id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
48672476
https://www.bbc.com/amharic/48672476
አሜሪካ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ተጨማሪ ወታደር ልትልክ ነው
አሜሪካ ከኢራን ጋር የገባችው ውጥረት በተካረረበት ማግስት ተጨማሪ 1ሺህ ወታደር ወደ መካከለኛው ምስራቅ ልትልክ መሆኗን አሳውቃለች።
የመከላከያ ተጠባባቂ ጸሐፊ የሆኑት ፓትሪክ ሻናሀን እንዳሉት ተጨማሪ ወታደር ማሰማራት ያስፈለገው የኢራን መንግስት በሚያሳው "ጠብ አጫሪ ባህሪ" የተነሳ ነው። የአሜሪካ ባህር ኃይል የኢራን አብዮታዊ ዘብ በነዳጅ ጫኝ መርከቦች ጥቃት አድርሷል በማለት ተጨማሪ ምስሎችን አውጥቷል። ኢራን ሰኞ እለት እንዳስታወቀችው ከእንግዲህ በኋላ በጎርጎሳውያኑ 2015 የኒውክለር ፕሮግራሟን ለመቀነስ የገባችውን ስምምነት እንድታከብር እንደማትገደድ አስታውቃለች። በአለም አቀፉ ማህበረሰብ የተቀመጠውን የዩራኒየም ውህድ ክምችት ገደብም ከፍ ለማድረግ ወስናለች። • "ለአውሮፕላኑ መከስከስ ፓይለቶች ተጠያቂ ሊሆኑ አይችሉም" አቶ ተወልደ ገብረማርያም • ሞሐመድ ሙርሲ ፍርድ ቤት ውስጥ ሞቱ • አምነስቲ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ለውጥ እንዲደረግበት ጠየቀ የአሜሪካ ጦር ወደ መካከለኛው ምስራቅ እንዲንቀሳቀስ መደረጉ የተገለፀው ሰኞ እለት ከሰአት በኋላ ነበር። ፓትሪክ ሻናሀን በመግለጫቸው ላይ እንዳስቀመጡት "አሜሪካ ከኢራን ጋር ግጭት ውስጥ መግባት አትፈልግም።" ነገር ግን እርምጃው የተወሰደው "በቀጠናው የተሰማሩ ወታደራዊ ኃይሎችን ደህንነትና የሀገርን ጥቅም ለማስጠበቅ" ነው ብለዋል። "የቅርብ ጊዜ የኢራን ጥቃት የሚያሳየው በኢራን ኃይሎች የሚፈፀመው ጠብ አጫሪ ባህሪና ቅጥረኛ ቡድኖች አሜሪካን ወታደራዊ ኃይልና በቀጠናው ላይ ያላትን ጥቅም አደጋ ላይ ለመጣል መንቀሳቀሳቸውን ነው" ብለዋል። አክለውም መከላከያ ኃይሉ ያለውን ሁኔታ እየፈተሸ የወታደሮቹን ቁጥር እንደአስፈላጊነቱ ይወስናል ብለዋል። የተሰማሩት ተጨማሪ ወታደሮች የት አካባቢ እንደሚመደቡ ይፋ የተደረገ ነገር የለም። ሰኞ እለት የተጨመሩት ወታደሮች ባለፈው ወር መጨረሻ ላይ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ካሰማሯቸው 1500 ወታደሮች በተጨማሪ መሆኑ ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማይክ ፖምፒዮ እሁድ እለት አሜሪካ ከኢራን ጋር ጦርነት መግጠም ባትፈልግም "ያሉትን አማራጮች በአጠቃላይ ግን ታያለች" ብለው ነበር። አክለውም ማክሰኞ እለት የመካከለኛው ምስራቅ ጦር አዛዦችን የሆኑትን እንደሚያገኙ ገልፀዋል። በ2015 ኢራን የኒውክለር ማበልፀግ ፕሮግራሟን ለመቀነስ ከአሜሪካና አውሮጳ ሀገራት ጋር ስምምነት ላይ ደርሳ ነበር። ነገር ግን ባለፈው አመት ፕሬዝዳንት ትራምፕ አሜሪካ የገባችውን ስምምነት ሰርዘው ዳግመኛ ኢራን ላይ ማዕቀብ ጥለዋል። ይህ ውሳኔያቸው የኢራንን ምጣኔ ሐብት ያሽመደመደው ሲሆን ኢራን በምላሹ የገባችውን ስምምነት በመተላለፍ የዩራኒየም ማበልፀግ ፕሮግራሟን ከፍ አድርጋዋለች። የአቶሚክ ኢነርጂ ባለስልጣኑ ይህንን በተናገሩበት መግለጫቸው አሁንም የአውሮጳ ሀገራት የአሜሪካን ማዕቀብ ማስቀረትና ኢራንን መታደግ ይችላሉ ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። እንግሊዝ፣ ፈረንሳይና ጀርመን ኢራንን በ2015 የገባችውን ስምምነት እንዳትጥስ ያስጠነቀቁ ሲሆን አሜሪካ ግን ኢራንን "ኒውክለርን ተጠቅማ ማስፈራሪያ የምታደርግ ሀገር" ብላታለች።
news-54188789
https://www.bbc.com/amharic/news-54188789
አቶ ልደቱ ያልተፈቀደ የጦር መሳሪያ በመያዝ ክስ ቀረበባቸው
የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) የብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ልደቱ አያሌው ያልተፈቀደ የጦር መሳሪያ በመያዝ ወንጀል ክስ እንደቀረበባቸው የፓርቲው ፕሬዝደንት ለቢቢሲ አረጋገጡ።
አቶ አዳነ እንዳሉት በዛሬው ዕለት የአቶ ልደቱ ጉዳይ ከዚህ በፊት ሲታይ ከነበረበት የቢሾፍቱ ከተማ በመውጣት በአዳማ ከተማ በሚገኝ ፍርድ ቤት እንደታየ ጠቅሰው ይህንንም የሰሙት ትናንት ማታ መሆኑን ገልጸዋል። በምሥራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ክስ የቀረበባቸው ልደቱ አያሌው ላይ ዐቃቤ ሕግ የጦር መሳሪያ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 22 ንዑስ አንቀጽ 3ን በመተላለፍ ያልተፈቀደ የጦር መሳሪያ በመያዝ መከሰሳቸውን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃንም ዘግበዋል። አቶ ልደቱ ከዚህ በፊት በቢሾፍቱ ወረዳ ፍርድ ቤት ጉዳያቸው ሲታይ ቆይቶ የቀረበባቸውን የምርመራ መዝገብ ቢዘጋውም ከእስር በነጻም ሆነ በዋስ ለመውጣት ሳይችሉ በእስር ላይ ቆይተው ሌላ ክስ ተመስርቶባቸዋል። ነገር ግን የፓርቲው ፕሬዝደንት አቶ አዳነ ታደሰ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ደብዳቤው ከወጣ በኋላ ትላንት [ረቡዕ] ምሽት ነው አቶ ልደቱ አዲስ ክስ እንደተመሠረተባቸው የተሰማው። "የቢሾፍቱ ፍርድ ቤት ነፃ ናቸው ናቸው ብሎ አሰናብቷቸው ነበር። እኛም በጠበቆቻችን አማካይነት ይግባኝ ጠይቀን ነበር። ነገር ግን የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ተፈፃሚ ሊሆን ስላልቻለ አቶ ልደቱ በትላንታው ዕለት ጠበቆቻቸውን 'እስካሁን ለረዳችሁኝ አመሰግናለሁ' ብለው አሰናብተዋቸዋል።" አቶ ልደቱ ትናንት [ረቡዕ] ጉዳያቸውን ይዘው ሲከታተሉ የነበሩትን ጠበቆቻቸውን ማሰናበታቸውን በጻፉት ደብዳቤ አሳውቀው ነበር። በዚህም ጉዳያቸው እየታየበት ባለው ሂደትቱ ላይ እምነት እንደሌላቸው በማሳወቅ ነው ጠበቆቻቸውን እንዳሰናበቱ የገለጹት። አቶ ልደቱ በደብዳቤያቸው ላይ እንዳሉት ባለፉት ስምንት የችሎት ሂደቶች ላይ የፖሊስና የዐቃቢ ሕግ ተገቢ ያልሆኑ ጥያቄዎች ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት ሲያገኙ መመልከታቸውን ጠቅሰው "የእኔ ሕጋዊ የመብት ጥያቄዎች ግን አንድም ጊዜ ተቀባይነት ሲያገኙ አልታዩም" በማለት እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱበትን ምክንያት ገልጸዋል። በፖለቲካ አመለካከታቸው ለእስር እንደተዳረጉ የገለጹት አቶ ልደቱ "በፖለቲካ አመለካከቴ እንድታሰር የወሰኑብኝ የፖለቲካ ሰዎች ስለወደፊቱ እድሌም የሚወስኑትን የፖለቲካ ውሳኔ በእስር ላይ ሆኜ እየተጠባበኩኝ እገኛለሁ" ብለዋል። ለእስራቸውም ቀደም ሲል ያዘጋጁት የሽግግር መንግሥት ምስረታ ሰነድና በታትሞ ያልተሰራጨው አዲሱ መጽሐፋቸው ምክንያቶች እንደሆኑ በማመን "በአጭሩ እኔ የታሰርኩት ለምን ወንጀል ፈጸምክ ተብዬ ሳይሆን ለምን አሰብክ ተብዬ ነው" ነው ሲሉ በደብዳቤያቸው ላይ ገልጸዋል። በዚህም ሳቢያ "ሕግ የፖለቲካ መሳሪያ በሆነበት ሁኔታ በሕግ ክርክር መብትን ማስከበር ስለማይቻል ከአሁን በኋላ ሕጋዊ ግዴታዬን ለመወጣት ቀጠሮ ሲሰጠኝ በችሎት ፊት ከመገኘት ባለፈ የሕግ ክርክር የማድረግ ፍላጎት የለኝም" ሲሉ ጠበቆቻቸውን አመስግነው ማሰናበታቸውን አመልክተዋል። የኢዴፓ ፕሬዝደናት አቶ አዳነም ለቢቢሲ "አቶ ልደቱ በፍትህ ሂደቱ ከዚህ በኋላ እምነት የለኝም። የመከራከርም ፍላጎት የለኝም ሲሉ ነው። ውሳኔው ፖለቲካዊ ስለሆነ ፖለቲካዊ መፍትሄ እስኪሰጠኝ ድረስ እሥር ቤት እቆያለሁ ብለው ነው ያሰናበቷቸው" ብለዋል። የአቶ ልደቱ ጠበቃቸውን የማሰናበታቸውን ውሳኔ የሚገልጸው ደብዳቤ ይፋ መሆኑን ተከትሎ አዲስ ክስ እንደተመሠረተባቸው መስማታቸውን ፕሬዝደንቱ ተናግረዋል። "እኛ ከቢሾፍቱ ወደዚህ [አደስ አበባ] እንደመጣን አዳማ ላይ ዐቃቤ ሕግ ክስ እንደመሠረተባቸው ተነግሮናል። ዛሬ [ሐሙስ] 4፡00 ቀጠሮ ተሰጥቷቸው ወደዚያ እያመራሁ ነው" ሲሉ ጉዳዩን ለመከታተል እያመሩ መሆኑን ገልጸዋል። ጨምረውም አቶ ልደቱ አያሌው ትናንት [ረቡዕ] ማታ 1፡30 ላይ የክፍላቸው በር ተንኳኩቶ 'ለጠዋት ተዘጋጅ ነገ [ሐሙስ] አዳማ ላይ ቀጠሮ አለህ' ተብሎ እንደተነገራቸው አቶ አዳነ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ልደቱ የተመሠተባቸው ክስ አዲስ እንደሆነና የክሱን ምንነት እስካሁን እንዳላወቁ ፕሬዝደንቱ ያስረዳሉ። ጠበቆቻቸው አዳማ ይገኛሉ? ምንም እንኳ አቶ ልደቱ ጠበቆቻቸውን ቢያሰናብቱም አዳማ ፍርድ ቤት በሚሰማው ክስ ላይ ጠበቆች እንደሚገኙ አቶ አዳነ ይናገራሉ። "አቶ አብዱልጀባር [ጠበቃ] ምን እንኳ ደብዳቤው ቢደርሰኝም ቋንቋውን በማያውቁበትና ክሱ ላይ ያለውን ጭብጥ በደንብ መረዳት በማይችሉበት ሁኔታ ትተናቸው አንሄድም። ስለዚህ እሳቸው ቢከለክሉኝም ዛሬ እገኛለሁ ብለውናል። ስለዚህ ወደዚያ [አዳማ] እየሄድን ነው።" አቶ ልደቱ ዛሬ አዳማ ላይ ከሚቀርብባቸው ክስ አስቀድሞ ጠበቆቻቸውን ሲያሰናብቱ 'እስካሁን ድረስ የተጓዝኩት ጉዞ በፖለቲካ መያዜን የሚያረጋግጥ ነው። ይህን ማረጋገጥ ከቻልኩ ለኔ በቂዬ ብለው' ተስፋ እንደቆረጡ የአዴፓ ፕሬዝደንት ይናገራሉ። አቶ አዳነ "በአዳማው የፍርድ ሂደትም ቢሆን የሚለወጥ ነገር ይኖራል ብለን አናምንም" ይላሉ። ነገር ግን በምን ዓይነት ሁኔታ ነገሮችን እናስኪድ የሚለውን ከሱ [አቶ ልደቱ] ጋር ተመካክረን የምናደርግ ይሆናል ባይ ናቸው። አቶ ልደቱን ለእሥር የተዳረጉት ከጥቂት ወራት በፊት በቢሾፍቱ ከተማ ተከስቶ የነበረውን አለመረጋጋት በማስተባበርና በመደገፍ ተጠርጥረው እንደሆነ ይታወሳል።
news-53021261
https://www.bbc.com/amharic/news-53021261
በመሪዋ ድንገተኛ ሞት ግራ መጋባት ውስጥ ያለችው ቡሩንዲ
ከሳምንታት በፊት በተደረገ ምርጫ ፓርቲያቸው ማሸነፉ የተነገረላቸው የቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ፒየር ንኩሩንዚዛ በድንገት ማለፍን ተከትሎ ማን ይተካቸዋል? በሚለው ጥያቄ ዙሪያ በአገሪቱ ግራ መጋባት ተፈጥሯል።
ፕሬዝዳንቱ ምርጫውን ማሸነፋቸውን ተከትሎ ወርሃ ነሐሴ ላይ ስልጣናቸውን እንደሚያስረክቡ ቢጠበቅም በሕገ መንግሥቱ መሰረት ለጊዜው የእሳቸውን ቦታ ሊተኩ የሚችሉት የፓርላማው አፈ ጉባኤ ናቸው። ነገር ግን እስካሁን ድረስ አፈ ጉባኤው ቃለ መሐላ ያልፈጸሙ ሲሆን የፕሬዝዳንቱ መንበርም ያለተተኪ ባዶ ሆኖ የስልጣን ክፍተት ተፈጥሯል። ካቢኔው ሐሙስ ዕለት ስብሰባውን ያደረገ ሲሆን ስብሰባውን የመሩት ከሁለቱ ምክትል ፕሬዝዳንቶች ተቀዳሚው ናቸው። በስብሰባውም በድንገት ያጋጠመውን የፕሬዝዳንቱን ሞት እንዴት እንደሚወጡት ተወያይተዋል። በአገሪቱ በተፈጠረው የስልጣን ክፍተት ምክንያት በገዢው ፓርቲ ውስጥ የስልጣን ሽኩቻ እንዳለ የተገለጸ ሲሆን፤ ከገዢው ፓርቲ ምክትሉ ኢቫሪስት ንዳዪሺምዬ እና የፓርላማው አፈ ጉባኤ ፓስካል ንያቤንዳ ዋነኛ ተፋላሚዎቹ ናቸው ተብሏል። ባሳለፍነው ጥር ወር ሁለቱም በገዢው ፓርቲ በኩል ፕሬዝዳንታዊ እጩ ለመሆኑ ሲዘጋጁ እንደነበርም ተገልጿል። ባለፉት 20 ዓመታት በስልጣን ላይ ሳሉ ህይወታቸው ያለፈ አፍሪካ አገራት/ግዛት መሪዎች የቡሩንዲ መንግሥት ቃል አቀባይ ፕሮስፐር ንታሆዋሚዬ ለቢቢሲ እንደገለጹት፤ አሁን ያለው ሁኔታ በፍርድ ቤት ይፈታል ብለዋል። "ከሕገ መንግሥት ፍርድ ቤቱ ጋር እየተመካከርን ነው። አሁን ያለውን የስልጣን ክፍተት እያጠናው ነው። ነገር ግን ጥቂት ቀናትን ሊወስድ ይችላል'' ብለዋል። በሌላ በኩል የፕሬዝዳንት ፒዬር ንኩሩንዚዛ ሞት ጉዳይ አሁንም በርካታ መላ ምቶችን እያስተናገደ ነው። በርካቶች ፕሬዝዳንቱ የሞቱት በኮሮናቫይረስ ነው ቢሉም መንግሥት መጀመሪያ ላይ እንዳለው በልብ ሕመም መሞታቸውን አጠንክሮ እየገለጸ ነው። የፕሬዝዳንቱን ሞት ተከትሎ በታወጀው የሰባት ቀናት ብሔራዊ ሐዘን ወቅት ሕዝብ በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ላይ ከመንፈሳዊ ዝማሬዎች ውጪ ሌሎች ሙዚቃዎች እንዳይከፈቱ የአገሪቱ ካቢኔ ወስኗል። ከዚህ በተጨማሪ በአገሪቱ የሚገኙ የመንግሥት እና የግል ሬዲዮ ጣቢያዎች የፕሬዝዳንቱ ሞት ከተነገረበት ዕለት አንስቶ መንፈሳዊ ዝማሬዎችን ብቻ ነው እያሰሙ ያሉት።
news-54034623
https://www.bbc.com/amharic/news-54034623
ሩስያ፡ ኔቶ የፑቲን መንግሥት ስለ ኖቪቾክ መርዛማ ኬሚካል መረጃ መስጠት አለበት አለ
የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ሩስያ ስለ ኖቪቾክ ፕሮግራሟ ለዓለም አቀፍ ተቆጣጣሪዎች መረጃ መስጠት አለባት አለ።
የመብት ተሟጋቹ አሌክሴ ናቫልኒ መመረዙን ተከትሎ ነው ስለ ኖቪቾክ ነርቭ ኤጀንት (መርዛማ ኬሚካል) መረጃ እንድትሰጥ የተጠየቀው። የኔቶ ጸሐፊ ጄንስ ስቶልበርግ አባላቱ ጥቃቱን አውግዘዋል ብለዋል። የመብት ተሟጋቹ በኖቪቾክ እንደተመረዘ “ማስረጃ አለ” ሲሉም አክለዋል። ሩስያ ግን ለአሌክሴ ሕክምና እያደረገ ያለው ሆስፒታል የሰጠውን ማብራሪያ አጣጥላለች። ድርጅቱ አስቸኳይ ስብሰባ ካደረገ በኋላ “ሩስያ በዓለም አቀፍ ምርመራ የኬሚካል መሣሪያ ላይ እገዳ እንዲጣል መተባበር አለባት። ስለ ኖቪቾክ ፕሮግራም ሙሉ መረጃ መስጠት አለባት” መባሉን ጸሐፊው አስታውቀዋል። ይህ ኬሚካል የቀድሞው ሰላይ ሰርጌ ሰኬሪፓልን እና ልጁን ለመመረዝም ውሎ ነበር። አባትና ልጅ እአአ በ2018 ዩኬ ውስጥ ሲመረዙ የሩስያ ወታደራዊ ስለላ መወቀሱ ይታወሳል። 20 አገራት ከመቶ በላይ የሩስያ ዲፕሎማቶችና ሰላዮችን ከአገራቸው አባረውም ነበር። ሩስያ ግን በጉዳዩ እጄ የለበትም ብላ ነበር። ጸሐፊው በተጨማሪም “ይሕ ዓለም አቀፍ መርህ መጣስ ነው። ስለዚህ ዓለም አቀፍ እርምጃ ያስፈልጋል” ብለዋል። በርካታ የሩስያ ከፍተኛ የሕዝብ እንደራሴዎች የኔቶን ጥያቄ ችላ ብለዋል። የሩስያ ፌደሬሽን ካውንስል ኮንስታንቲን ኮሳቼቭ፤ “አሌክሲ የኬሚካል መሣሪያ ስምምነትን በጣሰ ኬሚካል መመረዙ ሳይረጋገጥ ኔቶን በጉዳዩ ማስገባት ነገሩን ፖሊቲካዊ ማድረግ ነው” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ፑቲንን የሚቃወመው አሌክሲ የጸረ ሙስና አቀንቃኝ ነው። ከሳይቤሪያ ወደ ሞስኮ ሲሄድ አውሮፕላን ውስጥ ታሞ ጀርመን ለሕክምና ተወስዶ ነበር። ሩስያ የጀርመኑን የሕክምና ውጤት እንዳላየችና ተመርዟል የሚለውን ድምዳሜ እንደማትቀበል ተናግራለች። የአውሮፓ ሕብረት፤ የሩስያ መንግሥት ጉዳዩን በግልጽ እንዲመረምር ጠይቋል። የአሜሪካ ብሔራዊ የጸጥታ ካውንስልም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሩስያን ተጠያቂ ማድረግ እንዳለበት ገልጿል።
news-53233445
https://www.bbc.com/amharic/news-53233445
ስለአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ እስካሁን የምናውቀው
አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ሰኞ ምሽት 3፡30 አካባቢ በጥይት ተመትቶ መገደሉን ፖሊስ አስታውቋል።
ስለአርቲስቱ ግድያ እና ከግድያው ጋር ተያይዘው ስለተከሰቱ ነገሮች የእስካሁን የሚታወቁ ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው። የሃጫሉ ሁንዴሳ በጥይት ተመቶ የመገደል ዜና በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ መዘዋወር የጀመረው ከምሽት 5፡30 አካባቢ ጀምሮ ነበር። በርካቶች የታዋቂውን ድምጻዊ ግድያን በማስመልከት ሃዘናቸውን በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲገልጹ ነበር። ከዚያም ከእኩለ ለሊት በኋላ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በብሔራዊው ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው አርቲስት ሃጫሉ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ገላን ኮንዶሚኒየም ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ከምሽቱ 3፡30 አከባቢ በጥይት ተመቶ መገደሉን አረጋገጡ። ኮሚሽነሩ ጨምረውም በግድያው ወንጀል የተጠረጠሩ የተወሰኑ ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ገልጸዋል። ከእኩለ ለሊት በኋላ አዲስ አበባን ጨምሮ በበርካታ የኦሮሚያ ከተሞች ሰዎች ሃዘናቸውን ለመግለጽ ወደ መንገድ ወጡ። ሌሊቱን በፌስቡክ አማካኝነት ሲሰራጩ በነበሩ የቀጥታ ስርጭቶች፤ በርካቶች መንገድ ላይ በመውጣት ሲያለቅሱ ታይተዋል። በምሥራቅ እና ምዕራብ ኦሮሚያ ከተሞችም ንጋት ላይ መንገድ ዝግ የተደረገባቸው ከተሞች ነበሩ። የአስከሬን ሽኝት ከአዲስ አበባ የሃጫሉ ሁንዴሳ አስክሬን ወደ ትውልድ ከተማው አምቦ እንደተሸኘ የተነገረ ሲሆን። ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ሕዝብ የአርቲስቱን አስከሬን ለመሸኘት ወጥቷል። አስከሬን ለመሸኘት የወጡ ሰዎች ሃዘናቸውን በተለያየ መልክ ሲገልጹ ነበር። በዚህ ጊዜ ፖሊስ አስለቃሽ ጪስ ሲተኩስ በስፍራው የነበሩ ሰዎች በፌስቡክ የቀጥታ ካሰራጩት ምስል ላይ ታይቷል። በተጨማሪም የድምጻዊውን አስክሬን ለመሸኘት ከወጡ ሰዎችም ቢቢሲ አረጋግጧል። የአስከሬን አቀባበል በአምቦ ዛሬ ንጋት ላይ የአርቲስት ሃጫሉ አስከሬን በበርካታ አድናቂዎቹ ታጅቦ ወደ አምቦ ሲያመራ የነበረ ቢሆንም ቀብሩ መፈፀም ያለበት አዲስ አበባ ነው የሚሉ ተቃውሞዎች መሰማታቸውን ተከትሎ አስክሬኑ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ ተደርጎ ነበር። ወደ አዲስ አበባ ከተመለሰም በኋላ አስክሬኑ ስታዲየም አቅራቢያ በሚገኘው የኦሮሞ ባህል ማዕከል እንዲያረፍ ተደርጎ ቆይቷል። ከዚያም አስክሬኑ ወደ አምቦ በሄሊኮፕተር ተጭኖ ወደ ከአምቦ ከተማ በቅርብ ርቀት ወደ ሚገኘው ሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ መወሰዱ ተነግሯል። ማለዳ አምቦ ቁጥሩ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ሕዝብ አስክሬኑን ለመቀበል በመጠባበቅ ላይ ነበር። “የከተማው ሕዝብ ወደ ዋና መንገድ ወጥቷል። ከገጠርም በጣም ብዙ ሰዎች በፈረስ እየመጡ ነው” ሲሉ አንድ የከተማው ነዋሪ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችም በነዳጅ ማደያ እና ባንክ ቤቶች በመሳሰሉት ተቋማት አካባቢ እንጂ በብዛት በከተማዋ ውስጥ እንደማይታዩ አኚሁ ነዋሪ ጨምረው ተናግረው ነበር። የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ የቀብር ስነስርዓት መቼ እንደሚፈፀም ከቤተሰቡም ሆነ ከመንግሥት አካል እስካሁን ምንም የተባለ ነገር የለም። ሃጫሉ ከዚህ ቀደም ምን ብሎ ነበር? ሃጫሉ ሁንዴሳ ከዚህ ቀደም ቢቢሲን ጨምሮ ከሌሎች መገናኛ ብዙሃን ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ተደጋጋሚ የግድያ ዛቻዎች ይደርሰው እንደነበረ ተናግሯል። ከሳምንት በፊት ሰኔ 15/2012 ዓ.ም በኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ላይ በተላለፈው ቃለ መጠይቁ፤ ሃጫሉ “እየታገልኩ እኮ ነው የምኖረው” በማለት ተደጋጋሚ የግድያ ዛቻ እንደሚደርስበት ተናግሯል። የሃጫሉን ግድያ ተከትሎ ማን ምን አለ? ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ በድምጻዊው ሞት የተሰማቸውን ሀዘን "ውድ ህይወት አጥተናል" በማለት "የዚህ ድንቅና አንፀባራቂ ወጣት አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ህይወት መቀጠፍ ከተሰማ ጀምሮ በከባድ ሃዘን ውስጥ ለምንገኝ ሁሉ መፅናናትን እመኛለሁም" በማለት ሃዘናቸውን ገልጸዋል። የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በድምጻዊው ግድያ ከባድ ሐዘን እንደተሰማቸው ገልጸው "ሃጫሉን የገደለው ማንም ይሁን ማን ከህግ ማምለጥ አይችልም" ብለዋል። ጠቅላይ አቃቤ ሕጓ ጨምረውም "በዚህ እኩይ እና አስነዋሪ ተግባር የተሳተፉ በሕግ ዋጋቸውን ያገኛሉ" ሲሉ ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ “መራር ሃዘን . . .” ካሉ በኋላ በኦሮምኛ “ውስጤ ነው ያለቀሰው፣ ልቤ ነው የደማው” በማለት ሃዘናቸውን ገልጸዋል። በአሁኑ ሰዓት የአርቲስቱ አስክሬን ወደ አምቦ እየሄድ ይገኛል። የኢንተርኔት አገልግሎ በመቋረጡ ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘት አልተቻለም። በአዲስ አበባ፣ መቀሌ፣ ባህር ዳር፣ ነቀምት እና አምቦ የኢንተርኔት አግልግሎት መቋረጡን አረጋግጠናል። ቁጣና አለመረጋጋት የታዋቂው ሙዚቀኛ ሞትን ተከትሎ በአንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች ቁጣና አለመረጋጋት መከሰቱን ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል። በዚህም መሰረት ከአዲስ አበባ በስተ ምሥራቅ በምትገኘው በአዳማ ከተማ የተቃውሞ ሰልፎችና አለመረጋጋት እንዳለ ቢቢሲ ከቦታው አረጋግጧል። በከተማዋ አንዳንድ የመንግሥት ህንጻዎች ላይ ጉዳት እንደደረሰባቸው የዓይን ምስክሮች ለቢቢሲ ሪፖርተሮች ገልጸዋል። በአዳማ የሆስፒታል ምንጮች ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል እንዳጋገጡት ወደ ሆስፒታል በጥይት ተመትተው የመጡ ሰዎች ሲኖሩ ሶስት ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።በተጨማሪም በአዳማ ከተማ ለተቃውሞ ወደ ኦቢኤን የቴሌቪዥን ጣቢያ ሲያመሩ የነበሩ ሰልፈኞች በጸጥታ ኃይሎች የተበተኑ ሲሆን፤ አንድ ሰው መቁሰሉን የዓይን ምስክሮች ተናግረዋል።የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የትውልድ አካባቢ በሆነው ጅማ ውስጥም ሰልፎች እየተደሩጉ መሆኑን ከቦታው ያናገርናቸው ነዋሪዎች ገለጸዋል። ቢቢሲ ከጭሮ ማረጋገጥ እንደቻለው ሁለት ተቃዋሚ ሰልፈኞ በጥይት ተመትተው ሲሞቱ የመንግሥት ሕንጻዎችም ተቃጥለዋል።
news-51425054
https://www.bbc.com/amharic/news-51425054
ኬንያዊያን ማክሰኞ በቤታቸው የሚቀበሩትን ሞይን እየተሰናበቱ ነው
ኬንያን ለረጅም ጊዜ የመሩትን የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዳንኤል አራፕ ሞይን አስከሬን ለመሰናበት ኬንያዊያን በመዲናዋ ናይሮቢ በሚገኘው የፓርላማ ሕንጻ ሰልፍ ይዘው እየተሰናበቱ ነው።
የዳንኤል አራፕ ሞይ ስንብት ከፈረንጆቹ 1978 እስከ 2002 ድረስ የአገሪቱን የመጀመሪያ ፕሬዝዳንት ጀሞ ኬንያታን ተክተው ኬንያን በፕሬዝዳንትነት ለ24 ዓመታት የመሩት ዳንኤል አራፕ ሞይ፤ ማክሰኞ ዕለት ነበር በ95 ዓመታቸው የሞቱት። በስንብት ሥነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዳንኤል አራፕ ሞይን "ምልክት የሆኑ መሪ ናቸው" ብለዋቸዋል። በርግጥ ሞይ በሁለት ወገን ነው የሚታወሱት። ተቺዎቻቸው አምባገነን ነበሩ ሲሏቸው፤ ደጋፊዎቻቸው ደግሞ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት እንጅ አምባገነን አልነበሩም በማለት ይከራከሩላቸዋል። የፖለቲካ ተቃዋሚዎቻቸውን አይምሩም፤ በመግደልና በመግረፍ ይቀጧቸው ነበር በማለት ተቺዎቻቸው ይከሷቸዋል። በ1982 እ.አ.አ የተደረገውና የከሸፈው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ይህንን አምባገነንነት ባሕርይ እንዲላበሱ እንዳደረጋቸው ብዙዎች ይስማማሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ምንም እንኳ ስልጣናቸውን ከ24 ዓመታት በኋላ ያስተላለፉ ቢሆንም ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር በማድረግም ዳንኤል አራፕ ሞይ በኬንያዊያን ዘንድ ይወደሳሉ። የዳንኤል አራፕ ሞይ ስንብት በዛሬው ዕለት ታዲያ የእኒህን የቀድሞ መሪያቸውን አስከሬን ለመሰናበት ከሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል የተወጣጡ ኬንያዊያን በመዲናዋ ናይሮቢ ከፓርላማ ሕንጻ ፊት ለፊት ረጅም ሰልፍ ተሰልፈው ወረፋ እየጠበቁ በመሰናበት ላይ ይገኛሉ። አን ንጃምቢ የተባለች የ46 ዓመት ወይዘሮ የቀድሞ መሪዋን ለመሰናበት ከ100 ኪሎ ሜትር በላይ ተጉዛ ናይሮቢ ተገኝታለች። "ትምህርት ቤት በነጻ ወተት እንድንጠጣ ያደረጉንን አልረሳውም። በጣም ለጋስ ሰው ነበሩ፤ መቼም አልረሳቸውም" ብላለች። አክላም "በ1988 ትምህርት ቤት አግኝቻቸው በርትቼ መማር እንዳለብኝ መክረውኛል፤ ያን በማድረጋቸውም ትምህርቴን እንዳጠናቅቅ የትምህርት ወጪዬን የሸፈኑልኝ ያክል ተሰምቶኝ ትልቅ መሪዬ ናቸው ብዬ ነው የማስታውሳቸው" ብላለች። ዛሬ የመጀመሪያው የመሰናበቻ ቀን ሲሆን እስከ ሰኞ ድረስ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ኬንያዊያን በፓርላማው ሕንጻ እየተገኙ እንዲሰናበቱ እድል ተመቻችቶላቸዋል። የኬንያ ሁለተኛው ፕሬዝዳንት ዳንኤል አራፕ ሞይ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው በሚቀጥለው ማክሰኞ የሚደረግ ሲሆን፤ የሚቀበሩትም ከመዲናዋ ናይሮቢ 200 ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኘው የግል ቤታቸው ነው።
news-55745361
https://www.bbc.com/amharic/news-55745361
ኮሮናቫይረስ፡ በሜክሲኮ ሆስፒታል የኮቪድ-19 ክትባቶች ተሰረቁ
በሜክሲኮዋ ሞሬሎስ ግዛት በሚገኝ ሆስፒታል የኮቪድ-19 ክትባቶች ተሰርቀዋል ተብሏል።
ይህንንም ተከትሎ የአገሪቱ ጦር ምርመራ ከፍቷል። ሜክሲኮ ይህንንም ስርቆት ለመመርመርና ጥፋተኞቹንም በቁጥጥር ስር ለማዋል በመላው አገሪቷ ጦሯን አሰማርታለች። በዋናነትም በአገሪቷ አድራጊና ፈጣሪ ከሆኑት የማፊያ ቡድን እጅ ክትባቶቹም እንዳይገባ ስጋት ስለፈጠረም ነው ሰራዊቱ የተሰማራው። "ስርቆቱ ምናልባት የተፈፀመው ታማኝ ባልሆነ የሆስፒታሉ የክትባት ቡድን አባል ሊሆን ይችላል" የሚል መግለጫም ከመንግሥት በኩል ወጥቷል። የተዘረፈው የክትባት መጠን አልተጠቀሰም። ሜክሲኮ 129 ሚሊዮን ህዝቦቿን በነፃ ክትባት ለመክተብም ቃል ገብታለች። በአለም አቀፍ ደረጃ በወረርሽኙ ክፉኛ ከተጠቁ አገራት አንዷ የሆነቸው ሜክሲኮ 140 ሺህ ዜጎቿንም በቫይረሱ አጥታለች። ይህም አሃዝ ከአለም አራተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዜና በያዝነው ሳምንት ማክሰኞ ሶኖራ በምትባለው ግዛት ታጣቂዎች አንድ ሆስፒታል ውስጥ በመግባት ለኮሮናቫይረስ ህሙማን የሚውል የማገዣ መሳሪያ መተንፈሻ (ኦክስጅን) መዝረፋቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በዘገባው አስነብቧል። ዘራፊዎቹ በሆስፒታሉ ሰራተኞች ላይ ጥይት ከደገኑ በኋላ ኦክስጅኑ የት እንደሚቀመጥ ጠይቀዋቸዋል። በመቀጠልም ሶስት ኦክስጅን የተሞላበት መሳሪያና አራት የኦክስጅን ማስቀመጫን ይዘው ሄደዋል ተብሏል። በአገሪቱ ውስጥ የኦክስጅን ስርቆት በሌላለ አካባቢም እንዲሁ የተከሰተ ሲሆን በቅርቡም የተሰረቀ 44 የኦክስጅን መሳሪያዎችን የያዘ የከባድ ጭነት መኪና ሜክሲኮ ከተማ አቅራቢያ ተይዟል። በርካታ ዜጎች ህሙማን ቤተሰቦቻቸውን በየቤቶቻቸው እንዲያቆዩ በተገደዱበት ወቅት የማገዣ መሳሪያ መተንፈሻ (ኦከስስጅን)ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። አገሪቷ ባጋጠማት ከፍተኛ የኮሮናቫይረስ ህሙማንም ቁጥር ሆስፒታሎች ሞልተዋል።
48346453
https://www.bbc.com/amharic/48346453
ህወሀት እና ህግደፍ ይታረቁ ይሆን?
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ያካሄዱትን አውዳሚ ጦርነት ተከትሎ፤ ምንም የሰላም ጭላንጭል በሌለበት በራቸውን ለ20 ዓመታት ዘግተው ቆይተዋል።
አብርሃም ገብረሊባኖስ እና ሃብቶም ገብረሊባኖስ ብዙ ሰላም የማውረድ ጥረቶች ባልተሳኩባቸው ሁለት አስርት ዓመታት፤ የሁለቱን አገራት ሕዝቦችና ምሁራን አሰባስቦ በመንግሥታቱ ላይ ተጽእኖ በመፍጠር ሰላም ማውረድ ይቻላል ብለው ያመኑ ወንድማማቾች 'ሰለብሪቲ ኤቨንትስ' የተሰኘ ተቋም መሰረቱ። ወንድማማቾቹ አብርሃም ገብረሊባኖስ እና ሃብቶም ገብረሊባኖስ ላለፉት አራት ዓመታት የተለያዩ መድረኮች በማዘጋጀት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ቆይተዋል። አሁን ደግሞ ህወሀትንና ህግደፍን ለማስታረቅ እንቅስቃሴ መጀመራቸው ገልጸዋል። • "አሁን ያገኘነው ሰላም ከሰው ሳይሆን ከአምላክ ነው"- ዘማሪ ሳሙኤል ተስፋሚካኤል የመጀመሪያው እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ መሳካቱ የሚናገረው አብርሃም ገብረሊባኖስ፤ ''ሕዝቦች በአንድነት ሆነው መንግሥታቱ ወደእርቅ የሚመጡበትን መንገድ ሊፈልጉና ጫና ሊያሳድሩ ይችላሉ'' ይላል። 'ሰለብሪቲ ኤቨንትስ' የተባለው ተቋማቸው በተለያዩ ጊዜያት 'መዝሙር' እና 'ሰላም' የተሰኙ የምክክር መድረኮች አዘጋጅቷል። ''እንቅስቃሴው ከተጀመረ በኋላ የኢትዮጵያና የኤርትራ ሕዝቦች በያሉበት ሆነው ተጽእኖ መፍጠር ጀመሩ'' የሚለው አብርሃም፤ 'ሰለብሪቲ ኤቨንትስ' በሁለቱ አገራት ዙርያ የመፍትሄ ሃሳብ ማቅረብ እየቻሉ መድረክ ላላገኙ ምሁራን መድረክ እንደፈጠ ያስረዳል። የኢትዮጵያና የኤርትራ የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት መሪዎች እንዲቀራረቡ እንዲሁም ተጽእኖ እንዲፈጥሩ መሠራቱንም ያክላል። ''የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት እንዲወስን እኛና ሁለቱ ሕዝቦች ግፊት አድርገዋል። እንደ ፕሬዝደንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ያሉ ትልልቅ ሰዎች ተጽእኖ ማሳደራቸውም አይረሳም። ኤምባሲዎችም ግፊት ሲያደርጉ ነበር። መንግሥታቱም ይህን ያውቁት ነበር።'' • ኢትዮጵያና ኤርትራ የመጨረሻውን የሠላም ስምምነት ፈረሙ የሁለቱን አገራት ድንበር መከፈት ተከትሎ፤ 'ሰለብሪቲ ኤቨንትስ' በመቐለ ከተማ ያካሄደውና የሁለቱም አገራት አርቲስቶች የተሳተፉበት የሙዚቃ ዝግጅት፤ ጥልቅ የመነፋፈቅና የወንድማማችነት ስሜት የተንጸባረቀበት ነበር። ህወሀትንና ህግደፍን ማስታረቅ ለምን አስፈለገ? 'ሰለብሪቲ ኤቨንትስ' በምሁራን ታግዞ፣ በሁለቱም አገራት ጥናት እንዳካሄደ የሚገልጸው አብርሃም ገብረሊባኖስ፤ '' አሁን የተገኘው ሰላም ቀጣይና አስተማማኝ እንዲሆን ምን መሠራት አለበት? ብለን ጥናት ለማካሄድ ሞከርን፤ የሁለቱ ፓርቲዎች መኮራረፍ ረዥም ርቀት እንደማይወስደንና መታረቃቸው ለሰላሙ አስፈላጊ እንደሆነም ተረዳን'' ይላል። ተቋሙ ባካሄደው ጥናት፤ ህወሀትና ህግደፍ ማን ናቸው? የማያግባባቸው ነገር ምንድንነው? በመሀከላቸው የውጭ ጣልቃ ገብነት ነበረ? ሁለቱን ፓርቲዎች ለማስታረቅ የሚስችል ሁኔታ አለ? ግዜው ይፈቅዳል? ከሁለቱ ፓርቲዎች እርቅ የኤርትራ እና የትግራይ ሕዝቦች ምን ይጠቀማሉ? የሚሉና ሌሎችም ጉዳዮች በጥልቀት እንደተዳሰሱ አብርሃም ይገልጻል። • ኢትዮጵያና ኤርትራ፡ አዲስ ዓመትን በቡሬና በዛላምበሳ "ከጥናቱ ያገኘነው ሃሳብ የሁለቱ ድርጅቶች መቃቃር አሁንም ቢሆን በሕዝቦች ላይ ጫና እያሳደረ መሆኑን ነው። ተግባብተው መሥራት ባለመቻላቸው፤ ምስራቅ አፍሪካም መረጋጋት ኣልቻለም። ተቀናቃኝ እንጂ ለሰላምና ለልማት አብረው የሚሠሩ አይደሉም" ይላል አብርሃም። ጥናቱን ሲጨርሱ የሁለቱ አገራት ሰላም አስተማማኝ እንዲሆን ህወሀት እና ህግደፍ መታረቅ አለባቸው ወደሚል ድምዳሜ እንደደረሱ ይገልፃል። የአሁኑ የ 'ሰለብሪቲ ኤቨንትስ' ዓላማ ህወሀትና ሕዝባዊ ግንባር ችሮቻቸውን የሚፈቱበት መድረክ መፍጠር ነው። ይህን ማድረግ ከተቻለ ሰላሙ አስተማማኝ እንደሚሆን ያምናሉ። • ኤርትራ ላይ የተጣለው ማዕቀብ ተነሳ "ይህም የኤርትራና የትግራይ ሕዝቦች ያለሃሳብ እንዲያርሱ፣ እንዲሸምቱ፣ እንዲነግዱ፣ እንዲጋቡ ያደርጋል" የሚለው አብርሃም፤ አሁን ያለው ሁኔታ ግን ብዙ ስጋቶች ያዘለ እንደሆነ ይናገራል። ህወሀትና ሕዝባዊ ግንባር ሊታረቁ ይችላሉን? ከኢትዮጵያ የቀረበላቸውን የሰላም ጥሪ የተቀበሉት ፕሬዝደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ፤ የጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድን ጥሪ መቀበላቸውን ባሳወቁበት ወቅት፤ የህወሀትን ስም አንስተው "ጌም ኦቨር" (ጨዋታው አከተመ እንደማለት) ሲሉ ተደምጠዋል። ወደኢትዮጵያ በመጡበት ወቅትም ቀድሞ ሲመላለሱበት የነበረውን የትግራይን ምድር አለመርገጣቸው፤ ብዙዎች "ሰውየው ገና እንደተቀየሙ ነው" እንዲሉ አስገድዷቸዋል። በአንፃሩ አቶ አባይ ፀሃዬን የመሰሉ ከፍተኛ የህወሀት ሰዎች "እኛ ቂሙን ትተነዋል፤ እሳቸውም [ፕሬዚደንት ኢሳይያስ] ቢተዉት ምናለ?" ብለው ተናግረው ነበር። "ዋናው ሕዝቡ እነዚህ ድርጅቶች እንዲታረቁ መፈለጉ ነው። መሪዎቹ ላይ ጫና በመፍጠር ወደውይይት እንዲመጡ ማድረግ ሁለተኛው ነው" የሚለው አብርሃም፤ ሕዝቡ ሁለቱ ድርጅቶች እንዲታረቁ እንደሚፈልገግ ባደረጉት ጥናት አንዳረጋገጡ ይናገራል። ወደሁለቱ መንግሥታት ደብዳቤ ልከው አወንታዊ ምላሽ እንዳገኙ ገልጾ፤ "እምቢ ያለን የለም፤ እስከአሁን እየተባበሩን ነው" በማለት ተስፋ እንዳለ ይገልጻል።
news-42482296
https://www.bbc.com/amharic/news-42482296
ካናዳ የቬንዝዌላን አምባሳደር አባረረች
ካናዳ የቬንዝዌላውን አምባሳደር ዊልመር ባሪኤንቶስ ፈርናንዴዝ እና ምክትላቸውን አንጄላ ሄሬራ ከሀገር ላስወጣ ነው አለች።
ፕሬዝዳንት ማዱሮ በቀጣዩ የፈረንጆቹ ዓመት በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል። የካናዳ የውጪ ጉዳይ ሚንስትሯ ክርስችያ ፍሬላንድ ሀገራቸው ከዚህ ውሳኔ የደረሰችው ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ የካናዳ ዲፕሎማቶች ከካራካስ መባረራቸውን ተከትሎ ነው ብለዋል። ቬንዝዌላ በተደጋጋሚ ካናዳን በውስጥ ጉዳዬ ጣልቃ ትገባለች ስትል ከሳታለች። ካናዳ በበኩሏ የፕሬዝዳንት ማዱሮ መንግስት የሰብዓዊ መብት አያያዙ አስከፊ ነው ስትል ትወቅሳለች። ''እኛ ካናዳዊያን የዜጎቹን ሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ ምብት ነጥቆ መሰረታዊ አገልግሎቶችን ከሚያሳጣ መንግሥት ጋር ወዳጅነት ሊኖረን አይችልም'' ሲሉ የካናዳው የውጪ ጉዳይ ሚንስትሯ ክርስችያ ፍሬላንድ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። በመጠናቀቅ ላይ ባለው 2017 በነበሩ ጸረ-መንግሥት ተቋሞዎች ከ120 ሰዎች በላይ ህይወታቸውን አጥተዋል። በመጠናቀቅ ላይ ባለው 2017 በነበሩ ጸረ-መንግሥት ተቃውሞዎች ከ120 ሰዎች በላይ ህይወታቸውን አጥተዋል። የቬንዝዌላው አምባሳደር ከሀገር ውጪ መሆናቸውን እና ወደ ካናዳ እንዲገቡ አንደማይፈቀድላቸው እንዲሁም ምክትል አምባሳደሯ ካናዳን ለቀው አንዲወጡ እንደተነገራቸው የውጪ ጉዳይ ሚንስትሯ ጨምረው ተናግረዋል። የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደርም በፕሬዝዳንት ማዱሮ ላይ ማዕቀቦችን ጥሏል እንዲሁም ''አምባገነን'' ሲል ፈርጇቸዋል ማዱሮን። የቬንዙዌላ ተቃዋሚዎች ፕሬዝደንት ማዱሮ እና የቀድሞ ፕሬዝደንት ሁጎ ቻቬዝ በሶሻሊስት ሥርዓተ-መንግሥታቸው የቬንዝዌላን ኢኮኖሚ ክፉኛ ጎድተዋል ሲሉ ድምጻቸውን ያሰማሉ። ቬንዝዌላ በዓለማችን ላይ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበትን ካለባቸው ሀገራት አንዷ ስትሆን መድሃኒትን ጨምሮ መሰረታዊ የሚባሉ ሸቀጦች እጥረት በተደጋጋሚ ያጋጥማታል። የፕሬዝደንት ማዱሮ የስድስት ዓመት የስልጣን ዘመን እአአ 2019 ይጠናቀቃል። በቀጣዩ ዓመት በሚካሄደው ምርጫ ለተጨማሪ የስልጣን ዘመን እንደሚወዳደሩ አስታወቀዋል። ከጥቂት ቀናት በፊትም የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ማገዳቸው ተዘግቧል።
news-48009963
https://www.bbc.com/amharic/news-48009963
ስሪላንካ ውስጥ በተፈፀመ ተከታታይ ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 290 ደርሷል
ዕለተ ሰንበት፤ የስሪላንካ ሰዎች ሃገር ሰላም ብለው ፋሲካን እያከበሩ ሳለ ነበር ተከታታይ ጥቃቶች ቤተክርስትያናት እና ታዋቂ ሆቴሎች ላይ የተፈፀሙት።
ጥቃቱ የተጀመረው በሀገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 2፡45 ገደማ ነበር፤ ስድስት ተከታታይ ፍንዳታዎች ተከታትለውም ተሰሙ። የመጀመሪያዎቹ ዒላማዎች የነበሩት ሦስት ቤተክርስትያናት ሲሆኑ፤ ፋሲካን ሊያከብሩ የሄዱ ምዕመናንን ታሳቢ ያደረጉ ጥቃቶች ናቸው ተብለዋል። ለጥቆም በሀገሪቱ አሉ ከሚባሉ ሆቴሎች ሦስቱ ተመሳሳይ ጥቃት ተሰነዘረባቸው። ፖሊስ እነዚህን ጥቃቶች በጀ እያለ በነበረት ወቅት ደግሞ ሌሎች ሁለት ጥቃቶች ተከታትለው ተፈፀሙ። የሀገሪቱ አየር ኃይል ዘግየት ብሎ እንዳስታወቀው አንድ ፈንጂ ቁስ በዋና ከተማዋ ኮሎምቦ በሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ተገኝተል። • የማሊ መንግሥት ስልጣን ልልቀቅ አለ እስካሁን 500 ያክል ሰዎች ቀላል እና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ስሪላንካ ውስጥ ነዋሪ የሆኑ የሌላ ሀገራት ዜጎችም የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸው ታውቋል። ስሪላንካ ድንጋጤ ውስጥ ናት። ከእርስ በርስ ጦርነት ከወጡ አስር ዓመት እንኳን ያልሞላቸው የሃገሪቱ ዜጎች በዕለተ ፋሲካ ማለዳ በሰሙት ፍንዳታ ሰቀቀን ውስጥ መሆናቸውን በርካታ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ይገኛሉ። የስሪላንካው ጠቅላይ ሚኒስትር ራኒል የደህንነት ኃይላቸው ጥቃት ሊፈፀም እንደሚችል መረጃ ቢደርሰውም ፈጣን ምላሽ አልሰጠም ሲሉ ወቅሰዋል። «እኔም ሆንኩ ሚኒስትሮቼ ስለጥቃቱ ምንም የምናውቀው ነገር አልነበረም። ለምን ቅድመ ጥቆማ እንዳልደረሰን ማጣራት ይኖርብናል» ብለዋል። • የኢቲ 302 የመጨረሻዎቹ ስድስት ደቂቃዎች መንግሥት ዜፎቹን ለማረጋጋት የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም ሲሉም ተደምጠዋል ጠቅላዩ። ማኅበራዊ ድር-አምባዎች ለጊዜው ሊዘጉ እንደሚችሉም ወሬ እየተሰማ ነው። የሃገሪቱ ፖሊስ ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ እስካሁን 24 ሰዎችን በቁጥጥር ሥር አውያለሁ ቢልም፤ ጥቃቱን ማን እንደፈፀመው በውል የተለየ ነገር የለም። ኮሎምቦ የሚገኘው የቢቢሲው ዘጋቢ ባለሥልጣናት ነገሩኝ ብሎ እንደዘገበው ጥቃቱ የተፈፀመው በአንድ "ፅንፈኛ እስላማዊ ቡድን" ሳይሆን አልቀረም። ከሟቾቹ አብዛኛዎቹ የክርስትና እምነት ተከታይ ስሪላንካውያን እንደሆኑ የታወቀ ሲሆን፤ የሕንድ፣ ጃፓን፣ እንግሊዝ፣ ዴንማርክ፣ ፖርቱጋል፣ ቱርክና ኔዘርላንድስ ዜጎችም የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸው ተሰምቷል። • ሴቶች ስለምን የአሸባሪ ቡድኖች አባል ይሆናሉ?
news-47876993
https://www.bbc.com/amharic/news-47876993
ፌስቡክ የሞቱ ሰዎችን ገፅ ለማስተዳደር አዲስ አሰራር ቀየሰ
የፌስቡክ አካውንት ያላቸው ግለሰቦች ከሞቱ በኋላ አንዳንድ ማሳወቂያዎች ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጆቻቸው መድረሱ ብዙዎቹን ማሳዘኑና ማበሳጨቱን ተከትሎ ፌስቡክ መፍትሄ አግኝቻለሁ ብሏል።
ኩባንያው እንዳሳወቀው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን (ሰው ሰራሽ ንቃተ ህዋስን) በመጠቀም የሞቱ ሰዎችን ልደት ወይም የተለያዩ ዝግጅቶችን ለመጋበዝ የሚመጣውን ማሳወቂያ ያቆመዋል ተብሏል። •"የሞተው የኔ ያሬድ ነው ብዬ አላሰብኩም" የካፕቴን ያሬድ የ11 አመት ጓደኛ •"ምርኩዜን ነው ያጣሁት" የካፒቴን ያሬድ አባት በሟቾቹም የፌስቡክ ገፅ ላይ ሰዎች የፃፏቸው የሀዘን መልዕክቶች ለብቻ ተከፍለው ፤ ገፃቸው ማቾቹ እንደተውት ተደርጎ እንደሚቀመጥ ኩባንያው አሳውቋል። "ፌስቡክ ያጣናቸውን ግለሰቦች ትዝታቸውና መንፈሳቸውን የምናስታውስበትና ህያው የሚያደርግ መድረክ እንደሚሆን ተስፋ አለኝ" በማለት የፌስቡክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሼሪል ሳንድበርግ ተናግራለች። በተለያዩ ጊዜዎች ከሞቱ ሰዎች ጋር ግንኙነት እንዲፈጥሩ ፌስቡክ መልዕክት እንደሚልክላቸው በማስታወቅ ብዙዎች ቅሬታ ሲያቀርቡ ይሰማል። ከጎርጎሳውያኑ 2009 ዓ.ም ጀምሮ ፌስቡክ ለሟች ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው የማቾችን ስም በመጠቀም ማስታወሻ እንዲፅፉ የሚያስችል ስርአት መዘርጋቱን ተከትሎም በየወሩ 30 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ይፅፋሉ (ፖስት ያደርጋሉ)። ገፁ እንደማስታወሻነት ከተጠቀሙበት በኋላ ግን በህይወት እንዳሉ ሰዎች ማስታወቂያ መላክ እንዳይችል የሆነ ሲሆን ነገር ግን በማስታወሻነት ያልተጠቀሙበት የማቾች ፌስቡክ ገፆችን ግን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን በመጠቀም እንደሚያስተካክሉት አስታውቋል። •"እስካሁን ሙሉ የሰውነት ክፍል ማግኘት እንደተቸገርን ለቤተሰብ እያስረዳን ነው" አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ከዚህም በተጨማሪ ፌስቡክ እንዳሳወቀው የማስታወሻ የፌስቡክ ገፆቭ ማስታወሻ የሚል ክፍል ለብቻው የሚኖር ሲሆን ይህም የሟቾችን የፌስቡክ ገፃቸውን (አካውንታቸው) ምንም ሳይነካ ማስታወሻዎችንና የሀዘን መግለጫዎችን መፃፍ የሚያስችል ነው። የሚፃፉ ማስታወሻዎችን የሚቆጣጠሩት ተወካያቸው ሲሆን፤ ይህም የፌስቡክ ገፃቸውን ከሞቱ በኋላ እንዲቆጣጠርላቸው በሚያምኑትና በሚተኩት የሚሰራ ይሆናል። ማን ፖስት እንደሚያደርግና የአርትኦት ስራውን የሚሰራውን ሟች የወከለው ተተኪ ሰው ይሆናል። ከአስራ ስምንት አመት በታት የሆኑት የሚወክላቸውን ሰው የማይመርጡ ሲሆን አሳዳጊዎችና ቤተሰቦች ግን ፌስቡክን መጠየቅ እንደሚችሉ ተጠቅሷል። እንደዚህ አይነት ለውጦች ተግባራዊ እንዲሆኑ የተደረጉትም በአንዳንድ አጋጣሚዎች ሰዎች ለቀልድ በሀሰተኛ መንገድ ግለሰቦች እንደሞቱ አድርገው ለፌስቡክ ሪፖርት ማድረጋቸውን ተከትሎም እንደሆነ ተጠቅሷል።
news-47863481
https://www.bbc.com/amharic/news-47863481
የተባበሩት መንግስሥታት የትሪፖሊ አየር መንገድ ጥቃትን አወገዘ
የተባበሩት መንግሥታት በሊቢያ ውስጥ በስራ ላይ ያለ ብቸኛው አየር ማረፊያ ላይ የተደረገውን የአየር ድብደባ አጥብቆ እንደሚቃወመው አስታወቀ።
ጥቃት የደረሰበት አየር መንገድ ትናንት በሚቲጋ አየር ማረፊያ በተከፈተ ተኩስ ምክንያት ማንኛውም የአየርመንገዱ ስራዎች የተቋረጡ ሲሆን መንገደኞችን በቶሎ አካባቢውን ለቅቀው እንዲወጡ ተደርገዋል። እስካሁን ግን በሰው ህይወት ላይ ጉዳት እንዳልደረሰ እየተዘገበ ነው። ጥቃቱን የፈጸሙት በምስራቃዊ ሊቢያ በኩል ዋና ከተማዋን ለመያዝ እየተንቀሳቀሰ ያለው የጀነራል ካሊፋ ሃፍታር ወታደሮች ናቸው ሲል የተባበሩት መንግሥታት አስታውቋል። • የሊቢያ ፍርድ ቤት 45 ሰዎች ላይ ሞት ፈረደ • በሊቢያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሰቆቃ እስከመቼ? የጀነራል ካሊፋ ቃል አቀባይ አውሮፕላኖችና ንጹሃን ዜጎች ኢላማ እንዳልተደረጉ ማስታወቃቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። ጀነራል ካሊፋ ሃፍታር የሊቢያ ብሄራዊ ግንባርን የሚመሩ ሲሆን በተባበሩት መንግስታት የሚደገፈውን መንግስት ጠራርጎ በማስወጣት ዋና ከተማዋ ትሪፖሊን ለመቆጣጠር ጥረት ማድረግ ከጀመሩ ቆይተዋል። የሊቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፋዬዝ አል ሲራጅ በበኩላቸው ጀነራሉ የመፈንቅለ መንግስት ለማድረግ እየሞከሩ ነው በማለት ከሰዋል። የተባበሩት መንግሥታት ባወጣው መረጃ መሰረት በዋና ከተማዋ ትሪፖሊ ያለውን ተኩስ በመሸሽ ቢያንስ 2800 የሚደርሱ ሰዎች መኖሪያቸውን ለቅቀው ሄደዋል። •"አደጋውን ስሰማ በረራው ጠዋት እንዳልሆነ ራሴን አሳመንኩኝ" የረዳት አብራሪው ጓደኛ በሊቢያ የተባበሩት መንግስታት ልዩ መልእክተኛ ጋሳን ሳላሜ ሰኞ ዕለት እንዳስታወቁት የአየር ጥቃቱ ንፁሃን ዜጎች የሚጠቀሙባቸው መሰረተ ልማቶች ላይ ምንም አይነት እርምጃ ላለመውሰድ የተደረሰውን ስምምነት የሚጥስና ተቀባይነት የለውም ብለዋል። የጀነራል ካሊፋ ቃል አቀባይ አህመድ ሚስማሪ በአየር ማረፊያው ቆሞ የነበረ አንድ አውሮፕላን ብቻ የጥቃቱ ኢላማ እንደነበረ መግለጻቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። ጀነራል ካሊፋ ሃፍታር የሊቢያ የጤና ሚኒስትር መስሪያ ቤት እንዳስታወቀው እስካሁን በተደረጉ የተኩስ ልውውጦች የ25 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 80 ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል። የጀነራል ካሊፋ ሃፍታር ወታደሮች ደግሞ 19 ተዋጊዎቻቸውን እንዳጡ ገልጸዋል። • ታግተው የነበሩት የትሪፖሊ ከንቲባ ተለቀቁ • በሊቢያ በተፈጠረ ግጭት ከአራት መቶ በላይ እስረኞች አመለጡ ባሳለፍነው እሁድ ደግሞ በተባበሩት መንግስታት አደራዳሪነት ለሁለት ሰአታት የቆየ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ተደርሶ የነበረ ሲሆን ንጹሃን ዜጎችን ከአካባቢው ለማስወጣት የተደረገ ሙከራ ነበር። የትሪፖሊ ነዋሪዎችም ከባድ ጦርነት እነደሚመጣ በመገመት ምግብና ነዳጅ ከአሁኑ ማጠራቀም እየጀመሩ ነው።
news-57251119
https://www.bbc.com/amharic/news-57251119
በትግራይ ረሃብ ሊከሰት እንደሚችል ዩናይትድ ኪንግደምና የተባበሩት መንግሥታት ስጋታቸውን ገለጹ
አፋጣኝ እርምጃ ካልተወሰደ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ ያለው ሁኔታ ወደ አሳሳቢ የረሃብ አደጋ ሊደርስ እንደሚችል የዩናይትድ ኪንግደምና የተባበሩት መንግሥታት ባለሥልጣናት አሳሰቡ።
በሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች በሱዳን የስደተኛ ካምፖች ይገኛሉ በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ በወራት ጊዜ ውስጥ የረሃብ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል የዩናይትድ ኪንግደም ረሃብ የመከላከል ልዩ መልዕከተኛ የሆኑት ኒክ ዳየር አስጠንቅቀዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ጥረት ከፍ እንዲል ካልተደረገ በትግራይ ክልል ውስጥ "ከባድ የረሃብ አደጋ" ሊከሰት እንደሚችል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮችና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ባለሥልጣን ማርክ ሎውኮክ ለኤኤፍፒ ተናግረዋል። ሎውኮክ ለጸጥታው ምክር ቤት እንደተናገሩት በትግራይ ክልል 90 በመቶ ምርት ታጥቷል እንዲሁም 80 በመቶ የቀንድ ከብት ተዘርፈዋል ወይም ታርደዋል። በዚህም ሳቢያ በክልሉ ካሉ አምስት ሰዎች መካከል አንዱ ለምግብ ችግር ተጋልጧል ብለዋል። ባለሥልጣኑ ጨምረውም የተጠናከረ እርምጃ መውሰድ ካልተቻለ አሁን ያለው ሁኔታ የበለጠ እየተባባሰ ይሄዳል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። የዩናይትድ ኪንግደም ልዑኩ ኒክ ዳር በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ተጉዘው በግጭት በተጎዳው የትግራይ ክልል ካደረጉት ጉብኝትና ግምገማ በመነሳት ነው ስጋታቸውን የገለጹት። አሳሳቢ ግድያዎችና የመድፈር ድርጊቶችን የሚያመለክቱ ሪፖርቶችን በመጥቀስ ያለው ሁኔታ "አደገኛ" ነው ሲሉ ልዩ መልዕክተኛው ገልጸዋል። ኒክ ዳየር ጨምረውም የግብርና መገልገያዎች፣ የሰብል ዘር እንዲሁም መንደሮች መውደማቸውን በመግለጽ ያለውን ችግር አመልክተዋል። በተዘጉ መንገዶችና በውጊያዎች ምክንያት በክልሉ ከፍተኛ መጠን ያለው ሕዝብ ለመድረስ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝም ተናግረዋል። በተጨማሪም ከጥቂቶች በስተቀር በክልሉ ውስጥ በርካታ የጤና ማዕከላት መውደማቸው አሳሳቢው ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው፤ የጤና ችግር እንደ ረሃብ አደጋው ሁሉ ከፍ ያለ ስጋትን ይደቅናል ብለዋል። ኒክ ዳየር ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ውስጥ ባደረጉት ጉብኝት ከአገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ተገናኝተው በትግራይ ክልል ስላለው ሁኔታ መወያታቸውን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በዚህም ወቅት ሚኒስትሩ በክልሉ ሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች እየተደረገ ስለሚገኘው ድጋፍን ጨምሮ በክልሉ ስላለው የመልሶ ማቋቋምና ግንባታ ሥራዎች ማብራሪያ እንደሰጡ ተገልጿል። በተጨማሪም በክልሉ ተፈጽመዋል ስለተባሉት የመብት ጥሰቶችን በተመለከተ ከተለያዩ መንግሥታዊና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ጋር በመሆን ምርመራ ለመጀመር የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን አመልክተዋል። ከስድስት ወራት በፊት በተቀሰቀሰው ወታደራዊ ግጭት ሳቢያ በሰውና በመሰረተ ልማቶች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱ ሲነገር የቆየ ሲሆን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ነዋሪ የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚፈልግ የረድኤት ድርጅቶች ገልጸዋል።
news-46601691
https://www.bbc.com/amharic/news-46601691
አሜሪካ የመናዊቷ እናት በሞት አፋፍ ላይ ያለ ልጇን እንዳታይ ከለከለች
የመናዊቷ እናት በካሊፎርኒያ በሞት አፋፍ ላይ የሚገኝ ህፃን ልጇን ለማየት ወደ አሜሪካ እንዳትገባ ተከለከለች።
ህፃኑ እንደማይተርፍ ዶክተሮች ተናግረዋል የሁለት ዓመቱ ህፃን አብዱላህ ሃሰን የተወለደው ከአእምሮ ህመም ጋር ሲሆን ህይወቱን ማትረፍ እንደማይቻል ዶክተሮች ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት የህፃኑ እስትንፋስ ያለው በህክምና መሳሪያ ድጋፍ ሲሆን መሳሪያው ተነስቶ እስትንፋሱ እንዲቋረጥ ከመደረጉ በፊት እናቱ ለመጨረሻ ጊዜ ልታየው መፈለጓን ቤተ ዘመዶች ገልፀዋል። የህፃኑ እናት ልጇን ማየት ያልቻለችው የትራምፕ አስተዳደር በጣለው የጉዞ እገዳ ምክንያት እንደሆነ ቤተ ዘመዶቹ ጨምረው ገልፀዋል። ህፃኑ አብዱላህ እና አባቱ የተወለዱት አሜሪካ ውስጥ በመሆኑ የአሜሪካ ዜግነት አላቸው። • ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በቅዳሜው ውይይት ላይ ምን አሉ? • ብሄራዊ ባንክ ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ጋር የግሉን ዘርፍ ለማገዝ ስምምነቶችን አደረገ • የመን ''የዓለማችን አስከፊው ረሃብ'' ተጋርጦባታል የህፃኑ እናት በአሁኑ ወቅት የምትገኘው ግብፅ ሲሆን ህፃኑን እናቱ እንድታየው ወደ ግብፅ እንውሰደው ቢባል በጉዞው ሊሞት ስለሚችል ይህ የሚታሰብ እንዳልሆነ ተገልጿል። አባት ልጁን ለህክምና ወደ አሜሪካ ይዞት የሄደው ከሶስት ወራት በፊት የነበረ ሲሆን እናትም እንደ አስፈላጊነቱ ትከተለናለች በሚል እሳቤ ነበር። ነገር ግን ዶክተሮች የህፃኑ ህመም እጅግ ፅኑ መሆኑን ሲገልፁ እናት የግድ ከልጇ ጎን መሆን እንዳለባት በማመን ለቪዛ ማመልከቻ አስገቡ። ከአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት የደረሳቸው መልስ ግን እናት ቪዛ መከልከሏን የሚገልፅ ነበር። የአሜሪካ ባለስልጣናት ለቢቢሲ እንደገለፁት እናት በህጋዊ መንገድ ወደ አሜሪካ እንድትገባ የተቻላቸውን ሁሉ ማድረጋቸውን ገልፀዋል። "እናቱ የምትፈልገው ለመጨረሻ ጊዜ የልጃችንን እጅ መያዝ ነው" በማለት የ22 ዓመቱ የህፃኑ አባት አሊ ሃሳሳን ተናግሯል። የትራምፕ አስተዳደር ስራ እንደጀመረ በአብዛኞቹ የሙስሊም አገራት ላይ የጉዞ እገዳ መጣሉ የሚታወስ ነው። በዘህም የሊቢያ፣ የመን፣ ሶሪያ፣ ቬንዙዌላ እንዲሁም ሰሜን ኮሪያ ዜጎች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ሆኗል።
news-54109328
https://www.bbc.com/amharic/news-54109328
አውስትራሊያ ፡ ኒው ሳውዝ ዌልስ ግዛት አስተዳደርን ለሁለት የከፈለው የዱር እንስሳ
የአውስትራሊያዋ ኒው ሳውዝ ዌልስ ግዛት መንግሥት 'ኮዋላ' የተባሉትን የዱር እስሳት እንዴት እንጠብቅ በሚለው ፖሊሲ ላይ መስማማት አቅቷት ኃላፊዎቿ በሁለት ጎራ ተከፍለው እየተጨቃጨቁ ነው።
ከሰላሳ ዓመት በኋላ ከኒው ሳውዝ ዌልስ ትጠፋለች የተባለችው ኮዋላ ወደ መንግሥት መዋቅር በቅርቡ የተቀላቀለው ብሔራዊ ፓርቲ ከዚህ በኋላ መንግሥት የሚያቀርባቸውን ፖሊሲዎች እንደማይደግፍ ያስታወቀ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ለኮዋላዎች የተዘጋጀውን ፖሊሲ ስለሚቃወም ነው ብሏል። ነገር ግን የፓርቲው ምክትል ኃላፊ ጆን ባሪላሮ ''እኛ ኮዋላዎችን አንጠላም'' ብለዋል። አክለውም በፓርቲያቸው ውስጥ የሚገኙ ሕግ አውጪዎች ከዚህ በኋላ ከሊብራል ፓርቲ አባላት ጋር ፓርላማ ውስጥ መቀመጥ እንደማይፈልጉ ገልጸዋል። በሲድኒ ሄራልድ ''የኮዋላ ጦርነት'' የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ አለመግባባት ከመንግሥት የአካባቢ ጥበቃ ፖሊሲ እቅድ ጋር የተገናኘ ሲሆን ፖሊሲው ባለፈው ዓመት ታህሳስ ላይ ሕግ ሆኖ ጸድቋል። የሕጉ ዋና አላማም ኮዋላዎችን መጠበቅና መንከባከብ እንዲሁም መኖሪያ አካባቢያቸውን ምቹ ማድረግ ነው። ባሳለፍነው ሰኔ ወር ላይ ደግሞ አፋጣኝ እርምጃ የማይወሰድ ከሆነ ኮዋላዎች በአውሮፓውያኑ 2050 ከምድረ ገጽ ሊጠፉ እንደሚችሉ ተገልጾ ነበር። ባለፈው የፈረንጆቹ የበጋ ወቅት ተከስቶ በነበረው የዱር ሰደድ እሳት ደግሞ ሦስት ቢሊየን እንስሳትን ጎድቷል አልያም ገድሏል የሚል ግምት ተቀምጦ ነበር። ነገር ግን የፓርቲው ምክትል ኃላፊ ጆን ባሪላሮ ፖሊሲው ኮዋላዎችን ከመታደግ ባለፈ ዜጎችን ለሌሎች ችግሮች የሚያጋልጥና ሰፋፊ መሬት ያላቸውን ሰዎች መሬታቸውን እንዴት ማስተዳደር እንዳለባቸው ለመንገር የሚሞክር ነው በማለት ተችተዋል። ''እኛ እንደሚመስለን ፖሊሲው አካባቢውን ለመጽዳትና በክልሉ የሚገኙ የመሬት ባለቤቶችን ለማጥቃት የታሰበና ከኮዋላዎች ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው ነገር ነው'' ብለዋል። አክለውም ''ብሄራዊ ፓርቲው የኮዋላዎች ብዛት እንዲጨምር ይፈልጋል። እንደውም ኮዋላዎች አሁን ካላቸው ቁጥር በእጥፍ እንዲያድጉ እንፈልጋለን። እኛ ጸረ ኮዋላዎች አይደለንም'' ሲሉ ተናግረዋል። ነገር ግን የሊብራል ፓርቲው ፖለቲከኞች "እርምጃው ተገቢና የአካባቢውን ማሕበረሰብ የሚደግፍ ነው" ሲሉ ተደምጠዋል። የፌደራል ግሪንስ ፓርቲ መሪው አዳም ባንዲት በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክትም '' እነሱ የመንግሥትን የአካባቢ ጥበቃ ፖሊሲ የማይቀበሉት ሕግ የማያከብሩ የመሬት ባለቤቶች ተጨማሪ ኮዋላዎችን መግደል እንዲችሉ ነው'' ብለዋል። አንዳንድ የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋቾች ደግሞ እንደውም አሁን ያለው የመንግሥት ፖሊሲ እንስሳትን ከጉዳት ለመከላከል በቂ አይደለም ሲሉ ይሞግታሉ።
55814357
https://www.bbc.com/amharic/55814357
የግዙፉ ጎልድማን ሳክስ ባንክ ሥራ አስፈጻሚ ከደመወዛቸው 10 ሚሊዮን ዶላር ተቀነሰ
ከዓለማችን ግዙፍ ባንኮች አንዱ የሆነው ጎልድማን ሳክስ የሥራ አስፈጻሚውን ደመወዝ በ10 ሚሊዮን ዶላር ቀንሷል።
የጎልድማን ሳክስ የሥራ አስፈጻሚ ዴቪድ ሶሎሞን ዴቪድ ሶሎሞን ደመወዙ የተቆረጠባቸው ባንኩ ባለፉት ዓመታት ከገጠመው ምዝበራና ማጭበርበር ጋር የተያያዘ ነው። ሆኖም እሳቸው በዚህ 'ታላቅ ማጭበርበር' የሉበትም ተብሎ ተመስክሮላቸዋል። እሳቸው በምዝበራው እጃቸውን ባያስገቡም ባንኩ የከፍተኛ ኃላፊዎችን ደመወዝ ስለቀነሰ ነው የሳቸውንም ለመቀነስ የተገደደው ተብሏል። ከደመወዛቸው 10 ሚሊዮን ዶላር ባይቀነስ ኖሮ ዴቪድ ሶሎሞን ክፍያቸው 27 ሚሊዮን ዶላር ይደርስ ነበር። ይህ በባንኩ ታሪክ 'ታላቁ ማጭበርበር' እየተባለ የሚጠራው የገንዘብ ምዝበራ የተካሄደው ከማሌዢያ መንግሥት ጋር ሲሆን ማሊዢያ 1ኤምዲቢ የሚባል ሐሰተኛ የኢንቨስትመንት ፈንድ በማቋቋም ባንኩ ቦንዶችን እንዲሸጥ ከተደረገ በኋላ ገንዘቡ እንደተዘረፈ ተደርሶበታል። ይህ የሆነው በፈረንጆቹ 2012 ቢሆንም ምርመራው ዛሬም ድረስ አልተጠናቀቀም። የማሊዢያ መንግሥት ኢንቨስትመንት ፈንድ ከታላቁ ጎልድማን ሳክስ ጋር ፈንዱን እንዲሰበስብለት 600 ሚሊዮን ዶላር ክፍያ ፈጽሞለት ነበር በወቅቱ። ባንኩ በበኩሉ ቦንድ በመሸጥ በቢሊዮን ዶላሮች መሰብሰብ ችሎ ነበር። ገንዘቡ ግን እስከ አሁን የገባበት አልታወቀም። ይህ ብዙ አገራትና ክፍለ አህጉራትን ያካለለው ማጭበርበር የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩትን ናጂብ ራዛቅን 12 ዓመት እስር እንዲፈርድባቸው ያደረገ ነው። ቢሊየነሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ናጂብ ራዛቅ አሁንም ይግባኝ እያሉ ነው። ጎልድማን ሳክስ ይህ 'ተቋማዊ መደነቃቀፍ ነው እንጂ ሌላ አይደለም' ሲል ከቅሌቱ ራሱን ለማራቅ ሞክሮ አልፎታል። ጎልድማን ሳክስ ባንክ ለዚህ 1ኤምዲቢ (1MDB) ተብሎ ለሚጠራው ሀሰተኛ ኢንቨስትመንት የ6 ቢሊዮን ዶላር ፈንድ ቦንድ በመሸጥ አሰባስቦ ነበር። 1ኤምዲቢ ፈንድ ማሌዢያን የኢሲያ ስቶክ ማርኬት ማእከል አደርጋለሁ ብሎ የተነሳና በርካታ ኢንቨስትመንቶች ውስጥ ለመግባት ቃል የገባ ሐሳዊ ቢዝነስ ነበር። የኋላ ኋላ እንደተደረሰበት ተሰበሰብበ የተባለው ገንዘብ ብዙ ባንኮች እየተሽከረከረ፥ እየገባና እየወጣ በአመዛኙ እምጥ ይግባ ስምጥ ሳይታወቅ እስከዛሬም አለ። ጉዳዩን ለዓመታት ሲመረምሩ የነበሩ የፋይናንስ መርማሪዎች ጎልድማን ሳክስ ቀጥተኛ አጭበርባሪ ባይሆንም ቦንድ እየሰበሰበ የነበረው ለተጭበረበረ ኢንቨስትመንት እንደሆነ የሚያሳዩ በርካታ ምልክቶች ነበሩ ብሏል። ባንኩ ይህንን እያወቀ ነገሩን ቸል ብሎ ቆይቷል ብለው ይከሳሉ። 1ኤምዲቢ ፈንድ የማሊዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቀኝ እጅ የሆነ ጆ ሎው የሚባል ሰው ከጀርባ ሆኖ ይዘውረው እንደነበር ተደርሶበታል። በዚህ ቅሌት የተነሳ ሁለት የጎልድማን ሳክስ ባንክ ባልደረቦች የወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል። በዚህ ወቅት የጎልደን ሳክስ ባንክ ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት ሚስተር ሶሎሞን ደመወዛቸውና ጥቅማ ጥቅሙ አሁን ከተጠቀሰው 10 ሚሊዯን ዶላር ተጨማሪ የነበረ ሲሆን የቦርድ ዳይሬክተሮች ግን ከዚህ የ1ኤምዲቢ ቅሌት ጋር በተያያዘ ክፍያቸውን ቀንሶባቸዋል። የሥራ አስፈጻሚው ደመወዝ 10 ሚሊዮኑ ዶላር ተቀንሶበትም ወደ 17 ሚሊዮን ተኩል ደርሷል። ባንኩ ሚስትር ሶሎምን ስለዚህ የክፍለ ዘመኑ ማጭበርበር የሚያውቁት ነገር አልነበረም ሲል መስክሮላቸዋል። ሚስተር ሶሎሞን ክፍያቸው 2 ሚሊዮን በካሽ፣ 4 ሚሊዮን በቦነስ መልክ፣ እንዲሁም 10 ሚሊዮን ከስቶክ ጋር በተያያዘ ማካካሻ ክፍያ ተደርጎ ነው የሚከፈላቸው። ደመወዛቸው እንደ የሥራ ዘመኑ ትርፍና ኪሳራ ከፍና ዝቅ የሚል ነው። ጎልድማን ሳክስ ከዚህ የማጭበርበር ቅሌት ጋር በተያያዘ ለአራት አገራት 3 ቢሊዮን ዶላር መልሶ ለመክፈል ተስማምቶ ነበር። ይህን ክፍያ ሲፈጽም ግን ከዚህ ማጭበርበር ጋር የተያያዙ ምርመራዎች ሙሉ በሙሉ እንዲቆሙ በመጠየቅ ነው። በ2012 እና በ2013 ብቻ ባንኩ ይህንን ቦንድ ሽያጭ ለማሌዥያው 1ኤምዲቢ ፈንድ ለመሰብሰብ ለሚሰራው ሥራ 600 ሚሊዮን ዶላር ተከፍሎት ነበር። ይህ የክፍለ ዘመኑ ማጭበርበር ተብሎ የሚጠራው የባንኩ ቅሌት በአሜሪካ፥ በዩኬ፥ በሲንጋፖር፣ በሆንግኮንግ ከፍተኛ ምርመራዎች ለዓመታት ሲደረጉበት ነበር። ኮልድማን ሳክስ በዚህ የተጭበረበረ የቦንድ ሽያጭ ውስጥ በመሳተፉ ባንኩን 5 ቢሊዮን ዶላር አካባቢ አሳጥቶታል። ያም ሆኖ ባንኩ በተገባደደው የፈረንጆች ዓመት ትርፉ ወደ 44 ቢሊዮን ዶላር ተመንድጓል። ጎልድማን ሳክስ እና 1ኤምዲቢ ፈንድ የገቡበት የቢሊዮን ዶላር ማጭበርበር ብዙዎች ሚዲያዎች የሆሊውዱ ሊዮናርዶ ዲካፕሪዮ የተወነበትን 'ዘ ዎልፍ ኦፍ ዎል ስትሪት' ፊልም ጋር ያመሳስሉታል።
news-46423171
https://www.bbc.com/amharic/news-46423171
የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ያሳስበኛል እያሉ ነው
የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ በቤተክርስቲያኒቱ ቀሳውስት መካከል እየተፈጠረ ያለው የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት እጅጉን እንደሚያሳስባቸው አሳወቁ።
በሃይማኖታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ቃለ-መጠይቅ የሰጡት ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ጉዳይ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ነው ሲሉ ተደምጠዋል። የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን 'ዘመን አመጣሽ' ሲሉ የገለፁት ፖፕ ፍራንሲስ ቀሳውስት ከድርጊቱ በመቆጠብ ለጌታ ትዕዛዝ ተገዥ እንደሆኑ አሳስበዋል። • የሮማው ጳጳስ አለም የስደተኞችን ጉዳይ ቸል እንዳይል ተማጸኑ የካቶሊክ አብያተ ክርስትያናት ለቫቲካን የሚሆን ቄስ ሲመርጡ አስተውለው እንደሆን ጥሪ አቅርበዋል። ቄሶችን የሚያሰለጥኑ የኃይማኖት ሰዎች 'በሰብዓዊነት እና ስሜትን በመቆጣጠር' ብቁ እንዲሆኑ ሊያደርጓቸው ይገባል ሲሉም መልዕክት አክለዋል። በቅስና እና ምንኩስና ዓለም የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ቦታ እንደሌላቸው ነው ፖፕ ፍራንሲስ ያሳወቁት። • የጀርመን ቄሶች ቅሌት ሲጋለጥ በፈረንጆቹ 2013 ፖፕ ፍራንሲስ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ድርጊት ሃጥያት ነው የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ውስጥ መገኘት ግን አይደለም ብለው ትንሽ ወዝገብ የሚያደርግ አስተያየት መስጠታቸው ይታወሳል። «አንድ ሰው የተመሳሳይ ፆታ ውስጥ ሆኖ ፈጣሪን የሚፈልግ ከሆነና መልካም ምግባር ካለው እኔ ማን ሆኜ ነው የምፈርደው» ብለው ነበር አስተያየት የሰጡት።
55468542
https://www.bbc.com/amharic/55468542
የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል መውሰድ የሚችሏቸው 10 እርምጃዎች
የአየር ንብረት ለውጥ መላው ዓለምን ከሚያሳስቡ ሁነቶች አንዱ ነው። የአገራት መሪዎች በተለያየ ጉባኤ ይመክሩበታል። የአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋቾችም ግንዛቤ ለመፍጠር ይጥራሉ።
አገራት እንዲሁም ተቋሞች ካለባቸው ኃላፊነት ጎን ለጎን ግለሰቦችም የራሳቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት ይችላሉ። እርስዎም ቀጣዮቹን አስር እርምጃዎች ቢወስዱ ዓለምን ከአየር ንብረት ለውጥ ለመታደግ የሚደረገውን ጥረት ያግዛሉ። 1.ተረፈ ምርትን በድጋሚ ጥቅም ላይ ማዋል የተረፈ ምርቶች መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው። እንዲያውም በቀጣይ 20 ዓመታት የተረፈ ምርት መጠን 2 ቢሊዮን ቶን ይሆናል ተብሎ ይገመታል። ስለዚህም ተረፈ ምርቶችን በድጋሚ ጥቅም ላይ ማዋል አንዱ አማራጭ ነው። 2. የውሀ አካልን መጠበቅ በተለያዩ የምድር ክፍሎች የውሀ አካላት እየደረቁ መጥተዋል። ውሀ ውስጥ የሚኖሩ እንስሳት ላይ ጉዳት እየደረሰም ይገኛል። ይህም እጅግ አስጊ ነው። ስለዚህም ማንኛውም አይነት የውሀ አካል ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል። ከውሀ አካል ባሻገር የምድራችን የደን ሀብትም እየተመናመነ መጥቷል። እአአ ከ1960ዎቹ ወዲህ ግማሽ ያህሉ የዓለም የደን ሀብት ወድሟል። ብዝሀ ሕይወትም እየተቃወሰ ነው። ደን የካርቦን ልቀትን በማመቅ ምድር ከመጠን በላይ እንዳትሞቅ ያደርጋል። ስለዚህም ዛፍ መትከል እንዲሁም ደን አለመጨፍጨፍ የእያንዳንዱ ሰው ኃላፊነት ነው። 3. 'ሰልባጅ' መግዛት ልብስ ለመሥራት የሚውለውን ተፈጥሯዊ ግብአት ለመቆጠብ ሲባል የሚወሰዱ እርምጃዎችን ደግሞ እንመልከት። አንደኛው አማራጭ ልብስ ጥቅም ላይ የሚውልበትን እድሜ ማርዘም ነው። አንድ ሰው አልባሳቱን ለተወሰነ ጊዜ ከተጠቀመ በኋላ ለተራድኦ ድርጅቶች መስጠት ይችላል። በዚህ መንገድ ሚሊዮን ቶን የሚመዝኑ ጥቅም አልባ ተብለው የተጣሉ ልብሶችን ማዳንና አካባቢን መጠበቅ ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪ ጥቅም ላይ የዋሉ ወይም ሰልባጅ ልብሶችን መግዛት ሌላው መፍትሔ ነው። 4. የሕንጻ ካርበን ልቀትን መግታት 40 በመቶ የሚሆነው የምድር የካርቦን ልቀት የሚመነጨው ከግንባታ፣ ጥገና እና ሕንጻዎች ነው። በተለይም ቢሮ የሚበዛባቸው ሕንጻዎች ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳሉ። ይህንን ችግር መቅረፍ ከሚቻልባቸው መንገዶች አንዱ ጥብቅ ሕግ ማውጣትና ሕጉን የሚተላለፉን መቅጣት ነው። 5. ከመደብር ስለሚገዙት ቁሳቁስ ማወቅ ብዙ መደብሮች ስለሚሸጧቸው ቁሳቁሶች ግልጽ መረጃ አይሰጡም። ከቁሳቁሶች በተጨማሪ የምንገዛው ምግብ የትና በምን ሁኔታ እንደተመረተ ሊገለጽልን ይገባል። አንድ ምርት ሲዘጋጅና ሲጓጓዝ ምን ያህል ካርቦን እንደተለቀቀ በግልጽ ቢቀመጥ፤ ሁላችንም በመረጃ የተደገፈ ውሳኔ ላይ መድረስ እንችላለን። 6. ሴቶችን ትምህርት ቤት መላክ በየትኛውም የዓለም ጥግ ሴቶች መማር አለባቸው። የዓለም እኩሌታውን የያዙት ሴቶች እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ድረስ እንዲማሩ ምቹ ሁኔታዎች ሊመቻቹ ይገባል። ማኅበረሰቡ በተማረ ቁጥር ለአካባቢ ጥበቃ የሚሰጠው ትኩረት ያድጋል። 7. ምግብ አለማባከን ምግብ አስተርፎ መጣል የካርበን ልቀትን ከሚጨምሩ መካከል ይጠቀሳል። ዌስት ኤንድ ሪሶርስስ አክሽትን ፕሮግራም የተባለው የእርዳታ ድርጅት እንደሚለው በዩናይትድ ኪንግደም ብቻ 6.6 ሚሊዮን ቶን ምግብ ይጣላል። ምግብ ተርፎ እንዳይጣል፤ ምን ምግብ መግዛት እንደሚፈልጉ፣ ምን ያህል እንደሚመገቡ አስቀድሞ ማወቅ ይገባል። 8. ማኅበራዊ ሀይል ማመንጨት በእንግሊዘኛ ኮምዩኒቲ ኢነርጂ ይባላል። አንድ ማኅበረሰብ ተሰባስቦ ኃይል የሚያመነጭበት መንገድ ነው። የጋራ ሀይል ማመንጨት ከሚሠራበት አንዱ የኤሌክትሪክ ሀይል ዘርፍ ነው። ለምሳሌ ዴንማርክ ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት የንፋስ ሀይል ማመንጫዎች የማኅበረሰቡ የጋራ ንብረት ናቸው። 9. አትክልት ነክ ምግብ ማዘውተር አትክልት ነክ ምግብ ማዘውተር ምድርን ከአየር ንብረት ለውጥ ከሚታደጉ መፍትሔዎች አንዱ ነው። አትክልት፣ ፍራፍሬና ጥራጥሬ ማዘውተርና ስጋ መቀነስ ለግል ጤና ከመጥቀሙ ባሻገር አካባቢንም ከጉዳት ያድናል። 10. የካርቦን መጠንን መቀነስ በዚህ ትውልድ የሚከወኑ ነገሮች መጪው ትውልድ ላይ ጫና ማሳደራቸው አይቀርም። ታዲያ መጪውን ትውልድ ለመታደግ የካርቦን ልቀትን መቆጣጠር የግድ ነው። ስለዚህም የካርቦን ልቀታቸው አነስተኛ የሆኑ ምርቶችን መሸመት በማዘውተር የድርሻዎን መወጣት ይችላሉ።
news-52267351
https://www.bbc.com/amharic/news-52267351
ኮሮናቫይረስ፡ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በየመን የሚገኙ ኢትዯጵያውያን ስደተኞች ለኮሮናቫይረስ እንዳይጋለጡ ስጋት አለኝ አለ
ዓለም አቀፉ ስደተኞች ድርጅት በሳኡዲ አረቢያና የመን ድንበር በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ለኮሮናቫይረስ ለአደጋ ተጋልጠዋል ሲል አስታወቀ።
ቢቢሲ ባለፈው ሳምንት ያናገራቸውና በየመንና ሳኡዲ ድንበር አቅራቢያ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ባገኘው መረጃ መሰረት ከሁውቲ ታጣቂዎች በደረሰባቸው ጥቃት በየበረሃው መበተናቸውን ገልፀው ነበር። የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት የኮምዩኒኬሽን ኃላፊ ሄዶን ኦሊቪያ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ድርጅታቸው ስለሁኔታው እንደሚያውቅ አረጋግጠው ይህም እንደሚያሳስበው እና ስጋት እንደገባው ገልፀዋል። • ቢልጌትስ የኮሮናቫይረስ ሊከሰት እንደሚችል እንዴት ቀድመው ሊያውቁ ቻሉ? ድርጅቱ በየበረሃው ተበትነዋል የተባሉት ስደተኞቹን ቁጥር በውል ባያረጋግጥም ምንጮቻችን ግን በግምት ከ5 ሺህ በላይ የሚሆኑ ስደተኞች ሰአዳ በተባለ የየመን ግዛት ወደ ሳኡዲ አረቢያ ለመሻገር ሲሞክሩ ከኮሮናቫይረስ ጥርጣሬ ጋር በተያያዘ በሁለቱም ወገኖች መካከል አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል ብለዋል። እንደ ኃላፊዋ ገለፃ ይህ ስፍራ ከፍተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ያለበት ቦታ ነው። ስደተኞቹ ያሉበት ሁኔታን ለቢቢሲ ሲናገሩም በሁውቲ አማፂያንና በመን መንግሥት ወታደሮች መካከል ውጊያ በሚካሄድበት ስፍራ በየዕለቱ ውጊያ እንደሚካሄድ ጠቅሰው "በየዕለቱም ጥይት በላያችን ላይ እያፏጨ በስጋት ነው" ሲሉ ገልፀዋል። ቢቢሲ በየመን ድንበር አቅራቢያ የሚገኙና አደጋ ላይ ናቸው የተባሉትን ስደተኞች አግኝቶ ለማናገር በስፍራው ስልክ ግንኙነት የተቋረጠ በመሆኑ አልተቻለም። ቀደም ሲል ከሳምንት በፊት ከ4 ሺህ በላይ ስደተኞች ከመካከላቸው ወደ ሳኡዲ አረቢያ የተሻገሩ መሆኑን የገለፁ ስደተኞች እነርሱም ግን በእስር ቤት እንደሚገኙ ተናግረዋል። • ቻይና ከኮሮናቫይረስ ጋር ያደረገችውን ፍልሚያ በቅርብ የታዘበው ኢትዮጵያዊ ዶክተር እነዚህ ስደተኞች ስጋት ውስጥ የወደቁት በጦርነቱ ብቻ ሳይሆን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ታዛምታላችሁ በሚል በሚደርስባቸው ጥቃት ጭምር እንደሆነ ይናገራሉ። ኃላፊዋም በየመን አማፂያንና በሳኡዲ መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ቢደረግም አሁን ያለው ስጋት የጦርነት ብቻ ሳይሆን የቫይረሱ መስፋፋት በመሆኑ የስደተኞቹን ስጋት አይቀንሰውም ሲሉ ለቢቢሲ ገልፀዋል። ሄዶን ኦሊቪያ አክለውም ድርጅቱ ምን ማድረግ እንዳለበት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተነጋገረ መሆኑንና ያለውን ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ሊያሳይ በሚችል መልኩ ጥናት እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል። አክለውም በስደተኞች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት እንዲቆም እንዲሁም ከኮሮናቫይረስ ጋር በተየያዘ አገራት በበሸታው መከላከል ላይ ስደተኞችን የሚያካትት ስልት እንዲከተሉ እንዲሁም ዜግነታቸውንና ህጋዊነታቸውን ሳይመለከቱ ከዜጎቻቸው ጋር እኩል የጤና አገልግሎት እንዲያቀርቡላቸው ጠይቀዋል። • ልናውቃቸው የሚገቡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዝርዝር ይዘቶች በዚህ መካከል በጥቃቱ የተወሰኑ ስደተኞች ሞተው ሊሆን ይችላል ሲሉ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ወገኖች ስጋታቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል። በየመን የኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው መገኘቱ የተገለጸው በሳምንቱ መጨረሻ ነበር።
50163828
https://www.bbc.com/amharic/50163828
ዛሬ ዶዶላ ውስጥ በተቀሰቀሰ ግጭት የአራት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በሌሎች ከተሞችም የተቃውሞ ሠልፉ ቀጥሏል
በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ዛሬ በነበረ ግጭት አራት ሰዎች ሞተው ወደ ዶዶላ አጠቃላይ ሆስፒታል መምጣታቸውን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ቶላ ቢዮ ለቢቢሲ ተናገሩ።
ትናንት በአካባቢው ከጠዋት ጀምሮ ሠልፍ እንደነበር የተናገሩት ሜዲካል ዳይሬክተሩ ከሰዓት በኋላ ግን ይህ ሠልፍ መልኩን መቀየሩን ይናገራሉ። ሜዲካል ዳይሬክተሩ ትናንት ሁለት ሰዎች በጥይት ተመትተው መምጣታቸውንና ሕይወታቸው ማለፉን ገልፀው፤ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸውን ሦስት ሰዎች ደግሞ ምሽቱን ወደ ሻሸመኔና ሀዋሳ ለህክምና መላካቸውን ገልጸዋል። በአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ግለሰብ ለቢቢሲ እንደገለፁት የዛሬው ግጭት ሊቀሰቀስ የቻለው "ከሁለት ወር በፊት አንድ ወጣት መሳሪያ በመተኮሱ ለእርሱ በቀል ነው" ሲሉ ይናገራሉ። • በኦሮሚያ ከተሞች በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች 6 ሰዎች ተገደሉ በወቅቱ ምንም አይነት ጉዳት ባይደርስም ትናንት ሰልፉን ተከትሎ ግን ግጭት ተከስቶ ሰዎች መጎዳታቸውን፣ ቤቶች መቃጠላቸውን፣ ሱቆች መዘረፋቸውን ማየቱን ይናገራል። ዛሬ ማለዳ በአካባቢው ግጭት መቀስቀሱንም አረጋግጠው አራት ሰዎች በዱላ ተመትተው ወደ ሆስፒታል እንደመጡና ሕይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል። በጠቅላላው 6ሰዎች መሞታቸውንና አንዱ ወደ ሐዋሳ ከተላከ በኋላ ሕይወቱ ማለፉን ለቢቢሲ ገልጸዋል። በዶዶላ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ግለሰብ እንደሚናገሩት ግጭቱ የተከሰተው 02 ቀጠና አምስት በመባል በሚታወቀው ስፍራ ሲሆን ስድስት ቤቶች መቃጠላቸውንና ከብቶች መዘረፋቸውን እንዲሁም የንግድ ሱቆች መቃጠላቸውንና መዘረፋቸውን ይናገራሉ። ሰዎች መሞታቸውንና መቁሰላቸውን የሚናገሩት ነዋሪው የዛሬው ግጭት ከጸጥታ ኃይሎች ጋር ሳይሆን እርስ በእርስ የደረሰ መሆኑን ይናገራሉ። • "የተፈጸመው መሆን ያልነበረበት ትልቅ ስህተት ነው" • የድብ መራቢያ አካል የበላው አዳኝ በቁጥጥር ሥር ዋለ በአካባቢው ያለው ችግር ከፖሊስ ቁጥጥር በላይ ነው የሚሉት ግለሰቡ መከላከያ ገብቶ ሁኔታዎችን ማረጋጋቱን ይናገራሉ። ሁኔታው አስፈሪ ስለነበር ለሕይወታቸው የሰጉ ሰዎች በአካባቢው በምትገኘው ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው አንደሚገኙ ተናግረዋል። "እነዚህ ወደ ሆስፒታላችን የመጡ ናቸው" የሚሉት ሜዲካል ዳይሬክተሩ ሌሎች የሞቱ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ የሚል ወሬ ከአካባቢው ማህበረሰብ መስማታቸውን ይገልጻሉ። ዛሬም ተጎድተው ወደ ሆስፒታላቸው ከመጡ መካከል አንድ ግለሰብ ለከፍተኛ ሕክምና ወደ ሀዋሳ መላኩን ዶ/ር ቶላ ገልፀው በአሁኑ ሰዓት ወደ ከተማዋ የመከላከያ ሠራዊት መግባቱን ተናግረዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች የመከላከያ ሠራዊት ወደ በስፍራው መግባቱንና የተፈጠረውን ግጭት ለመቆጣጠርና ህብረተሰቡን እያረጋጋ መሆኑን አረጋግጠውልናል። ዛሬ ሐሙስ እስከ ቀትር ድረስ በድምሩ 50 የሚሆኑ ሰዎች ቀላልና መካከለኛ ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል እንደገቡና በድምሩ የ6 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ታውቋል። ተጎጂዎቹ በብዛት ወጣቶች እንደሆኑና በዱላና በድንጋይ ጉዳት የደረሰባቸው በርካታ መሆናቸውን ሰምተናል። ከተጎጂዎች መሀል የ11 ዓመት አዳጊ ይገኝበታል። ሌሎች የኦሮሚያ ከተሞች እንደምን አረፈዱ? ከትናንትናው የቀጠለ ሠላማዊ ሰልፍ ዛሬ ማለዳም በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች መካሄዳቸውን ቢቢሲ ያነጋገራቸው የተለያዩ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ። ድሬዳዋ፣ አምቦ፣ ሻሸመኔ፣ ቢሾፍቱ፣ ዶዶላን ጨምሮ በሌሎች ከተሞችም የተቃውሞ ሠልፎች የተካሄዱ ሲሆን ወደ አዲስ አበባ የሚወስዱ መንገዶችም መዘጋታቸውን ለማወቅ ችለናል። የተቃውሞ ሠልፍ የተካሄደባቸው ከተሞች ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች መገደባቸውን፣ የንግድ እንቅስቃሴ መስተጓጎሉን ያነጋገርናቸው የከተማዎቹ ነዋሪዎች ገልፀውልናል። በአምቦ ከተማ ዛሬ ቀጥሎ በዋለው የተቃውሞ ሰልፍ ምክንያት ከሰልፈኞች አምስቱ ከጸጥታ አካላት በተተኮሰ ጥይት ተመትተው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ካነጋገርናቸው ነዋሪዎች ሰምተናል። የተቃውሞ ሰልፈኞቹ ከጸጥታ ኃይሎች ጋር የተጋጩ ሲሆን የከተማዋ ደህንነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የከተማዋ ነዋሪ ጨምረው ተናግረዋል። አሁንም የተኩስ ድምጽ ይሰማል ያሉት ግለሰቡ ከትናንት ጀምሮ ሲካሄድ በነበረው ሰልፍ የሟቾች ቁጥር 4 መድረሱን ገልፀውልናል። ሌላ የከተማዋ ነዋሪ በዛሬው ሰልፍ አምስት ሰዎች በጥይት ቆስለው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የተናገሩ ሲሆን ሰልፈኞቹ የተመቱት በከተማ አስተዳደሩና መናሃሪያው መካከል ባለው መንገድ መሆኑን ተናግረዋል። ቢሾፍቱ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የቢሾፍቱ ከተማ ነዋሪዎች በከተማዋ ከትናንትና የቀጠለ ሰልፍ እንደነበር አረጋግጠዋል። ትናንትን የነበረውን የተቃውሞ ሰልፍ ተጻርረው የወጡ ወጣቶች ጋር ግጭት ተፈጥሮ እየበረታ መሄዱን የገለፁት ነዋሪዎች በተጻራሪ ቆሞ የነበረው ቡድን ወደ ቤተ እምነቶች ሄዶ መጠለሉን ለማወቅ ችለናል። በሰልፉ ላይ አንድ ወገንን ነጥሎ የሚቃወሙ መፈክሮች መሰማታቸውን የሚናገሩት የአካባቢው ነዋሪ ስለታማ ነገሮችና የጦር መሳሪያ ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሰልፈኞችንም ማየታቸውን ጨምረው ገልፀዋል። በከተማዋ ዛሬ ማለዳ ከፍተኛ ተኩስ ይሰማ እንደነበር የሚናገሩት ነዋሪዎች ትናንት ከባድ ጉዳት ባይደርስም ዛሬ ያለው ሁኔታ መልኩን ቀይሮ እንዳለና አስጊ እንደሆነ ነግረውናል። በተያያዘ ዜና በአዳማ ዛሬ ማለዳ ሰልፍ እና የጦር መሳሪያ ድምፅ ይሰማ እንደነበር የከተማዋ ነዋሪዎች ነግረውናል። ከጃዋር መሐመድ ጥበቃዎች መነሳት ጋር በተያያዘ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ትናንት በተለያዩ ቦታዎች ላይ የተካሄዱ ሰልፎችን ተከትሎ የስድስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን መዘገባችን ይታወሳል።
49862600
https://www.bbc.com/amharic/49862600
የደመራ አከባበር ከኢትዮጵያ እስከ ኬንያ
የመስቀል ደመራ በዓል እንዴት ተከበረ? ዘጋቢዎቻችን ከኢትዮጵያ፤ በአዲስ አበባ፣ በአዲግራት እና በባህር ዳር ያለውን ድባብ በፎቶ አስቃኝተውናል። በኬንያ መዲና ናይሮቢም በዓሉ በምን መንገድ እንደተከበረ በፎቶግራፍ ሰንደናል።
• በመስቀል ደመራ በዓል አከባበር 55 ሰዎች መታሰራቸውን የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት አስታወቀ • መስቀል በቤተ-ጉራጌ • ሁሌም አብሮን ያለው 'የመስቀል ወፍ' መስቀል በባህር ዳር በባህር ዳር ከተማ የመስቀል ደመራ በዓልን ለማክበር አደባባይ ከወጡ የሐይማኖት አባቶች መካከል አንዱ በባህር ዳር ከተማ የመስቀል በዓል አከባበር ላይ በገና የሚደረድሩ ታዳጊዎች ነበሩ በባህር ዳር ከተማ ሕዝበ ምዕመን የመስቀል ደመራ በዓልን ሲታደም የባህር ዳር ከተማ የመስቀል በዓል ላይ የተገኙ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች በባህር ዳር ከተማ ሕዝበ ምዕመን የመስቀል ደመራ በዓልን ሲታደም መስቀል በአዲስ አበባ አዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ የደመራ በዓል ሲከበር በመስቀል አደባባይ በዓሉን ለማክበር ከተገኙት መካከል በተሸለመ ፈረስ ላይ የተቀመጡት ይገኙበታል በመስቀል አደባባይ ስለ በዓሉ ሀይማኖታዊ ዳራ የሚያሳይ ትዕይንት ቀርቧል መስቀል በአዲግራት የመስቀል ደመራ በዓል በአዲግራት ከተማ ሲከበር የአዲግራት ከተማ የመስቀል ደመራ አከባበር በጠጅ የታጀበ ነበር የመስቀል ደመራ በዓል በአዲግራት ከተማ ሲከበር በአዲግራት ከተማ የኩናማ ብሔረሰብ ተወላጆች ባህላዊ ውዝዋዜ አቅርበዋል መስቀል በናይሮቢ በናይሮቢ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የመስቀል ደመራ በዓል ሲከበር በናይሮቢ የመስቀል ደመራ በዓል ሲከበር መዘምራን ወረብ አቅርበዋል በናይሮቢ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የመስቀል ደመራ በዓል ሲከበር በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር መለስ ዓለም ለበዓሉ ታዳሚዎች ንግግር አድርገዋል ነዋሪነታቸውን በናይሮቢ ያደረጉ ታዳጊዎች በበዓሉ ላይ ተገኝተዋል በናይሮቢ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የመስቀል ደመራ በዓል በድምቀት ተከብሯል
news-51187796
https://www.bbc.com/amharic/news-51187796
የትራምፕን የክስ ሂደት በቀላሉ እንዲገነዘቡ የሚረዱ 5 ወሳኝ ጥያቄዎች
በአሜሪካ ታሪክ ሶስተኛው ፕሬዝደንት ከስልጣናቸው እንዲነሱ የክስ ሂደት ተጀምሮባቸዋል።
(ከግራ ወደ ቀኝ) በሴኔቱ የዲሞክራቶች መሪ ቸክ ሹመር፣ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እና በሴኔቱ የሪፓብሊካን መሪ ሚች ማክኮኔል። ይህ የክስ ሂደት ፕሬዝደንት ትራምፕን ከስልጣናቸው ከማስወገዱም በተጨማሪ ዘብጥያ እስከመውረድ ሊያደርሳቸው ይችላል። የትራምፕ ከስልጣን መነሳት (ኢምፒችመት) ችሎት ሂደትን በቀላል እንዲገነዘቡ 5 ወሳኝ ጥያቄዎች ተመልሰዋል። 1) 'ኢምፒችመንት' ምንድነው? 'ክስ' የሚለው ቃል ሊተካው ይችላል። በቀላሉ ስልጣን ላይ የሚገኙ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ወንጀል ፈጽመው ከሆነ ተጠያቂ የሚደረጉበት የሕግ ስርዓት ወይም አካሄድ ማለት ነው። • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ለዶናልድ ትራምፕ ቅሬታ ምላሽ ሰጡ • እውን ሶስተኛው የዓለም ጦርነት ተቀስቅሶ እናየው ይሆን? እነሆ ምላሹ በዚህ ሂደት ፕሬዝደንት ትራምፕ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት "ኢምፒች" መደረጋቸው ይታወሳል። ይህ ማለት የትራምፕ ጉዳይ ከተወካዮች ምክር ቤት ወደ ሴኔቱ ተላልፏል ማለት ነው። ትራምፕ በቀረበባቸው ክስ መሠረት ጥፋተኛ ናቸው ወይስ አይደሉም ለሚለው ውሳኔ የሚሰጠው ሴኔቱ ይሆናል። 2) ትራምፕ የቀረበባቸው ክስ ምንድነው? ትራምፕ በሁለት አንቀጾች ክስ ቀርቦባቸዋል፤ ወይም 'ኢምፒች' ተደርገዋል። የመጀመሪያው 'ፕሬዝዳንቱ ስልጣናቸውን ያለአግባብ ተጠቅመዋል' የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ 'የምክር ቤቱን ስራ አደናቅፈዋል' የሚል ነው። ፕሬዝዳንት ትራምፕ በ2020 ምርጫ የመመረጥ እድላቸውን ለማስፋት በተቀናቃኛቸው ጆ ባይደን ላይ ምረመራ እንዲካሄድ የዩክሬን ፕሬዝደንት ላይ ጫና አድርገዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል። ጆ ባይደን የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝደንት ሳሉ ወንድ ልጃቸው በዩክሬን የንግድ ሥራ ላይ ተሰማርቶ ነበር። ታዲያ ትራምፕ፤ ተቀናቃኛቸውን ሊያሳጣ የሚችል መረጃ ለማግኘት የዩክሬን ፕሬዝደንት ላይ ጫና በማሳደር ሥልጣንን ያለ አግባብ መጠቀም የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል። ሁለተኛው ደግሞ ትራምፕ ለሚደረግባቸው ምርመራ መረጃዎችን ለመስጠት ተባባሪ ባለመሆናቸው የምክር ቤቱን ስራ በማደናቀፍ በሚለው ክስ ላይ ድምጽ ሰጥተዋል። ፕሬዝደንት ትራምፕ ግን የቀረቡባቸውን ክሰቦች ሙሉ በሙሉ ውድቅ ያደርጋሉ። 3) ከሴኔቱ ምን ይጠበቃል? በሴኔቱ የችሎቱን ወይም የክሱን አካሄድ የሚወስኑ ሁለት ቁልፍ የሴኔቱ አባላት አሉ። በሴኔቱ የሪፓብሊካን መሪ የሆኑት ሚች ማክኮኔል እና የዲሞክራት መሪው ቸክ ሹመር ናቸው። ሁለቱ መሪዎች ማስረጃዎች ለሴኔቱ በምን አይነት መልኩ ይቀርባሉ? የምስክሮች እማኘነትስ እንዴት ይስማሉ በሚሉ ጉዳዮች ላይ ቀድመው መስማማት አለባቸው። ትራምፕ ጥፋተኛ ናቸው ለማለት እና ከስልጣን ለማስነሳት የሴኔቱ 2/3 ድምጽ ያስፈልጋል። ይህ ማለት ከ100 የሴኔት መቀመጫ 67ቱ ትራምፕ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ማስተላለፍ ይኖርባቸዋል። የትራምፕ አጋር የሆኑት ሪፓብሊካኖች በሴኔቱ አብላጫ የሆነ 53 መቀመጫ አላቸው። የትራምፕ ተቀናቃኝ የሆኑት ዲሞክራቶች በሴኔቱ ያላቸው መቀመጫ 47 ብቻ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ትራምፕ ላይ የተነሳው ክስ ውድቅ ሊሆን እንደሚችል በርካቶች ገምተዋል። ከተገመተው ውጪ ሆኖ ትራምፕ ጥፋተኛ ሆነው ቢገኙ፤ ከስልጣን ይባረራሉ፤ ከዚያም ምክትል ፕሬዝደንት ማይክ ፔንስ መንበረ ስልጣኑን ይረከባሉ። በዚህ ብቻ ሳይወሰን፤ የትራምፕ ጉዳይ በወንጀል ሕግ ታይቶ ከስልጣን በኋላ ዘብጥያ ሊወርዱም ይችላሉ። 4) ትራምፕ በሴኔቱ ፊት ቀርበው መከላከያቸውን ያቀርቡ ይሆን? ፕሬዝደንት ትራምፕ ከሴኔቱ ፊት ቀርበው መከላከያዎቻቸውን ማቀረብ ይችላሉ። ይሁን እንጂ ጠበቆቻቸው እንጂ እሳቸው ከሴኔት ፊት ይቀርባሉ ተብሎ አይገመትም። • ዶናልድ ትራምፕን ከዝነኛው ፊልም ማን ቆርጦ ጣላቸው? • ዶናልድ ትራምፕ በመከሰስ ሶስተኛ የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆኑ ትራምፕ ምክትል ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በሴኔቱ ፊት ቀርበው እንዲመሰክሩላቸው አጥብቀው ይሻሉ። ዲሞክራቶች በበኩላቸው፤ የቀድሞ የብሔራዊ ደህንነት ኃላፊ ጆህን ቦልተን ጨምሮ ከፍተኛ የዋይት ሃውስ ባለስልጣናት ቃላቸውን እንዲሰጡ ይፈልጋሉ። 5) የዚህ ጉዳይ ማብቂያ መቼ ይሆን? ማንም በእርግጠኝነት መናገር ባይችልም የክስ ሂደቱ ለሳምንታት ሊዘልቅ ይችላል። የቢን ክሊንተን የክስ ሂደት አራት ሳምንታት ወስዷል። ዲሞክራቶች በተቻለ መጠን የክስ ሂደቱ እንዲጠናቀቅ ይፈልጋሉ። ምክንያቱም በ2020 ምርጫ ዲሞክራቶችን ወክሎ የሚወዳደረውን እጩ መምረጥ ይፈልጋሉና።
news-55693945
https://www.bbc.com/amharic/news-55693945
ኬ2 ተራራ፡ ኔፓላዊያን የዓለማችን ሁለተኛውን ትልቅ ተራራ በመውጣት አዲስ ክብረወሰን አስመዘገቡ
አስር አባላት ያሉት የኔፓል ተራራ ወጪዎች የዓለማችን ሁለተኛውን ትልቅ ተራራ ወጥቶ በማጠናቀቅ የመጀመሪያ በመሆን አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስመዘገቡ።
በርካታ ተራራ ወጪዎች 8ሺህ 611 ሜትር ከፍታ ያለውን ኬ2 ተራራ ወጥቶ ለማጠናቀቅ ተስፋ ሰንቀው ነበር የተነሱት። ይሁን እንጂ አንድ ስፔናዊ ተራራ ወጪ ተራራውን በመውረድ ላይ ሳለ በመውደቁ ሕይወቱ አልፏል። ከዓለማችን ትልቁ ተራራ ኤቨረስት በ200 ሜትር ብቻ የሚያንሰው ኬ2 ተራራ፤ በፓኪስታንና ቻይና ድንበር የሚያልፈው ካራኮራም ተራራ አካል ነው። ኬ2 ከ8 ሺህ ሜትር በላይ ከፍታ ካላቸው 14 ረዥም ተራራዎች አንዱ ነው። በክረምት ወራት ከሁሉም ተራራዎች ተመራጭ እንደሆነም ይታሰባል። ኬ2 ለረዥም ጊዜ 'አረመኔው ተራራ' በሚል መጠሪያ ይታወቃል። ይህን ስያሜ ያገኘው አሜሪካዊው ተራራ ወጪ ጆርጅ ቤል እአአ በ1953 ተራራውን ለመውጣት ጥረት በሚያደርግበት ጊዜ ከተናገረው የተወሰደ ነው። ጆርጅ "አንተን መግደል የሚፈልግ አረመኔ ተራራ ነው" ሲል ነበር በወቅቱ የተናገረው። በ2008 አስራ አንድ ተራራ ወጪዎች በዚሁ ተራራ ሕይወታቸውን አጥተዋል። ኔፓላዊያን ተራራ ወጪዎች 60 ሰዎችን ከያዘው ከሦስት ወይም ከአራት ተወዳዳሪ ቡድን ጋር ተበታትነው ነበር ተራራውን መውጣት የጀመሩት። በኋላ ላይ ግን አስሩ ኔፓላዊያን ታሪካዊውን ድል በኔፓል ስም ለማስመዝገብ በማለም አንድ ቡድን በመመስረት ተራራውን ወጥተው ማጠናቀቅ ችለዋል። ተራራ ወጪው ኒርማል ፑርጃ ያስመዘገቡትን ድል አስመልክቶ " የታሪኩ አካል በመሆናችን ኮርተናል፤ ትብብር፣ የቡድን ሥራ እና ቀና አመለካካት የማይቻል የሚመስልን ነገር ለመቻል እንደሚረዱ ለማሳየት ችለናል። " ብሏል። ይህን ተራራ ለመውጣት እአአ1987 እስከ 1988 በክረምት ወራት በቡድን በመሆን በርካታ ሙከራዎች የተደረጉ ሲሆን፤ እስካሁን ግን ከ7ሺህ 650 ከፍታ በላይ መውጣት የቻለ የለም።
news-41924877
https://www.bbc.com/amharic/news-41924877
ከስልጣን የተባረሩት የዚምባብዌ ምክትል ፕሬዝዳንት ምናንጋግዋ ሃገር ጥለው ተሰደዱ
ባሳለፍነው ሰኞ ከሥልጣን የተባረሩት የዚምባብዌ ምክትል ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ለሕይወታቸው ሰግተው ከሃገር መሸሻቸውን አጋሮቻቸው ተናገሩ።
የ93 ዓመቱ ፕሬዝደንት ሙጋቤ የቀድሞ ምክትላቸው ሥልጣኔን ለመውሰድ ሲያሴሩ ነበር ብለዋል። ረቡዕ ዕለት ሙጋቤ ለደጋፊዎቻቸው ንግግር ሲያደርጉ ''ምናንጋግዋ ወደ ቤተክርሰቲያን ሄዶ እኔ መቼ እንደምሞት ነብዩን ጠየቀ ንብዩም እኔ ሳልሆን እሱ ቀድሞ እንደሚሞት ነገርውታል'' ብለዋል። የሙጋቤ በባለቤት ቀዳማዊ እመቤት ግሬስ ሙጋቤ ምናንጋግዋን ሊተኩ እንደሚችሉ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷቸዋል። ''እባቡ በሃይል ጭንቅላቱን መመታት አለበት'' በማለት ከዚህ በፊት ግሬስ ሙጋቤ ምክትል ፕሬዝዳንቱን ከስልጣናቸው እንዲያነሱ ሮበርት ሙጋቤን ሲወተውቱ እንደነበርም ተወስቷል። በቀጣይ ወር ገዥው 'ዛኑ' ፓርቲ በሚያደርገው ስብሰባ ላይ የሙጋቤ ባለቤት ግሬስ ሙጋቤ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ይሾማሉ ተብሎም ይጠበቃል። ትናንት ዛኑ ፓርቲ የቀድሞ የደህንነት ሹሙንና ምክትል ርዕሰ-ብሔር ኤመርሰን ምናንጋግዋን ከፓርቲ አባልነት ሰርዟል። ''ምናንጋግዋን ለረዥም ጊዜ ድብቅ ማንነቱን እናውቅ ነበር። ለኔ ቅርብ በመሆኑ ብቻ በጀርባዬ አዝዬው ወደ ፕሬዝደንት ወንበር የምወስደው መስሎት ነበር። እኔ ግን አልሞትኩም፤ ከስልጣንም አልወረድኩም'' ሲሉ ሙጋቤ በሃራሬ ለተሰበሰቡ ደጋፊዎቻቸው ንግግር አድርገዋል። ሃገር ጥለው የተሰደዱት የቀድሞ ፕሬዝዳንት "ወደ ሃገሬ ተመልሼ ሙጋቤን እና ባለቤታቸውን ፓርቲውን በመቆጣጠራቸው እና ለግል ጥቅማቸው በማዋላቸው ለፍርድ አቀርባቸዋለሁ" ብለዋል። ጨምረውም የዛኑ ፓርቲ ባለስልጣናትን ፓርቲው እንዲጠለፍ እና ''የግል ንብረት'' እንዲሆን ተባብረዋል በማለት ኮንነዋል።
news-53542694
https://www.bbc.com/amharic/news-53542694
ጥቁሮች 'ባሪያ' እየተባሉ የሚጠሩባት አፍሪካዊት አገር
ጋዜጠኛ ዘይነብ ሞሐመድ ሳሊህ በአገሯ ጥቁሮች ስለሚደርስባቸው መድልዎ ይህን ፅፋለች።
ሪም ኮግሊን እና ኢሳም አብዱልራሂም ለመገባት ሲወስኑ በቆዳ ቀለማቸውን ልዩነት ምክንያት ትችት ገጥሟቸዋል [ማሳሰቢያ፡ ይህ ፅሑፍ አንዳንድ ፀያፍ ቃላት የይዟል] ከጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ ግድያ በኋላ ዘረኝነትን የሚቃወሙ ሰልፎች ዩናይትድ ስቴትስንና የተቀረውን ዓለም በናጡበት በአሁኑ ወቅት አገሬ ሱዳን ሌላ ዓለም ውስጥ ናት። የጥቁሮች ሕይወት ዋጋ አላት ወይም #BlackLivesMatter የተሰኘው የማኅበራዊ ድር-አምባ የንቅናቄ ጥሪ በሱዳን እምብዛም ቦታ አልነበረውም። በምትኩ ሰዎች ታዋቂው ሱዳናዊ እግር ኳሰኛ ኢሳም አብዱልራሂም ቀላ ያለች አረብ የሜክ-አፕ ባለሙያ የሆነችው ሪም ኮግሊን ሊያገባ መሆኑን ተከትሎ እየዘለፉት ይገኛሉ። "የምርሽን ነው? ንግሥት ባሪያዋን ስታገባ. . . ይህ ሃራም [ሃጥያት] ነው።" ይላል አንድ ግለሰብ ፌስቡክ ላይ የፃፈው አስተያየት። መሰል አስተያየቶች በርካታ ናቸው። ነገር ግን አብዛኛዎቹ ዜጎች ራሳቸውን አረብ እንጂ አፍሪካዊ አይደለንም ብለው በሚያስቡባት ሱዳን ይህ ብዙም አስደናቂ አይደለም። ሱዳን ሁሌም ነጣ ያለ የቆዳ ቀለም ባላቸውና አረብኛ በሚናገሩ ኃያላን ነው ስትገዛ የቆየችው። በደቡባዊና ምዕራባዊ ግዛት የሚገኙ ጥቁር ሱዳናዊያን ደግሞ መገለለና አድልዎ ሲደርስባቸው ከርሟል። ጋዜጦች ጭምር ጥቁሮችን ለመግለፅ 'ባሪያ' እንዲሁም ሌሎች አስፀያፊ ቃላት ሲጠቀሙ ይስተዋላል። ከጥቂት ቀናት በፊት አንድ እስላማዊ አምደኛ፤ የቀድሞው ፕሬዝደንት ኦማር አል-ባሽር ደጋፊ እንደሆነ በሚታመነው በዕለታዊው አል-ኢንታባሃ ጋዜጣ ላይ 'ጋነርስ' የተሰኘ የታዳጊ ሴቶች እግር ኳስ ቡድን አሠልጣኝን ባሪያ ሲል ገልጿታል። አነስ ያሉ ጸረ ዘረኝነት ተቃውሞዎች ተካሂደው ነበር በመዲናዋ ካርቱም ያሉ ሁሉም መገናኛ ብዙሃን ማለት ይቻላል የስርቆት ወንጀል ላይ የተሰማሩ ሰዎችን የአረብ ዘር ስለሌባቸው 'ኒግሮ' ሲሉ ይጠሯቸዋል። አብዱልራሂም እየደረሰበት ስላለው ጥቃት እንዲነግረኝ ስጠይቀው "የበለጠ ጥቃት እንዳይደርስብኝ በመፍራቴ ማኅበራዊ ገፆቼ ላይ ምንም ዓይነት ነገር መለጠፍ አስፈርቶኛል" ሲል ነግሮኛል። ነገር ግን የ29 ዓመቱና የ24 ዓመቷ ባልና ሚስት የጫጉላ ሽርሽራቸውን በፌሰቡክ ቀጥታ ሲያስተላልፉ ነበር። 'ፍቅር ውስጥ ነው ያለነው፤ የቆዳ ቀለማችን እዚህ ቦታ የለውም' ሲሉም ተደምጠዋል። በሌላ አጋጣሚ ደግሞ ለሴቶች መብት የሚከራከር ቡድን ኃላፊ የሆነች ሴት አንድ ወጣት ጥቁር ከነጭ አውሮፓዊት ሚስቱ ጋር ሆኖ የተነሳው ፎቶ ላይ 'ምናልባት ሚስት በዝንጀሮና በሰው መካከል ያለውን ፍጥረት እያፈላለገች ይሆናል' ስትል ፅፋለች። ከዚህ በኋላ ግን የደረሰባትን ወቀሳ ተከትሎ ኢህሳን ፋጊሪ ከኃላፊነቷ ራሷን ለማግለል ብትወስንም ድርጅቱ ግን አስባ ያደረግችው አይደለም በሚል አልቀበለውም ብሏል። ዘረኝነት ሱዳን ውስጥ በረቀቀ መንገድ ነው የሚቀርበው። አገሪቱ ነፃነቷን ካገኘች ጀምሮ ከፍተኛ ሥልጣን ላይ የሚገኙ ሰዎች ጠቅላላ ከሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የመጡ ናቸው - ከአረብ እና ከኑቢያ ጎሳዎች። ሁሉም የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች ማለት ይቻላል ከእነዚህ ጎሳዎች የመጡ ናቸው። ካርቱም ውስጥ ወደ አንድ ባንክ ወይም የመንግሥት መሥሪያ ቤት ብትገቡ በጣም ጥቁር ሰዎች ነው የምትመለከቱት። የሱዳን ባለሥልጣናት ያላቸው ሃብት ተዘርዝሮ ሊቀመጥ ይቅርና የሱዳን ሕዝብ በጎሳ ሲከፋፈል የሚኖረው ድርሻ በውል አልተቀመጠም። ነገር ግን ለጥቁሮች መብት የሚከራከርና መቀመጫውን ዳርፉር ያደረገ አንድ ቡድን ካርቱም ውስጥ 60 በመቶ የሚሆኑት ጥቁሮች ናቸው ይላል። ቀደም ባለው ዘመን ሱዳን ዋነኛ የባሪያ ንግድ ማዕከል ነበረች ሱዳን ውስጥ ያለው ዘረኝነት በአውሮፓውያኑ 1821 ካርቱም የባሪያ መነገጃ እንደሆን ከመወሰኑ ይጀምራል። ሱዳን ለዘመናት የባሪያ ንግድ መናኸሪያ ነበረች። በባርነት ንግድ ላይ የተሰማሩ ሰዎችም እስካዛሬ ድረስ ስማቸው በበጎ ይነሳል። መዲናዋ ካርቱም መሃል የሚገኝ አንድ መንገድ ዘል-ዙቢር ፓሻ ራህማ ይሰኛል። ሰውዬው ከሱዳን አንስቶ እስከ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክና ቻድ ድረስ የባሪያ ንግድን ያስፋፋ ነው። የታሪካ አጥኚዎች ግለሰቡ በተለይ ሴቶችን ከጥቁር አባይና ኑባ ተራሮች እንዲሁም ከኢትዮጵያ፤ ኦሮሚያ ክልል እየወሰደ ይነግድ እንደነበር ይናገራሉ። እሱ ብቻ ሳይሆን ሌሎች በባርነት ንግድ ስም ያተረፉ ሰዎች ዛሬም ይንቆለጳጰሳሉ። የባርያ ንግድ እስከ 2005 9 (እአአ) የሱዳን እርስ በርስ ጦርነት ድረስ እንደዘለቀ ይነገራል። ይህ የእርስ በርስ ጦርነት ጥቁር አፍሪካዊ ሱዳናውያን ከአረብኛ ተናጋሪ ሱዳናውያን ጋር እንዲለያዩ ምክንያት ሆኗል። አሁንም ቢሆንም ጥቁሮች በሚኖሩበት የሱዳን ክፍል በደልና ግፍ እንደሚፈፀም በስፋት ይደመጣል። ከአል-ባሽር መውደቅ በኋላ ሥልጣን የያዘው ወታደራዊውና ሲቪል ጥምር መንግሥት ሱዳን ውስጥ ያለውን ሥር የሰደደ ዘረኝነት መታገል ስለመቻሉ ማስረገጫ የለም። የአዲሱ መንግሥት አካል የሆነው ሱዳኒዝ ኮንግረስ ፓርቲ የጥላቻ ንግግርን የሚቀጣ ሕግ እያረቀቅኩ ነው ብሏል። ሕጉ ከፀደቀ ዘረኛ ቃላትን የሚጠቀሙ እስከ አምስት ዓመት እሥር ይጠብቃቸዋል። የመንግሥት ሥልጣን ላይ ያሉ ጥቂት ጥቁር ሱዳንውያን ግን ሁኔታዎች እጅግ ከባድ ናቸው ይላሉ።
news-51838457
https://www.bbc.com/amharic/news-51838457
ሳዑዲ አረቢያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ አገራት ላይ የጉዞ ዕገዳ ጣለች
በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሳዑዲ አረቢያ በተወሰኑ አገራት ላይ ጥላው የነበረውን የበረራና የጉዞ ዕገዳ በማስፋት ኢትዮጵያን ጨምሮ 12 አገራትንና የአውሮፓ ኅብረትን ማካተቱ የአገሪቱ የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን አሳወቁ።
አዲሱ የሳዑዲ ዕገዳ ከአውሮፓ ኅብረት አገራት በተጨማሪ ኢትዮጵያን፣ ኤርትራን፣ ደቡብ ሱዳንን፣ ሱዳንን፣ ኬንያን፣ ጂቡቲን፣ሶማሊያን፣ ስዊትዘርላንድን፣ ህንድን፣ ፓኪስታንን፣ ሲሪላንካንና ፊሊፒንስን የሚያካትት ነው። በሚሊዮኖች ከሚቆጠሩ በሳውዲ የሚገኙ ስደተኛ ሠራተኞች መካከል አብዛኞቹ እገዳው ከተጣለባቸውና ከተጠቀሱት አገራት የሄዱ እንደሆኑ ሮይተርስ በዘገባው አመልክቷል። የእገዳ ውሳኔው ከፊሊፒንስና ከህንድ የመጡ የጤና ባለሙያዎችን የማይመለከት ሲሆን በተጨማሪም አስፈላጊው ቅድመ ጥንቃቄ የተደረገባቸው ዜጎችን ለማስወጣት የሚደረጉ በረራዎች፣ የመርከብ ጉዞዎችና የንግድ በረራዎች ዕገዳው አይመለከታቸውም ተብሏል። • ሳዑዲ አረቢያ ወደ አገሯ የሚደረጉ ሐይማኖታዊ ጉዞዎችን አገደች • ኮሮናቫይረስ ሰዎችን ከእምነታቸው እየለየ ይሆን? • አረብ አገር የለፋችበትን 'በፍቅረኛዋ' ተጭበርብራ ባዶዋን የቀረችው ሻሼ ይህ ተጨማሪ ዕገዳ ይፋ እንዲሆን ምክንያት የሆነው ተጨማሪ አገራት በበሽታው የተያዙ ሰዎችን ማግኘታቸውን ካሳወቁ በኋላ ሲሆን የጉዞ እና የበረራና ዕገዳው የተጣለባቸውን አገራት 45 እንዳደረሰው ሮይተርስ ዘግቧል። የሳዑዲ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠቅሶ የወጣ መረጃ እንደሚያመለክተው በሽታው በተገኘባቸው አገራት ውስጥ የሚኖሩ የሳዑዲ ዜጎች በ72 ሠዓታት ውስጥ ወደ አገራቸው መመለስ እንደሚችሉም ተገልጿል። ሳዑዲ አረቢያ ጎረቤቶቿን አረብ አገራትን ጨምሮ ቀደም ሲል በ19 አገራት ላይ የጉዞ ዕገዳን ጥላ የነበረ ሲሆን፤ ወደ አገሪቱ በሚያስገቡ በሮች ላይ የጤና መረጃቸውንና የጉዞ ዝርዝራቸውን ለመግለጽ የማይፈልጉ ሰዎች 133 ሺህ ዶላር እንደሚቀጡም ተገልጿል። ሳዑዲ በሽታውን ለመከላከል አብዛኛው በበሽታው የተያዙ ሰዎች የተገኙበትና የነዳጅ ዘይት አምራች ከሆነው ቃጢፍ ከተባለው ክልል መግባትም ሆነ መውጣት ከልክላለች። በተጨማሪም ሳዑዲ ሐይማኖታዊ ጉዞን ያገደች ሲሆን በመላዋ አገሪቱ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችና ሲኒማ ቤቶች እንዲዘጉ አድርጋለች። እንዲሁም የተለያዩ ጉባኤዎችና ስፖርታዊ ውድድሮች የተሰረዙ ሲሆን በሚቀጥለው ሳምንት ይካሄዳል ተብሎ የነበረው የቡድን 20 የሚኒስትሮች ስብሰባም ለሌላ ጊዜ ተላልፏል።
news-53441804
https://www.bbc.com/amharic/news-53441804
ግብጽ በሊቢያ ውስጥ የምታደርገውን ጣልቃ ገብነት ቱርክ ተቃወመች
የቱርኩ ፕሬዝደንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን ሊቢያ ውስጥ እተካሄደ ባለው ግጭት የግብጽን ጣልቃ አጥብቀው ኮነኑ።
ኤርዶዋን ካይሮ በሊቢያ ግጭት ውስጥ ጀነራል ካሊፍ ሃፍታርን መደገፏ ሕገ-ወጥ ተግባር ነው ሲሉ ወንጅለዋል። በአሁኑ ወቅት ሊቢያ ውስት በሚካሄደው ግጭት ሁለት ዋነኛ ተቀናቃኝ ኃይሎች የሚገኙ ሲሆን አንደኛው በተባበሩት መንግሥታት እውቅና የተሰጠውና መቀመጫውን በትሪፖሊ ያደረገው በጠቅላይ ሚንስትር ፋዬዝ አል-ሴራጅ የሚመራው መንግሥት ነው ። ሌላኛው ደግሞ መቀመጫውን በምሥራቅ ሊቢያ ቶብሩክ እና ቤንጋዚ ከተሞች ያደረገውን በጀነራል ካሊፍ ሃፍታር የሚመራው አማጺ ኃይል ነው። ጀነራል ሃፍታር "እስላማዊ አሸባሪዎችን" እዋጋለሁ ማለታቸውን ተከትሎ ግብጽ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች እና ዮርዳኖስ ጽንፈኞች ከቀጠናው መጽዳት አለባቸው በማለት አጋርነታቸውን ከጀነራሉ ጋር አድርገዋል። ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት በሩሲያ መንግሥት ተከፋይ የሆኑ የሌሎች አገራት ቅጥረኛ ወታደሮች ከጀነራሉ ጎን ሆነው ይዋጉ ነበር። የክሬምሊን መንግሥት ግን ቀጥተኛ ተሳትፎ የለኝም ይሏል። በሌላኛው በኩል ደግሞ ቱርክ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እውቅና የያለውን መንግሥት ትደግፋለች። ኤርዶዋን በሊቢያ በእጅ አዙር ጦርነት በተፋፋመው የእርስ በእስር ጦርነት 'ጨዋታ' ቀያሪ ናቸው ይባላሉ። ለዚህም ምክንያት ኤርዱዋን ጦራቸውን ወደ ትሪፖሊ ካዘመቱ በኋላ በተመድ እውቅና ያለው መንግሥት በትሪፖሊ አቅራቢያ በነበሩ የጀነራሉ ጦር አባላት ላይ ድልን መቀናጀቱ ነው። ከመካከለኛው ምሥራቅ ፖለቲካ ውሰጥ ተገልላ የምትገኘው ኳታር፤ በሊቢያ ጉዳይ ከተባበሩት መንግሥታት እና ከቱርክ ጎን ተሰልፋለች። ጦራችን በሊቢያ ያለውን ሁኔታ መቀየር ይችላል የግብጹ ፕሬዝደንት አብዱል ፈታህ አል-ሲሰ ትናንት የአገራቸው ጦር በሊቢያ ያለውን ሁኔታ በፍጥነት እና በማያወላውል ሁኔታ የመቀየር አቅም እንዳለው መናገራቸው ተዘግቧል። ኤርዶዋን ግብጽ በሊቢያ ያላትን ተሳትፎ የኮነኑት የካይሮ መንግሥት ጦሩን ወደ ሊቢያ ላዘምት እችላለሁ የሚል ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ተከትሎ ነው። የቱርኩ ቴሌቪዝን በበኩሉ ኤርዶዋን "በግብጽ የተወሰዱት እርምጃዎች በተለይ ደግሞ መፈንቅለ መንግሥት ለማካሄድ ከሞከረው ሃፍታር ጋር መወገናቸው ሕገ-ወጥ መሆናቸውን ያሳያል" ማለታቸውን ዘግቧል።
news-44948941
https://www.bbc.com/amharic/news-44948941
በወልዲያ እና ፍኖተ ሰላም ማረሚያ ቤቶች በተነሳ እሳት በንብረትና ሰው ላይ ጉዳት ደረሰ
በምዕራብ ጎጃም ፍኖተ-ሰላም እና በሰሜን ወሎ ወልዲያ ከተሞች ውስጥ በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች ውስጥ የተቀሰቀሰን ግርግር ተከትሎ ባጋጠመ የእሳት ቃጠሎ በንብረት ላይ ውድመት መድረሱን የማረሚያ ቤቶቹ ኅላፊዎች ለቢቢሲ ተናገሩ።
በፍኖተ-ሰላም ከተማ ውስጥ የሚገኘው ማረሚያ ቤት ዛሬ ጠዋት 2 ሰዓት ላይ በወንዶች ማረሚያ ቤት ቆጠራ ሊካሄድ ሲል በታራሚዎች መካከል አምቧጓሮ መነሳቱን የሚናገሩት የማረሚያ ቤቱ ህዝብ ግንኙነት ረዳት ሳጅን ግርማ ሙሉጌታ ምክንያታቸው የአቃቢ ህጉ በቴሌቪዥን ቀርበው የሰጡት መግለጫ እንደሆነ ይናገራሉ። • በደብረ ማርቆስ ማረሚያ ቤት እሳት ተነሳ • በኬንያ በርካታ ትምህርት ቤቶች በተማሪዎች ተቃጠሉ ታራሚው ለምን አንፈታም በሚል ተቃውሞ ማሰማቱን የሚናገሩት ረዳት ሳጅን ግርማ አንቆጠርም በማለት ማስቸገራቸውን ገልፀዋል። የፖሊስ አባላት የታራሚውን ማመፅ ሲያዩ ወጥተው ጥበቃ ማጠናከራቸውን ወዲያውም በማረሚያ ቤቱ የሚገኘው የሸማ ማምረቻ ክፍል በእሳት እንደተያያዘ ያስረዳሉ። ጨምረውም 26 የታራሚዎች ማደሪያ ክፍሎች ሙሉ በሙሉ በእሳት መውደማቸውን፤ በእሳቱ የታራሚዎች አያያዝና የሬጅስትራር ቢሮም መቃጠሉንም ተናግረዋል። በቢሮው ውስጥ የነበሩት ኮምፒውተሮችን ማውጣት በመቻላቻው ከውድመት እንደተረፉ ገልፀዋል። በተመሳሳይ ዜና በወልዲያ ማረሚያ ቤት ዛሬ ጠዋት 2 ሰዓት ላይ እሳት መነሳቱንና ሙሉ በሙሉ የወንዶች ማደሪያ እንዲሁም የስልጠና ማዕከሉ መሳሪያዎችና ማዕከሉ መውደሙን የማረሚያ ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ኮማንደር እንዳለ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ተቃውሞው የጀመረው ሰሞኑን ስኳር ባለመኖሩ ሻይ ስላልነበራቸው ሻይ ይግባልን በማለት እንደሆነ ያስረዱት ኮማንደሩ አስከትለውም ታራሚዎቹ ድንጋይ ውርወራ መጀመራቸውን ገልፀዋል። • በደብረማርቆስ 'ባለስልጣኑ አርፈውበታል' የተባለው ሆቴል ጥቃት ደረሰበት • ቀኝ እጇን ለገበሬዎች የሰጠችው ኢትዮጵያዊቷ ሳይንቲስት እስካሁን ድረስ ሁለት ታራሚዎች መቁሰላቸውንም ጨምረው ነግረውናል። በትናንትናው ዕለት በደብረማርቆስ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ መድረሱም የሚታወስ ሲሆን አዲስ አበባ ቃሊቲና አርባ ምንጭ ውስጥ በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች ውስጥ ታራሚዎች ተመሳሳይ የእንፈታ ጥያቄ በማቅረብ አለመረጋጋት እንደነበር ተገልጿል።
news-49341423
https://www.bbc.com/amharic/news-49341423
ጃፓኖች ከሰውና ከእንስሳት የተዳቀሉ የሰው አካላትን ለመፍጠር ሙከራ ላይ ናቸው
የሰው ልጅ ለዘመናት ሰውንና እንስሳትን በማዳቀል አዲስ ፍጥረት የመፍጠር እሳቤዎች ነበሩት፤ ከነዚህም ውስጥ አንዱ በጥንታዊዋ ግሪክ ሰውና እንስሳትን በማዳቀል ለሚፈጠሩ ፍጡሮች ቺሜራ የሚል ስያሜ ሰጥተዋቸዋል።
የሳይንስና የቴክኖሎጂ ግኝቶች በላቁበት በዚህ ዘመን እነዚህ እሳቤዎች እውን ለመሆን ተቃርበዋል። በቅርቡም የጃፓን መንግሥት ለአንድ የሳይንቲስቶች ቡድን የሰው ልጅ አካላትን በእንስሳት ሽልና ማህፀን ውስጥ እንዲያድጉ ፍቃድ ሰጥቷል። •ሳይንቲስቱ መንትዮች ኤች አይ ቪ እንዳይዛቸው ዘረ መላቸውን አስተካከለ •የህጻናትን ዘረ መል ማስተካከል ክልክል ነው? ምርምሩን የሚመሩት ሂሮምትሱ ናካውቺ ሲሆኑ ከቶክዮና ከስታንፎርድ ዩኒቨርሰቲዎች የተውጣጡ ተመራማሪዎችን ያሳተፈው ይህ ፕሮጀክት ለዚህ ሙከራ ተብለው በተዘጋጁ አይጦች ሽል ላይ የሰውን ህዋስ በመውጋት የሰው ልጅ ጣፊያ እንዲፈጠርና እንዲያድግ የሚደረግ ሙከራ ይከናወናል ተብሏል። ሽሎቹም ካደጉ በኋላ በንቅለ ተከላ አማካኝነት ወደ ሌሎች እንስሶች ማህፀን እንዲገቡ ይደረጋል። የፕሮፌሰር ናኩቺም ዋነኛው አላማም የሰውን ልጅ አካላትን በእንስሳት ውስጥ መፍጠርና እነዚህንም አካሎች በንቅለ ተከላ አማካኝነት ወደ ሰው መግጠም (ማስገባት) መቻል ነው። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ጃፓን የሰው ህዋስ የተወጉ የእንስሳት ሽሎች በዐሥራ አራት ቀናት ውስጥ እንዲቋረጡ ታደርግ ነበር፤ በእንስሳት ማህፀን ውስጥም እንዲያድጉ አትፈቅድም ነበር። አሁን ያ እገዳው ተነስቶ ተመራማሪዎች ለፕሮጀክቶቻቸው ፍቃድ ማውጣት ይችላሉ ተብሏል። የሞራል ጥያቄዎች የሰውና የእንስሳን ህዋስ ማዳቀል በሚደረጉ የምርምር ዘርፍ ላይ የፕሮፌሰር ናካውቺ የመጀመሪያ ሙከራ አይደለም፤ እሳቸውና ሌሎች ተመራማሪዎች ከዚህ ቀደም የሰው ልጅ ህዋስን በአይጥ፣ በአሳማና በበግ ሺሎች ላይ ማሳደግ ችለዋል። የሳይንቲስቶቹ ዋነኛ አላማ እንደ ጣፊያ የመሳሰሉትን በከፍተኛ ደረጃ እጥረት የሚከሰትባቸው የሰው ልጅ አካላት በእንስሳት ውስጥ በመፍጠርና በማሳደግ ለንቅለ ተከላ ማዘጋጀት ነው። •''ለሴቶች ቦክስ ምን ያደርጋል እያሉ ያንቋሽሹናል'' ከሁለት ዓመታት በፊት ፕሮፌሰር ናካውቺ የስኳር ህመምተኛ አይጥ መፈወስ ችለዋል፤ ይህንንም ያደረጉት ጤነኛ የአይጥ ጣፊያን በአይጥ ሽል ውስጥ በማሳደግ ባደረጉት ንቅለ ተከላ ነው። ነገር ግን እስካሁን ባለው ከሰው ልጅ ህዋስ ጋር የተገናኙ ሙከራዎች ህጋዊ ሁኔታዎችን ሳያሟሉ በመቅረታቸው እንዲሁም ሙከራዎቹ ሊሳኩ ባለመቻላቸው እውን ሳይሆን ቀርቷል። ከዚህ በተጨማሪ ምርምሩ የሞራል ጥያቄዎችንም በማስነሳት ላይ ነው፤ ዋነኛውም አንገብጋቢ ጉዳይ የሰው ልጅ ህዋስን እንስሳት ውስጥ ካስገባነው በእንስሳት አእምሮ ውስጥ በመገኘት ልክ እንደሰው ልጅ አመዛዛኝ ሁኔታ ሊያላብሳቸው ይችላል የሚል ነው። ነገር ግን ፕሮፌሰር ናካውቺ ሳይንሳዊ ሙከራው የሰው ልጅ ህዋሶች ወደ ጣፊያው ብቻ እንዲሄድ የሚያደርግ ስምምነት ላይ በመድረሳቸው ነው ከጃፓን መንግሥት ፍቃድ ያገኙት። በሐምሌ ወርም ከጃፓን የትምህርት፣ ባህል፣ ስፖርትና ቴክኖሎጂ የተውጣጡ ልሂቃን የምርምር ሥራውን የተወሰኑ ነገሮችን አሟልቶና ሂደቱን ጠብቆ እስከሄደ ድረስ ቀጥልበት ብለውታል። 'የሰው ፊት ያላቸው እንስሳት' በአሁን ሰዓት እየተሞከረ ያለው በሳይንሳዊ መንገድ የሰውን ልጅ ጣፊያ እንዲያመርቱ ለማድረግ፤ በእንስሳት ሽል ላይ ጣፊያ የሚያመርተውን ዘረ መል ማቋረጥ ሲሆን ለወደፊት ደግሞ ጉበትና ኩላሊት የሚቀጥሉ ይሆናል ተብሏል። ከዚያም የእንስሳቱን ሽል የሰው ልጅ ህዋስ ይወጉትና ሽሉ ሙሉ በሙሉ በራሱ እንዲያድግ ይተውታል። ከዚያም ሽል በእንስሳት ማህፀን ውስጥ እንዲገባ ይደረጋል። ሚኒስቴሩ ለፕሮፌሰር ናካውቺ ፈቃድ የሰጠው ሙከራዎቹን በትንንሽ እንስሳት እንዲያካሂዱና በተቻለም መጠንም ዝርያቸው ከሰው ጋር የማይቀራረቡ መሆን አለባቸው በሚል እንደሆነ አያኮ ማሴዋ በጃፓን የብዝኃ ሕይወትና ደህንነት ዳይሬክተር ለቢቢሲ ገልፀዋል። ከዚህም በተጨማሪ ቡድኑ የሰው ልጅ ህዋሳትን የተሸከሙትን የእንስሶቹን ፅንስ አእምሮም በጥብቅ ይከታተላሉ ተብሏል። እንስሶቹ ከተወለዱም በኋላ ቁጥጥሩ ለሁለት ዓመታት የሚቀጥል ይሆናል ተብሏል። •በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት ፕሮፌሰር ናካውቺ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ምርምራቸውን መስከረም ወር ላይ ይጀምራሉ። በካሊፎርኒያ ስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ በተደረገ ሳይንሳዊ ሙከራ ፕሮፌሰር ናካውቺ የሰው ልጅ ህዋስን ከበግ እንቁላል ጋር በማጣመር በበግ ሽል ውስጥ አድርገውት ነበር። ከሃያ ስምንት ቀናት በኋላ ሽሉ ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ሆኗል። ሽሉ በጣም ጥቂት የሰው ልጅ ህዋስ እንደያዘና ምንም ዓይነት የሰው ምልክትም እንደሌለው ፕሮፌሰር ናካውቺ ለአሻይ ሺምቡን ጋዜጣ ተናግረዋል። "በበጓ ሰውነት ውስጥ ማደግ የቻሉት የሰው ልጅ ህዋሳት በጣም ጥቂት ናቸው፤ ምናልባትም ከሺዎች ወይም ከዐሥር ሺ ህዋሳት አንዱ ነው" በማለትም "በዚህ አካሄድ የሰው ፊት ያለው እንስሳ በጭራሽ ሊወለድ አይችልም" ብለዋል። የዝርያ ርቀት የሰው ልጅ ህዋሳትን በሌላ ዝርያ ማሳደግ ቀላል አይደለም። በቴክሳስ ዩኒቨርስቲ የሚገኙት ተመራማሪ ጁን ው እንደሚሉት ከሆነ ከሰውና ከእንስሳት የተዳቀሉ ሼሎችን ከሰው ልጅ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸው እንደ አሳማና በግ ማህፀን ውስጥ ለማሳደግ መሞከር ምንም ትርጉም የለውም ይላሉ። በነዚህ እንስሳት ውስጥ የሰው ልጅ ህዋስ የማደግ እድል የለውም ገና በሽል ውስጥ እያለ ይሞታል ብለውም ይከራከራሉ። ባለፈው ወር የስፔን ሳይንቲስቶች ከሰውና ከዝንጀሮ የተዳቀለ ሽል በቻይና በሚገኝ ላብራቶሪ መፍጠራቸውን ስፓኒሽ ደይሊ ኤልፓይስ ዘግቦ ነበር። ይህ ምርምርም ሲመራ የነበረው በፕሮፌሰር ጁዋን ካርሎስ ሲሆን ከዚህ ቀደምም ከሰውና አሳማ የተዳቀለ ሽል በላብራቶሪ ፈጥረዋል።
44639597
https://www.bbc.com/amharic/44639597
ናይጂሪያዊው ኮሜዲያን ከአሻንጉሊት ጋር ትዳር ሊመሠርት ነው
ቤንጃሚን ዋቹኩ ይባላል። ብዙዎች ሹጋ ሻ በሚለው የመድረክ ስሙ ነው የሚያውቁት።
ሹጋ ሻ በሚል የመድረክ ስም የሚታወቀው ናይጄሪያዊው ኮሜዲያን ከአሻንጉሊት ጋር ሦስት ጉልቻን አልሟል ዕውቅ ተዋናይና ኮሜዲያን ሲሆን እጅግ ቆንጆ ከሚላት ሴት አሻንጉሊት ጋር ኮስተር ያለ ፍቅር መጀመሩን ይፋ አድርጓል። ይህንን ተከትሎ የናይጄሪያ ማኀበራዊ ሚዲያ በጉዳዩ ላይ ለሁለት ተከፍሏል። ጉዳዩን እጅግ አስቀያሚ ድርጊት ሲሉ የሚኮንኑና፣ ነገሩ ፌዝ ነው ልጁን ተዉት በሚሉ ወገኖች ሚዲያው እየተናጠ ነው። ሶፊያ ከአብይ አሕመድ ጋር የራት ቀጠሮ ይዛለች ሳዑዲ ለሮቦት ዜግነት ሰጠች አሻንጉሊቷ እስትክክል ያሉ ጥፍሮች ያሏት፥ ውድ ጌጣጌጦች የምታደርግ ሲሆን የምትቀባቸው ሽቶዎች ብዙ ዋጋ የወጣባቸው እንደሆኑ ተነግሯል። ኮሜዲያኑ ታዲያ ከዚች ቀበጥ አሻንጉሊት ጋር ገበያ ሲሄድ፣ ሲኒማ ሲመለከት፣ በመኪና ሽው እልም ሲል ታይቷል። አንዳንድ አድናቂዎቹ "ታስጠላለህ' ሲሉት ሌሎች "ቀውሰሀል" ለይቶልሀል እያሉት ነው። ኮሜዲያኑ ለቢቢሲ እንደተናገረው ከሆነ ከአሻንጉሊቱ ጋር ስለጀመረው ፍቅር ለወላጅ እናቱ ማሳወቁንና እናቱ ብዙም ቅር እንዳልተሰኙበት ተናግሯል። በመሆኑም ሽማግሌ ለመላክና ትዳሩን እውን ለማድረግ መዘጋጀቱን ጠቆም አድርጓል። ቶንቶ እያለ የሚያቆላምጣት አሻንጉሊቱ መልከ መልካም ሴት ናት ተብሏል። "ሰላም ትሰጠኛለች፣ አታስመስልም፣ ደግሞም ልታስቀየመኝ አትችልም።" ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል።
news-53711893
https://www.bbc.com/amharic/news-53711893
ቤይሩት ፍንዳታ፡ በአደጋው 15 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ውድመት መድረሱ ተገለፀ
የዓለም መሪዎች ከአምስት ቀናት በፊት በከባድ ፍንዳታ ለተመታችው የሊባኖሷ መዲና ቤይሩት እርዳታ ለማሰባሰብ ዛሬ ጉባኤ እንደሚያካሂዱ ተገለፀ።
ይህ በበይነ መረብ (ቨርቹዋል) የሚካሄደው ስብሰባ በፈረንሳይና በተባበሩት መንግሥታት የተዘጋጀ ሲሆን ስምንት ሰዓት ላይ ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል። የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለአገሪቷ ዓለም አቀፍ ድጋፍ ለማሰባሰብ ማስተባበር እንደሚፈልጉ የተናገሩት ሐሙስ ዕለት ቤይሩትን በጎበኙበት ወቅት ነበር። ዛሬ የሚካሄደው ጉባኤ የሊባኖስ ዋና ዋና ዓለም አቀፍ አጋሮችን ለማሰባሰብና ከዓለም አቀፍ ማሕበረሰቡ አስቸኳይ ድጋፍ ለማሰባሰብ ያለመ መሆኑም ከፕሬዚዳንቱ ቢሮ የወጣው መግለጫ አመልክቷል። በጉባኤው ላይ የአውሮፓ ሕብረት አባል አገራት ተወካዮች ፣ ቻይና፣ ሩሲያ፣ ግብፅ፣ ጆርዳን እና ዩናይትድ ኪንግደም የሚሳተፉ ሲሆን ሌሎች በርካቶችም ተጋብዘዋል። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቤይሩት ስለተከሰተው ድንገተኛ አደጋ ከፕሬዚደንት ኢማኑኤል ጋር ተወያይተው እንደነበር ገልፀው፤ በስብሰባው ላይ ለመሳተፍ እንዳቀዱ በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል። በርካታ አገራት ቤይሩትን ለመርዳት በሚሊየን ዶላሮች የሚገመት እርዳታ፣ መርከቦች፣ የጤና ባለሙያዎችንና ቁሳቁሶችን ልከዋል። ይሁን እንጂ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በአገሪቷ ከፍተኛ ቀውስ ሊያጋጥም እንደሚችል በማስጠንቀቅ ተጨማሪ እርዳታ እንደሚያስፈልግ ጥሪ አቅርቧል። በርካታ ቤቶች የውሃና የኤሌክትሪክ አገልግሎት የተቋረጠባቸው ሲሆን የምግብ ፍጆታ እጥረት እንደሚያጋጥምም ስጋት አለ። ከዚህም ባሻገር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሥርጭት እየጨመረ ሲሆን ይህም በፍንዳታው በተጎዱ ሰዎች በተጨናነቁት ሆስፒታሎች ላይ ተጨማሪ ጫና ፈጥሯል። የዩኒሴፍ ቃል አቀባይ ማሪክሴ ሜርካዶ አርብ ዕለት ጀኔቫ ለሚገኙ ጋዜጠኞች "አፋጣኝና ከፍተኛ ድጋፍ" እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። የሊባኖስ ባለሥልጣናት 2 ሺህ ቶን የሚመዝን አሞኒየም ናይትሬት ደህንነቱ ባልተጠበቀ ሁኔታ ለስድስት ዓመታት ተከማችቶ በነበረበት መጋዘን በተከሰተው ፍንዳታ፤ 15 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ጉዳት እንደደረሰ ግምታቸውን አስቀምጠዋል። በፍንዳታው ቢያንስ 158 ሰዎች የሞቱ ሲሆን 5 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት አጋጥሟቸዋል፤ 300 ሺህ የሚሆኑት ቤት አልባ ሆነዋል። ይህንንም ተከትሎ ቅዳሜ ዕለት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መንግሥትን ለመቃወም አደባባይ የወጡ ሲሆን፤ ፖሊስም በመንግሥት መስሪያ ቤቶች ላይ ድንጋይ በመወርወር ተቃውሟቸውን ሲገልፁ በነበሩት ላይ አስለቃሽ ጭስ ረጭቷል። የአገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሰን ዲያብም ከዚህ ቀውስ ለመውጣት ቀድሞ ከተያዘው ጊዜ ቀድሞ ምርጫ እንዲካሄድ ሊጠይቁ እንደሚችሉ የተገለፀ ሲሆን በጉዳዩ ላይም ካቢኔው ሰኞ ውይይት ያደርግበታል ተብሏል። ቀደም ሲል በከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ የገባችው ሊባኖስ፤ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመዋጋት እየተጣጣረች ባለበት ሰዓት ነው ፍንዳታው ያጋጠማት። በአገሪቷ ያጋጠመውን የኢኮኖሚ ቀውስና የመገበያያ ገንዘቧ ዋጋ መውደቅ ተከትሎ ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ ፀረ መንግሥት ተቃውሞ ተቀስቅሶ ነበር።
46374274
https://www.bbc.com/amharic/46374274
የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እና የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ተዋሃዱ
የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ-ኦዴፓ እና በሌንጮ ለታ የሚመራው የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር-ኦዴግ ለመዋሃድ የመግባቢያ ሰነድ ላይ ዛሬ ከሰዓት ተፈራረሙ።
የኦዲግ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ለማ መገርሳ እና የኦዴግ ሊቀመንበር አቶ ሌንጮ ለታ በሁለቱ ፓርቲዎች መካከል የፖለቲካ መርህ ልዩነት አለመኖሩ እና በህዝብ ዘንድ ሁለቱ ፓርቲዎች እንዲዋሃዱ ፍላጎት መኖሩ ሁለቱ ፓርቲዎች እንዲዋሃዱ ምክንያት ሆኗል ተብሏል። የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት እና የኦዴፓ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ለማ መገርሳ፤ ''በአንድ አዕምሮ እና ልብ ለመስራት ከስምምነት ላይ ደርሰናል። ኦዴፓ በወጣቶች የተሞላ ፓርቲ ነው። ከኦዴግ ጋር ስንዋሃድ ጠንካራ ተቋም ይወጣናል'' ብለዋል። የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር አመራሮች ወደ ሃገር ከመምጣታቸው በፊት ''ሲረዱን'' ነበር ያሉት ፕሬዚዳንት ለማ፤ አብረን ለመስራት እድሉን ስላገኘን ከፍተኛ ደስታ ይሰማናል ብለዋል። ''ለአንድ ኦሮሞ ህዝብ ከ10 በላይ ሆነን ከምንታገል፤ ከእኛ ጋር አንድ አይነት ዓላማ እና ሰልት የሚከተሉ የፖለቲካ ድርጅቶችን መጥተው ቢቀላቀሉን አሁንም ለመቀበል ዝግጁ ነን። ይህም ለኦሮሚያ ብቻ ሳይሆን ለሃገርም ጠቀሜታው ከፍ ያለ ነው።'' ብለዋል። • ". . . ጥፍር መንቀል ሕጋዊ አይደለም ስንለው ብሔሩ ውስጥ ለመደበቅ ይሞክራል" ጠ/ሚ ዐብይ • "ፓስፖርት መስጠት አልተከለከለም" የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች ተቋም • ምርጫ ፡ የተቃዋሚዎችና የመንግሥት ወግ? የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ሌንጮ ለታ በበኩላቸው ''የመበታተን ባህል ወደ ችግር እና ድህነት ነው የሚወስደን'' ብለዋል። አቶ ሌንጮ ጨምረው ''ዛሬ ላይ የፓርቲዎች ውህደት ብቻ ሳይሆን የህዝብ አንድነት ጭምር ያስፈልገናል፤ የኦሮሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች እንደ ከዚህ ቀደሙ ሳይሆን እንደዛሬ ነው ማሰብ ያለብን'' ሲሉ ተናግረዋል። የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ኃላፊ የሆኑት አቶ አዲሱ አረጋ ዛሬ ከሰዓት በሰጡት መግለጫ በህዝቡ ዘንድ ፓርቲዎቹ እንዲዋሃዱ ያለው ፍላጎት እንዲሁም በኦዴፓ እና ኦዴግ መካከል የፖለቲካ መርህ ልዩነት አለመኖር ፓርቲዎቹ እንዲዋሃዱ ምክንያት ሆኖዋል ብለዋል። ከፓርቲዎቹ ውህደት በፊት ረዘም ያለ ውይይት መካሄዱን ያስታወሱት አቶ አዲሱ፤ ወደፊትም አንድ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ የፓርቲ መጠሪያ ስያሜ፣ አርማ እና በመሰል ሌሎች ጉዳዮች ላይ ይሰራል ብለዋል።
news-56439794
https://www.bbc.com/amharic/news-56439794
ትግራይ፡ ወደ ኢትዮጵያ መልዕክተኛ ለመላክ የተዘጋጀችው አሜሪካ 52 ሚሊዮን ዶላር ለገሰች
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በትግራይ ውስጥ ስለተከሰተው ቀውስና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር እንዲወያዩ መልዕከተኛ ወደ ኢትዮጵያ ሊልኩ ነው።
በተጨማሪም አሜሪካ ለእርዳታ የሚውል 52 ሚሊዮን ዶላር በትግራይ ግጭት የሰብአዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች የሚውል ድጋፍ እንደምትሰጥ በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቷ በኩል አስታውቃለች። የባይደን መልዕክተኛ የአሜሪካ ምክር ቤት አባል የሆኑት ክሪስ ኩንስ በትግራይ ክልል ስለተከሰተው ቀውስ፣ ስለሰብአዊ መብት ጥሰቶችና በሱዳንና ኢትዯጵያ መካከከል ያለው የድንበር አካባቢ አለመረጋጋት የፕሬዝዳንቱን ስጋት አንስተው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጋር እንደሚነጋገሩ መረጃዎች ጠቁመዋል። መልዕክተኛው ሴናተር ክሪስ ኩንስ ወደ ኢትዮጵያ በሚያደርጉት ጉዞ ወቅት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተጨማሪ ከአፍሪካ ሕብረት ኃላፊዎችም ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ተገልጿል። ባለፈው ሳምንት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ለአገሪቱ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ኢትዮጵያን በሚመለከት በሰጡት ማብራሪያ ላይ በትግራይ ክልል "የዘር ማጽዳት" ድርጊት ተፈጽሟል ብለው መናገራቸው ይታወሳል። የኢትዮጵያ መንግሥትም ይህንን ክስ "ተጨባጭነት የሌለውና ሐሰተኛ" በማለት የብሊንከንን ንግግር አጥብቆ ተቃውሞታል። በተያያዘ ዜና የአሜሪካ መንግሥት በትግራይ ክልል ለሚከናወን የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት የሚውል 52 ሚሊዮን ዶላር ማቅረቡን አስታውቋል። የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባወጣው መረጃ መሠረት ይህ እርዳታ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ እርዳታ አጋሮች በትግራይ ውስጥ የሚገኙትንና ወደ ሱዳን የተሰደዱ ድጋፍ ለሚሹ ሰዎች የሚሆን እርዳታ ለማቅረብ ያስችላቸዋል ብለዋል። የአሜሪካ መንግሥት የሚሰጠው ይህ የገንዘብ ድጋፍ ለተረጂዎች ህይወት አድን አገልግሎቶችን፣ መጠለያ፣ መሠረታዊ የጤና አገልግሎት፣ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ፣ ውሃና የንጽህና አቅርቦቶች የሚውል ይሆናል ተብሏል። አሜሪካ የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ሁኔታዎችን በማመቻቸት በኩል ያሳያውን ቁርጠኝነትና መሻሻል እንደምታደንቅ ገልጾ፤ "ትግራይ ውስጥ እየተባባሰ ያለው ሰብአዊ ቀውስ በእጅጉ እንደሚያሳስበው" አመልክቷል። ጨምሮም አስቸኳይ፣ የተሟላና ገደብ የሌለበት የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መንገዶች ለእርዳታ ሰጪ ድርጅቶችና ሠራተኞች መመቻቸት በግጭቱ ለችግር የተጋለጡ ሰዎች ፍላጎትን መሠረት ያደረጉ ወቅታዊ ድጋፍ ማድረግ እንደሚያስችል ጠቅሷል። "ፖለቲካዊ መፍትሔ አስካልተገኘ ድረስ የሰብአዊ ቀውሱ ሁኔታ እየተባባሰ ይቀጥላል" ያለው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ከዚህ በፊት እንዳለው አሁንም ደግሞ፤ ግጭቶች እንዲቆሙ፣ የኤርትራና የአማራ ክልላዊ ኃይሎች በአስቸኳይ ከትግራይ ክልል እንዲወጡ ጠይቋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ለዚህ ሰጥቶ በነበረው ምላሽ ላይ በግዛቱ ውስጥ ሕግን ለማስከበር በሚወስደው እርምጃ ውስጥ ስለሚያሰማራው የጸጥታ ኃይልን በተመለከተ በአሜሪካ በኩል የተጠቀሰው ነገር "በሉአላዊ አገር የውስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ መግባት ነው" ሲል መቃወሙ የሚታወስ ነው። የአሜሪካ መንግሥት በተጨማሪም በትግራይ ውስጥ ተፈጽመዋል ከተባሉት የሰብአዊ መብት ጥሰቶችና ግድያዎች ጋር በተያያዘ በግጭቱ ውስጥ ተሳታፊ ከሆኑ ከሁሉም ኃይሎች በኩል ያሉ አጥፊዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በመግለጫው ላይ አመልክቷል። የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግሥት ከአህጉራዊና ከዓለማ አቀፋዊ ተቋማት ጋር በመሆን ምርመራ እንዲካሄድ በጠየቀው መሰረት የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን በመርመራው ውስጥ ለመሳተፍ ፈቃደኛ መሆኑን መግለጹ ይታወቃል። በፌደራል መንግሥቱና የትግራይ ክልልን ያስተዳድር በነበረው ህወሓት መካከል በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ለረጅም ጊዜ ሲብላላ የቆየው አለመግባባት በጥቅምት ወር መጨረሻ የአገሪቱ ሠራዊት አንድ ክፍል በሆነው በሠሜን ዕዝ ላይ በተፈጸመው ጥቃት ሳቢያ ወደ ሙሉ ወታደራዊ ግጭት መሸጋገሩ ይታወሳል። በዚህም ሳቢያ አስካሁን የሞቱ ሰዎች ትክክለኛ ቁጥር ባይታወቅም በሺዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ሲገምት በመቶሺዎች ደግሞ በክልሉ ውስጥ ተፈናቅለው እርዳታና ድጋፍ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ። ከ60 ሺህ የሚበልጡ ሰዎች ደግሞ ግጭቱን በመሸሽ ወደ ሱዳን መሰደዳቸውን የእርዳታ ድርጅቶች ይገልጻሉ።
news-55737476
https://www.bbc.com/amharic/news-55737476
ትራምፕ ለመጨረሻ ጊዜ ዋይት ሃውስን ተሰናብተው ወጡ
የተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በዓለ ሲመት ሊፈፀም በተቃረበበት በአሁኑ ወቅት ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዋይት ሃውስን ተሰናብተው ወጥተዋል።
ለአራት አመት ከኖሩበት ቤተ መንግሥትም በሄሊኮፕተር በመሳፈር አቅራቢያው ወዳለው አንድሪውስ የሚባል ስፍራ ደርሰዋል። በዚያው አጠር ያለ ንግግር ካደረጉ በኋላም በአየር ኃይሉ አውሮፕላን ተጭነው ወደ ፍሎሪዳ ያቀናሉ። ከዋይት ሃውስም ሲወጡ አጠር ላለ ጊዜ ከሪፖርተሮች ጋር ያወሩ ሲሆን "ፕሬዚዳንት መሆን ትልቅ ክብር ነው" ማለታቸውንም ሲኤንኤን ዘግቧል። በዚሁ ሳምንት ማክሰኞ ባደረጉት የመሰናበቻ ቪዲዮ ለቀጣዩ አስተዳዳሪ አሜሪካውያን እንዲፀልዩ ቢጠይቁም ስም ከመጥራት ግን ተቆጥበዋል። ከዚህም በተጨማሪ በባለፉት አራት አመታት ባከናወኗቸው ተግባራት ከፍተኛ ኩራት እንደሚሰማቸው የገለፁት ትራምፕ በተለይም በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም በማምጣትና በአስርት አመታትም አገራቸው ጦርነት ውስጥ እንዳትሳተፍ ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል። የተከታያቸውን በዓለ ሲመት ባለመካፈልም ከአውሮፓውያኑ 1869 በኋላ የመጀመሪያ ፕሬዚዳንት ሆነዋል። ጆ ባይደን ቃለ መሃላቸውንም በአገሬው ሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት አካባቢ በቅርቡ ነውጥና ሁከት ባስተናገደው በዋሽንግተኑ ካፒቶል ሂል የሚፈፅሙ ይሆናል። የበዓለ ሲመቱንም ዝግጅት ደህንነትና ፀጥታ ለመቆጣጠር ከብሔራዊ ዘብ የተውጣጡ 25 ሺህ ሰራዊት ሰፍሯል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝም ምክንያት እንደ ወትሮው በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ታዳሚዎች አይሳተፉም። ከጆ ባይደንም በተጨማሪ የሴት ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆን በአሜሪካ ዘንድ ታሪክ የሰራችው ካማላ ሃሪስም ቃለ መሃላዋን ትፈፅማለች። ተመራጩ ፕሬዚዳንት ስልጣናቸውንም በይፋ ከመቆናጠጣቸው በፊት ሊያከናውኗቸው የሚገቡ አስራ አምስት ተግባራትን በዚሁ ሳምንት አስታውቀዋል። ከነዚህም መካከል የአየር ንብረት ለውጥ፣ እኩልነት፣ የስደተኞች ጉዳይና ኮሮናቫይረስ ተጠቃሽ ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ በመጀመሪያ ቀናቸው አወዛጋቢ የሆነውን ኪስቶን ኤክስ ኤል የተባለውን የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ፕሮጀክት እንደሚሰርዙ የአሜሪካ ሚዲያዎች ሪፖርት አድርገዋል። የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧው ፕሮጀክት አልሞ የነበረው የካናዳዊቷን ግዛት አልበርታንና የአሜሪካን ኔብራስካን ግዛትን የሚሸፍን 1 ሺህ 900 ኪሎሜትር እርዝማኔ እንዲኖረው ታቅዶ ነበር። የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋቾች እንዲሁም ቀደምት አሜሪካውያን ይህ ፕሮጀክት እውን እንዳይሆን ለአስር አመታት ያህል ታግለዋል።
news-41932977
https://www.bbc.com/amharic/news-41932977
ኦባማ ፍርድ ቤት ሊያገለግሉ ቢመጡም አገልግሎትዎ አያስፈልግም በሚል ተሰናበቱ
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ቺካጎ በሚገኘው ፍርድ ቤት እንደ ጁሪ (በአሜሪካ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል የተውጣጡ ፍርድ የሚቀመጡ ሰዎች) ሆነው ቢቀርቡም ዳኛው ለማገልገል ጥያቄ ሳይቀርብልዎት ነው የመጡት በሚል አሰናብተዋቸዋል።
የሳቸውንም መምጣት ተከትሎ ብዙዎች ዳሊ ሴንተር በሚባለው የማዘጋጃ ህንፃ ላይ 44ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ለማየት በጉጉት ተሰብስበው እየጠበቁት ነበር። ሳይመደቡም ፍርድ ቤት በጁሪነት መሄድ የተለመደ ቢሆንም ፤ ለኦባማ መሰናበታቸው ኦፊሴያላዊ ምክንያት አልተሰጠም። ኦባማ ሮብ ጥዋት ፍርድ ቤት የደረሱ ሲሆን ወደ ግማሽ ቀንም ላይ ተመልሰዋል። የቀድሞው ፕሬዚዳንት የህግ ፕሮፌሰር የነበሩ ሲሆን ቺካጎ ውስጥም መኖሪያ ቤት አላቸው። በጁሪም ውስጥ ለማገልገል ከሀገሪቷ 17 ዶላርም ወይም 430 ብር ይከፈላል። ኦባማ ከቤታቸው ኬንውድ አካባቢ ወጥተው በመኪናቸው ሲሄዱ የተለያዩ ሚዲያዎች በሄሊኮፕተሮች እያንዣበቡ እየቀረፁዋቸው ነበር። ያለ ከረባት ጃኬት ለብሰው የተገኙት ኦባማ 17ኛ ፎቅ ላይ ተገኝተው ከሌሎች የፍርድ ቤቱ ሰራተኞች ፣ ጋዜጠኞች ጋር ተገናኝተዋል። በፍርድ ቤቱ ለረዥም ጊዜ ያልቆዩ ሲሆን፤ዳኛውም በዘፈቀደ ኦባማን መርጠው አገልግሎታቸው እንደማያስፈልግ ነግረው አሰናብተዋቸዋል። ከመሄዳቸውም በፊት ኦባማ ጁሪውን ሊያገለግሉ ለመጡት በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል። አንዳንዶች የኦባማን መፅሀፍ በቦታው ይዘው በመምጣት እንዲፈርሙላቸው የጠየቁ ሲሆን ፤የፍርድ ቤቱን ሰራተኞች ጨምሮ ሌሎችም አብረዋቸው ፎቶ ተነስተዋል። ለጁሪነት የመጣች አንደኛዋ ደስታዋን መቆጣጠር አቅቷት የነበረ ሲሆን፤ ለአካባቢው ጋዜጣም የፕሬዚዳንቱን እጅ በጨበጠችበት ወቅት "እንደ ቅቤ እንደቀለጠች" ተናግራለች። የኦባማ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ካቲ ሂል እንደተናገሩት "የቀድሞው ፕሬዚዳንት በሀገሪቷ ዲሞክራሲ ውስጥ ከስልጣን በላይ ቀዳሚው ነገር ዜጋ መሆንን አሳይተዋል። በጁሪ ውስጥ ማገልገልን ደግሞ ዋናው የዜግነት ግዴታ ነው" በማለት ተናግረዋል። በመጀመሪያ አመታት የፕሬዚዳንትነታቸው ወቅት ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ተጠይቀው የነበረ ሲሆን ከፍርድቤቱም ቀጠሯቸውን ማስተላለፍ እንዲችሉ ፈቃድ አግኝተው ነበር። እንደ ምክንያትነትም ያቀረቡትም በኢራቅ ከምትገኘው የኩርዲስታን ግዛት ፕሬዚዳንት ቀጠሮ ስለነበራቸው ነው። ከሁለት ዓመታት በፊት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ ጁሪ እንዲያገለግሉ በዳላስ ቴክሳስ ተጠርተው የነበረ ሲሆን ፤ከሌሎች ጁሪ ከሚያገለግሉ ሰዎች ጋር ፎቶ ተነስተው በማጋራታቸው ተሰናብተዋል። ከአራት አመታትም በፊት በኒው ዮርክ የተደራጁ ቡድኖች የተኩስ ልውውጥን አስመልክቶ በነበረ ክስ ላይ በጁሪነት ሊያገለግሉ የመጡት ቢል ክሊንተንም ተሰናብተው ነበር።
news-55541615
https://www.bbc.com/amharic/news-55541615
ጥቁር አሜሪካዊውን በ7 ጥይት የመታው ነጭ ፖሊስ 'ክስ አይመሰረትበትም'
በዊስኮንሲን ግዛት፣ ኬኖሻ ከተማ ውስጥ ፖሊስ ሦስት ልጆቹ ፊት በጥይት ደብድቦት በተአምር የተረፈው ጄኮብ ብሌክ በጠበቃው በኩል የፍትሕ ያለህ እያለ ነው።
ጄኮብ ብሌክ የአካባቢው ዐቃቤ ሕግ ድርጊቱን በፈጸመው ፖሊስ ላይ የወንጀል ክስ አይመሰረትም ማለቱን ተከትሎ የጄኮብ ጠበቃ አሜሪካ ሦስት የፍትሕ ሥርዓት ነው ያላት ሲሉ ለሚዲያ ተናግረዋል። አንዱ ለነጭ ፖሊሶች፣ ሌላው ለተራው ሕዝብ እና የመጨረሸው ደግሞ ለጥቁሮች ነው ሲሉ ቁጣቸውን ገልጠዋል። ጄኮብ ደጅ ቆማ ወደነበረችው መኪናው ሲራመድ ሁለት ፖሊሶች በቅርብ ርቀት እየተከተሉት ነበር። የመኪናውን በር እንደከፈተ ግን 3 ሕጻናት ልጆቹ ከኋላ ወንበር ተቀምጠው ድርጊቱን እየተመለከቱ 7 ጥይቶች ከጀርባው ሲተኮሱበት ይታያል። ይህ በተንቀሳቃሽ ምሥል ዓለም የተመለከተው ቪዲዮ እያለ እስከአሁን በጉዳዩ ተጠያቂ የሚሆን አንድም ፖሊስ እንዳልተከሰሰ ተዘግቧል። ወደፊትም በወንጀል የሚጠየቅ የፖሊስ መኮንንም አይኖርም ተብሏል። የጄኮብ ጠበቃ ውሳኔውን ተከትሎ እንደተናገሩት፣ ዘረኛ በሆነው የፍትሕ ሥርዓት ውስጥ የ20 ሰከንድ ግልጽ የቪዲዮ ማስረጃን ውድቅ ለማድረግ ዐቃቢ ሕግ 4 ወራት ፈጅቶበታል ብለዋል። "ፍትሕ ቢኖር፤ ዓይናችን ለተመለከተው ነገር የሁለት ሰዓት ማብራሪያ አስፈላጊ አልነበረም" ሲሉም ተናግረዋል። ጥቁር አሜሪካዊው ጄኮብ ብሌክ 7 ጥይት በቅርብ ርቀት ተርፈከፍክፎበት በሕይወት ቢተርፍም ከወገብ በታች ሙሉ በሙሉ መንቀሳቀስ አይችልም። ጄኮብ ብሌክ ከኋላው በተደጋጋሚ በፖሊስ የተተኮሰበት ወደ መኪናው እያመራ በነበረ ቅጽበት የመኪናው በር እንደከፈተ ነበር። ይህ ሁሉ ሲሆን መኪናው ውስጥ ኋላ ወንበር ተቀምጠው የነበሩ ሦስት ሕጻናት ልጆቹ ድርጊቱን ተመልክተዋል። በጥቁር አሜሪካዊው ጄኮብ ብሌክ ላይ ነጭ ፖሊሶች ያደረሱት ጥቃት በዊስኮንሲንና በሌሎች የአሜሪካ ግዛቶች ከፍተኛ ቁጣን መቀስቀስ ይታወሳል። ድርጊቱን በነሐሴ 23/2020 (እአአ) የፈጸመው ፖሊስ ረስተን ሼስኪይ ይባላል። እስከአሁንም የወንጀል ክስ አልተመሰረተበትም። ይህን ድርጊት ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ ሁለት ሰዎች ተገድለው አንድ ሌላ ሰው በኬኖሻ ከተማ መቁሰሉ አይዘነጋም። ፖሊስ እንዴት ላይከሰስ ቻለ? የኬኖሻ ከተማ ዐቃቤ ሕግ ማይክል ግራቭሊ ድርጊቱን በፈጸመው የፖሊስ መኮንን ላይ እንድም የወንጀል ክስ አልተከፈተም፣ አይከፈትምም ብለዋል። የፖሊስ መኮንኑ ሼስኪ በጄኮብ ላይ በቅርብ ርቀት ጥይት አከታትሎ ሲተኩስበት አንድ መንገደኛ ነው ቅጽበቱን በቪዲዯ አስቀርቶ በመላው አሜሪካ ቁጣ እንዲቀሰቀስ ምክንያት የሆነው። ድርጊቱ የተፈጸመበት ክፍለ ከተማ ዐቃቤ ሕግ እንደሚሉት ክሱን መመሥረት አስፈላጊ የማይሆነው ፖሊስ መኮንኑ ድርጊቱን የፈጸምኩት ራሴን ለመከላከል ነው የሚለውን የክርክር ነጥብ መምዘዙ አይቀሬ ስለሚሆን ነው። የኬኖሻ የፖሊስ መኮንኖች ማኅበር እንደሚለው ጄኮብ በጊዜው ቢላ ይዞ የነበረ ሲሆን ያን እንዲጥል በፖሊስ መኮንኑ በሚስተር ሼስኪ በተደጋጋሚ ቢነገረውም ሊሰማ አልቻለም። የፖሊስ መኮንኑ ጠበቃ ብሬንዳን ማቲው እንዳሉት ደግሞ ጄኮብ ስለት ያለው መሳሪያ ይዞ ወደተኮሰበት ፖሊስ ዞሮ ጥቃት ለመፈጸም አስቦ ነበር። መርማሪዎች በበኩላቸው እንደሚሉት ፖሊሱ በመኪናው ወለል ላይ ስለት ያለው ነገር እንደተመለከተ ብቻ ጠቅሰዋል፣ ጄኮብ ብሌክ ስለቱን ለመጠቀም ሙከራ ስለማድረጉ ያሉት ነገር የለም። ቅጽበቱን የቀረጸው መንገደኛ በበኩሉ ለሲኤንኤን ቴሌቪዥን ሲናገር መቅረጽ ከመጀመሩ በፊት ፖሊስ ከጄኮብ ጋር ሲታገል፣ በጡጫ ሲመታውና በጨረር ማደንዘዣ መሳሪያ ሊያጠቃው ሲሞክር ነበር። እሱ ቪዲዮ መቅረጽ የጀመረው ከዚህ በኋላ ነበር። 20 ሰከንዶች በሚረዝመው በዚህ ቪዲዮ ላይ ጄኮብ ወደ ግል መኪናው ተራምዶ የፊት በሩን ሲከፍት በቅርብ ርቀት ደግሞ 2 ፖሊሶች ሲከተሉት ከዚያ ደግሞ የመኪናው በር እንደከፈተ አንድ ፖሊስ ከኋላው ጥይት ሲተኩስበት ይታያል። ቅጽበቱን የቀረጸው ሰው ፖሊስ ከመተኮሱ በፊት ቢላውን ጣለው እያለ መጮኹን መስማቱን ነገር ግን ቢላ አለማየቱን አስታውሷል። የአቃቤ ሕግ ውሳኔን ተከትሎ ቁጣ ይቀሰቀሳል በሚል በዊስኮንሲን ኬኖሻ 500 ተጨማሪ ፖሊሶች በተጠንቀቅ ተሰማርተዋል።
news-54735923
https://www.bbc.com/amharic/news-54735923
በኦሮሚያ ቤተ ክህነት አደራጅ ኮሚቴ እና በቅዱስ ሲኖዶስ መካከል የነበረው የዕርቅ ሂደት መጠናቀቁ ተገለጸ
በኦሮሚያ ቤተ ክህነት ጽህፈት ቤት አደራጅ ኮሚቴ እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ መካከል እየተካሄደ የነበረው የዕርቅ ሂደት መጠናቀቁን ሂደቱን ሲመሩ የነበሩ ሽማግሌዎች ገለጹ።
የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ጽህፈት ቤት አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ቀሲስ በላይ መኮንን የኦሮሚያ ቤተ ክህነት እንደሚያቋቁሙ መግለጻቸውን ተከትሎ ከቅዱስ ሲኖዶሱ ጋር አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል። ቤተ ክርስቲያኒቱ ባለፉት ጥቂት ቀናት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ስታደርግ ከተነሱ ነጥቦች አንዱ በቀሲስ በላይና በሲኖዶሱ መካከል ዕርቀ ሰላም ማውረድ እንደሆነ መዘገባችንም አይዘነጋም። የዕርቅ ሂደቱን ሲመሩ የነበሩ አባቶች ዛሬ ጥቅምት 19 ቀን 2013 ዓ. ም. በሰጡት መግለጫ፤ "በመጀመሪያ ቋሚ ሲኖዶስ፣ በመቀጠልም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ባጸደቀው መሠረት የዕርቅ ሂደቱ ተጠናቋል" ተብሏል። . "በእርቅ ውስጥ ሁሉም አሸናፊ ነው"- ቀሲስ በላይ . የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አባላት በንስሐ እስኪመለሱ ክህነታቸው ተያዘ በመግለጫው ኦሮሚያ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መዳከም ያሳሰባቸው ወገኖች ችግሩን ለመፍታት በሚል የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ለማቋቋም መወጠናቸውን በማስታወስ፤ "የተነሱት ችግሮች እንዳሉ በአባቶች፣ ሊቃውንትና ምእመናን ቢታመንም መፍትሔው የኦሮሚያ ቤተ ክህነት መቋቋም ነው? የሚለው በአባቶች እና በምእመናን ዘንድ መከፋፈል ፈጥሯል" ይላል። በኦሮሚያ አለ የሚባለውን የአገልግሎት መዳከም፣ በቋንቋው የሚያስተምሩ በቂ አገልጋዮች አለመኖር እና ሌሎችም የአስተዳደር ችግሮች እንዴት ይፈቱ? የሚለው ላይ ልዩነቶች እንደነበሩ ተገልጿል። ስለዚህም ችግሩን በውይይት ለመፍታት የተቋቋመው የሽማግሌዎች ቡድን የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አመራሮችን፣ ቋሚ ሲኖዶሱን እንዲሁም ሌሎችም ባለድርሻ አካላትን እንዳነጋገረ በመግለጫው ተመልክቷል። ላለፉት ስድስት ወራት ችግሩን ለመፍታት ውይይት ሲካሄድ እንደነበረም ተጠቅሷል። "በኦሮሚያ ያጋጠመው የአገልግሎት መዳከም በጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥር በሚቋቋም ጠንካራ አካል በኩል በአንድነት መፍታት የተሻለ መሆኑ በሁሉም ዘንድ ታምኖበታል" ሲልም መግለጫው ያትታል። በኦሮሚያ ያጋጠመው የአገልግሎት መዳከም የመላዋ ቤተ ክርስቲያን ፈተና ተደርጎ እንደሚወሰድ በመግለጽ "ቅዱስ ሲኖዶስ በወሰነው መሠረት በኦሮምኛ ቋንቋ የሚሰጠው አገልግሎት እጅግ በተጠናከረ መልኩ ለማካሄድ ሁሉም የቤተ ክርስቲያን ልጆች አንድ ሆነው እንዲነሱ አደራ እንላለን" ተብሏል።
news-46219166
https://www.bbc.com/amharic/news-46219166
የደህንነት ተቋሙ ምክትል የነበሩት አቶ ያሬድ ዘሪሁን ፍርድ ቤት ቀረቡ
የቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ምክትል ኃላፊ እና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል አቶ ያሬድ ዘሪሁን ፍርድ ቤት ቀረቡ።
አቶ ያሬድ ዘሪሁን አቶ ያሬድ ዘሪሁን ትናንት ሌሊት 5 ሰዓት ላይ በዱከም ከተማ ኮኬት ተብሎ በሚጠራው ሆቴል ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተዘግቦ ነበር። ተጠርጣሪው አቶ ያሬድ በዛሬ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት ቀርበዋል። ሰሞኑን በሙስናና በሰብዓዊ መብት ጥሰት የተጠረጠሩ ከ60 የሚበልጡ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎት ምክትል ሃላፊ የነበሩት አቶ ያሬድ ዘሪሁን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጠቅላይ አቃቤ ህግ ብርሃኑ ፀጋዬ በትዊተር ገፃቸው ላይ አረጋግጠዋል። ኢቢሲ እንደዘገበው አቶ ያሬድ ዘሪሁን በቁጥጥር ስር የዋሉት ትናንት ህዳር 5 ከምሽቱ 5 ሰዓት ላይ ወደ ኬንያ ለመሸሽ ሲሞክሩ በፌደራል ፖሊስና በኦሮሚያ ፖሊስ ክትትል ዱከም ከተማ ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡ በወቅቱም 22ሺህ ብር ፣ ሁለት መታወቂያ እና መንጃ ፈቃድ ይዘው መገኘታቸውን ዘገባው ጨምሮ ገልጿል። አቶ ያሬድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ተሾመው የነበረ ቢሆንም በአጭር ጊዜ ማለትም ከአንድ ወር በኋላ በጤና እክል ምክንያት በአቶ ዘይኑ ጀማል መተካታቸው የሚታወስ ነው። አቶ ያሬድ ወደ ፌደራል ፖሊስ ከመሄዳቸው በፊት ለረጅም ጊዜ በደህንነት ተቋሙ በምክትል ሃላፊነት ያገለገሉ ሲሆን የቀድሞ የተቋሙ ዋና ሃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋም ቀኝ እጅ እንደነበሩ ይነገራል። • ሜጀር ጄኔራል ክንፈ፡ ‘‘ደሞዜ አነስተኛ ስለሆነ ፍርድ ቤቱ ጠበቃ እንዲያቆምልኝ እጠይቃለሁ’’ ተጠርጣሪውን አቶ ያሬድ ለማስመለጥ ሞክረዋል የተባሉት የነፍስ አባታቸውና ሾፌራቸው ትናንት በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት ቀርበው ነበር። የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ማክሰኞ ሕዳር 3 ቀን 2011 ዓ. ከስልሳ በላይ በሚሆኑ ተጠርጣሪዎች ላይ ከሰብዓዊ መብት ጥሰትና ከሙስና ጋር በተያያዘ የተሰሩ ወንጀሎችን በተመለከተ ያደረገውን ምርመራ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
news-55156385
https://www.bbc.com/amharic/news-55156385
ቻይና ሰንደቅ ዓላማዋን ጨረቃ ላይ ተከለች
ቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ ሰንደቅ ዓላማዋን ጨረቃ ላይ ተከለች። ይህ የሆነው ተቀናቃኟ አሜሪካ ሰንደቅ አላማዋን ጨረቃ ላይ ካስቀመጠች ከ50 ዓመታት በኋላ መሆኑ ነው።
የቻይና ሰንደቅ ዓላማ በጨረቃ ላይ ከቻይና ብሔራዊ የህዋ አስተዳደር ተቋም ይፋ የተደረጉት ምስሎች ባለአምስት ኮከቡ ቀዩ የቻይና ሰንደቅ ዓላማ ነፋስ በሌለበት የጨረቃ ገጽ ላይ ተተክሎ ያሳያሉ። ምስሎቹ የተነሱት ቻንጌ-5 የተባለው የህዋ አሳሽ መንኮራኩር ሐሙስ ዕለት ከጨረቃ ላይ የአለት ናሙናዎችን ሰብስቦ ከመመለሱ በፊት እንደሆነ ተነግሯል። በቻይና መንግሥት የሚዘጋጀው 'ግሎባል ታይምስ' ጋዜጣ እንዳለው፤ የቻይና ሰንደቅ ዓላማ በጨረቃ ላይ መተከሉ የአሜሪካው አፖሎ 11 ጉዞ ወቅት የተፈጠረው አይነት "ደስታንና መነቃቃትን" ፈጥሯል። በጨረቃ ገጽ ላይ የተተከለው የቻይና ሰንደቅ ዓላማ 2 ሜትር ስፋትና 90 ሴንቲ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን ክብደቱም አንድ ኪሎ ያህል እንደሆነ ተነግሯል። "በምድር ላይ የምንጠቀመው አይነት ማንኛውም የሰንደቅ ዓላማ ጨርቅ በጨረቃ ላይ ያለውን ሁኔታ መቋቋም አይችሉም" ያሉት የጨረቃው ጉዞ ፕሮጀክት መሪ ሊ ዮንፌንግ ለግሎባል ታይምስ ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ሰንደቅ ዓላማው የተለያዩ የአየር ሁኔታዎችን እንዲቋቋም ተደርጎ ነው የተሰራው። የቻይና ሰንደቅ ዓላማ በጨረቃ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው ቀደም ሲል ወደ ጨረቃ በተጓዙት ቻንጌ-3 እና ቻንጌ-4 የተባሉት የአሰሳ መንኮራኩሮች ላይ በተሳሉት ባንዲራዎች አማካይነት ሲሆን፤ ከጨርቅ ተሰርቶ የጨረቃ ገጽ በሰንደቅ ላይ የተተከለው ግን የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። የቻይናን ሰንደቅ ዓላማ በመትከል የመጀመሪያው የሆነው ቻንጌ-5 የተባለው የህዋ ተልዕኮ ባለፉት ሰባት ዓመታት ቻይናን በተሳካ ሁኔታ ጨረቃ ላይ እንድታርፍ ካደረጉት ሦስተኛው ነው። ከዚህ በፊት በተደረጉት የቻይና ሁለት የጨረቃ ጉዞዎች ወቅት መንኮራኩሮቹ ላይ በቀለም ከተሳለው የቻይና ባንዲራ ውጪ በጨረቃ ገጽ ላይ የአገሪቱ ሰንደቅ አልተተከለም ነበር። አሜሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በጨረቃ ገጽ ላይ ሰንደቅ ዓላማዋን የተከለችው ከ50 ዓመታት በፊት እአአ በ1969 አፖሎ 11 የተባለችው መንኮራኩር ወደ ጨረቃ ባደረገችው ጉዞ ነበር። ከዚያ በኋላም እስከ 1972 (እአአ) በተደረጉ ጉዞዎች አምስት ጊዜ ሰንደቅ ዓላማዋን ጨረቃ ላይ ተክላለች። ከስምንት ዓመት በፊት በናሳ ሳተላይቶች የተነሱ ፎቶዎች እንዳሳዩት በጨረቃ ላይ ተተክለው ለዓመታት የቆዩት አምስቱም የአሜሪካ ሰንደቅ ዓላማዎች በቦታቸው ላይ የሚታዩ ቢሆንም በፀሐይ ብርሃን ምክንያት ደብዝዘው ወደ ነጭነት መቀየራቸውን ባለሙያዎች ለመገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል። የመጀመሪያውን የአሜሪካ ሰንደቅ ዓላማ ጨረቃ ላይ የተከለው ጠፈረተኛ በዝ አልድሪን ሲሆን፤ ከመንኮራኩሯ ግርጌ ተክሎት ነበረ። ምናልባትም መንኮራኩሯ ወደ ምድር ለመመለስ ስትነሳ በሚፈጠረው ከባድ ግፊት ከተተከለበት ቦታ ተነቅሎ ሳይወድቅ አይቀርም ብሎ ነበር። ጠፈርተኛው በዝ አልድሪን በጨረቃ ላይ ከተከለው የአሜሪካ ሰንደቅ ዓላማ ጎን (1969 እአአ)
news-52760643
https://www.bbc.com/amharic/news-52760643
የቀድሞ ነፃ ትግል ተፋላሚና ተዋናይ ሻድ ጋስፓርድ ልጁን ከመስጠም አድኖ ህይወቱ አለፈ
በኢንተርቴይንመንቱ ዘርፍ ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠው የነፃ ትግል ፍልሚያ 'ወርልድ ረስሊንግ ኢንተርቴይንመት የቀድሞ ተፋላሚና ኮከብ የነበረው ሻድ ጋስፓርድ አስከሬን በሎስ አንጀለስ በሚገኘው ቬኒስ የባህር ዳርቻ ተገኝቷል።
የ39 አመቱ ሼድ ጋስፓርድ ከአስር አመት ልጁ ጋር ከአራት ቀናት በፊት እየዋኘ በነበረበት ወቅት ባልተጠበቀ ማእበል መመታቱን ተከትሎ ለህይወት አዳኞቹ ለልጁ ቅድሚያ ሰጥተው እንዲያድኑት መናገሩን ተከትሎ ልጁ መትረፍ ችሏል። የህይወት አዳኞቹ ልጁን ቢያድኑም ሼድ ግን በመስጠሙ በተጨማሪም ለቀናት ያህልም አስከሬኑ ሊገኝ አልቻለም ነበር። "ሻድ በውቅያኖሱ ሰጠመ ነገር ግን ልጁን መጀመሪያ እንዲያድኑት ለህይወት አዳኞቹ ትእዛዝ ሰጥቶ ነው። ይህ ነው የአባት ፍቅር" በማለት ታዋቂው ተዋናይ ድዋይን ጆንሰን ወይም ዘሮክ ፅፏል። አክሎም ሻድ "ታላቅ ሰው ነበር። ለባለቤቱ፣ ለልጁ እንዲሁም ለቤተሰቡ ያለኝን ጥልቅ ሐዘን መግለፅ እፈልጋለሁ። ያፅናቸው። ሞቱ ያማል" ብሏል። የተዋናዩ ባለቤት ሲሊያናም የባለቤቷ አስከሬን ከመገኘቱ በፊት ልጇን ያዳኑትን አካላት አመስግናም ባሏም ፍለጋ ላይ ተስፋ እንዳላት ገልፃ ነበር። "ሻድ ታጋይ፣ ብርቱና ድንቅ ነፍስ ያለው ሰው ነው። በሰላም እንደሚገኝም ተስፋችን ነው፤ ፀሎትም እያደረግን ነው" ብላለች። ሆኖም በትናንትናው ዕለት በቬኒስ ባህር ዳርቻው ላይ ህይወት አዳኞች አስከሬን ማግኘታቸውን ሪፖርት መደረጉን ተከትሎ የሻድ መሆኑም ተረጋግጧል። "በአለም ላይ ላሉ የሻድ ጋስፓርድ አድናቂዎች ጋር በመሆን ሻድ የሚገርም ተሰጥኦ ያለው እንዲሁም ድንቅ አባት መሆኑን ልንዘክረው እንፈልጋለን" በማለት ሌላኛው የትግል ተፋላሚ ትሪፕል ኤች ገልጿል። "የሻድ መጨረሻ መሆኑን መስማት አንፈልግም ነበር። ቢሆንም ያለውን ተቀብለን እሱን በማጣታችን እናዝናለን እናም ህይወቱን እንዲሁም ድንቅ አባትነቱን እንዘክራለን" በማለት ሌላኛው ተፋላሚ ታይረስ ፅፏል ። አክሎም "የአባትነት ትርጉሙ አንተ ነህ። ህይወትን ልጅህን ለማዳን መስዋዕት የሆንከው" ብሏል። ከነፃ የትግል ተፋላሚነቱ ከአስር አመት በፊት ከተሰናበተ በኋላ በተለያዩ ፊልሞች ላይ ተውኗል። ከነዚህም መካከል በጎርጎሳውያኑ 2015 ከኬቪን ሃርትና ዊል ፌረል ጋር የተወነበት ጌት ሃርድ ይጠቀሳል። ዝነኛው የነፃ ትግል ተፋላሚው ዴቭ ባውቲሳ ስለ ሻድ በሚናገርበት ወቅት እያለቀሰም ነበር "ከህይወት በላይ ታላቅ ነበር" ብሏል። ዴቭ ሻድን ያየው ለመጨረሻ ጊዜ በኤምቲቪ የሙዚቃ ሽልማት ላይ ሲሆን "የተለያየ ፈልሞች ላይ በመተወን ስሙን እየተከለ ነበር። አሁን የለም፣ ሄዷል። ህልሞቹንም ማሳካት አይችልም" ካለ በኋላ "ሁላችንም ቢሆን ከህይወቱ ጉዞ እንዲሁም ለልጁ ከከፈለው መስዋዕትነት ልንማር ይገባልም"ብሏል
news-50815218
https://www.bbc.com/amharic/news-50815218
ኦባማ፡ ሴቶች ከወንዶች የተሻሉ ናቸው
ሁሉንም የዓለም ሃገራት የሚመሩት ሴቶች ቢሆኑ ኖሮ የተሻለ የህይወት ዘይቤ ይኖረን ነበረ ሲሉ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ተናገሩ።
በሲንጋፖር በተካሄደ መድረክ ላይ ሴቶች ፍጹም ባይሆኑም "ያለምንም ጥርጥር ከወንዶች የተሻሉ ናቸው" ብለዋል። ኦባማ ዓለማችን ከሚያጋጥሟት የአብዛኞቹ ችግሮች መነሾ ያረጁ ወንዶች በተለይ ስልጣን ላይ ያሉት ናቸው ሲሉ ተደምጠዋል። ኦባማ በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ዓለም በሴት መሪዎች ብትመራ ምን ልትመስል እንደምትችል ያልሙ እንደነበረ ተናግረዋል። "ሴቶች፣ አሁን እንድትረዱት የምፈልገው ፍጹም አይደላችሁም ግን ያለምንም ክርክር ከእኛ ትሻላላችሁ"ብለዋል። "በጣም በእርግጠኝነት የምናገረው ሁሉም ሃገር ለሁለት ዓመታት በሴቶች ቢመራ፤ የተሻለ የኑሮ ዘይቤ እና ደረጃ ይኖረናል። በሁሉም ዘርፍ ለውጥ እንመለከታለን" ብለዋል። ወደፊት ወደ ፖለቲካ መድረኩ የመመለስ ዕቅድ ካላቸው የተጠየቁት የቀድሞ ፕሬዝደንት፤ ይልቁንም ለሌሎች የፖለቲካ መሪዎች ቦታ መልቀቅ እንደሚያሳምናቸው አስረድተዋል። "ዓለምን በትኩረት ከተመለከትናት የችግሮቿ ምንጮች ብዙ ጊዜ ያረጁ ስልጣን ያለመልቀቅ አባዜ ያላቸው እምቢተኛ ወንዶች ናቸው" ብለዋል። "የፖለቲካ መሪዎች ማወቅ ያለባቸው እና ሁሌም እራሳቸውን ማስታወስ የሚገባቸው፤ እዛ ቦታ ላይ ተሹመው የተቀመጡት ሥራ ለማከናወን ነው። የህይወት ዘመናቸውን ለመጨረስ አይደለም እዛ የተቀመጡት።" ኦባማ አሜሪካን ለሁለት የስልጣን ዘመናት ከእአአ 2009 እስከ 2017 መምራታቸው ይታወሳል። ከዋይት ሃውስ ከወጡ በኋላ ከባለቤታቸው ሚሼል ኦባማ ጋር ባቋቋሙት ፋውንዴሽን በመላው ዓለም የሚገኙ ወጣት መሪዎችን እየደገፉ ይገኛሉ።
53274906
https://www.bbc.com/amharic/53274906
"አገሪቷ ስለተረጋጋች ኢንተርኔቱ በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚከፈት ተስፋ አደርጋለሁ"-ቢልለኔ ስዩም
በአገሪቱ ከተቋረጠ ቀናት የተቆጠሩት የኢንትርኔት አገልግሎት በቀጣይ ሳምንት ሊመለስ እንደሚችል በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት የሆኑት ቢልለኔ ስዩም ለቢቢሲ ኒውስዴይ ተናገሩ።
ቢልለኔ እንዳሉት የኢንተርኔት አገልግሎት የብሔር ጥላቻን ለማስፋፋት ጥቅም ላይ በመዋሉ መንግሥት አገሪቱንና ሕዝቡን የመጠበቅ ኃላፊነት ስላለበት ለማቋረጥ መገደዱን ተናግረዋል። ኢንተርኔት መቼ ይለቀቃል ተብለው ሲጠየቁ ነገሮች ወደ ቀደመው ሁኔታ እየተመለሱ መሆኑን ገልጸው በሚቀጥለው ሳምንት ውስጥ ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን ተናግረዋል። ቃል አቀባይዋ ለኒውስዴይ እንደተናገሩት በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባም ሆነ በኦሮሚያ ውስጥ ሁኔታዎች ወደ ቀደሞው መረጋጋታቸው መመለሳቸውን ገልጸዋል። ቢልለኔ ስዩም የሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በተቀሰቀሰ ግጭት 80 ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋው፤ አንዳንድ ሰዎች የቀብር ሥነ ሥርዓቱን በማስተጓጎል ችግር ለመፍጠር ቢሞክሩም ፖሊስ ግን በሰዎች ላይ አልተኮሰም ብለዋል። ጨምረውም ካለመረጋጋት ታሪክ ውስጥ እየወጣች ያለችውን አገር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ዲሞክራሲ ለመውሰድ ቁርጠኛ መሆናቸውን በመግለጽ ከጥቂት ዓመታት በፊት የማይቻል የነበረው በአሁኑ ሰዓት በርካታ ወገኖች ድምጻቸውን ማሰማት ችለዋል ሲሉም ተናግረዋል። ከሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው የተያዙ ሰሰዎች መኖራቸውን የተናገሩት ቃል አቀባይዋ፤ ነገር ግን ጉዳዩ በምርመራ ላይ ያለ በመሆኑ አስተያየት መስጠት እንደማይችሉ አስታውቀዋል። በተያያዘ ዜና የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በአዲስ አበባ ቢሯቸውን ከፍተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሦስት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ላይ ምርመራ እያደረገ መሆኑን አስታወቋል። እነዚህም የቴሌቪዥን ጣቢያዎች አስራት፣ ድምጺ ወያኔ እንዲሁም ኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ (ኦኤምኤን) ሲሆኑ ኦኤምኤን የአዲስ አበባ ቢሮው መዘጋቱ ታውቋል። የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን እንዳለው ለድምጺ ወያኔ እና ለትግራይ ቲቪ ጠንከር ያለ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ መጻፉን ገልጿል። ቢቢሲ ስማቸው ከተጠቀሱት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ከእራሳቸው ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እየሞከረ ቢሆንም እስካሁን አልተሳካም። ምላሻቸውን ለማግኘት ጥረታችን ይቀጥላል። የድምጺ ወያኔ ዋና ቢሮ መቀሌ የሚገኝ ሲሆን አስራትና ኦኤምኤን የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ደግሞ ዋና ስቱዲዮዋቸው በአሜሪካ መሆኑ ይታወቃል። በትናንትናው ዕለት ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ በሰጡት መግለጫ የከተማ አስተዳደሩ ከጥምር የፀጥታ ኃይል ጋር በመሆን የከተማዋን ሰላምና ሥርዓት ማስከበር መጀመሩንም ተናግረው ነበር። "ማናችንም ብንሆን ከአገር በታች ነን፣ ከሕግ በታች ነን" በማለት አገርንና ትውልድን ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው ጠቅሰው፤ አገር የማስተዳደር ሂደትን ለማደናቀፍ የሚሞክር የትኛውም አካልን "ትዕግስት ልክ አለው" በማለት "ከዚህ በኋላ በየትኛውም ሚዲያ፤ በየትኛውም ጽሁፍ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጭ፤ ግለሰብን ማዕከል ያደረገ፤ ሕዝብን ማዕከል ያደረገ የጥላቻ፤ የፕሮፖጋንዳ ሥራ አንታገስም" ማለታቸው ይታወሳል። ሲፒጄ በበኩሉ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ መዘጋቱ ከተሰማ በኋላ ባወጣው መግለጫ "የመንግሥት ባለስልጣናት በአስቸኳይ ኢንተርኔቱን እንዲመልሱት" ጠይቆ ነበር።
news-48400971
https://www.bbc.com/amharic/news-48400971
በቤኒሻንጉል ክልል ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር ዋሉ
በቅርቡ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተፈጥሮ ለበርካታ ሰዎች ሕይወት መጥፋትና መፈናቀል ምክንያት በነበረው የፀጥታ ችግር የተጠረጠሩ የአካባቢ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ።
የአማራ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት እንደዘገበው በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል የመተከል ዞን የፀጥታ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ፋንቻ አምሳያ እና የግልገል በለስ ከተማ ከንቲባ አቶ ጊሳ ዚፋህ እንደሚገኙበት ተጠቅሷል። •የተጠበቀውን ያህል የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች አልተመለሱም •"ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ ተስፋና ስጋት አለ" ኦባንግ ሜቶ የተጠቀሱት ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር የዋሉት በአካባቢው በተሰማራው የሀገር መከላከያ ሠራዊትና በፌዴራል ፖሊስ አባላት እንደሆነም ተጠቅሷል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፀጥታ ምክር ቤት ትናንት ባወጣው መግለጫ "የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥና በብጥብጡ ውስጥ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የተሳተፉ አካላትን ለሕግ ለማቅረብ" እንደሚሰራና ሕዝቡ ድጋፍ እንዲያደርግለት ጥሪ አድርጎ ነበር። ቀደም ሲልም ክልሉ መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ተከስቶ ከነበረው ግጭት ጋር ተያይዞ በወንጀል የተጠረጠሩ 33 ግለሰቦችን በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውና ከእነዚህም መካከል አንዱ የክልሉ ፖሊስ አባል መሆኑ ተገልጾ ነበር። ግጭቱ በተወሰኑ የክልሉ አካባቢዎች ተከስቶ ሞትና መፈናቀልን ካስከተለ በኋላ የመከላከያ ሰራዊትን ጨምሮ የፌደራል ፖሊስ ተሰማርቷል።
news-54970896
https://www.bbc.com/amharic/news-54970896
ትግራይ ፡ በቀጣይ ቀናት የመጨረሻው ሕግን የማስከበር ተግባር ይከናወናል፡ ጠ/ሚ ዐብይ
በቀጣይ ቀናት ውስጥ የመጨረሻው ሕግን የማስከበር ወሳኝ እርምጃ በትግራይ ውስጥ ባሉ ኃይሎች ላይ እንደሚወሰድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በትግራይ ክልል ተሰልፈው ያሉ የልዩ ኃይልና ሚሊሻ አባላት ለአገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት በሠላም እጃቸውን እንዲሰጡ በፌደራል መንግሥቱ የተቀመጠው የሦስት ቀናት ቀነገደብ መጠናቀቁን ተከትሎ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ዛሬ ጠዋት በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቸው ላይ በአማርኛ እና በትግርኛ ባሰፈሩት መልዕክት የትግራይ ልዩ ኃይልና የሚሊሺያ በሠላም እጁን በመስጠት እራሱንና ሕዝቡን እንዲያድን የተሰጠው ቀነገደብ ማብቃቱን አመልክተዋል። ከባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ለሦስት ቀናት ለትግራይ ክልል ኃይሎች ተቀመጠው ቀነ ገደብ መጠናቀቁን ተከትሎም "በቀጣይ ቀናት የመጨረሻው ሕግ የማስከበር ወሳኝ ተግባር ይከናወናል" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቀናት በፊት የትግራይ ልዩ ኃይልና በሚሊሻ "የስግብግቡ ጁንታ እኩይ ዓላማ ማስፈጸሚያ ከመሆን ይልቅ" እጁን በመስጠት በእራሱ ላይና በሕዝቡ ላይ የሚደርስን ጉዳት እንዲያስቀር ጥሪ አቅርበው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጨምረውም በተሰጠውን ቀነ ገደብ በመጠቀም እጃቸውን ለመከላከያ ሠራዊት የሰጡ "የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሺያ አባላት፣ ለወሰዱት ኃላፊነት የተሞላው ሕዝባቸውን የማዳን ውሳኔ" ምስጋናቸውን አቅርበዋል። አስካሁን ምን ያህል የልዩ ኃይሉና የሚሊሻ አባላት ለመከላከያ ሠራዊት እጃቸውን እንደሰጡ የተገለጸ ነገር ባይኖርም የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን እጃቸውን የሰጡ ያሏቸውን የትግራይ ልዩ ኃይል አባላት ባለፉት ቀናት ሲያቀርቡ ታይተዋል። ትግራይ ውስጥ በሚገኘው የሠሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መፈጸሙ ከተገለጸ በኋላ የተቀሰቀሰው ወታደራዊ ግጭት ሁለት ሳምንት ሊሆነው የተቃረበ ሲሆን ትክክለኛ አሃዝ ማግኘት በዚህ ሂደት የሞቱና ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች እንዳሉ እየተነገረ ነው። በግጭቱ ሳቢያም በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን እየሸሹ መሆናቸውን የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች እያመለከቱ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እነዚህ ዜጎች ወደ አገራቸው ተመልሰው እንዲቋቋሙ ለመርዳት መንግሥታቸው አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ትላንት ገልጸዋል። በፌደራል መንግሥቱና የትግራይን ክልል በሚያስተዳድረው ህወሓት መካከል የተከሰተው አለመግባባት ተካሮ ወደ ግጭት ካመራ በኋላ መንግሥት እየወሰደ ያለው እርምጃ ሕግን የማስከበር በመሆኑ የትግራይ ኃይሎችና አመራሮቹ እጃቸውን እንዲሰጡ ማሳሰቡ ይታወሳል።
news-53544129
https://www.bbc.com/amharic/news-53544129
የአቶ ልደቱ ጤና፣ የአቶ በቀለ የረሃብ አድማ እንዲሁም የአቶ ደጀኔ በኮሮና መያዝ
ከሳምንታት በፊት የተከሰተውን አለመረጋጋት ተከትሎ በቁጥጥር ስር ከዋሉት ፖለቲከኞች መካከል የተወሰኑት ዛሬ ችሎት ፊት ቀርበዋል።
አቶ ልደቱ አያሌው ፣ አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ደጀኔ ጣፋ በዚህም መሰረት ከኢዴፓ አቶ ልደቱ አያሌው ለመጀመሪያ ጊዜ በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኝ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ የጤናቸው ጉዳይ ተነስቶ ነበር። የኦፌኮው አቶ በቀለ ገርባ ደግሞ ዛሬ የችሎት ቀጠሮ የነበራቸው ሲሆን ባለቤታቸው ለቢቢሲ እንደተናገሩት አቶ በቀለ ከቅዳሜ ጀምሮ ምግብ አልበላም ማለታቸውንና የባንክ አካውንታቸው መታገዱን ገልጸዋል። • “ከቀን ሥራ ጀምሬ ለ30 ዓመታት ያፈራሁት ንብረት ነው የወደመብኝ” የባቱ ነዋሪ በተመሳሳይ ከኦፌኮ አቶ ደጀኔ ጣፋና አቶ ኮርሳ ደቻሳ ዛሬ ችሎት መቅረብ የነበረባቸው ቢሆንም የኮሮናቫይረስ ስለተገኘባቸው ህክምና ላይ በመሆናቸው በጠበቃቸው መወከላቸው ቢቢሲ ከጠበቃቸው ተረድቷል። የአቶ ልደቱ ጤናና ተጨማሪ ቀጠሮ ባለፈው አርብ በፌደራል ፖሊስ አዲስ አበባ ውስጥ ተይዘው ወደ ቢሾፍቱ የተወሰዱት አቶ ልደቱ አያሌው ከሦስት ቀናት እስር በኋላ ዛሬ በቢሾፍቱ ከተማ ውስጥ በሚገኝ ፍርድ ቤት መቅረባቸውን የፓርቲያቸው ሊቀመንበር አቶ አዳነ ታደሰ ለቢቢሲ ገለጹ። የአቶ ልደቱ ጠበቃ ለፍርድ ቤቱ ፖሊስ ጥርጣሬውን በአግባቡ የሚያሳይ በቂ ማስረጃ አለማቅረቡን በመጥቀስ ደንበኛቸው የአስምና የልብ ህመም ያለባቸው በመሆኑ ጤንነታቸው ከግምት ገብቶ በዋስ ተለቅቀው ጉዳያቸውን ከእስር ቤት ውጪ ሆነው ጉዳያቸው ቋሚ አድራሻቸው ባለበት አዲስ አበባ ውስጥ እንዲከታተሉ ጠይቀዋል። • ከሃጫሉ ሁንዴሳ መገደል በኋላ በአርሲ ዞን የተከሰተው ምንድን ነው? • በሁከቱ ከ1ሺህ በላይ መኖሪያና ንግድ ቤቶች፣ ከ240 በላይ ተሽከርካሪዎች ወድመዋል ነገር ግን የአቶ ልደቱን ጉዳይ የሚመለከተው ፍርድ ቤት ለታሳሪው ጤና አስፈላጊ መሻሻል እንዲደረግ በማዘዝ፣ የተጠረጠሩበት ድርጊት የተፈጸመው ቢሾፍቱ መሆኑንና ችሎቱም ጉዳዩን መመልከት ስልጣን እንዳለው ጠቅሶ አዲስ አበባ ይታይ የሚለውን ጥያቄ ውድቅ እንዳደረገው አቶ አዳነ ለቢቢሲ ገልጸዋል። በተጨማሪም ችሎቱ ፖሊስ ምርመራውን ለማከናወን የጠየቀውን ተጨማሪ የ14 ቀናት ጊዜ ተቀብሎ የአቶ ልደቱን ጉዳይ መልሶ ለመመልከት ለነሐሴ 4/2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ እንደተሰጠ የኢዴፓ ሊቀመንበር አቶ አዳነ ተናግረዋል። የአቶ በቀለ የረሃብ አድማና የባንክ አካውነት እገዳ በእስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አመራር አባል አቶ በቀለ ገርባ በረሃብ አድማ ላይ መሆናቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ ሃና ረጋሳ ለቢቢሲ ገለጹ። ለዚህም ምክንያቱ በሚጠይቋቸው ሰዎች ላይ የተጣለው ገደብ እንደሆነ ወ/ሮ ሃና ተናግረው አቶ በቀለን መጠየቅ የሚችሉት ሦስት ሰዎች ብቻ ሲሆኑ፣ እነሱም ባለቤታቸውና ሁለት ልጆቻቸው ብቻ እንዲሆን በመደረጉ "ከልጆቼ መርጬ እንዲጠይቁኝ አላደርግም፤ ልጆቼ እኔን ማግኘት አለባቸው፤ እኔም ልጆቼን ማግኘት አለብኝ" ማለታቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። • በትግራይ በሚደረገው ምርጫ እነማን ይሳተፋሉ? በእነዚህ ምክንያቶችም ከቅዳሜ ጀምሮ ምግብ እንዳልገባላቸው ጠቅሰው "ምግብ እንዲገባልኝ ስለፈቀዱ፤ ለእኔ ትልቅ ነገር አይደለም። አንድ እስረኛ የሚገባው መብት ካልተከበረልኝ ፤ ምግብም አታምጡልኝ" በማለት ምግብ እንዳይወስዱ እንደከለከሏቸው አስረድተዋል። ዛሬ ጠዋትም ቁርስ ይዘውላቸው እንደሄዱና "ፍርድቤት ሄጄ መናገር ያለብኝ ተናግሬ፣ መጠየቅ ያለብኝን ጠይቄ፣ መልስ ሳገኝ እበላለሁ" በማለት ምግቡን ተቀብለው እንዳስቀመጡት ገልፀዋል። ወ/ሮ ሃና አክለውም የአቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ የመላው ቤተሰቡ የባንክ አካውንት መታገዱንም ተናግረዋል። አካውንቱ ለምን እንደተዘጋ እንደማያውቁ የሚናገሩት ወ/ሮ ሃና፤ "በቀለም የመንግሥት ሠራተኛ ነው፤ ነጋዴም አይደለም። በአካውንታችን ላይ የተለየ ገንዘብ የለም። እኔም ቢሆን ሠራተኛ አይደለሁም" በማለት ለእለት መተዳዳሪያ ያስቀመጧትን ገንዘብ ሊያወጡ በሄዱበት የእርሳቸውና የባለቤታቸው አካውንት መታገዱ እንደተነገራቸው ገልጸዋል። ሰኞ ፍርድ ቤት ቀርበው የነበሩት አቶ በቀለ ገርባ ላይ ፖሊስ ተጨማሪ 14 ቀናት ምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን ባለመቀበል ስምንት ተጨማሪ ቀናት ሰጥቷል። የአቶ ደጀኔና የአቶ ኮርሳ በኮሮናቫይረስ መያዝ በቅርቡ ተከስቶ ከነበረው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው በእስር ላይ የቆዩት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አመራር አባል አቶ ደጀኔ ጣፋና አቶ ኮርሳ ደቻሳ የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸው ህክምና ላይ እንደሆኑ ጠበቃቸው አቶ ደጀኔ ፈቃዱ ለቢቢሲ ተናገሩ። በዚህም ሳቢያ ታሳሪዎቹ በቀጠሯቸው መሰረት ዛሬ የፍርድ ቤት መገኘት ሳይችሉ መቅረታቸውን ጠበቃው ገልጸዋል። • በሻሸመኔ ቤት ንብረት የወደመባቸው በምን ሁኔታ ላይ ናቸው? በወረርሽኙ ተይዘዋል የተባሉት ተጠርጣሪዎችን ጉዳይ የተመለከተው ችሎት ፖሊስ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ተጨማሪ ስምንት የምርመራ ቀናትን እንደፈቀደ አቶ ደጀኔ ለቢቢሲ ገልጸዋል።
news-49520569
https://www.bbc.com/amharic/news-49520569
በወፍራም ሴቶች የተሳለቀችው የቴሌቪዥን አቅራቢ ከሥራዋ ታገደች
ግብጻዊቷ የቴሌቪዥን አቅራቢ ሬሃም ሳኢድ ያለ ልክ ስለወፈሩ ሰዎች በሰጠችው አስተያየቷ ከሥራዋ ታግዳለች።
ሬሃም ሳኢድ አስተያየቱን የተናገረችው 'ሳባያ' በተሰኘው ቴሌቪዥን ፕሮግራሟ ላይ ነበር የሃገሪቱ ሚዲያ ተቆጣጣሪ ሬሃም በፕሮግራሟ ላይ በግብፅ ያሉ ሴቶችን የሚያስቆጣ ቃላትና ተጠቅማለች ብሏል። ጋዜጠኛዋ በምታቀርበው የቴሌቪዥን ፕሮግራሟ ላይ "ያለ ልክ የወፈሩ ሰዎች ለቤተሰባቸውም ሆነ ለአገር ሸክም ናቸው" የሚል አገላለፅ ተጠቅማለች። • ስመ ጥሩ ጋዜጠኛ ሃሰተኛ ዜና በመፈብረክ ከስራው ተባረረ • ኬንያዊው ጋዜጠኛ የ2018 ኮምላ ዱሞር ሽልማትን አሸነፈ ጋዜጠኛዋ በግሏ የኢንስታግራም ገጽ ላይ ጡረታ እየወጣች እንደሆነ በማስታወቅ የተባለውን አስተያየት አላልኩም ስትል አስተባብላለች። ሬሃም አስተያየቱን የተናገረችው ባለፈው ዓመት የአገሪቷ ፕሬዚደንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ የአገሪቷ ዜጎች ክብደታችሁን ቀንሱ ሲሉ ካስጠነቀቁ በኋላ ነበር። በወቅቱ ፕሬዚዳንቱ ግብጻዊያን ራሳቸውን መንከባከብ እንዳለባቸው ጥሪ አቅርበዋል። በአል ሃያህ የቴሌቪዥን ጣቢያ በሚተላለፈው የሬሃም 'ሳባያ' በተሰኘው የቴሌቪዥን የውይይት ፕሮግራም ላይ "ለከፋ ውፍረት የተዳረጉ ሴቶች በሰውነታቸው ውስጥ በሚፈጠር የኬሚካል ለውጥ (ቶክሲን) ሴትነታቸውንና ደስታቸውን ያጣሉ" ስትል አስተያየቷን ሰጥታለች። ሬሃም በዚህ አላበቃችም። "ወፍራም ሴቶች ወንዶችን አይማርኩም፤ በመሆኑም ብዙ ጊዜ ወፍራም የሆነችውን ሚስታቸውን ይፈታሉ፤ አሊያም ከእጮኛቸው ጋር ይለያያሉ" ብላለች። የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በጋዜጠኛዋ አስተያየት ላይ የትችት ውርጅብኝ አዝነበዋል። ሬሃም በኢንስታግራም ገጿ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ኢላማ እንደሆነች ገልፃ ጡረታ እየወጣች እንደሆነ አስፍራለች። "ታክቶኛል! ምክንያቱም ማንም ሰው ሊያንኳስሳችሁ ሲፈልግ በእንናተ ላይ የሚዲያ ዘመቻ ይከፍቱባችሁና የሌለ ወሬ ያስወሩባችኋል። ከዚያም የማታውቋቸውንና በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያሉ 200 ወይም 300 ወይም 400 ወይም 500 ሺህ ሰዎች አሉቧልታ እናንተን ይውጣችሏል" ብላለች። በዚህም ምከንያት ሰልችቶኛል አሁን ልጆቼን የምንከባከብበት ሰዓት ነው ብላለች። ሬሃም አክላም ላለፉት 12 ዓመታት ከልክ በላይ ውፍረት የተጋለጡ ሰዎችን ለመርዳት በርካታ ተግባራትን እንዳከናወነች ገልጻለች። የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢዋ መነጋገሪያ ስትሆን ይህ የመጀመሪያዋ አይደለም። በአንድ ወቅት የሶሪያ ስደተኞችን ለመጎብኘት ባቀናችበት ወቅት ስደተⶉቹን «ክብረ ቢስ ናቸው» በሚል መግለጿ መነጋገሪያ ሆና ነበር። በሌላ አጋጣሚም እንዲሁ አንድ በፈጣሪ መኖር የማታምን ሴት በፕሮግራሟ ስለ አስተሳሰቧ ለማናገር ከጋበዘቻት በኋላ ከፕሮግራሙ እንዳባረረቻት ተገልጿል።
news-42359396
https://www.bbc.com/amharic/news-42359396
ካለሁበት 14፡ "ብርዱ ሲከፋ፣ ቀኑም ሲያጥር የሀገሬ አየር በስንት ጣዕሙ እላለሁ።"
መባ ታደሰ እባላለሁ፤ በእንግሊዝ የኦክስፎርድ ከተማ ነዋሪ ነኝ። ለመጀመሪያ ጊዜ የትምህርት ዕድል ወዳገኘሁባት ለንደን ነበር የመጣሁት፤ የሁለተኛ ደረጃና የዩኒቨርሲቲ ትምህርቴንም እዛው አጠናቅቄ ለአስር ዓመታት ቆይቻለሁ።
ከዚያ በኋላ ግን ለንደን ሥራ የማግኘት ዕድሉ አስቸጋሪ ሆነ፤ እኔም ሌሎች አካባቢዎችን ማየት እፈልግ ስለነበር ከለንደን ወደ ኦክስፎርድ መጣሁ። አሁን እዚህ ከመጣሁ 4 ዓመት ሆኖኛል። ኮርፑስ ክሪስቲ በሚባል የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ጥላ ሥር በሚገኝ ኮሌጅ ውስጥ በኮንፈረንስ አስተዳዳር ክፍል ውስጥ እሠራለሁ፤ ኃላፊነቴም የዩነቨርሲቲ ኮሌጁን አገልግሎት መጠቀም የሚፈልጉ የውጭ ደንበኞችን ማገናኘትና ከተማሪዎች ጋር ያለውን ግንኙነት ማስተባበር ነው። እዚህ በመጣሁበት ወቅት የቢሮ ፖለቲካውንና አሠራሩን ለመረዳት ትንሽ ጊዜ ፈጅቶብኝ ነበር ግን በሂደት ሁሉንም ነገር ተላመድኩት። ባለሁባት ኦክስፎርድ የትምህርት አሰጣጥ ሥርዓቱ ጥራት ስላለው ሰፊ የተማረ ማህበረሰብ አላት። ከተማዋም ሀገሪቱ በከፍተኛ ትምህርት ከፍተኛ ቦታ ላይ እንድትደርስ ጉልህ ሚና ትጫወታለች። እዚህ ከመጣሁ ጀምሮ ሁልጊዜም የሚገርመኝ በነዋሪዎች መካከል ያለው ሰፊ የኑሮ ልዩነት ነው። እኔ በምሠራበት ኮሌጅ እንኳን መካከለኛ ገቢ ባላቸውና በባለፀጎቹ መካከል የሚታየው የአኗኗር ዘይቤ ከኛ በጣም የተለየ ነው ለምሳሌ አስተማሪዎች አንዳንዴ በብር ማዕድን በተሠሩ ማንኪያዎችና ሹካዎች ሲመገቡ አያለሁ ፤ ይሄ ልዩነት ሁሌም ያስገርመኛል። በዚህ ከተማ አቅም ኖሮኝ አንድ ነገር መለወጥ ብችል የሥራ ዕድሉን ለሁሉም ተወዳዳሪ አደርገው ነበር። ምክንያቱም እዚህ ብዙ ጊዜ የሥራ ዕድል የሚያገኙት ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የተመረቁ ተማሪዎች ናቸው፤ ስለዚህ የገበያ ውድድሩ ፍትሐዊ እንዲሆን ሁሉንም የሚያቅፍ የሥራ ዕድል እፈጥር ነበር። በእርግጥ ኦክስፎርድ በጣም ትንሽ ናት ግን ሁልጊዜም የአዲስ አበባዋን ፒያሳ የማስታውስበት ቦታ አለ። ምክንያቱም የከተማዋ ዋነኛ የንግድ ቦታ ትንሽ ትርምስ ይበዛዋል መንገዱ ጠቦ መኪኖች ለማለፍ ይቸገራሉ። ያንን ሳይ ሁሌም ሀገር ቤት ይመልሰኛል። ሁልጊዜም ቢሆን ከኢትዮጵያ የሚናፍቀኝ ነገር አየሩ ነው፤ አየሩ ቀለል ያለና ደስ የሚል ነው ፤ ብርዱም ሆነ ሙቀቱ የከፋ አይደለም፤ እዚህ ግን ብርዳማው ጊዜ በጣም እየረዘመ፣ በጋውንም ቀኑ እያጠር ሲሄድ የሀገሬ አየር በስንት ጣዕሙ እላለሁ። እዚህ ካለው ነገር ደግሞ በቤቴ መስኮት አሻፍሬ የማየው የኮሌጆቹና ዩኒቨርሲቲዎቹ ዕይታ በጣም ይመስጠኛል፤ ረዥም ዓመት የ400 እና የ500 ዕድሜ ያላቸውና በጣም የሚማርኩ ናቸው፤ ይህን በየጊዜው በማየቴ ዕድለኛ እንደሆንኩ አስባለሁ። ሌላው እዚህ በጣም የምወደውና ደስ ብሎኝ የምበላው የታይላንድ ምግብ 'ታይ ግሪን ከሪ' ይባላል። በስጋ፣ በዶሮም ሆነ በባሀር ውስጥ ምግቦች መሠራት የሚችል ጣፋጭ ምግብ ነው፤ ቤቴም ቢሆን ብዙ ጊዜ አብስለዋለሁ። በቅጽበት ወደ አንድ የሚያስደስተኝ ቦታ መሄድ ብችል እራሴን ድሬዳዋ ባገኘው ህልሜ ነው። ሕፃን ሆኜ ነው የሄድኩት ግን ሰዉ ተቀባይ መሆኑና የአየሩ ሞቃታማነት ይመቸኛል። ለክሪስቲን ዮሐንስ እንደነገራት የ'ካለሁበት' ቀጣይ ክፍል ለማግኘት ፦ ካለሁበት 15፡ "ራሴንና ልጆቼን የሰሜን ተራሮች ላይ ባገኝ በጣም ደስ ይለኝ ነበር" ካለሁበት 16 ፡ 'ጭራሹኑ መጥፎ ነገሮች እንዳይከሰቱ ማድረግ ብችል ደስታዬ ወደር የለውም'
news-56411449
https://www.bbc.com/amharic/news-56411449
አስትራዜኒካ የደም መርጋት ያስከትላል? የዓለም ጤና ድርጅት ክትባቱን ሊገመግም ነው
የዓለም ጤና ድርጅት ብዙ እየተወራበት ያለውን የኦክስፎርድ አስትራዜኒካን ውጤታማነትን በተለይም ከደም መርጋት ጋር ያለውን ተያያዥነት በክትባት ሊቃውንት ሊያስገመግም ነው፡፡
ክትባቱ ውጤታማ ነው ከተባለ በኋላ ብዙ አገራት ለሕዝባቸው ማደል ጀምረው ነበር፡፡ ሆኖም ደም እንዲረጋ ያደርጋል የሚል መረጃ መውጣቱን ተከትሎ ብዙ የአውሮፓ አገራት ለጊዜው የክትባት እደላው እንዲቆም ወስነዋል፡፡ አንዳንድ ክትባቱን የወሰዱ ሰዎች ደማቸው የመርጋት ምልክት በማሳየቱ ነው ስጋት የተፈጠረው፡፡ እነዚህ የክትባት ሊቃውንት ለግምገማ የሚቀመጡት ዛሬ ማክሰኞ ነው፡፡ በተመሳሳይ የአውሮጳ መድኃኒት ኤጀንሲ ኃላፊዎችም ዛሬ በጉዳዩ ላይ ለመምከር ይሰበሰባሉ ተብሏል፡፡ የክትባት ሊቃውንት ቡድን ሁኔታዎችን ከገመገመ በኋላ ኦክስፎርድ አስትራዜኒካ ክትባት ለሰዎች ቢሰጥ የከፋ ጉዳት እንደሌለው የሚያትት መግለጫ ሐሙስ ያወጣል ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡ በአውሮፓ ኅብረትና በታላቋ ብሪታኒያ በድምሩ 17 ሚሊዮን ዜጎች አስትራዜኒካ ክትባትን የወሰዱ ሲሆን ከዚህ ሁሉ ተከታቢ መሀል የደም መርጋት አጋጠማቸው የተባሉትን ሰዎች ቁጥር ከ40 አይበልጥም፡፡ አሁን ይህ ክትባት በእርግጥ የደም መርጋትን ያመጣል ወይ የሚለው በተጨባጭ የታወቀ ባይሆንም ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን እና ስፔንን ጨምሮ በርካታ አገራት ክትባቱን ለጊዜው ይቆየን ብለዋል፡፡ ቤልጂየም፣ ፖላንድ፣ ቼክ ሪፐብሊክና ዩክሬን ግን ክትባቱን ለሕዝባቸው ማደላቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት በበኩሉ ክትባቱ በእርግጥ የደም መርጋት ያስከትላል በሚለው ላይ አዲስ ምርመራ መጀመሩን ይፋ አድርጓል፡፡ ባለፈው ማክሰኞ የዓለም ጤና ድርጅት ቃል አቀባይ ክትባቱ ደም እንደሚያረጋ የተገኘ አንዳችም ተጨባጭ መረጃ የለም ብለው ነበር፡፡ በርከት ያሉ የጤና ባለሙያዎች እንደሚሉት ክትባቱን መውሰድ የጎንዮሽ ጉዳቱን በመፍራት ካለመውሰድ የተሻለ ነው፡፡ ክትባቱ ደም እንዲረጋ ያደርጋል የሚሉት አጋጣሚዎችም ከጠቅላላው ተከታቢ ቁጥር ጋር ሲነጻጸር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም ይላሉ፡፡
news-52618799
https://www.bbc.com/amharic/news-52618799
በአፍሪካ ከ63 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮናቫይረስ ቢያዙም የተጣለው ገደብ እየላላ ነው
የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል አዲስ ያወጣው አሃዝ እንደሚያመለክተው እስካሁን 63 ሺህ 325 በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች በአህጉሪቱ ውስጥ ተመዝግበዋል።
በተጨማሪም 2290 ሰዎች በወረርሽኙ ሳቢያ የሞቱ ሲሆን 21 ሺህ 821 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ማገገማቸው ተነግሯል። የወረርሽኙ መስፋፋት ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚደርስበት ጊዜ ገና እንደሆነ ባለሙያዎች እያስጠነቀቁ ቢሆንም በርካታ የአፍሪካ አገራት ለሳምንታት ጥለውት የነበረውን የእንቅስቃሴ ዕገዳ በዚህ ሳምንት ማላላት ጀምረዋል። በአፍሪካ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኮሮናቫይረስ ምርመራ በማድረግ ተጠቃሿ ደቡብ አፍሪካ ከ10 ሺህ በላይ የሚሆኑ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን አግኝታለች። የእንቅስቃሴ ገደቡ በአገራቱ ምጣኔ ሃብት ላይ ያስከተለው ጫና ጎልቶ መታየት በመጀመሩ አገራት የጣሉትን ገደብ ለማላላት እየወሰኑ ነው። በዚህም መሰረት ጂቡቲ፣ ማሊ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ጋቦን፣ ኒጀር እና ኡጋንዳ የበሽታውን መስፋፋት ለመቆጣጠር በሚል ለሳምንታት ጥለውት የነበረውን የእንቅስቃሴ እገዳ ለማላላት ያወጡትን ዕቅድ ይፋ አድርገዋል። በሌላ በኩል ደግሞ የምዕራብ አፍሪካ አገራቱ ላይቤሪያና ጋና የእንቅስቃሴ ገደቡን ለተጨማሪ ሳምንታት አራዝመውታል። በዚህ መሰረትም ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃ ዕገዳውን ለሁለት ሳምንት ሲያራዝሙት የጋናው ፕሬዝዳንት ናና አኩፎ አዶ ደግሞ ለሦስት ሳምንት አራዝመውታል። ማዳጋስካር ከአሪቲ የተዘጋጀ ነው የተባለውን መድኃኒት በስፋት እያስተዋወቀች ቢሆንም ተገቢው ሳይንሳዊ ሙከራ ስላልተደረገበት ጥያቄ እየተነሳበት ነው። ቢሆንም ታንዛኒያ፣ ጊኒ፣ ጊኒ ቢሳዎና ዲሞክራቲክ ኮንጎን የመሳሰሉ አገራት "መድኃኒቱን" አዘው ወደ አገራቸው እያስገቡ ሲሆን ማዳጋስካርም በግዛቷ ውስጥ እንዲሸጥ ፈቃድ ሰጥታለች። የዓለም ጤና ድርጅት 'የመድኃኒቱን' አስተማማኝነት በተመለከተ ምንም የተረጋገጠ ነገር ስለሌለ ሰዎች እንዳይጠቀሙ አስጠንቅቋል። የደቡብ አፍሪካው ጤና ሚኒስትር ለማዳጋስካር ባላስልጣናት እንደተናገሩት አገራቸው ከስራስር የተሰራውን መድኃኒት በሳይንሳዊ መንገድ ምርመራ ለማድረግ ፈቃደኛ መሆኗን ገልጻለች።
news-51797889
https://www.bbc.com/amharic/news-51797889
መንግሥት በፖለቲካ ፓርቲዎችና መገናኛ ብዙሃን ላይ እርምጃ እወስዳለሁ አለ
መንግሥት የሕዝብን አንድነትና አብሮነት እንዲሸረሸር በሚያደርጉ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የመገናኛ ብዙሃን ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ማስታወቁን ፋና ዘገበ።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ የሆኑት አቶ ንጉሡ ጥላሁን "በሕዝባዊ መድረኮችና በመገናኛ ብዙሃን በኩል የሚተላለፉ የጥላቻ ንግግሮች በአገር አንድነትና አብሮነት ላይ አደጋ ይደቅናሉ" ማለታቸውን ፋና ገልጿል። ኃላፊው ጨምረውም በመሰል ድርጊት በሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የመገናኛ ብዙሃን ላይ ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣንና ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር በመሆን መንግሥት ተገቢና ተመጣጣኝ ዕርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ መናገራቸውን ገልጿል። በትናንትናው ዕለት ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን በተመለከተ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ያካሄደው ዝግጅት ላይ የተደረገውን ንግግር ኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ (ኦኤምኤን) ማስተላለፉን በተመለከተም ኃላፊነቱ የሁለቱም ወገኖች መሆኑን ተናግረዋል። "ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌን የጣሰና ኢትዮጵያዊ ዕውነታን ያላገናዘበ የጥላቻ ንግግር ለዘመናት በአብሮነት ወደኖሩ ሕዝቦች መተላለፉን ተከትሎ ፓርቲውም ሆነ የመገናኛ ተቋሙ ተገቢውን ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው" ሲሉ አሳስበዋል። ትናንት አዳማ ላይ የነበረው ዝግጅት በኦኤምኤን በቀጥታ የተላለፈ ሲሆን አንዲት ተሳታፊ ያቀረበችው ሃሳብ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል፤ ቪዲዮውም ከአማርኛ ትርጉሙ ጋር በስፋት ሲዘዋወር ነበር። ጉዳዩ መነጋገሪያ ከመሆን አልፎ ውግዘትና ቁጣን በማኅበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ አስተናግዷል። ይህንንም ተከትሎ የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ዳይሬክተር አቶ ግርማ ጉተማ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ክስተቱን በተመለከተ የይቅርታ መልዕክት አስፍረዋል። አቶ ግርማ በጽሁፋቸው ኦኤምኤን ዝግጅቱን በቀጥታ እያስተላለፈ እንደነበርና ንግግሩን ማቋረጥ እንደነበረባቸው አምነው ነገር ግን እንዳልቻሉ አመልክተዋል። ነገር ግን ንግግሩ ካበቃ በኋላ ወዲያው ከማኅበራዊ ሚዲያና ከሳተላይት ላይ እንዲወርድ መደረጉን ገልጸዋል። ጨምረውም "በዚህ ከቁጥጥራችን ውጭ በሆነ ምክኒያት ኦኤምኤን ላይ ላኮረፋችሁ ተመልካቾቻን ሁሉ ይቅርታ እንጠይቃለን" ብለዋል። አቶ ንጉሡ ለፋና ጉዳዩን በተመለከተ የተፈጠረው ነገር ስህተት ብቻ ሳይሆን ጥፋት መሆኑን ተናግረዋል። አቶ ንጉሡ መንግሥት ለረጅም ጊዜ በመማማርና በመመካከር ላይ የተመሰረተ እንቅስቃሴን አማራጭ አድርጎ በትዕግስት መቆየቱንም አመልክተዋል። አሁን ግን በአገሪቱ ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ተግባራት በግልፅ እየተበራከቱ በመምጣታቸው መንግሥት እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምር ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣንና ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በዚህ ረገድ የሚስተዋሉ ክፍተቶች በፍጥነት እንዲታረሙ የማድረግ ኃላፊነት እንዳለባቸውም አቶ ንጉሡ አንስተዋል። የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣንም ከአንድነት ይልቅ ልዩነት ላይ ያተኮሩና ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ መገናኛ ብዙሃንን እንደማይታገስና በአዋጁ መሰረትም እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምር የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንደሰን አንዷለም መናገራቸውን ፋና ጨምሮ ገልጿል። በዚህም መሰረት በኦኤምኤን ላይ የተላለፈው መልዕክት ሙሉ ተንቀሳቃሽ ምስል ባለስልጣኑ እንደደረሰውና መልዕክቱ በባለሙያዎችና አመራሮች እየተገመገመ በመሆኑ በአጭር ጊዜ መረጃውን በማጥራት ውጤቱ ይፋ እንደሚደረግም ገልጸዋል።
news-55785213
https://www.bbc.com/amharic/news-55785213
ጉድጓድ ውስጥ ተቀብረው ከነበሩ ቻይናውያን የማዕድን ሰራተኞች መካከል አስራ አንዱ በሕይወት ወጡ
600 ሜትር ጉድጓድ ውስጥ ተቀብረው ከነበሩ ቻይናውያን የማዕድን ሰራተኞች መካከል አስራ አንዱ በሕይወት መውጣት ችለዋል።
የቻይና የማዕድን ሰራተኞች የቻይና ብዙሃን መገናኛዎች እንደዘገቡት 6 መቶ ሜትር ጥልቀት ካለው ጉድጓድ ውስጥ ገብተው ለሁለት ሳምንታት ከቆዩት የማዕድን ሰራተኞች መካከል አስራን አንዱንን በሕይወት ከጉድጓዱ ማውጣት ተችሏል። ባለፈው ጥር 2፣ በቻይና ሻንዶንግ ግዛት ውስጥ በሚገኘው ሁሻን የወርቅ ማዕድን ማውጫ የመውጫ ዋሻ ላይ በደረሰ ፍንዳታ ነበር የመውጫ በሩ ተዘግቶ የማዕድን ሰራተኞቹ ውስጥ እንዳሉ ታፍነው የቀሩት። 11 ሰራተኞች ወዲያውኑ ከፍንዳታው መትረፍ ቢችሉም አንደኛው ከቆይታ በኋላ ሕይወቱ አልፏል። ጉድጓዱ ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች ቴሌኮሙኒኬሽን የተሰራላቸው ሲሆን ምግብ እና መድሃኒትም በትንሽ ቀዳዳ እየተላከላቸው ነው። የፍንዳታው ምክንያት እስካሁን አልታወቀም። በሕይወት የተረፈው ሰው ብርሃን እንዳያስቸግረው በሚል ዓይኑ ተሸፍኖ ወዲያውኑ ወደ ሆስፒታል ተወስዷል ተብሏል። ይህ ሰው ምግብ እና ውሃ ከሚደርሳቸው 10 ሰዎች ካሉበት ቡድን በተለየ ሁኔታ ለብቻው የነበረ ነው። መጀመሪያው ሰው ከወጣ ከአንድ ሰዓት በኋላ ተጨማሪ ስምንት ሰዎች መውጣታቸውን የቻይና ብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል። ሰዎቹ ያሉበትን ቦታ ለማግኘት የሚደረገው ቁፋሮ ሳምንታትን ሊወስድ እንደሚችል ይጠበቃል። በሌላ በኩል ለአንደኛው ቡድን የሚላከው ምግብ እና መድሃኒት እንዳለ ሆኖ በሌላ ቦታ የሚገኙት የ11 ሰዎች እጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል ግን እስካሁን አልታወቀም። የእነዚህ ሰዎች በሕይወት መኖር የታወቀው አንድ ከእነሱ በ1 መቶ ሜትር ዝቅ ብሎ ከሚገኝ ሰው ጋር በነበራቸው ግንኙነት አማካኝነት ነው። ነገር ግን ከቆይታ በኋላ ከእዚህ ሰው ጋር የነበረው ግንኙነትም ተቋርጧል። እንዴት ወጥመድ ውስጥ ገቡ? ወደ ማዕድን መገኛው ውስጥ የሚወስደው ዋሻ ክፉኛ ተጎድቷል፤ ምክንያቱ ባልታወቀ ፍንዳታ ሳቢያም ግንኙነቶች ሙሉ በሙሉ ተቆራርጠዋል። ለአንድ ሳምንት ያክል በሕይወት ስለመኖራቸው የሚያሳይ ምንም ዓይነት ምልክት አልነበረም። የዛሬ ሳምንት እሁድ ግን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በቀጭን ቀዳዳ ውስጥ የላኩት ገመድ ሲጎተት ተሰማቸው። ከዚያም ማስታወሻ የተጻፈበት ቁራጭ ወረቀት ከ12 የማዕድን ሰራተኞች [11ዱ አንድ ቦታ አንደኛው ደግሞ ትንሽ ዝቅ ብሎ] በሕይት መኖራቸውን በመግለጽ መልዕክት ወደ ላይ ላኩ። ከዚያ በኋላ ግን 12ኛው ሰው ጋር የነበረው ግንኙነት ተቋረጠ። በሌላ በኩል ከ11ዱ መካከል ደግሞ አንደኛው ግለሰብ በፍንዳታው ወቅት ራሱ ላይ የመቁሰል አደጋ ደርሶበት ስለነበር ባለፈው ሐሙስ በዚሁ ምክንያት መሞቱ ታውቋል። በቻይና የማዕድን አደጋ ያልተለመደ አይደለም። የደኅንነት ቁጥጥሮች አተገባበር የላላ ነው። ባለፈው ታኅሥስ በከሰል ማዕድን ውስጥ በደረሰ የካርቦን ሞኖክሳይድ ልቀት ሳቢያ 23 ሰዎች ሞተዋል። በተመሳሳይ ችግር በመስከረም ወርም 16 ሰዎች ሞተዋል። በ2019 በደቡብ ምዕራብ ቻይና በደረሰ የከሰል ማዕድን ማውጫ ፍንዳታም እንዲሁ 14 ሰዎች ሞተው ነበር። የቻይና የማዕድን ሰራተኞች የማዕድን ሰራተኞቹ በምን ሁኔታ ናቸው ያሉት? አስሩ ሰዎች 600 ሜትር ጥልቀት ውስጥ ባለው የጨለማ ጉድጓድ ውስጥ ነው ያሉት። እነዚህ ሰዎች ከአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር ቀጣይነት ባለው ግንኙነት ውስጥ ይገኛሉ። መድሃኒትም ሆነ ምግብ በትንሽ ቀዳዳ ውስጥ ይላክላቸዋል። ገንፎ እና አልሚ የሆኑ ፈሳሽ ነገሮች እየተላኩላቸው ሲሆን ከጥቂት ቀናት በፊት ደግሞ ባሕላዊ ምግብ እና ወጣወጥ ነገር እንዲላክላቸው ጠይቀው ነበር። ስምንቱ ደህና መሆናቸው ሲታመን ሁለቱ ግን ከፍተኛ ጉዳት ሳይደርስባቸው እንዳልቀረ ተገምቷል። የመጀመሪያው ሰው ከወጣ ከአንድ ሰዓት በኋላ ተጨማሪ ስምንት ሰዎች በሕይወት መትረፋቸው እና መውጣታቸው ተረጋግጧል። ምናልባት በሙሉ ጤንነት ውስጥ ነበሩ ተብለው የተገመቱት ሳይሆኑ እንዳልቀሩ ይታመናል።
41819766
https://www.bbc.com/amharic/41819766
የኦሮሚያ ክልል ሟቾችን በተመለከተ በማህበራዊ ሚዲያ የቀረበው መረጃ የተሳሳተ ነው አለ
ከእሁድ ጀምሮ በኦሮምያ ክልል ነቀምት ከተማ የኢሬቻ በዓል በሚከበርበት ወቅት በተፈጠረ ሁከት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፤ ከሟቾች ማንነት ጋር ተያይዞ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨ መረጃ የተሳሰተ እንደሆነ የክልሉ መንግስት ለቢቢሲ ገልፀዋል።
የአከባቢው ፖሊስ ቆሞ እያየ በሚያሳይ ፎቶ ተደግፎ በነቀምት ከተማ ሦስት የትግራይ ተወላጆች በድንጋይ ተደብድበው መገደላቸው በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ የነበር ሲሆን የኦሮሚያ ክልል መንግሥት መረጃው ከእውነት የራቀ መሆኑ ገልፆ የማጣራት ሥራ እያከናወንኩ ነው ብሏል። የኦሮሚያ ክልል ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሓላፊ ከአከባቢው ፖሊስ ጣብያ አጣርቼ አገኘሁት ባሉት መረጃ መሰረት፤ የሟቾችን ማንነት በተመለከት ከትናንት ጀምሮ በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ የነበረው ይሄው መረጃ የተሳሰተ መሆኑን አረጋግጠዋል። አቶ አዲሱ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ በዚሁ በነቀምት ከተማ የኢሬቻ በዓል በሚከበርበት ወቅት በተነሳ ሁከት ከሞቱት ሦስት ሰዎች በተጨማሪ በሌሎች አስር ሰዎች ላይ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰ አረጋግጠዋል። የከተማዋ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ኮማንደር ጌታቸው ኢታና፤ ለግጭቱ መንስኤ ነው የተባለው ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ በግለሰቦች ቤት ተከማችቶ ተገኘ የሚለው መረጃ መሰረተ ቢስ መሆኑን ለአካባቢው ሬዲዮ ተናግረዋል። አንዳንድ ግለሰቦች ግጭቱን መነሻ በማድረግ የግለሰቦችን ሱቅ እና መጋዘኖች መዝረፋቸውንም ጨምረው ገልፀዋል። ይህንን ሁከት በመቀስቀስና በማነሳሰት የተጠረጠሩ 16 ግለሰቦች ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ በማድረግ ላይ መሆኑን አቶ አዲሱ ጨመረው ለቢቢሲ ተናግረዋል። የነቀምት ሪፈራል ሆስፒታል ኃላፊ አቶ አብርሃም ለቢቢሲ እንደገለፁት፤ ብድብደባውና በግጭቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ዘጠኝ ሰዎች ወደ ሆስፒታሉ መጥተዋል። አራቱ ውድያውኑ የህክምና እርዳታ አግኝተው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ፤ የተቀሩተ ግን አሁንም የህክምና አገልግሎት በማግኘት ላይ መሆናቸውን ጨምረው ገልፀዋል። በሁከቱ ጉዳት የደረሰባቸው የትግራይ ተወላጆች መኖራቸውን ማወቅ የተቻለ ቢሆንም፤ ስለ ሟቾቹ ማንነት በክልሉ የሚነገርው መረጃና ሌሎች የመረጃ ምንጮች እርስ በእርስ የሚጋጩ በመሆኑ፤ ቢቢሲ ከሶስተኛ አካል ማረጋገጥ አልቻለም። በተያያዘ ዜና የትግራይ ክልል መንግሥት በተለይ የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (ኦቢኤን) በቅርቡ አንድ ግለስብ "ዶላር ይዞ በህገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ ተገኝቷል" በሚል ብሄር ጠቅሶ ያቀረበው ዘገባ አደጋኛና በአስቸኳይ መታረም ያለበት ዘር ተኮር ዘገባ በሚል ጥቅምት 20/2010 ዓ.ም ላይ ደብዳቤ ፅፏል። ክልሉ በደብዳቤው ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ላቀረበው ቅሬታ የተጠቀሰው ተቋም አወንታዊ ምላሽ አለመስጠቱንም ይገልፃል። "በትግራይ ህዝብና በኦሮሞ ህዝብ መካከል ልዩነት መፍጠር አይቻልም" የሚሉት አቶ ኣዲሱ ኣረጋ፤ በበኩላቸው ቀደም ሲል ኦቢኤን በጥርጣሬ የተያዙ ግሰቦችን ከትግራይ ህዝብ ጋር አገናኝቶ መዘገቡ የተሳሳተ መሆኑን አምነዋል። የክልሉ የሚድያ ቦርድ በትናንትናው ዕለት ጉዳዩን ገምግሞ በሚድያው አዘጋገብ ላይ ከፍተኛ ስህተት መሰራቱን አመኖ ለሁለተኛ ጊዜ እንደዚህ ዓይነት ጥፋት እንዳይደገም ማስተካከያ እያደረጉ መሆናቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል። ጉዳዩን በዘገበው ጋዜጠኛም ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ መደረጉን አክለው ተናግረዋል። "ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ ስህተት ተሰርቶ ከሆነ ገና እንገመግማለን" ሲሉ ተናግረዋል። መቱን ጨምሮ በአንዳንድ ሥፍራዎች ብሄርን መሰረት ያደረጉ እስራትንና ማዋከብን በተመለከተ ስለሚነገረውም ክልሉ ተገቢውን ማጣራት እያደረገ መሆኑን አቶ አዲሱ ገልፀዋል።
50997427
https://www.bbc.com/amharic/50997427
ቴህራን ጥቃት ከፈፀመች በሚል አሜሪካ 52 የኢራን ተቋማት ላይ መሳሪያዋን አነጣጥራለች
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን አሜሪካውያንን አልያም የአሜሪካ ንብረቶች ላይ ጥቃት ብትፈጽም በምላሹ 52 የኢራን ተቋማት ላይ መሳሪያቸውን ማነጣጠራቸውን ገልጸው፤ ሁሉም በፍጥነት እና በማያዳግም ሁኔታ ምላሽ ይሰጣሉ ሲሉ ዝተዋል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን የአሜሪካ ተቋማትና ዜጎች ላይ ጥቃት እንዳትፈጽም አስጠነቀቁ ይህንን አስተያየታቸውን የሰጡት ኢራናዊው ከፍተኛ የጦር አበጋዝ ቃሲም ሱሊማኒ በአየር ጥቃት መገደላቸውን ተከትሎ ነው። ኢራንም የጄነራሏን ደም እንደምትመልስ ዝታለች። • ለማርስ የተጻፈው ብሔራዊ መዝሙር • ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ74 የዩኒቨርሲቲው ማሕበረሰብ ላይ እርምጃ ወሰደ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቲውተር ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት ኢራን በጄነራሉ ግድያ አጸፋ ለመስጠት "የአሜሪካ ንብረቶች ላይ ማነጣጠሯን በድፍረት እየተናገረች ትገኛለች" ብለዋል። አክለውም አሜሪካ 52 የኢራን ተቋማት ላይ ማነጣጠሯን በመግለጽ ኢራን ጥቃት ከፈጸመች "አንዳንዶቹ ለኢራንና ለኢራናውያን ባሕል ትልቅ ቦታ ያላቸው ናቸው፤ በፍጥነትና በማያዳግም ሁኔታ ነው ምላሽ የምንሰጠው" ብለዋል። "አሜሪካ ሌላ ማስፈራሪያ አትፈልግም" ሲሉም አክለዋል። ፕሬዝዳንቱ የኢራን 52 ስፍራዎች የተመረጡት በአውሮፓውያኑ 1979 በኢራን በሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ታግተው የነበሩትን 52 አሜሪካውያንን ለማስታወስ መሆኑን ገልፀዋል። እነዚህ የኢምባሲው ሠራተኞች ለአንድ አመት ያህል ታግተው ቆይተው ነበር። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ይህንን የትውተር መልዕክታቸውን ባሰፈሩ በጥቂት ደቂቃ ውስጥ የአሜሪካ መንግስት ተቋም የሆነ አንድ ድረገጽን "የኢራን ሳይበር ሰኪዩሪቲ ግሩፕ ሀከር" የተሰኘ የኮምፒዩተር ጠላፊ ቡድን እንዳይሰራ አድርጎታል። በፌደራሉ ዲፖዚተሪ ላይብረሪ ፕሮግራም ድረገፅ ላይ "ይህ ከእስላማዊ ሪፐብሊክ ኢራን የተላለፈ ነው" የሚል ጽሁፍም ይነበብ ነበር። "በቀጠናው ያሉ ወዳጆቻችንን መርዳት አናቆምም። የተጨቆኑ ፍልስጤማውያኖችን፣ የመኖችን፣ የሶሪያ ህዝብን፣ ኢራቅና ባህሬን ሁሌም በእኛ ይደገፋሉ" ይላል መልዕክቱ። • "'እኛ ድሆች ነን፤ ገንዘብ ከየት እናመጣለን' እያልን ስንደራደር ነበር" በጠገዴ ታግቶ የተገደለው ታዳጊ አባት በድረገፁ ላይ የቀረበው የትራምፕ ምስል ፊታቸው ላይ ተመትተው ሲደሙ ያሳያል። ጠላፊዎቹ "ይህ ትንሹ የኢራን የሳይበር አቅም ነው" ሲሉ መልዕክታቸውን ያጠናቅቃሉ። ምን ነበር የሆነው? ፔንታጎን ባወጣው የጽሑፍ መግለጫ "በፕሬዝደንቱ ትዕዛዝ፤ ከሃገር ውጪ የሚኖሩ አሜሪካዊያንን ደህንነት ለመጠበቅ የአሜሪካ ጦር በወሰደው የመከላከል እርምጃ ቃሲም ሱሊማኒን ገድሏል" ብሏል። "ጥቃቱ ኢላማ ያደረገው የወደፊት የኢራንን ጥቃት ለማስወገድ ነው። አሜሪካ ዜጎቿን እና ጥቅሞቿን ለማስጠበቅ በማንኛውም አካል ላይ፤ በየትኛውም የዓለማችን ሥፍራ ቢገኙ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰዷን ትቀጥላለች" ይላል የፔንታጎን መግለጫ። ፔንታጎን ከዚህ በተጨማሪም፤ ጀነራሉ በኢራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን ለመግደል ሲያሴር ነበር ብሏል። አሜሪካ ይህን ጥቃት የሰነዘረችው አደባባይ በወጡ ሰልፈኞች ባግዳድ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ ጥቃት ከተሰነዘረ በኋላ ነበር። በወቅቱ የኤምባሲው አሜሪካዊያን ጠባቂዎች ከሰልፈኞቹ ጋር ተጋጭተው ነበር። • "የህወሃትን ህልውና የሚወስን ልዩና ታሪካዊ ጉባዔ" ደብረፂወን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ፔንታጎን እንደሚለው ከሆነ ጀነራል ሱሊማኒ በኤምባሲው ላይ ጥቃቱ እንዲቃጣ ፍቃድ ሰጥተዋል። አሜሪካ በአየር ማረፊያው በወሰደችው ጥቃት ከጀነራሉ በተጨማሪ የኢራቅ ሚሊሻ መሪ አቡ ማሃዲ አል-ሙሃንዲስ እንደተገደሉ የኢራን አብዮት ጥበቃ አስታውቋል። የኢራን አብዮታዊ ጥበቃ፤ ከፍተኛ የጦር ኃላፊዎቹ የተገደሉት የአሜሪካ ሄሊኮፕተሮች በወሰዱት እርምጃ ነው ብሏል። የጀነራል ሱሊማኒ ግድያ በአሜሪካ ሁለት ጎራዎችን ፈጥሯል። የፕሬዝደንት ትራምፕ የፖለቲካ አጋር የሆኑት ሪፐብሊካኖች 'ሱሊማኒ የአሜሪካ ጠላት ነው' በማለት ግድያውን ደግፈዋል። የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ ማይክ ፖምፔዮ፤ ኢራቃዊያን የጀነራሉን ግድያ ተከትሎ ደስታቸውን ሲገልጹ የሚያሳይ ምስል በትዊተር ገጻቸው ላይ አጋርተዋል። በሌላ በኩል ዲሞክራቶች የሱሊማኒን ግድያ አጥብቀው ኮንነዋል። ፕሬዝደንት ትራምፕ ጀነራሉ እንዲገደሉ ትዕዛዝ ከመስጠታቸው በፊት ከአሜሪካ ኮንግረስ ፍቃድ መጠየቅ ነበረባቸው እያሉ ነው። ኢራናውያን በጀነራል ሱሊማኒ ግድያ ብስጭታቸውን እየገለጹ ነው። የኢራን ባለሥልጣናት በበኩላቸው ይህ የጦርነት ትንኮሳ ነው ብለውታል። ቃሲም ሱሊማኒ ማን ነበሩ? እ.አ.አ. ከ 1998 ጀምሮ ሜጀር ጀነራል ሱሊማኒ የኢራን ኩድስ ኃይል ሲመሩ ቆይተዋል። ይህ ኃይል ከሃገር ውጪ የሚፈጸሙ ሚስጥራዊ ኦፕሬሽኖችን የሚያከናውን ነው። ጀነራሉ በኢራቅ ውስጥ አይኤስ እና አል-ቃይዳን በመዋጋ ትልቅ አስተዋጽኦ ነበራቸው። ከዚህ በተጨማሪም፤ እኚህ የሽብር ቡድኖች እግራቸውን በኢራን እንዳይተክሉ ተከታትለው ድባቅ የመቷቸው ጀነራል ሱሌይማኒ ነበሩ ተብሏል። ጀነራሉ የሚመሩት ኃይል በሶሪያ ግጭት ውስጥ ተሳትፎ እንዳለው አምኗል። ለፕሬዝደንት በሽር አል-አሳድ ታማኝ ለሆኑ ወታደሮች የጦር ምክር ይሰጣል። እንዲሁም ለበሽር አል-አሳድ ታማኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ሺዓ ሙስሊሞችን አስታጥቋል። በኢራቅ ደግሞ አይኤስን እየታገሉ ለሚገኙ ለሺዓ ሙስሊም ሚሊሻዎች ድጋፍ ያደርጋል። በመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት የተከሰቱት ግጭቶች ጀነራሉ ኢራን ውስጥ እጅግ ዝነኛ ሰው እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። ጀነራል ሱሊማኒ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት የኢራን ከፍተኛ የጦር ሽልማት ተቀብለዋል። • ስለ ሀብት ማውራት ነውር የሆነባት አገር አሜሪካ በበኩሏ ጀነራሉ የሚመሩት የኩድስ ኃይል በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ አሜሪካን በጠላትነት በመፈረጅ በሽብር መናጥ ለሚፈልጉ ኃይሎች ፈንድ፣ ሥልጠና እና የጦር መሳሪያን ጨምሮ የቁስ ድጋፍ ያደርጋል ስትል ትወነጅላለች። አሜሪካ እንደምትለው ከሆነ ይህ የኩድስ ኃይል ድጋፍ ከሚያደርግላቸው ኃይሎች መካከል፤ የሌባኖሱ ሄዝቦላ እንዲሁም የፍልስጤሙ እስላማዊ ጅሃድ ተጠቃሽ ናቸው። የቀድሞ የሲአይኤ አለቃ የአሁኑ የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፔዮ የኢራንን አብዮታዊ ጥበቃ እና ኩድስ ኃይሉን "የሽብር ቡድን" ሲሉ ከወራት በፊት ፈርጀውት ነበር።
news-48633581
https://www.bbc.com/amharic/news-48633581
ኤርትራ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ስር ያሉ የጤና ተቋማትን ወሰደች
ከኤርትራ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ስር የሚገኙ የህክምና መስጫ ማዕከላት ለመንግሥት ተላልፈው እንዲሰጡ ተወስኗል።
በያዝነው ሳምንት የህክምና ማዕከላቱ አስተዳዳሪዎች ለመንግሥት አሳልፈው መስጠታቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ እንዲፈርሙ መጠየቃቸውን የቢቢሲ ትግርኛ ክፍል ከኤርትራ ያገኘው መረጃ ያሳያል። • በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ንግድ ተጧጡፏል ነገር ግን አብዛኛዎቹ የማዕከላቱ አስተዳዳሪዎች ሰነዱ ላይ ለመፈረም አለመስማማታቸውንና ከቤተክርስቲያኒቱ ሃላፊዎች ጋር እንዲነጋገሩ መጠየቃቸው ታውቋል። ይህን ተከትሎም ወታደሮች ሰራተኞቹን በማስወጣት ማዕከላቱን መዝጋታቸው ተገልጿል። እስካሁን ድረስ የኤርትራ መንግሥት ድርጊቱን ስለመፈጸሙ የተረጋገጠ ነገር ባይኖርም ባለፈው ሚያዝያ ወር ላይ የኤርትራ ካቶሊክ የሃይማኖት አባቶች ለሁሉም ሰው ፍትህን ለማረጋገጥ በማለት ሃገራዊ የእርቅ ሂደት እንዲጀመር ጠይቀው ነበር። • መስመር ያልያዘው የኢትዮ-ኤርትራ የንግድ ግንኙነት ወዴት ያመራል? ከኢትዮጵያ ጋር የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የሃይማኖት አባቶቹ በጻፉት ባለ 30 ገጽ ደብዳቤ ሃገሪቱ አንድ መሆን እንዳለባትና እርቅ እንደሚያስፈልግ ገልጸው ነበር። መንግሥት ማሻሻያዎችን እንዲያደርግና ህዝቡ ሃገሩን ለቅቆ የመሄድ ፍላጎት እንዳይኖረው እንዲሰራም ጠይቀው ነበር።
49786243
https://www.bbc.com/amharic/49786243
የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በተለያዩ ከተሞች ሰልፍ አካሄዱ
የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች ሰልፍ አካሂደዋል።
በደብረ ማርቆስ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የተቃውሞ ሰልፍ የተቃውሞ ሰልፍ ከተካሄደባቸው ስፍራዎች መካከል፤ የአማራ ክልል መዲና በሆነችው ባህርዳር፣ የሰሜን ወሎ ዞን ዋና ከተማ ወልዲያ እና ምሥራቅ ጎጃም ደብረ ማርቆስ ይጠቀሳሉ። • የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በተለያዩ ከተሞች ሰልፍ አካሄዱ • ቅዱስ ሲኖዶስ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አደራጅ ኮሚቴ ጥያቄን አወግዛለሁ አለ የሰልፉ ተሳታፊዎች በቤተክርስቲያኗ፣ በኃይማኖት አባቶች እና በምዕመኖቿ ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት ይቁም የሚል መልዕክት ይዘው ወጥተዋል። በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ከተሰሙ ድምጾች መካከል፤ ''በቤተ-ክርስቲያኗ እና በምዕመኖቿ ላይ የሚፈጸሙት ጥቃቶች ይቁሙ፣ ጥፋተኞች ለሕግ ይቅረቡ'' የሚሉ ይገኙበታል። በወልዲያ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የተቃውሞ ሰልፍ በደብረ ማርቆስ ከተማ የተካሄደውን ሰልፍ ከሚያስተባበሩት መካከል አንዱ የሆኑት አቶ በሪሁ ተስፋዬ "እጅግ በርካታ ሰዎች እየተሳተፉ የሚገኙበት ሰልፍ ሰላማዊ በሆነ መልኩ እየተከናወነ ነው" ብለዋል። በሰላማዊ ሰልፉ ላይ እየተሰሙ ካሉ መፈክሮች መካከል ''የቅዱስ ሲኖዶስ ድምጽ ይሰማ'' እና ''የቤተክርሰቲያን እና የኦሮቶዶክሶዊያን መገደል ይቁም'' የሚሉት ጎልተው እንደሚሰሙ አቶ በሪሁ ተናግረዋል። • ቅዱስ ሲኖዶስ የኦሮሚያ ቤተክህነት ፅህፈት ቤት ጥያቄን በሰላሳ ቀናት እንዲመልስ ተጠየቀ የዛሬ ሳምንት ዕሁድ በተመሳሳይ መልኩ በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደው ነበር። በደሴ፣ ደብረ ታቦር እና ጎንደር ከተማ በተካሄዱት እና በሰላም በተጠናቀቁት ሰላማዊ ሰልፎችም ''በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ቤተ-ክርስቲያን ያቀጠሉ እና ምዕመናንን የገደሉ ለፍርድ ይቅረቡ፣ መንግሥት ቤተ-ክርስቲያንን ሊያከብር ይገባል'' የሚሉ ተመሳሳይ የተቃውሞ ድምጾች ነበር የተሰሙት።
news-57306930
https://www.bbc.com/amharic/news-57306930
ምርጫ 2013፡ መራጮችን ከፓርቲዎች የሚያገናኘው መተግበሪያ ምን ይዞ መጣ?
በ1997ቱ ምርጫ ብዙዎች በጉጉት የተመለከቷቸውን የምርጫ ክርክሮች በማዘጋጀት የሚታወቀው ኢንተር አፍሪካ ግሩፕ ከሁለት ተቋማት ጋር በመተባበር መራጮችን ከፓርቲዎች የሚያገኛኝ ዋርካ የተሰኘ መተግበሪያ አስተዋውቋል።
የጀርመኑ የተራድኦ ድርጅት ፍሬድሪክ ኤበርት እስቲፍቱንግ እና አይስ አዲስ በቴክኖሎጂ የተሳተፉበት ይህ የመረጃ መተግበሪያ 19 ብሔራዊ ፓርቲዎችን ያቀፈ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። የፕሮጀክቱ ባለቤት ኢንተር አፍሪካ ከጊዜ ውሱንነት የተነሳ ክልላዊ ፓርቲዎችን ማካተት አለመቻሉን ተናግሯል። የተቋሙ የኮሚኒኬሽን አማካሪ ሰይፉ በኩረ ጽዮን (ዶ/ር) ለቢቢሲ እንደተናገሩት የዲጂታል የመረጃ ማዕከሉ የፓርቲዎችን ማኒፌስቶ፣ ፕሮግራም ብሎም አቋሞቻቸውን በቀላሉ በአንድ ቦታ ተደራሽ እንዲሆን ያደርጋል። እስካሁን ድረስ የሰባት የፖለቲካ ፓርቲዎች መረጃ ማካተት መቻሉን ብሎም የሦስት ፓርቲ መረጃዎችን በቅርቡ እንደሚያካትት ሰይፉ ተናግረዋል። በድረ ገፁ ላይ እንደተጠቀሰውም የምርጫ ቀን ሁለት ሳምንት እስከሚቀረው ድረስ ፓርቲዎች ምላሻቸውን ማስገባት እንደሚችሉ ይገልጻል። ዋርካ የሚለው ስያሜ የተመረጠው በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚታወቅ ዛፍ ስለሆነ እንደሆነ ሰይፉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። 'ዋርካ' በሶማልኛ ቋንቋ ዜና የሚል ትርጉም የያዘ መሆኑም ተጨማሪ ምክንያት እንደሆነ ገልፀዋል። የዚህ መተግበሪያ አላማ ከጊዜ ወደ ጊዜ የብዙዎች የመረጃ ማግኛ እየሆነ በመጣው የስማርት ስልክ ላይ በቀላሉ የፓርቲዎችን አቋም ማቅረብ መሆኑን ተቋሙ ለቢቢሲ ገልጿል። መተግበሪያው እንዴት ይሰራል? የዋርካ መተግበሪያ ካሉት አንኳር ግልጋሎቶች መካከል የተጠቃሚውን አቋም እና ፍላጎት በቀላሉ ከፓርቲዎች ጋር ማወዳደሩ ነው። በዋርካ የተዘጋጁት 25 መጠይቆች እስማማለሁ፣ አልስማማም ወይም ገለልተኛ ነኝ የሚሉ የመልስ አማራጮች አሏቸው። ከጥያቄዎቹ መካከልም "አሁን ያለው ብሔር- ተኮር የፌደራል አደረጃጀት ሊቀጥል ይገባል ወይ፣ አገር አቀፍ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ሊቀመጥ ይገባል ወይ፣ የመገንጠል መብት ከሕገ መንግስቱ ይውጣ ወይ እና አዲስ አበባ ራሷን የቻለች ክልል ትሁን ወይ" የሚሉት ይገኙበታል። ከመሬት ባለቤትነት፣ የፌደራል የሥራ ቋንቋ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥራ ዘመን ገደብ እና የጽንስ ማቋረጥን የሚመለከቱ ጥያቄዎችም ተካተውበታል። ተጠቃሚው ጥያቄዎቹን መልሶ ሲያበቃ አቋሙን ከሚፈልገው የፖለቲካ ፓርቲ ጋር የሚያነፃፅር ሲሆን መተግበሪያው የበለጠ ከተጠቃሚው መልሶች ጋር የሚቀራረቡ ፓርቲዎችን በመቶኛ ያስቀምጣል። እንዲሁም በ25ቱም ጥያቄዎች ላይ ፓርቲዎቹ የየራሳቸውን አቋም ያስረዳሉ። በአንድሮይድ መተግበሪያው እና ድረ ገፅ ላይ የፓርቲዎቹን ፕሮግራም የያዘው ዋርካ ከምርጫ ጋር የተያያዙ ሕጎችን በተመለከተ ከምርጫ ቦርድ የመረጃ ቋት ጋር የሚያገናኙ ማስፈንጠሪዎችን ይዟል። መተግበሪያው ውስጥ የተካተቱ ፓርቲዎች ገና የተሟላ መረጃ የላቸውም። ኢንተር አፍሪካ እነዚህን መረጃዎች ከፓርቲዎቹ ለመሰብሰብ ፈተና እንደሆነበት ሰይፉ (ዶ/ር) ተናግረዋል። አገልግሎቱ ለሕዝብ ይፋ ከተደረገ ገና አንድ ወር እንዳለሞላውም ጨምረው ገልፀዋል። ከምርጫ በኋላ ግልጋሎቱ ይቀጥላል? መተግበሪያው ካሉት መልኮች መካከል የፖለቲካ ፓርቲዎችን የማወያየት እና ከመራጮች ጋር የሚገናኙበት ዘዴ ሆኖ ማስቀጠል የፕሮጀክቱ አካል እንደሆነ ሰይፉ (ዶ/ር) ተናግረዋል። ይህም ከምርጫ በኋላም የሚቀጥል እንደሆ ያስረዳሉ። ፓርቲዎችን ገፅ ለገፅ የሚያገናኙ መድረኮችን ማዘጋጅት እና ከዚያ የሚገኙ ግብአቶችን ወደ መተግበሪያው ለማምጣት ማሰቡን ኢንተር አፍሪካ ግሩፕ ገልጿል። እንዲሁም ፓርቲዎቹ ከምርጫ በኋላ ምን አሉ ወይም ምን ሰሩ የሚለውን በመከታተል በመተግበሪያው ላይ እንደሚያካትት አመልክቷል። መተግበሪያው ከፊታችን ላለው ስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ የመረጃ ምንጭ ለመሆን ከታሰበው ጊዜ በላይ መጓተቱን ገልፀው ለዚህም የፖለቲካ ፓርቲዎች በወቅቱ መረጃዎችን አለማቅረባቸው ምክንያት ነው ብሏል። አገልግሎቱ በኢንተርኔት ላይ የተመሰረተ እንደመሆኑ በምርጫው ሰሞን የአገልግሎት መቋረጥ እንደስጋት የተያዘ መሆኑን ሰይፉ (ዶ/ር)ገልፀዋል። "ኢንተርኔት እንደማይቋረጥ ተስፋ እናደርጋለን። ይህ ግን የመንግሥት ውሳኔ ነው" ብለዋል። መተግበሪያው እስከአሁን በአማርኛ ቋንቋ ብቻ መረጃዎችን የሚያቀርብ ሲሆን በቀጣይ በተለያዩ የአገር ውስጥ ቋንቋዎች አማራጮችን ለማስፋት እቅድ መያዙን ሰይፉ (ዶ/ር) ተናግረዋል። ለፕሮጀክቱ የወጣውን ወጪ በተመለከተ ግልፅ የተደረገ መረጃ የለም።
news-57068727
https://www.bbc.com/amharic/news-57068727
በእስራኤልና ፍልስጥኤም የተነሳው ግጭት ከፍ ወዳለ ጦርነት እንዳያመራ ተፈርቷል
በእስራኤል ሰራዊትና በፍልስጥኤም ታጣቂዎች መካከል በጋዛ ሰርጥ የተነሳው ግጭት በከፍተኛ ሁኔታ ተጋግሎ ወደ ጦርነት እንዳያመራ መፈራቱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል።
አንድ ሺህ የሚገመቱ ሮኬቶች በፍልስጥኤም ታጣቂዎች መወንጨፈቻውን እስራኤል አስታውቃለች። እነዚህ ሮኬቶች በ38 ሰዓታት ሲሆን አብዛኛዎቹ ደግሞ ኢላማ ያደረጉት ቴልአቪቭን ነው። እስራኤል በበኩሏ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአየር ጥቃቶችን ማክሰኞና ረቡዕ የፈፀመች ሲሆን በጋዛ የሚገኙ ሁለት የመኖሪያ ህንፃዎችን ሙሉ በሙሉ አውድማለች። በያዝነው ሳምንት ሰኞ ጀምሮ 43 ፍልስጥኤማውያንና ስድስት እስራኤላውያን ተገድለዋል። ከነዚህም መካከል 13 ፍልስጥኤማውያን ህፃናት ይገኙበታል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ እንዳሉት ግጭቱ ከፍተኛ ስጋትን እንዳሳደረባቸው ነው። በአሁኑ ወቅት የጋዛ ጎዳናዎች በህንፃ ፍርስራሾች ተሞልተዋል። በእስራኤል አየር ጥቃቶች ምክንያት ህንፃዎች ወድመዋል፣ መኪኖች ተቃጥለዋል። አረብ እስራኤላውያን በተለያዩ የእስራኤል ከተሞች በቁጣ የተሞሉ ተቃውሞችን አድርገዋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ በቴልአቪቭ አቅራቢያ የምትገኘው ሎድ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተጥሎባታል። በሎድ ከተማ በተነሳው አመፅ መኪኖች ጋይተዋል እንዲሁም 12 ሰዎች ተጎድታል። የከተማው ከንቲባም ስማቸው ከእርስ በእርስ ጦርነት ጋር ተያይዞ እየተነሳ ይገኛል። ለሳምንታት ያህል በእስራኤል ፖሊስና በፍልስጥኤማውያን ሰልፈኞች መካከል የተፈጠረው ፍጥጫ ወደ ግጭት አምርቷል። በእስልምናና በአይሁድ እምነት ተከታዮች ዘንድ ቅድስት ተብላ የምትጠራው ስፍራ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ የሆነ መጋጋል ተፈጥሮ ነበር። ከአውሮፓውያኑ 2014 በኋላ በሁለቱ ኃይሎቸ መካከል የተፈጠረ ከፍተኛ ግጭት መሆኑንም እስራኤል አስታውቃለች። ከጋዛ ከተወነጨፉት 1 ሺህ 50 ሮኬቶችና ከባድ መሳሪያዎች መካከል 850ዎቹ በእስራኤል እንዳረፉና ሌሎች ደግሞ በሮኬት መቃወሚያ አማካኝነት ተመልሰው ወደ ጋዛ እንዳረፉ የእስራኤል ጦር አስታውቋል።
news-56742304
https://www.bbc.com/amharic/news-56742304
የቀድሞው የቡርኪናፋሶ ፕሬዚዳንት በአብዮተኛው ሳንካራ ግድያ ሊከሰሱ ነው
የቀድሞው የቡርኪናፋሶ ፕሬዚዳንት ብሌይዝ ኮምፓዎሬ በብዙዎች ዘንድ ቀጥተኛ አብዮተኛ ተብሎ በሚጠራው ቶማስ ሳንካራ ግድያ ሊከሰሱ ነው።
በአውሮፓውያኑ 1987 ከስልጣን የተወገደውና የተገደለው ቶማስ ሳንካራ ግድያ እንደሚጠየቁ ያስታወቀው ወታደራዊው ፍርድ ቤት ነው። ቡርኪናፋሶን ለአመታት ያስተዳደሩት ኮምፓዎሬ የስልጣናቸውን ዘመናቸውን ለማስረዘም ያደረጉትን ሙከራ ተከትሎ በአውሮፓውያኑ 2014 ለግዞት ተዳርገዋል። በቀጣዩ አመትም የእስር ትዕዛዝ ወጣባቸው። ወታደራዊው ፍርድ ቤት በያዝነው ሳምንት ማክሰኞ እንዳስታወቀው የቀድሞው ፕሬዚዳንት "በመንግሥታዊ ደህንነት ላይ ጥቃት በመፈፀም፣ ግድያን በማቀነባበርና አስከሬን በመደበቅ ወንጀል" ክስ ይጠየቃሉ ብሏል። ከቀድሞው ፕሬዚዳንት በተጨማሪ ሌሎች 13 ሰዎችም በቶማስ ሳንካራ ግድያ እንደሚጠየቁ ተዘግቧል። የእስር ትዕዛዝ የወጣባቸውና በቁጥጥር ስር ያልዋሉትን የቀድሞ ፕሬዚዳንት ለማምጣት ማክሰኞ እለት ትዕዛዝ እንደተላለፈ ከተከሳሾቹ መካከል የአንደኛው ጠበቃ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪል ተናግረዋል። ለአራት አመታት ያህል ብቻ በስልጣን ላይ የቆዩት አብዮተኛው ሳንካራ የአፍሪካ "ቼ ጉቬራ" ተብለው ይጠራሉ። አብዮተኛው መሪ ሳንካራ ጭቆናን አጥብቀው የሚጠየፉ፣ ለድሆች፣ ሴቶችን ጨምሮ መዋቅራዊ ጭቆና አለባቸው ብለው ለሚያምኗቸው ህዝቦች እኩልነትን የሚያቀነቅኑ፣ ቅኝ ገዥዎችንና ኢምፔሪያሊዝምን የሚቃወሙ፣ ህዝብ ለመብቱ እንዲነሳ ታግለው ያታገሉ እንደነበሩ ታሪክ ይዘክራቸዋል። ይኼም ብቻ ሳይሆን ምዕራባውያን በብድር ስም አፍሪካውያንን ይበዘብዛሉ በማለት የአለም ባንክና የአለም ገንዘብ ድርጅትን አጥብቀው በመተቸታቸው በምዕራባውያኑ ጥርስ ውስጥ እንዲገቡ ምክንያት ሆኗል።
news-56359826
https://www.bbc.com/amharic/news-56359826
የኮሮናቫይረስ ክትባት፡ የኮቪድ-19 ክትባትን የሚያስቆም ምንም ምክንያት የለም- የዓለም ጤና ድርጅት
የአስትራዜኔካ ክትባት የደም መርጋትን ስለማስከተሉ ምንም ዓይነት ማረጋገጫ ባለመኖሩ በዚህ ስጋት አገሮች ክትባቱን ከመስጠት መቆጠብ የለባቸውም ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።
ቡልጋሪያ፣ ዴንማርክ እና ኖርዌይ ክትባቱን መስጠት ማቆማቸው መነገሩ ይታወሳል። ይህንን በተመለከተ የዓለም ጤና ድርጅት ቃል አቀባይ እንዳሉት በክትባቱ እና በደም መርጋት መካከል ምንም አይነት ግንኙነት የለም። ማርጋሬት ሐሪስ እንዳሉት "እጅግ በጣም ጥሩ ክትባት" ስለሆነ ጥቅም ላይ መዋሉ መቀጠል አለበት። እስካሁን ወደ 5 ሚሊዮን የሚጠጉ አውሮፓውያን የአስትራዜኔካ ክትባትን ወስደዋል። አውሮፓ ውስጥ ክትባቱ ከተሰጠ በኋላ ወደ 30 የሚጠጉ የደም መርጋት አጋጣሚዎች መከሰታቸው የተነገረ ሲሆን፤ ደም በሚመልሰውን የደም ሥር (ዲቪቲ) ህመምን ተከትሎ የ50 ዓመት አዛውንት ጣልያን ውስጥ መሞታቸውን የሚገልጹ ዘገባዎችም ነበሩ። የዓለም የጤና ድርጅት ማንኛውንም የደኅንነት ጥያቄዎች የሚያከናውን በመሆኑ ሪፖርቶቹን እየመረመረ መሆኑን ሐሪስ ተናግረዋል። ነገር ግን በክትባቱ እና በተዘገበው የጤና ችግር መካከል ምንም ምክንያታዊ ግንኙነት አልተገኘም ብለዋል። አስትራዜኔካ አርብ ዕለት በክትባቱ ሰዎች ላይ የተመዘገበው የደም መርጋት "ከጠቅላላው ሕዝብ አንጻር ከሚጠበቀው እጅግ በጣም ዝቅተኛ ነው" ብሏል። ቃል አቀባዩ እንዳሉት ክትባቱን ከወሰዱ "ከ10 ሚሊዮን በላይ በሚሆኑት ላይ ያለን የደኅንነት መረጃ ትንተና ስጋቱ እየጨመረ መምጣቱን የሚያሳይ ማስረጃ የለም" ሲሉ ገልጸዋል። ቡልጋሪያ ክትባቱን ለማቆም የወሰነችው ዴንማርክ፣ አይስላንድ፣ ኖርዌይ እና ታይላንድ ተመሳሳይ እርምጃዎችን መውሰዳቸውን ተከትሎ ነው። ጣሊያን እና ኦስትሪያ በተወሰነ ጊዜ የተመረቱ ክትባቶችን ለጥንቃቄ እርምጃ በማለት መስጠት አቁመዋል። የአውሮፓ ሕብረት የመድኃኒት ተቆጣጣሪ የሆነው ዩሮፒያን ሜዲሲን ኤጄንሲ ቀደም ሲል እንደገለጸው ክትባቱ ለደም መርጋት ምክንያት ስለመሆኑ አንድም ማሳያ የለም። እንግሊዝን፣ ጀርመን፣ አውስትራሊያ እና ሜክሲኮን ጨምሮ ሌሎች አገራት ክትባቱን መስጠት እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። የጀርመን ጤና ጥበቃ ሚኒስትር የንስ ስፓን በበኩላቸው ክትባቱን ካገዱ አገራት ጋር እንደማይስማሙ ተናግረዋል። "እስካሁን ካወቅነው አንፃር ጥቅሙ ... ከጉዳቱ በእጅጉ የላቀ ነው" ብለዋል። ጊዜያዊ እገዳው በአቅርቦት መስተጓጎል ምክንያት ለተደናቀፈ የአውሮፓ የክትባት ዘመቻ ተጨማሪ እንቅፋት ሆኗል። የኦስትሪያው ቻንስለር ሴባስቲያን ኩርዝ የአውሮፓ ሕብረት አባል አገሮች የሕዝብ ብዛታቸውን መሠረት በማድረግ ለማከፋፈል እንደተስማሙት የኮሮናቫይረስ ክትባቶችን በፍትሃዊነት አያሰራጨ አይደለም ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል። አንዳንድ አገራት ግዥውን ለአውሮፓ ኮሚሽን ከመተው ይልቅ ከክትባት አምራቾች ጋር የጎንዮሽ ስምምነትን መድረስ እንደቻሉ ተናግረዋል። የጀርመን ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በጥር ወር 30 ሚሊዮን ክትባት ከፋይዘር ባዮኤንቴክ ለማግኘት ስምምነት መፈራረሙን አምኗል። አርብ ዕለት የዓለም የጤና ድርጅት ጆንሰን እና ጆንሰን የተባለውን እና አንድ ጊዜ ብቻ የሚሰጠውን ክትባት አፀድቋል። የአውሮፓ ሕብረት ክትባቱን ሐሙስ ያጸደቀው ሲሆን አሜሪካ፣ ካናዳ እና በደቡብ አፍሪካ ያሉ ተቆጣጣሪዎችም ክትባቱን ደግፈዋል። አውሮፓ ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል? በቅርብ ወራቶች ስርጭቱ ከቀነሱ በኋላ በበርካታ የአውሮፓ አገራት ውስጥ ቫይረሱ እንደገና ስርጭቱን እያሰፋ ነው። ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ፖላንድ እና ቱርክ ከፍተኛውን ቁጥር አስመዝግበዋል። መላው ጣሊያን ወደ ጥብቅ አስገዳጅ የእንቅስቃሴ እገዳ እርምጃዎች ልትገባ ተዘጋጅታለች። በዚህም ነዋሪዎች ለሥራ፣ ለጤና ምክንያቶች፣ ለአስፈላጊ ግብይት ወይም ለአደጋ ጊዜ ብቻ ከቤት መውጣት ይፈቀድላቸዋል። ሁሉም አስፈላጊ ያልሆኑ ግብይቶች እና እንደ ቡና ቤቶችና ምግብ ቤቶች ያሉት ዝግ ሆነው ይቆያሉ። ትምህርት ቤቶች በበይነ መረብ ትምህርት የሚሰጡ ይሆናል ተብሏል። በጣሊያን ውስጥ የሟቾች ጠቅላላ ቁጥር ሰኞ ዕለት ወደ 100,000 ከፍ ብሏል። የአገሪቱ ባለሥልጣናት እንዳሉት በአዲሱ የቫይረሱ ዝርያ ምክንያት የበሽታው ስርጭት መጠን እየጨመረ ነው።
news-53846118
https://www.bbc.com/amharic/news-53846118
ካፒታሊዝም፡ የአፕል ኩባንያ ሀብት ዋጋ ግምት ሁለት ትሪሊዮን ዶላር ደረሰ
የቴክኖሎጂው ኩባንያ አፕል በስቶክ ገበያ የሀብት ምጣኔ ግምት ከቢሊዮን ዶላሮች አልፎ በትሪሊዮን ዶላር የተገመተ ሁለተኛው የዓለም ኩባንያ ሆኗል፡፡
በአሜሪካ በ2 ትሪሊዮን ዶላር የሚገመት ሀብት ያለው ኩባንያ የለም፡፡ አፕል የመጀመርያው ሆኗል፡፡ ከዚህ ቀደምም አንድ ትሪሊዮን ዶላር ለመድረስ የመጀመርያው ሆኗል፤ በ2018 ዓ.ም መጀመርያ፡፡ አሁን የአፕል የአንድ ሼር ዋጋ ግምቱ $467.77 ዶላር ደርሷል፡፡ ትናንትና ረቡዕ በነበረው የስቶክ ገበያ የኩባንያው ጥቅል ሀብት 2ሚሊዮን ዶላር መድረሱ ተበስሯል፡፡ በዓለም ላይ 2 ትሪሊዮን ዶላር ጣሪያ ለመድረስ ብቸኛና የመጀመርያ የነበረው ኩባንያ የሳኡዲ አረቢያው የነዳጅ ድርጅት አራምኮ ነው፡፡ ሆኖም አራምኮ በስቶክ ገበያ የነበረው ዋጋ ባለፈው ታኅሣሥ ወር የነዳጅ ዋጋ ማሽቆልቆልን ተከትሎ የሼር ምጣኔውም በዚያው ወርዷል፡፡ ከዚያ ወዲያ የስቶክ ዋጋ ግምቱ 1.8 ትሪሊዮን ዶላር ላይ ተቀምጧል፡፡ በሐምሌ ወር አፕል አራምኮን በመብለጥ የዓለም እጅግ ሀብታሙ ድርጅት ሆኗል፡፡.በስቶክ ገበያም በጣም ተፈላጊ የግብይይት ኩባንያ በመሆን አዲስ ታሪክ አስመዝግቧል፡፡ የማያባራ ገበያ የአይፎን ስልኮችን ፈብራኪው አፕል በዚህ ዓመት የሼር ድርሻው በ 50% ነው የተመነደገው፡፡ ይህ የሆነው ታዲያ ዓለም በኮሮና ተህዋሲ በሚታመስበት ወቅት ነው፡፡ የኮቪድ መከሰት አፕል በኢሲያ በተለይም በቻይና ያሉ መደብሮቹን እንዲዘጋ አስገድዶታል፡፡ ቻይና በድርጅቱ ላይ ፖለቲካዊ ጫና ስታደርስ ነው የቆየችው፡፡ እንዲያም ሆኖ ነው የድርጅቱ የስቶክ ድርሻ ገበያው እየደመቀለት የሄደው፡፡ ብዙዎቹ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ከሌሎች ዘርፎች በተሻለ አስቸጋሪውን ጊዜ ለማለፍ የሚችሉበት አጋጣሚ የተፈጠረ ይመስላል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የስቶክ ድርሻቸው እየተመነደጉ ያሉት ከቴክኖሎጂ ጋር የተሳሰሩት ኩባንያዎች ናቸው፡፡ አፕል በዚህ የዓመቱ ሦስተኛው ምዕራፍ ላይ ማለትም ሐምሌ መጨረሻ ላይ ትርፉ ወደ 60 ቢሊዮን ዶላር መጠጋቱን አብስሯል፡፡ በአሜሪካ ከአፕል ቀጥሎ ከፍተኛ የስቶክ ግምት ዋጋ ያለው ኩባንያ አማዞን ሲሆን ምጣኔውም 1.7 ትሪሊዮን ዶላር ነው፡፡.
news-56392265
https://www.bbc.com/amharic/news-56392265
ቅርስ፡ በአውሮፓ ገበያ በሚሊዮን ፓውንዶች የሚቸበቸቡት አፍሪካዊ የጥበብ ውጤቶች
አንዲት ሴት ለንደን ወደ ሚገኘው ባርክሌይስ ባንክ ታመራለች። ጊዜው በፈረንጆቹ ሚያዚያ 2016 ነበር።
ሴትዮዋ ወደ ባንኩ ያመራችው በባንኩ ጥብቅ ካዝና ውስጥ ለ63 ዓመታት የቆየ ምስጢራዊ ንብረት ፈልጋ ነው። የባንኩ ሰዎች ወደ ምድር ቤት ይዘዋት ወረዱ። ሦስት ወንዶች ባንኩ ለደንበኞች ባዘጋጀው ፎቴ ላይ ተቀምጠው አላፊ አግዳሚውን በጥርጣሬ እየተመለከቱ ሴትየዋን ይጠብቃሉ። ከ20 ደቂቃ ገደማ በኋላ ሴትዮዋ አንድ በአሮጌ ልብስ የተጠቀለለ ዕቃ ይዛ ብቅ አለች። የተጠቀለለበትን ጨርቅ ስትገልጠው ሁሉም ሰው በአድናቆት አፉን ከፈተ። ከነሃስ የተሠራ የአንድ ወጣት ሃውልት አፈጠጠባቸው። አንገቱ ላይ ጌጥ አስሯል። ጭንቅላቱ ላይ ደግሞ ቅል መሳይ ነገር ተሸክሟል። የጭንቅላት ቅርጽ የያዘው ይህ ሐውልት በ16ኛው ክፍለ ዘመን የነበረን ንጉስ ወይም 'ኦባ' የሚወክል ነው። ፎቴው ላይ ተቀምጠው ከነበሩት ሦስት ወንዶች አንደኛው ደላላ ነው። ላንስ ኤንትዊዝል ይባላል። ሁለቱ ደግሞ አጫራቾች። ሰዎቹ ሐውልቱን ሲመለከቱ ቤኒን ብሮንዝ መሆኑን አልተጠራጠሩም። ከሦስቱ ወንዶች አንዱ የሆነው ደላላው ላንስ፤ በአፍሪካ ጥንታዊ ንብረቶች ዙሪያ የሚያጠነጥኑ መጽሓፍት የተደረደሩበት ቤተ-መጽሓፍት አሉት። ነገር ግን ሰውዬው ናይጄሪያንም ሆነ አህጉረ አፍሪካን በአካል አያውቃትም። ቢሆንም ከእንግሊዝ ሙዚዬም እስከ ፓሪስ፤ አልፎም እስከ ኒው ዮርክ ድረስ በመሄድ የሰበሰባቸውን ንብረቶች ይሸጣል። ሴትዬዋ ከሐውልቱ ላይ ጨርቁን ስታነሳ የተሰማውን ስሜት በቃላት መግለፅ አልቻለም። የኧርነስት ልጅ ሐውልቱን በታክሲ ወደ ቤት ይዛ ሄዳ እንድታስቀምጠው ነገራት። ይህ የቤኒን ብሮንዝ ወደ አውሮፓ የመጣው በ1897 ነው። የብሪታኒያ ወታደሮች የያኔዋ ምዕራብ ቤኒን ግዛት፤ የአሁኗ የናይጄሪያ ኤዶ ግዛትን ቅኝ በገዙ ጊዜ የዘረፉት ነው። ምንም እንኳን የቤኒን ብሮንዝ ወይም ነሃስ እየተባለ ይጠራ እንጂ የሚሠራው ከነሃስ ብቻ ሳይሆን ከብራስ [መዳብና የብረት ውህድ] ጭምር ነው። እነዚህ ንብረቶች በእንግሊዝ ሙዚየም ለሕዝብ ይፋ በሆኑ ጊዜ በርካታ ጎብኝዎችን አትርፈዋል። በቅኝ ግዛት ዘመን በእንግሊዝ ጋዜጣዎች ላይ 'የደም ከተማ' በመባል የምትታወቀው ቤኒን፤ አሁን ጋዜጦቹ እነዚህን ጥንታዊ ንብረቶቿን "አስደናቂ"፣ "አስገራሚ" እያሉ ያሞካሿቸዋል። ከቤኒን የተዘረፉት እነዚህ ጥንታዊ ንብረቶች አሁንም ድረስ በቅኝ ገዢዎች ቤት ይገኛሉ። ሌሎች ደግሞ ባለቤት እየቀያየሩ መዳረሻቸው አይታወቅም። መኖሪያው ኤዶ ግዛት ያደረገው አርቲስት ቮክቶር ኤሂካሜኖር፤ "እነዚህ ነሃሶች "የኛ መረጃዎች፣ ንብረቶች፣ የንጉሦቻችን 'ፎቶግራፎች' ናቸው። ሲዘረፉ ታሪካችንም ነው አብሮ የተዘረፈው"ይላል። ይሁን እንጂ የእነዚህ ንብረቶች ዋጋ አውሮፓ ውስጥ በጣም የናረ ስለሆነ ብዙዎች ቱጃር ሆነውባቸዋል። በ1953 ለንደን ውስጥ በተካሄደ ጨረታ አንድ የቤኒን ብሮንዝ 5 ሺህ 500 ዩሮ ዋጋ ነበረው። በ1968 ደግሞ ዋጋው ወደ 21 ሺህ ዩሮ አደጓል። በ2007 ኒው ዮርክ ውስጥ አንድ የቤኒን ብሮንዝ በ4.7 ዶላር ተሽጧል። በሞተው ደላላ ልጅ እጅ የሚገኘው የቤኒን ብሮንዝ ምን ያህል ዋጋ እንደሚያወጣ ላንስ ያውቀዋል። ገዢው ደግሞ ኒው ዮርክ ላይ በነበረው ጨረታ 4.7 ሚሊዮን መዥርጦ የገዛው ማንነቱ የማይታወቅ ግለሰብ እንደሚሆን ጥርጣሬ አልነበረውም። የአይሁዱ ግለሰብ ሴት ልጅ እጅ የነበረው የቤኒን ብሮንዝም በ10 ሚሊዮን ፓውንድ እንደተሸጠ ላንስ ይናገራል። ሴትዬዋ በዚህ ገንዘብ ሕይወቷን ቀይራበታለች። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አንዳንድ ሰዎች በእጃቸው ያሉ ጥንታዊ ንብረቶችን ለባለቤት ሃገራት እየመለሱ ነው። መኖሪያውን ዌልስ ያደረገ ዶክተር ከእነዚህ ግለሰቦች አንዱ ነው። ዶክተሩ ከአያቱ የወረሳቸውን ሁለት የቤኒን ብሮንዝ ሐውልቶችን መልሶ ቤኒን ከተማ ይዞ ሲገባ የጀግና አቀባበል ተደርጎለታል።
news-56262984
https://www.bbc.com/amharic/news-56262984
እውቁ የሬጌ አቀንቃኝ በኒ ዌይለር በ73 ዓመቱ አረፈ
በሬጌ ሙዚቃ እጅግ እውቅ ከሆኑት መካከል አንዱ የሆነው በኒ ዌይለር በ73 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
በኒ ዌይለር ከኪንግስተን ጀማይካ የተገኘው ይህ ሙዚቀኛ ከአብሮ አደግ ጓደኛው ቦብ ማርሌ ጋር በመሆን 'ዘ ዌይለርስ' (The Wailers) የተሰኘውን የሙዚቃ ቡድን መስርቷል። ሁለቱ ሙዚቀኞች 'ሲመር ዳውን' (Simmer Down) እና 'ሰቲር ኢት አፕ' (Stir It Up) በተሰኙት ሙዚቃዎቻቸው ዓለም አቀፍ እውቅናን ማትረፍ ችለው ነበር። ነገር ግን በአውሮፓውያኑ 1974 ላይ በኒ ዌይለር ከቡድኑ በመለየት ለብቻው ሙዚቃ መስራቱን ቀጥሎ ነበር። ከዚህ በኋላ በነበሩት ዓመታት እጅግ ስኬታማ የሚባል የሙዚቃ ዘመን ያሳለፈው በኒ ሶስት የግራሚ ሽልማቶችን ማሸነፍ የቻለ ሲሆን በአውሮፓውያኑ 2017 ላይ ደግሞ የጃማይካ ከፍተኛ ሽልማትን ማግኘት ችሏል። በኒ ሕይወቱ ማለፏ ይፋ የተደረገው በማናጀሩ ማኢን ስቶው እና የጀማይካ ባህል ሚኒስትር ኦሊቪያ ግሬንጅ አማካይነት ነው። ለበኒ ህይወት ማለፍ ምክንያቱ ምን እንደሆነ እስካሁን ድረስ የታወቅ ነገር የለም። ነገር ግን ከባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ጀምሮ በደም ግፊት ምክንያት ሆስፒታል አልጋ ላይ ተኝቶ ነበር። የሙዚቀኛውን ህልፈተ ሕይወት ተከትሎ በርካቶች ሀዘናቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። አድናቂዎቹ እና የሙዚቃ ባለሙያዎች ዓለም ትልቅ የሙዚቃ ባለሙያዋን አጣች በማለት ሀዘናቸውን ገልጸዋል። የጀማይካ ጠቅላይ ሚኒስትር አንድሪው ሆልነስም በሙዚቀኛው ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ''ለጀማይካ እና ለሬጌ ሙዚቃ ትልቅ የነበረ ሰው አጥተናል'' በማለት ገልጸዋል። የበኒን ሞት ተከትሎ ዘ ዌይለርስ የሚባለው የሙዚቃ ቡድን ከመሰረቱት ሙዚቀኞች መካከል በሕይወት የቀረው 'ዘ ስታር' በሚል ስሙ የሚታወቀው ኔቪል ኦራይሊ ሊቪንግስተን ብቻ ነው። ሊቪንግስተን ለመጀመሪያ ጊዜ ከቦብ ማርሌ ጋር የተዋወቀው ገና በልጅነቱ ሲሆን በስቴፊ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ሆነው ነበር በጋራ ሙዚቃ መስራት የጀመሩት። በአውሮፓውያኑ 1955 ላይ የቦብ ማርሌ አባት መሞታቸውን ተከትሎ የቦብ ማርሌ እናት ልጇን ይዛ ከሊቪንግስተን አባት ጋር መኖር ጀመረች። ይህ ተከትሎም ሁለቱ ጓደኛማቾች በአንድ ቤት ውስጥ እንደ አድገዋል። ሁለቱ ጓደኛማቾች ከሌሎች ሙዚቀኞች ጋር በመሆን ነበር ዘ ዌይለርስ የተሰኘውን የሙዚቃ ቡድን ማቋቋም የቻሉት። ምንም እንኳን ለታዳጊዎቹ በወቅቱ ከነበረው ድህነትና የጸጥታ ችግር የተነሳ ሙዚቃ መስራት ከባድ የነበረ ቢሆንም የዘመኑ ታዋቂ የሬጌ አቀንቃኝ ጀ ሂግስ እርዳታን አጊንተው ነበር። በእርሱ እርዳታም የሙዚቃ ችሎታቸውና እውቀታቸው መዳበር ችሏል። 1993 ላይ ደግሞ ቦብ ማርሌ እና ጓደኞቹ ስቱዲዮ ገብተው ሲመር ዳውን የተሰኘውን ሙዚቃ አቀነቀኑ። ሙዚቃው በዋነኝነት በኪንግስተን ከተማ የነበሩ የወንጀለኛ ቡድኖች መጣላታቸውን አቁመው ሰላም እንዲሰፍን የሚጠይቅ ነበር። የዚህን ሙዚቃ መለቀቅ ተከትሎ ቦብ ማርሌ እና በኒ ዌይለር እውቅና በመላው ጃማይካ አስተጋባ። ብዙም ሳይቆዩ ደግሞ የተለያዩ ሙዚቃዎችን ለማቅረብ በአሜሪካና እንግሊዝ መጓዝ ጀመሩ። ነገር እውቅናቸውን ተከትለው የመጡት ነገሮች ብዙም ያላስደሰተው በኒ 1973 ላይ እራሱን ከሙዚቃ ቡድኑ በመለየት ለብቻው ሙዚቃን መስራት ጀመረ። ለዚህም ያቀረበው ምክንያት በጉዟቸው ላይ የሚያደርጓቸው ነገሮች ከራስተፈሪያኖች አስተምህሮትና አኗኗር ጋር የማይጣጣሙ ነገሮችን ስላስተዋልኩኝ ነው ብሎ ነበር። ከዚህ በኋላ ነገር 1981 ላይ 'ሮክ ኤን ግሩቭ (Rock 'n' Groove) የለቀቀው አልበምና እና ሌሌች ስራዎቹም ከፍተኛ ተቃይነትና ተወዳጅነት አስገኝተውለታል። በ1990ዎቹ ደግሞ በምርጥ የሬጌ አልበም ዘርፍ ሶስት ጊዜ የግራሚ ሽልማትን ማግኘት ችሏል።
48291549
https://www.bbc.com/amharic/48291549
ሚኖ ራዮላ፡ የአውሮፓን እግር ኳስ የሚዘውረው ቱጃር 'ደላላ'
"ሚኖ" በተሰኘ ቅፅል ስሙ ይታወቃል፤ ሆላንዳዊው ካርሚን ራዮላ። የታዋቂዎቹ ፖል ፖግባ፣ ዝላታን ኢብራሂሞቪች፣ ሄንሪክ ሚኪታሪያንና ዴ ሊት የመሳሰሉ ተጨዋቾች ወኪል ነው።
ጣልያን ተወልዶ በኔዘርላንድስ ሃርለም ከተማ እንዳደገ የሚነገርለት ራዮላ የደች ዜግነት ያለው 'ምርጥ ደላላ' ነው። በልጅነቱ አባቱ በከፈቱት ሬስቶራንት ውስጥ ደፋ ቀና ብሎ አስተናግዷል። በጎንዮሽ ደግሞ ዩኒቨርሲቲ በመግባት በሕግ ተመርቋል። ጣልያንኛ፣ ጀርመንኛ፣ ስፓኒሽ፣ ፈረንሳይኛ፣ ፓርቹጊዝ፣ ደች እና እንግሊዝኛ ቋንቋዎችን አቀላጥፎ የሚናገረው ራዮላ ገና የ18 ዓመት ለጋ ሳለ ነበር ኔዝርላንድስ ውስጥ የሚገኝ አንድ የታዳጊዎች እግር ኳስ ኃላፊ ሆኖ ራሱን ያገኘው። ከዚያም የነብስ ጥሪው ወደሆነው የወኪልነት ሥራ ገባ፤ ለአንድ ወኪል ድርጅት ተቀጥሮ ይሠራም ጀመር። የመጀመሪያው ሥራ የሆነው ደግሞ ተስፋ የሚጣልባቸውን ታዳጊ ደች ተጫዋቾችን ለጣልያኑ ሴሪ ኤ ማሻሻጥ። • የአፍሪካ እግር ኳስ ቅሌት በታዳጊነታቸው በራዮላ ደላይነት ወደ ጣልያን ብሎም ወደ እንግሊዝ ገብተው ስማቸውን በጉልህ መፃፍ ከቻሉ ተጫዋቾች መካከል ዴኒስ ቤርግካምፕ የሚጠቀስ ነው። ምንም ቢሆን የራሥ የራሥ ነው ያለው ራዮላ ተቀጥሮ ይሠራበት የነበረበትን ድርጅት ለቆ የራሱን የውክልና ድርጅት ሊያቋቁም ቻለ። ለሃገሩ ቼክ ሪፐብሊክ ባሳየው ብቃት የአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች ዓይን አርፎበት የነበረው ፓቬል ኔድቬድ ከስፓርታ ፕራግ ወደ ላዚዮ እንዲዛወር ያደረገው ራዮላ ነበር። አሁን ላይ አውሮፓ ውስጥ ከሚጫወቱ እግር ኳሰኞች ስም ያላቸው 20 ገደማ ተጨዋቾች ውክልናቸውን ለራዮላ ሰጥተው ይንቀሳቀሳሉ። እንደ አውሮፓዊያኑ 2016 ላይ ራዮላ 'ታሪክ ሠራ'። ያኔ የዓለም ሬከርድ በነበረ ዋጋ ፖል ፖግባን ከዩቬንቱስ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ እንዲዛወር አደረገ፤ ዋጋው ደግሞ 105 ሚሊዮን ዩሮ። ጉደኛው ራዮላ ከዚህ ዝውውር 25 ሚሊዮን ዩሮ ገደማ ወደ ኪሱ እንዳስገባ ይነገራል። ከዚያ በኋላ ወደ አሜሪካዋ የባህር ዳርቻ ግዛት ማያሚ አቅንቶ 9 ሚሊዮን ዩሮ በማፍሰስ ቤተ-መንግሥት የሚያስንቅ መኖሪያ 'መንደር' ሸመተ። ፎርብስ የተሰኘው የቢዝነስ ጋዜጣ 2018 ላይ ባወጣው ዘገባ ራዮላ 69 ሚሊዮን ዶላር የተጣራ ገቢ ያለው ሲሆን በእርሱ ውክልና ሥራ ያሉ 70 ተጫዋቾች 629 ሚሊዮን ዶላር ሊያወጡ ይችላሉ ሲል አትቷል። • ''ብሔርተኝነት'' እያጠላበት ያለው እግር ኳስ ታላላቆቹ የአውሮፓ እግር ኳስ ክለቦች የራዮላ ስም ሲጠራ ይንቀጠቀጣሉ፤ ይነዝራቸዋል። ምክንያታቸው ደግሞ በእርሱ ውክልና ሥር ያሉ ተጨዋቾችን እንዳሻው ማዟዟር መቻሉ ነው። ሰውየው ያሻውን ከመናገር ወደኋላ የሚልም አይደለም። በአትንኩኝ ባይነቱ የሚታወቀው ራዮላ በእርሱ ውክልና ሥር ያሉ ተጨዋቾችን የሚተቹ የቀድሞ እግር ኳሰኞችም ሆነ ተንታኞችን በመወረፍ ይታወቃል። ከሰሞኑ ግን የራዮላን ጠላቶች ፊት ፈገግ ያሰኘ፤ ለጊዜውም ቢሆን ለክለቦችን እፎይታ የሰጠ ዜና ከወደ ጣልያን ተሰምቷል። ራዮላ በጣልያን እግርኳስ ፌዴሬሽን ከውክልና ሥራ መታገዱን የሚያትት። ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ አካል ፊፋም የጣልያን አቻውን ፈለግ በመከተል ራዮላ ላልተወሰነ ጊዜ ከወኪልነት ሥራው እንዲታገድ ውሳኔ አስተላለፈ። የጣልያና እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይህን ውሳኔ ለምን እንዳስተላለፈ ግልፅ ባይሆንም ራዮላ ግን «እገዳው ብርቅ አልሆነብኝም። እኔ ያልተመቸኝ ውሳኔው ፖለቲካዊ መሆኑ ነው» ሲል ተደምጧል። አክሎም «የጣልያን እግርኳስ ፌዴሬሽን የሃገሪቱን ኳስ ወደኋላ አስቀርቷል ብዬ የተናገርኳት ነገር ሳትቆረቁራቸው አትቀርም፤ በሃገሪቱ ሳላለው የእግር ኳስ ዘረኝት ጉዳይ አሳስቦኛል ማለቴም ይቅርታ ሳያስነፍገኝ አይቀርም» ሲል ተሳልቋል። ይህ ውሳኔ ያስደሰታቸው ቢኖሩም እንኳ የራዮላ መታገድ ለአንዳንድ ክለቦች ደግሞ ደንቃራን ይዞ የመጣ እንደሆነ እየተነገረ ነው። የአውሮፓ እግር ኳስ የዝውውር ገበያ በሚደራበት በዚህ ሰዓት የሰውዬ መታገድ ፖል ፖግባን መግዛት ይፈልጋሉ ከሚባሉት ማድሪዶች ጀምሮ የአያክስ ወጣቶችን ለመቀራመት ለቋመጡ ክለቦች የራስ ምታት መሆኑ አልቀረም።
48280313
https://www.bbc.com/amharic/48280313
በኤርትራ የማህበራዊ ድረ ገጾች አገልግሎት ተቋረጠ
በኤርትራ ውስጥ የማህበራዊ ድረ ገጽ የግንኙነት አገልግሎት መቋረጡን በሃገሪቱ የሚገኙ ምንጮች ለቢቢሲ አመለከቱ።
ከጥቂት ቀናት ወዲህ እንደ ፌስቡክና ሜሴንጀር ያሉ ማህበራዊ መድረኮችን መጠቀም እንዳልተቻለ የሃገሪቱ ዜጎች ተናግረዋል። ያገኘነው መረጃ እንሚያመለክተው ነዋሪዎች ከዚህ ቀደም በፌስቡክና በሜሴንጀር መልዕክት መላክና መቀበል ይችሉ ነበር። • ጉዞ ከአዲስ አበባ ወደ አሥመራ በፎቶ እነዚህን የተዘጉ የማህበራዊ ግንኙነት መድረኮች ለመጠቀምም ሰዎች ቪፒኤን የተባሉትን እገዳውን ለማለፍ የሚያስችሉ መተግበሪያዎች እንደሚጠቀሙም ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በኤርትራ በማህበራዊ የትስስር ድረ ገጾች ላይ ተጥሏል ስለተባለው እገዳ ምንነትና ምክንያቱን በተመለከተ እስካሁን በይፋ የተገለጸ ነገር የለም። አንዳንዶች እንደሚሉት ግን በአሁኑ ወቅት ኤርትራ የነጻነት በዓሏን ለማክበር እየተዘጋጀች በመሆኑ ከጸጥታ ጥበቃ ጋር የተያያዘ እርምጃ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመው ሌሎች ደግሞ በውጪ ሃገራት ያሉ የመንግሥት ተቃዋሚዎች በማህበራዊ ድረ ገጾች በኩል የሚያስተላልፉትን መልዕክት ለመከላከል የሚደረግ ጥረት እንደሆነ ይናገራሉ። ቢቢሲ ከኤርትራ መንግሥት በኩል በጉዳዩ ላይ ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም። • አሥመራ፡ የአዛውንቶች ከተማ የዓለም አቀፍ የኢንተርኔት ስርጭት መረጃ እንደሚያመለክተው ባለፈው ዓመት ኤርትራ ወስጥ 71 ሺህ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ሲኖሩ ይህም ከአጠቃላይ የሃገሪቱ ህዝብ ብዛት 1.3 በመቶውን ብቻ የሚሸፍን ነው። ኤርትራ በዓለማችን ውስጥ ዝቅተኛ የኢንተርኔት ተደራሽነት ካለባቸው ሃገራት መካከል ትመደባለች።
news-50991396
https://www.bbc.com/amharic/news-50991396
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከግጭት ጋር በተያያዘ በ74 የዩኒቨርሲቲው ማሕበረሰብ ላይ እርምጃ ወሰደ
በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በሚከሰቱ ግጭቶች የሰዎች ሕይወት አልፏል፣ የአካል ጉዳት አጋጥሟል፣ በንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል። ከእነዚህም ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ነበር።
ዩኒቨርሲቲው ችግሮቹን ለመፍታት "አንድ ተማሪ ለአንድ ቤተሰብ" የሚለውን ጨምሮ የተለያዩ መፍትሄ ይሆናሉ ያላቸውን ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል። በዚህም ታህሳስ 22/2012 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ፤ በግጭቶቹ በተለያየ ደረጃ ተሳትፈዋል ባላቸው ተማሪዎች፣ መምህራን፣ የአስተዳደር ሠራተኞችና የጤና ባለሙያ ላይ እርምጃ መወሰዱን የዩኒቨርሲቲው ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ይዳኝ ማንደፍሮ ለቢቢሲ ገልፀዋል። እርምጃው የተወሰደው ከኅዳር 4 ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው ከተፈጠሩ ግጭቶች ጋር በተያያዘ ነው። ኃላፊዋ እንዳሉት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩት ግለሰቦች በተለያዩ ማስረጃዎች፣ የዐይን ምስክሮች እና እጅ ከፍንጅ የተያዙ ሲሆኑ እንደየ ተሳትፏቸው ቅጣቱ ተላልፏል። ሰላማዊ የመማር ማስተማሩ ሂደት እንዳይቀጥል ለማደናቀፍ በተቀናጀ መልኩ በውጭም ካሉ ኃይሎች ግፊት በድርጊቱ ላይ የተሳተፉም ይገኙበታል ብለዋል። በዚህም መሠረት 2 ተማሪዎች ለአንድ ዓመት፣ 39 ተማሪዎች ደግሞ ለሁለት ዓመት ከትምህርታቸው እንዲታገዱ፣ እንዲሁም 11 ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ከትምህርታቸው እንዲሰናበቱ ተወስኗል። ከዚህም በተጨማሪ ለ7 መምህራን የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ፣ ለ3 መምህራን የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል። 3 መምህራን እና 8 የአስተዳደር ሠራተኞች እንዲሁም የጤና ባለሙያም ሙሉ ለሙሉ ከሥራ እንዲሰናበቱ ውሳኔ ተላልፏል። "የአምቡላንስ አሽከርካሪ ግጭት ሲከሰት በሥራ ገበታው ላይ ባለመገኘቱ፤ ለአንድ ተማሪ ሞት ምክንያት ሆኗል" በሚልም ሙሉ ለሙሉ ከሥራው ተሰናብቷል። የጦር መሳሪያ አስቀምጠው የተገኙ ፕሮክተሮችም እርምጃው ከተወሰደባቸው የአስተዳደር ሠራተኞች መካከል እንደሚገኙበት አክለዋል። • "'እኛ ድሆች ነን፤ ገንዘብ ከየት እናመጣለን' እያልን ስንደራደር ነበር" በጠገዴ ታግቶ የተገደለው ታዳጊ አባት በወቅቱ ከነበረው የተማሪው ግድያ ጋር በተያያዘ የተያዙ ሰዎች ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሆነ ያስታወሱት ኃላፊዋ፤ አሁን ላይ እርምጃ የተወሰደባቸው "ሁከት የፈጠሩ፣ ያባባሱ፣ ተማሪዎችን የሚስፈራሩ መልዕክቶችን ሲለጥፉ የተያዙ" ናቸው ብለዋል። ዩኒቨርሲቲው ከከተማው አስተዳደር፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የክልል ልዩ ኃይል እና ኮማንድ ፖስት ግብረ ኃይል ጋር በመቀናጀት በተደረገ ማጣራት የተገኙ ማስረጃዎች ላይ ተመስርተው የተጠረጠሩት ግለሰቦች ላይ እርምጃ መወሰዱን ኃላፊዋ አስረድተዋል። ውሳኔውን የፌደራል ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ባለሙያዎች ቡድን አባላት ከዩኒቨርሲቲው ሴናተሮች ጋር በመሆን ታህሳስ 22/2012 ዓ.ም ባካሄዱት ስብሰባ ነው ውሳኔውን ያሳለፉት። ከዚህም በኋላ የዩኒቨርሲቲውንም ሆነ የከተማውን ማህበረሰብ ሰላም ለማስከበር በመሰል ድርጊቶች ላይ በሚሳተፉ ማንኛውም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ሴኔቱ አስጠንቅቋል። ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከፌደራል መንግሥትም ጋር በመሆን በግቢው ውስጥ የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት የተለያዩ አማራጭ መፍትሔዎችን እያከናወነ እንደሆነ የሚገልፁት ኃላፊዋ "አንድ ተማሪ ለአንድ ቤተሰብ " የሚለውን ፕሮጀክት በምሳሌነት ይጠቅሳሉ። በዚህ ፕሮጀክት በዩኒቨርሲቲ ያሉ ተማሪዎች በችግራቸው ጊዜ የሚያማክሩት፣ የሚከታተላቸው፣ የሚጠይቃቸው ቤተሰብ የሚፈጥሩበት ነው። እነዚህ ወላጆች በዩኒቨርሲቲው የታመነባቸውና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንደሚወጡም የታመነባቸው ናቸው። "እኔም ለአራት ተማሪዎች ቤተሰብ ሆኛለሁ፤ እንደዋወላለን፤ እንጠያየቃለን" ብለዋል። ይህም ችግሮችን ለመፍታት እና ተማሪዎችን ለማረጋጋት በጎ አስተዋፅኦ እያደረገ እንደሆነ አክለዋል። በተያያዘ ዜና ታህሳስ 21/2012 ዓ.ም በወሎ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ተከስቶ በነበረው ግጭት ጉዳት ከደረሰባቸው 3 ተማሪዎች መካከል የአንድ ተማሪ ሕይወት ማለፉ ይታወቃል። በተማሪው ግድያ የተጠረጠረ አንድ ተማሪ ከነተባባሪዎቹ ታህሳስ 22 ከምሽቱ 4፡00 አካባቢ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ዩኒቨርሲቲው በፌስቡክ ገፁ አስታውቋል። ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ሥር ማዋል የተቻለው በተማሪዎች ጥቆማ በተማሪዎች ማደሪያ [ዶርም] በተደረገ ፍተሻ እንደሆነ አስታውቋል።
news-56439790
https://www.bbc.com/amharic/news-56439790
ትግራይ፡ ተመድ በትግራይ ተፈጽመዋል በተባሉ የመብት ጥሰቶች ምርመራ ላይ ለመሳተፍ ተስማማ
የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን በትግራይ ክልል የተከሰተው ግጭት አስከትሏል የተባለውን የመብቶች ጥሰት በጋራ ለመመርመር በኢትዮጵያ በኩል የቀረበውን ጥሪ መቀበሉን ገለጸ።
ሚሼል ባሽሌት በሚሼል ባሽሌት የሚመራው ኮሚሽኑ "ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኩል የጋራ ምርመራ ለማካሄድ የቀረበለትን ጥያቄ ተቀብሎ ሰኞ ዕለት አውንታዊ መልስ ሰጥቷል" ሲሉ ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን ቃል አቀባይ የሆኑት ጆናታን ፎውለር ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግረዋል። በጥቅምት ወር ማብቂያ ላይ የተቀሰቀሰውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች በትግራይ ክልል ውስጥ ከባድ የሰብአዊ መብቶች ጥሰትና የንበረት ውድመት መፈጸሙን የሚገልጹ ሪፖርቶችን አውጥተዋል። የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር የሆኑት ሚሼል ባሽሌት ከሳምንት በፊት ባወጡት መግለጫ በትግራይ ግጭት የተሳተፉ አካላት "የጦር እና በሰብአዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች ፈጽመው ሊሆን እንደሚችል" ገልጸው ነበር። ሚሸል ባሽሌት "የሚረብሹ" ያሏቸው የመደፈር፣ የዘፈቀደ ግድያ፣ መጠነ ሰፊ የንብረት ውድመትና ዘረፋ መፈጸማቸውን የሚያመለክቱ ሪፖርቶች እየወጡ መሆኑን ጠቅሰው፤ ግልጽና ነፃ ምርመራ ካልተካሄደና ጥሰቱን የፈፀሙትን አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግ ካልተቻለ እነዚህ ጥቃቶች ሊቀጥሉ እንደሚችሉ ስጋታቸውን ገልጸው ነበር። ኮሚሽነሯ ከትግራይ የሚወጡ ተያያዢነት ያላቸውና ተአማኒ ያሏቸውን ሪፖርቶች ጠቅሰው በግጭቱ ውስጥ ተሳታፊ በሆኑ የተለያዩ ወገኖች የተፈፀሙ ከባድ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች እና የሰብአዊ እርዳታ ሕጎች ጥሰት መፈጸማቸውን እንደሚያመለክቱ ተናግረዋል። በዚህም የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በትግራይ ክልል ተፈጸሙ የተባሉትንና እንደ ጦር ወንጀል ሊቆጠሩ የሚችሉ ሪፖርት የተደረጉ የጅምላ ግድያዎችን፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችንና ወሲባዊ ጥቃቶችን ለመመርመር እንዲችል ፈቃድ እንዲሰጠው ጠይቆ ነበር። የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ በእነዚህ ድርጊቶች ውስጥ ሳይሳተፉ አይቀሩም በሚል የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትን፣ ህወሓትን፣ የኤርትራ ወታደሮችን፣ የአማራ ክልል ኃይሎችን ጠቅሶ ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥትም ተፈጽመዋል ስለተባሉት የሰብአዊ መብት ጥሰቶችና ግድያዎችን በሚመለከት ከተለያዩ ወገኖች በኩል የሚወጡትን መረጃዎች መሠረት በማድረግ የአገሪቱን የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንን፣ ዐቃቤ ሕግን፣ የትግራይ ገዜያዊ አስተዳደርንና የፌደራል ፖሊስን ያካተተ ቡድን አቋቁሞ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን መግለጹ ይታወሳል። በተጨማሪም የአፍሪካ ሕብረትና ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት እየተደረገ ባለው ምርመራ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ በማድረግ ቀረቡትን ክሶች ለማጣራት ፈቃደኝነቱን አሳይቷል። ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚገኘው የሰሜን ዕዝ ላይ የህወሓት ኃይሎች የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ በተቀሰቀሰው ጦርነት ሳቢያ የጠፋው ህይወት ምን ያህል እንደሆነ በትክክል የማይታወቅ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ሳይሞቱ እንዳልቀሩ የእርዳታ ድርጅቶች ይገምታሉ። ከዚህ በተጨማሪም ግጭቱን በመሸሽ ከ60 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ድንበር ተሻግረው ወደ ሱዳን የገቡ ሲሆን በመቶ ሺህ የሚቆጠሩት ደግሞ እዚያው በክልሉ ውስጥ ተፈናቅለው እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑ ተገልጿል።
48183288
https://www.bbc.com/amharic/48183288
የቀድሞ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ኃላፊ የነበሩት አቶ ጌታቸው አሰፋ ላይ ክስ ተመሰረተ
አቶ ጌታቸው አሰፋን ጨምር በ26 የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ላይ ክስ መመስረቱን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አስታወቀ።
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት፤ ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል በሚል በፌደራል ፖሊስ ወንጀል መርማሪዎች፣ በማረሚያ ቤት የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም በብሔራዊ መረጃና ደህንነት የሥራ ኃላፊዎች ላይ የወንጀል ምርመራ ሲያካሂድ ነበር። • አቶ ጌታቸው አሰፋ በሚያውቋቸው አንደበት በዚህ መሰረት፤ አቃቤ ሕግ በወንጀል መርማሪዎች፣ በማረሚያ ቤቱ የሥራ ኃላፊዎች ላይ እንዲሁም በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ላይ በሦስት የተለያዩ መዝገቦች ክስ መስርቷል። በመርማሪዎች ላይ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተከፈተው እና በማረሚያ ቤት ኃላፊዎች በነበሩት ላይ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተከፈቱት መዛግብት የክስ ሂደት ቀጥሎ፤ ምስክር ለመስማት ተቀጥረዋል። በሦስተኛው መዝገብ ላይ 26 የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በጠቅላላው 46 ክሶች ተመስርቶባቸዋል። • አቶ ጌታቸው አሰፋ የእስር ትዕዛዝ እንደወጣባቸው ተገለፀ በክሶቹ ውስጥ 22ቱ ተከሳሾች በአሁኑ ወቅት በእስር ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ በሌላ በኩል የቀድሞ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ አቶ አጽብሃ ግደይ፣ አቶ አሠፋ በላይ እና አቶ ሽሻይ ልዑል በተባሉ የቀድሞ የአገልግሎቱ የሥራ ኃላፊዎች ላይ በሌሉበት ዛሬ ሚያዚያ 29 ቀን 2011 ዓ. ም. በከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ክስ ይመሰረትባችዋል፡፡ በአቶ ጌታቸው ላይ፤ በ1996 ዓ. ም. የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/1/ (ሀ) (ለ) እና 407/1/ (ለ) (ሐ) እና 407/3/ ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ ሥልጣንን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል መፈጸም እንዲሁም በ1996 ዓ. ም. የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1) ሀ እና ለ እንዲሁም የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9 /1/ (ለ) እና (ሐ) እና 9/3/ ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ ሥልጣንን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸዋል ሲል የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አስታውቋል። • አቶ ጌታቸው አሰፋ በየትኛው የሕግ አግባብ ተላልፈው ሊሰጡ ይችላሉ? በሌሎቹ ሁሉም ተከሳሾች ላይ፤ በ1996 ዓ. ም. የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/1/ (ሀ) (ለ) እና 407/1/ (ለ) (ሐ) እና 407/2/ ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል፣ ከባድ የሙስና ወንጀል መፈጸም እንዲሁም በ1996 ዓ. ም. የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1) ሀ እና ለ እንዲሁም የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9 /1/ (ለ) እና (ሐ) እና 9/2/ ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ ሥልጣንን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ክስ እንደተመሰረተባቸው ተመልክቷል። ሥልጣንን ያለአግባብ መጠቀም ክስ ሊቀርብባቸው የቻለው ተከሳሾች በግልጽ ከተሰጣቸው ሥልጣን ወይም ኃላፊነት አሳልፈው በመሥራት እንዲሁም ሥልጣናቸው ወይም ኃላፊነታቸው የማይፈቅድላቸውን በተለይም ሥልጣን ወይም ኃላፊነት ሳይኖራቸው በሌላ ሰው መብት ላይ ጉዳት እንዲደርስ በማሰብ በተበዳዮች ላይ ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመፈጸማቸው ነው ተብሏል።
57146509
https://www.bbc.com/amharic/57146509
ቢል ጌትስ ጾታዊ ግንኙነት ነበራቸው የሚል ምርምራ እየተካሄደባቸው ሳለ ከማይክሮሶፍት እራሳቸውን አገለሉ
ቢሊየነሩ ቢል ጌትስ ከ20 ዓመታት በፊት ከአንድ ሴት ሰራተኛ ጋር ጾታዊ ግንኙነት ነበራቸው የሚል ምርምራ እየተደረገባቸው ሳለ ከማይክሮሶፍት ቦርድ አባልነት እራሳቸውን አገለሉ።
ማይክሮሶፍት በቢሊየነበሩ ጠባይ ዙሪያ ሪፖርቶች ከደረሱት በኋላ ምርመራ እያደረገባቸው ባለባት ጊዜ ነበር ቢል ጌትስ እራሳቸውን ከማይክሮሶፍትን ማግለላቸው የተሰማው። ማይክሮሶፍት ከሕግ ተቋም ጋር በመሆነው ምርመራ መጀመሩን ያስታወቀ ሲሆን፤ ቅሬታውን ላቀረበችው ሠራተኛ ድጋፍ እየሰጠሁ ነው ብሏል። ሆኖም የባለሀብቱ ቃል አቀባይ የቢል ጌትስ ከማይክሮሶፍት መልቀቅ ከምርመራው ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም ብለዋል። ከኩባንያው ጋር በተያያዘ በሰውዬው ላይ ምርመራው የመጀመሩ ዜና እየተሰማ የመጣው ቢል ጌትስ ከባለቤታቸው ጋር መለያታቸው ከተገለጸ በኃላ ነው። ከቀናት በፊት ቢል ጌትስ 27 ዓመታት የቆየ ትዳራቸውን ለማፍረስ ከባለቤታቸው ጋር ከስምምነት መድረሳቸውን ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል። የማይክሮሶፍት ቃል አቀባይ ደግሞ በፈረንጆቹ 2019 መገባዳጃ ላይ ጌትስ በአውሮፓውያኑ 2000 "ከሴት ተቀጣሪ ጋር ግንኙነት ለመመስረት ፈልገው ነበር" የሚል ቅሬታ ኩባንያው መቀበሉን አስታውሰዋል። "ለዚሁ አላማ በኩባንያው ቦርድ የተዋቀረ ኮሚቴ የቀረበውን ጉዳይ ከሕግ ተቋም ጋር በመሆን ገምግሞታል" በለዋል። ቢል ጌትስ ባለፈው መጋቢት ወር ላይ ከማይክሮሶፍት የለቀቁት በቢልና ሜሊንዳ ፍውንዴሽን የበጎ አድራጎት ስራ ላይ የበለጠ ትኩረት ለማድረግ እንደነበረ ገልጸዋል። "ማይክሮሶፍትን በተመለከተ ከቦርድ መልቀቅ ከኩባንያው መራቅ ማለት አይደልም። ማይክሮሶፍት የህይወቴ ጠቃሚ ክፍል ሆኖ ይቀጥላል። ... ኩባንያው እያከናወነ ያለው ስራና ዓለምን ለመጥቅም ባለው ተግባር የበለጠ ተስፋ አለኝ" የሚል ጽሁፍ አስፍረዋል።
news-53583742
https://www.bbc.com/amharic/news-53583742
ካሜራ አምራቹ ኮዳክ ወረርሽኙን ለመዋጋት መድሃኒት ወደ ማምረት ገባ
ካሜራ በማምረት የሚታወቀው ግዙፉ የአሜሪካ ድርጅት ኮዳክ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመዋጋት መድሃኒት ወደ ማምረት ሥራ መግባቱ ተገለፀ።
ድርጅቱ ለዚህ ሥራውም ከአሜሪካ መንግሥት የ765 ሚሊየን ገንዘብ ብድር ያገኘ ሲሆን የኮሮናቫይረስን ለመዋጋት ለመድሃኒቶች የሚሆኑ ግብዓቶችን ያመርታልም ተብሏል። ብድሩ መሰጠቱ ይፋ በተደረገበት ጊዜም የአሜሪካ መንግሥት ለሕክምና አቅርቦት በሌሎች አገራት ላይ ጥገኛ መሆኑን መቀነስ እንደሚፈልግ አስታውቋል። ማክሰኞ ዕለት ይህ ዜና ከተሰማ በኋላ የኮዳክ አክሲዮኖች ከ60 በመቶ በላይ ጨምረዋል። የድርጅቱ ኃላፊ ጂም ኮንቲንነዛም "አሜሪካ በዚህ ረገድ ራሷን እንድትችል የመድሃኒት ግብዓቶችን በማምረት የዚህ አካል በመሆኑ ኮዳክ ኩራት ይሰማዋል። " ብለዋል። የመድሃኒቶቹን ግብዓቶች በስፋት ለማምረትም ሦስት ወይም አራት ዓመታት ሊወስድ እንደሚችል ኃላፊው አክለዋል። የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ፒተር ናቫሮ በበኩላቸው " ከዚህ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ከተማርን፤ የተማርነው፣ አሜሪካዊያን በጣም አስፈላጊ ለሆኑ መድሃኒቶቻቸው በውጭ መድሃኒት አቅርቦት ሰንሰለቶች ላይ ላይ ጥገኛ መሆናቸውን ነው።" ሲሉ ተናግረዋል። የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕም ኮዳክ ትልቅ የአሜሪካ ካምፓኒ መሆኑን በመጥቀስ "በአሜሪካ የመድሃኒት አምራች ኢንዱስትሪ ታሪክ ውስጥ በጣም ወሳኝ ከሆኑ ስምምነቶች አንዱ ይህ ነው" ብለዋል። የመድሃኒት አምራች ድርጅቶች ለኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት እየተሽቀዳደሙ ሲሆን የተወሰኑትም በሰዎች ላይ እየተሞከሩ ነው። ኮዳክም ወደ መድሃኒት ማምረት ሥራ የገባ ብቸኛ የፎቶግራፍ ድርጅት አይደለም። ከዚህ ቀደምም የጃፓኑ ፉጂ ፊልም ተስፋ የተጣለበት የኮቪድ-19 ክትባት እየሰራ ይገኛል። ይህ ክትባት በቅርቡ ሰው ላይ ይሞከራል ተብሎም ይጠበቃል። ኮዳክ ካምፓኒ የተመሰረው እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠር 1888 በጆርጅ ኢስትማን ነበር። ካምፓኒው መድሃኒት ማምረት የጀመረው ከአራት ዓመታት በፊት ቢሆንም አሁን ግን በአስደናቂ ሁኔታ በኒዮርክና ሜኒሶታ በሚገኙት ተቋማቱ ሥራውን እያስፋፋ ነው።
news-53133664
https://www.bbc.com/amharic/news-53133664
'የኢትዮጵያ ሕዝብ ይፍረደን' የጀነራል ሰዓረ እና ሜ/ጀነራል ገዛኢ ቤተሰቦች
ሰኔ 15/2011 ዓ.ም አመሻሽ፣ የአማራ ክልል ፕሬዚደንት አምባቸው መኮንን ( ዶ/ር) ጨምሮ ስብሰባ ላይ በነበሩ የአማራ ክልል አመራሮች ጥቃት ተፈጽሞ ተገድለዋል። በወቅቱ የደረሰውን ጥቃት በሚመለከት በመገናኛ ብዙሃን የተገለፀው "መፈንቀለ መንግሥት" ለማካሄድ ያለመ የሚል ነበር።
ከሰዓታት በኋላም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከባህዳሩ ክስተት በተጨማሪ ጥቃቱን ለማስቆም አዲስ አበባ በሚገኘው ቤታቸው ሆነው ወታደራዊ አመራር ይሰጡ የነበሩ የአገሪቱ ጦር ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀነራል ሰዓረ መኮንን ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ገለጹ። የጥቃቱ ሰለባ ግን ኤታማዦር ሹሙ ብቻ አልነበሩም። ለሥራ ጉዳይ በጀነራሉ ቤት የተገኙት ጡረተኛው ሜ/ጀነራል ገዛኢ አበራም ጭምር እንጂ። አገሪቱ ውስጥ ትልቅ ድንጋጤ ፈጥሮ የነበረው ግድያ አንድ ዓመት ቢሞላውም ፍትህ እንዳላገኙና "የአገር ባለውለታ" የነበሩት ጀነራሎች ችላ መባላቸውን የጀነራል ሰዓረ መኮነን እና የሜ/ጀነራል ገዛኢ አበራ ቤተሰቦች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ምን ነበር የተፈጠረው ? ጥቃቱ በተፈጸመበት ዕለት ከሰዓት በኋላ ጀነራል ሰዓረ መኮንን የአዲስ አበባ አስተዳደር ባዘጋጀው የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ላይ ተካፍለው እንደተመለሱ ባለቤታቸው ኮሎኔል ጽጌ አለማየሁ ያስታውሳሉ። ድንገት ግን መሪነታቸው የሚፈልግ ወታደራዊ ግዳጅ መኖሩን በስልክ ተደውሎ ተነገራቸው። ስለ ባህርዳሩ ክስተት ስልክ ደውለው የነገሯቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እንደሆኑ የሚገልጹት ኮ/ል ጽጌ አለማየሁ፤ በመሃል ሜ/ጀነራል ገዛኢ አበራ መምጣታቸውን ነገር ግን ጀነራል ሰዓረ በስልክ በሚመሩት ግዳጅ ተጠምደው ስለነበር ግቢ ውስጥ ይጠብቋቸው እንደነበር ይገልጻሉ። "ከምሽቱ 3፡12 ሲል በጉዳዩ ዙርያ የአማራ ቴሌቪዥን ምን እያስተላለፈ እንደነበረ እንዳይ ተነጋግረን ወደ ሳሎን ገባሁ። ገና ቴሌቪዥኑን ከፍቼ ቻናል በመምረጥ ላይ እያለሁ አንድ ጥይት ተተኮሰ፣ ከዚያም ተደጋገመ። ሮጬ ስወጣ ሁለቱም በያሉበት ተመትተው፣ ልጁ [ግድያውን የፈጸመው] ደግሞ ሰዓረ እግር ስር ወድቆ አገኘሁት። ጀነራል ገዛኢ ወድያው ነበር የተሰዋው፣ ጀነራል ሰዓረ ግን ጥበቃዎቹ አቅራቢያችን ወደሚገኝ ዋሽንግተን ሆስፒታል ወሰዱት" ይላሉ ኮሎኔል ጽጌ አለማየሁ። ከሜ/ጀነራል ገዛኢ አበራ አስከሬን እና በጀኔራሎቹ ግድያ ከሚጠረጠረውና መሬት ላይ ወድቆ ከነበረው የጀነራል ሰዓረ ጠባቂ አጠገብ በድንጋጤ ቆመው የነበሩት ኮሎኔል ጽጌ ጠባቂው ድንገት መሬት ላይ ተኝቶ የነበረው ተነስቶ ወደ ሰርቪስ ክፍል እንደሸሸና ሊይዘው ከሞከረ ሌላ ጠባቂ ጋር የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸውን ያስታውሳሉ። በ 2005 ዓ.ም በጡረታ ተሰናብተው የነበሩት ሜ/ጀነራል ገዛኢ አበራ፣ ለአጭር ጊዜ በግል ሥራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ቢሆንም፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የስልጣን ዘመን ተመልሰው በሙያቸው እንዲያገለሉ ተጠርተው እስከተገደሉበት ቀን ድረስ የመንግሥት ሥራ እየሰሩ እንደነበር ባለቤታቸው ወ/ሮ አበባ ዘሚካኤል ይናገራሉ። "በፐብሊክ ሰርቪስ አውቶቡሶች ቦርድ ሆኖ አቋቁሟል፣ በባሕርና ሎጂስቲክስ እንዲሁም ትራንስፖርት ሚኒስቴር ብዙ ሥራ ይሠራላቸው ነበር። ውጭ አገር እየተላከ ብዙ ስራ ይሰራ ነበር። ለመከላከያም የተለያዩ ስልጠናዎችን ሲሰጥ ቆይቷል። ለስሙ ጡረታ ወጣ ተባለ እንጂ የመንግሥት ሥራ ነበር የሚሰራው" ይላሉ። እሁድ ጠዋት ወደ መቀለ ለመጓዝ ፕሮግራም የነበራቸው ሜ/ጀነራል ገዛኢ አበራ፤ ቅዳሜ ሰኔ 15 አመሻሽ ላይ ለሥራ ጉዳይ ወደ ጀነራል ሰዓረ ቤት ጎራ አሉ። "ለሥራ ጉዳይ ነበር የሄደው። በመሃል ደውዬ 'አልመሸም?" አልኩት። 'እሺ ሰዓረ ስልክ ስለያዘ አልጨረስንም፤ መጣሁ' አለኝ። የመጨረሻ ንግግራችን ነበር። ቆይቼም ደውዬለት ነበር፤ ስልኩን አያነሳም። በኋላ ተደውሎ ተነገረኝ" በማለት ባለቤታቸው ሁኔታውን ያስታውሳሉ። "ጡረታ ቢወጣም አርፎ አያውቅም። ሁሌም ተው ለራስህ ጊዜ ስጥ እለው ነበር። እሱ ግን 'እኛ ከሞቱት ትርፍ ነን፤ ለመንግሥት እና ለአገር ነው እያገለገልኩ ያለሁት' ነበር የሚለኝ" ይላሉ። ግድያው ከተፈጸመ አንድ ዓመት የሞላው ቢሆንም ጉዳዩ በቂ ትኩረት እንዳልተሰጠው የሚናገሩት የጀነራል ሰዓረ ባለቤት ኮሎኔል ጽጌ አለማየሁ፣ በማኅበራዊ ሚድያ ከሚሰሙት ውጪ ስለጉዳዩ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ይህ ጉዳይ ለእኔ ትልቅ ስቃይ ነው። ሰዓረ እና ገዛኢ ሕዝብ እያገለገሉ ነው በእሳት የተቃጠሉት፡፡ . . .[ገዳዩ] ተይዟል ይባላል። . . . በፍትህ ዙርያ ምን እየተሰራ እንደሆነ የማውቀው ነገር የለም። ብዙ ሰው ይጠይቀኛል የማውቀው ነገር ግን የለም። ልባችን ጨልሟል፤ ቤታችን ጨልሟል" ይላሉ። አክለውም "ሰዓረ፤ ጠበቃ እና ጠያቂ ያጣ ሰው ነው። የሚቆምለት ሰው የለውም፤ እኛ አቅም የለንም። ከእኔ አቅም በላይ ነው። ማን ጋር ተሂዶ አቤት እንደሚባልም አላውቅም፤ ጨንቆኛል" ይላሉ። የሜ/ጀነራል ገዛኢ አበራ ባለቤትም፣ ". . .ሰዓረ እና ገዛኢ ትልልቅ መሪዎች ናቸው። የአገሪቱ ጀነራሎች ናቸው። በሥራ ላይ እያሉ ነው የተገደሉት። የፌደራል መንግሥት፣ የመከላከያ እና ደኅንነት ባለበት አገር ትልልቅ መሪዎች ማን ገደላቸው? ለምን? መልስ ማግኘት ይገባን ነበር። ለቤተሰቡ ዝምታው ከግድያው በላይ ነው የሆነብን . . ." ይላሉ። አክለውም "የማውቀውና ያነጋገረኝ ባለስልጣን የለም፤ እንደተጎዳን፣ ጥቃት እንደደረሰብን፣ ያን የመሰለ ሰው አጥተን በጭንቀትና በመጥፎ ሁኔታ ውስጥ እንዳለን ተረድቶ አይዟችሁ ያለን የለም፡፡ . . . የሚጠይቀኝ ባገኝ የሚሰማኝን እናገር ነበር. . . የኢትዮጵያ ሕዝብ ይፍረደን" በማለት ታጋይ አበባ ዘሚካኤል ለቢቢሲ ተናግረዋል።
news-45649070
https://www.bbc.com/amharic/news-45649070
የህንዶቹን አስራ አንድ አንበሶች ምን ገደላቸው?
በህንድ የሚገኙ የእንስሳት ጥበቃ ባለሙያዎች እንደገለጹት ባልተለመደ መልኩ በጉጅራት ግዛት ሞተው የተገኙትን 11 የእስያ አንበሶች የሞት ምክንያት እያጣሩ ነው።
የእስያ አንበሶች እ.አ.አ ከ2008 ጀምሮ በመጥፋት ስጋት ላይ ያሉ እንሰሳት ተብለው ነበር። በጉጅራት እንስሳት መጠበቂያ ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ የእስያ አንበሶች ይገኛሉ። ነገር ግን ይህን ያክል ቁጥር ያላቸው አንበሶች በተመሳሳይ ሰአት መሞታቸው በእንስሳት መጠበቂያው ውስጥ ያለውን አስቸጋሪ ሁኔታ የሚያሳይ ነው ተብሏል። እስካሁን ድረስ ለአንበሶቹ ሞት ምክንያት የሆነው ነገር ባይታወቅም፤ አንበሶቹ በመጠበቂያ ውስጥ የአደንና የማረፊያ ቦታ ለማግኘት በሚደርጉት ፍልሚያ ሳይሆን እንዳልቀረ ባለሙያዎቹ ገምተዋል። • ከአዕዋፍ እስከ አንበሳ ያሉ እንስሳት በግለሰቦች እጅ ለስቃይና ለጉዳት እየተዳረጉ ነው። • አንበሶችን ያባረረው ወጣት ምን አጋጠመው? የእንስሳት ጥበቃ ባለሙያው ጂኬ ሲንሃ እንደተናገረው ከሌላ አካባቢ የመጡ ሶስት አንበሶች መጠለያ ውስጥ የነበሩ ሶስት ደቦሎችን የገደሉ ሲሆን፤ የዚህ አይነት ባህሪ በአንበሶች ዘንድ የተለመደ ነው ብሏል። የተቀሩት ስምንት አንበሶች ግን በምን ምክንያት እንደሞቱ የታወቀ ነገር የለም። በህንዷ ጉጅራት ግዛት በሚገኘው የእንስሳት መጠበቂያ ውስጥ የሚኖሩት አንበሶች ከቦታው ጠባብነት የተነሳ የሚበሉትን ምግብም ሆነ መጠለያ ለማግኘት ከፍተኛ ትግል ማድረግ አለባቸው። በእንስሳት መጠበቂያው ከሚኖሩ አንበሶች መካከል 60 በመቶ የሚሆኑት የሚሞቱት በተፈጥሯዊ ምክንያት ሲሆን የተቀሩት 30 በመቶዎች ግን ተፈጥሯዊ ባልሆኑና ምክንያታቸው ባልታወቁ አጋጣሚዎች ይሞታሉ። • ከሺዎች እስከ ኳትሪሊየን እንስሳት በአንድ ቀን የሚወለዱባት ምድር • የዕለት ከዕለት ኑሮን የሚለውጡ ፈጠራዎች የአንበሶች አማካይ የመኖሪያ ዕድሜ ከ15 እስከ 16 ዓመት ሲሆን፤ ከ10 ዓመት በኋላ ግን አድኖ የመብላትና የመንቀሳቀስ አቅም ስለማይኖራቸው በአንድ አካባቢ ተወስነው የእርጅና ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ። የእንስሳት ጥበቃ ባለሙያው ጂኬ ሲንሃ ሌላ መላ ምት አስቀምጧል። ለቢቢሲ እንደተናገረው ''ሲዲቪ'' የተባለ በውሾች የተላለፍ ቫይረስ ሊሆን ይችላል አንበሶቹን የገደላቸው። የእንስሳት መጠበቂያው በቂ ጥበቃ ስለማይደረግለት አንበሶች ወደ ሰዎች መኖሪያ የሚወጡ ሲሆን፤ ውሻዎችም ቢሆን ወደ ጥብቅ ክልሉ ይገባሉ።
news-52208067
https://www.bbc.com/amharic/news-52208067
አሜሪካ የአል ሻባብን መስራች መግደሏን አስታወቀች
አሜሪካ የታጣቂ እስላማዊ ቡድን አል ሻባብ መስራች አባል የነበረውን ዩሱፍ ጂስ በሶማሊያ በፈጸመችው የአየር ጥቃት መግደሏን አስታወቀች።
ጀነራል ስቴፈን ታውንሴንድ አል-ሻባብ ግን እስካሁን ድረስ በጉዳዩ ላይ ያለው ነገር የለም፡፡ የአሜሪካ ኃይል የአፍሪካ ዕዝ አዛዥ የሆኑት ጀነራል ስቴፈን ታውንሴንድ፤ በአል- ሸባብ ውስጥ ከፍተኛ ኃላፊነት የነበረው ዩሱፍን ጨካኝና እና ገዳይ ሲሉ ገልጸውታል፡፡ ግለሰቡ በሶማሊያ እንዲሁም ከሶማሊያ ውጭ ጥቃቶችን ይፈጽሙ ነበር ተብሏል፡፡ ፕሬዝዳነት ዶናልድ ትራምፕ ሥልጣን ላይ ከወጡ በኋላ አሜሪካ በሶማሊያ ላይ የምትፈጽመው ጥቃት በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል። በመሆኑም አሜሪካ በፈጸመቻቸው የአየር ጥቃቶች በርካታ ወሳኝ የሆኑ የሶማሊያ ታጣቂዎች ተገድለዋል። ይሁን እንጂ ሁልጊዜም አንድ ጅሃዲስት በተገደለ ቁጥር ሌላኛው ቦታውን ለመተካት ጊዜ አይወስድበትም። አል ሻባብ በሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች ኢላማዎቹን የመምታትና ግዛቶችን የመቆጣጠር አቅሙ እስካሁንም እንዳለ ነው። ጀኔራል ቶውንሴንድ እንዳሉት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት አሜሪካ ሶማሊያ ውስጥ የምትፈጽመውን ጥቃት ለማቆም ያሰበች ነው። ነገር ግን የአልቃዳ መሪዎች፣ አል ሸባብ እና እስላማዊ ታጣቂ ቡድን አይ ኤስ የሽብር አጀንዳቸውን ለመፈጸም ወረርሽኙን እንደመልካም አጋጣሚ እንደሚጠቀሙት ስላስታወቁ አሜሪካ ጥቃቷን መቀጠል እንዳለበት ወስናለች። በሌላ በኩል የመብት ተሟጋቾች አሜሪካ በምትፈጽማቸው ጥቃቶች በርካታ ንጹሃን ሰዎች ለመገደላቸው ማስረጃ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡ አሜሪካ በምታደርሰው ጥቃት ንጹሃ ዜጎች መገደላቸውን በተመለከተ አልፎ አልፎም ቢሆን ትቀበላለች።
news-54875296
https://www.bbc.com/amharic/news-54875296
ትግራይ፡ በማይካድራ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን አብንና የአማራ ብልጽግና ፓርቲዎች ገለጹ
በሰሜን ምዕራብ የኢትዮጵያ ክፍል ሁመራ አቅራቢያ ማይካድራ ከተማ ውስጥ በሚገኙ በርካታ ነዋሪዎች ላይ ግድያ መፈጸሙን ሁለት የአማራ ክልል ፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ።
ጥቃቱ ተፈጸመ የተባለበት ማይካድራ ከሁመራ ከተማ በቅርብ እርቀት ላይ ትገኛለች ገዢው የአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲና ተቃዋሚው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ክሰተቱን አስመልከተው ባወጡት መግለጫ ላይ እንዳሰፈሩት በአካባቢው የነበረው የህወሓት ኃይል በአገሪቱ የመከላከያ ኃይል ተመትቶ ለመሸሽ በተገደደበት ጊዜ በማይካድራ ከተማ ነዋሪዎች ላይ ግድያ ፈጽሟል ብለዋል። የአማራ ክልል መንግሥት የሚያስተዳድረው መገናኛ ብዙሃንም በማይካድራ ነዋሪዎች ላይ ግድያ ተፈጽሟል ሲል ዘግቧል። ቢቢሲ በጉዳዩ ላይ ያነጋገራቸው የትግራይ ክልል የሕዝብና የመንግሥት ግንኙነት ምክትል ኃላፊ አቶ ሃዱሽ ካሱ የትግራይ ልዩ ኃይል "በምንም ዓይነት ሁኔታ ዘርን መሰረት አድርጎ ጥቃት አይፈጽምም" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። "የትግራይ ሕዝብና መንግሥት የዘር ፖለቲካ የሚከተሉ አይደሉም" ያሉት አቶ ሃዱሽ፤ የሚፈጸሙ ሌሎች ድርጊቶችን ለመሸፋፈን የተጠቀመበት ነው ሲሉ ገልፀዋል። በማይካድራ ከተማ ነዋሪዎች ላይ ተፈጸመ የተባለውን ጥቃት በተመለከተ ከአካባቢው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ቢቢሲ ጥረት ቢያደርግም ለጊዜው አልተሳካለትም። የአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ "ዝርዝሩ በፌደራል መንግሥት በስፋት እንደሚገለፅ ብንጠብቅም፤ ከትህነግ ቡድን ነፃ በወጣችው የማይካድራ ከተማ ነዋሪ በሆኑ የአማራ ወገኖቻችን ላይ ወንጀል ተፈፅሞባቸዋል" ሲል ገልጿል። ጨምሮም በዚህ ድርጊት የተገደሉት ሰዎች ቁጥር በሂደት ተጣርቶ ይፋ የሚደረግ መሆኑን በማመልከት "ግድያው በዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የሚያስጠይቅ ወንጀል መሆኑን እናምናለን" ብሏል። ተቃዋሚው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄም (አብን) ባወጣው መግለጫ ላይ በሽሽት ላይ ያለው ታጣቂ ኃይል "በማይካድራ ከተማና አካባቢው የነበረው የትሕነግ ጦር ከተማዋን ከመልቀቁ በፊት ንፁሀን ሰላማዊ ዜጎች ላይ ወንጀል እንደፈፀመባቸው" ተመሳሳይ ክስ አቅርቧል። ንቅናቄው ጨምሮም በጥቃቱ ህፃናትና ሴቶች ሳይቀሩ በአሰቃቂ ሁኔታ በጅምላ መገደላቸውን ገልጿል። የአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ "አሰቃቂ ወንጀል" ያለው ድርጊት የተፈፀመው "በሕዝቦች መካከል የእርስ በርስ ጦርነት እንዲቀሰቀስ ታስቦ መሆኑን" በመጥቀስ፤ የአማራ ሕዝብ "የትግራይን ሕዝብ እንደ ትላንቱ ሁሉ ዛሬም ከየትኛውም ጥቃት ጥላ ከለላ ሁነህ ይህን ጊዜ እንድታሳልፈው ይሁን" ሲል አሳስቧል። በተለያዩ አካባቢዎች ላይ ተመሳሳይ ጥቃቶች ሊፈጸሙ ይችላሉ ብሎ የሰጋው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) መንግሥት የቅድመ መከላከልና ንፁሀንን የመታደግ ሥራ ላይ ትኩረት እንዲደረግ በአፅንኦት ጠይቋል። ከዚህ ቀደም በደቡብና በኦሮሚያ ክልሎች ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች መፈጸማቸውን መንግሥት መግለጹ የሚታወስ ነው። አብን አክሎም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን የሚያጣራ ገለልተኛ ኮሚሽን እንዲሰየም አብን በመግለጫው ጠይቋል። በፌደራል መንግሥቱና በትግራይ ክልል አስተዳደር መካከል ለወራት የዘለቀው ውዝግብ ተካሮ በክልሉ በሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት መፈጸሙን በመግለጽ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ማዘዛቸው ይታወሳል።
48769919
https://www.bbc.com/amharic/48769919
የባለአደራ ምክር ቤት አባላት ከ 'መፈንቅለ መንግሥቱ' ጋር በተያያዘ በሽብር ፍርድ ቤት ቀረቡ
የፌደራል ፖሊስ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመሆን በአንድ መዝገብ ስድስት ተጠርጣሪዎችን ዛሬ ፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ የወንጀል ችሎት አቅርበዋል።
ግለሰቦቹ አንደኛ ተጠርጣሪ በሪሁን አዳነ፣ መርከቡ ኃይሌ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ ጌዴዮን ወንድወሰን፣ ማስተዋል አረጋና አቶ ሐየሎም ብርሃኔ ናቸው። ፖሊስ ግለሰቦቹ ፍርድ ቤት የቀረቡት በአማራ ክልል ተፈፀመ በተባለው "መፈንቅለ መንግሥት" እና አዲስ በአበባው ግድያ "እጃቸው አለበት፤ በተለያየ ደረጃ ተሳትፎ ያላቸው ስለሆነ ጠርጥሬያቸዋለሁ ፤ ህገ መንግሥታዊ ስርዓት ለመናድ፤ በሽብር ተግባር ተሳትፈዋል።" በማለቱ እንደሆነ የአራቱ ጠበቃ የሆነው አቶ ሄኖክ አክሊሉ ለቢቢሲ ገልጿል። አቶ መርከቡ ኃይሌና አቶ ስንታየሁ ቸኮል የምክርቤቱ አመራሮች ሲሆኑ አቶ ጌዴዮን ወንድወሰንም የባላደራ ምክር ቤቱ አባል ነው። አቶ በሪሁን አዳነ ጋዜጠኛ ሲሆን፤ አቶ ማስተዋል አረጋ የኮሌጅ መምህር መሆናቸውን የገለፀው አቶ ሄኖክ አቶ ኃየሎም ብርሃኔ ስለተባሉት ተጠርጣሪ ዝርዝር መረጃ እንደሌለው አመልክቷል። • የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክርቤት መግለጫ ምን ይላል? • "የዲሞክራሲ ጥማት የማይቀለበስበት ደረጃ ላይ መድረሱን ተመልክቻለሁ" ጠበቃው እንዳሉት ግለሰቦቹ በፀረ ሽብር አዋጅ መሰረት 28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል። ተጠርጣሪዎቹ አደረጉት የተባለው ነገር ተለይቶ በዝርዝር የቀረበ ሳይሆን በደፈናው "በመፈንቅለ መንግሥቱ" ጠርጥሬያቸዋለሁ የሚልና ዝርዝር ያልቀረበበት ነው። ስለዚህም በመፈንቅለ መንግሰቱ ይህን ይህን አድርገዋል ብለህ በሁሉም ተከሳሾች ላይ አቅርብ፣ በሁለተኛ ደረጃ በዛሬው እለት ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን ይዞ ስላልመጣ እነሱ ደግሞ የተከበረው ፍርድ ቤት መዝገቡን ይይልን እነዚህን ሰዎች ለመያዝ ምንም የሚያስጠረጥር ምክንያት የለም ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ማስረዳታቸውን ጠበቃ ሔኖክ ተናግረዋል። ክስ እንዳልተመሰረተ የሚናገረው አቶ ሔኖክ ማስረጃ ሊያሸሹ ስለሚችሉ በማረፊያ ቤት ቆይተው ምርመራው እንዲቀጥል ፖሊስ በጠየቀው መሰረት ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ፖሊስ አደረጉት የሚባለውን ነገር በዝርዝር ለየብቻ እንዲያቀርብ፤ የምርመራ መዝገብ ይዞ ባለመቅረቡም፤ የምርመራ መዝገብ ይዞ እንዲቀርብ በማለት ለሐምሌ 17 ቀጠሮ ትእዛዝ መስጠቱንም ያስረዳል። • “የኢህአፓና መኢሶን ነገር አማራ ክልል ላይ ሊከሰት ይችላል ብዬ ነበር” ግለሰቦቹ በትክክል መቼ እንደተያዙ ዝርዝሩን ባያውቅም ጥቃቱ ተፈፀመ ከተባለበት ከሰኔ 15 ቀን 2011ዓ.ም በኋላ ሰኔ 17 እና 18 መያዛቸውን ይናገራል። ተጠርጣሪዎቹ ባህርዳር ሄደው ነበር ? ለሚለው ጥያቄ በሁሉም እርግጠኛ ባይሆንም ከሳምንት በፊት አቶ ስንታየሁ ወደ ባህር ዳር እንደሄደ፤ ባህርዳር የሄዱት በመኪና ባላደራ ምክርቤቱ እሁድ እለት ሊያደርገው ለነበረው ህዝባዊ ስብሰባ እንደነበር ሄኖክ አስረድቷል። "ፖሊስ እንዳለው በስልክ እየተነጋገሩ ከጉዳዩ ጋር የተገናኘ ነገር ይፈፅሙ ነበር የሚል ጉዳይ አንስቷል። ፖሊስም ሁሉም ባህርዳር ሄደዋል ሳይሆን የሚለው ባህርዳር የሄዱትና ያልሄዱት ተሳትፎ አድርገዋል የሚል ነው" ሲልም አክሏል። ስድስተኛው ተጠርጣሪ ጄኔራል ሰዓረና ሜጀር ጄኔራል ገዛኢ አበራ ሽኝት ፕሮግራም ላይ "የሃገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ባሉበት ጥቃት ለማድረስ መሳሪያ ይዘው ተገኝተዋል" በሚል ሲያዝ ግለሰቡም የጥበቃ ስራ ስለሚሰራ መሳሪያ እንደያዘ ለፍርድ ቤቱ ማስረዳቱን አቶ ሔኖክ ይናገራል።
news-56884833
https://www.bbc.com/amharic/news-56884833
ኮቪድ-19፡ ቤት የመቀመጥ ገደብ ጉግልን ትርፋማ አድርጓል ተባለ
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ የተጣለው ቤት ውስጥ የመቀመጥ ገደብ ለጉግል ትርፋማነት አስተዋጽኦ አድርጓል ተባለ።
የጉግል ባለቤት ድርጅት የሆነው አልፋቤት ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ 17 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ትርፍ ያገኘ ሲሆን ይህም የ162 በመቶ ጭማሪ መሆኑ ተገልጿል። ለትርፋማነቱም ሰዎች በወረርሽኙ ሳቢያ እንቅስቃሴያቸው ሲገደብ የጉግልን አገልግሎቶች መጠቀማቸው በምክንያትነት ተቀምጧል። ያለፉት ሦስት ወራትም በድርጅቱ ታሪክ ከፍተኛ ትርፍ የተመዘገበበት ነው ተብሏል። ጉግል ይህን የትርፍ መጨመር "ደንበኞቼ ኢንተርኔት በመጠቀም የሚያከናውኗቸው ተግባራቶች መጨመር ያመጣው ነው" ሲል ገልጾታል። "ባለፈው ዓመት ሰዎች የጉግል መፈለጊያን ተጠቅመው ራሳቸውን ከመረጃ ላለማራቅ፣ ለመዝናናት እና ከሰዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማስቀጠል ሲጠቀሙት ቆይተዋል" ሲሉ የአልፋቤት እና ጉግል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሱንዳር ፒቻዪ ገልጸዋል። የዘርፉ ተንታኞችም የተዘጉ ኢኮኖሚዎች ሲከፈቱ እና የኢንተርኔት ላይ ማስታወቂያዎችም እየተበራከቱ ሲሄዱ ጉግል ከፍተኛ ትርፍ መሰብሰቡን ይቀጥላል ብለዋል። ጉግል ባለፈው ሦስት ወራት በአጠቃላይ ከመፈለጊያ ንግዱ [Search business] የሰበሰበውን ገቢ በ30 በመቶ በመጨመር ወደ 31 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ብሏል። ዩትዩብ ደግሞ በስድስት ቢሊዮን ዶላር ገቢ የ49 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። በሃርግሬቭስ ላንሱንግ የፍትሐዊነት ተንታኝ የሆኑት ሶፊ ሉንድ-ያትስ በበኩላቸው አልፋቤት "ጉግል በወረርሽኙ ሳቢያ በተገኘው ገቢ ልክ በክሬም ላይ እደተወረወረች ትልቅ ድመት ሆኗል" ሲሉ ትርፉን ገልጸውታል። የቴክኖሎጂ ግዙፉ ኩባንያ ጉግል፤ ባልተለመደ መልኩ የማስታወቂያ ንግድ ድርጅት ወደመሆን ማዘንበሉንም ተንታኙ ተናግረዋል። "የኮሮናቫይረስ ሲከሰት በተለይም የኢንተርኔት ላይ ግብይት በመጧጧፉ ምክንያት የአልፋቤት የንግድ ተቋማት ለእነዚህ ሸቀጦች ማስታወቂያ ማስነገራቸው ገቢያቸው እንዲተኮስ ምክንያት ሆኗል" ሲሉም ለከፍተኛ ትርፍ ያበቃውን ምክንያት አስረድተዋል። ይሁን እንጂ ጉግል ከተለያዩ ተቆጣጣሪ ተቋማት በተለይም ፍትሐዊ የንግድ ውድድርን እና የግል ምስጢር መጠበቅን በተመለከተ እያጋጠመው ያሉት ጥያቄዎች ዋና ተግዳሮቶቹ ሆነው ቀጥለዋል።
news-50285604
https://www.bbc.com/amharic/news-50285604
ኢትዮጵያና ኤርትራን የምታገናኘው ዛላምበሳ
ኢትዮጵያና ኤርትራ የሚዋሰኑበት የጉሎመኸዳ አካባቢ አርሶአደሮች መሃል አስፋልት መንገድ ላይ የታጨደ በመከመር እህል ከገለባ መለየቱን ተያይዘውታል። መንገዱ እንኳን መኪና ሰውም እየረገጠው አይደልም።
በተሽከርካሪ መንገድ ላይ እህል ሲወቃ "የዛላምበሳና አምበሰት ገለባን ህዝብ ከመለያየት ወሃን ከወተት መለየት ይቀላል" ይላሉ አዋቂዎች። ያኔ ድሮ ወንድም ከወንድም አልያም እህት ከእህት ሲጋጩ፤ እረኞች ሲኮራረፉ ኩርፊያው በአገር ሽማግሌዎች ይቀዘቅዝ ነበር። አምና መስከረም ወር ላይ የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥታት ስምምነት ላይ ሲደርሱ ህዝቡ ለራሱ በማሰብ የሰላም ሂደቱን ደግፏል። ዝሆኖች ሲጣሉ የሚጎዳው ሳሩ ነው እንዲሉ በጦርነቱ ህዝቡ ከፍተኛ ዋጋ ከፍሏል። • ኢትዮጵያና ኤርትራ የት ድረስ አብረው ይራመዳሉ? ድንበሩ ተዘግቶ በቆየባቸው 20 ዓመታት ውስጥ ከአንዱ ወገን የከበሮና ማሲንቆ ድምጽ ሲሰማ 'ማን ይሆን ወግ የደረሰው?' በማለት ባለበት ሆኖ ደስታውን ይጋራል። የጩኸትና ጥሩንባ ድምጽ በሰማ ቁጥርም ሐዘን እንደገጠመ ስለሚረዱ ገጻቸው ይገፋል። የመንግሥታቱን ስምምነት ተከትሎ የተከፈተው ድንበር ተመልሶ ሲዘጋ ቀድሞ ወደ ነበረው መለያየትና ችግር አንመለስም ያለ ህዝብ ድንበር ጥሶ በሌሊት ሳይሆን በቀን እየተገናኘ ነው። እንደገና ወደ ዛላምበሳ አቶ ዳኘው መዝገቦ ከሁለቱም ወገን ይወለዳሉ። የዛሬን አያርገውና ዕድሜ ተቆጥሮ እግራቸው መራመድ ሳያቅተው ከ20 ዓመት በፊት በዛላምበሳ 'መረብ' የሚባል ሆቴል ከፍተው ይሰሩ ነበር። ሁለቱ መንግሥታት ወደ ጦርነት በሚገቡበት ወቅት የጭነት መኪና እያሽከረከሩ ወደ ኢትዮጵያ ሄደው ሲመለሱ ጎንደር ላይ "በመጠጥ ወሃ ላይ መርዝ ለመጨመር ሞክሯል" በማለት አንድ ሰው ጥቆማ ሰጠ። ለተወሰነ ጊዜ እዚያው ታስረው ከቆዩ በኋላ ወደ ኤርትራ ተባረሩ። በዛላምበሳ ከተማ የነበረው መኖርያ ቤታቸውም በጦርነቱ ምክንያት ወደመ። ሆቴላቸውም በልጃቸው በኩል ለሌላ ሰው ተከራየ። • መስመር ያልያዘው የኢትዮ-ኤርትራ የንግድ ግንኙነት ወዴት ያመራል? አቶ ዳኘው አንድ ቀን "መንጋቱ አይቀርም" በማለት በኤርትራ ዓዲ ቀይሕ በሚባል ቦታ ሌላ 'መረብ' የተባላ ሆቴል በመክፈት ሥራቸውን ቀጠሉ። አቶ ዳኘው ሳይሞቱ ይጠብቁት የነበረው ቀን ደረሰ፤ የ75 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ ሆነው ዘላምበሳ ገቡ። 'መረብ ሆቴል' የሚል ጽሑፍ የሰፈረባት ሰሌዳቸው በበርካታ ጥይቶች ተበሳስታ አገኗት። በዚህ ተስፋ ሳይቆርጡ ሌላ ባለ አምስት ፎቅ ህንጻ ለመገንባት ቆርጠው ተነሱ። ዛሬ ላይ የህንጻው ሁለተኛው ፎቅ በማለቁ መረብ ሆቴልን በአዲስ መልኩ ከፍተው ሥራ ጀምረዋል። ለማስታወሻነትም በጥይት የተበሳችው ሰሌዳም ለማስታወሻነት ቦታዋ ላይ ትገኛለች። "እኔ ግንባታ ከጀመርኩ በኋላ ብዙ ሰዎች ተከትለውኛል። እየዘዋወረ በከተማዋ ውስጥ እየተሰራ ያለውን ለሚያይ ከተማዋ እንዴት እየሰፋች መሆኗን አይቶ መመስከር ይችላል" ይላሉ። በእርግጥም ዛላምበሳ መልሳ በሁለት እግሯ ለመቆም እየተነቃቃች ነው። ነዋሪዎቿ ዛሬም ተስፋ አልቆረጡም። ነገ ሌላ የተሻለ ቀን እንደሚመጣ ተስፋ በማድረግ ህንጻዎች መገንባታቸውን ቀጥለዋል። የአቶ ዳኘው መረብ ሆቴል የዛላምበሳ ገበያ በዕለተ ቅዳሜ የዛላምበሳ ገበያ ይደራል:፤ ኤርትራዊያን የገለባ ገጠር ኗሪዎች በጧት ወደ ከትማዋ ይተማሉ። ምንም እንኳን በኬላው ይገባ የነበረው ህዝብ ቢከለከልም ገደልና ሸንተረሩን አቆራርጦ በሌላ አቅጣጫ መግባቱን እንዳልተወ የከተማዋ ነዋሪዎች ይናገራሉ። ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡትን ኤርትራዊያን መጀመሪያ ወደ ዛላምበሳ ሲገቡ ናቅፋን ወደ ብር የሚመነዝሩ ኢትዮጵያዊያን አግኝተው ለመገበያየት የሚፈልጉትን ያህል ብር የመነዝሩላቸዋል። • ኤርትራ፡"እያስተማሩን ሳይሆን ባሪያ እያደረጉን ነው" በከተማዋ አንድ መቶ ናቅፋ በ230 የኢትዮጵያ ብር በጥቁር ገበያ እንደሚመነዘር ይህንን ከሚሰሩት ሰዎች አንዱ ይናገራል። ወደ ኢትዮጵያ የገባውን ናቅፋ ደግሞ መልሰው ገንዘቡን ለሚፈልጉ ኤርትራዊያን በ232 ይሸጡላቸዋል። ግልጽ ሜዳ ላይ በሚካሄደው የዛላምበሳ ገበያ ከሽንኩርት እስከ የቤት ውስጥ ቁሳቁሶች ይሸጣል። በሂደቱም ኢትዮጵያዊያን ይሸጣሉ ኤርትራዊያኑ ደግሞ ይገዛሉ። ቢቢሲ በገበያው ውስጥ ያገኛቸው አንዲት እናት እንደሚሉት ከኤርትራ የሚገባ የሚሸጥ ሸቀጥ የለም። ጤናን ፍለጋ ዛላምበሳ ከተማ ውስጥ የሚገኘው የጤና ጣቢያ የሁለቱንም አገር ህዝቦች ያገለገላል። አገልግሎቱ ብቻም ሳይሆን ክፍያውም አንድ አይነት ነው። የጤና ጣቢያው ተወካይ ሜዲካል ዳይሬክተር ሳምራዊት ብርሃነ እንደምትለው ኤርትራዊያኑ ወደ ጤና ጣቢያው የሚመጡበት ዋና ምክንያት በአቅራቢኣቸው የሚገለገሉበት ተቋም ስለሌላቸው መሆኑን እንደነገሯትና የተሻለ የህክም አገልግሎት ፍለጋም የሚመጡ እንዳሉም ትናገራለች። • ኤርትራ ፖለቲከኞችን እና ጋዜጠኞችን እንድትለቅ ተጠየቀ ቢሆንም ግን የጤና ጣቢያው የላቦራቶሪ መሳሪያ እንደሌለውና ምርመራ ለማሰራት በአቅራብያ ወደምትገኘው የፋፂ ከተማ ሆስፒታል መሄድ እንደሚጠበቅባቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ይናገራሉ። ለዚህ ደግሞ 17 ኪሎ ሜትር መጓዝ የግድ ነው። የዛላምበሳ ገበያ ተስፋ በጦርነቱ ወቅትና ከዚያም በኋላ በቅርብ ርቀት የሚያዩትን የእርሻ ማሳቸው እንኳን አርሰው ለመጠቀም ሳይችሉ መቆየታቸውን በማስታወስ መቀራረቡ ብዙ ነገሮችን እንደቀየረ ይናገራሉ። በአሁኑ ጊዜ የሁለቱም ወገን ያሉ እረኞች በአንድ መስክ ላይ እንደሚውሉ እንዲሁም ህዝቡ በአንድ ጥላ ስር ሃዘኑንም ሆነ ደስታውን የመጋራት ዕድል አግኝቷል። ከሁለቱም አገራት ህዝብ የሚሰማው ተስፋና ምኞት "ከአሁን በኋላ ወደ ነበርንበት መለያየት አንመለስም" የሚል ነው። • እንቅስቃሴ አልባዋ ምጽዋ በመጪው የኅዳር ላይ በሚከበረው የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ሐይማኖታዊ ጠበል ጸዲቅ ሥነ ሥርዓት ላይ ለመታደም ከዛላምበሳ ከተማ ወደ ጎረቤት የገለባ የገጠር መንደር እንደሚሄድ አንድ ወጣት ለቢቢሲ ተናግሯል። ይህም ምንም እንኳን የሁለቱም አገር መንግሥታት ቀጣይ ግንኙነታቸው የሚመራበትን ሥርዓት አስቀምጠው ባያጠናቅቁም ህዝቡ ግን ቀድሞ የተቋረጠውን ግንኙነት ጠግኖ ከመደበኛው ደረጃ ላይ ያደረሰው ይመስላል። የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ የማይታይበት የዛላምበሳ የመኪና መንገድም ጭር ከማለት ተላቆ ተላቆ ድንበሩ በተከፈተበት ወቅት እንደነበረው ዳግም አውቶቡሶችን በቅርቡ ማስተናገድ ይጀምራል ብለው ነዋሪዎች ተስፋ እየተጠባበቁ ነው።
news-53536500
https://www.bbc.com/amharic/news-53536500
የአንዲት የቴሌቪዥን ተመልካች የላከችው መልዕክት የጋዜጠኛዋን ጤና ታደገ
የጋዜጠኛዋ አንገት እብጠት መጨመሩን ያስተዋለች ተመልካች ለጋዜጠኛዋ ያደረሰችው መልዕክት የጋዜጠኛዋን ጤና ታድጓል።
የፍሎሪዳዋ ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ፕራይስ የያዛት ካንሰር እያደገ መምጣቱን ተመልክታ መልዕክት ለላከችላት ተመልካቿ ምስጋናዋን አቅርባለች። “ባለፈው ወር ከአንድ ተመልካች የኢሜይል መልዕክት ደረሶኝ ነበር” ስትል ለአንድ የፍሎሪዳ ግዛት ቴሌቪዥን ጣቢያ በዘጋቢነት የምትሠራው ቪክቶሪያ ፕራይስ ጽፋለች። “አንገቴ ላይ እብጠት ተመልክታ ‘እኔን አስታወስሽኝ’ ስትል ጻፈችልኝ” ብላለች ዘጋቢዋ። “የእሷ ካንስር ነበር። የእኔም ካንሰር ሆኖ ተገኝቷል” ብላለች ዘጋቢዋ ቪክቶሪያ ፕራይስ። ህክምናዋን ለመከታተል ሥራ ማቆሟንም ጋዜጠኛዋ ተናግራለች። በስም ያልተጠቀሰውችው የኢሜይል መልዕክቱን የላከችላትን ሴትን እጅግ በጣም አድርጌ አመሰግናለሁ ያለችው ጋዜጠኛወዋ፤ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን በሙሉ ትኩረት እየዘገበች ለራሷ ጤና ትኩረት ሳትሰጥ መቆየቷን ተናግራለች። “የክፍለ ዘመናችን ጉዳይ የሆነውን ኮሮናቫይረስ በምዘግብበት ወቅት የእኔ ጤና አነስተኛ ትኩረት ልሰጠው የምችለው ነገር ነበር” ብላለች። ከተመልካቿ መልዕክት ከደረሳት በኋላ ወደ ጤና ተቋም የሄደችው ቪክቶሪያ፤ የጉሮሮ ካንስር እንዳለባት እና አንገቷ ላይ ያለው እብጠት በቀዶ ጥገና መወገድ እንዳለበት ተነግሯታል። “ዶክተሮቹ አንገቴ ላይ ያለው እጢ እያደገ ስለሆነ በአስቸኳይ መነሳት እንዳለበት ነግረውኛል። የፊታችን ሰኞ የቀዶ ህክምና አደርጋለሁ” ብላለች። “ኢሜይሉ ባይደርሰኝ ኖሮ፣ ወደ ህክምን አልሄድም ነበር። ካንሰሩ አድጎ እጅግ አሰፈሪ ነገር ይከሰት ነበር” ስልት ጋዜጠኛዋ ጽፋለች። ተመልካቾች በቴሌቪዥን የሚመለከቷቸው ጋዜጠኞች የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ ሲያሳስቡ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። የቢቢሲውን ስፖርት ጋዜጠኛ ማርክ ላውረንሰንን የስፖርት ዘገባዎች ይመለከት የነበረ አንድ የጤና ባለሙያ ላውረንሰን ምርመራ እንዲያደርግ በጠቆመው መሠረት ላውረንሰን የካንሰር ህክምና እንዲጀምር አድርጎታል። ይህም ብቻ ሳይሆን ታሬክ ኤል ሙሳ የተባለው ጋዜጠኛ አንድ ነርስ አንገቱ ላይ ያስተዋለችውን እብጠት በተመለከተ ባደረሰችው ጥቆማ መሠረት ጋዜጠኛው ባደረገው ምርመራ ሁለተኛ ደረጃ ደርሶ ከነረው የጉሮሮ ካንሰር መዳን ችሏል።
news-42424927
https://www.bbc.com/amharic/news-42424927
ጉግል ስለእርስዎ የያዘውን መረጃ መሰረዝ እንደሚችሉ ያውቃሉ?
ወደ በይነ-መረብ (ኢንትርኔት) ገብተን ስለአንድ ነገር ለመፈለግ በዓለም ታዋቂውን የበይነ-መረብ ጉግልን እንጠቀማለን።
ጉግል ስለተጠቃሚዎቹ ብዙ ነገሮችን ያውቃል በዚህም ስለምን ጉዳይ እንደፈለግን፣ ፍላጎታችን ምን እንደሆነ፣ የትኞቹን ድረ-ገፆች እንደጎበኘን እና ሌሎችም ነገሮች ተመዝግበው ይታወቃሉ። "የጉግልን አገልግሎት ሲጠቀሙ ስለግል መረጃዎ እምነት ይጥሉብናል" ይህንን ጉግል በአጠቃቀም ደንቦችና ሁኔታዎችን በመጀመሪያ መስመር ላይ በማስፈር የተጠቃሚዎች መረጃ በአስተማማኝ ሁኔታ እንደሚያዙ በግልፅ ያሰፈረበት ነው። ነገር ግን ጉግል ከዚህ አንፃር ምናልባትም የማናውቀው ነገር ቢኖር ስለአጠቃቀማችን ተሰብስቦ የተያዘውን ማንኛውንም መረጃ ''ማይ አክቲቪቲ'' ወደሚለው ክፍል በመሄድ እስከጨረሻው መደምሰስ የሚያስችል መንገድ አለው። ቀጥሎ ይህንን ለማድረግ የሚያስችሉ በርካታ ቀላል መንገዶችን ይመልከቱ። 1. የተጠቀምኩትን ሰርዝ ምንግዜም ጉግልን ተጠቅመው ስለአንድ ነገር ሲፈልጉ፤ ጉግል ከአካውንትዎ ጋር አያይዞ ያስቀምጠዋል። እያንዳንዱን በበይነ-መረብ ላይ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ፣ ማለትም ስለሞሏቸው ሰነዶች ወይም የተመለከቷቸውን ኢሜይሎች በሙሉ ምንም ሳያስቀር መዝግቦ ይይዛል። ይህ ሁሉ መረጃ ''ማይ አክቲቪቲ'' በተባለ ስፍራ ላይ ተደራጅቶ ይቀመጣል። ስለዚህ የትም ሳይሆን ወደዚህ ቦታ ቀጥታ ይሂዱ። ከዚያም የተለየ ርዕስን ወይም ገፅን የሚፈልጉ ከሆነ የመፈለጊያ መንገዱን በመጠቀም መሰረዝ፣ አሊያም ደግሞ ሁሉንም የተመዘገበ መረጃ ወይም በተወሰነ የቀን ገደብ ውስጥ ያሉትን መሰረዝ ይቻላል። በዚህ ውስጥ ''ኑክሌር ኦፕሽን'' የሚለውን ከመረጥን ሁሉንም መረጃ እስከ ወዲያኛው ለመሰረዝ ያስችላል። ሲሰርዙ ከጉግል በኩል ሊገጥምዎ ስለሚችል እርምጃ ማስጠንቀቂያ ያገኛሉ። ቢሆንም ግን በተጨባጭ የጉግል አጠቃቀምዎን የኋላ ታሪክ በመሰረዝዎ በሚጠቀሙበት የጉግል አካውንትም ሆነ መተግበሪያዎች ላይ የሚፈጠር ችግር አይኖርም። 2. በዩቲዩብ ላይ የተጠቀሙትን በሙሉ ለመሰረዝ ጉግል ዩቲዩብን በመጠቀም ስለፈለጓቸው እና ስለተመለከቷቸው ምስሎች በሙሉ መዝግቦ ይይዛል። ነገር ግን ይህም በቀላሉ ልንሰርዘው የምንችለው ነው። መጀመሪያ በግራ በኩል ካሉት ዝርዝሮች መካከል ''ሂስትሪ'' የሚለውን ይጫኑ፤ ከዚያም ''ክሊር ኦል ሰርች ሂስትሪ'' እና ''ክሊር ዋች ሂስትሪ'' የሚሉትን ይጫኑ። ወይም ፍለጋ ካደረጉባቸው ርዕሶች ወይም ከተመለከቷቸው መካከል የሚፈልጉትን መርጠው መሰረዝ ይችላሉ። 3. ማስታወቂያ አስነጋሪዎች ስለእርስዎ የሚያውቁትን ለመሰረዝ ጉግል ስለእርስዎ ሁሉንም ነገር ከማወቁም በላይ የሚያውቀውንም መረጃ ለማስታወቂያ አስነጋሪዎች አሳልፎ ይሰጣል። ለዚህም ነው ከእርስዎ በጉግል አማካኝነት ፍለጋ ካደረጉባቸው ነገሮች ጋር የሚመሳሰሉ ማስታወቂያዎች በተደጋጋሚ የሚያዩት። ቢሆንም ግን አያስቡ፤ ስለእርስዎ ምን አይነት መረጃዎች ለማስታወቂያ አስነጋሪዎች እንደተሰጠ ለማወቅ ይችላሉ። ይህንንም ለማድረግ ወደ ጉግል አካውንትዎ ይግቡና ''ፐርሰናል ኢንፎ ኤንድ ፕራይቬሲ'' ወደሚለውን ክፍል ይሂዱ። እዚያም ''አድስ ሴቲንግስ'' የሚለውን አማራጭ በመጫን ''ማኔጅ አድስ ሴቲንግስ'' ወደሚለው ይሂዱ። ከዚያም ''አድስ ፐርሰናላይዜሽን'' የሚል አማራጭ ያገኛሉ። እናም በስተቀኝ በኩል ያለችውን ቁልፍ በማንሸራተት ከጉግል የተገኘውን መረጃዎትን መሰረት ያደረጉ ማስታወቂያዎች እንዳይደርስዎ ማድረግ ይችላሉ። ፈፅሞ ማስታወቂያ እንዳንቀበል የምናግድበት አማራጭ ግን የለንም። ይህን ሲያደርጉ ጉግል እርስዎ ካለዎት ፍላጎት አንፃር ተመሳሳይ ማስታወቂያዎችን እንደማያዩ ያስጠነቅቅዎታል ነገር ግን የመምረጥ ውሳኔው የእርስዎ ነው የሚሆነው። 4. የነበሩባቸውን የጉግል ቦታ ጠቋሚን ለመሰረዝ የሞባይል ስልክን የመሳሰሉ ዘመናዊ የመገልገያ መሳሪያዎችን የሚጠቀሙ ከሆነ የተጓዙባቸውን ቦታዎች በሙሉ መዝግቦ ይይዛል። በጉግል ቦታ ጠቋሚ በኩል የተመዘገቡትን የእርስዎን መረጃ ለመሰረዝ ይህንን ገፅ መመልከት ያስፈልግዎታል። የቦታ ጠቋሚውን መዝጋት የሚችሉ ሲሆን ቀን ወይም ሰዓት ለይተው የተመዘገቡ ቦታ ጠቋሚ መረጃዎችን መሰረዝ ይችላሉ። በተጨማሪም ''ኦን ዘ ዌስት ባስኬት በተን'' የሚለውን በመጫን ካደረጓቸው ጉዞዎች ውስጥ ወይም ደርሰውባቸው ከነበሩ ስፍራዎች መካከል መርጠው መሰረዝ ይችላሉ።
54689433
https://www.bbc.com/amharic/54689433
ፈረንሳይ ምርቶቿ ላይ ማዕቀብ እንዳይጣል የመካከለኛው ምሥራቅ አገራትን ጠየቀች
ፈረንሳይ የተለያዩ ቁሳቁሶቿ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል የሚደረጉ ቅስቀሳዎችን የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት እንዲያስቆሙ ጠየቀች።
በኩዌት፣ ጆርዳን እና ካታር የሚገኙ አንዳንድ መደብሮች የፈረንሳይ ምርቶችን ማስወገድ ጀምረዋል ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፤ ነብዩ መሐመድን የሚያሳዩ ካርቱኖችን መሣል ይቻላል የሚል አቋም ማንጸባረቃቸውን ተከትሎ የፈረንሳይ እቃዎች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ጥሪ እየተደረገ ነው። በኩዌት፣ ጆርዳን እና ካታር የሚገኙ አንዳንድ መደብሮች የፈረንሳይ ምርቶችን ማስወገድ ጀምረዋል። በሊቢያ፣ ሶርያ እና የጋዛ ሰርጥ ተቃውሞ ተካሂዷል። ፈረንሳያዊ መምህር ሳሙኤል ፓቲ፤ የነብዩ መሐመድን የካርቱን ሥዕል ለተማሪዎቹ ካሳየ በኋላ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደሉ ይታወሳል። ክስተቱን ተከትሎ ፕሬዘዳንት ማክሮን "ኢስላሚስቶች ነጋችንን መቆጣጠር ይፈልጋሉ። ፈረንሳይ ግን ካርቱን መሥራት አታቆምም" ብለው ነበር። የነብዩ መሐመድን እንዲሁም የአላህን ምስል ማሳየት በእስልምና የተከለከለ ነው። የማክሮን ንግግርም ቁጣ ቀስቅስሷል። . በፈረንሳይ አንገቱን ለተቀላው መምህር በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ድጋፋቸውን አሳዩ . ቻርሊ ሄብዶ መፅሄት አወዛጋቢውን የነብዩ መሐመድ ካርቱንን እንደገና አተመ ፈረንሳይ ከሃይማኖት ጣልቃ ገብነት ነጻ የሆነች አገር እንደሆነች ትገልጻለች። የአንድ ማኅበረሰብን ስሜት ላለመጉዳት በመጠንቀቅ ውስጥ የንግግር ነጻነት መገደብ የለበትም የሚል አቋም ታንጸባርቃለች። ማክሮን "መቼም ቢሆን እጅ አንሰጥም" ሲሉ ትዊት አድርገዋል። በቱርክ እና በፓኪስታን ያሉ የፖለቲካ መሪዎች ማክሮንን ተችተዋል። የሃይማኖት ነጻነትን እየተጋፉ እንዲሁም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ፈረንሳይ የሚኖሩ ሙስሊሞችን እያገለሉ እንደሆነም ገልጸዋል። የቱርኩ ፕሬዘዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን ማክሮን ስለ እስልምና ያላቸውን አቋም በተመለከተ "አእምሯቸውን ይመርመሩ" ብለዋል። ፈረንሳይ ቱርክ ከሚገኙ አምባሳደሯ ጋር ለመምከር ወደ ፈረንሳይ ጠርታቸዋለች። የፓኪስታኑ መሪ ኢምራን ከሀን "እስልምናን ሳይገነዘቡ ሃይማኖቱን እያጥላሉ ነው" ብለዋል። በወሩ በባቻ ላይ ማክሮን "እስላማዊ ገንጣይ" ያሏቸው ቡድኖች ላይ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስዱ ተናግረው ነበር። የምዕራብ አውሮፓ ትልቁ የሙስሊም ማኅበረሰብ ማክሮን፤ ሃይማኖታዊ ጫና እያደረጉባቸው እንደሆነና እንቅስቃሴያቸው ሙስሊም ጠል እንደሆነ ተናግረዋል። እአአ 2015 ላይ የፈረንሳዩ ሽሙጥ አዘል መጽሔት ቻርሊ ሄድቦ ላይ በተሰነዘረ ጥቃት 12 ሰዎች መገደላቸው አይዘነጋም። መጽሔቱ የነብዩ መሐመድን ካርቱን አትሞ ነበር። የፈረንሳይ ምርቶች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል የተደረገው ቅስቀሳ ባሳለፍነው እሑድ በጆርዳን፣ ካታር እና ኩዌት ያሉ አንዳንድ መደብሮች የፈረንሳይ ምርቶችን አስወግደዋል። የፈረንሳይ ውበት መጠበቂያ ምርቶች ከመደርደሪያ ተነስተዋል። ክዌት ውስጥ ትልቁ የአከፋፋዮች ማኅበር የፈረንሳይ ምርቶች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል አዟል። የሸማቾች ማኅበርም በተደጋጋሚ ነብዩ መሐመድን የሚያጥላሉ አስተያየቶች በመሰንዘራቸው ተመሳሳይ ትዕዛዝ አስተላልፏል። የፈረንሳይ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ባወጣው መግለጫ "ምርቶች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል የተደረገው ጥሪ መሠረተ ቢስ ነው። ይህ ጥሪና በጥቂት አክራሪዎች የሚጫሩ አገሪቱ ላይ የሚቃጡ ጥቃቶች መገታት አለባቸው" ብሏል። በሳኡዲ አረቢያ እንዲሁም በሌሎች የአረብ አገራትም የፈረንሳይ ምርቶች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል የሚጠይቁ የበይነ መረብ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል። የፈረንሳዩ መደብር ካርፉር እንዲዘጋ የሚጠይቀው ሀሽታግ፤ በሳኡዲ የትዊተር ተጠቃሚዎች ዘንድ ከነበሩ አነጋጋሪ ጉዳዮች ሁለተኛውን ደረጃ ይዟል። በሊቢያ፣ ጋዛ እና ሶርያ ፈረንሳይን የሚያወግዙ ተቃውሞዎች ተካሂደዋል።
news-44409392
https://www.bbc.com/amharic/news-44409392
የአፍሪካ እግር ኳስ ቅሌት
በምዕራብ አፍሪካ እና ኬንያ ከመቶ በላይ የሚሆኑ የእግር ኳስ ሃላፊዎች ከጨዋታ በፊት ገንዘብ ሲቀበሉ የሚያሳይ የምረመራ ዘገባ በቢቢሲ ከተላለፈ በኋላ ትልቅ መነጋገሪያ ሆኗል።
ዘገባው የተሰራው በታዋቂው የጋና የምርመራ ጋዜጠኛ አናስ አረሜያው ሲሆን፤ የአፍሪካ እግር ኳስ ማነቆዎችን በግልጽ ያሳየ ነው ተብሏል። ሁለት አመት የፈጀው እና ለብዙ ሰአታት የተቀረጸው ተንቀሳቃሽ ምስል የእግር ኳስ ዳኞች እና ሃላፊዎች ጨዋታዎች ከመካሄዳቸው በፊት ገንዘብ ሲቀበሉ ያሳያል። ይህ ቢቢሲ በተንቀሳቃሽ ምስሉ የተመለከተው ተግባር እና መሰል ድርጊቶች ተወዳጁን ስፖርት ለአመታት ወደኋላ ሲጎትቱት ቆይተዋል። በምስሉ ላይ ሃላፊዎች ከጋና እና ማሊ ብሄራዊ ቡድኖች ጨዋታ በፊት ገንዘብ ሲቀበሉ ያሳያል። የተሰጣቸው ገንዘብ ውጤት ይኑረው አይኑረው ባይታወቅም በጨዋታው ጋና አሸናፊ ነበረች። ኬንያዊው ራንዤ ማርዋ የሩሲያውን አለም ዋንጫ ከሚመሩት የመስመር ዳኞች መካከል አንዱ ነው። በምስሉ ላይ 600 ዶላር ከአንድ ሰው ሲቀበል ይታያል። የምርመራ ዘገባውን የሰራው ታዋቂው የምርመራ ጋዜጠኛ አናስ አረሜያው በሙያው የተካነ ነው። ብዙዎች ባይስማሙበትም መልኩ ምን እንደሚመስል ማንም ሰው አይቶት አያውቅም። ጋዜጠኛው የተጠቀመው መንገድ ትክክል አይደለም ሲል የህግ ባለሙያ የሆነው ቻርለስ ቤንተም ይሞግታል። ''አንድን ሰው አጓጊ የሆነ ገንዘብ እንዲወስድ ማጓጓት እና ከወሰደ በኋላ ሙሰና ብሎ መጥራት ትክክል አይደለም''። ''በህጉ መሰረት ሰጪውም ተቀባዩም እኩል ጥፋተኛ ናቸው'' ይላል። አናስ በበኩሉ ስላከናወነው ተግባር የራሱ መከራከሪያ አለው። በእያንዳንዱ ጨዋታ ሁሉንም ዳኞች የሚገዙ ህግ እና ደንቦች አሉ። የአፍሪካው ካፍም ሆነ አለማቀፉ ፊፋ፤ በየጊዜውለዳኞቻቸው ስለህጉ ስልጠና ይሰጣሉ የሚለው አናስ፤ ህጉን ማክበር ግዴታቸው ነው በማለት ይከራከራል። ''ማንም ኣላስገደዳቸውም፤ ገንዘቡን ሲቀበሉ የነበሩት ህዝብ በተሰበሰበበት ቦታ ነው ሲል የጉዳዩን አሳሲቢነት ያብራራል። በዘገባው ላይ የተካተቱትን ሶስት ሰዎች ቢቢሲ ለማነጋገር እና ሃሳባቸውን ለማካተት ያደረገው ጥረት አልተሳካም። ከዘገባው በኋላ ኬንያዊው የመስመር ዳኛ ራንዤ ማርዋ ከሩሲያው የአለም ዋንጫ ራሱን እነዳገለለ ፊፋ ገልጿል። የምርመራ ዘገባው የተሰራበት መንገድ ብዙ ጥያቄዎች ቢነሱበትም፤ የስፖርቱ አፍቃሪዎች ግን እግር ኳስ ምን ያህል እንደተበከለ አሳይቶናል እያሉ ነው። ትናንት በወጡ መረጃዎች መሰረት የጋናው የእግር ኳስ ማህበር ፕሬዝዳንት ገንዘብ ሲቀበሉ ያሚያሳየው ምስል ከተለቀቀ በኋላ፤ ጋና የእግር ኳስ ማህበሯን እንዳፈረሰች ተገልጿል። በምስሉ ላይ አንድ ሰው ባለሃብት በመምሰል እና የጋና እግር ኳስ ላይ መዋዕለ ንዋይ ለማፍስ እንደሚፈልግ በመግለጽ ለክዌሲ ንያንታኪ 65 ሺህ ዶላር ሲሰጣቸው ይታያል። የእግር ኳስ ማህበሩ ፕሬዝዳንት በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል። የጋና መንግስት በተወዳጁ ስፖርት ላይ እየተፈጸሙ ባሉ ወንጀሎች ምክነያት የሃገሪቱን እግር ኳስ ማህበር ለማፍረስ አስቸኳይ ውሳኔ እንዳስተላለፈ የመረጃ ሚኒስትሩ ሙስጣፋ አብዱል ሃሚድ ገልጸዋል። ክዌሲ ንያንታኪ የጋና የእግር ኳስ ማህበር ፕሬዝዳንት ፤ የካፍ ምክትል ፕሬዝዳነት እና የፊፋ ምክር ቤት አባል ናቸው።
news-56968688
https://www.bbc.com/amharic/news-56968688
ቢል ጌትስ እና ባለቤቱ ሚሊንዳ ከ27 ዓመታት የትዳር ሕይወት በኋላ ተለያዩ
ቢልየነሮቹ ቢል ጌትስ እና ባለቤቱ ሚሊንዳ ጌትስ ከ27 ዓመታት በፊት የመሰረቱትን ትዳር ማፍረሳቸውን ይፋ አደረጉ።
ቢል ጌትስ እና ሚሊንዳ ጌትስ ቢል ጌትስ እና ባለቤቱ፤ ''ከዚህ በኋላ እንደ ጥንዶች ሆነን መቀጠል አንችልም'' ብለዋል። ''ከብዙ ማሰብና ግንኙነታችንን ለማሻሻል ከሰራን በኋላ ትዳራችንን ማፍረሱ የተሻለ አማራጭ አድርገን ወስደናል'' ብለዋል በትዊተር ገጻቸው ላይ ባስቀመጡት መልዕክት። ሁለቱ ጥንዶች የተገናኙት በአውሮፓውያኑ 1980ዎቹ ውስጥ ሚሊንዳ የቢል ጌትስን ማይክሮሶፍት ተቋም በተቀላቀለችበት ወቅት ነበር። ቢሊየነሮቹ ጥንዶች በ27 ዓመታት የትዳር ዘመናቸው ሦስት ልጆችን ያፈሩ ሲሆን፤ በተለያዩ ዘርፎች ድጋፍ የሚያደርገውን 'ቢል ኤንድ ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን' አቋቁመዋል። ድርጅታቸውም የተለያዩ አይነት ተላላፊ በሽታዎችን ለመዋጋትና ለህጻናት ክትባቶችን ለማድረስ በቢሊየኖች የሚቆጠር ዶላር ፈሰስ አድርጓል። ቢል ጌትስ በፎርብስ መጽሄት መረጃ መሠረት የዓለማችን አራተኛው ቢሊየነር ሲሆን የተጣራ ሀብቱም 124 ቢሊየን እንደሆነ ተነግሯል። ቢል ጌትስ በአውሮፓውያኑ 1970ዎቹ ውስጥ ከባልደረባው ጋር በመሆን በዓለማችን ትልቁ የሶፍትዌር ድርጅት የሆነውን ማይክሮሶፍትን በመክፈት ነበር የጀመረው። ጥንዶቹ በትዊተር ገጻቸው ላይ ለተከታዮቻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ "ባለፉት 27 ዓመታት አስገራሚ የሆኑ ሦስት ልጆችን አሳድገናል፤ በመላው ዓለም የሰዎችን ችግር ለመፍታት የሚሰራ ድርጅት አንድ ላይ መስርተናል'' ብለዋል። ''አሁንም ቢሆን በዚህ ዓላማ ማመናችንን አናቆምም፤ በፋውንዴሽኑ ዙሪያ አንድ ላይ መስራታችንን እንቀጥላለን። ነገር ግን ከዚህ በኋላ በሚኖረን ቀሪው የሕይወታችን ዘመን እንደ ጥንዶች ሆነን መቀጠል እንደማንችል ተስማምተናል'' ብለዋል። አክለውም '' ቤተሰባችን ይህንን አዲስ የሕይወት ምዕራፍ በሚጀምርበት ወቅት የግል ህይወታችን ላይ ጣልቃ እንዳትገቡ እንጠይቃለን'' ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
news-51315501
https://www.bbc.com/amharic/news-51315501
"ጃዋር መሐመድ ኢትዮጵያዊ ነው" ኦፌኮ
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) በቅርቡ በአባልነት የመዘገበው ጃዋር መሐመድ ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ ነው ሲል ፓርቲው ተናገረ።
በአገሪቱ ሕግ መሰረት ኢትዮጵያዊ ዜግነት የሌላቸው ግለሰቦች በፖለቲካ ውስጥ መሳተፍ ስለማይችሉ ከዚህ ቀደም የአሜሪካ ዜግነት እንዳላቸው የተነገረው አቶ ጃዋር የፓርቲው አባል መሆናቸውን ተከትሎ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ከአንድም ሁለት ጊዜ ግለሰቡ ኢትዮጵያዊ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ እንዲቀርብ ለፓርቲው በደብዳቤ ጠይቋል። • ጃዋር ኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስን መቀላቀሉ ተረጋገጠ ይህንንም ያረጋገጡት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የፓርቲው ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጥሩነህ ገምታ፤ "ጃዋር መሐመድ ኢትዮጵያዊ እንዳይሆን ገደብ የሚጥልበት ሕግ የለም፤ ስለዚህም ኢትዮጵያዊ ነው" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ለረጅም ዓመታት የአሜሪካ ዜጋ እንደሆኑ የሚታወቁት አቶ ጃዋር መሐመድ በኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አባል ሆነው በቅርቡ ቀጥተኛ የፖለቲካ እንቀስቃሴ ውስጥ መግባታቸው ይታወሳል። በአገሪቱ ሕግ መሠረ አንድ የውጪ አገር ዜጋ የመምረጥም ሆነ የመመረጥ መብት እንደሌለው ይታወቃል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም አቶ ጃዋር መሐመድ አሜሪካዊ ዜግነታቸውን መመለሳቸውን እና ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን ማረጋጋጫ እንዲሰጥ ለኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) በደብዳቤ ጠይቋል። • "ክስተቱ 'የግድያ ሙከራ' እንደሆነ ነው የምረዳው" ጀዋር መሐመድ • ኃይሌ ገብረሥላሴ ለ78 ሰዎች ሞት ፌስቡክን ወቀሰ አቶ ጥሩነህ ገምታ "መጀመሪያም ሆነ ለሁለተኛ ጊዜ የተላከው የድብዳቤ ይዘት አንድ አይነት ነው። የአቶ ጃዋር መሐመድን የዜግነት ሁኔታን ነው የጠየቁን። የዚህን አገር ዜግነት አግኝቷል ወይስ አላገኝም የሚለው ነው። ቦርዱ በዜግነት ኢትዮጵያዊ ያልሆነ ሰው በምርጫ መሳተፍ እንማይችል ጠቀሶ ነው ጥያቄውን ያቀረበው" ይላሉ። አቶ ጥሩነህ አክለውም ከምርጫ ቦርድ ይህ ጥያቄ እንደቀረበላቸው ጃዋር መሐመድ በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጥ በጽሁፍ መጠየቃቸውን ተናገረው፤ ጃዋርም ለምርጫ ቦርድ ምላሽ የሚሆን መልስ "የዜግነት አዋጅ ቁጥር 378/1996" ጠቅሶ ለፓርቲው መስጠቱን አመልክተዋል። "ጃዋር ምላሽ እንዲሰጥ በጽሑፍ አሳወቅነው። እሱም ምላሽ ሰጥቶናል። ይህንንም ለቦርዱ ለመስጠት ዝግጅት ላይ ነው ያለነው። እስከ ጥር 29 ነው ምላሽ ስጡ ያሉን፤ እኛም አዋጅ 378/1996 አንቀጽ 22 ጠቅሰን ከዚያ በፊት ምላሽ እንሰጣቸዋለን" ብለዋል አቶ ጥሩነህ ገምታ። የኢትዮጵያ የዜግነት አዋጅ ቁጥር 378/1996 አንቀጽ 22 የኢትዮጵያን ዜግነት መልሶ ስለማግኘት ያትታል። አስቀድሞ ኢትዮጵያዊ የነበረና በሕግ የሌላ አገር ዜግነት ያገኘ ሰው፤ "አንደኛ ወደ አገር ተመልሶ እየኖረ ነው። ሁለተኛ ዜግነቱን ለአሜሪካ መልሷል። ሦስተኛ ደግሞ ለሚመለከተው አካል ዜግነቱን እንዲመለስለት አመልክቷል። ከዚህ ውጪ ሕግ የሚጠይቀው ነገር የለም። ስለዚህ ጃዋር መሐመድ የኢትዮጵያ ዜጋ ነው" ይላሉ። ከጥቂት ሳምንታት በፊት ጃዋር መሐመድ ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ፤ በምርጫው ላይ ለመሳተፍ የአሜሪካ ፓስፖርቱን የመመለስ ሂደቱ ከምን እንዳደረሰ ተጠይቆ የሰጠው ምላሽ፤ "ፓስፖርቴን መልሼያለሁ። በእኔ በኩል የሚጠበቀውን ጨርሻያለሁ። ምንም የሚያግደን ነገር የለም" ብሎ ነበር።
news-53386386
https://www.bbc.com/amharic/news-53386386
የአሜሪካ ፌደራል መንግሥት ከ17 ዓመታት በኋላ የሞት ቅጣት ሊያስፈጽም ነው
የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ውሳኔን ተከትሎ በአሜሪካ ከ17 ዓመታት በላይ ተቋርጦ የነበረው በፌደራል መንግሥቱ ተግባራዊ የሚደረግ የሞት ፍርድ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ ኢንዲያና ግዛት ውስጥ ሊፈጸም ነው።
ሦስት አባላት ያሉትን ቤተሰብ የገደለው ዳንኤል ልዊስ በግድያ ወንጀል ሞት የተፈረደበት ዳንኤል ልዊስ የተባለው ፍርደኛ ባለፈው አርብ ውሳኔው ተግባራዊ እንዳይረግበት በአንድ የፌደራል ዳኛ እግድ ተላልፎበት ነበር። ለዚህም የተሰጠው ምክንያት የሟቾች ቤተሰቦች ውሳኔው ተግባራዊ ሲሆን ለመገኘት ቢፈልጉም በኮሮናቫይረስ ስጋት ምክንያት መገኘት ስለማንችል ለሌላ ጊዜ ይዘዋወርልን በማለታቸው ነበር። ነገር ግን መንግሥት ይግባኝ ጠይቆ ውሳኔው እንዲቀለበስ የሚያደርግ ሕጋዊ ትዕዛዝ በማግኘቱ ብይኑ ተግባራዊ እንዲደረግ ተወስኗል። በአገሪቱ የሟች ቤተሰቦች በገዳይ ላይ የሞት ፍርዱ ሲፈጸም መገኘት እንዲችሉ የሚፈቅድ ሲሆን፤ ቤተሰቦችም ፍርዱ ለእነሱ አመቺ በሆነ ጊዜ ተግባራዊ እንዲሆን ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኝ እንደሚሉ ተነግሯል። የሞት ፍርደኛው የነጭ የበላይነት አቀንቃኝ የነበረ ሲሆን የአንድ ቤተሰብ ሦስት አባላትን አሰቃይቶ ከገደለ በኋላ አስከሬናቸውን ሐይቅ ውስጥ በመጨመሩ ሞት ተፈርዶበት ባለፈው ታኅሳስ ወር ላይ ነበር ቅጣቱ ተግባራዊ ሊደረግበት የነበረው። ነገር ግን ቅጣቱ እንዲዘገይ የተደረገው ፍርድ ቤቱ ውሳኔው ተግባራዊ እንዳይደረግ የሚያዝ ውሳኔ በማሳለፉ ነበር ወንጀለኛው እስካሁን በሕይወት የቆየው። ሴት ልጃቸውን፣ የልጅ ልጃቸውንና የልጃቸው ባል በግድያው ያጡት ኧርሊን ፒተርሰን ግን ወንጀለኛው በመርዝ መርፌ ተወግቶ መገደሉን ተቃውመውታል። ለሲኤን ኤን እንተናገሩትም "በልጄ ምክንያት የአንድ ሰው ሕይወት መጥፋቱ ለእሷ አሳፋሪ ነገር ነው" ሲሉ ወንጀለኛው እንዳይገደል እንደሚፈልጉ ተናግረዋል። በሐምሌና በነሐሴ ወር ተግባራዊ እንዲደረጉ ከታሰቡት አራት የሞት ፍርዶች መካከል የዳንኤል ልዊስ አንዱ ሲሆን አራቱም ወንጀለኞች ወንዶችና ህጻናትን በመግደል የተፈረደባቸው ናቸው። የሞት ቅጣትን በሚመለከት ያሉ መረጃዎችን የሚያሰባስበው ማዕከል እንዳለው እንደ አውሮፓውያኑ በ1988 እና በ2018 መካከል ባሉት ዓመታት ውስጥ 78 ሰዎች በአሜሪካ ፌደራል መንግሥቱ በቀረበባቸው ክስ ሞት ተፈርዶባቸዋል። ነገር ግን እስካሁን ሦስቱ ብቻ ነው ውሳኔው ተግባራዊ የተደረገባቸው፤ በአሁኑ ጊዜ 62 የሞት ፍርደኞች በፌደራሉ የዓለም በቃኝ እስር ቤቶች ውስጥ ቅጣታቸውን እየተጠባበቁ ይገኛሉ።
news-54456861
https://www.bbc.com/amharic/news-54456861
የአውሮፓ ፓርላማ ሳዑዲ የኢትዮጵያ ስደተኞችን ይዞታ በአፋጣኝ እንድታሻሽል ጠየቀ
የአውሮፓ ሕብረት ምክር ቤት በሳዑዲ አረቢያ እስር ቤቶች በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ የሚፈጸመውን አስከፊ አያያዝና የሰብአዊ መብት ጥሰት በጽኑ የሚያወግዝ የውሳኔ ሐሳብ አሳለፈ።
ፓርላማው ይህንን ውሳኔ ያሳለፈው በሳዑዲ አረቢያ፣ በኤርትራና በኒካራጓ ውስጥ ያሉ የሰብአዊ መብት ጉዳዮችን በተመለከተበት ጉባኤ ላይ ሲሆን፤ በዚህም በሳዑዲ ያሉ ኢትዮጵያዊያን አያያዝ ሁኔታ አሳሳቢ እንደሆነ በማንሳት ነው የውሳኔ ሐሳብ ያሳለፈው። የአውሮፓ ሕብረት ምክር ቤት አሁን ድረስ በሳዑዲ እስር ቤቶች ውስጥ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ተይዘው ሰብአዊ መብቶቻቸው ተጥሶ እንደሚገኝ ጠቅሶ ሁኔታውን አውግዞታል። ሕብረቱ ያስተላለፈው የውሳኔ ሃሳብ ተከትሎ የአውሮፓ ሕብረት ልዑኮች በሳኡዲ አረቢያ ማጎሪያ ጣቢያዎች ውስጥ የሚገኙ ስደተኞች እንደሚጎበኙ የአውሮፓ ሕብረት ፓርላማ አባል የሆኑት ሰሚራ ራፋኤላ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የሰብዓዊ መብቶች ሳይከበሩ ቀርተው ስንመለከት ለእኛ ሁሌም አሳሳቢ ነገር ነው የሚሉት ሰሚራ፣ የሰብዓዊ መበት ጥሰት በማንም ላይ የትም ቦታ ሲከሰት ድምጻችንን ከፍ አድርገን እንናገራለን ሲሉ ያስረዳሉ። ሕብረቱ ለምን አስቸኳይ የውሳኔ ሃሳብ እንዲሰጥ እንዳደረገ ሲያብራሩም፣ ከሳኡዲ አረቢያ እስር ቤቶች እየወጡ ያሉ ምስሎችን እንዲሁም ሪፖርቶችን መመልከታቸውንና የስደተኞቹ ጉዳይም እጅግ አሳሳቢ ሆኖ ማግኘታቸውን ገልፀዋል። የሂውማን ራይትስ ዎች ሪፖርትን የጠቀሰው ፓርላማው ከባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር አንስቶ በግድ ከየመን ተገፍተው እንዲወጡ የተደረጉ ነፍሰጡር ሴቶችና ህጻናት የሚገኙባቸው 30 ሺህ የሚደርሱ ኢትዮጵያዊያን ያለፍርድ በአሰቃቂ ሁኔታ ሳዑዲ ውስጥ ባሉ እስር ቤቶች እንደሚገኙ አመልክቷል።. ስለዚህም የአውሮፓ ሕብረት ምክር ቤት አባላት የሳዑዲ አረቢያ ባለስልጣናት ሴቶችና ህጻናትን ጨምሮ ለችግር የተጋለጡትን ቅድሚያ በመስጠት በአስቸኳይ እንዲለቁ ጥሪ አቅርቧል። ጨምረውም የሳዑዲ ባለስልጣናት በጦርነት ውስጥ ከምትገኘው ጎረቤት የመን ሸሽተው ወደ ግዛታቸው የሚገቡ ሰዎችን ደኅንነታቸው በተጠበቀ ሁኔታ ተቀብለው ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን ወደጠበቁ የማቆያ ማዕከላት እንዲገቡ ማድረግ አለባቸው ብለዋል። በምክር ቤቱ የተላለፈው የውሳኔ ሐሳብ በማጠቃለያው ላይ የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በእስር ቤት ውስጥ በሚገኙት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ የሚፈጸሙ ሰቆቃዎችና አስከፊ አያያዞች በአስቸኳይ እንዲቆሙና ለታሳሪዎቹ ተገቢው ሥነ አእምሯዊና አካላዊ እንክብካቤ እንዲደረግላቸው ጠይቋል። የሕብረቱ ፖርላማ አባል ሰሚራ ራፋኤላ እንደሚሉት የሕብረቱን የውሳኔ ሳኡዲ አረቢያ ስደተኞችን ይዛ የምትገኝበትን ሁኔታ በአፋጣኝ እንድታሻሽል ይጠይቃል። የአውሮፓ ሕብረት ልዑኮቹን ወደ ስፍራው ልኮ ስደተኞች ያሉበትን ሁኔታን ይጎበኛል። ስላሉበት ሁኔታም ስደተኞቹን ያነጋግራል። በዚህም በማጎሪያ ቤቶች ውስጥ እየሆነ ያለውን መረዳት ይቻላል። የሳኡዲ አረቢያ መንግሥት በፍጥነት ስደተኞች ተይዘው ያሉበትን ሁኔታ እንዲያሻሽልም ይፋዊ ጥሪ ቀርቦለታል። ከኢትዮጵያ እና ሳዑዲ አረቢያ መንግሥታት ጋር በአንድም ሆነ በሌላ መንግድ አብረን እንሰራለን የሚሉት ሰሚራ፣ በስደተኞቹ ላይ የሚደርሰውን በደል አይተን ዝም ብለን ማለፍ እንደማይችሉ ሁለቱም አገራት የስደተኞቹ ሰብዓዊ መበት እንዲከበር እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው ለቢቢሲ አክለው ተናግረዋል። በሳዑዲ አረቢያ በአስከፊ ሁኔታ በእስር ቤት የሚገኙትን ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን በሚመለከት የተለያዩ መገናኛ ብዙሃንና የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች ተደጋጋሚ ሪፖርቶችን ሲያቀርቡ ቆይተዋል። ኢትዮጵያውያን ስደተኞቹ ለጤናና ለህይወት አስጊ በሆነ ሁኔታ በተጨናነቁ እስር ቤቶች ለወራት ከመቆየታቸው የተነሳ ለተለያዩ ህመሞች መጋለጣቸውና ህይወታቸው ያለፈም እንዳለ ቢቢሲና የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን መዘገባቸው ይታወቃል። ምክር ቤቱ በተጨማሪም በኤርትራ የሚገኙ የህሊና እስረኞች በተለይም ከዛሬ 19 ዓመት በፊት ለእስር የተዳረገውን ስውዲናዊውን ዳዊት ይስሃቅን ጨምሮ በርካታ ጋዜጠኞች እንዲለቀቁ ጠይቋል።
news-42335106
https://www.bbc.com/amharic/news-42335106
"በእንቅልፍ ልቤ መኪናም ሞተርም ነድቻለሁ"
በእንቅልፍ ልብ የሚደረጉ ነገሮች በጣም አደገኛ ይሆናሉ። በተለይም ውሀ፣የተጨናነቁ መንገዶችና ከፍታዎች ካሉበት ከባድ ይሆናል።
በእንቅልፍ ልብ መንዳት ደግሞ በከፍተኛ ደረጃ አደገኛ ነው።የነርቭ ሀኪም የሆኑት ጋይ ሌቺዝነር ጃኪ የተባሉ ታካሚያቸው በእንቅልፍ ልባቸው ይነዱ እንደነበር ይናገራሉ። ጃኪ ከአሜሪካ ወደ ካናዳ እንደሄዱ የሚኖሩት ከአንዲት አዛውንት ጋር ነበር።አንድ ቀን አዛውንቷ ጃኪን 'የት ነው ሌሊት የሄድሽው?' ብለው ይጠይቃሉ። ጃኪም 'የትም አልሄድኩም' ሲሉ ይመልሳሉ። አዛውንቷም 'እንግዲያውስ ሌሊት ሞተር ብስክሌትሽን ይዘሽ ወጥተሽ ነበር' አሏቸው ፤ጃኪ በጣም ደነገጡ። ወዲያውም የራስ መከላከያቸውን አድርገው እንደነበር አዛውንቷን ጠየቁ። አዛውንቷም "ወደ ታች ወረድሽና የራስ መከላከያሽን አደረግሽ።ከዚያም ወተሽ የቆየሽው ለሃያ ደቂቃ ነበር" ሲሉ መለሱ። ሁሉንም ነገር በእንቅልፍ ልባቸው ያደረጉት ጃኪ ግን ምንም የሚያስታውሱት ነገር አልነበረም። ወጥተው እንደነበር የሚያሳይም ምንም ፍንጭ አልነበረም።ሁሌም እንደሚሆነው ሞተሩ ፣የራስ መከላከያውም ሁሉም በትክክል ወደ ቦታቸው ተመልሰው ነበር። ልጅ ሳሉ በትምህርት ቤት ክበባት ጉዞ ሲሄዱ ማንም ከጃኪ ጋር በአንድ ድንኳን ማደር አይፈልግም ነበር።ምክንያቱ ደግሞ ጃኪ ሲተኙ የሚያሰሙት የሚረብሽ ድምፅ ነበር። "ስተኛ ድምፅ አወጣለው።እንዲሁ ቀላል ድምፅ አልነበረም።የድብ ድምፅ ይመስል ስለነበር ከኔ ጋር መተኛት በጣም ይፈሩ ነበር።"በማለት ጃኪ ያስታውሳሉ። የያል ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ሚር ክሪገር ሌሊት እየተነሳ ብሄራዊ መዝሙር ዘምሮ ወደ አልጋው የሚመለስ አንድ ሰው እንደሚያውቁ ይናገራሉ። የአዋቂዎች ጉዞ ላይም ጃኪ ተቆጣጣሪ ነበሩ። "በሌሊት ተነስቼ ወደ ወንዝ እወርድ ነበር።ወደ ጫካ ውስጥም እገባ ነበር ቢከተሉኝም አይደርሱብኝም ነበር።በመጨረሻ ሰዎች ተልከው ነበር ወደ ቤት የምመለሰው።"ይላሉ። ጃኪ ካደጉ በኋላ ብቻም ሳይሆን ልጅ እያሉ በእንቅልፍ ልባቸው የተለያዩ ነገሮችን ያደርጉ ነበር።በተለይም በእንቅልፍ ልብ መብላት፣ ማውራትና ቅዠት በልጅነት ጊዜ የሚታዩ የተለመዱ ነገሮች ናቸው። "ወደ ምግብ ቤት እወርድ ነበር።ወደ ወላጆቼ ክፍል በመሄድም በሩን ከፍቼ ዝም ብዬ እቆም ነበር።ይህ እናቴን በጣም ይረብሻት ነበር።አባቴ ግን እጄን ይዞ ወደ ክፍሌ በመውሰድ ያስተኛኝ ነበር።"በማለት ያስታውሳሉ። ጃኪ ችግሩን ለመቅረፍ የመኪናቸውን ቁልፍ አብረዋቸው ለሚኖሩት አዛውንት በመስጠት የፈቱት መስሏቸው ነበር። ነገር ግን መኖሪያ ከቀየሩ በኋላ እዚያም ጎረቤቶቻቸው ሌሊት ወዴት እንደሚሄዱ ሲጠይቋቸው ችግሩ ከብዙ ዓመታት በኋም እንዳለባቸው ተረዱ። በእንቅልፍ ልባቸው መንዳታቸው ለጃኪ ፍፁም አዲስ ዜና አልነበረም።ነገር ግን በተለይም በእንቅልፍ ልባቸው ሞተር ከነዱ ረዥም ጊዜ ስለሆናቸው ነገሩ ትንሽ ገረማቸው። የሰዎች የዚህ ዓይነት ባህሪ ማሳየት እንደሚያስጨንቅ የያል ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ክሪገር ይናገራሉ። ጃኪም በእንቅልፍ ልባቸው ማሽከርከራቸው አደገኛ መሆኑን በመረዳት በመጨረሻ የዶክተር ምክር መጠየቅ ግድ ሆኖባቸዋል። ይህ የተወሳሰበ የአዕምሮ ነገር ለምንና እንዴት ሊከሰት ይችላል? እንደ ዶልፊንና ወፍ ያሉ እንስሳት በግማሽ አዕምሯቸው ሊተኙ ይችላሉ።ምክንያቱም በግማሽ አዕምሯቸው መዋኘትና መብረር ይችላሉና።በሰዎች ግን የዚህ ዓይነት ነገር የለም። ቢሆንም ግን እንቅልፍምንቃትም በሰው አዕምሮ በአንድ ጊዜ ሊከሰቱ እንደሚችሉ ማወቃቸውን የነርቭ ሀኪዎቹ ይናገራሉ። በእንቅልፍ ልብ ላይ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በእንቅልፍ ልብ ዕይታን፣እንቅስቃሴንና ስሜትን የሚቆጣጠረው የአዕምሮ ክፍል ሲነቃ ትውስታን፣ ውሳኔንና ምክንያታዊነትን የሚመለከተው ክፍል ደግሞ ጥልቅ ዕንቅልፍ ውስጥ ይሆናል። እንቅልፍ ልብ ከዘር ጋርም የሚገናኝ ነገር አለው። ወደ ጋይ ሆስፒታል ከሄዱ በርካታ ታካሚዎች ብዙዎቹ በዘራቸው በእንቅልፍ ልብ የተለያዩ ነገሮችን የሚያደርጉ የቤተሰብ አባላት እንዳሏቸው ተናግረዋል።በዚህ መሰረትም የተደረጉ ጥናቶች አሉ። ጃኪ በመጨረሻ በፍቃዳቸው ጋይ ሆስፒታል ቢገቡም መጀመሪያ የራሳቸውን ሁኔታ ለማሻሻል የተለያዩ ነገሮችን ሞክረዋል። ለምሳሌ መጀመሪያ ያደረጉት በር ላይ ደወል በማስቀመጥ ሌሊት በር ከፍተው ሲወጡ አብሯቸው ያለ ሰው እንዲሰማ ማድረግን ነበር። ከጃኪ ጋር ይኖሩ የነበሩት ኢድ ከባድ እንቅልፍ ይይዛቸው ስለነበር ደውሉን አይሰሙም ነበር።የደውሉን ድምፅ መጨመር ደግሞ ጎረቤት ይረብሽ ነበር። ስለዚህ ጃኪ በዚህ ፈንታ የበሩን ቁልፍ በሰዓት የሚሞላና በምስጢር ቁጥር የሚከፈት ሳጥን ውስጥ ያስቀምጡ ጀመር። ሳጥኑ ደግሞ ያለ ንጋት አስራ ሁለት ሰዓት አይከፈትም ነበር። ይህ ዘዴ ጃኪን በሌሊት በእንቅልፍ ልብ ከመንዳት አቅቧቸዋል። በእንቅልፍ ልብ የሚደረጉ ነገሮች ለአድራጊውም ለሌላውም አስቸጋሪ የሚሆኑበት ጊዜ አለ።በእኩለ ሌሊት በእንቅልፍ ልብ ስልክ መደወል፣መልዕክት መላክ ወይም ምግብ ማብሰል ብዙዎች የሚያደርጉት ነው። ነገር ግን ለብዙዎች በእንቅልፍ ልብ የሚደረግ ነገር ብዙ ድራማ አይበዛውም። በእንቅልፍ ልብ የተለያዩ ነገሮችን የሚያደርጉ ሰዎች በተለይም ከቤት ሲወጡ፣መኪና ሲነዱና እንደ ቢላ ያለ ነገር ሲይዙ ነገሮች አደገኛ እንደሚሆኑ የህክምና ባለሙያዎች ያስረዳሉ። እንቅልፍን በተደጋጋሚ ሊያቋርጡ የሚችሉ ነገሮችን በማስወገድ በእንቅልፍ ልብ የሚደረግን ነገር በተወሰነ መልኩ መቆጣጠር ይቻላል።ነገር ግን ነገሩ የከፋ ከሆነ መድኃኒት የተሻለ ይሆናል። ትንንሽ የሚመስሉ እርምጃዎችም ትልቅ መፍትሄ ሊያስገኙ ይችላሉ። ወደ አልጋ መሄጃንና ከእንቅልፍ መነሻ ሰዓትን የተወሰነ ማድረግ፣አልኮልና ውጥረትን ማስወገድ፣ካፌን መቀነስና የመሳለሉትን ነገሮች በማድረግ ጥሩ እንቅልፍ ማግኘት ይቻላል። ቀደም ባሉት ጊዜያት ንቃትና እንቅልፍ ሁለት የተለያዩ ሂደቶች ተደርገው የታዩ ነበር።አሁን ግን ነገሩ እንደዚያ ሳይሆን ሁለቱም በአንድ ጊዜ ሊከሰቱ እንደሚችሉ ታውቋል። በርግጥ እንቅልፍና ንቃት የአዕምሮ አንድ ሂደት ሁለት ጫፎች ናቸው።በእነዚህ ሁለት ጫፎች መሀከል አዕምሯችን ያለበት ቦታ የምናስታውሰውንና የምናደርገውን እንቅስቃሴ ይወስናል። እንቅልፍ በምናጣበት ወቅት የአዕምሯችን የተወሰነ ክፍል ይተኛል። ስለዚህ እንቅልፍ ስናጣ ነቅተንም ቢሆን የሆነው የአዕምሯችን ክፍል እንደ መተኛት ሊያደርገው ይችላል። አንዳንዴ ትኩረት የምናጣውና ነገሮችን ልብ ማለት የሚያቅተን ለዚህ ሊሆን ይችላል። በሌላ በኩል ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ ሆነን የአዕምሯችን ክፍል ግን ንቃት ላይ መሆን ሰዎች እንዴት በእንቅልፍ ልባቸው ይሄንን ያንን አደረጉ ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ይሆናል።
news-50848639
https://www.bbc.com/amharic/news-50848639
አውስትራሊያ፡ በእሳትና ከባድ ሙቀት ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ
በአውስትራሊያዋ ኒው ሳውዝ ዌልስ በታሪክ እጅግ ከባድ በተባለ ሙቀትና የደን ቃጠሎ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ ታውቋል።
በአውስትራሊያ ታሪክ ተመዝግቦ የማይታወቅ ነው የተባለው ሙቀት ባሳለፍነው ማክሰኞ 40.9 ዲግሪ ሴንቲግሬድ የደረሰ ሲሆን የሀገሪቱ ዜጎች ደግሞ ተቃጠልን፤ የዓለም መጨረሻ ቀርቧል መሰል ሲሉ ነበር። ነገር ግን በሳምንቱ መጨረሻ እንደውም የባሰ ከባድ ሙቀት ሊመዘገብ እንደሚችልና ሰደድ እሳቱ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚችል ባለሙያዎች አስጠንቅቀዋል። • ከኢትዮጵያ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ እስከ አውስትራሊያ ሰደድ እሳት • እርጉዟ የሰደድ እሳት ተከላካይ የኒው ሳውዝ ዌልስ ባለስልጣናት በአሁኑ ሰአት በተለያዩ ቦታዎች የተከሰቱ 100 እሳቶችን ለማጥፋት ደፋ ቀና እያሉ ሲሆን ሰደዱ ሃገሪቱን ማመስ ከጀመረ አንድ ወር አልፎታል። ዛሬ ጠዋትም ግዛቲቱ አስተዳዳሪ ግላዲስ ቤሬጂክሊያን እየተባባሰ ከመጣው እሳትና ከባድ ሙቀት ዜጎችን ለመታደግ በማሰብ ለሰባት ቀናት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል። በአውስትራሊያ በተደጋጋሚ የሚከሰቱት የዱር እሳት፣ ድርቅና ከባድ ሙቀት ሀገሪቱ ከአየር ጸባይ ለውጥ ጋር በተያያዘ ያላት ቁርጠኝነት ደካማ መሆኑን ማሳያ ሊሆን ይችላል ብለው የሚተቹም አልጠፉም። ከባድ ሙቀት ከየትኛው ተፈጥሮአዊ አደጋ በበለጠ በአውስትራሊያ በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ሞት ምክንያት ነው። ለዚህ ሁሉ መከራ መነሾው የሕንድ ውቅያኖስ ዲፖሌ (IOD) ሚቲዮሮሎጂካዊ ክስተት ሲሆን ውቅያኖሱን በሚጎራበቱና በምድር ወገብ አቅራቢያ ባሉ ሀገራት የዝናብ ስልትን ይቀይራል። • የተትረፈረፈ የሚመስለው አሸዋ እጥረት እያጋጠመው ነው ይህም ከምስራቅ አፍሪካ እስከ ኢንዶኔዢያ ድረስ የተለጠጠ ሲሆን የአየር ጠባዩ እስከ አውስትራሊያ ድረስ ርቆ ይስተዋላል። አውስትራሊያ ከባድ ድርቅ እና ሰደድ እሳት ሊከሰት እንደሚችል መረጃው ቢደርሳትም ምንም ማድረግ አልቻለችም። በያዝነው ሳምንትም ከባዱ ሙቀት ተባብሶ በመቀጠል እስከ 45 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ሊደርስ ይችላል ተብሏል። እስካሁን በአውስትራሊያ በክስተቶቹ ምክንያት ስድስት ሰዎች ሲሞቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ደግሞ ከጥቅም ውጪ ሆነዋል። በሚሊየን የሚቆጠር ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ደንም ወድሟል።
news-41651828
https://www.bbc.com/amharic/news-41651828
''ጫካ ውስጥ አስቀምጠው ለተከታታይ ቀናት ደፍረውኛል''
ኢብራሂም አሊ አብደላ በኢትዮጵያ-የሶማሌ ክልል ቀብሪ ደሃር ከተማ ከ20 ዓመታት በላይ የኖረ የኦሮሞ ብሄር ተወላጅ ነው። የተከሰተውን ሲያስታውስ፤ በወቅቱ እነደለመደው በጠዋት ተነስቶ ነበር።
የተፈናቃዮች በሐማሬሳ መጠለያ ውስጥ ''በድንገት መጥተው በዱላና በድንጋይ ሲደበድቡኝ ወደ ሥራዬ ለመሄድ ፈረሶቼን አዘጋጅቼ ነበር'' ይላል። በዚያን ዕለት የክልሉ ወጣቶች በልዩ ፖሊስና በአካባቢው ባለሥልጣናት እየታገዙ ኦሮሞዎች ላይ ድብደባ መፈፀም እንደጀመሩ ይናገራል። ''ህይወታችንን ለማትረፍ ጋሪዬን ጥዬ ከቤተሰቦቼ ጋር ወደጫካ ሸሸሁኝ'' ይላል ኢብራሂም። ኢብራሂም አሁን የሶማሌ ክልልን ለቀው በተለያዩ መጠለያዎች ካሉት 119 ሺህ ከሚደርሱ ተፈናቃዮች መካከል አንዱ ነው። ይህ ቁጥር የተገኘው ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የአደጋ መከላከል ኮሚሽን ነው። በሁለቱ ክልሎች መካከል የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ በኦሮሚያ በኩል ከ450 ሺህ በላይ ሰዎች የተፈናቀሉ ሲሆን ይህ ቁጥር በፍጥነት ወደ 600 ሺህ እየተጠጋ መሆኑን ኮሚሽኑ ይናራል። ኢብራሂም በአሁኑ ጊዜ በሐረር ከተማ በሚገኘው ከሶማሌ ክልል ተፈናቅለው የመጡ ከ4000 በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ባስጠለለው ሐማሬሳ በተባለ ጣቢያ ውስጥ ነው። በጣቢያው ውስጥ የሚኖሩ ተፈናቃዮች ያሉበት ሁኔታ አስቸጋሪ እንደሆነና አንዳንዶችም ለህይወታቸው አስጊ ሁኔታዎች እንዳሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በመጠለያው ውስጥ ያለ ክሊኒክ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች መካከል የተከሰተውን ግጭት የሚያብራሩ አምስት ነጥቦች የመጠለያ ኑሮ፡ ስቃይና ተስፋ በሐማሬሳ ጊዜያዊ የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ በሚገኘው ክሊኒክ ውስጥ ሙሉ ፊቷ የቆሰለ ሴት ተኝታለች። እሷ የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ አባላት ናቸው በምትላቸው ሰዎች ለቀናት መደፈሯን ትናገራለች። ''መጀመሪያ ከባለቤቴ ጋር ሆነን ያዙን'' ትላለች። ''ወደ ጫካ ወስደው አስረው ክፉኛ ደበደቡኝ። ከዚያም ለተከታታይ ቀናት የሚፈልጉትን ከፈፀሙ በኋላ መንገድ ላይ ጥለውኝ ሄዱ። ከአማራ ክልል የመጣ አንድ ሰው አግኝቶ ነው ወደ ሃኪም ቤት በመውሰድ የረዳኝ።'' የምትለው ይህች ሴት እስካሁን ባሏ የት እንደደረሰ እንደማታውቅ ትናገራለች። ሐማሬሳ የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ ለንግድ ተብሎ በብረት የተሠራ ትልቅ መጋዘን ነው። አንዳንድ ተፈናቃዮች ሲናገሩ እዚህ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ልጅ ይዞ መጠለል እጅጉን ከባድ ነው፤ የምናገኘው ምግብ እና መጠጥ በቂ አይደለም ይላሉ። የመፀዳጃ እና መታጠቢያ ስፍራ ጉዳይም እጅግ አሳሳቢ ነው። "አሁን ላይ የምግብ እጥረት የለም። ነገር ግን ተፈናቃዮቹ እንደለመዱት ማቅረብ በጣም ከባድ ነው" ይላሉ የምስራቅ ሓረርጌ ዞን አደጋ መከላከል ኮሚሽን ኃላፊ አቶ ጌታቸው ቶሌራ። በሌላ በኩል እያደገ የመጣውን የተፈናቃዮች ቁጥር መመገብ እጅግ ፈታኝ እየሆነ መምጣቱን የኮሚሽኑ ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ግርማ ዋታሬ ያስረዳሉ። ከእነዚህ ተግዳሮቶች አለፍ ሲል ተፈናቃዮቹ ከወታደሮች የሚደርስባቸው ማስፈራራት እና ዛቻ ፈተና እንደሆነባቸው ለቢቢሲ ይናገራሉ። የተፈናቃዮች ጣቢያውን ተዘዋውሮ የጎበኘው የቢቢሲ ሪፖርተር እንደታዘበው ጣቢያው በኦሮሚያ ፖሊስ ጥበቃ ስር ቢሆንም ሌሎች ወታደሮችን በዙሪያው መመልከት ችሏል። የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ስለጉዳዩ ለቢቢሲ ሲያስረዳ "ተፈናቃዮቹ ስለየትኛው ማስፈራራት እንደሚያወሩ መረጃው የለንም" ብሏል። እናቶችና ህፃናት በመጠለያው ውስጥ በቀጣይ. . . በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ብቻ ወደ 72ሺህ የሚሆኑ ተፈናቃዮች ይገኛሉ። እነዚህ ሰዎች መጀመሪያ ላይ በትምህርት ቤቶች እና ጊዜያዊ የመጠለያ ሥፍራዎች ነበር የሚገኙት። አሁን ግን ትምህርት ቤቶች ለትምህርት ክፍት በመሆናቸው ቅርብ ዘመድ ያላቸው ተፈናቃዮች ወደዚያ ሲያመሩ፤ የተቀሩት ደግሞ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ተጠልለው ይገኛሉ። ወ/ሮ ራዉላ አዩብ በቀብሪ በያህ ከተማ ለ12 ዓመታት በነጋዴነት ተሰማርተው ቆይተዋል። ግጭቱ ከመከሰቱ በፊት ራውላ የኢትዮጵያ-ሶማሌ ክልል ጎረቤቶቻቸው ጋር በሰላም ይኖሩ እንደነበር ያስውታውሳሉ። "በክልሉ ልዩ ኃይል የሚደገፉ ሰዎች ቤት ንብረታችንን አቃጠሉብን። ከዚህ በፊት እንደማያውቁን ሆኑብን" ይላሉ። ወ/ሮ ራዉላ በአሁኑ ወቅት ከባለቤታቸው እና ከሰባት ልጆቻቸው ጋር ፈዲስ አካባቢ እህታቸው በሰጠቸቻው አነስ ያለ ቤት ውስጥ ይኖራሉ። ነገር ግን እንደተፈናቃይ ተስፋ እየቆረጡ እንደሆነ ያስረዳሉ። የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን አደጋ መከላከል ቢሮ እንዳስታወቀው ለተፈናቃዮቹ በፊት ከሚሠሩት ሥራ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ሥራ ለማመቻቸት ዝግጅቶች እየተካሄዱ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ እስከ ጥቅምት 3/2010 ድረስ ለተፈናቃዮች የተሳበሰበው ገንዘብ መጠን 166 ሚሊዮን ብር ደርሷል።
41818229
https://www.bbc.com/amharic/41818229
የናይጀሪያ ህፃናት የኩፍኝ ወረርሽኝ አደጋ ላይ ናቸው
ኩፍኝ በከፍተኛ ሁኔታ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ ሲሆን፤ በቀላሉም በክትባት በሽታውን መከላከል ይቻላል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ካልተከተቡት 20 ሚሊዮን ህፃናት መካከል 3 ሚሊዮኑ ናይጀሪያ ውስጥ እንደሚገኙ አዲስ የወጣ ሪፖርት ያሳያል። ሁለቱ አፍሪካውያን ሀገሮች ኢትዮጵያና ኮንጎም ከሌሎች በተለየ መልኩ ቁጥራቸው ከፍ ያለ ያልተከተቡ ህፃናት ልጆች ያሉባቸው ሀገራት እንደሆኑ ሪፖርቱ ጨምሮ ያስረዳል። ይህ ሪፖርት የወጣው ዝናብ በማይዘንብበት በበጋ ወቅት ሊከሰቱ የሚችሉ ወረርሽኞች ስጋት በሆኑበት ወቅት ነው። በናይጀሪያ ከኅዳር እስከ መጋቢት ባለው ወቅት የከፋ የኩፍኝ ወረረሽኝ የሚከሰትበት ጊዜ ነው። በባለፈው ዓመት ከጥር እስከ መስከረም ባለው ወቅት በሰሜን ምሥራቅ ናይጀሪያ አካባቢ 3 ሺህ ያህል የሚሆኑ በኩፍኝ የተጠረጠሩ ህሙማን እንዳሉ ሪፖርት ተደርጓል። በዚሁ አካባቢ አሁንም ባሉት ግጭቶች የተነሳ የጤና ተቋማት ከአገልግሎት ውጭ ሲሆኑ፤ ሰባት ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎችም የጤና ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል። ይህ ሪፖርት እንደ ዓለም ጤና ድርጅት፣ የተባበሩት መንግሥታት የህፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው በጥምረት ያወጡት ሲሆን፤ ከዚህ በኋላም ከፍተኛ የሆነ ወረርሽኝ ሊከሰት እንደሚችል ጠቁሞ። በሽታው ውስብስብ ለሆኑት የሳንባ ምች፣ ዓይነ-ስውርነት እንዲሁም ለሞት እንደሚዳርግ ይገልፃል። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ለግጭት በተጋለጡ አካባቢዎች ላይ በቆየ የሁለት ሳምንት የክትባት ዘመቻ፤ ዕድሜያቸው ከአስር ወራት እስከ አስር ዓመት የሆኑ አራት ሚሊዮን ልጆች ተከትበዋል።
47242520
https://www.bbc.com/amharic/47242520
"ታከለ ኡማ አዲስ አበባን መምራት የለባቸውም"
በተደጋጋሚ ለእስር የተዳረገውና በሽብር ተከሶ ከሰባት አመታት እስር ቆይታ በኋላ ባለፈው አመት የተፈታው እስክንድር ነጋ የተለያዩ አስተያየቶች ብዙዎችን እያነጋገሩ እያወዛገቡም ይገኛሉ።
ከነዚህም ውስጥ በቅርቡ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ለአዲስ አበባ ህዝብ ጥቅም የቆሙ አይደሉም፤ "በምርጫ እንቀጣቸዋለን" የሚለው አስተያየቱ የሚጠቀስ ሲሆን ይህም ብዙዎችን እያወዛገበ ይገኛል። •እነ እስክንድር ነጋ ተለቀቁ •"በሰላማዊ ትግል እስከመጨረሻው በፅናት እንታገላለን" እስክንድር ነጋ "አዲስ አበባን መምራት የለባቸውም" የሚል ጠንካራ አቋም ያለው እስክንድር ለዚህ የሚያስቀምጠው "አቶ ታከለ ኡማ አብዛኛውን የአዲስ አበባን ህዝብ አመለካከት አይጋሩም፤ የአዲስ አበባን ህዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ፤ ለአዲስ አበባ ህዝብ መብት ለመከራከር አይችሉም።" የሚል ምክንያት ነው። በተለይም በህገመንግሥቱ የሰፈረውና ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም አላት የሚለው አቋማቸው የብዙኃኑን አዲስ አበቤ አመለካከት እንደማይወክል የሚናገረው እስክንድር ከንቲባው ለለውጡ ያደረጉት አስተዋፅኦ ግን መታወስ እንዳለበት ያስገነዝባል። "እኔ ታከለ ኡማን እንደ ሰው አከብራቸዋለሁ፤ በለውጡ ሂደትም አስተዋፅኦ አበርክተዋል፤ ለሱም ዋጋ እሰጣለሁ። ለዚህም ካደረጉት አስተዋፅኦ አንፃር በፌደራል የሚኒስትርነት ቦታ ወይም በኦሮሚያ ክልል መሾም ነበረባቸው።" ይላል "አዲስ አበባን እንዲመሩ መሾም አልነበረባቸውም" ብሎ አጥብቆ የሚከራከረው እስክንድር ሹመቱ በአጠቃላይ ሲታይም በሽግግሩ ላይ ያለውን ክፍተት የሚያሳይ ነው ብሎ ያምናል። "የብዙኃኑን አመለካከት እንደማይወክሉ እየታወቀ፤ እንዴት ከተማዋን እንዲመሩ ተመረጡ? ሲልም ይጠይቃል። •ከተማ ይፍሩ፡ ያልተነገረላቸው የአፍሪካ አንድነት ባለራዕይ ሃገሪቱ ላይ በተፈጠረው ለውጥ ደስተኛ መሆኑን የሚናገረው እስክንድር ለውጡ ለአመታት ሲጠበቅ የነበረ እንደሆነ ገልጿል። ለአመታት ተለያይቷቸው የነበረው ቤተሰቡን ማየት መቻሉ እንደ ግል ስኬት የሚቆጥረው እስክንድር "ቢቻል ሃገሪቷ ተረጋግታ ወደ አገር ቤት ቢመለሱ ደስ ይለኝ ነበር። ነገር ግን ባለፈው አንድ አመት ውስጥ ሃገሪቷ ስላልተረጋጋች ቤተሰቡ ወደ ሃገር ውስጥ መመለስ አልቻለም። ስለዚህ አሁንም እንደተለያየን ነው" ብሏል። ነገር ግን በሃገር ደረጃ " የዲሞክራሲያዊ ሽግግሩ መድረስ የሚገባው ቦታ ላይ ደርሷል ወይ?" የሚለውን ዋና ጥያቄ ሲመዝነው ለውጡ ባለፈው አንድ ዓመት እንደተፈለገው ሄዷል ብሎ እንደማያምን ይናገራል። "ከዚህም አልፈን መሄድ ነበረብን ብዬ አምናለሁ" ይላል። እንደ ምሳሌም የሚያነሳው አቶ ጌታቸው አሰፋ የእስር ትዕዛዝ ቢወጣባቸውም አለመታሰራቸው ያለውን ክፍተት የሚያሳይ ነው ብሏል። እስክንድር በተለይም ቄሮን በተመለከተ በሰጠው አስተያየት ብዙ ነቀፌታዎች የተሰነዘሩበት ሲሆን " እንዲፈታ ላደረገው ትግል ውለታ ቢስ ሆኗል" የሚል አስተያየትም አይሎ ወጥቷል። የሃሳብ ልዩነትን በፀጋ እንደሚቀበል የሚናገረው እስክንድር "የተለያዩ ሃሳቦች እንዲንሸራሸሩ ነው የታገልነው" ይላል። ነገር ግን ከቄሮ ጋር ተያይዞ በሰጠው አስተያየት ከሃሳብ ልዩነት አልፎ እንገድልሃለን የሚሉ ማስፈራሪያዎችንና ዛቻዎችን እንዳስተናገደ ይናገራል። "በአጠቃላይ ይሄ እንደ ሃገር መወገዝ አለበት፤ እንደተባለው ውለታ ቢስ ብሆንም እንኳ እኔ በሃሳብ እንጂ በዛቻ ልሸነፍ አይገባም" ይላል። ይሄ ኃይልን እንደ መሳሪያነት መጠቀም መፈለግን ሙጥኝ የማለት ባህል እንዳለም አመላካች ነው ይላል። እስክንድር ብዙ ጊዜ "አክራሪው ቄሮ" እያለ አስተያየት ቢሰጥም ቄሮን ለሁለት ይከፍለዋል። "ጤናማው ቄሮ እንዲሁም አክራሪው ቄሮ አለ። አክራሪው ቄሮ ለአገር አደጋ ነው ብያለሁ። አሁንም የማምንበት ጉዳይ ነው። በአጠቃላይ ቄሮ ለአገር፣ለዴሞክራሲው አደጋ ነው አላልኩም። አክራሪው ቄሮ አደጋ የሆነው በያዘው ፖለቲካዊ አመለካከት ወይም አቋም ሳይሆን ኃይልን ለመጠቀም በመፈለጉ ነው። ለዚህ ደግሞ አባ ቶርቤ በሚል ተደራጅተው የነበሩ ወጣቶች ማስረጃ ናቸው።" ይላል እሱ እንደሚለው ይህ ሃይልን የመጠቀም አካሄድ ደግሞ ቄሮ በተለይ አምባገነናዊውን ስርአት ለመጣል ያደረገውን እንቅስቃሴ አፍራሽ ነው። ስለዚህም "ከለውጡ በኋላ ሁለት ቄሮ አለ ፅንፈኛውን መታገል አለብን" ይላል። በተደጋጋሚ ለእስር የተዳረገው እስክንድር በአሁኑ ወቅት የኢትዮጲስ ጋዜጣ ባለቤት ነው። ቀደም ሲልም የሰርካለም ማተሚያ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ የነበረ ሲሆን በስሩም አስኳል፣ ሳተናውና ሚኒልክ የተባሉ ጋዜጦችንም ያሳትም ነበር። የ1997ዓ.ም ምርጫ ቀውስን ተከትሎ ጋዜጦቹ የተዘጉ ሲሆን ከዚያም በሽብር ለእስር የበቃው እስክንድር ከአንድ አመት በፊት ከበርካታ የፖለቲካ እስረኞች ጋር በይቅርታ እንደተፈታ የሚታወስ ነው።
news-47161690
https://www.bbc.com/amharic/news-47161690
የጌታቸው ረዳ ዕይታ፤ ስለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ
በወቅታዊ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ጉዳዮች እና በህውሃት ተሳትፎ ዙሪያ የቢቢሲው ጋዜጠኛ አለን ካሱጃ መቀሌ ተጉዞ አቶ ጌታቸው ረዳን አነጋግሯል።
አቶ ጌታቸው ረዳ አቶ ጌታቸው ረዳ ከአለን ጋር በነበራቸው ቆይታ በህውሃት እና በጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ መካከል ስላለው ግንኙነት እንዲሁም ጠቅላይ ሚንስትሩ ዙሪያ የአቶ ጌታቸው የግል አመለካከት ምን እንደሆነ ጠይቋል። • "በረከትና ታደሰ በሙስና መጠርጠራቸው አስደንቆኛል" አቶ ጌታቸው ረዳ አለን ስለ ስለ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ምን ያስባሉ ሲል ነበር ለአቶ ጌታቸው የመጀመሪያውን ጥያቄ የሰነዘረው። አቶ ጌታቸው፡ ዐብይ ተነሳሽነቱን እና ውሳኔ ላይ ለመድረስ ያለውን ድፍረት አደንቃለሁ። አለን፡ ወደ ኢትዮጵያ ከመጣሁ ወዲህ ከሰማኋቸው ነገሮች መካከል ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ጋር እርቅ ያወረዱት የህውሃት ሰዎች [እናንተ] ችግር እንዳትሆኑበት በማሰብ ነው የሚሉ አሉ . . . አቶ ጌታቸው፡ እኛ ችግር ሆነንበት አናውቅም አለን፡ እውነቱን ንገረኛ አቶ ጌታቸው፡ እውነቱን እየተናገርኩ ነው። አለን፡ የህውሃት መስራቾች ሁሌም ችግር ሆነውበታል [ጠ/ሚ ዐብይ ላይ]። አቶ ጌታቸው፡ አንዳንድ አካላት ሊኖሩ ይችላሉ። ቅር ስለተሰኙ የህውሃት፣ ኦዲፒ ወይም አዴፓ አካላት ሁሉ መናገር ባልችልም። እኔ ግን ከዐብይ ጋር ችግር የለብኝም። አንተ እንዳልከው ግን ዐብይ ከኢሳያስ ጋር ህውሃትን ከጨዋታ ውጪ ለማድረግ ቢያሴርብን፤ ከወሰናቸው ውሳኔዎች መካከል ትክክል አይሆንም ምክንያቱም አይሳካለትም። አለን፡ በትክክል አድርጓል እያልኩ አይደለም። ምናልባት ሰዎች የሚሉትን አንተም ሰምተኽዋል ብዬ አስባለሁ። አቶ ጌታቸው፡ ዐብይ ይህን አይነት እርምጃ ይወስዳል ብዬ አላስብም። አለን፡ ይህን ያልከው በጣም በተቆጣ ፊት ነው። አቶ ጌታቸው፡ አዎ በትክክል። ዐብይ በአጋር ፓርቲው ላይ እንዲያሴር ምንም አይነት ምክንያት አይታየኝም። • 'ለሼህ አላሙዲ መፈታት የጠቅላይ ሚንስትሩ አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነበር' አለን፡ እንደዚያ ቢያደርግ ትታገላለህ? አቶ ጌታቸው፡ ማድረግ ካለብኝ አዎ። አለን፡ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ለየትኛዎቹ ጉዳዮች ምላሽ መስጠት አለበት ብለህ ታስባለህ? አቶ ጌታቸው፡ ዐብይ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር መሆን ይኖርበታል። አለን፡ እየሆነ አይደለም? አቶ ጌታቸው፡ እኔ ከምጠብቀው በታቸው ቢሆንም ለመሆን እየሞከረ ነው። አለን፡ ምን እያደረገ አይደለም? አቶ ጌታቸው፡ የህዝቡን ፍላጎት መመልከት ይኖርበታል። የትግራይ ህዝብን ብቻ ሳይሆን የኦሮሞ ህዝብንም ጭምር። አለን፡ ለምሳሌ የትኛውን? አቶ ጌታቸው፡ ዐብይ ወደ ስልጣን የመጣው ወጣቱ ሥራ አጥነት ስላማረረው ነው። ኢትዮጵያ በፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ላይ የነበረች ቢሆንም በርካቶች ሥራ አጥ ነበሩ። አሁንም ቢሆን የዐብይ ትልቁ ኃላፊነት ለወጣቱ ምላሽ መስጠት ነው። በቃል ብቻ ተስፋ መስጠት ለችግሩ መፍትሄ ሊሆን አይችልም። አለን፡ ከዚህ ቀደም ከነበሩት መንግሥታት ይልቅ አሁን በኢትዮጵያ የተሻለ ነጻነት አለ ብለህ ታስባለህ? አቶ ጌታቸው፡ አዎ አለ። አሁን ላይ በርካቶች አደባባይ እየወጡ ድምጻቸውን ያስማሉ። ይህ ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት የሚቻል አልነበረም። ዋናው ነገር ግን በሁላችንም መካከል የሞራል ልዕልና ተፈጥሮ ሁሉም ለበለጸገች እና ለተረጋጋች ኢትዮጵያ ልንሰራ ይገባል። አለን፡ ከአናተ ጋር በነበረኝ ቆይታ የተረዳሁት ዐብይ ብዙ የተባለለት ሰው አድርገኽዋል? አቶ ጌታቸው፡ ስለ እሱ ብዙ ነገር ልልህ እችላለሁ። ዐብይ እራሱ የሚያውቀው ይመስለኛል። ዓለም አቀፉ ማህብረሰብ በተለይም ደግሞ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን እጅግ አሳሳች ተቋሞች ናቸው። እጅጉን ጎበዝ የሆንክ መሪ አድረገው ይነግሩሃል። ጥሩ መሪ መሆንህን ማወቅ ያለብህ ግን ከህዝብ ጋር - ከወጣቱ ጋር - ጥሩ ግንኙነት ሲኖርህ ነው። እነሱ ናቸው ችግር ሊያስከትሉብህ የሚችሉት። አልጀዚራ፣ ቢቢሲ ወይም ሲኤንኤን ምንም ያክል ቢያወድሱህ ለዜጎች የሥራ እድል ትፈጥራለህ ማለት አይደለም። ዐብይ ለወጣቱ ሥራ መስጠት ላይ ትኩረት እንዲያደርግ እፈልጋለሁ። አልን፡ ዐብይ አህመድ ምን አይነት ሰው ነው? አቶ ጌታቸው፡ ብዙ ለማሳካት የሚጥር ሰው ነው። የህዝቡን ዋነኛ ችግሮች ለመቅረፍ ትኩረት ከማድረግ ይልቅ ሁሉን ለማሳካት ጥረት ሲያደርግ ያለውን ሁሉ ሊያጣ ይችላል የሚል ስጋት አለኝ። በዐብይ ህልም እና ተነሳሽነት ችግራችንን በአንድ ላይ ልናልፍ እንደምንችል ይሰማኛል። ይሁን እንጂ እንደምናስበው ሁሌም መልካም ሃሳቦች ወደ ፈቀድነው ላያመሩን ይችላሉ፤ እንደሚባለው የቁልቁለት ጉዞ ምንም ጊዜም የሚጀመረው በበጎ ሃሳብ ነው።
43593870
https://www.bbc.com/amharic/43593870
ከአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚጠበቁ 10 ነገሮች
ኢትዮጵያ ለሦስት ዓመታት ያህል በሕዝባዊ ተቃውሞዎች ስትናጥ ቆይታለች። እነዚህ ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ለመግታት ገዢው ፓርቲ ከኃይል በተጨማሪ የተለያዩ እርምጃዎችን መውሰዱ ይታወሳል።
የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት ዶ/ር አብይ አህመድ ከእነዚህም መካከል የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን፣ ጋዜጠኞችን እና ጦማሪዎችን ከእስር መፍታት ይገኝበታል። ነገር ግን ተቃውሞዎች ሊቆሙ ስላልቻሉ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከፓርቲውም ከመንግሥት ስልጣን ለቀዋል። አዲሱ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን የመጡት ሀገሪቷ በርካታ ፈተናዎችን በተጋፈጠችበት ወቅት ነው። በዚህ ወቅት ከእርሳቸውም ሆነ ከፓርቲያቸው የተለየዩ ነገሮችን እንደሚጠብቁ ያነጋገርናቸው የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች እና የድሬዳዋ፣ ሀዋሳ፣ ወልዲያ፣ሀሮማያ እና አፋር ነዋሪዎች ነግረውናል። 1. የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማንሳት በኢትዮጵያ ከተነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞ በኋላ በተለያዩ ስፍራዎች የሰው እና የንብረት ውድመቶች ገጥመዋል። ይህንን ተከትሎም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን ሁኔታዎች የተረጋጉ ሲመስሉ አዋጁ ተነስቷል። ነገር ግን በቅርቡ በድጋሚ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተደንግጓል። ይህንን ተከትሎም የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ የተቀዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ የውጭ ሀገራት ኢምባሲዎች በአዋጁ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ በይፋ ገልፀዋል። እኛም ያነጋገርናቸው ምሁራን እና ፖለቲከኞች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አስፈላጊ ነው ብለው አያምኑም። አዋጁ ከተደነገገ በኋላም ለሐገሪቱ ሰላምና መረጋጋትን ሳይሆን ሁከት ሲፈጠር እና ሰዎች ሲሞቱም ታይቷል የሚሉት እነዚህ አካላት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከተሾሙ በኋላ የመጀመሪያ ሥራቸው ይህንን አዋጅ ማንሳት እንዲሆን ይጠይቃሉ። ለዚህ ደግሞ እንደመከራከሪያ ካቀረቧቸው መካከል አንዱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰጠው ስልጣንን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ስለሚገድበው ተመራጩ ሥራውን በአግባቡ እንዲሰራ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በቀዳሚነት ማንሳት አለበት የሚልም ይገኝበታል። 2. የፍትሕ ሥርዓቱን ማሻሻል በኢትዮጵያ ውስጥ የሕግ የበላይነት ሰፍኖ ለማየት በህግ ፊት ሁሉም አካላት እኩል መሆናቸው መረጋገጥ አለበት የሚሉት ምሁራኑና ፖለቲከኞቹ ለዚህ ደግሞ ፍርድ ቤት፣ ፖሊስ፣ ማረሚያ ቤት እንዲሁም ሌሎች የፍትህ ሥርዓቱ አካላት ሕጉን እና ሕገ-መንግስቱን ብቻ ተከትለው እንዲሰሩ ማድረግ እንደሚኖርባቸው ይመክራሉ። እነዚህ አካላት ከአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሚጠብቁት ነገር መካከል አንዱ የፍትህ ሥርዓቱን እንዲያሻሽሉ ነው። በተለይ ደግሞ ፍርድ ቤቶች ራሳቸውን ችለው ያለምንም ጫና ውሳኔ መስጠት የሚችሉበትን አቅም መፍጠር እንዳለባቸው ያምናሉ። 3. ከተለያዩ አካላት ጋር ውይይትና ድርድር ማድረግ የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ለ17 ቀናት ካደረገው ስብሰባ በኋላ ካስቀመጣቸው ነጥቦች መካከል አንዱ ለተሻለ ሀገራዊ መግባባትና የተረጋጋ ሰላማዊ የፖለቲካ ሥርዓት በሰላማዊ መንገድ ከሚንቀሳቀሱት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ለውይይትና ለድርድር መቀመጥን ነው። ስለዚህ ውይይትና ድርድር ተካሂዶ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር በሀገራችን እንዲኖር ማድረግ ሀገሪቱ ዳግመኛ እንዲህ አይነት የፖለቲካ አዙሪት ውስጥ እንዳትገባ እንደሚያደርጋት በፅኑ ያምናሉ። ወደ ዲሞክራሲ ለሚደረገው ሽግግር መደራደርና ሰጥቶ በመቀበል ላይ የተመሰረተ ሥርዓት መዘርጋት ወሳኝ መሆኑንም ያሰምሩበታል። 4. የፖለቲካና የህሊና እስረኞችን መፍታት በኢትዮጵያ ውስጥ በተቃውሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባላትና አመራሮች፣ በጋዜጠኞች፣ ጦማሪዎችና ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ላይ እስርና እንግልት ሲደርስ በተደጋጋሚ ተስተውሏል ይላሉ ያነጋገርናቸው የሰብአዊ መበብት ተሟጋቾች። ከእስር ያመለጡ በርካቶች ደግሞ በሃገር ውስጥ የሚፈፀምባቸውን ጥቃት በመሸሽ በስደት በህይወት መቆየትን መርጠዋል ሲሉም ያክላሉ። የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና ምሁራን እንደ ፀረ ሽብር ያሉ ሕጎች ከወጡ በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብአዊ መብቶች አያያዝና ለሰብአዊ መብት ተቆርቋሪዎች እየጠበበ ስለመጣው የመንቀሳቀሻ ስፍራም ያስረዳሉ። ስለዚህ የፖለቲከኞችና የህሊና እስረኞችን ሙሉ በሙሉ መፍታት ከአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስተር ከሚጠብቋቸው ሥራዎች መካከል ይገኙበታል። 5. የሰብአዊና የዲሞክራሲ መብቶችን ማሻሻል ምሁራኑ በሀገሪቱ ውስጥ ለተከታታይ ዓመታት በዘለቀው ሕዝባዊ ተቃውሞ ውስጥ እንደተስተዋለው የሰብአዊ መብቶችና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ ጥያቄዎች ሲቀርቡ ነበር ይላሉ። ተሿሚው ጠቅላይ ሚኒስትር በሕዝቡ ዘንድ ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ቃል የሚገቡ ከሆነ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እና የሲቪል ማሕበረሰብ ቷቋማት በነፃነት የሚንቀሳቀሱበት እንዲሁም ሃሳብ በነፃነት የሚንሸራሸርበት መድረክ ማግኘትን የሚደግፉ የህገ-መንግስቱ አንቀፆች የሚከበሩበት ምህዳር እንዲፈጠር ማድረግ ትልቁ የቤት ሥራቸው ይሆናል ብለው ያስባሉ። 6. በጦር ሠራዊቱ እና በደህንነቱ ውስጥ ተጠያቂነትን ማስፈን ያነጋገርናቸው የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና ምሁራን የጦር ሠራዊቱና የደህንነት ተቋማት ለህገ-መንግሥቱ እንዲሁም ለፓርላማ አባላት ያላቸው ተጠያቂነትን ማረጋገጥ እንዲሁም የሃገሪቱ የበላይ ህግ የሆነው ህገ-መንግሥት እንደሚያዘው በእነዚህ ተቋማት ወስጥ ያለውን የብሄር ተዋፅኦን ተመጣጣኝ ማድረግ አስፈላጊም እንዲሁም አስቸኳይ የቤት ሥራ ነው ይላሉ። 7.ሕገ-መንግስቱን ማክበር፤ ማስከበር አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር በኢህአዴግ ባህልና መመሪያዎች ሳይያዝ ሕገ-መንግሥቱ የሚሰጠውን ስልጣን ሳይጨምርና ሳይቀንስ ከተጠቀመበት ለውጥ ለማምጣት አይቸግረውም የሚሉት ምሁራን እና የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች የፌደራል እና የክልሎችን ስልጣን በሚመለከት፣ የፍትህ ሥርዓቱን ለማስተካከል፣ የሰብአዊ መብቶችን ለማክበርም ሆኑ ለሌሎች ጉዳዮች ሕገ መንግስቱን ማክበርና ማስከበር ላይ እንዲያተኩሩ ያሳስባሉ። በተጨማሪም ሀገሪቱን ማረጋጋት፣ የምትመራበት ፌደራላዊ ሥርዓት ለብዙ ችግር የዳረጋት ከመሆኑ አንፃር እሱን ማስተካከልም ከሥራቸው መካከል እንደሚገኝበት ያስታውሳሉ። 8. የምሁራንን ተሳትፎ ማሳደግ ዶ/ር አቢይ ከተማረው ወገን በመሆናቸው ምሁራንን በሀገራቸው ጉዳይ ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ ያደርጋሉ ብለው የሚያምኑት ደግሞ ምሁራን ናቸው። በፖለቲካዊ ተሳትፎ ውስጥ የማይታወቁ ምሁራንን በካቢኔያቸው ውስጥ እና ከዚያም ውጭ በማሳተፍ በጋራ መስራት ያስፈልጋል የሚሉት ምሁራኑ፤ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሥራቸውን ሲጀምሩ በሚፈፅሙት ቃለ-መሃላ እና በሚወስዷቸው እርምጃዎች ይህን እናያለን ብለው ይጠብቃሉ። 9. ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ ማድረግ በተጨማሪም ዓለም አቀፋዊ ግንኙነቶችንና የምሥራቅ አፍሪካ ቀጠናን የሚይዙበት መንገድ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብቃት መፈተኛዎች መሆናቸውንም ምሁራኑ ያስረዳሉ። በቀጣይም አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢትዮጵያ በተለያዩ ሃገራት ያላትን የሰላምና ደህንነት የማረጋጋት ሥራን ቀጣይነት ማረጋገጥ እንደሚጠበቅ፣ በቀጠናው ያላት ተሰሚነት ቀጣይነት እንዲኖረው መስራትም ያስፈልጋቸዋል ባይ ናቸው። 10. ለወጣቶች የሥራ እድልን ማስፋት በተለያዩ የሃገሪቱ ከተሞች የሚኖሩ ወጣቶች እንደሚናገሩት ዶ/ር አቢይ አህመድ ለወጣቶች ትኩረት ይሰጣሉ በማለት ተስፋ ያደርጋሉ። በሀገሪቱ ያለውን ሥራ አጥነትን ለማስተካከል እርምጃ ይወስዳሉ ብለውም ይጠብቃሉ። ያለውን የሥራ አጥነት ለማስተካከልም የተለያዩ ፖለቲካዊ ውሳኔዎች እንዲወሰድ የሚጠብቁት እነዚህ ወጣቶች፤ የመልካም አስተዳደር ችግር፣ የእኩል ተጠቃሚነት፣ ሰላም እና መረጋጋትን ማስተካከል ከቻሉ ሥራ አጥነቱ በቀላሉ ይቀረፋል ባይ ናቸው።
49590210
https://www.bbc.com/amharic/49590210
የስምንት ዓመት ልጁን በዕፅ አዘዋዋሪነት የመለመለው ግለሰብ ታሠረ
የጣልያን ፖሊስ የስምንት ዓመት ልጁን ለዕፅ አዘዋዋሪነት መልምሏል ያለውን ግለሰብ በቁጥጥር ሥር አዋለ።
አውገስቲኖ ካምባሪሪ የተባለው የ46 ዓመት ግለሰብ፤ የአደገኛ ዕፅ አዘዋዋሪ ቡድን መሪ ሲሆን፤ ልጁ ቡድኑን በምን መንገድ ማገዝ እንደሚችል ይነግረው እንደነበር ፖሊስ ገልጿል። ታዳጊው ገበያ ላይ በሚገኙት ዕፆች መካከል ያለውን ልዩነት ጠንቅቆ እንዲረዳ ስልጠና እንተሰጠውም ተነግሯል። የዕፅ አዘዋዋሪ ቡድኑ አባላት የሚግባቡበትን የሚስጥር ቋንቋም አባት ለልጁ አስተምሯል ተብሏል። • በችሎት አደባባይ የወጣው የኤል ቻፖ ገመና • አደንዛዥ ዕፅ የጫነ መኪና የፖሊስ መኪና ገጭቶ በቁጥጥር ሥር ዋለ • ከፍተኛ መጠን ያለው ዕፅ በአሜሪካና ሜክሲኮ ድንበር ተያዘ ከአውገስቲኖ ካምባሪሪ በተጨማሪ 13 ግለሰቦችም በቁጥጥር ሥር ውለዋል። ተጠርጣሪዎቹ ካላቢራ በተባለችው የጣልያን ግዛት ካናቢስ እና ኮኬይን ያዘዋውሩ ነበር ተብሏል።
news-54314466
https://www.bbc.com/amharic/news-54314466
ቴክሳስ: የከተማው ውሃ ጭንቅላትን በሚያጠቃ ገዳይ ተህዋሲ በመበከሉ ነዋሪዎች አትጠጡ ተባሉ
በአሜሪካዋ ቴክሳስ ግዛት የሌክ ጃክሰን ከተማ ነዋሪዎች የቧምቧ ውሃ እንዳይጠጡ ማስጠንቀቂያ ተላልፎላቸዋል።
ለዚህም ምከንያቱ ገዳይ የተባለና ጭንቅላትን የሚያጠቃ ረቂህ ተህዋሲ በከተማዋ የውሃ አቅርቦት ላይ በመገኘቱ ነው። በተደረጉ ምርመራዎችም ናይግሌሪያ ፎውለሪ የተባለ ረቂቅ ተህዋሲ በከተማዋ ውሃ ማሰራጫ ጣቢያና በመስመሮቹ ይገኛል ተብሏል። ይህ ረቂቅ ተህዋሲ አዕምሮን ከመጉዳቱ በላይ ይገድላልም ተብሏል። ምንም እንኳን በአሜሪካ ውስጥ እንዲህ አይነት ጉዳቶች የተለመዱ ባይሆኑም አይከሰቱም ማለት አይደለም። በጎሮጎሳውያኑ 2009-2018 ባሉት 34 ጉዳቶች ሪፖርት ተደርገዋል። የሌክ ጃክሰን ባለስልጣናት ውሃውን ለማከም እየሰሩ ቢሆንም ምን ያህል ጊዜ ግን እንደሚወስድ አልታወቀም። ለዚህም ነው በዚህ ሳምንት አርብ ላይ ለነዋሪው ውሃውን ለሽንት ቤት ካልሆነ ለመጠጥ እንዳይጠቀሙ የተነገራቸው፥ ምንም እንኳን ማስጠንቀቂያው ከሌክ ጃክሰን አልፎ ሌሎች የቴክሳስ አካባቢ ነዋሪዎችንም ደርሷቸው የነበረ ቢሆንም በትናንትናው ዕለት መጠቀም እንደሚችሉ ተነግሯቸዋል። ነገር ግን ከ2 ሺህ 700 ነዋሪዎች ባሉባት ሌክ ጃክሰን አሁንም ማስጠንቀቂያው እንዳለ ነው። የሌክ ጃክሰን ባለስልጣናት ውሃውን እንጠጣለን የሚሉም ካሉ አፍልተው እንዲጠጡ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል። ይህም ብቻ አይደለም ገላቸውን በሚታጠቡበትም ወቅት ውሃው በአፍንጫቸው ወይም በአፋቸው እንዳይገባም ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ተብለዋል። በተለይም ህፃናት፣ የእድሜ ባለፀጎችና በሽታን መቋቋም የማይችሉ ነዋሪዎች የበለጠ ተጋላጭ ሊሆኑ እንደሚችሉም የከተማዋ ባለስልጣናት በተደጋጋሚ እየተናገሩ ነው። ውሃውን ከመነሻው ለማከም እንዲሁም ለማስወገድ እየሞከሩ እንደሆነ ገልፀው ውሃው ለመጠጥ ከመብቃቱ በፊት በርካታ ምርመራዎችን እናካሂዳለን ብለዋል። ውሃው ረቂቅ ተህዋሲያን መያዙ የታወቀው የስድስት አመት ልጅ ባለፈው ወር መሞቱን ተከትሎ ሲሆን ከዚያም ጋር ተያይዞ ምርመራ ሲካሄድ ከውሃው ጋር ግንኙነት መኖሩንም የከተማዋ አስተዳዳሪ ሞደስቶ ሙንዶ ለሪፖርተሮች ተናግረዋል። ናይግለሪያ ፎውለሪ የሚባለ ረቂቅ ተህዋሲ በአለማችን ላይ በተፈጥሮ ውሃዎች ላይም ይገኛል። ያልታከመውን ውሃ የሚጠጡትም ረቂቅ ተህዋሲው ወደ ጭንቅላት ተጉዞም አዕምሮ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል። የአሜሪካው የበሽታዎች መከላከያና ቁጥጥር ማዕከል (ሲዲሲ) በበኩሉ እንዲህ አይነት ኢንፌክሽኖች የሚያጋጥሙት ሰው በቀላሉ በማያገኛቸው የተፈጥሮ ውሃዎች ላይ በሚዋኙበት ወቅት ነው ይላል። የተበከለውን ውሃ በመጠጣት እንዲህ አይነት ኢንፌክሽን እንደማያጋጥም የሚናገረው ማዕከሉ ከሰው ወደ ሰውም አይተላለፍም ይላል። በናይግሌሪያ ፎውለሪ የተጠቁ ሰዎች ከፍተኛ ሙቀት፣ ማቅለሽለሽ፣ ትውከት፣ የአንገትና ከፍተኛ ራስ ህመም የሚያጋጥማቸው ሲሆን፤ በርካታዎቹም በሳምንት ውስጥ ይሞታሉ። በባለፈው አመትም በአሜሪካዋ ግዛት ፍሎሪዳ ተመሳሳይ መበከል አጋጥሞ የነበረ ሲሆን በወቅቱም የጤና ኃላፊዎች ከቧንቧ ውሃ እንዳይጠጡ አስጠንቅቀው ነበር።
news-54237879
https://www.bbc.com/amharic/news-54237879
ማኅበራዊ ሚዲያ ፡ በርግጥ ትዊተር ዘረኛ ይሆን?
የማኅበራዊ ሚዲያዎች የተጠቃሚዎቻቸውን ምስል በማሳየት ረገድ የዘር መድልዖ ይፈጽማሉ ብለው አስበው አያውቁ ይሆናል፤ ትዊተር ግን እጅ ከፍንጅ ተይዟል።
አንድ ተጠቃሚ ትዊትር የሚች ኮኔል ምስልን ከባራክ ኦባማ በማስበለጥ እንደሚያሳይ ደርሶበታል ትዊትር የተጠቃሚዎቹ ምስልን በማሳየት ረገድ ከጥቁር ፊት ይልቅ የነጭን የበለጠ መምረጡን ከደረሱበት በኋላ ምርመራ እያደረገ መሆኑን አስታወቋል። ተጠቃሚዎች እንዳስተዋሉት ከሆነ አንድ የጥቁር ሰው ፊት እና የነጭ ሰው ፊት በተመሳሳይ ፖስት ላይ ቢኖሩ ትዊተር ለሞባይል ስልክ ተጠቃሚዎች ማሳየት የሚመርጠው የነጩን ግለሰብ ፊት ነው ተብሏል። ኩባንያው በበኩሉ የሚሰራበት አልጎሪዝም [የአሰራር ቀመር] የዘር እና የጾታ ፈተና ፍተሻ እንደተደረገለት አብራርቷል። አክሎም "የበለጠ ምዘና ማድረግ እንዳለብን ግልጽ ሆኗል" ሲል ተናግሯል። የትዊተር የቴክኖሎጂ የበላይ ኃላፊ ፓራግ አግራዋል እንዳሉት "ሞዴላችንን ተግባራዊ በምናደርግበት ወቅት ፍተሻ አድርገን ነበር፤ ነገር ግን ተከታታይ የሆነ ማሻሻያ ያስፈልገዋል።" በዚህ አላበቁም፤ "ይህንን የሕዝብ አስተያየትና ተከታታይ ፍተሻ ወድጄዋለሁ፤ እናም ከዚህ ለመማር ዝግጁ ነን" ብለዋል። ትዊትር ከተጠቃሚዎቹ ጥያቄ የተነሳበት በቫንኮቨር ካናዳ ውስጥ ነዋሪ የሆኑት የዩኒቨርስቲ አስተዳዳሪው ኮሊን ማድላንድ ከባልደረባቸው ጋር በዙም [በኢንተርኔት] ስብሰባ እያደረጉ እያለ የጓደኛቸውን ጭንቅላት ማየት መቸገራቸውን ተከትሎ ነበር። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ሶፍትዌሩ የጥቁር ሰውን ጭንቅላት እንደ ጀርባ ምስል (background) በመቁጠር ማስወገዱ ነው። ከዚያም ይህንኑ ቅሬታቸውን በትዊተር ሰሌዳቸው ላይ ሲያኖሩ ሌላ ነገር አስተዋሉ። ይህም ከጥቁር ወዳጃቸው ምስል ይልቅ የእርሳቸው የነጩን ምስል ተለይቶ በሞባይል ስልካቸው ላይ መታየቱ ነው። ይህ የግለሰቡ ግኝት በርካታ የትዊተር ተጠቃሚዎች የተለያዩ ነገሮችን እንዲሞክሩ አድርጓቸዋል። የትዊተር ዲዛይን ኃላፊ የሆኑት ዳንትሌይ ዳቪስ እንዳረጋገጡትም የትዊተር አልጎሪዝም የጥቁሩን ሰው ጢም እና መነጽር የሚያስተካክለው ምክንያቱ "ከቆዳው ጋር ያለው ውህደት ለማስተካከል" መሆኑን ተናግረዋል። ለቀረበው ትችትም በትዊተር ሰሌዳቸው ላይ ምላሽ ሲሰጡ "የናንተኑ ያህል ተናድጃለሁ። ይህንን ማስተካከል ያለብኝ እኔው ነኝ አስተካክለዋለሁ" ብለዋል። አክለውም "መቶ በመቶ ጥፋቱ የእኛ ነው። ማንም ኃላፊነቱን ሊወስድልን አይችልም" ሲሉ ስህተታቸውን ለማረም እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
news-54144152
https://www.bbc.com/amharic/news-54144152
ኮሮናቫይረስ፡ እስራኤል በኮቪድ-19 ምክንያት ዳግም በሯን ልትዘጋ ነው
እስራኤል የአይሑድ አዲስ ዓመት ከመግባቱ በፊት እየተስፋፋ ያለውን ኮሮና ለመመከት ጥብቅ እርምጃዎችን ልትወስድ ነው፡፡
ጥብቅ ብሔራዊ ውሸባ እንደሚኖርም ይፋ አድርጋለች፡፡ ከሚቀጥለው አርብ ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል የተባለው አዲስ መመርያ ለሦስት ሳምንታት ይዘልቃል፡፡ ናታንያሁ እርምጃው ‹‹ሁላችንንም ከባድ ዋጋ ያስከፍለናል ነገር ግን ማድረግ አለብን›› ብለዋል፡፡ እስራኤል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቀን በአማካይ በቫይረሱ የሚያዙባት ዜጎች ቁጥር 4ሺ በመድረሱ ድንጋጤ ተፈጥሯል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ናታንያሁ ላይም ተቃውሞው በርትቶባቸው ቆይቷል፡፡ ይህንን የጠቅላይ ሚኒስትሩን እርምጃ የተቃወሙ የቤቶች ልማት ሚኒስትሩ ያኮቭ ሊዝማን ሥራቸውን በገዛ ፈቃዳቸው ለቅቀዋል፡፡ ሚኒስትሩ የተቃወሙት በአይሁድ ትልቅ ክብረ በዓል ዋዜማ ይህ እርምጃ ለምን ይወሰዳል በሚል ነው፡፡ ሰውየው አክራሪ የአይሁድ እምነት ተከታይ መሆናቸው ይነገርላቸዋል፡፡ የአክራሪው ኦርቶዶክስ አይሁድ ፓርቲን የሚመሩትም እርሳቸው ናቸው፡፡ አይሁዳዊያን ትልቅ ቦታ የምንሰጣቸውን ክብረ በዓላት በተገቢው እንዳናከብር ያደርጋል ብለዋል፣ ያኮቭ ሊዝማን፡፡ ዮም ኪፐር በአይሁድ የቀን አቆጣጠር ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ምዕመናን ፈጣሪያቸውን ይቅርታ የሚለማመኑበት ቅዱስ ክብረ በዓል ነው፡፡ በሴፕቴምበር 27 ነበር የሚውለው፡፡ እስራኤል እስከአሁን በቫይረሱ የሞቱባት ዜጎቿ ብዛት 1ሺህ 108 ደርሷል፡፡ 153ሺህ ዜጎች ደግሞ ቫይረሱ አጥቅቷቸዋል፡፡ ናታንያሁ ትናንትና እሑድ ለሕዝባቸው ባደረጉት ንግግር የወረርሽኙን መስፋፋት አውስተው ዕለታዊ አማካይ ቁጥር 4ሺ መድረሱ የሚነግረን ነገር አንድ እርምጃ ካልወሰድን ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ እንደሚሆኑ ነው ብለዋል፡፡ እስራኤል የዜጎችን እንቅስቃሴ ስትገድብ ይህ ለ2ኛ ጊዜ ነው፡፡ መጀመርያ ከመጋቢት እስከ ግንቦት ተመሳሳይ እርምጃ ወስዳ እንደነበር ይታወሳል፡፡ አሁን ከአርብ ጀምሮ በሚተገበረው መመርያ መሰረት ከ10 ሰዎች በላይ ቤት ውስጥ መቀመጥ አይችሉም፡፡ ከ20 ሰዎች በላይ ደጅ መሰብሰብ አይችሉም፡፡ ገበያዎችና ትምህርት ቤቶች ይዘጋሉ፡፡ ማንኛውም ዜጋ ለሥራ ወደ መሥሪያ ቤት ካልሆነ ውጭ ከሚኖርበት ስፍራ 500 ሜትር ርቆ መሄድ አይችልም፡፡ ሱፐርማርኬቶችና ፋርማሲዎች ክፍት ሆነው ይቆያሉ፡፡ በቤት ውስጥ ከ10 ሰዎች በላይ መሰብሰብ መከልከሉ፣ እንዲሁም ደጅ 20 ሰዎች በላይ መሰብሰብ አለመቻላቸው ከየትኛውም ህብረተሰብ በላይ የአይሁድ እምነት ተከታዮችን ሕይወት የሚነካ ይሆናል፡፡ በዚህ መመርያ መሰረት አይሁዶች በምኩራባቸው መሰባሰብ አይችሉም፤ ለዘመን መለወጫቸው መዳረሻ እጅግ ቅዱስ ተደርጎ የሚታሰበውን ዮም ኪፐር በዓልን ከቤተሰብ ጋር ማክበርም ፈተና ይሆንባቸዋል፡፡ ይህ ከአርብ ጀምሮ ተግባር ላይ የሚውለው የሦስት ሳምንታት ብሔራዊ የጤና ወሸባ የእስራኤልን ኢኮኖሚ 2 ቢሊዮን ዶላር ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍለው የፋይናንስ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
news-55482259
https://www.bbc.com/amharic/news-55482259
አርጀንቲና ጽንስ ማቋረጥን ፈቀደች
የአርጀንቲና ሴናተሮች እስከ 14ኛው ሳምንት ድረስ ጽንስ ማቋረጥን መፈቀድ አለበት በሚለው ሕግ ዙሪያ ውይይትና ክርክር ካካሄዱ በኋላ መፍቀዳቸው ተሰምቷል።
38 ሴናተሮች ህጉን ደግፈው ድምጽ የሰጡ ሲሆን 29 ደግሞ መቃወማቸው ተሰምቷል። አሁን ባለው ሁኔታ አርጀንቲና ውስጥ ጽንስ ማቋረጥን የሚፈቀደው እናት ከተደፈረችና የጤናዋ ሁኔታ አስጊ ከሆነ ብቻ ነው። ሕጉ 'ቻምበር ኦፍ ዴፒዩቲስ' በተሰኘው የአርጀንቲና መንግሥት መዋቅር አልፎ ነበር ወደ ሴናተሮች ምክር ቤት የደረሰው። በፈረንጆቹ 2018 የአርጀንቲና ሴናተሮች ሕጉን ለማፅደቅ ድምፅ ሰጥተው በጠባብ ውጤት ሳይፀድቅ ቀርቶ ነበር። የመብት ተሟጋቾች ሕጉ እንዲፀድቅ ለዓመታት ሲወተውቱ የነበረ ሲሆን አሁን ሕጉ የፀደቀው የዛሬ ዓመት ሴናተሮቹ በጠባብ የድምጽ ብልጫ ውድቅ እንዲሆን ባደረጉ በዓመቱ ነው። የአርጀንቲና ፕሬዝዳንት አልቤርቶ ፈርናንዴዝ ሕጉን ደግፈው ንግግር አድርገው ስለነበር ለበርካታ የመብት ተሟጋቾች ምናልባትም በስተመጨረሻ ጽንስ ማቋረጥ የሚፈቅደው መመሪያ እውን ሊሆን ይችላል የሚል ፍንጭ ሰጥቷቸው ነበር። ሕጉ መጽደቁ በላቲን አሜሪካ ትልቅ ዜና ሆኗል። ሌሎች የላቲን አሜሪካ አገራትም አርጀንቲናን ፈለግ ይከተላሉ የሚል ተስፋ አጭሯል። የላቲን አሜሪካ ቀጣና ሃገራት በአብዛኛው የካቶሊክ እምነት ተከታይ በመሆናቸው ጽንስ ማቋረጥ ክልክል ነው። "ዛሬ ቀኑ የተስፋ ነው። ፍትሃዊ ያልሆኑ ሞቶችን የምናስወግድበት ቀን ነው ዛሬ" ብለዋል ኤኤፍፒ ዜና ወኪል ያነጋገራቸው ሴናተር ኖርማ ዱራንጎ። በላቲን አሜሪካ ትልቅ ተሰሚነት ያላት የካቶሊክ ቤተ-ክርስትያን ጽንስ ማቋረጥን አትፈቅድም። ቤተ-ክርስትያኗ ሴናተሮች ረቂቁን ውድቅ እንዲያደርጉትም ጥሪ አቅርባ ነበር። አርጀንቲናዊው የሮማ ካቶሊክ ሊቀ-ጳጳስ ፍራንሲስ ክርክሩ ከመጀመሩ ሰዓታት በፊት በትዊተር ገፃቸው "እያንዳንዱ የተገፋ ሕፃን የፈጣሪ ልጅ ነው" ሲሉ ፅፈዋል። ሕጉን የሚደግፉና የሚቃወሙ አርጀንቲናዊያን ከኮንግረስ መናኸሪያ ወጣ ብሎ ድምፃቸውን እያሰሙ ናቸው። አሁን ባለው ሁኔታ አርጀንቲና ውስጥ ጽንስ ማቋረጥ የሚፈቀደው እናት ከተደፈረችና የጤናዋ ሁኔታ አስጊ ከሆነ ነው። በሌላ በኩል በኤል-ሳልቫዶር፣ ኒካራግዋ እና በዶሚኒካን ሪፐብሊክ ጽንስ ማቋረጥ ሙሉ በሙሉ የተከለከለ ነው። በተቀሩት የላቲን አሜሪካ ሃገራት ደግሞ ጽንስ ማቋረጥ የሚፈቀደው በጣም ልዩ በሆኑ ጉዳዮች ጊዜ ብቻ ነው። ከሰፊው የደቡብ አሜሪካ ቀጣና ዩራጓይ፣ ጉያና እና አንዳንድ የሜክሲኮ ክልሎች ሴቶች ፅንስ ማስወረድ ከፈለጉ እንዲጠይቁ ያበረታታሉ። ባለፈው ጊዜ ረቂቁ ለአርጀንቲና ኮንግረስ ቀርቦ 38 ለ31 በሆነ ድምፅ ነው የወደቀው።
news-47489947
https://www.bbc.com/amharic/news-47489947
የጋራ መኖርያ ቤቶቹ በዕጣ መተላለፋቸውን የኦሮሚያ ክልል ተቃወመ
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዛሬ በክልሉ አንዳንድ ከተሞች የተደረገውን የተቃውሞ ሰልፍ ተከተትሎ ማምሻውን መግለጫ አውጥቷል። በመግለጫው እንደተመለከተውም ትናንት ለባለእድለኞች በዕጣ የተላለፉ የጋራ መኖርያ ቤቶችን በተመለከተ የጸና አቋም ወስጃለሁ ብሏል።
የአዲስ አበባም ሆነ ተያያዥ ጉዳዮች በቅደም ተከተል ምላሽ እንደሚያገኙ የተስማማንባቸው ጉዳዮች ነበሩ ያለው መግለጫው ነገር ግን በአዲስ አበባና ኦሮሚያ መካከል ያለው የወሰን ጉዳይ እልባት እስከሚያገኝ ድረስ የኦሮሚያን ወሰን ተሻግረው የተሠሩ መኖርያ ቤቶች በዕጣ መተላለፋቸው ተቀባይነት የለውም ሲል አስታውቋል። •"የጠቅላይ ሚኒስትሩ ትልቁ ስኬት ብዙ ሰው በተስፋ እንዲኖር ማድረጋቸው ነው" ዶ/ር ዮናስ አዳዬ በመሆኑም ይላል መግለጫው፣ በመሆኑም ይህ በዕጣ የማስተላለፉ ውሳኔ ሥራ ላይ እንዳይውል 'የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የጸና አቋም አለው'። መግለጫው ጨምሮ እንዳለው ይህ አቋም የተወሰደው በቀናነትና የሕዝባችን ተጠቃሚነት ለማስከበር እንጂ የሕዝቦችን በጋራ የመኖር እሴት ከመጥላት አይደለም፤ ይህንንም ሕዝቡ ሊገነዝብ ይገባል ብሏል። •የድኅረ ዐብይ ሚዲያ በምሁራኑ ዕይታ የክልሉ መንግሥት ከአዲስ አበባ ጋር በተገናኘ የሚነሱ ማናቸውንም አጀንዳዎች ከኦሮሚያ ሕዝብ ፍላጎትና ተጠቃሚነት አንጻር ብቻ እንደሚመለከተውም አስምሮበታል። በመሆኑም በአዲስ አበባ ዙርያ የሚሠራው ሥራ ከኦሮሚያ መንግሥትና ሕዝብ ዕውቅና ውጭ በመሆኑ ሕገ ወጥ ነው ብለን እናምናለን ይላል። •የእኩልነት ዓለም ብለው የሚገልጿት የአውራምባውያኑ አምባ አዲስ አበባ ላይ ከድንበርና ከቤቶች ጉዳይ ባለፈ የአዲስ አበባን የኦሮሞ ባለቤትነት ጥያቄ ለማረጋገጥ የጀመርነውን ሥራ አጠናክረን እንቀጥላለን ሲል መግለጫው ይደመድማል።
48729123
https://www.bbc.com/amharic/48729123
ትራምፕ ጦርነት ከተጀመረ ኢራን ከምድረ ገጽ ትጠፋለች ሲሉ አስጠነቀቁ
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር ጦርነት እንደማይፈልጉ ነገር ግን በሁለቱ ሃገራት መካከል ግጭት ከተጀመረ "ውድመት " እንደሚከሰት ተናገሩ።
የኢራን ቴሌቪዥን ተመትቶ ወደቀው ነው ያለውን ሰው አልባ አውሮፕላን አሳይቷል አርብ ዕለት ለኤንቢሲ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃለ ምልልስ አሜሪካ ከኢራን ጋር ለመነጋገር በሯ ክፍት መሆኑን አስታውቀዋል። ነገር ግን ኢራን የኒውክለር ጦር መሣሪያ እንዲኖራት እንደማይፈልጉ አልሸሸጉም። በዚህ ሳምንት ኢራን የአሜሪካን ሰው አልባ አውሮፕላን መትታ መጣሏን ተከትሎ አሜሪካ የአፀፋ እርምጃ ልትወስድ ወስና በመጨረሻ ሰዓት ውሳኔያቸውን መቀልበሳቸውንም ተናግረዋል። 150 ኢራናያውያን ሕይወታቸውን ያጣሉ በሚል ውሳኔያቸውን እንዳጠፉት ጨምረው ተናግረዋል። • "ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ትምህርት ቤት ሆኖኛል" ደበበ እሸቱ • ኮሎኔል መንግሥቱን ትግል ለመግጠም ቤተ መንግሥት የሄደው ደራሲ "አልወደድኩትም፤ የአፀፋ እርምጃው ተመጣጣኝ ነው ብዬ አላሰብኩም" ብለዋል። ኢራን ማክሰኞ ዕለት የአየር ክልሏን ጥሶ የገባውን የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን መትታ መጣሏን ተናግራለች። አሜሪካ ግን አውሮፕላኑ ዓለም አቀፉ የአየር ክልል ውስጥ ነበር ስትል ተከራክራለች። በሁለቱ ሃገራት መካከል ውጥረቱ እየተጋጋለና እየተካረረ ሲሆን አሜሪካ በቅርቡ ሁለት ነዳጅ ጫኝ መርከቦች ላይ የደረሰውን አደጋ ኢራን ፈፅማዋለች ስትል መክሰሷ ይታወሳል። ኢራን ደግሞ በምላሹ አቋርጣው የነበረውን የኒውክሌር ማብላላት እንደምትቀጥልበትና ከተቀመጠላት መጠንም ከፍ እንደምታደርግ ገልፃለች። ባለፈው ዓመት አሜሪካ እንዲሁም ሌሎች የአውሮፓ ሃገራት በ2015 ከኢራን ጋር የተፈራረሙትን ስምምነት አሜሪካ አልፈልግም ብላ መውጣቷ ይታወሳል። አሜሪካ፤ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ሰኞ ዕለት ተገናኝቶ በኢራን ጉዳይ ላይ እንዲመክር ጥሪ አቅርባለች።
52211344
https://www.bbc.com/amharic/52211344
ፌስቡክ ጥንዶች ብቻ በሚስጥር የሚያወሩበት መተግበሪያ ይፋ አደረገ
ፌስቡክ ጥንዶች ለብቻቸው የሆድ የሆዳቸውን የሚያወሩበት መተግበሪያ ይፋ አደረገ።
ይህ አዲሱ መተግበሪያ ቲዩንድ (Tuned ) የሚሰኝ ሲሆን ጥንዶች በጋራ መልዕክት እንዲለዋወጡ፣ ሙዚቃ እንዲጋሩ እናም ዲጂታል የሆነ የፎቶ አልበም እንዲያዘጋጁ የሚያስችላቸው ነው ተብሏል። ቲዩንድ በፌስቡክ አዳዲስ ምርቶች መሞከሪያ ቡድን አባላት የተሰራ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ትኩረቱን ያደረገውም አዲስ ማህበራዊ ሚዲያን ሀ ብሎ መፍጠር ነው። •"ከቤት አትውጡ የሚሉን ልጆቼን ምን እንዳበላቸው ነው?" •የአሜሪካዋ ግዛት ዊስኮንሰን አስገዳጁን ቤት የመቀመጥ ሕግ ተላልፋ ምርጫ አካሄደች መተግበሪያው ለጥንዶች "የብቻ ዓለም" ይሆናል የተባለ ሲሆን እንደዋትስ አፕ ግን መልዕክታቸው በሶስተኛ ወገን እንዳይጠለፍ ማድረግ የሚያስችል ቴክኖሎጂ እንዳልተሰራለት ተገልጿል። ከዚህ ይልቅ ቲዩንድ የፌስቡክ ተመሳሳይ የሆነ የዳታ ፖሊሲ ይከተላል፤ ይህም የደንበኞቹን አጠቃቀምና ባህሪ መረጃ በመሰብሰብ ተጠቃሚውን ታላሚ ያደረገ ማስታወቂያ መልቀቅ ላይ ትኩረት ያደርጋል። ይህም የዳታ ፖሊሲ ተጠቃሚዎች የግል መረጃቸውን ወይም ምስላቸውን በመተግበሪያው እንዳያጋሩ ሊያደርጋቸው ይችላል ተብሏል። ፌስ ቡክ አዲስ ስላስተዋወቀው ስለዚህ ምርት ከቢቢሲ ለቀረበለት ጥያቄ መልስ አልሰጠም። ይህ መተግበሪያ በአሜሪካና በካናዳ ላሉ የአይፎን ስልክ ተጠቃሚዎች ብቻ የተለቀቀ ሲሆን የፌስቡክ አካውንት እንዲኖር አይጠይቅም ተብሏል። •እስራኤል ዜጋዬን ለኢራን ሲሰልል ደረስኩበት አለች ፌስቡክ በ2018 ወደ ጥንዶች ዓለም እንደሚገባ አስታውቆ ነበር። እስካሁን ድረስ የፍቅር ጓደኛ አፈላላጊ የሆኑት ቲንደርንና በምብልን ለመፎካከር በ20 አገሮችም የሚሰራ መተግበሪያ አለው። ይህ አዲሱ መተግበሪያ ግን ከዚህ የተለየ ነው ተብሏል። ይህ አዲሱ የፌስቡክ ምርት ከሌላ መልዕክት መለዋወጫ አገልግሎቶች አይለይም። ተጠቃሚዎች ስልካቸውን በመጠቀም የሚፈልጉትን ሰው መገናኘት የሚችሉ ሲሆን ወዳጅነት ከመሰረቱም በኋላ ምስልና ድምጽ በቀላሉ መላላክ ይቻላል።
45748383
https://www.bbc.com/amharic/45748383
የኢህአዴግ ጉባኤ የሁለተኛ ቀን ውሎ
11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ ዛሬ ቀጥሎ የዋለ ሲሆን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሲወያይ ውሏል።
በአነስተኛ ቡድኖች እና በጋራ የተካሄዱት ውይይቶች በዋናነት በሁለት ጭብጦች ላይ ያተኮሩ እንደነበር ግንባሩን ወክለው ዛሬ አመሻሹን መግለጫ የሰጡት የፓርቲው፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣አጋር ድርጅቶች እና የሲቪክ ማኅበራት ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ፈቃዱ ተሰማ ገልፀዋል።አዲሱ መሪ ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ለፓርቲው ሊቀ -መንበር እና ለአገሪቱም ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ብቅ ካሉ በኋላ በአገሪቱ የታዩት ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ የለውጥ እርምጃዎች ቀዳሚ የውይይት ርዕስ ሆነው በጉባዔተኛው ተነስተዋል ብለዋል አቶ ፍቃዱ። • "ማንም ቢሆን ኢትዮጵያን ለብቻዬ ሰራኋት ሊል አይቻለውም" ጠ/ሚ ዐብይ • "እባካቹን ለቤተሰቦቼ ንገሩልኝ! መዋኘት አልችልም፤ ለቤተሰቦቼ ብቸኛ ነኝ" • የፍስሀ ተገኝ የቤተሰብ ፍለጋ ጉዞ ውይይቱን''ነፃ፣ ግልፅ እና የተሟሟቀ '' ሲሉ የገለፁት አስተባባሪው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ አመራር ከመጣ በኋላ እየታዩ ያሉ ለውጦችን "ህዝባዊ፣ ሕገ መንግሥታዊ እና ኢህአዴጋዊ" መልክ አላቸው ብለዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎች የመንግሥትን ጥሪ ተከትሎ ወደአገር መግባታቸውን፣ ከጎረቤት አገር ኤርትራ ጋር ሰላም መውረዱን፣ የፖለቲካ እስረኞች ከእስር እንዲለቀቁ መደረጉን እንዲሁም ቀጠናዊ ትስስር ለመፍጠር ሂደት መጀመሩን ፓርቲው በጉባዔው እንደ ስኬት አይቷቸዋል።ጉባኤተኛው በዲሞክራሲ ምህዳር መስፋት እና የተጀመረውን ለውጥ ማስቀጠል አስፈላጊነት ላይ መክሯል። ከዚህም በተጨማሪ በአስራ አንደኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት እየተደረገ ነው ሲሉ አቶ ፈቃዱ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ኢህአዴግ ከዚህ በኋላ "የተደራጀ ሌብነት፣ ልግመኛነት ፣ ውጤት አልባነት እና ስርዓተ አልበኝነትን" አይታገስም በእነዚህ ጉዳዮች ላይም "ቀይ መስመር" አስምሯል ሲሉ ተናግረዋል።