id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
news-52171485
https://www.bbc.com/amharic/news-52171485
በስፔን የሟቾች ቁጥር እየቀነሰ ቢሆንም የእንቅስቃሴ ገደቡ ይቆያል ተባለ
የስፔን ጠቅላይ ሚኒስት ፔድሮ ሳንቼዝ በአገራቸው ለተከታታይ ሁለት ቀናት በኮሮናቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር መቀነሱን ተከትሎ "የሽታው ከፍተኛ መጠን ላይ ደርሰናል" ሲሉ ተናገሩ።
ሳንቼዝ አክለውም በቤት ውስጥ የመቀመጡ መመሪያ ለቀጣዮቹ 20 ቀናት እንደተራዘመ ያስታወቁ ሲሆን ገደቡ "ሕይወትን ይታደጋል" ብለዋል። ይህ ሳምንት በቀን 809 ሰዎች የሞቱበት ዝቅተኛው ሆኖ ተመዝግቧል። በተያያዘ የስፔን ባለስልጣናት የአገሪቱ ሕዝብ ላይ የተጣለውን ደንብ ለማላላት ለእያንዳንዱ ግለሰብ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ለማግኘት እየጣሩ ነው። በስፔን በአሁኑ ወቅት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማግኘት አዳጋች ነው። መንግሥት ከዚህ ቀደም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ከሆስፒታል ውጪ ያለው ግልጋሎት እምብዛም ነው ሲል ተናግሮ ነበር። ይሁን እንጂ አሜሪካ አርብ ዕለት በማንኛውም ስፍራ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግን ከመከረች ወዲህ በምዕራቡ ዓለም ያለው አቋም እየተቀየረ መጥቷል። ኦስትሪያ፣ ቼክ ሪፐብሊክ፣ እስራኤል፣ ቱርክ ሕዝብ በሚሰበሰብባቸው ስፍራዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ ግዴታ መሆኑን ደንግገዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ 1.1 ሚሊዮን ሰዎች በኮቪድ-19 ሲያዙ ከ60 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ መሞታቸውን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሰቲ መረጃ ያሳያል። በስፔን ባለፉት 24 ሰዓታት 7,026 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን ይህም አርብ ዕለት ከነበረው 7,472 ቁጥር የቀነሰ ነው ተብሏል። በተጨማሪም እስካሁን ድረስ 11,744 ሰዎች በኮቪድ-19 የተነሳ የሞቱ ሲሆን አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ በጣሊያን ካለው በልጦ 124,736 መሆኑ ተገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሳንቼዝ ለሁለት ሳምንት ቤት የመቀመጥ እገዳውን ሲያራዝሙ ይህ ውሳኔ የጤና ባለሙያዎች እንዲያገግሙ ይረዳቸዋል ብለዋል። አክለውም አዳዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር መቆጣጠር ከተቻለ "ወደ አዲሱ ሕይወት በፍጥነት በመመለስ" ኢኮኖሚያችንን ዳግም መገንባት አለብን ሲሉ ተናግረዋል። ሳንቼዝ አዲሱ ሕይወት ያሉት አዲስ የንጽህና አጠባበቅ መመሪያ፣ እንዲሁም በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎችን የመለየት ተግባር እንደሚዘረጋ ለመግለጽ መሆኑን ጨምረው አስታውቀዋል። የአውሮፓ ሕብረትም ምጣኔ ሃብታዊ ተግዳሮትን በጋራ እንዲታገል "አውሮፓ በዚህ ሰዓት መውደቅ የለባትም" ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። "የስፔን ምጣኔ ሃብት ኪሳራ ውስጥ እንደሚወድቅ እሙን ነው፤ ስለዚህም ቫይረሱን ለመዋጋት ከሚመጣው ትውልድ ሃብት መውሰድ አለብን" ብለዋል። እስካሁን ድረስ ስፔን፣ ጣሊያን፣ ፈረንሳይና ሌሎች አገራት ለአውሮፓ ሕብረት፤ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የገጠማቸውን ኪሳራ ለመጋራት ጥሪ ቢያቀርቡም ሕብረቱ ግን በቀረበው እቅድ ላይ መስማማት አልቻለም።
news-47451867
https://www.bbc.com/amharic/news-47451867
የተማሪውን ልጅ አዝሎ ያስተማረው አሜሪካዊው መምህር አድናቆት ተቸረው
አንድ አሜሪካዊ የሂሳብ ፕሮፌሰር የተማሪውን ልጅ አዝሎ ማስተማሩ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ትኩረት እንዲስብ አድርጎታል።
አሳታ የተባለችው ህጻን አባት ዋይን ሄየር እንደተናገረው ሴት ልጁን የሚጠብቅለት ሰው በማጣቱ ነው ወደ ትምህርት ቤት አዝሎ ያመጣት። ነገር ግን ያልጠበቀው ነገር ተከሰተ። አስተማሪው ፕሮፌሰር ናታን አሌክሳንደር እኔ ልጅህን አዝዬልህ አንተ ለምን ዘና ብለህ ትምህርትህን አትከታተልም አለው። መምህሩ ከበድ ያለውን የሂሳብ ትምህርት ለተማሪዎቹ እያስረዳ ለ50 ደቂቃዎች ህጻኗን ሲያዝል አባቷ ደግሞ ጠረጴዛ ላይ አቀርቅሮ ማስታወሻ ይወስድ ነበር ተብሏል። • አራት ህጻናትን በአንዴ ያገኘው ቤተሰብ ተጨንቋል • በህክምና ስህተት የመከነው ህፃን የ34 ዓመቱ ፕሮፌሰር ናታን 'በዘፊድ' ለተባለው የዜና ምንጭ እንደገለጸው እስካሁን ልጅ አልወለደም። ነገር ግን ህጻኗ ምንም ባለመረበሿ በጣም ጥሩ አባት እንዳስመሰለችው በደስታ ተውጦ ተናግሯል። ''ታለቅሳለች ብዬ ፈርቼ ነበር፤ እሷ ግን እኔ ማስተማሬን ስቀጥል በተረጋጋ መንፈስ ትከታተለኝ ነበር።'' ብሏል የህጻኗ አባት በበኩሉ ''ሁሌም ቢሆን ልጄን ለመንከባከብ ስል ከክፍል በጊዜ እንደምወጣ ያስተዋለው መምህር ወደ ትምህርት ቤት ይዣት እንድመጣ ያበረታታኝ ነበር'' ብሏል። ሁለት ስራዎችን ደርቦ የሚሰራው አባት የሙሉ ሰአት ተማሪም ነው። ከሁለቱ ስራዎቹና ከትመህርቱ ጊዜ በማሸጋሸግ ነበር ሴት ልጁን የሚንከባከበው። አሁን ግን ሌላው ቢቀር ወደ ትምህርት ቤት ሲሄድ የልጁ ጉዳይ የሚያሳስበው አይመስልም። • የ7 ዓመቷ ህፃን መፀዳጃ ቤት አልሰራልኝም ስትል አባቷን ከሰሰች ፕሮፌሰር ናታን አሌክሳንደር ህጻኗን አዝሎ ሲያስተምር የሚያሳየወው ምስል በማህበራዊ ሚዲያ ተከታታዮች ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን አትርፎለታል። አንዳንዶች እንደውም በአሜሪካ መንግስት ህጻናት እንክብካቤ የሚሰጠው ትኩረት ዝቅተኛ መሆኑ ማሳያ ሊሆን ይችላል እያሉ ነው። ሌሎች ደግሞ የሰው ልጅ ምን ያህል ጥሩ ሆኖ እንደተፈጠረ ለመረዳት ይህንን ፎቶ መመልከት ብቻ በቂ ነው ብለዋል።
46437391
https://www.bbc.com/amharic/46437391
ለየት ያለው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ደብዳቤ ለየመኖች
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በጦርነት ለዓመታት እየታመሰች ላለቸው የመን እና ተፋላሚ ወገኖች ወደ ሰላም እንዲመጡ፣ እንዲሁም በስቃይ ውስጥ ያለውን ሕዝባቸውን ከከፋ ችግር እንዲታደጉት የሚጠይቅ ደብዳቤ ጽፈዋል።
ከተለመደ ፖለቲካዊ ዘዬ ወጣ ያለ ይዘት ያለው ይህ ደብዳቤ በየመን በጦርነት ተሳትፎ ያደረጉ የውጭ ኃይሎችን ከማውገዝም ሆነ ከመውቀስ የተቆጠበ ሲሆን በየመን ሁለት ጎራ ይዘው የሚዋጉ ወገኖችን ግን ክፉኛ ይወቅሳል። የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ በይፋ በድረ ገጹ ትናንት ባሰራጨው በዚህ መልዕክት የመን ውስጥ ላለው ምስቅልቅል የየመን ሕዝብን ብቸኛ ተጠያቂ ያደርጋል። በጥንታዊ ሥልጣኔ ውስጥ የመን የነበራትን ታላቅ ስፍራ በመዘርዘር የሚጀምረው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ አሊ ደብዳቤ የመን በሁለቱ ቅዱሳን መጻሕፍት የነበራትን ቦታና ክብር ለማጉላት ይሞክራል። በተለይም በብሉይ ኪዳን "የብልጽግና ምድር" መባሏን በጥንታዊ ግብጻዊያን "ቅዱስ ምድር" እየተባለች መሞካሸቷን በቁርዓንም እንዲሁ መጠቀሷን በመግለጽ ይጀምራል። • ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ስለተዘረፉ ቅርሶች ምን እናውቃለን? • ዓመታትን ያስቆጠሩ የወርቅ ሳንቲሞች ተገኙ ደብዳቤው ጨምሮ "ለእናንተ ለየመን ሕዝቦች፤ ለደስተኞቹ፤ ማንም አገር በነብዩ መሐመድ የናንተን ያህል አልተጠቀሰም" ካለ በኋላ "ነብዩ መሐመድ ይህንን ብለውም ነበር" ሲል ያጣቅሳል። "...የየመን ሕዝቦች ወደናንተ ይመጣሉ፤ የቅን ልቦና ባልተቤቶች፣ ገራገሮች...እና ብልህ ሕዝቦች..." ሲል። "በአንድ አምላክ የሚያምንና አንድ ሃይማኖት የሚከተል ሕዝብ ስለምን ጦርነት ውስጥ ይዘፈቃል?" ብሎም ይጠይቃል ደብዳቤው። ጦርነት ክልክል (ሐራም) ነው ሲልም መንፈሳዊ አንቀጾችን ጭምር እየጠቀሰ ይቀጥላል፤ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ለየመን ሕዝብ ይድረስልኝ ያሉት ይህ ጦማር። ደብዳቤው ተዋጊ ወገኖችን በጥብቅ የማውገዝ ዝንባሌም ከፍ ያለ ነው። "ስለምን ሥልጣኒያችሁን በገዛ እጃችሁ ታወድማላችሁ? ስለምን ክብራችሁን ታዋርዳላችሁ? ስለምን ልጆቻችሁን ወላጅ አልባ ታደርጋላችሁ? ስለምን ከልጆቻችሁ ደስታን ትሰርቃላችሁ? እናንተ በቅዱሳን መጻሕፍት 'ደስተኛ ሕዝቦች' ተብላችሁ የተወደሳችሁ አልነበራችሁምን?" ሲል ይጠይቃል። ዐብይ አሕመድ በዚህ ጦማራቸው ሁለቱንም ወገኖች 'ከንቱ ጦርነት ላይ ናችሁ' ሲሉም ደጋግመው ያስገነዝቧቸዋል። • ". . . ጥፍር መንቀል ሕጋዊ አይደለም ስንለው ብሔሩ ውስጥ ለመደበቅ ይሞክራል" ጠ/ሚ ዐብይ • ዐብይ አሕመድ ለኖቤል ሽልማት ታጭተዋል? ይህ ጦማር የአገሪቱን ጥንታዊ ገናናነት ካወሳ በኋላ በቀጣይ አንቀጽ ተዋጊ ወገኖችን በተመሳሳይ ወደማውገዝ ይመለሳል። "...አገሪቱን በሁሉም አቅጣጫ እያፈራረሳችሁ ያላችሁት [ለመሆኑ] ምን ለማግኘት ይሆን? ስለምን ምክንያት አልባ ትሆናላችሁ? በታላቁ ነብይ ብልሆች ተብላችሁ አልነበረምን? ስለምን የጦርነት ነጋሪት ትጎስማላችሁ? መነጋገርና መወያየትን እየቻላችሁ?" ብለዋል። ደብዳቤው በሁለተኛ ገጹ አሁን ላይ በየመን ለደረሰውና እየደረሰ ላለው ሁሉ ኃላፊነቱን የመናዊያን ብቻ እንዲወስዱ ይሞግታል። "እናንተ አሁን በጦርነት ለፈረሰችው የመን ኃላፊዎች ናችሁ" ሲልም ያሳስባል። በመጨረሻም የዕርቅና የሰላም ጥሪን የሚያቀርበው ይህ ደብዳቤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የማስታረቅ ሚና መጫወት እንደሚፈልጉ በቀጥታ ባይጠቅስም ለሚፈለግ ማንኛውም ትብብር ግን ዝግጁ እንደሆኑ ሳይጠቅስ አላለፈም። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አሊ በደብዳቢያቸው መጨረሻ፣ "አሁን ተጨባበጡ፤ በፍቅርና በንጹሕ ልብ ተዋደዱ፤ ብልህነታችሁ ብርሃን ይሁናችሁ...." ካሉ በኋላ "...የሚፈለግብንን ለማድረግ፣ እርቅን ለማምጣት፣ የደም መፋሰስን ለማቆም እናንተን ወደ ሰላምና ብልጽግና ለመመሰለስ የሚፈለግብንን ለማድረግ በእኛ በኩል ዝግጁ ነን" ሲሉ አስታውቀዋል።
news-42177222
https://www.bbc.com/amharic/news-42177222
ናይጄሪያ በሊቢያ ያሉ ስደተኛ ዜጎቿን ለመመለስ ማቀዷን ገለፀች
በቅርቡ በሊቢያ የሚገኙ አፍሪካውያን ስደተኞች እንደ ሸቀጥ በጨረታ ሲሸጡ የሚያሳይ ምስል ከወጣ በኋላ ነው የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ሙሐማዱ ቡሃሪ በሊቢያና በተለያዩ ሃገራት ያሉ ስደተኛ ዜጎቻቸውን ወደሃገራቸው ለመመለስ ቆርጠው መነሳታቸውን የተናገሩት።
ቡሃሪ ስደተኞቹ እንደ እንሰሳ ነው የተንገላቱት የሚል አስተያየት ካሰፈሩ በኋላ ናይጄሪያውን አስከፊውን ወደ አውሮፓ የሚደረግ ስደት የሚያቆሙበትን መፍትሄ ፍለጋ ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል። የቡሃሪ እወጃ በተባበሩት መንግሥታት የሚመራው የሊቢያ መንግሥት ስደተኞችን ወደሃገራቸው የመመለስ ሥራ አጠናክሮ መቀጠሉን ካሳወቀ ከጥቂት ሰዓታት በኃላ ነው የተሰማው። ማክሰኞ ምሽት ብቻ 240 የሚሆኑ ናይጄሪያውያን ስደተኞች በፈቃዳቸው የተባበሩት መንግሥታት ባዘጋጀላቸው በረራ ወደሃገራቸው ተመልሰዋል። የአሜሪካው የቴሌቪዥን ጣቢያ ሲኤንኤን ነበር ባሳለፍነው ሳምንት ሊቢያ አቋርጠው ወደ አውሮፓ ለመግባት ተስፋ አድርገው የወጡ አፍሪካውያን ስደተኞች በሕገ-ወጥ ሰው አዛዋዋሪዎች ተይዘው ለጉልበት ሥራ በጨረታ ሲሸጡ የሚያሳይ ምስል የለቀቀው። አሁን ላይ አንድ ሚሊዮን ገደማ ስደተኞች በሊቢያ እንደሚገኙ ይገመታል በኪትዲቯር መዲና አቢጃን እየተካሄደ ያለው የአፍሪካና አውሮፓ ሕብረት የሁለትዮሽ ጉባዓ ዋነኛ ትኩረቱን በዚህ ጉዳይ ላይ በስፋት እየመከረ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል። በጉባዔው ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት ቡሃሪ ባዩትና በሰሙት ነገር እጅግ መደንገጣቸውን ነው የተናገሩት። "አንዳንድ የሃገሬ ሰዎች ልክ እንደ ፍየል በጥቂት ዶላር ለጨረታ ሲቀርቡ ተመልክቻለሁ" ሲሉ ተደምጠዋል። ቡሃሪ ተመላሾቹ ወደ መደበኛ ሕይወታቸውን እንዲመለሱ ለማስቻል መንግሥታቸው ከፍተኛውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ቃል ገብተዋል። አልፎም ቦኮ ሐራምን ለመደምሰስና ትምህርት በናይጄሪያ ለማስፋፋት ቃል የገቡት ፕሬዚዳንቱ ዜጎቻቸው ሃገር መልቀቅን እንደ ትክክለኛ አማራጭ እንዳይወስዱ አሳስበዋል። ናይጄሪያ በምን መልኩ ስደተኛ ዜጎቿን ከሊቢያ ወደሃገራቸው እንደምትመልስ ግን በግልፅ የታወቀ ነገር የለም።
news-45493574
https://www.bbc.com/amharic/news-45493574
የሊቢያው ትሪፖሊ አየር ማረፊያ የሮኬት ጥቃት ሙከራ ተደረገበት
በሊቢያ አገልግሎት የሚሰጠው ብቸኛው የአየር ማረፊያ በተደረገበት የሮኬት ጥቃት ምክንያት በረራዎችን ለመሰረዝ ተገዷል።
በሊቢያ መዲና ትሪፖሊ የሚገኘው ሚቲጋ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ማክሰኞ ምሽት ገደማ ነው ጥቃቱ የተሰነዘረበት። በሰውም ሆነ በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት ይኖር እንደሁ በውል እንዳልተላወቀ እየተነገረ ይገኛል። • ሊቢያ ውስጥ 27 ሰዎች በቦምብ ጥቃት ተገደሉ በሊቢያ የሚገኙ ታጣቂ ኃይሎችን የእርስ በርስ ግጭት ተከትሎ ተዘግቶ የቆየው ይህ አየር ማረፊያ ባለፈው አርብ ነበር እንደገና አገልግሎት መስጠት የጀመረው። በተባበሩት መንግሥታት የሚደገፈው ኃይል መዲናዋ ትሪፖሊን ቢቆጣጠርም የተቀረው የሃገሪቱ ክፍል በታጣቂዎች ይዞታ ሥር ይገኛል። የሮኬት ጥቃት እንደተሰነዘረ በታወቀ ጊዜ ከግብፅ ይመጣ የነበረ ንብረትነቱ የሊቢያ አየር መንገድ የሆነ አውሮፕላን ወደ ምሥራቁ የሃገሪቱ ክፍል አቅጣጫውን እንዲቀይር ተደርጓል። • ካለሁበት 1፡ ''በሜዲትራንያን ባህር ከመስመጥ መትረፌ ሁሌም ይደንቀኛል" አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የተሰኘው ዜና ወኪል ምንጮቼ ነገሩኝ እንዳለው ሌሎችም በረራዎች ሚስራታ ወደ ተሰኘችው ከተማ አቅጣጫ ቀይረው በረራ እንዲያደርጉ ተገደዋል። ሊቢያ አየር መንገድ ሃገሪቱ ውስጥ ብቸኛው አገልግሎት ሰጭ ሲሆን ወደተወሰኑ የዓለም ሃገራት በረራ ያከናውናል። አየር መንገዱ፤ በደኅንነት ምክንያት ወደ አውሮጳ ሃገራት በረራ ማድረግ አይችልም። • ሊቢያ በህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ላይ የእስር ትዕዛዝ አወጣች
news-53400206
https://www.bbc.com/amharic/news-53400206
በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር ሲካሄድ የነበረው የህዳሴ ግድብ ድርድር ያለስምምነት ተቋጨ
በአፍሪካ ህብረት አሸማጋይነት ሲካሄድ የነበረው የሶስትዮሽ ድርድር ያለስምምነት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ስለሺ በቀለ በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል።
ሶስቱ ሃገራት፣ 11 ታዛቢዎችና ባለሙያዎች በተገኙበት ለአስራ አንድ ቀናት ያህልም ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅሰው ትናንት ምሽት ሶስት ሰአት ላይ መጠናቀቁም ሰፍሯል። እስካሁን በተካሄደው ድርድር መሻሻሎች ቢኖሩም በአጠቃላይ ስምምነት ላይ መድረስ እንዳልተቻለ የገለፀው የትዊተር ፅሁፉ በዛሬው ዕለትም አገራቱ የደረሱባቸውን ጉዳዮች ለመሪዎቹ እንዲሁም ሲያሸማግል ለነበረው አፍሪካ ህብረትም በሪፖርት መልክ ያቀርባሉ። የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበርን ጨምሮ አባለት አገራቱና የሶስቱ አገራት መሪዎች ሪፖርቱን ከገመገሙ በኋላም ድርድሩ ሊቀጥል እንደሚችል በፅሁፉ ላይ የሰፈረ ሲሆን፤ እነዚህ አካላት በሚሰጡት መመሪያም መሰረት ይሆናል ሲል ጨምሮ ገልጿል። ለአመታት የዘለቀው የሶስቱ አገራት ድርድር ያለምንም ውጤት ሲንከባለል መጥቶ ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሙሌትን በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ እጀምራለሁ ማለቷን ተከትሎ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በጉዳዩ ጣልቃ እንዲገባ ግብፅ መጠየቋ የሚታወስ ነው። ድርድሩ በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር መደረጉ ለኢትዮጵያ ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ስኬት የተባለ ሲሆን የግድቡ ውሃ አሞላልና አለቃቅ፣ የድርቅ የውሃ ስሌት፣ የግድቡ አስተዳደርና ቁጥጥር፣ የግድቡ ደህንነት ጉዳዮችን በተመለከተም የአገራቱ ቴክኒክና ህግ ባለሙያዎች እየተወያዩ ነበር ተብሏል። በአስረኛው ቀንም የሶስቱ አገራት የውሃና መስኖ ሚኒስትር የቴክኒካልና ህጋዊ ኮሚቴ ውይይቶችን መገምገማቸውንም የግብፅ የውሃና መስኖ ሚኒስቴርን ጠቅሶ 'ኢጅፕት ቱደይ' ዘግቧል። በተለይም በባለፈው ሳምንት ኢትዮጵያ ስምምነት ያልተደረሳባቸው ጉዳዮች ለሌላ ጊዜ ይተላለፉ ማለታቸው ከግብፅ በኩል ተቀባይነት አለማግኘቱንም ዘገባው አስነብቧል። የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ከሰሞኑ ለአገሪቱ ሚዲያዎች በሰጠው መግለጫ ድርድሩ ፍሬ አልባ እንደነበር ገልጿል። አረብ ኒውስ በበኩሉ ኢትዮጵያ ለአወዛጋቢዎቹ የህግ እና ቴክኒካዊ ጉዳዮች አማራጭ ሃሳቦችን ብታቀርብም በግብፅ ዘንድ ተቀባይነት እንዳላገኘ ዘግቧል። ኢትዮጵያ የአማራጭ ሃሳቧን በስምንተኛው የድርድር ቀን ማቅረቧን የገለፀው ዘገባው ስምምነት ያልተደረሰባቸውን ጉዳዮችንና ስምምነቶቹ ተግባራዊ መሆናቸውንም ለማየት አንድ የቴክኒክ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደዛ እንዲመራ ማሰቧን ዘግቧል። ግብፅ በበኩሏ ድርቅና የድርቅ ውሃ ስሌትን በተመለከተ አማራጭ ሃሳብ ማቅረቧን የውሃና መስኖ ሚኒስትሩን ጠቅሶ ዘግቧል። ቴክኒካል ጉዳዮችንም በተመለከተ አንዳንድ መሻሻሎች መኖራቸውንም የሱዳን የውሃና መስኖ ሚኒስቴርን ዋቢ በማድረግ ዘገባው አስነብቧል።
news-57264686
https://www.bbc.com/amharic/news-57264686
ምርጫ 2013፡ ምርጫ ቦርድ በእስር ላይ ያሉትን እነ እስክንድር ነጋን በዕጩነት ለመመዝገብ እንደሚቸገር አስታወቀ
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ሰበር ሰሚ ችሎት እነ አቶ እስክንድር ነጋ በዕጩነት ተመዝግበው መወዳደር እንደሚችሉ ያሳለፈውን ውሳኔ ለማስፈፀም እንደሚቸገር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።
ፍርድ ቤት በእስር ላይ ያሉት የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች ፕሬዚዳንቱን አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩምና አስካለ ደምሴ በመጪው ምርጫ በዕጩነት ተመዝግበው እንዲወዳደሩ ብይን ያስተላለፈው ሰኞ እለት ግንቦት 16 ነበር። ፍርድ ቤቱ በተጨማሪ መርጫ ቦርድ እስከ ግንቦት 19/2013 ዓ.ም ድረስ ተገቢውን ትዕዛዝ ለምርጫ ወረዳዎች አስተላልፎ እንደ ፍርዱ እንዲፈፀም ትዕዛዝ ማስተላለፉን ከምርጫ ቦርድ ከተገኘው መረጃ መረዳት ተችሏል። ምርጫ ቦርድ በበኩሉ በትናንትናው ዕለት ለባልደራስ እውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በፃፈው ደብዳቤ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ለማሰፈፀም እንደሚቸገር ገልጿል። ለዚህም እንደ ምክንያትነት ያቀረበው የተወዳዳሪ ዕጩዎች ምዝገባ የካቲት 30/2013 ዓ.ም መጠናቀቁ፣ በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የሚኖረው ስፍራ የሚወስን ሎተሪ መውጣቱ፤ የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ህትመትም ተጠናቆ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች የመላኩ ተግባር በቅርብ ጊዜ የሚከናወን በመሆኑ እንደሆነ አስታውቋል። ከዚህ ቀደም ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ በእስር ላይ ያሉ አመራሮቹን በተወዳዳሪ ዕጩነት እንዲመዘገቡለት ምርጫ ቦርድን ጠይቆ በመከልከሉ ከሕግ አግባብ ውጪ ነው ሲል ከሶ ነበር። ፓርቲው በመከራከሪያነት የሚያነሳውም የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጁን ነው። "ማንኛውም ሰው በሕግ ወይም በፍርድ ቤት ውሳኔ የመምረጥ ወይም የመመረጥ መብቱ ያልተገፈፈ እንደሆነ በዕጩነት ተወዳድረው መመዝገባቸው ሊከለከሉ አይገባም ብሎ ነበር። የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዕጩነት ተመዝግበው መወዳደር ይችላሉ የሚለውን ውሳኔ ተከትሎ የባልደራስ አመራሮች ባሉበት ሆነው የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ እንዲችሉ ፍርድ ቤቱን ጠይቀው ነበር። ነገር ግን የምርጫ ቦርድ ውሳኔን ተከትሎ ባልደራስ በማኅበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው መግለጫ "ምርጫ ቦርድ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ አላከብርም አለ" በማለት ያሰፈረ ሲሆን አስቸኳይም ስብሰባ መጥራቱን አስታውቋል።
news-51401845
https://www.bbc.com/amharic/news-51401845
በህንድ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ የ5 ዓመት ልጅ ተደፈረች
በህንድ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ የአምስት ዓመት ልጅ መደፈሯን ተከትሎ በወንጀሉ የተጠረጠረ የ25 ዓመት ወጣት በቁጥጥር ሥር ዋለ።
ግለሰቡ በወንጀሉ ተጠርጥሮ የታሰረው የህጻኗ ወላጆች ለፖሊስ ጥቆማ ከሰጡ በኋላ ነው። ሃኪሞች ታዳጊዋ ቅዳሜ ጠዋት ላይ መደፈሯን አረጋግጠው፤ የጤናዋ ሁኔታ ለክፉ የሚሰጥ ደረጃ ላይ አይደለም ብለዋል። የታዳጊዋ ወላጆች የኤምባሲው ሠራተኛ መሆናቸውና በኤምባሲው ቅጥር ግቢ ውስጥ እንደሚኖሩ ተነግሯል። የህንድ መገናኛ ብዙሃን ወላጅ አባቷ የኤምባሲው የጽዳት ሰራተኛ መሆናቸውን እየዘገቡ ይገኛሉ። በወንጀሉ የጠረጠረው ግለሰብም ወላጆች የኤምባሲው ሰራተኛ መሆናቸውን እና ከወላጆቹ ጋር በቅጥር ግቢው ውስጥ እንደሚኖር ተነግሯል። በብዙ ስልጡን ጠባቂዎች የሚጠበቀው የኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዴት ይህን መሰል ወንጀል ይፈጸማል በማለት በርካቶች እየጠየቁ ይገኛሉ። እንደመርማሪዎች ከሆነ የተጎጂና የተጠርጣሪው ወላጆች የሚተዋወቁ ሲሆን፤ ታዳጊዋ ስትጫወት ከተመለከታት በኋላ አባብሎ ወላጆቹ በሌሉበት ወቅት በታዳጊዋ ላይ ጥቃቱን ፈጽሟል። ታዳጊዋ ጥቃት ከተፈጸመባት በኋላ ወደ መኖሪያ ቤቷ ተመልሳ ያጋጠማትን ለእናቷ መናገሯን መርማሪዎቹ ተናግረዋል። የህንድ መንግሥት ከሁለት ዓመታት በፊት ታዳጊዎችን አስገድደው የሚደፍሩ ወንጀለኞች የሞት ቅጣት እንዲበየንባቸው ወስኗል። በህንድ ከሚፈጸሙ አራት የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች መካከል ቢያንስ አንዱ የሚፈጸመው እድሜያቸው ከ18 ዓመታት በታች በሆኑ ታዳጊዎች ላይ ነው።
50905756
https://www.bbc.com/amharic/50905756
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስተዳደር እና የሠራተኛ ማህበር እሰጥ አገባ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ውስጥ ከሚገኙት የሠራተኛ ማህበራት አንዱ ከአየር መንገዱ አስተዳደር ጋር እሰጥ አገባ ውስጥ ገብቷል።
በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ ሁለት የሠራተኛ ማህበራት ይገኛሉ። እኚህም፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር ይሰኛሉ። 'ቀዳማዊ' የምትለዋን ቃል በውስጡ የያዘው የሠራተኛ ማህበር የተመሰረተው ከ58 ዓመታት በፊት ሲሆን፤ ተቋሙ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ተብሎ ሲቋቋም፤ የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ሰራተኞችን ለማካተት እና አዲስ አመራሮችን ወደ ፊት ለማምጣት በአዲሱ ስያሜ ከሠራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር እውቅና ማግኘቱን የማህበሩ ዋና ጸሃፊ አቶ አብዱ ይመር ተናግረዋል። • የኢትዮ-ኤርትራ ድንበር መከፈትን መነሻ ያደረገው ፌስቲቫል • አቶ ለማ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጎልተው የወጡባቸው አጋጣሚዎች ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር ከአሰሪው ጋር በቅን መንፈስ በመደራደር የሠራተኛውን መብት እና ጥቅም እያስከበረ መሆኑን ከትናንት በስቲያ የማህበሩ ሥራ አስፈጻሚ አባላት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል። የዚህ ማህበር ሥራ አስፈጻሚዎች ይህን ይበሉ እንጂ፤ የሌላኛው ማህበር ማለትም፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር ሊቀ መንበር የሆኑት ካፒቴን የሺዋስ ፈንታሁን በዚህ ፈጽሞ አይስማሙም። ካፒቴን የሺዋስ "ማህበሩ አጠቃላይ የሆነ ችግር አለበት" ያሉ ሲሆን፤ ቀዳማዊ የምትለዋን ቃል የሚጠቀውም ማህበር "ለሠራተኞች መብት እና ጥቅም ከማስጠበቅ አንጻረ የነበረው ሚና እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። ዜሮ ነው ማለት ይቻላል" ይላሉ። ካፒቴን የሺዋስ እንደሚሉት ይህ ማህበር ከአስተዳደሩ ጋር ጥብቅ የሆነ ወዳጅነት ነው ያለው። የአየር መንገዱ የኮርፖሬት የሰው ኃይል አስተዳደር ምክትል ፕሬዝደንት የሆኑት አቶ መሳይ ሽፈራው፤ የአየር መንገዱ አስተዳደር እና ቀዳማዊው ማህበር ጥብቅ ወዳጅነት አላቸው የሚለው ወቀሳ ትክክል እንዳልሆነ ይናገራሉ። "ከዚህ ማህበር ጋር የተለየ ግንኙነት የለንም። አስተዳደሩ ለማንም አያዳለም። የተከለከሉት ነገር ካለ ሕጋዊ እንደመሆናቸው መጠየቅ ይችላሉ" ብለዋል። ከቀዳማዊው ማህበር ጋር አስተዳደራቸው እስካሁን ከ10 በላይ ስምምነቶችን መፈረሙን ያስረዱ ሲሆን፤ "አዲስ ማህበር ገና አባላቶቹን መዝግቦ አሳውቆን፣ በአባላት ጉዳዮች ላይ ተነጋግረን፣ 50+1 ሆኖ ሲመጣ ነው ገና በመጀመሪያው ስምምነት ላይ የምንነጋገረው። ስለዚህ 57 ዓመት ከኖረው ማህበር ጋር ራሳቸውን ማወዳደራቸው ትክክል አይደለም" ይላሉ አቶ መሳይ። • በመንግሥት መኪና የጦር መሳሪያ ሲዘዋወር ተያዘ አቶ መሳይ ጨምረውም፤ ማህበሩ ብዙ አስርት ዓመታት የተጓዘ እንደመሆኑ፤ በጊዜ ሂደት ውስጥ በቀዳማዊ ማህበሩና አስተዳደሩ መካከል የተገነባ ግንኙነት ሊኖር እንደሚችል ከጠቆሙ በኋላ ይህ ግን አስተዳደሩ ለቀዳማዊ ማህበሩ አድሎ ያደርጋል ማለት እንዳልሆነ ተናግረዋል። "ሠራተኛው ይበደላል" የኢትዮጵያ አየር መንገድ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር ሊቀ መንበር ካፒቴን የሺዋስ፤ በአየር መንገዱ ሠራተኞች ላይ በተለየ ደግሞ በእርሳቸው ማህበር አባላት ላይ አግባብ ያልሆኑ ጫናዎች እና አስተዳደራዊ እርምጃዎች እንደሚወሰዱ ይናገራሉ። ካፒቴን የሺዋስ እኚህ እርምጃዎች ከማስፈራሪያ እስከ ከሥራ ማገድ እንደሚደርሱ የሚናገሩ ሲሆን፤ ለዚህም ማሳያ የሚሆኑ እርሳቸው አግባብ አይደለም የሚሉትን ሁለት አስተዳዳራዊ እርምጃ የተወሰደባቸውን ሠራተኞች እንደ እማኝነት አቅርበዋል። ለግላዊነት ሲባል ስሙን የማንጠቅሰው የአየር መንገዱ አብራሪ እና የሠራተኛ ማህበሩ አባል የሆነ ግለሰብ፤ የማህበሩ አባላት አባል በሆኑበት የቴሌግራም ቡድን ውስጥ በሰጠው አስተያየት ከሥራው ታግዷል። ይህ አብራሪ ከሥራ የታገደበት ደብዳቤ ላይ በቴሌግራም ቡድኑ ላይ የሰጠው አስተያየት የአየር መንገዱን አስተዳደር የማይወክል ሐሰተኛ እና ዝና የሚያጎድፍ መሆኑን በመጥቀስ በሁለት ቀናት ውስጥ በጽሑፍ ምላሹን እንዲሰጥ እንዲሁም የድርጅቱን መታወቂያ በአስቸኳይ እንዲመልስ ይጠይቃል። • ''በፍርሀት የምንኖርና በሃገራችን እንደ ሁለተኛ ዜጋ የምንቆጠር ሰዎች ሆነናል'' አቶ መሳይ ለዚህ ምላሸ ሲሰጡ፤ "አንድ ሠራተኛ ቅሬታ ካለው ቅሬታውን የሚያቀርብበት አግባብ አለው። ከዚህ ቀደም ማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን በተመለከተ የላክነው ሰርኩላር አለ። በዚያ መሰረት የድርጅቱን እና የአስተዳደሩን ክብር የሚነካ ነገረ እንዳያደርጉ በላክነው ማስጠንቀቂያ መሰረት ነው እርምጃውን የወሰድነው" ብለዋል። ካፒቴን የሺዋስ አስተዳደሩ በሠራተኞች ላይ የሚያደርሰውን ጫና እንደማሳያነት ካቀረቡት ማስረጃዎች መካከል ሌላኛው፤ የአንድ አብራሪ ቤተሰብ አባል ስለ አየር መንገዱ ፌስቡክ ላይ በጻፉት አስተያየት ምክንያት አብራሪው የሶስት ዓመት ጥቅማ ጥቀሙን እንዲያጣ የተደረገበትን ደብዳቤ ዋቢ ነው። በስም የማንጠቅሰው የአብራሪው እናት አየር መንገዱ በነጻ በሰጠው የአየር ቲኬት በረራ ካደረጉ በኋላ ሻንጣቸው ይጠፋል። በዚህ ደስተኛ ያልሆኑት ሌላ የቤተሰብ አባል ቅሬታቸውን ፌስቡክ ላይ ይገልጻሉ። ከዚያም አየር መንገዱ በካፒቴኑ በኩል የቤተሰብ አባሉ አየር መንገዱን በተመለከተ የጻፉትን አስተያየት እንዲያነሱ አስደርጓል። ቀጥሎም አብራሪው የሶስት ዓመት የቲኬት ጥቅማ ጥቅሙ እንዲታገድ ተደርጓል። ይህ የእግድ ደብዳቤ ተፈርሞ የወጣው በአቶ መሳይ ሽፈራው ነው። "እኔ ነኝ ደብዳቤውን የጻፉኩት፤ በወቅቱ ካፒቴኑንም አነጋግሬዋለሁ፤ ድርጅቱ ለሠራተኛው ነጻ ቲኬት የመስጠት ግዴታ የለበትም። እንደ ጥቅም ነው የሚሰጠው። እንደ የራስ ቤት መደረግ የነበረበት ሻንጣውን እንዴት አድርገን እናገኘዋለን በሚለው ላይ ነው መነጋገር የነበረብን። ይህም ውሳኔ የተወሰነው ነጻ ቲኬት የምንሰጥበትን ፖሊሲ መሰረት በማድረግ ነው" ብለውናል። ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሠራተኞች መሠረታዊ ማህበር በአየር መንገዱ ላይ ከሚያቀርባቸው ክስ መካከል፤ የማህበሩ አባላት ከደሞዛቸው ተቆራጭ ሆኖ ወደ ማህበሩ አካውንት እንዲገባ ፈቃዳቸውን ቢሰጡም አስተዳደሩ ግን ይህን ተፈጻሚ ለማድረግ እምቢተኛ ሆኗል የሚለው ይገኝበታል። ካፒቴን የሺዋስ "እያንዳንዱ አባል ከደሞዜ ተቆራጭ ሆኖ ወደ ማህበሩ ገቢ ይደረግ ብሎ የፈረመበትን ወረቀት ይዘን ወደ አየር መንገዱ የሰው ሃብት አስተዳደር ብንሄድም አየር መንገዱ ደሞዝ አልቆርጥም በማለት ሕግ የጣለበትን ኃላፊነት አልተወጣም" ይላሉ። • ቆንጆ እንቅልፍ ምንድነው? ለእንቅልፍስ እንዴት መዘጋጀት አለብን? አቶ መሳይ ለዚህ ምላሽ ሲሰጡ፤ "ይህ እውነት አይደለም። አባላት መዝግበው ዝርዝር አቅርበውልናል። ከሰራተኛው ላይ ደሞዝ ለመቁረጥ ህጋዊ ፍቃድ የሚሰጠው ሰራተኛው ብቻ ነው። ይህ ደግሞ ሰራተኛው ራሱ ከደሞዜ ቆርጠህ አስገባ ሲለኝ እንጂ ማህበሩ ስላለ አይደለም" ይላሉ። አቶ መሳይ ጨምረው እንደተናገሩት፤ ከማህበሩ ሊቀ መንበር የደረሳቸው የአባላት ዝርዝር እንጂ ሊቀ መንበሩ እንደሚሉት አባላት ከደሞዛቸው ተቆራጭ እንዲሆን የፈቀዱበት ደብዳቤ አይደለም። ካፒቴን የሺህዋስ በሊቀ መንበርነት የሚመሩት የኢትዮጵያ አየር መንገድ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር 4900 በላይ አባላት እንዳሉት የገለጹ ሲሆን፤ ከሌላኛው ማህበረ እና ከአየር መንገዱ አስተዳደር ጋር ስለሚገኙበት ሁኔታ ነገ ማለትም አርብ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ ተናግረዋል።
news-52791489
https://www.bbc.com/amharic/news-52791489
ስለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምን ያህል ልንሰጋ ይገባል?
ኮሮናቫይረስ የማይታይ ገዳይ በሽታ እንደሆነ ተደጋግሞ ይገለጻል። ለመሆኑ በሽታው ከዚህ በላይ ምን ያህል አስከፊ ነው?
ቫይረሱ የማይታይ፣ ከያዘንም እስካሁን በሳይንስ የተረጋገጠ ክትባትም ሆነ መድኃኒት አልተገኘለትም። በመሆኑም በርካታ ሰዎች ከቤት ለመውጣት፣ ወደ መደበኛ ሕይወታቸው ለመመለስ፣ ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት ለመላክ ቢሰጉ ምንም የሚደንቅ አይደለም። ምክንያቱም ሁሉም ሰው ደህና መሆን ይፈልጋል፤ ነገር ግን ከዚህ ቀደም እንደነበረው ሕይወታችን ደኅንነታችን የተጠበቀ አይደለም። ቫይረሱ ከሚያሳድረው የጤና አደጋ ባሻገርም፤ ተያያዥ የሆኑ ከፍተኛ ቀውሶችን አስከትሏል። ለበሽታው ያለንን ተጋላጭነት እንዴት ልንቀንስ እንችላለን? ይህ ጥያቄ የብዙዎች ጭንቀት ነው። ታዲያ ይህንን ለማድረግ ምን ማድረግ ይኖርብናል? አንዳንድ ሰዎች እርግጠኛ እስኪኮን ድረስ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የተጣሉ ገደቦች ሊቀጥሉ ይገባል ይላሉ፤ ነገር ግን ገደቦቹ በራሳቸው አደጋ መሆናቸውን ከግምት ያስገቡ አይደሉም። የዩናይትድ ኪንግደም የህክምና አማካሪ ፕሮፌሰር ክሪስ ዊቲይ ይህንን ተያያዥ ቀውስ "የወረርሽኙ ቀጥተኛ ያልሆነ አደጋ" ሲሉ ይገልጹታል። ይህንን ለማስቀረት ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የተጣሉ ገደቦች በላሉ መጠን፤ ግለሰቦች እንዲሁም ጠቅላላ ማኅበረሰቡ የሚያጋጥማቸውን ችግሮች ሚዛናዊ ለማድረግ ውሳኔ ማሳለፍ አለባቸው። ሙሉ በሙሉ ደኅንነት የማይሰማን ለምንድን ነው? ይህንን ስሜት ብዙዎች ይጋሩታል። በኤደንብራ ዩኒቨርሲቲ የዓለም ሕብረተሰብ ጤና ኃላፊ ፕሮፌሰር ዲቪ ስሪዲሃር፤ ይህን ጥያቄ ለመመለስ ልንጠይቅ የሚገባው ጥያቄ ምን ያህል ደኅንነታችን ተጠብቋል? የሚለው ነው ይላሉ። "ወደፊትም ቢሆን አደጋ የማይኖርበት ምክንያት የለም" የሚሉት ፕሮፌሰሯ፤ ማሰብ ያለብን ልክ በዕለት ተዕለት እንደሚያጋጥሙን የመኪና ወይም የብስክሌት አደጋዎች ሁሉ ኮቪድ-19 በማኅበረሰቡ በሚቆይበት ዓለም ውስጥ አደጋውን እንዴት ልንቀንስ እንደምንችል መሆኑን ይገልጻሉ። ይህም መንግሥት ወረርሽኑን ለመቆጣጠር አካላዊ ርቀትን መጠበቅ፣ የቫይረሱን መከላከያ መሳሪዎች አቅርቦት፣ በምርመራ መጠን እና ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የመከታተል እርምጃዎች ይወስናል ብለዋል። አሁን አሁን በርካታ ገደቦች እየተነሱ ስለሆነ ለወደፊቱ ግለሰቦች የሚደርሱበት ውሳኔ ውሳኔና የሚወስዱት እርምጃ ሚናው ወሳኝ ነው። ምን አልባት ውሳኔው ትክክለኛ አማራጭ የመፈለግ ጉዳይ ሳይሆን የመጨረሻውን አስከፊ አማራጭ የመፈለግ ጉዳይም ሊሆን ይችላል። በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የአደጋ ስጋት ምሁር እና የመንግሥት አማካሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ዴቪድ ስፔንግልሃልተር በበኩላቸው፤ "አደጋውን በተገቢው መንገድ የመቆጣጠር ጉዳይ ጨዋታ ሆኗል" ይላሉ። በዚህም ምክንያት "እኛ እያጋጠመን ባለው የፈተና መጠንን መቆጣጠር እንፈልጋለን" ብለዋል። ይሁን እንጂ በአደጋው ላይ ጫና ያሳደሩብን ሁለት ምክንያቶች አሉ ይላሉ ፕሮፌሰሩ። አንደኛው በቫይረሱ እንዳንያዝ ሲሆን አንዴ ከተያዝን በኋላ ደግሞ የመሞት አሊያም በጠና መታመም ሌላኛው ነው። በሆስፒታል አሊያም በእንክብካቤ ማዕከላት ካልሆንን በስተቀር ለበሽታው ያለን ተጋላጭነትን የሚያሳየው መመሪያ የሚመጣው በብሔራዊ ስታስቲክስ መሥሪያ ቤት ከሚካሄደው የመንግሥት ክትትል ፕሮግራም ነው። ሰሞኑን የወጣው አንድ መረጃ እንደሚያሳየውም ከ400 ሰዎች አንዱ በቫይረሱ ይያዛል። ይህም በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ያለን የመገናኘት እድልን ከወሰንን፣ አካላዊ ርቀትን ከጠበቅን፤ የመያዝ ዕድሉ በጣም ጠባብ እንደሆነ ያሳያል። በመሆኑም መንግሥት ቫይረሱን ለመግታት ምርመራዎችን ካካሄደ፣ ቫይረሱን ለመቆጣጠር የሚካሄዱ ፕሮግራሞች ላይ ክትትል ካደረገ፣ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ሊቀንስ እንደሚችል ተስፋ ይሰጣል። አብዛኞቹ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የሚያጋጥማቸውም ከቀላል እስከ መካከለኛ ህመም ነው። በሆስፒታል የህክምና ክትትል የሚያስፈልገው ምልክት የሚያሳየው ከ20 ሰዎች መካከል አንዱ ነው። ለበሽታው ያለንን ተጋላጭነት እንዴት ልናውቅ እንችላለን? ከዚህ ቀደም ሲል የቆየ የጤና እክል ያለባቸው ሰዎች ለበሽታው የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው። ከ65 ዓመት በታች እድሜ ላይ የሚገኙ ሰዎች ያለህመም መሞታቸው የተለመደ አለመሆኑን አንድ ጥናት አመልክቷል። ምን አልባት ቀላሉ መንገድ የሚሆነው በሚቀጥሉት 12 ወራት መሞትን በተመለከተ ምን ያህል እንደምትጨነቁ ራሳችሁን መጠየቅ ነው። ከ20 ዓመት በላይ ከሆን በበሽታው የመያዝ እድላችን ለመጪዎቹ ወራት ያለን የመሞት እድል ነጸብራቅ ነው። ለምሳሌ 40 ዓመት የሆነው ሰው፤ በአማካይ በአንድ ዓመት ውስጥ ከአንድ ሺህ ሰዎች መካከል አንዱ የመሞት እድል አለው። በተመሳሳይ ከኮሮናቫይረስ የመዳን እድልም አይኖረውም። ይህም በአማካይ ለበሽታው ያለንን ተጋላጭነት የሚያሳይ ነው፤ ነገር ግን የሞት አደጋው በማንኛውም የእድሜ ክልል የሚገኙና የጤና እክል ባለባቸው ሰዎች ስለተያዘ፤ አብዛኛው ሰው ለበሽታው የመጋለጥ እድሉ ዝቅተኛ ነው። ህጻናት ከኮሮናቫይረስ ይልቅ እንደ ካንሰርና አደጋ ባሉ ሌሎች ምክንያቶች ለሞት የመጋለጥ እድላቸው ከፍ ያለ ነው። በወረርሽኙ ወቅት በቫይረሱ የሞቱት ከ15 ዓመት በታች ያሉ ህጻናት ሦስት ናቸው፤ ይህም በየዓመቱ በመኪና አደጋ ከሚሞቱ 50 ህጻናት ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ ቁጥር ነው። ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑትን መለየት ሁላችንም ለበሽታው ካለን ተጋላጭነት አንጻር ራሳችንን ለመጠበቅ ልብ ልንለው የሚገባው ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑትን መለየትን ነው። በአሁኑ ጊዜ ባለስልጣናትና የጤና ባለሙያዎች ብዙ ሰዎችን ራሳቸውን እንዲያገሉ እየጠየቁ ነው። እነዚህ ሰዎች ሌሎች ተጓዳኝ በሽታዎች ያሉባቸውንም ያካትታል። ከዚህም በተጨማሪ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ለበሽታው በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ ናቸው ተብለው ተለይተዋል። እነዚህም ከ70 ዓመት በላይ የሆኑትንና የስኳርና የልብ ሕመም ችግር ያለባቸውን የያዘ ነው። በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ በእድሜ መግፋት ዙሪያ ባለሙያ የሆኑት ፕሮፌሰር ሳራ ሃርበር "የተሸፋፈነና የዘፈቀደ የእድሜ አጠቃቀምን" በተመለከተ ያሳሰቡ ሲሆን፤ ለበሽታው የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎችን በጥንቃቄ መመልከት እንደሚያስፈልግ መክረዋል።
news-54119251
https://www.bbc.com/amharic/news-54119251
ሊሞት የተቃረበ አባታቸውን ሊሰናበቱ የፈለጉ አራት ልጆች ለለይቶ ማቆያ 600 ሺህ ብር ክፈሉ ተባሉ
በአውስትራሊያ በህይወትና በሞት መካከል ያለ አባታቸውን ሊሰናበቱ ከሌላ ከተማ ሊመጡ የፈለጉ አራት ልጆች ለሚያርፉበት ለይቶ ማቆያ ሆቴል አስራ ስድስት ሺህ ዶላር (600 ሺህ ብር) መክፈል አለባችሁ ተብለዋል።
ማርክ ኪንስና አራት ልጆቹ የ39 አመት አባታቸው በካንሰር ህመም በፀና የታመመ ሲሆን ኩዊንስላንድ በምትባለው ከተማ ቤቱ ውስጥ ይገኛል። አራቱ ልጆቹ ደግሞ በሌላኛዋ ከተማ ሲድኒ ናቸው ያሉት። የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት አውስትራሊያ ከከተማ ወደ ከተማ የሚደረግ እንቅስቃሴ ላይ ገደብ የጣለች ሲሆን የኩዊንስላንድ ባለስልጣናትም ለዚህ ሲሉ ህጉን እንዲያላሉት ብዙዎች ተማፅነዋቸዋል። ሁኔታው ቁጣን በመቀስቀሱም ከ200 ሺህ ዶላር በላይም ገንዘብ ተዋጥቷል። መጀመሪያ ላይ ህመምተኛው ማርክ ኪንስ አንድ ልጅ ብቻ ሊያየው እንደሚችልና ከልጆቹም መምረጥ እንዳለበት ተነግሮት ነበር። በኋላም የግዛቲቷ አስተዳደር ሁኔታውን አሻሽለው ሁሉም ልጆቹ መጥተው እንዲያዩትና እንዲሰናበቱት ፈቀዱ። ሆኖም ልጆቹ ለሁለት ሳምንታት ያህል በራሳቸው ወጪ በሆቴል ለይቶ ማቆያ እንዲገቡም እንደ ቅድመ ሁኔታ ተቀመጠላቸው። ከዚህም በተጨማሪም ልጆቹ አባታቸውን በሚጎበኙበት ወቅት ሰውነታቸው በሙሉ በመከላከያ መሸፈን አለበት። "ባለቤቴ እሱን ለማየት ይህን ያህል ክፍያ ክፈሉ እያላችሁን ነው? ለመቅበርስ ምን ያህል ሊያስወጣን ነው? አለችኝ" በማለት የልጆቹ አያት ብሩስ ላንግቦርን ለ7 ኒውስ ተናግረዋል። ልጆቹን አባታቸውን እንዲያዩና እንዲሰናበቱም ለማስቻል በጎ ፈንድ ሚ ገንዘብ እየተሰባሰበ ነው። መጀመሪያ ታቅዶ የነበረው 30 ሺህ ዶላር ለመሰብሰብ ቢሆንም ባልተጠበቀ ሁኔታም 200 ሺህ ዶላር ተዋጥቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰንም አንድ ሺህ ዶላር አዋጥተዋል። በገንዘብ ማሰባሰቢያው ድረገፅም በርካቶች ቤተሰቦቹን ያፅናኑ ሲሆን፤ የኩዊንስላንድ አስተዳደርም ከፍተኛ ትችትን እያስተናገደ ነው። በርካቶችም "ሊሞት የተቃረበ አባታቸውን እንዳያዩ እንዴት ይከለከላሉ? እንዲህ አይነት ገንዘብ ክፈሉ ማለትም አሳፋሪና ጨካኝነት ነው"ብለውታል። የኩዊንስላንድ የጤና ኃላፊዎች በበኩላቸው በአሁኑ ወቅት አለም አቀፍ ወረርሽኝ እየታገሉ ከመሆናቸው አንፃር ህዝቡን በተለይ ተጋላጭ ማህበረሰቡን መጠበቅ እንደሚያስፈልግ አስምረዋል።
news-49541151
https://www.bbc.com/amharic/news-49541151
በቴክሳስ በደረሰ ጅምላ ጥቃት ቢያንስ አምስት ሰዎች ሞተዋል
ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በቴክሳስ ግዛት በደረሰ ጅምላ ጥቃት ቢያንስ አምስት ሰዎች እንደተደገሉ ታውቋል።
በግዛቲቱ በአንድ ወር ውስጥ ለሁለተኛ ጎዜ በተከሰተው የጅምላ መሣሪያ ታጥቆ ያገኘው ሰው ላይ እየተኮሰ የነበረውን ታጣቂ በማስቆም ላይ ሳለ ተመትቶ መውደቁ ተነግሯል። ታጣቂው መኪናው ውስጥ ሳለ ነበር መንገደኞች እና ሞተር ብስክሌተኞች ላይ ይተኩስ የነበረው። ከዚያም አንድ መኪና ሰርቆ ጥቃቱን አጠናከረ። በዚህ መሃል አንድ ፖሊስ በተኮሰው ጥይት ተመትቶ ሊሞት ችሏል። በ30ዎቹ አጋማሽ ላይ እንደሚገኝ የተነገረለት ነጭ የጅምላ ጥቃት አድራሽ ለምን ጥቃቱን እንዳደረሰ እስካሁን አልታወቀም። ከአራት ሳምንታት በፊት እንዲሁ ቴክሳስ ግዛት ውስጥ ኤል ፓሶ በተሰኘች ከተማ አንድ ጅምላ ገዳይ የ22 ሰዎችን ሕይወት መቅጠፉ አይዘነጋም። ጥቃት አድራሹ ምሽት 4፡00 ሰዓት ገደማ መሃል መንገድ መኪናው ውስጥ ሳለ ፖሊሶች ሲያስቆሙት ነው መተኮስ የጀመረው ተብሏል። በትላንትናው ጥቃት ቢያንስ 20 ሰዎች ቆስለዋል፤ ከእነዚሀም ውስጥ ሶስቱ አባሎቼ ናቸው ብሏል ፖሊስ። ነገር ግን ሁሉም ተጎጂዎቹ በጥይት የተመቱ ሳይሆኑ ጥቃቱን ለማምለጥ ሲሞክሩ የተጎዱም አሉበት ሲል የከተማዋ ፖሊስ አክሏል። የኦዴሳ ከተማ ሆስፒታል ከተጎጂዎቹ መካከል የሁለት ዓመት ሕፃን እንደሚገኝ አሳውቆ 7 ሰዎች በሞት እና ሕይወት መካከል ናቸው ብሏል።
news-56622889
https://www.bbc.com/amharic/news-56622889
ከበርካታ ወንዶች ጋር ተፎካክራ በ12ኛ ክፍል ፈተና ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገበችው ሴት ተማሪ ማናት?
የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነ የ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተናን ከ350 ሺህ በላይ ተማሪዎች ተፈትነው ውጤታቸውን ማወቅ ችለዋል።
በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛው ውጤት የቅዱስ ዮሴፍ ተማሪ ብሩክ ባልካቸው 669 አስመዝግቧል። ሁለተኛ የወጣው ደግሞ የኤክዜል አዳማ ተማሪ የሆነው ናኦል በለጠ 665 አምጥቷል። እንደ ኤጀንሲው መረጃ ከ1ኛ እስከ 14ኛ ደራጃ የሚይዘውን ከፍተኛ ውጤት ያመጡት በሙሉ ወንዶች ናቸው። በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ 15ኛ የሆነቸው ሰዓዳ ጀማል ከሴት ተማሪዎች ቀዳሚዋ ናት። ሁለተኛ ደግሞ ቤዛዊት ብርሐኔ ስትሆን የክሩዝ ትምህርት ቤት ተማሪ መሆኗን የኤጀንሲው መረጃ ያሳያል። ሰዓዳ ጀማል ማን ነች? ሰዓዳ ጀማል ለቤተሰቦቿ የመጀመሪያ ልጅ ነች። ተወልዳ ያደገችው በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግራለች። ገና ታዳጊ እያለች ትምህርቷን ከተማው ላይ በሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች መማሯን ታስታውሳለች። "እስከ አራተኛ ክፍል ድረስ የተማርኩት አልቀለም የሚባል ትምህርት ቤት ነበር፤ ጎበዝ ተማሪ ነበርኩ" ትላች ሰዓዳ። ከ5ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ድረስ ወራቤ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ከ9 እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ደግሞ በስልጤ ልማት ማኅበር የተቋቋመው ሃይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተምራለች። የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ የሆነችው ሰዓዳ፣ ሃይረንዚ አዳሪ ትምህርት ቤት ተምራ ከፍተኛውን ውጤት ለማስመዝገብ በቅታለች። በመጀመሪያ ደረጃም ሆነ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶቿ የደረጃ ተማሪ እንደነበረች የምታስታውሰው ሰዓዳ 10ኛ ክፍል 4 ነጥብ በማምጣት በክልል እና በትምህርት ቤቷ የገንዘብ እና የሜዳሊያ እንዲሁም የተለያዩ ስጦታዎች ተበርክተውላታል። "10ኛ ክፍል 4 ነጥብ አምጥቼ ሳልፍ 2 ሺህ ብር ክልሉ ሸልሞኛል። ከትምህርት ቤቴ ደግሞ የተለያዩ ሽልማቶች እና ሜዳሊያ አግኝቻለሁ።" ለእህት ወንድሞቿ ሁሌም መልካም አርዓያ መሆኗን የምትናገረው ሰዓዳ፤ 11ኛ ክፍል የሚማረው ወንድሟ ጥሩ ውጤት እንደሚያስመዘግብ ትናገራለች። የፈተና ውጤቷን የሰማች ዕለት ሰዓዳ የምታውቀው ዘንድሮ በተሰጠው የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ለከፍተኛ ትምህርት የሚያበቃትን ጥሩ ውጤት ማምጣቷን እንጂ ብሔራዊ ፈተናው ከሴቶች አንደኛ መሆኗን የሰማችው ከቢቢሲ ነው። የቢቢሲ ጋዜጠኛዋ የምትነግራትን ማመን አልቻለችም። ድምጿ ውስጥ የሚፍለቀለቅ ሳቅ ሞልቶ "በጣም ነው ደስ ያለኝ፤ ለመጀመሪያ ጊዚ ካንቺ መስማቴ ነው" ስትል መለሰች። ሰዓዳ በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ካመጡ ተማሪዎች ስሟ በ15ኛ ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው፤ ከፊቷ የሚገኙ 14 ወንዶች ናቸው። እርሷ በአስራ አምስተኛነት ስትመጣ 650 ነጥብ አስመዝግባ ነው። በዚህም ደስታዋን ስትገልጽ፤ "ከፍተኛ ውጤት አመጣለሁ ብዬ ጠብቄ ነበር ግን ከሴቶች ቀዳሚ እሆናለሁ አላልኩም" ብላለች። ባለፈው ዓመት መሰጠት የነበረበት የ12ኛ ክፈል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ተራዝሞ ነበር። በኋላ ላይ ፈተናው በታብሌት ይሰጣል ተብሎ ሲጠበቅ ሌላ መዘግየት ተፈጠረ። በስተመጨረሻም ተማሪዎቹ በወረቀት እንዲፈተኑ ተወስኖ የካቲት መጨረሻ ላይ በአገር አቀፍ ደረጃ 350 ሺህ ተማሪዎች ፈተናውን ወሰዱ። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ ትምህርት ቤቶች በመዘጋታቸው ተማሪዎች ዓመቱን ሙሉ አልተማሩም። ነገር ግን መምህሮቿ የተለያዩ አጋዥ ማስታወሻዎችን በቴሌግራም ይልኩላቸው እንደነበር ሰዓዳ ገልጻለች። የሚያስፈልገኝ ነገር ሲኖር መምህራኖቼን ትምህርት ቤት ውስጥ በማንኛውም ሰዓት አገኛቸዋለሁ። ርዕሰ መምህራችንም በምክር ያበረታታኝ ነበር ብላለች። ሰዓዳ "የፈተናው በተደጋጋሚ መራዘም ከባድ ነበር፤ ተስፋ ያስቆርጣል። በኋላ ላይ የሚመጣውን ውጤት እያሰብኩኝ ራሴን ሳዘጋጅ ነበር" ትላለች። የፈተናው መራዘም ላይ በርካታ ተስፋ የሚያስቆርጡ ነገሮች እንደነበሩ የምታስታውሰው ሰዓዳ፤ ሁሌም ግን ወደፊት ያለውን ብሩህ ተስፋ በማሰብ ንባቤን እቀጥል ነበር ብላለች። መምህራኖቿ በተለያየ ጊዜ እርሷ እና ጓደኞቿን እንዲያጠኑ፣ ተስፋ እንዳይቆርጡ እና እንዳይዘናጉ ምክር እንደሰጧቸውም ትናገራለች። የፈተናው ውጤት በተገለጸበት ጊዜ በአጋጣሚ አያቷ ጋር የነበረችው ሰዓዳ ማለፊያ ነጥብ ማስመዝገቧን ስታውቅ መጀመሪያ የተናገረችው ለአያቷ ነበር። ከዚያ በኋላ ለእናትና ለአባቷ እንዲሁም ለጓደኞቿ ደውላ መናገሯን ትገልጻለች። ወላጆቿም በውጤቷ ከመደሰት ባሻገር "ከዚህ በላይ እንጠብቃለን" ማለታቸውን ትናገራለች። ሰዓዳ ቤት ውስጥ ጫና የለባትም። እናም ወላጆቿ ሁልጊዜም ከፍተኛ ውጤት እንድታመጣ ያበረታቷት፣ እንድታጠናም ሁኔታዎችን ያመቻቹላት እንደነበር ገልጻለች። ትምህርቷን ዘወትር በክፍል ውስጥ በሚገባ መከታተሏ፣ ፈተና ሲደርስ ከማንበብ ይልቅ ከስር ከስር ማጥናት መምረጧ ጥሩ ውጤት እንድታመጣ አግዟታል። "ፈተና ሲደርስ ማንበብ በሚገባ ሳይረዱ ወደ ፈተና መግባት ስለሚያስከትል ምርጫዬ አይደለም" በማለት ከፈተና በፊት ቀድሞ ማጥናት ልማዷ ማድረጓን ተናግራለች። "ፈተና ኖረም አልኖረም ማንበብ እወዳለሁ፣ ለማወቅ በሚል ነው የማነበው።" ከጓደኞች ጋር ስላነበበቻቸው ነገሮች መወያየት፣ መምህራኖቿንም በየጊዜው እንደምትጠይቅም ገልጻለች። ሕክምና ማጥናት የምኞቷ የሆነው ሰዓዳ በዚሁ መስክም በከፍተኛ ውጤት ተመርቃ ማኅበረሰቧን እና አገሯን ማገልገል የወደፊት ምኞቷ ነው።
news-48933188
https://www.bbc.com/amharic/news-48933188
"የለውጥ አመራሩን ሳይረፍድ ከጥፋት መመለስ ይቻላል" እስክንድር ነጋ
በጋዜጠኛና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እስክንድር ነጋ የሚመራው የባላደራ ምክር ቤት ዛሬ ሐምሌ 3፣ 2011 ዓ. ም በምክር ቤቱ ቢሮ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ተቋርጧል።
መግለጫው በዋነኛነት ያተኮረው ከሰሞኑ የታሠሩበት አባላቱን ኤልያስ ገብሩና ስንታየሁ ቸኮል ላይ ሲሆን፤ ከአንድ ዓመት በፊት እስረኞች ተፈተው የነበረው ሁኔታ ወደ ኋላ እንደተቀለበሰም እስክንድር ተናግሯል። • "ከጄ/ል አሳምነው ጋ በምንም ጉዳይ ያወራሁበት አጋጣሚ የለም" እስክንድር ነጋ • "ታከለ ኡማ አዲስ አበባን መምራት የለባቸውም" እስክንድር ነጋ "እስር ቤቶቻችን የህሊና እስረኞች አልባ የነበሩ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን የህሊና እስረኞች ያሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል፤ እነዚህም እስረኞች ኢ- ሰብአዊ በሆነ ሁኔታ ነው የተያዙት፤ ይህንንም መግለጫ ስንጠራ ያሉበትን ሁኔታ ለማሳወቅ እንዲሁም ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ለመጠየቅ ነው" ብሏል። መግለጫው ተጀምሮ ለምን ያህል ደቂቃ ተሰጥቶ እንደነበር በትክክል እንደማያውቅ ለቢቢሲ ገልጾ፤ መግለጫው ተነቦ ጋዜጠኞች ሁለት ጥያቄ ጠይቀው መልስ መስጠት ሲጀምሩ እንደተቋረጠ ተናግሯል። መግለጫው ለመቋረጥ የበቃው "ጥያቄ አለን" በሚሉ ሰዎች በተነሳ ረብሻ ሲሆን፤ በባላደራው ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ላይ የተገኙ በቁጥር 10 የሚሆኑ ወጣቶች ደምፃቸውን ከፍ አድርገው ''ባንዲራችን ይህ ነው'' በማለት ባለ ኮከቡን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ከፍ አድርገው ሲያሳዩ ነበር። ''አገር መገንባት ነው የምንፈልገው አንጂ ማፍረስ አይደለም''፣ ''አይሳካልህም''፣ ''ምክር ቤቱ ኦሮሞን ያገለለ ነው''፣ ''ታከለ [የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ] መጤ አይደለም''፣ ''አዲስ አበባ የሁሉም ናት'' የሚሉ መፈክሮችን ደጋግመው ሲያሰሙ ነበር። የነበረውን ሁኔታ አረጋግቶ መቀጠል አይቻልም ነበር ወይ? በሚል ከቢቢሲ ለቀረበለት ጥያቄ "ማረጋጋት አይቻልም" የሚል ምላሽ የሰጠው እስክንድር፤ የታቀደበት እንደነበርና የተደራጀም እንደነበር ገልጿል። "ሰንደቅ አላማዎቹ በደንብ ተዘጋጅተው፣ ጥቃት የሚያደርሱበት ስውር መሣሪያዎች ይዘው፤ የሚናገሩት ነገር በስሜት ሳይሆን በደንብ የተጠና እንደነበር የሚያመላክቱ ነገሮች አግኝተናል" ብሏል። ነገሮችን ለማረጋጋትና ሁኔታው ወደ ሌላ ከማምራቱም በፊት ቶሎ ከአዳራሹ እንደወጣም ይናገራል። • “የመከላከያው በአደባባይ ሚዲዎችን እከሳለሁ ማለት አስፈሪ ነው” ዶ/ር አብዲሳ ዘርዓይ • ለባለስልጣናቱ ግድያ አዴፓ ራሱን ተጠያቂ እንዲያደርግ ህወሐት ጠየቀ "የምናዝነው ከመልዕክቱ ይልቅ የተፈጠረው ነገር በመጉላቱ ነው፤ የተነሳንበትን ዋነኛ አላማ ውጦብናል፤ በዚህም በጣም እናዝናለን" ብሏል። መግለጫውን ከመስጠታቸው ከአንድ ቀን በፊት "የተለመዱ" የሚላቸው ማስፈራሪያዎችና ዛቻዎች እንደነበሩ የሚናገረው እስክንድር በስልክ፣ በቪዲዮም ማስፈራሪያ እንደደረሰው ገልጿል። ጥዋት ላይም ቢሮ ሊገባ በነበረበት ወቅት 'ሲቪል የለበሰ' አንድ ፖሊስ ቢሮ ላይ ጠብቆ እንዳይገባ ከልክሎት እንደገፈተረው ለቢቢሲ ተናግሯል። ከዚህም በተጨማሪ ጋዜጠኞች እንዳይገቡ እንደተከለከሉና የምክር ቤቱ አባል ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉና ሌላ አንድ አባል በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለው እንደነበር ግን ብዙም ሳይቆይ እንደተለቀቁ ገልጿል። በተደጋጋሚ የባልደራስ ምክር ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ሲዘጋጅ የተሰረዘበትን እስክንድር የፖለቲካ ምህዳሩ ስለመጥበቡ አንድ "ቁንፅል ማሳያ" ነው ይላል። ከዚህ በላይ ግን ሰሞኑን አገሪቱ ውስጥ ከተከሰቱ ችግሮች ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በፀረ-ሽብር ሕግ መጠየቃቸው "ግዙፋ ማሳያ" እንደሆነም ይናገራል። "አገራችን ወደ ኋላ እየተጓዘች ስለ መሆኗ፤ የተገባው ዲሞክራሲ፣ ይመጣል ተብሎ የተገባው ቃል ለመታጠፉ ምንም ማስረጃ የለም፤ ያ ትልቅ ማስረጃ ነው" ብሏል። አክሎም "በአጠቃላይ አገራችን ጥሩ አቅጣጫ ላይ አይደለም። ነገር ግን አሁንም መናገር የምፈልገው ተስፋ የሚያስቆርጥ አይደለም፤ ምንም እንኳን መብታችን እየተደፈጠጠ ቢሆንም መብታችን እየተነፈገ ቢሆንም፤ አዲሱ የለውጥ አመራር እየከጀለ ነው፤ በጥፋት መንገዱ ላይ አንድ እርምጃ ነው የወሰደው፤ ብዙ አልተጓዘም። ከዛ ሳይረፍድ መመለስ ይቻላል። ነገሮች ሳይባባሱ የማንመልሳቸው ደረጃ ሳንደርስ እንዲመለስ ነው ጥሪ ማስተላለፍ የምፈልገው" ብሏል። አገሪቷ እስካሁን የነበረችበት ሁኔታ "መስቀለኛ መንገድ" ነበር የሚለው እስክንድር፤ አሁን ደግሞ "ወደ ጥፋቱ የመሄድ አዝማሚያ " እንዳለ ይገልፃል። ከወዲሁ "መንግሥት አካሄዱን ሊያስተካክል እንደሚገባ" ይናገራል። በተለይም አባላቶቹ በፀረ ሽብር ሕጉ እየተጠየቁ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞም " ከዚህ በፊት ጦርነት እናውጃለን ተብሎ ነበር፤ ይሄው በዴሞክራሲ ሽግግሩ ላይ የታወጀ ጦርነት ነው፤ ከግድያ አንድ ደረጃ ዝቅ ያለው በሽብር መክሰስ ነው። ይህ የሚያዋጣ መንገድ አይደለም። የለውጡ አመራር ከዚህ የጥፋት መንገድ ሊስተካከል ይገባዋል። ለአገር፣ ለኢህአዴግም ሆነ ለራሳቸው የሚያዋጣው የዲሞክራሲ መንገድ ነው" ብሏል።
news-51382625
https://www.bbc.com/amharic/news-51382625
የኮሮናቫይረስ እስካሁን ትክክለኛ ስም እንደሌለው ያውቃሉ?
በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን አጥቅቶ፣ መቶዎችን ደግሞ በገደለው የወቅቱ የዓለማችን የጤና ስጋት የሆነው ቫይረስ አስካሁን ድረስ ትክክለኛ ስም እንዳልተሰጠው ያውቃሉ?
ወረርሽኙ እስካሁንም የሚታወቀው ኮሮናቫይረስ በሚል ስያሜ ነው። ነገር ግን ይህ ስም ቫይረሱ የሚገኝበት ዝርያ አጠቃላይ ስም ነው። ስለዚህም ተገቢውን ስያሜ ለበሽታው ለማግኘት ሳይንቲስቶች የቤተሙከራቸውን በር ዘግተው ጥረት ሲያደረጉ ቆይተዋል። አሁን ግን ተገቢውን ስያሜ ይፋ ለማድረግ እየተቃረቡ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ለዚህ ቫይረስ ስም መስጠት ለምን ይህን ያህል አስቸጋሪ ሆነ? "ለአዳዲስ ቫይረሶች ስም ማውጣት በአብዛኛው ቀስ ብሎ የሚመጣ ጉዳይ ነው፤ ሁሉም እንደሚረዳው እስካሁን ዋነኛው ትኩረት የተደረገው የሕብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ በሚወሰዱ እርምጃዎች ላይ ነው" ሲሉ በጆንስ ሆፕኪንስ ውስጥ በሚገኘው የጤና ደህንነት ማዕከል ውስጥ ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ክሪስታል ዋትሰን ይናገራሉ። ። አክለውም "ነገር ግን ስም መስጠቱ ቀዳሚ ጉዳይ የሚሆንባቸው ወቅቶችም አሉ" ይላሉ። ይህንን ቫይረስ ለመለየት ሳይንቲስቶች ኖቬላ ወይም "አዲስ" እያሉ ሲጠሩት ቆይተዋል። ቫይረሱ ኮሮናቫይረስ የሚል ስም ያገኘው በማጉሊያ መነጽር በሚታይበት ጊዜ ባለው ከዘውድ ጋር የሚመሳሰል ቅርጽ እንደሆነ ይነገራል። • ኮሮናቫይረስ፡ የወቅቱ አሳሳቢው የዓለማችን የጤና ስጋት • ቻይና አሜሪካን ኮሮናቫይረስን አስመልክቶ ፍራቻ እየነዛች ነው ስትል ወነጀለች የዓለም የጤና ድርጅትም ቫይረሱ በጊዜያዊነት 2019-ኤንኮቪ (2019-nCoV) ተብሎ እንዲጠራ አድርጓል። ይህም 2019 ቫይረሱ የተገኘበት ዓመትን የፈረንጆቹን አመት ሲወክል "ኤን" ደግሞ ኖቬላ ወይም "አዲስ" የሚለውን አመልክቶ "ኮቪ" የሚለው ደግሞ ኮሮናቫይረስን ይወክላል። "በሽታው አሁን ያለውን ስም ለመጠቀም ቀላል አይደለም፤ ስለዚህም የመገናኛ ብዙሃንና ሕዝቡ ቫይረሱን ለማመልከት ሌሎች ስሞችን እየተጠቀሙ ነው" ይላሉ ዶክተር ዋትሰን። በጎ ፍቃደኞች በቻእና አንድ የባቡር ጣቢያ ውስጥ በጸረ ተህዋስ ሲያጸዱ "ለቫይረሱ ትክክለኛውን ስያሜ የማንጠቀም ከሆነ የእራሱ ችግር ያስከትላል። ለምሳሌም የቻይና ቫይረስ በማለት ከተጠራ በአገሩ ዜጎች ላይ ችግርን ያስከትላል።" ማህበራዊ ሚዲያ በተስፋፋበት በዚህ ዘመን ይፋዊ ያልሆኑ ስሞች በፍጥነት ተሰራጭተው ስለሚለመዱ በተገቢ ስያሜ ለመተካት እጅግ አስቸጋሪ እንደሚሆን ይጠቅሳሉ። አዲስ ለሚከሰቱ የቫይረስ አይነቶች በአስቸኳይ ስያሜን የመስጠቱ ኃላፊነት ያለው የቫይረሶችን አፈጣጠርና ዝርያ የሚለይ ኢንተርናሽናል ኮሚቴ ኦን ታክሶኖሚ ኦፍ ቫይረስስ የተባለው ኮሚቴ ነው። • በቻይና የተከሰተው አዲስ ቫይረስ ምን ያህል አስጊ ነው? • የአውስትራሊያ ሳይንቲስቶች ኮሮና ቫይረስን 'ሊያመርቱ' ነው ከአስር ዓመት በፊት አጋጥሞ የነበረው ኤች1ኤን1 (H1N1) የተባለው ወረርሽኝ "የወፍ ጉንፋን" የሚል ስያሜን አግኝቶ ነበር። ይህም ምንም እንኳን በሽታው በሰዎች አማካይነት የሚዛመት ቢሆንም ግብጽ ያሏትን አሳማዎች በሙሉ አርዳ አስወግዳለች። ይፋዊ ስያሜዎችም እራሳቸው ችግርን ሊያስከትሉ ይችላሉ። ለዚህም ምሳሌ ከ4 ዓመታት በፊት ተከስቶ ለነበረው ሜርስ ቫይረስ የተሰጠውን ስያሜ የዓለም የጤና ድርጅት ተችቶት ነበር። ምክንያቱም ለበሽታው የተሰጠው ስያሜ አህጽሮተ ቃል ሲተነተን የመካከለኛው ምሥራቅ የመተንፈሻ አካል በሽታ የሚል በመሆኑ ነው። ድርጅቱ እንዳለው ለአንዳንድ የበሽታ አይነቶች የሚሰጠው ስያሜ በተወሰኑ የኃይማኖትና የጎሳ አባላት ላይ ተገቢ ያልሆነ የጉዞና የንግድ ግንኙነት እቀባንና ሌሎችንም ጉዳቶችን ሊያስከትል ይችላል። በዚህም ምክንያት ለኮሮናቫይረስ ትክክለኛ ስያሜ ሲወጣ በስሙ ውስጥ መካተት የለባቸውም ያላቸውን ነገሮች በመመሪያ መልክ ድርጅቱ እንደሚከተለው አስቀምጧል። በተጨማሪም ስያሜው ሲሰጥ ስሙ አጭርና ገላጭ መሆን እንዳለበትም አመልክቷል። አስራ አንድ ሰዎች ያሉበትና ለአዲሱ ወረርሽኝ ቀላልና ገላጭ ስያሜ ለማግኘት የተሰባሰበው ኮሚቴ ሁለት ሳምንታትን የፈጀበት ሲሆን አንድ ስያሜ ላይ ለመስማማትም ሁለት ቀናት አስፈልጎት እንደነበር የቡድኑ አባል የሆኑት ፕሮፌሰር ቤንጃሚን ኑማን ተናግረዋል። ኮሚቴው ለአዲሱ ወረርሽኝ ያገኘው ስያሜ አሁን በሳይንሳዊ ጆርናል ላይ እንዲታተም ያቀረበ ሲሆን በቀናት ውስጥም ይፋ እንደሚሆን ይጠበቃል። ኮሚቴው ስራውን ማጠናቀቁ ሕዝቡ ቫይረሱን እንዲረዳው ከማገዙ በተጨማሪ ግራመጋባትን በማስወገድ ጊዜን የሚቆጥብ ሲሆን ተመራማሪዎችም በሽታውን በመዋጋት ላይ እንዲያተኩሩ ያግዛል ተብሏል።
42550307
https://www.bbc.com/amharic/42550307
እስራኤል አፍሪካዊያን ስደተኞች እንዲወጡ አዘዘች
የእስራኤል መንግሥት በአስር ሺህዎች ለሚቆጠሩ አፍሪካዊያን ስደተኞች ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ካልሆንም እስር እንደሚጠብቃቸው ማስጠንቀቂያ አውጥቷል።
ስደተኞቹ እሰራኤልን በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ውስጥ ለቀው ለመውጣት ከተስማሙ 3500 ዶላር ይሰጣቸዋል ተብሏል። በአማራጭነትም ወደሃገራቸው ካልሆነም ወደሌላ ሦስተኛ ሃገር የመሄድ ምርጫም ቀርቦርላቸዋል። ነገር ግን ከቀነገደቡ በኋላ እስራኤል ውስጥ ለመቆየት ከወሰኑ ከሚያዚያ ወር ጀምሮ ስደተኞቹን ማሰር እንደሚጀምሩ ባለስልጣናቱ አስጠንቅቀዋል። የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት ይህ አወዛጋቢ ዕቅድ ዓለም አቀፍና የእስራኤል ህግን የሚቃረን ነው ብሏል። የእስራኤል መንግሥት ግን ስደተኞቹ እንዲመለሱ የሚደረገው 'በፈቃደኝነትና' ሰብአዊ ክብራቸውን በጠበቀ መንገድ ነው ይላል። ይህ ማስጠንቀቂያ ሕፃናትን፣ አረጋዊያንን፣ በባርነት ተይዘው የነበሩትንና የሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባ የሆኑትን ስደተኞች አይመለከትም። የእስራኤል የፍልሰትና ሥነ-ሕዝብ ባለስልጣን ቃል አቀባይ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ በአሁኑ ጊዜ 38 ሺህ ''ሰርጎገቦች'' ብለው የጠሯቸው ስደተኞች በእስራኤል ውስጥ እንዳሉና ከእነዚህ መካከልም 1420ዎቹ በእስር ቤቶች ውስጥ እንደሚገኙ ገልፀዋል። የእስራኤል መንግሥት ''ሰርጎገቦች'' የሚለውን ቃል ከሕጋዊዎቹ የድንበር መግቢያዎች ውጪ ወደ ሃገሪቱ የገቡ ሰዎችን ለማመልከት ይጠቀምበታል። አብዛኞቹ ስደተኞች ኤርትራዊያንና ሱዳናዊያን ሲሆኑ ወደእስራኤል የመጡት ከሚደርስባቸው ማሳደድና ከጦርነት ለማምለጥ እንደሆነ ቢናገሩም ባለስልጣናት ግን የተሻለ ኑሮ ፈልገው የመጡ እንደሆኑ ያምናሉ።
news-46212415
https://www.bbc.com/amharic/news-46212415
የ7 ዓመቷ ህጻን ግድያ፡ ''ከልክ ያለፈ ቅጣት የልጄን ህይወት አሳጣኝ'' የእምነት ክህደት ቃል
በደሴ ከተማ የሰባት ዓመት ልጅ ሬሳ በማዳበሪያ ተጠቅልሎ የተገኘው ጥቅምት 27፣ 2010 ዓ. ም ነበር። የልጅቷ አሟሟት ያስቆጣቸው የአካባቢው ነዋሪዎችም ንዴታቸውን ለመግለጽ አደባባይ ወጥተዋል።
በወቅቱ ልጅቷን ገድሏል በሚል የተጠረጠረው የልጅቷ የእንጀራ አባት በቁጥጥር ስር ውሏል። ሕዝቡ "ተጠርጣሪውን አሳልፋችሁ ስጡን" በማለት ቁጣውን አሰምቶ ነበር። የደሴ ከተማ አስተዳደር የፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ኮማንደር ደረጄ አሰፋ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ተጠርጣሪ ተብሎ የታሰረው የእንጀራ አባቷ ቢሆንም፤ የፖሊስ ምርመራን ተከትሎ የልጅቷ ገዳይ እናቷ ልትሆን እንደምትችል ተጠርጥሮ እናትየዋ በቁጥጥር ስር ውላለች። • ደሴ፡ የሰባት ዓመት ህፃን ገድሏል በተባለው የእንጀራ አባት ምክንያት ቁጣ ተቀሰቀሰ የልጅቷ እናት ትላንት ፍርድ ቤት የቀበረች ሲሆን፤ የእምነት ክህደት ቃሏን ሰጥታ የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ተወስኗል። ለእንጀራ አባቷ ደግሞ ሰባት ቀን ጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቷል። ኮማንደሩ እንደተናገሩት፤ የልጅቷ መጥፋት ለፖሊስ ሪፖርት የደረሰው ጥቅምት 24፣ 2011 ዓ. ም ነበር። የልጅቷ እናት አበባ ሙህዬ ዳውድ፤ በጸሎት ብርሀኑ የምትባል ልጇ ሰፈር ውስጥ ትጫወት ከነበረበት እንደተሰወረች ለፖሊስ ተናግራለች። ጥቅምት 27፣ 2011 ዓ. ም ከኡራኤል ቤተክርስቲያን ከፍ ብሎ የልጅቷ ሬሳ በአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝቶ ወደ ደሴ ሆስፒታል ተወሰደ። እናትየዋ፤ አቡበከር ሙሀመድ አህመድ ከተባለ አጋሯ የወለደቻትን ልጅ ለማሳደግ አቅም ስለሌላት የ40 ቀን ጨቅላ ሳለች ለጓደኛዋ ቤተሰቦች መስጠቷን ለፖሊስ ተናግራለች። • ኤርትራ ላይ የተጣለው ማዕቀብ ዛሬ ይነሳል • የህግ የበላይነት ሳይሸራረፍ እንዲተገበር የሚጠይቀው የትግራይ ክልል መግለጫ በሁኔታው የፍቅር ጓደኛዋ ተበሳጭቶ "ልጄን እንደጣልሻት ያንቺንም ልጅ ወስጄ እጥላለሁ" ብሎ እንደዛተባት ለፖሊስ ተናግራም ነበር። የልጅቷ አስክሬን ወደ አዲስ አበባ ለምርመራ ከተላከ በኋላ በምርመራው ወቅት "የልጅቷ እጅና እግሯ መታሰር፣ በወባ ትንኝ መከላከያ አጎበር ሬሳዋ መጠቅለሉ ምርመራውን ወደ እናትየዋ እንዲያመራ አደረገው" ይላሉ ኮማንደር ደረጄ። እናትየዋ በወቅቱ ሀዘን ተቀምጣ ነበር። ፖሊሶች ስለወንጀሉ ሲጠይቋት የእምነት ክህደት ቃሏን መስጠቷንም ኮምንደሩ ተናግረዋል። እናትየዋ ለፖሊስ እንዳሳወቀችው ከሟች ልጇ ጋር በመሆነ አራዳ ተብሎ በሚጠራው ገበያ ስትገበያይ ነበረ። ልጇም ጫማ እንዲገዛላት ጠየቀቻት። እናት 'አቅም የለኝም' በማለት መልስ ብትሰጣትም፤ ልጅቷ ግን መጠየቋን አላቆመችም። ቤት ከደረሱም በኋላም የልጅቷ ጥያቄ ሲቀጥል በንዴት በዘነዘና እንደመታቻት ለፖሊስ ተናግራለች። በእናትየው ለፖሊስ በሰጠችው ቃል መሰረት የልጅቷ ህይወት ያለፈው ወዲያው ነበር። እናትየዋ ለፖሊስ "ልጄ ጠፋች" ብላ ባመለከተችበት ተመሳሳይ ቀን የልጇን አስክሬን መጣሏን እንዳመነች ኮማንደሩ ገልጸዋል። ''ከልክ ያለፈ ቅጣት የልጄን ህይወት አሳጣኝ'' እንዳለችም ኮማንደሩ አክለዋል። እንትየዋ ከአጋሯ ጋር ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ አብራ ትኖር የነበረ ቢሆንም፣ በመካከላቸው አለመግባበት በመፈጠሩ እንደተለያዩ ኮማንደሩ ተናግረዋል። የልጅቷ ሬሳ ሲገኝ "ተደፍራለች፤ ሰውነቷ ተቆራርጧል" የሚል ያልተገጋገጠ ወሬ መሰራጨቱን ኮማንደሩ አስታውሰው፤ የአስክሬን ምርመራ ውጤቱ ገና በእጃቸው ባይገባም፤ ሬሳዋ ሲገኝ ሰውነቷ ላይ ችግር እንዳልደረሰ ገልጸዋል። ሆኖም የተሳሳተ መረጃ መሰራጨቱ በሕዝቡ ዘንድ ቁጣ ቀስቅሷል። በተሳሳተ መረጃ ፖሊሶች ላይ ጠቃት ተሰንዝሮ እንደነበረ የገለጹት ኮማንደሩ፤ በፖሊስ አባላት ላይ በተወረወረው ድንጋይ ስምንት አባላት ከባድና ቀላል ጉዳት እንደደረሰባቸው ኮማንደሩ ተናግረዋል።
news-47824786
https://www.bbc.com/amharic/news-47824786
አወዛጋቢው ግጭት በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር
በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ደዌ ሃረዋ ወረዳ በታጠቁ ኃይሎችና በአካባቢው ነዋሪ መካከል ግጭት ተቀስቅሶ ቢያንስ የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአማራ ክልል የሠላምና የህዝብ ደህንነት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ገደቤ ኃይሉ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ የአካባቢው ነዋሪ ግጭቱ የተፈጠረው በህዝቡ መካከል እንዳልሆነ ይናገራል። በአካባቢው ቀደም ብሎም ውጥረት እንደነበር የሚናገረው ይህ ነዋሪ ይህንን ለማስቆም በተለይ የገጠሩን ክፍል ለማረጋጋት ሲል የክልሉ መንግሥት ልዩ ኃይሎችን አስገብቶ ነበር ይላል። • በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር በተፈጠረ ግጭት ሰዎች ሞቱ እነዚህ ልዩ ኃይሎች የተሰማሩባቸው የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ወረዳዎች ነዋሪዎች ልዩ ኃይል መግባቱን በመቃወም፤ ተኩስም እንደነበር አክሏል። "በተለይ በፌስቡክ ሁኔታዎች እንዲባባሱ የሚያደረጉ ነገሮች ነበሩ" የሚለው ነዋሪው ከአራት ቀናት በፊት ውጥረት መኖሩን የሰማ ቢሆንም ረቡዕ ዕለት ማታ ከገጠሩ ክፍል ብዙ የተኩስ ድምፅ ይሰማ እንደነበር ገልጾልናል። በግጭቱም የሰዎች ሕይወት ማለፉን ቢሰማም በበኩሉ አንድ የልዩ ኃይል ሹፌር መሞቱን ከቅርብ ሰው ማረጋገጡን ነግሮናል፤ በአንፃሩ ዛሬ መረጋጋት እንዳለም ለቢቢሲ ተናግሯል። የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሠላምና የህዝብ ደህንነት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ገደቤ ኃይሉ በበኩላቸው ሰሞኑን በከሚሴ አካባቢ ደዌ ሃርዋ ቦራ ከተማ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አባላት እንደነበሩ ያረጋግጣሉ። "አካባቢው አልፎ አልፎ ግጭት የሚስተዋልበት በመሆኑና ይህንን ግጭትና በከተማው ከሚንቀሳቀሱ አንዳንድ ፀረ ሠላም ኃይሎች የህዝቡን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል የተንቀሳቀሰ ኃይል ነበር" ይላሉ ስለፀጥታ ኃይሉ ሲያስረዱ። • የብሔር ግጭት የሚንጣት ሀገር በዚያ አካባቢ አልፎ አልፎ መንደሮችም የሚቃጠሉበት ህዝቡም የሚሰናከልበት ሁኔታ እንዳለ ያስታወሱት ኃላፊው "ይህንን ለመቆጣጠር በተንቀሳቀሰው ኃይል ላይ ያልታወቀ ቡድንና በተለይ ደግሞ ራሱን በስውር እያደራጀ የሚንቀሳቀስ ፀረ ሠላም ኃይል አለ" ሲሉ ይገልፃሉ። ይህ ቡድንም የጸጥታ ኃይሉ ላይ ጥቃት ያደርስ የነበረ ቢሆንም ወደ ተረጋጋ ሁኔታ ተመልሶ ነበር ይላሉ። ይሁን እንጂ በዋናነት በአፋር እና በድንበር አቅራቢያ ባለው አካባቢ አልፎ አልፎ በተደራጀም ይሁን በተናጠል የሚደረጉ ጸጥታን የሚያውኩ እንቅስቃሴዎች መኖራቸውን ይናገራሉ። "የክልሉ ልዩ ኃይል ስምሪትም የተደረገው እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ነው" የሚሉት አቶ ገደቤ ይህንን ተከትሎ የተባሉት ኃይሎች ተኩስ ከፍተው የተኩስ ልውውጥ ተካሂዷል፤ ጉዳቶችም ደርሰዋል። በግጭቱም ሁለት የፀጥታ ኃይሎች ሕይወታቸው ሲያልፍ ሌሎች ሁለት የመቁሰል ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል። የጥፋት ኃይሎቹ እነማን እንደሆኑ የተጠየቁት ኃላፊው "እያጠራን ነው፤ በህቡዕ መንቀሳቀስ፣ በተደራጀ መንገድ የመንቀሳቀስ በተለይ በእኛ በኩል የኦነግ አባላት ያሉ ነው የሚመስለው። የተደራጀ መሣሪያ የያዘ አለ፣ የቡድን መሣሪያ የሚባሉትን የያዘ አለ፣ በዚያ አካባቢ ተኩሶ የመሄድ እና ጥፋት አድርሶ መሄድ ሁኔታም የቆየ ነው፤ አዲስ አይደለም" ሲሉ ይገልጻሉ። • የአማራ ክልል፣ መንግሥት የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጠየቀ እንዲህ ዓይነት ክስተቶች በዚህ አስተዳዳር ብቻ ሳይሆን በሰሜን ሸዋም አካባቢ አልፎ አልፎ የሚታዩ ችግሮች መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ነገር ግን "ችግሩ እየተፈታ ነው፤ ወደ ሠላምም እየተመጣ ነው ተብሎ የሚወሰድ አይደለም፤ ሥራ የሚጠይቅ ነገር አለው" ብለዋል። አቶ ገደቤ አክለውም "አካባቢውን ለማተራመስ አጀንዳ ያለው በዋናነት ከኦነግ አባላት ጋር ትስስር ያለው እንደሆነ ነው እያየን ያለነው፤ ወደፊት ይሄ ሊጠራና ሊገመገም ይችላል" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ይሁን እንጂ ከትናንት ጀምሮ የጸጥታ ችግር በአካባቢው አለመኖሩን የሚገልፁት ኃላፊው አሁንም ግን ህብረተሰቡ ላይ የሚታዩ ስጋቶች መኖራቸውን ያነሳሉ። "በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ስውር ሰዎች እስካሉ ድረስ አልፎ አልፎ የሚታይ ችግር አለ፤ ሰላም ለማምጣትም ስምሪታችንን እንደገና የማየት የመፈተሽና የማስተካከል ሥራ ይሠራል" ሲሉ ይገልፃሉ። ከህዝቡ ጋርም የአካባቢውን ሠላም በተደራጀ መልክ እንዲጠብቅና የሥራው ባለቤት እንዲሆን ከአካባቢው ማህበረሰብ እና ከአካባቢው የጸጥታ ኃይል ጋር በመቀናጀት እየተሠራ እንዳለም ለቢቢሲ አስታውቀዋል። • የአማራ ክልል፣ መንግሥት የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጠየቀ ይህንን ተከትሎም የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) "የራስን ጥፋት ለመደበቅ የኦነግን ስም ማጠልሸት ከተጠያቂነት አያስመልጥም፤ አሁንም ቢሆን ሰላማዊ ትግል ላይ ነው ያለነው፤ የአማራ ልዩ ኃይሉ ተግባር የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደርን በማፍረስ ወደ ሌላ ዞን ለመቀላቀል የሚደረግ የድንበር ማስፋፋት ነው ብለን እናምናለን" ሲል በፌስቡክ ገጹ ላይ መግለጫ አውጥቷል። ለተፈጠረው ችግር መጠየቅ ያለበትም ቡድኑን የሚቆጣጠረው የክልሉ መንግሥት እንጂ ኦነግ አለመሆኑንም በመግለጫው ጠቅሷል። የአማራ ክልል መንግሥት ኦነግን ከመክሰስና የህዝቡን ሰላም ከማናጋት እንዲቆጠብ ግንባሩ አሳስቧል። የአማራ ክልል የተፈጠረውን ችግር በሰላም እንዲቋጭ በመጠየቅ የፌደራሉ መንግሥትም ችግሩ ወደ ሌላ አቅጠጫ እንዳይሄድ እንዲቆጣጠረው በመግለጫው ጠይቋል። የአማራና የኦሮሞ ክልል የፀጥታ አካላት በሁለቱ ክልሎች የሚፈጠሩ የፀጥታ ችግሮችን ለመፍታት አብረው ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ባህር ዳር ላይ ባለፈው ሳምንት በሰጡት መግለጫ ማስታወቃቸው ይታወሳል።
news-50272650
https://www.bbc.com/amharic/news-50272650
ኩዌት በድረገጽ ሰዎችን ሲሸጡ የነበሩ ግለሰቦች ላይ እርምጃ መውሰድ ጀመረች
የኩዌት ባለስልጣናት የተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም ሰዎችን እንደ 'ባሪያ' ሲሸጡ የነበር ያሏቸው ግለሰቦች ላይ እርምጃ እየወሰዱ እንደሆነ ገለጹ።
የቢቢሲ አረብኛ ክፍል የምርመራ ቡድን በዚህ ሳምንት ባስተላላፈው ዘገባ፤ እንደ ጉግል እና አፕልን የመሳሰሉ የበይነ መረብ መድረኮችን በመጠቀም ኩዌታውያን ከተለያዩ አገራት የመጡ ስደተኞችን እንደሚሸጡ ያሳያል። በፌስቡክ ስር በሚተዳረው በኢንስታግራም ጭምርም ሰዎች እንደሚሸጡ ዘገባው ያትታል። • የስፔኑ ፍርድ ቤት ኃይል አልተጠቀሙም ያላቸውን 5 አስገድዶ ደፋሪዎች ነፃ አለ • የሠርጋቸው ቀን ምሽት ለትዳራቸው መፍረስ ምክንያት የሆነባቸው ሴቶች ለሽያጭ የሚቀርቡት አብዛኛዎቹ ሴቶች ሲሆኑ፤ ለቤት ሠራተኝነት ነው የሚፈለጉት። ሻጮቹም እንደ #maids for transfer እና #maids for sale የመሳሰሉ ሀሽታጎችን በመጠቀም ሴቶቹን ለሽያጭ ያቀርቧቸዋል። ይህንን መሰል ማስታወቂያዎችን በመጠቀም የቤት ሠራተኞችን ሲሸጡ የነበሩ ግለሰቦች ማስታወቂያቸውን እንዲያወርዱ መታዘዛቸውንም ባለስልጣናቱ ገልጸዋል። በተጨማሪም በዚህ ተግባር ተሰማርተው የሚገኙ ሰዎች በድጋሚ እንደማይፈጽሙት የሚገልጽ ሕጋዊ ወረቀት እንዲፈርሙና መጸጸታቸውን እንዲገልጹ ተደርገዋል በማለት ስለተወሰደው እርምጃ ገልጸዋል። ኢንስታግራም በበኩሉ ቢቢሲ ጉዳዩን ካሳወቀው በኋላ እርምጃ እንደወሰደ አስታውቋል። አክሎም ኢንስታግራምና ፌስቡክን በመጠቀም ሰዎችን ለሽያጭ ለማቅረብ የተከፈቱ ገጾችን እንደሚከታተልና እንደሚያግድ ገልጿል። ቢቢሲ የምርመራ ዘገባውን ሲሠራ በብዛት ጥቅም ላይ ሲውሉ የነበሩት ገጾች በሙሉ በአሁኑ ሰአት እንቅስቃሴያቸው ቆሟል። • "ሰውነቴ ወሲብ እንድፈጽም አይፈቅድልኝም'' የብዙ ሴቶች የጤና እክል በኩዌት የሰው አቅርቦት ባለስልጣን የሆኑት ዶክተር ሙባራክ አል አዚሚ ደግሞ በምርመራ ዘገባው ላይ የታየችውን የ16 ዓመት ጊኒያዊ ታዳጊ ጉዳይን በቅርበት እንደሚከታተሉትና ጥቅም ላይ የዋለው 'ፋቱ' የተባለው መተግበሪያ ምርመራ እንደሚደረግበት ገልጸዋል። በዘገባው የቀረበውና አንዲትን ሴት ለመሸጥ ሲስማማ የነበረው የፖሊስ አባልም ምርመራ እየተደረገበት ነው ተብሏል። ሌሎች ሰዎችም ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ሊውሉ እንደሚችሉ የተገለጸ ሲሆን ተጎጂዎችም ካሳ ይከፈላቸዋል ብለዋል ባለስልጣኑ።
51110717
https://www.bbc.com/amharic/51110717
የሌሶቶ ቀዳማዊት እመቤት በፖሊስ እየተፈለጉ ነው
የሌሶቶ ፖሊስ ከሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የቀድሞ ባለቤት ግድያ ጋር በተያያዘ የአሁኗን ቀዳማዊ እመቤት ለጥያቄ እንደሚፈልጋቸው ቢገልጽም ቀዳማዊ እመቤት ማይሲያህ ታባኔ ግን የገቡበት አልታወቀም ተብሏል።
በአውሮፓውያኑ 2017 የተገደሉት የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ጉዳይን ለማጣራትና የአሁኗ ቀዳማዊት እመቤት የት እንደሚገኙ ለማወቅ የሌሴቶ ፖሊስ የዓለማቀፍ ሕግ አስከባሪ ተቋማትን እርዳታም ጠይቋል። • ከፍየል ለምድ በሚሠራ ክር ሳቢያ የተቧቀሱት የሌሴቶ እንደራሴዎች • "ዕፀ ፋርስ በመሸጥ ልጆቼን አሳድጋለሁ" የሌሴቶዋ አምራች ፖሊስ እንዳለው ቀዳማዊት እመቤት ማይሲያህ ታባኔ ክስ ባይቀርብባቸውም ለጥያቄ ይፈለጋሉ። የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ሊፖሌሎ ታባኔ እንቆቅልሽ በሆነ መልኩ መሞት ከተሰማ በኋላ የሀገሬው ዜጎች ሆን ተብሎ የተሸፋፈነ ጉዳይ እንደሆነ ሲገልጹ ቆይተዋል። ሟች ቀዳማዊት እመቤት ከባለቤታቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ታባኔ ጋር በወቅቱ ተለያይተው የነበረ ቢሆንም ፍቺ ግን አልፈጸሙም። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ከአሁኗ ቀዳማዊት እመቤት በወቅቱ ግን እጮኛቸው ከነበሩት ማይሲያህ ታባኔ ጋር ግንኙነት መስርተው ነበር። ሁለቱም ሴቶች እኔ ነኝ ቀዳማዊት እመቤት በሚል ፍርድ ቤት እስከ መካሰስ የደረሱ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን ካጣራ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቀድሞ ባለቤታቸው ጋር ይፋዊ ፍቺ እስካልፈጸሙ ድረስ ሊፖሌሎ ታባኔ ቀዳማዊት እመቤት ሆነው እንዲቀጥሉ ብይን አስተላልፏል። በአውሮፓውያኑ 2017 ቀዳማዊት እመቤት ሊፖሌሎ ታባኔ ሞታቸው ከተሰማ ከሶስት ወራት በኋላም የአሁኗ ቀዳማዊት እመቤት ማይሲያህ ታባኔ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ትዳር መስርተዋል። • "ትውስታዎቼ መራር ናቸው"- ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩትና ገዢው ፓርቲ ' ኦል ቦሳቶ ኮንቬንሽን' በበኩሉ ፖሊስ ከጀመረው ምርመራ ጋር በተያያዘ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስልጣናቸው እንዲወርዱ ፍላጎት እንዳለው እየተዘገበ ነው። ፖሊስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀድሞ ባለቤታቸው በተገደለችበት አካባቢ ከነበረ ተንቀሳቃሽ ስልክ ጋር የተደዋወሉበት ማስረጃ እንዳለው የገለጸ ሲሆን እሳቸውንም ቢሆን ለጥያቄ እንደሚፈልጋቸው አስታውቋል። በጉዳዩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆነ ቀዳማዊት እመቤቷ ያሉት ነገር የለም።
news-54862294
https://www.bbc.com/amharic/news-54862294
ጃክ ማ 34 ቢሊዮን ዶላር ያጡበት ሳምንት
ያሳልፍነው ሳምንት ጃክ ማ በቻይና ታሪክ ሃብታሙ ሰው ሊያደርጋቸው ይችል ነበር። ነገር ግን ይህ አልሆነም።
ጃክ ማ የጃክ ማ ድርጅት የሆነው አንት ፋይናንሻል የአክሲዮን ገበያውን ይቀላቀላል ተብሎ ተጠብቆ ነበር። ይህ ድርጅት በሻንግሃይና በሆንግ ሆንግ የአክሲዮን ገበያዎች ላይ ውሎ 34 ቢሊዮን ዶላር በሚገመት ዋጋ ይሸጣል የሚል ዕቅድ ነበር። ነገር ግን አክሲዮኑ ገበያ ላይ ሊውል ደቂቃዎች ሲቀሩት የቻይና ፋይናንስ ቁጥጥር ሰዎች አግደውታል። ከዚህ አክሲዮን ገበያ የጃክ ማ ድርሻ 17 ቢሊዮን ዶላር ገደማ እንደሆነ ይነገራል። ይህ ደግሞ የሰውየውን ሃብት ወደ 80 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ያደርገው ነበር። ተንታኞች የቻይና መንግሥት ይህን ያደረገው የጃክ ማ ሃብት ካሰቡት በላይ ስለሆነና ይህም የሰውየውን ኃያልነት ከፍ ስለሚያደርገው ነው ይላሉ። ማ የቻይና መንግሥት ባለሥልጣናትን ነቅፎ ባለፈው ወር ሻንግሃይ ውስጥ በተካሄደ አንድ የቴክኖሎጂ ኮንፍረንስ ላይ አስተየት ሰጥተው ነበር። ሃንግዡ ውስጥ በድህነት ያደጉት የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ለመግባት ሁለት ጊዜ ተፈትነው ወድቀዋል። ብዙ ሥራ ለመቀጠር ሞክረው አልተሳካላቸውም። ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲን ለመቀላቀል 10 ጊዜ አመልክተዋል። አልፎም ኬአፍሲ ለተሰኘው የትኩስ ምግብ አቅራቢ ድርጅት ሠራተኛ ለመሆን አመልክተው ወድቀዋል። ሰውዬው ብዙ ጥረዋል። ወጥተዋል ወርደዋል። ማ፤ አሊባባ የተሰኘውን ድርጅት ያቋቋሙት በአውሮፓውያኑ 1999 ነው፤ ከጓደኞቻቸው ጋር ሆነ በተደበሩት 60 ሺህ ዶላር። አሁን ከዓለማችን ልጥጥ ሃብታሞች አንዱ የሆኑት ማ ከቻይና ባለሥልጣናት ጋር እሰጥ አገባ ሲገጥሙ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም። ነገር ግን የፋይናንስ ዘርፍ ተንታኞች፤ ማ የቻይና ባለሥልጣናትን ስለተናገሩ ብቻ አይደለም አንት ፋይናንሻል የተባለውን ድርጅት ይፋ ከማድረግ ያገዷቸው ይላሉ። የጃክ ማ አዲስ ድርጅት ተበዳሪዎችን ከባንኮች ጋር ማገናኘት ነው ሥራው። የቻይና ባለሥልጣናት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መሰል ድርጅቶች መበራከታቸው ስጋት ውስጥ ሳይከታቸው አይቀርም። ሮይተርስ የዜና ወኪል በርካታ ባንኮች ለችርቻሮ ነጋዴዎች በርካታ ገንዘብ እያበደሩ ነው ብሎ ዘግቧል። ይህ ደግሞ በጊዜ ብዛት የቻይና ምጣኔ ሃብት ላይ ተፅዕኖ እንዳያሳድር ተሰግቷል። የጃክ ማ ድርጅት አሁን ይከልከል እንጂ የቻይና ፋይናንስ ሕግን በማይጣረስ መልኩ በአዲስ ይዘት ሊመጣ ይችላል እየተባለ ነው። ጃክ ማ ድርጅታቸው እንዳይከፈት ሲታገድ በርካታ ቢሊዮን ዶላሮችን ቢያጡም እጁ ይሰጣሉ ተብሎ አይጠበቀም።
news-52986558
https://www.bbc.com/amharic/news-52986558
በቺካጎ ከተቃውሞ ጋር በተያያዘ ከዚህ በፊት ባልታየ ሁኔታ በርካታ ሰዎች ሞቱ
የቺካጎ ከተማ በስድሳ ዓመት ውስጥ በአንድ ቀን በርካታ ሰዎች የሞቱበትን ቀን አስተናግዳለች።
በዕለተ እሁድ ግንቦት 23 ከጆርጅ ፍሎይድ ሞት ጋር በተያያዘ በተደረገ የተቃውሞ ሰልፍ 18 ሰዎች ተገድለዋል። ግንቦት 22 እና 23 በተደረጉ ሰልፎች 85 ሰዎች በጥይት የተመቱ ሲሆን 24 ሰዎች ደግሞ መገደላቸውን ከዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቺካጎ የወንጀል ምርመራ ክፍል የተገኘው መረጃ ጠቁሟል። መረጃው እንደሚያሳያው አብዛኛዎቹ ተጎጂዎች ጥቁር አሜሪካውያን ናቸው። ቺካጎ ሰን-ታይም ጋዜጣ ይዞት የወጣው ዘገባ እንደጠቆመው ከተገደሉት እና ጉዳት ከደረሰባቸው 24 ሰዎች መካከል ተማሪዎች፣ ወላጆች እና ሠራተኞች ይገኙበታል። ከቺካጎ ዩኒቨርሲቲ የወንጀል ምርመራ ክፍል የተገኘው መረጃ ከ1961 (እአአ) ጀምሮ ያለውን ታሪክ የያዘ እንደሆነ በማስታወስ "እንዲህ አይነት ነገር በፍጹም ተመልክተን አናውቅም" ሲሉ ተመራማሪው ማክስ ካፑስቲን ለቺካኮ ሰን-ታይመስ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም በቺካጎ ከተማ ታሪክ በአንድ ቀን ውስጥ በርካታ ሰዎች የሞቱት 13 ሰዎች ሲሆኑ ዕለቱም ሐምሰሌ 23/1983 ዓ.ም. ነበር። የቺካጎ ከንቲባ ሎሪ ላይትፉት እንዳሉት 18 ሰዎች ተገድለዋል በተባለበት ቀን ለፖሊስ የተደረገው የድረሱልኝ ጥሪ ከ65 ሺህ በላይ ነበር። ይህም በአማካይ ለከተማው ፖሊስ ከሚደርሰው ጥሪ በ50 ሺህ የሚበልጥ ነው። የቺካጎ ከተማ ፖሊስ ለሰን-ታይምስ እንደተናገረው፤ ግንቦት 22 እና 23 ለፖሊስ በርካታ ጥሪዎች መደረጋቸውን በማስታወስ፤ በዜጎች ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶችን እና መነሻዎችን እየመረመረ መሆኑን አስታውቋል። "በአመጹ ህይወታቸውን ላጡ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ፍትህ ለመስጠት እንሰራለን" ብሏል የከተማዋ ፖሊስ። ቺካጎ ከዚህ ቀደምም ቢሆን ይመዘግብባት የነበረው የግድያ ወንጀል ከፍ ያለ ነው። ቺካጎ ከሁለቱ የአሜሪካ ግዙፍ ከተሞች በላይ ብዙ የግድያ ወንጀሎች ተመዝግበውባታል። እአአ 2018 በቺካጎ 561 ሰዎች በሌላ ሰው የተገደሉ ሲሆን ይህም በተመሳሳይ ዓመት በኒው ዮርክ እና ሎስ አንጀለስ ከተሞች ከተመዘገበው የግድያ ወንጀል ድምር በላይ ነው።
news-55232898
https://www.bbc.com/amharic/news-55232898
የአርጀንቲናዋ ሴናተር የማራዶና ምስል በገንዘብ ኖት ላይ እንዲታተም ጠየቁ
አንዲት አርጀንቲናዊ ሴናተር የእግር ኳስ ኮከቡ ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ምስል በአዲስ የገንዘብ ኖቶች ላይ እንዲታተም ሀሳብ ማቅረባቸው ተሰምቷል።
የቀድሞው የአርጀንቲና ኮከብ ተጫዋች እና በኋላም የአገሩ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበረው ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ያረፈው ቤቱ ውስጥ ሳለ በልብ ችግር እንደሆነ ተገልጿል። ማራዶና በዚህ ወር መጀመሪያ አካባቢ በአንጎሉ ውስጥ ላጋጠመው የደም መርጋት የተሳካ ቀዶ ሕክምና ተደርጎለት የነበረ ሲሆን በተከታይነትም ከአልኮል ሱስ ለመላቀቅ ሕክምና ይደረግለታል ተብሎ ነበር። ሴናተር ኖርማ ዱራናጎ ሰኞ ዕለት ለአገሪቱ ኮንግረስ ሃሳቡን ያቀረቡ ሲሆን በአገሪቱ ትልቁ የሆነው የ1 ሺ ፔሶ (የአርጀንቲና መገበያያ ገንዘብ) ላይ ምስሉ ቢቀረጽ ምን ይመስላችኋል ሲሉ ጠይቀዋል። ሴናተሯ እንደሚሉት የማራዶና የፊት ምስል በአንድ በኩል በለጀርባው በኩል ደግሞ እግር ኳሰኛው የሚታወቅባቸው ድንቅ ድንቅ ግቦች በምስል እንዲታተሙ ፍላጎት አላቸው። በዚህም መሰረት በ1 ሺ ፔሶ ላይ የዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ፊት እና በጀርባው ደግሞ በአውሮፓውያኑ 1986 በሜክሲኮው የዓለም ዋንጫ እንግሊዝ ላይ ያስቆጠራት ሁለተኛ ጎል ሊታተም እንደሚችል 'ላ ናሲዮን' የተባለው ጋዜጣ ዘግቧል። በተጨማሪም ሴናተሯ የማራዶና ምስል በቴምብሮች ላይም እንዲቀር ሀሳብ አቅርበዋል። '' ይሄ ሃሳብ እውቁን እግር ኳሰኛ ለማሰብ ብቻ ሳይሆን ኢኮኖሚያዊ ጥቅምም እንደሚኖረው ይገመታል። ጎብኘዒዎች ወደ አርጀንቲና ሲመጡ የማራዶና ምስል ባለበት ኖት መገበያያትና ለማስታወሻ ኖቱን ይዘው መሄድ እንዲመርጡ ያደርጋቸዋል'' ሲሉ አስረድተዋል ሴናተሯ። የዓለማችን የምንጊዜም ታላላቅ ተጫዋቾች ከሚባሉት አንዱ የሆነው ማራዶና አርጀንቲና እአአ በ1986 የዓለም ዋንጫ ባለቤት ስትሆን የቡድኑ አምበል የነበረ ሲሆን ድንቅ ችሎታውንና የታወቀባቸውን የኳስ ጥበቡን በማሳየት ዓለምን አስደምሞ ነበር። በተለይ በወቅቱ አርጀንቲና ከእንግሊዝ ጋር ባደረገችው የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ላይ እሱ "የእግዜር እጅ" ያላትና ዳኞች ሳያዩ በእጁ ያስቆጠራት ግብ ዘወትር ትታወሳለች። በተጨማሪም ለስፔኑ ባርሴሎናና ለጣሊያኑ ናፖሊ ቡድኖች በአውሮፓ ውስጥ የተጫወተ ሲሆን፤ በጣሊያን ሴሪ አ ውስጥም ሁለት ጊዜ ዋንጫ ለማንሳት በቅቶ ነበር። የአርጀንቲና እግር ኳስ ማኅበር የማራዶና ሞት በተሰማ ጊዜ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ባወጣው መግለጫ "በጀግናችን ሞት በጣሙን አዝነናል" በማለት "ሁልጊዜም በልባችን ውስጥ ትኖራለህ" ብሏል። ማራዶና ለአገሩ አርጀንቲና በአራት የዓለም ዋንጫ ውድድሮች ላይ በተደረጉ 91 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 34 ግቦችን አስቆጥሯል።
news-56099579
https://www.bbc.com/amharic/news-56099579
ኮሮናቫይረስ፡ በሰዎች ላይ የሚደረግ የክትባት ሙከራ ለመጀመሪያ ጊዜ ፈቃድ አገኘ
ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ጤናማ ወጣት በጎ ፈቃደኞች በዓለማችን የመጀመሪያ ነው በተባለ ሙከራ ላይ እየተሳተፉ ነው።
በጎ ፈቃደኞቹ ኮቪድ-19 በሰዎች ላይ ምን አይነት ጉዳት እንደሚያስከትልና ክትባቱ ምን እንደሚሰራ በትክከል ለማወቅ ሆን ተብሎ በቫይረሱ እንዲያዙ ይደረጋል። ጥናቱን ለማካሄድ የሚያስፈልገው ፈቃድ የተገኘ ሲሆን በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ደግሞ እድሜያቸው ከ18 እስከ 30 የሆኑ 90 ጤናማ በጎ ፈቃደኞች ይመረጣሉ። በጎ ፈቃደኞቹ ተመራማሪዎች ሁሉንም ነገር መቆጣጠር በሚችሉበት ሁኔታ ውስጥ ለቫይረሱ እንዲጋለጡ የሚደረግ ሲሆን ጤናቸው ላይ ምንም አይነት እክል እንዳይደርስ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረጋል ተብሏል። ዩናይትድ ኪንግደም እስካሁን ድረስ ከ15 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የኮሮናቫይረስ ክትባትን ሰጥታለች። በሰዎች ላይ የሚደርሱ ተጽኖዎችን የሚመረምሩ ጥናቶች እንደ ወባ፣ ታይፎይድ እና ኮሌራ ላሉ በሽታዎች መድሀኒቶችን በማግኘት ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። የሚደረጉት ሙከራዎች ተመራማሪዎች ምን ያክል ቅንጣት ኮሮረናቫይረስ ሰዎችን እንደሚያጋልጥ እንዲሁም የሰውነታችን በሽታ የመከላከል ስርአት እንዴት ምላሽ ይሰጣል የሚሉትን ነገሮች በአግባቡ ለመመርመር ይረዳሉ። በዚህም መሰረት ዶክተሮች በቫይረስ አማካይነት የሚመጣውን የኮቪድ-19 በሽታ በአግባቡ እንዲረዱትና ህክምናዎች እንዴት መሰጠት አለባቸው የሚለውን እንዲወስኑ ያግዛቸዋል። ይህ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው የሚካሄደው የተባለለት ጥናት በዩናይትድ ኪንግደም መንግስት፣ ኢምፔሪያል ኮሌጅ ለንደን አንዲሁም ሌሎች ተቋማት በሕብረት ነው የሚያካሂዱት ነው። መጀመሪያ ላይ ሙከራው ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ባለፈው ዓመት መጋቢት አካባቢ ሲዘዋወር የነበረ የኮሮናቫይረስ አይነት ጥቅም ላይ የሚያውል ሲሆን፤ ይህ የቫይረስ አይነት ጤናማ የሆኑ አዋቂዎች ላይ የሚያሳድረው የጤና እክል እምብዛም ነው ተብሏል። በዚህ ምክንያት ሆነ ተብሎ በቫይረሱ እንዲያዙ የሚደረጉት በጎ ፈቃደኞች ምንም ስጋት አይገባቸውም ብሏል ጥናቱን የሚያካሂደው የተመራማሪዎች ቡድን። መንግስት በአሁኑ ሰአት በጎ ፈቃደⶉች መጥተው እንዲመዘገቡና የጥናቱ አካል እንዲሆኑ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ለጊዜያቸውና ላበረከቱት አስተዋጽኦ ክፍያ እንደሚኖውም አስታውቋል።
55079317
https://www.bbc.com/amharic/55079317
ትግራይ፡ በትግራይ ክልል ለሰብዓዊ እርዳታ መተላለፊያ ሊመቻች መሆኑ ተገለፀ
የኢትዮጵያ መንግሥት የሠላም ሚኒስቴር የሚከታተለው የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መተላለፊያ ሊያመቻች መሆኑ ተገለጸ።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው በትግራይ ክልል የሰብአዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸውን ዜጎች እገዛ እያደረገም መሆኑን አስታውቋል። ምግብ፣ መድኃኒት፣ ውሃና አስፈላጊ የሚባሉ መሰረታዊ የእርዳታ አቅርቦቶችንም የፌደራል መንግሥት በተቆጣጠራቸው የትግራይ ክልል አካባቢዎች እየቀረበ መሆኑንም ጠቅሷል። ከዚህም በተጨማሪ ሦስት ሳምንታትን ያስቆተረውን ግጭት ፈርተው ወደ ሱዳን ለሸሹት ሰዎች መጠለያ ካምፖች እንደሚያቋቁም መግለጫው አስፍሯል። መንግሥት ጨምሮም በግጭቱ ሳቢያ ተፈናቅለው ወደ ቀያቸው ለመመለስ የሚፈልጉትን ዜጎች ለመርዳት ዝግጁ መሆኑን ገልጾ፤ በዚህ ሂደት ውስጥም የሰላማዊ ዜጎችን ደኅንነት ለመጠበቅና ለመደገፍ ከእርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ጋር ተባብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን በመግለጫው አመልክቷል። በኢትዮጵያ፣ ትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለውን ግጭት ሸሽተው የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ ማሻቀቡን ተከትሎ የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች በፌደራል መንግሥት የእርዳታ መስመር እንዲመቻች በተደጋጋሚ ሲጠይቁ ቆይተዋል። በግጭቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከ40 ሺህ በላይ መድረሱን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን፤ ዩኤንኤችሲአር ከቀናት በፊት አስታውቋል። የሰብዓዊ መብት እና እርዳታ ድርጅቶች ግጭቱ በቶሎ የማይቋጭ ከሆነ ከዚህ በበለጠ የሰብዓዊ ቀውስ ሊፈጠር ይችላል በማለት ስጋታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ። ከዚህም በተጨማሪ መንግሥት የሰብዓዊ እርዳታ እንዲቀርብም ያስችል ዘንድ መተላለፊያ እንደሚያመቻችም ተጠቅሷል። ባለስልጣናቱ ከተለያዩ የተባበሩት መንግሥታት ኤጀንሲዎችም ሆነ ድርጅቶች ጋር ለመስራትም ቁርጠኝነት እንዳለው መግለጫው አስፍሯል። በኢትዮጵያ ውስጥ የሰላማዊ ዜጎች ደኅንነት እንዲሁም በግጭቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችና የእርዳታ ድርጅት ሠራተኞች እንዳሳሰበውም ዩኤንኤችሲአር ማስታወቁ የሚታወስ ነው። ዩኤንኤችሲአርም ሆነ የተባበሩት መንግሥታት አጋሮች ሁለቱም ወገኖች የዓለም አቀፍ ሕግን አክብረው ንፁሃን ዜጎችን የመጠበቅ ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። ነፃ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀና እክል በሌለበት ሁኔታ የሰብዓዊ እርዳታ የሚደርስበት ሁኔታ እንዲመቻችም ጠይቋል። በኢትዮጵያ፣ በትግራይ ክልል ያሉ 100 ሺህ ኤርትራውያን ተፈናቃዮችም በግጭቱ ምክንያት አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ መግባታቸውንም ድርጅቱ ገልጿል። ምግብ፣ ውሃ፣ መድኃኒትን የመሳሰሉ መሰረታዊ የሚባሉ አቅርቦቶችን ማድረስ አስቸጋሪ በመሆኑም ለስደተኞቹ ያለው ክምችትም በሳምንት ውስጥ ሊያልቅ መቻሉ ከፍተኛ ስጋት ሆኖብኛል ብሏል ድርጅቱ። ሁለቱም አካላት ነፃና ደኅንነቱ በተጠበቀ መልኩ ዜጎች እርዳታ ወደሚያገኙበት ቦታ የመንቀሳቀስ መብታቸውን እንዲያከብሩ ዩኤንኤችሲአር ጠይቋል። ድርጅቱ አክሎም ተፈናቃዮች በብሔር ልዩነት ሳይደረግባቸው ደኅንነት ወደሚሰማቸው ቦታ አንዲንቀሳቀሱ የአገር ውስጥም ሆነ የዓለም አቀፍ ድንበሮችን እንዲያቋርጡም ሁለቱም ወገኖች ማመቻቸት አለባቸው ብሏል።
news-52211338
https://www.bbc.com/amharic/news-52211338
ኮሮናቫይረስ፡ የአሜሪካዋ ግዛት ዊስኮንሰን አስገዳጁን ቤት የመቀመጥ ሕግ ተላልፋ ምርጫ አካሄደች
በኮሮናቫይረስ በርካታ ዜጎቿን እያጣች ባለችው አሜሪካ በበርካታ ግዛቶች ቤት የመቀመጥ አስገዳጅ ሕግ ቢወሰንም የዊስኮንሰን ግዛት ይህንን ተላልፋ በትናንትናው እለት ምርጫ አካሂዳለች።
ጥቂት ቁጥር ባላቸው የምርጫ ጣቢያዎችም በርካታ ሰዎች ተሰልፈው ታይተዋል። የምርጫ ጣቢያ ሰራተኞችም ኦክስጅን መተላለፊያ ያለው ከእግር እስከ ጭንቅላት የሚሸፍን አልባሳት ለብሰው ታይተዋል። የዊስኮንሰን አስተዳዳሪ ምርጫውን ወደ ሰኔ ለማስተላለፍ አቅደው የነበረ ቢሆንም ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይህንን ውሳኔ ሽሮ ምርጫው መካሄድ አለበት ብሏል። •በኮሮናቫይረስ ከተያዙት ኢትዮጵያዊያን ሦስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው •"ከቤት አትውጡ የሚሉን ልጆቼን ምን እንዳበላቸው ነው?" ቀጣዩ የዴሞክራቲክ ፓርቲን ወክለው ለመወዳዳር እየተፋለሙ ያሉት ጆ ባይደንና በርኒ ሳንደርስን አሸናፊ ለመለየት ከተደረጉ የመጀመሪያ ዙር ምርጫዎችም አንዱ ነው። የዚህ ምርጫ አሸናፊም በፈረንጆቹ ህዳር ለተያዘው ምርጫ ከሪፐብሊካኑ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር የሚወዳደር ይሆናል። የአካባቢው ምርጫ አስፈፃሚዎችም በምርጫው ወቅት እንዲሁም በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ላይ ተገኝተዋል። •በኮሮናቫይረስ የወረርሽኝ 'ዘመን' ተስፋ የሚሰጡ 5 ነገሮች •በአማራ ክልል በቫይረሱ የተያዙ ግለሰቦች ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሰዎችን ለመለየት ክትትል እየተደረገ ነው አሜሪካ ለሦስት ሳምንታት ያህል ቤት መቀመጥ እንዲሁም እንቅስቃሴ የሚገድብ መመሪያ ብታወጣም ዊስኮንሰን ይህንን ሕግ ተላልፋ ምርጫ ስታካሂድ የመጀመሪያዋ ግዛት ሆናለች። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በመጠቃት አለምን እየመራች ባለችው አሜሪካ አራት መቶ ሺህ የሚጠጋ ሰው በቫይረሱ ተይዟል። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም ሕይወታቸውን አጥተዋል። አገሪቷ እንዲህ ባለ የጤና ቀውስ ባለችበት ሰዓት ምርጫ መካሄዱ ተተችቷል። ሌሎች ግዛቶች ምርጫውን ላልተወሰነ ጊዜ አራዝመውታል። እስካሁን ባለው መረጃ በዊስኮንሰን ግዛት 2 ሺህ 500 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 92 ግለሰቦች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል።
53831244
https://www.bbc.com/amharic/53831244
አሜሪካ፡ ትዊተር ቲክቶክን ለመግዛት ፍላጎት አሳየ
ትራምፕ የቻይናው ቲክቶክ ለአሜሪካው ኦራክል እንዲሸጥ እንደሚፈልጉ ተናገሩ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ የአሜሪካው ኦራክል ቲክቶክን ቢገዛው መልካም ነገር ነው አሉ፡፡ ይህን የተናገሩት ኦራክል የቻይናውን ዝነኛ የማኅበራዊ ትስስር መተግበሪያ ቲክቶክን ለመግዛት እየተነጋገረ ባለበት ሰዓት ነው፡፡ ኦራክል ቲክቶክን የሚገዛው በአሜሪካ፣ በአውስትራሊያና በኒዊዚላንድ ያለውን ድርሻና ገበያ ነው፡፡ ትራምፕ ባለፈው ሳምንት ለቲክቶክ ባለቤት ባይትዳንስ ኩባንያ የአሜሪካ ድርሻውን በ90 ቀናት ውስጥ እንዲሸጥ አስጠንቅቀው ካልሆነ ግን ቲክቶክ በአሜሪካ ይዘጋል ማለታቸው አይዘነጋም፡፡ የኦራክል ሊቀመንበር ላሪ ኤሊሰን የትራምፕ ቀንደኛ ደጋፊ ሲሆኑ ለምርጫ ቅስቀሳ የገንዘብ መዋጮ ከሚያሰባስቡላቸው ሰዎች አንዱ ነው፡፡ አሁን እየወጡ ያሉ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ ኦራክል ቲክቶክን ለመግዛት ከፍተኛ ፍላጎት አድሮበታል፡፡ ከተቻለም ከአውስትራሊያ፣ አሜሪካና ኒውዚላንድ ገበያው በተጨማሪ የካናዳን ለማካተት ይፈልጋል፡፡ ዶናልድ ትራምፕ በዚህ ወር መጀመርያ ላይ እንደተናገሩት ከሆነ ቲክቶክ ለአሜሪካ ኩባንያ ሲሸጥ መንግስት የተወሰነ ገንዘብ ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡ ይህ በአሜሪካ የነጻ ኢኮኖሚ ሥርዓት የተለመደ ነገር አይደለም፡፡ ዶናልድ ትራምፕ ቲክቶክ ከአሜረካ ድርሻውን ሽጦ ይውጣ በሚል 90 ቀናትን ያስቀመጡት ድርጅቱ የዜጎችን መረጃ እየቃረመ ለቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ አሳልፎ ይሰጣል በሚል ነው፡፡ ባይትዳንስ በበኩሉ ክሱን አስተባብሏል፡፡ ብዙዎች ቲክቶክ በቻይናና በአሜሪካ የንግድ ጦርነት ውስጥ የጦስ ዶሮ ሆኗል ብለው ያስባሉ፡፡ ከኦራክል ሌላ ማይክሮሶፍት ቲክቶክን ለመግዛት ከባለቤቱ ባይትዳንስ ኩባንያ ጋር ንግግር መጀመሩ ይታወሳል፡፡ ከሁለቱ ግዙፍ ኩባንያዎች ሌላ ትዊተርም ቲክቶክን ለመግዛት ፍላጎት አሳይቷል፡፡ ቲክቶክ በአጭር ጊዜ ውስጥ እጅግ ተወዳጅ የስልክ መተግበሪያ መሆኑን የሚያሳየው በዚህ ዓመት ብቻ 2 ቢሊዮን የዓለማችን ሰዎች ስልካቸው ላይ ጭነውታል፡፡
49862597
https://www.bbc.com/amharic/49862597
ሩስያ በረንዳ ላይ ማጤስ ከለከለች
ሩስያ በረንዳ ላይ ማጤስ መከልከሏ ተሰምቷል። በአገሪቱ አዲስ በተረቀቀው የእሳት አደጋ መከላከያ መመሪያ መሰረት፤ በጋራ መኖሪያ ቤቶች በረንዳ ላይ ሲጋራ ማጤስ አይቻልም።
በአገሪቱ አዲስ እየተረቀቀ ባለው የእሳት አደጋ መከላከያ መመሪያ መሰረት፤ በጋራ መኖሪያ ቤቶች በረንዳ ላይ ሲጋራ ማጤስ አይቻልም • ልባችን ከእድሜያችን ቀድሞ ሊያረጅ እንደሚችል ያውቃሉ? • 'ከጤናማ' የሕይወት ዘይቤነት ወደ ገዳይ ልማድነት የተሻገረው ሲጋራ • በቤታችን ውስጥ ያለ አየር የጤናችን ጠንቅ እንዳይሆን ማድረግ ያለብን ነገሮች አዲሱ መመሪያ፤ ሰዎች በሚሰባሰቡበት የትምህርት ቤት መኝታ ክፍል እና በሆቴል የእንግዳ መቀበያ ውስጥ ሲጋራ ማጤስ ይከለክላል። በረንዳ ላይ ክባብ የተባለውን ምግብ ማዘጋጀት እና ሻማ ማብራት እንደማይቻልም ተዘግቧል። ሲጋራ ማጤስ እንዲሁም ክብሪት መለኮስም ለእሳት አደጋ መነሻ ምክንያት እንደሆነ የሩስያ ባለሥልጣኖች የተናገሩ ሲሆን፤ መመሪያውን ጥሶ የተገኘ ግለሰብ፤ 47 ዶላር (3,000 ሩብል) ይቀጣል ተብሏል። በርካታ ሩስያውያን ሲጋራ የሚያጠሱት በረንዳ ላይ ሲሆን፤ መመሪያው ተግባራዊ ሲደረግ በጋራ መኖሪያ ህንጻዎች የምድር ቤት ለማጤስ ይገደዳሉ። አዲሱ መመሪያ ያልተዋጠላቸው ሩስያውያን "መንግሥት ሰዎች በገዛ ንብረታቸው እንዳይጠቀሙ እያደረገ ነው፤ በረንዳ ላይ ካልተጤሰ ታዲያ የት ይኬዳል?" ሲሉ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ አስተያየታቸውን ጽፈዋል። የሩስያ የሲጋራ አጫሾች መብት ተሟጋች ኃላፊ አንድሬይ ሎስክቶቭ፤ "መንግሥት ሲጋራ ማጤስ መከልከል የሚችልበት ቦታ ሁሉ እንዳይጤስ ከልክሏል። የቀረው በረንዳ ላይ ማጤስ ነበር፤ አሁን ግን እሱም ተከለከለ" ብሏል።
52532519
https://www.bbc.com/amharic/52532519
ኮሮናቫይረስ፡ አቅመ ደካሞችን እያማለለ የሚገኘው የማፊያዎች ገንዘብ
የኮሮናቫይረስ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ሕይወት እየቀጠፈ በሚገኝበት በዚህ ሰዓት የጣልያን ማፍያዎች በሚሊየኖች የሚቆጠር ገንዘብ ለማትረፍ ደፋ ቀና እያሉ ነው።
የአገሪቱ ባለስልጣናት እንደገለጹት ዜጎች በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ፊታቸውን ማፊያዎች ወደሚሰጡት የተለያየ አይነት ብድርና እርዳታ እያዞሩ ይገኛሉ። በጣልያን የሚታወቀው የኮሳ ኖስትራ ማፊያ ቡድን ዋና አለቃ ወንድም በሲሲሊ ደሴት ፓሌርሞ መንደር ለሚገኙ ችግረኛ ነዋሪዎች ምግብ እያከፋፈለ ይገኛል። ‘’ ብዙ ሰዎች ስልክ እየደወሉ ችግራቸውን እየነገሩኝ ያለቅሳሉ። ልጆቻቸውን መመገብ እንኳን እንዳልቻሉ ይነግሩኛል’’ ብሏል። • በስልጤ ዞን ኮቪድ-19 ያለባቸው ሴት እንዴት ሊገኙ ቻሉ? • ኢትዮጵያ ጂኤምኦ ለማምረትና ለመጠቀም አልተስማማችም • 7 ፓርቲዎች አሁን ላይ ላለው ችግር ምላሽ የሚሆነው 'ፖለቲካዊ መፍትሄ ነው' አሉ ‘’ አንዲት ወጣት ሴት በየቀኑ ነበር የምትደውልልኝ፤ አምስት ልጆች ያሏት ሲሆን ምን እንደምታበላቸው ጨንቋታል።‘’ የማፊያ ቡድኑ ወንድም አክሎም ‘’ሰዎችን መርዳት ማፊያ የሚያስብል ከሆነ፤ ኩሩ የማፊያ አባል ነኝ’’ ብሏል። በርካታ በማፊያዎች የተፈጸሙ ወንጀሎች ላይ ምስክርነቱን የሰጠውና ከዚህ በፊት የማፊያ አባል የነበረው ጋስፔሬ ሙቶሎ ግን በዚህ በጎ በሚመስል ተግባር ሰዎች ሊሸወዱ አይገባም ይላል። ‘’ እኔም ልክ እንደዚህ ነበር የማደርገው። ሰዎች በጣም ይወዱኛል፤ ችግራቸውን አሰማለሁ። ማፊያዎች ሁሌም በሰዎች ችግር በኩል ነው የሚገቡት። የሆነ ነገር እስከሚፈጠር ድረስ ትክክለኛ ማንነታቸውንና ፍላጎታቸውን ማወቅ አይቻልም።‘’ ‘’ እኔም ወንጀለኛ ነበርኩ። በዘመኔ ከ20 በላይ ሰዎችን ገድያለሁ።‘’ ጋስፔሬ ፖሊሶች ብቻ በሚያውቁትና ጥበቃ በሚያደርጉለት አድራሻው በማይታወቅ ቦታ ሆኖ ነው ይህንን መረጃ ለቢቢሲ ለመስጠት የቻለው። ‘’ ልጆች ሲራቡና የምትሰራበት የንግድ ቤት ኪሳራ ውስጥ ሲወድቅ ምንም አማራጭ ስለማይኖር እርዳታ ለማግኘት ሰዎች የቻሉትን ሁሉ ያደርጋሉ። ማፊያዎች የጠቀሙ መስለው የሚገቡት በዚህ መንገድ ነው’’ ይላል። ጋስፔሬ እንደሚለው ምግብ በነጻ ማከፋፈል በራሱ ድብቅ አጀንዳ አለው። ‘’ ይህን የሚያደርጉት ታማኝነትን ለማትረፍ ነው። እነሱ ዋነኛ ግባቸው በአካባቢዎቹ በነጻነት መንቀሳቀስና የሚፈልጉትን ማንኛውንም ነገር ያለማንም ጠያቂ ማከናወን ነው። ማህበረሰቡ ተቀብሏቸው ዝም ካለ ደግሞ ለእነሱ የተመቸ ይሆናል’’ የሚለው የተደራጀ ወንጀል መከላከል ላይ የሚሰራው ኒኮላ ግራቴሪ ነው። ‘’በዚህ የኮሮናቫይረስ ወቅት ደግሞ እንዲህ አይነት ነገሮች መበራከታቸው ግልጽ ነው። በጣም ትንሽ የሚባለውን ስጦታ እንኳን መቀበል አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሊከት ይችላል።‘’ ማርሴሎ በፓሌርሞ መሀል ውስጥ አነስተኛ ምግብ ቤት አለው። ከባለፈው መጋቢት ወር ጀምሮ ደግሞ ምግብ ቤቱ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ተዘግቷል። ‘’ አሁን ምንም አማራጭ የለኝም፤ ሌላው ማፊያዎቹ መጥተው ምግብ ቤቱን እስከሚገዙኝ እየጠበቅኩኝ ነው። ከዚህ በኋላ ደግሞ መክፈት የምችል አይመስለኝም።‘’ ማርሴሎ እንደሚለው የሆነ ሰው ይመጣና ሬስቶራንቱን ለመግዛት ዋጋ ያቀርባል ከትንሽ ድርድር በኋላ የእነሱ ያደርጉታል። ከዚህ በተጨማሪ እንደዚህ አይነት አስቸጋሪ ጊዜያት ለማፈያዎች ዋነኛ ምቹ አጋጣሚዎች ናቸው። ምክንያቱም ሰዎች አማራጭ ስለማይኖራቸው ትንሽም ይሁን ትልቅ ብድር ውስጥ ይገባሉ። ማፍያዎቹም ወጣም ወረደ ያንን ገንዘብ ከነወለዱ ከመቀበል ወደኋላ አይሉም። ከዚህ ባለፈም ምርጫ በደረሰ ጊዜ እነዚሁ ማፍያዎች ወደረዷቸው ሰዎች በመሄድ የሰራንላችሁን ውለታ የምትከፍሉበት ሰአት ደርሷል። እኛ የምንላችሁን ተወዳዳሪ ምረጡ ይሏቸዋል። ከማፊያ ብድር ወስደው ለተቸገሩ ሰዎች የተቋቋመው የጥሪ ማዕከል በጣልያን እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ከተጣለ በኋላ የሚቀርቡለት ቅሬታዎች 100% ጨምረዋል። ‘’ዜጎች ከመንግስታቸው አፋጣኝ እርዳታ ማግኘት የማይችሉ ከሆነ በማፊያዎች ወጥመድ ውስጥ መውደቃቸው አይቀሬ ነው’’ ትላለች የፀረ ማፍያ ቡድን ውስጥ የምትሰራው ኤንዛ ራንዶ። ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በኋላ የጣልያን ኢኮኖሚ 9.1 በመቶ እንደሚቀንስ ይጠበቃል። በዚህም ምክንያት በርካታ ጣልያናውያን በተለይም አነስተኛ ንግድ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ሰዎች ከባድ ፈተና ይጠብቃቸዋል። ‘’ ይህ ደግሞ ለማፊያዎቹ በጣም ምቹ አጋጣሚ ነው’’ ትላለች ኤንዛ። ምክሯም መንግስት ከማፊያዎቹ ቀድሞ ለዜጎቹ የብድር አቅርቦት ማመቻቸት እንዳለበት ነው። የጣልያን መንግስት እንዳስታወቀው ደግሞ ዜጎች እስከ 25 ሺ ዩሮ የሚደርስ ብድር መየጠቅ ይችላሉ። ነገር ግን እንደ ማርሴሎ ያሉ ዜጎች ይህን ያክል ገንዘብ ከመንግስት መበደር አይፈልጉም። ምክንያቱም ሱቆቻቸውን ቢከፍቱ እንኳን በአሁኑ ሰአት ምንም አይነት ደንበኛ ማግኘት ስለማይችሉ ብድራቸውን መክፈል አይችሉም። ስለዚህ ያላቸው አማራጭ የንግድ ሱቆቻቸውን ለማፊያዎች መሸጥ ነው። ማፊያዎቹ ደግሞ እንደዚህ አይነት አነስተኛ ሱቆችን ገንዘብ በሕገወጥ መንገድ ለማዘዋወር በእጅጉ ይፈልጓቸዋል።
news-55270806
https://www.bbc.com/amharic/news-55270806
ሞሮኮ ከእስራኤል ጋር ግንኙነት ለማሻሻል ተስማማች
ሞሮኮ ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለመጀመር ከተስማሙ የአረብ አገራት ዝርዝር ውስጥ ተካታለች።
የሞሮኮ ንጉስ ሞሐመድ ስድስተኛ እና የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ በአሜሪካ አደራዳሪነት የተደረሰውን ስምምነት ፕሬዝደንት ትራምፕ በትዊተር ገጻቸው ይፋ አድርገዋል። ሞሮኮ ከእስራኤል ጋር ከስምምነት መድረሷን ተከትሎ በዌስተርን ሳሃራ ግዛት ለምታነሳው የይገባኛል ጥያቄ አሜሪካ እውቅና ለመስጠት ተስማምታለች። በአልጄሪያ የሚደገፉ ፖሊሳሪኦ ግንባር በዌስተርን ሰሃራ የራስ ገዝ አስተዳደር ለመመስረት ከሞሮኮ ጋር ለበርካታ ዓመታት የዘለቀ አለመግባባት ውስጥ ነበሩ። ሞሮኮ ከነሐሴ ወር ወዲህ ከእስራሴል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማሻሻል ከስምምነት የደረሰች አራተኛዋ አገር ሆናለች። በቅርቡ የትራምፕ አስተዳደር ሱዳን፣ ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ እና ባህሬን ከእስራኤል ጋር ሰላም እንዲያወርዱ ማደራደሩ ይታወሳል። ከዚህ ቀደም ከእስራኤል ጋር የሰላም ስምምነት የፈረሙት ግብጽ እና ጆርዳን ሲደመሩ፤ ከአረብ ሊግ አባል አገራት ከእስራኤል ጋር የሰላም ስምምነት የደረሱት አገራት ቁጥር ወደ ስድስት ከፍ ይላል። ስምምነቱ ምን ይዟል? ትራምፕ በሁለቱ አገራት መካከል የተደረሰውን ስምምነት ይፋ አድርገዋል። “ሌላ ታሪካዊ ክስትተ” ብለውታል ፕሬዝደንት ትራምፕ። ሁለቱ ወዳጅ አራት እስራኤል እና ሞሮኮ ሙሉ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለመመስረት ተስማምተዋል ብለዋል ተሰናባቹ ፕሬዝደንት። ዋይት ሃውስ ሞሮኮ ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደምትጀምር፣ ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ትብብሮችን ለመጀመር መስማማቷን አስታውቋል። በራባት እና ቴል አቪዝ የላይዘን ቢሮዎች በፍጥነት ሥራ ለማስጀምር፤ ከዚያም ኤምባሲዎች ለመክፈት ተስማምተዋል ተብሏል። የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ በቴሌቪዥን በተላለፈው ንግግራቸው ስምምነቱን “ታሪካዊ” ያሉት ሲሆን፤ ለሞሮኮ ንጉስ ሞሐመድ ስድስተኛ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ሞሮኮም ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለመጀመር መስማማቷን የንጉሱ ቤተ-መንግሥት አረጋግጧል። ግብጽ፣ ዩኤኢ እና ባህሬን፤ ሁለቱ አገራት የደረሱትን ስምምነት በደስታ ተቀብለነዋል ብለዋል። የፍልስጤም መሪዎች ግን ስምምነቱን አጥላልተውታል። ፍልስጤማውያን የአረብ ሊግ አባላት ከእስራኤል ጋር የሰላም ስምምነት ማድረጋቸውን ሲቃወሙ ቆይተዋል። የፍልስጤም መሪዎች እስራኤል ከአረብ አገራት ጋር ዲፕሊማሲያዊ ግንኙነት እንድትጀምር መፈቀዱ መብታችንን እንድትጋፋ የሚያበረታታ ነው ብለዋል።
news-47731454
https://www.bbc.com/amharic/news-47731454
ሴተኛ አዳሪነት ባህል የሆነበት ማህበረሰብ
አብዛኛው የህንድ ማህበረሰብ ከሴት ይልቅ ወንድ ልጅ እንዲወለድለት ነው የሚፈልገው። ሂና ስትወለድ ግን ቤተሰቦቿ በተለየ መልኩ ነበር የተደሰቱት። ደስታቸው የመነጨውም ባልተለመደ መልኩ ወደፊት ምን እንደሚያሰሯት በማሰብ ነበር።
ራቅ ባለ የህንድ አካባቢ 'ባቻራ' ከተባለው ማህበረሰብ የተገኘችው ሂና ህይወቷን የምትመራው በወሲብ ንግድ ነው። ለብዙ መቶ ዓመታት የዚህ ማህበረሰብ አባላት መጀመሪያ የሚወለዱ ሴት ልጆቻቸውን ከ10 እስከ 12 ዓመት ሲሞላቸው ለገንዘብ ገላቸውን እንዲሸጡ ይገፏፏቸዋል። • የሴቶችና ወንዶች የኢኮኖሚ እኩልነት እንዴት ይስፈን? የመጀመሪያዋ ሴት ልጅ እድሜዋ ሲገፋ ቀጥላ የምትመጣው ሌላኛዋ የቤተሰቡ ሴት ልጅ እሷን ተክታ ወደ እዚህ ሥራ ትሰማራለች፤ ይህ ደግሞ ሁሉም ተቀብሎት የሚተገብረው የማህበረሰቡ ልምድ ነው። ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ በኖረው በዚህ ባህል የሚገኘውን ገንዘብ በሙሉ በሚባል ደረጃ የሚጠቀሙት ወንዶቹ ወይም የቤተሰቡ አባወራ ነው። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ሴቶቹ ሥራቸውን በትክክል መስራታቸውን የሚቆጣጠሩት አባቶች አልያም ወንድሞቻቸው ናቸው። ሌላው ቢቀር የዚህ ማህበረሰብ ሴቶች ሲዳሩ ቤተሰቦቻቸው ለጥሎሽ ረብጣ ገንዘብ ይጠይቃሉ። ምክንያቱ ደግሞ ወደ ወንዱ ቤተሰብ ከሄደች በኋላ ብዙ ገንዘብ እንደምታስገኝላቸው ስለሚታሰብ ነው። ''ምንም አማራጭ የለኝም'' ሂና ከተወለደችበት ጊዜ አንስቶ እድሜ ልኳን ለዚህ ተግባር ስትዘጋጅና ስትለማመድ ነው ያደገችው። ''ገና የ15 ዓመት ታዳጊ ሳለሁ ወደዚህ ሥራ ተገድጄ ገባሁ። ትምህርቴን ማቋረጥ ነበረበኝ፤ ምክንያቱም የእናቴንና የአያቴን ፈለግ መከተል ግዴታዬ ነበር'' ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች። • ብቻቸውን ወደ መዝናኛ ስፍራ የሚሄዱ ሴቶች ፈተና በእያንዳንዱ ቀን ከገጠር ሃብታሞች እስከ የከባድ ተሽከርካሪ ሾፌሮች ድረስ ደንበኞቿን ታስተናግዳለች። ''ልክ 18 ዓመት ሲሞላኝ የምሰራው ሥራ ትክክል እንዳልሆነ ይሰማኝ ጀመር። በጣም እናደድ ነበር፤ ግን ምን አማራጭ አለኝ?'' ''እኔ ይህንን ሰርቼ ገንዘብ ካላገኘሁ ቤተሰቤ በምን ይኖራል? ቤተሰቤ ይራባል።'' የባቻራ ማህበረሰብ አባላት ከሌሎቹ የህንድ ማህበረሰቦች ጋር ሲነጻጸሩ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ ገንዘብ ነክ ጥያቄዎቻቸውን የሚመልሱት ሴቶቹ ላይ በመተማመን ነው። በአካባቢው የሚንቀሳቀስ አንድ የበጎ አድራጎት ድርጅት ውስጥ የሚሰራው አካሽ ቾሃን እንደሚለው በዚህ ሥራ ከሚሰማሩት ሴቶች አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ከአስራ ስምንት ዓመት በታች ናቸው። ታዳጊ ህጻናቱ በአካባቢው በሚገኝ የጠፍር አልጋ ላይ ለብቻቸው ወይም ተሰብስበው በመቀመጥ ደንበኞቻቸውን ይጠባበቃሉ። በቅርበት ደግሞ አነስተኛ ሱቆች ይኖራሉ። ብዙ ጊዜ አንድ የቤተሰብ አባል በሱቋ ውስጥ ከደንበኞች ጋር ስለክፍያው መጠን ድርድር ያደርጋል። በድርድሩ መሰረትም አንድ ደንበኛ በአማካይ ከ40 እስከ 80 ብር ድረስ ይከፍላል። ነገር ግን ከዚህ በፊት ከወንድ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ያልፈጸመች ከሆነች ክፍያው እስከ 2000 ብር ድረስ ከፍ ሊል ይችላል። የህንድ ብሔራዊ ጋዜጣ ባወጣው መረጃ መሰረት ከ5500 የማህበረሰቡ አባላት ላይ የደም ናሙና ተወስዶ 15 በመቶ የሚሆኑት በደማቸው የኤች አይ ቪ ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። • "ከመቶ ምናምን ፓርቲ ሴት የምናገኘው አንድ ወይም ቢበዛ ሁለት ሊሆን ይችላል" ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ አብዛኞቹ ሴቶች ከሥራው ጋር በተያያዘ ያልተፈለገ እርግዝና ያጋጥማቸዋል የምትለው ሂና እራሷ ከጥቂት ዓመታት በፊት ሴት ልጅ እንደተገላገለች ትናገራለች። ''ብዙ ሴቶች ወዲያው ያረግዛሉ። ይሄ ሲታወቅ ብዙ ገንዘብ አግኝተው ልጃቸውን እራሳቸው እንዲንከባከቡ በሚል ምክንያት ከሌላ ጊዜው ተጨማሪ ደንበኛ እንዲያስተናግዱ ይገደዳሉ።'' ሂና የወሲብ ንግድ ውስጥ የሚሰተፉ ሴቶች ደግሞ እዚያው ማህበረሰባቸው ውስጥ አባል የሆነ ወንድ ማግባት አይችሉም። ሂና በጊዜ ብዛት ከአንድ በጎ አድራጎት ድርጅት ባገኘችው እርዳታ በመታገዝ ይህንን ልማድ ተፋልማ አሸንፋ መውጣት ችላለች። ነገር ግን አሁንም ብዙ ታዳጊ ሴቶች በዚሁ ልማድ ታስረው እንዳሉ ትናገራለች። ''በዚህ እርኩስ ልምድ ውስጥ ያለፈ ሰው ብቻ ነው መከራው ሊገባው የሚችለው። ሴቶቹ ምን እንደሚሰማቸው እኔ አውቃለው፤ ስለዚህ ይህንን ልምድ ለማስቀረት እሰራለሁ።'' የባቻራ ማህበረሰብ እስከ 33 ሺህ የሚደርሱ አባላት ያሉት ሲሆን 65 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ሴቶች ናቸው። የሴቶች ቁጥር ከፍተኛ የሆነበት ምክንያት ደግሞ ትንንሽ ሴት ህጻናት ታፍነው ወደዚህ አካባቢ ስለሚወሰዱ ነው። አካሽ እንደሚለው ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ 50 የሚደርሱ ህጻናትን ከዚህ ንግድ ማዳን ችለዋል። ''ሌላው ቢቀር ለዚሁ ተግባር ታፍና ተወስዳ የነበረች የሁለት ዓመት ህጻን ወደ አሳዳጊ ቤተሰቦች እንድትላክ አድርገናል።'' • ሴት ተመራቂዎች ለምን ሥራ አያገኙም? የህንድ መንግሥትና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በሚሰሯቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች ምክንያት ይህ ተግባር እየቀነሰ የመጣ ይመስላል። ወጣት ሴቶች በወሲብ ንግድ መሳተፍ አንፈልግም እያሉ ቤተሰባቸውን መሞገት ጀምረዋል። አንዳንዶቹም ከአካባቢው ራቅ ብለው በመሄድ ሌላ ሥራ ማፈላለግ ጀምረዋል። ትምህርታቸው ላይ ማተኮር የጀመሩም አሉ። ሂና እሷን ከዚህ ህይወት ካወጣት የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመሆን ለውጥ ለማምጣት እየሰራች ነው። ''ሌሎች ታዳጊ ሴቶች ድጋፍ ማግኘት እንደሚችሉና ከወሲብ ንግድ መውጣት እንደሚቻል ለማሳየት የቻልኩትን ሁሉ አደርጋለው'' ብላለች።
news-51134352
https://www.bbc.com/amharic/news-51134352
20 ወፎችን በቦርሳው የደበቀው አየር ማረፊያ ላይ ተያዘ
ቤልጂየማዊ ዜግነት ያለው ተጓዥ በፔሩ ዋና ከተማ በሚገኘው ሊማ አየር ማረፊያ በእጅ ሻንጣው 20 ወፎችን ደብቆ ከሃገር ሊወጣ ሲል በቁጥጥር ሥር ዋለ።
ሂዮጉ ኮኒንግስ የተባለው የ54 ዓመት ጎልማሳ፤ ወፎቹን በትናንሽ ካርቶኖች ውስጥ ካደረገ በኋላ በእጅ ሻንጣው ውስጥ ደብቆ ከሃገር ሊያስወጣ መሞከሩን የሃገሪቱ ፖሊስ አስታውቋል። ፖሊስ ጨምሮ እንደተናገረው፤ ግለሰቡ ወፎቹን ወደ ማድሪድ ስፔን ወስዶ ለመሸጥ አስቦ ነበር። ወፎቹ ጥበቃ የሚደረግላቸው የላቲን አሜሪካ ብርቅዬ አእዋፋት መሆናቸው ተነግሯል። 20ዎቹም ወፎች በሕይወት እንደተገኙ ይሁን እንጂ ለሰዓታት በትንሽዬ ካርቶን ውስጥ መቆየታቸውን ተከትሎ ላባቸው መርገፉን እና ፈሳሽ ከውስጣቸው እንደተመናመነ ምልክት ማሳየታቸውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። በቁጥጥር ሥር የዋለው ቤልጂየማዊ አእዋፋትን በሕገ-ወጥ መንገድ ማዘዋወር በሚል ክስ ተመስርቶበት በፔሩ እስር ቤት 5 ዓመታትን እንዲያሳልፍ ሊፈረድበት ይችላል ተብሏል። ወፎቹ በትናንሽ ካርቶኖች ውስጥ ነበር በዚህ መልክ የታሸጉት። ወፎቹ ለሰዓታት በካርቶን ውስጥ መቆየታቸውን ተከትሎ ላባቸው መርገፉን እና ፈሳሽ ከውስጣቸው እንደተመናመነ ምልክት ማሳየታቸውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። ወፎቹ በፔሩ ጥቅጥቅ ደን ውስጥ እና በኢኳዶር እና ቦሊቪያ ብቻ እንደሚገኙ ተነግሯል። በፔሩ ብርቅዬ የሆኑ አእዋፋት በብዛት የሚገኙ ሲሆን ሕገ-ወጥ የዱር እንስሳት አዘዋዋሪዎች ግን የፔሩ ብርቅዬ አእዋፋት ላይ የተጋረጡ ከፍተኛ ስጋት ሆነዋል ተብሏል። ወፎቹ ቀልብን የሚገዛው የላባቸው ቀለማት በአውሮፓ ገበያ ብዙ ገንዘብ ይጠየቅባቸዋል ተብሏል።
news-54217232
https://www.bbc.com/amharic/news-54217232
ፖለቲካ ፡ ለውጥ ለማምጣት የምን ያህል ሰዎች ተሳትፎን ይፈልጋል?
አንድን መሪ ከሥልጣን ለማስወገድ ምን ያህል ሰው መቃወም አለበት? የሚያዋጣው ነውጥ የቀላቀለ ተቃውሞ ነው ወይስ ሰላማዊ?
ከማይዘነጉ ንቅናቄዎች መካከል እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ1980ዎቹ የነበረው የፖላንድ ተቃውሞ፣ የደቡብ አፍሪካው የጸረ አፓርታይድ ትግል፣ የቱኒዝያውን ፕሬዘዳንት ያስወገደው የጃዝሚን አብዮት እና የፀደይ አብዮት (አረብ ስፕሪንግ) ይጠቀሳሉ። እነዚህ ጉልህ ለውጥ ማምጣት የቻሉ ንቅናቄዎች ናቸው። ወደ ቅርብ ጊዜ አብዮት ስንመጣ ደግሞ ቤላሩስን እናገኛለን። ፕሬዘዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ምርጫ አሸንፌያለሁ ማለታቸውን ተከትሎ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለተቃውሞ ወጥተዋል። በርካቶች ታስረዋል፣ ስቃይና እንግልት እንደደረሰባቸው የሚናገሩም አሉ። ሆኖም ግን ተቃውሞው ሰላማዊ በሆነ መንገድ ቀጥሏል። ለመሆኑ ተቃውሞው ግቡን ይመታል? የሚለውን ለመመለስ ታሪክን መመልከት ያሻል። ነውጠኛ ተቃውሞ የቱ ነው? የሀርቫንድ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንቲስት ኤሪካ ቼንዌዝ በአምባገነን ሥርዓቶች ላይ ስለሚነሳ ተቃውሞ አጥንተዋል። አምባገነናዊ ሥርዓት ውስጥ ሕዝብ መሪውን ለማስወገድ ምርጫ ማካሄድ አይችልም። ስለ ተቃውሞ ሲነሳ የትኛው ነውጥ የቀላቀለ የትኛውስ ሰላማዊ ነው? የሚለውም ያከራክራል። ንብረት ሲወድም ተቃውሞው ነውጠኛ ነው ይባላል? ሰዎች አካላዊ ጥቃት ሳያደርሱ ዘረኛ ስድብ ቢሳደቡስ? ራስን ማቃጠል ወይም የረሀብ አድማ መምታትስ ነውጥ የቀላቀሉ የተቃውሞ መንገዶች ናቸው? ለእያንዳንዱ ሁኔታ ግልጽ በሆነ መንገድ ነውጠኛ ወይም ኢ-ነውጠኛ የሚል ትርጓሜ መስጠት ይከብዳል። ሆኖም ግን ነውጥ በቀላቀለና በሰላማዊ ተቃውሞ መካከል ያሉ ልዩነቶችን መረዳት እንችላለን። ለምሳሌ ሰውን መግደል ነውጠኛ መሆኑ አያጠያይቅም። ሰላማዊ ሰልፍ፣ ፊርማ ማሰባሰብ፣ አድማ መምታትና አንድን ሁነት ረግጦ መውጣት ሰላማዊ ተቃውሞ ናቸው። አንድ ጥናት 198 አይነት ሰላማዊ ተቃውሞዎች እንዳሉ ያሳያል። ሳይንቲስቷ ከ1990 እስከ 2006 በተሰበሰበ መረጃ ላይ ጥናት ሠርተው፤ ሰላማዊ ተቃውሞ ውጤታማ የመሆን እድሉ ሰፊ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል። ሰላማዊ ተቃውሞ ውጤት ያስገኛል? ነውጥ የቀላቀለ ተቃውሞ ድጋፍ ሊያጣ እንደሚችል ተመራማሪዎች ይናገራሉ። ሰላማዊ ተቃውሞ ሲካሄድ የሚቀላቀሉ እንደሚበራከቱ፣ በአጭር ጊዜና ያለ ምንም ልዩ ስልጠና ሊከናወን እንደሚችልም ያክላሉ። ታዳጊዎች፣ አካል ጉዳተኞች፣ ሴቶች እና አዛውንቶች ሰላማዊ ተቃውሞ ይቀላቀላሉ። ቡልዶዘር አብዮትን እንደ ምሳሌ እንውሰድ። ወታደሮች ለምን ተቃዋሚዎች ላይ እንዳልተኮሱ ሲጠየቁ፤ ተቃዋሚዎቹን ስለምናውቃቸው ነው ብለው ነበር። ተቃዋሚዎቹ ጓደኞቻቸው፣ የአክስታቸው ልጆች፣ ጎረቤቶቻቸው ወዘተ. . . ነበሩ። የፖለቲካ ሳይንቲስቷ ኤሪካ እንደሚሉት፤ 3.5 በመቶ ሕዝብ ከተቃወመ ለውጥ ማምጣት ይችላል። ቤላሩስን ማሳያ ብናደርግ፤ 3.5 በመቶ ማለት ከአገሪቱ ዘጠኝ ሚሊዮን ዜጎች 300,000 ማለት ነው። በመዲናዋ ሚንስክ በተካሄደው ተቃውሞ ወደ አስር ሺህ ሰዎች ተሳትፈዋል። አሶሽየትድ ፕሬስ 200,000 ተቃዋሚዎች መገኘታቸውን የዘገበበት ወቅት ነበር። 3.5 በመቶ የሚለው ቁጥር በሁሉም አገር ይሠራል ማለት አይደለም። አንዳንድ ንቅናቄዎች በአነስተኛ ቁጥርም ግባቸውን መተዋል። ከፍተኛ ሕዝብ አሳትፈው የከሸፉ አብዮቶችም አሉ። ለዚህ የ2011 የባህሬን እንቅስቃሴ ይጠቀሳል። በመላው ዓለም ከትጥቅ ትግል ይልቅ ሰላማዊ ተቃውሞ እየተዘወተረ የመጣ የትግል ስልት መሆኑን የኤሪካ ጥናት ይጠቁማል። ከ2010 እስከ 2019 ባሉት ዓመታት የታዩ ተቃውሞዎች በሰው ልጅ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሰላማዊ ናቸው። በሌላ በኩል ከአስር ነውጥ የቀላቀሉ ተቃውሞዎች ዘጠኙ ይከሽፋሉ። በቀደመው ዘመን ከሁለት ሰላማዊ ተቃውሞዎች አንዱ ይሳካ ነበር። አሁን ላይ ከሦስት ሰላማዊ ተቃውሞዎች ፍሬያማ የሚሆነው አንዱ ብቻ ነው። መንግሥት ግልበጣ ከ2006 ወዲህ አንዳንድ ለውጦች እየተስተዋሉ ነው። የሱዳኑ ኦማር አልበሽር ከሥልጣን ተወግደው በሳምንታት ውስጥ የአልጄሪያው ፕሬዘዳንት አብዱልአዚዝ ቡተፍሊካም ተመሳሳይ እጣ ደርሷቸዋል። እንዲህ አይነት የመንግሥት ግልበጣዎች ቁጥር እየቀነሰ ነው። የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመን ላይ እንደመሆናችን ዲጂታል አብዮት ሲቀጣጠል እናያለን። መረጃ በቀላሉ ይንሸራሸራል። ቀጣዩ የተቃውሞ ሰልፍ የት እንደሚካሄድ ለማወቅም አይከብድም። ሆኖም ግን ዲጂታል አብዮትን እንዴት ማስተጓጎል እንደሚቻል መሪዎች ያውቃሉ። ኤሪካ እንደሚሉት፤ መሰል አብዮቶችን ለማስቆም የዲጂታል ስለላ እና ሰርጎ ገብ እርምጃዎች ይወሰዳሉ። በማኅበራዊ ሚዲያ ሐሰተኛ መረጃ እና ፕሮፓጋንዳም ይነዛል። በቤላሩስ ተቃዋሚዎች ስልካቸው እየተፈተሸ ነው። እንደ ቴሌግራም ባለ መልዕክት መለዋወጫ ስለ ተቃውሞው መረጃ አግኝተው እንደሆነም ይጣራል። የቴሌግራም ቡድን የከፈቱ ሰዎች ታስረዋል። ቴሌግራም በበኩሉ የቡድኑ አባላት ዝርዝር ፖሊስ እጅ ከመግባቱ በፊት ቡድኖቹ እንዲከስሙ ያደርጋል። ታዲያ ፕሬዘዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ሥልጣናቸውን ይዘው ይቆዩ ይሆን? ወይስ ተቃዋሚዎች ድል ይነሳሉ? አብረን የምናየው ይሆናል።
news-56697407
https://www.bbc.com/amharic/news-56697407
ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ሃብታም አገራት ለክትባት ያሳዩትን ስግብግብነት ተቹ
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በድሃና ሃብታም አገራት ውስጥ ያለውን የኮሮናቫይረስ ክትባት አቅርቦት ፍትሐዊ አለመሆን አሳፋሪ እንደሆነ ተናገሩ።
በኮቫክስ በኩል ለደሃ አገራት የሚቀርብ የክትባት ጭነት ዳይሬክተሩ እንደገለጹት በሁሉም አገራት ክትባቱ ተዳርሶ ለማየት የነበረው የረዥም ጊዜ ዕቅድ ሳይሳካ መቅረቱን አውስተዋል። የዓለም ጤና ድርጅት የኮቪድ-19 ክትባትን በፍትሐዊነት ለድሃና ሃብታም አገራት በእኩል ለማዳረስ በአያሌው ሲታትር ነበር። ይህንኑ ዕቅዱን እውን ለማድረግም ኮቫክስ የተሰኘ ፕሮጀክት ዘርግቶ ሰፊ የሥራ እንቅስቃሴ ውስጥ ነበር። ኮቫክስ ለድሃ አገራት ክትባቱን ለማዳረስ የተቋቋመ የአገራት ጥምረት ነው። እስከ አሁን ለ100 ድሃ አገራት 38 ሚሊዮን ብልቃጥ ክትባቶችን ማደረስ ችሏል። ሆኖም ይህ ከዕቅዱ በታች ነው። ኮቫክስ ሲቋቋም ዕቅዱ የነበረው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለ190 አገራት 2 ቢሊዮን ብልቃጦችን ማድረስ ነበር። 92 ድሃ አገራት ልክ ሃብታም አገሮች ያላቸውን የክትባት አቅርቦት በተመሳሳይ ጊዜ እንዲያገኙ ለማስቻልም እየሰራ ነበር። ሆኖም ኮቫክስ ይህ ዕቅዱ ተፋርሶበታል። "በድሃና ሃብታም አገራት መካከል ያለው ልዩነት አስደንጋጭ ነው" ብለዋል ዶ/ር ቴድሮስ ትናንት አርብ በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ። "በአማካይ ከሃብታም አገራት ከ4 ሰው አንዱ ክትባቱ ደርሶታል። በድሃ አገራት ግን ከ500 ሰዎች አንዱ ብቻ ነው ክትባቱ የደረሰው" ሲሉ የኢፍትሐዊነቱን ምጣኔ አብራርተዋል። ኮቫክስ እንደ እቅዱ ቢሆን ኖሮ በመጋቢት መጨረሻ 100 ሚሊዮን ብልቃጦችን ለድሃ አገራት ማድረስ ነበር። አሁን ማሳካት የቻለው ግን 38 ሚሊዮኑን ብቻ ነው። ዶ/ር ቴድሮስ በመጋቢት መጨረሻ የነበረውን እቅድ በሚያዝያ ወይም ግንቦት ለማሳካት እየተፍጨረጨርን ነው ብለዋል። ዶ/ር ቴድሮስ አንዳንድ አገራት ኮቫክስን ቸል ብለው የቀጥታ የሁለትዮሽ ስምምነት እያደረጉ አግኝተናቸዋል ያሉ ሲሆን፤ ይህንንም የሚያደርጉት የንግድና የፖለቲካ ትርፍን አስልተው ነው ሲሉ አምርረው ተችተዋቸዋል። ይህ የሁለትዮሽ ስምምነት በድሃና ሃብታም አገራት የሚኖረውን የክትባት አቅርቦት መመጣጠን ጨርሶውኑ እንዲፋለስ ያደርገዋልም ብለዋል። በዚህ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት መባቻ ዶ/ር ቴድሮስ የሃብታም አገራትን ስግብግብነትና ራስ ወዳድነትን ክፉኛ ወቅሰው እንደነበረ ይታወሳል። "ለኔ ብቻ የሚለው አስተሳሰብ መልሶ ራሰን የሚጎዳ ነው፤ ምክንያቱም ለኔ ብቻ ብሎ ክትባቱን ማከማቸት ወረርሽኙን መጋዘን ውስጥ የማከማቸት ያህል ነው" ሲሉ ሃብታም አገራት ላይ የታየውን የሞራል ውድቅትና ስግብግብነትን ተችተው ነበር። በታላቋ ብሪታኒያ፣ በአሜሪካ በአውሮጳ፣ በሩሲያና በቻይና የተመረቱ ክትባቶች በስፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው። ሆኖም ክትባቶቹ ለአገራቱ እየደረሱ ያሉበት መንገድ ኢፍትሐዊነት የሚንጸባረቅበት ነው። ሃብታም አገራት 4 ቢሊዮን ተኩል የሚሆኑ የክትባት ብልቃጦችን ለራሳቸው ደብቀው ይዘዋል። ነገር ግን መካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አገራት 670 ሚሊዮን ጠብታዎችን ብቻ ነው ማግኘት የቻሉት።
44583151
https://www.bbc.com/amharic/44583151
የተጠበቀውን ያህል የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች አልተመለሱም
ባለፈው ጥቅምት ወር በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ማንነት ላይ ያነጣጠር ጥቃት በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ ከደረሰ በኋላ የተፈናቀሉ ዜጎች እንዲመለሱ ጥሪ ቢቀርብም የተመላሾች ቁጥር የተጠበቀውን ያህል አልሆነም።
ተመላሾች በአንፃሩ ቃል የተገባውን ያህል ማቋቋሚያ አላገኘንም ይላሉ። ትናንት በተቀሰቀሰ አዲስ ግጭት የሰዎች ህይወት አልፏል። "ወደዚህ የመጣሁት ያለኝን ንብረት ጥዬ ነው። በምን ተቋቁሜ ለመስራት ነው ወደዚያ የምመለሰው?" ስትል ጥሩ ፈንታየሁ ትጠይቃለች። ጥያቄው የጥሩ ብቻ አይደለም። በመቶዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮችም ጭምር እንጂ። ጥሩ ከቤንሻንጉል ጉምዝ ተፈናቅለው ባህር ዳር ከተማ የሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ከተጠለሉ ከመቶ ሰላሳ የሚልቁ ግለሰቦች አንዷ ናት። የመኖሪያ ቀየዋን ጥላ ከተፈናቀለች ወራት ተቆጥሯል፤ በባህር ዳር የምግብ ዋስትና ግቢ ከዚያም በተለያዩ አብያተ ክርስትያናት ቅፅር ውስጥ መጠለያዋን አድርጋለች። የሀያ አምስት ዓመቷ ጥሩ የሁለት ልጆች እናት ስትሆን የአምስት ዓመት ልጇን ከዘመድ አስጠግታ ያለፉትን ሁለት ወራት በቤተ ክርስትያኑ ውስጥ ኖራለች። የካማሼ ዞን ተፈናቃዮች አሁንም ስጋት ላይ እንደሆኑ ገለፁ "የክልሉን መንግሥት በእግዚአብሔር ስም ጠይቁልን..." ተፈናቃዮች ወደ ቀደመ መኖሪያቸው እንዲመለሱ የቀረበው ጥሪ ጥሩን ያሳመናት አይመስልም። "ተመልሼ ሄጄ የምሰራው የለም። መንግሥት መጠለያና መቋቋሚያ ሰጥቶን እራሳችንን እንድናስተዳድር እጠብቃለሁ" ስትል ትናገራለች። አስተያየቷን ሌላኛው ተፈናቃይ አቶ አዕምሮ ተገኘም ይጋሩታል። ያለፉትን ሰባት ዓመታት በኖሩበት በካማሼ ዞን የሎጂ ጋንፎይ ወረዳ ግብርናን እና የልብስ ስፌት ሥራን አጣምረው በመስራት ይተዳደሩ ነበር። ባለፈው ጥቅምት ብሄር ተኮር ጥቃት ሲሰነዘር "ተደብድቤ፥ በህክምናና በፀበል ነው የዳንኩት፤ የተመታሁት እጄ አሁንም በቅጡ አይሰራም" ይላሉ። የስፌት መኪናቸው መቃጠሉ እንዲሁም ከብቶቻቸውን ጥለው መምጣታቸው ወደነበሩበት መመለስን አዳጋች እንዳደረገባቸው ይናገራሉ። ቢቢሲ መፈናቀል በተከሰተበት የበሎጂ ጋንፎይ ወረዳ ተገኝቶ መረዳት እንደቻለው የተመላሾቹ ቁጥር ከስድሳ አይዘልም፤ ከእነዚህም መካከል አርባ አምስት ያህሉ ብቻ ከአራት መቶ ኪሎ ሜትር በላይ እርቃ ከምትገኘው የባህር ዳር ከተማ የተመለሱ ሲሆን አስራ አምስት አባዎራዎች ደግሞ ተጠልለውባት ከነበረችው የወረዳው መዲና ሶጌ ከተማ የተመለሱ መሆናቸውን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፀጋየ ተሰማ ገልፀውልናል። "በእኛ ክልል እና በአማራ ክልል ባለስልጣናት የተቋቋመ ኮሚቴ አለ፤ 'ኮሚቴውም ተፈናቃዮቹን ለመመለስ በመስራት ላይ ይገኛል" ሲሉ አስተዳዳሪው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከሕዝብ ጋር በተደረገ ውይይት ፀጥታ መሪ የስጋት ምንጭ መሆኑን መረዳታቸውን የሚያስረዱት አቶ ፀጋየ በስፍራው በቂ የሆነ ፀጥታ አስከባሪ ኃይል መስፈሩንም ጨምረው ገልፀዋል። የአማራ ክልልን ወክለው ተፈናቃዮችን የመመለስ እና የማቋቋማው ሥራን ሲያስተባብሩ ያገኛናቸው በቤንሻንጉል ክልል የብዐዴን ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተመስገን ኃይሉ የፀጥታ ችግሮችን ከመቅረፍ በዘለለ ተመላሾቹ ወደቀደመ መተዳደሪያቸው እስኪመለሱ ድጋፍ የመቸር አስፈላጊነት አፅንዖት ሰጥተው ይናገራሉ። እርሳቸው እንደሚሉት ወደ ቤንሻንጉል ጉምዝ ተመልሰው ለሄዱ ሰዎች የቤት ውስጥ ቁሳ ቁስ እየተከፋፈለ ይገኛል፤ የእርሻ ወቅት በመሆኑ ጸረ አረምና መርጫ ተገዝቷል፤ የሳርና እንጨት ቤት የተቃጠለባቸው ሰዎች ተለይተው በክልሉ ድጋፍ ቤት ይሰራላቸዋል። ይሁንና ወደ ቤንሻንጉል ተመለሱ የሚለውን ጥሪ ያልተቀበሉ 136 አባዎራዎች እስካሁንም በባህር ዳር ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴዴራል ተጠልለው እየኖሩ ሲሆን፥ በአማራ ክልል ልዩ ልዩ ወረዳዎች ወደሚገኙ ዘመዶቻቸው የሄዱ ተፈናቃዮች መኖራቸውንም አረጋግጠናል። ለተፈናቃዮቹ የሚደረገውን ድጋፍ፥ ከሶጌ ከተማ አስራ ሁለት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደምትገኘው የበለው ዴዴሳ ቀበሌ ሄድን እውነታውን ለመመልከት ያደረግነው ጥረት የዞኑ ባለስልጣናትን ይሁንታ ሳያገኝ ቀርቷል። ለሰዓታትን እንድንቆይ በተገደድንበት የወረዳው አስተዳደር ፅህፈት ቤት ውስጥ ውጥረት የነገሰበት ስብሰባ በእሁድ ቀን ሲከናወን ያስተዋልን ሲሆን፥ ከአስተዳደራዊ ችግሮች ጋር በተያያዘ በዞኑ በቅርቡ ሹም ሽር ሊኖር እንደሚችል የፅህፈት ቤቱ ሰራተኞች ግምታቸውን አካፍለውናል። በካምሽ ዞን በጉምዝና በአማራ እንዲሁም በኦሮሞ ተወላጆች መካከል ለዓመታት የዘለቀ መሬት ተከራይቶ በማረስና ምርትን በመካፈል ላይ የተመሰረተ የስራ ግንኙነት እንዳለ ነዋሪዎችም የአጥቢያው ባለስልጣናትም ያስረዳሉ። ይሁንና የስራ ቅራኔዎች እንዲሁም ግለሰባዊ ግጭቶች የብሄር መልክ የሚይዙባቸው አጋጣሚዎች ጥቂት እንዳልሆኑም ይመሰክራሉ። ከወር በፊት ከባህር ዳር ወደ ቤንሻንጉል የተመለሰውና በስልክ ያነጋገርነው አርሶ አደር ግን ቃል የተገባውን ያህል ማቋቋሚያ አለማግኘቱን ወደ ግብርናው ለመመለስ አለመቻሉንም ገልጾልናል። ባህር ዳር ሳለ "ወንድሞቻችንን፣ እህቶቻችንንና ንብረታችንን ወዳጣንበት ቦታ አንመለስም" ቢሉም ነገሮች እንደሚመለሱ ቃል ተገብቶላቸው ነበር። "ሙሉ ቀለብ ይሰጣችኃል። ቤት ይሰራላችኋል። ለወደመባችሁ ንብረት ካሳ ይሰጣችኋል ተብለን ነበር" ይላል። ወደ ቤንሻንጉል ሲመለስ ግን የጠበቀውን እንዳላገኘ ይናገራል። ሰፊ ቤተሰብ ላለው ሰው ከማይበቃ ስንዴ፣ ድስትና ጄሪካን ያለፈ የተሰጣቸው ባለመኖሩ ያማርራል። "ቤት ያላችሁ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ ተባለ። ቤት የሌለን በረንዳ ላይ ዝናብ እየመታን፣ ረሀብ እየተጫወተብን ነው" ሲል የጠበቀውን ስላላገኘ እሮሮውን ያሰማል። በሌላ በኩል በዚያው በቤንሻንጉል ክልል ማንዱራ ወረዳ ትናንትና በጉሙዝ በተቀሰቀሰ ግጭት ሰዎች መሞታቸውን ከወረዳው አስተዳዳሪ አቶ መልኬ ማረጋግጥ ችለናል። አስተዳዳሪው ዝርዝር መረጃ ለመስጠት ግን ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
news-57068234
https://www.bbc.com/amharic/news-57068234
የናይጄሪያዋ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ሽቶዎች አጠቃቀም ዙሪያ ማስጠንቀቂያ ሰጠች
የናይጄሪያዋ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ሽቶዎች አጠቃቀም ዙሪያ ማስጠንቀቂያ ሰጠች
በጸሎት ወቅት ሻማ እና ሽቶ በፈጠሩት እሳት አንድ ግለሰብ መሞቱን ተከትሎ ከናይጄሪያ ታላላቅ አብያተ ክርስቲያናት አንዷ ማስጠንቀቂያ እንድትሰጥ ተገዳለች፡፡ ነጭ ልብስ በመልበስ በባዶ እግራቸው መንፈሳዊ አገልግሎት በመከታተል የሚታወቁ ምዕመናን ያሏት የሰለስቲያል የክርስቶስ ቤተክርስቲያን በምዕራብ ናይጄሪያ ስሟ የገነነ ነው። በመላው ናይጄሪያ እና በአንዳንድ ሃገራትም ቤተ እምነቶች አላት፡፡ ካዮዴ ባድሩ ባለፈው ሰኞ ሌጎስ በሚገኘው ቤተክርስቲያን በግል በተዘጋጀ መንፈፈሳዊ ዝግጅት ላይ ሻማዎችን በማብራት ሲጸልዩ ነበር አደጋው የደረሰባቸው፡፡ የቤተክርስቲያኗ አባቶች ለባድሩ እየጸልዩ ነበር። ጸሎቱን የሚመሩት ቄስ ጠጋ ብለው ሽቶውን ሲነሰንሱበት አቅራቢያው ባለው ሻማ ምክንያት ሳይቀጣጠል አልቀረም ተብሎ ይታሰባል፡፡ አብዛኛዎቹ የእምነቱ ተከታዮች ተቀጣጣይ ከሆኑ እንደ ጥጥ እና ሐር ካሉ ጨርቆች የተሠሩ ነጭ ልብሶችን ይለብሳሉ። በዕለቱ ተመሳሳይ ነጭ ልብስ ለብሰው የነበሩት ባድሩን እሳቱ በፍጥነት ነበር ያቃጠላቸው፡፡ በደረሰው ቃጠሎ ህክምና ሲያገኙ ቆይተውም ሐሙስ ዕለት በሆስፒታል ህይወታቸው አልፏል፡፡ የቤተክርስቲያኗ አስተዳዳሪ ቄስ ኢሞሌሚታን ኦጆ ከቢቢሲ ፒጂን ጋር በነበራቸው ቆይታ የጸሎቱን ፕሮግራሙን የመሩት አባት እና በቦታው የነበሩ አንዳንድ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል፡፡ ቤተክርስቲያኗ በጸሎት ፕሮግራሞች ወቅት ብርሃንን እና ጥሩ ሽታን ለማመላከት ሻማዎችን እና ሽቶዎችን ትጠቀማለች፡፡ ምዕመናን በአብዛኛው የራሳቸውን ሽቶ የሚጠቀሙ ቢሆንም አብያተ ክርስቲያኗ ለሽያጭ ያቀረበችውንም የሚጠቀሙ አሉ፡፡ ሽቶዎቹ ከመጠን በላይ የማይነሰነስ ሲሆን ምዕመናኑም ከውሃ ጋር እንዲቀልሏቸው ይመከራሉ፡፡ የባድሩ ሽቶ በዚህ ረገድ ስለመዘጋጀቱ የታወቀ ነገር የለም፡፡ ቤተክርስቲያኗ ባሰራጨችው መግለጫ "ከበራ ሻማ ጋር ለመርጨት የተዘጋጁ መንፈሳዊ ሽቶዎች ውሃ ሊቀላቀልባቸው ይገባል" ብላለች፡፡ በመግለጫዋም "መንፈሳዊ ሽቶዎችን መርጨት ወይም ማፍሰስ የሰለስቲያል የክርስቶስ ቤተክርስቲያን መሠረታዊ ሥርዓቶች አካል ያልሆነ ከውጭ የመጣ ባህል ነው" ስትል አክላለች፡፡ ቱጃሩ ባድሩ መኖሪያቸው ዱባይ ሲሆን ለምስጋና ስነ ስርዓት ነበር አባል ወደሆኑበት ቤተክርስትያን ያቀኑት፡፡ ሌላ ዘገባ ደግሞ ባለሃብቱ ወደ ናይጄሪያ ያቀኑት በእሳቸው ድጋፍ ትምህርታቸውን ከኪነጥበብ እና ቴክኖሎጂ አካዳሚ ያጠናቀቁ 40 ተማሪዎች የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ለመገኘት ነው ሲል አስነብቧል፡፡ በቤኒን ፖርቶ-ኖቮ እአአ በ 1947 በሬቨረንድ ሳሙኤል ቢሌሆ ኦሾፋ የተቋቋመችው የሰለስቲያል የክርስቶስ ቤተክርስቲያን በመላው ዓለም ቅርንጫፎች እንዳሏት ትናገራለች፡፡
news-50191988
https://www.bbc.com/amharic/news-50191988
ዴኒስ ንክሩንዚዛ፡ የብሩንዲ ቀዳማዊት እመቤት በመካኖች ላይ የሚደርስን ጥቃት በመቃወም አቀነቀኑ
የብሩንዲ ቀዳማዊት እመቤት ዴኒስ ንክሩንዚዛ የልጅ እናት መሆን ባልቻሉ ሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በመቃወም ለሚካሄደው ዘመቻ አቀንቅነዋል።
የሙዚቃው ትዕይንት አንዲት ሚስት ባሏ ከደጅ ወደ ቤት ሲገባ ስትቀበለውና እራት እንዲመገብ ስትጋብዘው፤ ከዚያም በተጀመረ ጭቅጭቅ ሲደበድባት በማሳየት ይጀምራል። • "ሊወልዱ እያማጡም የእናታቸውን ስም ነው የሚጠሩት" ሚዲዋይፍ • ላጤ እናት መሆን የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ሴቶች "በዚህ ቤት ውስጥ አንቺ ምንም እርባና የሌለሽ ሴት ነሽ" ይላል ባልየው። "የሌሎች ሴቶች ሆድ በህፃናት ሲያዝ፤ የአንች ሆድ ግን ሁል ጊዜ የሚሞላው በጥራጥሬ ነው" ሲልም ይዘልፋታል። ከዚያም የ49 ዓመቷ ቀዳማዊት እመቤት ዴኒስ፤ ነገር ለማብረድ ወደ ጥንዶቹ ሳሎን በማምራት ጣልቃ ይገባሉ። "ስለ መካንነት ማወቅ የሚቻለው ዶክተር ካማከርን በኋላ ነው" ሲሉ ሲያሸማግሉ ይሰማሉ። "መካንነት በሴትም ሆነ በወንድ ላይ ሊከሰት ይችላል" ሲሉም ያክላሉ። በቀጣዩ ትዕይንት ላይ ደግሞ ቀዳማዊት እመቤቷ ከሌሎች ሙዚቀኞች ፣ ዳንሰኞችና ጋር ሲዘፍኑ ይታያሉ። "ሴቶች የተፈጠሩት እናት ለመሆን ብቻ አይደለም፤ ከዚህ በላይ መሆን ይችላሉ" ተቀባዮቹ ይከተላሉ። ከጎርጎሳውያኑ 1994 ጀምሮ ከፕሬዚዳንት ፔሬ ኑክሪንዚዛ ጋር በትዳር ተጣምረው የሚኖሩት ቀዳማዊት እመቤት ዴኒስ፤ ባሎች ለሚስቶቻቸው ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። "መካንነት ሁለቱንም ጥንዶች የሚመለከት ሲሆን ፤ የግጭት መነሻም መሆን የለበትም' ሲሉ አዚመዋል። • የሴቶችና ወንዶች የኢኮኖሚ እኩልነት እንዴት ይስፈን? የአምስት ልጆች ወላጆችና በርካታ ልጆችን በማደጎ ያሳደጉት ጥንዶቹ ፕሬዚደንት ፔሬ ንክሩንዚዛ እና ዴኒስ ንክሩንዚዛ ፤ ኃይማኖታዊ በመሆናቸውና መደበኛ የፀሎት ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ይታወቃሉ። የስደተኛ ጉዳዮች ኃላፊ የነበሩት ቀዳማዊት እመቤቷ ሰባኪም ነበሩ። አሁን በቅርቡ ያወጡትና 'ሴቶች ልጅ ከመውለድም በላይ ናቸው' የሚለው ዜማቸው በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በዋትስ አፕ' የተለቀቀ ሲሆን በእንዲህ ዓይነት ተንቀሳቃሽ ምስል ዓለማዊ መዝሙር ሲዘምሩም ይህ የመጀመሪያቸው ነው ተብሏል። የ4 ደቂቃ ርዝማኔ ያለው ይሄው ሙዚቃ በፌስቡክ ገፆችም ላይ ተንሸራሽሯል። ቀዳማዊት እመቤቷ አሁን በለቀቁት ሙዚቃ ከማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ምስጋና የተቸራቸው ቢሆንም፤ አንዳንዶች ግን ጥቃቱ በተመሳሳይም በወንዶችም ላይ ይፈፀማል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። በብሩንዲ አባታዊ ስርዓት [የወንዶች የበላይነት የሰፈነበት] ማህበረሰብ ጥንዶች ጋብቻ ከመሠረቱ በኋላ ልጆች መውለድ ካልቻሉ በራሳቸው እንዲያፍሩ እና እንዲሸማቀቁ ተፅዕኖ ይደረግባቸዋል። በአብዛኛው የመካንነት ምንጯም ሴቷ ችግር እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል። አንዳንድ ጥንዶችም በዚህ ምክንያት ለመለያየት ይገደዳሉ።
news-52370483
https://www.bbc.com/amharic/news-52370483
ኮሮናቫይረስ፡ የዓለም ጤና ድርጅት ሠራተኛ የኮቪድ-19 ናሙና ሲሰበስቡ ተገደሉ
የዓለም ጤና ድርጅት ሹፌር በማይናማር የኮቪድ-19 ናሙና እየሰበሰቡ ሳለ ተገደሉ።
ግለሰቡ ፓዩ ሶኔ ዊን ማኡንግ የሚባሉ ሲሆን፣ የተባበሩት መንግሥታት ዓርማን ያነገበ መኪና እያሽከረከሩ እያለ በራክሂኔ ግዛት በተተኮሰባቸው ጥይት መሞታቸው ታውቋል። የተባበሩት መንግሥታት በመንግሥት ወታደሮችና በአራካን ብሄርተኛ አማፂያን መካከል ሰሞኑን ግጭት ተቀስቅሶ በርካታ ንፁኃን መሞታቸውን ገልጧል። • ለሕክምና ከሄዱበት ሕንድ መመለስ ያልቻሉ ኢትዮጵያዊያን ችግር ላይ ነን አሉ • ዶ/ር ቴድሮስ ፖለቲካዊ አለመግባባት ህይወት ለማዳን የሚደረገን ጥረት እንዳያደናቅፍ አስጠነቀቁ • የ68 ዓመቷ ናይጄሪያዊት አዛውንት መንታ ልጆች ተገላገሉ ሰኞ ዕለት በተገደለው የዓለም ጤና ድርጅት ሹፌር ሞት የማይናማር ወታደሮችም ሆኑ የአራካን አማፂያን እርስ በርስ እየተወነጃጀሉ ይገኛሉ። የማይናማር ወታደርም ሆነ የአርካን አማፂ በግድያው እጃችን የለበትም ሲሉ አስተባብለዋል። የማይናማር ወታደር ቃል አቀባይ የሆኑት ማጅ ጄን ቱንቱን ኒይ፣ ጦሩ የተባበሩት መንግሥታትን መኪና የሚያጠቃበት ምክንያት የለውም ብለዋል። "ለእኛ ለአገራችን ነው የሚሰሩት" በማለት ለሮይተርስ የተናገሩት ቃል አቀባዩ " ለዚያም ኃላፊነት አለብን" ብለዋል። በማይናማር የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ፅህፈት ቤት የ28 ዓመቱ ሹፌር፣ ሚንብያ ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ በወታደራዊ ፍተሻ ጣቢያ አቅራቢያ መገደሉን ጠቅሶ "እጅጉን ማዘኑን" ገልጿል። በፌስቡክ ላይ እንደተገለፀው ከሆነ የተባበሩት መንግሥታት ሹፌር የሞተበትና አንድ የመንግሥት ሠራተኛ የቆሰለበት ይህ ጥቃት የደረሰው የአገሪቱ "ጤናና ስፖርት ሚኒስቴርን ለማገዝ" ከሲትዌ ወደ ያንጎን የኮቪድ-19 ቅኝት ናሙና ለመሰብሰብ እየሄዱ ሳለ መሆኑን ገልጾ፣ ጥቃቱን ማን እንደፈፀመ ያለው ተጨማሪ ነገር የለም። የሹፌሩ አባት ህታይ ዊን ማኡንግ "አዝኛለሁ" በማለት ልባቸው መሰበሩን ተናግረዋል። "ራሴን ለማረጋጋት እየሞከርኩ ያለሁት ግዳጁን እየተወጣ እያለ መሞቱን በማሰብ ነው" ያሉት አባቱ አክለውም "ማንም ሰው ለመሄድ ፈቃደኛ ባልሆነበት ወቅት በግጭት መካከል ነው የሄደው" ብለዋል። ዩናይትድ ኪንግደምም ሆነ አሜሪካ ዓለም አቀፉን ወረርሽኝ ለመከላከል እንዲቻል ግጭቱ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል። በማይናማር እስካሁን ድረስ 80 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲገለጽ አራት ሰዎች መሞታቸው ተመዝግቧል። የአራካን አማፂያን ቡድሂስት ሲሆኑ ላለፉት ሁለት ዓመታት ራሳቸውን የማስተዳደር ነፃነታቸው እንዲከበር እየተዋጉ ነው። አማፂያኑ ለአንድ ወር የተኩስ አቁም ለማድረግ ቢስማሙም መንግሥት ግን ጥያቄያቸውን ውድቅ አድርጎታል።
news-53593978
https://www.bbc.com/amharic/news-53593978
አውሮፓ ሁለተኛ ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ያሰጋታል?
የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን አውሮፓ ሁለተኛ ዙር የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ እንደሚያሰጋት ተናግረው ነበር። ነገር ግን ለዚህ ግምት ማስረጃ ሊሆን የሚችል ነገር አለ?
ሁለተኛ ዙር ወረርሽኝ ተከሰተ ማለት ደግሞ እንደገና በርካቶች ሃዘናቸው ሲመለስ፣ ሲሞቱ ልንመለከት ነው ማለት ነው። ከመጀመሪያው የዓለም ጦርነት በኋላ ተከስቶ የነበረው 'ስፓኒሽ ፍሉ' ያጋጠመው ይሄ ነበር። በሁለተኛ ዙር የጀመረው በሽታው ግን ከመጀመሪያው ይበልጥ ከባድና ገዳይ ነበር። በዓለም ጤና ድርጅት የሚሰሩት ማርጋሬት ሃሪስ ግልጽ ለማድረግ እንደሞከሩት የመጀመሪያው ዙር ወረርሽኝ በራሱ ገና በመላው ዓለም እየተሰራጨ ነው የሚገኘው። እንደ ደቡብ ኮሪያ እና ሲንጋፖር ያሉ አገራት ገና ከጅምሩ ጠበቅ ያሉ እርምጃዎችን በመውሰድና ንክኪ ያላቸው ሰዎችን በቶሎ በማግኘት የቫይረሱን ስርጭት ከሌሎች አገራት በተሻለ መቆጣጠር ችለዋል። ነገር ግን እንደ ዩኬ፣ ፈረንሳይ፣ ስፔን እና ጣልያን ያሉት አገራት ደግሞ እንቅስቃሴን ሙሉ በሙሉ መገደብ ላይ በማተኮር ሰርተዋል። ይህን ያደረጉበት ምክንያት ደግሞ ረቀቅ ያለ ተላላፊ በሽታዎችን መከታተልና መቆጣጠር የሚያስችል የጤና ስርአት ስላልነበራቸው ነው። ምንም እንኳን ትንሽ ዘግየት ያለ ቢመስልም እነዚህም አገራት ቫይረሱን በመቆጣጠር ረገድ በርካታ እምርታዎችን አስመዝግበዋል። ነገር ግን አሁንም ቢሆን ወረርሽኙ በድጋሚ የመከሰት ምልክቶችን እያሳየ ነው፤ በተለይ ደግሞ ስፔን ውስጥ። በኖርዊች ሜዲካል ትምህርት ቤት መምህርና የኮቪድ ባለሙያ የሆኑት ፕሮፌሰር ፖል ሀንተር እንደሚሉት ወረርሽኙ ሁለተኛ ዙር ላይ አልደረሰም። አሁን እየሆነ ያለውን እንዴት እናስረዳው? ተብለው የተጠየቁት ፕሮፌሰሩ '' ከመዘናጋት ጋር አብሮ የሚመጣ የስርጭት መጠን መጨመር እንጂ ሁለተኛ ዙር አይደለም'' ብለዋል። ይህንን ወረርሽኝ ለመቆጣጠር በዋነኛነት ቫይረሱ ያለባቸውን በምርመራ ማግኘትና ንክኪዎችን መለየት፣ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ እና የግልልና የአካባቢን ንጽህና መጠበቅ ወሳኝ ናቸው። ስለዚህ መንግሥታትና ዜጎች እነዚህን እርምጃዎች መውሰድ ላይ ሲዘናጉ ነው ቁጥሩ የሚጨምረው እንጂ ሁለተኛው ዙር መጥቶ አይደለም ይላሉ የዘርፉ ባለሙያዎች። አክለውም በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ገና ከዚህም በላይ እየጨመረ ሊሄድ ይችላል ይላሉ። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት እየጠበቀ የሚከሰት ችግር ሳይሆን ትልቅ ‘ማእበል’ መሆኑን አስጠንቅቋል። የዓለም ጤና ድርጅት በበኩሉ ወረርሽኙ እንደ ጉንፋን ወይም ኢንፍሉዌንዛ ወቅትን ጠብቆ የመጥፋት እና የመመለስ ባሕርይ ስለሌለው ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አስጠንቅቋል። በተለይም ደግሞ በፈረንጆቹ የበጋ ወቅት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችና መዘናጋቶች አሳሳቢ መሆናቸውንና ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ድርጅቱ አስታውቋል።
52450158
https://www.bbc.com/amharic/52450158
በዩናይትድ ኪንግደም ኮሮናቫይረስ በተያዙ ህፃናት ላይ ያልተለመደ ምልክት መታየቱ ተገለፀ
የብሔራዊ ጤና አገልግሎት (ኤንኤችኤስ) የሕክምና ባለሙያዎች ሕፃናት ላይ ያልተለመደ ነገር ግን አደገኛ የሆነ ምልክትን በሚገባ እንዲመለከቱ አስጠነቀቀ። ይህ ለዶክተሮቹ የተገለፀው ምናልባት ያልተለመደው ምልክት የኮሮናቫይረስ ኢንፌክሽን ምልክት ሊሆን ይችላል በሚል ነው።
ለጠቅላላ ሐኪሞች በአስቸኳይ የተላከው መልዕክት እንደሚለው ከሆነ በሎንዶንም ሆነ በዩናይትድ ኪንግደም የተለያዩ አካባቢዎች በጽኑ ሕሙማን ክፍል የሚገኙ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሕፃናት ያልተለመዱ ምልከቶች እንደሚታይባቸው ይጠቅሳል። ይህም ከፍሉ ምልክት በተጨማሪ "የተለያዩ አካል ክፍሎች በአንድ ላይ መቆጣት"መሆኑን በመጥቀስ እንዲህ አይነት ምልክት ከታየባቸው ህፃናት መካከል አንዳንዶቹ በኮሮናቫይረስ ተይዘው መገኘታቸውን ይገልፃል። • ስለቫይረሱ ከሚናፈሱት በጥቂቱ፡ የአሪቲ መድኃኒትነት፣ የአለምን ህዝብ መቆጣጠሪያ መንገድ • በኒውዮርክ የመድኃኒት መደብሮች የኮሮና ምርመራ ሊጀመር ነው • የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ማድረግ የግድ አስፈላጊ ሊሆን ነው? በርግጥ ቁጥራቸው ዝቅተኛ ነው ከማለት ውጪ ምን ያህል ህፃናት እንዲህ አይነት ምልክት እንዳሳዩ የተገለፀ ነገር የለም። በእንግሊዝ የብሔራዊ ጤና አገልግሎት (ኤንኤችኤስ) ሐኪም የሆኑት ስቴፈን ፖዊስ እንዲህ ያልተለመደ እና ጽኑ ሕመም በህፃናት ላይ ስለመታየቱ የተለያዩ ሪፖርቶችን ማየታቸውን ይናገራሉ። " እነዚህን ሪፖርቶች የተመለከትነው ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ነው። ባለሙያዎቻችንን ጉዳዩን አጽንኦት ሰጥተው በአስቸኳይ እንዲመለከቱት ጠይቀናል" ብለዋል። በእንግሊዝ ብሔራዊ ጤና አገልግሎት በኩል የወጣው ሪፖርት በሕፃናት ላይ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ የተለያዩ አካላት መቆጣት " እየጨመረ የመጣ አሳሳቢ ጉዳይ" ብሎታል። እነዚህ በተለያየ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ህጻናት በከፍተኛ ሁኔታ መታመማቸው ተገልጿል። ከፍተኛ የሆነ ሙቀት፣ ዝቅተኛ የደም ግፊት፣ የሰውነት ሽፍታ እንዲሁም ለመተንፈስ መቸገር እንደሚታይባቸው ተገልጿል። አንዳንዶቹም የሆድ እቃ ህመም፣ ማስመለስ ወይንም ተቅማጥ፣ የልብ አካባቢ ማቃጠል እንዲሁም ያልተለመደ የደም ውጤት እንደሚስተዋልባቸው ተገልጿል። ባለሙያዎች እነዚህ ምልክቶች የሚታዩት ሰውነት የተለያዩ ኢንፌክሽኖችን በሚዋጋበት ወቅት መሆኑን ይገልፃሉ። የተላለፈው መልዕክት እንዲህ አይነት ምልክት የሚያሳዩ ህፃናት በፍጥነት ሕክምና ማግኘት አለባቸው ይላል። ባለሙያዎች አክለውም በጣም ጥቂት ቁጥር ያላቸው ህፃናት ብቻ በኮሮናቫይረስ በጽኑ ታመው ታይተዋል፤ ከመላው ዓለም የሚመጣ መረጃ እንደሚያሳየው በዓለም ላይ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ቁጥር አንፃር ህፃናት በጣም ጥቂት ናቸው። ዶ/ር ናዚማ ፓታን በካምብሪጅ የህጻናት ጽኑ ሕሙማን አማካሪ ሲሆኑ በስፔንና በጣሊያን ያሉ ባለሙያዎች ተመሳሳይ ምልክት ያሳዩ ሕፃናትን ማግኘታቸውን ሪፖርት ማድረጋቸውን ገልፀዋል። " በአጠቃላይ ህፃናት ኮሮናቫይረስን ተከትሎ የሚመጣን ከባድ የሳንባ ኢንፌክሽን የመቋቋም አቅማቸው ከፍተኛ መሆኑን አስተውለናል፤ ወደ ጽኑ ሕሙማን ክፍልም የገቡ ህፃናት ቁጥር በጣም አነስተኛ ነው" ብለዋል። አሁን የምንጠብቀው ይላሉ ዶ/ር ናዚም እንዲህ አይነት ምልክት የሚያሳዩ ህፃናት ከባክቴሪያ ኢንፌክሽን ጋር የተያያዘ እና ህይወትን አደጋ ላይ የሚጥለው (toxic shock syndrome) እና የደም ቧንቧንና ልብን የሚያጠቃው የካዋስኪ በሽታ ምልክቶችን ማሳየት አለማሳየታቸውን ነው ብለዋል።
news-49278449
https://www.bbc.com/amharic/news-49278449
ናይጄሪያ ውስጥ 'ሰልፊ' ሲነሱ የነበሩ ሦስት ተማሪዎች ሞቱ
ናይጄሪያ ውስጥ በአንድ ድልድይ ላይ ሆነው እራሳቸውን በሞባይል ስልካቸው ፎቶ (ሰልፊ) ሲያነሱ ከነበሩ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል ሦስቱ ሕይወታቸው አለፈ።
ተማሪዎቹ በስልካቸው ፎቶ ለመነሳት ተሰብስበው ነው አደጋው የደረሰው በሰሜናዊ ናይጄሪያ የሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሞት ምክንያት የሆነው ተሰብስበው እራሳቸውን ፎቶ ሲያነሱበት የነበረው ድልድይ ተደርምሶ እንደሆነ 'ፐንች' የተሰኘው ጋዜጣ ዘግቧል። • ወጣቱ እራሱን 'ሰልፊ' ሲያነሳ ህይወቱ አለፈ • 'ሰልፊ' ለደህንነት ሲባል ሊከለከል ነው ቡዋቺ በምትባለው የናይጄሪያ ግዛት ውስጥ በሚገኘው የአቡባካር ታፋዋ ባላዋ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተማሪ የሆኑት ወጣቶች የሞቱት በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የመማሪያ ክፍሎችንና የተማሪዎቹን መኖሪያ የሚያገናኛው ከብረት የተሰራ ድልድይ ሰኞ እለት በመፍረሱ ነው። የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዝዳንት ሙሃመድ አብዱልአዚዝ ስለአደጋው ሲናገሩ "ተማሪዎቹ ከባድ ዝናብ ከጣለ በኋላ በድልድዩ በኩል ሲያቋርጡ አካባቢው ለፎቶ አመቺ ነው በማለት በሞባይሎቻቸው ፎቶ መነሳት ጀመሩ" ብለዋል። ከዚያም ከ10 እና ከ15 ሰው በላይ መያዝ በማይችለው የመተላለፊያ ድልድይ ላይ ከ30 በላይ ተማሪዎች ተሰብስበው ፎቷቸውን በማንሳት ላይ ሳሉ ነው አደጋው የደረሰው ይላሉ ምክትል ፕሬዝዳንቱ። • "ሰልፊ" ፎቶ እና የሞራል መላሸቅ • ማላዊቷ ነርስ በማዋለጃ ክፍል 'ሰልፊ' በመነሳቷ ከስራ ታገደች "ድልድዩ ሲሰራ ከባድ ጭነት እንዲሸከም ሳይሆን ተማሪዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ አቋርጠው ከአንደኛው ህንጻ ወደሌላኛው እንዲሸጋገሩበት ብቻ ነበር" ሲሉ ለድልድዩ መደርመስ መሸከም ከሚችለው በላይ ሰው ስለተሰበሰበ መሆኑን ተናግረዋል- ምክትል ፕሬዝዳንቱ። ስለአደጋው የወጡ አንዳንድ ዘገባዎች ከሞቱት ሦስት ተማሪዎች በተጨማሪ የተወሰኑ ተማሪዎች እንዳልተገኙ ቢያመለክቱም ምክትል ፕሬዝዳንቱ ግን ሐሰት መሆኑን ገልጸዋል። በዚህ በተማሪዎቹ ላይ በደረሰው አደጋ ምክንያት ማክሰኞ ዕለት የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ እንዳደረጉና ወደ አንደኛው የዩኒቨርሲቲው ግቢ የሚያስገቡ መንገዶችን በመዝጋት ሠራተኞች ወደ ውስጥ እንዳይገቡ አግደው እንደነበር ተገልጿል።
news-50654887
https://www.bbc.com/amharic/news-50654887
ኬንያዊቷ ታዳጊ አንድን ግለሰብ ከጎርፍ ለማዳን ስትጥር ህይወቷ አለፈ
አንዲት ኬንያዊት ታዳጊ አንድን ግለሰብ ከጎርፍ ለማዳን ስትጥር ሰምጣ ህይወቷ አልፏል።
ከመዲናዋ ናይሮቢ ወጣ ብሎ በሚገኘው ካንዲሲ የሚባል ወንዝ ገብታ ነው ህይወቷ ያለፈው፤ የአስራ ዘጠኝ ዓመቷ አን ዱኩ። አን እየተገነባ በነበረ ድልድይ ስር አድኑኝ እያለ በመማፀን ላይ የነበረ ግለሰብን ጩኸት ሰምታ ነው ለእርዳታው የመጣችው። ግለሰቡ ህይወቱ ቢተርፍም እሷ ግን ወንዝ ውስጥ በመውደቋ ህይወቷ አልፏል። •"የቱሪስት ማግኔት" የሆነችው ቬኒስ ከተማን ጎርፍ እያስጨነቃት ነው •መሬት መንሸራተትና ጎርፍ በደቡብ ኢትዮጵያ ጥፋት አደረሰ እናቷ ኤልዛቤት ሙቱኩ ለቢቢሲ ጋዜጠኛ እንደተናገሩት "ወንዝ ውስጥ ስትታገል አየሁዋት፤ ህይወቷንም ለማዳን ሞክሬያለሁ። 'አና አና' ብዬ እየጠራሁዋት ነበር። እሷንም ለመጎተት እንዲያስችለኝ እንጨት መወርወር አስቤ ነበር። ነገር ግን የወንዙ ማዕበል በጣም ከፍተኛ ስለነበር፤ ልጄን ጥርግ አድርጎ ወሰዳት" በማለት እንባ እየተናነቃቸው ተናግረዋል። በዚህ ሳምንት ከሰኞ ጀምሮ በምሥራቅ አፍሪካ በከፍተኛ ሁኔታ ሲጥል የነበረውን ዝናብ ተከትሎ ነው ወንዙ ከመጠን በላይ የሞላው። ነገር ግን ነዋሪዎች እንደሚሉት ባለፉት ሁለት ዓመታት ሰባት ሰዎች በወንዙ ተወስደው ለሞት ተዳርገዋል። •ኢትዮጵያ ሳተላይት ማምጠቅ ለምን አስፈለጋት? •በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት ወንዙን ለመሻገር ያገለግል የነበረው አሮጌ ድልድይ ከሁለት ዓመት በፊት የፈረሰ ሲሆን አዲሱ ድልድይ ባለመጠናቀቁ ነዋሪዎች ድንጋይ ከላይ በመደርድር እየተሻገሩ መሆኑ ተገልጿል። የሟቿ ታላቅ እህት ማርያም ዜኔት ለቢቢሲ እንደገለፀችው መንደራቸውን ከዋናው ገበያ ጋር የሚያገናኘው ድልድይን ማጠናቀቅ የአካባቢው ባለስልጣናት ኃላፊነት ቢሆንም፤ ይህንን ባለማድረጋቸውም ጥፋተኞች ናቸው ብላለች። "ባለፉት ሁለት ዓመታት ብዙ ሰዎች ድልድዩን ሊያቋርጡ በሚሞክሩበት ወቅት ህይወታቸው አልፏል። ባለስልጣናቱ መጥተው ሃዘናቸውን ከመግለፅ ውጪ ምንም ያደረጉልን ነገር የለም። ዛሬ እህቴ ሞተች? ነገስ ቀጣዩ ማነው? ድልድዩ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ሲሄዱም የሚመላለሱበት ነው። አዲስ መገንባት ካልቻሉ የድሮውን ለምን አፈረሱት?" በማለትም ትጠይቃለች። በልጃቸው ሞት ልባቸው የተሰበረው እናት "በጣም አዝኛለሁ። የወደፊቱ መሪ፤ ወይም መምህር ትሆን ነበር። በዚህ ድልድይ ምክንያት የልጄን ሕይወት ማጣቴ ህመሜን አክብዶታል" ብለዋል።
news-53386498
https://www.bbc.com/amharic/news-53386498
ሱዳን ለ30 ዓመታት የዘለቀውን ጥብቅ የእስልምና ሕግን አሻሻለች
ከ30 ዓመታት በላይ በእስልምና መርሆች ስትተዳደር የነበረችው ሱዳን፤ ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች የአልኮል መጠጥ እንዲጠጡ ከመፍቀዷ በተጨማሪ ሐይማኖት የመቀየር መብትን ጨምሮ በርካታ ለውጦችን ይፋ አደረገች።
ሙስሊም ያልሆኑ ሱዳናውን የአልኮም መጠጥ እንዲጠጡ ተፈቅዶላቸዋል የሱዳን ፍትህ ሚንስቴር ሰዎች ለፈጸሙት 'ኢ-ሞራላዊ ተግባር' በአደባባይ እንዲገረፉ የሚያዘው ትዕዛዝ እንዲቆም መታወጁንም አስታውዋል። የፍትህ ሚንስትሩ ነስረዲን አብዱለባሪ "የሰዎችን ሰብዓዊ መብት የሚጥሱ ሕጎችን በሙሉ እናስወግዳለን" ብለዋል። ቀደም ሲል ሱዳን የሴት ልጅ ግርዛትን ሕገ ወጥ ድርጊት በማለት ከልክላለች። በአዲሱ ሕግ መሠረት ሴቶች ጉዞ ለማድረግ ከወንድ የቤተሰብ አባል ፍቃድ ማግኘት አይጠበቅባቸውም። አዲሶቹ ሕጎች የትኞቹ ናቸው? ከዚህ ቀደም በሱዳን የአልኮል መጠጥ መጠጣት አይፈቀድም ነበር። አሁን ግን ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች አልኮል በቤታቸው መጠቀም ይችላሉ። ይሁን እንጂ ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች ሙስሊሞች ባሉበት ቦታ አልኮል ሲጠጡ ቢገኙ ቅጣት እንደሚጣልባቸው ተነግሯል። የእስልምና እምነት ተከታዮች ግን አሁንም ቢሆን አልኮል መጠጣት አይፈቀድላቸውም ሲሉ የፍትህ ሚንስትሩ ተናግረዋል። ሙስሊም ያለሆኑ ግሰቦች አልኮል ከመጠቀም ባሻገር፤ መሽጥ እና ከውጪ ማስገባት ይችላሉ ተብሏል። የሱዳን መንግሥት ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰኩት 3 በመቶ የሚሆኑ ሙስሊም ያልሆኑ ሱዳናውያንን መብትን ለመጠበቅ ነው ብሏል። በሱዳን እስከ ዛሬ ድረስ የእስልምን ሐይማኖትን የሚቀይሩ ሰዎች የሞት ቅጣትን ጨምሮ ከባድ ቅጣት ይጣልባቸው ነበር። እንደማሳያ እአአ 2014 ሜሪያም ይህያ ኢብራሂም የተባለችው ሴት ክርስቲያን ወንድ ካገባች በኋላ በስቅላት እንድትቀጣ ተፍርዶባት ነበር። በወቅቱ ነብሰ ጡር የነበረችው ሜሪያም ምንም እንኳ የፍርድ ውሳኔው ሳይፈጸምባት ከሱዳን መውጣት ብትችልም በርካቶች መሰል ሕጎች ተፈጻሚነታቸው እንዲቆም ሲጠይቁ ቆይተዋል። ሜሪያም ይህያ ኢብራሂም ከክርስቲያን ባለቤቷ ጋር ከዚህ በተጨማሪ ሰዎች የማኅበረሰቡን ሞራል የሚጥስ ተግባር ፈጽመዋል ተብለው በአደባባይ እንዲገረፉ የሚያዘው ሕግ እንዲቀር ተወስኗል። እአአ 1980ዎች የተጣለው ጥብቅ የእስልምና ሕጎች በሱዳን ለረዥም ጊዜ ለቆየው የእርስ በእርስ ጦርነት ከዚያም ደቡብ ሱዳን ነጻነቷን እንድታገኝ ምክንያት ነበር። አብዛኛው ደቡብ ሱዳናውያን የክርስትን ወይም ሌሎች ባህላዊ እምነቶች ተከታይ ናቸው።
news-49880787
https://www.bbc.com/amharic/news-49880787
በአሜሪካ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ ላይ አልሻባብ ጥቃት መሰንዘሩ ተነገረ
ከሶማሊያ የወጡ መረጃዎች እንዳመለከቱት የአሜሪካ ወታደሮች የሶማሊያ አቻቸውን በሚያሰለጥኑበት ወታደራዊ ካምፕ ላይ ጂሃዲስት ኃይሎች ጥቃት መፈጸማቸው ተነገረ።
ጥቃት የተፈጸመበት የጦር ሰፈር የአካባቢው ነዋሪዎች እንዳሉት በደቡባዊ ሶማሊያ የታችኛው ሸበሌ ክልል ውስጥ ባሊዶግሌ የአውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ ተኩስና ከባድ ፍንዳታ እንደነበር ተናግረዋል። የእስላማዊ ታጣቂ ቡድኑ አልሻባብ እንደሆነ በተነገረው ድረ ገፅ ላይ ጥቃት አድራሹ ቡድን መኪና ላይ የተጠመደ ቦምብ መግቢያ በሩ አካባቢ ያፈነዱ ሲሆን ከፍንዳታው በኋላ ታጣቂዎቻቸው ወደ ውስጥ እንዲገቡ አድርገዋል። • ቀነኒሳ 'ከሞት እንደመነሳት' ነው ባለው ሁኔታ ማራቶንን አሸነፈ የወታደራዊ ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት ጂሃዲስቶቹ ወደ ኋላ አፈግፍገዋል። አልሻባብ ባወጣው መግለጫ ጥቃቱን እንደፈጸመ አስታውቋል። "በከባድ የሚጠበቀውን ካምፕ ጥሰው ከገቡ በኋላ ወታደራዊ ተቋሙ ውስጥ ከነበሩት የውጪ ኃይሎች ጋር ታተኩሰዋል" ብሏል በመግለጫው። ወታደራዊ ካምፑ ከዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ በስተምዕራብ 100 ኪሎ ሜትሮች ያህል ርቆ የሚገኝ ሲሆን፤ ካምፑ የአሜሪካና የሶማሊያ ልዩ ኃይሎች እንዲሁም የኡጋንዳ ሠላም አስከባሪዎች የሚገኙበት መሆኑም ተነግሯል። • የአማራ ክልል ፖሊስ ረዳት ኮሚሽነር በቁጥጥር ስር ዋሉ በሌላ ዜና አንድ የጣሊያን ወታደራዊ ኮንቮይ ሞቃዲሾ ውስጥ በፍንዳታ ጥቃት እንደደረሰበት የጣሊያን መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል። ነገር ግን በጥቃቱ የደረሰ ጉዳትን በተመለከተ ምንም አልተነገረም። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ አሜሪካ ከአልቃኢዳ ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚነገረው አልሻባብ ላይ የምታካሂደውን የአየር ጥቃት አጠናክራለች። የሶማሊያ ባለስልጣናት እንደሚሉት ቡድኑ በአሜሪካ የሚፈጸምበትን የአየር ጥቃት ለመበቀል ሞዋዲሾ ውስጥ የሚፈጽመውን ጥቃት አጠናክሮታል። የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደሚለው አልሻባብ በሶማሊያ በርካታ ቦታዎችን የተቆጣጠረ ሲሆን አጥፍቶ ጠፊዎችን በመጠቀም ከፍተኛ ጥቃቶችን የመፈጸም አቅም አለው ብሏል።
news-54170608
https://www.bbc.com/amharic/news-54170608
ኢኮኖሚ ፡ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችል ሙዲስ ጠቆመ
ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫውን ማራዘሟን ተከትሎ የተፈጠረው አለመግባባት በአገሪቱ የሚከናወኑ የኢንቨስትመንት ውሳኔዎች ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ሙዲስ የተሰኘው የአሜሪካ የቢዝነስና ፋይናንስ ተቋም ጠቆመ።
አገራዊው ምርጫ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ቢራዘምም ባለፈው ሳምንት በትግራይ ክልላዊ ምርጫ ተካሂዷል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ምርጫውን “ሕገ ወጥ” ማለታቸው እንዲሁም የፌደሬሽን ምክር ቤት "ምርጫው እንዳልተካሄደ ይቆጠራል" እንደተባለ ይታወሳል። ሙዲስ እንዳለው፤ ባለፉት ዓመታት ፖለቲካዊ ውጥረቶች ያስከተሏቸው ግጭቶች የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ስጋት ከፍተኛ አድርጎታል። ሙዲስ ግንቦት ላይ የኢትዮጵያን ነጥብ ከቢ1 ወደ ቢ2 ዝቅ አድርጎታል። ለዚህም በምክንያትነት የተቀመጠው ከውጪ ምንዛሪ ገቢ ይልቅ እዳ ማመዘኑ ነው። ነሐሴ ላይ በኮቪድ-19 ምክንያት ኢትዮጵያ አሉታዊ ግምት ተሰጥቷታል። ወረርሽኙ በግብርና እና በመስተንግዶ ዘርፍ ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ እንዲሁም መንግሥት ገቢው ቢቀንስም ወጪው መናሩ እንደ ምክንያት ተጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ ከግብጽና ከሱዳን ጋር ስምምነት ላይ ሳትደርስ ታላቁ ህዳሴ ግድብን መሙላት መጀሯም ተጠቅሷል። በተያያዥም አስፈላጊ የጥንቃቄ እርምጃዎች ሳይወሰዱ ሙሌቱ መጀመሩ የውጪ አገራት ኢንቨስትመንቶች እንዲቀንሱ ሊያደርግ እንደሚችል ተገልጿል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ቀደም ሲል አሜሪካ ለኢትዮጵያ ለመስጠት መድባ የነበረው እርዳታ ላይ እገዳ መጣሏን ይፋ አድርጋለች። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን በጥሩ ሁኔታ ማስቀጠል መቻሏ ወደ አገሪቱ ኢንቨስትመንት እየሳበ መሆኑን ሙዲስ ገልጿል። ለዓመታት በመሠረተ ልማት ዝርጋታው ዘርፍ የውጪ ኢንቨስትመንት ከሳበች በኋላ፤ አይኤምኤፍ በፍጥነት ምጣኔ ሀብታቸው እያደገ ያሉ ካላቸው የአፍሪካ አገሮች ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያ ትገኝበታለች። ሙዲስ የተባለው ተቋም ዓለም አቀፋዊ በሆኑ በተለያዩ የፋይናንስና ምጣኔ ሃብት እንዲሁም የብድር ጉዳዮች ላይ ምርምሮችን በማድረግ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ በመነሳትም የአገራትን የብድር አዋጭነት ደረጃ ያወጣል። ሙዲስ በዓለም ላይ ካሉ ከሦስቱ ተሰሚነት ካላቸው ተመሳሳይ ተቋማት አንዱ ሲሆን አገራትና መዋዕለ ነዋይ አፍሳሾች ሙዲስን የመሳሰሉ የምጣኔ ሀብትና የፋይናንስ ተቋማት በሚያወጧቸው ትንተናዎችና ደረጃዎች ላይ በመመርኮዝ ቁልፍ ውሳኔዎችን ያሳልፋሉ።
news-52218285
https://www.bbc.com/amharic/news-52218285
የአፍሪካ መሪዎች ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖምን ከትራምፕ እየተከላከሉ ነው
የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም የግድያ ዛቻ እና የዘረኛ ንግግር ጥቃት እየተሰነዘረባቸው መሆኑን ተናገሩ።
ዶ/ር ቴድሮስ "የግድያ ዛቻ ደርሶብኛል፤ እኔ ግን ግድ አይሰጠኝም" ሲሉ የተቃጣባቸውን ጥቃት ጠንከር ባሉ ቃላቶች በሰጡት መግለጫ አጣጥለዋል። "ከሁለትና ከሦስት ወር በላይ ዘረኛ ጥቃቶች ተሰንዝረውብኛል። ጥቁር፣ ባርያ ተብያለሁ። እውነቱን ለመናገር እኔ በጥቁርነቴ እኮራለሁ። የሚባለው ነገርም ግድ አይሰጠኝም" ሲሉም አክለዋል። "በዘረኛ ንግግር በግል ጥቃት ሲደርስብኝ የበታችነት ስሜት ስለማይሰማኝ ምንም አይመስለኝም። ምክንያቱም እኔ ኩሩ ጥቁር ነኝ።" ኃላፊው በሰጡት መግለጫ ላለፉት ሦስት ወራት እሳቸው ላይ ያነጣጠሩ ዘለፋዎች እንደተሰሙ ገልጸዋል። ሆኖም ግን እሳቸውን የሚያሳዝናቸው አህጉሪቱ ላይ የተቃጡ ጥቃቶች እንደሆኑ አክለዋል። "መላው ጥቁር ሕዝብ እና መላው አፍሪካ ሲዘለፍ ግን አልታገስም፤ ያኔ ሰዎች መስመር እያለፉ ነው እላለሁ። እኔ የግድያ ዛቻ ሲደርስብኝ ምንም አልመሰለኝም፤ መልስም አልሰጠሁም። እንደ ማኅበረብ ሲሰድቡን ግን መታገስ የለብንም" ብለዋል። የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ማክሰኞ ዕለት፤ የዓለም ጤና ድርጅትን "በዋነኛነት በአሜሪካ ቢደጎምም፤ በጣም ለቻይና የወገነ ድርጅት ነው" ሲሉ ተደምጠዋል። ለድርጅቱ ድጋፍ ማድረጌን ላቆም እችላለሁ ሲሉም አስፈራርተዋል። ይህንን ንግግር ተከትሎ የአፍሪካ መሪዎች ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖምን ከትራምፕ እየተከላከሉ ነው። የሩዋንዳው ፕሬዘዳንት ፖል ካጋሜ፣ የናሚቢያው ፕሬዘዳንት ሀጌ ጄኒግቦ፣ የናይጄሪያ ፕሬዝደንት ጽ/ቤት እና የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሞሳ ፋኪ ማሐማት ለዶ/ር ቴድሮስን ድጋፋቸው ከገለጹ መሪዎች ተጠቃሽ ናቸው። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሞሳ ፋኪ ማሐማት ከዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊው ጎን ነኝ ማለታቸውን ተከትሎ፤ ፖል ካጋሜ "እኔም እስማማለሁ፤ ትችቱ ለዶ/ር ቴድሮስ፣ ለዓለም ጤና ድርጅት እና ለቻይና ነው ወይስ በጋራ ነው ጥቃት የተሰነዘረባቸው?" ብለዋል። የናሚቢያው ፕሬዘዳንት ሀጌ ጄኒግቦ "የመላው ዓለም ትብብር አስፈላጊ በሆነበት ሰዓት አብሮነትን ያሳዩ እውነተኛ መሪ" ሲሉ ዶ/ር ቴድሮስን ገልጸዋል። ፕሬዝደንት ትራምፕ ለዓለም ጤና ድርጅት የማደርገውን ድጋፍ አቋርጣለሁ ስለማለታቸው የተጠየቁት ደ/ር ቴድሮስ፤ "ኮሮናቫይረስን ለፖለቲካ ፍጆታ ማዋል የለብንም" ብለዋል። ሁሉም አካላት ቫይረሱን መከላከል ላይ ማተኮር እንጂ ኮሮናቫይረስን ለፖለቲካ መጠቀሚያነት ማዋል የለብንም ሲሉም ተናግረዋል። በተጨማሪም ዶ/ር ቴድሮስ አሜሪካ ለድርጅቱ ለምታደርገው የገንዘብ ድጋፍ አመስግነው፤ ድጋፉ ይቀጥላል ብለው እንደሚተማመኑም ገልጸዋል። "በአገራችን ድንበር ውስጥ ብቻ ልንኖር አንችልም። ዓለም እጅግ እየጠበበች ነው። ከመቼውም ጊዜ በላይ አብሮነት ያስፈልገናል" ሲሉም ተናግረዋል።
53829448
https://www.bbc.com/amharic/53829448
ጃዋር መሐመድ፡ በኦሮሚያ እና ድሬዳዋ ባጋጠሙ ግጭቶች ቢያንስ አራት ሰዎች መገደላቸው ተነገረ
ትናንት እና ከትናንት በስቲያ በኦሮሚያ ክልል የሃረርጌ ዞኖች፣ በምዕራብ አርሲ ዞን እና በድሬዳዋ ከተማ ባጋጠሙ ግጭቶች ቢያንስ 4 ሰዎች መገደላቸውን እና በርካቶች መቁሰላቸውን ፖሊስ፣ የሆስፒታል ምንጮች እና የየአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገልጸዋል።
ጭሮ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር የሚገኘው የአቶ ጃዋር መሐመድ ጤና ታውኳል የሚለው ዜና መሰማቱን ተከትሎ ሰዎች ከትናንት በስቲያ እና ትናንት በጭሮ ለተቃውሞ ከወጡ በኋላ ግጭት ተከስቶ ቢያንስ ሁለት ሰዎች መገደላቸውን የሆስፒታል ምንጭ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የጭሮ ሆስፒታል ተጠባባቂ ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ሳዳም አሉዋን በጥይት ተመትተው ወደ ሆስፒታላቸው ከመጡ 24 ሰዎች መካከል የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ትናንት ለቢቢሲ ተናግረዋል። "በጥይት ተመትተው የመጡ ሰዎች አሉ። አጠቃላይ ቁጥራቸው 24 ነው። ከእነዚህ መካከል የ2 ሰዎች ሕይወት አልፏል" ብለዋል። ዶ/ር ሳዳም "ከሞቱት መካከል አንዷ ትልቅ ሴት ነች። በ40ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ ትሆናለች። ጀርባዋን ተመትታ ነው የተገደለችው። ሌላኛው በ20ዎቹ ውስጥ የሚገኝ ወጣት ወንድ ነው። እሱም ከጀርባው ነው የተመታው" ሲሉ ተናግረዋል። እንደ ዶ/ር ሳዳም ከሆነ፤ አንድ በጽኑ የተጎዳ ወጣት ለተጨማሪ የሕክምና እርዳታ ወደ አዳማ መላኩን ተናግረው፤ የተቀሩት አብዛኛዎቹ እጃቸውን እና እግራቸውን የተመቱ እና የአጥንት መሰበር ያጋጠማቸው መሆናቸውን ገልጸዋል። ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸውን እንዳንገልጽ የጠየቁን የጭሮ ከተማ ነዋሪ፤ ከትናንት በስቲያ ከሰዓት 11 ሰዓት አካባቢ ቀበሌ 03 ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ ግጭት ተከስቶ እንደነበረ ተናግረዋል። ትናንትም ከጭሮ ዙሪያ በርካቶች ለተቃውሞ ወደ ጭሮ ከተማ በሚመጡበት ወቅት የመንግሥት የጸጥታ ኃይል ሰዎቹን ለመበተን ተኩስ መክፈታቸውን ተናግረዋል። ድሬዳዋ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ትናንት በሰጠው መግለጫ በከተማዋ ከተከሰተው ሁከት እና ረብሻ ጋር ተያይዞ የሁለት ሰው ህይወት ማለፉን እና በአራት ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ መድረሱን አስታውቋል። የከተማው ፖሊስ አስተዳደር "እኩይ አላማን ያነገቡ ኃይሎች ሰላማዊው ህብረተሰብ ውስጥ ተሸሽገው "12.12.12" በሚል ከውጪ የተሰጣቸውን የጥፋት ተልዕኮ ለማስፈፀም ላይ ታች ሲሉ የዋሉና የጣሩ ቢሆንም በጸጥታ ሃይላችን እና በሰላም ወዳዱ የከተማችን ነዋሪ ጥረት የጥፋት ድግሳቸው መና አድርጎ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል" ብሏል በመግለጫው። የከተማው ፖሊስ ጨምሮም፤ ለከተማዋ ሰላም እና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር 'ለአፍታም ሸብረክ እንደማንል በድጋሚ ማረጋገጥ እንወዳለን' ሲል አስታውቋል። አወዳይ ትናንት እና ከትናንት በስትያ (ሰኞ 11/12/2012 እና ማክሰኞ 12/12/2012) በአወዳይ ከተማ ለተቃውሞ የወጡ ሰዎች ከመንግሥት የጸጥታ ኃይል ጋር መጋጨታቸው ተነግሯል። አንድ የአወዳይ ከተማ ነዋሪ ሰኞ እኩለ ቀን ላይ አቶ ጃዋር ታመዋል የሚለው ዜና ሲሰማ፤ 'ጃዋር መታከም አለበት፣ ከእስር መለቀቅ አለበት' የሚሉ መፈክሮችን የሚያሰሙ ወጣቶች መሰባሰብ ሲጀምሩ የመንግሥት የጸጥታ ኃይል አባላት ሰዎችን ለመበተን ተኩስ መክፈት መጀመራቸውን ለቢቢሲ ተናግሯል። "መፈክር እያሰሙ ሰልፍ ለመውጣት ሲሞክሩ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል እና መከላከያ ሰራዊት ሰዎችን ማስቆም ጀመሩ። ከዛ ተኩስ ተከፍቶ ወደ 10 ሰዎች በጥይት ተመተዋል" ያሉ ሲሆን እኚህ የዐይን እማኝ ሁለት ሰዎች በጥይት ተመትተው መገደላቸውን አስረድቷል። ማክሰኞ እለትም በአወዳይ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ሙከራ መደረጉን የከተማ ነዋሪው ለቢቢሲ ተናግሯል። "ከ4 ሰዓት ጀምሮ ሰልፍ ሲካሄድ ነበር። በሽር የሚባል አካባቢ ተኩስ ተከፍቶ አንድ ሰው ተገድሏል። ከተማው አሁን ጸጥ ብላለች። የትራንስፖርት እንቅስቃሴ የለም። ሱቆችም ዝግ ናቸው" ብሏል። ሐረር የተቃውሞ ሰልፍ እና የገበያ አድማ መደረግ አለበት የሚሉ ሰዎች ለተቃውሞ ትናንት ረፋድ ላይ ለመሰባሰብ ሲሞክሩ በመንግሥት ጦር መበተናቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ሐረር ከተማ በሚገኘው የሃረማያ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ውስጥ ሕክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ቢቢሲ ካነጋገራቸው የሐረር ከተማ ነዋሪዎች ሰምቷል። ሻሸመኔ በተመሳሳይ በሻሸመኔ ከተማም የአቶ ጃዋር የመታመም ዜና ሲሰማ "ሰዎች እየተጯጯሁ ወደ ዋና መንገድ መውጣት" መጀመራቸው ተነግሯል። አንድ የከተማው ነዋሪ ለቢቢሲ ስትናገር፤ በተፈጠረው አለመረጋጋት ተኩስ ተከፍቶ አንድ በጥይት ተመቶ የወደቀ ወጣት መመልከቷን ተናግራለች። የክልል መንግሥት ምላሽ የኦሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ባልቻ በበኩላቸው፤ በአርሲ እና ሃረርጌ ዞኖች ግጭት መከሰቱን ገልጸው፤ በሰው እና በንብረት ላይ ስለደረሰው የጉዳት መጠን ግን መረጃ እስካሁን እንደሌላቸው ተናግረዋል። "ስለ ሻሸመኔ ብዙ መረጃ የለኝም። እንደ ዶዶላ እና አሳሳ ባሉ ከተሞች ግን እንደዚህ አይነት [የግጭት] ምልክቶች ታይተዋል። በአወዳይም መንገድ ለመዝጋት ጥረት ተደርጎ ነበር። ይህ ግን ከሙከራ ያለፈ አይደለም" በማለት አቶ ጌታቸው ለቢቢሲ ገልፀዋል። ቃል አቀባዩ ምንም እንኳ በተለያዩ አካላት በመላው ኦሮሚያ የሚጸና የተቃውሞ እና የገበያ አድማ ጥሪዎች ቢቀርቡም ይህ ሳይሳካ መቅረቱን ተናግረዋል። "በየትኛው የኦሮሚያ አቅጣጫ የመጓዝ እቅድ ያለው መሄድ ይችላል። መንገድ የተዘጋበት አካባቢ ስለመኖሩ ምንም አይነት መረጃ የለኝም" ብለዋል አቶ ጌታቸው። "በዚህች አገር ሁሉም ሰው ከሕግ ፊት እኩል ነው። በሕግ መጠየቅ ያለበት በሕግ ይጠየቃል" ያሉት አቶ ጌታቸው፤ ሰዎች ድምጻቸውን በሰላማዊ መልኩ ማሰማት የሚፈልጉ ከሆነ ሕጋዊ ስርዓቱን ተከትለው ለሚመለከተው አካል ስለ ሰላማዊ ሰልፉ አሳውቀው ድማጻቸውን ማሰማት ይችላሉ። ከዚህ ውጪ በዘፈቀደ የሚኖርባት አገር አይደለችም" ብለዋል። "ከአሁን በኋላ በፈለጉበት እየኖሩ የአመጽ እና የመንገድ መዝጋት ጥሪ በማቅረብ ተግባራዊ ለማድረግ መሞከር የሚቻል አይደለም" ሲሉም አቶ ጌታቸው አክለዋል።
news-53978475
https://www.bbc.com/amharic/news-53978475
ስደት፡ የአውሮፓ ሃገራትና የስደተኞች ቀውስ
የዛሬ አምስት ዓመት ከአንድ ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ስደተኞች ድንበር አቋርጠው ወደ አውሮፓ ገቡ።
አብዛኛዎቹ የተሻለ ሕይወት በማሰብ በአገራቸው ያለውን ጦርነትና ግጭት በመሸሽ ነው ወደ አውሮፓ የመጡት። በመንገዳቸውም እራሳቸውን ለአደጋ አጋልጠው ነው የሚጓዙት። ነገር ግን የስደተኞቹ በድንገት መፍለስ በአውሮፓ ከፍተኛ ምስቅልቅል ፈጠረ። የሰብአዊም ፖለቲካዊም ምስቅልቅል። አንዳንድ አገራት ስደተኞቹን ለመቀበል እጃቸውን ሲዘረጉ ሌሎች ደግሞ ስደተኞቹን ለማስቀረት ድንበራቸው ላይ አጥር መገንባት ጀመሩ። እንደ አህጉር ግን አውሮፓ የስደተⶉቹን ሁኔታ መቆጣጠር አቅቷት ተንገዳግዳ ነበር። የስደተⶉቹ በብዛት ወደ አውሮፓ መግባት ጫና አሁንም ድረስ አለ። ላራ ታሃን ሶሪያ ውስጥ ሒሳብ አስተማሪ ነበረች። '' ከ2011 ጦርነት በፊት የነበረኝ ሕይወት በጣም ጥሩ ነበር። አሌፖ ውስጥ በሒሳብ አስተማሪነት በማገኘው ገቢ ሁለት ልጆቼን አስተዳደር ነበር። ነገር ግን ድንገት ጦርነቱ ተጀመረ'' ስትል እንዴት ለመሰደድ እንደተገደደች ታስረዳለች። ''ልክ ጦርነቱ ሲጀምር አገሬ ውስጥ ምንም ተስፋ እንደሌለኝ ተረዳሁ። በከተማው ውስጥ መኪናዬን ሳሽከረክር በየመንገዱ የሞቱ ሰዎችን ሬሳ እምለከት ነበር። ስለዚህ በወቅቱ የነበረኝ ቀላል አማራጭ ወደ ቱርክ መሄድ ነበር።'' በሶሪያ የተቀሰቀሰው የእርስ በርስ ጦርነት ቱርክን በስደተኞች ጉዳይ በዓለም አይን ውስጥ እንድትገባ አደረጋት። ከግሪክና ቡልጋሪያ ጋር በድንበር መዋሰኗ ደግሞ ወደ አውሮፓ መግባት ለሚፈልጉ ስደተኞች በጣም ተመራጭና ቀላል አማራጭ አድርጓታል። በአውሮፓውያኑ 2015 ላይ ጦርነቱን በመሸሽ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሶሪያውያን ስደተኞች ወደ ቱርክ ገብተዋል። ነገር ግን ጣልያን ውስጥ ደግሞ የስደተⶉች ጉዳይ ለዓመታት ችግር ሆኖ የቆየ ነገር ነበር። ለሰሜን አፍሪካ ቅርብ መሆኗ የሜዲተራኒያን ባህርን ለማቋረጥ ድፍረቱ ያላቸውና እስከሞት ሊያደርስ የሚችለውን የባህር ጉዞ የማያስጨንቃቸው አቅጣጫቸውን ወደ ጣልያን አድርገው ነበር። በዚያን ዓመት ላይ በባልካን በምትገኘው ሰርቢያ ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ ከመካከለኛው ምስራቅ የመጡ ስደተኞችን መመልከት የተለመደ ነበር። ላራ ሁለት እህቶቿ ጀርመን ውስጥ ነው የሚኖሩት። ወደ ቱርክ ከመጣች በኋላ ደግሞ የልጆቿ የወደፊት እጣ ፈንታ ቱርክ እንዳልሆነች ተረዳሁ ትላለች። ለዚህም ነው የተሻለ ሕይወት ፍለጋ ወደ ጀርመን ለመሄድ የወሰነችው። በወቅቱ ጀርመን ከጦርነት የሚሸሹ ስዎችን በመቀበልና በማስተናገድ ለስደተኞች ጥሩ አገር እንደሆነች ይነገርላት ነበር። በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተⶉች መስከረም ወር 2015 ላይ መጉረፍ ሲጀምሩ የአገሬው ዜጋ በባቡር ጣቢያ በመገኘትና ስጦታ በማዘጋጀት እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋቸዋል። በጣም አስገራሚ ሁኔታ ነበር። ላራ ልክ የጀርመኗ ዋና ከተማ ሙኒክ ስትደርስ እጅግ ከባድ ዝናብ እየዘነበ ነበር። '' ለእኔ እንደዛ ኤእነት ዝናብ መመልከት በጣም አስገራሚ ነበር። በበጋ ወቅት ዝናብ ኤእቼ አላውቅም። በሌላ በኩል ስለስደተኞች ጥሩ አመለካከት ያላቸው ብዙ ሰዎችን ተዋውቄያለው'' ትላለች። በተመሳሳይ በስዊድን የነበረው ሁኔታም ለስደተኞቹ ምቹ ነበር። አገሪቱ ለስደተኞች ምቹ ከሚባሉት መካከል ነበረች በወቅቱ። ስደተኞቹ ወደ ስዊድን ሲገቡ አንዳንድ ሰዎች እንኳን በደህና መጣችሁ ብለው ተቀብለዋቸዋል። ሳማር ጃቢር ጆርዳን ውስጥ የኤንጂነሪንግ ምሩቅ ነው። የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እያሉ ልክ እንደ ጀርመን ሁሉ ስዊድንም ስደተኞችን ተቀብላ በአግባቡ እንደምታስተናግድ እሰሙ ነበር። ''ሕይወቴ አደጋ ላይ ስለነበረ ጆርዳንን ለቅቄ ወጣሁ። እህቴ ስዊድን ውስጥ ትኖር ስለነበር ከእሷ ጋር እንደምንገናኝ በማሰብ ነበር የወጣሁት። ልክ ስዊድን ስደርስ ከረጅም ዓመት በኋላ ነጻነት ተሰማኝ። ጀርመን ደግሞ በወቅቱ ስደተኞቹ ወደ ድንበሯ ሲገኑ መኖሪያ ቤት እንዲያገኙ ለማድረግ ስትጥር ነበር። ነገር ግን የስደተⶉች ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ ሲመጣ ሁኔታው ከቁጥጥር ውጪና ከአቅም በላይ እየሆነ መጣ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወደ ስዊድን የሚመጡት ስደተኞችንም ቢሆን ከከተማ ራቅ ወዳሉ ስፍራዎች መወሰድ ተጀመረ። ምንም እንኳን አገሪቱ ስደተኞችን መቀበል ባታቆምም ሁኔታዎች ግን እየከበዱ መጡ። ቀስ በቀስም 2016 ላይ ስደተⶉች በባልካን አገራት በኩል የሚገቡበት መንገድ ተዘጋ። በዚህም ምክንያት ወደ አውሮፓ የሚገቡት ስደተኞች ቁጥር መቀነስ አሳየ። የአውሮፓ ሕብረትም ከቱርክ ጋር ስምምነት ላይ ደረሰ። ሕብረቱ ለቱርክ በቢሊየኖች የሚቆጠሩ ዶላሮችን ለመስጠትና አገሪቱ ደግሞ በተራዋ ግሪካ ደሴት የመጡ የሶሪያ ስደተኞችን ተመልሳ እንድትቀበል ተስማሙ። ይህም ስምምነት የስደተኞችን ቁጥር በእጅጉ ቀነሰው። በጀርመን 2015 ላይ በአዲስ ዓመት ዋዜማ አንዲት ጀርመናዊት ወጣት ከሰሜን አፍሪካ በመጡ ሰዎች ጥቃት ደረሰባት። በተጨማሪም በገና ወቅት ከቱኒዚያ በመጣ አንድ ስደተኛ የተፈጸመው የሽብር ጥቃት ጀርመናውያን ለስደተኞች ያላቸውን አመለካከት ቆም ብለው እንዲያጤኑ አስገድዷቸዋል። በስዊድንም ቢሆን ከስደተⶉች ጋር የተያያዙ ወንጀሎች የፖለቲከኞች መከራሪያ ነጥብ መሆነ ጀመሩ። የአገሪቱ ፖሊስም ቢሆን ስደተⶉች በብዛት በሚኖሩበት አካባቢ የወንጀል ቁጥር ከፍ ያለ እንደሆነ አልካደም። ላራ ታሃን በአሁኑ ወቅት ጀርመን ውስጥ መኖር ጀምራለች። ''ሴት ልጄ ትምህርት ቤት ጥሩ ሁኔታ ላይ ነች። ሁለታችንም ጀርመንኛ በአግባቡ መናገር የቻልን ሲሆን ብዙ ጓደⶉችንም አፍርተናል'' በቱርክ ያለውም ሁኔታ በእጅጉ ተቀያይሯል። አገሪቱ ከስደተⶉች መተላለፊያነት ወደ ስደተኞች ዋነኛ ማዕከልነት ተቀይራለች። በአንዳንድ አካባቢዎች የሶሪያ ስደተⶉች ብቻ የሚኖሩባቸው መንገዶች አሉ። ሱቆቹም፣ ምግብ ቤቶቹም የሶሪያውያን ነው። በዚህም ምክንያት በርካታ ሶሪያውያን ወደ አገራቸውም ሆነ ወደ ሌላ የአውሮፓ አገር መሄድ አይፈልጉም። ምክንያቱም አብዛኛዎቹ ቱርክ ውስጥ ተደላድለውና ቤተሰብ መስርተው መኖር ጀምረዋል፤ እንዲሁም ጥሩ የገቢ ምንጭ አላቸው።
news-51159938
https://www.bbc.com/amharic/news-51159938
በትግራይ የወረዳነት ጥያቄ ባነሱ ነዋሪዎች የመቀሌ- ሳምረ መንገድ ከተዘጋ አራተኛ ቀኑን ይዟል
ከመቀሌ ከተማ ወደ ሳምረ የሚወስደው መንገድ "ወረዳችን ይመለስልን" በሚሉ የሕንጣሎ ነዋሪዎች ደንጎላት በሚባል አካባቢ ከተዘጋ አራተኛ ቀኑን ይዟል።
'ሕንጣሎ ወጀራት' ተብሎ ይጠራ የነበረው ወረዳ ለሁለት ተከፍሎ፤ ወጀራት ራሱን የቻለ ወረዳ ሲሆን፤ 11 ጣቢያዎች ያሉት ሕንጣሎ ደግሞ ሒዋነ ከምትባል ሌላ ወረዳ ጋር እንዲካተት ተደርጓል። ሒዋነ ከምትባለው ወረዳ ጋር እንዲቀላቀሉ የተደረጉት የሕንጣሎ ነዋሪች፤ እራሳችንን የቻለ ሕንጣሎ የተባለ ወረዳ ሊኖረን ይገባል እንጂ ከሒዋነ ወረዳ ጋር መቀላቀል የለብንም የሚል ቅሬታ ነው የሚያነሱት። • ኢትዮጵያ እና ግብፅ 'ቅድመ ስምምነት' ላይ ደረሱ • ሩስያ መንግሥቴን በትኛለሁ ስትል ምን ማለቷ ነው? ከነዋሪዎቹ እንደሰማነው አሁን በተጀመረው አዲስ የአስተዳደር መዋቅር፤ ወጀራት ከ1-9 ጣቢያዎች ያሉት ሲሆን ሕንጣሎ ግን ሒዋነ ወደሚባል ወረዳ እንዲቀላቀል ተደርጓል። ታዲያ ነዋሪዎቹ የራሳችን ወረዳ ይኑረን፤ በቅርብ አገልግሎት እንድናገኝ ይሁን በማለት ነው እየጠየቁ ያሉት። "ምላሽ ካልተሰጠን ተቃውሟችን ይቀጥላል፤ ወደ ቤታችን አንመለስም" ይላሉ ነዋሪዎቹ። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪ "የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ደብረጽዮን ባመጣው አዲስ አሠራር ፤ ነዋሪዎች ከ10 ኪሎሜትር በላይ ርቀው መገልገል የለባቸውም ሲሉ ነበር። እኛ ግን አሁን ተባረን አገልግሎት ለማግኘት የምንጓዘው ትንሹ ርቀት 30 ኪሎ ሜትር ነው" ይላሉ። መንገድ መዝጋት መፍትሄ ነው ወይ? በማለት የተጠየቁት ነዋሪው፤ መንገድ መዝጋት ፍትሃዊ ባይሆንም ፍትህ ስላጣን ነው መንገድ የዘጋነው ብለዋል። "ከእኛ መካከልም መቀሌ መሄድ ያለባት አራስ አለች፤ ሕመምተኛ አለ፤ ነገር ግን መሠረታዊ ሕይወታችን አደጋ ላይ ስለወደቀ ነው ይህንን ጊዜያዊ ችግራችንን ብንቋቋም ይሻላል ያልነው። ወረዳችንን አሳልፎ ለሌላ መስጠት ተገቢ አይደለም" ይላሉ። የአካባቢው ነዋሪዎች ኮሚቴ ወኪል አቶ ደሱ ፀጋየም ይህንን ጥያቄ ማቅረብ ከጀመሩ ስድስት ወራት መቆጠራቸውን ይናገራሉ። እርሳቸው እንደሚሉት ቅሬታቸውን ለማቅረብ ያልሄዱበት፤ ያልደረሱበት ቦታ የለም። በወረዳ እና በዞን የሚገኙ የፍትሕም ሆነ የፀጥታ አካላትን አዳርሰዋል። ነገር ግን ያገኙት ምላሽ የለም። "እኛ መንግሥት በደነገገው ሕግ መሠረት ሁሉንም አሟልተናል። አንደኛ ከ115 ሺህ ሕዝብ በላይ ነን። ሁለተኛ መንግሥት 'ከ10 ኪሎ ሜትር በላይ ተጉዞ የወረዳ አገልግሎት ማግኘት የለበትም' ነው የሚለው እኛ ግን ከ30 በላይ ኪሎ ሜትር በላይ ሄደን ነው ይህንን አገልግሎት የምናገኘው፤ ስለዚህ የልማት ጥያቄያችን እንዲመለስልን ነው የምንፈልገው" ሲሉ ጥያቄያቸውን ለቢቢሲ አስረድተዋል። ነገር ግን ይህንን ጥያቄ ማንሳት ከጀመሩ መንፈቅ ቢሞላቸውም፤ የፖለቲካ አስተዳዳሪዎችን መልስ እንዲሰጧቸው ቢጠይቁም ጆሮ የሰጣቸው የለም። አቶ ደሱ "በተቃራኒው በዞንና በወረዳ ፖሊስ አማካኝነት ያስፈራሩን ገቡ፤ ለተቃውሞ የወጡ ነዋሪዎችም መንገድ በመዝጋታቸው ወደ ገበያ የሚሄዱ ከብቶች ሳይቀሩ መንገድ ላይ ነው የዋሉት፤ መንገድ ዝግ ነው፤ ይሄው እንዲህ ከሆነ ቀናት ተቆጥረዋል" ብለዋል። ከአካባቢው ነዋሪዎች እንደሰማነው መንገዱ በመዘጋቱ ከትናንት በስቲያ እስከ 150 የሚደርሱ መኪኖች መንገድ ላይ ሲጉላሉ እንደነበር አስታውሰዋል። የነዋሪዎቹን ጥያቄ ይዘን ምላሽ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል አማካሪ አቶ ተሾመ፤ የነዋሪዎቹ ጥያቄ እንደተመለሰላቸው ተናግረዋል። አቶ ተሾመ "ወረዳቸው ተመልሶላቸዋል፤ የእነርሱ ጥያቄ የወረዳው ዋና ከተማ ደንጎላት ትሁን ወይስ ሒዋነ የሚል ነው" በማለት ይህንን ጥያቄ የሚመልሰው ደግሞ የወረዳው ምክር ቤት መሆኑን አስረድተዋል። ጥያቄያቸው አልተመለሰልንም የሚሉት ነዋሪዎች፤ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እንዲያነጋግሯቸው ነው የሚፈልጉት ይህ ለምን አልሆነም? ያልናቸው አቶ ተሾመ፤ "ዝም ተብሎ የሚመጣበት ቦታ አይደለም፤ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በሌላ ሥራ ተጠምደዋል፤ በቀጠሮ ከመጣችሁ ትስተናገዳላችሁ አልናቸው። እንዴት እናድርግ? "ይላሉ። ነዋሪዎች ግን መስተዳደሩ ጋር ጭራሽኑ አናገናኛችሁም መባላቸውን ያነሳንላቸው አቶ ተሾመ፤ ራሳቸው እንዳነጋገሯቸው በመግለፅ ይህ ሀሰት መሆኑን ገልፀዋል።
news-55169534
https://www.bbc.com/amharic/news-55169534
ህንዳዊው ሙስሊም የሂንዱ ሴት እምነት በመቀየር ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ዋለ
በህንዷ ኡታር ፕራዴሽ ግዛት አንድ ሙስሊም ግለሰብ የሂንዱ እምነት ተከታይ የሆነችን ሴት ወደ እስልምና ሊቀይር ሞክሯል በማለት ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎታል።
አገሪቷ ባወጣችው ፀረ- እምነት መቀየር ህግም ተጠርጥሮ የታሰረው የመጀመሪያው ግለሰብ ሆኗል። ህጉ በአክራሪ ሂንዱዎች "የፍቅር ጂሃድ" ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ሙስሊም ወንዶች ሂንዱ ሴቶችን በጋብቻ ውስጥ እምነታቸውን እንዲቀይሩ ያደርጓቸዋል የሚለውንም ለማመላከት የሚጠቀሙበት ነው። ይህ ህግ በህንድ ውስጥ "ሙስሊም ጠል" ነው በሚልም ከፍተኛ ትችትን እያስተናገደ ነው። ሆኖም ህጉ በተጨማሪ አራት ግዛቶች ተቀባይነት ያገኘ ሲሆን "የፍቅር ጂሃድ"ን ለመቃወም በሚል ግዛቶቹ እያረቀቁት ነው ተብሏል። የኡታር ፕራዴሽ ፖሊስ ግለሰቡ በቁጥጥር ስር መዋሉንም በትዊተር ገፁ በትናንትናው ዕለት አሳውቋል። ባለፈው ሳምንት የልጅቷ አባት እምነትሽን ካልቀየርሽ በሚል ጫናም እንዲሁም ማስፈራሪያ እያደረሰባት ነው በማለት ሪፖርት አድርገዋል። ግለሰቧ ከሰውየው ጋር በፍቅር ግንኙነት ውስጥ እንደነበረችና ሌላ ሰውም እንዳገባች ተዘግቧል። እምነት ልትቀይር ሞክረሃል የተባለው ግለሰብ ለአስራ ቀናት ያህል ቀጠሮ የተጠየቀበት ሲሆን ከሴትዮዋ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለውና ንፁህ እንደሆነም ለሪፖርተሮች ተናግሯል። ዋስ የሚከለክለው አዲሱ ህግ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ አስር አመትም ያስቀጣል። "የፍቅር ጂሃድ ህግ ምንድን ነው? ኡታር ፕራዴሽ ግዛት በግድ ወይም በማጭበርበር የሚደረግን የእምነት ቅየራ ለመታገል በሚል አዲሱን ህግ በማፅደቅ የመጀመሪያዋ ሆናለች። ግዛቷ ግን የመጨረሻ አትሆንም ቢያንስ አራት ግዛቶች "የፍቅርን ጂሃድ" እንዋጋለን በሚል ህጉን ለማፅደቅ እቅድ ይዘዋል። ኡታር ፕራዱሽን ጨምሮ አምስቱ ግዛቶችን የሚመራው ባሃራቲያ ጃናታ ፓርቲ ሲሆን ከዚህ ቀደምም በፀረ- እስልምና አመላካከቶቹ ወቀሳ ሲደርስበት ነበር። "የፍቅር ጂሃድ" የቀኝ ክንፍ አክራሪ ሂንዱ ቡድኖች ከዚህ ቀደም ሲጠቀሙበት የነበረና በህንድ ህገ መንግሥትም እውቅና የሌለው ነው በማለትም "አስነዋሪ" በማለት ተችዎች ይናገራሉ።
45080640
https://www.bbc.com/amharic/45080640
በድሬዳዋ ከተማ በተከሰተ ግጭት የ10 ሰዎች ህይወት ጠፋ
ትናንት እሁድ በድሬዳዋ ከተማ ብሔርን የለየ ግጭት ተከስቶ በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ።
ቢቢሲ በስልክ ያነጋገራቸው የዓይን እማኞች እንደሚሉት ግጭቱ የተቀሰቀሰው በኦሮሞዎችና በሶማሌዎች መካከል እንደሆነ ገልፀዋል። ትናንት ረፋድ ላይ ገንደ ገራዳ በሚባለው አካባቢ የጃዋር መሃመድን ወደ ኢትዮጵያ መመለስ አስመልክቶ የተሰባሰቡ ሰዎች ሲጨፍሩ አንደኛው ወገን ጥቃት ሊፈፀምብን ነው በሚል ያልተጣራ መረጃ ምክንያት መሆኑን ሰምቻለሁ ትላለች አንዲት የዓይን እማኝ። • በድሬዳዋ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አልታወጀም ተባለ • የደቦ ጥቃትና ያስከተለው ስጋት "ከዚያ በኋላ የነበረው ሁኔታ በጣም ከባድ ነበር፤ ዘር እየተለየ ነው የዱላና የድንጋይ እሩምታ የነበረው፤ ሁሉ ነገር ድብልቅልቅ ያለ ነበር " ብላለች። ከዚህም በተጨማሪ ቤቶች ሲቃጠሉና መመልከቷንና ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ማየቷን ተናግራለች። የደቦ ጥቃቱ በተለይም ቁጠባ፣ ፖሊስ መሬት፣ ሼክ ሃቢብ፣ ገንደ ገራዳና ቢላል ተብለው በሚጠሩ አካባቢዎች ከአንዱ ወደሌላው እየተዛመተ ሄዶ ነበር ። ኦሮሞና ሶማሌዎች እርስ በእርስ እንጂ ማናቸውም ቢሆን ሌላ ብሄርን አላጠቁም ብትልም ግጭቱ በማን ፍላጎት እየተካሄደ እንዳለ ግን መለየት አስቸጋሪ ሆኖባታል። • በሶማሌ ክልል በተከሰተ ቀውስ ህይወት ሲጠፋ አብያተ-ክርስቲያናት ተቃጠሉ "እኛ ከጎናችንም ከፊታችን ኦሮሞዎችም ሶማሌዎችም አሉ፤ ጎረምሶቹም አዋቂዎቹም አንድ ላይ ቆመው እያወሩ ነው፤ ከየት አካባቢ የመጣው ሰው ጸብ እንደሚፈልግ ራሱ ግራ ነው የሚያጋባው" ሌላኛው የዓይን እማኝ ገንደ ገራ፣ ፖሊስ መሬት፣ ቁጠባ፣ አዲስ ኬላ የመከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ በአካባቢዎቹ በመስፈር በቡድን ተደራጅተው ለጸብ የሚወጡ ወጣቶችን ለመበተን የአስለቃሽ ጋዝ መልቀቃቸውን ነግሮናል። አክሎም በዚህ ግጭት እስካሁን ዘጠኝ ሰዎች መሞታቸውንና በርካቶች መቁሰላቸውን ሲናገር ሌላዋ ወጣት ደግሞ የሟቾቹን ቁጥር አምስት ብቻ ነው ትላለች። የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ዲፂዥን ኃላፊ ዋና ሳጅን ባንታለም ግርማ በበኩላቸው በድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 09 አንዳንድ መንደሮች ላይ ግጭቱ እንደተጀመረ ተናግረዋል። በከተማዋ ውስጥ በነበረው ግጭት በደረሰ ቃጠሎ የአስር ሰዎች ህይወት ማለፉን የተናገሩት የፀጥታ ኃይሉ ግጭቱን ለማብረድ ኃላፊነቱን በአግባቡ እየተወጣ መሆኑን አስረድተዋል። የግጭቱ መንስኤ ፖሊስ እያጣራ መሆኑን የሚናገሩት ኃላፊው የከተማው አስተዳደር የብሄር መልክ እንደሌለው እንደሚያምን ገልፀዋል። ነገር ግን አንዳንዶች የብሔር መልክ ለማስያዝ እንደሞከሩም አስረድተዋል።
news-50893697
https://www.bbc.com/amharic/news-50893697
ቦይንግ ዋና ሥራ አስፈፃሚውን አባረረ
አውሮፕላን አምራቹ ኩባንያ ቦይንግ፤ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዴኒስ ሚሌንበርግ ከኃላፊነታቸው አነሳ።
እርሳቸውን ከኃላፊነት የማንሳቱ እንቅስቃሴ የመጣው አውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖችን ማምረቱን ለጊዜው ሊያቋርጥ እንደሚችል ከገለፀ በኋላ ነው። • ቦይንግ ትርፋማነቴ ቀንሷል አለ • ቦይንግ የ737 ማክስ ሶፍትዌርን አሻሽያለሁ አለ የቦይንግ ምርት የሆኑት ሁለት 737 ማክስ 800 አውሮፕላኖች መከስከሳቸውን ተከትሎ ለዘጠኝ ወራት ያህል ሞዴሉ እገዳ ተጥሎበት ቆይቷል። የአሁኑ ሊቀመንበር ዴቪድ ካልሆን የዋና ሥራ አስፈፃሚ ኃላፊነቱን እና ፕሬዚደንት ሆነው ከፈረንጆቹ ጥር 13 ጀምሮ ማገልገል ይጀምራሉ። ላውረንስ ኬልነር ደግሞ የድርጅቱ የቦርድ ኃላፊ ሆነው ሊያገለግሉ እንደሚችሉም አክሏል። "የዳይሬክተሮች ቦርድ፤ በካምፓኒው ላይ በራስ መተማመንን ለመመለስ፣ ወደፊት ተጠናክሮ ለመቀጠል እንዲሁም ከደንበኞች፣ ተቆጣጣሪዎች እና ሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር ያለን ግንኙነት ለማጠናከር፤ አመራር መቀየር አስፈላጊ እንደሆነ ወስኗል" ሲል ቦይንግ በመግለጫው ምክንያቱን አስቀምጧል። • ቦይንግ ለተጎጂ ቤተሰቦች 100ሚ. ዶላር ሊሰጥ ነው በካምፓኒው አዲስ አመራር ሥር፤ ቦይንግ ከፌደራል አቪየሽን ባለሥልጣን [FAA] እንዲሁም ከተቆጣጣሪዎች እና ደንበኞች ጋር ግልፅ የሆነ፣ ውጤታማና የተቀላጠፈ ኮሚዩኒኬሽን እንዲኖረው የሚያስችል አሰራርም እንደሚያሻሽል አክሏል። ቦይንግ 737 ማክስ 800 አውሮፕላን ኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰከሰውን አውሮፕላን ጨምሮ ሁለት የከፉ አደጋዎች መድረሳቸው ይታወሳል። መጋቢት ላይ ኢቲ 302 ቦይንግ 737 ማክስ 800 ሲከሰከስ በአውሮፕላኑን ተሳፍረው የነበሩ 157 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል። ከኢቲ በፊት የኢንዶኔዥያው ላየን ኤር ተከስክሶ 189 ሰዎች መሞታቸውም አይዘነጋም። ተሻሻለ የተባለው ሶፍትዌር ምንድነው? ኤምካስ (ማኑቨሪንግ ካራክተርስቲክስ ኦግመንቴሽን ሲስተም) ለሚለው ምህጻረ ቃል ነው። ይህ ሲስተም አውሮፕላኑን የሞተሩ ክብደትና የተቀመጠበትን ቦታ ምክንያት አድርጎ እንዳይቆምና እንዳያጋድል ያደርገዋል። ይህም አውሮፕላኑ ሽቅብ በሚወጣ ጊዜ የሚያሳየውን ዝማሜ ተከትሎ ሚዛኑን እንዲያስጠብቀው ለማድረግ የተሠራ ነበር። ነገር ግን የኢንዶኒዢያው ላየን አውሮፕላን ምርመራ ውጤት እንዳመላከተው ይህ ሴንሰር አውሮፕላኑ በአፍጢሙ እንዲደፋ የሚያደርግበት ሁኔታ አለ። ይህም የሚሆነው ሚዛኑን ለመጠበቅ የሚልከው መልዕክት (ሲግናል) እርስበርሱ የሚጣረስ በመሆኑ ነው። ይህም ከአብራሪዎቹ ቁጥጥር ውጭ የሚሆን ነገር ነው። የተከሰከሰው የኢንዶኒዢያ አየር መንገድ ከ20 ጊዜ በላይ የአውሮፕላኑ አፍንጫ ቁልቁል እንዲያዘምና እንዲምዘገዘግ አድርጎታል። አሁን ቦይንግ አድሼዋለሁ የሚለው ሶፍትዌር በአውሮፕላኑ አፍንጫ የምትገኘው ሴንሰር እርስበርሱ የሚጣረስ ምልእክት ካስተላለፈ ኤምካስ የተሰኘውን መቆጣጠሪያ ልክ እንደ ኤሌክትሪክ ባልቦላ ራሱን በራሱ እንዲያጠፋ የሚያደርግ ነው።
news-45807519
https://www.bbc.com/amharic/news-45807519
እንግሊዝ የጋዜጠኛ ጀማልን ጉዳይ በዋዛ እንደማትመለከተው ገለጸች
ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ደብዛው እንደጠፋ የቀረው የሳዑዲው ጋዜጠኛ ዓለምን እያነጋገረ ነው። እንግሊዝ ጉዳዩን በዋዛ እንደማትመለከተው አስታውቃለች።
የሳዑዲን ንጉሣዊ አስተዳደርን ክፉኛ በመተቸት የሚታወቀው ጋዜጠኛ ጀማል ካሹጊ በኢስታንቡል የሳዑዲ ቆንስላ አንዳንድ ከጋብቻ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ወረቀቶችን ለመፈራረም ገብቶ በዚያው ቀልጦ ቀርቷል። ደጅ ኾና ስትጠብቀው የነበረችው ቱርካዊቷ እጮኛው ለ11 ሰዓታት ያህል በር በሩን ብትመለከትም ጀማል ከኤምባሲው ቅጥር ወደ ውጭ አልወጣም። • በገዛ አገሩ ኤምባሲ ውስጥ የተገደለው ጋዜጠኛ • ኢትዮጵያዊዋ ሰው አልባ አውሮፕላን ጋዜጠኛ ጀማል ቆንስላው ውስጥ ከመዝለቁ በፊት ለእጮኛው ተናገረ እንደተባለው "ምናልባት የቀረሁ እንደሆነ ለቱርኩ ፕሬዚዳንት ልዩ ረዳት ስልክ ደውለሽ አሳውቂ" ብሏታል። ይህም ጀማል ኤምባሲው አደጋ ሊያደርስበት እንደሚችል ጥርጣሬ እንደነበረው አመላክቷል። የጀማል እጮኛ ሄቲሲ ሳኡዲ ቆንስላ በር ላይ ለበርካታ ሰዓታት ስትጠብቀው ነበር የቱርክ ባለሥልጣናት ጀማል ቆንስላው ውስጥ እንደተገደለ ይጠረጥራሉ። የወንጀል ምርመራ ባለሞያዎችም ወደ ቆንስላው ዘልቀው ሰፊ ምርመራ ለመጀመር እንዲፈቀድላቸውም ጠይቀዋል። ሳዑዲ በበኩሏ ግድያውን አስተባብላለች። ጥቂት ጋዜጠኞችን ወደ ውስጥ እንዲገቡ በማድረግም የደበቅነው ነገር የለም ስትል መሳቢያና ኮሞዲኖ ጭምር በማስጎብኘት ለማረጋገጥ ሞክራለች። የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለሳዑዲው አቻቸው አዲል አልጁበይር በስልክ እንደተናገሩት "ወደጅነት የጋራ እሴቶችን በማክበር ላይ መመሥረት ይኖርበታል" ብለዋል። እንደሚባለው ጋዜጠኛው ቆንስላው ውስጥ ተገድሎ ከሆነም እንግሊዝ "ነገሩን እንዲሁ እንደዋዛ" እንደማትመለከተው አስታውቃለች። ሪያድ እንደምትለው ከሆነ ጀማል ቆንሱላውን ለቆ ወጥቷል። ቱርክ በበኩሏ ሳዑዲን ይህንኑ የሚያረጋግጥ መረጃን እንድትሰጥ እየወተወተች ነው። ጀማል በሳዑዲ ዕለታዊ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅና የንጉሣዊያን ቤተሰብም አማካሪ ነበር። የኋላ ኋላ ሁኔታዎች አላምር ሲሉት አገሩን ጥሎ በአሜሪካ በስደት መኖር ጀመረ። የዋሺንግተን ፖስት አምደኛ ሳለ የመሐመድ ቢን ሳልማን አስተዳደርን ክፉኛ የሚተቹ ጽሑፎችን ያትም ነበር። በጉዳዩ ላይ ዝምታን የመረጡት ዶናልድ ትራምፕ እስካሁን በጉዳዩ ላይ የሚያውቁት ተራው ሕዝብ የሚያውቀውን ያህል ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል። ሆኖም በነገሩ ላይ ከሳዑዲ ባለሥልጣናት ጋር በቅርቡ እንደሚነጋገሩበት ጠቁመዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔ ሳዑዲ ለምርመራው በሯን ክፍት እንድታደርግ ጠይቀዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በበኩሉ ነገሩን በአስቸኳይ ገለልተኛ ቡድን ተዋቅሮ እንዲመረመር ጠይቋል። የሳዑዲው ልዑል መሐመድ ቢን ሳልማን ለቡሉምበርግ በጉዳዩ ላይ በሰጡት አስተያየት እርሳቸውም የጀማልን መጨረሻ ለማወቅ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል። ጨምረውም "ጀማል ኤምባሲያችንን ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ወይም ከአንድ ሰዓት በኋላ ለቆ ወጥቷል" ብለዋል።
news-51670283
https://www.bbc.com/amharic/news-51670283
የዓለም አክስዮን ገበያ በኮረናቫይረስ እየተቃወሰ መሆኑ ተገለፀ
በዓለም አቀፍ ደረጃ የአክስዮን ገበያ ከአውሮፓውያኑ የ2008 የዓለም የገንዘብ ቀውስ ወዲህ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ መቃወሱ ተነገረ።
በእስያ የተቀሰቀሰው ኮረናቫይረስ አውሮፓ መድረሱን ተከትሎ የእስያ ገበያዎች በአክስዮን ገበያ መናጋት ክፉኛ ችግር ውስጥ ገብተዋል። የዋልስትሪት ዶጆንስ ሰንጠረዥ ትናንት በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ዝቅተኛ ነጥብ ተመዝግቦበታል። ተመሳሳይ የአክስዮን ገበያ ማሽቆልቆል በጃፓን፣ አውስትራሊያ፣ ኮሪያና ቻይና የአክስዮን ገበያዎች የተመዘገበ ሲሆን ይህም ባለሃብቶችን ክፉኛ እንደጎዳ ተገልጿል። በተለይም የኮረናቫይረስ በጣልያን መቀስቀስ ከተገመተው በላይ ቫይረሱ የዓለም ኢኮኖሚ ላይ ተፅእኖ ሊያሳሰድር ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል። የቻይናው እውቅ የኢኮኖሚ ባለሙያ ኢሪስ ፓንግ "ገበያዎቹ በጣም ተስፋ ነበራቸው፤ አሁን ግን በጣም ተስፋቢስ ሊሆኑ ይችላሉ" ሲሉ ስጋታቸውን አስቀምጠዋል። • "ኮሮናቫይረስ በአሜሪካ የሥራ ዕድልን ሊያሳድግ ይችላል" • ኮሮናቫይረስ፡ የወቅቱ አሳሳቢው የዓለማችን የጤና ስጋት • ኮሮናቫይረስ፡ ምን ያህል አሳሳቢ ነው? የኢኮኖሚ ተንታኙ እንደሚሉት መጀመሪያ ላይ ኮሮናቫይረስ የቻይና ችግር ብቻ እንደሚሆን ተገምቶ ስለነበር የእስያ ገበያ ብዙም በኮረናቫይረስ አልተቃውሰም ነበር። ነገር ግን ቫይረሱ ጎረቤት ደቡብ ኮሪያን ሲያንቀጠቅጥ እንዲሁም ጃፓንን ክፉኛ ሲያሰጋ የአህጉሪቱ ገበያ የኮረናቫይረስ ወላፈን ያቃጥለው ጀመር። በሌላ በኩል ኮረናቫይረስ እንደተቀሰቀሰ ወዲያው ተናግቶ የነበረው የእስያ አክስዮን ገበያ መልሶ መረጋጋት ችሎ ነበር፤ ዳግም አሁን እስኪናጋ ድረስ። ነገሮች አሁን እየሄዱ ባለበት ሁኔታ የቫይረሱን ስርጭት እንዴት መግታት ይቻላል የሚለው እስካልታወቀ ድረስ ኮረናቫይረስ ዓለምዓቀፍ ኢኮኖሚ ላይ ሊያደርስ የሚችለው ተፅእኖን መገመት ከባድ እንደሆነ ነው የኢኮኖሚ ተንታኞች እየገለፁ ያሉት።
news-45408628
https://www.bbc.com/amharic/news-45408628
የውጪ ኩባንያዎች በሎጂስቲክስ ዘርፍ እንዲሰማሩ ተፈቀደ
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድ የአምራቹን ዘርፍ ዕድገት ለማፋጠንና ኢንቨስትመንትን እንዲሁም የውጭ ንግድ አፈፃፀምን በበቂ መጠን ለማሳደግ የሚያግዝ ነው ያለውን ውሳኔ አሳልፏል።
በዚህም በአገር ውስጥ ባለሃብቶች ብቻ ተወስኖ የነበረውን ዕቃዎችን የማሸግ፣ የማስተላለፍ እና የመርከብ ውክልና አገልግሎቶችን በመስጠት የኢንቨስትመንት መስክ ዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ ኩባንያዎች ከ49 በመቶ ያላለፈ ድርሻ ይዘው ከአገር ውስጥ የሎጂስቲክስ ኩባንያዎች ጋር በሽርክና አብረው መስራት እንዲችሉ ውሳኔ አስተላልፏል። • የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ የአልጀርስ ስምምነትን ተግባራዊ ለማድረግ ወሰነ • አንዳንድ ነጥቦች በሥራ አስፈፃሚው መግለጫ ዙሪያ •ከኢትዮ- ቻይና ወዳጅነት ጀርባ ቀደም ባሉት ጊዜያት የአምራቹን ዘርፍ ዕድገት ለማፋጠን፣ ኢንቨስትመንትን ለመሳብና የውጭ ንግድ አፈፃፀምን በበቂ መጠን ለማሳደግ የሎጂስቲክስ እና የጉምሩክ አሰራሮችን ማሻሻል እንደሚገባ ታምኖ ውሳኔው ሲጠበቅ እንደነበረ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ዛሬ ባወጠው መግለጫ አመልክቷል። ጨምሮም ዘርፉ ካሉበት ውስንነቶች መካከል የውጭ ባለሃብቶች ተሳትፎ በመገደቡ በውጪ ንግድ ምርት የሥራ ዘርፍ እና በሌሎች የገቢና ወጭ ሥራ ላይ የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ማግኘት አለመቻላቸው ጠቅሷል። በተለይ ዓለም አቀፍ አምራች ድርጅቶች በሌሎች ተወዳዳሪ በሆኑ ሃገራት በቀላሉ የሚጠቀሙባቸውን አገልግሎቶች በሃገር ውስጥ ማግኘት ባለመቻላቸው በዓለም ገበያ ተወዳዳሪነታቸውን እየጎዳው እንደሚገኝ በተደጋጋሚ ሲገልፁ መቆየታቸውን መግለጫው አመልክቷል። ስለዚህም ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ተኮር በሆነውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተለዋዋጭ ከሆነው የሎጂስቲክስ ኢንዱስትሪ ጋር አብራ እንድትጓዝ ለማድረግና ዘርፉ ለሌሎች የኢንዱስትሪ ዘርፎችና እራሱን ችሎ ለሃገሪቱ ኢኮኖሚ አስተዋፅኦ የሚያበረክትበትን አሰራር ለመዘርጋት እንዲያስችል ማሻሻያ መደረጉ ተገልጿል። በዚህም ዓለም አቀፍ ልምድ ያላቸው የሎጂስቲክስ ኩባንያዎች ከሃገር ውስጥ ኩባንያዎች ጋር በሽርክና አብሮ መስራት የሚያስችላቸውን ማሻሻያዎች በማድረግ የአገር ውስጥ ኩባንያዎችን ተወዳዳሪነትና ውሳኔ ሰጪነት አቅም ለማስጠበቅ፣ ብሎም የቴክኖሎጂና የልምድ ልውውጥ ላይ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ ለማስቻል የውጭ ባለሃብቶች አናሳ ድርሻ በሚይዙበት መልኩ ዘርፉን ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት ማድረጉ ተገልጿል። የኢንቨስትመንት ቦርዱም በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ለአገር ውስጥ ባለሃብቶች ብቻ ተከልሎ የነበረውን ዕቃዎችን የማሸግ፣ የማስተላለፍ እና የመርከብ ውክልና አገልግሎቶችን በመስጠት የኢንቨስትመንት መስክ ዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ ኩባንያዎች ከግማሽ በታች ድርሻ ይዘው ከአገር ውስጥ የሎጂስቲክስ ኩባንያዎች ጋር በሽርክና አብረው መስራት እንዲችሉ ውሳኔ አስተላልፏል።
45262161
https://www.bbc.com/amharic/45262161
የአገልግል ምግብ አምሮዎታል?
አገልግል ሲባል ወደ ብዙዎች ህሊና የሚመጣው ለረዥም ጉዞ የተሰነቀ ጥኡም ምግብና በዛፍ ጥላ ተከልሎ ማዕዱን መቋደስ ነው።
ምግብ በአገልግል ያደርሳሉ ወዳጅ ዘመድ ለመጠየቅ ወይም ከከተማ ወጥቶ ለመዝናናት ሲታሰብ ቤት ውስጥ ጉድ ጉድ ብሎ በተፈለገው ቀን፣ ለተፈለገው መሰናዶ ምግብ ማዘጋጀትም የተለመደ ነው። ቤላ-ዶና የተባለ የምግብ ዝግጅትና መስተንግዶ ተቋም፤ አገልግል ቤት ውስጥ የማሰናዳትን ልማድ 'አዘምኖ'፤ "እናንተ ስለምትሄዱበት ቦታ ብቻ አስቡ፤ የምግብ ዝግጅቱን ለኛ ተውት" እያለ ነው። •ሻደይ፦ለሴቶች፣ በሴቶች ፌስቲቫል •ወሲባዊ ትንኮሳን የሚከላከል ካፖርት ተፈለሰፈ •ፍኖተ ካርታው ወደ ቀድሞ የትምህርት ፖሊሲ ሊመልሰን ይሆን ? በስራ በመወጠር አልያም በሌላ ምክንያት ጊዜ ያጡ ግለሰቦችን ታሳቢ በማድረግ የተጀመረ አገልግሎት ነው። ለቅሶ ለመድረስ፣ ዘመድ ለመጠየቅ ወይም ለሌላ ጉዳይም ምግብ የሚያሰናዱ ተቋሞችን መቅጠር እየተለመደ መጥቷል። ለምግብ ዝግጅት ብቻ ሳይሆን ለመስተንግዶም ተቋም መቅጠር የሚሹ ግለሰቦች መብዛታቸው ደግሞ ነጋዴዎችን ወደ ዘርፉ እየሳበ ነው። በቀን ከ15 እስከ 50 ትእዛዝ ይቀበላሉ በዘርፉ አዋጭነት ከተሳቡ አንዱ ብስራት በላይነህ ነው። የኢኮኖሚክስ ምሩቅ ነው። የመኪና ኪራይ፣ የኤሌክትሮኒክስ ሽያጭ፣ የቴሌቭዥንና ሬድዮ ማስታወቂያ ይሰራ ነበር። አሁን ግን አትራፊ ወዳለው የምግብ ዝግጅትና አቅርቦት ገብቶ ቤላ-ዶናን አቋቁሟል። መነሻ ያደረገው ምሳ ቋጥሮ መሸጥን ነበር። ቤታቸው ምግብ ለማዘጋጀት ጊዜ ወይም ፍላጎቱ ለሌላቸው ሰዎች ቢሯቸው ድረስ ምሳ ቋጥሮ መላክ ከጀመረ ወራት ተቆጥረዋል። ምሳ ሰአት ላይ፤ ምግብ በምሳ እቃ እንዲላክላቸው የሚፈልጉ ሰራተኞች የሚጠበቅባቸው ስልከ መደወል ብቻ ነው። የሚፈልጉትን የምግብ አይነት ያዛሉ። ከዛም ምሳ ሰአት ላይ ትኩስ ምግብ ይወሰድላቸዋል። "ለደንበኞቻችን ትኩስ ምግብ፣ በተመጣጣኝ ዋጋ፣ ያሉበት ቦታ ድረስ ለማቅረብ አስበን ነው ስራውን የጀመርነው" ይላል። ንግዱ እየተጧጧፈ ሲመጣ ምግብ በአገልግል ወደ ማድረስ ተሸጋገረ። ምግቡ የሚዘጋጀው አዲሱ ገበያ አካባቢ ነው። በምሳ እቃ ሀያ ሁለት፣ ቦሌ፣ መርካቶ፣ አውቶብስ ተራ፣ ጳውሎስ ሆስፒታል አካባቢም ይደርሳል። በአገልግል ሲሆን ግን የሰፈሮች ድንበር አይገድበውም። "ሽሮም፣ ዶሮም አለን" ብስራት ምግብ በአገልግል ወደማቅረቡ ስራ የገባው በምግብ ዝግጅት ከሰለጠነች ዘመዱ ጋር ነበር። የሚኖሩበት ቤት ውስጥ ምግብ በማዘጋጀት ከጀመሩ በኃላ ስራው ሲሰፋ ተጨማሪ ምግብ አብሳዮች ቀጠሩ። የጸምና የፍስክ ምግብ ያቀርባሉ ምግብ መሰናዶውን በአንድ በኩል ሲያካሂዱ፤ ተረክበው በየአስፈላጊው ቦታ የሚያደርሱ ተቀጣሪዎችም አሏቸው። ስለ አገልግሎታቸው የሚያስተዋውቁት በፌስቡክ ሲሆን፤ በማህበራዊ ሚዲያ ያልደረሷቸውን ደግሞ በያሉበት በመሄድ በራሪ ወረቀት ይበትናሉ። ንግዱ በዋነኛነት የሚካሄደው በቢሮዎችና ሱቆች ስለሆነ በነዚህ አካባቢዎች ራሳቸውን ከማስተዋወቅ አይቦዝኑም። በቀን ከ 15 እስከ 50 ትእዛዝ ይቀበላሉ። የምግብ ዝርዝሩ የጾምና የፍስክ፤ የሀገር ውስጥና የባህር ማዶ በሚል ተከፍሏል። ክትፎ፣ ጥብስ ፍርፍር፣ መኮሮኒ፣ ሩዝ. . . ዝርዝሩ ሰፊ ነው። ሽሮና ፓስታን የመሰሉ ምግቦች በምሳ እቃ ከ 40 እስከ 45 ብር ይሸጣሉ። ክትፎ ደግሞ በ85 ብር። በአገልግል ሲሆን፤ ሰባት የጾም ምግቦች ተካተው 73 ብር ያስከፍላል። ለአምስት አይነት የፍስክ ምግብ 85 ብር ይከፈላል። ወደድ የሚለው በብዙዎች የሚወደደው ዶሮ ነው። ሙሉ ዶሮ ወጥ፣ ከአይብና ከ 12 እንቁላል ጋር 900 ብር ነው። "ሰዎች 'የቤት የቤት የሚል ምግብ ነው' ይሉናል'" የሚለው ብስራት በተለይም መካከለኛ ገቢ ያላቸውን ታሳቢ ማድረጋቸውን ይገልጻል። "ወደ አስቤዛ ሸመታ መግባት እንፈልጋለን" 'ዘመነኛ' የሚባለው ኑሮ ቤት ውስጥ ይሰሩ የነበሩ ምግቦችን ወደ ተቋም እያዘዋወረ ይመስላል። ብስራትም የማህበረሰቡን ፍላጎት ተንተርሶ የቅመማ ቅመም ዝግጅትና የአስቤዛ ሸመታ ውስጥም ለመግባት አስቧል። ምግብ በምሳ እቃ ያደርሳሉ "ግባችን የሰውን ህይወት ማቅለል ነው" ይላል። ስራውን ሲጀምሩ ብዙ ሰው እውን በአገልግል ያመጣሉ? ብሎ ይጠራጠር ነበር። አሁን ግን ተአማኒነት እያገኙ እንደሆነ ያምናል። "በብዙ ቦታዎች አገልግል አልተተወም፤ ምናልባት የዘነጉት ወጣቶች ካሉ እያስታወስናቸው እንደሆነ ይሰማኛል" ይላል። በጊዜ ሂደት የአስቤዛ ሸመታን እንደሚያስለምዱም ያምናል።
news-56398441
https://www.bbc.com/amharic/news-56398441
በሞዛምቢክ ህጻናት አንገታቸውን እየተቀሉ መሆናቸውን ሴቭ ዘ ችልድረን ገለፀ
በሞዛምቢክ ካቦ ዴልጋዶ አውራጃ የ 11 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሕፃናት ጭምር አንገታቸውን እየተቀላ ነው ሲል ሴቭ ዘ ችልድረን ገለጸ።
አንዲት እናት ከሌሎቹ ልጆቿ ጋር በተደበቀችበት የ 12 ዓመቱን ልጇ በተመሳሳይ መንገድ ሲገደል ማየቷን ለሴቭ ዘ ችልድረን ገልጻለች። የሽምቅ ጥቃቱ ከተጀመረበት ከጎርጎሮሳዊያኑ 2017 አንስቶ ከ 2500 በላይ ሰዎች ሲገደሉ 700 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ቤታቸውን ጥለው ተሰደዋል፡፡ ከእስላማዊ መንግስት (አይ ኤስ) ጋር ግንኙነት ያላቸው ታጣቂዎች በአካባቢው ለተፈጠረው ግጭት ምክንያት ናቸው፡፡ ሴቭ ዘ ችልድረን በሪፖርቱ ከጥቃቱ በስተጀርባ ማን እንዳለ አልገለጸም። ሆኖም ከታንዛኒያ ጋር በሚያዋስነው እና በጋዝ በበለፀገው በሰሜናዊ የአገሪቱ አውራጃ አሰቃቂ ትዕይንቶችን ተፈናቃዮች መመልከታቸውን ገልጿል፡፡ ለደህንነቷ ሲባል ስሟ ያልተጠቀሰው አንዲት እናት እርሷ እና ሌሎች ልጆቿ በተደበቁበት የትልቅ ልጇ አንገት ሲቀላ መመልከቷን ትናገራለች፡፡ "በዚያች ሌሊት መንደራችን ጥቃት ደርሶበት ቤቶችም ተቃጥለዋል" ብላለች፡፡ "ጥቃቱ ሲጀመር ከአራቱ ልጆቼ ጋር ቤት ነበርኩ። ወደ ጫካ ለማምለጥ ስንሞክር የበኩር ልጄን ወስደው አንገቱን ቀሉት። እኛም እንዳንገደል በመፍራት ምንም ማድረግ አልቻልንም" ስትል ገልጻለች። ሌላኛው እናት ደግሞ ልጇ በታጣቂዎቹ ሲገደል እርሷ እና ሌሎች ሦስት ልጆቿ ደግሞ ለመሸሽ መገደዳቸውን ተናግራለች፡፡ "የ 11 ዓመቱ ልጄ ከተገደለ በኋላ በመንደራችን መቆየቱ ስጋት ፈጥሮብናል" ብላለች፡፡ "ሌላ መንደር ወደ ሚገኘው የአባቴ ቤት ብንሄድም ከቀናት በኋላ ጥቃቶቹም እዚያም ቀጠሉ" ስትል ገልጻለች፡፡ በሴቭ ዘ ቺልድረን የሞዛምቢክ ዳይሬክተር የሆኑት ቻንስ ብሪግስ በበኩላቸው በሕፃናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች "ከፍተኛ ህመም ፈጥሮብናል" ብለዋል፡፡ "ሠራተኞቻችን በመጠለያ ጣቢያዎች የሚነገራቸውን የመከራ ታሪኮች ሲሰሙ በእንባ ታጥበዋል" ብለዋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት በበኩሉ የታጣቂዎቹን ድርጊት "ቃላት ከሚገልጹት በላይ ጭካኔ የተሞላበት" ሲል ገልጾታል። ሞዛምቢክ ከአጠቃላይ ህዝቧ 18 በመቶው ሙስሊም ነው ታጣቂዎቹ እነማን ናቸው? ታጣቂዎቹ በአካባቢው አል-ሸባብ በመባል የሚታወቁ ሲሆን የአረብኛ ትርጉሙም ወጣቶች ማለት ነው፡፡ ይህም አብዛኛዎቹ ሙስሊም በሆኑባት ካቦ ዴልጋዶ ከሚኖሩ ሥራ አጥ ወጣቶች ድጋፍ እንደሚያገኝ ያሳያል፡፡ ተመሳሳይ ስም ያለው ቡድን በሶማሊያ ከአስር ዓመታት በላይ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ የሶማሊያው ቡድን አጋርነቱን ለአልቃይዳ ሲሰጥ የሞዛምቢኩ ቡድን ለተቀናቃኙ አይ ኤስ መሆኑን ይናገራል። አንዳንድ ተንታኞች የአማጽያኑ መሰረት በማህበራዊ-ኢኮኖሚያዊ ቅሬታዎች ላይ የተመሠረተ እንደሆነ ያምናሉ። ብዙዎቹ የአካባቢው ነዋሪዎች ከክልሉ ሩቢ (እንደ አልማዝ ያለ የከበረ ድንጋይ ነው) እና ጋዝ ያገኙት ጥቅም አነስተኛ መሆኑን ጠቅሰው ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡ ባለፈው ዓመት አንድ የታጣቂ መሪ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት "እኛ [ከተሞቹን] የምንይዘው መንግሥት ፍትሃዊ አለመሆኑን ለማሳየት ነው፡፡ ድሆችን እያዋረደ ትርፉን ለበላዮች ይሰጣል" ብለዋል፡፡ ግለሰቡ ስለ እስልምና ያወራ ሲሆን "እስላማዊ መንግሥት ስለመመስረት እንጂ ስለ ኢ-አማኝ መንግሥት" ፍላጎት እንደሌለው ተናግሯል። በሞዛምቢክ ጦር ይፈጸማሉ የተባሉ በደሎችንም በመጥቀስ መንግሥት "ኢ-ፍትሃዊ" ነው ሲል በተደጋጋሚ ያማርራል፡፡ ብሪግስ ለቢቢሲ ወርልድ ሰርቪስ እንደገለጹት ማኒፌስቶ ስለሌላቸው ትክክለኛ መነሻቸውን ማወቅ ከባድ ነው፡፡ "ወጣቶችን ለውትድርና እንዲቀላቀሏቸው ይጠየቁና አሻፈረኝ ካሉ ይገደላሉ። አንዳንድ ጊዜም አንገታቸውን ተቀልቶ ነው የሚገደሉት፡፡ በእውነቱ መጨረሻው ምን እንደሆነ መገመት ከባድ ነው" ብለዋል፡፡ የደቡብ አፍሪካ ጳጳስት ጉባኤ ልዑካን ቡድን ባለፈው ዓመት የካቦ ዴልጋዶ ዋና ከተማ የሆነችውን ፔምባን ከጎበኙ በኋላ "ሁሉም የብዙ አገራት ኮርፖሬሽኖች የክልሉን የማዕድንና የጋዝ ሃብቶች በመቆጣጠራቸው ጦርነቱ መጀመሩን ያናገርናቸው በሙሉ ተስማምተውበታል ማለት ይቻላል" ብለዋል፡፡ ካቦ ዴልጋዶ ምን ትመስላለች? ካቦ ዴልጋዶ በሞዛምቢክ ካሉ እጅግ በጣም ድሃ አውራጃዎች አንዷ ስትሆን ከፍተኛ ያልተማሩ ሰዎች እና ሥራ አጥ ያለባት ናት፡፡ ከጎርጎሮሳዊያኑ 2009 እስከ 2010 ባለው ጊዜ ውስጥ በጣም ብዙ የሩቢ እና ግዙፍ የጋዝ ጉድጓዶች መገኘታቸው፣ የአካባቢው ሰዎች የሥራ ዕድል እና የተሻለ ህይወት እንደሚኖራቸው ገምተው ነበር። ነገር ግን እነዚህ ተስፋዎች ብዙም ሳይቆዩ በንነዋል፡፡ ሞዛምቢክ በ1975 ነፃነቷን ከተቀዳጀች ጀምሮ እያስተዳደራት የቆየው ፍሬሊሞ ፓርቲ አመራሮች እየተጠቀሙ ነው በሚል ቅሬታ ይቀርብባቸዋል፡፡ መንግሥት ዋና ትኩረቱ ወታደራዊ መፍትሄ መፈለግ ላይ ቢሆንም ሠራዊቱ ለመዋጋት በቂ አቅም የለውም፡፡ በመዲናዋ ማፑቶ የሚገኙት የአሜሪካ ኤምባሲ ባለሥልጣናት የአሜሪካ ወታደሮች ለሁለት ወራት ወታደሮችን በማሰልጠን "የሕክምናና የመገናኛ መሣሪያዎችን" እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል፡፡ ለሞዛምቢክ ኃይሎች ስልጠና እንደሚሰጥ የአውሮፓ ህብረትም ባለፈው ዓመት አስታውቋል፡፡ ይህም ሞዛምቢክ ታጣቂዎችን ለመዋጋት እንዲረዷት የሩሲያ እና የደቡብ አፍሪካ ቅጥረኞችን መመልመሏን ተከትሎ የመጣ ነው፡፡ የሩሲያ ቅጥረኞች በአመጸኞቹ የደረሰባቸውን ኪሳራ ተከትሎ ከካቦ ዴልጋዶ መውጣታቸው ተገልጿል፡፡
55255789
https://www.bbc.com/amharic/55255789
የባይደን ልጅ ላይ የግብር ምርመራ እየተካሄደ ነው
የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ሆነው የተመረጡት የጆ ባይደን ልጅ፤ ሀንተር ባይደን የግብር ምርመራ እየተካሄደበት መሆኑን አስታወቀ።
ምርመራው እየተከናወነ የሚገኘው ዳልዌር ባሉ ዐቃቤ ሕጎች ነው። ሀንተር ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት እንደሰጠና ምርመራው ገለልተኛ ከሆነ ምንም ሕገ-ወጥ ተግባር እንዳልፈጸመ እንደሚታወቅ ገልጿል። ጆ ባይደን "ልጄ ብዙ ነገር አሳልፏል። ባለፉት ጥቂት ወራት ጥቃት ሲሰነዘርበት ነበር። ግን አልሰበረውም። እኮራበታለሁ" ሲሉ ሀንተርን አሞግሰዋል። ሀንተር ስለ ምርመራው ዝርዝር መረጃ አልሰጠም። የ50 ዓመቱ የባይደን ልጅ በምርጫ ቅስቀሳው ወቅት በተደጋጋሚ የሪፐብሊካኖች ትችት ኢላማ ሆኗል። በተለይም ሃንተር በዩክሬን እና ቻይና ባለው የንግድ ተሳትፎ ሲብጠለጠል ቆይቷል። በባራክ ኦበማ ዘመነ መንግሥት ምክትል ፕሬዘዳንት የሆኑት ባይደን ስማቸው ከቢዝነሶቹ ጀርባ ይነሳል። ዶናልድ ትራምፕ ዩክሬን የባይደን ቤተሰብ ላይ ምርመራ እንድታደርግ ጫና ፈጥረዋል በሚል ባለፈው ዓመት ምርመራ ተደርጎባቸው እንደነበር ይታወሳል። ሆኖም ግን ትራምፕ ነፃ ተብለው ምርመራው ተገባዷል። ባይደን ካቢኔያቸውን እያዋቀሩ ሳለ ነው ልጃቸው ላይ ምርመራ መከፈቱ የተሰማው። በቀጣዩ ወር ባይደን በዓለ ሲመታቸው ሲከናወን ምርመራው ካልተጠናቀቀ፤ ምርመራውን የሚመሩት ባይደን የሚመርጧቸው ዐቃቤ ሕግ ይሆናሉ። ሀንተር ላይ ምርመራ ሊደረግ እንደሚችል የሚጠቁሙ መረጃዎች ለወራት ሲወጡ ነበር። ምርመራው እንዲካሄድ ትራምፕ ጫና አሳድረዋል ሲሉ የሚወቅሷቸው ቢኖሩም፤ ምርመራውን የሚመሩት ዐቃቤ ሕግ ዴቪድ ዌይስ በሙያው የተከበሩ ናቸው። ዐቃቤ ሕጉን የመረጧቸው ትራምፕ ቢሆኑም፤ በኦባማ አስተዳደር ምክትል ዐቃቤ ሕግ ሆነው አገልግለዋል።
47963855
https://www.bbc.com/amharic/47963855
ኢትዮጵያ ከውጭ ምንዛሬ እጥረት አዙሪት እንዴት ትውጣ?
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ያላት መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት የሁለት ወር ከስድስት ቀን ፍላጎትን የሚሸፍን እንደሆነና ይህም ለመድሃኒትና ለነዳጅ የሚውል እንደሆነ ከጥቂት ቀናት በፊት ተዘግቧል።
አገሪቱ የሁለት ወር ተኩል ብቻ መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ነው ያላት ማለት ምን ማለት ነው? ለኢኮኖሚ ኤክስፐርቱ ዶ/ር አሰፋ አድማሴ ያነሳነው ጥያቄ ነበር። አገሪቱ በመደበኛ ሁኔታ ባለፉት ዓመታት ከሶስት ወር የሚበልጥ መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ኖሯት አያውቅም። "ያለው መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ለሁለት ወር ብቻ የሚሆነው ማለት ያለውን አሟጠን እጃችንን አጣጥፈን እንቀመጣለን ማለት አይደለም" በማለት በተጠቀሰው ሁለት ወር እና ጥቂት ቀናት ጊዜ ውስጥ ከውጭ በሚላክ ገንዘብ፣ በእርዳታ ፣ በብድርና በወጪ ንግድም የሚመጣ የውጭ ምንዛሬ ይኖራል ይላሉ። • ሱዳን በህዳሴው ግድብ ጉዳይ አቋሟን ትቀይር ይሆን? ከውጭ እቃዎችን ለማስገባት የሚውል መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት አስፈላጊ ቢሆንም አገሪቱ ለሁለት ወራትና ጥቂት ቀናት የሚሆን ነው ያላት ማለት የሚያሸብር ነገር እንዳልሆነ ያስረግጣሉ። በርግጥም ክምችቱ ትንሽ ነው ስጋትም ያሳድራል ነገር ግን በዚሁ አበቃ ማለት አይደለም ይላሉ። አገራት ምን ያህል ክምችት እንዲኖራቸው ይመከራል? ምንም እንኳ በተፃፈ ህግ ባይሆንም እንደ አሰራር የአለም የገንዘብ ድርጅት አይ ኤም ኤፍ አገራ ከሶስት እስከ ስድስት ወር መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት እንዲኖራቸው ይመክራል። ያነጋገርናቸው ሌላው የኢኮኖሚ ኤክስፐርት ዶ/ር እዮብ ተስፋዬ የሶስት ወር ክምችት በቂ ሊባል የሚችል ሲሆን ብዙ ጊዜ ችግሮች ሊከሰቱ የሚችሉት መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ከሶስት ወር በታች ሲሆን እንደሆነ ይገልፃሉ። እንደ ኢትዮጵያ ላሉ አገራት የሶስት ወር ክምችት መያዝ ጥሩ እንደሆነ ቢመከርም መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሶስት ወር ያነሰ መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ይዞ መገኘትን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የተላመደው እንጂ እንግዳው አለመሆኑን ነው። በአስቸጋሪ፤ በመደበኛ ሁኔታም እውነታው ይህው ነው። ለሶስት ወር የተባለውም መሻሻል እንጂ ሁልጊዜ ሶስት ወር ሆኖ መቅረትም ግን የለበትም። የመጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ "በደርግ መውደቂያ፣ በኢትዮጵያና ኤርትራ ጦርነት ወቅትም የአስር ቀን ነበር" የሚሉት ዶ/ር እዮብ የዛሬ ዓመት በተመሳሳይ ወቅት የመጠባበቂያ ክምችቱ የሶስት ሳምንት ብቻ እንደነበርም ያስታውሳሉ። እናም የዛሬው ክምችት ከዚያ እያለ እያለ ያደገ ነው። ከኤክስፖርት የሚገኘው ገቢ በጣም ውስን በመሆኑ ፣ ከውጭ ከሚላክ ገንዘብ የሚገኘው የውጭ ምንዛሬም የተሻሻለው በቅርብ በመሆኑና አሁንም ብዙው በጥቁር ገበያ የሚተላለፍ በመሆኑ ፣ ከአገልግሎት ሰጪ ዘርፉ የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ የተሻሻለው ገና በቅርቡ በመሆኑ የመጠባበቂያ ክምችቱ ሊያድግ እንዳልቻለም ያስረዳሉ። ነገር ግን የአሁኑን የአገሪቱ መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት አነስተኛ መሆንን የተለየ የሚያደርገው የውጭ እዳ ጫና የበረታበት ጊዜ ላይ መሆኑ እንደሆነ ይገልፃሉ። ስለዚህም በዚህ የእዳ ጫና ምክንያት መጠባበቂያው ሳይነካ ከውጭ ለሚገቡ እቃዎች የሚቀርብ የውጭ ምንዛሬም ከፍተኛ እጥረት አለ። ይህ ከዚህ ቀደምም ሞልቶም አያውቅም። • የመይሳው ካሳ የልጅ ልጆች የመጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት አገልግሎት ምንድን ነው? በዓለም አቀፍ ገበያ ባልተጠበቀ መልኩ የነገሮች ዋጋ ሲንር ፤ ለምሳሌ የነዳጅ ዋጋ ሳይታሰብ ቢጨምር ወይም በአገራት መካከል በተፈጠረ ግጭት የእቃዎች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ሲጨምር የሚፈጠር ችግርን ለመቋቋም የሚውል ነው። ከዚህ በተጨማሪም ለኢንቨስተሮች መተማመኛም ነው። ኢንቨስተሮች መዋእለ ነዋያቸውን ለማፍሰስ ሲያስቡ የሚያዩት የመጀመሪያ ነገር የአገሪቱ መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ምን ያህል ነው? እንዲሁም የውጭ ምንዛሬ አያያዙ ምን ይመስላል? የሚለውን እንደሆነ ዶ/ር እዮብ ይናገራሉ። የውጭ ምንዛሬ ዋጋን በማስተካከል እረገድም ምን ይደረግ? የሚለውን አቅጣጫ ጠቋሚም ነው። ለምሳሌ የዶላር ዋጋ ከፍ ሲል ገበያውን ለማስተካከል ይረዳል። ከውጭ ምንዛሬ እጥረት አዙሪት እንዴት ይወጣ? አገሪቱን ለዓመታት እየተሽከረከረችበት ካለው የውጭ ምንዛሬ እጥረት ችግር ለመታደግ የወጪ ንግድ ላይ በርትቶ ከመስራት ውጪ ሌላ አማራጭ አለ ብለው እንደማያምኑ ዶ/ር አሰፋ ይናገራሉ። መንግሥትም ብዙ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን እየገነባ ያለው ለዚሁ ሲባል ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እንደሆነ ይጠቅሳሉ። ከዚህ አንፃር የአገሪቱ የወጪ ንግድ ያለበት ሁኔታ መፍትሄ ለመሆን ተስፋ የሚጣልበት ነው ወይ? የሚለው ወሳኝ ጥያቄ ነው። መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከወጪ ንግድ የሚገኘው ገቢ እየቀነሰ ፤ የወጪ ንግድን እንደ ዋነኛ ዘርፍ ያለመቁጠር አዝማሚያም እየተፈጠረ ነው። ጥቂት የማይባሉ በወጪ ንግድ ላይ የተሰማሩት ፈልገውት ሳይሆን ይልቁንም ለማስመጣት ስራቸው እንዲረዳቸው ብለው ነው። በአገሪቱ ሳይፈታ እየተሽከረከረ ያለው የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ለመፍታት የዘላቂ ስትራቴጂ አስፈላጊነትን አፅንኦት የሚሰጡት ዶ/ር እዮብ ፤ ለወጪ ንግድ እየተሰጠ ያለው ትኩረት ሊቀጥል ቢገባም የአቅጣጫ ለውጥ ያስፈልጋል ይላሉ። በዓለም አቀፍ ዋጋ መውረድ ከቡና ብዙ ማግኘት አልቻልንም የዚህ ዓመት አፈፃፀሙ ጥሩ አይደለም እያሉ ማለፍ ሳይሆን ይህ ባይሳካ ያንን እያሉ አማራጮችን ማስቀመጥ እንሚያስፈልግ ያሳስባሉ። እንደ ግብርና ፣ ንግድ፣ ኢንዱስትሪ እንዲሁም ማእድን ሚኒስቴር ያሉ የተለያዩ መስሪያቤቶች በተናጥል የወጪ ንግድን እናበረታታለን ይላሉ። ነገር ግን ይህ የተበታተነ አሰራርን ሰብስቦ አገሪቱ የተቀናጀ የወጪ ንግድ ስትራቴጂ እንዲኖራት ማድረግ ግድ ነው ይላሉ ዶ/ር እዮብ። እንደ እሳቸው አስተያየት ከውጭ ከሚላክ ገንዘብ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘትና ለመጠቀምም የሚያዋጣ አካሄድ መከተል አስፈላጊ ነው ይላሉ። ምክንያቱም ብዙዎች ፊታቸውን ያዞሩት ወደ ጥቁር ገበያው ነውና። ቱሪዝም ትኩረት ይደረግበት የሚሉት ሌላ ዘርፍ ሲሆን "ተስፋ የተጣለበት ኢንዱስትሪ ፓርክስ እንደተባለለት ነው ወይ ብሎ መመርመር የሚያስፈልግም ይመስለኛል"ሲሉ ያክላሉ። መንግሥት የውጭ ምንዛሬ ተመንን ገበያው እንዲወስን ማድረግን ቀጣይ አቅጣጫ አድርጎ ያስቀመጠ መሆኑን በተመለከተም በሚቀጥሉት ሁለትና ሶስት ዓመታትም የሚሳካ እንደማይመስላቸው ግምታቸውን ያስቀምጣሉ። • የፖለቲካ አለመረጋጋት ለኢንስትመንት ደንቃራ ሆኖ ነበር
news-52280928
https://www.bbc.com/amharic/news-52280928
ኮሮናቫይረስ፡ ዴንማርክ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የዘጋችውን በሯን ለመክፈት ለምን ቸኮለች?
ዴንማርክ የእንቅስቀሴ እቀባዋን ለማላላት ተፍ ተፍ እያለች ነው። ከነገ ረቡዕ ጀምሮ 11 ዓመትና ከዚያ በታች ያሉ አዳጊዎች ወደ ትምህርት ቤት መመለስ ይችላሉ።
ጭር ያሉት የኮፐንሃገን ጉዳናዎች ይህን ለማድረግ ከአውሮፓ አገሮች ቀዳሚዋ ናት። ዴንማርክ ከወራት በፊት ወረርሽኙ ሲጀማምር ሰሞን ትምህርት ቤቶችንም ሆነ የንግድ ተቋማትን ለመዝጋት ከቀዳሚ አገራት ተርታ ነበረች። "ከሚያስፈልገን ጊዜ በላይ በራችንን መዝጋት ያለብን አይመስለንም" ብለዋል ክብርት ጠቅላይ ሚኒስትር ሜት ፍሬድሪክሰን። ከሞላ ጎደል የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በዴንማርክ በቁጥጥር ሥር የዋለ ይመስላል። መንግሥት የአገሪቱን ምጣኔ ሀብት እንደገና ማንቀሳቀስ ይፈልጋል። ዴንማርክ እየወሰደችው ያለው እርምጃ ግን ግብታዊ የሚባል አይደለም። በከፍተኛ ጥንቃቄ እየሆነ ያለ ነው። ንግዶችና ሌሎች እንቅስቃሴዎች እየተከፈቱ የሚመጡትም ቀስ በቀስ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሯ ፍሪድሪክሰን እንዳሉት ነገሩ በቀጭን ገመድ ሚዛንን ጠብቆ እንደመራመድ ያለ ነው። "ሁሉንም ነገር በአንድ ጊዜ ከከፈትነው፣ ወረርሽኙ በአንድ ጊዜ ሰማይ ይነካል፤ ያን ጊዜ በድጋሚ ለመዝጋት እንገደዳለን" ብለዋል። ሆኖም ዴንማርክ ድንበሮቿ ዝግ እንደሆኑ ይቆያሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ሜት ፍሬድሪክሰን ከዴንማርክ ሌላ የትኞቹ አገራት በራቸውን እየከፈቱ ነው? ኖርዌይና ኦስትሪያም የዴንማርክን ፈለግ እየተከተሉ ነው። ቀስ በቀስ በራቸውን በትንሹ መክፈት ይዘዋል። ኦስትሪያ እንዲያውም ዛሬ ማክሰኞ ሱቆችን ከፋፍታለች። ሆቴሎችና ሬስቶራንቶችም ቀስ በቀስ እየተከፈቱ ነው። ኖርዌይ ከ6 ቀናት በኋላ በኤፕሪል 20፣ የመዋዕለ ሕጻናትና አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲሄዱ ትፈቅዳለች። ቡልጋሪያ የገበሬዎች እርሻ እንዲከፈት ፈቅዳለች። በቼክ ሪፐብሊክ ደግሞ መናፈሻዎች ተከፍተዋል። የሕንጻ መሣሪያ መደብሮች ወደ ሥራ ተመልሰዋል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ክፉኛ የተመሰቃቀለችው ስፔንም ከሰኞ ጀምሮ አንዳንድ እንቅስቃሴዎቿ ወደነበሩበት ይመለሳሉ ተብሏል። ዜጎች የአፍ-አፍንጫ ጭምብል በየአውቶቡስ ተራና ባቡር ጣቢያ ይታደላቸዋል ተብሏል። ከነዚህ የአውሮፓ አገራት ውጭ ያሉት ግን ከወረርሽኙ በፊት የነበረውን እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል ወደነበረበት ለመመለስ ጊዜው ገና ነው ብለው ያምናሉ። የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶሚኒክ ራብ "እንዲህ ዓይነቱን ነገር ለማሰብ የምንሞክርበት ወቅት ላይ አይደለንም" ብለዋል። ዴንማርክ ለምን ቸኮለች ታዲያ? ከሌሎች የአውሮፓ አገሮች ጋር ሲነጻጸር ዴንማርክ እግዱን በመጣሉም ሆነ በማንሳቱ ቀዳሚ ናት ብለናል። ለምሳሌ የመጀመርያውን እግድ የጣለችው ከዩናይትድ ኪንግደም በሁለት ሳምንት ቀድማ በማርች 11 አካባቢ ነበር። ያን ጊዜ ዴንማርክ ከ10 ሰው በላይ በአንድ ቦታ እንዳይሰባሰብ፣ ሠራተኞች ወደ ሥራ እንዳይሄዱ፣ ድንበሮችም እንዲዘጉ ነበር የወሰነችው። ይህ ግን ከጎረቤቷ ስዊድን ፍጹም የተለየ ውሳኔ ነበር። በስዊድን ብዙዎቹ ነገሮች ከወረርሽኙ በፊት እንደነበሩ ነው ያሉት ማለት ይቻላል። በቅርቡ ብቻ ከ500 ሰዎች በላይ መሰብሰብ የሚከለክለውን ደንብ ወደ 50 ዝቅ አድርጋለች። ነገር ግን የዴንማርክን የወረርሽኝ ጊዜ ደንብ ከነፈረንሳይና ጣሊያን እንዲሁም ዩናይትድ ኪንግደም ጋር ካስተያየነው እጅግ የላላ ሆኖ እናገኘዋለን። ለምሳሌ ዴንማርክ ቤት ውስጥ ቆልፋችሁ ዋሉ የሚል ደንብ አልነበራትም። ቡና ቤቶች፣ ስፖርት ቤቶችና ጸጉር ቤቶች ዝግ እንዲሆኑ ብታዝም አነስተኛ ሱቆች ዝግ እንዲሆኑ ግን አልደነገገችም። የጤና ስታትስቲክስ ቁጥሮች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ዴንማርክ ከብዙ የአውሮፓ አገሮች በአንጻራዊነት ልል የነበሩ ድንጋጌዎቿ ጎድቷታል ብሎ መደምደም ይከብዳል። እስከ ሰሞኑ ድረስ ዴንማርክ የሞቱባት 260 ሰዎች ብቻ ናቸው። ተያዙ የተባሉት ሰዎች ቁጥርም 6 ሺህ አካባቢ ነው። ይህ ከነጣሊያንና ስፔን እንዲሁም ከዩናይትድ ኪንግደም ጋር ሲነጻጸር እዚህ ግባ የሚባል ቁጥር አይደለም። ምንም እንኳ አንድ ሞትም ቢሆን ሕይወት ስለሆነ የሚያስቆጭ ቢሆንም። ከሁሉ በላይ ደግሞ ልዩ የሚያደርጋት በዴንማርክ ወደ ጽኑ ሕሙማን የሚገቡ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ መምጣቱ ነው፤ ከዚህ ወር መግቢያ ጀምሮ። ዴንማርክ በዚህ ሰዓት የመደበኛ ታማሚ አልጋ፣ የጽኑ ሕሙማን አልጋዎችና የሕክምና መሣሪያዎች በሽበሽ ናቸው። አሁን ዴንማርክ እየተዘጋጀች ያለችው ድንገት ወረርሽኙ ቢያገረሽ በአንድ ጊዜ በርካታ ዜጎችን ለመመርመር የሚያስችል አቅም መፍጠር ላይ ነው። በዚህ ጊዜ በር መክፈት፣ እቀባን ማንሳት ያዋጣል? የዓለም ጤና ድርጅት አለቃ ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም አገራት በራቸውን ለመክፈት የሚያሳዩት ጉጉት አሳስቧቸዋል። እጅግ ጥንቃቄ የሚሻ ጉዳይ ነው ሲሉ ነው ያስቀመጡት፤ ትናንትና። ዴንማርክ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤቶች ስትልክ ደንቦች ተፈጻሚ ይሆናሉ። ለምሳሌ ተማሪዎች ተጠጋግተው አይቀመጡም፤ ተጠጋግተው አይጫወቱም። እንዲያውም ተማሪዎች ከክፍል ውስጥ ተቀምጠው ሳይሆን ደጅ ሆነው ነው በብዛት የሚማሩት። በዴንማርክ አዳጊዎችን ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ውሳኔ በሕዝብ ላይ ምን ስሜት አሳደረ ሲል ቢቢሲ ገምግሟል። ለምሳሌ አንድ የፌስቡክ ማኅበር ተከፍቷል። "ልጄ የኮቪድ-19 መሞከሪያ አይጥ አይደለም" የሚል ነው የማኅበሩ ስም። በአጭር ጊዜ 35 ሺህ ሰዎች ወደውት አባል ሆነዋል። ሌላ አንዲት የገበያ ጥናት ባለሞያ ስለ ውሳኔው ለቢቢሲ ስትናገር፣ "ሦስት ልጆች አሉኝ፤ ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ ምንም ስጋት የለብኝም፤ እኔም ሥራዬን ከቤት ሆኜ ለማቀላጠፍ ይመቸኛል" ብላለች። የዴንማርክ መንግሥት ልጆች ትምህርት እንዲጀምሩ ስለመወሰኑ ወላጆች ያላቸውን አስተያየት የሰበሰበ አንድ ተቋም 86 ከመቶ የሚሆኑት በውሳኔው ደስተኞች ናቸው ብሏል።
news-48762852
https://www.bbc.com/amharic/news-48762852
ዶ/ር አምባቸው በሚያውቋቸው አንደበት
ቅዳሜ ሰኔ 15 2011 ዓ. ም "በመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ" ሕይወታቸውን ካጡት መካከል አንዱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር አምባቸው መኮንን ናቸው።
ዛሬ በባህር ዳር ከተማ ሥርዓተ ቀብራቸው የሚፈጸመው ዶ/ር አምባቸው እንዲሁም አማካሪያቸው አቶ እዘዝ ዋሴና የአማራ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ምግባሩ ከበደ በሚያውቋቸው እንዴት ይታወሳሉ? አቶ ደሴ አስሜ የአማራ ክልል የኢንዱስትሪ ፓርኮች ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሲሆኑ አቶ ደሳለኝ አሰራደ ደግሞ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር የመሠረተ ልማት ጉዳዮች አማካሪ ናቸው። አቶ ደሴ እና አቶ ደሳለኝ፤ ዶ/ር አምባቸው መኮንን እና በጥቃቱ ሕይወታቸውን ያጡትን ባልደረቦቻቸውን በቅርበት ያውቋቸዋል። • "ከፍተኛ ችግር ውስጥ ገብተናል. . . ግን እናሸንፋለን" • “የኢህአፓና መኢሶን ነገር አማራ ክልል ላይ ሊከሰት ይችላል ብዬ ነበር” • ስለ'መፈንቅለ መንግሥት' ሙከራው እስካሁን የማናውቃቸው ነገሮች አቶ ደሴ በጥቃቱ ሕይወታቸውን ያጡት ሦስቱም አመራሮች ከልጅነታቸው ጀምሮ ለሕዝብ ለውጥ እና ልማት ለማምጣት ሲታገሉ የቆዩ ናቸው ካሉ በኋላ፤ ''የታየውን ለውጥ በዋነኛነት ከፊት ሆነው የመሩት እነሱ ነበሩ። የመጣው ለውጥ ከግብ ሳይደርስ፤ ሕዝቡ በሚፈልጋቸው ወሳኝ ሰዓት ላይ ማጣታችን ያስቆጫል'' ይላሉ። ''ዶ/ር አምባቸው እጅግ የተለየ ባህሪ ነው ያለው። አመራር ነኝ ብሎ ሳይኮራ ከትልቅ ከትንሹ ጨዋታ የሚወድ፣ ራሱን ዝቅ አድርጎ ከህብረተሰቡ ጋር የሚነጋገር እና ቅን የሆነ አመለካከት ያለው ጓዳችን ነበረ።'' ሲሉ የአማራ ክልል አራት ወራት የመሩትንና በ48 ዓመታቸው ያረፉትን የቀድሞውን የክልሉን ርዕሰ መስተዳደርን ይገልጿቸዋል። ''ሦስቱም ጓደኞቼ ነበሩ'' የሚሉት አቶ ደሴ፤ ከዶ/ር አምባቸው ጋር ይቀራረቡ እንደነበር ይናገራሉ። ''ትምህርት ቤት ሳለ እንኳ ቀዳሚ ተማሪ ነበረ። የተሻለ እውቀት እና ግንዛቤ ስለነበረው ከአገር ውጪ ሄዶ እንዲማር ሁሉ ተደርጓል'' በማለት ይናገራሉ። አቶ ደሴ ዶ/ር አምባቸው በተማሩባቸው የትምህርት ዘርፎች ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ እንደተመረቁ ጨምረው ተናግረዋል። አቶ ደሳለኝ አሰራደ በበኩላቸው ያጣነው "አራት አመራሮች ነው" ይላሉ። ከብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌ ጋር በስተመጨረሻ የተፈጠረው ነገር እንዳለ ሆኖ ክልሉ እንዲሁም አገሪቷ አራት ሰዎችን ማጣቷን ይገልጻሉ። ''ሦስቱም አመራሮቹ ጓደኞቼም የሥራ ባልደረቦቼም ነበሩ። ሁሉም አንድ አመራር ሊኖረው የሚገባውን ሰብዕና የተላበሱ ናቸው'' ያሉ ሲሆን፤ ''አማራ ክልል ወሳኝ ሰዎች አጥቷል'' ብለዋል። አቶ ደሳለኝ ከዶ/ር አምባቸው ጋር የሚተዋወቁት ከ1980ዎቹ ጀምሮ ነው። ''ከአምባቸው (ዶ/ር) የማይተዋወቅ ሰው ለተወሰኑ ደቂቃዎች እንኳ አብሮት ቢሆን ተዋውቆና ተሳስቆ ነው የሚለያየው። ዶ/ር አምባቸው ግልጽ፣ ሃሜት የማይወድ እና የተሰማውን የሚናገር። ለተሰጠው ኃላፊነት ተገዢ የሆነ ሰው ነበር'' ይላሉ። ''አምባቸው ደፋር ነው'' የሚሉት አቶ ደሳለኝ፤ ''ከዛሬ 15 ዓመት በፊት ለመጀመሪያ ግዜ በክልሉ የፖለቲካ ጉዞ ውስጥ በይፋ "የአማራ ህዝብ እንደ ብሄር ጨቋኝ ነው" የሚለው አስተሳሰብ ትክክል አይደለም ብሎ በይፋ የተናገረው አምባቸው ነበር። ይህንን በመናገሩም በግል ሕይወቱ ብዙ ፈተና ገጥሞት ነበር። እነዚያን ፈተናዎች በጽናት አልፎ ለዚህ ኃላፊነት የበቃ ሰው ነበር።'' ይላሉ አቶ ደሳለኝ።
news-55690053
https://www.bbc.com/amharic/news-55690053
ትግራይ ፡ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የህወሓትን ሕጋዊ ሰውነት ሰረዘ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይን (ህወሓት) ሕጋዊ ሰውነት መሰረዙን አስታወቀ።
ቦርዱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ህወሓት በአመጻ ተግባር ላይ መሰማራቱን በተመለከተ ለማጣራት በፓርቲው የተሰጡ መግለጫዎችንና "በይፋ የሚታወቁ ጥሬ ሃቆችን በማቅረብ ፓርቲው ኃይልን መሠረት ያደረገ የአመጻ ተግባር ላይ መሣተፉን" በማረጋገጡ መሆኑን ገልጿል። በዚህ መሠረትም ቦርዱን ሕጋዊ ሂደቶችን በመከተል "የፓርቲውን ሕጋዊ ሰውነት ሰርዞታል" በማለት የፓርቲው ኃላፊዎች በፓርቲው ስም መንቀሳቀስ እንደማይችሉም ውሳኔ ማሳለፉን አሳውቋል። የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ጨምሮም ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በፓርቲውና በፓርቲው አመራሮች ላይ በሚያደርገው ምርመራ የሚገኙ በህወሓት ስም የተመዘገቡ ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀስ ንብረቶችን በተመለከተ ያገኘውን ዝርዝር መረጃ እንዲያሳውቀው ጠይቋል። በዚህም መሠረት የፓርቲው ንብረት ተጣርቶ ዕዳ ካለበት ለዕዳው መሸፈኛ እንዲውል፤ እዳውን ሸፍኖ የሚተርፍ ንብረት ከተገኘ ቀሪው ገንዘብና ንብረት ለሥነ ዜጋና መራጮች ትምህርት እንዲውል ቦርዱ ወስኗል። የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ እንዳለው፤ ፓርቲው መልስ የመስጠት እድል እንዲያገኝ በሚል በፓርቲውና በቦርዱ መካከል አገናኝ በመሆን ይሰሩ የነበሩት ያላቸውና በስም ያልተቀሳቸውን የፓርቲውን የአዲስ አበባ ቢሮ የቀድሞ ተወካይ ለማነጋገር ጥረት ያደረገ መሆኑን ገልጾ "ተወካዩም ፓርቲውን መወከል እንደማይችሉ ገልጸዋል" ብለዋል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በህወሓት ላይ ካስተላለፈው ውሳኔ በተጨማሪ ሦስት በትግራይ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሕገወጥ ምርጫ ላይ በመሳረፍና በአመጽ ተግባር ላይ ተሰማርተዋል በሚል መረጃ መሠረት ማብራሪያ እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ህወሓት ከ17 ዓመታት የትጥቅ ትግል በኋላ ወታደራዊውን መንግሥት ከጣለ በኋላ ኢህአዴግ የተባለውን የአራት ፓርቲዎች ግንባር በበላይነት መስርቶ አገሪቱን ለሦስት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ ሲመራ መቆየቱ ይታወሳል። በህወሓት የበላይነት ሲመራ በነበረው የኢትዮጵያ መንግሥት ላይ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሕዝባዊ ተቃውሞ እያየለ በመጣበት በ2010 ዓ. ም. ላይ በወሰደው የለውጥ እርምጃ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ህወሓት ቀደም ሲል በመንግሥት ላይ የነበረውን የበላይነት ሙሉ ለሙሉ ማጣቱ ይታወሳል። ህወሓት ዋነኛ አባል የነበረበት አውራው ፓርቲ ኢህአዴግ በጠቅላይ ሚኒስትሩ መሪነት ከስሞ ብልጽንና የተሰኘው ፓርቲ ሲመሰረት ቀሪዎቹ የግንባሩ አባላት ወደ አዲሱ ፓርቲ ሲጠቃለሉ ህወሓት ከውህዱ የብልጽግና ፓርቲ እራሱን አግልሎ ከጠቅላይ ሚኒስትሩና ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብቶ ቆይቶ ነበር። ባለፈው ዓመት ሊካሄድ ታስቦ የነበረው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለሌላ ጊዜ እንዲሸጋገር ሲደረግ ህወሓት በምርጫ ቦርድና በፌደራል መንግሥቱ እውቅናን ያላገኘ ክልላዊ ምርጫ አካሂዶ ሙሉ በሙሉ ሊባል የሚያስችለውን የክልሉን ምክር ቤት ወንበር ማሸነፉ ይታወሳል። ከዚህ ምርጫ በኋላ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር የነበረው የተበላሸ ግንኙነት ይበልጡኑ እየተካረረ ከሄደ በኋላ ጥቅምት ወር ማብቂያ ላይ በትግራይ ክልል በነበረው የሰሜን ዕዝ ላይ የተሰነዘረውን ጥቃት ተከትሎ የፌደራል መንግሥቱ ባካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ ህወሓት ከክልሉ አስተዳዳሪነት ተወግዷል። በክልሉ በነበረው የፌደራሉ ሠራዊት ላይ ጥቃት እንዲፈጸምና ግጭት እንዲቀሰቀስ በማድረግ የህወሓት አመራሮች ተጠያቂ ሆነው በፌደራል ፖሊስና በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የፍርድ ቤት የእስር ትዕዛዝ ወጥቶባቸው እየተፈለጉ ይገኛሉ። ከእነዚህም መካከል ጥቂት የማይባሉት የህወሓት ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራሮች በቁጥጥር ስር ሲውሉ ሌሎች ደግሞ እርምጃ እንደተወሰደባቸው የአገሪቱ ሠራዊት አሳውቋል። ከዚህ በተጨማሪም ቦርዱ በትግራይ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሦስት ፓርቲዎች ስለእንቅስቃሴያቸው ማብራሪያ እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል። በዚህም ሠረት ብሔራዊ ባይቶ አባይ ትግራይ (ባይቶና) እና ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሣወት) ባለፈው ዓመት ማብቂያ ላይ ሕገ ወጥ በተባለው ምርጫ ላይ በመሳተፍና የፓርቲዎቹ አመራሮች በአመጽ ተግባር ላይ በመሰማራታቸውን የሚያመለክት መረጃ በመገኘቱ ማብራሪያ እንዲያቀርቡ ታዘዋል። በተጨማሪም ዓሲምባ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ዓዴፓ) በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምዝገባ ሂደት ላይ እያለ በትግራይ ክልል በተካሄደው የተናጠል ምርጫ ላይ ስለመሳተፉ ማብራሪያ እንዲያቀርብ መታዘዙ ተገልጿል።
news-54949213
https://www.bbc.com/amharic/news-54949213
ኢራን የአልቃይዳው መሪ ቴህራን ውስጥ አልተገደለም አለች
ባሳለፍነው ነሀሴ ወር ላይ አንድ የታጣቂው አልቃይዳ ቡድን መሪ በዋና ከተማዋ ቴህራን ውስጥ ተገድሏል መባሉን ኢራን አስተባብላለች።
ኒው ዮርክ ታይምስ እንደዘገበው የአልቃይዳ ምክትል መሪ የሆነውና ቁልፍ ሰው ነው የሚባልለት አብዱላህ አህመድ አብዱላህ በአሜሪካ ጥያቄ መሰረት በቴህራን በሚገኝ አደባባይ በእስራኤል ወታደሮች ተተኩሶበት ተገድሏል። ኢራን በበኩሏ ምንም አይነት የአልቃይዳ 'አሸባሪዎች' በአገር ውስጥ እንደማይገኙ አስታውቃለች። አብዱላህ አህመድ በአውሮፓውያኑ 1998 በአፍሪካ በሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲዎች የደረሱ ጥቃቶችን አቅዷል እንዲሁም አቀነባብሯል የሚል ክስ ይቀርብበት ነበር። በቅጽል ስሙ አቡ ሙሃሙድ አል ማስሪ በመባል የሚታወቀው የአልቃይዳ ምክትል መሪ ከሴት ልጁ ጋር በመንገድ ላይ በመጓዝ ሳለ በሞተር ሳይክል የመጡ ሁለት ቅጥረኛ ነብሰ ገዳዮች ተኩሰው ገድለዋለቸዋል ሲል ኒው ዮርክ ታይምስ አንድ ማንነቱ ያልታወቀ የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊን ዋቢ በማድረግ ዘግቦ ነበር። በሪፖርቱ መሰረት ኢራን የእብዱላህን ሞት ለመሸፋፈን እንደሞከረች የተገለጸ ሲሆን የኢራን እና የሊባኖስ መገናኛ ብዙሃን ደግሞ የተገደለው ግለሰብ አንድ ሊባኖሳዊ የታሪክ መምህርና እንደሆነና ሴት ልጁም አብራው እንደተገደለች ዘግበዋል። ነገር ግን የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሪፖርቱን ያጣጣለው ሲሆን ''አንዳንድ ጊዜ ኒው ዋሽንግተን እና ቴል አቪቭ በሐሰት ኢራንን ከመሰል ቡድኖች ጋር ለማገናኘት ይሞክራሉ፤ ሐሰተኛ መረጃዎችንም ለመገናኛ ብዙሀን አሳልፈው በመስጠት ቡድኖቹ ለሚፈጽሙት የሽብር ጥቃት ኃላፊነት ላላመውሰድ ይሞክራሉ'' ይላል ሚኒስቴሩ ያወጣው መግለጫ። የእስራኤል ቻናል 12 የተባለው ጣቢያ በበኩሉ የደህንነት ኃላፊዎችን በመጥቀስ ''የአብዱላህ ሞት በእስራኤል እና አሜሪካ የጋራ ፍላጎት የተደረገ እንደሆነና የአልቃይዳ ኃላፊው በመላው ዓለም የሚገኙ ይሁዳውያንን ለመግደል በርካታ ሙከራዎችን አድርጓል'' በማለት ዘግቧል። የአሜሪካ የደህንነት መስሪያቤት ባወጣው ወቅታዊ መረጃ የአልቃይዳ መሪዎች "የቡድኑን ዓለም አቀፍ አደረጃጀት እያጎለበተና በምዕራቡ ዓለም ላይ ጥቃት እንዲፈፅሙ እያበረታታ ነው" ብሏል። የተባበሩት መንግስታት በያዝነው ዓመት መግቢያ ላይ ያወጣው የሽብርተኝነት መረጃ "አልቃይዳ በውስጥ ለውስጥ ራሱን እያደራጀ ከምንግዜውም በላይ ጠንካራ እየሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃም እያደገ መጥቷል" ይላል። የአሜሪካ ደህንነት ኃይል ተከታታይ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት፣ የቢንላደን መገደልና የአይኤስ ቡድን መጠናከር አልቃይዳ አዳዲስ ዘዴዎችን እንዲጠቀም አስገድደውታል። አልቃይዳም አሁን ከተለያዩ ቡድኖች ጋር ግንኙነት በመፍጠር በአፍሪካ፣ መካከለኛው ምስራቅና ደቡብ እስያ ቅርንጫፎች አለው። ለአልቃይዳ መሪነት ራሳቸውን ያስገበሩት አማፂ ቡድኖች በተለያዩ ማህበረሰቦች ውስጥ በስውር የሚንቀሳቀሱ ናቸው።
news-53174928
https://www.bbc.com/amharic/news-53174928
ተስፋ የተጣለበት የኮሮናቫይረስ ክትባት በሰዎች ላይ እየተሞከረ ነው
በሙከራ ላይ የሚገኘውና ትልቅ ተስፋ የተጣለበት የኮሮናቫይረስ ክትባት በዩናይትድ ኪንግደም በጎ ፈቃደኞች ላይ እየተሞከረ ነው።
በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ ለ300 ሰዎች ላይ ይሰጣል የተባለውን ክትባት የሚመሩት ከኢምፔሪያል ኮሌጅ ሎንዶን ፕሮፌሰር ሮቢን ሻቶክ ናቸው። ክትባቱ በሰዎች ላይ ከመሞከሩ በፊት በእንሰሳት ላይ ተሞክሮ አበረታች ውጤት አሳይቷል። ክትባቱ ጉዳት እንደማያስከትልና ሰውነት የመከላከያ ሴሎችን እንዲያመርት እንደሚያነቃቃው በእንሰሳት ላይ በተደረገው ሙከራ ተረጋግጧል። በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ የሚገኙ ተመራማሪዎች ከዚህ ሙከራ በፊት በሰው ላይ ክትባታቸውን እየሞከሩ ይገኛሉ። የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ክትባት ሙከራ እየተደረገ ያለው በመላው ዓለም ነው። በዓለም ዙሪያ በትንሹ 120 የክትባት ሙከራዎች በመካሄድ ላይ ናቸው። ከአፍሪካ ይህ ሙከራ በደቡብ አፍሪካ በሚገኙ በጎ ፈቃደኞች እየተወሰደ ነው። የኢምፔሪያል ኮሌጅ ኦፍ ለንደን ክትባት ዛሬ በዩናይትድ ኪንግደም ሲጀመር የ39 ዓመቷ የፋይናንስ ባለሞያ ካቲ ከመጀመሪያዎቹ በጎ ፈቃደኞች አንዷ ሆና ተመዝግባለች። ለምን በጎ ፈቃደኛ መሆን እንደፈለገች ከቢቢሲ ተጠይቃ "ተህዋሱን ለመዋጋት የእኔን ሚና መጫወት ስለፈለኩ ነው" ብላለች። በዚህ ረገድ የእኔ ሚና ምን መሆን እንዳለበት አላውቅም ነበር፤ ይህ አጋጣሚ ሲፈጠር ፈቃደኛ ለመሆን አላቅማማሁም ብላለች። በዚህ የመጀመሪያ ዙር ሙከራ የሚታዩ ውጤቶች ከተመዘገቡ በኋላ በሚቀጥለው ጥቅምት ክትባቱ ሌሎች 6ሺህ ሰዎችን እንዲያሳትፍ ተደርጎ ይሞከራል። የኢምፔሪያል ኮሌጅ ሳይንቲስቶች ተስፋ እንደሚያደርጉት ክትባቱ ስኬታማ ከሆነ በሚቀጥለው ዓመት አጋማሽ በመላው ዓለም መሰራጨት ይጀምራል። በአሁን ሰዓት በመላው ዓለም 120 ቤተሙከራዎች ክትባት ለማግኘት እየሰሩ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ ከቤተ ሙከራ አልወጡም። በክሊኒካል ሙከራ ደረጃ የሚገኙት 13 ብቻ ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ 5ቱ በቻይና፣ 3 በአሜሪካ፣ 2 በዩናይትድ ኪንግደም እንዲሁም በጀርመን፣ በአውስትራሊያና በሩሲያ አንድ አንድ ይገኛሉ። አሁን በዩናይትድ ኪንግደም እየተደረጉ ላሉት ሁለት ሙከራዎች 46 ሚሊዮን ፓውንድ በጀት እንደተመደበላቸው ተነግሯል።
news-43496177
https://www.bbc.com/amharic/news-43496177
የቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ፈተናዎች
የገዥው ፓርቲ የኢህአዴግ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከመጋቢት ሁለት እስከ መጋቢት አስር ድረስ ሲያካሂድ የቆየውን ስብሰባ ማጠናቀቁን ተከትሎ የፓርቲው ምክር ቤት ስብሰባውን ጀምሯል።
ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ስብሰባውን ሲያጠናቅቅ በሰጠው መግለጫ በሃገሪቱ ውስጥ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮችን "የአመራር ድክመት የወለዳቸው" ሲል የገለፃቸው ሲሆን ይህንን ለማረም የሚያስችል "አመለካከት እና አንድነት" የሚፈጥር ሁኔታ መኖሩን ማረጋገጡንም ተናግሯል። ምክር ቤቱ በጉባኤው ከአንድ ወር በፊት የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ ያቀረቡትን አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ተክቶ ፓርቲውን በሊቀ መንበርነት፤ ኢትዮጵያን ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትርነት የሚያስተዳድሩትን መሪ ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል። አሁን ትልቁ ጥያቄ የሚሆነው እውን የአዲስ መጭው ጠቅላይ ሚኒስትር የቤት ስራዎች ምን ምን ናቸው? የሚለው ነው። "እኔ ከአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የምጠብቀው የፍትህ ስርዓቱን እንዲያሻሻል ነው። በተለይ ደግሞ ፍርድ ቤቶች ራሳቸውን ችለው ያለምንም ጫና ውሳኔ መስጠት የሚለችሉበትን አቅም መፍጠር እንዳለበት አምናለሁ። ሲሉ የኢህአዴግ ምርክ ቤት ስብሰባ መቋጨትን በጉጉት እየጠበቁ እንዳሉ የነገሩን የድሬዳዋ ነዋሪ ያስረዳሉ። አክለውም "የተወካዮች ምክር ቤት አባላት የሚሰማቸውን በመናገር እንዲሁም የሕዝቡን ድምፅ በማስተጋባት ከቀድሞው የተለየ አካሄድ ሊከተሉ ይገባል። ካልሆነ ግን ለኔ 'ጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ አያጣፍጥ' እንዳይሆን እሰጋለሁ" ይላሉ። ፖለቲካው ላይ ወደሚሳተፉ አቅንተን ያናገርናቸው የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ የሽዋስ አሰፋ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ችግሮች ሊቀረፉ የሚችሉት ሕዝቡ በፍላጎቱ በመረጠው ፓርቲ ሲተዳደር መሆኑን ይናገራሉ። ፓርቲያቸው በህዝብ ምርጫ አብልጦ እንደሚያምን የሚገልፁት አቶ የሽዋስ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ግን የተለየ ፖለቲካዊ አቋም ካላቸው ወገኖች ጋር ለውይይት መቀመጥን ቅድሚያ ሰጥቶ የሚሰራና ተቋማዊ ማሻሻዎችን ለማድረግ የሚተጋ መሪ ቢመረጥ ለሃገሪቱ የሚበጅ ነው ይላሉ። ከተመራጩ ጠቅላይ ሚኒስትር ማንነት በበለጠ ይዟቸው የሚመጣቸው ኃሳቦች እንደሚያሳስቧቸው የሚናገሩት አቶ የሽዋስ ተስፋቸው የተቆጠበ መሆኑ ግን አይደብቁም። "ኢህአዴግ ከዚህ በፊት በሚጠቀምባቸው ዘዴዎችም ሆነ ማስፈራሪያዎች ሊገዛ አይችልም። ማንም ቢሆን የሚመጣው ማንነቱ ሳይሆን የሚያጓጓን ይዞ የሚመጣው ነገር ምንድነው? ምን ያህልስ የህዝቡንድ ድምፅ ለመስማት ዝግጁ ነው። ይህ ነው እንጂ ኢህአዴግ አንድ ድርጅት አንድ ሥርዓት ስለሆነ የተለየ ነገር በጣም በጉጉት የምንጠብቀው ነገር የለንም።" "አዲስ ተሿሚው ጠቅላይ ሚኒስትር ተደቅነው የሚጠብቁት ውስብስብ ፈተናዎችን ለመጋፈጥ ብሎም ለመቅረፍ የፖለቲካ ዝግጁነት፣ ቁርጠኝነት እና አቅም እንዳለው ማሳየት ይገባዋል" የሚሉት ደግሞ የአፍሪካ ቀንድ የፖለቲካ እና የደህንነት ጉዳዮችን የሚያጠኑት ተመራማሪው ለአቶ ሃሌሉያ ሉሌ ናቸው። "በዋነኛነት ህዝቡ የሚጠይቃቸው ጥያቄዎች መመለስ አለባቸው ብዬ አምናለሁ። የመጀመሪያው ጥያቄ እንግዲህ የዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበር ጉዳይ ይመስለኛል። ተቃዋሚ ፓርቲዎች እና የሲቪል ማሕበረሰብ ቷቋማት በነፃነት የሚንቀሳቀሱበት እንዲሁም ሃሳብ በነፃነት የሚንሸራሸርበት መድረክ ማግኘትን የሚደግፉ የህገ-መንግስቱ አንቀፆች የሚከበሩበት ምህዳር እንዲፈጠር ማድረግ ትልቁ የቤት ሥራ ነው ብዬ አስባለሁ።" አቶ ሃሌሉያ አክለውም "የጦር ሰራዊቱና የደህንነትና ስለላ ተቋማት ለህገ-መንግሥቱ እንዲሁም ለፓርላማ አባላት ያላቸው ተጠያቂነት ማረጋገጥ እንዲሁም የሃገሪቱ የበላይ ህግ የሆነው ህገ-መንግሥት እንደሚያዘው በእነዚህ ተቋማት ወስጥ ያለውን የብሄር ተዋፅኦ ማረጋገጥ አስፈላጊም አስቸኳይም የቤት ሥራ ይመስለኛል" ይላሉ። አቶ ሃሌሉያ ሉሌ ተሿሚው ጠቅላይ ሚኒስትር በሕዝቡ ዘንድ ለተነሱ ጥያቄዎች ዕውቅና ከመስጠት ባሻገር፤ ምላሽ የሚቀርብበት ግልፅ የጊዜ ሰሌዳ ማስቀመጥ እንደሚጠበቅበት፤ ይህም የሕዝቡን ትዕግስት ለማግኘት እንደሚጠቅመው ጨምረው ተናግረዋል። ምሁሩ ሃሳባቸውን ሲያጠናቅቁ ካለፉት ጥቂት ዓመታት አንስቶ በአገሪቱ ለሚታየው ፖለቲካዊ ቀውስ ገፊ ምክንያቶች እና ከሚነሱ ጥያቄዎች መካከል እንዳንዶቹ በአጭር ጊዜ ሊመለሱ የሚችሉ ቢሆኑም ሌሎቹ ደግሞ ዘለግ ያለ ጊዜን የሚሹ መዋቅራዊ መፍትሄዎችን ይፈልጋሉ ይላሉ። ተሿሚው ጠቅላይ ሚኒስትር ሕዝቦች ላነሷቸው ጥያቄዎች ዕውቅና ከመስጠትም ባሻገር ምላሽ የሚቀርብበት ግልፅ የጊዜ ሰሌዳ ማስቅመጥ እንደሚጠበቅበት ይህም የሕዝቡን ትዕግስት ለማግኘት እንደሚጠቅመውም ይከራከራሉ።
news-52590640
https://www.bbc.com/amharic/news-52590640
ኮሮናቫይረስ፡ በሕንድ በባቡር ሀዲድ ላይ ተኝተው የነበሩ 16 ስደተኛ ሠራተኞች ተገጭተው ሞቱ
ሕንድ ውስጥ ማሃራሽትራ በምትባለው ግዛት 16 ሰዎች በእቃ ጫኝ ባቡር ተገጭተው መሞታቸው ተነገ። ይህንንም ተከትሎ ባለስልጣናት በአደጋው ዙሪያ ምርመራ እንዲደረግ አዘዋል።
የሕንድ መንግሥት ካሉበት ከተማ ወደ ትውልድ ቀያቸው መሄድ ለሚፈልጉ ሠራተኞች የተለየ ባቡር ማዘጋጀቱን ገልፆ ነበር ሟቾቹ ከሌላ አካባቢ መጥተው በከተሞች የሚሰሩ ስደተኛ ሠራተኞች ነበሩ የተባለ ሲሆን ወደ ቀያቸው ለመሄድ ባቡር የሚያገኙበት ስፍራ ሀዲዱ ላይ ተኝተው ነበር ተብሏል። ሕንድ ስደተኛ ሠራተኞቹ ወደ ቀያቸው የሚያደርስ የተለየ ባቡር ማዘጋጀቷ ተገልጿል። ሕንድ የኮረናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል የእንቅስቃሴ ገደብ ጥላ በነበረበት ወቅት በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ስደተኛ ሠራተኞች ወደ ትውልድ መንደራቸው በእግራቸው ጉዞ ጀምረዋል። የሕንድ ስደተኛ ሠራተኞች ከአገሪቱ የተለያዩ የገጠር መንደሮች የተሻለ ክፍያና ህይወት በመፈለግ ወደ ከተሞች የፈለሱ ናቸው። የባቡር ጣብያው ሠራተኞች ስደተኞቹ ወደ አውራንጋባድ የሚወስደውን አውራ ጎዳና ይዘው እየሄዱ የነበረ ቢሆንም በኋላ ግን ወደ አውራንጋባድ የሚወስደው ባቡር መስመር ላይ መጥተዋል ብለዋል። ስደተኞቹ በእግራቸው 36 ኪሎ ሜትር ያህል ከተጓዙ በኋላ በድካም በመዛላቸው የባቡር ሀዲዱ ላይ መተኛታቸውም ተነግሯል። እንደ አገር ውስጥ መገናኛ ብዙኀን ዘገባ ከሆነ በእንቅስቃሴ ገደቡ ምክንያት ባቡር አይመጣም ብለው በማሰባቸው ሀዲዱ ላይ ተኝተዋል። በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኀን ላይ የሚዘዋወሩ ምስሎች ላይ እንደሚታየው ከስደተኞቹ አስክሬን አቅራቢያ ደረቅ ዳቦ ወድቆ ይታያል። ሕንድ ከአንድ ወር ከአስራምስት ቀን በፊት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ያለምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ የእንቅስቃሴ ገደብ ስትጥል ከሌላ አካባቢ ወደ ከተሞች የመጡ ሠራተኞች የምንመገበው እናጣለን ብለው በመስጋታቸው በእግራቸው ወደ ትውልድ ቀያቸው መመለስ ጀምረዋል። በርካቶች የመጓጓዣ እንቅስቃሴ በመቆሙ ምክንያት በእግራቸው ወደ ትውልድ ቀያቸው ለመመለስ መገደዳቸው በአገሪቱ ውስጥ ትልቅ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። የእንቅስቃሴ ገደቡ በተወሰነ መልኩ መላላቱን ተከትሎ የሕንድ መንግሥት ስደተኞቹ በተዘጋጀላቸው ልዩ ባቡርና አውቶቡስ ወደ አካባቢያቸው መመለስ እንደሚችሉ ተናግሯል። የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር በ16 ሰዎች ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል።
news-55570555
https://www.bbc.com/amharic/news-55570555
የአሜሪካ ምክር ቤት፡ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች ከቀሰቀሱት ግርግር ጋር በተያያዘ አራት ሰዎች ሞቱ
ዋሺንግተን ውስጥ የተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች የአገሪቱን ምክር ቤት ጥሰው መግባታቸውን ተከትሎ በተፈጠረ ፍጥጫ አራት ሰዎች መሞታቸው ተነገረ።
ካፒቶል ሒል በተባለው የምክር ቤቱ ህንጻ ላይ በተቃዋሚዎቹ በተፈጸመው ወረራና ተከትሎት በተፈጠረው ግጭትና ግርግር በቀዳሚነት አንዲት ሴት በፖሊስ ተተኩሶባት እንደሞተች የተዘገበ ሲሆን፤ ኋላ ላይ ደግሞ ተጨማሪ ሦስት ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል። ከሞቱት በተጨማሪ አስካሁን ድረስ ከ50 በላይ ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 47ቱ የተያዙት የተጣለውን የሰዓት እላፊ ገደብ በመጣሳቸው ነው ተብሏል። ከዚህ ባሻገር ቢያንስ 14 የሚደርሱ የፖሊስ አባላት ላይ የመቁሰል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከመካከላቸው ሁለቱ ሆስፒታል መግባታቸው ተነግሯል። ወራራ በአሜሪካ ምክር ቤት ላይ በዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ የአሜሪካ መንግሥት መቀመጫ የሆነው የካፒቶል ሒል ግዙፍ ህንጻ ላይ የትራምፕ ደጋፊዎች ወረራ ፈጽመው ለሰዓታት ግርግር ተፈጥሮ ነበር። ይህ በአሜሪካ ውስጥ ይሆናል ተብሎ የማይጠበቅ ድርጊት የተፈጸመው ከሰዓታት በፊት ነው። የዶናልድ ትራምፕ ነውጠኛ ደጋፊዎች ካፒቶል ሒልን ከተቆጣጠሩ በኋላ ንብረት ሲያወድሙና ለፕሬዝዳንቱ ያላቸውን የማይናወጽ ፍቅር ሲገልጹ ተስተውለዋል። ካፒቶል ሒል የአሜሪካ መንግሥት መቀመጫ ሲሆን የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት በቀኝ፣ የሕግ መምሪያው ምክር ቤት መሰብሰቢያ ደግሞ በግራ በኩል የሚገኝበት፣ በርካታ ቢሮዎች ያሉበት ታሪካዊ ሕንጻ ነው። ሕንጻው ከ18ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የነበረ ነው። የአገሪቱ ሕዝብ እንደራሴዎች ተሰብስበው ቀጣዩ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የምርጫ ውጤት ዙሪያ በመነጋገር ላይ ሳሉ ነው በድንገት በሺህ የሚቆጠሩ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች ምክር ቤቱን ሰብረው የገቡት። ትዕይቱን ለዓለም በቀጥታ ያስተላልፉ የነበሩ የዜና ማሰራጫዎች ድርጊቱን ማመን ተስኗቸው ለሰዓታት ፕሮግራማቸውን አጥፈው ነውጡን አሰራጭተዋል። ይህ ያልተጠበቀ ክስተት በሚሆንበት ጊዜ ስብሰባ ላይ የነበሩ የሕዝብ እንደራሴዎች በፖሊስ ታጅበው ወዳልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል። በተቀሰቀሰው ግርግር ሳቢያ የዋሺንግተን ከንቲባ በከተማዋ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ የሰዓት እላፊ ገደብ ጥለዋል። የካፒቶል ሂል አካባቢም ሙሉ በሙሉ ዝግ እንዲሆን ተደርጓል። ዶናልድ ትራምፕ መጀመሪያ አካባቢ ደጋፊዎቻቸውን ድርጊቱን እንዲገፉበት የሚያበረታቱ መልዕክቶችን እየላኩ የነበረ ሲሆን በኋላ ላይ ግን ሰላማዊ እንዲሆኑና ወደቤታቸውም እንዲሄዱ የሚያሳስብ መልዕክትን አስተላልፈዋል። የሕግ መምሪያውና የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት አባላት በአንድ ተሰብስበው በሚነጋገሩበት ወቅት ነውጥ በመነሳቱ የጆ ባይደንን ፕሬዝዳንታዊ ድል የማጽደቁን ውይይት ለጊዜ ተቋርጦ ነበር። በዚህ ዓለምን ጉድ ባሰኘ ነውጥ አራት ሰው መሞታቸው የተዘገበ ሲሆን በርካታ የጸጥታ አስከባሪዎችም ላይ ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ፖሊስ አስለቃሽ ጭስ በመተኮስ ሁኔታዎችን ለመቆጣጠር ሲሞክር ታይቷል። ነውጠኞቹ በተደጋጋሚ "ምርጫው ተጭበርብሯል" እንዲሁም "ዶናልድ ትራምፕ ይምራን" የሚሉ መፈክሮችን ሲያሰሙ ነበር። የምሽቱ አስደናቂ የሆነው ክስተት ወደ አዳራሹ በኃይል ጥሰው ከገቡት ተቃዋሚዎች አንዱ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት በሚቀመጡበት የሴኔት ሸንጎ ወንበር ላይ እግሩን ሰቅሎ መታየቱ ነበር። ዶናልድ ትራምፕ በመጨረሻ በቪዲዮ ባስተላለፉ መልዕክት ለደጋፊዎቻቸው "ሕመማችሁ ይሰማኛል፤ ምንኛ እንደተጎዳችሁ ይገባኛል። በቃ አሁን ወደቤት መሄድ ነው ያለባችሁ። ሰው እንዲጎዳብን አንፈልግም" ብለዋቸዋል። ጆ ባይደን በቴሌቪዥን ቀርበው በቀጥታ ለሕዝባቸው ባደረጉት ንግግር"በአሜሪካ ዲሞክራሲ ላይ ጥቃት ተሰንዝሯል" ብለዋል። ተቀናቃኛቸው ትራምፕም በአስቸኳይ ወጥተው ውንብድና ላይ ያሉ ደጋፊዎቻቸውን አደብ እንዲያሲዙ ጠይቀዋል። ካፒቶል ሒል በነውጥ ላይ እያለ ከዋሺንግተን ዲሲ በሚጎራበቱ ግዛቶች የአሜሪካ ወታደሮች በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ሆነዋል። የካፒቶል ሒል ፖሊሶችን ለመደገፍም ኤፍቢአይ ወደ ስፍራው ተሰማርቷል። በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶችም ነውጡ ከተስፋፋ በሚል ከፍተኛ ፍርሃት እንደረበበ ሚዲያዎች እየዘገቡ ነው።
news-54970897
https://www.bbc.com/amharic/news-54970897
ትግራይ፡ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የህወሓት ናቸው ያላቸውን የ34 ተቋማት የባንክ አካውንት አሳገደ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የህወሓት የንግድ ድርጅቶች ናቸው በተባሉ ከሰላሳ በላይ የሚሆኑ ተቋማት የባንክ አካውንት ላይ ዕግድ እንዲጣልባቸው ማስድረጉን ገለጸ።
ዐቃቤ ሕግ እንዳለው ድርጅቶቹ የአገሪቱን ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት "በኃይል ለመናድ ከሚንቀሳቀሰው ከህወሓት ጋር ግንኙነት አላቸው" በማለት በሌሎች ድርጊቶች ውስጥ እንደሚሳተፉ ገልጿል። በተጨማሪም ተቋማቱን ዘር ተኮር ጥቃትና የሽብር ድርጊት እንዲፈጸም የገንዘብ ድጋፍ በማቅረብ፣ በመመሳጠር፣ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ፣ በግብር ስወራና የሙስና ወንጀል ድርጊቶች ውስጥ ስለመሳተፋቸው ምርመራ ለመጀመር የሚያስችል በቂ ማስረጃ እንደተገኘባቸው ዐቃቤ ሕግ ባወጣው መግለቻ ላይ ጠቁሟል። በዚህ የዐቃቤ ሕግ እርምጃ የ34 የህወሓት ድርጅቶች በአገሪቱ ውስጥ ባሉ በሁሉም ባንኮች ውስጥ ያላቸው ገንዘብ እንዲሁም የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ላይ እገዳ እንዲጣል አስደርጓል። ይህ እርምጃ አስፈላጊ የሆነውም ተቋማቱ ሀብታቸውን ለማሸሽ ጥረት በማድረግ ላይ እንደሆኑ በቂ ማስረጃ በመቅረቡ ንብረቶች ሳይሸሹ ተገቢውን ቁጥጥር በማድረግ ውሳኔ እስኪሰጥባቸው ድረስ ተገቢው ቁጥጥር ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ እንደሆነ ዐቃቤ ሕግ ገልጿል። ዕግዱ የተጣለባቸው የምርትና የንግድ ተቋማት ሲሆኑ በፋይናንስ፣ በማዕድን፣ በጨርቃጨርቅ፣ በግንባታ፣ በጅምላ ንግድ፣ በትራንስፖርት፣ በፋብሪካ ምርቶችና በመሳሰሉት ዘርፎች የተሰማሩ ከመሆናቸው በተጨማሪ ከህወሓት ጋር የጠበቀ ቁርኝት እንዳላቸውቸው ሲነገር የቆዩ ድርጅቶች ናቸው። ከእነዚህም መካከል በአገሪቱ ካሉ ትላልቅ የግንባታ ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው ሱር ኮንስትራክሽን፣ በአስመጪነትና በጅምላ ንግድ የሚታወቀው ጉና የንግድ ሥራዎች ድርጅት፣ የጨርቃ ጨርቅ አምራቹ አልምዳ፣ የሲሚንቶ ፋብሪካው መሰቦ፣ በትራንስፖርትና በውጪ ንግድ ላይ ተሰማርቶ የቆየው ትራንስ ኢትዮጵያ ተጠቅሰዋል። በተጨማሪም መድኃኒት አምራቹ አዲስ ፋርማሱቲካል፣ ማዕድን አውጪው ኢዛና ማዕድን፣ የከባድ ተሽከርካሪዎች አካልን የሚያመርተውና የሚገጣጥመው መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጅነሪንግ፣ የአገር አቋራጭ የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የተሰማራው ሠላም የሕዝብ ማመላለሻ ማኅበር፣ የህትመት ሥራዎችን የሚሰራው ሜጋ ማተሚያ ድርጅት ይገኙባቸዋል። ከእነዚህ በተጨማሪም ሌሎች በርካታ የንግድና የአገልግሎት ድርጅቶች የባንክ አካውንት ነው እንዳይንቀሳቀስ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያሳገደው። እነዚህ ተቋማት በአገሪቱ ውስጥ በምርትና በአገልግሎታቸው ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ የሚያንቀሳቅሱ ሲሆን፤ የድርጅቶቹን አካውንት የመዝጋት እርምጃ የተወሰደው መንግሥት በህወሓት በሚመሩት የትግራይ ልዩ ኃይሎች እርምጃ መውሰድ ከጀመረ ከሁለት ሳምንት በኋላ ነው። በህወሓት በሚመራው የትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኘው የፌደራል ሠራዊት ላይ ጥቃት ፈፅሟል መባሉን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በክልሉ ልዩ ኃይል ላይ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ካዘዙ በኋላ የተለያዩ እርምጃዎች ተወስደዋል። የህወሓት ናቸው በተባሉት በእነዚህ የምርትና የአገልግሎት ድርጅቶች ላይ ከተወሰደው እርምጃ ቀደም ብሎ ዐቃቤ ሕግ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በነበሩ የህወሓት አባላትን ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ተደርጓል። በተጨማሪም የድርጅቱን ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ በመከላከያ፣ በፌደራልና በክልሉ የፖሊስ ኃይል ውስጥ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታ ላይ የነበሩ 96 የሚደርሱ ግለሰቦችን የመያዣ ትዕዛዝ ማውጣቱ ይታወሳል>
news-55255845
https://www.bbc.com/amharic/news-55255845
ትግራይ፡ ሁለት ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ሠራተኞቻቸው ትግራይ ውስጥ መገደላቸውን ገለጹ
ሁለት ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅቶች ትግራይ ውስጥ ከተከሰተው ግጭት ጋር በተያያዘ ሠራተኞቻቸው መገደላቸውን ገለጹ።
ዳኒሽ ሪፊውጂ ካውንስል እና ኢንተርናሽናል ሬስኪው ኮሚቴ (አይአርሲ) ድርጅቶች ናቸው በትግራይ ክልል ውስጥ ባልደረቦቻቸው መገደላቸውን ይፋ ያደረጉት። ዳኒሽ ሪፊውጂ ካውንስል ባሳለፍነው ወር ሦስት የሰብዓዊ እርዳታ ሠራተኞቹ መገደላቸውን ሲያስታውቅ፤ ኢንተርናሽናል ሬስኪው ኮሚቴ (አይአርሲ) በበኩሉ በሽሬ ከተማ ህጻጽ የሰደተኞች መጠለያ ካምፕ ይሰራ የነበረ ባልደረባው መገደሉን አስታውቋል። ዳኒሽ ሪፊውጂ ካውንስል የተገደሉት በትግራይ ካሉት ፕሮጀክት ጣቢያዎች በአንደኛው ቦታ በጥበቃ ሥራ የተሰማሩት ናቸው ብሏል። ካውንስሉ በአከባቢው የቴሌኮም አገልግሎት ባለመኖሩ እንዲሁም ወደ ስፍራው ለመጓዝ የደኅንነት ስጋት በመኖሩ የሟች ቤተሰቦችን ማግኘት እና ድጋፍ ማድረግ አለመቻሉን አስታውቋል። አይአርሲ በበኩሉ በሠራተኛው የተገደለው ኅዳር 10 መሆኑን አረጋግጦ፤ በሠራተኛው መገደል የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን የገለጸ ሲሆን የተገደለው ሠራተኛ ማንነትን ግን ይፋ ከማድረግ ተቆጥቧል። አይአርሲ በአከባቢው የቴሌኮም አገልግሎት በመቋረጡ፤ የሠራተኛውን የአሟሟቱን ሁኔታ በተመለከተ ዝርዝር ሁኔታ ማጣራት ለማድረግ አለመቻሉን አስታውቋል። ከዚህ ቀደም ሮይተርስ የዜና ወኪል የዲፕሎማቲክና የሰብአዊ እርዳታ ድርጅት ምንጮችን ጠቅሶ፤ በሁለት የተለያዩ የውጪ የተራድኦ ድርጅቶች ተቀጥረው ይሠሩ የነበሩ አራት የሰብአዊ እርዳታ ሠራተኞች በኢትዮጵያና በኤርትራ ድንበር አቅራቢያ ተገድለዋል ሲል ዘግቦ ነበር። ሮይተርስ በዘገባው በየትኛው አካል ሠራተኞች እንደተገደሉ ያለው ነገር የለም። ከአንድ ሳምንት በፊት ስለጉዳዩ የሚያውቁት እንደለ በቢቢሲ የተጠየቁት የዲሞክራሲ ግንባታ ሚንሰትር ዛዲግ አብረሃ፤ "አሁን ስለዚህ ጉዳይ የማውቀው ነገር የለም። ገና መረጃው እየተጠራ ነው ያለው። የስልክ አገልግሎትን እየመለስን፣ መንገዶችን እያስተካከልን ነው ያለነው" የሚል ምላሽ ሰጥተው ነበር። ኢንርናሽል ሬስኪው ኮሚቴ በመላው ዓለም የሰብዓዊ ቀውስ በሚከሰትባቸው ስፍራዎች ሰዎች የጤና፣ የትምህርት አገልግሎቶችን እንዲያገኙ እና ደኅንነታቸው እንዲጠበቅ የሚሰራ ዓለም አቀፍ የተራድኦ ደርጅት ነው። በተያያዘ ከቀናት በፊት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ትግራይ ውስጥ የኢትዮጵያ ወታደሮች የፍተሻ ጣቢያ በጣሱ የተባበሩት መንግሥታት ሠራተኞች ላይ እንደተኮሱና በቁጥጥር ስር እንዳዋሏቸው በሰጡት መግለጫ ተናግረው ነበር። የመንግሥታቱ ድርጅት ሠራተኞች ባለፈው ሳምንት እሁድ ኅዳር 27/2013 ዓ.ም የኤርትራ ስደተኞች የሚገኙበትን ማዕከልን ለመጎብኘት ሲያቀኑ የነበሩና ፍተሻ ጣቢያዎችን ጥሰው አልፈዋል ተብሏል። አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እንዳሉት የድርጅቱ ሠራተኞ ወዳልተፈቀደላቸው አካባቢ በመግባት የመንግሥትን መመሪያ በመተለለፋቸው ነው የተተኮሰባቸውና የተያዙት። በፌደራል መንግሥትና በህወሓት መካከል ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በተቀሰቀሰው ወታደራዊ ግጭት ምክንያት የሰብአዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ችግር ላይ መውደቃቸው የተነገረ ሲሆን በክልሉ ያለው ሁኔታ እንቅስቃሴያቸው ላይ የእራሱ ተጽእኖ ሊኖረው እንደሚችል ሲገልጹ ቆይተዋል። የሰብአዊ እርዳታ ከሚያስፈልጋቸው ነዋሪዎች በተጨማሪ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ የስደተኞች ካምፖች ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ጉዳይ አሳሳቢም እንደሆነም እየተገለፀ ነው። በትግራይ ክልል የተካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ ማብቃቱ በመንግሥት ከተገለጸ በኋላ ሰብአዊ እርዳታ ሰጪዎች ወደ ክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ ድጋፍ እንዲያቀርቡ ከተባበሩት መንግሥታት ጋር ስምምነት መደረሱ ይታወሳል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ታህሳስ 02/2013 ባወጣው መግለጫ የፌደራል መንግሥቱ በትግራይ ክልል የሚደረጉ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቶች አስተማማኛና ደኅንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን የማድረግ ኃላፊነት እንዳለበት ለዚህም አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ቁርተኛ መሆኑን ገልጿል። ጨምሮም ቀደም ሲል ከተባበሩት መንግሥታት ጋር በተደረሰው ስምምነት መሰረት የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መስመሮች እንደሚመቻቹ አመልክቷል።
news-50068555
https://www.bbc.com/amharic/news-50068555
እሷ ማናት #2፡ ዘቢብ ካቩማ የተባበሩት መንግሥት ሴቶች ዋና ኃላፊ
ዘቢብ ካቩማ እባላለሁ የሁለት ወንዶችና የአንዲት ሴት ልጅ እናት ነኝ። ባለቤቴ ፖል ካቩማ ይባላል። ነዋሪነቴ ኬንያ ሲሆን ለምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የተባበሩት መንግሥታት ሴቶች ክፍል ዋና ኃላፊ ነኝ።
ዘቢብ ካቩማ የተባበሩት መንግሥታት ሴቶች ክፍል ዋና ኃላፊ ኑሮን 'ሀ' ብዬ ስጀምር ስለ መድረሻዬ የማውቀው ነገር የነበረ አይመስለኝም። ወደኋላ መለስ ብዬ ሳስበው ግን እንዲያው የነገሮች ሂደት ነው ቀስ ብለው ዛሬ ያለሁበት ያመጡኝ ብዬ እንዳስብ ያደርገኛል። ገና ልጅ እያለሁ ነበር በወንዶች እና በሴቶች መካከል ያሉትን ልዩነቶች ማየት የጀመርኩት። እርሱም ሰዎች ለሁለቱ ፆታዎች ያሏቸው አመለካከቶች የተለያዩ መሆናቸውን ስላየሁ ነበር። ሁልጊዜ እራሴን፣ የማደርጋቸውን ነገሮች በሙሉ እና ብቃቴንም ጭምር ማስረዳትም ሆነ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅብኝ እንደነበር ተረዳሁኝ። እናቴን በትኩረት እየተከታተልኩ በማደጌ ደግሞ ከወንዶች እና ከሴቶች የሚጠበቁት ነገሮች የተለያዩ መሆናቸውን ቶሎ ደረስኩበት። ለእነዚህ ልዩነቶች የነበረኝ ትኩረት ነው አሁን የደረስኩበት ደረጃ እንድደርስ የገፋፋኝ ብዬም አምናለሁ። እውነቱን ለመናገር በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ አይደለም በዋና ኃላፊነት በመሥሪያ ቤቱ ውስጥ እሠራለሁም ብዬ ጠብቄ አላውቅም ነበር። ጭራሽ ትኩረቴን የማይስብ ድርጅት ነበር። ሕይወት ደግሞ የራሷ መስመር አላት መሰለኝ በሂደት እራሴን እዚህ ቦታ ላይ አግኝቼዋለሁ። ማስተርሴን በኮሎምብያ ዩኒቨርሲቲ እየሠራሁ ሳለ ነበር የሥራ ልምምድ ዕድል ዩኤንዲፒ በተሰኘው የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም ውስጥ አግኝቼ ለተወሰነ ጊዜ የሠራሁት። ከዚያም ትምህርቴን ጨርሼ በአጋጣሚ ኬንያ ለጉብኝት መጥቼ ሳለ ነው በተባበሩት መንግሥታት ፌምኔት የተሰኘው ክፍል ውስጥ ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ ሳገኝ አመልክቼ ነው ወደ ድርጅቱ የገባሁት። ቀስ በቀስም በሥራዬ እድገት እያገኘሁ የኬንያ ዋና ኃላፊ ሆንኩኝ ቀጥሎ ደግሞ አሁን እየሠራሁበት ወዳለው የምሥራቅና የደቡብ አፍሪካ ዋና ኃላፊ በመሆን ከፍ ወዳለ ደረጃ ደረስኩ። 'ኔስትሌ' የተሰኘው ድርጅት በኬንያ ለሴቶች ብቃት ፕሮግራም ሲፈርሙ አሁን ሳስበው ሕልሜን እንዳሳካሁ ነው የምቆጥረው። ብዙ ሰዎች እዚህ እንደምሠራ ሲያውቁ "እናንተ መሥሪያ ቤት ወንዶች አሉ?" በማለት የሚጠይቁኝ የመጀመሪያ ጥያቄ ነው። ለሴቶች የሚቆም ድርጅት በመሆኑ ሴቶች ብቻ ያለን ይመስላቸዋል። በእርግጥ በቁጥር የምንበዛው ሴቶች ብንሆንም ወንዶችም ግን አብረውን ይሠራሉ። እንደዚህ ዓይነትና ከሥራችን አንፃር 'ለምን' የመሳሰሉ ጥያቄዎች ሲቀርቡልኝ ያስገርመኛል፤ ምክንያቱም ሴት መሆን በእራሱ ብዙ ውጣ ውረዶችን ያስከትላል በተለይ በሥራ ገበታ ላይ። ይህን የምልበት ደግሞ ምክንያት አለኝ። ደግነቱ በምሠራበት ቦታ ብዙዎቻችን ሴቶች በመሆናችን ብዙ ሴቶችን ከተቃራኒ ፆታ የሚደርሱባቸው የተለያዩ ችግሮች አይገጥሙንም። እንደዚያም ሆኖ ግን በዚህ ዓለም ሴት መሆን በእራሱ ችግር ነው። በተለይ ሃሳቧን ያለምንም ችግር ያለምንም ማንገራገር የምትገልፅ ሴት መሆን ፈተና አለው። እኔንም ጭምር 'ጉረኛ ነሽ' እና 'ጠብራራ ነሽ' የመሳሰሉ አስተያየቶችን የሚሰጡኝ ሰዎች ብዙ ናቸው። ሰዎች በትንሽ ምክንያት ያላቸው አመለካከት፣ አነጋገራቸውና ሁኔታቸው ሲቀያየር ማየትም የተለመደ ነው። ለምሳሌ ብዙ ሴቶች በተሰበሰቡት ክፍል ውስጥ አንድ ወንድ ቢኖር፤ መቃለዱንና አኳዃኑን ያየ ሰው እና የተገላቢጦሽ ሆኖ ደግሞ አንድ ሴት ወንዶች በተሰበሰቡበት ብትቃለድ ሁለቱ ግለሰቦች በተመሳሳይ ዓይን አይታዩም። እራሴም ብሆን ሴትን በማይበት ጊዜ በአለባበሷ፣ በአነጋገሯ እና በምታቀርባቸው ሃሳቦች ላለመገምገም እጥራለሁ። ማንነታችንን ማወቅ አለብን ከዚያም ደግሞ ያለ ምንም ማንገራገር እራሳችንን መሆን አለብን ብዬ ስለማምን ማለት ነው። ጠንካራ መሆን ብዙ እንደሚጠይቅ አውቃለሁ። ከእራሴ ተሞክሮ የተማርኩትም ይኼንኑ ነው። የማይረሳኝ ተማሪ እያለሁ ሕንድን የማየት ፍላጎት ነበረኝ። ለባህልም፣ ለኃይማኖት ያለን ቦታ፣ ለቤተሰብ የምንሰጠው ቦታና ሌሎችም ነገሮች በጣም ይመሳሰሉብኝ ስለነበር በዓይኔ ማየት ፈልጌ ወደ ሕንድ አቀናሁ። ብቻዬን ነበርኩኝ። ሃገሪቷንም አካለልኳት። ቀስ በቀስ ግን ነዋሪዎቹ ግራ ይጋቡ እንደነበር ለመገንዘብ አላስቸገረኝም። ሲገባኝ፤ ሴት መሆኔ፣ ወጣት መሆኔ፣ ብቻዬን መሆኔ እና ከዚያም አልፎ ደግሞ የቆዳዬን ቀለም አይተው ከየት መምጣቴም ሆነ ማንነቴ በጣም አወዛግቧቸው ነበር። በባህላቸው ወጣት ሴት ልጅ ለዚያውም ያላገባች ሴት ብቻዋን ሃገር ማቋረጥ አይደለም በሰፈሯ መንገድ አትሄድም። ስደተኞችና በተለያዩ የተፈጥሮ አደጋዎች ጉዳት ለደረሰባቸው ሴቶች የብቃትና እርዳታ ፕሮግራም ላይ አንድ ቀን የሦስት ሰዓት መንገድ ለመጓዝ በአውቶብስ ተሳፍሬ ከአጠገቤ የነበረው ወንድ ሲተሻሸኝና ቀስ እያለ እግሬን ሲነካካኝ፤ የማደርገው ነበር የጠፋኝ። ምክንያቱም የተጠባበቀ ባስ ውስጥ ነን። መቆም፣ መነሳትም ሆነ መንቀሳቀስ አልቻልኩም በዚያ ላይ ላነጋግረው ብሞክር እንኳን በቋንቋ መግባባት አልቻልንም። ሴትነቴ በጣም ተሰማኝ። ይህን ለማድረግ የገፋፋው ምንም ይሁን ምን ማንነቴን እየተጋፋ ነው። እዚያ ቦታ ላይ መገኘቴ ውስጤን እንዲከፋው ቢያደርግም እንደ ማንኛውም ሰው እዚያ የመሆን መብቴ ግን መጠበቅ አለበት። ለዚያ ነው ሁሌም ለሌሎች "የመተንፈስ፣ የመኖር እና ያላችሁበትን ቦታ የመያዝ መብት አላችሁ" የምለው። ከሥራዬ አንፃር አብዛኛውን ጊዜ ሴቶችን በሙሉ ወደ እኩልነት የምንገፋፋ ሊመስል ቢችልም ይህ አለመሆኑን ግን ማስረዳት እፈልጋለሁ። ምክንያቱም እያልን ያለነው ወንዶች የሚያደርጉትን በሙሉ ወይም ባሉበት ቦታ ሁሉ ሴቶችም እኩል ቦታ ይያዙ ሳይሆን ማድረግ የሚፈልጓቸውንና መሆን በሚፈልጉባቸው ቦታዎች የመሆን መብታቸው ይጠበቅ ነው፤ ይህ ነው እኩልነት። አንዳንድ ሴቶች በርግጥ ልጆቻቸውን ማሳደግ ሊመርጡ ይችላሉ ይህም ቢሆን መብታቸው ነው። ሌሎች ተቀጥረው መሥራትን፣ ሌሎች ደግሞ በእራሳቸው የንግድ ሥራ መሰማራት ሊፈልጉ ይችላሉ፤ ይህም ቢሆን መብታቸው ነው። በስመ ሴት ሁሉንም ሴት በአንድ ላይ መፈረጅ ተገቢ አይደለም። ሴቶችን ማብቃት ሲባል በቢሮ ሥራ ውስጥ ወይንም በንግድ የተሰማሩት ብቻ ላይ ያተኮረ መሆን የለበትም። ሁሉም ሴት በየራሳቸው መንገድ የተለያዩ ችግሮችን መወጣታቸው ስለማይቀር ክብርም ሆነ አድናቆት የምናደርገው ለተወሰኑ ሴቶች ብቻ መሆን የለበትም ማለት ነው። የማብቃት ሥራችን ግን ብቻውን ትርጉም አይሰጥም። ምክንያቱም ፖሊሲ የሚነድፉ እና በመንግሥት ደረጃ ውሳኔ የሚወስኑ ንግግሩም ላይ ሆነ ሥራው ላይ ካልተሳተፉ የምናስቀምጣቸው ፕሮግራሞች ፕሮጀክቱ ሲያልቅ መቋረጣቸው አይቀርም። ለዚህም ነው ብቻችንን አንሠራም የምንለው። ከድሮም የሚያስገርመኝ ነገር ቢኖር ወንዶች በሙሉ የሚያደንቁትን ሰው ሲጠየቁ ከእናቶቻቸው ወይም ከአያቶቻቸው አያልፍም። ለምንድን ነው ታድያ ይህን ፍቅርና አድናቆት ለሌሎች ሴቶች ማሳየት የማይችሉት እያልኩ እራሴን እጠይቃለሁ። ይህም ብዙ ጊዜ ደግሞ ከአስተዳደጋችን አያልፍም። ለምን ቢባል ወንዶችን ጠንካራ እንዲሆኑ ሴቶችን ደግሞ አሳቢ እንዲሆኑ እያደርግን ነው የምናሳድጋቸው። ይህ በእራሱ መጥፎ ነው ለማለት ሳይሆን ሁለቱም ፆታዎች ሁለቱንም እንዲሆኑ ብናደርጋቸው ምን አለበት ነው ይምለው። እሷ ማናት? የሚለው ጥንቅራችን ያሰቡበትን ዓላማ ለማሳካት ብዙ ውጣውረዶችን ያሳለፉ ሴቶችን ታሪክ የምናስቃኝበት ነው።
news-49835532
https://www.bbc.com/amharic/news-49835532
ደቡብ አፍሪካ፡ የመጤ ጠል ጥቃት የማያስቆማቸው ስደተኞች
ደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ አንድሪው ሃርዲን እንደሚለው በቅርቡ የሌሎች ሃገራት ዜጎች ላይ ከደረሰው ጥቃት በኋላ በአንዳንድ ሃገሪቱ ክፍሎች ''የጉልቤዎች ፖለቲካ'' ተንሰራፍቷል።
ከጥቂት ሳምንታት በፊት የንግድ ማእከል በሆነው የጆሃንስበርግ ምስራቃዊ ክፍል የውጪ ሀገራት ዜጎች የንግድ ተቋማት ላይ በደቦ በተፈፀመ ጥቃት አስር ሰዎች ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን ከሟቾቹ መካከል ሁለቱ የውጪ ዜጎች መሆናቸው ይታወሳል። • የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ሃላፊ ተዘረፉ • ራማፎሳ በሌሎች አፍሪካውያን ላይ በደረሰው ጥቃት ማፈራቸውን ገለፁ ጥቃቱ የተጀመረው የዕቃ ጫኝ መኪና አሽከርካሪዎች ከሌላ ሀገራት የመጡ ግለሰቦች ስራችንን እየነጠቁ ነው በሚል የስራ ማቆም አድማ ካደረጉ በኋላ ነው። ምንም እንኳ ደቡብ አፍሪካ ባላት የስራ እድል የተነሳ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በርካታ ወጣቶች ቢፈልሱም በሃገሪቱ ዜጎች ዘንድ ከፍተኛ የሆነ የሥራ አጥ ቁጥር አለ፤ ለዚህም አንዳንድ የሀገሪቱ ዜጎች ከሌላ ሀገር የመጡ ግለሰቦች ሥራቸውን እየነጠቋቸው እንደሆነ ያስባሉ። በተለይ ደግሞ 'ካትልሆንግ' በምትባለው አነስተኛ ከተማ ያለው ሁኔታ ተመሳሳይ ጥቃቶች ላለመፈጸማቸው ምንም ማስተማማኛ የለም። በከተማዋ የአካባቢውን ነዋሪዎች በማስተባበር የሚታወቀው ፓፒ ፓፒ '' ድንገት ሊፈነዳ እንደሚችል ቦምብ ማለት ነው'' ሲል ይገልጸዋል ሁኔታውን። በጥቃቱ ህይወቱ ስላለፈው ዚምባብዌያዊ ሲያወራም '' አባረው ከያዙት በኋላ በገዛ መኪናው ውስጥ ነው በእሳት ያቃጠሉት'' ብሏል። '' እነዚህ አካባቢዎች ከደቡብ አፍሪካውያን ይልቅ በስደተኞች የተሞሉ ናቸው። መንግስት ምንም ነገር አቅዶ እያደረገ አይደለም፤ ድንገት ነው እርምጃ የሚወስደው። ሌላው ቢቀር መሰረታዊ ግልጋሎቶች እንኳን በአግባቡ አልተሟሉም'' በማለት ነዋሪዎቹ ያሉበትን ሁኔታ ያብራራል። አንድሪው ሃርዲን ቀረብ ብሎ የነጋገራቸው በመንገድ ላይ ቁጭ ብለው የነበሩ ወጣቶች በመጀመሪያ አጋጣሚውን ሌሎች የወንጀል ቡድኖች ተጠቀሙበት እንጂ ጥቃቱ እምብዛም የሚባል ነበር ብለዋል። ትንሽ ቆይተው ግን የሌላ ሃገር ዜጎች እንዴት ስራ እንዳሳጧቸው ማማረር ጀመሩ። '' እኔ የሌላ ሃገር ዜጎችን አልጠላም፤ ነገር ግን እነዚህ ሰዎች ማንኛውም አይነት ስራ ከመስራት ወደኋላ አይሉም። ስራውን እጅግ ዝቅተኛ በሆነ ዋጋ ለመስራት ስለሚሞክሩ እኛ እንዴት ስራ እናግኝ'' ሲል አንድ ወጣት ሁኔታውን ያስረዳል። ሌላኛው ወጣትም በዚሁ ሃሳብ በመስማማት ''በደንብ ሊከፈለው የሚገባ ስራን በትንሽ ዋጋ ይሠሩታል። በዛ ላይ ደግሞ ከራሳቸው ዜጋ ውጪ ሰራተኛ አይቀጥሩም፤ ስለዚህ ለእኛ ስራ ማግኘት በጣም ከባድ ነው'' ብሏል። የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሲል ራማፎሳ በቅርቡ መጤ ጠል በሆኑ የአፍሪካ ዜጎች የደረሰው ጥቃት እጅግ አድርጎ እንደሚያሳፍራቸው በመግለጽ ይቅርታ ጠይቀው ነበር። ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገውና አነስተኛ ግሮሰሪውን በትልቅ የደህንነት መጠበቂያ አጥር የከለለው የ 23 ዓመት ኢትዮጵያዊ ስደተኛ '' ጥቃቶቹን ፈርቼ ይህንን ስራ ባቆም ምን እንደምሆን አላውቅም። ምንም አማራጭ የለኝም፤ የት እንደምሄድ እንኳን አላውቅም'' ብሏል። • ታዋቂ አፍሪካውያን ወደ ደቡብ አፍሪካ አንሄድም አሉ • በደቡብ አፍሪካው ዝርፊያ ከአርባ በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ በደቡብ አፍሪካ ካሉት ከ50 ሚሊየን በላይ ዜጎች በተጨማሪ 3.6 ሚሊየን የሚደርሱ ስደተኞች እንደሚገኙ የሀገሪቱ ስታስቲስቲክስ ቢሮ በቅርቡ ያወጣው መረጃ ያሳያል። 70 በመቶ የሚሆኑት ስደተኞች ደግሞ እንደ ዚምባብዌ፣ ሞዛምቢክና ሌሴቶ ካሉ የጎረቤት ሃገራት ነው የሚመጡት። ጆሃንስበርግ በሚገኘው ዊትስ ዩኒቨርሲቲ የስደተኞች ጉዳይ ባለሙያ የሆኑት ሎረን ላንዳው እንደሚሉት በአሁኑ ሰአት የአፍሪካ ከተሞች ትልቅ የሆነው የስራ አጦች ቁጥር እያሰቃያቸው ነው። '' እኔ የአንድ ከተማ አስተዳዳሪ ብሆን በጣም ነበር የምፈራው፤ ምክንያቱም ከተሞቹ መሸከም ከሚችሉት በላይ በሰዎች ተጨናነቀዋል። ሌጎስ፣ ናይሮቢ አልያም ጆሃንሰበርግን ብንወስድ ገና ከዚህ በኋላ እየሰፉ ይመጣሉ። የስራ ፈላጊውም ቁጥር አብሮ ይጨምራል።'' 30 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ስራ አጥ በሆነባት ሀገር ወጣቶች በአፋጣኝ ስራ ማግኘት ካልቻሉ መጤ ጠልነትና አመጽ የማይቀሩ ነገሮች መሆናቸውን ባለሙያው ያስረዳሉ። ''በተጨማሪም የመንደር ፖለቲከኞች ስልጣናቸውን ለማስጠበቅና በህዝቡ ዘንድ ተወዳጅነት ለማግኘት የፌደራሉ መንግስት የውጭ ሃገር ዜጎችን እንዲያባርር የሚጠይቁ መልእክቶችን በተደጋጋሚ ማሰማታቸው በህዝቡ ዘንድ ሁሌም ቁጣ ይቀሰቅሳል።'' በማለት ጉዳዩ ምን ያክል የተወሳሰበና በአጭር ጊዜ ለመፍታት አስቸጋሪ እንደሆነ ያስረዳሉ ባለሙያው።
news-53133221
https://www.bbc.com/amharic/news-53133221
ዚምባብዌ የቅንጡ ባለሀብቶቿን የሀብት ምንጭ ልትመረምር ነው
የገንዘብ ግሽበት በዳዴ እያስኬዳት የምትገኘው ዜምባብዌ ህመሟ ሮበርት ሙጋቤ ነበሩ ቢባልም ዛሬም መሻሻል አልሰመረላትም፡፡
በአገሪቱ ያለውን ምጣኔ ሀብታዊ ዝቅጠት ለመገደብ የዚምባቡዌ ባለሥልጣናት አዳዲስ ሙከራዎችን ይዘዋል፡፡ ትናንት ይፋ የሆነ መረጃ እንደሚያስረዳው በዝምባብዌ አንድ ባለሀብት ፍርድ ቤት ከሙስና ነጻ ቢያደርገውም እንኳ የሀብት ምንጩን አሳማኝ በሆነ ሁኔታ ማስረዳት ካልቻለ ሀብት ንብረቱ ይታገድበታል፡፡ የዚምባብዌ የጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ማታንዳ ሞዮ እንዳሉት ከዚህ በኋላ የሚቀናጡ ባለሀብቶች ላይ ቁጥጥር ይደረጋል፡፡ አሁን አሁን በዚያች አገር ሕዝቦች የዕለት ጉርሳቸውን ማግኘት እየተሳናቸው መጥቷል፡፡ ውሃና መብራት እንኳ በቅጡ ማግኘት ቅንጦት ሆኗል፡፡ የዳቦና የነዳጅ ወረፋውም አይጣል ነው፡፡ ዜጎች መኪናቸው ላይ ነዳጅ ጠብ ለማድረግ ከአንድ ቀን በላይ የተሰለፉበት አጋጣሚም ነበር፡፡ "አሁን የተያያዝነው ምርመራ ዘዴ የቅንጦት አኗኗር ዘዬን በሚከተሉ ባለሀብቶች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግን ነው፡፡ እንዲቀናጡ ያስቻላቸውን ገንዘቡን ከየት አመጡት? የሚቀናጡበት ሁኔታና ሀብታቸውስ አሳማኝ ነው? ለመሆኑ ግብር ከፍለው ነው የሚቀናጡበት? የሚለውን እናጠናለን" ብለዋል ኮሚሽነር ሞዮ። የጸረ ሙስና ኮሚሽኑ በዚህ መንገድ የሰዎችን የሀብት ምንጭ እንዲመረምር ሥልጣን የተሰጠው በ2019 ነበር፡፡ በዚህ መንገድ ምርመራ የሚደረግባቸው የዚምባብዌ ባለሀብቶች ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሄደው የተጠየቁትን ማብራሪያ መስጠት ይኖርባቸዋል፤ ካልሆነ ግን ሀብት ንብረታቸው ይታገዳል፡፡ ዚምባብዌ ይህን የምርመራ ዘዴ በመጠቀም ደረጃ የመጀመርያ አገር አይደለችም፡፡ በዚህ የምርመራ ዘዴ መሰረት ባለሀብቱ የሀብት ምንጩን ንጹሕነት በቅጡ የማስረዳት ዕዳ ይኖርበታል፡፡ የሙስና ጉዳዮችን በማጥናት የሚታወቀው ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል በቅርቡ ዚምባብዌ የኮሮናቫይረስ ሕክምና ቁሳቁሶች ግዢ ጨረታ ሂደትን ለሙስና የተጋለጠ እንደነበር ስጋቱን ገልጾ ነበር፡፡ ድርጅቱ እንዳለው ቁሳቁሶቹ ዋጋ እጅጉኑ ተጋኖ ነው ግዢ የተፈጸመው፤ ይህም ሙስና መኖሩን አመላካች ነው ብሎ ነበር፡፡ ይህን ተከትሎ የዚምባብዌ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ኦባዲህ ሞዮ የግዢ ሥርዓትን ባለመከተል ክስ ተከፍቶባቸዋል፡፡ በሐምሌ ወር ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
news-46285794
https://www.bbc.com/amharic/news-46285794
የምግብ እጥረት የመካከለኛው ምስራቋን የመንን እየፈተናት ነው
የመን ውስጥ ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ 85 ሺ ህጻናት በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምክንያት ህይወታቸው ሳያልፍ እንዳልቀረ ሴቭዘቺልድረን የተባለው ምግባረ ሰናይ ድርጅት አስታወቀ።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለፈው ወር ባወጣው ሪፖርት 14 ሚሊዮን የመናውያን ከባድ ረሃብ ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ገልጾ ነበር። ለዚህ ሀሉ መነሾው ደግሞ ሶስተኛ ዓመቱን የያዘው የእርስ በርስ ጦርነት ሲሆን፤ ያስከተለው ጉዳትም በዓለማችን ካጋጠሙ ሰብዓዊ ቀውሶች ትልቁ አስብሎታል። እስካሁን 6800 ንጹሃን ዜጎች ህይወታቸው ሲያልፍ፤ ከ10 ሺ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው የተባበሩት መንግሥታት መግለጫ ያሳያል። • ተጠርጣሪዎችን የመያዝ ዘመቻው ብሔር ላይ ያነጣጠረ ነው? • ባለፉት ሁለት ዓመታት 700 ሺህ ሰዎች ከሶማሌ ክልል ተፈናቅለዋል ከዚህ በተጨማሪ 22 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ሰብዓዊ ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን፤ የምግብ እጥረት ደግሞ አብዛኛውን የሃገሬውን ሰው እየፈተነ ያለ ጉዳይ ነው። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ከእነዚህ ሁሉ አስቸጋሪ ፈተናዎች ያለፉት ደግሞ በኮሌራ ወረርሽኝ እየተጠቁ እንደሆነና በበሽታው ምክንያት1.2 ሚሊዮን ሰዎች ህይወታቸው አደጋ ላይ መሆኑ ተጠቁሟል። 85 ሺዎቹ ህጻናት በምግብ እጥረት መሞታቸውን ለማረጋገጥና መረጃ ለማሰባሰብ እጅግ ፈታኝ እንደነበረ የረድኤት ድርጅቱ ገልጿል። ለዚህ ዋነኛ ምክንያቱ ደግሞ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የሃገሪቱ የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋማት በጦርነቱ መውደማቸው ነው። ከጦርነቱ የተረፉት የጤና ተቋማት ውስጥ አገልግሎት ማግኘት እጅግ ውድ ስለሚሆን አብዛኛዎቹ ህጻናት ህይወታቸው ሲያልፍ እንኳን በተገቢው ሁኔታ አልተመዘገቡም። • «በሸካ ዞን የመንግሥት ቢሮዎች ለወራት ሥራ ፈተዋል. . .» • ስደተኞቹ ሊቢያ ወደብ ላይ ከመርከብ አንወርድም አሉ 85 ሺዎቹ ህጻናት ህይወታቸው ያለፈው እ.አ.አ. ከሚያዚያ 2015 እስከ ጥቅምት 2018 ድረስ እንደሆነ ተጠቁሟል። አልቆም ያለው ጦርነት የሃገሪቱን የገንዘብ አቅም እጅግ ያዳከመው ሲሆን፤ የምግብና አስፈላጊ እቃዎች ዋጋ በአሳሳቢ ሁኔታ እየጨመረ ነው። የመን ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነውን ምግብ ከውጪ የምታስገባበት ወደብ በአማጺያን ቁጥጥር ሲሆን፤ በሃገሪቱ ያለው የምግብ ክምችት 4.4 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች ብቻ የሚበቃ እንደሆነ ሴቭዘቺልድረን አስታውቋል።
48809945
https://www.bbc.com/amharic/48809945
አዴፓ የከሸፈውን መፈንቅለ መንግሥት ያቀነባበሩትና የመሩት "የእናት ጡት ነካሾች" ናቸው አለ
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ሰኔ 15 በአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮችና በመከላከያ ሠራዊት ጄነራሎች ላይ የተፈፀመውን ግድያ አስመልክቶ አስቸኳይ ስብሰባ በማካሄድ ባለስድስት ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።
በመግለጫው ላይ ሰኔ 15/2011 ዓ.ም የተካሄደውን የከፍተኛ አመራሮች ግድያና መፈንቅለ መንግሥቱን ያቀነባበሩና በድርጊቱ የተሳተፉ አካላትንም አውግዟል። የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ፓርቲ ከታገለባቸው ጉዳዮች መካከል "የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት እንዲከበር" መሆኑን አስታውሶ ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌን ጨምሮ ሌሎች ግለሰቦች ከታሰሩበት ነፃ እንዲወጡ በግምባር ቀደምትነት የታገሉትን አመራሮች "በግፍና በጭካኔ መግደል የእናት ጡት ነካሽነት እና ክህደት" ነው በማለት ድርጊቱን አውግዟል። • "ብ/ጄነራል አሳምነው በባጃጅ ለማምለጥ ሲሞክሩ ነው የተገደሉት'' • በኢትዮጵያ የኤሊ አደን ለምን አየተበራከተ መጣ? • በፌስታል ተጥላ ለተገኘችው ልጅ የጉዲፈቻ ጥያቄዎች ጎረፉላት አክሎም "በከሸፈው መፈንቅለ-መንግሥት የተፈፀመው ጥቃትና ወንጀል እንዲሁም የአመራሮቻችን የግፍ አገዳደል የአማራን ሕዝብ ያሳፈረና ያዋረደ ሆኖ ሳለ ወንጀሉን ለመሸፋፈን እና ለማሳነስ ሆነ ተብሎ አሉቧልታ በመንዛት ህዝባችንን ለማደናገር እና አቅጣጫ ለማሳት የምትሰሩ አካላት ከዚህ ዕኩይ ድርጊታችሁ ተቆጠቡ" ሲል አሳስቧል። የማዕከላዊ ኮሚቴው መግለጫ በከሸፈው መፈንቅለ-መንግሥት እጃቸው ያለበትን ግለሰቦችና ቡድኖች በህግ ቁጥጥር ስር የማዋል ሥራው በሁሉም አካላት ርብርብ "በአጠረ ጊዜና በተሳካ ሁኔታ የተፈፀመ መሆኑን" ጠቅሶ "አሁንም ወንጀለኞችን ሙሉ በሙሉ በህግ ቁጥጥር ስር የማዋልና ህጋዊ እርምጃ የመውሰድ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል" ሲል አስታውቋል። በክልሉ በተደጋጋሚ የታዩ የሰላም መደፍረሶችን በማንሳትም የፀጥታ መዋቅሩን መልሶ ለማጠናከርና በክልሉ አስተማማኝ ሰላምና ደህንነት እንዲረጋገጥ "በልዩ ሁኔታ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ አስፈላጊው ሁሉ ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል" ብሏል። ድርጅቱ ውስጣዊ አንድነቱ የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ እንደሚገኝ አስታውሶ የድርጅቱን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም የክልሉንና የኢትዮጵያን ሕዝቦች፤ "ከመቼውም ጊዜ በላይ በአንድነት በመቆም የተፈጠረውን ፈተና" በብቃት ለማለፍና አገራችንን ለመታደግ በፅናት እንድትቆሙ" በማለት ጥሪውን አቅርቧል። አክሎም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የተለያዩ አካላት መረጋጋትን፣ ሠላምና አንድነትን የሚያጠናክሩ ሥራዎች ላይ በማተኮር በኃላፊነት ስሜት መንቀሳቀስ እንደሚጠበቅባቸው አስታውሷል። በመጨረሻም የከሸፈው መፈንቅለ መንግሥት በአማራ ክልልና ሕዝብ ላይ ብቻ የተፈፀመ ሳይሆን በመላው ኢትዮጵያዊያን ላይ የተፈፀመ ጥቃት መሆኑን በመግለፅ በዚህ ወቅት ከጎኑ የነበሩትን በአጠቃላይ አመስግኗል።
news-50038493
https://www.bbc.com/amharic/news-50038493
ካሊፎርኒያ ከእንስሳት ፀጉር የሚሰሩ ምርቶችን በማገድ የመጀመሪያዋ የአሜሪካ ግዛት ሆነች
ካሊፎርኒያ፤ ከእንስሳት ፀጉር የሚሠሩ ምርቶች እንዳይመረቱና እንዳይሸጡ በማገድ የመጀመሪያዋ የአሜሪካ ግዛት ሆነች።
በመሆኑም የግዛቷ ነዋሪዎች ከ2023 ጀምሮ ከእንስሳት ፀጉር የተሠሩ ምርቶችን መሸጥም ሆነ አልባሳት፣ ጫማ፣ ቦርሳዎችን መሥራት አይችሉም። ውሳኔው እገዳው እንዲጣል ለተወሰነ ጊዜ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበሩትን የእንስሳት መብት ተሟጋቾች አስደስቷል። • ከሺዎች እስከ ኳትሪሊየን እንስሳት በአንድ ቀን የሚወለዱባት ምድር • ብዝኀ ሕይወት ምንድን ነው? ለምንስ ግድ ይሰጠናል? የግዛቷ አስተዳዳሪ ጌቪን ኒውሰም፤ ከድመት፣ ከውሻና ከፈረስ በስተቀር ሌሎችን እንስሳት በሰርከስ ትዕይንት ጥቅም ላይ እንዳይውሉ የሚከለክለውን ረቂቅ ሕግም ፈርመዋል። ነገር ግን ሕጉ በሰሜን አሜሪካ የሚዘወተረውን የኮርማ እና የፈረስ ግልቢያ ስፖርት ላይ ተግባራዊ አይሆንም። "በእንስሳት ደህንነት ጥበቃ ዙሪያ ካሊፎርኒያ መሪ ናት፤ ዛሬ ደግሞ አስተዳዳሩ ከእንስሳት ፀጉር የተሠሩ ምርቶችን እንዳይሸጥ ለማድረግ ሕግ አውጥቷል" ሲሉ አስተዳዳሪው ጋቪን በመግለጫቸው ተናግረዋል። እገዳው ግን በቆዳ ምርቶች ላይ ማለትም በላም፣ በአጋዘን፣ በበግና በፍየል ቆዳ ላይ ተፈፃሚ እንደማይሆን የሳንፍራንሲስኮ ክሮኒቸል ዘግቧል። ከዚህም በተጨማሪ በእንስሳት አምሳያ ከእንስሳት ምርቶች የሚሠሩ አሻንጉሊቶች ላይ ተግባራዊ እንደማይሆንም ተነግሯል። ይህንን ሕግ ጥሶ የተገኘም እስከ 500 ዶላር ቅጣት፤ ሕጉን በተደጋጋሚ ለጣሰም እስከ 1000 ዶላር ያስቀጣል። የአሜሪካ ሁዩማን ሶሳይቲ አሜሪካ የግዛቷን አስተዳደር እና ሕግ አውጪዎቹን እንዲሁም የካሊፎርኒያ ዜጎች ገበያቸው በእንስሳት ፀጉር የተሠሩ ምርቶች ፍላጎቶችን እንዲያስተናግዱ ባለመፍቀዳቸው አድናቆቱን ችሯል። ይሁን እንጂ ውሳኔው የእንስሳት ተዋፅኦ የማይጠቀሙትን አክራሪ ቬጋኖች (እንስሳትንም ሆነ የእንስሳት ተዋፅኦ የማይጠቀሙ) አጀንዳ ለማስተናገድ ከፀጉር የሚሠሩ ምርቶችን በመከልከል፤ በምንለብሰውና በምንመገበው ላይ እገዳ ለመጣል አንድ እርምጃ ነው ሲል ፈር ኢንፎርሜሽን ካውንስል ተችቶታል። ባሳለፍነው ግንቦት ወር አንድ በፋሽን የተሠማራ ድርጅት እስከ 2020 ድረስ የእንስሳትን ፀጉር መጠቀም እንደሚያቆም አስታውቆ ነበር። በየካቲት ወርም እንዲሁ የእንግሊዙ ሰልፍሪጅስ ከየካቲት 2020 ጀምሮ የእንስሳት ቆዳ ውጤቶችን መሸጥ ሊያግድ እንደሚችል ማስታወቁ ይታወሳል።
54510332
https://www.bbc.com/amharic/54510332
እስራኤል 2,000 ቤተ እስራኤላውያንን ለመቀበል ፈቀደች
እስራኤል 2,000 ቤተ እስራኤላውያን ወደ አገሯ እንዲገቡ ፈቀደች። ይህም ለዓሠርታት ለዘለቀው ጥያቄያቸው ምላሽ የሰጠ ውሳኔ ነው።
ኢትዮጵያውያኑ ወደ እስራኤል ለመጓዝ ለዓመታት ሲጠባበቁ ከነበሩ ወደ 8,000 የሚጠጉ የአይሁድ እምነት ተከታዮች መካከል ናቸው። ቤተ እስራኤላውያኑ፤ እስራኤል የመኖር መብት ጥያቄያቸው ለዓመታት ሲነሳ የነበረ ነው። ለአብዛኞቹ አይሁዳውያን የእስራኤል ዜግነት የማግኘት መብት የሚሰጠው ሂደት ለነሱ አይሠራም። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ1980ዎቹ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በሚሥጥራዊ ተልዕኮ ወደ እስራኤል ተወስደዋል። አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን የአይሁድ እምነት ተከታዮች ያኔ ከሄዱት ቤተ እስራኤላውያን ጋር የደም ትስስር አላቸው። ሆኖም ግን ከዛ በኋላ ወደ እስራኤል መሄድ የተፈቀደላቸው ጥቂቶቹ ብቻ ሲሆኑ፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን አይሁዶች በጎንደር እና አዲስ አበባ በሚገኙ ማቆያዎች ይገኛሉ። ማኅበረሰቡ ከቤተ እስራኤላውያን የዘር ግንድ የሚመዘዝ ሲሆን፤ በ1880ዎቹ አውሮፓውያን ሚሽነሪዎች ክርስቲያን አድርገዋቸው ነበር። . ቲፋኒ ሃዲሽ፡ ጥቁርነትና ይሁዳዊነት . ከኢትዮጵያ የሄደችው ቤተ እስራኤላዊት በሚኒስትርነት ተሾመች . 119 ቤተ እስራኤላውያን ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል አቀኑ . በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ወደ ፅዮን ውሰዱን ተማፅኖ ከዛ ግን ወደ አይሁድ እምነት ተመልሰዋል። ሆኖም የእስራኤል የአገር ውስጥ ሚንስትር እንደ ሙሉ የአይሁድ እምነት ተከታይ እውቅና አልሰጣቸውም። እስራኤል እንዲሄዱ መፈቀድ አለበት ወይስ የለበትም? የሚለው እስራኤል በሚኖሩ ቤተ እስራኤላውያን ሳይቀር መከፋፈል ፈጥሯል። አንዳንድ ቤተ እስራኤላውያን፤ ኢትዮጵያውያን የእምነቱ ተከታዮች እስራኤል የመኖር መብት አላቸው ሲሉ፤ ሌሎች ደግሞ አይሁዳዊ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያን ናቸው በማለት ሐሳቡን አይቀበሉትም። . "ወደ እናት ሃገራችን እስራኤል ውሰዱን" . መባረር ወይም እስር የሚጠብቃቸው ስደተኞች በእስራኤል በቅርቡ በስደተኞች ጉዳይ ሚንስትርነት የተሾሙት ትውልደ ኢትዮጵያዊት ኒና ታማኖ-ሻታ በበኩላቸው፤ 2,000 ቤተ እስራኤላውያን ወደ እስራኤል እንዲገቡ በመፈቀዱ ደስታቸውን ገልጸዋል። በትዊተር ገጻቸው "በጣም ደስ ብሎኛል" ሲሉም ጽፈዋል። ሚንስትሯ እስከ ቀጣዩ ዓመት ማገባደጃ ድረስ ቤተ እስራኤላውያንን ወደ እስራኤል ለመውሰድ ቃል ገብተው ነበር። ቤተ እስራኤላውያን መጀመሪያ ላይ ወደ እስራኤል የተወሰዱት ከሱዳን የስደተኞች ማቆያዎች ነበር። በ1980ዎቹ መባቻ ላይ የእስራኤሉ የስለላ ተቋም ሞሳድ ጉዟቸውን እንዳመቻቸም ይታወሳል። ውሳኔውን ያስተላለፉት የያኔው ጠቅላይ ሚንስትር ነበሩ። በቀጣይም በ1991 በርካታ ኢትዮጵያውያን ወደ እስራኤል ተወስደዋል። ቤተ እስራኤላውያኑ ከእስራኤል ማኅበረሰብ ጋር ተዋህደው ለመኖር ያሚያደርጉት ጥረት ቀላል አይደለም። ብዙዎቹ ሥራ አጥ ሲሆኑ፤ መድልዎም ይደርስባቸዋል።
47720207
https://www.bbc.com/amharic/47720207
ሰማይ ላይ ወልዳ አሥመራ የምትታረሰው ኢትዮጵያዊት
ጀነቲ ሁሴን መሐመድ ትባላለች፤ የስምንት ወር ነፍሰ ጡር ነበረች። ኑሮዋን የመሠረተችው ደግሞ ባሕር ማዶ፤ ሳዑዲ።
ቅዳሜ ዕለት ታዲያ በቤተሰቦቿ ተከ'ባ ለመውለድ፣ በሀገሯ እና በወገኖቿ መካከልም ለመታረስ በማሰብ፣ ከሳውዲ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ ጓዟን ሸካክፋ አውሮፕላን ተሳፈረች። አውሮፕላኑ የኤርትራ አየር ክልል ውስጥ እንደገባ ግን ያላሰበችው ነገር ገጠማት፤ ምጥ ፈትሮ ያዛት። ዕለቱ ቅዳሜ፣ ሰዓቱም ከማለዳው 1 ሰዓት ከሩብ ነበር። "ከሳውዲ ስነሳ ደህና ነበርኩ" የምትለው ጀነቲ አውሮፕላን ላይ እወልዳለሁ ብላ እንዳላሰበች ለቢቢሲ ተናግራለች። አውሮፕላን ላይ ከመውጣቷ በፊት ክትትል አድርጋ እንደነበር ስንጠይቃትም ከበረራ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ጁምዓ [ዓርብ] ሆስፒታል ሄዳ ዶክተሮች በቅርብ አትወልጂም እንዳሏት ታስታውሳለች። በነገታው ምጧ ይፋፋማል ብሎ ያሰበም ኾነ ያለመ ማን ነበር? • አንዳንድ ጥያቄዎች ለ"108ኛው" ፓርቲ • ኢትዮጵያዊያን ቶሎ አያረጁም? • ጌዲዮ በዐቢይ ጉብኝት ማግስት አውሮፕላኑ ከሳዑዲ ተነስቶ ቅድሚያ ጅዳ ሲያርፍ "የሆነ የመርገጥ ስሜትና ፈሳሽ ውሃ ሲፈሰኝ ተሰምቶኛል" ትላለች ጀነቲ፤ ሁኔታው የድንጋጤ ወይም የሌላ ህመም ነው ብላ በማሰብ ለማንም አልተነፈሰችም። "በቅርብ እወልዳለሁ ብዬ ስላላሰብኩ ዝም አልኩ" እነዚህን ምልክቶቿን ከራሷ ውጪ ለሌላ ሰው ያላዋየችው ጀነቲ አውሮፕላኑ ተነስቶ በረራ ሲጀምርም በዝምታዋ ፀናች። ነገር ግን "ጢያራው ከተነሳ 10 ወይ 20 ደቂቃ በኋላ ጓደኞቼን አሞኛል፤ አስተናጋጆቹን ንገሯቸው አልኳቸው። አስተናጋጆቹም መጥተው ሽርት ውሃ መፍሰስ ምናምን ከሆነ ምጥ ነው ብለው ወደ ሆነ ቦታ ወሰዱኝ" ትላለች። በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበረው ቦታ ጥበት ለምጥ እንዳስቸገራት የምትናገረው ጀኒት ሊያስተኟት ሲሉ ሽርት ውኃዋ መፍሰሱን ታስታውሳለች። አስተናጋጆቹ በሁኔታው ተደናግጠው ባለሙያ ከተሳፋሪዎቹ መካከል እንዳለ ቢጠይቁም ባለመገኘቱ እራሳቸው እንደረዷት ትዝ ይላታል። ይህ ሁሉ ሲሆን የነ ጀነቲ አውሮፕላን በአስመራ አየር ክልል እየበረረ እንጂ መሬት አልረገጠም። መንታ በሰማይ ላይ ብዙ ሰዎች ጀነቲ ልጆቿን የተገላገለችው በኤርትራ አስመራ እንደሆነ ነው የገባቸው። እውነታው ትንሽ ይለያል። "የመጀመሪያዋ ልጄ አውሮፕላኑ ከማረፉ በፊት የተወለደች ሲሆን ሁለተኛዋ ግን አውሮፕላኑ አርፎ ሞተሩን ለማብረድ እየተንደረደረ ነበር የተወለደችው" በማለት መንታ ልጆች የታቀፈችበትን የሰማይ ላይ ድራማ በስሱ ታስታውሳለች። 'ስም አወጣሽላቸው?' ብለን ስንጠይቃት ነገሩን እንዳላሰበችበት በሚያሳብቅ አግራሞት፣ "...ወላሂ ማን እንደምላቸው ገና እያሰብኩበት ነው" ብላለች። ጀኒት መንታ ስትወልድ የመጀመሪያዋ ነው። ከዚህ በፊት አንድ ወንድና ሁለት ሴት ልጆች አሏት። አሁን ምድር ላይ የተወለዱ ሦስት ልጆቿን ጨምራ በሰማይ ከተወለዱት ሁለቱ ጋር የአምስት ልጆች እናት ሆናለች። ቅዳሜ ዕለት ልጆቿን አውሮፕላን ላይ በሰላም ከተገላገለች በኋላ በቀጥታ የተወሰደችው በአስመራ ከተማ ትልቅ ወደሚባለው ኦሮታ ሪፈራል ሆስፒታል ነው። የሆስፒታሉ የሕፃናት ሐኪም ዶ/ር ዘሚካኤል ዕቁበም ጀኒት በአውሮፕላን ውስጥ በሰላም መውለዷን አረጋግጠው እነርሱ በፍጥነት በስፍራው በመድረስ ድህረ የወሊድ ህክምና እንደሰጧት ገልፀዋል። ጀኒት ቅዳሜ፣ መጋቢት 14፣ ብትወልድም እስከዛሬ ድረስ ወደ ሀገሯ ያልተሸኘችው የሁለተኛዋ መንታ ጨቅላ የደም ማነስ ሁኔታ ስለነበራት ነው ብለዋል። አሁን የደምዋ መጠንና አመጋገቧም እየተስተካከለ መጥቷል ያሉት ዶ/ር ዘሚካኤል ጨቅላዋ ሙሉ ጤንነቷ ከተመለሰ በኋላ ሁሉም ወደቤታቸው እንደሚሄዱ አረጋግጠዋል። በአስመራ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ እንደሆነ የኤምባሲው ሁለተኛ ፀሐፊ የሆኑት አቶ ዘሪሁን መገርሳ ነግረውናል። ለመሆኑ በተርሚናል አምጦ፣ በሰው አገር ሰማይ ወልዶ፣ በአሥመራ ታርሶ...የልጆቹ ዜግነት ከወዴት ነው?
news-50953720
https://www.bbc.com/amharic/news-50953720
ሱዳን በእስር ቤት የነበረን መምህር ገድለዋል በተባሉት ላይ የሞት ፍርድ አስተላለፈች
የሱዳን ፍርድ ቤት አንድ አስተማሪን በእስር ላይ ሳለ አሰቃይተው ለሞት ዳርገውታል በሚል በ29 የደህንነት አባላት ላይ የሞት ፍርድ አስተላለፈ።
ተቃዋሚዎች በፍርድ ቤቱ ደጅ ላይ ተሰባስበው ፍትህ እንዲሰጥ ሲጠይቁ ነበር የ36 ዓመቱ አስተማሪ አሕመድ አል ክሄር፤ በእስር ላይ ሳለ ይህችን ዓለም የተሰናበተው ባሳለፍነው ዓመት በፈረንጆቹ የካቲት ወር ነበር። አሕመድ የቀድሞ አገሪቷ ፕሬዚደንት ኦማር አል በሽር ተቃውሞ ላይ በመሳተፉ ነበር ለእስር የተዳረገው። • ኦማር አል-በሽር: ከየት ወደየት? • የሞት ፍርድ ተፈርዶበት የነበረው ኬንያዊ የሕግ ዲግሪውን አጠናቀቀ ባለፈው ሚያዚያ ወር በሽር ከሥልጣን ከተወገዱ በወራት ውስጥ እንዲህ ዓይነት ፍርድ ሲተላለፍ ይህ የመጀመሪያው ነው። አቃቤ ሕግ የሞት ፍርዱን ተገቢ ቅጣት ነው ብለውታል። ፍርዱ ከተላለፈ በኋላም፤ ዳኛው የአሕመድን ወንድም፣ ስአድን 29ኙ የደህንነት አባላት ይቅርታ እንዲደረግላቸው ይፈልግ እንደሆነ ጠይቀውት ነበር። እርሱ ግን እንዲገደሉ እንደሚፈልግ ተናግሯል። የተከሳሾቹ ጠበቃ በበኩሉ ይግባኝ እንደሚል ገልጿል። ፍርድ ቤቱ ባገኘው ማስረጃ፤ መምህር አሕመድ አል ክሄር፤ በአገሪቷ ምስራቃዊ ግዛት ካሳላ በእስር ላይ በነበረበት ወቅት በደህንነት አባላቱ ድብደባ ተፈፅሞበታል። ለስቃይም ተዳርጓል። የመምህር አሕመድ ጉዳይ በመላ አገሪቷ ትኩረትን የሳበ ነበር። ግድያውም በ75 ዓመቱ ፕሬዚደንት አል በሽር ላይ ተቃውሞ አስነስቷል። ውሳኔውን ለመስማትም በዋና መዲናዋ ካርቱም አቅራቢያ በምትገኘው ኦምዱርማን ከተማ ፍርድ ቤት ውጭ በርካቶች ተሰባስበው አካባቢውን አጨናንቀውት ታይተዋል። ሱዳን በቀድሞው ፕሬዚደንት ኦማር አል በሽር አገዛዝ ሥር፤ በአውሮፓዊያኑ 2018 በሁለት ግለሰቦች ላይ የሞት ፍርድ አስተላልፋ፤ ቅጣቱን ፈፅማለች። • አሜሪካ ከ16 ዓመት በኋላ የሞት ቅጣት ልትጀምር ነው በሱዳን ለወራት በቆየው ተቃውሞ ቢያንስ 170 ሰዎች ተገድለዋል። በመጨረሻም ኦማር አል በሽር ለ30 ዓመታት ከዘለቀው መንበራቸው በወታደራዊ ኃይሉ ከሥልጣናቸው ተወግደዋል። በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የቀድሞ ፕሬዚደንቱ ከሳዑዲ ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማን ከተቀበሉት 25 ሚሊየን ዶላር ጋር በሚያያዝ የሙስና ወንጀል ሁለት ዓመታትን በእስር እንዲያሳልፉ ተፈርዶባቸዋል። ፍርድ ቤቱ በማረሚያ ቤት እንዲቆዩም ውሳኔ አስተላልፏል። አል በሽር ግን ከሳዑዲው ልዑል የተቀበሉትን ገንዘብ አስመልክቶም ከሳዑዲ ጋር ባላቸው ስትራቴጂካዊ ግንኙነት የተበረከተ እንደሆነ ገልፀው፤ "ለግል ጥቅም ሳይሆን ለእርዳታ የተሰጠ ነው" ሲሉ በክሱ ላይ ቅሬታቸውን አሰምተዋል። አል በሽር እርሳቸውን ወደ ሥልጣን ካወጣቸውና በአውሮፓዊያኑ 1989 ከተደረገው መፈንቅለ መንግሥት፣ ከዘር ማጥፋት እና የተቃዋሚዎች ግድያ ጋር በተያያዘም ሌሎች ክሶችም አሉባቸው።
news-46347238
https://www.bbc.com/amharic/news-46347238
ታሪክ እየቀየሩ ያሉት ሴቶች
በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ስር ኢትዮጵያ እየተቀየረች ይመስላል። ሴቶች ከተለመደውና ባህላዊ ከሆነው በቤተሰብ ላይ የተንጠለጠለን ሃላፊነት በማለፍ ከፍተኛ በሚባሉ መንግሥታዊ ቦታዎች እየታዩ ነው።
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት መዓዛ አሸናፊ አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያዊያን በቀድሞው ዘመን ስለነበረችው ታላቋ ንግሥት ሳባ በኩራት ሲያወሩ ቢደመጡም፤ ማህበረሰቡ ግን አሁንም የወንዶች የበላይነት የሚንጸባረቅበትና ተቀባይነት ያለው አስተሳሰብ ነው። ''የማህበረሰቡ የአፍ መፍቻ የወንዶች የበላይነት ነው። ከልጅነታችን ጀምሮ ሴቶችን ዝቅ አድርገን እየተመለከትን ነው ያደግነው" ትላለች የሥርዓተ-ጾታና የህግ ባለሙያዋ ህሊና ብርሃኑ። • የሴቶች መብት ታጋይዋ ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ማን ናቸው? • "የመከላከያ ሚኒስቴርን በተሻለ መልኩ መምራት ይቻላል" ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ሴት የሰራችው ቤት መሰረት የለውም የሚለው አባባልና ሌሎች ተመሳሳይ አነጋገሮች ደግሞ በማህበረሰቡ ውስጥ ላለው ሴቶችን ዝቅ አድርጎ የመመለክት ማሳያ ናቸው ትላለች ህሊና። 102.5 ሚሊዮን ከሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥ ግማሾቹ ሴቶች ሲሆኑ፤ አብዛኛዎቹ በገጠራማ አካባቢዎች የሚኖሩት ሴቶች ሃላፊነት ደግሞ ህጻናትን ከመንከባከብና እንደ ውሃ መቅዳት፣ ምግብ ማብሰል ያሉ የቤት ውስጥ ሥራዎችን ከመስራት አይዘልም። ከኢትዮጵያ መንግሥትና ተባባሪ አካላት የተገኘ መረጃ እንደሚያሳየው፤ እነዚህ ሁሉ ጉዳዮች ወደ ኋላ በሚጎትቷት ሃገር ውስጥ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ሴቶችን ወደ ከፍተኛ መንግሥታዊ ሃላፊነቶች የማምጣት ውሳኔ በብዙዎች ዘንድ ይሁንታን አግኝቷል። • ከኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ እስከ ሣህለወርቅ ዘውዴ • "ማንም መብታችንን ሊሰጠን ስለማይችል፤ ሴቶች ማንንም ሳይጠብቁ በራሳቸው መታገል አለባቸው" ብዙ የመብት ተሟጋቾችም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ የሚቀጥሉ ከሆነ፤ ለሴቶች የሚሰጠውን ግምት የሚቀይሩ ብዙ ለውጦች ወደፊትም ልናይ እንችላለን እያሉ ነው። የ42 ዓመቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሾሟቸው 20 ሚኒስትሮች መካከል ግማሾቹ ሴቶች ሲሆኑ፤ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ግን ሃላፊነቱን የሰጡት ለአራት ሴቶች ብቻ ነበር። በአሁኑ ሰዓትም በአፍሪካ ውስጥ በከፍተኛ የመንግሥት ሃላፊነት ቦታዎች ላይ የሴቶች እኩል ተሳትፎ ያለው በኢትዮጵያና ሩዋንዳ ብቻ ነው። ከዚህ በተጨማሪም ያለእድሜ ጋብቻን ለማስቀረት ያደረገችው ከፍተኛ ትግል ላይ ተመስርታ ታዋቂዋ የሆሊዉድ ተዋናይት 'አንጀሊና ጆሊ' በአውሮፓውያኑ በ2014 ፊልም እሰከመስራት ያደረሰችው የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና ጠበቃ መዓዛ አሸናፊን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አድርገው ሾመዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ በተለያዩ ሃላፊነት ቦታዎች ላይ የሰሩት ሳህለወርቅ ዘውዴ የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙ ሲሆን፤ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዋ ቢልለኔ ስዩም ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪ ተብለው ሥራቸውን ጀምዋል። የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በአሁኑ ሰአት በአፍሪካ ብቸኛዋ ሴት ፕሬዝዳንት ናቸው። ለሴቶች መብት የሚከራከረው የየሎ እንቅናቄ አባል የሆነችው ረድኤት ክፍሌ ለቢቢሲ ስትናገር ''እንደዚህ አይነት ነገር አይተን አናውቅም። ለአይናችን አዲስ ነው። ሃላፊነቱ ምንም ይሁን ምን የአመራር ክህሎታቸውን ለማሳደግ ይረዳቸዋል'' ብላለች። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሴቶች ያላቸውን ክብርና እምነት ገና የበዓለ ሲመታቸው ንግግር ላይ ስለ ለእናታቸው ምስጋና በማቅረበ ነው ያሳዩት። ''እናቴ ልክ እንደማንኛዋም ኢትዮጵያዊ እናት ሩህሩህና ጠንካራ ሰራተኛ ነበረች፤ ምንም እንኳን አሁን በህይወት ባትኖርም ላመሰግናት እፈልጋለው'' ብለው ነበር። ''በተጨማሪም የእናቴን ቦታ በመተካት ላገዘችኝ ባለቤቴም ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለው'' የሚለው ንግግራቸው በከፍተኛ ጭበጨባ ነበር ፓርላማው የተቀበለው። 'ሴቶች ከወንዶች አንጻር ከሙስና የጸዱ ናቸው' ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው ወር ውሳኔያቸውን ሲያስረዱ ''ሴቶች ከወንዶች አንጻር ከሙስና የራቁ ናቸው። የምንፈለገውን ሰላም ለማምጣትም ይረዱናል'' ብለው ነበር። ከ60 በላይ የመንግሥት ሃላፊዎች፣ የመንግሥታዊው ተቋም ሜቴክ ዋና ሃላፊና የቀድሞ የደህንነት ቢሮው ምክትል ከሙስናና ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ሲውሉ ብዙ ሰዎች ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አመክንዮም እውነት ነበር እንዲሉ አድርጓቸዋል። አበባ ገብረስላሴ በ1997 ምርጫ ወቅት በግሏ የፓርላማ አባል ለመሆን ተወዳድራ አልተሳካላትም ነበር፤ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ እርምጃዎች ደግሞ ወደፊት ብዙ ለውጥ ይዞ እንደሚመጣ ታስባለች። • ወ/ሪት ብርቱካን በወዳጆቻቸው አንደበት በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት አቶ መኮንን ፍሰሃ እንደሚሉት ከሆነ ግን እነዚህ ወደ ከፍተኛ ስልጣን የመጡት ሴቶች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሳሳቱ እንኳን አይሆንም ብሎ የመከራከር አቅም ላይኖራቸው ይችላል። የህግ ባለሙያዋ ህሊና ግን በዚህ ሃሳብ አትስማማም። ''እነዚህ ሴቶች ወደ ስልጣን የመጡት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሁንታን ስላገኙ ብቻ ወይም በሥርዓቱ ችሮታ ሳይሆን፤ ለቦታው የሚመጥን ከፍተኛ ብቃት ስላላቸውና ጠንካራ ሰራተኞች ስለሆኑ ነው'' ትላለች። ድፍረት ሆሊዉድ ውስጥ ታይቷል ጥቂት ስለ ድፍረት ፊልም? የአሁኗ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት መዓዛ አሸናፊ የኢትዮጵያ ህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበርን በመመስረትና ሴቶች ላይ የሚስተዋሉ አግላይ ህጎችን በመቃወም ትታወቃለች። ለመዓዛ አሸናፊ እንደ ትልቅ ስኬት የሚቆጠርላት አንዲት የ14 ዓመት ታዳጊን ወክላ ፍርድ ቤት የተከራከረችበት አጋጣሚ ነው። ልጅቷ ፍርድ ቤት የቀረበችው ጠልፎ ወደ ቤቱ በመውሰድ አስገድዶ የደፈራትን ባሏን በመግደል ወንጀል ተከሳ ነበር። በፍርድ ቤት ክርክር መዓዛ አሸነፈች። ከዚህ አጋጣሚ በኋላም ኢትዮጵያ የጠለፋ ጋብቻን ከለከለች። ይህ ክስተት ብዙ ዓለማቀፍ እውቅና ያላቸው ሰዎች አይን መሳብ ቻለ። ታዋቂዋ የሆሊዉድ ተዋናይት አንጀሊና ጆሊ በዚህ ታሪክ ላይ ተመስርቶ ተሰራውን ''ድፍረት'' የተባለውን ፊልም ፕሮዲዩስ አደረገችው። ወ/ሮ መዓዛ ''ሁልጊዜም የማስበው ስለ አገልግሎት እንጂ ስለ ሹመት አይደለም''ሲሉ ሹመቱን እንዳልጠበቁት ቢገልጹም፤ ሹመቱ ''ትልቅ ክብር ነው" ብለዋል።
54690655
https://www.bbc.com/amharic/54690655
የአማራ ክልላዊ መንግሥት በክልሉ የተጠራው ሠልፍ ዕውቅና የለውም አለ
የአማራ ክልላዊ መንግሥት የፊታችን ረቡዕ በክልሉ ከተሞች የተጠራው ሠላማዊ ሠልፍ ዕውቅና የለውም ሲል አስታወቀ።
የአማራ የክልል መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ይህን ያስታወቁት የአማራ የክልል መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ናቸው። አቶ ግዛቸው በማህበራዊ ሚዲያ የተጠራው ሠልፍ ክልሉ እንዲረጋጋ ለማይፈልጉ ኃይሎች ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር የሚመች ነው ብለዋል። የአማራ ክልልንም ሆነ ህዝቡን መሠረት በማድረግ በክልሉም ሆነ ከክልሉ ውጭ ግጭት በመፍጠር አገር ለማተራመስ የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው ሃይሎች አሉ ሲሉ ተናግረዋል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) "በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈጸመውን ዘር ማጥፋት የሚያወግዝ " የተቃውሞ ሰልፍ ጠርቷል። አብን ጥቅምት 18 በአማራ ክልል ከተሞች ጥቅምት 22 ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ ሰልፍ ለማካሄድ ነው በፌስቡክ ገጹ ላይ ጥሪ ያስተላለፈው። እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ ከሆነ እነዚህ ጸረ ለውጥ ሃይሎች የብሔር፣ የሃይማኖት እና የኢኮኖሚ አጀንዳ በመፍጠር አማራ በደል እንዲደርስበት እና ዝቅ እንዲል መሥራት ከጀመሩ ሰነባብወተዋል። ይህ ዓላማቸው በክልሉ ውስጥ አልሳካ ሲላቸው በቅርቡ በቤኒሻንጉል አሁን ደግሞ በጉራ ፈርዳ ወረዳ ሠላማዊ ዜጎችን በግፍ እየገደሉ ነው ብለዋል። ክልሉ ግድያውን በተመለከተ ከሚመለከታቸው ክልሎች ጋር በመሆን አጥፊዎች በህግ እንዲቀጡ እና ህግ እንዲከበር እየሠሩ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በርካታዎችም ለህግ የቀረቡ መሆኑን ጠቅሰዋል። የተጠራው ልፍ ዕውቅና የለውም ያሉት አቶ ግዛቸው "ችግሩን ሰልፍ በማድረግ ብቻ አይፈታም። ሰልፍ መፍትሔ ቢሆን የክልሉ መንግሥትም ገዢውን ፓርቲ በማስተባበር ሰልፍ በጠራ ነበር" ብለዋል። ጸጉረ ልውጦች ሰልፉን በመጠቀም ግርግር ለመፍጠር እረየሰሩ መሆኑ ስለሚታወቅ መንግሥት ዕቀውቅና አይሰጠውም ብለዋል። "በግምት አይደለም የምንነጋገረው። በተጨባጭ እዚህ ከልል ላይ ሰልፍ ቢካሄድ አሁን ባለው ሁኔታ ግጭቶች ይከሰታሉ። የተዘጋጁ የሚፈነዱ ቦምቦች አሉ" ሲሉ ተናግረዋል። የክልሉ ህዝብ በተጠራው ሰልፍ ላይ እንዳይሳተፍ፤ አስተባባሪዎችም ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ጥሪ አቅርበዋል። ሰልፍ በሚወጡም ላይ ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል። አቶ ግዛቸው መግለጫ እስከተሰጠበት ሰዓት ድረስ ሰልፍ ለማድረግ ጥያቄ አለመቅረቡንም ጨምረው ተናግረዋል።
news-52195662
https://www.bbc.com/amharic/news-52195662
ኮሮና ቫይረስ፦ የወባ መድሃኒቶች ለምን ገነኑ?
የኮሮና ቫይረስ ወርርሽኝ በአለም በሰፊው መዛመት የሰው ልጅን ባሸበረበት በአሁኑ ወቅት መድኃኒቱን ለማግኘት የተለያዩ አገራት ሳይንሳዊ ምርምሮችንና ሙከራዎችን አቀላጥፈው በመስራት ላይ ናቸው።
ከዚሁም ጋር ተያይዞ የኮሮናቫይረስን ለማዳን ፀረ - ወባ መድኃኒቶች ጥቅም አላቸው በሚልም ክሎሮኪንና ሃይድሮክሲክሎሮኪን ተፈላጊነትም በከፍተኛ መጠን እየጨመረ ነው። • በኮሮናቫይረስ የወረርሽኝ 'ዘመን' ተስፋ የሚሰጡ 5 ነገሮች • በአማራ ክልል ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የትምህርት ተቋማት ለመጠለያነት ተዘጋጁ ምንም እንኳን የአለም አቀፉ ጤና ድርጅት ለፈዋሽነታቸው ምንም አይነት ማስረጃ የለም ቢልም አንዳንድ አገራት በፀና ለታመሙ የኮሮና ህሙማንን ለማከም እንጠቀምበታለን በማለት ላይ ናቸው። ስለ መድሃኒቶቹ ምን ያህል እናውቃለን? የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተደጋጋሚ በሚያደርጓቸው ጋዜጣዊ መግለጫዎች "እነዚህን መድሃኒቶች ብትሞክሯቸው ምንድን ነው የምታጡት?" ሲሉ ተደምጠዋል። የብራዚሉ ፕሬዚዳንት ጄይር ቦልሶናሮም "መድሃኒቶቹ እየሰሩ ነው፤ ያድናሉም" ማለታቸውን ተከትሎ ሃሰተኛ መረጃን በማስተላለፍ በሚል ፌስቡክ መልእክታቸውን ከገፁ ላይ አጥፍቷል። ክሎሮኪን የወባ ህመምን ለማከም በተለይም ትኩሳትን ለመቀነስ ለአመታት ያገለገለ ሲሆን የኮሮና ቫይረስም በሰውነት ውስጥ ገብቶ ጉዳት እንዳያስከትል ማገድ ይችላልም የሚል ከፍተኛ ተስፋ ተጥሏል። "በላብራቶሪ ውስጥ በምናይበት ወቅት ክሎሮኪንኮሮና ቫይረስን ማገድ ይችላል። እናም ከአንዳንድ የጤና ባለሙያዎችም እንደተገኘው መረጃ መድኃኒቱ የኮሮናቫይረስን ህሙማን ማከም እንደሚያስችል ነው" በማለት የቢቢሲ ጤና ዘጋቢ ጄምስ ጋላግሄር ተናግሯል። ምንም እንኳን አንዳንድ የጤና ባለሙያዎች ይህንን ይበሉ እንጂ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ለማከም በተደረገ ሙከራ ሙሉ በሙሉ አመርቂ ውጤት ማምጣት ያልተቻለ ሲሆን አንድ የፈረንሳይ ጥናት ደግሞ ምንም ውጤት እንደሌለው አመላክቷል። ከዚህም በተጨማሪ መድሃኒቱ ለተጓዳኝ ችግሮች ማለትም ለጉበትና ለኩላሊት ጉዳት ይዳርጋል ተብሏል። "የመድሃኒቱን ውጤታማነት ለመረዳት በከፍተኛ መጠንና ጥራት ሙከራዎች ልናደርግ ይገባል" በማለት የኦክስፎርዱ ተመራማሪ ኮሜ ጊቢንጄ ይናገራሉ። እስካሁን ባለው በአሜሪካ፣ በእንግሊዝ፣ ስፔንና ቻይና ሃያ የሚሆኑ ሙከራዎች ተሞክረዋል። እንግሊዝ በቫይረሱ ለተጠቁ ህሙማን የወባ መድሃኒት እፎይታ ሊሆን ከቻለ በሚል ምርመራዋን አጠናክራ የቀጠለች ሲሆን አሜሪካ በበኩሏ ክሎሮኪን፣ ሃይድሮክሲክሎሮኪንና የህመም ማስታገሻ የሆነውን ዛይትሮማክከስ በማጣመር ምርምሮችን እያካሄደች ነው። •በዓለም ላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሆነ •ሕይወት እንቅስቃሴ በተገደበባቸው የአማራ ክልል ከተሞች የትኞቹ አገራት ፈቃድ ሰጡ? የአሜሪካው የምግብና የመድሃኒት ቁጥጥር አስተዳደር መድሃኒቶቹ የኮሮናቫይረስ ህመሙማን ለማከም እንዲውሉ ለተወሰኑ ሆስፒታሎች ፈቃድ ሰጥቷል። ምንም እንኳን አስተዳደሩ ሙሉ በሙሉ መድኃኒቱ ይፈውሳል ብሎ ባያረጋግጥም ሆስፒታሎች የኮቪድ 19 ህሙማንን ለማከም በሚጠይቁበት ጊዜ ካላው የክምችት ክፍል በመስጠት ላይ ነው። የአሜሪካ መንግሥት ሰላሳ ሚሊዮን የሃይድሮክሲክሎሮኪን እንክብሎችን ከጀርመን የመድኃኒት ማምረቻ በእርዳታ እንዳገኘ ገልጿል። ሌሎች ሃገራት በየደረጃው መድሃኒቱን በመጠቀም ላይ ናቸው። ፈረንሳይ የኮሮና ህሙማንን እንዲያክሙ ፈቃድ ብትሰጥም የመድኃኒት ተቆጣጣሪዎች የጎንዮሽ ጉዳቱ ላይ ማስጠንቀቂያ እየሰጡ ነው። የህንድ ጤና ሚኒስቴር በበኩሉ ሃይድሮክሲክሮኪን ለጤና ባለሙያዎች መከላከያ እንዲሆናቸው እንዲሁም በህመሙ ከተጠቁ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎች እንዲወስዱት ፈቅዷል። የተለያዩ የመካከለኛው ምስራቅ አገራትም ሙከራዎችን እያደረጉ ናቸው። ሃይድሮክሲክሎሮኪንን በመጀመሪያ ደረጃ መጠቀም ጀምሬያለሁ የምትለውን ባህሬንን ጨምሮ፣ ሞሮኮ፣ አልጀሪያና ቱኒዝያም መድሃኒቱ በተግባር ላይ እንዲውል ፈቅደዋል። በቂ ክሎሮኪን አለ? መድኃኒቱ በከፍተኛ ሁኔታ እየተፈለገ በመምጣቱም አገራት እጥረት እያጋጠማቸው ነው ተብሏል። ክሎሮኪንም ሆነ ሌሎች የወባ መድሃኒቶች በታዳጊ አገራት ውስጥ በብዛት ይገኙ ነበር። አሁን ካለው ፍላጎትም ጋር ተያይዞ እጥረት በማጋጠሙ አገራት የተለያዩ እርምጃዎችን ለመውሰድ ተገደዋል። ዮርዳኖስ መድሃኒቱ እንዳይሸጥ የከለከለች ሲሆን ኩዌት በበኩሏ መድሃኒቶቹ በመንግሥት ሆስፒታሎችና የጤና ማእከላት ብቻ እንዲገኙ ውሳኔ አስተላልፋለች። ኬንያ በበኩሏ ያለ ፈቃድ መድሃኒቶቹ እንዳይሸጡ ስትከለክል ህንድ ደግሞ ወደ ውጭ የመላክ እገዳን ጥላለች። ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ መድሃኒቶቹ እንዲላኩላቸው የጠየቁዋቸው ሲሆን ህንድም ልትልክ ተችላለች ተብሏል። መድሃኒቱ የወባ በሽታ አዳኝነቱ በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነሱ አገልግሎት ላይ እንዳይውል ከአመታት በፊት በናይጄሪያ የታገደ ቢሆንም አሁንም ወባን ብዙዎች ይጠቀሙበታል ተብሏል። በተለይም ቻይና ክሎሮኪን ለኮሮና ቫይረስ ህሙማን እየሰጠች ነው የሚለውን ዜና ተከትሎ ብዙዎች ማከማቸት ጀምረዋል። ነገር ግን የናይጀሪያ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማእከል የአለም ጤና ድርጅት ፈቃድ እስካልሰጠ ድረስ መድሃኒቱን መጠቀም አይቻልም እያሉ ነው። ባለስልጣናቱ እንዳሳወቁት ክሎሮኪንን በከፍተኛ መጠን ወስደው የተመረዙ ሰዎች መኖራቸውን ነው።
news-56318554
https://www.bbc.com/amharic/news-56318554
ያለፈው ዓመት የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና መሰጠት ተጀመረ
የ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ከዛሬ ሰኞ የካቲት 29/2013 ዓ.ም ጀምሮ በመላ ኢትዮጵያ መሰጠት ተጀመረ።
በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ወደዚህ ዓመት የተሸጋገረው የ2012 ዓ.ም ፈተና ከካቲት 29 ጀምሮ እስከ መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በመላው አገሪቱ ይሰጣል። ከሌሎች ክልሎች በተለየ በትግራይ ክልል የሚገኙ ተፈታኝ ተማሪዎች በክልሉ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እንደሚወስዱ ትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁ አይዘነጋም። ተፈታኞቹ ፈተናቸውን የሚወስዱባቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም መቀሌ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና ራያ የኒቨርስቲዎች መሆናቸው የትምህርት ሚኒስቴር ቀደም ብሎ አስታውቋል። ትምህርት ሚኒስቴር በኦንላይን ሊሰጥ የነበረውን የ2012 ዓ.ም አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በወረቀት እንደሚሆን ቀደም ብሎ መግለጹ አይዘነጋም። የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር) 450 ሺህ ታብሌቶች እስከ ታኅሳስ መጨረሻ ድረስ ከውጭ እንደሚገቡ እና 12 ሺህ ላፕቶፖች ደግሞ ለፈታኞች ለማከፋፈል ዝግጁ መሆናችውን ተናግረው ነበር። በኋላ ላይ ግን በኦንላይን ለመስጠት የታሰበው የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና በኮቪድ-19 ምክንያት መፈተኛ ታብሌቶች በጊዜ ወደ አገር ውስጥ መግባት ባለመቻላቸው ፈተናውን በወረቀት ለመስጠት መወሰኑ ተገልጿል። የትምህርት ሚኒስቴር በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን እስከ ጥር መጨረሻ ድረስ ለመስጠት እቅድ ይዞ ነበር። ዛሬ በተጀመረው አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ከ250 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለከፍተኛ የትምህርት ተቋም ሊያበቋቸው የሚችሉ በተለያዩ የትምህርት አይነቶች የሚሰጡ ፈተናዎችን ይወስዳሉ።
51117205
https://www.bbc.com/amharic/51117205
የቀድሞ የኦነግ ጦር መሪ ጃል መሮ ከሕወሃት ጋር እየሠራ ነው?
በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙ አራት ዞኖች የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦ እንደሚገኝ ይታወቃል።
በአራቱም የወለጋ ዞኖች ማለትም፤ ቄለም ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ ምዕራብ ወለጋና ምስራቅ ወለጋ የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ የተቋረጠ ሲሆን፤ የስልክ አገልግሎት የሌለባቸው ደግሞ ምዕራብ ወለጋና የቄለም ወለጋ ዞኖች ናቸው። የቴሌኮም አገልግሎቶች መቋረጥን አስመልክቶ ከኢትዮ ቴሌኮምም ይሁን ከመንግሥት የተሰጠ በቂ ምላሽ ማግኘት አልተቻለም። ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የቴሌኮም አገልግሎቶቹ እንዲቋረጡ የተደረጉት መንግሥት በምዕራብ ኦሮሚያ በሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ቡድን ላይ ኦፕሬሽን እያካሄደ ነው የሚሉ መላ ምቶች በስፋት ሲነገሩ ቆይቷል። ቢቢሲ ይህን ከአካባቢው ነዋሪዎች ለማረጋገጥ ያደረገው ጥረት የቴሌኮም አገልግሎት ባለመኖሩ አልተሳካም። በምዕራብ ኦሮሚያ የሚንቀሳቀሰው የቀድሞ የኦነግ ጦር አዛዥ ኩምሳ ዲሪባ በትግል ስሙ በስፋት የሚታወቀው ጃል መሮ በምዕራብ ኦሮሚያ እየተከናወነ ስላለው ጉዳይ ጠይቀናል። ጃል መሮ ለጥቂት ደቂቃዎች ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርጓል። መሮ የሚገኘው የት ነው? የጃል መሮ እንቀስቃሴን የሚነቅፉ ፖለቲከኞች በአሁኑ ሰዓት መሮ ከወለጋ ውጪ ከሌሎች አካላት ጋር በትብብር እየሰራ ስለመሆኑ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ይሰማሉ። የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት በሌለበት ወለጋ በስልክ አግኝተን ነው ያናገርነው። የት ነው የምትገኘው? ወለጋ ውስጥ ከሆንክስ ስልክ እንዴት ሊሰራ ቻለ? የሚለው የመጀመሪያው ጥያቄ ነበር። የስልክና የሞባይል ዳታ ግንኙነት መቋረጡን የሚናገረው ጃል መሮ፤ "እንዳሰቡት በኦሮሞ ነጻነት ጦር ሊገኝ የታሰበው የበላይነት መሳካት ስላልቻለ በተለየ መንገድ ሊሄዱበት የወሰኑት ውሳኔ ነው እየተካሄደ ያለው" ይላል። "መንግሥት ሲፈልግ አግልግሎቱን ለአንድ ዓመት ይዝጋው። ጦራችን በየዕለቱ በተሟላ መልኩ ግንኙነት ማድረጉን እንደቀጠለ ነው። ኪሳራው ለመንግሥት እንጂ በእኛ ግነኙነት ላይ ምንም ተጽዕኖ አያሳድርም" በማለት የተሟላ አገልግሎት እንዳለው ጠቁሟል። ጃል መሮ ከሌሎች አካላት ጋር አብሮ እየሰራ ነው ለሚለው ጉዳይ ምላሽ ሲሰጥ፤ "ስትፈልጉ መሮ ሞቷል ስትፈልጉ. . . ስትፈልጉ መሮ መቀሌ ነው ያለው... ከዚህ ቀደም ኮሎኔል ገመቹ አያና እና ዳውድ ኢብሳ ሲናገሩት እንደነበረው፤ የኦሮሞን ሕዝብ ትግል ከሚደግፉ ማናቸውም አካላት ጋር አብረን ልንሰራ እንችላለን። ይህ መብታችን ነው። ለምን ሰይጣን አይሆንም። ኦሮሞን ነጻ የሚያወጣ ከሆነ አብረነው [ሰይጣን] ልንሰራ እንችላለን። ይሁን እንጂ እንደሚባለው ከህወሃት ጋር አብረን ልንሰራ አንችልም። ብዙ ጠባሳ አለብን ከህወሃት ጋር ፈጽሞ ልንሰራ አንችልም" ብሏል። "እኔ የምገኘው ኦሮሚያ ጫካ ውስጥ በወለጋ የቡና ዛፍ ሥር ነው" በማለት መሮ ምላሹን ሰጥቷል። የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እገታ 17 የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በጸጥታ ስጋት ወደ ትውልድ ቀያቸው ሲያመሩ ደምቢ ዶሎ እና ጋምቤላ መካከል ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት መታገታቸው ይታወሳል። ቢቢሲ ያነጋገራት ከአጋቾቹ ያመለጠች ተማሪ እገታው እንዴት እንደተፈጸም፣ ከአጋቾቹ እንዴት እንዳመለጠች እና የአጋቾቹ ጥያቄ ምን እንደነበረ ተናግራለች። ምንም እንኳ የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው፤ ታግተው ከነበሩት ተማሪዎች መካከል አብዛኞቹ እንዲለቀቁ መደረጋቸውን ተናግረዋል። ኃለፊው ይህን ይበሉ እንጂ፤ የተማሪዎቹ ወላጆች ''ማን ይለቀቅ ፤ ማን አይለቀቅ እስካሁን አላወቅንም'' እያሉ ይገኛሉ። ተማሪዎቹን ያገታቸው የትኛው አካል እንደሆነ በይፋ ባይነገርም፤ በምዕራብ ኦሮሚያ ታጥቆ የሚንቀሳቀሰው እና በድሪባ ኩምሳ የሚመራው ኃይል ስለመሆኑ ብዙዎች ግምታቸው አስቀምጠዋል። ጃል መሮ ግን "ይህን ለመጀመሪያ ጊዜ እየሰማሁ ያለሁት ከእናንተ ነው። የትግል ዓላማችን ከተማሪዎች ጋር አይገናኝም። በተማሪዎቹ ላይም ይህን የተባለውን አይነት ተግባር አልፈጸምንም። እንደተለመደው የእኛን ስም ለማጉደፍ የተወራ ነው እንጂ በፍጽም እንዲህ አይነት ተግባር አሁንም ወደፊትም እንፈጽምም።'' መሮ ተማሪዎቹ ታግተውበታል በሚባለው ሥፍራ በኮንትሮባንድ ንግድ ሥራ ላይ ታጥቀው የተሰማሩ አካላት መኖራቸውን ተናግሮ፤ የእሱ ጦር ግን በአካባቢው እንደሌለ ይናገራል። በመንግሥት ኃላፊዎች ላይ ያነጣጠሩ ግድያዎች በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙ የመንግሥት ኃላፊዎች ላይ ያነጣጠሩ ግድያዎች ዜናን መስማት የተለመደ ሆኗል። የጥቃት ዒላማዎቹ የሚያነጣጥሩት በአካባቢው ባለሥልጣናት ላይ ብቻ ሳይሆን፤ ለሥራ ወደ ወለጋ ዞኖች የሚንቀሳቀሱ ኃላፊዎችንም ይጨምራል። ለእነዚህም ባለሥልጣናት ግድያ ተጠያቂ የሚደረገው በጃል መሮ የሚመራው የታጣቂ ቡድን ነው። ጃል መሮ ግን መንግሥት የእርሱን ጦር ለማዳከም እየተጠቀመበት ያለው ስትራቴጂ መሆኑን እንጂ የእርሱ ጦር ይህን መሰል ተግባር እንደማይፈጽም ይናገራል። "በምስራቅ በኩል ኦሮሞን እና ሱማሌን እንዳጫረሱት ሁሉ አሁንም በዚህ በኩል የኦሮሞ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ለማጋጨት ነው" ይላል። የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከዚህ ቀደም ታጥቆ የሚንቀሳቀስ ጦር እንደሌላቸው መናገራቸው ይታወሳል።
46534692
https://www.bbc.com/amharic/46534692
ሞዛምቢክ ሰላሳ ሺ የማይታወቁ ሰራተኞች አሏት
የሞዛምቢክ መንግሥት፣ የመንግሥት ሰራተኞችን ክፍያ ኦዲት በተደረገበት ወቅት 30ሺ የማይታወቁ ሰራተኞች አግኝቻለሁ ብሏል።
አንዳንዶቹ ላልሰሩበት ስራ ደመወዝ የሚከፈላቸው፣ የሞቱና ሐሰተኛ ስሞች ተገኝተውበታል። የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስተሯ ካርሜሊታ ናማሹሉ እንደገለፁት ከሆነም ለነዚህ ሰራተኞች የተጭበረበረ ክፍያ ለመክፈል 250 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስወጣቸው ነው። በሀገሪቷ ላይ ያለውን የመንግሥት ባለስልጣናት የስራ አፈፃፀም ለመገምገም በተከናወነው ኦዲት ላይ ነው ይህ ክፍተት የተገኘው። •መጠየቅ ካለብን የምንጠየቀው በጋራ ነው፡ አባይ ፀሐዬ •የኦሮሚያ ተቃውሞዎች ምን ይጠቁማሉ? ይህ የማጭበርበር ሂደት ሙስናን በሚገመግመው ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ኢንዴክስ ዝርዝር ውስጥ ሀገሪቷን 153ኛ ደረጃ ያስቀምጣታል። ሚኒስትሯ ጨምረው እንደተናገሩት 348ሺ ሰራተኞች ግምገማው ውስጥ ተካተዋል። የሞዛምቢክ መንግሥት የተለያዩ ተቋማት የሚያወጡትን ገንዘብ ለመቆጣጠር እቅድ እንደነደፈም አስታውቋል።
news-56277300
https://www.bbc.com/amharic/news-56277300
ትግራይ፡ "እኛ መንግሥት ነን፤ ምን እያደረክ እንደሆነ እናውቃለን"
የቢቢሲው ዘጋቢ ግርማይ ገብሩ በቅርቡ በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀለ ውስጥ በቁጥጥር ስር ከዋሉት የመገናኛ ብዙኃን ሠራተኞች መካከል ሲሆን ስለተፈጠረው ነገር በአንደበቱ እንዲህ ሲል ያስረዳል።
ግርማይ ገብሩ ላለፉት አራት ዓመታት ለቢቢሲ ሲሰራ ቆይቷል በቁጥጥር ስር የዋልኩት በልደቴ ዕለት አመሻሽ ላይ ነበር። በወቅቱ ከጓደኞቼ ጋር እንደተለመደው ሰኞ ዕለት እየተጨዋወትን ነበር።መሳሪያ የታጠቁት ወታደሮች ቡና የምጠጣበትን ቤት በድንገት ሲከቡ ምናልባት ሌላ ሰው ፈልገው ነበር የመሰለኝ። አንድ ወታደር መጣና ተረጋጉ ሲለን ወደጨዋታችን ተመለስን። ነገር ግን ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የሲቪል ልብስ የለበሱ የደኅንነት አባላት ቀረቡን። "ማን ናችሁ?'' ሲል አንደኛው ጮኽ። "ስማችሁን ንገሩን!" "እኔ ግርማይ ገብሩ እባላለሁ'' አልኩኝ። ያልጠበኩት ነገር ሆነ። "በትክክል፤ ስንፈልግ የነበረው አንተን ነው" ከዚያም ከጓደኞቼ ጋር ወደውጪ እንድንወጣ ተደረግን። በርካቶች በአግራሞት ሲመለከቱን የነበረ ሲሆን የቀበሌ መታወቂያዬንና የቢቢሲ መታወቂያዬን ሰጠኋቸው። ወዲያው አንደኛው የደኅንነት አባል ፊቴ አካባቢ በጥፊ መታኝ። አንድ ወታደር በመሀል ጣልቃ ገባና እንዲተወኝ ነገረው። ከዚያም ወደ መኪና ጫኑኝ። ሁሉም ነገር በፍጥነት እየተከናወነ ስለነበር ለምን እንደወሰዱን እንኳን ለመጠየቅ ጊዜ አላገኘንም። በከተማው በሚገኘው ወታደራዊ ካምፕ ከደረስን በኋላ እንኳን ማንም ስለምንም የነገረን አልነበረም። የትግራይ ግጭት ነገር ግን ከደኅንነት አባላቱ አንደኛው ቀረብ ብሎ "ግርማይ እኛ መንግሥት ነን፤ እናም በየቀኑ የምታደርገውን በሙሉ እናውቃለን። ምን እንደምታወራ፣ ምን አይነት መልዕክቶች እንደምትልክ እናውቃለን። ቁርስ፣ ምሳና እራትህን ምን እንደምትበላም እናውቃለን'' አለኝ። "ምን ሳደርግ እንደነበር እስቲ ንገረኝ'' አልኩት። "ምን አይነት መልዕክቶችን ስልክ እንደነበር ንገረኝ።'' ጥቅምት ላይ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ለቢቢሲ ምንም አይነት ዘገባ ሰርቼ አላውቅም። በወቅቱ ለደኅንነቴ ተብሎ ዘገባዎችን እንዳልሰራ ተነግሮኝ ነበር። "ምን ስትል እንደነበርና ምን ስታስብ እንደነበር የምትነግረን አንተ ነህ። በኋላ ላይ ትነግረኛለህ" አለኝ። አንድ የስልክ ጥሪ ብቻ ይሄ ምርመራ ሳይሆን ማስጠንቀቂያ ነው። መጀመሪያ ላይ የሁላችን ስልክ ተወስዶብን የነበረ ሲሆን አንድ ወታደራዊ ኃላፊ ግን ስልካችንን መለሰልንና አንድ ጊዜ እንድንደውል ነገረን። ልክ ለባለቤቴ ደውዬ ስለሆነው ነገር ስነግራት በጣም ደንግጣ ነበር። ነገር ግን ደህና እንደሆንኩ እና ምንም እንዳታስብ ነገርኳት። በወታደራዊ ካምፑ ውስጥ ካሉት ሌሎች ሰዎች ከሞላ ጎደል በተሻለ መልኩ ነበር የተስተናገድነው። ነገር ግን ስድስታችንም የምንተኛው በአንድ ክፍል ውስጥ መሬት ላይ ነበር። ለመጸዳጃ ደግሞ የፕላስቲክ ኮዳ ነበር የሚሰጠን። ሁላችንም በቀጣይ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ስረላላወቅን በጣም ደንግጠንና ግራ ተጋብተን ነበር። እኔ መተኛት አልቻልኩም። ጠዋት ላይ የደኅንነት አባላቱ መጥተው እቤቴ በመሄድ ብርበራ ማድረገው እንደሚፈልጉና በላፕቶፔ እና በስልኬ ውስጥ መረጃ ካለ ማጣራት እንደሚፈልጉ ነገረኝ። ነገር ግን ቤቴን አልፈተሹም ነበር። የሚፈልጉት መረጃ በሙሉ ጭንቅላቴ ውስጥ ስለሚገኝ በጥያቄ ምርመራ ሊያደርጉብኝ እንደሚፈልጉም ነገሩኝ። ነገር ግን እስከዚያ ሰዓት ድረስ ለምን በቁጥጥር ስር እንደዋልን አልነገሩንም ነበር። ምንም ይሁን ምን የፈጸሙኩት ጥፋት እንደሌለ ግን እርግጠኛ ነበርኩ። "እኔ ጋዜጠኛ ነኝ። ነጻ ሰው ነኝ፤ እናም የፈለጋችሁትን ልትጠይቁኝ ትችላላችሁ'' አልኩኝ። ነገር ግን ማንም አልጠየቀኝም። እንደውም ማክሰኞ ጠዋት ላይ መቀለ መሀል ወደሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ጣቢያ ተወሰድን። ሁኔታው እዚያ የከፋ ነበር። አልጋ የሌለበት አንድ ክፍል ውስጥ አስገቡኝ። ክፍሏ 2.5 ሜትር በ3 ሜትር ትሆናለች፤ በውስጧ ግን ሌሎች 13 ሰዎች ነበሩ። በጣም ይሞቅ ነበር፤ በአቅራቢያ ከነበረው የመጸዳጃ ቤት ፍሳሽ ማጠራቀሚያ የሚመጣው ሽታ ደግሞ ነገሮችን በጣም ከባድ አደረገው። "የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ እሰጥ ነበር'' ምናልባት ሌሊት ላይ መጸዳጃ ቤት መሄድ ካስፈለገን ተብሎ አሁንም የፕላስቲክ ኮዳ ተሰጠን። ነገር ግን ቀኑን ሙሉ የበላሁት አንዲት ብርቱካን ስለነበረች ኮዳው እንደማያስፈልገኝ ገብቶኝ ነበር። ከበስተግራዬ በኩል አንድ ሰው ያስል ስለነበር ኮሮናቫይረስ እንዳይዘኝ ሰግቼም ነበር። እንደ እድል ሆኖ የት እንደምገኝ የሰሙ ጓደኞቼ ያለሁበት ድረስ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንዲሁም ሳኒታይዘር አመጡልኝና በክፍሉ ለነበሩት በሙሉ አከፋፈልኩኝ። ረቡዕ ጠዋት ላይ አንድ ፖሊስ ተጠግቶኝ እቃዎቼን እንደሰብስብና ወደቤቴ መሄድ እንደምችል ነገረኝ። ነገር ግን ለምን በቁጥጥር ስር እንደዋልኩ ምንም አይነት ማብራሪያ አልተሰጠኝም ነበር። ቢቢሲም ቢሆን ለምን በቁጥጥር ስር እንደዋልኩ መንግሥትን እንደጠየቀ አውቃለው። እኔ ወደቤት ስመለስ ባለቤቴ፣ እናቴ እና ልጆቼ አንድ ላይ ነበሩ። በደስታ ሲያለቅሱ አየኋቸው። በጣም ያሳሰበኝ ነገር ፖሊስ ጣቢያ እያለሁ እንዳልታመም ነበር። አሁን ተረጋግቻለሁ፤ ትንሽ እረፍት እንደማገኝ ተስፋ አደርጋለሁ።
news-50792432
https://www.bbc.com/amharic/news-50792432
ቤተ ክርስቲያኒቱ 'አጭር ቀሚስ ለብሳችሁ ባትመጡ ደስ ይለኛል' አለች
በኬንያ ናይሮቢ የምትገኝ አንዲት ቤተ ክርስቲያን ሴቶች አጫጭር ቀሚሶችን እየለበሳችሁ እየመጣችሁ ተቸግሪያለሁ ብላለች።
በኬንያ በስፋት የሚሰራጨው የኬንያ ዴይሊ ኔሽን እንደዘገበው ከሆነ ቤተ ክርስቲያኒቱ 'ሴት ምዕመናን እባካችሁ አለባበሳችሁን ፈሪሀ እግዚአብሔር ያደረበት ብታደርጉ' ስትል ተማጽናለች ብሏል። ቅዱስ ጴጥሮስ ክላቨር ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ናት ይህን መልእክት ያስተላለፈችው። በተለይ መልእክቱ የተለላፈበት መንገድ ለብዙዎች መነጋገሪያ ሆኗል። • "በጎጃም ማርያም ቤተክርስቲያን ለመስጊድ 3ሺ ብር ረድታለች' ተባልኩኝ" ሐጂ ዑመር ኢድሪስ • ኤርትራ፡ ''እናቶች ከህጻናት ልጆቻቸው ጋር ታስረዋል'' ቤተ ክርስቲያኒቱ ይህንን መልእክት ለምእመናኑ ያስተላለፈችው የቤተ ክርስቲያኒቱ መግቢያ በር ላይ የሰሌዳ ማስታወቂያ በመስቀል ጭምር ነው። በዚህ ማስታወቂያ ላይ ሴት ምእመናን ሊለብሷቸው አይገባም ያለቻቸውን 10 ዓይነት አለባበሶችን በፎቶ ጭምር በማስደገፍ ዘርዝራለች። ከነዚህ መሀል አጭሬ ቀሚስ (ሚኒስከርት)፣ ታፋው ላይ የተቦዳደሰ ጂንስ ሱሪ፣ "ቀይ ሰይጣን" የሚል ጽሑፍ ያለበት ቲሸርት፣ የተገላለጠ ገላን የሚያሳይ ረዥም ቀሚስና ሌሎችንም ይጨምራል። ቤተ ክርስቲያኒቱ ይህን መመሪያ በሚተላፈሉት ላይ ምን እርምጃ እንደምትወስድ ያለችው ነገር የለም።
news-46738585
https://www.bbc.com/amharic/news-46738585
13 አስደናቂ የፓስፖርት እውነታዎች
ፓስፖርት ለሰዎች እንቅስቃሴ ወሳኝ የሆነ የጉዞ ሰነድ ነው። ይህ ሰነድ ስለተጓዦች ማንነት ዝርዝር መረጃን የያዘ ሲሆን ሃገራት ባለፓስፖርቶቹ ወደ ድንበራቸው እንዲገቡ መፍቀዳቸውን የሚገልጹበትም ነው።
በዓለም ላይ ያሉ ሃገራት የየራሳቸው የሆኑ የተለያየ አይነት ፓስፖርቶችን ለዜጎቻቸው ይሰጣሉ። ከእንዚህ ፓስፖርቶች ጋር በተያያዘ አስደናቂ እውነታዎችን እነሆ. . . 1. ለየት ያለ ምስል በፓስፖርት ላይ የስካንዴኔቪያን ሃገራትን ፓስፖርቶች በመመርመሪያ ብርሃን ውስጥ ስንመለከታቸው የአካባቢው መለያ የሆነው አንጸባራቂ የሠሜናዊ ብርሃን ምስል በገጾቹ ላይ ይታያል። በስካንዴኔቪያን ፓስፖርቶች ላይ የሚታየው ምስል 2. የመጀመሪያው ፓስፖርት መጽሃፍ ቅዱስ ላይ ተጠቅሷል በመጽሃፈ ነህሚያ ላይ የፋርሱ ንጉስ አርጤቅስ በጁዲያ ግዛት በኩል ለሚያልፍ ባለስልጣን ያለችግር እንዲጓዝ የሚፈቅድ የይለፍ ደብዳቤን ሰጥቶ ነበር። ይህም መጀመሪያው ፓስፖርት እንደሆነ ይታመናል። 3. ፓስፖርቶች ፎቶግራፎችን ብቻ የያዙ ነበሩ የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት መጀመርን ተከትሎ አንድ ለጀርመን የሚሰራ ሰላይ በሃሰተኛ የአሜሪካ ፓስፖርት ወደ ብሪታኒያ ከገባ በኋላ ፓስፖርቶች ፎቶግራፍ ብቻ እንዲኖራቸው ተደረገ። • "ፓስፖርት መስጠት አልተከለከለም" የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች ተቋም 4. ክብደት ከጨመሩ ወይም ከቀነሱ ፓስፖርት ይቀይራሉ አሜሪካ ውስጥ ክብደት ከጨመሩ ወይም ከቀነሱ፣ ፊትዎ ላይ ቀዶ ጥገና ካደረጉ፣ ከተነቀሱ ወይም ንቅሳት ካስወገዱ እንዲሁም ለጌጥ የሚሆኑ ቀዳዳዎችን ካስበጁ በአዲሱ ገጽታዎ መሰረት ፓስፖርትዎን ማሳደስ ይኖርብዎታል። 5. የቤተሰብ ፎቶ ለፓስፖርት ተቀባይነት ነበረው ፎቶግራፍ ፓስፖርት ለማግኘት አስፈላጊ በሆነበት የመጀመሪያ ጊዜያት የፈለጉትን አይነት ፎቶ ማቅረብ ይችሉ ነበር። ከቤተሰብዎ ጋር የተነሱትንም ፎቶ ቢሆን ተቀባይነት ነበረው። ፓስፖርት የአገልግሎት ጊዜው ከማብቃቱ ከወራት በፊት መታደስ አለበት 6. የፓስፖርት የአገልግሎት ጊዜ የሚያበቃው መቼ ነው? ጉዞ ለማድረግ ሲያስቡ ፓስፖርትዎ አገልግሎት የሚያበቃው ቢያንስ ስድስት ወር እንዳለው ያረጋግጡ። አብዛኞቹ የአውሮፓ ሃገራትን ጨምሮ አንዳንድ ሃገራት ተጓዦች ወደ ድንበራቸው ከሚገቡበት ቀን አንስቶ ፓስፖርታቸው ለሦስት ወራት የሚያገለግል መሆን እንዳለበት ያሳስባሉ። ነገር ግን ተጓዦች አስተማማኝና በቂ ጊዜ እንዲኖራቸው ከስድስት ወር በላይ እንዲሆን ይመከራል። ቻይና፣ ኢንዶኔዢያ፣ ሩሲያ፣ ሳኡዲ አረቢያና ሌሎች ሃገራትም የተጓዦች ፓስፖርት የስድስት ወራት የአገልግሎት ጊዜ እንዲኖረው ይጠይቃሉ። ይህም የሆነው ተጓዦች በጉዞ ላይ እንዳሉ የፓስፖርታቸው የአገልግሎት ጊዜ አብቅቶ ወደ መጡበት ለመመለስ ችግር እንዳይገጥማቸው ለማድረግ ነው። • ፓስፖርት፡ የሰዎችን እንቅስቃሴ የወሰነ ሰነድ 7. በኩዊንስላንድ በኩል ወደ አውስትራሊያ ለሚገቡ ፓስፖርት አያስፈልግም ይህ የተፈቀደው ግን ከአውስትራሊያ አቅራቢያ ከምትገኘው የፓፓዋ ኒው ጊኒ ደሴት ውስጥ ያሉና ተለይተው ከተጠቀሱ ዘጠኝ መንደሮች ለመጡ ነዋሪዎች ብቻ ነው። ለዚህም ምክንያቱ ፓፓዋ ኒው ጊኒ ነጻነቷን ስታገኝ ከአውስትራሊያ ጋር በደረሰችው ልዩ ስምምነት መሰረት የአካባቢው ነዋሪዎች ያለፓስፖርት እንዲገቡ ስለተፈቀደ ነው። 8. ቫቲካን የኢሚግሬሽን ተቆጣጣሪ የላትም ቫቲካን ምንም አይነት የኢሚግሬሽን ቁጥጥር ባይኖራትም፤ ጳጳሱ የቫቲካን ቁጥር አንድ ፓስፖርት ነው ያላቸው። ሁሉም አሜሪካዊያን ፓስፖርት የላቸውም 9. በርካታ አሜሪካዊያን ፓስፖርት የላቸውም የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት እንዳለው ከአጠቃላዩ የአሜሪካ ዜጎች ከግማሽ ያነሱት ናቸው ፓስፖርት ያላቸው። 10. ቶንጋ ፓስፖርቶች ትሸጥ ነበር 170 የደቡባዊ ፓሲፊክ ደሴቶችን የምትይዘው ቶንጋ የተባለችው ሃገር ለአንድ ፓስፖርት 20 ሺህ ዶላር እያስከፈለች ትሸጥ ነበር። ሟቹ የፖሊኔዢያ ሉአላዊ ግዛት ንጉሥ ቱፋሁ ቱፑ የሃገራቸውን ገቢ ለማሳደግ ሲሉ የግዛቲቱ ዜጎች ላልሆኑ ሰዎች ጭምር የቶንጋን ፓስፖርት ይሸጡ እንደነበረ ይነገራል። • ''የዓለም ዜጋ'' 11. የሚንቀሳቀሱ የሚመስሉ ምስሎች በፓስፖርት ላይ በጉዞ ላይ እያሉ መሰላቸት ቢገጥምዎ የስሎቬኒያና የፊንላንድ ፓስፖርት ያላቸው ሰዎች ፓስፖርታቸውን በመጠቀም ዘና የማለት ዕድል አላቸው። የፓስፖርቶቹን ገጾች ወደፊት በፍጥነት እንዲገለጡ ሲያደርጉ በፓስፖርቱ ገጾች የግርጌ ጠርዝ ላይ ያሉት ምስሎች ሲንቀሳቀሱ መመልከት ይችላሉ። ይህን መጫወቻ የሚመስል ተንቀሳቃሽ ምስል አላቸው 12. በሃሰተኛ መንገድ ለመስራት አስቸጋሪው ፓስፖርት የኒካራጓ ፓስፖርት 89 የተለያዩ አይነት አስመስሎ መስራትን ለመከላከል የሚያስችሉ የደህንነት ገጽታዎች አሉት። እነዚህም በግልጽ የሚታዩና በስውር የሰፈሩ ናቸው። በዚህም ምክንያት የኒካራጓ ፓስፖርት በዓለም ላይ ካሉ ፓስፖርቶች ሁሉ ሀሰተኛ ለመስራት አስቸጋሪው እንደሆነ ተነግሯል። • ድምፅ ፈታዮቹ መረዋዎች 13. ንግሥቲቱ ፓስፖርት የላቸውም የዩናይትድ ኪንግደሟ ንግሥት ኤልሳቤጥ ሁለተኛ ለዜጎቻቸው ፓስፖርትን የሚሰጡ በመሆናቸው ፓስፖርት መያዝ አያስፈልጋቸውም ይላሉ አንዳንዶች። ነገር ግን ንግሥቲቱ ምስጢራዊ ሰነዶች አሏቸው። እነዚህ ሰነዶችም የሚገኙትና የሚዘዋወሩት በንግሥቲቱ መልዕክተኞች እጅ ነው። እነዚህ የጉዞ ሰነዶችም 15 እንደሆኑ ይነገራል።
47354033
https://www.bbc.com/amharic/47354033
መጠጥ የ130 ሰው ህይወት ቀጠፈ
በሻይ ቅጠል ልማት ላይ የሚሠሩ ሕንዳዉያን ባለፈዉ ሀሙስ ለደስታ ብለዉ የተጎነጩት አልኮል ህይወታቸዉን አሳጥቷቸዋል።
በመጠጡ ጉዳት የደረሰባቸው ሕንዳውያን ሠራተኞች እቅዳቸዉ የተለያየ መጠን ያለዉ የታሸገ አልኮል ገዝተዉ ከጓደኞቻቸዉ ጋር መደሰት ነበር። አልኮሉ የተመረዘ በመሆኑ ግን ከጠጡት ሰዎች መካከል ቢያንስ 130 የሚሆኑት እስከ ትናንት እሁድ ድረስ በተለያዩ ሆስፒታሎች እርዳታ ቢደረግላቸዉም መትረፍ አልቻሉም። ቢቢሲ ጎላግሃት ሆስፒታል ሲታከም ያገኘዉ ተጎጅ እንደሚናገረዉ፤ መጀመሪያ ምንም የተለየ ስሜት አልነበረዉም። ከደቂቃዎች በኋላ ግን የራስ ምታቱ እየጨመረ በመምጣቱ ለመተኛትም ሆነ ለመመገብ ከተቸገረ በኋላ ራሱን ስቷል። • ቻይናና ህንድ በውሃ ምክንያት ተፋጠዋል • የኬፕታውን ባለስልጣናት ሃገር በቀል ያልሁኖ ዛፎችን ሊያስወግዱ ነው በዛው ሆስፒታል የሚሰሩት ዶ/ር ራቱል ቦርዶሎይ እንተናገሩት፤ ተጎጂዎቹ ወደ ሆስፒታል ሲሄዱ ከፍተኛ ማስመለስ፣ የደረት ህመም እና የመተንፈስ ችግር ገጥሟቸዉ ነበር። አብዛኛዎቹ ተጎድተዉ ስለነበርና አልኮሉ መርዛማ ስለሆነ ማትረፍ አልተቻለም። ጉዳዩ በተከሰተበት ሰሜናዊ ሕንድ እስካሁን ከሞቱት 130 ሰዎች በተጨማሪ 200 ሰዎችም በዚሁ የተመረዘ አልኮል ሳቢያ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸዉ ይገኛል። የተመረዘውን አልኮሉን አሰራጭተዋል የተባሉ ግለሰቦችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል። ከ2011 ወዲህ ይህን ያህል ሰዉ በተመረዘ አልኮል ምክንያት ሲሞት ለመጀመሪያ ጊዜ ነዉ። በ2011 ዌስት ቤንጋል በተባለዉ የሕንድ ግዛት ውስጥ በተመሳሳይ ክስተት 170 ሰዎች መሞታቸዉ ይታወሳል።
news-55129515
https://www.bbc.com/amharic/news-55129515
ኮሮናቫይረስ ፡ ኬንያ ባለስልጣኖቿ የኮቪድ-19 ክትባትን ከቻይና እንዲፈለጉ አዘዘች
የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የአገራቸው የጤና ባለስልጣናት ለኮሮናቫይረስ መከላከያ የሚሆን ክትባት ከቻይና እንዲያፈላልጉ አዘዙ።
ኬንያ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው በቅርቡ አገልግሎት ላይ ይውላሉ ከተባሉት ክትባቶች ምዕራባዊያን ባለጸጋ አገራት 3.8 ቢሊዮን የክትባት ምርት ለመግዛት ማዘዛቸው ይፋ ከተደረገ በኋላ ነው። በዚህም መሠረት ፕሬዝዳንት ኬንያታ የጤና ጥበቃ መስሪያ ቤታቸው ቻይና እያዘጋጀች ካለው ክትባት ውስጥ ለዜጎቻቸው የሚሆን እንዲገዛ አዘዋል። "ኬንያ ውስጥ ኮሮናቫይረስ በከፋ ሁኔታ ተመልሶ እየተከሰተ ይመስላል፤ በተለያዩ ግዛቶች ውስጥ ያለው የበሽታው መስፋፋት እየጨመረ ነው" ያሉት የኬንያ ጤና ሚኒስትር ሙታሂ ካግዌ ናቸው። በተለያዩ አገራት ውስጥ እየተዘጋጀ ያለው የኮቪድ-19 ክትባትን በተለይ ለታዳጊ አገራት ለማቅረብ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ተደራሽነቱ ፈታኝ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ዢንፒንግ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ ቃል እንደገቡት፤ ቻይና እያደረገችው ያለው የክትባት ሙከራ ውጤታማ ሆኖ ከተሳካ ለአፍሪካ አገራት በርካሽ ዋጋ እንደሚያቀርቡ ተናግረው ነበር። በሽታው መጀመሪያ በአገሯ የተከሰተው ቻይና በወረርሽኙ አያያዟ በኩል ብዙ ትችት ቀርቦባት ነበር። ክትባቱን ለአፍሪካ አገራት በቅናሽ አቅርባለሁ ማለቷም የተሰነዘረባትን ወቀሳ ለማርገብ ጥሩ እርምጃ እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ። በአሁኑ ጊዜ ኬንያ ውስጥ በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲና በመድኃኒት አምራቹ አስትራዜኒካ አማካይነት የተዘጋጀው ክትባት ሙከራ እየተደረገበት ነው። ቻይና እያዘጋጀችው ያለው ክትባት ሙከራ እየተደረገባቸው ካሉ አራት አገራት መካከል ከአፍሪካ ግብጽና ሞሮኮ ይገኙበታል። የቻይና የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል እንዳለው፤ በአገሪቱ ውስጥ የተዘጋጁና አስፈላጊው ምርምር ተደርጎባቸው በሦስተኛ ደረጃ ክሊኒካዊ ሙከራ ላይ የሚገኙ አምስት የክትባት አይነቶች አሉ። ምንም እንኳን ምን ያህል ውጤታማ እንደሆኑ የሚያመለክት መረጃ ባይወጣም ኬንያ በአገሯ ውስጥም ክትባት ለመስራት ምርምር እያደረገች ትገኛለች። በአሁኑ ጊዜ በኬንያ ውስጥ ከ80 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን፤ በበሽታው ሰበብም ከ1,400 በላይ ሰዎች በአገሪቱ ውስጥ ለሞት ተዳርገዋል።
news-46683583
https://www.bbc.com/amharic/news-46683583
በአሜሪካ ድንበር ላይ ተይዞ የነበረው ጓቲማላዊው ስደተኛ ህፃን ሞተ
በአሜሪካ ድንበር ላይ ተይዞ የነበረው የስምንት አመቱ ጓቲማላዊ ስደተኛ ህይወቱ ማለፉን የአሜሪካ ኢሚግሬሽን ባለስልጣናት አስታወቁ።
የቴክሳስ የምክር ቤት አባል የልጁ ስም ፌሊፔ አሎንዞ ጎሜዝ እንደሆነም ገልፀዋል። ሰኞ ዕለት ህፃኑ ህመም ታይቶበት የነበረ ሲሆን፤ ከአባቱም ጋር ሆስፒታል ተወስደው ከፍተኛ ሙቀትና ጉንፋን ስለነበራቸው የህመም ማስታገሻ እንደተሰጣቸው ተገልጿል። በዛኑ ቀን ወደ አመሻሹ አካባቢ ህፃኑ እያስመለሰው ስለነበር ለተጨማሪ ህክምና ሆስፒታል ተመልሶ ቢሄድም ከሰዓታት በኋላ እንደሞተ ተነግሯል። • የአንዱ እርግማን ለአንዱ ምርቃን፡ ኢትዮጵያን መጠጊያ ያደረጉ የስደተኞች ታሪክ • አፍጋናዊቷ ስደተኛ በኢትዮጵያ • ፈረንሳይ ስደተኞችን የተመለከተ ጥብቅ ሕግ አወጣች የሜክሲኮና የአሜሪካን ድንበር ሊያቋርጡ ሲሉ ተይዘው ከነበሩ ህፃናት መካከል በዚህ ወር ብቻ ይህ ህፃን ሲሞት ሁለተኛው ነው። ከዚህ ቀደምም ጃክሊን ካል የተባለች የሰባት አመት ህፃን ስደተኛ መሞቷ የሚታወስ ነው። ልጅቷም ከጓቲማላ የመጣች እንደሆነች ተዘግቧል። የቴክሳስ ምክር ቤት አባል ጃኩይን ካስትሮ የህፃኑ ሞት ላይ ከፍተኛ ምርመራ ሊከፈት እንደሚገባ አስታውቀዋል። "ስደተኞችም ሆነ ጥገኝነት ጠያቂዎች በአሜሪካ መንግሥት ጥላ ስር እስካሉ ድረስ የሚያስፈልጋቸውን ህክምና ልናሟላ ይገባል። እንደ ሰውም ክብር ልንሰጣቸው ይገባል" ብለዋል። ባለስልጣኑ ጨምረውም አስተዳደሩ ስደተኞችን ከድንበር መመለሱ ቤተሰቦችንና ህፃናትን አደጋ ላይ እየጣለ ነው ብለዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ከመካከለኛው አሜሪካ በመነሳት የአሜሪካ ድንበሮችን ያቋርጣሉ። እነዚህ ስደተኞች ድህነትን፣ ግጭትንናና እንግልትን ሸሽተው ሲሆን ብዙዎቹም ከጓቲማላ፣ ሆንዱራስና ኤልሳልቫዶር ናቸው ተብሏል። ከአሜሪካ ባለስልጣናት በኩል በሕገ ወጥ መንገድ የሚገባ ማንኛውም ሰው እስር እንደሚጠብቀው ቢያስጠነቅቁም አሁንም ብዙዎች የተሻለ ህይወት ፍለጋ ድንበሮችን ያቆራርጣሉ። ጄክሊን ካል እንዴት ሞተች? ጄክሊን ከአባቷ ጋር ከብዙ ስደተኞች ጋር በመሆን ድንበሩን አቋርጠው ለአሜሪካ ባለስልጣናት እጃቸውን ሰጡ። ጄክሊን ከጥቂት ቀናት በኋላ ከፍተኛ ትኩሳት ያጋጠማት ሲሆን፤ ጉበቷ ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ሆኖ ከቀናት በኋላ ሞተች። የሞቷን ዜና በመጀመሪያ የዘገበው ዋሽንግተን ፖስት በድንበር ላይ ያሉ ባለስልጣናትን አናግሮ እንደሰራው፤ በከፍተኛ ውሃ ጥምና ድንጋጤ ምክንያት ጉበቷ ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ እንደሆነ ነው። በተጨማሪም ለቀናት ያህል ምግብና ውሃም እንዳላገኘችም ጨምሮ ዘግቧል። የጄክሊን ካል እናት በልጇ ቀብር ላይ የጄክሊን አባት አሁንም በአሜሪካ ድንበር ላይ ያለ ሲሆን የመጨረሻ ውሳኔም እየጠበቀ ነው። የህፃኗ ሬሳ ወደ ጓቲማላ የተመለሰ ሲሆን ቀብሯም በትናንትናው ዕለት ተፈፅሟል።
news-44897334
https://www.bbc.com/amharic/news-44897334
የኤርትራ ዋና ከተማ አሥመራ በቢቢሲ ዘጋቢ ዓይን
የአሥመራ ነዋሪዎች ከእንግዳ ጋር ሰላምታ ሲለዋወጡ እጅን ከመጨበጥ ይልቅ ማቀፍን ይመርጣሉ።
የሞቀ እንቅስቃሴ የማይታይባቸው የአሥመራ ጎዳናዎች እንግዳው የአስር ሺህዎች ነብስ በበላ መሪር ጦርነት ማግስት ለሃያ ዓመታት ያህል ተኮራርፈው የነበሩት ኤርትራ እና ኢትዮጵያ ሰላም ማውረዳቸውን ተከትሎ ከአዲስ አበባ የመጣ ተጓዥ መሆኑን ሲያውቁ ደግሞ እቅፉን ያጠብቃሉ፣ ፈገግታ ያዘንባሉ፣ ሰላምታው ዘለግ ይላል፣ የደስታ መግለጫ ይግተለተላል። ለዓመታት ተነጣጥለው የኖሩ ቤተሰቦች፣ ዘመዳሞችና ወዳጆች ዳግመኛ ሲገናኙ መመልከት ልብን የሚነካውን ያህል፤ የማይተዋወቁ ተቃቅፈው ሰላም ሲባባሉ ሲወረገረጉ ማየት ጥያቄን ያጭራል። የጋርዮሽ ታሪክ፣ የባህል፣ የቋንቋ እና የሥነ-ልቦና ፈርጆች ያሰናሰሏቸው እነዚህ ሕዝቦች እንደምን እንዲህ ለረዘመ ጊዜ መቀራረብ ተሳናቸው? ባልተጠበቀ ፍጥነት ያልተለመደ ቀረቤታ መመስረት የቻሉት የሁለቱ አገራት መሪዎች ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እነዚህን የልዩነት ዓመታት "የባከኑ ጊዜያት" ብለው ሲገልጿቸው ተደምጠዋል። መሪዎቹ ከሁለቱ አገራት ግንኙነት ጋር በተያያዘ የአዲስ ምዕራፍ መከፈትን ብስራት ሲያውጁ፤ በዚያውም እነዚህን የባከኑ ጊዜያት ለማካካስ ቃል ገብተዋል። አዲሱ ምዕራፍ በጊዜ ሒደት ምን ዓይነት ይዘት እና ቅርፅ እንደሚኖረው ጥርት ብሎ እንዳልገባቸው የሚገልፁ የአሥመራ ነዋሪዎች አልጠፉም። በክፍለ አህጉሩ፣ ከዚያም አልፎ በአህጉሩ በፖለቲካ እና በምጣኔ ሃብት አቅሟ እየደረጀች ያለችው ኢትዮጵያ የአንድ ወቅት አካሏን መልሳ ትውጥ ይሆን የሚል ስጋት በስሱም ቢሆን መኖሩ አልቀረም። ምናልባትም ይህንን ብዙም ያልተነገረ ስጋት ለማርከስ አስበው፤ አሊያም የሁለቱን አገሮች የዳግም ግንኙነት ዳዴ ከወዲሁ በግልፅ መስፈሪያዎች ለማስቀመጥ ፈልገው፤ የአገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል የእርስ በእርስ መከባበር እንዲሁም ግዛታዊ ሉዓላዊነት የኢትዮ-ኤርትራ አዲስ ወዳጅነት ውሃ ልክ መሆናቸውን ደጋግመው እና አስረግጠው ይናገራሉ። በአሥመራ ጎዳናዎች ላይ ወጣት ወንዶችን በብዛት መመልከት ያዳግታል የአዛውንቶች ከተማ ለበርካታ ዓመታት ኤርትራን "የአፍሪካዋ ሰሜን ኮርያ" እያሉ በአሉታ መግለፅ የተለመደ ሆኖ ቆይቷል። የማያኮራ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ፣ የተቃውሞ ድምፆች አፈና፣ የመንግሥት አድራጊ ፈጣሪነት እና ለተቀረው ዓለም ራሷን ዘግታ የመነነች አገር ተደርጋ መቆጠሯ ነው ለንፅፅሩ መነሾ የሆነው። ባለስልጣናቷ ለትችቶቹም ሆነ ለአገሪቷን የዓመታት መናኒነት እምብዛም ዕውቅና ሲሰጡት ባይስተዋልም፤ በኤርትራ ላይ ከየአቅጣጫው ተደቅነው ቆይተዋል የሚሏቸው የህልውና ስጋቶች ቅድሚያ የሚሰጧቸው ጉዳዮች ላይ ጫና ማሳረፋቸውን ይጠቅሳሉ። • የኤርትራና የኢትዮጵያ መጪው ፈተና • ''የኤርትራ ኢኮኖሚያዊ ዕቅድ የተነደፈው በኢትዮጵያ ሃብት ላይ ነበር'' አምባሳደር አውዓሎም ወልዱ እንዲያም ሆኖ ባለፉት ዓመታት የአገሪቱ መንግሥት ብሔራዊ ኩራትን በህዝቡ ዘንድ ለማስረፅ በርትቶ ሲሰራ መባጀቱን መገመት አያዳግትም። "ኤርትራዊ ነኝ፤ ኩሩ ነኝ" የሚሉ ማስታወቂያዎች በመንግሥት መስሪያ ቤቶች ተለጥፈው ይታያሉ። የአገር ፍቅር መንፈስን የማስረፁ አንዱ አስፈላጊነት አገሪቱ ከምታካሂደው የብሔራዊ ውትድርና አገልግሎት ጋር የሚገናኝበት ክር ይኖርም ይሆናል። ሆኖም ከማዕቀብ፣ ከዓለም መገለል እና ከተደጋጋሚ ግጭቶች ጋር በተገናኘ የኤርትራ ምጣኔ ሃብት ክፉኛ መደቆሱ ይሄንን ብሄራዊ ኩራት ለልምሻ ሳያጋልጠው አልቀረም። በአሥመራ ጎዳናዎች ላይ ወጣት ወንዶችን በብዛት መመልከት ያዳግታል። ሴቶች፣ ታዳጊዎች እና አዛውንቶች በርክተው ይታያሉ። ይህንን ትዝብታችንን ያጋራናቸው ሁለት የከተማዋ ነዋሪዎች ጉዳዩን ከስደት ጋር አያይዘውታል። በየዓመቱ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኤርትራዊያን ወጣቶች (ከመካከላቸውም አያሌዎቹ ወንዶች ናቸው) ድህነትን፣ ውትድርና እና አፈናን ሸሽተው ወደአውሮፓ መሰደዳቸው ይዘገባል። በአገሪቱ የስልጣን መዋቅሮች የሚገኙ ኃላፊዎችም በብዛት ኤርትራ ራሷን የቻለች አገር ከሆነችበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን በመንበራቸው ወይንም በተመሳሳይ የኃላፊነት ቦታዎች የቆዩ ሆነው ይስተዋላሉ። በከተማዋ ያለውን የንግድ እንቅስቃሴ የተሟሟቀ ነው ማለት የሚያስቸግር ሲሆን፤ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረጉ ወጣቶች በቂ የሥራ አማራጭ አለ ብለው እንደማያምኑ ነግረውናል። ኢንተርኔት እና ስልክ በአሥመራ ከተማ የገመድ አልባ ድረ-ገፅ አቅርቦት ያላቸው ሆቴሎች እና የኢንተርኔት ካፌዎች ቢኖሩም የአገልግሎታቸው ጥራት እና ፍጥነት የሚያመረቃ አይደለም። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ450 በላይ መንገደኞችን ይዞ የመጀመሪያ ጉዞውን ወደአሥመራ ባደረገበት ዕለት በርካታ ተጓዦች የኢንተርኔት ግልጋሎትን ለማግኘት ወዲያ ወዲህ ሲባትሉ ታዘበናል። • ኤርትራ የሐይማኖት እሥረኞችን ፈታች • የንግድ ሽርክና ከኤርትራ ጋር? የከተማዋ የአገልግሎት ዘርፍ ከፍ ያለ ቁጥር ያላቸው እንግዶችን በአንድ ጊዜ የማስተናገድ አቅም ያዳበረ አይመስልም። የተንቀሳቃሽ ስልክን መጠቀም የሚሻ እንግዳ ሲም ካርድ በአፋጣኝ ማግኘት የማይቻለው ሲሆን፤ በከተማዋ ልዩ ልዩ ስፍራዎች ባሉ እና በካርድ በሚሰሩ የህዝብ ስልክ ሳጥኖች መደዋወል በርካቶች የሚመርጡት የመገናኛ ስልት ነው። የሁለቱን መሪዎች ምስል ከሚሸጡ ታዳጊዎች አንዱ ፍቅረ-ዐብይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ምናልባትም በቅርብ ጊዜ አሥመራን መጎብኘታቸውን ተከትሎ በከተማዋ ከፍተኛ ተወዳጅነት ሳያተርፉ አልቀሩም። በአደባባዮች ላይ ህፃናት ምስሎቻቸውን የያዙ አልባሳትን እንዲሁም ተለጣፊ ጌጦችን ይሸጣሉ፤ ሱቆች፣ የሽያጭ መደብሮች እንዲሁም የምሽት ክበቦች የእርሳቸውን እና የፕሬዚዳንት ኢሳያስን ፎቶዎች ለጥፈው ይታያሉ። • ወደ አሥመራ ለመጓዝ ማወቅ የሚገባዎ 6 ነጥቦች ከዚህም ባሻገር ስለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚናገሩ በተለያዩ የዕድሜ ክልል የሚገኙ ነዋሪዎች፤ አድናቆታቸውን ገልፀው የሚጠግቡ አይመስልም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚመሯት ኢትዮጵያ ባለፉት ሦስት ወራት የተመዘገበውን ዓይነት ፈጣን ለውጥ በአገራቸው ማየት ይፈልጉ እንደሆነ የጠየቅናቸው ነዋሪዎች በተቆጠበ ቋንቋ የለውጥ ተስፋቸውን አጋርተውናል። በሳምንቱ አጋማሽ ኤርትራ ከሃይማኖት ጋር በተያያዘ እስር ላይ የቆዩ ከሰላሳ በላይ እስረኞችን የለቀቀች ሲሆን ይህ እርምጃ በሌሎች የለውጥ እንቅስቃሴዎች ይታጀብ እንደሆነ ገና ግልፅ አይደለም። በአሥመራ ካሉ የምሽት ቤቶች አንዱ አማርኛ በአሥመራ ኤርትራ እና ኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን በይፋ ዳግም ከመጀመራቸው፣ በአካል ተነጣጥለው የቆዩ ቤተሰቦችም ዳግም ከመገናኘታቸው በፊት በሁለቱ አገራት ህዝቦች መካከል ተዘርግቶ የቆየ ኪነ-ጥበባዊ ድልድይ የነበረ ይመስላል። በጥሩ ይዞታ ላይ በሚገኙ የአስመራ መንገዶች የሚንፈላሰሱ ታክሲዎች የኢትዮጵያ፤ በተለይም የአማርኛ ሙዚቃዎችን እንዲሁም መንፈሳዊ መዝሙሮችን ያጫውታሉ። የከተማዋ የመዝናኛ ማዕከላት ታዳሚዎቻቸውን በአማርኛ ሙዚቃዎች ያስቦርቃሉ። በአማርኛ ቋንቋ የሚሰራጩ ሥነ-ጥበባዊ የቴሌቭዥን መርሃ-ግብሮች በዛ ያሉ ታዳሚዎች አሏቸው። ለአማራኛ የቴሌቭዥን ድራማዎች ልዩ ፍቅር እንዳላቸው ያጫወቱን ወጣቶች ድራማዎቹ የአማርኛ ቋንቋን ለመልመድ እንዳገዟቸውም ጨምረው ነግረውናል። ከአሥመራ የመጀመሪያ ተጓዦች መካከል የነበሩ ዝነኛ ተዋንያን በኤርትራዊያን አድናቂዎቻቸው ደመቅ ያለ አቀባበልም ተደርጎላቸዋል።
news-49007287
https://www.bbc.com/amharic/news-49007287
የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ የሞት ማስፈራሪያ እንደደረሳቸው አስታወቁ
የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ በርሳቸው አመራር ወቅት የተፈፀመውን የሙስና ጉዳዮች ለሚያጣራው ቡድን የምስክርነት ቃል መስጠታቸውን ተከትሎ የሞት ማስፈራሪያ ለሳቸውም ሆነ ለቤተሰባቸው እንደደረሳቸው አስታውቀዋል።
ዛሬ ሐምሌ 9፣2011ዓ.ም የማጣራት ስራውን ለሚመሩት ዳኛ እንደተናገሩት ማስፈራሪያው የደረሳቸው ሐምሌ 8፣2011 ዓ.ም የሰጡትን የምስክርነት ቃል ተከትሎ ነው ብለዋል። በዚሁም ቀን በሰጡት የምስክርነት ቃል የመግደል ሙከራ እንደተሞከረባቸው አሳውቀው ነበር። • ጃኮብ ዙማ ስልጣን ለቀቁ • የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዙማን የሙስና ቅሌት የሚያጋልጥ ምርመራ ተጀመረ በባለፈው ዓመት ከስልጣን በኃይል የተወገዱት ጃኮብ ዙማ ስልጣናቸውን ያላአግባብ በመጠቀም ሙስናን ፈፅመዋል የሚሉ ውንጀላዎች ቢቀርብባቸውም እሳቸው ግን ክደዋል። ጃኮብ ዙማን ተክተው ወደ ስልጣን የመጡት ምክትላቸው ሲሪል ራማፎሳ በበኩላቸው ሙስናን ለመታገል ቁርጠኝነት እንዳላቸው ቃል በመግባት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማን ዘጠኝ አመት የስልጣን ቆይታም የባከነ ጊዜ ብለውታል። ሰኞ ዕለት የ77 አመቱ ዕድሜ ባለፀጋ ጃኮብ ዙማ የቀረቡባበቸው ውንጀላዎች እሳቸውን "ከፖለቲካው እይታ ለማጥፋት የተቀነባበረ" ነው ብለውታል። በዛሬው ዕለትም ጃኮብ ዙማ ለዳኛው እንደገለፁት ረዳታቸው እሳቸውንና ልጆቻቸውን እንደሚገድሏቸው የሚገልጽ የማስፈራሪያ የስልክ ጥሪ መቀበሏን አስረድተዋል። 'ስቴት ካፕቸር' የተሰኘው ምርመራ ጃኮብ ዙማ አወዛጋቢ ከሚባለው ቱጃር የጉብታ ቤተሰብ የነበራቸውን ያላግባብ ግንኙነት፤ እንዲሁም ስልጣናቸውን በመጠቀም ከፍተኛ የአገሪቱ ሚንስትሮች በአገሪቱ የፖለቲካ ውሳኔ ጫና ማሳደርና ከፍተኛ ጨረታዎችን በሙስና ማሸነፍን ይመለከታል። ሁሉም አካላት ውንጀላውን አይቀበሉትም። • የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዙማን የሙስና ቅሌት የሚያጋልጥ ምርመራ ተጀመረ "የሙስና ንጉስ ተደርጌ በሰዎች ዘንድ እንድጠላ ተደርጌያለሁ" በማለት ሰኞ እለት ለዳኛው ሬይ ዞንዶ ተናግረዋል። በደቡብ አፍሪካ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ለውጦችን ለማምጣት በሚጥሩበት ወቅት አሜሪካና እንግሊዝ ለአመታት አሁንም እሳቸውን ለማሳጣት እንደሚሰሩ ተናግረዋል። ሌሎች ከውጭ የመጡ የሰለጠኑ ወኪሎች ሊመርዟቸው እንደሞከሩም ጨምረው ተናግረዋል።
news-49264237
https://www.bbc.com/amharic/news-49264237
ለዓመታት ወንድ ልጅ ያልተወለደባት ከተማ
ወንድ ልጅ ከተወለደ ዓመታት የተቆጠሩባት በደቡብ ፖላንድ የምትገኝ አንዲት ትንሽ ከተማ ከንቲባ፤ ወንድ ልጅ ለሚወልዱ ጥንዶች ሽልማት እንደሚሰጡ አሳወቁ።
በከተማዋ ወንድ ልጅ ከተወለደ አስር ዓመት ሊሆን የተቃረበ ሲሆን ይህም የከተማዋን አስተዳዳሪ ሳያሳስባቸው አልቀረም። • ለዓመታት የተጠፋፉት የወላይታ ሶዶዋ እናትና የኖርዝ ኬሮላይናዋ ልጃቸው እምብዛም የዜና ርዕስ ሆና የማታውቀው ሚየሲች ኦድርዛንሰኪ የተባለችው ከተማ የወንድ ልጆች መወለድን ለማበረታታት በወሰደችው እርምጃ መነጋገሪያ ሆናለች። አንድ መቶ ያህል ቤቶች ብቻ ያሏት ይህች ከተማ ሰፋፊ የእርሻ መሬት የሚገኝባት ሲሆን፤ ህጻናትን ለማሳደግ አመቺ ቦታ ናት ተብሎ ይታሰባል። ነገር ግን ባለፉት ዓመታት የአካባቢውን ነዋሪ ያሳሰበው ነገር የተወለዱት ህጻናት ሴቶች ብቻ መሆናቸው ነው። በከተማዋ ያለው የወሊድ መጠን እጅግ በጣም አነስተኛ የሚባል ሲሆን፤ የመጨረሻው ወንድ ልጅ ከተወለደ በኋላ ባሉት ዓመታት ውስጥ 12 ህጻናት የተወለዱ ሲሆን ሁሉም ሴቶች ናቸው ተብሏል። • የሕንድ 21 ሚሊዮን 'ያለተፈለጉ' ሴት ልጆች • ወንዶች በአደባባይ ላይ ልጆች ቢያዝሉስ? የወንዶች ቁጥር መቀነስ ጉዳይ በስፋት ትኩረት ያገኘው በከተማዋ የሚገኙ ሴቶች አንድ የበጎ ፈቃድ የእሳት አደጋ ሠራተኛን አሰልጣኛቸው እንዲሆን ከጠየቁት በኋላ ነው። ሴቶች ብቻ የሆኑበት የከተማው ቡድን አካባቢያዊ ውድድሮችን ካሸነፉ በኋላ ጋዜጠኞችና ተመራማሪዎች ጥያቄ በማንሳታቸው ጉዳዩ ትኩረት ማግኘቱም ተጠቅሷል። የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ከንቲባ ራጅሙንድ ፍሪችኮ እንደተናገሩት፤ በጉጉት የሚጠበቀው ወንድ ልጅ ድንቅ ሽልማት የሚበረከትለት ሲሆን አንድ ዛፍ በስሙ ይሰየምለታል።
news-45142163
https://www.bbc.com/amharic/news-45142163
«ኦነግ ሀገር ለመገንጠል ነው የምሠራው ብሎ አያውቅም» ሽጉጥ ገለታ (ዶ/ር)
ግማሽ ምዕተ ዓመት የደፈነውን የ "ኦሮሞ ነጻነት ግንባር" ፍኖተ-ትግል የሚገልጹ ሁለት ቁልፍ ቃላት ብናስስ "ጠረጴዛ" እና "ጠመንጃ"ን እናገኛለን።
"ጠረጴዛ" ግንባሩ የአሮሞ ሕዝብን ጥቅም እና ፍላጎት ለማሳካት ያደረጋቸውን ሰላማዊ የድርድር አፍታዎች ይወክላል። "በ1991 የሽግግር ዘመን ወቅት ተሳትፈን ነበር።የሰላም እና ዲሞክራሲ በር የተከፈተ መስሎን…፣ኾኖም በ1992 ሀገር ዓቀፍ ምርጫ ወቅት ኢህአዴግ ያሳየውን [ያልተገባ ሁኔታ] ተከትሎ ወደ ትጥቅ ትግል ለመግባት ተገደናል" ሲሉ የድርጅቱ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ሽጉጥ ገለታ (ዶ/ር) ያስታውሳሉ። "ጠመንጃ"ው ደግሞ በጠረጴዛ ዙሪያ የጠየቃቸው ጥያቄዎች ባለመሟላታቸው ከበርሀ እስከ ጫካ ሲፋለም የከረመባቸውን ዓመታት ይጠቁማል። • ''በደኖ የሚባል ቦታን ረግጨው አላውቅም'' አቶ ሌንጮ ለታ • ከምዕራብ ኦሮሚያ ከተሞች ጥቃት ጀርባ ያለው ማን ነው? ከባሌ ጫካ እስከ ኢትዮ-ኬንያ ድንበር ከዚያም አልፎ እስከ ኤርትራ በርሃ የሚዘረጉ የደም መፋሰስ ዘመናትን ያስታውሳል። ኦነግ ከሰሞኑ ዳግም ወደ 'ጠረጴዛው' መጥቷል። "መንግሥት አሳማኝ ጥረት እያደረገ መስሎ ስለታየን፤ ለትጥቅ ትግል የሚገፋፉትን ነገሮች ወደኋላ ትተን ወደ ሀገር ቤት ለመግባት ወስነናል።" የሚሉት የድርጅቱ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ "በሕዝቡ መሐል ሆነን ለሰላም፣ዲሞክራሲ እና ፍትህ የምናደርገው ትግል ጠቀሜታ ያለው ስለመሰለን[ከዚህ ውሳኔ] ደርሰናል።" ይላሉ። ይህን የተናገሩት ከሰሞኑ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚደንት አቶ ለማ መገርሳ ወደ አስመራ በማቅናት እዚያ መሽገው ከከረሙት የኦነግ መሪ ዳውድ ኢብሳ ጋር ያደረጉትን ስምምነት ተከትሎ ስለተላላፈው ድርጅታዊ ውሳኔ ሲያስረዱ ነው። ኦነግ የመገንጠል ጥያቄን ትቷል? የአሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር ለዓመታት ካራመዳቸው አቋሞቹ መካከል አንዱ «የሕዝቦች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት እስከ መገንጠል» የሚለው እና በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 39(1) ላይ የተጠቀሰው ሐሳብ «እንዲተገበር» መጠየቁ ነው። ጥቂት የማይባሉ የፖለቲካው ዓለም ሰዎች አንቀጹን ኢትዮጵያን ለመበታተን የተቀመጠ ሕግ አድርገው የሚቆጥሩትን ያክል ኦነግን ደግሞ አንቀጹን ተጠቅሞ ከኢትዮጵያ የተገነጠለች 'ኦሮሚያ' የተባለች ሀገር ለመመሥረት ሊጠቀምበት እንዳቆበቆበ ቡድን አድርገው ይቆጥሩታል። ለዚህም ነው ኦነግ ወደ ሀገር ቤት ሊመለስ መሆኑ በተሰማ ማግስት ከተሰሙ ጥያቄዎች ሁሉ «ኦነግ የሚታወቅበት የመገንጠል አቋም ላይ ለውጥ አድርጎ ይሆን?» የሚለው ጎልቶ የወጣው። ዶ/ር ሽጉጥ ገለታ በዚህ ጉዳይ ላይ በሁለት የሚከፈሉ መልስ አሏቸው።መልሶቻቸው ራስን በራስ ከማስተዳደር እና ከመገንጠል ፅንሰ ሐሳብ የሚመነጩ ይመስላሉ። እሳቸው እንደሚሉት ሕዝቦች እራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ ፣የግለሰብ እና የሕዝብ መብቶች ተጣጥመው እንዲከበሩ የሚጠይቀው የድርጅታቸው አቋም ላይ "ከበፊቱ የተለወጠም ሆነ አዲስ የተጨመረ" አቋም የለም። • ፓርላማው የኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7 የሽብርተኝነት ፍረጃ መነሳትን አፀደቀ • ''ኦነግ በሚቀጥሉት ቀናት ወደ አገር ቤት ይገባል'' ኦሮሚያን ከኢትዮጵያ ግዛት ገንጥሎ በማስተዳደር ጉዳይ ለሚነሱ ጥያቄዎች የድርጅቱ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ መልሳቸውን የሚጀምሩት ጥያቄው በተሳሳተ መንገድ በድርጅቱ ላይ የተለጠፈ መሆኑን በመጥቀስ ነው። "የድርጅቱን ጥያቄ የመገንጠል፣የዘረኝነት፣የአክራሪነት ጥያቄ ነው [እየተባለ]የሚወረወሩበት [ውንጀላዎች] አሉ። ኦነግ በታሪኩ ውስጥ በኢትዮጵያ ውስጥ ከነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች እራሱን ገለልተኛ አድርጎ ለሀገር መገንጠል ነው የምሠራው ብሎ በግልፅ የተናገረበት ጊዜ የለም።" ሲሉ ያስረግጣሉ። "ከኢትዮጵያ ምሥረታ ጀምሮ የኦሮሞ ሕዝብ የተያዘው በኃይል ነው።" በማለት የሚሞግቱት ኃላፊው ቀጥለው የመጡ አገዛዞች የሕዝቦችን ፍላጎት እና ስሜት ለማክበር አለመፍቀዳቸው የችግሮች መነሻ ኾኖ መቆየቱን ያነሳሉ። ድርጅታቸው ለዚህ መፍትሄ የሚሆነውን፣ ሕዝቦች በመብታቸው ላይ ለመወሰን ያላቸውን ልዑላዊነት እንዲከበር መታገል፣ባሻቸው አስተዳደራዊ ብሂል እና ቋንቋ ካለ ከልካይ እንዲጠቀሙ መሟገትን በመሰሉ የመብት ጥያቄዎች ላይ መሥራትን ወደፊትም እንደሚገፋበት ያሰምሩበታል። የኦነግ ጦር ዕጣ ፋንታ ከ1983 ዓ. ም የሥርዓት ለውጥ በኋላ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሠራዊት ካላቸው ተፋላሚዎች መካከል አንዱ ኦነግ እንደነበር ይነገራል። ይሄ ጦር በተለያየ ጊዜያት በተቃጣበት ጥቃት እና በአስተናገዳቸው የድርጅቱ መሰንጠቅ ሰበብ ቁጥሩ በዓመታት ውስጥ ቢቀንስም አሁንም በኤርትራ በርሃዎች የሚንቀሳቀስ ታጣቂ ክንፍ አለው። ኦነግ ወደ ሰላማዊ ትግል ሊመለስ ስምም ማድረጉን ተከትሎ የዚህ ጦር ዕጣስ ምን ይሆናል የሚል ጥያቄ መነሳቱ አልቀረም። የድርጅቱ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ዶ/ር ሽጉጥ የሠራዊቱ አባላት እንዴት ወደ ሰላማዊ ሕይወታቸው እንደሚመለሱ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ስምምነት ላይ እንደደረሰና ዝርዝሩም በቅርቡ ይፋ እንደሚሆን ፍንጭ ሰጥተዋል። የኦነግ ነገ፡ ጠረጴዛ ወይስ ጠመንጃ? በአዲሱ ኢትዮጵያ መንግሥት እና ኦነግ ስምምነት መሠረት ድርጅቱ መርሃ ግብሮችን ለሕዝብ እንዲያስተዋውቅ ፣ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች እንዲያደርግ እንደተፈቀደለት ዶ/ር ሽጉጥ ይጠቅሳሉ። በዚህም መሠረት በህቡዕ ድርጅቱን ሲያገለግሉ የነበሩ ወገኖች ወደ አዲሱ ሰለማዊ ትግል በይፋ ይጠራሉ።የድርጅቱ ሊቀመንበር እና ከፍተኛ አመራሮች ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ። ድርጅቱ ከሌሎች ፖለቲካ ድርጅቶች ጋር በመሆን በወንድማማችነት ዑደቱን ይቀጥላል። እኒህ እንቅስቃሴዎች ታዲኣ ኦነግ ከጠመንጃ ወደ ጠረጴዛው እየመጣ እንደሆነ ፍንጭ የሚሰጡ ይመስላሉ፤ እስከ መቼ እንደሚዘልቅ ባይታወቅም።
news-52203904
https://www.bbc.com/amharic/news-52203904
በእንቅስቃሴ ላይ በተጣለው ገደብ ለችግር ለተጋለጡ የአማራ ክልል ድጋፍ እያደረገ ነው
የአማራ ክልል መንግሥት የኮሮናቫይረስ መስፋፋትን ለመግታት እንቅስቃሴዎችን ባገደባት ባህር ዳር ከተማ ለሚገኙ ችግረኞች የምግብ ድጋፍ እያደረገ መሆኑ ተገለጸ።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ፋንታ ማንደፍሮ ለቢቢሲ እንደተናገሩት እገዳውን ተግባራዊ ከማድረግ ጎን ለጎን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይና ለችግር ተጋላጭ የሆኑ የኅብረተሰቡ ክፍሎችን የማገዝ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል። "በዕለታዊ ገቢ የሚኖሩትን ከሰኞ ጀምሮ ቤት ለቤት በመሄድ በነፍስ ወከፍ ስሌት የዱቄት እድላ እየተደረገ ነው። በተጨማሪም በከተማው ከንቲባ በኩል አቅርቦቱ እንደቀጠለ ነው" ብለዋል። በተጨማሪም የጎዳና ተዳዳሪዎችንና በቤተ እምነት አካባቢዎች የሚገኙ ችግረኛ ሰዎች በመሰብሰብ መስተዳደሩ በመመገብ ላይ መሆኑን ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አስረድተዋል። በእንቅስቃሴ እገዳው ወቅት ቀረው ነዋሪ የአቅርቦት ችግር እንዳይገጥመው መግዛት ለሚችለው የኅብረተሰብ ክፍል ደግሞ ሰፈር ለሰፈር የሽንኩርት፣ ድንችና የአትክልት ምርቶች እንዲቀርቡ እየተደረገ መሆኑንና ሌሎችም መሰረታዊ ሸቀጦች ለማሰራጨት እየተሠራ መሆኑን ዶ/ር ፋንታ ማንደፍሮ ገልጸዋል። ይህ የአቅርቦት ሥራም አርሶ አደሮችም ሆኑ ማኅበራት በእንቅስቃሴ እገዳው ወቅት ኢኮኖሚያቸውን በመጠኑም ቢሆን እንዲደግፉ ጭምር የተጀመረ መሆኑን አመልክተዋል። በአማራ ክልል ሁለት ግለሰቦች የኮሮናቫይረስ እንዳለባቸው ከተረጋገጠ በኋላ በተለይ በአዲስ ቅዳም፣ እንጅባራ፣ ቲሊሊና በባህር ዳር ከተሞች ለ14 ቀናት ማንኛውንም ዓይነት የተሽከርካም ሆነ የሕዝብ እንቅስቃሴ እንዳይደረግ መወሰኑ ይታወሳል። ይህንንም በተመለከተ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ፋንታ ማንደፍሮ በቫይረሱ ምክንያት የተወሰደ እርምጃ መሆኑን ጠቅሰው "እስከ ትላንት ድረስ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ሪፖርት እንደደረሳቸው እና ማህበረሰቡም እየተጋገዘ" መሆኑን ጠቁመዋል። በአራቱ ከተሞች ማንኛውንም ዓይነት የተሽከርካም ሆነ የሕዝብ እንቅስቃሴ እንዳይደረግ ቢወሰንም ወደ ባህር ዳር የሚደረግ የአውሮፕላን በረራ እስካሁን እንደቀጠለ ነው። "የአውሮፕላን ጉዞን በተመለከተ የሚወስነው ፌደራል መንግሥት ነው" ያሉት ዶ/ር ፋንታ በአውሮፕላን ማረፊያው ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ግን በተለይ ለቢቢሲ ገልጸዋል። በቀን እስከ አምስት የነበረው ወደ ባህር ዳር የሚደረግ በረራ አሁን ወደ አንድ ዝቅ ማለቱን ጠቁመው በዚህም "ቁልፍ ሥራ" የሚያካሂዱ ሰዎች እንደሚንቀሳቀሱ ተናግረዋል። በከተሞቹ ማንኛውንም ዓይነት የተሽከርካም ሆነ የሕዝብ እንቅስቃሴ እንዳይደረግ የተላለፈው ውሳኔ እስከመቼ እንደሚቆይ ሲናገሩም "ይቀጥላል አይቀጥልምን አሁን መወሰን አንችልም። የተዘጋበት ዋናው ምክንያት ቫይረሱ ስለተገኘ ነው" ብለዋል። በዚህም በ14 ቀናት ውስጥ ምልክት ያሳዩ ሰዎችን ወደ ለይቶ ማቆያ ለማስገባት የታመሙም ካሉ ህክምና ለመስጠት ነው። ውሳኔው ህይወት ለማቆየት የተደረገ መሆኑን ጠቅሰው ውሳኔው ይቀጥል አይቀጥል በሚለው ላይ ለመወሰን 14ቱ ቀናት ተጠናቀው "የህክምና ቡድን የሚሰጠውን ምክር እንከተላለን፤ ከማኅበረሰቡም ጋር እንወያያለን" ብለዋል።
news-57101749
https://www.bbc.com/amharic/news-57101749
ቻይና መንኩራኩሯን ማርስ ላይ በማሳረፍ ከአሜሪካ ቀጥሎ ሁለተኛዋ አገር ሆነች
ቻይና መንኩራኩሯን ማርስ ላይ ስኬታማ በሆነ ሁኔታ ማሳረፏን የአገሪቱ ብሔራዊ መገኛ ብዙኀን ዘገበ።
ባለስድስት እግሩ እና ዙሁሮንግ የተሰኘው ሮቦት ወደ ማርስ የተላከው በፕላኔቷ ሰሜናዊ ንፍቀ ክበብ ላይ የሚገኝ አንድ ክፍልን ዒላማ አድርጎ ነው። ይህ ሮቦት የመከላከያ እቃዎችን፣ ፓራሹት እንዲሁም ወደ ምድር ለመመለስ የሚረዳ ሮኬት ይዟል። በማርስ ላይ መንኩራኩር ለማሳረፍ ያለውን ፈታኝ ሂደት በመጥቀስ ሮቦቱ የማርስን ምድር በስኬት በመርገጡ ተደንቋል። እስካሁን ድረስ በማርስ ላይ መንኩራኩሯን በማሳረፍ ስኬታማ የነበረችው አሜሪካ ብቻ ነበረች። ይህ ማርስን እየተሽከረከረ የሚቃኝ ሮቦት መንኩራኩር ቻይናን ሁለተኛ ያደረጋታል ተብሏል። ዙህሮንግ ማለት የእሳት አምላክ ማለት ሲሆን ወደ ማርስ የተወነጨፈው ከፕላኔቱ በላይ በየካቲት ወር ከደረሰችው ታይናዌን-1 ኦርቢተር ነው። ማርስን ለመርገጥ ረዥም ጊዜ የፈጀው አካባቢው ላይ ቅኝት ሲደረግ፣ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ምስል ሲወሰድ እና ለማረፍ ምቹ የሆነ ስፍራ ሲመረጥ ነው ተብሏል። የዚህ ሁሉ ዓላማው በተቻለ መጠን ሸለቆዎችን እና ትልቅ ቋጥኞችን ለማስወገድ በማሰብ መሆኑንም አክለው ተናግረዋል። በአሁኑ ሰዓት ማርስ የምትገኝበት ርቀት 320 ሚሊዮን ኪሎ ሜትር ሲሆን አንድ የሬዲዮ መልዕክት ከፕላኔቷ ምድር ላይ ለመድረስ 18 ደቂቃ ይፈጅበታል። ዙህሮንግ ማርስ ላይ እየቀረበች በነበረበት ወቅት እያንዳንዱ ሂደት በተናጥል መታየት እንደነበረበት መሃንዲሶቹ ይናገራሉ። ሮቦቱ ወደ ማርስ ከባቢ አየር ሲገባ ፣ ያለመንገራገጭ እንዲያርፍ እንዲሁም መመለሱን በሚመለከትም ተመሳሳይ የሆነ ቅደም ተከተል እና ሂደትን ይከተላል። በሚመረጥ ቅጽበትም ይህ ማርስን የሚዞር ሮቦት ከታይናዌን ኦርቢተር ወደታች እንዲምዘገዘግ ይደረጋል። ወደ ምድር በሚመጣበት ወቅት ፍጥነቱን ለመቀነስ የሚረዳ ሙቅን የሚቋቋም ልባስ የተገጠመለት ሲሆን፣ የያዘውም ፓራሹት ቢሆን ይህንኑ ይረዳዋል። በስተመጨረሻም ሮቦቱ ላይ የተገጠመው ሮኬት በመወንጨፍ ወደ ምድር የሚያደርገውን ጉዞ ያሳልጣል። ቻይና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፈታኝ የሆነውን የሕዋ ላይ ምርምር በስኬት እየተወጣችው ትገኛለች። በቅርቡ ሁለት መንኮራኩሮችን በጨረቃ ላይ በማሳረፍ ብቃቷን ያስመሰከረችው ቻይና አሁን ደግሞ በማርስ ላይ መንኮራኩሯን አስቀምጣለች። አሁን ተመራማሪዎች 90 ቀናት አላቸው። ማርስ ላይ አንድ ቀን ማለት 24 ሰዓት ከ39 ደቂቃ ነው። ሮቦቱ ፎቶ የሚያነሳበት ካሜራ የማርስን ምድር በማሰስ የማዕድን ሃብቷን ማጥናት የሚያስችለው እና ከመሬት በታች ያለን ውሃ ለመፈተሽ የሚያግዝ መሳሪያዎች ተገጥመውለታል።
news-42502191
https://www.bbc.com/amharic/news-42502191
ከንቲባ ለመሆን ፈተናዎችን የሰበረች
አንዳንዶች በአልጄሪያ ሴቶች በሚኖሩበት ከተማ ከንቲባ ከመሆን ፕሬዝዳንት መሆን ይቀላቸዋል ይላሉ።
ዛሂ ቤንካራ በአልጄሪያ ከንቲባ ሆነው ከተመረጡ 4 ሴቶች መካከል አንዷ ነች ዛሂ ቤንካራ ደግሞ ይህንን ከማንም በላይ ጠንቅቃ ታውቃለች። በሰሜን አፍሪካ ሃገራት በቅርቡ ከተደረጉ ምርጫዎች ከ 4 ሴቶች መካከል ከንቲባ ሆና የተመረጠች ነች። የሷ ድል የበለጠ የሚያስደንቀው የምትኖርበት ከተማ ቺጋራ ባህሪይ ሲታይ ነው። በምስራቃዊ አልጄሪያ የምትገኘው ይህች ከተማ ባህል ስር የሰደደባት እና ሴቶች እንደዚህ አይነት ህዝባዊ ሃላፊነቶች ላይ እምብዛም የማይታዩባት ነች። እዚህ ላይ ደግሞ እስላማዊ ለሆነ ፖለቲካ ፓርቲ መወዳደሯ ሲጨመር በዋናነት የለዘብተኞችን ድጋፍ ያሳጣታል። እንደዛም ሆኖ ማሸነፏ የበለጠ አስገራሚ ነው። ይህች ሴት በአካባቢዋ ፕሮፌሰሯ እየተባለች ነው የምትጠራው፤ ያ ደግሞ ያላትን ተወዳችነት ያሳያል። "የመረጡኝ ስለሚያቁኝ ነው። ለነሱ ያደረኩትን ያውቃሉ እናም ያምኑኛል"ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች። በርግጥም የትምህርት ደረጃዋና የስራ ልምዷ መሳጭ ነው፤ ወ/ሮ ቤንካራ የመብት ተሟጋች ብቻ አይደለችም፤ በማህበረሰቡ ውስጥ የተቸገሩትን ትደግፋለች፤ በአካባቢዋ በሚገኝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትም ለአመታት እስላማዊ ሕግን ስታስተምርም ቆይታለች። ይህ ግን በመማሪያ ክፍል ውስጥ ብቻ የተገደበ አልነበረም፤ በመስኪዶች፣ በበጎ አድራጎት ማህበራት እና በተለያዩ ማህበረሰብ ውይይቶች ላይ እስላማዊ ህግን፥ ትምህርት እና የሰው ልጅ እድገትን ታስተምራለች። በአልጄሪያ ከ1962 ጀምሮ ሴቶች በምርጫ መወዳደር እና ስልጣን መያዝ ይችሉ ነበር በምርጫ ለመወዳደር ፍላጎት እንዳላት ስትገልፅ በማህበረሰቧ ውስጥ ቀድሞም የነበራት ድጋፍ እንዳለ ነበር። "ዛሂ እንደማንኛዋም ሴት አይደለችም ከ 15 ወንዶች ትበልጣለች" ሲል ተናግሯል አንድ ደጋፊዋ። የምትወዳደረው እስላማዊ ፓርቲን ወክላ መሆኑ እንደታወቀ ግን ምስሏ በማህበራዊ ድረ ገፅ በፍጥነት መሽከርከር ጀመረ፣ ከወግ አጥባቂዎች ከለዘብተኛ ፓርቲ ደጋፊዎችም ዘንድ የተለያዩ ነገሮች መሰንዘር ጀመሩ። አንዳንድ ኃይማኖተኛ ያልሆኑ መራጮች ደግሞ በሂጃቧ መሳለቅ ጀመሩ፤ ሌሎቹ ደግሞ በተክለሰውነቷ። ወ/ሮ ቤንካራ ከቁብም አልፃፈችውም። "ተሳዳቢ እና ግድ የማይሰጣቸው ሰዎች ለሰው ልጅ የሚያስፈልገው ነገር በምሰራው ስራ ብቁ ሆኜ መገኘቴ እና ለሰው ልጅ የማደርጋቸው ነገሮች ጥሩ መሆናቸውን ቀስ ብለው ይማራሉ፤ ይረዳሉም " ብላለች። እሷ ይህንን ብትልም ጠንካራ ወግ አጥባቂዎች የመወዳደር ብቃቷን ይጠራጠራሉ። "ፈጣሪ በሴቶች የሚመሩ ሕዝቦችን ረግሟል" ሲል አንድ ሰው ማህበራዊ ድረ ገፅ ላይ ፅፏል። ሌሎች ደግሞ "ሴቶች ቤት ውስጥ መቆየት አለባቸው የሚለውን ከገሃነም የሚጠብቅሽን የነብያችንን አስተምህሮ ተላልፈሻል" ሲሉ ያስጠነቅቃሉ። ወ/ሮ ባንካራ እነዚህን አስተያየቶችን ማየቷን እና ለመዋጋት መሞከሯን አልሸሸገችም። "በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ረዥም ሰአት ወስጄ በእስልምና ሴቶችን ለመንግስት ስልጣን መምረጥ ስህተት ነው የሚሉትን ተከራክሬያለሁ" ብላለች። " እንዲህ አይነት የተሳሳተ ሃሳብ የያዙ ሰዎችን እንዴት ማሳመን እነዳለብኝ አውቃለሁ፤ በርካቶቹም አእምሯቸውን ቀይረው በመጨረሻ ለኔ ድምፃቸውን ሰጥተዋል።" ለወ/ሮ ቤንካራ የሚታገሉ ሌሎችም አሉ። "በሃገሬ ሕዝቦች አፈርኩ" ሲል አንዱ ፅፏል፤ "በጠንካራዋ ሴት ላይ ያልተገባ አስተያየት እየሰጣችሁ ነው። እናንተ በምግባራችሁ ብታንሱም እሷ ግን ጠንካራ፣ የተማረች አልጄሪያዊ ሙስሊም ናት። ለምን ግን ለሃገራችን የሚጠቅም ሃሳብ አታነሱም?'' እንደ ቤንካራ ያሉ ሴቶች ሌሎች የነሱን መንገድ እንዲከተሉ ያነሳሱ ይሆን? ድጋፉ ደግሞ ማንነታቸው ከማይታወቁ የበይነ መረብ ሰዎች ብቻ አይደለም የሚመጣው። የሐረካት ሙጅታማ ኢስሊም መሪ ሆነው አብደልማጂድ ሜንሳራ ጠንካራ ተወዳዳሪዎች እንዳሉባት ያውቃል። "ጠንካራ ሰብዕና ያላት፣ ብቁ እና የተሰጠች ናት። የምትሰራውን ታውቃለች" ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። እሷም እሱ ልክ እንደሆነ ታወቃለች፤ ሰዎች እንድትወድቅ ይፈልጋሉ እሷ ግን ፈፅሞ አስባው አታውቅም። "ለደጋፊዎቼ ማረጋገጥ የምፈልገው እኔን በመምረጣቸው አለመሳሳታቸውን ነው" ትላለች "ሙስናን፣በስልጣን መባለግን እና አላግባብ መጠቀምን እዋጋለሁ። ሁሌም እንደማደርገው ለመረጠኝ ከተማ ሕዝብ እሰራለሁ። "
54597781
https://www.bbc.com/amharic/54597781
ትራምፕና ባይደን የሚለያዩባቸው 8 ቁልፍ ጉዳዮች
እርግጥ ነው እስከአሁን ከ20 ሚሊዮን በላይ አሜሪካዊያን ድምጽ ሰጥተዋል። ይፋዊ የምርጫ ቀኑ 15 ቀናት ብቻ ነው የቀሩት።
ለመሆኑ ጆ ባይደንና ዶናልድ ትራምፕ የፖሊሲ ልዩነታቸው ምንድነው? 1. ኮሮናቫይረስ ፕሬዝዳንት ትራምፕ፡- ትራምፕ የኮሮና ግብረ ኃይል አቋቁመው ተህዋሲውን ሲዋጉ ነበር። አሁን የዚህ ግብረ ኃይል ተግባር ተዘግተው የነበሩ ግዛቶች እንዲከፈቱ ማድረግና ሥራ ሞቅ ሞቅ እንዲል ማበረታታት ነው ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ ክትባት በፍጥነት እንዲዳረስ እየሰራሁ ነው ይላሉ። በቅርቡ ሁላችሁም ክትባት ትወጋላችሁ፣ ኮሮና ታሪክ ይሆናል ሲሉም ቃል ገብተዋል። 10 ቢሊዮን ዶላር ለዚሁ መድበዋል። ጆ ባይደን፡- የትራምፕ ግብረ ኃይል ሕዝብ አስጨርሷል ብለው ያምናሉ። 250ሺ ሕዝብ የሞተው ትራምፕ በሚከተሉት ልል ፖሊሲ ነው ይላሉ። ከተመረጥኩ በብሔራዊ ደረጃ ተህዋሲውን (ተጠቂዎችን) እግር በእግር የሚከታተል ፕሮግራም ይፋ አደርጋለሁ ይላሉ። በአንድ ግዛት በትንሹ 10 የምርመራ ጣቢያ አዘጋጃለሁ ብለዋል። የኮቪድ ምርመራ ለሁሉም ዜጋ በነጻ አደርሳለሁም ብለዋል። ሌላው በብሔራዊ ደረጃ ጭምብል ግዴታ ያደርጋሉ። 2. አየር ንብረት ጉዳይ ፕሬዝዳንት ትራምፕ፡- የአየር ንብረት ለውጥ ብሎ ነገር የለም፤ ቅጥፈት ነው ይላሉ። ታዳሽ ያልሆኑ የኃይል አቅርቦትን ማስፋፋት ይሻሉ። ነዳጅና ጋዝ ፍለጋ እንዲቀጥል፣ እንዲጧጧፍ ያበረታታሉ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ስጋት በሚል የሚወጣ ወጪ እንዲቆም ያደርጋሉ። ከፓሪስ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ወጥተዋል። ጆ ባይደን፡- ነጩ ቤተ መንግሥት እንደገቡ ወዲያውኑ ወደ ፓሪሱን የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት መልሰው ለመግባት ይሻሉ። አሜሪካ በ2050 ዜሮ የካርበን ልቀት ላይ እንድትደርስ ይሰራሉ። 2 ትሪሊዮን ዶላር በአረንጓዴ ታዳሽ ኃይል ያወጣሉ። የነዳጅና ጋዝ ፍለጋ እንዲቆም ያደርጋሉ። 3ኛ፡- በምጣኔ ሀብት ጉዳይ ፕሬዝዳንት ትራምፕ፡- በ10 ወራት 10 ሚሊዮን የሥራ እድል ለመፍጠር ቃል ገብተዋል። 1 ሚሊዮን አነስተኛና ጥቃቅን ሥራ እፈጥራለሁ ብለዋል። የግብር እፎይታ ለትልልቅ ኩባንያዎች በመስጠት ሥራ ፈጠራ እንዲፋፋም አደርጋለሁ ይላሉ። ጆ ባይደን፡- ከሀብታም ኩባንያዎች ግብር በመጫን ሕዝቡን የሚጠቅሙ ልማቶች ላይ አተኩራለሁ ይላሉ። ነገር ግን ግብር የምጭነው ገቢያቸው በዓመት 400 ሚሊዮን ዶላር በሚያገኙ ግዙፍ ኩባንያዎች ላይ ብቻ ነው ብለዋል። በቀን ዜጎች የሚያገኙት ትንሹ የምንዳ ምጣኔ በሰዓት 15 ዶላር እንዲሆን አደርጋለሁ ብለዋል። አሁን ያለው ትንሹ በሰዓት የሚከፈለው 7.25 ዶላር ነው። 4ኛ፡- በኅብረተሰብ ጤና ጉዳይ ፕሬዝዳንት ትራምፕ፡- የኦባማ የጤና መድኅን ጨርሶ ለማጥፋት ይፈልጋሉ። በዚህ ‹አፎርደብል ኬር አክት› በሚባለው አዋጅ መሰረት የፌዴራል መንግሥት የግል የጤና መድኅን ሰጪዎችን ይቆጣጠራል። መድኅን ሰጪዎች ቀደም ብሎ የጤና እክል ያለባቸው ሰዎችን መድኅን ሲጠይቁ የሕክምና ወጪ አልሸፍንም ማለት አይችሉም። ትራምፕ ግን ይህንን ረብ የለሽ ኦባማ ኬር ቀዳድጄ በሌላ ጥዬ በሌላ እተከዋለሁ እያሉ ይዝታሉ። የመድኃኒት ዋጋ አሁን ካለበት እንዲወርድ አደርጋለሁ፤ በርካሽ ከሌሎች አገሮች መድኃኒት እንዲገባም እፈቅዳለሁ ብለዋል። ጆ ባይደን፡- የኦባማ የጤና ሽፋን መድኅንን አስጠብቃለሁ ይላሉ። በዕድሜ የገፉ ሰዎች የሚያገኙትን የጤና ትሩፋቶችን አስፋፋለሁ፤ ለዚህ ትሩፋት የሚያበቃውን ዕድሜም ከ65 ወደ 60 አወርደዋለሁ ብለዋል። ሁሉም አሜሪካዊያን የኅብረተሰብ ጤና መድኅን የመመዝገብ ምርጫ እንዲኖራቸው አደርጋለሁ ሲሉ ቃል ገብተዋል። 5ኛ፡- የውጭ ፖሊሲ ጉዳይ ፕሬዝዳንት ትራምፕ፡- በውጭ አገር ያሉ ወታደሮችን ለእናት አገራቸው አበቃለሁ ይላሉ። የንግድ ታሪፍ በቻይና ላይ እጭንባታለው ብለዋል። ጆ ባይደን፡- ትራምፕ ያበላሹትን የውጭ ግንኙነት አስተካክላለሁ፤ አሜሪካ ያስቀየመቻቸውን ወዳጆቿን ልብ እጠግናለሁ ብለዋል። ከኢራንና ከቻይና ጋር የሚከተሉት ፖሊሲም ትራምፕ ጋር የሚቀረን ነው። 6ኛ፡-ዘርና ዘረኝነትን በተመለከተ ፕሬዝዳንት ትራምፕ፡- በአሜሪካ ፖሊስና ጸጥታ አስከባሪዎች ዘንድ መዋቅራዊ ዘረኝነት የለም ብለው ያምናሉ። ፖሊስ ማንቁርት ማነቁን ባይደግፉም ሕግን ማስከበር አለበት፣ ሥርዓት አልበኝነት እንዲነግስ መፈቀድ የለበትም ይላሉ። ከፖሊስ ይልቅ ወንበዴዎች የሚሏቸውን ሰልፈኞች ማውገዝ ይመርጣሉ። ጆ ባይደን፡ -ዘረኝነት በፖሊስና ጸጥታ አስከባሪዎች ዘንድ መዋቅራዊ ቅርጽ ይዟል ብለው ያምናሉ። ይህንንም ለማጥፋት እሰራለሁ ብለዋል። 7ኛ፡- የጦር መሣሪያን በተመለከተ ፕሬዝዳንት ትራምፕ፡- ትራምፕ የአሜሪካ ሕገ መንግሥት 2ኛው ማሻሻያ ለአሜሪካዊያን የጦር መሣሪያ የመታጠቅ ሙሉ መብትን አጎናጽፏል ብለው የተለጠጠ ትርጓሜ ይሰጡታል። የጦር መሣሪያ ገዢዎች ላይ የኋላ ታሪክ ጥናት መደረግ አለበት ብለው ነበር፣ በ2019 ዓ.ም የደረሱ ግብታዊ ጥቃቶችን ተከትሎ። ሆኖም እስከዛሬ በዚህ ረገድ ተግባራዊ ያደረጉት አንዳችም ነገር የለም። ጆ ባይደን፡- በጦር መሣሪያ ረገድ ቁጥጥር ማጥበቅ ይፈልጋሉ። ለምሳሌ የገዢዎችን የኋላ ታሪክ ማጥናትና መመዝገብ፣ አንድ ዜጋ በወር መግዛት የሚችለው የመሣሪያ ብዛት አንድ ብቻ እንዲሆን ማድረግ፣ ቸልተኛ የመሣሪያ አምራቾችና ሻጮችን ተጠያቂ ማድረግ፣ ለዜጎች መሸጥ የሚችሉ የጦር መሣሪያ ዓይነትም በሕግ እንዲወሰን ማድረግ ይፈልጋሉ። 8ኛ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞችን በተመለከተ ፕሬዝዳንት ትራምፕ፡- ሕገ መንግሥቱ በሰጠኝ ሥልጣን በሟቿ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ምትክ ሌላ እጩ የመሰየም መብት አለኝ ብለው ያምናሉ። ይህንንም ተከትሎ ወግ አጥባቂዋን ኤሚ ባሬትን በእጩነት አቅርበዋል። ሴትየዋ ሥራ በይፋ ሲጀምሩ የመጀመርያ ሥራቸው የሚሆነው በአሜሪካ የጽንስ ማቋረጥ መብት ላይ ድምጽ መስጠት ነው። ከዚህ በፊት በነበራቸው አቋም ትራምፕም ሆኑ ባሬት ጽንስ ማቋረጥ በአሜሪካ ሕገ ወጥ እንዲሆን ይሻሉ። ጆ ባይደን፡- ይህ በጎደሉት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ምትክ ሰው መሾም ያለበት ከምርጫ በኋላ ነው፣ የግዛት ዕድሜውን እየጨረሰ ያለ ፕሬዝዳንት በአሜሪካ ሕዝብ ፍላጎት ላይ መወሰን የለበትም ብለው ያምናሉ። ጽንስ የማቋረጥ መብት ሕጋዊ እንዲሆንም ይሻሉ፡፡
news-49282169
https://www.bbc.com/amharic/news-49282169
በጆሀንስበርግ ፖሊስ ባካሄደው አሰሳ ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ 1200 ሰዎች ታሰሩ
በደቡብ አፍሪካ የንግድ መዲና ጆሀንስበርግ ልዩ ስሙ ጂፒ አካባቢ ፖሊስ ባካሄደው አሰሳ በንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ 1200 ሰዎች መታሰራቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገለጹ።
በጂፒ አካባቢ የሬስቶራንት ባለቤት የሆነው አቶ ተከስተ ሹምዬ ለቢቢሲ እንደተናገረው በትናንትናው ዕለት ነሐሴ 1/2011 ዓ.ም ጠዋት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ፖሊሶች ከተለያየ መስመር በመሆን ቦታውን በመዝጋት ወደ አካባቢው መጥተው ህገወጥና ሐሰተኛ ምርቶችን እንቆጣጠራለን በማለት የጅምላ እስር መፈጸማቸውን ገልጿል። • በባርነት ከመሸጥ የተረፉት 64 ኢትዮጵያዊያን አቶ ተከስተ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ከዚህ ቀደም ከፖሊስ ጋር በተፈጠረ ግጭት ምክንያት አፈሳ ይኖራል በሚል የንግድ ቦታቸውን ዘግተው እንደነበርም ያስረዳል። በአካባቢው የተገኙ ግለሰቦች ያለምንም ማጣራት መታፈሳቸውንና ወደ እስር ቤት መወሰዳቸውን ገልጾ፤ ያላቸው ሕጋዊ ወረቀት እንዲሁም ከሳምንት በፊት በተከሰተ ግጭት በፖሊስ ላይ ድንጋይ በመወርወር ያልተሳተፉ መሆናቸው ተጣርቶ እንደሚፈቱ መገለፁንም ይናገራል። "በትናንትናው ዕለት ፖሊሶች ቀኑን ሙሉ ሰዎችን ሲያፍሱ ነበር" የሚለው ተከስተ የእሱም ምግብ ቤት ተዘግቶ ፖሊሶች በአካባቢው ሰዎች እንዳይዘዋወሩ በመከልከላቸው ሰራተኞቹ ከውስጥ ተቆልፎባቸው ማምሸታቸውን ገልጿል። አቶ ተከስተ ወደ ሥራ አካባቢው በደረሰበት ወቅት ስፍራው ከፍተኛ ቅጥር ባለው የፖሊስ ኃይል ተከቦ የነበረ ሲሆን፤ እሱም ክስተቱን በርቀት መከታተሉንና በኋላም ወደ ሬስቶራንቱ ማምራቱን ይናገራል። • በደቡብ አፍሪካ በየቀኑ 57 ሰዎች ይገደላሉ "ምንም እንኳን የፖሊሶቹ ምክንያት ህገወጥ (ሐሰተኛ ምርቶችን) ለመቆጣጠር የሚል ቢሆንም በህጋዊ መንገድ ከቻይና እቃ ከሚያስመጡ ሰዎች ላይ በርካታ እቃዎች ተወስደዋል፤ ከህገወጡ በበለጠ የተጎዱትም እነዚህ ናቸው። ህገወጥ ህገወጥ ነው ማንም ቢሆን የሚከላከላቸውም ሆነ ተዉ የሚላቸው አካል የለም። ግን በህጋዊ መንገድ የሚሰራውን ነጋዴ በከፍተኛ ሁኔታ ተፅዕኖ አድርሶበታል" ይላል። ፖሊሶች ከሄዱ በኋላ ወደ አመሻሽ ላይ በቅርብ ርቀት የሚኖሩ ሰዎች አጋጣሚውን በመጠቀም ለዘረፋ መጥተው የነበሩ ሲሆን መጠነኛ ግጭትም ተፈጥሮ ሳይባባስና ችግር ሳይፈጠር በሰላም እንደተፈታም ይናገራል። ተከስተ እንደሚናገረው ይህ ጉዳይ አሁን የተፈጠረ ሳይሆን ከባለፉት ስምንት ዓመታት በፊት ጀምሮ ሲንከባለል የመጣ ነገር መሆኑን ያስረዳል። ለብዙ ስመጥር የስፖርት አልባሳት ኩባንያዎች ተወካይ የሆነ አንድ ግለሰብ በፖሊስ ታጅቦ ኢትዮጵያዊያን በሚነግዱባቸው ቦታ በመምጣት ሐሰተኛ ብራንድና ህገወጥ ናቸው በሚል በተደጋሚ እቃዎችን እንደሚያስወስድ አቶ ተከስተ ይናገራል። • ደቡብ አፍሪካ በወሮበሎች ላይ የጦር ሠራዊቷን አዘመተች አክሎም እቃዎቹ በህጉ መሰረት መቃጠል ወይም ለመንግሥት መግባት የነበረባቸው ቢሆንም በተለያዩ ግንኙነቶች የተወሰዱት እቃዎች ተመልሰው እዚው ቦታ ገበያ ላይ መዋላቸው በንግዱ ላይ በተሰማሩ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ምሬት መፍጠሩንም ያስዳል። "ህገወጥ ነው ተብሎ ከተወሰደ ወይ መቃጠል ነው ያለበት ወይም ለመንግሥት ነው መግባት ያለበት ነገር ግን ተመልሶ ገበያ ላይ የሚገኝ ከሆነ ዘረፋ ነው የያዙት ማለት ነው" ይላል። በተለይም በተወሰነ ጊዜ ይመጣ የነበረው ግለሰብ በተደጋጋሚ በወር እስከ አራት ጊዜ ድረስ መምጣቱ ኢትዮጵያዊያኖችን እንዳሰላቸ ገልጿል። ግለሰቡ ሲመጣም ለአንድ ህንፃ የሚሆን የፍርድ ቤት መፈተሻ ወረቀት ይዞ ቢመጣም ያልተፈቀደለትን ሁሉንም ሱቆች እንደሚፈትሽ ይገልፃል። አብዛኛውን ጊዜም በፖሊስ ታጅቦ ከመምጣቱ አንፃር ብዙው ኢትዮጵያዊያን እሱን የመጋፈጥ አቅም እንደሌላቸው ተከስተ ያስረዳል። ግለሰቡ እየገፋ መጥቶ የሰዎችን ንብረት መንጠቅና ማጉላላት፣ አካላዊ ጥቃት፣ መገፍተርና ማመናጨቅ በመደጋገሙ የተነሳ ኢትዮጵያዊያን ክስ አቅርበው ጉዳዩም በፍርድ ሂደት ላይ እንደሆነ ኢትዮጵያዊያኑ ይናገራሉ። • ታዳጊዎቹን አብራሪዎች ሲረዱ የነበሩት ፓይለቶች በአውሮፕላን አደጋ ሞቱ በፍርድ ሂደቱም ምክንያት አካባቢው ላይ እንዳይደርስ በመከልከሉ ያልመጣው ይህ ግለሰብ ከጥቂት ቀናት በፊት በብረት ለበስ መኪና ተጭኖ ከፖሊሶች ጋር የመጣ ሲሆን በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያዊያን ድንጋይ መወርወር እንደጀመሩ ተነግሯል። "ባልተጠበቀ ሰዓት እየመጣ ነገር በመቆስቆሱ፤ ሰዉ ደግሞ ብዙ ንብረት ስለተወሰደበት፤ የፍርድ ሂደቱን ጥሶ በመምጣቱ ከፖሊስ ጋር ግጭት ተፈጠረ፤ ድንጋይም መወርወር ተጀመረ" በማለት ኢትዮጵያዊያኑ ይናገራሉ። ይህ ሁኔታም በከፍተኛ ሁኔታ ተባብሶ የሃገሪቱ መገናና ብዙሃን "እንዴት ግለሰቦች ፖሊስ ላይ ድንጋይ ይወረውራሉ" በሚል ጉዳዩ እንደተካረረ የሚናገረው በጂፒ አካባቢ በግል ሥራ የሚተዳደረው ሔኖክ ለማ ነው። እስከ ላይኛው የመንግሥት መዋቅር ድረስ ቁጣን እንደቀሰቀም ይናገራል። ተከስተ እንደሚለው በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ኢትዮጵያዊያን ነጋዴዎች በፖሊስ ላይ ድንጋይ ሲወረውሩ የሚያሳይ ቪዲዮ በከፍተኛ ሁኔታ ከመሰራጨቱ ጋር ተያይዞ ይህ አፈሳ መካሄዱን ይገልፃል። • ኢትዮጵያዊያን ዛምቢያ ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋሉ ይህም ሁኔታ እስከ ላይኛው የመንግሥት አካል በመድረሱ ትላንት ለተፈጠረው የጅምላ እስር ምክንያት መሆኑንም ያስረዳል። በእስር ላይ ስላሉ ግለሰቦች ዘርዘር ያለ መረጃ እንደሌለው የገለፀው ተከስተ እንደ ቀድሞው ከሆነ በሰባት ቀን ውስጥ ሊለቀቁ እንደሚችሉ ግምቱን አስቀምጧል። ሔኖክ በበኩሉ ብዙ ኢትዮጵዊያን እስርን በመፍራት ቤተሰቦቻቸውንም ሆነ ጓደኞቻቸውን ሊጠይቁ አልቻሉም ብሏል። አሁንም ጂፒ አካባቢ የሚገኙ ሱቆች ዝግ ሲሆኑ በአካባቢው ውር ውር የሚሉ ግለሰቦች እንዳሉ ተከስተ ይናገራል። የትናንቱን ክስተት ተከትሎ ሰባት የፖሊስ መኮንኖች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ አሳውቋል። ከሰባቱ ፖሊሶች መካከል አምስቱ በህገወጥነት የተወረሱ ሸቀጦችን መልሰው ለሱቆቹ ባለቤቶች በመሸጥ እንደሚከሰሱ የተነገረ ሲሆን፤ ሁለቱ ደግሞ ፖሊስ ሊያካሂድ ስላቀዳቸው አሰሳዎች ቀድመው መረጃ በመስጠት ተከሰዋል። በርካቶች ለእስር በተዳረጉበት የትናንቱ አሰሳ ከፍተኛ መጠን ያላቸው ህገወጥና ሐሰተኛ ሸቀጦች መያዛቸውን እንዲሁም በመቶዎቹ የሚቆጠሩ ተጠርጣሪ ህገወጥ ስደተኞችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አሳውቋል። ቢቢሲ ያናገራቸው ኢትዮጵያዊያን በፖሊስ የተያዙት ወገኖቻቸው አንድ ሺህ ሁለት መቶ እንደሚደርሱ ይናገሩ እንጂ ፖሊስ እስካሁን ስለተያዙት ሰዎች ዜግነትና አሃዝ በይፋ ያወጣው መረጃ የለም።
news-54077777
https://www.bbc.com/amharic/news-54077777
የትግራይ ምርጫ፡ ትልልቆቹ የህወሓት እጩዎች የት ተወዳደሩ?
በኢትዮጵያ በነሐሴ መጨረሻ ላይ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው ምርጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ ከተላለፈ በኋላ በትግራይ በተናጠል የሚካሄደው ምርጫ ሕገ ወጥና ተቀባይነት የሌለው ነው በማለት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ቢወስንም ዛሬ እየተካሄደ ነው።
ለወራት በፌደራሉና በትግራይ ክልል መንግሥት መካከል ያለመግባባት ምንጭ ሆኖ የቆየው ክልላዊው ምርጫ ዛሬ ጳጉሜ 04/2012 ዓ.ም አገሪቱ ካሏት 10 ክልሎችና ሁለት የከተማ አስተዳደሮች በተለየ በትግራይ ክልል ውስጥ ይካሄዳል። በዚህ ምርጫ ላለፉት 30 ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ በብቸኝነት በህወሓት ተይዞ ለቆየው የክልሉ ምክር ቤት መቀመጫዎች 5 ፓርቲዎቹ ይወዳደራሉ። በምርጫው ተቃዋሚዎች ሰምሮላቸው የትኛውንም ያህል መቀመጫ ቢያገኙ በክልሉ ታሪክ በምክር ቤቱ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ከህወሓት ውጪ የሆነ ድምጽ የመሰማት ዕድል ያገኛል። በዚህ ምርጫም ከህወሓት አንጻር በክልሉ የፖለቲካ መድረክ ላይ አዲስ የሆኑት አራት ፓርቲዎች ለፉክክር ቀርበዋል። እነርሱም ሳልሳይ ወያኔ፣ ባይቶና፣ የትግራይ ነጻነት ፓርቲ እና የአሲምባ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሲሆኑ አራት ግለሰቦች በግል ይወዳደራሉ። በምርጫው የሚሳተፉት ፓርቲዎች ባካሄዷቸው ክርክሮች ላይ እንዳንጸባረቁት በተለያዩ መስኮች ካሏቸው ፕሮግራሞች ባሻገር ከማዕከላዊው መንግሥት ጋር ስለሚኖራቸው ግንኙነት አንስተው ዓላማቸውን አንጸባርቀዋል። በዚህም ክልሉ በፌደራላዊ ሥርዓት ከቀሪው የአገሪቱ ክልሎች ጋር ተሳስሮ እንዲቀጥል ከመፈለግ አንስቶ በኮንፌዴሬሽን የላላ ግንኙነት እንዲኖር የሚፈልጉና ከዚህም ከፍ ሲል ነጻ ሪፐብሊክ የመመስረት ፍላጎትም ተንጸባርቋል። በዚህ ምርጫ 190 መቀመጫዎች ላሉት ምክር ቤት 625 እጩዎች ለመወዳደር ቀርበዋል። ከ2.7 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ድምጽ ለመስጠት እንደተመዘገበ ያስታወቀው የትግራይ ምርጫ ኮሚሽን ድምጽ መስጠቱ የሚከናወንባቸው 2684 የምርጫ ጣቢያዎች እንዳሉ አስታውቋል። ክልሉ ምርጫውን እንዲያስፈጽምለት ብሔራዊውን የምርጫ ቦርድን ቢጠይቅም ካለው የወረርሽኝ ሁኔታ አንጻር በመላው አገሪቱ ከተወሰነው ውጪ ምርጫውን ማካሄድ እንደማይችል አሳውቆ ጥያቄውን ሳይቀበለው መቅረቱ ይታወሳል። በዚህም ምክንያት ነበር ክልሉ ከራሱ በጀት በማውጣት የምርጫ ኮሚሽን መስርቶ ምርጫውን ለማካሄድ በመወሰን ከዛሬው የድምጽ መስጫ ቀን ላይ የተደረሰው። ዋነኞቹ የህወሓት እጩዎች በፌደራል መንግሥቱና በተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ ጉልህ ሚና የነበራቸው ዋና ዋና የህወሓት አባላት በዚህ በምርጫው በተለያዩ ጣቢያዎች ከተፎካካሪዎቻቸው ጋር ለውድድር ቀርበዋል። የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንትና የህወሓት ሊቀመንበር የሆኑት ደብረጽዮን ገብረሚካኤል፣ በአድዋ ከተማ ፓርቲያቸውን ወክለው ሲወዳደሩ፣ እዚያው አድዋ ውስጥ ባሉ ቦታዎች ላይ ደግሞ የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበርና የቀድሞዋ የንግድ ሚኒስትር ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር (ሞንጆሪኖ) እና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የነበሩት አቶ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ ይወዳደራሉ። በመቀለ የምርጫ አካባባቢ ህወሓትን ወክለው ከሚወዳደሩት መካከል በገዛ ፈቃዳቸው ኃላፊነታቸውን ከጥቂት ወራት በፊት የለቀቁት የቀድሞዋ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ኬሪያ ኢብራሂም፣ በሕግ የሚፈለጉት የቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ዋና ዳይሬክተር የአቶ ጌታቸው አሰፋ ወንድም ዳንኤል አሰፋ በዕጩነት ቀርበዋል። የአዲግራት ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶክትር ዛይድ ነጋሽ በአዲግራት የህወሓት እጩ ሆነው ቀርበዋል። የቀድሞው የኮሙኑኬሽን ሚኒስትርና በተለያዩ የማዕከላዊው መንግሥት ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ የሰሩት አቶ ጌታቸው ረዳ ህወሓትን ወክለው አላማጣ ውስጥ ሲቀርቡ የመቀለ ዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ክንደያ ገብረሕይወት (ፕሮፌሰር) እንደርታ በመቀለ አካባቢ ቀርበዋል። በተለያዩ የምርጫ አካባቢዎች ህወሓት ከተጠቀሱት በተጨማሪ በርካታ እጩዎችን ያቀረበ ሲሆን፣ ተፎካካሪዎችም ከፍተኛ የፓርቲ አመራሮቻቸውን ጨምሮ በርካታ አባሎቻቸውን በምክር ቤቱ ውስጥ መቀመጫ ለመያዝ በዕጩነት አቅርበዋል። ቀደም ሲልም የክልሉ ምክር ቤት ከዚህ በፊት ሲሰራበት የነበረውን የአብላጫ ድምጽ የውክልና ሥርዓት በመቀየር ቅይጥ ትይዩ በሚባለው የውክልና ሥርዓት እንዲተካ ወስኖ፣ ይህም አሁን በሚካሄደው ምርጫ ተግባራዊ ይሆናል። ይህም ፓርቲዎች በአጠቃላይ ከሚያገኙት ድምጽ አንጻር በምክር ቤቱ ውክልና እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው። በተጨማሪም በምክር ቤቱ ውስጥ ካሉ መቀመጫዎች ውስጥ 80 በመቶዎቹ አብላጫ ድምጽ ባገኘው የፖለቲካ ድርጅት የሚያዙ ሲሆን፤ 20 በመቶው ደግሞ በተመጣጣኝ ውክልና ለተወዳዳሪ ድርጅቶች እንዲከፋፈል ይደረጋል ተብሏል።