id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
54869789
https://www.bbc.com/amharic/54869789
ሥነ -ምግብ፡ ህጻናት በአመጋገብ ምክንያት ቁመታቸው በ20 ሴንቲ ሜትር ሊያጥር ይችላል
ህጻናት በአመጋገብ ምክንያት ቁመታቸው በ20 ሴንቲ ሜትር ሊያጥር እንደሚችል ተጠቆመ።
በደካማ የአመጋገብ ስርዓት ምክንያት ዕድሜያቸው ለትምህርት በደረሱ ሕፃናት መካከል የ20 ሴ.ሜ አማካይ የቁመት ልዩነት እንዲኖር አስተዋፅዖ ሊያበረክት ይችላል ተብሏል። በ2019 ጥናት ረዣዥሞቹ የ19 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ወንዶች በኔዘርላንድስ (183.8 ሴ.ሜ ) ሲኖሩ እና አጭሩ ደግሞ በቲሞር ሌስቴ (160.1ሴ.ሜ) እንደሚኖር ተዘግቧል። ጥናቱ በዘ ላንሴት የሕክምና መጽሔት ነው ይፋ የተደረገው። እንደ ተመራማሪዎቹ ከሆነ በዓለም ዙሪያ በህፃናት ቁመት እና ክብደት ላይ የታዩ ለውጦችን መከታተል የሚመገቡትን የተመጣጠነ ምግብ እና አካባቢያቸው ምን ያህል ጤናማ ነው የሚለውን ለማወቅ ስለሚረዳ አስፈላጊ ነው። የምርምር ቡድኑ እ.አ.አ ከ1985 እስከ 2019 ባለው ጊዜ ውስጥ ከ2000 በላይ ጥናቶች የተካተቱ ከ5 እስከ 19 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ከ65 ሚሊዮን በላይ ሕፃናትን እና ታዳጊዎችን መረጃ ተንትኗል። በ2019 በሰሜን-ምዕራብ እና በመካከለኛው አውሮፓ (ለምሳሌ በኔዘርላንድስ እና በሞንቴኔግሮ ያሉ) ሕፃናት እና ታዳጊዎች በዓለም ላይ በአማካይ ረዥሞች መሆናቸውን ለማወቅ ችለዋል። በአማካይ አጫጭር የሆኑት የ19 ዓመት ዕድሜ ወጣቶች ደግሞ በደቡብ እና በደቡብ ምስራቅ እስያ፣ በላቲን አሜሪካ እና በምስራቅ አፍሪካ ይኖራሉ። እ.ኤ.አ. በ2019 ትንታኔ እንደሚያመለክተው፦ ጤናማ ክብደት ያለው ትርፍ ጥናቱ ከዚህ በተጨማሪም የህፃናቱን ቁመት ካላቸው ክብደት ጋር ያለው ምጥጥን (ቢኤምአይ) ጤናማ ስለመሆን አለመሆኑም ተመልክቷል። እንደ ተመራማሪዎቹ ትልቁ ቢኤምአይ ያላቸው ታዳጊዎች በፓስፊክ ደሴቶች፣ በመካከለኛው ምስራቅ፣ በአሜሪካ እና በኒው ዚላንድ ይኖራሉ። በጣም ዝቅተኛ ቢኤምአይ ያላቸው የ19 ዓመት ወጣቶች የሚኖሩት እንደ ሕንድ እና ባንግላዴሽ ባሉ የደቡብ እስያ አገሮች ውስጥ ነው። በጥናቱ በጣም ዝቅተኛ እና ከፍተኛ ቢኤምአይ ባሉባቸው ሀገሮች መካከል ያለው ልዩነት 25 ኪ.ግ ገደማ መሆኑን ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል። በአንዳንድ አገሮች ሕፃናት በአምስት ዓመታቸው ጤናማ ቢኤምአይ ቢኖራቸውም ዕድሜያቸው 19 ዓመት ሲሆን ከመጠን በላይ የመሆን ዕድሉ ሰፊ ነው።
41738975
https://www.bbc.com/amharic/41738975
ሙጋቤ ሹመቱን ሀገራቸው ትምባሆ አምራች ስለሆነች አይቀበሉም ነበር።
የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ የዓለም ጤና ድርጅት የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ሹመትን አገራቸው የትምባሆ አምራች ከሚባሉ አንዷ በመሆኗ ሹመቱን ለመውሰድ በጭራሽ ፈቃደኛ እንደማይሆኑ መንግስታዊው ጋዜጣ ሄራልድ የመንግስት ቃል አቀባይ የሆኑትን ጆርጅ
ቻራምባን በመጥቀስ ዘግቧል። ሙጋቤ የሹመቱን ዜና የሰሙት በመገናኛ ብዙኃን ሲሆን በኦፊሴያላዊ ደረጃ ምንም ጥያቄ ያልቀረበ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ "ጉዳዩን አሳፋሪ ነው " ሲሉ ጆርጅ ቻራምባ ተናግረዋል። ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር በመሆን ሲሾሙ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ናቸው። የዓለም ጤና ድርጅት ትምባሆ ላይ ግልፅ አቋም ያለው ሲሆን ሙጋቤም ከአገሪቷ ብሔራዊ ፍላጎት ጋር የማይጣጣም ዘመቻን በመከተል ዋነኛ የገንዘብ ምንጭ የሆነውን ትምባሆን ከማብቀል፣ ከመሸጥ እንደማትቆጠብ ተናግረዋል። ዚምባብዌ የትምባሆ ምርቷን ታቁም የሚለውን ሙጋቤ አይስማሙም "ምክንያቱም የሲጋራ አጫሾች ማጨስ ይፈልጋሉ፤ ከሲጋራ በላይ መጥፎና ገዳይ የሆኑ መጠጦች እንደነ ዊስኪና ቢራ በዓለም ይመረታሉ፤ ይሸጣሉም" በማለት ጆርጅ ቻምባራ ተናግረዋል። በአለም ዓቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የትምባሆ አምራች ከሚባሉ አገራት ዚምባብዌ አንዷ ናት ዶክተር ቴድሮስ የሙጋቤን ሹመት ባለፈው ሳምንት ያስተላለፉት የማይተላለፉ በሽታዎችን ለመከላከል በአቻዎቻቸው ላይ ተፅእኖ ማሳደር ይችላሉ በሚል ነበር። የእንግሊዝና የካናዳ መንግስታትን ጨምሮ ከፍተኛ ዓለም አቀፍ ውግዘት ስለደረሰባቸውም ሹመቱን ቀልብሰውታል። አራት አስርት ዓመታት ሊደፍን ትንሽ በቀራቸው አመራር የመጀመሪያዎቹ 20 ዓመታት ሙጋቤ የተሻለ የጤና ስርዓትን መዘርጋት ችለው ነበር። ከዚምባብዌ የኢኮኖሚ ማሽቆልቆል ጋር ተያይዞ የጤና ስርዓቱም ከፍተኛ ተፅእኖ ደርሶበታል። የህክምና ባለሙያዎች ያለደሞዝ በሚሰሩበት፤ መድኃኒቶች በከፍተኛ ሁኔታ በሚያጥሩበት ሁኔታ በተቃራኒው ሙጋቤ ህክምናን ለመሻት ወደውጭ ይጓዛሉ።
50400832
https://www.bbc.com/amharic/50400832
ስለ ወሲብ እንዲያስቡ የማይፈቀድላቸው የኢራን ተቃዋሚዎ ቡድን አባላት
የኢራን መንግሥት ዋነኛ ተቃዋሚ ቡድን የሆነው ሙጃሂዲን-ኢ-ኻልቅ አባላት ለስድስት ዓመታት መቀመጫቸው አልባኒያ አድርገው ቆይተዋል። ነገር ግን በርካታ አባላት በየቀኑ ቡድኑን ጥለው ይኮበልላሉ። ምክንያታቸው ደግሞ የቡድኑ ሕግ እጅግ ጠበቅ ያለ መሆኑ ነው።
ቡድኑ፤ አባላቱ ከወሲብ እንዲቆጠቡ እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ያላቸው ግንኙነትም የተገደበ እንዲሆን ያስገድዳል። ይህንን ቡድን ለመቀላቀል ወደ አልባኒያ ዋና ከተማ ቲራና ቢመጡም ያላሰቡት ገጥሟቸዋል። «ከባለቤቴና ከልጄ ጋር ካወራሁ 37 ዓመታት አለፈኝ። የሞትኩ መስሏቸው ነበር። 'ኧረ አለሁ፤ አልባኒያ እየኖርኩ ነው' ስላቸው አለቀሱ።» ከበርካታ ዓመታት በኋላ ቤተሰቦቹን በስልክ ያገኘው የ60 ዓመቱ ጎላም ሚራዚ ከሁለት ዓመት በፊት ነበር ቡድኑን ጥሎ የሸሸው። አሁን ቲራና ውስጥ ከተቃዋሚም ከመንግሥትም ጎራ ሳይሆን ይኖራል። የተቃዋሚው ቡድን አባላት ግን ለኢራን መንግሥት እየሰለለ ነው ሲሉ ይጠረጥሩታል። ኤምኢኬ በሚል ቅጥያ የሚታወቀው ይህ ተቃዋሚ ቡድን እጅግ የከፋ ታሪክ ያለው ነው። እስላማዊ ማርክሲስት የነበረው ቡድን የ1979 [በግሪጎሪ አቆጣጠር] የኢራን አብዮትን ደግፎ ከአያቶላህ ኮሚኒ ጋር ቢያብርም የኋላ ኋላ ቁርሾ መፈጠሩ አልቀረም። የዛኔ ነው የቡድኑ አባላት ሕይወታቸውን ለማቆየት ሽሽት የጀመሩት። ጎላም ሚራዚ የኢራን ጦር ሠራዊት አባል ነበር። በኢራን - ኢራቅ ጦርነት ወቅት በሳዳም ሁሴን ወታደሮች ተይዞ ኢራቅ ውስጥ ለ8 ዓመታት በእሥር ከረመ። ከዚያ ሲወጣ ነው የተቃዋሚውን ጎራ የተቀላቀለው። ኤምኢኬ መሸሸጊያውን አልባኒያ ካደረገ በኋላ በመቶዎች የሚቆጠሩ አባላት ኮብልለዋል። አንዳንዶቹ ለሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ገንዘብ ሰጥተው ወደ ሌሎች የአውⶂጳ ሃገራት ተሰደዋል። ሚራዚን ጨምሮ በርካቶች ግን አሁንም አልባኒያ ይኖራሉ። ሃገር የላቸውም፤ ሥራም ማግኘት አይችሉም። ከኢራቅ ወደ አልባኒያ ኤምኢኬ በአውሮጳ እና በዩናይትድ ስቴትስ አሸባሪ ቡድን ተደርጎ ይቆጠር ነበር። ሳዳም ሁሴን የቡድኑ ቀንደኛ ደጋፊና አቃፊ ነበሩ። ሳዳም ሁሴን ሲገደሉ ግን ቡድኑ ብቻውን ቀረ። አባላቱን እያሳደዱ የሚያጠቁም በዙ። ይሄኔ ነው የአሜሪካ መንግሥት 3 ሺህ ገደማ የኤምኢኬ አባላትን ከአልባኒያ መንግሥት ጋር በተደረገ ስምምነት ወደ ቲራና ያጋዘው። ይህ የሆነው ከስድስት ዓመታት በፊት ነው። ለሚራዚና ጓደኞቹ ሕይወት አልባኒያ ውስጥ ለየት ያለ ነበር። ሚራዚ አልባኒያ ውስጥ ታዳጊዎች እንኳ ሳይቀር የእጅ ስልክ ይዘው ሲመለከት መገረሙ አልቀረም። የቡድኑ አባላት እንደልባቸው መውጣት መግባት ጀመሩ። አንፃራዊ ነፃነት ያጣጥሙም ጀመር። ሌላኛው የቡድኑ አባል የነበረው ሃሳን ሄይራኒ ከሚኖሩበት ሕንፃ ጓሮ ስፖርት እንድንሠራ አለቆቻችን ያዙን ነበር ሲል ያወሳል። ሄይራኒ እና ጓደኞቹ ግን ተደብቀው በመውጣት 'ኢንተርኔት ካፌዎችን' ይጎበኛሉ። ቤተሰቦቻቸውንም ያናግራሉ። ከሁለት ዓመት በፊት ግን ኤምኢኬ የአድራሻ ለውጥ አደረገ። ከዋና ከተማዋ 30 ኪሎ ሜትር ራቅ ብሎ ከሚገኝ ሥፍራ ላይ ዋና መናኸሪያውን አደረገ። በብረት አጥር ወደ ተሸበበው አዲስ ሕንፃ ለመግባት ፈቃድ ማግኘት ግድ ይላል። ባለፈው ሐምሌ ኤምኢኬ 'ኢራንን ነፃ ትውጣ' የተሰኘ ዝግጅት አዘጋጅቶ በርካቶች ተገኝተው ነበር። የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጠበቃ ሩዲ ጉሊያኒም እንግዳ ነበሩ። የቡድኑ ማኒፌስቶ በኢራን ሰበዓዊ መብት እንዲከበር፤ የፆታ እኩልነት እንዲሰፍንና አሳታፊ ዴሞክራሲ እንዲሰራፋ ያትታል። ሃሰን ሄይራኒ ግን ምኑም አይዋጥለትም። ቡድኑን ጥዬ የኮበለልኩት አመራሮቻችን ጨቋኝ ስለሆኑ ነው ይላል፤ በተለይ ደግሞ የግል ሕይወትን በተመለከተ ይላል በ20ዎቹ ዕድሜው ላይ ሳለ ቡድኑን የተቀላቀለው ሄይራኒ። «አንዲት ማስታወሻ ደብተር ነበረችን። ወሲብን የተመለከተ ምንም ዓይነት ነገር ቢያጋጥመን እንድንፅፈበት ተብሎ የተሰጠን። ለምሳሌ 'ዛሬ ጥዋት ብልቴ ቆሞ ነበር' ብለን እንፅፋለን።» ኤምኢኬ የፍቅር ግንኙነትና ትዳር አይፈቅድም። በቀደመው ጊዜ ግን እንዲህ አልነበረም። ባለትዳሮች ልጆቻቸውን ይዘው ይቀላቀሉም ነበር። ነገር ግን ከኢራን ወታደሮች ጋር በነበር ውጊያ ኤምኢኪ መሸነፉን ተከትሎ ሕግ እንዲጠብቅ ሆነ። በፍቅር ግንኙነቶች ምክንያት መዘነጋት መጥቷል ያሉ አዛዦች ነገሩን አከረሩት። ትዳሮች ፈረሱ፤ ሕፃናት ወደ መጡበት ተላኩ። ማስታወሻ ደብተሯ ላይ ግላዊ ሕልሞቻቸውን ሳይቀር መፃፍ ግዴታ ነው። «ለምሳሌ ቴሌቪዥን ላይ ሕፃናት አይቼ 'አኔም ልጆች በኖሩኝ ብዬ ተመኘሁ' ብለን እንፅፍ ነበር» ይላል ሄይራኒ። በየቀኑ ስብሰባ ይካሄዳል፤ ወታደሮቹም የፃፉትን በአዛዦቻቸው ፊት ማንበብ አለባቸው። ሄይራኒ ሸሽቶ የመጣውን የካምፕ ኑሮው ከጆርጅ ኦርዌል መፅሐፍ ጋር ያመሳስለዋል፤ 'አኒማል ፋርም' ወይም የእንስሳት ገበያ። ቢቢሲ ኤምኢኬን ለማነጋገር ያደረገው ጥረት ቡድኑ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ምክንያት አልተሳካም። ቲራና የሚኖሩት ሙጃሂዲኖችን ለመግደል የኢራን መንግሥት ለመግደል እያሤረ ነው ሲል የአውሮጳ ሕብረት ይኮንናል። በአልባኒያ የኢራን ኤምባሲ ስለጉዳዩ ለቢቢሲ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል። ሚራዚም ብቻ ሳይሆን ሄይራኒም ለኢራን መንግሥት ይሰልላል ተብሎ ይጠረጠራል። ሁለቱም ክሱን ያስተባብላሉ። ሁለቱም አልባኒያ ውስጥ ኑሯቸውን መሥርተው ይኖራሉ። የ40 ዓመቱ ሄይራኒ አንዲት አልባኒያዊት የፍቅር ጓደኛ አለችው። ጎላም ግን ጤና ይጎለዋል። ከቤተሰቡ መለየቱ ሁሌም ያንገበግበዋል። ገና በጨቅላነቱ ጥሎት የሄደው ልጁ አሁን 40 ዓመት ሆኖታል። በዋትስአፕ ቢነጋገሩም መቼም በአካል እንደመገናኘት አይሆንም። የኢራን ኤምባሲ ሄዶ ለእርዳታ እጁን ዘርግቷል። ኢራን የሚገኙት ቤተሰቦቹም መጥተው መጠየቅ እንዲቻላቸው አሳስበዋል። ሰሚ ጆሮ ያገኙ ግን አይመስልም። ሚራዚ ግን ተስፋ ያደርጋል። ዜግነት አልባ ቢሆንም፤ ፓስፖርት ባይኖረውም ሕልሙን ግን አልተነሳም።
news-51322212
https://www.bbc.com/amharic/news-51322212
አምስት የአፍሪካ አየር መንገዶች ወደ ቻይና የሚያደርጉትን በረራ አቋረጡ
በቻይና በተስፋፋው የኮሮናቫይረስ ምክንያት አምስት አየር መንገዶች ወደ ቻእና የሚያደርጉትን በረራ አቋረጡ።
የኬንያ፣ የሩዋንዳ፣ የማዳጋስካር፣ የሞሪሸስ እና የሞሮኮ አየር መንገዶች ወደ ቻይናና ከቻይና ያደርጓቸው የነበሩትን ሁሉንም ጉዞዎች ለጊዜው ማቆማቸውን አስታወቀዋል። አየር መንገዶቹ ከዚህ ውሳኔያቸው በፊት ወደ ቻይና ወይም ከቻይና ለመጓዝ ትኬት ቆርጠው የነበሩ ደንበኞቻቸውን ገንዘብ ለመመለስ ወይም በሌላ መስመር እንዲመጡ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። በአፍሪካ ካሉ ጥቂት ግዙፍ አየር መንገዶች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን ትናንት ሐሙስ እንዳስታወቀው ወደ ቻይና የሚያደርጋቸው ሁሉም በረራዎቹ ይቀጥላሉ። አየር መንገዱ "መንገደኞቹንና ሠራተኞቹን" ካለው ስጋት ለመጠበቅ ከቻይናና ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር እየሰራ ነው። • በኮሮናቫይረስ ሳይያዙ አይቀሩም ተብለው የተጠረጠሩት ኢትዮጵያውያን ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸውን ተነገረ • ኮሮናቫይረስ፡ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች በቻይና • "ኮሮናቫይረስ በአሜሪካ የሥራ ዕድልን ሊያሳድግ ይችላል" የዓለም የጤና ድርጅት የኮሮናቫይረስ የወቅቱ ዋነኛ የጤና ስጋት መሆኑን ማወጁን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና በሚያደርጋቸው በረራዎች ላይ እስካሁን የለወጠው ነገር የለም። ትናንት የዓለም የጤና ድርጅት የኮሮናቫይረስ አሳሳቢ መሆኑን ቢያውጅም፤ ወደ ቻይና የሚደረግ ጉዞና ንግድን የሚያስተጓጉል ምንም ምክንያት እንደሌለ ገልጾ ነበር። በወረርሽኙ ምክንያት ከ200 በላይ ሰዎች ቻይና ውስጥ የሞቱ ሲሆን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቢያንስ በሌሎች 18 አገራት ውስጥ ተገኝተዋል። ስድስት በበሽታው የተጠረጠሩ ሰዎች በአፍሪካ ውስጥ ተገኝተው የነበሩ ቢሆንም በተደረገላቸው ምርመራ ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው ተረጋግጧል። በሽታው ከተቀሰቀሰባት የቻይናዋ ዉሃን ከተማ ማክሰኞ ዕለት ወደ ኬንያ የተመለሰ አንድ ተማሪ በበሽታው ተጠርጥሮ በተለየ ቦታ ምርመራና ክትትል ሲደረግበት ቆይቶ ከበሽታው ነጻ መሆኑ ታውቋል። ኢትዮጵያ ውስጥም አራት በበሽታው የተጠረጠሩ ሰዎች ተገኝተው የነበረ ቢሆንም የደም ናሙናቸው ወደ ደቡብ አፍሪካ ተልኮ ቫይረሱ እንደሌለባቸው ተረጋግጧል። የኬንያ አየር መንገድ ወደ ቻይና የሚደረጉ በረራዎችን ላልተወሰነ ጊዜ ማቋረጡን ካሳወቀ በኋላ፤ የበረራ እገዳው ምን ያህል ጊዜ ሊቆይ እንደሚችል ከአገሪቱ የጤናና የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር እየተማከረ መሆኑን አሳውቋል። አየር መንገዱ አክሎም በቻይና መስመር ወደ ታይላንድ ዋና ከተማ ባንኮክ የሚያደርገው በረራ ግን ባለበት እንደሚቀጥል ገልጿል።
news-55383518
https://www.bbc.com/amharic/news-55383518
ኮሮናቫይረስ፡ በቱርክ የኦክስጅን ቬንትሌተር ፈንድቶ የኮሮና ህሙማንን ገደለ
በቱርክ በሚገኝ የኮሮናቫይረስ ህሙማን ማዕከል የኦክስጅን ቬንትሌተር ፈንድቶ ዘጠኝ የኮሮና ህሙማንን ገድሏል።
አደጋው ያጋጠመው ጋዚንቴፕ በምትባለው ግዛት የሚገኘው የሳንኮ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል ነው። የቬንትሌተሩም መፈንዳትም በፅኑ ህሙማኑ ክፍል ውስጥ እሳት ማስነሳቱንም የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል። አንደኛው ህመምተኛም ወደ ሌላ ሆስፒታል ሊዛወር ሲል ነው የሞተው ተብሏል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ 2 ሚሊዮን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የተመዘገቡ ሲሆን 17 ሺህ 610 ሰዎችም ህይወታቸውን ማጣታቸውን ከጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የተገኘው መረጃ ያስረዳል። ፍንዳታው ባስከተለው እሳት የደረሰ ጉዳት እንደሌለም ሪፖርት የተደረገ ሲሆን ወዲያውም እሳቱን ለማጥፋት ርብርብ ተደርጓል። ሟቾቹ ከ56-85 እድሜ የሚገመቱ መሆኑንም ከሆስፒታሉ የወጣው መግለጫ ያሳያል። የኦክስጅን ቬንትሌተር ፍንዳታው እንዴት ተከሰተ ለሚለውም ምርመራ ተከፍቷል። በፅኑ ህሙማን የሚገኙ በርካታ ሌሎች ህመምተኞችም አቅራቢያው ወደሚገኝ ሆስፒታልም ህክምና እንዲያገኙ መወሰዳቸውንም የጋዚያንቴፕ አስተዳደር ቢሮ በመግለጫው ጠቅሷል። "ባለስልጣናቱ የሚያስፈልገውን እርምጃም እየወሰዱ ነው" ብሏል መግለጫው። አክሎም በሞቱ ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ፣ ዘመዶች መፅናናትን ተመኝቷል። የቱርክ ፕሬዚዳንት ኢብራሒም ካሊን ቃለ አቀባይም በትዊተር ገፃቸው "ለቆሰሉት በቶሎ እንዲያገግሙ እንመኛለን" በማለት ምኞታቸውን አስተላልፈዋል። በባለፈው ወር እንዲሁ በሮማንያ በተነሳ እሳት 10 የኮሮናቫይረስ ህሙማን ህይወታቸው አልፏል። ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ለእሳቱ መነሻ የሆነው አንድ የህክምና ቁሳቁስ በእሳት ተያይዞ አቅራቢያ የነበረውን የኦክስጅን ሲሊንደር በማቀጣጠሉ ነው። በጥር ወርም እንዲሁ በሩሲያዋ ቼልያቢንስክ ግዛት በሚገኝ ጊዜያው የኮሮናቫይረስ ሆስፒታል ውስጥ የኦክስጅን ክፍሉ ውስጥ ፍንዳታ በመነሳቱ እሳት አስከትሏል። በቦታው የነበሩ 150 የኮሮናቫይረስ ህመምተኞችም በአስቸኳይ እንዲወጡ መደረጋቸውንም የሩሲያ ድንገተኛና አስከቸኳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
news-55275918
https://www.bbc.com/amharic/news-55275918
የሐሰት ኤችአይቪ ፖዘቲቭ ውጤት የሚያሳየው የኮቪድ-19 ክትባት ውድቅ ሆነ
ብዙ ተስፋ ተጥሎበት አውስትራሊያ ውስጥ ሙከራ እየተደረገለት የነበረው የኮሮናቫይረስ ክትባት ተሳታፊዎች ላይ የሐሰት የኤችአይቪ ውጤት በማሳየቱ ውድቅ ተደርጓል።
አውስትራሊያ ከዚህ ተስፋ ከተጣለበት ክትባት 51 ሚሊዮን ብልቃጦች ለመግዛት አቅዳ ነበር። አውስትራሊያ በምትኩ እንደ አስትራዜኔካ ያሉ ውጤታማ ክትባቶችን ለመግዛት ቅድመ ትዕዛዝ አስቀምጣለች። ሲኤስኤል እና የአውስትራሊያው ኩዊንስላንድ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ያበለፀጉትን ክትባት የወሰዱ ሰዎች ደም ሲመረመር ኤችአይቪ ፖዘቲቭ የሚል ውጤት ያሳያል። ነገር ግን ተሳታፊዎቹ የኤችአይቪ ምርመራ ሲደርግላቸው ደማቸው ንፁህ ሆኖ ተገኝቷል። የሙከራ ደረጃ ላይ የነበረው ክትባት በሽታ ተከላካይ ህዋሳትን በማመንጨት ረገድ ውጤታማ ተብሎ ነበር። ነገር ግን ክትባቱ ከኮሮናቫይረስ ባለፈ በአንዳንድ ተሳታፊዎች ላይ ኤችአይቪ ቫይረስን የሚከላከሉ ሴሎች አምርቷል። ይህ ማለት ደግሞ ተሳታፊዎቹ የሐሰት ኤችአይቪ ፖዘቲቭ ውጤት ይታይባቸዋል ማለት ነው። ነገር ግን በደማቸው ውስጥ ቫይረሱ አልተገኘም። ክትባቱን ሲያመርቱ የነበሩ ተመራማሪዎች ስህተቱን ለማረም ቢያንስ አንድ ዓመት ይፈጃል ማለታቸውን ተከትሎ ምርምሩ ውድቅ እንዲሆን ተደርጓል። ፕሮጀክቱን በጣምራ ከሚመሩት ሳይንቲስቶች መካከል አንዱ የሆኑት ፖል ያንግ ውሳኔው እጅግ 'ልብ ሰባሪ' ነው፤ ምክንያቱ ለ11 ወራት ምርምር ስናደርግ ቆይተናል ብለዋል። አውስትራሊያ ኮሮናቫይረስ በሕብረተሰቡ ዘንድ እንዳይሰራጭ ለማድረግ በሠራችው ሥራ ተመስግናለች። የሃገሪቱ የጤና ሙያተኞች ምንም እንኳ ሃገሪቱ ወረርሽኙን እየተቆጣጠረች ቢሆንም በሚቀጥለው ዓመት በሚደርሱ ሁለት ክትባቶች ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ይቻላል ይላሉ። የአውስትራሊያ መንግሥት ምናልባት በሃገር ውስጥ የሚመረቱ ክትባቶች ባይሳኩ በሚል ዝግጅት እንዳደረገ ተናግሯል። ለዚህም ዝግጅት እንዲሆን ከተለያዩ ክትባት አምራች ኩባንያዎች ጋር ስምምነት መድረሱን መንግሥት አስታውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን "ሕዝባችንን ሙሉ በሙሉ ለማስከተብ ከያዝነው የጊዜ ገደብ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ልናስከትብ እንችላለን" ሲሉ ተደምጠዋል። አውስትራሊያ ካዘዘችው መካከል አንዱ የሆነው በኦክስፎርድና አስታራዜኔካ ጥምረት የሚመረተው ክትባት ውጤታማነቱ ቢረጋገጥም ከፈቃድ ሰጪዎች ይሁንታ እየተጠባበቀ ይገኛል። አውስትራሊያዊያን በሚቀጥለው የፈረንጆቹ ዓመት መባቻ ክትባት ማግኘት ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል። 25 ሚሊዮን ሕዝብ ያላት አውስትራሊያ ባለፈው ሳምንት አንድ ሰው ብቻ በቫይረሱ ተይዞብኛል ብላለች። የኮሮናቫይረስ በዓለም ዙሪያ መሰራጨት ከጀመረ ወዲህ በሃሪቱ 28 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ እንደተያዙ ሲረጋገጥ 908 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል። ይህ ቁጥር ከሌሎች አደጉ ከሚባሉ ሃገራት ጋር ሲነፃፀር እጅግ ያነሰ ነው።
news-53260522
https://www.bbc.com/amharic/news-53260522
የሃጫሉን ግድያ ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል የ78 ሰዎች ህይወት መጥፋቱ ተገለጸ
የታዋቂው ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በተከሰተ አለመረጋጋት የ78 ሰዎች ህይወት ማለፉን ክልሉ አስታውቋል።
ከነዚህም መካከል ሶስቱ የመንግሥት የፀጥታ አስከባሪ ኃይል አባላት መሆናቸውንም የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በዛሬው ዕለት ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ቢቢሲ ለየኦሮሚያ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ጥዋት በደወለበት ወቅት ከሃጫሉ ሞት ጋር በተያያዘ በኦሮሚያ ተቀስቅሶ በነበረው ተቃውሞ ቢያንስ 67 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸውን አረጋግጠዋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር በበኩላቸው ትናንት ማታ በሰጡት መግለጫ በዜጎች ላይ ደረሰ ባሉት ጉዳት "ትናንት እና ዛሬ 8 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል" ያሉ ሲሆን ፣ ነዋሪዎች ህይወታቸው ያለፈው "በቦምብ፣ ጥይት፣ በድንጋይ እና በመሳሰሉት ነው" ብለዋል። አክለውም የጸጥታ ችግር ለማረጋጋት ተልዕኮ ተሰጥቷቸው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የፖሊስ አባላት ላይ ከቀላል እስከ ሞት ድረስ ጉዳት ደርሶባቸዋል ያሉት ኮሚሽነሩ "ዛሬ [ረቡዕ] እና ትናንት [ማክሰኞ] 57 የሚሆኑ የፌደራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ላይ ጉዳት ደርሷል" በማለት ሁለት አባላት ህይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል። በሺህዎች የሚቆጠሩ አድናቂዎቹ የድምጻዊውን አስከሬን ለመሸኘትና ዛሬ በሚፈጸመው በቀብሩ ላይ ለመገኘት አምቦ ከተማ ውስጥ መሰብሰባቸው ተገልጿል። ማክሰኞ ዕለት የፌደራል ፖሊስ ፖለቲከኛውን ጃዋር መሐመድን ጨምሮ 35 ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የገለጸ ሲሆን ትናንት ደግሞ የባልደራስ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆነውን እስክንድር ነጋን ይዞ ማሰሩን አሳውቋል። ፖሊስ ከግድያው ጋር ተያያዘ ሁለት ተጠርጣሪዎችን መያዙን ቢገልጽም እስካሁን ሃጫሉ በማንና ለምን እንደተገደለ የተገለጸ ነገር የለም። "የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላትን ጨምሮ አስከ ትናንት ማክሰኞ ቢያንስ 67 ሰዎች ተገድለዋል" ሲሉ የኦሮሚያ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በተጨማሪም በርካታ ሰዎች በከባድ ሁኔታ መቁሰላቸውና በንብረትም ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን አቶ ጌታቸው ባልቻ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ማክሰኞ ረፋድ ላይ አለመረጋጋቱ እየተባባሰ ወደ ሌሎች የኦሮሚያ አካባቢዎች ሲዛመት መንግሥት የኢንተርኔት አገልግሎትን እንዲቋረጥ አድርጓል። ትናንት ረቡዕም የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ የትውልድ ከተማ በሆነችው አምቦ ውስጥ በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ አምስት ሰዎች መሞታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናትና የሆስፒታል ምንጮች ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ዱላና ብረት የያዙ በቡድን የተሰባሰቡ ሰዎች በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች ጥቃትና ዘረፋ የመፈጸም አዝማሚያ በመታየቱ መንግሥት የጦር ሠራዊቱን በመዲናዋ እንዳሰማራ ሮይተርስ ዘግቧል።
news-56884831
https://www.bbc.com/amharic/news-56884831
አቶ ተኮላ አይፎክሩ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ
በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር የነበሩት ተኮላ አይፎክሩ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽንን እንዲመሩ መሾማቸው ታወቀ።
አቶ ተኮላ ከትናንት ሚያዚያ 19/2013 ዓ.ም ጀምሮ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው መመደባቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። የቀድሞው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ከሁለት ዓመታት በላይ በኃላፊነቱ ሲሰሩ ቆይተዋል። አዲሱ ኮሚሽነር አቶ ተኮላ ከሦስት ዓመት በፊት በፌደራል ፖሊስ ውስጥ በኃላፊነት ከመመደባቸው አስቀድሞ በአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በተለያዩ ቦታዎች አገልግለዋል። ከዚያ በፊትም በደቡብ ወሎ ዞን የኮምቦልቻ ከተማ ፖሊስ አዛዥ፣ የአምባሰል ወረዳ፣ የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሆነው ሠርተዋል። በተጨማሪም አቶ ተኮላ የክልሉ ማረሚያ ቤቶች ዋና ኮሚሽነር የነበሩ ሲሆን በሠላም ማስከበር ሥራ ላይም ተሰማርተው የበኩላቸውን ተወጥተዋል። የፌደራል ፖሊስ መሥሪያ ቤትን ከተቀላቀሉ በኋላም በምርመራ ቢሮ፤ የፋይናንስ እና ሎጂስቲክስ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ሆነው አገልግለዋል። አቶ ተኮላ በሠላም እና ደኅንነት የማስተርስ ዲግሪ አላቸው። ቅርቡ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶችና በተፈፀሙ ጥቃቶች የበርካታ ሰዎች ሕይወት መጥፋቱንና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ ነው አቶ ተኮላ ወደ ኃላፊነት የመጡት። በተለይ በሰሜን ሸዋ ዞን በሚገኙ ወረዳዎች በታጣቂዎች ተፈፀመ በተባለው ጥቃት ቁጥሩ በውል የማይታወቅ የሰው ሕይወት አልፏል፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩም ከቀያቸው መፈናቀላቸው ተገልጿል። ሮይተርስ አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣንን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው 'በግጭቱ' 200 ያህል ሰዎች መገደላቸውን ዘግቧል። በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች በክልሉም ሆነ ከክልሉ ውጪ በአማራ ተወላጆች ላይ የሚደርሰውን ግድያና መፈናቀል የሚያወግዙና እንዲቆም የሚጠይቁ የተቃውሞ ሰልፎች ባለፈው ሳምንት ለተከታታይ ቀናት ተካሂደዋል። ይህንንም ተከትሎ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር መግለጫ ሰጥተው ነበር። አቶ አገኘሁ በመግለጫቸው ፤ በተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች በአማራ ተወላጆች ላይ ጥቃት እንደሚፈፀም ገልጸው፤ "ከክልሉ ውጭ ያለው አማራ እንዲህ ሆነ እያልን ባለንበት ሁኔታ፤ በራሳችን ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደርና ሰሜን ሸዋ ዞን ጥቃት ተፈፅሟል" ብለዋል። በጥቃቱ በርካቶች መገደላቸውን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ጥቃቱን የፈፀመው ኃይል የሰለጠነ፣ የታጠቀ ኃይል እንደሆነና ኃይሉ ከተለያየ አካባቢ ሰልጥኖ የመጣ፤ ወይም በአካባቢው ያለ ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም "ጥቃት ለምን ደረሰብን ሳይሆን ጥቃቱ ሲደርስብን የት ነበርን? ምን እያደረግን ነበር? የክልሉ የጸጥታ መዋቅርምን ይሰራ ነበር?፣ የክልሉ የመረጃ መዋቅርስ ምን ነበር?" ሲሉ የጸጥታ መዋቅሩን እንደሚገመግሙና ያጋጠሙ ችግር ለመፍታት እያጣራን ነው ማለታቸው ይታወሳል። አቶ ተኮላን ወደ ክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አመራርነት ያመጣቸው ርዕሰ መስተዳደሩ እንዳሉት በጸጥታው መዋቅር ላይ የተደረገ ግምገማን ተከትሎ ሊሆን ይችላል።
news-51598225
https://www.bbc.com/amharic/news-51598225
ደቡብ ኮሪያ ውስጥ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በአንድ ቀን ውስጥ በእጥፍ ጨመረ
በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በአንድ ቀን ውስጥ ከእጥፍ በላይ መጨመሩን የደቡብ ኮሪያ ባለስልጣናት አስታወቁ።
ባለስልጣናቱ እንዳሉት ከትናንት አርብ ጀምሮ ባለው መረጃ ዛሬ ቅዳሜ ብቻ 229 አዳዲስ በኮሮናቫይረስ የተጠረጠሩ ሰዎች ተገኝተው በተደረገው ምርምራ ቫይረሱ እንደለባቸው ተረጋግጧል። ይህም በአገሪቱ ያሉትን በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 433 ከፍ አድርጎታል። የደቡብ ኮሪያ ምክትል የጤና ጥበቃ ሚኒስትር እንዳሉት የበሽታው ወረርሽኝ "አሳሳቢ የሆነ አዲስ ደረጃ ላይ ሰርሷል"። ባለስልጣናት እንዳረጋገጡት አዲሶቹ በበሽታው ከተያዙት ሰዎች መካከል አብዛኞቹ በአገሪቱ ደቡብ ምሥራቅ በምትገኘው የዴጉ ከተማ ውስጥ በሚገኝ አንድ ሆስፒታልና የሐይማኖት ስፍራ ጋር የተያያዙ ናቸው። እስካሁን በበሽታው በደቡብ ኮሪያ ውስጥ ሁለት ሰዎች የሞቱ ሲሆን ቁጥሩም እየጨመረ ሊሄድ ይችላል የሚል ስጋት አለ። የበሽታው ምንጭ እንደሆነ የተጠረጠረው ሆስፒታል በሚገኝበት ዴጉ አቅራቢያ ያለው ቾንግዶ የተባለው አካባቢ ልዩ ቁጥጥር የሚደረግባቸው አካባቢዎች ተብለው ተለይተዋል። በዚህ የተነሳ በዴጉ ከተማ ያሉ ጎዳናዎችም ጭር ብለዋል። ደቡብ ኮሪያ ከ76 ሺህ በላይ በበሽታው የተያዙ ሰዎችና ከ2 ሺህ ሦስት መቶ በላይ ከሞቱባት ቻይና ቀጥሎ ከፍተኛው የተረጋገጠ የህሙማን ቁጥር ያለባት አገር ሆናለች። የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክትር የሆኑት ዶ/ር ቴድሮስ አድሐኖም እንዳሉት፤ አዲስ እየታየ ያለው የወረርሽኙ ስርጭት ፍጥነት እጅጉን አሳሳቢ ነው። በተለይ ደግሞ ደካማ የጤና አጠባበቅ ሥርዓት ባላቸው የአፍሪካ አገራት ውስጥ በሽታው ከተከሰተ የሚያስከትለው ቀውስ አሳስቧቸዋል።
49771011
https://www.bbc.com/amharic/49771011
በመላው ዓለም ከ4 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ያሳተፈው ሰላማዊ ሰልፍ
በመላው ዓለም የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ዓለማችን በአየር ንብረት ለውጥ እየተጎዳች መሆኑን በማስመልከት በትናንትናው እለት ሰላማዊ ሠልፍ አካሂደዋል።
ሠልፉ የተጠራው በአየር ንብረት ለውጥ የመብት ተሟጋቿ ግሬታ ተንበርግ ሲሆን፤ ከአውስትራሊያ እስከ ኒው ዮርክ፣ ከእስያ እስከ አፍሪካ ከሊቅ እስከ ደቂቅ እንደተሳተፉበት ተነግሯል። ሠልፈኞቹ መፈክሮችን ይዘው የወጡ ሲሆን፤ በአንድነት ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ የተለያዩ መፈክሮችን ሲያሰሙ ተስተውለዋል። ይህ ሠልፍ፤ የሠው ልጅ ያስከተለውን የዓለም ሙቀት መጨመር በመቃወም የተደረገ ትልቁ ሠልፍ ነው ተብሏል። • የአየር ንብረት ለውጥ፤ የት ደረስን? • ምድር በአስፈሪ ሁኔታ እየሞቀች ነው ግሬታ በሰልፉ ላይ "ቤታችን በእሳት እየነደደ ነው" በማለት " እንደዘበት ቆመን በዝምታ አንመለከትም" ስትልም አክላለች። ሠልፉ የተጀመረው በፓሲፊክና እስያ ሲሆን፤ በኒው ዮርክ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሠልፈኛ ወጥቶ ተቀላቅሏል። የሚቀጥለው ሳምንት የተባበሩት መንግሥታት በማንሀተን ከሚያካሄደው ጉባዔ ቀደም ብሎ ነው ሠልፉ የተካሄደው። የመብት ተሟጋቾች ጉባዔው የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚያስችሉ ወሳኝ ውሳኔዎች እንዲተላለፉበት ጥሪ አቅርበዋል። ግሬታ ከዚህ በፊትም በ2018 ተቃውሞዋን ያሰማች ሲሆን፤ በወቅቱ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ላይ እንዲቀሩ በማድረግ ነበር ጥያቄዋን ለዓለም ሕዝብ ያሰማችው። ይህ ድርጊቷ ተማሪዎችን እና ሌሎች ግለሰቦች ትግሏን እንዲቀላቀሉ አነሳስቷል። ትላንት የሆነው ምን ነበር? ሰላማዊ ሠልፉን የጀመሩት በውቅያኖስ ውሃ መጠን መጨመር የተጎዱት በኪርባቲ፣ በሰለሞን ደሴቶች እና በቫኑአቱ፣ የሚገኙ የፓሲፊክ ደሴት ነዋሪዎች ናቸው። እነዚህ ነዋሪዎች በድረገጾች ላይ የለጠፏቸው መልዕክቶች እንደሚያሳዪት "እየሰመጥን አይደለም፣ እየታገልን ነው" ይላል። በአውስትራሊያም 35 ሺህ የሚሆኑ ሠልፈኞች እንደተቀላቀሉ ተገምቷል። አውስትራሊያ በሙቀት መጨመርና የባህር ውሃ መሞቅ በከፍተኛ ሁኔታ ከሚሰቃዩ አገራት መካከል አንዷ ነች። ከእነዚህ አገራት ሠልፉ ወደ እስያ፣ አውሮጳ፣ እና አፍሪካ እንዲሁም አሜሪካ ተስፋፍቷል። • በኦሮሚያ ብክለት አስከትለዋል በተባሉ ፋብሪካዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ • ኢትዮጵያ የአሜሪካን የፕላስቲክ ቆሻሻዎች እንደማትቀበል ገለፀች በአፍሪካ በጋና የሚገኙ ተማሪዎች ሰልፍ ያደረጉ ሲሆን፤ በባህር ዳርቻ የሚኖሩ ዜጎች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በተከሰተ ጎርፍ እየተጎዱ ነው ሲሉ ተናግረዋል። አንድ ጥናት እንደሚያመለክተው ግን በጋና 44 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ስለ አየር ንብረት ለውጥ ሰምቶ አያውቅም። በታይላንድ እና በሕንድ የሚገኙ ሠልፈኞች፤ የሞቱ በማስመሰል መሬት ላይ በመውደቅ መንግሥታቱ ወሳኝ የሆነ ምላሽ እንዲሰጧቸው ጠይቀዋል። በጀርመን በ500 ትላልቅና ትናንሽ ከተሞች ሠልፉ ሲካሄድ፤ የአገሪቱ ጥምር መንግሥት ግሪን ሀውስን ለመቀነስ ያለመ የ54 ቢሊየን ዮሮ ፓኬጅ አስተዋውቋል። በዩኬ በአራት አገራት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሰልፉን መቀላቀላቸው ተነግሯል። የሚቀጥለው ሳምንት የተባበሩት መንግሥታት ጉባዔ ሲካሄድም ሌላ ሠልፍ ይኖራል ተብሏል። ግሬታ ተንበርግ ምን አለች? አዳጊዋ የመብት ተሟጋች ግሬታ፤ አርብ ዕለት እንደ ዝነኛ አርቲስት ነው ከሠልፈኞቹ ሠላምታ የቀረበላት። በኒው ዮርክ ባተሪ ፓርክ የተሰበሰቡ ሠልፈኞች ስሟን ደጋግመው ሲጠሩ ተሰምተዋል። "በታሪክ ከተደረጉ የአየር ንብረት ለውጥ ሠልፎች ሁሉ ይህ ትልቁ ነው፤ እናም ሁላችንም በራሳችን ልንኮራ ይገባናል፤ ምክንያቱም ይህንን ማድረግ የቻልነው በጋራ ነው" ስትል ለሠልፈኞቹ ተናግራለች። • የቡና ምርትና ጣዕም አደጋ ላይ ነው • "የከተማ መስፋፋት የኢትዮጵያን ብዝሀ ሕይወት አደጋ ላይ ጥሏል" ዶ/ር መለሰ ማርዮ በዓለማችን ላይ በአጠቃላይ ሠልፉን የተቀላቀሉት ግለሰቦች አራት ሚሊየን ይሆናሉ ያለችው ግሬታ "አሁንም እየቆጠርን ነው" ስትል ቁጥሩ ከዚህ እንደሚልቅ ፍንጭ ሰጥታለች። "ይህ የአደጋ ጊዜ ነው፤ ቤታችን በእሳት ተያይዟል። ቤቱ ደግሞ የእኛ የአዳጊዎች ብቻ አይደለም፤ ሁላችንም የምንኖረው እዚህ ነው፤ ስለዚህ ሁላችንንም ይጎዳናል" ስትል ለሠልፈኞቹ ተናግራለች። በሄደችበት የዓለማችን ክፍል ሁሉ "ውጤት አልባ ቃል ኪዳኖች ሁሉ ተመሳሳየይ ናቸው፣ ውሸቶቹ ተመሳሳይ ናቸው፣ ተግባር የማይታይባቸው እንቅስቃሴዎች ተመሳሳይ ናቸው" ስትል ትናገራለች። • ትላልቅ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድቦች "አዋጭ አይደሉም" የዓለማችን አይን የተባበሩት መንግሥታት የሚሰበሰቡ መሪዎች ላይ ሊሆን ይገባዋል፤ እናም "እንደሰሙን ለማረጋገጥ የመሪነት ሚናውን የመውሰድ እድሉ በእጃቸው ነው" የምትለው ግሬታ፤ "በእኛ ድርጊት ስጋት የገባው ካለ፤ የሕዝብ ኃይል ይህንን ነው የሚመስለው" ብላለች ንግግሯን ከማጠናቀቋ በፊት። "ይህ ገና የመጀመሪያው ነው" በማለትም " ፈለጉትም አልፈለጉት ለውጥ ይመጣል" ብላለች። ግሬታ ተንበርግ ማን ነች? ስውዲናዊቷ ግሬታ ተንበርግ ለመጀመሪያ ጌዜ ተቃውሞ ያደረገችው በትምህርት ቤቶች ነው። ባለፈው ዓመት በነሐሴ ወር ላይ በአገሯ የሕዝብ እንደራሴ ምክር ቤት ፊት ለፊት "ለአየር ንብረት ለውጥ፤ ከትምህርት ቤት መቅረት" በማለት ተቃውሞዋን አካሂዳለች። ይህ ድርጊቷ ሌሎች ተማሪዎችንና ሰዎችን በመላው ዓለም ያነሳሳ ሲሆን፤ እርሷንም ለኖቤል የሰላም ሽልማት እንድትታጭ አድርጓታል። ግሬታ የሚቀጥለው ሳምንት ለተባበሩት መንግሥታት ከምታደርገው ንግግር ቀደም ብሎ፤ የአሜሪካ ባለስልጣናትን የአየር ንብረት ለውጥን ለመግታት የተሻለ ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርባለች። "እናንተ ምንም ሳትሠሩ፤ እኛ ምን ያህል እንዳነሳሳናችሁ ልትነግሩን አትጥሩን" ብላለች።
54343337
https://www.bbc.com/amharic/54343337
አሜሪካ ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት 2.9 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ ድጋፍ አደረገች
አሜሪካ ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት 2.9 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ ድጋፍ አደረገች
አሜሪካ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትን አቅም ለማጠናከር የሚውል የሥልጠና እና የቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጓን በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ አስታወቀ። በዚህ ወር አሜሪካ የመከላከያ መሥሪያ ቤት 2.9 ሚሊየን ዋጋ የሚያወጣ የሥልጠናና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል። ድጋፉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰውን አል-ሻባብ እና ሌሎች አሸባሪ ቡድኖች የሚያደርሱትን አደጋ ለመመከት የሚያደርገውን ጥረት ለመደገፍ መሆኑን በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲው ገልጿል። ድጋፍ ከተደረጉ ቁሳቁሶች መካከልም ላንድ ክሩዘር ተሽከርካሪዎች፣ የወታደር ተሽከርካሪዎች፣ አምቡላንስ፣ የጭነትና የነዳጅ መኪናዎች፣ የውሃ ማጠራቀሚያዎች፣ ለዘመቻ ማዕከላት የሚሆኑ ኮምፒዩተሮች እና ለምሽት አሰሳ የሚውሉ መሳሪያዎች ይገኙበታል። የአሜሪካ መከላከያ መሥሪያ ቤት ከኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን የገለፀው ኤምባሲው፤ የተደረገው ድጋፍም የዚሁ አካል መሆኑን አስታውሷል። አሜሪካ እና ኢትዮጵያ የወታደራዊ ስልጠና፣ የሰላም ማስከበር እንዲሁም የፀረ ሽብር ዓላማዎችን የሚደግፉ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ያካተተ ለረዥም ጊዜ የቆየ አጋርነት ፈጥረዋል።
news-45132287
https://www.bbc.com/amharic/news-45132287
የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ) በሰሜን ወሎ ዞን በወልዲያ እና አካባቢው የመብት ጥሰት ተፈጽሟል አለ
ሰመጉ በወልዲያ እና አካባቢው የመብት ጥሰት ተፈጽሟል አለ። የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ሃሙስ ነሐሴ 3 ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት በሰሜን ወሎ ዞን በወልዲያ እና አካባቢዋ የመብት ጥሰት መፈጸሙን ጥቁሟል።
የኢትዮጵያ አስተዳደር ክልል እና ዞን-ሰመጉ ሪፖርቱ እንደሚለው ሕገ-መንግሥታዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ድንጋጌዎችን በመተላለፍ በአማራ ክልል፤ የሰሜን ወሎ ዞን በሚገኙ ከተሞች የሚኖሩ ዜጎች ላይ ግድያ ተፈጽሟል። የሟቾችን ስም እና ዕድሜ በመዘርዘር ከህዳር እስከ የካቲት 2010 ዓ.ም. ድረስ በመንግሥት የጸጥታ አስከባሪ ኃይሎች 17 ሰዎች መገደላቸውን ሪፖርቱ ጠቁሟል። • ''ይህን ስላደረገ ነው የተገደለው' ብሎ የሚነግረን እንኳ አላገኘንም'' • ሰመጉ በኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች የፀጥታ አካላት የመብት ጥሰቶችን መፈፀማቸውን በሪፖርቱ ገለፀ ከዚህ በተጨማሪም የአካል ጉዳየት የደረሰባቸውን ዜጎች ዝርዝርም ይዞ ወጥቷል። ሰመጉ እንደሚለው የዚህ መግለጫ አቢይ አላማ፤ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን በበቂ ማስረጃ አስደግፎ በማቅረብ መፍትሄ እንዲሰጣቸው፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዳይፈጸሙ የመከላከል እርምጃ እንዲወስድ ለማሳሰብ፣ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ካሳ እንዲሰጣቸውና ድርጊቱን የፈጸሙና ያስፈጸሙ አካላት በህግ እንዲጠየቁ እንዲሁም የአሰራር ማስተካከያዎች እንዲደረጉ ለመጠየቅ ነው ብሏል። በዚህ መግለጫ ውስጥ የተካተቱት የሞትና የአካል ጉዳት ማስረጃዎች በአብዛኛው የተገኙት ከሆስፒታሎችና ከጤና ጣቢያዎች ሲሆን፤ ቀሪዎቹ ግን የሰመጉ መርማሪዎች የመብት ጥሰት በተፈጸመባቸው አካባቢዎች በመዘዋወር ከሟች እና ከተጎጂ ቤተሰቦች እንዲሁም ከአይን እማኞች ያገኛቸው እንደሆኑ በሪፖርቱ ተጠቅሷል። ሰመጉ በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን የተፈጸሙትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና ጉባኤው በውስን አቅሙ ለማጣራት የቻለው የመብት ጥሰት ብቻ በሪፖርት ውስጥ ማንጸባረቁን ገልጿል። የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔው እንደሚለው ከሆነ የደረሱትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች አስመልክቶ የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት እና የሰሜን ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ መረጃዎች እንዲሰጡት ቢጠይቅም ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። • የደቦ ጥቃትና ያስከተለው ስጋት ሰመጉ በሪፖርቱ ማጠቃለያ ላይ፤ መንግስት ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች በቂ ትኩረት በመስጠትና በማዳመጥ፣ ለግጭቶቹ መቀስቀስ ምክንያት የሆኑትን ምንጮች በማጥናት እንዲሁም ህጋዊና ዴሞክራሲያዊ እርምጃዎችን በመውሰድ በሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ላይ እጃቸው ያለበት አካላትን ተጠያቂ በማድረግ፣ ዜጎችን በሀገራቸው በእኩልነትና በሰላም የሚኖሩበትን ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲያመቻች በመግለጫው ጥሪውን አቅርቧል።
news-45657239
https://www.bbc.com/amharic/news-45657239
ጉባኤው ብአዴንን የት ያደርሰዋል?
በገዢው ግንባር ኢህአዴግ ጥምረት ውስጥ በተካሄደው የለውጥ እንቅስቃሴ ጉልህ ሚና አላቸው ተብለው ከሚጠቀሱት ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው ብአዴን ድርጅታዊ ጉባኤውን ያካሂዳል።
የብአዴን ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን እና ምክትል ሊቀመንበር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የአማራ ክልል ገዢ ፓርቲ ሆኖ በቆየባቸው ባለፉት 27 ዓመታት ውስጥ በውስጡ አንዳንድ ለውጦችን እያደረገ በገዢው ግንባር አባልነት ዘልቋል። • የብአዴን መግለጫ፡- ከስያሜ መቀየር እስከ ኢትዮ ሱዳን ድንበር • አቶ በረከት ስምኦን ሥልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ የብአዴን መስራች አባላት ዋነኛ መሠረታቸው ከሆነው ኢህአፓ በመለየት መንቀሳቀስ በጀመሩበት ጊዜ መጠሪያቸውን ኢህዴን (የኢትዮጵያ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ) የሚል አድርገው ነበር። ነገር ግን በገዢው ግንባር ውስጥ ያሉት ሦስት ድርጅቶች የተወሰነ ሕዝብና አካባቢን የሚወክል መጠሪያ በመያዛቸው ኢህዴን በተለይ የአማራ ህዝብን ወካይ የኢህአዴግ አባል መሆኑን ለማጉላት ስያሜውን ወደ ብአዴን ቀይረ። ከዚህ ውጪ ግን እንደቀሪዎቹ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች በግንባሩ ስር በመሆን ተመሳሳይ ለውጦችንና ውሳኔዎችን በክልሉ ውስጥ ሲወስንና ሲያስፈፅም ቆይቷል። በዚህም በርካቶች ብአዴን የራሱ የሆነ ፖለቲካዊ አቋም የሌለው እንዲሁም መጠሪያው ያደረገውን ህዝብ ጥቅምና መብት ማስከበር የማይችል ድርጅት ነው በማለት ሲተቹት ቆይቷል። • አቶ በረከት ስምኦን ከብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት ታገዱ በተለይ ከአማራ ክልል ውጪ የሚኖሩ አማሮች የተለያዩ ችግሮች ሲገጥሟቸው ብአዴን አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ በመሆን የሚጠበቅበትን አልተወጣም የሚሉ በርካቶች ናቸው። ለረዥም ጊዜ የተለያዩ አካላት በድርጅቱ ከፍተኛ አመራር ላይ ያሉት ግለሰቦች ከአማራ ህዝብ አብራክ የወጡ ባለመሆናቸው በአግባቡ ሊወክሉት አይችሉም በማለት ከንቅናቄው እንዲወጡ በተለያየ መንገድ ሲቀሰቅሱ ቆይተዋል። ግለሰቦቹ የወከሉትን ህዝብ በአግባቡ አላገለገሉም ከመባላቸው ባሻገር የድርጅቱንና የህዝብን ንብረት አባክነዋል፤ እንዲሁም እንደቤተሰብ ንብረት ተገልግለውባቸዋል የሚሉ ወቀሳዎችም ሲቀርቡባቸው ነበር። በዚህም ሳቢያ በተለያዩ ስፍራዎች ወቀሳና ተቃውሞዎች ሲቀርቡበት የቆየው ብአዴን ንቁ ሆኖ በኢህአዴግ ውስጥ በመንቀሳቀስ የህዝቡንና የክልሉን ጥቅም የሚያስከብሩ ሥራዎችን እንዲሰራ ከውስጥም ከውጪም ግፊቶች ሲደረጉበት ቆይቷል። በተለይ ከ2008 ወዲህ በተለያዩ የሃገሪቱና የክልሉ አካባቢዎች እየተጠናከረ የመጣው ህዝባዊ እንቅስቃሴ ንቅናቄውን ብቻ ሳይሆን ኢህአዴግን ጭምር ስጋት ውስጥ በማስገባቱ በግንባሩ ውስጥ ለውጦችን ለማድረግ ሰፊና ተከታታይ ስብሰባዎች ተካሂደው ነበር። • ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር የፍቅር ግንኙነት አለዎት? በግንባሩና በመንግሥት አመራር ላይ ለውጦችን ይዞ የመጣው ተከታታይ ስብሰባና ግምገማ በኢህአዴግና አባል ድርጅቶቹ ውስጥም ከፍተኛ የሚባል፣ ታይቶ የማይታወቅ ለውጥና መነቃቃትን በመፍጠሩ በርካቶች ብአዴንም ይህንን ለውጥ በማጠናከር በኩል አስተዋጽኦ እንደነበረው ይናገራሉ። ከዚህ ጋር ተያይዞም የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ በነሐሴ ወር አጋማሽ ባደረገው መደበኛ ስብሰባ አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳን በጥረት ኮርፖሬት ላይ በፈጠሩት ችግር ምክንያት እስከ ድርጅቱ ጉባኤ ድረስ ከማዕከላዊ ኮሚቴ ታግደው እንዲቆዩ ውሳኔ አሳልፏል። ከዚህ ውሳኔ በኋላ የታገዱት አባላት ከንቅናቄው አመራሮች ጋር በመገናኛ ብዙሃን እሰጥ አገባ ገጥመው ነበር። • አቶ ታደሰ ካሳ፡ "…ወሎዬ ነኝ፤ መታወቂያዬም አማራ የሚል ነው" የአሁኑ ጠቅላላ ጉባኤም በአቶ በረከትና በአቶ ታደሰ ላይ የመጨረሻ ውሳኔውን ከማሳለፍ ባሻገር ሌሎች መስራችና ነባር አባላቱን እንደሚያሰናብት እየተነገረ ነው። ግልጽ ያልሆነው ነገር እነዚህ የሚሰናበቱት አመራሮች ኦዴፓ (ኦህዴድ) እንዳደረገው በክብር ይሰናበቱ ይሆን የሚለው ነው። የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ለረጅም ጊዜ ሲተቹበት የቆየው አዳዲስና ወጣት አመራሮችን አለማብቃታቸው ዋነኛው ሲሆን በድርጅቱ ውስጥ ያልተጠበቁ ለውጦችን ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ እንዳመጡ የሚነገርላቸው ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑ በኋላ ወጣቶችን ወደ አመራር የማምጣቱ ጥያቄ በየአባል ድርጅቶቹ ውስጥ ዋነኛ አጀንዳ ሆኗል። በዚህም ኦዴፓ እንዳደረገው ብአዴንም በርካታ ቀደምት የድርጅቱን አመራሮች በማሰናበት አዳዲስ ወጣቶችን ወደፊት ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል። በዚህም የበርካታ የክልሉን ወጣቶች ቀልብ እየሳበ ያለውን የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ተግዳሮት ለመቋቋም ሊጠቀምበት ይችላል። • «ወይዘሮ ጎሜዝ፤ እርስዎ አያገባዎትም! አርፈው ይቀመጡ በልልኝ» ብአዴን "የለውጡ ቀጣይነት ለአማራ ህዝቦች ተጠቃሚነትና ዲሞክራሲያዊ አንድነት " በሚል መሪ ሀሳብ የሚያካሂደው 12ኛ ደርጅታዊ ጉባኤ በወሳኝ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። በዚህም በተለያዩ መስኮች የለውጥ እርምጃዎችን በመውሰድ በክልሉ ህዝብ ዘንድ ተመራጭ የፖለቲካ ድርጅት ሆኖ መገኘት የሚያስችሉትን ውሳኔዎች እንደሚሰጥበት ንቅናቄው በተለያዩ አጋጣሚዎች አሳውቋል። ከዚህ በተጨማሪም የብአዴን አቻ ኦህዴድ እንዳደረገውና የንቅናቄው አባላት ጥያቄ እንደሆነ የተነገረው የድርጅቱን ስያሜ ጨምሮ ሌሎች ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይም ማሻሻያ እንደሚያደረግ ይጠበቃል። ከዚህ ጋር በተያያዘም ባለፉት ዓመታት የአማራ ክልልን ጨምሮ በመላ ኢትዮጵያ ለህዝቦች መፈናቀልና መሰደድ፣ ለህይወት መጥፋትና ንብረት መውደም ምክንያት የሆኑ የወሰንና የማንነት ጥያቄዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው ለመፍታት የሚረዱ መንገዶች ላይ ውይይት እንደሚያደርግም ተጠቅሷል። በተጨማሪም በድርጅቱ ስር ያሉ የልማት ድርጅቶች፣ ማለትም ጥረት ኮርፖሬት እና የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም፣ የተባሉት ድርጅቶች ተጠሪነታቸው ለክልሉ መንግሥት እንዲሆን ተወስኗል።
news-54143953
https://www.bbc.com/amharic/news-54143953
የዓለም ጤና ድርጅት በአንድ ቀን ከፍተኛውን የኮቪድ-19 ህሙማን መዘገበ
የዓለም ጤና ድርጅት በአንድ ቀን ቫይረሱ የተገኘባው ሰዎች ከፍተኛውን ቁጥር መመዝገቡን ገለጸ። በ24 ሰዓት ውስጥ 307 ሺህ 930 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።
በአንድ ቀን 5 ሺህ 500 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ የሞቱ ሲሆን፤ ይህም የሟቾችን ቁጥር 917 ሺህ 417 አድርሶታል። በበሽታው በተያዙ ሰዎች ቁጥር ሕንድ፣ አሜሪካ እና ብራዚል ቀዳሚ ናቸው። በመላው ዓለም 28 ሚሊዮን ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። ከነዚህ ገሚሱ የአሜሪካ ነዋሪዎች ናቸው። ከዚህ ቀደም በአንድ ቀን ከፍተኛ የህሙማን ቁጥር የተመዘገበው ከስምንት ቀን በፊት ሲሆን፤ ቁጥሩም 306,857 እንደነበር ተገልጿል። በዓለም ጤና ድርጅት አሐዝ መሠረት፤ ትላንት በሕንድ 94,372፣ በአሜሪካ 45,523 እና በብራዚል 43,718 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። በሕንድ እና በአሜሪካ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ሲሞቱ፤ በብራዚል 847 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ሕንድ ነሐሴ ላይ ወደ 2 ሚሊዮን ገደማ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ሪፖረት አድርጋለች። ይህም ቫይረሱ መሰራጨት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በአንድ ወር የተመዘገበ ከፍተኛ ቁጥር ነው። በአገሪቱ በአማካይ በአንድ ቀን 64,000 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ይያዛሉ። ይህም በሐምሌ ከነበረው 84 በመቶ ጨምሯል። መስከረም ከገባ ወዲህ በየቀኑ የሚሞቱ ሰዎች 1,000 ይጠጋሉ። በብራዚል ከአራት ሚሊዮን በላይ ሰዎች በበሽታው ተይዘዋል። ከላቲን አሜሪካ አገሮች ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር የታየውም በብራዚል ነው። እስካሁን 131,000 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በዓለም በበሽታው ከተያዙ ሰዎች አንድ አራተኛው የሚገኙት በአሜሪካ ነው። እስካሁን ከስድስት ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወረርሽኙ ተይዘዋል። ከሐምሌ ወዲህ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ እየናረ መጥቷል። እስካሁን 194,000 ሰዎች የሞቱ ሲሆን፤ ከዓለም ከፍተኛው የሟቾች ቁጥር የተመዘገበውም በአሜሪካ ነው። ሌሎች አገራትስ? አውሮፓ ውስጥ በየቀኑ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ ነው። ቫይረሱ ሊያገረሽ ይችላል የሚል ስጋትም አለ። በከፍተኛ ሁኔታ ቫይረሱ ጉዳት ባደረሰባቸው አካባቢዎች እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ተጥሏል። ሰዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል እንዲያደርጉና አካላዊ ርቀት እንዲጠብቁም ማሳሰቢያ እየተሰጠ ይገኛል። ቫይረሱ ዳግመኛ ካገረሸባቸው አገሮች መካከል ፔሩ፣ እስራኤል፣ ደቡብ ኮርያ እና አውስትራሊያ ይጠቀሳሉ። እሁድ በአውስትራሊያዋ ቪክቶሪያ ከተማ ፖሊስ 70 ተቃዋሚዎችን አስሯል። ግለሰቦቹ ከቤት ያለመውጣት ሕግን በመተላለፋቸው ነበር በቁጥጥር ስር የዋሉት። በሜልቦርን በተካሄደው ተቃውሞ ላይ ቢያንስ ወደ 250 ሰዎች ተሳትፈዋል። ስለ ወረርሽኙ የሴራ ትንታኔዎች ሲስተጋቡም ነበር። በሌላ በኩል እስራኤል እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ልታደርግ መሆኑ ተገልጿል። የአይሁዳውያን አዲስ ዓመት አርብ ሲከበር፤ እስከ ሦስት ሳምንት የሚቆዩ ጠንካራ የጥንቃቄ እርምጃዎች ይተላለፋሉ ተብሎም ይጠበቃል። በእስራኤል153,000 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን፤ 1,108 መሞታቸውን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ አሐዝ ይጠቁማል።
news-45757791
https://www.bbc.com/amharic/news-45757791
የ2018 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊዎች ዴኒስ ሙክዌጄ እና ናዲያ ሙራድ ሆኑ
ዴኒስ ሙክዌጄ እና ናዲያ ሙራድ የ2018 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል። አሸናፊዎቹ በግጭትና ጦርነት ቀጠናዎች ወሲባዊ ጥቃት እንደ መሳሪያ እንዳይውል ባደረጉት ጥረት መረጣቸው ታውቋል።
ዴኒስ ሙክዌጄ እና ናዲያ ሙራድ ኮንጓዊው ዶክተር ዴኒስ ሙክዌጄ የማህፀን ሀኪም ሲሆኑ የወሲብ ጥቃት ሰለባ ለሆኑ ሴቶች ህክምና በመስጠት አስተዋፅኦ ሲያደርጉ ቆይተዋል። በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ ግዛት በተፈፀመ ጥቃት ሰለባ የሆኑ ከ50 ሺህ በላይ ሴቶችን አክመዋል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቿ ኢራቃዊቷ ናዲያ ሙራድ ከአራት ዓመታት በፊት በእስላማዊ ታጣቂ ቡድን ታግታ የወሲባዊ ጥቃት ሰለባ የሆነች ወጣት ስትሆን ይህንንም ለመታገል ያላሰለሰ ትግል ስታደርግ እንደነበር ተገልጿል። • ኢትዮጵያዊው የ100 ሜትር ክብረወሰን ባለቤት ምርጫውን የተከናወነው 5 አባላት ባሉት ኮሚቴ 331 ዕጩዎች ለሽልማቱ ቀርበው ነበር ። ከእነዚህም መካከል 216 ግለሰቦች ሲሆኑ 115ቱ ደግሞ ቡድኖች መሆናቸውን ኮሚቴው ጠቁሟል። በኖቤል ሽልማት አሰራር መሰረት ዕጩዎች ለህዝብ ይፋ የሚደረጉት ከ50 ዓመታት በኋላ ነው። የሁለቱ ኮሪያ መሪዎች የአሸናፊነቱ ቅድሚያ ግምት ከተሰጣቸው ግለሰቦች መካከል ይገኙበታል። የሰሜን ኮሪያው መሪ በሰብዓዊ መብት አያያዘቸው በተደጋጋሚ ቢወቀሱም ከደቡብ ኮሪያው አቻቸው ጋር በመሆን በሁለቱ ሃገራት መካከል የቆየውን ውጥረት ለማርገብ የወሰዷቸው እርምጃዎች የሽልማቱ ተመራጭ ያደርጋቸዋል የሚሉት በርካቶች ነበሩ። • ዐብይ አሕመድ ለኖቤል ሽልማት ታጭተዋል? ሌላው ሽልማቱን ሊያሸንፉ ይችላሉ ተብለው ቅድሚያ ግምት ከተሰጣቸው መሪዎች መካከል እንዱ ዶናልድ ትራምፕ ናቸው። ትራምፕ በኮሪያ ባህረሰላጤ ሰላም ለማስፈን እንዲሁም ሰሜን ኮሪያ ኒኩለር ቦንም ከማበልጸግ እንድተቆጠብ ላደረጉ ያላሰለሰ ጥረት ሽልማቱን ሊያሸንፉ ይችላሉ ተብሏል። በእስር ላይ የሚገኘው ጸሃፊው ራኢፍ ባዳዊ፣ ሊቀ ጳጳስ ፈራንሲስ እና የካታሎንያ የነጻነት መሪ ካርለስ ፑይግዴሞንት ሽልማቱን ያሸንፋሉ ተብሎ ግምት ከተሰጣቸው መካከል ይገኙበታል። የዘንድሮውን የኖቤል የሰላም ሽልማት ያሸንፋሉ ተብለው ግምት ከተሰጣቸው ሌሎች ግለሰቦች መካከል እስር ላይ የሚገኘው ጸሃፊው ራኢፍ ባዳዊ፣ ሊቀ ጳጳስ ፈራንሲስ እና የካታሎንያ የነጻነት መሪ ካርለስ ፑይግዴሞንት ይገኙበታል። የሳውዲ ዜግነት ያለው ጸሃፊው ራኢፍ ባዳዊ ፣ ''የመገናኛ አውታሮችን በመጠቀም እስልምናን ዘልፏል'' በሚል ክስ ላለፉት 6 ዓመታት በሳውዲ እስር ቤት ውስጥ ይገኛል። በስፔን መንግሥት ሕጋዊ እውቅና ባልነበረው ሕዝበ ውሳኔ ካታላኖች በካርለስ ፑይግዴሞንት እየተመሩ ከስፔን ተገንጥለው ሃገር ለመመስረት ሙከራ አድርገው ነበር። ሕዝበ ውሳኔውን ተከትሎም ካርለስ ከስፔን ሸሽተው በቤልጅም እየኖሩ ይገኛሉ። • "ካታሎንያ ከስፔን ተገንጥላ አገር የመሆን መብቷን አሸነፈች" ከግለሰቦቹ በተጨማሪ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ሽልማቱን ሊያሸንፍ ይችላል ከተባሉ ድርጅቶች መካከል አንዱ ነው። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድስ ከዕጩዎቹ መካከል እንዱ ሊሆኑ አይችሉም? ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ከፍተኛ የሕዝብ ድጋፍ ማግኘት ብቻም ሳይሆን የኖቤል ሽልማት እንዲያገኙም ጭምር ዘመቻ ተከፍቶ ነበር። ይሁን እንጂ የኖቤልን የሰላም ሽልማትን የጊዜ ሰሌዳ ስንመለከት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የ2018 የኖቤል ሽልማት እጩ የመሆናቸው ነገርን አጠያያቂ ያደርገዋል። የኖቤል ኮሚቴ የጊዜ ሰሌዳ እንደሚከተለው ነው። መስከረም፡- በፈረንጆች መስከረም (ሴፕቴምበር) የኖርዌይ ኖቤል ኮሚቴ እጩዎችን ለመቀበል ይሰናዳል። እጩ የመቀበሉ ሥራ ለቀጣይ ስድስት ወራት ይጸናል። እጮዎቹን መጠቆም የሚችሉት ከላይ የተዘረዘሩት ብቁ ጠቋሚ የተባሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ብቻ ናቸው። የካቲት፡- በየካቲት የእጩዎች መቀበያ ጊዜ ያበቃል። ከየካቲት 1 በፊት ያልተጠቆመ በዚያ ዓመት እጩ መሆን አይችልም። መጋቢት፡-ኮሚቴው የእጮዎችን ዝርዝር ያቀርባል። ከእጮዎቹ ውስጥ ከ20 እስከ 30 የሚሆኑትን ብቻ ለተጨማሪ ማጣሪያ ይቀርባሉ። ጥቅምት፦ በጥቅምት መጀመርያ ኮሚቴው አሸናፊውን በድምጽ ብልጫ ይመርጣል። ይግባኝ የማይባልበት ምርጫ ነው ታዲያ። በታኀሳስ፦ 10 (በፈረንጆቹ) በኦስሎ ኖርዌይ የሽልማት ሥነ ሥርዓቱ ይካሄዳል። የኖቤል ሽልማት ከአንድ ዓመት ዘለግ ያለ ጊዜን የሚወስድ ሂደት ነው። ኾኖም ጥቆማ የመቀበያ ጊዜ ከፈረንጆች መስከረም ጀምሮ ለ6 ወራት የሚዘልቅ ነው። ይህ እንግዲህ መጪውን የመስከረም ወር ሳይሆን የ2017ቱን ወር አንድ ብሎ የሚጀምር ነው። የእጩ መስኮቱ ከተዘጋ ከሁለት ወራት በኋላ ወደ ሥልጣን የመጡት ዐብይ አሕመድ ቢያንስ የ2018 የኖቤል ሽልማት እጩ የመሆናቸው ዐድል ጠባብ ያደርገዋል። ምናልባት የኖቤል ኮሚቴው በመጨረሻዎቹ ጊዜያት እጩ የመጨመር ሥልጣን ስላለው ያ ተግባራዊ ከሆነ ጠባብ እጩ የመሆን እድል ሊኖራቸው ይችላል።
news-44599509
https://www.bbc.com/amharic/news-44599509
በሳዑዲ አረቢያ ሴቶች ላይ ተጥሎ የነበረው የማሽከርከር እገዳ ተነሳ
ከአስርት ዓመታት በፊት የወጣውና ሴቶች እንዳያሽከረክሩ የሚያግደው ሕግ መነሳቱን ተከትሎ የሳዑዲ ሴቶች የማሽከርከር ፈቃድ አግኝተዋል።
ሀናን ኢስካን ለመጀመርያ ጊዜ መኪና በማሽከርከሯ ቤተሰቦቿ ደስታቸውን እየገለጹላት ነው። ሳዑዲ አረቢያ ከዓለማችን ለሴቶች የማሽከርከር ፈቃድ የማትሰጥ ብቸኛዋ አገር የነበረች ሲሆን በዚህም ምክንያት ሴቶች ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ የወንዶችን መልካም ፍቃድ ጠባቂ ሆነው ቆይተዋል። በዚህም ሳቢያ ሾፌር አሊያም መኪና ሊያሽከረክር የሚችል ወንድ ዘመድ ለመቅጠር ይገደዱ ነበር። በአገሪቱ የሚገኙ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ሴቶች የማሽከርከር ፈቃድ እንዲያገኙ ለዓመታት ግፊት ሲያደርጉ ቆይተዋል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል እንዳስታወቀው በሴቶች የማሽከርከር መብት ስሟ ቀድሞ የሚነሳውን ሎጃኢን ሃትሎልን ጨምሮ በትንሹ ስምንት የሴቶች መብት ተሟጋቾች ተይዘው፤ በአሸባሪነት ተፈርጀው ረዘም ላለ ጊዜ እስራት ተፈርዶባቸዋል። የማሽከርከር እገዳው ሕግ በአውሮፓውያኑ መስከረም ወር የተሻሻለ ሲሆን በያዝነው ወር መጀመሪያ ሕጋዊ የማሽከርከር ፈቃድ ለዐስር ሴቶች መሰጠት ተጀምሮ ነበር። ስለሆነም ሴቶች በወንዶች ሞግዚትነት የሚቆዩበትን ሕግ እንዳበቃለት ተነግሯል። "ይህ ለሳዑዲ ሴቶች ታሪካዊ አጋጣሚ ነው" ሲሉ የሳዑዲ ቴሌቪዥን አቅራቢ ሳዲቃ አል-ዶሳሪ ለኤኤፍፒ ተናግረዋል። የ ሃያ አንድ ዓመቷ የሕክምና ተማሪ ሀቱን ቢን ዳኪል በበኩሏ ለረጂም ሰዓት ቆመን ሾፌር የምንጠብቅበት ሰዓት አክትሟል ፤ ከዚህ በኋላ ወንዶች አያስፈልጉንም " በማለት አጋጣሚውን ገልፀዋለች።
news-49143339
https://www.bbc.com/amharic/news-49143339
ናይጄሪያ ውስጥ ታግተው የቆዩ ቱርካዊያን ተለቀቁ
በናይጄሪያዋ ምዕራባዊ ግዛት ክዋራ ውስጥ በታጣቂዎች ታግተው የነበሩ አራት የቱርክ ዜጎች ከሳምንት እገታ በኋላ መለቀቃቸው ፖሊስ ገለጸ።
የግንባታ ሰራተኞች የሆኑት አራቱ ቱርካዊያን ከአንድ ቡና ቤት የታገቱት ባለፈው ሳምንት ነበር። ታጣቂዎቹ ታጋቾቹን ለመልቀቅ አንድ ሚሊዮን ዶላር እንዲሰጣቸው ጠይቀው የነበረ ቢሆንም፤ "ያለምንም ቅድመ ሁኔታ" ምንም ገንዘብ ሳይከፈል መለቀቃቸውን ፖሊስ አስታውቋል። • የሐዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ለምርጫ ቦርድ አቤቱታ አቀረቡ ናይጄሪያ ውስጥ የውጭ ዜጎችና ታዋቂ የሃገሪቱን ዜጎች ኢላማ ያደረጉ እገታዎች ተደጋጋሚና የተለመዱ ናቸው። ከሁለት ሳምንታት በፊትም የባህር ላይ ዘራፊዎች ከናይጄሪያ የባህር ዳርቻ ዋ ብሎ አንዲት የጭነት መርከብ ላይ ጥቃት ፈጽመው አስር ቱርካዊያን መርከበኞችን አግተዋል። የታጋቾቹ እጣ ፈንታም እስካሁን ድረስ አልታወቀም። የክዋሬ ግዛት የፖሊስ ኮሚሽነር የሆኑት ካዮዴ ኢግቤቶኩን ለቢቢሲ እንደተናገሩት ቱርካዊያኑ የግንባታ ሰራተኞች አርብ ዕለት ነው ጫካ ውስጥ የተገኙት። ታጋቾቹን የማስለቀቅ ተልዕኮ በግዛቲቱ ፖሊሶች፣ በአካባቢው ታጣቂዎችና ከዋና ከተማዋ አቡጃ በተላኩ የፖሊስ መኮንኖች ጥምረት ነበር የተካሄደው። • መገደል፣ መደፈር፣ መዘረፍ ማብቂያ የሌለው የኢትዮጵያውያን የስደት ጉዞ የግዛቲቱ ፖሊስ ኮሚሽነር እንዳሉት ታጋቾቹ ከመገኘታቸው በፊት ፖሊስ የያዛቸው ሦስት አጋቾች ቱርካዊያኑን ለማስለቀቅ እንደረዱ ተናግረዋል። "አጋቾቹ ሲያዙ በተቀሩት ተባባሪዎቻቸው ላይ ተጽእኖ በመፍጠሩ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ታጋቾቹን እንዲለቁ አድርጓቸዋል" በማለት ፖሊስ ሌሎቹን አጋቾች ለመያዝ ክትትል እያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል። አራቱ ቱርካዊያን ታጋቾች ከተለቀቁ በኋላ የህክምና ምርመራ ተደርጎላቸዋል። በናይጄሪያ የሚገኙት የቱርክ አምባሳደርም እገታው ያለጉዳት በማብቃቱ መደሰታቸውን ገልጸው ተልዕኮው የተሳተፉትን በሙሉ ማመስገናቸው ተዘግቧል።
news-47053066
https://www.bbc.com/amharic/news-47053066
ከሞቃዲሾ ወደ አዲስ አበባ ሊጓዝ የነበረው እስረኛ ጥቃት ደረሰበት
ወደ አዲስ አበባ ሊጓዝ ሲል ሞቃዲሾ ላይ ተይዞ እስር ቤት የነበረ የብሪታኒያ ዜጋ አብረውት በነበሩ እስረኞች በምላጭ ከተፈጸመበት ጥቃት መትረፉን የእስርቤቱ ባለስልጣናት ለቢቢሲ ተናገሩ።
ለግል የደህንነት ጥበቃ ተቋም የሚሰራው አንቶኒ ቶማስ ኮክስ ላይ በሞቃዲሾ በሚገኘው ማዕከላዊ እስር ቤት ከተፈጸመው ጥቃት ጀርባ በእስር ቤቱ የሚገኙ ተጠርጣሪ የጽንፈኛ እስላማዊ ቡድን አባላት ይኙበታል ተብሏል። • የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ41 ዓመታት በኋላ ወደ ሶማሊያ በረራ ጀመረ • ለአካል ክፍላቸው ሲባል ህጻናት ተገድለው ተገኙ አንቶኒ ቶማስ ኮክስ ለእስር የተዳረገው ከአስር ቀናት በፊት ከሞቃዲሾ ወደ አዲስ አበባ ለመጓዝ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ በተደረገ ፍተሻ ወቅት የአስለቃሽ ጋዝ ተተኳሾች ሻንጣው ውስጥ በደህንነት ባለስልጣናት ስለተገኘበት ነው። ግለሰቡ የያዘውን ነገር ባለማሳወቁ የሕዝብን ደህንነት አደጋ ላይ በመጣል ወንጀል ይከሰሳል ተብሏል። የሞቃዲሾ ማዕከላዊ እስር ቤት ምክትል አስተዳዳሪ የሆኑት አብዲካሪም አሊ ፍራህ እንደተናገሩት፤ ታሳሪው ላይ ጥቃቱ በተፈጸመበት ጊዜ በአንገቱ ላይ ቀላል የመቆረጥ ጉዳት ደርሶበታል ብለዋል። አስተዳዳሪው ጨምረውም የእስር ቤቱ ጠባቂዎች ስለጥቃቱ ወዲያውኑ መረጃ በማግኘታቸው ግለሰቡን ከከፋ አደጋ ለማዳን ችለዋል ሲሉ ተናግረዋል። • በረከት ስምኦን ከየት ተነስተው እዚህ ደረሱ "ከተጠርጣሪዎቹ አንዱ የግለሰቡን አንገት በምላጭ ለመቁረጥ ሲሞክር ልናስቆመው ችለናል። በዚህም መካከልም በጣም ቀላል ቁስለት ደርሶበታል። ነገር ግን አሁን ደህና ነው" ሲሉ አፍራህ ለቢቢሲ ሶማሊኛ ተናግረዋል። በጥቃቱ ተሳትፈዋል የተባሉት ሁለት ግለሰቦች የእስላማዊ ታጣቂ በቡድኖች አባላት እንደሆኑ እንደሚጠረጠር የእስር ቤቱ ምክትል አስተዳዳሪ ተናግረዋል። አንደኛው የአል ሻባብ አባል እንደሆነ ሲታሰብ ሌላኛው ደግሞ የእስላማዊው መንግሥት (አይሲስ) አባል እንደሆነ ይታመናል። ሁለቱም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሚደገፈውን የሶማሊያ መንግሥት የሚወጉ ቡድኖች ናቸው። የኤምባሲ ባለስልጣናትና ግለሰቡ ይሰራበታል የተባለው የአሜሪካ የግል የደህንነት ተቋም የሆነው ባንክሮፍት ሰራተኞች እስር ቤቱን መጎብኘታቸው ተገልጿል።
news-51513603
https://www.bbc.com/amharic/news-51513603
በአፍሪካ የመጀመሪያው የተረጋገጠ የኮሮና ቫይረስ ህመምተኛ ተገኘ
በአፍሪካ ውስጥ የመጀመሪያው በኮሮና ቫይረስ መያዙ የተረጋገጠ ህመምተኛ ግብጽ ውስጥ መገኘቱ ተነገረ።
ይህም ለግብጽ የመጀመሪያው በበሽታው የተጠረጠረና በሽታው የተገኘበት ሰው መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ግለሰቡም በአህጉሪቱ የተገኘ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ሆኗል። የግብጽ የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በሽታው የተገኘበት ግለሰብ የውጪ አገር ዜግነት ያለው መሆኑን ቢገልጽም ከየት አገር እንደመጣ ግን አላመለከተም። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አክሎም ስለበሽታው ክስተት ለዓለም የጤና ድርጅት ማሳወቁንና በበሽታው የተያዘው ግለሰብም በአንድ ሆስፒታል ውስጥ ተለይቶ ክትትል እየተደረገለት መሆኑን ገልጿል። የአፍሪካ አገራት ከቻይና ጋር ባላቸው የጠበቀ ግንኙነት ምክንያት በሽታው በአጭር ጊዜ አፍሪካ ውስጥ ሊታይ እንደሚችል የጤና ባለሙያዎች ቀደም ሲል ሲያስጠነቅቁ ነበር። በሽታው በወረርሽኝ መልክ መከሰቱና በተለያዩ አገራት ውስጥ መታየቱ ከተነገረ በኋላ ጥቂት የማይባሉ የአፍሪካ አገራት፣ የበሽታው ምልክት የታየባቸው ሰዎችን እንዳገኙ ቢገልጹም በኋላ ላይ በተደረጉ ምርመራዎች ግለሰቦቹ ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው ተረጋግጧል። ከቻይናዋ የዉሃን ከተማ ተነስቶ ወደ ተለያዩ አገራት የተዛመተው ይህ በሽታ እስካሁን ድረስ ከ1ሺህ 500 በላይ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የሚበዙት ቻይናውያን ናቸው።
news-47084926
https://www.bbc.com/amharic/news-47084926
ለምን ኢትዮጵያዊያን ጥቂት ሥጋ ይመገባሉ?
ኢትዮጵያዊያን የተለያየ አይነት ባሕላዊ ምግቦች ያሏቸው ሲሆን በተለይ ጥሬ ሥጋና ከሥጋ የሚሰሩ ምግቦች ጎልተው ይታያሉ፤ በዚህም በርካቶች ኢትዮጵያዊያን የሥጋ አዘውታሪዎች እንደሆኑ ይሰማቸዋል። ነገር ግን እውነታው ይህ አይደለም።
በቅርቡ የተደረገ አንድ ጥናት እንዳመለከተው ኢትዮጵያዊያን ዝቅተኛ መጠን ያለው ሥጋ ከሚመገቡ ዜጎች መካከል ቀዳሚዎቹ እንደሆነ አመልክቷል። የተገኘው መረጃ እንደሚለው በመካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በዓመት 7 ኪሎግራም ሥጋ ብቻ ይመገባሉ። ይህ ደግሞ በአፍሪካ ደረጃ ሲታይ እንኳን በታችኛው ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው። • ልጆችዎ ጤናማ ምግብ እንዲመገቡ ማድረጊያ መላዎች ሩዋንዳዊያን 8 ኪሎ ግራም እንዲሁም የናይጄሪያ ዜጎች 9 ኪሎ ግራም ሥጋን ይመገባሉ። ጎረቤት የኬንያና የሱዳን ዜጎችም ከኢትዮጵያዊያን ከፍ ያለ የሥጋ መጠን እንደሚመገቡ ተጠቅሷል። በመንግሥት ድርጅት ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩት 46 ዓመቱ ጎልማሳ አቶ መላኩ ጥላሁን አዘውትረው ሥጋን መመገብ ከሚፈልጉ ሰዎች መካከል መሆናቸውን ቢያምኑም በዋናነት የሥጋ ዋጋ መናር እንደፈለጉት እንዳይመገቡ እንዳገዳቸው ይናገራሉ። "ጾም ካልሆነ በስተቀር በየእለቱ ሥጋ ብመገብ ደስ ይለኛል። ነገር ግን 200 እና 300 ብር ለአንድ ኪሎ እያወጡ መግዛት ለእንደ እኔ አይነቱ የወር ደሞዝተኛ አስቸጋሪ ነው" ይላሉ። አቶ መላኩ አልፎ አልፎ አምሮታቸውን ለማስታገስ ሲሉ በጥቂቱ ሥጋ እንደሚገዙ ይናገራሉ። "በአብዛኛው ግን በበዓላት ሰሞን ነው የሥጋ አምሮቴን የምወጣው" ይላሉ። • ስለ አንጀታችን የማያውቋቸው ስድስት አስገራሚ እውነታዎች አንዳንዶች ለጤንነታቸው ከሚያደርጉት ጥንቃቄ የተነሳ ለሥጋ ያላቸው ፍላጎት ዝቅተኛ በመሆኑ ከሥጋ ቢርቁም የዋጋው ውድነት በርካቶችን ከሥጋ እንዲርቁ አድጓቸዋል። ከዚህ አንጻር የአትክልትና የፍራፍሬ ዋጋ ዝቅተኛ መሆን ለጤና ብቻ ሳይሆን ከወጪ አኳያም ተመራጭ እየሆነ ነው። የቤት እመቤት የሆኑት ወ/ሮ የማርሸት ጽጌ የሥጋ ዋጋ ከጊዜ ወደጊዜ እየተወደደ መሄዱ እንጂ ሥጋ ከቤተሰባቸው ማዕድ ላይ በየእለቱ ባይለይ ይመርጣሉ። "ለሥጋ የሚወጣው ወጪ ከሌሎች የምግብ ሸቀጦች አንጻር ከፍ ያለ በመሆኑ ለማብቃቃት ስል ከተቻለ በሳምንት አንድም ሁለትም ጊዜ ለቤተሰቤ ከሥጋ የተዘጋጀ ምግብ አቀርባለሁ" ይላሉ። እንደ ወ/ሮ የማርሸት ሁሉ በርካታ ሰዎች አዘውትረው ሥጋ መብላትን ቢፈልጉም የዋጋው መናር እንዲሸሹት እንዳደረጋቸው ይናገራሉ። በአዲስ አበባ ውስጥ የሥጋ እንደየቦታው እና 'ጥራቱ' በተለያየ ዋጋ ለሽያጭ ይቀርባል። አንድ ኪሎ ሥጋ ከ150 ብር እሰከ 400 ብር የሚሸጥባቸው ቦታዎች አሉ። ስለዚህም ለበርካቶች ከሥጋ መራቅ ዋነኛው ምክንያት የመግዛት አቅም እንደሆነ በርካቶች ይስማማሉ። የተደረገው ጥናትም በታዳጊ ሃገራት የሥጋ ፍጆታ ዝቅተኛ እንዲሆን ያደረገው የገቢ ጉዳይ ነው። በተጨማሪም የሥጋ ፍጆታቸው በጨመሩ ሃገራት ውስጥ የታየው እድገት ከገቢ ጋር እንሚያያዝ ይታመናል። ሥጋ በብዛት የሚበላባቸዉ ሀገራት ይህ በተጨማሪ ጤናማ ለመሆን፣ አካባቢ ላይ ያላቸዉን ተፅዕኖ ለመቀነስ እና የእንስሳትን ደህንነት ለመጠበቅ ያላቸዉን ሚና ያሳያል። ጥናቱ እንዳመለከተው 1/3ተኛ የሚሆኑ እንግሊዛዊያን ሥጋ መመገብን እንዳቆሙ ወይም እንደቀነሱ ሲናገሩ 2/3ተኛ የሚሆኑት አሜሪካዊያን ደግሞ ከአንድ ኪሎ ሥጋ በታች እንደሚመገቡ ይናገራሉ። ባለፉት 50 ዓመታት የሥጋ ፍጆታ በፍጥነት አድጓል፤ በምርት በኩልም ዛሬ የሥጋ ምርት በ1960ዎቹ ከሚመረተው አምስት እጥፍ አካባቢ ጨምሯል። • የአለም የምግብ ቀን: አስገራሚ የአለማችን ምግቦች በዚህ ጊዜ ዉስጥም የህዝብ ቁጥር ከእጥፍ በላይ አድጓል። ነገር ግን ይህ ብቻ ለሥጋ ፍጆታ መጨመር በቂ ምክንያት አይደለም።ሌላኛዉ ምክንያት የሰዎች ገቢ መጨመር እንደሆነ ይታመናል። የተለያዩ የዓለም ሀገራት የሥጋ ፍጆታ ሲወዳደር ሀብታም የሆኑት ሀገራት የበለጠ ሥጋ እንደሚጠቀሙ ያሳያል። ይህም በዓለማችን የህዝብ ቁጥር መጨመር ብቻ ሳይሆን ሰዎች ሥጋን የመግዛት አቅም መጨመርም ለፍጆታ መጨመር ምክንያት ነዉ። ብዙ ሥጋ የሚበላዉ ማን ነዉ? በዓለም ላይ ያለውን ሥጋን የመመገብ ልምድ ስንመለከት ከሃብት ጋር ከፍተኛ ቁርኝት ኖሮት እናገኘዋለን። በዚህም በበለፀገው የምዕራቡ ዓለም ሥጋ በከፍተኛ ሁኔታ ይበላል። በብዙዎቹ ምዕራብ አውሮፓ ሀገራት አንድ ሰዉ ከ80 እስከ 90 ኪሎ ሥጋ በዓመት ይመገባል። በተቃራኒዉ የድሃ ሀገራት ዜጎች እጅግ አነስተኛ መጠን ያለው ሥጋ ይመገባሉ። ኢትዮጵያዊያንም ከዚሁ ምድብ ውስጥ የሚካተቱ ሲሆን በአማካይ አንድ ኢትዮጵያዊ 7 ኪሎ ግራም ብቻ ይመገባሉ። ይህ ማለት ደግሞ አሃዙ አንድ አዉሮፓዊ ከሚመገበው የሥጋ መጠን በአስር እጥፍ ያንሳል። የመካከለኛ ገቢ ሃገራት የስጋ ፍላጎት መጨመር የዓለማችን ሃብታም ሃገራት ነዋሪዎች ከፍተኛ መጠን ያለው ሥጋ ሲመገቡ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸዉ ሀገራት ደግሞ አነስተኛ የሥጋ ይመገባሉ። ይህ ላለፉት 50 ዓመታት የቀጠለ ሲሆን አሁን ግን መጠኑ እየጨመረ እንደሆነ ይታመናል። ለዚህ ምክንያቱ የመካከለኛ ገቢ ሃገራት ቁጥር መጨመር ነዉ። ባለፉት 10 ዓመታት ፈጣን የሆነ የኢኮኖሚ እድገት ያሳዩ ሀገራት እንደ የቻይና እና የብራዚል ዜጎች በመጠኑ ከፍተኛ የሆነ ሥጋን እየተመገቡ ነው። • ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን? በኬንያ የሥጋ ፍጆታ ላለፉት 50 ዓመታት በጣም በትንሹ የተለወጠ ሲሆን በተቃራኒዉ ግን በቻይና በ1960 በአማካኝ በዓመት ከ5 ኪሎ በታች ይመገብ የነበረ ሰው በመጨረሻዎቹ 1980 መጠኑ ወደ 20 ኪሎ አድጓል። በተጨማሪም ላለፉት ጥቂት አስርት ዓመታት ከ3 እጥፍ በላይ አድጎ ወደ 60 ኪሎ ግራም ደርሷል። በተመሳሳይ መልኩ በብራዚል የሥጋ ፍጆታ ብዙዎቹን አዉሮፓ አገራት በመብለጥ ከ1990ዎቹ ከጥፍ በላይ አድጓል። የሥጋ ፍጆታ በምዕራቡ ዓለም እየቀነሰ ነዉ ወይስ? ብዙ አውሮፓዉያን እና አሜሪካውያን የሚመገቡትን የሥጋ መጠን ለመቀነስ እየሞከርን ነው ይላሉ። ነገር ግን ውጤቱ ይህን አያመለክትም። በቅርቡ የአሜሪካ የግብርና መስሪያ ቤት እንዳወጣው መረጃ ከሆነ የአንድ ሰው የሥጋ ፍጆታ ላለፉት ጥቂት ዓመታት ጭማሪ አሳይቷል። የምዕራቡ ዓለም ነዋሪዎች የሚጠቀሙት የሥጋ መጠን በትንሹ ጭማሪ ቢያሳይም የሚመገቡት የሥጋ አይነት ግን ለውጥ ይታይበታል። የአእዋፋት የሥጋ ውጤቶች መጨመር ሲያሳይ የበሬ እና የአሳማ ሥጋ አጠቃቀም ግን ቅናሽ አሳይቷል። የሥጋ ተፅእኖ በአካባቢ ላይ የተመጣጠነ የሥጋ እና የወተት ውጤቶችን መጠቀም የሰዎችን ጤና ያሻሽላል። በተለይ አነስተኛ ገቢ ላላቸዉ ሀገራት ነዋሪዎች ጠቀሜታቸዉ የላቀ ነው ምክንያቱ ደግሞ የተለያዩ አይነት ተመጣጣኝ ምግቦች ስለማያገኙ ነው። ነገር ግን ከመጠኑ ያለፈ ቀይ ሥጋን መመገብ ለልብ፣ ለስትሮክ እና ለካንሰር በሽታዎች ያጋልጣል። የዶሮ ሥጋን በቀይ ስጋ ምትክ መመገብ በጎ ምርጫ ነው። ይህ ለውጥም ለተፈጥሮ አካባቢ ደህንነት እጅጉን ይጠቅማል። ከብቶች የሚመገቡትን መኖ ወደ ሥጋ በመቀየር ረገድ የሌሎቹን እንስሳት ያህል ብቁ አይደሉም። • አመጋገባችን ማረጥን ሊያፋጥን ወይም ሊያዘገይ ይችላል ከብቶች ከዶሮዎች አንፃር ከ3 እስከ 10 እጥፍ የመሬት፣ ውሃ እና አካባቢን የሚበክል ጋዝ ልቀት ላይ አስተዋፅኦ አላቸው። አሳማዎች ደግሞ ከሁለቱ መሃል ላይ የመደባሉ። ለወደፊቱ የተመጣጠነና አስተማማኝ የሆነ የሥጋ አጠቃቀምን በሀገሮች መካከል ለመፍጠር በጥቂት የማይባሉ ለውጦች ያስፈልጋሉ፤ ይህም የምንመገበውን የሥጋ አይነት መቀየር ብቻ ሳይሆን መጠኑንም መቀነስ ያካትታል ተብሏል።
news-48571968
https://www.bbc.com/amharic/news-48571968
አምስት ጂ ኢንተርኔት ምን አዲስ ነገር አለው?
በኢትዮጵያ 3ጂ ኢንተርኔት ትግል ሲሆን ሌሎች ሃገራት ደግሞ ፈር ቀዳጅ ያሏቸውን የቴክኖሎጂ ውጤታቸውን እያስተዋወቁ ነው፤ እንግሊዝም ከሰሞኑ አምስት ጂ ኔትወርኳን አስተዋውቃለች።
ደንበኞች ለረጅም ጊዜ ከመጓጓታቸው አንፃር ብዙዎች የተደሰቱበት ቢሆንም ግራ መጋባቱ እንዳለም ተገልጿል። በመጀመሪያ ደረጃ እንደ ቴክኖሎጂው አዲስነት ዋጋው ብዙ የሚቀመስ አልሆነም፤ ኔትወርኩ በሁሉም አይነት ተንቀሳቃሽ ስልክ ስለማይሰራ ለዚህ ቴክኖሎጂ የሚሆን ስልክ ለመግዛት በአንድ ጊዜ የሚከፈል 7650 ብር ከዚያም በየወሩ 2430 ብር መክፈል ደንበኞች ይጠበቅባቸዋል። •ሁዋዌ የተጣለበት እገዳ የስልኩ ተጠቃሚዎች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል? ይህ ክፍያ ግን በየወሩ 10 ጊጋ ባይት ዳታ ብቻ የሚጠቀሙ ከሆነ ነው እንጂ እንዲያው ሌሎች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እጭናለሁ ካሉ ሌላ ተጨማሪ ክፍያ ያስፈልጋል። የአምስት ጂ ኔትወርክን በመጀመር ፈር ቀዳጅ የሆነው የእንግሊዙ ቴሌኮሚዩኒኬሽን ቢቲ አካል የሆነው የተንቀሳቃሽ ስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት ሰጪው ኢኢ የተባለው ድርጅት ነው። ቮዳፎን የተሰኘው ድርጅትም በቅርቡ የአምስት ጂ ኔትወርክ አገልግሎት ለመስጠት በዝግጅት ላይ መሆኑም ታውቋል። ነገር ግን ብዙዎች አገልግሎቱን ለመጠቀም አልተቻኮሉም፤ መጠበቅን መርጠዋል። • የጉግልና የሁዋዌ ፍጥጫ አፍሪካዊያንን የሚያሳስብ ነው? የተንቀሳቃሽ ስልኮችን የውስጥ ቁስ አምራች የሆነው ኳልኮም የአምስት ጂ ኔትወርክ አገልግሎት የሚሰጡ ተንቀሳቃሽ ስልኮች የባትሪ ቆይታቸው ረዘም ያለ ጊዜ እንደሚሆን ቃል ገብቷል። ምን ያህል ፈጣን ነው? የእንግሊዝ ኮሚዩኒኬሽን ተቆጣጣሪው ድርጅት ኦፍ ኮም እንደሚለው የአምስት ጂ ኔትወርክ ፍጥነት በሰከንድ 20 ጊጋ ባይት እንደሚሆን ነው። የአንድ ፊልም ጭብጡን እስኪያነቡ በሚወስደው ጊዜ ከፍተኛ ጥራት ያለውን ፊልሙን ዳውንሎድ አድርገው መጨረስ ይችላሉ እንደ ማለት ነው። • በሁዋዌ ስልኮች ላይ ፌስ ቡክን መጠቀም ሊቆም ይሆን? ነገር ግን ለአሁኑ ደንበኞች ብዙ እንዳይጠብቁ ድርጅቱ ያስጠነቅቃል፤ ምክንያቱም አገልግሎቱን የሚሰጠው ኢኢ የአምስት ጂ ኔትወርክ ለመዘርጋት የሚጠቀመው መስመር በሰከንድ ያለው ፍጥነት አስር ጊጋ ባይት ብቻ ሲሆን ይህ ለአንድ ተጠቃሚ ብቻ ሳይሆን፤ ለሌሎችም የሚጋራ ይሆናል። በዚህም መሰረት በአማካኝ አንድ ደንበኛ የሚያገኘው የፍጥነት መጠን በሰከንድ 150-200 ሜጋ ባይት ሊሆን እንደሚችልና፤ ብዙ ሰው በማይጠቀምበት ወቅት ለአንዳንድ እድለኞች እስከ አንድ ጊጋ ባይት ሊደርስ ይችል ተብሏል። ፈጣን ኢንተርኔት ብቻ ይሆን? ምንም እንኳን ደንበኞችን ለመሳብ ለጊዜው የአምስት ጂ ኔትወርክ እየተዋወቀ ያለው ከፈጣን ኢንተርኔት ጋር በተያያዘ መልኩ ቢሆንም ለዘላቂው ግን አምስት ጂ ኔትወርክ ያላቸው ስልኮች በአንድ ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን ስልኮች በላይ መገናኘት የሚያስችል ኔትወርክ ተዘርግቶላቸዋል። ነገር ግን ይህንን ሁሉ ለማከናወን ከአውቶብስ ማረፊያ ጀምሮ በተለያዩ ቦታዎች አዳዲስ አንቴናዎች መትከል ያስፈልጋል ተብሏል። • በሞባይሎ ኢንተርኔት ወጪ ተማረዋል? ከግለሰቦች በተጨማሪ የደንበኞችን መረጃ በመሰብሰብ ለንግድም ሆነ እንዲሁም ለደህንነት ሥራ ለሚጠቀሙበት ለመንግሥትም ሆነ ለተለያዩ ድርጅቶችም ከፍተኛ ጥቅም እንዳለውም ተገልጿል። ከዚህም በተጨማሪ ለተለያዩ ደንበኞች በሚፈልጉት መጠን ኔትወርክ የሚያከፋፍል ሲሆን ለምሳሌ የአደጋ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ደንበኞችም ዩቲዩብና ሌሎች ዳታን የሚጨርሱ አገልግሎቶች ተጠቃሚዎች ምንም እንዳይደናቀፉ ይደረጋል። ይህ ከጥቂት ዓመታትም በኋላ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል። የሁዋዌስ ነገር እንዴት ነው? ከደህንነት ጉዳዮች ጋር ተያይዞ የቻይናው ኩባንያ ሁዋዌ የአምስት ጂ ኔትወርክ እቅዱ እገዳ ይገጥመዋል ተብሏል። ባለፈው ወር ኩባንያው ለአምስት ጂ ኔትወርኩ አንቴናና ሌሎችም ቁሶች ፍቃድ ሊሰጠው የሚመስሉ ፍንጮች ቢታዩም የጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይን መልቀቅ ተከትሎ የማይሆን ነው ተብሏል። የኩባንያውን መሰረተ ልማት ማገዱ ለአገልግሎት ሰጪዎቹ ራስ ምታት እንደሚሆን እየተነገረ ነው። ኢኢና ቮዳፎን ይጠቀሙባቸው የነበሩ የሁዋዌ የውስጥ አካላትን እንዳይጠቀሙ ከተገደዱ ሥራቸውን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያከብደ እየተነገረ ነው። •ኢትዮ ቴሌኮም... ወዴት? ወዴት? ሁለቱም ድርጅቶች እንደገለፁት የሁዋዌ መገለገያዎችን የውስጥ ክፍሎች መሀንዲሶቻቸው ለመተካት ከተገደዱ የአምስት ጂ ኔትወርክ አገልግሎታቸውን ሊያዘገየው እንደሚችል ነው። የአገሪቱ ስልክ አምራቾችም ሆነ ኢንተርኔት አገልግሎት ሰጪዎች በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ከሁዋዌ ጋር በመነካካታቸው ብዙ ነገሮች ሊወሳሰቡ ይችላሉ እየተባለ ነው። ምንም እንኳን አምስት ጂ ኢንተርኔትን ለመጀመር ከአውሮፓ ሃገራት እንግሊዝ ፈር ቀዳጅ ብትሆንም ከሁዋዌ ጋር በተያያዘ ለመላው አገሪቷ ሽፋን ለመስጠት እንቅፋት እንደሚሆንና ሌሎቹም ሊቀድሟት ይችላሉ እየተባለ ነው።
news-54282143
https://www.bbc.com/amharic/news-54282143
ጃዋር መሐመድ ፡ 18 ተከሳሾች ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ ተወሰነ
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእነ አቶ ጃዋር መዝገብ የተመሰረተውን ክስ ለማንበብ ለመስከረም 21/2013 ቀጠሮ ያዘ።
በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤቱ በተከሳሾች ላይ የተመሰረተውን ክስ ለማንበብ ቀጠሮ ይዞ የነበረ ቢሆንም ከተከሳሽ ጠበቆች በቀረበ ጥያቄ መሰረት ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ ተደርጓል። በሌላ በኩል ፍርድ ቤቱ ከዚህ በኋላ እነ አቶ ጃዋርን ጨምሮ ሌሎች 18 ተከሳሾች ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ አዟል። እስካሁን ድረስ እነ አቶ ጃዋር አዲስ አበባ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማዕከል ይገኙ ነበር። የዛሬ ውሎ በዛሬው ችሎት በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ መዝገብ ስር ከተከሰሱትና በአገር ውስጥ ከሚገኙት መካከል አቶ ደጀኔ ጣፋ እና አቶ መስተዋርድ ተማም ለሁለተኛ ጊዜ አልቀረቡም። ከአገር ውጪ የሚገኙ ተከሳሾችን በተመለከተም ፖሊስ እነዚህ ተከሳሾች ለማቅረብ የተሰጠው ጊዜ ቀጠሮ አጭር ስለሆነ ለማስፈፀም እንዳልቻለ ዐቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል። ጠበቆች በበኩላቸው እነዚህ ሰዎች ውጪ አገር እንዳሉ እንዲሁም ክሱ በሌሉበት እንደተከፈተ እየታወቀ፣ ፖሊስ ይዞ እንዲያቀርብ በሚል ምክንያት ቀጠሮ ማስረዘም ትክክል አይደለም በማለት ተከራክረዋል። የአቶ ደጀኔ ጣፋንና መስተዋርድ ተማምን ጉዳይ በተመለከተ ሁለቱ ተከሳሾች በሌላ መዝገብ ተከሰው ስላሉ በዛሬው ቀጠሮ ላይ መቅረብ እንዳልቻሉ ዐቃቤ ሕግ አስረድቷል። በሌላ በኩል አቶ ደጀኔ ጣፋ በቤተሰቦቻቸው እየተጎበኙ እንዳልሆነ እና አስፈላጊውን ነገሮች እያገኙ እንዳልሆነ ጠበቃቸው ለፍርድ ቤቱ አቤቱታቸውን አሰምተዋል። በዛሬው ችሎት ላይ የተናገሩት አቶ ሸምሰዲን ጠሃ ታመው ሐኪም ቤት እየተመላለሱ እንዳሉ በመግለጽ የሕክምና ቀጠሮ እያለባቸው በመከልከላቸው ሕመማቸው እየበረታባቸው መሆኑን በማንሳት አቤቱታ አቅርበዋል። ክስ ለመስማት ለዛሬ ተይዞ የነበረው የችሎት ቀጠሮ በአቶ ደጀኔ እና አቶ መስተዋርድ አለመገኘት የተነሳ ክሱ ይነበብ አይነበብ በሚለው ላይ በጠበቆች እና በዐቃቤ ሕግ መካከል ረዥም ክርክር ተካሂዷል። ጠበቆች፤ ደጀኔ እና መስተዋርድ ስላልቀረቡ ክሳቸው በአንድ ቦታ መሰማት አለበት፣ እኛም ያለንን ተቃውሞ በአንድ ቦታ ስለምናቀርብ ሌላ ቀጠሮ ይሰጠን ሲሉ ጠይቀዋል። በሌላ በኩል ሌሎች በዚህ መዝገብ ስር የተከሰሱ ተከሳሾችን በሚገኙበት ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ አግኝተን ለማወያየት አልቻልንም በማለት ጠበቆች ቅሬታቸውን አሰምተዋል። ወደ ማረሚያ ቤት ዐቃቤ ሕግ ተከሳሾችን ክሱ እጃቸው ከደረሰ በኋላ አሁን በጊዜያዊነት ከቆዩበት ስፍራ ወደ ማረሚያ ቤት በመሄድ ተመሳሳይ ወደ በሆነ ቦታ መታሰር አለባቸው ሲል ጠይቋል። ጠበቆች በበኩላቸው ከአንድ እስከ ሦስት ያሉት ተከሳሾች በፖለቲካ ውስጥ ትልቅ ድርሻ ያላቸው ስለሆኑ ለደኅንነታቸው ሲባል አሁን እንዲቆዩ ከተደረገበት ስፍራ መቀየር የለባቸውም ሲል ተከራክሯል። ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ ትዕዛዝ አስተላልፏል። በዚህም መሰረት ተከሳሾች የሚቆዩበትን በተመለከተ ተከሳሾች ከአሁን በኋላ ወደ ማረሚያ ቤት እንዲዛወሩ ትዕዛዝ አስተላልፏል፟። ከሳምንት በፊት ፍርድ ቤቱ በሽብር ድርጊት ክስ የቀረበባቸው የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ሊቀመንበር አቶ እስክንድር ነጋን ጉዳያቸውን ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በመሆን አንዲከታተሉ መወሰኑ ይታወሳል። ውጪ አገር ያሉ ተከሳሾችን በተመለከተ የፌደራል ፖሊስ በሚቀጥለው ቀጠሮ ላይ ቀርቦ የደረሰበትን እንዲያብራራ አዟል።
news-47621600
https://www.bbc.com/amharic/news-47621600
የዓለማችን ውድ እና ርካሽ ከተሞች ይፋ ሆኑ
ፓሪስ፣ ሆንግ ኮንግና ሴንጋፑር የምድራችን እጅግ ለኑሮ ውድ የሆኑ ከተሞች በመሆን በአንድነት የቀዳሚነቱን ቦታ ያዙ።
በሰላሳ ዓመታት ውስጥ ሦስት ከተሞች በአንድ ላይ ተመሳሳይ የውድነት ደረጃ ላይ ሲገኙ ይህ የመጀመሪያው እንደሆነም ተነግሯል። የኢኮኖሚስት ኢንተለጀንስ ዩኒት በሚያደረገው ጥናት መሰረት በየዓመቱ በዓለም ላይ የኑሮ ውድነት የሚስተዋልባቸውንና በአንጻሩ ደግሞ ርካሽ የሆኑ ከተሞችን በጥናት ላይ ተመስርቶ ዝርዝራቸውን ያወጣል። • ለኑሮ ምቹ የሆኑ 10 ከተሞች ይፋ ሆኑ የዚህ ዓመቱ ጥናት በ133 የዓለማችን ከተሞች ላይ የተደረገ ሲሆን መሰረታዊ የሚባሉ የኑሮ ጥያቄዎችን መነሻ አድርጎ ነው የተከናወነው። ለምሳሌ የዳቦ ዋጋ ምን ያክል ያለመዋዠቅ ይቀጥላል? ሰዎች የውበት ሳሎን ገብተው ምን ያክል ይከፍላሉ? የሚሉ ሁኔታዎችን ታሳቢ አድርጓል። በዚህም መሰረት የፈረንሳይዋ መዲና ፓሪስ ከሲንጋፖርና ሆነግ ኮንግ ጋር የዓለማችን ውድ ከተማ ሆነዋል። ፓሪስ ባለፈው ዓመት ሁለተኛ ደረጃ ላይ የነበረች ሲሆን ከአውሮፓ ህብረት ቀጠና ውስጥ ብቸኛዋ የኑሮ ውድነት የተሰቀለባት ከተማ ያደርጋታል። • ካይሮ፡ ለሴቶች በጣም አደገኛ ከሆኑ ከተሞች አንዷ ለምሳሌ በፓሪስ አማካዩ የሴቶች የውበት ሳሎን ክፍያ 119.04 ዶላር ነው። ተመሳሳይ አገልግሎትን ግን ዙሪክ ውስጥ በ73.97 ዶላርና የጃፓኗ ኦሳካ ከተማ ውስጥ ደግሞ በ53.46 ዶላር ማግኘት ይቻላል። በአጠቃላይ የአለማችን ውድ 10 ከተሞች የሚከተሉት ናቸው ብሏቸዋል። 1. ሲንጋፖር (ሲንጋፖር) 1. ፓሪስ (ፈረንሳይ) 1. ሆንግ ኮንግ (ቻይና) 4. ዙሪክ (ስዊዘርላንድ) 5. ጀኔቫ (ሰዊዘርላንድ) 5. ኦሳካ (ጃፓን) 7. ሴዑል (ደቡብ ኮሪያ) 7. ኮፐንሃግን (ዴንማርክ) 7. ኒው ዮርክ (አሜሪካ) 10. ቴል አቪቭ (እስራኤል) 10. ሎስ አንጀለስ (አሜሪካ) • የአየር ብክለት በከተሞች ለሚደረጉ ማራቶኖች ስጋት ነው? ተቋሙ በሌላ በኩልም ዓለም ላይ በትንሽ ገንዘብ መኖር የሚቻልባቸው ርካሽ ከተሞች የትኞቹ ናቸው የሚለውንም አጥንቷል። የሚገርመው ነገር ግን በዚህኛው ዝርዝር ውስጥ የሚገኙት አብዛኛዎቹ ከተሞች በፖለቲካ እና በምጣኔ ሃብት ኪሳራ የደረሰባቸው ሀገራት ከተሞች ሲሆኑ ህንድ ሦስት ከተሞችን በማስመዝገብ ቀዳሚ ነች። እነዚህም ከተሞች 1. ካራካስ (ቬንዝዌላ) 2. ደማሰቆ (ሶሪያ) 3. ታሽኬንት (ኡዝበኪስታን) 4. አልማቲ (ካዛኪስታን) 5. ባንጋሎር (ህንድ) 6. ካራቺ (ፓኪስታን) 6. ሌጎስ (ናይጀሪያ) 7. ቦኖስ አይረስ (አርጀንቲና) 7. ቺናይ (ህንድ) 8. ኒው ደልሂ (ህንድ)
news-49781620
https://www.bbc.com/amharic/news-49781620
ኢትዮጵያ በዚህ ወር ልታመጥቀው የነበረውን ሳተላይት ወደ ታህሳስ ማዘዋወሯ ተነገረ
ኢትየጵያ በዚህ ወር ልታመጥቀው የነበረው ሳተላይት ወደ ታህሳስ 17 ቀን 2012 ዓ. ም. መዘዋወሩን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሰለሞን በላይ ለቢቢሲ ተናገሩ።
ኢትዮጵያ የመሬት ምልከታ ሳተላይት (Earth Observation Satellite) በዚህ ዓመት መባቻ ላይ ከቻይና ለማምጠቅ እቅድ ይዛ እንደነበረ ይታወሳል። ዶ/ር ሰለሞን ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ ሳተላይቱን የምትቆጣጠርበት እና የምታዝበትን ጣቢያ (ግራውንድ ስቴሽን) በከፍተኛ ዝናብ ምክንያት መሞከር ስላልተቻለ፤ ሳተላይቱ የሚመጥቅበት ቀን ተሸጋግሯል። • ኢትዮጵያ ሳተላይት ማምጠቅ ለምን አስፈለጋት? • በሳተላይቶች ዙሪያ ሰባት አስደናቂ እውነታዎች • ኬንያ ሳተላይት ልታመጥቅ ነው የሳተላይት ግንባታው በተያዘለት ጊዜ መጠናቀቁን ገልጸው፤ መቆጣጠሪያ ጣቢያው በአግባቡ ሳይሞከር ሳተላይቱን ማምጠቅ ስለማይቻል፤ ከቻይና አጋሮቻቸው ጋር በመመካከር ወደ ታህሳስ ለማዘዋወር መወሰናቸውን አስረድተዋል። "የጣቢያው ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል፤ የሚቀረን መሞከር ነው። ታህሳስ ላይ መቶ በመቶ ይመጥቃል" ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ። ይህ ሳተላይት ከምድር ወደ ህዋ ከተመነጠቀ በኋላ መሬትን እየቃኘ መረጃዎችን በፎቶ ይመዘግባል። እንደያስፈላጊነቱም መረጃውን ወደ ምድር ይልካል። አፍሪካ ውስጥ እስካሁን ሳተላይቱን ያመጠቁ በጣት የሚቆጠሩ አገሮች ሲሆኑ፤ ኢትዮጵያም የአምጣቂዎቹን ቡድን ለመቀላቀል ከሦስት ዓመት በፊት መሰናዶ መጀመሯ ይታወሳል። ዓለም ላይ ሳተላይት ማምጠቂያ (ላውንቸር) ያላቸው ጥቂት አገሮች ሲሆኑ፤ ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ባደረገችው ስምምነት መሰረት፤ ሳተላይቱ ከቻይና የሚመጥቅ ይሆናል። የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሉት፤ ሳተላይቱ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቆጣጠር፣ የተፈጥሮ አደጋዎች ከመድረሳቸው በፊት አስቀድሞ ለመተንበይ፣ ደህንነትን ለመጠበቅ ወዘተርፈ ይውላል። የደን ቁጥር፣ የአየር ንብረት ለውጥና ሌሎችም መረጃዎች ከተሰበቡ በኋላ እንደ ጎርፍ ያሉ አደጋዎች ከመከሰታቸው በፊት መተንበይ እና መከላከል ይቻላል። ዶ/ር ሰለሞን ስለ ሳተላይቱ ሲያብራሩ፤ አንድ የግብርና አካባቢን የሚያሳይ ፎቶግራፍ ስለ እርሻ መሬቱ፣ ስለ ውሀው፣ ስለ አፈሩ ዝርዘር መረጃ ይሰጣል ይላሉ። መረጃዎቹን በመጠቀም ምርታማ የሆኑ አካባቢዎችን መለየት፣ የምርት መጠንን በትክክል ማወቅም ይቻላል። ኢንዱስትሪዎች እየተስፋፉ በመጡባት ኢትዮጵያ፤ ፋብሪካዎች የት መገንባት አለባቸው? ለሚለው ጥያቄ የሳተላይቱ መረጃ መልስ ሊሰጥ ይችላል። ሕዝብ መቁጠር ሲያስፈልግ ከዘልማዳዊው መንገድ ሳተላይቱን መጠቀም ይመረጣል። ትክክለኛ መረጃ ከማግኘት፣ ገንዘብና የሰው ሀይል ከማዳን አንጻርም የተሻለው አማራጭ ነው። ኢትዮጵያ እነዚህን መረጃዎች ሳተላይት አምጥቀው ፎቶ ከሚያስነሱ አገሮች ትሸምት እንደነበርም ዋና ዳይሬክተሩ ያስረዳሉ። የሳተላይቱ ግንባታ የተጀመረው ከቻይና በተገኘ 6 ሚሊየን ዶላር ሲሆን፤ ቻይናውያን ኢንጂነሮች ኢዮጵያውያንን እያሰለጠኑ ሳተላይቱ ቻይና ውስጥ እንዲሁም በከፊል ኢትዮጵያ ውስጥ ተገንብቷል።
news-48327459
https://www.bbc.com/amharic/news-48327459
"የተፈናቃዮች አያያዝ ከሰብዓዊነት የራቀ ነው" ሪፊዩጂ ኢንተርናሽናል
ባለፈው ዓመት በደቡብ ኢትዮጵያ በሚገኙ ማኅበረሰቦች መካከል የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የተፈናቀሉ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን በግዳጅ ወደቀያቸው እንዲመለሱ የማድረግ ጥረት እንዳሳሰበው ሪፊዩጂ ኢንተርናሽናል የተባለው ግብረሰናይ ድርጅት አስታወቀ።
ድርጅቱ ባወጣው ተፈናቃዮችን የተመለከተ ሪፖርት ላይ በተለያዩ መጠለያዎች ውስጥ የሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በጫና ወደቀያቸው እንዲመለሱ ግፊት እየተደረገባቸው መሆኑን አመልክቷል። • አምስት ነጥቦች ስለጌዲዮ ተፈናቃዮች "ይህ የመንግሥት እርምጃ፤ ያለውን የሰብዓዊ ቀውስ ሁኔታ የበለጠ የከፋ ያደርገዋል" ሲሉ ባለፈው መስከረም ወር ወደ አካባቢ ተጉዘው የነበሩት የግብረሰናይ ድርጅቱ ባለሙያ ማርክ ያርኔል ተናግረዋል። ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ አቅንቶ የነበረው የሪፊዩጂ ኢንተርናሽናል ልኡክ እንዳለው የመንግሥት ባለሥልጣናት ተፈናቃዮቹ ወደመጡበት እንዲመለሱ ለማስገደድ ወደተጠለሉባቸው ካምፖች ድጋፍ እንዳይደርስ እንደሚደረግ አመልክቷል። በተጨማሪም ወደቀያቸው ከተመለሱ እርዳታን እንደሚያገኙ ቢነገራቸውም ቤታቸው በግጭቱ መውደሙንና በአካባቢያቸውም አስተማማኝ የደህንነት ሁኔታ እንደሌለ ተገልጿል። • ጌዲዮ በዐቢይ ጉብኝት ማግስት ቢሆንም ግን ባለፈው ወር በፌደራል መንግሥቱ የቀረበው የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን የሚመለከተው ዕቅድ ላይ ተፈናቃዮችን ወደቀያቸው የመመለሱ ሥራ "በፈቃደኝነታቸው ላይ የተመሰረተ፣ ደህንነታቸው የተጠበቀና ዘላቂ ድጋፍን የሚያገኙበት" እንደሚሆን ተገልጾ ነበር ይላል ሪፖርቱ። ሪፊዩጂ ኢንተርናሽናል እንደሚለው መንግሥት በተቃራኒው ተፈናቃዮችን በማስገደድ እንዲመለሱ እየያደረገ ነው ይላል። አክሎም በአሁኑ ወቅት ተፈናቃዮቹ ተጠልለውባቸው የነበሩ ቦታዎችን በማፍረስ ጭምር ጫና እየተደረገባቸው መሆኑን አሰታውቋል። መንግሥት ስደተኞችን በተመለከተ እየወሰደ ባለው እርምጃ ከዓለም ዙሪያ እየተመሰገነ ባለበት በዚህ ወቅት፤ የራሱን ተፈናቃይ ዜጎችን የያዘበት መንገድ አሳፋሪ ብቻ ሳይሆን ከሰብዓዊነት የራቀ ነው" ሲሉ ኮንነውታል። ያርኔል እንዳሉት "ይህ መሰረታዊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነው።" • የጌዲዮ ተፈናቃዮች የከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት አጋጥሟቸዋል ሪፊዩጂ ኢንተርናሽናል አክሎም አሁን እየተካሄደ ያለው የመመለስ ጥረት በፈቃደኝነት፣ በዘላቂነትና ከተፈናቃዮቹ ጋር በመተባበር የሚደረግ እስከሚሆን ድረስ እንዲቆም እንዲደረግ ጥሪውን አቅርቧል። ከሳምንት በፊት ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪ ቢለኔ ስዩም እንደተናገሩት በተለያዩ ምክንያቶች የተፈናቀሉ ሰዎችን ወደቀያቸው ለመመለስ መንግሥት ጥረት እያደረገ መሆኑን አመልክተው 875 ሺህ የሚደርሱት መመለሳቸውን ገልጸው ነበር። ተፈናቃዮቹ ወደቀያቸው በሚመለሱበት ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው አያያዝ ተግባራዊ እንደሚደረግና ደህንነታቸው ተጠብቆ የሚያስፈልጋቸው መሠረተ ልማት ተሟልቶ እንዲሆን መንግሥት ጥረት እንደሚያደርግ ጨምረው መግለጻቸው ይታወሳል።
55914753
https://www.bbc.com/amharic/55914753
ፈረንሳይ አዛውንት ዜጎቼን አስትራዜኒካ ክትባትን አልከትብም አለች
የፈረንሳይ የጤና ሚኒስቴር አስትራዜኔካ የኮቪድ ክትባትን በዕድሜ ለገፉ ዜጎች መሰጠት የለበትም ሲል ወሰነ።
ምክንያቱ ደግሞ ክትባቱ በአዛውንቶች ዘንድ የሚያመጣው የጎንዮሽ ጉዳትን በተመለከተ አጥጋቢ ምርምር አልተደረገም፣ የተደረገው ምርምር ውጤትን የሚያሳይ መረጃም ገና አልደረሰንም በሚል ነው። ክትባቱ አይሰጣቸውም የተባሉት ዕድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ ለሆኑት ዜጎች ነው። የአውሮጳ ኅብረት የመድኃኒት ቁጥጥር ክፍል ኦክስፎርድ አስትራዜኒካ ክትባት ለሁሉም አዋቂዎች መሰጠት ይችላል ብሎ ያጸደቀ ሲሆን ነገር ግን አባል አገራት የፈለጉትን የዕድሜ ወሰን ሊያስቀምጡ ይችላሉ ሲል መብት ሰጥቷል። ከፈረንሳይ ቀደም ብሎ ጀርመንና ኦስትሪያ ተመሳሳይ ውሳኔ ላይ መድረሳቸው መዘገቡ ይታወሳል። አገራቱ ከ65 ዓመት በላይ ለሆኑ ዜጎች ክትባቱን ለመስጠት የሰጉት በቂ የምርምር መረጃ ወይም ዳታ አልቀረበም በሚል ነው። የፈረንሳይ ጤና ሚኒስቴር እንዳለው በክትባቱ ዙርያ ሙሉ ዳታ በሚቀጥለው ሳምንት ይደርሳል። እስከዚያ ግን ከ65 ዓመት በታች ላሉት ብቻ ክትባት እንሰጣለን ብሏል። ክትባቱን በቅድሚያ የሚያገኙት ዕድሜያቸው ከ50 እስከ 65 የሆኑትና የሥራ ባህሪያቸው ለተህዋሲው ተጋላጭ ያደረጋቸው ዜጎች ናቸው። በፈረንሳይ እስከ አሁን 1.5 ሚሊዮን ዜጎች ክትባት ደርሷቸዋል። የፈረንሳይን ያህል ሕዝብ ያላት ታላቋ ብሪታኒያ 10 ሚሊዮን ሕዝቦቿን ከትባ ጨርሳለች። ሆኖም የአውሮጳ ኅብረት ጉዳዮች ኃላፊ ሚኒስትር ክሌመንት በሰጡት አስተያየት ታላቋ ብሪታኒያ ለዜጎች የሚሰጠውን ሁለት ጠብታ ለጊዜው አንድ አንድ በማደል ትልቅ አደጋን ጋብዘዋል ሲሉ በሬዲዮ አስተያየተ ሰጥተዋል። ሳይንቲስቶች አንድ ሰው አንድ ጠብታን ወስዶ ሁለተኛውን ከሚጠብቅ ሁለቱን ጠብታ ቢወስድ ነው የተሻለው ነው የሚሉት ያሉት ሚኒስትሩ ዩኬ ግን አሻፈረኝ ብላለች ሲሉ ተችተዋል። አስትራ ዜኒካ በሳምንታት ልዩነት 2 ጠብታዎችን መወጋትን የሚሻ የክትባት ዓይነት ነው። የአውሮጳ ኅብረት አገራት ሚኒስትሮች ይህ ክትባት ለየትኛው ዕድሜ ላሉ ይሰጥ በሚለው እየተወዛገቡ ነው። ጀርመን እና ኦስትሪያ ከ65 በታች ለሆኑት ብቻ ለመስጠት ሲወስኑ ቤልጂየም ግን ከ55 በታች ብቻ ነው የምሰጠው ብላለች። ጣሊያንም በተመሳሳይ ከ55 ዕድሜ በታች ብቻ ላሉት ክትባት ለማደል ወስናለች። ስዊድንና ፖላንድም ተመሳሳይ ውሳኔ ላይ ደርሰዋል።
news-46204836
https://www.bbc.com/amharic/news-46204836
ታይላንዳዊው የ13 ዓመቱ ቦክሰኛ አኑቻ ኮቻና በቦክስ ውድድር ሳቢያ ሕይወቱ አለፈ
የ13 ዓመቱ ታዳጊ የቦክስ ውድድር ሳቢያ ሕይወቱ ማለፉን ተከትሎ ታይላንድ የህፃናት የቦክስ ውድድርን እንድታግድ የነበሩ ጥያቄዎች በርትተው ቀጥለዋል።
ታዳጊው የቦክስ ውድድር የጀመረው በ8 ዓመት ዕድሜው ነበር አኑቻ ኮቻና በአንድ ግብረ ሰናይ ድርጅት ባዘጋጀው ውድድር ላይ ባጋጠመው የጭንቅላት ውስጣዊ ደም መፍሰስ ለሁለት ቀናት ህክምና ሲከታተል ቆይቶ ሕይወቱ አልፏል። የታቃራኒ ቡድን አባላት እንደገለፁት ታዳጊዎቹ ራሳቸውን ከአደጋ የሚከላከሉበት ትጥቅ አላጠለቁም ነበር። በዚህም ሳቢያ በውድድሩ ወቅት ታዳጊው ከመውደቁ በፊት ጭንቅላቱ ላይ መመታቱ ታውቋል። ታዳጊው ከ8 ዓመት ዕድሜው አንስቶ ቤተሰቦቹን ለመርዳት 170 ግጥሚያዎችን አድርጓል። • ንጉሡ ከሞቱ ከዓመት በኋላ የመጨረሻ ስንብት እየተካሄደ ነው በታይላንድ 'ሟይ' ተብሎ የሚጠራው የታዮች የቦክስ ውድድር በአገሪቱ በስፋት የሚታወቅ ነው። በሺዎች የሚቆጠሩ ተጋጣሚዎችና ቤተሰቦቻቸው ውድድሩን ገንዘብ የማግኛ መንገድ አድርገውታል። ይሁን እንጂ ይህንን ስፖርት ለማካሄድ ህጉ ክፍተት እንዳለበት ተደጋግሞ ይነሳል። በተቃራኒው አንዳንድ ሰዎች ህፃናቱን ከአደጋ ለመጠበቅ ሲባል ውድድሩን ለማገድ የሚደረገውን ጥረት አስፈላጊ አይደለም ሲሉ ይቃወማሉ፤ ምክንያታቸው ደግሞ በአገሪቱ ያለው ባህላዊ የቦክስ ውድድር አካል መሆን አለባቸው የሚል ነው። ይሁን እንጂ የጉዳዩን አደገኝነት ያሳሰበው የታይ ምክርቤትም ከ12 ዓመት በታች የቦክስ ውድድርን ለማገድ ህጉን እየመረመሩ ይገኛሉ። በታዳጊው አኑቻ ህልፈት በርካታ የታይ ነዋሪዎች አዝነዋል፤ በመካከለኛው ሳሙት ፕራካን ግዛት የተደረገው ውድድር ላይ የተነሳውን የቦክሰኛውን ምስል በመጋራት ሀዘናቸውን እየገለፁ ነው። በርካታ ቁጥር ያላቸው የቦክስ ከዋክብትም ሃዘናቸውን ገልፀዋል። • ሟች አሳዳጊውን የሚጠባበቀው ውሻ • "ሃገሬን ሳላስብ የዋልኩበት፤ ያደርኩበት ቀን የለም" ብርቱካን ሚደቅሳ የታይላንድ የብሔራዊ ስፖርት ባለስልጣን ባለፈው ዓመት ባወጣው መረጃ በአገሪቱ ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ከ10 ሺህ በላይ ቦክሰኞች ተመዝግበዋል። ስፖርትን የተመለከተው የብሔራዊ ህግ አውጭ ጉባዔ ምክትል ኃላፊ ገን አዱሌኣድጂ ኢንታፖግ በበኩላቸው " ዕድሜያቸው ከ12-15 ያሉ ህፃን ቦክሰኞች መመዝገብ፤ ከቤተሰቦቻቸው ፈቃድ ማግኘት እንዲሁም ራሳቸውን ከአደጋ የሚጠብቁበት ልብስ መልበስ አለባቸው " ሲሉ ተናግረዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ዘመቻ የሚያካሄዱ ቡድኖች ለውድድሩ አነስተኛው ዕድሜ 18 ዓመት መሆን አለበት ሲሉ ጠይቀዋል። ከአኑቻ ሞት ቀደም ብሎ ጣላኒያዊው ቦክሰኛ ክርስቲያን ዳጊኦ በውድድር ላይ ሕይወቱ ማለፉ የሚታወስ ነው።
news-49548035
https://www.bbc.com/amharic/news-49548035
"በክልሉ ታጥቆ የሚንቀሳቀስ ኃይል እናስቆማለን" የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት
በመጪው ዓመት በክልሉ ውስጥ ታጥቆ የሚንቀሳቀስ አካል እንዳይኖር አደርጋለሁ ሲል የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አስታወቀ።
ከመንግሥት ውጪ በሕገ-ወጥ መንገድ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀስ አካል እንዳይኖር ይደረጋል ሲሉ የክልሉ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ አድማሱ ዳምጠው ተናግረዋል። አቶ አድማሱ ይህን ያሉት ክልሉን የሚያስተዳድረው የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ እና የክልሉ መንግሥት በመጪው አዲስ የሥራ ዘመን ላይ ትኩረት አድርገው የሚሰሩባቸው ቁልፍ ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጠኞችን ሰብስበው ዛሬ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው። ቁጥራቸው እና የታጠቁት መሳሪያ በውል የማይታወቅ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ኃይሎች በምዕራብ እና ደቡብ ኦሮሚያ እንደሚንቀሳቀሱ ይታወቃል። ከዚህ ቀደም ኦነግ ታጣቂ ኃይሎቹን እንደማያውቃቸው ያሳወቀ ሲሆን፤ ታጣቂዎቹም ከፓርቲው ጋር ግንኙነት እንደሌላቸው ይፋ አድርገዋል። በምዕራብ ኦሮሚያ የሚንቀሳቀሰው ኃይል የጦር መሪ የሆነው ኩምሳ ዲሪባ ወይም መሮ፤ በምዕራቡ ክፍል የሚገኘው ኃይል የትጥቅ ትግል ማድረጉን እንደሚቀጥል በተደጋጋሚ ለቢቢሲ ተናግሯል። የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በበኩላቸው ኦነግ ታጥቆ የሚንቀሳቀስ የጦር ኃይል አይኖረውም በማለት ተናግረው ነበር። • የኦነግ ጦር መሪ በትግላችን እንቀጥላለን አለ • "ከ[እኛ] የተለየን ጦር 5 በመቶ እንኳ አይሆንም" መሮ የኦነግ ጦር አዛዥ አቶ አድማሱ በመጪው ዓመት ሰላምን እና ጸጥታን ማስከበር ዋነኛው የመንግሥት ትኩረት መሆኑን ተናግረዋል። "ሕግ የሚተላለፍ አካልን ለሕግ እናቀርባለን። ኦሮሚያ ሕግን ተላልፎ መኖር የማይቻልበት ክልል መሆኑን በመጪው ዓመት እናስመሰክራለን።" ብለዋል ቃል አቀባዩ። የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በክልሉ ውስጥ ለእስር እየተዳረጉ ነው ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ አድማሱ ሲመልሱ፤ "ከዚህ በፊት ሲከናወኑ የቆዩት ሕግን የማስከበር ስራዎች ናቸው" ሲሉ መልሰዋል። የምርጫ ጉዳይ . . . በቀጣዩ ዓመት የሚካሄደውን ምርጫ በተመለከተ የክልሉ መንግሥትም ሆነ ክልሉን የሚያስተዳድረው ፓርቲ ምርጫው ጊዜውን ጠብቆ እንዲካሄድ ፍላጎት አላቸው ብለዋል። "ምርጫ ዲሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ እና ያለ ጸጥታ ችግር እንዲካሄድ ስራዎች ይከናወናሉ" ብለዋል አቶ አድማሱ። አቶ አድማሱ እንደሚሉት ከሆነ በቀን ለ8 ሰዓት ብቻ በመስራት የህዝቡን ፍላጎት ማሟላት ስለማይቻል የመንግሥት ሰራተኞች በሳምንት ለተጨማሪ አምስት ሰዓታት ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል። እንደ ቃል አቀባዩ ከሆነ በሳምንት ለተጨማሪ 5 ሰዓት የመስራት ፍላጎቱ የመነጫው ከክልሉ የመንግሥት ሰራተኞች ነው። የኮንትሮባንድ ንግድ፣ ግብርና፣ ትምህርት እና የጤና ጉዳዮች ትኩረት የሚሰጣቸው መሆኑን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።
news-41545300
https://www.bbc.com/amharic/news-41545300
ኢትዮጵያዊቷ ኮከብ ‘የ2017 የምስራቅ አፍሪካ ምርጥ ዲዛይነር’ ሆነች
ኢትዮጵያዊቷ ኮከብ ባለፈው ቅዳሜ በተካሄደው የኬንያ የፋሽን ሽልማት 'የ2017 የምስራቅ አፍሪካ ምርጥ ዲዛይነር' ሆና ተመርጣለች።
ውድድሩ ለወራት በድረ ገጽ ድምጽ ሲሰጥበት ቆይቶ የዘርፉ ባለሙያዎች ሙያዊ ዳኝነት ታክሎበት ፍጻሜውን አግኝቷል። የሽልማቱ አንዱ ዘርፍ በሆነው 'የምስራቅ አፍሪካ ምርጥ ዲዛይነር' ውድድር ደግሞ በናይሮቢ የምትኖረው ኢትዮጵያዊቷ ኮከብ ዘመድ አሸናፊ ሆናለች። ባለፈው ቅዳሜ በናይሮቢ በተካሄደው የውድድሩ ማሳረጊያ መርሃ ግብር ኮከብ የፋሽን ትርዒት አቅርባ ሽልማቷንም ከአዘጋጆቹ ተቀብላለች። ኮከብ ለዚህ ሽልማት ከኬንያ፣ ከሩዋንዳና ከታንዛኒያ እጩ ከሆኑ አምስት ሌሎች ዲዛይነሮች ጋር ተፎካከራለች። የሽልማቱ አላማ በኢንዱስትሪው የራሳቸውን አዲስ እይታ ተጠቅመው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ዲዛይነሮች ክብር መስጠት እንደሆነ በአዘጋጆቹ ድረገጽ ላይ ሰፍሯል። የመገምገሚያ መስፈርቶቹ ደግሞ አዳዲስ ፈጠራ ፣ ጥሩ የዲዛይን አጨራረስ፣ የግል ምልከታና ለሌሎች አርአያ መሆናቸውን ይጨምራል። ኮከብ ከአውሮፓውያኑ 2009 ጀምሮ ባቋቋመችው ኮኪ ዲዛይንስ የኢትዮጵያና ሌሎች የአፍሪካ አልባሳትን እያዋሃደች የአፍሪካን ባህል በዲዛይኖቿ ታስተሳስራለች። በቅኝ ከተገዙባት ብሪታኒያ የመጣው የኬንያ ዳኞች አለባበስ የነጻነት ተምሳሌት በሆነ ካባ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀየረው በኮኪ ዲዛይንስ ነው። በውድድሩ በ2017 በፋሽን ኢንዱስትሪ በ13 ዘርፎች ስኬት ያስመዘገቡ ተሸልመዋል የኬንያ ዳኞችን አለባበስ የቀየረች ኢትዮጵያዊት ከጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ልብስ በተጨማሪ ደግሞ ሌሎች አፍሪካውያን የሚቀምሙላትን ባህላዊና ዘመናዊ ልብሶች ታዘጋጃለች። ለሴቶች ፣ ለወንዶችና ለልጆች ለልዩ ዝግጅት፣ ለሥራ ቦታና ለበዓላት የሚሆኑ ንድፎችን ቀርጻ በተለያዩ የፋሽን ትርዒቶች ላይ ታሳያለች፤ ለገበያም ታቀርባለች። የኢትዮጵያን ባህላዊ የሸማ ጨርቆችና ጥለቶችን ከሌላ ዘመናዊ ጨርቅ ጋራ እያዋሃደች ለየእለት ሥራ ምቹ በሚሆን መልኩ ስታዘጋጅ ቆይታለች። በነዚህ ሁሉ ሥራዎቿ ታዲያ የምትከተለው መርህ የፋሽን ሚና 'የቀድሞውን ባህላዊ አልባሳት ከዘመኑ ጋር እያዋሃዱ የማሳደግ እንጂ እነርሱን ጥሎ በአዳዲሶች የመተካት ሊሆን አይገባም' የሚል ነው።
46191689
https://www.bbc.com/amharic/46191689
ዋትስ አፕ ላይ በተነዛ ሐሰተኛ ወሬ ምክንያት ተቃጥለው የተገደሉት የሜክሲኮ ዜጎች
በሜክሲኮ አንዲት ትንሽ ከተማ ልጆችን ስለሚያግቱ ግለሰቦች ዋትስአፕ ላይ ወሬ ተነዛ። ወሬው ውሸት ነበር፣ ነገር ግን መንጋው ፍርድ ሰጠ። ሁለቱን ሰዎች ከነህይወታቸው እሳት ለኩሶ አቃጠላቸው።
ማንም የወሬውን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ አልሞከረም። በነሐሴ ወር በአንዱ ቀን ሜክሲኮ የምትገኘው ትንሽ መንደር በሰልፈኞች ጩኸት ትናጥ ጀመር። ሰልፈኞቹ በአካባቢው ፖሊስ ጣቢያ በራፍ ላይ ተሰብስበዋል። በየደቂቃው ቁጥራቸው እየጨመረ ይሄዳል። • የዓመቱ ሐሰተኛ ዜናዎች በአፍሪካ • አይሸወዱ፡ እውነቱን ከሐሰት ይለዩ • 'ሃሰተኛ ዜና '፡ የኢትዮጵያ የማሕበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ስጋት? ፖሊስ በሌላ ጥፋት በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ሁለት ሰዎች ልጆችን በማገት አለመጠርጠራቸውን ለማስረዳት ቢሞክርም ሰሚ ጆሮ አልነበረም። ፖሊስ ጣቢያው ውስጥ የ21 ዓመቱ ሪካርዶ ፍሎሬስ እና አጎቱ አልቤርቶ ፍሎሬስ ተቀምጠዋል። ሪካርዶ በሌላ ከተማ የህግ ትምህርቱን የሚከታተል ወጣት ነው። አጎቱም ቢሆን መኖሪያው ሌላ ከተማ ነው። ሁለቱም ዘመድ ጥየቃ ብለው ነው ወደዚች ከተማ የመጡት። ትናንትና ደግሞ እቃ ለመሸማመት ብለው ገበያ ወጥተው ነበር። ከፖሊስ ጣቢያው ውጭ የተሰበሰበው የሰው ጎርፍ ግን በዋትስ አፕ በሚንሸራሸረው መልዕክት ተወስዷል። "ወደ ከተማችን የህፃናት አጋቾች ገብተዋል ሁላችሁም ተጠንቀቁ" ይላል መልዕክቱ። አክሎም "እነዚህ የህፃናት አጋቾች የአካል ውስጥን በመክፈት የተለያዩ የአካል ክፍሎችን ይወስዳሉ። ሰሞኑን እድሜያቸው 4፣ 8ና 14 የሆኑ ህፃናት ከጠፉ በኋላ ሞተው የተገኙ ሲሆን አካላቸው ተከፍቶ የውስጥ አካላቸው እንደተሰረቀ ማወቅ ተችሏል። የሆድ እቃቸው ባዶ ነበር።" የሪካርዶ እና አልቤርቶ በአካባቢው በሚገኝ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት አካባቢ መታየት ወሬው ክንፍ አውጥቶ እንዲበርና በእያንዳንዱ የመንደሯ ነዋሪ ልብ ውስጥ ፍርሃት እንዲነግስ አድርጓል። ወደ ፖሊስ ጣቢያ የተመመው አብዛኛው ሰው የፍራንሲስኮ ማርቴንዝን መልዕክት ተከትሎ ነው። እንደ ፖሊስ መረጃ ከሆነ ይህ በከተማዋ ለረጅም ጊዜ የኖረ ግለሰብ ይህንን መረጃ በፌስ ቡክና በዋትስ አፕ ሲያሰራጩ ከነበሩት ግለሰቦች መካከል አንዱ ነው። ሪካርዶና አልቤርቶን ከመወንጀል አልፎ በፖሊስ ጣቢያ ተገኝቶ በስልኩ የፌስቡክ የቀጥታ ስርጭት ጀመረ። በቀጥታ ለሚከታተሉትም የከተማችን ነዋሪዎች "ኑና ድጋፋችሁን አሳዩ፤ እመኑኝ ህፃናትን የሚሰርቁት ሌቦች እዚህ ናቸው" በማለት ቀሰቀሰ። ፍራንሲስኮ ይህንን ሲያደርግ ማኑኤል የሚባል ግለሰብ ፖሊስ ጣቢያው አካባቢ የሚገኝ ቤተክርስቲያን ደወል ቤት ላይ በመውጣት ሪካርዶና አልቤርቶን ፖሊስ ሊለቃቸው ነው በማለት ደወል በመደወል የአካባቢውን ህዝብ ቀሰቀሰ። ሶስተኛ ሰው በድምፅ ማጉያ ነዳጅ መግዣ ገንዘብ እናዋጣ በማለት እየቀሰቀሰ ፖሊስ ጣቢያውን የከበባትን ወፈ ሰማይ ሰው እየጠየቀ መሰብሰብ ጀመረ። ከዚህ በኋላ ፖሊስ ጣቢያውን የከበባት ሰው በኋይል ወደ ውስጥ ገብቶ ሪካርዶንና አልቤርቶን እየጎተተ አወጣቸው። ሁሉም በቻለው ሁሉ ይቀጠቅጣቸው ገባ። ሌላው ደግሞ ይህንን በተንቀሳቃሽ ስልኩ ለማስቀረት መቅረፅ ጀመረ። በኋላም ነዳጅ አርከፍክፈውባቸው ክብሪት ጫሩ። የአይን እማኞች እንደመሰከሩት ከመቃጠላቸው በፊት ሪካርዶ በድብደባው ብዛት ሞቶ ነበር። አልቤርቶ ግን ከነህይወቱ ነው የተቃጠለው። ተቃጥሎ የከሰለው የሰዎቹ ሬሳ ከሌላ ከተማ የመንግስት ሰዎች እስኪመጡ ድረስ መንገዱ ላይ ነበር። የቃጠሎውም ሽታም ከአየሩ ላይ አልጠፋም። የሪካርዶ አያት የሟቾቹን ማንነት መለየት እንዲችሉ ተጠርተው በስፍራው ሲደርሱ የተሰበሰበው ሰው ተበትኖ ጥቂት ግለሰቦች ብቻ ናቸው የቀሩት። የሪካርዶ እናት የተሻለ ህይወት ፍለጋ አሜሪካ ከገባች ሰነባብታለች። ልጇ ህፃናት ስርቆት ተጠርጥሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋለ በከተማዋ የሚገኙ ጓደኞቿ ልጅሽ ታሰረ ብለው መረጃ በፌስ ቡክ ገጿ ላይ የላኩላት ወዲያው ነበር። መልዕክቱ ከአንድ ሰው ብቻ የመጣ አልነበረም። ከተለያየ ሰዎች እንጂ። በኋላ ላይም በቀጥታ የፌስ ቡክ ስርጭት ልጇ ሲደበደብ ኋላም ላይ ነዳጅ አርከፍክፈው ሲያቃጥሉት አየች። "እባካችሁ አትደብድቡት አትግደሉት ወንጀለኛ አይደለም" ስትል መልዕክት ላከች። ማንም የሚሰማት ግን አልነበረም። መልካም ወሬን ያቀብላት የነበረው ማህበራዊ ሚዲያ የልጇን ሞት በቀጥታ አሳያት። እንደ አካባቢው ባለስልጣናት ከሆነ 5 ሰዎች ለወንጀል በማነሳሳት 4 ደግሞ በግድያው በቀጥታ በመሳተፍ ተከሰው ታስረዋል። ነገር ግን ሌላ 2 ቀስቃሾችና 4 በግድያው የተሳተፉ ግለሰቦች አምልጠዋል።
news-57188529
https://www.bbc.com/amharic/news-57188529
ኢትዮጵያ በአገር አቀፍ ደረጃ በበሽታ የሚሞቱ ሰዎችን መጠን ለማወቅ መመሪያ አዘጋጀች
ኢትዮጵያ በአገር አፍ ደረጃ በበሽታ ምክንያት የሚሞቱ ሰዎችን መጠን ለማወቅ የሚያስችል የቅኝት መመሪያ ማዘጋጀቷን ቢቢሲ ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ካገኘው መረጃ መረዳት ችሏል።
በአገሪቱ ውስጥ ያለውን የሞት መጠን ለማወቅ የሚያስችል የቅኝት መመሪያ ለማዘጋጅት መነሻ የሆነው የኮሮኖቫይረስ ወረርሽኝ መሆኑም ተገልጿል። መመሪያወው በማህበረሰቡ ውስጥ በበሽታ የሚሞቱ ሰዎችን ጭምር ማካተት እንደሚኖርበት ታምኖ የአገሪቱን የሞት መጠን የሚያሳውቅ መመሪያ ተዘጋጅቷል ተብሏል። በተለይም እንዲህ አይነት ወረርሽኞች ሲከሰቱ የሞቱን መጠን በትክክል ለማወቅ፣ ከዚህ ቀደም የነበረውን የሞት መጠን ለመገምገም፣ በሽታው የትኛውን የማህበረሰብ ክፍል በፆታ፣ በእድሜና ሌሎች መስፈርቶች አስመልክቶ የትኛውን አካል ነው እያጠቃ ነው የሚለውን በተመለከተ መመሪያው ምላሽ ይሰጣል ተብሏል። መመሪያው ይፋ የተደረገው ግንቦት 11፣ 2013 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ነው። መመሪያው ይፋ መሆኑን አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት የጤና ክስተቶች ቅኝትና ምላሽ መስጠት ዳይሬክቶሬት የእናቶችና ጨቅላ ህጻናት ሞት ዳሰሳ እና ምላሽ መስጠት ቡድን አስተባባሪ ወ/ሮ ሮዚና ታሪኩ ከመረጃዎች አሰባሰብና መለኪያ ጋርም ተያይዞ ወሳኝ የሚባሉ ጉዳዮች በመመሪያው መካተታቸውን አስታውቀዋል። መመሪያው መጠናቀቁን አስመልክቶ አዳማ በነበረው ዝግጅት ላይ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ እንደተናገሩት መመሪያው የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ጉዳት ሳያደርሱ ለመከላከልና ለመቆጣጠር አስፈላጊ ነው ብለዋል። መመሪያውን በማዘጋጀቱ በኩል የጤና ሚኒስቴር ባለሙያዎች፣ የክልሎች የህብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር እና የአጋር ድርጅት ተወካይ ባለሙያዎች ተሳትፎ ማድረጋቸውም ከመረጃው መረዳት ተችሏል።
57318949
https://www.bbc.com/amharic/57318949
የፈቱላህ ጉለን የወንድም ልጅ ከናይሮቢ ጎዳና ታፍኖ ወደ ቱርክ መወሰዱ ተነገረ
የሃይማኖት መምህሩ ፈቱላህ ጉለን የወንድም ልጅ በቱርክ የደኅንነት አባላት ተይዞ ወደ ቱርክ መወሰዱን የቱርክ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ።
ሰልሀዲን ጉለን በአጎቱ የሚመራውና በቱርክ ሕገ ወጥ የተባለው ስብስብ አባል በመሆኑ ነው የተያዘው። አሁን የት እንደሚገኝ ግን አልተገለጸም። ኬንያ ውስጥ የምታስተምረው ባለቤቱ፤ ከግንቦት መጀመሪያ አንስቶ ጠፍቶ እንደነበር እና ከናይሮቢ ታፍኖ ስለመወሰዱ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በለቀቀችው ቪድዮ አስታውቃለች። ግለሰቡ ከኬንያ መዲና ታፍኖ ስለመወሰዱ ባለቤት ትናገር እንጂ አናዱሉ የዜና ወኪል ባወጣው ዘገባ ላይ የቱርክ ብሔራዊ ደኅንነት ተቋም (ኤምአይቲ) ሰልሀዲንን ያሰረው ከኬንያ መንግሥት ጋር ተስማምቶ ስለመሆኑ የተባለ ነገር የለም። የቱርኩ አናዶሉ የዜና ወኪል ያተመው ፎቶ ሰልሀዲን በካቴና ታስሮ፣ በግራና በቀኙ የቱርክ ሰንደቅ አላማ ተሰቅሎ ያሳያል። ከቱርክ የተሰደዱት ፈቱላህ ጉለን እአአ በ2016 የከሸፈውን መፈንቅለ መንግሥት በማቀናበር ተከሰዋል። በወቅቱ 251 ሰዎች ሲሞቱ 2,000 ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ሰልሀዲን እና አጎቱ በመፈንቅለ መንግሥቱ እጃችን የለበትም ብለዋል። ፈቱላህ በተከታዮቻቸው ዘንድ መንፈሳዊ መሪ ተብለው ይጠራሉ። በቱርክ ሁለተኛው ኃያል ሰው ተብለውም ይጠራሉ። ጉለን የተባለው ንቅናቄያቸው አሜሪካ ውስጥ ትምህርት ቤቶች እና የተራድኦ ድርጅቶችን ይዟል። እሳቸውም የሚኖሩት አሜሪካ ነው። ቱርክ የጉለን ንቅናቄን የሽብር ተቋም ብላ ፈርጃለች። ፈቱላህ ግን በቱርክ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ እንዳልተሳተፉ ይናገራሉ። ከመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው ወዲህ አሜሪካ በስደት እየኖሩ ሲሆን፤ አሜሪካ ፈቱላህን ለቱርክ አሳልፋ እንድትሰጥም ተጠይቋል። የቱርኩ ፕሬዝደንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን፤ ከፈቱላህ ጉለን ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ከ100,000 በላይ መምህራን፣ ዳኞችና የመንግሥት ሠራተኞችን አባረዋል። ክስ ከተመሠረተባቸው መካከል 2,500 የሚጠጉት የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዋል። በአፍሪካ እና በባኪንስ የጉላህ ንቅናቄ አባል ናቸው የተባሉ ሰዎችንም ቱርክ በቁጥጥር ሥር አውላለች። 2018 ላይ ስድስት ቱርካውያን ኮሶቮ ውስጥ ከተያዙ በኋላ ፖለቲካዊ ቀውስ መቀስቀሱ አይዘነጋም። የኮሶቮ የውስጥ ጉዳይ ሚንስትር እና የደኅንነት ኃላፊ ከሥልጣናቸው ተነስተውም ነበር።
news-52498999
https://www.bbc.com/amharic/news-52498999
ሱዳን የሴት ልጅ ግርዛት ላይ እገዳ ጣለች
ሱዳን የሴት ልጅ ግርዛት ወንጀል መሆኑን በመደንገግ ሲፈፅም የተገኘ ግለሰብ የሦስት ዓመት እስር እንደሚጠብቀው አስታወቀች።
የሴት ልጅ ግርዛት ሲፈጸም የብልት ከንፈሮችን እና ቂንጥርን መቁረጥን ያካትታል ይህ የተገለፀው አዲስ ባሻሻለችው ሕግ ላይ መሆኑን ሮይተርስ የዘገበ ሲሆን ሕጉ የተሻሻለው ከአስር ቀን በፊት ነው ብሏል። የሴት ልጅ ግርዛት ሆነ ተብሎ የሴት ልጅን የመራቢያ ክፍል አካል መቁረጥ ማለት ነው። • የሕንድ 21 ሚሊዮን 'ያለተፈለጉ' ሴት ልጆች • ኢትዮጵያ ውስጥ መካኖች ወልደው እየሳሙ ነው • የመደፈሬን ታሪክ ከስልሳ ሰባት ዓመታት በኋላ የተናገርኩበት ምክንያት የዓለም ጤና ድርጅት ብዙ ጊዜ የሴት ልጅ ግርዛት ሲፈጸም የብልት ከንፈሮችን እና ቂንጥርን መቁረጥን ያካትታል ይላል። ሱዳን ይህ ተግባር በከፍተኛ ሁኔታ ከሚፈፀምባቸው የአፍሪካ አገራት መካከል አንዷናት። የተባበሩት መንግሥታት በዓለማችን በህይወት ያሉ ወደ 200 ሚሊዮን የሚጠጉ ሴቶች እና ህጻናት ላይ በተለያየ ደረጃ የግርዛት ተግባራት ተፈጽሞባቸዋል ይላል። የሴት ልጅ ግርዛት በስፋት እየተፈጸመ ያለው ወደ 27 በሚጠጉ የአፍሪካ እና መካከለኛው ምሥራቅ አገራት ሲሆን፤ በእስያ እና ደቡብ አሜሪካ በሚገኙ አገራትም ውስጥ ድርጊቱ ይፈጸማል። የተባበሩት መንግሥታት እንደሚለው ከሆነ በአውሮፓ፣ በሰሜን አሜሪካ፣ በአውስትራሊያ እና በኒው ዚላንድ የሚኖሩ ስደተኞች ሕግን በመተላለፍ ሴት ልጆቻቸውን ያስገርዛሉ። የሴት ልጅ ግርዛትን በሕግ ካገዱ የአፍሪካ አገራት ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ኬንያ፣ ሞሪሺየስ፣ ማሊ፣ ላይቤሪያ፣ ቤኒን፣ ቡርኪናፋሶ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ቻድ፣ ኮትዲቯር፣ ጅቡቲ፣ ግብጽ፣ ጋና፣ ጊኒ፣ ጊኒ ቢሳዎ፣ ኒጀርና ናይጄሪያ ይገኙበታል። የተባበሩት መንግሥታት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሴት ልጅ ግርዛት እንዲቆም ጥሪ እያቀረበ ነው። የግርዛት አይነቶች አራት አይነት የግርዛት አይነቶች አሉ።
44923371
https://www.bbc.com/amharic/44923371
የዶክተር ዐብይ አሕመድ 'ፑሽ አፕ'
ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ከ3ሺህ የሚልቁ የዩኒቨርስቲ መምሕራንን በጽህፈት ቤታቸው ጋብዘው ውይይት አካሄደዋል።
በስብሰባው መሐል ዘና የሚያደርጉ ሁኔታዎች አልጠፉም። በመሐል ጥያቄዎች እየተጠየቁ በፍቃደኝነት ወደ መድረክ የሚወጡ ሰዎችን ጋበዙ። ስምንት መምህራን ወደ መድረክ ከወጡ በኋላ የ'ፑሽ አፕ' ውድድር ተካሄደ። ሳይደክሙ በርካታ 'ፑሽ አፕ' በጽናት የሠሩ ሦስት መምህራት ወደ ቻይና ለ15 ቀን ሥልጠና እንደሚሄዱ አብስረዋቸዋል። ቆየት ብለውም ሁሉም ወደ መድረክ የወጡ መምህራን የዚሁ እድል ተሳታፊ እንደሚሆኑ ቃል ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ከመምህራኑ ጋር አብረው እየሠሩ፣ ጎን ለጎን ስፖርቱን በትክክል የማይሠሩትን መምህራን ይከታተሉ ነበር ብለዋል ተሳታፊዎች። በተመሳሳይ ሴት መምህራንን ወደ መድረክ ሲጋበዙ በርካታ ሴቶች እድሉን ለመጠቀም ወደ መድረክ የወጡ ሲሆን ለሁሉም የቻይና ጉብኝት ዕድል ሰጥተዋቸዋል። • "ኢህአዴግ ተዳክሟል ብላችሁ እንዳትሳሳቱ" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ • የዐብይ ቀጣይ ፈተናዎች • የጠቅላይ ሚኒስትሩ 100 ቀናት የ 'ፑሽ አፕ' ጉዳይ በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን ሰፊ መነጋገሪያ የሆነ ሲሆን አንዳንዶች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ማድረጋቸው ምቾት እንዳልሰጣቸው ሲገልጹ ሌሎች ደግሞ መምህራኑን እንዴት ማስተማር እንዳለባቸው በድርጊት ለማስተማር ያደረጉት ነው ሲሉ ተከራክረዋል። የፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ዘግይቶ መምጣት መድረኩ ከሞላ በኋላ ዘግየት ብለው የመጡት ፕሮፌሰር በየነ ወደ ፊት ወንበር እንዲመጡ የጋበዟቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነበሩ ብለውናል ተሳታፊዎች። ፕሮፌሰሩ ወደፊት ሲራመዱም የመምህራኑ ደመቅ ያለ ጭብጨባ እንዳጀባቸው ያስተዋሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖለቲካ ተፎካካሪ መሆናቸውን ታሳቢ በማድረግ ይሄ ጭብጨባ ፕሮፌሰሩ ላበረከቱት አስተዋጽኦ እንጂ ለምርጫ አይደለም መቼም ሲሉ ቀልደዋል። የ42ቱ መምህራን ጉዳይ ከ25 ዓመታት በፊት ባንጸባረቁት አመለካከትና ባነሱት የአካዳሚያዊ ነጻነት ምክንያት ከዩኒቨርስቲ የተባረሩ መምህራን ወደ ሥራ ገበታቸው ለመመለስ መንግሥት ዝግጁ እንደሆነ አቶ ዐብይ አሕመድ መጥቀሳቸውን አቶ ፍጹም አረጋ በትዊተር ገጻቸው ላይ ጠቅሰዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ለትምህርት ጥራት ጋሬጣ ናቸው ተብለው ከተጠቀሱ ጉዳዮች አንዱ ፖለቲካዊ ሥራ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ሰተት ብሎ መግባቱ እንደሆነ ተነስቷል። የመመህራንና የተማሪዎች የአንድ ለአምስት አደረጃጀትም እንደ መነሻ ተጠቅሷል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበኩላቸው ዋናው ችግር የፖለቲካው ወደ ዩኒቨርስቲ መግባት ሳይሆን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ዳካማ ሆነው ወደኋላ እየተጎተተ መሆናቸው ነው ብለዋል። የከፍተኛ ትምህርት አቅምና ተጽእኖ ፈጣሪነት መላላት ነው ችግሩ ሲሉ ሰፋ ያለ ማብራሪያ መስጠታቸውን ያነጋገርናቸው ተሳታፊዎች ተናግረዋል። የውይይቱ ትኩረት በዛሬው የጠቅላይ ሚኒስትሩና የዩኒቨርስቲ መምህራን ውይይት በርካታ ርዕሰ ጉዳዮች የተነሱ ሲሆን የትምህርት ጥራት፣ የተቋማት ግንባታ፣ የኑሮ ውድነት፣ የኤርትራ ጉዳይና ሌሎች በርካታ ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች በጥያቄ መልክ መነሳታቸውን ተሳታፊዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ለስብሰባ ተሳትፎ የተመረጡ መምህራ በተለያየ መንገድ ዩኒቨርስቲያቸውን እንዲወከሉ የተመረጡ ሲሆን አንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች በምርምርና ማስተማር ጎላ ያለ ነጥብ ያስመዘገቡ መምህራንን ለስብሰባው መርጠው መላካቸውን፣ ሌሎች ደግሞ በድምጽ ብልጫ መምህራኑን ልከዋል። የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ጥላዬ ጌቴ አጭር ማብራሪ ካቀረቡ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ወደ መድረክ የጋበዟቸው ሲሆን ዶክተር ዐብይ አሕመድ በበኩላቸው በብዛት እናንተን መስማት ነው የምፈልገው ብለው ተሳታፊዎችን ለጥያቄ እንደጋበዙ ተገልጿል። • "ኢህአዴግ ተዳክሟል ብላችሁ እንዳትሳሳቱ" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከአክሱም ዩኒቨርስቲ የተወከለው መምህር ሙሉ ማእሾ ለቢቢሲ እንደተናገረው ከዚህ ቀደም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰፋ ያለ ገለጻ በማድረግ የሚታወቁ ሲሆን በዚህ ስብሰባ ግን በቀጥታ ወደ ተሳታፊዎች እንዳመሩ ተናግሯል። "ዛሬ ብዙ አላወራም፥ ከናንተ ለመማር ነው የምፈልገው፣ ሐሳቦቻችሁን እንደ ግብአት እንድጠቀምባቸው" ብለው ለተሳታፊዎች እድል ሰጥተዋል። ተሳታፊዎችም በነጻነት የሚሰማቸውን ተናግረዋል። ውይይቱ ከትምህርት ጥራት ባሻገር የአገር ደህንነት፣ የዜጎች መፈናቀል፣ ሉአላዊነት ላይ ሐሳቦች ተንሸራሽረውበታል። በኤርትራ ጉዳይ ከባድመ በፊት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱ እንዲቀድም የተፈለገበትን ምክንያትም ዶክተር ዐብይ ለመምህራቱ አብራርተዋል። የትምህርት ጥራትን በተመለከተም ፍኖተ ካርታ እየተዘጋጀ እንደሆነና ከፍ ያለ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራበት፣ በመጨረሻም ወደ መምህራኑ ወርዶ ሰፊ ውይይት እንደሚደረግበት መናገራቸውን፣ "ብዙዎቹ ጥራትን የተመለከቱ ዛሬ የተነሱና ጥያቄዎችም ሆኑ ስጋቶች" በዚሁ የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ አማካኝነት እንደሚመለሱ መግለጻቸውን ዶክተር ፍሬው አሞኘ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከአሜሪካ የወንጀል ምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ) መጋበዙን በተመለከተም ጥያቄ መነሳቱንና ጠቅላይ ሚኒስትሩ የድሀ ሉአላዊነት አለመኖሩን፣ እኛ ባንፈልግም ያደጉ አገራት መንግሥታት ምን እየተካሄደ እንደሆነ እኛ ባናውቅም እነሱ ያውቃሉ ሲሉ የሉአላዊነት ጉዳይ ላይ ማብራራታቸውን ከወለጋ ዩኒቨርስቲ የተሳተፈው አቶ ተፈሪ ፍሪሳ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "መድረኩ ሰፊ ጊዜን ለመምህራን የሰጠ፣ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን ምክረ ሐሳቦችን ጭምር እንዲያነሱ የፈቀደ ደስ የሚል መድረክ ነበር" ብለዋል የባህር ዳሩ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ፍሬው አሞኘ። ውይይቱ ከጠዋት እስከ ምሳ ሰዓት የዘለቀ ነበር።
news-56659417
https://www.bbc.com/amharic/news-56659417
በጠለፋ 'ጋብቻ' የተገደለችው ሴት ጉዳይ ከፍተኛ ቁጣን ቀሰቀሰ
በጠለፋ ጋብቻ ለመፈፀም በሚል አንዲት ሴት ተጠልፋ መገደሏ ከፍተኛ ቁጣን አስነስቷል።
ይህ የተፈፀመው በእስያ በምትገኘው ካይሪጊስታን በምትባለው አገር ነው። የ27 አመት እድሜ ያላት አይዛዳ ካናትቤኮቫ የተጠለፈችው ሰኞ እለት ሲሆን ሶስት ወንዶችም ገፍተው መኪና ውስጥ ከተቷት። ከነዚህ ውስጥ አንደኛው በግድ ሊያገባት የፈለገው ሰው ነው ተብሏል። የጠለፋው ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በከፍተኛ ሁኔታ ቢጋራም ፖሊስ መኪናውን ለማግኘት አዳጋች ሆኖበት ነበር። አይዛዳ ከተጠለፈች ከሁለት ቀናት በኋላ አስከሬኗ አንድ ከጥቅም ውጭ በሆነ መኪና ውስጥ ሊገኝ ችሏል። አስከሬኗ የተገኘው በአንድ እረኛ አማካኝነት ከመዲናዋ ቢሽከክ ወጣ ብሎ በሚገኝ ሜዳ ነው። ጠልፎ ገድሏታል ተብሎ የሚታመነው ግለሰብ አስከሬንም በዚያው ስፍራ ተገኝቷል። ፖሊስ የግለሰቡን አሟሟት አስመልክቶ እንደሚለው የሞተው በቢላ እንደሆነና ራሱንም እንደገደለ ፍንጮች ማግኘቱን ነው። የሟቿ ቤተሰቦች እንደተናገሩት ልጃቸው ግለሰቡን እንደምታውቀውና ከዚህ በፊትም ትንኮሳዎች ሲያደርስባት እንደነበርና ከዚህ ተግባሩም እንዲታቀብ መጠየቃቸውን ነው። ግለሰቧን በመጥለፍ የተባበሩት ሌሎች ሶስት ወንዶች በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋሉ የአገሬው ሚዲያ ዘግቧል። የግለሰቧን ግድያ ተከትሎም በመቶዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በያዝነው ሳምንት ሃሙስ "አሳፋሪ" ነው በማለት በቁጣ ሲጮሁ ተሰምተዋል። ከዚህም በተጨማሪ የአገሪቱ የውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር እንዲለቁ ጥሪ አቅርበዋል። በአገሪቷ ውስጥ የጠለፋ ጋብቻ በከፍተኛ ሁኔታ ተስፋፍቷል። ምንም እንኳን አንዳንዶች የጠለፋ ጋብቻ የካይርጊዝ የቀደመ ባህል ነው ብለው ቢከራከሩም ተመራማሪዎች በበኩላቸው በመካከለኛ እስያዊቷ አገር መስፋፋትን ያሳየው ከጥቂት አስርት አመታት በፊት ነው ይላሉ። በአውሮፓውያኑ 2013 የጠለፋ ጋብቻ ህገወጥ ሆኖ በህግ ቢደነገግም ሪፖርት የሚያደርጉ ሴቶች ቁጥር በጣም አናሳ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ለዚህም እንደ ምክንያትነት የሚጠቀሰው ሊደርስባቸው የሚችለውን አፀፋዊ ምላሽ በመፍራት እንደሆነ ተነግሯል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው በአገሪቷ ከሚፈፀሙ አምስት ጋብቻዎች መካከል አንዱ አስገዳጅ በሆነ ሁኔታ ሴቷ ተጠልፋ እንደሆነ ነው።
43918193
https://www.bbc.com/amharic/43918193
ካለሁበት 30፡ መስቀል እና አረፋን ሳስታውስ ውስጤ ይረበሻል
ስሜ አሸናፊ ተስፋዬ ይባላል፡፡በአሁኑ ወቅት በደቡባዊ አፍሪካ ክፍል በምትገኘው አንጎላ በመኖር ላይ እገኛለሁ። ከኢትዮጵያ ወጥቼ አንጎላ እስክደርስ ባሉት ጊዜያት ውስጥ የተለያዩ ፈታኝ ሁነቶችን አልፌለሁ። ከጋዜጠኝነት ወደ እስረኝነት
ሀገር ቤት በነበርኩበት ወቅት በፋና ሬዲዮ ውስጥ በጋዜጠኝነት አገለግል ነበር። በ2004 ዓ.ም የተሻለ ኑሮን በመሻት የመጀመሪያ ጉዞዬን ወደ ሱዳን ካርቱም አደረግኩ። የካርቱም ኑሮዬ ብዙ ሳይገፋ ‹ኡምዱርማን› በተባለ እስር ቤት ውስጥ ለአንድ ወር ያህል ያቆየኝ ክስተት ተፈጠረ። በዚህ እስር ቤት ከተለያዩ ቦታዎች የመጡ ኢትዮጵያዊያን ነበሩ። ዜግነትህን እንድትጠላ የሚያደርግህ ቦታ ነው። የእህቴ ባለቤት ኤፍሬም ገ/እዝጊ ዋስ ሆኖ እና የሚከፈለውን ከፍሎ ከኡምዱርማን እስር ቤት ከወጣሁ በኋላ "አንጎላ ለሥራ ጥሩ ነው" ሲባል እሰማ ስለነበር ወደዚያ ለማቅናት ወሰንኩ። ወደ አንጎላ ለማምራት በማሰብ መተላለፊያ እንድትሆነኝ ወደ መረጥኳት ኬንያ በረርኩ። ሆኖም ጆሞ ኬንያታ አውሮፕላን ማረፊያ በደረስኩ ጊዜ የያዝከው ቪዛ ህጋዊ አይደለም በሚል ለድጋሚ እስር ተዳረግኩ። ኬንያ ውስጥ ለአምስት ቀናት ያህል ታስሬያለሁ። ከሰሩ የሚታደግባት ካሾፉ የሚጠፉባት ሀገር እግዚአብሔር አሳክቶሎኝ በድጋሚ ከተፈታሁ በኋላ ወደ አንጎላ አቀናሁ። በዚህ ሀገር ውስጥ ከሌሎች ሀገራት የመጡ ስደተኞች ይኖራሉ። በርከት ያሉ ኤርትራዊያን እና ጥቂት የማይባሉ ኢትዮጵያዊን ኑሯቸውን በዚህች ሀገር ውስጥ ይመራሉ። ኢትዮጵዊያን እና ኤርትራዊያን ተፈቃቅረው የሚኖሩበት ቦታ ነው። የሁለቱ ሃገራት ዜጎች በተለያዩ ሥራዎች ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ። ብዙ ጊዜ አንድ "ሀበሻ መጣ!" ሲባል ሥራ የሚጀምረው ከኤርትራዊያን ጋር አብሮ በመስራት ነው፡፡ ከኤርትራ የመጡ ዶክተሮች፣ ከኢትዮጵያ የመጡ እንጂነሮች እዚህ ሱቅ በሱቅ ውስጥ ሥራ ላይ ተሰማርተው ሊገኙ ይችላሉ። አንጎላ ከሰራህ የምታድግባት ካሾፍክ ደግሞ የምትገደልህ ሀገር ናት፡፡ አንጎላ ውስጥ እየኖርኩ ያለሁት ከባለቤቴ እና ከአንድ ልጄ ጋር ነው። የምተዳደረው ፎቶ በማንሳትና ሠርግና የመሳሰሉ ዝግጅቶችን ቪዲዮ በመቅረጽ ነው። ይሄን የማከናውነው 'አሹ' በሚሰኝ ስቱዲዮዬ በኩል ነው፡፡ ከቦም ዲያ እስከ ፉንጂ (አንጎላን በጥቂቱ) ሞቃት የአየር ንብረት ያላት አንጎላ ህዝቦቿ ሰው አክባሪና ቂም የማይይዙ ናቸው። አንዳንዴ በጥቅማቸው ከመጣህ ግን እስከ መግደል የሚያደርስ እርምጃ ሊወስዱ ይችላሉ። የመግባቢያ ቋንቋቸው ፖርቹጊዝ ነው፣ 'ቦን ዲያ' ማለት እንደምን አደርክ፣ 'ቦአ ታርድ' ማለት ደግሞ እንደምን ዋልክ ማለት ሲሆን፣ 'ቦን ናይት' ደግሞ ደህና እደር እንደምንለው ዓይነት ነው። የኢትዮጵያ ምግብ አንጎላ ውስጥም ይገኛል። በጤፍ ቦታ ሩዝና ስንዴ ተፈጭቶ ለእንጀራነት ይውላል። ሽሮ እና በርበሬ ከኢትዮጵያ አሊያም በቅርባችን ካለችው ደቡብ አፍሪካ እንዲመጣ እንደርጋለን። ሆኖም አንጎላዊያንም ጣፋጭ ምግብ አላቸው። ተወዳጁ ምግብ ፉንጂ ይባላል፣ ፉንጂ እንደ እኛ ሀገር ገንፎ ያለ ሲሆን ከበቆሎ ዱቄት ነው የሚሰራ። የሀገር ናፍቆትና ህልም ከሀገሬ ብዙ ነገር ይናፍቀኛል። በጉራጌ ማህበረሰብ ባህል እንደማደጌ መስቀል በጣም ይናፍቀኛል፣ ግርግሩ፣ ባህሉ ከአንዱ ቤት ወደ አንዱ ቤት እየተጠራራን የምናደርገው ነገር የኢትዮጵያዊነት ፍቅር ደስ ይለኝ ነበር። በጋዜጠኝነት ህይወቴ ወቅት 'አሸናፊ ጉራጌ ነው' ተብሎ ነበር የመስቀል መሰናዶዎችን እንድዘግብ በዚያውም ወደ ቤተሰብ እንድሄድ የሚደረገው ነገርም ይታወሰኛል። መስቀል እና አረፋን ሳስታውስ ውስጤ ይረበሻል። በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በጋዜጠኝነት ህይወቴ በተለይ በመስሪያ ቤት ውስጥ የነበሩ አስቂኝ ትውስታዎች ይመጡብኛል። አንዳንዶቹንም ሳስታውስ ፈገግ ያሰኙኛል። አንደኛው ከአነስተኛ ደሞዛችን አንጻር የምናዘወትረው 'አደይ አበባ' የሚባለው ምግብ ነው። ምግቡ 'አደይ አበባ' የተባለው ብዙ የእንጀራ ፍርፍር ላይ ለናሙና ያክል ሁለት እንቁላሎች ተፈርፍረው ስለሚነሰነሱበት ነው፡፡ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር በቃል የተናገሩትን በተግባር የሚደግሙት ከሆነና በሀገራችን የእኩልነት መንፈስ የሚመጣ ከሆነ፣ ወደ ሀገሬ ተመልሼ የምወደውን ሥራ መቀጠል እፈልጋለሁ። የራሴን የአየር ሰዓት ገዝቼ አሊያም የራሴን ስቱዲዮ አቋቁሜ የጋዜጠኝነት ሥራዬን ለመቀጠል፣ በፊልም ሥራዎች ላይ የመሳተፍ ህልምም አለኝ። በጋዜጠኝነት ዘመኔ ሕይወት በየፈርጁ የሚባል መሰናዶ ነበረኝ። የመቃብር ቆፋሪዎችን፣ የምሽት ቤት ጠበቂዎችን(ጋርዶችን)፣ የሌሊት የታክሲ ሾፌሮችን የመሳሰሉ ብዙ ታሪካቸው ያልተገለጡ ሰዎችን ህይወት አስፍቼ የማሳየቱ ህልምም አለኝ። ማን ያውቃል የተሰደድን ጋዜጠኞች የእኛ የምንለው ሬዲዮ ጣቢያ ይከፈትና ያለምነውን የምንሰራበት ዘመን ይመጣል። እስከዚው ድረስ የእኛ ሰው በአንጎላ በሚለው ገጼ በኩል ሥራዎቼን እያጋራሁ እቆያለሁ፡፡ በቸር ያገናኘን ለሐብታሙ ስዩም እንደነገረው የ'ካለሁበት' ቀጣይ ክፍሎችን ለማግኘት ፦ ካለሁበት 31፡ ''ብዙ ትውስታዎቼ ከዛፍና ከጭቃ አያልፉም'' ካለሁበት 32፡ "ኑሮን ፈታኝ የሚያደርገው ባህላቸው ነው"
56797641
https://www.bbc.com/amharic/56797641
በጦርነት ስትታመስ የከረመችው ሶሪያ ምርጫ ልታካሂድ ነው
ለዓመታት በእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ የቆየችው ሶሪያ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ልታካሂድ መሆኑን አስታወቀች።
የሶሪያ መሪ በሽር አል አሳድ እአአ 2018 ላይ የአገሪቱ ፓርላማ በቀጣዩ ወር የአገሪቱን ፕሬዘዳንት ለመምረጥ የሚያስችል ምርጫ እንደሚካሄድ ይፋ አድርጓል። ይህም የፕሬዳንት በሽር አል አሳድ ስልጣንን ለቀጣይ ሰባት ዓመታ ለማረጋገጥ የታሰበ ሳይሆን እንደማይቀር ተነግሯል። ከ 10 ዓመታ በላይ የዘለቀው የእርስ በእርስ ጦርነት በቀጠለበት እና የኢኮኖሚ ቀውሱም ባየለበት በዚህ ወቅት አሳድ ጠንካራ ተፎካካሪዎች ይኖራቸዋል ተብሎ አይጠበቅም። በአሳድ የሚመራው የሶርያ መንግሥት ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ያለባቸውን አካባቢዎች ተቆጣጥሮ ይገኛል። በ 10 ዓመቱ ጦርነት ከ400 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ የሶሪያ ግማሽ የሚሆነው ህዝብም አገር ለቆ ተሰዷል። ከአንድ ወር በኃላ የሚካሄደው ይህ ምርጫም ለመጪው ሰባት ዓመታት ሶሪያን የሚመራውን ፕሬዘዳንት የሚመረጥበት እንደሚሆን ተገልጿል። ከዛሬ ጀምሮ ከፕሬዘዳንቱ ጋር የሚወዳደሩ እጩዎች መመዝገብ ይጀምራል። በመላው አለም ያሉ ሶሪያዊያንም ከምርጫው እለት ስድስት ቀናት ቀደም ብለው ኤምባሲ በመሄድ ለመራጭነት መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል። ይህ ምርጫም የእርስ በእርስ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ የሚደረግ ሁለተኛ ምርጫ ነው። እኤአ በ 2014 የተካሄደው ምርጫ ዴሞክራሲያዊ ያልሆነ ብሎም ህገ ወጥ በሚል በተቃዋሚዎች እዲሁም በአሜሪካ እና በአውሮፓ ህብረት ውድቅ የተደረገ ነበር። በዚህ ምርጫ አሳድ 92 በመቶ ድምፅ በማግኘት ነበር አሸንፊያለሁ ያሉት። ይህ ምርጫ ከአስርተ አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ግዜ ከአሳድ ቤተሰብ ውጪ ያለ ሰው እንዲወዳደር የተፈቀደበት ምርጫ የነበረ ሲሆን ሁለቱ ተፎካካሪዎች ግን እምብዛም የማይታወቁ ነበሩ።
news-51145406
https://www.bbc.com/amharic/news-51145406
የሶሪያ ጦርነት፡ የማህበረሰብ መሪዎች በበርሊን የምስጢር የሰላም ጉባዔ አካሄዱ
በዚህ ሳምንት ጥቂት የሶሪያ የማህበረሰብ መሪዎች በበርሊን በምስጢር ተገናኝተዋል። የተገናኙበት ዓላማ አገራቸውን የደም እምባ እያስነባ ላለው የእርስ በርስ ክፍፍል እልባት ለመስጠት ነው።
በዚህ ጉባኤ ላይ አንዳንዶቹ የራሳቸው ወታደሮች ያሏቸው የሱኒ ጎሳ መሪዎች፤ ከበሽር አላሳድ ጋር የቅርብ ግንኙነት ያላቸው እና ከፍተኛ ኃፊነት ያላቸው ሰዎች ጋር ፊት ለፊት ተቀምጠዋል። ክርስቲያኖችን፣ ኩርዶችን፣ ዱሩዜ፣ ሱኒ እና አላውቴስን ጨምሮ ከሶሪያ በጣም ወሳኝ ከሆኑ ቤተሰቦች፣ ጎሳዎች እና ማሕበረሰብ የተውጣጡ ወደ 20 የሚጠጉት ቁልፍ ሰዎች፤ በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው ነበር የተወያዩት። • ‘ቤቴን ከ28 ስደተኞች ጋር እጋራለሁ’ • በጦርነት የተጎሳቆሉ ስደተኞች መዳረሻቸው የት ነው? በሶሪያ በበሽር አላሳድ መንግሥትና በታጠቁ ኃይሎች የሚሰራጨውን እርስ እርስ የሚያጋጭ ትርክት ለመዋጋት ወደ ጀርመን በርሊን ያቀኑ ግለሰቦች በሶሪያ ማሕበረሰብ አሉ የሚባሉ መሪዎች ናቸው። አብዛኞቹ ለሶሪያ መንግሥት ቅርበት ያላቸውና ሙሉ በሙሉ ባይደግፉትም ከደማስቆ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያላቸው ናቸው። ሌሎቹ ደግሞ በፕሬዚደንት በሽር አላሳድ አገዛዝ ሥር መከራን የቀመሱ እና ወደ ታጠቀው ተቃዋሚ ኃይል ያልተቀላቀሉ ናቸው። አንዳንዶቹ ደግሞ ጦርነትን ሸሽተው በስደት ተቀማጭነታቸውን ጀርመን ያደረጉ ናቸው። "እነዚህ ሰዎች ራሳቸውን የሚያዩት ከታጠቁ ኃይሎችም ሆነ ከመንግሥት ጋር እንዲሁም በአገራቸው ውስጥ ጦርነት ከሚያካሂዱ አካላት ጋር ወገንተኝነት የሌላቸውን 70 በመቶ የሶሪያን ሕዝብ እንደወከሉ ነው።" ሲሉ በመካከለኛው ምስራቅ የፖለቲካ ተንታኝ ዳንኤል ጌርላች ተናግረዋል። ዳንኤል ጌርላች በጀርመን የሚገኙ ሶሪያዊያንን የሚረዱ እና ይህን ስብሰባ ያስተባበሩ ናቸው። ጉባዔውን በርሊን ማካሄድ ለምን አስፈለገ? ስብሰባው በግልና በአውሮፓ መንግሥታት የተደገፈ ሲሆን በበርሊን የመካሄዱ ምክንያት ጀርመን በአንፃራዊ መልኩ ገለልተኛ አገር ሆና በመገኘቷ ነው ተብሏል። በሶሪያ ጦርነት መካሄድ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በርካታ ሶሪያዊያን የተሰደዱት ወደ ጀርመን ነበር፤ በመሆኑም ጀርመን አሁን በርካታ ሶሪያዊያን ማሕበረሰብ ያለባት አገር ሆናለች። በስብሰባው ላይ የነበረው ድባብ አስደሳች ነበር ቢባልም አንዳንድ የስብሰባው ተሳታፊዎች በጉባዔው በመሳተፋቸው ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ሊጥሉ ይችላል የሚል ስጋት አለ። በበሽር አላሳድ መንግሥትና በእስላማዊ ታጣቂዎች ዐይን እንደ ክህደትም ሊታይ ይችላል። በቀል ይደርስብናል ከሚለው ስጋት ውጭም አንዳንዶች በምስጢር ወደ በርሊን ያቀኑ ሲሆን፤ ተሳታፊዎች የእጅ ስልካቸውንም መግቢያው በር ላይ ትተው ወደ ጉባኤው በመግባታቸው ስጋት አድሮባቸዋል። • አቶ ለማ ለምን ዝምታን መረጡ? • "ህክምና የሚጀምረው ከአመኔታ ነው" የ23 ዓመቱ ዶ/ር አቤኔዘር ብርሃኑ ከኢራቅ ጋር በሚዋሰነው የሶሪያ ድንበር በሚገኘው ሰፊው የሱኒ አረብ ጎሳ መሪ የሆኑት ሼህ አሚር አል ዳንዳል፤ በጦርነቱ ወንድማቸውን አጥተዋል። ታዲያ "በግጭቱ ከተሳተፉ ሰዎች ጋር እንዴት መነጋገር ቻሉ?" ተብለው ተጠይቀው ነበር። "ሁላችንም ተሸናፊዎች ነን፤ ስለዚህ ቁስላችንን ማከም እንፈልጋለን፤ ይህ ግጭት ይቀጥላል ማለት ሌላ ኪሳራ ነው" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። አዲስ የገቡት ቃል ምንድን ነው? በፈረንጆቹ ኅዳር 2017 የዚህ ቡድን መስራቾች መጀመሪያ 'ኮድ ኦፍ ኮንዳክት ፎር ሲሪያን ኮኤግዚስታንስ' የተሰኘ የሰላም ስምምነት ተፈራርመዋል። ሰነዱ በሁሉም የአገሪቷ አካባቢ የሚገኙ ማህበረሰቦች ሊስማሙበት የሚችሉባቸውን ደንቦች ያካተተ ነበር። ይህም ያለምንም ብሔርም ሆነ ሃይማኖት ጣልቃ ገብነት ሁሉም ሶሪያዊያን እኩል መሆናቸውን አካቷል። ባለፈው ረቡዕ ምሽት ከእልህ አስጨራሽ ክርክር በኋላ፤ በሌሎች የሃይማኖት፣ ቤተሰብ እና ብሔር አባላት በተፈፀመው ወንጀል ማንም ሰው ተጠያቂ እንደማይደረግ ስምምነት ላይ ደርሰዋል። የዚህ ዓላማም በተወሰነ ቡድን ላይ የበቀል እርምጃን ለማስወገድ ነው።
news-52423904
https://www.bbc.com/amharic/news-52423904
ፌስቡክ በአንድ ጊዜ 50 ሰዎች ጋር የሚደውሉበት ቴክኖሎጂ ይዞ መጥቷል
ፌስቡክ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰዎች በቪድዮ ጥሪ መገናኘት ማብዛታቸውን ተከትሎ በዋትስአፕና ሜሴንጀር አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ይዞ ብቅ ብሏል።
'ሜሴንጀር ሩምስ' የተባለው የመልዕክት መላላኪያን ተጠቅመው ለ50 ሰዎች የቪድዮ ጥሪ ማድረግ ይችላሉ። ኩባንያው ለቢቢሲ እንደተናገረው አዳዲሶቹ ለውጦት ከታሰበላቸው ጊዜ በፊት ቀድመው ይፋ የሆኑት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ነው። የማርክ ዙከርበርግ ድርጅት ሰዎች ሳይጋበዙ ወደ ቪድዮ ጥሪዎቹ እንዳይመጡ የሚከላከል መላም አበጅቷል። አዳዲሶቹ ቴክኖሎጂዎች ከአርብ ጀምሮ ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ላሉ ተጠቃሚዎች ክፍት ሲሆኑ ለሁሉም የፌስቡክ ተጠቃሚ ለማድረስ ሳምንታት ሊወስድ ይችላል ተብሏል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በርካታ የቪድዮ ጥሪ መተግበሪያዎች የገበያ ፀሐይ ወጥቶላቸዋል። ፌስቡክ እንደሚለው በሜሰንጄር አማካይነት የሚካሄዱ የቪድዮ ጥሪዎች ከባለፈው ዓመት እጥፍ ጨምረዋል። የፌስቡክ ተቀናቃኙ ዙም የሰተኘው የቪድዮ ጥሪ መተግበሪያ በአንድ ቀን እስከ 300 ሚሊዮን ደንበኞች እያስተናገደ እንደሆነ ይናገራል። ለወትሮው መሰል አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ሕዝብ በሞላው አዳራሽ ይፋ የሚያደርገው ፌስቡክ አሁን ግን በአለቃው ማርክ ዙከርበርግ አማካይነት በድረ-ገፅ ለማሳወቅ ተገዷል። የቪድዮ ጥሪ የሚደርሳቸው ሰዎች ወደ ጥሪው በፈለጉት ሰዓት መግባትም ሆነ መውጣት ይችላሉ። ኩባንያው ይህንን ቴክኖሎጂ በዋትስአፕና ኢንስታግራም ላይም ሊተግብር እንደሆነ አሳውቋል። ዋትስአፕ ላይ የነበረው ለአራት ሰው ብቻ የሚደረግ የቪድዮ ጥሪ ወደ ስምንት አድጓል። ፌስቡክ ላይ ደግሞ ቀጥታ ሥርጭት የሚያካሂዱ ሰዎች ከሌሎች ጋር መግባት እንዲችሉ ሆኗል። ኢንስታግራም ላይቭ የተሰኘው ዘዴ ደግሞ በዴስክቶፕ እውን እንዲሆን ተደርጓል። የሙከራ ሥርጭቶች በርካታ የሜሴንጀር ተጠቃሚዎች ባሉባቸው አርጀንቲናና ፖላንድ የተካሄዱ ሲሆን ለሙከራው እስከ 20 ሰው ድረስ እንዲሳተፍ ተደርጓል። ፌስቡክ ይህንን ቴክኖሎጂ ሲያብላላ ከሌሎች መሰል ቴክኖሊጂዎች ልምድ እንደቀሰመ አምኗል።
news-55155666
https://www.bbc.com/amharic/news-55155666
ስዊዲን ፡ ወንድ ልጃቸውን ለ30 ዓመት ቤት ቆልፈው ያስቀመጡት እናት ተያዙ
የስዊድን ፖሊስ አንዲት በዋና ከተማዋ ስቶክሆልም የሚኖሩ እናት ልጃቸውን ያለ አግባብ አስረዋል በሚል በቁጥጥር ሥር አውሏቸዋል።
ልጁ የተገኘበት ህንጻ ሴትዮዋ የሚኖሩት ከስቶክሆልም ወጣ ብሎ በሚገኝ ሰፈር ነው። አሁን 40 ዓመት የሞላው ልጃቸው ምናልባት ላለፉት 30 ዓመታት ቤት ውስጥ ታስሮ ነበር የኖረው የሚል ጥርጣሬን አሳድሯል። በሕክምና ላይ የሚገኘው ይህ ጎልማሳ የሴትዮዋ ልጅ ተቆልፎበት ከነበረው አፓርታማ በተገኘበት ወቅት ቆሳስሎና ቆሽሾ እንዲሁም ከባድ መጎሳቀል ውስጥ እንደኖረ በሚያሳብቅ መልኩ ነበር። እናት የፖሊስን ክስ አስተባብለዋል። እንዴት ከ30 ዓመት በኋላ ሊገኝ ቻለ? ይህ ጎልማሳ ልጃቸው ሊገኝ የቻለው ባለፈው እሑድ ነው። እናቱ ድንገት በመታመማቸውን ሆስፒታል ይወሰዳሉ። እሳቸው ሆስፒታል በሄዱበት ጊዜ ሴት ልጃቸው ወደ ቤት በድንገት ትመጣለች። ለ30 ዓመታት የታሰረውን ልጅ ያገኘችው ሴት የታጋቹ ታናሽ እህት ስትሆን ወደ መኖርያቸው የሄደችውም እሑድ ነበር። ወደ እናቷ ቤት የሄደችውም መታመማቸውን በመስማቷ እንደሆነ ለስዊድን ዜና ማሰራጫ ተናግራለች። እሷ ከቤት ወጥታ የራሷን ኑሮ የጀመረችው ገና ወጣት እያለች ሲሆን ከዚያ በኋላ ወንድሟን ለዘመናት አይታው እንደማታውቅ አብራርታለች። ልጅ እያሉ ግን ወንድሟ ትምህርት ቤት እንዳይሄድ በድንገት በእናቷ ሲወሰን ይህን ለሚመለከታቸው ሰዎች መናገሯን አስታውሳለች። ወንድሟ ትምህርት ቤት መሄድ የተወው በ11 ዓመቱ ነበር። እሑድ ዕለት ወደ እናቷ አፓርታማ በሄደች ጊዜ ያደገችበትን ቤት አንድ ክፍል በር ስትከፍት ሽንት ሽንት የሚል ሽታ እንዳጋጠማት ተናግራለች። ሰው ካለ በሚል “እዚህ ቤት! ሄሎ!” እያለች ጨለማ ክፍሉ ውስጥ ስትጣራ የሆነ እንቅስቃሴ እንዳስተዋለች አብራርታለች። ድምጹን ወደሰማችበት አቅጣጫ ስትራመድ በአንድ ጥግ ኩርምት ብሎ የተቀመጠ ሰው ተመለከተች። ያ ሰው አዳፋ ልብስ ለብሶና እግሩ አካባቢ ቆሳስሎ ነበር። “እሱም ወንድሜ ለ30 ዓመታት ያላየሁት ወንድሜ ነበር” ብላለች። “እንዳየኝ እንደምንም ቆሞ ለመቆም እየሞከረ ስሜን ደጋግሞ ይጠራኝ ነበር። ጥርሶቹ በሙሉ ወላልቀዋል። ስለዚህ ቃላት በትክክል ማውጣት አይችልም ነበር” ብላለች። በጣም የገረማትም ከዚህ ዘመን በኋላ እንዴት እንዳልረሳት ብቻ ሳይሆን ሲያያት ምንም ፍርሃት እንዴት እንዳልተሰማው ነው። የ40 ዓመት ጎልማሳ የሆነው ወንድሟ ሆስፒታል እንደደረሰ የሆስፒታል ሰዎች ጉዳዩን ለፖሊስ በማሳወቃቸው ነው እናት በቁጥጥር ሥር የዋሉት። የስቶክሆልም አቃቢ ሕግ ኢማ ኦልሰን ግለሰቡ ቀዶ ጥገና ሕክምና እንዳደረገ ከመግለጽ ውጭ ተጨማሪ ያሉት ነገር የለም። የፖሊስ ቃል አቀባይ ኦላ ኦስተርሊንግ በበኩላቸው ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት ይህ ሰው በእናቱ ለስንት ዘመን ቤት ውስጥ እንደታሰረ ገና የምናጣ ራው ጉዳይ ቢሆንም ነገር ግን ለብዙ ዓመታት በር ተቆልፎበት እንደኖረ ማረጋገጥ ይቻላል ብለዋል። እናቱ ለምን ልጃቸውን አሰሩት? ኤቪቲ የስዊድን ቴሌቪዥን በጉዳዩ ላይ የሴትየዋን ሴት ልጅ አነጋግሮ ባቀረበው ዘገባ እንዳለው አጋች እናት የመጀመርያ ወንድ ልጃቸው ሞቶባቸዋል። በዚህም ከፍተኛ ሐዘን ይሰማቸው ነበር። ከሞት እንዲነሳላቸውም በጽኑ ይለምኑ ነበር። ከዚያ በኋላ የወለዱትን ይህንን ወንድ ልጃቸውን የሰየሙትም ሞቶ መሪር ሐዘን ውስጥ በከተታቸው የበኩር ልጃቸው ስም ነበር። ምናልባት ይህንን ልጃቸውን ለ30 ዓመታት ከርሳቸው ጋር አስረው ያቆዩት ከዚሁ ሞት ፍርሃት ጋር ተያይዞ ጤናማ ባልሆነ የቁጥጥር ስሜት በፈጠረው ሥነ ልቡና ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል።
news-54567469
https://www.bbc.com/amharic/news-54567469
አንበጣ፡ በአማራ ክልል ከ30 ሺህ ሄክታር በላይ የሰብል ምርት በአንበጣ መንጋ ጉዳት ደርሶበታል
አቶ ሐሰን አህመድ ማሳቸውን የወረረውን የአንበጣ መንጋ ማባረሩን ትተው ባለቤታቸውን ሲያጽናኑ ዋሉ። "ከሁሉም በላይ ባለቤቴን ማትረፌ ትልቅ ነገር ነው" ይላሉ።
አቶ ሐሰን አህመድ፣ በራያ ቆቦ ወረዳ ዲቢ ቀበሌ አንቱ የተባሉ አርሶ አደር ናቸው። ማሽላ፣ ጤፍ፣ በቆሎ እና ሽምብራ የመሳሰሉትን አዝዕርት በማምረት ኑሯቸውን ይመራሉ። ዘንድሮ ከወትሮው በተለየ መልኩ የክረምቱ ዝናብ የሰጠ ስለነበር የአቶ ሐሰንን አዝመራ ሙሉና ለአይን ግቡ አድርጎላቸዋል። 15 ጥማድ [4 ሄክታር የሚጠጋ] መሬታቸውን ማሽላ ዘርተው ውጤቱን ከአንድ ወር በኋላ ለማግኘት እየተጠባበቁ ነበር። ከዚህ ማሳ፣ ልክ እንደ ዘንድሮው ሁሉ የክረምቱ ዝናብ በማይጓደልበት ወቅት ከ80 እስከ 100 ኩንታል ማሽላ ያመርቱ እንደነበርም ለቢቢሲ ተናግረዋል። ዘንድሮ ደግሞ ሰብሉ በጥሩ ሁኔታ እያደገ ስለነበር ከወትሮው ከፍ ያለ ካልሆነ ደግሞ ተመሳሳይ ምርት እንደሚያገኙ እርግጠኛ ነበሩ። የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋሁን መንግሥቴ ለቢቢሲ እንደገለጹት፤ በክልሉ የአንበጣ መንጋ በአራት ዞኖች፣ በ18 ወረዳዎች እና በ136 ቀበሌዎች ተከስቷል። አቶ ሐሰን ከአሁን በፊት አንዱ ልጃቸው ለቤቱ ተጨማሪ ገቢ አስገኛለሁ ብሎ ወደ አረብ አገር ሥራ ፍለጋ ሂዶ ነበር። ቤቱንም በገቢ አልደጎመም እርሱም አልተመለሰም። እዚያው ሞቶባቸው "ወይኔ ልጄን ባልላከኩት ኖሮ" እያሉ ለዓመታት የልጃቸው ጸጸት አልወጣላቸውም። ጸጸቱን ለመወጣት ያቀዱት በቂ ምርት አምርተው ቀሪ ልጆቻቸው የወንድማቸው እጣ እንዳይገጥማቸው ፍላጎታቸውን ለማሟላት እና ለማስተማር ነው። ይህንን ለማሳካት ደግሞ የዘንድሮ የሰብል አያያዝ ትልቅ ተስፋ ሰጥቷቸው ነበር። ከዚህም በተጨማሪ አቶ ሐሰን ከሚያገኙት ምርት ግማሹን ሽጠው ደካማ የሳር ጎጇቸውን በተንጣለለ የቆርቆሮ ክዳን ቤት ለመቀየር እቅድ አስቀምጠዋል። ሁሉም እውን ሊሆን ቢበዛ የሁለት፣ ካነሰ ደግሞ የአንድ ወር ጊዜ ብቻ ቀርቷቸው ነበር። ይህ ሁሉ እቅድ ግን ተስፋ ሆኖ የቆየው እስከ መስከረም 6 2013 ዓ.ም ነው። በዚህ ዕለት ያልተጠበቀ ክስተት መጣ። የአንበጣ መንጋ። የጣልኩብሽ ተስፋ እኔን ይዞ ጠፋ. . . ብዙ ተስፋ የጣሉበት የአቶ ሐሰን 15 ጥማድ የማሽላ ማሳ በአንበጣ ተወረረ። የሚችሉትን ያክል ቀን ከሌሊት አንበጣን ታገሉት፣ ነገር ግን ድካሙ ፍሬ አልባ ሆነ፤ አንበጣው አሸነፋቸው። ያ ለስንት ያቀዱለት ሰብላቸው አሁን ያለበትን ሁኔታ "የታሰበው 100 ኩንታል ይቅርና ለዘር የሚሆን አንድ ጣሳም [አንድ ኪሎ] አይገኝበት" በማለት ይገልጹታል። አሁን ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ መሆኑን ይናገራሉ። አቶ ሐሰን ሌላ የስምንት ጥማድ [4 ሄክታር] እርሻቸው ደግሞ በበቆሎ ሰብል የተሸፈነ ነው። 15 ጥማድ ማሳቸውን ያወደመው የአንበጣ መንጋ፣ በዚህ ይበቃዎት አላላቸውም። ሁለተኛ ምዕራፍ የጥቃት ዘመቻውን የበቆሎ ማሳቸው ላይ አሳረፈ ነው። ሰሞኑን በአውሮፕላን በሚደረግ የኬሚካል ርጭትም በመታገዝ መከላከል ሲደረግ ቆይቷል፣ ጉዳቱ ግን አልቀነሰም። አቶ ሐሰንም ከመስከረም ስድስት ጀምረው ሌላ ሥራ በማቆም፣ መደበኛ ሥራቸው ከልጆቻቸው ጋር የአንበጣ መንጋ ማባረር ቢሆንም የማሽላ ሰብላቸው ሙሉ በሙሉ በመውደሞ በቆሎአቸውን ለመታደግ እየተውተረተሩ ነው። ከሰሞኑ ግን ከልጆቻቸው በተጨማሪ ባለቤታቸውም ማሳቸውን ከአንበጣ ለመካለከል ወደ ማገዝ ጀምረዋል። የአቶ ሐሰን ባለቤት ያዩትን ማመን አልቻሉም። ያ በየዓመቱ እየተጫነ ጓዳና ጎተራቸውን ሲያጨናንቅ የነበረው ግዙፉ ማሳቸው ራቁቱን ቀርቷል። "ባለቤቴ የወደመውን ሰብል ስትመለከት ራሷን ሳተችብኝ፣ ልጆቼን ምን ላበላቸው ነው ብላ ተጨነቀችብኝ፣ ቤታችን በሰፊው የተለመደበት ስለነበር አሁን ባዶ ማሳ ስታይ ነገ ምን ልንሆን ነው ብላ ራሷን ሳተችብኝ፣ ስለዚህ አንበጣ መከላከሉን ትቼ እርሷን ሳጽናና ዋልኩ። እርሷን በሕይወት ማትረፌ ራሱ ትልቅ ደሰታ ተሰምቶኛል" በማለት ባለቤታቸው የወደመውን ሰብል ሲመለከቱ የተሰማቸውን ስሜት ያብራራሉ። አሁን ከሁለተኛው ማሳቸው የተወሰነ ነገር ለማትረፍ የሞት ሽረት ትግል እያደረጉ ቢሆንም እንዲሁ ዝም ብሎ ላለማስበላት እንጂ ተስፋቸው ተሟጥጧል። ቀጣይ ዝናብ ጥሎ በበልግ ለማምረት፣ ካልሆነ ደግሞ መንግሥት የሚሰጠው ነገር ካለ እርሱን የሕይወት ማቆያ ለማድረግ ተስፋ ሰንቀዋል። ሌላኛው አርሶ አደር ይማም መሃመድ በዚሁ የራያ ቆቦ ወረዳ ያያ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው። አንበጣው ቀድሞ ሲገባ የመጀመሪያ ጥፋቱን የጀመረው ከእርሳቸው ማሳ ነው። "ሁሉንም እርሻዎቼን አንበጣው ሙሉ በሙሉ አውድሟቸዋል። አሁን አንበጣ የምከላከለው የሌሎች አርሶ አደሮችን ማሳ ለማትረፍ ነው" ይላሉ። እርሳቸው የሚኖሩበትን ያያ ቀበሌ ጨምሮ በወረዳው የሚገኙ ሁለት ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ የዘንድሮ ሰብላቸው በአንበጣ መንጋ ወድሟል። በአጠቃላይ በራያ ቆቦ ወረዳ 16 ቀበሌዎች በአንበጣ መንጋው ተወርረዋል። በሰውና በአውሮፕላን የታገዘ የኬሚካል ርጭት እንዲሁም የመከላከል ሥራ ቢሰራም ለአንድ ወር ያክል አንበጣውን ከአካባቢው ሙሉ በሙሉ ማጥፋት አልተቻለም። በአማራ ክልል ከሰሜን ሸዋ እስከ ሰሜን ወሎ ድረስ የአንበጣ መንጋው ከፍተኛ ጉዳት ካስተናገደባቸው ወረዳዎች አንዱ የሃብሩ ወረዳ ነው። በወረዳው ሰባት ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ በአንበጣ መንጋው ወድመዋል። አርሶ አደር አሊ ሰዒድ ከእነዚህ ቀበሌዎች አንዷ በሆነችው ጥልፌ ቀበሌ ይኖራሉ። ከአራት እርሻዎቻቸው መካከል የ13 ጥማድ [3 ሄክታር በላይ] መሬት ወድሞባቸዋል። አንድ እርሻ ማትረፋቸውን የሚናገሩት አቶ አሊ፣ "የተረፈው እርሻ የአንድ ወር ቀለብ እንኳን የሚሆን አይደለም፣ ዓመት ሙሉ የደከምንበት እንኳን ለእኛ ለከብቶቻችንም የሚሆን እንዳይተርፍ አድርጎ አውድሞብናል" በማለት አንበጣው ያደረሰባቸውን ጉዳት ይገልጻሉ። የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋሁን መንግሥቴ የአንበጣ መንጋው በክልሉ 4 ዞኖች፣ 18 ወረዳዎች በ136 ቀበሌዎች መከሰቱን ለቢቢሲ ተናግረዋል። በእነዚህ አካባቢዎች በአጠቃላይ 328 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ መውረሩን የተናገሩት አቶ ተስፋሁን ግማሽ የሚሆነውን መሬት የአውሮፕላን ርጭትን ጨምሮ በተለያዩ የመከላከያ ዘዴዎች የመከላከል ሥራ ተሠርቶበታል ሲሉ ይናገራሉ። የአንበጣ መንጋው 87 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ በሰብልና በእንስሳት መኖ ላይ ጉዳት አድርሷል የሚሉት አቶ ተስፋሁን፣ ከእነዚህም መካከል 30 ሺህ 500 ሄክታር የሚሆነው የሰብል ምርት መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል። የአንበጣ መንጋው ባደረሰው ከፍተኛ ውድመት የተጎዱ አርሶ አደሮችን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ድጋፍ ለማድረግ ሥራ እየተሠራ መሆኑንም ምክትል ቢሮ ኃላፊው ተናግረዋል።
news-56697409
https://www.bbc.com/amharic/news-56697409
በግብጽ የ3ሺህ ዓመት ዕድሜን ያስቆጠረ አስደናቂ ጥንታዊ ከተማ ተገኘ
ግብጽ አሸዋ ቀብሮት የነበረና 3ሺህ ዓመታት ዘመንን ያስቆጠረ ግዙፍ ጥንታዊ ከተማን በቁፋሮ አገኘች።
የተገኘው ጥንታዊ ከተማ ይህ የቁፋሮ ግኝት ከፈርኦን ቱቱካሙን መቃብር ቀጥሎ እጅግ አስደናቂ የቁፋሮ ውጤት ተብሎ ተሞካሽቷል። ዕውቁ ኢጂብቶሎጂስቱ (የግብጽ ጥንታዊ ታሪክ አጥኚ) ዛሒ ሐዋስ የዚህን ወርቃማ ጥንታዊ ከተማ ግኝትን ሐሙስ ዕለት ለዓለም አብስረዋል። ዛሒ ሐዋስ እንዳሉት ከሆነ በግብጽ ታሪክ ይህ ጥንታዊ ከተማ እስከዛሬ ከተገኙ ጥንታዊ ከተሞች ሁሉ በግዝፈቱም ሆነ በያዘው አንጡራ ቅርስም ቢሆን የሚስተካከለው የለም። የዚህ ከተማ ግኝት እውን የሆነው ሳምንታትን ብቻ በፈጀ ቁፋሮ ሲሆን አሸዋ መማስ የተጀመረው ገና በመስከረም ወር ላይ ነበር። ይህ ግዙፍ ጥንታዊ ከተማ በታሪክ ውስጥ የሚታወቀው በፈርኦን አሜንሆቴፕ ሣልሣዊ ዘመነ መንግሥት ነበር። ይህ ንጉሥ ጥንታዊት ግብጽን የገዛው ከ1391 እስከ 1353 ዓመተ ዓለም (ከክርስቶስ ልደት በፊት) ነበር። ይህ አሁን የተገኘው ከተማ ስሙ አቴን ይባል ነበር። ከፈርኦን ንጉሥ አሜንሆቴፕ ሣልሣዊ ሌላ ቀዳማዊ ፈርኦን እና ዝነኛውና ትንሹ ፈርኦን ቱቱንካሙን ይህን ከተማ መናገሻቸው አድርገውት በታሪክ ተዘግቦ ይገኛል። የእነዚህ ሁለት ፈርኦኖች መቃብር ለሺህ ዘመናት በመልካም ይዞታ ላይ እንደኖረ በ1922 በእንግሊዛዊው ዕውቅ የአርኪዮሎጂ ጥናት ባለሙያ ሃዋርድ ካርተር መገኘቱ ይታወሳል። የኢጂፕቶሎጂ ፕሮፌሰርና የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት ቤሲ ብራያን የዚህን ጥንታዊ ከተማ መገኘት ከፈርኦን ቱቱንካምን መቃብር መገኘት ቀጥሎ ለዓለም የተበሰረ እጅግ ወሳኙ ግኝት ሲሉ አሞካሽተውታል። ፕሮፌሰሯ እንደሚሉት የዚህ ጥንታዊ ከተማ መገኘት በጥንታዊ ግብጻውያን አኗኗር ዙሪያ ብዙ የሚነግረን ነገር ይኖራል። ይህ ጥንታዊ ከተማ መገኘቱን ተከትሎ በርካታ ጠቃሚ ነገሮችም በግኝቱ ተካተዋል። ከእነዚህ መካከልም ውድ ጌጣጌጦች፣ በቀለም ያጌጡ የእንስራና ሌሎች የፈርኦኑ ምልክት ያለባቸው የዕደ ጥበብ ውጤቶች ይገኙበታል። ከተገኙት ቅርሶች መካከል ይህ የቁፋሮ ቡድን የዚህን ከተማ ፍለጋ የጀመረው ከካይሮ በስተደቡብ 500 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ቫሊ ኦፍ ኪንግስ ምዕራብ ሉክዘር አካባቢ ነበር። "ቁፋሮው በተጀመረ በሳምንታት ውስጥ ሁሉንም የከርሰ ምድር ጥናት ተመራማሪዎችን ራሳቸውን ጉድ ባሰኘ ሁኔታ የሸክላ ድርድሮች መታየት ጀመሩ፤ ይህም የጥንታዊ ከተማውን አቅጣጫ መራን" ብለዋል ታዋቂው ኢጂፕቶሎጂስቱ ዶ/ር ሐዋስ። የግኝቱ ሌላው አስደናቂ መልክ ደግሞ የጥንታዊ ከተማው አስደናቂ ግንቦችና አንዳንድ የመኖርያ መንደሮች እንዲሁም ቤቶችም ከዕለታዊ ቁሳቁሶቻቸው ጭምር መገኘታቸው ነው። 7ኛ ወሩን ባስቆጠረው የቁፋሮ ፍለጋ ከተገኙት አስደናቂ ነገሮች መሀል የከተማዋ አስተዳደር፣ የመኖርያ ሰፈሮች እና ዳቦ ቤት ይገኝበታል ተብሏል። ከዚህ ቀደም በርካታ የውጭ አገር ተመራማሪዎች ይህን ጥንታዊ ከተማ ለማግኘት ብዙ ጥረት አድርገው ሳይሳካላቸው ቀርቶ ነበር። አሁንም በዚህ ጥንታዊ ከተማ ሌሎች ቁሳቁሶችን ፍለጋ የቀጠለ ሲሆን ተስፋ የተጣለው የፈርኦን ዕውቅ ነገሥታት መቃብርና ውድ ሀብቶቻቸው የተቀበሩበትን ቦታ ፈልጎ ማግኘት ነው። ግብጽ ከከሸፈው የፀደይ አብዮት ወዲህ ተዳክሞ የቆየውን የቱሪዝም ዘርፍ በከፍተኛ ሁኔታ ማነቃቃት ከፍተኛ ፍላጎት አላት። ይህ ግኝት በዚህ ረገድ ትልቅ ውጤት ያስገኝላታል ተብሎ ይጠበቃል። ባለፈው ሳምንት ግብጽ የጥንታዊ መሪዎቿን መቃብርና በመሚ ዘዴ የደረቁ የፈርኦኖችን አስከሬን ወደ ካይሮ ማዘዋወሯ ይታወሳል። ይህ ሂደት 18 እጅግ ጥንታዊ ንጉሦችንና 4 ንግሥቶችን ያካተተ ነበር። እስከዛሬ ከቆዩበት የግብጽ ሙዚየም ወደ አዲሱ ብሔራዊ ሙዝየም ነው የተወሰዱት። ይህ አዲስ ብሔራዊ ሙዝየም 1 ቢሊዮን ዶላር ወጪ የወጣበት እጅግ ዘመናዊ መካነ ቅርስ ነው። ከእነዚህ ወደ አዲሱ መካነ ቅርስ ከተዛወሩት የፈርኦን አስከሬኖች መካከል የአሜንሆቴፕ ሣልሣዊና ባለቤቱ ንግሥት ቲዬ አስከሬኖች ይገኙበታል።
52195575
https://www.bbc.com/amharic/52195575
ኮሮናቫይረስ፡ ለመሆኑ ጽኑ ሕሙማን ክፍል ምንድን ነው?
ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ትናንት አመሻሽ ላይ ሕመማቸው ስለበረታ ወደ ጽኑ ሕሙማን ክፍል መግባታቸው ተሰምቷል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት እንዳለው በሐኪሞቻቸው ምክርና ለቅድመ ጥንቃቄ በሚል የተሻለ የቅርብ ክትትል ወደሚያገኙበት ክፍል መግባታቸውን ገልጿል። ለመሆኑ ጽኑ ሕሙማን ክፍል ምንድን ነው? የሕክምና ባለሙያዎች የጽኑ ሕሙማንን ክፍል በእንግሊዘኛ ምህጻረ ቃሉ አይሲዩ (ICU) ሲሉ ይጠሩታል። ይህ ክፍል በጠና የታመሙ ሕሙማን በሐኪሞቻቸው የቅርብ ክትትል እየተደረገላቸው የሚታከሙበት ክፍል ነው። እነዚህ ክፍሎች በተቻለ መጠን በአስፈላጊ የሕክምና ቁሳቁሶች የተደራጁ መሆን ይኖርባቸዋል። አንድ ታካሚ በተለያየ ምክንያት ወደ ጽኑ ሕሙማን ክፍል ገብቶ መታከም ሊያስፈልገው ይችላል። አንዳንድ ሕሙማን ከቀዶ ሕክምና በኋላ እስኪያገግሙ ድረስ በዚህ ክፍል እንዲቆዩ ሲደረግ፣ አንዳንዶች ደግሞ ከከባድ የመኪና ወይንም ሌላ አደጋ በኋላ በዚህ ክፍል የሕክምና ክትትልና ድጋፍ ይደረግላቸዋል። ኮሮናቫይረስ የሚያጠቃው የመተንፈሻ አካላትን በመሆኑ ወደ ጽኑ ሕክምና ክፍል የሚገባ ታማሚ የመተንፈስ ችግር አጋጥሞት ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ይህ ማለት የመተንፈሻ ማሽን ሊገጠምለት ይችላል ወይንም በማሽን ታግዞ መተንፈስ ያስፈልገዋል ማለት እንዳልሆነ ባለሙያዎች ያብራራሉ። በርግጥ በጽኑ ሕሙማን ክፍል ያሉ ታካሚዎች የተለያዩ መሳሪያዎች ተገጥመውላቸው የመተንፈስ ችግራቸው እንዲቃለል ሊደረግ እንደሚችል የዘርፉ ባለሙያዎች ያስረዳሉ። ከእነዚህም መካከል CPAP ሲሆን ታካሚው በሚደረግለት ጭምብል በኩል ኦክስጅን እንዲያገኝ የሚረዳው መሳሪያ ነው። በዚህ የሕሙማን ክፍል የሚቆዩ ታካሚዎች የሚያስፈልጋቸው መድኃኒት እየተሰጣቸው መሻሻል እስኪያሳዩ ድረስ ክትትል እየተደረገላቸው ይቆያሉ። ታካሚው መሻሻል እንዳሳየ ግን ወደ ተኝቶ ታካሚዎች ወይንም ሌላ ክፍል የሚዛወር እና የክፍሉን አልጋ ለሌሎች በአፋጣኝ የዚህ ክፍል እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሕሙማን የሚለቁ ይሆናል። አንዳንድ ሕሙማን ለተወሰኑ ቀናት በዚህ ክፍል መቆየት ሲያስፈልጋቸው፣ አንዳንዶች ግን ለሳምንታትና ለወራት ቆይተው መታከም ይኖርባቸዋል።
news-42540503
https://www.bbc.com/amharic/news-42540503
ካለሁበት 17 ፡ ከሰው አልፎ ለእንሰሳት ቦታ በሚሰጥበት ከተማ ውስጥ ነው የምኖረው
ስሜ ሔዋን ወሌ ይባላል መኖሪያዬን በኢስታንቡል ቱርክ ነው ያደረግሁት። ከኢትዮጵያ ከወጣሁ ወደ አሥር ዓመታት ሆኖኛል።
በመጀመሪያም ስወጣ የትምህርት ዕድል አጋጥሞኝ ወደ ሞሮኮ ነበር ያቀናሁት። እዚያም ስምንት ዓመታት ኖሪያለሁ። ሥራ እንደጀመርኩም ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት ወደ ኢስታንቡል የሚያመጣ አጋጣሚን አግኝቼ ነበር የመጣሁት። የተመረቅሁት በፋርማሲ ትምህርት ሲሆን አሁን የምሠራው በዚሁ ዘርፍ በሚሠራ ተቋም ውስጥ ነው። በይበልጥ የማተኩረው በፋርማሲ ዲጂታል ማርኬቲንግ ላይ ሆኖ የፋርማሲ ዕቃዎችንና ውጤቶች ሽያጭ የሚመለከት ዘርፍ ላይ ነው። የእዚህ ሃገር ነዋሪዎች እንደ ሃገሬ ሕዝብ ሰው ወዳድና እንግዳ ተቀባይ ናቸው። ሆኖም ግን ኢስታንቡልን ከአዲስ አበባ ጋር ለማመሳሰል በጣም ይከብደኛል። ኢስታንቡል በሁለት አህጉራት ላይ የተቀመጠች ብትሆንም ድልድዩ ያገናኛቸዋል ሁለቱም ከተሞች የራሳቸው ውበትና ግርማ ሞገስ ቢኖራቸውም፤ ኢስታንቡልን ይበልጥ ለየት የሚያደርጋት በሁለት አህጉር ላይ የተቀመጠችው በዓለም ብቸኛዋ ከተማ መሆኗ ነው። ቦስፎረስ የተሰኘው ወንዝ ኢስታንቡልን በአንድ በኩል በአውሮፓ ላይ ሲያሳርፋት በምሥራቅ በኩል ደግሞ እስያ ላይ ያሳርፋታል። ይህም ደግሞ ከተማዋን በጣም ውብ ያደርጋታል። በተለይ በውሃ የተከበበች መሆኗን እወደዋለሁ። አዲስ አበባ በብዛት የተለያዩ ፎቆች ግንባታ ላይ ትገኛለች በኢስታንቡል ግን ግንባታው አብቅቶ ከተማዋን የበለጠ ማስዋብ ላይ ናቸው። የተለያዩ ውብ አትክልቶችን የያዙ ብዙ የሕዝብ መናፈሻ ቦታዎች ይገኙባታል። ከዚያም በተጨማሪም በውሃው ዳርቻ ለእግረኛና ለሳይክል ነጂዎች ታስቦ የተዘጋጁ መንገዶችም አሉ። የሕዝብ መናፈሻ ቱርክ የምትታወቅበት አንደኛው ምግብ ኬባብ ወይም ዶነር በመባል የሚታወቀው ነው። እኔም ብሆን በጣም ነው የምወደው። በተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት ላይ የተለመደ ምግብ ቢሆንም እንኳን ቱርክ የኬባብ መዲና ናት ለማለት አያዳግትም። ኬባብ የተለያዩ ሥጋዎችን በተለይ የበሬ ሥጋን ለረጅም ሰዓታት አብስለው ከተለያዩ ቅመማት ጋር በማዋሃድ በስስ ቂጣ ጠቅልለው ያቀርቡታል። ከዚህም በላይ በጣም ስመገበው የሚያስደስተኝ ጣፋጫቸው ነው። ቱርኮች የተለያዩ ጣፋጭ ምግቦችን ይሠራሉ፤ አንዱን ጣፋጭ ከሌላው ማበላለጥ የማያታሰብ ቢሆንም እኔ ግን ባቅላቫ ነው የምወደው። (በግራ) ባቅላቫ እና (በቀኝ) ዶነር ወይም ኬባብ ቤተሰቦቼ ቢናፍቁኝም ከሃገር ቤት እየናፈቀኝ የመጣው ቤተ-ክርስቲያን ማሰቀደስ ነው። ምክንያቱም እዚህ የእራስ የሆነ ቤተ-ክርስቲያን ለማግኘት ከባድ ነው። ሆኖም ሃገሬን ለማሰብና ሃሳቤን ለማሰባሰብ በምፈልግበት ጊዜ በመስኮቴ ወደ ውጪ እመለከታለሁ። በከተማዋ በርካታ ሕንፃዎች ስላሉ አብዛኛውን ጊዜ ሕንፃ ብቻ ነው የሚታየኝ። ሆኖም ግን የምኖርበት ስፍራ ከፍታ ላይ በመሆኑ በተለይ ሌሊት ያለውን እይታ እወደዋለሁ። ከተማዋን ምሽት ላይ በመብራት ተውባ ከቤቴ ስለምቃኛት ደስ ይለኛል። ማታ ማታ በሳሎኔ መስኮት ከተማዋ በመብራት ተንቆጥቁጣ አያታለሁ እዚህ ከመጣሁ አንስቶ የሚገርመኝ ለእንሰሳት በተለይ ደግሞ ለውሻ ያላቸው ቦታና ክብር ነው። የእንሰሳት ብዙም አፍቃሪ አልነበርኩም፤ አሁን ግን በጣም ትኩረቴን እየሳቡት ነው። በከተማው ያሉት የመንገድ ላይ ውሾች በደንብ የተመገቡ፣ ውሃም እንደልባቸው የሚያገኙ፣ ሕክምናም የተሟላላቸው እንደሆኑ አያለሁ። ይህ ሁኔታ ይገርመኝም ስለነበር እንዴት ሊሆን እንደቻለ ስጠይቅ መንግሥት ተገቢውን እርዳታ እንደሚያደርግ ሰዎች ነግረውኛል። በከተማ ውስጥ አሉ ከሚባሉት የሕዝብ መናፈሻዎች መካከል ብዙዎቹ ለውሻ ታስበው የተመቻቹ ናቸው። ይህም ብቻ አይደለም የበለጠ አስገርሞኝ የነበረው በበረዶ ወቅት የገበያ ስፍራዎች በሙሉ የውሾች ማደሪያ መሆናቸው ነው። ከሰው አልፎ ለእንሰሳ ቦታ የሚሰጥ ከተማ ውስጥ መኖሬ ሁሌም ያስገርመኛል። የከተማዋን ውበትና ሁለመናዋን ብወደውም እንኳን፤ ያለውን የትራፊክ መጨናነቅ መቀነስ ብችል ደስ ይለኝ ነበር። ከተማዋ በሁለት አህጉር ላይ እንደመቀመጧ ነዋሪው በአንደኛው ክፍል እየኖረ በሌላኛው ስለሚሠራ መንገድ ላይ ምንጊዜም ሰው አይጠፋም። በመጓጓዣ በኩል ሜትሮ (የመሬት ውስጥ ባቡር) ስላለ በዙ አልቸገርም፤ ቢሆንም በሥራና በትምህርት ቤት መግቢያና መውጫ ሰዓታት ላይ መንገዶች በሙሉ ይዘጋጋሉ። እንደዚያም ሆኖ ግን ለኢስታንቡል ያለኝን ፍቅር አይቀንስም። በተለይ በዚህ ወቅት ያለው ቅዝቃዜ ግን ከባድ ስለሆነ ምቾት አይሰጠኝም ። ሕዝቡ ለሰዉ ፍቅር ስላለው ብዙ ነገር ቀሎኝ ነው የምኖረው። ዕድለኛ ሆኜ የማውቃቸው ሰዎችም መልካሞች ስለሆኑ በኢስታንቡል መኖርን ቀላል አድርገውልኛል። ምንም ቢሆን እናትን የሚያክል ነገር ስለሌለ፤ ብችል በቅጽበት እናቴ ጉያ ውስጥ እራሴን ባገኝ እመኛለሁ። ለክሪስቲን ዮሐንስ እንደነገረቻት የ'ካለሁበት' ቀጣይ ክፍል ለማግኘት ፦ ካለሁበት 18፡ አውስትራሊያ መጥቼ እርቃናቸውን የሚሄዱ ሰዎችን ሳይ በጣም ደነገጥኩኝ ካለሁበት 19፡ እንጀራ ማግኘት የማይታሰብባት ከተማ - ሌጎስ
news-44234736
https://www.bbc.com/amharic/news-44234736
ህክምናቸውን አቋርጠው የወጡ የኢቦላ ታማሚዎች ሞቱ
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በህክምና ተቋም የሚገኙ የኢቦላ ታማሚዎችን ቤተሰቦቻቸው ወደ ቤተክርስቲያን ሊወስዷቸው በመፈለጋቸው ምክንያት ህክምናውን አቋርጠው እንደወጡ የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።
የአለም ጤና ድርጅት ባለሙያ የሆኑት ኢውጌኔ ካባምቢ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የታማሚዎቹ ዘመዶች በድንበር የለሽ ሃኪሞች ድርጅት በሚመራው ማዕከል በመምጣት ለፀሎት ሊወስዷቸው እንደሚፈልጉ ገልፀውላቸዋል። በቦታው የሚገኙ ባለሙያዎች ህክምናቸውን እንዲቀጥሉ ሊያሳምኗቸው ጥረት ቢያደርጉም አልተሳካላቸውም። በኋላም በሞተር ሳይክል እንደተወሰዱ ገልፀዋል። እነርሱን ለመፈለግ የፖሊስ ትዕዛዝም ወጥቶ ነበር። ይሁን እንጂ ህክምናውን ጥለው ከወጡ ታማሚዎች አንዱ ቤቱ ከደረሰ በኋላ ህይወቱ ያለፈ ሲሆን በጥንቃቄ መቅበር ይቻል ዘንድም አስከሬኑ ወደ ህክምና ተቋሙ ተመልሷል። አንደኛው ምባንዳካ ከተማ ወደሚገኝ የህክምና ቦታ የተመለሰ ሲሆን ህክምናቸውን ትተው ከሄዱት ሶስት ታማሚዎች መካከል ሁለቱ ሞተዋል። "እንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች መፈጠራቸው ለጤና ባለሙያዎቹ አዲስ ተግዳሮት ሆኗቸዋል። የዚህን ተላላፊ በሽታ ስርጭት ለመግታትም ፈታኝ ያደርገዋል።" ብለዋል። ኢቦላ መድሃኒት የሌለው በሽታ ሲሆን፤ አንድ ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ በሚኖርባት ምባንዳካ ቫይረሱ በፍጥነት ሊዛመት ይችላል ሲሉ የጤና ባለሙያዎቹ ስጋታቸውን ገልፀዋል። በመሆኑም ተነጥሎ ለብቻ በተዘጋጀ ቦታ ክትትሉን ማድረግ ስርጭቱን ለመቆጣጠር የሚያስችል ዋነኛው መንገድ እንደሆነም ተገልጿል። "ህክምናውን አስገድዶ መስጠት ወረርሽኙን ለመቆጣጠር መፍትሄ አይሆንም" ያሉት ባለሙያው "ታማሚውን መከታተል ግን ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው" ይላሉ። በመሆኑም ህክምናቸውን አቋርጠው የወጡት ሶስቱ ታማሚዎች ቤተሰቦች ላይ ክትትል እየተደረገ ሲሆን የተወሰኑት ክትባቱን ተከትበዋል። የአለም ጤና ድርጅት እንዳስታወቀው ኢቦላ ዳግም ካገረሸ በኋላ አምሳ ስምንት ኬዞች ተመዝግበዋል። ከእነዚህ መካከል ሃያ ሰባቱ የሞቱ ሲሆን ከሟቾቹ የሶስቱ በኢቦላ ምክንያት እንደሆነ ተረጋግጧል።
news-54077781
https://www.bbc.com/amharic/news-54077781
ሊባኖስ ፡ በቤይሩት ወደብ ላይ ከባድ የእሳት አደጋ አጋጠመ
ከአንድ ወር በፊት በተከሰተ ከባድ ፍንዳታ ቢያንስ 190 ሰዎች በሞቱባት በሊባኖሷ ዋና ከተማ ቤይሩት በሚገኘው ወደብ ላይ ከባድ የእሳት ቃጠሎ ተነሳ።
እሳቱ የተቀሰቀሰው በወደቡ የቀረጥ ነጻ ክልል ውስጥ በሚገኝ ዘይትና ጎማ በተከማቸበት መጋዘን ላይ ሲሆን፤ ባለስልጣናት የእሳት አደጋውን በዚያው ቦታ ላይ ለመቆጣጠር ተችሏል ብለዋል። እስካሁን በእሳቱ ሳቢያ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ የተነገረ ሲሆን፤ የአደጋው መነሻ አልታወቀም። በከቃጠሎው የሚወጣው ጥቁር ጭስም በከተማዋ ሰማይ ላይ ይታያል። የእሳት አደጋ ሠራተኞች በአደጋው ቦታ እሳቱን ለመቆጣጠር እየጣሩ ሲሆን የአገሪቱ ሠራዊትም ሄሊኮፕተሮችን በመጠቀም እሳቱን ለማጥፋት እየጣረ መሆኑን አመልክቷል። የሊባኖስ ቀይ መስቀል ኃላፊ ጆርጅ ካታኒሐ እንዳሉት በአደጋው ምክንያት አንዳንድ ሰዎች ለመተንፈስ የመቸገር ሁኔታ እንዳጋጠቸው ቢገልጹም ይፋ የሆነ ጉዳት ግን እስካሁን እንዳልደረሰ ለሮይተርስ ተናግረዋል። ኃላፊ ጨምረውም ባለፈው ጊዜ እንዳጋጠመው በእሳቱ የተነሳ ፍንዳታ ሊያጋጥም ይችላል የሚል ስጋት እንደሌለ ተናግረዋል። ቢሆንም ግን በአደጋው ሳቢያ አንዳንድ ነዋሪዎች ፍርሃት እንደተፈጠረባቸው ገልጸዋል። ያለፈው ወር ፍንዳታ የተከሰተው በወደቡ ላይ ተከማችቶ የነበረ 2,750 ቶን የሚሆን አሞኒየም ናይትሬት የተባለ ኬሚካል በእሳት ተያይዞ ሲሆን በአደጋውም ሳቢያ በአገሪቱ ከባድ ተቃውሞ ተቀስቅሶ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥራቸውን ለመልቅ ተገደው ነበር። በኬሚካሉ ፍንዳታ ሳቢያ በከተማዋ ላይ ከባድ ውድመት የደረሰ ሲሆን በርካታ ቤቶችና ሕንጻዎች ፈራርሰዋል። በዚህም ምክንያት ከሞቱት ከ190 በላይ ሰዎች በተጨማሪ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የመቁሰል አደጋ ሲደርስባቸው 300 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ቤት አልባ ሆነዋል።
news-53675025
https://www.bbc.com/amharic/news-53675025
ነፍስ በማጥፋት ወንጀል ለ27 ዓመት እስር ቤት የማቀቀው ቻይናዊ ነፃ ነህ ተባለ
በምስራቅ ቻይና በግድያ ወንጀል 27 ዓመት ተፈርዶበት የነበረው ቻይናዊ ነፃ ነህ ተብሎ ተለቀቀ።
ዛንግ ዩሃን እ.ኤ.አ በ1993 ሁለት ልጆችን በመግደል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር በዋለበት ወቅት ፖሊስ ጥፋቱን እንዲያምን እንዳሰቃየውና እንዳስገደደው ተናግሮ ነበር። ዛንግ በቻይና ለ9778 ቀናት፤ በዢያንግዢ ማረሚያ ቤት በስህተት ለረዥም ጊዜ የታሰረ ሰው ሆኖ ተመዝግቧል። የዛንግን የክስ መዝገብ ዳግም ያንቀሳቀሱት አቃብያነ ህጎች በወቅቱ የሰጠው የእምነት ክህደት ቃል ወጥነት ይጎድለው እንደነበር በመግለጽ ከተፈፀመው ወንጀል ጋርም እንደማይገናኝ ተናግረዋል። ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብሎ 27 ዓመት በእስር ቤት ውስጥ ላሳለፈበት ወንጀል በቂ ማስረጃ የለም ብሎ በመወሰኑ በነጻ ተለቅቋል። ታዛቢዎች ቻይና በወንጀል ተጠርጥረውና በስህተት ተፈርዶባቸው በእስር ቤት የሚገኙ ሰዎችን ለመልቀቅ ፈቃደኝነት እያሳየች ነው ሲሉ ተናግረዋል። ይህ ግን የፖለቲከኛ እስረኞችን አይጨምርም ተብሏል። በቻይና መገናኛ ብዙኀን የቀረበው ምስል እንዳሳየው ዛንግ ከእስር ቤት ከወጣ በኋላ ከ83 ዓመት እናቱ ጋርና ከቀድሞ ባለቤቱ ጋር ተገናኝቷል። በቻይና ፖሊስ በተለያዩ ወንጀሎች የተጠረጠሩ ሰዎች ላይ ምርመራ በሚያደርግበት ወቅት ድብደባ እንደሚፈጽም፣ እንደሚያሰቃይ፣ እንቅልፍ እንደሚከለክል፣ በሲጋራ እንደሚያቃጥል፣ ይነገራል። ከዚህ ቀደም በወንጀል የተጠረጠሩ ሰዎች በዚህ ሁሉ ውስጥ አልፈው የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ ይደረግ ነበር። እ.ኤ.አ በ2010 ግን የቻይና የሕግ ስርዓት አስገዳጅ የሆነን ምርመራ ለማስቀረት መስራት ጀመረ። የሞት ፍርድም ቢሆን በቻይና ጠቅላይ ፍርድ ቤት መጽደቅ ያለበት ሲሆን የተፈፀመ ወንጀል ላይ የሚሰጥ ፍርድም በተጠርጣሪው የእምነት ክህደት ቃል ላይ ብቻ እንዳይመሰረት ተወስኗል። ዛንግ ከቀድሞ ሚስቱ፣ ሶንግ ጋር ከመለያየታቸው በፊት ሁለት ወንድ ልጆች ወልደዋል። ሶንግ ድጋሚ ብታገባም የቀድሞ ባለቤቷን ይግባኝ ክስ ግን ትከታተልና ትደግፍ ነበር። "የችሎቱን ውሳኔ ስሰማ በጣም ነው ደስ ያለኝ" ብላለች ሶንግ። ዛንግ በእስር ቤት ላባከናቸው ዓመታት ካሳ እንደሚከፈለው ችሎቱ ወስኗል። "ከደንበኛዬ ጋር ስለ ካሳው መጠን እንነጋገርበታለን" ብለዋል የዛንግ ጠበቃ፣ ዋንግ ፌይ ለቻይና ዴይሊ። አክለውም "እንዲህ ዓይነት የሕግ ጥሰት የፈጸሙትንም ተጠያቂ ለማድረግ እቅድ አለን።" ዛንግ በቁጥጥር ስር የዋለው እ.ኤ.አ በ1993 ሲሆን ሁለት ወጣቶች በናንቻንግ ግዛት ጂያንግዢ ከተማ በውሃ ኩሬ ውስጥ አስከሬናቸው መገኘቱን ተከትሎ ነው። ዛንግ የሟቾቹ ጎረቤት ሲሆን በወቅቱ በግድያ ወንጀል ተጠርጥሮ ነበር በቁጥጥር ስር የዋለው። በ1995 የናንቻንግ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ነህ በማለት ሞት የፈረደበት ቢሆንም ነገር ግን ፍርዱ ሁለት ዓመት ከታሰረ በኋላ በእድሜ ይፍታህ ተቀይሮለታል። ዛንግ በምርመራ ወቅት ስቃይ እንደደረሰበት በመግለጽ ነጻ መሆኑን ሲከራከር ነበር። ነገር ግን በወቅቱ ይግባኝ ያለው ጉዳይ ውጤት ሳያስገኝለት ቀርቷል። ከዚያ በኋላ በ2019 መጋቢት ወር ላይ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጉዳዩን ዳግም ለማየት ተስማምቶ ዛንግ በቂ ባልሆነ ማስረጃ እስር ቤት መወርወሩን በመግለጽ ነፃ ነህ ብሎታል። ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ቲያን ጋንሊን እንዳሉት "ያገኘናቸውን ማስረጃዎች ከፈተሽን በኋላ የዛንግን ወንጀል የሚያስረዱ ቀጥተኛ ማስረጃዎች ማግኘት አልቻልንም። ስለዚህ አቃቢያነ ህጎቹ ያቀረቡትን ሃሳብ ተቀብለን ዛንግን ነፃ መሆኑን የሚገልጽ ውሳኔ አሳልፈናል።" በ1993 ሁለቱን ወጣቶች ማን እንደገደላቸው እስካሁን ድረስ አልታወቀም።
54891101
https://www.bbc.com/amharic/54891101
ኮሮናቫይረስ: እውን በጉጉት የተጠበቀው የኮሮናቫይረስ ክትባት ተገኘ?
ዓለም በጉጉት ሲጠብቅ የቆየው የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ አዎንታዊ ውቴት አስመዝግቦ "ወሳኝ ምዕራፍ" ላይ መድረሱ ተዘግቧል።
በፒፊዘር እና ባዮኤንቴክ የተሠራው ክትባት የመጀመሪያ ግኝቶች እንዳሳዩት ክትባቱ ከ90% በላይ የሚሆኑ ሰዎች በኮቪድ -19 እንዳይያዙ ሊያደርግ ይችላል። በፒፊዘር እና ባዮኤንቴክ ምን አሳኩ? ደረጃ 3 ሙከራ በመባል በሚታወቀው የክትባት የመጨረሻው ዙር ሙከራ መረጃን በማጋራት የመጀመሪያዎቹ ሆነዋል። ይህ በክትባት ፍለጋ ውስጥ አንዳንድ የሙከራ ክትባቶች የማይሳኩበት ወሳኝ ደረጃ ላይ ነው፡፡ ክትባቱ ሙሉ በሙሉ የሙከራ አካሄድን ያልፋል። በዚህም የቫይረሱን የጄኔቲክ ኮድ በከፊል ለሰዎች በመስጠት ሰውነት ቫይረሱን የሚከላከልበትን ስርዓት እንዲፈጥር የሚያሰለጥን ዘዴ ነው። ክትባቱ ወደ 43 ሺህ ለሚጠጉ ሰዎች የተሰጠ ሲሆን ምንም የደህንነት ስጋትም አልተነሳበትም፡፡ ክትባቱ ለገበያ የሚቀርበው መቼ ነው? ፒፊዘር በፈረንጆቹ ዓመት መጨረሻ 50 ሚሊዮን ብልቃጦችን እንዲሁም በ2021 መጨረሻ 1.3 ቢሊዮን ያህል ለማቅረብ እችላለሁ ብሎ ያምናል። እንግሊዝ ቀድም 30 ሚሊዮን ብልቃጦችን ያዘዘች ሲሆን እ.ኤ.አ. በ2020 መጨረሻ 10 ሚሊዮን ብልቃጦችን ታገኛለች ተብሎ ይጠበቃል። መጀመሪያ 'ማን ይከተባል?' የሚለው የሚወሰነው ክትባቱ በሚቀርብበት ጊዜ ኮቪድ-19 ካለው የስርጭት ሁኔታ እና ክትባቱ ለነማን በጣም ውጤታማ ይሆናል በሚለው ይወሰናል፡፡ ለምሳሌ እንግሊዝ በጣም ተጋላጭ ከሆኑ የጤና ባለሙያዎች እና በሽታው የበልጥ ይጸናባቸዋል ከሚባሉት ለእነማን ቅድሚያ መስጠት እንዳለበት አልወሰነችም፡፡ ሰፋ ተደርጎ ከታየ ዕድሜያቸው ከ80ዎቹ በላይ የሆኑ፣ ቤት ውስጥ አንክብካቤ ለሚደረግላቸው እና ለጤና ሠራተኞች ቅድሚያ ይሰጣል የሚል ግምት አለ፡፡ ዕድሜ ለኮቪድ ትልቁ ተጋላጭነት እስካሁን ድረስ ነው ፣ ስለሆነም ዕድሜዎ እየጨመረ በሄደ መጠን በፍጥነት ክትባት ሊወስዱ ይችላሉ። እንደ ባለሙያዎች ከሆነ ክትባቱ እስከ 2021 አጋማሽ ድረስ በስፋት ላይገኝ ይችላል፡፡ ሌሎች የሚዘጋጁ ክትባቶችስ አሉ? በሌሎች ድርጅቶች የሚሠሩ እና በሦስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ክትባቶች ሙከራ ተጨማሪ ውጤቶች በሚቀጥሉት ሳምንታት እና ወራቶች ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። በመጨረሻው የሙከራ ደረጃ ላይ የሚገኙ 10 ተጨማሪ ክትባቶች አሉ። ቀዳሚዎቹ ተፎካካሪዎቹ የሚከተሉት ናቸው * የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እና አስትራዜኔካ ክትባት- እንግሊዝ * ሞደርና- አሜሪካ * ካንሳይኖ በቻይና ከሚገኘው የቤጂንግ የባዮቴክኖሎጂ ተቋም ጋር- ቻይና * ጋማሊያ ምርምር ተቋም-ሩሲያ * ጆንሰን * ቤጂንግ የባዮሎጂካል ምርቶች ተቋም እና ሲኖፋርማ- ቻይና * ሲኖቫክ እና ኢንስቲዩቶ ቡታንታን- ብራዚል * የውሃን የባዮሎጂካል ምርቶች ተቋም እና ሲኖፋርማ- ቻይና * ኖቫቫክስ- አሜሪካ አራት ኮሮናቫይረስ ዓይነቶች በሰው ልጆች ውስጥ እንደተዘዋወሩ ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡ ሌሎቹ የተለመዱ የጉንፋን ምልክቶችን የሚያስከትሉ ሲሆን ለየተውኛውም ክትባት አልተገኝም፡፡ የተለያዩ የክትባት ዓይነቶች አሉ? የክትባት ዋናው ዓላማ የቫይረስን የተወሰኑ ክፍሎች ለሰውነት በሽታን የመከላከል ስርዓት በማሳየት እንደ ወራሪ ቆጥሮ እንዴት መዋጋት እንደሚቻል ማስተማር ነው፡፡ ሆኖም ይህንን ለማድረግ የተለያዩ መንገዶች አሉ። ተመራማሪዎችም የተለያዩ አካሄዶችን እየተጠቀሙ ነው፡፡ የፕፊዘር እና የሞደርና ክትባቶች የኮሮናቫይረስ የጄኔቲክ ኮድ ቁርጥራጮችን ወደ ሰውነት በማስገባት የሚሠሩ ናቸው፡፡ አንዴ ወደ ሰውነት ከገባ በኋላ ሰውነትን በማሰልጠን የቫይራል ፕሮቲኖችን ማዘጋጀት ይጀምራል። ዘዴው ሙሉ በሙሉ አዲስ ነው። የኦክስፎርድ እና የሩሲያው ክትባቶች ደግሞ ቺምፓንዚዎችን የሚይዝ እና ጉዳት የሌለው ቫይረስ በመውሰድ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በማመሳሰል ምላሽ ለማግኘት ተስፋ እያደረጉ ነው፡፡ ሁለቱ በቻይና የሚሞከሩት ታላላቅ ክትባቶች ዋናውን ቫይረስ ቢጠቀሙም ቫይረሱ በሽታ እንዳያስከተል በማድረግ ይጠቀሙበታል፡፡ የትኛው ዘዴ የተሻለ ውጤት እንደሚያስገኝ መረዳቱ ጠቃሚ ነው። ሰዎች ሆን ብለው በበሽታው የሚያስይዙ ሙከራዎች ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ አሁንም ምን መደረግ አለበት? * በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ክትባቶችን በከፍተኛ ደረጃ ለማምረት የሚያስችል መንገድ መዘጋጀት አለበት * ተቆጣጣሪዎች ክትባቱን ከመሰጠቱ በፊት ይሁንታ መስጠት አለባቸው * በመጨረሻም አብዛኛዉን የዓለም ህዝብ ክትባቱን መከተብ ትልቅ የሎጅስቲክ ፈተና ይሆናል ምን ያህል ሰዎች መከተብ አለባቸው? የክትባቱ ውጤታማነት ሳይታውቅ ምን ያህል ሰዎች መከተብ እንዳለባቸው ማወቅ ከባድ ነው። ቫይረሱ በቀላሉ እንዳይሰራጭ ለማቆም ከ60-70% የሚሆነው የዓለም ህዝብ ቫይረሱን የመከላከል አቅም ሊኖረው ይገባል ተብሎ ይታሰባል (ኸርድ ኢሙኒቲ በመባል ይታወቃል)፡፡ በሌላ አባባል ክትባቱ ከሠራ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች መከተብ አለባቸው። ክትባት ለምን ያስፈልገናል? ሕይወትዎ ወደ መደበኛ ሁኔታ እንዲመለስ ከፈለጉ ክትባት ያስፈልገናል፡፡ አሁንም ድረስ እጅግ በጣም ብዙ ሰዎች ለኮሮቫይረስ ተጋላጭ ናቸው፡፡ እየተጣሉ ያሉ ገደቦች ናቸው ብዙዎች እንዳይሞቱ እያገዘ የሚገኘው፡፡ ክትባቶች ሰውነታችን በሽታውን እንዲቋቋም ያስተምሩታል፡፡ በመጀመሪያ በኮሮናቫይረስ መያዝን ሊያስቆም ወይም ኮቪድ-19ን ገዳይነት ዝቅ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ክትባቱ ከተሻሻሉ ህክምናዎች ጋር ጎን ለጎን ሲሰጥ ከችግሩ ‹የመውጫ› ጥሩ ስትራቴጂ ይሆናል፡፡
50669803
https://www.bbc.com/amharic/50669803
ደራሲ፣ መምህርና ጋዜጠኛ ካሕሳይ ገብረእግዚአብሔር "ደፋር ጸሐፊ ነበር"
የደራሲ፣ መምህርና ጋዜጠኛ ካሕሳይ ገብረእግዚአብሔር ሥርዓተ ቀብር ዛሬ ተፈፅሟል።
ሕዳር 24 ቀን 2012 ዓ. ም. ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ጸሐፊው፤ ሥርዓተ ቀብራቸው ዛሬ ህዳር 25 ቀን 2012 ዓ. ም. መቀለ በሚገኘው በአዲሽምድህን ማሪያም ቤተክርሲቲያን ይፈጸማል። መምህር ካሕሳይ በኢትዮጵያ ሬዲዮ እሁድ ፕሮግራም ወጎችን በማቅረብ ይታወቃሉ። በሦስት ቅጽ ከተጻፈው "ኀብረ ብዕር" የተሰኘው መጽሐፍ በተጨማሪ "ብፁአን እነማን ናቸው?"፣ "ምንኩስና በኢትዮጵያ"፣ "ባህል እና ክርስትያናዊ ትውፊት በኢትዮጵያ" እና "ምስጢረ ፊደል ወትርጓሜሁ፤ የፊደል ምስጢር ከነትርጉሙ" የተሰኙ መጻሕፍትም ጽፈዋል። "ኀብረ ብዕር" የወጎች፣ የግጥሞች፣ የሽለላ እና የቦታ ሥያሜዎች ስብስብ ነው። በኢትዮጵያ ሬዲዮ የእሁድ ፕሮግራም፣ ወጎች በማቅረብ የሚታወቁት ደራሲ፣ ጋዜጠኛ እንዲሁም የወግ ጸሐፊ ካሕሳይ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በሚታተመው "ዜና ቤተክርስትያን" ጋዜጣ ምክትል ዋና አዘጋጅም ነበሩ። • በኦሮምኛና በትግርኛ አፋቸውን የፈቱ የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ባለውለታዎች • ለኢትዮጵያዊያን የንባብ ወዳጆች ምርጡ መጽሐፍ የትኛው ነው? ደራሲና ጋዜጠኛ ካሕሳይ፤ በመምህርነት እንዲሁም በርዕሰ መምህርነት ሠርተዋል። በ "ሠርቶ አደር" ጋዜጣ የሐረር ሪፖርተር የነበሩ ሲሆን፤ ከደርግ መውደቅ በኋላ በሐረርጌ ክፍለ አገር በትምህርት መገናኛ ድርጅት በፕሮግራም አዘጋጅነት፣ በአፍሪካ ቀንድ መጽሔት የምሥራቅ ኢትዮጵያ ዘጋቢም ነበሩ። "ዜና ቤተክርስትያን" በተባለው ጋዜጣ በምክትል አዘጋጅነት የሠሩትም እስከ ሕይወታቸው ፍጻሜ ድረስ ነበር። ካሕሳይ ገ/እግዚአብሔር፤ ባደረባቸው ሕመም በጦር ኃይሎች፣ በቤተ ዛታ፣ እንዲሁም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታሎች ህክምናቸውን ቢከታተሉም፤ ስላልተሻላቸው ከነሐሴ መግቢያ ጀምሮ ቤታቸው ከአልጋ ላይ መዋላቸውን የሚቀርቧቸው ሰዎች ገልጸዋል። ደራሲ፣ መምህርና ጋዜጠኛ ካሕሳይ፤ የሦስት ልጆች አባት ነበሩ። • ከብራና ወደ ኮምፒውተር . . . • ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ፡ ያናገሩና ያነጋገሩ ድርሰቶቹ "ካሕሳይ ደፋር ጸሐፊ ነው" ደራሲ ጌታቸው በለጠ ከካሕሳይ ጋር ዘለግ ላለ ጊዜ ይተዋወቃሉ። ከድርሰት ሥራ ባሻገር "አዲስ ዘመን" እና "የዛሬይቱ ኢትዮጵያ" ጋዜጦች ላይ በብዕር ስም በሚጻጻፉበት ዘመን ይተዋወቁ እንደነበር ጌታቸው ያስታውሳል። "ትልቁ የካሕሳይ ጥንካሬ ሁለገብ መሆኑ ነው። በጋዜጠኛነቱም፣ በኢትዮጵያ ባህላዊ ጉዳዮች ላይ፤ በተለይ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል ባህል ላይ፤ ከሀይማኖት ጋር በተያያዙ ርዕሰ ጉዳዮችም ደፍረው ከሚጽፉ ጸሐፊዎች መካከል ነው" ሲል ይገልጻቸዋል። ጌታቸው እንደሚለው፤ ደራሲ፣ መምህርና ጋዜጠኛ ካሕሳይ የሚያምኑበትን ነገር ደፍረው ከመናገር፣ የማይስማሙበትን ከመሞገት ወደኋላ አይሉም። እንደምሳሌ የሚጠቅሱት፤ በኢትዮጵያ የምንኩስና ታሪክ ውስጥ ያነሷቸውን ጠንካራ ሀሳቦች ነው። ደራሲያን ማኅበረሰባዊ ጫና፣ ኃይማኖታዊ ጫና እና ፖለቲካዊ ጫናም እንዳለባቸው ጠቅሶ፤ ካሕሳይ ይህንን ማለፋቸው "ከሁኔታዎች በላይ ለህሊናው እና ለሙያው ታማኝ እንደሆነ ያሳያል" ሲል ያስረዳል። • የ2010 የጥበብ ክራሞት • ተፈጥሮን በብሩሽ የሚመዘግበው መዝገቡ "የትኛውንም ጉዳይ ከብሔርም ሆነ ከሀይማኖት ጋር ሳይፈርጁ እውነት ብቻ ይዘው ይሄዳሉ" ሙዓዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት፤ ካሕሳይ ገብረእግዚአብሔርን፤ በብዕር ስም ለኢትዮጵያ ሬዲዮ እሁድ ጠዋት ፕሮግራም ጅግጅጋ ሆነው ሲያቀርቡ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ እንደሚያስታውሳቸው ገልጾ፤ በኋላም ወደ ቤተ ክህነት መጥተው በቅርበት አብረው መሥራታቸውን ይናገራል። ቤተ ክህነት ውስጥ የ "ዜና ቤተክርስትያን" ጋዜጣ ምክትል አዘጋጅ ሆነው እንዳገለገሉም ያስታውሳል። ዲ/ን ዳንኤል፤ ካሕሳይ መጽሐፋቸውን በሚጽፉበት ወቅት ይመካከሩ እንደነበር አስታውሶ፤ "አሁን ባለንበት ዘመን፤ የኢትዮጵያን ትውፊቶች፣ በገበሬው ዘንድ ያሉትን በተለይ በአማራና በትግራይ አካባቢ የሚነገሩትን ጥንታዊ ትውፊቶችና በትውፊቶች ውስጥ ያሉትን እውቀቶች፤ የመምህር ካሕሳይን ያህል የሚያውቃቸው አለ ብሎ ማለት ያስቸግረኛል" ሲል ይናገራል። በፎክሎርና ባህል ጥናት ላይ የተሰማሩ ምሁራን፤ የጥናት ዘዴውን ያውቁት ይሆናል የሚለው ዲያቆን ዳንኤል፤ ይዘቱን በእርሳቸው መጠንና ዝርዝር የሚያውቅ አለ ብሎ ለማለት እንደሚከብደው ጨምሮ ያስረዳል። ካሕሳይ ላመኑበት ነገር ወደኋላ የማይሉ ናቸው የሚለው ዲ/ን ዳንኤል፤ የትኛውንም ጉዳይ ከብሔርም ሆነ ከሀይማኖት ጋርም ሳይፈርጁ እውነት ብቻ ይዘው እንደሚሄዱም ይናገራል። መምህር ካሕሳይ በአንድ ወቅት ከመነኮሳት ጋር በተያያዘ የጻፉት መጽሐፍ፤ ከአዲስ አበባ አገረ ስብከት ሰዎች ጋር እንዳጋጫቸው በማስታወስም፤ "መጽሐፋቸውን ለማስመረቅ አዳራሽ ሲከለከሉ ከአዳራሽ ውጪ መንገድ ላይ አስመርቀዋል" ይላል። "ላመኑበት ነገር ቆራጥና የሀሳብ ሰው ናቸው" የሚለው ዲ/ን ዳንኤል፤ ሦስቱም የ "ኅብረ ብዕር" ቅጾች በያዟቸው እውቀቶች ብልጫ፤ ከሥራዎቻቸው ሁሉ ገዝፈው እንደሚታዩት ይናገራል። ቃላዊና ትውፊታዊ መረጃዎችን በጽሑፍ በማስቀረታቸውና ያንን ትልልቅ እውቀት ለትውልድ በማሸጋገራቸው ሲታወሱ ቢኖሩ ደስ እንደሚለው ጨምሮ ገልጿል። "በዕጽዋት ላይ ይመራመር ነበር" ካሕሳይን ለዓመታት ከሚያውቋቸው መካከል አንዱ የሆኑት ጋዜጠኛ ንጉሤ አክሊሉ፤ ካሕሳይን የሚገልጿቸው "እውነተኛ፤ ሀቀኛ፣ ለጋዜጠኝነት፣ ለመምህርነት፣ ለደራሲነት የሚገባ ሰው ነው" በማለት ነው። ካሕሳይ ከሚያምኑበት ጉዳይ ውጪ የማይጽፉ፣ የማይናገሩ ሰው እንደነበሩም ያስታውሳሉ። "ቤተ ክህነት ውስጥ ሆኖ የሚያያቸውን ስህተቶች ሁሉ በመጽሐፍ ለንባብ ያበቃ ጎበዝ፣ ደፋር ጋዜጠኛ ነው" ሲሉም ንጉሤ ይገልጻሉ። ከ40 ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ሬድዮ፣ በእሑድ መርሀ ግብር ካሕሳይ በጽሑፍ፣ ንጉሤ ደግሞ በድምጽ ይሳተፉ ነበር። "ካሕሳይ ሳይንቲስትም ነው" የሚሉት ንጉሤ፤ በሥነ ሕይወት (ባዮሎጂ) ዲፕሎማ ያላቸው ካሕሳይ፤ በእጽዋት ላይ ምርምር ያደርጉ እንደነበርም ያክላሉ። ለሥነ ጽሑፍ ሥራ ሲዘዋወሩ በእጽዋት ላይ ጥናት ያደርጉ እንደነበር ይገልጻሉ። "እስካሁን እድሜው የረዘመው በእነዚህ እጽዋት አማካይነት የባህል መድኃኒቶችን እያዘጋጀ ስለሚጠቀም ነው" ሲሉም ይናገራሉ። ከየትኛውም የአገሪቱ ክፍል ተወላጆች ጋር፤ ብሔርና ቋንቋን መሰረት ሳያደርጉ፤ በስምምነት መሥራት እንደሚችሉም ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። "ሞቱ ለአገር ጉዳት ነው" ሲሉም ንጉሤ ተናግረዋል።
news-56439791
https://www.bbc.com/amharic/news-56439791
ሳሚያ ሱሉሁ ሐሳን ቃለ መሃላ ፈጽመው የታንዛኒያ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሆኑ
ሳሚያ ሱሉሁ ሐሳን ቃለ መሃላ ፈጽመው ሥልጣን በመረከብ የመጀመሪያዋ የታንዛኒያ ሴት ፕሬዝዳንት ለመሆን በቁ።
ሳሚያ ሱሉሁ ሐሰን ሳሚያ የፕሬዝዳንትነት መንበሩን የተረከቡት ዳሬ ሰላም በሚገኘው ቤተ መንግሥት ውስጥ በአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኃላፊ ኢብራሂም ጁማ አማካይነት በፈጸሙት ቃለ መሃላ ነው። ፕሬዝዳንት ሳሚያ ወደዚህ ሥልጣን የመጡት ቀዳሚው ፕሬዝዳንት ጆን ፖምቤ ማጉፉሊ በልብ ችግር ምክንያት ህይወታቸው ማለፉን ተከትሎ ነው። የአገሪቱ ስድስተኛ ፕሬዝዳንት ለመሆን የበቁት ፕሬዝዳንት ሳሚያ 61 ዓመታቸው ሲሆን ላለፉት አምሰት ዓመታት በምክትል ፕሬዝዳንትነት አገልግለዋል። በታንዛኒያ ሕገ መንግሥት መሠረት አዲሷ ፕሬዝዳንት ለቀጣኦቾ አምስት ዓመታት በመሪነት አገሪቱን ያስተዳድራሉ። ፕሬዝዳንት ሳሊሃ ረቡዕ ሌሊት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው የተነገረውን የታንዛንያ የፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊን ቦታ እንደሚተኩ ሲተበቅ ነበር። ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ ሁለተኛውን የአምስት ዓመት የስልጣን ዘመናቸውን በዚህ ዓመት የጀመሩ ሲሆን በድንገት በማለፋቸው ምክትል ፕሬዝዳንቷ ቀሪውን ጊዜ በመሪነት ያገለግላሉ ተብሏል። ይህም ለምሥራቅ አፍሪካዋ አገር ስድስተኛና የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲያደርጋቸው፤ ከፊል ራስ ገዝ አስተዳደር ከሆነችው የዛንዚባር ደሴቶች የመጡ ሁለተኛ ፕሬዝዳንት ይሆናሉ። ሳሚያ የታንዛኒያን ፕሬዝዳንትንት መንበር ለመረከብ የሚያስችላቸውን ቃለ መሀላ ከፈጸሙ በኋላ እርሳቸው ይዘውት የነበረውን የምክትል ፕሬዝዳንትንት ቦታ የሚይዝ ዕጩ ለመሰየም ከፓርቲያቸው አመራሮች ጋር ይመክራሉ ተብሏል። በታንዛኒያ ሕገ መንግሥት መሠረት ሳሚያ የዛንዚባር ደሴት ተወካይ በመሆናቸው ምክትላቸው ከቀሪው የአገሪቱ ክፍል የሚወከሉ ይሆናሉ። ለምክትልነት የሚሰየሙት ዕጩ ከአገሪቱ ፓርላማ አባላት የ50 በመቶውን ይሁንታ ማግኘት ይኖርባቸዋል። በአገሪቱ ሕግ መሠረት ሳሚያ ሱሉሁ ሐሰን ሦስትና ከዚያ በላይ ለሆኑ ዓመታት በፕሬዝዳንትንት ከቆዩ በቀጣይ ዙር በሚኖር ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አንድ ጊዜ ብቻ እንዲወዳደሩ ይፈቀድላቸዋል። ሳሚያ ሱሉሁ ሐሰን በፖለቲካው መድረክ ላይ ትኩረትን ያገኙት በ2014 (እአአ) አዲሱ የአገሪቱ ሕገ መንግሥት ረቂቅ ሲዘጋጅ የጉባኤው ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ሲሾሙ ነበር። ከአንድ ዓመት በኋላ ደግሞ የገዢው የሲ ሲ ኤም ፓርቲ ፕሬዝዳንታዊ ዕጩ ተወዳዳሪ የነበሩት የጆን ማጉፉሊ ምክትል በመሆን በዕጩነት ቀረቡ። በምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻቸው ወቅት አብረዋቸው ሲጓዙ የነበሩትን የሙዚቀኛ ቡድን አባላትን 'ማማ' ወይም 'እናታችን' ብለው እንዲጠሯቸው መጠየቃቸውን ተዘግቧል። አብረዋቸው የሠሩ ፖለቲከኞች እንደሚናገሩት ግለሰቧ የታንዛኒያ ዜጎች የማየት ዕድል ያላገኙት የመሪነት አቅም እንዳላቸው ይመሰክራሉ። "የተለመደ ፖለቲከኛ ዓይነት ትመስላለች፤ ነገር ግን እምቅ አቅሟ በጣም ትልቅ መሆኑን ከእርሷ ጋር በቅርበት በሰራሁበት ጊዜ ለመመልከት ችያለሁ" ሲሉ የሕግ ባለሙያው ጃንዋሪ ማክባም ለቢቢሲ ስዋሂሊ። ሌሎች ደግሞ ደፋር እና የማይወላውሉ ፖለቲከኛ እንደሆኑ ይናገሩላቸዋል። ከሦስት ዓመት በፊት በዋና ከተማዋ ዶዶማ ከተፈፀመባቸው የግድያ ሙከራ የተረፉትን የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ቱንዱ ሊሱን ሆስፒታል ድረስ በመሄድ ጠይቀዋቸዋል። ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን ባለትዳር ሲሆኑ ከባለቤታቸው ሃፊድ አሚር አራት ልጆች አሏቸው። ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከ1993-1994* - ሲልቪ ኪኒጊ፤ ሚልቺር ንዳዳዬ ከተገደሉ በኋላ የብሩንዲ ባላደራ ፕሬዝዳንት ሆኑ ከ2006-2018 - ኤለን ሰርሊፍ ጆንሰን፤ የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ከ2009 - ሮዝ ፍራንሲን ሮጎምቤ፤ የፕሬዝዳንት ኦማር ቦንጎ ሞትን ተከትሎ የጋቦን ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ሆኑ ከ2012 - ሞኒክ ኦህሳን ቤልፑ፤ ፕሬዝዳንት አንሩድ ጀግነት ሥልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ የሞሪሼስ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆኑ ከ2012-2014 - ጆይስ ባንዳ፤ ከፕሬዝዳንት ቢንጉዋ ሙታሪካ ሞት በኋላ የማላዊ ፕሬዝዳንት ሆኑ ከ2014-2016 - ካትሪን ሳምባ ፓንዛ፤ በአገሪቱ ፓርላማ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የሽግግር ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ ከ2015-2018 - አሚናህ ጉሪብ ፋኪም፤ የሞሪሺስ ፓርላማ ፕሬዝዳንት አድርጎ መረጣቸው ከ2018- አስካሁን ሳህለወርቅ ዘውዴ፤ በኢትዮጵያ ፓርላማ ለፕሬዝዳንትነት የተሾሙ * ሁሉም የአውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ነው ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊን ታንዛኒያውያን በምን ያስታውሷቸዋል?
news-48242853
https://www.bbc.com/amharic/news-48242853
የአርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም ሐውልት ተመረቀ
ኦቴሎ፣ ቴዎድሮስ፣ መቃብር ቆፋሪው፣ ባለካባና ባለዳባ፣ ንጉሥ አርማህ፣ የሠርጉ ዋዜማና በሌሎቹም ትያትሮቹ ይታወቃል። ገመና፣ ባለ ጉዳይ እና ሌሎችም የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማዎቹ በርካቶች ያስታውሱታል - አንጋፋው አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም።
አርቲስቱ ባደረበት የኩላሊት ሕመም በተወለደ በ62 ዓመቱ ሕይወቱ ያለፈው ባለፈው ሐምሌ ወር ነበር። ሐውልቱም ዛሬ ግንቦት 4/ 2011 ዓ.ም በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በሚገኘው መካነ መቃብሩ ላይ ሐውልት ቆሞለታል። • ቀራፂው ስለ አፄ ኃይለ ሥላሴ ሐውልት ይናገራል አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም የኩላሊት ሕመም አጋጥሞት ሳለ የሕክምና ገንዘብ ሲያሰባስብ የነበረው ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ አርቲስት ቴዎድሮስ ተስፋዬ ለቢቢሲ እንደገለፀው ዛሬ ከጠዋቱ 1፡00 ላይ ታላላቅ የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣ አድናቂዎቹና ቤተሰቦቹ በተገኙበት ሐውልቱ ተመርቋል። ሐውልቱ ከ'ፋይበር ግላስ' የተሠራ ሲሆን በሠዓሊና ቀራፂ ተፈሪ መኮንን ተቀርጿል። አርቲስት ቴዎድሮስ ምን ያህል ወጪ እንደወጣ ለጊዜው መግለፅ እንደሚከብደው ቢናገርም "አርቲስት ፍቃዱ ከማረፉ በፊት ለኩላሊት ታማሚዋ ከሰጠው ገንዘብ ጋር ተደምሮ በዚህኛው ኮሚቴ የሂሳብ ቁጥር ከሚገኝ ገንዘብ ወደ 700 ሺህ ብር ገደማ ወጥቶበታል" ብሎናል። • መነኩሴው ለምን በቁጥጥር ሥር ዋሉ? በሐውልቱ ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ፣ የተወለደበትና ያረፈበት ዓ.ም የተፃፈ ሲሆን መጨረሻ ላይ ግን " ይህንን ሐውልት የኢትዮጵያ ሕዝብ አሠሩላቸው" የሚል ሰፍሮበታል። ይህም ከኢትዮጵያ ሕዝብ በተሰባሰበው ገንዘብ መሠራቱን ለመግለፅ ታስቦ እንደተፃፈ ነግሮናል። በመጨረሻም አርቲስት ቴዎድሮስ፤ የተውኔት አባት ተዋናይ ወጋየሁ ንጋቱ ሐውልት መፍረሱንና ሐውልቱ የት እንዳለ እንደማይታወቅ ገልፆ፤ የተዋናይ ፍቃዱ ተክለማሪያም ሐውልትም ለበርካታ ዓመታት ባገለገለበት ትያትር ቤት ቢቆም ጥሩ ነበር ሲል ሃሳቡን ይገልፃል። "መካነ መቃብሩ ላይ ማስታወሻ ቆሞ፤ ሐውልቱ የሠራበት ትያትር ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ቢቆም ምንኛ ደስ ባለኝ፤ ብዙ ሺህ ሰው ያየው ነበር" ሲልም አክሏል። ይሁን እንጂ አሁንም የመድረኩ ንጉስ አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም በዚህ መልኩ መታሰቡ ደስታ የሚሰጥና የሚገባውም ነው ብሏል። ገንዘብ ለማሰባሰብ ተዋቅሮ የነበረው ኮሚቴ አባላት ውዝግብ ውስጥ እንደገቡ የሚታወስ ሲሆን አርቲስት ቴዎድሮስ ተስፋዬ እንደነገረን 'ዋናው ኮሚቴ (መጀመሪያ የተዋቀረው ኮሚቴ)' ከዛሬ ጀምሮ ኮሚቴው መፍረሱን በማሳወቅ የምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ተጠናቋል።
news-41606611
https://www.bbc.com/amharic/news-41606611
ትራምፕ፡ የኢራን የኑክሊዬር ስምምነትን አቋርጣለሁ
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የነበረውን የኑክሊዬር ስምምነት በማቋረጥ ፊት ለፊት መጋፈጥ የሚያስችል ዕቅድ እንደሚነድፉ ይጠበቃል።
አሜሪካ ስምምነቱን ከመሰረዟ በፊት ለኮንግረሱ 60 ቀናትን በመስጠት እንደገና ማዕቀብ ይጣል አይጣል የሚለውን የሚወስኑበት ይሆናል። በዚህም ጉዳይ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን ከአውሮፓና ከቻይና አቻዎቻቸው ጋር እየመከሩ እንደሆነ ባለልስልጣናት ይናገራሉ። የኑክሊዬር ስምምነቱ እንዳይሻር በአሜሪካ ውስጥና በውጭ አገራትም ትራምፕ ላይ ተፅዕኖ ለማድረግ እየተሞከረ ነው። ከሁለት ዓመታት በፊት በነበረው ስምምነት መሰረት ኢራን የኑክሊዬር ፕሮግራሟን ለማቆምና በተወሰነ መንገድ የተጣለባት ማዕቀብ የሚነሳበት ስምምነት ላይ ደርሰው እንደነበር የሚታወስ ነው። ትራምፕ በተደጋጋሚ ስምምነቱ ላይ ከፍተኛ ትችት ከማቅረብ በተጨማሪ በምርጫ ዘመቻቸውም ወቅት ይህንን ስምምነት እንደሚያስወግዱትም ቃል ገብተው ነበር። ኮንግረሱ በየሦስት ወራት ኢራን የስምምነት ቃሏን መጠበቋን የሚያረጋግጥ ሲሆን ትራምፕም ሁለት ጊዜ ማረጋገጫ ሰጥተዋል። ትራምፕ ስምምነቱን ላይከተሉ ይችላሉ የሚሉት ጥርጣሬዎች በአሜሪካ ደጋፊ አገራትና በአንዳንድ አስተዳደሩ አባላት መደናገጥን ፈጥሯል። መከላከያ ሚኒስትሩ ጀምስ ማቲስ በዚህ ወር መጀመሪያ ለሴኔቱ ስምምነቱን ወደጎን መተው ከአገራዊ ፍላጎት ጋር አይጣጣምም ብለዋል። ትራምፕ የኢራንን የኑክሊዬር ስምምነትን "መጥፎ ስምምነት" በማለት ለመሰረዝ ዝተዋል። በአሜሪካ ህግ መሰረት ይሄንን ስምምነት ለማስተካከል ኢራን የተወሰነውን የስምምነቱን አካል እንዳላከበረችና የነበረው ማዕቀብም እንዲቀጥል መረጃ መቅረብ ይኖርበታል። እንደገና ማዕቀብ የመጣሉን ሁኔታ በህግ አውጭዎቹም የሚወሰን ይሆናል። የስምምነቱ ተችዎችም ቢሆኑ ኢራን ስምምነቱን ባላፈረሰችበት ሁኔታ አሜሪካ ስምምነቱን ብትጥስ ተአማኒነቷን ጥያቄ ውስጥ እንደሚከተው የይናገራሉ። የሪፐብሊካን ፓርቲ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ሊቀ መንበር ኤድ ሮይስ ስምምነቱ ችግር ያለበት ቢሆንም ልንተገብረው ይገባል ብለዋል። የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይና የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮንም ትራምፕ በስምምነቱ እንዲቀጥሉም መክረዋል። ትራምፕ በተደጋጋሚ ኢራን የስምምነቱን "መንፈስ" ሰብራዋለች ቢሉም፤ የዓለም አቀፍ አውቶሚክ ኤጀንሲ በዚህ አይስማማም በተቃራኒው ኢራን ስምምነቷን እንዳከበረች እያለ ነው። ከሁለት ዓመት በፊት የተደረገው ስምምነት ኢራን የኑክሊዬር መሳሪያዎችን ምርት እንድታቆም የሚል ሲሆን፤ በምላሹም ዓለም አቀፍ የዘይት ሽያጭ እንዳታደርግ ይከለክላት የነበረው ማዕቀብ ተነስቶላታል። ሙሉ በሙሉ የማዕቀቡ መነሳት በኢራን ላይ የሚወሰን ሲሆን፤ የዩራንየም ክምችቷን መቀነስ እንዲሁም መርማሪዎች አገሪቷ ውስጥ እንዲገቡ መተባበርን ይመለከታል።
news-45327588
https://www.bbc.com/amharic/news-45327588
ቶዮታ ያለአሽከርካሪ የሚንቀሳቀሱ መኪናዎችን ሊያሰማራ ነው
ታዋቂው የጃፓን የመኪና አምራች ኩባንያ ቶዮታ ''ኡበር'' የተባለው የከተማ ውስጥ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተቋም ጋር አብሮ ለመስራት 500 ሚሊዮን ዶላር ሊመድብ ነው።
በየመንገዱ የሚሰማሩት መኪናዎች ያለአሽከርካሪ የሚንቀሳቀሱ ሲሆን፤ ተጠቃሚዎች ስልኮቻቸው ላይ በሚጭኗቸው የኡበር መተግበሪያ በኩል ጥሪ ሲያቀርቡ ተሽከርካሪዎቹ ያሉበት ድረስ መጥተው አገልግሎቱን ይሰጧቸዋል። ያለአሽከርካሪ የሚንቀሳቀሱትን መኪናዎች በብዛት አምርቶ በቅርብ ዓመታት ወደ አገልግሎት ለማስገባት እንዳሰበ ቶዮታ ገልጿል። • ለፌስቡክ ሱሰኞች የተገነባው አስፋልት ተመረቀ • የውጪ ሀገር ጥሪዎች ለምን በኢትዮጵያ ቁጥር ይወጣሉ? ተሽከርካሪዎቹ ተጠቃሚዎቹ ያሉበት ቦታ ድረስ መጥተው በማንሳት ወደሚፈልጉት ቦታ ማድረስ እንዲችሉ የሚያደርጋችው የፈጠራ ውጤት በቶዮታ ባለሙያዎች ተሰርቶ እንደተዘጋጀ ተገልጿል። የሙከራ ጊዜው በታሰበለት ጊዜ የሚጠናቀቅ ከሆነም ተሽከርካሪዎቹ በ2021 አገልግሎት ላይ እንደሚውሉ ቶዮታ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል። የቶዮታ መኪና አምራች ኩባንያ ምክትል ስራ አስኪያጅ ሺጄኪ ቶሞያማ እንዳሉት በድርጅታቸውና ''በኡበር'' መካከል የተደረሰው ስምምነት ለደንበኞቻቸው ደህንነቱ የተጠበቀና ገደብ የሌለበት እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ለማገዝ ነው። • ጉግል ኢንተርኔትን በላስቲክ ከረጢት ይዞ ኬንያ ገብቷል ከዚህ በፊት ግን አሜሪካ ውስጥ ''በኡበር'' አማይነት ያለአሽከርካሪ የሚሰራ መኪና ለሙከራ ተሰማርቶ ባደረሰው አደጋ የአንድ ግለሰብ ህይወት መጥፋቱ የሚታወስ ነው። ከቶዮታ ጋር የተደረሰው ስምምነት እንደዚህ አይነት አደጋዎችን ለማስቀረት እንደሆነ ተገልጿል።
news-54933830
https://www.bbc.com/amharic/news-54933830
ትግራይ፡ በማይካድራ የተፈጸመው ግድያ 'የጦር ወንጀል' ሊሆን እንደሚችል ተመድ ጠቆመ
በትግራይ ክልል ማይካድራ ከተማ በርካታ ዜጎች ተገድለዋል የሚል ሪፖርት መውጣቱን ተከትሎ "ግድያዎቹ መረጋገጥ ከቻሉ እንደ ጦር ወንጀል ይቆጠራል" በማለት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስጠንቅቋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኃላፊ ሚሼል ባችሌት በማይካድራ ከተማ ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ በስለት ተገድለዋል የሚለው ሪፖርትም እንዲጣራ ጠይቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጭፍጨፋውን የፈፀሙት የህወሓት ታጣቂዎች ናቸው ቢሉም የትግራይ ክልል ባለስልጣናት በበኩላቸው በግድያዎቹ እጃችን የለበትም በማለት ውድቅ አድርገውታል። የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደብረ ፅዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ውንጀላዎቹ "መሰረት" የሌላቸው ናቸው ማለታቸውንም አጃንሰ ፍራንስ ፕሬስ እሳቸውን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በበኩላቸው የፌደራል መንግሥት የምዕራብ ትግራይን "ነፃ ካወጣ" በኋላ የህወሓት ታጣቂዎች በማይካድራ ከተማ በርካታ ንፁሃን ዜጎችን "በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለዋል" ብለዋል። የማይካድራ ከተማ በትግራይ ክልል ደቡብ ምዕራብ ዞን ትገኛለች። የግድያውን ሪፖርት ያወጣው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ግድያውን ማን እንደፈጸመው ለማረጋገጥ አለመቻሉን አመልክቷል። ነገር ግን ያነጋገራቸው የአይን እማኞች ከፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ጋር የሚዋጉትን የህወሓት ታማኝ ኃይሎች ጥቃቱን እንደፈጸሙ ይከሳሉ። ግድያዎቹ መረጋገጥ ከቻሉም በፌደራል መንግሥትና በትግራይ ክልል መካከል በተነሳው ጦርነት የተገደሉ በርካታ ንፁሃን ዜጎች ያደርጋቸዋል። ከሳምንት በላይ ባስቆጠረው ግጭት በትግራይ ክልል የስልክም ሆነ የኢንተርኔት አገልግሎት ባለመኖሩ ስለ ግጭቱ መረጃ ለማግኘት አዳጋች አድርጎታል። ሚሼል ባችሌት እንዳሉት በኢትዮጵያ እየተከሰተ ያለው ሁኔታ ስጋት እንደፈጠረባቸው ጠቅሰው "ከዚህ በበለጠ ግፎች ከመፈፀማቸው በፊት ለመከላከል ያስችል ዘንድ የውጊያው መቆም ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ ነው ብለዋል። ጥቃት የደረሰባቸው እነማን ናቸው? እንደ አምነስቲ ሪፖርት ከሆነ ግድያዎቹ የተፈፀሙት ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም ምሽት ነው። በማይካድራ ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በስለት ተወግተው ወይም ተቀጥቅጠው እንደተገደሉ አምነስቲ አረጋግጫለሁ ብሏል። በከተማዋ "በየቦታው ወድቀው የሚታዩና በአልጋ ላይ የሚታዩ አስከሬኖችን አሰቃቂ ፎቶግራፎችና ቪዲዮዎችን የተረጋገጡ" ናቸው ብሏል። ጥቃት የደረሰባቸው ግለሰቦች የቀን ሰራተኞች እንደሚመስሉ የተጠቀሰ ሲሆን በግጭቱም ምንም አይነት ተሳትፎ የላቸውም ብሏል። ከየት እንደመጡም ማረጋገጥ እንዳልተቻለም ድርጅቱ አክሎ ገልጿል። የአይን እማኞችን ዋቢ አድርጌያለሁ ያለው አምነስቲ "ጥቃት የደረሰባቸው ግለሰቦች በስለታማ ነገሮች ለምሳሌም ያህል በቢላና በቆንጨራ ነው" ብለዋል። አንዳንድ የአይን እማኞች ከፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ጋር የሚዋጉትን የህወሓት ታማኝ ኃይሎች ሉግዲ በምትባል ቦታ መሸነፋቸውን ተከትሎ ጥቃቱን እንደፈጸሙ ይከሳሉ። የትግራይ ክልል ይህንን "መሰረት" የለውም በሚል አልተቀበለውም። ከዚህም በተጨማሪ በመቀለና በአዲግራት በደረሰ የአየር ጥቃት ንፁሃን ዜጎች መገደላቸውን ደብረፅዮን (ዶ/ር) ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግረዋል። "በርካቶች በየአቅጣጫው በመሮጥ ሸሽተዋል። የዚህ ግጭት ዋነኛ መዘዝ መፈናቀል ነው። እውነት ነው የሞቱም ሆነ የተጎዱ ሰዎች አሉ። ነገር ግን እስካሁን ቁጥሩን አናውቅም። ይህን ለመቆጣጠር በጣም ትልቅ ነው" ማለታቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ አስነብቧል። ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሻከረ የመጣው የፌደራልና የትግራይ ክልል መንግሥት ግንኙነት የማይታረቅ ደረጃ ደርሶ ከሳምንት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የትግራይ ልዩ ኃይል በክልሉ የሚገኘውን የመከላከያ ሰሜን ዕዝ ካምፕ ላይ ጥቃት ማድረሱን ገልፀው ጦርነት መከፈቱን አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው የመከላከያ ሠራዊት በኮማንድ ፖስት እየተመራ "አገሩን የማዳን ተልዕኮውን እንዲወጣ ትዕዛዝ ተሰጥቶታል" ብለዋል። የትግራይ ክልል በበኩሉ በክልሉ የሚገኙት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰሜን ዕዝ ሰራዊት አባላትና አዛዦች ከትግራይ ክልል መንግሥት ጎን ለመሰለፍ ወስነዋል ማለቱ ይታወሳል። ከዚህም በተጨማሪ የፌደራል መንግሥት የአየር ጥቃትም እያደረሰ ነው ተብሏል። በዚህም ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን የተሰደዱ ሲሆን የሱዳን መንግሥትም በስደተኞች መጠለያ ካምፕ ውስጥ አስገባቸዋለሁ ብሏል።
news-52934665
https://www.bbc.com/amharic/news-52934665
የ75 አመቱን ግለሰብ ገፍትረው የጣሉት ፖሊሶች ክስ ተመሰረተባቸው
በአሜሪካ ኒውዮርክ ከተማ የ75 አመት የእድሜ ባለፀጋን ገፍተው መሬት ላይ የጣሉ ሁለት ፖሊሶች ክስ ተመስርቶባቸዋል።
ግለሰቡ ቦታው ላይ የተገኙት የጆርጅ ፍሎይድን ግድያ ለመቃወም ነበር ተብሏል። የዕድሜ ባለፀጋውን መሬት ላይ በጣሉት ወቅትም ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውንም ከተቀረፀው ቪዲዮ መረዳት ይቻላል። የ39 አመቱ አሮን ቶርጋልስኪና የ32 አመቱ ሮበርት ማካቤ ወንጀሉን አልፈፀምንም ሲሉ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል። ለጊዜው ያለ ዋስ ቢለቀቁም ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ የሰባት አመት እስር ይጠብቃቸዋል። በዚህ ሳምንት ሐሙስ እለት ማርቲን ጉጊኖ የተባሉትን ግለሰብ በገፈተሯቸው ወቅት ግለሰቡ ወደኋላ በጀርባቸው አስፓልቱ ላይ ወድቀዋል። ወዲያውም ነው ከጭንቅላታቸው ደም መፍሰስ የጀመረው። በአሁኑ ሰዓት ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን በጥሩ ጤንነትም ላይ ይገኛሉ ተብሏል። በነጭ ፖሊስ የተገደለውን ጆርጅ ፍሎይድን ተከትሎ የተቀጣጠለውን የፀረ ዘረኝነት ተቃውሞም ለማብረድ ግዛቶች የሰዓት እላፊ አዋጅን አሳልፈዋል። በኒውዮርክም የሰዓት እላፊ አዋጅ የተጣለ ሲሆን ይህንንም ለማስከበር ፖሊሶቹ በቦታው ነበሩ ተብሏል። የአደጋ ጊዜ ምላሽ የሚሰጠው ቡድን አባላት የሆኑት ሁለቱ ፖሊሶች የዕድሜ ባለፀጋውን የገፈተሩበት ቪዲዮ መውጣቱን ተከትሎ ያለ ደመወዝ ከስራቸው እንዲታገዱ ውሳኔ ተላልፏል። የነሱ ከስራ መታገድንም ተከትሎ የቡድኑ አምሳ ሰባት አባላትም ከስራቸው ለቀዋል። በትናንትናው ዕለትም 100 የሚሆኑ ደጋፊዎች፣ ፖሊሶች፣ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ክሱን በመቃወም በቡፋሎ ፍርድ ቤት የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል።
news-49404159
https://www.bbc.com/amharic/news-49404159
አሜሪካ፡ 'እርጉዝ እንደነበርኩ አላወቅኩም' ያለችው እናት ነፃ ወጣች
የገዛ ልጅሽን መፀዳጃ ቤት ወስጥ ገድለሽ ጥለሻል ተብላ ተከሳ የነበረችው የ21 ዓመቷ ኤል ሳልቫዶራዊት ነፃ ወጣች።
ኸርናንዴዝ ወንጀሉን ፈፅማለች ተብላ ከተያዘች ጀምሮ እሥር ቤት ለ33 ወራት ከርማለች ኸርናንዴዝ ሆዷን ከፉኛ ሲቆርጣት ወደ ሽንት ቤት ታመራለች። እዚያም እያለች ራሷን ትስታለች። ወደ ሆስፒታል ስትወሰድ ዶክተሮች 'ልጅ ወልደሻል ነገር ግን በሕይወት የለም' ይሏታል። ኸርናንዴዝ 'ወንዶች በቡድን ሆነው ደፍረውኛል፤ እኔ እርጉዝ መሆኔን አላወቅኩም ነበር' ስትል ላለፉት 33 ወራት ብትከራከርም ሰሚ አላገኘችም ነበር። አቃቤ ሕግ የሴቲቱ ጥፋት 40 ዓመት ያስቀጣል ሲል ቢሞግትም አልተሳካለትም። የኸርናንዴዝ ጉዳይ ዓለምን በአግራሞት ሰቅዞ የያዘ ጉዳይ ነበር። በተለይ የሴት መብት ተሟጋቾች ለ21 ዓመቷ ወጣት እናት ሽንጣቸውን ገትረው ሲከራከሩ ከርመዋል። ላቲን አሜሪካዊቷ ኤል ሳልቫዶር ውርጃን በተለመከተ ጥብቅ ሕግ ካላቸው የዓለም ሃገራት አንዷ ነች። በየትኛውም ዓይነት ሁኔታ ውርጃ ማካሄድ አይፈቀድም። ይህን ፈፅመው የተገኙ ከ2-8 ዓመት እሥር ይጠብቃቸዋል። የኸርናንዴዝ ክስ እንዲህ ሊከር የቻለው ውርጃ ብቻ ሳይሆን የነብስ ማጥፋት ወንጀል ፈፅማለች ተብላ በመከሰሷ ነው። ጥፈተኛ ሆና ብትገኝ በትንሹ የ30 ዓመት የከርቸሌ ኑሮ ይጠብቃት ነበር ተብሏል። «ክብሩ ይስፋ፤ ፍትህ አግኝቻለሁ» ስትል ነበር ከውሳኔው በኋላ መፈናፈኛ ላሳጧት የሚድያ ሰዎች ስሜቷን የገለፀችው። ኸርናንዴዝ ወንጀሉን ፈፅማለች ተብላ ከተያዘች ጀምሮ እሥር ቤት ለ33 ወራት ከርማለች። «ሕልሜ ትምህርቴን መቀጠል ነው። ደስተኛ ነኝ» ብላለች ሲል ኤኤፍፒ የተሰኘው የዜና ወኪል ፅፏል። ኤል ሳልቫዶር ውስጥ ነፃ ከወጣችው ሴት በፊት ተመሳሳይ ወንጀል ፈፅመዋል ተብለው ሕይወታቸውን ከፍርግርጉ ጀርባ እየመሩ የሚገኙ በርካታ ሴቶች እንዳሉ ይነገራል። የኸርናንዴዝ ነፃ መውጣት ለእነዚህ ሴቶች ትልቅ ተስፋ እንደሆነ የሕግ ሰዎች የመብት ተሟጋቾች ያትታሉ። አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተሰኘው ድርጅት 'ለኤል ሳልቫዶር ሴቶች ትልቅ ድልን ያጎናፀፈ ፍርድ' ሲል ብይኑን ገልፆታል።
45251401
https://www.bbc.com/amharic/45251401
የኮፊ አናን ዋና ረዳት ኢትዮጵያዊት እንደነበሩ ያውቁ ኖሯል?
የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ኮፊ አናን በ80 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት መለየታቸው ከተሰማ ጀምሮ በርካቶች ሃዘናቸውን ሲገልጹ ሰንብተዋል።
የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ኮፊ አናን በሰብዓዊ ዕርዳታ ሥራቸው የኖቤል ተሸላሚ የነበሩት ኮፊ አናን፤ እአአ 1938 ጎልድ ኮስት ተብላ ትጠራ በነበረችው ጋና ነበር ከመንትያ እህታቸው ጋር የተወለዱት። ኮፊ አታ አናን ሙሉ ስማቸው ሲሆን አካን በሚባል ቋንቋ የመጀመሪያ ስማቸው ''በዕለተ አርብ የተወለደ'' ማለት ሲሆን አታ ማለት ደግሞ ''መንትያ'' ማለት ነው። በተባበሩት መንግስታት ሳሉ ለ20 ዓመታት ረዳታቸው ሆነው የሠሩት ኢትዮጵያዊት ወይዘሮ ነበሩ። • የአፍሪካ ተፈጥሯዊ ሃብቶች ዘረፋ ሲጋለጥ ለበርካታ ዓመታት የኮፊ አናን የቅርብ ረዳት በመሆን የሰሩት ወይዘሮ ዋጋየ አሰበ ምንም እንኳ ዛሬ በህይወት ባይኖሩም ሴት ልጃቸው ማርታ ተስፋዬ ስለ ኮፊ አናን የምታስታውሰውን ለቢቢሲ ተናግራለች። የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ ከመሆናቸው በፊትና ከሆኑም በኋላ ለ22 አመታት አብረው እንደሰሩ ማርታ ትናገራለች። ማርታ ተስፋዬ ተወልዳ ያደገችው በአሜሪካን ሃገር ዋሽንግተን ዲሲ ነው። ''ወላጅ እናቴ ከኮፊ አናን ጋር ለ22 ዓመታት የቅርብ ረዳት ሆና አብራ ሰርታለች። በርካታ ሃገራትም አብረው ተጉዘዋል'' የምትለው ማርታ፤ ብዙ ጊዜ ኮፊ አናንን በአካል ማግኘቷን ትናገራለች። ኮፊ አናንን "በጣም ደግ ሰው ነበሩ'' ስትል ትገልጻቸዋለች። ኮፊ አናን እሷ ወደምትኖርበት ከተማ በመጡ ቁጥር ስልክ ይደውሉላትና ያገኟትም እንደነበር ማርታ ትናገራለች። ''ቀስ ብሎ ነው የሚያወራው። ሲናገር ግርማ ሞገስ ነበረው። ልጅ እያለሁ ''አንክል ኮፊ'' (አጎቴ ኮፊ) ብለሽ ጥሪኝ ይለኝ ነበር'' ትላለች ማርታ። ወላጅ እናቷ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ 4 ዓመት እንደሆናቸው የምትናገረው ማርታ፤ የኮፊ አናን ሞት ስትሰማ እጅጉን ማዘኗን ትገልጻለች። ''በህይወት ሳለ በርካታ መልካም ነገሮችን ሰርቷል። ብዙ ሰው እንዲህ አይነት ተግባር በህይወቱ መፈጸም ይከብደዋል። እሱ ግን ያንን ፈፅሟል።'' ትላለች። ''ኒውዮርክ ወደሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ዋና መስሪያ ቤት በሄድኩ ቁጥር 38ኛ ፎቅ ላይ ሆኖ፤ ሙሉ ሱፍ ለብሶ እና ጥቁር ገብስማ ጸጉሩ አይረሳኝም'' ትላለች። • ታላቁ ዲፕሎማት ኮፊ አናን ሲታወሱ
news-51624964
https://www.bbc.com/amharic/news-51624964
ኮሮናቫይረስ፡ የመጀመሪያውን የቫይረሱን ተጠቂ ማግኘት ምን ያህል አስፈላጊ ነው? ከምናስበው በላይ
የቻይና ባለሥልጣናት እና ባለሙያዎች የመጀመሪያው የኮሮናቫይረስ ተጠቂን ለማግኘት እየተሯሯጡ ነው።
'ፔሸንት ዜሮ' የተሰኘውን የመጀመሪያውን ተጠቂ የማግኘት 'ሚሽን' ቀጥሏል። ግን በሽተኛውን ማግኘት ለምን አስፈለገ? 'ፔሸንት ዜሮ' አንድ በሽታ ሲከሰት የመጀመሪያው ተጠቂን ለመለየት የሚጠቀሙበት ቃል ነው። አንድ ወረረሽኝ ሲከሰት የመጀመሪያውን የቫይረስ ወይም ባክቴሪያ ተጠቂ ማግኘት ወሳኝ ነው። ይህም ከየት፣ ወዴት እና እንዴት የሚሉ ጥያቄዎችን ይመልሳል። እነኚህን ጥያቄዎች መመለስ ቫይረሱ ወይም ባክቴሪያው እንዳይዛመት፤ እንዲሁም መድኃኒት እንዲገኝለት ያገዛል። የኮሮኖቫይረስ የመጀመሪያ ተጠቂ ይታወቃል? መልሱ - አይታወቅም ነው። የቻይና ባለሥልጣናት የመጀመሪያ የኮሮና ቫይረስ ክስተት ሪፖርት የተደረገው ታኅሳስ 2012 ውስጥ ነው ይላሉ። የኒሞኒያ አይነት ባሕርይ ያለው ኮሮና መጀመሪያ የተከሰተባት ቦታ ሁቤይ ግዛት ውስጥ የምትገኘው ዉሃን ከተማ ናት። በሽታው ዉሃን ውስጥ የሚገኝ አንድ ቄራ ውስጥ እንደጀመረም ይገመታል። አሁን ላይ ከተመዘገው 75 ሺህ የበሽታው ተጠቂ መካከል 82 በመቶው ምንጩ ከዉሃን ከተማ ውስጥ ነው። ነገር ግን የቻይና አጥኚዎች ይፋ ያደረጉት አንድ ጥናት እንደሚያትተው በኮቪድ-19 የተጠቃው የመጀመሪያው ሰው የታየው ኅዳር 21/2012 ነው። ይህ ሰው ደግሞ ወደ ሥጋ መሸጫው ቄራ አልሄደም። ጉምቱው ዶክተር ዉ ዌንጁዋን የመጀመሪያ የተመዘገበ ተጠቂ አንድ ሸምገል ያሉና የመርሳት በሽታ ያለባቸው ሰው ናቸው ሲሉ ለቢቢሲ የቻይና አገልግሎት ተናግረዋል። «የባሕር እንስሳት ሥጋ ከሚሸጥበት ሥፍራ ራቅ ብሎ የሚኖር ሰው ነው። በሽተኛ ስለሆነ ደግሞ ወደ ውጭ አይወጣም።» ዶክተሩ አክለው እንደሚናገሩት ሌሎች ሦስት ሰዎች በሚቀጥሉት ቀናት ተመሳሳይ ምልክት አሳዩ። ከሦስቱ ሁለቱ ወደ ቄራው ብቅ ብለው የማያውቁ ናቸው። ቢሆንም አጥኚዎቹ ያገኙት መረጃ እንደሚያሳየው በመጀመሪያዎቹ ቀናት ወደ ሆስፒታል መጥተው ከተመረመሩ 41 ሰዎች መካከል 27ቱ ወደ ቄራው ሄደዋል። የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው፤ በሽታው መጀመሪያ ከእንስሳ ወደ ሰው ተላለፈ። ከዚያ ከሰው ወደ ሰው ተዛመተ የሚለው ፅንሰ-ሃሳብ አሁንም ይሠራል። የኢቦላ ቫይረስ የተቀሰቀሰው በአንድ የሁለት ዓመት ሕፃን ልጅ እንደሆነ ይነገራል አንድ ሰው ወረርሽኝ መቀስቀስ ይችላል? በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር 2014 ምዕራብ አፍሪካ ውስጥ ድጋሚ ተከስቶ እስከ አሜሪካ የደረሰው የኢቦላ ቫይረስ የ11 ሺህ ሰዎችን ህይወት እንደቀጠፍ ይታመናል። አልፎም 28 ሺህ ሰዎችን በክሏል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት ዘግቧል። ሳይንቲስቶች ቫይረሱ የተነሳው ከአንድ ሰው ነው ይላሉ - ከአንድ የሁለት ዓመት ጊኒያዊ ጨቅላ። አክለውም ጨቅላው የሌሊት ወፎች ከሠፈሩበት ዛፍ ቫይረሱን ሳያገኝ አይቀርም ይላሉ። የመጀመሪያዋ 'ፔሸንት ዜሮ' ሜሪ ማሎን ትባላለች። ቅፅል ስሟም 'ታይፎይድ' ሜሪ ይባላል። ታይፎይድ ኒው ዮርክ ውስጥ በ1906 ላይ ሲከሰት አዛምታለች በሚል ነው ይህ ቅፅል ስም የተሰጣት። በርካታ የጤና ባለሙያዎች የመጀሪያ የበሽታ ተጠቂ የሆነን ሰው ማንነት ይፋ ማድረግ አይፈልጉም። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ የተሳሳተ መረጃ እንዳይሰራጭ ካለ ፍራቻ ነው። ከዚያም ሲያልፍ 'ፔሸንት ዜሮ' የተሰኘው ግለሰብ ላይ መገለል እንዳይደርስ በማሰብ ነው። ለምሳሌ ኤድስ ሲከሰት የመጀመሪያው ተጠቂ ተብሎ የታወጀው ሰው በስህተት ነበር ስያሜውን ያገኘው። ከሦስት አስርት ዓመታት በኋላ ነው ሳይንቲስቶች ግለሰቡ የመጀሪያው እንዳልሆነ ያሳወቁት። ወጣም ወረደ የመጀመሪያውን ተጠቂ ማግኘት እጅግ አስፈላጊ ነው ይላሉ አጥኚዎች። ከዚህ ተጠቂ ታሪክ በመነሳት ደግሞ ለሽታው መድኃኒት የመሥራት ዕድል ሊኖር ይችላልና።
news-51956834
https://www.bbc.com/amharic/news-51956834
የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ቅድመ ዝግጁነትና ምላሽ ቡድን ምን እየሰራ ነው?
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ከሚደረገው ጥረት ጋር ተያይዞ የተለያዩ ቅሬታዎች ይሰማሉ። ከእነዚህም መካከል የነጻ የስልክ ጥሪ አገልግሎት፣ በአየር ማረፊያ የሚደረገው ምርመራ፣ ሕዝባዊ ስብሰባዎችና የውሃ አቅርቦት ችግርን የተመለከቱ ጉዳዮች ይነሳሉ።
ይህንን በተመለከተ በኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት የኮቪድ-19 [ኮሮናቫይረስ] የቅድመ ዝግጁነትና ምላሽ አስተባባሪ አቶ ዘውዱ አሰፋ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ምላሽ እንዲሰጡን ጠይቀናቸው ነበር። በሽታውን በተመለከተ መረጃ ለመስጠት የተዘጋጀው ነጻ የጥሪ ማዕከል 8335 ላይ በርካታ ሰዎች በመደወል መረጃ ለማግኘትና መረጃ ለመስጠት ጥረት ቢያደርጉም አፋጣኝና አጥጋቢ ምላሽ እየሰጠ አይደለም የሚል ቅሬታዎችን እያሰሙ ነው። • ለሶስት ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው 61 ዓመት የኖሩት ዶክተር ሃምሊን ካትሪን ማን ናቸው? • ስለ ኮሮናቫይረስ ሊያውቋቸው የሚገቡ ወሳኝ ነጥቦች ይህንን በተመለከተ አቶ ዘውዱ በሰጡት ምላሽ በሽታው የሚያሳየው ምልክት የጉንፋን ዓይነት ስለሆነ ብዙ ሰዎች ሪፖርት እንደሚያደርጉና ይህ ደግሞ ካለው የሰው ኃይልና በተጠንቀቅ ላይ ካሉ የአምቡላንሶች ቁጥር አንፃር ከፍተኛ የሚባል እንደሆነም ያመለክታሉ። ጨምረውም በብሔራዊ ደረጃ ላለው ችግር ምላሽ ለመስጠት ያሉት አምቡላንሶችን ከሦስት ወደ ዘጠኝ እንዲያድግና ከሰው ኃይል አንጻርም ቡድኑም ሃያ እንዲሆን መደረጉን ይናገራሉ። እሳቸው እንደሚሉት "በአዲስ አበባ ደረጃም የአምቡላንሶችን ቁጥር ከሁለት ወደ አስር እንዲያድግ ተደርጓል። ይህም ሆኖ ግን በ8335 የሚደርሱንን ጥቆማዎች ሁሉ ለመድረስ አስቸጋሪ ነው" ይላሉ። ለጤና ተቋማት ሰፊው ህዝብ ከሚጠቀምበት መስመር የተለየ ሁለት የውስጥ መስመሮች መዘጋጀታቸውን የሚናገሩት አቶ ዘውዱ፤ ከግለሰቦች እንዲሁም ከጤና ተቋማት የሚደርሷቸው ጥቆማዎች ካለው አቅም በላይ መሆኑን ያረጋግጣሉ። ከጥቂት ቀናት በፊት ከዱባይ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ወደ አዲስ አበባ የገባች አንዲት እንግሊዛዊት ዲፕሎማት በኮሮናቫይረስ መያዟን ተከትሎ በአውሮፕላን ማረፊያው የሚደረግ የሙቀት ልኬት አስተማማኝነት ላይ ጥያቄን አስነስቷል። ይህንን በተመለከተ አቶ ዘውዱ ሲናገሩ በየትኛውም ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ትኩሳት የሌላቸው መንገደኞች ምንም ሳይታይባቸው ማለፋቸው እርግጥ እንደሆነ ጠቅሰዋል። • በጣሊያን በኮሮናቫይረስ በአንድ ቀን ብቻ 475 ሰዎች ሞቱ • ሁለት ኢትዮጵያዊያን ጣሊያን ውስጥ በኮሮናቫይረስ መሞታቸው ተረጋገጠ "ትኩሳት የሌለው ሰው የሙቀት ልየታውን የማለፍ እድሉ ከፍተኛ ነው የሚሆነው፤ ይህም በተለያየ ምክንያት ሊሆን ይችላል። በሚያርፍበት ጊዜ ሙቀት ላይኖረው ይችላል፤ በተጨማሪም ትኩሳትን የሚቀንሱ መድሃኒቶችን በመውሰድም የማለፍ እድሉም ከፍተኛ ይሆናል" ይላሉ። እሳቸው እንደሚሉት ዋናው ትኩረት መሆን ያለበት መንገደኞች ከየትኛው አገር ነው የመጡት፣ ከዚያም ወደ ኅብረተሰቡ የሚቀላቀሉም ይሁን ወደ ጤና ተቋም የሚሄዱ እነሱን መከታተል የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑን ተናገረው፤ ከዚህ አኳያም አስፈላጊው ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል። አሁን ባለው ሁኔታ ከበሽታው ስጋት አንጻር ሰዎች የፊት መሸፈኛ ጭንብልን ማድረግ የለባቸውም ብለው የሚያምኑት ባለሙያው አቶ ዘውዱ ይልቁንም ኅብረተሰቡ የፊት ጭንብል እንዲሁም እጅን ከተህዋሲያን የሚያጸዳ ፈሳሽ [ሳኒታይዘር] ለመግዛት በየቦታው የሚያደርገው ከፍተኛ ግፊያና ግርግርን ሥርዓት ለማስያዝም ቡድናቸው እየሰራ እንደሆነ አስረድተዋል። ጨምረውም የበሽታው ክስተት እየተሰጠ ያለው መረጃ ገና በመጀመሪያ ደረጃ ላይ እንደመሆኑ፤ በጤና ተቋማት የሚሰጡ ምክረ ሃሳቦች ቶሎ ተግባራዊ ሲሆኑ ባይታይም በሂደት ግን የሚሰጡት መረጃዎች በኅብረተሰቡ ዘንድ ሊሰርፅ እንደሚችልና በቀላሉ ተግባራዊ እንደሚደረጉ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል። ከውሃ እጥረት እንዲሁም ከትራንስፖርት አጠቃቀም ጋር በተያያዘ መደረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎችና የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ጀምሮ የሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት በመከላከል ሥራው ባለድርሻ እንዲሆኑና መደረግ ያለባቸውን ነገሮች ተግባራዊ እንዲደረጉ እየተሰራ መሆኑን አቶ ዘውዱ አሰፋ አመልክተዋል። የፊት መሸፈኛ ጭምብል የሚያስፈልገው ማን ነው?
news-46017230
https://www.bbc.com/amharic/news-46017230
ሐረር ከተማ በፈረቃ ውሃ ማግኘት ጀምራለች
ለወራት በውሃ ጥም ስትቃጠል የከረመችው ሐረር በፈረቃም ቢሆን ውሃ ማግኘት መጀመሯ ተሰምቷል።
ባለፈው ሳምንት ሐረር ከተማ ያሉ ሰፈሮች እስከ ዘጠኝ ወር ድረስ ውሃ ሳያገኙ እንደቆዩ መዘገባችን ይታወሳል፤ የሐረር ከተማ ሰዎችም የድረሱልን ጥሪ አቅርበው ነበር። የሐረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ሥራ አስኪያጅ አቶ ተወለዳ አብዶሽ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የከተማዋ አንድ ሦስተኛ ክፍል የቧንቧ ውሃ ማግኘት ጀምሯል። «የችግሩ ዋነኛ ምንጭ የነበረው የዓለማያ ውሃ አቅርቦት ፕሮጀክት ከኦሮሚያ መስተዳድር እና ከዓለማያ እና አወዳይ አስተዳደር ጋር በመነጋገር ጣቢያው አገልግሎት መስጠት እንዲቀጥል ተደርጓል» ይላሉ ባለስልጣኑ። • በዝምታ የምትጠማ ከተማ -ሐረር አክለውም «ከዓለማያ የሚመጣውን ውሃ ከድሬዳዋ ከሚመጣው ጋር በማጣመር ቢያንስ የከተማዋን አንድ ሦስተኛ ክፍል በማዳረስ ለማረጋጋት እየጣርን ነው» ብለዋል አቶ ተወለዳ። በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ደግሞ ሌሎች ውሃ ያልደረሳቸውን ቦታዎች በፈረቃ የማዳረስ ዕቅድ እንዳላቸው ባለሥልጣኑ አሳውቀዋል። የኤረር የውሃ መስመር ችግር እስካሁን እንዳልተፈታ የጠቆሙት አቶ ተወለዳ በሚቀጥሉት ሁለት ሦስት ቀናት ችግሩ እንደሚቀረፍ እምነት አላቸው። ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ያሰቡት ነገር እንዳለ የተጠየቁት ሥራ አስኪያጁ «ሌሎች ውሃ አመንጪ ጉድጓዶች ቆፍረን መስመር ለመዘርጋት ዝግጅት ላይ ነን» ብለው፤ ወደ ሐረር ከተማ ውሃ የሚያሰራጩ መስመሮችን በማብዛት ሥራ መጠመዳቸውን ጠቁመዋል። • መስመር ያልያዘው የኢትዮ-ኤርትራ የንግድ ግንኙነት አክለውም «ለሚቀጥሉት አምስትና አስር ዓመታት ከተማዋ ምን ያህል ውሃ ያስፈልጋታል የሚል ጥናት ልናካሂድም ነው» ብለዋል። አቶ ዳንኤል በርሄ በሐረር ከተማ የሆቴል ባለቤት ናቸው። ላለፈው አንድ ወር በሳምንት ከግለሰብ ከቦቴ ውሀ በ2000 ብር እንደገዙ ያስታውሳሉ። አሁን ግን ውሃ መጥቶ «ትልልቅ ማጠራቀሚያቸውንም ባሊውንም ሞልተናል» ይላሉ፤ ሌሎች ከእርሳቸው ሰፈር በከፋ ለአራት ወራት ያክል ውሃ ያላገኙ ሥፍራዎች እንዳሉ በመጠቆም። ችግሩ ፀንቶባቸው የቆዩ ቦታዎች ቅድሚያ ተሰጥቷቸው የውሃ አቅርቦት እንዲኖራቸው መደረጉን ባለሥልጣኑ አክለው ነግረውናል። «ቅድሚያ የሰጠናቸው ለረዥም ወራት ውሃ የሚባል ያላገኙ አካባቢዎችን ነው፤ ለምሳሌ በተለምዶ ጊዮርጊስ ጋራ እና ከራስ ሆቴል በላይ ያሉ አካባቢዎችን ነው። ከራስ ሆቴል በታች ያሉትም ቢበዛ በአራት ቀናት ውስጥ ውሃ እንደሚያገኙ እምነቴ ነው» ብለዋል አቶ ተወለዳ። ባለስልጣኑ አክለውም «10 ሚሊዮን ብር ካልተሰጠን የዓለማያ ውሃ ጣቢያ አግልግሎት እንዲሰጥ አንፈቅድም ያሉ ሰዎችን አደብ በማስያዝ የኦሮሚያ ክልል አስተዋፅኦ አበርክቷል» ይላሉ። የሐረር ከተማ ነዋሪዎች የመጠጥ ውሃ ችግራቸውን ለማስታገስ የታሸገ ውሃ በመግዛት ለተጨማሪ ወጪ መዳረጋቸውን ገልፀውልን እንደነበር አይዘነጋም። ውሃ ሲጠፋ 55 ኪሎ ሜትር ድረስ ተጉዘው የሚቀዱ እንዳሉ እና ይህንን ማድረግ የሚችሉት መኪና ያላቸው እንደሆኑም የችግሩን ግዝፈት እንደሚያሳይ ተነግሮ ነበር። • በአላማጣ ግጭት ቢያንስ 5 ሰዎች መገደላቸው ተነገረ
45557454
https://www.bbc.com/amharic/45557454
በአርባ ምንጭ የሃገር ሽማግሌዎች ውድመትን ተከላከሉ
በጋሞ ባህል መሠረት ማንኛውም ሰላምን የሚያደፈርስ ሁከት፣ ብጥብጥ፣ ረብሻ፣ ግጭት በሚኖርበት ጊዜ፤ ሁኔታውን ለማብረድና ለመፍታት የሃገር ሽማግሌዎች ያላቸው ተቀባይነት ከፍተኛ ነው።
የአርባ ምንጭ የሃገር ሽማግሌዎች ርጥብ ሳር ይዘው ያደረጉት የመጨረሻ ተማፅኖ በባህሉ መሠረት በተለይ በርካታ ሕዝብ ባለበት ቦታ፤ ሕዝብ መደማመጥ፣ መነጋገር፣ መግባባትና 'አንተም ተው፤ አንተም ተው' ማለት በማይቻልበት ቦታ ላይ የትኞቹም የባህል አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ በእድሜ የገፉ አዛውንቶች እርጥብ ሳር አሊያም ቅጠል ይዘው ከቆሙ ማንኛውም የሚደረግ እንቅስቃሴ ይቆማል። መደማመጥና መነጋገር ይጀመራል፤ ይህም ሲወርድ ሲወራረድ የመጣና ማህበረሰቡ ሰላምን የሚያረጋግጥበት አንዱ እሴት ነው። ሳር አሊያም እርጥብ ቅጠል የሰላም ምልክት ሲሆን ሰላም ማውረድ፣ ረብሻና ብጥብጡን ማቆም የሚል ትርጓሜ አለው። በሳምንቱ የመገባደጃ ቀናት በኦሮሚያ ክልል ፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን አካባቢዎች በተፈፀሙ ጥቃቶች በርካቶች ለሞት ሲዳረጉ በሺዎች የሚቆጠሩት ቀያቸውን ጥለው ሸሽተዋል። ብሔር ላይ ያነጣጠሩ ናቸው በተባሉትና አሸዋ ሜዳ፣ ከታ፣ ቡራዮ አካባቢዎች በተፈፀሙ ጥቃቶች የንብረት መውደምና ዝርፊያ መፈፀሙም ተገልጿል። • በአዲስ አበባ ከጸጥታ ኃይሎች ጋር ባጋጠመ ግጭት 5 ሰዎች ተገደሉ • ስለተፈፀመው ጥቃት እስካሁን የምናውቀው ድርጊቱ በርካቶችን ያስቆጣ ነበር። በዚህም በአዲስ አበባና በአርባምንጭ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል። በአርባ ምንጭ ከተማ በነቂስ የወጡት ወጣቶችም በአካባቢው በወገኖቻቸው ላይ የተፈፀመው አሰቃቂ ግድያና የደረሰው እንግልትን አውግዘዋል። በአካባቢው የሚገኙ በኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክና በኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ላይ ድንጋይ በመወርወር ስሜታቸውን የገለፁም ነበሩ። ሁኔታው ያላማራቸው የአገር ሽማግሌዎች በጋሞ ባህል መሠረት የባሰ ጉዳት ሊደርስባቸው በነበሩት ንብረቶች ፊት ለፊት በመንበርከክና እርጥብ ሳር በመያዝ በቁጣ የገነፈሉትን ወጣቶች ከጥቃት ራሳቸውን እንዲያቅቡ አረጋግተዋል። • ስለተፈፀመው ጥቃት እስካሁን የምናውቀው በአካባቢው የአገር ሽማግሌ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ሰዲቃ ስሜ፤ "የሰላማዊ ተቃውሞው ዓላማ ንብረት ማውደምና በሰው ላይ ጥቃት ማድረስ አልነበረም፤ ሙከራው እንዳለ ስናይ የባንኮቹን ጠባቂዎች በማግባባትና እርጥብ ሳር ይዘን በመንበርከክ ወጣቶቹ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አድርገናል" ይላሉ። እኝህን የአገር ሽማግሌ ባነጋገርናቸው ሰዓት ጥቃት ሊደርስባቸው በነበሩት ባንኮች ላይ ምንም ጉዳት አለመድረሱን እያረጋገጡ እንደነበርም ነግረውናል። በአርባ ምንጭ የሃገር ሽማግሌዎች እርጥብ ሳር ይዘው በተቃውሞው ወቅት ከወጣቶቹ መካከል ነበርኩ ያለን ገነሻ ማዳ "በጋሞ የለቅሶ ባህል በጭፈራ መልክ ለሞቱት የሚያለቅሱ ነበሩ፤ በሌላ በኩል የተፈፀመው ድርጊት አግባብ አይደለም፤ ጋሞ ሰው አይገድልም፤ ቢበደል እንኳን ይቅር ይላል የሚሉ ድምፆችን በጋሞኛ ሲያሰሙ ነበር" ብሎናል። ገነሻ እንደሚለው በዚህ ጊዜ ድንጋይ በመያዝ ንብረት ላይ ጉዳት ሊያደርሱ የነበሩት ወጣቶች የሃገር ሽማግሌዎች ተንበርክከው ባደረጉት የመጨረሻ ተማጽኖ በርዷል። በባህሉ መሠረት ይህንን ልመና የተላለፈ እርግማን ይደርስበታል ተብሎ ስለሚታመን ወጣቱ ይህንን ከመተላለፍ ተቆጥቧል። በመሆኑም እንደተፈራው በንብረትና በሰው ላይ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ አልፏል። አደባባይ የወጣው ሕዝብም ተቃውሞውን በሰላም ገልፆ ወደየመጣበት ተመልሷል በማለት ይናገራል። • 'በእኔ በኩል ሒሳቤን ዘግቻለሁ ' አቶ ታምራት ላይኔ ሌላኛው ያነጋገርናቸው የሐገር ሽማግሌ አቶ አንጀሎ አርሾ "በጋሞ ተወላጆች ላይና በሌሎች ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችን ላይ የተፈፀመውን ዘግናኝ ጥቃት፣ መደፈር፣ ንብረት ማውደምና ላይ የደረሰው በደል በማውገዝ ሕዝቡ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥቷል" ይላሉ። በጋሞ የለቅሶ ባህል መሠረትም በእንብርክክ እየሄዱ በርካቶች ሃዘናቸውን ሲገልፁም አስተውለዋል። ይሁን እንጂ ሁኔታውን ወደ ሌላ ብጥብጥ ለማሸጋገር የሚሞክሩ እንደነበሩ ያልሸሸጉት የአገር ሽማግሌው፤ "በአርባ ምንጭ ከተማ በሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ጥቃት ለመፈፀም ተነሳስተው ፊት ለፊት ያገኟቸውን ባንኮችና የግለሰብ ቤቶች ለመግባት ወጣቱ ገንፍሎ ተነስቶ የነበረ ቢሆንም፤ በጋሞ ባህላዊ ሥርዓት ተማፅኖና ልመና ሁኔታውን በሰላማዊ ሁኔታ ለማለፍ ተችሏል" ብለዋል። በአካባቢው በሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች ላይም ጉዳት እንዳይደርስ በጋሞ ሽማግሌዎች የተደረገው የመከላከል ሥርዓት ለሌሎችም ትምህርት የሚሆን ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። • በተፈናቃዮች ብዛት ኢትዮጵያ ከዓለም ቀዳሚ ሆነች • ቄሮ፣ ሴታዊት፣ ፋኖ…የትውልዱ ድምጾች የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ፍትህ፣ ፀጥታና ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ገበየሁ ጣራ በበኩላቸው ሕዝቡ በጋሞ ተወላጆች ላይ የደረሰውን ጥቃት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ሕጋዊ ጥያቄ ያቀረበና ፈቃድ እንደተሰጠው ገልፀዋል። ነገር ግን በመካከላቸው የሃሳብ ልዩነት ተፈጥሮ ወደ ስታዲየም በመሄድ ፋንታ ንብረት ለማውደም ያመሩት እንደነበሩ ይናገራሉ። የፀጥታ ኃይሎችም ንብረት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ለመከላከል ወደ ሰማይ ሲተኩሱ እንደነበር ተናግረዋል። በዚህም ወቅት በባረቀ ጥይት የ2 ሰዎች ሕይወት ሲያፍ፤ 3 ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሶዶ ሆስፒታል ተልከው ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኙ ገልፀዋል። በንብረት ላይ የደረሰ ውድመት አለመኖሩን የተናገሩት ኃላፊው አጋጣሚውን በመጠቀም ብጥብጥ ለመፍጠር የሞከሩ 20 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አቶ ገበየሁ ለቢቢሲ አስረድተዋል። በከተማዋ ዛሬ መደበኛ እንቅስቃሴዎች እንደተጀመሩና በሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ እንደምትገኝ ገልፀዋል።
news-44242281
https://www.bbc.com/amharic/news-44242281
ራስዎን ካላስፈላጊ የስልክ ጥሪ እንዴት ይታደጋሉ?
እኩለ ለሊት ላይ ነው። ከኃይለኛ እንቅልፍ የስልክዎ ጩኸት ይቀሰቅስዎታል። ስልክዎን ሲመልሱ በሌላኛው የስልኩ ጫፍ ምላሽ የሚሰጥዎ ሰው ባይኖርስ?
የማይስፈልግ የስልክ ጥሪ ሊደርስዎት ይችላል 'ሄሎ' በሚል ሰው ፈንታ የህክምና ኢንሹራንስ ይፈልጉ እንደሆነ የሮቦት ድምጽ ቢጠይቅዎስ? ከጣፋጭ እንቅልፍዎ የተነሱት ያለምንም ምክንያት በመሆኑ ይበሳጫሉ። ተመሳሳይ ሁነት ከአንዴም ሁለት ሦስቴ ሊገጥም ይችላል። ነገሩ ወዲህ ነው። በስልክ የሚሰማው ድምጽ የማሽን ሲሆን 'ሮቦኮልስ' በመባል ይታወቃል። በስልክ የሚተላለፈው ድምጽ ከጥሪው በፊት የተቀዳ የማሽን አልያም የሮቦት ድምጽ ነው። የስልክ ጥሪውን በህጋዊ መንገድ የሚጠቀሙበት ቢኖሩም ባልተገባ ሁኔታ ለንግድ የሚያውሉትም አልታጡም። ለአብነት አሜሪካና ካናዳን ብንወስድ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ ይጠቀሙበታል። አየር መንገዶችም ማስታወቂያ ለመንገር ይገለገሉበታል። ባለፈው ሚያዝያ አሜሪካ ውስጥ 3,400 ሚሊየን የሮቦኮል ጥሪዎች ለ 324 ሚሊዮን ሰዎች መድረሳቸውን የካሊፎርኒያው ዩሜል ድርጅት አሳውቋል። በዋነኛነት ጥሪውን የሚያደርጉት የህክምና እና የመኪና ኢንሹራንስ ድርጅቶች እንዲሁም የቤት ደላላዎችና ሥራ አፈላላጊዎች ናቸው። እነዚህ ድርጅቶች ለሰዎች የሚደውሉት በዘፈቀደ ነው። ለአንድ ግለሰብ በቀን ወይም በሳምንት ውስጥ በርካታ ጊዜ ሊደውሉ ይችላሉ። አንዳንድ ድርጅቶች በደቂቃ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠር ጥሪ ማድረግ ይችላሉ። ሮቦኮል እንደሀሰተኛ ኢሜል ነው ፌደራል ትሬድ ኮሚሽን የተሰኘው ድርጅት እንደሚያመለክተው የስልክ ጥሪው ሲደረግ የደዋዩ ቁጥር ሊደበቅ ወይም የተሳሳተ ቁጥር ሊወጣ ይችላል። ትክክለኛ የስልክ ቁጥር በመጠቀምም ጥሪው የሚተላለፍበት አጋጣሚ አለ። ባለፈው ዓመት በአንድ ወር ውስጥ 375 ሺህ ሰዎች ስለስልክ ጥሪዎቹ ቅሬታ አቅርበዋል። ድርጅቱ እንደሚለው የስልክ ጥሪዎቹ ሲደረጉ ደዋዮቹ ያሉበትን ቦታ መደበቅ የሚችሉበት ቴክኖሎጂ ስለሚጠቀሙ ከየት እንደተደወለ ለማወቅ አስቸጋሪ ነው። እነዚህ ጥሪዎች ሲደርሱዎ ምን ማድረግ እንዳለብዎት ያውቃሉ? መሰል ጥሪ ሲደርስዎት መጀመሪያ ማድረግ ያለብዎት ስልኩን በፍጥነት መዝጋት ነው። በስልክዎ ላይ ቁጥር እንዲያስገቡ ቢጠየቁም አያስገቡ። ቁጥር አስገቡ ማለት ራስዎን ለተጨማሪ ስልክ ጥሪዎች አጋለጡ ማለት ነው። አስከትለው የስልክዎን ሲም ለገዙበት ድርጅት ስለሁኔታው ያሳውቁ። ደዋዩን ወደ ስልክዎ እንዳይደውል ማድረግ ይችላሉ። ቲሎውስ ወይም ሁኮልስ የተባሉ ድረ ገጾች መሰል ጥሪዎችን ለማመልከት የተዘጋጁ ስለሆኑ መጠቀም ይችላሉ። የቴክኖሎጂ መረጃዎች የሚሰራጩበት ዘ ቨርጅ የተባለው የዩቲዩብ ገጽ አርታኢ የሆነው ክሪስ ዌልች "በየቀኑ ስድስት የተሳሳቱ ጥሪዎች ይደርሱኛል" ይላል። ከጥሪዎቹ መሀከል ትርጉም አልባ የሆኑ ማስፈራሪያዎች ይገኙበታል። "ግብር ካልከፈሉ ይታሰራሉ" የሚል መልዕክትን እንደምሳሌ የሚጠቅሰው ክሪስ "መልዕክቶቹ በጣም ይረብሻሉ" ይላል። ክሪስ እንደመፍትሄ የሚያስቀመወጠው ስልክ ቁጥሩን መዝግቦ ሲደውል እንዳይታይ ማገድ (ብሎክ ማድረግ) ነው። ሮቦኮል የሚያደርገውን ስልክ ቁጥር ማመልከትም ይቻላል። የማይፈልጉት ጥሪ ከሆነ ስልኩን ይዝጉት ጥሪ ለማገድ የሚያስችል መተግበሪያ ያላቸው የስልክ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች አሉ። አግልግሎቱን ለማግኘት ጥያቄ ማቅረብም ይቻላል። ሮቦኮል የሚያስቸግራቸው ሰዎች የተለያዩ መተግበሪያዎችን መጫንም ይችላሉ። ዩሜል፣ ሮቦኪለር፣ ትሩኮለር ወይም ሂያ የተባሉ መተግበሪያዎችን ክሪስ ይጠቅሳል። ክሪስ እንደሚናገረው ስልክ ሲገዛ ሮቦኮል ማገድ የሚችል መተግበሪያ አላቸው። ለአብነት ያህል የሳምሰንግ ጋላክሲ ኤስ እና ኖት ስልኮች የሮቦኮል ማስጠንቀቂያ ይሰጣሉ። የስልክ ቀፎ ላይ ከተመዘገቡ ቁጥሮች ውጪ ሲደውሉ ተጠቃሚው እንዳያይ የሚያስችሉ መንገዶች አሉ። 'ዱ ኖት ዲስተርብ' የሚል ቁልፍ ስልክ ላይ በመጫን የማይፈለጉ ጥሪዎችን መከላከል ይቻላል። የአንድሮይድና አይፎን ስልኮች ከተመዘገቡ ስልኮች ውጪ ጥሪ ያለመቀብ አማራጭ ይሰጣሉ። ክሪስ እንደሚለው አንድ ሰው የሚፈልጋቸውን ስልኮች እስከመዘገበ ድረስ ባልተፈለጉ ጥሪዎች እንዳይረበሽ ማድገግ የተሻለ አማራጭ ነው።
51044174
https://www.bbc.com/amharic/51044174
ሜጋንና ሃሪ የቤተ-መንግሥት ኃላፊነት በቃኝ ማለታቸው የእንግሊዝ ንጉሳዊ ቤተሰብን አስቆጥቷል
የሱሴክስ ንጉስ እና ንግስት በመባል የሚታወቁት ሜጋን ሜርከልና ልዑል ሃሪ የቤተ-መንግሥት ኃላፊነት ይብቃን ማለታቸው የተሰማው ትላንት ምሽት ነው።
ሜጋንና ሃሪ ውሳኔውን የወሰኑት የእንግሊዝ ንጉሳዊ ቤተሰብን ሳያማክሩ መሆኑ ልዑላኑን እንዳስቆጣ ቢቢሲ መረዳት ችሏል። የባኪንግሃም ቤተ-መንግሥት ልዑላን ምንም እንኳ ስለ ሜጋንና ሃሪ የወደፊት ዕጣ ፈንታ በመምከር ላይ የነበሩ ቢሆንም ይህንን ውሳኔ አልጠበቁትም ነበር ተብሏል። • "ወንድ ወይ ሴት መሆን ትልቅ ቦታ ለመድረስ አያግዝም ወይ አያስቀርም" • ሶማሊያውያን፤ አውስትራሊያን ግመሎቻችን መልሺልን እያሉ ነው ዕለተ ረቡዕ ውሳኔያቸውን አስመልክተው የፅሑፍ ሃተታ የለቀቁት ሜጋንና ሃሪ ውሳኔው ላይ የደረሱት ለበርካታ ወራት ከመከርንና ከዘከርን በኋላ ነው ብለዋል። ባልና ሚስቱ ከነባር የቤተ-መንግሥት ኃላፊነታቸው ወርደው በገንዘብ ራሳቸውን ለመቻል እንደሚጥሩም አሳውቀዋል። አልፎም ከዚህ በኋላ ተቀማጭነታቸውን በእንግሊዝና በሰሜን አሜሪካ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። ለንግስቲቱ ተገዥነታችን ግን ሁሌም ይቀጥላል ሲሉም በመግለጫቸው አስታውቀዋል። «እንግሊዝም ሆነ አሜሪካ መመላለሳችን ለልጃችን መልካም አጋጣሚ ነው። ምክንያቱም የእንግሊዝ ንጉሳዊ ቤተሰቡን እንዳይረሳ ያግዘዋል። አልፎም ስለወደፊታችን እንድናስብ ይረዳል።» ባልና ሚስቱ የሱሴክስ ልዑላዊ እርዳታ ድርጅት አቋቁመው በአፍሪካና አሜሪካ በመዘዋወር ሴቶችን ለማበረታታት እንደሚሠሩ ይፋ አድርገዋል። የባልና ሚስቱ ውሳኔ ወደፊት ምን ዓይነት የቤተ-መንግሥት ኃላፊነት ነው የሚኖራቸው የሚል ጥያቄን መጫሩ አልቀረም። ነገር ግን ለሜጋንና ቧላ ተራ ሕይወት መምራት እጅግ ከባድ እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ። ዋነኛው ምክንያት ደግሞ መገናኛ ብዙሃን ለጥንዶቸ የሚሰጡት ትኩረት ነው። ተንታኞች፤ ጥንዶቹ ከመጋባታቸው በፊትም ቢሆን ሚስት በትወና፤ ባል ደግሞ በልዑልነቱ ታዋቂ የነበሩ በመሆናቸው ሕይወት ቀላል ይሆንላቸዋል ብሎ ማሰብ ዘብት ነው ባይ ናቸው። እንደውም መገናኛ ብዙሃን ጥንዶቹን አጥምዶ የዜና ማዕድ ላይ ለማቅረብ ከመቼውም የበለጠ ይተጋሉ፤ ምክንያቱም ባልና ሚስቱ ከሌሎች ንጉሳውያን ቤተሰብ አባላት ወጣ ባለ ተግባራቸው ይታወቃሉና። ብዙዎች ከንጉሳዊ ተግባራት በማፈንገጥ የምትታወሰው የልዑል ሃሪ እናት ልዕልት ዳያናን ከጥንዶቹ ባሕሪይ ጋር ያመሳስሉታል። • "በተስፋ፣ በስጋት፣ በቁጭት መካከል ነው ያለሁት" ጀዋር መሐመድ • ከ6ሺህ ሰዎች በላይ የሞቱበት የኩፍን ወረርሽኝ ቢሆንም ውሳኔያቸውን ንጉሳዊ ቤተሰቡን ሳያሳውቁ ይፋ ማድረጋቸው ግራ አጋቢ ነው የሚሉ አልጠፉም። ምንም ቢሆን ለንጉሳዊው ቤተሰብ ኃላፊነት አለባቸው ሲሉ አመክንዮዋቸውን ያስቀምጣሉ። አልፎም ጥንዶቹ ከቤተ-መንግሥት ኃላፊነታቸው ከወረዱ በኋላ ለኑሯቸው እና ደህንነታቸው ክፍያውን የሚፈፅመው ማነው የሚለው የግብር ከፋዩ ጥያቄ እንደሆነ ይዘገባል። ጥንዶቹ በገንዘብ ራሳችንን እንችላለን ይበሉ እንጂ ለጊዜው የቤተ-መንግሥት ገንዘብ እንደሚጠቀሙ ይታወቃል። ከቤተ-መንግሥት ከወጡ የት ነው የሚኖሩት? ማነውስ በገንዘብ የሚረዳቸው? ከሎሎች ንጉሳውያን ቤተሰብ አባላት ጋር የሚኖራቸው ግንኙነትስ? ያልተመለሱ ጥያቄዎች ናቸው። ሌላው እንግሊዛውያንን እያነጋገረ ያለው ጉዳይ ንጉሳዊው ቤተሰብ እያከተመ ይሆን ወይ የሚለው ነው። ጥንዶቹ በተለይ የእንግሊዝ መገናኛ ብዙሃን አላስቀምጥ እንዳሏቸው እሙን ነው። ሜይል የተሰኘውን ጋዜጣ መክሰሳቸውም ይታወሳል።
49737876
https://www.bbc.com/amharic/49737876
በየትኛው አቀማመጥ ቢፀዳዱ ጤናማ ይሆናሉ?
ከሙሉ ሕይወታችን በአማካይ ወደ ስድስት ወር ያህሉን የምናሳልፈው ስንፀዳዳ መሆኑን ያውቃሉ?
ከሕይወታችን ወደ ስድስት ወር ያህሉን የምናሳልፈው ስንጸዳዳ ነው በዓመት ውስጥ የአንድ ሰው ሰገራ ሲመዘን 145 ኪሎ ግራም ይሆናል። ይህ ማለት ደግሞ አንድ ሰው በዓመት ሁለቴ ከክብደቱ እጥፍ የሚመዝን ሰገራ ያስወግዳል ማለት ነው። በሕይወታችን ግዙፍ ቦታ ያለው የመፀዳዳት ጉዳይ ከጤናችን ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው። ለመፀዳዳት የምትቀመጡበት መንገድ በጤናችሁ ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር የምታውቁ ስንቶቻችሁ ናችሁ? • መጻሕፍትን ማንበብና መጻፍ ለአዕምሮ ጤና • ሞባይል ለኢትዮጵያ እናቶችና ህፃናት ጤና ለመሆኑ መፀዳጃ ላይ ስንት ሰዓት ያጠፋሉ? በ20ኛው ክፍለ ዘመን እኩሌታ ላይ በአፍሪካ ገጠራማ አካባቢዎች የሚሠሩ ሀኪሞች፤ አንዳችም ከ 'ጋስትሮኢንተስታይናል' (ምግብ የመፍጨትና ሰገራ የማስወገድ ሂደት) ጋር የተያያዘ የጤና እክል ያለበት ሰው አልገጠማቸውም ነበር። ነገሩ ሀኪሞቹን አስገርሟቸው ነበር። ከአፍሪካ ውጪ በሌሎች ታዳጊ በሚባሉ አህጉሮችም ምግብ ፈጭቶ ሰገራ ከማስወገድ ጋር የተያያዘ እክል ያለበት ሰው እምብዛም አልነበረም። መላ ምታቸው የነበረው ነገሩ የአመጋገብ ሥርዐት ውጤት ይሆናል የሚል ነበር። እውነታው ግን ያ አልነበረም። ሀኪሞቹ ለጥያቄያቸው መልስ ያገኙት፤ ከሰዎች ሰውነት የሚወገደው ሰገራ የሚጠራቀምበት የጊዜ ርዝመትና ሰዎች ሲፀዳዱ የሚቀመጡበት መንገድ ነበር። ቁጢጥ በማለት መጸዳዳት የሚቻልባቸው መጸዳጃዎች ቁጭ ብሎ ለመጸዳዳት ከተዘጋጁት በበለጠ ይገኛሉ ምዕራባውያኑ መፀዳጃ ቤት በገቡ ቁጥር ቢያንሰ ከ114 እስከ 130 ሰከንድ ይቆያሉ። በተቃራኒው ታዳጊ በሚባሉ አገሮች አንድ ሰው መፀዳጃ ቤት የሚቆየው ለ51 ሰከንድ ብቻ ነው። ምዕራባውያኑ ቁጭ ተብሎ መፀዳዳት የሚቻልበት መጸዳጃ ሲጠቀሙ፤ ታዳጊ የሚባሉ አገሮች ደግሞ ቁጢጥ ብሎ መፀዳዳት ያዘወትራሉ። ተመራማሪዎች እንደሚሉት፤ ለአጭር ጊዜ መፀዳጃ ቤት መቀመጥ ጤናማ ነው። ስንፀዳዳ መቀመጫችን አካባቢ 90 ዲግሪ ይታጠፋል። ይህም በአካባቢው የሚገኘው ጡንቻ አንጀታችንን እንዲጫነው ያደርጋል። • ለ10 ዓመታት እጆቹን ያልታጠበው የቴሌቪዥን አቅራቢ • ዘመናዊውን የመፀዳጃ መቀመጫ የፈጠረው ሰዓት ሠሪ ቁጭ ብሎ ለመፀዳዳት የሚያስችለው ፈጠራ የመጀመሪያው መፀዳጃ ሥራ ላይ የዋለው ከጥንታዊ ሜሶፖታሚያ ሥልጣኔ ወዲህ እንደሆነ ይነገራል። ከክርስቶስ ልደት 315 ዓመታት በፊት ሮም 144 የሕዝብ መፀዳጃ ነበራት። ሮም ውስጥ የተገነባውና 2,000 ዓመታት ያስቆጠረው መፀዳጃ፤ ጎን ለጎን የተሠሩ 50 የመፀዳጃ ጉድጓዶች የያዘ ነበር። የሮም የሕዝብ መፀዳጃ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ 1592 ላይ ውሃ የሚያፈስ መፀዳጃ ተፈልስፎ ነበር። 1880 ላይ ደግሞ አንድ እንግሊዛዊ ዓለምን ያስገረመ መፀዳጃ ይዞ ብቅ አለ። መፀዳጃው ሰዎች ቁጭ ብለው የሚጠቀሙበት ሲሆን፤ ከመፀዳጃ ውስጥ ቆሻሻን ያስወግዳል። የሚፀዳዱበት መንገድ ጤናዎ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድረው እንዴት ነው? ብዙዎች ለመፀዳዳት ሲያምጡ ይስተዋላል። ለዚህ ችግር ምክንያት ከሆኑት መካከል የምግብ አለመፈጨት፣ የሰገራ መድረቅና የአንጀት ህመም ይጠቀሳሉ። ተመራማሪዎች እንደሚሉት፤ ልንፀዳዳ ስንል የምንቀመጥበት መንገድም የጤና እክል ያስከትላል። ምዕራባውያን የሚያዘወትሩት የመፀዳጃ አይነት ለጤና እክሉ ምክንያት እንደሆነ ተመራማሪዎች ያስረዳሉ። በምንፀዳዳበት ወቅት ጉልበታችንን ከ90 ወደ 30 ዲግሪ ከፍ በማድረግ ችግሩን መቅረፍ ይቻላል በኮርኔል ዩኒቨርስቲ የሚሠሩት ፕሮፌሰር አሌክሳንደር ኪራ፤ ሰዎች ቁጢጥ ከማለት ይልቅ ቁጭ ብለው እንዲፀዳዱ የተሠራው መፀዳጃ የችግሩ ምንጭ እንደሆነ ይናገራሉ። ተመራማሪዎች እንደሚሉት፤ በምንፀዳዳበት ወቅት ጉልበታችንን ከ90 ወደ 30 ዲግሪ ከፍ በማድረግ ችግሩን መቅረፍ ይቻላል። እግራችንን ከፍ ስናደርግ አንጀታችንን ከመተጣጠፍ እናድናለን። መፀዳጃ ፊት ለፊት ዱካ አስቀምጦ፣ በምንፀዳዳበት ወቅት እግራችንን ዱካው ላይ ማውጣትን ተመራማሪዎች ይመክራሉ።
news-50779211
https://www.bbc.com/amharic/news-50779211
ለየት ያለው የታይላንድ የማሳጅ ጥበብ በባህላዊ ቅርስነት ተመዘገበ
ጠንከር ያለው የታይላንድ ባህላዊ ጀርባን የማሸት ዘዴ ከፍተኛ ቦታ በሚሰጠው የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ዝርዝር ውስጥ ተመዘገበ።
'ኑዋድ ታይ' የተባለው ይህ ባህላዊ መታሻ ጥበብ ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፉ ባህሎችና የተለያዩ ተግባራት በሚመዘገብበት የሰው ልጅ ወካይ የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርሶች መካከል አንዱ ሆኗል። በዚህም ለቀጣይ ትውልድ ተጠብቀው መቆየት ካለባቸው ባህላዊ ተግባራት መካከል አንዱ ተደርጎ እንዲመዘገብ ሆኗል። • ከብራና ወደ ኮምፒውተር . . . • ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ስለተዘረፉ ቅርሶች ምን እናውቃለን? እነዚህ የማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶች ዝርዝር ለተለያዩ ግንባታዎችና ቦታዎች ዕውቅና ከሚሰጠው ከዓለም የቅርሶች ዝርዝር የተለየ ነው። ባህላዊ ቅርሶች ዝርዝር ውስጥ እስካሁን በሦስት ዘርፎች የተከፈሉና ከ127 አገራት የተወጣጡ 550 ቅርሶች ተመዝግበዋል። በዝርዝሩ ውስጥ በየዓመቱ የተለያዩ ቅርሶች ተመዝግበው ይካተታሉ። ይህ የታይላንድ የማሸት ጥበብ ከሌሎች የተለየ ሲሆን በተለያዩ የሰውነት አቅጣጫዎች በኩል በመሆን የተለያዩ ተከታታይ እንቅስቃሴዎችን ያካተተ መሆኑም ተነግሯል። • ላሊበላ፡ የመፍትሔ ያለህ የሚለው ብሔራዊ ቅርስ • 600 ዓመታትን ያስቆጠረው የሣር ድልድይ የ'ናኡድ ታይ' ባለሙያዎች የማሸቱን ተግባር ሲያከናውኑ ምንም አይነት ቅባትም ሆነ ዘይት የማይጠቀሙ ሲሆን እጃቸውን ብቻ ሳይሆን አንዳንድ ጊዜም ክንዳቸውንና ጉልበታቸውንም ይጠቀማሉ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የባህልና የሳይንስ ተቋም (ዩኔስኮ) እንዳለው ይህ ተግባር ከጥንት ጀምሮ በታይላንድ ማኅበረሰብ ውስጥ የነበረ ሲሆን በግብርና ሥራ ላይ የጡንቻ ህመም ሲገጥማቸው በየመንደሩ ያሉ የማሸት ሙያ ያላቸው ሰዎች ጋር በመሄድ ይታሹ ነበር። በዩኔስኮ የማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶች መዝገብ ውስጥ ከሚካተቱት መካከል መዝሙርና ዘፈኖችን ጨምሮ የተነገሩ ታሪኮች ሲኖሩበት እነዚህም ለቀጣይ ትውልድ ተጠብቀው ቢተላለፉ ጠቃሚ ይሆናሉ የተባሉትን ነው።
news-51550266
https://www.bbc.com/amharic/news-51550266
ፖምፔዮ በግድቡ ዙሪያ የሚካሄደው ውይይት በቅርቡ መቋጫ እንደሚያገኝ ጠቆሙ
የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአሜሪካው አቻቸው ማይክ ፖምፔዮ ጋር ዛሬ ከሰዓት በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።
የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፔዮ፤ የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ ግንኙነት በርካታ ዓመታትን አስቆጥሯል ያሉ ሲሆን፤ ከ1930ዎቹ ጀምሮ ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሲያካሂዱ መቆየታቸውን አስታውሰዋል። በአሜሪካዋ ዋሽንግተን ዲ.ሲ በርካታ ቁጥር ያለው የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ መኖሩን የጠቆሙት ፖምፒዮ በዛሬው መግለጫቸው በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ እና በመጪው ምርጫ ላይ የአገራቸውን አቋም አንጸባርቀዋል። የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሬዝደንት ትራምፕ ሦስቱንም አገራት ሊያስማማ የሚችል ስምምነት እንዲፈጠር ቅድሚያ የሰጡት ጉዳይ ነው ብለዋል ማይክ ፖምፔዮ። የግድቡ ግንባታ በአሜሪካ የገንዘብ ሚንስትር እና በዓለም ባንክ አደራዳሪነት ሲካሄድ መቆየቱን እና የየአገራቱ የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ልዩነቶቻቸውን ለመፍታት ወደ ዋሽንግተን በተደጋጋሚ መጓዛቸውን አስታውሰዋል። ፖምፒዮ "የመግባቢያ ነጥቦች እየተጠናቀቁ ወደ ስምምነት ተቃርቧል። አሁንም ግን የሚቀር ሥራ አለ" ብለዋል። "የሦስቱ አገራት መሪዎችም ሆኑ አሜሪካ፤ የሁሉንም አገራት ፍላጎት ያማከል ስምምነት እንዲደረስ ነው ጥረት ሲደረግ የቆየው። ብዙ ሥራ ይቀረናል፤ በቀጣዩ ወር ግን እንደሚጠናቀቅ ተስፋ አደርጋለሁ" ብለዋል። ምርጫ "የአብይ አስተዳደር ተጠያቂ እና ሁሉን አሳታፊ በሆነ የዲሞክራሲ ሥርዓት ያምናል፤ አሜሪካም እንዲሁ" ያሉት የቀድሞ የሲአይኤ አለቃ ማይክ ፖምፔዮ፤ ስለቀጣዩ ምርጫ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር መወያየታቸውን ተናግረዋል። ቀጣዩ ምርጫ ነጻ እና ታዓማኒነት ያለው ሆኖ ሁሉንም እንደሚያሳትፍ ተወያይተናል ብለዋል። አንበጣ መንጋን መከላከል በአፍሪካ ቀንድ የተከሰተውን አንበጣ መንጋ ለመከላከል አሜሪካ ድጋፍ እንደምታደርግ አስታውቀዋል። በኬንያ፣ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል አሜሪካ የ8 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ እንደምታደረግ አስታውቀዋል። በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው ለውጥ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉት የለውጥ ሥራዎች ሕዝቡን በረዥም ጊዜ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ናቸው ያሉት ፖምፔዮ፤ "በእዚህ ላይ የእኛ አስተዋጽኦ በተቻለን መጠን መደገፍ ነው" ብለዋል። "እንዲህ ዓይነት ትልልቅ ለውጦች ሲካሄዱ ውጤቶች በፍጥነት ላይታዩ ይችላሉ" ያሉት ፖምፔዮ፤ በአፍሪካ መዲና ከሴት ርዕሰ ብሔር ጋር ተገናኝተው መወያየታቸው እንዳስደነቃቸው አልሸሸጉም።
news-54886812
https://www.bbc.com/amharic/news-54886812
የባይደን መመረጥ ለአፍሪካ አዲስ እድል ይዞ ይመጣል ተባለ
በአሜሪካ አዲስ ፕሬዝዳንት መመረጡ የአፍሪካ አገራት ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የነበራቸውን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት እንደ አዲስ የሚጀምሩበት እድል እንደሚሰጣቸው ተነገረ።
ይህንን ያሉት መቀመጫውን ዋሽንግተን ዲሲ ያደረገውና አሜሪካውያን በአፍሪካ መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ የሚያበረታታው 'ኮርፖሬት ካውንስል አፍሪካ' የቀድሞ ፕሬዝዳንት ስቴፈን ሃይስ ናቸው። እሳቸው እንደሚሉት ጆ ባይደን ወደ ስራ ሲገቡ ከአፍሪካ ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት ዙሪያ አዳዲስ ፖሊሲዎችን ይዘው ይመጣሉ። ''ከዚህ በፊት ከነበረው የተሻለና አዳዲስ አሰራሮችን ያካተተ አካሄድ እንደሚኖር አስባለሁ። ምክንያቱም ከፕሬዝዳንቱ ጋር የሚመጡት ሰዎች ያለምንም ጥርጥር ከትራምፕ አስተዳደር በተሻለ ለአፍሪካ ቅርበት ያላቸው ናቸው'' ብለዋል። የቀድሞው የካውንስሉ ፕሬዝዳንት ከቻይና ጋር በተያያዘ ስለሚኖረውም ፉክክር ሀሳባቸውን ሰጥተዋል። ''ጆ ባይደን የአሜሪካና ቻይና ፉክክር ላይ የሚያተኩሩ አይመስለኝም። ነገር ግን አሜሪካና አፍሪካ በቢዝነስና ፖለቲካው ረገድ ተባብረው የሚሰሩባቸውን መንገዶች ማጠናከር ላይ ትኩረት ያደርጋሉ ብዬ አስባለሁ'' ''እንደሚመስለኝ አፍሪካውያን ከአሜሪካ ጋር ሊሰሩባቸው የሚችሉባቸው ዘርፎች እንደ ጤና፣ ግብርና እንዲሁም በመረጃና ቴክኖሎጂ አካባቢዎች ናቸው'' በርካታ የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚጠቅሱት አፍሪካ 'ከአጎዋ' ስምምነት በርካታ ጥቅሞችን ያገኘች ሲሆን አህጉሪቱ የተለያዩ ምርቶቿን ወደ አሜሪካ ገበያዎች ለማቅረብ በእጅጉ ረድቷታል። ስምምነቱ በአውሮፓውያኑ 2025 ላይ የሚያበቃ ሲሆን ቀደም ብለው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ደግሞ በአጠቃላይ ከሚደረግ ስምምነት ይልቅ በተናጥል ከአገራት ጋር መደራደርን እንደሚመርጡ ገልጸው ነበር። በዚህ ተጠቃሚ ከሆኑ አገራት መካከል ኬንያ በቀዳሚነት ትጠቀሳለች። ''አፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና መመስረት ከቻለች ከአሜሪካ ጋር ዘርፈ ብዙ ስምምነቶች ለመድረስ ቀላል ይሆናል'' ይላሉ ባለሙያው።
47177920
https://www.bbc.com/amharic/47177920
በጎንደር የተለያዩ ዞኖች በተከሰተ ግጭት 39ሺህ ሰዎች ተፈናቀሉ
ሰሞኑን በጎንደር እና ዙሪያው በተከሰቱ ግጭቶች በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን እና በሺዎች የሚቆጠሩ መፈናቀላቸውን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ።
የአማራ ክልል ኮሙኑኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰማኸኝ አስረስ የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊው አቶ አሰማኸኝ አስረስ ዛሬ ከሰዓት ጋዜጠኞችን ሰብስበው ''ሰሞኑን በማዕከላዊ ጎንደር በምስራቅ ደንቢያ ወረዳ፣ ላይ አርማጨሆ እንዲሁም በጭልጋ አካባቢ ግጭቶች ተከስተው በሰዎች ሕይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል። ጎንደር አካባቢ በተፈጠረው ግጭት የተፈናቃዮች ቁጥር ወደ 39ሺህ ደርሷል'' ብለዋል። አቶ አሰማኸኝ በባህር ዳር ከተማ በሰጡት መግለጫ፤ የዛሬ ሳምንት በዕለተ ዓርብ ጥር 24 በማዕከላዊ ጎንደር ሰፍሮ የነበረው የመከላከያ 24ኛ ክፍለ ጦር ቦታውን ለቅቆ 33ኛው ክፍለ ጦር እስኪረከብ ድረስ በተፈጠረው ክፍተት፤ ፅንፈኛ ያሏቸው ቡድኖች የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ላይ ተኩስ ከፍተው በሁለቱም ወገኖች መካከል የሰው ሕይወት መጥፋቱን ተናግረዋል። ከዚያ በኋላ ባሉት ቀናት የተለያዩ ቀበሌዎች የሰው ሕይወት መጥፋቱን እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤቶች በእሳት እንዲጋዩ መደረጋቸውን አብራርተዋል። • በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በተፈጠረ ግጭት በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ • የማንነት ጥያቄዎች የጎሉበት የአማራ ክልል ከተሞች ሰልፍ ጥር 27፣ 28 እና 29 በነባሩ ጭልጋ ወረዳ መቋሚያ ማርያም፣ ችሃ ማንጊያ፣ አማኑኤል ቀን ወጣ፣ ናራ እና አንከር አደዛ በተሰኙ ቀበሌዎች፤ ቤቶች መቃጠላቸውን እንዲሁም ጥር 29 እና 30 ደምቢያ ወረዳ ሰቀልተ ሰሃ መንጌ እና ድርማራ ቀበሌዎች ቤቶች መቃጠላቸውን እና በድርማራ ቀበሌ የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉን ጨምረው ተናግረዋል። እንደ አቶ አሰማኸን ገለፃ ትናንት ማታ በጎንደር በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ወጣቶች የከብት ማደለቢያ ላይ ቃጠሎ ደርሶ 40 የቀንድ ከብቶች ተቃጥለዋል። ቃጠሎው ከአለመረጋጋቱ ጋር መያያዝ አለመያያዙን ገና መጣራት እንዳለበትም ጨምረው አብራርተዋል። አቶ አሰማኸኝ በመቀጠል ያብራሩት፤ በምዕራብ ጎንደርም ግጭት እንደነበረና በዚህም ምክንያት በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ነው። ከዚህ በፊት የተፈጠረው ችግር መረጋጋት ቢያሳይም በቅርቡ ግን መተማ አካባቢ ችግር ተከስቶ የሰው ሕይወት ማለፉን አስረድተዋል። ''በምዕራብ ጎንደር ተከስቶ የነበረው ግጭት ወደ ሰላም እየመጣ ነው። ነገር ግን ጥር 30 በምዕራብ ጎንደር መተማ ወረዳ ግጭት ተከስቶ የአንድ ሰው ሕይወት አልፏል'' ብለዋል። • የጎንደር ሙስሊሞች እና የመስቀል በዓል • ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወልቃይትን አስመልክቶ ምላሽ ሰጡ ለመሆኑ በግጭቱ የተፈናቀሉ ሰዎች ምን እየተደረገላቸው ነው ተብለው ተጠይቀው፤ መንግሥት የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ እንደሆነ ገልፀው ማህበረሰቡ ዛሬም እርስ በእርሱ እየተደጋገፈ መሆኑንም ጠቅሰዋል። በዛሬው ዕለት ከጎንደር አርማጨሆ የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም 2 ሰዎች በመታገታቸው ምክንያት ሌሎች ላይ የማሳደድ ተግባር በመፈፀሙ መቋረጡን ተናግረዋል። የማዕከላዊ ጎንደር ዞን የፖሊስ መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ኮማንደር እንየው ዘውዴ ደግሞ ለቢቢሲ ሲናገሩ ''አማራ እና ቅማንት ለረዥም ዓመታት አብረው የኖሩ እና ወደፊትም አብረው የሚኖሩ ሕዝቦች ናቸው። ነገር ግን በመካከላቸው ሌላ ኃይል ገብቶ ደም እያቃባ ይገኛል። እሱን ለመከላከል የክልሉ ኃይል እና ሃገር መከላከያ በመቀናጀት ሥራ እየተሠራ ነው''ብለዋል። ኮማንደር እንየው ''ሌላ ኃይል'' ያሉት ቡድን የትኛው እንደሆነ እንዲነግሩን ላቀረብንላቸው ጥያቄ ''ይሄ ግልጽ ነው። ሁሉም ያውቀዋል። የአደባባይ ምስጢር ነው'' ከማለት ውጪ እሳቸው ''ኃይል'' አቶ አሰማኸኝ ደግሞ ''ጸንፈኛው ቡድን'' ያሉትን አካል በስም ከመጥቀስ ተቆጥበዋል።
news-57074348
https://www.bbc.com/amharic/news-57074348
በሩሲያ ትምህርት ቤት በተከፈተ ተኩስ ተማሪዎች እና መምህር ተገደሉ
በሩሲያ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት በተከፈተ ተኩስ ተማሪዎች እና መምህራን ተገደሉ።
በጥቃቱ የተገደሉ ተማሪዎች አሃዝን በተመለከተ የተለያዩ ዘገባዎች ቢወጡም የአከባቢው ባለስልጣናት ግን ቢያንስ 7 ታዳጊ ተማሪዎች መገደላቸውን አረጋግጠዋል። ከሟቾቹ በተጨማሪ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ልጆች ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። ፖሊስ ከሩሲያ መዲና 820 ኪ.ሜትር ርቃ በምትገኘው ታታርስታን ግዛት በደረሰው ጥቃት የተጠረጠረ አንድ ወጣት በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታውቋል። የግዛቷ ፕሬዝደንት ጥቃቱን 'አሳዛኝ’ ያሉት ሲሆን፤ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን በበኩላቸው የአገሪቱን የጦር መሳሪያ ቁጥጥር ሕግን እንደሚያጠብቁ ተናግረዋል። ስለ ጥቃቱ እስካሁን የምናውቀው በትምህርት ቤቱ ላይ ተኩስ እንደተከፈተ ፖሊስ እና የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በትምህርት ቤት አቅራቢያ በፍጥነት ነበር የደረሱት። በማሕበራዊ ሚዲያ በስፋት የተጋሩ ምስሎች ላይ ተማሪዎች እራሳቸውን ለማዳን በመስኮት ሲዘሉ ታይተዋል። አንድ የሩሲያ ቴሌቪዥን ጣቢያ ከሟቾቹ መካከል ሁለቱ ሕይወታቸው ያለፈው ከሁለተኛ ፎቅ ላይ በመስኮት በኩል ከዘለሉ በኋላ ነው ሲል ዘግቧል። የግዛቷ አስተዳዳሪ 4 ወንድ እና 3 ሴት የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው ብለዋል። አንድ መምህርም መገደሉን የግዛቷ አስተዳዳሪ ጽ/ቤት አስታውቋል። ከሟቾች በተጨማሪ 6 ተማሪዎች ለሕይወታቸው አስጊ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ ብለዋል። የአከባቢው ባለስልጣናት ጥቃቱን ያደረሰው አንድ ግለሰብ ብቻ ነው ብለዋል። “አንድ የ19 ዓመት አሸባሪ በቁጥጥር ሥር ውሏል። የጦር መሳሪያ መሸጫ መደብር ባለቤት ነው” ሲሉ የግዛቷ አስተዳዳሪ ተናግረዋል። ጥቃቱ እንደተሰማ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን የአገሪቱ ደህንነት ተቋም በሕብረተሰቡ ውስጥ ተሰራጭቶ ስለሚገኘው የጦር መሳሪያ አይነት ዝርዝር መረጃ እንዲያቀርቡላቸው ማዘዛቸውን የክሬምሊን ቃል አቀባይ ተናግረዋል። ፖሊስ ጥቃት ሳያደርስ አይቀርም የተባለው ግለሰብ የሚኖርበት አከባቢ የቤት ለቤት ፍተሻ እያደረገ ስለመሆኑ የአገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
44107374
https://www.bbc.com/amharic/44107374
ኢቦላ ለምን አገረሸ?
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኢቦላ አገርሸቷል። ነገር ግን በሽታው መቼ እና እንዴት በድጋሚ ሊከሰት ይችላል የሚለውን ለመገመት አዳጋች ነው። የተጋረጠውን አደጋ እንዴት መከላከል እንደምንችል እናውቃለን።
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሰሜን ምዕራብ አካባቢ የምትገኘው ቢኮሮ ከተማ የታየው የቫይረሱ ማገርሸት ከዚህ ቀድሞ የተከሰተውንና በምዕራብ አፍሪካ አስራ አንድ ሺህ ሰዎች ህይወት መቀጠፍን እንዲሁም ሃያ ስምንት ሺህ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙበትን አስደንጋጭና አስፈሪ ጊዜ ያስታውሰናል። በያዝነው ዓመት ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ምንም እንኳን ከሟቾቹ ሁለቱ ብቻ በቫይረሱ መያዛቸው ቢረጋገጥም የሞቱትን አሰራ ሰምንት ሰዎችን ጨምሮ ሰላሳ የሚደርሱ ተጠርጣሪዎች ተገኝተዋል። ኢቦላ ለምን አገረሸ? ባለፈው ዓመት የተከሰተው አሳዛኝ አጋጣሚ ድጋሚ እንዳያንሰራራ ምን እየተሰራ ነው? የሚለው መነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል። ኢቦላ ለምን ከቁጥጥር ውጭ ሆነ? ኢቦላ በቫይረስ ከተያዘው ሰው ሰውነት በሚወጣ በጣም አነስተኛ መጠን ባለው ፈሳሽ ሳይቀር በመተላለፉና ያልተለመዱ ምልክቶች ስላሉት ችግሩን ከቁጥጥር ውጭ ያደርገዋል። በቅርቡ ኢቦላ ያገረሸባት- ቢኮሮ የንግድ ከተማ በመሆኗ፣ በዋና ዋና ወንዞች መከበቧ እንዲሁም ድንበር አካባቢ በመገኘቷ ትኩረትን እንድታገኝ አድርጓል። ምክንያቱ ደግሞ ሰዎች የሚገኛኙበት፣ የንግድ ልውውጥ የሚያደርጉበትና እንቅስቃሴዎች የሚዘወተሩበት በመሆኑ ቫይረሱ የሚዛመትበትን እድል ስለሚያፋጥነው ነው። እንደ አውሮፓውያኑ ከ 2014-2016 በምዕራብ አፍሪካ የተከሰተው ኢቦላ መነሻው ጊኒ ውስጥ በምትገኝ ትንሽ መንደር ውስጥ ሲሆን፤ መጀመሪያ በቫይረሱ የተያዘውም እደሜው ሁለት ዓመት የሚሆነው ህፃን ነበር። በሽታው በጊኒ እንዲሁም በጎረቤቶቿ ሴራሊዮንና ላይቤሪያ በተለይ በከተሞች አካባቢ በፍጥነት ተሰራጭቶ ነበር። ዲሞክራቲክ ኮንጎ ከእነዚህ አገራት በብዙ ሺህ ማይል ርቀት ብትገኝም ልታመልጥ ግን አልቻለችም። ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ካጋጠማት አሳዛኝ አጋጣሚ በ2017 የተከሰተው የኢቦላ ማገርሸት አንዱ ነው። ከቫይረሱ ነፃ የሆኑ ሰዎች ቫይረሱ ስር ሰዶ ከማንሰራራቱ በፊት ሰዎች እንዳይያዙና እንዳይዛመት ማድረግ ይቻላል። በተፋጠናና በተቀናጀ መልኩ መስራት ከተቻለ ከመጀመሪያው የበሽታውን ስእረጭት መግታት ይቻላል። የጤና ባለሙያዎች፣ ተመራማሪዎች፣ የዓለም ጤና ድርጅትና በጎ አድራጊ ድርጅቶች ቫይረሱ ያገረሸበት አካባቢ የመጀመሪያ ምላሻቸውን እየሰጡ ነው። ቫይረሱ የሚተላለፍባቸውን መንገዶች መለየትን ቅድሚያ የሰጡት ጉዳይ ሲሆን በተቻላቸው አቅም ማንም ሰው በቫይረሱ እንዳይያዝ ተግተው እየሰሩ ነው። ኢቦላ ተገኘባቸው የተባሉ ሰዎችም በአካባቢው በሚገኝ የጤና ተቋም ህክምና እየተደረገላቸው ነው። ጭምብል በማድረግ፣ የእጅ ጓንቶችን በመጠቀም፣ ጋዎን በመልበስ ጥንቃቄ የተሞላበት እንቅስቃሴ ማድረግ ጠቀሜታው ላቅ ያለ ነው። በተጨማሪም ህብረተሰቡ በቂ የሆነ ግንዛቤ እንዲያገኝና ኢቦላን በተመለከተ ምላሽ ከሚሰጡ ቡድኖች ጋር መረጃዎችን መለዋወጥ ያስፈልጋል። የህሙማን ደም ናሙና ለምርመራ ኪንሻሳ የሚገኘው ብሄራዊ ላቦራቶሪ እንደተላከም ተገልጿል። በአውሮፓውያኑ ከ2014-16 በምዕራብ አፍሪካ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በኢቦላ ህይወታቸውን አጥተዋል ክትባቱስ? እስካሁን ኢቦላ ተገኝቶባቸዋል የተባሉ አምስት ቀጠናዎች የተለዩ ሲሆን የሞቱት ዜር በተሰኘው ቀጠና ነው። በእነዚህ ቀጠናዎች ለመጠባበቂያ የተዘጋጀው ክትባት ለድንገተኛ ክስተቶች ይውላል። በእንግሊዝና በኖርዌይ መንግሥት ድጋፍ እንደ አውሮፓውያኑ በ2016 ክትባቱ ተቀባይነት ያገኘ ቢሆንም ለሰዎች እንዲሰጥ እስካሁን ሙሉ በሙሉ ፈቃድ አልተገኘም። ይሁን እንጂ ሰዎች እንዲጠቀሙበት ለማዋል ለመጠባበቂ 300ሺህ የሚሆኑ ክትባቶች ተዘጋጅተዋል። ክትባቱ ቫይረሱ ይኖርባቸዋል ተብለው ለተጠረጠሩ ህሙማን፣ ለቫይረሱ ተጋላጭ ለሆኑ የጤና ባለሙያዎች መሰጠት እንዳለበት የዓለም ጤና ድርጅት አሳስቧል። ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የጤና ሚኒስቴር ውሳኔ ብቸኛው አማራጭ ነው። በእርግጥ በቅርቡ ላገረሸው ኢቦላ የአገሪቷ መንግሥት ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን ያሳየ ቢሆንም ብቻውን ግን ምን ማድረግ አይችልም። ዓለም አቀፍ እርዳታ፣ አፋጣኝና የተቀላጠፈ ምላሽ ከሁሉም ይጠበቃል። ኢቦላ በቀላሉ ሊጠፋ እንደሚችል ተስፋ በማድረግ የሚያጋጥሙትን እያንዳንዱን ጥቃቅን ችግሮች በመፍታት ችግሩ ስር ሳይሰድ አሁን ባለበት ደረጃ ማስቀረት ይቻላል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።
news-50703982
https://www.bbc.com/amharic/news-50703982
የዓለማችን ውቅያኖሶች ኦክስጂን እያጠራቸው ነው
የአየር ጸባይ ለውጥና የውሀ አካላት በተለያዩ ነገሮች መበከል ምክንያት በውቅያኖሶች ውስጥ የሚገኘው ኦክስጂን መጠን መቀነስ በርካታ የአሳ ዝርያዎችን ሊያጠፋ እንደሚችል ተገለጸ።
በዚሁ ዙሪያ ጥናቱ የሰሩ ተመራማሪዎች እንደሚሉት 700 ከሚሆኑ የተለያዩ የውቅያኖስ ክፍሎች ላይ በተደረገ ጥናት ውቅያኖሶቹ በእጅጉ ኦክስጂን እያጠራቸው ሲሆን በአውሮፓውያኑ ከ1960ዎቹ ጀምሮ ከፍተኛ መቀነስ ታይቷል። • ዛፎችና የአእምሮ ጤና ምን ያገናኛቸዋል? • የውሃ እጥረት ዋነኛው የዓለማችን ስጋት በዚህም ምክንያት እንደ ቱና፣ ማርሊን እና ሻርክ ያሉ የአሳ ዝርያዎች የመጥፋት አደጋ ተጋርጦባቸዋል። ወደ ውሃ አካላት የሚለቀቁ ኬሚካሎች ደግሞ ለኦክስጂን መጠን መቀነስ ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው። በተለያዩ ፋብሪካዎችና ትላልቅ እርሻዎች የሚለቀቁት እንደ ናይትሮጂን እና ፎስፈረስ ያሉ ኬሚካሎች በተለይ ደግሞ በዳርቻዎች አካባቢ ለሚገኙ አሳዎች መሞት ምክንያት ናቸው። ከዚህ በተጨማሪ የአየር ጸባይ ለውጥም ከፍተኛ ተጽዕኖ እየፈጠረ ነው። ከምን ጊዜውም በበለጠ ከፍተኛ መጠን ያለው ካርቦን ዳይኦክሳይ ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቅ ሲሆን ይህ ደግሞ ከፍተኛ ሙቀት እንዲፈጠር ያደርጋል። ውቅያኖሶችና ሌሎች ትልልቅ የውሀ አካላት ሙቀቱን ሰብስበው ይይዙታል። ሙቅ ውሀ ደግሞ በውስጡ ብዙ ኦክስጂን መያዝ አይችልም። ተመራማሪዎቹ እንደገመቱት አ.አ.አ. ከ 1960 እስከ 2010 ባሉት ዓመታት በውቅያኖሶች የሚገኘው የኦክስጂን መጠን በአማካይ 2 በመቶ ቀንሷል። ምናልባት ይህ ቁጥር ትንሽ ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን ቁጥሩ የዓለማችን አማካይ ስለሆነ ነው እንጂ በአንዳንድ ሞቃታማ አካባቢዎች እስከ 40 በመቶ ድረስ ቀንሷል። እንደ ቱና፣ ማርሊን እና ሻርክ ያሉ የአሳ ዝርያዎች በተለየ ሁኔታ ከፍተኛ የኦክስጂን መጠን በውሃ ውስጥ ይፈልጋሉ። ይህ ሁኔታ ለነዚህ የዓለማችን ህዝብ በብዛት ለሚመገባቸው አሳዎች መጥፎ ዜና ነው። • የ21ኛው ክፍለ ዘመን ነዳጅ. . . ውሃ! ትልልቅ አሳዎች በውሀ ውስጥ ለመንቀሳቀስ ከፍተኛ ሃይል የሚያስፈልጋቸው ሲሆን ያለ ኦክስጂን ደግሞ ይህ የማይታሰብ ነው። ታዲያ እነዚህ አሳዎች ኦክስጂን ፍለጋ ትልቅ ወደሚባለው የውቂያኖስ ክፍል መሸሽን እየመረጡ ነው። ሀገራት በዚሁ ውቅያኖሶችን የመበከል ስራቸው የሚቀጥሉ ከሆነ እ.አ.አ. በ 2100 የምንላቸውን አሳዎች አናገኛቸውም ማለት ነው። ይህ ደግሞ አንድ የምግብ ምንጭ ከሰው ልጆች ተነጠቀ ማለት ነው። የውቅያኖሶች አሰራር አሁንም የሰው ልጅ ሙሉ በሙሉ ተመራምሮ ያልደረሰበት እንደመሆኑ እንዲህ አይነት እክሎች ምን አይነት አደጋ ይዘው ሊመጡ እንደሚችሉ መገመት እጅግ ከባድ ነው።
news-54145139
https://www.bbc.com/amharic/news-54145139
ትግራይ፡ በክልላዊው ምርጫ ተቃዋሚዎች አንድ ወንበር ብቻ አገኙ
ባለፈው ሳምንት ትግራይ ክልል ከተካሄደው ምርጫ ተርፈው ከነበሩትና በተመጣጣኝ ውክልና እንደሚከፋፈሉ ከተገለፀው 38 የምክር ቤት መቀመጫዎች ህወሓት 37.35ቱን ማግኘቱ ተገለጸ።
በዚህም መሰረት የክልሉ ምክር ቤት ካለው 190 መቀመጫዎች ውስጥ 189ኙን በማግኘት ከአንድ መቀመጫ በስተቀር ሁሉንም መውሰዱን ምርጫ ኮሚሽነሩ መምህር ኪዳነማርያም ለጋዜጠኞች ገልጸዋል። በምርጫው ከተሰጠው አጠቃላይ 10 ሚሊዮን 840 ሺህ 159 ድምጽም ህወሓት 10 ሚሊዮን 655 ሺህ 840 የመራጮች ድምጽ በማግኘት፣ አጠቃላዩን በሚባል ደረጃ የምክር ቤቱን ወንበር ተቆጣጥሮታል። በክፍፍሉ ቀመር መሰረት 0.65 ድምጽ ያገኘው ባይቶና የተባለው ፓርቲ ቀሪዋን ብቸኛ አንድ ወንበር እንደሚወስድም ተገልጿል። በተመጣጣኝ ውክልና እንደሚከፋፈሉ ከተገለጹት 38ቱ የምክር ቤቱ መቀመጫዎች ከተሰጡት የመራጮች ድምጽ አንጻር የአንዱ ወንበር ውክልና 285,267.3 የነበረ ሲሆን ከህወሓት ውጪ ይህን ያህል ድምጽ ያገኘ ፓርቲ የለም። በምርጫው ከተሳተፉት አምስት ፓርቲዎች መካከል ክልሉን በብቸኝነት ላለፉት 30 ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ ያስተዳደረው ህወሓት 10,655,840 ድምጽ፣ ተፎካካሪ ፓርቲ ሆነው የቀረቡት አዳዲሶቹ ፓርቲዎች ባይቶና 93,495 ድምጽ፣ የትግራይ ነጻነት ድርጅት 58,779 ድምጽ፣ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ 27, 987 ድምጽ እና ዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ደግሞ 3,088 ድምጽ አግኝተዋል። የምርጫ ኮሚሽኑ እንዳስታወቀው ጳጉሜ 04/2012 ዓ.ም በተካሄደው የትግራይ ክልል ምርጫ ድምጽ ለመስጠት ከተመዘገቡት 2,789,254 መራጮች ውስጥ 2,757,495 ሕዝብ በምርጫው ላይ ተሳትፏል ተብሏል። ይህም 98.8% እንደሆነ ተመልክቷል። በተጨማሪም ድምጽ ከሰጡ መራጮች መካከልም 31,759 ድምጽ ለየትኛውም ተወዳዳሪ ሳይሆኑ የባከኑ እንደሆነ መመዝገቡን ኮሚሽኑ አሳውቋል። በመላው አገሪቱ በነሐሴ ወር ይካሄዳል ተብሎ የነበረው ምርጫ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ በተወካዮችና በፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ተወሰነ ቢሆንም፤ የትግራይ ክልል ግን በተናጠል ምረጫውን ለማካሄድ በመወሰኑ ሲያወዛግብ ቆይቶ ነበር። በዚህም መሰረት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምርጫው ሕገ ወጥና ተፈጻሚነት የሌለው እንደሆነ ከምርጫው አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባው መግለጹ ይታወሳል።
news-47650243
https://www.bbc.com/amharic/news-47650243
ግብፅ መንግሥትን ተሳደበ ያለችውን ፀሃፊ ከሰሰች
ታዋቂው ግብጻው ፀሃፊ አላ አል አስዋኒ የሃገሪቱን ፕሬዝዳንቱ፣ የጦር ሠራዊቱንና የፍትህ ሥርዓቱን ተሳድበሃል በሚል በወታደራዊ አቃቢ ህግ ተከስኩ አለ።
በአሜሪካ ኑሮውን ያደረገው አስዋኒ ክሱ ከመጨረሻ መፅሃፉ 'ዘ ሪፐብሊክ፡ አስ ኢፍ' እና ለዶቼ ቬሌ በአረበኛ ከፃፋቸው ፅሁፎች ጋር ተያያዥነት አለው ብሏል። • ግብጻዊቷ ዘፋኝ አባይ ላይ ቀልደሻል ተብላ እስር ተፈረደባት ክሱን የግብፅን ሕገ መንግሥት "በግልጽ የሻረ" ነው በማለት አውግዞታል። የአስዋኒ ታዋቂው 'ዘ ያኮቢያን ቢዩልዲንግ' የተሰኘው መፅሃፍ ከአንድ ሚሊዮን ቅጂዎች በላይ በ35 ቋንቋዎች ተሽጧል። መፅሃፉ ካይሮ የሚገኝ ጥንታዊ ህንፃን ተጠቅሞ በጊዜው በነበሩት የፕሬዝዳንት ሆስኒ ሙባረክ አስተዳደር ስር ያለችው ግብፅ ውስጥ ተስፋፍቶ ያለውን ሙስና እና የማህበረሰብ ችግር ያሳያል። 'ዘ ሪፐብሊክ አስ ኢፍ' የተሰኘው መፅሃፍ ባለፈው ዓመት የታተመ ሲሆን እ.አ.አ በ2011 ፕሬዝዳንት ሙባረክ ስልጣን እንዲለቁ ያስገድደውን የህዝብ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ላይ ያጠነጥናል። የግብፅን የመንግሥት ተቋማትን፣ ምክር ቤቱን፣ ሥገ-መንግሥቱን እና ፍርድ ቤቶቹን የሚተቸው ይህ መፅሃፉ በግብፅ እንዳይሸጥም ተከልክሏል። • ሶሪያውያን ስደተኞች በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ባሳለፈው ሳምንት ማክሰኞ ለዶቼ ቬሌ በፃፈው ፅሁፍም ላይ አስዋኒ "በወታደራዊ ፍርድ ቤት መንግሥትን በመስደብ እና በመንግሥት ላይ ጥላቻን በማነሳሳት በሚል መከሰሴን አውቄአለው። አስዋኒ "ብቸኛው የፈፀምኩት ወንጀል ቢኖር ፀሃፊ መሆኔ፣ ሃሳቤን በነፃነት መግለፄና [ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ] ሲሲም ቢሆኑ መተቸት በሚገባቸው በመተቸቴ ነው" ብሏል። ይህን የተናገረው እ.አ.አ በ2013 በዲሞክራሲያዊ ምርጫ የተመረጠውን የሙባረክን ተከታይ መንግሥት በወታደራዊ ኃይል ከስልጣን ያባረሩትን ከፍተኛ ወታደራዊ መሪን ጠቅሶ ነው። 'ዘ ኢጂፕት ቱደይ' የተሰኘ ጋዜጣ አስዋኒ በዋናነት የተከሰሰው መጋቢት 4 ዶቼ ቬሌ ላይ በፃፈው የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ሲሲ በዋና መሠረተ ልማቶችና በሲቪል ሠራተኛ ቦታ ወታደሮችን መሾማቸውን በሚተቸው ፅሁፉ ነው ብሏል። • የወሲብ ቪዲዮ ህይወቷን ያሳጣት ወጣት አስዎኒ የተመሰረተበት ክስ የግብፅን ሕገ መንግሥት "ሃሳብንና የግል አስተያየትን የመግለፅ መብት የተጠበቀ ነው የሚለውን" አንቀፅ 65 እና ግብፅ የተስማማችበትን ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብትን የሚደነግገውን አንቀፅ 19 የጣሰ ነው። ፀሃፊው በተጨማሪም ለ"አደገኛ" የስም ማጥፋት ተጋልጫለው ብሎ፤ በዚህም በካይሮ አየር መንገድ ምንጊዜም ስሄድ እጉላላለሁ ብሏል። አስዋኒ "ወንጀሌ ሃሳቤን በነፃነት መግለፅ ከሆነ በሃሳቦቼ ኩራት ይሰማኛል" ብሏል። ብዙ የግብፅ አክቲቪስቶች ለአስዋኒ ድጋፋቸውን ያሳዩ ሲሆን የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆነው ጀማል ኢድ "አስዋኒን አከብረዋለው፤ ያደረገው ነገር ወንጀል ከሆነ ይህን የማድረግ መብቱን እደግፋለው" ብሎ ፅፏል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች እንደሚሉት ፕሬዝዳንት አልሲሲ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እስከ 60ሺህ የሚደርሱ ተቃዋሚዎችን አስረዋል። በሌላ ዜና ማክሰኞ ዕለት የግብፅ መገናኛ ብዙሃን ከፍተኛ ምክር ቤት በማህበራዊ ድረገፅ ላይ የሚገኙ ከ5ሺህ በላይ ተከታይ ያላቸው የተሳሳተ መረጃና ሰዎች ህግ እንዲተላለፉ የሚያነሳሱ አካውንቶችን እንዲዘጋ ስልጣን ተሰጥቶታል። አካውንቶችን እንዲከታተል የተደረገው አካልም የማህበራዊ ድረገፅ ባለቤቶቹን እስከ 14 500 የአሜሪካ ዶላር የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሳይጠብቅ መቅጣት ይችላል።
news-46792636
https://www.bbc.com/amharic/news-46792636
በጥዋት ከእንቅልፍ መነሳት ውጤታማ ያደርጋል?
ሁላችንም በተለምዶ የምናደርገው አልያም ብዙ ሰዎች የሚነግሩን በጊዜ ተኝቶ በጠዋት መነሳት ውጤታማ እንደሚያደርግ ነው።
የታዋቂው የስልክ አምራች አፕል ዋና ስራ አስኪያጅ ቲም ኩክ ከእንቅልፉ ሌሊት 9፡45 ሲሆን የሚነሳው፤ የፊያት መኪና አምራች ድርጀት ሃላፊ ደግሞ 9፡30 ነው ከአልጋው የሚወርደው። ነገር ግን አንዳንድ ውጤታማ የሆኑ ሰዎች በጠዋት መነሳት ስለሚወዱ፤ ሁሉም ውጤታማ ሰዎች ይህንን ይከተላሉ ማለት አይደለም። ምናልባትም ልዩነቱን ሊፈጥር የሚችለው በጠዋት ተነስቶ እንቅስቃሴ ማድረግ፣ የቀኑን ውሎ አስቀድሞ ማቀድ፣ ቁርስ በትክክል መመገብና በመሳሰሉት ሊሆን ይችላል። • እንቅልፍ እንዲህ ጠቃሚ ነገር ኖሯል? • "ካልሲ ምን ያደርጋል?" አይንስታይን በቅርቡ የተሰራ አንድ ጥናት እንሚያሳየው ግን 50 በመቶ የሚሆነው የዓለማችን ህዝብ በጠዋት መነሳትም በጊዜ መተኛትም ላይ እምብዛም ሲሆን በሁለቱ መካከል የሚቀመጥ ነው። ከአራት ሰዎች አንዱ በጠዋት መነሳት የሚወድ ሲሆን ከሌሎች አራት ሰዎች መካከል ደግሙ አንዱ አምሽቶ መተኛት የሚወድ ነው። ጥናቱ እንደጠቆመው በጠዋት የሚነሱ ሰዎችና አምሽተው በሚተኙ ሰዎች መካከል ያለው ልዩነት በቀኝ የአንጎላቸው ክፍል ውስጥ ያለው እንቅስቃሴ ነው። በጠዋት የሚነሱት ነገሮችን ማሰላሰል የሚችሉና ተባባሪዎች ሲሆኑ አምሽተው የሚተኙት ደግሞ ከፍ ያለ የፈጠራ ችሎታና ግለኝነት ያጠቃቸዋል። በጠዋት የሚነሱ ሰዎች ለራሳቸው ከፍ ያለ ግብ ማስቀመጥ የሚወዱና ስለወደፊቱ አብዝተው የሚጨነቁ ናቸው። በዚህ ዙሪያ የተሰሩ ብዜ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት የጠዋት ሰዎች ቶሎ የማይሸነፉ፣ ነገሮችን በራሳቸው የሚያከናውኑና ተስማምተው መስራች የሚችሉ ናቸው። በተቃራኒው አምሽተው የሚተኙና አርፍደው የሚነሱት ግን የድብርት ስሜት የሚስተዋልባቸውና ለመጠጥ እንዲሁም ሲጋራ ሱስ የተጋለጡ ናቸው ይላሉ። ምንም እንኳን የጠዋቶቹ ሰዎች ትምህርት ላይ ከፍ ያለ ውጤት የማስመዝገብ አቅም ቢኖራቸውም፤ አርፍደው የሚነሱት ግን ከፍ ያለ የማስታወስ ችሎታ፣ አዲስ ነገሮችን ቶሎ መላመድና አዳዲስ ሃሳቦችን ማፍለቅ ይችላሉ። የትልልቅ ድርጅቶች ሃላፊ ለመሆንና ስኬታማ ለመሆን በጠዋት መነሳት ወሳኝ ነው ብለው ያምናሉ? ከሌሊቱ 11 ሰአት ለመነሳት በስልክዎ አላርም ይሞላሉ? ይህን ከማድረግዎ በፊት እነዚህን ነገሮች ከግምት ውስጥ ያስገቡ። • ከወንበርና ከሲጋራ የቱ ይገድላል? • ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን? ሰዎች በሚመቻቸውና የመጫጫን ስሜት በማይፈጥርባቸው ሰአት ከእንቅልፋቸው መነሳት ከቻሉ በጠዋት ከሚነሱት ያልተናነሰ ውጤታማና ደስተኛ መሆን እንደሚችሉ በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የሚያስተምሩት ካታሪና ዉልፍ ይገልጻሉ። በሌላ በኩል እራስን በጠዋት እንዲነሱ ማስገደድ ላልተፈለገ የጤና እክል ሊያጋልጥም ይችላል ይላል። አንዳንድ ጥናቶች እንሚያሳዩት ደግሞ በጠዋት የመነሳትና አርፍዶ የመነሳት ልማድ 47 በመቶ የሚሆነውን የምንወርሰው ከቤተሰቦቻችን ነው። በጠዋት የመነሳት ፍላጎት እንደ ልምዳችን የሚወሰን ሲሆን ህጻናት ብዙ ጊዜ በጠዋት መነሳት ይመርጣሉ። እያደጉ ሲመጡና በተለይ ደግሞ በሃያዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ ሲሆኑ አርፍዶ ወደመነሳት ያዘነብላሉ። ወደ ሃምሳዎቹ የተጠጉት ደግሞ ተመልሰው በጠዋት መነሳትን ያዘወትራሉ። ሰዎች ስኬታማነትንና ደስተኝነትን በጠዋት ከመነሳት ጋር እንዲያያይዙት የሚገደዱት ደግሞ ትምህርትም ሆነ ስራ ብዙ ጊዜ የሚጀምሩት ከጠዋቱ 2 ሰአት ጀምሮ ባለው ጊዜ ሲለሆነ ነው። ስለዚህ በጠዋት መነሳት የሚችሉ ሰዎች ትምህርቱንም ሆነ ስራውን ከአርፋጆቹ በተሻለ የመፈጸምና ስኬታማ የመሆን እድል ሊኖራቸው ይችላል። • "በእንቅልፍ ልቤ መኪናም ሞተርም ነድቻለሁ" • ደስታን አጥብቀን ስለፈለግን ለምን አናገኘውም? በሌላ በኩል በጠዋት ከሚነሱት ጋር እኩል ለመሆንና በዚህ ፈጣን ዓለም ውስጥ ለመቆየት ሲሉ አርፍደው የሚነሱት ሰዎች ብዙ የፈጠራ ስራዎችንና አዳዲስ ሃሳቦችን እነዲያመነጩ ይገደዳሉ። ''ብዙዎቻችን በጠዋት የሚነሱ ሰዎች ንቁና ውጤታማ እንዲሁም አርፍደው የሚነሱት ደግሞ ሰነፍና አርፋጆች እንደሆኑ እየተነገረን ስለሆነ ያደግነው፤ በጠዋት መነሳትን እንፈልጋለን።'' ''ነገር ግን በጠዋት መነሳታችን ብቻ ስኬታማ አልያም የትልቅ ድርጅት ባለቤት አያደርገንም። ዋናው ነገር ከእንቅልፋችን ከተነሳን በኋላ የምንሰራው ስራ ነው'' ይላሉ በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ባዮሎጂ የሚያስተምሩት ካትሪና ዉልፍ።
42792722
https://www.bbc.com/amharic/42792722
''ወንድሜን በአምስት ጥይት በሳስተው ነው የገደሉት''
በወልዲያ ከተማ በጥምቀት በዓል ማግስት የተከሰተውን ተቃውሞ ተከትሎ የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ በርካቶች ህይወታቸውን ማጣታቸው ይታወቃል።
ገብረመስቀል ጌታቸው መንግሥት የሟቾች ቁጥር ሰባት ነው ቢልም ያነጋገርናቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ግን የሟቾችን እና የቁስለኞችን ቁጥር ከፍ ያደርጉታል። ከከተማዋ ነዋሪዎች እንደሰማነው ከሟቾቹ መካከል አዛውንቶች እና እድሚያቸው በአስራዎቹ መጀመሪያ ላይ የሚገኙ ሁለት ታዳጊዎች ይገኙበታል። ከዚህ በተጨማሪ በጥምቀት በዓል ማግስት ከተገደሉት መካከል በወልዲያ ከተማ በብረታ ብረት ሥራው የሚታወቀው ገብረመስቀል ጌታቸው ይገኝበታል። ገብረመስቀል እድሜው ወደ 35 የሚጠጋ ሲሆን ባለትዳር እና የ5 ዓመት ሴት ልጅ አባት ነበር። ገብረመስቀልን በቅርብ የሚያውቁት ጠንካራ ሰራተኛ ስለመሆኑ ይመስክሩለታል። ብረመስቀል የብረታ ብረት ድርጅት የነበረው ሲሆን በወልዲያ ከተማም የንግድ ህንጻ እየገነባ ነበር። ገብረመስቀል በተገደለበት ቀን እና አሁን ቤተሰቡ ስለሚገኘበት ሁኔታ ወንድሙን ኪዳኔ ጌታቸውን አነጋግረነው ነበር። ገብረመስቀል ጥር 12 የሚካኤል ታቦትን ሽኘቶ ሲመለስ መብራት ኃይል የሚባል ቦታ ላይ በጸጥታ ኃይሎች በተተኮሱ ጥይቶች እንደተገደለ ከቤተሰቡ ሰምተናል። ወንድሙ ኪዳኔ ''ወንድሜን አምስት ቦታ ነው በሳስተው የገደሉት። እንዳይተርፍ ነው 5 ጊዜ በጥይት የመቱት'' ሲል በምሬት ይናገራል። ኪዳኔ ዕለቱን ሲያስታውስ ''ግርግር እንደተነሳ ደጋግሜ ስልክ ደወልኩለት፤ አያነሳም። ብጠብቀውም መልሶ አይደውልም። በጣም ስለተጨነኩኝ ወደ ሆስፒታል ልፈልገው ሄድኩኝ። ''አንገቱ ላይ፣ ደረቱ ላይ፣ ሆዱ ላይ እና ብልቱ ላይ አምስት ጊዜ በጥይት የተመታ እና በደም የተሸፈነውን የወንድሜን አስከሬን ሆስፒታል ውስጥ አገኘሁ'' ይላል ሁኔታውን ሲያስታውስ። ''ማመን ነው ያቀተኝ። ወንድሜ ላይ ግፍ ነው የተፈጸመው። ገብረመስቀል አንድ ጥይት የሚበቃው ልጅ ነበር። የቤተሰቡን አንጀት ነው የቆረጡት። እናቱን ወዳጅ፤ አባቱን አክባሪ ነበር። እሱን ብቻ ሳይሆን ቤተሰቡን ነው የገደሉት። የአምስት ዓመት ሴት ልጅ አለችው አሁን የተፈጠረውን ነገር መቀበል አልቻለችም'' ሲል ኪዳኔ በቁጭት ይናገራል። ኪዳኔ እንደሚለው ገብረመስቀል ታቦት ሸኝቶ ሲመለስ መብራት ኃይል አካባቢ በነበረበት ወቅት ምንም አይነተ ረብሻ አልነበረም። ''ለምን መግደል እንዳስፈለጋቸው አላውቅም። ይህን ስላደረገ ነው የተገደለው የሚለን እንኳ አላገኘንም'' ይላል። ከአንድ ወር በፊት ሌላ ታናሽ ወንድማቸውን በህመም እንዳጡ የሚናገረው ኪዳኔ ''በሃዘን ላይ መሪር ሃዘን ነው የጨመሩብን'' ሲል ይናገራል። ''የታናሽ ወንድማችንን 40 ቀን እንኳን ሳናወጣ ነው ሃዘን ላይ እያለን ሃዘን የተጨመረብን'' ብሏል። እሁድ ዕለትም ጸጥታ አስከባሪዎች የቀብር በሥርዓቱ እንዳንፈጽም እክል ሲፈጥሩብን ነበር የሚለው ኪዳኔ ''አስክሬኑ ቅዳሜ ምሽት ወልዲያ ኪዳነምህረት ቤተ-ክርስቲያን ፍትሃት ሲደረግበት አደረ፤ ከዚያም ከኪዳነምህረት አውጥተን ለቀብር ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን ስናመራ፤ መከላከያዎች እና አድማ በታኞች ጥይት እና አስለቃሽ ጪስ በመተኮስ ለቀብር የመጣን ህዝብ ሲበትኑ ነበር'' በማለት ኪዳኔ ያስረዳል። የክልሉን ርዕሰ-መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ባለስልጣናት መኖሪያ ቤታቸው በመምጣት እንዳነጋገሯቸው የሚናገረው ኪዳኔ ''እኛም የወንድማችን ገዳይ ተለይቶ ለፍርድ ይቅረብልን። የወንድማችን ደም ፈሶ መቅረት የለበትም ስንል ነግረናቸዋል'' ይላል። የክልሉ ርዕሰ-መስተዳደር ወልዲያ ላይ ከተፈጸመው ግድያ በኋላ በሰጡት መግለጫ ጉዳዩ በጥንቃቄ ተጣርቶ ውጤቱ ለህዝብ ይፍ ይሆናል ማለታቸው ይታወሳል። ትናንት አመሻሽ ላይ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ራቪና ሻምዳሳኒ በጄኔቫ ላይ ባወጡት መግለጫ ''በኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች የሚወስዱት የኃይል እርምጃዎች እጅጉን አሳስቦናል'' ብለዋል። ኮሚሽኑ ገለልተኛ እና አድልዎ በሌለው አካል አስቸኳይ ምርመራ ተካሂዶ ጥፋተኞች ከህግ ፊት እንዲቀርቡ በማለት ባወጣው መግለጫ አሳስቧል። የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የጸጥታ ኃይሎች የሚወስዱት እርምጃ አሳስቦኛል አለ
news-53326845
https://www.bbc.com/amharic/news-53326845
“እኛ በህይወት እያለን የኢትዮጵያን መፍረስ አንፈቅድም” ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከእንደራሴዎ ለቀረቡላቸው በርካታ ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የደቡብ ክልል የተለያዩ ዞኖችን በሚመለከት ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ በክልሉ የአደረጃጀት ጉዳይን በሚመለከት ያሉ ጥያቄዎችን ለመመለስ ጥናቶች መደረጋቸውን በማንሳት አሁን ግን ጉዳዩ ተጠናቆ ፌዴሬሸን ምክር ቤት እጅ እንደሚገኝ አስታውሰዋል። "ከአሁን በኋላ ጉዳዩ የሚመለከተው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ነው" ካሉ በኋላ በአንዳንድ ዞኖች በመንግሥት ስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች ማስቸገራቸውን ገልፀዋል። "እዚህም እዚያም መጉረስ የሚፈልጉ" ያሏቸው እነነዚህ ግለሰቦች በመንግሥት መኪና [ኮብራ] ተቀምጠው ክልሉን የሚያተራምሱ አሉ በማለት አስተጠንቅቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ስለህዳሴ ግድብ በሰጡት ማብራሪያ ግድቡ ግንባታው ተጠናቅቆ ውሃ መያዝ እንደሚጀምር ተናግረው በዚህ ጉዳይ ላይ መንግሥት ወደኋላ እንደማይመለስ አረጋግጠዋል። አርቲስ ሃጫሉ ሁንዴሳ በአሰቃቂ ሁኔታ ሕይወቱ ሲቀጠፍ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት የአባይን ጉዳይ እያየ እንደነበር አስታውሰዋል። ድምጻዊ ሃጫሉን "ጀግናና ቆራጥ ታጋይ ነበር" ሲሉም አሞካሽተውታል። ከሃጫሉ ግድያ በኋላ የሚነሱ በተለያዩ ዜናዎች የሚፈለገው "የኢትዮጵያ መንግሥት ዓይኑን ከህዳሴ ግድቡ ላይ እንዲያነሳ ነው" ሲሉም ተናግረዋል። "ሰበር ዜናዎች እንሰማለን፣ ቋሚ ሰበር ዜናችን ግን አገራዊ ትልማችንን ማሳካት ነው" በማለት ከዚያ ላይ ዓይናችንን አናነሳም ብለዋል። አዳዲስ ጉዳዮችን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እያመጡ ላሉ አካላት በማለት "አገር አፍርሶ፣ ብሔርን ከብሔር አባልቶ መንግሥት መሆን አይቻልም" ሲሉም ተናግረዋል። እያባሉ መንግሥት መሆን አይቻልም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ሰው በግፍ እየገደሉ እና ንብረት እያወደሙ አገር መምራት አይቻልም ቁስሉም በአንድ ቀን አይሽርም ሲሉ አስረድተዋል። "ለጉርሻ ስንጣላ ሌላው መሶቡ እንዳይሰረቅብን" በማለት የጉዳዩን አሳሳቢነትና የሚያስፈልገውን ጥንቃቄ ገልፀዋል። አሁንም በግራ በቀኝ ሰው ለመግደልና ለሽብር የምትዘጋጁ በማለትም ቆም ብለው እንዲያስቡ አስጠንቅቀዋል። "እርግጠኛ ሆኜ የምነግራችሁ የሚሞት ይሞታል እንጂ የጀመርነው አይቆምም" በማለት መንግሥት የጀመራቸው የልማት ሥራዎችን እንደሚያስቀጥል አብራርተዋል። ከአገር ውጪ በመሆን በአገር ውስጥ ተቃውሞ እንዲካሄድ ለሚቀሰቅሱ ሰዎች ደግሞ "ከአገር ውጪ ሆኖ ተነስ ተቀመጥ ማለት ድል አምጥቶ አያውቅም ወደፊትም አያመጣም" በማለት በተለይ የሃጫሉ ሁንዴሳን ሞት ተከትሎ አመጽ መቀጠል አለበት ለሚሉ ግለሰቦችና ቡድኖች "ቢያንስ ቢያንስ የሃጫሉን መንገድ መከተል አለባችሁ" ብለዋል። ይህ ሥርዓት ነው ያልተመቸን የሚል አካል የውጊያ መድረኩ እዚህ ስለሆነ እዚህ መጥቶ የሚያሰልፈው ኃይል ፊት ለፊት ሆኖ ትግል ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉም አብራርተዋል። "መቀመጫውን እያፈረሰ ለአገረ እታገላለሁ ማለት ሞኝነት ነው" በማለትም የኦሮሞ ሕዝብ የትጥቅ ትግል ያስፈልገዋል ብዬ አላምንም ሲሉም አክለዋል። ዐብይ ኦሮሞ አይደለም የሚል ፖለቲካ በማለት ሲያብራሩም "የእኔን ኦሮሞነት ሰው የሚሰጥ የሚከለክለኝ አይደለም፤. . . ለኦሮሞ የማይጠቅም ዐብይ፣ ለአማራም አይጠቅምም፤ ለወላይታም አይጠቅም፤.... " ብለዋል። "የኦሮሞ ሕዝብ ነጻ እንዲሆን፣ እኩል እንዲሆን አምኜ ታግያለሁ" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ሌሎቹን እንዲጨቁን አስቤ አላውቅም ካሉ በኋላ "አሁን ያለው አካሄድ የኦሮሞን ድል ወደኋላ መመለስ ነው" ሲሉ አስረድተዋል። "ማንም ሰው ኢትዮጵያን እንዲያፈርስ እኛ እያለን አንፈቅድም፤ ማንም ሰው ከኢትዮጵያ በታች ነው" ብለዋል። መንግሥትን መስደብና መንቀፍ አስጠይቆ አያውቅም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስድድብ ምነክንያት ዲሞክራሲን ወደ ኋላ አንመልስም በሚል መንግሥታቸው ዝም ብሎ መቆየቱን አስረድተዋል። "አሁን በአገር ተመጣ" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ኢትዮጵያን ማፍረስ የሚቻለው መጀመሪያ እኛን ካፈረስክ በኋላ ነው" "በማለት እኛ ተቀምጠን ኢትዮጵያን ማፍረስ የማይፈቀድ መሆኑን በደንብ መገንዘብ ተገቢ ነው ሲሉ ተናግረዋል። "ኦሮሞን የሚከፋፍል ፖለቲካ፤ ኢትዮጵያን የሚከፋፍል ፖለቲካ አይጠቅምም። ኦሮሞ አንድ ነው ከሌሎች የኢትዮጵያ ወንድሞቹ ጋር ኢትዮጵያን ይገነባል" ብለዋል። እኛ በህይወት እያለን የኢትዮጵያን መፍረስ አንፈቅድም ካሉ በኋላ "ማንም ሰው ከኢትዮጵያ በታች ነው" ብለዋል።
46901925
https://www.bbc.com/amharic/46901925
ሕንድ፡ ለሴቶች የተከለከለ ተራራን የወጣችው የመጀመሪያ ሴት
ዳንያ ሳናል የተባለች ሕንዳዊት ለወንዶች ብቻ የተፈቀደ ተራራ በመውጣት ግንባር ቀደም ሆናለች።
ዳንያ ሳናል ተራራውን የወጣች የመጀመሪያ ሕንዳዊት ናት ተራራው አግስታይኮዳም ይባላል። ተራራው 6,128 ጫማ (1,868 ሜትር) ርዝመት አለው። ይህን ተራራውን መውጣት እንደ ሀይማኖታዊ ጉዞ ይቆጠራል። • ቻይናና ህንድ በውሃ ምክንያት ተፋጠዋል የሕንድ ፍርድ ቤት በቅርቡ ሴቶች ተራራውን እንዲወጡ ከመፍቀዱ በፊት፤ ተራራው ጫፍ መድረስ የተፈቀደው ለወንዶች ብቻ ነበር። ዳንያ ተራራውን በመውጣት ታሪክ ብትሰራም፤ የሂንዱ እምነት ተከታይ የቀዬው ነዋሪዎች ሴቶች ተራራውን እንዲወጡ በመፈቀዱ ደስተኛ አይደሉም። የ38 ዓመቷ ዳንያ ለቢቢሲ እንደተናረችው፤ ተራራውን ስትወጣ ሊያስቆማት የሞከረ ሰው አልነበረም። የመብት ተሟጋቾች የዳንያ ጉዞ ለሴቶች መብት መከበር የሚያደርጉት ትግል መገለጫ መሆኑን ተናግረዋል። • የሕንድ 21 ሚሊዮን 'ያለተፈለጉ' ሴት ልጆች ሴቶች ተራራውን መውጣት እንዲፈቀድላቸው የድጋፍ ፊርማ አሰባስበው ወደ ሕንድ ፍርድ ቤት ያቀኑ ሴቶች ደስታቸውን ገልጸዋል። ከሴቶቹ አንዷ ዲቫያ ዲቫክራን "የሴቶችን ጭቆና ለማስቆም አንድ ርቀት ወደፊት ተራምደናል" ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች። በሕንዷ ካርላ የሚገኘው አግስታይኮዳም ተራራ ከአካባቢው ተራሮች በርዝመት ሁለተኛው ነው። የአካባቢው ተወላጆች ሴቶች ተራራውን እንዲወጡ መፈቀዱ 'እምነታችንን ይጻረራል' ቢሉም ፍርድ ቤቱ አቤቱታቸውን ውድቅ አድርጎታል። • በምዕራብ ኢትዮጵያ ሕንዳውያን የግንባታ ሠራተኞች ታገቱ ዳንያ ተራራውን እየወጡ ከነበሩ 100 ወንዶች ብቸኛዋ ሴት ነበረች። በቀጣይ ሳምንታት የእሷን ፈለግ በመከተል ወደ 100 ሴቶች ተራራውን ለመውጣት ተመዝግበዋል።
49822025
https://www.bbc.com/amharic/49822025
"የእንጀራ አባቴ ሁለት ታዳጊዎችን ገደለ፤ እኔ ግን ገዳዮችን የሚጠቁም ካርታ ሠራሁ"
የሸርሊ ሙዲ የልጅነት ሕይወት በስቃይ የተሞላ ነው። ወላጅ እናቷ ያለ ርህራሔ ስትደበድባት ከቤቷ መጥፋትን አማራጭ ብታደርግም፤ የአውስትራሊያ የደህንነት ኃላፊዎች ወደ እናቷ ዘንድ ይመልሷት ነበር።
ሸርሊ ሙዲ እናቷ ስትደበድባት፣ እሷ ስትኮበልል፣ ኃላፊዎች ወደ እናቷ ሲመልሷት፣ ዳግመኛ እናቷ ስትደበድባት ዓመታት ተቆጥረዋል። በሰቆቃ የተሞላ ልጅነት ምን እንደሚመስል ሸርሊ ጠንቅቃ ብታውቅም፤ እጅግ የከፋ ነገር የተከሰተው እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ1990 ነበር። በወቅቱ የሸርሊ የእንጀራ አባት የዘጠኝ ዓመት ታዳጊን ጠልፎ፣ በአሰቃቂ ሁኔታ ደፍሮ፣ ታዳጊዋን ገድሏል። ስቴሲ-አን ትሬሲ የተባለችው ታዳጊ አስክሬን የተገኘው በቆሻሻ መጣያ ላስቲክ ውስጥ ነበር። የሸርሊ የእንጀራ አባት ቤሪ ሀድሎው የዘጠኝ ዓመቷን ታዳጊ ሲገድል የ18 ዓመት ወጣት ነበረች። ሸርሊ በወቅቱ ከእናቷ ቤት ወጥታ ሥራ ይዛ ነበር። ታናሽ እህቷ ኬረን ችግር ውስጥ እንደሆነች ስትነግራት ግን ሸርሊ ሥራውን ትታ ወደ ቤት ለመመለስ ወሰነች። • "አትግደሉን!"፡ የቱርክ ሴቶች • "ደላላው ወደ ቤቱ ወሰደኝ፤ በዚያው ቀን አስገድዶ ደፈረኝ" ቤሪ ድሎው በተከሰሰበት ወንጀል ጥፋተኛ ተብሏል "እናቴ ፍርድ ቤት ውስጥ ድጋፍ ስትሰጠው ማየት ያሳዝናል" የእንጀራ አባቷ ወደ ቤት እየወሰዳት ሳለ፤ አንዲት ታዳጊ እንደጠፋች ነገራት። "ይህንን ብሎኝ በነጋታው ልጅቷን ይፈልጉ የነበሩ ሰዎችን ማገዝ ጀመረ። በአደጋ ጊዜ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የሚሰጡ ግለሰቦች የሚለብሱትን የደንብ ልብስ አድርጎ ታዳጊዋን የሚያፈላልጉ ሰዎችን ተቀላቀለ።" ብዙም ሳይቆይ ፖሊሶች የቤታቸውን በር አንኳኩ። የእንጀራ አባቷም በቁጥጥር ሥር ዋለ። የሸርሊ እናት ሊዮኒ ባለቤቷን ስትደግፍ፤ ሸርሊ ግን እንጀራ አባቷን ተቃውማ ለምስክርነት ቆመች። "እናቴ ፍርድ ቤት ውስጥ ድጋፍ ስትሰጠው ማየት ያሳዝናል" በማለት ወቅቱን ትገልጻለች። እናቷ እና የእንጀራ አባቷ ምንም እንዳልተፈጠረ የታዳጊዋ የቀብር ሥነ ሥርዐት ላይ ተገኝተው እንደነበረ ስታስታውስ ጥልቅ ሀዘን ይሰማታል። • የሴቶች ብቻ መጓጓዣዎች ትንኮሳን ይቀንሳሉ? • የተነጠቀ ልጅነት ስቴሲ-አን ትሬሲ ተደፍራ የተገደለችው በዘጠኝ ዓመቷ ነበር የሸርሊ የእንጀራ አባት ስቴሲ-አንን ከመግደሉ በፊት የሌላ ህጻን ሕይወትም ቀጥፎ ነበር። ሳንድራ ቤከን የተባለች የአምስት ዓመት ታዳጊ ጠልፎ፣ ደፍሮ፣ ገድሏታል። ግለሰቡ ይኖር የነበረው በሁለቱ ታዳጊዎች ቤት አቅራቢያ ነበር። የአምስት ዓመቷን ታዳጊ በመግደሉ ከታሠረ በኋላ የእሥር ጊዜውን ሳይጨርስ ተለቅቆ ነበር። ከእሥር በተለቀቀበት ወቅት የዘጠኝ ዓመቷን ታዳጊ ገድሏል። "ከእሥር መለቀቅ አይገባውም ነበር" ትላለች ሸርሊ። እናቷ ይህንን ግለሰብ ወደ ቤቷ ማስገባቷን እንዲሁም መደገፏን ስታስብ ነገሩ የበለጠ ያስቆጣታል። ሸርሊ አሁን 48 ዓመቷ ሲሆን፤ እናቷን ለመጨረሻ ጊዜ ያየቻት የ21 ዓመት ወጣት ሳለች ነበር። የእንጀራ አባቷ እሥር ላይ እያለ ሞቷል። በአምሰት ዓመቷ የተገደለችው ሳንድራ ቤከን "የስቴሲ-አን ሞት እንደሚዘነጋ ሳስብ ያናድደኛል" ሸርሊ የእንጀራ አባቷ ከታሠረ በኋላ መልካም ሕይወት ለመምራት እንዳዳገታት ትናገራለች። ሕይወቷ መስመር መያዝ የጀመረው ትምህርቷን ጨርሳ ጋዜጠኛ ስትሆን ነበር። "ስቴሲ-አንን ሳላስታውሳት አድሬ አላውቅም፤ ስለሞቷ ሳስብ ጥፋተኛነት ይሰማኛል" የጥፋተኛነት ስሜቷ ወደ ቁጣ ተሸጋገረ። አንዳች ነገር ማድረግ እንደሚገባትም ታስብ ጀመር። በትርፍ ጊዜዋ ወሲባዊ ጥቃት ደርሶባቸው ሕይወታቸው ያለፈ ሴቶች እና ህጻናትን መረጃ በመሰብሰብ 'አውስትራሊያን ፌሚሳይድ ኤንድ ቻይልድ ዴዝ ማፕ' መሰረተች። 'አውስትራሊያን ፌሚሳይድ ኤንድ ቻይልድ ዴዝ ማፕ' በጉግል ላይ የሚገኝ ካርታ ነው። ከ1880ዎቹ አንስቶ አውስትራሊያ ውስጥ ወሲባዊ ጥቃት ደርሶባቸው የሞቱ ህጻናት እና ሴቶችን ያሳያል። "የስቴሲ-አን ሞት እንደሚዘነጋ ሳስብ ያናድደኛል" ትላለች። ሕይወታቸው የተቀጠፈ ህጻናት እና ሴቶች እንደዋዛ እንዳይረሱ ካርታው እንደሚረዳም ታምናለች። በአገሪቱ የተለያዩ ግዛቶች የተገደሉ ሴቶች በካርታው ላይ በሮዝ የልብ ምልክት ተወክለዋል። አንድ ሰው እያንዳንዱን የልብ ምልክት በመጫን ስለሴቶቹ ማንነት ማወቅ ይችላል። ስለ ጥቃቱ የተጻፉ ዘገባዎችም ይገኛሉ። • ዩክሬናዊቷ የምክር ቤት አባል ከደረሰባት የአሲድ ጥቃት በኋላ ሕይወቷ አለፈ • በጃፓን የሴቶችን መቀመጫ የሚጎነትሉ ወንዶችን ለመከላከል ሥውር ማኅተም ተዘጋጀ ከ1880ዎቹ አንስቶ አውስትራሊያ ውስጥ ወሲባዊ ጥቃት ደርሶባቸው የሞቱ ህጻናት እና ሴቶችን የሚያሳየው ካርታ "ሁሉም አገር ወታደሮቹን የሚዘክርበት ቀን አለው። ጥቃት ደርሶባቸው የሞቱ ግን ይረሳሉ። ጥቃት የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ማሳየት እፈልጋለሁ። ሴቶችም፣ ወንዶችም እንዲሁም ህጻናትም ጭምር ጥቃት የሚደርስባቸው በወንዶች ነው።" አውስትራሊያ ውስጥ በአንድ ሳምንት በአማካይ አንድ ሴት በአጋሯ ወይም በቀድሞ የፍቅር ጓደኛዋ ትገደላለች። ሸርሊ በካርታው የመዘገበችው የመጀመሪያ ታሪክ የስቴሲ-አን ሲሆን እስካሁን የ1,880 ሰዎች ታሪክ አካታለች። ሸርሊ በ20ዎቹ እድሜ ሳለች በእናቷ ድብደባ ይደርስባት የነበረው ሸርሊ ካርታውን የሠራችው ከሕይወት ተሞክሮዋ በመነሳት ነው። ካርታው በሴቶች እና በህጻናት ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለማስቆም ከጀመረቻቸው ንቅናቄዎች አንዱ ነው። ካርታው በ12 ወር ብቻ 500,000 ጊዜ ታይቷል። ሸርሊ ንቅናቄውን የምታከናውነው ያለመሰናክል አይደለም። ብዙዎች እንደሚገሏት፣ እንደሚደፍሯት ይዝቱባታል። ከዚህ በፊት ፈረሷ ተገሏል። ውሻዋም ተመርዞ ነበር። ፖሊሶች ምርመራ እያደረጉ ሲሆን፤ በዋነኛነት የሚጠረጥሩት በአቅራቢያዋ የሚኖሩ ወንዶችን ነው። "ካርታው ጥቃቱ ምን ያህል ስር የሰደደ እንደሆነ ስለሚያሳይ ወንዶቹ ካርታውን ማጥፋት ይፈልጋሉ" ትላለች። ከዚህ በተቃራኒው ሸርሊ አውስትራሊያ ውስጥ ለከፍተኛ የጋዜጠኞች ሽልማት ታጭታለች። "እውቅና ማግኘት ደስ ይላል" ስትል የተሰማትን ትገልጻለች።
news-48591412
https://www.bbc.com/amharic/news-48591412
ህንድ ውስጥ ህፃኗን ደፍረው የገደሉ በእድሜ ልክ እስራት ተቀጡ
በህንድ በምትተዳደረው ካሽሚር ግዛት ውስጥ የስምንት አመት ልጅ ደፍረው፣ አሰቃይተው የገደሏት ሶስት ግለሰቦች የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዋል።
ከዚህ በተጨማሪ መረጃ አደባብሰው አጥፍተዋል የተባሉ ሶስት ፖሊሶች በአምስት አመት እስር እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ወስኗል። ከአርብቶ አደር ቤተሰብ የተወለደችው ህፃኗ ካቱዋ ከተማ አካባቢ በሚገኝ ጫካ ውስጥ ተገድላ የተገኘችው ባለፈው አመት ነበር። የልጅቷ መገደል በከፍተኛ ሁኔታ የሚዲያ ሽፋን ያገኘው የሂንዱ ቀኝ ክንፍ አክራሪዎች በወንጀሉ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን እስር ተቃውመው ሰልፍ በማድረጋቸው ነበር። •የተደፈረችው የ3 ዓመት ህፃን በአስጊ ሁኔታ ትገኛለች የመንግሥት የቀድሞ ኃላፊን ጨምሮ አራት ፖሊሶችና አንድ እድሜው ያልደረሰ ህፃን ልጅ በአጠቃላይ ስምንት ግለሰቦች ተጠርጥረው ተይዘው ነበር። አንደኛው ግለሰብ በነፃ ሲለቀቅ የህፃኑ ጉዳይ ለብቻ እንደሚታይ ተዘግቧል። ሁሉም ከወንጀሉ ነፃ እንደሆኑ ክደው ነበር። •ደሴ፡ የሰባት ዓመት ህፃን ገድሏል በተባለው የእንጀራ አባት ምክንያት ቁጣ ተቀሰቀሰ የልጅቷ ጉዳይ በከፍተኛ ሁኔታ ሽፋን ከማግኘቱ አንፃር አገሪቷንም ከአስራ ሁለት አመት በታች ለሚደፈሩ ህፃናት የሞት ፍርድን የሚደነግግ አዲስ ህግ እንድታሳልፍ አድርጓቷል። ነገር ግን የሞት ፍርዱ የመጨረሻ ውሳኔ የሚወሰነው በዳኞቹ ይሆናል። በባለፈው አመት ጥር ወር ላይ የጠፋችው የስምንት አመቷ ህፃን ከሶስት ሳምንት በኋላ ስትገኝ ሰውነቷ በማይሆን ሁኔታ ነበር። እንደ ወንጀል መርማሪዎች ከሆነ ህፃኗ በአካባቢው በሚገኝ የእምነት ቦታ ላይ በሚገኝ ቦታ ማደንዘዣ እየተሰጣት እንደቆየች ነው። ክሱ እንደሚያሳየው ለቀናት የተደፈረች ሲሆን፤ ከመገደሏም በፊት በከፍተኛ ሁኔታ አካላዊ ድብደባ እንደደረሰባት ነው። ህፃኗ ኢላማ የተደረገችው በአካባቢው የሚገኙ የጉጃር ጎሳዎችን ከአካባቢው ለቀው እንዲወጡ ለማሰገደድ እንደሆነም ተገልጿል። •የተነጠቀ ልጅነት •"በወንድሜ ለአምስት ዓመታት ተደፍሬአለሁ" በህንድ በየደቂቃው አስራ አምስት ሴቶች እንደሚደፈሩ ከሶስት አመት በፊት የወጣ መረጃ የሚያሳይ ሲሆን በተለይም በህፃናት ላይ የሚደርስ ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው። የቢቢሲ ጊታ ፓንዲ ከደልሂ እንደገለፀችው ህንድ በአለም ላይ በህፃናት በሚደርስ ወሲባዊ ጥቃት አንደኛ ብትሆንም ጉዳዩ ችላ የተባለና ሪፖርት የማይደረጉ ጥቃቶችም ከፍተኛ ሊሆኑ እንደሚችሉ ነው። የቢቢሲዋ ዘጋቢ ዲቭያ አርያ የህፃኗን እናት ባናገረችበት ወቅት የህፃኗን እናት ሳገኛት ከትልቋ ልጇና ከሌሎች ቤተሰቦች ጋር ተሰባስባ ነው። ፍየልና በጎቻቸው በአካባቢያቸው የሚገኘውን ሳር እየጋጡ የነበረ ሲሆን እኔ ሳገኛቸው ፍርዱን አልሰሙም ነበር። የስድስቱንም የፍርድ ውሳኔ ለእናቷ ስነግራት ምርር ብላ አልቅሳ ይህንን የምስራች ስላበሰርኳት መረቀችኝ። ፍርድ ቤቱ የሚገኝበት ቦታ ለመሄድ አቅማቸው ስለማይፈቅድ ባሉበት ቦታ በተስፋ እየጠበቁ ነበር። "በፍትህ የማምን ሰው ነኝ እናም አምላክም ጥንካሬውን ስጠኝ" ብላለች በተለይም ለልጃቸው ህይወት በዋነኝነት ተጠያቂ ያሏቸውን ሁለቱን ግለሰቦች የሞት ፍርድ ካልተፈረደባቸው ይግባኝ እንደሚሉ ተናግራ ነበር "ለልጃችን ፍትህ እስከምናገኝ እኔም ሆነ ባለቤቴ እህልም ሆነ ውሃ አንቀምስም" ብላለች የ15 አመቷ የህፃኗ ታላቅ እህት በበኩሏ እሷም ሆነ የእድሜ እኩዮቿ የሂንዱ እምነት ተከታይ ወንዶችን በመፍራት ከትልቅ ሰው ጋር ካልሆኑ ብቻቸውን የትም እንደማይሄዱ ተናግራለች።
news-47067653
https://www.bbc.com/amharic/news-47067653
ሳዑዲ አረቢያ የጸረ-ሙስና ዘመቻዋ መጠናቀቁን አስታወቀች
ሳዑዲ አረቢያ ከአንድ ዓመት በፊት ጀምሬ ነበረ ያለችውን የፀረ-ሙስና ዘመቻ አጠናቅቄያለሁ ስትል አወጀች።
ሳዑዲ ወደ 200 የሚጠጉ ልዑሎችን፣ ሚንስትሮችን፣ ባለሃብቶችን ሪያድ በሚገኘው ባለ 5 ኮከብ ሆቴል ውስጥ በቁጥጥር ሥር አቆይታ ነበር። ከ14 ወራት በፊት ተጀምሮ በነበረው የፀረ-ሙስና ዘመቻ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ቢሊየነር አሊ-አላሙዲንን ጨምሮ በመቶዎች ሚቆጠሩ የንጉሣዊያን ቤተሰብ አባላት እና ቢሊየነር ነጋዴዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ነበር። የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት 100 ቢሊየን ዶላር በጥሬ ገንዘብ እና በቁስ መልክ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ሰዎች መሰብሰቡን አስታውቋል። የባህር ሰላጤዋ ንጉሣዊ ግዛት አስተዳዳሪዎች እንደሚሉት ከሆነ በቁጥጥር ሥር ውለው ከነበሩት 87 ግለሰቦች የቀረበባቸውን ክስ በማመናቸው ከመግባባት ላይ ተደርሷል። • 'ለሼህ አላሙዲ መፈታት የጠቅላይ ሚንስትሩ አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነበር' 8ቱ ደግሞ የቀረበባቸውን ክስ ስላላመኑ ጉዳያቸው ለአቃቤ ሕግ ተላልፎ ተሰጥቷል። 56 ሰዎች ጉዳይ ደግሞ ውሳኔ ያላገኘ የወንጀል ክስ ስላለባቸው ጉዳያቸው አልተጠናቀቀም ተብሏል። የሳዑዲ መንግሥት ያካሄደውን የፀረ-ሙስና ዘመቻን ተከትሎ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል ሼህ መሐመድ ሁሴን አሊ-አላሙዲ ከቀናት በፊት ከእስር መለቀቃቸው ይታወሳል። • ስለ ጀማል ኻሾጂ አሟሟት እስካሁን የምናውቃቸው እውነታዎች ሳዑዲ ወደ 200 የሚጠጉ ልዑላንን፣ ሚንስትሮችን እና የንግድ ኃላፊዎችን ሪያድ በሚገኘው ባለ 5 ኮከቡ ቅንጡ 'ዘ ሪትዝ ካርልተን' ሆቴል ውስጥ በቁጥጥር ሥር አቆይታ ነበር። የጸረ-ሙስና ዘመቻው በልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሰልማን ነበር የተጀመረው የፀረ-ሙስና ዘመቻው የተጀመረው ተጽዕኖ ፈጣሪነታቸው እየጨመረ በመጣው በልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሰልማን ነበር። ልዑል አልጋ ወራሹ የሳዑዲ ጋዜጠኛ ጀማል ኻሾግጂ በኢስታንቡል የሳዑዲ ቆንስላ ውስጥ መገደሉን ተከትሎ ከፍተኛ ጫና ውስጥ ወድቀው ነበር።
news-56121977
https://www.bbc.com/amharic/news-56121977
በሞቃዲሾ ቤተ መንግሥት አቅራቢያ ጥቃት መፈጸሙ ተነገረ
ታጣቂዎች ሞቃዲሾ ውስጥ ለሚገኘው ቤተ መንግሥት ቅርብ በሆነ አንድ ሆቴል ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን የሶማሊያ መንግሥት ተገለፀ።
የአገሪቱ የደኅንነት ሚኒስትር ዛሬ ማለዳ በሰጡት አጭር መግለጫ ላይ ጥቃቱ ከሽፏል ብለው ነበር። ዛሬ ማለዳ በሞቃድሾ በሚገኘው አደን አዴ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በረራ መቋረጡን ቢቢሲ አረጋገጠ። በአውረሮፕላን ማረፊያው አቅራቢያ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር የተዘገበ ሲሆን፣ ዛሬ ጠዋት ወደ ዋና ከተማዋ በረራ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጉዞ መሰረዙን የአውሮፕላን ማረፊያው የውስጥ ምንጮች ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ትናንት ምሽት ጥቃቱ በተፈፀመበት ስፍራ አቅራቢያ የሚኖሩ ሰዎች እንደተናገሩት ትናንት ምሽት ከባድ የመሳሪያ ተኩስ ሰምተው ነበር። ይህ ጥቃት የተፈፀመው የሶማሊያ ተቃዋሚዎች የፕሬዝዳንት አብዱላሂ ፎርማጆ የሥልጣን ዘመን ማብቃትን ምከንያት በማድረግ ተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ማቀዳቸውን ከተሰማ ከሰዓታት በኋላ ነው። የፕሬዝዳንት ፎርማጆ የሥልጣን ዘመን ያበቃው ባለፈው ሳምንት ሲሆን ይህም አገሪቷን የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ከትቷል። ፕሬዝዳንቱ ከአምስት የክልል ፕሬዝዳንቶች ጋር አገሪቱ ከገባችበት አጣብቂኝ እንዴት መውጣት እንደምትችል ምክክር ያደርጋሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው። የመንግሥት ወታደሮች እና ለዕጩዎች ታማኝ የሆኑ ታጣቂዎች ትናንት ምሽት ለቤተመንግሥቱ ቅርብ በሆነው ማይዳ ሆቴል አካባቢ ነበር የተኩስ ልውውጥ ያደረጉት። በዚህ ሆቴል ውስጥ ሁለት የአገሪቱ የቀድሞ ፕሬዝዳንቶች፣ ሼክ ሻሪፍ እና ሀሰን ሼክ ይገኙ ነበር። የፌደራል መንግሥቱ እና የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ጥቃቱን በሚመለከት እርስ በእርስ እየተወነጃጀሉ ነው። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ ለጥቃቱ የፌደራል መንግሥቱን ተጠያቂ ያደረጉ ሲሆን፣ ዜጎች በሰላም ተቃውሟቸውን ለመግለጽ በሚዘጋጁበት ወቅት የሥልጣን ዘመናቸው ያበቃው ፕሬዝዳንት "ከዜጎች ጋር ደም ለመቃባት ማሰባቸው" ያሳዝናል ብለዋል። ለዚህ ውንጀላ ምላሽ የሰጡት የአገሪቱ ደኅንነት ሚኒስትር ጥቃቱ የተፈፀመው በፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተወዳዳሪ እጩዎች ነው ብለዋል። አክለውም የመንግሥት ወታደሮች ጥቃቱ ምላሽ መስጠታቸውንና መከላከላቸውን ገልፀዋል። በአሁን ሰዓት ሞቃዲሾ መንገዶች ዝግ ሲሆኑ፣ በአውራ ጎዳናዎችም ልዩ ስልጠና የወሰዱ ወታደሮች ተሰማርተው ጥበቃው ተጠናክሯል። ተቃዋሚዎች ዛሬ በከተማዋ ጠርተውት የነበረውን የተቃውሞ ሰልፍ የሶማሊያ ብሔራዊ ወታደራዊ ኃይል አባላት ተኩስ ስለከፈቱባቸው እንዲቋረጥ አድርገዋል። ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ ቀጣይ እርምጃቸውን ለማስታወቅ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የሥልጣን ዘመናቸው ያበቃውን ፕሬዝዳንት ፎርማጆን ከሥልጣን እንዲወርዱ ጠይቀዋል። በትናንትናው ምሽት ጥቃት ምን ያህል ሰው ጉዳት እንደደሰበት የታወቀ ነገር የለም። በሶማሊያ የፖለቲካ ውጥረቱ እና ቀውሱ እየከፋ ይሄዳል የሚል ስጋት በበርካቶች ዘንድ እየተስተዋለ ነው። የሶማሊያ ፕሬዝዳንት አራት ዓመት የሥልጠና ዘመን ያበቃው ባለፈው ሳምነት ሲሆን ተቃዋሚዎች ከአሁን በኋላ ለፕሬዝዳንቱ እውቅና እንደማይሰጡ ተናግረዋል። መንግሥት በበኩሉ አዲስ አስተዳዳር እስኪመረጥ ድረስ ፕሬዝዳንቱ ስልጣናቸው ላይ ይቆያሉ ብሏል። አዲሱ አስተዳደር መቼ ይመረጣል የሚለው ግን የታወቀ ነገር የለም።
news-47851138
https://www.bbc.com/amharic/news-47851138
በሰሜን ሸዋ በተከሰተ ግጭት ህይወት ጠፍቷል ንብረት ወድሟል
ቅዳሜና እሁድ በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ባጋጠመ ግጭት ሰዎች መሞታቸውንና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተነገረ።
በባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ተከስቶ ውጥረት ቅዳሜ እለት ተቀሰቅሶ እሁድም በቀጠለው ግጭት የዘጠኝ ሰዎች ህይወት መጥፋቱንና በርካቶች መቁሰላቸውን የአጣዬ ከተማ ከንቲባ አቶ ጌታቸው በቀለ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። • አወዛጋቢው ግጭት በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ከንቲባው ጨምረውም በግጭቱ የታጠቁ ኃይሎች መሳተፋቸውንና የዘረፋ ድርጊትም ተከስቶ እንደነበር ተናግረው ክስተቱ ከክልሉ ልዩ ኃይል አቅም በላይ በመሆኑ የሃገር መከላከያ ሠራዊት እንዲገባ መደረጉንም አመልክተዋል። ግጭቱ ከአጣዬ ባሻገር በካራቆሬ፣ በማጀቴና በዙሪያቸው ባሉ አካባቢዎች መከሰቱን የተናገሩት ነዋሪዎች በቡድን የተደራጁ ታጣቂዎች በድርጊቱ ተሳታፊ እነደሆኑም ተናግረዋል። በጥቃቱ በሰው ህይወት ላይ ከደረሰው ጉዳት ባሻገር "በቤተ እምነቶች፣ በግለሰብ መኖሪያና በንግድ ተቋማት ላይ" ጥቃት መፈጸሙን የአማራ መገናኛ ብዙሃን ያናገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል። • በአፋር ክልል በተፈጸመ ጥቃት የሰው ህይወት መጥፋቱ ተሰማ የአማራ ክልል የሰላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ ምክትል ኅላፊ ኮሎኔል አለበል አማረ እንደተናገሩት ከእሁድ ከሰዓት በኋላ ጀምሮ የፀጥታ ኃይሎች ወደ አካባቢዎቹ በመግባታቸው ሁኔታዎች መረጋጋታቸውን ተናግረዋል። ኅላፊው የፀጥታ ጨምረውም በተደራጀ ሁኔታ በመታጠቅ የሕዝብን ሰላም እያደፈረሰ ያለውን ቡድን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር የተቀናጀ ሥራ እንደሚከናወንም ገልጸዋል። በግጭቱ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በየአካባቢው በሚገኙ የጤና ተቋማት ህክምና እንዲያገኙ እየተደረገ ሲሆን ከፍተኛ ህክምና የሚያስፈልጋቸውንም ወደሌሎች አካባቢዎች እንደተወሰዱ ተገልጿል። • የዐቢይ ለውጥ፡ በመስቀለኛ መንገድ ላይ? የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አምባቸው መኮንን (ዶ/ር) እሁድ አመሻሽ ላይ በሰጡት መግለጫ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ባጋጠሙ ግጭቶች በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ በደረሰው ጉዳት ማዘናቸውን ተናግረዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም የግጭቱን ምክንያት እና ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦችን በተመለከተ በማጣራት ለሕዝቡ ይፋ እንደሚደረግ ተናግረዋል። የአካባቢውን ሰላም ወደነበረበት ለመመለስ አመራሮች ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር እየሠሩ መሆኑን አመልክተው፤ በቀጣይም ከፌደራልና ከክልል የፀጥታ አካላት ጋር እንደሚሠራ ገልጸዋል።
57291563
https://www.bbc.com/amharic/57291563
ዛምቢያ ለዕድሜ ልክ እስረኞች የሁለት ሳምንት ዕረፍት ፈቀደች
በዛምቢያ የዕድሜ ልክ እስረኞች ተገምግመው "ጥሩ ሥነ ምግባር" ካሳዩ ቤተሰቦቻቸውን ለመጎብኘት የሁለት ሳምንት ዕረፍት ማግኘት ይጀምራሉ፡፡
በፕሬዚዳንት ኤድጋር ሉንጉ በተፈረመው አዲስ ሕግ መሠረት ኅብረተሰቡ ላይ አደጋ አይፈጥሩም ተብለው የተመረጡት እስረኞች ፈቃድ ይሰጣቸዋል፡፡ እንደ ዛምቢያ ኮሚሽነር ጄነራል ቺሴላ ቼሌሼ ከሆነ መጸጸታቸውን የሚያሳዩ እና ከወንጀል የራቁ እስረኞች በአዲሱ ሕግ ይጠቀማሉ። ፍርደኞቹ እነዚህ መብቶችን የሚያገኙት የዛምቢያ ማረሚያ አገልግሎት ለፕሬዝዳንት ሉንጉ በጽሑፍ ካሳወቃቸው ብቻ ነው ተብሏል። "ወንጀል ከፈጸሙ ግን ፈቃዳቸው ይሰረዛል" ብለዋል፡፡ አያይዘውም "ኮሚሽን ጄኔራሉ እስረኞች የግል ወይም የቤተሰብ ጉዳዮችን እንዲታደሙ ፈቃድ የመስጠት መብት ያለው ሲሆን፤ ጊዜው በተለያዩ ሁኔታዎች በጄኔራል ኮሚሽነር ጽህፈት ቤት የሚወሰን እና የሚሰጥ ነው" ሲሉ አክለዋል። አንዳንድ የዛምቢያ ዜጎች በትዊተር ገጻቸው አዲሱን ሕግ ለወንጀለኞች "የፌሽታ ቀን" ሲሉ ሰይመውታል፡፡
news-45267854
https://www.bbc.com/amharic/news-45267854
የኡጋንዳ ወታደሮች ጋዜጠኛ በመደብደባቸው ሰራዊቱ ይቅርታ ጠየቀ
ባልተለመደ መልኩ ሰራዊቱ ይቅርታ የጠየቀው በእስር ለሚገኘው እውቁ ዘፋኝና ተቃዋሚ ቦቢ ዋይን የተደረገውን የድጋፍ ሰልፍ በመዘገብ ላይ የነበር አንድ ጋዜጠኛ በወታደሮች ሲደበደብ የሚያሳይ ቪዲዮ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ መውጣቱን ተከትሎ ነው።
ሰኞ እለት ብዙዎች ቦቢ ዋይን እንዲፈታ አደባባይ ወጥተው ተቃውሟቸውን ገልፀዋል ሁኔታውን አስመልክቶ ሰራዊቱ ያወጣው የፅሁፍ መግለጫ የወታደሮቹ ተግባር የሙያ ስነምግባርን የጣሰ እንደሆነና ወታደሮቹም እንደሚታሰሩ ይገልፃል። ባለፈው ሳምንት ተቃዋሚ የፓርላማ አባል የሆነው ቦቢ ዋይንና ሌሎች አራት የፓርላማ አባላት መታሰርን ተከትሎ በኡጋንዳ ውጥረት ነግሷል። በሙዚቃው እውቅናን ያተረፈው ቦቢ ዋይን እንደ አውሮፓውያኑ ባለፈው ዓመት በግል የፓርላማ አባል ሆኖ ተመረጠ። . ለህዳሴ ግድብ ግንባታ መዘግየት ምን አይነት መፍትሔዎች እየተሰጡ ነው? . አፍሪካዊው ወጣት ለወባ በሽታ መፍትሄ ይዞ መጥቷል . የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዙማን የሙስና ቅሌት የሚያጋልጥ ምርመራ ተጀመረ ምናልባትም በአገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውንና የአገሪቱን ፕሬዚዳንት ዩዎሪ ሙሴቬኒን በመቃወም የተደረገን የወጣቶች ንቅናቄ የመራ ሰው እንደሆነ የቢቢሲዋ ዘጋቢ ካትሪን ባያሩሃንጋ ትናገራለች። መረጃዎች እንደሚያሳዩት የዛሬዋ ኡጋንዳ በርካታ ዜጎች እንደ አውሮፓውያኑ በ1986 ሙሴቬኒ ስልጣን ሲይዙ አልተወለዱም። ይህ ሙሴቬኒ ስልጣን ላይ ረዥም ጊዜ ከቆዩ የአፍሪካ መሪዎች አንዱ መሆናቸውን ያሳያል። ቀደም ሲል መቀመጫውን ኒውዮርክ ያደረገው ሂውማን ራይትስ ዋች የኡጋንዳ ፖሊስና ወታደር መገናኛ ብዙሃንን ማጥቃት እንዲያቆም እንዲሁም የሰላማዊ ሰልፈኞችን መብት እንዲያከብር ማሳሰቢያ አውጥቶ ነበር።
53127354
https://www.bbc.com/amharic/53127354
"እንደ ቆሻሻ ነው አውጥተው የወረወሩን" ኢትዮጵያውያኑ በሊባኖስ
በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት እየተባባሰ የመጣውን የሊባኖስ ምጣኔ ሃብት ማሽቆልቆል የኢትዮጵያውያኑን የቤት ሠራተኞችንም ኑሮ አክፍቶባቸዋል።
በርካታ መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሊባኖሳውያንም ለቤት ሠራተኞቻቸው መክፈል አንችልም በሚልም እያባረሩ ይገኛሉ። በዚህ ሳምንትም 100 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የቤት ሠራተኞች በመዲናዋ ቤይሩት በሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ በር ላይ አሰሪዎቻቸው አምጥተው ትተዋቸው ሄደዋል። ሦስት ኢትዮጵያውያን የቤት ሠራተኞች በአንድ ሰዓት ውስጥ በቆንስላው በር ላይ አሰሪዎቻቸው ትተዋቸው ሲሄዱ የቢቢሲው ጋዜጠኛ ማርቲን ፔሺየንስ ለመታዘብ ችሏል። በርካታ ኢትዮጵያውያን የቤት ሠራተኞች ሲብረከረኩ፣ ሲያለቅሱ እንዲሁም የሚሄዱበት የሚጠለሉበት ጥፍት ብሏቸው ታይተዋል። አንዳንዶቹም ግራ በመጋባት ሲንቀጠቀጡና ሲጮኹ፣ አንደኛው አሰሪም ከኋላ ያነገተውን ሽጉጥ ሲመዝም ታይቷል። በቆንስላው በር በቀዝቃዛው አስፓልት በስስ ምንጣፍ ላይ ተኝተው የሚያሳየውም ምስልም የሚረብሽ ነው። በበሩ ላይ ተበትነው የሚታዩት ኢትዮጵያውንም እርስ በርሳቸው ሲፅናኑ፣ እንዲሁም ተደጋግፈው ይታያሉ። የኮሮናቫይረስ ወረርሸኝን ተከትሎ በደረሰው ጫና ምክንያት አሰሪዎቻቸው ደመወዝ ሳይከፍሉ ኢትዮጵያውያኑን አባረዋቸዋል። በርካታ ሠራተኞችም የሚላስ የሚቀመስ እንዳጡም ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በፊት ብዙዎች የእለት ጉርሳቸውን በቤት ሠራተኝነት በሚያገኟት ደመወዝም መሸፈን ይችሉ ነበር። ከእነዚህም ውስጥ ኢትዮጵያዊቷ ሎሚ አንደኛዋ ናት። የወራት ደመወዟን በአሰሪዋ ያልተከፈላት ሎሚ ሁኔታው ከድጡ ወደማጡ ሆኖባታል። "ወደአገራችን እባካችሁ መልሱን፤ አሰሪዎቻችን ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ውስጥ አላገኙንም ፤ እኛ ቆሻሻ አይደለንም እንደዚህ እንደ ቆሻሻ የሚወረውሩን" ብላለች። ትዕግስት መስፍን የምትባል በጎ ፈቃደኛ በቦታው ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን እርዳታ እያደረገች ሲሆን፤ ሁሉም ወደ አገራችን መልሱን የሚል ተማፅኖቻውን እያሰሙ እንደሆነና ወረርሽኙን ተከትሎ የአየር ማረፊያዎች ከመዘጋታች አንፃር ጊዜያዊ መፍትሄ ሊፈለግላቸው ይገባልም ብላለች። "በረራ እስኪጀመር ድረስ ቤትውስጥ እንዲቆዩና የሚሰሩበትም መንገድ እንዲመቻችላቸው" በቆንስላው ውስጥም ባሉ መጠለያዎች ውስጥ በጊዜያዊነት ማረፊያ እንዲሰጣቸው ጠይቃለች። "ለምን ኤምባሲውን ከፍተው ማደሪያ አይሰጧቸውም? ስህተት ነው" ትላለች ትዕግስት። የሠራተኛ መብት ተከራካሪዎች እንደሚሉት የቤት ሠራተኞቹ ሁኔታ የከፋ ደረጃ ላይ ደርሷል፤ ካፋላ በተባለው አወዛጋቢና አግላይ ሥርዓትም መብታቸው ተገቷል። ፋራህ ሳልካ የተባለችው የፀረ- ዘረኝነት እንቅስቃሴ ዳይሬክተር እንደምትለውም በርካታ ቁጥር ያላቸውን ሠራተኞችን ይህ ሥርዓት ከሊባኖስ የሠራተኛ ሕግ ሆን ብሎ ያገላቸዋል ትላለች። ለምሳሌ ማግኘት የሚገባቸው ክፍያ፣ ዓመታዊ ፈቃድ፣ የሳምንት እረፍት እንዲሁም በቀን ውስጥ ምን ያህል ሰዓት መስራት አለባቸው የሚለው በሙሉ እንዳይመለከታቸው ተደርጓል። ከዚህም በተጨማሪ በአሰሪዎቻቸው በደል ቢደርስባቸው መውጣት የሚችሉበት እንዲሁም አቤቱታ ማቅረብ እንዳይችሉ ተደርገዋል። "ይሄ ሥርዓት ማለት በቤታችን ውስጥ ያለ የዘመኑ ባርነት ነው" ብላለች። አንዳንዶች አገሪቱ ውስጥ ባሉ የእርዳታ ድርጅት መጠለያ የተሰጣቸው ሲሆን መንግሥትም የቻልኩትን እያደረግኩ ነው ብሏል። ማርሊን አታላህ የሊባኖስ የሠራተኞች ሚኒስቴር ዳይሬክተር ጄኔራል እንደተናገሩት ከኢትዮጵያ ቆንስላ ጋር አብረን እየሰራን ነው ብለዋል። ኢትዮጵያውያኑ የቤት ሠራተኞች በሆቴል ውስጥ ለሁለት ቀናት ያህል እንዳሳደሯቸውና ወደ መጠለያዎችም ወስደናቸዋል ብለዋል። ለቤት ሠራተኞቹ ደመወዝ ባለመከፈልም ሆነ በመባረራቸው የተከሰሰ አሰሪ የለም፤ ነገር ግን ምርመራዎች እንደተጀመሩ ዳይሬክተሯ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ቆንስላ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል።
44870249
https://www.bbc.com/amharic/44870249
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት ሰራተኞች የሥራ ማቆም አድማ መቱ
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት ሰራተኞች ከአሰሪዎች ጋር ባለ ችግር፣ ባልተመቻቸ የሥራ ቦታና በሥራ ጫና ችግር ምክንያት የሥራ ማቆም አድማ ላይ መሆናቸውን ስማቸው እንዳይገለፅ የጠየቁ የቋሙ ሰራተኞች ለቢቢሲ ገልፁ።
ሠራተኞቹ እንደሚሉት በአሁኑ ወቅት መስሪያ ቤታቸውን ለቀው እንዳይወጡ በፖሊስ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸዋል። ይህንንም ተከትሎ ኩባንያው የቻይና ዜግነት ያላቸው የባቡር አሽከርካሪዎች ባቡሮቹን እንዲያንቀሳቅሱ ጠርተዋቸዋል። • በሃገሪቱ የተከሰቱት ቀውሶችና አዲስ አበባ • ከአዲስ አበባ ወደ አስመራ የሚወስዱ አውራ ጎዳናዎች "በወር ከ330 ሰዓት በላይ ነው የምሰራው። የሚከፈለኝ ግን ከ175 እስከ 180 ሰዓት የሚሆነው ብቻ ነው" ነው የሚሉት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት የባቡር አሽከርካሪ፤ ረዥም ሰዓታት ካለክፍያ መስራት ብቻ ሳይሆን ያልተመቻቸ የሥራ ሁኔታም ሌላ ችግር እንደሆነ ይናገራሉ። ከባቡር አሽከርካሪዎቹ (ትሬይን ማስተር) መካከል አንዱ እንደሚለው የሰራተኞቹ ጥያቄ ባቡሩ ሥራ ከጀመረበት መስከረም 8/2008 ዓ.ም ጀምሮ ሲንከባበል የመጣ ነው። የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሙሉቀን አሰፋም ይህ ጥያቄ ለዓመታት ሲንከባለል የመጣ መሆኑን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ጉዳዩ ስድስት ጊዜ በኢትዮጵያ ምድር ባቡር ቦርድ መታየቱንና የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ብቻውንም መመለስ አይችልም በመባሉ ወደ ሌላ ሂደት መሸጋገሩን ተናግረዋል። "ለአንድ ዓመት ሙሉ በበዓላትም ቀን ጨምር እንሰራ ነበር፤ ምንም እረፍት የለንም። ለምሳሌ በመጀመሪያ ቀን አንድ ሰው በማታ ፈረቃ 7̄ ሰዓት ከ 30 ገብቶ ሌሊት 6 ሰዓት ላይ ይጨርሳል፤ በቀጣዩ ቀን ደግሞ ከጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ ማታ 12 ሰዓት ድረስ ይሰራል" ሲል አንዱ አሽከርካሪ የነበረውን የሥራ ሁኔታ ይናገራል። በእነዚህ ሁለት ቀናት ታዲያ ማደሪያቸው ባቡሮቹ በሚነሱባቸው አያት ወይም ቃሊቲ ባሉ የማረፊያ ክፍሎች ውስጥ የማደረግ ግዴታ እንዳለባቸው ነው ጨምሮ የተናገረው። "ከማደሪያ ውጪ ወደየትም እንድንሄድ አይፈቀድም፣ ወደየትም መሄድ አይቻልም፣ ትራንስፖርትም የለም፣ አይፈቀድምም ይህን የተላለፈ ቅጣት ይጣልበታል። በሦስተኛው ቀን በማለዳው ፈረቃ ከሌሊቱ 10 ሰዓት እስከ ጠዋቱ 4 ሰዓት ከሰራን በኋላ ነው መውጣት የሚፈቀድልን" ብሏል። • የኢትዮጵያና የኤርትራ አየር መንገዶች በሽርክና ሊሰሩ ነው • ዶላር በጥቁር ገበያ ለምን ቀነሰ? በአንድ ክፍል ውስጥ ስምንት ሆነው እንደሚያድሩ የሚገልጸው ሌላኛው የባቡር አሽከርካሪ አኗኗራቸው ጤናቸው ላይ ጫና እየፈጠረ መሆኑንም አመልክቷል። በዚህ ሁኔታ ለአንድ ዓመት ምንም አይነት የተጨማሪ ሰዓት፤ የማታ ፈረቃ ክፍያም ሆነ የትራንስፖርት ጥቅማ ጥቅሞች ክፍያ ሳይፈጸምላቸው እንደሰሩና፤ ለዚህ ሥራቸውም በወር የሚያገኙት ደሞዝ በጣም አነስተኛ እንደሆነ ሰራተኞቹ ተናግረዋል። እናም የሥራ ሁኔታቸው እንዲስተካከልና የማግኘት የሚገባቸው ጥቅማ ጥቅም እንዲከበር እንዲሁም የደሞዝ ጭማሪ እንዲደርግላቸው በመጠየቅ ሥራ እንዳቆሙ ተናግረዋል። "ይህንን ጥያቄም በተደጋጋሚ ለአስተዳደሩ፣ ለትራንስፖርት ሚኒስቴር፣ ለመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴርም ሆነ ለባቡር ኮርፖሬሸን ብናቀብርም ምንም አይነት ምላሽ አላገኘንም። ማንም መጥቶ ያናገረን የለም አሁን ግን ሥራው ሲቆም መጥተዋል፣ ሊያነጋግሩንም ፍላጎት አሳይተዋል" ሲሉ ሰራተኞቹ ተናግረዋል። ቻይናዊያኑ የባቡር አሽከርካሪዎች ከሁለት ዓመታት በፊት ቦታቸውን ለኢትዮጵያውያን አስረክበው መውጣታቸው የሚታወስ ነው። ባቡር አሽከርካሪዎቹ እንደሚሉት ከአንድ ዓመት በፊት ለስልጠና ቻይና ቲያንጂን ሳሉ ይህንኑ ጥያቄያቸውን ማንሳታቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል። የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሙሉቀን የሥራ ማቆም አድማውን በተመለከተ "በቅርቡ ከተቋቋመው የሰራተኛ ማህበር ጋር ለረጅም ጊዜ ድርድር ከተደረገ በኋላ ስምምነት ተደርሷል። በእኔ እይታ የብዙ ጊዜ ጥያቄያቸው የጥቅማ ጥቅም ጉዳይ በመሆኑ ዛሬ አድማ ለመምታት አይዳርግም" ብለዋል። ማደሪያዎቹንም በተመለከተ ሲናገሩም የተዘጋጁት ሰራተኞቹ አረፍ እንዲሉበት እንጂ እንደመኖሪያ እንዲቆጠሩ እንዳልሆነ አመልክተው፤ "ሌሊት ለሚገባ ሰራተኛ ለራሱ ሲባል ማታ አርፎ ጠዋት ሥራ የሚቀጥልበትን ፣ ቤት መሄድ የማይችሉበት ሁኔታ ሲፈጠር ደግሞ አርፎ ለቀጣይ ሥራ ሙሉ ኃይል የሚያገኙበትን መንገድ ለማመቻቸት የተዘጋጁ ናቸው" ብለዋል። የባቡር አሽከርካሪዎቹ ከዚህ ቀደም አራት ባልደረቦቻቸው ለምን ጥያቄ አነሳችሁ በሚል ከሥራ መባረራቸውንም ይገልፃሉ። ባለሙያዎቹ እንዳሉት አድማ በመምታታቸው በከተማዋ በሁሉም አቅጣጫዎች የባቡር ጉዞ አገልግሎት ተቋርጧል።
news-55407743
https://www.bbc.com/amharic/news-55407743
ኮሮናቫይረስ ፡ በአዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ምክንያት አገራት ጥብቅ እርምጃ እየወሰዱ ነው
በዩናይትድ ኪንግደም የተገኘው አዲሱ የኮሮናቫይረስ አይነት መላው ዓለምን አስግቷል።
አገራት ወደ ዩናይትድ ኪንግደም የሚደረግ በረራን አግደዋል። በዚህም ከ40 በላይ አገራት ከዩናይትድ ኪንግደም ወደ አገራቸው የሚደረጉ በረራዎችን አግደዋል። የአውሮፓ ሕብረት አባል አገራትም በዚህ ዙሪያ የጋራ ፖሊሲ ለማውጣት እየተወያዩ ነው። ዴንማርክ ውስጥ አዲሱ የቫይረስ ዝርያ በመታየቱ ስዊድን ወደ ዴንማርክ የሚደረግ ጉዞ አግዳለች። ዝርያው በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰራጭ ነው። በከፍተኛ ደረጃ ጎጂ ስለመሆኑ ግን እስካሁን የተገኘ መረጃ የለም። የዓለም ጤና ድርጅቱ ማይክ ራየን እንደሚሉት፤ አዲሱ የቫይረስ ዝርያ በወረርሽኙ ዝግመተ ለውጥ ሂደት የሚጠበቅ ነው። የዩናይትድ ኪንግደም የጤና ሚንስትር ጸሐፊ ማት ሀንኮክ ከሰጡት ማብራሪያ በተቃራኒው አዲሱ ዝርያ "ከቁጥጥር አልወጣም" ብለዋል። ዩናይትድ ኪንግደም ከተገኘው የቫይረስ ዝርያ የተለየ አዲስ ዝርያ በደቡብ አፍሪካም ተገኝቷል። የደቡብ አፍሪካ ተጓዦች ላይ እገዳ እየተጣለም ነው። አውሮፓ ውስጥ የተከሰተው ምንድነው? አዲሱን የቫይረስ ዝርያ ስርጭት ለመግታት ብዙ የአውሮፓ አገሮች ወደ ዩናይትድ ኪንግደም በረራ አቋርጠዋል። ፈረንሳይ ተጓዦች ላይ ክልከላ መጣሏን ተከትሎ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚንስትር ከፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ንግድ ስለሚቀጥልበት መንገድ እንደሚነጋገሩ አስታውቀዋል። ፈረንሳይ ተጓዦች ላይና የጭነት መኪና ላይም እገዳ ጥላለች። የንግድ ሚንስትሩ ክሌመንት ባውኔ ቀጣዩን እርምጃቸውን እንሚያሳውቁ ተናግረዋል። ብራስልስ ውስጥ 27ቱ የአውሮፓ ሕብረት አባል አገሮች እየመከሩ ሲሆን፤ የጋራ ስምምነት ላይ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል። ቫይረሱ በተቀረው ዓለም ሕንድ፣ ኢራን፣ ካናዳና ሌሎችም አገሮች ዩናይትድ ኪንግደም ላይ የበረራ እግድ ጥለዋል። አሜሪካም በረራ ታቆማለች ተብሎ ይጠበቃል። ሳዑዲ አረቢያ፣ ኩዌት እና ኦማን ድንበራቸውን ለዓለም አቀፍ ተጓዦች ዝግ አድርገዋል። እስካሁን የአዲሱ ቫይረስ ዝርያ በዴንማርክ፣ አውስትራሊያ፣ ጣልያን እና ኔዘርላንድስ ተገኝቷል። አንዳንድ ባለሙያዎች እንደሚሉት፤ የቫይረሱ ዝርያ ከተገኘባቸው ቦታዎች ውጪም ተሰራጭቶ ሊሆን ይችላል። ዩናይትድ ኪንግደም የዘረ መል ቅንጣት ላይ ጥናት በማድረጓ አዲሱን የቫይረስ ዝርያ እንደደረሰችበትም አስረድተዋል። በቤልጄም የሚሠሩት የቫይረስ አጥኚ ማርክ ቫን፤ "በቀጣይ ቀናት አዲሱ የቫይረሱ ዝርያ በብዙ አገሮች ይገኛል ብለን እንጠብቃለን" ብለዋል።
news-49043053
https://www.bbc.com/amharic/news-49043053
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአሥመራ ጎዳናዎች ላይ መኪና ሲያሽከረክሩ ታይተዋል
ለጉብኝት ወደ ኤርትራ የተጓዙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ መኪና እያሽከረከሩ ከኤርትራው ፕሬስዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የሚታዩበት ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መነጋገሪያ ሆኗል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ መኪና እያሽከረከሩ ከውጪ ሃገር መሪ ጋር ሲታዩ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም። ባለፈው ዓመትም የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ልዑል ሞሐመድ ቢን ዛይድ ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ መኪና እያሽረከሩ ታይተዋል። • የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት ኢኮኖሚያዊ ትርፍ? ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በሁለቱ ሃገራትና በአካባቢያዊ ጉዳዮች ለመመካከር ለሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አሥመራ የገቡት ሐሙስ ነበር። ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ በፍጥጫ የቆየውን ግንኙነት ለማሻሻል ያስቻለውንና ፈር ቀዳጅ የተባለውን የመጀመሪያ ጉዟቸውን ወደ አሥመራ ካደረጉ ከአንድ ዓመት በኋላ የተደረገ ነው። • መስመር ያልያዘው የኢትዮ-ኤርትራ የንግድ ግንኙነት ወዴት ያመራል? ይህንን ጉብኝት በተመለከተ የኤርትራ መንግሥት ቴሌቪዥን ባሳየው ምስል ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከልኡካን ቡድናቸው ጋር በአሥመራ ጎዳናዎች ላይ በእግራቸው ሲጓዙ፤ ከዚያም ጠቅላይ ሚኒስትሩ መኪና እያሽከረከሩ ከሁለቱ መሪዎች የጉብኝቱ አካል የሆኑ ስፍራዎችን እየተዘዋወሩ ሲመለከቱ ያሳያል። ይህ ቪዲዮም በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛ ዘርፎች ላይ በስፋት እየተዘዋወረ ሲሆን የተለያዩ ሰዎችም በቪዲዮው ላይ አስተያየታቸውን እየሰጡ ነው። ናቲ ብርሃኔ ይፍሩ የተባሉት ግለሰብ በትዊተር ላይ እንዳሰፈሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንግዳ ሆነው ሳለ ስለምን አስተናጋጁን ፕሬዝዳንት አሳፍረው እንደሚያጓጉዙ ይጠይቅና፤ ኤርትራ የተረጋጋች መሆኗን ለማሳየት የተደረገ ገጽታ ግንባታ እንደሆነ ይጠቅሳል። ሁለቱ ሃጋራት ባለፈው ዓመት ግንኙነታቸውን ለማሻሻል የሚጠቅሙ የተለያዩ ስምምነቶችን የተፈራረሙ ቢሆንም የአየር መጓጓዣ አገልግሎት መልሶ መጀመሩና ኤምባሲዎቻቸውን መልሶ ከመክፈት ባሻገር ጉልህ የሆነ እንቅስቃሴ እስካሁን አልታየም። • በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ንግድ ተጧጡፏል አንዳንዶች በዚህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ባለፈው ዓመት የተጀመሩትን ሥራዎች ወደተግባር ለመቀየርና በሌሎች ጉዳዮችም ላይ በጋራ ለመስራት ሊሆን እንደሚችል ይናገራሉ። በሁለቱ ሃገራት መካከል ያሉት የድንበር መተላለፊያዎች ለተወሰነ ጊዜ ተከፍተው ነጻ የሰዎችና የሸቀጦች ዝውውር የነበረ ሲሆን አሁን ግን መዘጋታቸውን የድንበር አካባቢ ነዋሪዎች ይናገራሉ። በተጨማሪም ለሁለቱ ሃገራት ደም አፋሳሽ ጦርነት ምክንያት የሆነችው ባድመን በተመለከተ የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ መሰረት እስካሁን ኢትዮጵያ ቦታውን ለኤርትራ እንዳለቀቀች ይነገራል። ነገር ግን የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል በሁለቱ ሃገራት መካከል እየተካሄደ ያለው ግንኙነት ጠንካራና በሂደት ላይ እንደሆነ ይጠቅሳሉ።
news-47650245
https://www.bbc.com/amharic/news-47650245
ቁንጅና ተስፋዬ፡ ፋሽንን ከሕንፃ ንድፍ ጋር ያዛመደችው ዲዛይነር
ምርጫዋ ባይሆንም የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂና ማኔጅመንት ትምህርትን ተምራ ወደ ልብስ ንድፍ ሙያ አዘነበለች።
ቁንጅና ተስፋዬ "በዩኒቨርሲቲ የነበረኝ ቆይታ በማልፈልገው የትምህርት ዘርፍ ቢሆንም እንዲህ ፍላጎት በሌለኝ ነገር ላይ ጉልበቴንና ጊዜዬን ማፍሰስ መቻሌ የምወደውን ነገር ብሠራ ደግሞ ከዚህ በላይ ውጤታማ መሆን እንደምችል በእራሴ ላይ እምነት የፈጠረብኝ ቆይታ ነበር" ትላለች። ቁንጅና በ2006 ዓ.ም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ስትቀላቀል ፋሽን ዲዛይን ትምህርትን የመከታተል ፍላጎቷን ዩኒቨርሲቲው ውስጥ ማሳካት ስላልቻለች የሥዕል ዝንባሌዋን ለመጠቀም ሥነ-ሕንፃ 'አርኪቴክቸር' ወይም የምህንድስና አስተዳደር 'ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት' ለማጥናት ወሰነች። በዚህም "የፋሽን ዲዛይን ለመሥራት ጊዜ ስለሚሰጠኝ የኮንስትራክሽን ማኔጅመንትን መረጥኩኝ" ትላለች። • ታዋቂ ኢትዮጵያዊያን አርቲስቶች ለመዋብ ምን ያህል ይከፍላሉ? "አስተማሪዎቻችን አርክቴክቶች ስለነበሩ የሕንፃ ዲዛይን እንዴት እንደሚሠራ ለማወቅ ዕድሉን ሰጠኝ" የምትለው ቁንጅና ትምህርቱ የመጀመሪያ ምርጫዋ ባይሆንም ትምህርቱ ባካተታቸው የሕንፃ ንድፍ ትምህርቶች የፈጠራና የዲዛይን ችሎታዋን በተለያየ መልኩ ማዳበር እንድትችል ዕድል እንደሰጣት ትናገራለች። በ2010 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስትመረቅ በተመሳሳይ ዓመት ደግሞ የአፍሪካን ሞዛይክ ፋሽን ዲዛይን ውድድር በፈጠራና ተስፋ የተጣለባት ዲዛይነር በመሆን አርቲ-ቴክቸር (አርትንና አርኪቴክቸርን ያቀላቀለ ስያሜ) በተባለ ስብስቧ አሸንፋለች። አርቲ-ቴክቸር (አርትንና አርኪቴክቸርን ያቀላቀለ ስያሜ) ቁንጅና "2010 ዓ.ም ሁለቱን የተለያዩ ዓለሞቼን ያጣመርኩበት ዓመት ነው" ስትል "አፍሪካ ሞዛይክ ያሸነፍኩበት ዲዛይን 'አርቲ-ቴክቸር' ብዬ የሰየምኩትም በውስጡ ሥነ -ሕንፃን ከሥዕል ጥበብ ጋር አዛምጄ ስለሠራሁት ነው" ትላለች። • አክሱምና ላሊበላ ለስራዎቹ መስፈርት የሆኑት ዲዛይነር ልብሶቿ ከሕንፃ ዲዛይን የተዋሱትን መልክ ስትገልፅ ቀጥተኛ መስመሮች፣ ማዕዘናዊ ቅርፆችንና የሕንፃ ንድፍ ላይ የሚካተቱ የተለያዩ ምልክቶችን ትጠቅሳለች። "የአፍሪካ ሞዛይክን ሳሸንፍና ከዩኒቨርሲቲ ስመረቅ ሁለቱንም በአንድ ላይ አጣምሬ መጠቀም እንደምችል የተረዳሁበት፤ እናም ምንም እንኳን አንዱን መርጬ የተማርኩት ባይሆንም በመንገዱ ለተሰጥዖዬ የእራሱን አስተዋፅዖ አድርጎልኝ የሁለት ስኬቶችን ደስታ ማክበር የቻልኩበት ጊዜ ነበር" ትላለች። ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ የሚያጠኑት ዘርፍ በፍላጎታቸው ቢሆን ብዙዎች ስኬታማ ሊሆኑ ይችላሉ ብላ የምታመነው ቁንጅና "እኔ የኮንስትራክሽን ማኔጅመንትን ስማር እኔን የሚስቡኝ የዲዛይን ክፍሎች ካልሆኑ በስተቀር ብዙዎቹን ክፍል ውስጥ ቁጭ ብዬ ሌላ ነገር ስስል ነው ያሳለፍኩት" ትላለች። ልብስ ዲዛይን የማድረግ ተሰጥዖዋን በጊዜ ማሳየት የጀመረችው ቁንጅና አጀማመርዋን ስታስታውስ፤ በማህበራዊ ሚዲያም ላይ የሠራቻቸውን ልብሶች ታቀርብ ነበር። "አንዴ ውጪ ያለች አክስቴ የሠራሁትን በፌስቡክ አይታ ወዲያውኑ የመስፊያ ማሽን ላከችልኝ፤ ከዚያም በእራሴ ቤት ውስጥ መለማመድ ጀመርኩ" ትላለች። የመጀመሪያ ዲዛይኖቿ 12ኛ ክፍል የአካባቢ ጥበቃ ቀን በተመለከተ ከወዳደቁ ነገሮች የሠራችውና የዩኒቨርሲቲ አንደኛ ዓመት ተማሪ በነበረችበት ወቅት የተሳተፈችበት በሴቶች ቀን ላይ ያተኮረ የፋሽን ሾው እንደሆኑ ቁንጅና ታስታውሳለች። አራተኛ ዓመት ተማሪ ሆና ለልምምድ ስትወጣ ጎን ለጎን የፋሽን ዲዛይን ትምህርትን መከታተል የጀመረችው ቁንጅና ሁለት የተለያዩ ትምህርቶችን እየተማሩ ለማስኬድ መሞከር በጣም ከባድ እንደሆነ ትናገራለች። • የኬንያ ዳኞችን አለባበስ የቀየረች ኢትዮጵያዊት ሁለቱንም ትምህርቶቼን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማጠናቀቅ "የዩኒቨርስቲ ትምህርት ቦታዬ ጦር ኃይሎች መሃል አዲስ አበባ ሆኖ አፍሪካ ሞዛይክ ዲዛይን ሴንተር ደግሞ ከከተማው ውጪ ለገጣፎ ነበር፤ ብዙ ጊዜ ምሳ ያመልጠኛል ግን ያው ለፈለግሽው ነገር መስዋዕት መክፈል ብዙም አያስቸግርም" ትላለች። • ፓሪስን፣ ኒዮርክን፣ ዱባይን ... ወደ አዲስ አበባ በአሁኑ ወቅት የመጀመሪያ መደብሯን ከፍታ ሙሉ ለሙሉ የፋሽን ዲዛይን ላይ የምትሠራው ቁንጅና፤ የፋሽን ዓለሙም የእራሱ የሆኑ ፈተናዎች እንዳሉት ትናገራለች። "የሃገር ውስጥ ጨርቅ እጥረት፥ ከውጭ የሚገባም ጨርቅ በአንድ ዓይነት ጥራት አለማግኘትና የፋሽን ኢንደስትሪው በደንብ አለመደገፍ መሰናክሎች ናቸው" ብትልም በምትወደው ሙያ የበለጠ ስኬታማ ለመሆን ጥረቷን እንደምትቀጥል ትናገራለች።
news-48198782
https://www.bbc.com/amharic/news-48198782
እንግሊዛውያን አብዝተው ወሲብ እየፈጸሙ አይደለም ተባለ
በሀገር አቀፍ ደረጃ የተከናወነ አንድ ጥናት እንግሊዛውያን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ብዙ ወሲብ እየፈጸሙ እንዳልሆነ አመለከተ።
'ብሪቲሽ ሜዲካል ጆርናል' ላይ የሰፈረው ጥናት እንደሚያመላክተው፤ በጥናቱ ከተሳተፉት መካከል ሲሶው ባለፈው አንድ ወር ወሲብ አልፈጸሙም። በጥናቱ ምላሻቸውን ከሰጡት ከ34,000 ሰዎች መካከል ከ16-44 ዕድሜ የሚገኙ ግማሽ ያህሉ ቢያንስ በሳምንት አንድ ግዜ ወሲብ እንደሚፈጽሙ ተናግረዋል። እድሜያቸው ከ25 ዓመት በላይ የሆኑ እና አብረው የሚኖሩ ጥንዶች ባለፉት ዓመታት ለተመዘገበው አነስተኛ የወሲብ መጠን ትልቁን ድርሻ አበርክተዋል ተብሏል። የጥናቱ ውጤት እንደሚያመላክተው፤ 41 በመቶ የሚሆኑ ዕድሜያቸው ከ16-44 የሚሆኑት ተሳታፊዎች ባለፈው አንድ ወር ቢያንስ በሳምንት አንድ ግዜ ወሲብ ፈጽመዋል። • የሥራ ቦታ ወሲባዊ ትንኮሳ የቱ ነው? • 'የሴቶች ቫያግራ' በአፍሪካዊቷ ሃገር ባለፈው አንድ ወር ወሲብ አልፈጸምኩም የሚሉ ሴቶች ቁጥር በ6 በመቶ የጨመረ ሲሆን የወንዶች ቁጥር ደግሞ በ3 በመቶ ጨምሯል። ቁጥሩ ለምን ቀነሰ? ተመራማሪዎች እንደሚሉት እንግሊዛውያን ወሲብ መፈጸም የቀነሱት ድንግል ሆኖ ለመቆየት ካለ ፍላጎት ጋር የሚያያዝ አይደለም። ይልቁንም ወሲብ የመፈጸም ቁጥር የቀነሰው ከዚህ ቀደም ብዙ ወሲብ ይፈጽሙ በነበሩ ሰዎች ዘንድ ነው። እድሜያቸው ጠና ያለ ባለትዳሮች ወሲብ የሚፈጽሙበት ግዜ እያሽቆለቆለ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ በጥናቱ ከተሳተፉ ግማሽ ያህሉ ሴቶች እና ሁለት ሦስተኛ የሚሆኑት ወንዶች አሁን ከሚፈጽሙት በላይ በበለጠ ወሲብ መፈጸም እንፈልጋለን ብለዋል። ብዙ ግዜ ወሲብ መፈጸም እንደሚፈልጉ የጠቆሙት ደግሞ አብዛኛዎቹ በትዳር ወይም አብረው የሚኖሩ ጥንዶች ናቸው። ሥራ በዛ? ድካም ወይስ ጭንቀት? የጥናቱ መሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ኬይል ዌሊንግስ ''የሚደንቀው ነገር በዚህ ተጎጂ የሆኑት በመካከለኛ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ናቸው። እኚህ ወንድ እና ሴቶች ብዙ ጊዜ በሥራ የሚወጠሩ፣ ልጆቻቸውን እና በእድሜ የገፉ ወላጆቻቸውን የመንከባከብ ኃላፊነት ያለባቸው ሰዎች ናቸው'' ይላሉ። • 100 ሺህ ብር፤ ብልትን ለማወፈር • የወሲብ ቪዲዮ ህይወቷን ያሳጣት ወጣት ፕሮፌሰር ኬይል የጥናቱን ውጤት ሲያስረዱ ''ለሰው ልጅ ጤንነት ዋናው ነገር ምን ያህል ግዜ ወሲብ ተፈጸመ የሚለው ሳይሆን ወሲብ መፈጸም ምን ያክል ትርጉም ይሰጣል የሚለው ነው'' ይላሉ። ፕሬፌሰሩ እንደሚሉት፤ በርካቶች በውስጣቸው ሌሎች ሰዎች ከእነሱ በተሻለ መልኩ ብዙ ወሲብ እንደሚፈጽሙ ሊያስቡ ይችላሉ። "ይህ ጥናት ግን በተመሳሳይ መልኩ በርካቶች ብዙ ወሲብ እንደማይፈጽሙ እና ብቻቸውን እንዳልሆኑ እንዲሰማቸው ያደርጋቸዋል'' በማለት ያስረዳሉ። የወሲብ አማካሪው ፒተር ሳዲንግተን ግን ''ዋናው ጥራት እንጂ ብዛት አይደለም። አንድ ሰው በድርጊቱ ደስተኛ ከነበረ የመድገሙ አጋጣሚ ከፍ ያለ ነው። ይሁን እንጂ ለወሲብ ጊዜ መስጠት ያስፈልጋል። እንደው በድንገት የሚደረግ ነገር አይደለም። ምናልባትም በማስታወሻችን ላይ ቀጠሮ ማኖር ሊረዳን ይችላል'' ይላሉ።
48291667
https://www.bbc.com/amharic/48291667
የ63 ሚሊዮን ብር መኪና ሰርቆ የተሰወረው ግለሰብ ዱካው ጠፍቷል
ጀርመን ውስጥ መኪና ለማስተዋወቅ በተዘጋጀ መሰናዶ ላይ ቀርቦ የነበረና 2.2 ሚሊየን ዶላር (63 ሚሊዮን ብር ገደማ) የሚያወጣ መኪና ተሰርቆ እንደነበር ፖሊሶች ይፋ አድርገዋል።
2.2 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣው መኪና ቅንጡ ከሆኑ ተሽከርካሪዎች አንዱ የሆነው ፌራሪ መኪናን ዘርፏል የተባለው ግለሰብ፤ መሰናዶው ላይ ተገኝቶ መኪናውን ለሙከራ ለመንዳት ጥያቄ ያቀርባል። ግለሰቡ መኪናውን የመግዛት ፍላጎት ስላሳየ መኪናውን ነድቶ እንዲሞክረው ተፈቀደለት። ግለሰቡ ግን የመኪናውን መሪ ጨብጦ ብዙም ሳይቆይ መኪናውን በፍጥነት እየነዳ ከአካባቢው ተሰውሯል። • የምርጥ ተዋናይቷን ኦስካር ሽልማት የሰረቀው በቁጥጥር ስር ዋለ ፓሊሶች እንዳሉት፤ መኪናውን ያያችሁ ሰዎች ጠቁሙን የሚል ማሳሳሰቢያ ማስነገራቸውን ተከትሎ መኪናው አንድ ጋራዥ ውስጥ ተደብቆ ተገኝቷል። ተጠርጣሪው ግለሰብ ግን እስካሁን በቁጥጥር ስር አልዋለም። መኪናውን ለሽያጭ ያቀረበው ድርጅት ኃላፊ እንዳሉት፤ ተጠርጣሪው መኪናውን ይዞ ከመሰወሩ በፊት ለድርጅቱ በተደጋጋሚ ይደውል፣ ኢሜልም ይልክ ነበር። • ኢትዮጵያ ሀይቆቿን መጠበቅ ለምን ተሳናት? አየርላንዳዊው የፎርሙላ 1 ተወዳዳሪ ኤዲ አይርቪን በመኪናው እ. አ. አ. ከ1996 እስከ 1999 ተወዳድሮበታል። መኪናው ታሪካዊ እንደመሆኑ በሚሊዮኖች ማውጣቱም ብዙም አያስገርምም። መሰል መኪናዎች ከአንድ እስከ ሦስት ሚሊየን ዶላር ይሸጣሉ። • የፓኪስታን ዲፕሎማት የኪስ ቦርሳ ሰረቁ የመኪናው አምራች ድርጅት የተሰረቀው ፌራሪ 288 GTO መኪና 272 ብቻ ነበር የሠራው።
45705049
https://www.bbc.com/amharic/45705049
ኤርትራ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የካሳ ጥያቄ አቀረበች
ኤርትራ ለዓመታት በተጣለባት ማዕቀብ ምክንያት ላጋጠማት ችግር የተባበሩት መንግሥት ድርጅት ካሳ እንዲከፍላት ጠየቀች።
የኤርትራው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቶ ዑስማን ሳልሕ በ73ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መደበኛ ጉባዔ ላይ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር ሃገራቸው በተጣለባት ማዕቀብ ምክንያት ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እንዳጋጠማትና ለዚህም ካሳ እንደሚገባት ገልፀዋል። • የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ጦርነት ሲታወስ በ2009 ላይ የተጣለው የመሳርያ ግዢ ማዕቀብ ላለፉት 9 ዓመታት በመፅናቱ በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከባድ ችግር እንዳስከተለም አስረድተዋል። "የኤርትራ ህዝብ ማዕቀቡ እንዲነሳለት ብቻ ሳይሆን ለደረሰበት ውድቀትና ለከሰራቸው ዕድሎች ነው ካሳ እየጠየቀ ያለው" ያሉት ሚንስትሩ ካሳውም በኤርትራና ኢትዮጵያ መካከል ለተጀመረው የሰላም ጉዞ የሁለትዮሽ ጥቅሞች እንደሚውል ተናግረዋል። • ኤርትራ በምሽት ድንበር ማቋረጥን ከለከለች ሚንስትሩ "ሕጋዊ ያልሆነ" በማለት የገለፁት በኤርትራ ላይ የተጣለው ማዕቀብ እንዳይነሳ የፀጥታው ምክር ቤት አባል ሃገራት እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል። ከኢትዮጵያ ጋር የነበረው አለመግባባት ዓለም-ዓቀፍ ተቀባይነት ባለው የሰላም ውል መሰረት በተፈታበት በአሁኑ ጊዜ ማዕቀቡ እንዲቀጥል የተፈለገበት ምክንያት ግልፅ አለመሆኑን በመጥቀስ ማዕቀቡ ተነስቶ የኤርትራ ህዝብ ካሳ እንዲከፈለው በማለት ጠይቀዋል። ለሁለት አስርት ዓመታት ተፋጠው የነበሩት ኤርትራና ኢትዮጵያ ጉዟቸው ምን ይመስላል?
news-43491315
https://www.bbc.com/amharic/news-43491315
የንፁህ ውሃ ችግር ካለባቸው ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ናት
የዓለም ውሃ ቀንን በማስመልከት የወጣ አዲስ ሪፖርት እንዳመለከተው ንፁህ የመጠጥ ውሃ የማያገኙ ሰዎች ቁጥር ወደ 844 ሚሊዮን ከፍ እንዳለ አመልክቷል።
ዋተር ኤይድ የተባለው በጎ አድራጎት ድርጅትም የንፁህ ውሃ አቀርቦት ሳይኖር፤ ከጤና፣ ከትምህርትና ከፆታ እኩልነት ጋር የተያያዙ ዓለም አቀፍ ግቦችን ማሳካት ስለማይቻል ፖለቲከኞች ለውሃ አቅርቦት ትኩረት እንዲሰጡ ጥሪ አቀርቧል። በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ ዘጠኝ ሰዎች መካከል አንዱ የንፁህ ውሃ አቅርቦት የለውም። ዋተር ኤይድ የተባለው የበጎ አድራጎት ድርጅት ይህንን እንዲል ያስቻለው፤ ሰዎች ምን ያህል ውሃን በቤታቸው ውስጥ ያገኛሉ ወይም ንፁህ ውሃን ለመቅዳት ከግማሽ ሰዓት በላይ በእግራቸው ለመጓዝ ይገደዳሉ የሚለውን በማጥናት ነው። ንፁህ ውሃን የማያገኙ ሰዎችን ብዛትን በተመለከተ አብዛኛውን ቁጥር የሚይዙት ቻይናዊያንና ሕንዳዊያን ናቸው። ነገር ግን ሃገሮች ካላቸው የህዝብ ቁጥር አንፃር በመቶኛ ሲሰላ የውሃ ችግር በተለይ በአፍሪካ የከፋ ነው። በንፁህ ውሃ አቅርቦት ችግር በቀዳሚነት የሚጠቀሱት ሃጋራትም ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ኡጋንዳ፣ ሶማሊያና የዲሞክራቲክ ኮንጎ ናቸው። ዋትር ኤይድ እንደሚለው 800 የሚደርሱ ከአምስት ዓመት በታች ዕድሜ ያላቸው ህፃናት ከንፁህ ውሃ እጦት ጋር በቀጥታ ግንኙነት ባላቸውና ከተቅማጥ ጋር በተያያዙ ህመሞች በየዕለቱ ለሞት ይዳረጋሉ። የወደፊቱን የዓለም የንፁህ ውሃ አቅርቦትን ከማረጋገጥ የበለጠ አሳሳቢ ጉዳይ ስለሌለ መሪዎች ለጉዳዩ ከፍ ያለ ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው የበጎ አድራጎት ድርጅቱ አሳስቧል። የደቡብ አፍሪካ ከተማ የሆነችው ኬፕታውን ባለሥልታናት በቅርቡ እንዳስጠነቀቁት ዝናብ ካልዘነበ በመጪው ነሃሴ ወር ላይ በከተማዋ ያሉ የውሃ መስመሮች የውሃ አቅርቦታቸው ይቋረጣል። ከተማዋ የገጠማት የውሃ እጥረት በምድራችን ላይ ያለው የውሃ ሃብት ምንያህል ለአደጋ እንደተጋለጠ የሚያሳይ ነው ተብሏል።ነገር ግን ንፅህናው የተጠበቀ የውሃ አቅርቦትን የማያገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የምድራችን ነዋሪዎች የገጠማቸው ስጋት፤ የኬፕታውን ከተማ ከገጠማት ችግር በእጅጉ የከፋ እንደሆነ ተነግሯል።
news-49025533
https://www.bbc.com/amharic/news-49025533
"ምርጫ ቦርድ ያላቸው ነገሮች ህጋዊ መሰረት የላቸውም" የህግ ባለሙያ
በትናንትናው ዕለት ሐምሌ9፣2011ዓ.ም የሲዳማ ዞንን የክልልነት ጥያቄን ለመወሰን በአምስት ወራት ውስጥ ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ወስኗል።
ከዚህም በተጨማሪ ከቦርዱ የሚጠበቁ ተግባራትንና ሂደቱ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትም የሚጠበቅባቸውን ዝግጅት አስቀምጧል ምርጫ ቦርድ በመግለጫው። መግለጫው ያስቀመጣቸው ነገሮች "ህጋዊ መሰረት የሌላቸው" ናቸው የሚሉት የህግ ባለሙያው አቶ አብርሃም ቃሬሶ ናቸው። እንደ ምክንያትነት ከሚያነሷቸው ጉዳዮች መካከልም ምርጫ ቦርድ በአምስት ወራት ውስጥ ህዝበ ውሳኔ አካሂዳለሁ ማለቱ በህገ መንግሥቱ መሰረት የለውም ይላሉ። •በሲዳማ ክልልነት ጉዳይ ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ የምርጫ ቦርድ ወሰነ •ለሲዳማ ክልልነት 'ይሁንታ ተሰጠ' በሚል በርካቶች ደስታቸውን እየገለጹ ነው እሳቸው እንደሚሉት ምክንያቱም ህዝበ ውሳኔው መካሄድ ያለበት ክልል ለመሆን የሚጠይቀው ምክር ቤት በወሰነ በአንድ አመት ውስጥ ነው። "ህገ መንግሥቱ እንደሚለው ምርጫ ቦርድ ያለው ስልጣን የህዝቡ ውሳኔ ነው አይደለም የሚለውን በህዝበ ውሳኔ እንዲያጣራ ብቻ ነው።" ይላሉ •'ከሕግ ውጪ' የተዋሃዱት አምስቱ ክልሎች ከዚህ በተጨማሪ የህግ ባለሙያው ጥያቄ የሚያነሱበት ሌላኛው ጉዳይ የክልሉም የዞኑም አስተዳደር ዋና ከተማ ሆና የምታገለግለው የሀዋሳ ከተማ ህዝበ ውሳኔው የሲዳማን ክልልነት ካረጋገጠ፤ ሁለቱ አካላት የሚኖራቸውን መብትና፣ የሃብት ክፍፍል ጥያቄዎችን የሚያስተናግዱበት አሰራር አዘጋጅተው ለቦርዱ እንዲያሳውቁ የሚለው ነው። "ምርጫ ቦርድ በዚህ ላይ ስልጣን የለውም፤ ምርጫ ቦርድ የተሰጠው ስልጣን የሲዳማ ህዝብ ክልል መሆን ይፈልጋል ወይስ አይፈልግም የሚለውን በህዝበ ውሳኔ ማጣራት ነው። እሱንም የደቡብ ክልል ማድረግ ስለማይችል እንዲደግፈው ነው" ይላሉ በመግለጫው ላይ በሲዳማ ዞን የሚኖሩ የሌሎች ብሄር ብሔረሰብ አባላት ከህዝበ ውሳኔው በኋላ የሚኖራቸውን ህጋዊ የመብቶች ጥበቃ አስመልክቶ የደቡብ ክልል አስተዳደራዊና ህጋዊ ማእቀፍ በማዘጋጀት ለቦርዱ እንዲያሳውቅ የሚለውም የምርጫ ቦርድ ተግባር እንዳልሆነ የህግ ባለሙያው ያስረዳሉ። "በመሰረቱ በሲዳማ ዞን እንደ ህዝብ የሚኖር ሌላ ብሄር የለም። ግለሰቦች ናቸው ያሉት። ነገር ግን ቢኖርም እንኳን በህጉ መሰረት ይህ የምርጫ ቦርድ ውሳኔ አይደለም።መግለጫው ምርጫ ቦርድ ከተሰጠው ስልጣን በላይ የሌለውን ስልጣን መጠቀሙን የሚያመላክት ነው" በማለት ይደመድማሉ። ፖለቲካዊ ውሳኔዎች የሚመለከቱት የደቡብ ምክር ቤትን ነው የሚሉት የህግ ባለሙያው የደቡብ ክልል አስፈፃሚዎችን እንጂ ምርጫ ቦርድን አይደለም። ከዚህም በተጨማሪ የኤጀቶ አስተባባሪ ራሔል ኢሳያስ በበኩሏ በህግ ባለሙያው ሀሳብ ትስማማለች። ክልል የመሆን ጥያቄው ለዞኑ ከቀረበ አንድ አመት የሚሆነው ሐምሌ 11 ሲሆን ይህንንም ውሳኔ የሚመለከተው ምርጫ ቦርድን ሳይሆን ምክር ቤቱን ነው ትላለች። "የክልል ጥያቄ ህገ መንግሥቱ እንደሚያዘው በምክር ቤቱ ከቀረበ በአንድ አመት ውስጥ ህዝበ ውሳኔ ተካሂዶ ምላሽ ማግኘት አለበት" ትላለች። በዚህም መሰረት የሲዳማ ክልል መሆንን በነገው ዕለት ሐምሌ 11፣2011 ዓ.ም እንደሚያውጁ ለቢቢሲ ገልፃለች። "አምስት ወር ጠብቁ የሚለውን ሐሳብ አንስማባትም፤ እነሱ ናቸው እንጂ ህጉን ያላከበሩት እኛ በህጉ መሰረት እየተመራን ነው" ትላለች። የሲዳማ ህዝብ ራሱን ለማስተዳደር በብዙ አመታት በሰላማዊ መንገድ የታገሉ መሆናቸውን የምትናገረው ራሔል "እኛ ለውጥ አለ፣ዴሞክራሲ አለ ብለን ጥያቄያችንን በሰላማዊ መንገድ አቅርበናል። መንግሥትም እውነትም ዲሞክራሲ መኖሩን የተፃፈው ህግ እንደሚሰራ ያሳየን ነው የምለው። ሁከት አንፈልግም፤ አንድም ሰው እንዲሞት አንፈልግም" በማለት ገልፃለች። ከምርጫ ቦርድ ጋር ተቃርኖ ወይም ከፌደራል መንግሥት ውጭ የሚሆን አይደለም ወይ በሚል ከቢቢሲ ለቀረበላት ጥያቄ "ከመንግሥት ጋር የሚያጋጭ ነገር ይኖራል ብለን አናስብም" ብላለች የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሚሊዮን ማትዮስን በተደጋጋሚ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
news-44721169
https://www.bbc.com/amharic/news-44721169
6 ሚሊዮን ብር፡ በማንዴላ እሥር ቤት ለማደር
ደቡብ አፍሪቃውያን ኔልሰን ማንዴላ ለነፃነት በሚታገሉበት ወቅት ታስረውበት በነበረው ክፍላቸው አንድ ሌሊት ያሳልፉ ዘንድ ዕድል ቀርቦላቸዋል።
በጨረታ መልክ የመጣው ዕድል ግን ጠረቅ ያለ ገንዘብ የሚጠይቅ ነው፤ ዝቅተኛው 250 ሺህ ዶላር፤ በብር ሲመነዘር ደግሞ ከ6 ሚሊዮን በላይ። በሮበን ደሴት ላይ የሚገኘው ይህ እሥር ቤት የቀድሞው የደቡብ አፍሪቃ መሪ ኔልሰን ማንዴላ ለ27 ዓመታት ታስረውበት የነበረ ነው። ጨረታው 67 ሰዎችን የሚያካትት ሲሆን እኚህ ሰዎች ማንዴላ ባደሩባት ክፍል ለማደር በትንሹ 6.8 ሚሊዮን ብር መክፈል ይጠበቅባቸዋል። ጨረታው ለ12 ቀናት የሚቆይ ሲሆን በኔልሰን ማንዴላ የውልደት ቀን ውጤቱ ይፋ እንደሚሆን ይጠበቃል። ከጨረታው የሚገኝ ገንዘብ ለታራሚዎች የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ለሚያቀርብ አንድ ድርጅት እንደሚሰጥ የጨረታው አዘጋጆች ይፋ አድርገዋል። ማንዴላ ከእሥር የተለቀቁት በአውሮጳውያኑ 1990 ሲሆን ከአራት ዓመታት በኋላ በተደረገ ምርጫ በማሸነፍ የመጀመሪያ ጥቁር ደቡብ አፍሪቃዊ ፕሬዚዳንት መሆን ችለዋል። በበርካቶች ዘንድ የነፃነት አባት ተደርገው የሚቆጠሩትን ኔልሰን ማንዴላ የዛሬ 5 ዓመት ገደማ ነበር በ95 ዓመታቸው ይህችን ዓለም የተሰናበቱት።
news-53075006
https://www.bbc.com/amharic/news-53075006
ትራምፕ በአሜሪካ የፖሊስ ኃይል ላይ ለውጥ እንዲደረግ ልዩ ውሳኔ አሳለፉ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአገሪቱ ፖሊስ ኃይል ላይ አዳዲስና በርካታ የለውጥ እርምጃዎች እንዲካሄዱ የሚያደርግ ፕሬዝዳንታዊ ውሳኔን ፈርመው አጸደቁ።
ትራምፕ ይህንን ከፍተኛ ውሳኔን ያጸደቁት በፖሊስ ላይ የሚያገኘውን በጀት እንዲቋረጥ ወይም ሙሉ ለሙሉ እንዲበተን የሚጠይቁ ሃሳቦችን ውድቅ አድርገው ነው። ትራምፕ የጆርጅ ፍሎይድን ግድያ ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ ተረብሸው ቆይተዋል። የፖለቲካ ምኅዳሩን በአሉታዊ መልኩ አውኮት የነበረውን ይህንን በነውጥ የታጀበ ተቃውሞ ረገብ ለማድረግ ሲሉ ነው ዶናልድ ትራምፕ ይህንን ፕሬዝዳንታዊ ውሳኔ ይፋ ያደረጉት። ፕሬዝዳንታዊ ውሳኔው በፌዴራል ደረጃ ሁሉንም ሕግ አስፈጻሚዎች የሚያስገደድ ከሕግ በታች ያለ ሕግ ሆኖ ያገለግላል። በአሜሪካ ፖሊሶች ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ በሚያደርጉት ግብግብ ያልተመጣጠነ ኃይልን እንዳይጠቀሙ አዲስ የሕግ ሐሳቦች በሕግ መምሪያው ምክር ቤት ሲዘጋጁ መቆየታቸው ይታወሳል። እነዚህ ረቂቅ የሕግ ሐሳቦች ገና በሂደት ላይ ያሉ ሲሆን ዶናልድ ትራምፕ ከፈረሙት ማሻሻያ በጠነከረ መልኩ አዲስና ጠንካራ የሕግ ማሻሻያ ሊቀርብ እንደሚችል ይጠበቃል። ዶናልድ ትራምፕ የፈረሙት አዲስ ውሳኔ በዋናነት የፌዴራል ፖሊስ በጀትን ከማሳደግና የፖሊስ አሰራርና ስልጠናን ከማዘመን ጋር የተያያዘ ነው። የፕሬዝዳንታዊ ሥልጣናቸውን ተጠቅመው ዶናልድ ትራምፕ ባጸደቁት በዚህ ልዩ ውሳኔ መሠረት ፖሊስ የተጠርጣሪዎችን አንገት ማነቅና መጠምለል አይችልም። ዶናልድ ትራምፕ ተግባራዊ እንዲደረግ የፈረሙት የትናንቱ ማሻሻያ የፌዴራል መንግሥቱ ሕግ አስፈጸሚ አካላት ላይ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፤ ከፖሊስ ቁጥጥር ጋር በተያያዘ የፖሊስ ሠራዊት አሰራሩን ያዘምናል፤ ለዚህም የሚሆን በርከት ያለ ገንዘብ ከፌዴራል ካዝና እንዲለቀቅ ያስችላል። ባለፉት ቀናት በፖሊስ ያልተመጣጠነ እርምጃ ቤተሰባቸውን ያጡ በርካታ ጥቁር አሜሪካዊያን በነጩ ቤተ መንግሥት ጠርተው ማነጋገራቸውን የጠቀሱት ትራምፕ ማሻሻያ ማድረጉ አስፈላጊና ጊዜ የማይሰጥ ነው ብለዋል። የፖሊሶችን ተጠያቂነት ማሳደግ፣ የአሰራር ግልጽነት እንዲኖር ማድረግ እና በፖሊስ ሥልጠናና ምልመላ ዙርያ ትኩረት አድርጎ መስራት ያሻል ብለዋል ትራምፕ ፊርማ ባኖሩበት ወቅት ለጋዜጠኞች። ባለፈው ወር የተገደለውን ጆርጅ ፍሎይድን በማሰብ ተቃውሞዎች ከተቀጣጠሉ በኋላ ራይሻርድ ብሩክስ የተባለ ሌላ ጥቁር አሜሪካዊ ባለፈው አርብ በአትላንታ ፖሊስ በሽጉጥ ተመትቶ መገደሉ እየሰከነ የነበረውን ተቃውሞ አባብሶት ቆይቷል። የዶናልድ ትራምፕ አዲስ ፕሬዝዳንታዊ ውሳኔ ይፋ የተደረገው ዲሞክራቶችና ሪፐብሊካን በአሜሪካ የሕግ መምሪያ ምክር ቤት የፖሊስ አሰራርን በተመለከተ የማሻሻያ ረቂቅ እያሰናዱ ባለበት ጊዜ ነው። የዶናልድ ትራምፕ አዲስ ፕሬዝዳንታዊ ውሳኔ በዋናነት ትኩረት ያደረገው ፌዴራል መንግሥት ለፖሊስ ሁሉን አቀፍ ማሻሻያ እንዲያደርግ የገንዘብ ድጎማ ማድረግ ላይ ነው። በጥቁሮች ላይ ሚፈጸሙ ግፎችን የሚቃወሙ በርካታ ሰልፎች ተካሂደዋል ፕሬዝዳንቱ ፊርማቸውን ያኖሩበት አዲስ ሕግ የሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ይዟል። • በፌዴራል ደረጃ በፖሊሶች ላይ የሚቀርብን ቅሬታ መዝግቦ የሚይዝና የሚከታተል አገር አቀፍ የመረጃ ቋት ማዘጋጀት። ይህም መጥፎ ባህሪ የተጸናወታቸውና ሥነ ምግባር የሌላቸው ፖሊሶችን ዱካ ለመከታተል ይረዳል ተብሎ የታሰበ ነው። • የሱስ ተጠቂዎችንና የጎዳና ተዳዳሪዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል በሚደረግ ሂደት ውስጥ በዚህ ዘርፍ የሰለጠኑ የማኅበረሰብ እርዳታ ሰጪ ባለሞያዎች ከፖሊስ ጋር አብረው እንዲሆኑ ማድረግ። • ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን በሚያድንበት ወቅት ጆርጅ ፍሎይድ የደረሰበት ዓይነት ማጅራትን ቆልፎ የመያዝ የኃይል እርምጃ ተግባራዊ እንዳይደረግ ማድረግን ያካትታል። ዋይት ሐውስ እንደሚለው ይህ የፕሬዝዳንቱ መመሪያ ማሳካት የፈለገው በአሜሪካ ፖሊስንና ማኅበረሰቡን ማቀራረብ ነው። በዚህ መመሪያ ፖሊሶች የተጠርጣሪን ማጅራት መጠምለል ወይም ቆልፎ መያዝ እንዳይችሉ ቢያዝም ፖሊስ ሕይወቴ አደጋ ላይ ነው ብሎ ካሰበ ግን ተጠርጣሪውን በዚያ መንገድ ሊይዘው መብት ይሰጠዋል። የፕሬዝዳንቱ ተቺዎች ውሳኔው አይረባም እያሉ ነው። የሴኔት ዲሞክራቲክ ፖርቲ ተወካይ ቸክ ሹመር የፕሬዝዳንቱ ሕግ በቂ ስላልሆነ ሕግ አውጪ የምክር ቤት አባላት ጠንከር ያለ ሕግ በቶሎ ማርቀቅ ይገባቸዋል ብለዋል። "በሚያሳዝን ሁኔታ ፕሬዝዳንቱ ያወጡት ትዕዛዝ ትርጉም ባለው ደረጃ ለውጥና ተጠያቂነትን የሚያመጣ አይደለም፤ የአሜሪካ ሕዝብ የጠየቀው ይህን አልነበረም" ብለዋል ሹመር። "የሕግ መምሪያው ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ በበኩላቸው የዘረኝነትን ወረርሽኝ ለማስቆምም ሆነ የፖሊስን ግፍ ለመገደብ የማይጠቅም መናኛ መመሪያ ብለውታል" የትራምፕን ልዩ ማሻሻያ። የፕሬዝዳንቱ መመሪያ በፖሊስና በጥቁር ተጠቂዎች ዘንድ ከፍተኛ ችግር የፈጠረውን የሕግ ክፍተት የሚደፍን አለመሆኑ በብዙ አስተችቶታል። ይህም በሕግ ቋንቋ "ኳሊፋይድ ኢሚዩኒቲ" የሚባለው ነው። በዚህም መሰረት አንድ ሕግ አስከባሪ አጥፍቶ እንኳ ቢሆን ጥፋቱ ጥፋት የሚሆነው በሕግ ፊት የሕገ መንግሥት መብቶችን ሆን ብሎ ስለመጣሱ ግልጽና የማያሻማ መረጃ ሲቀርብበት ብቻ ነው ይላል። ይህ የሕግ ክፍተት ፖሊሶች በእንዝላልነት ሰው ገድለውም ቢሆን እነሱን ፍርድ ቤት አስቀርቦ ማስወሰንን ዳገት ያደርገዋል። የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የአሜሪካ ቢሮ ባልደረባ ክሪስቲና ሮዝ ትራምፕ የፈረሙት የሕግ ማሻሻያ መመሪያ መዋቅራዊ የዘረኝነት ችግሩን እንደማይፈታው ሲተቹ የሚከተለውን ብለዋል። "በጥይት ለቆሰለ ሰው ጥይቱን ሳያወጡ ፋሻ የመጠቅለል ያህል ነው" አዳዲስ ሕጎች እየተረቀቁ ነው በሚኒያፖሊስ የከተማዋ ምክር ቤት አባላት የፖሊስን በጀት በመወሰን ለሌላ ተግባር ማዋል ሀሳብ አቅርበዋል። በአትላንታ የራይሻርድ ብሩክስን በፖሊስ መገደል ተከትሎ ከንቲባ ኬይሻ በርካታ ለውጦች እንደሚደረግ ቃል ገብተዋል። ከእነዚህም ማሻሻያዎች አንዱ አንድ ፖሊስ ከመስመር ሲወጣ ባልደረቦቹ ጣልቃ ገብተው የማስቆም መብትና ግዴታን የሚሰጥ ነው። ከአትላንታ ሌላ ሳንፍራንሲስኮ፣ ሎስ አንጀለስ፣ ኒው ዮርክና ቺካጎ ሁሉም ከፖሊስ የኃይል አጠቃቀም ጋር ተያይዞ ማሻሻያ እንደሚያደርጉና ዘረኛ ፖሊሶችን ከሥራ እንደሚያግዱ ዝተዋል። የኒው ዮርኩ ገዢ አንድሩ ኩሞ ባለፈው ሰኞ የፈረሙት አዲስ መመሪያ ፖሊስ አሰሳ በሚያደርግበት ወቅት ካሜራ የተገጠመለት የደንብ ልብስ እንዲለብስ ያስገድዳል። በተጨማሪም የፖሊስን የሥነ ምግባር ጥሰት የሚመረምር አዲስ ቢሮ ለማቀቀም ያስችላል። በፌዴራል ደረጃ ደግሞ የሕግ መምሪያው ምክር ቤት የዲሞክራቲክ ፓርቲ አባላት አዲስ ረቂቅ ሕግ አቅርበዋል። ይህ ረቂቅ ሕግ ተጠርጣሪን አንቆ መያዝ፣ ሳያንኳኩ በር ገንጥሎ መግባት፣ ባለቤት ሳያስፈቅዱ የሰው ቤት ዘው ብሎ መግባትን ይከለክላል።
news-55156384
https://www.bbc.com/amharic/news-55156384
ትምኒት ገብሩ ፡ የጉግል ሠራተኞች ከሥራዋ ከተባረረችው ትውልደ ኢትዮጵያዊት ጎን መቆማቸውን ገለጹ
በመቶዎች የሚቆጠሩ የጉግል ሠራተኞች በድርጅታቸው ከሥራዋ የተባረረችውን ትውልደ ኢትዮጵያዊት ታዋቂ የቴክኖሎጂ ተመራማሪዋ ትምኒት ገብሩ (ዶ/ር) የሚደግፈውን ደብዳቤ በመፈረም ከጓኗ መቆማቸውን አሳወቁ።
የአርቴፌሻል ኢንተለጀንስ (ሰው ሰራሽ ልህቀት) ተመራማሪዋ ትምኒት፤ ከቀናት በፊት እንዳሳወቀችው ጉግል ከሥራዋ ያባረራት "ድርጅቱ ትኩረት የተነፈጋቸው ድምጾችን ያፍናል" በማለት ለሥራ ባልደረቦቿ የኢሜል መልዕክት ከላከች በኋላ ነው። ይህንንም ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ የጉግል ባልደረቦች በእርግጥም የዓለማችን ግዙፉ የቴክኖሎጂ ተቋም ጉግልን በዘረኝነትና መልዕክቶችን ቀድሞ በመመርመር (ሳንሱር) የሚከሰውን ደብዳቤ በመፈረም ከትምኒት ጎን ቆመዋል። ከዚህ በተጨማሪም ጉግል በትምኒት ላይ የወሰደውን እርምጃ በመቃወም የትዊተር ተጠቃሚዎች ከትምኒት ጎን መቆማቸውን #ቢሊቭብላክዊመን [#BelieveBlackWomen] በሚለው መሪ ቃል ድጋፍ እያሰባሰቡ ነው። ነገር ግን ጉግል ትምኒት ከሥራዋ ስለመባረሯ ያቀረበችውን ምክንያት አስተባብሏል። ዶ/ር ትምኒት በቴክኖሎጂው ዘርፍ እጅግ ትኩረትን ባገኘው በሰው ሰራሽ ልህቀትና ተያያዥ በሆነው የሥነ ምግባር ዘርፍ ከፍተኛ ዝናን ያተረፈች ተመራማሪ ነች። በተለይ የፊት ገጽታን በሚለየው የፌሻል ሪኮግኒሽን ቴክኖሎጂ ወደ አንድ የዘር ቡድን ማተኮርን በተመለከተ ባከናወነችው ሥራ በስፋት ትታወቃለች። በዚህም በዘርፉ የተሰማሩ ተቋማት ጥቁሮችን ያካተተ ሥራ አለመስራታቸውን አጥብቃ ተችታለች። ትምኒት ካከናወነቻቸው በርካታ ታዋቂ የምርምር ሥራዎች መካከል በአንዱ አብራት የሠራችው ጆይ ቦላምዊኒ በሰጠችው ምስክርነት "ትምኒት ከጉግል ከፍ ያለ ነገር ማግኘት ይገባት ነበር" ብላለች። "ትምኒት በሰው ሰራሽ ልህቀት ላይ የሚደረጉ ምርምሮች ሥነ ምግባርን የተከተሉ፣ ጥልቀት ኖሯቸው አስተማማኝነታቸው የተረጋገጠ እንዲሆን በድፍረት ስለጠየቀች ከሥራዋ መባረሯ በዘርፉ ጉግል ያለውን ተአማኒነት የሚጎዳ ነው" በማለት የትምኒትን መባረር ተቃውማለች። ጨምራም ትምኒት በሰው ሰራሽ የልህቀት ዘርፍ በኩል ላበረከተችው አስተዋጽኦ ብቻ ሳይሆን "የእኩልነት ጥያቄን በትህትናና በልበ ሙሉነት በማንሳቷ ውለታዋ አለብን" ስትል ተናግራለች። ዶ/ር ትምኒት ከምትሰራበት ጉግል ጋር ስለተፈጠረው ነገር እንደተናገረችው፤ እረፍት ለመውጣት እየተዘጋጀች ባለበት ጊዜ ከባልደረቦቿ ጋር ስላዘጋጀችው አንድ የምርምር ጽሁፍ በሚወያይ ስብሰባ ላይ እንድትሳተፍ ተጋበዘች። በዚያ ውይይት ላይ በምርምር ያዘጋጀችውን ጽሁፍ ውድቅ እንድታደርገው ትዕዛዝ እንደተሰጣትና ጉግልም በጉዳዩ ላይ ለመወያየት ዝግጁ እንዳልነበረ ገልጻለች። በመልዕክቱ ላይም "በዚህ ድርጅት ውስጥ ዕውቅናና ዋጋ የተሰጠን ሰዎች ስላልሆንን በጉዳዩ ምንም አይነት ውይይት ለማድረግ የሚያስችል ፍላጎት የለም" በማለት አስፍራ ነበር። ጨምራም "ምንም አይነት ውጤት ስለማይኖረው እያዘጋጃችሁት ያለውን ሰነድ መጻፍ አቁሙ" ብላም ነበር። የጉግልን ውሳኔ ያልተቀበለችው ዶ/ር ትምኒትም ከምርምር ጽሁፉ ላይ ስሟን ለማውጣት ለድርጅቱ ቁልፍ የሚባሉ ቅድመ ሁኔታዎችን በማስቀመጥ የማይሟሉ ከሆነ የራሷ ውሳኔ ላይ እንደምትደርስ አሳውቃ ነበር። ነገር ግን ከጉግል የተሰጣት ምላሽ "ጉግልን ለመልቀቅ ውሳኔሽን እናከብራለን . . . በዚህም መሰረት የሥራ መልቀቂያሽን ተቀብለነዋል" በማለት ለሥራ ባልደረቦቿ የጻፈችው ኢሜል የድርጅቱን ደንብ የማይከተል መሆኑን በመግለጽ ሥራዋን በቶሎ እንድትለቅ የሚል ነበር። ትምኒትም ሥራዋን በገዛ ፈቃዷ ሳይሆን የለቀቀችው የጉግል የሰው ሰራሽ ምርምሮችን የሚመራው ዘርፍ ከፍተኛ ኃላፊ በሆነው ጄፍ ዲን ከሥራዋ እንደተሰናበተች በመግለጽ ትዊት አድርጋ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆነ። "የጉግል ሥራ አመራር በእኔ ላይ እንደወሰነ እገምታለሁ" ብላለች። የጉግል ከፍተኛ ኃላፊ የሆነው ጄፍ ዲን በኢሜል በሰጠው ምላሽ ስለትምኒት ከሥራ መሰናበት "በርካታ በግምት ላይ የተነመሰረቱ የተሳሳቱ ነገሮች አሉ" በማለት ስለጉዳዩ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥቷል። ዲን እንደሚለው፤ በዶ/ር ትምኒት የተዘጋጀው የምርምር ወረቀት "ከማቅረቢያው ጊዜ አንድ ቀን ቀደም ብሎ የገባ ስለሆነ ጉግል ጽሁፉን የሚገመግምበት በቂ ጊዜ አልነበረውም" ጨምሮም "ወረቀቱ በርካታ አስፈላጊ ምርምሮችን ችላ ያለ ነው" ብሏል። ትምኒትም በኢሜል በሰጠችው ምላሽ፤ "በሥራዋ ላይ ለመቆየት፤ ምርምሩን በመገምገም አስተያየት የሰጡና በግምገማው የተሳተፉ ሰዎች ማንነት እንዲሁም የሰጡት አስተያየት እንዲገለጽ ጠየቀች። ሌሎች መሟላት አለባቸው ያለቻቸውን በርካታ ቅድመ ሁኔታዎችንም አስቀመጠች። የጠየቀቻቸው ነገሮች የማይሟሉ ከሆኑ ጉግልን እንደምትለቅ በማሳወቋ እኛም ውሳኔዋን ተቀብለነዋል" ብሏል። የትምኒትና የታዋቂው ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ውዝግብ በዘርፉ ባሉ ባለሙያዎችና የታላላቅ መገናኛ ብዙሃን ዋነኛ ርዕስ ሆኗል።
50640650
https://www.bbc.com/amharic/50640650
''ለ 12 ዓመታት ባልተደፈረው ቦክስ ኢትዮጵያን በኦሎምፒክ መወከል እፈልጋለሁ'' ተመስገን ምትኩ
ተመስገን ምትኩ ይባላል። ባሳለፍነው ዓመት የኢትዮጵያ ቦክስ ፌደሬሽን ባዘጋጀው የቦክስ ክለቦች ሻምፒዮና በ75 ኪሎ ግራም አጠቃላይ አሸናፊ ሲሆን የዓመቱ ምርጥ ቦክሰኛ ተብሎም ተመርጧል።
ገና የ22 ዓመት ወጣት ነው። በቅርቡ ሃገሩን ወክሎ ኦሎምፒክ ላይ እንደሚሳተፍ ተስፋ ተጥሎበታል። 2005 ዓ.ም. ክረምት ላይ በታላቅ ወንድሙ ገፋፊነት በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሶስት ወጣቶች ማዕከል ቦክስ የጀመረው ተመስገን ከቦክስ ይልቅ ለቴኳንዶ ፍቅር እንደነበረው ይገልጻል። • የስፖርት ውርርድ አዲሱ የወጣቶች ሱስ ይሆን? • “በአምስት የዓለም ዋንጫዎች ወርቅ እንዲመጣ ምክንያት ነኝ” አትሌት ገብረእግዚአብሔር ''ሰፈር ውስጥ አስቸጋሪ ልጅ ስለነበርኩ ወንድሜ ቦክሱንም እየሰራሁ ስነምግባሬም እንዲስተካካል በማሰብ ቦክስ ወስዶ አስመዘገበኝ።'' ክረምቱ መጨረሻ ላይ የውድድር ዕድል አግኝቶ አሰልጣኙ ለመወዳደር ፍላጎት እንዳለው ሲጠይቁት በደስታ ነበር የተቀበለው፤ ተመስገን። ''ድፍረትና ከነበሩት ልጆች የተሻለ ጉልበት ስለነበረኝ ለግጥሚያው ተስማማሁ። ነገር ግን ብዙም ልምድ ስላልነበረኝ በዝረራ ተሸንፌ ወጣሁ። በጣም እልህ ይዞኝ ስለነበር ያሸነፈኝን ልጅ መልሼ ለማግኘት ስል በቦክሱ በርትቼ ቀጠልኩበት።'' ምንም እንኳን በዝረራ ያሸነፈውን ቦክሰኛ ለመግጠም ብሎ በቦክሱ ቢቀጥልም ጭራሽ ክረምቱ ሲያበቃ ሁለቱም በተመሳሳይ ክለብ ውስጥ ተቀጠሩ። በወቅቱ በ57 ኪሎ ይወዳደር የነበረ ሲሆን በ60 እንዲሁም በ 63 ኪሎም ጭምር ተወዳድሯል። የቀድሞው ኒያላ የአሁኑ ማራቶን ክለብ ተወዳዳሪው ተመስገን በ 2006 ዓ.ም. የክፍለ ከተማዎች ውድድር አሸናፊ በመሆን አዲስ አበባን ወክሎ አዳማ ላይ በተካሄደው የሀገር አቀፍ ፕሮጀክቶች ውድድር ተካፈለ። በውድድሩም በ 63 ኪሎ ግራም የተወዳደረው ተመስገን የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳሊያውን ማግኘት ችሏል። በ2008 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በተካሄደው 'ሴሚ ፕሮፌሽናል' (የከፊል ፕሮፌሽናል) ውድድር ላይ ተሳታፊ የነበረው ተመስገን በ 64 ኪሎ ግራም ወርቅ ሜዳሊያ አገኘ። በተመሳሳይ ውድድር 2010 ዓ.ም. ደግሞ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነ። የኢትዮጵያ ቦክስ ፌደሬሽን በዓመት አራት ጊዜ የሚያዘጋጀው ብሄራዊ የክለቦች ሻምፒዮና በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ይካሄዳሉ። በ2011 ዓ.ም ድሬዳዋ ላይ በተደረገው የመጀመሪያው ዙር ውድድርም ተመስገን በ63 ኪሎ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ነበር። ሁለተኛው ዙር ወላይታ ላይ ተካሂዶ እዛም ተመሳሳይ የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘ ሲሆን በደሴ በተካሄደው ሶስተኛው ዙርም አሸናፊ በመሆን ጨርሷል። የዓመቱ የመጨረሻውና አራተኛው የአዲስ አበባ ክለቦች አቋም መለኪያ ላይ ደግሞ አሁንም የወርቅ ሜዳሊያ በማምጣት ያለመሸነፍ ጉዞውን ቀጠለ። በሀገር ውስጥ ውድድሮች ሁሉንም በሚባል ደረጃ አብዛኛውን በድል ማጠናቀቅ የቻለው ተመስገን በአፍሪካና በዓለም ደረጃ ሃገሩን የመወከል እድሎችንም አግኝቷል። 2010 ዓ.ም. ላይ በአፍሪካ ምድብ ሞሮኮ በተካሄደው የዓለም ወጣቶች ማጣሪያ ጨዋታ ላይ ሀገሩን ወክሎ በመሳተፍ ሶስተኛ ወጥቶ የነሀስ ሜዳሊያ ተሸላሚም ነበር። በዚሁም ሃንጋሪ ለሚካሄደው የዓለም ወጣቶች ውድድር አለፈ። ነገር ግን ከውድድሩ በኋላ አንድ ያልጠበቀው ነገር ተፈጠረ። የኢትዮጵያ ቦክስ ፌደሬሽን በወቅቱ በጀት የለኝም በማለት ተመስገን ወደ ሀንጋሪ እንደማይሄድ ተነገረው። '' ሀገሬን ወክዬ ውጤት እንደማመጣ እርግጠኛ ነበርኩ፤ የሚቆጨኝ ነገር ቢኖር እሱን ማሳካት አለመቻሌ ነው። እርግጠኛ የሆንኩበት ምክንያት በሞሮኮው ውድድር በትንንሽ ስህተቶች ነበር የተሸነፍኩት። ከአብዛኛዎቹ ተወዳዳሪዎች የተሻልኩ ነበርኩኝ፤ ነገር ግን ሀገር ውስጥ ብቻ ካገኘሁት ስልጠና አንጻር ብዙ የዓለማቀፍ ህጎችን ስለማላውቅ አንደኛ መውጣት አልቻልኩም።'' ላለፉት 12 ተከታታይ ዓመታት ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ መድረክ በቦክስ የሚወክላት አላገኘችም። ተመስገን ምትኩ ግን ያሉበትን ማጣሪያዎች በድል አጠናቅቆ ሀገሩን በቦክስ ወደ ኦሎምፒክ መድረክ መመለስ እንደሚፈልግ ይናገራል። ለመሆኑ በኢትዮጵያ ያለው የቦክስ ስልጠና ምን ይመስላል? እስከዛሬ በሄደባቸው ውድደሮችና ስልጠናዎች በሙሉ ብዙ ታዳጊ ልጆች ከፍተኛ የሆነ ተፈጥሮአዊ አቅም ቢኖራቸውም የሚያገኙት ስልጠና ግን ከልምድ የመጣ ብቻ እንደሆነ ተመስገን ያስረዳል። ''በተፈጥሮ ያገኙት አካላዊ ብቃት ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መዳበር ሲገባው እንደነገሩ ስለሆነ ስልጠና የሚሰጣቸው፤ በዓለማቀፍ ደረጃ መፎካከርም ሆነ ብቃታቸውን ማሳደግ አይችሉም።'' ይላል ከዚህ በተጨማሪም በጣም ከባድ ስልጠናዎችን ከሰሩ በኋላ የሚያገኙት ምግብ ለሰውነት ግንባታ የማይጠቅምና የላብ መተኪያ እንኳን አለመሆኑ ችግር እንደፈጠረባቸው ያስረዳል። በአሁኑ ሰአት ለብሄራዊ ቡድን ሲመረጡ በቀን ሶስት ጊዜ ስልጠና የሚሰሩ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ስልጠና ሶስት ሰአት የሚፈጅ ሲሆን ከሌሊቱ 11 ሰአት፣ ጠዋት ሶስት ሰአት እና ከሰአት በኋላ ዘጠኝ ሰአት ላይ ስልጠናቸውን ይሰራሉ። ''ነገር ግን ከስልጠና በኋላ እዚህ ግባ እንኳን የማይባል ወጥ ነው የሚቀርብልን። ያው ሁሌም በጀት የለንም ነው የምንባለው። እንደዚህ ደክመን ሰልጥነን ተገቢውን ምግብ ካላገኘን እንዴት ነው ከሌሎች ተወዳዳሪዎች ጋር መፎካካር የምንችለው?'' በማለት ይጠይቃል። ከዚህም በተጨማሪ በብሄራዊ ቡድን ደረጃም ሆነ በክለብ ስልጠና የሚሰሩበት ቦታ አዳራሽ ብቻ እንጂ ተገቢው የስልጠና መሳሪያዎች እንኳን ያልተሟሉለት እንደሆነም ተመስገን ይናገራል። ''ሌላው ቀርቶ ፌደሬሽኑ ለስልጠና ጓንት ብቻ ነው የሚያቀርብልን። እንደ ቁምጣ እና ሌሎች ትጥቆችን የምናሟላው በራሳችን ነው። አንዳንዴም ባለን ልብስ ስልጠና እንሰራለን።'' በማለት ያለውን ዘርፈ ብዙ ችግር ይናገራል። • በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን ፌስቲቫል፡ ሙዚቃ፣ ኳስ፣ ፍቅርና ቡጢ.. • ከመኪኖች ይልቅ ብስክሌቶች የሚበዙባት ከተማ ተመስገን ሌላው በኢትዮጵያ ያለውን የቦክስ ስፖርት ወደኋላ እየጎተተው ያለው የዳኝነት ችግር እና ከክፍያ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች እንደሆኑ ያስባል። ''ዳኞች ተገቢውን ዓለማቀፍ ስልጠና አያገኙም፤ ከዚህ በተጨማሪም የማዳላት ነገር ይስተዋላል። በሌላ በኩል አድካሚ ስልጠና ለሚሰሩ ቦክሰኞች የሚቀርበው ክፍያ በጣም ትንሽ ነው።'' ይላል። በብሄራዊ ቡድን ደረጃ እንኳን ምንም አይነት ክፍያ እንኳን እንደሌለ የሚገልጸው ተመስገን ሃገር ወክለው በውጪ ሃገራት የሚሳተፉ ቦክሰኞች ምናልባት እስከ 5 ሺ ብር የሚደርስ ለተሳትፎ እንደሚሰጣቸው ያስታውሳል። ተመስገን በ 2020 በጃፓን አዘጋጅነት ለሚካሄደው ኦሎምፒክ ሀገሩን ወክሎ ለመሳተፍ በደቡብ አፍሪካና በካሜሩን የኦሎምፒክ ማጣሪያ ግጥሚያዎች ይጠብቁታል። ተጋጣሚዎቹን በማሸነፍ በቦክስ ውድድር ሀገሩን በኦሎምፒክ ለመወከል ተስፋ ሰንቆ በአሁኑ ሰአት ስልጠናውን እያከናወነ ይገኛል።
news-47946126
https://www.bbc.com/amharic/news-47946126
በጋምቤላ ክልል 89 ታራሚዎች ከማረሚያ ቤት ማምለጣቸው ተሰማ
ትናንት ከረፋዱ 4፡30 አካባቢ 89 ታራሚዎች ከጋምቤላ ማረሚያ ቤት ማምለጣቸውን የክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪ ኃላፊ አቶ ኡዶል ለጉዋ ለቢቢሲ ገለፁ።
እርሳቸው እንደሚሉት በማረሚያ ቤቱ በመጠጥ ውሃ ሽሚያ ምክንያት በሁለት ታራሚዎች መካከል ግጭት ይነሳል። በወቅቱ የነበሩት ስድስት ተረኛ ጠባቂዎች ግጭቱን ለማብረድ በመካከላቸው ይገባሉ። ይሁን እንጂ ታራሚዎቹ ፖሊሶቹን በመደብደብ በዋናው በር በኩል አምልጠዋል ብለዋል። • የምክር ቤቱ ስብሰባ ኢህአዴግን ወዴት ይመራው ይሆን? አቶ ኡዶል ለጊዜው የደረሳቸው መረጃ ይሄ ይሁን እንጂ ድርጊቱ ለመጥፋት ቅድመ ዝግጅት የተደረገበት ሳይሆን እንደማይቀር መንግሥት ጥርጣሬ አለው ብለዋል። "የውሃ እጥረት በሌለበት አካባቢ የመጠጥ ውሃ የግጭት መነሻ መሆኑ በራሱ ተቀባይነት" የለውም ሲሉ ያክላሉ። 316 ታራሚዎች በሚገኙበት በዚህ ማረሚያ ቤት 14 ተረኛ ጠባቂዎች የሚመደቡ ሲሆን ትናንት ግን ስድስት የጥበቃ ፖሊስ አባላት ብቻ እንደነበሩ ታውቋል። ቀሪዎቹ ስምንት ተረኛ ጠባቂዎች እስረኞች ወደ ፍርድ ቤቶች ለማድረስ ሄደው እንደነበር መስማታቸውን ኃላፊው ነግረውናል። • ትውስታ- የዛሬ 20 ዓመት ኢትዮጵያ ሞባይል ስልክን ስትተዋወቅ አቶ ኡዶል በስፍራው ሄደው ያነጋገሯቸው ፖሊሶችም "በሁለቱ ታራሚዎች መካከል ያለውን ግጭት ለመፍታት በመካከል ስንገባ በድንጋይ ደብድበውን ጥለውን ወጡ" ሲሉ ገልፀውላቸዋል። እስረኞቹ በግድያና በተለያዩ ወንጀሎች የተፈረደባቸው ሲሆኑ የፖለቲከኛ እስረኞች አለመሆናቸው ተናግረዋል። • "ኢትዮጵያ የከሸፈች ሀገር እየሆነች ነው" ሻለቃ ዳዊት ከእስር ቤቱ አምልጠው የወጡት ታራሚዎች እስካሁን ያልተያዙ ሲሆን ምርመራና ክትትል እየተደረገ ነው ብለዋል ኃላፊው። በአካባቢው የሙቀት ወቅት በመሆኑ እስረኞች ከክፍላቸው ወጥተው በግቢው ውስጥ ባሉ ቦታዎች እየተዘዋወሩ መቆየት የተለመደ ነው።
news-48263575
https://www.bbc.com/amharic/news-48263575
"ልዩ ነዳጅ መኖሩን አልደረስንበትም" የማዕድን፣ የፔትሮሊየምና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር
ትናንት ግንቦት 5 ቀን 2011 ዓ.ም የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በትግራይ ክልል በዓይነቱ ልዩ የሆነ ነዳጅ መኖሩ በጥናት መረጋጋጡን አስታውቀዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ይህን ያሉት በመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ በሚገኘው ኬይ ፒ አር የተሰኘው የህንድ ኩባንያ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ሲሆን፤ በትግራይ ክልል በሚገኙ እምባ አላጀ፣ ነበለት እና ዓዲግራት ባሉት ተራራማ አካባቢዎች በዓይነቱ ልዩ የሆነው የነዳጅ ክምችት እንደሚገኝ መናገራቸውን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። • "ነዳጅ የማውጣት ስራውን ለማስቆም የቻልነውን ሁሉ እናደርጋለን" የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር በአውሮፓውያኑ 2018 ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲና ተቋማት የተውጣጡ የአጥኝዎች ቡድን 'Economic geology value of oil shale deposits: Ethiopia Tigray and Jordan' በሚል ባሳተሙት ጥናታዊ ጽሁፋቸው በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የሼል ኦይል ክምችት እንደሚገኝ ፅፈዋል። ከእነዚህ ቦታዎች አንዱ የሆነው ትግራይ ክልል ከፍተኛ የሆነ የሼል ኦይል ክምችት እንደሚገኝበትም በጥናታዊ ፅሁፉ ላይ ተመላክቷል። በጥናቱ እንደተገለፀው ይህ የነዳጅ ዘይትም ብዙውን የክልሉን ቦታ የሚሸፍነውን - በአዲግራት አሸዋማ አለት ሥር በስፋት የተሰራጨ ነው። በመሆኑም ብዘት፣ ዕዳጋ ዓርቢ፣ ነበለት እና አጽቢ የሚባሉ አካባቢዎች መገኘቱንም ጥናቱ አትቷል። በትግራይ ክልል ይገኛል የተባለው የነዳጅ ክምችትም ወደ 3.89 ቢሊየን ቶን የሚጠጋ እንደሆነ በጥናታቸው አመላክተዋል። በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚገኘው ይህ የኦይል ሼል ክምችትም ከ55-60 በመቶው የካርቦን ይዘት እንዳላቸው ጥናቱ በዝርዝር አስቀምጧል። ጉዳዩን አስመልክተን ያነጋገርናቸው በኢፌዲሪ የማዕድን፣ የፔትሮሊየምና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሙያ ዶ/ር ቀጸላ ታደሰ ከዚህ ቀደም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የነዳጅ ዘይት ክምችት እንዳሉ የሚያመላክቱ ጥናቶች መኖራቸውን ያስታውሳሉ። ነገር ግን አሁን በትግራይ ክልል ሼል ኦይል ተገኘ ስለመባሉ "ይህ መግለጫ ተጨባጭና አስተማማኝ የሚሆነው የቁፋሮ ሥራና በቤተሙከራው ውጤቶች ተደግፎ ሲቀርብ ነው" ብለዋል። እርሳቸው እንደሚሉት የተለያዩ የነዳጅ ዓይነቶች ያሉ ሲሆን ሼል ኦይል የአለት ዓይነቱ በተለያዩ ዘዴዎች በመሰነጣጠቅና ጋዝ እንዲያመነጭ በማድረግ የሚመረት የተፈጥሮ ጋዝ ነው። የዚህ ዓይነት የተፈጥሮ ነዳጅ በሰሜን አሜሪካ በስፋት አገልግሎት ላይ እንደሚውል ይጠቅሳሉ። ይሁን እንጂ በአካባቢው የተለመደ 'ሼል ሮክ' አለት እንዳለ የሚናገሩት ባለሙያው አሁን በትግራይ ክልል ተገኘ የተባለው 'ሼል ኦይል' መሆኑን በጥናት እንዳልተደረሰበት ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይህንንም 'ሼል ኦይል' ለማጥናት የመጣ ኩባንያ እንደሌለም አክለዋል። የአጥኚዎች ቡድን ነዳጁ ስለመገኘቱ ብቻም ሳይሆን ትግራይ ውስጥ ያለው ክምችት ወደ 4 ቢሊዮን ቶን አካባቢ መሆኑን እንደሚጠቁም ያነሳንላቸው ዶ/ር ቀጸላ፤ የአጥኚዎች ቡድን ስለመኖሩ እንደማያውቁ በመግለፅ "አንደኛ በላብራቶሪ መደገፍ አለበት፤ የተካሄዱ ሥራዎችም የሉም፤ በመሆኑም በግምት እንዲህ ነው ማለት አይቻልም፤ በመሆኑም ተዓማኒነት እንዲኖረው መተመንና በማስረጃ መደገፍ አለበት" ሲሉ መልሰዋል። "ባይጋነን ጥሩ ነው፤ ተጨባጭ ነገር ሲኖር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ግልፅ የሆነ መግለጫ ይሰጣል፤ የሕዝብን ልብ ትርታ ለመጨመር ጥረት ባይደረግ " ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። • ኢትዮጵያ በዱቤ ተጨማሪ ነዳጅ ከሳኡዲ አረቢያ ጠየቀች ከዚህ ቀደምም በመቀሌ ተፋሰስ በተባለው አካባቢ የነዳጅ ክምችት መኖሩን የሚያውቁ ሲሆን ሚንስቴር መሥሪያ ቤቱ ለተለያዩ ባለሃብቶች በማስተዋወቅ ጥናቶች እየተካሄዱ መቆየታቸውን ነግረውናል። የነዳጅ ክምችቱ እንዳለ የታወቀውም በግምት የዛሬ ሃያ ወይም ሰላሳ ዓመት ገደማ ይሆነዋል ብለዋል። በእነዚህ ጊዜያትም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ መዋዕለ ንዋያቸውን በፍለጋው ላይ ለማፍሰስ የሚፈቅዱ ባለሃብቶችን ሲፈለግ እንደቆየ ያስረዳሉ። በጥናቱም በአገሪቱ ካሉ ስድስት የነዳጅ መፈለግ የሚያስችል ተፋሰሶች አንዱ መቀሌ ተፋሰስ እንደሆነም አስታውሰዋል። • ዚምባብዌ የነዳጅ ቁፋሮ ልትጀምር ነው የመሥሪያ ቤቱ ዋና ሥራ ቢፈለግ ሊገኝበት እንደሚችል ማስተዋወቅና ማሳየት እንደሆነ በመግለፅ ጉዳዩ አሁንም በጥናት ላይ መሆኑን ዶ/ር ቀጸላ ገልፀዋል። ባለፉት ሰባ ዓመታት በአገሪቱ በተደረጉ የነዳጅ ፍለጋ ጥናቶችም አመርቂ የሆነ ውጤት የተገኘበት የኦጋዴኑ ብቻ መሆኑን ገልፀውልናል። ማንኛውንም የሥነ ምድር ሐብት የሚያጠናው ተቋም የኢትዮጵያ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ በጉዳዩ ላይ ጥናት ስለመኖሩ ጠይቀናቸው ነበር። የተቋሙ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ታምሩ መርሻ ከሠላሳ ዓመታት በፊት በተደረገው ጥናት በተለያዩ አካባቢዎች የተለያየ መጠን ያለው የነዳጅ ክምችት እንደሚኖር ከሌሎች አገራት ኩባንያዎች ጋር በመሆን ጥናት ተካሂዶ እንደነበር ያስታውሳሉ። እርሳቸው እንደሚሉት በዚህ ከሠላሳ ዓመት በፊት በተጠና ጥናት ከፍተኛ ክምችት የሚገኝበት የኦጋዴን ቤንዚን ፣ አባይ ሸለቆ፣ በስምጥ ሸለቆ (ከአፋር እስከ ደቡብ ኦሞ)፣ በጋምቤላ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ፣ በመቀሌ እና መተማ ተፋሰስ የተለያየ መጠን ያለው የነዳጅ ክምችት መኖሩን ጥናቶች እንደሚያሳዩ ተናግረዋል። መሥሪያ ቤቱ የመንግሥት ፖሊሲ ከመቀየሩ ጋር ተያይዞ የሕዝቡን ፍላጎት የሚያሟሉና የሕዝቡን ችግር የሚፈቱ ሌሎች ማዕድኖች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደጀመረ በመግለፅ አሁን ይፋ የተደረገው የነዳጅ ዓይነት ጥናት እንደሌላቸው ተናግረዋል።