id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
news-45742583
https://www.bbc.com/amharic/news-45742583
ስለአዲሱ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ጥቂት እንንገርዎ
ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ሆነው ተሾሙ።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩትን ኢንጅነር ስመኘው በቀለን ህልፈት ተከትሎ ምክትል ስራ አስኪያጅ ሆነው ሲሰሩ የነበሩት ኢንጂነር ኤፍሬም ወ/ኪዳን የርሳቸውን ቦታ ተክተው ላለፉት ሁለት ወራት በጊዜያዊነት ሲያገለግሉ ነበር። በትናንትናው ዕለት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ የግድቡን የግንባታ ፕሮጀክት ለሚመሩ ግለሰቦች ኃላፊነት ሰጥተዋል። በመሆኑም ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው ሲሾሙ ኢንጅነር ኤፍሬም ወ/ኪዳንና አቶ ፈቃዱ ከበደ ምክትል ስራ አስኪያጅ ሆነው እንዲሰሩ መመደባቸውን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። • ለህዳሴ ግድብ ግንባታ መዘግየት ምን አይነት መፍትሔዎች እየተሰጡ ነው? ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ማን ናቸው? ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ በምንህንድስና ሙያ በተለያዩ ቦታዎች ሲያገለግሉ ቆይተዋል። *በግቤ አንድ ፕሮጀክት ላይ በምህንድስ ሙያ ሲያገለግሉ፤ በዚያው ፕሮጀክት ላይ ከ1999 -2004 ድረስ ምክትል ስራ አስፈፃሚ በመሆን ሰርተዋል። በኢትዮጵያ መብራት ኃይል ድርጅት የኤሌክትሮ መካኒካል ክፍል ኃላፊ ሆነው ሲያገለግሉም ነበር። ኢንጂነር ክፍሌ ከ2006-2010 ድረስ በጣና በለስ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው ሰርተዋል። በ2011 የታላቁ ህዳሴ ግድብ ከተጀመረ በኋላ ከአንድ ዓመት በላይ የፕሮጀክቱ የኤሌክትሮ መካኒካል ክፍል ዋና ስራ አስኪያጅ ነበሩ። • ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሕይወታቸው ያለፈው በጥይት ተመተው ነው፡ ፌደራል ፖሊስ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ የህዳሴው ግድብ ስራ አስኪያጅ ሆነው ሲሾሙ ኢንጅነር ክፍሌ ደግሞ ከ1000 ኪሎሜትር በላይ የሚረዝመውን ኢትዮጵያና ኬንያን የሚያገናኘውን የመብራት ኃይል ዝርጋታ ፕሮጀክት ከ2013-2014 ስራ አስኪያጅ ሆነው ሲሰሩ ነበር። ከዚያ በኋላም እስከ 2016 የኢትዮጵያ የኃይል ማመንጫ ውስጥ የፕሮግራም ኃላፊ ( Generation program officer) ሆነዋል። የስራ አስፈፃሚው አማካሪ በመሆን ካገለገሉ በኋላ ወደ ግል ስራ ተመልሰው እየሰሩ ሳለ ነው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው የተሾሙት • «የምታገለው ለማንም ብሔር የበላይነት አይደለም» አቶ በቀለ ገርባ የትምህርት ደረጃ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ወለጋ ተወልደው ያደጉ ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በመንዲ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት፤ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በቤተል ደምቢዶሎ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል። በ1984 በኤሌክትሪካል ምህንድስና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል። ከዚያም በተለያዩ ቦታዎች ሲያገለግሉ ቆይተው በ1999 ለስልጠና ወደ ጀርመን አገር አቅንተው ለ15 ወራት ተጨማሪ ስልጠና ተከታትለዋል። በ2015 ከእንግሊዝ ሳል ፎርድ ዩኒቨርሲቲ በፕሮጀክት ማኔጅመንት ሁለተኛ ድግሪያቸውን ተቀብለዋል። * ከላይ የተጠቀሱት ሁሉም የዘመን አቆጣጠሮች እንደ አውሮፓውያኑ ናቸው።
news-52816677
https://www.bbc.com/amharic/news-52816677
የሩሲያ ቅጥረኞች ሊቢያን ቀጣይዋ ሶሪያ እንዳያደርጓት ተሰግቷል
የአምባገነኑን የሙአመር ጋዳፊን ሞት ተከትሎ ወደ ዲሞክራሲ ትገባለች የተባለችው ሊቢያ ወደለየለት ቀውስ ካመራች ድፍን 10 ዓመት ልትደፍን ነው።
ባለፈው ሳምንት የተማረከ የሩሲያ ከባድ ጦር መሳሪያ አንድ የቀጠናው ተንታኝ ሊቢያ ከዚህ በኋላ ወደ ፍጹም ሰላም ለመምጣት ሌላ 10 ዓመት ይወስድባታል ሲሉ ተነብየዋል። ምክንያታቸው ደግሞ በዚያች አገር በርካታ የውጭ ኃይሎች እጃቸውን ማስገባታቸው ነው። በቀዳሚነት ምሥራቅ ሊቢያን የሚቆጣጠረው የጦር ጄኔራሉ ኻሊፋ ሃፍጣርን የሚደግፉት ግብጽ የተባበሩት ኢምሬትስ እና ሩሲያ ሲሆኑ ውስጥ ውስጡን ፈረንሳዮችም ድጋፍ ያደርጉለታል። በተባበሩት መንግሥታት እውቅና ያገኘውን የትሪፖሊ መንግሥት ደግሞ ኳታር በተለይ ደግሞ ቱርክ ታግዘዋለች። የረመዳን ወር ከገባ ወዲህ ከጦርነት አፍታ ብንወስድ አይሻልም ወይ ሲል የሰላም ጥሪ ያቀረበው ጄኔራል ሃፍጣር ሲቆጣጠራቸው የነበሩ ገዢ መሬቶቹን ተነጥቆ ነበር። እንዲያው አንዳንዶች ኻሊፋ ሃፍጣር አብቅቶለታል ለማለት ዳድቷቸው ታይተዋል። ሆኖም ዛሬ አሜሪካ ይፋ ባደረገችው መረጃ ጄኔራሉን ለመደገፍ ሩሲያ ረቂቅ የጦር መሣሪያ ወደ ሰሜን አፍሪካዊቷ አገር ሊቢያ በገፍ እያስገገባች ነው። ይህ የአሜሪካ መረጃ እውነት ከሆነና ጦርነት ካገረሸ ሊቢያ ዳግማዊ ሶሪያ የመሆን እጣ ፈንታ ሊገጥማት ይችላል ተብሏል። የአሜሪካ የአፍሪካ ወታደራዊ ጉዳዮች እዝ (አፍሪኮም) ይፋ ባደረገው መረጃ ሩሲያ ቅጥረኛ ተዋጊዎችን ለማገዝ የሚሆኑ ተዋጊ ጄቶችን ወደ ሊቢያ እያጋዘች ነው። በሊቢያ ቅጥረኛ ተዋጊ ሆኖ የሚሰራው የሩሲያ የጦር ኩባንያ ዋግነር ግሩፕ ሲሆን ንብረትነቱም በእጅ አዙር የፑቲንና አስተዳደራቸው እንደሆነ በስፋት ይታመናል። ይህን ቅጥረኛ ጦር ወደዚያ መላኳ ሩሲያ በጦርነቱ እንደአገር እጇ እንደሌለበት ለማስተባበል ምቹ እንዲሆንላት የዘየደችው መላ መሆኑ ነው። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ከሰሞኑ ውጊያ ካልቀናው ጄኔራል ኻሊፋ ሃፍጣር ጋር የስልክ ቆይታ ማድረጋቸው ተሰምቷል። አሜሪካ እንደምትከሰው የሩሲያ ተዋጊ ጄቶች በሶሪያ ምድር የአፍታ እረፍት እያደረጉ ስሪታቸው የራሺያ እንዳይመስል ቀለም እየተቀቡ ወደ ሊቢያ እያቀኑ ያሉት። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እውቅና ያለው የሊቢያ መንግሥት ሰሞኑን እንደገለጸው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በቱርክ ድጋፍ ከ1ሺ በላይ የሩሲያ ቅጥረኞች ከሊቢያ ተገፍተው ወጥተዋል። በአንቶኖቭ አውሮፕላን ተጭነውም ወደ ሩሲያ ሄደዋል። ሩሲያም ሆነች ኻሊፋ ሃፍጣር ይህን ዘገባ አላስተባበሉም። የቱርክ ሳባህ ጋዜጣ የትሪፖሊ ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ ትናንት ስምንት የሩሲያ ሚግ-29 ጄቶች እንዲሁም ሱ-24 የጦር አውሮፕላኖች ከሶሪያ ተነስተው ወደ ሊቢያ በረዋል። ሊቢያ በነዳጅ ሀብቷ እጅግ የናጠጠች ሀብታም አገር መሆኗና የውጭ ኃያላን አገሪቱንም ሆነ አካባቢውን ለመቆጣጠር ካላቸው ላቅ ያለ ፍላጎት የተነሳ በዚያች አገር የውክልና ጦርነት ከማድረግ አልፈው ትሪፖሊን የፍልሚያ መድረክ አስመስለዋታል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንዲሁም የአውሮፓ ኅብረት፣ ቀጥሎም የጀመርኗ መራሂተ መንግሥት በተለያዩ ጊዜያት በዚያች አገር እጃቸውን ያስገቡ ኃይሎችን ወደ ጠረጴዛ ውይይት ጋብዘው የሰላም ስምምነቶችን ያስፈረሙ ሲሆን ተግባራዊነቱ ግን ቧልት ሆኗል።
news-50542193
https://www.bbc.com/amharic/news-50542193
ቻይና እሥር ቤት ያሉ ሙስሊም ዜጓቿን እያሰቃየች ነው
ለመጀመሪያ ጊዜ ከቻይና ሾልከው የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊም ቻይናውያን በግዳጅ እምነታቸውን እንዲተው እየተደረጉ ነው።
በምዕራባዊዋ የቻይና ክፍል ዢንጂያንግ የሚገኙት 'ካምፖች' በፈቃዳቸው ለሚቀላቀሉ ዜጎች ትምህርት የሚሰጥበት ነው ስትል ቻይና ታስተባብላለች። ነገር ግን ቢቢሲ ያገኛቸው ኦፊሴላዊ መረጃዎች እሥረኞቹ ተዘግቶባቸው እምነትና አስተሳሰባቸውን እንዲቀይሩ ስቃይ የበዛበት ቅጣት እንደሚደርስባቸው ያሳያሉ። በእንግሊዝ የቻይና አምባሰደር መረጃዎቹን ሃሰተኛ ዜና ሲሉ ያጣጥሏቸዋል። ቢቢሲ ፓናሮማን ጨምሮ ከሌሎች 17 ዓለም አቀፍ ሚድያዎች ጋር የሚሠራው ዓለም አቀፉ የመርማሪ ጋዜጠኞች ኮንሰሪተም ነው መረጃዎቹን ይፋ ያደረገው። አንድ ሚሊዮን ገደማ ቻይናውያን እንደሚኖርባቸው የተጠረጠሩት እኒህ 'ካምፖች' ውስጥ በግዳጅ እንዲኖሩ የሚደረጉት አብዛኛዎቹ የዊገር ሙስሊሞች ናቸው ተብሏል። ኮንሰሪተሙ ያገኘው አንድ ጥብቅ መረጃ የቀድሞው የዢንጂያንግ ክፍለ ግዛት ደህንነት ኃላፊ ለእሥር ቤቱ ኃላፊዎች የፃፉት ደብዳቤ ይገኝበታል። ደብዳቤው ኃላፊዎቹ እሥር ቤቱን በጥብቅ ደህንነት እንዲያስጠብቁት፤ ከረር ያለ ዲስፕሊን እንዲከተሉ፤ ማንም ሊያመልጥ እንዳይሞክርና ከበድ ያለ ቅጣት እንዲጣል የሚያዝ ነው። አልፎም ማንዳሪን የተሰኘው የቻይና ኦፊሴላዊ ቋንቋ ብቸኛው የመግባብያ ቋንቋ እንዲሆን፤ ኑዛዜ እንዲለመድ፤ ተማሪዎች ለውጥ እንዲያመጡ እና ካሜራዎች በሚታዩ ቦታዎች እንዲሰቀሉ የሚሉ ትዕዛዞችን ያዘለ ነው። ሌላው ቀርቶ ተማሪዎች የሚተኙበት አልጋ አቀማመጥ፤ ለምግብ የሚሰለፉበት ሥነ-ሥርዓት፤ ትምህርት ቤት የሚቀመጡበት ሁኔታ አንዳች እንዳይዛነፍ ትዕዛዝ ተላልፏል። ከቻይና መንግሥት ያመለጡት መረጃዎች ተማሪዎቹ አንዲት እንኳ ዲስፐልኢን ጥሰው ቢገኙ ከባድ ቅጣት እንዲመደርስባቸውና የእያንዷንዷ ደቂቃ ሕይወታቸው ክትትል እንደሚደረገበት ያሳያሉ። ተማሪዎች ከእሥር ቤቱ የሚወጡት የምር ለውጥ አምጥተዋል ተብሎ ሲታመንባቸው እንደሆነም ተደርሶበታል። አንደ ሌላ ያመለጠ ዶኪዩመንት ደግሞ የሌላ ሃገር ዜግነት ያላቸው የዊገር ሙስሊሞች ተለይተው እንዲታሠሩና ኑሯቸውን በሌሎች ሃገራት ያደረጉ ደግሞ በመኪና እንዲጋዙ መደረጋቸውን ያትታል። በእንግሊዝ የቻይና አምባሰደር ሊዩ ዢያዎሚንግ እርምጃዎች ስኬታማ መሆናቸውን ለማስረገጥ ባለፉት ሶስት ዓመታት በቻይና አንዳችም የሽብር አደጋ አለመድረሱን ያነሳሉ። የእያንዳንዱ ዜጋዋን የዕለተ'ለት ሕይወት ትሰልላች የምትባለው ቻይና በመብት ተሟጋቾች ዘንድ ከፍተኛ ወቀሳ ይደርሳባታል።
news-51520205
https://www.bbc.com/amharic/news-51520205
በደም እጥረት እየተፈተነች ያለቸው ኬንያ
ኬንያ በበርካታ ሆስፒታሎቿ የደም እጥረት እያጋጠመ መሆኑን ተከትሎ የታማሚዎች ቤተሰብና ጓደኞች ደም ለጋሽ ፍለጋ እንደሚንከራተቱ የኬንያ ቀይ መስቀል አስታውቋል።
ማህበሩ ይህንን ችግር ለመቅረፍ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በተለይም ትዊተርን በመጠቀም ዜጎች ደም እንዲለግሱ ጥሪውን እያስተላላፈ ነው። • የደም ሻጮችና ለጋሾች ሠልፍ • በሰው ክፋይ ሕይወት መዝራት - የኩላሊት ንቅለ ተከላ በአጠቃላይ የደም ለጋሾችን ቁጥር ከፍ ለማድረግ ከሚሰራው ቅስቀሳ በተጨማሪ እስካሁን የ 10 ደም ፈላጊዎችን ምስል በትዊተር ገጻቸው ላይ በመለጠፍ ኬንያውያን ሕይወታቸውን እንዲታደጉ እስከመጠየቅ ደርሰዋል። ለመሆኑ ኬንያ ምን ያህል ደም ያስፈልጋታል እጥረቱስ ለምን ተፈጠረ? በዓለም አቀፉ ጤና ድርጅት መመሪያ መሰረት ኬንያ ካላት የህዝብ ቁጥር አንጻርና ሊኖሩ የሚገቡ ደም ለጋሾችን ከግምት በማስገባት በዓመት እስከ 1 ሚሊየን ዩኒት ደም ከለጋሾች መገኘት አለበት። ኬንያ በአሁኑ ሰአት 47 ሚሊየን ህዝብ ያላት ሲሆን 1 % የሚሆነው ዜጋ ብቻ እንኳን ደም ቢለግስ በዓመት 470 ሺ ዩኒት ደም ማግኝት ይቻል ነበር። ነገር ግን በፈረንጆቹ 2018/2019 በተሰበሰበ መረጃ መሰረት አገሪቱ በዓመት መሰብሰብ የቻለችው 164 ሺ ዩኒት ብቻ ነው። በዚህም ምክንያት ኬንያውያን ደም ለመለገስ ብዙም ፍላጎት ከሌላቸው ሀገራት መካከል ሆናለች። ከላይ የተጠቀሰው ቁጥርም በቅርብ ዓመታት ለውጥ የሚያመጣ አይመስልም። ከዚህ በተጨማሪ በ 2018 ደማቸውን ከለገሱ ኬንያውያን መካከል 77 % የሚሆኑት የመጀመሪያ ጊዜ ለጋሾች ናቸው። ይህ ደግሞ ምን ያክል የደም ልገሳ ባህል በኬንያ የተዳከመ እንደሆነ ያሳያል። በቋሚነት ደም የሚለግሱ ሰዎች ቀጣይነት ባለው መልኩ የደም ክምችት እንዲኖር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላቸው ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚለግሱትን ለማግኘትና ለማሳመን የሚፈጀውን ገንዘብና ጊዜም ይቆጥባል። ባለፉት ዓመታት ኬንያ ከሚያስፈልጋት የደም ክምችት 80 % አካባቢ የሚሆነው የሚገኘው ከለጋሽ ሀገራት በሚገኝ እርዳታ እንደነበር አንድ የመንግሥት ድርጅት ያወጣው ሪፖርት ያሳያል። • ‘በአስራ አራት ዓመቴ ስደፈር የሚያሳይ ቪዲዮ በወሲብ ፊልም ድረገፅ ላይ ነበር' ዋነኛው ድጋፍ ሰጪ ደግሞ የአሜሪካ መንግስት ነው። 'ፔፕፋር' በመባል የሚታወቀውና ከኤች አይ ቪ ኤድስ ጋር በተገናኘ ለሚሰቃዩ በመላው ዓለም ለሚገኙ በሸተኞች የደምና ሌሎች ድጋፎችን ይሰጥ ነበር ይኸው ፕሮግራም። ኬንያ ደግሞ የዚህ ፕሮግራም ዋነኛ ተጠቃሚ የነበረች ሲሆን ባሳለፍነው መስከረም ላይ ግን ለፕሮግራሙ የሚሰጠው የገንዘብ ድጋፍ ተቋርጧል። በዚሁ ጉዳይ ላይ የሚሰሩትና የመንግሥት ሀላፊ የሆኑት ሩዌይዳ ኦቦ እንደሚሉት ኬንያ በፕሮግራሙ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ጥገኛ ነበረች። '' የአሜሪካ መንግሥት የገንዘብ ድጋፉን ሲያቆም ሀገሪቱ መጠባበቂያም ሆነ ሌላ አማራጭ አልነበራትም'' ብለዋል። የኬንያ ብሄራዊ ደም ማዕከል ሀላፊ የሆኑት ዶክተር ፍሪዳህ ጎቬዲ በበኩላቸው መንግስት ድንገት በተፈጠረው ነገር ግራ መጋባቱንና አፋጣኝ እርምጃ ግን መወሰድ እንዳለበት አሳስበዋል። '' ልክ መስከረም ላይ ፕሮግራሙ ሲቋረጥ በቀን የምናገኘው ደም 1000 ዩኒት ብቻ ነበር። በቀን ቢያንስ ቢያንስ በትንሹ 1500 ዩኒት የሚያስፈልግ ሲሆን በዓለማቀፍ ደረጃ ግን በቀን 3000 ዩኒት ግዴታ ነው።'' • ክትባት ከየት ተነስቶ የት ደረሰ? ዶክተር ፍሪዳህ እንደሚሉት አብዛኛዎቹ ኬንያውያን ስለደም ልገሳ የተሳሳተ አመለካከት ነው ያላቸው። '' አንዳንድ ሰዎች ደም ከለገሱ የሚሞቱ ይመስላቸዋል፤ ወይም ደግሞ ደማቸው ከሌላ ሰው ደም ጋር ከተቀላቀለ ለመንፈሳቸው ጥሩ እንዳለልሆነ ያምናሉ። ሌሎች ደግሞ ደም ከሰጡ በኋላ በዛውም የሌሎች በሽታዎች ምርመራ ስለሚደረግ ውጤቱን ለመስማት እሱን ይፈራሉ።'' የኬንያ መንግሥት ዜጎች ደም በፈቃዳቸው እንዲለግሱ የተለያዩ ግንዛቤ ማስጨበጫ ዝግጅቶችን ያካሂዳል። በተለይ ደግሞ ጎልማሶችን ለማሳተፍ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው። በአሁኑ ሰአት አብዛኛው ደም የሚገኘው ከሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ነው።
news-54814573
https://www.bbc.com/amharic/news-54814573
የትግራይ እና የፌደራል መንግሥት ከየት ወዴት?
በትግራይ ክልል ገዥ ፓርቲ ሕወሓትና በማዕከላዊው መንግሥት መካከል ያለው ቁርሾ ወደ ተኩስ ልውውጥ አምርቷል። አልፎም ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።
ለመሆኑ የሕወሓትና የፌዴራል መንግሥቱ ቁርሾ የጀመረው እንዴትና መቼ ነው? ሰኔ 6፣ 2010 ዓ. ም. - ሕወሓት የፌዴራል መንግሥት ከኤርትራ መንግሥት ጋር ሰላም ለመፍጠር ማቀዱን የሚተች መግለጫ አወጣ። መግለጫው በያኔው ኢሕአዴግ ውስጥ ያሉ 36 ሕግ መወሰኛና 180 የምክር ቤት አባላት አስቿኳይ ስብሰባ እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረበ። የስብሰባው ዋነኛ ዓላማ የባድመ ጉዳይ ነበር። ጥቅምት 5፣ 2012ዓ. ም. - ሕወሓት ኢሕአዴግ ከስሞ እንደ አንደ ፓርቲ ሊዋቀር መሆኑን ተቃወመ። በወቅቱ ድርጅቱ በምክንያትነት ያቀረበው አንድ ውህድ ፓርቲ መዋቀሩ ለአንድነት አደጋ ነው የሚል ነበር። ሕወሓት የኢሕአዴግን መክሰም በመቃወም የአዲሱ ፓርቲ [ብልፅግና ፓርቲ] አካል እንደማይሆን አሳወቀ። ጥቅምት 9፣ 2012 ዓ. ም.- የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ የኢህአዴግ መሥራች የሆነው ሕወሓት አዲስ አሃዳዊ ፓርቲ ማዋቀር አያስፈልግም ማለቱን ተቹ። . መከላከያ ሠራዊት በሕወሃት ላይ የኃይል እርምጃ እንዲወስድ መታዘዙ ተሰማ . የሚኒስትሮች ምክር ቤት በትግራይ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ . የአሜሪካና የእንግሊዝ ኤምባሲዎች ውጥረቱ እንዲረግብ ጠየቁ ጥቅምት 29፣ 2012ዓ. ም.- ኢሕአዴግ ከስሞ አንድ ዉህድ ፓርቲ እንዲቋቋም ተወሰነ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ በትዊተር ገፃቸው "የኢሕዴግ አባላት አንድ ፓርቲ ለማዋቀር ያደርግነው ስብሰባ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል። አንድ ወጥ ፓርቲ መዋቀሩ የፌዴራል ሥርዓቱን ያጠናክረዋል፤ ድምፅ ለሌላቸውም ድምፅ ይሆናል" ሲሉ ፅፈው ነበር። ኅዳር 7፣ 2012 ዓ. ም.- ሕወሓት፤ ኢሕአዴግ ሙስናን በመታገል ሰበብ የትግራይ ሰዎችን ዒላማ እያደረገ ነው ሲል ተቸ። ኅዳር 10፤ 2012ዓ. ም.- ሕወሓት፤ ኢሕአዴግ አባል ፓርቲዎችን ለማዋቀር የሚያስችል ሥልጣን የለውም አለ። "የኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ አንድ ፓርቲ ማወቀር ላይ ሳይወያይ ውሳኔ ወስኗል፤ ይህ ደግሞ ሕጋዊ አይደለም" በማለት በኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እንደማይገኝ አስታወቀ። ኅዳር 11፣ 2012ዓ. ም.- የኢሕአዴግ ምክር ቤት ፓርቲው ከስሞ ብልፅግና ፓርቲ እንዲቋቋም ያለተቃውሞ ወሰነ። ሕወሓት በስብሰባው ላይ አልተገኘም ነበር። ኅዳር 16፣ 2012 ዓ. ም.- ሕወሓት፤ ኢሕአዴግ አባላቱን በአንድ ፓርቲ ጥላ ሥር ማዋቀር የሻተው በርካታ ሕዝብ ያላቸው ክልሎችን ለመጥቀም ነው ሲል ወነጀለ። "ውሳኔው እኩልነት ላይ የተመሠረተ አንድነት አያመጣም። ጨቋኝ መሪና ተጨቋኝ ሕዝብ ይፈጥራል እንጂ" ብሎ ነበር ሕወሓት በወቅቱ። ኅዳር 23፣ 2012ዓ. ም.- ሕወሓት "ሕገ መንግሥቱንና ፌዴራል ሥርዓቱን የሚታደግ ብሔራዊ መድረክ" የተሰኘ መድረክ በማዘጋጀት የብልፅግናን መዋቀር ተቃወመ። በወቅቱ የሕወሓት ምክትል ኃላፊ የነበሩት ደብረፂዮን ገብረሚካኤል "ሕገ መንግሥቱ በግለፅ እየተጣሰ ነው፤ ሰላም እየራቀ ነው፤ የዜጎች ደህንነት አደጋ ላይ ወድቋል፤ ከቆየ መሰደድና የንብረት ውድመት ተስፋፍቷል" ሲሉ ተደምጠዋል። ኅዳር 29፣ 2012ዓ. ም. - የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ [ትሕዴን] ከሕወሓት ጋር መዋሃዱን ይፋ አደረገ። የፓርቲው ሊቀ መንበር ተስፋዬ መኮንን "አሁን ያለውን የኢትዮጵያዊ ሁኔታ በማየት ፓርቲያችን ከስሞ ከሕወሓት ጋር ለመዋሃድ ወስነናል" ብለው ነበር። ታኅሣሥ 7፣ 2012ዓ. ም.- ሕወሓት፤ ብልፅግና ፓርቲ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስላልተመዘገበ ሕጋዊ ፓርቲ አይደለም ሲል ኮነነ። የሕወሓት ከፍተኛ አመራር የሆኑት ጌታቸው ረዳ "ብልፅግና ሃሰት ነው። ግልፅ የሆነ ራዕይና አቅጣጫ የለውም" ሲሉ ተደመጡ። ታኅሣሥ 20፣ 2012ዓ. ም.- ኢሕአዴግን የመሠረቱት ሶስቱ ፓርቲዎች [ብአዴን፣ ኦህዴድና ደህዴን] ክደውናል ሲል ሕወሓት ወቀሰ። ግንቦት 29፣ 2012ዓ. ም.- ሕወሓት ብልፅግና ሕጋዊ አይደለም በማለት ፓርቲውን እንደማይቀላቀል አሳወቀ። ሕወሓት በወቅቱ ባወጣው መግለጫ "ኢሕአዴግ በመሥራች አባላቱ ክህደት ምክንያት ከስሟል። ምክር ቤታችን ይህን ድርጊት ይቃወማል" ብሎ ነበር። ጥር 13፣ 2012ዓ. ም.- ጠ/ሚ አብይ አሕመድ የሕወሓት አባላትን ዒላማ እያደረጉ ነው ሲል ሕወሓትን ወቀሱ። በወቅቱ ጠ/ሚ አቢይ፤ ፈትለወርቅ ገብረእግዚያአብሔርን ከሥልጣናቸው ማንሳታቸውን ተከትሎ ነው ሕወሓት ይህን መግለጫ ያወጣው። ጥር 16፣ 2013ዓ. ም.- የአማራ ክልል፤ ሕወሓት በጥምቀት በዓል ወቅት "የሽብር ድርጊት ለመፈፀም" ቡድኖች ልኳል ሲል የትግራይ ክልል ገዥ ፓርቲን ወቀሰ። "ሽብር አድራሾች" በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንም አሳወቀ። ጥር 25፣ 2012ዓ. ም.- ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ፓርላማ ቀርበው ሚኒስቴሮችን በብሔራቸው ምክንያት እንዳላባረሩ ተናገሩ። ካቢኔያቸውን የማዋቀር ሥልጣን እንዳላቸውም ተናገሩ። የትግራይ ሕዝብ የፈለገው መንግሥት አካል መሆን ይችላል ሲሉም ተናገሩ። ጥር 26፣ 2012ዓ. ም.- ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሕወሓትና ለብልፅግና ንብረት አከፋፈለ። ይህ የሆነው ሕወሓት ለቦርዱ ደብዳቤ ከፃፈ በኋላ ነው። የካቲት 1፣ 2012 ዓ. ም.- የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሕወሓት የሰላም ሂደቱን እያደናቀፈ ነው ሲሉ ወቀሱ። የኤርትራው ማስታወቂያ ሚኒስቴር የማነ ገብረመስቀልም ይህን የሚያንፀባርቅ ፅሑፍ ፃፉ። ሚያዝያ 27፣ 2012ዓ. ም.- ሕወሓት ክልላዊ ምርጫ እንደሚያደርግ አስታወቀ። የፌዴራል መንግሥት በኮቪድ-19 ምክንያት ምርጫው እንዲራዘም ማድረጉ ይታወሳል። ጳጉሜ 4፣ 2012ዓ. ም.- የትግራይ ክልል ምርጫ አካሄደ። መስከረም 1፣ 2013ዓ. ም.- ሕወሓት ክልላዊውን ምርጫ ማሸነፉን ይፋ አደረገ። በክልሉ ምርጫ ኮሚሽን መሠረት ሕወሓት ከ2.6 ሚሊዮን መራጮች 98.2 በመቶ ድምፅ በማግኘት ነው ያሸነፈው። መስከረም 26፣ 2013ዓ. ም. - የሕወሓት አባል የሆኑ የመንግሥት ሠራተኞች ወደ ትግራይ ክልል እንዲመለሱ ትዕዛዝ አስተላለፈ። መስከረም 25 የተደረገው የፓርላማ መክፈቻም ህገ ወጥ ሲል ፈረጀ። ጥቅምት 14፣ 2013ዓ. ም. - የፌዴራል መንግሥት ወታደራዊ የሥልጣን ሹም ሽር ሊያደርግ ነው መባሉን ተከትሎ የትግራይ ክልል ማዕከላዊው መንግሥት ይህን ማድረግ የሚያስችል ሥልጣን የለውም አለ። ጥቅምት 18፣ 2013ዓ. ም.- አንድ ነባር ወታደራዊ መኮንን ወደ መቀለ እንዳይገቡ ሕወሓት አገደ። አልፎም የሰሜን ዕዝን ለመምራት አዲስ የተሾሙት ሜጀር ጄነራል በላይ ስዩም ወደ ክልሉ መግባት እንደማይችሉ አሳወቀ። ጥቅምት 22፣ 2013ዓ. ም. - የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሕወሓትን እርምጃ ተከትሎ መሰል እርምጃዎችን እንደማይታገስ አስታወቀ።
news-51670285
https://www.bbc.com/amharic/news-51670285
ኮሮናቫይረስ፡ በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ ነን ያሉት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ ላኩ
ኮሮናቫይረስ በተቀሰቀሰባት የቻይናዋ ሁቤ ግዛት ዉሃን ከተማ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች 'ወደ አገራችን እንመለስ' ሲሉ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ደብዳቤ መፃፋቸውን የተማሪዎቹ ኅብረት ፕሬዝዳንት ዘሃራ አብዱልሃዲ ለቢቢሲ ገለፀች።
በዉሃን የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኅብረት 'ወደ አገራችን መልሱን' የሚለውን የተማፅኖ ደብዳቤ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴርም መላካቸውን ጠቁመዋል። ተማሪዎቹ ቤይጂንግ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከሳምንታት በፊት ወደ አገራቸው ለመመለስ ጥያቄ ማቅረባቸውን መዘገባችን ይታወሳል። የቻይና መንግሥት በወረርሽኙ ምክንያት መውታትም ሆነ መግባት ከከለከለባት የዉሃን ከተማ መውጣት የሚችሉበትን ሁኔታ ቢያመቻች አብዛኞቹ ተማሪዎች ወጪያቸውን ራሳቸው ሸፍነው ወደ ኢትዮጵያ መመለስ እንደሚፈልጉ ኅብረቱ ለተማሪዎቹ አሰራጭቶት በነበረው መጠይቅ ለማረጋገጥ ችሏል። ምንም እንኳ የቻይና መንግሥት አስፈላጊ ነገሮችን እያቀረበላቸው ቢሆንም ተማሪዎች ከባድ የሥነ ልቦና ጫና ላይ በመሆናቸው የግድ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ ለመፃፍ መገደዳቸውን ዘሃራ ትናገራለች። በዋጆንግ ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ዲግሪ ትምህርቷን እየተከታተለች ያለች ስሟ እንዲገለፅ ያልፈለገች ተማሪ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ስለምትኖር የምግብ አቅርቦት ቢኖራትም ከአንድ ወር በላይ በአንድ ክፍል ውስጥ በርና መስኮት ተዘግቶ "በቫይረሱ ከአሁን አሁን ተያዝኩ አልተያዝኩ" በሚል ከባድ የሥነ ልቦና ስቃይ ውስጥ እንዳለች ለቢቢሲ ገልፃለች። "በቀን ሦስት ጊዜ ከሚመጣው ምግብ በየትኛው ምክንያት በቫይረሱ እያዝ ይሆን ብዬ በጣም እጨነቃለሁ። ምክንያቱም ቫይረስ ነው አይቼ ምጠርገው ነገር አደለም፤ አየሩን ይቀይርልኛል ብዬ ኤሲ አበራለሁ ብሶብኝ መስኮት ከከፈትኩ በጭንቀት ጌታ ሆይ አደራህን እያልኩ ነው" በማለት ያለችበትን ሁኔታ ለማስረዳት ትሞክራለች። ወረርሽኙ በፈጠረው ተመሳሳይ የሥነ ልቦና ጫና ምክንያት ከቅርብ ጓደኞቻቸው ጋር እንኳ መግባባት ያቃታቸው ተማሪዎች መኖራቸውን የምትናገረው የተማሪዎቹ ኅብረት ፕሬዝዳንት ዘሃራ "የቀን ቅዥት ደረጃ የደረሱ ተማሪዎች አሉ" ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች። ዘሃራ እንደምትለው የአንዳንዶቹ ተማሪዎች የሥነ ልቦና ችግር ህክምና ወደሚያስፈልግበት ደረጃ የደረሰ በመሆኑ የዩኒቨርሲቲ ኃላፊዎችን ማነጋገር ሁሉ ግድ ሊል ይችላል። በተለይም በነገሮች ይደናገጡና ይረበሹ የነበሩ ልጆች አሁን አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ገብተዋል። አንድ ክፍል ውስጥ አብሮት የሚኖር ጓደኛው ምን ዓይነት የሥነ ልቦና ችግር ላይ እንዳለ የገለፀልን አንድ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪ "በዚህ ሳምንት ያየሁበት ነገር አብሬው የኖርኩት ጓደኛዬ አልመስል ብሎኛል። ነገሩ በጣም ሲያሳስበን ለዩኒቨርሲቲው አሳውቀናል" ያሉበትን ሁኔታ ገልጿል። በተጨማሪም ከአራት ቀናት በፊት የካዛክስታን ዜጋ የሆነች ተማሪ በቫይረሱ መያዝ ደግሞ ይበልጥ ብዙዎቹን እንደረበሻቸው ይህ ተማሪ ይናገራል። በዉሃን የተማሪዎች ኅብረት ለጠቅላይ ሚኒስትሩና ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ደብዳቤውን የላከው ከትናንት በስቲያ ሲሆን ደብዳቤው ለመድረሱ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ማረጋገጫ እንደደረሳቸው የኅብረቱ ፕሬዝዳንት ዘሃራ ገልፃለች። ምንም እንኳ ተመሳሳይ ማረጋገጫ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ባይደርሳቸውም ደብዳቤያቸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መድረሱን በሌላ መንገድ ማረጋገጣቸውንም ተናግራለች። ቢቢሲ የተማሪዎቹን ደብዳቤና ጥያቄ በተመለከተ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና የበሽታውን ጉዳይ በዋናነት ከሚከታተለው ከኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል። ወረርሽኙ ከተከሰተ በኋላ በቻይና የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች ወደ አገራቸው ለመመለስ በተደጋጋሚ ላቀረቡት ጥያቄ መንግሥት መጀመሪያ ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋል የሚል ምላሽ መስጠቱ የሚታወስ ነው። በግልፅ ባይሆንም እስካሁን በመንግሥት እየተሰጣቸው ያለው ምላሽ ተማሪዎቹን ላይቶ ማስቀመጥ የሚቻልበት ቦታ የለም የሚል እንደሆ ዘሃራ ትገልፃለች። ተማሪዎቹ መንግሥት ወደ አገራቸው መልሷቸው በለይቶ ማከሚያ ቢያስቀምጣቸውም ሆነ ሌሎች አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን ለማድረግ የሚያስችለውን እርምጃ ቢወስድ ተባባሪ እንደሆኑ ኅብረቱ በደብዳቤው ላይ አስፍሯል። ተማሪዎቹ ለቢቢሲ እንደገለጹት የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች ለማሟላት በሚል ከመንግሥት ለእያንዳንዳቸው የተላከላቸውን 400 ዶላር ከትናንት ጀምሮ እየወሰዱ ነው።
news-54073991
https://www.bbc.com/amharic/news-54073991
ቱርክ፡ በምሽት መዝናኛ ስፍራ ጥቃት ያደረሰው ከ1ሺህ ዓመት በላይ ተፈረደበት
የቱርክ ፍርድ ቤት ኢስታንቡል ከተማ በሚገኝ የምሸት መዝናኛ ስፍራ ጥቃት አድርሶ ለ39 ሰዎች ሞት ምክንያት በሆነውን ግለሰብ ላይ ከ1ሺህ ዓመት በላይ እስር ፈረደበት።
የቱርክ ፖሊስ በወቅቱ ይፋ እንዳደረገው ጥቃቱን የፈጸመው አብዱልካዲር ማሽሪፖቭ ከብዙ ፍለጋ በኋላ በቁጥጥር ሥር ውሏል። የኡዝቤኪስታን ዜጋ የሆነው አብዱልካዲር ማሽሪፖቭ የተላለፈበት የፍርድ ውሳኔ ከ40 የእድሜ ልክ እስራት ጋር የሚስተካከል ነው ተብሏል። ግለሰቡ ጥቃቱን ያደረሰው የአውሮፓውያኑ የ2017 አዲስ ዓመት መቀበያ ዋዜማ ላይ ሲሆን የፍርድ ሂደቱም ለሦስት ዓመታት ዘልቋል። አብዱልካዲር ማሽሪፖቭ የእስላሚክ ስቴት (አይኤስ) አባል ነው ተብሏል። በምሸት መዝናኛ ስፍራው ላይ ለደረሰው ጉዳትም ጽንፈኛው ቡድን ተጠያቂ ተደርጓል። ግለሰቡ በግድያ እና የቱርክን ሕገ-መንግሥት መተላለፍ በሚሉ ክሶች ነው ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘው። አለያስ ማማሳሪፖቭ የተባለው ሌላ ግለሰብ ደግሞ በምሽት መዝናኛ ስፍራው ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ተባባሪ ሆኗል ተብሎ በተመሳሳይ ከ1ሺህ ዓመት በላይ በእስር እንዲያሳልፍ ተበይኖበታል። የእስላሚክ ስቴትስ አባል መሆናቸውን ያመኑ 48 ሰዎችም በእስር እንዲቀጡ የቱርክ ፍርድ ቤት ውሳኔ ማስተላለፉን አናዱሉ የዜና ወኪል ዘግቧል። ጥቃቱ እንዴት ተፈጸመ? ከሦስት ዓመት በፊት አዲስ ዓመትን ለመቀበል ሬይና ተብሎ በሚጠራው የምሽት ክበብ በመዝናናት ላይ የነበሩ ሰዎች ላይ አብዱልካዲር ማሽሪፖቭ የተባለው ግለሰብ ተኩስ ከፍቷል። በደኅንነት ካሜራ የተቀረጹ ተንቀሳቃሽ ምስሎች እንደሚያሳዩት ማሽሪፖቭ አውቶማቲክ መሳሪያውን አውጥቶ ያለ ማቀረጥ ሰዎች ላይ ሲተኩስ ይታያል። መሳሪያውን መልሶ ጥይት እስኪያጎርስ ጊዜ እንዲያገኝ የእጅ ቦምብ ሰዎች ላይ ሲወረውርም ነበር ተብሏል። ጥቃቱን አድርሶ ከስፍራው ከመሰወሩ በፊት ጉዳት ደርሶባቸው ወድቀው የሚገኙ ሰዎች መሞታቸውን ለማረጋገጥ በጥይት ሲመታ ነበር። በጥቃቱ ከተገደሉት መካከል የእስራኤል፣ የፈረንሳይ፣ የቱኒዚያ፣ የሊባኖስ፣ የሕንድ፣ የቤልጄም፣ የዮርዳኖስ እና ሳዑዲ አረቢያ ዜጎች ይገኙበታል። ከጥቃቱ በኋላ ለሁለት ሳምንታት ተሰውሮ የቆየው ማሽሪፖቭ ከብዙ ፍለጋ በኋላ በቱርክ ፖሊስ ተይዟል።
news-46054072
https://www.bbc.com/amharic/news-46054072
የ29 ዓመቷ የህክምና ዶክተርና ኢንጅነር ዕልልታ ጉዞ
" በአንድ የትምህርት ዓይነት ብዙ ተማሪዎች ውጤት ሲበላሽብን መምህሩ ለእናንተ የህክምና ትምህርት አይገባችሁም አለን፤ በጣም ነበር የተናደድኩት"
ቢሾፍቱ ተወልዳ ያገደችው ዕልልታ ነጋ 2001 ዓ.ም. ላይ ነበር የህክምና ትምህርት ለመከታተል መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተመድባ ወደዚያው ያቀናችው ። ለሶስት ዓመታት ያህል ትምህርቷን ስትከታተል ብትቆይም ነገሮች እንዳሰበችው እንዳልቀለሉላት ታስታውሳለች። "አንዳንድ ሰው ችሎታሽን አቅምሽን ይንቃል፤ በአንድ የትምህርት ዓይነት ብዙ ተማሪዎች ውጤት ተበላሸብን፤ ህክምና ደግሞ በአንድ ኮርስ ከወደቅሽ ለመቀጠል በጣም ይከብዳል፤ ያኔ አስተማሪው 'ለእናንተ ሜዲሲን አይገባችሁም' አለን፤ ሶስት ዓመት ሙሉ ቆይተሽ እንደዚህ ስትባይ በጣም ይሰማል፤ እኔ ደግሞ ከልጅነቴ ጀምሮ ነበር ህክምና መማር የምፈልገው፤ እንደዛ ስባል በጣም ነበር የተናደድኩት፤ ከዚያ ሞራሌ ስለተነካ ቤተሰቦቼን ነግሬያቸው እኔ በቃ እዚህ በፍጹም አልቀጥልም ነበር ያልኩት፤ ግን በህክምና ትምህርት ጨርሼ ተመልሼ ሄጄ እንደማናድደው ነበር ያሰብኩት።" •"የመከላከያ ሚኒስቴርን በተሻለ መልኩ መምራት ይቻላል" ኢንጂነር አይሻ መሀመድ •አዲሷ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ማን ናቸው? •ከኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ እስከ ሣህለወርቅ ዘውዴ ዕልልታ አቅሟን ለማሳየት ቆርጣ ወደ አዲስ አበባ ተመልሳ በቤቴል ሜዲካል ኮሌጅ የህክምና ትምህርቷን እንደ አዲስ ሀ ብላ ጀመረች፤ ግን አሁንም አንድ ነገር አዕምሮዋን ይከነክናት ነበር። "አብሬያቸው ስማር ከነበሩ ልጆች ወደ ኋላ መቅረቴ በጣም ነበር የሚሰማኝ" የምትለው ዕልልታ በጓደኞቿ ጉትጎታ ይህን ስሜት የማሸነፊያ መንገድ አገኘች። "የነገርኳቸው ሁሉ 'ያምሻል እንዴ?" ነበር ያሉኝ "እንዲያውም እኔ ዶክተር ብቻ አይደለም መሃንዲስም እሆናለሁ አልኩኝ፤ የነገርኳቸው ሁሉ 'ያምሻል እንዴ?' ነበር ያሉኝ፤ አትችይውም ተይ ይከብድሻል፤ ይቅርብሽ የሚለኝ ብዙ ሰው ነበረ፤ እናቴ ራሱ በጣም ነበረ የተከራከችኝ።" ዕልልታ የብዙሃኑ ተቃውሞ ቢበረታባትም የሂሳብና የፊዚክስ ትምህርት እንደምትወድ ከሚያውቁት ጓደኞቿን ግን ሙሉ የሞራል ድጋፍ አገኘች። የሲቪል ምህንድስናውን ትምህርት በድፍረት ስትገፋበት ደግሞ አይዞሽ በርቺ የሚላት ሰው እየበዛ መጣ። "እኔም ትምህርቱን ወደድኩት፤ ለህክምናው ትምህርት ማንበብና ተግባራዊ ልምምዶችን ማድረግ ይጠበቅብኛል፤ ምህንድስናው ደግሞ በብዛት ካልኩሌሽን (የሂሳብ ቀመር) ነው፤ እሱን ስሰራ ጭንቅላቴ ፈታ ይላል፤ የህክምናው ንባብ ሲበዛብኝ ወደ ምህንድስናው ዞር ብዬ ቀመሩን እየሰራሁ ራሴን አነቃቃ ነበር።" አሁን ዕልልታ ይህንን ፈታኝ ጊዜ አልፋ በሰባት ዓመታት ውስጥ ሁለቱንም ጎን ለጎን እያስኬደች በ29 ዓመቷ ባለፈው ዓመት የህክምናና የምህንድስና ዲግሪ ባለቤት ሆናለች። በትምህርትና በፈተና ወቅት ያሳለፈቻቸውን ከባድና አልህ አስጨራሽ ጊዜያት ሁሉ የምትረታቸው የመጨረሻውን ፍሬ በማሰብ እንደነበር ትናገራለች። "በጣም ብዙ ጊዜ 'ምን እንቀልቅሎኝ ነው?' ብዬ አውቃለሁ፤ ለምሳሌ ፈተና በጣም ሲደራረብብኝ ሁለቱንም ለማንበብና ለመስራት ስጥር ውዬ የማድርባቸው ጊዜያት ነበሩ፤ የምህንድስናው ፈተና ብዙ ጊዜ 9 ሰዓት ላይ ነበር የሚሆነው። ስለዚህ የህክምናውን ጠዋት ተፈትኜ እየሮጥኩኝ ወደ ምህንድስናው ነበር የምሄደው፤ በጣም ስልችት ብሎኝ ልተወው እልና መልሼ ግን የመጨረሻውን ድሌን ማሰቤ ነው እንድገፋበት ያደረገኝ።" "ሰው ሳያያኝ ተደብቄ አልቅሼ አውቃለሁ" የህክምና ዶክተሯና መሐንዲሷ ዕልልታ ነጋ የህክምናውንን ትምህርት በቀን የሲቪል ምህንድስናውን ደግሞ በማታው ክፍለ ጊዜ ነበር የተማረቸው። ለሁለቱም ጊዜዋን ለማብቃቃት ደግሞ አስቀድሞ መዘጋጀት የሁልጊዜ መርኋ ነው። "የፈተና ቀኖች በብዛት ቀደም ብለው ነው የሚወጡት፤ በተለይም የተደራረቡ ፕሮግራሞች ካሉኝ እነሱን ቶሎ ብዬ ነው ለማጣራት የምሞክረው፤ እስከምችለውና ንቁ እስከሆንኩበት ሰዓት ደረስ በደንብ አጠናለሁ፤ እንቅልፌ ሲመጣ ያው በጭንቀት ቢሆንም እተኛለሁ፤ ፈተናዎች በጣም ከተደራረቡቡኝ ግን አልተኛም፤ እንቅልፍ ይነሳኛል፤ በተለይ ለህክምና ተማሪዎች በየዓመቱ መጨረሻ የሚደረግልን የቃል ፈተና (Oral examination) ሲደርሰ ደግሞ የማልተኛበት ጊዜ ይበዛል'" ዕልልታ እንዲያውም እንዳንዴ የቤት ውስጥ ስራ በማገዝ የተረፈውን ጊዜዬን እጠቀማለሁ ትላለች። ይሁንና የሚያስፈልጋትና ያላት ጊዜ አልጣጣም ብሏት መቼም የማትዘነጋገቸው፤ ስሜቷን መቆጣጠር ያልቻለችባቸውም ጊዜያትም አልፈዋል። "በህክምና ወደተግባራዊ ልምምድ ከመገባቱ በፊት የሚሰጠው የብቃት ማረጋጋጫ ፈተና ላይ ትንሽ ተቸግሬ ነበር፤ በጣም ከመጨናነቄ የተነሳ አስመልሶኝ ነበር፤ አንዳንዴ ደግሞ ፈተና በጣም ሲደራረብብኝ ለምን መረጥኩት? ምን ይሻለኛል? እያልኩኝ ሰው ሳያያኝ ተደብቄ አልቅሼ አውቃለሁ፤ አሁን ያ ቀን አልፎ ሳየው እያስታወስኩ እስቃለሁኝ።" ዕልልታ ከትምህርቷ አልፎ ከሌሎች ጋር የምታሳልፈው ጊዜ ስላልነበራት እንደመዝናኛ የምትቆጥረው አብረዋት ከሚማሩት ጓደኞቻ ጋር በሻይ ሰዓት የሚኖራቸውን ጨዋታ ነበር። "እኔ ስጀምር አትችይውም ተብዬ ነበር" አሁንም ቢሆን ህምክናውንም ሆነ ምህንድስናውን በመቀመር በምህንድስናው ያገኘችውን እውቀት በህክምና ተቋማት በተግባር ልምምድ ያስተዋለቻቸውን የአሰራር ግድፈቶች የማስተካከል ህልም አላት። "ለምሳሌ በርካታ ሆስፒታሎች ያየሁት በሕክምና ላይ ያለ ሰው ሲያርፍ እስከሬኑ የሚያልፈው በታካሚውና በአስታማሚዎች መሃል ነው፤ ይሄ ደግሞ ሌላው ታካሚን እኔም ቀጣይ ነኝ በሚል ተስፋውን ያሳጣል፣ አስታማሚንም ያጨናንቃል። አንዳንድ ሆስፒታሎች ደግሞ ለአካል ጉዳተኞችና በዊልቼር ለሚንቀሳቀሱ አረጋውያን የሚመቹ አይደሉም፤ ወይ ደረጃ ብቻ ወይ ደግሞ ደረጃና ሊፍት (አሳንሰር) ነው ያላቸው፤ እና ይህ መቀየር አለበት። ታካሚ አመላላሾችም መብራት ጠፍቶ ሊፍት ካልሰራ ተሸክመው ነው የሚሄዱት፤ እነዚህን ነገሮች ለወደፊት በምህንድስና ማስተካከል አፈልጋለሁ።" በሰባት ዓመታት ውስጥ ያገኘቻቸውን ሁለት የመጀመሪያ ዲግሪዎች በቀጣዮቹ ሰባት አመታት ውስጥ ደግሞ ወደተሻለ የትምህርት ብቃት ለማሳደግ ወጥናለች- መሃንዲሷ ዶክተር ዕልልታ ነጋ። "በኢንጅነሪንጉ ማስተርስ መስራት 'በህምክምናው ደግሞሞ የአጥንት ስፔሻሊስት መሆን እፈልጋለሁ። ከሲቪል ምህንድስናውም ጋር እኮ ይሄዳል፤ የተሰበረን አጥንት መጀመሪያ የነበረበትን ቦታ ጠብቆ መስራት ስለሆነ፤ ከዚህም በላይ ግን በተግባር ልምምዴ ወቅት በራስ ደስታ ሆስፒታል ያስተማረኝ ዶክተር የስራ ብቃትና ውጤቶችን ሳይ ወደዚያ አድልቻለሁ።" ዕልልታ እንዲህ ያሉ ፍላጎቶች የበርካታ ሴቶች መሆናቸውን ብትረዳም እስኪሳኩ ድረስ እስከመጨረሻው መታገልን ያሳለፍኳቸው ፈታኝ ግን ፍሬያማ ዓመታት አስተምረውኛል ትላለች። "እኔ ስጀምር አትችይውም ተብዬ ነበር፤ ግን ሞክሬው ተሳክቶልኛል፤ መጨረሻውን ብቻ ነበር የማየው። እንደ ሴት ብዙ ነገር ነው እኛ ላይ የሚጣለው፤ ግን ለሰው ብለን ህልማችን አንተወው።"
news-52398777
https://www.bbc.com/amharic/news-52398777
ኮሮናቫይረስ፡ በቺካጎ የኢትዮጵያውያን ማህበር መስራች አቶ መንግሥቴ አስረሴ በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው አለፈ
በቺካጎ የኢትዮጵያውያን ማኅበር መስራች አቶ መንግሥቴ አስረሴ ህይወታቸው በኮሮናቫይረስ ምክንያት ማለፉን ማኅበሩ ከሰዓታት በፊት በፌስቡክ ገፁ አስታውቋል።
ማኅበሩ በመስራቹና የመጀመሪያው ፕሬዚዳንቱ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልፆ በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅ እንደነበሩም አስታውሷል። ኢትዮጵያውያንን በማሰባሰብ፣ ለማኅበረሰቡ የቅርብ ደራሽ የነበሩት አቶ መንግሥቴ በቺካጎ የኢትዮጵያውያንን ማኅበር የመሰረቱትም ከ36 ዓመታት በፊት ነበር። በቺካጎ አካባቢ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዋልታ በመሆን፣ ድጋፍን በመቸር ይታወቁ ነበር የተባሉት አቶ መንግሥቴ ትንሽ፣ ትልቅ ሳይሉ ከሁሉ ጋር በመቀራረብ አንድነትን፣ ህብረትን በማምጣት በብዙዎች ዘንድ መወደድ የቻሉ ናቸው ተብሏል። በብዙዎችም ዘንድ ጋሽ መንግሥቴ ተብለው ይጠሩ እንደነበርም ማኅበሩ አስታውሶ በአሁኑም ወቅት በቦርድ አባልነት እያገለገሉ ነበር ብሏል። የአቶ መንግሥቴ ሞት በቺካጎ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤና ሃዘንን ያስከተለ ሲሆን በርካቶችም በፌስቡክስ የተሰማቸውን አስፍረዋል። "እኔም ሆነ ቤተሰቤ በጣም ነው የደነገጥነው። ወዳጄ ነበር፣ የማኅበረሰቡም ዋልታና ማገር ነበር። ሞታቸውንም አሁንም ማመን አልቻልኩም። ጋሽ መንግሥቴ በሁላችንም ህይወት ውስጥ የማይረሳ ትውስታን ጥሏል። በልባችንም ለዘላለም ይኖራል። ነፍሱን በሰማይ ያሳርፍ" ብለዋል ኪሮስ ተወልደ ገብርኤል የተባሉ ኢትዮጵያዊ። "እኔም ሆነ ባለቤቴ የተሰማንን ሃዘን ለመግለፅ ቃላት ያጥረናል። የተከበሩ፣ የረዥም ጊዜ ወዳጃችንን ጋሽ መንግሥቴ ማጣታችን ልባችንን ሰብሮታል። ነፍስዎን በሰማይ ያኑር። መቼም ቢሆን አይረሱም። ለቤተሰባቸው መፅናናትን ያምጣላቸው" በማለት አቶ ብርሃነ ሺፈራው አስፍረዋል። "ጋሽ መንግሥቴ አብሮ የመስራት እድል አግኝቼ ነበር። በጣም ታላቅ ሰው ነበሩ። ማመን ይከብዳል፤ በጣምም ያሳዝናል። አላህ ነፍሳቸውን በሰማይ ያሳርፍ። ለቤተሰባቸውም ሆነ ለማኅበረሰቡ ጥንካሬና ፅናት ይስጣቸው" ብሏል አቢቹ ኢድሪስ። ብዙዎችም በህይወት እያሉ ምን አይነት ታላቅ ሰው እንደነበሩ የዘከሩ ሲሆን ለቺካጎ ማኅበረሰብ ታላቅ ሰው፣ መካሪ፣ ታላቅ አባት እንዳጡም ገልፀዋል። ማኅበሩ እንዳሳወቀው የቀብር ሥነ ሥርዓታቸውንም በተመለከተ ለኮቪድ-19 ህሙማን በሚደረገው የአቀባበር ሥርዓት መሰረት እንደሚሆን ገልፆ፤ በዚህም መሰረት የቅርብ ቤተሰቦች እንደሚገኙም አስፍሯል። ባለፈው ሳምንት በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ እንደተናገሩት ከአንድ መቶ በላይ ኢትዮጵያዊያን በበሽታው መሞታቸውን መናገራቸው ይታወሳል። በኮሮናቫይረስ ክፉኛ ከተጠቁ አገራት መካከል ቀዳሚዋ እንደሆነች የተነገረላት አሜሪካ ውስጥ እስካሁን ከ46 ሺህ በላይ ሰዎች በበሽታው ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን ከ841 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ በወረርሽኙ መያዛቸው ተረጋግጧል።
news-56968682
https://www.bbc.com/amharic/news-56968682
መከላከያ ‘ነብይ’ እዩ ጩፋ ላይ ክስ ልመሰርት ነው አለ
የአገረ መከላከያ ሠራዊት በ'ነብይ' እዩ ጩፋ ላይ ክስ ሊመሰርት መሆኑን አስታወቀ።
የአገር መከላከያ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ 'ነብይ' እዩ ጩፋ የሠራዊቱን ስምና ታማኝነት በማሳጣት ለግል ፍላጎትና ጥቅም በማን አለብኝነትና ኃላፊነት በጎደለው አኳኋን ለፈፀመው ድርጊት በሕግ ይጠየቃል ሲሉ የአገር መከላከያ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ተናግረዋል። መከላከያ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ፤ "እዩ ጩፋ የተባለ በሐይማኖት ስም ፣ እየተከተሉኝ ነው ያላቸውን ግለሰቦች ክብር ባልጠበቀ መልኩ፣ ከነ ዩኒፎርማቸው፣ በቪዲዮና ፎቶ ቀርጾ በአደባባይ እንዲሰራጭ አድርጓል" ብሏል። "ጥቂት የሠራዊታችን አባላትም ይህን ፍላጎት ለማሟላት የሁሉም ኢትዮጵያውያን መለያ የሆነውን ወታደራዊ የደንብ ልብስ ለብሰው ተሳታፊ የሆኑ እንደነበሩ ተረጋግጧል" ብሏል። ከሰሞኑ የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ደንብ ልብስን የለበሱ ሰዎች 'ነብይ' እዩ ጩፋ በሚያገለግልበት መድረክ ላይ የደንብ ልብስ ለብሰው መገኘታቸውን የሚያሳይ ምስል በሰፊው ተሰራጭቶ ነበር። አነጋጋሪው 'ነብይ' እዩ ጩፋ ከዚህ ቀደም ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ ብዙውን ጊዜ እግሩን በመሰንዘር የአጋንንት ማስወጣት ተግባራትን እንደሚፈጽም ተናግሮ ነበር። የአገር መከላከያ ሠራዊት ከዚህ ቀደምም በጉዳዩ ላይ መግለጫ ሰጥቶ ነበር። እንደ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ከሆነ "የሠራዊታችን አባላት የፈለጉትን ዕምነት የመከተል መብት አላቸው። ይሁን እንጂ የተከበረውን የኢትዮጵያ ህዝቦች መመኪያ የሆነውን የደንብ ልብስ በመልበስ ማምለክ ፈጽሞ የተከለከለ ነው" ሲሉ ተናግረው ነበር። መከላከያ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ "የደንብ ልብስ ለብሰው ተሳታፊ የሆኑ አባላት በቁጥጥር ሥር ውለው ጉዳያቸውንም ወደ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ለማቅረብ የማጣራት ሥራ እየተሠራ ይገኛል" ብለዋል። የሕዝብ ግነኙነት ዳይሬክተሩ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ጥፋት በተለያዩ የእምነት ተቋማት የተገኙ አባላት ላይ የእርምት እርምጃ ተወስዶ እንደነበር አስታውሰው፤ "ወደፊትም ማንኛውም የሠራዊቱ አባል የየትኛውም እምነት ተከታይ ቢሆን በእንደዚህ አይነት ተግባር ውስጥ ተሳትፎ ከተገኘ ተጠያቂ ይሆናል" ብለዋል። "ሠራዊታችን በጋብቻ፣ በቀብር ጊዜ እና በእምነት ቦታዎች ክብሩን በጠበቀ መልኩ የሚከወኑ ስርዓቶች አሉት። ሠራዊቱም ከህዝብ የወጣ በመሆኑ በየግሉ ሐይማኖት ያለው መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። በኛ በኩል በህጋችን የተፈቀዱና የተከለከሉ ጉዳዮችን የማስረፅ ሥራም ይሠራል" ብለዋል። እዩ ጩፋ በፈውስ ትዕይንቶች፣ 'አጋንንትን በካራቴ በመጣል'ና በሌሎችም በርካታ ምክንያቶች አነጋጋሪና አወዛጋቢ ስለመሆኑ ከሁለት ዓመታት በፊት ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርጎ ነበር። እዩ ጩፋ ከእዩ ጋር የተደረገውን ሙሉ ቃለ ምልልስ እዚህ ማንበብ ይችላሉ። እዩ ጩፋ፡ ማን ነው ነብይ ያለህ?
news-56582177
https://www.bbc.com/amharic/news-56582177
ጉግል ማፕስ ለሥነ ምህዳር ተስማሚ የሆኑ መስመሮችን ማሳየት ሊጀምር ነው
ጉግል ማፕስ አሽከርካሪዎችን በተቀመጡ መስፈርቶች መሰረት የበለጠ ተስማሚ ሥነ ምህዳር (ኢኮ ፍሬንድሊ) ባለው አካባቢ እንዲያሽከረክሩ ማመልከት ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ።
ይህ አቅጣጫ ጠቋሚ መተግበሪያ የትራፊክ እንቅስቃሴንና የመንገድ ሁኔታን ከግምት ውስጥ በማስገባት አነስተኛ የካርቦን ልቀት ጉዞ ማድረግ የሚቻልበትን መስመር ይጠቁማል። ጉግል ይህ አሰራር በቅድሚያ በአሜሪካ ተግባራዊ እንደሚሆን ከዚያም በዓመቱ መጨረሻ አካባቢ ደግሞ "በመላው ዓለም ለማስፋት" እቅድ መኖሩን አስታውቋል። ይህ አዲሱ አሰራር ጉግል የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት ያለው ቁርጠኝነት ማሳያ ነው ተብሏል። መተግበሪያው ሥራውን ሲጀምር ተጠቃሚዎች ካልቀየሩት በስተቀር አማራጩ "ለሥነ ምሕዳር ተስማሚ" ላይ እንደሚሆን ተገልጿል። ሌሎች ፈጣን መንገዶች በኖሩ ጊዜ ጉግል አማራጮችን አቅርቦ ተጠቃሚዎች አነስተኛ የካርበን ልቀት ያለበትን መስመር እንዲመርጡ ያደርጋል ተብሏል። የጉግል ምርቶች ዳይሬክተር የሆኑት ራሰል ዲከር "ያየነው ነገር ለግማሽ ያህሉ መንገድ ለሥነ ምህዳር ተስማሚ የሆነ አማራጭ በዝቅተኛ ዋጋ ወይንም ያለምንም የዋጋ ለውጥ ማመልከት እንደምንችል ነው" ብለዋል። ይህ አቅጣጫ መፈለጊያ መተግበሪያ ባለቤቱ አልፋቤት ሲሆን መተግበሪያው የካርበን ልቀትን የተለያዩ መኪናዎችን እንዲሁም መንገዶችን በመውሰድ እንዲሁም የአሜሪካ መንግሥት ብሔራዊ የኃይል ላብራቶሪ መረጃዎችን በመቀመር መፈተሹን ገልጿል። "ይህ ሦስት ነገሮች በአንድነት ሲጣመሩ ጥሩ ማሳያ ነው መረጃ፣ ዘላቂነት እና የደንበኛ ምርጫ" ያለው ደግሞ የአማካሪ ድርጅቱ ኬይርኒ ባልደረባ ሲዳርት ፓታክ ነው። "ለውሳኔ እየወላወሉ የነበሩትንም ከፍጥነት፣ ከአዋጭነት እና ከዋጋ አንጻር እንዲወስኑ ይረዳቸዋል" ሲል አክሏል። ከሰኔ ወር ጀምሮ ጉግል አሽከርካሪዎችን አነስተኛ የካርበን ልቀት ባለበት መስመር እንዲያሽከረክሩ ማሳሰቢያ ይልክላቸዋል። ይህ በጀርመን፣ በፈረንሳይ፣ በኔዘርላንድስ፣ በስፔን እና በዩናይትድ ኪንግደም የተለመደ አሰራር ነው። "ከአምስተርዳም እስከ ጃካርታ ባሉ ከተሞች አነስተኛ የካርበን ልቀት ያላቸው ስፍራዎች ተለይተዋል። በእነዚህ አካባቢዎች አየሩ ንፁህ እንደሆነ እንዲቆይ በሚል የተወሰኑ የናፍጣ መኪኖች እንዳይንቀሳቀሱ ገደብ ተጥሎባቸዋል" ብሏል ጉግል። "ያሉ ጥረቶችን ለማገዝ አሽከርካሪዎች በእነዚህ አካባቢዎች ሲነዱ የበለጠ ለማንቃት የሚያስችል ሥርዓት ላይ እየሰራን ነው።" በዚህ ዓመት አዲሱ የጉግል ገጽታ ይፋ ሲደረግ የጉግል ማፕስ ተጠቃሚዎች በአንድ አካባቢ ከሚገኙ የመጓጓዣ አማራጮች (ባቡር፣ አውቶቡስ፣ ብስክሌት) መካከል በአንድ ስፍራ መምረጥ እንዲችሉ ይደረጋል ተብሏል። ይህ ግዙፍ የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያ የተፈጥሮ አካባቢ የሚጠቀምበትንና ከተሞች በ2030 የካርበን ልቀት ነጻ እንዲሆኑ እንደሚሰራ ቃል ገብቷል።
news-51723916
https://www.bbc.com/amharic/news-51723916
በኮሮናቫይረስ ፍራቻ በእግር ሰላምታ የሰጡት ፕሬዚዳንት
ከሰሞኑ የዓለምን ልብ ሰቅዞ የያዘውና ለብዙ ሺዎች ሰዎች ህይወት መቀጠፍ ምክንያት የሆነው የኮሮናቫይረስ መዛመት ነው። ከሃዘኑና ከፍራቻውም ጋር ተያይዞ አንዳንድ አስገራሚ ዜናዎችም እየተሰሙ ነው።
በዛሬው እለትም የታንዛንያ ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ ከተቀናቃኛቸው ማሊም ሰይፍ ሸሪፍ ሐማድ ጋር እንደተለመደው በእጅ ሳይሆን በእግራቸው ለሰላምታ ሲጨባበጡ የሚያሳየው ፎቶ በፅህፈት ቤታቸው በኩል ወጥቶ ብዙዎችን አስደምሟል። የእጅ ሰላምታን ያስወገዱበትም ምክንያት በኮሮና ቫይረስ ፍራቻ መሆኑም ተገልጿል። የአገሪቱ የጤና ሚኒስትርም የኮሮናቫይረስን ለመከላከል መወሰድ ከሚገባቸው እርምጃዎች መካከል የእጅ ንክኪ ማስወገድ አንዱ ነው ማለቱን ተከትሎ ነው ፕሬዚዳንቱ ይህንን ተግባራዊ እያደረጉ ያሉት። እስካሁን ባለው መረጃ 3ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት የሞቱ ሲሆን ከፍተኛ ቁጥር ያለውም ሟች የሚገኘው የቫይረሱ መነሻ በሆነችው ዉሃን ከተማ ነው። አብዛኛው ሞት እየተከሰተ ያለው በቻይና ቢሆንም በባለፉት ሁለት ቀናት ግን በሌሎች አገሮች ያለው የቫይረሱ መዛመት በዘጠኝ እጥፍ ጨምሯል ተብሏል። የተለያዩ አገራት የቫይረሱን መዛመት ለመከላከል የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰዱ ሲሆን፤ ታንዛንያን ጨምሮ በመላው ዓለም ያሉ መንግሥታት ማንኛውንም ንክኪ ዜጎቻቸው እንዲያስወግዱ እየመከሩ ነው። መሳሳም፣ መተቃቀፍ እንዲሁም ማንኛውንም የእጅ ሰላምታ እባካችሁ አስወግዱ በማለት እየተማፀኑ ነው። ታንዛንያ ውስጥ እስካሁን በቫይረሱ የተያዘ ሰው ባይኖርም በአፍሪካ ውስጥ በግብፅ፣ ሞሮኮ፣ ቱኒዝያ፣ ናይጄሪያ፣ ሴኔጋል ቫይረሱ የያዛቸው ሰዎች መኖራቸው ተረጋግጧል።
50697607
https://www.bbc.com/amharic/50697607
ፍርድ ቤት እየሄደች ሳለ በእሳት የተቃጠለችው ሕንዳዊት ሞተች
አስገድደው ደፍረውኛል ብላ በከሰሰቻቸው ግለሰቦች ላይ ምስክርነት ለመስጠት ወደ ፍርድ ቤት እየሄደች ሳለች በእሳት የተቃጠለችው ሕንዳዊት ሕይወቷ አለፈ።
የ23 ዓመቷ ሕንዳዊት፤ ባለፈው ሳምንት ሀሙስ ወደ ፍርድ ቤት እየሄደች ሳለ ነበር በእሳት የተቃጠለችው። በሰሜናዊ ሕንድ ኡናዎ የተባለች ግዛት ውስጥ የሚኖሩ ሁለት ወንዶችን በአስገድዶ መድፈር የከሰሰችው ሕንዳዊት፤ የእሳት ቃጠሎ ከደረሰባት በኋላ በደልሂ ሆስፒታል ህክምና እየተከታተለች ነበር። • "አትግደሉን!"፡ የቱርክ ሴቶች • ፆታዊ ትንኮሳን ደርሶብኛል በማለቷ ተቃጥላ እንድትሞት የተደረገችው ወጣት • አሲድን እንደ መሳሪያ የአገሪቱ ፖሊስ እንዳለው፤ ተከሳሾቹን ጨምሮ አምስት ወንዶች በቁጥጥር ሥር ውለዋል። የሟቿ እህት፤ ቤተሰባቸው ክሱን እንደሚገፋበት እና ተጠርጣሪዎቹ በሞት እንዲቀጡ እንደምትፈልግም ለቢቢሲ ገልጻለች። ከሰባት ዓመት በፊት፤ በሕንዷ መዲና ደልሂ፤ አንዲት ወጣት አውቶብስ ውስጥ በቡድን ተደፍራ ከተገደለች ወዲህ በአገሪቱ ሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃት የበርካቶች መነጋገሪያ ቢሆንም፤ የተጠቂዎችን ቁጥር መቀነስ አልተቻለም። መንግሥት እንደሚለው፤ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ2017 ብቻ 33,658 ሴቶች ተደፍረዋል። በዚህ አሀዝ መሰረት በቀን በአማካይ 92 ሴቶች ይደፈራሉ። ከዚህ ቀደም፤ የሕንድ ገዢ ፓርቲ አባልን በአስገድዶ መድፈር የከሰሰች ሴት በመኪና አደጋ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባት ይታወሳል። ሁለት አክስቶቿ የተገደሉ ሲሆን፤ ጠበቃዋም ጉዳት ደርሶባቸዋል። ፖሊስ በግለሰቡ ላይ የግድያ ክስ ከፍቷል። ባለፈው ሳምንት በደቡባዊ ሕንድ በምትገኘው ሀይደርባድ ግዛት፤ አንዲት የእንስሳት ሀኪምን ደፍሮ በመግደል የተጠረጠሩ አራት ግለሰቦች በፖሊስ ተገድለዋል። የተጠርጣሪዎቹ መገደል ከፍተኛ ቁጣ ቀስቅሷል።
news-49800282
https://www.bbc.com/amharic/news-49800282
ደም የለበሰው የኢንዶኔዥያ ሰማይ 'ማርስ' የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል
በኢንዶኔዥያ ጃምቢ ክልል ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ይታይ የነበረው ደም የለበሰ ይመስል ነበር። የዚህም ምክንያት አብዛኛውን የሃገሪቱን ክፍል የሚሸፍነው ደን የእሳት ሰለባ መሆኑ ነው።
የዓለም መጨረሻን የሚተነትኑ ፊልሞች ላይ የሚታየውን የዓለም መጨረሻን ዕጣ ፈንታ የሚመስለውን ጃምቢ በተሰኘው የኢንዶኔዥያ አካባቢ ከሰሞኑ ይታይ የነበረው ሰማይ። የሰማዩን ፎቶግራፎች ያጋራችው የጃምቢ ክልል ነዋሪ 'ዓይኖቿን እና ጉሮሮዋን ያማት' እንደነበር አሳውቃለች። በየዓመቱ ኢንዶኔዥያ ውስጥ የሚነሱት እሳቶች ሰማይን የሚሸፍኑ ከመሆናቸውም በተጨማሪ አጠቃላዩን የእስያን ምሥራቅ ክፍል ጭስ ማልበሳቸው የተለመደ ክስተት ነው። ይህ ያልተለመደ የሰማይ ክስተት 'ሬይሌይ ስካተሪንግ' በሚባል እንደሚታወቅ የሜትሮሎጂ ባለሙያ ለቢቢሲ አሳውቀዋል። ባለፈው ቅዳሜ እኩለ ቀን አካባቢ የተከሰተውን ክስተት በፎቶ ካሜራዋ ያስቀረቻቸው ኤካ ዉላንዳሪ የምትባል የሜካር ሳሪ ነዋሪ ናት። ያን ዕለት የነበረው ጭስ "በጣም ክብደት ነበረው" በማለት ገልፃዋለች። ፎቶግራፎቹ የውሸት ናቸው ሲሉ የነበሩትን አንሺዋ ተቃውማለች የ21 ዓመቷ ወጣት ፎቶግራፎቹን በፌስቡክ ላይ ያጋራች ሲሆን፤ ካጋራችበት ሰዓት አንስቶ ከ34 ሺህ ጊዜ በላይ ሲጋራ ቆይቷል። ብዙ ሰዎች ያነሳቻቸውን ፎቶግራፎች ለማመን እንደተቸገሩ ለቢቢሲ ትናግራለች። "እነዚህ ፎቶግራፎች ግን የእውነተኛ ናቸው። በስልኬ ነው ያነሳዃቸው" በማለት ጭሱ ሰኞም ጠዋት እንደቀጠለ ትናገራለች። የሜካር ሳሪ መንደር ሰማይ ደማቅ ቀይ ሆኖ ነበር። ኋላም የትዊተር ማህበራዊ ድረ ገፅ ተጠቃሚ ተመሳሳይ ፎቶግራፎችን ሲያጋራ ነበር። "ይህ ማርስ አይደለም። ጃምቢ ነው" ሲል ዙኒ ሾፊ ያቱን ኒሳ ይጽፋል። አክሎም "እኛ ሰዎች እንደመሆናችን ንፁህ አየር ነው የሚያስፈልገን እንጂ ጭስ አይደለም" ብሏል። በኢንዶኔዥያ ሜቴዎሮሎጂ ተቋም በአካባቢው ደመቅ ያሉ ብዛት ያላቸው ምልክቶች ታይተው ነበር። የሲንጋፖር ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ኮህ ቲዬ ዮንግ ክስተቱ 'ሬይሌይ ስካተሪንግ' የሚባል መሆኑን ያስረዱ ሲሆን ይህም በጭሱ ወቅት በሚፈጠሩ ጥቃቅን ነገሮች የሚፈጠሩ መሆኑን ያስረዳሉ። "በጭሱ ወቅት 1 ማይክሮሜትር የሚያክሉ ጥቃቅን ነገሮች በብዛት የሚገኙ ሲሆን እነርሱ ግን የምናየውን ብርሃን ቀለም አይቀይሩም" በማለት ለቢቢሲ አክለው ያስረዳሉ። "ከዚህም በቁጥርም በመጠንም የሚያንሱ ጥቃቅን ነገሮች ልናገኝ እንችላለን እነርሱም ከሰማያዊ ይልቅ ብርሃን ሲያርፍባቸው ቀይ ብርሃን የማንፀባረቅ ዝንባሌ አላቸው" ይላሉ። ፎቶግራፎቹ በእኩለ ቀን ላይ መነሳታቸው ብርሃኑ ይበልጥ ቀይ መስለው እንዲታዩ ያደረጉ ይሆናል በማለትም ያስረዳሉ። "ፀሐይ ከአናታችን በላይ ከሆነች ብርሃኑ ቀይ ሆኖ ይታየናል።" ፕሮፌሰሩም አክለው ይህ ክስተት የአየሩን ሙቀት የመቀየር አቅም እንደሌለው ይናገራሉ። የዚህ ዓመቱ ጭስ ከሌሎቹ ዓመታት ይልቅ ከባድ ነበር። በኢንዶኔዥያ እና ማሌዥያ ፀሃያማ ወቅቶች የደን እሳት አደጋዎች የተለመዱ ናቸው። አንዳንዴም ትላልቅ ድርጅቶችና አንዳንድ አርሶ አደሮች ፀሃያማ ወቅቱን ለመጠቀም ሲሉ ለመትከል እንዲመቻቸው የደኑን ቦታ በማቃጠል ለመውሰድ በሚጥሩበት ጊዜ እሳት ይነሳል። ደንን እየቆረጡ የማቃጠሉ ዘዴ በብዙ የዓለም ክፍሎች ሰው የሚጠቀምበት ዘዴ ነው ምክንያቱም የታመመን ሰብል በቀላሉ እና ብዙ ገንዘብ በማይፈጅ ሁኔታ ማስለቀቅ የሚችሉበት ብቸኛው መንገድ በመሆኑ ነው። ሆኖም እነዚህ እሳቶች አብዛኛውን ጊዜ ከሰው ቁጥጥር ውጪ ይሆኑና ለማቃጠል ያልታሰቡትን የደን ስፍራዎች ያያይዛሉ። በኢንዶኔዥያ ይህ ዘዴ በሕግ የሚያስቀጣ ቢሆንም ለረዥም ዓመታት የሚጠቀሙበት ዘዴ ሆኖ ቀርቷል፤ ብዙዎች እንደውም የመንግሥት ድክመት እና ሙስና ውጤት ነው ይላሉ።
news-52328125
https://www.bbc.com/amharic/news-52328125
ኮሮናቫይረስ፡ ኢንሹራንስና ቤት ለኮሮናቫይረስ ጤና አገልግሎት ሰጪዎች
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋትን ለመቀነስ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ወይም ከህመምተኞች መራቅ ለጤና ባለሙያዎች አማራጭ አይደለም።
ዶክተር ሊያ ታደሰ በብዙ አገራት እየሆነ እንዳለው በኢትዮጵያም የጤና ባለሙያዎችም ሆነ በቀጥታ ከህሙማኑ ጋር የሚሰሩ ሰዎች ምርመራ ማድረግ፣ በአምቡላንስ መውሰድ፣ ለህመምተኞቹ ድጋፍና ምቾትን እንዲሁም መድኃኒትን ከማዘዝ ጀምሮ ለብዙዎች ስጋት የሆነውን ቫይረስ በቀጥታ እየተጋፈጡት ይገኛሉ። በዚህም ምክንያት በርካታ የጤና ባለሙያዎችም ሆነ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ህይወታቸው አደጋ ውስጥ ገብቷል። ከሰሞኑም የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የሚሰሩ ድጋፍ ሰጪ አካላትም ሆነ የጤና ባለሙያዎች በኢንሹራንስ እንዲሸፈኑ ውሳኔ ላይ ደርሷል። ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው ወረርሽኙን ለመቆጣጠር እየሰሩ ያሉ ባለሙያዎኞች ለስድስት ወር ያህል የኢንሹራንስ ሽፋን ለመስጠት ስምምነት ላይ መደረሱን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል። ኢንሹራንሱ ዶክተሮችና ነርሶችን ብቻ ሳይሆን በፅዳት ላይ የተሰማሩ፣ የአምቡላንስ አሽከርካሪዎች ወይም ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች ጋር በቀጥታ የሚሰሩ ሠራተኞችን በሙሉ ይመለከታል። "ቫይረሱ ለጤና ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆን በሌላ ሥራ ለተሰማሩት እንደ ፅዳት ወይም የአምቡላንስ ሾፌሮች ስጋት ሆኗል። ለበሽታውም ተጋላጭ ናቸው። በዚህ ምክንያት በሽታው ቢይዛቸውና ህይወታቸው አደጋ ላይ ቢወድቅ ምን መሆን አለበት? የሚለውን ታሳቢ በማድግ ነው የኢንሹራንስ ስፋን እንዲያገኙ የተወሰነው" ብለዋል ሚኒስትሯ ለቢቢሲ። ይህንን የኢንሹራንስ ሽፋን የሚሰጠው የኢትዮጵያ መድን ድርጅት እንደሆነና አገልግሎቱን ያቀረበው በነፃ እንደሆነና ሃሳቡም ከእራሱ ከድርጅቱ የመጣ መሆኑን ሚኒስትሯ ጠቅሰዋል። በተጨማሪም ሌሎች ለመደገፍ ፍላጎት ያላቸው የኢንሹራንስ አገልግሎት ሰጪዎች ጋርም ውይይት መጀመሩን ያመላከቱት ሚኒስትሯ መንግሥትም ሰፋ ባለ መንገድ የኢንሹራንስ ሽፋን የሚሰጥበትን መንገድ እየቀየሰ መሆኑን ተናግረዋል። ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎችም ሆነ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ቁጥር በየጊዜው የሚለዋወጥና እየጨመረ የሚሄድ ከመሆኑ አንፃር የኢንሹራንሱ ሽፋንም ሆነ የመኖሪያ ቤት የሚያገኙ ሰዎችን ቁጥር በትክክል መናገር ከባድ እንደሆነም ገልፀዋል። ዶክትር ሊያ እንደሚሉት በአገሪቱ ውስጥ የቫይረሱን ወረርሽኝ ለመቆጣጠር በሺህዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞች ተሰማርተዋል፤ በዚህ ዓመት እንኳን አዲስ የተቀጠሩ 3800 ባለሙያዎች አሉ። ኢንሹራንስ ሽፋኑም እነዚህን ጨምሮ ለወደፊቱ የሚቀጠሩትንም የሚያካትት ይሆናል። ከኢንሹራንስም በተጨማሪ የኮቪድ-19 ህክምና በሚሰጥባቸው ማዕከላት ቀጥታ ፈጣን ምላሽ እየሰጡ ያሉ የጤና ባለሙያዎች ወደየቤታቸው መመላለሱ ስጋት በመፍጠሩ ከዚህ ስጋት ነፃ ሆነው የሚሰሩበትም ሁኔታ ለማመቻቸት ቤቶች እንዲሰጣቸው መወሰኑን አመልክተዋለወ። አንዳንድ ሆስፒታሎች በተለይም ማስተማሪያ ያላቸው ተቋማት ተማሪዎች ይጠቀሙባቸው የነበሩ ዶርሚተሪዎች (የማደሪያ ክፍሎች) ተማሪዎቹ በአሁኑ ወቅት ስለሌሉ ለዚህ አገልግሎት እያዋሉ መሆኑን ሚኒስትሯ ተናግረዋል። ከዚህም በተጨማሪም በቅርቡ ኖህ ሪል ስቴት የተባለው የግል ድርጅት የሰጠውን አፓርትመንት (የጋራ መኖሪያ ቤት) አልጋዎችና ቁሳቁሶች ተሟልተውለት ለጤና ባለሙያዎቹ አገልግሎት እንደሚውል ሚኒስትሯ ለቢቢሲ ገልፀዋል። ምንም እንኳን ኢንሹራንሱ ለሁሉም ሰራተኞች ቢሆንም የቤት አሰጣጡ ግን እንደ ጤና ባለሙያዎቹ የአኗኗር ሁኔታ እንደሚወሰን ሚኒስትሯ አስረድተዋል። አሁን ባለው መሰረት ከስድስት መቶ በላይ ለሆኑ ባለሙያዎች ቤት እንዲሰጣቸው ተለይተዋል፤ ይህም በአዲስ አበባ ሲሆን በየክልሉ ደግሞ ዩኒቨርስቲዎችም እየተዘጋጁ ነው። ምርመራና የመለየት ሥራ በአገሪቱ ውስጥ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ100 በላይ ሲሆን በአጠቃላይ የተመረመረው ሰውም ቁጥር አስር ሺህ አይደርስም። ይህም ከአገሪቱ አጠቃላይ ሕዝብ አንጻር በጣም ጥቂት ነው። የኢትዮጵያም የምርመራ ቁጥር በዓለም ትንሹ ከሚባለው ውስጥ ነው። የዓለም ጤና ድርጅት በተደጋጋሚ ቫይረሱ በማኅበረሰቡ ዘንድ የመዛመቱን ሁኔታ ማወቅ የሚቻለው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው ሲመረመር ነው በማለትም ምክሩን ለአገራት ይለግሳል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር ትልቁና ዋነኛው ሥራ የምርመራ አቅምን መጨመር እንደሆነ የሚናገሩት የጤና ሚኒስትሯ "ከአራት አስከ አምስት ሺህ የሚሆኑ ሰዎችን በቀን ለመርመር እቅድ ያለ ሲሆን፤ ይህም በሽታው ወደ ማኅበረሰቡ ተሰራጭቷል ወይስ አልተሰራጨም የሚለውን በርግጠኝነትም ለማወቅም ያስችላል" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚህም መሰረት በተለያየ የጤና ማዕከላት ላይ ያሉ የሳንባና ማንኛውም የመተንፈሻ አካላት ችግሮች ያለባቸውን፣ ማኅበረሰቡ ውስጥ ደግሞ ተጋላጭ ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎችን የመመርመር ሥራ እንደሚጀመርም አስረድተዋል። በቀን ያለውንም የመመርመር ሁኔታ ከማስፋት ጎን ለጎንም በአዲስ አበባም ይሁን በክልል የሚገኙ ላብራቶሪዎችንም አዲስ አበባም በየክልሉ የማስፋት ሥራ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ አሁን በአዲስ አበባ ሦስት በክልሎች ደግሞ አምስት በአጠቃላይ ስምንት ላብራቶሪዎች መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም እስካሁን ድረስ በሽታው ተገኘባቸው በተባሉ አካባቢዎች በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ፣ በአዳማ፣ በባህር ዳርና አዲስ ቅዳም የሙቀት ልኬት የመስራትና ሁኔታዎችንም የመቃኘት ሥራ እየተሰራ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ተጋላጭ ናቸው ተብለው የታሰቡ 640 ሰዎች ተመርምረው ሁሉም ነፃ የሆኑ ሲሆን "በአብዛኛው በቫይረሱ የተያዙት ከውጭ የመጡ ሰዎች ናቸው። ነገር ግን በተወሰነ መልኩ የውጭ ጉዞ ታሪክ የሌላቸውም ሰዎች ላይ በሽታው ስለተገኘ ይሄንን ሰፋ አደርገን የመመርመር ሥራ እንሰራለን" ብለዋል የጤና ሚኒስትሯ ዶክትር ሊያ ታደሰ ለቢቢሲ።
49685480
https://www.bbc.com/amharic/49685480
የሳዑዲዋ ልዕልት በፓሪስ የቧንቧ ሠራተኛውን በማገቷ ተፈረደባት
የሳዑዲዋ ልዕልት በፈረንሳይ በሚገኘው ቅንጡ መኖሪያዋ የቧንቧ ሠራተኛ በመደብደብና በማገት ተከሳ፤ ከዚህ በኋላ ሌላ ጥፋት ካጠፋች ተፈፃሚ የሚሆን የአሥር ወር ቅጣት ተፈረደባት።
የሳዑዲው ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማን የሳዑዲው ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማን እህት የሆነችው የ43 ዓመቷ ሐሳ ቢንት ሳልማን የንጉሥ ሰልማን ሴት ልጅ ነች። የግል ጠባቂዋ ቧንቧ ሠራተኛውን እንዲደበድብ አዛለች ተብላ የተከሰሰች ሲሆን፤ የሠራተኛው ጥፋት ነው ያለችው ደግሞ የቤቷን የውስጥ ክፍል ፎቶ ማንሳቱን ነበር። የቧንቧ ሠራተኛው አሽራፍ ኢድ እንደተናገረው፤ የግል ጠባቂዋ ጠፍንጎ ካሰረው በኋላ የልዕልቷን እግር እንዲስም አስገድዶታል። • ከ22 ዓመት በኋላ በ 'ጉግል ማፕ' አስክሬኑ የተገኘው ግለሰብ • በዓመቱ አነጋጋሪ ከነበሩ ጉዳዮች ጥቂቱ ሐሙስ ዕለት ችሎት የዋለው የፈረንሳይ ፍርድ ቤት፤ ልዕልቷ በተመሰረተባት ክስ ጥፋተኛ ነች ሲል ፍርዱን ሰጥቷል። ልዕልቷ በቁጥጥር ሥር እንድትውል ዓለም አቀፍ ማዘዣ የወጣባት ሲሆን፤ በተአቅቦ የ10 ሺህ ዩሮ ቅጣት እንድትከፍል ተወስኖባታል። ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ በኋላ፤ የልዕልቷ ጠበቃ የሆኑት ኢማኑዔል ሞይኔ፤ የቧንቧ ሠራተኛው ውንጀላ "በምኞት የተሞላ" ነው በማለት ይግባኝ እንደሚሉ ተናግረዋል። ምን ነበር የሆነው? እኤአ በ2016 መስከረም ወር ላይ፣ ኢድ ፈረንሳይ ውስጥ ወደሚገኝ የልዕልቷ ቅንጡ መኖሪያ አፓርትመንት አምስተኛ ፎቅ የተበላሸ የእጅ መታጠቢያ እንዲጠግን ጥሪ ቀረበለት። ግብፃዊው ሠራተኛ፤ መታጠቢያ ክፍሉን ሲመለከተው አላስቻለውም። ስልኩን መዥረጥ አድርጎ አውጥቶ ፎቶ ማንሳት ጀመረ። በእርግጥ "ለሥራዬ የሚረዳኝ ነገር ስላየሁ ነው ያነሳሁት" ብሏል። ነገር ግን ልዕልቷ በመስታወት ውስጥ የሚታየው ምስሏ ፎቶ ውስጥ መግባቱ አስቆጣት። ከዚያም የግል ጠባቂዋን ሰይድን ጠርታ አስሮ እንዲገርፈው አዘዘች። ቧንቧ ሠራተኛው እንደሚለው፤ እግሯን እንዲስም ተገዷል፤ ለበርካታ ሰዓታትም እንዳይወጣ ታግቶ ቆይቷል። እንደውም ልዕልቷ የሆነ ሰዓት ላይ ብልጭ ብሎባት "ይህንን ውሻ ግደለው፤ ሊኖር አይገባውም" ብላ ነበር ብሏል። • "የአምባቸው ሕልም የተጠናከረ አማራን፣ የበለጸገች ኢትዮጵያን ማየት ነበር" አቶ ቹቹ አለባቸው የልዕልቷ ጠባቂ ሐምሌ ወር ላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ እንዳስረዳው፤ ወደ መታጠቢያ ቤት የሄደው የልዕልቲቱን የድረሱልኝ ጩኸት ሰምቶ ነበር። ሲደርስም ልዕልቲቱና ቧንቧ ሠራተኛው ስልኩን ይዘው ይታሉ ነበር። "ከዛም የዚህ ሠራተኛ ዓላማ ምን እንደሆን ባለማወቄ በጉልበት ስልኩን አስጥየዋለሁ" ብሏል። ምስሉን ሊሸጠው አስቦ ይሆናል ሲል ግምቱንም ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል። በሳዑዲ ሕግ መሰረት ልዕልቲቱን ፎቶ ማንሳት ክልክል ነው። የልዕልቲቱ ጠበቃ፤ የቧንቧ ሠራተኛው ከክስተቱ በኋላ በተከታታይ ወደ አፓርታማው እንደሄደና የ21ሺህ ዩሮ ክፍያ እንደጠየቀ ተናግሯል። የሳዑዲዋ ልዕልት ሐሳ፤ በበጎ አድራጎቷ እና በሴቶች መብት ተከራካሪነትዋ የምትንቆለጳጰስ ናት።
news-54106443
https://www.bbc.com/amharic/news-54106443
ኮሮናቫይረስ፡ መድኃኒት ነው ስለሚባልለት ተክል ምን ያህል እናውቃለን?
አፍሪካዊቷ አገር ማዳጋስካር ባሳለፍነው ሚያዝያ ወር ላይ አገር በቀል የሆነ ተክልን በመጠቀም ለኮሮረናቫይረስ የሚሆን መድኃኒት ማግኘቷን ካስታወቀች በኋላ የዓለምን ትኩረት መሳብ ችላ ነበር።
አርትሚዝያ የተባለውና ከአርቲ ጋር የሚመሳሰለው ተክልን በመጠቀም የተሰራው የሚጠጣ 'መድኃኒት' በአገሪቱ ፕሬዝዳንት አንድሬይ ራጆሊና ሲሞካሽ ነበር። የዓለም ጤና ድርጅት በበኩሉ በዋነኛነት የወባ በሽታን ለማከም ጥቅም ላይ ከሚውለው አርትሚዝያ ተክል የሚሰራው 'መድኃኒት' በትክክል ኮቪድ-19ኝን እንደሚያድን በሳይንሳዊ መንገድ እስካሁን አልተረጋገጠም ሲል ቆይቷል። ለመሆኑ ስለዚህ ተክል ባህሪዎችና አጠቃላይ ሁኔታ ምን ያክል እናውቃለን? አርትሚዝያ ከየት መጣ? አርትሚዝያ ዋናው መገኛው ከወደ እሲያ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ግን በመላው ዓለም በሚገኙኛ ፀሐያማና ሞቃታማ የአየር ጸባይ ባላቸው አገራት በብዛት ይታያል። በዋነኛነት ተክሉ ቻይና ውስጥ ላለፉት 2 ሺህ ዓመታት ለባህላዊ መድኃኒትነት ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል። በዚህም እንደ ወባ፣ ትኩሳትና ሌሎች ህመሞችን ለማከም ያገለግል ነበር። ይህ ተክል በቻይናውያን ዘንድ 'ኪንጋኦ' ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ከመድኃኒትነት በተጨማሪ አርትሚዝያ የአልኮል መጠጦችም ውስጥ ይጨመራል። የማዳጋስካሩ ፕሬዝዳንት ከአርቲ የተሰራውን ጭማቂ ይዘው አርትሚዝያ ኮቪድ-19ኝን ያክም ይሆን? የማዳጋስካሩ ፕሬዝዳንት አንድሬይ ራጆሊና ባሳለፍነው ሚያዝያ ወር ላይ ከአርትሚዝያ የተሰራው የሚጠጣ 'መድኃኒት' ላይ ሙከራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን በመግለጽ 'መድኃኒቱ' ኮቪድ-19ኝን ለማከም መዋል እንደሚችል ደርሰንበታል ብለዋል። በያዝነው የፈረንጆቹ መስከረም ወርም ቢሆን ይህንኑ አስተያየታቸውን ደግመውታል። ነገር ግን በይፋ ሊታይ የሚችል ማረጋገጫ እስካሁን ድረስ ማዳጋስካር ማቅረብ አልቻለችም። በተጨማሪም 'መድኃኒቱን' ለመስራት ምን አይነት ሂደት እንደተከተሉና ተክሉ ምን ያህል ጥቅም ላይ እንደዋለ የተገለጸ ነገር አለመኖሩ በርካቶች ጥርጣሬ ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል። ማዳጋስካር ግን እነዚህን ሁሉ አስተያየቶች ወደጎን በማለት እንደውም ይህንኑ ተክል በመጠቀም ለኮቪድ-19 የሚሆን የሚዋጥ መድኃኒት ማምረት የጀመረች ሲሆን በመርፌ መልክ የሚሰጥ መድኃኒትም በማዘጋጀት ላይ ናት። ለእነዚህ 'መድኃኒቶች' ደግሞ ክሊኒካዊ ሙከራዋን አጠናክራ መቀጠሏን ማዳጋስካር አስታውቃለች። የጀርመን እና የዴንማርክ ተመራማሪዎች ደግሞ አርትሚዝያ ምን ያክል ውጤታማ ሊሆን ይችላል የሚለውን እና እውን ኮቪድ-19ኝን ማከም ይችላል የሚለውን ለማረጋገጥ ጥናት በማካሄድ ላይ ይገኛሉ። አዲስ በሰሩት ጥናትም ተክሉ ኮቪድ-19ኝን የማዳከም አቅም እንዳለው ላቦራቶሪ ውስጥ ማረጋገጥ እንደቻሉ ገልጸዋል። ምንም እንኳን የተመራማሪዎቹ ጥናት በገለልተኛ ባለሙያዎች ባይገመገምም ከተክሉ የተወሰደው ቅንጣት የቫይረሱን እንቅስቃሴ መግታትና ማቀዝቀዝና ኃይለኛቱን መቀነስ እንደሚችል ተገልጿል። ተመራማሪዎቹ በአሜሪካው ኬንተኪ ዩኒቨርሲቲ ስር ሆነው የሚሰሩ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ክሊኒካዊ ሙከራ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆናቸውም ተገልጿል። ቻይናም ብትሆን በዚሁ ተክል ላይ ምርምሮችን ማድረግ እንደጀመረች አስታውቃለች። በባህላዊ መንገድ ጥቅም ላይ ይውል የነበረውን ተክል በዘመናዊ ምርምርና እውቅት በመደገፍ የሚደረገው ለኮሮናቫይረስ ፍቱን መድኃኒት የማግኘት ሥራም ተጠናክሮ ቀጥሏል። በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ተመራማሪዎችም ቢሆኑ አርትሚዝያ ኮቪድ-19ኝን ምን ያክል ማከም ይችላል የሚለውን ማወቅ በማሰብ በላብራቶሪ ምርምር ማድረግ ከጀመረች ሰነባብታለች። የዓለም ጤና ድርጅት ግን አሁንም ቢሆን ከአርትሚዝያ ስለተሰራው 'መድኃኒት' ከማደዳስካር የተብራራ መረጃ አላገኘሁም እያለ ነው። የድርጅቱ የአፍሪካ አማካሪ ዢን ባፕቲስት ኒኬማ ለቢቢሲ እንደገለጹት ድርጅቱ በሚያገኘው መረጃ ላይ በመመስረት ክሊኒካል ሙከራዎች ላይ መሳተፍ እንደሚፈልግ ገልጸዋል። አሁን ግን የዓለም ጤና ድርጅት አርትሚዝያ ኮቪድ-19ኝን ስለማከሙ ማረጋገጫ የሚሆን መረጃ እንዳለገኘ ገልጿል።
44890476
https://www.bbc.com/amharic/44890476
ከኢትዮጵያና ከኤርትራ ንግድ ትስስር ማን ይጠቀማል?
የኢትዮጵያና የኤርትራ ወደ ሰላም መምጣት ከምንም በላይ በብዙ መንገድ ተሳስረው ሳለ ለዓመታት ለተለያዩት የሁለቱ አገራት ህዝቦች መገናኘት ትልቅ ነገር መሆኑ አያጠራጥርም።
ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ በርኸ (ግራ) እና አቶ ክብሮም ዳፍላ (ቀኝ) የሰላሙ ወደ ንግድ ግንኙነት መሸጋገር ደግሞ አገራቱን ተጠቃሚ እንደሚያደርጋቸው ይጠበቃል። ወደብ ለሌላት ኢትዮጵያ የአሰብ ወደብን መጠቀም ትልቅ እፎይታ ሲሆን ኤርትራንም አትራፊ ያደርጋታል። የኢትዮጵያና የኤርትራ አየር መንገዶች በጋራ መስራትም ሌላው የንግድ ትስስር መስመር ነው። ከእነዚህና ከሌሎችም የንግድ ትስስሮች አገራቱ ሲጠቀሙ ህዝቡም ተጠቃሚ እንደሚሆን አይጠረጠርም። የሰላም እርምጃው ለሁለቱ አገራት ህዝቦች መገናኘትና አብሮ መኖር ትልቅ ነገር ቢሆንም ከንግድ ግንኙነቱ ኤርትራም እንደ አገር እንደማታተርፍ ህዝቡም እንደማይጠቀም የሚናገሩ አሉ። የኤርትራ አገር ውስጥ ገቢ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ኃላፊ፣ ከዚያም ለሶስት ዓመታት የኤርትራ አየር መንገድ ዋና ስራ አስኪያጅ በመሆን ለዓመታት ያገለገሉት አቶ ክብሮም ዳፍላ ከእነዚህ ሰዎች አንዱ ናቸው። ስለ ኤርትራ መንግሥት ምጣኔ ሃብታዊ እርምጃ በጥቅሉ ስለ አገሪቱ ኢኮኖሚ በቅርበት የሚያውቁት አቶ ክብሮም "የሁለቱን ህዝቦች ልብ የሚያሳርፍ በመሆኑ የግንኙነቱ መጀመር ትልቅ ነገር ነው" ቢሉም በተለይም ከንግድ ግንኙነቱ ኤርትራና ኤርትራዊያን አይጠቀሙም ሲሉ ያስረግጣሉ። ኢትዮጵያ ሰፊ የንግድ ስርአት ያላት አገር በመሆኗ ከኤርትራ ጋር የተለያዩ የንግድ ስምምነቶችን ስታደርግ ኢትዯጵያዊያን ኢንቨስተሮች ኩባንያዎች ታሳቢ ተደርገው ሲሆን በተቃራኒው በኤርትራ በኩል ግን የዚህ አይነት መዋቅር አለመኖር በቀዳሚነት የሚያስቀምጡት ነጥብ ነው። "በኢትዯጵያ በኩል ነገሮች ክፍት ናቸው። በኤርትራ በኩል ደግሞ ነገሮች ዝግ የተደረጉት እንዲሁ ሳይሆን በህግና በስርዓት ነው። ይህ የወጪ ንግድ ላይም ይሁን ገቢ ላይ ኢትዮጵያዊያን ያለ ውድድር መሳተፍ የሚችሉበት እድል ይፈጠራል። ኤርትራዊ ምንም ውስጥ አይገባም ማለት ነው" የሚሉት አቶ ክብሮም ዘላቂ መሆኑ ቢያጠራጥርም አጋጣሚው ለኢትዮጵያ ሎተሪ ነው ይላሉ። የንግድ ሽርክናውን የሚሸከም ስርአት ኤርትራ ውስጥ እንደሌለና ይህም 20 ዓመታትን እንዳስቆጠረ ይናገራሉ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ህዝብ ምንም ስለማይጠቀም ለተጠቃሚነቱ የተዘጉ በሮች ሁሉ እንዲከፈቱ ህዝቡ መጠየቅ እንዳለበት ያሳስባሉ። ከኤርትራ ጋር በሚደረገው የምጣኔ ሃብት ትስስር ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ይጠቀማሉ ቢሉም በኤርትራ በኩል ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሥርዓት እስካልተዘረጋ ድረስ የኢትዮጵያ ጥቅምም እንደታሰበው ሊሄድ እንደማይችል አቶ ክብሮም ያስረዳሉ። እንደ እሳቸው ገለፃ አሁን ኤርትራ ውስጥ ባለው እውነታ የንግድ ትስስሩ በኢትዮጵያ ብቻ ወደ ፊት ሊራመድ ስለማይችል የመገታት አደጋ አለበት። የኤርትራ መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር የጀመረው የንግድ ትስስር እንደ ባንክ ባሉ ተቋማት እና የፋይናንስ ሥርዓት ካልታገዘ በቀር ለሳቸው ነገሩ ቴአትር እንጂ ሌላ አይሆንም። በጥቅሉ ለሳቸው ይህ ነው የሚባል የፖለቲካና የምጣኔ ሃብት ስርዓት ከሌሎው የኤርትራ መንግስት ጋር የሚደረግ ንግድ ለኤርትራዊያን ምን ጠብ የሚያደርገው ነገር አይኖረውም። በኢትዮጵያ ብቻም ወደ ፊት ሊራመድ አይችልም። በተስፋ ላይ ተስፋ የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ በርኸ ጅቡቲ ወደብ ላይ ባለው ጫና እቃዎች ከስድት ወር በላይ ወደቡ ላይ እየተቀመጡ በመሆናቸው ከመቸገሯም አልፎ በዓመት እስከ አንድ ቢሊዮን ዶላር እየከፈለች ላለችው ኢትዮጵያ በኤርትራ ወደቦች መጠቀም ትልቅ ነገር እንደሆነ ይገልፃሉ። ከኤርትራ አየር መንገድ ጋር በሽርክና ለመስራት የተስማማው የኢትዮጵያ አየር መንገድም በትልቁ ተጠቃሚ እንደሚሆን ያምናሉ። የኤርትራን አየር ክልል ማቋረጥ ባለመቻል ሲደረጉ የነበሩ ረዥም በረራዎችን አሁን ማሳጠር በመቻሉም የኢትዮጵያ አየር መንገድም ተጠቃሚ እንደሚሆን ይጠቅሳሉ። በተለይም ለምፅዋ ወደብ ቅርብ የሆኑት ትግራይና አማራ ክልሎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑም ያመለክታሉ። ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ የኤርትራ ወደቦችን ኢትዮጵያ ስትጠቀም የስራ እድሎች እንደሚፈጠሩና የኤርትራ ህዝቦች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተስፋ አላቸው። ተስፋቸው ግን የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ኢትዮጵያ መጥተው ከተናገሯቸው ነገሮች በመነሳት በቀጣይም አገሪቷ ህገመንግስቷን በማፅደቅ ህዝቡም መሪውን ይመርጣል በሚል ተስፋ ላይ የተመሰረተ ነው። ነገሮች ካልተቀየሩ ትልቁ ችግር ለኤርትራ እንጂ ለኢትዮጵያ እንደማይሆን ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ ይገልፃሉ። ኢትዮጵያ ከጅቡቲ፣ ከሶማሌላንድና ከሱዳን ጋር ራስዋ የምትቆጣጠረው ወደብ ለማግኘት እየተነጋገረች መሆኗን በማስረጃነት ይጠቅሳሉ። ኤርትራዊያን ወጣቶች ለጦርነት የሚዘጋጁ ሳይሆኑ አምራች የሚሆኑበት፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኤርትራ ዲያስፖራ በአገር ውስጥ ኢንቨስት የሚያደርግበት ሥርዓት ካልተዘረጋ ነገሩ ሁሉ ትርጉም እንደማይኖረው አገሪቱንም ወደ ቀደመ ቀውስ ሊመልሳት እንደሚችል ያመለክታሉ። በኤርትራ የሚፈለገው ለውጥ እንዲመጣ ህዝቡ ጥረት ሊያደርግ እንሚገባ ያምናሉ። በሌላ በኩል ከኢትዮጵያ ጋር የተጀመረው ግንኙነትም አዎንታዊ ተፅእኖ እንደሚኖረውም ተስፋ ያደርጋሉ።
news-56192210
https://www.bbc.com/amharic/news-56192210
የእንግሊዙ ልዑል ሃሪ የአገሩ ሚዲያዎች የአዕምሮ ጤናው ላይ እክል እንደፈጠሩ ተናገረ
የእንግሊዙ ልዑል ሃሪ የአገሪቱ ሚዲያዎች የባለትዳሮቹን ህይወት መበጥበጣቸውን ተከትሎ ቤተሰቦቹን ለመጠበቅ ሲል ከንጉሳዊው ኃላፊነት ራሱን ገሸሽ ማድረጉን አስታውቋል።
ፕሪንስ ሃሪ ቲቪ ቻት የተባለውን ፕሮግራም አዘጋጅ ጄምስ ኮርደን ጋር ባደረገው ቆይታ "ሚዲያው ስለኛ የሚዘግበው ጉዳይ የአእምሮ ጤናዬ ላይ እክል እየፈጠረ ነው"፤ "አባት ወይም ባለቤት እንደሚያደርገው ቤተሰቤን ቅድሚያ ሰጥቻለሁ" ብሏል። የበኪንግሃም ቤተ መንግሥት ባለፈው ሳምንት እንዳስታወቀው ልዑሉና ባለቤቱ ሜጋን መርክል ወደቀደመ የንጉሳውያን ቤተሰብ ኃላፊነታቸው እንደማይመለሱ አረጋግጧል። ልዑሉ በበኩሉ ሙሉ በሙሉ መሰናበት ሳይሆን ጊዜያዊ ነው ብሏል። ሁለተኛ ልጃቸውን እየጠበቁ ያሉት ባለትዳሮቹ፤ አርቺ ከተባለ የአንድ አመት ልጃቸው ጋር መኖሪያቸውን በአሜሪካዋ ካሊፎርኒያ አድርገዋል። ከንጉሳዊው ስርዓት ኃላፊነትም ሙሉ በሙሉ መገለላቸውን ያሳወቁት በጥር ወር ላይ ነበር። በወቅቱም የቤተ መንግሥት መጠሪያቸውንም ሆነ ገንዘብ እንደማይጠቀሙ አሳውቀው ነበር። " በርካቶች የሆነውን እንዳዩት የሚረብሽ ወቅት ነበር። ሁላችንም የእንግሊዝ ሚዲያ እንዴት እንደሆኑ እውነታውን እንረዳለን። የአዕምሮ ጤናዬ ላይ ከፍተኛ እክል እያስከተለም ነበር፤ ይሄ መርዛማ ሁኔታም መቆም አለበት አልኩኝ" ብሏል ከጋዜጠኛው ጋር ባደረገው ቆይታ ሆኖም እሱም ሆነ ባለቤቱ ህዝቡን ከማገልገል ስራቸው እንደማያፈገፍጉ ልዑሉ አስረድቷል። ባለትዳሮቹ ከዚህ ቀደም አንድ ሚዲያን መክሰሳቸው ይታወሳል። ዘ ሜይል ሰንደይ የተባለውን ጋዜጣ ሜጋን ለአባቷ የፃፈችውን ደብዳቤ ማተሙን ተከትሎ ከሰውት የነበረ ሲሆን ብይኑም ለነሱ ሆኗል። በወቅቱም ክሱን ያስገባችው ባለቤቱ ሜጋን ስትሆን ሁኔታው "ልቡን እንደሰበረውና" በአጠቃላይ ሚዲያዎች የከፈቱባትን ዘመቻ "ጭካኔ የተሞላበት" ብሎታል። በህይወት የሌለችውን እናቱን ልዕልት ዲያናን በመጥቀስም "ከፍተኛ ፍራቻዬ ታሪክ ራሱን እየደገመ መሆኑ ነው" በማለትም በወቅቱ ባወጣው መግለጫ አስፍሯል። በቅርቡም ልዑል ሃሪ ይኸው ጋዜጣ ልዑሉ ለንጉሳውያን ስርዓቱ ጀርባውን ሰጥቷል በሚልም አንድ ፅሁፍ ማውጣቱን ተከትሎ ሃሰተኛ መረጃ በማሰራጨትም በሚል ከሷል።
news-51971185
https://www.bbc.com/amharic/news-51971185
ኮሮናቫይረስ፡ የኢትዮጵያ ኪነጥበብ ባለሙያዎች መልዕክት ስለ ኮሮናቫይረስ
የተለያዩ የኪነጥበብ ባለሙያዎች በጋራ በመሆን ስለ ኮሮናቫይረስ ግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክቶች በተንቀሳቃሽ ምስሎች በመስራት በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኀን እየለቀቁ መሆኑን የቡድኑ አባል የሆነው የፊልም ባለሙያ ክብረዓለም ፋንታ ለቢቢሲ ገለጸ።
እነዚህ "እጅ አንስጥ እጅ እንንሳ" እና "አብረን እንጂ ብቻችንን አንድንም" የሚሉ መልዕክቶች የያዙ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጁ ናቸው። አቶ ክብረዓለም ከእርሱ ባሻገር ሚካኤል ሚሊዮን፣ አክሊሉ ገብረመድኅን፣ ሰው መሆን ይስማው መኖራቸውን በመግለጽ የተለያዩ ቋንቋ ተናጋሪ የኪነጥበብ ባለሙያዎች መልዕክቱን በማስተላለፍም መሳተፋቸውን ይናገራል። የ Twitter ይዘት መጨረሻ, 1 ይህ በተለያዩ ማኅበራዊ መገናኛ ብዙኀን የተሰራጨው የግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክት በአማርኛ፣ በኦሮምኛ፣ በትግርኛ፣ በሲዳምኛና በጌዲዮኛ መሰራቱን አክሊሉ ለቢቢሲ አረጋግጧል። ባለሙያዎቹን በማኅበራዊ ሚዲያ ጥሪ በማቅረብ ለማሰባሰብ ሙከራ መደረጉን በመግለጽ በቂ ባለሙያ በበጎ ፈቃደኝነት ባለመምጣቱ የጃኖ ባንድ አባሉን ኃይሉ መርጋንና ተዋናይት ማኅደር አሰፋን በግል በማናገር እንዲሳተፉ ማድረጋቸውን ይጠቅሳል። ይህንን የግንዛቤ ማስጨበበጫ መልዕክትን ለማዘጋጀት ምክንያታቸው ምን እንደሆነ ያብራራው ክብርዓለም፤ በርካታ ሰዎች ስለኮሮናቫይረስ መረጃው ቢኖራቸውም መዘናጋት በማየታቸውና የጉዳዩ አሳሳቢነትን አቅልሎ የማየት ጉዳይ በመኖሩ ለመስራት መወሰናቸውን ይናገራል። ክብረዓለም የሌሎችን አገራት ተሞክሮም በመጥቀስ የተለያዩ የተሳሳቱ ግንዛቤዎች በማኅበረሰቡ ውስጥ መኖራቸውና ይህም በፍጥነት መታረም እንዳለበት ያስረዳል። አንዳንድ ሰዎች ወጣቶችን አይነካምና አፍሪካዊያንን አይዝም የሚሉ ተሳሳቱ አመለካከቶችን መስማታቸውና የሚናገረው አክሊሉ፤ የጥንቃቄ መልዕክቶችን ሰምቶ የምር በመውሰድ ተግባራዊ ማድረግ ላይ ዳተኝነት በመመልከታቸው በዚህ መንገድ መልዕክቱን ለማስተላለፍ መወሰናቸውን ያስረዳል። የመጣውን ነገር በጋራ ካልሆነ ለብቻችን አንችለውም የሚለው ክብረዓለም፤ ሁሉም ተጽዕኖ ማሳደር የሚችል ሰው የበኩሉን በኃላፊነት መማድረግ እንዳለበት ያስረዳል። አክሊሉ እንደሚለው ሁሉንም የጥንቃቄና፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክቶች እነርሱ መስራት እንደማይፈልጉ በመጥቀስ ስልክ ያላቸው እና ተሰሚነቱ ያላቸው ግለሰቦች በስልካቸው አጫጭር መልዕክቶችን በመቅረጽ ለተከታዮቻቸው ቢያስተላልፉ ይህ ወረርሽኝ የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ በማድረግ በኩል አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ ይችላሉ። በአሁኑ ሰዓት መስማት ለተሳናቸው በምልክት ቋንቋ እንዲሁም ለተለያዩ ኃይማኖት ተከታዮች መልዕክቶችን እያዘጋጁ መሆኑን በመጥቀስ ሁሉም ሰው መረጃውን በተለያዩ ቋንቋዎች እንዲያስተላልፉ ጥሪያቸውን ያስተላልፋሉ። ተንቀሳቃሽ ምስሉን ማንኛውም ግለሰብ ሆነ ተቋም በባለቤትነት ወስዶ መጠቀም እንደሚችል በመግለጽም ምስሎቹን ለመስራት አራቱ ባለሙያዎች ከኪሳቸው በማውጣት ወጪውን እንደሸፈኑ ገልጿል።
news-48412625
https://www.bbc.com/amharic/news-48412625
በሶማሌ ክልል የጄል ኦጋዴን እስር ቤት ኃላፊ ተይዞ ለኢትዮጵያ ተሰጠ
ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኘው የሶማሌ ክልል ውስጥ በርካታ አሰቃቂ ድርጊቶች ሲፈጸምበት እንደቆየ የሚነገርለት የጄል ኦጋዴን እስር ቤት ኃላፊ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ።
ሐሰን ኢስማኤል ኢብራሂም "ሐሰን ዴሬ" • አብዲ ሞሃመድ ኡመር በቁጥጥር ስር ዋሉ የቀድሞው የእስር ቤቱ ኃላፊ ሐሰን ኢስማኤል ኢብራሂም በቅጽል ስሙ "ሐሰን ዴሬ" ሶማሊያ ውስጥ በቁጥጥር ሥር ውሎ ለኢትዮጵያ ተላልፎ በመሰጠቱ ወደ ጅግጅጋ ተወስዷል። ግለሰቡ ክስ ወደ ተመሰረተበት አዲስ አበባ ሊወሰድ እንደሚችልም ተነግሯል። ምንጮች ለቢቢሲ እንደተናገሩት ግለሰቡ የተያዘው ሶማሊያን ከኢትዮጵያ ጋር በምታዋስነው ጎልደጎብ ተብላ በምትጠራው የድንበር ከተማ ውስጥ ነዋሪዎች ለጸጥታ ኃይሎች በሰጡት ጥቆማ አማካይነት ነው። ግለሰቡ በሶማሌ ክልል ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ እስር ቤቶች ውስጥ በተለይ ደግሞ ጄል ኦጋዴን ተብሎ በሚታወቀው እስር ቤት ውስጥ ተፈጽመዋል በሚባሉ ሰቆቃዎችና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ውስጥ ዋነኛ ሚና አለው ተብሎ ሲፈለግ ቆይቷል። • «አቶ ገዱም ሆነ ደመቀ እኛም ብንፈተሽ ግድፈት አለብን ማለታቸውን አስታውሳለሁ» የአቶ ታደሰ (ጥንቅሹ) ባለቤት ሐሰን ኢስማኤል (ሐሰን ዴሬ) የቀድሞውን የክልሉን ፕሬዝዳንት አብዲ መሐመድ ኦማርን ጨምሮ በሶማሌ ክልል ውስጥ በተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ምክንያት ክስ ከተመሰረተባቸው 40 ያህል ተጠርጣሪዎች መካከል አንዱ እንደሆነም ተነግሯል። ግለሰቡ በቀድሞው የሶማሌ ክልል መስተዳደር ውስጥ በከፍተኛ የደኅነትና የጸጥታ ኃላፊነቶች ላይ በተለያዩ ጊዜያት የሰራ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የሶማሌ ክልል የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ፣ የማረሚያ ቤቶች ኃላፊ፣ የጄል ኦጋዴን ኃላፊ እና በክልሉ ልዩ ፖሊስ ውስጥም በኮሎኔልነት አገልግሏል። በሶማሌ ክልል የሚገኙ እስር ቤቶች በተለይ ደግሞ ጄል ኦጋዴን ውስጥ ተይዘው የነበሩ እስረኞች ላይ አሰቃቂ ድርጊቶች ይፈጸሙባቸው እንደነበር የፌደራል መንግሥቱና የክልሉ መንግሥት ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል። • «ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ በረከት አናግረውናል» የአቶ በረከት ስምዖን ባለቤት በእስር ቤቱ ይገኙ በነበሩ በመቶች በሚቆጠሩ እስረኞች ላይ ይፈጸሙ ከነበሩት ድርጊቶች መካከል ከመሬት በታች ባሉ ጨለማ ጉድጓድ ውስጥ ማስቀመጥ፣ የተለያዩ ዓይነት ሰቆቃዎች፣ ከአደገኛ የዱር እንስሳት ጋር እስረኞችን ማስቀመጥ፣ አስገድዶ መድፈርና የመሳሰሉ ድርጊቶች እንደነበሩ ተገልጿል።
45711490
https://www.bbc.com/amharic/45711490
መላኩ ፈንታና ጀነራል አሳምነው ለአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ተመረጡ
ከወራት በፊት ከእስር የተፈቱት አቶ መላኩ ፈንታ እና ጀነራል አሳምነው ፅጌ ጨምሮ ያልተጠበቁ ግለሰቦች የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ሆነው ተመረጡ።
አዴፓ ለቀናት ድርጅታዊ ጉባኤውን ባህር ዳር ውስጥ ሲያካሂድ ቆይቶ ዛሬ ይፋ እንዳደረገው ለዕጩነት ከቀረቡት መካከል በፈቃዳቸው ለመልቀቅ ጥያቄ አቅርበው የነበሩት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን የፓርቲው ሊቀመንበር እንዲሁም የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ ሰይሟል። አዴፓ በተጨማሪም ለፓርቲውና ለኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ አባልነት አስራ ሶስት ሰዎችን አሳውቋል። ለማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ከተሰየሙት ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባዋ ወ/ሮ ዳግማዊት፣ የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን፣ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ዶክተር ስዩም መስፍን እና የአዲስ አበባ መገናኛ ብዙሃን ውስጥ የሥራ ኃላፊ የሆኑት ወይዘሮ እናታለም መለሰ ይገኙበታል። ለጉባኤው የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እንዲሆኑ የቀረቡት 75 ግለሰቦች የነበሩ ሲሆን ከእነዚህም መካከል 65ቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነው ተመርጠዋል። ከድርጅቱ ነባር አመራሮች መካከል አቶ ከበደ ጫኔ፣ አቶ መኮንን ወሰንየለህ፣ ወ/ሮ ፍሬህይወት አያሌው፣ ወ/ሮ ብስራት ጋሻው ጠና፣ አቶ ጌታቸው አምባዬ፣ ወ/ሮ ዘነቡ ታደሰ፣ አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን ከድርጅቱ እንዲሰናበቱ ተወስኗል። • በቤንሻንጉል ጉምዝ ከ50 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተሰማ • ኢትዮጵያ 8.5 በመቶ ዕድገት ታሥመዘግባለች፡ አይ.ኤም.ኤፍ. በሌላ በኩል የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) የቀድሞውን ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ 23 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቱን አሰናብቷል። በሀዋሳ ከተማ እያተካሄደ ባለው ጉባኤ ከተሰናበቱት ነባር አመራሮች መካከል አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ሽፈራው ሽጉጤ፣ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ፣ ሲራጅ ፈጌሳ፣ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና መኩሪያ ኃይሌ ይገኙበታል። ማእከላዊ ኮሚቴ እስከ 10ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ በእግድ እንዲቆዩ አድርጓቸው የነበረውን አቶ ሳሙኤል ደምሴ፣ ከሰተብርሃን አድማሱ (ዶ/ር) እና ወ/ሮ አማረች ኤርሚያስን ከድርጅቱ አሰናብቷል። ከባለፈው ረቡዕ ጀምሮ በመቀሌ ሲካሄድ የቆየው 13ኛ የህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት)ድርጅታዊ ጉባኤም ዛሬ ተጠናቋል። ሕወሓት ዶ/ር ደብረፅዮንና ወ/ሮ ፈትለወርቅ ሊቀ-መንበርና ምክትል ሊቀ-መንበር አድርጎ መርጧል። ከዚህ በተጨማሪም ድርጅቱ አቶ ጌታቸው ረዳ፣ አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም እና አዲስዓለም ቤለማ (ዶ/ር) ጨምሮ 11 አባላትን ለኢህአዴግና ለሕወሓት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች አባላትን መርጧል። ነገር ግን ከአስራ አንዱ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ከሞላ ጎደል ነባር የድርጅቱ ታጋዮች ሲሆኑ አዲስና ወጣት አባላት አለማካተታቸው ታውቋል። ሕወሓት ቀደም ሲል የነበረውን የድርጅቱን የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ቁጥርን ከ45 ወደ 55 ያሰደገ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥም 15 የሚሆኑት ወጣትና አዳዲስ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ናቸው። የድርጅቱ ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል በጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይ ባደረጉት ንግግር ጉባኤው ዴሞክራሲያዊ ትግል የተደረገበት እና ታሪካዊ ነበር ብለዋል።
news-54165435
https://www.bbc.com/amharic/news-54165435
ኮሮናቫይረስ፡ በሕንድ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር 5 ሚሊየን አለፈ
በሕንድ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አምስት ሚሊየን ማለፉ ተገለፀ። ይህም አገሪቱን በአሜሪካ በመቀጠል በቫይረሱ ክፉኛ የተጎዳች እንድትሆን አድርጓታል።
በሕንድ በአንድ ቀን ብቻ እስከ 90 000 ሰዎች በኮቪድ-19 እየተያዙ ሲሆን ቫይረሱም በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ ነው ተብሏል። እስካሁን ድረስ በአገሪቱ ከ80 ሺህ በላይ ሰዎች ሲሞቱ፣ በቫይረሱ ምክንያት በጽኑ ለታመሙ አልጋ እንዲሁም የኦክስጅን አቅርቦት እጥረት ተከስቷል። በሕንድ የቫይረሱ ስርጭት እየተስፋፋ የመጣው በመጋቢት ወር ተጥሎ የነበረውን የእንቅስቃሴ ገደብ የምጣኔ ሃብቱን ለማነቃቃት በሚል ከተነሳ ወዲህ ነው። ቫይረሱ ወደትንንሽ ከተሞች ከመሰራጨቱ በፊት እንደ ሙምባይና ደልሂ ያሉ ግዙፍ ከተሞችን ክፉኛ አጥቅቶ ነበር። ሕንድ ምጣኔ ሃብቷን ክፍት ማድረግ በጀመረችበትና ሰዎች ወደ ስራ በተመለሱበት ወቅት የቫይረሱ ስርጭት እየተስፋፋ መምጣቱ ተስተውሏል። ባለፉት ሳምንት ብቻ 600,000 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው በምርመራ ተረጋግጧል። በሕንድ አሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 5,020,359 የደረሰ ሲሆን፣ ባለፈው 24 ሰዓታት ብቻ 90,123 መያዛቸው መታወቁ ተገልጿል። በአገሪቱ የኦክስጅን ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ኦክስጅን አምራች ኢንደስትሪዎች ገልፀዋል። በዚህ ወር ብቻ ሆስፒታሎችና የእንክብካቤ ማዕከላት 2,700 ቶን ኦክስጅን የተጠቀሙ ሲሆን፣ በሚያዚያ ወር ግን 750 ቶን ብቻ ነበር ፍጆታቸው ተብሏል። የቫይረሱ ስርጭት እየጨመረባቸው ከሚገኙ የህንድ ከተሞች መካከል ማሃራሽትራ፣ ማድያ ፕራዴሽ፣ ጉጅራት፣ ራጃስታን፣ ቴሌንጋና፣ አንድሃራ ፕራዴሽ ናቸው።
news-52507019
https://www.bbc.com/amharic/news-52507019
ኮሮናቫይረስ በጋና፡ የኦንላይን የቀብር ሥነ ስርዓት እና ምርጫ
በጋና ወረርሽኙ ከተከሰተ በኋላ ያለውን የቀብር ሥነ ሥርዓት እና ምርጫን በተመለከተ ስላለው አዲስ ልማድ ጋዜጠኛና የቀድሞዋ የጋና የመንግሥት ሚኒስተር ኤልሳቤት ኦሄኔ የሚከተለውን ለቢቢሲ ጽፈዋል።
"ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በኋላ ሕይወት ከተለመደው ተለዋውጧል። ልክ እንደመተቃቀፍና መጨባበጥ ይቀራል ብሎ ማንም ሰው አልሞት እንደማያውቀው ሁሉ ወረርሽኙን ለመታገል ስንል ብዙ እየተማርን ነው፡፡ አካላዊ መራራቅ፣ ራስን ማግለል እና ለይቶ ማቆያ በየእለቱ የምንጠቀማቸው ቃላት ሆነዋል፡፡ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል፤ ወላጆች ልጆቻቸው ምን ያህል ምግብ እንደሚመገቡ ማወቅ ጀምረዋል፡፡ በጋና በኮሮናቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 16 ቢሆንም ከመናገር የምንቆጠባቸው ነገሮች መጥተዋል- መቃብር ቦታዎች ሞልተዋል የሚል፡፡ የቀብር ሥነ ስርዓት ለመፈጸም መሰባሰብ ተክልክሏል፡፡ በመሆኑም በተለመደው መልኩ ወዳጅ ዘመድ ተሰባስቦ የሚወዱትን ሰው አልቅሶ መሸኘት ቀርቷል፡፡ በግል የቀብር ሥነ ስርዓት መፈጸም ቢቻልም ከ25 በላይ ሰዎች መገኘት አይችሉም፡፡ ይህ ደግሞ ለጋናዊያን የማይታገሱት ልማድ ሆኗል፡፡ በመሆኑም ይህ አስከፊ በሽታ ይጠፋል በሚል ተስፋ እና ለሟቾቹ በተከበረ መልኩ የቀብር ሥርዓት ለመፈጸም የሞቱ ሰዎችን አስክሬን በመቃብር ቤቶች ማስቀመጣችንን ቀጥለናል፡፡ በአዲሱ ውሳኔ መሰረት በጋና የቀብር ሥነ ስርዓት በቴክኖሎጅ የተደገፈ ሆኗል፡፡ የቀብር ሥነ ስርዓቱ ቁጥራቸው 25 ወይም ከዚያ በታች የሚገኙ ሲሆን፤ ሥነ ስርዓቱ ግን በቀጥታ በኦንላይን ሥርጭት ይተላለፋል፡፡ በመሆኑም በርካታ ሰዎች ቤታቸው ተቀምጠው በላፕቶፓቸው ሥነ ስርዓቱን ይካፈላሉ፡፡ ይህ ልምድ በዚሁ ከቀጠለ የቀብር ሥነ ስርዓት አፈጻጸማችን ሁኔታ ይቀየራል፡፡ እኔ ባለፈው ሳምንት በኢንተርኔት አማካኝነት የቀብር ሥነ ስርዓት ላይ ተገኝቻለሁ፡፡ ጅንስና ቲሸርት ለብሼ፤ ማንም ሰው በእንዲህ ዓይነት አለባበስ መልኩ ቀብር ሥነ ስርዓት ላይ አይገኝም፡፡ የፋሲካ በዓል የተከበረበትን እሁድ ጨምሮ ሰባት እሁዶችን ቤተ ክርስቲያን ሳንሄድ አሳልፈናል፡፡ ኮሮናቫይረስ ለሁላችንም አስፈሪ ከመሆኑም በላይ ድራማ ይመስላል፡፡ በአሁኑ ሰዓት በቅዱስ ረመዳን ወር ላይ እንገኛለን፡፡ ሙስሊሞች ያለ ሕብረት ጸሎት ጾም ጀምረዋል፡፡ ከማፍጠሪያ በፊት ወደ መስጊድ በመሄድ የሚያደርጉት የሕብረት አምልኮም ቀርቷል፡፡ ባልተረጋጋ ጊዜ ውስጥ ስላለን አብዛኞቻችን ይህንን ተቀብለነዋል፡፡ የጋና መዲና አክራ እና አካባቢዋ እንዲሁም ሁለተኛ ከተማዋ ኩማሲ ለሦስት ሳምንታት ያህል በእንቅስቃሴ ገድብ ውስጥ ነበሩ፡፡ አሁን እንኳን ሰዎች መንቀሳቀስ ይችላሉ፡፡" ምርጫ በሚመጣው የፈርንጆቹ ታህሳስ ወር የፕሬዚደንትና የፓርላማ ምርጫ ይካሄዳል፡፡ እዚህ ምርጫ ሲካሄድ ብዙ ጊዜ ግጭቶች ይፈጥራሉ፡፡ የምርጫ ዘመቻዎችም የደመቁና የተጨናነቁ ናቸው፡፡ ታዲያ ብጥብጥ እንዳይፈጠር እድል ላለመስጠት ዝግጅቱ የተካሄደው በጣም በተጨናናቀ የጊዜ ሰሌዳ ነው፡፡ ከዚያ ቫይረሱ ገባ፤ ቫይረሱ የመጀመሪያውን ተግዳሮት የጣለው በብሔራው ምዝገባ ባለስልጣን ላይ ነው፡፡ ለምርጫው መጀመሪያ የሚደረገው መታወቂያ መስጠት ነበር፡፡ በቫይረሱ ምክንያት ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ከ16 ዓመት በላይ ላሉት መታወቂያ ሰጥቶ መጨረስ አልቻለም፡፡ የምርጫ ቦርድ ደግሞ አዲስ መራጮችን ምዝገባ ማጠናቀር ይፈልጋል፤ ይሁን እንጅ ተቃዋሚው የብሔራዊ ዲሞክራቲክ ኮንግረስ ፓርቲ ምንም አልመዘገበም፡፡ በርግጥ ኮሚሽኑ ምዝገባ ሂደቱን ከሳምንት በፊት ለማጠናቀቅ እቅድ ቢኖረውም የሰዎች መሰባሰብ በመከልከሉ ባለበት ቆሟል፡፡ በዚህ ምርጫ ገዥውን ፓርቲ ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሶስተኛ ጊዜ የሚፋጠጡበት ነው፡፡ የምርጫ ዘመቻዎችን እንዴት ማካሄድ እንደሚቻልም ግራ ያጋባ ጉዳይ ሆኗል፤ ለፓርቲዎች ክርክርም ፍላጎቱም እምብዛም ነው፡፡ የአገሪቷ ፕሬዚደንት ናና አኩፎ አዶ ወረርሽኙ ከተከሰተ አንስቶ እስካሁን ስምንት ጊዜ መግለጫ የሰጡ ሲሆን ሕዝቡም ንግግራቸውን ተቀብሏል፡፡ ካደረጓቸው ንግግሮች መነጋጋሪያ የነበረው "ኢኮኖሚያችንን እንዴት እንደምናንሰራራው እናውቃለን፤ የማናውቀው ሰዎችን ወደ ሕይወት እንዴት መመለስ እንደምንችል ነው " የሚለው ነበር፡፡ ፕሬዚደንቱ "ቫይረሱ ፖለቲካዊ ቀለም የለውም፤ ፖለቲካዊ ለማድረግም ጊዜው አሁን አይደለም፤ የጋራ ጠላታችንን መታገል አለብን" ብለዋል፡፡
news-54145140
https://www.bbc.com/amharic/news-54145140
ኦነግ ፡ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አቶ ዳውድ ኢብሳን ማገዱን ለምርጫ ቦርድ አስታወቀ
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የኦነግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የግንባሩ የረጅም ጊዜ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዳውድ ኢብሳን ከፓርቲው ኃላፊነት ማገዱን በፃፈው ደብዳቤ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማስታወቁን ቦርዱ ለቢቢሲ አረጋገጠ።
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቃል አቀባይ ሶሊያና ሽመልስ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የግንባሩ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ለቦርዱ በላከው ደብዳቤ ላይ ባካሄደው ስብሰባ መሰረት "አቶ ዳውድ ኢብሳ የሥነ ምግባር ጥሰት ፈፅመዋል" ብሎ ከግንባሩ አመራርነት መታገዳቸውን ገልጿል። ጉዳዩን በተመለከተም የፓርቲው የሥነ ሥርዓትና ቁጥጥር ኮሚቴ መላኩንም በደብዳቤው አስታውቋል። ቃል አቀባይዋ እንደገለጹት የደረሳቸው ደብዳቤ በኦሮሞ ነፃነት ግንባር ምክትል ሊቀመንበር አቶ አራርሶ ቢቂላ የተፈረመ ነው። በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው እገዳ ሲያደርግ ለሥነ ሥርዓትና ቁጥጥር ኮሚቴ እንደሚልክ የገለጹት ሶሊያና፤ በደብዳቤው ላይ ለኮሚቴውን ማሳወቃቸውን ከመገለጹ ውጪ ከቦርዱ የጠየቁት ምንም ዓይነት ውሳኔ አለመኖሩን ተናግረዋል። ታግደዋል ከተባሉት ከአቶ ዳውድ ኢብሳ በኩልም ሌላ ደብዳቤ እንደደረሳቸው ቃል አቀባይዋ ገልፀዋል። ነገር ግን ደብዳቤው ከዚህ በፊት በነበረው የሥነ ሥርዓትና ቁጥጥር ኮሚቴ የተፃፈ ሲሆን ቀደም ሲል የተካሄዱ የፓርቲውን ስብሰባዎች የተመለከተ እንጂ ከእገዳው ጋር የተያያዘ አለመሆኑንም አስረድተዋል። በመሆኑም ቦርዱ ከሁለቱም ወገኖች የሚመጡ ደብዳቤዎችን መተዳዳሪያ ደንባቸውን እና የፖለቲካ ፓርቲዎች መተዳዳሪያ አዋጅን መሰረት አድርጎ እንደሚመረምር አክለዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከፍተኛ አመራሮች መካከል ልዩነት ተፈጥሮ ውዝግብ እንደነበረ የሚታወስ ሲሆን፤ በግንባሩ የረዥም ጊዜ ሊቀመነበር አቶ ዳውድ ኢብሳ እና በምክትል ሊቀመበሩ በአቶ አራርሶ ቢቂላ የሚመሩ ሁለት ጎራዎች መፈጠራቸው እየታየ ነው። በዚህም ሳቢያ አንደኛው ወገን ሌላኛውን እውቅና ከመንሳት ጀምሮ የእገዳ ውሳኔዎችን እያስተላለፈ ይገኛል። የኦነግ ቃል አቀባይ እንደሆኑ የሚናገሩት አቶ ቀጄላ መርዳሳ የአቶ ዳውድ ኢብሳ ከሊቀመንበርነት መታገድ ሕጋዊ መንገድን የተከተለ ነው በማለት ሲያረጋግጡ፤ በተመሳሳይ የኦነግ ቃል አቀባይ ነኝ የሚሉት አቶ መሐመድ ረጋሳ ደግሞ አቶ ዳውድ ኢብሳን ያገዱት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ከዚህ ቀደም እራሳቸው ታግደዋል ይላሉ። አቶ ቀጄላ እንደሚሉት "ሕግ የተላለፉ፤ የሥነ ምግባር ጥሰት የፈጸሙ በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሊታገዱ ይችላሉ። ይህ የፓርቲው አሰራር ነው" በማለት እርምጃው ሕጋዊ እንደሆነ አመልክተዋል። አቶ መሐመድ የአቶ ዳውድ ኢብሳ መታገድን በተመለከተ "በመንግሥት ሚዲያዎች መግለጫ መሰጠቱን ሰምተናል። ይህ መግለጫ ከኦነግ የወጣ አይደለም፤ ኦነግ አያውቀውም" በማለት መግለጫውን ያወጡት ሰዎች ከግንባሩ የታገዱ መሆናቸውንም ተናግረዋል። ጨምረውም እገዳው አቶ ዳውድ ኢብሳ በተገኙበት ነሐሴ ወር ላይ በተካሄደ ስብሰባ የሕግና የቁጥጥር ኮሚቴ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ የኦነግ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑትን አቶ አራርሶ በቂላን ጨምሮ 6 የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ታግደዋል ብለዋል። የሊቀመንበሩን መታገድ በተመለከተ ዕሁድ ዕለት ከድርጅቱ የወጣ ነው የተባለው ረጅም መግለጫ ላይ አቶ ዳውድ ኢብሳን ግንባሩን ጎድቷል በተባሉ በተለያዩ ጥፋቶች የሚከስ ሲሆን ድርጅቱንም ለአራተኛ ጊዜ በመከፋፈል ላይ መሆኑን ገልጿል። መግለጫው አቶ ዳውድን የድርጅቱን ሀብትና ንብረት እንዲሁም ስልጣንን ያላግባብ በመጠቀም፣ በአባላት ላይ ሐሰተኛ ውንጀላዎችን በማቅረብና ድርጅቱ ያልፈቀዳቸውን ግንኙነቶች በማድረግ ከግንባሩ ሊቀመንበርነታቸው እንዲነሱ እንደተደረገ መግለጫው አመልክቷል። በመሆኑም የሊቀመንበሩ ጉዳይ ተጣርቶ በቀጣዩ የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ውሳኔ አስኪያገኝ ድረስ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በወሰነው መሰረት ከኃላፊነታቸው "ታግደው እንደሚቆዩ ለድርጅቱ አባላት፣ ለደጋፊዎቹ፣ ለኦሮሞ ሕዝብና ለሌሎች አካላት እናሳውቃለን" ብሏል። መግለጫው በማጠቃለያው ላይ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጠቅላላ ጉባዔ ተደርጎ አዲስ መሪ እስኪመረጥ ድረስ የድርጅቱ ተወካይና መሪ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ አራርሶ ቢቂላ ሆነው እንደሚቆዩ አሳውቋል።
news-55937231
https://www.bbc.com/amharic/news-55937231
የኡጋንዳዊ አማፂ ቡድን አመራር የነበረው በጦር ወንጀሎች ጥፋተኛ ሆኖ ተገኘ
የኡጋንዳው ሎርድ ሬዚስታንስ አርሚ የተሰኘው አማፂ ቡድን አመራር ነበር የተባለው የቀድሞው ህፃን ወታደር ዶሚኒክ ኦንግዌን በጦር ወንጀሎች የአለም አቀፉ ወንጀል ፍርድ ቤት (አይሲሲ) ጥፋተኛ ሆኖ አግኝቶታል።
ታሪካዊ በተባለው የፍርድ ሂደት ዶሚኒክ ኦንግዌር ለአለም አቀፉ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ሆኖ በቀረበው አስገዳጅ እርግዝና የጥፋተኝነት ብያኔ ተላልፎበታል። በነውጠኛነቱ በሚታወቀው የኡጋንዳው ሎርድ ሬዚስታንስ አርሚ በአስፈሪነቱ ስሙ የሚጠራው ዶሚኒክ በአለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ሲቀርብ የመጀመሪያ ግለሰብ ነው። በመሪው ላይ የቀረቡበት ክሶች በአውሮፓውያኑ 2004 የተፈናቀሉ ኡጋንዳውያን መጠለያ በሆኑ አራት ካምፖች ላይ ጥቃት አድርሷል በሚል ሲሆን ከቀረቡበት 70 የጦር ወንጀሎችና በሰብዓዊነት ላይ የሚፈፀም ወንጀል ክሶች መካከል በ61ዱ ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል። ፍርድ ቤቱም ከ4ሺህ በላይ የተጠቂ እማኞችን ምስክርነት ሰምቷል። እስካሁን ባለው የእስር ጊዜ ያልተበየነበት ቢሆንም የእድሜ ልክ እስራት ሊጠብቀው ይችላል ተብሏል። በህፃንነቱ ለወታደርነት ተጠልፎ የአማፂው ቡደን አባል የሆነው ዶሚኒክ ክሱም በሚታይበት ወቅት ጥፋተኛና ተጠቂ ሆኖ መቅረቡ ለፍርድ ቤቱ ግራ አጋቢ ነበር ተብሏል። በአማፂው ቡድን ተጠልፎ የህፃን ወታደር የሆነው ዶሚኒክ በኋላም በተለያዩ ማዕረጎች አልፎ የኃላፊው ጆሴፍ ኮኒ ምክትል ለመሆን በቅቶ ነበር። የዶሚኒክ ጠበቆች ከሆኑት አንዱ ክሪስፐስ አይና ኦዶንጎ ይግባኝ እንደሚጠይቁ ተናግረው ውሳኔው "እንደ ቦንብ ፍንዳታ ነው" ብለዋል። የሂውማን ራይትስ ዋች አካል የሆነው አለም አቀፉ የፍትህ ፕሮግራም ዳይሬክተር ኤሊሱ ኬፕለር በውሳኔው ደስተኛ እንደሆኑ ተናግረዋል። "በሎርድ ሬዚስታንስ አርሚ የተበየነ የመጀመሪያና ብቸኛው ውሳኔ በመሆኑ ወሳኝ ነው" በማለት መናገራቸውን አጃንስ ፍራንስ ፐሬስ በዘገባው አስነብቧል። ዶሚኒክ ኦንግዌን ማን ነው?
news-52254197
https://www.bbc.com/amharic/news-52254197
“ገደቦችን በአጭር ጊዜ ማንሳት ወረርሽኙ በአስከፊ ሁኔታ እንዲሰራጭ ያደርጋል” ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም
አገራት እንቅስቃሴ ላይ የጣሉትን ገደብ በአጭር ጊዜ ካነሱ፤ የወረርሺኙ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ ሊጨምር እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።
የድርጅቱ ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም እንዳሉት፤ ምንም እንኳን እንቅስቃሴ ላይ የተጣለው ገደብ በአገራት ምጣኔ ኃብት ላይ ጫና ቢያሳድርም፤ መንግሥታት እገዳውን ከማንሳታቸው በፊት ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል። ቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ የተሰራጨባቸው ስፔን እና ጣልያን እንቅስቃሴ ላይ የጣሉትን እገዳ ባያነሱም፤ እርምጃዎቻቸውን እያላሉ ነው። ዶ/ር ቴድሮስ፤ በአንዳንድ የአውሮፓ አገራት የወረርሽኙ ስርጭት እየቀነሰ እንደሆነ ተናግረዋል። የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የተጣሉ እገዳዎች እንዲላሉ፤ የዓለም ጤና ድርጅት ከተለያዬ አገራት ጋር እየተነጋገረ ቢሆንም፤ እርምጃው በአጭር ጊዜ ሊወሰድ እንደማይገባ አስረድተዋል። “የተጣሉትን ገደቦች በአጭር ጊዜ ማንሳት ወረርሽኙ በአስከፊ ሁኔታ እንዲሰራጭ ያደርጋል” ብለዋል ኃላፊው። ስፔን የፋብሪካ እና የግንባታ ሠራተኞች ወደ ሥራ እንዲመለሱ ለመፍቀድ እየተዘጋጀች ነው። ሆኖም ዜጎች ማኅበራዊ ርቀትን መጠበቅ እንዳያቆሙ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል። አገሪቱ ከ17 ቀናት በኋላ አነስተኛውን የሟቾች ቁጥር ያስመዘገበችው አርብ ነበር። እስካሁን በስፔን በቫይረሱ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች 15,843 ደርሰዋል። የጣልያኑ ጠቅላይ ሚንስትር ጁሴፔ ኮንቴ እስከቀጣዩ ወር እንቅስቃሴ እንዲገታ ትዕዛዝ ሰጥተዋል። ሆኖም ካለፈው ወር ጀምሮ የተዘጉ አንዳንድ የንግድ ዘርፎች እንዲከፈቱ ተወስኗል። መጻሕፍት ቤቶች፣ የልጆች አልባሳት ሱቆች በድጋሚ ከሚከፈቱት መካከል ይጠቀሳሉ። እስካሁን አገልግሎት እየሰጡ የነበሩት የመድኃኒት እና የምግብ መደብሮች ብቻ ነበሩ። ባለፈው አርብ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር 570 የደረሰ ሲሆን፤ በቫይረሱ የሚያዙ አዲስ ሰዎች ቁጥር ከ4,204 ወደ 3,951 ወርዷል። ሌሎች አገራትስ ምን እርምጃ ወሰዱ? የአየርላንድ ጠቅላይ ሚንስትር ሊዮ ቫራድከር አገራቸው ውስጥ እስከ ቀጣይ ወር ድረስ እንቅስቃሴ እንደሚቆም ተናግረዋል። ቱርክ በ31 ከተሞቿ የ48 ሰዓት የሰዓት እላፊ ገደብ ጥላለች። ፖርቹጋል ደግሞ እስከሚቀጥለው ወር ድረስ የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንግጋለች። ዩናይትድ ኪንግደም የቫይረሱ ስርጭት እስኪቀንስ የእንቅስቃሴ ገደብ አይነሳም ብላለች። በደቡብ አፍሪካ ለ21 ቀናት ታውጆ የነበረው የእንቅስቃሴ እገዳ በሁለት ሳምንት ተራዝሟል። የቫይረሱ ስርጭት እየቀነሰ ነው? የዓለም ጤና ድርጅት፤ በአንዳንድ የአውሮፓ አገራት የበሽታው ስርጭት ዝግ እያለ መሆኑን ባለፈው አርብ በሰጠው መግለጫ ጠቁሟል። ከኋይት ሀውስ፤ ዴቦራ ብሪክስ እንደተናገሩት፤ ወረርሽኙ ከፍተኛ ደረጃ አለመድረሱን የሚያሳዩ ተስፋ ሰጪ ምልክቶች አሉ። በሌላ በኩል በሽታው ወደሌሎች አገሮች እየተሰራጨ መሆኑን ዶ/ር ቴድሮስ ተናግረዋል። በተለይም በአፍሪካ በገጠራማ አካባቢዎች ቫይረሱ እየተስፋፋ መጥቷልም ብለዋል። “በአፍሪካ ከ16 በላይ አገራት ውስጥ በሽታው ወደ ማኅበረሰቡ ተሰራጭቷል። ከከተሞች አንጻር ደካማ የጤና ሥርዓት ያላቸው ገጠራማ አካባቢዎች በእጅጉ ይፈተናሉ” ሲሉ ዶ/ር ቴድሮስ ተናግረዋል።
49575670
https://www.bbc.com/amharic/49575670
"የሴቶች የንፅህና መጠበቂያን ከቀረጥ ነፃ እናደርጋለን" ዶ/ር አሚር አማን
የጤና ጥበቃ ሚንስትሩ ዶ/ር አሚር አማን የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ሞዴስን ከቀረጥ ነፃ ለማድረግ እየሠሩ እንደሆነ ለቢቢሲ ገለጹ።
ዶ/ር አሚር አማን የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ (ሞዴስ) በተመጣጠነ ዋጋ እንዲቀርብ እንዲሁም ተደራሽነቱ እንዲሰፋ አንዱ እርምጃ ከቀረጥ ነፃ ማድረግ እንደሆነ ሚንስትሩ አስረድተዋል። የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ እንደማንኛውም መድኃኒት እና የህክምና አገልግሎት መስጫ መሣሪያ ተመርቶ እንዲሰራጭ ለማድረግ እቅድ እንደተያዘም ገልጸዋል። ዶ/ር አሚን እንዳሉት፤ የደረሱበትን ውሳኔ በሚመጣው አዲስ ዓመት ከፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ከሚመለከታቸው ተቋሞች ጋር በመሆን ለሕዝብ ይፋ ያደርጋሉ። • 'አስጸያፊ' ከመባል ኦስካር ወደማሸነፍ • ‘ማርያም ሰባ’፡ የራስን ቁስል በራስ ማከም "በግሌና እንደ ጤና ጥበቃ ሚንስትርነቴም፤ የንፅህና መጠበቂያ ማግኘት የእያንዳንዷ ሴት መብት መሆኑን አምናለሁ" ያሉት ዶ/ር አሚን፤ መንግሥት ለሴቶች የንፅህና መጠበቂያ የማቅረብ ኃላፊነት እንዳለበትም ገልጸዋል። ሚንስትሩ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ መንግሥት ለአቅመ ደካማ ሴቶች የንፅህና መጠበቂያ በነፃ የማቅረብ ኃላፊነት እንዳለበት አስረድተዋል። የንፅህና መጠበቂያ መግዛት ለሚችሉ ሴቶች ደግሞ ምርቱ በተመጣጠነ ዋጋ ገበያ ላይ መቅረብ እንዳለበት አክለዋል። የንፅህና መጠበቂያ አለማግኘት በሴቶች የሥነ ተዋልዶ ጤና እንዲሁም በትምህርት ላይም ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል። • ኢቦላ ለምን አገረሸ? • የኢቦላ መድሃኒት ላይ የተደረገ ሙከራ 90 በመቶ ውጤት አሳየ የጤና ጥበቃ ሚንስትሩ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የኢቦላ ወረርሺኝ ቢከሰት በአፋጣኝ ምላሽ የሚሰጥ ቡድን እንደተቋቋመም ገልጸዋል። በአዲስ አበባ፣ በድሬ ዳዋ እና በመቐለ አውሮፕላን ማረፊያዎች በኩል ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ግለሰቦች ላይ የኢቦላ ምርመራ እንደሚደረግም ሚንስትሩ አክለዋል። ከአውሮፕላን ማረፊያዎቹ በተጨማሪ በ28 ኬላዎች ላይም ምርመራው ይካሄዳል። "ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚመጡ ሰዎችን የጤና ሁኔታ የሚከታተል ቡድን አዋቅረናል። ሰዎቹ ወደ አገር ውስጥ ከገቡበት ቀን ጀምሮ ለአሥር ቀናት ክትትል ይደረጋል" ሲሉ አስረድተዋል። ዶ/ር አሚር እንዳሉት፤ ኢቦላን ለመከላከል እንቅስቃሴ የተጀመረው ከአምስት ዓመት በፊት ነበር። በወቅቱ ቫይረሱ በምዕራብ አፍሪካ አገራት አሳሳቢ ከነበሩ ወረርሽኞች ግንባር ቀደሙ ስለነበር ኢትዮጵያ የህክምና ባለሙያዎችን ወደ ምዕራብ አፍሪካ አገራት ልካ ነበር። "ባለሙያዎቹን የላክናቸው አገራቱን ከማገዝ ጎን ለጎን ኢትዮጵያን ከወረርሽኙ ለመከላከል ምን ማድረግ እንዳለብን ትምህርት ቀስመው እንዲመጡ ጭምርም ነበር" ሲሉ ተናግረዋል። የህክምና ባለሙያዎቹ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ፤ ወረርሽኙ ድንገት ቢከሰት በአፋጣኝ ምላሽ የሚሰጥ ቡድን መዋቀሩን ገልጸዋል። በአሁን ወቅት ኢቦላ በተለይም በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከፍተኛ ቀውስ መፍጠሩን ተከትሎ ይህ ቡድን በተጠንቀቅ እየጠበቀ መሆኑንም አክለዋል። • የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት የተፈጸሙትን ጥቃቶች አወገዙ • የማዉ ጫካን ለማዳን 60 ሺ ኬንያውያን ከመኖሪያቸው ተባረሩ ወረርሽኙ ቢከሰት በቫይረሱ የተያዙ ግለሰቦች ተለይተው ክትትል የሚደረግበት ልዩ ቦታ በአዲስ አበባ ይገኛል። በክልል ከተሞችም ይህንን አገልግሎት የሚሰጡ 11 ልዩ ቦታዎች መዘጋጀታቸውንም ሚንስትሩ ገልጸዋል።
news-46542473
https://www.bbc.com/amharic/news-46542473
ሕንዳዊቷ ህፃን ሃኒፋ ዛራ በመፀዳጃ ቤት ምክንያት አባቷን ለፖሊስ ከሰሰች
የ7 ዓመቷ ህንዳዊት አባቷ መፀዳጃ ቤት ሊሰራላት የገባላትን ቃል ባለመጠበቁ ወደ ፖሊስ ጣቢያ በማምራት ክስ አቅርባለች።
ሃኒፋ ዛራ የተባለችው ይህች ሕፃን አባቷ "አታሎኛል፤ ስለዚህ መታሰር ይገባዋል" ስትል ለፖሊስ ደብዳቤ ፅፋለች። ምክንያቷ ደግሞ በመኖሪያ ቤታቸው ምቹ የሆነ መፀዳጃ ቤት ባለመኖሩ ደጅ ሰዎች እያዩኝ መፀዳዳት ያሳፍረኛል ብላለች። • በህንድ ጥቅም ላይ የዋሉ የንፅህና መጠበቂያ ጨርቆች ለምን ተፈለጉ? • መጠየቅ ካለብን የምንጠየቀው በጋራ ነው፡ አባይ ፀሐዬ እንደ የተባበሩት መንግሥታት የህፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) ሪፖርት አብዛኞቹ የህንድ ዜጎች መፀዳጃ ቤት የሌላቸው ሲሆን 500 ሚሊዮን የሚሆኑት በግላጭ ቦታዎች ለመፀዳዳት ይገደዳሉ። በተቃራኒው በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ መፀዳጃ ቤቶች የተገነቡ ቢሆንም በአግባቡ አይጠቀሙባቸውም። በህንድ ምዕራባዊ ግዛት በሆነችው አምቡራ ከቤተሰቦቿ ጋር የምትኖረው ሃኒፋ ሳትሸማቀቅ የምትጠቀምበት መፀዳጃ ቤት ኖሯት አያውቅም። ሃኒፋ ለቢቢሲ እንደተናገረችው፤ ጎረቤቶቿ መፀዳጃ ቤት ስላላቸው እነሱም መፀዳጃ ቤት እንዲኖራቸው ደጋግማ አባቷ እንዲገነባላት ትጠይቀው ነበር። ይህንን ጥያቄ ስታቀርብ የመዋለ ህፃናት ተማሪ ነበረች። "ደጅ ወጥቼ ስጠቀም በጣም ነው የማፍረው፤ ሰዎች አተኩረው ሲያዩኝም ጥሩ ስሜት አይሰማኝም" የምትለው ሃኒፋ በተለይ ትምህርት ቤት ንፅህናው ባልተጠበቀ ቦታ መፀዳዳት ስለሚያስከትላቸው የጤና ችግሮች ትምህርት ካገኘች በኋላ ጥያቄውን ለማቅረብ እንደተነሳሳች ትናገራለች። ለፖሊስ በፃፈችው ደብዳቤ ላይ እንደገለፀችው በትምህርቷ ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ ከቻለች መፀዳጃ ቤት እንደሚገነባላት አባቷ ቃል ገብቶላት ነበር። አሁን የሁለተኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ሃኒፋ ከመዋለ ሕፃናት ትምህርት ጀምሮ ከፍተኛ ውጤት ብታስመዘግብም፤ አባቷ የገባላት ቃል ተፈፃሚ ሊሆንላት አልቻለም። " እንሰራላን አታስቢ " የሚል መፅናኛ ብቻ እንደሚነግራት ታስረዳለች። "በመሆኑም የአባቴ ተግባር ከማጭበርበርና ማታለል ያልተናነሰ በመሆኑ እሰሩት፤ የማታስሩት ከሆነ ግን ፖሊስ መፀዳጃ ቤቱን መቼ ሊሰራ እንደሚችል ገልፆ እንዲፈርም ማድረግ አለበት" ስትል ቀጭን ትዕዛዝ ሰጥታለች። ሃኒፋ ለፖሊስ የፃፈችው ደብዳቤ አባቷ ኢህሳኑላህ መፀዳጃ ቤቱን መገንባት የጀመሩ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ ስራ ስለሌላቸው ለመጨረስ በቂ ገንዘብ እንደሌላቸው ለቢቢሲ ገልፀዋል። "ሃኒፋን ጊዜ እንድትሰጠኝ ጠይቄያታለሁ፤ ነገር ግን ቃሌን ልጠብቅ ባለመቻሌ ልታነጋግረኝ ፈቃደኛ አይደለችም" ብለዋል። እርሷም በበኩሏ "እስከ መቼ መወትወት አለብኝ፤ ገንዘብ ሳይኖረው ፤ሁል ጊዜም ተማሳሳይ ነገር ነው የሚነግረኝ" ስትል ትሞግታለች። በዚህም ምክንያት ወደ ፖሊስ ለመሄድ እንደተገደደች ታስረዳለች። ከዚያም ባለፈው ሰኞ ከእናቷ ማሃሪን ጋር በመሆን ከትምህርት ቤቷ አቅራቢያ ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ አመሩ። "በቦርሳዋ የያዘቻቸውን ደብዳቤና የትምህርት የምስክር ወረቀቷን ጠረጴዛ ላይ አስተካክላ አስቀመጠች፤ ከዚያም 'መፀዳጃ ቤት ልትሰጠኝ ትችላልህ?'" ስትል ጠየቀችኝ ይላል የፖሊስ ኃላፊው ቫላርማቲ። ጥያቄዋን ያዳመጡት ፖሊሶች ለአባቷ ጥሪ ያቀርባሉ። "ሲነገረኝ በልጄና በባለቤቴ ላይ አንዳች አደጋ የደረሰባቸው ነበር የመሰልኝ'' ይላል የሃኒፋ አባት። ምንም እንኳን ጉዳዩ በዚህ መልክ ወደ እርሱ ይመጣል ብሎ ባይገምትም ለመስሪያ ቤቶችና ለህግ አካላት እየከፈላ ሌላ ሰው ደብዳቤ የሚያፅፈው አባት ልጁ ለፖሊስ በፃፈችው ደብዳቤ መደነቁ አልቀረም ታዲያ። በሃኒፋ ሐቀኛ ጥያቄ ልባቸው የተነካው የፖሊስ አባላትም ችላ ሳይሉ ችግሩን ለመፍታት ጥረት አድርገዋል። የእርሷ ጥያቄ የአካባቢው ባለስልጣናት ሃኒፋ በምትገኝበት አካባቢ ከ 500 በላይ መፀዳጃ ቤት ለመገንባት ገንዘብ ለማሰባሰብ አቅደዋል። በመሆኑም በትምህርት ቤት ልጆች ወላጆቻቸው በመኖሪያ ቤት መፀዳጃ ቤት እንዲገነቡላቸው እንዲጠይቁ ትምህርት ለመስጠት እንዳሰቡ ኮሚሽነር ኤስ ፓርታሳራቲይ አስረድተዋል። • 100 ሴቶች፡ የነጻነት ቅርጫት ፕሮጀክት • የሃምዛ ሃሚድ ገመድ አልባ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መንግስትም በመጭው ዓመት እያንዳንዱ ቤተሰብ መፀዳጃ ቤት እንዲኖራቸው ያቀደ ቢሆንም እቅዱ ግን ችግር አላጣውም። በቅርብ የተጠና ጥናት እንደሚያሳየው በገጠራማዋ ህንድ 89 በመቶ የሚሆኑት ህንዳውያን መፀዳጃ ቤትን ማፅዳት እንዲሁም በቅርባቸው እንዲገኝ አይፈልጉም። ሃኒፋ ግን በጥያቄዋ ምክንያት ከአባቷ ጋር ለተከታታይ 10 ቀናት ተኮራርፈው ቢቆዩም ፖሊስ መካከላቸው ገብቶ እርቅ አውርዶላቸው በደስታ መተቃቀፍ ችለዋል።
news-46015199
https://www.bbc.com/amharic/news-46015199
የማንነት ጥያቄዎች የጎሉበት የአማራ ክልል ከተሞች ሰልፍ
በባለፈው ሳምንት መጨረሻ በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች ሰልፎች የተደረጉ ሲሆን በሰልፎቹ ላይ "የወልቃይት እና የራያ የማንነት ጥያቄዎች ሊመለሱ ይገባል፤ ለጣናና ለላልይበላ አፋጣኝ ትኩረት ይሰጥ" የሚሉ መፈክሮችም በከፍተኛ ሁኔታ የታዩበት ነው።
ሰልፎቹ በባህርዳር፣ በደሴ፣ በደብረ ብርሃን፣ ጎንደር፣ ደብረ ታቦር ፣ ወልድያ፣ ሰቆጣ፣ ላልይበላ ተካሂደዋል። ሰልፎቹ በሰላም እንደተጠናቀቁ የተዘገበ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪም በሰሞኑ አላማጣ ከተማ የማንነት ጥያቄን ባነሱና የፀጥታ ኃይሎችጋር በተፈጠረ ግጭት አምስት ሰዎች መሞታቸውንም በማስመልከት፤ መብታቸውን ስለጠየቁ በዜጎች ላይ ጥቃት ሊደርስባቸውም አይገባም የሚሉም መልዕክቶች ተላልፈዋል። ሰልፈኞቹ በማንነት ጥያቄ ምክንያት የሚደርሱ ግፎች እና በደሎች ሊቆሙ ይገባል በሚልም መንግሥት መፍትሔ እንዲሰጥ ጠይቀዋል። •ያልታበሰው የላሊበላ እንባ •ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፡ በሚያውቋቸው ሰዎች አንደበት •አዲሷ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ማን ናቸው? ሰላማዊ ሰልፉ የአማራ ክልል የዞን ከተሞች ችግሮቻቸውን በሰላማዊ መንገድ የገለፁበት እንደሆነም የሰልፉ አስተባባሪዎችን በመጥቀስ የአማራ ክልል መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። በተለያዩ የክልሉ ከተሞች ላይ ጎልቶ ያታየው የማንነት ጥያቄ ተገቢው ምላሽ እንዲሰጠው የሚጠይቅ ሲሆን በተጨማሪም ለአደጋ ተጋልጠዋል ስለተባሉት የክልሉ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ሃብቶች ስለሆኑት ላልይበላና ጣና ሃይቅን ለመታደግ መንግሥት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል። በደብረ ብርሃን በነበረው ሰልፍ ላይ አስተባባሪው ለህዝቡ ባስተላለፉት መልዕክት "አማራ በአማራነቱ የሚሸማቀቅበት ምንም ሁኔታ ሊኖር አይገባም፤ የሰሜን ሸዋ እና የአካባቢው ነዋሪዎች ከወልቃይት እና ከራያ ህዝብ ጎን መሆናችን ለመግለፅ እወዳለሁ" በማለት አቶ አማረ መልዕክት እንዳስተላለፉ የአማራ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። በክልሉ መዲና ባህርዳር ላይ በነበረው ሰልፍ የተለያዩ ጥያቄዎችን የተንፀባረቁ ሲሆን ለጣና ሐይቅና ለላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት የፌዴራል መንግሥትን ትኩረት እንዲሰጥ፣ የማንነት ጥየቄዎች በአፋጣኝ ምላሽ እንዲያገኙ፣ በተለያዩ አካባቢዎች በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች እንዲቆሙ፣ ሕገ መንግሥቱ ላይ መሻሻል እንዲደረግና፣ በአማራ ብሔርተኝነት ላይ የሚደረገው የጥላቻ ዘመቻ አንዲቆምና የክልሉ ገዢ ፓርቲ አዴፓ ከአማራ ሕዝብ ጎን እንዲቆም የሚጠይቁ ናቸው። የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አማረ ዓለሙ‹‹ያስተላለፋችሁትን መልዕክት ለሚመለከተው አካል ማድረስ ብቻ ሳይሆን ለተፈፃሚነቱ ከጎናችሁ ሆነን እንደምንሠራ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ›› እንዳሉ የክልሉ መገኛኛ ብዙሃን ተዘግቧል። በተያያዘም የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በትናንትናው ዕለት ወደ አማራ ክልል ተጉዘው የሰልፈኞቹ ዋነኛ ትኩረት ከሆኑት መካከል በአደገኛ ወራሪ አረም አደጋ ላይ የወደቀውን የጣና ሃይቅንና አፋጣኝ ጥገና የሚፈልጉትን የላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ጎብኝተው መንግሥት አስፈላጊውን ነገር እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል።
52873325
https://www.bbc.com/amharic/52873325
ሩሲያና ቱርክ የሚፎካከሩባት ሊቢያ
ሊቢያ አንድ ምዕራፍ አጠናቅቃ ወደ ሌላ እየተሸገገረች ይመስላል። ነገር ግን ቀጣዩ ምዕራፍም ለአገሪቱ መጻዒ እድል መልካም ነገር ይዞ ይመጣል ብሎ አፍን ሞልቶ መናገር አይቻልም።
ሊቢያ የቀድሞ መሪዋ ሞአመድ ጋዳፊ ከስልጣን ከተወገዱና ከተገደሉ ወዲህ በእርስ በእርስ ጦርነትና በውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት ምስቅልቅሏ ወጥቷል። ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ጄነራል ካሊፍ ኻፍታር፣ በምሥራቅ ሊቢያ ጠንካራውን ጦር የሚመሩት ግለሰብ፣ በአገሪቱ ምዕራባዊ ክፍል የምትገኘውንና ዋናዋ መዲናን ትሪፖሊን ለመቆጣጠር እልህ አስጨራሽ ጦርነት አካሂደዋል። በተባበሩት መንግሥታት እውቅና ያለውን የትሪፖሊውን መንግሥት በመደገፍ ቱርክ ጦሯን ያዘመተች ሲሆን ጄነራል ኻፍታርም ቢሆኑ ደጋፊ አላጡም። ከሩሲያ የመጡ እና በሺህዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች ከጎናቸው ናቸው። ነገር ግን ይህ የሁለት ወገኖች ድጋፍ ለሊቢያውያን ሁሌም የሚሹትን ሰላም አምጥቶላቸዋል ማለት አይደለም። እንደውም ሊቢያን በቅርበት የሚመለከቱ አሁንም ኪሳራውን የሚሸከሙት ሊቢያውያን ናቸው ሲሉ ይናገራሉ። ሊቢያውያን አገራቸው በተፈጥሮ ጋዝና በነዳጅ ሃብት የበለፀገች ብትሆንም የሚያስቡትን ሰላም፣ ደህንንት፣ ትምህርት፣ የጤና አገልግሎት፣ እንዲሁም የተረጋጋ ህይወት ሊያመጣላቸው አልቻለም። ቤታቸው በጦርነቱ ምክንያት ያልወደመባቸው ሊቢያውያን ራሳችን ከኮሮናቫይረስ ለመከላከል ብቻ ሳይሆን ከተባራሪ ጥይትም ለመከላከል በሚል ቤታቸውን ቆልፈው ተቀምጠዋል። የእርስ በእርስ ጦርነቱ በርካታ ጤና ጣቢያዎችንና ሆስፒታሎችን አውድሟል። በምዕራብ ሊቢያ ወደ 200 ሺህ ሊቢያውያን ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን የሂውመን ራይትስ ዎች ሪፖርት ያሳያል። የውጪ ኃይሎችና ሊቢያ ጄነራል ኻፍታር ወደፊት የመጡት እአአ በ2014 ነበር። በወቅቱ ሊቢያ በርስ በርስ ጦርነት ትታመስ ነበር። የሊቢያ ሁለተኛዋ ትልቋ ከተማ ከሆነችው ቤንጋዚ አክራሪ እስላማዊ ቡድኖችን ካስወገዱ በኋላ ጄነራሉ ስማቸው ጎልቶ መጠራት ጀመረ። ጄነራል ኻፍታር በሊቢያ ስማቸው በሚገባ የሚታወቅ የጦር መኮንን ናቸው። ጄነራሉ ጋዳፊ ስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት አሜሪካ ተቀምጠው፣ የሲአይኤ መቀመጫ በሆነችው ከተማ፣ የጋዳፊን ውድቀት ሲያሴሩ ነበር። የአሁኗ ሊቢያ ራሷን በሁለት መንግሥታት መካከል አግኝታዋለች። ጄነራል ኻፍታር መቀመጫቸውን በአገሪቱ ምሥራቃዊ ክፍል ከምትገኘው ቤንጋዚ አድርገው አገሪቱን አንድ ለማድረግ ወደ ምዕራብ በመገስገስ ትሪፖሊ ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት ሰንዝረዋል። አላማቸው የዓለም አቀፍ መንግሥታት እውቅና ያለውን እና በፋዬዝ አል ሳራጅ የሚመራውን መንግሥት መጣል ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ፋዬዝ አል ሳራጅን የሚደግፉት መንግሥታት ቱርክ፣ ኳታርና ጣልያን ሲሆኑ ጄነራል ካሊፍ ኻፍታርን የሚደግፉት ደግሞ የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ፣ ዮርዳኖስ፣ ግብጽ፣ ሩሲያ፣ ፈረንሳይ ናቸው። በርስ በርስ ጦርነት ወቅት የውጭ አገራት እጃቸውን እንደሚያስገቡ እሙን ነው። ሊቢያ ደግሞ የየትኛውም አገር አይን ሊያርፍባት የምትችል አገር ናት። በአፍሪካ ትልቁ የሆነው የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት የሚገኝበት በመሆኗ የአገራት ልብ መቋመጡ አይቀርም። ከሰባት ሚሊዮን በታች የሕዝብ ብዛት ያላት ሊቢያ ከአወሮፓ በቅርብ ርቀት ላይ መገኘቷ ሌላው የበርካቶችን ልብ የሚያማልል ነው። ሊቢያ በቀጥታ ነዳጇን በሜዲትራያኒያን ላይ አቋርጣ ለአውሮፓ ገበያ ስታቀርብ በተቃራኒው የባሕረ ሰላጤው አገራት ደግሞ እጅግ አደገኛ በሆነ የባህር መስመር ላይ ምርታቸውን በማጓጓዝ ይሸጣሉ። ጄነራል ኻፍታር ሁነኛ ወዳጆች ሩሲያ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ እና ግብጽ ናቸው። • በምዕራብ ወለጋ የአራት ልጆች እናት የሆኑትን ግለሰብ ማን ገደላቸው? ለትሪፖሊው መንግሥት ደግሞ ቱርክ ጠንካራ አጋር ናት። አሜሪካ በዶናልድ ትራምፕ የሥልጣን ዘመን ጠቅላይ ሚኒስትር ሳራጅንም ሆነ ጄነራል ኻፍታርን የሚደግፉ ምልክቶች ልካለች። ነገር ግን ይህ ምልክት የእስላማዊ አክራሪ አማፂያንን በቦንብ ከመደብደብ ያለፈ ድጋፍ አላሳየም። አሁን ትልቁ ስጋት የሩሲያው ፕሬዝዳንት ፑቲን በሊቢያ እግራቸው ስር ሰዶ ልክ እንደ ሶሪያ ያለ ሁኔታ ይፈጠራል የሚል ነው። በሊቢያ አሁን እየተካሄደ ያለው ጦርነት ከሶሪያ ጋር የሚያመሳስለው ነገር እየተፈጠረ ነው። የእርስ በእርሱ ጦርነት መደምደሚያ ያለው በውጪ ኃይሎች እጅ ይመስላል። በሊቢያ በእጅ አዙር የሚደረገው ጦርነት የሶሪያ ቅጣይ ነው የሚሉ ወገኖች እንደማስረጃነት የሚያቀርቡት ሁለቱም ወገኖች ወታደሮቻቸውን ሶሪያ በመላክ ልምድ ለማግኘት መሞከራቸውን በማንሳት ነው። የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋንና የሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን በሶሪያ የተገበሩትን በሊቢያ አስልተው መምጣታቸው ግልጽ ነው። በሊቢያ የሚዋጉት ሩሲያውያን ዋግነር ግሩፕ ከተሰኘ ተቋም የተገኙ ናቸው፤ ይህ ተቋም ደግሞ ለፕሬዝዳንት ፑቲን ቅርብ በሆነ ሰው የሚመራ መሆኑ ይታወቃል። የዋግነር ተዋጊዎች በሶሪያ ጦርነት ላይ ተሳትፈዋል። ሩሲያውያን የጦር አውሮፕላኖቻቸውን ወደ ሊቢያ ስታሰማራ ቱርክ በበኩሏ ሰው አልባ የጦር አውሮፕላን አዝምታለች።
41911331
https://www.bbc.com/amharic/41911331
ዶናልድ ትራምፕ ሰሜን ኮሪያን "እንዳትሞክሩን" ሲሉ አስጠነቀቁ
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ለደቡብ ኮሪያ ፓርላም ንግግር በሚያደርጉበት ወቅት ለሰሜን ኮሪያን መሪዋ ኪም ጆንግ-ኡን ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክት አስተላልፈዋል።
"እንዳትንቁን። እንዳትሞክሩን" ሲሉም ተስምተዋል። በሰሜን ኮሪያ ያለውን ሁኔታም "የጨለማ ሕይወት" ሲሉ ወርፈዋል። ለኪም ጆንግ-ኡን ቀጥተኛ የሆነ መልዕክት ሲያስተላልፉም "የታጠቅከው መሣሪያ ደህንነትህን አያስጠብቅልህም። ይልቁንስ አመራርህን ወደ መቀመቅ ይከተዋል" ብለዋል ትራምፕ። ትራምፕ የአህጉረ እስያ ጉበኝት አካል በሆነችው ደቡብ ኮሪያ ለሁለት ቀናት ይቆያሉ። ከኮሪያ ጦርነት በኋላ ደቡብ ኮሪያ ከሰሜን ኮሪያ በተለየ ብዙ እድገቶችና ለውጦች አምጥታለች ሲሉም አጋራቸው ደቡብ ኮሪያን አንቆለጳጵሰዋል። "ሰሜን ኮሪያ በወታደራዊ አገዛዝ ውስጥ ያለች ነች፤ ሕዝቦችዋም ባርነት ውስጥ ያሉ ናቸው" ሲሉ የኪምን ሃገር ወቅሰዋል። ፒዮንግያንግ የአሜሪካንን ዝምታ እንደ ድክመት አይታው ከሆነ ተሳስታለች ያሉት ትራምፕ፤ አሁን ላይ ያለው የአሜሪካ አመራር ለየት ያለ እንደሆነና ኪም የኒውክሊዬር ጦር መሣሪያቸው ላይ መተማመናቸውን እንዲያቆሙ አሳስበዋል። "ሰሜን ኮሪያ አያቶችህ ያለሙትን ዓይነት ገነት አይደለችም። ይልቁንስ ማንም ሊኖርበት የማይገባ ገሃነም ቦታ ነው" በማለት ሰሜን ኮሪያን የመሰረቱትን የኪምን አያት ኪም ሱንግን ወቅሰዋል። የተቀረው ዓለም በተለይ ደግሞ ቻይና እና ሩስያ ፒዮንግያንግ ላይ ጫና ሊያሳድሩ እንደሚገባ ሳይጠቅሱም አላለፉም። ''ዓለምን በኒውክሊዬር መሣሪያ ሊያጠፋ የሚዝትን ሰው ማንም አይታገስም። ኃላፊነት ያለበት ሁሉ ለሰሜን ኮሪያ ድጋፍ ሆነ እርዳታ በመንፈግ የኪምን አመራር ገሸሽ ሊያደርግ ይገባል" ሲሉ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። ትራምፕ በሰሜን ደቡብ ኮሪያ ድንበር መካከል በሚገኝ ከጦርነት ነፃ ወደሆነ ቀጠና ሊያደርጉት የነበረው ጉብኝት በከባድ የአየር ሁኔታ ምክንያት ሊቀር ችሏል። የሰሜን ኮሪያ ጉዳይ በትራምፕ የእስያ ጉብኝት አጀንዳ ላይ ቁጥር አንድ ሆኖ ይገኛል። ትራምፕ ጉብኝታቸውን በጃፓን የጀመሩ ሲሆን ከደቡብ ኮሪያ በኋላ ቻይናን ለጥቆም ቪየትናምንና ፊሊፒንስን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል።
48508693
https://www.bbc.com/amharic/48508693
ፈረንሳይ፡ ስደተኞችን ወደ እንግሊዝ እንዲያቋርጡ የረዳው ኢማም ዘብጥያ ወረደ
የፈረንሳይ ፍርድ ቤት ስደተኞች በአየር በተሞላ ጀልባ ወደ እንግሊዝ እንዲያቋርጡ ረድቷል ያለውን ኢማም በሁለት አመት እስር ቀጣ።
የ39 አመቱ ኢራናዊ በርካታ ስደተኞች ከሰሜናዊ ፈረንሳይ ወደ እንግሊዝ እንዲያቋርጡ አመቻችቷል በሚል ክስ ቀርቦበት ነበር። ኢማሙ በሚሰብክበት መስጂድ የሚካፈል የ29 አመቱ ሴኔጋላዊ በምስክርነት ቀርቧል። ኢማሙ ዘጠኝ ወር ዘብጥያ ወርዶ ካሳለፈ በኋላ ለሶስት አመት ደግሞ ኖርድ እና ፓስ ዴ ካሊስን እንዳይጎበኝ እግድ ተጥሎበታል። በፈረንሳይ መገናኛ ብዙኀን ማንነቱ ያልተገለፀው ኢማም የፍርድ ውሳኔውን ሲሰማ ራሱን ስቶ ወድቋል። • ''ወደ ኢትዮጵያ የምናደርገውን ጉዞ አንሰርዝም'' • በተቃውሞ እየተናጠች ባለችው ሱዳን ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ ቀረበ • ጄይ-ዚ የመጀመሪያው ራፐር ቢሊየነር ሆነ ኢማሙ ስድስት ወይም ሰባት በአየር የሚሞሉ ጀልባዎችን መስጠቱን ማመኑ ተዘግቧል። ምርመራው የተጀመረው ባለፈው መጋቢት ወር በሰሜናዊ ፈረንሳይ ባህር ዳርቻ የሕይወት አድን ጃኬት፣ ጀልባና መቅዘፊያ ከተገኘ በኋላ ነው። እንደ አቃቤ ሕግ መረጃ ከሆነ ኢማሙ ከተደራጁ የሕገወጥ ሰዎች አዘዋዋሪዎች ጋር ግንኙነት ያለው ሲሆን ለሚያቀርበው እያንዳንዱ ጀልባም ኮሚሽን ይቀበል ነበር ተብሏል። ፖሊስ ሁለት ጀልባዎችን እና ተያያዥ ቁሳቁሶችን በኢማሙ መኖሪያ ያገኘ ሲሆን ሁለት ሰዎች ከእርሱ ጀልባ መግዛታቸውን የእምነት ቃላቸውን ሰትተዋል ተብሏል። ኢማሙም በቤልጂየም ድንበር የሚገኝ አንድ ሱቅ በመሄድ ጀልባውን መግዛቱን ተናግሯል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከፈረንሳይ ወደ እንግሊዝ በአነስተኛ ጀልባ የሚያቋርጡ ስደተኞች እየተበራከቱ መጥተዋል።
53823765
https://www.bbc.com/amharic/53823765
አዲስ አበባ፡ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ሆነው ተመረጡ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የኢፌድሪ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የነበሩትን ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።
ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ወ/ሮ አዳነች የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል ስላልሆኑ ነው ምክትል ከንቲባ በመሆን የከንቲባ ኃላፊነትን የሚወጡት። ወ/ሮ አዳነች፤ ከ85 የምክር ቤት አባላት በ77 ድጋፍ በ6 ተቃውሞ እና በ2 ድምጸ ተዐቅቦ ሹመታቸው በአዲስ አበባ ምክር ቤት ጸድቋል። የቀድሞ ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ የማዕድን እና ኢነርጂ ሚንስትር ሆነው መሾማቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በዛሬው ዕለት አዳዲስ ሹመቶችን መስጠታቸው ይታወሳል። ከሰሞኑ ከኦሮሚያ የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ አባልነታቸው የታገዱት አቶ ለማ መገርሳ ከመከላከያ ሚነስትርነታቸው ተነስተዋል። በአቶ ለማ ምትክ ቀንዓ ያደታ (ዶ/ር) የመከላከያ ሚንስትር ሆነው መሾማቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ፌስቡክ ገፅ ከሰፈረው መረጃ መረዳት ተችሏል። ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ወደ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ካቢኔ የመጡት የገቢዎች ሚኒስትር መሆን ነበር። ከዚያም የሃገሪቱ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በመሆን አገልግለዋል። ወ/ሮ አዳነች ወደ ሚኒስትርነት ቦታ ከመምጣታቸው በፊት የአዳማ ከንቲባ እንዲሁም የኦዴፓ ማዕከላዊ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል።
41719254
https://www.bbc.com/amharic/41719254
አቤ ሰሜን ኮሪያን እመክታለሁ አሉ
የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ እሁድ በተደረገው ምርጫ እንደሚያሸንፉ ካረጋገጡ በኋላ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ባለው ፍጥጫ ዙሪያ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስዱ ገልፀዋል።
የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ጠቅላይ ሚኒስትር አቤ ከጊዜው ቀደም ብለው ምርጫ እንዲካሄድ የጠሩት ከሰሜን ኮሪያ በኩል ያለውን ስጋትና ሌሎች ጃፓንን የገጠሟትን ችግሮች ለማስወገድ ድጋፍ ለማግኘት ነው። የጃፓን መገናኛ ብዙሃን እነደዘገቡት በጠቅላይ ሚኒስትር አቤ የሚመራው ጥምረት በፓርላማው የነበረውን የሁለት ሦስተኛ የበላይነት ማስጠበቅ ችሏል። ይህም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጃፓን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ያፀደቀችውን በየትኛውም ፍጥጫ ውስጥ እንዳትገባ የሚከለክለውን ሕገ-መንግሥት ለማሻሻል በሩን ይከፍትላቸዋል። ቀደም ሲል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጃፓን መከላከያ ኃይል መደበኛ ትኩረት እንዲያገኝ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፤ ይህም የጦር ሠራዊቱ እንዲጠናከር የሚያደርግ በመሆኑ ወታደራዊ ግንባታን መልሶ ያመጣል በሚል ትችት ተሰንዝሮባቸዋል። ከምርጫው በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደተናገሩት ''ቃል በገባሁት መሰረት ቀዳሚው ሥራዬ የሚሆነው ሰሜን ኮሪያን ጠንከር ባለ ሁኔታ መጋፈጥ ነው። ለዚህም ጠንካራ ዲፕሎማሲ ያስፈልጋል'' ብለዋል። ከሁለት ወራት በፊት ፖለቲካዊ ቀውስ ገጥሟቸው የነበሩት ሺንዞ አቤ፤ ሰሜን ኮሪያ በጃፓኗ ደሴት ሆካይዶ ላይ ያለፉ የሚሳኤል ሙከራዎችን ካደረገች በኋላ ከፖለቲካዊ ቀውሱ ለማንሰራራት ችለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ምርጫ ማሸነፋቸው ፓርቲያቸው በቀጣይ በሚያደርገው የመሪ ምርጫ ላይ ለሦስተኛ ጊዜ የመመረጥ እድላቸውን ከፍ ያደርግላቸዋል ተብሏል። ይህ ከሆነም ሺንዞ አቤ ለረዥም ጊዜ ጃፓንን የመሩ ጠቅላይ ሚኒስትር የመሆን እድልን ያገኛሉ።
news-50514286
https://www.bbc.com/amharic/news-50514286
ያልተፈላ ወተት ለጤና ጠቃሚ ነው ጎጂ?
ያልተፈላ ወተት ወይም በሳይንሱ 'ፓስቸራይዝ' ያልተደረገ ወተት መጠጣት የሰውነታችን በሽታ የመከላከል አቅምን ከመጨመር ባለፈ የተለያዩ አለርጂዎችን መከላከልና ሥርዓተ ልመትን (የምግብ በሰውነታችን ውስጥ መዋሃድን) የማፋጠን ጥቅም እንዳለው ይነገራል።
ነገር ግን ወተትን ማፍላት አስፈላጊ የሆነበት የራሱ ምክንያት አለው። በጥሬ ወተት ውስጥ ያሉትን ባክቴሪያዎች ለመግደልና ወተቱ ሳይበላሽ ረዘም ላለ ጊዜ እንዲቆይ ለማድረግ ነው። • ባለጊዜው የግመል ወተት እንግሊዝ፣ ዌልስ፣ ስኮትላንድ እና ሰሜን አየርላንድ ውስጥ ፓስቸራይዝ ያልተደረገ ወተት በሱፐርማርኬቶችም ሆነ በትንንሽ ሱቆች ውስጥ በህግ የተከለከለ ነው። ለመሆኑ ጥሬ ወተት በጣም ወሳኝ ምግብ ነው ወይስ ለጤና ጎጂ ነው? ብዙዎቻችን ወተት የምንጠጣው በውስጡ ብዙ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን ስለያዘ ነው። ነገር ግን በወተት ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ቫይታሚኖች ሙቀትን መቋቋም የማይችሉ ናቸው። ይህ ማለት ደግሞ እሳት ሲነካቸው ለሰውነታችን ሊያበረክቱ የሚችሉት ጥቅማቸው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ይጠፋል ማለት ነው። ካናዳ ውስጥ በተሰራ አንድ ጥናት መሰረት ወተትን ስናፈላው ጥቅሙን የማጣቱ እድል ዝቅተኛ ነው። ነገር ግን ቫይታሚን ቢ2 የሚባለው ንጥረ ነገር በሙቀቱ ምክንያት ሊጠፋ ይችላል። • ጨቅላ ልጅዎትን ከአቅም በላይ እየመገቡ ይሆን? አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ያልተፈላ ወተትን መጠጣት የሚመርጡት ለሰውነታችን ጠቃሚ የሆኑ ባክቴሪያዎችን በውስጡ ይዟል ብለው ስለሚያምኑ ነው። ማፍላት በባህሪው ጠቃሚውንም ጎጂውንም ባክቴሪያ ይገድላል። ነገር ግን ትኩስ ከላም በታለበ ወተት ውስጥ የጠቃሚ ባክቴሪያዎች ቁጥር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። እንዲያውም ወተት ሳይፈላ ለቀናት ሲቆይና እርጎን ወይም አይብን ወደመሳሰሉ የምግብ አይነቶች ሲቀየር በውስጡ በጣም ብዙ ጠቃሚ ባክቴሪያዎችን ይይዛል። አለርጂዎችን ከመከላከልና በሽታ የመከላከል አቅምን ከመጨመር አንጻር ያልተፈላ ወተት ብዙ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ቢገለጽም አመርቂ የሆነ ውጤት ግን እስካሁን አልተገኘም። በግብርና ሥራ በሚተዳደሩ ቤተሰቦች ላይ በተሰራ አንድ ጥናት ላይ የቤተሰቡ አባላት ያለባቸው የአለርጂ መጠን ዝቅ ያለና በሽታን የመከላከል አቅማቸው ደግሞ ከፍተኛ እንደሆነ ተጠቁሟል። ነገር ግን ይህ የሆነው ያልተፈላ ወተት ስለጠጡ ይሁን አይሁን እርግጠኛ መረጃ ማግኘት አልተቻለም። • ሥራ ቦታ ጋደም ማለት መፈቀድ አለበት? የእንግሊዙ የምግብ ደረጃዎች አውጪ ባለስልጣን ደግሞ ያልተፈላ ወተት በውስጡ የሚይዛቸው ጎጂ ባክቴሪያዎች የምግብ መመረዝን ሊያስከትሉ ይችላሉ ይላል። አክሎም በሽታን የመካከል አቅማቸው ዝቅተኛ የሆኑ ነፍሰ ጡር ሴቶች፣ ህጻናትና በእድሜ የገፉ ሰዎች ያልተፈላ ወተትን ለመቅመስ እንኳን ማሰብ የለባቸውም ብሏል። ያልተፈላ ወተት ሳልሞኔላ፣ ኢኮላይ እና ካምፒሎባክተር የሚባሉ ጎጂ ባክቴሪያዎች በውስጡ ይገኝበታል። በእንግሊዙ ሰሬይ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ማይክሮባዮሎጂ መምህር የሆኑት ዶክተር ዮርግ ጉቴሬዝ እንደሚሉት ያልተፈላ ወተት መጠጣት ለጤና ጎጂ ነው። ባልተፈላ ወተት ውስጥ የሚገኙ ባክቴሪያዎች የአንጀት በሽታ ከማስከተል ባለፈ እስከ ሞት ሊያደርሱ እንደሚችሉም ያስረዳሉ።
news-47239091
https://www.bbc.com/amharic/news-47239091
አፕል ሴቶችን ከመንቀሳቀስ የሚያግድ የሳዑዲ መተግበሪያ ሊመረምር ነው
ሴቶችን በመከታተል ከጉዞ ማገድ የሚያስችል የሳዑዲ አረቢያ መተግበሪያ ላይ ምርመራ ሊያካሂድ መሆኑን አፕል አስታወቀ።
መተግበሪያው ሴቶችን ተከትሎ ከጉዞ ለማገድ ይውላል የአፕል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቲም ኩክ፤ 'አብሽር' ስለተባለው መተግበሪያ የሚያውቁት ነገር እንዳልነበረ ከኤንፒአር ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ አሳውቀዋል። መተግበሪያው ላይ ምርመራ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል። የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች መተግበሪያውን ተቃውመውታል። • ሳዑዲ ለሮቦት ዜግነት ሰጠች • ታሪክ እየቀየሩ ያሉት ሴቶች • ሳዑዲ የፀረ-ሙስና ዘመቻዬን አጠናቀቅኩ አለች የአሜሪካው ሴናተር ሮን ዋይደን፤ አፕልና ጉግል መተግበሪያውን፤ ከመተግበሪያ መደብራቸው (ስቶር) እንዲሰርዙ ጠይቀዋል። ሴቶች ከሳዑዲ አረቢያ ለመውጣት ከአባታቸው፣ ከባለቤታቸው ወይም ሌላ የቅርብ ወንድ (ጋርዲያን) ፍቃድ ማግኘት አለባቸው። አብሽር የተባለው መተግበሪያ፤ የመንጃ ፍቃድ የሚያድስ ክፍልን ጨምሮ በተለያዩ የመንግሥት ተቋሞች ጥቅም ላይ ይውላል። ሴቶች ከሀገር እንዳይወጡ የመከላከል ሂደትን ቀላል የሚያደርግ ሲሆን፤ በስልክ ላይ ተጭኖ ጥቅም ላይ ይውላል። መተግበሪያው በሳዑዲ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ጥቅም ላይ እንዲውል ታስቦ የተሰራ ሲሆን፤ ለበርካታ ዓመታትም አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል። ከአንድ ሚሊዮን ጊዜ በላይም ተጭኗል። • ኢንጅነር አይሻ መሃመድ የሃገር መከላከያ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ • የጀማል ኻሾግጂን ግድያ ለመሸፈን 'ባለሙያዎች ተልከዋል' ወንዶች ሚስቶቻቸውን፣ እህቶቻቸውን ወይም ሴት ልጆቻቸውን በመተግበሪያው መዝግበው ከሀገሪቱ ውጪ ከሚደረግ በረራ ያግዷቸዋል። አንዲት ሴት ከሳዑዲ ለመውጣት ብትሞክር መተግበሪያው ለወንዱ ማሳሰቢያ (ኖቲፊኬሽን) ይልካል። የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች "እንዲህ አይነት መተግበሪያዎች የሴቶችን መብት ይጥሳሉ" ሲሉ ኮንነዋል። ሴናተር ሮን ዋይደን፤ "የሳዑዲ አገዛዝ ሴቶችን መጨቆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው። ሆኖም የአሜሪካ ተቋሞች የሳዑዲን ጭቆና መደገፍ የለባቸውም" ብለዋል። አንዳንድ ሴቶች ወንዶች ስልክ ላይ ያለውን መተግበሪያ አሰራር (ሴቲንግ) በመቀየር መጓጓዝ እንዲችሉ ማድረጋቸው ተጠቁሟል። በጉዳዩ ላይ ቢቢሲ ከጉግል ምላሽ ቢጠይቅም ለማግኘት አልቻለም።
48197205
https://www.bbc.com/amharic/48197205
አዲሷ የኖርዌይ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር "ያሻችሁን ብሉ፣ ጠጡ፣ አጭሱ" ማለታቸው አስወገዛቸው
ኖርዌይ የጤና ጥበቃ ሚንስትር አድርጋ የሾመቻቸው ግለሰብ ዜጎች የፈለጉትን ያህል ይብሉ፣ ይጠጡ፣ ያጭሱ በማለታቸው መነጋገሪያ ሆነዋል።
ሲልቪያ ሊስታውግ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ተደርገው የተሾሙት አርብ እለት ሲሆን፤ አጫሾች መገለል እንዲሰማቸው ሲደረጉ መኖራቸውንም ተናግረዋል። እኚህ ልወደድ ባይ ናቸው የተባሉት የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በፀረ ስደተኛ አቋማቸው ይታወቃሉ። ከዓመት በፊትም ከነበራቸው የመንግሥት ኃላፊነት የወረዱት የሀገሪቱን ደህንነት ስጋት ውስጥ የሚጥል ውሳኔ ደግፈዋል በሚል በቀረበባቸው ተቃውሞ ነበር። • አቶ ጌታቸው አሰፋ ላይ ክስ ተመሰረተ የሚኒስትሯን ሃሳብ የሚያብጠለጥሉ ግለሰቦች፤ ስለ ማህበረሰብ ጤና አንድም እውቀት የላቸውም ሲሉ ይኮንኗቸዋል። ሚኒስትሯ ግን ለሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት ምላሽ ላይ "የማህበረሰብ ጤና እውቀት የላትም ለሚለው ውንጀላ ያለኝ መልስ ቀላል ነው። የሞራል ልዕልናን ለማስጠበቅ የምቆም ፖሊስ ሆኜ ሰዎች ህይወታቸውን እንዴት መኖር እንዳለባቸው ለመንገር አልሞክርም። ነገር ግን ሰዎች መረጃ አግኝተው የራሳቸውን ውሳኔ እንዲወስኑ አደርጋለሁ" ብለዋል። • በሁለት ትውልደ ኢትዮጵያውያን ግድያ የሚፈለገው ለአሜሪካ ተላልፎ ተሰጠ አክለውም "ዜጎች የሚፈልጉትን ያህል እንዲያጨሱ፣ እንዲጠጡ እና ስጋ እንዲበሉ መፈቀድ አለበት፤ ዜጎች የትኛው ጤናማ እንደሆነና እንዳልሆነ ያውቃሉ፤ ባለስልጣናት የሚጠበቅባቸው መረጃ መስጠት ብቻ ይመስለኛል" ብለዋል። ሚኒስትሯ ከዚህ ቀደም አዘውትረው ያጨሱ የነበሩ ሲሆን አሁን ግን አልፎ አልፎ ብቻ እንደሚያጨሱ ይናገራሉ። • ቦይንግ አደጋው ከመድረሱ በፊት ችግሩን አውቅ ነበር አለ "የሚያጨሱ ሰዎች እንዲሸማቀቁ፣ ተደብቀው እንዲያጨሱ ይደረጋል፤ ይህ ረብ የለሽ ነው። ማጨስ ጤና ቢጎዳም ግለሰቦች ይህንን መወሰን ያለባቸው ራሳቸው ናቸው። እንደ መንግሥት ማድረግ ያለብን መረጃ መስጠት ብቻ ነው" ሲሉም አቋማቸውን ግልፅ ያደርጋሉ። ግለሰቧ ከዚህ ቀደም በሽብር ተግባር የተጠረጠሩ ግለሰቦች የኖርዌይ ዜግነታቸውን እንዲነጠቁ የሚፀድቅ ሕግ ሲፀድቅ በመቃወማቸው የተነሳ ከሀገሪቱ ደህንነት ይልቅ "ለአሸባሪዎች መብት" ቆመዋል በሚል ከነበራቸው ኃላፊነት እንዲነሱ መደረጋቸው እታወቃል።
50010680
https://www.bbc.com/amharic/50010680
ኡጋንዳ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያን ላይ የሞት ቅጣት ልትጥል ነው
የኡጋንዳ ስነ-ምግባርና ግብረገብነት ሚኒስትር እ.አ.አ. በ2014 ቀርቶ የነበረውን የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት የሚፈጽሙ ሰዎችን በሞት የሚቀጣውን ህግ በድጋሚ ሊያስተዋውቅ መሆኑን ገለጸ።
ሚኒስትሩ ሲሞን ሎኮዶ ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደተናገሩት አዲሱ ረቂቅ ወደ ህግነት ሲቀየር የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ሲፈፅሙ የተገኙ የሞት ፍርድ ይጠብቃቸዋል። '' አሁን በስራ ላይ ያለው የወንጀለኛ መቅጫ ህጋችን ውስንነት ይታይበታል። ተግባሩ ወንጀል መሆኑን ብቻ ነው የሚገልጸው። በዚህ ተግባር ተሰማርቶ የሚገኝ ማንኛውም ሰው ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኝ ማድረግ እንፈልጋለን። ጥፋተኛ የተባሉትም የሞት ፍርድ ይፈረድባቸዋል።'' ሚኒስትሩ አክለውም ''የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ለኡጋንውዳውያን ተፈጥሯዊ አይደለም። የዚሁ ሃሳብ አቀንቃኞች በትምህርት ቤቶች ጭምር ተፈጥሯዊና ምንም ችግር የሌለው ነው በማለት አባላትን ሲመለምሉ ነበር'' ብለዋል። • ''ወደ ኢትዮጵያ የምናደርገውን ጉዞ አንሰርዝም'' • ታንዛኒያ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎችን አድና ልታስር ነው በ2014 የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ረቂቅ ህጉን ለማጽደቅና ጠበቅ ያለ ቅጣት እንዲኖር ፊርማቸውን ቢያኖሩም በዛው ዓመት የሃገሪቱ ሕገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ውድቅ አድርጎት ነበር። ሲሞን ሎኮዶ እንደገለጹት ረቂቅ ህጉ በመጪዎቹ ሳምንታት ለተወካዮች ምክር የሚቀርብ ሲሆን በአሁኑ ግን የፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ እና የህዝብ ተወካዮችን ድጋፍ አግኝቷል። ለህዝብ ተወካዮች ቀርቦም ሁለት ሶስተኛ ድምጽ አግኝቶ ተግባራዊ እንደሚሆን እንገምታለን ሲሉ ተደምጠዋል ሚኒስትሩ። ከአምስት ዓመት በፊት ሃገሪቱ ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ስትጀምር አሜሪካን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት የቪዛ ክልከላ፣ ድጋፍ ማቆምና ወታደራዊ ልምምድ እስከ ማገድ ደርሰው ነበር። • በዓመቱ አነጋጋሪ ከነበሩ ጉዳዮች ጥቂቱ ሚኒስትሩ ግን ማንኛውም አይነት ምላሽ እንደማያስቆማቸውም ሲገልፁ ''ማንም እንዲያስፈራራን አንፈቅድም። እርምጃው በተለይ በበጀትና አስተዳደር ዙሪያ ያሉ ደጋፊዎቻችንን እንደሚያስቆጣ እናውቃለን። ነገር ግን የእኛ ያልሆነ ባህልን ሊጭኑብን ለሚያስቡ ሰዎች አንገታችንን ደፍተን ማሳየት አንፈልግም'' ብለዋል።
news-52823937
https://www.bbc.com/amharic/news-52823937
ፓኪስታናዊው ህንድ'በሰላይነት' የያዘቻት 'እርግቤን' ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይመልሱልኝ እያለ ነው
ከሰሞኑ ህንድ በሰላይነት የያዘቻት እርግብ እንድትለቀቅ ባለቤት ነኝ ያለው ፓኪስታናዊ የሃገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲን ጠይቋል።
በህንድ አራት ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኝ የድንበር ከተማ ላይ ነዋሪ የሆነው ግለሰብ እርግቧን የለቀቃት የኢድ አልፈጥርን በዓል ለማክበር እንደሆነ አሳውቋል። የህንድ ፖሊስ በበኩሉ እርግቧ በእግሯ ላይ ቀለበት እንዳላትና የተለያዩ ሚስጥራዊ ኮዶችን (የይለፍ ቃል) የያዘች መሆኗን ገልፀው፤ የይለፍ ቃሉ (ኮዱ) ምን እንደሆነም እየመረመሩ እንደሆነ አሳውቀዋል። ግለሰቡ በበኩሉ የይለፍ ቃል የተባለው የስልክ ቁጥር መሆኑን አስታውቋል። የፓኪስታኑ ዳውን ጋዜጣ በበኩሉ የእርግቧ ባለቤት ስሙ ሃቢቡላህ መሆኑንና በርካታ እርግቦችም እንዳሉት ዘግቧል። እርግቦቹ የሰላም ምልክት መሆናቸውንና ህንድ "ይህችን ምንም ያላጠፋች ነፃ እርግብ ጥቃት እንዳታደርስባት" መናገሩን ጋዜጣው ሃቢቡላህን ዋቢ አደርጎ ዘግቧል። እርግቧ የተያዘች ህንድና ፓኪስታን ይገባኛል በሚሏት የካሽሚር ግዛት ሲሆን፤ በህንድ በኩል በምትደዳደረው ግዛትም እርግቧ መግባቷን ተከትሎ የአካባቢው ማህበረሰብ ለፖሊስ አሳልፈው ሰጥተዋታል። ከፓኪስታን የበረረች እርግብ በህንድ ባለስልጣናት 'በሰላይነት' ስትፈረጅ የመጀመሪያዋ አይደለም። በጎርጎሳውያኑ 2015 አንዲት ነጭ እርግብ በሁለቱ ሃገራት ድንበር በኩል ስታንዣብብ በአስራ አራት አመት ታዳጊ ጠቋሚነት ታስራ ነበር። እንዲሁ በጎርጎሳውያኑ 2016ም የህንዱን ጠቅላይ ሚኒስትር ማስፈራሪያ ወረቀት ተገኘባት የተባለች ሌላ እርግብ በቁጥጥር ስር ውላለች። ሁለቱ ሃገራት ለዘመናት ተፋጠው የሚገኙ ሲሆን፤ በጎርጎሳውያኑ 1971ም ከፍተኛ ጦርነት ውስጥ ገብተው ነበር። በተለይም በካሽሚር ግዛት ይገባኛል የተነሳ ሁለቱ ሃገራት ስምምነት ላይ መድረስ አልቻሉም።
news-47972715
https://www.bbc.com/amharic/news-47972715
ባንግላዲሽ፡ ፆታዊ ትንኮሳ ደርሶብኛል በማለቷ ተቃጥላ እንድትሞት የተደረገችው ወጣት
ኑስራት ጃሃን ራፊ በትምህርት ቤቷ ቅጥር ግቢ ውስጥ ነዳጅ ተርከፍክፎባት፤ በእሳት ተቃጥላ እንድትሞት ተደርጋለች። ከሁለት ሳምንታት በፊት የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ፆታዊ ትንኮሳ አድርሶብኛል ስትል ለፖሊስ አሳውቃ ነበር።
ኑስራት ጃሃን የ19 ዓመት ወጣት ነበረች። ባንግላዴሽ ውስጥ ፌኒ በምትሰኝ አነስተኛ ከተማ ውስጥ የእስልምና ትምህርት ቤት ውስጥ ትምህርቷን ስትከታተል ቆይታለች። መጋቢት 18 2011 ዓ.ም የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ኑስራትን ወደ ቢሮው ያስጠራታል። ከዚያም ኑስራት እንደምትለው ርዕሰ መምህሩ ባልተገባ ሁኔታ ይነካካት ጀመረ። ከዚያም ከቢሮው ሮጣ አመለጠች። የባንግላዴሽ ሴቶች ከማህብረሰቡ እና ከቤተሰቦቻቸው የሚደርስባቸውን መገለል እና ሃፍረት በመፍራት የሚፈፀምባቸውን ፆታዊ ትንኮሳዎች አይናገሩም። ኑስራት ግን ርዕሰ መምህሩ የፈፀመባትን መናገር ብቻ ሳይሆን በቤተሰቦቿ እርዳታ ጉዳዩን ፖሊስ ጋር ወሰደችው። ፖሊስ ግን ቃሏን ተቀብሎ ጉዳዩን እያጣራ ከለላ ማድረግ ሲገባው ኑስራትን ማብጠልጠል ጀመረ። በዕለቱ ተረኛ የነበረው ፖሊስ ኑስራት ቃሏን ስትሰጥ ቪዲዮ እየቀረፃት ነበር። ኑስራት ቃሏን እየሰጠች በፖሊሱ መቀረፅ አላስደሰታትም። በተቀረፀው ቪዲዮ በግልፅ እንደሚታየው ኑስራት በእጇ ፊቷን ለመሸፈን ጥረት ታደርግ ነበር። በተንቀሳቃሽ ምስሉም ፖሊሱ የኑስራትን ቅሬታ ''ይህ ትልቅ ጉዳይ'' አይደለም እያለ ሲያጣጥል ይሰማል። ይህ ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት ተሰራጭቷል። ኑስራት ላይ የተፈፀመው አስከፊ ተግባር በርካቶችን አስቆጥቷል። ወደ ፖሊስ ጣቢያው ሄዳ ቃሏን ከሰጠች በኋላ፤ ርዕሰ መምህሩ በቁጥጥር ሥር እንዲውል ተደረገ። ይህ ግን ለኑስራት ችግርት ፈጠረ። በቡድን የተደራጁ ወንዶች ርዕሰ መምህሩ ከእስር እንዲለቀቁ ሰልፍ ማድረግ ጀመሩ። ተቃውሞ ሰልፉን ሲያስተባብሩ ከነበሩት መካከል ኑስራት የምትማርበት ትምህርት ቤት ተማሪ የሆኑ ሁለት ወንዶች ይገኙበታል። የአከባቢው ፖለቲከኞችም የተቃውሞ ሰልፉ ተሳታፊ ሆነዋል። በርካቶች ለርዕሰ መምህሩ መታሰር ኑስራትን ተጠያቂ ማድረግ ጀመሩ። ወላጆቿም የልጃቸው ደህንነት ያሰጋቸው ጀመር። ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ ለፖሊስ ቃሏን ከሰጠች ከ11 ቀናት በኋላ ኑስራት ማጠቃለያ ፈተና ለመፈተን ወደ ትምህርት ቤቷ ሄደች። ''ደህንነቷ ስላሰጋን ትምህርት ቤት ድረስ ይዣት ሄድኩ። ወደ ትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ እንዳልገባ ግን ተከለከልኩ።'' ይላል የኑስራት ወንድም መሃሙዱል ሃሰን ኖማን። "እንዳልገባ ባይከለክሉኝ ኖሮ፤ ይህን መሰል ተግባር በእህቴ ላይ አይፈፅሙም ነበር'' ሲል ጨምሮ ይናገራል። የኑስራት ወንድም መሃሙዱል ሃሰን ኖማን በኑስራት የቀብር ሥነ-ሥርዓት ላይ ሃዘኑን ሲገልጽ። ኑስራት በሰጠችው ቃል መሠረት አንድ የክፍል ጓደኛዋ፣ ጓደኛቸው እየተደበደበች እንደሆነ በመንገር ኑስራትን የትምህርት ቤቱ ሕንፃ ጣሪያ ላይ ይዛት ትወጣለች። ጣሪያው ላይ የጠበቃት ግን ሴት ለመምሰል ዓይነ እርግብ የለበሱ (ዓይናቸው ብቻ የሚያሳይ ሂጃብ) አምስት የሚሆኑ ወንዶች ነበሩ። ከዚያም ኑስራትን በመክበብ በርዕሰ መምህሩ ላይ ያቀረበችውን ክስ እንድታነሳ ያስፈራሯታል። ኑስራት ግን እንደማታደርገው ትናገራለች። ከዚያም ነዳጅ አርከፍክፈውባት እሳት ለኩሰው አቃጠሏት። የመርማሪ ፖሊሶች ኃላፊ ባንድ ኩማር ማጁመደር እንዳሉት ተጠርጣሪዎቹ ''ኑስራት እራሷን ያጠፋች ለማስመሰል አስበው ነበር'' ሃሳባቸው ሳይሳካ የቀረው ተጠርጣሪዎቹ ኑስራት ሕይወቷ ያለፈ መስሏቸው አካባቢውን ጥለው ከሄዱ በኋላ ኑስራት እስተንፋሷ ሳይወጣ ቃሏን በመስጠቷ ነው። ''አንደኛው ተጠርጣሪ የኑስራትን ጭንቅላት በእጆቹ ወጥሮ ከመሬት አጣብቆ ይዞ ስለነበረና ጭነቅላቷ ላይ ነዳጅ ስላላፈሰሱ ከአንገቷ በላይ አልተቃጠለችም። በዚህም ሕይወቷ ሊቆይ ችሏል'' ሲሉ የፖሊስ አዛዡ ለቢቢሲ ቤንጋሊ ቋንቋ አገልግሎት ተናግረዋል። ኑስራት አካባቢው ወደሚገኝ ሆስፒታል ስትወሰድ 80 በመቶ የሚሆነው የሰውነት ክፍሏ ተቃጥሏል። ጉዳቷ ከሆስፒታሉ የማከም አቅም በላይ በመሆኑም ዋና ከተማ ወደሚገኝ ዳካ የሕክምና ኮሌጅ ሆስፒታል ተልካለች። አምቡላንስ ውስጥ ሳለች ሕይወቷ ሊተርፍ እንደማይችል የተረዳችው ኑስራት በወንድሟ ስልክ የቪዲዮ መልዕክት ቀርፃ አሰቀመጠች። በቪዲዮ ላይም ''አስተማሪው ነካክቶኛል። እስትንፋሴ እስኪቋረጥ ድረስ ይህን ወንጀል እፋለማለሁ'' ስትል ትታያለች። ጉዳት ካደረሱባት መካከልም የተወሰኑትን ማንነትም ይፋ አድርጋለች። ሚያዝያ 1 ላይ ሕይወቷ አለፈ። በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በትውልድ ከተማዋ የቀብር ሥነ-ሥርዓቷ ላይ ተገኙ። ፖሊስ እስካሁን 15 ሰዎችን በቁጥጥር ሥር አውሏል። ከእነዚህም መካከል ሰባቱ ከግድያው ጋር በቀጥታ ግንኙነት አላቸው ተብሏል። ተቃውሞ ሰልፍ ሲያስተባብሩ የነበሩ ሁለቱ ወንድ ተማሪዎችም ከታሳሪዎቹ መካከል ይገኙበታል። ለፖሊስ ቃሏን ስትሰጥ ቪዲዮ የቀረፃት ፖሊስ ወደ ሌላ ክፍል ተዛውሯል። የባንግላዴሸ ጠቅላይ ሚንስትር ሼክህ ሃሲና የኑስራትን ቤተሰቦች አግኝተው ያነጋገሩ ሲሆን በወንጀሉ የተሳተፉ ሰዎች በሙሉ ለፍርድ እንደሚቀርቡ ቃል ገብተውላቸዋል። የኑስራታ ቀብር ሥነ-ሥርዓት የኑስራታ ሞት በርካቶችን አበሳጭቷል። በባንግላዴሸም መነጋገሪያ ሆኗል። አንዲት ሴት ''ሴት ልጅ እንዲኖረኝ ሁሌም እመኛለሁ። እዚህ ሃገር ውስጥ ሴት ልጅ መውለድ ማለት ለሕይወቷ ሁሌም መስጋት ማለት ነው'' ስትል በፌስቡክ ገፇ ላይ አስፈራለች። በባንግላዴሽ የሴቶች መብት ላይ ትኩረት አድርገው የሚሠሩ የመብት ተሟጋች ቡድኖች እንደሚሉት እ.አ.አ 2018 ላይ ብቻ 940 የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች ተመዝግበዋል።
45274305
https://www.bbc.com/amharic/45274305
ጎዳና ተዳዳሪዎችን በህክምና መታደግ
መኮንን ገብረመድህን ጅግጅጋ ይኖር ነበር። በጅግጅጋ የተቀሰቀሰው አለመረጋጋት ግን ቤት ንብረቱን ጥሎ ወደ አዲስ አበባ እንዲሸሽ አስገድዶታል። አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ አካባቢ ጎዳና ላይ ከወደቀ ስድስት ቀናት ተቆጥረዋል።
ለጎዳና ተዳዳሪዎች ነጻ ህክምና ተሰጥቷል መኮንን ለሁለት ዓመት ያህል አይኑን ይጋርደው ነበር። ለጎዳና ተዳዳሪዎች ነጻ ህክምና እንደሚሰጥ ሲሰማ እድሉን ለመጠቀም ህክምናው ወደሚሰጥበት ቦታ አቀና። "ስለ ጤና ችግሬ ስነግራቸው ካርድ አወጡልኝና ጳውሎስ፣ ራስ ደስታ ወይም ሚኒሊክ ሄደህ በነጻ መታከም ትችላለህ አሉኝ" ይላል። • ጤና የራቀው የፈለገ ህይወት ሆስፒታል • ትዳር ከባድ የጤና ችግሮችን ለመከላከል ይህ ለመኮንን መልካም ዜና ነው። የጎዳና ተዳዳሪዎችን ህይወት ፈታኝ ከሚያደርጉ እውነታዎች አንዱ የህክምና አገልግሎት ለማግኘት አለመቻላቸው ሲሆን፤ ይህንን ከግምት በማስገባት ነሀሴ 16፣ 2010 ዓ. ም. መስቀል አደባባይ አካባቢ ነጻ የህክምና አገልግሎት ተሰጥቷል። የህክምና አገልግሎት የመስጠት ሀሳቡ ጠንሳሾች 'ዘመን' የተሰኘው የቴሌቭዥን ተከታታይ ድራማ አዘጋጆችና ተዋንያን እንዲሁም የጤና ጥበቃ ሚንስትር ናቸው። የ'ዘመን' ድራማ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ደረጀ አርአያን ያገኘነው የጎዳና ተዳዳሪዎች ህክምናውን እንዲያገኙ ቅስቀሳ በማድረግ ህክምናው ወደሚሰጥበት ቦታ ሲወስድ ነበር። በየአካባቢው የሚገኙ የጎዳና ተዳዳሪዎች ህክምናው ወደሚሰጥበት ቦታ ሄደው የህክምና ካርድ እንዲያገኙ ማሳመን ቀላል እንዳልነበርም ተገልጿል። አዲስ አበባ ውስጥ ለሚኖሩ የጎዳና ተዳዳሪዎች 1000 የህከምና ካርዶች ተዘጋጅተዋል። በካርዱ ነጻ ህክምና ከማግኘታቸው በተጨማሪ መድሀኒትም በነጻ ይሰጣቸዋል። ነሀሴ 16 የነበረው ነጻ የህክምና አገልግሎት ውስጥ ሴተኛ አዳሪዎችም ተካተው ነበር። እስከ እኩለ ለሊት ድረስ በተንቀሳቃሽ መኪና ባሉበት ቦታ ሆነው ህክምና እንዲያገኙ ተደርጓል። በተንቀሳቃሽ አምቡላንሶችም አገልግሎት ተሰጥቷል ደረጀና የተቀሩት የድራማው አዘጋጆችና ተዋንያን በጤናው ዘርፍ በጎ አገልግሎት መስጠት የጀመሩት ሀምሌ 16፣ 2010 ዓ. ም. ነበር። ሰኔ 16 መስቀል አደባባይ የደረሰውን የቦንብ ፍንዳታ ተከትሎ ተጎጂዎችንና ሌሎችም ህሙማንን በመጠየቅ፣ ሆስፒታሎችን በማጽዳት የበኩላቸው አስተዋጽኦ አበርክተዋል። ይህንን ባደረጉበት በወሩ ለጎዳና ተዳዳሪዎች የነጻ ህክምና በመስጠት ተሳትፎ አድርገዋል። "የበጎ ፍቃድ አገልግሎት እንዲለመድ እንፈልጋለን፤ ስለዚህ በየወሩ 16ኛው ቀን ላይ በተለያየ ዘርፍ አገልግሎት እንሰጣለን" ይላል። በሚቀጥለው ወር ከግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለጎዳና ተዳዳሪዎች የሚሆን ገንዘብ የሚሰባሰብበት የእራት መርሀ ግብር ለማዘጋጀት አስበዋል። በቀጣይ ወራት የትራፊክ አደጋን በመቀነስና በሌላም መንገድ እንደሚሳተፉ ተናግሯል። ለጎዳና ተዳዳሪዎቹ ህክምና ስትሰጥ ያገኘናት ዶክተር ማህሌት ብርሀኑ የጳውሎስ ሆስፒታል ሰራተኛ ናት። በመስቀል አደባባይ አስር ሀኪሞችን ጨምሮ፣ ነርሶች፣ የላብራቶሪ ቴክኒሺያኖች መገኘታቸውን ትናገራለች። ተንቀሳቃሽ አንቡላንስም በቦታው ተገኝቷል። የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ ከመስጠት ባሻገር ተጨማሪ ህክምና ለሚያስፈልጋቸው ሪፈር ጽፈዋል። ጳውሎስ፣ ጴጥሮስ፣ ሚኒሊክ፣ አለርትና የካቲት 12 የጎዳና ተዳዳሪዎቹ በነጻ ህክምና ማግኘት ከሚችሉባቸው ሆስፒታሎች መካከል ይጠቀሳሉ። የነጻ ህክምና ካርድ ተሰጥቷቸዋል ዶክተር ማህሌት እንደምትለው፤ የጎዳና ተዳዳሪዎች የጤና እክል ሲገጥማቸው ወደ ህክምና መስጫ ሄደው በነጻ መታከም እንደሚችሉ ግንዛቤ ማስጨበጥ ከግቦቻቸው አንዱ ነው። እሷ ህክምና ከሰጠቻቸው መካከል ለዓመታት ህክምና ያላገኙ ግለሰቦች ይገኙበታል። "መታከም ብዙ ወጪ ይጠይቃል። መድሀኒትም ውድ ነው ብለው በማሰብ ህመማቸውን ችለው የሚኖሩ ብዙ ናቸው። የነጻ ህክምና ካርድ ካላቸው ግን በማንኛውም ሰአት መታከም ይችላሉ" ትላለች። "የዋስትና ካርድ" ብላ የምትጠራውን የነጻ ህክምና ካርድ የያዙ የጎዳና ተዳዳሪዎች ድንገተኛ አደጋ ሲገጥማቸውም በቀላሉ ህክምና ማግኘት ይችላሉ።
news-53907912
https://www.bbc.com/amharic/news-53907912
ኮሮናቫይረስ፡ መማሪያ ክፍሎችን ወደ ዶሮ ማርቢያነት የለወጠው ኮሮናቫይረስ
በኬንያ ለወራት የተዘጉት ትምህርት ቤቶች ለሌላ አገልግሎት እየዋሉ ነው።
በቀድሞው የትምህርት ክፍል ውስጥ ዶሮ ማርባት የጀመረው ጆሴፍ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ትምህርት ቤቶች ከተዘጉ ወራቶች ተቆጥረዋል። በአንዳንድ አገራት ትምህርት ቤቶች እየተከፈቱ ቢሆንም ፤ ቀድመው የከፈቱት ደግሞ የቫይረሱ ሥርጭት በመስፋፋቱ እንደገና እየዘጉ ነው። ወረርሽኙ ግራ አጋቢ ሆኗል። በኬንያም ትምህርት ቤቶች እስከ መጭው ጥር ወር ድረስ አይከፈቱም ተብሏል። ይህም በርካታ የግል ትምህርት ቤቶችን ህልውና ፈታኝ አድርጎታል። ይህንን ተከትሎም አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ወደ ሌላ ተግባር ተለውጠዋል። በኬንያ ካሉ የግል ትምህርት ቤቶች አንዱ የሆነው ምዌ ብሬትረን፤ መማሪያ ክፍሎች ውስጥ ይሰማ የነበረው የተማሪዎች የቀለም ዜማ በዶሮ ጫጩቶች ጩኸት ተሞልቷል። በጥቁር ሰሌዳው ላይ ይፃፉ የነበሩ የሒሳብ ስሌቶችም፤ አሁን የበሽታው ክትባት መቼ ሊገኝ ይችላል በሚል መርሃ ግብር ተተክተዋል። የማዕከላዊ ኬንያ ትምህርት ቤት ባለቤት ጆሴፍ ሜና፤ በወረርሽኙ ሳቢያ ትምህርት ቤቱ በመዘጋቱና የተወሰነ ገንዘብ ለማግኘት ሲል ወደ ዶሮ እርባታ ፊቱን አዙሯል። መጋቢት ወር ላይ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ሲነገር፤ ውሳኔው የባንክ ብድር ለሚከፍለው ጆሴፍ ዱብዳ ነበር የሆነበት። መጀመሪያ ላይ በሁኔታው ሰማይ ምድሩ የተገለባበጠ ያህል ቢሰማውም በኋላ ላይ ኑሯቸውን የሚደጉም አንድ ነገር መሥራት እንዳለባቸው መወሰናቸውን ጆሴፍ ይናገራል። የግል ትምህርት ቤቶች እንደመሆናቸው ገቢያቸው በተማሪዎች ክፍያ ላይ የተመሰረተ ነው፤ በመሆኑም ትምህርት በመዘጋቱ ለሰራተኞቻቸው መክፈል እንዳይችሉ ሆነዋል። የተማሪዎች የመጫወቻ ሜዳ የተለያዩ አትክልቶች እየተተከሉበት ነው በዚህም በርካታ መምህራን ከፍተኛ የገንዘብ ችግር ገጥሟቸዋል። በማዕከላዊ ኬንያ የሚገኘው ሌላኛው ትምህርት ቤት ሮካ ፕሪፓራቶሪም በዚህ ችግር የተነሳ የትምህርት ቤቱን ቅጥር ግቢ ወደ እርሻ ለውጧል። ትምህርት ቤቱን ከ23 ዓመታት በፊት የመሰረቱት ጀምስ ኩንጉ፤ “ነገሮች እንደዚህ አስከፊ ሆነው አያውቁም” ብለዋል። በግቢው ውስጥ የተማሪዎች መጫዋቻ ሜዳ የነበረው፤ አሁን የጓሮ አትክልት ማብቀያ ሆኗል። “ሁኔታው በሥነ ልቦናም እጅግ ጎድቶናል፤ ነገር ግን እንዲህ ማድረጋችን ቢያንስ እንዳንሰላች ረድቶናል፤ ይህም እንደ አንድ የሥነ ልቦና ሕክምና ነው” ብለዋል ጀምስ። እንደ የኬንያ የግል ትምህርት ቤቶች ማህበር ከሆነ በኦንላይን ትምህርት መስጠት የቻሉት በጣት የሚቆጠሩ ናቸው። እነርሱም ቢሆኑ የሚያገኙት ገቢ ለመምህራኑ መሰረታዊ ፍጆታቸውን እንኳን የሚሸፍን አይደለም። በግል ትምህርት ቤቶች ከሚሰሩ ከ300 ሺህ በላይ ሰራተኞች 95 በመቶ የሚሆኑት ያለ ደመወዝ ፈቃድ እንዲወጡ መደረጋቸውንም የማህበሩ ሊቀመንበር ፒተር ንዶሮ ተናግረዋል። ከዚህም በተጨማሪ 133 ትምህርት ቤቶች ጭራሹኑ ለመዝጋት ተገደዋል። የመምህራን እጣ ፈንታሁለቱ ትምህርት ቤቶች አማራጭ የገቢ ምንጭ ቢያገኙም፤ ባለቤቶቹ ግን ለአምስት ወራት ያለ ክፍያ ስለቆዩት መምህራን እጣ ፈንታ ተጨንቀዋል። አንዳንድ መምህራን ‘የሚሰራ ነገር ካለ’ ሲሉ የሚጠይቋቸው መምህራን መኖሩንም የሚናገሩት ጆሴፍ፤ እንኳን ለእነርሱ ለመትረፍ ራሳቸውንም ለመመገብ በቂ ገንዘብ እንደሌላቸው ይናገራሉ። በዚህም ምክንያት በርካቶች ወደ ሌላ አማራጭ የሙያ ዘርፍ እየተሰማሩ ነው። የግል ትምህርት ቤቶች ማህበሩ እያጋጠማቸው ላለው የገንዘብ ችግር መንግሥት በአጠቃላይ 65 ሚሊየን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ እንዲሰጣቸው ይፈልጋል። የገንዘብ ድጋፉ ካልተደረገላቸው ግን “አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ባሉበት መቆየት አይችሉም” ብሏል። የትምህር ሚኒስቴር ለትምህርት ቤቶቹ ብድር በማዘጋጀት ድጋፍ ቢያደርግም፤ የማህበሩ ሊቀመንበር ግን ይህ ሁሉንም ትምህርት ቤቶች ሊታደግ አይችልም የሚል ስጋት አላቸው።
news-45649050
https://www.bbc.com/amharic/news-45649050
የጎንደር ከተማ ሙስሊሞች ለመስቀል በዓል አደባባይን ሲያፀዱ ውለዋል
የጎንደር ከተማ ሙስሊሞች ለክርስትና ዕምነት ተከታዮች ያላቸውን አለኝታነት ለማሳየት የደመራ በዓል የሚከበርበትን ስፍራ በዘመቻ አፅድተዋል።
በፅዳት ዘመቻው የተሳተፉ ቁጥራቸው ወደ ሁለት መቶ የሚጠጉ ወገኖች በተለምዶ መስቀል አደባባይ የሚባለውን የከተማዋን ስፍራ በዛሬው ዕለት ለሚከበረው የደመራ በዓል ትናንት በዋዜማው ምቹ እንደደረጉ እማኞች ለቢቢሲ ተናግረዋል። • በእርጥብ ሳርና ቅጠል ጥቃትን ያስቆሙ አባቶች «ክርስቲያን ወንድሞቻችን የአረፋ በዓል በሚከበርበት ወቅት ፣በጋራ በመውጣት እኛ ሙስሊሞች የምንሰግድበት ስፍራ ማፅዳታቸውን መሰረት በማድረግ እኛም ይሄንን ተግባር ፈፅመናል፣» ሲሉ ለቢቢሲ የተናገሩት አቶ አብዲየ ኑር የተባሉ የዘመቻው ተሳታፊ በቀጣይ ጊዜያትም መሰል ዘመቻዎችን የመቀላቀል ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል። ከአንድ ወር በፊት በጅግጅጋ ከተማ በቤተ-ክርስቲያናት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ የክርስትና እና እስልምና አማኞች ተቻችለው በሚኖሩባት ጎንደር ተመሳሳይ ግጭት እንዳይፈጠር የሰጉና ውጥረቱን በሰናይ ግብር ለመመከት የወጠኑ ወጣቶች በጋራ በእስልምና ዕምነት በዓላት ወቅት የሚሰገድበትን ስታዲየም ሲያፀዱ የሚያሳይ መስል ከዚህ ቀደም በማህበራዊ ገፆች ዘንድ መሰራጨቱ ይታወሳል። እኒህን ወጣቶች ከአስተባበሩት መካከል አንዱ የሆነው ወጣት ይሁኔ ዳኘው በዛሬው ዘመቻ ውስጥም ተሳታፊ ነበር። «እንደምታውቁት ጎንደር የቱሪዝም መዳረሻ ናት።የሚጎበኙን ሰዎች (በሃይማኖታዊ ግጭቶች ሰበብ) የደህነነት ስጋት እንዲሰማቸው አንፈልግም።ክርስቲያኑ የመስጊዶች ጠባቂ፣ሙስሊሞች የቤተክርስቲያናት ጠባቂ የሚያደርጉ የአብሮነት ስራዎችን ለመስራት የምንፈልገውም ለዚሁ ነው» ሲል አስረድቷል። • ለመብረር የተዘጋጁት ልጃገረዶች ሽኩር መኮነን ሌላኛው በዛሬው የፅዳት ስራ ከተሰማሩ የእስልምና ዕምነት ተከታዮች ውሰጥ አንዱ ነው። ዘመቻውን የተቀላቀለው በሁለቱ ሃይማኖቶች ተከታዮች መካከል ያለውን ወንድማማችነት እና አብሮነት መንፈስ የሚያሳይ ተግባር ነው ብሎ በማመኑ መሆኑን ነግሮናል። ሽኩር ወትሮም ቢሆን ኢትዮጵያዊያን ሃይማኖታዊ ጠብ ውስጥ ሊገቡ እንደማይገባ ያወሳል። «ሲጀመር ሃይማኖት የመጣው ለሰው ልጆች ባህሪ ማስተካከያ እንጂ ልዩነት መፍጠሪያ አይደለም። ዕምነት ልዩነት መፍጠሪያ ሳይሆን፣ ነብስን መቆጣጠሪያ ነው። ጥሩ ዕምነት ያለው ሰው ለሌላውም ጥሩውን ይመኛል፣» በማለት ከማለዳው ጀምሮ እስከ አመሻሽ በዘለቀው የፅዳት ዘመቻ የተሳተፈበት ምክንያት ለቢቢሲ አስረድቷል።
news-48836230
https://www.bbc.com/amharic/news-48836230
አምስት ሰዎች ደቡብ ወሎ ለጋምቦ ውስጥ በደቦ ጥቃት ተገደሉ
ሰኔ 21 ቀን 2011 ዓ. ም በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን፣ ለጋምቦ ወረዳ "ህጻናት አፍነው ሊወስዱ ነው" በሚል አምስት ግለሰቦች በአካባቢው ነዋሪዎች በደቦ መገደላቸውን የለጋምቦ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አባተ አረጋ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ሰዎቹን በመግደል ከተጠረጠሩት ግለሰቦች መካከል እስካሁን አራት ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የለጋምቦ ወረዳ የአስተዳደርና ፀጥታ ኃላፊ አቶ ከበደ ይማም ለቢቢሲ አረጋግጣዋል። • በኢትዮጵያ የመንጋ ፍትህ የሰው ህይወት እየቀጠፈ ነው አቶ አባተ እንደተናገሩት፤ አምስቱ ግለሰቦች በአንድ የወረዳው ነዋሪ ቤት አርፈው ነበር። በወረዳው እየተንቀሳቀሱ ሳለም "ህጻናት አፍነው ይወስዳሉ" የሚል ያልተጣራ መረጃ ተሰራጭቶ ስለነበር የአካባቢው ማኅበረሰብ ጥቃት ሰንዝሮባቸዋል፤ በደረሰባቸው አሰቃቂ ድብደባም ሕይወታቸው አልፏል። አምስቱ ግለሰቦች በተገደሉበት ቦታ ወደ 300 ሰዎች ገደማ እንደነበሩና ፖሊሶች ሁኔታውን መቆጣጠር ስላልቻሉ መሸሻቸውንም ተናግረዋል። ግለሰቦቹ "ህጻናት አፍነው ሊወስዱ ነው የሚል ውዥንብር ተፈጥሮ ነበር" የሚሉት አቶ አባተ፤ "ድርጊቱ ቢፈጸም እንኳን ለፖሊስ ተላልፈው ይሰጣሉ እንጂ በእንዲህ አይነት አሰቃቂ ሁኔታ ሰው መገደል የለበትም" ብለዋል። ድርጊቱን በማውገዝ ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር ውይይት እያደረጉ መሆኑንም አክለዋል። • እንደወጡ የቀሩት ተመራማሪዎች ኦቶ ከበደ "ይህ አሳፋሪና አሳዛኝ ድርጊት የተፈጸመው ልጅ ሳይታፈን በጥርጣሬ ብቻ ነው። ሕዝብ በደቦ ፍትህ መስጠት እንደሌለበትም ከኅብረተሰቡ ጋር እየተነጋገርን ነው" ብለዋል። ከዚህ ቀደም ደቡብ ወሎ ውስጥ አንድ ልጅ ታፍና ተወስዳለች የሚል መረጃ ተሰራጭቶ ነበር። ከዚህ ውጪ ግን በአካባቢው ከልጅ ማፈን ጋር የተያያዘ ነገር ተከስቶ አንደማያውቅ ገልጸዋል። ግለሰቦቹ ከአዲስ አበባ፣ ከከሚሴ፣ ከሳይንትና ከደሴ ወደ ወረዳው የሄዱ ሲሆን፤ አንደኛው ግለሰብ ከየት አካባቢ እንደሄደ አለመታወቁን አቶ ከበደ ገልጸዋል። ሰዎቹ "ዘመድ ለመጠየቅ" ወደ አካባቢው ማቅናታቸውን እንደተናገሩ ግልጸው፤ ወደ አካባቢው የሄዱበት ምክንያት እስከሚጣራ ድረስ ያሳረፋቸው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን ጨምረው ተናግረዋል። • በሶማሌ ክልል ከ10 የሚበልጡ አብያተ ክርስትያናት ጥቃት ደረሰባቸው መታወቂያቸው ላይ ባለው መረጃ መሰረት ግለሰቦቹ በግብርና፣ በንግድ፣ የተሰማሩ እንደነበሩ አቶ ከበደ ገልጸዋል። "ግለሰቦቹ በዱላና ምሳር ጥቃት ደርሶባቸዋል፤ በአካባቢው ተኩስም ነበር" ሲሉ የጸጥታ አስተዳዳሪው የደረሰውን ጥቃት ተናግረዋል። የግለሰቦቹ አስክሬን ወደ የቤተሰቦቻቸው መላኩንና የሦስቱ ሥርዐተ ቀብር መፈጸሙን ገልጸዋል።
news-56658890
https://www.bbc.com/amharic/news-56658890
የፓሪስ መቆሸሽ ተቃውሞን ቀሰቀሰ
ውቧ ከተማ ፓሪስ መንገዶቿ ተቆፋፍረዋል፣ ቆሻሻ ሞልቷቸዋል ያሉ ዜጎች በኦንላይን ላይ ተቃውሞ ቀስቅሰዋል፡፡
ተቃዋሚዎቹ የጀመሩት ይህ ተቃውሞ ቆሻሻ መንገዶችንና በጊዜ ያልተነሱ የቆሻሻ ገንዳዎችን ፎቶ እያነሱ በማኅበራዊ የትስስር መድረኮች የማጋለጥ ተግባር ከፍተኛ ተቀባይነት በማግኘቱ ሺዎች ተቀላቅለውታል፡፡ የሚጋሩት ፎቶዎችም በማኅበራዊ ሚዲያ እንደ ሰደድ እሳት ተዛምተዋል፡፡ የፓሪስ ባለሥልጣናት በበኩላቸው ይህ ‹‹ስምን የማጠልሸት ፖለቲካዊ ዘመቻ›› እንጂ ሌላ አይደለም ብለዋል፡፡ ‹ቆሻሺት ፓሪስ› የሚል የዘመቻ የወል ስም በመክፈት ያልተጠገኑ ጎዳናዎችንና ያልተነሱ ቆሻሻዎችን ፎቶ በማንሳት የማጋለጡን ቅስቀሳ ማን እንደጀመረው አይታወቅም፡፡ ሆኖም ዘመቻው በተለይም በፈረንጆች ፋሲካ አካባቢ ተዛምቶ ሰንብቷል፡፡ የፓሪስ ምክትል ከንቲባ ዘመቻውን ፖለቲካዊ ብለውታል፡፡ ፓሪስን ማጽዳት ቀላል ሥራ እንዳልሆነ የጠቀሱት ምክትል ከንቲባው ፓሪስ ሚሊዮኖች እጅግ በተጣበበ ሥፍራ የሚኖሩባት ውብ ከተማ እንደሆነች መዘንጋት የለበትም ብለዋል፡፡ ዘመቻውን በትዊተር የተቀላቀለ አንድ ነዋሪ ፓሪስ ለዓመታት ብርሃናማዋና ውቧ የዓለም ከተማ ከሚለው ስሟ ጋር የሚመጥን ጽዳት እንደሌላት ጠቅሶ ለዚህም ከንቲባ አን ሂዳልጎን ተጠያቂ አድርጓል፡፡ የቀኝ አክራሪዋ ፖለቲከኛ መሪን ሌፔን ይህን የተቃውሞ ዘመቻ የተቀላቀለች ሲሆን በትዊተር ሰሌዳዋ ‹የፓሪስን ቆሻሻ ክምር ማየት ለፓሪሳዊያን ልብ የሚሰብር ነው› ስትል ፅፋለች፡፡ ምክትል ከንቲባው በሰጡት ምላሽ ‹አንድ ሰው የቀኑን አስቀያሚ አጋጣሚ ብቻ ፎቶ ቢያነሳ የሰውየው ሕይወት አስቀያሚ ነው ብለን መደምደም የለብንን፡፡ እውነታውን ለማየት አይናችንን እንግለጥ› ሲሉ ዘመቻው የከተማዋን መጥፎ ገጽታ ብቻ የማጉላት እንደሆነ አመላክተዋል፡፡ ፓሪስ ከ2 ሚሊዮን ሰዎች በላይ በ10 ኪሎ ሜትር ባልራቀ ዙርያ ገብ የሚኖሩባት በየዓመቱ ከ30 ሚሊዮን በላይ ጎብኚዎች የሚያዘወትሯት ከተማ ናት፡፡
news-55561320
https://www.bbc.com/amharic/news-55561320
የአሜሪካ ምክር ቤት፡ ደጋፊዎቻቸው የአገሪቱ ምክር ቤትን ከወረሩ በኋላ ትራምፕ ከትዊተርና ከፌስቡክ ታገዱ
ተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዋነኛዎቹ የማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር ገጾች እንዲታገዱ ሆነዋል።
ይህ እርምጃ የተወሰደባቸው ደጋፊዎቻቸው የካፒቶል ሂል ግቢን መውረራቸውና አደጋ ማድረሳቸውን ተከትሎ ነው። ዓለምን ባስገረመውና በአሜሪካ ምድር ይሆናል ተብሎ ባልተጠበቀ ነውጥ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች የታችኛውና የላይኛው ምክር ቤት መሰብሰቢያ የሚገኝበትንና የመንግሥት መቀመጫ የሆነውን ካፒቶል ሒልን ጥሰው በመግባት አደጋ ያደረሱት ከሰዓታት በፊት ነው። ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎቻቸውን ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ጠንካራ መልእክት ያስተላልፋሉ ተብሎ በሚጠበቅበት ሰዓት 'እወዳችኋለሁ' የሚል መልእክት አስተላልፈዋል። ይህ ብቻ ሳይሆን የተለመደውን ምርጫው ተጭበርብሯል የሚለውን ያልተጨበጠ ክስም በማኅበራዊ ገጻቸው አስተላልፈዋል። ትዊተር ሦስት የትራምፕ መልእክቶችን ከገጹ እንዲወገዱ እንደጠየቀ ይፋ ያደረገ ሲሆን ከፖሊሲያችን ጋር የሚጻረሩ መልእክቶች ስለሆኑ ነው መወገድ ያለባቸው ብሏል። ካልተወገዱ ግን ትራምፕን እስከመጨረሻው ከትዊተር አሰናብታቸዋለሁ ብሏል። ይህም ትዊተር ዶናልድ ትራምፕን እስከመጨረሻው ለማሰናበት በርካታ ቀናትን ላይጠብቅ ይችላል ማለት ነው። የትዊተር ውሳኔ በእንዲህ ሳለ ፌስቡክ በበኩሉ ትራምፕን ለ24 ሰዓታት እግድ ጥሎባቸዋል። ዩትዩብ በበኩሉ የትራምፕን ቪዲዯዎች ከገጹ እንዲወርዱ አድርጓል። ፌስቡክ ለምን ትራምፕን ለ24 ሰዓታት ከገጹ እንዳገደ በገለጸበት መግለጫው ምክንያቱም እየታየ ላለው ነውጥ ትራምፕ ማባባስ እንጂ ማብረድ ባለመቻላቸው ነው ብሏል። የትራምፕ ደጋፊዎች የአሜሪካ መንግሥት መቀመጫ የሆነውን ካፒቶል ሒልን ሰብረው በመግባት ከፖሊስ ጋር የተጋጩ ሲሆን በዚህ ዓለምን ጉድ ባሰኘው ነውጥ የአንዲት ሴት ሕይወት ማለፉም ተነግሯል። የትራምፕ ደጋፊዎች ካፒቶል ሒልን ጥሰው ጥቃት ሲፈጽሙ የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት በጆ ባይደን ጉዳይና ድል እየተከራከረ ነበር። በሁለቱ ምክር ቤቶች ሪፐብሊካኖችና ዲሞክራቶች የኖቬምበሩን የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ያሸነፉትን ጆ ባይደንን ውጤት ማጽደቅና አለማጽደቅ ላይ እየተነጋገሩ በነበረበት ሰዓት ነው የትራምፕ ደጋፊዎች ያልተጠበቀ እርምጃ የወሰዱት። ይህ ነውጥ ከመከሰቱ በፊት ትራምፕ በዋሺንግተን ናሸናል ሞል ለደጋፊዎቻቸው ምርጫው ተዘርፏል ሲሉ ነበር። ይህ ከሆነ ከሰዓታት በኋላ ደጋፊዎቹ ካፒቶል ሒልን ጥሰው ገብተው ጉዳት ማድረስ ጀመሩ። ትራምፕ ድርጊቱን ያወግዛሉ ሲባል በቪዲዯ ቀርበው ምርጫው ተጨበርብሯል የሚለውን ንግግር ደገሙት። ይህ አልበቃ ብሎም ነውጠኞቹን እወዳችኋለሁ። ጀግኖች ናችሁ ያልዋቸው። ዩ ትዩብ ይህንን የፕሬዝዳንቱን ንግግር የኔን ፖሊሲ የማይከተል ስለሆነ አስወግጄዋለሁ ብሏል። ትዊተር በበኩሉ ይህንን ቪዲዮ ከማስወገድ ይልቅ ሰዎች እንዳያጋሩት እና መውደዳቸውን የሚያሳየውን ምልክት (ላይክ እንዳያደርጉት)፣ ከቪዲዯው ሥር አስተያየት እንዳይሰጡ በማድረግ የቪዲዯ መልእክቱ እንዳይዛመት አድርጎ ነበር። በኋላ ላይ ግን ቪዲዯውን ሙሉ በሙሉ አስወግዶ ፕሬዝዳንቱም ለጊዜው ከትዊተር እንዲሰናበቱ አድርጓቸዋል። ካፒቶል ሒልን የመውረሩ የነውጥ እንቅስቃሴ ሲስተባበር የነበረው በዋናነት እነዚህኑ ማኅበራዊ የትስስር መድረኮችን በመጠቀም ነበር።
news-50816068
https://www.bbc.com/amharic/news-50816068
በጀርመን ከፍተኛ የናዚ ኃላፊ የነበረ ግለሰብ መቃብር ተከፍቶ ተገኘ
በጀርመን መዲና በርሊን የናዚ ከፍተኛ አመራር የነበረው ሬይንሃርድ ሄድሪክ መቃብር ተከፍቶ መገኘቱን ፖሊስ አስታወቀ።
በናዚ አውሮፓ የሚገኙ የአይሁዶችን ግድያ ካቀነባበሩ ኃላፊዎች መካከል ሄድሪክ ተጠቃሹ ነው ፖሊስ በቼኮስሎቫኪያ ሰላይ እአአ 1942 የተገደለው ሬይንሃርድ ሄድሪክ፤ ስለ ማንነቱ ምንም ያልተፃፈበት መቃብሩ ተከፍቶ ተገኝቷል ብሏል። የመቃብር ስፍራው ሰራተኛ ነበር ባሳለፍነው ሐሙስ ጠዋት መቃብሩ ተከፍቶ የተመለከተው። ፖሊስ መቃብሩን የከፈተውን ግለሰብ እየፈለገ እንደሆነ ያስታወቀ ሲሆን፤ የሟች አጥንት ግን አለመነካቱን አስታውቋል። በናዚ በአውሮፓ የሚገኙ የአይሁዶችን ግድያ ካቀነባበሩ ኃላፊዎች መካከል ሄድሪክ ተጠቃሹ ነው። እአአ 1942 ላይ 'ዋንሴ' ተብሎ በሚታወቀው ኮንፍረንስ የሂትለር የጅምላ ግድያ እቅድ የወጣበትን ስብሰባ የመራው ሄድሪክ ነበር። የመቃብር ስፍራን ጸጥታ ማደፍረስ ወይም መቃብርን ማፈራረስ እና መቆፈር በጀርመን በሕግ ያስጠይቃል። የናዚ ደጋፊ ወይም አድናቂ የሆኑ ሰዎች የናዚ የመቃብር ስፍራዎችን የአምልኮ ቦታ እንዳያደርጉት ወይም የናዚ ጥላቻ ያላቸው ሰዎች መቃብሮቹን እንዳያወድሟቸው በማሰብ የናዚ አባላት የመቃብር ስፍራ ምንም ምልክት አይደረግባቸውም። ስምም ሌላም መረጃ ጭምር። የሄድሪክን መቃብር የከፈተው ግለሰብ ግን መቃብሩ የማን እንደሆነ ያውቅ ነበር ተብሏል። የሄድሪክ የመቃብር ስፍራ "ጨካኙ ገዳይ" ተብሎ የሚታወቀው ሄድሪክ፤ ከናዚ ጦር አዛዥ ሄኔሪክ ሂምለር ሥር ሆኖ ለአጠቃላይ የናዚ አስተዳደር የደህንነት ኦፊሰር ሆኖ ሰርቷል። አዶልፍ ሂትለር ሄድሪክን "ባለ ብረት ልቡ ሰው" እያለ ይጠራው ነበር። ሁለት የቼክ ሪፓብሊክ ግዛቶቸን ያስተዳደረው ሄድሪክ፤ እግሊዞች ያሰለጠኑት የቼኮስላቫኪያ ሰላይ ሄድሪክ መኪናው ውስጥ እያለ ጥቃት ከሰነዘረበት በኋላ ባጋጠመው ጉዳት ህይወቱ አልፏል። በአጸፋውም ናዚዎች ሊዲስ ተብላ በምትጠራ መንደር ውስጥ የሚገኙ እድሜያቸው ከ15 ዓመት በላይ የሆኑ ወንዶችን በሙሉ የገደሉ ሲሆን ሴቶች እና ህጻናትን ደግሞ የጅምላ ግድያ ወደሚፈጸምባቸው ማጎሪያ ስፍራ ወስደዋል።
news-56707834
https://www.bbc.com/amharic/news-56707834
ታዋቂው ግሪካዊ የወንጀል ዘጋቢ በጥይት ተገደለ
ታዋቂው ግሪካዊ የወንጀል ዘጋቢ በተተኮሰበት ጥይት መገደሉን ተከትሎ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪይራኮስ ሚትሶታክሲ ፈጣን የሆነ ምርመራ እንዲከፈት አዘዋል።
ጊዮርጊስ ካራይቫዝ የተባለው ጋዜጠኛ የተገደለው በያዝነው ሳምነት አርብ በዋና ከተማዋ አቴንስ ከሚገኘው ቤቱ አቅራቢያ ነው። ሁለት ግለሰቦች ቢያንስ ስድስት ጊዜ ተኩሰው እንደገደሉትም ተዘግቧል። ሞቱ " ሁላችንንም ድንጋጤ ውስጥ ከቶናል" በማለት የመንግሥት ቃለ አቀባይ ተናግረዋል። በሚዲያ ነፃነት ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች በበኩላቸው ጊዮርጊስ የተገደለበት ምክንያት ከስራው ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ ሊጣራ እንደሚገባ አሳስበዋል። ጊዮርጊስ የተደራጁ ወንጀሎችንና ሙስናን በማጋለጥ ዝናን አትርፏል። ጋዜጠኛው የግል ለሆነው ስታር ቴሌቪዥን እንዲሁም ብሎኮ ለተባለ ድረ ገፅ ይሰራ ነበር። ከስራ ተመልሶ ቤቱ አካባቢ ሲደርስ ከመኪናው በወጣበት ቅፅበት እንደተተኮሰበትም አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የአይን እማኞች ነገሩኝ ብሎ ዘግቧል። የተገደለበት አካባቢም በርካታ የሽጉጥ ቀለሃዎች መሰብሰባቸውን ከፖሊስ ምንጮች መረዳት ተችሏል። "ጋዜጠኛው የተገደለው በአልሞ ተኳሾች ነው" በማለት ስሜ አይጠቀስ ያለ ፖሊስ ለሮይተርስ የዜና ወኪል ተናግሯል። ከግድያው በፊት "ጊዮርጊስ ማስፈራሪያ ደርሶኛል አላለም እንዲሁም የፖሊስ ጥበቃም ያስፈልገኛል አለማለቱን" አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በዘገባበው አስነብቧል። የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ቮን ደር ሊየን በእንዲህ አይነት አሰቃቂና አሳዛኝ ሁኔታ መገደሉን በማውገዝ ፍትህ ይገባዋል ብለዋል። የአውሮፓ ፓርላማ አፈ ጉባኤ ዴቪድ ሳሶሊ በኩላቸው የጋዜጠኛውን ሞት "አሳዛኝ ነው" በማለት በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል። በአውሮፖ ህብረት አባል አገራት ከዚህ በፊት የተገደለው ጃን ኩኪያክ የተባለው ጋዜጠኛ ከሶስት አመት በፊት ነበር። የስሎቫኪያ ዜግነት ያለው ይህ ጋዜጠኛ ግድያ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል።
news-56236704
https://www.bbc.com/amharic/news-56236704
ትግራይ፡ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር እና ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ መወያየታቸው ተነገረ
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጋር መወያየታቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታወቀ።
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ እና የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ እንዳሉት፤ የውጭ ጉዳይ ኃላፊው በውይይታቸው በትግራይ ክልል ያለው የሰብአዊ እርዳናታና የሰብአዊ መብቶች ቀውስ አሜሪካንን እንደሚያሳስባት አጽንኦት ሰጥተው ከጠቅላይ ሚኒስተሩ ጋር መነጋገራቸው ተገልጿል። አንቶኒ ብሊንከን እየጨመረ የመጣ ያሉትን ግድያዎችና የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ ታማኝ ያሏቸውን ሪፖርቶች በመጥቀስ የኢትዮጵያ መንግሥት ስደተኞችን ጨምሮ ሰላማዊ ሰዎችን እንዲጠብቅ እንዲሁም ተጨማሪ ጥሰቶች እንዳይፈጸሙ ጠይቀዋል። የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስተሩና ጠቅላይ ሚኒስትሩ አደረጉት ስለተባለው ንግግር በተመለከተ በኢትዮጵያ በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በውይይታቸው በአስቸኳይ ግጭቶች ቆመው የአማራ ክልል የጸጥታ ኃይሎችን ጨምሮ የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል እንዲወጡ አጥብቀው መጠየቃቸው የወጣው መግለጫ አመልክቷል። በተመሳሳይ ከቀናት በፊት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በትግራይ ይገኛሉ ያላቸው የኤርትራ ሠራዊት እና የአማራ ክልል ኃይሎች ከክልሉ መውጣት አለባቸው ሲል መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። የኢትዮጵያ መንግሥት ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት መግለጫ በሰጠው ጠንካራ ምላሽ አገሪቱ በግዛቷ ውስጥ የጸጥታ መዋቅሯን በማሰማራት በኩል ካላት ሉአላዊ መብት አንጻር ጣልቃ መግባት ነው በሚል የአሜሪካንን መግለጫ በጽኑ ተቃውሞታል። ምንም እንኳ የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥትም ይሁን የኤርትራ መንግሥት በትግራይ በተካሄደው ግጭት ኤርትራ ተሳትፎ የላትም ቢሉም፤ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ከዚህ ቀደም የኤርትራ ጦር ወደ ትግራይ ክልል መግባቱን የሚገልጽ መረጃ ማውጣቱ ይታወሳል። ብሊንከን ከጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ ጋር በነበራቸው ወይይት፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ገለልተኛ፣ ዓለም አቀፍና ተአማኒ መርመራዎች ተፈጸሙ በተባሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ እንዲካሄድና ፈጻሚዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር እንዲሰራ መጠየቃቸው ተገልጿል። ባሳለፍነው ዓርብ ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል በአክሱም ከተማ ከ200 በላይ ንጹሃን ዜጎች በኤርትራ ሠራዊት ተገድለዋል የሚል ሪፖርት ማውጣቱ ይታወሳል። አምነስቲ ይህ የጅምላ ግድያ በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል ሊሆን ይችላል ብሎ ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት "ባልተሟላ መረጃና ውስን በሆነ የጥናት ዘዴ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው" ሲል ተችቷል። የኤርትራ መንግሥትም በተመሳሳይ የአምነስቲን ሪፖርት እንደማይቀበለው ገልጿል። ኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል ሪፖርቱ በአብዛኛው መሠረት ያደረገው ሱዳን ውስጥ ባለው ሐምዳይት የስደተኞች መጠለያ ውስጥ ያሉ 31 ግለሰቦችን ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት የአምነስቲ ሪፖርት የጥናት ዘዴ ይተች እንጂ መንግሥት ገለልተኛ ቡድን በማቋቋም ተፈጽመዋል የተባሉ በደሎችን የሚመረምር ቡድን ለማዋቀር ዝግጁ መሆኑን አስታውቆ ነበር። የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚንሰትሩ አንቶኒ ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጋር ባደረጉት ውይይት በቅርቡ ኢትዮጵያ ወደ ትግራይ ክልል የሚደረጉ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦቶች ያለምንም ገደብ እንዲካሄዱ መፍቀዷን አድንቀዋል። በተጨማሪም አሜሪካ ግጭቱ መፍትሔ እንዲያገኝ ለመርዳት ዝግጁ መሆኗንና በመላው ኢትዮጵያ የሚያስፈልግ ህይወት አድን የሰብአዊ እርዳታን በማቅረብ በኩል ያላትን ፈቃደኝነት ገልጸዋል።
49661465
https://www.bbc.com/amharic/49661465
መከላከያ የሶሪያ እና የየመን ዜጋ የሆኑ የአይኤስ አባላትን በቁጥጥር ሥር አዋልኩ አለ
የአገር መከላከያ ሠራዊት፤ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በርካታ የጽንፈኛው እስላማዊ ቡድን-አይኤስ አባላትን በቁጥጥር ሥር አዋልኩ አለ።
የአይኤስ አርማ የኢታማዦር ሹሙ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት ኮለኔል ተስፋዬ አያሌው፤ የጽንፈኛ ቡድኑ አባላት ናቸው የተባሉ ተጠርጣሪዎች ጅግጅጋ፣ ድሬ ዳዋ፣ ሞያሌ እና ዶሎ ከተማዎችን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች ውስጥ መያዛቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። በተለያየ ሥፍራ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ግለሰቦች ቁጥር ምን ያህል እንደሆነ የተጠየቁት ኮለኔሉ፤ "በቁጥር በጣም ብዙ ናቸው። መረጃው ገና ተጣርቶ አልደረሰንም" ብለዋል። ከተጠርጣሪዎቹ መካከል ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የሶማሊያ፣ የሶሪያ እና የየመን ዜጎች እንደሚገኙበት ተናግረዋል። "አብዛኞቹ ተጠርጣሪዎች አማርኛ ቋንቋ ተምረው የተላኩ ናቸው" ብለዋል። • መከላከያ በዛላምበሳ ድንበር እንዲቆይ ስምምነት ተደረሰ • የጀማል ኻሾግጂ አገዳደል በዝርዝር ይፋ ሆነ • "ሰዓረ ሙዚቃ በጣም ያዝናናው ነበር" ጄኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳዔ ከዚህ ቀደም አይኤስ በአማርኛ ቋንቋ የጽሑፍ መልዕክቶችን በቴሌግራም አማካኝነት ማስተላለፍ እንደሚጀምሩ ማስታወቂያ አሰራጭተው እንደነበረ ይታወሳል። አይኤስ በኢትዮጵያ ላይ ምን አይነት ጫና እያሳደረ ነው? መከላከያስ ይህን ለመከላከል ምን እያደረገ ነው? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ኮለኔል ተስፋዬ፤ "የአገራችን የደህንነት ጥበቃ ጠንካራ ስለሆነ ወደ ኢትዮጵያ ዘልቀው መግባት ባለመቻላቸው፤ ፕሮፖጋንዳ ብቻ ነው የሚነዙት። ድንበር አካባቢዎች ላይ ከፍተኛ ጥበቃ እያደረግን ነው" ሲሉ መልሰዋል። አብዛኞቹ ተጠርጣሪዎች ለድንበር ቅርብ በሆኑ ከተሞች አቅራቢያ ከተቀጣጣይ መሣሪያዎች ጋር መያዛቸውን የሚናገሩት ኮለኔል ተስፋዬ፤ ከዚህ ቀደም የአይኤስ ተጠርጣሪ ነው ተብሎ ኢትዮጵያ ውስጥ በቁጥጥር ሥር የዋለ አካል እንዳልነበረ ይገልጻሉ። "ከዚህ ቀደም የአይኤስ አባላት የሆኑ ሰዎችን በሶማሊያ በቁጥጥር ሥር አውለናል። እነሱንም ለሶማሊያ መንግሥት ነው አሳልፈን የምንሰጠው" ብለዋል። "ስልጠና ሲሰጣቸውና ወደ ኢትዮጵያ ሲላኩም ጭምር መረጃው ነበረን" ያሉት ኮለኔል ተስፋዬ፤ የአይኤስ አባላት እንቅስቃሴን በተመለከተ መንግሥት መረጃ እንደነበረው ጠቁመዋል። ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት በተለያያ ጊዜ እንደሆነ የተናገሩት ኮለኔል ተስፋዬ፤ ሁሉም የተያዙት አይኤስ በአማርኛ ቋንቋ ጽሑፎችን ማሰራጨት ከጀመረ በኋላ መሆኑን ተናግረዋል። "ቁጥራቸው አነስተኛ ቢሆንም፤ ሥራ ፍለጋ ከአገር የሚሰደዱ ወጣቶችን መንገድ ላይ በመያዝ 'ሥራ እንሰጣችኋላን' በማለት እያታለሏቸው ስልጠና እየሰጧቸው ነው" የሚሉት ኮለኔል ተስፋዬ፤ "በኢትዮጵያ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል አብዛኛዎቹ የሶሪያ እና የየመን ፓስፖርት ያላቸው ሰዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።
48946713
https://www.bbc.com/amharic/48946713
የቀደመው ዘመናዊ ሰው ከአፍሪካ ውጪ ተገኘ
ተመራማሪዎች ከዘመናዊ ሰው ጋር ተቀራራቢ የሆነ ዝርያ ከአፍሪካ ውጪ አገኙ።
በግሪክ የተገኘው የራስ ቅል አውሮጳ በኒያንደርታሎች በተወረረችበት ወቅት 210 ሺህ ዓመት ያስቆጠረ ነው ተብሏል። ጥናቱ ይፋ እንዳደረገው፤ የሰው ልጅ ከአፍሪካ ወደ አውሮጳ ቅድመ ፍልሰት ስለማድረጉ ታሪክ ምንም አይነት የዘረመል ማስረጃ የለውም ለሚለው ሌላ አስረጅ ሆኖ ቀርቧል። ይህ ግኝት የታተመው 'ኔቸር' በተሰኘው ጆርናል ላይ ነው። ተመራማሪዎች በ1970ዎቹ በግሪክ አፒዲማ ዋሻ ውስጥ ሁለት ጠቃሚ ቅሪተ አካል አግኝተው ነበር። • ለባለስልጣናቱ ግድያ አዴፓ ራሱን ተጠያቂ እንዲያደርግ ህወሐት ጠየቀ • "የለውጥ አመራሩን ሳይረፍድ ከጥፋት መመለስ ይቻላል" እስክንድር ነጋ አንዱ በጣም የተዛባ ሌላኛው ደግሞ ያልተሟላ ነበር። ቢሆንም ተመራማሪዎች የተለያዩ ሳይንሳዊ ዘዴዎችን በመጠቀም የቅሪተ አካሉን ምስጢር ሊደርሱበት ችለዋል። ይህም ተመራማሪዎቹ በግሪክ ከዛሬ 210 ሺህ ዓመት በፊት ጥንታዊ ሰው በርከት ብሎ ይኖር ነበር እንዲሉ አስችሏቸዋል። ከአፍሪካ ውጪ የሚገኘው የዓለማችን ሕዝብ ከየት መጣሁ? ብሎ ለሚለው ጥያቄ ሲመልስ ከአፍሪካ መፍለሱን ይናገራል። መቼ? ለሚለው ደግሞ ከ60 ሺህ ዓመት በፊት የተመራማሪዎች መልስ ነው። ይህ ዘመናዊ ሰው ወደ አውሮጳና እስያ ሲሄድ በመንገዱ ላይ ያገኛቸውን እነ ኒያንደርታልና ዴኒሶቫንስን እየተኩ መሄዳቸው ይታመናል። ነገር ግን ዘመኑ ጥንታዊ ሰው (ሆሞሳፒያንስ) ከአፍሪካ ወደ ሌሎች የዓለማችን ክፍል መፍለስ የጀመረበት የመጀመሪያው ጊዜ አይደለም። የሆሞሳፒያንስ ቅሪተ አካል በ1990ዎቹ በእስራኤል ከስኩሁል እና ቃፍዜህ የተገኘ ሲሆን፤ እድሜውም ከ90 ሺህ እስከ 125 ሺህ ድረስ ተገምቷል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ጥንታዊ ሰው ከአፍሪካ ወደ አውሮጳና ወደ እስያ ያደረገውን ፍልሰት በሚመለከት የሚደረጉ ጥናቶች ላይ አንዳንድ ፍንጮች እየተገኙ መሆናቸውን ተመራማሪዎች ያስረዳሉ። • የታገዱት ሞተረኞች እሮሮ እያሰሙ ነው ቻይና ውስት በዳኦክሲያንና ዝሂሬዶንግ የተገኘው ቅሪተ አካል እድሜው በ80 ሺህና በ120 ሺህ መካከል ተገምቷል። የዘረመል ጥናቶች ላይ ምርምር የሚያደርጉ ሰዎች፤ ከአፍሪካ የሄዱና ኒያንደርታሎች ተዳቅለው አግኝተናል ብለዋል። በጀርመኖቹ የኒያንደርታሎች መዳቀል የተፈጠረው 219 ሺህ እና በ460 ሺህ ዓመታት መካከል ነው። ነገር ግን አሁንም ሆሞሳፒያንስ መዳቀሉ ላይ ተሳትፈውበታል ወይስ ሌላ ጥንታዊ የአፍሪካ ቡድን አለ ለሚለው መልስ አልተገኘለትም።
news-56674360
https://www.bbc.com/amharic/news-56674360
ትግራይ፡ የኢትዮጵያ ሠራዊት ትግራይ ውስጥ ግድያ ፈጽሟል መባሉን ሐሰት ነው አለ
በትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ተፈጸሙ የተባሉት የመብት ጥሰቶች ሐሰት ናቸው ሲል ሠራዊቱ ምላሽ ሰጠ።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል መሐመድ ተሰማ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ላይ እንደተናገሩት "ትግራይ ውስጥ ሠራዊቱ ንጹሃንን ፈጅቷል በሚል የሚናፈሰው ሐሰተኛ ወሬ በህወሓት ተላላኪዎች የተቀነባበረ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። ጨምረውም የመከላከያ ሠራዊቱ በወሰደው እርምጃ "የህወሓት ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መደመሰሱን" ተናግረው፤ ይሁን እንጂ የቀሩ የቡድኑ አንዳንድ አባላት "የሸፍታነትን ባህሪ ተላበሰው፤ አካባቢዎች በአሳቻ ስፍራ ላይ በሕዝቡ ላይ ዘረፋ፣ እንግልትና ግድያ እየፈፀሙ ናቸው" ሲሉ ተናግረዋል። በዚህም የተነሳ እነዚህ ታጣቂዎች ሰላማዊ ሰዎችን በመጨፍጨፍ አገርና ሕዝብን ድርጊቱ በመከላከያ ሠራዊት ላይ የተፈፀመ ለማስመሰል የተለያዩ ተግባራትን እየፈጸሙ ነው ብለዋል። የቢቢሲ 'አፍሪካ አይ' ፕሮግራም ባደረገው ምርመራ በትግራይ ውስጥ ማኅበረ ዴጎ በሚባል ስፍራ በኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት ጭፍጨፋ መፈጸሙን የሚያመለክቱ ማስረጃዎች ማግኘቱን ባለፈው ሳምንት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። በዚህም የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ቢያንስ 15 ወንዶች የተገደሉበትን ትክክለኛውን ቦታ ለመለየት ችሏል። የታጠቁና የወታደር የደንብ ልብስ የለበሱ ሰዎች ያልታጠቁ ወንዶችን ከአንድ የገደል አፋፍ ላይ በመውሰድ አንዳንዶቹን ላይ በቅርብ ርቀት በመተኮስ አስከሬኖችን ወደ ገደል ገፍተው ሲጨምሩ የሚያሳይ ቪዲዮ በየካቲት ወር መጨረሻ ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ መውጣቱን ተከትሎ ነበር 'አፍሪካ አይ' ምርመራውን ያደረገው። ቢቢሲ ይህ ድርጊት የተፈጸመው የኢትዮጵያ ሠራዊት የህወሓት ኃይሎችን እየተዋጋ ባለበት ትግራይ ክልል ውስጥ ማኅበረ ዴጎ ከተባለች ከተማ አቅራቢያ መሆኑን አረጋግጧል። በወቅቱ ቢቢሲ ያገኛቸውን ማስረጃዎች ለኢትዮጵያ መንግሥት በማቅረብ ምላሽ የጠየቀ ሲሆን መንግሥት "በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የወጡ ነገሮችና ክሶች እንደ ማስረጃ ሊወሰዱ አይችሉም" በማለት "ገለልተኛ ምርመራዎችን ለማካሄድ የትግራይ ክልል ክፍት ነው" ሲል መልስ ሰጥቶ ነበር። ከዚያ በኋላ ግን በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ ኤምባሲ የፌደራል ፖሊስ፣ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ምርመራ ለማድረግ ወደ ስፍራው ማቅናታቸውን ገልፆ መግለጫ አውጥቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው እንደተናገሩት፣ ትግራይ ውስጥ በኢትዮጵያ ሠራዊት ተፈጸሙ ስለተባሉት ጥፋቶች አስፈላጊው ምርመራ ተደርጎ አጥፊዎች በሕግ እንደሚጠየቁ መናገራቸው ይታወሳል። ሜጀር ጀነራል መሐመድ ተሰማ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ምን አለ? ረቡዕ ዕለት በተሰጠው መግለጫ ህወሓት ግድያዎቹን በመፈፀም፣ የቪዲዮ ምስል በማቀናበር የአገሪቱ መከላከያ ሠራዊት የፈፀመው አስመስለው በማሰራጨት ስም ለማጥፋት እንደሞከሩ ሜጀር ጀነራል መሐመድ ተናግረዋል። በተጨማሪም የመከላከያ የሚዲያ ሥራዎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ብርጋዲየር ጀነራል ኩማ ሚደክሳ በቪዲዮው ላይ ዝርዝር ማብራሪያን ሰጥተዋል። በዚህም መሠረት በቪዲዮው ላይ የሚታዩት የሠራዊቱን የደንብ ልብስ ቢለብሱም አባላት እንዳልሆኑ ገልጸው፤ የደንብ ልብሱ በህወሓት ኃይሎች መዘረፉን ተናግረዋል። ለዚህም ለሠራዊቱ የሚሰጠው ልብስ ለእያንዳንዱ በልኩ የቀረበ ሲሆን በቪዲዮው ላይ የሚታዩት ግን ከልካቸው በላይ የሆነ የደንብ ልብስ በመልበሳቸው እጃቸው ላይ እንደሚያስታውቅ እንዲሁም በወገብ ላይ የያዙት ትጥቅ የሠራዊቱ አባላት እንዳልሆነ ተናግረዋል። ዳይሬክተሩ "ቪዲዮው ሦስት የተለያዩ ምስሎችንና ቦታዎችን በማቀናበር የቀረበ ሐሰተኛ ምሰል ነው" በማለት ቪዲዮዎቹ በካሜራና በሞባይል ተቀርጾ የተለያዩ ቦታዎችን እንደሚያመለክት ገልጸዋል። የመጀመሪያው ቪዲዮ በካሜራ የተቀረጸ ሲሆን የሚታየው ስፍራ ከሁለተኛው ቪዲዮ የተለየ ነው በማለት ልዩነቱ ሜዳማና ገደላማ መሆናቸውን ጠቁመው ሦስተኛው ቪዲዮ አስከሬን የሚታይበት እንደሆነና ይህ ቪዲዮ በሞባይል የተቀረጸ መሆኑን ገልጸዋል። ብርጋዲየር ጀነራል ኩማ በቪዲዮዎቹ ላይ የሚታዩ ዝርዝሮችን በማንሳት የተሰራጩት ምስሎት በተለያዩ መሳሪያዎችና ቦታዎች ሆን ተብለው ተዘጋጅተው የተቀረጹና ሐሰተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ጨምረውም የአገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት ጥብቅ የዕዝ ሰንሰለት ያለውና ቁጥጥር የሚደረግበት በመሆኑ እያንዳንዱ ክስተት ስለሚታወቅ እንዲህ አይነቱን ወንጀል አይፈጽምም ሲሉ አስተባብለዋል። ሜጀር ጀነራል መሐመድ ተሰማም እነዚህ የተቀናበሩ ቪዲዮዎች "በህወሓት ተላላኪዎች በውሸት ተቀናብሮ ሕዝብን ለማደናገር የተሰሩ ናቸው" በማለት ሠራዊቱ ድርጊቱን እንዳልፈጸመ ተናግረዋል። አክለውም የአገር መከላከያ ሠራዊት በሥነ ምግባር የተገነባ ሕዝባዊ መሰረት ያለው በመሆኑ እንዲህ አይነቱን ሕዝብን የሚጎዳ ተግባር አይፈጽምም ብለዋል። ትግራይ ውስጥ ግጭቱ የተቀሰቀሰው ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የህወሓት ኃይሎች በመንግሥት ጦር ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ካዘዙ በኋላ ነበር። በትግራይ ክልል ውስጥ በተካሄደው ወታደራዊ ግጭት ሳቢያ ምን ያህል ሰዎች እንደሞቱ የሚታወቅ ነገር ባይኖርም አሃዙ በበርካታ ሺዎች ሊሆን እንደሚችል የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ይናገራሉ። ከዚህ ባሻገርም በግጭቱ ውስጥ ተሳታፊ በሆኑ ኃይሎች ግድያዎች፣ ጾታዊ ጥቃቶች፣ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ዘረፋና የንብረት ውድመቶች መፈጸማቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ባወጧቸው ሪፖርቶች ላይ አመልከተዋል። በተጨማሪም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዳለው በግጭቱ ሳቢያ ከሁለት ሚሊዮን ሰዎች በላይ ለመፈናቀል የተዳረጉ ሲሆን፤ ከአራት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ የሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ናቸው። ከቪዲዮዎቹ ከአንዱ ላይ የተወሰደ ምስል
news-45755907
https://www.bbc.com/amharic/news-45755907
የ2018 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ዛሬ ረፋድ ይፋ ይደረጋል
የ2018 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ዛሬ ረፋድ ይፋ ይደረጋል። ምርጫውን የሚያከናውነው 5 አባላት ያሉት ኮሚቴ የዘንድሮ የኖቤል የሰላም ሽልማት ዕጩዎች ቁጥር 331 መሆኑን አሳውቋል።
ከእነዚህም መካከል 216 ግለሰቦች ሲሆኑ 115ቱ ደግሞ ቡድኖች መሆናቸውን ኮሚቴው ጠቁሟል። በኖቤል ሽልማት አሰራር መሰረት ዕጩዎች ለህዝብ ይፋ የሚደረጉት ከ50 ዓመታት በኋላ ነው። ዕጩዎቹ እነማን እንደሆኑ ባይታወቅም በርካቶች የዘንድሮውን የኖቤል ሽልማት ማን ሊያሸንፍ እንደሚችል የራሳቸውን ግምት እየሰጡ ይገኛሉ። የሁለቱ ኮሪያ መሪዎች የአሸናፊነቱ ቅደሚያ ግምት ከተሰጣቸው ግለሰቦች መካከል ይገኙበታል። የሰሜን ኮሪያው መሪ በሰብዓዊ መብት አያያዘቸው በተደጋጋሚ ቢወቀሱም ከደቡብ ኮሪያው አቻቸው ጋር በመሆን በሁለቱ ሃገራት መካከል የቆየውን ውጥረት ለማርገብ የወሰዷቸው እርምጃዎች የሽልማቱ ተመራጭ ያደርጋቸዋል የሚሉት በርካቶች ናቸው። • ዐብይ አሕመድ ለኖቤል ሽልማት ታጭተዋል? ሌላው ሽልማቱን ሊያሸንፉ ይችላሉ ተብለው ቅድሚያ ግምት ከተሰጣቸው መሪዎች መካከል እንዱ ዶናልድ ትራምፕ ናቸው። ትራምፕ በኮሪያ ባህረሰላጤ ሰላም ለማስፈን እንዲሁም ሰሜን ኮሪያ ኒኩለር ቦንም ከማበልጸግ እንድተቆጠብ ላደረጉ ያላሰለሰ ጥረት ሽልማቱን ሊያሸንፉ ይችላሉ ተብሏል። በእስር ላይ የሚገኘው ጸሃፊው ራኢፍ ባዳዊ፣ ሊቀ ጳጳስ ፈራንሲስ እና የካታሎንያ የነጻነት መሪ ካርለስ ፑይግዴሞንት ሽልማቱን ያሸንፋሉ ተብሎ ግምት ከተሰጣቸው መካከል ይገኙበታል። የዘንድሮውን የኖቤል የሰላም ሽልማት ያሸንፋሉ ተብለው ግምት ከተሰጣቸው ሌሎች ግለሰቦች መካከል እስር ላይ የሚገኘው ጸሃፊው ራኢፍ ባዳዊ፣ ሊቀ ጳጳስ ፈራንሲስ እና የካታሎንያ የነጻነት መሪ ካርለስ ፑይግዴሞንት ይገኙበታል። የሳውዲ ዜግነት ያለው ጸሃፊው ራኢፍ ባዳዊ ፣ ''የመገናኛ አውታሮችን በመጠቀም እስልምናን ዘልፏል'' በሚል ክስ ላለፉት 6 ዓመታት በሳውዲ እስር ቤት ውስጥ ይገኛል። በስፔን መንግሥት ሕጋዊ እውቅና ባልነበረው ሕዝበ ውሳኔ ካታላኖች በካርለስ ፑይግዴሞንት እየተመሩ ከስፔን ተገንጥለው ሃገር ለመመስረት ሙከራ አድርገው ነበር። ሕዝበ ውሳኔውን ተከትሎም ካርለስ ከስፔን ሸሽተው በቤልጅም እየኖሩ ይገኛሉ። • "ካታሎንያ ከስፔን ተገንጥላ አገር የመሆን መብቷን አሸነፈች" ከግለሰቦቹ በተጨማሪ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ሽልማቱን ሊያሸንፍ ይችላል ከተባሉ ድርጅቶች መካከል አንዱ ነው። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድስ ከዕጩዎቹ መካከል እንዱ ሊሆኑ አይችሉም? ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ከፍተኛ የሕዝብ ድጋፍ ማግኘት ብቻም ሳይሆን የኖቤል ሽልማት እንዲያገኙም ጭምር ዘመቻ ተከፍቶ ነበር። ይሁን እንጂ የኖቤልን የሰላም ሽልማትን የጊዜ ሰሌዳ ስንመለከት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የ2018 የኖቤል ሽልማት እጩ የመሆናቸው ነገርን አጠያያቂ ያደርገዋል። የኖቤል ኮሚቴ የጊዜ ሰሌዳ እንደሚከተለው ነው። መስከረም፡- በፈረንጆች መስከረም (ሴፕቴምበር) የኖርዌይ ኖቤል ኮሚቴ እጩዎችን ለመቀበል ይሰናዳል። እጩ የመቀበሉ ሥራ ለቀጣይ ስድስት ወራት ይጸናል። እጮዎቹን መጠቆም የሚችሉት ከላይ የተዘረዘሩት ብቁ ጠቋሚ የተባሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ብቻ ናቸው። የካቲት፡- በየካቲት የእጩዎች መቀበያ ጊዜ ያበቃል። ከየካቲት 1 በፊት ያልተጠቆመ በዚያ ዓመት እጩ መሆን አይችልም። መጋቢት፡-ኮሚቴው የእጮዎችን ዝርዝር ያቀርባል። ከእጮዎቹ ውስጥ ከ20 እስከ 30 የሚሆኑትን ብቻ ለተጨማሪ ማጣሪያ ይቀርባሉ። ጥቅምት፦ በጥቅምት መጀመርያ ኮሚቴው አሸናፊውን በድምጽ ብልጫ ይመርጣል። ይግባኝ የማይባልበት ምርጫ ነው ታዲያ። በታኀሳስ፦ 10 (በፈረንጆቹ) በኦስሎ ኖርዌይ የሽልማት ሥነ ሥርዓቱ ይካሄዳል። የኖቤል ሽልማት ከአንድ ዓመት ዘለግ ያለ ጊዜን የሚወስድ ሂደት ነው። ኾኖም ጥቆማ የመቀበያ ጊዜ ከፈረንጆች መስከረም ጀምሮ ለ6 ወራት የሚዘልቅ ነው። ይህ እንግዲህ መጪውን የመስከረም ወር ሳይሆን የ2017ቱን ወር አንድ ብሎ የሚጀምር ነው። የእጩ መስኮቱ ከተዘጋ ከሁለት ወራት በኋላ ወደ ሥልጣን የመጡት ዐብይ አሕመድ ቢያንስ የ2018 የኖቤል ሽልማት እጩ የመሆናቸው ዐድል ጠባብ ያደርገዋል። ምናልባት የኖቤል ኮሚቴው በመጨረሻዎቹ ጊዜያት እጩ የመጨመር ሥልጣን ስላለው ያ ተግባራዊ ከሆነ ጠባብ እጩ የመሆን እድል ሊኖራቸው ይችላል።
news-55547005
https://www.bbc.com/amharic/news-55547005
በቤንሻንጉል በተፈጸሙ ጥቃቶች ሰበብ 100 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸው ተገለጸ
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሐምሌ ወር ጀምሮ በተፈጸሙ ጥቃቶች ለደኅንነታቸው በመስጋት ቤት ንብረታቸውን ጥለው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 100 ሺህ መድረሱን የክልሉ መንግሥት ለቢቢሲ አስታወቀ።
የቤንሻንጉል ከልል አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ታረቀኝ ታሲሳ እንዳሉት በቅርቡ በቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ ከተፈጸመውና ጥቃት በኋላ ቀያቸውን ጥለው የሸሹትን ጨምሮ 100 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን አረጋግጠዋል። በክልሉ መተከል ዞን አምስት ወረዳዎች ከሐምሌ ወር 2012 ዓ.ም ወዲህ ዳግም መፈናቀል መከሰቱን የተናገሩት አቶ ታረቀኝ፤ እነሱም ማንኩሽ፣ ድባጢ፣ ቡለን፣ ወንበራ እና ማንዱራ ወረዳዎች መሆናቸውን አመልክተዋል። በዳንጉራ፣ በኩጂ እና አዲስ ዓለም ወረዳዎች ተፈናቃዮች መኖራቸውን የተናገሩት ኃላፊው፤ ከእነዚህ መካከል ስድስ ሺህ የሚሆኑት ጉባ የሚባል አካባቢ፣ 6 ሺህ 800 የሚሆኑት ደግሞ ወንበራ፣ ማንዱራ 12 ሺህ፣ በድባጤ 14 ሺህ፣ በቡለን ደግሞ 51 ሺህ የሚጠጉ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ አብራርተዋል። በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ ታኅሳስ 13/2013 ዓ. ም ንጋት ላይ በታጣቂዎች በተጸፈመ ጥቃት 207 ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን በወቅቱ የአካባቢው ባለስልጣን ለቢቢሲ አረጋግጠው ነበር። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንም በጥቃቱ ስለተገደሉት ሰዎች ዝርዝር ሲገልጽ ከሟቾቹ መካከል አዋቂዎቹ 133 ወንዶችና 35 ሴቶች ሲሆኑ፤ አንድ የስድስት ወር ሕጻንን ጨምሮ 17 ሕጻናት ተገድለዋል ብሎ ነበር። አክሎም የቀሩት 20 ሰዎች ደግሞ አዛውንቶች መሆናቸው ገልጾ ነበር። የቤንሻንጉል ክልል ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በነበሩ ግጭቶች የተነሳ መፈናቀል እንደነበር የገለፁት አቶ ታረቀኝ፣ ነገር ግን እነዚህን ሰዎች እስከ 2012 ድረስ ሙሉ በሙሉ ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን አስታውሰዋል። አሁን ግን ከሐምሌ ወር ጀምሮ በተፈጸሙ ተከታታይ ጥቃቶች በክልሉ የተለያዩ ስፍራዎች ሰዎች ተፈናቅለው የዕለት እርዳታ ጠባቂ መሆናቸውን ተናግረዋል። በክልሉ አምስት ወረዳዎች ተፈናቅለው የመንግሥትን እርዳታ ከሚጠብቁ ግለሰቦች በተጨማሪ፣ ወደ አጎራባች ክልሎች የተሰደዱ መኖራችን ገልፀው ቻግኒ ከተማ ላይ፣ ማንጡራ ቀበሌ እንዲሁም ራንች በሚባል ስፍራ በርካታ ተፈናቃዮች መኖራቸውን መረጃ እንዳላቸው ተናግረዋል። ከተፈናቃዮቹ ውስጥ ሕጻናት፣ ሴቶች እና አረጋውያን እንዳሉበት የሚገልፁት አቶ ታረቀኝ፤ ለሕጻናት እና ለሚያጠቡ እናቶች አልሚ ምግብ እንዲሆን ለተፈናቃይ በነፍስ ወከፍ በወር 15 ኪሎ የእርዳታ እህል እንደሚሰጥ ገልፀዋል። የተፈናቃይ ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን የሚናገሩት ኃላፊው ይህንንም ከክልሉ አቅም በላይ በመሆኑ ለፌደራል አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ማሳወቃቸውን ተናግረዋል። የእርዳታ ሥርጭቱን በተለያዩ አካባቢዎች ለማዳረስ ከስፋቱ እንጻር አስቸጋሪ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን በተቻለ መጠን ለማዳረስ ጥረት እና ርብርብ እየተደረገ መሆኑንም አክለዋል። በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ የተወሰኑ ተፈናቃዮች አሁንም የደኅንነት ስጋት እንዳለባቸው እና በሚሊሻ ብቻ መጠበቃቸው ስጋት ውስጥ እንደጣላቸው የተጠየቁት ኮሚሽነሩ፣ ስጋቱ መኖሩን ገልፀው ነገር ግን ኮማንድ ፖስቱ በቅርብ ርቀት ሆኖ እየጠበቀ ነው ብለዋል። ከክልሉ በተጨማሪ ከፌደራል፣ ከበጎ አድራጎት ድርጅቶች እንዲሁም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመጣን የምግብ እና አልባሳት እርዳታን በፍጥነት ወደ መጠለያ ጣብያዎቹ ለማድረስ መኪኖች መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። በዞኑ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ተፈናቅለው ድጋፍ ለሚፈልጉ ከ100 ሺህ በላይ ዜጎች ክልል አቀፍ የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ሥራ እንደጀመረ መገለፁ ይታወሳል። አቶ ታረቀኝ በዘላቂነት ተፈናቃዮቹ ወደ መጡበት አካባቢ እንዲመለሱ እና እንደሚቋቋሙ ለማድረግም እየተሰራ መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል። ለበርካታ ሰዎች መፈናቀል ምክንያት የሆነውን በቅርቡ የተጸፈመውን ጥቃት ተከትሎ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ ከ40 በላይ ታጣቂዎችን መግደላቸው ተገልጾ የነበረ ሲሆን፤ ከቀናት በፊትም በነዋሪዎች ላይ ጥቃት ሲፈጽሙ ከነበሩት ታጣቂዎች መካከል 17ቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ኮማንድ ፖስት ማስታወቁ ይታወሳል። ከዚህ በተጨማሪ በክልሉ በመተከል ዞን በተለይ በቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ በተፈፀመው አሰቃቂ ግድያ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው ዘጠኝ የክልልና የዞን አመራሮች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የክልሉ ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ለቢቢሲ ገልጾ ነበር።
news-49706065
https://www.bbc.com/amharic/news-49706065
ከወርቅ የተሰራው የመጸዳጃ ቤት መቀመጫ ተሰረቀ
እንግሊዝ ውስጥ በ18 ካራት ወርቅ የተሰራ የመጸዳጃ ቤት መቀመጫ ከብሌንሄይም ቤተ-መንግሥት መሰረቁ ተሰምቷል።
አንድ የዘራፊዎች ቡድን ወደ ቤተ-መንግሥቱ ሰብሮ በመግባት ይህንን ድንቅ የጥበብ ስራ ሰርቀዋል ሲል ፖሊስ አስታውቋል። አገልግሎት ይሰጥ የነበረው ይህ መጸዳጃ ቤት መቀመጫ (ሲንክ) አሜሪካ የሚል ስያሜ ተሰጥቶት የነበረ ሲሆን ጎብኚዎች ወደ ቤተ-መንግሥቱ ሲመጡ መጠቀም ይችሉ እንደነበር ተገልጿል። • በፈረንጅ "ናይት ክለብ" ጉራግኛ ሲደለቅ • እራስን ለማጥፋት ከማሰብ ወደ ሚሊየነርነት መቀመጫው እስካሁን የት እንዳለ ባይታወቅም ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ግን አንድ የ66 ዓመት ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉ ታውቋል። ዘራፊዎቹ የሽንት ቤት መቀመጫውን ነቅለው ሲወስዱ የውሃ ማስተላለፊያው በመፈንዳቱ ክፍሉ በውሃ መሞላቱን ፖሊስ አስታውቋል። ባለፍነው ሐሙስ በቤተ-መንግሥቱ በተከፈተው የስነ-ጥበብ ኤግዚቢሽን ለህዝብ ቀርቦ የነበረው የወርቅ የመጸዳጃ ቤት መቀመጫ (ሲንክ) የተሰራው በጣልያናዊው አርቲስት ማውሪዚዮ ካቴላን ነበር። የእንግሊዙ ታዋቂ የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር ሰር ዊንስተን ቸርችል የተወለዱበትና የ18ኛው ክፍለዘመን ስሪት የሆነው ቤተ-መንግስሥት በዓለም ቅርስነት ተመዝግቧል። ነገር ግን ከስርቆቱ በኋላ ምርመራው እስኪጠናቀቅ በማለት ለጎብኚዎች ዝግ እንዲሆን ተደርጓል። • ድሬ ዳዋ ስለሚገኙት የለገ ኦዳ የዋሻ ሥዕሎች ያውቃሉ? • መጻሕፍትን ማንበብና መጻፍ ለአዕምሮ ጤና ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተሉት የሚገኙት የፖሊስ መርማሪ ጄስ ሚልን እንደገለጹት ከወርቅ የተሰራውን የመጸዳጃ ቤት መቀመጫ ለመስረቅ ዘራፊዎቹ ቢያንስ ሁለት መኪናዎችን ተጠቅመዋል። ''እስካሁን ንብረቱን ማስመለስ ባንችልም የምርመራ ስራችንን አጠናክረን ቀጥለናል። በቅርቡም ውጤት እንደምናገኝና ተጠያቂዎቹን ህግ ፊት እንደምናቀርብ ተስፋ አደርጋለሁ።'' ብለዋል። ከወርቅ የተሰራው የመጸዳጃ ቤት መቀመጫ እ.አ.አ. በ2017 ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በስጦታ መልክ እንዲወስዱት ተጠይቀው ነበር።
57159218
https://www.bbc.com/amharic/57159218
የኬንያ ራስ ተፈሪያኖች ዕፀ ፋርስ ለመንፈሳዊ አገልግሎት እንዲፈቀድላቸው ፍርድ ቤቱን ጠየቁ
የኬንያ ራስ ተፈሪያኖች ዕፀ ፋርስን ለመንፈሳዊ አገልግሎት እንዲጠቀሙበት ይቻል ዘንድ ጉዳዪን ወደ ፍርድ ቤት ወስደውታል።
ጥያቄው የቀረበው ዘ ራስ ተፋሪ ሶሳይቲ ኦፍ ኬንያ በሚባለው ማህበር ነው። ማህበሩ ራሱን እንደ አናሳ አባላት ያሉት የእምነት ቡድን አድርጎ የሚጠራ ሲሆን በአገሪቱ ያሉት ህጎች የሃይማኖታዊ ልምዶቻቸውን በነፃነት እንዳያካሂዱና አባላቱንም በፍራቻ ሸብቦ ይዟቸዋል ብሏል። የራስ ተፈሪያን እምነት ተከታዮች ማስፈራራቶች፣ ማዋከብ እንደሚደርስባቸው የገለፀው ማህበሩ በቤታቸውና በአምልኮ ቦታቸውም እንዲሁ ተደጋጋሚ ፍተሻዎች እንደሚደረግባቸው አስታውቋል። ሻድራክ ዋምቡይና አሌክሳንደር ምዌንድዋ የተባሉት ጠበቆች እንደሚከራከሩት ዕፀ ፋርስ "ቅዱስ እንደሆነና" አማኞችንም "ከፈጣሪ ጋር የሚያገናኛቸው" ነው ይላሉ። ጠበቆቹ የኬንያን ባለስልጣናት የቡድኑ ሃይማኖታዊ መብት ባለማክበርም ወንጅለዋቸዋል። ከሁለት አመታት በፊት የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የራስ ተፈሪያን እንቅስቃሴ እንደ ማንኛውም የሃይማኖት ቡድን ነው ሲል የበየነ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ እንደ ማንኛውም እምነት መብታቸው እንዲከበርም አዟል። ፍርድ ቤቱ ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈው አንድ አባት ልጁ ድሬድ ፀጉሯን እንድትቆረጥ ትምህርት ቤቷ መመለሱን ተከትሎ ነው። አባትየው ልጁ ፀጉሯ ድሬድ የሆነው የራስተፈሪያን እምነት ተከታዮች በመሆናቸው ነው በማለት ትምህርት ቤቱን ከሶ ነበር።
news-45256493
https://www.bbc.com/amharic/news-45256493
ለኡጋንዳዊው ሙዚቀኛና ተቃዋሚ ቦቢ ዋይን በተደረገ ሰልፍ 70 ሰዎች ታሰሩ
የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዎሪ ሙሴቬኒ ተቺና ተቃዋሚ የፓርላማ አባል የሆነው ኡጋንዳዊው ዘፋኝ መታሰርን በመቃወም በርካቶች ከቅዳሜ ጀምሮ በአገሪቱ መዲና ካምፓላ የተቃውሞ ሰልፍ እያካሄዱ ነው።
ቦቢ ዋይን እንደ አውሮፓውያኑ ባለፈው ዓመት በግል ተቃዋሚ ሆኖ ፓርላማ የገባው ዋነኛ የሚባሉ ተቃዋሚ ፓርቲ ተወዳዳሪዎችን በማሸነፍ ነበር እስከ ትናንትና ማለትም የተቃውሞው ሶስተኛ ቀን 70 የሚሆኑ ተቃውሞ ሰልፈኞች በፖሊስ ታስረዋል። ተቃውሞ ሰልፈኞቹ ጎማ በማቃጠል፣ ድንጋይ በመወርወርና መንገድ በመዝጋት ድምፃቸውን ለማሰማት ሞክረዋል። ፖሊስም አስለቃሽ ጭስ ተጠቅሟል ወደ ላይም ጥይት ተኩሷል። የኡጋንዳ ህግ ባለሙያ ማህበረሰብ በአገሪቱ የተቃውሞ ድምፆችን ለማጥፋት እየተደረገ ያለውን አካሄድ እየተቃወመው ነው። . የጅግጅጋ ተፈናቃዮች በአዲስ አበባ ጎዳና ላይ ወድቀዋል . ኢትዮጵያዊቷ የኮፊ አናን ዋና ረዳት . ለህዳሴ ግድብ ግንባታ መዘግየት ምን አይነት መፍትሔዎች እየተሰጡ ነው? ተቃውሞ ሰልፈኞቹ አደባባይ የወጡት በእስር ላይ የሚገኘው ተቃዋሚ ፖለቲከኛው ሮበርት ካያጉላኒ ወይም በሙዚቃ ስሙ የሚታወቀው ቦቢ ዋይን ድብደባ ደርሶበታል በሚል ነው። ሙሴቬኒ ግን በመንግስት ቁጥጥር ስር የሚገኘው ቦቢ ዋይን ምንም አይነት ድብደባም ሆነ አካላዊ ጉዳት እንዳልደረሰበት ተናግረዋል። ባለፈው ወር ቦቢ ዋይን መንግስት ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ላይ ግብር ለመጣል ያወጣውን ህግን በመቃወም ከብዙዎች ጋር ሆኖ ተቃውሞ ሰልፍ ወጥቶ ነበር። የኡጋንዳ ገዥው ፓርቲ ናሽናል ሬዚስታንስ ሙቭመንት(ኤን አር ኤም) በአገሪቱ ፕሬዘዳንት የመሆን እድሜን በ75 የሚገድበውን የህገመንግስት አንቀፅ ለማውጣት ሲደረግ ትልቅ ተቃውሞ የመራው ቦቢ ዋይን ነበር። ቦቢ ዋይን በፓርላማ ድምፃቸውን ከሚያሰሙ ተቃዋሚዎች ግንባር ቀደሙ ነው።
news-47067656
https://www.bbc.com/amharic/news-47067656
ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያዎቹ ምንጫቸው ከወዴት ነው?
ሽጉጥ፣ ጥይት፣ መትረየስ፣ ቦምብ. . . በቦቴ፣ በአይሱዙ ሲዘዋወሩ ተያዙ የሚሉ ወሬዎችን ጆሯችን የተላመደው ይመስላል። የጦር መሳሪያዎች መሃል ሃገር የሚገኙ ከተሞችን ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች በተደጋጋሚ የመያዛቸው ነገር ደግሞ በርካቶችን እያሳሰበ ያለ ጉዳይ ሆኗል።
በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ በቁጥጥር ሥር ዋለ የተባሉ የጦር መሳሪያዎች በቅርቡ እየተስፋፋ ለመጣው የሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ተጠያቂው ማነው? ተብለው የተጠየቁት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እንደሻው ጣሰው፤ "የሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውሩ የሚከናወነው ለውጡን በማይደግፉ አካላት ነው" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ኮሚሽነር እንደሻው ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውሩ አሁን ያለበትን ደረጃ ሲያስረዱ ''በአንዳንድ የሃገሪቱ ስፍራዎች የጦር መሳሪያ ዝውውሩ እንደጨመረ እና በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ በተደረገው ቁጥጥር የዝውውር መጠኑ ቀንሷል" ይላሉ። • ሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር መበራከት ምንን ያመለክታል? በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው ሕገ-ወጥ መሳሪያ ዝውውር ምንጩ አንድ ብቻ ሳይሆን በርከት ያለ እንደሆነ ይታመናል። በመንግሥት እጅ የነበሩ ጦር መሳሪያዎችም በዚህ ውስጥ እንደሚገኙ ኮሚሽነሩ ያመለክታሉ ''ሕገ-ወጥ መሳሪያዎች ከውጪ ብቻ አይደለም የሚመጡት። ሃገሪቱ ውስጥ ካሉ የመሳሪያ ግምጃ ቤቶች ውስጥ በተለያዩ ኃይሎች ተዘርፈው የተወሰዱም ይገኙበታል።'' እንደ ኮሚሽነሩ ከሆነ፤ ከሃገር ውስጥ ከተዘረፉ መሳሪያዎች ውጪ ከደቡብ ሱዳን፣ ከጅቡቲ እና ከሶማሊያ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ሕገ-ወጥ መሳሪያዎችም መጠናቸው ቀላል የሚባል አይደለም። • በምዕራብ ኦሮሚያ የኦነግ ጦር አዛዥ ስለወቅታዊው ሁኔታ ምን ይላል? የሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመግታት ከህብረተሰቡ ጋር በተቀናጀ መልኩ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ የሚናገሩት ኮሚሽነር እንደሻው ጣሰው፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ወደ ስልጣን መምጣትን ተከትሎ የጦር መሳሪያ ዝውውር መጨመሩን ያምናሉ። ኮሚሽነሩ ለዚህ እንደ ማሳያ የሚያቀርቡት ''ከለውጡ በፊት የነብስ ወከፍ የጦር መሳሪያ ዝውውር እንደነበረ መረጃዎች ያሳያሉ። አሁን ግን ከነብስ ወከፍ መሳሪያዎች አለፍ ብሎ መትረየስና ቦምብን የመሳሰሉ የቡድን ጦር መሳሪያዎች በሕገ-ወጥ ዝውውር ውስጥ እየታዩ ነው'' ይላሉ። በዚህ የጦር መሳሪያ ዝውውር ውስጥ በሽብር ተግባር ላይ እንደተሰማራው አል-ሻባብን አይነት የውጪ ቡድኖች ከተሞች ውስጥ ጉዳት ለማድረስ ባላቸው ፍላጎት የተነሳ እጃቸው ሊኖር ይችላል የሚሉት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ከዚህ በተጨማሪ "በጦር መሳሪያ ንግድ መክበር የሚፈልጉ ግለሰቦችም ለጦር መሳሪያ ዝውውሩ መጨመር ተጠያቂ ናቸው" ይላሉ። • ወደ ካናዳ መሄድ አስበዋል? ከአጭበርባሪዎች ይጠንቀቁ በተለያዩ ቦታዎች የሚያጋጥሙት አለመረጋጋቶች ዜጎች ደህንነት እንዳይሰማ እያደረገ ሲሆን፤ ይህም የጦር መሳሪያ ፍላጎት እንዲጨምር እንዳደረገ ይታመናል። "በዜጎች ላይ እና በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ላይ ጉዳት ለማድረስ ፍላጎት በመኖሩ የጦር መሳሪያ ፍላጎት መጨመሩን" ኮሚሽነር እንደሻው ይናገራሉ። የፀጥታ ጉዳዮች ተንተኝ የሆኑት አቶ ዳደ ደስታ ደግሞ በሃገሪቱ ውስጥ የሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር የተበራከተው በኢትዮጵያ ያለውን የፖለቲካ እና የመዋቅር ለውጥ ተከትሎ የወንጀል መከላከል መዋቅሮች በመዳከማቸው እንደሆነ ይጠቁማሉ። • ሳዑዲ የፀረ-ሙስና ዘመቻዬን አጠናቀቅኩ አለች አቶ ዳደ ከዚህ በተጨማሪ በአንዳንድ ክልሎች የሚሰራጩ መረጃዎች ለሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር መበራከት ምክንያት ሆነዋል ይላሉ። ለዚህም እንደምሳሌ የሚያስቀምጡት መሳሪያ ማስመዝገብ ይቻላል ተብሎ በስፋት መወራቱ ሰዎች የጦር መሳሪያ እንዲገዙ እንዳበረታታ ያምናሉ። ''በተጨማሪም አሁን ካለንበት ተጨባጭ ሁኔታ በመነሳት በግለሰቦች ዘንድ ስጋት አለ። በዚህም የጦር መሳሪያ የመታጠቅ እሽቅድድም አለ። የጦር መሳሪያ መታጠቅ ፍላጎት የሌለው ሰው እንኳ ቢሆን በዙሪያው ያለ ሰው መሳሪያ ይዞ ሲያይ እሱም መሳሪያ ለመያዝ ይፈልጋል'' ሲሉ ያስረዳሉ። በሃገሪቱ ውስጥ በስፋት የሚዘዋወሩት የጦር መሳሪያዎች ምንጭን በተመለከተ የፀጥታ ጉዳዮች ተንታኙ አቶ ዳደ፤ ''የጦር መሳሪያ ከየት መጣ ብለን መጠየቅ አንችልም። ምክንያቱም የምንገኝበት ቀጠና ለረዥም ዓመታት ከፍተኛ የሆነ የእርስ በስርስ እና ደንበር ዘለል ጦርነቶች ሲካሄድበት የነበረ ቀጠና ነው'' በማለት በርካታ ምንጮች እንዳሉ አመልክተዋል። በየእለቱ ከሚወጡት ዘገባዎች አንጻር ከአራቱም የሃገሪቱ አቅጣጫዎች ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ እንቅስቃሴ እንዳለ አመልካቾች ናቸው። በፀጥታ ኃይሎች የተያዙት የጦር መሳሪያዎች መጠን ከፍተኛ ቢሆንም፤ ሳይያዙ ወደ ተለያዩ ሰዎች እጅ የገቡት ቁጥር ምን ሊያስከትሉ እንደሚችሉ አለመታወቁ በርካቶችን ስጋት ላይ ጥሏል።
news-56080924
https://www.bbc.com/amharic/news-56080924
አዲሷ የዓለም ንግድ ድርጅት አለቃ ስለ ኮቪድ ክትባት ማስጠንቀቂያ ሰጡ
አዲሷ የዓለም ንግድ ድርጅት ኃላፊ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የተከሰተውን ወረርሽኝ ለመፍታት ክትባትን መደበቅ መወገድ አለበት፡፡
ንጎዚ ኦኮንጆ-ኢዊላ “የበለፀጉ አገራት ህዝባቸውን እየተከተቡ እና ድሃ አገራት መጠበቃቸው” መቆም አለበት ብለዋል፡፡ ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በርካታ ሃገራት በድንበራቸው ውስጥ የሚሠሩ ክትባቶች ወደ ውጭ እንዳይላክ ለመከላከል ሞክረዋል፡፡ ዶ/ር ኦኮንጆ-ኢዊላ ክልከላው በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚደረገውን የመከላከል ሥራ እንደሚያደናቅፍ ተናግረዋል፡፡ “የበሽታው ወረርሽኝ ተፈጥሮ እና የተለያየ ዓይነት ዝርያዎች በመኖራቸው እያንዳንዱ ሀገር ህዝቡን በመከተብ የመከላከል እርምጃ እስካልወሰደ ድረስ ማንም ሀገር ደህንነት እንደማይሰማው ያደርገዋል” ብለዋል፡፡ የክትባት አለቃ እስከ ባለፈው ዓመት ማብቂያ ድረስ ዶ/ር ንጎዚ ኦኮንጆ-ኢዊላ በዓለም ዙሪያ የክትባት ተደራሽነትን ለማሳደግ ያለመው ዓለም አቀፍ የክትባት ጥምረትን (GAVI) ይመሩ ነበር። አሁን የዓለም ንግድ ድርጅት በዚህ ረገድ የሚከናወኑ ወሳኝ ሥራዎች እንዳሉ ይገልጻሉ፡፡ ብዙ መድሃኒት አምራቾችን በማበረታታት ክትባቱንማምረት እንዲቻል የዓለም ንግድ ድርጅት በአዕምሯዊ ንብረት ላይ ያለውን አቋም እንዲያለዝብ የሚጠይቁ ወገኖች አሉ። ዶ/ር ንጎዚ ኦኮንጆ-ኢዊላ “አንዳንድ ታዳጊ አገራት ነፃ እንዲሆኑላቸው ሲጠይቁ ያደጉ አገራት ግን ይህ በአዕምሯዊ ንብረት ላይ እንቅፋት ሊሆን ይችላል ሲሉ ይሰማቸዋል” ብለዋል፡፡ እሳቸው ግን “ሦስተኛው አማራጭ ደግሞ የአዕምሯዊ ንብረት ጉዳዮች በአግባቡ መያዛቸውን እያረጋገጡ በቂ አቅርቦቶች እንዲኖሩ ለአምራቾች ፈቃድ መስጠት ይቻል” ይላሉ፡፡ የኦክስፎር ድአስትራዜኔካ ክትባት በሰጠው ፈቃድ ተጠቅሞ የህንዱ ሴረም ኢንስቲትዩት ክትባት እያመረተ መሆኑን በምሳሌነት ይነሳል፡፡ አዲሷን የዓለም ንግድ ድርጅት መሪን የሚገጥም እጅግ አንገብጋቢ ፈተና ወረርሽኙ ቢሆንም እሱ ብቻ ግን አይደለም፡፡ ህግጋቱ ጊዜ ያለፈባቸው እና ራሱንከዓለም ኢኮኖሚ ጋር ለማላመድ ቀርፋፋ ነው ብለው በሚያምኑ በርካታ አገራት ዘንድ ድርጅቱ ጠቃሚ መሆኑን ለማሳየት ትግል ላይ ይገኛል። ከቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ድጋፍ ባለማግኘቱ ከተጓተተው የምርጫ ሂደት በኋላ ዶ/ር ንጎዚ ኦኮንጆ-ኢዊላ አዲሱ ኃላፊነት ምን እንደሆነ ያስታውሳሉ። “የመጀመሪያዋ ሴት እና የመጀመሪያዋ አፍሪካዊ በመሆኔ እኮራለሁ” ብለዋል፡፡ በዓለም ባንክ ኃላፊነት በሁለተኛ ደረጃ ላይ በነበሩበት ወቅት ያገኙትን ዝና እንዲሁም የናይጄሪያ ፋይናንስ ሚኒስትር በመሆን ሃገራቸው ከዓለም አቀፍ ዕዳዎች ላይ ከፍተኛ ቅናሽ ማድረጋቸውን ለመቀጠል ይፈልጋሉ፡፡ “የዓለም ንግድ ድርጅት ህጎችን በማዘመን የ 21 ኛው ክፍለዘመን እውነታዎችን በማሟላት በአባላቱ መካከል በተሰበረውን የመተማመን እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ብዙ መሠራት ያለበት ጉዳይ” አለ ይላሉ፡፡ የኮሮናቫይረስ ተግዳሮቶችን መቋቋም ከተቻለ እነዚያ “ትናንሽ ሂደቶች፣ ቀደምት ድሎች እና ስኬቶች መተማመንን ለመፍጠር እና ትልቁን ማሻሻያ እንዲደረግ ያስችላሉ” ብለዋል፡፡ የአሜሪካ-ቻይና የንግድ ጦርነት የዓለም ንግድ ድርጅት የማስፈፀሚያ ስልቶች ስለሌሉት የአሜሪካ-ቻይና የንግድ ጦርነት ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር የታገለበት ሌላኛው ጉዳይ ነው፡፡ ባለፈው ዓመት ግን የአሜሪካ ታሪፎች ከዓለም አቀፍ የንግድ ህጎች ጋር የማይጣጣሙ ናቸው የሚል ብይን ሰጥቷል፡፡ ዶ/ር ንጎዚ ኦኮንጆ-ኢዊላ “እነዚህን ችግሮች ለመፍታት አሜሪካም ሆነ ቻይና አንድ ላይ እንዲሰባሰቡ ለማድረግ በጣም አጋዥ ልንሆን እንችላለን” ብለዋል፡፡ የዓለም ንግድ ድርጅት በብዙ መስኮች መሻሻል ለማምጣት የተቸገረበት አንዱ ምክንያት ውሳኔ የሚሰጠው በ164 አባል ሃገራቱ ውሳኔ በመሆኑ ነው፡፡ ውሳኔዎች በጋራ መግባባት ላይ ሳይሆን በአብላጫ ድምፅ መወሰን ይኖርባቸዋል ወይ ተብለው ለተጠየቁት ዶ/ር ኦኮንጆ-ኢዊላ “ይህ የውሳኔ አሰጣጥ ዘይቤ ፈጠራዎችን ወይም ለአባላቱ የሚወሰዱ እርምጃዎችን የሚያደናቅፍ መሆን የለበትም” ብለዋል፡፡
news-55445101
https://www.bbc.com/amharic/news-55445101
ሕዋ ላይ እንዴት ለአንድ ዓመት ይኖራል?
ከአራት ዓመት በፊት ከናሳ በጡረታ የተገለለው ስኮት ኬሊ ጠፈርተኛ ነው። ለአንድ ዓመት ያህል ሕዋ ላይ ኖሯል።
ጠፈርተኛ ስኮት ኬሊ ለአንድ ዓመት ያህል ሕዋ ላይ ኖሯል። ጠፈርተኛው 'ኢንዱራንስ' የተባለ መጽሐፍ አሳትሟል ። እአአ 2015 ላይ በሩስያው መንኮራኩር ውስጥ ከነበሩት አንዱ ነበር። ከሩስያውያኑ ጌኔዲ ፓዳካላ እና ሚካሂል ኮርኒንኮ ጋር ሳሉ፤ አንድ ብረታማ ቁስ በሰከንድ 14 ኪሎ ሜትር እየተምዘገዘገ ወደ መንኮራኩራቸው እየተጠጋ መሆኑ ተነገራቸው። መንኮራኩራቸው ከተመታ በሕይወት የመትረፍ እድል አይኖራቸውም። ስኮት እንደዚህ ያለ ለሕይወት የሚያሰጋ ነገር ሲገጥመው የመጀመሪያው አይደለም። "አደጋ ቢደርስ ኖሮ ሦስታችንም በሚሊሰከንዶች ጊዜ ውስጥ እንደ አቶም በሚሊዮን አቅጣጫዎች እንበተን ነበር" ይላል። የሕዋ ላይ ኑሮ ከምድር ጋር የሚያመሳስለው ጥቂት ነገር አለ። በቪድዮ መደዋወል፣ ማጽዳት ወዘተ. . . በአብዛኛው ግን ሕዋ ፈታኝ ነው። ስኮት ከ2007 አንስቶ ሦስት ጊዜ ወደ ሕዋ ተጉዟል። እውቅና ያተረፈው ግን ከ2005 እስከ 2016 በሕዋ ባደረገው ቆይታ ነው። ከሱ በፊት ረዥም ጊዜ ሕዋ ላይ የኖረው አሜሪካዊ ጠፈርተኛ ማይክል ሎፔዝ 100 ቀናት ቆይቷል። ስኮት ይህንን ክብረ ወሰን ሰብሯል። ሌላ ስኮት የሚታወቅበት ነገር መንታ ወንድሙ ማርክ ነው። እንደሱው ናሳ ውስጥ ይሠራል። ስኮት ሕዋ ላይ አንድ ዓመት ሲኖር አንድም ቀን ወደ መሬት ለመመለስ እንዳልጓጓ ይናገራል። "ከአንድ ዓመት በላይ የሚያስቆየኝ ምክንያት ባገኝም እዛው እሆን ነበር" ነው የሚለው። አንዳንድ ጠፈርተኞች ሕዋ ላይ ያለው የብቸኛነት ኑሮ የሥነ ልቦና ጫና ያሳድርባቸዋል። መንታ ወንድሙ ማርክ እንደሱው ናሳ ውስጥ ይሠራል። ስኮት ግን "ዋናው ነገር ራስን ማዝናናት መቻል ነው። ለሁሉም ሰው ቀላል ነው ማለት ግን አይደለም" ብሎ ያምናል። ለሱ ከሕዋ ኑሮ ከባዱ እንደልብ ከመንኮራኩር መውጣት አለመቻል ነው። በጠባብ ቦታ ከሰዎች ጋር ለረዥም ጊዜ አብሮ መኖርም ቀላል አይደለም። በሌላ በኩል ደግሞ ከሌሎች ጠፈርተኞች ጋር ጥብቅ ወዳጅነት ይፈጠራል። ስኮት ሕዋ ላይ አብረውት ከኖሩ ጠፈርተኞች ጋር ምድር ሲመለስም በወዳጅነት ቀጥሏል። ዓለም አቀፉ የሕዋ ተቋም የአገሮች ትብብር ተምሳሌት እንደሆነ ይናገራል። ሕዋ ላይ ሳለ ከሥራ በተጨማሪ ዘና ይልም ነበር። በተለይም የዝንጀሮ ልብስ መልበስ በጣም ያዝናናዋል። የዝንጀሮ መልክ ያለውን ልብስ የሰጠው ናሳ የሚሠራው መንታ ወንድሙ ነው። ወንድማማቾቹ ያደጉት ኒው ጀርሲ ሲሆን፤ ቤተሰቦቻቸው ፖሊሶች ናቸው። ስኮት እና ማርክ ልጅ ሳሉ ጀምሮ አደገኛ ነገር መሞከር ይወዳሉ። በተደጋጋሚ ጉዳት ይደርስባቸውም ነበር። ትምህርት ቤት ሲገቡ ማርክ ጎበዝ ሆነ። ስኮት በተቃራኒው ዝንጉ ነበር። ኮሌጅ ሲገቡ ማርክ ስኮትን ይመክረው እንደነበር ያስታውሳል። ስኮት መጀመሪያ ላይ የውጊያ አውሮፕላን አብራሪ ሆነ። በመጀመሪያው የገልፍ ጦርነት ወቅት ተሠማርቶም ነበር። 1996 ላይ ከወንድሙ ጋር ናሳን ተቀላቀለ። ወንድማማቾቹ በአንድ መንኮራኩር አብራሪነት ተሳትፈዋል። 2003 ላይ ኮሎምቢያ የተባለ መንኮራኩር ወደ ምድር ሲመለስ ተከስክሶ ሰባት ጠፈርተኞች ሞተዋል። ያ አጋጣሚ የመንኮርኩር በረራ አስጊነትን ያሳየ ነበር። የናሳ የደህንነት ፖሊሲም ተተችቷል። ያኔ ከሞቱት ጠፈርተኞች አንዱ የስኮት ጓደኛ ነው። ቢቢሲ ቃለ መጠይቅ ሲያደርግለት ዓለም አቀፍ የመንኮራኩር ደህንነት ጉባኤ ላይ ንግግር ለማድረግ ሲዘጋጅ ነበር። ስኮት ለአንድ ዓመት ወደ ሕዋ ሊጓዝ እንደሆነ ሲነገር ትኩረታቸው ከተሳቡ መካከል የዘረ መል ተመራማሪዎች ይገኙበታል። አንድ ሰው ዘለግ ላለ ጊዜ ሕዋ ላይ ሲኖር የሚያድርበትን ተጽዕኖ ለመረዳት፤ ስኮትን እና መንታ ወንድሙ ማርክን ለማነጻጸር ነበር ተመራማሪዎቹ ያሰቡት። የስኮትን ሰውነት ምድር ላይ ከቀረው ወንድሙ ጋር በማወዳደር የሥነ ልቦና፣ በሽታ የመከላከል እና የዘረ መል መዋቅር ለውጡን ገምግመዋል። የስኮት ዘረ መል መዋቅር ላይ የታየው ለውጥ ለጨረራ መጋለጡ ያሳደረበትን ተጽዕኖ ያሳየ ነበር። ስኮት ከሕዋ ሲመለስ የክሮሞዞም፣ የደም፣ የሰውነት መጠን ለውጥም አሳይቷል። ወደ መሬት ከተመለሰ በኋላ ግን ወደ ቀደመው ተክለ ሰውነቱ ተመልሷል። ስኮት ከሕዋ ከተመለሰ አራት ዓመታት አስቆጥሯል። በቆይታው ለውጥ ያስተዋለው እይታው እንደሆነ ይናገራል። ተመራማሪዎች መንታዎቹ ላይ የሠሩት ጥናት፤ ሰዎችን ወደ ማርስ ለመላክ ለተያዘው እቅድም መረጃ ሰጥቷል። ከመሬት 34 ሚሊዮን ማይል ወደምትርቀው ማርስ ተጉዞ ወደ ምድር ለመመለስ ዘጠኝ ወራት ይወስዳል። ጠፈርተኞች ለጨረራ የሚጋለጡት በአስር እጥፍ ስለሆነ ለካንሰር ወይም ለሌላ ህመም ሊጋለጡ እንደሚችሉ ይሰጋል። "ያለው አማራጭ ራስን መከላከያ መንገድ ማግኘት ወይም በፍጥነት ወደ ማርስ መድረስ ነው። ካልሆነ ግን ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል አምኖ መጓዝ ነው" ይላል ስኮት። አሁን ከናሳ ጡረታ ወጥቶ ዴንቨር ውስጥ ከባለቤቱ ጋር ይኖራል። በተለያዩ መድረኮች ስለ ሕዋ ቆይታው ንግግር በማድረግ እና በመጻፍ ጊዜውን ያሳልፋል። ከዚህ በኋላ ምናልባትንም ወደ ሕዋ የሚላክ የሮኬን መንኮራኩር አብራሪ ከተፈለገ ስኮት ይጠራ ይሆናል።
news-55876531
https://www.bbc.com/amharic/news-55876531
የፑቲን እንደሆነ ሲነገር የነበረው ቤተ መንግሥት "ባለቤት ነኝ" የሚል ሰው ተገኘ
የሩሲያ ቢሊየነር አርካዲ ሮተንበርግ በብላክ ሲ የሚገኙው ግዙፉ ቤት የኔ እንጂ የቭላድሚር ፑቲን አይደለም አሉ፡፡
ቢሊየነሩ ይህን ያሉት ይህ ግዙፍና ቅንጡ ቤት የቭላድሚር ፑቲን የግል መንደላቀቂያቸው ነው የሚል ዜና መውጣቱን ተከትሎ በሰጡት ማስተባበያ ነው፡፡ ከሳምንት በፊት በአሌክሲ ናቫልኒ የተለቀቀ አንድ የቪዲዮ ሪፖርት ይህን እጅግ ቅንጡና እጅግ ግዙፍ መኖርያ ቤት ንብረትነቱ የፑቲን እንደሆነ የሚገልጽ ነበር፡፡ ቪዲዮው በመላው ሩሲያ መነጋገርያ ከመሆኑም በላይ በአጭር ጊዜ ውስጥ መቶ ሚሊዮን ሰዎች ተመልክተውታል፡፡ የቪዲዮውን መውጣት ተከትሎም ተቃውሞዎች ተበራክተው ነበር፡፡ ፑቲን ይህን ዘገባ ‹ተልካሻ› ሲሉ ነበር ያጣጣሉት፡፡ ቪዲዮውንም ‹በጣም ደባሪ› ሲሉ ተሳልቀውበት ነበር፡፡ ቭላድሚር ፑቲን ለእንዲህ ዓይነት ትችቶች በቀጥታ ምላሽ የመስጠት ዝንባሌ እምብዛምም የላቸውም፡፡ ሩሲያዊው ቢሊየነርና የፑቲን የቅርብ ወዳጅ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ሮተንበርግ ትናንት ቅዳሜ ነው ወደ ሚዲያ ወጥተው ‹ቤተ መንግሥቱ የኔ ነው፤ የፑቲን አይደለም› ብለዋል፡፡ ይህ ግዙፍ መኖርያ ቤት ግንባታው በጥቂት ዓመታት ውስጥ ከተጠናቀቀ በኋላ አፓርትመንት ሆቴል እንዲሆን ፍላጎት አለኝ ሲሉም ተናግረዋል፡፡ ይህ የቢሊየነሩ ማስተባበያ የመጣው በሩሲያ የፕሬዝዳንት ፑቲን ተቺዎች ላይ የሚደርሰው እስርና እንግልት በተስፋፋበት ወቅት ነው፡፡ ይህ ግዙፍ ቤተ መንግሥት ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያወጣ ይገመታል፡፡ የዚህ ቤተመንግሥት ቪዲዮ በሩሲያ የማኅበራዊ ሚዲያዎች ትልቅ መነጋገርያ ከሆነ በኋላ ተቃውሞዎች ፈንድተው ከ4ሺ በላይ ሰዎች ታስረዋል፡፡ የብዙዎቹ ሰልፈኞች ጥያቄ ተመርዞ በተአምር ሕይወቱ የተረፈችው የፑቲን ተቺ አሌክሴ ከእስር እንዲፈታ የሚጠይቁ ነበሩ፡፡ አሌክሴ ናቫልሪል በሩሲያ ከተመረዘ በኋላ በርሊን ሕክምና ተደርጎለት ወደ ሩሲያ በድፍረት ሲመለስ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ይታወሳል፡፡ ከአሌክሴ ጋር ግንኙነታ አላቸው የተባሉ ሚዲያዎችና ግለሰቦች ተለቅመው የታሰሩ ሲሆን በሰብአዊ መብት ዙርያ የሚሰሩ በርካታ ድርጅቶችም ተዘግተዋል፡፡ በሩሲያ ዛሬ እሑድም ተቃውሞ ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ቢሊየነሩ አርካዴ ሮተንበርግ በሩሲያ እውቅ ሲሆን የፑቲን ቀኝ እጅ እንደሆነም ይነገርለታል፡፡ ቢሊየነሩ በተለይ ድልድይና የጋዝ ቧንቧ መስመሮችን በመገንባት የሚታወቅ ግዙፍ ተቋራጭ ኩባንያ ባለቤት ነው፡፡ ሮተንበርግ የቭላድሚር ፑቲን የቅርብ ወዳጅ ብቻም ሳይሆን አብሮ አደግ ናቸው፡፡ በልጅነታቸውም ጁዶ ስፖርት አብረው ይጫወቱ ነበር ተብሏል፡፡ ቢሊየነሩ አሜሪካ 2014 በሩሲያ ባለሃብቶች ላይ በጣለችው ማእቀብ ስሙ የተካተተ ሰው ነው፡፡ ተቺዎች ይህ ቢሊየነር ‹ቤተ መንግሥቱ የኔ እንጂ የፑቲን አይደለም› እንዲል የተደረገው በራሳቸው በፑቲን ትእዛዝ ሊሆን ይችላል ብለው ይጠረጥራሉ፡፡
news-54094329
https://www.bbc.com/amharic/news-54094329
የትግረይ ምርጫ፡ በትግራይ ክልላዊ ምርጫ ህወሓት ማሸነፉ ተገለፀ
በትግራይ ክልል ጳጉሜ 4/2012 ዓ.ም በተደረገው ክልላዊ ምርጫ ህወሓት በአብላጫ ድምጽ ማሸነፉ ተነገረ።
ኮሚሽነር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም የክልሉ የምርጫ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሙሉ ወርቅ ኪዳነማርያም በተለይ ለቢቢሲ እንደገለፁት ህወሓት ከአጠቃላይ የመራጮች ድምጽ በአብላጫነት አሸናፊ ሆኗል። በዚህም የተነሳ የክልሉ ምክር ቤት ካለው 190 ውስጥ 152ቱ በህወሓት የሚያዝ ሲሆን 38ቱ ደግሞ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ይከፋፈላል ተብሏል። ህወሓት የምክር ቤቱን መቀመጫ 80 በመቶ (98.2) ሲይዝ በቅርቡ የክልሉ ምክር ቤት ባደረገው የውክልና ማሻሻያ ውሳኔ መሰረት ቀሪው 20 በመቶ ደግሞ የክልሉ ምክር ቤት በሚወስነው መሰረት በምርጫ ተፎካካሪ ለነበሩ ፓርቲዎች ይከፋፈላል ተብሏል። በምርጫው ባይቶና፣ ትግራይ ነጻነት፣ ሳልሳይ ወያነ እንዲሁም አሲምባ እንደ ቅደም ተከተላቸው ድምጽ ማግኘታቸው ተገልጿል። ፓርቲዎቹ በቅደም ተከተል ያገኙት ድምፅ፦ በክልሉ ምርጫ ክልሉን የሚያስተዳድረውን ህወሓትን ጨምሮ 5 ፓርቲዎች መሳተፋቸው ይታወሳል። በዚህ ምርጫ 190 መቀመጫዎች ላሉት ምክር ቤት 625 እጩዎች ለመወዳደር ቀርበው የነበረ ሲሆን፤ ከ2.7 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ድምጽ ለመስጠት ተመዝግቦ ከ97 በመቶ በላይ ሕዝብ ድምጽ መስጠቱን የትግራይ ምርጫ ኮሚሽን አመልክቷል። በኢትዮጵያ በነሐሴ መጨረሻ ላይ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው ምርጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ ከተላለፈ በኋላ በትግራይ በተናጠል የሚካሄደው ምርጫ ሕገ ወጥና ተቀባይነት የሌለው ነው በማለት የፌዴሬሽን ምክር ቤት መወሰኑ ይታወሳል።
news-42658951
https://www.bbc.com/amharic/news-42658951
ፌስቡክ በመረጃ ፍሰት ላይ ማሻሻያ ሊያደርግ ነው
ፌስቡክ የዜና መረጃዎችን የሚሰጥበትን አካሄድ በማሻሻል ከንግድ ድርጅቶች፣ ከተቋማትና ከመገናኛ ብዙሃን ለሚመጡ መረጃዎች የሚሰጠውን ትኩረት ዝቅ ሊያደርግ ነው።
ለውጡ ከፍተኛ መሆኑን በዘርፉ ያሉ እየገለጹ ነው የፌስቡክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማርክ ዙከርበርግ በገጹ ላይ እንዳስነበበው በቤተሰብ እና በጓደኛሞች መካከል ውይይት ለሚፈጥሩ ይዘቶች ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣል። ፌስቡክን የሚጠቀሙ ድርጅቶች የሚለቋቸው መረጃዎች ያላቸው ተደራሽነት በዚህ ምክንያት እንደሚቀንስ ፌስቡክ አስታውቋል። ይህ ለውጥ በመጪዎቹ ሳምንታት ተግባራዊ ይደረጋል። "የንግድ ድርጅቶች፣ መገናኛ ብዙሃን እና ሌሎች ተቋማት የሚያወጧቸው መረጃዎች የግል መረጃዎችን በማሳነስ የግለሰቦችን የፌስቡክ ገጽ እየሞሉት ነው፤ የሚል አስተያየት ከተጠቃሚዎች ስለደረስን ነው ግለሰቦች ብዙ ትስስር እንዲኖራቸው ለመስራት የወሰነው" ሲል ዙከርበርግ ጽፏል። ከመሰል ድርጅቶች የሚመጡ ይዘቶች እንዲተዋወቁ የሚፈለግ ከሆነም ህብረተሰቡን የሚያወያዩ ሊሆኑ ይገባል ሲል ይገልጻል። ውይይት የሚያጭሩ የቀጥታ የፌስቡክ ስርጭቶች እንደምሳሌ ተጠቅሰዋል። "ይህንን ለውጥ በማድረግ ሰዎች ፌስቡክ ላይ የሚቆዩበት ጊዜ እና አንዳንድ የተሳትፎ መለኪያዎች እንደሚቀንሱ እጠብቃለሁ" ብሏል። "ሆኖም በፌስቡክ ላይ የምታሳልፉት ጊዜ የበለጠ ውጤታማ ይሆናል" ሲል ዙከርበርግ አስታውቋል። እ.አ.አ. በ2018 ፌስቡክን "በመጠገን" ተጠቃሚዎችን ከጥቃት ለመጠበቅ እና በገጹ ላይ የሚኖራቸውን ቆይታ ውጤታማ ለማድረግ እንደሚሰራ ቀደም ሲል ዙከርበርግ አስታውቆ ነበር። ፌስቡክን ከአንዳንድ ሃገራት እንደሚጠብቅም ቃል ገብቶ ነበር። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሩሲያን ጨምሮ አንዳንድ አካላት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያሉትን ይዘቶች ለመቀየር ሞክረዋ። የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ባልደረባ ሆኑት ላውራ ሃዛርድ ኦዌን "በጣም ጠቃሚ ለውጥ ነው" ብለዋል። "አታሚዎች ላይ ይበልጥ ተጽዕኖ ይኖረዋል። በገጻችን ላይ የምንመለከታቸው ዜናዎች ቁጥር አነስተኛ ነው የሚሆነው" ብለዋል። ሆኖም ፌስቡክ የትኛዎቹን መረጃዎች ቅድሚያ በመስጠት ለመልቀቅ ዝግጁ እንደሆነ ግልጽ አይደለም ሲሉ ገልጸዋል።
53407894
https://www.bbc.com/amharic/53407894
የትራምፕ አስተዳደር የውጪ አገር ተማሪዎችን ወደ አገራቸው የመመለስ እቅድን ውድቅ አደረገ
የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በኮሮናቫይረስ ወረርሽን ሳቢያ ትምህርታቸውን በበይነ መረብ አማካኝነት የሚከታተሉ የውጪ አገር ተማሪዎችን ወደ አገራቸው የመመለስ እቅድን ውድቅ ማድረጉ ተገለፀ።
እቅዱ ውድቅ የተደረገው ፖሊሲው ከተዋወቀ ከአንድ ሳምንት በኋላ ነበር። ባለፈው ሳምንት የውጪ አገር ተማሪዎች በአካል ቀርበው ትምህርታቸውን መከታተል የማይችሉ ከሆነ አሜሪካ ውስጥ እንዲቆዩ እንደማይፈቀድላቸው ተነግሯቸው ነበር። በወረርሽኙ ሳቢያ መጋቢት ወር ላይ የትምህርት አጋማሽ አጠናቀው ወደ አገራቸው ተመልሰው የነበሩ ተማሪዎችም ትምህርታቸው በበይነ መረብ እየተሰጠ በመሆኑ ወደ አሜሪካ ለመመለስ አይፈቀድላችሁም ተብለው ነበር። የአገሪቷ የስደተኞችና ጉምሩክ የሚመለከተው ኤጀንሲም በበኩሉ ሰዎች ይህንን ሕግ የማያከብሩ ከሆነ ወደ አገራቸው ተጠርንፈው እንደሚመለሱ ማስታወቁ ይታወሳል። ይህንን ተከትሎም የማሳቹስቴትስ የቴክኖሎጂ ተቋም እና ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ መንግሥት ተማሪዎቹን ለመመለስ የያዘውን እቅድ ተከትሎ መንግሥትን ከሰው ነበር። በማሳቹስቴትስ የዲስትሪክት ዳኛ አሊሰን ቡሮንስ በጉዳዩ ላይ ስምምነት ላይ መደረሱን ተናግረዋል። ስምምነቱ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በተከሰተበት መጋቢት ወር ላይ ተግባራዊ የተደረገውና የውጭ አገር ተማሪዎች ትምህርታቸውን በበይነ መረብ እንዲከታተሉና በአገሪቷም ሕጋዊ ሆነው እንዲቆዩ መፈቀዱን ኒው ዮርክ ታይምስ ዘግቧል። በየዓመቱ በርካታ ቁጥር ያላቸው የውጪ አገር ተማሪዎች ለትምህርት ወደ አሜሪካ ይጓዛሉ። ለዩኒቨርሲቲዎችም ከፍተኛ የሆነ ገቢ ያስገኛሉ። ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ የቫይረሱ ሥርጭት መስፋፋቱን ተከትሎ ተማሪዎች ለአዲሱ የትምህርት ዘመን ወደ ትምህርት ገበታቸው ሲመለሱ ትምህርቱ በበይነ መረብ አማካኝት እንደሚሰጥ አስታውቋል። የማሳቹስቴትስ የቴክኖሎጂ ተቋምም ልክ እንደሌሎቹ የትምህርት ተቋማት በበይነ መረብ ትምህርት መስጠቱን እንደሚቀጥል ገልጿል።
news-50597494
https://www.bbc.com/amharic/news-50597494
ተሰናባቹ ኡናይ ኤምሪን ሊተኳቸው የሚችሉ 7 አሰልጣኞች
አርሰናል ክለቡን ለ18 ወራት ያሰለጠኑት ስፔናዊው ኡናይ ኤምሪን ከስራቸው አሰናብቷል።
ፓሪሴንት-ጀርሜይን ጋር የፈረንሳይ ሊግ ዋንጫ እና ከሲቪያ ጋር ሶስት የዩሮፓ ሊግ ዋንጫዎችን ማንሳት የቻሉት ኡናይ ኤምሪ በአርሰናል አመርቂ ውጤት ማምጣት ባለመቻላቸው ዛሬ የክለቡ አስተዳደር እንዳሰናበታቸው ገልጿል። • የስኮትላንድ እግር ኳስ ማህበር ታዳጊዎች ኳስ በቴስታ እንዳይመቱ ሊያግድ ነው • ከመኪኖች ይልቅ ብስክሌቶች የሚበዙባት ከተማ ክለቡ ቋሚ አሰልጣኝ እስኪያገኝ ድረስ፤ በረዳት አሰልጣኝ እና በቀድሞ የአርሰናል አማካይ ፍሬዲ ሉንበርግ በግዜያዊነት ይሰለጥናል ተብሏል። መድፈኞቹ ባለፉት 7 ጨዋታዎች ማሸነፍ ሳይችሉ የቀሩ ሲሆን፤ ትናንት ምሽት የዩሮፓ ሊግ የምድብ ጨዋታ በሺዎች በሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው ፊትና በሜዳቸው በጀርመኑ ክለብ ኢንትራ ፍራክፈርት 2 ለ 1 ተሸንፈዋል። ለመሆኑ ተሰናባቹ ኡናይ ኤምሪን ማን ሊተካቸው ይችላል? ኑኖ ኤስፒሪቱ ሳንቶስ 1. ኑኖ ኤስፒሪቶ ሳንቶስ ኡናይን ይተካሉ ተብለው ከተገመቱ አሠልጣኖች መካከል በዋነኛነት ስማቸው እየተነሳ ያለው የወቅቱ የዎልቨርሃምፕተን አሠልጣኝ ኑኖ ኤስፔሪቶ ሳንቶስ ናቸው። ኑኖ ኤስፒሪቶ ሳንቶስ ዎልቭስን ይዘው በፕሪሚየር ሊጉ ሰንተረዥ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠው ይገኛሉ። ማክሲሚሎኢያኖ አሌግሪኒ 2. ማሲሚላኖ አሌግሪ ስካይ ስፖርት እንደዘገበው ኡናይ ኤምሪ ከአርሰናል ከተለያዩ በኋላ በማሲሚላኖ አሌግሪ እና በአርሰናል ክለብ መካከል ግንኙነቶች ተጀምሯል። በቅርቡ ከጁቬንቱስ የተለያዩት አሌግሪ ከአሮጊቷ ጋር ውጤታማ የሚባል ጊዜን አሳልፈዋል። አሌግሪ ከጁቬንቱስ ጋር አምስት የሴሪያአ እና አራት ኮፓ ኢታሊያ ዋንጫዎችን ከማንሳታቸውም በተጨማሪ ሁለት ጊዜ ለቻምፒያንስ ሊግ ፍጻሜ መድረስ ችለዋል። ካርሎ አንቾሎቲ 3. ካርሎ አንቾሎቲ ናፖሊን እያሰለጠኑ የሚገኙት ካርሎ አንቾሎቲ ሌላው ኡናይ ኤምረን ይተካሉ ተብለው ከተገመቱት አሰልጣኞች መካከል ይገኙበታል። • «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ ጣሊያናዊው አንቾሎቲ የውድድሩ ዘመን እስኪናቀቅ ድረስ ከናፖሊ ጋር ኮንትራት ቢኖርባቸውም፤ አሰልጣኙ ወደ ኤምሬትስ ሊያቀኑ እንደሚችል በስፋት እየተዘገበ ነው። ብሬንዳን ሮጀርስ 4. ብሬንዳን ሮጀርስ ሌስተር ሲቲዎች ዘንድሮ ደንቅ የሚባል የውድድር ዘመን እያሳለፉ ይገኛሉ። በብሬንዳን ሮጀርስ የሚመሩት ቀበሮዎቹ ካለፉት 10 ጨዋታዎች አርሰናልን ጨምሮ በድንቅ ጨዋታ 9 ግጥሚያዎችን በድል ማጠናቀቅ ችለዋል። ብሬንዳን ሮጀርስ ወደ ኢሚሬትስ እንዲያቀኑ የበርካታ የአርሰናል ደጋፊዎች ምኞት ነው። ማይክል አርቴታ 5. ማይክል አርቴታ ኡናይ ኤምሪ አርሰናልን እንዲያሰለጥኑ ከመሾማቸው በፊት፤ ክለቡን ለማሰልጠን ስሙ በስፋት ሲነሳ የነበረው ማይክል አርቴታ ነበር። የቀድሞ የአርሰናል ተጫዋች ባለፉት ሶስት ዓመታት ከከማንችሰተር ሲቲው ፔፕ ጋርዲዎላ ሥር ሆኖ የአሰልጠኝነትን ክህሎት ሲማር ቆይቷል። ረዳት አሰልጣኙ አርቴታ፤ ማንችሰተር ሲቲ ሁለት የፕሪሚር ሊግ ዋንጫ፣ ሁለት የሊግ ዋንጫዎችን እና ኤፍ ኤ ዋንጫዎች እንዲያነሳ የበኩሉን አስተዋጽኦ አበርክቷል። ፓትሪክ ቪዬራ 6. ፓትሪክ ቪዬራ ሌላው የቀድሞ የአርሰናል ባለታሪክ አማካይ ፓትሪክ ቪዬራ ቀጣዩ የአርሰናል አሰልጣኝ ሊሆን እንደሚችል እየተጠቀሰ ነው። • የሆንግ ኮንግን የዘር መድልዎ የሚፋለሙ አፍሪካዊያን እግር ኳስ ተጫዋቾች ቪዬራ የማይረሳውን የአርሰናል ወርቃማ የ2003/4 የድል የውድድር ዘመን አንበል በመሆን ክለቡን መርቷል። የፈረንሳዩን ኒስ እግር ኳስ ክለብ እያሰለጠነ የሚገኘው ቪዬራ የሚፈለገውን ውጤት እያስመዘገበ ባይሆንም፤ መድፈኞቹ የቼልሲን አርዓያ የሚከተሉ ከሆነ፤ ቪዬራ የአርሰናል አሰልጣኝ ሆኖ ሊሾም እንደሚችል እየተጠቆመ ነው። ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ 7. ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ በቅርቡ ከፖተንሃም አሰልጣኝነት የተነሱት ፖቸቲኖ፤ ሌላው ቀጣዩ የአርሰናል አሰልጣኝ ይሆናሉ ተብለው ከተገመቱ አሰልጣኖች መካከል ይገኙበታል። የቶተነሃም ባላንጣ የሆነው አርሰናልን ለማሰልጠን ፍላጎት ይኖራቸው ይሆን? ሲሉ የሚጠይቁም አልጠፉም። ፖቸቲኖ ከአርሰናል ውጪ፤ የባየር ሚዩኒክ፣ ሪያል ማድሪድ ወይም ባርሴሎና አሰልጣኝ ለሆኑ እንደሚችሉ በስፋት እየተገመተ ይገኛል።
news-47171290
https://www.bbc.com/amharic/news-47171290
ጣልያን በተሸነፈችበት አድዋ ቆንስላዋን ለምን ከፈተች?
የአውሮፓ ሀገራት በጀርመኑ መሪ ቢስማርክ አስተባባሪነት የአፍሪካን ሀገራት ለመቀራመት መስማማታቸውን ተከትሎ የአፍሪካ ሀገራትን በቁጥጥራቸው አዋሉ።
በአድዋ የሚገኘው የጣልያን ቆንስላ የሀገራቱ መንግሥታት በተስማሙበት መሰረት አፍሪካን በቅኝ ግዛት ቁጥጥር ስር የማዋል ተግባሩ ተጀመረ። የኢትዮጵያ ቀኝ ገዢ እንድትሆን የተመረጠችው ጣልያንም ጦርዋን አዝምታ ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጋር በአድዋ ውጊያ ገጥማ ድል ተነሳች። •የታሪክ ቁንጮዋ ከተማ ይፍሩን ዕውቅና የነፈገችው ኢትዮጵያ ጣልያን ከዛ በፊትም በዶጋሊ ሽንፈት አጋጥሟት የነበረ ቢሆንም ይህኛው ሽንፈት ግን በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ሽፋን አግኝቶ የጣልያን ብሄራዊ ክብር ዝቅ ያደረገ ውጊያ ሆኖ በታሪክ ተመዝግቦ ይገኛል። ጣልያን በተሸነፈችበት ቦታ ቆንስላዋንለምን ከፈተች? ጣልያን በአድዋ ጦርነት ከተሸነፈች ከስድስት ወራት በኋላ እዛው ድባቅ በተመታችበት ስፍራ ቆንስላዋን ከፈተች። የኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ሆና ሳለ ጣልያን ቆንስላዋን በአድዋ መክፈት የፈለገችበት ምክንያት ብዙዎችን በወቅቱ አስገርሟል። •"ሌቱም አይነጋልኝ" የተባለላት የውቤ በረሃ ትዝታዎች እንዲሁ ሲታይ ጣልያን ቆንስላዋን በአድዋ መክፈት የፈለገችው ሁለቱም ነጻ ሀገራት እንደመሆናቸው መጠን ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኘነታቸው እንዲጠናከር ከመፈለግ የተነሳ እንደሆነ በአክሱም ዩኒቨርስቲ የአርኪኦሎጂ እና ታሪክ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ተክለብርሃን ለገሰ የታሪክ መጽሃፍትን ዋቢ በማድረግ ቢናገሩም የሚቃረን ጉዳይ እንዳለ አልካዱም። "እነዚህ የተጠቀሱት ምክንያቶች ቆንስላዋን ዋና ከተማ በሆነችው አዲስ አበባ በማድረግ ሊሰሩ ይችሉ የነበሩ ናቸው" ይላሉ ከዚህ ሁሉ በላይ ዋነኛው ምክንያቷ የሚሉት ግን በአድዋ ያጣችውን ድል ለማግኘት ጥናት ለማካሄድ ነበር ይላሉ። •የተነጠቀ ልጅነት በዚህም መሰረት የጣልያን መንግሥት በአድዋ ጦርነት ላይ ሰራዊቱ ሊሸነፍ የቻለው የተካሄደበትን የአድዋ ገጸ ምድር አስፈላጊውን ጥናት ባለማካሄዱ እንደሆነ ገምግመዋል የሚሉት መምህር ተክለብርሃን ጣልያን ለሽንፈቴ ምክንያት ያለችውንም የአድዋን ተራሮች በቅርበት ለማጥናት ታስቦ ቆንስላዉን እንደተከፈተ ያብራራሉ። ጣልያን ከ 40 አመታት በኋላ እንደገና ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት ቆንስላው የተለያዩ ጥናቶችን በማጥናት ድልን ለመቀዳጀት እንደጠቀማቸውም መምህሩ ያስረዳሉ። በቆንስላው ቅጥር ግቢ ውስጥ በአድዋ አቅራብያ የሚገኘውን ትልቁን የሰሎዳ ተራራን ያክላል የተባለውን የሰንደቅ አላማ መስቀያ ብረት ይገኛል። ይህ ትልቅ የሰንደቅ አላማ ብረት የተተከለበት ዋነኛ አላማ ደግሞ ጣልያን በተሸነፈበችበት ቦታ ላይ ሰንደቅ አላማቸውን በረዥም ብረት ከፍ አድርጎ በማውለብለብ ሽንፈታቸውን ለማካካስ እንደ ምልክትነት እንደተጠቀሙበት በትግራይ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ የቱሪዝም ባለሙያ አቶ ጽጌ ኃይለማርያም ገልጸዋል። እንደ ባለሙያው ገለጻ ቆንስላው ከተራሮቹ ጥናት በተጨማሪ የህዝቡን የአሸናፊነት ምስጢርም ለማወቅ እንደነበር የከተማዋ ሽማግሌዎችን በማጣቀስ ይገልፃሉ። በአድዋ የሚገኘው የጣልያን ቆንስላ ቆንስላው በምን ደረጃ ላይ ይገኛል? ቆንስላው በያኔ የሮማውያን ኪነ ህንጻ ጥበብ የተሰራ ባለ ሶስት ፎቅ ህንጻ ነው። እስካሁን በጣልያንም ይሁን በኢትዮጵያ መንግሥት ምንም እድሳት ያልተደረገለት ሲሆን የትምህርት ቁሳቁሶች ማከማቻ ሆኖ ይገኛል። በውስጡ የወዳደቁ እና የተሰባበሩ ወንበሮች ይገኛሉ። የትግራይ ባህል እና ቱሪዝም ይህንን ታሪካዊ ቦታ ያውቀው እንደሆነ ለቢሮው ሰራተኛ አቶ ጽጌ ኃይለማርያም ቢቢሲ ጥያቄ ያቀረበላቸው ሲሆን፤ የትግራይ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ለአድዋ ማዘጋጃ ቤት ጥያቄ እንዳቀረበ እና ታድሶ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ሀሳብ እንዳለ ገልፀዋል። ይህ በኪነ ህንጻው ውብ የሆነውን ቆንስላ በማደስ የጣልያን ጎብኚዎችን ብቻ ትኩረት አድርጎ እንኳ ቢሰራ ዋነኛ የቱሪዝም መዳረሻ ሊሆን እንደሚችል የአክሱም ዩኒቨርስቲ መምህሩ አቶ ተክለብርሃን ያስረዳሉ። በአድዋ የሚገኘው የጣልያን ቆንስላ
48456101
https://www.bbc.com/amharic/48456101
የፌደራል ዋና ኦዲተር፡ የተሟላ የወጪ ማስረጃ ሳይቀርብ ከ1.4 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጓል
የፌደራል ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት፤ የሂሳብ አያያዝ ግድፈቶች፣ የውስጥ ቁጥጥር ድክመቶችና አፈጻጸማቸው ከሕግ ውጪ የሆኑ የተባሉ የአሠራር ችግሮችን ይፋ ተደርገዋል።
ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ በሪፖርቱ መሰረት፤ በውጪ ጉዳይ ሚንስቴር 810,060፣ በሰመራ ዩኒቨርስቲ 123,599፣ በጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ 27,173 በድምሩ 960,832 ብር ጉድለት ተገኝቷል። • "ሕዝብ እንዲጠይቅ አድርገናል" ዋና ኦዲተር ገመቹ ዱቢሶ በበጀት ዓመቱ መጨረሻ በሂሳብ መግለጫ ሪፖርት የተደረገውና በቆጠራ የተገኘው ጥሬ ገንዘብ መካከል በሁለት የገቢዎችና ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች፤ ቆጠራው ከመዝገብ ጋር ሲነጻጸር 102,532 ብር በማነስ ልዩነት እንደታየበትም ተመልክቷል። በተጨማሪም በ14 መሥሪያ ቤቶችና በ14 ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች የተለያዩ የጥሬ ገንዘብና የባንክ ሂሳብ አያያዝ ድክመቶች መኖራቸው መረጋገጡን ዋና ኦዲተሩ ገመቹ አሳውቀዋል። በ129 መሥሪያ ቤቶችም 4,252,562,207 ብር በወቅቱ ሳይወራረድ መገኘቱ ተገልጿል። • "በራሷ ገቢ የምትተማመንና መቆም የምትችል ሀገር ማየት እሻለሁ"ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በወቅቱ ያልተወራረደ ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብ ከተገኘባቸው መሥሪያ ቤቶች ውስጥ የብሔራዊ አደጋ ስጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽን 608,731,337 ብር፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 441,828,292 ብር፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ 322,520,418 ብር፣ የቀድሞ ውሀ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር 282,965,014 ብር፣ መቀሌ ዩኒቨርስቲ 250,218,048 ብር፣ የትምህርት ሚኒስቴር 232,084,916 ብር፣ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ 160,457,088 ብር፣ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር 108,079,052 ብር እንዲሁም የመንግሥት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 111,362,647 ብር ይገኙበታል። በዘጠኝ መሥሪያ ቤቶችና በስድስት ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች ከመቼ ጀምሮ በተሰብሳቢነት እንደተመዘገበና በማን እንደተመዘገበ በቂ መረጃ ያልተገኘበት 1,298,391,518 ብር መገኘቱን ዋና ኦዲተሩ የገለጹ ሲሆን፤ በዚህ ከፍተኛውን ድርሻ የያዙት የአገር መከላከያ ሚንስቴርና የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ናቸው ተብሏል። መሰብሰብ የሚገባቸውን ገቢ ካልሰበሰቡ መሥሪያ ቤቶች መካከል በቀድሞው ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና መሥሪያ ቤትና በሥሩ ባሉ 15 ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች 302,835,172 ብር ሳይሰበሰብ ቀርቷል። • የኦነግ ጦር መሪ በትግላችን እንቀጥላለን አለ በኦዲት ሪፖርቱ እንደተገለጸው፤ በ100 መሥሪያ ቤቶችና ስምንት ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች በጨረታ መፈጸም ሲገባቸው ያለጨረታ 802,199,221 ብር በቀጥታ ግዢ ተፈጽሟል። ከዚህ በተጨማሪ ግልጽ ጨረታ ማውጣት ሲገባቸው በዋጋ ማወዳደሪያ የተፈጸሙ፣ የዋጋ ማወዳደሪያ ሳይሰበሰብ ግዢ የተፈጸሙ በአጠቃላይ የመንግሥት የግዢ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ ያልተከተለ የ 956,822,601 ብር ግዢ ተገኝቷል። ከግዢ አዋጅና መመሪያ ውጪ ግዢ ፈጽመዋል ከተባሉ መሥሪያ ቤቶች መካከል የብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን፣ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴርና የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ይገኙበታል። • የቦይንግ ኃላፊ የሟቾችን ቤተሰቦች በይፋ ይቅርታ ጠየቁ የትምህርት ሚንስቴር፣ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽሕፈት ቤትና ሌሎችም ተቋሞች ደንብና መመሪያ ሳይጠብቁ ክፍያ መፈጸማቸውን የፌደራል ዋና ኦዲተሩ አቶ ገመቹ የገለጹ ሲሆን፤ በአጠቃላይ በ77 መሥሪያ ቤቶችና በሰባት ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች 145,676,300 ብር ከደንብና መመሪያ ውጪ ተከፍሎ ተገኝቷል። 63 መሥሪያ ቤቶች የተሟላ የወጪ ማስረጃ ሳይቀርብ የ1,475,867,250 ብር ወጪ ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ከነዚህ መካከል ብሔራዊ አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን፣ አገር መከላከያ ሚነስቴርና የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር እና ጋምቤላ፣ ወልቂጤ፣ ዋቻሞ እና ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲዎች ይገኙበታል። የንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት እና የውል ስምምነት የወጪ ማስረጃ ሆነው ሊቀርቡ የሚችሉ ማስረጃዎች ናቸው። • የተሟላ የወጪ ማስረጃ ሳይቀርብ ከ1.4 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጓል አራት ዩኒቨርሲቲዎች የግንባታ ሥራ ፕሮጀክት የማማከር ፍቃድ በሌላቸው የግንባታ ጽህፈት ቤቶች 114,959,683 ብር ወጪ አድርገዋል። አንድ ዩነቨርስቲ በአማካሪ ባልጸደቀ የክፍያ የምስክር ወረቀት 36,232,839 ብር ክፍያ መፈጸሙንም ዋና ኦዲተሩ ተናግረዋል። ትምህርት ሚኒስቴር ተጨማሪ ሥራ ውል ስምምነት ሳይፈርም 18,629,844 ብር፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ደግሞ ሕግ የሚፈቅደው የመጀመሪያው ውል እስከ 30 በመቶ ሆኖ ሳለ ከተፈቀደው በላይ የ1,270,586 ብር ውል መግባቱ ተገልጿል።
news-55868495
https://www.bbc.com/amharic/news-55868495
ትግራይ፡ በማይካድራ ግድያ ከተጠረጠሩት መካከል 36ቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ
ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በማካይድራ የሰዎች ግድያ ላይ የተሳተፉ 279 ተጠርጣሪዎች መኖራቸውን ከተሰበሰቡ መረጃዎች መረዳት እንደቻለ ገለፀ።
አቃቤ ሕግ በትናንትናው ዕለት ከፌደራል ፖሊስ ጋር በመሆን መግለጫ የሰጠ ሲሆን ከተጠርጣሪዎች መካከልም 36ቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቋል። በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሙስና እና የተደራጁ ወንጀል ጉዳዮች ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ፍቃዱ ጸጋ እና የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራል እና የወንጀል ምርመራ ቢሮ ኃላፊ ዘላለም መንግስቴ በጋራ በሰጡት መግለጫ ላይ አብዛኞቹ ተጠርጣሪዎች ወደ ሱዳን ማምለጣቸውን ተናግረዋል። በማይካድራ ጥቃት የተፈፀመው በፌደራል መንግሥትና በሕወሓት ኃይሎች መካከል ጥቅምት 24፣ 2013 ዓ.ም ግጭት ከተቀሰቀሰ ጥቂት ቀናት በኋላ፤ ጥቅምት 30፣ 2013 ዓ.ም ሰኞ ዕለት ሲሆን የሰብአዊ መብት ቡድኖች በጥቃቱ ከ600 በላይ ሰዎች ተገድለዋል ሲሉ ተናግረዋል። ጥቃቱ የተፈፀመው ጥቅምት 30፣ 2013 ዓ. ም ከሰዓት በኋላ 9፡ 00 ሰዓት ላይ የነበረ ሲሆን አስከሚቀጥለው ቀን ጠዋት ድረስ መቀጠሉን ነዋሪዎቹ በወቅቱ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። ከዚህ ጥቃት ጋር በተያያዘ የሟቾችን ቁጥር ለማወቅ ከጤና ሚኒስቴር የሀኪሞች ቡድን ተልኮ፤ 117 ጉድጓዶች የተገኙ ሲሆን አስክሬኖችን መርምሮ የሟቾቹን ብዛት እና የሞት ምክንያት ለማወቅ እየተሰራ መሆኑን አቶ ፍቃዱ ገልፀዋል። አቶ ፍቃዱ አክለውም፤ ይህ የሕክምና ባለሙያዎች ቡድን ሪፖርት እስኪደርስ ድረስ ትክክለኛው በጥቃቱ የሞቱ ሰዎችን ብዛት መግለጽ እንደማይቻል አስታውቀው "መሬት ባለው እውነት እና በየሚዲያው የተገለጸው" መካከል ልዩነት መኖሩን በማብራሪያቸው አስረድተዋል፡፡ የማይካድራ ከተማ በትግራይ ክልል ደቡብ ምዕራብ ዞን የምትገኝ ስትሆን ጥቅምት 24፣ 2013 ዓ. ም ሕወሓት ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ግጭት ውስጥ ከገባ በኋላ በርካታ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ይፋ ተደርጎ ነበር። በወቅቱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኃላፊ ሚሼል ባችሌት በማይካድራ ከተማ ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ በስለት ተገድለዋል የሚለው ሪፖርት እንዲጣራ ጠይቀው ነበር። አምነስቲ ኢንተርናሽናል በወቅቱ ባወጣው ሪፖርት ጥቃቱን ማን እንደፈጸመው ለማረጋገጥ አለመቻሉን አመልክቷል። ነገር ግን ያነጋገራቸው የአይን እማኞች ከፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ጋር የሚዋጉትን የህወሓት ታማኝ ኃይሎች ይከስሳሉ። አምነስቲ ኢንትርናሽናል በማይካድራ ስለተፈጸመው ነገር ለማረጋገጥ ከጥቃቱ በኋላ ወደ ስፍራው የሄዱ እማኞችን ያነጋገረ ሲሆን፤ በከተማዋ ውስጥ በየቦታው የወደቁ አስከሬኖችንና ከጥቃቱ ቆስለው የተረፉ ሰዎችን እንደተመለከቱ ተናግረው ነበር። አብዛኞቹ አስከሬኖች የተገኙት በከተማዋ ማዕከላዊ ክፍል ውስጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሚገኝበት አካባቢና በአቅራቢያው ወደምትገኝ የሁመራ ከተማ የሚያመራውን መንገድ ተከትሎ መሆኑን የአይን እማኞችና የተገኙት ምስሎች ጠቁመዋል። ሪፖርቱ በወጣበት ወቅት የትግራይን ክልል እያስተዳደሩ የነበሩት ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ውንጀላዎቹን "መሰረት የሌላቸው ናቸው" ማለታቸውን አጃንሰ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቦ ነበር። የሰብአዊ መብቶች ተቆርቋሪው ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል እንዳለው በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ በምትገኘው ማይካድራ ከተማ ውስጥ በተፈጸመው በዚህ ጥቃት ቁጥራቸው በመቶዎች ሊቆጠሩ የሚችሉ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ በስለት ተገድለዋል። ድርጅቱ ከማይካድራ ከተማ የወጡና በየቦታው ወድቀው የሚታዩ አስከሬኖችን የሚያሳዩ አሰቃቂ ፎቶግራፎችንና ቪዲዮዎችን በመመርመር ምስሎቹ የቅርብ ጊዜና ስፍራውም ማይካድራ መሆኑን ለማረጋገጥ መቻሉን ገልጾ ነበር። በአገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ተፈጸመ የተባለውን ጥቃት ተከትሎ ለወራት በውዝግብ ውስጥ ቆይተው የነበሩት የፌደራል መንግሥት እና የትግራይ ክልል አስተዳደር ጥቅምት 24፣ 2013 ዓ. ም ወደ ግልጽ ጦርነት መግባታቸው ይታወሳል። የፌደራል መንግሥቱ መቀሌን ከተቆጣጠረ በኋላ ጦርነቱ መጠናቀቁን የገለፀ ቢሆንም አሁንም ግን በተለያዩ አካባቢዎች ውጊያ እንደሚካሄድ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ድርጅቶች በሪፖርታቸው እየገለፁ ነው። ከዚህ ግጭት ጋር በተያያዘ 60 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ወደ ሱዳን ሲሸሹ በሚሊዮኖች ሚቆጠሩ ደግሞ በአገር ውስጥ ተፈናቅለው የሰብዓዊ እርዳታ እየጠበቁ ይገኛሉ። በትግራይ አሁንም የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ያልተመለሰ ሲሆን የሰብዓዊ ርዳታ ድርጅቶችም እርዳታ ለሚፈልጉ ለማድረስ እንደልብ መንቀሳቀስ አለመቻላቸውን በመግለጽ ተደጋጋሚ መግለጫ አውጥተዋል።
news-55241937
https://www.bbc.com/amharic/news-55241937
እስራኤል ፡ አረቡ ባለሃብት በእስራኤሉ ዘረኛ ክለብ ላይ ገንዘባቸውን ለማፍሰስ ለምን መረጡ?
ከቀናት በፊት በመቶዎች የሚቆጠሩ ፅንፈኛ የሚባለው የእስራኤሉ ቤይታር ጄሩሳሌም እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች የቡድኑን ልምምድ በማቋረጥ ሜዳውን ወረሩት።
ደጋፊዎቹ በቁጣና በንዴት ሜዳውን የወረሩት ክለቡ ከሚወዳደርበት የእስራኤል ሊግ ወደታች ለመውረድ እየተንገታገተ በመሆኑ አይደለም። ነገሩ ወዲህ ነው። የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ንጉሣዊ ቤተሰብ አባል የሆኑት ቱጃር በክለቡ ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ስምምነት ላይ መደረሱን ተከትሎ ነው ቁጣቸውን የገለፁት። ክለቡም ከሁለት ቀናት በፊት ከሼክ ሃማድ ቢን ካሊፋ አል ናይን ጋር የኢንቨስትመንት ስምምነቶች ላይ መድረሱን አስታውቆ ነበር። የቤይታር ደጋፊዎች በፀረ-አረብ፣ ፀረ-ሙስሊም፣ እብሪተኛና ፀበኛ ባህርያቸው የታወቁና ስምም አትርፈዋል። ከሰሞኑም ሜዳውን ብቻ መውረር ሳይሆን በቤይታር ስታዲየምም ላይ አፀያፊ የሚባሉ የግራፊቲ ምስሎችን በግድግዳዎች ላይ ስለዋል። ምንም እንኳን የቤይታር ደጋፊዎች ምላሽ የከፋ ቢሆን በአንዳንድ አረብ አስተያየት ሰጭዎች ዘንድ ስምምነቱ ተቀባይነት አላገኘም። በሬድዮ የስፖርት ፕሮግራም አቅራቢው ሳይድ ሃስን ለኒውዮርክ ታይምስ እንደተናገረው ስምምነቱ "አሳፋሪ" ነው በማለት ነበር። በተለይም የክለቡ ደጋፊዎች ፀረ-አረብ አቋም እንዳላቸው እየታወቀ ክለቡ ላይ ኢንቨስት መደረጉን ተችቷል። በስምምነቱም መሰረት አል ናህያን በሚቀጥሉት አስር ዓመታት 92 ሚሊዮን ዶላር መዋዕለ ንዋያቸውን የሚያፈሱ ሲሆን 50 በመቶም የክለቡ የባለቤትነት ድርሻ ይኖራቸዋል። ክለቡ በአሁኑ ወቅት በሊጉ ባለው ደረጃ ከአስራ አራት ቡድኖች መካከል አስራ አንደኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። የእስራኤል መንግሥትና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማደስ በመስከረም ላይ ፊርማ ማኖራቸውን ተከትሎ እንዲህ አይነት የንግድ ስምምነቶች በሁለቱ አገራት መካከል እየጎረፉ ነው ተብሏል። ባለ መጥፎ ስሙ ክለብ የአሁኑ በሁለቱ አገራት መካከል የተከናወነ ቁልፍ ስምምነት ባያደርገውም የቤይታር ስምምነት በከፍተኛ ሁኔታ አወዛጋቢ ነው። በእስራኤል ብሔራዊ ቡድንን ጨምሮ በተለያዩ ክለቦች የይሁዲና አረብ ተጫዋቾች በአንድ ላይ ቢኖሩም ቤይታር አንድም አረብ ተጫዋች በታሪኩ አስፈርሞ አያውቅም። ሆኖም በክለቡ ታዳጊ ቡድን ውስጥ አረቦች አሉ። በጎሮጎሳውያኑ 2013 ክለቡ ሁለት ሙስሊም ተጫዋቾችን ከቺቺንያ ማስፈረሙን ተከትሎ የቤይታር ቢሮ በደጋፊዎቹ ተቃጥሏል። ክለቡ በሚያደርጋቸው ጨዋታዎችም ላይ "ሞት ለአረቦች" የሚሉ መፈክሮችና ዝማሬዎች እንዲሁም አፀያፊ የሚባሉ ፅሁፎችን ከደጋፊዎቹ በኩል መሰስማትና ማየት የተለመደ ነው። የክለቡ ባለቤት ይህንን ባህርይ ለመቀየር ቢሞክሩም ብዙ ፍሬ አላፈራም ተብሏል። አዲስ ባለቤት፣ ሲንከባለሉ የመጡ ችግሮች በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፉ ሚሊዮነር የሆኑት ሞሼ ሆጌግ የተባሉት ግለሰብ ከሁለት ዓመት በፊት ክለቡን ገዙት። ሞሼ የተወለዱት እስራኤል ቢሆንም አባታቸው ቱኒዝያዊ ሲሆኑ እናታቸው ደግሞ የሞሮኮም ዝርያ አላቸው ተብሏል። ከዓመት በፊት የክለቡ ባለቤት ሞሼ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ ዘረኛ የሆኑ ጉዳዮችን እንደማይታገሱና ዘረኛ በሆኑ ደጋፊዎችም ላይ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ቁርጠኛ መሆናቸውን አስታውቀዋል። "የማንንም ህይወት ማበላሸት እየሞከርኩ አይደለም። የአባታቸውና እናታቸውንም ሚና እየወሰድኩ አይደለም። ለማስተማርም እየሞከርኩ አይደለም ያ የኔ ሥራ አይደለም" ብለዋል ሞሼ። አክለውም "ነገር ግን ያን ባህርይ ወደ ስታዲየም ሲያመጡት በተሰበሰበውም ሕዝብ ላይ ሆነ በአገራችን ላይ መጥፎ ነፀብራቅ ነው። ያንን ደግሞ አልቀበለውም" ብለዋል። ሞሼም ቢሆኑ "ነጥብ ለማስቆጠር" በሚል አረብ ተጫዋች እንደማያስፈርሙ ቢናገሩም፤ ለስፖርታዊ ምክንያቶች ሲሉ ግን ለማስፈረም ወደኋላ እንደማይሉና ፍራቻም እንደሌላቸው አሳውቀዋል። "የተጫዋች እምነቱ፣ ቀለሙ ምንም ይሁን ግድ አይሰጠኝም። ቡድኑን መርዳት ይችላል ወይ? ጥሩ ተጫዋች ነው የሚለው ጉዳይ ነው የሚያሳስበኝ" ብለዋል። "የአረቦቹ ተጫዋቾች ይፈርሙም አይፈርሙም እስራኤላዊ የሆጉ ጎበዝ አረብ ተጫዋቾች አሉ። አንደኛውን ልናስፈርም እንችላለን" ብለዋል ሞሼ። በተለይም ከአረቡ ቱጃር አልናህያን ጋር የተረደገውን ስምምነት ሞሼ ይበል የሚያሰኝ ነው ብለውታል። "በአንድ ላይ ሆነን ክለቡን በአዲስ መልክ በመተባበር፣ ስኬትና ወንድማማችነት በተሞላበት መልኩ እናድሰዋለን" በማለትም ተናግረዋል። ንግድና ጓደኝነት አልናህያን በቤይታር ኢንቨስት እንዲያደርጉ ዋነኛ ምክንያታቸውም ከሞሼ ጋር ያላቸው የዓመታት የንግድ ሽርክናውና ወዳጅነት እንደሆነ ተናግረዋል። ስምምነቱ መፈረሙንም ተከትሎ አል ናህያ የክለቡ አጋር በመሆናቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልፀዋል። "ክለቡ እያከናወነው ስላለው ለውጥ ሰምቻለሁ። በዚህም ተሳታፊ በመሆኔ ደስተኛ ነኝ" ብለዋል። የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ናታንያሁን ግለ ህይወት የፃፈው ጋዜጠኛው አንሸል ፊፈር በበኩሉ የቤይታር ደጋፊዎች ከእስራኤል ገዢ ፓርቲ ሊኩዊድ ጋር ፅኑ ቁርኝት እንዳላቸው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ናታንያሁም በጨዋታዎች ወቅት ከፅንፈኞቹ ደጋፊዎች ጋር አንድ ላይ ፎቶም ተነስተዋል። "አል ናህያ በቤይታር ጄሩሳሌም ኢንቨስት ለማድረግ መወሰናወች ምንም ተቃርኖ የለውም። ቤተሰባቸው በአጠቃላይ ከእስራኤል መሪዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር ቁልፍ በሚባሉ ጉዳዮች ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ውሳኔ ላይ ደርሰዋል" በማለትም ጋዜጠኛው ይናገራል። ይሄ ብቻ አይደለም አል ናህያ ከሁለት ቀናት በፊት በተድበሰበሰ መልኩ ኢየሩሳሌም የእስራኤል መዲና እንደሆነች የሚጠቁም ንግግር አድርገዋል። ለአስርት ዓመታት በዘለቀው የእስራኤልና ፍልስጥኤም ግጭትና የእየሩሳሌም ሁኔታ ዋነኛና አወዛጋቢ ጉዳያቸውም ነው። እስራኤል መላው ኢየሩሳሌም ግዛቴና መዲናዬ ናት የምትል ሲሆን ይህ በአሜሪካ ቢደገፍም በርካታ አገራት ይቃወሙታል። ፍልስጥኤማውያን በበኩላቸው እስራኤል በጎሮጎሳውያኑ 1967 በተካሄደው ጦርነት በወረራ የያዘችውን ምሥራቅ እየሩሳሌም መጪዋ መዲናችን ናት ይላሉ። እስራኤልና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ግንኙነታቸውን ለማደስ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ ፍልስጥኤም መዲናዋን ምሥራቅ እየሩሳሌም ባደረገ መልኩ ግዛቷን የምትመሰርትበትን ሁኔታም እንደምታግዝ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አስታውቃለች።
49659056
https://www.bbc.com/amharic/49659056
የአረብ አገራት እስራኤልን ኮነኑ
የአረብ አገራት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ከዌስት ባንክ ይዞታ ከፊሉን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ማቀዳቸውን ተችተዋል።
ቤንጃሚን ኔታንያሁ የሚቀጥለው ሳምንት የሚካሄደውን የእስራኤል ጠቅላላ ምርጫ ተከትሎ፤ እቅዱ እንደሚተገበር ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል። የጆርዳን፣ የቱርክ እና የሳዑዲ አመራሮች እቅዱን በጥብቅ ተችተዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በእቅዳቸው የጠቀሷቸው ጆርዳን ቫሊ እና ዴድ ሲ የዌስት ባንክ አንድ ሦስተኛ ይዞታ ሲሆኑ፤ የአረብ ሊግ እቅዱን "አደገኛ" እና "ኃይል የተሞላው" ሲል ኮንኖታል። ከዓለም አቀፍ ሕግ ጋር የሚጻረር እቅድ ነውም ብለዋል። • አሜሪካ ፍልስጤምን አስጠነቀቀች • እስራኤል በፍልስጤም ይዞታ ሥር የሚገኙ ቤቶችን እያፈረሰች ነው የፍልስጤሙ ዲፕሎማት ሳዒብ ኤራካት "ይህ እርምጃ ወንጀል ነው፤ የሰላም ጭላንጭልን ያዳፍናል" ብለዋል። እስራኤል ከጎርጎሮሳውያኑ 1967 ጀምሮ ዌስት ባንክን ይዞታዋ ብታደርግም በቁጥጥር ሥር ግን አልዋለም ነበር። ፍልስጤም ነፃ አገርነቷን ስታውጅ ይህ ቦታ ግዛቷ እንደሚሆን ትገልጻለች። እሰራኤል ደህንነቷን ለመጠበቅ ስትል በጆርዳን ያላትን ይዞታ እንደማትለቅ ጠቅላይ ሚንስትሩ መናገራቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚንስትሩ እቅዳቸውን ይፋ ያደረጉት ከምረጡኝ ቅስቀሳቸው ጋር በተያያዘ ነው። የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በእስራኤልና በፍልስጤም መካከል የሰላም ስምምነት እንዲፈረም ካደረጉ፤ በዌስት ባንክ ያሉ የአይሁዳውያን ሰፈራዎችን እንደሚጠቀልሉም ገልጸዋል። ኔታንያሁ የሚመሩት ፓርቲ ከተቀናቃኝ ፓርቲዎች ጋር ከፍተኛ ፉክክር እያደረገ ይገኛል። የቢቢሲ የመካከለኛው ምስራቅ ተንታኝ ቶም ቤትማን እንደሚለው፤ የጠቅላይ ሚንስትሩ እቅድ የቀኝ ዘመሞችን ድጋፍ ለማግኘት ያለመ ነው። • "ሰዓረ ሙዚቃ በጣም ያዝናናው ነበር" ጄኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳዔ • ''አባቴ የቼልሲ ደጋፊ ነበር'' የሜጄር ጄኔራል ገዛዒ አበራ ልጅ ከኔታንያሁ ፓርቲ በተቃራኒው ያለው የ 'ብሉ' እና 'ዋይት' ፓርቲዎች ጥምር መሪ ያሪ ላፒድ "እቅዱ ያለመው ድምፅ ለማግኘት እንጂ ግዛት ለማግኘት አይደለም" ብለዋል። የጆርዳን ጠቅላይ ሚንስትር አይማን ሳፋዲ እቅዱ "አካባቢውን ዳግመኛ ወደ ቀውስ የሚወስድ ነው" ብለዋል። የቱርክ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሜቩልት ካቩስጎሉ እቅዱን "ዘረኛ" ሲሉ ኮንነውታል። የሳዑዲ አመራሮችም እቅዱን ተችተው የ 'ኦርጋናይዜሽን ኦፍ ኢስላሚክ ኮኦፕሬሽን' 57 አባል አገራትን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል።
51353273
https://www.bbc.com/amharic/51353273
በኮሮናቫይረስ ከተጠረጠሩ አራት አዲስ ሰዎች አንዱ በአክሱም እንደሚገኝ ተገለፀ
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በኮሮናቫይረስ ሳይያዙ አይቀሩም የተባሉ ሌሎች አዲስ አራት ሰዎች መገኘታቸውን አስታወቀ።
የጤና ኢንስቲትዩቱ ይህንን ያሳወቀው በዛሬው እለት በሰጠው መግለጫ ሲሆን፤ በቫይረሱ የተጠረጠሩት ሶስቱ ኢትዮጵያውያን አንዱ ደግሞ ቻይናዊ መሆናቸው ተነግሯል። ከዚህ ቀደም አራት ሰዎች በቫይረሱ ተጠርጥረው በለይቶ ማቆያ እንዲቆዩ ከተደረገ በኋላ የደም ናሙናቸው ወደ ደቡብ አፍሪካ ተልኮ ከኮሮናቫይረስ ነጻ መሆናቸው ሲረጋገጥ ከለይቶ ማቆያ እንዲወጡ መደረጉ ይታወሳል። •ኮሮናቫይረስ፡ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች በቻይና • በኮሮናቫይረስ ሳይያዙ አይቀሩም ተብለው የተጠረጠሩ 4 ሰዎች በአዲስ አበባ ተገኙ በበሽታው ከተጠረጠሩ አንዱ በአክሱም እንደሚገኝ የተቀሩት ደግሞ በቦሌ ጨፌ በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገላቸው እንደሆነ ኢንስቲቲዩቱ ያሳወቀ ሲሆን፤ የአራቱም ግለሰቦች ናሙናቸው ተወስዶ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመላክ ዝግጅት መጠናቀቁ ተነግሯል። አክሱም ላይ በለይቶ ማቆያ እንዲቆይ የተደረገው ግለሰብ የበሽታው ምልክቶችን በራሱ ላይ በማየቱ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ማደረጉን ተከትሎ እንደተለየ ተነግሯል። ኢንስቲትዩቱ አክሎም እንደገለፀው በቦሌ አለም አቀፍ አየር መንገድ እና እና ሃያ ሰባት የተለያዩ የድንበር መግቢያ እና መውጫ ኬላዎች ላይ የማጣራት ምርመራ እየተደረገ እንደሆነ ነው። •ከቻይና ውጪ የመጀመሪያው ግለሰብ በኮሮና ቫይረስ ሞተ ይህ ምርመራ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ያላቸውን ተጓዦችን የሚለይ ሲሆን ይሄም የቫይረሱ የበሽታ ምልክት የሚያሳዩትን ለመለየት እንደሚረዳም ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል። እስከ ጥር 24/2012 ድረስ 47,162 ተጓዦች የሙቀት መለያ ምርመራ እንደተደረገላቸው እና ከእነዚህ ውስጥ 1,695ቱ የመጡት ቫይረሱ ሪፖርት ከተደረገባቸው አገራት መሆኑን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል። ከቻይና የሚመጡ ሁሉንም ተጓዦች በሃገር ውሰጥ በሚቆዩበት ወቅት አድራሻቸውን የሚመዘገብ ሲሆን ለአስራ አራት ቀናትም የሚከታተል ቡድን መቋቋሙንም ተገልጿል። በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል ተብለው የሚጠረጠሩ ታካሚዎችንም ለመውሰድ አራት ተሽከርካሪዎችና ሁለት አምቡላንሶች የተመደቡ መሆኑ ተገልፆ ፤ ለዚሀም የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፤ በቦሌ ጨፌ ያለ የህክምና ቦታ እና የየካ ኮተቤ ሆስፒታል ለህክምና መስጫነት ተመርጠዋል።
news-54723542
https://www.bbc.com/amharic/news-54723542
በኢትዮጵያ ያሉ ኤርትራውያን ስደተኞች መድልዎ እየደረሰባቸው እንደሆነ ገለፁ
በመቶ ሺዎች የሚሆኑ ስደተኞችን በመጠለያ ማዕከላት በምትቀበለው ኢትዮጵያ ወደ አገሪቷ የሚገቡ ኤርትራውያን ስደተኞች መድልዎ እየደረሰባቸው እንደሆነ ቅሬታቸውን አሰሙ።
ኤርትራውያን ስደተኞቹ "ወታደሮችና የመንግሥት ሰራተኞች" ያልሆናችሁ ወደ ስደተኞች ካምፕ አትገቡም በሚል ተከልክለናልም እያሉ ነው። ከኤርትራ በተለያዩ ምክንያቶች ጠፍተው የመጡና የኢትዮጵያ ድንበርንም አቋርጠው የገቡ ስደተኞች በአሁኑ ወቅት በትግራይ ክልል በሚገኙ የድንበር ከተሞች ተጠልለውም ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን ይናገራሉ። በዓዲግራት፣ ዛላምበሳ፣ ሽራሮ፣ ዓዲ ነብር፣ ራማ እና ገርሁስርናይ በሚባሉት ከተሞችም ስደተኞቹ በትምህርት ቤቶች ውስጥ ተጠልለው እንዳሉም ቢቢሲ ለመረዳት ችሏል። ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር መሰረት ወደ ኢትዮጵያ ተሻግረው የሚገቡ ኤርትራውያን ስደተኞች በድንበር አካባቢ በሚገኙ ጊዜያዊ መጠለያዎች ውስጥ እንዲቆዩ ይደረግ ነበር። ከባለፈው አመት ጥር ወር ጀምሮ እነዚህ ጊዜያዊ ማቆያ ማዕከላት የተዘጉ ሲሆን የስደተኞችና ከስደት ተመላሽ ጉዳዮች ኤጀንሲ ሰራተኞች ኤርትራውያን ወደሚገኙበት የለይቶ ማቆያ ቦታ በመሄድም የምዝገባና የማጣራት ስራ እያከናወኑ ይገኛሉ። በዓዲግራት ዩኒቨርስቲ የለይቶ ማቆያ ጊዜያቸውን ጨርሰው በአሁኑ ወቅት በቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ ኤርትራውያን ስላሉበት ፈታኝ ሁኔታ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ለደህንነቴ ሲባል ስሜ አይጠቀስ ያለችው የ22 ዓመቷ ኤርትራዊ ከ18 አመት በላይ የሆናቸው ኤርትራውያን የብሄራዊ አገልግሎት አካል የሆነው የሳዋ ማሰልጠኛ ማእከል መግባታቸው አስገዳጅ ከመሆኑ ጋር ተያይዞም እሷ ስለማታምንበት ሸሽታ መሰደዷን ትናገራለች። ከኢትዮጵያ የስደተኞች ካምፕ የሚመጡ ባለሞያዎች ወታደሮች ለይተው እየወሰዱ እንደሆነ ተናግራለች:: "ዓለምአቀፍ የስደተኞች ጉዳይ የሚመለከተው ተቋም ሁሉንም ስደተኞች በእኩል እንደሚያይ ነበር የምናውቀው። እዚህ ከመጣን በኋላ ግን መድልዎ እንደሚፈፀም እየተመለክትን ነው:: ወታደሮችን ለይተው ሲወስዱ አይተናል:: እኛም ውትድርናን ሸሽተን ነው የመጣነው" በማለትም ትናገራለች። እስካሁንም ባለው ወቅት የዓዲግራት ህዝብ ቁርስ፣ ምሳና እራት እያቀረበ የመገባቸው ቢሆንም በባለፉት ሁለት ቀናት ግን በመቋረጡ መቸገራቸውን ትገልፃለች። ከዚህም በተጨማሪ "በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ" በአሁኑ ወቅት ስደተኞቹ የተጠለሉበት ኮሌጅ ትምህርት ለመጀመር ፅዳት እያካሄዱም በመሆኑ መውደቂያቸው እንዳሳሰባቸው ጭንቀትዋን አጋርታለች። "ወደየትም እንደምንሄድ አስጨንቆናል" ብላለች። በተመሳሳይ ለደህንነቷ ስሜ ይደበቅ ያለችና ከደቡባዊ ዞን ሰንዓፈ ከተማ የመጣችው የ19 ዓመቷ የ11ኛክፍል ተማሪ በበኩሏ መጠለያ የሚጠይቅ ስደተኛ እንዴት መብቱ እንደሚታገድ ግራ እንደተጋባች ትናገራለች። ከኤርትራ ከመጣችበት እለት ጀምሮ አንድ ወር ከሁለት ሳምንት በለይቶ ማቆያ ውስጥ መቆየቷ በጣም እንዳሳዘናት ገልፃ ለምን ወደ ስደተኞች ካምፕ እንደማያስገቧቸውም በምትጠይቅበትም ወቅት ግልፅ መልስ የሚሰጣቸውም አካል እንዳላገኙ ትናገራለች። ዓዲግራት ከተማ በሚገኘው የቴክኒክና የሙያ ማሰልጠኛ ማዕከልም ከነበሩት 130 ኤርትራውያንም መካከል 30 የሚሆኑት ብቻ ወደ ስደተኞች ካምፕ መወሰዳቸውንም ለቢቢሲ ገልፃለች። "በቋንቋ መግባባት የማይችሉ ህፃናት የያዙ እናቶች ደም እያነቡ ይገኛሉ" በማለት ችግሩ ምን ያህል አስከፊ እንደሆነ ታስረዳለች። በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል በሚገኙ አራት የስደተኞች መጠለያ ካምፕ እንዲሁም በአፋር ክልል በሚገኘው አንድ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ በሺዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያንም ሰፍረው ይገኛሉ። ከአንድ ዓመት በፊት በነበረው አሰራር ወደ ስደተኞች ካምፕ ለመግባት መስፈርትም ሆነ ምንም ዓይነት ክልከላ እንዳልነበር ይታወቃል። በቅርቡ ግን ወደ ስደተኞች ካምፕ ለማግባት የማጣራት ስራው እየከረረና እየጠበቀ የመጣ መሆኑንም በመግለፅ ወታደሮችና የመንግሥት ሰራተኞች ያልሆኑትን ስደተኞች ወደ ካምፑ እንዳይገቡ መከልከላቸው አግላይ መሆኑንም ይናገራሉ። በአሁኑ ወቅት በዓዲግራት 105፣ በራማ 95፣ በዛላምበሳ 44፣ በገርሁስርናይ 124፣ በዓዲ ነብርእድ 53፣ እንዲሁም በሸራሮ 460 በአጠቃላይ 881 ኤርትራውያን ስደተኞች ወደ ካምፕ ለመግባት በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ ቢቢሲ ከተለያዩ ምንጮች ባጠናቀረው መረጃ መረዳት ችሏል። "ወደ ስደተኞች ካምፕ እንዳንገባ ተከልክለናል" የሚለውን ቅሬታም በሚመለከት ቢቢሲ ጥያቄ ያቀረበላቸው የስደተኞችና ከስደት ተመላሽ ጉዳዮች ኤጀንሲ ሰራተኛ ከዚህ ቀደም የነበረው የስደተኞች አቀባባበል አሰራር ተሻሽሏል ብለዋል። ስሜ አይገለፅ ያሉት እኚሁ ሰራተኛ ኤርትራዊ መሆን ብቻ ወደ ስደተኞች ካምፕ ለመግባት እንደ ቅድመ ሁኔታ እንደማይቀርብና በተሻሻለው አዋጅ መሰረት መመዘኛውን የሚያሟሉ ብቻ ተጣርተው እንደሚገቡ አስታውቀዋል። በተለይም ደግሞ ከኤርትራ ተነስተው በአውሮፕላን በአዲስ አበባ በኩል የሚመጡትን ኤርትራውያን ስደተኞች ወደ ካምፕ መግባት እንደማይችሉም ገልፀዋል።
news-48729331
https://www.bbc.com/amharic/news-48729331
600 ዓመታትን ያስቆጠረው የሣር ድልድይ
በፔሩ አፐሪማክ ግዛት አንድን ትልቅ ወንዝ ለመሻገር በሣር የተሠራን ድልድይ መሻገር ግድ ይላል። የሣር ድልድዩ ለአንድ ዓመት የሚያገለግል ሲሆን በየዓመቱ በአዲስ ገመድ ይተካና አሮጌው በታች ይደረደራል።
የ'ኬስዋቻካ' ድልድይ በእጅ በተፈተለ የሣር ገመድ የሚሠራና በየዓመቱ እየተተካ ከ600 ዓመታት በላይ የኖረ ነው። ከኢንካ ሥልጣኔ መገለጫ ከሆኑት ከተሞች መካከል ከአንዷ ጋር የሚያገናኝ እንደሆነ የሚነገርለት ይህ ድልድይ በ2013 በዪኔስኮ በቅርስነት ተመዝግቧል። • በጂንስ የተሞሸሩት ጥንዶች • ትራምፕ ጦርነት ከተጀመረ ኢራን ከምድረ ገጽ ትጠፋለች ሲሉ አስጠነቀቁ • "እንዴት ለሴት ልጅ የወንዶች ክለብ ይሰጣል?' ተብሎ ነበር" መሠረት ማኒ ድልድይ የመገንባት ባህሉ ከትውልድ ትውልድ እየተላለፈ ወጣቶች አሮጌውን ገመድ በአዲስ እየተኩ በየዓመቱ ለድልድዩ አዲስ መንፈስና ጥንካሬ ያላብሱታል። ድልድዩን የሚሠሩት ወንዶች ብቻ እንዲሆኑ የነዋሪዎቹ ባህል ያስገድዳል። ሴቶች ገመዶችን እየፈተሉ ከወንዙ አፋፍ ላይ ከሚገኝ ሸለቋማ ስፍራ እንዲቀመጡ ይደረጋል። በመጀመሪያው መልሶ የመገንባት ቀን ወንዶች ተሰባስበው ትልልቅ ገመዶችን ወጥረው በትንንሾቹ ያጠላልፋሉ። አጠቃላይ የድልድዩ ስፋት የሰው እግር ውፍረት ያክል ባላቸው ስድስት ገመዶች ላይ ያርፋል። ስድስቶቹ ወፋፍራም ገመዶች እያንዳንዳቸው ከ120 ቀጫጭን የሣር ግማዶችን ይሠራሉ። እያንዳንዱ ቤተሰብ ባለሁለት ፈትል፣ ከጠንካራ ሣር የተገመደ በአካባቢው አጠራር 'ኮያ ኢቹ' የሚባል ገመድ ማበርከት ይኖርበታል። ድልድይን በሚያዘጋጁበት ወቅት ገመዱ የመተጣጠፍ ባህርይ እንዲኖረው ሣሩ ወደገመድነት ከመፈተሉ በፊት በድንጋይ ይቀጠቀጥና ውሃ ውስጥ ይዘፈዘፋል። በድልድይ ሥራው ወቅት ከፊሉ ሰው፣ የድልድይ ሥራውን የሚያሳልጡ ሠራተኞች እንዳይራቡ ከወንዙ የሚጠመዱ ዓሣዎችን፣ አሳማና ዶሮዎችን በድንች ከሽኖ ለምግብነት ያሰናዳል። አዲሱ ድልድይ እንደተጠናቀቀም አሮጌው ይቆረጥና ወንዙ ላይ እንዲንሳፈፍ ይደረጋል። ከስድስቱ ትልልቅ ገመዶች አራቱ መረማመጃ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ሁለቱ ደግሞ ለእጅ መደገፊያና ሚዛን መጠበቂያ ሆነው በጎን በኩል በአጥር መልኩ ቋሚ ሆነው ይሠራሉ። ስድስቱንም ገመዶች ሚዛናቸውን በጠበቀ መልኩ ተወጥረው ከወንዙ ጫፍና ጫፍ በትልልቅ ድንጋይ እንዳይበጠሱ ተደረጎ ይታሰራሉ። በዚህም ማንም ያለፍርሃት ወንዙን በገመድ ድልድዩ አማካኝነት ይሻገራል። ድልድዩን ለመሥራት ምንም ዓይነት ዘመናዊ መሣሪያ አያስፈልግም፤ አይጠቀሙምም። የሚያስፈልገው ሁለተ ነገር ብቻ ነው። ሰውና ሣር። በየዓመቱ ሰኔ በገባ በሁለተኛው እሁድ የሚደረገው የ'ኬስዋቻካ' ድልድይ ግንባታ አራት ቀናትን የሚወስድ ሲሆን በመጠናቀቂያው ዕለት የሙዚቃና የምግብ ድግስ ማሰናዳት የፍፃሜው ማብሰሪያና ማድመቂያ ናቸው።
news-56277295
https://www.bbc.com/amharic/news-56277295
ትግራይ፡ የኤርትራ ወታደሮች እንዲወጡ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አቋም መያዙ ተገለጸ
የኤርትራ ሠራዊት ከትግራይ ክልል እንዲወጣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አንድ አይነት አቋም መያዙን የአስተዳደሩ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ለቢቢሲ ተናገሩ።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የጽፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገብረ መስቀል ካሳ እንዳሉት የኤርትራ ሠራዊት በክልላቸው ውስጥ እንዳለ ከመግለጻቸው በተጫማሪ "በክልሉ ውስጥ ያሉ አካባቢዎችን ተቆጣጥረዋል። ወንጀሎችንም ፈጽመዋል" ሲሉ ከስሰዋል። የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት በትግራይ ክልል የተከሰተውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ የኤርትራ ሠራዊት በክልሉ ውስጥ እንደሚገኝ ቢገልጹም የኢትዮጵያም ሆነ የኤርትራ መንግሥታት ጉዳዩን ሲያስተባብሉ መቆየታቸው ይታወሳል። የኤርትራ ወታደሮች ትግራይ ውስጥ መኖራቸውን በተመለከተ "ሕዝቡ በዓይኑ ያየው እውነታ ነው" ያሉት አቶ ገብረ መስቀል፤ "ስለዚህም ጊዜያዊ አስተዳደሩ ወታደሮቹ ከክልሉ መውጣት አለባቸው ሲል አቋም ይዟል" በማለት በአንድ ድምጽ መወሰናቸውን ተናግረዋል። የአሜሪካ መንግሥት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባለፈው ሳምንት ትግራይ ውስጥ ይገኛሉ ያላቸውን የኤርትራ ወታደሮችን የአማራ ክልል ኃይሎች እንዲወጡ የጠየቀ ሲሆን የውጭ ጉዳይ ኃላፊው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጋር ተወያይተዋል። ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የህወሓት ኃይሎች የሰሜን እዝ ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የአገሪቱ መከላከያ ኃይል እርምጃ እንዲወስድ ትዕዛዝ መስጠታቸው ይታወሳል። ከዚያ በኋላም ጠቅለይ ሚኒስትር ዐብይ በክልሉ እየተካሄደ የነበረው "ሕግ የማስከበር ዘመቻ" የፌደራል መንግሥቱ ኃይሎች መቀለን ከተቆጣጠሩ በኋላ መጠናቀቁን አስታውቀው ነበር። ነገር ግን ከዚያ በኋላም በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶች እየተካሄዱ መሆኑን የዓለም አቀፍ ተቋማት የገለፁ ሲሆን ከ60 ሺህ በላይ ሰዎች ወደ ሱዳን ሲሰደዱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ደግሞ የእለት ምግብ እርዳታ እየተሰጣቸው ይገኛል። ባለፈው ሳምንት የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው ሪፖርት በትግራይ ክልል ውስጥ የኤርትራ ወታደሮች መኖራቸውን አረጋግጦ፤ በአክሱም ከተማ ውስጥ በወሰዱት እርምጃ ከ200 በላይ ሰዎችን ገድለዋል ብሏል። ከዚህ በተጨማሪ የጽህፈት ቤት ኃላፊው በአማራ ክልል ኃይሎች የክልሉ ግዛቶች መያዛቸውን ገልጸው፤ ይህንንም በተመለከተ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ግልጽ አቋም እንዳለው አመልክተዋል "አስተዳደሩ ህወሓት ያስተዳድረው ከነበረው ግዛት በሴንቲሜትር የቀነሰ ክልልን አያስተዳድርም" ብለዋል። አቶ ገብረ መስቀል እንዳሉት ጊዜያዊ አስተዳደሩ በሕገ መንግሥቱ ላይ የተገለጸውን የትግራይ ክልልን እንደሚያስተዳድር ገልጸው፤ "እነዚህን ቦታዎች ከሕግ ውጪ የያዙ ኃይሎች የአገሪቱን ሕገ መንግሥት እየተጻረሩ ነው" ብለዋል። አጠቃላዩ ምዕራባዊ የትግራይ ክፍል እንዲሁም በደቡብ አላማጣ፣ ኮረምና ሌሎች የገጠር አካባቢዎች በአሁኑ ጊዜ በአማራ ክልል ስር መሆናቸውን አመልክተው፤ ይህንንም ለፌደራል መንግሥቱ ሪፖርት ተደርጎ ኃይሎቹ ከአካባቢዎቹ እንዲወጡ በተደጋጋሚ መጠየቃቸውን ገልጸዋል። "ግፊት የምናደርገው የተሰማራው ኃይል እንዲወጣ ብቻ ሳይሆን በአካባቢዎቹ የሚፈጸሙ ወንጀሎች እንዲቆሙና ፈጻሚዎቹ በሕግ እንዲጠየቁ ነው" ሲሉ አቶ ገብረ መስቀል ተናግረዋል። የአማራ ክልል ቀደም ሲል በተካሄደው የክልል አወቃቀር ወቅት ያለአግባብ ከግዛቱ ተወስደው ወደ ትግራይ የተካለሉ አካባቢዎች መኖራቸውን ሲገልጽ መቆየቱ የሚታወስ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ የአድዋ ድል በዓልን በማስመልከት በተዘጋጀ መድረክ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር የሆኑት አቶ አገኘሁ ተሻገር ባደረጉት ንግግር "በወልቃይት ጠገዴ የተደረገው ውጊያ ማንነትን ለማረጋገጥ እንጂ መሬት ለመውረር አይደለም፤ ከዚህ በኋላ ነፃ ወጥተናል" ሲሉ ተናግረው ነበር። የአማራ መገናኛ ብዙሃን ርዕሰ መስተዳደሩን ጠቅሶ እንደዘገበው "በማይካድራ፣ በሁመራ፣ በወልቃይት ጠገዴ፣ በዳንሻ፣ በራያ፣ በአላማጣ፣ በኮረም እና በሌሎች አካባቢዎች በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ" በህወሓት አማካኝነት ተፈናቅለዋል ሲሉ ለሚቀርበው ክስ ምላሽ ሰጥተዋል። በክልሉ ያጋጠመውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ ተፈጽመዋል ከተባሉ ጥቃቶች መካከል በሴቶች ላይ የደረሰውን ጾታዊ ጥቃትን በተመለከተ የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ የተፈጸሙ ጾታዊ ጥቃቶች በተመለከተ መረጃዎችን እያሰባሰበ መሆኑን የተናገሩት አቶ ገብረ መስቀል "ጥቃቱ ከተፈጸመባቸው መካከል በርካቶቹ ወደ ህክምና ተቋማት አልመጡም" ብለዋል። አቶ ገብረ መስቀል ካሳ አክለውም "ሕግ ማስከበር የተባለው ወታደራዊ ዘመቻ በክልሉ ውስጥ ከፍተኛ ውድመትን አስከትሏል" በሰዎች ላይ ሁሉም አይነት ወንጀሎች ተፈጽመዋል ብለዋል። የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደርም በትግራይ ካለው የአስቸኳይ አዋጅ ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ አደጋዎችና ወንጀሎችን እንዲያስቆሙ ከፌደራል መንግሥቱና የፌደሬሽን ምክር ቤትን መጠየቁን ገልጸዋል። ጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ የህወሓት ኃይሎች በትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኘው የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ላይ ጥቃት ከፈጸሙ በኋላ የተቀሰቀሰውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የትግራይ ክልል መስተዳደር እንዲፈርስ መወሰኑ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ በክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተጥሎ የተለያዩ ወገኖች ተሳታፊ የሆኑበት ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ተደርጎ ክልሉን የማስተደደር ሥራ እያከናወነ መሆኑ ይታወቃል።
54078490
https://www.bbc.com/amharic/54078490
ዓለም ተስፋ የጣለበት የኦክስፎርድ የኮሮና ክትባት ምርምር እንዲቆም ተደረገ
የመጨረሻ የክሊኒካል ሙከራ ላይ የነበረውና ትልቅ ተስፋ ተጥሎበት የቆየው የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ከመድሃኒት አምራቹ አስትራዜኔካ ኩባንያ ጋር እያበለጸጉት የነበረው የኮሮና ክትባት ነበር።
ምርምሩ ለጊዜው ባለበት ይቁም ተብሏል። ምክንያቱ ደግሞ የክትባት ቅንጣቱን የወሰዱ በጎ ፍቃደኛ ተሳታፊዎች ህመም ስላጋጠማቸው ነው። ይሁን እንጂ ግዙፉ የመድኃኒት አምራች አስትራዜኔካ ይህ የሚያደናግጥ ሳይሆን የሚያጋጥም ነው ይላል። ህመም የተሰማቸው ተሳታፊዎች ለምን ህመም እንደተሰማቸው ለማወቅ ጊዜ ይፈልጋል። የኦክስትፎርድና የአስትራዜኔካ የምርምር ውጤት የዓለም አገራት ትንፋሻቸውን ውጠው በጉጉት ሲጠብቁት የነበረ ነው። በዓለም ላይ በክትባት ሙከራ ውስጥ እያለፉ ካሉ ደርዘን ከሚሞሉ የምርምር ሥራዎች ሁሉ ይህ ግዙፉና ተስፋም የተጣለበት ነበር። ቀድሞ ለሕዝብ ይደርሳል፣ ዓለምን ይታደጋል ተብሎም ነበር። ይህ የኦክስፎርድና አስትራዜኔካ የጥምረት የክትባት ምርምር ምዕራፍ 3 ደርሶ ነበር። ይህም ማለት ዋናዎቹን የምዕራፍ 1 እና 2 አልፎ፣ ፈዋሽነቱ ተረጋግጦ በብዙ ቁጥር ሰዎች ላይ መሞከር የጀመረ ማለት ነው። በአሜሪካ፣ በዩኬ፣ በደቡብ አፍሪካና በብራዚል የሚገኙ 30ሺ ሰዎች ይህንን ክትባት እንዲወስዱ ተደርጎ ምን ዓይነት ምልክት እንደሚያሳዩ እየተጠበቀ ነበር። ምዕራፍ 3 የመድኃኒት ሙከራዎች በርካታ ሺህ ሰዎች የሚሳተፉባቸው ከመሆናቸው ባሻገር ዓመታትን ይወስዳሉ። አሁን ባለው የዓለም ጉጉት ግን አመታት ይጠበቃሉ ወይ የሚለው አጠያያቂ ነው። ቀጥሎ ምን ይደረጋል? እንዲህ ዓይነት ነገር ሲያጋጥም በሕክምናው ዓለም አዲስ አይደለም። 3ኛ ምዕራፍ የደረሱ የመድኃኒት ሙከራዎች ተሳታፊዎች የተለየ ሕመም ሲያጋጥማቸው ለጊዜው እንዲቆሙ ይደረጋል። አሁን የሆነውም ይኸው ነው። ከዚህ በኋላ ገለልተኛ የተመራማሪዎች ቡድን በጉዳዩ እንዲገባ ይደረጋል። የተወሰዱ ጥንቃቄዎችን ከፈተሸ በኋላ ሁሉም ሂደቶች ትክክል ነበሩ ተብሎ ሲታሰብ የመድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ሙከራውና ምርምሩ እንዲቀጥል ሊወስን ይችላል። "እንዲህ ሰፊ በሆኑ ሙከራዎች በተሳታፊዎች ላይ ህመም መከሰቱ አዲስ ነገር አይደለም። ነገር ግን ገለልተኛ ወገን ሊያጣራው ይገባል" ብለዋል የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ቃል አቀባይ። የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ምርምሩን ለጊዜው እንዲያቆም ሲደረግ ደግሞ ይህ የመጀመርያው አይደለም። ከተሞከረባቸው ሰዎች የተወሰኑት አሟቸው ሆስፒታል ሲገቡ ምርምሮች ሁሉ ባሉበት ይቆማሉ። ይህ የተለመደ አሰራር ነው ይላል፣ የቢቢሲ የጤና ጉዳዮች ዘጋቢ። እንዲያውም ምርምሩ በጥቂት ቀናት ውስጥ ይቀጥል ሊባልም ይችላል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መድኃኒቱን ከኅዳር 3 ምርጫ በፊት አጥብቄ እፈልገዋለሁ ሲሉ ነበር።
news-53174927
https://www.bbc.com/amharic/news-53174927
ሕጻናትን በኢንስታግራም ሊሸጡ የነበሩ በቁጥጥር ሥር ዋሉ
ሁለት ሕጻናትን በኢንስታግራም ለመሸጥ ሲያግባቡ የነበሩ ሦስት ሰዎች ኢራን ውስጥ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
አገሪቱ በተጣለባት መዕቀብ ሳቢያ ኢራናዊያን ኑሮ ከብዶባቸዋል የቴህራን ፖሊስ ሹም ብርጋዲየር ጄኔራል ሁሴን ራሂሚ እንደተናገሩት ከሕጻናቱ አንዱ ገና ከተወለደ 20 ቀን አልሞላውም። ሌላኛዋ ልጅ 2 ወሯ ነበር። ሕጻናቱን ሊሸጡ የነበሩት ሰዎች ልጆቹን በ500 ዶላር ገዝተዋቸው በኢንስታግራም በኩል በ2 ሺህ ዶላር ሊሸጧቸው ሲሉ ነው የተያዙት። ከአንድ ሕጻን ከ1 ሺህ 500 እስከ 2ሺ ዶላር ለማትረፍ አስበው ነበር ተብሏል እነዚህ ግለሰቦች። በቁጥጥር ከዋሉት ውስጥ አንዱ የሕጻናት ነጋዴ እንደተናገረው ልጆቹን ያገኛቸው እጅግ ድሀ ከሆኑ ቤተሰቦች ነበር። እየሸጧቸው የነበረውም የተሻለ ኑሮ ሊያኖራቸው ለሚችል የተደላደለ ቤተሰብ ነው። ብርጋዲየር ጄኔራል ራሂሚ ለኢራን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት ሕጻናቱ ለገበያ ስለመቅረባቸው በኢንስታግራም ማስታወቂው መውጣቱን በሰሙ ጊዜ ክትትል ጀምረዋል። ራሂሚ እንዳሉት ወደ 15 ገጽ ከሚሆን የሽያጭ ስምምነት ወረቀት ውስጥ የእምቦቀቅሎቹን ፎቶግራፍና የደላሎቹን ምሥል ማግኘታቸውን፣ ከዚያም ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል። አሁን ጨቅላዎቹ ለሕጻናት ተንከባካቢ ድርጅት ተሰጥተዋል። ተጠርጣሪዎቹ በበኩላቸው እኛ ሕጻናቱ የተሻለ ሕይወት እንዲያገኙ በሚል ያደረግነው ነው ብለው ድርጊታቸውን ቅዱስ ተግባር አድርገው ተከራክረዋል። በኢራን እንዲህ ዓይነቱ ዜና ሲሰማ ይህ የመጀመርያ አይደለም። በዚህ ዓመት መባቻ ለምሳሌ ጎርጋን በሚባል አውራጃ አራት ሴቶችና አንድ ወንድ በድህነት ውስጥ ያሉ እርጉዞችንና አራሶችን እያፈላለጉ ልጅ ለመግዛት ሲደራደሩ በቁጥጥር ሥር ውለው ነበር። በርካታ ኢራናዊያን በተለያዩ ምክንያቶች ልጅ ለመውለድ ያላቸው ፍላጎት በመቀነሱ ምክንያት በአገሪቱ አዲስ የሚወለዱ ህጻናት ቁጥር እያሽቆለቆለ መሆኑን መንግሥት አሳወቋል። ይህም በሕዝብ ብዛቷ ላይ ተጽእኖን እያደረሰ በመሆኑ በመንግሥት የሕክምና ተቋማት ውስጥ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት እንዳይሰጥ በቅርቡ አዟል።
48703124
https://www.bbc.com/amharic/48703124
ኢትዮጵያ የአሜሪካን የፕላስቲክ ቆሻሻዎች እንደማትቀበል ገለፀች
ከጥቂት ቀናት በፊት በመቶ ሺዎች የሚቆጠር የአሜሪካ ፕላስቲክ ተረፈ ምርት (ቆሻሻ) ከሚላክባቸው አገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗን ዘ ጋርዲያን የተባለው ጋዜጣ ባወጣው የምርመራ ዘገባ ላይ ተጠቅሶ ነበር።
ጋዜጣው የአሜሪካንን የቆሻሻ አወጋገድ ምስጢር ባጋለጠበት በዚህ ዓለም አቀፍ የምርመራ ዘገባው የፕላስቲክ ቆሻሻዎች ወደየት ነው የሚሄዱት በሚልም ለዘመናት የአሜሪካ የፕላስቲክ ቆሻሻ መጣያ የነበሩት ቻይናን የመሳሰሉ ሃገራት ፖሊሲያቸውን በመቀየራቸው ሌሎች ደሃ ሃገራት እንደተመረጡ ያትታል። •የፕላስቲክ ብክለትን እንደሚያስቆም ተስፋ የተደረገበት ስምምነት ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ባንግላዴሽ፣ ላኦስ፣ ሴኔጋል ቀጣዮቹ የአሜሪካ የፕላስቲክ ቆሻሻ መጣያ ስፍራዎች መሆናቸውን በጠቀሰው በዚህ ዘገባ፤ የአገራቱ የአካባቢ ጥበቃ ፖሊሲ የላላ መሆኑ እንዲሁም፤ ፕላስቲኮችን መልሶ ጥቅም የማዋል ሥራ (ሪሳይክል) ኃይል አባካኝ በመሆናቸው እነዚህም ሃገራት ደግሞ ርካሽ የሰው ጉልበት ስላላቸው ተመራጭ እንዳደረጋቸው ጠቅሷል። ይህንንም ተከትሎ በተለያዩ ማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ላይ ብዙ ኢትዮጵያዊያን "እንዴት የሃብታም ሃገራት ቆሻሻ ማራገፊያ እንሆናለን?" በማለት ጠንካራ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። ነገር ግን ወደ ኢትዮጵያ እንዲወገድ ይመጣል ስለተባለው ቆሻሻ የወጣው መረጃ ትክክል እንዳልሆነ የፌደራል የአካባቢ፣ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ለቢቢሲ ገልጿል። • ዌል የተባለው የባህር እንስሳ 6 ኪሎ ያህል ኩባያ ውጦ ተገኘ የፕላስቲክ ቆሻሻ የሃገሪቱ ከፍተኛ ችግር በሆነበት ወቅት ኢትዮጵያ ከውጭ የምትቀበልበት ምንም ምክንያት እንደሌለ ነው በፌደራል አካባቢ፣ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን የአካባቢ ብክለት ሁኔታ ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ የአየር ብክለት ክትትልና ቁጥጥር ባለሙያ አቶ መሰረት አብዲሳ የገለጹት። "የፕላስቲክ ቆሻሻ ከፍተኛ የብክለት ምንጭ ነው፤ ይህንንም ለመከላከልም በሃገር ደረጃ ከፍተኛ ሥራ እየተሰራ ነው፤ ፍቃድ የሚሰጠውም አካል ፍቃድ የሚሰጥ አይመስለኝም፤ አይሰጥምም" በማለት መንግሥት በከተሞች አካባቢ ያለውን ብክለት ችግር ከመቆጣጠር ከፍተኛ ትኩረት በተሰጠበት ወቅት ከሌላ ሃገር ቆሻሻ ለማስገባት ፈቃደኛ አይሆንም ብለዋል። ጉዳዩን የተመለከተው ሥራ በእርሳቸው መስሪያ ቤት በኩል ከመሰራቱ አንፃር ክትትል እንደሚያደርጉ የተናገሩት አቶ መሰረት በጋርዲያን ላይ የወጣው መረጃ ስህተት እንደሆነ ገልፀዋል። የተባለውን ቆሻሻ "ሃገሪቷ በፕላስቲክ ምርቶችና አወጋገዱ እየተቸገረች ባለችበት ሁኔታ እንደማትቀበል" ገልፀዋል። "ይሄ መሆን አይችልም፤ እንዴትስ እናስገባለን?" በማለት አቶ መሰረት ፈርጠም ብለው በጉዳዩ ላይ ጥያቄ አንስተዋል። የፕላስቲክ ተረፈ ምርቶች ይግባ ቢባል ፈቃድ ሰጭው አካል የትኛው ነው ተብለው ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ ባለሙያው ሲመልሱ "የፕላስቲክ ጉዳዮችን የሚመለከት በፌደራል አካባቢ፣ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ውስጥ ደረቅ ቆሻሻና አደገኛ ኬሚካሎች የሚባል ዲፓርትመንት አለ" ብለዋል። ግን ከዚህ በተጨማሪ እንደተባለው በሚዲያ ብቻ ዝም ብሎ ይፋ እንደማይደረግና የእርሳቸውም ቢሮ እንዲሁም ጉምሩክም ሆነ ሌሎች አካለት በሃገር አቀፍ ደረጃ መታወቅ ያለበት ጉዳይ እንደሆነ አመልክተዋል። "ይህ አካባቢንም ሆነ ሰውን የሚጎዳ ከመሆኑ አንፃር ዝም ብሎ በሚዲያ ብቻ ስለተነገረ የሚገባ አይደለም፤ በሃገር ደረጃ ይፋ ሊደረግ ይገባል። ከዚህ አንጻር ለቆሻሻው ፍቃድ የሚሰጥ አካል ይኖራል ብዬ አላስብም" ብለዋል። • የጄኔራል ደምሴ ቡልቶ ልጅ 'መራር' ትዝታ አንዳንድ የግል ድርጅቶች የፕላስቲክ ግብአቶችን በግላቸው ለመጠቀም ሊያስገቡ እንደሚችሉ የጠቆሙት አቶ መሰረት "የሚያስገቡም ከሆን ቀድመው ከሚመለከተው አካል ፍቃድ መውሰድ አለባቸው፤ ብዙ ሂደትም አለው" ብለዋል። አቶ መሰረት ሃገሪቷ በፕላስቲክ ምርቶች ላይ ጠንካራ አቋም እንዳላት ገልፀው፤ በአዋጁ መሰረት የፕላስቲክ ቆሻሻዎችን ለማስወገድ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገና የተለያዩ ፋብሪካዎች እየተስፋፉ መሆኑንም ገልፀዋል። ከዚህም በተጨማሪም የፕላስቲክ ምርቶችን ፈጭቶ ወደ ውጭም እየተላከ ነው ብለዋል። ለወደፊትም እንደሌሎች ጎረቤት ሃገራት ከፕላስቲክ ነፃ የሆነ ከተማም ሆነ አገር መፍጠር እንደሚቻልም ባለሙሉ ተስፋ ናቸው።
news-52328123
https://www.bbc.com/amharic/news-52328123
የባህር ዳሩ የኮሮናቫይረስ ህክምና ማዕከል የመሳሪያዎች ጥያቄ
ከአዲስ አበባ ውጪ ለኮሮናቫይረስ ህሙማን ክትትልና የህክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘው የባህር ዳር የመከላከያ ሆስፒታል ለሥራው የሚያስፈልጉ ግብዓቶች እንዲሟሉ ባለሙያዎች ጠየቁ።
ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የህክምና ባለሙያ ለቢቢሲ እነደገለጹት አሁን በሆስፒታሉ ያሉት ሦስት ታካሚዎች ሲሆኑ እነሱም ጥሩ ሁኔታ ላይ መገኘታቸው ባለው ግብዓት ለመሥራት እንዳስቻላቸው ጠቁመዋል። ነገር ግን ወረርሽኙ ተስፋፍቶ "10 ወይም 20 ሰው ቢመጣ በዚህ ቁመና መሥራት አንችልም" ሲሉ ስጋታቸውን አስቀምጠው በቶሎ ቀድሞ መዘጋጀት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። ማዕከሉ ውስጥ ለኮሮናቫይረስ ህሙማን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ የህክምና መሣሪያዎችና ባለሙያዎች ራሳቸውን ከቫይረሱ የሚከላከሉበት ቁሳቁሶች በቁጥር አነስተኛ ናቸው ብለዋል። ካናገርናቸው ባለሙያዎች መካከል አንዱ "ሜካኒካል ቬንትሌተር የሚበባለው የጽኑ ህሙማን ማሽን አንድ ነው ያለው። የልብ መመርመሪያ ማሽንና ሌሎችም ማሽኖች አልተሟሉም። ለባለሙያዎች መከላከያ የሚውሉ ግብዓቶች የሉም" በማለት ለማሟለት ቸልተኝነት እንዳለ ይናገራሉ። በዚሁ ጉዳይ ላይ ምላሽ የሰጡት የክልሉ የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መልካሙ አብቴ፤ አሁን ያለውን ሥራ ለመሥራት የሚያክል በቂ ግብዓት መኖሩን ጠቅሰው የህሙማን ቁጥር ከፍ ካለ ተጨማሪ መሣሪያዎች እንደሚያስፈልጉ አመልክተዋል። "ይህንን ጉዳይ ከጤና ጥበቃ ሚንስቴር ጋር እየተነጋገርን ነው። ግዢዎችን እየተካሄዱ መሆናቸው ተገልጾልናል፤ ከዚህ በኋላ የሚሰጠን ነው የሚሆነው። እኛምን ባሉን መንገዶች የምናሟላ ይሆናል።" ከላብራቶሪ መሣሪዎች ጋር ተያይዞም "መመርመሪያዎችን ለማሟላት እየሠራን ነው። ማሽኖችን እያሟላን ነው። አሁን የሚከናወነውን የህክምና ሥራ የሚያስተጓጉል ግን አይደልም" ብለዋል። ኃላፊው በተጨማሪም የተለየ ተጋላጭነት ላላቸው በባለሙያዎች የጤና ጥበቃ ሚንስቴር የሚገባ ጥቅማ ጥቅምን በተመለከተ እያስጠና መሆኑን ገልጸው በቅርቡ ይፋ ይደረግል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። ባህር ዳር በሚገኘው የኮሮናቫይረስ ህክምና በሚሰጥበት ማዕከል ውስጥ ሦስት ታካሚዎች ብቻ ያሉ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለት በክልሉ ሁለት ተጨማሪ ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የጤና ጥበቃ ሚንስቴር አስታውቋል።
news-51625624
https://www.bbc.com/amharic/news-51625624
ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንተርኔት ሲቋረጥ ምን ይከሰታል?
ማርቆስ ለማ ከቢሮው መስኮት ሆኖ አዲስ አበባን እየቃኛት ነው። ቢሮው የሚገኝበት ቦታ የአዲስ አበባን ውብ ገጽታ በቀላሉ ያሳየዋል። ማርቆስ አይስአዲስ የተሰኘ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ተቋም መስራች ነው።
ከሌሎች ጋር ተጋርቶ የሚሰራበት ቢሮው ለሥራ ፈጠራ በነቁ እና በጥቁር ቡና በተነቃቁ የፈጠራ ባለሙያዎች የተሞላ ነው። ይህ የፈጠራ ባለሙያን መሰባሰቢያ ግን የሰው ዘር ዝር ሳይልበት የሚቀርበት ወቅት አለው-ኢንተርኔት ሲቋረጥ። አክሰስ ናው የተባለ የዲጂታል መብት ተሟጋች ለቢቢሲ ያጋራው መረጃ እንደሚያሳየው እአአ በ2019 ብቻ በ33 አገራት ይኹነኝ ተብሎ 200 ጊዜ ያህል ኢንተርኔት ተቋርጧል። "እዚህ ሰው መምጣት ያቆማል፤ ማንም ድርሽ አይልም፤ ቢመጡም አንኳ ለረዥም ጊዜ አይቆዩም። ምክንያቱም ያለ ኢንተርኔት ምን ሊሰሩ ይችላሉ?" ሲል ይጠይቃል ማርቆስ። "ሶፍትዌር ዴቬሎፕ የማድረግ ኮንትራት ተቀብለን በወቅቱ ማስረከብ ባለመቻላችን ተነጥቀናል። ምክንያቱም የኢንተርኔት መቋረጥ ነበር። ዓለም አቀፍ ደንበኞቻችንም እነርሱን ገሸሽ የሚያደርግ አገልግሎት እንዳለን ያስባሉ፤ ነገርግን ምንም ማድረግ አንችልም።" በስልክ ትዕዛዝ ተቀብለው የሚያደርሱ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች በስልካቸው ትዕዛዝ እስኪመጣ ተሰባስበው ይጠብቃሉ። ነገር ግን "ኢንተርኔት በሌለበት ማን በኦንላየን ወይም መተግበሪያ ተጠቅሞ ማዘዝ ይችላል?" ይላል ማርቆስ። "እዚህ ኢንተርኔት መዘጋት በንግድ ተቋማትና በሰዎች እንቅስቃሴ ላይ ተጽዕኖ አለው።" ማርቆስ ለማ ከድርጅቱ አይስአዲስ አርማ ጎን ኢንተርኔትን ማቋረጥ ኢንተርኔት ማቋረጥ በኢትዮጵያ ብቻ የሚከሰት የንግድ ሥራን ብቻም የሚያስተጓጉል አይደለም። አክሰስ ናው የተሰኘው ቡድን በሰራው ጥናት በዓለም ላይ የኢንተርኔት መቋረጥ በአስር ሚሊየኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን በተለያየ ምክንያት የጎዳ ሲሆን በዓለም የተለያዩ ስፍራዎችም ላይ ይከሰታል። መንግሥታት የተወሰነ አካባቢ ኢንተርኔት እንዳያገኝ ሲፈልጉ የኢንተርኔት አቅራቢው ተቋም ባልቦላውን እንዲያጠፋ ያዛሉ፤ አልያም ደግሞ የተወሰነ የድረገጽ አገልግሎትን ብቻ እንዳይሰራ ያደርጋሉ። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እንዲህ አይነት እርምጃዎች መንግሥታት ጭቆናን የሚያካሂዱበት መሳሪያ ነው በማለት ስጋታቸውን ይገልጻሉ። የመብት ተሟጋቹ ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ኢንተርኔት መቋረጥ ሕዝባዊ ተቃውሞዎች በሚበረታባቸው ወቅቶችና አካባቢዎች ላይ ጎልቶ ይታያል። በ2019 ብቻ ኢንተርኔት የተቋረጠባቸው አገራት ሲጠኑ 60 ህዝባዊ ተቃውሞዎች በነበረበት ወቅት 12ቱ ደግሞ በምርጫ ጊዜ መሆናቸውን ያሳያል። መንግሥታት አንዳንዴ ኢንተርኔት የተቋረጠው የሕዝብ ደህንነትን ለማረጋገጥ እና ሐሰተኛ ዜና እንዳይዛመት ለመከላከል እንደሆነ በመግለጽ ድርጊቱን ያስተባብላሉ። ይህንን ሃሳብ የሚቃወሙ አካላት ግን የመረጃ ፍሰትንና የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ለማጨናገፍ ሆን ተብሎ የሚጠቀሙበት መንገድ መሆኑን በመግለጽ ይተቻሉ። የተባበሩት መንግሥታት ኢንተርኔትን የማግኘት መብት ሰብዓዊ መብት ነው ብሎ የደነገገው እኤአ በ2016 ነው። ነገር ግን ሁሉም የዓለማችን መሪዎች የዚህ ሃሳብ ደጋፊዎች ወይም አቀንቃኞች አይደሉም። እኤአ በ2019 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ኢንተርኔት "ውሃ ወይንም አየር አይደለም" በማለት የኢንተርኔት መቋረጥ የአገር መረጋጋትን ለማረጋጋጥ አስፈላጊ የሚሆንበት ጊዜ እንዳለ ተናግረው ነበር። ማርቆስ ለማ በዚህ ሀሳብ በጣም ነው የሚበሳጨው። "መንግሥት ኢንተርኔትን እንደ አስፈላጊ ነገር አያየውም። ኢንተርኔትን እንደ ማህበራዊ መገናኛ ብዙኀን ብቻ ነው የሚያየው፣ ስለዚህ የኢንተርኔትን ምጣኔ ሃብታዊ ፋይዳውን አይመለከቱትም።" በብዛት ኢንተርኔትን በማቋረጥ ህንድ ቀዳሚ ናት የባለፈው የፈረንጆች ዓመት መረጃ እንደሚያመለክተው በዓመቱ ከየትኛውም አገር በበለጠ ህንድ ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው በተደጋጋሚ ኢንተርኔትን የመዝጋት ሁኔታ ተከስቷል። የሞባይል ኢንተርኔትና የብሮድባንድ አገልግሎቶች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ውስጥ በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ ለ121 ጊዜ እንዲዘጉ ተደርገዋል። አብዛኛው ማለትም 67 በመቶው ደግሞ ያጋጠመው በህንድ በምትተዳደረው በአወዛጋቢዋ የካሽሚር ግዛት ውስጥ ነው። የማዕከላዊ አፍሪካ አገር የሆነችው ቻድ ደግሞ እስካሁን ከታዩት የኢንተርኔት ማቋረጦች መካከል ለረጅም ጊዜ የዘለቀውን በማስተናገድ ቀዳሚ ሆናለች። በአገሪቱ በፈረንጆቹ 2018 ላይ የተዘጋው የኢንተርኔት አገልግሎት ከ15 ወራት በላይ ሳይከፈት ቆይቷል። ሱዳንና ኢራቅ ውስጥ በተካሄዱ ተቃውሞዎች ውስጥ ተሳታፊ የነበሩ ሰዎች በኢንተርኔት መዘጋት የተነሳ እንቅስቃሴያቸውን ሲያስተባብሩ የነበረው ከኢንተርኔት ግንኙነት ውጪ ሆነው ነበር። የእያንዳንዱ ኢንተርኔትን የመዝጋት እርምጃ ከሚሸፍነው ቦታ አንጻር የሚኖረው ተጽእኖ የተለያየ ነው። በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ውስን ከሆኑ የማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃንን የመዝጋት እርምጃ አንስቶ ሁሉንም የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ማቋረጥ የሚከሰትበት ሁኔታ አለ። "ቶርቲንግ" የኢንተርኔት አገልግሎትን የመቆጣጠር አይነት እገዳ ሲሆን መከሰቱንም ለመከታተል አስቸጋሪው ነው። ይህም የሚከሰተው መንግሥታት የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ቀርፋፋ እንዲሆን በማድረግ ነው። ይህም 4ጂ የነበረውን ፈጣኑን የኢንተርኔት ትስስር ወደ 2ጂ በማውረድ ቪዲዮዎችን ለማጋራት ወይም በቀጥታ ለማስተላለፍ ከማይቻልበት ደረጃ ያደርሰዋል። ይህ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ታጂክስታን ውስጥ ፌስቡክን፣ ትዊተርንና ኢንስታግራምን ጨምሮ በአብዛኞቹ የማኅበራዊ ትስስር መድረኮች ላይ አጋጥሟል። ሩሲያንና ኢራንን የመሳሰሉ አገራት ደግሞ በኢንተርኔት ላይ ያላቸውን ቁጥጥር ሊያጠናክር የሚያስችል በአገራቸው ውስጥ ብቻ ተወስኖ የሚሰራ የኢንተርኔተ አገልግሎትን እየገነቡና እየፈተሹ መሆናቸው ይነገራል። የዲጂታል መብቶች ተከራካሪው አክሰስ ናው የተባለው ቡድን እንደሚለው "በርካታ አገራት የተቺዎቻቸውን ድምጽ ለማፈን ወይም ማንም ሳያይና ሳይሰማ ሌሎች የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ለመፈጸም ሲሉ የመጨረሻውን ኢንተርኔትን የመዝጋት እርምጃ ከሌሎች አገራት በመማር ተግባራዊ እያደረጉ ነው።"
news-45488744
https://www.bbc.com/amharic/news-45488744
ድንበር ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች ከዛሬ ጀምሮ ለቀው ይወጣሉ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ በኢትዯጵያና በኤርትራ ድንበር ላይ ለዓመታት ሰፍረው የነበሩት የኢትዮጵያ ወታደሮች ከዛሬ ጀምሮ ለቀው መውጣት እንደሚጀምሩ አስታወቁ።
ይህ የሚሆነውም ከሃያ ዓመታት በኋላ ተዘግቶ የነበረው የሁለቱ አገራት ድንበር እንደገና ዛሬ መከፈቱን ተከትሎ ነው። በድንበር መክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የሁለቱን አገራት ወታደሮች ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከሁለቱም ሃገራት መሪዎቹን አጅበዋቸው ነበር። ዋነኛ የጦር ግንባር ሆነው ለሁለት አስርት ዓመታት በቆዩት የቡሬና የዛላምበሳ የድንበር አካባቢ መሪዎቹ ተገኝተው ነበር። • ኢትዮጵያና ኤርትራ፡ አዲስ ዓመትን በቡሬ ግንባር • የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት 20ኛ ዓመት - መቋጫ ያላገኘ ፍጥጫ ከ1992 ዓ.ም ጦርነት በኋላ የሁለቱን አገራት ህዝቦች የሚያደርጉትን ንግድና እንቅስቃሴን ገትቶ የቆየውን ግንብ ትናንት የሁለቱ አገራት ወታደሮች መንገዶችን በመክፈት በድንበር ላይ ለእንቅስቃሴ አመቺ ሁኔታ ለመፍጠር ጥረት ሲያደርጉ ነበር። በተባበሩት መንግሥት አሸማጋይነት በአውሮፓውያኑ 2000 የተደረገው የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሳይሆን መቆየት አገራቱን በባላንጣነት አቆይቷል። ወታደሮችን ከድንበር አካባቢ እንዲለቁ ማድረግም የኤርትራ ዋነኛ ፍላጎቷ የነበረ ሲሆን ኢትዮጵያ በ2000 የተደረገውን የድንበር ኮሚሽኑን ጥሳለች ተብላ ተወቅሳበታለች። አሁን ሁለቱም አገራት በቅርቡ በተፈራረሙት የሰላም ስምምነት ከ1990ዎቹ መጨረሻ አንስቶ ምንም ዓይነት ግንኙነት ያልነበራቸውን ሁለቱን አገራት ግንኙነት በማይታመን መልኩ እየለወጠ ይገኛል። የጊዜ ሠሌዳ • ግንቦት 16/1985 ዓ.ም፡ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ነፃ መውጣቷ በይፋ ታወጀ • ሚያዚያ 28/90 ዓ.ም፡ የድንበር ጦርነቱ ተጀመረ • ሰኔ 11/1992 ዓ.ም፡ ጦርነቱን ለማቆም ስምምነት ተፈረመ • ታህሳስ 03/1993 ዓ.ም፡ የአልጀርስ የሰላም ስምምነት ተፈረመ • ሚያዚያ 05/1994 ዓ.ም፡ የኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ኮሚሽን ይግባኝ የሌለውን ውሳኔውን አሳወቀ
48019534
https://www.bbc.com/amharic/48019534
ወባ ይከላከላል የተባለለት ክትባት ማላዊ ውስጥ ሙከራ ላይ ሊውል ነው
በዓለም ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው የተባለለት የወባ በሽታ ክትባት ማላዊ ውስጥ ለሚገኙ ሕፃናት በሙከራ መልክ ሊሰጥ መሆኑ ተሰምቷል።
ክትባቱ የሰውነትን የመከላከል አቅም በማጎልበት የወባ ትንኝ የምታመጣውን የወባ ባክቴሪያ ያዳክማል ተብሏል። ከዚህ በፊት በተደረገው ሙከራ መረዳት እንደተቻለው፤ ዕድሜያቸው ከ5-17 ወራት የሆኑ ሕፃናት ክትባቱን ወስደው ከበሽታው መጠበቅ ችለዋል። • በኢትዮጵያ የቢጫ ወባ ወረርሽኝ 10 ሰዎችን ገደለ ገዳዩን የወባ በሽታ ከምድረ-ገፅ ለማጥፋት የተደረገው ጥረት የተሳካ ቢመስልም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን በሽታው ማንሰራራት አሳይቶ ነበር። ዓለም ላይ በወባ ምክንያት ሕይወታቸው ካለፈ ግማሽ ሚሊየን ገደማ ሰዎች መካከል 90 በመቶው አፍሪቃ ውስጥ እንደሚገኙ፤ አብዛኞቹም ሕፃናት እንደሆኑ ጥናት ይጠቁማል። ምንም እንኳ ማላዊ የወባ በሽታን ለመከላከል ሁሉንም ዓይነት መላ ብትጠቀምም ቀንደኛዋ የበሽታው ተጠቂ መሆኗ ግን አልቀረም። በግሪጎሪያን አቆጣጠር 2017 ላይ ብቻ 5 ሚሊዮን የማሊ ዜጎች በወባ በሽታ ተጠቅተዋል። ማላዊን ጨምሮ ኬንያ እና ጋና አርቲኤስኤስ የተሰኘውን የወባ በሽታ ክትባት ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲሞክሩ የተመረጡ ሃገራት ናቸው። ሃገራቱ የተመረጡበት መሥፈርት ደግሞ ወባን ለማጥፋት በየቤቱ አጎበር እስከመዘርጋት ቢደርሱም በሽታው ሊቀንስ አለመቻሉ ነው። • የቢጫ ወባ ካርድ በቦሌ ለሚወጡ ሁሉ ግዴታ ሊሆን ነው? ክትባቱ ለሦስት አሥርት ዓመታት ያህል አሉ በተባሉ ሳይንቲስቶች ሲብላላ የቆየ መሆኑም ተዘግቧል፤ እስካሁንም 1 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ወጭ እንደሆነበት ተነግሯል። የክትባቱን ሂደት በበላይነት የሚቆጣጠረው የዓለም ጤና ድርጅት ነው። የክትባቱ የመከላከል አቅም 40 በመቶ ቢሆንም ከሌሎች መከላከያ መንገዶች ጋር በመሆን ለውጥ ሊያመጣ ይችላል ይላል ድርጅቱ። ክትባቱ ለአንድ ሕፃን አራት ጊዜ የሚሰጥ ሲሆን ለሦስት ተከታታይ ጊዜ በየወሩ እንዲሁም የመጨረሻው ከ18 ወራት በኋላ ይወሰዳል። እስከ 2023 ይቆያል የተባለለት ይህ የክትባት ሂደት ማላዊ ውስጥ ከተጀመረ በኋላ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ኬንያ እና ጋና ላይ የሚቀጥል ይሆናል። • ሃሰተኛ መድሃኒቶችን ለገበያ ያቀረቡ ተፈረደባቸው
news-56198629
https://www.bbc.com/amharic/news-56198629
ፌስቡክ የሚየንማር መንፈቅለ-መንግሥት መሪዎችን ከገፁ አገደ
ግዙፉ ማሕበራዊ ድር-አምባ ፌስቡክ የሚየንማር ወታደራዊ መሪዎችንና አጋሮቻቸውን ከገፁ አግዷል።
ኩባንያው እንዳለው ውሳኔውን የወሰደው "የሚየንማር ወታደራዊ መሪዎች ፌስቡክና ኢንስታግራም እንዲጠቀሙ ማድረግ ያለውን አደጋ ካጤነ' በኋላ ነው። የሃገሪቱ ወታደራዊ ኃይል የ2020 ምርጫ የተጭበረበረ ነው ለማለት ፌስቡክን እንደ አንድ መድረክ ተጠቅሞ ነበር። ከሚየንማር 54 ሚሊዮን ሕዝብ መካከል ከግማሽ በላዩ ፌስቡክ ይጠቀማሉ። ለአንዳንዶች ፌስቡክ ማለት በይነ-መረብ ማለት ነው። ኩባንያው ከቀናት በፊት የሃገሪቱን ወታደራዊ ኃይል ገፅ የፌስቡክን አጠቃቀም ሕግ ጥሷል በማለት ማገዱ ይታወሳል። ወታደራዊው ኃይል በመንፈቅለ-መንግሥት ሥልጣን ከያዘ በኋላ ተቃዋሚዎችን አሥሯል፤ የኢንተርኔት አገልግሎት አቋርጧል፤ እንዲሁም ማሕበራዊ ድር አምባዎች እንዲዘጉ አዟል። ፌስቡክ ረቡዕ አመሻሹን ባወጣው መግለጫ በፈረንጆቹ የካቲት 1 ከተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት በኋላ ወታደራዊ መሪዎቹን ማገድ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ ብሏል። መፈንቅለ-መንግሥቱን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ ቢያንስ ሶስት ሰልፈኞችና አንድ ፖሊስ ተገድለዋል። ወታደራዊው መንግሥት ምርጫ በማሸነፍ ሥልጣን የያዙ ግለሰቦችን አሥሯል። ፌስቡክ ጨምሮ ከሚየንማር ወታደራዊ ኃይል ጋር ግንኙነት ያላቸው የንግድ ተቋማት በገፁ ማስታወቂያ እንዳያስኬዱ እንደሚያግድ አስታውቋል። ግዙፉ ፌስቡክ እንዳለው እገዳው እንደ ጤና እና ትምህርት ሚኒስቴር ያሉ ሕዝብ አገልጋይ መሥሪያ ቤቶችን የሚመለከት አይደለም። ወታደራዊው ኃይል ተቃውሞችን ለማርገብ በሚል ፌስቡክን ለተወሰነ ጊዙ ያክል አግዶ ነበር። ሚየንማር ውስጥ በፌስቡክ አማካይነት ሃሰተኛ ዜናዎች ብዙ ጊዜ ይሰራጫሉ። በርካታ የመብት ተሟጋቾችም ይህን ሲተቹ ቆይተዋል። መፈንቅለ-መንግሥቱ ከመካሄዱ ቀደም ብሎ በፌስቡክ አማካኝነት የቡድሃ እምነት በሚበዛባት ሃገር የኃይማኖት ግጭት እንዳይነሳ ይፈራ ነበር። በፈረንጆቹ 2014 ፀረ-ሙስሊም የሆኑት መነኩሴ አሺን ዊራቱ አንዲት የቡድሃ እምነት ተከታይ ታዳጊ በሙስሊም ወንዶች ተደፍራለች ብለው መልዕክት አጋርተው ነበር። ከቀናት በኋላ በዚህ ዜና ምክንያት በተነሳ ግጭት ሁለት ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል። ከግድያው በኋላ መረጃውን ያጣራው ፖሊስ መነኩሴው ያሰራጩት መረጃ ሙሉ በሙሉ ሃሰተኛ እንደሆነ ደርሶበታል። በ2017 ደግሞ በሮሂንጃ ሙስሊሞች ላይ በተነሳው ጥቃት ወቅት የፌስቡክ ስም በክፉ ሲነሳ ነበር። አሁን የወታደሩ መሪ የሆኑት ሚን ኦንግ ሂያንግ በወቅት የሮሂንጃ ሙስሊሞች ከባንግላዴሽ የመጡ ናቸው ማለታቸው ይታወሳል። ምንም እንኳ የሮሂንጃ ሙስሊሞች ለዘመናት በቀድሞዋ በርማ በአሁኗ ሚየንማር ቢኖሩም በወቅቱ በደረሰባቸው ጥቃት ምክንያት ወደ በርካቶች ወደ ባንግላዴሽ ሸሽተው ነበር። ፌስቡክ አሁን የወታደራዊ ኃይሉን መሪ ሚን ኦንግን ጨምሮ ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ከገፁ አግዷል። ፌስቡክ የአንድ ሃገር ወታደራዊም ሆነ ፖለቲካዊ ባለሥልጣን ሲያግድ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ፌስቡክ ሃሰተኛ መረጃዎች በገፁ ላይ ሲንሰራፉ አፀፋዊ ምላሽ አይሰጥም ተብሎ ብዙ ጊዜ ይተቻል።
50217514
https://www.bbc.com/amharic/50217514
በእዳ ተይዞ የነበረው ብቸኛው የዚምባብዌ አውሮፕላን በረራ ጀመረ
ባሳለፍነው ሳምንት በእዳ ተይዞ የነበረው ብቸኛው የኤይር ዚምባብዌ አውሮፕላን በረራ ጀመረ።
ኤይር ዚምባብዌ በአንድ አውሮፕላን ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ብቸኛ መዳረሻውም ጆሃንስበርግ ከተማ ነው ይህ ብቸኛ አውሮፕላን ወደ ደቡብ አፍሪካ፣ ጆሃንስበርግ በረራ ካደረገ በኋላ ነበር ለደቡብ አፍሪካ መንግሥት መክፈል የነበረበትን እዳ እስኪከፈል ተይዞ የቆየው። የዚምባብዌ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ኤይር ዚምባብዌ፤ በጆሃንስበርግ አየር ማረፊያ የአገልግሎት ክፍያዎች ውዝፍ እዳ አለበት ተብሏል። አየር መንገዱ ያለበት የዕዳ መጠን እና አውሮፕላኑን ነጻ ለማውጣት ምን ያክል ክፍያ እንደፈጸም አልተገለጸም። • የዝሆን ግልገሎች ለዓለም ንግድ እንዳይቀርቡ ታገደ • የቀድሞው የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ አረፉ • ዚምባብዌ እንዴት ሰነበተች? ባለቤትነቱ የዚምባብዌ መንግሥት የሆነው ኤይር ዚምባብዌ፤ በአንድ አውሮፕላን ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ብቸኛ መዳረሻውም ጆሃንስበርግ ከተማ ነው። "በረራችንን ዛሬ ጀምረናል። አውሮፕላኑ ዛሬ ጠዋት ወደ ጆህንስበርግ በረራ አድርጓል" ሲሉ የኤይር ዚምባብዌ ኮርፖሬት አግልግሎቶች ኃላፊ የሆኑት ታፋደዘዋ ማንዶዜ ለሄርልድ ኒውስ ተናግረዋል። "በረራ ለማድረግ የሚያስፈልገንን ፍቃድ አግኝተናል። የሚጠበቅብንን ክፍያዎችም ፈጽመናል" ብለዋል። ኤይር ዚምባብዌ እአአ 2017 ላይ በተከማቸበት ከፍተኛ ውዝፍ እዳ ከግማሽ በላይ ሠራተኞቹን ለማሰናበት ተገዶ ነበር። ይህም ብቻ ሳይሆን ኤይር ዚምባብዌ በደህንነት ስጋት ምክንያት በአውሮፓ አገራት አየር ክልል የመብረር ፍቃድ የለውም።
news-47952952
https://www.bbc.com/amharic/news-47952952
ሴኔጋላዊ ወንዶችን ልጅ እንዲያዝሉ ያደረገችው የፎቶ ባለሙያ
በሴኔጋል መዲና ዳካር ጎዳናዎች ላይ ወንዶች ልጆቻቸውን በጀርባቸው አዝለው ፎቶ ማንሳቷ ይህንን ያህል ግርምት ይፈጥራል ብላ ባታስብም ከማህበረሰቡ ያገኘችው አድናቆት እንዳስደመማት የፎቶ ባለሙያዋ ማርታ ሞሬይራስ ትናገራለች።
የሲቪል መኃንዲሱ ቢራማና ልጁ ንዴዬ በጎዳናዎች ላይ ፎቶ በምታነሳበትም ወቅት ከፍተኛ ቁጥር ባለው ሕዝብ ተከብባ የነበረ ሲሆን ይሄም ለሥራዋ አስቸጋሪ እንደነበር ስፔናዊቷ የፎቶግራፍ ባለሙያ ትናገራለች፤ "የሚያጨበጭቡ ነበሩ፤ በአንዳንድ አጋጣሚም የተሰሰበው ሕዝብ ከፍተኛ በመሆኑ ፎቶ ለማንሳት እክል ፈጥሮብኝ ነበር" ብላለች። •"ማንም መብታችንን ሊሰጠን ስለማይችል፤ ሴቶች ማንንም ሳይጠብቁ በራሳቸው መታገል አለባቸው" አክላም "መንገድ ላይ ፎቶ ሳነሳ የሚያገኙኝ ሴቶች በሙሉ በደስታ ጨብጠውኝ 'እንዲህ ዓይነት ነገር በየቀኑ እኮ አያጋጥምም፤ እስቲ ባሌን ልደውልለት' ይሉኛል። ሥራዎቿ በዚህ ዓመት የሶኒ ዓለም አቀፍ የፎቶ ሽልማት ላይ ለእጩነት ከተመረጡት መካከል ሲሆኑ ሃሳቡም የመጣላት ሴኔጋልን ከ11 ዓመታት በፊት በጎበኘችበት ወቅት ያነሳቻቸውን ፎቶዎች ስታገላብጥ አብዛኛው የፎቶዎቿ ስብስብም ሴቶች ልጆች አዝለው የሚያሳይ የነበረ ሲሆን፣ ያም ወንዶች ለምን እንደማያዝሉም ጥያቄ እንዳጫረባት ትናገራለች። •"የመከላከያ ሚኒስቴርን በተሻለ መልኩ መምራት ይቻላል" ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ኩምባ ከልጇ ቢንታ ጋር ሴኔጋል የሚገኙ ወንዶች ጓደኞቿም ጋር በመደወል ልጆቻቸውን ያዝሉ እንደሆነ በምትጠይቅበት ወቅትም ያገኘችው ምላሽም በቤት ውስጥ እንደሚይዙ ነገር ግን በአደባባይ በፍፁም እንደማያዝሉ ነው። የፋይንናንስ አማካሪው ዴምባና ልጁ ኤሊ ያደረገችው ጥናትና ቃለ መጠይቆች እንደሚያሳየው ዳካር በጣም ውድ ከሚባሉት ከተሞች አንዷ በመሆኗና ባልና ሚስቱም ውጭ ሥራ ስለሚሠሩ ባሎች ልጅ የመንከባከቡን ሚና እንደሚወጡ ነው። ያነጋገረቻቸው ወንዶች እንደገለፁላት ከሆነ የቤት ውስጥ ሥራዎችን ተከፋፈለው ይሠራሉ። ብዙዎቹ ልጅ የመንከባከቡንም ሆነ፣ የማስጠናቱን ጉዳይ ለባለቤቶቻቸው እንደማይተዉና በከፍተኛ ሁኔታ ይሳተፋሉ። •አዲሷ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ማን ናቸው? "ባለቤቴም እንደኔ ውጭ ትሠራለች፤ እና የቤቱን ሥራ እንዴት ብቻዋን ትወጣዋለች?" በሚልም አንደኛው አስተያየቱን ሰጥቷል። "ምንም እንኳን ወንዶች በልጆች አስተዳደግ ላይ ቢሳተፉም አባቶች ከልጆቻቸው ጋር ሲጫወቱ፣ ትምህርት ቤት ሲወስዷቸው ወይም ሲያጥቧቸው አይታዩም" ትላለች። የቪዲዮ ባለሙያው ሼክና ልጁ ዞ ያነጋገረቻቸውን አባቶችም የአባትነት ሚናቸውን ሲወጡ በሚያጎላ መልኩ ፎቶ ማንሳትም ጀመረች። የኮምፒውተር ባለሙያው ጁልስና ልጁ ጄድ በመጀመሪያ ልጆቻቸውን አቅፈው ፎቶ ለመነሳት ሲስማሙ፤ አዝላችሁስ ብላ በምትጠይቅበት ወቅት በአብዛኛው ያገኘቸው ምላሽ ልጆች አዝለን ጎዳና ላይ አንወጣም የሚል ቢሆንም ማርታ ተስፋ ሳትቆርጥ ቀስ በቀስ ምቾት ሰጥቷቸው እንዲነሱ እንዳግባባቻቸው ትናገራለች። የሙዚቃ ፕሮዲውሰሩ ሙላየና ልጆቹ ሐሰንና ማሊክ ፎቶዎቹን ለማንሳት እሰከ ሦስት ወር የፈጀባት ሲሆን ባለፈው ዓመትም በነበረው በጥበቡ ዓለም ከፍተኛ ስፍራ በሚሰጠው የዳካር ኮንቴምፖራሪ ዓውደ ርዕይም ላይ ሥራዎቿን አቅርባለች። ሥራዎቿም በአውደ ርዕዩ ላይ መነጋገሪያ ሆነው ነበር። የፎቶ ባለሙያው ማህሙድና ልጁ ዘካሪያ ፎቶዎቿ በማህበረሰቡ አመለካከት ላይ የተለየ ሃሳብን መፈንጠቅ የቻለ ሲሆን በተለይም ታዋቂው ራፐር ባዱ መሳተፍ ከፍተኛ ተፅዕኖን መፍጠር ችሏል። ታዋቂው ራፐር ባዱና ልጁ ማህሙድ "በማህበረሰቡ ዘንድ ስመጥር የሆኑ ወንዶች መሳተፋቸው ለብዙዎች አርዓያ ከመሆኑም በላይ ወንዶች ልጆች ማዘላቸው ምንም ማለት አይደለም የሚለውን ውይይት ለመፍጠር ምክንያት ሆኗል" ትላለች ማርታ ሌሎች ታዋቂ ሰዎችንም በፎቶዎቿ እንዲካተቱ ብትጠይቅም ለስማቸው ፈርተው አይሆንም እንዳሏትም ትናገራለች። የእንጨት ዲዛይነሩ ስኮርፒዮንና ልጁ አፍሪካ ፎቶዎቹ የተገኙት ከማርታ ሞሬይራስ ነው
44723898
https://www.bbc.com/amharic/44723898
ናይጄሪያዊው የባህል ሃኪም የተማመነበት ጥይት ማርከሻ ባለመስራቱ ሞተ
አንድ ናይጄሪያዊ የባህል ህኪምና አዋቂ የተማመነበት የጥይት ማርከሻ ባለመስራቱ ለሞት ተዳረገ።
ጥይት ያከሽፋሉ የሚባሉ ባህላዊ መድሃኒቶችን መሸጥም ሆነ መጠቀም ናይጄሪያ ውስጥ የተለመደ ነው የ26 ዓመቱ ቺናካ አድዙዌ ጥይት ያከሽፋል ብሎ ያመነበትን መድሃኒት በአንገቱ ካጠለቀ በኋላ አንድ ደንበኛው ለሙከራ ጥይት በእሱ አቅጣጫ እንዲተኩስ ማዘዙን ተከትሎ ነው ህይወቱ ያለፈው። የአገሪቱ ደቡብ ምሥራቅ ክፍል ፖሊስ ደንበኛውን በግድያ በቁጥጥር ስር አውሎታል። የባህል ህክምናና ባህላዊ እምነት በናይጄሪያ የተለመደ ነገር በመሆኑ የብዙዎች ለተለያዩ ህመሞች የባህል ሃኪሞችን ማማከርም በተመሳሳይ የተለመደ ነው። ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ጥይት ያከሽፋል በሚል ከባህላዊ አምልኮ ጋር በተያያዘ ብዙዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። በተያዘው የአውሮፓውያን ዓመት መጀመሪያ ላይ ባህላዊ መድሃኒት አዋቂ ጥይት ያከሽፋል ያለውን መድሃኒት ጠጥቶ የመድሃኒቱን መስራት ለማረጋገጥ ሲል ባደረገው ሙከራ አንድ ግለሰብ ህይወቱን ማጣቱን ተከትሎ መድሃኒት ሸጩ በቁጥጥር ስር ውሏል።
news-45716831
https://www.bbc.com/amharic/news-45716831
ሰሜንና ደቡብ ኮሪያ በድንበር አካባቢ የተቀበሩ ፈንጂዎችን ማንሳት ጀመሩ
የሰሜን እና ደቡብ ኮሪያ ወታደሮች በድንበር አካባቢ ተቀብረው የነበሩ ከ800 ሺህ የሚበልጡ ተቀጣጣይ ፈንጂዎችን ማጽዳት መጀመራቸውን የሃገራቱ ባለስልጣናት ገልጸዋል።
የሁለቱም ሃገራት ወታደሮች በሚንቀሳቀሱባት በደቡብ ኮሪያ የምትገኘው ፓንሙጆም መንደር የተጀመረው የማጽዳት ሥራ የተሳካ እንደነበር ተገልጿል። እዚህ ውሳኔ ላይ ተደረሰው ሁለቱ የኮሪያ መሪዎች ኪም ጆንግ ኡን እና ሙን ጄ ኢን ባለፈው ወር ፒዮንግያንግ ውስጥ ከተስማሙ በኋላ ነው። • አቶ መላኩና ጄነራል አሳምነው ለማዕከላዊ ኮሚቴ ተመረጡ ከዚህ በተጨማሪም የታጠቁ ኃይሎች ፊት ለፊት ሆነው ድንበር የሚጠብቁበት የወታደራዊ ቀጠና በሚቀጥሉት 20 ቀናት ውስጥ ነጻ እንደሚሆን የደቡብ ኮሪያው መከላከያ ሚኒስትር ገልጸዋል። ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሲደረግ በድንበሮቹ በቅርብ ርቀት የሚገኙት የጥበቃ ቤቶች እንዲሁም ከባድ መሳሪያዎችን በማንሳት ያልታጠቁ ወታደሮችን ብቻ በቦታዎቹ ለማስቀመጥም ታስቧል። • ህገወጥ ወታደራዊ ስልጠና ሲሰጡ የነበሩ ቻይናውያን ታሰሩ ባለፈው ሚያዚያ ደቡብ ኮሪያ በድንበር አካባቢ ትላልቅ የድምጽ ማጉያዎችን በመጠቀም ስታስተላልፋቸው የነበሩትን ፖለቲካዊ ፕሮፓጋንዳዎች እንደምታቆም ገልጻ ነበር። ወታደራዊ ቀጠናው 250 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 4 ኪሎ ሜትር ስፋት ያለውና እስከ ኮሪያ ሰርጥ ድረስ የሚዘልቅ ሲሆን፤ እጅግ ከባድ በሚባሉ ተቀጣጣይ ፈንጂዎች፣ የኤሌክትሪክ ሽቦዎችና የጠበቃ ካሜራዎች የታጠረ ነው። • በእራስ ውስጥ ሌሎችን ማየት ከዚህ በተጨማሪ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የታጠቁ ወታደሮች በሁለቱም የድንበሩ አካባቢዎች ጥበቃ ያደርጋሉ። ባለፈው ህዳር ወር አንድ የሰሜን ኮሪያ ወታደር ቀጠናውን በማለፍ ወደ ደቡብ ለማለፍ ሲሞክር በራሱ ሃገር ወታደሮች ተተኩሶበት መቁሰሉ ይታወሳል።
news-50267377
https://www.bbc.com/amharic/news-50267377
ኤርትራ፡ "ሲአይኤ መፈንቅለ መንግሥት አሲሮብኝ ነበር"
ዛሬ የኤርትራ መንግሥት ባወጣው ያልተለመደ መግለጫ ሲአይኤን በመፈንቅለ መንግሥት ሽረባ ይከሳል። የእስራኤል የስለለ መረብ ሞሳድንም ስም በማጥፋት ተባብሯል ይላል።
የኤርትራ መንግሥት ይህን ስኢረ መንግሥት ተሸርቦብኝ ነበር የሚለው በፈረንጆች 2011 ላይ ነው። ይህንኑ የተመለከተ ሁነኛ ምሥጢራዊ መረጃ እጄ ገብቷል ብሏል። ምስጢራዊው የመፈንቅለ መንግሥት ሴራው በኤርትራ ውስጥ ልክ እንደ "አረቡ ጸደይ" ዓይነት ሕዝባዊ ተቃውሞና አመጽ የማስነሳት ጥንስስ ነበረበትም ብሏል። • ግዙፎቹ የቴሌኮም ተቋማት ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ለመግባት እየተዘጋጁ ነው • የአልጀርስ ስምምነት፡ ባላንጣነትን የወለደው የ‹‹ሰላም ሰነድ›› ይህ በትግርኛ ቋንቋ ዛሬ አርብ የተሰራጨው የኤርትራ መንግሥት መግለጫ የመፈንቅለ መንግሥት ሴራውን ለመጎንጎን በኬንያ መዲና ናይሮቢ ተሰብስበው ነበር ያላቸውን ተቋማትና ግለሰቦች በስም ሳይቀር ይዘረዝራል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን (ዩኤንኤችሲአር) ኤርትራዊያንን በገፍ እንዲሰደዱ የማሳለጥ ሥራ እንዲሰራ በሲአይኤ ይታዘዝ ነበር ይላል። 'ሴረኞቹ' የኤርትራ የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን አባላትም አገራቸውን ጥለው እንዲኮበልሉ ያባብሏቸው ነበር ሲልም ይከሳል። በ2009 በኬንያ ተሳትፎ ያደረገው የኤርትራ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ከፊል አባላት ወደ አገር ቤት ለመመለስ አሻፈረኝ ማለታቸው ይታወሳል። በቅርቡ ደግሞ አራት የብሔራዊ ቡድን አባላት በኡጋንዳ በተመሳሳይ ጥገኝነት ጠይቀው እንደሚገኙና ለደህንነታቸው በመስጋት ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ የድብቅ ኑሮ እንደሚኖሩ መዘገባችን ይታወሳል። የዛሬው መግለጫ በስም የሚጠቅሳቸው 'የመፈንቅለ መንግሥት ጠንሳሾች' አመጽ ከተቀሰቀሰ በኋላ ልክ ጋዳፊ ላይ እንዳደረጉት ወታደራዊ ጥቃት ለመፈጸም ሲያብሰለስሉ ነበር ይላል። የእስራኤሉ ሞሳድ በበኩሉ የኤርትራ መንግሥት ከመካከለኛው ምሥራቅ ከሚንቀሳቀሱ አሸባሪ ቡድኖች ጋር እንደሚሰራ የሚገልጹ ሐሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት ተሳትፎ ማድረጉን ያወሳል። የኤርትራ ወጣቶችን የማስኮብለል ተደጋጋሚ ሴራ ነበር የሚለው መግለጫው፤የኤርትራ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ኤርትራዊያንን በሕገወጥ ሰው ማስተላለፍ ሥራ እጃቸውን አስገብተዋል ሲል በተቀነባበረ መልኩ በሐሰት ይከስ የነበረው ሞሳድ ነው ይላል። የኤርትራ መንግሥት ይፋ ባደረገው 'ምሥጢራዊ' ሰነድ ከተጠቀሱት ጉዳዮች መሐል የሚከተለው ሐሳብ ይገኝበታል። "በኤርትራ የመንግሥት ለውጥ የሚሻ እንቅስቃሴ መጠበቅ ከንቱ ህልም ነው። ስለሆነም፤ የኤርትራን መንግሥት ለማስወገድ፡ የአገሪቱን ወታደራዊ ባህሪ ጠንቅቆ የሚያውቅ የውጭ ኃይል መጠቀም ይኖርብናል። ይህንን የሚያሟላ ደግሞ የ'ወያኔ' ሥርዓተ ነው።" ይላል። ይኸው ሰነድ አያይዞም፣ "የኢትዮጵያ መንግሥት የኤርትራ መንግሥትን ወታደራዊ አቋም በሚመለከት ያቀረበልን ጥናት ተጨባጭና በአጭር ግዜ ለውጥ ለማምጣት ተስፋ ሰጪ ነው" ካለ በኋላ 'አትቸኩሉ' ስለተባሉ እንጂ፤ [እ.ኢ.አ] ከ1998 ጦርነት በኋላ በድጋሚ ጦርነት ለመክፈት ፈልገው ነበር። የኤርትራን መንግሥት ለመገልበጥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና አጋሮቹ ሙሉ ድጋፍ አግኝተው ነበር"ሲል ያትታል። ሰነዱን ጠቅሶ መግለጫው "...ጎን ለጎን ደግሞ በናይሮቢ የቀጠርነው ቄስ፡ ኢትዮጵያን ኤርትራን አንድነት እንዲሰብክ ሥራው ጀምሯል። ይሄ ደግሞ በ'ፍሪዶም ሃውስ' የሚደጎም ሆኖ፡ ገና ከአሁኑ ፍሬ ማፍራት ጀምሯል።"ሲል የግለሰቡን ማንነት በስም ሳይጠቀስ ያልፈዋል። የኤርትራ መንግሥት ይህን መግለጫ ባልተለመደ መልኩ ለምን በዚህ ሰዓት ማውጣት እንደፈለገ ግልጽ አይደለም። በጉዳዩ ላይ የአሜሪካና የእስራኤል መንግሥታትን ምላሽ ለማካተት የተደረገው ሙከራ ፍሬ አላፈራም።
news-53820466
https://www.bbc.com/amharic/news-53820466
አሜሪካ፡ ዘበኛ ሆኖ በሰራበት ሆስፒታል የሕክምና ትምህርት የጀመረው ጥቁር አሜሪካዊ
የቀድሞው የሆስፒታል ዘበኛ ወደ ሆስፒታሉ ተመለሰ፡፡ ለጥበቃ ግን አይደለም፡፡ ሊታከምም አይደለም፡፡ ምናልባት ሊያክም ይሆናል፡፡ ለጊዜው የሕክምና ትምህርት ጀምሯል፡፡ እንዴት አሳካው?
የዛሬ 11 ዓመት ራስል ላዴት በባተን ሩዥ ሆስፒታል ጥበቃ ነበር፡፡ በዘበኝነት እየሠራ ታዲያ ከእጁ በትር ሳይሆን የጥናት ካርዶችን ነበር በብዛት ይዞ የሚታየው፡፡ ያን ጊዜ ኬሜስትሪ እየተማረ ነበር በትርፍ ሰዓቱ፡፡ አሁን ፒኤችዲ (PhD) ደርሷል፡፡ ሦስተኛ ዲግሪ፡፡ ቀጥሎ ኤምዲ የህክምና ዶክተሬቱን ለማግኘት እየተማረ ነው፡፡ የሚማረው በሉዊዚያና ቱሌን ዩኒቨርስቲ ነው፡፡ ‹‹ሕልሜ እውን እየሆነ እንዳለ ይሰማኛል›› ብሏል ለቢቢሲ፡፡ አሁን እሱ ራሱ የብዙዎች መነጋገርያ እየሆነ እንደመጣ ገብቶታል፡፡ ድሮ ዘበኛ እያለ ዞር ብሎ የሚያየው ሰው እንኳ አልነበረም፡፡ እሱ ሌላውን ዞር ብሎ ያያል እንጂ፡፡ የሥራው ባህሪም ስለነበረ፡፡ ራስል ባለፈው ዓመት እንዲሁ በሌላ ነገር ስሙ ሲነሳ፣ ሲወሳ ነበር፡፡ በሊዊዚያና የባሪያ ፍንገላ መታሰቢያ ሙዝየም ውስጥ ግሩም የሆነ የፎቶ አውደ ርዕይ አሰናድቶ ነበር፡፡ የፎቶ አውደ ርዕዩ 15 ጥቁር ሴት የሕክምና ተማሪዎችን የያዘ ነበር፡፡ ይህ ሥራው በበይነ መረብ ድንገቴ ትኩረት አግኝቶ እንደ ሰደድ እሳት ተሰራጨ፡፡ ከፍተኛ ዝናና እውቅናን አስገኘለት፡፡ ይህን ተከትሎ ‹‹15 ዋይት ኮትስ›› የሚባል ድርጅት መሠረተ፡፡ የድርጅቱ ዓላማ ክፍያ መክፈል የማይችሉ ጥቁር አሜሪካዊያንን በፋይናንስ ማገዝ ነበር፡፡ ራስል በአውድ ርዕዩ ያቀረባቸውን ፎቶዎች ቅጂ በአሜሪካ ለሚገኙ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሙሉ ልኳል፡፡ ይህን ያደረገው ጥቁር ልጆችን ለማነቃቃት ነበር፡፡ የሚቀጥለው ጥቁር አሜሪካዊ ትውልድ በሽተኛ ሳይሆን ሐኪም በመሆን እንዲታወቅ ለማድረግ፡፡ ‹‹አሁን ዝም ብለሽ ሄደሽ የሆኑ ሕጻናትን 'ሐኪም ማንን ይመስላል?' ብትያቸው፣ ቶሎ ወደ አእምሯቸው የሚመጣው ነጭ ጋውን የለበሰ ነጭ ሰውዬ ነው›› የሚለው ራስል ይህንን ገጽታ ለመቀየር በሚል እሳቤ ፎቶዎችን ወደትምህርት ቤቶች እንደላካቸው ለቢቢሲ ዘጋቢ ነግሯታል፡፡. እንዴት ከሆስፒታል ዘበኝነት ተነስቶ ሐኪም ሆነ? ትንሽ ወደኋላ ሸርተት ብለን ልጅነቱን እንቃኝ… ራስል በሌክ ቻርለስ፣ ሉዊዚያና ከእናቱ ጋር በድህነት ነበር ያደገው፡፡ እንኳንስ ፒኤችዲ ሊሰራ፣ እንኳንስ ኤምዲ ለማግኘት ሊማር ቀርቶ ዩኒቨርስቲ ደጅ እረግጣለሁ ብሎ አስቦ አያውቅም፡፡ ራስል ሦስተኛው ዲግሪውን የሠራው በሞለኩዩላር ኦንኮሎጂ ዘርፍ ነው፡፡ ይህ የሱን ልጅነት ለሚያውቅ ሰው አስደናቂ ነው፡፡ ልጅ ሳለ ራስል ትዝ የሚለው ሀብታሞች የጣሉትን ምግብ ለማግኘት ከእህቱ ጋር ቆሻሻ ገንዳ ውስጥ ትራፊ ሲፈልጉ ነው፡፡ ‹‹እኔ ይመስለኝ የነበረው ሀብታሞች ብቻ የሚገቡበት ቦታ ነበር›› ይላል ድሮ ስለ ኮሌጅ የነበረውን ስሜት ለቢቢሲ ሲናገር፡፡ ልክ 2ኛ ደረጃ ትምህርቱን ሲጨርስ አየር ኃይል ውስጥ ገባ፡፡ እንደማምለጫም፣ እንደ መደበቂያም… ‹‹ወታደር ቤት ያገኛቸው ሰዎች ጠንካሮች ነበሩ፡፡ ስኬት ለማንም ሰው የሚደረስበት ነገር እንደሆነ የተማርኩት በወታደር ቤት ነው›› ይላል፡፡ በዋሺንግተን ዲሲ በኋላም በፔንሳኮላ፣ ፍሎሪዳ በወታደራዊ ክሪፕቶሎጂ ቴክኒሻንነት ሰለጠነ፡፡ ‹‹እየተማርኩ ስሄድ ዓለም ባለ ብዙ አማራጭ፣ ባለብዙ እድሎች እንደሆነችው እየገባኝ መጣ፡፡ እይታዬም ሰፋ፡፡›› በፔንሰኮላ ከተማ የወደፊት የትዳር አጋሩን አገኘ፡፡ የትደር አጋሩን ሲገልጻት፣ ‹‹በትምህርት እንዳምን ያደረገችኝ እሷ ናት፡፡›› ይላል፡፡ በአየር ኃይል ውስጥ በርከት ያሉ አገሮች እየተዟዟረ ከሰራ በኋላ ከሚስቱ ጋር የተረጋጋ ኑሮ ለመጀመር ሲል ከወታደር ቤት ራሱን አሰናበተ፡፡ ከ2009 ጀምሮ በበተን ሮዥ፣ ሊዊዚያና መኖር ጀመሩ፡፡ እሱ እዚያው ከተማ በሳውዘርን ዩኒቨርስቲ እና በኤም ኤንድ ኤም ኮሌጅ ተመዘገበ፡፡ እነዚህ ከፍተኛ ተቋማት በቀደመው ጊዜ የሚታወቁት የጥቁሮች ትምህርት ቤት ሆነው ነው፡፡ ያን ጊዜ በነዚህ ኮሌጆች በስካላርሺፕ (ነፃ የትምህርት እድል አግኝቶ) ትምህርቱን እየተከታተለ የነበረ ቢሆንም ሙሉ ጊዜውን ለትምህርት ማዋል አይችልም ነበር፡፡ ማታ ማታ መሥራት ነበረበት፡፡ በዚያን ጊዜ ነበር የጥበቃ ሥራ በበተን ሮዥ ጠቅላላ ሆስፒታል ውስጥ ያገኘው፡፡ ቀን ቀን ይማርና ማታ ማታ ሆስፒታሉን ይጠብቃል፡፡ በዚያው መሀል ክፍተት ሲያገኝ የጥናት ካርዶቹን ያገላብጣል፡፡ ቅዳሜ ሲደርስ ደግሞ የጥበቃ ተራውን ለተረኛ ዘበኛ አስረክቦ ወደ ፔንሰኮላ ከተማ ይከንፋል፡፡ እዚያ ደግሞ ሌላ ሥራ አለው፡፡ በዚህ መሀል የመጀመርያ ልጁ ተወለደች፡፡ በዚህን ጊዜ ነበር ይበልጥ ጠንክሮ ከልሰራና የተሻለ ገቢ ማግኘት ካልጀመረ መጪው ጊዜ ለርሱም፣ ለሚስቱም፣ ለትንስዋ ልጁም ፈታኝ እንደሚሆን የተረዳው፡፡ ወደ ኒውዮርክ ሄዶ በሞሎኪውላር ኦንኮሎጂ ሦስተኛ ዲግሪውን ያዘ፡፡ ‹‹ልክ ፒኤች ዲ መያዝ ስችል ምንም ነገር ማሳካት እንደምችል ተገለጠልኝ›› ይላል፡፡ ሁለተኛ ሴት ልጁ በየካቲት 20፣ 2018 ተወለደች፡፡ ይህ ሴት ልጁን ያገኘበት ዕለት ከቱሌን ዩኒቨርስቲ የሕክምና ትምህርት ቤት ‹‹ተቀብለንሀል!›› የተባለበት ቀን መሆኑ አስገረመው፡፡ ድሮ ጥበቃ ይሰራበት የነበረበት ትምህርት ቤት ሲመለስ የድሮ አለቃውን አመስግኗል፡፡ ‹‹በጥበቃ ሥራ ላይ ሳለሁ ተደብቄ ሳጠና አይቶኝ አላባረረኝም፡፡›› ራስል የሕክምና ትምህርቱን ሲጨርስ የሕፃናት ሕክምናና የአእምሮ ጤና ሕክምና ዘርፎች ለይ መሥራት ይፈልጋል፡፡ ምክንያቱም በዚህ ረገድ ጥቁር አሜሪካዊያንን መርዳት ይፈልጋልና፡፡ እሱ የተጓዘበት መንገድና ስኬት ድህነት እጣ ፈንታችን ነው ብለው እጃቸውን አጣጥፈው የሚቀመጡ አፍሪካ-አሜሪካዊ ወገኖቹን ያነቃቃል ብሎ ያምናል፡፡
42869441
https://www.bbc.com/amharic/42869441
የሕንድ 21 ሚሊዮን 'ያለተፈለጉ' ሴት ልጆች
ሕንድ ውስጥ ያሉ ወላጆች ከሴት ልጅ ይልቅ ወንድ ልጅ እንዲኖራቸው ባላቸው ፍላጎት የተነሳ 21 ሚሊዮን የሚደርሱ 'ያለተፈለጉ' ሴት ልጆች በሃገሪቱ እንዳሉ አንድ የመንግሥት ሪፖርት አመለከተ።
የሕንድ የገንዘብ ሚኒስቴር ያወጣው ሪፖርት እንደሚለው በርካታ ጥንዶች ወንድ ልጅ ለማግኘት ሲሉ መውለዳቸውን ይቀጥላሉ። ሪፖርቱን ያዘጋጁት ባለሙያዎች እንዳሉት ይህ ሁኔታ በፆታ ምርጫ ምክንያት ከሚደረገው የፅንስ ማቋረጥ የተሻለው አማራጭ ቢሆንም ለሴት ልጆች ሊሰጥ የሚገባው ትኩረትን በከፍተኛ ደረጃ ሊቀንሰው እንደሚችል ያስጠነቅቃሉ። በወላጆች መካከል ያለው የወንድ ልጅ ምርጫን በተመለከተ ''የህንድ ዜጎች ሊነጋገሩበት የሚገባ ጉዳይ ነው'' ይላሉ ባለሙያዎቹ። የሪፖርቱ አዘጋጆች እንደደረሱበት ወንድ ልጅ እንዲኖራቸው የሚሹ ወላጆች ሴት ልጅ መፀነሷን ሲያውቁ በሚያደርጉት የፅንስ መቋረጥ ሳቢያ ከአጠቃላዩ የሃገሪቱ ህዝብ 63 ሚሊዮን ሴቶች እንዲጎድሉ ምክንያት ሆኗል። በተጨማሪም የበለጠ እንክብካቤ ከሴት ልጅ ይልቅ ለወንድ ልጆች ይሰጣል። ምንም እንኳን የፅንስን ፆታ ለማወቅ ምርመራ ማድረግ ሕንድ ውስጥ ሕገ-ወጥ ቢሆንም ምርመራው ስለሚከናወን በፆታ ምርጫ ሰበብ ለሚካሄድ የፅንስ ማቋረጥ እድልን ፈጥሯል። ወላጆች ወንድ ልጆችን እንዲመርጡ ከሚያደርጓቸው ነገሮች መካከል ንብረት ለሴት ልጆች ሳይሆን ለወንዶች ስለሚተላለፍ፣ ጋብቻ ሲታሰብም የሴቷ ቤተሰብ ጥሎሽ እንዲሰጥ ስለሚጠየቅ እና ሴቶች ካገቡ በኋላ ወደባሎቻቸው ቤት ስሚገቡ እንደሆነ ይነገራል። ይህን በህብረተሰቡ ዘንድ ያለው ጠንካራ ወንድ ልጆች የማግኘት ምርጫን መሰረት አድርጎ አንድ የሃገሪቱ ጋዜጣ በሳይንስ ድጋፍ የሌለውን ወንድ ልጅ የማግኛ ዘዴዎች ብሎ እስከማተም አድርሶታል። ጋዜጣው ካሰፈራቸው ዘዴዎች መካከል በመኝታ ጊዜ ወደ ምዕራብ ዞሮ መተኛት እና ከሳምንቱ ቀናት በተወሰኑት ውስጥ ግንኙነት መፈፀም ወንድ ልጅ ለማግኘት ይረዳል የሚል ይገኝበታል። የወንድ ልጆች ምርጫ ከሚታይባቸው የሕንድ ግዛቶች መካከል ፑንጃብና ሃሪያና ቀዳሚዎቹ ሲሆኑ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ያለችው ግዛት ሜጋላያ ናት። በፑንጃብና ሃሪያና ግዛቶች ከሰባት ዓመት በታች ላሉ 1200 ወንድ ልጆች አንፃር 1000 ሴት ልጆች ብቻ እንዳሉ በተደረገው ጥናት ተደርሶበታል።
news-53970595
https://www.bbc.com/amharic/news-53970595
አውስትራሊያ: በአንድ ግለሰብ ቤት የተገኙት ሁለት ዘንዶዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
በአውስትራሊያ ክዊንስላንድ ነዋሪ የሆነው ዳቪድ ታቴ ቤቱ የደረሰው እንደ ሁልጊዜው አገር አማን ነው ብሎ ነበር።
ነገር ግን ሁለት ግዙፍ ዘንዶዎች በቤቱ ጣርያ በኩል በኮርኒስ ውስጥ ሾልከው በመግባት ቀድመውት ቤት ውስጥ ተሰይመዋል። ዳቪድ ታቴ አንዱን ዘንዶ መኝታ ቤት ውስጥ ሌላኛውን ደግሞ በሳሎኑ ውስጥ ሲያገኛቸው አይኑን ማመን አልቻለም። እያንዳንዳቸው 22 ኪሎ ግራም የሚመዝኑት እነዚህ ዘንዶዎች የዳቪድ ቤት ውስጥ እንግድነት ሳይሰማቸው ወዲያ ወዲህ ሲሉ ነበር ተብሏል። እባብና ዘንዶዎችን በማደንና በመያዝ ጥርሱን የነቀለው ስቲቨን ብራውን የእባቦቹን ክብደት ተመልክቶ " አጃኢብ ነው" ብሏል። ሁለቱ ዘንዶዎች እንዴት ዳቪድ ቤት ሊገኙ ቻሉ ለሚለው እስካሁን ድረስ ያለው መላ ምት ነው። ከመላ ምቱ አንዱ ሁለቱ ወንድ ዘንዶዎች በሴት ምክንያት እሰጥ አገባ ውስጥ ገብተው እዚህ ቤት ኮርኒስ ውስጥ ደርሰዋል የሚል ነው። ሴቷ ዘንዶ ከወዴት አለች ብሎ ለሚጠይቅ እርሱ ያልተቋጨው የጥያቄው ቁልፍ መልስ ነው። እነዚህ ዘንዶዎች 2. 8 እና 2.5 ሜትር ያህል ይረዝማሉ። የቤቱ ባለቤት አቶ ዳቪድ ታቴ ከዚህ ቀደም በቤቴ ጣርያ ላይ እባብ ፀሐይ ሲሞቅ አይቼ አውቃለሁ ብሏል። " ቤቴ ስመጣ . . . በማዕድ ቤቱ ኮርኒስ ተዘንጥሎ ጠረጴዛው ላይ ወድቋል" ሲል ለካሪየር ሜይል ዘግቧል። የኮርኒሱን መነደል ያየው ዳቪድ፣ ቤቱን ዞር ዞር ብሎ ሲመለከት ዘንዶውን አገኘው። ወዲያው ዘንዶ ለሚይዘው ግለሰብ በመደወል ቤቱ ውስጥ የተገኙትን ጥቁር እንግዶች "በፍጥነት እንዲሰናበቱ" ተደርጓል ብሏል። " በእጄ ንክችም ማድረግ አልፈለኩም" ሲል ለጋዜጣው አስረድቷል። አቶ ብራውን በሰሜን ብሪዝበን የእባብ ያዢዎችና መላሾች ድርጅት ውስጥ የሚሰራ ሲሆን ለቢቢሲ " እነዚህ ሁለቱ ዘንዶዎች ከዚህ ቀደም ከተለመዱት ግዙፍ እባቦች በተለየ ትልቅ ናቸው" ብሏል። በፌስ ቡክ ገፁ ላይ እንደገለፀው ዳቪድ መኖሪያ ቤት እስኪደርስ ድረስ ኮርኒሱን ነድለው መግባታቸውን አላወቀም ነበር። " አሁን የእባቦች መራብያ ወቅት ነው፤ ስለዚህ እባቦቹ ከተለመደው ጊዜ የተለየ ባህሪ ያሳያሉ፤ የበጋው ሙቀቱ እየጨመረ ስለሚመጣ ፈጣን ይሆናሉ" ብሏል ለቢቢሲ። ብራውን አክሎ ሰዎች እባብ የሚያጋጥማቸው ከሆነ ባሉበት ቆመው እባቡ እስኪያልፍ ድረስ መታገሥ ብልህነት መሆኑን መክሯል። " ሁሉም እባቦች አደገኛ ነገር ያዩ በመሰላቸው ወቅት ማምለጥ ነው የሚፈልጉት" ሲል አክሏል።
news-54008737
https://www.bbc.com/amharic/news-54008737
የጠቅላይ ሚንስትር ሞዲ የትዊተር አካውንት ተጠለፈ
ትዊተር የጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ የትዊተር አካውንት መጠለፉን ይፋ አደረገ።
ይህ ተጠለፈ የተባለው የትዊተር ገጽ ከጠቅላይ ሚንስትሩ የግል ድረ-ገጽ ጋር ቁርኝነት ያለው ነው ተብሏል። ትዊተር የጠቅላይ ሚንስትሩን አካውንት ከመረጃ መንታፊዎች እጅ አውጥቻለሁ ብሏል። አካውንቱ ተጠልፎ በነበረበት ወቅት ሰዎች ክሪፕቶካረንሲዎችን በመጠቀም ለአቸኳይ እርዳታ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ሲያቀርብ ነበር። ይህ ከሞዲ ድረ-ገጽ ጋር ግነኙነት አለው የተባለው አካውንት ከ2.5 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች አሉት። ከ61 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያሉት የሞዲ የግል የትዊተር ገጽ ግን ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰበት ተገልጿል። ትዊተር ስለጉዳዩ መረጃውን እንደደረሰው ተጠልፎ የነበረውን የትዊተር አካውንት ደህንነት ማረጋገጡን አስታውቋል። የታዋዊ ሰዎች የትዊተር አካውንት ሲጠለፍ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በሐምሌ ወር የአሜሪካ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ እጩ ሆነው የቀረቡት ጆ ባይደን እንዲሁም የቴስላ መስራቹ ኤለን መስክ አካውንቶች ተጠልፈው ነበር። ትዊተር ከሁለት ወራት በፊት የታዋቂ ግለሰቦች የሆኑ 130 አካውንቶች ላይ የሳይበር ጥቃት ለመሰንዘር ሙከራ ተደርጎ አንደነበረ አስታውቋል። ይሁን እንጂ በመረጃ መንታፊዎች ቁጥጥር ሥር የገቡት አነስተኛ ቁጥር ያላቸው አካውንቶች ብቻ ናቸው። የጥቃቱ ኢላማ ከነበሩ ዝነኛ ሰዎች መካከል ባራክ ኦባማ፣ ኤለን መሰክ፣ ካንዬ ዌስት እና ቢል ጌትስ ተጠቃሽ ናቸው። ኤፍቢአይ ምርመራውን እንዲያከናውን ተጠይቆም ነበር።
news-56088539
https://www.bbc.com/amharic/news-56088539
ኮሮናቫይረስ፡ ኩባ የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማምረት የምታደርገው ጥረት ይሳካ ይሆን?
በኩባዋ ዋና ከተማ ሃቫና የሚገኘው ፊንሌይ የክትባት ኢንስቲትዩት ምናልባት ከሌሎች የዓለማችን ማዕከላት አንጻር ሲታይ ያረጀና ጊዜ ያለፈበት ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን በዚህ ማዕከል የሚሰራው የምርምር ሥራ እጅግ ዘመናዊ ነው።
የአገሪቱ ከፍተኛ ተመራማሪዎች እረፍት አልባ ረጅም ፈረቃዎችን ጭምር በመስራት ለኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ መፍትሄ ለማግኘት ደፋ ቀና እያሉ ነው። የክትባቱ ስም 'ሶቤሬና 2' የሚባል ሲሆን በኩባ ተመራማሪዎች ኩባ ውስጥ የተሰራ ነው። ይህ ክትባት በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ በጎ ፈቃደኞች ላይ ይሞከራል። ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት ባለፉት ሳምንታት በተደረጉ ክሊኒካዊ ሙከራዎች በጣም አመርቂ የሚባል ውጤት የተመዘገበ ሲሆን ይህ አገሪቱ ክትባቱን ለማግኘት በምታደርገው ጥረት ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የኢንስቲትይቱ ዳይሬክተር ዶክተር ቪሴንቴ ቬሬዝ ቤንኮሞ ገልጸዋል። በኩባ መንግሥት እቅድ መሰረት ክትባቱ ክሊኒካዊ ሙከራውን ከጨረሰ በኋላ በያዝነው የአውሮፓውያኑ ዓመት መጨረሻ አካባቢ ለሁሉም ዜጎች መሰጠት ይጀመራል። "የእኛ እቅድ በመጀመሪያ ሕዝባችንን መከተብ ነው'' ይላሉ ዶክተር ቪሴንቴ። "ከሕዝባችን በኋላ ምናልባት ለሌሎች አገራት መላክ ልንጀምር እንችላለን። ከ2021 መጨረሻ በኋላ ምናልባት 100 ሚሊየን የክትባት ብልቃጦችን አምርተን ሕዝባችን ሙሉ በሙሉ ለመከተብ እቅድ ይዘናል።" ይህ ክትባት የአሜሪካም ሆነ የየትኛውም አገር እርዳታ አልተደረገለትም። ኩባ በባዮቴክኖሎጂ ከ30 ዓመታት በላይ ልምድ ያላት አገር እንደመሆኗ ይህ ምንም የሚገርም ነገር አይደለም። በ1980ዎቹ መጨረሻ አካባቢ የኩባ ሳይንቲስቶች ለማጅራት ገትር ቢ (ሚኒንጃይተስ) ክትባት ካመረቱ የመጀመሪያዎቹ ሲሆኑ የወቅቱ የአገሪቱ መሪ ፊደል ካስትሮ መሰል ሥራዎችን ለማበረታታት ነበር ፊንሌይ የክትባት ኢንስቲትዩት እንዲቋቋም ያደረጉት። በአሜሪካ መድኃኒት አምራች ኩባንያዎች የሚሰሩ መድኃኒቶች ወደ ኩባ እንዳይገቡ ሲደረግ አገሪቱ በራሷ መንገድ መድኃኒቶቹን ማምረት ትችላለች በማለት ፊደል ካስትሮ ይከራከሩ ነበር። ነገር ግን አሁን ባለው ቴክኖሎጂ እና ዘመናዊ አሰራር እንኳን ያለ ሌሎች አገራት ድጋፍና እርዳታ 100 ሚሊዮን የክትባት ብልቃጦችን አምርቶ ሕዝቡን መከተብ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። "ክትባቱን በማምረት ሂደቱ ላይ ግንኙነት የፈጠርነው ከአውሮፓ አገራትና እና ካናዳ ጋር ነው። ከጣልያን እና ፈረንሳይ የመጡ ተመራማሪዎችም በሂደቱ ላይ ይሳተፋሉ" ብለዋል ዶክተር ቪሴንቴ ቬሬዝ። አክለውም "በሚያሳዝን ሁኔታ እስካሁን ድረስ ምንም አይነት የአሜሪካ ተሳትፎ የለም። ምናልባት ወደፊት በመሰል ሂደቶች ላይ ትብብር ሊኖረን እንደሚችል ተስፋ እናደርጋለን" ብለዋል። እንደ ፓን አሜሪካን ሄልዝ ኦርጋናይዜሽን መሰል ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ኩባ ለኮሮረናቫይረስ የሚሆነውን ክትባት በማግኘት የመጀመሪያዋ የላቲን አሜሪካ አገር እንደምትሆን ተስፋ ያደርጋሉ። "ኩባ ክትባቱን እንደምታገኝ ተስፋ እናደርጋለን'' ይላሉ በኩባ የድርጅቱ ተወካይ ዶክተር ሆዜ ሞቫ። ''የሶብሬና 2 ክትባት ሁለተኛ ደረጃ ሙከራ ውጤትን ከሰማን በኋላ ሂደቱን በቅርበት ስንከታተለው ነበር። ካለፈው ዓመት መጨረሻ አካባቢ ጀምሮ ኩባ የክትባቱን ውጤታማነትና ደኅንነት ስትመረምር እንደነበርም እናውቃለን።'' በአሁኑ ጊዜ በክትባቱ ዙሪያ ያለው ጉጉት ትልቅ ነው። በመጀመሪያ አገሪቱ በየቀኑ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ ነው። ወረርሽኙ በጀመረበት የመጀመሪያዎቹ ወራት ውስጥ በየቀኑ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ እየተያዙ የነበረ ሲሆን ከብራዚልና ሜክሲኮ ጋር ሲነጻጸር ግን ቁጥሩ ብዙም አስፈሪ አይደለም። ነገር ግን የአገሪቱን የጤና ሥርዓት በእጅጉ ፈትኖታል። ባሳለፍነው የአውሮፓውያኑ ዓመት አጋማሽ ላይ ኩባ የወረርሽኙን ስርጭት መግታት ችላ ነበር። በዋነኛነት አየር ማረፊያዎችን በመዝጋትና የማኅበረሰቡን እንቅስቃሴ በመገደብ ነበር ይህንን ማሳካት የቻለችው። ሐምሌ እና ነሐሴ ላይ በጣም ዝቅተኛ የሚባል ስርጭትና ሞት ነበር የተመዘገበው። የፓን አሜሪካን ሄልዝ ኦርጋናይዜሽን ተወካዩ በአሁኑ ጊዜ ያለው የቫይረሱ ስርጭት መቆጣጠር ከማይቻልበት ደረጃ ላይ አልደረሰም ብለው ያስባሉ። ነገር ግን ኩባ ውስጥ በወረርሽኙ ምክንያት በርካታ እንቅስቃሴዎች በመገደባቸው በጣም ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ መላሸቅ አጋጥሟታል። እንደውም ከቀዝቃዛው ጦርነት በኋላ ከፍተኛው የኢኮኖሚ መድቀቅ ነው እየተባለ ነው። ክትባቱ በአገር ውስጥ የሚገኝ ከሆነ ደግሞ ሕዝቡን ከመክተብ ባለፈ ከሽያጭ ሊገኝ የሚችለው ገቢ ኢኮኖሚውን በከፍተኛ ሁኔታ ሊረዳው ይችላል ተብሎ ይታመናል። በተጨማሪም ከትባቱን ከሌሎች አገራት ማስመጣት ሊያስከትለው የሚችለውን ወጪ ይቀንሳል። ኮሮረናቫይረስን ተከትሎ በኩባ በተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት ባለፈው ዓመት ብቻ ኢኮኖሚው 11 በመቶ ኪሳራ አጋጥሞታል። በተጨማሪም የምግብ ሱቆችና ሱፐር ማርኬቶች አካባቢ ከፍተኛ ሰልፍና ግፊያም ታይቷል። በዚህ ወቅት ሁሉም ህጻናት ከትምህርት ቤት ቀርተዋል፣ የንግድ እንቅስቃሴዎች በእጅጉ ተቀዛቅዘዋል፣ የእንቅስቃሴ ገደቦችም ቢሆን የዜጎችን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ አስቸጋሪ አድርጎታል። ስለዚህ የክትባቱ ዜና በርካቶች በጉጉት እንዲጠብቁት አድርጓቸዋል። የዚህ ክትባት ውጤታማ መሆን የዜጎችን ጤንነት ከመጠበቅ ባለፈ ለጎረቤት አገራት ከሚደረገው ሽያጭ የሚገኘው ገቢ ኢኮኖሚውን እንደሚያነቃቃው ይታመናል።
43454620
https://www.bbc.com/amharic/43454620
ቭላድሚር ፑቲን በሰፊ ልዩነት አሸነፉ
የሩስያው ፕሬዚደንት እንደሚያሸንፉ በተገመተው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ተፎካካሪዎቻቸውን በሰፊ ልዩነት በመርታት ለቀጣዩ ስድስት መሪ የሚያደርጋቸውን ድል ተቀዳጅተዋል።
ሩስያን በፕሬዚደንትነትና በጠቅላይ ሚኒስትርነት ከአውሮፓውያኑ 1999 ጀምሮ የመሩት ቭላድሚር ፑቲን ከ76 በመቶ በላይ ድምፅ በማምጣት ነው ምርጫውን ማሸነፍ የቻሉት። ዋነኛ ተቀናቃኛቸው አሌክሲ ናቫልኚ በምርጫው እንዳይሳተፉ መታገዳቸው አይዘነጋም። ድሉን አስመልክቶ ለደጋፊዎቻቸው ሞስኮ ላይ ንግግር ያደረጉት ፑቲን "መራጮች ያለፉትን ዓመታት ስኬቶች ከግምት ማስገባታቸው ያስደስታል" ሲሉ ተደምጠዋል። ከውጤቱ በኋላ ከጋዘጤኞች "የዛሬ ስድስት ዓመት በሚደረገው ምርጫስ ይወዳደራሉ?" በሚል የቀረበላቸውን ጥያቄ ፑቲን በፈገግታ በታጀበ መልኩ "ጥያቄው ትንሽ አስቂኝ ነው። እስከ 100 ዓመቴ ድረስ እዚህ የምቆይ ይመስላችኋል? አልቆይም" ሲሉ መልሰዋል። ፑቲን 2012 ላይ የነበረውን ምርጫ በ62 በመቶ ድምፅ ነበር ያሸነፉት። አሁን ላይ በሰፊ ውጤት ማሸነፋቸው ከመጀመሪያውም የተገመተ ነበር። ሚሊየነሩ ኮሚኒስት ፓቬል ግሩዲኒን 12 ድምፅ በማምጣት ሁለተኛ ወጥተዋል። የፑቲን የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን ውጤቱን "አስደናቂ" ሲል ገልፆታል። ምርጫው መቃረቢያ ወቅት በአንዳድ አካባቢዎች ነፃ ምግብ ሲታደል እንዲሁም በሸቀጦች ላይ ቅናሽ ዋጋ ተስተውሎ ነበር። በድምፅ መስጫ ቦታዎች የተሰቀሉ ተንቀሳቃሽ ምስለ የሚያነሱ መሣሪያዎች አንዳንድ አካባቢዎች የምርጫ አስተናባሪዎች የምርጫ ሳጥኖችን በወረቀቶች ሲሞሉ አሳይተዋል። በምርጫው እንዳይሳተፉ የተደረጉት ዋነኛው ተቀናቃኝ ናልቫኚ ውጤቱን ሲሰሙ ጆሮዋቸውን ማመን እንዳቃታቸውና ቁጣቸውን መቆጣጠር እንደተሳናቸው ተናግረዋል። ከምርጫው በፊት በነበረው ጊዜ ጎሎስ የተሰኘው ገለልተኛ የምርጫ ተቆጣጣሪ ቡድን በመቶ የሚቆጠሩ ፍትሃዊነት የጎደላቸው ክስተቶችን ዘግቦ ነበር።
news-54920743
https://www.bbc.com/amharic/news-54920743
ደራሲ ቺማማንዳ የአሸናፊዎች አሸናፊ ተብላ ተሸለመች
ናይጄሪያዊቷ ፀሓፊ ቺማማንዳ ንጎዚ አዲቼ የአሸናፊዎች አሸናፊ ተብላ ተሸልማለች።
ታዋቂ ድርሰቷም 'ሃፍ ኦፍ ኤ የሎው ሰን' (Half of a Yellow Sun) በሴቶች የልብወለድ ድርሰትም በ25 አመታት ውስጥ ያሸነፈው ምርጥ መፅሃፍ ተብሏል። ደራሲዋ ሽልማቱን በጎሮጎሳውያኑ 2007 ያሸነፈች ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት ሌሎች ከዚህ ቀደም ሽልማቱን ካሸነፉ 25 ደራሲዎች ጋር ተወዳድራ በህዝብ ምርጫም ማሸነፍ ችላለች። ከዚህ ቀደም ሽልማቱን ማሸነፍ የቻሉት ዛዲ ስሚዝ፣ በህይወት የሌለችው አንድሪያ ሌቪ፣ ሊዮኔል ሽሪቨር፣ ሮዝ ትሪሜይንና ማጊ ኦ ፋሬል ናቸው። ይህ ሽልማት ከዚህ ቀደም ኦሬንጅና ቤይሊስ ሽልማቶች በመባልም ይታወቃል። 'ሃፍ ኦፍ ኤ የሎው ሰን' መቼቱን ያደረገው በናይጄሪያ ሲሆን ባይፋሪያን ጦርነት ላይ ያጠነጠነ ነው። ድርሰቱም ቅኝ ግዛት፣ የብሔር ታማኝነት፣ መደብ፣ ዘር እንዲሁም የሴቶችን ብቃት ይዳስሳል። በጎሮጎሳውያኑ 2006 የወጣው ይህ መፅሃፍ በአለም አቀፉ ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትንና መወደድን አትርፏል። መፅሃፉ ወደ ፊልምም በጎሮጎሳውያኑ 2013 ተቀይሯል። "የአሸናፊዎች አሸናፊ ተብዬ መመረጤ በጣም ከፍተኛ ደስተኛ ነኝ። ከዚህ ቀደም ይሄ ሽልማት በአለም አቀፉ ዘንድ ከፍተኛ አንባቢን ፈጥሮልኛል፤ በርካታ ድንቅ ፀሃፊዎችንም ስራዎች አሳውቆኛል" በማለት ቺማማንዳ ተናግራለች። ከ8 ሺህ 500 ሰዎች በላይ አንባቢያን ድምፃቸውን በመስጠት የመረጡም ሲሆን በርካቶችም በሽልማቱ የዲጂታል ቡክ ክለብ ተጋብዘው አስተያየቶቻቸውን አጋርተዋል።
news-52433115
https://www.bbc.com/amharic/news-52433115
ኮሮናቫይረስ በኢኳዶር፡ በኮሮና ቫይረስ ሞተዋል የተባሉት "አልሞትኩም እህቴ ጋር ደውሉልኝ" አሉ
ክፉኛ በኮሮናቫይረስ በተጠቃችው በላቲን አሜሪካዊቷ አገር ኢኳዶር ሆስፒታሎች በግርግር፣ በተረበሹና ሃዘን በተሞላባቸው ዜጎቿ ተሞልተዋል።
አብዛኞቹ በኮሮናቫይረስ ሞተዋል የተባሉ የቤተሰቦቻቸውንና የወዳጆቻቸውን አስከሬን ለመውሰድ ነው የሚመጡት። በዚህም መካከልም አንዳንድ አስደንጋጭ ዜናዎች መሰማታቸው አልቀረም። ከሰሞኑ ሞተዋል የተባሉ ሴት ሆስፒታሉ ማንነታቸውን በማሳሳቱ ምክንያት በህይወት መገኘታቸው አነጋጋሪ ሆኗል። የ74 ዓመቷ የዕድሜ ባለፀጋ አልባ ማሩሪ ቤተሰቦች መሞታቸውን የተረዱት ባለፈው ወር ነበር፤ ጭራሽ ሆስፒታሉ በባህሉ መስረት እንደሚደረገው አስከሬናቸውን አቃጥሎ አመዳቸውንም ለቤተሰብ ልኳል። ነገር ግን ማሩሪ ለሦስት ሳምንታት እራሳቸውን ስተው [ኮማ] ከቆዩ በኋላ ነቅተው ዶክተሮቹን ለእህታቸው እንዲደውሉላቸው ጠይቀዋል። የአስከሬኖች መጥፋት ማሩሪ በኢኳዶር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ማዕከል በምትባለው የጓያኩል ከተማ ወደሚገኘው ሆስፒታል በኮሮናቫይረስ ታመው ነው የገቡት። በከተማዋ ውስጥ ሆስፒታል ሳይደርሱ በኮሮናቫይረስ ምክንያት በየቤታቸው የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ ባለስልጣናቱ አስከሬኖችን መሰብሰብ ከብዷቸዋል። 17 ሚሊዮን የሕዝብ ብዛት ባላት ኢኳዶር 22 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ ስድስት መቶ ሰዎችም ህይወታቸውን አጥተዋል። ይሄ ግን በሆስፒታል ውስጥ የተመዘገበ መረጃ ነው፤ በቤታቸው የሞቱ ሰዎች ቁጥር በሺህዎች የሚቆጠር ነው ተብሏል። ኢነስ ሳሊናስና ባለቤቷ ፍላደልፊዮ መጋቢት 21/2012 ዓ.ም ነው ህይወታቸው ያለፈው። ቤተሰቦቻቸው በኮሮናቫይረስ ለሞቱ ሰዎች በሚደረገው ጥንቃቄ መሰረት አስከሬኖቹን እንዲያነሱ ለባለስልጣናቱ ደውለው ቢያሳውቁም አራት ቀናት ያህል መጠበቅ ነበረባቸው። ከመጡም በኋላ በፕላስቲክ ጠቅልለው ወሰዷቸው፤ እናም ሲቀበሩ እንደሚያሳዉቋቸው እንደነገሯቸውም የሟቿ እህት በርታ ትናገራለች። ነገር ግን ባለስልጣናቱም ሳይደውሉ የውሃ ሽታ ሆነው ቀሩ። እናም እነበርታ ግራ ቢገባቸውም ጉዳዩን ለመንግሥት ባለስልጣናት አሳውቀዋል፤ አስከሬኖቹን ምን እንዳረጓቸው እንዲያሳውቋቸውም ደብዳቤ አስገብተው እየጠበቁ ነው። የፈራረሰ የጤና ሥርዓት የነበርታ ትግል የአንድ ቤተሰብ ታሪክ ብቻ አይደለም በተቃራኒው በኢኳዶር ውስጥ የብዙ ቤተሰቦችን ታሪክ የሚወክል ነው። በርካታ ቤተሰቦች አስከሬኖችን ፍለጋ ወደ ሆስፒታሎችና ወደ መካነ መቃብሮች ይሄዳሉ፤ ፖሊስ ጋር ይደውላሉ። በጓያኩል የተከሰተው ከፍተኛ የሞት አሃዝ ከተማዋ ከምትቋቋመው በላይ በመሆኑ የአገሪቱን የጤና ሥርዓት ፍርስርሱን አውጥቶታል። በርካታ ሆስፒታሎች አስከሬኖችን ከአገልግሎት ውጭ ወደሆኑ የመጋዘን ቦታዎች ልከዋል። አስከሬኖቹም በመጋዘኖቹ ውስጥ እየበሰበሱ ነው። የቤተሰቦቻቸውንም አስከሬን ለማግኘት ማገላበጥ ይኖርባቸዋል፤ የተደራረቡ አስከሬኖችን ማንሳትና መጣልም ግዴታ ሆኖባቸዋል። ዳሪዮ ፊጉኤሮዋ የእናቱን አስከሬን ለማግኘት አሰቃቂ ያለውን በርካታ የሞቱ ሰዎችን አስከሬን ማገላበጥ ነበረበት። "ለቀናት ያህል የእናታችንን አስከሬን ለመቀበል ሆስፒታል እየጠበቅን ነበር፤ ምላሽ የሚሰጠን ስናጣ ሌሎች አስከሬን ከሚጠብቁ ሰዎች ጋር በአንድነት ተሰባስበን አንደኛውን ጠባቂ አስከሬኑ ወደተቀመጠበት ቦታ እንዲወስደን ጫና አደረግንበት።" "የፊት ጭምብልና ጓንት አጠለቅንና አስከሬኖቹ ወደተቀመጡበት ክፍል ገባን። አስከሬኖቹ የተቀመጡበት መንገድ አሰቃቂ ነው፣ በጣም የሚያበሳጭና የሚያሳዝን ነው። አስከሬኖቹ በፕላስቲክ ተጠቅልለው አንዱ ባንዱ ላይ ተደራርቧል" ይላል። ተአምር በዚህ ሁሉ ቀውስ መካከል የማሩሪ በህይወት መኖር ብዙዎችን አስደምሟል። የቤተሰባቸው ደስታ ይህ ነው የሚባል አይደለም፣ በቃላት መግለፅም ከብዷቸዋል። ግራ የገባቸው ቢኖር የማሩሪ ተብሎ የመጣው አመድ የማን ነው የሚለው ጥያቄን መመለስ አለመቻላቸው ነው። ከፍተኛ ትኩሳትና ለመተንፈስ በመቸገራቸው ሆስፒታል የገቡት ማሩሪ መጋቢት 18/2012 ዓ.ም ሞቱ ተብሎ ሆስፒታሉ ለቤተሰባቸው አረዳቸው። ቤተሰባቸውም አስከሬን ማስቀመጫ ክፍል ተወስደው በሽታው እንዳይዛመት በሚልም ራቅ ብለው እንዲያዩ ተደረጉ። "ፊቷን ማየት ፈራሁኝ" የሚለው የእህታቸው ልጅ ጄይሚ ሞርላ "ከአስከሬኑ በአንድ ሜትር ተኩል ርቀት ላይ ነው የነበርኩት። ካየሁት አስከሬን ጋር ፀጉራቸው ተመሳሳይ ነው። የቆዳቸው ቀለምም እንዲሁ" በማለት ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪል ተናግሯል። የማሩሪ የተባለውም አስከሬን ተወስዶ ተቃጠለ፤ እንዲሁም አመዳቸውም ለቤተሰቡ ተላከ። በወቅቱ ራሳቸውን የማያውቁት ማሩሪ ከሦስት ሳምንታት እራሳቸውን ስተው ከቆዩ በኋላ እህታቸው ጋር እንዲደውሉ ዶክተሮቹን ጠየቁ። "ተአምር ነው። ለወር ያህልም ሞታለች ብለን እያዘንን ነበር" ያሉት እህታቸው አሩራ "የማን እንደሆነ የማናውቀው አመድ ቤታችን አለ" ብለዋል። ማልቀሻ ሲታጣ ሆስፒታሉ ለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ ጠይቋል። ቤተሰባቸው ግን አስከሬኑን ለማቃጠል ላወጡት ገንዘብ መንግሥት ካሳ እንዲከፍላቸው ጠይቀዋል። ማሩሪ ቤታቸው ተመልሰዋል፤ ለመኖር ሁለተኛ እድል አግኝተው አዲስ ህይወት ጀምረዋል። እንቅልፍ እንዲመቻቸውም በማለት ቤተሰባቸው አዲስ ፍራሽም ገዝቶላቸዋል። ምንም እንኳን የማሩሪ ቤተሰቦች በህይወት መኖራቸውን ተረድተው እፎይታ ቢያገኙም ብዙዎች የቤተሰቦቻቸውንና የወዳጆቻቸውን አስከሬን ፍለጋ መባዘናቸውን ቀጥሏል። ባለው ቀውስና ቫይረሱም ይዛመታል በሚለው ፍራቻ ብዙዎች ቤተሰቦቻቸውን ሳይሰናበቱ ነው ከዚች ዓለም በሞት የተለዩት። ሃዘኑስ እንዴት ይወጣላቸዋል? ቤተሰቦቿን በኮሮናቫይረስ ያጣችው የሳሊና ትንሿ ልጅ ሁሉም ቤተሰብ ገንዘብ አዋጥቶ መቀበሪያ ቦታ አዘጋጅቶላቸው ነበር ትላለች። "ነገር ግን አስከሬኑን ሳይሰጡን እንዴት እንቅበራቸው?" ብላም ትጠይቃለች። "አባቴና እናቴ የት እንዳሉ አለማወቅ ልብ ይሰብራል። የት ሄጄስ ላልቅስ፣ ሃዘኔንስ የት ልወጣ?"በማለትም ሃዘን በሰበረው ድምጿ ትጠይቃለች።
news-50150503
https://www.bbc.com/amharic/news-50150503
የጃዋር ጥበቃ መነሳት ወሬና የቀሰቀሰው ቁጣ
የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ዳይሬክተር ጃዋር መሀመድ በመንግሥት ተመድበውለት የነበሩት የደህንነት ጥበቃ አባላት በምሽት እንዲነሱብኝ ታዘዋል በሚል በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያስተላለፈው መልዕክት ቁጣና ተቃውሞን ቀሰቀሰ።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽር እንደሻው ጣሰው በዚህም ሳቢያ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የተቃውሞ ሰልፎች ያጋጠሙ ሲሆን በርካታ ወጣቶችም ድርጊቱን በመቃወም አዲስ አበባ በሚገኘው የጃዋር መሀመድ ቤት አቅራቢያ ተሰብስበዋል። የጸጥታ ኃይሎችም በአካባቢው ተሰማርተው እንዳሉ የዓይን እማኞች ለቢቢሲ ገልጸዋል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽር እንደሻው ጣሰው በሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኀን ላይ ቀርበው እንዳስረዱት፤ ጃዋር መሀመድ ለተከታዮቻቸውና ለደጋፊዎቻቸው ልታሰር ነው፣ ጥቃት ሊደርስብኝ ነው በማለት ያስተላለፉት መልዕክት ስህተት ነው ብለዋል። "በፖሊስ ተወሰደብኝ ያሉት እርምጃ ስህተት ነው" በማለትም "በመንግሥትም በፖሊስም በኩል ምንም ዓይነት እርምጃ አልተወሰደባቸውም" ሲሉ ተናግረዋል። ፖሊስ እንደወትሮው የየእለት ተግባሩን እያከናወነ እንደሚገኝም ጨምረው አመልክተዋል። ፖሊስ ለውጡን ተከትሎ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ፖለቲከኞችና አክቲቪስቶች በሚንቀሳቀሱበትና በሚኖሩበት ስፍራ ችግር እንዳያጋጥማቸው የጥበቃ ከለላ ሲያደርግ መቆየቱን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። በተጨማሪም በሀገር ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስተዋለ የመጣውን ሰላምና መረጋጋት ከግንዛቤ በማስገባት እንደማንኛውም ግለሰብ በሰላም ተንቀሳቅሰው መኖር እንደሚችሉ ስለታመነበት "የግል ጥበቃዎችን የማንሳት ሥራ ስንሰራ ቆይተናል" ብለዋል። ወደፊትም ያሉትን ሁኔታዎች በማየትና አስፈላጊ የሆኑና ያልሆኑትን በመለየት የማንሳት እንደሚቀጥል ተናግረዋል። የተዘጉ መንገዶች እንዲከፈቱና መደበኛ እንቅስቃሴዎች እንዲቀጥሉ ጥሪ ያስተላለፉ ሲሆን ፖሊስ የሕግ ማስከበር ሥራውን እንደሚቀጥል አመልክተዋል። • "አሁን ያለው ሁኔታ ከቀጠለ ነገ ወደ እርስ በርስ ጦርነት እንደሚገባ ግልጽ ነው" አቦይ ስብሃት • በዓለማችን የተበራከቱት የተቃውሞ ሰልፎች የሚያመሳስላቸው ነገር ይኖር ይሆን? • "ለውጡ ሐዲዱን ስቷል ብዬ ነው የማምነው" አርቲስት ታማኝ በየነ ጃዋር እንደሚለው ማክሰኞ ዕኩለ ሌሊት አቅራቢያ ሁለት መኪኖች ወደሚኖርበት ቤት አካባቢ በመምጣት ጥበቃዎቹን "እኔ ሳላውቅ እቃቸውን ይዘው ቤቱን ለቀው እንዲወጡ" እንደተነገራቸው በፌስ ቡክ ገጹ ላይ አስፍሯል። አክሎም ጥበቃዎቹ ለምን እንዲወጡ እንደጠየቁና ለስልጠና እንደሆነ እንደተነገራቸው እነሱም እንዳልተቀበሉ፣ ከዚያም ስልክ ተደውሎላቸው በአስቸኳይ ቤቱን ለቀው ካልወጡ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ጠቅሷል። በጥበቃዎቹ ላይ ግፊቱ ሲበረታ ከእንቅልፉ ቀስቅሰው ሁኔታውን እንደነገሩትና እሱም ወደ አዛዡ ጋር ደውሎ ማብራሪያ እንደጠየቀና በመጀመሪያ ላይ "የተለመደው ጥበቃዎችን የመቀየር ሂደት መሆኑን" እንደተነገረው፤ ከዚያም ኃላፊው የተሰጠውን ትዕዛዝ ብቻ እያስፈጸመ መሆኑን ጽፏል። ጃዋር ቀጥሎም ጉዳዩን የበለጠ ለማወቅ ከፖለቲካና ከጸጥታ አመራሮች ጋር መነጋገሩን እነሱም የተከሰተውን ነገር ከስር መሰረቱ ለማወቅ ቃል እንደገቡለት ገልጿል። ይህንንም ተከትሎ በቤቱ አካባቢ በርካታ ደጋፊዎቹ መሰብሰባቸውንና በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች በጃዋር ላይ የሚገጥሙ ማንኛውንም ነገሮች በመቃወም ሰልፎች እየተካሄዱ ነው። በአንዳንድ ቦታዎችም መንገዶች መዘጋታቸውንና የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ መገታቱን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በአካባቢያቸው ያለውን ሁኔታ በተመለከተ የሚገልጹ ሰዎች በፎቶ ጭምር እያመለከቱ ነው።
news-54201264
https://www.bbc.com/amharic/news-54201264
የባራክ ኦባማ መጽሐፍ በቅርቡ ገበያ ላይ ይውላል
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ መጽሐፍ ጽፈዋል፡፡
የኅዳሩን የአሜሪካ ምርጫ አስታኮ ገበያ ላይ ይውላል ተብሏል፡፡ የአሜሪካ የመጀመርያው ጥቁር ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ መጽሐፉ የፕሬዝዳንት ዘመኔን ትውስታዎች በሐቅ ያሰፈርኩበት ነው ብለዋል፡፡ የመጽሐፉ ርእስ ኤ ፕሮሚስድ ላንድ ‹‹A Promised Land›› የሚል ሲሆን በኅዳር 17 የአሜሪካ ምርጫን በሁለት ሳምንት ተከትሎ ገበያ ላይ ይውላል። የዲሞክራቲክ ፓርቲ መሪ የነበሩት ባራክ አሜሪካንን ለሁለት የስልጣን ዘመን መርተዋል፡፡ የአሁኑ የዲሞክራቲክ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪና የዶናልድ ትራምፕ ተፋላሚ የኦባማ ምክትል ሆነው ለ8 ዓመታት አገልግለዋል፡፡ ኦባማ በትዊተር ሰሌዳቸው ያሰፈሩት መልእክት ‹‹መጽሐፍ ጽፎ እንደመጨረስ ያለ መልካም ስሜት አላውቅም፡፡ በዚህኛው መጽሐፌ ጥሩ ስሜት ነው ያለኝ ብለዋል፡፡ የኦባማ መጽሐፍ ዳጎስ ያለ ነው፡፡ 768 ገጾች አሉት፡፡ ዝነኛው ፔንጉይን ራንደም ሀውስ ያሳተመው ሲሆን ወደ 25 ቋንቋዎች ተመልሷል ተብሏል፡፡ ኦባማ በመጽሐፋቸው አሜሪካንነና ዓለምን ችግር ውስጥ ከትቶ ስለነበረው ስለ ፋይናንስ ቀውስ፣ ስለ ጤና መድኅን እንዲሁም ስለ ቢን ላደን አገዳደል አውስተዋል፡፡ 44ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ከዚህ ቀደም ሦስት መጻሕፍትን አበርክተዋል፡፡ ድሪምስ ፍሮም ማይ ፋዘር፣ ዘ ኦደሲቲ ኦፍ ሆፕ እንዲሁም ኦፍ ስሪ ሲንግ የሚል የልጆች መጽሐፍ አላቸው፡፡ ባለቤታቸው ክብርት ሚሼል ኦባማ የጻፈችው ቢካሚንግ የተሰኘ መጽሐፍ በ5 ወራት 10 ሚሊዮን ቅጂ በመሸጥ የዓለምን ክብረ ወሰን ይዟል፡፡
news-44707893
https://www.bbc.com/amharic/news-44707893
ልጁን ጡት ያጠባው አባት
በአሜሪካ ዊስኮንሰን ግዛት የሚኖሩ ባልና ሚስት ልጃቸውን ለመገላገል ወደ ሆስፒታል አቅንተው አባትየው አስቦት የማያውቀው ነገር ገጥሞታል።
የእናት እርግዝና የተወሳሰበ ከመሆኑ በተጨማሪ ከፍተኛ የደም ግፊት ስላጋጠማት በቀዶ ጥገና ልትገላገል ችላለች። ልጅቷ ከተወለደች በኋላም ችግሩ ባለመቀረፉ ልጇን ልታቅፍና ልታጠባም አልቻለችም። አባት 3.6 ኪሎ ግራም የምትመዝነውን ልጁን ሰውነታቸው እንዲነካካ በማለት ልብሱን አውልቆ መጀመሪያም እንዳቀፋት ተናግሯል። ጡጦ መጥባት እንዳለባትና በእጁ ጠብ እያረገ አፏን ሊያርሰው እንደሚገባ ነርሷ ነገረችው። ነርሷም በመቀጠል ጡቱን እንዲሰጣትና እንዲያጠባት ነገረችው። ''ምንም ነገር ከመሞከር ወደኋላ ስለማልልና ሁሌም ስለምቀልድ ለምን አልሞክረውም አልኩ" ብሏል። ነርሷም አባትየው ጡት ላይ ፕላስቲክ በመለጠፍ ወተቱ በሲሪንጅ እንዲተላለፍ አድርጋለች። "ጠብቼ አላደግኩም፤ መቼም ቢሆን በሺ አመታት በጭራሽ የማላስበው ጉዳይ ነው። ልጄንም ለማጥባት የመጀመሪያው ሆኛለሁ" ብሏል። "አማቴ የምታየውን ነገር ማመን አልቻለችም" ያለው አባት "አያቴ በመጀመሪያ ምንም ማለት ባይፈልግም በመጨረሻ ግን ሁኔታውን ተቀብሎታል"በማለት ተናግሯል። "ከልጄ ጋር ለየት ያለ ግንኙነት እንዳለኝ ተሰምቶኛል። ልጄ ለወደፊትም ጡት እንደዚህም መጥባቱን ትለምደዋለች ብየ ተስፋ አደርጋለሁ" ብሏል። ጡት እያጠባ የሚያሳዩ ፎቶዎች በማህበራዊ ሚዲያ ዘንድ መልካም ተቀባይነትንም አግኝተዋል። እንዲህ አይነት አማራጭ በማቅረቧ ነርሷን ያመሰገኑ እንዳሉ ሁሉ አባትየው ጡት ማጥባቱ ግራ ያጋባቸውም አልታጡም። ፎቶዎቹ በማህበራዊ ሚዲያዎች ሰላሳ ሺ ያህል ጊዜ የተጋራ ሲሆን ብዙዎችም መልካም አስተያየትን ችረውታል። "መልካም አባት ለመሆን ነው ይህንን ያደረግኩት፤ ምሳሌ ለሆኑኝ ነርሶችም ጀግንነትን ለማሳየት ነው። ከነሱ የበለጠ ማንንም አታገኝም።ከዚህ ሁሉ በላይ የሆኑትን እናቶችን መዘንጋት የለብህም " ብሏል።
news-48891711
https://www.bbc.com/amharic/news-48891711
"መግለጫ የምንሰጠው ሰዎችም ልንታሰር እንችላለን" የአማራ ክልል ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሰኔ 15/2011 ዓ. ም የተፈጠረውን ክስተት ተከትሎ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር እንዲውሉ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።
የጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ሳባ ደመቀ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ እስከ አሁን ከ220 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሲሆን፤ የፌደራልና የክልል ዐቃቤ ሕጎች እንዲሁም መርማሪዎች ባሉበት ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራው እየተካሄደ ይገኛል። • የብ/ጄነራል አሳምነው ፅጌ ሚስት መታሰራቸውን ልጃቸው ገለጸች በቁጥጥር ሥር የዋሉት ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ስለመቅረባቸውና ክስ ስለመመስረቱ መግለጽ እንደማይችሉ ምክትል ኃላፊዋ ገልጸው፤ "የተያዙት ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ያሉ ናቸው" ብለዋል። ከአማራ ክልል አመራሮች መካከል ተጠርጣሪ ተብለው የታሠሩ ሰዎች ነገሩ እስከሚረጋጋ መታሰራቸው ተገልጾ እንደነበር ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ "እስከሚረጋጋ በሚል አይደለም፤ እንደ ምርመራ ቡድን በሥራ ኃላፊነታቸው ወይም በተለያየ መንገድ ተጠርጥረው የሚያዙ ሰዎችን ሌብል [የተለየ ስያሜ] አልሰጠናቸውም" ሲሉ መልሰዋል። የጠቅላይ ዐቃዐ ሕጉ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ሳባ፤ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሰዎች በተከሰተው ነገር ተሳትፏቸው ምን ነበር? የሚለውን የምርመራ ሂደቱ እንደሚፈታውም አክለዋል። • "ሌሎችንም ከፍተኛ ባለስልጣናት የመግደል ዕቅድ ነበረ" እንደ ጄነራል ተፈራ ማሞና ኮለኔል አለበል አማረ ያሉ የክልሉ አመራሮች የሰኔ 15ቱን 'የመፈንቅለ መንግሥት' ሙከራ በተመለከተ በቴሌቭዥን ማብራሪያ ሲሰጡ ነበር። ከድርጊቱ ጀርባ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩት ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌ 'አግተዋቸው ነበር' ከተባሉ አመራሮች መካከልም ይገኙበታል። ሆኖም እነዚህ አመራሮች አሁን ተጠርጣሪ ተብለው በቁጥጥር ሥር ውለዋል። ስለዚህ ተቃርኖ ምክትል ቢሮ ኃላፊዋ ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል። "በሚዲያ ያቀረባቸው አካል ለተለያየ አላማ ሊያቀርባቸው ይችላል። ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች የፀጥታውን ኃይል የሚመሩ ሰዎች ናቸው። እጅ ከፍንጅ የተያዘ ሰው ስላልነበረም ስለተፈጠረው ነገር ቀርበው [በሚዲያ] ሊያስረዱ ይችላሉ። ቀርበው ያስረዱበት አላማ እኛ ከያዝነው ጉዳይ ጋር ያን ያህል የሚገናኝ አይደለም" በማለት አመራሮቹ እንደማንኛውም ተጠርጣሪ መያዛቸውንም አክለዋል። • "በዚህ መንገድ መገደላቸው ከፍተኛ የፀጥታ ችግር መኖሩን ያሳያል" ጄነራል ፃድቃን የጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ሳባ እንደገለጹት፤ ማንኛውም አካል ተጠርጣሪ እስከሆነ ድረስ በቁጥጥር ሥር ይውላል። "ነገ ከነገ ወዲያ መግለጫ ከሰጠነው ሰዎች ውስጥም ማንኛችንም ልንገባ [እስር ቤት] የምንችልበት እድል እንዳለ መገመት ያስፈልጋል። ምንም መተማመኛ የለም" ሲሉም ተናግረዋል። በተያያዘም የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽንና የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አርብ እለት በሰጡት መግለጫ፤ 218 የሚሆኑ ሰዎች ባህር ዳር ውስጥ ከተከሰተው ችግር ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አስታውቋል።