዋል። አዲሱ ፕሬዝዳንት በይፋ ኃላፊነታቸውን የሚረከቡትና ቃለ መሀላ የሚፈጽሙበት የበአለ ሲመት ቀን ደግሞ ጥር 12 ላይ በዋሽንግተን ዲሲ ካፒቶል ህንጻ ደረጃ ላይ ይካሄዳል። በመቀጠልም አዲሱ ፕሬዝዳንት ወደ ዋይት ሀውስ በመሄድ ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት እዛው ይቆያሉ። |
news-49793800 | https://www.bbc.com/amharic/news-49793800 | የቡሩንዲ ባለስልጣን የካቶሊክ ቀሳውስትን አወገዙ | የቡሩንዲ ባለስልጣናት አለመቻቻልንና ፖለቲካዊ ጥቃቶችን በማውገዝ ከዚህ ጋር በተያያዘ አንዳንድ የሃገሪቱ የካቶሊክ ቀሳውስት እንዲወገዙ ጠየቁ። | የቡሩንዲ ፕሬዝዳንት ቃል አቀባይ ዊሊ ኒያሚትዌ በትዊትር ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት አንዳንድ ቀሳውስት እሳት በሚጭሩ ቃላት "መርዛማ ጥላቻን እየረጩ ነው" ሲሉ ከሰዋቸዋል። እሁድ ዕለት ከመንግሥት የተለየ አመለካከት ያላቸው ሰዎች እንደሚሳደዱና አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎችም እንዳይንቀሳቀሱ እንደተደረጉ የሚገልጽ ከቤተ-ክርስቲያኒቱ የቀሳውስት ጉባኤ የተላለፈ መልዕክት በካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ እንደተነበበ ተገልጿል። • አፍሪካዊያን ተወዳጅ ምግባቸውን መተው ሊኖርባቸው ይሆን? • አሜሪካ ለምን ከምድር በታች ነዳጅ ዘይት ትደብቃለች? መልዕክቱን ጠቅሶ ኤኤፍፒ እንደዘገበው "ከመንግሥት የተለየ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ላይ የሚወሰደው ፖለቲካዊ እርምጃ እስከ ግድያ ይደርሳል. . ." እንደሚል ተገልጿል። በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የተባበሩት መንግሥታት ቡድን እንዳስጠነቀቀው ሊካሄድ ከታሰበው ምርጫ ቀደም ብሎ በሰብዓዊነት ላይ ወንጀሎች እየተፈጸሙ መሆኑን ገልጾ ነበር። ከአራት ዓመት በፊት ፕሬዝዳንት ፒየር ንኩሩንዚዛ ለሦስተኛ የስልጣን ዘመን በምርጫ ለመወዳደር መወሰናቸውን ተከትሎ በተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ ቡሩንዲ ፖለቲካዊ ቀውስ ውስጥ ተዘፍቃ ነበር። በክስተቱም ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች ሲገደሉ አለመረጋጋቱን በመሸሽ 400 ሺህ ሰዎች ሃገሪቱን ጥለው ተሰደዋል። ምንም እንኳን ፕሬዝዳንት ንኩሩንዚዛ በቅርቡ ይካሄዳል በሚባለው ምርጫ ላይ የመሳተፍ ፍላጎት እንደሌላቸው ቢነገርም ባለፈው ዓመት የሃገሪቱን ሕገ መንግሥት ለማሻሻል በተደረገው ሕዝበ ውሳኔ ፕሬዝዳንቱ ለቀጣዮቹ 14 ዓመታት በመንበራቸው ላይ እንዲቆዩ ሆኖ ተሻሽሏል። |
44079206 | https://www.bbc.com/amharic/44079206 | “የኢትዮጵያ መንግሥት እንደ አንዳንድ የአፍሪካ አገራት ደመወዝ ለመክፈል አይበደርም” | በፈጣን የኢኮኖሚ እድገቷ የምትጠቀሰው ኢትዮጵያ በቅርቡ የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይ ኤም ኤፍ ባወጣው የአፍሪካ ሃገራት ምጣኔ ሃብታዊ ዘገባ ላይ የእዳ መጠኗ ከፍተኛ እንደሆነ አትቷል። | ኢትዮጵያም የእዳ ጫናዋ መጠን ከአጠቃላይ የሃገር ውስጥ ምርቷ 56.2 በመቶ ድርሻ እንደሆነ ተጠቅሶ ከአገራቱ ተርታ ተመድባለች ። ምንም እንኳን ተቋሙ ብድሩ አስጊ ደረጃ ላይ እንደሆነ ቢገልፅም በተቃራኒው ብድር እንደ ችግር ሊታይ አይገባም የሚሉት የግብርናና ምጣኔ ሐብት ባለሙያ ዶክተር ደምስ ጫንያለው እንደ ምሳሌነት የሚጠቅሱትም በብድር የምትመራው አሜሪካ መሆኗን ይጠቅሳሉ። "ብድር መውሰድ የሚያስገርም ነገር አይደለም። ማንኛውም እድገት ከመበደር በነፃ እንቅስቃሴ አይደለም። ዋናው ጥያቄ ለምን ተግባር ይውላል የሚለው ነው" ይላሉ። "የኢትዮጵያ መንግሥት እንደ አንዳንድ የአፍሪካ አገራት ደመወዝ ለመክፈል አይበደርም" ይላሉ ባለሙያው። ኢትዮጵያ ብድር የምትበደረው ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት እንደሆነ የሚናገሩት ዶክተር ደምስ አይኤም ኤፍና የዓለም ባንክ የመሳሰሉ ተቋማት ለአገሪቱ የተለያዩ መሰረተ ልማቶች ብድር እንደማይሰጡም ይገልፃሉ። "የመንገድ ሥራዎች ለመስራት፣ ግድቦችን ለመገንባት፣ ለመብራት መስፋፋት፣ ቴሌኮሚዩኒኬሽን አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ፣ ለባቡር መስምረ ዝርጋታ እና ለመሳሰሉት ኢትዮጵያ ብድር የምትወስደው ከቻይናና ከህንድ ነው" ይላሉ። አንድ የብድር መጠን ሊነፃፀር የሚገባው ከመክፈል አቅም ጋር ነው። ብድሩን ተጠቅሞ ገቢ ማግኘትና በወቅቱ መክፈል እስከተቻለ ድረስ ሪፖርቱ እንደሚለው የሚረብሽ ነገር የለውም። በዚህም ምክንያት የኢትዮጵያ መንግሥት ለምን ተበደረ የሚል አቋም የላቸውም። በዚህ ዓመት ለአንዳንድ ላልተጠበቀ የዋጋ ግሽበት ምክንያቱ በቅርብ ጊዜ ተግባራዊ የሆነው የኢትዮጵያ መገበያያ የሆነው ብር ከዶላር ጋር ያለው አቅም እንዲቀንስ መደረጉ ሲሆን ይህም በእነዚህ ድርጅቶች ጫና መሆኑን ዶክተር ደምስ ይናገራሉ። ይሁን እንጂ አሁንም የዋጋ ጭማሪው ምክንያታዊ ባለመሆኑ ነዋሪዎች ያማርራሉ። "በመሰረታዊ የምግብ ፍጆታችን ላይ የዋጋ ጭማሪ አለ። ችግሩ ከባለፈውም ወር የባሰ ነው። እያንዳንዱ ነገር ላይ ከአራት ብር እስከ ስድስት ብር የዋጋ ጭማሪ አለው። በግንባታ ጥሬ እቃዎችም ላይ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ጭማሬ በመኖሩ ኑሯችንን ፈታኝ አድርጎታል" በማለት የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ሰብለ እሸቴ ይናገራሉ። የውጭ ምንዛሬው ማሻሻያ ላይ የተወሰደው እርምጃ ተገቢ እንዳልነበረም ዶክተር ደምስ ይናገራሉ። "ውሳኔው ያልተጠበቀ የዋጋ ግሽበት ጭማሪዎችን እንደሚያስከትል ቀድሞ በመረዳት መንግሥት መጠንቀቅ የነበረበት ቢሆንም አሁንም የሚስተካከልበትን መንገድ እንደሚጠብቁ" ይናገራሉ። የአይ አም ኤፍ ሪፖርት ጨምሮም ኢትዮጵያ ውስጥ ለመሠረታዊ ፍጆታ የሚውሉ እቃዎች ዋጋ ከቀን ወደ ቀን እያሻቀበ መጥቷል። "ሪፖርቱ ከመውጣቱ አስቀድሞ የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲና ብሄራዊ ባንክ ይህንን አሃዝ ያውቁታል ። ተቋሙ መረጃውን ከእነርሱ ወስዶ ነው የሚያወጣው፤ነገር ግን ይሄንን እንዴት እንቆጣጠረዋለን የሚለው ላይ ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋል።" ይላሉ። ሌሎች የክትትልና የቁጥጥር መንገዶች ካሉ መፈተሽ ይገባልም ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ቢሆንም ግን በአገር ውስጥ በሚመረቱና ከውጭ አገር በሚገቡ ምርቶች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራትም ሌላኛው አማራጭ እንደሆነ ይጠቁማሉ። ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በሚፈለገው መጠን እንዲገቡና ከገቡ በኋላ አገር ውስጥ ካለው ዋጋ ትርፍ አንፃር የሚሸጥበትን ዋጋ መለየት ያስፈልጋል ሲሉም ያስረዳሉ ። ከዚህ በተጨማሪም ያለውን ክፍትት በመጠቀም ከዋጋው በላይ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎች ስላሉ የሚገቡ ምርቶች፣ ከውጭ በድጎማ የሚገቡ ግብዓቶችንና በአገር ውስጥ የምርት ውጤቶችን በመከታተልና በመቆጣጠር መስራት እንደሚያስፈልግ ይገልፃሉ። በተለያዩ ደረጃ ያሉ የገንዘብ ተቋማት ይህንን በማከናወን ላይ ናቸው ሲሉ ሃሳባቸውን ያሳርጋሉ። |
news-47288496 | https://www.bbc.com/amharic/news-47288496 | የዛሬ 74 ዓመት የተሳመው 'ከንፈር' ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ | እጅግ ከሚወደዱና ከተጨበጨበላቸው ፎቶግራፎች አንዱ ነው። በአሜሪካ ብቻም ሳይሆን በዓለም ዙርያ ይህ ምስል ተወዳጅ ነው። ዝነኛም ነው። ስሜት ኮርኳሪም ነው። ያለ ምክንያት ግን አይደለም። | ምሥሉ በዓለም ዙሪያ በትልልቅ አውደ ርዕዮች ቀርቦ አድናቆትን አትርፏል 2ኛው የዓለም ጦርነት ማብቃቱን ተከትሎ አንድ የአሜሪካ ጦር መርከበኛ ድንገት በኒውዮርክ ጎዳና ላይ የነበረችን ቆንጆ ጎተት አድርጎ ከንፈሯን ጎረሰው። ምንም አላስተረፈም። ያን ቅጽበት የፎቶ ጥበበኛው አልፍሬድ አይዠንስታድ በካሜራው አስቀረው። ያ ምሥል 'ላይፍ' በተባለው መጽሔትም ታተመ። ከዚያ ወዲህ በመጽሔቱ ብቻ ሳይሆን በሚሊዮኖች ልብ ላይ የታተመ የዓለማችን እጹብ ድንቅ ፎቶ ሆኖ ኖረ። • ባህልን በኤሌክትሮኒክ ሙዚቃ የቀመመው ሮፍናን • “ከወጡት ስራዎቼ ይልቅ ገና የሚወጡት ናቸው ትልቅ ቦታ ያላቸው” አለማየሁ ገላጋይ • ተፈጥሮን በብሩሽ የሚመዘግበው መዝገቡ ያ ጎበዝ ሳሚ መርከበኛ ስሙ ጆርጅ ማንዶሳ ይባላል። በተወለደ በ95 ዓመቱ ትናንት ማረፉ ተሰምቷል። የ21 ዓመቷ ተሳሚ ቆንጆ ግሬታ ዚመር ፍሬድማን ትባላለች። በ2016 ነበር ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው። ኖራ ኖራ በ92 ዓመቷ ማለት ነው። የፎቶግራፍ ጥበበኛው አልፍሬድ አይዠንስታድ ያኔ ሳሚና ተሳሚዎቹ እነማን እንደሆኑ ሁሉ አልገለጸም ነበር። ኋላ ነው ነገሩ ይፋ የሆነው። እንደመታደል ኾኖ መርከበኛው የደንብ ልብሱን ለብሶ ድንገት እየበረረ አንዲትን ቆንጆ ሲስም ቅጽበቱን በካሜራ ቀለበው። ነገሩ ችሎታ ከምንለው ዕድል ብንለው ይቀላል። ይህ የሆነው ነሐሴ 14 ቀን 1945 ነበር። "ድንገት በካሜራዬ ሌንስ ውስጥ አንድ ጉብል [ከሰልፍ መስመር ወጥቶ] ድንገት አንዲት ኮረዳን እንቅ አድርጎ ሲስማት ተመለከትኩ። የካሜራዬን ቁልፍ ተጫንኩት። ኮረዳዋ ነጣ ያለ የነርስ ደንብ ልብስ ነበር የለበሰችው። [ጎልታ ትታየኝ ነበር] እንዲያ ባትለብስ ኖሮ ይህን ምስል ስለማግኘቴ እጠራጠራለሁ" ብሎ ነበር፤ አልፍሬድ። • ተፈራ ነጋሽ፡ "በነገራችን ላይ ሙዚቃ አልተውኩም" ወይዘሪት ፍሬድማን ያኔ የጥርስ ሐኪም ረዳት ነበረች። ስለዚያ አስደናቂ ፎቶግራፍ ያወቀችው ግን ምስሉ ከወጣ ከ16 ዓመት በኋላ በ1960 ነበር። "ያን ያህልም እኮ የፍቅር መሳሳም አልነበረም። እንዲሁ በፈንጠዚያ ላይ ነበርን፤ በቃ ይኸው ነው" ብላ ነበር፤ ስለዚያ ፎቶግራፍ ስትናገር። ዓለም ግን ይህን ፎቶግራፍ በዚያ መንገድ አልወሰደውም። ከብዙ እልቂት በኋላ ጃፓን ለአሜሪካ ጦር እጅ የሰጠችበትና የአሜሪካ አሸናፊነት የተበሰረበት ዕለትም በመሆኑ የዚያ ፎቶግራፍ ትርጉምና ዝና በአያሌው ገዝፎ ኖሯል። |
news-52614930 | https://www.bbc.com/amharic/news-52614930 | ኮሮናቫይረስ፡ ምስጢራዊ የቀብር ሥነ ሥርዓት የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታት እየረዳ ነው | ደቡብ አፍሪካ ያወጣችው ሰዎች እንዳይሰበሰቡ የሚከለክለው ሕግ ዜጎች በርካታ ልማዶቻቸውን እንዲተዉ ያስገደዳቸው ቢሆንም አንድ የተረሳ ምስጢራዊ የቀብር ሥነ ሥርዓት ግን እንዲያስራራ አድርጓል። | በደቡብ አፍሪካ ቀብር ላይ የሚገኙ ሰዎች ቁጥር ገደብ ተጥሎበታል በቅርቡ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በአንድ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኙ 40 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተይዘው ነበር። ወርሀ መጋቢት ላይ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በመላው አገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከማወጃቸውና ሰዎች በአንድ ቦታ ላይ እንዳይሰበሰቡ ከመከልከላቸው አንድ ሳምንት በፊት በሰሜናዊ ኬፕ ታውን የማጆላ መንደር ነዋሪዎች የሆኑ 100 ሰዎች በአንድ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ታድመው ነበር። በዚህም ሳቢያ በአሁኑ ጊዜ ይህች መንደር የአገሪቱ የኮሮናቫይረስ ማዕከል ሆናለች። በመንደሪቱ የነበረውን የቀብር ሥነ ሥርዓት የታደሙና በሌሎች ሁለት ከተሞች በተመሳሳይ ሥርዓት ላይ ተካፋይ የነበሩት 200 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን በመላው አገሪቱ ካለው ቁጥር በቀብር ላይ በበሽታው የተያዙ ሰዎች አንድ አራተኛውን ይይዛሉ። የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ተብሎ በወጣው ሕግ መሰረት በአንድ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ 50 ሰዎች መታደም እንደሚችሉ የተገለጸ ሲሆን ለአንዳንዶች ግን ይህ ቁጥር አሁንም ትንሽ ነው። የሰሜናዊ ኬፕ ታውን አውራጃ ጤና ጽህፈት ቤት ቃል አቀባይ የሆኑት ሲዝዌ ኩፔሎ እንደሚሉት ሰው የሞተባቸው ቤተሰቦች ሕጉን በመተላለፍ የቫይረሱን ስርጭት እያባባሱት ነው። "በአውራጃዋ ያለው የቀብር ሥነ ሥርዓት አፈጻጸም በጣም አሳስቦናል" ብለዋል። "የአካባቢው አዛውንት መሪዎች ባቀረቡት ሀሳብ መሰረት ሁሉም ሟቾች ተመሳሳይ የቀብር ሥነ ሥርዓት እንዲኖራቸው ተስማምተናል። ሁሉም ከአስከሬን ማቆያ ተወስደው ወዲያው እንዲቀበሩ የቀረበው ሀሳብ አስማምቶን ነበር።" ነገር ግን ማኅበረሰቡ ለብዙ ዓመታት ሲተገብረው የነበረውን የቀብር ሥነ ሥርዓትና ሌሎች ማኅበራዊ ክንውኖችን በአንድ ጊዜ ለመተው ፈቃደኛ ሊሆን አልቻለም። ከቀበር በኋላ ተሰብስቦ መመገብና አብሮ መቆየት የተለመደ ባህል ነው የባህል ጥናት ባለሙያ የሆኑት ፕሮፌሰር ሶማዶዳ ፊኬኒ እንደሚሉት እንደዚህ አይነት ክንውኖች በማኅበረሰቡ ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸውና የአንድን ሰው የህይወት ጉዞ የሚዘክሩ ናቸው። "በተለይ አፍሪካውያን እነዚህን ክንውኖች ማኅበራዊ መስተጋብር ለመፍጠርና የዕለት ተዕለት ኑሯቸውን ለማሳለጥ ይጠቀሙባቸዋል። የቀብር ሥነ ሥርዓት ብቻ ሳይሆን እንደ ሠርግ፤ ሐይማኖታዊ ሥነ ሠርዓቶችና ሌሎችም ከዚህ ውስጥ ይካተታሉ።" በበርካታ የአፍሪካ አገራት አንድ ግለሰብ ሲሞት ቤተሰቦችና ዘመድ አዝማድ የቀብር ሥነ ሥርዓቱን ለመታደምና የቅርብ ቤተሰቦችን ለማጽናናት ረጅም ርቀት ተጉዘው ቀብር ላይ ይገኛሉ። ጓደኛና ጎረቤት ደግሞ በተደጋጋሚ ወደ ሟች ቤተሰቦች በመሄድ ለማጽናናት ይሞክራሉ፤ በቻሉት መጠንም እርዳታ ለማድረግም ይጥራሉ። ለማጽናናት የሚመጣውን ሰው ለማስተናገድ ደግሞ ከብት ይታረዳል እንዲሁም ሌሎች አይነት ምግቦች ይሰራሉ። በዚህ ወቅት ደግሞ የምግብ መስሪያ እቃዎችና መመገቢያዎች በበርካታ ሰዎች እጅ ይነካካሉ። በተጨማሪም የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ሲፈጸመም ለመቃብር ቦታ መቆፈሪያነት ጥቅም ላይ የሚውሉት መሳሪያዎችም በብዙ ሰዎች እጅ ይገባሉ። በተጨማሪም ለማጽናናት የሚመጣው ሰው ቤተሰቡን እያቀፈ ነው ሀዘኑን የሚገልጸው። ቤተሰቡ ከሚያውቃቸውና ከሚቀርባቸው ሰዎች በተጨማሪ ደግሞ መንገደኛ እንኳን የለቅሶ ድምጽ ሲሰማ ገብቶ ማጽናናት የተለመደ ነው። እነዚህ ሁሉ ሁኔታዎች ታዲያ የኮሮናቫይረስን ለማስተላለፍ በእጅጉ የተመቹ ናቸው። የቀብር ሥነ ሥርዓቶች ጥቂት ሰው ብቻ የሚገኝባቸው ሆነዋል በዚህ መልኩ የሚተላለፈውን የኮሮረናቫይረስ ለመግታት ደግሞ የአካባቢው ንጉሥ ዝዌሎዙኮ ማቲዋኔ፤ በርካታ ሰዎች ታድመውባቸው የሚፈጽሙትን የቀብር ሥነ ሥርዓት በመከልከል ‘ኡኩቁሼካ’ የሚባለው ምስጢራዊ የቀብር ሥነ ሥርዓት ተመልሶ ተግባራዊ እንዲሆን አዘዋል። የንጉሡ ቃል አቀባይ ንኮሲ ራኑጋ እንዳለው ውሳኔው የተላለፈው ከሌሎች የአካባቢው መሪዎች ጋር ውይይት በማድረግ ነው። ማኅበረሰባችንን ከከባድ ወረርሽኝ ለመከላከል ነው ጥረት እያደረግን ያለነው። በዚህ የቀብር ሥነ ሥርዓት መሰረት ሟች በመጀመሪያው አልያም በሁለተኛው ቀን እንዲቀበር ይደረጋል። በተጨማሪም ግለሰቡ ሲሞት አጠገቡ የነበሩ ሰዎች ብቻ ናቸው በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ መገኘት የሚችሉት።" በንጉሡ ግዛት ስር የሚገኙት የቁምቡ፣ ትሶሎ፣ ኡግዬ፣ ማክሊር እና ሌሎች አጎራባች ከተሞች ይህንን የቀብር ሥነ ሥርዓት እየፈጸሙ ይገኛሉ። "ወደዚህ ባህላዊና ምስጢራዊ ቀብር ሥነ ሥርዓት መመለሳችን የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። ቤተሰቦችም ከቀብር ሥነ ሥርዓቱ በኋላ በአግባቡ እራሳቸውን እንዲያጸዱ ይሄው ባህል ያስገድዳል።" ሌላው ቀርቶ አንድ አባሉ የሞተበት ቤተሰብ የቀብር ሥነ ሥርዓቱን ለማስፈጸም ቀላል የማይባል ገንዘብ ነበር የሚያወጣው። በተለይ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ በታገደበት በዚህ ወቅት ቤተሰቦች ሥራ ሰርተው ገንዘብ ማግኘት አይችሉም። ቃል አቀባዩ እንደሚሉት አንዳንድ ቤተሰቦች እንዲያውም ብዙ ሰው የሚታደምበት የቀብር ሥርዓት ለመፈጸም ብዙ ገንዘብ ከቤተሰብና ጎረቤት ይበደራሉ። ስለዚህ አሁን ተግባራዊ እየተደረገ ቆየት ያለው ባህላዊ የቀብር ሥርዓት የቫይረሱን ስርጭት ከመግታት ባለፈ ቤተሰቦች የሚያጋጥማቸውን ኢኮኖሚያዊ ጫናም ቀለል ያደርገዋል። በአሁኑ ሰዓት አዲስ አይነት የቀብር ሥርዓት ማካሄድ አስፈላጊ የሆነው በገጠሪቱ የደቡብ አፍሪካ ክፍል ውስጥ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ተተሞች ውስጥ ጭምር ነው። በዚህ የወረርሽኝ ጊዜ በተለይ በበርካታ ትልልቅ ከተሞች ውስጥ ያለው የመቃብር ስፍራ ውስንነት ባለስልጣናት ብዙ ሰዎችን በአንድ ቦታ ላይ እስከ መቅበር ሊያደርስ እንደሚችል ስጋታቸውን እየገለጹ ነው። ስለዚህም ይህ አይነነቱ ምስጢራዊ የቀብር ሥነ ሥርዓት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መስፋፋትን ከመግታት ባሻገር በሟች ቤተሰብና የሐዘን ሥነ ሥርዓቱን በሚታደሙ ሰዎች ላይ የሚኖረውን የወጪ ጫና ያቀላል ተብሎ ይታሰባል። |
news-56745429 | https://www.bbc.com/amharic/news-56745429 | ትግራይ፡ በአድዋ 'የኤርትራ ወታደሮች በከፈቱት ተኩስ' ነዋሪዎች መገደላቸው ተገለጸ | በአድዋ ከተማ ሚያዚያ 04/2013 ዓ.ም፣ ሰኞ ረፋድ አካባቢ የኤርትራ ወታደሮች በከፈቱት ተኩስ ነዋሪዎች እንደተገደሉና እንደቆሰሉ ተገለጸ። | በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የአክሱምና የማዕከላዊ ዞን ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ እንዳሉት ተኩሱ በኤርትራ ወታደሮች መከፈቱን ለቢቢሲ አረጋግጠው፤ በዚህም ሳቢያ ቢያንስ አንድ ሰው እንደሞተ ሲናገሩ ነዋሪዎች ግን ቁጥሩ ስምንት ነው ብለዋል። ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ደግሞ በክስተቱ ሦስት ሰዎች በኤርትራ ወታደሮች መገደላቸውንና ቢያነስ 19 ሰዎች መቁሰላቸውን ማረጋገጡን ለቢቢሲ ገልጿል። ድርጅቱ ጨምሮም ይህ ሁኔታ የኤርትራ ወታደሮች አሁንም በትግራይ ክልል ውስጥ እንደሚገኙ ያመለክታል ብሏል። ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቀው የአክሱም ሆስፒታል ዶክተር ከትናንት ረፋድ ጀምሮ እስከ ከሰዓት በኋላ ድረስ 20 የቆሰሉ ሰዎች ከአድዋ እንደመጡ ለቢቢሲ ተናግሯል። ዓለም አቀፉ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ማኅበር (ኤምኤስኤፍ) እንዳለው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችን ከአድዋ ሆስፒታል እንዳመጣቸው የሚናገረው ይህ ዶክተር "ሁለት ሴቶች የሚገኙባቸው 20 ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች እያከምን ነው" ብሏል። ኤምኤስኤፍ በበኩሉ ትናንት በትዊተር እንደገለጸው ሰኞ እለት 18 ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ አድዋ ኪዳነምህረት ሆስፒታል እንደመጡና እርዳታ እንደተደረገላቸው በመጥቀስ፤ 11 ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ለከፍተኛ ህክምና ወደ አክሱም ሆስፒታል ተልከዋል ብሏል። "ወታደሮቹ ጥቃት በደረሰባቸው ሰዎች ላይ መተኮሳቸው ነግረውኛል" ብሏል። የአካል ጉዳት ከደረሰባቸው ስድስቱ ከፍተኛ ጉዳት ስለ ደረሰባቸው በጽኑ የህክምና ክትትል ውስጥ ሲሆኑ፤ ከእነዚህ አንዷ ሴት እንደሆነች ቢቢሲ ያነጋገረው ሐኪም ገልጿል። የህክምና ባለሙያው እንደሚለው አንዳንዶቹ ሆዳቸው ላይ፤ የተቀሩት ደግሞ በተለያየ የሰውነታቸው ክፍል ጉዳት ደርሶባቸዋል። እነዚህ በ20ዎቹ መጀመሪያ የእድሜ ክልል የሚገኙ ሲሆን አንድ በ60ዎቹ የሚገኙ ግለሰብ እንደሆኑ ለማወቅ ችለናል። ጥቃቱ በአድዋ መናኽሪያ በመባል በሚታወቀው አካባቢ እንደሆነ ያረጋገጡልን በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የአክሱምና የማዕከላዊ ዞን ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አስገዶም ስዩም፤ በመኪና ተጭነው ሲሄዱ የነበሩት የኤርትራ ወታደሮች "አንድ የባጃጅ አሽከርካሪ መንገድ ዘጋብን" በሚል ጥቃት እንደፈጸሙ ተናግረዋል። "ባለ ባጃጁ ጉዳት ደርሶበታል፤ አንድ ሰው እንደሞተም መረጃው ደርሶኛል። ሌሎች አምስት ሰዎች ደግሞ ተመትተው አክሱም ሪፈራል ሆስፒታል ይገኛሉ" ብለዋል። በተጨማሪም "የአክሱም ሕዝብም ሲሮጥ ነው የዋለው፤ የኤርትራ ወታደሮች ያገኙትን ሰው እየገደሉ እየመጡ ነው የሚል ስልክ ወደ አክሱም ተደወለ። ሕዝቡም ንብረቱን ትቶ፣ የከፈተው ሱቅ ሳይዘጋ ሸሸ" ሲሉ አቶ አስገዶም ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚህ ጉዳይ የኤርትራ መንግሥት የሰጠው ማብራሪያ የለም። በጉዳዩ ላይ የትግራይ ግብረ ኃይል ኃላፊ ሌተናል ጀነራል ዮሐንስ ገብረመስቀልና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማብራሪያ እንዲሰጡን ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ባለፈው ሳምንት ግን የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግረው የገቡት የኤርትራ ወታደሮች መውጣት እንደጀመሩ የኢትዮጵያ መንግሥት ገልጾ ነበር። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ተጠቂዎችና ኗሪዎች እንደሚሉት የኤርትራ ወታደራዊ ልብስ የለበሱ ታጣቂዎች ጥቃት እንደፈፀሙ ነው። የአካል ጉዳት ደርሶበት አክሱም ሆስፒታል ላይ ከሚገኙት ታካሚዎች አንዱ የሆነው በጸጉር ሥራ ላይ የተሰማራው ወጣት፤ ሰኞ ጠዋት ወደ ሥራ እየሄደ ዲጋዲግ ተብሎ በሚጠራው የአውቶብሶች መናኽሪያ መኪና ላይ ሆነው የሚተኩሱ የኤርትራ ወታደር ልብስ የለበሱ ወታደሮች በጥይት እንደመቱት ለቢቢሲ ገልጿል። "ሁለት የኤርትራ ሠራዊት የጫኑ የጭነት መኪኖች አንበሳ ባንክ አካባቢ ሲደርሱ መተኮስ ጀመሩ። አጋጣሚ አጠገቤ አንድ ሱቅ ነበርና ወደ እዚያ ልገባ ስሮጥ ሦስት ጊዜ ተኮሱብኝ። ሁለት ከጀርባዬ አንድ ደግሞ ሆዴ ላይ መታኝ።" ተመሳሳይ ቆስሎ ሆስፒታል ውስጥ የሚገኘው ሌላ ታካሚ አምስት ጥይት እንደተተኮሰበት በመግለጽ "አንዱ አንገቴ አካባቢ፣ ሦስት ከጀርባዬ፣ አንድ ደግሞ እጄን መቶኛል" ብሏል። ሰኞ እለት ጥቃቱ ሲፈጸም አካባቢው ላይ ማን ነበር ብሎ ቢቢሲ የጠየቀው ሌላ የአድዋ ከተማ ኗሪ በበኩሉ" ወታደሮቹ ወደ ከተማዋ ሲገቡ፣ ጥቃቱ ከመፈጸሙ በፊት አድዋ ላይ ምንም አይነት ጦርነት አልነበረም" ብሏል። ከሰሞኑ የኤርትራ ሠራዊትን አስመልክቶ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች መልስና ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከትግራይ ክልል ግጭት ጋር ተያይዞ በተደጋጋሚ ሲነሳ ለነበረው የኤርትራ ሠራዊት ተሳትፎ ምላሽ ሰጥተዋል። በዚህም የኤርትራ ሠራዊት በድንበር አካባቢ "የደኅንነት ስጋት እንዳለበት" ገልጾ በዚያው አካባቢ ሠራዊቱ እንዳለ ያስረዱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ፣ ለዚህም ምክንያቱ "በኢትዮጵያ ሠራዊት ላይ በህወሓት የተፈጸመው ጥቃት እንደሆነ" ተናግረው ነበር። በዚሁ ወቅት በተጨማሪ ትግራይ ውስጥ የሰብአዊ መብት ጥሰትና በደሎች መፈጸማቸውን የሚያመለክቱ መረጃዎች መኖራቸውን ጠቅሰው መንግሥታቸው የድርጊቱ ፈጻሚዎች ላይ እርምጃ ይወስዳል ብለዋል። "እኛ ወታደሩን የላክነው ወንጀለኞችን እንዲቆጣጠር እንጂ እንዲደፍር አይደለም። በዚህ ወንጀል የተሰማራ ወታደር ካለ በሕግ ተጠያቂ ይደረጋል" ማለታቸው የሚታወስ ነው። በፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልልን ሲያስተዳድር በነበረው ህወሓት መካከል ለረዥም ጊዜ የዘለቀው መቃቃርና አለመግባባት ተካሮ የህወሓት ኃይሎች የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል በማለት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የፌደራሉን ጦር ወደ ትግራይ ማዝመታቸው ይታወሳል። በትግራይ ክልል ውስጥ በተካሄደው ወታደራዊ ግጭት ሳቢያ ምን ያህል ሰዎች እንደሞቱ የሚታወቅ ነገር ባይኖርም አሃዙ በበርካታ ሺዎች ሊሆን እንደሚችል የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ይናገራሉ። ከዚህ ባሻገርም በግጭቱ ውስጥ ተሳታፊ በሆኑ ኃይሎች ግድያዎች፣ ጾታዊ ጥቃቶች፣ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ዘረፋና የንብረት ውድመቶች መፈጸማቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ባወጧቸው ሪፖርቶች ላይ አመልከተዋል። በተጨማሪም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዳለው በግጭቱ ሳቢያ ከሁለት ሚሊዮን ሰዎች በላይ ለመፈናቀል የተዳረጉ ሲሆን፤ ከአራት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ የሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ናቸው። |
news-48500958 | https://www.bbc.com/amharic/news-48500958 | በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ 5 ሰዎች ተገደሉ | በቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል ዳንጉር ወረዳ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ አምስት ሰዎች ተገደሉ። | ቅዳሜ ዕለት ዘጠኝ ሰዎች ቆታ ከምትባል ቀበሌ እቃ ጭነው ሲጓዙ ተኩስ ተከፍቶባቸው አምስቱ ወዲህ ህይወታቸው ሲያልፍ አራቱ ደግሞ መቁስላቸውን ስማቸውን እንዲጠቀስ የማይፈልጉ የአከባቢው ነዋሪ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጥቃቱ ቀደም ሲል በአካባቢው አጋጥሞ በነበረው ግጭት ስጋት ያደረባቸው ሰዎች ንብረታቸውን በተሽከርካሪ ጭነው ከአካባቢው ለመውጣት በመጓዝ ላይ በነበሩበት ጊዜ ነው። • በካማሼ ዞን ግጭት እጃቸው አለበት የተባሉ በቁጥጥር ስር ዋሉ ስለክስተቱ ቢቢሲ ያናገራቸው አንድ የዳንጉር ወረዳ ነዋሪ ''መንገድ በድንጋይ የዘጉ ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው አምስት ሰዎችን ገደሉ'' ሲሉ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። የሟቾች አስክሬን እዚሁ ይቀበር ወይስ ወደ ትውልድ ቀያቸው ይላክ በሚለው ላይ በአከባቢው ነዋሪዎች እና መከላከያ መካከል አለመግባባት እንደተፈጠረም ለማወቅ ችላናል። ''ማምቡክ ከተማ 'በለስ ቁጥር ሁለት' በሚበላው ቦታ አስክሬን የት ይቀበር በሚለ በተፈጠረው አለመግባባት ነዋሪዎች መከላከያዎች ላይ ድንጋይ መወርወር ጀመሩ። ከዚያም መከላከያዎች በከፈቱት ተኩስ አራት ሰዎች ቆሰሉ'' ሲሉ ሌላው የማምቡክ ከተማ ነዋሪ ለቢቢሲ ተናግረዋል። • በቤኒሻንጉል ክልል ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር ዋሉ በግጭቱ የቆሰሉት ወደ መተከል ዞን ፓዌ ሆስፒታል መወሰዳቸው ታውቋል። የአማራ መገናኛ ብዙሃን በበኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግጭት ለማረጋጋት ያቀኑትን የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር የኢኮኖሚ አማካሪ አቶ አየነው በላይን ጠቅሶ እንደዘገበው ጥቃቱ የተሰነዘረው ግንቦት 24/2011 ምሽት 12:30 አካባቢ ሲሆን ንብረታቸውን ከቀያቸው ለማውጣት በመኪና በማጓጓዝ ላይ በነበሩ ወገኖች ላይ ለዘረፋ የተሰማሩ አካላት ጥቃቱን እንደፈጸሙ ተነግሯል። ዘገባው አክሎም በጥቃቱ የአምስት ሰዎች ህይዎት ማለፉን እና አራት ሰዎች መቁሰላቸውን ዘግቧል። • ሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር መበራከት ምንን ያመለክታል? ትናንት ደግሞ አስከሬን ወደ ቤተሰብ ለመውሰድ በሚደረግ እንቅስቃሴ በነዋሪዎችና ማንቡክ በሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት አባላት መካከል ግጭት ተፈጥሮ የአንድ ሰው ህይዎት ማለፉን፤ ሦስት ነዋሪዎች እና ስድስት የመከላከያ አባላት ጉዳት እንደደረሰባቸው የአማራ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። አንድ የማንዱር ወረዳ ነዋሪ በወረዳው ከፍተኛ የሆነ የደህንነት ስጋትና አለመረጋጋት እንዳለ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የቤንሻንጉል ጉሙዝ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽፈህ ፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ገለታ ሃይሉ በበኩላቸው "ትናንት ዳንጉሩ ወረዳ ላይ ከዚህ ቀደም በተከሰተው ግጭት ቤተሰቡ ሙሉ ለሙሉ ተገድሎበት የነበረ አንድ ግለሰብ ከተወሰኑ ሰዎች ጋር በመሆን በአምስት ሰዎች ላይ ድርጊቱን ስለመፈጸሙ መረጃ ደርሶኛል" ብለዋል። "ግለሰቡ ቀደም ሲል አባወረኛ በሚባል ጎጥ ላይ ቤተሰቡ ተገድሎበት ነበር። በዚህም በበቀል ነው እነዚህ 5 ሰዎች መንገድ ላይ ጠብቆ ህይወታቸውን ያጠፋው" ሲሉ ገልጸዋል። በአካባቢው የሠላም ኮንፈረንስ ከተካሄደ በኋላ ግጭት እንዴት ሊፈጠር ቻለ ተብለው የተጠየቁት አቶ ገለታ "ወይይቱ ለውጥ አላመጣም ማለት አይቻልም። ብዙሃን ማግኘት በሚችለው ደረጃ ውይይት ተካሂዷል። ወሳኝ አካላትና ተሰሚነት ያላቸው ሽማግሌዎችና የሃይማኖት መሪዎችን ባሳተፈ መልኩ ነው ውይይቱ እና ኮንፈረንሱ የተካሄደው።" "ከመረጃ ውጭ የሆኑ ግለሰቦች ሊሆኑ ይችላሉ ወይም ደግሞ ይህንን ሊፈጽም የቻለው ለበቀል የተንቀሳቀሰ አካል ስለሆነ እስከታች ላለው ማህበረሰብ የተወሰነ ሥራ ያስፈልጋል" ብለዋል። የዳንጉር ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ካሳሁን አምስት ሰዎች መገዳላቸውን እና ስድስት መቁሰላቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠው፤ በወንጀሉ የተጠረጠሩ ሁለት ሰዎች መያዛቸውን እና ሌሎች ሁለት ሰዎች እየተፈለጉ መሆኑን ተናግረዋል። • "ሕይወቴን ብቻ ይዤ መውጣት ነው የምፈልገው" የወረዳው አስተዳዳሪ በአከባቢው ይህን መሰል ገጭት መከሰት የጀመረው ሚያዝያ 17 በአሽከርካሪ እና በተሳፋሪዎች መካከል በተከሰተ አለመግባባት መሆኑን እና በዚህም በተለያዩ ጊዜያት ወደ 30 የሚጠጉ ሰዎች መገደላቸውን እና የደረሱበት ያልታቁ ሰዎች መኖራቸውን አስታውሰዋል። በአካባቢው ቀደም ሲል ተከስቶ የነበረውን ግጭት ለመከላከል በቤኒሻንጉል እና አማራ ክልሎች አጎራባች ቦታዎች ላይ ኮማንድ ፖስት ተዋቅሮ ወደ ሥራ የተገባ ሲሆን ከግጭቱ ጋር በተያያዘ 8 አመራሮች እና ሌሎች 69 ግለሰቦች ተጠርጥረው መያዛቸውን ይታወሳል። |
55792458 | https://www.bbc.com/amharic/55792458 | እስራኤል የማትሪክ ፈተና ለሚቀመጡ ተማሪዎቿ ክትባት መስጠት ጀመረች | እስራኤል ዕድሜያቸው ከ16 እስከ 18 የሚሆኑ ወጣቶችን ኮቪድ ክትባት መስጠት ጀመረች። | ለነዚህ ወጣቶች ክትባቱ እንዲሰጠት የሆነው የማትሪክ ፈተና ሊቀመጡ ስለሆነ ነው። እስራኤል 9 ሚሊዮን ከሚሆነው ሕዝቧ ውስጥ ሩብ ያህሉ የመጀመርያውን የክትባት ጠብታ ወስዷል። የክትባቱ አይነትም ፋይዘር ሰራሹ መሆኑ ታውቋል። እስራኤል ለዜጎቿ ክትባት መስጠት የጀመረችው ባለፈው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ አካባቢ ከዲሴምበር 19 ጀምሮ ነው። ክትባቱ ሲጀመር ቅድሚያ የተሰጣቸው እድሜያቸው ለገፉ አዛውንቶች ሲሆን ከዚያም ተጋላጭ ለሆኑ ዜጎች ነበር። አሁን ዕድሜያቸው ከ40 በላይ የሆኑ ዜጎች ክትባቱን በመወሰድ ላይ ናቸው። እስራኤል ኢኮኖሚዋን በየካቲት ወር ሙሉ በሙሉ ለመክፈት እየታተረች ነው። የእስራኤል የትምህርት ሚኒስትር እንዳሉት አሁን ወጣት ተማሪዎችን መከተብ የተጀመረው ወደ ትምህርት እንዲመለሱና ፈተና እንዲቀመጡ ለማስቻል ነው። ወጣት ተማሪዎቹ ክትባቱን የሚወስዱት በወላጆቻቸው ፈቃድ ነው። እስራኤል ያሉ ተማሪዎች የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ሲጨርሱ የሚወስዱት የማትሪክ ፈተና ወደ ዩኒቨርስቲ ለመግባት አለመግባት የሚለዩበት ነው። የሚያመጡት ውጤትም በውትድርና ተሳትፏቸው ላይ ወሳኝ ሚና አለው። በእስራኤል ዜጎች ለተወሰነ ጊዜ የግዴታ የውትድርና አገልግሎትን ይሰጣሉ። የአገሪቱ የትምህርት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ክትባቱ መሰጠቱን እየቀጠለ ቢሆንም በሚቀጥለው ወር ትምህርት ስለመጀመር አለመጀመሩ ለመናገር ጊዜው ገና ነው። እስራኤል ክትባት በመስጠት ከአለም ፈጣኗ አገር ሆና ነው በዲሴምበር 19 የጀመረችው። በፈረንጆቹ 2020 መገባደጃ የሕዝቧን 10 እጅ ከትባ ጨርሳለች። እስራኤል 600ሺህ በተህዋሲው የተያዙ ዜጎች ያሏት ሲሆን 4ሺ የሚሆኑት ሞተውባታል። ትናንት የእሰራኤል መንግሥት ባወጣው አዲስ መመርያ የመንገደኞች በረራን ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ የጥር ወርን ሙሉ ማገዱን አስታውቋል። ይህም ተህዋሲውን ለመቆጣጠር የሚደረግ ጥረት አንድ አካል ነው። ቤንያሚን ኔትንያሁ እንደተናገሩት ይህ የበረራ እገድ አዲሱ የኮቪድ ዝርያ ወደ እስራኤል እንዳይገባ ለማድረግ የሚወሰድ ጥብቅ እርምጃ ነው ብለዋል። በአሁኑ ጊዜ የውጭ ዜጎች ወደ እስራኤል እንዲገቡ እየተፈቀደላቸው አይደለም። እስራኤል በአጭር ጊዜ ውስጥ ሙሉ 9 ሚሊዮን ዜጎቿን ጸረ ኮቪድ ክትባት በመከተብ የዓለም የመጀመርያዋ አገር ለመሆን ቀን ተሌት እየሰራች ትገኛለች። |
news-53789764 | https://www.bbc.com/amharic/news-53789764 | የቀነኒሳ በቀለ ክብረ ወሰን በኡጋንዳዊው ወጣት ተሰበረ | ኡጋንዳዲው ጆሹዋ ቼፕቴጌ በፈረንሳይ ሞናኮ በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ለ16 ዓመታት በቀነኒሳ በቀለ ተይዞ የነበረውን የ5000 ሜትር ሩጫ ክብረ ወሰን በሁለት ሰከንድ ማሻሻል ችሏል። | ጆሽዋ ቼፕቴጌ የ23 ዓመቱ ወጣት ባላፈው ዓመት በዶሃ የዓለም ሻምፒዮና ላይ የ10 ሺህ ሜትር አሸናፊ በሆነበት ወቅት የ5 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰንን ለማሻሻል እቅድ እንዳለው ገልጾ የነበረ ሲሆን በቅርብ ዓመታት ያሳካዋል ተብሎ ግን አልተገመተም ነበር። ነገር ግን በትላንቱ የሞናኮው ውድድር ላይ 5 ሺህ ሜትሩን 12 ደቂቃ 35.36 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመጨረስ ቀነኒሳን ክብረ ወሰን መስበር ችሏል። ቀነኒሳ በቀለ የዛሬ 16 ዓመት ክብረ ወሰኑን ሲያስመዘግብ ውድድሩን የጨረሰው በ12 ደቂቃ 37 ሰከንድ ከ35 ማይክሮ ሰከንድ ነበር። በሚያስገርም ሁኔታ ቼፕቴጌ በዚህ ዓመት ክብረ ወሰን ሲሰብር ይሄ ሁለተኛው ነው። ባለፈው የካቲት ወር ላይ ደግሞ በተካሄደ የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ሰዓት ማሻሻል እንደቻለ ተነግሯል። ''ሞናኮ በጣም ልዩ ቦታ ናት፤ የዓለም ክብረ ወሰኖችን ልሰብርባት የምችልባት ከተማ ናት'' ሲል በደስታ ተውጦ ቼፕቴጌ ተናግሯል። ''በዚህ ዓመት በእውነቱ ሞራልን ሰብሰብ አድርጎ ለመስራት ትንሽ ይከብዳል፤ ምክንያቱም በወረርሽኙ ምክንያት ሰዎች ከቤታቸው አይወጡም፤ ብዙ ነገሮችም በፊት እንደነበሩት አይደሉም፤ ተቀይረዋል። ነገር ግን በዚህ ሁኔታ ውስጥ በማሸነፌ በጣም ደስተኛ ነኝ።'' በሌሎች ውድድሮች የዓለም ሻምፒዮኑ ኖዋህ ሊይስ የ200 ሜትር ውድድሩን በ19 ሰከንድ ከ72 ማይክሮሰከንድ በሆነ ሰዓት በማሸነፍ አይበገሬነቱን አሳይቷል። ታናሽ ወንድሙ ጆሴፈስ ደግሞ በመጀመሪያው የዳይመንድ ሊግ ተሳትፎው እሱን ተከትሎ ሁለተኛ ሆኖ መጨረስ ችሏል። ኖርዌያዊው ዓለም ሻምፒዮን ካርስተን ዋርሆልም ደግሞ በ400 ሜትር መሰናክል ውድድር በአውሮፓውያኑ 1992 በኬቨን ያንግ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን መስበር ችሏል። ለብቻው ለማለት በሚያስደፍር መልኩ ሲሮጥ የነበረው ካርስተን ውድድሩን በ47 ሰከንድ ከ10 ማይክሮ ሰከንድ ጨርሷል። ኬንያዊቷ ሄለን ኦቢሪ ደግሞ የሴቶች 5 ሺህ ሜትር ውድድሩን በበላይነት ስታጠናቅቅ ሲፋን ሀሰን ደግሞ ጥቂት ዙሮች ሲቀሩት ውድድሩን አቋርጣ ወጥታለች። 5 ሺህ ብቻ ሰዎች እንዲመለከቱት በተፈቀደው የሞናኮው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ላይ ተመልካቾች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ ግዴታቸው ሲሆን አካላዊ ርቀትም መጠበቅ ነበረባቸው። |
54744271 | https://www.bbc.com/amharic/54744271 | በኒው ዚላንድ ሰዎች በፍቃዳቸው እንዲሞቱ የሚደነግግ ሕግ ሊወጣ ነው | በኒው ዚላንድ በጠና የታመሙ ሰዎች በፍቃዳቸው እንዲሞቱ የሚደነግግ ሕግ ሊወጣ ነው። | ባለፈው ወር በተካሄደ ሕዝበ ውሳኔ 65.2% መራጮች የፍቃድ ሞትን ደግፈዋል። ዩትኔዝያ ወይም የፈቃድ ሞት በጠና የታመሙ ወይም ከስድስት ወር በላይ እንደማይኖሩ የተነገራቸው ሰዎች በህክምና እርዳታ ሕይወታቸው እንዲያልፍ የሚደረግበት ሂደት ነው። ሕጉ በቀጣዩ ዓመት ጥቅምት ወር ጸድቆ ይተገበራል ተብሎ ይጠበቃል። ኒው ዚላንድ ሕጉን ካጸደቀች የፈቃድ ሞት ከሚተገበርባቸው ጥቂት አገሮች አንዷ ትሆናለች። ዩትኔዝያ ከተፈቀደባቸው አገሮች ኔዘርላንድ እና ካናዳ ይጠቀሳሉ። ኒው ዚላንዳውያን ባለፈው ወር መሪያቸውን ሲመርጡ ስለ ፈቃድ ሞት እና ዕጸ ፋርስ ሕዝበ ውሳኔ አድርገዋል። ዕጸ ፋርስን ለመዝናኛ መጠቀም ሕጋዊ እንዲሆን ድምጽ የሰጡት 46.1% ብቻ ሲሆኑ፤ 53.1% ተቃውመዋል። የፈቃድ ሞትን ጠቅላይ ሚንስትር ጀሲንዳ አርደን እንዲሁም ተቀናቃኛቸው ጁዲት ኮሊንስም ይደግፉታል። ሕዝቡም ሕጋዊ ይሁን ብሎ እንደሚመርጥ ይጠበቅ ነበር። ባለቤቱ የሞተችበት ማት ቪከርስ "ርህራሄ እና ደግነት አሸንፈዋል። በጠና የታመሙ ኒው ዚላንዳውያን ሕይወታቸውን ማሳለፍ ስለሚችሉ ደስ ብሎኛል" ሲል የተሰማውን ገልጿል። ጠበቃ የነበረችው ባለቤቱ የአንጎል እጢ ሲገኝባት በፈቃዷ ለመሞት ክስ ብትመሠረትም ሳታሸንፍ በጠና ታማ ከአምስት ዓመታት በፊት ሞታለች። "ባለቤቴ መሞት አትሻም ነበር። ማንም ሰው መሞት አይፈልግም። ነገር ግን መኖር የምርጫ ጉዳይ ነው። ስቃይ እየበረታ ሲሄድ መሞት አንዱ ምርጫ መሆን አለበት" ብሏል። አንድ ሰው በፈቃዱ ለመሞት በጠና የታመመ ወይም ከስድስት ወር በላይ እንደማይኖር የተረጋገጠ መሆን አለበት። ሰውነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተዳከመ እንደሄደና ውሳኔው ላይ ለመድረስ በቂ መረጃ እንዳለው ማረጋገጥም ተገቢ ነው። ሂደቱ የሚመራው በዶክተር ወይም በነርስ ነው። አንድ ሰው እድሜው ስለገፋ፣ የአእምሮ ህመም ስላለበት ወይም የአካል ጉዳት ስላለበት የፍቃድ ሞት ሕግን መተግበር አይችልም። ሕጉን የሚቃወሙ ሰዎች "እንድንኖር እንጂ እንድንሞት አትርዱን" ሲሉ ምክር ቤት ሄደው ተቃውሞ አሰምተዋል። ሕጉ ለማኅበረሰቡ አስጊ እንደሆነ እና ራስን ማጥፋትን ለመግታት ከወጣ መርህ ጋር እንደሚቃረን ይናገራሉ። ሌላው መከራከሪያ ነጥብ በጠና የታመሙ ሰዎች የቤተሰብ ሸክም ላለመሆን ብለው በፈቃዳቸው ሊሞቱ ይችላሉ የሚለው ነው። ዩትኔዝያን አጥብቆ ሲተች የነበረ ቡድን "የኒው ዚላንድ ዜጎች የተሳሳተ ሕግ እንዲጸድቅ ድምጽ በመስጠታቸው አዝነናል" ሲል መግለጫ አውጥቷል። የፈቃድ ሞትን ሕጋዊ ያደረጉ አገሮች የኒው ዚላንድን ሕዝበ ውሳኔ በቅርበት ሲከታተሉ ነበር። ከነዚህ መካከል ቤልጄም፣ ካናዳ፣ ኮሎምቢያ፣ ሉግዘምበርግ እና ኔዘርላንድስ ይጠቀሳሉ። በኔዘርላንድስ በህክምና ታግዞ ራስን ማጥፋት ይቻላል። በአሜሪካ ያሉ ብዙ ግዛቶች እና የአውስትራሊያዋ ቪክቶሪያ በህክምና የታገዘ ሞትን ፈቅደዋል። |
news-55677505 | https://www.bbc.com/amharic/news-55677505 | ትግራይ፡ የአውሮፓ ሕብረት በትግራይ ክልል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ የሚሰጠውን የበጀት ድጋፍ አገደ | የአውሮፓ ሕብረት ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን የ107 ሚሊዮን ዶላር የበጀት ድጋፍን የሰብዓዊ ርዳታ ድርጅቶች በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚፈልጉ ሰዎች ያለ አንዳች ገደብ ዕርዳታ ማቅረብ እስኪችሉ ድረስ ማገዱን አስታወቀ። | የአውሮፓ ሕብርት የበጀት ድጎማውን ያዘገየው በትግራይ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ነው የአውሮፓ ሕብረት ባወጣው ጽሑፍ ላይ የሕብረቱ ከፍተኛ ዲፕሎማት ጆሴፕ ቦሬል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በትግራይ የተከሰተውን ግጭት ለማስቆም ቀደም ሲል ካገኙት የሰላም ኖቤል ሽልማት አንጻር እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቀዋል። አክለውም "ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነን፣ ነገር ግን ለሰብዓዊ እርዳታ አቅራቢዎች ያለው ዕድል ክፍት እስካልሆነ ድረስ የአውሮፓ ሕብረት የታቀደውን የበጀት ድጋፍ ለኢትዮጵያ መንግሥት አይሰጥም" ብለዋል። ሮይተርስ በጉዳዩ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጽህፈት ቤትን ምላሽ የጠየቀ ቢሆንም አስተያየታቸውን ለማግኘት እንዳልቻለ ገልጿል። ከዚህ ቀደም የአውሮፓ ሕብረት ለኢትዮጵያ ከመደበው የበጀት ድጋፍ ውስጥ 90 ሚሊዮን ዩሮ (110 ሚሊዮን ዶላር) እንዲዘገይ ያሳለፈው ውሳኔ በተመለከተ እርምጃው በተሳሳተ ግምገማ ላይ የተመሰረተ ነው ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት ቅሬታውን ገልፆ ነበር። በወቅቱ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሆኑት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ ሕብረቱ የደረሰበት ውሳኔ "ሁኔታውን በተገቢው ሁኔታ ካለመገንዘብ" የተወሰደ ነው ሲሉ ገልፀውት ነበር። በታኅሣስ ወር የኢትዮጵያ መንግሥት ከተባበሩት መንግሥታት ጋር ርዳታ ድርጅቶች በክልሉ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች እርዳታ ማድረስ እንዲችሉ ስምምነት ላይ መድረሱን ገልጾ ነበር። በትግራይ ክልል ግጭት የተቀሰቀሰው ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በወቅቱ ክልሉን ያስተዳድር የነበረው ሕወሓት የሰሜን ዕዝን ማጥቃቱ ከተገለፀ በኋላ ነበር። ከዚህ በኋላ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የክልሉ ነዋሪዎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው ወደተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሲሸሹ፣ ከ50,000 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ወደ ሱዳን ተሰድደዋል። በኅዳር ወር መጨረሻ ላይ የፌደራል መንግሥቱ የህወሓት ኃይልን አሸንፎ የክልሉን ዋና ከተማ፣ መቀሌን መቆጣጠሩን እንዲሁም ጦርነቱ ማብቃቱን ማስታወቁ ይታወሳል። የተባበሩት መንግሥታት ግን አሁንም በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ጦርነት እየተካሄደ ስለመሆኑ መረጃ አለ ሲል ገልጿል። በታኅሣስ ወር የአውሮፓ ሕብረት በትግራይ ክልል የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ ለኢትዮጵያ መንግሥት የመደበውን የበጀት ድጎማ ማዘግየቱ ተሰምቶ ነበር። ቦሬል በትግራይ ክልል የተቀሰቀሰው ግጭት "ሕግን ከማስከበር በላይ ነው" በማለት ለአጠቃላይ ቀጠናው መረጋጋት ስጋት ነው ማለታቸውም ተሰግቧል። "ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች፣ ግድያዎች፣ ዘረፋዎች፣ አስገድዶ የመድፈር ድርጊቶችና ስደተኞችን በግዴታ ወደ አገራቸው መመለስና የጦር ወንጀል ድርጊቶች ሊሆኑ የሚችሉ ክስተቶችን በተመለከተ በተከታታይ መረጃ ይደርሰናል" ብለዋል። ጨምረውም "ይልቁንም ግጭቱ ወደ ቀጠናዊ ወደ መሆን የመሸጋገር እድል አለው፣ ለምሳሌ የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ግጭት ውስጥ መሳተፋቸው፣ የኢትዮጵያ ወታደሮች ከሶማሊያ መውጣታቸው" በማለት አስረጅ ጠቅሰዋል። የአውሮፓ ሕብረት ባለፉት ሰባት ዓመታት በኢትዯጵያ ላሉ የሌላ አገር ስደተኞች ካደረገው የ409 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ በተጨማሪ፣ 815 ሚሊዮን ዩሮ የእርዳታ ድጋፍ አድርጓል። የተባበሩት መንግሥታት ሐሙስ ዕለት በትግራይ ክልል በሚገኙና በርካታ ኤርትራውያን ስደተኞች በተጠለሉባቸው ሁለት መጠለያ ጣቢያዎች የዓለም አቀፍ ሕግ ጥሰት መኖሩን አስታውቆ ነበር። ድርጅቱ አክሎም በሽመልባና ህጻጽ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች በቅርቡ ቃጠሎ መድረሱንና ውድመት መኖሩን የሳተላይት ምስሎች እንደሚያሳዩ ይፋ አድርጓል። የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት በእነዚህ የመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ የሰብዓዊ እርዳታ እጥረት መኖሩን አስታውቆ፣ ባለፉት 10 ቀናት ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት መኖሩንም ገልጿል። ድርጅቱ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነቱ ከየትኛው ወገን እንደሆነ ግን ያለው ነገር የለም። የኤርትራው ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል ዛሬ አርብ፣ በትዊተር ገጻቸው ላይ "የተባበሩት መንግሥታት ስደተኞች ድርጅት በድጋሚ ኤርትራ ላይ ሌላ ኃላፊነት የጎደለው ስም የማጥፋት ዘመቻውን ቀጥሏል" ሲሉ ጽፈዋል። የኤርትራና የኢትዮጵያ መንግሥታት በተደጋጋሚ የኤርትራ ጦር በትግራይ ግጭት ውስጥ አልተሳተፈም ቢሉም፣ አንድ የኢትዮጵያ ጄነራል ግን የኤርትራ ወታደሮች ሳይጋበዙ መግባታቸውን በክልሉ መገናኛ ብዙሃን ላይ ሲናገሩ ተደምጠዋል። ቦሬል አክለውም ሱዳንና ኢትዮጵያ በድንበራቸው አካባቢ የገቡበትን ውጥረት እንዲያረግቡ ጠይቀዋል። ኢትዮጵያ ሰሞኑን የኢትዮጵያ ገበሬዎች በሚገኙበትና ሱዳን የእኔ ነው በማለት በኃይል በተቆጠጠረችው አካባቢ በምታሰፍራቸው ወታደሮች ምክንያት ትዕግስቷ እየተሟጠጠ መሆኑን ገልጻለች። የሱዳን መከላከያ ሚኒስትር በበኩሉ የኢትዮጵያ ተዋጊ ጄት የአየር ክልሉን ጥሶ መግባቱን በመግለጽ ድርጊቱን "አደገኛና ተገቢ ያልሆነ ውጥረት መፍጠር" ሲል ገልጾታል። |
45505753 | https://www.bbc.com/amharic/45505753 | የሕዝብ ፍላጎት ካለ ባንዲራን መቀየር ይቻላል፡ ጠ/ሚ ዐብይ | ጠቅላይ ሚንስትሩ ዐብይ አህመድ ዛሬ ረፋዱ ላይ ለተወሰኑ የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ላይ እንዳሉት በሰንደቅ አላማ ምክንያት አለመግባባትና ግጭት መፈጠር እንደሌለበት አሳስበዋል። | ባለፉት ጥቂት ወራት በተለያዩ የሃገሪቱ ስፍራዎች ዜጎች ለተቃውሞም ሆነ ለድጋፍ አደባባይ ሲወጡ የወደዱትን ሰንደቅ ዓላማ በመያዝ በአደባባይ መታየት የተለመደ ሆኗል። ከወራት በፊት ለእስረ ይዳርጉ የነበሩ ሰንደቅ አላማዎች ዛሬ ሰዎች እንደፈቀዳቸው ይዘው ሲንቀሳቀሱ ይስተዋላል። ትናንት ረፋዱ ላይ በአዲስ አበባ ከተማ የፊታችን ቅዳሜ ወደ ሃገር የሚመለሱትን የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦነግ) ከፍተኛ አመራሮችን ለመቀበል በማሰብ የኦነግ ባንዲራን በመንገዶች ጠርዥ ላይ በቀለም በሚቀቡ ወጣቶች እና እነሱን በተቃወሙ ነዋሪዎች መካከል ግጭት ተከስቶ ነበር። ስንደቅ ዓላማን በተመለከተ እና በሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ የሰጡት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ ''ባንዲራ የሃገር ወይም የፓርቲ የሃሳብ መግለጫ እና ማሳያ አርማ ነው። የትኛውም ቡድን ሃሳቡን በነጻነት የመግለጽ መብት አለው። ይህም መብት ባንዲራን ይጨምራል'' ብለዋል። • "የሰንደቅ ዓላማ ጉዳይ የህዝቡን ውይይት መጠየቁ አይቀሬ ነው" - አቶ ንጉሡ ጥላሁን • የቀድሞው የሶማሌ ክልል ሰንደቅ አላማ እንዲመለሰ ተደረገ ''ያለን ተሞክሮ አንዱ አንዱን አሸንፎ ስልጣን ይዞ ገዢ መሆን እንጂ መሪ መሆን አይደለም። እንደ ማሕብረሰብ አሸንፈን አናውቅም። አሸንፈን የምናውቀው ወራሪዎችን ብቻ ነው። አሁን እኛ እያልን ያለነው፤ አንዱ አሸናፊ ሌላው ተሸናፊ ይሁን ሳይሆን ሁሉም አሸናፊ የሚሆንበት አውድ ይፈጠር ነው'' ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ጨምረውም፤ አሜሪካ 13 ጊዜ ባንዲራዋን መቀየሯን በማስታወስ ''የኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎት ከሆነ ሕገ-መንግሥታዊ በሆነ መልኩ መክሮ፣ ዘክሮ እና ደምጽ ሰጥቶ ባንዲራው ሊቀየር ይችላል። ለዚህ ግን ትዕግስት የሌለው ተሸናፊ ነው'' ብለዋል። ''በቀን ሁለት ጊዜ በልቶ የማያድር ዜጋ ባለባት ሃገር የህዝብን ጥቅም እንዴት እናስጠብቅ ብሎ ከማሰብ ይልቅ፤ ጉልበቱን ለማሳየት ይሚፍጨረጨር ኃይል ካለ ማንም የማያሸንፍበት እልቂት ውስጥ እንገባለን። የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያሸንፍ የሚፈልግ ኃይል ሰጥቶ መቀበልን ማወቅ ይኖርበታል'' ሲሉም ተደምጠዋል። 'ሆርን ኦፍ አፍሪካ' ጠቅላይ ሚንስትሩ ዛሬ ረፋዱ ላይ በሰጡት መግለጫ መግለጫ ላይም መተባበርና በአንድነት መቆም በኢትዮጵያዊያን መካከል ብቻ መሆን ያለበት ነገር ሳይሆን የአካባቢውን ሃገራት በማቀፍ ትስስር መፍጠር እንደሚገባ ተናግረዋል። ''ኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ኤርትራ፣ ጅቡቲ እና ሶማሊያ አንድ ላይ ብንሰባሰብ በምሥራቅ አፍሪካ ኃያል ሃገር መፍጠር እንችላለን። ለሁላችን የሚበቃ መሬት፣ ውሃ እና ነዳጅ ያለው ሃገር እንፈጥራለን። ተበታትነን ግን ተሰልፈን ቻይናን ስንለምን እንኖራለን። ህዝቡም ይህን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ሃሳቡን በመደገፍ ከጎናችን እንዲቆም ጥሪዬን አቀርባለሁ።'' በማለት በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ሃገራት ተሰባስበው አንድ ኃያል ሃገር እንዲመሰረት ፍላጎት እንዳላቸው ጠቁመው አልፈዋል። |
news-50583014 | https://www.bbc.com/amharic/news-50583014 | ከትናንት በስቲያ ሁለት የምዕራብ ሸዋ ባለስልጣናት በጥይት ተትመተው ተገደሉ | በምዕራብ ኦሮሚያ የሚገኘው የጀልዱ ወረዳ አመራር የሆኑ ሁለት የአካባቢው ባለስልጣናት ከትናንት በስቲያ ማንነታቸው አልታወቀም በተባሉ ታጣቂዎች መገደላቸው ተነገረ። | የጀልዱ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ረጋኔ ከበበ እና የጎጆ ከተማ የፖለቲካ ዘረፍ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ገረመው በጎጆ ከተማ ማክሰኞ ምሽት 12 ሰዓት አካባቢ በጥይት ተመትተው መገደላቸውን የኦሮሚያ ክልል የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዴሬሳ ተረፈ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። • "በኢትዮ ቴሌኮም ኃላፊ ግድያ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር የዋለ የለም" የነቀምቴ ፖሊስ አዛዥ • "የኢትዮ ቴሌኮም ኃላፊዎች ሕይወቱን ማዳን ይችሉ ነበር" የአቶ ገመቺስ ባለቤት ወ/ሮ መሰረት በክልሉ ይህን መሰል በመንግሥት ኃላፊዎች ላይ ያነጣጠረ ግድያ ሲፈጸም ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ አይደለም። ባለፈው ሳምንት እንኳ አንድ የምዕራብ ሸዋ ዞን ባለስልጣን በተመሳሳይ በጥይት ተመትተው ተገድለዋል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያም ማንነታቸው በውል ያልተገለጹ ታጣቂዎች የነቀምቴ ከተማ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ኃላፊ የነበሩትን ኮማንደር ጫላ ደጋጋን መግደላቸው ተነግሯል። በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በተለይም በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙ የተለያዩ ዞኖች ከዚህ ቀደም በተለያዩ የመንግሥት ኃላፊነት ላይ ያሉ ሰዎችን ኢላማ ያደረጉ ግድያዎች በተደጋጋሚ ሲፈጸሙ ቆይተዋል። ከዚህ በተጨማሪም ከመንግሥት ባለስልጣናቱ ባሻገር ሰላማዊ የአካባቢዎቹ ነዋሪዎችና የውጪ ዜጎችን ጨምሮ በተለያዩ ሙያ ላይ የተሰማሩ ሰዎችም ማንነታቸው በውል ባልተገለጹ ታጣቂዎች ተገድለዋል። የኦሮሚያ ክልል የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዴሬሳ ተረፈ ለቢቢሲ ሲናገሩ፤ በክልሉ በሚገኙ ባለስልጣናት ላይ ኢላማ እያደረገ የመጣውን ይህን ግድያ ለማስቆም በቅርቡ የተቋቋመው እና 'ጋዲሳ ሆገንሰ ኦሮሞ' የሚሰኘው አካል ከመንግሥት ጋር በመሆን መፍትሄ እያፈላለገ እንደሆነ ተናግረዋል። • በምዕራብ ወለጋ ዞን የኦሮሚያ የመንግሥት ኃላፊ በታጣቂዎች ተገደሉ በኦሮሚያ ጉዳዮች ላይ ትኩረት የሚያደርጉ ፓርቲዎች ስብስብ መድረክ የሆነው 'ጋዲሳ ሆግንሰ ኦሮሞ' የኦሮሞ ህዝብን ማዕከል ያደረጉ ፓርቲዎች አብረው ለመስረት ከስምምነት ደርሰው ከሁለት ወራት በፊት ያቋቋሙት አካል ነው። በ'ጋዲስ ሆግንሰ ኦሮሞ' ምስረታ ላይ አቶ ለማ መገርሳ፣ ዳውድ ኢብሳ፣ መረራ ጉዲና (ዶ/ር)፣ ብርጋዴር ጀነራል ከማል ገልቹ እና በቀለ ገርባ ፓርቲዎቻቸውን ወክለው ፊርማቸውን ካኖሩ አመራሮች መካከል ይገኙበታል። አቶ ዴሬሳ "ለኦሮሞ ህዝብ እንታገላለን የሚሉ አካላት ትግላቸው በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲሆን ነው የመንግሥት ፍላጎት" ይላሉ። አክለውም "አለመረዳዳት ነው እንጂ ኦሮሞ ኦሮሞን ገድሎ የሚገኝ ጥቅም የለም፤ ኪሳራ ነው ማለት ነው" ብለዋል አቶ ዴሬሳ። በተለይ በምዕራባዊ የኦሮሚያ አካባቢዎች በተደጋጋሚ ላጋጠመው ባለስልጣናትን ኢላማ ላደረገው ግድያ ተጠያቂውን ለመለየት አስቸጋሪ እንደሆነ የሚናገሩት አቶ ዴሬሳ፤ "ታጥቆ የሚንቀሳቀስ ኃይል ባለበት ሁኔታ እከሌ ነው ማለት አይቻልም፤ እርስ በእርስ መጠቋቆም ነው የሚሆነው" ብለዋል። • የምዕራብ ኦሮሚያ ነዋሪዎች ስጋትና ሰቆቃ ይህንን ጥቃት ለማስቆም በአጠቃላይ "እንደ መንግሥት ያለን አቋም የጦር መሳሪያ አያስፈልግም የሚል ነው" በማለት ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ወገኖች ወደ ሰላማዊው መድረክ እንዲመጡ እንደሚፈለግ አመልክተዋል። በተጨማሪም አቶ ዴሬሳ "ሰላም በሌለበት እና ታጥቆ የሚንቀሳቀስ አካል ባለበት ሁኔታ ለወንጀሉ ተጠያቂው እገሌ ነው ብሎ መደምደም አስቸጋሪ ነው የሚሆነው" ያሉ ሲሆን፤ ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያዎችን መቆጣጠር እና የህግ የበላይነትን ማስከበር መሰል ወንጀሎች እንዳይፈጸሙ ማድረግ ይቻላል ብለዋል። በምዕራቡ የአገሪቱ አካባቢ የተፈጸሙ ጥቃቶችን በተመለከተ ኃላፊነቱን የወሰደ ቡድን ባይኖርም ድርጊቱ በተለይ ኢላማ ከሚያደርጋቸው የመንግሥት ባለስልጣናት አንጻር ምናልባት ፖለቲካዊ ዓላማ ሊኖረው ይችላል ተብሎ ይገመታል። ቀደም ሲል አንዳንድ ባለስልጣንትና የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች እንደሚገምቱት ከኦነግ አፈንግጦ የወጣና በአካባቢው የሚንቀሳቀስ ቡድን ጥቃቱን እየፈጸመ ሊሆን እንደሚችል ይናገራሉ። የአካባቢውን ሰላም ለማስከበር የዕዝ ማዕከል (ኮማንድ ፖስት) የተቋቋመ ቢሆንም ስለጥቃቱ ፈጻሚዎችም ሆነ ከጥቃቶቹ በኋላ ስለተወሰዱ እርምጃዎች እስካሁን የሰጠው መግለጫ የለም። |
news-55677497 | https://www.bbc.com/amharic/news-55677497 | ሱዳን በምሥራቃዊ ግዛቷ የአየር ክልል በረራ እንዳይካሄድ አገደች | ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስናት ምሥራቃዊው የአል-ቀዳሪፍ ግዛት ላይ ማንኛውንም የአየር በረራ እንዳይካሄድ አገደች። | የሱዳን ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን ሐሙስ ዕለት "በአገሪቱ ምሥራቃዊ ክፍል የአል ቀዳሪፍና የአል ፋሽጋ አየር ክልል ላይ ማንኛውም በረራ እንዳይካሄድ" ውሳኔ መተላለፉን የሱዳን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የአገሪቱ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን ኃላፊ ኢብራሂም አድላን እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት ረቡዕ ዕለት የኢትዮጵያ አየር ኃይል የሱዳንን አየር ክልልን ጥሶ ገብቷል በሚል አገራቸው ከከሰሰች በኋላ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ምንም ዓይነት ምላሽ አልሰጠም። ይህንን ተከትሎም ሱዳን ኢትዮጵያን እንዲህ አይነት ድርጊት "መዘዙ የከፋ ይሆናል" በማለት አስጠንቅቃለች። የሱዳን ወታደሮች ኢትዮጵያውያን የሚኖሩባቸውን የእርሻ መሬቶችን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ ኢትዮጵያ ጉዳዩን አለዝባ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት ያላትን ፍላጎት በመግለጫዎች ብታሳውቅም ነገሮች እየተጠናከሩና እየተባባሱ በመምጣት ላይ ናቸው። ባለፈው ሳምንት በድንበር አካባቢ ያለውን አለመግባባት በተመለከተ ጉዳዩ በሁለቱ አገራት መንግሥታት አማካይነት በሠላማዊ መንገድ እንደሚፈታና ለዚህም ጥረት እያደረገች እንደሆነ ስትገልጽ የነበረችው ኢትዮጵያ ከሱዳን ሠራዊት በኩል የሚደረገው እንቅስቃሴ እንዳሳሰባት ገልጻለች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እንደተናገሩት በድንበር አካባቢ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እየበረታ መጥቷል። ከሁለት ወር በፊት በትግራይ ክልል የተከሰተውን ግጭት በመጠቀም የሱዳን ጦር ድንበር ጥሶ መግባቱን የገለጹት ቃል አቀባዩ፣ አሁን ደግሞ "የሱዳን ወታደራዊ ኃይል በድንበር አካባቢ ወደ ተጨማሪ ቦታዎች ዘልቆ ለመግባት የተጠናከረ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው" ሲሉ ከስሰዋል። ችግሩን በትዕግስትና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት መሞከር "ፍርሃት ወይም መወላወል አይደለም" ያሉት አምባሳደር ዲና፣ አካባቢውን ከግጭት ለመጠበቅ ሲባል ኢትዮጵያ ጉዳዮች እንዳይካረሩ ለማድረግ እየጣረች ቢሆንም ይህ ታጋሽነት ገደብ እንዳለው ሲሉ አመልክተዋል። ኢትዮጵያ ሱዳን ድንበሬን ጥሳ ገብታለች በሚል ስትከስ፣ የሱዳን ጦር በበኩሉ የኢትዮጵያ ሚሊሽያ ላለፉት 25 ዓመታት በቁጥጥሩ ስር አድርጎት የነበረውን የራሳችንን መሬት መልሰን ይዘናል ሲል መናገሩ ይታወሳል። ከሳምንታት በፊት ወደ አወዛጋቢው የድንበር አካባቢ የሱዳን ሠራዊት ዘልቆ ከገባ በኋላ በእርሻ ማሳዎችና በንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ሁለት ሺህ የሚሆኑ ነዋሪዎች መፈናቀላቸው ተነግሯል። ከሁለት ሳምንት በፊት የሱዳን የማስታወቂያ ሚኒስትር ለሮይትርስ ዜና እንደተናገሩት ሠራዊታቸው ይገባናል የሚሉትን ከኢትዮጵያ ጋር የሚዋሰኑበትን አብዛኛውን አካመቆጣጠሩን ገልጸው ነበር። ኢትዮጵያ ሱዳን በሁለቱ አገራት መካከል የነበረውን ስምምነት ጥሳለች በማለት በተደጋጋሚ የከሰሰች ሲሆን፤ በድንበር አካባቢ ያለው ሁኔታ ወደ ነበረበት ተመልሶ ችግሩ በውይይት እንዲፈታ በተደጋጋሚ ጠይቃለች። የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ለመሆኑ ከዚህ ድንበር ጋር በተያያዘ ያለው ታሪክ ምንድነው? ኢትዮጵያና ሱዳን የሚጋሩት ድንበር ርዝመት 750 ኪሎ ሜትር ያካላል። ነገር ግን ይህ ድንበር አብዛኛው ርቀት ግልጽ በሆነ መንገድ መሬት ላይ አልተመላከተም። ይህን ለማሳካት ተደጋጋሚ ንግግሮች ተጀምረው በተደጋጋሚ ተቋርጠዋል። ዶ/ር ወንድወሰን ተሾመ የተባሉ ተመራማሪ፤ "የአፍሪካ ቅኝ ግዛት ዘመን ድንበሮች በተለይም የሱዳንና ኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ" በተሰኘና በእንግሊዝኛ በተጻፈ ጥናታቸው እንደገለጹት የሁለቱ አገሮች ድንበር የአሁን ጊዜ ወሰን እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ1902 እና በ1907 የተደረጉ የአንግሎ-ኢትዮጵያ የካርታ ላይ ምልከታ ስምምነቶችን መሠረት ያደረጉ ናቸው። በቅኝ ግዛት ወቅት በሱዳንና በኢትዮጵያ መሬት ላይ ለተመላከቱ ድንበሮች ኃላፊነቱ ተሰጥቶት የነበረው ሁነኛ ሰው የአይሪሽ ተጓዥና አሳሽ የነበረው ቻርለስ ግዊይን ነበር። የሱዳን ገዳሪፍና ብሉ ናይል ግዛቶች ከአማራ ክልል ጋር ይዋሰናሉ። በ1908 ነበር በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ድንበር የተሰመረው።። የአልፋሽቃ ማዕዘን ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በይገባኛል የምትወዛገብብት አካባቢ ረዥም የግዛት ድንበር ነው ያላት። ሁለቱም አገሮች ለም ነው የሚባለውን ፋሽቃ አካባቢን እጅጉኑ ይፈልጉታል። ይህ በሁለቱ አገሮች ዓይን ውስጥ ያለው አካባቢ የአልፋሽቃ ማዕዘን ወይም የአልፋሽቃ ጥግ ተብሎ ይጠራል። በዚህ ድንበር ሁለቱም አቅጣጫ የሚገኙ ገበሬዎች ባሻገራቸው ያሉ ለም መሬቶች ላይ ያማትራሉ። አልፋሽቃ ማዕዘን በደቡብ ምሥራቅ ሱዳን ምሥራቃዊ ገዳሪፍ የሚገኝ ለም መሬት ነው። አልፋሽቃ መሬት 250 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሸፍንና 600 ሺህ ኤክር ለም መሬትን የሚሸፍን ነው። ለለምነቱ ምክንያት የሆኑት እንደ አትባራ፣ ሰቲት እና ባስላም ወንዞችም በቅርብ ይገኛሉ። ሁለቱ መንግሥታት ከዚህ ቀደም ይህንን አወዛጋቢ ድንበር በድጋሚ ለማስመር፣ የጋራ ፕሮጀክቶችን ለመጀመር እና የአካባቢው ሕዝብ ተጠቃሚ ለማድረግ ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር። ቀደም ካለው አስተዳደር ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግሥት በአገሬው ሕዝብ ሉአላዊ መሬቱን ቆርሶ እየሰጠ ነው በሚል ተደጋጋሚ ወቀሳ ሲቀርብበት ነው የቆየው። እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2014 የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እና የወቅቱ ሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር ሐሰን አልበሽር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸውን ድንበሩ መሬት ላይ የሚመላከትበትን የመጨረሻ ቀን እንዲያሳውቁ መመርያ አስተላልፈውላቸው ነበር። ሆኖም አወዛጋቢውን ድንበር መሬት ላይ የማመላከቱ ሥራ እስከዛሬም አልተሳካም፡፡ |
news-52414668 | https://www.bbc.com/amharic/news-52414668 | ታዋቂው ሳኡዲ አረቢያዊው መብት ተሟጋች በእስር ቤት ሳሉ 'ህይወታቸው አለፈ' | እአአ ከ2013 ጀምሮ በእስር ላይ የነበሩት የሳኡዲ አረቢያ ታዋቂ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች በእስር ቤት መሞታቸውን አክቲቪስቶች ተናገሩ። | ዶክትር አብዱላህ አል-ሃሚድ የሳኡዲ ሲቪል እና ፖለቲካ መብቶች ማኅበር መስራች የነበሩ ሲሆን በስትሮክ ተመተው በህይወት እና ሞት መካከል መቆየታቸው ተነግሯል። የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች ዶ/ር አብዱላህ አል-ሃሚድ ከእስር እንዲለቀቁ በተደጋጋሚ ጫና ሲያሳድሩ ቆይተዋል። በሰብዓዊ መብት አያያዝ የሚተቸው የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በአክቲቪስቱ የሞት ሪፖርት ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል። የ69 ዓመት አዛውንት ከሆኑት ዶ/ር አብዱላህ አል-ሃሚድ ጋር ሞሐመድ አል-ቃሃታኒ የተባሉ አክቲቪስትም ለእስር ተዳርገው ነበር። ሁለቱ አክቲቪስቶች "አለመረጋጋትን በመፍጠር" ጥፋተኛ ተብለው እያንዳንዳቸው የ10 እና 11 ዓመት እስር ተበይኖባቸው ነበር። የሳኡዲ አረቢያ የመብት ተሟጋቾች ዶ/ር አል-ሃሚድ በቂ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ አልተደረገም ሲሉ የሳኡዲ አረቢያን መንግሥት ይተቻሉ። ዶ/ር አል-ሃሚድ ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ ጤናቸው መቃወሱ ተነግሯል። መቀመጫቸውን ዩናይትድ ኪንግደም የደረጉት እና የሳኡዲ መንግሥት ተቺ የሆኑት መምህርት ማዳዊ አል-ራሺድ፤ ዶ/ር አል-ሃሚድን "የሰብዓዊ መብት ትግል ምልክት" ሲሉ ይገልጿቸዋል። የሳኡዲ የሲቪል እና ፖለቲካል መብቶች ማኅበር መስራቾቹ ክስ ከተመሰረተባቸው በኋላ እንዲዘጋ ተደርጓል። |
news-56144351 | https://www.bbc.com/amharic/news-56144351 | አሜሪካ የቀድሞ የናዚ ማጎሪያ ካምፕ ጠባቂን በ95 አመታቸው አሳልፋ ሰጠች | አሜሪካ የአንደኛው ናዚ ማጎሪያ ካምፕ ጠባቂ የነበሩትን የ95 አመቱን ግለሰብ ሰሞኑን ለጀርመን ኣሳልፋ ሰጥታለች። | ፍሬዲሪክ ካርል በርገር የተባሉት የቀድሞ ጥበቃ ከአውሮፓውያኑ 1959 ጀምሮ ነዋሪነታቸውን በአሜሪካ አድርገው የነበረ ሲሆን በትናንትናው ዕለትም ነው ወደ ፍራንክፈርት የበረሩት። በርገር፣ ኑንጋሜ ተብሎ በሚጠራው የማጎሪያ ካምፕ በጥበቃነት ይሰሩ እንደነበር ቢያምኑም ምንም አይነት ግድያም ሆነ የእስረኞችን ስቃይ አልተመለከትኩም ብለዋል። የጀርመን አቃቤ ህጎችም እንዲሁ በግለሰቡ ላይ ጠንከር ያለ ማስረጃ ባለማግኘታቸው ክሱን እንደተውት ተሰምቷል። ሆኖም የጀርመን ፖሊስ ግለሰቡን ለምርመራ እፈልገዋለሁ ያለ ሲሆን ከሰሞኑም ፖሊስ ጥያቄ እንደሚያቀርብለት ተነግሯል። ክሱ እንደገና ይከፈታል የሚለው ጉዳይም አዛውንቱ በሚሉት የሚወሰን ይሆናል። በባለፈው አመት የስደተኞችን የጥገኝነት ጥያቄ የሚመለከት የአሜሪካ ፍርድ ቤት ዳኛ የሆኑት ሬቤካ ሆልት የማጎሪያ ካምፑ ውስጥ የነበሩ እስረኞች አስከፊ በሚባል ሁኔታ እንደነበሩና በርካቶችም በድካም እስኪሞቱ ድረስ ለበዝባዥ የጉልበት ስራ ተዳርገዋል በሚል ግለሰቡ በአስገዳጅ ሁኔታ ወደ ጀርመን እንዲላኩ ውሳኔው የተላለፈው። በነበረው ችሎት ሲሰማ አዛውንቱ በርገር ከካምፕ ለማምለጥ ይሞክሩ የነበሩ እስረኞችን ሲመልሱ እንደነበር አምነዋል። የአሜሪካ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሞንቲ ዊልኪንሰን ከሰሞኑ እንዳሉት በርገር ለጀርመን ተላልፈው መሰጠታቸው አገራቸው ለፍትህ ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው። "አሜሪካ በናዚ ማጎሪያ ካምፖች በሰብዓዊነት ላይ የሚፈፀም ወንጀል ለተሳተፉ፣ ሌሎች ጭፍጨፋዎችንም ሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ላደረሱ ግለሰቦች መደበቂያ አይደለችም" በማለት ጠቅላይ አቃቤ ህጉ ተናግረዋል። በርገር ከዋሽንግተን ፖስት ጋር ባደረጉት ቆይታ በካምፑ የጥበቃ ሥራ ላይ ተሰማርተው የነበሩት ለአጭር ጊዜ እንደሆነና መሳሪያም ይይዙ እንዳልነበር አስረድተዋል። ለዘመናት አሜሪካ የኖሩት አዛውንቱ በርገር የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ተከትሎ "ከ75 ዓመታት በኋላ፣ ይህ የሚገርም ነው ለማመንም ይከብደኛል። ከቤቴ እኮ ነው በግድ እያስወጣችሁኝ ያላችሁት" ብለዋል። የጀርመን አቃቤ ህግ በናዚ ማጎሪያ ካምፕ ተሳትፎ አላቸው የተባሉ ግለሰቦችን ከማደን አላቆመም። ከሰሞኑ በናዚ የማጎሪያ ካምፕ ውስጥ ፀሃፊ ነበሩ ነበሩ የተባሉ የ95 አመት አዛውንት በሰሜን ጀርመን ውስጥ በጅምላ ግድያ ወንጀል ተወንጅለዋል። ኢምግራንድ ኤፍ የተባሉት አዛውንት ሃምበርግ በሚገኝ የአረጋውንያን እንክብካቤ ማዕከል የሚኖሩ ሲሆን ከአስር ሺህ በላይ ክሶች ቀርበውባቸዋል። ስተትሆፍ በተባለው አሰቃቂ የማጎሪያ ካምፕ ውስጥ ፀሃፊ የነበሩ ሲሆን በካምፑ ውስጥ በነበረው የጅምላ ግድያና ጭፍጨፋ አስተባብረዋል በሚልም ነው እየተወነጀሉ ያሉት። በሁለተኛው አለም ጦርነት ወቅት በዚሁ ማጎሪያ ካምፑም 65 ሺህ ሰዎች እንደሞቱ ተገልጿል። |
41495282 | https://www.bbc.com/amharic/41495282 | የላስ ቬጋሱ ታጣቂ ካሜራዎችን በሆቴሉ ውስጥ ገጥሞ ነበር | የ64 ዓመቱ ፓዶክ 59 ሰዎችን በገደለበት እና ከ500 በላይ ሰዎችን ባቆሰለበት ጥቃት የፖሊስን እንቅስቃሴ ለመቃኘት በማሰብ በነበረበት የሆቴል ክፍል ውስጥ እና በአቅራቢያው ካሜራዎችን ገጥሞ እንደነበር ፖሊስ አስታወቀ። | በሆቴል ከፍል ውስጥ የተገኘ መሳሪያ በሆቴሉ መተላለፊያዎች (ኮሪደሮች) የገጠማቸው ሁለት ካሜራዎች እና በበር ላይ የገጠመው ካሜራ ''የፖሊሶችን ወይም ፀጥታ አስከባሪዎችን'' እንቅስቃሴ እንዲቃኝ አስችሎታል ብሏል ፖሊስ። እሰካሁን ፓዶክ ጥቃቱን ለመፈፀም ምን እንዳነሳሳው ግልፅ የሆነ ነገር ባይኖርም ጥቃቱን ለመፈፀም ከፍተኛ ዝግጅት አድርጎበት ነበር። የፖሊስ አዛዥ ጆሴፍ ሎምባርዶ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ''ጥቃቱ ከመፈፀሙ በፊት ከፍተኛ ቅድመ ዝግጅት እንዳደረገ እርግጠኞች ነን'' ብለዋል። የላስ ቬጋሱ ጥቃት ፈጻሚ ስቴፈን ፓዶክ ማነው? ስለምን የላስ ቬጋሱ አጥቂ 'ሽብርተኛ' አልተባለም? ይህ ጥቃት የአሜሪክ የጦር መሳሪያ አያያዝ ህግ ላይ ክርክር ፍጥሯል። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ''በሕጉ ላይ መነጋገር ካስፈለገን የምንነጋገርበት ጊዜ አሁን አይደለም'' ብለዋል። ፖሊስ ፓዶክ ጥቃቱን ከፈፀመበት ክፍል ውስጥ 23 መሳሪያዎችን ሲያገኝ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥም የተለያዩ መሳሪያዎችን እና ፈንጂዎችን አግኝቷል። ጥቃቱ ሲፈፀም ከተቀረፁ ምስሎችና ድምፆች በመነሳት መረዳት እንደተቻለው ፓዶክ የተጠቀማቸው መሳሪያዎች በፍጥነት እንዲተኩሱ ለማድረግ የተለያዩ መለዋወጫዎችን በመጠቀም አሻሽሎ ነበር። |
news-54351586 | https://www.bbc.com/amharic/news-54351586 | እርጉዟን ሴት እየረጋገጠ የደበደባት አውስትራሊያዊ ተፈረደበት | የዛሬ ዓመት ግድም ኅዳር ወር በአውስትራሊያ ሲድኒ፣ በአንድ ሬስቶራንት በረንዳ ላይ እርጉዝ ሴትን ደብድቦ የዓለም መነጋገርያ የነበረው ነጭ አክራሪ ተፈረደበት። | የ44 ዓመቱ ስቲፕ ሎዚና፣ ወ/ሮ ራና ኢላዝማር ተባለች የ32 ዓመት እርጉዝ ሴትን ነበር አስተኝቶ የረጋገጣት። ወ/ሮ ራና ኢላዝማር ያን የዘጠኝ ወር እርጉዝ ሳለች ነበረ፤ ከጓደኞቿ ጋር ካፌ ቁጭ ብላ ሻይ ቡና በማለት ላይ ሳለች ያልተጠበቀ ነገር የደረሰባት። ይህ ሰው ድንገት ወደርሷ ተጠግቶ ገንዘብ እንድትሰጠው የጠየቃት ሲሆን ወዲያውኑ ባልተጠበቀ ሁኔታ አካላዊ ጥቃት ሰንዝሮባታል። ክስተቱን የሚያሳየው ቪዲዮ በማኅበራዊ ሚዲያ በከፍተኛ ሁኔታ ከተጋራ በኋላ በአውስትራሊያ ብቻም ሳይሆን በመላው ዓለም ትልቅ መነጋገርያ ለመሆን በቅቶ ነበር። ጉዳዩን የተመለከተው የሲድኒ ፍርድ ቤት ሰውየው ድርጊቱን በ"ሙስሊም ጠልነት" የፈጸመው እንደሆነ ደርሶበታል፤ ግለሰቡ ድብደባውን ሲፈጽምም "እናንተ እስላሞች…" እያለ ይናገር ነበር ብሏል ዐቃቤ ሕግ። ሰውየው ነፍሰጡሯን ሴት 14 ጊዜ በቡጢ ከነረታት በኋላ በእግሩ ጭንቅላቷን መቷታል። በመጨረሻ የካፌው ተስተናጋጆች ተጋግዘው እርጉዟን ሴት ታድገዋታል። ክስተቱን የሚያሳየው የደኅንነት ቪዲዮ በአውስራሊያ ሚዲያዎች ከታየ በኋላ በርካታ ሰዎች ቁጣቸውን ገልጸዋል። የሴቶች ጥቃት ይብቃ የሚሉ እንቅስቃሴዎችም እንዲቀሰቀሱ ምክንያት ሆኗል። ወ/ሮ ኤላዝማር ለፍርድ ቤት ጥቃቱ የደረሰባት ሙስሊም በመሆኗ እንደሆነ ተናግራለች። ሙስሊም ጠልነትና የሴቶች ጥቃት እንዲቆም ጠይቃለች። ዳኛው ክርስቶፈር ክሬግ ሰውየው ጤናው የተቃወሰ እንደሆነ ከተናገሩ በኋላ ጥቃቱ በእሷም ሆነ በሚወለደው ልጅ ላይ ከፍተኛ አደጋ ሊያደርስ ይችል እንደነበር አብራርተዋል። ወ/ሮ ኤላዝማር "መልካም ሰዎች ባያስጥሉኝ ኖሮ ሞቼ ነበር" ብላለች። ከጥቃቱ የታደጓትን ሰዎችም አመስግናለች። ሆኖም ግን ለፍርድ ቤት እንዳብራራችው ከዚያ ጥቃት በኋላ ደጅ የመውጣት ፍርሃት እንዳደረባትና የደረሰባትን ጥቃት ለተመለቱት አራት ህጻን ልጆቿ ስለ ጉዳዩ ማብራራት ከባድ እንደሆነባት በመግለጽ የሥነ ልቦና ጫናውን አብራርታለች። ጥቃት ፈጻሚው በበኩሉ ጠበቃ አልፈልግም ብሎ ራሱ ፍርድ ቤት የተከራከረ ሲሆን ብዙም ስሜት የማይሰጡ ነገሮችን በፍርድ ቤት ይናገር ነበር ሲሉ የአውስራሊያ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ዳኛው ፍርድ ሲሰጡ ሰውየው ከዚህ ቀደም ስኪዞፎርኒያ የተባለ የአእምሮ ህመም ተጠቂ እንደሆነ ተናግረዋል። ወንጀለኛው በ2022 ዓ.ም በኋላ በምሕረት ከእስር ቤት ለውጣት ማመልከት ይችላል። |
news-54187347 | https://www.bbc.com/amharic/news-54187347 | የናይጄሪያዋ ግዛት ደፋሪዎች እንዲኮላሹ በህግ ፈቀደች | የናይጄሪያዋ ካዱና ግዛት ደፋሪዎች በህክምና እንዲኮላሹ ህግ አፅድቃለች። | የግዛቷ አስተዳዳሪ ናስር አህመድ ኤል ሩፋይ ባለፈው ሳምንት የቀረበላቸውን ረቂቅ ህግ በትናንትናው እለት በመፈረም አፅድቀውታል። ህጉ ከአስራ አራት አመት በታች ያሉ ህፃናትን የደፈሩ እንዲኮላሹ ብቻ ሳይሆን የሞት ፍርድንም አካቷል። የተደፈሩት ደግሞ ከአስራ አራት አመት በላይ ከሆኑ በህክምና እንዲኮላሹ እንዲሁም የእድሜ ልክ እስራት ቅጣት ይጠብቃቸዋል። ህፃናትን የሚደፍሩ ሴቶችም ቢሆኑ የማህፀን ቱቧቸው እንዲወገድ የሚደረግ ሲሆን የሞት ቅጣትም በተጨማሪ ተካቶበታል። የመደፈር ጥቃት የደረሰባቸው ከአስራ አራት አመት በታች ያሉ ህፃናት በአባሪነት የህክምና ሪፖርት ማምጣት ይኖርባቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ ህፃናትን የሚደፍሩ ሰዎች ዝርዝርም በሚዲያ እንደሚወጣና ለህዝቡም ይፋ ይሆናል ተብሏል። የግዛቲቱ አስተዳዳሪ በትናንትናው ዕለት ረቂቅ ህጉ ላይ መፈረማቸውንና ህግ ሆኖም እንደፀደቀ ያስታወቁት በትዊተር ገፃቸው ነው። በናይጄሪያ ካሉ ግዛቶች መካከል እንዲህ አይነት ህግ በማፅደቅ ካዱና ቀዳሚ ሆናለች። የናይጀሪያ ፌደራል መንግሥት ደፋሪዎችን ከአስራ አራት አመት እስከ እድሜ ልክ እስራት ቢቀጣም ግዛቶች ግን የራሳቸውን ህግ ማውጣት ይችላሉ። የተደፈሩ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ በማህበረሰቡ ካለው ተጠቂዎችን ጥፋተኛ ከማድረግ እሳቤ አንፃር ብዙዎች ደፍረው ወደ ህግ ቦታ አይሄዱም። ደፍረው ሪፖርት ያደረጉትም ቢሆን ክስ ተመሰርቶ የሚፈረድባቸውም ጥቂቶች ናቸው። በሰኔ ወር ላይ በርካታ የናይጄሪያ ግዛት አስተዳዳሪዎች እየጨመረ የመጣውን የሴቶች መደፈርና ጥቃት አስመልክቶ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስተላልፈው ነበር። በናይጄሪያ ከጎርጎሳውያኑ 2015 ጀምሮ የተፈረደባቸው 40 ደፋሪዎች ብቻ እንደሆኑ የተገኘው መረጃ ያሳያል። አገሪቷም ህጓን አሻሽላለች። የመድፈር ክስን አስቸጋሪ የሚያደርገው አቃቤ ህግ ማስረጃ ማምጣት ስለሚኖርበት አድካሚና ቴክኒካል ጉዳዪ የተወሳሰበ እንደሚያደርገው ይነገራል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ የተጣለው የእንቅስቃሴ መገደብም የሚደፈሩ ሴቶችን ቁጥር እንዲያሻቅብ አድርጎታል። በሃምሌ ወር የ22 አመት እድሜ ያላት የዩኒቨርስቲ ተማሪ ተደፍራ መገደሏ ከፍተኛ ቁጣን ፈጥሯል። ይህንንም ተከትሎ ናይጄሪያውያን ንዴታቸውን ለመግለፅ ጎዳና ላይ ወጥተዋል፤ 'ዊ አር ታየርድ' (ደክሞናል) በሚልም በትዊተር ላይ ዘመቻ ተጀምሮም ነበር። በርካቶችም የሞት ቅጣትን ጨምሮ ጠበቅ ያለ ህግ እንዲወጣም ጠይቀዋል። በህክምና የማኮላሸት ቅጣት በአንዳንድ አገራት ተግባራዊ ቢሆንም አወዛጋቢ ነው። |
news-45730511 | https://www.bbc.com/amharic/news-45730511 | ከቤንሻንጉል ካማሼና አካባቢዎቹ ለተፈናቀሉ ወገኖች የደረሰው ቤተሰብ | በቤኒሻንጉል ክልል የዞን፣ የወረዳ አመራሮችና የፀጥታ ኃይሎች ላይ በተከፈተ ተኩስ የ4 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ ከ75 ሺ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል። | በበሎይ ጅጋንፎይ ወረዳ ስር ሳይ ዳለቻ ቀበሌ ግጭት የነበረ ሲሆን በግጭቱም 75 ቤቶች ተቃጥለዋል ብለዋል የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አበራ ባይታ። በዚሁ ወረዳ ጅጋንፎይ ቀበሌ በጭበጭ በምትባል አካባቢ ላይ ቤቶች መቃጠላቸውን ጠቅሰው ሌሎች ቀበሌዎችም ላይ ተመሳሳይ ግጭቶች መከሰሰታቸውን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ተናግረዋል። የተፈናቀሉት ሰዎች ከቤንሻንጉል ብቻ ሳይሆን ክልሉን ከሚያዋስኑት የኦሮሚያ ቀበሌዎችም እንደሆነ የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ሳስጋ ወረዳ ዱራበሎ፣ ካምፕ፣ በሎበሬዳ፣ ስምንተኛ ከሚባሉት ቀበሌዎች በስጋት ምክንያት ወደ ነቀምትና በሎበሬዳ ወደሚገኙ ማዕከሎች ተፈናቅለው እንደሚገኙ ተናግረዋል። • አቶ ጌታቸው አሰፋ የሀዋሳውን ጉባኤ ይታደማሉ? • የአይኤስ ታጣቂዎች ኢትዮጵያዊያንን ገደሉ ተፈናቃዮቹ መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸው እንዲሟሉ ደግሞ የነቀምትና አካባቢዋ ነዋሪዎች የተለያዩ ድጋፎችን እያደረጉ ነው። ቢቢሲ ያነጋገረው ኤርጋማ ታምራት ብርሃኑ ከቤተሰቦቹ ጋር በመሆን እስካሁን ለ1000 ተፈናቃዮች ምግብና መጠጥ እያቀረቡ እንደሆነ ተናግሯል። ''ሙሉ የቤተሰቡ አባላት ልጆቼንም ጨምሮ ምግብ እያቀረብንላቸው ነው። ባለቤቴ ምግቡን ትሰራለች፤ እኔ ደግሞ አንዳንዴ ምሳ እንኳን ሳልበላ ወንድምና እህቶቼን እያስተናገድኳቸው ነው።'' ይላል። ይሁን እንጂ አሁንም በመንግስት በኩል ትልቅ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸውና የወለዱ እናቶች እንኳን ልጆቻቸውን ይዘው ቀዝቃዛ የሲሚንቶ ወለል ላይ እየተኙ ነው በማለት ያሉበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ያብራራል። በተጨማሪም የኦሮሚያ ክልል ወጣቶች ወይም ቄሮዎች እርዳታ እያደረጉላቸው እንደሆነና እነሱ ሰብስበው ያመጡላቸው ልብስ ባይኖር ለብሰውት እንኳን የሚያድሩት ነገር እንደሌላቸው ነግሮናል። የአርጆ ደዴሳ ስኳር ፋብሪካ ሰራተኞችም ከደሞዛቸው በመቀነስ 500 ሺ ብር፣ በነፍስ ወከፍ ከሚሰጣቸው በመቀነስ 62 ኩንታል ስኳር መለገሳቸውንና ፋብሪካው ደግሞ ተጨማሪ የ100 ሺ ብር ድጋፍ ማድረጉን የህዝብ ተሳትፎና ልማት ቢሮ ምክትል ሃላፊ የሆኑት አቶ ሙሉጌታ ፋንታሁን ተናግረዋል። • «የምታገለው ለማንም ብሔር የበላይነት አይደለም» አቶ በቀለ ገርባ • «ማስተር ፕላኑ ተመልሶ ይመጣል» አቶ ኩማ ደመቅሳ የምስራቅ ወለጋ የአደጋ መከላከልና ቁጥጥር ቢሮ ሃላፊ የሆኑት አቶ አዱኛ ገለታ በበኩላቸው ከክልልና ከፌደራል መንግስት ድጋፎች ቶሎ እንዲያገኙ እየሰሩ እንደሆነ ገልጸዋል። እስካሁን ድረስም ከፌደራል መንግስት 800 ኩንታል ስንዴ እንደደረሳቸውና እርዳታ የጫኑ ተጨማሪ 8 ተሽከርካሪዎች በመንገድ ላይ መሆናቸውን አክለዋል። የምግብ ዘይትም ቢሆን ለተፈናቃዮች እየታደለ እንደሆነና የተለያዩ እርዳታ የሚሰጡ ኮሚቴዎች ተቋቁመው የህክምና እርዳታ ለተፈናቃዮቹ እየተደረገላቸው ነው ብለዋል። ''የምስራቅ ወለጋና የነቀምት ህዝብ እያደረገው ያለው ድጋፍ ትልቅ ነው፤ እስካሁን ድረስ ያለነው ህዝቡ አንዱ ለአንዱ የመድረስ ባህሉ ከፍተኛ ስለሆነ ነው።'' ብለዋል ተፈናቃዮቹ። ያነጋገርናቸው በወለጋ ዩኒቨርስቲ ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮችም ከእራሱ አልፎ ለሌሎች የሚኖረው ህዝብ በሁሉም መልኩ ህይወታችንን እየታደገልን ነው ብለዋል። |
news-49631098 | https://www.bbc.com/amharic/news-49631098 | ታሊባን፡ የሰላም ድርድሩ መቋረጥ የሚጎዳው አሜሪካንን ነው | የታሊባን ከፍተኛ መሪዎች የሰላም ድርድሩ መቋረጡ በዋነኛነት የሚጎዳው አሜሪካንን እንጂ እኛ አይደለም አሉ። | ታሊባን ባወጣው የጽሁፍ መግለጫ በሁለቱ አካላት መካከል ሲደረግ የነበረው የሰላም ድርድር እስከ መጨረሻው ሰዓት ድረስ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ነበር ብሏል። ይህ የሰላም ድርድር በአፍጋኒስታን ለ18 ዓመታት የዘለቀውን ጦርነት ለማስቆም እድል ይሰጥ ነበር በማለት የታሊባን መሪዎች ለድርድሩ መቋረጥ አሜሪካንን ተጠያቂ አድርገዋል። • አፍጋናዊቷ ስደተኛ በኢትዮጵያ • በካቡል ሠርግ ላይ በተወረወረ ቦንብ የ63 ሰዎች ህይወት አለፈ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከታሊባን ጋር እየተካሄደ የነበረውን የሰላም ስምምነት ስለመሰረዛቸው ትናንት ማስታወቃቸው ይታወሳል። ሐሙስ ዕለት በአፍጋኒስታን መዲና ካቡል በተፈጸመው እና ታሊባን ኃላፊነቱን በወሰደው ጥቃት አንድ የአሜሪካ ወታደር መገደሉን ትራምፕ የሰላም ስምምነቱን ለመሰረዝ ምክንያት ሆኗቸዋል። አሜሪካዊው ወታደር መገደሉ ከተሰማ በኋላ፤ ትራምፕ በትዊተር ገጻቸው ላይ "በአስቸኳይ ውይይቶቹ እና የሰላም ድርድሩ እንዲቆም አዝዣለሁ" ብለዋል። በጥቃቱ ከአሜሪካዊው ወታደር በተጨማሪ ሌሎች 11 ሰዎች ተገድለዋል። ሁለቱ አካላት ከሰላም ስምምነት እንዲደርሱ የአሜሪካ መንግሥት እና የታሊባን ተወካዮች በኳታር ዶሃ ከዘጠኝ ጊዜ በላይ ተገናኝተው መክረዋል። የሰላም ስምምነቱ አደራዳሪዎች ከቀናት በፊት አሜሪካ እና ታሊባን 'በመርህ ደረጃ' ከሰላም ስምምነት ደርሰዋል ብለው ነበር። የታሊባን ቃል አቀባይ ዛቢሁላህ ሙጀሂድ በካቡል በሰጡት መግለጫ የደረሰውን ጥቃት ምክንያት በማድረግ የሰላም ድርድሩን ማቋረጣቸው አሜሪካዊያኑ ብስለት እና ልምድ እንደሚጎድላቸው ያሳያል ብለዋል። ቃለ አቀባዩ እንደሚሉት ከሆነ ታሊባን እና የአፍጋኒስታን መንግሥት ከ12 ቀናት በኋላ ተገናኘተው ሊመክሩ ቀጠሮ ይዘዋል። የሰላም ስምምነቱ ተፈጻሚ ቢሆን ኖሮ አሜሪካ ወደ አፍጋኒስታን ካዘመተቻቸው ወታደሮች መካከል 5400 የሚሆኑት በ20 ሳምንታት ውስጥ ልታስወጣ ነበር። እ.አ.አ. 2001 መስከረም 1 ላይ በአሜሪካ ላይ ከተሰነዘረው ጥቃት በኋላ ነበር አሜሪካ ለአሸባሪ ቡድኖች ድጋፍ ያደርጋል ያለችውን የታሊባን መንግሥትን ከስልጣን ለማውረድ አፍጋኒስታንን የወረረችው። በአሁኑ ሰዓት አሜሪካ በአፍጋኒስታን ከ14ሺህ በላይ ወታደሮች አሏት። • የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር መልቀቂያ አስገቡ ታሊባን በምፈጽማቸው ጥቃቶች ዒላማ የማደርው የውጪ ሃገር ኃይሎችን ነው ይበል እንጂ በጥቃቶቹ ለከፍተኛ ጉዳት የሚዳረጉት ንጹሐን የአፍጋኒስታን ዜጎች ናቸው። አሜሪካ አፍጋኒስታንን ከወረረች ወዲህ ከ3500 በላይ የውጪ ሃገራት ጥምር ኃይሎች ተገድለዋል። ከእነዚህም መካከል 2300 የሚሆኑት አሜሪካውያን ናቸው። ባለፉት 18 ዓመታት ምን ያክል የአፍጋኒስታን ሲቪሎች፣ የመንግሥት ወታደሮች እና ታጣቂ ሚሊሻዎች ህይወታቸውን እንዳጡ በውል አይታወቅም። ከወራት በፊት የተባበሩት መንግሥታት ባወጣው ሪፖርት ከ32ሺህ በላይ ሲቪሎች ተገድሏል ያለ ሲሆን ሌሎች ተቋማት በበኩላቸው የውጪ ኃይሎችን ሲፋለሙ የነበሩ ከ42 ሺህ በላይ ሚሊሻዎች መገደላቸውን ይጠቁማሉ። |
43041310 | https://www.bbc.com/amharic/43041310 | ጋቦን፡ በሆስፒታል ክፍያ መያዣነት የቆየችው ህፃን ነፃ ሆነች | ጋቦናዊት እናት ለአንድ የግል ክሊኒክ ክፍያ ባለመፈፀሟ ምክንያት ልጇን በተያዥነት ለወራት ከያዘባት በኋላ ህፃኗ የለቀቀ ሲሆን እናቷም እፎይታ እንዳገኘች ገልፃለች። | የህፃኗ እናት ለቢቢሲ እንደገለፀችውም በባለፉት አምስት ወራት ከልጇም ጋር በመለያየቷ ጡቷ እንደደረቀ ነው። ይህ ጉዳይ ሀገሪቷን በድንጋጤ ያንቀጠቀጠ ሲሆን በምላሹም ማህበረሰቡ ድጋፍን ችሯታል። በቤተሰቡም ስም ዘመቻ ከተከፈተ በኋላ ነው ወደ መቶ ሺ ብር የነበረው የሆስፒታል ክፍያ የተከፈለው። ለዚህ ክፍያ አስተዋፅኦ ካደረጉት መካከል አንዱ ፕሬዚዳንቱ አሊ ቦንጎ ናቸው። የክሊኒኩ ዳይሬክተር ሰኞ ዕለት ህፃናትን በመጥለፍ ክስ እስር ቤት የገቡ ሲሆን ከአንድ ቀንም በኋላ ክሱ ውድቅ እንደተደረገ የቢቢሲ አፍሪክ ቻርለስ ሰቴፋን ከመዲናዋ ሊበርቪል ዘግቧል። ህፃኗ ኤንጅልም በመጨረሻ በዚህ ሳምንት በመዲናዋ ሰሜን የሚገኘውን ክሊኒክንም ለቃ መሄድ እንደቻለችም ተገልጿል። የህፃኗ እናት ሶኒያ ኦኮሜ ለቢቢሲ እንደገፀችው ምንም እንኳን እፎይታን ብታገኝም ከምሬት በኋላ የመጣ ነው ብለዋል " ልጄን መልሼ በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ። በጣም የሚያሳዝነኝ ጉዳይ ግን ልጄን አሁን ማጥባት አልችልም ምክንያቱም ጡቴ ደርቋል" ብላለች። ከዚህም በተጨማሪ ህፃኗ ክትባት አልተሰጣትም በሚልም አማራለች። የጋቦን ሚዲያ ታይም እንደዘገበው ይህ ክፍያ ህፃኗ ያለጊዜዋ በመወለዷ በህፃናት ማቆያ ለ35 ቀናት የቆየችበት ነው። |
news-54314402 | https://www.bbc.com/amharic/news-54314402 | ዘረኝነት፡ በፓሪስ የባሪያ ንግድን ለተቃወመችው ሴት ሐውልት ሊቆምላት ነው | በፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ስር በነበረችው የካሪቢያን ደሴት 'ጉዋድሎፕ' ውስጥ በአውሮፓውያኑ 1802 የባሪያ ንግድን በመቃወምና አመጽ በመቀስቀስ ለምትታወቀው ጥቁር ሴት ፓሪስ ውስጥ ሐውልት ሊቆምላት እንደሆነ ተገልጿል። | ይህች ጀግና ሴት 'ሶሊትዩድ' በሚል ስም ብቻ የተጠቀሰች ሲሆን ምናልባትም በወቅቱ ከተያዘች በኋላ ሳትገደል እንዳልቀረች ይታመናል። በዝች ሴት ስም የተሰየመውን የሕዝብ መዝናኛ ቅዳሜ ዕለት መርቀው የከፈቱት የፓሪሷ ከንቲባ አን ሂዳልጎ ሶሊትዩድ ''ጀግኒት'' እና ''ጠንካራ ተምሳሌት'' በማለት አሞካሽተዋታል። በአሜሪካ የተጀመረውን የ'ብላክ ላይቭስ ማተር' እንቅስቃሴን ተከትሎ በፈረንሳይም ከዚህ በፊት ከነበራት የቅኝ ግዛት ታሪክ ጋር በተያያዘ በርካታ ጥያቄዎች መጠየቅ ጀምረዋል። በቅርቡም የፈረንሳይን የቅኝ ግዛት አካሄድ እንዳረቀቀና ለቅኝ ግዛት መስፋፋት ብዙ እንደሰራ የሚነገርለት ዦን ባፕቲስት ኮልበርት እንዴት ፓሪስ ውስጥ በሚገኘው የአገሪቱ ፓርላማ ውጪ ላይ ሐውልት ይቆምለታል በሚል ተቃውሞ ተነስቶ ነበር። ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ደግሞ እንደዚህ አይነት ሐውቶችን ማፍረስ ተገቢ አይደለም በማለት ተከራክረዋል። እንደ ዦን ባፕቲስት ኮልበርት ያሉ በ17ኛው ክፍለ ዘመን ለባሪያ ንግድ አስተዋጽ ያደረጉ ሰዎች ሐውልትና ማስታወሻዎች መኖራቸው የኋላውን ታሪካችንን ጠንቅቀን እንድናውቅና እንድንማርበት ይረዳልም ማለታቸው አይዘነጋም። በዩኔስኮ መዝገብ ላይ በተገኘ መረጃ መሰረት ሶሊትዩድ የተቀላቀለ ዘር ያላት ሲሆን በወቅቱ በፈረንሳይ አብዮት እንዲወገድ ተደርጎ የነበረውን የባሪያ ንግድ ናፖሊዮን ቦናፓርቴ እንደገና መልሶት ነበር። ሶሊትዩድም የባሪያ ንግድን በመቃወም የሽምቅ ውጊያ በማድረግ ላይ ሳሉ በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል አንዷ ነች። ከተያዘችም በኋላ በሞት እንድትቀጣ ተደርጓል። ነገር ግን በተጻፈው ታሪኳ ላይ ከመገደሏ በፊት ልጅ እንድተወልድ ተደርጋ ነበር ይላል። በፈረንሳይኛ ይህ ቃል ሌላ ትርጉም አለው። ምናለባትም ከመሞቷ በፊት እንደ ግርፊያ ባለ የማሰቃያ መንገድ እንድትሰቃይ ተደርጋ ነበር ማለትም ሊሆን ይችላል። ሶሊትዩድ በአውሮፓውያኑ 1972 በታዋቂው የፈረንሳይ ጸሀፊ አንድሬ ሽዋርትዝ ባርት ተጠቅሳ የነበረ ሲሆን ጉዋድሎፕ ውስት ደግሞ በስሟ ሐውልት ቆሞላታል። አሁን ደግሞ በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ ሐውልት ሊቆምላት ነው። ምንም እንኳን ፓሪስ ውስጥ ለጥቁር ሴቶች ሐውልት ማቆም የተለመደ ባይሆንም ሶሊትዩድግ ግን ሐውልት ቢቆምላት በርካቶች ደስተኛ እንደሚሆኑ ሀሳባቸውን ገልጸዋል። |
news-49875293 | https://www.bbc.com/amharic/news-49875293 | ሕንድ ውቅያኖስ ውስጥ የገባው መኪና እየተፈለገ ነው | ከኬንያ ሞምባሳ ወደብ ወደ ባህር ዳርቻው የእቃና የሰው ማሻገሪያ መርከብ ላይ ሆኖ ሲያቋርጥ የነበረ መኪና ሕንድ ውቅያኖስ ውስጥ ገብቶ እየተፈለገ መሆኑ ተገለፀ። | መኪናው ውስጥ ሦስት ሰዎች ሳይኖሩ እንዳልቀረ የኬንያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። • በፀሐይ የሚሰራው የሕዝብ ማመላለሻ ጀልባ • በወለደች በ30 ደቂቃ ውስጥ የተፈተነችው ተማሪ ስንት አስመዘገበች? አደጋው ትናንት ያጋጠመ ሲሆን ከሞምባሳን ወደ ሊኮኒን በማቋረጥ ላይ ሳለ መሃል ላይ ሲደርስ ወደ ኋላ በመንሸራተቱ አደጋው እንዳጋጠመው ታውቋል። አደጋው ሲደርስ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስልም በትዊትር ላይ በስፋት ተሰራጭቷል። የ Twitter ይዘት መጨረሻ, 1 የዓይን እማኞች ለዴይሊ ኔሽን ጋዜጣ እንደተናገሩት እንዲት ሴትና ሕፃን መኪናው ውስጥ ነበሩ። "አንዲት ሴትና ወንድ ልጅ መኪናው ውስጥ ሆነው ተመልክቻለሁ፤ መኪናው ሲገለበጥ ሴትዮዋ ስትጮህና እርዳታ ስትጠይቅ ነበር። ከዚያም የነፍስ አድን ሠራተኞችን እንዲደርሱላቸው ላኩላቸው" ብለዋል። ዴይሊ ኔሽን ፖሊስን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው በመኪናው ውስጥ የነበሩ ሰዎች ቁጥር አራት ነው። የኬንያ የመርከብ አገልግሎት ባለሥልጣን ፍለጋውና የነፍስ አድን ሥራው እንደቀጠለ አስታውቋል። የሰው እና ዕቃ ማሻገሪያ መርከቡ ኦፕሬተር እስካሁን በፍለጋው ምንም ፍንጭ አለመገኘቱን በትዊተር ገፃቸው አስታውቀዋል። |
news-51520108 | https://www.bbc.com/amharic/news-51520108 | ቻይና፡ በኮሮና የሚያዙ አዳዲስ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ነው ተባለ | በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ አዳዲስ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መሆኑን ቻይና አስታውቃለች። ይህም ሁኔታ የታየው በባለፉት ሶስት ቀናት መሆኑም ተዘግቧል። | ባለፈው ሳምንት እሁድ ባለስልጣናቱ 2ሺ 9 አዳዲስ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን እንዲሁም በመላው ሃገሪቱ 142 ሰዎች መሞታቸውን ተናግረው ነበር። በሳምንቱም መጀመሪያ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ማሻቀብ አሳይቶ የነበረ ቢሆንም ከቀናት በኋላ መረጋጋት እንዲሁም ማሽቆልቆል አሳይቷል ብለዋል። እስካሁን ባለው መረጃ 68 ሺ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ደግሞ 1665 ደርሷል። • ኢትዮጵያውያን፡ የአስወጡን ድምጽ በጎሉባት የቻይናዋ ዉሃን • በሽታውን ለመደበቅ ባለስልጣናት ዶክተሮችን ያስፈራሩ ነበር ከቻይና ውጭ ባሉ ሃገራት 500 ግለሰቦች በሰላሳ ሃገራት ውስጥ የተያዙ ሲሆን፤ አራት ሞቶችም ተከስተዋል። እነዚህም በፈረንሳይ፣ ሆንግ ኮንግ፣ ፊሊፒንስና ጃፖን ናቸው። የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነስን አስመልክቶ " ወረርሽኙን መቆጣጠር እንደቻልን ማሳያ ነው" ብለዋል። "የቫይረሱን መዛመት ለመቆጣጠር ያላሰለሰ ጥረት አድርገናል፤ በውጤቱም ከፍተኛ እመርታ አሳይተናል። እኛ ያከናወንነውን ተግባር መስራት የሚችል ሃገር የለም" ብለዋል። እስካሁን ባለው መረጃ • ኮሮና ቫይረስ መጠሪያ ስሙን አገኘ • ስለአዲሱ ኮሮና ቫይረስ ማወቅ የሚገባዎ ነጥቦች ቅዳሜ እለት የአለም አቀፉ የጤና ድርጅት ኃላፊ ዶር ቴድሮስ አድሃኖም ቻይና ለወረርሽኙ የሰጠችውን ትኩረት አድንቀዋል። "ቻይና የቫይረሱን መዛመት በመቆጣጠር ሌላው ዓለም እንዲዘጋጅ ጊዜን መለገስ ችላለች፤ ምን ያህል ጊዜ እንዳለን ባናውቅም። ከቻይና ውጭ ባሉ ሃገራት ያለው የመዛመት ሁኔታ ዝቅተኛ መሆኑንም ማየት ተስፋ የሚሰጥ ነገር ነው" ብለዋል። ከአስር ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ቻይናውያን የቫይረሱን መዛመት ለመቆጣጠር በሚል ከእለት እለት እንቅስቃሴያቸው ተገድበዋል። ከፍተኛ ትኩረት የተሰጣት የቫይረሱ መነሻ የሆነቸው የሁቤ ግዛት ውሃን ከተማ ስትሆን፤ በውሃን እንቅስቃሴ ከተገደበ ሳምንታት ተቆጥረዋል፤ ከተማዋም ከሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች ተቆራርጣለች። |
news-50839154 | https://www.bbc.com/amharic/news-50839154 | የኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጁ በዋጋ የሚያንራቸው ምርቶች | የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ታህሳስ 7 2012 ዓ.ም ባካሄደው ስድስተኛ መደበኛ ስበሰባው የተለያዩ ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቶ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል። | ከእነዚህ ረቂቅ አዋጆች መካከል ተሻሽሎ የቀረበው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ይገኝበታል። በሥራ ላይ የሚገኘው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ያሉበትን ጉድለቶች መቅረፍ ያስችላል ተብሎ የቀረበው ይህ ረቂቅ አዋጅ፤ በሃገር ውስጥ በሚመረቱና ከውጪ በሚገቡ የተመረጡ ምርቶች ላይ ተጨማሪ ታክስ ጥሏል። •ኢኮኖሚያዊ ተቃውሞና ያስከተለው ውጤት •"ማርታ፣ ለምን ለምን ሞተች?" ረቂቅ አዋጁ የኤክሳይዝ ታክስ እንዲጣልባቸው የለያቸው የምርቶች አይነት የሚከተሉት አይነት ናቸው። መሠረታዊ በመሆናቸው ምክንያት የገበያ ተፈላጊነታቸው አይቀንሱም የተባሉት የምርቶች አይነት፤ እቃዎቹ ኤክሳይዝ ታክስ ስለተጣለባቸው በተጠቃሚዎች ላይ ብዙም የዋጋ ልዩነት የማያመጡ፤ ነገር ግን ለመንግስት ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኙ ስለመሆናቸው ተነግሯል። •'የአልባኒያ ተቃዋሚዎች' በትግራይ በረቂቅ አዋጁ ላይ የኤክሳይዝ ታክስ እንዲጣልባቸው ከተለዩ ምርቶች መካከል የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው። ኤክሳይዝ ታክስ ለመንግሥት ከፍተኛ ገቢ ከማስገኘቱ በተጨማሪ፤ ከውጪ የሚገቡ እቃዎች ሃገር ውስጥ የተመረቱትን ከገበያ ውጭ እንዳያደርጓቸው ታስቦ ይጣልባቸዋል። ይህም የሃገር ውስጥ አምራቾችን እንደሚያበረታታ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ኤክሳይዝ ታክስ በአምራቹ ወይም አስመጪው ይከፈላል። ምርቶች የተመረቱት በሃገር ውስጥ ከሆነ፤ ከተመረቱበት ወር ቀጥሎ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ እንዲሁም ምርቶቹ ከውጪ የሚገቡ ከሆነ አስመጪው ግለሰብ ወይም ድርጅቱ ከጉምሩክ ክልል በሚያወጣበት ጊዜ ታክሱ ይከፈላል፡፡ ይህ ረቂቅ አዋጅ የሚጸድቅ ከሆነ የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ 307/1995 ተሽሮ በዚህ አዋጅ ይተካል። በተጨማሪም ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረን ማንኛውም ሕግ፣ መመሪያ ወይም አሠራር ይህንን አዋጅ በሚመለከት ተፈፃሚነት አይኖረውም። |
news-55584056 | https://www.bbc.com/amharic/news-55584056 | አሜሪካ፡ የትራምፕ ሥልጣን ዘመን ማብቃትና 25ኛው አሜንድመንት | የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሥልጣን ዘመናቸው ሊያበቃ የቀራቸው ከሁለት ሳምንታት ያነሰ እድሜ ብቻ ነው። | ነገር ግን በትናንትናው ዕለት ነውጠኛ ደጋፊዎቻቸው የመንግሥት መቀመጫና የሁለቱ ምክር ቤቶች አዳራሾች የሚገኙበትን ግዙፉን የካፒቶል ሒል ህንጻን ጥሰው መግባታቸውን ተከትሎ ከፍተኛ የሴኔት ምክር ቤት አባላት ፕሬዝዳንቱ ከስልጣን እንዲባረሩ እየጠየቁ ነው። ለዚህም የአሜሪካ ሕገመንግሥት 25ኛው አሜንድመንት [ማሻሻያ] እየተጠቀሰ ነው። ይህ ማሻሻያ አንድ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት አካላዊ ወይም አእምሯዊ ጤና ከራቀው ምክት ፕሬዝዳንቱ ቦታውን በተጠባባቂነት ተረክቦ አገሪቱን እንዲመራ ያዛል። ሆኖም ይህ እንዲተገበር የምክር ቤቱ አፈጉባኤ ናንሲ ፔሎሲን ጨምሮ በትንሹ 8 የካቢኔ አባላት በጉዳዩ ላይ መስማማት አለባቸው። ነገር ግን ይህ የመሆን እድሉ ለጊዜው ጠባብ ነው ተብሏል። የትራምፕ ነውጠኛ ደጋፊዎች ካፒቶል ሒልን ጥሰው ሲገቡ ታህታይና የላዕላይ ምክር ቤት አባላት የባይደንን መመረጥ ከግዛት ተወካዮች የማረጋገጥ ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው ይህንኑ በመካሄድ ላይ ነበሩ። አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲና ምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፔንስም በሸንጎ ላይ ተገኝተው ነበር። ይህንን ለአሜሪካ እንግዳ የሆነ ድርጊት ተከትሎ የሕግ መምሪያ ምክር ቤት አፈ ጉባኤዋ ናንሲ ፔሎሲ 25ኛውን የሕገ መንግሥት ማሻሻያ በመጥቀስ ትራምፕ አሜሪካንን ለመምራት ብቁ ስላልሆኑ ከዋይት ሐውስ እንዲባረሩ ጥያቄ አቅርበዋል። ይህን ጥያቄ በርካታ ዲሞክራቶችና ጥቂት ሪፐብሊካኖች ጭምር ድጋፍ ሰጥተውታል። የሴኔት ዲሞክራት ተጠሪ ቸክ ሹመር ትራምፕ አመጽ በማቀጣጠላቸው ከሥራ ሊባረሩ ይገባል ብለዋል። ቸክ ሹመር አክለውም "ምክትል ፕሬዝዳንቱ እና ካቢኔው ይህንን ለማድረግ የማይፈልጉ ከሆነ፣ ኮንግረሱ ዳግመኛ ፕሬዝዳንቱን ከሥልጣን እንዲነሱ ለማየት መሰብሰብ አለበት" ብለዋል። ዶናልድ ትራምፕ ከዋይት ሐውስ እንዲወገዱ እንቅስቃሴ የተጀመረ ሲሆን ለድርጊታቸው ክስ እንዲመሰረትባቸውም ናንሲ ፒሎሲ ጥሪ አድርገዋል። ክሱ ተፈጻሚ እንዲሆን ግን ዲሞክራቶች የሪፐብሊካኖችን ድጋፍ ማግኘት አለባቸው። ምክንያቱም ክሱ እንዲፈጸም የምክር ቤቱ ሁለት ሦስተኛው ድምጽ ስለሚያስፈልግ ነው። ይህ የመሳካት እድሉም አነስተኛ ነው። አፈጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ትራምፕ በኮቪድ-19 ታመው በነበረበት ጊዜ ስለ 25ኛው ማሻሻያ ሲያስረዱ ይህ እንዴት ሊሰራ ይችላል? 25ኛው አሜንድመንት ፕሬዝዳንቱ ኃላፊነቶቹን መወጣት በማይችልበት ጊዜ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ስልጣኑን በጊዜያዊ ፕሬዝዳንትነት ተረክቦ እንዲያስተዳድር ይፈቅዳል። ለምሳሌ ፕሬዝዳንቱ በአእምሮም ሆነ በአካላዊ ጤና ምክንያት ኃላፊነታቸውን መወጣት ባይችሉ እንደማለት ነው። በአሁኑ ሰዓት መነጋገሪያ እየሆነ ያለው የዚህ አሜንድመት አንቀጽ አራት ነው። ይህ አንቀጽ ምክትል ፕሬዝዳንቱ እንዲሁም የካቢኔው አብላጫ አባላት ፕሬዝዳንቱ ኃላፊነታቸውን መወጣት አልቻሉም ብለው እንዲወስኑ እድል ይሰጣቸዋል። ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፊርማቸው ያረፈበትን ደብዳቤ መላክ የሚጠበቅባቸው ሲሆን፣ ሴኔቱም ፕሬዝዳንቱ ሥልጣንና ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ብቁ አይደሉም ሲል ያፀድቃል። በዚህ ጊዜ ምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፔንስ ሙሉ በሙሉ ሥልጣኑን ተረክበው አገሪቱን ማስተዳደር ይጀምራሉ። ፕሬዝዳንቱ በጽሁፍ ምላሽ እንዲሰጡ እድል የሚሰጣቸው ሲሆን ውሳኔውን ተቃርነው ከቀረቡ ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ እንዲወስን ይደረጋል። ፕሬዝዳንቱን ከሥልጣናቸው ለማውረድ በታህታይና ላዕላይ ምክር ቤት አባላት የሚሰጥ የትኛውም ድምጽ አብላጫውን ወይንም ሁለት ሦስተኛውን ማግኘት አለበት። ይህ ጉዳይ መፍትሄ እስኪያገኝ ድረስም ምክትል ፕሬዝዳንቱ፣ የፕሬዝዳንቱን ሥልጣን ተረክበው ያስተዳድራሉ። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ላይ 25ኛው አሜንድመንትን ለመጠቀም ንግግር ሲደረግ ይህ መጀመሪያው አይደለም። ፕሬዝዳንቱ በኮቪድ-19 ተይዘው በነበረበት በጥቅምት ወር ላይ አገሪቱን ለመምራት ሕመማቸው አያስችላቸውም በሚል ተነስቶ ነበር። በዚሁ ወቅት የተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ናንሲ ፔሎሲ፣ በ25ኛው አሜንድመንት ላይ መሰረት ያደረገ እና የፕሬዝዳንቱን ጤና ለሥራ ብቁ መሆን አለመሆኑን የሚፈትሽ ሕግ አስተዋውቀው ነበር። ከዚህ በፊት ጥቅም ላይ ውሎ ያውቃል? 25ኛው አሜንድመንት በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1967፣ ጆን ኦፍ ኬኔዲ ከተገደሉ አራት ዓመት በኋላ፣ ፕሬዝዳንቱ በተለያየ ምክንያት ሥልጣንና ኃላፊነታቸውን ባልተወጡ ወቅት ማን ይተካቸዋል የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ በሚል ጸድቋል። በዚህም የተነሳ በርካታ ፕሬዝዳንቶች ይህንን የሕግ ማሻሻያ [አሜንድመንት]፣ በይበልጥ ደግሞ በጊዜያዊነት ሥልጣንን ለምክትላቸው ማስተላለፍ የሚፈቅደውን ክፍል፣ አንቀጽ ሦስትን ተጠቅመውበታል። በ2002 እና በ2007 ፕሬዝዳንት ጆርጅ ደብሊው ቡሽ የአንጀት ህክምና በሚያደርጉበት ወቅት ምክትላቸው እንዲተኳቸው አድርገዋል። ፕሬዝዳንት ሮናልድ ሬገን በ1985 ለካንሰር ህክምና ሆስፒታል በገቡበት ወቅት ተመሳሳዩን አድርገዋል። ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ 25ኛው አሜንድመንትን በመጠቀም የትኛውም ፕሬዝዳንት ከሥልጣን እንዲወርድ ተደርጎ አያውቅም። ፕሬዝዳንቱ ከሥልጣን በሌላ በምን ምክንያት ሊወርዱ ይችላሉ? ዲሞክራቶች ፕሬዝዳንት ትራምፕ የፖለቲካ ተቀናቃኛቸውን ለማጥፋት ከውጪ ኃይሎች ድጋፍ ጠይቀዋል በሚለው ውንጀላ የተነሳ እንዲጠየቁላቸው ክስ አቅርበው ነበር። በወቅቱ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ውንጀላውን የካዱ ሲሆን " የሌለን ነገር ፍለጋና እርባና ቢስ" ሲሉ አጣጥለውታል። ውንጀላው የተሰማው ፕሬዝዳንቱ ከዩክሬኑ አቻቸው ጋር ያደረጉትን የስልክ ልውውጥ ተከትሎ በቀረበ መረጃ ላይ ነው። መረጃውን ለዲሞክራቶች ሹክ ያለው ግለሰብ ማንነት ባይገለጽም፣ ትራምፕ ዩክሬን የቀድሞው ምክትል ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንና ልጃቸው ላይ የሙስና ምርመራ እንድትጀመር በወታደራዊ እርዳታ አስታከው አስፈራርተዋል ብለዋል ዲሞክራቶች። ይህም ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በታሪክ በሥልጣን ላይ እያሉ የተከሰሱ ብቸኛው ፕሬዝዳንት ያደርጋቸዋል። የአሜሪካ ሕገመንግሥት ፕሬዝዳንቱ ከሥልጣን ሊወርድ የሚችልባቸውን ምክንያቶች ሲዘረዝር "በአገር መክዳት ወንጀል፣ ሙስና አልያም በሌላ ከፍተኛ ወንጀል ወይንም በደል ፈጽመው ከተከሰሱ" ነው ይላል። ይህ ግን ከወንጀል ይልቅ ፖለቲካዊ ነው። እንዲህ አይነት ጉዳዮች ሁለት ደረጃዎች ያሏቸው ሲሆን በመጀመሪያ ለተወካዮች ምክር ቤት ይቀርብና ካለፈ ወደ ሴኔቱ ተመርቶ ይታያል። ነገር ግን በአሜሪካ ታሪክ ፕሬዝዳንቱን ከሥልጣን ለማውረድ የሚያበቃ አብላጫ ሁለት ሦስተኛ የተወካዮች ድምጽ ተገኘቶ አያውቅም። |
news-45974820 | https://www.bbc.com/amharic/news-45974820 | በአሜሪካ የዲሞክራት ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ዒላማው ያደረገው ቦምብ የላከው ግለሰብ እየታደነ ነው | ረቡዕ ዕለት ተቀጣጣይ ፈንጂ ይሆናሉ ተብለው የተጠረጠሩ ፖስታዎች ኒውዮርክ፣ ዋሺንግተን ዲሲ፣ እና ፍሎሪዳ መድረሳቸውን የደኅንነት ባለሥልጣኖች ተናግረዋል። | የአሜሪካ ፌደራል ወንጀል ምርመራ ፖሊስ እንዳስታወቀው ቦምቦቹ የተላኩት ለሒላሪ ክሊንተን፣ ለባራክ ኦባማ፣ ለቀድሞው የአሜሪካ የስለላ ተቋም ዳይሬክተር ጆን ብሬነን፣ ለቀድሞ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ኤሪክ ሆልደር፣ ለካሊፎርኒያ ግዛት የዲሞክራቲክ ተወካይ ማክሲን ዋተርስ እና ሌሎች ነው። ረቡዕ ዕለት የሲ ኤን ኤን ቢሮ ኃላፊ ዘንድ የተላከው ፓስታ በመድረሱ ሠራተኞች የኒውዮርክ ቢሮውን ለቅቀው እንዲወጡ ተደርጓል። • ኦብነግ የፖለቲካ አላማውን በሰላማዊ መንገድ ለማከናወን ተስማማ • አዲሷ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ማን ናቸው? • በኢትዮጵያ አደገኛ ከሆኑት መንገዶች አንዱ የበርካቶችን ሕይወት እየቀጠፈ ነው ለሒላሪ ክሊንተንና ለባራክ ኦባማ የተላከው ፖስታ ግን ለእነርሱ ከመድረሱ በፊት የደኅንነት አባላት እጅ ገብቷል። ይህን ተከትሎም ለቀድሞው ምክትል ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እንደተላከ የታመነ ፖስታ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል። ሁሉም ፖስታዎች በተመሳሳይ መልኩ የታሸጉና ከፍሎሪዳዋ የምክር ቤት አባል የተላከ እንደሆነ ይጠቅሳሉ። ምንም እንኳ ስማቸው ሲፃፍ ስህተት ቢኖርበትም ተወካይዋ ግን በዚህ ጉዳይ ስማቸው መነሳቱ ረብሿቸዋል። ለሲኤንኤን የተላከው ቦምብ ምስል ከዚህ በኋላ አንዳንድ የዲሞክራት ተወካዮች ዶናልድ ትራምፕ ባለፉት ጊዜያት ባካሄዷቸው ንግግሮች ጠብ በመቀስቀስ ወቅሰዋቸዋል። የትራምፕ ደጋፊዎች በበኩላቸው "ይህ ቦምብ ዲሞክራቶች ምርጫ ለማሸነፍ የዶለቱት ሴራ ነው" ሲሉ ተደምጠዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ በተደጋጋሚ ጋዜጠኞችን በተለይ ደግሞ ሲ ኤን ኤንን "ሐሰተኛ ዜና" እና "የሕዝብ ጠላት" በማለት ያወግዙ ነበር። ባለፈው ሳምንትም ትራምፕ የምክር ቤት አባል የሆኑት ሪፐብሊካን አንድ ጋዜጠኛን አሽቀንጥረው በመጣላቸው ሰውየውን አሞካሽተዋቸው ነበር። እስካሁን ድረስ ፖሊስ ስለተጠርጣሪዎቹ ምንም የሰጠው መረጃ የለም። ሆኖም አደን ላይ ነኝ ብሏል። ይህ ጥቃት የተከሰተው አሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤትና የአካባቢ ሥልጣናት የመዳረሻ ምርጫ ሊካሄድ ሁለት ሳምንት ሲቀረውና የአሜሪካ ፖለቲካ በጦዘበት ጊዜ ነው። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕም ሕዝቡ የሰለጠነ ፖለቲካን እንዲያራምድ፣ መገናኛ ቡዙኃንም ከጥላቻ ፖለቲካ ራሳቸውን እንዲቆጥቡ ጠይቀዋል። |
news-55899183 | https://www.bbc.com/amharic/news-55899183 | አሜሪካ የሳን ሱ ቺ እስርን ተከትሎ ሚያናማር ላይ ማዕቀብ እጥላለሁ ስትል አስጠነቀቀች | በሚያናማር የአገሪቱ ጦር መፈንቅለ መንግሥት ማድረጉን ተከትሎ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶ ባይደን በሚያናማር ላይማዕቀብ ሊጥሉ እንደሚችሉ አስጠነቀቁ። | በቀድሞዋ በርማ በዛሬዋ ሚያናማር የነበረውን አምባገነናዊ ወታደራዊ መንግሥት ተከትሎ በአሜሪካ ለረዥም ጊዜ ማዕቀብ ተጥሎ ቆይቶ ነበር። ትናንት በሚያንማር የአገሪቱ ጦር መፈንቅለ መንግሥት አከናውኗል። ወታደሮች ሥልጣን መቆጣጠራቸውን ይፋ ያደረጉት የሲቪል መንግሥት አባላትን በቁጥጥር ሥር ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው። የኖቤል ሰላም ሽልማት ተሸላሚዋ ኦንግ ሳን ሱ ቺ እና ሌሎች የፖለቲካ መሪዎች ተይዘው ወዳልታወቀ ሥፍራ ተወስደዋል። የተባበሩት መንግሥታት፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና የአውሮፓ ሕብረት በበርማ የተደረገውን መፈንቅለ መንግሥት አጥብቀው ኮንነዋል። ከእአአ 1989-2010 በእስር ቆይተው የነበሩት ሳን ሱ ቺ በቁጥጥር ሥር ከመዋላቸው በፊት ለደጋፊዎቻቸው በጻፉት ደብዳቤ “መፈንቅለ መንግሥቱን ተቃወሙ” ብለዋል። ሳን ሱ ቺ መፈንቅለ መንግሥቱ በአገሪቱ ወታደራዊ አምባገነናዊ ስርዓትን ያመጣል ሲሉ ጽፈዋል ተብሏል። በሚያንማር በወታደሩ እና በሲቪል አስተዳደሩ መካከል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ውጥረት ተከስቶ ነበር። ባለፈው ሕዳር በተደረገ ምርጫ የሳን ሱ ቺ ፓርቲ 'ናሽናል ሊግ ፎር ዲሞክራሲ' መንግሥት ለመመሥረት የሚያስችለውን የመቀመጫ ቁጥር ማግኘት ችሎ ነበር። ሆኖም የአገሪቱ ጦር ምርጫው ተጭበርብሯል ሲሉ ቆይቷል። ጦሩ መፈንቅለ መንግሥቱን ካደረገ በኋላ የ11 ሚንስትሮችን እና ሚንስትር ዲኤታዎችን ሹም ሽር አድርጓል። በሌሎች እንዲተኩ ከተደረጉ ሚንሰትሮች መካከል የፋይናንስ፣ የጤና እና የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ይገኙበታል። ፕሬዝደንት ባይደን ባወጡት መግለጫ የአገሪቱ ጦር የሕዝቡን ፍላጎት ቀልብሶ ስልጣን መቆጣጠሩ አግባብ አይደለም ብለዋል። አሜሪካ ከ10 ዓመታት በላይ በበርማ ላይ ጥላ የነበረውን ማዕቀብ ያነሳችው አገሪቱ ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መሸጋገሯን ተከትሎ ነው። ባይደን፤ “በየትኛውም ስፍራ በዲሞክራሲ ላይ ጥቃት ሲደርስ አሜሪካ ወደጎን አትልም” ብለዋል። ይሁን እንጂ የፖለቲካ ተንታኞች የአገሪቱ ጦር መፈንቅለ መንግሥቱን ለማደረግ ሲነሳ አሜሪካ ማዕቀብ እንደምትጥል ቀድሞ ያውቃል። ከአሜሪካ ማዕቀብ ይልቅ መፈንቅለ መንግሥቱን ተከትሎ ቻይና፣ ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ የሚሰጡት ምላሽ ለጦሩ አሳሳቢ ጉዳይ ነው ተብሏል። ከዚህ ቀደም ቻይና የሚያንማር ጉዳይ ውስጣዊ ጉዳይ ነው በማለት ዓለም አቀፍ ጣልቃ ገብነትን ተቃውማ ነበር። በቀጠናው ከሚገኙት አገራት መካከል ካምቦዲያ፣ ታይናላንድ እና ፊሊፒንስ በበኩላቸው የበርማ ጉዳይ የአገሪቱ ውስጣዊ ጉዳይ ነው በማለት ጣልቃ መግባት እንደማይሹ ገልጸዋል። በሚያናማር ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል? ይህ መፈንቅለ መንግሥት በአገሪቷ ዜጎች ዘንድ ከፍተኛ ፍርሃትን ፈጥሯል። በርማ ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትእንደምትሸጋገር ተስፋን ሰንቀው ለነበሩት ዜጎች የሳን ሱ ቺ እና ሌሎች ሲቪል ፖለቲከኞች እስር እና መፈንቅለመግሥት የዲሞክራሲ ተስፋን ያጨለመ ሆኖባቸዋል። አውራ ጊዳናዎች ጸጥ እረጭ ብለው ታይተዋል። በዋና ከተማ ጎዳናዎች ላይ ብዛት ያላቸው የአገሪቱ ጦር አባላትተሰማርተው ታይተዋል። ሰኞ ዕለት ተቋርጦ የነበረው የስልክ እና ኢንተርኔት ግነኙነት ማክሰኞ ንጋት ላይ ተመልሷል። የአገሪቱ ዋነኛ አየር ማረፊያ ግን አሁንም ዝግ እንደሆነ ነው። ትናንት የሆነው ምን ነበር? ትናንት [ሰኞ] ወታደሮች የአገሪቱን ሥልጣን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠራቸውና መሪያቸውም ኮማንደር ሚነ ኦንግ ሌይንግመሆናቸውን ተናግረዋል። በርካታ ወታደሮች በአገሪቱ ዋና ከተማ ናይፒታው እና በሌላኛዋ ትልቋ ከተማ ያንጎን ጎዳናዎች በብዛት ታይተዋል። የሞባይልና ኢንተርኔ አገልግሎት እንዲሁም ስልክ በስፋት የተቋረጠባቸው ዋና ዋና ከተሞች ላይ ሲሆን የአገሪቱብሔራዊ ቴሌቪዥን ሥርጭት ለማድረስ እክል ገጥሞኛል በማለት ተቋርጧል። በርካታ ወታደሮችም በተለያዩ ቦታዎች እየሄዱ የሲቪል አስተዳደሩ ሚኒስትሮች የነበሩ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ሲያውሉነበር። የቢቢሲዋ የደቡብ ምሥራቅ ኢሲያ ወኪል እንደምትለው ከሆነ ሳን ሱ ቺ በአገሪቱ ዜጎች ዘንድ ትልቅ ተቀባይነትአላቸው። ሰፊ የሕዝብ ድጋፍ ያላትን ሳን ሱ ቺን የመሰሉ ፖለቲከኞችን ማሰር ትልቅ ውሳኔ ነው። ይህ ምርጫ የወታደራዊ መንግሥት አስተዳደር ካበቃበት ከ2011 ወዲህ ሲካሄድ ለ2ኛ ጊዜ ነው። ነገር ግን ይህን ምርጫ ወታደሩ ሳይቀበለው ቀርቶ ነበር። ይህን ተከትሎም ምናልባት ወታደሩ መፈንቅለ መንግሥት ያደርግ ይሆናል የሚል ፍርሃት ነግሶ ቆይቶ ነበር። ኦንግ ሳን ሱ ቺ ማን ናቸው? ሳን ሱ ቺ የበርማ የነጻነት አባት የሚባሉት የጄኔራል ኦንግ ሳን ሴት ልጅ ናቸው። አባቷ የተገደሉት እሷ ገና የ2 ዓመት ልጅ ሳለች ነበር። የተገደሉትም በርማ ከእንግሊዝ ነጻነቷን ከመቀዳጀቷ ጥቂትቀደም ብሎ በፈረንጆቹ በ1948 ነበር። ሳን ሱ ቺ በአንድ ወቅት ለዲሞክራሲና ሰብዓዊ መብት ትልቅ ተምሳሌት ተደርገው ነበር የሚታዩት። ምክንያቱምምሕረት አያውቁም ከሚባሉት የምያንማር ወታደራዊ ኃይሎች በተጻጻራሪ በመቆም በአገሪቱ ዲሞክራሲ እንዲሰፍንበመታገል ረዥም ዓመታት ሳልፈዋል። ይህን ተከትሎም በ1991 የኖቤል የሰላም ሽልማትን ማሸነፍ ችለው ነበር። ሳን ሱ ቺ ሽልማቱን ያሸነፉት በቁም እስር ላይ ሳሉ ነበር። ሳን ሱ ቺ ለ15 ዓመታት በእስር ከቆዩ በኋላ በ2010 ነጻ ወጥተዋል። በ25 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በተደረገ ምርጫም ፓርቲያቸው ትልቅ ድል አግኝቶ ወደ ሥልጣን መምጣት ችሎነበር። ሆኖም የአገሪቱ ሕገ መንግሥት ሳን ሱ ቺ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ አልፈቀደም። ምክንያቱም የሳን ሱ ቺ ልጆችየውጭ ዜጎች ስለሆኑ ነበር። በዚህም የተነሳ መንግሥትን የሚመሩት ከጀርባ ሆነው ነው። ሳን ሱ ቺ አሁን 75 ዓመትሆኗቸዋል። የሰላም ኖቤል አሸናፊ የሆኑት ሳን ሱ ቺ በሚያናማር የሮሒንጋ ሙስሊሞች ላይ ለደረሰው ግፍና መከራ ቸልተኝነትበማሳየታቸው ከበርካታ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ያገኟቸው ክብርና እውቅናዎችን ተነጥቀዋል። ሆኖም በአገሯ ውስጥ ሳን ሱ ቺ በቡድሃ ብዙኃን ዘንድ ሰፊ ተቀባይነት አላት። |
news-54680262 | https://www.bbc.com/amharic/news-54680262 | በአፍጋኒስታን የትምህርት ማዕከል ላይ በተፈጸመ ጥቃት 18 ሰዎች ተገደሉ | በአፍጋኒስታን መዲና ካቡል በአንድ የትምህርት ማዕከል ውስጥ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት ቢያንስ 18 ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ በርካታ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ባለስልጣናት ገልጸዋል። | የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት እንዳስታወቀው ጥቃቱ የተፈጸመው በአንድ በአጥፍቶ ጠፊ ሲሆን አደጋው ደረሰው ደግሞ በግል የትምህርት ተቋም ላይ ነው። ትምህርት ቤቱ በዋነኛነት የሸዒአ ሙስሊም ተማሪዎችን የሚማሩበት ሲሆን ብዙ ጊዜ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን በማስተናገድ የሚታወቅ ነበር። ከቦምብ ጥቃቱ በኋላ በርካቶች ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። ከፍንዳታው ከፍተኛነት የተነሳም የሟቾች ቁጥር እየጨመረ ሊመጣ እንደሚችል ተጠቁሟል። ኢስላሚክ ስቴት ቡድን (አይሲስ) በማህበራዊ መገናኛ ብዙሀን በኩል ባስተላለፋቸው ምልዕክቶች ለጥቃቱ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ የገለጸ ሲሆን ጥቃቱን ስለመፈጸሙ የሚያረጋግጥ ያቀረበው ምንም ማስረጃ የለም። ከጥቃቱ በኋላ ታሊባን እጁ እንደሌለበት አስታውቋል። ''አንድ ፈንጂ የታጠቀ አጥፍቶ ጠፊ የትምህርት ማዕከሉ ውስጥ ገባ። የጥበቃ አባላት እርምጃ ከመውሰዳቸው በፊት ፈንጂውን አፈነዳው'' ብለዋል የአገር ውሰጥ ጉዳዮች ሚንስቴር ቃል አቀባይ ታሪቅ አሪያን። አሊ ራዛ የተባሉ የአካባቢው ነዋሪ ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል እንደተናገሩት በፍንዳታው ሕይወታቸው ያለፈው እና ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች ወደ ማዕከሉ ለመግባት በመጠባበቅ ላይ የነበሩ ናቸው። ''ከማዕከሉ በ100 ሜትር ርቀት ላይ ነበር እኔ የቆምኩት፤ ልክ ፍንዳታው ሲደርስ እኔንም ወረወረኝ'' ብለዋል። አፍጋኒስታን ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን ያስተናገደች ሲሆን አብዛኛዎቹ ጥቃቶች የተፈጸሙት ደግሞ በታሊባን ነው። የአፍጋኒስታን ሺአ ሙስሊም ማህበረሰቦች ከዚህ በፊት በሱኒ አክራሪ ሙስሊሞች ጥቃት ይደርስባቸው ነበር። ጥቃት አድራሹ ደግሞ በብዛት አይኤስ ሲሆን የሺአ ሙስሊሞች አስተምህሮ ትክክል አይደለም ብሎ ያምናል። እንዲህ አይነት ጥቃት በትምህርት ማዕከል ውስጥ ሲፈጸም በአፍጋኒስታን ይህ የመጀመሪያው አይደለም። ከዚህ በፊትም በአውሮፓውያኑ 2018 አንድ ተማሪዎች የሚያጠኑበት ማዕከል ላይ በተፈጸመ ጥቃት 48 ሰዎች መሞታቸው የሚታወስ ነው። ከሟቾቹ መካከል አብዛኛዎቹ ተማሪዎች ነበሩ። በወቅቱም አይኤስ ለጥቃቱ ኃላፊነቱን ወስዶ ነበር። |
news-53282428 | https://www.bbc.com/amharic/news-53282428 | ከታሰሩ ፖለቲከኞች ውስጥ ‘የተደበደበ’ እና ‘በረሃብ አድማ’ ላይ ያሉ መኖራቸው ተነገረ | የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር እንደተደበደቡ ጠበቃቸው ሲናገሩ አቶ ጃዋር መሐመድና አቶ በቀለ ገርባ የረሃብ አድማ ላይ መሆናቸውን አንድ የፓርቲያቸው ኃላፊ ተናግረዋል። | የአቶ እስክንድር ነጋ ጠበቃ የሆኑት አቶ ሔኖክ የሸዋሉል ለቢቢሲ እንደተናገሩት ደንበኛቸው በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ለማግኘት እንዳልቻሉ ገልጸው፤ ዛሬ ፖሊስ በእስክንድር ቤት ላይ ፍተሻ ለማድረግ ይዘዋቸው እንደሄዱና ድብደባ እንደተፈፀመባቸው ቤተሰቦቻቸው እንዳሳወቋቸው ጠበቃው ገልፀዋል። አቶ እስክንድር ከማንም ሰው ጋር እንዳይገናኙ መከልከላቸውን የሚገልጹት አቶ ሔኖክ፤ ጠበቃ በመሆናቸው ዝርዝር ለመጠየቅ ቢሞክሩም ሳይሳካላቸው መቅረቱን ተናግረዋል። በሌላ ዜና ከኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አመራሮች አንዱ የሆኑት አቶ አዲሱ ቡላላ ምግብና ልብስ ለማድረስ ወደ እስር ቤት የሄደችውን የጃዋር እህትን በመጥቀስ እንደገለጹት "ምግብ አልቀበልም የረሃብ አድማ ላይ ነኝ" ሲሉ ልብስ ብቻ መቀበላቸውን ገልጸው አቶ በቀለም የረሃብ አድማውን መቀላቀላቸውን እንደሚያውቁ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የሁለቱ ፖለቲከኞች ፓርቲ የሆነው ኦፌኮ ጠበቆችን አነጋግሮ ታሳሪዎቹን እንዲያነጋግሩና አሁን ያሉበትን ሁኔታ እንዲያውቁ ተልከው ነበር የሚሉት አቶ አዲሱ፤ "አርብ ስለሆነ ዛሬ ማግኘት አትችሉም፤ ማክሰኞ ተመልሳችሁ ኑ" መባላቸውን ተናግረዋል። አቶ አዲሱ የግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር መዋል አግባብነት የሌለውና በሕግ ቁጥጥር ስር ከዋሉ ጊዜ ጀምሮም ከቤተቦቻቸው፣ ከጠበቆቻቸውና ከሐኪሞቻቸው ጋር የመገናኘት ሕጋዊ መብት ቢኖራቸውም ይህ እየተጠበቀላቸው አይደለም ሲሉ ከስሰዋል። የአቶ እስክንድር ነጋ ጠበቃ አቶ ሔኖክ አክለውም ዛሬ ጠዋት ወደ የባልደራስ ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሲያመሩ፤ ትናንት ምሽት ተዘግተው የነበሩት የቢሮው በሮች ተከፍተው ንብረቶች በየቦታው ወድቀው ማግኘታቸውን ተናግረዋል። ባደረጉት ማጣራትም ማንም ታዛቢ ባልተገኘበት ፖሊስ ወደ ፓርቲው ጽህፈት ቤት መጥቶ እንደነበርና ቢሮው ውስጥ ፍተሻ እንደተደረገበት እዚያ አካባቢ ከነበሩ የዓይን እማኞች ማረጋገጣቸውን ገልፀዋል። ከአቶ እስክንድር ጋር አቶ ስንታየሁ ቸኮል ታስረው እንደሚገኙ የገለጹት ጠበቃው ሁለቱ የፓርቲው አመራሮች በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ወይም በተለምዶ ሦስተኛ በሚባለው ጣቢያ እንደሚገኙ ገልጸዋል። በፖሊስ ቁጥጥር ስር ስለሚገኙበት ሁኔታ በተመለከተ ማብራሪያ ለማግኘት የፌደራል ፖሊስ ቃል አቀባይ የሆኑትን አቶ ጄይላን አብዲን አናግረን ስለተባሉት ጉዳዮች የደረሳቸው መረጃ እንደሌለ ተናግረዋል። ከዚህ ባሻገርም ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪዎቻችን ምላሽ ባለማግኘታቸው ሊሳካ አልቻለም። ፖሊስ የሚሰጠው ምላሽ ካለ ለማስተናገድ ሙከራችንን እንቀጥላለን። አቶ እስክንድር ነጋ፣ አቶ በቀለ ገርባና አቶ ጃዋር መሐመድ ለእስር የተዳረጉት ባለፈው ሰኞ ምሽት አዲስ አበባ ውስጥ ባልታወቁ ሰዎች የተገደለውን ታዋቂ ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን ሞት ተከትሎ ከተከሰተው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ ነው። የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሁከት ለመቀስቀስ በመሞከር ተጠርጥረው እንደታሰሩ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ መግለጹ ይታወሳል። አቶ ጃዋር መሐመድን ጨምሮ 35 ሰዎች ለእስር የተዳረጉት ደግሞ ከድምጻዊው አስክሬን ሽኝት ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ግርግርና ባጋጠመ ሞት ምክንያት እንደሆነ የፌደራል ፖሊስና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሸኖች በጋራ በሰጡት መግለጫ ማስታወቃቸው ይታወሳል። |
54635972 | https://www.bbc.com/amharic/54635972 | ልደቱ አያሌው፡ የቢሾፍቱ ፖሊስ አቶ ልደቱ የታሰሩት ሕገ መንግሥቱን በመናድ በሚለው ክስ መሆኑን ገለፀ | የቢሾፍቱ ፖሊስ መምሪያ አቶ ልደቱ ሕገወጥ መሳሪያ በመያዝ በሚለው ክስ በዋስ መለቀቃቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ለፍርድ ቤት አቀረበ። | ፖሊስ ዛሬ፣ ሐሙስ፣ ለፍርድ ቤት ባስገባው ደብዳቤ አቶ ልደቱ አያሌው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ያሉት ሕገ መንግሥቱን በመናድ በሚለው ክስ መሆኑን ተናግሯል። የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፕሬዚዳንት አቶ አዳነ ታደሰ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በ9/2/13 የቢሾፍቱ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ትዕዛዝ መታዘዙንና በዚሁ ትዕዛዝ መሰረት በ10/2/13 በመዝገብ ቁጥር 670/2013 መለቀቃቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ለፍርድ ቤቱ አቅርበዋል።። በምስራቅ ሸዋ ዞን የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምድብ ችሎት ሕገ መንግሥቱን በኃይል ለመናድ በሚል አዲስ ክስ ስለተመሰረተባቸው መልሰን በፖሊስ መዝገብ ቁጥር 171/2013 አስረናቸዋል ደብዳቤው እንደሚል አክለው ተናግረዋል። ደብዳቤው ለተከሳሽ ጠበቆችም በግልባጭ እንዲደርስ የተደረገ ሲሆን በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ የምስክሮችን ቃል መርምሮ ብይን ለመስጠት ለ26/2/2013 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። አቶ ልደቱ ነገ ሕገ መንግሥቱን በኃይል ለመናድ በሚለው ክስ ቀጠሮ ስላላቸው ፍርድ ቤት ይቀርባሉ። የምሥራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ አቶ ልደቱ አያሌውን በአንድ መዝገብ ፈትቶ፣ በሌላ ማሰሩን የሚያሳይ ማስረጃ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ የሰጠው ትናንት ረብዕ ሰጥቶ ነበር።። በምሥራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዋስትና እንዲፈቱ ተደጋጋሚ ትዕዛዝ የተሰጠላቸው አቶ ልደቱ አያሌው ዛሬ ማለዳ፣ ጥቅምት 11/2013 ዓ.ም ችሎት ላይ ተገኝተው ነበር። ፍርድ ቤቱ ትዕዛዙን የሰጠው አቶ ልደቱ ማክሰኞ ዕለት በታሰሩበት ፖሊስ ጣቢያ በዚህ አኳኋን እንደታሰሩ እንደተነገራቸው ለችሎት ካስረዱ በኋላ ነው። አቶ ልደቱ ትናንት ረብዑ፣ የምሥራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተገኙት በ9/2/2013 ዓ. ም ችሎት በቀረቡበት ወቅት የተሰጡት ሁለት ትዕዛዞችን ለመከታተል መሆኑን አቶ አዳነ ለቢቢሲ ገልፀው ነበር። በባለፈው ቀጠሮ የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ መቅረባቸውን ያስታወሱት አቶ አዳነ፤ አዛዡ አቶ ልደቱን ያልፈቱበትን ምክንያት ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ ፍርድ ቤቱን ስላላሳመነው አቶ ልደቱን ለቅቀው ሪፖርት እንዲያደርጉ አለበለዚያ ግን እርምጃ እንደሚወስድ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ተናግረዋል። ሌላው ትዕዛዝ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አቶ ልደቱ ለምን ሊለቀቁ እንዳልቻሉ ቀርቦ ማብራሪያ እንዲሰጥ የሚል ነበር። በዚሁ መሠረት የቢሾፍቱ ፖሊስ መምሪያ በአቶ ልደቱ አጃቢ በኩል አቶ ልደቱን ለምን እንዳልለቀቋቸው ምላሽ ሰጥቷል። የቢሾፍቱ ፖሊስ መምሪያ አቶ ልደቱን 'ሕገ ወጥ መሣሪያ ይዞ በመገኘት' በተከሰሱበት መዝገብ እንደለቀቃቸው ምላሽ በመስጠት፣ ነገር ግን በሌላ ክስ ስለሚጠየቁ በ13/2/2013 ዓ. ም ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀጠሮ ስላላቸው አለመለቀቃቸውን አስረድቷል። አቶ ልደቱ በዚህ ጉዳይ ላይ ለችሎቱ "ትናንት [ማክሰኞ] ከቀኑ 10 ሰዓት ከ20 ላይ አንድ ፖሊስ መጥቶ 'በዚህኛው መዝገብ ፈትተንሃል በሌላኛው መዝገብ ክስ ታስረሃል፤ ይህንን እንድታውቀው ነው' በሚል ነግሮኝ ከመሄዱ ውጪ አልተለቀኩም" ማለታቸውን አቶ አዳነ ተናግረዋል። ፍርድ ቤቱም "በቃል ለቅቄያሁ ማለት አይሠራም፤ በፍርድ ቤቱ ጊዜ መቀለድ አይገባም፤ ስለዚህ ነገ የቢሾፍቱ ፖሊስ መምሪያ አቶ ልደቱን መልቀቁን በጽሁፍ ማረጋገጫ ጽፎ እንዲያመጣ" በሚል ትዕዛዝ አስተላልፏል። አቶ ልደቱ በበኩላቸው ያላቸውን ቅሬታ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል። ፍርድ ቤቱ እስካሁን እየሄደበት ያለው መንገድ ፍፁም ተገቢነት ያለው ነው ያሉት አቶ ልደቱ፤ ሕግን ለመተርጎም እያሳየ ያለው ቁርጠኝነት በጣም ደስ ይላል ማለታቸውን አቶ አዳነ ተናግረዋል። ለዚህም ምስጋና በማቅረብ "ግን አሁን በፍርድ ቤቱ ላይ እየተሠራ ያለው አማተሮች የሚሠሩት አይነት ቴአትር ነው" በማለት "በዚህ ሁኔታ በፍትሕ ሥርዓቱ እና በእናንተም ጊዜ ላይ እኔም አብሬ መቀለድ አልፈልግም። ስለዚህ ፖሊስ አልለቅም እንዳለኝ በታሪክ ይመዝገብልኝ። እና ወደ ቀጣዩ የክርክር ምዕራፍ ብንሸጋገር ነው የሚሻለው" የሚል ጥያቄ ማንሳታቸውን አቶ አዳነ ገልፀዋል። ፍርድ ቤቱ በበኩሉ "አሁን እየተጣሰ ያለው ሕግ ብቻ ሳይሆን ሕገ መንግሥቱም ጭምር ነው" በማለት ባለው አቅም ሁሉ ይህንን ለማስከበር ጥረቱን እንደሚቀጥል ምላሽ ሰጥቷል ብለዋል። የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተወካይ በበኩላቸው አቶ ልደቱ ያልተለቀቁበትን ምክንያት ለፍርድ ቤቱ በጽሁፍ ምላሽ ሰጥተዋል። እነርሱም የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እንደገለፀው፤ "አቶ ልደቱ ሕገ መንግሥቱን በኃይል ለመናድ ክስ ስለተመሰረተባቸው ነው ያልተለቀቁት" የሚል መረጃ ከቢሾፍቱ ፖሊስ መምሪያ መረጃ እንደደረሳቸው ገልፀዋል። ፍርድ ቤቱ ግን "የምንነጋገረው ስለዚህ መዝገብ ነው" በማለት አቶ ልደቱ በ100 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ተብሎ ለምን አልተለቀቁም? በማለት "በፍርድ ቤቱ ጊዜ ነው የምትቀልዱት። ይህ በፍትሕ ሥርዓቱም በሕገ መንግሥቱም ላይ መቀለድ ነው" ብሏል። ስለዚህም ነገ አቶ ልደቱ መለቀቃቸውን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ 8 ሰዓት ላይ ይዛችሁ ቅረቡ የሚል ትዕዛዝ ተላልፏል። አቶ አዳነ "ነገ ደብዳቤውን ጽፈው ይመጣሉ? ጽፈውስ ቢመጡ አቶ ልደቱ ይለቀቃል? የሚለው በኛ እምነት ያንን የሚያደርጉ አይመስለንም። ምክንያቱም አቶ ልደቱ በምንም ተአምር ለአንድና ለሁለት ቀን ብቻ ሳይሆን ለአንድ ደቂቃም ነፃነቱን አንዲያገኝ በመንግሥት በኩል ፍላጎት የለም። አቶ ልደቱ ይለቀቃሉ ብለን እኛም ተስፋ አናደርግም።" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። |
52541184 | https://www.bbc.com/amharic/52541184 | ምክር ቤቱ 'ሕገ-መንግሥታዊ ትርጓሜ መጠየቅ' የሚለውን አማራጭ አጸደቀ | የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የም/ቤቱን 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን በ15ኛ መደበኛ ስብሰባው 'ሕገ-መንግስታዊ ትርጓሜ መጠየቅ' የሚለውን አማራጭ የውሳኔ ሀሳብ አጽደቀ። | ምክር ቤቱ ባካሄደው ስብሰባ በኮቪድ-19 ምክንያት በነሐሴ ወር ለማካሄድ ታቅዶ የነበረውን ምርጫ ማስፈጸም አስቸጋሪ በመሆኑ መንግሥት የምርጫ ጊዜን በማራዘም ምርጫውን ማካሄድ ያስችላሉ ካላቸው አራት አማራጮች መካከል ነው 'ሕገ-መንግስታዊ ትርጓሜ መጠየቅ' የሚለውን አማራጭ ማጽደቁ ተዘግቧል። • የጠቅላይ ሚንስትሩ አራት አማራጮች • 7 ፓርቲዎች አሁን ላይ ላለው ችግር ምላሽ የሚሆነው 'ፖለቲካዊ መፍትሄ ነው' አሉ መንግሥት አቅርቧቸው የነበሩት አራት አማራጮች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን መበተን፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ፣ ሕገ-መንግሥትን ማሻሻል እና የሕገ-መንግሥት ትርጓሜ መጠየቅ የሚሉ ናቸው። በምክር ቤቱ ውሳኔ መሠረት ጉዳዩ ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ያመራል ማለት ነው። መንግሥት ያቀረባቸው ሁሉም አማራጮች የራሳቸው የሆነ ጠንካራ እና ደካማ ጎን እንዳላቸው የዘርፉ ባለሙያዎች ሲናገሩ ቆይተዋል። 'ሕገ-መንግስታዊ ትርጓሜ መጠየቅ' የሚለው አማራጭ ሲነሱበት ከነበሩ ድክመቶች መካከል፤ "የአምስት ዓመት ገደቡ በፌዴሬሽን ምርክር ቤት ላይም ይሰራል። ይህ ማለት የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕገ-መንግሥት ትርጓሜ የሚጠየቀው በራሱ ጉዳይ ላይ ነው" የሚለው ይገኝበታል። ትናንት ምሽት 7 የፖለቲካ ፓርቲዎች ባወጡት የጋራ መግለጫ ላይም ይህን አማራጭ ሲሉ "የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሕገ-መንግስቱን ለመተርጎም ስልጣን ቢኖረውም በሕገ-መንግሥቱ ምርጫን ማስተላለፍንም ሆነ የመንግሥት ስልጣንን ማራዘም የሚመለከት አንቀጽ ፈጽሞ በሕገ-መንግስቱ ባለመካተቱ የፌዴሬሽን ምክንር ቤት በሕገ-መንግሥቱ ያልተካተቱ ጉዳዮችን መተርጎም አይችልም" የሚል ትችት ተሰንዝሮበታል። ምክር ቤቱ ዛሬ በዋለው ስብሰባ፤ የምክር ቤቱ አባላት መንግሥት ባቀረባቸው አራት አማራጮች ላይ ጥያቄዎችን እና አስተያየቶችን ሰጥተዋል። • ህወሐት ክልላዊ ምርጫ ለማከናወን ዝግጅት አደርጋለሁ አለ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጪ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆኑት የተከበሩ አቶ ተስፋዬ ዳባ ከዚህ ቀደም ሕዝቡ ያላመነባቸው አዋጆች ይደረጉ እንደነበር አስታውሰው የቀረቡት የውሳኔ ሃሳቦች ሕገ-መንግስቱን መሰረት ያደረጉ ናቸው ስለማለታቸው የምክር ቤቱ ፌስቡክ ገጽ አስነብቧል። የተከበሩ አቶ ተስፋዬ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 102 ምርጫን ማካሄድ የፌዴራል መንግስትና የምርጫ ቦርድ ሥልጣንና ተግባር መሆኑን ጠቁመው ቦርዱ ምርጫን ለማራዘም ያቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ተገቢና ህገመንግስታዊ በመሆኑ ከዚህ ውጭ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ኢ-ህገ መንግስታዊ መሆናቸውንም አሳስበዋል፡፡ |
news-53956717 | https://www.bbc.com/amharic/news-53956717 | ልዩ ፍላጎት፡ የደቡብ አፍሪካ ፖሊሶች የአዕምሮ እድገት ውስንነት ባለበት ታዳጊ ግድያ በቁጥጥር ሥር ዋሉ | የ16 ዓመት ታዳጊን ተኩሰው 'በመግደል' ሁለት የደቡብ አፍሪካ ፖሊሶች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለፀ። | የታዳጊው ናታኔል ግድያን ተከትሎ የኤልዶራዶ ፓርክ ነዋሪዎች ተቃውሟቸውን አሰምተዋል ናታኔል ጁሊየስ የተባለው ታዳጊ 'ዳውንስ ሲንድረም' [የአዕምሮ እድገት ውስንነት] የነበረበት ነው ተብሏል። ታዳጊው በጆሃንስበርግ ኤልዶራዶ ፓርክ የመኖሪያ መንደር የተገደለው ብስኩት ለመግዛት በወጣበት እንደሆነም የሟች ቤተሰቦች ተናግረዋል። ልጃቸው የተገደለውም ባለበት የጤና እክል ምክንያት ፖሊስ ለጠየቀው ጥያቄ መልስ መስጠት ባለመቻሉ ነው ብለዋል ቤተሰቦቹ። • ልጆች ኮሮናቫይረስን ያስተላልፋሉ? • ወንዶች የማያወሯቸው አምስት አሳሳቢ ነገሮች ፖሊስ መጀመሪያ ላይ ታዳጊው በፖሊሶች እና በወንበዴዎች መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ተሳትፎ እንደነበር ተናግሮ ነበር። ይሁን እንጂ ገለልተኛ የሆነው የፖሊስ መርማሪ ዳሬክቶሬት በእጁ የገባውን መረጃ በጥንቃቄ ከተመለከተ በኋላ ፖሊሶቹን ለማሰር እንደወሰነ ተናግሯል። ፖሊሶቹ በግድያ ወንጀል እንደሚከሰሱ የተገለፀ ሲሆን፤ "በፍርድ ሒደቱ ሊረቱ እንደሚችሉ" በፖሊስ የተፈፀሙ ከባድ ወንጀሎችን የሚመረምረው ይኸው ገለልተኛ ተቋም አስታውቋል። የታዳጊውን ግድያ ተከትሎ በአገሪቷ ከፍተኛ ተቃውሞ ተቀስቅሶ ነበር። • በርካታ አካል ጉዳተኞችን ከዊልቸር ላይ ያነሳው ኢትዮጵያዊ ተቃውሞው የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ ሕዝቡ እንዲረጋጋ ወጥተው እስከመጠየቅ ያደረሰ ነበር። ዳውንስ ሲንድረም ምንድን ነው? 'ዳውንስ ሲንድረም' የተባለው የአዕምሮ እድገት ውስንነት ስያሜውን ያገኘው በመጀመሪያ የበሽታውን ዓይነት በለዩት ዶክተር ጆን ላንግዶን ዳውን ስም ነው። ለዚህ የጤና እክል የተዳረጉ ሰዎች ከውልደት ጀምሮ አካላዊና አዕምሯዊ እድገት ውስንነት ይታይባቸዋል። ይህ የጤና እክል በአብዛኛው የሚከሰተው በተዛባ የዘረ መል ችግር ምክንያት ነው። አንድ ጤነኛ ሰው 21 ክሮሞዞሞች ሁለት እጥፍ [48] ያለው ሲሆን ለዳውንስ ሲንድረም የሚጋለጡት ሦስት እጥፍ በሚሆንበት ጊዜ ነው። ዳውንስ ሲንድረም ከዘር፣ ብሔር፣ ከኢኮኖሚ ደረጃ ወይም ሃይማኖት ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም። |
news-54165522 | https://www.bbc.com/amharic/news-54165522 | ሊባኖስ፡ በቤሩት ወደብ አቅራቢያ በሚገኝ መገበያያ እሳት ተነሳ | በሊባኖስ መዲና ቤሩት ወደብ አቅራቢያ ግንባታ ላይ የሚገኝ መገበያያ ውስጥ የእሳት አደጋ ተነሳ። ይህ በሳምንት ውስጥ በቤሩት የተከሰተ ሦስተኛ አደጋ ነው። | በመገበያያው ጣሪያ ላይ በከፊል ጉዳት የደረሰ ሲሆን፤ አደጋ ተከላካዮች እሳቱን በአፋጣኝ ማጥፋት ችለዋል። እስካሁን ጉዳት የደረሰበት ሰው ሪፖርት አልተደረገም። የእሳቱ መንስኤም አልታወቀም። የመገበያያው ዲዛይን የተሠራው በእንግሊዛዊ ኢራቃዊ አርክቴክት ዛሀ ሀዲድ ነበር። የሚገኘውም ወደብ አቅራቢያ ባለ አንድ የንግድ ማዕከል ነው። ከስድስት ሳምንታት በፊት በወደቡ በተከሰተው ፍንዳታ ወደ 200 ሰዎች እንደሞቱና 6,000 ሰዎች እንደቆሰሉ ይታወሳል። በአካል ላይ ያስከተለው ጉዳት 4.6 ቢሊዮን ዶላር፤ ምጣኔ ሀብት ላይ የደረሰው ጉዳት ደግሞ 3.5 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ይገመታል። 2,750 ቶን አሞንየም ናይትሬት ፈንድቶ ስለተከሰተው ፍንዳታ አሁንም ምርመራ እየተደረገ ነው። ባለፈው ሳምንት የተከሰቱ ሁለት እሳት አደጋዎች ነዋሪዎችን አስደንግጠዋል፤ አስቆጥተዋልም። መሪዎች በችላ ባይነትና በሙስናም እየተወቀሱ ነው። ባለፈው ማክሰኞ መጠነኛ እሳት ተነስቶ በአፋጣኝ ጠፍቷል። ሀሙስ ደግሞ ወደቡ አቅራቢያ በሚገኝ የእርዳታ ቁሳቁስ ማቆያ ውስጥ ከፍተኛ እሳት ተቀስቅሶ ነበር። ዛሬ ስለተነሳው እሳት የተጠየቀ ጆ ሳይግ የተባለ ግለሰብ “ያሳዝናል፤ ለማመን ይቸግራል። በየቀኑ ችግር ይገጥመናል” ሲል ለሮይተርስ ተናግሯል። ሊባኖስ የገባችበት ቀውስ መገበያያ ገንዘቧ ዋጋ እንዲያጣ፣ ሥራ አጥነት እንዲጨምር እንዲሁም ድህነት እንዲንሰራፋ ምክንያት ሆኗል። ከሳምንታት በፊት የተከሰተውን ፍንዳታ ተከትሎ የአገሪቱ አስተዳዳሪዎች ሥራ ለቀዋል። ተተኪው መንግሥት ከምዕራባውኑ የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ለውጥ ማምጣት እንዳለበት ጫና እየተደረገ ነው። ጆ ሳይግ የተባለው ግለሰብ ግን “ተመሳሳይ ሰዎች ከሆኑ ለውጥ አይመጣም” ብሏል። |
news-54915500 | https://www.bbc.com/amharic/news-54915500 | ትግራይ ፡ ዶ/ር ሙሉ ነጋ የትግራይ ክልል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ዶክተር ሙሉ ነጋ የትግራይ ክልል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው መሾማቸውን ገለጹ። | ዶ/ር ሙሉ ነጋ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳስታወቁት በፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔና በሚኒስትሮች ምክር የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስተዳደርን በተመለከተ በወጣው ደንብ መሰረት ዶ/ር ሙሉ ነጋ እንደተሾሙ አመልክተዋል። በዚህም መሠረት ዋና ሥራ አስፈጻሚው በክልሉ በሕጋዊነት ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የክልሉን መንግሥት ሥራ አስፈጻሚ መዋቅሮች የሚመሩ ኃላፊዎችን መልምለው ይሾማሉ ብለዋል። ዶ/ር ሙሉ ነጋ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ከሚያዚያ 2012 ዓ.ም ጀምሮ ተሹመው ሲያገለግሉ ቆይተዋል። ከዚህ ቀደምም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በመምህርነት፣ በተመራማሪነትና በሥራ ኃላፊነት ማገልገላቸውን ለማወቅ ተችሏል። በፌደራል መንግሥቱና አሁን ክልሉን እያስተዳደረ ባለው ህወሓት መካከል የነበረው አለመግባባት ወደ ወታደራዊ ግጭት መሸጋገሩን ተከትሎ የፌደራል መንግሥቱ የትግራይ ክልልን በተመለከተ የተለያዩ እርምጃዎችን መውሰዱ ይታወሳል። በዚህም መሰረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት በክልሉ ላይ ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ከደነገገ በኋላ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቋል። ይህንንም ተከትሎ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የፌደራል መንግሥት በትግራይ ክልል ጣልቃ እንዲገባና ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ወስኗል። በወቅቱ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የትግራይ ክልል በክልሉ የሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት በማድረስ የፌዴራሉን ሰላምና ጸጥታ ማናጋት ሕገመንግስታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የጣለ እንቅስቃሴ ወይም ድርጊት በመፈጸሙ ሕገ መንግሥቱን ማስከበር አስፈላጊ መሆኑን ገልጾ ነበር። አሁን ወደ ጦርነት የተሸጋገረው በፌደራል መንግሥቱና በትግራይ ክልል መስተዳደር በኩል የነበረው ቅራኔ እየተባባሰ የመጣው ባለፈው ዓመት ሊካሄድ የታቀደው ምርጫ በኮሮናቫይረስ ስጋት ምክንያት እንደማይካሄድ ከታወቀ በኋላ በትግራይ የተናጠል ምርጫ በመደረጉ ሳቢያ ነው። ይህንንም ተከትሎ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምርጫውን ሕገወጥና ተፈጻሚነት የሌለው እንደሆነ መወሰኑን ተከትሎ ማዕከላዊው መንግሥት ከክልሉ መስተዳደር ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳያካሂድና የበጀት ድጋፍ እንዳይሰጥ ከወሰነ በኋላ ነገሮች እየተካረሩ መሄዳቸው ይታወሳል። ይህ ጦርነትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በብሔራዊው ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው እስካሁን የደረሰው የጉዳት መጠን በይፋ ያልተነገረለት ጥቃት በትግራይ ልዩ ኃይል በሰሜን ዕዝ ላይ መፈጸሙን ከገለጹ በኋላ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ማዘዛቸውን ተከትሎ ነው። ይህንንም ተከትሎ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በትግራይ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የደነገገ ሲሆን የተወካዮች ምክር ቤትም ውሳኔውን ተቀብሎ ማጽደቁ ይታወሳል። በተጨማሪም የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ ክልል የተከሰተውን ሁኔታ ተከትሎ የፌደራል መንግሥት በክልሉ ውስጥ ጣልቃ እንዲገባና ክልሉን የሚመራ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ወስኗል። |
news-52563345 | https://www.bbc.com/amharic/news-52563345 | ኮሮናቫይረስ፡ በእንቅስቃሴ ገደቡ ወቅት በርካታ አፍሪካውያን የምግብ እጥረት ያጋጥማቸዋል | የዳሰሳ ጥናት ከተካሄደባቸው ከ20 የአፍሪካ አገራት ዜጎች መካከል ሁለት ሶስተኛው ለ14 ቀናት በቤት እንዲቆዩ ቢገደዱ በቀናት ልዩነት ምግብ እንጨርሳለን ያሉ ሲሆን ከግማሽ በላይ የሆኑት ደግሞ ባዶ ኪሳቸውን እንደሚቀሩ ተናግረዋል። | የዳሰሳ ጥናቱን ያካሄደው የአፍሪካ የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከል ሲሆን፤ የጥናቱ ውጤት የአፍሪካ አገራት መሪዎች ኮሮናቫይረስን ለመከላከል ወደፊት ምን አይነት ፖሊሶዎችን መቅረጽ እንዳለባቸው ጥቆማ ይሰጣል ተብሏል። በሪፖርቱ መንግሥታት የሚያወጧቸው ፖሊሲዎች የዜጎችን ተጨባጭ ሁኔታ ያላገናዘቡ ከሆኑ ግጭት እና አለመረጋጋት ሊከሰት እንደሚችል ተጠቁሟል። ጥናቱ በ20 አገራት የሚገኙ 28 ከተሞች ላይ በመጋቢት ወር የተከናወነ ነው። ሪፖርቱ በአንዳንድ አገራት ዜጎች በኮቪድ ምክንያት ከደረሰባቸው ጫና ለመላቀቅ መንግሥት ድጋፍ እንዲያደርግላቸው አደባባይ መውጣታቸው፤ ሰዎች ምን አይነት ጫና ውስጥ እንዳሉ ያሳያል ይላል ሪፖርቱ። ሪፖርቱ ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብ ሲጥሉ በዜጎቻቸው ድጋፍ የተቸራቸው መንግሥታት ነበሩ ብሏል። በዳሰሳ ጥናቱ የገቢ መጠናቸው አስተኛ የሆኑ ሰዎች፤ በቤት እንዲቀመጡ ቢታዘዙ በአንድ ሳምንት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ያስቀመጡትን ጥሪት እንደሚጨርሱ ተናግረዋል። ጥናቱን ያካሄዱ ተመራማሪዎች መንግሥታት ዜጎቻቸውን ከቤት አትውጡ ከማለታቸው በፊት እነዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ምን እንዳስገደዳቸው ወቅታዊ እና በቂ የሆነ መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ሲሉ ምክረ ሃሳብ ለግሰዋል። በተጨማሪም መንግሥት ተጨማሪ ምርመራዎችን ለማድረግ፣ በበሽታው ሳይያዙ አይቀሩም ተብለው የሚጠረጠሩ ሰዎችን ለመለየት እና በበሽታው የተያዙ ሰዎችን ለማከም የጤና ስርዓቱን ማሻሻል ላይ ትኩረት እንዲሰጡ ምክር ሰጥተዋል። በአፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 48 ሺህ 22 የደረሰ ሲሆን፣ ከነዚህም መካከል 16ሺህ 19 አገግመዋል፣ 1ሺህ 878 ቱ ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል። |
46259192 | https://www.bbc.com/amharic/46259192 | በሸካ ዞን ባለው አለመረጋጋት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ለወራት ሥራ እንደፈቱ ተነገረ | በደቡብ ብሔር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል በምትገኘው ሸካ ዞን የተለያዩ ግጭቶች መሰማት ከጀመሩ ጥቂት ወራቶችን አስቆጠሩ። | ይህም አለመረጋጋት በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ የተመደቡ ተማሪዎችን የትምህርት ጉዳይ አስተጓጉሏል። የዚህ ችግር መንስኤ በነዚህ ጥቂት ወራት የተከሰተ ሳይሆን ከ1985 ዓ.ም. ጀምሮ የሸኮ ሕዝብ ራሳችን በራሳችን እናስተዳድር የሚለው ጥያቄ ምላሽ ሳያገኝ መቅረቱ እንደሆነ በሥራ ምክንያት ነዋሪነቱን አዲስ አበባ ያደረገውና የአካባዊው ተወላጅ ኮስትር ሙልዬ ይናገራል። የያደገበትን አካባቢ 'ትንሿ ኢትዮጵያ' ሲል የሚጠራው ኮስትር የሸካ ዞን የብዙ ህዘቦች መናኸሪያም እንደሆነች ይናገራል። በተለይም ከጥቂት ጊዜ ወራት በፊት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ የሆኑት ወ/ሮ ሙፈሪያት ከማል የአካባቢውን ሕዝብ ሊያናግሩ ከመጡ ወዲህ ደግሞ ነገሮች መባባሳቸውን የከተማዋ ሰላም ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ መንገሻ አዲስ ይናገራሉ። የሸካ ዞን የመዠንገር፣ ሸካ እና ሸኮ ብሔሮች የሚኖሩበት ሲሆን፤ ከአፈ ጉባዔዋ ጋር በነበረው ውይይት ላይ የተሳተፉት ሰዎች እኛን የማይወክሉ ናቸው በሚል መንስዔ ችግሩ እንደተባባሰ ኮስትር ለቢቢሲ ገልጿል። «አፈ ጉባዔዋ ውይይት ላይ ሳሉ፤ ከአዳራሹ ውጭ ያሉ ወጣቶች ተቃውሞ በማሰማታቸው ወጥተው አነጋግረዋቸዋል። ቢሆንም ጉዳዩ ሊፈታ ስላልቻለ የአካባቢው ሕዝብ ተቃውሞውን በሥራ ማቆም አድማ እየገለፀ ነው፤ ትምህርት ቤቶችም ዝግ ናቸው» ብሏል ኮስትር። በቴፒ ከተማ እና የኪ በተሰኘችው ወረዳ ከሆስፒታል በቀር ሌሎች የመንግሥት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ሥራ ላይ እንዳልሆኑ ከነዋሪዎችና ከቴፒ ከተማ ፀጥታና ፍትህ ኃላፊ ከሆኑት ከአቶ ተሥፋዬ አለም ሰምተናል። የከተማዋ ነዋሪዎች ጉዳዩን ለክልልም ሆነ ለፌዴራል መንግሥት እንዳቀረቡና ምንም አይነት ምላሽ እንዳልተሰጣቸውም ምሬታቸውን አሰምተዋል። • "በኢትዮጵያ 93 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ መጸዳጃ ቤት የለውም" ከተማዋ ባለመረጋጋቷና የንግድም ሆነ ሌሎች እንቅስቃሴዎች በመቆማቸው ምክንያት ልጆቻቸውን አዲስ አበባ ድረስ ልከው እያስተማሩ ያሉ ነዋሪዎች እንዳሉ ኮስትር ያስረዳል። «እንግዲህ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ሕዝብ አሁንም ተቸግሮ ነው ያለው፤ የቴፒ ዩኒቨርሲቲም ተማሪዎችን ያልጠራበት ምክንያት ይህ ነው።» ይላል የአካባቢው ሕዝብ ትኩረት እንዲሰጠው ነው እንቅስቃሴዎችን ወደማቆም የተገባው ሲል ኮስትር ሁኔታውን ያስረዳል፤ «ቢያንስ የፌዴራል ቢሮ ዝግ ሲሆን ለምን ሆነ ብሎ የሚመጣ አካል ይኖራል በሚል" እንደሆነ የሚናገረው ኮስትር «አዲሱ የክልሉ አስተዳዳሪ አቶ ሚሊዮን ማቲዮስም ጉዳዩን ያውቁታል፤ ሶስት ወር ገደማ ሆነው። ነገር ግን ምንም ዓይነት ምላሽ አላገኘንም።» ብሏል። ጥያቄው ምንድነው? የደቡብ ክልል መንግሥት የዞን እና ክልል እንሁን ጥያቄዎችን በመመለስ እና በመመርመር የተጠመደ ይመስላል። «የክልሉ መንግሥት ጉዳዩን በደንብ ያውቀዋል፤ በቅርቡ ዞኖችን እንደ አዲስ ሲያዋቅር እንኳ የእኛን አካባቢ ጥያቄ ችላ ብሎታል» በማለት ኮስትር ቅሬታውን ያሰማል። የሸካ ዞን በዋናነት የሶስት ብሔር ተወላጆች ይኖሩበታል፤ ሸካ፣ ሸኮ እና መዠንገር። ከእነዚህ ብሔሮች መሃል የሸካ የበላይነት ስላለ እኛ ራሳችን በራሳችን እንደ ዞን ማስተዳደር እንድንችል ይሁን ዋነኛው ጥያቄ እንደሆነ ኮስትር እና አቶ መንገሻ ያስረዳሉ። ትላንት ረፋዱ ላይ በቴፒ ከተማ አለመረጋጋት ነበር የሚሉት አቶ መንገሻ፤ ጥያቄያቸው ከራስን ማስተዳደር ወደ መሠረተ ልማት ጥያቄ ወርዷል። ጥያቄያቸውንም ለክልል ምክር ቤት እንዲሁም ለፌዴሬሽን እንዳቀረቡ ገልፀዋል። "በጣም በርካታ ሕዝብ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥቶ ጩኸቱን አሰምቷል። አሁንም ቢሮዎች አገልግሎት እየሰጡ አይደሉም። በሺዎች የሚቆጠሩ የሸኮ እና የመዠንገር ተወላጆች ዛሬ ወደ ከተማ ወጥተው አወያዩን፤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥያቄያችንን የመሠረተ ልማት ነው ማለቱ ተገቢ አይደለም ብለው ወጥተዋል።» ብለዋል፥ • የሰው ልጅ ዘር እየመነመነ ነው የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ዋና አማካሪ የሆኑት አኔሳ መልኮ ሁኔታውን አጥንተን ምላሽ እንሰጣለን ብንልም የሚሰማን ማግኘት አልቻልንም ይላሉ። «ራሳችንን በራሳችን እናስተዳድር የሚሉ አሉ። እኛ ይህ ትክክል ነው ብለን ዛሬውን ምላሽ መስጠት አንችልም። በጥናት ወደፊት ይታያል ተብሎ ተነግሯቸዋል። ዛሬውኑ ይደረገልን፤ ዛሬውኑ ይጠና የሚሉ አሉ" በማለት ለቢቢሲ ተናግረዋል አቶ አኔሳ የአቶ ሚሊዮን አስተዳደር ሁኔታውን በማረጋጋት ሥራ ላይ መጠመዱን ይናገራሉ። «አመራሩ የማረጋጋት ሥራ ላይ ነው፤ ከዚህ ውጭ የሆነ ነገር እንዳይኖር ነው የምንሰጋው። ዋናው ሰላምና መረጋጋት ነው።» ለአለመረጋጋቱ ዋናው መንስዔ የሕዝቡ ጥያቄ አለመመለስ ሆኖ ሳለ ጥያቄው መፍትሄ ሳይበጅለት ሰላም ማምጣት አይከብድም ወይ የሚል ጥያቄ ለአማካሪው ሰንዝረንላቸው ነበር። «ጥናት ይካሄዳል ብያለሁ እኮ፤ አጥኚ ቡድኑም በሰላም መንቀሳቀስ መቻል አለበት። መደማመጥ ከሌለ፤ እኔ ያልኩት ብቻ ይሰማ የሚል ባለበት እንዴት መሥራት ይቻላል?» በማለት ጥያቄ ያነሳሉ የደቡብ ክልል የገጠር ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑት አቶ አክሊሉ የአካባቢውን ነዋሪዎች ለማነጋገር ትላንት በሥፍራው ቢገኙም ሰዎች እየመረጡ እንጂ ሁላችንንም አላነገሩንም ሲሉ ነዋሪዎቹ ይወቅሳሉ። ኃላፊውን ለማግኘት ቢቢሲ በተደጋጋሚ ስልክ ቢደውልም ተንቀሳቃሽ ስልካቸው ሊነሳ አልቻለም። በአካባቢው የፌዴራል እና የክልል የፀጥታ ኃይሎች ተሰማርተው ፀጥታ ለማስከበር እየጣሩ እንደሆነና፤ አከባቢው አሁንም ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንደማይስተዋልበት ኮስትር ይናገራል ። • የደህንነት ተቋሙ ምክትል የነበሩት አቶ ያሬድ ዘሪሁን ፍርድ ቤት ቀረቡ |
46134516 | https://www.bbc.com/amharic/46134516 | ኢትዮጵያዊቷ የኒውዮርክ ነዋሪ የኤል ቻፖን የፍርድ ሂደት ለመዳኘት ተመረጠች | ረቡዕ ዕለት 12 የኒውዮርክ ከተማ ነዋሪዎች የሜክሲኮ ዜጋ የሆነው የአደንዛዥ ዕፅ ነጋዴና ከበርቴ የኤል ቻፖ ጉዝማን ጉዳይን ለመዳኘት ተመርጠው ተሾመዋል። ከመካከላቸውም አንዲት ኢትዮጵያዊ እንደምትገኝ ሮይተርስ ዘግቧል። | ዮዋኪን ጉዝማን "ኤል ቻፖ" በኒው ዮርክ ከፍተኛ ትበቃ በሚደረግለት እስር ቤት የሚገኝ ሲሆን 11 ክሶች ይጠብቁታል በኤል ቻፖ እጣ ፈንታ ላይ ለመወሰን ከተመረጡት 12 ሰዎች መካከል ሰባቱ ሴቶች ሲሆኑ አምስቱ ደግሞ ወንዶች ናቸው። ጉዳይን ከሚመለከቱ መካከል ሦስቱ በስደት ወደ አሜሪካ የገቡ ናቸው ተብሏል። ሁሉም በዳኝነቱ የሚሳተፉ ሰዎች ስለ ኤል ቻፖ ሰምተው የሚያውቁ ሲሆን ገለልተኛ ሆኖ ፍርድ ለመስጠትም ቃል ገብተዋል። ኢትዮጵያዊቷ ግን ስለእርሱ "አንዳችም የማወቀው ነገር የለም" ማለቷ ተዘግቧል። • «ያለቋንቋው ሳያስተምር ያደገ ሃገር እኔ አላውቅም» ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ • ሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር መበራከት ምንን ያመለክታል? ከጉዝማን ጠበቆች መካከል አንዱ የሆኑት ኤድዋርዶ ባላሬዞ "በተመረጡት ዳኞቹ ደስተኞች ነን" ብለዋል። አሁን የተሰየሙት ዳኞች ሥራቸውን ማጠናቀቅ ባይችሉ ስድስት ተጠባባቂዎች ተዘጋጅተዋል። በፍርድ ሂደቱ የሚሳተፉት ሰዎች ማንነት ይፋ የማይገለፅ ሲሆን ወደ ፍርድ ቤቱ ሲገቡም ሆነ ሲወጡም በታጠቁ የፌደራል ፖሊሶች ይታጀባሉ። አቃቢያነ ህጎቹ የዳኞቹ ደህንነት በሚገባ መጠበቅ ያስፈለገበትን ምክንያት ሲያስረዱ ጉዝማን ምስክሮችን በማስፈራራት ሲከፋም እንዲገደሉ በማዘዝ ስለሚታወቅ ነው፤ ያሉ ሲሆን ጠበቆቹ ግን መሰረተ ቢስ ሲሉ አጣጥለውታል። "ከህገ መንግሥት ቀረጻ ጀምሮ ተሳታፊ ነበርኩኝ" - መዓዛ አሸናፊ በርካታ ዳኞች ለደህንነታቸው በመስጋት በኤል ቻፖ የፍርድ ሂደት ውስጥ አንሳተፍም ማለታቸው ታውቋል። አራት ወር ሊፈጅ ይችላል የተባለው የፍርድ ሂደት በሚቀጥለው ሳምንት ማክሰኞ የተከሳሽ ጠበቆች በሚያቀርቡት አቤቱታ ይጀመራል ተብሏል። የ61 ዓመቱ ኤል ቻፖ ሜክሲኮ ውስጥ የራሱን የዕፅ ቡድን የሚመራ ሲሆን በዓለም ላይ ኃያል የሆነ የዕፅ አከፋፋይ መረቡን እንደዘረጋ ይነገርለታል። ጉዝማን ለአሜሪካ ተላልፎ የተሰጠው በ2017 ሲሆን ከሜክሲኮ እስር ቤቶች ሁለት ጊዜ ያህል አምልጦ ተይዟል። የጉዝማን ጠበቆች ደንበኛቸው በዕፅ ማዘዋወሩ ውስጥ ሚናው ዝቅተኛ እንደነበረው ለማስረዳት መዘጋጀታቸው ተሰምቷል። የአሜሪካ አቃቤያነ ህጎች በጉዝማን መሪነት ወደ አሜሪካ ሄሮይን፣ ኮኬይን፣ ማሪዋና እና ሌሎች ዕጾችን ያስገባ እንደነበር ገልፀዋል። ሜክሲኮዋዊው ኤል ቻፖ ጉዝማን አሜሪካ ውስጥ አደንዛዥ ዕፅ በማዘዋወር የተከሰሰ ሲሆን የፍርድ ሂደቱ በሚቀጥለው ሳምንት ይጀምራል። |
47398281 | https://www.bbc.com/amharic/47398281 | በከፊል አንድ አይነት ስለሆኑ መንትያዎች ሰምተው ያውቃሉ? | በከፊል አንድ አይነት የሆኑ መንትያዎች ለሁለተኛ ጊዜ ተወልደዋል። የህክምና ባለሙያዎች እንዳረጋገጡት ይህ ክስተት ከዚህ በፊት የተፈጠረው አንዴ ብቻ ነው። | በዓለም በከፊል አንድ አይነት መንትዮች የተፈጠሩት ሁለት ጊዜ ብቻ ነው አንዲት እናት በአውስትራሊያ፣ ብሪዝቤን ውስጥ የጸነሰቻቸው ልጆች በከፊል አንድ አይነት የሆኑ መንትዮች ናቸው። • መንትዮቹ ዶክተሮች እየሩሳሌምና ቃልኪዳን ልጆቹ ወንድና ሴት ሲሆኑ በእናታቸዉ በኩል ተመሳሳይ ናቸው። ከአባታቸው የዘር ቅንጣት (ዲኤንኤ) ግን የተለየየ የዘር ፍሬ በመዉሰዳቸዉ አይመሳሰሉም። ባለሙያዎች እንደሚሉት እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎች በጣም ዉስን ከመሆናቸዉም በላይ ቢከሰት እንኳ ጽንሱ የማደግ እድል የለውም። የህክምና ሂደቱን የተከታተሉት ፕሮፌሰር ኒኮላስ ፊስክ እንደገለጹት በስድሰተኛዉ ሳምንት በተደረገ ምርመራ ጽንሱ ተመሳሳይ መንትያዎች እንዳሉት የሚያሳይ ግኝት ነበረዉ። ነገር ግን 14ኛው ሳምንት ላይ የተደረገዉ ምርመራ ጽንሱ በከፊል አንድ አይነት መንትያዎችን መያዙ ተረጋግጧል። በከፊል ተመሳሳይ ጽንስ እንዴት ተፈጠረ? አንድ የወንድ ዘር በተመሳሳይ ጊዜ የአንዲትን የሴት እንቁላል ብቻ ሰብሮ እንዲበለጽግ ካደረገና ለሁለት ከተከፈለ ተመሳሳይ መንትያ ይፈጠራል። በዚህ መልኩ የሚፈጠሩ ልጆች ተመሳሳይ ጾታ ሲኖራቸዉ ተመሳሳይ አካላዊ ቅርጽና ባህሪ ይኖራቸዋል። • መገረዝ የቀጠፈው ህይወት የተለያዩ መንትያዎች የሚፈጠሩት ሁለት የሴት እንቁላሎች ለየብቻቸዉ በሁለት የተለያየ የወንድ ዘር ሲበለጽጉ ነው። እነዚህ ልጆች በጾታ ተመሳሳይ ሊሆኑም ላይሆኑም ይችላሉ። አንድ ላይ ከመወለዳቸው በስተቀር ምንም የጋራ ነገር አይኖራቸውም። ልክ እንደማንኛዉም ወንድምና እህት የመልክ መቀራረብ ካልሆነ መንታ በመሆናቸዉ የሚጋሩት ነገር አይኖርም። አሁን መነጋገሪያ የሆነው በከፊል አንድ አይነት የሆኑ መንትያዎች ጉዳይ ነው። ክስተቱ የሚፈጠረዉ የአንድ ሴት እንቁላል በሁለት የወንድ ዘር ሲበለጽግ ነው። በሳይንሱ መሰረት አንድ እንቁላል በሁለት የወንድ ዘር ከበለጸገ እንቁላሉ ሲከፈል ሶስት ክሮሞዞም ይኖረዋል። ነገር ግን ብዙ ጊዜ የተለመደው ሁለት ነው (ይህ ማለት አንድ ከእናት አንድ ከአባት)። • የህጻናትን ዘረ መል ማስተካከል ክልክል ነው? ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በዚህ መልኩ የሚፈጠር ክሮሞዞም ህይወት የመሆን እድል የለውም። ምክንያቱም ሁለት ከአባት ስለሆነ በሁለት የወንድ ዘር አንድ እንቁላል ሊበለጽግ አይችልም። ነገር ግን በአውስትራሊያ፣ ብሪዝቤን ይህ ክስተት ባልተለመደ መልኩ ህይወት ያላቸዉ ልጆችን ፈጥሯል። ካሁን በፊት ተመሳሳይ ክስተት እንደ አውሮፓውያኑ በ2007 በአሜሪካ ውስጥ ተከስቶ ነበር። |
news-53803498 | https://www.bbc.com/amharic/news-53803498 | ሥራ ፈጠራ፡ ኮካ እና ፔፕሲን ያሸነፉት ሁለቱ ተማሪዎች | ማይክሮ ሜይገርት እና ሎሬንዝ ሃምፕል የኮላ ኩባንያ ለመመስረት ሲያስቡ ተማሪዎች ነበሩ። ተማሪ መሆን ብቻ ሳይሆን የለስላሳ መጠጥ እንዴት ማምረት እንደሚችሉ ፈጽሞ እውቀቱ አልነበራቸውም። | ፍሪትዝ ኮላ ለገበያ የቀረበው እኤአ በ2003 ነው የወጣትነት ልበ ሙሉነትና ተስፋ በደም ስራቸው ይራወጣል፤ የይቻላል መንፈስ ከፊታቸውን ያለ ተግዳሮት ሁሉ አስረስቷቸዋል። ለምን ትንሽ ጎግል ላይ የተወሰነ ነገር አናነብም ሲሉ ወሰኑ። " ኮላን ለመስራት የሚያገለግሉ ንጥረ ነገሮችን ጎግል ላይ አሰስን" ይላል ማርኮ፤ በወቅቱ የ28 ዓመት ወጣት ነበር። በይነ መረቡ ግን የኮላን ምስጢር በመስጠት ስራቸውን ሊያቀልለው አልፈለገም፤ ስለዚህ እነዚህ ሁለት የልጅነት ጓደኛሞች ሌላ አማራጭ መፈለግ ነበረባቸው። ሁለቱ ጓደኛሞች በሰሜናዊ ጀርመን ሃምቡርግ ነው ያደጉት፤ ስልካቸውን አንስተው ወደ ተለያዩ የቢራ ጠማቂዎች ዘንድ ደወሉ፤ ተስፋቸው ኮላ መስራት የሚያስችል ንጥረ ነገር በመቀመም እንዲረዷቸው እንዲሁም መጠጡን እንዲያሽጉላቸው ነው። ነገር ግን በወቅቱ ሁሉም ቢራ ጠማቂዎች ጀርመን አለኝ የምትለውን ፒልስነር የተሰኘ መጠጥና ሌሎች ቢራዎችን በመጥመቅ ተጠምደው ነበር። ማይክሮ እንደሚለው ከሆነ "በመቶዎች የሚቆጠሩ" ጠማቂዎች ጋር ደውለዋል። ደግሞም ጥሪያቸውን የመለሱት ጠማቂዎችም ቢሆኑ ወጣቶቹ ለምን ለስላሳ መጠጥ ማምረት እንደፈለጉ በጥርጣሬ ተሞልተው ይጠይቋቸው ነበር። አንድ ሰው ግን እሺ አላቸው። " በስተመጨረሻ በምዕራብ ጀርመን አንድ አነስተኛ የቢራ መጥመቂያ ባለቤት ከእኛ ጋር ለመስራት ተስማማ" የሚለው ማይክሮ " የጠመቃ ባለሙያው ' ኑና ጎብኙኝ እናም የሆነ ነገር እንሰራለን' " እንዳላቸው ያስታውሳል። በዚያ ዓመት መጨረሻ ላይ ማይክሮ እና ሎሬንዝ 170 ሳጥን የፍሪትዝ ኮላ አምርተው ለመሸጥ አዘጋጁ። 170 ሳጥን ወደ 4,080 ጠርሙስ ገደማ እንደሚደርስ ይናገራሉ። ይህንን ምርት ይዞ ወደ ትልልቅ የገበያ አዳራሾችና ሌሎች ቸርቻሪዎች ጋር ከመሄድ በቀጥታ መጠጥ ቤቶች እየሄዱ ማከፋፈልን መረጡ። ሁለቱም ለስላሳቸውን በመኪናዎቻቸው ላይ ጭነው ሃምቡርግ ውስጥ በሚገኙ መጠጥ ቤቶች እየዞሩ በቀጥታ ለመሸጥ ሞክረዋል። አሁን የለስላሳ መጠጡ ስም በመላው ጀርመን ይታወቃል። ባለፈው ዓመት ብቻ ከኮካ ኮላ ቀጥሎ የተሸጠ የለስላሳ መጠጥ ምርት ነው። ባለፈው ዓመት 71 ሚሊዮን ጠርሙስ ለስላሳ መጠጥ መሸጣቸውን ገለልተኛ የሆነ የገበያ ጥናት ቡድን አረጋግጧል። በወቅቱ ኮካ ኮላ 74 ሚሊዮን ሲሸጥ ፔፕሲ ደግሞ 337,000 ሸጧል። በርግጥ ኮካ እና ፔፕሲ በፕላስቲክና ቆርቆሮ የታሸጉ መጠጦቻቸው በብዛት ተሸጠዋል። ቢሆንም 17 ዓመት እድሜ ላለው ለጋ የንግድ ሃሳብ ትልቅ ስኬት ነው ተብሏል። የለስላሳ መጠጡ ምርት ለአምስት ፋብሪካዎች ተሰጥቷል በ2003 ማይክሮ እና ሎሬንዝ የራሳቸውን ምስል ለንግድ አርማ ምልክትነት ለመጠቀም ወሰኑ። ማይክሮ ይህንን ለምን እንደመረጡ ሲናገር ያለው ርካሽ አማራጭ በወቅቱ እርሱ ነበር ይላል። "ፊታችንን እንዲህ አድርጎ ለማሳመር የከፈልነው 100 ዩሮ ብቻ ነው" ይላል ማይክሮ። " ጎረቤታችንን ፎቷችንን በፎቶሾፕ እንዲሰራውና ብራንዳችንን ለማስመዝገብ የከፈልነው 70 ዩሮ ነው እናም የራሳችንን የፍሪትዝ ኮላ ፎንት ፈጠርን" ብሏል የ44 ዓመቱ ማይክሮ። ለጓደኛሞቹ በወቅቱ የባለቀለም ህትመት ውድ ስለነበር በጥቁርና ነጭ ማስጻፍንም መርጠዋል። የምርታቸውንም ስም ለማውጣት የመረጡት ተጠቃሚዎች እንዲመርጡ ማድረግን ነው። 40 ያህል ስሞችን በወረቀት ላይ ካሰፈሩ በኋላ ከአንድ የመገበያያ ስፍራ ውጪ የተሰባሰቡ ሰዎች እንዲመርጡ አደረጉ። በጀርመኖች ዘንድ የተለመደው ስም፣ ፍሪትዝ ተመረጠ። መጠጡም ላይ ቢሆን ጣዕሙ ከኮካ ኮላ ወይንም ከፔፕሲ እንዲለይ ፈልገዋል። ስለዚህ አነስተኛ የስኳር መጠን እንዲሁም የሎሚ ጭማቂ ጨምረውበታል። በተጨማሪ ደግሞ ከሌሎቹ ላቅ ያለ ካፌይን መጠቀማቸውን ማይክሮ ይናገራል። "የኛን ኮላ ስትጠጡ በጣም ጣፋጭ አይደለም ነገር ግን ጠንከር ያለ ካፌይን አለው" የሚለው ማይክሮ፣ ስለዚህ ገበያውን ከሚመሩት ለስላሳ መጠጦች በበለጠ ሁኔታ በሶስት እጥፍ ካፌይን መጨመራቸውን ገልጿል። ማይክሮ መጀመሪያ አካባቢ የእነርሱን ምርት ተቀብሎ ለማከፋፈልም ሆነ ለመሸጥ ፍላጎት የነበረው ድርጅት አለመግኘታቸውን ያስታውሳል። " በርካታ ሰዎች ከለመዱት ኮላ ይልቅ የኛን ለመጠጣትም ሆነ ለመመኮር አይፈልጉም ነበር።" የመጠጥ ቤት ባለቤቶችንና ኃላፊዎችን ለማሳመን፣ አልሸጥ ያላቸውን መጠጥ ለመመለስ እና የከፈሉትን ዋጋ ለመመለስ ቃል በመግባት ማከፋፈል ጀመሩ። እነ ማይክሮ ቀን ተሌት ደክመው መስራታቸው ፍሬ አፈራ እና መጠጣቸው ተወደደ። ወጣቶቹ ማይክሮና ሎሬንዝ ይዘ ውየመጡትን የለስላሳ መጠጥ ያስተዋሉ ደንበኞች "እስቲ እንሞክረው" በማለት እድል ሰጥዋቸው። ማይክሮና ሎሬንዝ የራሳቸውን ቢሮ ለመክፈትም ሆነ የመጀመሪያውን ሰራተኛ ለመቅጠር ሶስት ዓመት ፈጅቶባቸዋል። እስከዚያ ድረስ ቢሮ እንኳ አልነበራቸውም። ነገር ግን ምርታቸው ተጠቃሚዎቹ እየወደዱት በመጡ ቁጥር ዝናው እየናኘ መጣ። መደበኛ ማስታወቂያ ከማስነገር ይልቅ ዝናውን ተጠቃሚዎች እየተቀባበሉት፣ የሰሙት ላልሰሙት እያዳረሱ ሄዱ። ዛሬ ለስላሳ መጠጣቸው በመላው አውሮጳ መጠጥ ቤቶችና ሱቆች ውስጥ ይሸጣል። ከጀርመን በኋላ ዋነኛ ገበያቸው ኔዘርላንድስ፣ ፖላንድ፣ ቤልጂየም እና ኦስትሪያ ነው። በአሁን ሰዓት ፍሪትዝ ኮላ በአምስት ፋብሪካዎች ውስጥ እየታሸገ የሚከፋፈል ሲሆን ከስኳር ነፃ፣ በተለያየ የፍራፍሬ ጣዕም ማምረት ጀምሯል። ምንም እንኳ ድርጅቱ የገቢና ወጪውን አስልቶ ይፋ ባያደርግም ፎርብስ ግን በ2018፣ በ2015 የድርጅቱ ሽያጭ 7.4 ሚሊዮን ዩሮ እንደነበር ገልጿል። ከ2016 ጀምሮ ማይክሮ ሃምቡርገግ የሚገኘውን ንግዱን እየመራ የሚገኝ ሲሆን፣ ሎሬንዝ ግን በዚያ ዓመት ከጓደኛው ጋር በመለያየት ሌላ ስራ ላይ ለመሰማራት ወስኗል። ማይክሮ በአሁኑ ሰዓት የድርጅቱን ሁለት ሶስተኛ በባለቤትነት ሲይዝ ሌሎች ባለሃብቶች ደግሞ አንድ ሶስተኛ ድርሻውን ይዘዋል። ከ17 ዓመት በፊት ማንም አላመነንም ነበር የሚለው ማይክሮ፣ 'በዓለም ላይ ትልቅ ከሆኑ ድርጅቶች ጋር ለመፎካከር የምትፈልጉት ምንኛ ጅል ብትሆኑ ነው' መባላቸውን ያስታውሳል። ነገር ግን ለሁለቱ ጓደኛሞች ይህ የፈጠራ ሃሳብ ደስታን የሚፈጥር እና የበለጠ ታግለው ማሸነፍ የሚፈልጉት ተግዳሮት ሆኖ ነበር የተሰማቸው። "ዛሬ 280 ሰዎች ቀጥሬ አሰራለሁ። በኩባንያ ውስጥ በቂ የሆነ ውጣ ውረድ አለኝ፤ ስለዚህ ሌላ ነገር መስራት አልፈልግም። የምሰራውን እወደዋለሁ" ይላል። |
news-54019065 | https://www.bbc.com/amharic/news-54019065 | ትግራይ ፡ ምርጫውን ለማስቆም የሚተላለፍ ውሳኔ የጦርነት አዋጅ ነው፡ የትግራይ ክልል | በትግራይ ክልል ሊካሄድ የታሰበውን ምርጫ ለማስቆም በፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚተላለፍ ማንኛውም ውሳኔ እንደ ጦርነት አዋጅ እንደሚቆጥረው የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ። | መግለጫው የወጣው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከቀናት በፊት ነገ ቅዳሜ የሚካሄድ አስቸኳይ ስብሰባን መጥራቱን አስመለክቶ ነው። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለአባላቱ ባስተላለፈው ጥሪ ላይ 5ኛ የፓርላማ ዘመን 5ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ አስቻኳይ ስብሰባ ነሐሴ 30/2ዐ12 ዓ.ም እንደሚካሄድ ከማሳወቅ ውጪ በምን አጀንዳ ላይ ውይይት እንደሚካሄድ የገለጸው ነገር ባይኖርም፤ የትግራይ ክልል ሥራ አስፈጻሚ በክልሉ በሚካሄድ ምርጫ ላይ የሚሰጥን ውሳኔ እንደማይቀበለው ከወዲሁ አሳውቋል። የክልሉ ሥራ አስፈጻሚ መግለጫ የፌደሬሽን ምክር ቤት የጠራውን አስቸኳይ ስብሰባ "ያልተለመደና አጀንዳው የማይታወቅ" ሲል ቢጠቅሰውም በትግራይ የሚካሄደው ምርጫን የሚመለከቱ ውሳኔዎች ሊተላለፉ እንደሚችሉ ባስቀመጣቸው ሃሳቦች አመልክቷል። የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት በ27/12/2012 ዓ.ም ለፌዴሬሽን ምክር ቤቱ በጻፈው ደብዳቤ ምክር ቤቱ አስቸኳይ ጉባዔ ለማካሄድ በሚያስብበት ወቅት አጀንዳውን ለአባላቱ መግለጽ እንደሚጠበቅበት አስረድቶ፣ በተደጋጋሚ ስለአጀንዳው መጠየቁን ገልጿል። ሆኖም ግን አጀንዳውን ሳያውቁ እንዲሳተፉ መጋበዛቸውን በመጥቀስ አስቀድሞ አጀንዳው የማይገለፅላቸው ከሆነ " ለመሳተፍ እንደማይችሉ" አስፍሯል። የሥራ አስፈጻሚው መግለጫ እንዳለው "ምርጫውን ለማስቆም ወይም ለማደናቀፍ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚወስደው ማናቸውም ውሳኔ እንደጦርነት አዋጅ ይቆጠራል" ከማለቱ በተጨማሪ "በዚህ ምክንያት ለሚፈጠር ችግር ተጠያቂው የፌዴሬሽን ምክር ቤትና ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሆናቸው ሊታወቅ ይገባል" ሲል ብሏል። በዚህም ምርጫውን ለማስቆም የሚተላለፍ ውሳኔ ተቀባይነት እንደሌለው በመግለጽ "ሕዝቡ በምርጫ የሚያስተዳድረውን አካል እንዲመርጥ ሊበረታታ የገባዋል እንጂ ይህን ሂደት ለማስቆም የሚደረግ ጥረት ፀረ ዲሞክራሲያዊ" መሆኑን አመልክቷል። መግለጫው በትግራይ ክልል ስድስተኛው ዙር ምርጫ ጊዜውን ጠብቆ እንዲካሄድ ከወራት በፊት ውሳኔ መተላለፉን አስታውሶ፤ ይህንንም ለማሳካት በክልሉ ያሉት የሚመለከታቸው አካላት የሚጠበቅባቸውን እያከናወኑ በመሆናቸው ክልሉ በምርጫው "ሕግና ሥርዓትን ተከትሎ በሕዝብ ውሳኔ መሰረት ቀጣዩ የክልሉ መንግሥት የሚቋቋም ይሆናል" ብሏል። ቀደም ሲል የትግራይ ክልል ከሌሎቹ የአገሪቱ ክልሎች በተለየ ምርጫውን በተናጠል ለመካሄድ መወሰኑን ተከትሎ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ይህ ውሳኔ ሕገወጥ መሆኑን በመግለጽ ክልሉ ምርጫ ለማካሄድ ከሚያደረገው እንቅስቃሴ እንደቆጠብ አሳስቦ ነበር። ክልሉም ይህንን በመቃወም ምላሽ ሰጥቶ ምርጫውን በማካሄድ ገፍቶ ለምርጫው ከአንድ ሳምንት ያነሰ ጊዜ ቀርቷል። ሐሙስ ምሽት የወጣው መግለጫ ሕዝቡን በማሳተፍ ለሁሉም ግልጽ በሆነ ሁኔታ ምርጫውን ለማካሄድ ወደ ፍጻሜው መደረሱን ጠቅሶ በዚህ ጊዜ የሚደረግ ማንኛውንም ጣልቃ ገብነት "በአገሪቱ ህልውና ላይ አደጋን የሚጥል መሆኑ ሊታወቅ ይገባል" ሲል አስጠንቅቋል። በዚህም መሰረት ምርጫው በአገሪቱና በክልሉ ሕግ መሰረት የሚካሄድ በመሆኑ በማንኛውም ጣልቃ ገብነትና ጫና ሂደቱ እንደማይቆም አመልክቶ "ሕዝቡም ይህንን ለመመከት እንዲዘጋጅ" ጥሪ ከማቅረቡ በተጨማሪ የአገሪቱ "ብሔር ብሔረሰቦችና ፌደራሊስት ኃይሎች" ከጎኑ እንዲቆሙ ጠይቋል። በመላው አገሪቱ በነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ ሊካሄድ ታቅዶ የበረው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ በሕዝብ ተወካዮች እና በፌዴሬሽን ምክር ቤት ቢወሰንም የትግራይ ክልል ምርጫውን በተናጠል ለማካሄድ ወስኖ ጳጉሜ 04/2012 ዓ.ም ለማካሄድ ተዘጋጅቷል። ይህንን በተመለከተም የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሐምሌ ወር መጨረሻ ላይ የትግራይ ክልል መንግሥት ምርጫ ለማካሄድ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ እንዲያቆም የሚያሳስብ ደብዳቤ ለክልሉ መጻፉ ይታወሳል። ምክር ቤቱ በዚህ ደብዳቤው ላይ እንዳመለከተው የትግራይ ክልል የተሰጠውን ማሳሰቢያ ሳይቀበል ቀርቶ "ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ በሚጥል" ድርጊቱ የሚገፋ ከሆነ፤ የፌዴሬሽን ምክር ቤት "በሕገ መንግሥቱና በሌሎች ሕጎች የተሰጠውን ስልጣን ለመተግበር እንደሚገደድ" አስጠንቅቆ ነበር። ለዚህም የትግራይ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ በሰጡት ምላሽ የደረሳቸው ማስጠንቀቂያ ሕገ መንግሥታዊ መሰረት የሌለው መሆኑን በመግለጽ "የሕገ መንግሥት መርሆዎችን የሚጥስ፣ የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን ሉአላዊ የስልጣን ባለቤትነትን የሚጻረር" በመሆኑ የትግራይ ክልል መንግሥትና ሕዝብ እንደሚቃወሙት ገልፀው እንደማይቀበሉት አሳውቀዋል። በክልሉ የታቀደው ምርጫ ሊካሄድ ቀናት የቀሩት ሲሆን አጀንዳው ምን እንደሆነ እስካሁን ያልታወቀ አስቸኳይ ስብሰባ የፌዴሬሽን ምክርቤት ለማካሄድ ጥሪ ማቅረቡን ተከትሎ ነው የትግራይ ክልል ይህንን መግለጫ ያወጣው። |
news-53957592 | https://www.bbc.com/amharic/news-53957592 | ኮቪድ -19፡ ልጆች ኮሮናቫይረስን ያስተላልፋሉ? | ደቡብ ኮርያ የተሠራ ጥናት እንደሚያሳየው፤ ልጆች ኮሮናቫይረስን አፍንጫቸው ላይ ይዘው እስከ ሦስት ሳምንታት መቆየት ይችላሉ። | ከዚህ ቀደም የተሠሩ ጥናቶች፤ በርካታ ልጆች መጠነኛ የበሽታውን ምልክት እንደሚያሳዩ ወይም እስከነጭራሹ ምልክት እንደማይታይባቸው ይጠቁማሉ። እነዚህ ግኝቶች ልጆች ምን ያህል በሽታውን ያሰራጫሉ? ለሚለውና እስካሁን ግልጽ ምላሽ ላልተገኘለት ጉዳይ ፍንጭ ይሰጣሉ። ለወራት እንቅስቃሴ አቁመው በነበሩ አገሮች ትምህርት ቤቶች እየተከፈቱ ነው። አካላዊ ርቀትና ንጽህናን መጠበቅ መዘንጋት እንደሌለበትም ተመራማሪዎች ይናገራሉ። ኮቪድ-19 እና ልጆችን በተመለከተ ሦስት ዋና ጥያቄዎች እንዳሉ የሚናገሩት የሮያል ኮሌጅ ፕሮፌሰር ራሰል ቪነር ናቸው። የሚከተሉት ጥያቄዎቻቸው ናቸው፦ ልጆች በቫይረሱ እንደሚያዙ በጥናቱ ተረጋግጧል። ፕ/ር ራሰል እንደሚሉት፤ ከፀረ እንግዳ አካላት (አንቲቦዲ) ምርመራ በተገኘ መረጃ መሠረት በተለይም ከ12 ዓመት በታች ያሉ ልጆች ከአዋቂዎች ባነሰ ለቫይረሱ ይጋለጣሉ። • የ2013 የትምህርት ዘመንን ለማስጀመር ምን እየተሰራ ነው? • ኮሮናቫይረስ በማገርሸቱ ደቡብ ኮሪያ ትምህርት ቤቶች ተመልሰው እንዲዘጉ አዘዘች ልጆች በቫይረሱ ከተያዙ የአዋቂዎች ያህል እንደማይታመሙም ሳይንቲስቶች እርግጠኛ ናቸው። እንዲያውም በርካታ ልጆች የበሽታውን ምልክት አያሳዩም። እምብዛም መልስ ያልተገኘለት ጥያቄ ልጆች በሽታውን ወደ ሌላ ሰው ያስተላልፋሉ የሚለው ነው። የደቡብ ኮርያው ጥናትም እዚህ ላይ ያተኮረ ነው። የደቡብ ኮርያው ጥናት ምን ይላል? ጥናቱ የተሠራው 91 ልጆች ላይ ነው። መጠነኛ ወይም ምንም ምልክት የማያሳዩ ልጆች እስከ ሦስት ሳምንት ድረስ ቫይረሱ እንደሚቆይ ከናሙና መረዳት ተችሏል። አፍንጫቸው ላይ የቫይረሱ ምልክት መገኘቱ፤ ልጆች በሽታውን ወደ ሌላ ሰው ማስተላልፍ እንደሚችሉ እንደሚጠቁም የጥናቱ ጸሐፊዎች አስረድተዋል። ደቡብ ኮርያ በምታካሂደው ምርመራና በሽታው ካለባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች በምትለይበት ሂደት አማካይነት፤ የበሽታውን ምልክት የማያሳዩ ሰዎች ሳይቀሩ ይገኛሉ። ህሙማን ከተለዩ በኋላ ከቫይረሱ ነፃ እስኪሆኑ በተደጋጋሚ ተመርምረዋል። ጥናቱ ልጆች ቫይረሱን እንደሚሸከሙ፣ ወደ ሌሎች ሰዎች ሊያስተላልፉ እንደሚችሉም ጠቁሟል። ሆኖም ግን ለሁሉም ጥያቄዎች መልስ አልሰጠም። ልጆች አፍንጫ ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል ማለት የአዋቂዎች ያህል ቫይረሱን ያስተላልፋሉ ማለት አይደለም። በሕፃናት ሕክምና ክፍል የሚሠሩት ዶ/ር ሮበርታ ዲባሲ ልጆች ቫይረሱን ሊያስተላልፉ አይችሉም ማለት እንደማይቻል ያስረዳሉ። የቫይረሱ ዘረ መል ከመተንፈሻ አካላት በሚወሰድ ናሙና ላይ መገኘቱ በሽታውን ከማስተላለፍ ጋር የግድ እንደማይተሳሰር የሚናገሩት ደግሞ የሊቨርፑል ዩኒቨርስቲ ፕ/ር ካሉም ሰምፕል ናቸው። የጥናቱ ድምዳሜ ምንድን ነው? ልጆችም ይሁን አዋቂዎች መጠነኛ ወይም ምንም አይነት ምልክት ካላሳዩ በሽታውን የማስተላለፍ እድላቸው አናሳ መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ። የማያስሉ ወይም የማያስነጥሱ ሰዎች ቫይረሱን ወደ አየር እምብዛም አይለቁም። ሆኖም ግን ምልክት የማያሳዩ ሰዎች በሽታውን አያሰራጩም ማለት አይደለም። ዶክተሩ እንደሚሉት፤ አብዛኞቹ ልጆች በተወሰነ ደረጃ ወይም ሊታይ በማይችል ሁኔታ ነው በቫይረሱ ሊያዙ የሚችሉት። በማኅበረሰቡ ውስጥ ቫይረሱን ሊያሰራጩ ግን ይችላሉ። |
44206716 | https://www.bbc.com/amharic/44206716 | በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እስረኞች አሁንም በሳዑዲ እስር ቤት ይገኛሉ | ስሜ አይጠቀስ ብሎ አስተያየቱን ለቢቢሲ የሰጠው ግለሰብ ከሁለት አመት በፊት ከየመን ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሲሄድ ነበር ለእስር የተዳረገው። በሳዑዲ ጅዳ ጂዛኔ እስር ቤት ከሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን እስረኞች አንዱ ነው። | ባለፈው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ በሳዑዲ ያሉ እስረኞችን ለማስፈታት የመደራደራቸው ዜና ተስፋ ሰጥቶታል። "ዜናው እውን ከሆነ በህይወቴ አዲስ ምዕራፍ ይከፈታል" ብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው ሳምንት አርብ ከሳዑዲው አልጋ ወራሽ ልዑል መሀመድ ቢን ሳልማን ጋር በኢትዮጵያና ሳዑዲ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙርያ መክረዋል። ከተወያዩባቸው ጉዳዮች መሀከልም ኢትዮጵያውያን እስረኞችን ማስፈታት ይገኝበታል። በመሪዎቹ ስምምነት መሰረት በመቶዎች የሚቆጠሩ እስረኞች ተለቀው ወደ ኢትዮጵያ እየተመለሱ ነው። አስተያየቱን ለቢቢሲ የሰጠው እስረኛ አብረውት እስር ላይ ያሉትን ሰዎች ቁጥር በትክክል ባያውቅም "በግምት ወደ 5,000 የሚሆኑ እስረኞች አሉ" ብሏል። በእስር ቤቱ ተንቀሳቃሽ ስልክ መጠቀም ስለሚቻል እስረኛውን ያነጋገርነው ወደተንቀሳቃሽ ስልኩ ደውለን ነበር። "እስከ አሁን ምንም አልተፈረደብኝም" ቢልም እስር ላይ ይገኛል። ኢትዮጵያውያኑ ከሶስት አመት በላይ መታሰራቸውን ገልጿል። "ከሁለትና ከሶስት ከአመት በላይ የቆዩ ሰዎች አሉ። ሁኔታው በጣም አስጊና አስፈሪ ነው" ብሏል። አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ወደ ሳዑዲ ያቀኑት የተሻለ ህይወትን በመሻት እንደሆነ ይናገራል። "እዚህ የመጣነው ለእንጀራ ጉዳይ ነው። ለእንጀራ ስንል ተሸውደን እዚህ ገብተናል።" ሲል ያለበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ገልጿል። "አንድ ሰው ወንጀል ፈጽሞ ሲታሰር መማር ነው ያለበት እኛ ግን እየተማርን ሳይሆን እየተሰቃየን ነው። መፍትሔ ያስፈልገናል። መፍትሔውንም በደስታ እንቀበላለን" ሲልም ተስፋውን ለቢቢሲ አካፍሏል። በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንጽላ ጽህፈት ቤት አምባሳደር አቶ ውብሸት ደምሴ በሳዑዲ እስር ቤቶች ከፍተኛ ፍርደኞች የሆኑ ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙ ተናግረዋል። በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አሚን አብዱል ቀድር እንደሚናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ከሳዑዲ አረቢያ መንግስት ጋር ባደረጉት ስምምነት በመቶዎች የሚቆጠሩ እስረኞች ከእስር ተለቀው ወደ ቀያቸው እየተመለሱ ይገኛሉ። የተቀሩትም የሚመለሱበትን ሁኔታ እየተመቻቸ እንደሆነ ገልፀዋል። ሁለቱ መሪዎች የደረሱበት መግባባት እስረኞቹ እንዲፈቱ ምክንያት ሆኗል ብለዋል። እስካሁን በሁለት ዙር እስረኞች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ መደረጉን ይናገራሉ። የሁለቱ የአገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እየተሸጋገረ እንደሆነ የተናገሩት አምባሳደሩ የተጀመረው እስረኞችን የማስፈታት ስራ ጊዜና ትዕግስትን የሚጠይቅ እንደሆነ አስረድተዋል። ያነጋገርናቸው በሳዑዲ ጅዛን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እስረኞች "ሳዑዲ የሚገኘው የኢትዯጵያ ኤምባሲን እርዳታ ፈልገን በተደጋጋሚ ብንደውልም ምላሽ ተሰጥቶን አያውቅም። አገር እንደሌለን ነው የሚሰማን" ይላሉ። አምባሳደሩ በበኩላቸው "በሳዑዲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ በህግ ጥላ ስር ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን እስረኞችን ክትትል ያደርጋል" ብለዋል። አምባሳደሩ እንደሚሉት እስረኞቹ የሳዑዲን ህግ ተላልፈው ቢገኙም ምህረት እንዲደረግላቸው በአገር ደረጃ ጥረት እየተደረገ ይገኛል። "ተገቢውን ምላሽ እየሰጠናቸው ነው። አገራቸው ለዜጎቿ ያላትን ተቆርቋሪነት አሳይተናል" ብለዋል። እስረኞቹ በፍርድ ቤት ውሳኔ የተሰጣቸው በመሆናቸው ለማስፈታት መንግስት በጀመረው ሁኔታ በትዕግስት እንደሚቀጥል ተናግረዋል። "የአገሪቱን ህግና ስርዓት በመረዳትና የፍርድ ሂደቶችን በማጣራት በብርቱ ጥንቃቄ መስራትም ያስፈልጋል" ሲሉም አክለዋል። በተለይም ወደ ሳዑዲ የሚሄዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር መጨመሩ አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል። አምባሳደሩ እስረኞችን ከማስፈታት ባሻገር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን እየሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ሼክ ሁሴን አሊ አላሙድን ከእስር የማስፈታት ጉዳይም ተነስቶ ነበር። "በመግባባት ላይ የተመሰረተ ቢሆንም የአገሪቱን ህግና ስርዓት በጠበቀ መልኩ ከሳዑዲ አልጋ ወራሽ ልዑል መሃመድ ኢን ሰልማን ጋር ተወያይተውበታል። ጉዳዩም በቀጣይ እንደሚታይ በሳዑዲ በኩል ማረጋገጫ አግኝተናል" ብለዋል። |
news-56036908 | https://www.bbc.com/amharic/news-56036908 | ምርጫ 2013 ፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አባላት ሚና ምንድነው? | ሳምንታት የቀሩትን 6ኛውን የኢትዮጵያ አገራዊ ምርጫ ለማስፈጸም አምስቱ የምርጫ ቦርድ አባላት ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። | ብርቱካን ሚደቅሳ (ወ/ሪ)፣ አበራ ደገፉ (ዶ/ር)፣ ብዙወርቅ ከተተ (ወ/ት) ፣ አቶ ውብሽት አየለ ቦርዱ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑትን ብርቱካን ሚደቅሳ (ወ/ሪት)ን ጨምሮ አምስት አባላት አሉት። አቶ ውብሽት አየለ፣ ብዙወርቅ ከተተ (ወ/ሪት)፣ አበራ ደገፉ (ዶ/ር) እና ፍቅሬ ገ/ሕይወት የምርጫ ቦርድ አባላት በመሆን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሾማቸው ይታወሳል። የቦርዱ አባላት ሚናቸው ምንድነው? አምስት አባላት ያለው የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ምርጫ እና ሕዝበ ውሳኔን በተመለከተ ከፍተኛውን የመወሰን ኃላፊነት የያዘ አካል ነው። በዚህም ቁልፍ ውሳኔን የማሳለፍ ስልጣን አለው። በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ 1133/2011 መሠረት ቦርዱ በሕገ መንግሥቱ እና በምርጫ ሕግ መሠረት የሚካሄድን ማንኛውንም ምርጫ እና ሕዝበ ውሳኔ በገለልተኝነት ያስፈጽማል። የምርጫ ቦርድ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት ደግሞ በምርጫ ሂደት የምርጫ ውጤትን የሚያዛንፍ የሕግ ጥሰት ተከስቷል ብለው ሲያምኑ ውጤቱን መሰረዝና ድጋሚ ምርጫ እንዲካሄድ የመወሰን ስልጣን አላቸው። የሥራ አመራር ቦርዱ የምርጫ ቦርድ የመጨረሻው ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አካል ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን የምርጫ ውጤቶች ይፋ ከመደረጋቸው በፊት የምርጫ ውጤቶችን ያጸድቃል። የምርጫ ሕጎችን ማስፈጸም፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን መቆጣጠር፣ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ድጎማ ማከፋፈል፣ ለምርጫ ታዛቢዎች ፈቃድ መስጠት እና መቆጣጠር፣ የምርጫ ቁሳቁሶችን ማሰናዳት እንዲሁም በጀት አዘጋጅቶ ሥራ ላይ ማዋል የሚሉት ከቦርዱ ስልጣን እና ተግባር መካከል ተጠቃሽ ናቸው። የቦርዱ አባላት እንዴት ይመረጣሉ? የቦርድ አባላት የሚመረጡት ዝርዝር ሥነ-ሥርዓቶችን ተከትሎ ነው። በቅድሚያ ጠቅላይ ሚንስትሩ እጩ የቦርድ አባላትን የሚመለምል ኮሚቴ ያቋቁሟሉ። የዚህ ኮሚቴ አባላት ደግሞ ከተለያዩ የሕብረተሰቡ ክፍል የሚወጣጡ እና ገለልተኛ የሆኑ ግለሰቦችን ያቀፈ መሆን ይኖርበታል። ከሐይማኖት ተቋማት፣ ከሳይንስ አካዳሚ፣ ከሠራተኞች ኮንፌዴሬሽን፣ ከንግድና ማኅበራት፣ ከሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እንዲሁም ከሲቪል ማኅበራት እና ከአገር ሽማግሌዎች የሚመረጡ ሰዎች የኮሚቴው አባላት ይሆናሉ። ከዚያም ይህ ኮሚቴ የምርጫ ቦርድ አባል ሊሆኑ የሚችሉ እጩዎችን ጥቆማ ከሕዝብ፣ ከፖለቲካ ድርጅቶች እና ከሲቪል ማኅበራት ይቀበላል። ኮሚቴው ከተጠቆሙት ሰዎች ውስጥ የቦርድ አባላት ሊሆኑ የሚችሉ እጩዎችን በመለየትና ፍቃደኝነታቸውን በማረጋገጥ የእጩዎቹን ዝርዝር ለሕዝብ ይፋ በማድረግ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ያቀርባል። ጠቅላይ ሚንስትሩም የእጩዎቹ ስም ዝርዝር ከኮሚቴው ከደረሰባቸው በኋላ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር በቀረቡት እጩዎች ላይ ምክክር ያደርጋሉ። ከምክክሩ በኋላ ጠቅላይ ሚንስትሩ እጩዎቹን ለሹመት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀርባሉ። ምክር ቤቱም የቀረቡት እጩዎችን በአብላጫ ድምጽ ሲያጸድቅ እጩዎቹ የቦርዱ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት ሆነው ይሾማሉ። ብርቱካን ሚደቅሳ- የቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ (ወ/ት) የቦርዱ ሰብሳቢ ናቸው። ከሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በሕዝብ አስተዳደር ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ያገኙት ብርቱካን ሚደቅሳ፤ ቀደም ሲል የፌዴራል ፍርድ ቤት ዳኛ ሆነው አገልግለዋል። ብርቱካን ወደ ስደት ከመሄዳቸው በፊት በተቃዋሚ ፓርቲ በአመራር ቦታ በፖለቲካው ውስጥ ይንቀሳቃሱ እንደነበረ ይታወሳል። ብዙ የተባለለትን የ1997 ዓ.ም ምርጫን ተከትሎም ከተነሳው ውዝግብ ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ ለእስር የተዳረጉ ሲሆን የዕድሜ ልክ እስራትም ተፈርዶባቸው ነበር። ከእስር ከወጡ በኋላ ወደ አሜሪካ ተጉዘው ጥናቶችን አድርገዋል። ከሰባት ዓመታት ስደት በኋላም በ2011 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን እንዲመሩ ተሹመዋል። በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን በሊቀ መንበርነት እየመሩ ይገኛሉ። አቶ ውብሸት አየለ - የቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ምሩቅ ናቸው። በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በዳኝነት አገልግለዋል። ከዳኝነት ሥራቸው ለቀው የራሳቸውን ቢሮ በመክፈት የሕግ አማካሪ እና ጠበቃ ሆነው ሠርተዋል። አቶ ውብሸት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን በማማከር፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ውይይት በማስተባበር እንዲሁም በሌሎች የቦርዱ እንቅስቃሴዎች ላይ በሙያቸው ተሳትፎ ሲያደርጉ መቆየታቸው ተጠቅሷል። አቶ ውብሸት በሲቪክ ማኅበራት እና ማኅበረሰባዊ እንቅስቃሴዎች ከፍተኛ ተሳትፎ እንደሚያደርጉ ተጠቁሟል። አበራ ደገፋ (ዶ/ር) - የቦርድ አባል አበራ ደገፋ (ዶ/ር ) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ተባባሪ ፕሮፌሰር ናቸው። የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በሶሻል ወርክ እና ሶሻል ዴቨሎፕመንት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አግኝተዋል። በተጨማሪም፣ በኔዘርላንድስ ከሚገኘው ኢንስቲትዩት ፎር ሶሻል ስተዲስ፣ በዓለም አቀፍ ሕግ እና ልማት የድኅረ ምረቃ ዲፕሎማ አላቸው። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመደበኛው የመምህርነት ሥራቸው ባሻገር በልዩ ልዩ ከፍተኛ ኃላፊነቶች በሙያቸው እንዳገለገሉ የሚነገርላቸው አበራ (ዶ/ር)፤ በዘመን ባንክ፣ በፍትሕ ሚኒስቴር የጠበቆች አስተዳደር ጉባኤ እና በኦሮሚያ የሕግ ጆርናል የቦርድ አባል በመሆን መስራታቸው ይጠቀሳል። የምርጫ ቦርድ አባል ሆነው ከመሾማቸው በፊት በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሕግ እና የፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባኤ እንዲሁም የአስተዳደር ወሰንና ማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባል ሆነዋል። ብዙወርቅ ከተተ (ወ/ሪት) - የቦርድ አባል ብዙርቅ ከተተ(ወ/ሪት) የከፍተኛ ትምህርታቸውን ከኩባ ሐቫና ዩኒቨርሲቲ የውጪ ቋንቋዎች ትምህርት ክፍል በሥነ ቋንቋ የሁለተኛ ደረጃ ዲግሪ አግኝተዋል። ብዙወርቅ (ወ/ሪት) በልዩ ልዩ ተቋማት አገልግለዋል። ከእነርሱም መካከል የቀድሞው የአደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን፣ አክሽን ኤይድ ኢንተርናሽናል ይገኙበታል። በግጭት አፈታት እና መከላከል ላይ በሚሠራው የጀርመን አማካሪ ድርጅት ውስጥም፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፕሮጄክት አስተባባሪ ሆነው ሠርተዋል። ብዙወርቅ (ወ/ሪት) በመልካም አስተዳደር፣ በአቅም ግንባታ እና ሲቪክ ተሳትፎን በማበረታታት ላይ የሚሠራ፤ 'ዜጋ ለዕድገት' የተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት መሥራች እና የቦርድ ሊቀ መንበር ሆነው አገልግለዋል። አቶ ፍቅሬ ገ/ሕይወት አቶ ፍቅሬ ገ/ሕይወት ከቦርድ አባልነታቸው በገዛ ፍቃዳቸው የለቀቁትን ጌታሁን ካሳ (ዶ/ር) በመተካት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተጓደለ የአንድ የምርጫ ቦርድ አባል ቦታ ጥቅምት ወር ላይ አቶ ፍቅሬ ገ/ሕይወትን ሹሟል። አዲሱ የምርጫ ቦርድ አባል አቶ ፍቅሬ /ሕይወት በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በመምህርነት ያገለገሉ መሆኑን ተገልጿል። |
45675457 | https://www.bbc.com/amharic/45675457 | ኢትዮጵያ 8.5 በመቶ ዕድገት ታሥመዘግባለች፡ አይ.ኤም.ኤፍ. | ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ.ኤም.ኤፍ.) ከፍተኛ ኃላፊዎች ለሁለት ሳምንታት ያክል የቆየ ጉብኝት በኢትዮጵያ አድርገው ተመልሰዋል። | በጉብኝታቸው መጨረሻ ላይም ኢትዮጵያ ከ2018/19 ባለው የፈረንጆቹ ዓመት የ8.5 በመቶ እድገት እንደምታስመዘግብ ትንበያቸውን አስቀምጠዋል። ድርጅቱ ትንበያውን ለማስቀመጥ ከተመለከታቸው መስፈርቶች መካከል የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አስተዳደር በቅርቡ ተግባራዊ እንዲደረግ ያዘዘው በመንግሥት ስር የነበሩ ተቋማትን ለግል ባለሃብቶች በሽያጭ መልክ ማዘጋጀት አንዱ ነው። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዶክተር ሰኢድ ኑሩ የኢኮኖሚው እድገት ተስፋ ያለው ሆኖ መቀመጡ የውጭና የአገር ውስጥ ባለሃብቶችን ለመሳብ አስተዋፅኦ ያደርጋል ይላሉ። «ፖለቲካው ከተረጋጋ እና ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት አመቺ ነች ተብሎ ተስፋ ከተደረገ እንደባለፉት ዓመታት ከ10 በላይ ባይሆንም 8.5 በመቶ ማደግ ይቻላል ብለው ያሰቡ ይመስለኛል» ሲሉ መላ ምታቸውን ያስቀምጣሉ። • በሰኔው የቦምብ ጥቃት የተጠረጠሩ አምስት ግለሰቦች ላይ ክስ መሰረተ • የካማሼ ዞን አመራሮች በታጣቂዎች ተገደሉ • የኢንዱስትሪ ፓርኮች ፈተና እና ተስፋ ዶ/ር ሰዒድ ድርጅቱ እያንዳንዱን ዘርፍ በዝርዝር አስቀምጦ ትንታኔ ስላልሰጠ አስተያየት ለመስጠትም ከባድ ነው በማለት፤ «ባሉት ነባራዊ መረጃዎች ላይ ተመሥርተው ባለሙያዎቹ የራሳቸውን ትንበያ ይሰጣሉ፤ መረጃውንም ከመንግሥት ይጋራሉ ብዬ አስባለሁ» ይላሉ። እንደ ዶ/ር ሰዒድ ሁሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሃብት ምሁር የሆኑት ተባባሪ ፕሮፌሰር ተኬ ዓለሙ «ዋናው ነገር ሰላም ነው» ብለዋል። «አይ.ኤም.ኤፍን የመሳሰሉ ድርጅቶቹ ተዓማኒነታቸው አያጠራጥርም፤ ከባዱ ነገር ተፈፃሚነቱ ላይ ነው እንጅ» ይላሉ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተኬ። ተባባሪ ፕሮፌሰር ተኬ «እነ አሜሪካ ቢሆኑ ይህ ትልቅ አሃዝ ነው፤ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሃገራት ግን 8.5 በመቶ ዕድገት ትልቅ የሚባል አይደለም» ይላሉ። «ይህ እንዳይሆን ሊያግደው የሚችለው ዋነኛው ነገር አለመረጋጋት ነው እንጅ 8.5 በመቶ እድገት በዓመት ያን ያህል ትልቅ ቁጥር ሆኖ ላይሳካ ይችላሉ የሚል ጥርጣሬ ውስጥ የሚከት አይደለም» ይላሉ። • የሰሞኑ የአዲስ አበባ እስርና ሕጋዊ ጥያቄዎች • የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕጩ ወሲባዊ ጥቃት አላደረስኩም አሉ • የመጀመሪያዎቹ የዓለማችን የሂሳብ ሊቆች ነገሮችን እንዴት ይቆጥሩ ነበር ? በመንግሥት ስር የነበሩ ተቋማትን ወደ ግል ባለሃብቶች የማዘዋወሩ ጉዳይ አጨቃጫቂነቱ የቀጠለ ይመስላል። «የመንግሥት ንበረቶች ገና ወደግል ባለሃብቶች ተሸጋግረው ምጣኔ ሃብቱ ላይ የሚኖራቸው አስተዋጽኦና እውነተኛው ውጤት እስኪታይ ድረስ ከሁለት ዓመት በላይ ሊፈጅ ይችላል» የዶ/ር ሰዒድ ሃሳብ ነው። የመንግስት ድርጀቶቹ ገና ወደ ግሉ ዘርፍ ዞረው የረጅም ጊዜ ውጤቱ እስኪታይ ድረስና ውሳኔው ትክክለኛና ውጤታማ ይሆናል አይሆንም የሚለውን ለመወሰን ጊዜው ገና ነው። እንደውም ዋናው ጥያቄ መሆን ያለበት ድርጅቶቹ ከዚህ በኋላ ተጨማሪ እሴት ይዘው ይመጣሉ ወይ? ሌላውን የኢኮኖሚ ዘርፍ ማቀላጠፍ የሚችል ብቃት ይኖራቸዋል ወይ? መሆን አለበት ሲሉ ሃሳባቸውን ያጠናክራሉ። ኢትዮጵያ ከተለያዩ አለማቀፍ የገንዘብ አበዳሪ ድርጅቶችና ሃገራት ብዙ እዳ መሸከሟና የጀመረቻቸው ትላልቅ ፕሮጀክቶች በታሰበላቸው ጊዜ መጠናቀቅ አለመቻላቸው እየታየ ሃገሪቱ በዚህ ያክል ቁጥር ታድጋለች ብሎ መገመት ይቻላል ወይ? ለዶ/ር ሰኢድ ያቀረብናለቸው ጥያቄ ነው። አይ ኤም ኤፍ ተስማማበትም አልተስማማበትም የኢትዮጵያ መንግስት የጀመራቸውን ፕሮጀክቶች ለማስጨረስ ገንዘብ ማግኘት ካቃተው፤ ከኤክስፖርት መቀነስ ጋር ተያይዞ ካጋጠመው የውጪ ምንዛሪ እጥረት ጎን ለጎን የብድር ጫናው በራሱ የሚያገኘውን የውጪ ምንዛሪ ይቀንሳል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ የተባለውን 8.5 በመቶ እድገት ማስመዝገብ አስቸጋሪ ነው። ተአምራዊ እድገት ሊመጣ አይችልም ሲሉ ድርጅቱ ያስቀመጠውን ትንበያ ማሳከት ለኢትዮጵያ ሊከብድ እንደሚችል ጠቁመዋል። |
news-46998888 | https://www.bbc.com/amharic/news-46998888 | አቶ በረከትና አቶ ታደሰ በባህር ዳሩ ፍርድቤት | ረቡዕ እለት ከአዲስ አበባ በፖሊስ ተይዘው የነበሩት አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደረሰ ካሳ ዛሬ ባህር ዳር ውስጥ ፍርድ ቤት ቀረቡ። | ሁለቱ ግለሰቦች ባህር ዳር በሚገኘው የባህርዳር አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን አቃቤ ህግ ለምርመራ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆ ነበር። አቶ በረከትና አቶ ታደሰ ለምን ከአዲስ አበባ ተይዘው ጉዳያቸው ባህር ዳር ውስጥ እንዲታይ እንደተደረገና ዋስትና ተሰጥቷቸው ጉዳያቸውን በውጪ ሆነው እንዲከታተሉ ጠይቀው ነበር። • "በረከትና ታደሰ በሙስና መጠርጠራቸው አስደንቆኛል" አቶ ጌታቸው ረዳ አቃቤ ሕግም የተጠረጠሩበት ጥፋት የተፈፀመው በአማራ ክልል ውስጥ በመሆኑ ጉዳያቸው መታየት ያለበት ባህር ዳር ውስጥ እንደሆነ ጠቅሶ የተጠረጠሩበት ድርጊት ከባድ በመሆኑና በዋስትና ቢለቀቁ መረጃና ሰነዶችን ሊያጠፉ ይችላሉ በማለት ጥያቄታቸውን ተቃውሞታል። ጉዳዩን ለመመልከት የተሰየሙት ዳኞችም ለጥቂት ደቂቃዎች በቀረቡት ጥያቄዎችና መልሶች ላይ ከመከሩ በኋላ አቃቤ ህግ የጠየቀውን የጊዜ ቀጠሮ በመፍቀድ አቶ በረከትና አቶ ታደሰ በእስር ቤት እንዲቆዩ ወስኗል። • አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ ወደ ባህር ዳር ተወሰዱ የሁለቱ ተጠርጣሪዎችን ጉዳይ ለመመልከትም ለየካቲት 01/2011 ቀጠሮ ሰጥቷል። በዛሬው የመጀመሪያ ችሎት ለአቶ በረከትና አቶ ታደረሰ ክሳቸው በጽሑፍ ቀርቦላቸዋል። በክሱ ላይ አስተያየታቸውን የተጠየቁት አቶ በረከት ሕገ መንግሥቱንና የፍትህ ሥርዓቱን በሚፃረር መልኩ ችግር እንደገጠማቸው ተናግረዋል። "ባለሁበትና በሌለሁበት በተደጋጋሚ የደቦ ፍርድ ገጥሞኛል" ያሉት አቶ በረከት በደብረ ማርቆስ ከተማ የገጠማቸውን ችግር በምሳሌነት አንስተዋል። ትናንት ለምርመራ በፖሊስ ጣቢያ ሲንቀሳቀሱ "ሌባ፣ ነፍሰ ገዳይና ወንጀለኛ" ሲባሉ እንደነበርም በተጨማሪም ትናንት ፍርድ ቤት ያልቀረቡት የፀጥታ ስጋት አለ ተብሎ እንደሆነም ተናግረዋል። ቤተሰቦቻቸው የፍርድ ሂደታቸውን እንዳይከታተሉ መደረጉንና የቀረበባቸውን ክስ ጠበቆች ይዘው ለመከራከር ዝግጁ እንደሆኑ እንዲሁም ጉዳያቸውን ውጪ ሆነው መከታተል እንዲችሉ አቶ በረከት ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል። • በረከት ስምኦን ከየት ተነስተው እዚህ ደረሱ "ያለ ፍርድ ቤት ተፈርዶብኝ የታሰርኩ ያህል ይሰማኛል" ያሉት አቶ ታደሰ ካሳ ደግሞ በባለሥልጣናት እና በመገናኛ ብዙሃን "ሌቦች እና ዘራፊዎች" መባላቸውን ጠቅሰው በቀረበባቸው ክስ ላይ ለመከራከር ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል። አክለውም "ጉዳዩ ከ90 በመቶ በላይ ተጠናቋል ስለተባልን የ14 ቀን ቀጠሮ መጠየቅ ተገቢ አይደለም" ብለው ውጪ ሆነው መከራከር እንዲችሉ እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል። አቶ ታደሰ በተጨማሪም የዳሽን ቢራ ዋና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ በመሆኑ ጉዳያቸው ከባህር ዳር ይልቅ አዲስ አበባ እንዲታይ አመልክተው ፤ በሽተኛ መሆናቸውንና ቤተሰባቸውም ያለው አዲስ አበባ መሆኑን ጠቅሰው ምግብም በሥርዓት እየቀረበላቸው አለመሆኑን ተናግረዋል። አቃቤ ሕግ በበኩሉ የተጠረጠሩበት ወንጀል ሰፊ ምርመራ እና በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ምስክሮችን ማናገር ስለሚያስፈልግ የተጠየቀው የጊዜ ቀጠሮ እንዲፈቅድ ጠይቋል። በተጠርጣሪዎቹ ለተነሱት የተለያዩ ጥያቄዎች አቃቤ በሰጠው ምላሽም ትናንት ፍርድ ቤት ፋይል ቢከፈትም ጊዜው ስላልበቃ እንዳልቀረቡ፣ ከምግብ ጋር ተያይዞ አቅም በሚችለው ሁኔታ አየቀረበ መሆኑንና ቤተሰቦቻቸው ምግብ እንዲያቀርቡ እንደሚመቻች ገልጿል። ግራ ቀኙን የተመለከተው ፍርድ ቤትም ተመዘበረ የተባለው ሃብት የክልሉ በመሆኑ የክልሉ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ማየት እንደሚችልና ከተፈፀመው ወንጀል ከባድነት እና ከሰነድ ማሰባሰብ አንፃር የ14 ቀን ቀጠሮውን ፈቅዷል። ፍርድ ቤቱ ጨምሮም ግለሰቦቹ የነበራቸውን ስልጣን ከግምት በማስገባት ልዩ ጠበቃ የሚያስፈለልጋቸው መሆኑን ጠቅሶ ጥንቃቄና አስፈላጊው ጥበቃ እንዲደረግላቸው ትዕዛዝ ሰጥቷል። |
news-54012503 | https://www.bbc.com/amharic/news-54012503 | ሲዲሲ የኮቪድ-19 ክትባት የሚሰራጭበት መንገድ ላይ የአሜሪካ ግዛቶች ቀድመው እንዲዘጋጁ አሳሰበ | የአሜሪካው የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ) የአሜሪካ ግዛቶች የጤና ኃላፊዎች የኮሮናቫይረስ ክትባት የበለጠ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ቀድሞ የሚታደልበት አማራጭ ላይ ቀድመው እንዲዘጋጁ ማሳሰቡ ተነገረ። | ሲዲሲ ትናንት በድረ-ገጹ ላይ ባወጣው ጽሑፍ ላይ ክትባቱ ለበሽታው የበለጠ ተጋለጭ ለሆኑ ሰዎች እስከ ጥቅምት አጋማሽ ሊሰራጭ እንደሚችል ጠቁሟል። “ሲዲሲ ግዛቶች ቀድመው እንዲዘጋጁ በማሰብ ዝግጁ ሊሆን የሚችል የክትባት መጠን እና ጊዜን ለግዛቶች አሳውቋል። ከጥቅምት አጋማሽ እስከ ሕዳር መጨረሻ ድረስ መጠናቸው አነስተኛ ቢሆንም የክትባት ስርጭት ሊኖር ይችላል” ሲሉ የሲዲሲ ቃል አቀባይ ለሬውተርስ ተናግረዋል። ኒው ዮርክ ታይመስ ደግሞ ቀደም ሲል ሲዲሲ ከሁሉም 50 የአሜሪካ ግዛቶች እና አምስት ግዙፍ ከተሞች ከስርጭት ጋር ተያይዞ ያሉ የእቅድ መረጃዎችን ጠይቋል። በኒው ዮርክ ታይምስ ዘገባ ላይ ሲዲሲ ጥቅምት አጋማሽ ላይ በቁጥር አነስተኛ የሆኑ አንድ ወይም ሁለት የኮቪድ-19 ክትባቶች ለስርጭት ዝግጁ ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠቁሟል። ለበሽታው የበለጠ ተጋላጭ ናቸው ለተባሉ እንደ የጤና ባለሙያዎች፣ ለደህንነት ሰራተኞች እና እድሜያቸው የገፉ ሰዎችን የሚንከባከቡ ነርሶች እና ባልደረቦች ክትባቱ ያለ ክፍያ ይሰጣቸዋል ይላል የሲዲሲው ዶክመንት። የተላላፊ በሽታዎች ባለሙያው ዶ/ር አንቶኒዮ ፋውቺ ለኤምኤስኤንቢሲ ቴሌቪዥን ትናንት ሲናገሩ፤ ለኮቪድ-19 ክትባት ተሳትፎ እያደረጉ ያሉ ሰዎች ከፍተኛ ቁጥርን ከግምት በማስገባት እስከ ሕዳር ወር ድረስ የትኛው የኮቪድ-19 ክትባት ደህንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ እንደሚሆን መለየት ይቻላል ብለዋል። ሞደርና፣ አስትራዜኔካ እና ፐፊዘር የተሰኙ መድሃኒት አምራቾች ደህንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ የሆነ የኮቪድ-19 ክትባት ለማዘጋጀት ጥረት ላይ ይገኛሉ። |
news-53739082 | https://www.bbc.com/amharic/news-53739082 | በሩስያ የኮቪድ-19 ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ፍቃድ አገኘ | የሩስያው ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን የኮቪድ-19 ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ፍቃድ ማግኘቱን ተናገሩ። | በአገራቸው ላለፉት ሁለት ወራት በሰዎች ላይ ሙከራ እየተደረገበት የነበረው ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል መፈቀዱን ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል። ክትባቱ አስፈላጊውን የምርመራ ሂደት ማለፉን የገለጹት ፑቲን፤ ልጃቸው ክትባቱን እየወሰደች እንደምትገኝም ተናግረዋል። ጥቅምት ላይ ክትባቱን በጅምላ የመስጠት እቅድ እንዳለ የአገሪቱ አመራሮች ቢናገሩም፤ ባለሙያዎች የሩስያ የክትባት ምርምር እየሄደ ያለበት ፍጥነት ላይ ጥያቄ አንስተዋል። ባለፈው ሳምንት፤ የዓለም ጤና ድርጅት ሩስያ ክትባት ስታመርት ዓለም አቀፍ ሕግጋትን እንድትከተል ማሳሰቡ አይዘነጋም። የሩስያ ክትባት ድርጅቱ በሦስተኛ ደረጃ ሙከራ ላይ ካስቀመጣቸው ክትባቶች አንዱ አይደለም። እነዚህ ክትባቶች በሰዎች ላይ ተሞክረው ተጨማሪ ምርምር መካሄድ አለበት። ፕሬዘዳንት ፑቲን ግን፤ በሞስኮው ጋማሊያ ተቋም ውስጥ የተሠራው ክትባት ቫይረሱን “በዘላቂነት ለመከላከል የሚያስችል” ነው ብለዋል። የሩስያ የጤና ሚንስትር ሚካኤሊ ሙራሽኮ፤ ክትባቱ “በጣም ውጤታማና ደህንነቱ የሚያስተማምን” ነው ብለዋል። ክትባቱ የሰው ልጆች ኮቪድ-19ን ድል የሚነሱበት እርምጃ እንደሆነም አክለዋል። ባለፈው ሳምንት፤ የሩስያ መንግሥት ክትባቱ ላይ ስኬታማ ምርምር እንዳካሄደ አስታውቆ፤ በጅምላ ክትባቱን መስጠት እንደሚጀምር ይፋ አድርጎ ነበር። በመላው ዓለም ወደ 100 የሚጠጉ ክትባቶች ላይ ምርምር እየተደረገ ይገኛል። ከነዚህ መካከል በሰው ላይ ሙከራ የተካሄደባቸውም አሉ። ክትባት የማግኘት ሂደቱ ፈጣን ቢሆንም በርካታ ባለሙያዎች እስከ ቀጣዩ ዓመት አጋማሽ ድረስ ክትባት በስፋት አይዳረስም ይላሉ። የዓለም ጤና ድርጅት ቃል አቀባይ ክርስቲያን ሊንድሜር “አንዳንዴ በግላቸው ምርምር የሚያካሂዱ ሰዎች ውጤታም እንደሆኑ ይናገራሉ። ይህም እጅግ መልካም ዜና ነው” ብለዋል። ቃል አቀባዩ አያይዘውም፤ ውጤታማ ክትባት በማግኘት እና በምርምር ደረጃዎች በማለፍ መካከል ሰፊ ልዩነት እንዳለ አስምረውበታል። |
news-53231193 | https://www.bbc.com/amharic/news-53231193 | ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ማን ነው? | ሃጫሉ ሁንዴሳ ተወልዶ ያደገው ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ አንድ መቶ ኪሎ ሜትሮች ርቃ በምተገኘው አምቦ ከተማ ውስጥ ነው። | እናቱ ወይዘሮ ጉደቱ ሆራ፣ ሃጫሉ ከልጅነቱ ታሪክን መስማትና የመንገርና ዝንባሌውንና ችሎታውን ጠንቅቀው ተረድተውት ስለነበር ከመጀመሪያው አንስቶ ያበረታቱት እንደነበር በተደጋጋሚ ሃጫሉ ያስታውሳል። አባቱ አቶ ሁንዴሳ ቦንሳ ደግሞ ልጃቸው ሃጫሉ በትምህርቱ ዓለም ገፍቶ ዶክተር ወይም የዩኒቨርሲቲተ መምህር እንዲሆንላቸው ከፍተኛ ፍላጎት ነበራቸው። ሃጫሉ ግን ገና ከልጅነቱ ጀምሮ በፍቅሯ ለወደቀላት ሙዚቃ ነበር መላው ትኩረቱ። በአስራዎቹ እድሜው ላይ እያለ እንኳን የበርካቶችን ስሜት የሚኮረኩሩ ሙዚቃዎችን ይጫወት ነበር። ሃጫሉ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሳለ በ1995 ዓ.ም የ17 ዓመት ታዳጊ እንዳለ ታስሮ ለአምስት ዓመታት አምቦ በሚገኘው እስር ቤት አሳልፏል። ፖለቲካዊ መልዕክት ያላቸውና ተወዳጅ የኦሮሞ የትግል ሙዚቃዎችን ማቀንቀኑን እንዲያቆም ለማድረግ መታሰሩን ሃጫሉ ይናገራል። ነገር ግን መታሰሩ እንደውም ይበልጥ በሥራው እንዲገፋበትና በሰዎች ላይ የሚደርሰውን ግፍ እና ጭቆና የበለጠ እንዲገባው ማድረጉን በአንድ ወቅት ተናግሮ ነበር። በእስር ላይ ሳለም ነበር የሙዚቃ ግጥሞችን ዜማዎችን መጻፍ የጀመረው። ከአምስት ዓመታት በኋላ ሲለቀቅ የደረሰበትን በደል ለመቃወምና ለሚሊየኖች ድምጽ ለመሆን ወስኖ እንደወጣ ይናገራል ሃጫሉ። በአጭር ጊዜም በኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ ዘንድ ብቻ ሳይሆን በመላዋ አገሪቱ ተወዳጅ የሆነለትን 'ሳኚ ሞቲ' የተሰኘውን አልበሙ አቀረበ። የዚህ የሙዚቃ ስብስብ አብዛኛዎቹ ግጥሞችና ዜማዎች ሃጫሉ በእስር ላይ እያለ የሰራቸው እንደነበሩ ይነገራል። በወቅቱ በሃያዎቹ መጀመሪያ የእድሜ ክልል ውስጥ የነበረው ሃጫሉም በዚህ አልበሙ በተለይ ደግሞ የአልበሙ መጠሪያ በነበረው ሙዚቃው ቋንቋውን በማይችሉ ሰዎች ዘንድም ታዋቂነትን ለማትረፍ ችሎ ነበር። ከጥቂት ዓመት በኋላም ወደ አሜሪካ የሙዚቃ ሥራዎቹን ለማቅረብ በሄደበት ጊዜ ሁለተኛውንና "ዋኤ ኬኛ" አልያም "የእኛ ነገር" የሚል ትርጉም ያለውን አልበሙን ለቀቀ። በወቅቱ አልበሙ አማዞን ላይ በከፍተኛ ሁኔታ በመሸጥ ከፍተኛ ትኩረትን አግኝቶ የነበረ ሲሆን፤ የሃጫሉ ተወዳጅነትም የበለጠ እየተጠናከረ መጣ። ሃጫሉ እንደሚለው "ሙዚቃ ለእኔ ህይወቴ ነው። ውስጤ ነው ያለው። የሕዝቤን የአኗኗር ዘዬ የማሳውቅበት፣ የሆዴን የምገልጽበት ነው። ሙዚቃ ሁሉ ነገሬ ነው፤ ዘመድም ጠላትም ያፈራሁበት።" ሃጫሉ ተወዳጅ የሆኑ የኦሮሞ የሙዚቃ ስልቶችን ከዘመናዊው ሙዚቃ ጋር በማጣመር በሚያቀርባቸው ሥራዎቹ ብዙዎችን ጆሮና ቀልብ ለመማረክ አስችሎታል። በአገሪቱ የሚገኙ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያዎችም ሙዚቃዎቹን በተደጋጋሚ በማጫወታቸው በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ሰዎች ዘንድ አድናቆትን ማግኘት ችሏል። ከሦስት ዓመት በፊት በአገሪቱ ተቀስቅሶ ከነበረው ጸረ መንግሥት ተቃውሞ ጋር በተያያዘ በተለይ በኦሮሚያ ክልል ሲካሄድ በነበረው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ወቅት የሃጫሉ ያወጣው 'ማላን ጂራ' የተሰኘው ነጠላ ሙዚቃው ከፍተኛ ተወዳጅነትን ከማትረፍ አልፎ የእንቅስቃሴው መነቃቂያ ሆኖ ነበር። ሃጫሉ የመንግሥት ባለስልጣናት በሚገኙባቸውና በቀጥታ በቴሌቪዥን በሚቀርቡ በትልልቅ የሙዚቃ መድረኮች ላይ በመገኘት ሙዚቃዎቹን በሚያቀርብበት ጊዜ ያለፍርሃት የሚሰማውን ፖለቲካዊ ጉዳዮችንም በማቅረብ በድፍረቱ ይታወቃል። ባለትዳርና የሦስት ልጆች አባት የነበረው የ36 ዓመቱ ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ሰኞ ሰኔ 22/2012 ዓ.ም አዲስ አበባ ውስጥ በተፈጸመበት ጥቃት ህይወቱ አልፏል። |
news-51260439 | https://www.bbc.com/amharic/news-51260439 | አውስትራሊያዊቷ ኬክ በፍጥነት በመብላት ውድድር ላይ ሳሉ ሞቱ | በአውስትራሊያ አንዲት ሴት ብዙ ኬክ በፍጥነት በመብላት ውድድር ላይ ሳሉ ሕይወታቸው አልፏል። | ሴትዯዋ ሲበሉት የነበረው ላሚንግተን ኬክ ሴትየዋ 60 ዓመታቸው ሲሆን በኪውንስላንድ ሃርቬይ ቤይ ውስጥ በሚገኝ ቢች ሃውስ በተባለ ሆቴል ኬክ ቶሎ በልቶ የመጨረስ ውድድር ላይ ሳሉ ነበር ራሳቸውን ስተው የወደቁት። ተወዳዳሪዎቹ ቀደም ብለው ላሚንግተን የተሰኘውን ከቼኮሌትና ከኮኮነት የተሠራ ኬክ ሲበሉ ነበር። ሴትዮዋ በወቅቱ የመጀመርያ እርዳታ ተደርጎላቸው ሆስፒታል በፍጥነት የተወሰዱ ቢሆንም ሕይወታቸን ማትረፍ ግን አልተቻለም። • የታገቱት ተማሪዎች፡ የቤተሰብ ሰቀቀን፤ የማሕበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ጩኸት • በትራምፕ የድጋፍ ደብዳቤ ወደ አሜሪካ ያቀናችው የአሲድ ጥቃት የደረሰባት ኢትዮጵያዊት የዐይን እማኞች እንደሚሉት ሴትየዋ በውድድሩ ላይ አንዱን ኬክ ጎርሰው ሌላ ለመድገም ሲሞክሩና ሲታገላቸው እንደነበር መመልከታቸውን ተናግረዋል። ኋላ ላይ በወጡ የተንቀሳቃሽ ምሥሎች መረዳት እንደተቻለው በሆቴሉ ውስጥ የተገኙ ጠጪዎች ለተወዳዳሪዎቹ እያጨበጨቡ ድጋፍ ሲሰጡ ነበር። ተወዳዳሪዎቹ ከሚመገቡት ኬክ በተጨማሪ በብርጭቆ ውሃ ቀርቦላቸው እንደነበረም ተንቀሳቃሽ ምሥሉ መስክሯል። በሃርቬይ ቤይ የሚገኘው የቢች ሃውስ ሆቴል ፌስቡክ ገጽ ለሴትዮዋ ቤተሰቦችና ወዳጆች መጽናናትን ተመኝቷል። በአውስትራሊያ የድል ቀን ምግብ በፍጥነት በልቶ የመጨረስ ውድድር እጅግ የሚዘወተር መዝናኛ ነው። የአውስትራሊያ የድል ቀን አውሮፓዊያኑ አውስትራሊያ የደረሱበትን ቀን የሚዘክር በዓል ነው። በዚህ የድል ቀን ተወዳዳሪዎች ሆትዶግ፣ ኬክ፣ ወይም ሌሎች ምግቦችን በፍጥነት ከተመገቡ ዳጎስ ያለ ሽልማትን ያሸንፋሉ። |
51470899 | https://www.bbc.com/amharic/51470899 | ኮሮና ቫይረስ መጠሪያ ስሙን አገኘ | የዓለም ጤና ድርጅት ከፍተኛ ኃላፊዎች በኮሮና ቫይረስ የሚከሰተውን በሽታ ኮቪድ-19 ብለን ሰይመነዋል ሲሉ ተናገሩ። | በጄኔቫ ለተሰበሰቡት ጋዜጠኞች "ለበሽታው ስያሜ አግኝተንለታል፤ ኮቪድ-19 ተብሎ ይጠራል" ያሉት የዓለም ጤና ድርጅት የበላይ ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ናቸው። በአሁን ሰአት ቫይረሱ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈ ሲሆን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ተይዘዋል። ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የአለምመሪዎች ቫይረሱን ለመዋጋት በብርቱ እንዲታገሉ ጥሪ አቅርበዋል። • የኮሮናቫይረስ እስካሁን ትክክለኛ ስም እንደሌለው ያውቃሉ? • ኮሮናቫይረስ፡ ምን ያህል አሳሳቢ ነው? ኮሮና ቫይረስ በሽታው የሚገኝበት የቫይረስ ቡድን ስያሜ ሲሆን፣ የበሽታው የተለየ መጠሪያ አለመሆኑ ተነግሯል። ዓለምአቀፍ የቫይረስ ታክሶኖሚ ኮሚቴ በሽታውን ሳርስ-ኮቪ-2 (SARS-CoV-2 ) ነው በማለት መለየቱ ተሰምቷል። ተመራማሪዎች ይህንን ቫይረስ በጅምላ ስሙ በመጥራት ግርታን ከመፍጠር ስም እንዲወጣለት ሲወተውቱ፣ አክለውም ሀገራትን ለይቶ ማግለልም ሆነ መፈረጅ እንዲቀር ነበር። ዶክተር ቴዎድሮስ ስለ ቫይረሱ ስያሜ በተናገሩበት መግለጫ ላይ " ለቫይረሱ ስያሜ ስንሰጥ የትኛውንም መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ የማይገልፅ፣ እንስሳትን፣ ግለሰብንም ሆነ ቡድንን የማይነካ እንዲሁም ለአጠራር ምቹ የሆነ እንዲሆንና ከቫይረሱ ጋር ግንኙነት ያለው እንዲሆን ጥረናል" ብለዋል። " ስም በሽታውን ለመከላከል፤ ትክክል ያልሆነን ወይንም መገለልን የሚያስከትል ነገርን እንዳንጠቀም ይከላከላል። እንዲሁም ለወደፊቱ ኮሮና ቫይረስ እንደገና በወረርሽኝ መልክ ቢከሰት ወጥ የሆነ አጠቃቀም እንድንከተል ያግዘናል" ብለዋል። • አፍሪካ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል አቅሙ አላት? • ቻይና በ 6 ቀናት ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ ሆስፒታል ልትገነባ ነው አዲሱ ስያሜ"ኮሮና"፣ "ቫይረስ" እና "ዲዝዝ"(በሽታ) ከሚሉት ቃላት እንዲሁም ከተከሰተበት ዓመተ ምህረት 2019 የተወሰደ መሆኑ ታውቋል። ኮሮና ቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ መከሰቱ የተመዘገበው ባለፈው ሕዳር ወር እንደ ጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር ዴሴምበር 31 2019 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል። በአሁኑ ሰዓት በቻይና ብቻ 42 ሺህ 200 ሰዎች መያዛቸው የተመዘገበ ሲሆን በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር በ2002-2003 ተከስቶ በርካቶችን ከገደለው የሳርስ ወረርሽኝ ይበልጣል። ቻይና ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን በአግባቡ አልያዙም ያለቻቸውን ከፍተኛ ባለስልጣናት ከሥልጣን አንስታለች። የሁቤይ ጤና ኮሚሽን የፓርቲው ጸሐፊ እንዲሁም የኮሚሽኑ የበላይ ኃላፊ ከሥራቸው ከተነሱት ባለስልጣናት መካከል ናቸው። እነዚህ ከፍተኛ ሹማምንት በቻይና ከበሽታው ጋር በተያያዘ ከስልጣናቸው የተነሱ የመጀመሪያዎቹ ከፍተኛ ባለስልጣናት ናቸው። • የአውስትራሊያ ሳይንቲስቶች ኮሮና ቫይረስን 'ሊያመርቱ' ነው • የኮሮናቫይረስ ምልክት ያሳዩ 14 ኢትዮጵያውያን ነፃ ሆነው ተገኙ የአካባቢው የቀይ መስቀል ምክትል ኃላፊም የመጣውን እርዳታ በአግባቡ ካለማድረስ ጋር በተያያዘ "ኃላፊነትን በተገቢው ሁኔታ አለመወጣት" በሚል ከሥራቸው ተሰናብተዋል። በትናንትናው ዕለትም የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮናቫይረስ በሽታን ምልክት አሳይተው የነበሩ አስራ አራት ኢትዮጵያውያን ከላብራቶሪ ምርመራ በኋላ ነፃ መሆናቸው አስታውቋል። |
news-56036401 | https://www.bbc.com/amharic/news-56036401 | ምንጭ- 6768 ለአካል ጉዳተኞች የተዘጋጀ የመረጃ ማዕከል | ኢትዮጵያ ሴንተር ፎር ዲሴቢሊቲ ኤንድ ዴቨሎፕመንት (ኢሲዲዲ) በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ነው የተባለ እና ለአካል ጉዳተኞች መረጃ የሚሰጥ 6768 የነጻ ጥሪ ማዕከል ማቋቋሙን የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ተክሌ ለቢቢሲ ተናገሩ። | ይህ ምንጭ የተሰኘ አሳታፊ የሆነ የድምጽ መልእክትን የሚያደርስ (IVR) የስልክ የመረጃ ማእከል ሲሆን፤ በኢትዮጲያ ለመጀመሪያ ጊዜ አገልግሎት መስጠት የጀመረ የመረጃ ማእከል መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል። የዚህ የመረጃ ማእከል ዋና አላማ ከአካል ጉዳት ጋራ የተያያዙ አስፈላጊ በድምጽ የተዘጋጁ መረጃዎችን ለአካል ጉዳተኛው እና ለተቀረው ማህበረሰብ ማቅረብ ነው። ከዚህም በተጨማሪ አካል ጉዳተኞች ጥያቄ ቢኖራቸው ወይንም ማካፈል የሚፈልጉት ልምድ ካለ ድምጻቸውን ቀርፀው መላክ እንደሚችሉ አቶ መላኩ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይህ አገልግሎት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የሚሰራ መሆኑንም ኃላፊው አክለዋል። ይህንን የአጭር የስልክ ቁጥር ኢትዮ ቴሌኮም በነጻ እንደሰጠና ሰርቨሩ ኢትዮ ቴሌኮም ዳታ ማዕከል ውስጥ መቀመጡን አክለው ተናግረዋል። እኤአ በ2011 የዓለም ባንክ እና የዓለም ጤና ድርጅት ባወጡት መረጃ መሰረት ከአለም ሕዝብ 15 በመቶ ያህሉ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ወደ 17.6 በመቶው የሕብረተሰብ ክፍል የአካል ጉዳተኛ ነው። ይህ የነጻ አገልግሎት በሙከራ ደረጃ ነው ያለው ያሉት ኃላፊው፤ ለጊዜው አገልግሎቱ በአማርኛ ቋንቋ ብቻ መጀመሩን በመግለጽ፤ በቀጣይ በሌሎች የአገሪቱ ቋንቋዎች እንደሚሰጡ አስረድተዋል። በኢትዮጵያ መረጃ ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ አይደለም የሚሉት አቶ መላኩ በርካታ የመረጃ ተደራሽነት ክፍተት መኖሩንም ይጠቁማሉ። አገልግሎቱን ለማግኘት በማንኛውም ዓይነት ስልክ መደወል እንደሚቻል እንዲሁም ኢንተርኔት እንደማያስፈልግ ኃላፊው ጨምረው አስረድተዋል። አቶ መላኩ፤ ወደዚህ የጥሪ ማዕከል እንደ ሌሎች የጥሪ ማዕከሎች ተገልጋዮች ሲደውሉ የስልክ ኦፕሬተሮች ወይንም ባለሙያዎች አንስተው መልስ የሚሰጡበት አለመሆኑንን ይናገራሉ። ተጠቃሚዎች በሚደውሉበት ወቅት ከመጀመሪያ ጊዜ ደዋዮች አጠቃላይ መረጃ እንደሚወስድም ጨምረው ተናግረዋል። ይህ መሰረታዊ መረጃ ስለተጠቃሚዎች በማወቅ ወደፊት ሥራውን ለማስፋት በማሰብ መዘጋጀቱን አቶ መላኩ ያስረዳሉ። ይህ አስፈላጊ በድምጽ የተዘጋጁ መረጃዎችን የያዘው አገልግሎት ስምንት ክፍሎች እንዳሉት አቶ መላኩ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ወቅት ተናግረዋል። ከአገልግሎቶቹ መካከልም ስለ አካል ጉዳተኞች በኢትዮጵያ ውስጥ ያለን አዲስ መረጃ መግለጽ፣ ስለ አካል ጉዳተኛነት ጠቅላላ መረጃ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለ አካል ጉዳተኞች ያሉ ሕጎች፣ አካል ጉዳተኝነት ምን ማለት እንደሆነ፣ ከአካል ጉደተኞች ጋር የሚሰሩ ምን ዓይነት ቋንቋ መጠቀም እንዳለባቸው የሚያስረዱ መረጃዎች መያዙን አብራርተዋል። ሌላው ይህ የነጻ ጥሪ ማዕከል ስለ አካቶ ጤና ከሥነ ተዋልዶ፣ ተደራሽ ስለሆኑ የጤና ተቋማት እና ስለ ጾታዊ ጥቃት፣ ስለ አካቶ ትምህርት፣ ስለ አካቶ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና፣ ስለ ሥራ እና ሥራ ገበያ፣ የሥራ እድሎች መረጃ ይሰጣል ሲሉ ይናገራሉ። የኢትዮጵያ ቴሌኮም አጋራቸው በመሆኑም ድርጅቱ ስለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚያስተዋውቅ ክፍልም እንዳለው ጨምረው ተናግረዋል። "አካል ጉዳተኝነት እንደፈተነኝ ይኖራል" |
54308130 | https://www.bbc.com/amharic/54308130 | ስዊዘርላንድ ድንበሯን ከአውሮጳ ኅብረት በመዝጋት ጉዳይ ላይ ሕዝበ ውሳኔ አካሄደች | ስዊዝ ድምጽ ሰጪዎች በከፍተኛ ድምጽ ሐሳቡን ውድቅ አድርገውታል። | የአውሮጳ ኅብረት አገራት ሰዎች በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ የሚፈቅደውን ሕግ ለመቀልበስ ነበር ሕዝበ ውሳኔው የተካሄደው። ድምጽ ከሰጡት ውስጥ 62% የሚሆኑት ከአውሮጳ አባል አገራት ጋር ነጻ እንቅስቃሴ ይቀጥል ያሉ ሲሆን 38% የሚሆኑት ብቻ ድንበራችንን እንዝጋ ብለዋል። ስዊዘርላንድ የአውሮጳ ኅብረት አባል አገር አይደለችም። ነገር ግን ከኅብረቱ ጋር በርካታ የትብብር ስምምነቶችን ታደርጋለች። ከብራስልስ ጋር በቅርብ ትሰራለች። ይህም የአውሮጳ ነጻ የንግድ ቀጠና ተሳታፊ እንድትሆነ አስችሏታል። ድንበራችንን ጠርቅመን እንዝጋ የሚለው ሐሳብ ለሕዝብ ውሳኔ የቀረበው የስዊዝ ፒፕልስ ፓርቲ ወይም በምኅጻረ ቃሉ ኤስቪፒ ተብሎ የሚጠራው የፖለቲካ ድርጅት ባቀረበው ሐሳብ መሠረት ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ ከ6 ዓመት በፊት ስደተኞችን ከአውሮጳ ኅብረት በኮታ በመቀበል ጉዳይ ላይ ሕዝበ ውሳኔ ተደርጎ ነበር። በስዊዘርላንድ በፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙርያ ሕዝበ ውሳኔ ማድረግ የተለመደ ተግባር ነው። ቀጥተኛ ዲሞክራሲን በማራመድ የምትታወቀዋ ስዊዘርላንድ በአካባቢያዊና በአገራዊ ጉዳዮች ሕዝቡ ምን እንደሚፈልግ የሚጠየቀው በተወካዮቹ ሳይሆኑ በቀጥታ ድምጽ በመስጠት ነው። ነጻ እንቅስቃሴ መኖር የለበትም የሚሉ ወገኖች ስዊዘርላንድ ድንበሮቿን ሙሉ በሙሉ እንድትቆጣጠርና የምትፈልጋቸው ስደተኞች ብቻ አገራችን እንዲገቡ ማድረግ እንችላለን ብለው ያምናሉ። ከአውሮጳ አገራት ጋር ነጻ እንቅስቃሴ ሊቀጥል ይገባል የሚሉት ደግሞ አሁን ያለውን ጤናማ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ያውካል፣ በሺ የሚቆጠሩ የስዊዝ ዜጎች በሌሎች የአውሮጳ አገራት እንደልብ ተንቀሳቅሰው ለመስራት እንዳይችሉ ያደርጋል ሲሉ ቆይተዋል። ስዊዘርላንድ ወደብ አልባ ሀብታም አገር ስትሆን ለብዙ ዓመታት በዓለምና አካባቢያዊ ፖለቲካ ጉዳዮች ገለልተኛ በመሆን ትታወቃለች። |
news-50038628 | https://www.bbc.com/amharic/news-50038628 | በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ የሞቱ ሰዎች አጽም ለቤተሰቦቻቸው እየተሰጠ ነው | ከወራት በፊት በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ግለሰቦች አጽም ለቤተሰቦቻቸው እየተሰጠ ነው። | በአደጋው ህይታቸውን ያጡ ኬንያውያን አስክሬን ለቤተሰቦቻቸው እየተሰጠ ነው። እለተ እሁድ መጋቢት 1/2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ ጠዋት 2፡38 ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ለሚያደርገው በረራ ጉዞ በጀመረ ከስድስት ደቂቃዎች በኋላ ነበር አደጋው የደረሰው። •"የሞተው የኔ ያሬድ ነው ብዬ አላሰብኩም" የካፕቴን ያሬድ የ11 አመት ጓደኛ •"እስካሁን ሙሉ የሰውነት ክፍል ማግኘት እንደተቸገርን ለቤተሰብ እያስረዳን ነው" አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ቦይንግ 737 ማክስ የተከሰከሰው ቢሾፍቱ አቅራቢያ ሲሆን 149 መንገደኞችንና 8 የበረራ ሰራተኞችን አሳፍሮ ነበር። በወቅቱ ተሳፍረው የነበሩት 157 መንገደኞች ከሰላሳ አገራት የተውጣጡ ሲሆኑ ከአደጋው የተረፈ ሰው አልነበረም። አደጋው በመላው ዓለም ድንጋጤን የፈጠረና ያሳዘነም ነበር። ከእነዚህም ውስጥ ከፍተኛውን ቁጥር የያዙት 32 ኬንያውያን ሲሆኑ አጽማቸውም ወደ ሃገራቸው ለመመለስ በዝግጅት ላይ ነው። አደጋውንም ተከትሎ "በጣም የሚያሳዝነው ነገር እስካሁንም በጣም የተወሰኑትን የሰውነት ክፍሎች እንጂ ሙሉ የሰውነት ክፍል አላገኘንም፤ ይህ ደግሞ ለቀሪ ሥራዎችም ትልቅ ፈተና እንደሚሆንብን እንጠብቃለን፤ ለሃዘንተኛ ቤተሰቦችም ይህን ችግር እያሰረዳናቸው ነው" በማለት የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ለቢቢሲ ገልፀው ነበር። •"አደጋውን ስሰማ በረራው ጠዋት እንዳልሆነ ራሴን አሳመንኩኝ" የረዳት አብራሪው ጓደኛ የሟቾቹን አስከሬን ለመለየት የዲኤንኤ ምርመራ የተደረገ ሲሆን፤ የሰባት ወራት ጊዜም ፈጅቷል። በቦሌ አየር ማረፊያ የቤተሰቦቻቸውን፣ የዘመድ ወዳጆቻቸውን አስከሬን ሊወስዱ የመጡ ግለሰቦች በሃዘን ድባብ ውስጥ ነበሩ። ከአደጋው በኋላም ለመጀመሪያ ጊዜ ነው አስከሬናቸውን ማየት የቻሉት። በዛሬው ዕለትም በኬንያ በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ግለሰቦች የሃዘን ሥነ ሥርዓትም ይካሄዳል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለስልጣናት እንደተናገሩት መለየት ያልተቻለ አስከሬን እንዲሁም ሌሎች ቁሳቁሶች አደጋው በተከሰተበት አካባቢ በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ግለሰቦች በሚሰራው የማስታወሻ ስፍራ የሚቀበር ይሆናል። |
news-52817037 | https://www.bbc.com/amharic/news-52817037 | ትዊተር የትራምፕ ያሰፈሩት መልዕክት 'አሳሳች ሊሆን ይችላል' አለ | ትዊተር ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በገጻቸው ያሰፈሩት መልዕክት አሳሳች ሊሆን ስለሚችል ለመጀመሪያ ጊዜ 'ማጣራትን የሚፈልግ ሊሆን ይችላል' የሚል ማሳሰቢያ አስቀመጠ። | ዶናልድ ትራምፕ በትዊተር ገጻቸው ባሳፈሩት መልዕክት ስር መልዕክቱን የሚያነቡ ሰዎች በፕሬዝደንቱ የሰፈረው መልዕክ እውነተኛነትን እንዲያጣሩ የሚመክር ምልክት ትዊተር አኑሯል። ትዊተር ዶናልድ ትራምፕ በገጻቸው ላይ ያሰፈሩት መልዕክት 'አሳሳች ሊሆን ይችላል' ያለው የራሱን 'አሳሳች መረጃ ፖሊስ' መሠረት በማድረግ ነው። ትራምፕ በትዊተር ገጻቸው 'በፖስታ አማካኝነት የሚላክ እና የሚመለስ የድምጽ መስጫ ሥርዓት ትክክለኛ ውጤትን አያሳይም' የሚል ሃሳብ ያለው ጽሑፍ ነበር በትዊተር ገጻቸው ላይ ያሰፈሩት። ትዊተር እውነትነታቸው በሚያጠራጥሩ የትዊተር መልዕክቶች ስር ተጠቃሚዎች ስለተጠቀሱት ጉዳዮች ተጨማሪ መረጃዎችን እንዲያጣሩ ለማሳሰብ ሰማያዊ የቃለ አጋኖ [ ! ] መልዕክት የስቀምጣል። ዶናልድ ትራምፕ ለትዊተር ምላሽ ይሆን ዘንድ፤ የማኅበራዊ ሚዲያው መድረኩ 'ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን ያፍናል' ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ላይ ጸፈዋል። ትዊተር በገጹ ላይ የሚወጡ ሐሰተኛ ወይም አሳሳች መልዕክቶች ላይ ሰማያዊን ቃለ አጋኖ መልዕክት ማስቀመጥ እንደሚቀጥል አስታውቋል። አሜሪካ ከአምስት ወራት በኋላ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ታካሂዳለች። ትራምፕ የሪፐብሊካን ፓርቲን ወክለው ለሁለተኛ ዙር የሚወዳደሩ ሲሆን ዲሞክራቱ ጆ ባይደን ደግሞ የትራምፕ ተቀናቃኝ ሆነው ይቀርባሉ። በዚህ ምርጫ የኮሮናቫይረስ ስጋት የሚቀጥል ከሆነ፤ አሜሪካውያን ወደ ምርጫ ጣቢያ ሳይሄዱ በፖስታ ቤት በኩል በሚላክ የደምጽ መስጫ ወረቀት ላይ የሚሹትን እጩ ይምረጡ የሚለው አማራጭ በስፋት እየተመከረበት ነው። አንድ የምርምር ተቋማ ይፋ እንዳደረገው 66 በመቶ የሚሆኑ አሜሪካውያን ድምጻቸውን ለመስጠት ወደ ምርጫ ጣቢያ የመሄድ ፍላጎት የለንም ብለዋል። ለዚህም ዋነኛ ስጋታቸው ለኮሮናቫይረስ ልንጋለጥ እንችላለን የሚለው ነው። ዋሽንግተን፣ ኦሪጎን እና ኮሎራዶን ጨምሮ አምስት የአሜሪካ ግዛቶች ምርጫን የሚያካሂዱት በፖስታ የሚላኩ የምርጫ ድምጽ መስጫ ወረቀቶች ላይ በመመስረት ነው። |
news-51470949 | https://www.bbc.com/amharic/news-51470949 | ሶማሊያ፡ ታዳጊዋን ደፍረው ለህልፈት የዳረጉት በጥይት ተደብድበው ተገደሉ | በሶማሊያ ሰሜን ምስራቅ ግዛት የአስራ ሁለት አመት ታዳጊዋን የደፈሩ ሁለት ወንዶች በተኳሽ ቡድን በጥይት እንዲገደሉ ፍርድ ቤቱ ባዘዘው መሰረት ቅጣቱ በትናንትናው እለት ተፈፃሚ ሆኖባቸዋል። | የፑንት ላንድ ነዋሪ የሆነችው አይሻ ኢልያስ አደን ጋልካዮ ከሚባለው አካባባቢ ቁጥራቸው የማይታወቅ ወንዶች ጠልፈው ከወሰዷት በኋላ በቡድን ደፍረው የጣሏት ቤቷ አካባቢ ነበር። ሁኔታው ከፍተኛ ድንጋጤንና ቁጣን ያስከተለ ሲሆን ብዙዎች በሰልፍ ሃገሪቷን አጥለቅልቀውት ነበር። •‘በአስራ አራት ዓመቴ ስደፈር የሚያሳይ ቪዲዮ በወሲብ ፊልም ድረገፅ ላይ ነበር' • የአስገድዶ መደፈር ክሷን ለመከታተል የሄደችው ወጣት በእሳት ተቃጠለች • የተነጠቀ ልጅነት አስር ተጠርጣሪዎች ታዳጊዋን በመድፈር ተይዘው የነበረ ሲሆን የአካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ሶስቱን ጥፋተኛ ሆነው አግኝቷቸዋል። ግለሰቦቹን ለመጀመሪያ ጊዜ የዲኤንኤ (ዘረ መል) ማስረጃን በመጠቀም ጥፋተኛነታቸው መረጋገጡን አቃቤ ህግጋትም አሳውቀዋል። ጥፋተኛ ሆነው የተገኙት አብዲፈታህ አብዱራህማን ዋርሳሜና አብዲሻኩር ሞሃመድ ዲጌ፣ ቦሳሶ በሚገኝ አደባባይ ላይ በተኳሽ ቡድን በትናንትናው እለት በጥይት እንደተገደሉ ዘ ጋሮዌ የተባለው ድረገፅ አስነብቧል። •በህንድ በቡድን ተደፍራ የተገደለችው ዶክተር ጉዳይ ከፍተኛ ቁጣን ቀሰቀሰ ሶስተኛ ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘው አብዲሰላም አብዲራህማን በሞት የተቀጣው የአብዲፈታህ ወንድም ሲሆን ምንም እንኳን የሞት ፍርድ ቢፈረድበትም ቅጣቱ ተግባራዊ ሳይደረግበት ቀርቷል። የታዳጊዋ አይሻ አባት ኢልያስ አደን ለፑንት ላንድ መንግሥታዊ ጣቢያ እንደተናገሩት የአብዲሰላምን ቅጣት ሁኔታው እንደገና እስኪገመገም ፍርድ ቤቱ ለአስር ቀናት እንዲያዘገየው መጠየቃቸውን ነው። "እንዲህ አይነት አይቀጡ ቅጣት በተለይ የሞት ፍርድ የማያዳግም ምክር ያስተላልፋል። የሶማሊያ ሴቶችም ደህንነታቸው የተጠበቀ ይሆናል" ብለዋል አቶ አደን። መደፈርና ሌሎች ፆታዊ ጥቃቶች በሶማሊያ በቅርብ አመታት መበራከታቸውን የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ይናገራሉ። |
52889720 | https://www.bbc.com/amharic/52889720 | ትራምፕ ሩስያ ወደ ቡድን 7 ትመለስ ቢሉም አባል አገራቱ ተቃውመዋል | የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሩስያ፤ ወደ ቡድን 7 (G7) እንድትመለስ ቢፈልጉም ዩናይትድ ኪንግደም እና ካናዳ ተቃውመዋል። | ትራምፕ፤ በዚህ ወር ሊካሄድ እቅድ ተይዞለት የነበረውን የቡድን 7 ስብሰባ ለመስከረም አስተላልፈዋል። ባለፈው እሁድ በሰጡት መግለጫ የቡድን ሰባት አገራት ሩስያን ወደ ቡድኑ መልሰው እንዲቀላቅሉ ጠይቀዋል። ሩስያን ወደ ቡድኑ ለመመለስ እንዳቀዱም ለፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን በስልክ ነግረዋል። አሜሪካ በምታስተናግደው የዘንድሮ ስብሰባ፤ ካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣልያን፣ ጃፓንና ዩኬ ይገኛሉ። ስለትብብር ይወያያሉ ተብሎም ይጠበቃል። ሆኖም ግን የካናዳና ዩኬ መሪዎች የሩስያን ወደ ቡድኑ መመለስ እንደማይቀበሉ እሁድ ተናግረዋል። ሩስያ ቀድሞ ቡድን ስምንት (G8) ተብሎ ከሚጠራው የአገራት ስብስብ የተባረረችው ክሬሚያን የግዛቷ አካል በማድረጓ ነበር። ከተባረረች ስድስት ዓመት ሆኗታል። • የፌስቡክ ሠራተኞች በመሥሪያ ቤታቸው ድርጊት ተበሳጩ • ዙም መሰብሰቢያ ብቻ ሳይሆን ከሥራ ማባረሪያም ሆኗል • ትራምፕ ተቃውሞው የማይበርድ ከሆነ ወታደር እንደሚያዘምቱ ዛቱ “ሩስያ ከጂ7 የተባረረችው ክሬሚያን ስለወረረች ነው። ዓለም አቀፍ ሕግጋት መጣስ በመቀጠሏ ነው ከቡድኑ ውጪ የተደረገችው። ተመልሳም አትገባም” ብለዋል የካናዳው ጠቅላይ ሚንስትር ጀስቲን ትሩዶ። የዩኬው ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን ቃል አቀባይ፤ ሩስያ ወደ ቡድኑ ትግባ የሚል ሀሳብ ቢቀርብ፤ ድምጽን በድምጽ በመሻር መብታቸው እንደሚቃወሙ አስታውቀዋል። “ሩስያ ነውጠኛና ሰላም የሚያውኩ ድርጊቶችን እስካላቆመች ወደ ቡድኑ እንድትመለስ አንደግፍም” ብለዋል። ከሦስት ዓመታት በፊት የቀድሞ የሩስያ ሰላይ በእንግሊዝ መገደሉን ተከትሎ፤ የዩናይትድ ኪንግደምና ሩስያ ግንኙነት ሻክሯል። ዩኬ እና ካናዳ ፑቲን የቡድን ሰባትን ስብሰባ በአሜሪካ መታደማቸውን አልተቃወሙም። ከዚህ በፊት የቡድኑ አባል ያልሆኑ አገራት ስብሰባ ተሳትፈው ያውቃሉ። የቡድኑ አባል አገራት ሩስያ እንድትመለስ አንፈልግም ቢሉም፤ ትራምፕ በተደጋጋሚ ለሩስያ ድጋፋቸውን አሳይተዋል። እአአ 2018 ላይ በተካሄደ የቡድን 7 ስብሰባ “ሩስያ ብትመለስ ጠቃሚ ትሆናለች” ብለው ነበር። ባለፈው እሁድ በሰጡት መግለጫም ይህንኑ አቋም መልሰው አስተጋብተዋል። “ቡድኑ ዓለም ላይ እየተከናወነ ያለውን ነገር አይወክልም” ሲሉም፤ ሩስያ፣ ደቡብ ኮርያ፣ አውስትራሊያ እና ሕንድ ወደ ቡድኑ ይቀላቀሉ ብለዋል። የደቡብ ኮርያ እንዲሁም የአውስትራሊያ መሪዎች አሜሪካ በሚካሄደው ስብሰባ ላይ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው አስታውቀዋል። ባለፈው ሳምንት የጀርመኗ መራሔተ መንግሥት አንጌላ መርክል፤ በኮሮናቫይረስ ስጋት የቡድኑን ስብሰባ በአካል እንደማይሳተፉ አስታውቀዋል። የተሻለ ምጣኔ ሀብትን መሠረት አድርገው የተሰባሰቡት ሰባት አገራት፤ በየዓመቱ እየተገናኙ ስለ ዓለም አቀፍ አስተዳደር፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የደህንነትና የምጣኔ ሀብት ጉዳይ ይወያያሉ። አባላቱ መርሃችን የሚሉት፤ ነፃነት፣ የሰብዓዊ መብት መከበር፣ ዴሞክራሲ፣ የሕግ የበላይነትና ዘላቂነት ያለው እድገትን ነው። |
news-49348042 | https://www.bbc.com/amharic/news-49348042 | በባሕር ዳር ለበቀል የተነሳች ሴት በአንድ ኃላፊ ላይ የአሲድ ጥቃት ፈጸመች | አንዲት ግለሰብ ባሕር ዳር ውስጥ በሚገኘው የክልሉ የመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ውስጥ በሚሰሩ ኃላፊ ላይ አሲድ በመድፋት ጥቃት ፈጽማ ጉዳት እንዳደረሰችባቸው ፖሊስ ለቢቢሲ ገለጸ። | ድርጊቱ የተፈጸመው ነሐሴ 02/2011 ዓ.ም ጠዋት ላይ ሲሆን ግለሰቧ ባሕር ዳር በሚገኘው የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ የስምሪት ዳይሬክቶሬት ዳይሬከተሩን ለማግኘት እንደምትፈልግ ብትገልጽም ኃላፊው ስብሰባ ላይ እንደሆኑ ተገልጾላት ትመለሳለች። ግለሰቧ በድጋሚ በዚያኑ ቀን ከሰዓት በኋላ ተመልሳ ወደ ኃላፊው ቢሮ እንደመጣች በባሕር ዳር ከተማ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ የምርመራ የሥራ ሂደት አባል የሆኑት ምክትል ኢንስፔክተር ይስማው ታሪኩ በዕለቱ የተፈፀመውን ለቢቢሲ አስረድተዋል። • "ሌሎች ሴቶች ላይ የአሲድ ጥቃት ሳይ ይረብሸኛል፤ ህመሜን ያስታውሰኛል" ካሚላት መህዲ ግለሰቧ በ2008 ዓ.ም በህጋዊ መንገድ 'እፎይታ' በሚባል ማህበር የተመዘገበ ባጃጅ መግዛቷን እና በዚህም ለተወሰነ ግዜ የስምሪት መርሃ ግብር ወጥቶላት ባጃጇ በሥራ ላይ ተሰማርቶ መቆየቱን ተናግረዋል። ኢንስፔክተር ይስማው ጨምረውም "በኋላ ላይ ተጠርጣሪዋ 'ምክንያቱን አላውቀውም' በምትለው ሁኔታ የማህበሩ ታፔላ እንዲነሳ ተደርገ፤ ባጃጇም እንድትያዝ ተደረገች" ይላሉ። • አሲድን እንደ መሳሪያ ግለሰቧ ይህ እንዲሆን ያደረገው ቀደም ሲል የባሕር ዳር መንገድ ትራንስፖርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ የነበሩት እና አሁን የክልሉ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ የስምሪት ዳይሬክቶሬት ዳይሬከተር የሆኑት አቶ ደመላሽ ስንሻው ናቸው ብላ ማሰቧን ፖሊስ ተናግሯል። በድርጊቱ የተጠረጠረችው ግለሰብ ለፖሊስ ቃሏን እንደሰጠችው፤ ጥቃቱን ለመፈጸም አሲድ ገዝታ ነሐሴ 2 ቀን ጠዋት ወደ አቶ ደመላሽ ቢሮ ብትሄድም ስብስባ ላይ ናቸው ስለተባለች ተመልሳለች። • በህንድ ከመደፈር ለመዳን የታገሉትን ሴቶች ፀገራቸውን በመላጨት ያሸማቀቁት ታሰሩ ከሰዓት በኋላ ስትመለስ ግን አቶ ደመላሽን ቢሯቸው ውስጥ ሥራ ላይ እንዳሉ ታገኛቸዋለች። ከዚያም ተጠርጣሪዋ በጆግ ይዛው የመጣችውን አሲድ ከቅርብ እርቀት ላይ ሆና በግለሰቡ ላይ እንደደፋችና ምን እንደተከሰተ መለስ ብላ ሳታይ እየሮጠች መውጣቷን ለፖሊስ ቃሏን ሰጥታለች። ተጠርጣሪዋ ድርጊቱን ፈጽማ ለማምለጥ ብትሞክርም በአካባቢው በነበሩ ሰዎች ትብብር በቁጥጥር ሥር የዋለች ሲሆን ጥቃቱ የተፈጸመባቸው ግለሰብም ወዲያውኑ ወደ ሐኪም ቤት ተወስደው ህክምና እንዲያገኙ ተደርጓል። የተደፋባቸው አሲድ ሙሉ ለሙሉ ሰውነታቸው ላይ ስላላረፈ በግለሰቡ ላይ የከፋ ጉዳት እንዳላደረሰ የተገለጸ ሲሆን፤ ነገር ግን አሲዱ በተጎጂው ሁለት እጆች ላይ በማረፉ እጃቸው መጥቆር እና እብጠት፣ ሆዳቸው ላይ የመጥቆር ምልክቶች እንዲሁም በፊታቸው ላይም አልፎ አልፎ የመቃጠል ጉዳት ደርሶባቸዋል። ተጠርጣሪዋ ጥቃቱን ለመፈጸም የተጠቀመችበትን አሲድ ለመኪና ባትሪ በሚል እንደገዛችው ለፖሊስ የተናገረች ሲሆን ፖሊስም የአሲዱን ምንጭ ለማወቅ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ተናግሯል። • መአዛን በስለት ወግቶ ከፖሊስ ያመለጠው አሁንም አልተያዘም ጥቃቱ የተፈጸመባቸው አቶ ደመላሽን በሥራቸው ግለሰቧን ኢላማ እንዳላደረጉና ሌሎችም ከስምሪት ቦታቸው ውጪ የሚሰሩ ባጃጆችን ሥርዓት ለማስከበር ሲባል ሌሎችም እንደተያዙ ለፖሊስ ተናግረዋል። ፖሊስ በአሁኑ ወቅት የተጠርጣሪ እና የተጎጂን ቃል እንዲሁም ሌሎች ማስረጃዎችን እንዳሰባሰበና አስፈላጊውን ማስረጃና ምስክሮችን አሟልቶ መዝገቡ በፍጥነት እንዲታይ ወደ ባሕር ዳር ፍትህ ጽህፈት ቤት መላኩን ለቢቢሲ ገልጸዋል። ጥቃቱ የተፈጸመባቸው አቶ ደመላሽ ስንሻው እያደረጉ የነበረውን የህክምና ክትትል አጠናቀው ከሆስፒታል መውጣታቸውን አረጋግጠናል። |
52873328 | https://www.bbc.com/amharic/52873328 | ደቡብ አፍሪካዊያን ቢራ ጠምቷቸዋል | ደቡብ አፍሪካዊያን ከዛሬ ጀምሮ መጠጥ መግዛት ይፈቀድላቸዋል፡፡ በዚያች አገር ላለፉት ሁለት ወራት ክልከላ ተጥሎባቸው ከነበሩ ነገሮች አንዱ መጠጥ መግዛት ነበር፡፡ | ደቡብ አፍሪካ ወረርሽኙን ለመግታት በዓለም ላይ ጥብቅ የክልከላ ደንቦችን ካወጡ አገሮች ተርታ ተመድባ ቆይታለች፡፡ ከዛሬ ጀምሮ በሚላላው በዚህ ጥብቅ መመሪያ ዜጎች መጠጥ መግዛት ቢችሉም መጠጡን መጠጣት የሚችሉት ግን ቤታቸው ወስደው ነው፡፡ • በሕንድ የወር አበባ ላይ ያሉ ሴቶች ለምን ማዕድቤት እንዳይገቡ ይከለከላሉ? • በሩሲያ 380ሺ ሰዎች በኮሮና ተይዘው ሟቾች እንዴት 4ሺ ብቻ ሆኑ? • ምርጥ የጤና ሥርዓት ካላቸው አገራት አምስቱ ከኮቪድ ወረርሽኝ ጋር የመጠጥ ክልከላ ማድረግ ያስፈለገበተ ምክንያት በዚያች አገር ሰዎች ሲሰክሩ ጸብ አይጠፋምና ተጎጂዎች የሆስፒታል አልጋ ያጣብባሉ ከሚል ስጋት ሲሆን ሌላኛው ምክንያት ደግሞ ዜጎች ከቤት እንዳይወጡ ተደርጎ መጠጥ ግዢ ቢፈቀድ በተለይም በሴቶች ላይ የሚደርሰው የቤት ውስጥ ጥቃት ይበራከታል የሚል ስጋት ስለነበረ ነው፡፡ በደቡብ አፍሪካ ከመጠጥ ስካር ጋር የተያያዙ የቡድን ጸቦች በስፋት የሚመዘገቡባት አገር ናት፡፡ በደቡብ አፍሪካ በሳምንቱ መጨረሻዎች ፖሊስ ጣቢያዎችም ሆኑ በሆስፒታሎች ከመጠጥ ኃይል ጋር ተያይዘው የሚፈጠሩ ወንጀሎችና ጉዳቶች የትየሌሌ ናቸው፡፡ ሰሞኑን ከፖሊስም ሆነ ከሀኪሞች የተገኙ መረጃዎች እንደመሰከሩት የመጠጥ ሽያዥ እቀባ በተጣለባቸው ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ የወንጀል፣ የጸብና የአካላዊ ጉዳት መጠኖች በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሰው ታይተዋል፡፡ በዚህ ለሁለት ወራት በጸናው የመጠጥ እቀባ መመርያ ወንጀልንና ጥቃትን መቀነስ ቢቻልም ቢራ ጠማቂዎች፣ ውስኪ ቸርቻሪዎችና ዋይን ፋብሪካዎች መንግሥት ንግዳችን ላይ ጉዳት አድርሶብናል ሲሉ ወቅሰዋል፡፡ መንግሥት በበኩሉ እኔም እኮ ከናንተ ሽያጭ አገኝ የነበረው የግብር ገቢ ቀርቶብኛል ሲል ምላሽ ሰጥቷል፡፡ በደቡብ አፍሪካ 31ሺ ዜጎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡ |
50949852 | https://www.bbc.com/amharic/50949852 | የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ወደቤታቸው ሊመልስ ነው | የወለጋ ዩኒቨርሲቲ እስከ ረቡዕ ታህሳስ 22 2012 ዓ.ም. ድረስ ትምህርት የማይጀመር ከሆነ ተማሪዎች ወደቤታቸው እንዲሄዱ ሴኔቱ መወሰኑን አስታወቀ። | ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ታህሳስ 20/2012 ዓ.ም. ያወጣው መግለጫ ላለፉት አራት ሳምንታት ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት ለማስጀመር በተደጋጋሚ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል ይላል። • የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ወደቤታቸው ለመላክ ለምን ወሰነ? • በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንቅስቃሴ ላይ ጊዜያዊ ገደብ ተጣለ ሆኖም እስከ ታህሳስ 20/2012 ዓ.ም. ድረስ ትምህርት መጀመር አለመቻሉንና መሻሻሎች አለመታየታቸውን ማረጋገጥ ችለናል ይላል መግለጫው። በዚህም ምክንያት በሴሚስተሩና በአጠቃላይ በዓመቱ የትምህርት መርሀ ግብር ላይ ጫና ማሳደሩን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል። በመሆኑም እስከ ረቡዕ ታህሳስ 22 2012 ዓ.ም. ድረስ ትምህርት የማይጀመር ከሆነ ተማሪዎች የክሊራንስ ቅጽ በመሙላትና የሚመለከታቸው የቢሮ ሀላፊዎችን በማስፈረም እንዲሁም በእጃቸው የሚገኙ የዩኒቨርሲቲው ንብረቶችን በመመለስ የሚጠበቅባቸውን አሟልተው ግቢውን ለቅቀው እንዲወጡ ሲል የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎቹ መልእክቱን አስተላልፏል። አክሎም ትምህርት እየተከታተሉ ካሉ ተማሪዎች ውጪ ማንኛውም ዩኒቨርሲቲው የሚሰጠውን አገልግሎቶች እንደሚያቋርጥ ገልጿል። የመልሶ ቅበላ ጊዜ ደግሞ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን ወደፊት እንደአስፈላጊነቱ እንደሚገልጽ ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ሀሰን የሱፍ (ፒኤችዲ) ለቢቢሲ እንደተናገሩት ተማሪዎች እስከ ረቡዕ ድረስ ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ ፈቃደኛ ከሆኑ የመማር ማስተማሩ ሂደት ይቀጥላል። ነገር ግን ተማሪዎች የደህንነት ስጋት አለብን ወደቤታችን መሄድ እንፈልጋለን ካሉ በመመሪያው መሰረት ወደቤታቸው መሄድ ይችላሉ። '' አሁን ባለው ሁኔታ ከበድ ያለ የጸጥታ ችግር የለም፤ ስለዚህ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ነበር ጥረት ስናደርግ የነበረው። ነገር ግን ተማሪዎቹ በመቆየታቸው ደስተኞች ስላልሆኑ ሴኔቱ ይህንን አማራጭ አቅርቧል'' ብለዋል። • ዩኒቨርስቲዎች በፌደራል ፖሊስ እንዲጠበቁ መወሰኑ ተገለፀ ባለፈው ቅዳሜ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አንድ ተማሪ መገደሉን ተከትሎ ባጋጠመ አለመረጋጋት ምክንያት ተማሪዎች ወደቤታቸው እንዲመለሱ ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል። የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዝዳንት ረዳት ፕሮፌሰር አባያ ደገፋ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማቆም ያደረሳቸውን ምክንያት ለቢቢሲ ሲያስረዱ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት የተማሪዎችን ህይወት ከአደጋ ለማጠበቅ ሲል ወደቤት ለመላክ ወስኗል ብለው ነበር። |
45327508 | https://www.bbc.com/amharic/45327508 | ስቃይ የደረሰበት ኡጋንዳዊ ፖለቲከኛ ቦቢ ዋይን ተፈታ | ከሙዚቃ ሕይወት ወደ ፖለቲካ ሕይወቱን ያዞረው ኡጋንዳዊው ታዋቂ ሰው ቦቢ ዋይን ከቀናት እሥር በኋላ በዋስ እንዲለቀቅ ሆኗል። | ቦቢ ዋይንን ጨምሮ ሌሎች በሃገር ክህደት የተከሰሱ 33 ኡጋንዳዊያን ናቸው ትላንት ከሰዓት በኋላ በዋስ የተለቀቁት። 'የደሃ መንደር ፕሬዝደንት' በሚል ቅፅል ስያሜ የሚታወቀው ቦቢ ዋይን ፍርድ ቤት የቀረበው በክራንች ድጋፍ ነበር። • ለኡጋንዳዊው ሙዚቀኛና ተቃዋሚ በተደረገ ሰልፍ 70 ሰዎች ታሰሩ • ኡጋንዳዊው ሙዚቀኛ በሃገር ክህደት ተከሰሰ • የኡጋንዳ ወታደሮች ጋዜጠኛ በመደብደባቸው ሰራዊቱ ይቅርታ ጠየቀ ቦቢ ዋይንን በቁጥጥር ሥር ያዋለው የኡጋንዳ ወታደራዊ ኃይል ግለሰቡን አሰቃይቷል የሚለውን ክስ 'መሠረተ ቢስ' ሲል አጣጥሎታል። በመዝገብ ስሙ ሮበርት ኪያጉላኒ በመባል የሚታወቀው ቦቢ ዋይን የዛሬ ሁለት ሳምንት ገደማ ነበር ለደጋፊዎቹ ንግግር እያደረገ ሳለ በቁጥጥር ሥር የዋለው። ክስ ከተመሰረተባቸው ግለሰቦች መካከል አንድ የ51 ዓመት ግለሰብ ፍርድ ቤት ውስጥ ሳሉ ራሳቸውን መሳታቸውን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ ለተወሰነ ሰዓት ያክል በአንድ እግሩ ቆሞ እንደነበር የቢቢሲዋ ካትከሪን ከስፍራው ዘግባለች። ቦቢ ዋይን ለእሥር ከመዳረጉ በፊት «ይኸው እኔ መስያቸው ሹፌሬን ገደሉት» በማለት አንድ አሰቃቂ ፎቶ የትዊተር ገፁ ላይ ለጥፎ ነበር። የግለሰቡ ጠበቃዎች ደንበኛችን ስቃይና እንግልት ደርሶበታል ቢሉም የሙሴቬኒ መንግሥት ግን ወቀሳውን 'ሃሰት' ብሎታል። የተከለከለ የጦር መሣሪያ በመያዝ በሚል ክስ በወታደራዊ ፍርድ ቤት እንዲከሰስ ተፈርዶበት የነበረው ቦቢ ዋይን ኋላ ላይ ጉዳዩ በመደበኛ ፍርድ እንዲታይ ሆኖለታል፤ ክሱን የሃገር ክህደት በሚል ተቀይሯል። የ36 ዓመቱ ሙዚቀኛ ቦቢ ዋይንን ጨምሮ ሌሎቹ ተከሳሾች በፈረንጆቹ ነሃሴ 30 ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል። |
news-48199197 | https://www.bbc.com/amharic/news-48199197 | አሲያ ቢቢ፡ ከዓመታት እስር በኋላ ፓኪስታንን ለቃ ወጣች | በእስልምና ኃይማኖት ላይ ስድብ ሰንዝረሻል ተብላ ክስ የተመሰረተባት ፓኪስታኒያዊቷ ክርስቲያን አሲያ ቢቢ ከእስር ከተለቀቀች በኋላ ፓኪስታንን ለቃ መውጣቷን ባለስልጣናት አረጋገጡ። | አሲያ ቢቢ ክስ ከተመሰረተባት በኋላ ዓመታትን በእስር አሳልፋለች • ፓኪስታን ክርስትያኗን ቢቢን ከእስር ለቀቀች አሲያ ቢቢ ሙልታን በአውሮፓውያኑ 2010 ነበር እስልምና ኃይማኖትንና ነብዩ መሐመድ ላይ ስድብ ሰንዝረሻል በሚል የተከሰሰችው። ዓመታትን በእስር ያሳለፈችው ግለሰቧ እንደምትለቀቅ ከተሰማ በኋላ በርካቶች የተቃውሞ ድምጻቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል። የፓኪስታን መንግሥት ከእስር ብትለቀቅም ከሀገር እንዳትወጣ እንዲከለከል በፍርድ ቤት እንደሚጠይቅ ተናግሮ ነበር። በርካቶች አሲያ ቢቢ የእስልምና ኃይማኖትን ተሳድባለች በማለት በስቅላት እንድትገደል የሚጠይቁ ነበሩ። የአንድ እስላማዊ ቡድን መሪ ሶስቱም የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዳኞች "ሊገደሉ ይገባል" ሲል ተናግሮ የነበረ ሲሆን በጠንካራ ተቃውሞው የሚታወቀው ቲ ሊፒ ፓርቲ የቢቢ መለቀቅ ከመንግሥት ጋር ያለን ስምምነት መፍረስ ምልክት ነው ሲል መናገሩ የሚታወስ ነው። ቢሆንም በአገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክሱ የተነሳላት ባለፈው ዓመት የነበረ ሲሆን የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ በአክራሪዎች ዘንድ ተቃውሞ ገጥሞታል። ይህንንም ተከትሎ በርካታ ሐገራት ለአሲያ ቢቢ ጥገኝነት ለመስጠት ፈቃደኛ ሆነው ነበር። • ተቃዋሚዎቿ ፊት ፎቶ የተነሳችው ሙስሊም ሴት አሲያ ቢቢ ፍርድ ቤት በቀረበችበት ችሎቶች ላይ ሁሉ ጥፋተኛ እንዳልሆነች ስትናገር ቆይታለች። አሲያ ቢቢ ተብላ የምትታወቀው አሲያ ኖሬ ፓኪስታንን ለቃ የምትወጣበት መንገድ እሰከሚመቻችላት ድረስም ሚስጥራዊነቱ በተጠበቀ ስፍራ እዚያው ፓኪስታን ውስጥ ስትኖር ነበር። • "መንግሥት የሚደግፈው የሙስሊሙን ሕብረተሠብ ነው" ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የፓኪስታን ባለስልጣናት አሲያ ቢቢ ፓኪስታንን ለቃ እንደወጣች ዛሬ የገለፁ ሲሆን የሄደችበትን አገር ግን ግልፅ አላደረጉም። ይሁን እንጂ ጠበቃዋ ሳይፍ ኡል ማሉክ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ኢሲያ ቢቢ ካናዳ ገብታለች። ልጆቿም በካናዳ ጥገኝነት ተሰጥቷቸዋል። የ48 ዓመቷ አሲያ ቢቢ የአራት ልጆች እናት ስትሆን ኃይማኖት ላይ ስድብ በመሰንዘር የሞት ፍርድ ተፈርዶባት የነበረች የመጀመሪያዋ ሴት ናት። በፓኪስታን ከአውሮፓውያኑ 1990 ጀምሮ በትንሹ 65 የሚሆኑ ሰዎች በእስልምና ኃይማኖት ላይ ስድብ በመሰንዘራቸው ተገድለዋል። |
news-49069912 | https://www.bbc.com/amharic/news-49069912 | አቶ ተመስገን ጥሩነህ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ | ዛሬ ሐምሌ 15 ቀን 2011 ዓ.ም አቶ ተመስገን ጥሩነህ በአማራ ክልል ምክር ቤት የክልሉ ርዕሰ መስተዳደድር ሆነው ተሹመዋል። | አቶ ተመስገን ከክልል እስከ ፌደራል በተለያዩ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች በተለያየ የኃላፊነት ደረጃ አገልግለዋል። በቅርቡም በሚንስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚንስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ በመሆን ሲያገለግሉ ነበር። • "አሁንም እያጣራን ማሰሩም፤ መፍታቱም ይቀጥላል" ኮሚሽነር አበረ • ስለ'መፈንቅለ መንግሥት' ሙከራው እስካሁን የማናውቃቸው ነገሮች በምስራቅ ጎጃም ብቸና የተወለዱት አቶ ተመስገን ጥሩነህ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በትውልድ አካባቢያቸው ጎተራ እና ብቸና በላይ ዘለቀ ትምህርት ቤት አጠናቀዋል። የመጀመሪያ ድግሪያቸውን ከማይክሮ ሊንክ ኮሌጅ በኮምፒዩተር ሳይንስ፤ ሁለተኛ ድግሪያቸውን ደግሞ እንግሊዝ ሀገር ከሚገኘው ግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ በአመራርና አስተዳደር ተከታትለዋል። ከዚያም በአማራ ክልል የርዕሰ መስተዳድሩ የፀጥታ እና ቴክኖሎጂ አማካሪ፣ የአማራ ገጠር መንገዶች ባለሥልጣን ምክትል ሥራ አስኪያጅ፣ የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የምሥራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ፤ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን አገልግለዋል፡፡ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር እና የኢትዮ-ቴሌኮም ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ በመሆንም ሠርተዋል፡፡ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ መሥራች ከመሆን ባለፈ በዚሁ መስሪያ ቤት ከመምሪያ ኃላፊነት እስከ ዋና ዳይሬክተርነት አገልግለዋል፡፡ አቶ ተመስገን የሀገር መከላከያ ሠራዊት መረጃ ዋና መምሪያ፣ የኤሌክትሮኒክስ እና የቴክኒካል መረጃ መምሪያ ኃላፊም ነበሩ። በመከላከያ ሠራዊት ውስጥም እስከ ሻለቃነት ማዕረግ ደርሰዋል- አቶ ተመስገን ጥሩነህ። እስከ ዛሬ ሐምሌ 15/2011 ዓ.ም ድረስ በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡ አቶ ተመስገን ዛሬ ክልሉን በርዕሰ መስተዳድርነት ለማገልገል ቃለ መሃላ ፈፅመዋል። • አዴፓ እነ ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌን "የእናት ጡት ነካሾች" አለ አቶ ተመስገን የወሰንና የማንነት ጥያቄዎችን በሕግ እንዲመለሱ እና የሕግ የበላይነትን ለማስፈን እንደሚተጉ፣ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ የቱሪስት መስህቦች ላይ ከቀደመው በበለጠ ትኩረት እንደሚያደርጉ፣ ለሥራ እድል ፈጠራ፣ ለትምህርት ጥራት፣ ለመኖሪያ ቤቶች ግንባታ፣ ለኢንቨስትመንት እድገት፣ በሴቶች አቅም ማጎልበት ላይ እንዲሁም በሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ጠንክረው እንደሚሰሩ ለምክር ቤቱ ቃል ገብተዋል። ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በክልሉ ተፈፀመ በተባለው 'መፈንቅለ መንግሥት' የክልሉ ፕሬዚዳንት የነበሩት ዶ/ር አምባቸው መኮነን፣ ሌሎች የአዴፓ አመራሮችና የፀጥታ አካላት ከተገደሉ አንድ ወር በኋላ ነው ሹመቱ የተካሄደው። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የሆኑት አቶ ላቀ አያሌው ክልሉን በጊዜያዊነት ሲመሩ መቆየታቸው ይታወሳል። |
42668069 | https://www.bbc.com/amharic/42668069 | በፌስቡክ ማስታወቂያ የተሳካ ጋብቻ | የፌስቡክ ተጠቃሚ ከሆኑ እስከዛሬ የተለየ ፖስት ሳያጋጥምዎ አይቀርም። ያልተጠበቀ የጓደኝነት ጥያቄ ቀርቦልዎት ወይም ከአንድ መልዕክት ጋር ስምዎ ተያይዞ (ታግ) ተደርገው ያውቁ ይሆናል። የማይፈልጉት ፎቶ በጓደኞችዎ ተለጥፎቦዎትም ይሆናል። | አንድ ናይጄሪያዊ ያደረገው ግን ፍፁም የተለየ ነው። ቺዲማ አዴሙ ታህሳስ 21 ቀን ልታገባው የምትፈልግ ሴት ካለች ምላሽ እንድትሰጠው ፍላጎቱን ፌስቡክ ላይ አሰፈረ። የሚፈልጋት አይነት ሴት ከመጣች ምንም ጊዜ ሳያጠፋ እንደሚያገባት፣ ጋብቻው የሚፈፀምበትን እንዲሁም የሚስት ፍለጋ ማስታወቂያው የሚያበቃበትን ቀን ሁሉ በዝርዝር አስቀምጦ ነበር። ናይጄሪያዊው በርካታ ምላሾችን ያገኘ ሲሆን ሶፊ ሊጆማ የተባለች ሴት ምላሽ ግን ትኩረቱን ሳበው። ለእሱ ፌስቡክ ፖስት 'ላገባህ እፈልጋለው' የሚል መልስ ሰጠች። እሷ መጀመሪያ ነገሩን እንደቀልድ ነበር ያየችው። ነገር ግን ከናይጄሪያዊው ያገኘችው የፌስቡክ የውስጥ መልዕክትና ስልክ ህይወቷን ቀየረው። በስልክ በተነጋገሩ በሁለተኛው ቀን ከአቡጃ ተነስቶ 500 ኪሎ ሜትር እሷ ወደ ምትኖርበት ምሥራቃዊ ናይጄሪያ ተጓዘ። ከአንድ መደብር በር ላይ ቆማ ነበር የጠበቀችው። ነገሩ እንደተያዩ በፍቅር መውደቅ የሚባለው አይነት እንደሆነ ሶፊ ታስታውሳለች። ከምታውቃቸው ወንዶች ሁሉ እሱ በጣም መልከ መልካም እንደሆነ ትናገራለች። ለሁለት ሰዓት ያህል ከተነጋገሩ በኋላ እዚያው አካባቢ ይኖር የነበረ አጎቱ ጋር እንዲሄዱ ጠየቃት። ለአጎቱ ሊያገባት የሚፈልጋት ሴት እሷ እንደሆነች ነገራቸው። አጎቱም ይሁንታቸውን ገለፁ። እንደ ቺዲማ ሁሉ መላ ቤተሰቡ ጊዜ ማጥፋት አልፈለገም። ቺዲማ በመጣበት ኢግቦ ባህል መሰረት ለጋብቻ የቤተሰብ ይሁንታ ወሳኝ ነው። ለፌስቡክ ማስታወቂያው መልስ በሰጠች በስድስት ቀን ውስጥ ተጋቡ። በፌስ ቡክ ተገናኙ በባህላቸው መሰረት ተጋቡ። ባህልና ቴክኖሎጂ ሲገጣጠሙ ማለት እንዲህ ነው። |
news-50937651 | https://www.bbc.com/amharic/news-50937651 | የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ወደቤታቸው ለመላክ ለምን ወሰነ? | የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አንድ ተማሪ መገደሉን ተከትሎ ባጋጠመ አለመረጋጋት ምክንያት ተማሪዎች ወደቤታቸው እንዲመለሱ ውሳኔ አስተላልፏል። | የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዝዳንት ረዳት ፕሮፌሰር አባያ ደገፋ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማቆም ያደረሳቸውን ምክንያት ለቢቢሲ ሲያስረዱ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት የተማሪዎችን ህይወት ከአደጋ ለማጠበቅ ሲል ወደቤት ለመላክ ወስኗል ብለዋል። '' ከሀገሪቱ የፖለቲካ ሁኔታና ከግቢው ውጪ ባሉ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ምክንያት ምንም የማያውቁ ተማሪዎች ህይወታቸው እንዳያጡ በማሰብ ነው ውሳኔውን ያስተላለፍነው።'' ብለዋል • በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንቅስቃሴ ላይ ጊዜያዊ ገደብ ተጣለ • ዩኒቨርስቲዎች በፌደራል ፖሊስ እንዲጠበቁ መወሰኑ ተገለፀ በትናንት ዕለት የሶስተኛ ዓመት የባንኪንግና ፋይናንስ ተማሪ የሆነው ይሁኔ አለማየሁ ማንነታቸው ባልታወቀ ሰዎች መገደሉን ምክትል ፕሬዚዳንቱ አረጋግጠው፤ በዚህም ምክንያት በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ረብሻና ውጥረት ተባብሷል። ባለፈው ወር አንድ ተማሪ ከፎቅ ላይ ተወርውሮ መገደሉም የሚታወስ ነው። ከተማሪው ሞት ጋር ተያይዞ የተከሰተውን ግርግር ለማረጋጋት ዩኒቨርሲቲው ጥረት ቢያደርግም እንዳልተሳካ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል። ባለፉት ሁለት ሳምንታት ደግሞ በተማሪዎች መካከል የሚከሰቱ ግጭቶች ተበራክተው የነበረ ሲሆን፤ እርስ በርስ መጣላቱም ከፍቶ ስለት እስከመጠቀም ተደርሶም እንደነበረ ያስረዳሉ። '' አንድ ተማሪ በስለት ጉዳት ደርሶበት በህይወትና በሞት መካከል ሆኖ ሲሰቃይ ነበር፤ ይህንን የተመለከቱ ተማሪዎችም ወደቤታቸው ለመመለስ ፍላጎት አሳይተዋል፤ እኛም ተማሪዎቹን ለማረጋጋት ጥረት ስናደርግ ነበር።'' ብለዋል። ትናንት ህይወቱ ያለፈው ተማሪ ይሁኔ በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ብሎክ 29 በሚባል ህንጻ አካባቢ ነው ጉዳት ደርሶበት የተገኘው። '' ግጭቱ ሲከሰሰት በግቢው ውስጥ ነበርኩኝ፤ ተማሪው የደረሰበትን ጉዳት የተመለከቱ ተማሪዎች ደግሞ ከፖሊስ ጋር ግጭት ውስጥ ገብተው ነበር። ግጭቱ ተባብሶ በመቀጠሉና ከዩኒቨርሲቲው ቁጥጥር ውጭ ሆኗል።'' በማለትም ለቢቢሲ ገልፀዋል። ከዚህ በፊት በተከሰቱ ግጭቶች ምክንያት ወንበሮችና ሌሎች የትምህርት መገልገያ ቁሳቁሶች ጉዳት ደርሶባቸው የነበረ ሲሆን እነሱን የማስጠገን ስራው ሳይጠናቀቅ ይሄኛው ክስተት መፈጠሩን ምክትል ፕሬዝዳንቱ አክለዋል። ''ተማሪዎች ወደቤተሰቦቻቸው ተመልሰው እረፍት እንዲያገኙና በአልንም በዛው እንዲያከብሩ በማለት ላልተወሰነ ጊዜ ከዩኒቨርሲቲው ግቢ ውጪ እንዲያሳልፉ እኛ ደግሞ የተፈጸመውን ወንጀል አጣርተን እርምጃ እንድናስወስድ ሴኔቱ ወስኗል።'' በማለትም አስረድተዋል። በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ውስጥ ደግሞ ተማሪዎችን ወደቤተሰቦቻቸው የመመለስ ስራውን እንደሚጀምሩ ገልፀው፤ "በአሁኑ ሰአት ከ2 እስከ 3 ሺ የሚደርሱ ተማሪዎች በግቢው ውስጥ አሉ ሲሆን በመቆየታቸው ደስተኞችም አይደሉም።'' ከዚህ በፊት ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደግቢው ተመልሰው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ጥሪ ሲያደርግ ነበር። አሁን ደግሞ ከአንድ ተማሪ ሞት ጋር ተያይዞ ተማሪዎች በድጋሚ ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ መወሰኑ ችግሩ ምን ያክል አሳሳቢ መሆኑን ማሳያ ነው። • ከ20 ዓመት በኋላ የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆናል? ''ተማሪዎቹን ከማጓጓዝ ጋር በተያያዘ ቢያንስ እስከ አዲስ አበባ አድርሰናቸው ሌሎች ተቋማት ደግሞ ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲያደርሷቸው እናደርጋለን፤ ዩኒቨርሲቲውም ከሰኞ ታህሳስ 20 2012 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ አገልግሎቱን ያቋርጣል።'' ብለዋል ምክትል ፕሬዝዳንቱ። ስለ ሟች ተማሪ የምናውቀው ምዕራብ ወለጋ የተወለደው ይሁኔ፣ ያደገው ያለ አባት ሲሆን እናቱ በእንጨት ለቀማ ተሰማርተው ነው ያስተማሩት። በአሁኑ ሰዓት የመመረቂያ ጽሁፉን ለማጠናቀቅ እየሰራ እንደነበር ምክትል ፕሬዝዳንቱ አስታውሰዋል። ተማሪ ይሁኔ ማን እንደገደለው እርግጠኛ የሆነ መረጃ ማግኘት ባይቻልም የተለያዩ መረጃዎች ለዩኒቨርሲቲው እንደደረሱትም አክለዋል። ''የመረጃዎቹን ትክክለኛነት ለማጣራት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር እየሰራን ነው።'' የሆስፒታል መረጃ ደግሞ ተማሪው ድብደባ ከተፈጸመበት በኋላ ለህክምና ሲወሰድ መኪና ውስጥ ህይወቱ ማለፉን ያሳያል። |
news-53935479 | https://www.bbc.com/amharic/news-53935479 | ፖሊስ፡ ኢዜማ "መስፈርት ባለማሟላቱ" ስብሰባውን መከልከሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ | የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ አለ ስላለው "የመሬት ወረራ እና ኢፍትሃዊ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እደላን" በተመለከ ሊሰጥ የነበረው መግለጫ ተከለከለ። | ፓርቲ ዛሬ [አርብ] ረፋድ አምስት ሰዓት ላይ በራስ ሆቴል ሊሰጠው የነበረው መግለጫ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በፖሊስ በመከልከሉ መስተጓጎሉን የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ ለቢቢሲ ገልጸዋል። አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ መግለጫው እንዲቋረጥ የተደረገው የፖርቲው አመራሮች ፈቃድ ሳይኖራቸው ስብሰባ ማድረግ ስለማይችሉ መሆኑን ገልጿል። አቶ ናትናኤል ጋዜጣዊ መግለጫውን በተመለከተ ከዚህ ቀደም መግለጫ ሲሰጡ እንደሚያደርጉት ሁሉ ቀድመው ለሆቴሉ ማስታወቃቸውንና ለሰላም ሚኒስቴርም ደብዳቤ ማስገባታቸውን ገልፀውልናል። ፓርቲው መግለጫውን ሊሰጥ የነበረው በአዲስ አበባ ውስጥ የሚደረግ "የመሬት ወረራን" እና "የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኢፍትሃዊ እደላ"ን በተመለከተ የሚደርሱ ጥቆማዎችን መሰረት በማድረግ ጥናት እንዲያደርግ በፓርቲው ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የሚመራ አንድ ኮሚቴ ተቋቁሞ ጥናት ካደረገ በኋላ፣ ውጤቱን ይፋ ለማድረግ እንደነበር አቶ ናትናኤል አስታውቀዋል። በፖሊስ የተከለከለው የዛሬው መግለጫም የኮሚቴውን የጥናት ውጤት ለሕዝብና ለጋዜጠኞች ይፋ ለማድረግ ያለመ እንደነበር የፓርቲው የሕዝብ ግንኑነት ኃላፊ አስረድተዋል። ይሁን እንጂ መግለጫውን ለመስጠት ሆቴሉ ቦታውን አዘጋጅቶ፤ ጋዜጠኞችም በቦታው ደርሰው፤ እነርሱም በቦታው ቢገኙም በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጋዜጣዊ መግለጫውን እንዳያደርጉ መከልከላቸውን ተናግረዋል። በዚህም ምክንያት ጋዜጣዊ መግለጫው ሳይደረግ ቀርቷል ብለዋል። ፖሊስ የሰጣቸውን ምክንያት የጠየቅናቸው አቶ ናትናኤል፤ "መግለጫውን ማድረግ እንደምትችሉ ከበላይ አካል ትዕዛዝ ይምጣልን" የሚል መልስ እንደሰጧቸው እና የበላይ አካል ካሏቸው አካላት መካከል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የፀጥታና አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊን መጥቀሳቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል። በዚህም መሰረት ከተጠቀሱት አካላት አንዳንዶችን በአካል ማግኘት ቢችሉም ትዕዛዙን መስጠት ግን አልቻሉም ብለዋል። ከዚህ በፊት ኢዜማ በአዲስ አበባ የሚደረግ "የመሬት ወረራ እና ኢፍትሃዊ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እደላ" ጋር ተያይዞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማብራሪያ እንዲሰጠው ቢጠይቅም ምላሽ አለማግኘቱን አቶ ናትናኤል አስታውሰዋል። ማብራሪያ እንዲሰጠው የጠየቀው የጥናት ቡድኑ ያገኛቸውን ውጤቶች በማያያዝ በጉዳዩ ላይ ያላቸውን ምልከታ ለማካተት በማሰብ እንደነበር አክለዋል። "ሪፖርቱን ከአንድ ወገን ብቻ ሳይሆን፤ ከሁሉም ወገን መረጃ ሰብስቦ ማካተት ተገቢ ነው፤ በሚል እምነት በእነርሱ በኩል ያለውን መረጃ ለማካተት ነበር የጠየቅነው" ብለዋል አቶ ናትናኤል። ደብዳቤውን ለአዲስ አበባ ከንቲባ ጽህፈት ቤት፣ ለቤቶች ልማት ኤጀንሲ እና ለመሬት ልማት ቢሮ ማስገባታቸውን ገልፀው፤ የከንቲባ ጽ/ቤት ደብዳቤውን ተቀብሎ ምላሽ አለመስጠቱን፤ ሁለቱ መሥሪያ ቤቶች ደግሞ ደብዳቤውን ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ገልፀዋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ የሆኑት ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ ለቢቢሲ ፓርቲው መግለጫውን እንዳይሰጥ የተከለከለው "ማሟላት የነበረበትን መስፈርት ባለማሟላቱ " መሆኑን ተናግረዋል። ዋና ኢንስፔክተሩ ኢትዮጵያ ያለችው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ መሆኑን በማስታወስ፣ በዚህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት ስብሰባዎች መካሄድ ያለባቸው ለኮሮናቫይረስ በማያጋልጥ ሁኔታ መሆኑን ተናግረዋል። ነገር ግን ይህንን ባላሟላ መልኩ ስብሰባዎችን ማድረግ "የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መጣስ በመሆኑ" ፖሊስ ስብሰባውን መከልከሉን ተናግረዋል። ፓርቲው ፈቃድ አለማግኘቱን የገለፁት የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያው ፈቃድ በሚያገኙበት ወቅት ጥበቃም ስለሚደረግላቸው "ያኔ ስብሰባውን ማካሄድ ይችላሉ" ብለዋል። ፓርቲው አስፈቅደናል ደብዳቤ እስኪመጣ ድረስ ስብሰባ እናካሄድ ማለቱን በመጥቀስም "ፈቃድ ሳይኖራቸው ስብሰባ ማድረግ ስለማይችሉ እና መስፈርቱን ስላላሟሉ ስብሰባው ተከልክሏል" ሲሉ ምላሻቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። |
news-55484473 | https://www.bbc.com/amharic/news-55484473 | ፍትህ ለዓለማችን 'ታዋቂው ዘፈን' አቀናባሪ | በዝምባቡዌያውያን ዘንድ እንደ ሙዚቃ አባት የሚቆጠረው ሙንያ ቻኔስታ አሜሪካዊያን አንድ የሙዚቃ ሥራን 'የኔ ነው'፤ 'የኔ ነው' ሲባባሉ ሲመለከት አንዳች ነገር ወረረው። | ሙዚቃው 'ዘ ላየን ስሊፕስ ቱናይት' ይሰኛል። ስለአንበሳ ከተሠሩ ሙዚቃዎች በዓለም ተወዳጁ ነው ይባልለታል። የሙዚቃው የመጀመሪያ መጠሪያ ምቡቤ ነው። የዚህ ሙዚቃ አቀናባሪ ደቡብ አፍሪካዊው ሶሎሞን ሊንዳ የሚላስ የሚቀመስ አጥቶ በፈረንጆቹ 1962 ነው የሞተው። በዚህ ጥዑም ዜማ ምክንያት አሜሪካውያን አርቲስቶች ብዙ ሲባጠቁ ሶሎሞን ግን በኩላሊት ሕመም ምክንያት በሆስፒታል አልጋው ላይ ሲሰቃይ ነበር። በፈረንጆቹ 2019 ኔትፍሊክስ በተሰኘው የበይነ መረብ ፊልም ማከራያ ገፅ ላይ የተለቀቀ አንድ ዘጋቢ ፊልም የዚህን ሙዚቃ አመጣጥ ይቃኛል። በዚህ ዘጋቢ ፊልም ላይ ደቡብ አፍሪካዊው ፀሐፊ ራያን ማላን ታዋቂው ሙዚቃ የሶሎሞን ሥራ እንደሆነ አብጠርጥሮ ያስረዳል። ሶሎሞን ይህን ሙዚቃ ከዙሉ ብሔረሰብ ሕብረ ዘማሪዎች [አካፔላ] ጋር በመሆን ነው የሠራው። ይህ የሙዚቃ ዲዝኒ የተባለው የፊልም አምራች በ1994 የለቀቀው ዝነኛ የካርቱን ፊልም 'ዘ ላየን ኪንግ' ማጀቢያ ነው። ነገር ግን የሶሎሞን ቤተሰቦች አሁንም በድህነት እየማቀቁ ነው። ቻኔስታ ይህን ዘጋቢ ፊልም ከተመለከተ በኋላ ልቡ በጣም እንደተነካ ይናገራል። አፉን በእጁ ሸፍኖ ግን አልተቀመጠም። ስለ ሶሎሞን ማጥናት ጀመረ። ሶሎሞን በፈረንጆቹ 1939 ጆሃንስበርግ በሚገኘው ኢቭኒንግ በርድስ የሙዚቃ ስቱዲዮ ይሠራ ነበር። በዚህ ወቅት ነው ይህን ሙዚቃ ከሕብረ ዘማሪዎቹ ጋር በመሆነ የሠራው። "ለመጀመሪያ ጊዜ የተሠራው ሥራ አሁን ላይ የባለቤትነት መብት የለውም። የሕዝብ ሥራ ነው ማለት ነው። ያኔ ነው ሁሉ ነገር የሚጀምረው።" የሙዚቃውን ቃና እያቃና ይህን ዘመን ተሻጋሪ ሥራ የሠራው ሶሎሞን በወቅቱ ለሙዚቃው 10 ሺሊንግ ነበር የተከፈለው። ነገር ግን ይህ ሥራ በ1940ዎቹ ታዋቂነቱ እየጨመረ መጣ። ይህ ሙዚቃ ባህር ተሻግሮ አሜሪካ ገባ። በወቅቱ በሐገረሰብ ሙዘቃ አሜሪካዊያንን ሲያስጨፍሩ የነበሩት ዘ ዊቨርስ ህን ሙዚቃ ተንተርሰው የራሳቸውን ሥራ ለሕዝብ አቀረቡ። የነሱ ሥራ መጠሪያው ዊሞዌህ ነበር። በሶሎሞን ሥራ ላይ ሕብረ ዘማሪዎቹ 'ዊዩምቡቤ' እያለ ሲዘፍኑ የሰሙት አሜሪካዊያኑ ሙዚቀኞች 'ዊሞዌህ' መስሏቸው በዚህ ሰየሙት። 'ዊዩምቡቤ ማለት በዙሉ ቋንቋ 'አንተ አንበሳ ነህ' ማለት ነው። የሶሎሞንን ሕይወት ያጠናው ቻኔስታ ሙዚቃው የተሰራው በደቡብ አፍሪካ በልጅነት ዘመን እረኞች ከአንበሳ ጋር ያላቸውን ትንቅንቅ ለማሳየት ነው ይላል። የሐገረሰብ ሙዚቀኞቹ ይህን ሙዚቃ ለአሜሪካዊያን ጆሮ እንዲስማማ አድርገው የሠሩት በ1950ዎቹ ነው። በ1960ዎቹ አሜሪካዊው የሙዚቃ ግጥም ገጣሚ ጆርጅ ዴቪድ [In the jungle, the mighty jungle, the lion sleeps tonight] የሚል እንግሊዝኛ ግጥም አክሎበት ዘ ቶክንስ ለተሰኘው ባንድ ሰጠው። ይህ 'ዘ ላየን ስሊፕስ ቱናይት' የተሰኘው ሥራ ነው አሁን የዚህ ሙዚቃ የመብት ባለቤት። ቻኔስታ ምቡቤ የተሰኘውን የመጀመሪያውን ሙዚቃ እንደ አዲስ ሠርቶ ለሕዝብ ማቅረብ ይፈልጋል። "ከሶዌቶ ጎስፕል ኳየር ጋር የዚህን ሙዚቃ ክብር ለመመለስ እየሠራሁ ነበር" ይላል ለሶኒ የሚሠራው የሙዚቃ አቀናባሪው ቻኔስታ። ነገር ግን ይህ አልሳካ ሲለው ዘ ማሆቴላ ክዊንስ እየተባሉ ከሚጠሩት ደቡብ አፍሪካዊያኑ ሴት አቀንቃኞች ጋር ለመሥራት አቅዷል። ከእነዚህ ሙዚቀኞች ባለፈው ከሁለት 'ዲጄዎች' ጋር ተባብሮ ዘመናዊ ቅመም ሊያስገባበት አቅዷል። ቻኔስታ ከዚህ ሙዚቃ ገቢ 45 በመቶው ለሶሎሞን ቤተሰቦች የሚሆን ነው ይላል። ምንም እንኳ አሜሪካዊያኑ ሙዚቀኞች እንደሚያገኙት ረብጣ ዶላር ባይሆንም ምናልባትም ሶሎሞን ሊንዳ በቻኔስታ ሥራ ፍትህ ያገኘ ይሆናል። |
Subsets and Splits
No saved queries yet
Save your SQL queries to embed, download, and access them later. Queries will appear here once saved.