id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
news-57097408
https://www.bbc.com/amharic/news-57097408
እስራኤል ወታደራዊ አመራሮችን መግደሏን ተከትሎ የሀማስ ታጣቂዎች በርካታ ሮኬቶችን ተኮሱ
ከሰሞኑ በእስራኤልና ፍልስጥኤም መካከል ግጭት ዳግም ካገረሸ በኃላ ትላንት እስራኤል በከፈተችው የአየር ድብደባ የሃማስ ወታዳራዊ አዛዦችን ገድላለች።
በጋዛ የደረሰው የአየር ጥቃት በጋዛ የሚገኝ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጥ ህንጻን ወደ ፍርስራሽነት ቀይራለች። ለዚህም የአጸፋ እርምጃ ሀማስ በርካታ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል አስወንጭፏል። ቀጣናው የገባበት ቀውስ ወደለየለት ጦርነት እንዳይሸጋገር የተባበሩት መንግስታት ድርጀት ስጋቱን ገልጾል። ይህ ግጭት በእስራኤል ውስጥ በአይሁዶችና በእስራኤል አረቦች መካከልም የጎዳና ላይ ሁከት እንዲፈጠር ሰበብ ሆኗል። ፖለቲካዊ አመራሮች ውጥረቱን እንዲያረግቡ ተማጽኖ አቅርበዋል። በዚህ ግጭት ምክንያት በጋዛ በትንሹ 67 በእስራኤል ደግሞ 7 ሰዎች ተገድለዋል። ካሳምንታት ውእረት በኃላ ባለፈው ሰኞ በምስራቃዊ እየሩሳሌም ለሙሰሊሞችም ይሁን ለአይሁዶች ቅድስት ተብላ በምትቆጠር ስፍራ መነሻነት ወደ ግጭት ያመራው። ግጭቱ በተጀመረ በሁለተኛ ቀን ደግሞ ክልስ አይሁዶችና አረቦች ተቀላቅለው በሚኖሩበት የእስራኤል አካባቢ በተፈጠረ ሁከት ምክንያት 36 የፖሊስ መኮንኖች መጎዳታቸውን የእስራኤል ፖሊስ ገልጾል ይህንንም ተከትሎ 374 ሰዎች ታስረዋል። ትላንትና ደግሞ [ዕረቡ] በጋዛ ውስጥ የሚገኙ ታጣቂዎች ደግሞ 130 ሚሳኤሎችን መተኮሳቸውን ገልጸዋል። ይህም በጋዛ የሚገኘው አል ሻሩቅ ህንጻ በእስራኤል ለደረሰበት ጥቃት አጸፋ መሆኑንም ተናግረዋል። በእስራኤል የአየር ድብደባ ከጥቅም ውጪ የሆነው አል ሻራርቁ በጋዛ 3ተኛው ረጅም ህንጻ ነበር። እስራኤል በበኩሏ የሀማስን ከፍተኛ አመራሮች መግደሏን አስታውቃለች። በተጨማሪም ሚሳኤል የሚተኮስባቸውን አካባቢዎች ኢላማ አድርጋ ጥቃት መፈጸሞንም ገልጻለች። ሀማስ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦቹና "ሌሎች አመራሮች" እንደተገደሉበት አረጋግጦል። የእስራኤል የመከላከያ ሰራዊት ሰሞኑን ጋዛ ላይ ያደረጋቸው ወታደራዊ ድብደባዎች ከ2014 በኃላ ትልቁ ነው ብሏል።
news-54001231
https://www.bbc.com/amharic/news-54001231
በቻርሊ ሄብዶ ጥቃት ተባባሪ ናቸው የተባሉ ለፍርድ ቀረቡ
በፈረንጆቹ 2015 ፈረንሳይ በሚገኘው ቻርሊ ሄብዶ የተሰኘ ስላቃዊ ይዘት ያለው ጋዜጣ መሥሪያ ቤት ላይ ለደረሰው ጥቃት ተባባሪ ናቸው የተባሉ 14 ሰዎች ችሎት ውለዋል።
አብዛኛዎቹ ተጠርጣሪዎች ፓሪስ የሚገኝ ፍርድ ቤት በአካል ሲቀርቡ 3 ተጠርጣሪዎች ደግሞ በሌሉበት ጉዳያቸው እየታየ ነው። ተጠርጣሪዎቹ ኢስላማዊ ታጣቂዎች በጋዜጣው አዘጋጆች ላይ ጥቃት እንዲያደርሱ ተባብረዋል፤ 12 ሰዎች እንዲገደሉም ምክንያት ሆነዋል ተብለው ነው የተከሰሱት። በተያያዘ ጥቃት በወቅቱ አንድ ታጣቂ ፖሊስ ገድሎ ሲያበቃ ወደ አንድ አይሁድ መደብር አቅንቶ ሌሎች አራት ሰዎችን ገድሏል። ጥር 2015 ላይ ፈረንሳይን ባሸበረው በዚህ ጥቃት በሶስት ቀናት ውስጥ 17 ሰዎች ተገድለዋል። ይህ ጥቃት በፈንሳይ በጂሃዲስቶች የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ያቀጣጠለ ሲሆን በድምሩ 250 በተለያዩ ወቅቶች በጂሃዲስቶች በተፈጸሙ ጥቃቶች ተገድለዋል። እነዚህን ተከታታይ ጥቃቶች ተከትሎ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ፈረንሳውያንና የሌሎች ሃገራት ዜጎች 'ጀ ስዊ ቻርሊ’ [እኔ ቻርሊ ነኝ] የሚል መፈክር ያለው ተቃውሞ አሰምተዋል። ጋዜጣው የፍርድ ሂደቱ መጀመሩን አስመልክቶ ነብዩ ሞሐመድን የተመለከተ አነጋጋሪ የካርቱን ምስል አትሟል። ይህ ምስል በርካታ የእስልምና እምነት ተከታይ ባላቸው ሃገራት ዘንድ ቁጣን ጭሯል። ፕሬዝደንት ኢማኑዔል ማክሮ ይህንን ተከትሎ ፈረንሳይ ውስጥ የፕሬስ ነፃነት ቦታ አለው ሲሉ ተከላክለዋል። ችሎቱ ላይ ምን እየተባለ ነው? 11 ተጠርጣሪዎች ዕለተ ረቡዕ በተሰየመው ችሎት ላይ ተገኝተዋል። ስማቸውንና የሥራ መስካቸውን ከጠቀሱ በኋላ ለፍርድ ቤቱ ላለመዋሸት ቃል ገብተዋል። የፍርድ ሂደቱ ቢያንስ ለ4 ወራት የዘገየው በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ነው። በፍርድ ቤቱ ዙሪያ ጠንከር ያለ የፀጥታ ኃይሎች ጥበቃ ይስተዋላል። በጥቃቱ ተባብረዋል የተባሉት ተጠርጣሪዎች የጦር መሣሪያ በመያዝና ለጥቃቱ አስፈላጊ መረጃዎችን በመስጠት ነው የተከሰሱት። ጥቃቱ ቻርሊ ሄብዶ በተሰኘው ስላቃዊ ጋዜጣ፣ በፖሊስና ሃይፐር ካሸር የገበያ ማዕከል ላይ ነው የተፈፀመው። በሌሉበት ፍርዳቸው እየታየ ያሉ ሶስት ተጠርጣሪዎች ወደ ሶሪያና ኢራቅ ሳይገቡ እንዳልቀረ ይጠረጠራል። ዘገባዎች እንደሚሉት ሁለቱ ኢስላሚክ ስቴት [አይኤስ] ላይ በተወሰደ የቦንብ ጥቃት ሳይሞቱ አልቀሩም። 200 ያክል ከሳሾችና ከጥቃቱ የተረፉ ሰዎች ምስክርነታቸውን ለመስጠት ችሎት ተገኝተዋል። ባለፈው ሰኞ ፀረ-ሽብር አቃቤ ሕግ ዢን ፍራንኳ ሪካርድ ‘ለፍርድ የቀረቡት ጥቃቅን እርዳታ ያደረጉ ሰዎች ናቸው’ መባሉን ተቃውመዋል። በችሎቱ ላይ ከተገኙት መካከል የገበያ ማዕከሉ ሠራተኛ የነበረው ማሊየተወለደው ሙስሊሙ ላሳን ባቲሊ አንዱ ነበር። ግለሰቡ በወቅቱ በርካታ ሸማቾን ደብቆ ከጥቃት በማትረፉ ምስጋና ተችሮታል፤ የፈረንሳይ ዜግነትም አግኝቷል። የፍርድ ሂደቱ እስከ ወርሃ ኅዳር ድረስ ሊቆይ እንደሚችል ይገመታል። ተጠርጣሪዎች ከባድ ጥበቃ እየተደረገላቸው በአንድ የመስታወት ክፍል ውስጥ ሆነው ነው ፍርዳቸውን እየተከታተሉ ያሉት። ሁሉም ተጠርጣሪዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል በማድረጋቸው ምክንያት ፊታቸው ላይ ያለውን ስሜት ማንበብ አልተቻለም። በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎች ቤተሰቦች ጥቃቱ እንዴት እንደተቀነባበረ ማወቅ ይሹ ነበር። 2015 ላይ ምን ተፈጠረ? በፈንረጆቹ 2015 ሁለቱ ወንድማማቾች ሸሪፍ እና ሰዒድ ኩዋቺ የቻርሊ ሄብዶ ጋዜጣ ቢሮን ጥሰው ገቡ። አረንጓዴ የወታደር ልብስ አድርገው የነበሩት ወንድማማቾች የጋዜጣው ሠራተኞች ላይ ጥይት ማርከፍከፍ ጀመሩ። በወቅቱ የጋዜጣው አርታኢ የነበረው ግለሰብን ጨምሮ ሌሎች አራት ሰራተኞች ወዲያው ተገደሉ። ከቆይታ በኋላ ፖሊስ ሥፍራውን ቢከብም በጥቃቱ ማብቂያ ስምንት ጋዜጠኞችና ሁለት የፖሊስ መኮንኖች መሞታቸው ይፋ ሆነ። ከቀናት በኋላ በተፈፀመ ሌላ ጥቃት ደሞ ሃይፐር ካሸር የተባለ ገበያ ውስጥ ተኩስ የከፈተው አመዲ ኩሊባሊ የተሰኘ ጂሃዲስት ሶስት ሰዎችን ገደለ። ሰውዬው ወደ ገበያው ከመምጣቱ በፊት አንድ የፖሊስ መኮንን ገድሎ ነበር። ፖሊስ ወደ ገበያው ከደረሰ በኋላ ጂሃዲስቱን ገድሎ ታግተው የነበሩ ሰዎችን አስለቀቀ። በጥቃቱ እጃቸው አለበት የተባሉ ሰዎች አብዛኛዎቹ በቁጥጥር ሥር ውለዋል።
44234796
https://www.bbc.com/amharic/44234796
ሰዎችን ከሲኖ ትራክ የገለበጠው አሽከርካሪ በቁጥጥር ስር ዋለ
ለሃይማኖታዊ ክብረ-በዓል ለማጓጓዝ በሲኖትራክ የጭነት መኪና ላይ ያሳፈራቸውን ሰዎች ለጉዳት በሚዳርግ ሁኔታ ገልብጧል የተባለው አሽከርካሪ በቁጥጥር ስር መዋሉን የፎገራ ወረዳ ፖሊስን ጠቅሶ የአማራ መገናኛ ብዙሃን ዘገበ።
በፎገራ ሰዎችን የገለበጠው ሲኖትራክ በፎገራ ወረዳ በሚገኘው የክርስቶስ ሰምራ ገዳም በየዓመቱ ግንቦት አስራ ሁለት የክርስቶስ ሰምራ በዓል በድምቀት ይከበራል። በዘንድሮው ክብረ በዓል አንድ የሲኖ ትራክ አሽከርካሪ በዓሉን ለመታደም ሄደው ወደ ቀያቸው ለመመለስ መኪናው ላይ የተሳፈሩ በርካታ ሰዎችን ሜዳ ላይ መገልበጡ ብዙዎችን በማህበራዊ ሚዲያ እያነጋገረ ይገኛል። ሰዎች እንደ አሸዋና ጠጠር የመገልበጣቸው ጉዳይ የግርምት፣ የትዝብትና ቀልድ አዘል አስተያየትም አስተናግዷል። በቀን ስራ የሚተዳደረው ጌታሰው የማታ የክርስቶስ ሰምራ ክብረ በዓል ላይ ከተገኙት አማኞች አንዱ ነው። ባለፉት ዓመታት እንደነበረው ስለታቸውን ለማድረስ ሲሉ ለአማኞች ነፃ የመጓጓዣ አገልግሎት የሚሰጡ ሰዎች ከተገኙ እሰየው፤ ካልሆነ ግን አማኞች ተሰባስበው ወደ በዓሉ ስፍራ የሚወስዳቸው መኪና ይኮናተራሉ። ካልሆነም በእግር ይጓዛሉ። "ወደ አካባቢው ለመድረስ መደበኛ መጓጓዣ የለም" የሚለው ጌታሰው በግምት አምስት ሰዓት ይፈጃል ያለውን መንገድ በተደጋጋሚ በእግሩ ተጉዟል። ጌታሰው የዘንድሮውን በዓል የተካፈለው ከወረታ ከተማ ነፃ የመጓጓዣ አገልግሎት አግኝቶ ነበር። መሄድ ብቻ ሳይሆን መመለስም አለና በዓሉ እንደተጠናቀቀ ወደ ቤታቸው ለመመለስ ከሌሎች አማኞች ጋር ሲኖ ትራክ ተሳፈሩ።ከተሳፋሪዎቹ መካከል ሴቶችና ህፃናትም ይገኙበታል። ብዙዎቹ አሽከርካሪው የጫናቸው ስለቱን ለማድረስ እንደሆነ በማመን ጉዞ ይጀምራሉ። ብዙም ሳይርቁ ግን ገዳሙ አቅራቢያ የሚገኝ ሜዳ ላይ መኪናው ቆመ። አሽከርካሪው ተሳፋሪዎች በሙሉ ሰላሳ ብር እንዲከፍሉ ይጠይቃል። ተሳፋሪዎቹ በበኩላቸው "በነፃ ነው የተሳፈርነው አንከፍልም" ሲሉ ይመልሱለታል። የተሳፋሪዎቹ እምቢታ ያስቆጣው አሽከርካሪም "ካልሆነ እገለብጣችኋለሁ" ሲል ማስፈራራት ይጀምራል። ነገሩ ያላማራቸው ተሳፋሪዎቹ "እንዳትገለብጠን፤ ከመኪናው እንወርዳለን ሲሉ" መጯጯህ ይጀምራሉ። የተወሰኑ ሰዎች ከመኪናው መዝለል ይጀምራሉ። አሽከርካሪው ግን በድንገት አሸዋና ድንጋይ እንደሚገለብጠው ሰዎቹን ሜዳው ላይ ይዘረግፋቸዋል። ከመገልበጡ በፊት ከመኪናው የዘለሉ ሰዎች ቢኖሩም አብዛኞቹ ሰዎች ተገልብጠው መሬት ላይ በመውደቃቸው ጉዳት አጋጥሟቸዋል። ጌታሰው እንደሚለው መኪናው የስለት ስለመሰላቸው ገንዘብ ለመክፈል ካለመፍቀዳቸው በላይ ገንዘብም አልነበራቸውም። አሽከርካሪው በመኪናው ሙሉ የነበሩትን ሰዎች ሲገለብጥም ጉዳት ደርሶበታል። "ቀኝ እጄ አይሰራም። መንጋጋዬም ታሟል። የቁስለት መርፌ ሰጥተውኛል። ስራ መስራትም አልቻልኩም" ሲል ያለበትን ሁኔታ ይገልጻል። በአሁን ወቅት ህክምና እየተከታተለ ሲሆን አሽከርካሪው ለፍርድ እንዲቀርብ በወረታ ከተማ ቀበሌ 4 ፖሊስ ጽህፈት ቤት አመልክቷል። የአይን እማኙ እንደሚናገረው አሽከርካሪው የመኪናውን መገልበጫ እስከ መጨረሻው ከፍ አድርጎ ሰዎቹን አራግፏል። ላለመውደቅ በመገልበጫው ጫፍ የተንጠላጠሉ ሰዎች ነበሩ። አንዳንዶቹ ደግሞ ከመኪናው ዘለው ወርደዋል። በፎገራ ወረዳ የወረታ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ባለሙያ አቶ ሀይሌ ብርሀኔ እንደሚሉት አሽከርካሪውና ተሳፋሪዎቹ ሂሳብ ክፈሉ በሚል እሰጣ ገባ ውስጥ ከገቡ በኋላ ነበር አሽከርካሪው ሰዎቹን የገለበጣቸው። "ሰዎቹን ለማስፈራራት የተጠቀመበት መንገድ ነው። እድለኛ ሆነው ነው እንጂ እንዳደረገው ነገር ሰው ሊጎዳ ይችል ነበር" ይላሉ። "የተወሰኑ ሰዎች ከመኪናው ዘለው ወርደዋል። የከፋ ጉዳት አልደረሰም። የፎገራ ወረዳ ፖሊስ ሰዎቹንና የመኪናውን ታርጋ ቁጥር እያጣራ ነው" ብለዋል። መኪናው አሸዋ የሚጫንበት እንደሆነና አሽከርካሪውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ሂደት ላይ መሆናቸውንም አክለዋል። የፎገራ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤትን ስለጉዳዩ ለመጠየቅ ያደረግነው ሙከራ ባይሳካም፤ ዘግይቶ ባገኘነው መረጃ ፖሊስ ተጠርጣሪ አሽከርካሪውንና ከባድ የጭነት መኪናውን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ ነው።
56870711
https://www.bbc.com/amharic/56870711
የደኅንነትና የፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል፡ ብሔራዊ ደኅንነትን በሚፈታተኑ ላይ የማያዳግም እርምጃ መውሰድ ተጀምሯል
የኢትዮጵያ መንግሥት የአገሪቱን ብሔራዊ ደኅንነትን በሚፈታተኑ ጉዳዮች ላይ የማያዳግም እርምጃ መውሰድ መጀመሩን የደኅንነትና የፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ።
ግብረ ኃይሉ ይህንን ያለው የአገሪቱ የጸጥታና የደኅንነት ተቋማት የጸረ-ሰላም ኃይሎችን እንቅስቃሴ እንደማይታገስ የገለጸበትን መግለጫ አርብ ምሽት ባወጣበት ጊዜ ነው። ጨምሮም "ሕዝባዊ እምቢተኝነትን በመፍጥር አገሪቱን ወደ ግጭትና ትርምስ ውስጥ ለመክተት የውስጥና የውጭ ኃይሎች ተጣምረው እንቅስቃሴዎች እያደረጉ መሆኑን የሚያመለክት በበቂ መረጃና ማስረጃ አረጋግጫለሁ" ሲል የደኅንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይሉ አስታወቋል። ይህ የደኅንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል ከአገር መከላከያ ሚኒስቴር፣ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንና ከመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ የተውጣጣ ነው። መንግሥት አግባብ በሆነ መልኩ ከማንነት፣ ከአስተዳደር ወሰንና ራስን በራስ ከማስተዳደር ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን ለመመለስ እየሠራ በሚገኝበት ወቅት እነዚህ ኃይሎች ተጣምረው አገሪቱን ወደ ትርምስ ለማስገባት ጥረት እያደረጉ ነው ብሏል። ግብረ ኃይሉ ይህን ተልዕኮ ለመፈጸም የተዘጋጁ ሰነዶችና የጥፋቱን ተዋናይ አካላትንም የሚግልጽ መረጃ በደኅንነትና በጸጥታ መዋቅሩ እጅ መግባቱንም ጠቁሟል። የቅርብ ጊዜያት ግድያ እና መፈናቀል ግብረ ኃይሉ የጥፋት ኃይሎች ሰሞኑን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች መንግሥትን ያሳዘን ሕዝብን ያስቆጣ በንጹሃን ዜጎች ላይ ሞትና መፈናቀል ፈጽመዋል ብሏል። በዚህም መግለጫው በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እና በኦሮሞ ብሔረስብ አስተዳደር አካባቢ በተፈፀሙ ጥቃቶች የንጹሃን ዜጎች ህይወት ማለፉን፣ ንብረት መውደሙን እንዲሁም በርካታ ሰዎች ከቀዬቻው መፈናቀላቸውን አውስቷል። ለዚህም ክስትት "ከውስጥና ከውጭ የተደራጁ የጥፋት ኃይሎች" ተጠያቂ ናቸው በማለት በመግለጫው ላይ ከሷል። በተጨማሪም በአማራ ክልል በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የቅማንት ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃትም የፀጥታ አካላትን ጨምሮ የንፁሃን ዜጎች ህይወት ማለፉን እና ንብረት መውደሙን መግለጫው አትቷል። ከዚህ በተጨማሪም በአፋርና በሱማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የንጹሃንን ሕይወት የቀጠፉ ግጭቶች ማጋጠማቸውን በመግለጫው ተጠቅሷል። ሕዳሴ ግድብ የግብረ ኃይሉ መግለጫ "በቅንጅት የሚሠሩት የውስጥና የውጭ ጸረ ሰላም ኃይሎች የሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በታለመለት ጊዜ እንዳይካሄድና እንዲስተጓጎል የጉሙዝ ታጣቂዎችን አሰልጥነውና አስታጥቀው በአካባቢው አሰርማርተዋል" ይላል። ይህንንም ተከትሎ የእነዚህን ኃይሎች ሴራ ለማክሸፍ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የደኅንነት ግብረ ኃይሉ መግለጫ አመልክቷል። የግብረ ኃይሉ መግለጫ የኦነግ-ሸኔ ታጣቂ ቡድን የመንግሥትን ትኩረት ለመበተን በንጹሃን ዜጎች ላይ ግድያዎችን እና ጥቃቶችን እንደሚፈጽም ገልጿል። "ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰበት ያለው የኦነግ-ሸኔ ታጣቂ ቡድንን . . . ሙሉ በሙሉ ለማስቆም በቡድኑ ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃም ተጠናክሮ መቀጠሉን የጋራ ግብረ ኃይሉ ማሳወቅ ይወዳል" ብሏል። ግብረ ኃይሉ የውስጥና የውጭ ኃይሎች የማኅበራዊ ሚዲያ አንቂዎችንና በመንግሥት መዋቅር ውስጥ የተሰገሰጉ አካላትን ጭምር በመጠቀም የአገር ሕልውናን አደጋ ላይ ለመጣል እየተረባረቡ መሆኑን ሕዝቡ ሊገነዘብ ይገባል ሲል አሳስቧል። ግብረ ኃይሉ ይህንን መግለጫ ያወጣው አገሪቱ ብሔራዊ ለማካሄድ በተዘጋጀችበት ጊዜ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ታጣቂዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት በመፈጸም ከባድ ጥፋትን ከፈጸሙ በኋላ ነው። በተለይ በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን ባለፈው ሳምንት በተፈጸመው ጥቃት አስካሁን ቁጥሩ በውል ያልተገለጸ ሰው ህይወት ያለፈ ሲሆን በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ለመፈናቀል መዳረጋቸውን የአካባቢው ባለሥልታናት ገልጸዋል። ይህንንም ተከትሎ በአማራ ክልል ውስጥ ባሉ አካባቢዎች እየተጠናቀቀ ባለው ሳምንት ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ለተከታታይ ቀናት በሚፈጸሙ ጥቃቶች በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈጸመውን ግድያ አዕተቃወሙ ነው። በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከልና ካማሺ ዞኖች፣ በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋና በኦሮሞብሔረሰብ ዞን በርካታ ሰዎችን ለህልፈት የዳረጉ ተደጋጋሚ ጥቃቶች ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ በታጣቂዎች መፈጸሙ ይታወሳል።
news-41121480
https://www.bbc.com/amharic/news-41121480
ኬንያ ድጋሚ ምርጫ እንድታካሂድ ፍርድ ቤት ወሰነ።
የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኡ ሁሩ ያሸነፉበት ያለፈው ምርጫ ተሽሮ በስድሳ ቀናት ውስጥ አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ ውሳኔ አስተላለፈ።
የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ጠቅላይ ፍርድ ምርጫው እንደገና እንዲካሄድ መወሰኑን ተከትሎ የናሳ ፓርቲ ደጋፊዎች ደስታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ። እ.አ.አ. ነሐሴ 8 2017 የተካሄደው የኬንያ ጠቅላላ እና ፕሬዚደንታዊ ምርጫ አሁሩ ኬንያታን ድጋሚ መሾሙ ይታወቃል። ነግር ግን የተቃዋሚ ፓርቲው ናሳ ዕጩ ራይላ አዲንጋ ምርጫው በኮምፕዩተር አማካኝነት ተጭበርብሯል በማለት ጉዳዩን ወደ ጠቅላይ ፍርደ በመውሰድ ከሰዋል። ጉዳዩን ለሳምንት ያህል የመረመረው የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ዛሬ መስረም 1 2017 ባሰታላለፈው ውሳኔ ምርጫው በድጋሚ እንዲካሄድ በአብላጫ ድምፅ ወስኗል። ሰባት ዳኛዎችን ያቀፈው የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አንድ ዳኛ በህመም ምክንያት መገኘት ባይችሉም አራት ለሁለት በሆነ አብላጫ ድምፅ ነው ውሳኔውን ያስተላለፈው። በውሳኔው መሰረት ኬንያ በድጋሚ በስድሳ ቀናት ውስጥ ምርጫ ማከናወን ይጠበቅባታል። ውሳኔውን ተከትሎ የተቃዋሚ ፓርቲው ናሳ ዕጩ ራይላ አዲንጋ ደጋፊዎች በርዕሰ መዲናዋ ናይሮቢ እና የአዲንጋ ደጋፊዎች ይበዙባታል በምትባለው ኪሱሙ ከተማ ደስታቸውን ሲገልፁ ተስተውለዋል።
news-53996770
https://www.bbc.com/amharic/news-53996770
የትግራይ ክልል ስደተኞቹን መቀሌ እንዲያሳርፏቸው ለሳዑዲ መንግሥት ደብዳቤ ፃፈ
በሳዑዲ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊ ስደተኞች መካከል 2 ሺዎቹን የመመለስ ስራ ከአምስት ቀናት በኋላ እንደሚጀመር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት አስታውቋል።
በእስር ቤቱ በተስፋፋው የቆዳ በሽታ ብዙዎቹ ተጠቅተዋል በአሁኑ ሰዓትም 2 ሺህ ስደተኛ ዜጎች ዝርዝር እንደተለየና የመመለሱም ስራ ከጳጉሜ ሶስት- እስከ መስከረም 26 ይከናወናል ብሏል። ከዚህም በተጨማሪ በእስር ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያንንም ቅድሚያ በመስጠት እንደሚከናወንም ተገልጿል። በተለያየ ጊዜ ስደተኞችን የመመለስ ስራ የኢትዮጵያ መንግሥት ቢሰራም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በከፍተኛ ሁኔታ ጫና እንዳሳረፈ መግለጫው ጠቁሟል። በዚህም ችግርም ውስጥ ተሁኖ 3 ሺህ 500 የሚሆኑ ስደተኞችን በመመለስ በለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲገቡ ወደመጡበት ስፍራም የመላክ ስራ ተሰርቷል ብሏል በመግለጫው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል ለሳዑዲ መንግሥት ከወር በፊት በፃፉት ደብዳቤ ዜጎቹን ከሳዑዲ አረቢያ በአየር አንስቶ ወደ መቀሌ እንዲያደርስላቸው ጠይቀዋል። ደብዳቤው የኢትዮጵያና የሳዑዲ ከጥንት ጀምሮ ያላቸውን የተሳሳረ ታሪክ እንዲሁም በትግራይ ያለውን አል ነጃሺ መስጂድ ለዚህም ማሳያ መሆኑን በመጥቀስ ትብብር ያስፈልጋል ብሏል። ለዘመናት በተለይም በደርግ አገዛዝ ወቅት በርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መሸሻ አድርገው ሳዑዲ አረቢያን እንደቆዩና ከድህነት፣ ረሃብም ሆነ የተሻለ ኑሮን የፈለጉ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሳዑዲ እንደ ሁለተኛ አገራቸው ሆና ቆይታለች ብለዋል። በቅርብ አመታትም በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከትግራይ ክልል ቀይባህርን አቋርጠው የመንን በመሻገር ወደ ሳዑዲ አረቢያ ተሻግረዋል። በአሁኑ ሰዓት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በርካታ ስደተኞች የሚያዙበት ሁኔታ እንደተቀየረ የገለፀው ደብዳቤው በርካታዎቹ ከትግራይ ክልል መሆናቸውን አስምሯል። "የኢትዮጵያ የፌደራል መንግሥት በማያሳምን መልኩ ስደተኞቹን ለመቀበል ፈቃደኛ አይደለም" ያለው ደብዳቤ ክልሉ ዜጎቹን ለመቀበል ፈቃደኛ እንደሆነም አትቷል። የሳዑዲ መንግሥት ስደተኞቹን መቀሌ በሚገኘው አሉላ አባ ነጋ አለም አቀፍ አየር መንገድ እንዲያደርሳቸውም ጠይቋል። ይህን ማድረግ የማይቻል ከሆነ ከኮሮናቫይረሰ መጠበቅ ይቻል ዘንድ የተሟላ አቅርቦት ወዳሏቸው የስደተኛ መጠለያዎች የሳዑዲ መንግሥት አንዲያስገባቸው ጠይቋል። ከሰሞኑ በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ኢ-ሰብዓዊ በሆነ ሁኔታ በእስር ቤት ታጉረው ለተለያዩ በሽታዎችና ሞቶች መዳረጋቸው አነጋጋሪ ሆኗል። ከሰሞኑ የእንግሊዙ ጋዜጣ ቴሌግራፍ ታሳሪዎቹ በስልካቸው ከላኳቸው ፎቶዎች መካከል ከመስኮት ላይ ራሱን የገደለ ግለሰብና በብርድ ልብስ የተጠቀለለ አስከሬን መታየቱ ስደተኞቹ ያሉበትን ሰቆቃ አስደንጋጭ አድርጎታል። ያሉበት መከራና ስቃይ የምድር ሲኦል የሆነባቸው እነዚህ ስደተኞች ራሳቸውን ለማጥፋት የተገደዱና በመተፋፈጋቸውም ሞተዋል ተብሏል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ስደተኞች ምግብ፣ ውሃ እጥረትና ከሰው በታች ሆነው ህይወታቸውን ለመግፋት በመገደዳቸው ስቃያቸውን ለመግለፅ ቃል አጥተዋል። በስቃይ ያሉት ሰደተኞች ለባለፉት ስድስት ወራት በዚህ መልኩ ያሳለፉ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ የሳዑዲ መንግሥት ከነመኖራቸው እንደረሳቸው በምሬት ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም አንድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተወካይ ወደ እስር ቤቱ መጥቶ እንዳናገራቸውና መንግሥት ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ጥረት እያደረገ መሆኑን ቢገልጽላቸውም ምንም ነገር ሳይሰሙ በመከራ ኑሯቸውን ለመግፋት እንደተገደዱ ቢቢሲ ያናገራቸው ነዋሪዎች ገልፀዋል። ከሰው በታች በሆነ ሁኔታ ስደተኞቹ መያዛቸው በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ዘንድ ውግዘትን ፈጥሯል ከሳዑዲ መንግሥት በኩል በመንግሥት በሚተዳደሩት እስር ቤቶች ውስጥ በሙሉ ስላለው ሁኔታ ምርመራ" እያደረገ መሆኑን ገልጾ "በእርግጥም አስፈላጊው ነገሮች የተጓደለ ሆኖ ከተገኘ የማስተካከያ እርምጃ ይወሰዳል" ሲል ገልጿል። ሚኒስቴሩ በበኩሉ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የትኛውም አገር ያሉ ስደተኛ ዜጎቹን አልቀበልም ብላ እንደማታውቅና ነገር ግን አቀባበሉ አስፈላጊውን አቅምን በተከተለ መርህ ነው ብሏል። በባለፉት ሶስት አመታትም ከ40 ሺ በላይ ዜጎቿን ከሳኡዲ አረቢያ እንደተቀበለችም ለዚህም ማሳያ ነው ነው ብሏል። ስደተኞቹን ለመመለስ የተለያዩ ተቋማትና ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በመጣመር የስደተኞቹን ማንነት የመለየት፣ ዜግነትን የማረጋጋጥ፣ ትራንስፖርትን ጨምሮ ከተመለሱም በኋላ የስነ ልቦና ድጋፍ፣ ራሳቸውን ማስቻልና ከህብረተሰቡ ጋር የመቀላለቀል ስራም አስፈላጊነቱን አስምሯል። በቤይሩት ከተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት በመስራቷ አገሪቷ ውጤታማ መሆኗን የጠቀሰው መግለጫው በአሁኑ ሰዓትም በየመን ከተባበሩት መንግሥታት ጋር እንዲሁም ከሳኡዲ መንግሥት ጋር እየሰሩ መሆኑን አስፍሯል። በተለይም ከየመን ድንበር ተሻግረው ወደ ሳዑዲ አረቢያ በህገወጥ አዘዋዋሪዎች መንገድ ከፍተኛ ገፈት እየቀመሱ ሲሆን ቁጥሩም በከፍተኛ ሁኔታ ቢጨምርም ሳዑዲ እነዚህን ስደተኞችን ከመቀበል ችላ እንዳላለችና የኢትዮጵያ መንግሥት ለዚህ ምስጋናውን ችሯል። በሳዑዲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ልዑክም እነዚህን እስር ቤቶች ሁኔታ የሚጎበኝና የሚቆጣጠሩ ሰራተኞች በቋሚነት እንዳሰማራ ጠቅሷል። የሰዎች ህገ ወጥ ዝውውርና መመለስ የተወሳሰበ ሂደት ከመሆኑ አንፃር ስደተኞችን መመለስ ብቻ ሳይሆን ደህንነታቸው በተጠበቀ መልኩ መሆኑ፣ ዘላቂ በሆነ ሁኔታ በአገር ውስጥ የሚኖሩበትንና ከህዝቡ ጋር ተመልሰው የሚቋቋሙበት መንገድ መፈለግ እንደሚያስፈልግም አስምሯል። ስደተኞችን ወደ አገር ቤት የመመለሱ ሥራው የተለያዩ የፌደራል ሚንስቴር መስሪያ ቤቶችን፣ ኤምባሲዎችን እና የክልል ቢሮዎችን በቅንጅት የሚሰሩት ነው ብሏል።
news-44473437
https://www.bbc.com/amharic/news-44473437
በሲዳማ የዘመን አቆጣጠር 2011 ጀመረ
የሲዳማ ብሄር የዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምበላላ በዓል በዚህ ሳምንት በሃዋሳ ከተማ በተለያዩ በደማቅ ሥነ-ሥርዓቶች ተከብሯል። ከሁሉም የሲዳማ ዞን ወረዳዎች የተውጣጡ የሃገር ሽማግሌዎች፣ የአካባቢው ተወላጆች እንዲሁም የተለያዩ ቱሪስቶች በዓሉን ታድመዋል።
ቢቢሲ ያነጋገረው የአካባቢው ተወላጅ እና ጋዜጠኛ አለሙ አመዬ፤ ''ይህ የዘመን አቆጣጠረር የሲዳማ ብሄረሰብ የፀሃይ፣ የጨረቃ እና የከዋክብት የተፈጥሮ ኡደትን እያሰላ ዘመን የሚቆጥርበት ጥበብ ነው''ይላል። የሃገር ሽማግሌዎች ''አያንቱዎች'' ሲሆኑ የበዓሉን ቀን የሚቆጥሩት፤ ከእሮብ ጀምሮ በሲዳማ ብሄር አቆጣጠር 2011 ዓ.ም ነው። ሁሉም ሰው በተለይ በሃገር ሽማግሌዎቹ ቤት ከበዓሉ አንድ ቀን በፊት ተሰባስቦ በዓሉን ማክበር ይጀምራል ይላል አለሙ። ለበዓሉ ድምቀትም ''ቡርሻሌ'' የሚባል ከቆጮ እና ከወተት የሚሰራ የአካባቢው ልዩ ባህላዊ ምግብ ይቀርባል። የሲዳማ ብሄረሰብ የዘመን መቀበያ ከመሆኑም ባሻገር፤ ዘመዳሞች የሚጠያየቁበት፣ የተጣሉ ሰዎች የሚታረቁበት እንዲሁም ሃገር በቀል እውቀቶች ለተተኪው ትውልድ የሚተላለፍበት ትልቅ በዓል እንደሆነ አለሙ ይናገራል። ከበዓሉ በፊት ምንም አይነት ሥጋ ማንኛውም ሰው አይመገብም። ምክንያቱም በዓሉ የፍቅር ማሳያ ስለሆነ የቤት እንስሳት አይነኩም፤ ዛፍም ቢሆን አይቆረጥም ሲል ያስረዳል አለሙ። በዓሉ በዚሁ የሚያበቃ አይደለም የሚለው አለሙ፤ በሃያ ሦስቱም የሲዳማ ወረዳዎች ከሁለት እስከ ሦስት ሳምንት ያህል ጊዜ በደማቅ ሥርዓት እና በተለያዩ ሃገረሰባዊ ጭፈራዎች እንደሚከበር ይገልጻል። የማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶችን በዋነኛነት የሚመዘግበው የዩኔስኮ በይነ-መንግሥታዊ ኮሚቴ ከህዳር 20 እስከ 24 2008 በናሚቢያ መዲና ዊንድሆክ ባደረገው 10ኛ ስብሰባው፤ ለውሳኔ ከቀረቡለት 35 ባህላዊ ቅርሶች መካከል የሲዳማ ብሄር የዘመን መለወጫ የሆነውን ፍቼ ጫምባላላን የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ ብሎ መዝግቦታል። ፍቼ ጫምባላላ የሲዳማ ህዝብ የአዲስ ዓመት በዓል ብቻ ሳይሆን፤ በዓሉ በሚከበርበት ወቅት የሀገር ሽማግሌዎች ለተተኪዉ ትውልድ ስለ ሥራ ክቡርነት እና ተግባብቶ፣ ተከባብሮ አብሮ መኖርን የሚያስተምሩበት መድረክ መሆኑን የ«ዩኔስኮ» ጋዜጣዊ መግለጫ አስቀምጧል።
news-52409795
https://www.bbc.com/amharic/news-52409795
ኮሮናቫይረስ፡ ተስፋ የተጣለበት የኮሮናቫይረስ ክትባት በሰው ላይ ሙከራው ተጀመረ
የመጀመሪያው በሰው ላይ የሚደረግ የኮሮናቫይረስ ክትባት አውሮፓ ውስጥ ተጀምሯል።
ኦክስፎርድ ውስጥ የተጀመረው ይህ ሙከራ በሁለት በጎ ፈቃደኞች ላይ ይጀመር እንጂ 800 ሰዎች ይሳተፉበታል። ከ800 በጎ ፈቃደኞች መካከል ግማሹ የኮሮናቫይረስ ክትባት እንደሚሰጣቸው ሲነገር የተቀሩት ደግሞ የማጅራት ገትር መከላከይ ይሰጣቸዋል ተብሏል። ነገር ግን በጎ ፈቃደኞቹ የትኛውን ክትባት እንደወሰዱ አይነገራቸውም። ክትባቱ በኦክስፎርድ ዩነቨርሲቲ ባለሙያዎች በሦስት ወራት የበለፀገ ነው። ምርምሩን የመሩት ፕሮፌሰር ሳራህ ጊልበርት በክትባቱ ከፍተኛ የራስ መተማመን እንዳላቸው ይናገራሉ። "እርግጥ ነው ሰዎች ላይ መሞከር አለብን። በትክክል መሥራቱንም ማረጋገጥ ይኖርብናል። አልፎም ሰዎች በኮሮናቫይረስ መልሰው አለመያዛቸውን ማረጋገጥ ግድ ይላል። ከዚያ በኋላ ነው ወደ ሕዝብ ሊሠራጭ የሚችለው።" ወደ ሰው እንዳይተላለፍ የተደረገው ይህ ክትባት ከቺምፓንዚ ከተገኘ ደካማ ጉንፋን የተሠራ ነው። የምርምር ቡድኑ ከዚህ በፊት ሜርስ የተሰኘ ሌላ ዓይነት ኮሮናቫይረስን የሚከላከል መድኃኒት ሠርቶ ውጤታማ ሆኗል። ክትባቱ እንደሚሠራ የሚታወቀው ሙከራ ከተደረገባቸው ሰዎች ምን ያክሉ ላይ ውጤታማ ሆኗል የሚለው ሲለይ ነው። ነገር ግን ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ከመጣ ሙከራ የሚደርግባቸው ሰዎች ቁጥር ሊቀንስ ይችላል። የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር አንድሪው ፖላርድ ሙከራውን ለማጣደፍ እየተሯሯጡ እንደሆነ ይናገራሉ። በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት 5 ሺህ ሰዎች ላይ ሙከራው እንደሚቀጥልና ሙከራ የሚደርግባቸው ሰዎች የዕድሜ ገደብ እንደማይኖረው ታውቋል። ቢሆንም ዕድሜያቸው የገፋ ሰዎች የመከላከል አቅማቸው የደከመ ስለሆነ ተጨማሪ ምርመራ ይደርግባቸዋል። የኦክስፎርድ ተመራማሪዎች ከአውሮፓ አልፎ አፍሪካ ውስጥም የክትባት ሙከራ የማድረግ ሐሳብ አላቸው። የመጀመሪያዋ ሃገር ደግሞ ኬንያ ልትሆን ትችላለች። ምንም እንኳ በጎ ፈቃደኞችን ሆን ብሎ ኮሮናቫይረስ በማስያዝ እነሱ ላይ ክትባቱ ይሥራ አይሥራ መሞከር ቢቻልም ይህ የሙያውን ሥነ-ምግባር የሚፃረር ነው። ነገር ግን ክትባቱ ውጤታማነቱ አስተማማኝ የሚባል ደረጃ ላይ ከደረሰ ይህንን ማድረግ እንደሚጀምሩ ፕሮፌሰር አንድሪው ያስረዳሉ። ክትባቱ ከፍተኛ ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ እየተሞከረ እንደሆነ ፕሮፌሰሩ ማስመር ይፈልጋሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ. . . በሌላ በኩል ተስፋ ተጥሎበት የነበረ አንድ መድኃኒት በመጀመሪያ የክሊኒክ ሙከራው እንደከሸፈ የዓለም ጤና ድርጅት በስህተት ያተመው አንድ ዕትም አሳብቋል። መድኃኒቱ ቻይና ውስጥ ሲሆን የተሞከረው እንደታሰበው የተሞከረባቸውን ሰዎች የመከላከል አቅም ማሳደግ አልቻለም። ቢሆንም መድኃኒቱን የሠራው የአሜሪካ ድርጅት በስህተት የታተመው መረጃ ጥናቱን አልተረዳውም ይላል። የዓለም ጤና ድርጅት መረጃውን ከድረ-ገፁ ላይ አውርዶታል። መረጃው የተሟላ ስላልሆነ ነው ያወርድኩትም ሲል ማብራሪያ ሰጥቷል።
news-53922806
https://www.bbc.com/amharic/news-53922806
አውስትራሊያ፡ ለምን የአሥር ዓመት ታዳጊዎች ይታሰራሉ?
አውስትራሊያ ውስጥ በወንጀል ለመጠየቅ ትንሹ እድሜ ዓሥር ነው። ጠበቆች፣ ሐኪሞች እንዲሁም የአቦርጂናል መብት ተሟጋቾች ይህ ሕግ እንዲቀየር ንቅናቄ እያደረጉ ይገኛሉ።
ንቅናቄው በወንጀል ለመጠየቅ ትንሹ እድሜ 14 መሆን አለበት ይላል። ባለፈው ወር የአገሪቱ ከፍተኛ ሕግ አውጪዎች ጉዳዩን በተመከተ ውሳኔ ላይ ለመድረስ እስከ ቀጣዩ ዓመት ጊዜ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። በሌላ በኩል የአውስትራሊያ መዲና አስተዳደር (አውስትራሊያን ካፒታል ቴሪቶሪ) ትንሹ በወንጀል መጠየቂያ እድሜ 14 እንዲሆን ወስኗል። የተቀሩት የአገሪቱ ግዛቶችም ተመሳሳይ ውሳኔ ላይ እንዲደርሱ የንቅናቄው መሪዎች ይፈልጋሉ። ትንሹ በወንጀል መጠየቂያ እድሜ ዓሥር መሆኑ ለምን ተቃውሞ አስነሳ? ከብዙ አገሮች አንጻር አውስትራሊያ ሰዎችን በወንጀል ተጠያቂ የምታደርግበት እድሜ ትንሽ ነው። የዓሥር ዓመት ልጅ በቁጥጥር ስር ሊውል፣ ፍርድ ቤት ሊቀርብ ወይም ሊታሰርም ይችላል። ጀርመንን እንደ ማነጻጸሪያ ብንወስድ አንድ ሰው በወንጀል የሚጠየቅበት ትንሹ እድሜ 14 ነው። ፖርቹጋል ውስጥ 16፣ ላክሰምበርግ ውስጥ ደግሞ 18 ነው። በሌላ በኩል ኢንግላንድ እና ዌልስ ውስጥ ትንሹ በወንጀል መጠየቂያ እድሜ 10 ነው። የተባበሩት መንግሥታት አምና ባወጣው መርህ መሠረት ትንሹ በወንጀል መጠየቂያ እድሜ 14 መሆን አለበት። በአውስትራሊያው ሕግ የበለጠ ተጎጂ የሆኑት ቀደምት ማኅበረሰቦች ናቸው። አንድ ጥናት እንደሚያሳየው፤ እአአ ከ2018 እስከ 2019 ባሉት ዓመታት ከ10 እስከ 13 ዓመት የሆናቸው 600 ልጆች ማረሚያ ቤት ይገኛሉ። ከነዚህ 65 በመቶው ቀደምት ማኅበረሰቦቹ አቦርጂናሎች እና ቶረስ ስታሪት አይላንደሮች ናቸው። ከመላው አውስትራሊያ ቀደምት ማኅበረሰቦች 3 በመቶ ብቻ ናቸው። አንድ ጥናት እንደሚያሳየው፤ የቀደምት ማኅበረሰብ ልጆች የመታሰር እድላቸው ከተቀሩት አውስትራሊያውያን 17 በመቶ ይጨምራል። በአገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ይህ ቁጥር 43 በመቶ ነው። ‘ብላክ ላይቭስ ማተር’ ሕዝቡን አነሳስቷል አውስትራሊያ ሕጓን እንድትቀይር ለዓመታት ሲጠየቅ ነበር። ሰኔ ላይ ‘ሬይዝ ዘ ኤጅ’ ወይም እድሜውን ከፍ አድርጉት የሚል ንቅናቄ ተጀምሮ ነበር። በአሜሪካ ለጥቁሮች መብት የሚሟገተው ‘ብላክ ላይቭስ ማተር’ ከአሜሪካ አልፎ በበርካታ አገራት ያሉ ትግሎችን አቀጣጥሏል። አውስትራሊያ ውስጥ በቁጥጥር ስር የዋሉ ጥቁሮች ሞትና የዘር መድልዎን የተመለከቱ ተቃውሞዎችም እንደ አዲስ ተነሳስተዋል። በአገሪቱ የተሰራ ጥናት እንደሚያሳየው በርካታ አውስትራሊያውያን ሕጉ እንዲሻሻል ይፈልጋሉ። ባለፈው ዓመት የ12 ዓመት አቦርጂናል ለተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ክንፍ ንግግር ካደረገ በኋላ ዓለም ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቷል። ዱጃን ሆሳን የተባለው ታዳጊ ጄኔቫ ውስጥ “ትልልቅ ሰዎች የ10 ዓመት ታዳጊዎችን ማሰር እንዲያቆሙ እፈልጋለሁ” ሲል ንግግር አድርጓል። አቦርጂናሎችን ያማከለ የትምህርት ሥርዓት ቢዘረጋ፤ ታዳጊዎችን ከመታሰር እንደሚታደግም ተናግሯል። ልጆችን ማሰር የወንጀል መጠንን እንደማይቀንስ የሕግ ባለሙያዎች ይናገራሉ። በልጅነታቸው የሚታሰሩ ልጆች ለወደፊትም በማረሚያ ቤት ሕይወታቸውን የማሳለፍ እድላቸው ሰፊ እንደሆነም ያክላሉ። የአውስትራሊያ የሕክምና ባለሙያዎች ከጤና አንጻር ሰዎች በወንጀል የሚጠየቁበት እድሜ ከፍ እንዲል ይፈልጋሉ። ልጆች ሊታሰሩ ሳይሆን የህክምና ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚገባም ባለሙያዎቹ ያመለክታሉ። ሕግ አውጪዎች እስካሁን ውሳኔ ላይ አልደረሱም ዓቃቤ ሕግ ጉዳዩን በተመለከተ የደረሰበትን ውሳኔ ባለፈው ወር ያሳውቃል ተብሎ ሲጠበቅ ነበር። ነገር ግን ውሳኔው የሚገለጽበት ወቅት ተራዝሟል። ዓቃቤ ሕግ ማርክ ስፒክማን ባለፈው ወር ለጋዜጠኞች “በወንጀል መጠየቂያ ትንሹ እድሜን ከፍ ማድረግ ወይም አለማድረግ የመርህ ጉዳይ ነው። እድሜው ከፍ ካለ ግን አማራጭ መቀመጥ አለበት” ብለዋል። ልጆች ወንጀል ሲፈጽሙ በምን መንገድ ሁኔታውን መቆጣጠር እንደሚቻል አማራጭ መቀመጥ አለበት ይላሉ ዓቃቤ ሕጉ። የመብት ተሟጋቾች በበኩላቸው ልጆችን ከማሰር ውጪ ብዙ አማራጮች አሉ ሲሉ ይከራከራሉ። ቀደምት ማኅበረሰቦች እንደ መፍትሔ የሚያስቀምጡት ሕብረተሰቡን ያማከለ ንግግርን ነው። ከመጠጥና አደንዛዥ እፅ ጋር በተያያዘ ችግር የሚገጥማቸው ልጆችና ቤተሰቦቻቸው የሥነ ልቦና ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው የሚናገሩም አሉ። የመብት ተሟጋቾች ድጋፍ እያገኙ መምጣታቸው ሕጉ እንዲቀየር ያግዛል ብለው ያምናሉ። የወንጀል ነክ ጉዳዮች መምህሩ ክሪስ ከነን፤ “ዘረኝነትን ለማስወገድና ፍትሕ እንዲሰፍን ሰዎች በወንጀል የሚጠየቁበት እድሜ ከፍ ማለት አለበት” ብለዋል።
news-52689882
https://www.bbc.com/amharic/news-52689882
ትራምፕ፤ ኦባማ የሾሟቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና መርማሪ ስቲቭ ሊኒክን አባረሩ
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና መርማሪ የሆኑት ስቲቭ ሊኒክ በዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከተባረሩ በርካታ ከፍተኛ የመንግሥት ሠራተኞች አንዱ ሆነዋል።
ፕሬዝደንት ትራምፕ፤ ስቲቭ ሊኒክ በራስ መተማመናቸውን አጥተዋል፤ በሚቀጥሉት 30 ቀናት ሥራቸውን ይለቃሉ ብለዋል። ዋና መርማሪ ሊኒክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማይክ ፓምፔዮን ሥልጣናቸውን ያለአግባብ ተጠቅመዋል በሚል እየመረመሯቸው ነበር። ዴሞክራቶች፤ ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደራቸው የሚፈፅመውን አግባብነት የሌለው ተግባር የሚጠይቁ ሰዎችን እያባረሩ ነው ሲሉ ይተቻሉ። ዶናልትድ ትራምፕ፤ ለዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ዴሞክራቷ ናንሲ ፔሎሲ በላኩት ደብዳቤ 'ምንም እንኳ ዋና መርማሪ መሾሙ ቅር ባይለኝም፤ በመርማሪው ላይ ያለኝ በራስ መተማመን ቀንሷል' ሲሉ ምክንያታቸውን አስቀምጠዋል። መርማሪው በማይክ ፖምፔዮ ላይ ምርመራ መጀመራቸው የታወቀው ከሥራቸው እንደተባረሩ ከተነገረ በኋላ ነው። 'ይህ ፕሬዝደንቱ ከታማኝ አገልጋዮቻቸው መካከል አንዱ የሆነቱት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላይ ምርመራ በመከፈቱ ሆነ ብለው ያደረጉት ነገር ነው' ይላሉ ዴሞክራቱ ኤሊየት ኤንጅል። ዴሞክራቱ ኤሊየት፤ ማይክ ፖምፔዮ ላይ የተከፈተው ክስ ዝርዝር ምን እንደሆነ ከመናገር ተቆጥበዋል። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የኮንገግረሱ አማካሪዎች፤ ፖምፔዮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሠራተኞችን ለግል ሥራቸው አዘዋቸዋል የሚል ክስ ቀርቦ መርማሪ ሊኒክ ይህንን ሲመለከቱ ነበር ይላሉ። የሕግ ባለሙያው ሊኒክ በቀድሞው ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ሲሆን የተሾሙት፤ ኃላፊነታቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት አግባብነት የሌለው ተግባር ሲፈፅም ማጋለጥ እንዲሁም አላስፈላጊ ወጪዎችን መመዝገብ ነበር። አፈ-ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ፤ ሰውዬው ኃላፊነታቸውን በሕጉ መሠረት እየተወጡ የነበሩ ናቸው። ሕገ-መንግሥቱን በመጠበቃቸው ነው የተቀጡት ሲሉ የትራምፕን ውሳኔ ነቅፈዋል። አልፎም ፕሬዝደንቱ ኃላፊነታቸውን በሕጉ መሠረት እየተወጠ ያሉ የመንግሥት ሠራተኞችን ከማባረር እንዲቆጠቡ አሳስበዋል። ሌሎችም ዴሞክራቶች የሰውዬው መባረር እንዳላስደሰታቸው እየገለፁ ይገኛሉ። ትራምፕ፤ ባለፈው ወር የደኅንነት ኮሚቴውን መርማሪ ሚካኤል አትኪንሰንን ማበረራቸው አይዘነጋም።
news-45597872
https://www.bbc.com/amharic/news-45597872
ትራምፕ ስፔን ሰሃራ በረሃ ላይ አጥር እንድትገነባ መከሩ
በአውሮፓ ላጋጠመው የስደተኞች ቀውስ የሰሃራ በረሃን የሚያካልል አጥር መገንባት መፍትሄ ነው ሲሉ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ለስፔን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር መምከራቸው ተነገረ።
ስፔን በአንድ ግዛቷ ድንበር ላይ ስደተኞቸን ለመከላከል የገነባችው አጥር የቀድሞው የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት የነበሩትና አሁን የስፔን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ጆሴፍ ቦሬል ግን ትራም በሰጧቸው ምክር እንዳልተስማሙ ገልፀዋል። ሚኒስትሩ ይህን ምክር ከትራምፕ የሰሙት ባለፈው ሰኔ ወር ላይ በአሜሪካ ባደረጉት ጉብኝት ወቅት ነበር። • የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችና ወላጆቻቸው ስጋት • በበእርጥብ ሳርና ቅጠል ጥቃትን ያስቆሙ አባቶች ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለምርጫ በሚወዳደሩበት ጊዜ በሜክሲኮና በሃገራቸው መካከል ግንብ እንደሚገነቡ የገቡት ቃል በተለይ የሚታወቁበት የቅስቀሳቸው ዋና ጉዳይ ነበር። የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቦሬል ይህን ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር የነበራቸውን ውይይት ይፋ ያደረጉት በዚህ ሳምንት ማድሪድ ውስጥ በተካሄደ የምሳ ግብዣ ላይ ሲሆን፤ የስፔን የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤትም ይህንኑ ለቢቢሲ አረጋግጠወል። ትራምፕ "ከሰሃራ ጋር የሚያዋስናችሁ ድንበር ርዝመት እኛን ከሜክሲኮ ጋር ከሚያዋስነን ድንበር የሚበልጥ ሊሆን አይችልም" ማለታቸውን ቦሬል ጠቅሰዋል። አሜሪካንን ከሜክሲኮ ጋር የሚያዋስናት ድንበር ርዝመቱ 1954 ማይሎች ሲሆን የሰሃራ በረሃ ግን 3ሺህ ማይሎችን ይረዝማል። • ትራምፕ፡ የኢራን የኑክሊዬር ስምምነትን አቋርጣለሁ • ልባችን ከእድሜያችን ቀድሞ ሊያረጅ እንደሚችል ያውቃሉ? ስፔን ከሰሃራ በረሃ ጋር የሚያገናኝ ግዛት የሌላት ቢሆንም በሰሜን አፍሪካ የባሕር ዳርቻ አካባቢ በአወዛጋቢ የሽቦ አጥር ከሞሮኮ ተለይተው የሚገኙ ሁለት ትንንሽ ግዛቶች አሏት። እነዚህ ግዛቶችም ግጭቶችንና ጭቆናን በመሸሽ የተሻለ ህይወት ፍለጋ ወደ አውሮፓ ለመሻገር ለሚፈልጉ አፍሪካዊያን ስደተኞች ተመራጭ ስፍራዎች ሆነው ቆይተዋል። ከባለፈው ዓመት ጥር ወር አንስቶም ቢያንስ 35 ሺህ የሚሆኑ ሰነድ የሌላቸው ስደተኞች ወደ ስፔን የገቡ ሲሆን ይህም ከየትኛውም አውሮፓዊ ሃገር በላቀ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ስደተኛ የተቀበለች ሃገር ያደርጋታል።
news-54752425
https://www.bbc.com/amharic/news-54752425
በኬንያው የገበያ ማዕከል የሽብር ጥቃት ሁለት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ
በኬንያዋ መዲና ናይሮቢ የሚገኘው ዌስት ጌት የገበያ ማዕከል ላይ ጥቃት ፈፅመዋል በሚል በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ከነበሩት መካከል ሁለቱ በ18ና 33 አመት እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ወስኗል።
እስር የተበየነባቸው ግለሰቦች መሃመድ አህመድ አብዲና ሁሴን ሃሰን ሙስጠፋ ሲሆኑ የሽብር ተግባሩን በማቀነባበር እንዲሁም ለጥቃት አድራሾቹ ድጋፍ ሰጥተዋል በሚል ክስ ነው። በአልሻባብ ደረሰ በተባለው በዚህ ጥቃት ቢያንስ 67 ሰዎች ሞተዋል ተብሏል። ጥቃቱ የደረሰው በጎሮጎሳውያኑ 2013 ነው። የሽብር ጥቃቱን በዋነኝነት የፈፀሙት አራቱ ታጣቂዎች በመገበያያ ማዕከሉ ፍርስራሽ ተገድለው እንደተገኙ የኬንያ መንግሥት አሳውቋል። በዌስት ጌት የመገበያያ ማእከል በደረሰው ጥቃት ታጣቂዎች በሸማቾች ላይ ተኩስ የከፈቱ ሲሆን፤ ለአራት ቀናት ያህልም ቆይቷል። በዚህም ቢያንስ 62 ንፁሃን ዜጎች፣አምስት ፖሊሶችና አራት ታጣቂዎች ተገድለዋል። በሽብር ጥቃቱ ተጠርጥሮ የነበረው ሌላኛው ግለሰብ ፍርድ ቤት በነፃ ቢያሰናብተውም ባልታወቁ ታጣቂዎች መታገቱ ተሰምቷል። ሊባን አብዱላሂ ኦማር የተባለው ግለሰብ በዚህ ሽብር ጥቃት እጁ የለበትም ብሎ ፍርድ ቤቱ ከሶስት ሳምንታት በፊት በነፃ ቢያሰናብተውም ያለበት አይታወቅም። ወንድሙ የሽብር ጥቃቱን ካደረሱት መካከል አንዱ ነው የተባለ ሲሆን በወቅቱም በፖሊስ ተገድሏል። የሶማሌ ስደተኛ የሆነው ሊባን የታገተውም ከፖሊስ ፀረ-ሽብር ቢሮ ሲወጣ መሆኑንም የእስልምና እምነት ተከታዮች የሰብዓዊ መብት ላይ የሚሰራ መንግሥታዊ ድርጅት ዳይሬክተር ኬሌፍ ካሊፋ ለቢቢሲ አሳውቀዋል፥ ታስሮበት ከነበረው ካማቲ እስር ቤትም ከተለቀቀ በኋላም ፀረ-ሽብር ቢሮው የሄደው መጨረስ ያለበትን ጉዳዮችም ለማጠናቀቅ ነው ተብሏል። ያገቱት ግለሰቦችን ማንነት በተመለከተ ማንም አስተያየት ከመስጠት ቢቆጠብም በጠራራ ፀሃይና በቀን እንዲህ ታጥቀው ሊባንን ሊያግቱት የሚችሉት ከፖሊስ ፀረ-ሽብር ቢሮ ጋር ግንኙነት ያላቸው እንደሆኑ በርካቶች እየተናገሩ ነው። በሽብር ተጠርጥረው ፍርድ ቤት በነፃ ያሰናበታቸው ግለሰቦች አብዛኛውን ጊዜ ደብዛቸው ይጠፋል ወይም ተገድለው ይገኛሉ። በግድያቸውም ሆነ በመጥፋታቸው ተጠያቂ የሚሆን አካልም የለም። ሶማሊያ መሰረቴ ነው የሚለው አልሸባብ በርካታ ጥቃቶችን በኬንያ አድርሷል። ኬንያ ሽብርተኝነትን እዋጋለሁ በሚል ወታደሮቿን በሶማሊያ አሰማርታለች።
news-52226209
https://www.bbc.com/amharic/news-52226209
በድህረ-ኮሮና ዘመን በዓለም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ድሃ ይሆናሉ
የዚህ ቫይረስ ምጣኔ ሀብታዊ ጉዳት ገና ተሰፍሮ አላለቀም፡፡ የተባበሩት መንግሥት ድርጅት ባወጣው አንድ ሪፖርት እንዳለው ቢያንስ ግማሽ ቢሊዮን ሰዎች ወደ ድህነት ይወረወራሉ፡፡
የኢንዶኔዥያ አርሶ አደሮች ይህ ማለት ድህነት በዓለም ላይ በዚህ ደረጃ ሲጨምር ከ30 ዓመት በኋላ ይህ የመጀመርያው ይሆናል፡፡ ይህ አስደንጋጭ ሪፖርት የወጣው የዓለም ባንክ፣ የዓለማቀፉ የገንዘብ ፈንድ እና የጂ-20 ብልጹግ አገራት ሚኒስትሮች በአንድ ተሰብስበው ለመምከር ሳምንት ሲቀራቸው ነው፡፡ የአውስትራሊ ናሽናል ዩኒቨርስቲ ተመራማሪ ክሪስቶፈር ሆሊ እንደሚሉት ኮቪድ-19 ከሚያመጣው የጤና ቀውስ የበለጠ የምጣኔ ቀውስ ይከሰታል፡፡ ይህ ጥንቅር በዓለም ከ4መቶ እስከ 6መቶ ሚሊዮን ሰዎች ሙልጭ ያለ ድህነትን ይቀላቀላሉ ይላል፡፡ • በሽታውን ለመግታት ከዚህም በላይ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚችል ተገለጸ • ኮሮናቫይረስን ለመቆጣጠር የፈጠራ ሥራዎቹን ያበረከተው ወጣት ይህም ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዘላቂ የልማት ግብ ደንቃራ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ይህ ዘላቂ የልማት ግብ በ2030 ድህነትን ለማጥፋት ያለመ ነበር፡፡ ‹‹የምርምር ውጤታችን እንደሚያሳየው በታዳጊ አገራት በአስቸኳይና በአስደናቂ ፍጥነት የድህነት ሴፍትኔት ካልተዘረጋ ኋላ ጉድ ነው የሚፈላው›› ይላሉ የኪንግስ ኮሌጅ ባልደረባ ፐሮፌሰር አንዲ ሰምነር፡፡ ይህ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የሚገድለውን ገድሎ፣ የሚያጠፋውን ጥፋት አድርሶ ዓለም ወደ ተለመደው የኑሮ ምህዋሯ ስትመለስ 7.8 ቢሊዮን የሚገመተው የዓለም ሕዝብ ግማሹ እልም ወዳለ ድህነት እንደሚገባ ጥናቱ ይተነብያል፡፡ ከዚህ ውስጥ 40 ከመቶው አዲስ ድህ ቤቱ በምሥራቅ ኢሲያና ፓስፊክ ሲሆን አንድ ሦስተኛው ደግሞ በሰሀራ በታች በሚገኙ አገራትና በደቡብ ኢሲያ ይሆናል፡፡ በዚህ ሳምንት መጨረሻ 100 የሚሆኑ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች የድሀ አገራት እዳ በአስቸኳይ እንዲሰረዝ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡ ይህም በድምሩ 25 ቢሊዮን ዶላር ይጠጋል፡፡
52672622
https://www.bbc.com/amharic/52672622
ኮሮናቫይረስ፡ 47 ሚሊዮን ሴቶች የወሊድ መቆጣጠሪያ ላያገኙ ይችላሉ-የተባበሩት መንግሥታት
በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በአስር ሚሊየኖች የሚቆጠሩ ሴቶች የእርግዝና መከላከያ ላያገኙ እንደሚችሉና በዚህም የተነሳ ያልታቀደ እርግዝና ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል የተባበሩት መንግሥታት ሥነ ሕዝብ ፈንድ (ዩኤንኤፍፒኤ) አስታወቀ።
" በ114 ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገራት የሚገኙ 47 ሚሊዮን ሴቶች የወሊድ መቆጣጠሪያ ላያገኙ ይችላሉ" ይላል የድርጅቱ ሪፖርት። " አገራት የሚጥሉት የእንቅስቃሴ ገደብ ለስድስት ወራት ከቀጠለ 7 ሚሊዮን ያልታቀደ እርግዝና ሊከሰት ይችላል፤ መሰረታዊ የጤና አገልግሎትም ይስተጓጎላል። የእንቅስቃሴ ገደቡ ለሚቀጥልበት እያንዳንዱ ሶስት ወራትም ተጨማሪ ሁለት ሚሊዮን ሴቶች የወሊድ መቆጣጠሪያ ላይጠቀሙ ይችላሉ" ይላል ሪፖርቱ በተጨማሪ። • ኮሮናቫይረስና ጫት ቃሚዎች • የማሽተትና የመቅመስ ስሜቷን ያጣችው ሼፍ ይህ ደግሞ እንደ ፊሊፒንስ ባሉ ጽንስ ማቋረጥ ወንጀል በሆነባቸው እና በማህበረሰብ የጤና ማዕከላት እና የቤት ለቤት የጤና ፕሮግራሞች ላይ በሚሰጡ የወሊድ መቆጣጠሪያ አቅርቦቶች ላይ ለተደገፉ ሴቶች አሳሳቢ ነው። "በፊሊፒንስ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ወደ 1.2 ሚሊየን ሴቶች ያልታቀደ እርግዝና ሊገጥማቸው ይችላል" ያሉት በፊሊፒንስ የተባበሩት መንግሥታት ተወካይ ዶ/ር ጆሴፍ ሲንጊህ ናቸው። አክለውም ይህ የከፋው ግምት ሲሆን በዚህ ዓመት በተከሰተው ወረርሽኝ ምክንያት የወሊድ መቆጣጠሪያ አቅርቦት በግማሽ ከቀነሰ የሚከሰት ነው ብለዋል። ያልታቀደ እርግዝና ከነርሶች፣ አዋላጆች እንዲሁም በድንገተኛ ጊዜ እንክብካቤ ጉድለት ጋር ተያይዞ የእናቶች ሞትን ሊያስከትል እንደሚችል ቡድኑ ጨምሮ ገልጿል። የመድሃኒት እጥረት " የኮንዶምና የተወሰኑ የእርግዝና መከላከያ መድሃኒቶች ክምችት እጥረት ገጥሞናል" ያሉት ደግሞ ሩትስ ኦፍ ሄልዝ የተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት የሚመሩት አሚና ኤቫንጀሊስታ ስዋንፖኤል ናቸው። የእርሳቸው ቡድን የስነ ተዋልዶ አገልግሎቶችን በፑሬቶ ፕሪንቼሳ እና ገጠራማ የፊሊፒንስ መንደሮች የሚያቀርብ ሲሆን ከኮሮናወረርሽኝ መከሰት በኋላ ግን መድሃኒቶችን ለማጓጓዝ የሚያስችል የመጓጓዣ እጥረት በመፈጠሩ የክምችት እጥረት ገትሟቸዋል። የመንግሥት ብሔራዊ የቤተሰብ ፕሮግራም ለቢቢሲ እንደተናገረው በቂ የወሊድ መቆጣጠሪያ ክምችት ቢኖረውም በሁሉም ግዛቶቹ ለማከፋፈል ግን ችግር አጋጥሞታል። "በእግሯ አስር ኪሎሜትር ተጉዛ መጥታ አገልግሎቱን የምታገኝ ሴት አለች። አሁን በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በተዘጉ መንገዶች ሳብያ በየፍተሻ ጣብያው ለሚያስቆሟት የፀጥታ ኃይሎች ወዴት እንደምትሄድና የምትሄድበትን ምክንያት ማስረዳት ይጠበቅባታል" ብለዋል ለፑሬቶ ፕሬቼሳ የጤና ቢሮ የሚሰሩት አናሊዛ ሄሬራ። • አሜሪካ ቻይናን 'የኮሮናቫይረስ ምርምሬን መዘበረች' ስትል ወነጀለች • መጨባበጥ ቀረ? ከመጨባበጥ ውጪ ስላሉ ሰላምታዎችስ ያውቃሉ? በፊሊፒንስ በተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ የተነሳ በአንዳንድ አካባቢዎች ለአንድ ቤተሰብ አንድ ሰው ብቻ መንቀሳቀስ እንዲችል ፈቃድ ተሰጥቶታል። " የመንቀሳቀሻ ፈቃዱ ወንድ ብቻ አይልም፤ ነገር ግን ብዙ ጊዜ ወንዶች ናቸው የሚንቀሳቀሱት" ብለዋል የመንግሥታዊ ያልሆነው ድርጅት ኃላፊ ስዋንፖኤል። አክለውም " በተለይ የትዳር አጋሯ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንደምትጠቀም ለማያውቅ ሴት መድሃኒቶቹን ማግኘት ፈታኝ ነው" ይላሉ። አሁን ድረስ መድሃኒታቸውን የጨረሱ ሴቶች ተጨማሪ ማግኘት እንደሚፈልጉ ቢናገሩም መንቀሳቀሻ አጥተው መቸገራቸውን እንደሚነግሯቸው ገልፀዋል። ይህንን ችግር የበለጠ የከፋ የሚያደርገው ደግሞ በቤት ውስጥ መቀመጥ ውሳኔው ወቅት የትዳር አጋር አብሮ ቤት መገኘቱ ነው "በተለይ በተፈጥሮ መንገድ የሚከላከሉ የፊሊፒንስ ሴቶች ፈተና ይገጥማቸዋል፤ እርግዝና በሚከሰትበት ወቅት ከወሲብ መታቀብ የሚመርጡ ቢሆንም አሁን ግን የትዳር አጋሯ ቤት ውስጥ አብሮ በመዋሉ የተነሳ ይህ አዳጋች ነው" ይላሉ። በጎርጎሳውያኑ በ2017 በፊሊፒንስ የተሰራ አንድ ጥናት ለአቅመ ሄዋን ከደረሱና ካላገቡ ሴቶች መካከል 49 በመቶ ያህሉ ምንም ዓይነት የወሊድ ቆጣጠሪያ እንደማይጠቀሙ ያሳያል። ያገቡ እና ማርገዝ ከማይፈልጉ ሴቶች መካከል ደግሞ 17 በመቶ የወሊድ መቆጣጠሪያ አይጠቀሙም። " በፊሊፒንስ የሚገኙ ሴቶች የወሊድ መቆጣጠሪያ የማይጠቀሙበት ዋነኛ ምክንያት የጎንዮሽ ጉዳትን በመፍራትና የፀረ ስነተዋልዶ ጤና ትምህርቶች በሚያሰራጯቸው ከእውነታ የራቁ መረጃዎች የተነሳ ነው" ይላሉ የዩኤንኤፍፒኤ ተወካይ ዶ/ር ጆሴፍ ማይክል ሲንግ። " አብዛኛው ፊሊፒንሳዊ የካቶሊክ እምነት ተከታይ ሲሆን ወግ አጥባቂ የኃይማኖት አባቶች ደግሞ በየቤተ እምነቶቹ በብዛት ይገኛሉ፤ እንዲሁም በደቡባዊ ፊሊፒንስ ደግሞ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሙስሊም የኃይማኖት አስተማሪዎች አሉ" ሲሉ ያክላሉ። ያልታቀደ እርግዝና ሴቶች ላይ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ስነልቦናዊ ጉዳት ያደርሳል።
news-55298834
https://www.bbc.com/amharic/news-55298834
ኮሮናቫይረስ፡ የዋይት ሃውስ አባላት ክትባቱን ቀድመው ሊወስዱ ነው
በትራምፕ አስተዳደር ውስጥ ከፍተኛ ባለስልጣናት የሆኑ የዋይት ሃውስ አባላት ክትባቱን ቀድመው ከሚወሰዱት አሜሪካውን መካከል እንደሚሆኑ ተገለጸ።
አሜሪካ የፋይዘር/ባዮንቴክ ሰራሹን የኮቪድ-19 ክትባቶቹን "ወደ ሁሉም ግዛቶቿ" ማከፋፈለች መጀመሯ ተገልጿል። አሜሪካ ዜጎቿን ዛሬ መከተብ የምትጀምር ሲሆን እስከ መጋቢት ማገባደጃ ድርስ 100 ሚሊዮን ሰዎችን ለመከተብ ታቅዷል ተብሏል። የአሜሪካ ባለስልጣናት ክትባቱን ቅድሚያ የሚያገኙት ለበሽታው የበለጠ ተጋላጭ የሆኑት የጤና ባለሙያዎችና በእንክክብካቤ ማዕከላት የሚገኙ አረጋውያን ናቸው ብለው የነበረ ቢሆንም አሜሪካ መገናኛ ብዙሃን የዋይት ሃውስ ባለስልጣናትን ጠቀሰው እንደዘገቡት የዋይት ሃውስ አባላት ክትባቱን ቀድመው ከሚወስዱ አሜሪካውያን ተርታ ተሰልፈዋል። አንድ ስማቸው ያልተጠቀሰ የአሜሪካ ባለስልጣን ለሮይተርስ እንደተናገሩት፤ የዋይት ሃውስ አባላት ክትባቱን ቀድመው ማግኘታቸው የመንግሥት ሠራዎች ሳይቋረጡ እንዲከናወኑ ይረዳል። በመጀመሪያው ዙር ክትባቱን የማከፋፈል ሥራ ለ3 ሚሊዮን ዜጎቿ የሚሆን ክትባቶች በመላው የአሜሪካ ግዛቶች እየደረሰ ነው። የክትባት ስርጭቱን በበላይነት የሚቆጣጠሩት የአሜሪካ ጦር ጀነራል ጉስታፍ ፔርና ዛሬ ሰኞ ክትባቱ በአሜሪካ 145 ቦታዎች ይላካል ብለዋል። ክትባቱ በግዙፍ አውሮፕላኖች እየተከፋፈለ ይገኛል ነገ እና ከነገ በስቲያ ደግሞ ክትባቱ ወደ ተጨማሪ 491 ቦታዎች ይላከል ብለዋል ጀነራል ጉስታፍ። አሜሪካ ፋይዘር/ባዮንቴክ ያበለጸጉትን የኮሮናቫይረስ ክትባት ለአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት እንዲውል ፍቃድ መስጠቷ ይታወሳል። ይህ ክትባት የኮሮናቫይረስ በሽታን በመከላከል 95 በመቶ አስተማማኝ መሆኑ ተገልጿል። ይኸው ተመሳሳይ ክትባት በዩኬ ጥቅም ላይ መዋል የተጀመረ ሲሆን በካናዳ፣ ባህሬንና ሳዑዲ አረቢያም ፈቃድ አግኝቷል። በኮሮናቫይረስ ክፉኛ እየተጠቃችው ባለው አሜሪካ ከትናንት በስቲያ ብቻ 3 ሺህ 309 ዜጎቿን አጥታለች። አኃዙን ሪፖርት ያደረገው የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ ድረገፅ የበለጠ እንደሚያስረዳው በአለም ላይ ከፍተኛ በቀን የተመዘገበ ሞትም አድርጎታል። የፋይዘር/ባዮንቴክ የኮሮናቫይረስ ክትባትን ለአስቸኳይ ጊዜ መጠቀም ፍቃድ እንዲያገኝ በከፍተኛ ሁኔታ በትራምፕ አስተዳደር ጫና የተደረገበት የምግብና መድኃኒት አስተዳደርም ውሳኔውን የወረርሽኙ "አዲስ ምዕራፍ" ብለውታል።
news-57173548
https://www.bbc.com/amharic/news-57173548
ዐቃቤ ሕግ ምስክሮቹ የደኅንነት ስጋት እንዳለባቸው በማስረጃ እንዲያረጋገጥ ተጠየቀ
ዐቃቤ ሕግ በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የክስ መዝገብ ሥር በተከሰሱ ሰዎች ላይ "የማቀርባቸው ምስክሮች ቃላቸውን በይፋ ለመስጠት ስጋት አለባቸው" ማለቱን ተከትሎ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዐቃቤ ሕግ በምስክሮቹ ላይ ያለውን ስጋት በማስረጃ እንዲቀርብ ጠየቀ።
ዐቃቤ ሕግ በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ ላይ የጠራኋቸው ምስክሮቼ የደኅንነት ስጋት ስላለባቸው በዝግ ችሎት እና ከመጋረጃ ጀርባ ምስክርነታቸውን ይስጡ በማለት ሲከራከር መቆየቱ ይታወሳል። ፍርድ ቤቱ በበኩሉ በምስክሮች ላይ ሊኖር የሚችልን ስጋት በማስረጃ ተደግፎ ዐቃቤ ሕግ ለታችኛው ፍርድ ቤት ማለትም ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዲያቀርብ ወስኗል። በዚህ መሠረት ዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ናቸው ብሎ የቆጠራቸው 146 ሰዎች ቃላቸውን በግልጽ ችሎት በመስጠታቸው ሊያጋጥማቸው ስለሚችለው የደኅንነት ስጋት በማስረጃ አስደግፎ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀርባል ማለት ነው። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ችሎት ከዚህ ቀደም በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የክስ መዝገብ ሥር ከተከሰሱ ሰዎች ጋር በተያያዘ፤ "የዐቃቤ ሕግ መስክሮች በግልጽ ችሎት ቃላቸውን ይስጡ" ሲል የሰጠውን ብይን በመቃወም ነበር የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያለው። የዐቃቤ ሕግ መስክሮች በግልጽ ችሎት አልያም ከመጋረጃ በስተጀርባ እና በዝግ ችሎት ቃላቸውን ይስጡ የሚለው ጉዳይ ዐቃቤ ሕግ እና የተከሳሽ ጠበቆችን ሲያከራክር ቆይቷል። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቀጣይ ዐቃቤ ሕግ በሚያቀርበውን ማስረጃ እንዲሁም በዐቃቤ ሕግ እና በተከሳሾች/የተከሳሽ ጠበቆች መካከል የሚከናወነውን ክርክር መሠረት አድርጎ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። የዐቃቤ ሕግ እና የተከሳሽ ጠበቆች ክርክር ዐቃቤ ሕግ፤ ከዚህ ቀደም ምስክሮቼ "የደኅንነት ስጋት አለባቸው ወይስ የለባቸውም፤ እንዲሁም በዝግ ችሎት እና ከመጋረጃ ጀርባ መስክርነት ይስጡ የሚለውን ለመመርመር እና ውሳኔ ለመስጠት ፍርድ ቤት ስልጣን የለውም" ሲል ተከራክሯል። ዐቃቤ ሕግ ይህን የመመርመር እና ውሳኔ የመስጠት ስልጣን ያለው የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ነው ሲል ተከራክሯል። ይሁን እንጂ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ፤ ችሎቱ ክፍት ወይስ ዝግ ይሁን በሚለው እንዲሁም አንድ ምስክር ቃል መስጠት ያለበት በይፋ ነው ወይስ ከመጋረጃ በስተጀርባ በሚለው ላይ ውሳኔ መስጠት የሚችለው ፍርድ ቤቱ ነው ሲል ውስኗል። በሌላ በኩል በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የክስ መዝገብ ሥር የተከሰሱት ሰዎች የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና የአመራሮቹ ጠባቂዎች ናቸው፣ ብዙ ደጋፊዎች አሏቸው፣ ምስክሮቻችን በይፋ ቃላቸውን የሚሰጡ ከሆነ ጉዳት ሊደርስባቸው ይችላል ሲል ዐቃቤ ሕግ ከዚህ በፊት ተከራክሯል። የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ከመጋረጃ ጀርባ ቃላቸውን የሚሰጡ ከሆነ የደንበኞቻቸውን በክፍት ችሎት የመዳኘት መብት የሚጋፋ ነው በማለት ሲከራከሩ ቆይተዋል። የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ከመጋረጃ ጀርባ ቃላቸውን የሚሰጡ ከሆነ ደንበኞቻቸውን መስቀለኛ ጥያቄ ለመየቅ ይከብዳቸዋል ሲሉም ተከራክረዋል። ከዚህ በተጨማሪም ጠበቆች ደንበኞቻቸው ላይ የቀረበው ክስ ከሰባት ዓመት እስራት እስከ በሞት የሚያስቀጣ ስለሆነ፤ መሰል ክስ የቀረበባቸው ተከሳሾች የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች "ከመጋረጃ ጀርባ ቃላቸውን ይስጡ ማለቱ ፍትሃዊ አይሆንም" ብለው ነበር። በሌላ በኩል ዐቃቤ ሕግ በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የክስ መዝገብ ሥር የተከሰሱ ሰዎች የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ናቸው ሲል ላቀረበው መከራከሪያ ጠበቆች በክስ መዝገቡ ሥር የተካተቱ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ቁጥር ከሦስት አይዘልም ሲሉ ተከራክረው ነበር። አቶ ጃዋር መሐመድና አብረዋቸው ፍርድ ቤት የቀረቡት ግለሰቦች ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር በታዋቂው ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ላይ የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ ከተከሰተው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ ነበር ለእስር የተዳረጉት። አንድ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ በእስር ላይ የሚገኙት ተከሳሾች ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ይገኛል።
50848550
https://www.bbc.com/amharic/50848550
በሺዎች የሚቆጠሩ የጀርመን ተማሪዎች የኢሜላቸውን ይለፍ ቃል ለማግኘት ወረፋ ይዘዋል
በጀርመን 38ሺህ ተማሪዎች ኢሜላቸውን ለመክፈት እንዲችሉ አዲስ የይለፍ ቃል ለማግኘት በአካል ተገኝተው ወረፋ እንዲጠብቁ መደረጉ ተሰማ።
ይህ የሆነው ዩኒቨርስቲው የሳይበር ጥቃት ከደረሰበት በኋላ ነው። በጁስቱስ ሊቤግ ዩኒቨርስቲ (ጄኤልዩ) ተማሪ የሆኑት "ሕጋዊ አሰራር" በሚል ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ እንዲያቀርቡም ተጠይቀዋል። ከሳምንት በፊት የደረሰው የሳይበር ጥቃት በአጠቃላይ የዩኒቨርስቲው ኢንተርኔትን ከስራ ውጪ አድርጎት ነበር። • እሷ ማናት፡ ከሊስትሮነት እስከ ከተማ አውቶቡስ አሽከርካሪነት • የኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጁ በዋጋ የሚያንራቸው ምርቶች • 'የአልባኒያ ተቃዋሚዎች' በትግራይ ተማሪዎች ስለጥቃቱ ከተገለጸላቸው በኋላ ከጀርመን የሳይበር ደህንነት ጥናት ማዕከል ጋር በመሆን ምርመራ እየተደረገ ነው ተብለዋል። ዩኒቨርስቲው ባወጣው ማስታወቂያ ላይ " ሁሉም የዩኒቨርስቲው ሰራተኞችና ተማሪዎች በአካል በመገኘት የኢሜል ይለፍ ቃላቸውን መውሰድ ይጠበቅባቸዋል" ብሏል። ተማሪዎቹ መታወቂያ ካርዳቸውን በመያዝ ወደ ዩኒቨርስቲው የአካል ብቃት መስሪያ ስፍራ በትውልድ ቀናቸው ቅደም ተከተል መሰረት እንዲመጡ ተጠይቀዋል። በተለጠፈው ዝርዝር መሰረት ተማሪዎቹን በሙሉ አስተናግዶ ለመጨረስ አምስት ቀናትን ይወስዳል። ይህ በእንዲህ እያለ ዩኒቨርስቲው 1200 የፍላሽ ዲስኮች ለሰራተኞቹ ያዘጋጀ ሲሆን፤ በዚህም ሁሉም በዩኒቨርስቲው የሚገኙ ኮምፒውተሮችን ከቫይረስ እንዲጸዱ ይደረጋል ብሏል።
45874565
https://www.bbc.com/amharic/45874565
ከሃያዎቹ ሚኒስትሮች አስሩ ሴቶች ናቸው
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሁለተኛና ሶስተኛ መደበኛ ጉባዔ 410 አባላት በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በአዲሱ የካቢኔ ሹመታቸው ከሃያዎቹ ሚኒስትሮች አስሩን ሴቶች አድርገው ሾመዋል።
በዚህም መሰረት ኢንጅነር አይሻ መሃመድ የሃገር መከላከያ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙ ሲሆን በኢትዮጵያም ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሆነ ተገልጿል። ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል የሰላም ሚኒስትር፣ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር፣ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የገቢዎች ሚኒስትር፣ ዶክተር ሂሩት ወልደማሪያም የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር፣ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የትራንስፖርት ሚኒስትር፣ ወይዘሪት የዓለም ፀጋዬ አስፋው የሴቶች፣ ሕፃናት እና ወጣቶች ሚኒስትር እንዲሁም ዶ/ር ፍፁም አሰፋ የፕላንና ልማት ኮሚሽን ሆነው ተሹመዋል። •''ታሪክ ተሰራ! አባታችን በጣም ኮርተንብሃል'' •"ለወታደራዊ ደኅንነቱ የማንቂያ ደወል ነው" •"ማንም መብታችንን ሊሰጠን ስለማይችል፤ ሴቶች ማንንም ሳይጠብቁ በራሳቸው መታገል አለባቸው" የምክር ቤቱን ሦስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን አንደኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባዔ፣ የአስፈፃሚ አካላት ስልጣንና ተግባር ላይ የወጣውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለማፅደቅና የአፈ ጉባዔዋን መልቀቂያን መቀበልን በሚመለከቱ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቷል። በዚህም መሰረት ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐብይ አህመድ የአስፈፃሚ አካላት ስልጣንን ተግባር የተመለከተውን ረቂቅ አዋጅ አብራርተዋል። በማብራሪያቸውም የማሻሻያው ሥራ አስተማማኝ ሰላም የማረጋጥ ጉዳይ የኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎትና ጠንከር ያለ ጥያቄ በመሆኑ፣ ፍትሃዊና ፈጣን ልማት እንዲሁም የእኩል ተጠቃሚነት ጉዳይ አንገብጋቢ በመሆኑ፣ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች አሟልቶ ለማክበር፣ ከሌብነት የፀዳ ቅን አገልግሎት የመስጠትና የአገልጋይነት ስሜት የተላባሱ ተቋማትን መገንባት አስፈላጊ በመሆኑ ነው ብለዋል። የመንግሥት መዋቅር ሃብት ፈጣሪ የሆነውን የሰው ሃብት ትኩረት ሰጥቶ ወጭ ቆጣቢ በሆነ መንገድ የተሰጠውን ተልዕኮ ማሳካት በሚያስችል አግባብ እንዲደራጅ ሃሳብ ቀርቧል። "ተቋም ከሁኔታዎች ጋር የሚለዋወጥ ኃላፊነት ያለው፣ የሚወለድ፣ የሚያድግ፣ የሚታመም፣ የሚታከም ደግሞም የሚሞት በመሆኑ ሰዋዊ ባህሪውን ተላብሶ እንዲቀጥል ያለመ ነው" ብለዋል። ተቋም ማለት ቋሚ ማለት አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ የተዋቀረው የካቢኔ አደረጃጀት የታሰበውን የእድገት ጉዞ የሚያሳካ እንደሚሆን እምንት እንዳላቸው ገልፀዋል። ምክርቤ ቱም የተሻለ አደረጃጀት ውስጣቸውን ፈትሸው አመራራቸውን እንዲያጠናክሩና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሚሰራው ሪፎርም በተሰናሰለና ፈጣን ጉዞ የአስፈፃሚ አካላት የአደረጃጀት ጥናት ለምክር ቤት ቀርቦ በጠቅላይ ሚንስትሩ የቀረበው ስለተደገፈ ጥያቄ ለሚያቀርቡ ዕድል ተሰጥቷል። የተለያዩ ጥያቄዎች ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባቀረቡት በመንግሥት መስሪያ ቤቶች ስልጣን እና ተግባር ማሻሻያ ረቂቅ ላይ እየቀረቡ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የደን እና አካባቢ ሚኒስትር ወደ ኮሚሽንነት ዝቅ መደረጉ ኢትዮጵያ እከተለዋለሁ ከምትለው አረንጓዴ ምጣኔ ኃብት ጋር አይጋጭም ወይ? ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መስሪያ ቤቶችን በደንብ የማቋቋም እና የማጠፍ የበዛ ስልጣን አልተሰጠውም ወይ? የሚሉ ይገኙባቸዋል። የሚኒስትር መስሪያ ቤቶች ቁጥር ከሃያ ስምንት ወደ ሃያ እንዲያንስ የተደረገ ሲሆን ይህም ወጭ ቆጣቢ በሆነ መንገድ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት እንደሚያስችል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ተናግረዋል። የመንግሥት አስፈፃሚ አካላት ስልጣን እና ተግባር ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅ 1097/211 በሙሉ ድምፅ ፀድቋል። በአዋጁ መሰረት የተቋቋሙት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች 19 ሲሆኑ የፕላን ኮሚሽን ደግሞ 20ኛው የካቢኔ አባል መስሪያ ቤት ሆኖ ፀድቋል፡፡ 1. ሰላም ሚኒስትር- ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል 2. የአገር መከላከያ ሚኒስትር -ኢንጂነር አይሻ መሀመድ 3. የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትር - አቶ አህመድ ሺዴ 4. የግብርና ሚኒስትር -አቶ ኡመር ሁሴን 5. የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር -ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ብረእግዚያብሔር 6. የገቢዎች ሚኒስትር - ወ/ሮ አዳነች አቤቤ 7. የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር - ዶ/ር ጌታሁን መኩሪያ 8. የትራንስፖርት ሚኒስትር - ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ 9. የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር -አቶ ዣንጥራር አባይ 10. የትምህርት ሚኒስትር -ዶ/ር ጥላዬ ጌቱ 11. የማዕድና ነዳጅ ሚኒስትር- ዶ/ር ሳሙኤል ሁርቆ 12. የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር - ዶ/ር ሒሩት ወልደማርያም 13. የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትር- ወ/ሪት የአለም ፀጋዬ 14. የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር- ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ 15. የባህልናቱሪዝም ሚኒስትር - ዶ/ር ሒሩት ካሳው 16. ጠቅላይ አቃቤ ህግ - አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ 17. የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር - ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ 18. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር- ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ 19. የጤና ጥበቃ ሚኒስትር -ዶ/ር አሚር አማን 20. የፕላን ኮሚሽን- ዶ/ር ፍፁም አሰፋ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተሿሚ ሚኒስትሮች ሌብነትን የሚፀየፍ፣ ቅንነት የተሞላበት ስርዓትን የሚዘረጉ እንዲሆኑ ለሰራተኞች ቅርብ እንዲሆኑ የለውጥ ሂደትን (ሪፎርምን) በራሳቸው የሚያመጡ፥ የስራ ሰዓትን የሚያከብሩ ትጉሃን እንዲሆኑ ስቆ ማስተናገድን፣ አገልጋይ መሆንን፣ የሰራተኞችን ሸክም የሚረዱ እንዲሆኑ ፕሮቶኮል የሚያስጠብቁ፣ ስነ ምግባርን የሚያሰርፁ እንዲሆኑስብሰባ በመቀነስና ብዙውን ጊዜ በስራ የሚያሳልፉ እንዲሆኑ መመሪያ ሰጥተዋል። ከዕለቱ አጀንዳዎች አንዱ የነበረውን የክብርት አፈ ጉባዔዋን የስራ መልቀቂያን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተቀብሎታል። የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሚኒስትር የታጠፈ ሲሆን፤ በስሩ ይከወኑ የነበሩ ሥራዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ስር የሚቋቋም የፕሬስ ቢሮ የሚፈፀሙ ይሆናል።በኮሚሽን ደረጃ የተቋቋሙ ተቋማት ደግሞ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣ የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን፣ የአካባቢ ደህንነትና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን፣ ቱሪዝም ኢትዮጵያ ኮሚሽን፣ የፕላንና ልማት ኮሚሽን ና ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ናቸው።
news-49281160
https://www.bbc.com/amharic/news-49281160
በምዕራብ ሀረርጌ ዞን በተሰነዘረ ጥቃት ሰባት ሰዎች መሞታቸው ተገለፀ
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሀረርጌ ዞን በተሰነዘረ ጥቃት የሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ። ጥቃቱ የተሰነዘረው ኦሮሚያ ክልልን ከአፋር በምታዋስነው ጉምቢ ቦርደዴ ወረዳ ጉምቢ ቀበሌ ነው።
የሁለቱ ክልል አጎራባች ማህበረሰቦች ለረዥም ጊዜ አብረው የኖሩ ቢሆንም ዛሬ ነሐሴ 2 ቀን 2011 ዓ.ም ባልታወቀ ምክንያት ከአፋር ክልል አጎራባች ቀበሌ በኩል ጥቃት መሰንዘሩን የምዕራብ ሃረርጌ ዞን ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ፍቃዱ ሚሊዮን ለቢቢሲ ተናግረዋል። • ኤርትራ በሳዋ ባደረገችው ወታደራዊ ትዕይንት ምን እያለች ይሆን? • በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን ፌስቲቫል፡ ሙዚቃ፣ ኳስ፣ ፍቅርና ቡጢ.. ''ባልታወቀ ምክንያት የተወሰኑ ግለሰቦች መሳሪያ ይዘው ወደ ኦሮሚያ ክልል ጉምቢ ቀበሌ ገብተው ከጠዋቱ 12 ጀምሮ ጥቃት አድርሰዋል'' ብለዋል። በጥቃቱ የጉምቢ ቀበሌ ኗሪ የሆኑ 7 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ ጉዳት የደረሰባቸው 3 ደግሞ በአዳማ ከተማ ህክምና እየተከታተሉ እንደሆነም ሃላፊው አክለዋል። ሌላኛው ያነጋገርናቸው የምዕራብ ሃረርጌ ዞን የፀጥታ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ከድር መሃመድ ጥቃቱ የተፈፀመው በአፋር ልዩ ሃይል ነው ቢሉም አቶ ፍቃዱ ግን እስካሁን ባለው መረጃ ጥቃቱን የፈፀሙት ከፊል አርሶ አደሮች እንደሆኑ ይገልፃሉ። ''ጥቃቱን የፈጸሙት አካላት ወደፊት በፖሊስና በሚመለከታቸው አካላት ተጣርቶ የሚቀርብ መሆኑ እንዳለ ሆኖ አሁን ከአካባቢው ነዋሪዎች መረዳት እንደቻልነው ግን ጥቃት አድራሾቹ የሚታወቁና በአጎራባች ቀበሌ የሚኖሩ የአፋር ክልል ነዋሪ ከፊል አርሶ አደሮች ናቸው። ከጀርባ ሌላ ሃይል ይኑር አይኑር የሚለው ግን ገና ወደፊት ተጣርቶ ለህዝቡ ግልጽ የሚሆን ነገር ነው'' በማለት አክለዋል። • የጄኔራል ደምሴ ቡልቶ ልጅ 'መራር' ትዝታ ጉዳዩን አስመልክተን ያነጋገርናቸው የአፋር ክልል ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ አህመድ መሀመድም በአፋር በኩል አንድ ሰው መቁሰሉንና እስካሁን ጥቃቱን ማን እንደፈፀመ የሚታወቅ ነገር አለመኖሩንም ይናገራሉ። ''አሁን ቦታው ላይ የመከላከያ ሰራዊትና ፌደራል ፖሊስ አስገብተን የማረጋጋትና የማጣራት ስራ እየተሰራ ነው። በህዝቡ ላይ ጉዳት ያደረሱ አካላትም ተለይተው ለህግ እንዲቀርቡ ተስማምተናል።'' ከጥቃቱ ጋር ተያያዘ እስካሁን በቁጥጥር ስር የዋለ እንደሌለም አቶ አህመድ አረጋግጠዋል።
55752213
https://www.bbc.com/amharic/55752213
የዓለም መሪዎች ባይደንን ምን አሏቸው?
የዓለም መሪዎች አዲሱን የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደንን እንኳን ደስ አለዎት እያሉ ነው።
ለአራት ዓመታት ከዘለቀው የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በኋላ ከአሜሪካ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማደስም ተስፋ አድርገዋል። በርካታ መሪዎች የአየር ንብረት ለውጥ፣ ኮሮናቫይረስና ሌሎችም ጉዳዮችን በተመለከተ ከባይደን ጋር ተባብረው ለመሥራት እንደሚሹ ተናግረዋል። የተለያዩ አገራት መሪዎች ለባይደን ያስተላለፉትን መልዕክት እንመልከት፦ ቦሪስ ጆንሰን የዩናይትድ ኪንግደሙ ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን "ከባይደን ጋር አብሬ ለመሥራት ጓጉቻለሁ። በአገሮቻችን መካከል ያለውን ግንኙነት እናጠናክራለን። በደህንነት፣ ወረርሽኙን በመዋጋትና በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ በጋራ እንሠራለን" ብለዋል። ጀስቲን ትሩዶ የካናዳው ጠቅላይ ሚንስትር ጀስቲን ትሩዶ፤ ወረርሽኙን ለመግታት ሁለቱ አገራት ተባብረው መሥራት እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። "ምጣኔ ሀብታችን እንዲያገግም እና ዜጎች የተሻለ ሕይወት እንዲኖሩ እናደርጋለን። አካታችነትን እናበረታታለን። መካከለኛ ገቢ ላላቸው ሰዎች የሥራ እድል ለመፍጠር፣ በመላው ዓለም ዴሞክራሲና ሰላም ለማስፈንም እንሠራለን" ሲሉም ለባይደን መልዕክት አስተላልፈዋል። የአውሮፓ ኮሚሽን የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዘዳንት ቮን ደር ሌይን "አሜሪካ ተመልሳለች። አውሮፓም በተጠንቀቅ እየጠበቀች ነው። ከታማኟ የቀድሞ ወዳጃችን ጋር እንደ አዲስ ተባብረን ከባይደን ጋር በጋራ እንሠራለን" ብለዋል። የቻይናው አምባሳደር በአሜሪካ የቻይና አምባሳደር ቹ ቲካኒ፤ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማሳለጥ ከባይደን ጋር ተባብረው እንደሚሠሩ ገልጸዋል። ይህም የኅብረተሰብ ጤና እና የአየር ንብረት ለውጥን ይመለከታል። የጀርመን ፕሬዘዳንት የጀርመኑ ፕሬዘዳንት ፍራንክ ዋልተር ስቴንሚር "ዛሬ ለዴሞክራሲ ቀን ወጣ" ብለዋል። አሜሪካ በርካታ መሰናክሎች ገጥመዋት እንደነበርና አገሪቱን ለመፈረካከስ የተደረገው ሙከራ እንዳልተሳካ አስምረውበታል። "ጆ ባይደን ቃለ መሐላ ፈጽመው ዋይት ሀውስ በመግባታቸው እፎይታ ተሰምቶኛል። ጀርመናውያንም የኔን ስሜት ይጋራሉ" ሲሉም አስተያየት ሰጥተዋል። ኢማኑኤል ማክሮን የፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን "ዛሬ በአሜሪካውያን ታሪክ ትልቅ ቀን ነው። አብረናችሁ ነን። በጋራ መሰናክሎችን እናልፋለን። እንኳን ወደ ፓሪሱ ስምምነት ተመለሳችሁ" በማለት ነው የተናገሩት። የሩስያ አምባሳደር በአሜሪካ የሩስያ አምባሳደር አናቶሊ አንቶቭ፤ የባይደንን በዓለ ሲመት እንደተከታተሉ ተናግረው "በአሜሪካ ታሪክ አዲስ ገጽ ነው። የሩስያና የአሜሪካ ግንኙነትም ታድሷል" ሲሉ ሐሳባቸውን አስረድተዋል። ጁሴፔ ኮንቴ የጣልያኑ ጠቅላይ ሚንስትር ጁሴፔ ኮንቴ ከባይደን ጋር አገራቸው ተባብራ እንደምትሠራ ተናግረዋል። እንደ ጂ-20 ፕሬዘዳንትነታቸው ከአሜሪካ ጋር የጋራ አጀንዳ እንዳላቸው አስታውሰው፤ ማኅበራዊ አካታችነት እና አረንጓዴ ልማትን በተመለከተ የጋራ እንቅስቃሴ ለማድረግ ቃል ገብተዋል። ደቡብ ኮርያ የደቡብ ኮርያው ጠቅላይ ሚንስትር ሙን ጄኢን "ጆ ባይደን እንኳን ደስ አለዎት። አሜሪካ ተመልሳለች። ዴሞክራሲን ከዚህም በላይ እናበለጽገዋለን" ብለዋል። ጃፓን የጃፓኑ ጠቅላይ ሚንስትር ዮሺዴ ሱጋ ጆ ባይደንን እንዲሁም ምክትላቸው ከማላ ሐሪስን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋቸዋል። የሁለትዮሽ ትብብሩን ለማሳደግ እንደሚጣጣሩም አያይዘው ጠቅሰዋል። ታይዋን የታይዋኑ ፕሬዘዳንት ሲ ኢንግዋን በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ትስስር እንደሚጠናከር ቃል ገብተው፤ የባይደን ፓሊሲዎች ሲተገበሩ ለማየት እንደሚሹ ጠቁመዋል። ንሬንደራ ሞዲ የሕንዱ ፕሬዘዳንት ንሬንድራ ሞዲ፤ በሕንድና አሜሪካ መካከል የጋራ አጀንዳዎች እንዳሉ ጠቅሰው፤ "የምጣኔ ሀብትና የሕዝብ ለሕዝብ ትስስራችንን እናጠናክራለን" ብለዋል። አየርላንድ የአየርላንድ ጠቅላይ ሚንስትር ሚካኤል ማርቲን "ባይደን የአየርላንድ የዘር ግንድ አላቸው። ታሪክ ከሳቸው ብዙ ይጠብቃል። ስኬታቸው እኛንም ያኮራናል" ሲሉ ነበር መልዕክት ያስተላለፉት። ስኮት ሞሪሰን የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚንስትር ስኮት ሞሪሰን "ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማክተም አንስቶ መልካም ወዳጆች ነን። በቀጠናው ሰላም፣ በአየር ንብረት ለውጥና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ተባብረን እንሠራለን" ሲሉ ተደምጠዋል። ጀሲንዳ አርደን የኒው ዚላንዷ ጠቅላይ ሚንስትር ጀሲንዳ አርደን ሁለቱ አገሮች የጋራ ኢንቨስትመንቶች እንዳሏቸው ተናግረዋል። ባይደን አሜሪካን ወደ ዓለም ጤና ድርጅት አባልነት መመለሳቸውንም አሞግሰዋል። ቤንያሚን ኔታንያሁ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ "ባይደን እና ሐሪስ እንኳን ለታሪካዊ ቀን አደረሳችሁ። እኔና ባይደን ዓመታት የዘለቀ ወዳጅነት አለን። የጋራ ችግሮቻችንን ፈትተን የእስራኤልና አሜሪካን ግንኙነት እናጠናክራለን" ብለዋል። ሐሰን ሮሀኒ የኢራኑ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሮሀኒ "የአምባገነኑ ዘመን አክትሟል። ባይደን ወደ ሕጋዊ አሠራር ተመልሰው ያለፉትን አራት ዓመታት ጠባሳ ያስወግዳሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን" ሲሉ ተናግረዋል። ፓፕ ፍራንሴስ ፓፕ ፍራንሲስ የባይደን አስተዳደር ፓለቲካዊ፣ ሃይማኖታዊና የሥነ ምግባር ዋጋ የጎላበት እንደሚሆን ተስፋ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። "የጥበብ መጀመሪያ የሆነው እግዚአብሔር በአገሩ ሰላም እንዲያሰፍንና ለመላው ዓለም በጎ ነገር እንዲያመጣ እጸልያለሁ" ሲሉም ተመኝተዋል። ዳላይ ላማ የቲቤት የሃይማኖት አባት ዳላይ ላማ፤ ዓለም የገጠማትን የአየር ንብረት ለውጥ ችግር አንስተው፤ ባይደን ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠታቸው አመስግነዋቸዋል።
news-53075012
https://www.bbc.com/amharic/news-53075012
'ትሁቱ' እና 'ሐይማኖተኛው' ጀነራል አዲሱ የቡሩንዲ ፕሬዝዳንት ማን ናቸው?
ዛሬ የሥልጣን መንበራቸውን በቃለ መሐላ የሚረከቡት የ52 ዓመቱ የቡሩንዲው ተመራጩ ፕሬዝዳንት ኤቬሪስት ንዳይሺሜዬ በብዙዎች ዘንድ "ትሁት" እና "ሐይማኖተኛ" እንደሆኑ ይነገርላቸዋል።
ተመራጩ ፕሬዝዳንት ኤቬሪስት ንዳይሺሜዬ ወዳጃቸውና የትግል አጋራቸው ሟቹ ፕሬዝደናት ፒየር ንኩሩንዚዛ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ባለፉት አስራ አምስት ዓመታት ውስጥ በአገሪቱ ውስጥ "ከፍተኛ ተጽዕኖ" የነበራቸው ጀነራል ሆነው ቆይተዋል። በብዛት 'ኔቫ' በመባል የሚታወቁት ሜጀር ጀነራል ኤቬሪስት ንዳይሺሜዬ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1968 በማዕከላዊ ቡሩንዲ በምትገኘው የአገሪቱ የፖለቲካ ማዕከል ጊቴጋ ግዛት ውስጥ ነው የተወለዱት። በዴሞክራሲያዊ ምርጫ አሸንፈው ወደስልጣን መጥተው የነበሩት የሚልቺየር ንዳዳዬ ግድያን ተከትሎ በ1993 (እአአ) የእርስ በርስ ጦርነት ሲቀሰቀስ ኤቬሪስት ንዳይሺሜዬ በቡሩንዲ ዩኒቨርስቲ ውስጥ የሕግ ተማሪ ነበሩ። በወቅቱ ልክ እንደ ቀድሞው ፕሬዝዳንት ሁሉ እሳቸውም በዋና ከተማዋ ቡጁምቡራ ውስጥ በሁቱ ተማሪዎች ላይ ከተፈጸመው ግድያ ተረፈዋል። ከዚህ በኋላም ሸሽተው ከአገራቸው በመውጣት በቱትሲዎች የሚመራውን መንግሥት ከሚፋለሙት አማጺያን ጋር ተቀላቀሉ። ኤቬሪስት ንዳይሺሜዬ የቀድሞው መሪ ፒየር ንኩሩንዚዛ ወደስልጣን ከመምጣታቸው በፊት ደጋፊያቸው በመሆን ታንዛኒያ ውስጥ በመንግሥትና በአማጺያኑ መካከል የሠላም ንግግር በሚደረግበት ጊዜ በቅርበት አብረዋቸው ይሰሩ ነበር። አማጺያኑ ከመንግሥት ጋር የስልጣን መጋራት ስምምነት ላይ ሲደርሱ ኤቬሪስት ንዳይሺሜዬ የቡሩንዲ ጦር ምክትል ኤታማዦር ሹም ሲሆኑ ንኩሩንዚዛ ደግሞ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሆኑ። ከዚያም ንኩሩንዚዛ የፕሬዝዳንትነት ቦታውን ሲይዙ እሳቸው የፕሬዝዳንቱ ወታደራዊ አማካሪ ከመሆናቸው ጥቂት ቀደም ብሎ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትርም ሆነው ነበር። ከአስር ዓመት በኋላም ኤቬሪስት ንዳይሺሜዬ የገዢው ፓርቲ ዋና ጸሐፊ በመሆን እስከዚህ ዓመት ድረስ ቆይተው ባለፈው ወር የተካሄደው ምርጫ ሲቃረብ ንኩሩንዚዛ የፕሬዝዳንትንቱን ቦታ እንዲይዙ እጩ አደረጓቸው። ተመራጩ ፕሬዝዳንት የስድስት ልጆች አባት ሲሆኑ የሮማ ካቶሊክ ዕምነት ተከታይ ሲሆኑ ሟቹ ንኩሩንዚዛ ይከተሉት የነበረውና "እግዚአብሔርን ማጉላት" የሚሉትን የፖለቲካ አመለካከት እንደሚያራምዱ ይነገርላቸዋል። አዲሱ ፕሬዝዳንት ኤቬሪስት ንዳይሺሜዬ ዛሬ ሐሙስ በመሪነት የሚረከቧት ቡሩንዲ በዲፕሎማሲው መስክ የተገለለችና ከለጋሾች ጋር ያላት ግንኙነትም የሻከረ ነው። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ንኩሩንዚዛ በስልጣን ዘመናቸው በተቃዋሚዎቻቸው፣ በጋዜጠኞችና በመብት ተከራካሪዎች ላይ በሚወስዱት ጠንካራ እርምጃ በሰብአዊ መብቶች ጥሰት ሲከሰሱ ቆይተዋል። ቡሩንዲ የኮሮናቫይረስ ስጋት ያጠላባት ስትሆን ሟቹ ፕሬዝዳንት ግን ችግሩን ሲያቃልሉት ቆይተዋል። ከአምስት ዓመት በፊት በንኩሩንዚዛ ላይ የተሞከረውን መፈንቅለ መንግሥትን ተከትሎ በሺህዎች የሚቆጠሩ የቡሩንዲ ዜጎች በጎረቤት አገራት ውስጥ ወደ ሚገኙ የስደተኛ ካምፖች ፈልሰዋል። ዛሬ የቡሩንዲ መሪነት መንበርን የሚረከቡት ኤቬሪስት ንዳይሺሜዬ የሚመሰርቱት አዲስ መንግሥት ከዚህ በፊት ታጥፎ የነበረውን የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታን ወደነበረበት ይመልሳል ተብሎ ይጠበቃል።
45085714
https://www.bbc.com/amharic/45085714
በጅግጅጋ ግጭት ሸሽተው የተሸሸጉ ሰዎች በከፋ ችግር ላይ ናቸው ተባለ
በጂግጂጋ ከተማ ዛሬም የክልሉ ልዩ ኃይልና ከሚፈፀሙ ጥቃቶች ሸሽተው በተሸሸጉ ወገኖች መካከል ግጭት መፈጠሩን የዓይን ዕማኞች ለቢቢሲ ተናገሩ።
ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸውን የደበቁ አንድ የረድኤት ድርጅት ባልደረባ ዛሬ ረፋድ ላይ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ከተለያዩ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች፣ አብያተ ክርስቲያናትና ግብረሰናይ ድርጅቶች የተውጣጡ ተወካዮች እና የሀገር ሸማግሌዎች ወደ ክልሉ ፕሬዝዳንት አብዲ መሃመድ ኦማር በማቅናት መወያየታቸውን ገልፀዋል። በውይይቱ ወቅት ፕሬዚዳንቱ ችግሩ የተፈጠረው የፌዴራል መንግሥት ወታደሮች በክልሉ ጉዳይ ጣልቃ በመግባታቸው መሆኑን ተናግረዋል። ጨምረውም ቅዳሜ ዕለት በተፈጠረው ነገር ማዘናቸውን ገልፀው፤ ጥፋትና ውድመት ያስከተሉት «የአክራሪ እስልምና ቡድኖች» መሆናቸውንና ህዝቦች አሁንም በወንድማማችነት እንዲኖሩ የተቻላቸውን እንደሚያደርጉ እንደነገሯቸው አጋርተውናል። ተወካዮቹ በየአብያተ-ክርስቲያናቱ የተጠጉ ወገኖች በረሃብ እና እርዛት ውስጥ መሆናቸውን በመናገር የሚቀመስ ምግብ የክልሉ መንግሥት ማደል እንዲጀምር በጠየቁት መሰረት ዳቦ፣ ተምር እና ውሃ በመኪና ተጭኖ በየአብያተ-ክርስቲያናቱ ተጓጉዟል። ሆኖም በከተማው ቀበሌ 06 በሚገኘው መሠረተ-ክርስቶስ ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ የተጠለሉ ወጣቶችና የክልሉ ልዩ ኃይል በምግብ ዕደላው ወቅት መጋጨታቸውን ገልፀዋል። ከግጭቱ ጋር ተያይዞ የዓይን እማኙ የልዩ ኃይል ፖሊስ አባላት በከፈቱት የሩምታ ተኩስ ሦስት ወጣቶች ተመትተው ሲወድቁ ማየታቸውን ተናግረው ቢቢሲም በስፍራው ካሉ ሰዎች ይህንን ለማረጋገጥ ችሏል። የረድኤት ድርጅት ሠራተኛ የሆኑት የዓይን እማኝ እንደሚሉት የተመለከቱት የምግብ እጥረት አሳሳቢ መሆኑን ሲጠቁሙ «ጥሬ ማንጎ ለመብላት የሚንሰፈሰፉ ሰዎችን በዓይኔ አይቻለሁ ብለዋል። የሸሹ ሰዎች ተጠልለውባቸው የሚገኙ አብያተ-ክርስቲኣናትን የተመለከቱ ሌላ የዓይን እማኝ ደግሞ ነፍሰጡሮችና ሕፃናት በከፋ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ ተናግረዋል። ግጭቱ ከተከሰተ በኋላ ከከተማዋ ለመውጣት ያልቻሉና ተሸሽገው የሚላስ የሚቀመስ ያጡ ወገኖች የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ መሆኑንም የዓይን እማኞቹ አክለው ተናግረዋል። የሚመለከታቸውን የክልሉ ኅላፊዎች በጉዳዩ ላይ ለማነጋገር ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል።
news-53354288
https://www.bbc.com/amharic/news-53354288
ትራምፕ ገነዘብ ነክ መረጃዎችን ለአቃቤ ህግጋት እንዲያስረክቡ ፍርድ ቤት ወሰነ
የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ገንዘብ ነክ መረጃዎችን ለኒውዮርክ አቃቤ ህግጋት እንዲያስረክቡ ውሳኔ አስተላልፏል።
አቃቤ ህግጋቱ ፕሬዚዳንቱ የሚሰጧቸው መረጃዎችንም በመመርኮዝ ከግብር ጋር የተገናኙ ጉዳዮችን ይመረምራሉ። በተያያዘ ዜናም ይህ መረጃቸው ለኮንግረስ መሰጠት የለበትም የሚል ውሳኔም አስተላልፏል። ከአራት አስርት አመታት በፊት መሪ የነበሩት ሪቻርድ ኒክሰን በኋላ ገንዘብ ነክ ወይም ከግብር ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ይፋ እንዲያደርጉ ሲጠየቁ ትራምፕ የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ናቸው። የትራምፕ ጠበቆች በበኩላቸው ፕሬዚዳንቱ በስልጣን ላይ እስካሉ ድረስ መረጃዎችን ያለማሳየት መብት አላቸውም በማለት እየተከራከሩ ነው። ኮንግረስም የመጠየቅ ህጋዊ መሰረት የለውም እያሉ ነው። ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በበኩሉ ፕሬዚዳንቱ ያለመጠየቅ እንዲሁም መረጃዎችን ያለማሳየት መብት አላቸው የሚለውን ውድቅ አድርጎታል፤ ከወንጀል ምርመራዎች ነፃ ሊሆኑ አይገባምም ብሏል። "ከሁለት መቶ አመት በፊት የተመሰረተው የፍትህ ስርአታችን መሪም ይሁን ማንኛውም ዜጋ በወንጀል ምርመራዎች ሲጠየቅ መረጃዎችን ማስረከብ አለበት" በማለት ፍርድ ቤቱ አስታውቋል። " ይህንን መርህ ዛሬ የምናረጋግጥበት ነው" ብሏል። ትራምፕ በበኩላቸው ከግብር ጋር የተያያዘ ወንጀል ፈፅመዋል የሚለውን መሰረተ ቢስ ነው በማለት አጣጥለዋል፤ ምንም አልፈፀምኩም ሲሉ ክደዋል። ሁለት የዲሞክራት ፓርቲ አባላት የሆኑ ተወካዮችና የኒውዮርክ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለአመታት ያህል ትራምፕ ከግብር ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ይፋ እንዲያደርጉ ሲጠይቁ ነበር። ይህም መረጃም በስልጣን ላይ ያሉ መሪዎችን በተመለከተ ያለው ህግ ምን ያህል ጥብቅ እንደሆነም ለመፈተሽ ነው። ከዚህ በተጨማሪም ከሶስት አመታት በፊት ወሲባዊ ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሁለት ሴቶችን ዝም ለማስባል ገንዘብ መከፈሉንና ይህንንም ክፍያ ለመሸፈን መረጃዎች ተፈብርከዋልም የተባለውንም ለማጣራትም ይረዳል ተብሏል።
news-49069913
https://www.bbc.com/amharic/news-49069913
ቻይና፡ በዕፅ ዝውውር የተጠረጠረችው ናዝራዊት ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረበች
እፅ በማዘዋወር ተጠርጥራ ቻይና ጉዋንዡ እስር ቤት የምትገኘው ኢትዮጵያዊቷ ናዝራዊት አበራ ከወር በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት መቅረቧንና የመጨረሻውን ፍርድ እየተጠባበቁ እንደሆነ እህቷ ቤተልሔም አበራ ለቢቢሲ ገለፁ።
ናዝራዊት አበራ በቻይና በእፅ ዝውውር ተጠርጥራ በቁጥጥር ሥር መዋሏ ከተሰማ ስድስት ወራቶች አልፈዋል። • “ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ከደወሉልን በኋላ ተረጋግተናል” የናዝራዊት አበራ እህት • "ናዝራዊት አበራ ላይ ክስ አልተመሰረተም" የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ታዲያ ባለፈው ወር ሰኔ 20 ቀን 2011 ዓ.ም ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረበችው። 5.2 ኪሎ ግራም [ከዚህ ቀደም 1 ኪሎ ግራም የሚመዝን እፅ እንደነበር ገልፀውልን ነበር] የሚመዝነውን በሻምፖ መልክ የተያዘጋጀ ኮኬይን የተሰኘ እፅ ማን እንደሰጣትና እንዴት ልትያዝ እንደቻለች ለአገሪቱ ፍርድ ቤት አስረድታለች። የቻይና መንግሥት ያቆመላት ጠበቃም ናዝራዊት ከአገር ወጥታ እንደማታውቅ የሚያሳይ የጉዞ ታሪክ ማስረጃ፣ ከወንጀል ነፃ መሆኗን፣ የትምህርቷንና የሥራዋን ሁኔታ -ኢንጂነር እንደሆነች የሚያመለክት ማስረጃ ማቅረቡን እህቷ ቤተልሔም አበራ ገልፀውልናል። እህቷ ማስረጃዎቹ የቀረበባትን ክስ ለመከላከል የላኩት መሆኑን በመጥቀስ "የቻይና ሕግ ከባድ ሳይሆን አይቀርም፤ እንዳሰብነው እየሄደ አይደለም ግን ተስፋ አንቆርጥም" ብለዋል። በሌላ በኩል አቃቤ ሕግ ሆነ ብላ ድርጊቱን እንደፈፀመችና የተማረች ሆና ሳለ በስህተት ይህን መቀበል አልነበረባትም ሲል ክሱን ማሰማቱን ነግረውናል። "በድጋሚ መቼ ፍርድ ቤት እንደምትቀርብ ቁርጥ ያለ ቀን አይታወቅም" የሚሉት እህቷ ቤተልሔም፤ በቻይና ሕግ መሠረት አንድ ሰው ፍርድ ቤት ከቀረበ ከሃያ ቀናት አሊያም ከወር በኋላ የመጨረሻው ብይን እንደሚሰጥ መረጃ እንዳላቸው ይናገራሉ። • በቻይና የተደረሱት ስምምነቶች የትኞቹ ናቸው? በመሆኑም የናዝራዊትን የመጨረሻ ብይን በተስፋ እየተጠባበቁ መሆናቸውን ነግረውናል። እርሳቸው እንደሚሉት በእስር ላይ ያለችውን ናዝራዊትን በአካል መጎብኘት ባይቻልም ሁለት ጊዜ ደብዳቤ ልካላቸዋለች። "መጀመሪያ አካባቢ የጉዳዩ ክብደት አልገባትም ነበር፤ እመጣለሁ ነበር የምትለው። አሁን ላይ ክብደቱም ገብቷት ጭንቀቷ ጨምሯል።" ሲሉ ናዝራዊት ስላለችበት ሁኔታ ያስረዳሉ። በደብዳቤዋ ላይም 'የተሳሳተ ሰው በማመኔ ቤተሰቦቼንም እኔንም ብዙ መስዋዕትነት አስከፈልኩ፤ ወጥቼ አኮራችኋለሁ' የሚል ሃሳብ አስፍራለች። እንደ ቤተሰብ አሁንም በወር የተወሰነ ገንዘብ እንደሚልኩላትና ቻይና ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶችም በወር አንድ ጊዜ እንደሚጎበኟት፤ አስፈላጊ በሆነበት ጊዜም እንደሚሄዱ ገልፀውልናል። በቻይና አንድ ሰው እፅ ሲያዘዋውር ከተገኘ የሞት ፍርድ እንዲበየንበት የሚያዘው ሕግ በናዝራዊት ላይ ተግባራዊ ይሆናል በሚል በቤተሰቦቿ፣ በቅርብ ዘመዶቿ እንዲሁም በበርካታ ሰዎች ዘንድ ስጋትን አሳድሯል። ጉዳዩንም ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦች በቅርበት እየተከታተሉት እንደሆነ መገለፁ ይታወሳል።
news-53681457
https://www.bbc.com/amharic/news-53681457
በሕንድ በኮቪድ-19 ፅኑ ህሙማን ክፍል በተነሳ እሳት ስምንት ሰዎች ሞቱ
በሕንድ ምዕራባዊ ከተማ አህሜዳባድ በሚገኝ የኮቪድ -19 ሆስፒታል ከፅኑ ህሙማን ክፍል በተነሳ እሳት ሳቢያ የስምንት ህሙማን ሕይወት ማለፉ ተገለፀ።
የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ራጀሽ ብሃት ለቢቢሲ እንደተናገሩት እሳቱ የተነሳው አንድ የሆስፒታሉ ሰራተኛ የበሽታ መከላከያ መሳሪያ ባጋጠመ የኤሌክትሪክ ችግር ሳቢያ በእሳት በመያያዙ ነው ብለዋል። ሰራተኛዋ በድንጋጤ ወደ ፅኑ ሕሙማን ክፍል የገባች ሲሆን እሳቱም በዚያ መዛመቱን የገለፁት ባለሙያው፤ ይህንንም ተከትሎ አንድ የሆስፒታሉ ዳሬክተር በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ መጀመሩን አስረድተዋል። ባለሙያው አክለውም ምሽት 3፡30 ገደማ የተነሳው የእሳት አደጋው ከአንድ ሰዓት በኋላ በቁጥጥር ሥር መዋሉን እና በዚያው የሚገኙ 40 ህሙማንም ወደ ሌላ ክፍል መዛወራቸውን ገልፀዋል። ይህንን ተከትሎም እርሳቸውና የእሳትና ድንገተኛ ክፍል ቡድን ከህሙማኑ ጋር የቅርብ ንክክኪ ስለነበራቸው ወደ ለይቶ ማቆያ እንደሚገቡ ተናግረዋል። ዋና ከተማዋ አህሜዳባድ የሆነችው ጉጃራት ግዛት ሚኒስተር ሆነው ያገለገሉትና ጠቅላይ ሚኒስተር ናሬዳንድራ፤ በተፈጠረው አደጋ ማዘናቸውን ገልፀው ለተጎጂ ቤተሰቦች የመቋቋሚያ ድጋፍ እንደሚደረግ በትዊትር ገፃቸው አስፍረዋል። አሁን በሥራ ላይ ያሉት የግዛቷ ሚኒስተር ቪጃይ ሩፓኒ በበኩላቸው ሃዘናቸውን ገልፀው በአደጋው ላይ ምርምራ እንደሚደረግ ቃል ገብተዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የተወሰኑት ተጎጂዎች ቤተሰቦች "ሆስፒታሉ እሳት አደጋ ክፍል ለመጥራት ዘግይቶ ነበር" በማለት አንዳንድ የተጎጂ ቤተሰቦች ስለ አደጋው እንዳልተነገራቸው ይከሳሉ። " የሆስፒታሉ ሰራተኞች ምንም ዓይነት መረጃ አልሰጡንም። ማንም እሳቱ እንዴት ሊነሳ እንደቻለ እና ምን እንደተፈጠረ የነገረን የለም" ሲሉ አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ግለሰብ የነበረውን ሁኔታ ተናግረዋል። ፖሊስ ለአደጋው ተጠያቂ የሆነውን አካል ለመለየት ሦስት ቀናት የሰጠ ሲሆን፤ አደጋውን አንደ ድንገተኛ አደጋ በመመዝገብ አንድ የሆስፒታሉን ዳይሬክተር በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።
news-54668867
https://www.bbc.com/amharic/news-54668867
ሱዳን ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት ለማደስ ስምምነት ላይ መድረሷ ተነገረ
ሱዳን ከእስራኤል ጋር በሚኖራት ግንኙነት ዙሪያ ስምምነት ላይ መደረሱን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስታውቀዋል። ሱዳንም ከእስራኤል ጋር ግንኙነቷን ያደሰች ሌላኛዋ የአረብ ሊግ አባል አገር ሆናለች።
ሱዳን ከሶስት አስርት አመታት በላይ የገዙዋት ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር ከስልጣን መወገድ ተከትሎ የአሜሪካና የሱዳን ግንኙነት መሻሻሉም እየተናገረ ነው። ሱዳን ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል ደፋ ቀና ስትል የነበረው ከአሜሪካ አሸባሪነትን ከሚደግፉ አገራት ዝርዝር ውስጥ እንድትሰርዛት ለማድረግ እንደሆነ በርካቶች ሲገልጹ ቆይተው ነበር። እአአ 1948 ላይ እስራኤል እንደ አገር እራሷን ካወጀች ወዲህ ሱዳን ከአገሪቱ ጋር ያላትን ግንኙነት ወስና ነበር። ከሰሞኑ ደግሞ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ እና ባህሬንም ከእስራኤል ጋር ያላቸውን ግንኙነት በተመለከተ ስምምነት ላይ መድረሳቸው የሚታወስ ነው። በተመሳሳይ እስራኤልና ባህሬን ግንኙነታቸውን ሙሉ በሙሉ ለማሻሻል ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ይፋ ያደረጉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ነበሩ። በወቅቱ "ሁለተኛዋ የአረብ አገር ከእስራኤል አገር የሰላም ስምምነት ላይ ትደርሳለች።" ሲሉ ትዊተር ገፋቸው ላይ አስፍረው ነበር። ለበርካታ አስርታት በርካታ የአረብ አገራት እስራኤልን የፍልስጥኤም ጉዳይ ከተፈታ በኋላ ግንኙነታቸውን እንደሚቀጥሉ በመግለጽ አግልለው ነበር። ነገር ግን ባለፈው ወር የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል ስምንት ላይ ደርሳለች። በእስራኤል እና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መካከል ያለው ግንኙነት የተለሳለሰው በአሜሪካ አሸማግይነት ሲሆን፤ ነሐሴ 13 ነበር ወዳጅነታቸውን ይፋ ያደረጉት። በአብዛኛው የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ይህ ዜና በመልካም ቢወሰድም፤ ፍልስጥኤም ግን ተቃውሞዋን ገልጻለች። በተለይም የአረብ ኤምሬትስ ለፍልስጥኤም እውቅና ካልሰጠችው እስራኤል ጋር ግንኙነት መፍጠራቸው፤ ፍልስጥኤምን መክዳት ነው ተብሏል። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፤ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ጋር ዳግመኛ መወዳጀታቸውን አስታከው በወረራ የተያዘውን ዌስት ባንክ በግዳጅ የእስራኤል ይዞታ የማድረግ እቅዳቸውን ለማዘግየት ተስማምተዋል። ጆርዳን ደግሞ በአውሮፓውያኑ 1994 ከእስራኤል ጋር የሰላም ስምምነት የፈረመች ሲሆን ግብጽ ደግሞ 1979 ላይ ከስምምነት መድረሷ የሚታወስ ነው። ፕሬዝደንት ትራምፕ ሱዳንን አሸባሪነትን ከሚደግፉ አገራት ዝርዝር ውስጥ ካስወጡ በኋላ ጋዜጠኞች ወደ ዋይት ሀውስ ክቡ ክፍል እንዲገቡ ከተደረገ በኋላ ፕሬዝዳንቱ በስልክ ከሱዳን እና እስራኤል መሪዎች ጋር አውርተዋል። የፕሬዝዳንቱ ረዳት ጁድ ዴር በሁለቱ አገራት መካከል ስምምነት መፍጠር በመካካለኛው ምስራቅ ሰላምን ለማጠናከርና ቀጠናውን ለማረጋጋት ትልቅ ቦታ እንደሚኖረው ገልጸዋል። የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ አገራቸው አሸባሪነትን ከሚደግፉ አገራት ዝርዝር ውስጥ መሰረዟን በማስመለከት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን አመስግነዋል። በስልክ በነበራቸው ቆይታ የእስራኤሉም ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ '' የሰላምን ግዛት እያሰፋን በመሆኑ ደስተኞች ነን፤ ለዚህ ስኬት ለነበሮት ውጤታማ አመራርም ምስጋና ይገባዎታል'' ብለዋል። ዶናልድ ትራምፕ ደግሞ ''ገና ከዚህ በኋላም በርካታ ስምምነቶች ይመጣሉ'' ሲሉ ተደምጠዋል። ነገር ግን የፍልስጤም ነጻ አውጭ ድርጅት ከፍተኛ ኃላፊው ዋሴል አቡ የዑሱፍ እስራኤል ከሱዳን ጋር የደረሰችው ስምምነት ፍልስጤማውያንን በጀርባ በኩል በስለት እንደመውጋት ነው ብለዋል።
41346599
https://www.bbc.com/amharic/41346599
ለዓለማችን የምግብ ደህንነት ስጋት የሆነው ተምች ወደ ኢትዮጵያ ዘልቋል
የኢትዮጵያ መንግስት እንዳስታወቀው ከ8.5 ሚሊዮን በላይ የሆኑ ዜጎቹ የመጠጥ ውሃ እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ላይ ናቸው። በተለይ ደግሞ በደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል የተከሰተው የዝናብ እጥረት በአካባቢው ያሉ ነዋሪዎችን የከፋ የምግብ እጥረት ላይ ጥሏቸዋል።
በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ፎል አርሚ ወርም የተሰኘ ተምች በስብል፤ በተለይ ደግሞ በበቆሎ ላይ እያደረሰ ያለው ጉዳት እየባሰ መጥቷል። ተምቹ ባለፈው ዓመት በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ተከስቶ የሰብል ምርት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አደርሷል። ፎል አርሚ ወርም? ፎል አርሚ ወርም የተሰኘው ተምች እንደ አባጨጓሬ ያለ ነብሳት ሲሆን ወደ ቢራቢሮነት ከመቀየሩ በፊት በጣም ብዙ ምግብ የሚበላ ተመች ነው። ተምቹ ከዚህ በፊት 'አፍሪካን ኣርሚ ወርም' እየተባለ ከሚጠራው ሰበል በይ ነብሳት ጋር ተመሳሳይነት ያለው ሲሆን ከወደ አማሪካ አካባቢ የመጣ እንደሆነ ይታመናል። ተምቹ በተለይ በቆሎ ላይ ከፍተኛ ውድመት የሚያደርስ ሲሆን ሌሎችም እንደ ጥጥ፣ ቦሎቄ፣ ድንች፣ እና የትምባሆ ሰብሎች ላይ ውድመት ያደርሳል። ይህ ተምች ወረራ በሚያደርስበት የሰብል ማሳ ላይ ቢያንስ ሶስት አራተኛው ስፍራ ላይ ጥፋት ያደርሳል። ፎል አርሚ ወርም አዲስ ከመሆኑ የተነሳ መንግስታት፣ ማሕበረሰቡ እና አርሶ አደሮች እንዴት አድርገው መከላከል እንዳለባቸው መላ እስኪመቱ ደረስ ተምቹ ከፋ ያለ ጉዳት አድርሷል። ተምቹ የአየር ሁኔታው ሞቃት እና እርጥብ በሚሆንበት ወቅት የሚራባ ሲሆን በበልግ እና መኸር ወቅት በበቆሎ ምርት ላይ ትልቅ ጉዳት ያደርሳል። እንደ ተባበሩት መንግስታት የምግብ እና ግብርና ድርጅት ገለፃ ተምቹ ወደ አፍሪካ ዘልቆ የገባው በፈረንጆቹ 2016 ዓ.ም. ሲሆን በስምንት ሳምንታት ብቻ ደቡባዊ የአፍሪካ ሀገራት ላይ ላቅ ያለ ጉዳት አድርሷል። በዚህ መልክ አህጉሪቱን ያካለለው ተምቹ በወርሃ የካቲት ኢትዮጵያ ገብቷል። "ተምቹ ከአባጨጓሬነት ዘመኑ ይልቅ ወደ ቢራቢሮነት ሲቀየር ሰብል ላይ ብዙ ጥፋት ያደርሳል። ለዚህም ነው በጣም ብዙ ቦታ በአጭር ጊዜ ማዳረስ የቻለው" በማለት ማብራርያ የሚሰጡት የዘርፉ ባለሙያ ፕሮፌሰር ኬን ዊልሰን ናቸው። ፎል አርሚ ወርም በኢትዮጵያ ተምቹ አሁን ላይ ከ20 በላይ የአፍሪካ ሀገራትን ያደረሰ ሲሆን ሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፔ የመጀመሪያዋ ተጠቂ ሀገር ናት። በኢትዮጵያም ተምቹ በጋምቤላ፣ ኦሮሚያ እና ደቡብ ክልሎች በመስፋፋት ጉዳት ካደረሰ በኋላ ወደ አፋር፣ አማራ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች እየተዛመተ ነው። ነገር ግን እስካሁን ምን ያህል ጉዳት እንዳደረሰ በእግጠኝነት መናገር አልተቻለም። ቢሆንም ግን ለተከሰተው የምግብ እጥረት የራሱን አስተዋፅኦ እንዳበረከተ አፍን ሞልቶ መናገር ይቻላል። ፎል አርሚ ወርምን በፀረ-ተባይ ኬሚካል ማስወገድ ቢቻልም ነገር ግን ተምቹ በአንዳንድ ቦታዎች ፀረ-ተባይ ኬሚካሎችን መላመድ መጀመሩን ባለሙያዎች ይናገራሉ። ተመራማሪዎች ተምቹን የሚያጠፋ ቫይረስ ለመስራት ከመሞከር ጀምሮ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለማበጀት ሩጫ ላይ ናቸው። በቀጣይ. . . የተባበሩት መንግስታት የምግብ እና ግብርና ድርጅት እንደሚያስጠነቅቀው ተምቹ በአፍሪካ ተጨማሪ ሀገራትን ከማዳራሱም በላይ ወደ አውሮፓ እና እስያም ሊያመራ ይችላል። የሳይንስ ተቋማትም ፎል አርሚ ወርም የተሰኘው ተምች ለዓለማችን የምግብ ደህንነት ስጋት የሆነ ሲሉ ፈርጀውታል።
news-44314624
https://www.bbc.com/amharic/news-44314624
ኢትዮጵያ ከዓለም ጥቂት አጫሾች ያሉባት አገር ናት
ትምባሆ ማጤስ በማቆም ፈረንሳዊያንን የሚያህል አልተገኘም። በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ አንድ ሚሊዮን ዜጎች የትምባሆን ነገር በቃን ብለዋል። ይህም ከ2016 እስከ 2017 ብቻ የሆነ ነው።
አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ፈረንሳዊያን የትምባሆ ነገር በቃን ብለዋል በርካታ አገራት የትምባሆ ስርጭትን ለመግታት ፖሊሲያቸውን ከልሰዋል። ያም ሆኖ በዓለም ላይ የአጫሾች ቁጥር ሲጨምር እንጂ ሲቀንስ አይታይም። ዛሬ የዓለም ትምባሆ ያለማጤስ ቀን ከመሆኑ ጋር አስታከን የአጫሽ አገራትን ዝርዝር አቅርበናል። 1. ኪሪባቲ ኪሪባቲ የምትባል የማዕከላዊ ፓሲፊክ ደሴት በአጫሾች ቁጥር በዓለም ቀዳሚዋ ናት። ከሕዝቧ ሁለት ሦስተኛ ወንዶች ትምባሆ የሚያጤስ ነው። ከሴቶች ደግሞ አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ደግሞ አጫሾች ናቸው። ኪሪባቲ ደሴት በትምባሆ ላይ የምትጥለው ግብር ትንሽ ነው በዚህች አገር 103,000 ሕዝብ ይኖራል። በትምባሆ ላይ የተጣለው ግብር አነስተኛ ሲሆን ሕዝቡ በቀላሉ በየትም ቦታ ትምባሆን ማግኘት ይችላል። 2. ሞንቴኔግሮ ምሥራቅ አውሮፓዊቷ አገር ሞንቴኔግሮ ከአውሮፓ በአጫሽ ቁጥር የሚያህላት የለም። 46 በመቶ ሕዝቧ ሱሰኛ ሆኗል። የባልካኗ ሞንቴኔግሮ የሕዝብ ቁጥሯ 633,000 የሚጠጋ ሲሆን 4,124 ሲጋራዎች በየቀኑ በአዋቂዎች ይጨሳሉ። ምንም እንኳ በአደባባይና ሕዝብ በተሰበሰበባቸው ቦታዎች ማጤስ በአገሪቱ ሕግ የተከለከለ ቢሆንም ሕዝቦቿ ግን በቢሮዎች፣ በምግብ ቤቶች፣ ብሎም በሕዝብ መጓጓዣ ውስጥ እንደልብ ትምባሆን ይምጋሉ። በግሪክ የጠቅላላ ወንድ ሕዝቦቿ እኩሌታ ትምባሆ ያጨሳል 3. ግሪክ ግሪክ 3ኛው ከፍተኛ የአጫሽ ቁጥር እድገት ያስመዘገበች አገር ናት። ከወንድ ዜጎቿ ግማሹ ትምባሆን ከአፋቸው አይነጥሉም። የሚገርመው 35 በመቶ የሚሆኑ ግሪካዊያን ሴቶችም ቢሆን ማጤስን ማዘውተራቸው ነው። ምንም እንኳ ከ2008 ጀምሮ በሕዝብ አደባባዮች ሲጃራ ማቡነን በሕግ የተከለከለ ቢሆንም ሕጉ ትዝ የሚለው አጫሽ ግን የለም። ብዙ ግሪካዊያን ዛሬም በየአደባባዩ ትምባሆን ያምቦለቡላሉ። ከግሪክ ቀጥሎ ኢስቲሞርና ራሺያ በርካታ አጫሾች ያሉባቸው አገራት ናቸው። በኢስቲሞር ፓኬት ሲጋራ ከአንድ ዶላር በታች ይሸጣል ራሺያ ራሺያ በዓለም አጫሾች ዝርዝር አምስተኛዋ አገር ናት። 60 ከመቶ የሚሆኑ ለአቅመ ማጤስ የደረሱ ወንድ ዜጎቿ ትምባሆ አይለያቸውም። የሴቶች ድርሻ 23 ከመቶ ነው። ሥራ ቦታና የሕዝብ መጓጓዣዎች ላይ ማጤስ ክልክል ቢሆንም የማያቋርጥ የሲጃራ ማስታወቂያዎች መበራከታቸው የአጫሾችን ቁጥር ሳያሳድገው አልቀረም። በአንዳንድ የራሺያ ሱቆች ፓኮ ሲጋራ ከአንድ ዶላር በታች ይገኛል። የራሺያ የትምባሆ ገበያ 22 ቢሊዮን ዶላር እንደሚሆን ይገመታል። የራሺያ የትምባሆ ገበያ ከ22 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሆነ ይገመታል ጥቂት አጫሾች የሚገኙባቸው አገራት እንደመታደል ሆኖ ከነዚህ አገራት ውስጥ ኢትዯጵያ አንዷ ሆናለች። ጋና፣ ናይጄሪያ፣ ጎረቤት ኤርትራና ፓናማም በዝርዝሩ ይገኙበታል። በበርካታ የአፍሪካ አገራት ሴቶች ትምባሆ ማጤሳቸው እንደ ነውር ይታያል ከአፍሪካዊያን 14 ከመቶዎቹ አጫሾች ሲሆኑ የወንዶች ድርሻ እስከ 80 ከመቶ ይደርሳል። የሴቶች ቁጥር ዝቅተኛ መሆኑ የኢኮኖሚ ጥገኛ ከመሆናቸው ጋር ይያያዛል ተብሏል። የሴቶች ሲጃራ ማጤስ እንደ ማኅበረሰብ ነውር መታየቱ የአፍሪካ ሴት አጫሾችን ቁጥር ሳይቀንሰው አልቀረም። ጫት መቃም ከፍ ያለ ጊዚያዊ መነቃቃትና ምርቃና ውስጥ ይከታል ከሲጃራ ይልቅ ጫት በአፍሪካ ቀንድ ተወዳጅ እየሆነ መምጣቱ የትምባሆ ወዳጆች ቁጥር በቃሚዎች ሳይተካ አልቀረም። የዓለም የጤና ድርጅት እንደሚለው በዓለም 10 ሚሊዮን የሚሆኑ ሕዝቦች ጫት ይቅማሉ። ሴት አጫሾች ዴንማርክ በሴት አጫሾች ቁጥር የሚስተካከላት የለም። በዚያች አገር ትምባሆን በመማግ ከወንዶች ይልቅ የሴቶች ቁጥር ይበልጣሉ። 19.3 ከመቶ የሚሆኑ ዴንማርካዊያን ሴቶች ትምባሆን የሙጥኝ ብለዋል። በዴንማርክ ከወንድ አጫሾች ቁጥር የሴቶቹ ላቅ ያለ ነው በየዓመቱ ትምባሆ 7 ሚሊዮን የዓለም ዜጎችን ይገድላል።
news-56715604
https://www.bbc.com/amharic/news-56715604
'ምንም ጥቅም ስለሌለኝ በቃ ራሴን እንደሞተ ሰው ነው የምቆጠረው'
ከ38 ባላነሱ አገራት ላለፉት 20 ዓመታት ሴቶች በግዳጅ ወይም ያለፈቃዳቸው መሃን እንዲሆኑ መገደዳቸውን ሪፖርቶችን አመላክተዋል። ከእነዚህ መካከል የተወሰኑት ሴቶች ሲወልዱ ከፈቃዳቸው ውጭ የተገደዱ ናቸው።
ባለፉት 20 ዓመታት ቢያንስ በ38 አገራት ውስጥ ሴቶች ያለፈቃዳቸው እንዲመክኑ ተደርገዋል በፕሮፌሰር ሳም ሮውላንድስ በተደረገው ጥናት መሰረት በሁሉም የአለም አህጉራት ውስጥ የሚገኘውን ያለፈቃድ መካን ማድረግን እንዲያቆሙ እና መንግስታት ተጠያቂዎችን በህግ እንዲጠየቁ የተባበሩት መንግስታት ጥሪ አቅርቧል። የጎሳ አናሳ ማህበረሰቦች፣ በኤች አይ ቪ የተያዙ ሴቶች እና ጾታ የሚለውጡትን ጨምሮ ሌሎች የተገለሉ ቡድኖች በዓለም ዙሪያ ይህ እንደሚገጥማቸው ታውቋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጤና ጥበቃ መብት ባለሙያዋ ዶ/ር ትላለንግ ሞፎከንግ "በዓለም አቀፍ ደረጃ ከመሃንነት ጋር በተያያዘ የመድልዎ እና የመብት ጥሰት አለ። ይህ እስከ ዛሬም ድረስ ቀጥሏል። ይህ በራሱ እኔ እንደማስበው አጠቃላይ የመብት ጥሰት ነው" ይላሉ። የግዳጅ መሃንነት በታሪክ ተሻለ ዘር ለመፍጠር መሣሪያ ሆኖ ያገለገለ ሲሆን እንደ ናዚ ጀርመን ካሉትም ጋር የተቆራኘ ነው፡፡ ጥናቱ እንደሚያመለክተው ግን እስከ 21ኛው ክፍለዘመን እንደቀጠለ ይጠቁማል። ዚሺሎ ድሉድላ በጎርጎሮሳዊያኑ 2011 በደቡብ አፍሪካ በሆስፒታል ውስጥ በምትወልድበት ጊዜ መሃን እንድሆን ስትደረግ ፈቃደኛ አንዳልነበረች ተናግራለች። የ50 ዓመቷ የሦስት ልጆች እናት እንደምትለው "በግዳጅ መሃን መሆን ለእኔ ትልቅ ጭካኔ ነው። ምክንያቱም የእኔ ምኞት ስላልነበረ በጭራሽ አልስማማም፡፡ ስለዚህ ነገር ብረሳው ብመኝም አልተሳካም። በሕይወት እያሉ ከሞተ ሰው ጋር አንድ ነዎት። ሆኖም እንደሞቱ ነው የሚቆጠሩት" ብላለች። "እኔ በሕይወት ሳለሁ የሞትኩኝ ነኝ ምክንያቱም እኔ ምንም ጥቅም የሌለኝ እንደሆንኩ አውቃለሁ" ትላለች፡፡ ዚሺሎ ድሉድላ እንድትመክን ሲደረግ ፈቃዷን አልተጠየቀችም ነበር ዚሺሎ እንደምትለው ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ስላለባት ብቻ ያለ ፈቃድ መሃን እንደሆነች ታምናለች፡፡ ዶ / ር ሞፎክንግ እንደሚሉት "ብዙ ሴቶች የሆኑት ነገር ሆስፒታል ውስጥ በነበሩበት ጊዜ መ ብታቸው ተጥሰዋል ማለት ነው፡፡" "ሁሉም ጥቁር ናቸው። አብዛኛዎቹም ከገጠር የመጡ ናቸው፡፡ መሃን እንዲሆኑ ለማስማማት የስምምነት ቅጽ እንዲፈርሙ የተገደዱት ወይም ጫና የደረሰባቸው ናቸው፡፡" ዚሺሎ የወለደችበት ሆስፒታል የህክምና ማስረጃዎቿ እንደሚያሳዩት በቀዶ ጥገና ከመውለዷ በፊት መሃን ለመሆን እንደፈቀደች ይናገራል፡፡ እንደመግለጫው ከሆነ ይህ የሆነበት ምክንያት ቀደም ሲል ሁለት ቀዶ ጥገና ስላደረገች እና ከብዙ ቀዶ ጥገናዎች በጤና ላይ ስጋት ስለሚጨመሩ ሴቶች ከሦስተኛው በኋላ መሃን እንዲሆኑ ማድረግ መደበኛ ተግባር መሆኑን ነው፡፡ ለቢቢሲ እንደገለጹትም "ሴቶች በግዳጅ ወይም በተጽዕኖ መሃን አይሆኑም… [በተጨማሪም] አንዳንዶች ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ ምኞታቸው ይከበራል" ብለዋል ፡፡ ዚሺሎን እና ሌሎች በርካታ ሴቶች ጋር ስምምነት-አልባ መሃን የማድረግ ክሶች ዙሪያ የደቡብ አፍሪካ የሥርዓተ-ፆታ እኩልነት ኮሚሽን ባለፈው ዓመት ምርመራ አድርጓል፡፡ እንደ ዶ/ር ሞፎክንግ ከሆነ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ብዙም አልተሠራም ብለዋል፡፡ "የደቡብ አፍሪካ የጤና ስርዓት እና መንግስት በፆታ እኩልነት ኮሚሽነር ሪፖርት ውስጥ የተካተቱትን ሴቶች የገፋ ነው" ብለዋል፡፡ "መምሪያው በራሱ እነዚህ ከባድ ጥሰቶች በእነሱ ቁጥጥር ስር መከናወናቸውን በይፋ ለመቀበል እና ለማመን ገና ነው፡፡" የደቡብ አፍሪካ የጤና መምሪያ ከቢቢሲ ለቀረበለት ጥያቄ የሰጠው ምላሽ የለም፡፡ ሆኖም በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለፍላጎት መሃን የማድረግ ተግባር በኤች አይ ቪ ባለባቸው ሴቶች ላይ ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ ለምሳሌ ካናዳ ውስጥ አራት የአገሬው ቀደምት ተወላጅ ሴቶች ከ 2005 እስከ 2010 ባለው ጊዜ ውስጥ ከወሊድ ጋር የተዛመዱ መሃን የማድረጎች እንዲኖሩ ግፊት እንደተደረገባቸው ግሎባል ፐብሊክ ሄልዝ ያወጣው ዘገባ ይገልጻል፡፡ ሪፖርቱ በተጨማሪም በቼክ ሪፐብሊክ፣ በሃንጋሪ እና በስሎቫኪያ የሮማ ሴቶች ከተወለዱበት ጊዜ አንስቶ የመሃን መሆንን እንዲቀበሉ በመድኃኒትነት እንደታዘዘላቸው ያሳያል። ሴቶች ካለፈቃዳቸው እንዳይመክኑ የሚደረገውን ጥረት የሚመሩት ዶ/ር ትላሌንጋ ሞፎኬንግ ግለሰቦች በሀገራቸው ውስጥ ባሉ ህጎች ሲገደዱ ወይም ተቀስቅሰው በግዴታ መሃን እንዲሆኑ መደረም ታይቷል፡፡ በጃፓን ጾታ የቀየሩ ሰዎች ያላቸው ሰዎች በሕጋዊ መንገድ በመረጡት ጾታቸው እንዲኖሩ ለማስቻል መሃን መደረግ አለባቸው፡፡ የቀዶ ጥገና ሕክምናው ካላከናወኑ ማግባት ወይም እንደ ፓስፖርቶች ያሉ ኦፊሴላዊ ሰነዶች ላይ ጾታቸውን የመቀየር መሰረታዊ መብቶቻቸው ይገድባል፡፡ በሕንድ ደግሞ ግዛቶች የህዝብ ብዛትን ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ቤተሰቦቻቸውን በሁለት ልጆች ላይ ለሚወስኑ ጥንዶች በግብር፣ በሥራ እና በትምህርት ላይ ማበረታቻዎችን ይሰጣሉ፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ጥቅማ ጥቅም ከዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የመጡ ወጣቶች ብዙውን ጊዜ በማይቀለበስ ሂደት እንዲያልፉ ሊያበረታታቸው ይችላል በሚል በባለሙያዎች ቅሬታ ይቀርብበታል፡፡ በእንግሊዝ የሚገኘው የቦርንማውዝ ዩኒቨርሲቲ ባልደረባ የሆኑት ፕሮፌሰር ሳም ሮውላንድስ እና ዶ/ር ጄፍሪ ዋል እንደሚሉት ህንድ መሃንነትን እምቢ ባሉ ባለትዳሮች ላይ የምግብ ራሽን ካርድን እንደመከልከል ያሉ ማዕቀቦችን ተጠቅማለች፡፡ ሪፖርቱ እንደሚያመለክተው መሃን መደረጋቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ያልቻሉ ሰዎች ለልጆቻቸው አልሚ ምግብ መከልከላቸውን ጠቁሟል፡፡ ከዚህም በላይ ቴሌቪዥኖችን፣ ማብሰያዎችን እና የገንዘብ ድጎማዎችን ጨምሮ የተለያዩ ማበረታቻዎች እንደሚሰጡ ማስረጃዎች አስደግው ሪፖርት አድርገዋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ እነዚህ የገንዘብ ማበረታቻዎች ድምር ከአማካይ ወርሃዊ ደመወዝ እጥፍ ይሆናል፡፡ ያለፍቃድ የመሃን የማድረግ ምሳሌዎች በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ሲሆን እንደዶ/ር ሞፎክንግ ከሆነ መንግስታት እና ክልሎች የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች መሆን አለባቸው፡፡ "ስሜትን የሚያደክም ነው። ሆኖም አንዳችን ለሌላው ከመሆን ውጭ ምርጫ የለንም። እኔ ራሴ ሴት ነኝ፣ ጥቁር ነኝ፣ የደቡብ አፍሪካ የገጠር ከተማ ነዋሪ ነኝ። በራሴ እኩዮች እና በራሴ ማህበረሰብ ላይ የተከናወኑ አስቀያሚዎቹን አንዳንድ ጉዳዮች አውቃለሁ። ግን ውጤታማ የሆነ መፍትሄ የለም "ብለዋል፡፡ "ሥራዬ በጤናው መብት ላይ ልዩ ዘጋቢ እንደመሆኔ መጠን በእነዚህ ሪፖርቶች ላይ ትክክለኛ እና ውጤታማ ምርመራ የማድረግ ግዴታ እንዳለባቸው ማሳሰብ ነው። ወንጀለኞችም በሕግ መጠየቅ አለባቸው፡፡" "እነዚህ በጣም ከባድ እና ኢ-ሰብዓዊ [ሂደቶች] ሴቶች የሚያዙበት መንገድ ነው። ስለሆነም በህግ፣ በፖሊሲም ይሁን በተግባር እንዲቀጥል መፍቀድ የለብንም " ብለዋል።
news-46691338
https://www.bbc.com/amharic/news-46691338
የኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ስለመዘጋቱ መረጃ የለኝም፡ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር
ባለፉት ጥቂት ቀናት እንደተዘጋ ስለሚነገረው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበርን በተመለከተ መረጃ እንደሌላቸው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ተናገሩ።
ቃል አቀባዩ ይህንን የተናገሩት ዛሬ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ነው። አቶ መለስ ጨምረውም ስለጉዳዩ ዝርዝር መረጃ ይዘው በቅርቡ አስተያየት እንደሚሰጡ ተናግረዋል። በተያያዘም በኢትዮጵያ የኤርትራ አምባሳደር አቶ ሰመረ ርዕሶም የሹሙት ደብዳቤያቸውን ዛሬ ለፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ማቅረባቸውን፤ በቅርቡ በፕሬዚዳንቷ በአምባሳደርነት የተሾሙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ መለስ አለም አሳውቀዋል። አቶ መለስ በመግለጫቸው ያነሱት ሌላኛው ነጥብ በመጭው ታህሳስ 22/ 2011 ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀውን የኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባልነት ነው። • "ለረዥም ጊዜ ፖለቲካ ውስጥ የመቆየት ፍላጎት የለኝም" ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ለሁለት ዓመታት ያህል ተለዋጭ አባልነቱን ይዛ የቆየችው ኢትዮጵያን በመተካት ደቡብ አፍሪካ ቦታውን ትረከባለች። ኢትዮጵያ የተለዋጭ አባልነቱን ስትይዝ በታሪኳ ለሦስተኛ ጊዜ ነበር። አቶ መለስ የኢትዮጵያን የቆይታ ጊዜ "ስኬታማ" እና "የሐገር ጥቅም ያስጠበቀ" ነበር ሲሉ ገልፀውታል። • ኦዲፒ፡ ኦነግ እንደ አዲስ ጦር መልምሎ እያሰለጠነ ነው የአፍሪቃ ቀንድ ደህንነት እንዲሁም ዓለም አቀፍ ሰላም የማስጠበቅ እንቅስቃሴዎች ኢትዮጵያ በተለዋጭ አባልነቷ ወቅት ትኩረት ሰጥታ የሠራችባቸው ጉዳዮች ናቸው ብለዋል አቶ መለስ። በተለይም በደቡብ ሱዳን እና በሶማሊያ ጉዳይ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታውም ምክር ቤት ይከናወኑ በነበሩ ውይይቶች እና የውሳኔ ኃሳቦች ላይ የኢትዮጵያ ግብዐት ፋይዳው ላቅ ያለ ነበር እንደቃል አቀባዩ አነጋገር። ቃል አቀባዩ እንደተናገሩት ባለፉት ስድስት ወራት ባህር አቋርጠው ወደ ሳዑዲ አረቢያ የተጓዙ እና የጉዞ ሰነድ የሌላቸው 44500 ኢትዮጵያዊያንን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሌሎች አካላት ጋር በመተባበር ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ አድርጓል። • እርቀ-ሰላም እና ይቅርታ፡ ከደቡብ አፍሪካ እስከ ኢትዮጵያ ህይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው ወደ ሳዑዲ አረቢያ የሚሄዱ ዜጎች ቁጥር እየቀነሰ ያለመሆኑን የገለፁት አቶ መለስ ጅዳ የሚገኘው ቆንስላ ሁለት ባለሞያዎችን ለዚሁ ጉዳይ መድበዋል ብለዋል። ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ ከአራት ሺህ በላይ ዜጎችን ከተለያዩ የአፍሪካ እና የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት እንዲመለሱ ተደጓርል ሲሉም አክለው ተናግረዋል። ህጋዊ የስራ ስምሪት ስምምነት ከተለያዩ አገራት ጋር መፈራረም መጀመሩን የተናገሩት ቃል አቀባዩ ህገ ወጥ የሰው ዝውውር መስመሮች ሦስት መሆናቸውን አውስተዋል። በዋናነት ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በመነሳት፤ በኬንያ በኩል መዳረሻውን ደቡብ አፍሪካ የሚያደርገው የመጀመሪያው መስመር ሲሆን አዲስ አበባን እና አማራ ክልልን ማዕከሉ አድርጎ በሱዳን ወደ ሊብያ እና ከዚያም ወደ አውሮፓ የሚሄደው ሌላኛው መስመር ነው። አማራና ትግራይ እንዲሁም አፋርን ማዕከል ያደረገ እና በየመን ወደ ሳዑዲ አረቢያ የሚያቀናው ደግሞ ሌላኛው መስመር ነው ተብሏል።
47465797
https://www.bbc.com/amharic/47465797
በማይታዩ ፕሬዚዳንት የምትመራው አልጀሪያ
የአልጀሪያው ፕሬዝዳንት አብዱላዚዝ ቡተፍሊካ የ82 አመት አዛውንት ናቸው።
እንደ ጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር በ2014 በሀገሪቱ በተካሄደው ምርጫ አሸንፈው በ1999 የተረከቡትን ስልጣን ሲያስቀጥሉ በቴሌቭዥን መስኮት ብቅ ብለው መልዕክት አስተላልፈዋል። ከዚያን ቀን ጀምሮ ግን የውሃ ሽታ ሆነዋል። ሀገሪቱም በማይታይ ፕሬዚዳንት መመራት ከጀመረች እነሆ ስድስት አመት ሆናት። •በ82 ዓመት አዛውንት የምትመራው አልጄሪያ ፈተና ገጥሟታል ለስድስት አመታት አልጀሪያውያን ፕሬዝዳንታቸውን አይተዋቸው አያውቅም። አሁን ላይ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ደግሞ ፕሬዝዳንቱ መናገር አይችሉም ፤ እራሳቸውንም መርዳት ስለማይችሉ በጋሪ (wheelchair) እየተገፉ ነው የሚንቀሳቀሱት። ይህም ምስል የተገኘው ከሶስት አመት በፊት የሀገሪቱን ፓርላማ ሲከፍቱ በተደረገ አጭር ቀረጻ ነው። •የእኩልነት አለም ብለው የሚገልጿት የአውራምባውያኑ አምባ በዚህ ሶስት አመት ጊዜ ውስጥ ደግሞ የበለጠ ተዳክመው እንደሚሆን ይጠበቃል። ነገሮች በአወዛጋቢነታቸው ቢቀጥሉም በእንደዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆነውም በሚቀጥለው ሚያዝያ አልጀሪያ ለምታካሂደው ምርጫ ሊወዳደሩ ይችላሉ መባሉ ግርምትን አጭሯል። ይህን ተከተሎም የአልጀሪያ ተማሪዎች ፥ መምህራንና ጋዜጠኞች ተቃውሟቸውን እየገለጹ ነው። ይህ በመሆኑም ካሁን በፊት በጎረቤቶቿ ሊቢያ እና ቱኒዚያ የነበረው የርስበርስ ጦርነት በአልጀሪያም እንዳይደገም ተሰግቷል። •"ማንም መብታችንን ሊሰጠን ስለማይችል፤ ሴቶች ማንንም ሳይጠብቁ በራሳቸው መታገል አለባቸው" በአልጀሪያ በ2002 በተጠናቀቀው የርስ በርስ ግጭት 150000 ዜጎች ህይዎታቸውን ማጣታቸው ይታወሳል። አልጀሪያ በ1962 ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ነጻነቷን ካገኘችበት ጊዜ ጀምሮ አሁን ስልጣኑን በያዘው ፓርቲ ብቻ ነው እየተመራች የምትገኘው።
52179254
https://www.bbc.com/amharic/52179254
ኮሮናቫይረስ፡ በአሜሪካ አንዲት ነብር ኮሮናቫይረስ ተገኘባት
አራት ዓመት ዕድሜ ያላትና የማላየን የነብር ዝርያ የሆነች "ታይገር" አሜሪካ ውስጥ በኮቪድ-19 ቫይረስ ተጠቂ እንደሆነች በምርመራ ተረጋገጠ።
በኒው ዮርክ ከተማ ብሮኒክስ መካነ-እንሰሳት ውስጥ ነዋሪ የነበረችው የነብር ዘር በኮሮናቫይረስ ተጠቂ ስለመሆኗ የአይዋ የእንስሳት ህክምና አገልግሎት ላቦራቶሪ አረጋግጧል። ናዲያ የሚል ስም የተሰጣት ይቺ የነብር ዘር እህቶቿን ጨምሮ ሁለት አሙር ታይገሮች እንዲሁም ሦስት የአፍሪካ አናብስት ከሰሞኑ በተመሳሳይ ደረቅ ሳል ምልክት ሲያሳዩ ነበር። አሁን ግን ሁሉም በማገገም ላይ ናቸው ተብሏል። ናዲያ የተባለችው የነብር ዝርያ ምናልባትም ከመካነ-እንሰሳቱ ጠባቂ ቫይረሱ እንደተጋባባት ጊዜያዊ ግምት ተወስዷል። የዚህ የኒውዮርክ የእንሰሳት ጥበቃ ባለሥልጣን ባወጣው መግለጫ "ነብሯ" ላይ ምርመራ የተደረገው በጠቅላላ በኒው ዮርክ ካላው ነባራዊ ሁኔታ በመነሳት ሲሆን እነሰሳት ላይ የሚደረገው ምርመራ ለጠቅላላው የኮቪድ-19 ጥናትና ምርምር ትልቅ ግብአት ሊሆን እንደሚችል ግምቱን ገልጿል። የአካባቢ ጥበቃና የተፈጥሮ ተቆርቋሪዎች ኮሮናቫይረስ በሰው ልጆች በሚስፋፋው መጠን በዱር እንሰሳት መሀል በስፋት የሚሰራጭ ከሆነ አካባቢንና ተፈጥሮን እንዳያመናምን ከፍተኛ ስጋት ገብቷቸዋል።
50217504
https://www.bbc.com/amharic/50217504
የዘመናዊ ሰው መነሻ በቦትስዋና መገኘቱ ተነገረ
በሰሜናዊ ቦትስዋና የሚገኘው ዛምቢዚ ወንዝ ዛሬ ላይ በጨው ግግር ቢሸፈንም ጥንት በሰፊ ሀይቅ የተሸፈነ ቦታ ነበር። ይህ አካባቢ የዘመናዊ ሰው ዝርያ መነሻ እንደሆነ ተመራማሪዎች ገልጸዋል።
ዛምቢዚ ወንዝ ዛሬ ላይ በጨው ግግር ቢሸፈንም ጥንት በሰፊ ሀይቅ የተሸፈነ ቦታ ነበር አካባቢው ከ200,000 ዓመታት በፊት የነበሩ ሰዎች መኖሪያ ነበር ተብሎ ይታመናል። በዘመኑ የነበሩ ሰዎች ለ70,000 ዓመታት ያህል በሥፍራው ኖረዋል። የአካባቢው የአየር ንብረት ሲለወጥ ግን ለም መሬት ፍለጋ መሰደዳቸውን ተመራማሪዎች ይናገራሉ። • በአፋር 3.8 ሚሊዮን ዓመት ያስቆጠረ ሙሉ የራስ ቅል መገኘቱ ተገለጸ • እስራኤል በቁፋሮ መስጂድ አገኘች አውስትራሊያ በሚገኘው 'ጄኔቫ ኢንስቲትዮት ኦፍ ሜዲካል ሪሰርች' የተባለ ተቋም የዘረ መል ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ጄነሳ ሀይስች እንደሚሉት፤ ከ200,000 ዓመታት በፊት ዘመናዊ የሰው ልጅ አፍሪካ ውስጥ ስለመኖሩ ማስረጃ አለ። "የሰው ልጆች መነሻ አካባቢ የት ነው? የሚለውና እንዴት ወደሌሎች አካባቢዎች እንደተጓጓዙ ለዓመታት አከራካሪ ነበር" ሲሉ አስረድተዋል። ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት፤ ጥንታዊ ሰዎች ማካጋዲካጋዲ የተባለ ሀይቅ አካባቢ ሰፍረው ነበር። በዚህ ለምለም ቦታ ለ70,000 ዓመታት ከኖሩ በኋላ ወደሌሎች አካባቢዎች ተጉዘዋል። • የሠላም ተጓዧ ሉሲ (ድንቅነሽ) ምን ደረሰች? • የቀደመው ዘመናዊ ሰው ከአፍሪካ ውጪ ተገኘ • የጥንታዊ ሰው የፊት ገጽታ ይፋ ተደረገ በሰሜናዊ ቦትስዋና የሚገኘው አካባቢ የዘመናዊ ሰው መነሻ ነው ተብሏል ተመራማሪዎቹ የሰው ልጆችን ዘረ መል ናሙና በመውሰድ እና የአየር ንብረት ለውጥን በማጥናት አፍሪካ ከ200,000 ዓመታት በፊት ምን ትመስል እንደነበር የሚያሳይ ሞዴል ሠርተዋል። በሌላ በኩል አንዳንድ ተመራማሪዎች የሰው ልጆችን ዘረ መል በማጥናት ብቻ የሰው ልጆች መነሻ ይህ አካባቢ ነበር ለማለት አይቻልም ሲሉ አዲሱ ጥናት ላይ ጥያቄ አንስተዋል። የሰው ልጆች ቅሪተ አካል ላይ በተሠራ ጥናት የሰው ልጅ መነሻ ምስራቅ አፍሪካ መሆኗን የሚያሳይ መረጃ መገኘቱን እንደማስረጃ በመጠቀም የተከራከሩም አሉ።
news-48864580
https://www.bbc.com/amharic/news-48864580
ተመድ በሊቢያ የተፈጸመው የጦር ወንጀል ሊሆን ይችላል አለ
የተባበሩት መንግሥታት በሊቢያ የተፈጸመው ጥቃት የጦር ወንጀል ሊሆን ይችላል አለ።
ስደተኞች ታጉረው የሚቆዩባቸው እስር ቤቶች በመንግሥት የሚተዳደሩ ሲሆኑ አብዛኞቹ መጠለያዎች የሚገኙት ደግሞ ከአማፂያን ጋር ጦርነት በሚደረግባቸው ስፍራዎች ነው። በሊቢያ የስደተኞች ማቆያ ላይ በደረሰ የአየር ጥቃት በትንሹ 44 ስደተኞች መሞታቸውን እና ቢያስ 130 ሰዎች ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው የሊቢያ መንግሥት አስታውቋል። ከሞቱት መካከል አብዛኞቹ አፍሪካውያን ስደተኞች ናቸው ተብሏል። በተባበሩት መንግሥታት እውቅና የተሰጠው የሊቢያ መንግሥት ለጥቃቱ በጄነራል ካሊፍ ሃፍታር የሚመራውን ቡደን ተጠያቂ አድርጓል። የተባበሩት መንግሥታት ኃላፊዎች ከመዲናዋ ወጣ ባለ የስደተኞች ማቆያ ላይ የደረሰውን ጥቃት የጦር ወንጀል ሊያስብለው የሚችል መስፈርቶች አሟልቷል ብለዋል። • በሊቢያ በስደተኞች መጠለያ በደረሰ የአየር ጥቃት በርካቶች ሞቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሊቢያ ወደ አውሮፓ መሻገር ለሚፈልጉ ስደተኞች መነሻ ሆናለች። ሊቢያን ለረዥም ጊዜ ሲያስተዳድሯት የነበሩት ሙአመር ጋዳፊ እ.ኤ.አ በ2011 ከሥልጣን ከወረዱ በኋላ አገሪቱ በግጭት እየታመሰች ሲሆን፤ የተለያዩ የጦር አበጋዞች በሚቆጣጠሯቸው ስፍራዎች ተከፋፍላም ትገኛለች። በርካታ ስደተኞች በመንግሥት እስር ቤቶች ውስጥ ታጉረው ይገኛሉ። የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር የሆኑት ሚሼል ባቼሌት፤ ማክሰኞ ዕለት ጥቃት የተሰነዘረበት እስር ቤት በሊቢያ ለሚንቀሳቀሱ የጦር ቡድኖች በሙሉ በስፍራው ሲቪል ሰዎች ብቻ እንደሚኖሩበት መረጃ ተላልፏል ብለዋል። • ሊቢያ ውስጥ 27 ሰዎች በቦምብ ጥቃት ተገደሉ "ይህ ጥቃት የተፈጸመበተን ሁኔታ ስንመለከት በትክክልም ከጦር ወንጀለኝነት ጋር የሚስተካከል ነው" ብለዋል። በመጠለያው ላይ ጥቃት ሲሰነዘር ይህ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን ኮሚሽነሯ ጨምረው ተናግረዋል። የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በጥቃቱ እጅግ ማዘናቸውን እና ጥፋተኞችን ወደ ፍርድ ለማቅረብ ገለልተኛ አጣሪ ቡድን ጉዳዩን እንዲመረምር አዘዋል። የኤኤፍፒ ዘገባ እንጠቆመው፤ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ካውንስል የተፈጸመውን ጥቃት በማውገዝ መግለጫ ለማውጣት ቢሰበሰብም ተሳታፊዎች ሳይስማሙ ስበሰባው ተጠናቋል። እንደዘገባው ከሆነ የአሜሪካ ተወካዮች በመግለጫው ላይ ፊርማቸውን ከማኖራቸው በፊት ከዋሽንግተን ፍቃድ ማግኘት ይኖርብናል ማለታቸው መግለጫው እንዳይወጣ አድርጓል። • ስደተኞቹ ሊቢያ ወደብ ላይ ከመርከብ አንወርድም አሉ ታጅኡራ የሚባለው እስር ቤት 600 ስደተኞችን በውስጡ ይዟል። ማክሰኞ ዕለት የተፈጸመው ጥቃት ያነጣጠረውም በእስር ቤቱ ላይ ነበር። ከተጎጂዎቹ መካከል ሴቶች እና ህጻናት እንደሚገኙበት የተባበሩት መንግሥታት ባልደረባ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የሊቢያ መንግሥት የጤና ሚንስትር የሆኑት ዶ/ር ካሃሊድ ቢን አቲያ ጥቃቱ የተሰነዘረበትን ስፍራ ለቢቢሲ ሲገልጹ "ሰው በየስፍራው ነበር፣ መጠላያ ካምፑ ወድሟል፣ ሰዎች እያለቀሱ ነው፣ አከባቢው በደም ተሸፍኗል፣ መብራት ተቋርጧል" ብለዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ በሊቢያ ተሻግረው አውሮፓ ለመድረስ የሚያስቡ ስደተኞች የሚቆዩት መንግሥት በሚቆጣጠራቸው የስደተኛ ማቆያዎች ሲሆን አብዛኞቹ መጠለያዎች የሚገኙት ከአማፂያን ጋር ጦርነት በሚደረግባቸው ስፍራዎች ነው። በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የእነዚህ መጠለያ ጣቢያዎች አያያዝ ትችት ይቀርብበታል።
42538893
https://www.bbc.com/amharic/42538893
ቻይና የዝሆን ጥርስ ንግድን አገደች
ቻይና የዓለም ትልቁ የዝሆን ጥርስ ገበያ ሆና ቆይታ በአዲሱ የፈረንጆች ዓመት በሃገሯ የሚከናወን ማንኛውም የዝሆን ጥርስ ግብይት ሕገ-ወጥ እንደሆነ አውጃለች።
ይህ ውሳኔዋም የቀሩትን ዝሆኖች ለመጠበቅ ለሚደረገው ጥረት አንድ ትልቅ እርምጃ ነው ተብሎ ተወድሷል። ዝሆኖችን ለመታደግ የሚሰሩ ተቆርቋሪዎች እንደሚያምኑት 30ሺህ ያህል የአፍሪካ ዝሆኖች በየዓመቱ በአዳኞች ይገደላሉ። የቻይና መንግሥታዊ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ባለፈው ዓመት የዝሆን ጥርስ ዋጋ በ65 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል። በተጨማሪም ወደቻይና ሲገባ የሚያዘው የዝሆን ጥርስ መጠን በ80 በመቶ መቀነሱም ዥንዋ ዘግቧል። የዝሆን ጥርስ ንግድን የማገዱ ውሳኔ ይፋ የሆነው በተጠናቀቀው የፈረንጆች ዓመት ሲሆን ተግባራዊ የሆነውም በዓመቱ የመጨረሻ ዕለት ጀምሮ ነው። ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ላይ በዝሆን ጥርስ ምርትና ንግድ ላይ ተሰማርተው የነበሩ 67 ተቋማት የተዘጉ ሲሆን የተቀሩት 105ቱ ደግሞ እሁድ ዕለት እንደተዘጉ ተነግሯል። የዱር እንሰሳ ደህንነት ተከራካሪ የሆነው ተቋም ዜናውን ተከትሎ ''የዓለም ትልቁ የዝሆን ጥርስ ገበያ በሮች ሲዘጉ ማየት እጅጉን ያስደስታል'' ብሏል። የዝሆን ጥርስ ዋነኛ የመገበያያ ስፍራ እንደሆነች የሚነገርላት ሆንግ ኮንግን ግን አዲሱ ሕግ የማይመለከታት መሆኑ አሳሳቢ ነው ተብሏል። ነገር ግን ግዛቲቱ የእራሷን የዝሆን ጥርስ ንግድን የሚያግድ ሕግ ለማውጣት በሂደት ላይ መሆኗም ተነግሯል።
news-42686437
https://www.bbc.com/amharic/news-42686437
የትራምፕ እቅድ “የክፍለዘመኑ ጥፊ ነው”: መሃሙድ አባስ
የፍልስጤሙ ፕሬዝዳንት መሃሙድ አባስ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የመካከለኛው ምስራቅ የሰላም ጥረትን "የክፍለ ዘመኑ ጥፊ" ሲሉ ገልፀውታል።
(መሐከል የተቀመጡት) የፍልስጤም ፕሬዝዳንት የሆኑት መሃሙድ አባስ የፍልስጤማውያን አመራሮች በተሰበሰቡበት አፅንኦት ሰጥተው እነደተናገሩት፤ ከአሜሪካ እየሩሳሌምን የእስራኤል ዋና ከተማ አድርጋ ከተቀበለች በኋላ ከአሜሪካ የሚመጣ ማንኛውንም የሰላም እቅድ እንደማይቀበሉ ተናግረዋል። በተጨማሪም እስራኤል በ1995 የተጀመረውን የኦስሎ ስምምነት የሰላም ሂደትን ወደጎን በማለቷ ወቅሰዋታል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ፍልስጤም የሰላም ድርድሩን አልቀበልም ካለች እርዳታ ለማቋረጥ ዝተዋል። በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ አጨቃጫቂው እየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማነት ውሳኔ ለሰላም ድርድሩ "ከጠረጴዛው ላይ መነሳት" ሰበብ ሆኗል ሲሉም ተናግረው ነበር። ፍልስጤማውያን በበኩላቸው ውሳኔው የሚያሳየው አሜሪካ ገለልተኛ ሆና ልትሸመግል እንደማትችል ነው ብለዋል። የፍልስጤም አመራሮች ለትራምፕ እርምጃ መልስ ጠንከር ያለ ምላሽ ለመስጠት ለሁለት ቀናት ያህል በራማላህ ስብሰባ ተቀምጠዋል። ባለፈው ወር የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ አሜሪካ ለእየሩሳሌም በሰጠችው እውቅና ማዘኑን ከገለፀ በኋላ አባስ የትረምፕን ምክረ ሃሳብ ውድቅ አድርገዋል። ቅዳሜ እለት ለፍልስጤማውያን ፓርቲ አመራሮች በራማላህ ባደረጉት ንግግር "የክፍለ ዘመኑ ድርድር የክፍለ ዘመኑ ጥፊ ሆኗል፤ በዚህም ተቀባይነት የለውም" ብለዋል። "ኦስሎ ስል ነበር፤ ነገር ግን ኦስሎ የለም፤ እስራኤል ኦስሎ እንዲያበቃ አድርጋዋለች" ሲሉም አክለዋል። ከዋሽንግተን ምንም እንኳን ዝርዝር መረጃው ይፋ ባይሆንም ለባለፉት ወራት አዲስ የሰላም እቅድ እያረቀቀች ነው። እየሩሳሌም በአለም ላይ ከፍተኛ የይገባኛል ጥያቄ ከሚነሳባቸው ከተሞች መካከል አንዷ ነች። እስራኤል ሙሉ እየሩሳሌም ዋና ከተማዋ እንድትሆን ትፈልጋለች። ፍልስጤማውያን በበኩላቸው ምስራቅ እየሩሳሌምን ፣ በ1967 በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ወቅት የተያዘው፣ የወደፊቷ ፍልስጤም ዋና ከተማ እንዲሆን ይፈልጋሉ። ነገርግን ፕሬዝዳንት ትራምፕ ምንም እንኳ በቀጠናው አለመረጋጋት ይከሰታል ቢባሉም እየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማነትን በይፋ ተቀብለዋል። የአሜሪካ ኤምባሲንም የበርካታ ዲፕሎማቶች መቀመጫ ከሆነችው ቴላቪቭ ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚዛወር ተናግረዋል።
news-54333190
https://www.bbc.com/amharic/news-54333190
ምጣኔ ሐብት ፡ ከብር ለውጡ በኋላ የወርቅ ዋጋ ለምን ጨመረ?
ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ መደብሮች የወርቅ ዋጋ ጭማሪ ማሳየቱን ነጋዴዎችና ገዢዎች ለቢቢሲ ገለጹ።
ቢቢሲ በመሐል አዲስ አበባ ፒያሳ አካባቢ በሚገኙ የወርቅ መሸጫ መደብሮች ተዘዋውሮ እንደተረዳው የወርቅ መግዣ እና የመሸጫ ዋጋዎች ላይ ጭማሪዎች ታይተዋል። በተለይ ኢትዮጵያ የብር ኖቶቿን መቀየሯን ይፋ ካደረገችበት ከመስከረም ወር መጀመሪያ አንስቶ ጭማሪው በተለይ ከፍ ማለቱን በአዲስ አበባ ከተማ በወርቅ ንግድ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች እና ሠራተኞች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ቢቢሲ አዲስ አበባ ውስጥ ዋነኛ የወርቅ መሸጫ መደብሮች በሚገኙበት በፒያሳ አካባቢ ቅኝት ባደረገበት በባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ 21 ካራት ወርቅ በግራም ከሦስት ሺህ ሰባት መቶ ብር እስከ አራት ሺህ ብር ይሸጣል መባሉን ከነጋዴዎቹ ለማረጋገጥ ችሏል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መስከረም አስራ ሰባት ቀን ያስቀመጠው የወርቅ የመግዣ ዋጋ ለሃያ አንድ ካራት 2012 ብር ከስድሳ አራት ሳንቲም ሲሆን፤ የጥራት ደረጃው ላቅ ላለው የሃያ አራት ካራት ወርቅ ደግሞ 2300 ብር ከአስራ ስድስት ሳንቲም ዋጋ ሆኖ ተቀምጦለታል። ባለፉት ጥቂት ወራት የወርቅ ዋጋ ጭማሪ ሲያሳይ መቆየቱን ቢቢሲ አግኝቶ ካናገራቸው የወርቅ መሸጫ መደብሮቹ ባለቤቶች እና ሠራተኞች ተረድቷል። ይሁንና የወርቅ ዋጋ ጭማሪው በተለይ የብር ኖቶች መቀየር ይፋ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ የበለጠ ከፍ ማለቱን በወርቅ ንግድ ላይ የተሰማሩት ነጋዴዎች ጨምረው ተናግረዋል። "ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ በግራም እስከ አምስት መቶ ብር ድረስ ጨምሯል" ስትል በአንድ የጌጣጌጥ መሸጫ መደብር ውስጥ የምትሰራ እንስት ለቢቢሲ ተናግራለች። ከግለሰቦች ቀለበት፣ ሃብል፣ የጆሮ ጉትቻና የመሳሰሉ የወርቅ ጌጣጌጦችን በመግዛት አትርፎ በመሸጥ የሚተዳደርና ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ አንድ ወጣት ደግሞ ጭማሪው ከሽያጭ በተጨማሪም በግዢም ላይ እየተስተዋለ እንደሚገኝ ተናግሯል። "ከአንድ ወር በፊት አንድ ግራም የሃያ አንድ ካራት ወርቅ አንድ ሺህ ብር፤ ከፍ ሲል ደግሞ አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር ከሰው ላይ እገዛ ነበር" የሚለው ወጣት "ባለፈው አስራ አምስት ቀን ውስጥ ግን ብዙ ጭማሪ አሳይቷል" በማለት ባለፈው አርብ አንድ ግራም ወርቅ ሁለት ሺህ አንድ መቶ ሃምሳ ብር መግዛቱን ተናግሯል። ከሌላው ጊዜ በተለየ ወርቅ የሚገዙ ሰዎች ፍላጎት መጨመር ዋጋውን ማናሩን የሚናገረው ይህ ወጣት፤ ከብር ኖቶች ቅያሪው ጋር ተያይዞ የተከማቸ ገንዘብን ወደአስተማማኝ ውድ ዕቃ መቀየር የሚፈልጉ ሰዎች ሳይኖሩ እንደማይቀሩ ግምቱን አስቀምጧል። "የገንዘብ ኖቶች ለውጡ ሳይጠበቅ ዱብ ያለ በመሆኑ ውዥንብር እና እርግጠኛ ያለመሆን ስሜቶች ፈጥሯል" የሚሉት የምጣኔ ሐብት ጉዳዮች ተንታኙ አብዱልመናን መሃመድ ናቸው። ከዚህም ጋር ተያይዞ ገንዘብ በእጃቸው ላይ ያላቸው ሰዎች ደኅንነታቸው አስተማማኝ በሆኑ ንብረቶች ላይ ብራቸውን ለማዋል መፈለጋቸውን በወርቅ ግብይቱ ላይ የታየውን የዋጋ ለውጥ እንደምሳሌ በማንሳት ይገልፃሉ፤ "ይህም በእነዚህ ንብረቶች ዋጋ ላይ የመናር ምክንያት ሊሆን ይችላል" ባይ ናቸው። "መኪና እና ቤትን የመሳሰሉ ቋሚ ንብረቶችን እንዲሁም ወርቅን የመሳሰሉ ሌሎች ንብረቶች ላይ ገንዘብን ማዋል እንደአማራጭ ስለሚወሰድ ተፈላጊነታቸው መጨመሩ የሚጠበቅ ነው" ሲሉ ለቢቢሲ የተናገሩት አብዱልመናን፤ በሕገ ወጥ መልኩ የተገኘ ገንዘብን ለመሸሸግም ወርቅ ቀላል መንገድ ነው ይላሉ። "ስለዚህም የወርቅ የዋጋ ጭማሪን የፈጠረው የገንዘብ ኖት ለውጡ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም" ሲሉ እምነታቸውን ይገልጻሉ። ባለፈው ዓመት ወርሃ ግንቦት ላይ ብሔራዊ ባንክ ከ63 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት ወርቅ ወደ ገበያ መቅረቡን ገልፆ እንደነበር ይታወሳል። በወቅቱ የባንኩ ገዥ የሆኑት ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ይህ የተጠቀሰው የወርቅ መጠን ከፍተኛ እንደነበርና ለመንፈቅ ዓመት ያህል የቁልቁል ይጓዝ የነበረው የወርቅ አቅርቦትን መጠን የቀየረ መሆኑን ተናግረው ነበር። ለወትሮውም ብሔራዊ ባንክ ወርቅን በሚገዛበት እና በነጋዴዎች ገበያ ላይ በሚሸጥበት ዋጋ መካከል ልዩነት መኖሩን የጠቀሱት ባለሞያው፤ ይህም ጌጣጌጥ ቤቶች ለንድፍ ሥራዎች፣ ለአገልግሎት ወጪዎች እና ለትርፍ በሚጨምሩት ገንዘብ ምክንያት ይመጣ እንደነበር ያስረዳሉ። በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት ወደ ውጭ በሚላክ ወርቅ መጠን ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ነበረው የሚሉት አብዱልመናን ይህንን ከግምንት ውስጥ በማስገባት በወርሃ ሐምሌ በብሔራዊ ባንክ የዋጋ ሽግሽግ ተደርጓል ብለዋል።
news-50754154
https://www.bbc.com/amharic/news-50754154
ደቡብ ሱዳንና የዓለም ሙቀት መጨመር ምን አገናኛቸው?
ተመራማሪዎች በከባቢ አየር ላይ የሚቴን (CH4) ልቀት እየጨመረ መምጣት ምክንያቱ ምንድን ነው እያሉ ሲመራመሩ ቆይተው በመጨረሻም መልሱን ከደቡብ ሱዳን መስክ አገኘነው ብለዋል።
በኢደንብራ ዩኒቨርስቲ መሪነት በተደረገው ምርምር ከፍተኛ መጠን ያለው የሚቴን ልቀት ከደቡብ ሱዳን ረግረጋማ ስፍራ እንደሚመነጭ ተደርሶበታል። በሳተላይት የተወሰዱ ምስሎች እንደሚያሳዩት የምስራቅ አፍሪካዋ ሀገር ከቪክቶሪያ ሐይቅና ሌሎች ገባሪዎች ውሃ የሚያገኝ ሰፊ ረግረጋማ ስፍራ አላት። • እሷ ማናት?: ለነፃነትም ለጥበብም ያልታከቱ እጆች • የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ የማይዳሰስ የዓለም ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ ተወሰነ ይህ ደግሞ ይላሉ አጥኚዎቹ ከረግረጋማ ስፍራ የሚመነጨውን የሚቴን ልቀት መጠን እንዲጨምር ያደርጋል። እ.ኤ.አ. ከ2010 እስከ 2016 ከምስራቅ አፍሪካ የተወሰደው መረጃ ሲታይ በልቀት መጠኑ ከአለም ላይ ሶስተኛ ደረጃን ይይዛል ሲሉ ተናግረዋል። "ያገኘነውን ውጤት መሬት ላይ ሄዶ እውነታውን ለማረጋገጥ ወይንም ደግሞ የተሳሳተ ነው ለማለት አይቻልም፤ ነገር ግን ያለን መረጃ ከዚህ ጋር የሰመረ ነው" ብለዋል ፕሮፌሰር ፖል ፓልመር። " የሱዳኑ ረግረጋማ ስፍራ እየሰፋ ስለመሄዱ ገለልተኛ መረጃ አለን፤ ይህንን ደግሞ ከአየር ላይ የተወሰደው መረጃም ያሳያል፤ የበለጠ አረንጓዴ እየሆነ ነው የሄደው [አካባቢው]" ብለዋል ለቢቢሲ። ሚቴን እንደ ካርቦን ኦክሳይድ ሁሉ ከፍተኛ አቅም ያለው የግሪን ሀውስ ጋዝ ሲሆን በከባቢ አየር ላይ በከፍተኛ መጠን በመገኘት ለዓለም ሙቀት መጨመር ምክንያት ይሆናል። ሚቴን በከባቢ አየር ላይ ያለው መጠን ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ ነው የመጣው። • "የተመረጥኩት በኖቤል ሽልማት ኮሚቴው ነው" ቤቲ ጂ በአለማችን ላይ ለሚቴን ልቀት ምክንያት ናቸው ተብለው ከሚጠቀሱት መካከል የግብርና ስራ እና የቅሪተ አካል ነዳጅ መጠቀም መሆኑ ቢጠቀስም ሌሎች ምክንያቶችም እንዳሉ ተመራማሪዎች ይናገራሉ። የኢደንብራ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች በአፍሪካ ረግረጋማና ውሃ ገብ ስፍራዎች የጃፓንን ሳተላይት በመጠቀም በሚመለከቱበት ወቅት ከደቡብ ሱዳን ከፍተኛ የሚቴን ልቀት እንደሚመነጭ መገንዘባቸውን ይናገራሉ። ይህ የሆነው እ.ኤ.አ. ከ2011 እስከ 2014 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ሲሆን አካባቢውም ሱድ እንደሚባል ተናግረዋል። ይህ የኤደንብራ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች ቡድን ግኝቱን በሳይንስ ጆርናል ላይ ያሳተመ ሲሆን የሱድ ረግረጋማ ስፍራ ለዓለማችን የሚቴን ልቀት ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳል ሲል ደምድሟል። ዶ/ር ሉንት "ሠፊ ቦታን የሚሸፍን ነው፤ ስለዚህ ከዚህ ስፍራ ከፍተኛ መጠን ያለው ሚቴን ቢመነጭ የሚደንቅ አይደለም፤ ሱድ 40ሺህ ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ስፍራ ነው" ብለዋል ለቢቢሲ።
news-48325703
https://www.bbc.com/amharic/news-48325703
በናይሮቢ ወንዞች የአስከሬኖች መገኘት አሳሳቢ ሆኗል
የኬንያ ባለሥልጣናት በዋና ከተማዋ ናይሮቢ እያካሄዱት ባለው ወንዞችን የማጽዳት ዘመቻ ወቅት ተጨማሪ ሁለት የሕጻናት አስከሬኖች ማግኘታቸውን አስታወቁ።
በናይሮቢ ከሚገኙ ወንዞች አንዱ በርካታ ሰዎችን ባሳተፈው በዚህ የጽዳት ዘመቻ በናይሮቢ ከሚገኙ ትላልቅ የድሆች መኖሪያ የሆነው የኮሮጎቾ አካባቢን አቋርጦ በሚያልፈውና ክፉኛ እንደተበከለ ከሚነገርለት ወንዝ ነው አስከሬኖቹ የተገኙት። • 22 ኢትዮጵያዊያን ናይሮቢ ውስጥ ተያዙ መንታ እንደሆኑ የተገመቱት ሕጻናት በወንዙ ውስጥ ሲገኙ በፕላስቲክ መያዣ ውስጥ እንደሆነ የተናገሩት ባለስልጣናቱ አንደኛው ሕይወቱ ያለፈ ሲሆን ሌላኛው እንደሚተነፍስ ነገር ግን ለማትረፍ እንዳልተቻለ ገልጸዋል። የናይሮቢ ከተማ ገዢ የሆኑት ማይክ ሶንኮ ጉዳዩን አስመልክተው እንደተናገሩት ይህ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው ነገር በጣም አሳሳቢ እንደሆነና ፖሊስ እሳቸው የሚጠረጥሯቸው ሆስፒታሎችና ክሊኒኮች ላይ ምርመራ እንዲያደርግ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። አስከሬናቸው የተገኘው ህጻናት ወላጆች ማንነት ስለማይታወቅ በተገኙበት አካባቢ እንዲቀበር መደረጉን የናይሮቢ ከተማ ገዢ ቃል አቀባይ ለቢቢሲ ተናግረዋል። • ኬንያዊቷ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሞታ ተገኘች ባለስልጣናት ጨምረውም በከተማዋ በሚካሄደው ወንዞችን የማጽዳት ዘመቻ ባለፉት ጥቂት ወራት የበርካታ ሰዎች አስከሬኖች እንደተገኙ ጠቅሰው፤ በተለይ የጨቅላ ህጻናቱ አስከሬን በተለያዩ ስፍራዎች ከሚፈጸሙ የጽንስ ማቋረጥ ድርጊቶች ጋር ሊያያዝ እንደሚችል አመልክተዋል። ቀደም ሲል በተካሄዱት የጽዳት ዘመቻዎች የስምንት ሕጻናትን አስከሬን ጨምሮ የአራት ጎልማሶች አስከሬኖች ከወንዞቹ ውስጥ መገኘቱም ተገልጿል።
news-52674586
https://www.bbc.com/amharic/news-52674586
ኮሮናቫይረስ፡የአሜሪካ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ጉባኤ የህፃናትን ወሲባዊ ጥቃት በሚያሳይ ቪዲዮ ተጠለፈ
በካሊፎርኒያ የሚገኝ አንድ ቤተክርስቲያን ዙም የሚባለውን የቪዲዮና የድምፅ መነጋገሪያ መተግበሪያን ከሰሞኑ እንደሚከስ አስታውቋል።
ዙም ከሰሞኑ የተጠቃሚዎች ቁጥር ከ10 ሚሊዮን ወደ 200 ሚሊዮን አድጓል ለክሱ ምክንያት የሆነውም መተግበሪያውን በመጠቀም ሲደረግ የነበረውን የቪዲዮ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ጠላፊዎች የህፃናትን ወሲባዊ ብዝበዛ የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በመለጠፋቸው ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቱ ተሳታፊ የሆኑትን ሰዎች ኮምፒውተሮች በመጥለፍ "የሚረብሹና የሚዘገንኑ ቪዲዮዎችን" መለጠፋቸውንም በቅዱስ ጳውሎስ ሉተራን የክስ ወረቀት ያስረዳል። •ምርመራ የተጀመረባቸው የአሜሪካ ምክር ቤት ደህንነት ኃላፊ ከስራ ለቀቁ •በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት 47 ሚሊየን ሴቶች የወሊድ መቆጣጠሪያ ላያገኙ ይችላሉ-የተባበሩት መንግሥታት የሳንፍራንሲስኮ ቤተ ክርስቲያን ኃላፊ አባላትም በወቅቱ የዙምን ኩባንያ እርዳታ ለመጠየቅ ቢሞክሩም ድርጅቱ ግን ለማስቆምም ምንም አለማድረጉን ክሱ ጠቁሟል። የዙም ኩባንያ ቃለ አቀባይ ባወጡት መግለጫ "ይህ አሰቃቂ ተግባር ነው" በማለት አውግዘውታል። "በዚህ አፀያፊ ተግባር ተፅእኖ ለደረሳባቸው ሁሉ ሃዘኔታችን ይድረሳቸው" ያለው ኩባንያው "ጠለፋው ደረሰ በተባለበት ቀን ወንጀለኞች በመከታተል ያገኘናቸው ሲሆን፤ መተግበሪያው እንዳይጠቀሙ ሙሉ በሙሉ ከማገድ በተጨማሪ መረጃቸውንም ለሚመለከታቸው ባለስልጣናት አስተላልፈናል" ብሏል። •ኮሮናቫይረስን እየተከላከልን በጥንቃቄ ምርጫ እናደርጋለን፡ ዶ/ር ደብረፅዮን •በሊባኖስ ኢትዮጵያውያን በኮሮናቫይረስ መያዛቸው እየተነገረ ነው ኩባንያው ከሰሞኑ የመተግበሪያው ደህንነት ለመጠበቅ የተለያዩ ማሻሻያዎች ማድረጉን ጠቅሶ፤ በተጨማሪም የዙም ተጠቃሚዎች ለስብሰባውም ሆነ ጉባኤውን ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ የይለፍ ቃሎችን (ፓስወርድ) በሚስጥራዊነት ሊጠብቁ ይገባል ሲል መክሯል። የተለያዩ የቤተክርስቲያን ቡድኖች የይለፍ ቃሎችን ለሁሉም ሰው ዝም ብለው እንደሚያጋሩም ኩባንያው ገልጿል። በኮሮናቫይረስ ምክንያት እንቅስቃሴዎችም ሆነ ስብሰባዎች ላይ ገደብ መጣሉን ተከትሎ በርካታ ሰዎችን በስብሰባም ሆነ በጉባኤ ለማሳተፍ ለሚፈልጉ የተለያዩ ተቋማትም ሆነ ቡድኖች ዙም ተመራጭ መተግበሪያ ሆኗል። ሆኖም ተፈላጊነቱ በከፍተኛ ሁኔታ ቢጨምርም ከደህንነትና የግል መረጃን ከመጠበቅ አንፃር በርካታ ጥያቄዎች እየተነሱበት ነው። 'ዙምቦምቢንግ' በሚልም መጠሪያ በርካታ ጠላፊዎች ስብሰባዎችን በመጥለፍ ዘረኛ ስድቦችን፣ እንዲሁም ወሲባዊ ይዘት ያላቸው ቪዲዮዎችን እያጋሩም ይገኛሉ። በሳንፍራንሲስኮ የሚገኘው ጥንታዊው የቅዱስ ጳውሎስ ቤተክርስቲያን ባቀረበው ክስ ላይ አንደኛው ጠላፊው ከዚህ ቀደም የሚታወቅና "ወሲባዊ ጥቃቶችን" ያደረሰ መሆኑን ጠቅሰው፤ በተደጋጋሚም ባለስልጣናቶችን አሳውቀው እንደነበር ጠቅሰዋል። ስምንቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ተሳታፊዎቹ አብዛኛዎቹ ጡረተኞች ሲሆኑ ኮምፒውተራቸውን በመጥለፍ ልቅ ወሲብ የሚያሳዩ ቪዲየዎች ተለቀውባቸዋል። "ቪዲዮዎቹ አሰቃቂና አፀያፊ ናቸው። ህፃናትና ጨቅላዎች ላይ በትልልቅ ሰዎች አማካኝነት የወሲብ ተግባር ሲፈፀምባቸው፤ ወሲባዊ ጥቃትና ብዝበዛም ሲያስተናግዱም ይታያል" ብሏል ክሱ። ተሳታፊዎቹ ቪዲዮውን ለማስቆም ቢሞክርም እንደገና ይጀምራል፤ እናም ጠላፊው በተደጋጋሚ ጥቃት አድርሷል። ቤተ ክርስቲያኗ ለደረሰባት ጉዳት፣ ውል በመጣስ እንዲሁም ያልተገባ የንግድ አሰራር በሚልም ዙም ካሳ እንዲከፍል ጠይቃለች።
news-53010376
https://www.bbc.com/amharic/news-53010376
ተጠርጣሪዋን ከሞተር ሳይክል ጋር አስረው እንድትጎተት ያደረጉ ፖሊሶች ታሰሩ
በኬንያ የ21 ዓመቷ ተጠርጣሪ ከሞተር ሳይክል ጋር ታስራ መሬት ላይ ከተጎተተች በኋላ ሦስት የኬንያ ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ሥር ውለዋል።
ከሞተር ሳይክል ጋር ታስራ መሬት ላይ የተጎተተችው ሰው አንዱ የፖሊስ አባል ሞተር ሳይክሉን ሲያሽከረክር፣ ሌላኛው ደግሞ ወጣቷን ሲገረፍ ሦስተኛው የፖሊስ አባል ድግሞ ድርጊቱን በሞባይል ስልኩ ሲቀርጽ ነበር። በስርቆት ወንጀል ተባባሪ ነሽ ተብላ የተጠረጠረችው ሜርሲ ቼሪኖ፤ ሶሰቱ የፖሊስ አባላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ስትማጸን ነበር። "እንዴት በሕይወት እንደተረፍኩ አላውቅም" ስትል ጥቃቱ የደረሰባት የ21 ዓመት ወጣት ለኬንያው ስታንዳርድ ጋዜጣ ተናግራለች። እንደ ጋዜጣው ዘገባ ከሆነ ድርጊቱ የተፈጸመው ከመዲናዋ ናይሮቢ በሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ ኦሌንጉሩኔ ተብሎ በሚጠራ አከባቢ እሁድ ዕለት ነበር። የአከባቢው ነዋሪዎች ጣልቃ ከገቡ በኋላ ወጣቷ ወደ ሆስፒታል ተወስዳ ህክምና እየተደረገላት ነው ተብሏል። ፖሊስ ባደረሰባት ጥቃት አንድ እግሯ መሰበሩን እና ሌሎች ጉዳቶቸም እንደደረሱባት ተነግሯል። በበርካታ ኬንያውን ዘንድ ቁጣን የቀሰቀሰው ድርጊት ተንቀሳቃሽ ምስል በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት ተጋርቷል። ወጣቷ ከሞተር ሳይክል ጋር ታስራ፤ ልብሷ እና የውስጥ ሱሪዋ እስከ ጉልበቷ ድረስ ወርዶ ስትጎተት ያሳያል። የተንቀሳቃሽ ምስሉ መጨረሻ በበርካታ ሰዎች ተከባ ያሳያል። "ምሕረት እንዲያደርጉልኝ ስማጸን ነበር። ማናቸውም ግን ሊሰሙኝ አልፈቀዱም" ስትል ለስታንዳርድ ጋዜጣ ከሆስፒታል አልጋ ላይ ሆና ተናግራለች። "ይህ ሁሉ ሲፈጸምብኝ ምክንያቱን አላውቅም" ስትል ሜርሲ ጨምራ ተናግራለች። ሲቲዝን የተባለው ቴሌቪዥን እንደዘገበው ደግሞ፤ ሜርሲ ከአንድ የፖሊስ ባልደረባ መኖሪያ ቤት ንብረት የዘረፉ ወጣቶች ተባባሪ ነሽ የሚል ክስ ቀርቦባታል። የናኩሩ ግዛት አስተዳዳሪ የፖሊሶቹ ተግባር ተቀባይነት የሌለው እና የማንታገሰው ነው ብለዋል። የኬንያ የወንጀል ምርመራ ክፍል በበኩሉ ሦስቱ ፖሊሶች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አስታውሶ፤ በፖሊስ አባላቶቹ ላይ ምርመራ እየተካሄደ ስለመሆኑ ተጠቁሟል። የኬንያ ፖሊስ በተለይ ደግሞ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የተጣሉ ክልከላዎችን ሲያስፈጽም በዜጎች ላይ የሰብዓዊ መብት ጥስተ ይፈጽማል ተብሎ ይወቀሳል። ባሳለፍነው ሳምንት ፖሊስ መንግሥት የጣለውን ሰዓት እላፊ ሲያስፈጽም 15 ሰዎችን ገድሏል ሲል አንድ ገለልተኛ የሆነ ተቋም አስታውቋል።
news-53446334
https://www.bbc.com/amharic/news-53446334
የትምህርት ቤት የቤት ስራ ያልሰራችው ጥቁር አሜሪካዊቷ ተማሪ መታሰሯ ተቃውሞ ቀሰቀሰ
አንዲት የአስራ አምስት አመት ታዳጊ የቤት ስራዋን ባለማጠናቀቋ የሚቺጋን ዳኛ እስር ማዘዛቸውን ተከትሎ ተቃውሞ ተነስቷል።
ታዳጊዋ ከዚህ ቀደም በሰራቸው ወንጀል በማስጠንቀቂያ ታልፋ የነበረ ሲሆን አሁን በበይነመረብ የሚሰጠውን የቤት ስራ ባለመስራቷ ያንን በምክር ታልፋ የነበረውን ሁኔታ ጥሰሻል በሚልም ነው እስር የተወሰነባት። ጥቁር አሜሪካዊቷ ታዳጊ ግሬስ ከግንቦት አጋማሽ ጀምሮም በእስር ላይ ነች ተብሏል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከትምህርት ቤቷ እንዲሁም ከፍርድ ቤቱ ደጃፍ ተሰባስበውም ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው። የአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በትናንትናው ዕለት ጉዳይዋን እንደገና እንደሚያየውም አስታውቋል። ፕሮ ፐብሊካ በዚህ ሳምንት ባወጣው ፅሁፍም የታዳጊዋን እናት ቃለ መጠይቅ በማድረግ ግሬስ ያለባትንም ህመም አስፍሯል። ሚያዝያ ወር ላይ እቃ ሰርቀሻል እንዲሁም ጥቃት ፈፅመሻል በሚል ተወንጅላ በዙም ፍርድ ቤት ቀርባ የነበረ ሲሆን ፍርድ ቤቱም በማስጠንቀቂያ አልፏታል። ባህርይዋ ክትትል እንዲደረግበት በሚልም ፍርድ ቤቱ ሲወስን የትምህርት ቤት ጥናቶቿንና የቤት ስራዎቿን ማከናወን የአመክሮው አንድ አካልም ነው ተብሏል። ፕሮ ፐብሊካ እንደዘገበው ግሬስ በማስጠንቀቂያ የታለፈችበት ቀንም ትምህርት ቤት በበይነ መረብ እንዲሆን የተወሰነበት ጋር ከመገጣጠሙ አንፃር፤ በቅርበት ድጋፍ የሚሰጡ መምህራን ባለማግኘቷም ፈታኝ ሆኖባት እንደነበር አስፍሯል። ግንቦት ወር አጋማሽ ላይም የኦክላንድ ግዛት የቤተሰብ ፍርድ ቤት ክፍል ይህንን አመክሮ ጥሳ እንደሆነ ያየ ሲሆን ዳኛ ሜሪ ኤለን ብሬናን የትምህርት ቤት የቤት ስራ አለመስራቷ በማስጠንቀቂያ የታለፈችበትን ጥሳለች "ለማህበረሰቡም ጠንቅ ናት" በማለት እንድታተሰር ወስነዋል። በግሮቭስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችና መምህራን ተቃውሟቸውን እያሰሙ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ግሬስ እንድትለቀቅ ፊርማቸውን አኑረዋል። "በርካታ ተማሪዎች በዚህ መንፈቀ አመት ወደኋላ ቀርተዋል። የቤት ስራ ለመስራት ብዙዎች ፍላጎትም የላቸውም፤ እየሰሩም አይደለም። መምህራንም በበይነ መረብ ብዙ እያስተማሩ አይደለም።" በማለት የ18 አመቷ ተማሪ ፕሩደንስ ካንተር ለሮይተርስ የዜና ወኪል ተናግራለች። የማህበራዊ ጥናት መምህር ጆፍ ዊከርሻም ለሮይተርስ እንደተናገሩት "ጉዳይዋን ሲከታተሉ የነበሩ ሰዎችም ሆኑ ዳኛዋ በዚህ ወረርሽኝ ወቅት የትምህርት አሰጣጡን፣ የቤት ስራም ሆነ ፈተና እንዴት እንደተቀየረ አልገባቸውም። ግሬስ ላይ የወሰኑት ኢ-ፍትሃዊ ነው" ብለዋል። ግሬስ ነፃ ትውጣ ከሚሉ መፈክሮችም ጋር ብላክ ላይቭስ ማተርም የሚሉ መፈክሮችም ጎን ለጎን ሰልፈኞች ይዘው ነበር። "ግሬስ ነጭ ተማሪ ብትሆን በቁጥጥር ስር አትውልም፤ ማረሚያ ቤትም አትገባም" በማለት እናቷ ሼሪ ክራውሊ ለአካባቢው ሚዲያ ተናግረዋል። የግሬስ ጠበቆች በአስቸኳይ ሁኔታዋ እንዲታይ መጠየቃቸውን ተከትሎ የሚቺጋን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዳይዋን እንደገና እንደሚያየው አሳውቋል።
news-56924984
https://www.bbc.com/amharic/news-56924984
ኢትዮ ቴሌኮም አስፋፋሁት ያለው 4 ጂ ምንድን ነው?
በስልክዎ ኢንተርኔት ሲጠቀሙ ባለዎት የኢንተርኔት ፍጥነት የተለያዩ ምልክቶችን ይመለከታሉ።
E፣ O፣ GPRS፣ 3 ጂ እና 4 ጂጥቂቶቹ ናቸው። 4 ጂ ከእነዚህ መካከል ፈጣን የሚባለው ነው። 4 ጂ ኤል ቲ ኢ በሚልም ሊገለጽ ይችላል 'Long Term Evolution' ወይም በግርድፉ የረጅም ጊዜ ዝግመተ ለውጥ በሚል ሊተረጎም ይችላል። እጅግ ፈጣን የተባለለት የ'አምስተኛ ትውልድ' ወይም 5 ጂ የሞባይል ኢንተርኔት ጥቅም ላይ ከዋለም ዋል አደር ብሏል። ቴክኖሎጂው ሁሉም ዘንድ አልደረሰም። ቢደርስም ለዚህ የተዘጋጀ ስልክ ያስፈልጋል። ለሞባይል ኢንተርኔት ፍጥነት ዓለም አቀፍ ደረጃዎች ባይኖሩም የኢንተርኔት አቅራቢዎች አንደኛው ትውልድ ወደሌላኛው በማቅናት ወደ አራተኛው እና አምስተኛው ትውልድ እየዘለቁ ነው፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም ኢትዮ ቴሌኮም ከ50.7 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች እንዳሉት ይገልጻል። ኩባንያው አሉኝ ከሚላቸው ከ50.7 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች መካከል ከ 48 .9 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚዎች ናቸው። ከ 23.5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ የዳታ እና ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ናቸው። የኢንተርኔት አገልግሎትን እአአ በ1997 ይፋ ሲያደርግ ከሁለት ዓመት በኋላ ደግሞ የተንቀሳቃሽ ስልክ አገልግሎት ጀመረ። በ2007 የ3ጂ አገልግሎት ይፋ አድርጓል። "የ4 ጂ ኤልቲኢ አገልግሎት ከፍተኛ ፍጥነትና ባንድዊድዝ እንዲሁም አስተማማኝ የዳታ አገልግሎት የሚሰጥ እንደመሆኑ ደንበኞቻችን አገልግሎታቸውን ዲጂታይዝ ለማድረግ፣ ምርታማነትን ለማሳደግ እና በአጠቃላይ የቴሌኮም አገልግሎት ላይ ያላቸውን ተሞክሮ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያሳድግ ነው" በሚል ኢትዮ ቴሌኮም 4ጂ/ኤልቲኢ ኢንተርኔትን በ2015 ነበር በአዲስ አበባ ያስጀመረው። ለዓመታት በአዲስ አበባ ብቻ ይሰጥ የነበረው የ 4 ጂ አገልግሎትን"በአዲስ አበባና በሁሉም ክልሎች የዳታ ትራፊክ ዕድገትና ፍላጎትን መሠረት ያደረገ የ4 ጂ ኤልቲኢ አገልግሎት የማስፋፊያ ሥራዎችን በማከናወን በቀጣይ በሌሎች የክልል ከተሞች ተመሳሳይ አገልግሎት ለማስጀመር የሚያስችሉ ቅድመ ሥራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ" ብሏል ኩባንያው በድረገጹ። አገልግሎቱን በተለያዩ አካባቢዎች በማድረስ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ብቻ አገልግሎቱን አስጀምሯል። ከአዲስ አበባ ውጭ ለመጀመሪያ ጊዜ በደቡብ ምሥራቅ 'ሪጅን' በሚገኙት አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ዱከም፣ ገላን፣ ሞጆ እና አዋሽ መልካሳ አገልግሎቱን ለደንበኞቹ ማድረስ ችሏል፡፡ ቀጣይ ተረኞች ደግሞ ባህር ዳር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ፍኖተ ሰላም፣ ቡሬ፣ ዳንግላ፣ እንጅባራ እና ቻግኒ ሆነዋል፡፡ በደቡብ ደቡብ ምዕራብ 'ሪጅን' ውስጥ በሚገኙ ስድስት ከተሞች ማለትም በወላይታ ሶዶ፣ በአርባ ምንጭ፣ በሆሳዕና፣ በወልቂጤ፣ በቡታጅራ እና በጂንካ የአራተኛው ትውልድ የማስፋፊያ ፕሮጀከቱን አጠናቆ አገልግሎቱ ተጀምሯል፡፡ ኩባንያው ለህብረተሰቡ ያቀረበውን የ4 ጂ ኢንተርኔት ለመጠቀም የሚያስፈልገውን የተንቀስቃቃሽ ስልክ ለህብረተሰቡ 'በተመጣጣኝ ዋጋ' እንዲያቀርቡ አስተላልፏል። "በኩባንያችን የሦስት ዓመት የዕድገት ስትራቴጂ ላይ እንዳመላከትነው በአዲስ አበባና በሁሉም ክልሎች የዳታ ትራፊክ እድገትና ፍላጎትን መሠረት ያደረገ የየ4 ጂ ኤልቲኢ አገልግሎት የማስፋፊያ ሥራዎችን ለማከናወን ታቅዶ እየሠራ ይገኛል" ብሏል። በቀጣይ ወራትም በሌሎች የክልል ከተሞች ተመሳሳይ አገልግሎት ለማስጀመር የሚያስችሉ ቅድመ ሥራዎች እያከናወንኩ ሲል በድረገጹ አስነብቧል። ለመሆኑ እነዚህ ኢትዮቴሌኮም አስፋፋው ያለው 4 ጂ እና ሌሎች የተንቀሳቃሽ ስልክ የኢንተርኔት ትውልዶች ምንድናቸው? 1ጂ 1ጂ ወይም የመጀመሪያው ትውልድ የሞባይል ዳታ እአአ በ 1991 ተዋወቀ፡፡ 1 ጂ አናሎግ የሆነ የመረጃ መለዋወጫ ዘዴ ነው፡ በ 1 ጂ ጥሪዎችን ማስተላል ብቻ ነው የሚቻለው። 2ጂ 2 ጂ የጽሑፍ መልዕክቶችን አስተዋውቋል። በኤስኤምኤስ በመባል የሚታወቀው 2 ጂ የጽሑፍ መልዕክቶችን ለመላክ አስችሏል፡፡ 2 ጂ በተጨማሪም ኤምኤምኤስ (መልቲሚዲያ ሜሴጂንግ ሰርቪስ) የተባለ የምስል መልዕክቶች ማስተላለፊያም አስተዋውቋል፡፡ በሞባይል ስልኮች ላይ ጂኤስኤም፣ ጂፒአርኤስ ፣ ኢዲጂኢ የሚባሉ አገልግሎቶች አሉት። 3ጂ የቪዲዮ ጥሪ እአአ በ 2001 ይፋ ሆነ። 3ጂ እና የ2 ሜጋባይትስ በሰከንድ (ወይም በሰከንድ 0.25 ሜጋ ባይት) መረጃው መለዋወጥ የሚያስችል አገልግሎት የመጀመሪያዎቹ ስማርት ተንቀሳቃሽ ስልኮች ለገበያ ሲቀርቡ ተዋወቀ፡፡ እጅግ ፈጣን ባይሆንም ገመድ አልባ የኢንተርኔት በማቅረብ የመጀመሪያው ሲሆን የቪዲዮ ጥሪ እንዲኖር አስችሏል፡፡ ለማስረዳት ያህልም 4.26 ጊጋ ባይት መረጃ ለማውረድ ከአምስት ሰዓት በላይ ይጠይቃል። 4ጂ 2010 ደግሞ 4 ጂን ይዞ ብቅ አለ። በሚሰጠው ፈጣን ግንኙነትም የሞባይል ጌሞችን እስከወዲያኛው ቀይሯል፡፡ አሁን በሥራ ላይ የሚገኘው በጣም ፈጣኑ 4 ጂ የሞባይል ኔትዎርክ በአማካይ በሰከንድ 45 ሜጋ ባይት ይሰጣል። ኢንዱስትሪው በሰከንድ አንድ ጊጋ ባይት የመድረስ ህልም አለው። በ 3 ጂ ተመሳሳይ ፊልም ለማውረድ ከአምስት ሰዓታት በላይ ይወስድ የነበረው ጊዜ 4 ጂ ላይ ከ 8 ደቂቃ በታች እንዲሆን አስችሏል ተብሎ ይገመታል። 5ጂ ምን ማለት ነው? የቀጣዩ ትውልድ የሞባይል በይነመረብ ግንኙነት ሲሆን በጣም ፈጣን ዳታ የማውረድ እና የመጫን አገልግሎትን ይሰጣል። የሬዲዮ ሰፔክትረም በመጠቀም እጅግ በጣም ብዙ መሣሪያዎችን በአንድ ጊዜ የሞባይል ኢንተርኔቱን እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ፡፡ አሁን በስማርት ስልኮቻችን የምንሠራቸውን ማንኛውንም ነገር በፍጥነት እና በተሻለ ለማከናወን ያስችለናል። ድሮኖች፣ መኪኖች እና የሞባይል ጌሞች በዚህ ፈጣን ኢንተርኔት በመጠቀም የተሻለ ግልጋሎት ይሰጣሉ፡፡ የሞባይል ቪዲዮዎች በቅጽበት እና ከመቆራረጥ ነፃ በሆነ መልኩ ይቀርባሉ ፡፡ የቪዲዮ ጥሪዎች ይበልጥ ንጹህ እና መንቀጥቀጥ ሳይኖራቸው ለደንበኞች ይደርሳሉ። ቴክኖሎጂውን በመጠቀም በሚጠለቁ ቁሳቁሶች አማካኝነት ድንገተኛ ሁኔታ ሲከሰት ወዲያውኑ ሐኪሞችን በማሳወቅ ጤንነትዎን በወቅቱ ሊቆጣጠሩት ይችላሉ ፡፡ 5 ጂ ከ 10 እስከ 20 እጥፍ የሆነ ፍጥነት ማሳካት ይችላል ይላል የቺፕ አምራቹ ኩዋልኮም፡፡ በዚህ ፍጥነት በአንድ ደቂቃ ባለከፍተኛ ጥራት ፊልም ማውረድ ያስችሉዎታል። ኢትዮቴሌኮም 5 ጂን ለደንበኞቹ ለማድረስ የያዘው ዕቅድ እንዳለ ከቢቢሲ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ አልሰጠም።
news-50833026
https://www.bbc.com/amharic/news-50833026
''በፍርሀት የምንኖርና በሃገራችን እንደ ሁለተኛ ዜጋ የምንቆጠር ሰዎች ሆነናል''
ልክ እንደ አብዛኛዎቹ ህንዳውያን ሙስሊሞች የወደፊቱ እጣ ፈንታዬ ምን ሊሆን እንደሚችል በማሰብ ነው ቀናቶቼን የማሳልፈው።
በሀይማኖቴ ምክንያት ስራ አላገኝ ይሆን? ተከራይቼ ከምኖርበት ቤት እባረር ይሆን? የደቦ ጥቃት ይደርስብኝ ይሆን? ይሄ ፍራቻዬ ማብቂያ ይኖረው ይሆን? በዩኒቨርሲቲያችን አለመረጋጋት ተከስቶ በነበረበት ወቅት እናቴ '' አይዞሽ ትዕግስት ይኑርሽ'' ብላኝ ነበር ትላለች በህንዷ ዋና ከተማ ኒው ደልሂ በሚገኘው ጃሚያ ሚሊያ ኢዝላሚያ ዩኒቨርሲቲ ትምህርቷን የምትከታተለው ሪካት ሀሽሚ። በዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ተደብድበዋል፣ በቤተ መጻህፍትና የተማሪዎች ማደሪያ ውስጥ ጭምር አስለቃሽ ጭስ ጥቅም ላይ ውሏል፤ ይሄ ሁሉ የሆነው ሀገሪቱ ያወጣችውን አዲስ ህግ ለመቃወም የወጡትን ተማሪዎች ለማስቆም ነበር። • ክፍያ ባልከፈለ ተማሪ እጅ ላይ ማህተም የመታው ትምህርት ቤት ተወገዘ • ህንድ አሜሪካን ይጎዳል የተባለ የንግድ ታሪፍ ልታስተዋውቅ ነው በአዲሱ ህግ መሰረት ጥቃት የሚደርስባቸውና ከሌሎች ሀገራት የሚመጡ የስድስት ሀይማኖት ተከታዮች የህንድ ዜግነት የሚያገኙ ሲሆን ከባንግላዲሽ፣ ፓኪስታን እና አፍጋኒስታን የሚመጡ ሙስሊሞች ግን ዜግነት ማግኘት አይችሉም። ሙስሊሞች ተመርጠው እንዲገለሉ የተደረገ ሲሆን ይህ ህጋዊ የማግለል ሂደት ነው ለበርካታ ተማሪዎች ለተቃውሞ ወደ መንገድ መውጣት ምክንያት የሆነው። ''ፖሊስ ተማሪዎቹ መኪናዎችን በእሳት እንዳቃጠሉና አመጽ እንዲነሳ ማድረጋቸውን ገልጿል፤ ነገር ግን የሚያቀርቡት ምንም አይነት ማስረጃ የላቸውም'' ትላለች። ''ማንም ሰው ጉዳት አልደረሰበትም ይላሉ፤ ታዲያ ተጎድተው ሆስፒታል የተኙት ተማሪዎች ከየት መጡ? '' በኒው ደልሂ ዩኒቨርሲቲ የጥርስ ህክምና በማጥናት ላይ ሲሆን የምገኘው እስከዛሬ በነበረኝ ቆይታ በርካታ ሰላማዊ የሆኑ ተቃውሞዎችን ተመልክቻለው። የተቃውሞዎቹ አካል ባልሆንም ነገሮች በአጭር ጊዜ ውስጥ ከቁጥጥር ውጪ ሲሆኑ ተመልክቻለሁ፤ በግርግሩም ተጎጂ ሆኛለሁ። ፖሊስ ተማሪዎች ላይ ተከታታይ ጥቃቶችን ሲፈጽም ተመልክቻለሁ። ፖሊሶች ወደ ማደሪያ ክፍሎቻችን ሲመጡ አስታውሳለሁ። የክፍሉን መብራት አጥፍተን የሌለን ለማስመሰል ሞክረናል። እንደ እድል ሆኖ ፖሊሶቹ ሳያገኙን ምሽቱ አለፈ። ነገር ግን ትንሽ ቆይተን አንድ ነገር ተገነዘብን። ፖሊሶቹ ግቢውን ሲያስሱ የነበረው መንግሥትን ለመቃወም የወጡትን ብቻ ፍለጋ ሳይሆን ሙስሊሞችን እንደሆነ። በልጅነቴ በርካታ የሂንዱ ሃይማኖት መዝሙሮችን እየሰማሁ ከእንቅልፌ ስነቃ አስታውሳለሁ። ሙስሊም ቤተሰቦቼ በብዛት የሂንዱ ሀይማኖት ተከታዮች በሚኖሩበት ምስራቃዊ ኦዲሻ ግዛት ነበር ጎጇቸውን የቀለሱት። ሁሌም ቢሆን በዓላት ሲደርሱ ተሰባስበን ነበር የምናከብረው። የኢድ በአል ላይ ሂንዱ ጎረቤቶቻችን እኔና ወንድምና እህቶቼን እጃችን ላይ ሂና ሲቀቡን አስታውሳለሁ። አንዳንድ የሂንዱ ሀይማኖት ተከታይ ጓደኞቼ ደግሞ በሩዝና በስጋ በቆንጆ ሁኔታ የሚሰራውን 'ቢርያኒ' ለመብላት ወደቤታችን ይመጡ ነበር። ከምንኖርበት አካባቢ መስጂድ ባይኖርም አባቴ ግድ አልነበረውም፤ ምክንያቱም እስልምናን አይከተልም ነበር። እናቴ ግን በቤት ውስጥ በቀን አምስት ጊዜ የሰላት ጸሎት ታደርስ ነበር። • ቻይና ሙስሊም ልጆችን ከቤተሰቦቻቸው እየነጠለች ነው በጣም ብዙ የሂንዱ ሃይማኖት ተከታዮች በሚማሩበት ትምህርት ቤት ነበር የምማረው፤ አንድም ቀን ስለሀይማኖታችን ልዩነት ስናወራ አላስታውስም። እስከ አሁኗ ሰአት ድረስ ሙስሊምነቴ መለያዬ ሆኖ አያውቅም ነበር። አሁን ነገሮች ሁሉ በፍጥነት ተቀያይረዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ 'ስጋ ተመጋቢዎቹ' እየተባልን መለየት ተጀምሯል። ማህበረሰቡን የሚበክሉ ደፋሪዎች፣ ፓኪስታንን የሚደግፉ አሸባሪዎችና ህንድን ለመቆጣጠር የተነሱ ማህበረሰቦች ናቸው እንባላለን። እውነታው ግን በፍርሀት የምንኖርና በሃገራችን እንደ ሁለተኛ ዜጋ የምንቆጠር መሆናችን ነው። የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልእክት ''ሰላም፣ አንድነት እና ወንድማማችነታችንን የምናጠናክርበት ጊዜ ላይ እንገኛለን'' ብለዋል። ከአንድ ቀን ቀደም ብለው ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች እንዲህ የሚል መልእክት አስተላልፈዋል። '' ንብረቶችን በእሳት የሚያቃጥሉ በቴሌቪዥን መታየት ይችላሉ እኮ... በለበሱት ልብስ ልንለያቸውም እንችላለን።'' ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ማለቱ በቀጥታ ሙስሊሞችን ነው የሚመለተከው፤ ስለሂጃባችንም ነው አስተያየቱን የሰጠው ትላለች ሪካት ሀሽሚ። ሂጃብ ማድረግ የጀመርኩት በ16 ዓመቴ ቢሆንም አሁን ላይ የ 22 ዓመት ወጣት ሆኜ ግን ከምን ጊዜውም በበለጠ ስለሀይማኖቴ የሚነገረው የተሳሳተ አስተያየት ሰላም ይነሳኛል። ማግለልን እንደ አማራጭ የሚወስዱ ፖሊሲዎችን ከመተቸት ወደኋላ አልልም። ነገር ግን ሁሌም ቢሆን ብሄራዊነትን የማልወድና ጸረ ሂንዱ ተደርጌ ነው የምቆጠረው። ሀይማኖትና ብሄራዊነት በእጅጉ የተጣበቁበት አስቸጋሪና አስፈሪ ጊዜ ላይ ነው የምንገኘው። አንዳንድ ጊዜ በመንገድ ላይ ሂጃብ ለብሼ ስሄድ ሰዎች በትኩረትና በመጠራጠር ሲመለከቱኝ አስተውላለሁ። ሁሉንም አቅፋ የምትይዘውና እኔ የማውቃት ህንድ ይህች አይደለችም። 200 ሚሊየን የምንሆነው የህንድ ሙስሊሞች በፍርሀት እየኖርን ነው።
news-52932154
https://www.bbc.com/amharic/news-52932154
በኮቪድ-19 ምክንያት በክትባቶች ስለተስጓጎሉ በቀን 6 ሺህ ሕጻናት ይሞታሉ
ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወዲህ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕጻናት ሊሞቱ ይችላሉ። የሚሞቱት ታዲያ በኮሮናቫይረስ አይደለም። በሽታው ባመጣው ጣጣ እንጂ።
በብዙ የዓለም ደሀ አገራት ኮቪድ-19 በደቀነው ስጋት የተነሳ ለሌሎች በሽታዎች ይሰጥ የነበረውን የክትባት መርሐ ግብርን አመሳቅቅሎታል፤ አደናቅፎታል። በትንሹ 68 አገራት ለሕጻናት ይሰጡት የነበረውን መደበኛ የክትባት መርሐግብራቸው በኮቪድ-19 ምክንያት እንደተቋረጠባቸው የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። አገራቱ የክትባት ዘመቻን እንዲያቋርጡ የተመከሩትም በዚህ የዓለም ጤና ድርጅት በራሱ ነው። ምክንያቱም የዘመቻ ክትባት የማኅበረሰብ ጥግግትን ይጨምራል፤ ይህ ደግሞ ለኮሮናቫይረስ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል በሚል ስጋት ነው። ከአንድ በሽታ እድናለሁ ብሎ በሌላ በሽታ መያዝ በዚህ የወረርሽኝ ዘመን ጥግግት አደጋ እንደሚያመጣ እውን ሆኖ ሳለ በዚያው መጠን መደበኛ ክትባቶች መደናቀፋቸው ደግሞ ዞሮ ዞሮ ለብዙ ሕጻናት ሞት ምክንያት መሆኑ እየተገለጸ ነው። ብዙ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችም ጉዳዩ አሳስቦናል እያሉ ነው። የተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ)፣ ሳቢን የቫክሲን ኢንስቲትዩት (ጋቪ) እና የክትባት ቅንጅት (ቫክሲን አሊየንስ) ይህ የክትባቶች መስተጓጎል እያስጨነቀን ነው፤ አንድ መፍትሄ እንፈልግ እያሉ ነው። በአንድ በኩል ነፍስ እናድናለን እያልን በሌላ በኩል ነፍስ እያጠፋን ነው፤ የሚሉት ድርጅቶቹ ክትባት ይቁም የተባለበትን ሦስት አበይት ምክንያቶችን ጠቅሰዋል። አንዱ ወላጆች ለክትባት ብለው ከቤት ሲወጡ ቫይረሱ እንዳይዛቸው ስለሚሰጉ ነው። ሁለተኛው ደግሞ የጤና ባለሞያዎች በሙሉ ኃይላቸው እየተረባረቡ ያሉት ኮሮናቫይረስን ለመዋጋት በመሆኑ ለሌሎች ክትባቶች ጊዜም ቦታም የላቸውም። ሦስተኛው ምክንያት ደግሞ ክትባቶችን ወደ አገር ውስጥ ብሎም ወደ ጤና ጣቢያዎች ለማድረስ የጉዞ እቀባዎች በመኖራቸው ነው። "ለምሳሌ ኩፍኝ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው፤ ኮሌራም እንዲሁ" ይላሉ የዩኒሴፍ ዳይሬክተር ሄኔሪታ ፎሬ። "ይህ ሌላ ያላሰብነው ጥልፍልፍ ችግር ይዞብን ይመጠል። እነዚህ አሁን እያንሰራሩ ያሉ የሕጻናት በሽታዎች ዓለም የተቆጣጠራቸው በሽታዎች ነበሩ" ሲሉ አስታውሰው "አሁን ከፍተኛው ስጋት፤ በጥሩ ሁኔታ ሥርጭታቸው ተገትቶ የነበረውና በመጥፋት ላይ የነበሩ በሽታዎች ዳግም የማንሰራራት ዕድል ማግኘታቸው ነው" ብለዋል። ለምሳሌ በኒጀር ከአንድ ሺህ ሰዎች በላይ በኮቪድ-19 ተይዘዋል። በዋና ከተማዋ ወትሮ በወላጆችና ልጆች ጢም ብሎ ይሞላ የነበረ ጤና ጣቢያ ባዶውን በጸጥታ ተውጧል። ይህም ወረርሽኙ የፈጠረው ፍርሃት ነው። መደበኛ ክትባት መቋረጡን ተከትሎ አካል ጉዳትን ብሎም ሞትን የሚያስከትለው ፖሊዮ በዚያች አገር እያንሰራራ ነው። በጥቅምት ወር ብቻ ፖሊዮ በ4 ኒጀራዊያን ህጻናት ላይ ተመዝግቧል። ይህ ለኒጀርም ለዓለምም መልካም ዜና አይደለም። 80 ሚሊዮን ሕጸናት ክትባት አምልጧቸዋል ወትሮ ይሰጡ የነበሩ መደበኛ ክትባቶች በኮቪድ-19 ምክንያት በመስተጓጎላቻ በደቡብ ምሥራቅ እሲያ 34.8 ሚሊዮን፣ በአፍሪካ 22.9 ሚሊዮን ሕጻናት ክትባት አምልጧቸዋል። በኔፓልና በካምቦዲያ ኩፍኝ የተቀሰቀሰ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ደግሞ ኮሌራ፣ ቢጫ ወባና ኩፍኝ ወረርሽኞች ማንሰራራታቸው ተመለክቷል። የጆንስ ሆፕኪንስ ብሉምበርግ የኅብረተሰብ ጤና ማዕከል ባጠናው ጥናት እነዚህ መደበኛ ክትባቶች በመስተጓጎላቸው በዓለም በየቀኑ 6 ሺህ ሕጻናት እየሞቱ ነው። የዓለም ጤና ድርጅት የክትባት ጉዳዮች ክፍል ኃላፊ ኬቲ ኦብራያን እንደተናገሩት እየከሰሙ የነበሩ በሽታዎች አሁን ዳግም እንዳያንሰራሩ ፍርሃት ገብቶናል ብለዋል። "በሽታዎቹ አንዴ ማንሰራራት ከጀመሩ በመላው ዓለም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የልጆች ሞት ይመዘገባል" ብለዋል። ዳይሬክተሯ ኬቲ እንደሚሉት ይህ ሁኔታ እንዳይከሰት ማድረግ ይቻላል፤ የመንግሥታት ትብብርና ቁርጠኝነት ካለ። ይህ ከመደበኛ ክትባቶች መስተጓጎል ጋር ተያይዞ የተደቀነው ስጋት ለውይይት የቀረበው የዓለም መንግሥታት ትናንት ሐሙስ የዓለም የክትባት ቀንን በማመልከት በቪዲዮ በተበሰቡበት ወቅት ነው። የስብሰባው አሰናጅ ዩናይትድ ኪንግደም ነበረች። በዚህ ስብሰባ ማጠቃለያ ሀብታም አገራት እና በጎ አድራጊዎች በድምሩ 7.4 ቢሊዮን ዶላር የሚሆን ገንዘብ እንዲለግሱ ይጠበቃል። ይህም እነ ጋቪ እና ቫክሲን አሊያንስ ያሉ ድርጅቶች ወሳኝ ክትባቶችን ለድሀ አገራት ሳያቋርጡ እንዲያቀርቡ ለማስቻል ይረዳቸዋል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ ስብሰባ በድሀ አገራት መደበኛ ክትባቶች በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጊዜ እንዴት ሊሰጡ ይገባል ለሚለው ቁልፍ ጥያቄ ያቀረበው ቁልጭ ያለ መፍትሄ የለም።
news-48782366
https://www.bbc.com/amharic/news-48782366
የኤርትራ መንግሥት፡ 'የካቶሊክ ጤና ተቋማትን መውሰዴ ትክክል ነው' አለ
የኤርትራ መንግሥት በቅርቡ የካቶሊክ ቤተክርስትያን ንብረት የሆኑ የጤና አገልግሎት መስጫ ጣብያዎችን መውረሱን ተከትሎ ለመጡ ትችቶች ምላሽ ሰጥቷል።
በተባበሩት መንግሥታት የኤርትራ ልዩ መልዕክተኛ ዳንዔላ ካርቬትዝ፤ «ጉዳዩ የኤርትራ መንግሥት ምን ያህል ሰብዓዊ መብትን እየጨቆነ እንደሆነና ሁኔታዎች እንዳልተቀየሩ የሚያሳይ ነው» ሲሉ ተደምጠዋል። የኤርትራ መንግሥት «መልዕክተኛዋ ድምዳሜ ላይ የደረሱት የተሳሳተ መረጃ ይዘው ነው» ሲል ወርፏቸዋል። በኤርትራ መንግሥት መረጃ ሚኒስቴር በኩል የወጣው ምላሽ «እንደ ዓለማዊ [ሴኩላር] ሃገር ማንኛውም ዓይነት የኃይማኖት ተቋም የሪፈራል ሕክምና ሊሰጥ አይገባም» ሲል ያትታል። «በመሆኑም ተቋማት በመረጡት መስክ ተሰማርተው ሕብረተሰባዊ አገልግሎት መስጠት አይችሉም፤ ይህ የእነርሱ ተከታይ ያልሆነ ላይ አድልዎ እንደማድረስ የሚቆጠር ነው» ሲል መግለጫው ያክላል። • ኤርትራ ካሳ ጠየቀች የማስታወቂያ ሚኒስቴሩ መግለጫ 'ሁሉም ኃይማኖታዊ ተቋማት ጤና ተቋሞቻቸውን ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የማስረከብ ግዴታ እንዳለባቸው' ያስታውቃል። በሌላ ቋንቋ መንግሥት ሕጉን ተከተለ እንጂ ስህተት አልሠራም ነው የኤርትራ መንግሥት አመክንዮ። ባለፈው ወር መገባደጃ ገደማ ነበር የኤርትራ መንግሥት የሮማ ካቶሊክ ቤተ-ክርስትያን ንብረት የሆኑ የጤና ተቋማትን የወረሰው። 22 ያክል የጤና አገልግሎት ሰጭ ጣቢያዎቿ የተዘረፉባት የኤርትራ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስትያን የመንግሥት ድርጊት ተቃውማለች። የጤና ጣብያዎቹ በመንግሥት እጅ መውደቅ በገጠር አካባቢ ላሉ እናቶች እና ሕፃናት እክል ይሆናል ቢባልም የኤርትራ መንግሥት በጤና አሰጣጥ በኩል አልታማም ብሏል። • ኤርትራ የሃይማኖት እሥረኞችን ፈታች
news-54776092
https://www.bbc.com/amharic/news-54776092
ኮሮናቫይረስ፡ ዋይት ሀውስ በዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ ንግግር ተቆጣ
ዋይት ሀውስ፤ ከፍተኛ የተላላፊ በሽታዎች ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ፤ ስለ ኮሮናቫይረስ ያደረጉት ንግግር ፖለቲካዊ አላማ ያለው ነው ሲል ከሰሰ።
ዶ/ር ፋውቺ ከዋሽንግተን ፖስት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ አሜሪካ “ከፍተኛ ጉዳት ገጥሟታል” ብለዋል። አሜሪካ ከየትኛው አገር በበለጠ በወረርሽኙ ሳቢያ ዜጎቿን አጥታለች። በጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ መረጃ መሠረት ከ230,000 በላይ ሰዎች ሞተዋል። ከዘጠኝ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ደግሞ በቫይረሱ ተይዟል። ዶ/ር ፋውቺ በቃለ ምልልሱ ላይ “ወደቀዝቃዛው ወቅት ስንገባ ነገሮች ይባባሳሉ” ብለዋል። በተያያዥም ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ተቀናቃኛቸው ጆ ባይደን ስለ ወረርሽኙ ያላቸውን አቋም ገምግመዋል። ባይደን ለቫይረሱ ተገቢውን ትኩረት እንደሰጡት “ከሕብረተሰብ ጤና እና ከምጣኔ ሀብት አንጻርም በቁምነገር እየተከታተሉት ነው” በማለት ገልጸዋል። አሜሪካ የሕብረተሰብ ጤናን በተመለከተ ለውጥ ማምጣት እንዳለባት አሳስበዋል። በዚህ የዶ/ር ፋውቺ አስተያየት ዋይት ሀውስ ደስተኛ አልሆነም። ባይደን ምርጫውን እንዲያሸንፉ የሚገፋ ምላሽ ነው በማለትም ዶክተሩን ተችተዋል። ቃል አቀባዩ ጁድ ደሬ፤ “አስተያየቱ ተቀባይነት የለውም። ከመርህ ውጪ ነው። ዶ/ር ፋውቺ የኮሮናቫይረስ ግብረ ኃይል አባል እንደመሆናቸው ለለውጥ መገፋፋት ነበር የሚጠበቅባቸው። እሳቸው ግን ፕሬዘዳንቱን በመተቸት ለተቀናቃኛቸው ወገንተኝነት አሳይተዋል” ብሏል። የወረርሽኙ ጉዳይ በትራምፕ እና በባይደን መካከል ዋነኛ ከሆኑት መከራከሪያ ነጥቦች አንዱ ነው።ባይደን “ውሳኔያችን ሳይንስን የተመረኮዘ መሆን አለበት” ብለው፤ ምርጫውን ካሸነፉ እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ሊኖር እንደሚችል ጠቁመዋል። ትራምፕ በበኩላቸው፤ ባይደን እንቅስቃሴ ላይ ገደብ በመጣል አሜሪካውያንን የምጣኔ ሀብት ቀውስ ውስጥ ይከታሉ ብለዋል። “ባይደንን ከመራጥችሁ ትምህርት ቤት አይከፈትም። ተማሪዎች አይመረቁም። ሠርግ አይኖርም። ገና አይከበርም” ብለዋል። ባይደን የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ኮሮናቫይረስን ለመከላከል የወጡ መርሆችን ተከትለው ነው። በሌላ በኩል ትራምፕ አካላዊ ርቀት ሳይጠበቅ በርካታ ዜጎች የተገኙባቸው የምረጡኝ ቅስቀሳዎች አካሂደዋል። ኮሮናቫይረስ በፕሬዝዳንት ትራምፕ አንደበት!
news-49399048
https://www.bbc.com/amharic/news-49399048
አሸዋ የሰረቁ ፈረንሳያውያን ጥንዶች ለእስር ተዳረጉ
40 ኪሎ ግራም አሽዋ ሰርቀዋል ተብለው የተጠረጠሩት ፈረንሳያውያን ጥንዶች ቢያንስ የስድስት ዓመት እስራት ይጠብቃቸዋል ተባለ።
አውሮፓውያን ጉብኚዎች በተለይ ደግሞ ጣሊያናዊያን ከደሴቷ አሸዋ ከወሰዱ በኋላ በግብይት ድረ-ገጾች ላይ ለጨረታ በከፍተኛ ገንዘብ ይሸጣሉ። ጥንዶቹ በሜዲትራኒያን ባህር ላይ ከሚገኑ ደሴቶች አንዷ ከሆነችው ሰርዲኒያ ደሴት ወስደዋል የተባለው 40 ኪሎ ግራም አሸዋ መኪናቸው ውስጥ ተገኝቷል። ለጉብኝት ወደስፍራው ያቀኑት ጥንዶቹ አሸዋውን የወሰድነው "እንደ ማስታወሻ" እንዲሆነን እንጂ አሸዋ መውሰድ ወንጀል እንደሆነ እያወቅን አይደለም ብለው ተከራክረዋል። • ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ፡ ያናገሩና ያነጋገሩ ድርሰቶቹ • አፋር ውስጥ የሞተችው እስራኤላዊት የገጠማት ምን ነበር? • መተማ ዮሐንስ በተያዙት ተሽከርካሪዎች ላይ ምርመራ እየተደረገ ነው ዝና ገናናው የሰርዲኒያው ነጭ አሸዋ እንደ ህዝብ ንብረት የሚቆጠር ሲሆን ከደሴቱ ላይ መውሰድም የተከለከለ ነው። የደሴቷ ነዋሪዎች አሸዋውን ጨምሮ ሌሎች ንብረቶቻችን እየተዘረፉብን ነው ሲሉ በተደጋጋሚ ቅሬታቸውን ያሰሙ ነበር። ከሰርዲኒያ ደሴት ላይ ዛጎሎች፣ ልዩ ጠጠሮች እና አሸዋ መውሰድ ወንጀል ተደርጎ ከሁለት ዓመት በፊት በህግ ከ1-7 ዓመት የሚያስቀጣ ሕግ ሆኖ ተቀምጧል። ሁለቱ ፈንሳያውያን በአሸዋ ከተሞሉ 14 ፕላሰቲክ ጠርሙሶች ጋር በቁጥጥር ሥር የዋሉት ከሰርዲኒያ ደሴት ወደ ፈንረንሳይ የሚወስዳቸው መርከብን ከተሳፈሩ በኋላ ነበር። ጥንዶቹ በአሸዋ ከተሞሉ 14 ፕላሰቲክ ጠርሙሶች ጋር ነበር በቁጥጥር ሥር የዋሉት የደሴቷ ባለስልጣናት በየዓመቱ ከደሴቷ ብዙ ቶን አሽዋ እየተሰረቀ መሆኑ እጅጉን አሳስቧቸዋል። "አሽዋማ የባህር ዳርቻዎች የደሴቷ መስህብ ናቸው። የደሴቷ አሸዋ እየተሸረሸረ እና በስርቆት እየቀነሰ ነው። " ሲሉ የደሴቷ ነዋሪ እና የተፈጥሮ ሃብት ተመራማሪው ፒአረሉጊ ኮኮ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አውሮፓውያን ጉብኚዎች በተለይ ደግሞ ጣሊያናዊያን ከደሴቷ አሸዋ ከወሰዱ በኋላ በግብይት ድረ-ገጾች ላይ ለጨረታ በከፍተኛ ገንዘብ ይሸጣሉ።
55882702
https://www.bbc.com/amharic/55882702
በኢስዋቲኒ (ስዋዚላንድ) በኮቪድ ምክንያት የአስክሬን መጠቅለያ እጥረት ተከሰተ
በኢስዋቲኒ (ስዋዚላንድ) በኮቪድ ምክንያት የአስክሬን መጠቅለያ እጥረት ተከሰተ
ስሟን ከስዋዚላንድ ወደ ኢስዋቲኒ የቀየረችው የደቡባዊ አፍሪካ አገር በኮቪድ ታማሚዎች ምክንያት የአስክሬን መጠቅለያ እጥረት ገጥሟታል፡፡ በሉቦምቦ የሪፈራል ሆስፒታል የጤና ሠራተኞች እንዲሁም በጉድሼፐርድ ሚሽን ሆስፒታል የጤና መኮንኖች ለታይምስ ኦፍ ስዋዚላንድ እንደተናገሩት የአስክሬን ላስቲክ እጥረት በማጋጠሙ የተነሳ ሬሳ በአንሶላ ለመጠቅለል ተገደዋል፡፡ እጥረቱ የተከሰተው ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ ነው፡፡ ችግሩን ተከትሎ የአስክሬን ፌስታል አቅራቢዎች እንዲወዳደሩ ጨረታ ወጥቷል፡፡ የጤና ሚኒስትር ሊዚ ንኮሲ ስለችግር መጀመርያ መረጃ እንዳልደረሳቸው ተናግረዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ ትንሽዋ ደቡብ አፍሪካዊት አገር ኢስዋቲኒ የጤና መኮንኖች በበቂ ባለመኖራቸው የዓለም ጤና ድርጅት ትብብር እንዲያደርግ ጠይቃለች፡፡ ይህን ተከትሎም 28 የጤና መኮንኖች ወደዚያች አምርተዋል፡፡ ከነዚህ መሀል 11 ሐኪሞች የተላኩት በታላቋ ብሪታኒያ አማካኝነት ነው፡፡ በተህዋሲው ክፉኛ የተሽመደመደችውን ደቡብ አፍሪካን የምትዋሰነው ኢስዋቲኒ 15ሺ ዜጎቿ ታመውባታል፡፡ 574 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል፡፡ ኢስዋቲኒ በአፍሪካ በቆዳ ስፋት ትንሽ ከሚባሉና የባሕር በር ከሌላቸው አገራት ተርታ ስትሆን የሕዝብ ብዛቷም 1.1 ሚሊዮን አካባቢ ብቻ ነው፡
50470264
https://www.bbc.com/amharic/50470264
ሳይንቲስቶች ውሃ ለመቆጠብ ዓይነ-ምድር አንሸራታች ሽንት ቤት ሠርተዋል
አሜሪካዊያን ሳይንቲስቶች ውሃ መቆጠብ ያስችል ዘንድ ዓይነ-ምድር አንሸራታች ቅባት ሠርተናል እያሉ ነው።
የፔን ስቴት ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች፤ አዲሱ ፈጠራ መጸዳጃ ቤት ውስጥ ዓይነ-ምድርን ለመጠራረግ የምናፈሰውን ውሃ በ90 በመቶ ይቀንሳል ይላሉ። አልፎም የመፃዳጃ ቤት ነጭ የሸክላ መቀመጫ ላይ የሚከማችን ባክቴሪያ ያጠፋል፤ አላስፈላጊ ሽታንም ያስወግዳል ይላሉ ተመራማሪዎቹ። • "በኢትዮጵያ 93 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ መጸዳጃ ቤት የለውም" ቅባቱ የሽንት ቤት መቀመጫ ላይ የሚረጭ ሲሆን ዓይነ-ምድርና ሽንትን በፍጥነት ወደታች እንዲዘልቅ ያደርጋል። በየቀኑ በዓለማችን 141 ቢሊዮን ሊትር ውሃ ለሽንት ቤት ጥቅም ይውላል። አፍሪካ ውስጥ ለመጠጥ ውሃ የሚውለው መጠን ከዚህ አሃዝ በስድስት እጥፍ ያነሰ ነው። የተመራማሪዎቹ ዋነኛ ዓላማ ፈጠራው ሰዎች ለዓይነ-ምድር መጠራሪጊያ የሚያውሉትን ንፁህ ውሃ መጠን መቀነስ ነው። • ስለ አንጀታችን የማያውቋቸው ስድስት አስገራሚ እውነታዎች «ቡድናችን ተፈጥሮን መሠረት ያደረገ ጠንካራ ፈሳሽ ሠርቷል። መፀዳጃ ቤት ራሱን በራሱ እንዲያፀዳ የሚያደርገው ፈሳሽ ምርት ፀረ-ባክቴሪያ ነው» ይላሉ የፔን ስቴት ዩነቨርሲቲው ተባባሪ ፕሮፌሰር ታክ-ሲንግ ዎንግ። «ዓይነ-ምድር ከመጸዳጃ ቤት መቀመጫ ላይ ሲጣበቅ ለተጠቃሚዎች ቀፋፊ ከመሆኑ ባሻገር ጤናማ አይደለም» የሚሉት ተመራማሪ ዓላማቸው በዓለም ዙሪያ በጎ ተፅዕኖ ፈጣሪ ቴክኖሎጂ መፍጠር እንደሆነ ያስረዳሉ። ፈጠራው መቼ ለገበያ ቀርቦ ሰዎች ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ለጊዜው የተባለ ነገር የለም።
news-53775703
https://www.bbc.com/amharic/news-53775703
ሃጫሉ ሁንዴሳ፡ የጥቃት ሰለባዎች አሁንም ማስፈራሪያና ዛቻ እየደረሰባቸው መሆኑን ኢሰመኮ ገለጸ
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ባደረገው ምርመራ የጥቃት ሰለባዎች የነበሩት ሰዎች አሁንም የደኅንነት ስጋት እንዳለባቸው አመለከተ።
ከሃጫሉ ግድያ በኋላ በተከሰተ ሁከት ከፍተኛ የንብረት ውድመት ከተከሰተባቸው ስፍራዎች መካከል ሻሸመኔ ከተማ አንዷ ነች ኮሚሽኑ ለሁለት ሳምንታትም ከ40 በላይ ችግሩ ተከስቶባቸዋል በተባሉ የኦሮሚያ አካባቢዎች ላይ ያሉ ጉዳት የደረሰባቸውን ግለሰቦች፣ ቤተሰቦቻቸውን እንዲሁም ምስክሮችንና የመንግሥት አካላትን በማነጋገር መረጃ በማሰባሰብ አሁን ያሉበትን ሁኔታ በመገምገም ዝርዝር የምርመራው ግኝቶችና የመፍትሄ ሀሳቦች አቅርቧል። የነዋሪዎች የጥቃት ስጋት ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ ላይ ምርመራ በተደረገባቸው በአብዛኞቹ አካባቢዎች መረጋጋት ያለ ቢሆንም በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ በሚኖሩ ሰዎች ዘንድ አጠቃላይ የደኅንነት ስጋት እንዳለና ተጎጂዎቹ አሁንም በተለያዩ ቡድኖች የጥቃት ማስፈራሪያና ዛቻዎች እየደረሳቸው እንደሆነ ለኮሚሽኑ መናገራቸውን ጠቅሷል። መግለጫው እንደማሳያ በዶዶላ ከተማ የሚገኙ ተጠቂዎች በሐምሌ 9 ቀን 2012 ዓ.ም ከ60 በላይ ሰዎች ስም ተዘርዝሮ ከተማውን ለቅቀው እንዲወጡ ካልሆነ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው የሚገልጽ የማስጠንቀቂያ ወረቀት መሰራጨቱን ከነዋሪዎች መረጃ አግኝቻለሁ ብሏል። እንዲሁም በባቱ (ዝዋይ) ከተማ ተጎጂዎች ከተማውን ለቅቀው እንዲወጡ የሚል ማስፈራሪያ በስልክና በአካል እየደረሳቸው መሆኑን፤ በሻሸመኔ ከተማ ደግሞ ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች ቤት ለቤት በመሄድ ከ5 እስከ 10 ሺህ ብር ካላመጣችሁ አሁንም ንብረታችሁን እናቃጥላለን እንዲሁም እንገላችኋለን በማለት ዛቻ እንደሚደርሳቸው ተናግረዋል ብሏል። ከዚህ በተጨማሪም በተወሰኑ አካባቢዎች በመንግሥት የፀጥታ አካላት ሳይቀር ሰዎች እየተደበደቡና ዛቻ እየተፈፀመባቸው መሆኑን የጠቀሰው የኮሚሽኑ ሪፖርት በምሳሌነትም የቡራዩ ከተማ በተለይ ከታ ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ እንዲሁም የጉና ወረዳ ነገሌ ከተማ ጠቅሷል። ኮሚሽኑ በነዋሪዎች ላይ ያለውን የደኅንነት ስጋት በተመለከተም መንግሥት የሰዎችን ሰብዓዊ መብቶች አክብሮ የመንቀሳቀስና በሌሎች መንግሥታዊ ባልሆኑ አካላትም ጥሰት እንዳይከሰት የመከላከልና ጥበቃ የማድረግ ኃላፊነት አለበት ብሏል። የችግሩ ሰለባዎች ከጉዳታቸው ሳያገግሙ ለሌላ ጥቃት እንዳይዳረጉ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ጠቅሶ፤ የሚመለከታቸው የፌዴራል መንግሥትና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አስተዳደርና የፀጥታ አካላት የነዋሪዎችን ደኅንነት እንዲያስጠብቁ፣ አጥፊዎችን እንዲቆጣጠሩና የሕግ አስከባሪ እና የፀጥታ አካላት ኃላፊነታቸውን ሲወጡ ሰብዓዊ መብቶች እንዲያከብሩ ጠይቋል። የተፈናቀሉ ሰዎች ያሉበት ሁኔታ ኮሚሽኑ ባደረገው ምርመራ አለመረጋጋቱ ተከስቶባቸው በነበሩት አካባቢዎች የሚገኙ ሰዎች "አካላዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት እንደደረሰባቸው" ለማወቅ እንደቻለ ገልጿል። ስለዚህም ለተጎጂዎቹ የሚያስፈልጉ ሰብዓዊና ሌሎች ድጋፎችን ማቅረብ እንዲሁም የተፈናቀሉት ደግሞ ተገቢውን ጥበቃ በማድረግ ወደ ቤታቸው የሚመለሱበትን ሁኔታ ማመቻቸት ጊዜ የማይሰጠው በመሆኑ ትኩረት በመስጠት ዕለታዊ ድጋፍና በዘላቂነት የሚቋቋሙበት መፍትሔ መሰጠት እንዳለበት ጠቅሷል። ከዚህ አንጻርም የመኖሪያ ቤታቸውና ንብረታቸው የወደመባቸው ተጎጂዎች አሁን ድረስ በሰው ቤትና በአብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ መሆኑንና እነዚህን ሰዎች ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ የሚደረገው ጥረት ዝቅተኛ መሆኑን፣ በተለያዩ ወገኖች የሚሰጣቸው የዕለት ምግብ እርዳታና የህክምና አገልግሎትእንዲሁም በቂ አለመሆኑን ጠቅሷል። በተወሰኑ አካባቢዎችም በተለይም በአብያተ ክርስትያናትና በሌሎች ቦታዎች የተጠለሉ ሰዎችን "ለደኅንነታቸው ማረጋገጫ ባልተሰጠበት ሁኔታ የመንግሥት ኃላፊዎች ወደ ቤታችሁ ካልተመለሳችሁ እርዳታ አታገኙም" የሚል አስገዳጅ ቅድመ ሁኔታ መጫናቸውና ሻሸመኔና አጋርፋ ለአብነት በመጥቀስ ይህ ግፊት ተገቢ አለመሆኑንም አመልክቷል። ኮሚሽኑ የችግሩ ሰለባዎች ያሉበትን ሁኔታ ከግምት ውስጥ መንግሥት አፋጣኝ ድጋፍ እንዲያደርግና በተለይም ያለው የኮቪድ-19 ወረርሽኝና የክረምት ወቅት በመሆኑ ተጎጂዎች ለተጨማሪ ችግር እንዳይዳረጉ ቅድሚያ በመስጠት አስፈላጊው ሁሉ እንዲደረግ በተጨማሪም ግብረሰናይ ድርጅቶችም ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቋል። የእስረኞች አያያዝ ከተከሰተው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች በእስር ላይ እንደሚገኙ የገለጸው ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል በተለይ በጎበኛቸው የእስር ቦታዎች አሳሳቢ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ችግሮች መመልከቱን ገልጿል። ከእነዚህም ውስጥ ተጠርጣሪዎች በአነስተኛ ቦታ ውስጥ በተጨናነቀ ሁኔታ መታሰራቸውን ለወረርሽኝ ያላቸውን ተጋላጭነት እንደሚጨምረው ሪፒርቱ ጠቅሶ፤ የምግብና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ አቅርቦት አነስተኛ መሆኑ፣ በተወሰኑ ታሳሪዎች ላይ ድብደባና ኢሰብዓዊ አያያዝ ጥሰት መፈጸምና አለመጣራቱ እንዲሁም ተጠያቂነት ያለመኖሩን አመልከልቷል። በተጨማሪም በአንዳንድ አካባቢዎች ሕፃናትና አዋቂዎች አንድ ላይ መታሰራቸውን ኮሚሽኑ እንደችግር ያነሳው ሲሆን የተወሰኑ ታሳሪዎች በአፋጣኝ ወደ ፍርድ ቤት አለማቅረባቸው እንዲሁም ፍርድ ቤት በዋስትና የለቀቃቸውን እስረኞች በተለያዩ ምክንያቶች በእስር እንዲቆዩ መደረጋቸውን ገልጿል። በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ ከተሞች ተከስቶ በነበረው ሁከት ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች ቤት ንብረታቸው ወድሞባቸው እርዳታን ያስፈልጋቸው እንደነበር የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ከሳምንታት በፊት ለቢቢሲ መናገራቸው ይታወሳል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በልሉ 523 መኖሪያ ቤቶች የተቃጠሉ ሲሆን 499 መኖሪያ ቤቶች ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጸው፤ በተጨማሪም 195 ሆቴሎች መቃጠላቸውን ሌሎች 32 ሆቴሎች ደግሞ በንብረታቸው ላይ የመሰባበር ጉዳት መድረሱን አቶ ጌታቸው ተናግረዋል። ከሁከቱ ጋር ተያይዞም በሺህዎች የሚቆተሩ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል።
54341609
https://www.bbc.com/amharic/54341609
ኮሮናቫይረስ፡ በኢትዮጵያ በአስከሬን ላይ የሚደረገው የኮሮናቫይረስ ምርመራ መቆሙ ተገለፀ
ኢትዮጵያ ከአስከሬን ላይ ናሙና በመውሰድ ታደርገውን የነበረውን የኮሮናቫይረስ ምርመራ ማቆሟን አስታውቃለች።
ይህንን ያስታወቀችውም የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በፃፈው ደብዳቤ ነው። የአለም ስጋት ሆኖ የቀጠለውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ስርጭት ለመግታት አገሪቷ የተለያዩ የመካላከልና የመቆጣጠር ስራዎችን እየሰራች እንደነበር የጠቀሰው ደብዳቤው ከነዚህም መካከል ከአስከሬን የላብራቶሪ ናሙና መውሰድም ነበር። የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትና ጤና ሚኒስቴር ከተለያዩ ባለድርሻ አካላትም ጋር በመሆን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመግታት የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ ማስተባበሪያ ማዕከል በሟቋቋም የቫይረሱን ስርጭትና መጠን ለማወቅም ከተሰሩ ስራዎች መካከል ከአስከሬን የሚወሰድ የላብራቶሪ ናሙና መሆኑን አስታውሷል። ሆኖም በአሁኑ ወቅት የአገሪቱ የቫይረሱ የማህበረሰብ ስርጭት ከ95 በመቶ በላይ በመሆኑና ከአስከሬን ይደረግ የነበረው የናሙና ምርመራም በህዝቡም ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ ሲያስነሳበትም እንደነበር ደብዳቤው ጠቅሶ በነዚህም ምክንያቶች እንዲቆም ተወስኗል። በአሁኑ ወቅትም የብሄራዊ የኮቪድ-19 መከላከልና እና መቆጣጠር ግብረ ኃይል በወቅቱ ያለውን አለም አቀፋዊና ሃገራዊ ስርጭት ከግምት ውስጥ በማስገባትም ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ልዩ ትኩረት በመስጠትም የመከላከሉና የምርመራው ስራ ይቀጥላል ተብሏል። ከዚህም በተጨማሪ ማንኛውንም ሞት በኮሮናቫይረስ እንደሆነ ተደርጎም በቀብር ስነ ስርአቱ ላይ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባም አሳስቧል። ከሰባት ወራት በፊት የመጀመሪያው የኮሮናቫይረስ የተገኘባት ኢትዮጵያ እስከዛሬዋ እለት፣ መስከረም 19፣ 2013 ዓ.ም ባለው መረጃ በአገሪቷ ውስጥ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች 73 ሺህ 944 የደረሰ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 1 ሺህ 177 ዜጎቿን በሞት ተነጥቃለች። በበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥርም 30 ሺህ 753 የደረሰ ሲሆን በአጠቃላይ ለ1 ሚሊዮን 260 ሺህ 929 የላብራቶሪ ምርመራዎችን አከናውናለች።
news-52179257
https://www.bbc.com/amharic/news-52179257
ኮሮናቫይረስ፡ "ኮንቴጀን" በኮሮና ምክንያት ቀን የወጣለት ፊልም
በሆሊውድ ሲኒማ ታሪክ እንደዚህ ወቅት በሽታና ወረርሽኝ ላይ ያተኮሩ ፊልሞች ተፈላጊ ሆነው አያውቁም። በተለይ በዚህ ረገድ አንድ ፊልም ከ10 ዓመት በኋላ ቀን ወጥቶለታል፤ ኮንቴጀን።
ስለ ኮንቴጀን ከማውራታችን በፊት ሌሎች በኮሮና ምክንያት ገበያው የደራላቸው ፊልሞችን እንቃኝ፡፡ በነባራዊ ሁኔታ ላይ መሠረት ያደረጉ ተከታታይ የቴሌቪዥን ዘጋቢ ፊልሞች (Docuseries) እጅግ ተፈላጊ ሆነዋል፤ በተለይም ጭብጣቸው ወረርሽኝ ላይ የሆኑቱ። ለምሳሌ 'How to Prevent an Outbreak' እጅግ የብዙ ተመልካችን ልብ ገዝቷል፤ ኔትፍሊክስ በዚህ ፊልም ተመልካቾች ቁጥር ተጨናንቋል። 93 Days (2016)፣ Outbreak (1995)፣ Warld War Z (2013)፣ I am Legend (2007)፣ Old Boy (2003)፣ The Light House (2019)፤ ሌሎቹ ተቀራራቢ ጭብጥ የያዙና በስፋት ተመልካች ያገኙ ፊልሞች ሆነዋል። ወደ በኋላ በአጭር በአጭሩ ጭብጦቻቸውን እንዳስሳለን። ኮንቴጀን በድንገት ቀን የወጣለት ፊልም ኮንቴጀን በፈረንጆች 2011 የወጣ ፊልም ነው። ጥቁር ስክሪኑ ሲገለጥ ከባድ ደረቅ ሳል ይሰማል። ፊልሙ ስለከፋ ወረርኝ እንደሆነ የምንገምተውም ያኔ ነው። ያ ከባድ፣ አስጨናቂ ደረቅ ሳል ከተዋናይት ጉዌት ፓትሮው የሚወጣ ነው። በፊልሙ ቤቲ ኢምሆፍን ሆና ነው የምትጫወተው ጉዌት። ከሆንግ ኮንግ ወደ ሚኒያፑሊስ (ሜኔሶታ) ስትጓዝ ነው በሽታውን ይዛው የምትመጣው። ሞት ከዚህ ይጀምራል። መጀመርያ ወንድ ልጇ ይሞታል። ወዲያውኑ እሷ ትከተለዋለች፤ የ'ርሷ ባል ሆኖ የሚሰራው ማት ዴመን በቤተሰቡ ሞት ያዝናል። እርሱ ግን ለቫይረሱ ተጠቂ አይሆንም። ሆኖም የፓትሮው ከሆንግ ኮንግ ወደ ሚኒሶታ የመመለስ ጉዞ ሲጠና በድብቅ ቺካጎ ጎራ ብላ እንደነበር ይደረስበታል። የኮንቴጀን ጭብጡ ከሆንግኮንግ በሚነሳ ወረርሽኝ ላይ ያተኮረ ሲሆን ብዙዎቹ የፊልሙ የታሪክ መዋቅሮች አሁን ካለው ኮሮና ጋር ተቀራራቢ ትርክት አላቸው። ወረርሽኙ ከእሲያ መነሳቱ አንድ አስገራሚ ግጥምጥሞሽ ሆኖ ተመዝግቧል። ኮንቴጀን ሌሎች ከኮሮና የሚያቀራርቡት በርካታ የሲኒማ ገቢሮችም አሉት። ለዚህም ነው ፊልሙ ንግርት ነው እስከመባል የደረሰው። በፊልሙ ላይ ስመጥር ተዋንያን ይገኙበታል። ፈርጦቹ እንስት ተዋንያን ጉዌት ፓትሮው እና ኬት ዊንስሌት እንዲሁም እውቆቹ ማት ዴመንና ሎውረንስ ፊሽበርን እና ጁድ ሎው ድንቅ ብቃታቸውን አሳይተውበታል። በነገራችሁ ላይ ኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ የሥነ ጤና ትምህርት ክፍል እነዚህን ስመጥር ተዋያን ከ10 ዓመት በኋላ በድጋሚ በቪዲዮ ስልክ እንዲገናኙ በማድረግ ለኅብረተሰቡ ስለ ወረርሽኙ ትምህርት እንዲሰጡ አድርጎ ውጤታማ ሥራ ሠርቷል። ስለ ኮሮና መልዕክቱ በ'ነርሱ አንደበት እንዲተላለፍ የሆነው ኮንቴጀን ፊልም በመላው ዓለም በከፍተኛ ቁጥር እየታየ በመሆኑ የተዋንያኑን ተሰሚነት ለመጠቀም ታስቦ ነው። ኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ገና ድሮ ከመነሻውም (በ2011) ማለት ነው፤ በፊልሙ ላይ ስለ ቫይረስ ወረርሽኝ ጠቃሚ ሳይንሳዊ ግብአት በመስጠት ተሳትፎ ነበረው። ለዚህም ይሆናል ከሳይንስ ብዙም ያልራቀው። ፊልሙ እንደብዙዎቹ የሆሊውድ "የጥፋት ሲኒማዎች" በሰው ልጆች ላይ መዓት ሲመጣ የሚያሳይበት መንገድ የተጋነነ አለመሆኑ ልዩ ያደርገዋል። እነዚህ ሰዎች ኮሮና እንደሚመጣ ገና ድሮ ታይቷቸው ነበር እንዴ የሚያሰኙ የታሪኩ ገቢሮችም በፊልሙ ላይ እዚህም እዚያም ይገኛሉ። ለምሳሌ በአማካይ የሰው ልጅ ፊቱን በደቂቃ አምስት ጊዜ እንደሚነካካና ይህም ቫይረሱን እንደሚያሰራጨው፤ ቫይረሱ የተነሳበት እሲያ መሆኑና ቫይረሱ ወደተቀረው ዓለም እንዴት እንደተሰራጨ በፊልሙ የሚተርክበት መንገድ ከኮሮና እጅግ ተቀራራቢ ሆኗል። ‹‹በቅጽበት 200 ሰው እንደቅጠል ሲረግፍ በፊልሜ እያሳየሁ ተራ ግነት መፍጠር አልፈለኩም›› ብሎ ነበር የኮንቴጀን ፊልም ዳይሬክተር ስቲቨን ሶደርበርግ፤ ገና ያኔ ፊልሙ የተለቀቀ ሰሞን። ስቲቨን ለምን ከተለመደው የሆሊውድ ግነት ገሸሽ እንዳለ ሲጠየቅ ‹‹አንድን ፊልም ይበልጥ ግነት በጨመርክበት ቁጥር ተመልካችህን ከእውኑ ዓለም እንዲርቅና የፈጠራ ሲኒማ እያየ እንደሆነ እንዲሰማው ታደርገዋለህ። ይህ እንዲሆን ስላልፈለኩ ነው›› ብሏል፡፡ የዚህ ፊልም አንዱና ዋንኛው ስኬት በቫይረስ ወረርሽኝ ዙርያ የቅርብ ሳይንቲስቶችን ምክር መሠረት አድርጎ መሠራቱ ነው የሚሉም አልጠፉም። ኮንቴጀን ፊልም ከዛሬው እውነታ ጋር በማጠጋጋት እጅግ ስኬታማ ሆኗል ብንልም በርካታ ተመሳሳይ በዚህ ዘውግ የሚገኙ የሲኒማ ውጤቶች መሠረታቸው የሰዎች በወረርሽኝ የመያዝ ፍርሃት ላይ የቆሙ ናቸው። ለምሳሌ የዞምቢ ፊልሞችን ማንሳት ይቻላል። 28 days Later (2002)፡ በዳኒ ቦየል ዳይሬክተርነት የተሰራ ሲሆን ማጠንጠኛው በእንግሊዝ የሚፈጠር ምስጢራዊ ወረርሽኝ ነው። የሚደንቀው በፊልሙ አንድ ክፍል ዋና ተዋናዩ በሎንዶን ከተማ ጭርታ መሀል ዌስትምኒስትር አቅራቢያ በሚገኝ ድልድይ ብቻውን ግራ ተጋብቶ ሲዋልል ያሳያል። ነዋሪዎች ቤታቸው ተከተው በሲኒማው መታየቱ ከአሁን የሎንዶን እውነታ ጋር እጅግ ተቀራራቢ ያደርገዋል። 93 days፡በዳይሬክተር ስቲቭ ጉከስ የተሰራ ፊልም ሲሆን በናይጄሪያ በኢቦላ ተይዞ ሌጎስ የገባን ሰው መሰረት አድርጎ፣ የጤና ባለሞያዎች ኢቦላን ለመቆጣጠር የሞት ሽረት ትግል ሲያደርጉ ያሳያል። ፊልሙ በያዘው ጭብጥ ለዚህ የኮሮና ዘመን ተስማሚ በመሆኑ ተመራጭ ሆኗል። outbreak (1995)፡ በዎልጋንግ ፒተርሰን ዳይሬክት የተደረገ ፊልም ሲሆን ከአፍሪካ ወደ ካሊፎርኒያ በመጣ አንድ ዝንጀሮ አማካኝነት የሚከሰት የቫይረስ ወረርሽኝን መሠረት ያደረገ ታሪክ ነው፡፡ በፊልሙ ስመጥሮቹ ደስቲን ሆፍማን ሬኔ ሩሶና ሞርጋን ፍሪማን ይተውኑበታል። Warld War Z ፡ ብራድ ፒት በዋናነት የሚተውንበት ሲኒማ ሲሆን አንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቀድሞ ባልደረባ ምንነቱ ያልታወቀ ወረርሽኝ ለማቆም በመላው ዓለም ሲሯሯጥ የሚደርስበትን ውጣ ውረድ የሚተርክ ፊልም ነው፤ ዳይሬክተሩ ማይክ ፎስተር ነው። I am Legend: የሳይንሳዊ ልቦለድ ዘውግ ያለው የፍራንሲስ ሎውረን ፊልም ነው። በዚህ ፊልም ኒውዮርክ ከተማ መዓት ከደረሰባት በኋላ ዊል ስሚዝ ብቻውን ሲንከራተት ይታያል። አሁን በኒውዮርክ ካለው እውነታና ሁኔታ አንጻር I am Legend እጅግ ተቀራራቢ በመሆኑ ይህ ፊልም በጭብጡ ምክንያት ተፈላጊ እንዲሆን ሳያደርገው አልቀረም። Old Boy፡ ዋናው ገጸ ባሕሪ ከተጠለፈ በኋላ ለ15 ዓመታት ከአጋቹ በቀር ከሰው ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ሳይኖረው የሚኖረውን ሕይወት የሚቃኝ ፊልም ነው። አሁን በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ቤታቸውን ቆልፈው እንዲቀመጡ በመገደዳቸው ይህ ታሪክ ከዚህ እውነታ መቀራረቡ ተፈላጊ ሳያደርገው አልቀረም። The Light House (2019): ከአስጨናቂ (ሆረር) ዘውግ የሚመደበውን ይህንን ሲኒማ ሮበርት ኤገርስ ዳይሬክት አድርጎታል። በአንዲት ደሴት (ኒው ኢንግላንድ አይላንድ) ላይ ለብቻቸው ተነጥለው በሚኖሩ ሁለት ሰዎች የአእምሮ ጤንነታቸውን ለማቆየት ሲጥሩ የሚያሳይ ሲኒማ ነው።
news-50900388
https://www.bbc.com/amharic/news-50900388
የአልኮል ችግር ያለባቸው ወንዶች ጥቃት የመፈጸም እድላቸው ከፍ ያለ ነው
የአልኮል ወይም የማንኛውም አይነት ሱስ ያለባቸው ወንዶች አጋሮቻቸው ላይ ጥቃት የመፈጸም እድላቸው ሱስ ከሌለባቸው ሰዎች በስድስት ወይም ሰባት እጥፍ ከፍ እንደሚል አንድ ጥናት ጠቆመ።
'ፕሎስ ሜድሲን' የሚባለው የበይነ መረብ ጆርናል ላይ የታተመው ጥናት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የጤና መዛግብትንና የ16 ዓመታት የፖሊስ ሪፖርትን እንደ መነሻ አድርጎ ነው የተሰራው። • አልኮል የማይሸጥባቸው መጠጥ ቤቶች • ለአንድ ወር ከአልኮል መታቀብ የሚኖረው አስደናቂ ውጤት የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰሯ ሲና ፋዜል ጥናቱን የመሩት ሲሆን ''ባገኘነው ውጤት መሰረት የአልኮልና ሌሎች ሱሶችን መቆጣጠርና ማከም ከቻልን በተለይ በሴቶች ላይ በቤት ውስጥ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን መቀነስ እንችላለን'' ብለዋል። ''ሱስ እንዳይከሰት ቀድሞ መከላከል እንዲሁም ከተከሰተ በኋላ በአግባቡ መከታተል የሚችል ስርዓት መገንባት ያስፈልጋል። ጥቃት ፈጻሚዎችም ሱሰኛ ስለሆኑ ብቻ በቀላሉ መታለፍ የለባቸውም።'' የእንግሊዝ፣ አሜሪካ እና ስዊድን ባለሙያዎችን ያሳተፈው ጥናት ከአውሮፓውያኑ 1998 እስከ 2013 ባሉት ዓመታት የአልኮልና ሌሎች ሱሶች ያሉባቸው 140 ሺ ወንዶችን መረጃ ተጠቅሟል። በመቀጠልም እነዚህ ሰዎች ምን ያክል ጊዜ ሰዎችን እንዳስፈራሩ፣ ጾታዊም ሆነ ሌላ ጥቃት መፈጸማቸውን እና ምን ያክል ጊዜ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተመልክቷል። በዚህ መሰረት በአልኮል የሚጠቁ ወንዶች ሱሱ ከሌለባቸው ጋር ሲነጻጸሩ በፍቅር አጋሮቻቸው ላይ ጥቃት የመፈጸም እድላቸው ከስድስት እስከ ሰባት እጥፍ ከፍ እንደሚል ተመራማሪዎቹ ደርሰንበታል ብለዋል። የአልኮል ችግር ያለባቸው ወንዶች 2.1 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ በተለያዩ ምክንያቶች በፖሊስ ቁጥጥር ውለዋል። • የስዊዘርላንድ መንግሥት ቡና ለህይወት አስፈላጊ እንዳልሆነ ገለፀ ከዚሁ ጥናት የተገኘው ሌላ ወሳኝ መረጃ ደግሞ የአልኮል ሱሰኛ ወንዶች በፍቅር አጋሮቻቸውም ሆነ ሌሎች ላይ ጥቃት የሚፈጽሙት በሰከሩበት ወቅት ብቻ አለመሆኑ ነው። ባልጠጡበት ወቅት እንኳን በጣም ሰዎችን መቆጣጠር የሚወዱና ቁጡ ናቸው ይላል ጥናቱ። በሌላ በኩል እንደ ቀላል የሚታዩ የአእምሮ ጤና ችግሮችም ወንዶች ፊታቸውን ወደ አልኮልና ሌሎች ሱስ አስያዥ ንጥረነገሮች እንዲያዞሩ ያደርጋቸዋል።
44195205
https://www.bbc.com/amharic/44195205
ፎቶ ግራፍን ለታሪክ መንገሪያ
የፎቶ ግራፍ ባለሙያዋ ማርታ ታደሰ የመጀመሪያ ዲግሪዋን ከድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ በኮምፒውተር ሳይንስ አግኝታለች። የሁለተኛ ዲግሪዋን ደግሞ በዴቬሎፕመንታል ሳይንስ ሰርታለች።
ፎቶን ማንሳት በልጅነቷ የጀመረችው ማርታ፤ የትኛውም ትምህርት ቤት፣ የትኛውም ተቋም ደጃፍ ፎቶ ግራፍ ለመማር ብላ አለመርገጧን ትናገራለች። "ራሴን ነው ያስተማርኩት" የምትለው ማርታ ፎቶዎቿን ለአድናቂዎቿ የምታደርሰው ኢንስታግራምን በመጠቀም ነው። የፎቶግራፍ ሙያዋንም ሀ ብላ የጀመረችውም በልጅነቷ ቤት ውስጥ ባገኘቸው ካሜራ ሲሆን 14 ዓመት አብራት የኖረችዋን ውሻ በማንሳት ነው። "ካሜራውን የገዛችው እህቴ ናት" ትላለች። የቤተሰቦቿን ሞባይል ስጡኝ እያለች ስታስቸግር ያየችው እህቷ ካሜራ ገዝታ እንደሰጠቻትም ታስታውሳለች። በካሜራው ቀኑን ሙሉ ውሻዋን ስታነሳ ትውል እንደነበር የምትናገረው ማርታ በሂደት "ጓደኞቿን እስቲ ላንሳችሁ እያለች በመጠየቅ" እጇን ማፍታታት ክህሎቷን ማዳበር ቀጠለች። "እህቴ ያንን ካሜራ ገዝታ ባትሰጠኝ ኖሮ ዛሬ ያለሁበት ስፍራ ላይ እገኛለሁ ብዬ አላስብም" ትላለች። ከንግግርና ከፅሑፍ ይልቅ ፎቶ ማርታን የሚያውቋት ሲናገሩ በፎቶ ብቻ ሳይሆን በፅሑፍም ራሷን መግለፅ ጎበዝ እንደሆነች ይናገራሉ። እርሷ ግን ወደፎቶ የማድላቷን ምክንያት ሁለቱ ክህሎቶቿ መግለፅ የምትፈልጋቸውን ነገሮች የበለጠ ለመግለጥ ስላልረዷት እንደሆነ ትናገራለች። ፎቶ የበለጠ ዝንባሌዋ እንደሆነ የምትናገረው ማርታ በብዛት በምታነሳቸው ፎቶዎች የሰው ልጅ ፊትን ማሳየት ትመርጣለች። "ታሪካችን ከማንነታችን ጋር ይያያዛል፤ ያ ደግሞ የበለጠ ፊታችን ላይ ይነበባል። ፎቶዎቹ ለምፅፋቸው ነገሮች የበለጠ የሚጨምሩልኝ ነገሮች አሉ "ትላለች። ማርታ በምታነሳቸው ፎቶ ግራፎች ምን ማድረግ እችላለሁ? ብላ ዘወትር ስታስብ በተለያየ ምክንያት ለችግር የተጋለጡ አካላት ያለባቸውን ችግር፣ ጉዳታቸውን፣ በደላቸውን ለቀሪው ማህበረሰብ በማሳየት መርዳት እንደምትፈልግ ትናገራለች። "ለምሳሌ በአሁኑ ሰአት የሀገር ውስጥ ጉዲፈቻን ለማስተዋወቅ አንድ ፕሮጀክት ይዤ እየሰራሁ ነው። ወላጅ የሌላቸውን ልጆች ታሪክ፣ የእነሱን ጉዳት በፎቶ ለመናገር ብችል ደስ ይለኛል ትላለች። በሙያዬ ስለተገፉ ሰዎች ለሌሎች ብናገር እና ታዳሚዬ አንድ ነገር ማድረግ ቢችል ደስታዬ ወደር የለውም።" ትላለች። የስርአተ ፆታ እኩልነት ማርታ በፎቶ ታሪክን ስትናገር በዋናነት የስርአተ ዖታ እኩልነት ላይ ታዘነብላለች። በፎቶዎቿ የተወሰነ ክፍል ላይ ብቻ ማተኮር እንደማትፈልግ የምትናገረው ማርታ የተመጣጠነ ውክልና በስራዎቿ ውስጥ ቢታይ ቀዳሚ ፍላጎቷ ነው። በተለያየ የብዙሃን መገናኛ ውስጥ የአንድ ወገን ውክልና ግዘፍ ነስቶ ሊታይ እንደሚችል የምትጠቅሰው ማርታ እንደ ጾታ እኩልነት አቀንቃኝነቴ የሁለቱም ወገኖች ውክልናን በስራዬ ማሳየት አላማዬ ነው ትላለች። የማርታ ታደሰ ስራዎች የሰራተኛውን መደብ፣ የሰው ልጅ የእለት ተእለት እንቅስቃሴዎች ላይም ያተኩራሉ። ማርታ ስለ አዲስ አበባ ሲወራ ስለልማቷ ብቻ መወራት እንደሌለበትና ፤ ከዚህ በስተጀርባ ያለ ሕዝብ፣ በተለያየ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚኖር አዲስ አበቤን በፎቶ መወከል አለብኝ የሚል ፅኑ አቋም አላት። "መወከል የምፈልገው ሁሉንም ነው፤ በክልል፣ በፆታ፣ በእድሜ፣ በሐይማኖት ከፋፍዬ ታሪክን መንገር አልፈልግም" ትላለች። ፎቶን በምክንያት ማርታ የሚያስደስታትን ፎቶ እንደምታነሳ ብትናገርም ፎቶዎቿን በምክንያት ብቻ ማንሳት እንደሚኖርባት ሁሌም ታስባለች። "ፎቶን ሳነሳ አንድ ምክንያት መኖር አለበት፤ እኔ ራሴን የጎዳና ላይ ፎቶ ግራፍ አንሺ ነኝ ብዬ አላስብም። በርግጥ የሚያስደስተኝን ነገር አነሳለሁ። ግን ሰበብ ነገር በስራዎቼ ውስጥ ቢኖሩ እመርጣለሁ" ትላለች። አንድን ፎቶ ለማንሳት ታሪኩ መጀመሪያ መረዳት የመጀመሪያ ስራዋ ሲሆን ከታሪኩ ጋር ራሷን ካዛመደች በኋላ ፎቶዎችን እንደምታነሳ ትናገራለች። ይህንን ማድረጓ ደግሞ የሚረዳት የፎቶዎቿን ተመልካቾች ከአልፎ ሂያጅ አድናቂነት ወደ ጠያቂነት እንዲመጡ ለማድረግ እንደሆነ ትናገራለች። "ፎቶዎቼን የሚያዩ ሰዎች ይሄ ፎቶ ሲያምር ብቻ ብለው እንዲሄዱ አልፈልግም። ካዩ በኋላ ምን ማድረግ እችላለሁ የሚለው ጥያቄ በውስጣቸው ቢነሳ እመርጣለሁ" በማለት ታስረዳለች። እንደምሳሌነት ስትጠቅስም በጾታ ጥቃት ላይ የሰራችው ፕሮጀክትን ታስታውሳለች። ለዚህ የፎቶ ስራ ያቀረበችው ከ 4 እስከ 6 የሚሆኑ ፎቶዎችን እንደነበሩ የምታስታውሰው ማርታ ፎቶዎቹን ያዩ ግለሰቦች ስለ ጾታዊ ጥቃት ግንዛቤያቸውን ማሳደግ ብቻ ሳይሆን ከዛ በኋላ ምን ማድረግ አለብኝ የሚለው ላይ ውይይት በመፍጠር ረገድ የበኩሏን አስታዋፅኦ ማድረጓን ትናገራለች። ማርታ በስራዎቿ የስርዓተ ፆታ እኩልነትን ብቻ ሳይሆን በወር አበባ ወቅት የሴቶች ልምድ እንዲሁም የወንዶች አረዳድ ምን ይመስላል በሚል የፎቶ ስራዎቿን ሰርታለች። ይህ በመሀል ከተማም ሆነ በክልል ከተሞች እንደነውር የሚቆጠር እና ግልፅ ውይይት የማይደረግበት ጉዳይ በመሆኑ በግልፅ መነጋገር በሴቶቹ ጤና ላይ ለውጥ እንደሚያመጣ ለማሳየት በኢንስታግራም ላይ ፎቶዎቿን አጋርታለች። ይህ ደግሞ በወጣቶቹ ዘንድ መነጋገርን በመፍጠር ለውጥ ለማምጣት እንደረዳት ታስታውሳለች። ኢንስታግራምን እንደ መድረክ ማርታ ስራዎቿን በዋናነት የምታቀርበው የማህበራዊ ሚዲያ በሆነው በኢንስታግራም በኩል ነው። ኢንስታግራምን ስትጠቀም ይኸኛው ወገን ቢያየው ብላ አስባ እንዳልሆነ የምትናገረዋ ማርታ በመጀመሪያ እንዲሁ ስራዎቿን ለማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚው የማጋራት ሀሳብ ብቻ እንደነበራት ታስታወሳለች። እግረ መንገድ ግን ከሐገር ውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዋነኛ የስራዎቿ ተደራሽ እንደሆኑ ትናገራለች። በተለይ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለስራ ስትንቀሳቀስ የምታነሳቸውን ፎቶግራፎች መሃል ከተማ ተቀምጦ ሌሎቹን የሀገሪቷን ክፍሎች ላላየው እንዲሁም ከሀገር ውጭ ለሚኖረው ስለነዛ ስፍራዎች ፎቶዎቿ ጠቋሚ መረጃዎች በመስጠት የራሳቸውን ድርሻ እንደሚጫወቱ ትናገራለች። በአዲስ አበባ እና በተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን በፎቶዎቿ ስለሌሎች አካባቢዎች በአፍ ከሚነገሩ ታሪኮች ውጭ እውነታውን ማሳየት እንደምትፈልግም ትናገራለች። ከዚህም በተጨማሪ የምዕራቡ አለም መገናኛ ብዙሃን ስለኢትዮጵያ እና አፍሪካ ያላቸውን አንድ ጥግ የያዘ ግንዛቤ ሌላ እውነታም አለ የሚለውን ለማሳየት እንደምትጠቀምበትም ታስረዳለች። ከኢንስታግራም በተጨማሪ ከሁለት ጓደኞቿ ጋር በመሆን የሴት ልጅ ግርዛት፣ ጥቃት እና መደፈር ላይ የፎቶ አውደ ርዕይ አዘጋጅታ ታውቃለች። እንዲሁም የተፈጥሯዊ ፀጉር በሚል ርዕስ ክሮሲንግ ባውንደሪስ ባዘጋጀው አውደ ርዕይ ላይም ተሳትፋለች።
news-51382626
https://www.bbc.com/amharic/news-51382626
ከአምልኮ ቦታ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ 'ግጭት' 7 ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተነገረ
ማክሰኞ እኩለ ሌሊት ገደማ በአዲስ አበባ 22 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከጸጥታ ኃይሎች ጋር ተፈጥሮ በነበረ ግጭት የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነግሯል።
በጉዳዩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ መግለጫ የሰጡ ሲሆን፤ እስካሁን ከግጭቱ ጋር በተያያዘ 7 ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ተናግረዋል። ምክትል ከንቲባው ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉት 7 ሰዎች መካከል አመራሮች ይገኙበታል ቢሉም አመራሮቹ የኃላፊነት ደረጃ አልጠቀሱም። ምክትል ከንቲባው ከሰዓታት በፊትም በፌስቡክ ገጻቸው ላይ በግጭቱ የሁለት ወጣቶች ህይወት ማለፉ እንዳሳዘናቸው ገልጸው "በየትኛውም ወገን ያሉ የጥፋቱ አካላትን በሕግ እንዲጠየቁ እናደርጋለን" ብለው ነበር። የሚፈልጉት ይዘት የለም የ Facebook ይዘት መጨረሻ, 1 ምክትል ከንቲባው ከይዞታ ይገባኛል ጥያቄዎች ጋር በተያያዘ አስተዳደራቸው ጥያቄዎችን ሲመልስ መቆየቱን አመልክተው፤ "በመንግሥት እና በሐይማኖት ተቋማት ውስጥ በሚገኙ ጥቂት አጥፊዎች ምክንያት በከተማችን ይሆናል ያላልነው፤ እንዳይሆንም የለፋንበት ድርጊት ተፈጽሟል" በማለት ሃዘናቸውን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፅዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አመሻሽ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ቤተክርስቲያኗ ትናንት ምሽት በተፈጠረ አለመግባባት የሁለት ወጣቶች ህይወት ማለፉ እንዳሳዘናት ገልጸዋል። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጉዳዮችን በውይይትና በሰከነ መንፈስ መፍታት እየተቻለ የተፈጠረው ችግር ተገቢ ያልሆነ እና መፈጠር የሌለበት ነው ብለዋል። የወንጀል ምርመራወእን ሂደት ዝርዝር ሪፖርት ለህዝብ ይፋ እንዲሆንም ጥሪ አቅርበዋል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን የአዲስ አበባ ሐገረ ስብከት የካህናት አስተዳዳር ኃላፊ የሆኑት መላዕከ ሕይወት አባ ወልደየሱስ ሰይፉ ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት በግጭቱ ሁለት ወጣቶች በጥይት ሲገደሉ ሌሎች ደግሞ ቆስለው ሆስፒታል ገብተዋል። ግጭቱ የተቀሰቀሰው በአካባቢው ባለ አንድ የታጠረ ቦታ ምክንያት መሆኑን ለቢቢሲ የገለጹት ነዋሪዎች ፖሊስ ለምን እርምጃውን በወድቅት ሌሊት መውሰድ እንደፈለገ እንቆቅልሽ እንደሆነባቸው ተናግረዋል። • "የደባ ፖለቲካውን ማስቆም ፈተና ሆኗል፤ ግን ኢትዮጵያን የምናስቀጥል መሆኑን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ" • "የተማሪዎቹ ዕገታ እንደ አገር ከገጠሙን ችግሮች አንዱ ነው" ም/ጠ/ሚ ደመቀ መላዕከ ሕይወት አባ ወልደየሱስ ስለክስተቱ ለቢቢሲ እንደተናገሩት "ለመንፈሳዊ ክብረ በዐል ዝግጅት እየተደረገ፣ ኅብረተሰቡ ፀሎት እያደረገ እያለ ነው በአሳቻ ሰዓት ላይ ከሌሊቱ ስድስት ተኩል ጀምሮ ፖሊስ እርምጃ መውሰድ የጀመረው።" የቦታውን ባለቤትነት በተመለከተ ከአስር ዓመት በፊት ጥያቄ ቀርቦበት በጊዜው በመንግሥት ባለስልጣናት መቀያየር ምክንያት ምላሽ ሳያገኝ የቆዬ ሒደት እንዳለ ጠቅሰው "የአዲስ አበባ ሐገረ ስብከት ይፋዊ ደብዳቤ ለወረዳው ፅፎ እየተከታተለ ነበር" ብለዋል። መላዕከ ሕይወት አባ ወልደየሱስ ሰይፉ አክለውም በክስተቱ የሞቱ ወጣቶችን ቤተሰቦችን በማግኘት ማፅናናታቸውንና ጉዳት የደረሰባቸውንም ለማግኘት እየሞከሩ መሆኑን ተናግረዋል። ቢቢሲ በትክክል የተፈጠረውን እንዲሁም የደረሰውን ጉዳት ለማጣራት ለፌደራል ፖሊስ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ቢደውልም፤ ጉዳዩን በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስን ማነጋገር እንዳለበት ተነግሮታል። የአዲስ አበባ ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት ኮማንደር ፋሲካ ለተደጋጋሚ የስልክ ጥሪዎች እና የፅሁፍ መልዕክቶች ምላሽ አልሰጡም። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን ስልክም እንዲሁ ሳይመለስ ቀርቷል። ሌሊት ምንድን ነው የተከሰተው? ማክሰኞ ሌሊት ተኩስን ያስተናገደው ሃያ ሁለት በተለምዶ ቀበሌ 24 አካባቢ ረቡዕ ማለዳ የፀጥታ ኃይሎች ተበራክተውበት ተስተውሏል። ለወትሮው ገና በማለዳው ደጆቻቸውን ከፍተው፣ ሞቅ ባሉ ሙዚቃዎች የደንበኞችን ቀልብ ለመግዛት የሚሞክሩ እና ከጎላጉል ሕንፃ አንስተው በግንባታ ላይ እስካለው አደይ አበባ ስታዲዬም ድረስ የተሰደሩ የንግድ መደብሮች፣ የአልባሳት መሸጫዎች እና አገልግሎት አቅራቢዎች በሮቻቸውን ዘጋግተዋል። ባንኮች እና አንዳንድ ሆቴሎች ብቻ የተለመደ ሥራቸውን ይከውናሉ። ከየሱቆቹ እና የአልባሳት መደበሮች የተዘጉ በሮች ጎን በርካታ ሰዎች በቡድን በቡድን ሰብሰብ ብለው ምሽቱን ሲከናወን ስላደረው ክስተት ይወያያሉ። ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል አካባቢ ወደ ሃያ የሚጠጉ አድማ በታኝ ፖሊሶች ይገኛሉ። • በትግራይ ደንበኞች ከባንክ የሚፈልጉትን ገንዘብ ለማውጣት ተቸገርን አሉ • የአድዋ ድልና የሰባት ቤት አገው ፈረሰኞች ምንና ምን ናቸው? በአካባቢው የተሰማሩ እና የአዲስ አበባ ፖሊስን የደንብ ልብስ የለበሱ የፀጥታ ኃይሎች ቁጥር ግን ከዚህም ይልቃል። በስፍራው የተገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ የግጭት መንስዔ ሆኗል ወደተባለለት ከሆስፒታሉ በጥቂት መቶ ሜትሮች ርቀት ገባ ብሎ ወደሚገኘው የታጠረ ቦታ መጠጋትም ሆነ ፎቶ ማነሳት እንደማይፈቀድለት በፀጥታ ኃይሎች አማካኝነት ተነግሮታል። ነገር ግን በታጠረው ቦታ ውስጥ ፍርስራሽ እንጨቶችን እና ሰማያዊ የድንኳን ጨርቅን ከርቀት መመልከት ችሏል። ከቦታው ብዙም ሳይርቅ በሚገኝ የመጠጥ መደብር የምትሰራ ወጣት ለቢቢሲ እንደገለፀችው ተኩስ መሰማት የጀመረው እኩለ ሌሊት ገደማ ሲሆን፣ ተኩሱም ዘለግ ላለ ሰዓት የቀጠለ እና እርሷ እንደምትለው በግርግር ድምፅ የታጀበ ነበር። "ጦርነት የተነሳ ወይም መንግሥት የወደቀ መስሎኝ ነበር እኔማ" ትላለች ወጣቷ በወቅቱ የነበራትን ስሜት ለቢቢሲ ስትገለፅ። ከፀጥታ ኃይሎች በጥቂት ርቀት ወጣቶች በአጀብ በአጀብ ቆመው የሚሆነውን ይከታተላሉ። ከመካከላቸው አንደኛው በስፍራው አዲስ የፈለቀ ፀበል መኖሩን እና እርሱን ተከትሎም ቤተ ክርስትያን ይሰራል ሲባል እንደሰማ ለቢቢሲ ተናግሯል። ይሁን እንጂ ማክሰኞ ሌሊት እርሱ ቦታው የተያዘው እና የታጠረው በሕገ ወጥ መልኩ ነው ያሉ የፀጥታ አካላት መጥተው ማፋረስ ሲጀምሩ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር መጋጨታቸውን ተራግሯል።
news-53500902
https://www.bbc.com/amharic/news-53500902
በግድቡ የተጠራቀመው ውሃ በቀጣይ ዓመት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ያስችላል ተባለ
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ድግብ የመጀመሪያ ዙር ውሃ ሙሌት መጠናቀቁ ይፋ ከሆነ በኋላ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትሩ በቀጣይ ዓመት በተወሰነ ደረጃ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት እንደሚጀምር ገለጹ።
ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ (ዶ/ር፤ ኢ/ር ) እንዳሉት ትናንት ምሽት ታላቁ የህዳሴ ግድብ “የሚያስፈልገውን 4.9 ቢ.ኪዩቢክ ሜትር በመያዝ ከግድቡ አናት ላይ ፈሷል ይህም የተሳካው ወደታችኛው ተፋሰስ የሚሄደው ውሃ ሳይቋረጥ ነው” ብለዋል። በትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት “ይህ ውጤት ዋነኛ ምዕራፍ ነው። ይህ በግድቡ የተያዘው ውሃ በመጪው ዓመት በሁለት ተርባይኖች ኃይል ማመንጨት ያስችለናል፤ ግንባታችንም ይቀጥላል” ብለዋል ሚንስትሩ። ሚኒስትር ስለሺ ከመልዕክታቸው በተጨማሪ ግድቡ ሞልቶ ውሃው በግድቡ አናት ላይ ሲፈስ የሚያሳይ ምስል በትዊተር ገጻቸው ላይ አጋርተዋል። ይህም እንደተባለው ግድቡ ውሃ መያዙን የሚያመላክት ምስል በትዊተር ገጻቸው አውጥተዋል። ሚኒስትሩ የእንኳን ደስ ያለን መልዕክታቸውን ባስተላለፉበት የትዊተር ጽሑፍ ላይ ግድቡ ከመሞላቱ በፊት እና ከሞላ በኋላ የሚያሳዩ ፎቶግራፎችን ለጥፈዋል። ስለሺ (ዶ/ር፤ ኢ/ር) ያጋሩት ግድቡ ውሃ ከመያዙ በፊት የነበረው ገጽታ ከዚህ በታች ያለው ነው። ገድቡ ውሃ መያዝ ከጀመረ በኋላ ደግሞ ይህን ይመስላል። ትናንት ምሽት የተደረገው የመሪዎች ውይይት "የሰከነና ጥሩ ነበር” ያሉት የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚንስትሩ፤ “ስምምነት ባልተደረሰባቸው የቴክኒክና የሕግ ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ በቀጣይ ጉዳዮች አካሄድ ስምምነት ተደርጓል” ብለዋል። በዚህም መሰረት፤ “የሁሉም ደረጃ ውሃ ሙሊት ጉዳይ በአጭር ጊዜ ሙሉ በሙሉ ስምምነት እንዲደረስ ዘላቂና ሁሉን አቀፍ የሆነ ስምምነት፤ የወደፊት የውሃ አጠቃቀምን ጨምሮ በወደፊት ድርድሮች እንዲቋጩ መሪዎቹ ወስነዋል” ብለዋል።
news-55991562
https://www.bbc.com/amharic/news-55991562
የሚየንማር የአደባባይ ተቃውሞ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ
ከሰሞኑ መፈንቅለ መንግሥት በተነሳባት ሚየንማር ነዋሪዎቿ ተቃውሟቸውን ለመግለፅ አደባባይ ላይ መውጣታቸውን ተከትሎ ፖሊስ ውሃ በመርጨት ሰልፈኞቹን ሊበትን ሞክሯል።
ተቃዋሚዎቹ አደባባይ ላይ የወጡት በርካታ ሰዎች መሰብሰብ የሚከለክለውን እግድ በመተላለፍ ነው። ስልጣን በኃይል የተቆጣጠረው ጦር ያንጎንና ማንዳላይ በመሳሰሉ ከተሞች ከአምስት ሰዎች በላይ መሰብሰብ አይቻልም የሚል ትዕዛዝ ከማስተላለፍ በተጨማሪ የሰዓት እላፊ አዋጅ ጥሏል። ሆኖም ተቃዋሚዎቹ አራተኛ ቀን ባስቆጠረው የጎዳና ላይ ሰልፍ በኃይል የተገረሰሱትን አን ሳን ሱቺን ከስልጣን መወገድ እየተቃወሙ ነው። ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር መመለስ አለበት በማለት ጥሪያቸውን እያሰሙ ነው። የአገሪቱ የመንግሥት ሚዲያ በበኩሉ ህግ የማያከብሩ ብሎ በጠራቸው እነዚህ ተቃዋሚዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ቢያስጠነቅቅም ሰልፈኞቹ ፍንክች አላሉም። በባጎ ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተቃዋሚዎች ውሃ የሚረጩ ፖሊሶችን ተጋፍጠዋል። ሚየንማር ናው በተባለው የዜና ወኪል መሰረት በመዲናዋ ናይ ፓይ ታው ፖሊስ ተቃዋሚዎችን ለመበተን ውሃ በመርጨቱ ጉዳት የደረሰባቸው አሉ ብሏል። ኢንሴይንና ማናዳላይ በመሳሰሉ ከተሞች እንዲሁ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተቃዋሚዎች መሰብሰባቸውን ከቦታው የወጡ ፎቶዎች ያሳያሉ። "ማስጠንቀቂያቸው አያስፈራንም። ለዚያም ነው ዛሬም ለተቃውሞ የመጣነው። ምርጫው ተጭበርብሯል በማለት ስልጣን መቆጣጠራቸውን አንቀበለውም። ወታደራዊ አምባገነንነትን በጭራሽ አንፈልግም" በማለት ቲይን ዊን ሶ የተባሉ መምህር ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግረዋል። በአገሪቱ ህዝባዊ ተቃውሞ እየተካሄደ ሲሆን በተለያዩ ከተሞች በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎችን ለመበተን ፖሊስ ውሃ የተጠቀመው ለመጀመሪያ ጊዜ በትናንትናው እለት ነው። የጦሩ መሪ ሚን አንግ ሂላይንግ ማንኛውም ሰው "ከህግ በላይ ሊሆን አይችልም" በማለት ቢያስጠነቅቁም ተቃወሚዎቹን በቀጥታ ከማስፈራራት ተቆጥበዋል።
news-54884495
https://www.bbc.com/amharic/news-54884495
የትራምፕ አስተዳደር “ምርጫው አልተጠናቀቀም” እያሉ ነው
የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ቃለ አቀባይ የጆ ባይደን ድል ለመገዳደር የምናካሂደው ሕጋዊ ትግል ገና መጀመሩ ነው አሉ።
“ምርጫው አልተጠናቀቀም። ገና ብዙ ይቀረዋል” ሲሉ የዋይት ሃውስ ፕሬስ ሴክሬታሪ ኬሊ ማኬኔኒ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ፕሬስ ሴክሬታሪዋ ምርጫው ተጭበርብሯል ብለው ቢከሱም ለዚህ ማስረጃ የሚሆን ግን አላቀረቡም። ሪፓብሊካኑ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በምርጫው መሸነፋቸውን አምነው አልተቀበሉም። ዲሞክራቱ ጆ ባይደን ባሳለፍነው ቅዳሜ የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫን ማሸነፋቸው መታወጁን ተከትሎ ስልጣን ከመረከባቸው በፊት ቅድመ ዝግጅቶቻቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግን በአንዳንድ ቁልፍ ግዛቶች በምርጫ ውጤት ላይ ሕጋዊ ጥያቄዎችን አነሳለሁ እያሉ ነው። ትናንት ምሽት ላይም በትዊተር ገጻቸው በድምጽ አሰጣጥ ላይ “መገመት የሚከብድ እና ሕገ-ወጥ” ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል። ትራምፕ ለዚህ ክሳቸው ማስረጃ ማቅረብ አልቻሉም። የትራምፕ ጠበቆች ተጭበርብሯል የሚሉት ምኑን ነው? ሰኞ ዕለት በዋይት ሃውስ በነበረው መግለጫ ላይ የትራምፕ አስተዳደር በምርጫው ላይ ማጭበርበር ስላለ የፕሬስ አካላት ጉዳዩን በማጣራት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቋል። ፎክስ ኒውስ የዋይት ሃውሱ መግለጫ ማስረጃ አያቀርብም በማለት መግለጫውን አቋርጧል። የትራምፕ ጠበቆች በቁልፍ ግዛቶች የሚያነሷቸው ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው። ፔንሲልቬኒያ የትራምፕ ጠበቆች በፔንሲልቬኒያ ግዛት በሚገኙ ግዛቶች የሪፐብሊካን ምርጫ ታዛቢዎች ወደ ምርጫ ጣቢያዎች መሄድ አለመቻላቸውን በማስመልከት በፌደራል ፍርድ ቤት ክስ መስረተው ነበር። ጠበቆቹ ፍርድ ቤቱ ባይደን በፔንሲልቬኒያ ግዛት ማሸነፋቸውን እንዳያረጋግጥ የሚጠይቅ ነው። ፍርድ ቤቱ ግን ይህን ክስ ውድቅ አድርጎታል። ሚሺጋን ባይደን በዚህ ግዛት እንደሚያሸንፉ ተገምቷል። የትራምፕ የቅስቀሳ ቡድን በምርጫው ዕለት የሪፐብሊካን ምርጫ ታዛቢዎች ወደ ድምጽ መቁጠሪያ ጣቢያዎች ገብተው መታዘብ አልቻሉም በሚል ምክንያት በሚሺጋን የድምጽ ቆጠራው እንዲቆም ያቀረቡት ጥያቄ በፍርድ ቤት ውድቅ ተደርጎባቸዋል። የፍርድ ቤቱ ዳኛ የትራምፕ ጠበቆች ጥያቄን ውድቅ ያደረጉት በቂ ማስረጃ መቅረብ አልቻሉም በሚል ነው። ዊስኮንሰን የትራምፕ የቅስቀሳ ቡድን በዊስኮንሰን ግዛት ዳግም ቆጠራ እንዲካሄድ እጠይቃለሁ ብሏል። በዊስኮንሰን ግዛት ድምጽ ተቆጥሮ አልተጠናቀቀም፤ በዚህም የጠበቆቹ ጥያቄ መቼ ምላሽ ሊያገኝ እንደሚችል ግልጽ አይደለም። ኔቫዳ የኔቫዳ ሪፐብሊካን ፓርቲ "ከዚህ ቀደም የኔቫዳ ነዋሪ የነበሩ እና አሁን በሌላ ስፍራ የሚኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የምርጫ ሕጉን ተላለፈው ድምጽ እንዲሰጡ ተደርጓል" ብሏል። የፕሬዝደንት ትራምፕ ጠበቆች ነዋሪነታቸው ኔቫዳ ግዛት ሳይሆን በኔቫዳ ድምጽ የሰጡ የሰዎች ስም ዝርዝርን ይፋ አድርገዋል። ምርጫ አስፈጻሚዎች ግን የተጣሰ የምርጫ ሕግ የለም እያሉ ነው። አሪዞና የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን አባላት ቅዳሜ ዕለት በሕጋዊ መንገድ ድምጽ ለመስጠት የተመዘገቡ ድምጽ ሰጪዎች ድምጻቸው እንዳይቆጠር ተደርጓል በማለት በአሪዞና ይግባኝ ብለዋል። ይህ የይግባኝ ጉዳይ በፍርድ ቤት እየተመረመረ ይገኛል።
46727861
https://www.bbc.com/amharic/46727861
ስልክዎ እንደተጠለፈ የሚያሳዩ ሰባት ምልክቶች
ተንቀሳቃሽ ስልክዎ ስለእርስዎ ብዙ መረጃዎችን ሊይዝ ይችላል፤ ይህም እጅግ ግላዊ የሆኑና ሌሎች ሰዎች እንዲያዩዋቸው የማይፈልጓቸው መልእክቶች፣ የይለፍ ቃሎችና አድራሻዎችን ያካትታል።
ስለዚህ ስልክዎ መጠለፉን (ሃክ መደረጉን) ካወቁ ወዲያውኑ እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ ነው። ነገር ግን አብዛኛዎቻችን ስልኮቻችን እንደተጠለፉ እንኳን ላናውቅ እንችላለን። • በሞባይልዎ የኢንተርኔት ወጪ ተማረዋል? ጥሩ ዜና ግን አለ። ይህንን ለማወቅ የግድ የቴክኖሎጂ እውቀትዎ ከፍ ያለ መሆን የለበትም። እነዚህን ምልክቶችን በተንቀሳቃሽ ስልክዎት ላይ ካስተዋሉ፤ የመጠለፉ እድል ከፍተኛ ሊሆን ይችላል። 1. የስልክዎ ፍጥነት ከቀነሰ ተንቀሳቃሽ ስልክዎ ከሌላው ጊዜ በተለየ ትዕዛዞችን ለማከናወን ረዘም ያለ ጊዜ የሚፈጅ ከሆነ፤ ባዕድ ሶፍትዌሮች (ማልዌር) እያስቸገሩት ነው ማለት ነው። እነዚህ ማልዌር የተባሉት ቫይረሶች ዋነኛ ሥራቸው የስልክዎን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ማዘግየት ሊሆን ስለሚችል፤ በአፋጣኝ ማስወገድ ተገቢ ነው። ነገር ግን ብዙ መተግበሪያዎች በስልክዎት ላይ ካሉም ፍጥነት ላይ ተጽእኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ። 2. ስልክዎ በጣም የሚግል ከሆነ ስልክዎት ከተለመደው ከፍ ባለ ሁኔታ የሚግል ከሆነ፤ ችግር አለ ማለት ነው። በፍጥነት እርምጃ ይውሰዱ አልያም ባለሙያ ያማክሩ። • የስልክዎን ባትሪን ለረዥም ጊዜ ለመጠቀም ይህ የሚሆነው አላስፈላጊና የሆኑና ተመሳስለው የገቡ ቫይረሶች እርስዎ ያላዘዙትን ሥራ እያከናወኑ ናቸው ማለት ነው። 3. የስልክዎ የባትሪ ኃይል ቶሎ የሚያልቅ ከሆነ ስልክዎ ከፍተኛ ሙቀት አለው ማለት ደግሞ የባትሪው ኃይል ቶሎ ቶሎ ያልቃል ማለት ነው። ምናልባት ስልክዎ አዳዲስ መተግበሪያዎችንና ሶፍትዌሮችን ለማደስ በሚሞክርበት ወቅት የባትሪውን ኃይል ሊጨርስ ይችላል። ነገር ግን ምክንያቱ ይህ ካልሆነ ስልክዎ ተጠልፎ ሊሆን እንደሚችል ማሰብ አለብዎ። 4. ወደ ማያውቁት ሰው መልዕክት ከተላከ ወይም ከማያውቁት ሰው መልዕክት ከደረስዎ ብዙ ጊዜ እርስዎ የማያውቋቸው መልእክቶች የሚላኩት በዋትሳፕና በመሳሰሉ መተግበሪያዎች በኩል ሲሆን፤ የሚላከው ደግሞ ወደ ጓደኛዎት አልያም ወደ የማያውቁት ሰው ሊሆን ይችላል። • የሃምዛ ሃሚድ ገመድ አልባ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ወደ እርስዎ የሚላኩ መልዕክቶች ደግሞ ብዙ ጊዜ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ የሚሉ ማሳሰቢያዎች ይበዟቸዋል። ወዲያው እርምጃዎ መሆን ያለብዎት ታዲያ መልዕክቱን ከመክፈትዎት በፊት ማጥፋት ነው። 5. ከበይነ መረብ የሚመጡ ድንገተኛ መልዕክቶች ስልክዎን በመጠቀም በይነ መረብን (ኢንትርኔት) በሚያስሱበት ወቅት ወደ ሌላ ድረ-ገጽ የሚያሸጋግሩ መልዕክቶች በተደጋጋሚ የሚመጡ ከሆነ የስልክዎ መጠለፍ ነገር እውን ሊሆን ይችላል። መልዕክቱን ሲጫኑ በአንድ ጊዜ ወደ ሁለትና ሦስት የድህ-ረገጾች አድራሻዎች የሚመራዎ ከሆነ በፍጥነት ይውጡ። ራስዎን ካላስፈላጊ የስልክ ጥሪ እንዴት ይታደጋሉ? 6. አጠራጣሪ መተግበሪያዎችና ገንዘብ ነክ ጥያቄዎች አንዳንድ ጊዜ እርስዎ ያልገዙት ወይም ከበይነ መረብ ያላወረዱት መተግበሪያ ስልክዎት ላይ ሊመለከቱ ይችላሉ። ምናልባትም የሞባይል ዳታ እና የጽሁፍ መልዕክት ላይ የዋጋ ጭማሪም ሊያስተውሉ ይችላሉ። የክሬዲት ካርድና የሞባይል ገንዘብ ማንቀሳቀሻ መንገዶችን የሚጠቀሙ ከሆነ ይህ ሁኔታ ለጠላፊዎች ምቹ አጋጣሚ ሊፈጥርላቸው ይችላልና ይጠንቀቁ። ስለዚህ የይለፍ ቃሎችንና የግል መረጃዎችን ስልክዎት ላይ ባያስቀምጡ ይመረጣል፤ አልያም በጠላፊዎች እንዳይገኝ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። 7. ያልተለመዱ ድምጾች የድምጽ ጥሪ በሚያደርጉበት ወቅት ያልተለመዱና ከዚህ በፊት ያልነበሩ ድምጾች የሚሰማዎት ከሆን ምናልባት ስልክዎ የጠላፊዎች ሰላባ ሆኖ ሊሆን ይችላል። ይባስ ብሎም የስልክ ጥሪዎችዎ እየተቀዱም ሊሆን ይችላል። • ራስዎን ካላስፈላጊ የስልክ ጥሪ እንዴት ይታደጋሉ? መፍትሄዎች • የስልክ ማጽጃዎችን ከታማኝ ምንጭ ማግኘት • እርስዎ የማያውቋቸውን መተግበሪያዎች ከስልክዎ ማጥፋት • ብዙ ሰው የሚጠቀማቸው ነጻ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን አለመጠቀም • ስልክዎን በቀላሉ ሊታወቅ በማይችል የይለፍ ቃል መዝጋት • ከማይታወቁ ምንጮች መተግበሪያዎችን አለመጫን • ስልክዎና በስልክዎ ላይ ያሉ መተግበሪያዎችን ቶሎ ቶሎ ማሳደስ • የስልክ ክፍያዎንና የዳታ አጠቃቀምዎን ይቆጣጠሩ
47770242
https://www.bbc.com/amharic/47770242
ኒፕሲ ሐስል፡ በአባቱ ኤርትራዊ የሆነው ራፐር በሎስ አንጀለስ ተገደለ
የሎስ አንጀለሱ ታዋቂ ራፐር፣ ኤርምያስ አስገዶም (ኒፕሲ ሐስል) በተከፈተበት ተኩስ ሎስ አንደለስ ውስጥ መገደሉን የአሜሪካ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።
የ33 ዓመቱ ራፐር በርካታ ቦታዎች ላይ በጥይት መመታቱን እና ሆስፒታል እንደደረሰ ሕይወቱ ማለፉን ሎስ አንጀለስ ታይምስ ዘግቧል። ሌሎች ሁለት ሰዎችም በተተኮሰባቸው ጥይት ቆስለዋል። • ኦሮምኛ ዘፋኙ ለደስታ በተተኮሰ ጥይት ህይወቱን አጣ • ተፈራ ነጋሽ፡ "በነገራችን ላይ ሙዚቃ አልተውኩም" • ድምፅ ፈታዮቹ መረዋዎች ከኤርትራዊ አባት እና ጥቁር አሜሪካዊ እናት የተወለደው ኤርሚያስ አስገዶም በዚህ ዓመት ለሽያጭ ያበቃው አልበሙ በግራሚ የምርጥ ራፕ አልበሞች ምርጫ ላይ እጩ ለመሆን በቅቶ ነበር። የኤርትራ የኢንፎርሜሽን ሚንስትሩ የማነ ገ/መስቀል የኤርሚያስ አስግዶም ሞት እጅጉን እንዳሳዘናቸው ያሰፈሩ ሲሆን ለቤተሰቦቹመ መጽናናት ከተመኙ በኋላ ኤርሚያስ ከአንድ ዓመት በፊት ሃገሩን ጎብኝቶ ነበር ሲሉ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል። ሞቱ ካስደነገጣቸው ታዋቂ ሰዎች መካከል ፋራል ዊሊያምስ እና ሪሃና ይገኙበታል። ሪሃና "በዚህ ዜና መንፈሴ ታውኳል" ስትል የቲውተር ገጿ ላይ አስፍራለች። ኤርሚያስ አስገዶም ተወልዶ ያደገው በደቡባዊ ሎስ አንጀለስ ሲሆን በተለያዩ የማህበረሰብ አቀፍ ስራዎችና በኪነጥበብ ስራዎች ላይ በመሳተፍ ይታወቃል። "ያደኩት በውንብድና ቡድኖች ውስጥ ነው" ሲል ለሎስ አንጀለስ ታይምስ በአንድ ወቅት ቃለ መጠይቅ ሰጥቶ ነበር "... ሞት፣ ግድያ የየእለት ትዕይንቶቻችን ነበሩ። በጦርነት ቀጠና ውስጥ እንደመኖር ነው፤ ከዚህ መንደር ሰዎች ሲሞቱ ከቁብ አይቆጠርም ነበር።" ከግራ ወደ ቀኝ ድሬክ፣ ኤርሚያስ እና ራፐር ቲ-አይ እአአ 2010 ኤርሚያስ ከመገደሉ በፊት በነበረ አንድ እሁድ "አምርሮ የሚጠላህ ሲኖር መባረክ ነው" በማለት በቲውተር ገፁ ላይ አስፍሯል። • የኬንያ ዳኞችን አለባበስ የቀየረች ኢትዮጵያዊት
news-50937634
https://www.bbc.com/amharic/news-50937634
አሜሪካ በታሪኳ ከፍተኛ የጅምላ ግድያ የተፈጸመበት ዓመት አስመዘገበች
ሊገባደድ ጥቂት ቀናት ብቻ በቀሩት የፈረንጆቹ 2019 አሜሪኳ በታሪኳ እጅግ ከፍተኛ የሚባል የጅምላ ግድያ ማስተናገዷ ተገለጸ።
አሶሺየትድ ፕረስ፣ ዩኤስኤ ቱዴይ እና ኖርዝኢስተርን ዩኒቨርሲቲ በትብብር ባጠናቀሩት መረጃ መሰረት በዓመቱ 41 ክስተቶች የተመዘገቡ ሲሆን በጥቃቶቹም 211 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። አንድ ጥቃት የጀምላ ግድያ ነው ተብሎ የሚፈረጀው ከጥቃት ፈጻሚው በተጨማሪ አራት ወይም ከዚያ በላይ ሰዎች ሲገደሉ ነው። • የቴክሳሱ የጅምላ ተኳሽ ከሥራ ተሰናብቶ ነበር ተባለ • የአእምሮ ጤና ሰባኪው ፓስተር ራሱን አጠፋ በአሜሪካ በሚጠናቀቀው ዓመት ለበርካቶች ሞት ምክንያት ከሆኑት የጅምላ ግድያዎች መካከል በወርሀ ግንቦት ቨርጂኒያ ቢች 12 ሰዎች የተገደሉበትና ነሀሴ ላይ ደግሞ በኤል ፓሶ 22 ሰዎች የሞቱበት የሚጠቀሱ ናቸው። በመረጃው መሰረት በአርባ አንዱም ጥቃቶች 33 የጦር መሳሪያዎች አገልግሎት ላይ የዋሉ ሲሆን ካሊፎርኒያ 8 የጅምላ ግድያዎችን በማስተናገድ ከሁሉም ግዛቶች ከፍተኛውን ቁጥር አስመዝግባለች። መረጃው ሲያጠናቅሩ የነበሩት ባለሙያዎች እንደገለጹት ከፈረንጆቹ 1970 በፊትም ሆነ በኋላ እንዲህ አይነት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጅምላ ግድያ ቁጥር አልተመዘገበም። በሁለተኝነት የተቀመጠው ዓመት ደግሞ 2006 ሲሆን፤ በወቅቱ 38 ጥቃቶች ተመዝግበዋል። ምንም እንኳን 2019 ከፍተኛውን የጅምላ ድግያ ክስተቶች ቢያስተናግድም በ2017 ለ224 ሰዎች ሞት ምክንያት የሆኑ ጥቃቶችም የማይዘነጉ ናቸው። በዚሁ ዓመት በላስ ቬጋ የሙዚቃ ድግስ በመታደም ላይ የነበሩ ሰዎች ተኩስ ተከፍቶባቸው 59 ሰዎች በቦታው ሞተዋል። • ታላቋ ፀሐፊ ቶኒ ሞሪሰን ስትታወስ በአሜሪካ አሁንም ዜጎች የጦር መሳሪያ እንዳይዙ ሙሉ በሙሉ መከልከል የተሳናት ሲሆን ይህን ያክል ዜጎች በየዓመቱ ህይወታቸውን እያጡ መንግሥት ለምን ዝምታን መረጠ? የሚሉ በርካቶች ናቸው። በነሀሴ ወር ኤል ፓሶ ላይ 22 ሰዎች ከተገደሉ በኋላ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጠንከር ያለ ውይይት በጦር መሳሪያዎች ዙሪያ እንደሚደረግ ገልጸው ነበር።
49916459
https://www.bbc.com/amharic/49916459
በኮንጎ የ'ሕገወጥ' የማዕድን ፈላጊዎች ላይ ጉድጓድ ተደርምሶ በርካቶች ሞቱ
በዲሞክራቲክ ኮንጎ ወርቅ በሕገወጥ መንገድ ሲያወጡ የነበሩ ሰዎች ላይ ጉድጓድ ተደርምሶ ቢያንስ 14 ሰዎች መሞታቸው ተዘገበ።
የመንግሥት አስተዳደር ሚኒስትር የሆኑት ስቲቭ ምቢካዪ እንዳሉት ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሶስት ሰዎች ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። ጉድጓዱ ውስጥ አፈር ተደርምሶባቸው የቀሩ ካሉ በሚል ፍለጋው እንደቀጠለ ነው። በዲሞክራቲክ ኮንጎ ሕገ ወጥ ማዕድን ፈላጊዎች ላይ እንዲህ አይነት አደጋ የተለመደ ሲሆን የደህንነት መጠበቂያዎችም እጅጉን ኋላ ቀር ናቸው ተብሏል። ምቢካዪ በትዊተራቸው ላይ እንዳሉት ከሆነ የሟቾቹ ቁጥር ከዚህም ሊጨምር ይችላል። • እንቅስቃሴ አልባዋ ምጽዋ • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ቀጣዩ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ እንደሚሆን ተናገሩ • ለ21 ዓመታት የኢትዮጵያን ቅርስ ደብቀው ያቆዩት ኢትዮጵያዊ የዜጎች መብት ተሟጋች የሆነው ጀስቲን ኪያንጋ አሱማኒ፣ አደጋው ረቡዕ ረፋዱ ላይ መድረሱን ገልጾ፣ ማዕድን አውጪዎቹ እየቆፈሩ የነበረው ማኔይማ በተሰኘቸው ግዛት እንደነበር ተናግሯል። አደጋው በደረሰበት ወቅት "እድሜያቸው 18 ያልሞላ ታዳጊዎችና ነፍሰጡር ሴቶች በስፍራው ማዕድን ፍለጋ ላይ ተሰማርተው ነበር" ሲል አክሏል። በሰኔ ወር ላይ በኮንጎዋ ሉአላባ ግዛት፣ ኮፐርና ኮባልት ማዕድን እየፈለጉ የነበሩ በርካቶች ጉድጓድ ተደርምሶባቸው መሞታቸው ይታወሳል። ዲሞክራቲክ ኮንጎን ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በተሻለ የመዳብ፣ ኮባልት፣ ዳይመንድ፣ እና ወርቅ ክምችት ያላት ብትሆንም ሕዝቦቿ ግን ዛሬም በከፋ ድህነት ስር ይኖራሉ። በማዕድን በበለፀጉ አካባቢዎች በሕገወጥ መልኩ የሚደረጉ የማዕድን ፍለጋዎች የተስፋፉ ሲሆን ይህንን ለማስቆም በፀጥታ ኃይሉ የሚወሰዱ እርምጃዎች በሙሉ ፍሬ አልባ ሆነው ቀርተዋል።
48361914
https://www.bbc.com/amharic/48361914
ዋሺንግተን ሟቾች ወደአፈር እንዲቀየሩ ፈቀደች
ዋሺንግተን የሰው ልጅ ከሞተ በኋላ ወደአፈርነት እንዲቀየር በመፍቀድ ከአሜሪካ ግዛቶች ቀዳሚ ሆነች።
አዲስ በወጣው ሕግ መሰረት ሰዎች ከሞቱ በኋላ ወደ አፈርነት ለመለወጥ ከፈቀዱ ፍላጎታቸው እውን ይሆናል። አንድ ሰው ከሞተ በኋላ ግብአተ መሬቱን መፈፀም አልያም ማቃጠልን እንደሚቻል ሁሉ ይህም እንደ አማራጭ ይታያል። የመቃብር ስፍራ እጥረት ባለባቸው ከተሞችም ተግባራዊ አማራጭ ሆኖ ይቀርባል። • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በቅርበት የተከታተሉት የእራት ግብዣ • ኤምአርአይ ምንድነው? • የሰዎችን ማንነት የሚለየው ቴክኖሎጂ እያከራከረ ነው የሟቾች አስክሬን እንዲበሰብስና አፈር እንዲሆን ከተደረገ በኋላ ቤተሰቦች አፈሩን በመውሰድ አበባ ወይም ዛፍ ሊተክሉበት፣ ሰብል ሊያለሙበት ይችላሉ። ይህ ሕግ የተፈረመው ማክሰኞ እለት ነው። ካትሪን ስፔድ ይህ ሕግ እንዲፀድቅ ስትወተውት የነበረ ሲሆን፤ ይህንን አገልግሎት የሚሰጥ የመጀመሪያውን ድርጅት አቋቁማለች። "የሟቾችን ገላ ወደአፈር መቀየር ከመቅበር፣ ከማቃጠል፣ ይልቅ ተፈጥሯዊ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ አስተማማኝ ሲሆን ውጤቱም የካርቦን ልቀትን የሚቀንስና የመሬት አጠቃቀማችንን የሚያስተካክል ነው" ብላለች ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል በላከችው መግለጫ። የስፔድ ድርጅት የሰውን ገላ ለማፈራረስ በባለስድስት ጎን እቃ ውስጥ ካስቀመጡ በኋላ በአልፋልፋ፣ በእንጨት ስብርባሪና በሳር ይሞሉታል። ሳጥኑ በሚገባ ከታሸገ በኋላ በ30 ቀን ውስጥ ፍርስርስ ብሎ ሁለት ጋሪ አፈር ይወጣዋል። በአሁኑ ሰአት አካባቢን የማይጎዱ የቀብር ሥርአቶች እየተበረታቱ ይገኛሉ። ስዊድን የሰው ልጅን 'አፈር ነህና አፈር ትሆናለህ' በማለት አስቀድማ ሕጉን ያፀደቀች ሲሆን፤ በዩናይትድ ኪንግደም ያለሬሳ ሳጥን ወይንም የአፈርን ተፈጥሮ በማይጎዱ ሌሎች ነገሮች መቀበር በሕግ ፀድቋል።
news-55631981
https://www.bbc.com/amharic/news-55631981
ዐቃቤ ሕግ በእነአቶ ጃዋር መሐመድ ላይ የክስ ማሻሻያ እንዲያቀርብ ታዘዘ
የአቶ ጃዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 21 ተከሳሾች ጉዳይ ዛሬ [ማክሰኞ] የተመለከተው ፍርድ ቤት ያቀረቡትን የክስ መከላከያ ውድቅ አድርጎ ዐቃቤ ሕግ የክስ ማሻሻያ እንዲያቀርብ አዘዘ።
አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ጃዋር መሐመድ እና አቶ ሃምዛ አዳነ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የፀረ ሽብር እና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች አንደኛ ችሎት አቶ ጃዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 21 ሰዎች ያቀረቡትን የክስ መከላከያ ውድቅ አድርጓል። ተከሳሾቹ ከዚህ በፊት ፍርድ ቤቱ ክሳቸውን ለማየት ሥልጣን እንደሌለውና ወንጀሉ ተፈፀመ የተባለው በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመሆኑ እንዲሁም ኦሮሚያ ከአዲስ አበባ ጋር ያላትን ልዩ ጥቅም በመጥቀስ ክሳቸው ወደ ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሄዶ መታየት አንዳለበት መከላከያ አቅርበው ነበር። ከዚህም በተጨማሪም የአስተዳዳር አዋጅና የጦር መሳሪያ ቁጥጥር እንዲሁም የቴሌኮም ማጭበርበርን አስመልክቶ ተከሳሾች መከላከያ አቅርበው ነበር። ክሳቸው ሕገ መንግሥቱ የሚሰጠውን እኩልነት በጣሰ መልኩ ነው የቀረበው በሚል በመከላከያ ላይ ያካተቱ ሲሆን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ለዚህም ክስ መልስ ሰጥቶ ነበር። በፍርድ ቤቱ ውሎ እነአቶ ጃዋር መሐመድም ያቀረቡት እነዚህ የክስ መከላከያዎች በችሎቱ በሙሉ ድምጽ ውድቅ ያደረገ ሲሆን በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ ዐቃቤ ሕግ ክሶቹ ላይ ማሻሻያ እንዲያቀርብ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ዐቃቤ ሕግም ክሶቹን አስተካክሎ እንዲያቀርብ የአንድ ወር ጊዜ እንዲሰጠው የጠየቀ ቢሆንም ተከሳሾችና ጠበቆቻቸው ግን ተቃውመውታል። የሕግ የበላይነት ማስከበር፣ ለተከሳሾች ፍትሕ መስጠት፣ ተጎጂዎች ካሳ እንዲያገኙ ከታሰበም ጉዳዩ በፍጥነት እንዲታይ የተናገሩት ጠበቆች የተሰጠው ቀጠሮ እንዲያጥር ጠይቀዋል። በተጨማሪም ከተከሳሾች ውስጥ "መንግሥት ያሰረን ወንጀል ሰርተን ሳይሆን ምርጫ ላይ እንዳንሳተፍ ነው" ያሉት አቶ ሐምዛ አዳነ የቀጠሮው ጊዜ እንዲያጥር ጠይቀዋል። ፍርድቤቱም የሁለቱን ወገን ክርክር ካዳመጠ በኋላ ለጥር 14/2013 ዓ.ም ቀጠሮ ይዟል። ችሎት ላይ ምን ተባለ? አለብን ካሉት የደኅንነት ስጋት በመነሳት ባሉበት ቦታ ጊዜያዊ ችሎት እንዲቋቋምላቸው የጠየቁና ባለፉት ሦስት ቀጠሮዎች ያልተገኙት አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ሐምዛ አዳነና አቶ ሸምሰዲን ጠሃ በዛሬው ችሎት ላይ ተገኝተዋል። ከዚህ ቀደም በነበረው ቀጠሮ ላይ ፍርድ ቤቱ የሰጠው ትዕዛዝ እንዳሳዘናቸው አቶ በቀለ ገርባና አቶ ጃዋር መሐመድ ተናግረዋል። "እኛ አንቀርብም ያልን በማስመሰል 'በግድ ፍርድ ቤት ይቅረቡ' ተብሎ ትዕዛዝ መውጣቱ በጣም አሳዝኖናል፤ በዚህም መሰረት ለደኅንነታችን እየሰጋን ነው የምንመጣው" በማለት ወደ ፍርድ ቤት የመጡበትን ሁኔታ ገልጸዋል። አቶ በቀለ ገርባ ከደኅንነታቸው በተጨማሪ የሚደርስባቸው ጥቃት አገሪቷን ችግር ውስጥ እንደሚከታት በመናገር፣ ለሚያጋጥመው ችግር መንግሥትና ችሎቱ ተጠያቂ እንደሚሆኑ ተናግረዋል። አቶ ጃዋር መሐመድም፣ አገሪቷ ውስጥ ያለው የደኅንነት ሁኔታ አስቸጋሪ መሆኑ በመግለጽ "አንዳች ነገር ቢደርስብን፣ በዚህ ምክንያት አገሪቷ ላይ ችግር ቢመጣ፣ ሸኔ ሻዕብያ እያሉ ምክንያት መስጠት አያዋጣም። የምትጠየቁት እናንተ የሕግ ባለመያዎችና መንግሥት ነው" ብለዋል። ዳኞቹ በበኩላቸው ትዕዛዝ በሚሰጡበት ወቅት ወደ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ የሚል እምነት ኖሯቸው መሆኑን በመጥቀስ "የፍርድ ቤትን ትዕዛዝ አታከብሩም የሚል እምነት የለንም። በግድ መቅረብ አለባቸው የሚለውን ትዕዛዝ የሰጠነው እንደ አማራጭ ነው" ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ እነአቶ ጃዋር መሐመድ ያቀረቡትን ክስ በስፋት ማየታቸውን በመናገር፣ የደኅንነታችሁን ሁኔታ እንከታተላለን። ወደዚህ የምትመጡበትንም ሁኔታ እንከታተላለን ብለዋል። በሌላ በኩል የመንግሥት ሚዲያዎችና አንዳንድ የግል ሚዲያዎች ዘገባቸው ወገንተኝነት እንዳለበት ቅሬታ ያቀረቡት ደግሞ አቶ ደጀኔ ጣፋ ሲሆኑ፣ የመገናኛ ብዙሃኑ የፍርድ ቤት ውሎን በአግባቡ አንዲያቀርቡ "ይህንን ፍርድ ቤቱ እንዲያሳስብልን" በማለት ጠይቀዋል። ፍርድ ቤቱም ሚዲያዎቹ ችሎቱ ላይ የተባለውንና የችሎቱን ውሎ ብቻ እንዲዘግቡ አሳስቧል። የአቶ ጃዋርና የ24 ሰዎች የክስ መዝገብ በሰኔ ወር 2012 ዓ.ም ከሃጫሉ ግድያ በኋላ በቁጥጥር ሥር የዋሉት አቶ ጃዋር መሐመድና በክስ መዝገባቸው ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ሰዎች የሽብር ወንጀልን ለመቆጣጠርና ለመከላከል በወጣው አዋጅ፣ የቴሌኮም ወንጀልን ለመከላከል በወጣው አዋጅ፣ የአስተዳደርና የጦር መሳሪያ አጠቃቀም ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅንና የአገሪቱን ወንጀል ሕግ የተለያዩ አንቀጾችን በመተላለፍ ነው የተከሰሱት። አቶ ደጀኔ ጉተማ፣ ዶ/ር ብርሃነ መስቀል አበበና ፀጋዬ ረጋሳ አገር ውስጥ የሌሎና በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ መዝገብ ውስጥ ከተከሰሱት መካከል ናቸው። የድምጻዊ ሃጫሉ ግድያን ተከትሎ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ተከስቶ ከነበረ ሁከት ጋር ተያይዞ ነበር እነአቶ ጃዋር መሐመድ በቁጥጥር ሥር የዋሉት። ከዚያም በኋላ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ጃዋር መሐመድን ጨምሮ 24 ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ክስ መክፈቱ ይታወሳል። ይኹን እንጂ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ሐምዛ አዳነና አቶ ሸምሰዲን ጠሃ ለደኅንነታችን እንሰጋለን ብለው ሲናገሩ ነበር። ስለዚህም ይህን ጉዳይ ከግምት ውስጥ በማስገባት በሚገኙበት ማረሚያ ቤት ውስጥ ጊዜያዊ ችሎት እንዲቋቋምላቸው መጠየቃቸው ይታወሳል።
news-55211960
https://www.bbc.com/amharic/news-55211960
ኮሮረናቫይረስ፡ የትራምፕ ጠበቃ በኮቪድ-19 ተይዘው ሆስፒታል ገቡ
የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የግል ጠበቃና የቀድሞው የኒውዮርክ ከተማ ከንቲባ ሩዲ ጁሊያኒ በኮቪድ-19 ከተያዙ በኋላ ወደ ሆስፒታል መግባታቸው ተገለጸ።
የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጠበቃ ሩዲ ጁሊያኒ ፕሬዝደንት ትራምፕ የጠበቃቸውን ሆስፒታል መግባት በማስመልከት ጠበቃው ቶሎ እንዲሻላቸው ምኞታቸውን በትዊተር ገጻቸው ላይ ገልጸዋል። ጠበቃው ጁሊያኒ ከምርጫው በኋላ የትራምፕን የፍርድ ቤት ክርክር ሲመሩ የቆዩ ናቸው። የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን የ76 ዓመቱ ጠበቃ ሕመም ጸንቶባቸው ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ሜድስታር ጆርጅታዎን ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል እንዲገቡ መደረጉን በስፋት ዘግበዋል። የቀድሞ የኒው ዮርክ ከተማ ከንቲባ የአሁኑ የፕሬዝዳንቱ ጠበቃ መልካም ምኞት የገለጹላቸውን አመስግነው ከሕመማቸው እያገገሙ እንደሆነ ገልጸዋል። በዋይት ሐውስ የሚሰራው የጠበቃው ልጅ አንድረው ጁሊያኒ ወላጅ አባቱ እረፍት እያደረጉ እና እየተሻላቸው መሆኑን ገልጿል። ጠበቃው ጁሊያኒ የትኞቹን የበሽታው ምልክቶች እያሳዩ እንደሆነ አልተገለጸም። እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ አሃዝ ከሆነ በአሜሪካ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 14.6 ሚሊዮን የተቃረበ ሲሆን ከ281 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ሕመሞች ሕይወታቸው አልፏል። ይህም በዓለማችን ከፍተኛው ነው። ጠበቃው የምርጫውን ውጤት ለማስቀየር ወደ በርካታ ግዛቶች ተዘዋውረዋል። በጉዟቸው ወቅትም ጁሊያኒ የኮሮናቫይረስ ክልከላዎችን ሲተላለፉ ታይተዋል ተብሏል። የአፍ እና አፈንጫ መሸፋኛ ሳይደርጉ እና ርቀታቸውን ሳይጠበቁ ጁሊያኒ ተስተውለዋል። ባሳለፍነው ሐሙስ ጆርጂያ ግዛት የነበሩት ጁሊያኒ፤ ምንም አይነት ማስረጃ ሳያቀርቡ በጆርጂያ የተካሄደው ምርጫ ተጭበርብሯል ሲሉ ከሰው ነበር። ጠበቃውን ጨምሮ በርካታ የትራምፕ የቅርብ አማካሪዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። ቦሪስ ኢፕስታይን እና ኬይሊ ማኬንሊ በቅርቡ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡ የፕሬዝዳንት ትራምፕ የቅርብ አማካሪዎች ናቸው።
news-52153012
https://www.bbc.com/amharic/news-52153012
ሰሜን ኮሪያ ኮሮና የለብኝም ትላለች፤ እንዴት እንመናት?
አንድም ሰው በኮሮና አልተያዘብኝም ትላለች ሰሜን ኮሪያ። ጥብቅ እርምጃ ስለምወስድና ድንበሮቼን ከርችሜ ነው ይህን ውጤት ያመጣሁት ስትል ታብራራለች።
ይህንን ለመቀበል እቸገራለሁ ይላሉ በደቡብ ኮሪያ የአሜሪካ ጦር ኮማንደር። ሌላ ሰሜን ኮሪያዊ ኤክስፐርት በበኩላቸው የተያዘ ሰው አይኖርም ባይባልም በብዙ ቁጥር ላይሆን ይችላል ሲሉ ይገምታሉ። በዚህ ወቅት በመላው ዓለም የተያዦች ቁጥር 1 ሚሊዮን አልፏል። ከ53ሺ በላይ ደግሞ ሕይወታቸው አልፏል። ሰሜን ኮሪያ ግን በዚህ ቁጥር ውስጥ የኔ ዜጋ አንድም የለበትም ትላለች። ፓክ ዮንግ ሱ የተባሉ የሰሜን ኮሪያ የጤና ባለሥልጣን አንድም ሰው እንዳልተያዘ በድጋሚ አረጋግጠው ይህም የሆነው ድንበሮቻችንን ስለዘጋን፣ ወደ አገራችን የገባውን ለይተን ስላስቀመጥንና ሰው የሚበዛባቸው አካባቢዎችን በሙሉ ጸረ ቫይረስ መድኃኒት በመርጨታችን ነው ይላሉ። ይህ ግን ምን ያህል እውነት ነው? የአሜሪካ የጦር ጄኔራል ሮበርት አብራምስ ሰሜን ኮሪያ የምትለው ነገር ቅጥፈት ነው ይላሉ። አርሳቸው በጎረቤት ደቡብ ኮሪያ የሚገኘው የአሜሪካ ጦር አዛዥ ናቸው። ‹‹እኛ ባለን መረጃ ይህ እውነት እንዳልሆነ አሳምረን እናውቃለን›› ይላሉ ጄኔራሉ። ሆኖም ጄኔራሉ የተያዙት ሰሜን ኮሪያዊያን ምን ያህል እንደሆኑና የት እንደሚገኙ መናገር አልቻሉም። ኦሊቨር ሆታም በሰሜን ኮሪያ ዙርያ የሚሰራ ሚዲያ ተቋም ማኔጂንግ ኤዲተር ነው። ሰሜን ኮሪያ የምትለውን ለማመን እቸገራለሁ ይላል። ‹‹የማይመስል ነገር ነው፤ ከቻይናና ከደቡብ ኮሪያ የምትጎራበት አገር ናት። በተለይ ከቻይና ጋር በጥብቅ ንግድ ተሳስራለች። እንዴት ታዲያ ራሷን ጠብቃ መቆየት ይቻላታል?›› ሆኖም ኦሊቨር ኮሮና በሰሜን ኮሪያ ውስጥ ቢኖርም በወረርሽኝ ደረጃ ከቁጥጥር ውጭ ሆኗል ብሎ አያምንም። ቶሎ ብለው የወሰዷቸው እርምጃዎች ይህ እንዳይሆን እንዳደረገ ይገመታል። ሰሜን ኮሪያ ወረርሽኙ በቻይና ገና እንደተከሰተ ነበር እርምጃ መውሰድ የጀመረችው፤ ድንበር መዝጋት፣ የውጭ ዜጎችን ለይቶ ማስቀመጥ፣ ወዘተ። እንደ ኤን ኬ ዜና ጣቢያ ከሆነ ደግሞ መጀመርያ አካባቢ 10 ሺ ዜጎችን ለይታ አስቀምጣ ነበር፤ አሁንም ድረስ 500 የሚሆኑት ከዚያ አልወጡም። ሰሜን ኮሪያዊየን ስለ ቫይረሱ ሰምተው ይሆን? ሚስተር ሆታን እንደሚለው አብዛኛው ሰሜን ኮሪያዊ በዓለም ላይ ምን እየተከናወነ እንደሆነ መረጃ ላይኖረው ይችላል። ሆኖም ሰሜን ኮሪያ ወረርሽኙን ለማቆም ያደረገችው ተግባር በየጊዜው በአገር ውስጥ ሚዲያ በስፋት ይነገራል። ስለዚህ መረጃው በስፋት አለ ማለት ነው። ፍዮዶር ቴትስኪ ደግሞ በኩክሚን ዩኒቨርስቲ ተመራማሪ ናቸው። እርሳቸው እንደሚሉት ሰሜን ኮሪያ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ ቀልብ የሚሰውር ፕሮፓጋንዳ ዘመቻ አለ። በዚያውም ሕዝቡን በንጽህና አጠባበቅ ጉዳይና ቫይረሱን እንዴት መከላከል እንደሚቻል ያስተምራሉ። ሰሜን ኮሪያ በቂ የጤና መሠረተ ልማት አላት? የዚህ ጥያቄ መልስ አዎ የሚል ነው። ብዙዎች ሰሜን ኮሪያ በዚህ ረገድ የተንኮታኮተች አገር አድርገው ነው የሚያስቧት። ይህ ግን እውነት አይደለም። ሚስተር ቴርቲስኪ እንደሚሉት የሰሜን ኮሪያ የጤና መሠረተ ልማት ከርሷ ጋር በጂዲፒ ተቀራራቢ ከሆኑ አገራት ጋር ሲነጻጻር እጅግ እጅግ የተሻለ ነው። ‹‹ያደረጉት ምንድነው… ብዙ የጤና ባለሞያን አሰልጥነዋል፤ ብዙ ሐኪሞች አሏቸው፤ ምንም እንኳ የሚከፈላቸው ኢምንት ቢሆንም፤ ሆኖም የጤና አቅርቦትን ለሕዝባቸው በአጥጋቢ ሁኔታ የሚሰጡ ናቸው።›› ያም ሆኖ በአገሪቱ የተጣለው ማእቀብ በቂ የጤና ግብአቶችን እንዳትሸምት አድርጓታል። ሚስተር ሆቶም በበኩላቸው የጤና አቅርቦቱ በፕዮንግያንግ ይበል የሚያሰኝ ቢሆንም በገጠሪቱ ሰሜን ኮሪያ ግን የሚታሰብ አይደለም ይላሉ። በገጠር መብራትና ውሃ የሌላቸው ሆስፒታሎችን ልታገኝ ትችላለህ ይላሉ ሚስተር ሆቶም ሰሜን ኮሪያ ኮሮና ቢኖርባት ለምን ትደብቃለች? ለሰሜን ኮሪያ ቫይረሱ ወደ አገሪቱ መግባቱን ማመን ሽንፈት ተደርጎ ነው የሚታሰበው። ሚስተር ሆታም እንደሚሉት አገሪቱ ቫይረሱ እንዳልገባ ብዙ ፕሮፓጋንዳ ስለነዛችና ለመከላከልም ብዙ ርቀት ስለተጓዘች ቫይረሱ ቢገባም ገባ ለማለት ከባድ ይሆንባታል። በዚያ ላይ ሰሜን ኮሪያ የሽንፈት ተምሳሌት ተደርጋ እንድትሳል አትፈቅድም። ‹‹በዚያች አገር ስለ ሰሜን ኮሪያ መልካም የማይመስል መረጃ መስጠት አሳፋሪ ነገር ነው። በዚያች አገር ያልተጻፈ የአሰራር ባህል ‹‹መልካም ነገር ካልሆነ ዝም በል›› የሚል መርህን የሚከተል ነው። ይሉ ተመራማሪው ሚስተር ቴርቲትስኪ።
news-50640423
https://www.bbc.com/amharic/news-50640423
የአሜሪካና የቻይና እሰጣገባ ኢንተርኔትን ለሁለት እየከፈለው ይሆን?
ቻይናውያን የተቀረው ዓለም እንደ ልቡ ኢንተርኔትን በርብሮ የሚያገኛቸውን መረጃዎች ማግኘት አይችሉም። ለምሳሌ አንድ ቻይናዊ በጉግል መፈለጊያ ላይ ገብቶ ቻይና ብሎ ቢጽፍ የሚያገኘው መረጃ የተቀረው ዓለም ከሚያገኘው በእጅጉ የተለየ ነው።
የዓለማችን ከፍተኛው የህዝብ ቁጥር የምትይዘው ቻይና ኢንተርኔት በእጅጉ ቁጥጥር ከሚደረግባቸው ሀገራት የመጀመሪያውን ረድፍ ትይዛለች። የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሉት ደግሞ በቅርቡ ኢንተርኔት ለሁለት ይከፈላል፤ በቻይና የሚመራውና በአሜሪካ የሚመራው ተብሎ። • ሁሉንም በደህንነት ካሜራ የምትመለከተው ቻይና • ኢትዮ ቴሌኮም... ወዴት? ወዴት? ይህንን ሀሳብ ባለፈው ዓመት ወደፊት ያመጡት የጉግል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኤሪክ ሽሚት ናቸው። የቻይና ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች መንግሥት እንዲያዩት የሚፈቅድላቸውን መረጃዎች ብቻ ነው መመልከት የሚችሉት፤ ለምሳሌም እንደ ፌስቡክ፣ ትዊተር፣ ድሮፕቦክስ ወይንም ፒንትረስት ያሉ የማህበራዊ ሚዲያዎችና መገልገያዎችን መጠቀምም አይችሉም። በታይናንሜን አደባባይ ስለተፈጸመው ጭፍጨፋም ሆነ ማንኛውም ስለ ፕሬዚዳንታቸው ሺ ዢን ፒንግ የተሰጡ ትችቶችን በኢንተርኔት ላይ ፈልገው መመልከት አይችሉም። ምንም እንኳን ቻይና በዓለማችን ትልቁን የህዝብ ቁጥር ብትይዝም ትልልቅ የሚባሉ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ መስራት ባለመቻላቸውና መረጃ እንደ ልብ መቀያየር ባለመቻሉ ምክንያት ቻይናን ለቅቀው መሄድ እየመረጡ ነው። ሌላው ቀርቶ ወደ ቻይና ገበያዎች መግባት የሚፈልጉ ድርጅቶች ኢንተርኔት የተገደበ በመሆኑና ደንበኞቻቸውን እንደልብ ማግኘት ስለማይችሉ ወደ ሌሎች ሃገራት መሄድን ይመርጣሉ። ግዙፉ አፕል እንኳን እ.አ.አ. በ2017 ለቻይና ገበያ ከሚያቀርባቸው ስልኮች ላይ 'የኒውዮርክ ታይምስ' እና 'ስካይፕ' መተግበሪያዎችን እንዲያጠፋ ቀጭን ትእዛዝ ተሰትቶት ነበር። የአሜሪካው ስልክ አምራች ኩባንያም ሳያቅማማ ትእዛዙን ፈጽሟል። 'ሊንክድኢን' የተሰኘው የማህበራዊ ሚዲያ መገልገያ በመላው ዓለም የሚገኙ ስራ ፈላጊዎችንና እና ቀጣሪዎችን በአንድ መድረክ ለማገናኘት ተብሎ የተሰራ ቢሆንም ቻይናውያን ተጠቃሚዎች ከቻይና ውጪ ካሉ ሰዎች ጋር መገናኘት አይችሉም። በተጨማሪም ማንኛውም ፖለቲካዊ መልእክት ያለውን ገጽ ቻይናውያን እንዳያገኙት ይደረጋል። • ቻይና እሥር ቤት ያሉ ሙስሊም ዜጓቿን እያሰቃየች ነው በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ብሪቲሽ ኮሎምቢያ የቻይና ዘመናዊ ባህሎች ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ሬንሬን ያንግ እንደሚሉት የቻይና መንግስት ይህን ሁሉ ቁጥጥር የሚያደርገው ዜጎች ስለ ኮሙኒስት ፓርቲው እና ስለሃገራቸው ያላቸውን አመለካካት ለመቆጣጠር እንደሆነ ይናገራሉ። የቻይና ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ጉግል እና ዋትስአፕን መጠቀም ባይችሉም ባይዱ እና ዊቻት የተባሉ አማራጮች ቀርበውላቸዋል።
news-53328682
https://www.bbc.com/amharic/news-53328682
በሃጫሉ ግድያ የተቀሰቀሰው ውዝግብና የህወሓት ምላሽ
በድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ተጠርጥርው አስራ አራት የሚደርሱ ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ የታወቀ ሲሆን ግድያው በማን እና ለምን ዓላማስ እንደተፈጸመ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።
የተለያዩ ወገኖች በግድያው ዙሪያ በርከት ያሉ መላምቶችንና ተጠያቂዎችን በማንሳት እየተከራከሩ ቢሆንም እስካሁን ለግድያው ኃላፊነት የወሰደም ይሁን በፖሊስ የተገለጸ ወገን ባይኖርም ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ በሚወጡ መግለጫዎች መወነጃጀሎች እየተስተዋሉ ነው። በግልጽም ባይሆን አንዳንድ ባለስልጣናት ከግድያውና ግድያውን ተከትሎ ሞትን ውድመትን ካስከተለው ሁከት ጀርባ የኦነግ ሸኔ እና የህወሓት የተቀናጀ እጅ እንዳለም ከመንግሥት በኩል በሚወጡ መግለጫዎች ተንፀባርቋል። የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ባለፈው ሳምንት በድምጻዊ ሃጫሉ የቀብር ዕለት በክልሉ ቴሌቪዥን ላይ ተመሳሳይ ክስ ያቀረቡ ሲሆን የክልሉ መንግሥትም ባወጣው መግለጫ ላይ ይህንኑ ውንጀላ ደግሞታል። ባለፈው ሳምንት የተከሰተውን አለመረጋጋትና ያስከተለውን ጉዳት በተመለከተ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ማብራሪያ የሰጡት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት አቶ ንጉሡ ጥላሁንም በስም አይጥቀሱት እንጂ ህወሓት በቀውሱ ውስጥ እጁን እንዳለበት አመልክተዋል። አቶ ንጉሡ በአገሪቱ ውስጥ አለመረጋጋት ለመፍጠር እየጣሩ ነው ካሏቸው ቡድኖች መካከል የኦነግ ሸኔ ቡድንን በስም ጠቅሰው ሌላኛውን ወገን ደግሞ "ቀደም ሲል በስልጣን ላይ የነበረው ቡድን" በሚል ቃል ጠቁመዋል። ቀጥለውም ለትግራይ ወጣትና ሕዝብ መልዕከት ያስተላለፉት አቶ ንጉሱ "አፍራሽ ተልእኮ" አለው ያሉትን "ዘራፊው ቡድን የተፈጠረው ብጥብጥና ቀውስን በዋናነት፣ በአዝማችነት፣ በአቃጅነት የሚመራ መሆኑን በመረዳት፣ ይህንን ዘራፊ ቡድን በቃህ ሊለው ይገባል" ብለዋል። ይህንንም ተከትሎ የህወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የፌደራል መንግሥት የሚወቅስ መግለጫ አውጥቷል። "በአገርና ህዝብ ላይ ለደረሰውና ለሚደርሰው ጥፋት ብቸኛው ተጠያቂ የአራት ኪሎው አምባገነን አሃዳዊው ቡድን ነው" ሲልም ከስሷል። መግለጫው አክሎም "ለይስሙላ ሰላም ፍቅርና ይቅርታ እየሰበከ ወደ ስልጣን ኮርቻ እየተፈናጠጠ" በማለትም "ከውስጥና ከውጪ ያገኘውን ድጋፍ በመጠቀም ስልጣኑን ለማደላደልና ሕብረ ብሔራዊነትን ለማፍረስና አሃዳዊ ሥርዓት ለመመስረት ተጠቅሞበታል" ሲል አስፍሯል። በአገሪቱ ውስጥ ከተከሰተው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ በህወሓት ላይ የሚቀርቡ ክሶችን በተመለከተ በተለይም በድምጻዊው ግድያ ውስጥ ድርጅታቸው አለበት የሚለውን ውንጀላ በተመለከተ የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳን የቢቢሲው ፎከስ ኦን አፍሪካ ፕሮግራም ጠይቋቸው ነበር። "ለፖለቲካ ጥቅም ሰዎችን የመግደል አማራጭን የሚከተል ድርጅት አይደለም" በማለት የመለሱት አቶ ጌታቸው "ህወሓት ሰዎችን በማስወገድ ፖለቲካዊ ነጥብ በማስቆጠር የሚያምን ድርጅት አይደለም፤ ይህንንም ለማድረግ ምንም ምክንያት የለውም። ስለዚህ ህወሓትን በሃጫሉ ግድያ መክሰስ ጭልጥ ያለ ውሸት ነው" ሲሉ ክሱን አጣጥለውታል። ይልቁንም አቶ ጌታቸው በተራቸው የክሱን አቅጣጫ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩና አጋሮቻቸው አዙረው "የሃጫሉን እንቅስቃሴ የሚቃወሙ ሰዎች ነበሩ። ይህም የሚጠቁመው በጠቅላይ ሚኒስትሩና በዙሪያቸው ወዳሉ ሰዎች ነው" ብለዋል። አክለውም በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ ውስጥ ለሚከሰቱ ማናቸውም መጥፎ ነገሮች ህወሓትን ተጠያቂ ማድረግ የተለመደ ጉዳይ እየሆነ መምጣቱን ጠቅሰው እንዲያውም ጠቅላይ ሚኒስትሩን በአገሪቱ ውስጥ እየተከሰቱ ላሉት ችግሮች ተጠያቂ አድርገዋቸዋል። በአገሪቱ ውስጥ በአጠቃላይ የተፈጠረውን ችግርም ለመፍታት በገዢው ፓርቲና በህወሓት መካከል ብቻ ሳይሆን በሁሉም ፖለቲካ ፓርቲዎችና ቡድኖች መካከል ተቀራርቦ በመወያየት ብቻ ለተፈጠረው ቀውስ መፍትሄ ማምጣት እንደሚቻል ጠቁመዋል። ድርጅታቸው ህወሓትም ባወጣው መግለጫ ሕዝቡን "በትግልህ ያስመዘገብካቸውን መብቶች ላለማስነጠቅ ብቻ ሳይሆን አምባገነናዊ አሃዳዊ ኃይሎች በማንኛውም መስክ የሚሸርቡትን ሴራ ለመመከትና ሕብረ ብሔራዊ ፌደራላዊ ሥርዓቱን ከጥፋት ለመታደግ ከመሰል ኃይሎች ጎን ተሰልፈህ በቁርጠኝነት ለመታገል ዝግጁነትህን ይበልጥ አጠናክር" ሲል ጥሪ አቅርቧል። አክሎም የክልሉን ሕዝብ "ለወሳኝ ፍልሚያ በተጠንቀቅ እንዲቆም" ጥሪ አስተላልፏል። ህወሓት የኢህአዴግ ወራሽ ከሆነው የብልጽግና ፓርቲ እራሱን ካገለለ በኋላ ከማዕከላዊው መንግሥት ጋር ያለው ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበላሸ አሁን ካለበት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። በተለይ ብሔራዊው ምርጫ በኮሮናቫይረስ ምክንያት መራዘሙና በስልጣን ላይ ያለው አስተዳደር ቀጣዩ ምርጫ እስኪካሄድ እንዲቀጥል ከተወሰነ በኋላ ውዝግቡ የበለጠ እየተካረረ መጥቷል። ከሃጫሉ ግድያ እንዲሁም ተከትሎ በተከሰተው ሁከት ዙሪያ መካሰሱ እየተባባሰ መጥቶ በግልጽ መወነጃጀልና ህወሓትም ለሕዝቡ ቀጥሎ ለሚከሰተው ነገር እንዲዘጋጅ ጥሪ አቅርቧል። በቀጣይ ምን ሊከሰት እንደሚችል መገመትም አስቸጋሪ የሆነ ሲሆን የከፋ ነገርም እንዳይመጣም በርካታ የፖለቲካ ተንታኞች ያስጠነቅቃሉ።
news-53323318
https://www.bbc.com/amharic/news-53323318
ኮሮናቫይረስ፡ በበይነመረብ የሚማሩ የውጭ አገር ተማሪዎች ከአሜሪካ እንዲወጡ መወሰኑ ቁጣን ቀሰቀሰ
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ስርጭት ለመግታት በሚል የተለያዩ የትምህርት ተቋማት በአካል ማስተማርን በበይነ መረብ ወደሚደረግ አማራጭ የትምህርት ስርአት ተክተውታል። ከዚህም ጋር ተያይዞ በአሜሪካ ውስጥ በተማሪ ቪዛ ያሉ የውጭ አገር ተማሪዎች አገሪቷን ለቀው እንዲወጡ ተወስኗል።
የውጭ አገራት ዜጎችን በተመለከተ በበላይነት የሚመራው የመንግሥት ተቋም አይስ (ኢሚግሬሽን ኤንድ ከስተምስ ኢንፎርስመንት) ተማሪዎቹ በበይነ መረብ ብቻ የሚማሩ ከሆነ ከአገር እንዲወጡ እንደሚደረግም አስታውቋል። ያላቸው አማራጭም የሚማሩባቸውን ተቋማት በመቀየር በአካል ትምህርት የሚወስዱበትን መንገድ ማመቻቸት አለባቸው ተብሏል። በርካታ የአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ሆኖ ከመቀጠሉም ጋር ተያይዞ በሚቀጥለው አመትም ቢሆን ትምህርትን በበይነ መረብ ለማካሄድም እያሰቡ ነው። በዚህም የተነሳ ምን ያህል ተማሪዎች ተፅእኖ ውስጥ እንደሚወድቁ ቁጥሩ አልተጠቀሰም። ለጊዜው በጊዜያዊነት ወደበይነ መረብ ትምህርት ያሸጋገሩ ተቋማት ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎችና ለአጭር ጊዜ ትምህርት በአሜሪካ ውስጥ ያሉ ተማሪዎች በአገሪቷ ውስጥ እንዲቆዩና እንዲያጠናቅቁ ይደረጋል። ይሄ ሁኔታ ግን ለሚቀጥለው አመት የትምህርት ወቅት ተግባራዊ አይሆንም። ውሳኔውም ኤፍ 1ና ኤም1 የተሰኙ ቪዛ ያላቸውን ተማሪዎች እንደሚመለከትም ከአይስ መግለጫ መረዳት ይቻላል። ከሰሞኑ ሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ለሚቀጥለው አመት ትምህርት በበይነ መረብ እንደሚሆን አሳውቋል። በግቢው ማደሪያ ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎችም ቢሆኑ በበይነ መረብ እንዲማሩ ተወስኗል። ክሮኒክል ኦፍ ሃየር ኤዱኬሽን ከተባለው ድርጅት በተገኘው መረጃ 9 በመቶ የሚሆኑት ዩኒቨርስቲዎች በመጪው በጋ ትምህርቶቻቸውን በበይነ መረብ ለማካሄድ እንደወሰኑ ነው። ሁኔታው ግን በሚቀጥሉት ወራት ሊቀየር ይችላል። የሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ላሪ ባኮው ባወጡት መግለጫም አይስ ያወጣውንም መመሪያ ተቃውመውታል። ከዚህም በተጨማሪ የዲሞክራቷ ሴናተርም ኤልዛቤት ዋረን "ዩኒቨርስቲዎች በበይነ መረብ በማስተማራቸው ምክንያት ተማሪዎችን ከአሜሪካ ማስወጣት ጨካኝነት፣ ትርጉም የሌለውና ፀረ-የውጭ አገር ዜጎች ነው" ብለዋል በተባበሩት መንግሥታት የአሜሪካ አምባሳደርን ጨምሮ በርካታዎች ይህንን ውሳኔ ያወገዙት ሲሆን በተለያዩ ሃገራት ያሉትን ሁኔታዎች እንዲሁም በአገራት መካከል ያለውን የሰዓት ልዩነት ያላጤነ ነው ብለውታል። በሳውዝ ፍሎሪዻ ዩኒቨርስቲ የድህረ ምረቃ ትምህርቱን እየተከታተለ ያለው ፓኪስታናዊው ሙሃመድ ኤሃብ ራሱል ውሳኔው ለአለም አቀፍ ተማሪዎች አስደንጋጭ ነው ብሏል። "እንደ አለም አቀፍ ተማሪነታችንና በአገሪቷ ውስጥም አናሳ እንደመሆናችን መጠን አሜሪካ ውስጥ ለመቆየት ሁሌም ምክንያት አቅርቡ መባል አጣብቂኝ ውስጥ የሚከት ጉዳይ ነው። በዩኒቨርስቲው ትምህርታችንን ለመጪው አመታት እንከታተል አንከታተል እንኳን አናውቅም፤ ይሔ አሳሳቢ ነው" ብሏል።
news-52131802
https://www.bbc.com/amharic/news-52131802
በኮሮናቫይረስ ዘመን እጅግ ተፈላጊው መሣሪያ፤ ቬንትሌተር
የዓለም መንግሥታት የመተንፈሻ መርጃ መሣሪያ ጉዳይ እንዲህ ያስጨነቃቸው ለምንድነው?
በዚህ ወቅት በዓለም አንድ እጅግ ተፈላጊ ምርት አለ። የመተንፈሻ መርጃ መሣሪያ ወይም ቬንትሌተር ይባላል። ይህንን መሣሪያ ከትራምፕ እስከ ሞዲ፣ ከጁሴፔ ኮንቴ እስከ ሩሃኒ፣ ከማክሮን እስከ ማዱሮ በጥብቅ ይፈልጉታል። ለምን? መልሱ አጭር ነው። ለመተንፈስ። በሌላ አባባል ይህ መሣሪያ በበቂ የሌላቸው አገራት የሕዝባቸውን ጥቂት የማይባል ቁጥር ሊያጡ ይችላሉ። ምክንያቱም በኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው በሽታው ሲጠናበት ከሁሉ በላይ ለመተንፈስ ይቸገራልና ነው። በቬንትሌተር ካልታገዘ ደግሞ መዳን እየቻለም ቢሆን ይቺን ዓለም ይሰናበታል። የመተንፈሻ መርጃ መሣሪያው የሚሰራው እንዴት ነው? በአጭሩ ለማስረዳት ቬንትሌተር የሰውነታችንን የአተነፋፈስ ሥርዓት ተክቶ የሚሠራ ማሽን ነው። ሳምባችን እክል ሲገጥመው ነፍሳችን ከመሰወሯ በፊት ይህ ቬንትሌተር ከተገጠመልን ዕድሜ ቀጥል ይሆናል። ምክንያቱ ሌላ አይደለም፤ በቬንትሌተሩ ምክንያት የመተንፈስ ተግባር ስለሚሳለጥ ነው። ዶ/ር ቴድሮስ የሚመሩት የዓለም የጤና ድርጅት እንደሚለው በኮቪድ-19 ከተያዙት መካከል 80 ከመቶው በሽተኞች የሆስፒታል ውስብስብ ክትትል ሳያሻቸው ሊድኑ ይችላሉ። ነገር ግን ከ6ቱ በሽተኞች ቢያንስ አንዱ የመተንፈስ ችግር ይገጥመዋል። ይህም የሚሆነው ቫይረሱ ሳምባን ስለሚያውክ ነው። በዚህ ወቅት ቬንትሌተር ከሌለ ግለሰቡን ማዳን የማይታሰብ ነው። ሁለት ዓይነት የሳምባ መርጃ መሣሪያ (ቬንትሌተር) አለ። በሕክምና ሁለት ዓይነት መተንፈሻ መርጃ መሣሪያ አለ። አንዱ መካኒካል ቬንትሌተር ነው። ሌላኛው ደግሞ ቱቦ-አልባ ቬንትሌተር ይሰኛል። መካኒካል ቬንትሌተር የአየር ቱቦ በአፍ በኩል እንዲገባ ተደርጎ ታማሚው ካርቦንዳይኦክሳይድ እንዲያስወጣና ኦክሲጅን እንዲያስገባ የሚያደርግ ነው። ቱቦ-አልባው ቬንትሌተር ወይም በእንግሊዝኛው (Non Invasive Ventilator) ግን ወደ ሳምባ የሚወርድ ቧንቧ ሳይኖረው አፍና አፍንጫ ላይ በሚደረግ ጭምብል ብቻ የሚሰራ ነው። ቬንትሌተሮቹ ሂሙዲፋየር [እርጥበት የሚፈጥር] ክፍል አላቸው። ይህም ማለት ወደ ሰውነት የሚገባን ሙቀትና እርጥበት የሚቆጣጠርና ሁኔታው ለሰውነት ሙቀት ተስማሚ በሆነ መጠን እንዲሆን የሚያደርግ ነው። በዚህ ወቅት በሽተኞች የመተንፈሻ አካል ጡንቻዎች ዘና እንዲሉላቸው የሚያስችል መድኃኒት ይሰጣቸዋል። መጠነኛ የኮሮና ቫይረስ ምልክቶችን የሚያሳዩ በሽተኞች ግን የፊት ጭምብል ቬንትሌተር ብቻ ሊሰጣቸው ይችላል። ይህም በአፍና አፍንጫ በኩል በግፊት አየር ወደ ሳምባ እንዲገባ የማድረግ ዘዴ ነው። እንደ ኮፍያ የሚጠለቀው ቬንትሌተር የለንደን ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ መሐንዲሶች ከመርሴዲስ ፎርሙላ-1 አቻዎቻቸው ጋር በመሆን አዲስ ዓይነት አጋዥ የመተንፈሻ መሣሪያ ለመሥራት ሙከራ ላይ ናቸው። ነገሮች በታሰበው መልኩ ከሄዱ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በቀን 1ሺ የመተንፈሻ መሣሪያን ማምረት ይችላሉ። ይህ ለእንግሊዛዊያን ነው። ይህ አዲሱ ምርት እንደ ኮፍያ የሚጠለቅና መላው ፊትን የሚሸፍን ነው። በሰሜን ጣሊያን ሎምባርዲ በኮቪድ-19 በተያዙ በሽተኞች ላይ በተደረገ ሙከራ 50 ከመቶ የሚሆኑት ከአፍ ወደ ሳምባ የሚወርድ የአየር ትቦ ማስገባት ሳያስፈልጋቸው በዚህ አዲሱ የመተንፈሻ መሣሪያ (የትንፋሽ ኮፍያ) መተንፈስ ይቻላቸዋል ተብሏል። ይህ በጭንቅላት የሚጠለቀው አዲሱ የመተንፈሻ ኮፍያ ቫይረሱ ከበሽተኞች ትንፋሽ ጋር አየር ላይ ለደቂቃም ቢሆን እንዳይቆይ ስለሚያስችል ተመራጭ አድርጎታል። ሁሉም ዓይነት የመተንፈሻ መርጃ መሣሪያዎች በባለሞያ ካልታጋዙ ድንገተኛ ሞትን የሚያስከትሉ ናቸው። አገራት ስንት መተንፈሻ መሣሪያ ያስፈልጋቸዋል? የእንግሊዝ ብሔራዊ ጤና አገልግሎት (NHS) ለጊዜው በእጁ የሚገኘው የመተንፈሻ መርጃ መሣሪያ ቁጥር 8175 ብቻ እንደሆነ ይፋ አድርጓል። ይህ ቁጥር እየመጣ ካለው አደጋ አንጻር ሲነጻጸር በጣም ትንሽ ነው። በትንሹ 30 ሺህ ያህል ያስፈልጋል። ይህን ቁጥር ለማሳካት በእንግሊዝ ትልልቅ ኩባንያዎች እየተረባረቡ ነው። በእንግሊዝ ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም ሌላ ቁሳቁስ አምራጭ ድርጅቶች ሳይቀሩ "ዳይ ወደ ቬንትሌተር ምርት ግቡ!" ተብለዋል። በእንግሊዝ ከሁሉም ትኩረት የሳበው በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲና በኪንግስ ኮሌጅ ሳይንቲስቶችና መሐንዲሶች ጥምረት እውን ሊሆን የተቃረበው ባለ ርካሽ ዋጋ የመተንፈሻ መርጃ መሣሪያ ነው። ህንድ በህንድ 1.3 ቢሊዮን ሕዝብ ቤቱ እንዲጸና ከተደረገ በኋላ ክፉ ቀን ሊመጣ ነው በሚል የቬንትሌተር ምርት ተጧጡፏል። በተለይም ወጣት መሀንዲሶች ኪስ የማይጎዳና ቶሎ ሊደርስ የሚችል የመተንፈሻ መርጃ መሣሪያ ለመፍጠር ቀን ተሌት እየሠሩ ነው። ህንድ ለዚህ ሁሉ ሕዝቧ ያላት የመተንፈሻ መርጃ መሣሪያ ቁጥር 48 ሺህ ብቻ ነው። ከዚህ ውስጥ ምን ያህሉ በትክክል እንደሚሰራ እንኳ የሚያውቅ የለም። አሜሪካ አንድ የካሊፎርኒያ ኩባንያ ከዚህ በፊት አገልግሎት ላይ የነበሩና የተበላሹ የመተንፈሻ መርጃ መሣሪያዎችን መልሶ በመጠገኑ እየተሞካሸ ነው። ብሉም ኢነርጂ የተባለው ይህ ኩባንያ 170 ቬንትሌተሮችን ነው አድሶ ወደ ሥራ የሚያስገባው። ቴስላ በበኩሉ 1255 የመተንፈሻ መርጃ መሣሪያዎችን ከ3 የተመሰከረላቸው አምራች ኩባንያዎች በመግዛት ለኒው ዮርኩ አስተዳዳሪ አስረክቧል። የኒው ዮርኩ ገዢ ለስጦታው አመስግነው በቀጣይ ሳምንታት እነዚህ መሣሪያዎች በርካታ ሕይወትን ይታደጉልናል ብለዋል። ኒው ዮርክ እስከ 30 ሺህ የመተንፈሻ መርጃ መሣሪያ ያስፈልጋታል። መኪና አምራቹ ቴስላ ብቻ ሳይሆን ጄኔራል ሞተርስ እና ፎርድም ይህንን እጅግ አስፈላጊ የመተንፈሻ መርጃ መሣሪያ በማምረት ተጠምደዋል። ሶሳይቲ ኦፍ ክሪቲካል ኬር ሚዲስን እንዳለው ከሆነ አሜሪካ እስከ 960 ሺህ የመተንፈሻ መርጃ መሣሪያዎች ሊያስፈልጋት ይችላል። እንደ ኢትዮጵያ ያሉ በጤና ዘርፍ ብዙ ርቀት ያልሄዱ አገራት ትልቅ ፈተና ይኸው መሣሪያ እንደሚሆን ይታሰባል። ምክንያቱም ከ6ቱ ታማሚዎች አንዱ በዚህ ቬንትሌተር ካልታገዘ ሕይወትን ማቆየት ከባድ ነውና። አይበለውና በርካታ ሰዎች በኮቪድ 19 ቢያዙ አገሪቱ ያላት የቬንትሌተር ቁጥር በበቂ ሊዳረስ አይቻለውም። ብዙ አገራት ያሏቸው ቬንትሌተሮች ያረጁና ለዚህ በሽታ የማይመጥኑ ናቸው እየተባለ ነው። እነሱም ቢሆኑ በሌሎች በሽታዎች በሚሰቃዩ ሰዎች ተይዘዋል። ማሊ የሕዝቧ ቁጥር ወደ 20 ሚሊዮን ይጠጋል፡፡ ያሏት የመተንፈሻ መርጃ መሣሪያዎች ግን 56 ናቸው።
news-56900923
https://www.bbc.com/amharic/news-56900923
ወደ አገር ገቡ በተባሉት ገጀራዎች ላይ የፌዴራል ፖሊስ ምርመራ እያደረኩ ነው አለ
ወደ አገር ውስጥ ገብተው በጉምሩክ አማካይነት ስለተያዙት ከፍተኛ መጠን ያላቸውን ገጀራዎች በተመለከተ የፌዴራል ፖሊስ ምርመራ እያደረገ መሆኑ ተገለጸ።
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ጄላን አብዲ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ገጀራዎቹ የገቡበት ሰነድን ጨምሮ ለምን አገልግሎት ወደ ኢትዮጵያ እንደገቡ ዝርዝር ምርመራ እየተደረገ ነው ብለዋል። ትናንት [ሰኞ] የተለያዩ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን የገቢዎች ሚኒስቴርን ጠቅሰው በትልቅ ኮንቴይነር ተጭነው "በሕገ ወጥ ሰነድ ወደ አገር ውስጥ የገቡ ገጀራዎች መያዛቸውን" ተዘግቦ ነበር። የገቢዎች ሚኒስቴር በፌስቡክ ገጹ ላይ ከምስል ጋር እንዳሰፈረው መነሻቸው ቻይና የሆኑትና ብዛታችው 186 ሺህ 240 የሆኑትን ገጀራዎችን ሞጆ ደረቅ ወደብ ከደረሱ በኋላ አስመጪው "ከፌዴራል ፖሊስ የተፈቀደለት በማስመሰል እና ሐሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት ለማሳለፍ ሞክሯል" ሲል አመልክቷል። ሆኖም የቀረበው ሰነድ ሕጋዊነት ገና እየተጣራ ባለበት ሁኔታ እንዲህ አይነት ትክክል ያልሆነ መረጃ መውጣቱን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ጄላን አብዲ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ገጀራዎቹ ተገቢውን ታክስ ከፍለው በሕጋዊ መንገድ ሞጆ መድረሳቸውን የገለጹት ኃላፊው ሞጆ ከደረሱ በኋላ አስመጪው እቃዎቹን ለመውስድ ጥያቄ ማቅረባቸውን አስታውሰዋል። ሆኖም "በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታ" ምክንያት ከፌዴራል ፖሊስ ማረጋገጫ እንዲያመጡ በጉምሩክ ኮሚሽን በኩል መጠየቃቸውን ገልጸዋል። በዚህም "የምርጫ ጊዜ ስለሆነ ከፖሊስ ፍቃድ አምጡ ሲሏቸው የሆነ ወረቀት አጽፈው ይመጣሉ። ጉምሩክ ደግሞ ይሄ ነገር መጣራት አለበት ብሎ እሱ እየተጣራ ነው። ተጣርቶ ፎርጅድ [ሐሰተኛ ሰነድ] መሆኑ ከተረጋገጠ ሰዎቹ ተጠያቂ ይሆናሉ" ብለዋል አቶ ጄላን። አሁን ላይ ግን ምንም የተረጋገጠ ነገር አለመኖሩንም ጠቁመዋል። አስመጪዎቹ ገጀራዎቹን ያስገቡበት ምክንያትም እየተጠራ ነው ያለው ያሉት ኃላፊው በእነርሱ በኩል ግን '"ለልማት" ሥራ እንደሆነ መግለጻቸውን ጠቁመዋል። እናም ይህ ጉዳይ በምርመራ ሂደት ላይ እያለ መረጃው መሰራጨቱን አመልክተው ፖሊስ ግን ገጀራዎቹ የገቡበት ሰነድ ትክክለኛነትና ለምን ጉዳይ ወደአገር ውስጥ እንደገባ ምርመራ እኣደረገ መሆኑን አመልክተዋል። በምርጫና በአገራዊ የጸጥታ ሁኔታ ምክንያት ከሳምንታት በፊት የግብርና ሚኒስቴር ከውጪ አገር ያስገባቸው ገጀራዎች እንዳይሰራጩ እገዳ መጣሉንም አቶ ጄይላን ለቢቢሲ ገልጸዋል። የገቢዎች ሚንስቴር በሕገወጥ መንገድ ወደ አገር ውስጥ ሊገባ የነበረ 186 ሺህ በላይ ገጀራ መያዙን እና የዕቃው ባለቤት እና አስተላላፊው /ትራንዚተሩ/ ተይዘው ጉዳዩ በምርመራ ላይ እንደሚገኝ በይፋዊ ፌስቡክ ገጹ ላይ አስታውቋል። ሚኒስቴሩ ከ15 ቀን በፊት በአንድ አስመጪ ብዛቱ 186,240 የሆነ ገጀራ በአራት ባለ 20 ጫማ ኮንቴይነሮች ከቻይና ተጭኖ ሞጆ ጉምሩክ ተጓጉዞ መድረሱን አመልክቷል። ዕቃው በዲክላራሲዮን ቁጥር 4-1919/21 ተመዝግቦ ወደ አገር ውስጥ እንዲገባ ከፌዴራል ፖሊስ የተፈቀደለት በማስመሰል እና ሐሰተኛ ሰነድ አዘጋጅቶ ለገቢ ዕቃ አወጣጥ የሰነድ መርማሪው አቅርቦ ሰነዱ ተመርምሮ ከ7.7ሚሊዮን ብር በላይ ቀረጥና ታክስ ተከፍሎበት ተለቆ እንደነበር አስታውቋል። ገጀራው ከተለቀቀ በኋላ በጉምሩክ ኮሚሽን እና በሞጆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኢንተለጀንስ በኩል ክትትል ተደርጎ የቀረበው ሰነድ ሲጣራ ሐሰተኛ እና ዕቃውም ወደ አገር ውስጥ እንዲገባ ከፌዴራል ፖሊስ ፈቃድ ያልተሰጠው መሆኑ መረጋገጡንም ጠቁሟል። ይህ ጉዳዩ ከ15 ቀን በፊት የተከሰተ ቢሆንም፤ አስመጪው ያቀረብኩት ሰነድ ሕጋዊ ነው በማለት ቅሬታ ስላቀረበ ከፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጋር በጋራ ሲጣራ ቆይቶ ሰነዱ ሐሰተኛ እና ከፌደራል ፖሊስ ፍቃድ ያልተሰጠው መሆኑ መረጋገጡን ሚኒስቴሩ አመልክቷል።
41606615
https://www.bbc.com/amharic/41606615
በመጨረሻ ዙማ ይከሰሱ ይሆን?
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ በሙስና፣ በማጭበርበር፣ ገንዘብ በሕገ-ወጥ መንገድ በማዘዋወርና የህዝብን ገንዘብ ያለአግባብ በመጠቀም እንዲከሰሱ ይግባኝ ሰሚ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወሰነ።
ከ17 ዓመት በፊት ከነበረ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ስምምነት ጋር በተያያዘ አቃቤ ህግ 783 የሚሆኑ የሙስና ክሶች እንዲቀርቡም ከታችኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ ጋር ተስማምቷል። ይህ ክስ ከስምንት ዓመት በፊት ወደ ጎን ተትቶ ዙማ ፕሬዚዳንት ለመሆን ችለዋል። ዙማ ንፁህ ነኝ ማለታቸውንም ቀጥለዋል። ክሱ ከ12 ዓመታት በፊት ለዙማ ጥቅም ሲል ሻቢር ሼክ የተባለ ነጋዴ ከፈረንሳይ የመሳሪያ አምራች ኩባንያ ጉቦ በመቀበል ጥፋተኛ ከሆነበት ድርጊት ጋርም ይገናኛል። ይህ ክስ በጊዜው ዙማም ላይ ቀርቦ የነበረ ቢሆንም ከስምንት ዓመት በፊት ውድቅ ተደርጓል። ዙማም ሆኑ ሌሎች የመንግሥት ባለስልጣናት ከተዋጊ ጀቶች፣ ጀልባዎች እንዲሁም ከጦር መሳሪያ ግዢዎች ጋር በተያያዘ ገንዘብ ወስደዋልም ተብለው ይወነጀላሉ። ዲሞክራቲክ አሊያንስ ፓርቲ ባለፈው ዓመት እንደገና ክስ የመሰረተ ሲሆን ፕሪቶሪያ የሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ክሱን ተቀብሏል። የፕሬዚዳንቱ የህግ አማካሪዎች ውሳኔውን "ያልበሰለ አካሄድ" ብለውታል። የስለላ የስልክ ንግግሮች ይህ የሙስና ክስ በቀላሉ እንደማያበቃ እየተነገረ ነው። ፕሬዚዳንት ዙማ በ783 የሙስና ክሶች ወደ ፍርድ ቤት እንዳይሄዱ ብዙ ታግላዋል። ከዓመታት በፊት አነጋጋሪ በሆነ ሁኔታ ክሱ ውድቅ የተደረገው፤ የደህንነት ሰዎች የአቃቤ ህጎችን የስልክ ንግግር ጠልፈው በማሰማት "ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት" ታይቶበታል በሚል ነበር። ይህንን ተከትሎም ዙማ ከሳምንታት በኋላ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት በመሆን አሸነፉ። ይህ የስልክ ንግግር በአደባባይ ያልተገለጠ ሲሆን፤ ተቃዋሚዎቻቸው የሙስናው ክሱ ተመልሶ እንዲንቀሳቀስ ብዙ ታግለዋል። ፍርድ ቤቱ በፅንሰ-ሃሳብ ደረጃ ይግባኙን ቢቀበለውም በተግባር ግን አቃቤ ህግ ክሱን ያጓትተዋል የሚሉም አልታጡም። የዙማ የአመራር ጊዜ ከሁለት ዓመታት በኋላ የሚያበቃ ሲሆን ለሶስተኛ ዙር መመረጥ አይችሉም። ከአፓርታይድ ሥርዓት መወገድ በኋላ በደቡብ አፍሪካ ወደ ሥልጣን ከመጡ አነጋጋሪ አመራሮች ቀዳሚ የሆኑት ዙማ፤ ለዓመታት በፓርላማው ስምንት ያህል ጊዜ የመተማመኛ ድምፅ ቢሰጥባቸውም በመንበራቸው ላይ ለመቆየት ችለዋል።
news-57097407
https://www.bbc.com/amharic/news-57097407
የማንዴላ የልጅ ልጅ በፖሊስ ጥቃት ተሰነዘረብኝ አለ
የመጀመሪያው የደቡብ አፍሪካ ጥቁር ፕሬዝዳንት ኔልሰን ማንዴላ የልጅ ልጅ ፖሊስ "ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት አድርሶብኛል" በሚል ክስ እንደሚመሰርት የመገናኛ ብዙሃን ዘገቡ፡፡
ኔልሰን ማንዴላ ያደጉበትን የመቀሄኬዝዌኒን ቅርስ ከሌሎች ሦስት ሰዎች ጋር ጎብኝተው በሌሊት ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ፖሊሱ አስቁሟቸው እንደደበደቧቸው ማይቡዬ ማንዴላ ተናግሯል፡፡ ክስተቱ የተፈጸፈመው ግንቦት 8 ነው ተብሏል፡፡ ፖሊሶቹ ጭንቅላቱ ላይ መምታትን ጨምሮ "የጭካኔ" ድርጊቶች እንደፈጸሙባቸው ተናግሯል። በዚህም ከግራ ዓይኑ በላይ መሰንጠቁን ገልጿል፡፡ ጥቃቱ ከመፈፀሙ በፊት ፖሊስ ተሳፍረውበት የነበሩትን መኪና ለመፈተሽ ጥያቄ ማቅረቡን ተናግሯል፡፡ "መሬት ላይ እንድንተኛ መጠየቅ ሲጀምሩ ፈቃደኛ ባለመሆን መኪናውን ተደግፌ ቆሜ እንድፈተሽ ጠየቅኩኝ። ይህን ያልኩት በዋነኝነት ዝናብ ስለነበረና እና በጠጠር መንገድ ላይ ስለሆንን ነበር" ሲል ለአይኦኤል የዜና አውታር አስረድቷል፡፡ ማይቡዬ ማንዴላ ከደረሰባቸው ጥቃት በኋላ በፌስቡክ ገጹ ፎቶዎቹን አጋርቷል፡፡ በምስራቅ ኬፕ አውራጃ ለሚገኘው ማዲይራ ፖሊስ መምሪያም ስሞታውን አስገብቷል፡፡ መምሪያው ምንም አስተያየት ሳይሰጥ ጉዳዩን አውቀዋለሁ ማለቱም ተዘግቧል፡፡
news-55040275
https://www.bbc.com/amharic/news-55040275
ትግራይ፡ በባሕር ዳር ከተማ ላይ ለሦስተኛ ጊዜ ጥቃት መፈጸሙ ተነገረ
ዛሬ ንጋት 12፡20 አካባቢ በባሕር ዳር ከተማ ላይ በሁለት ሳምንት ውስጥ ለሦስተኛ ጊዜ ከባድ የፍንዳታ ድምጽ መሰማቱን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ።
ቢቢሲ ያነጋገራቸው አንድ ነዋሪ ሦስት ፍንዳታ መስማታቸውን ሲናገሩ ሌላኛው ነዋሪ ደግሞ ሁለት የፍንዳታ ድምጽ መስማታቸውንና ከዚህ ቀደም ከተፈጸሙት የሮኬት ጥቃቶች ጋር ተመሳሳይ መሆናቸውን ገልጸዋል። በስፍራው የሚገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ ንጋት ላይ ቢያንስ ሁለት ከባድ የፍንዳታ ድምጽ በከተማዋ መሰማቱን አረጋግጧል። በጉዳዩ ላይ እስካሁን የክልሉ መንግሥትም ሆነ የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት ያሉት ነገር የለም። ቢቢሲ የዛሬ ጠዋቱ ፍንዳታ የሮኬት ጥቃት ስለመሆኑና ጥቃቱ ዒላማ ምን እንደነበረ እንዲሁም የደረሰ ጉዳት መኖር አለመኖሩን እስካሁን ማረጋገጥ አልቻለም። ከዚህ ቀደም የሮኬት ፍንፍንዳታዎቹን ተከትሎ የተኩስ ድምጽ ይሰማ እንደነበረ ያስታወሱት ነዋሪዎቹ፤ ዛሬ ንጋት ላይ ካጋጠመው ፍንዳታ በኋላ ግን ምንም አይነት የተኩስ ድምጽ አለመሰማቱን ተናግረዋል። ጥቃቱን በተመለከተ ከአማራ ክልልም ሆነ ከፌደራል መንግሥቱ የተሰጠ ምንም መግለጫ የሌለ ሲሆን፤ ሰኞ ከሰዓት በኋላ በትግራይ ቴሌቪዝን ላይ ጥቃቱ የባሕር ዳር አውሮፕላን ማረፊያን ኢላማ አድርጎ በህወሓት መፈጸሙን ተገልጿል። ከዚህ ቀደም ኅዳር 05 እና ባለፈው ሳምንት ማብቂያ አርብ ኅዳር 11/2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል ኃይሎች የሮኬት ጥቃቶች በከተማ ላይ ተፈጽመው የነበረ ሲሆን ዛሬ ንጋት ላይ የተፈጸመው ፍንዳታ በከተማዋ ውስጥ ሲያጋጥም ለሦስተኛ ጊዜ መሆኑ ነው። ከዚህ ቀደም በባሕዳር ከተማ ላይ ሁለት ጊዜ እንዲሁም በጎንደር ከተማ ላይ አንድ የሮኬት ጥቃት የተፈጸመ ሲሆን ከሁለቱ ከተሞች በተጨማሪም ወደ ኤርትራ መዲና አሥመራም ሮኬት ተተኩሶ እንደነበረ ይታወሳል። ከዚህ በፊት በባሕር ዳር ከተማ ላይ የተፈሙት ሁለት የሮኬት ጥቃቶች ጉዳት አለማድረሳቸው የተገለጸ ሲሆን ኢላማ ያደረጉትም በከተማዋ የሚገኘውን አየር ማረፊያ ነበር ተብሏል። ለእነዚህ የሮኬት ጥቃቶች የህውሓት ከፍተኛ አመራሮች ኃላፊነቱን ወስደዋል። የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል ይልማ መርዳሳ በሮኬት ጥቃቱ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል። በፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልልን በሚመራው ህወሓት መካከል ለወራት የቆየው አለመግባባትና መካሰስ ባለፈው ዓመት ማብቂያ ላይ በትግራይ ክልል በተናጠል የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ መባባሱ ይታወሳል። በጥቅምት ወር ማብቂያ ላይ በትግራይ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ ላይ በክልሉ ኃይሎች ጥቃት መፈጸሙን በመግለጽ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ማዘዛቸውን ተከትሎ ፍጥጫው ወደ ግጭት አምርቶ ሦስተኛ ሳምንቱን ሊደፍን ተቃርቧል።
41332692
https://www.bbc.com/amharic/41332692
በዩጋንዳ ሕይወትን ከዜሮ የሚጀምሩት ስደተኞች
ሶስት፣ አራት፣ አምስት፣ ስድስት፣ ሰባት. . . ሰማያዊ ጃኬት ሰልፉን የሚመራው ሰው በእጁ ከያዘው መዝገብ ላይ ቁጥሮች ይቆጥራል። ጅምላ የሚሆኑ ሴቶች ኮረብታ የሚወጣውን ባለሰማያዊ ጃኬት ሰው ይከተሉታል። ሰውየው ኮረብታውን እንዳጋመሰ ቆመ።
ደቡብ ሱዳናውያን ስደተኞች መሬታቸውን ለመውሰድ ሰልፍ ላይ ዞር ብሎ ሰልፉ መጀመሪያ ላይ የቆመችውን ሴት "ይህ ያንቺ ቦታ ነው" አላት። ሀምሳ ሜትር ያህል ከሴትየዋ ከራቀ በኋላ ድንበሯን አመላከታት። የዩጋንዳ ስደተኞችን የመቀበል ፖሊሲ በተግባር ሲገለፅ ይህን ይመስላል። በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍል በሚገኙ መጠለያዎች ኡጋንዳ ከደቡብ ሱዳን ብቻ የሚመጡ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ስደተኞችን አስጠልላለች። ስደተኞቹ የተሳጣቸው መሬት ላይ የሞቀ የስደት ኑሮ መምራት ጀምረዋል። አልፎም ከእርዳታ ድርጅቶች የተሰጣቸውን ዘር በመጠቀም በእርሻ ዘርፍም የተሰማሩ አሉ። አንዳንዶቹም ፍየል ማርባት ጀምረዋል። ዩጋንዳ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ብዛት ያለው ስደተኛ በመቀበል ቁጥር አንድ ላይ የምትገኝ ሀገር ነች። ከተለያየ የአለም ክፍል ሀገራቸውን ጥለው የሚመጡ ስደተኞችን እጆቿን ዘርግታ በመቀበል ዩጋንዳ ግንባር ቀደም ሆናለች። አዲስ ለሚመጡ ስደተኞችም በመስጠት አቀባበላቸውን አሳይተዋል ። ነገር ግን ዋናው ጥያቄ ከመመንጠርያ (ገጀራ) በቀር እጃቸው ላይ ምንም የሌላቸው ስደተኞች በምን ተአምር ይህንን መሬት ወደ ቤትነት ይቀይሩታል የሚለው ነው። ለስደተኞቹ ቤት መስሪያ ከላስቲክ፣ ቋሚ እንጨቶች፣ ገመድ እና መመንጠሪያ የዘለለ ነገር አይሰጣቸውም። ምንም ነገር ከመስራታቸው በፊት መሬቱን በመመንጠሪያው ማስተካከል ግድ ይላቸዋል። ጨቅላ በጀርባዋ ያዘለችው ደቡብ ሱዳናዊቷ ስደተኛ ጆሴፊን ፎኒ አይኗ ሩቅ የማየት ችግር ስላለበት አገሯ ቀዶ ጥገና አካሂዳለች። ጆሴፊን ለእርዳታው ብቁ ትሁን አትሁን ግልፅ አይደለም እንጂ አንዳንድ እርዳታ የሚያሻቸው ስደተኞችም ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው። ለጊዘው ግን ዞር ዞር ብላ የተሰጣት መሬት ላይ ያለውን ሳር ከተመለከተች በኋላ "ለዛሬ እዚህ እንተኛለን" አለች። በዩጋንዳም ሆነ በዓለም ትልቁ የስደተኞች መጠለያ በዩምቤ ግዛት የሚገኘው 'ቢዲ ቢዲ' መጠለያ በውስጡ 275 ሺህ ስደኞችን አቅፏል። የጆሴፊን መፃኢ ዕጣ ፈንታም ወደዚህ ግዙፍ የስደተኞች መጠለያ ነው። ከተከፈተ ዓመት ያስቆጠረው ይህ ጣቢያ በጭቃ ቤቶች የተሞላ ነው። ስፍራው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከጥቅጥቅ ጫቃነት ወደ የጭቃ ቤቶች መናኸሪያ መለወጡ ብዙዎችን ያሰደመመ ነው። ሌላኛዋ ስደተኛ ክርስቲን አይሻ ባሏን ትታ ወደ 'ቢዲ ቢዲ' ስደተኞች መጠለያ ከመጣች እነሆ ዓመት ደፈነች። በተሰጣት መሬት ላይ የጭቃ ቤት የሰራችው የማንንም እርዳታ ሳትፈልግ ነበር። የቤት ጣሪያዋን የተሻለ እንዲሆን ሜርሲ የተባለች ልዩ ፍላጎት የሚያሻት ታዳጊን በመንከባከብ ገቢ ታገኛለች። ከዛም በተጨማሪ የራሷን ስድስት ልጆችም ማሳደግም አለባት። ከክርስቲን ጋር አብራ ከደቡብ ሱዳን የተሰሰደችው ሮዝ አቡዋም እዚህ ስደተኞች ጣቢያ ብቻዋን ኑሮዋን ለመግፋት ተገዳለች። "ምርጫ የለኝም። ባለቤቴ ተገድሏል። እዚህ ብቻዬን ነኝ።" በማለት በሀዘኔታ ትናገራለች
news-45649051
https://www.bbc.com/amharic/news-45649051
በጋምቤላ ከተማ በተነሳ ግጭት የዘጠኝ ሰዎች ህይወት አለፈ
ከትናንት በስቲያ በጋምቤላ ከተማ በተነሳ ግጭት የዘጠኝ ሰዎች ህይወት ማለፉንና 21 ሰዎች ለጉዳት መዳረጋቸውን የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ኦባንግ ሜቶ አስታወቁ።
አቶ ኦባንግ «ወጣቶቹ የተገደሉት ከፀጥታ ኃይሎች በበተኮሰ ጥይት ነው፤ ጥያቄያቸው ደግሞ የመልካም አስተዳደር ነበር» ይላሉ። የጋምቤላ ከተማ ነዋሪ ጋትዊች ጋልዋክ የግጭቱን መንስዔ ሲያስረዱ፤ በአኝዋክ እና ኑዌር ወጣቶች መካከል የተነሳ ግርግር ነው ቢሉም፤ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ኦባንግ ግን ጉዳዩ የመልካም አስተዳደር ነው፤ ጥያቄውም የቆየ ነው ይላሉ። • በመቱ ዩኒቨርስቲ ብሔር ተኮር ውጥረት ነግሷል «የጋምቤላ ችግር የቆየ፣ የሰነበተ ነው። የክልሉ ነዋሪዎች በተለይ ደግሞ ወጣቶች የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ማቅረብ ከጀመሩ ዓመታት አልፈዋል። ነገር ግን ምን ዓይነት መፍትሄ አልመጣም። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደሥልጣን ከመጡ ወዲህም ቢሆን ሌሎች ክልሎች የመልካም አስተዳደር ጥያቄ በማንሳት ምላሽ ሲያገኙ የኛ ግን ተረስቷል» በማለት አቶ ኦባንፍ ሃሳባቸውን ያጠናክራሉ። የጋምቤላ ከተማ ነዋሪዎች ይህን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ይዘው ሰልፍ የወጡት ሰኞ ዕለት ጠዋት እንደሆነ አቶ ኦባንግ ይናገራሉ። «ወጣቶቹ ጉዳያቸውን በሰላማዊ መንገድ ነበር ሲያቀርቡ የነበረው» የሚሉት አቶ ኦባንግ «አንድ ጎማ ከማቃጠል በቀር ዱላ አልያዙ፤ ድንጋይ አልወረወሩ» በማተለት የነበረውን ሁኔታ ያስረዳሉ። ከዛ በኋላ ግን የፀጥታ ኃይሎች ወደ ሰላማዊ ሰልፈኞቹ መተኮስ እንደጀመሩ ነው አቶ ኦባንግ የሚናገሩት። «ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ተኩሱ የሚለው ትዕዛዝ ከየት እንደመጣ ሊጣራ ይገባል» ይላሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ኦባንግ። • የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችና ወላጆቻቸው ስጋት በዚህ ጉዳይ የጋምቤላ ክልል አስተዳደር ያለው ነገር የለም፤ ቢቢሲ የክልሉን ባለስልጣናት ለማነጋጋር ያደረገነው ተደጋጋሚ ሙከራም ሊሳካ አልቻለም። አቶ ኦባንግ «የክልሉ ፕሬዝደንትን በጉዳዩ ዙሪያ ለማነጋገር ሞክሬ ስልክ ሊነሳልኝ ባለመቻሉ ምላሽ አላገኘሁም» ይላሉ። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አዲስ አበባ በመዝለቅ ስለሁኔታው ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር እንደተወያዩና ጠ/ሚኒስትሩ «ኃላፊነት እንወስዳለን» እንዳሏቸው ይናገራሉ። የፌዴራል መንግሥት ጣልቃ ገብቶ ሁኔታውን እንዲያረጋጋና ለመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጥ፤ እንዲሁም ጥፋት የፈፀሙ እንዲጠየቁ የተቻላቸውን እንደሚያደርጉ ነው አቶ ኦባንግ የሚያብራሩት። የኃይማኖት አባቶች እና የሃገር ሽማግሌዎች ተባብረው ሁኔታውን ለጊዜው እንዳረጋጉትና አሁን ከተማዋ አንፃራዊ መረጋገት እንደታየባት ማወቅ ችለናል። • ''አሁንም ቢሆን አርበኞች ግንቦት 7 አልፈረሰም'' አቶ ኤፍሬም ማዴቦ
news-48173949
https://www.bbc.com/amharic/news-48173949
የቦስኒያ ጦርነት፡ በጦርነት ወድሞ የነበረው አላድዛ መስጊድ ተከፈተ
በአውሮፓውያኑ ከ1992-1995 በቦስኒያ በተካሄደው ጦርነት የወደመው የአላድዝ መስጊድ ጥገና ተደርጎለት ከሦስት አስርት ዓመታት በኋላ እንደገና ተከፈተ።
አላድዛ መስጊድ ሙሉ በሙሉ ከወደመ ከዓመታት በኋላ እንደገና ተገንብቷል ቦስኒያ በሚገኘው በዚህ መስጊድ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በመገኘት የመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱን ታድመዋል። በፎካ ከተማ የሚገኘው አላድዛ መስጊድ በቦስኒያ እና ሰርቢያ መካከል የብሔር ግጭት ለመቀስቀስ በማሰብ ነበር ኢላማ የተደረገው። • በፆም ወቅት ሰውነታችን ውስጥ ምን ይካሄዳል? በ16 ኛው ክፍለዘመን በኦቶማን የኪነ ህንፃ ጠበብቶች የተሠራ እንደሆነ የሚነገርለት መስጊዱ በጦርነቱ ከወደመ በኋላ መልሶ ለመገንባት ዓመታትን የወሰደ ሲሆን ቱርክን ጨምሮ ሌሎች አገራት የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል። በጦርነቱ በፈንጂ እስኪወድምም ድረስ አገልግሎት ይሰጥ ነበር ተብሏል። በፍንዳታው የወደቀው ዋናው የመስጊዱ አካል በድንጋይ የተገነባ ሲሆን በአደጋው የፈራረሱትንና የተዳፈኑት በቁፋሮ እንዲወጡ ተደርገዋል። በጦርነቱ ወቅት በፎካ ከተማ ሰርቢያን ያልሆኑ ሰዎች ግድያ ይፈፀምባቸው ነበር። በዚህም ሳቢያ ይህ አካባቢ ሰርቢንጂ ተብሎ የተሰየመ ሲሆን በአውሮፓውያኑ 2004 የቦስኒያ ፍርድ ቤት የቀድሞ ስሟ እንዲመለስላት ውሳኔ አስተላልፈዋል። • የቻይና ሙስሊሞች ምድራዊ 'ጀሐነም' ሲጋለጥ ታዲያ በዛሬው ዕለት በቦስኒያ የሚገኙ ህዝበ ሙስሊሞችም የመስጊዱን በድጋሜ መከፈት በድምቀት እያከበሩ ይገኛሉ። " ዛሬ ሰዎች በዚህ አካባቢ ሰላም እንዳገኙና ደህንነታቸው እንደተመለሰላቸው ለማየት ችለናል " ሲሉ የቡድኑ መሪ ሁሴን ካቫዞቪቸ በዝግጅቱ ላይ ሲናገሩ ተደምጠዋል። የቱርክ የባህል ሚንስትር መህምት ኑሪ ኢርሶይ በበኩላቸው "ጥላቻና ዘረኝነት ቁሳቁስን ሊያወድም ይችላል፤ ነገርግን የነበረን ባህልና ኃይማኖት ማጥፋት ግን አይችልም " ብለዋል በዝግጅቱ ላይ። በቦስኒያ የአሜሪካ መልዕክተኛም "ይህ መስጊድ ለወደፊቱን ትውልድ ተስፋን የሚሰጥና የሚያስተሳስር ነው" ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ባለፈው ዓመት የቀድሞው የቦስኒያ ሰርብ ወታደር ፈንጂ በመቅበር ተሳትፈሃል ተብሎ ክስ እንደቀረበበት ይታወሳል። ፎካ ከተማ ከጦርነቱ በፊት ካላት 41 ሺህ ገደማ የህዝብ ብዛት ግማሽ ያህሉ ሙስሊም ሲሆኑ አሁን ግን ቁጥራቸው ከአንድ ሺህ ያነሰ እንደሆነ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።
news-54768126
https://www.bbc.com/amharic/news-54768126
ሕዳሴ ግድቡ ለሱዳን ምን ይዞ ይመጣል? ከሱዳናዊቷ አንደበት
ሱዳናዊቷ ጋዜጠኛ ዘይነብ ሞሐመድ ሳሊህ፤ ኢትዮጵያ እየገነባች ያለችው አጨቃጫቂው ግድብ ለሱዳን ሊያመጣቸው ስለሚችላቸው በረከቶች ለቢቢሲ በላከችው ደብዳቤ እንደሚከተለው ታስነብባለች።
የሱዳን አርሶ አደር በዚህ ዓመት ሱዳን ባልተጠበቀ ጎርፍ ተጥለቅልቃ ከ100 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። ከ875 ሺህ በላይ ሱዳናውያን ላይ ደግሞ ጉዳትን አስከትሏል። ይህ ብቻ አይደለም። የናይል ወንዝ ውሃ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ መኖሪያ መንደሮችን ሙሉ በሙሉ አውድሟል። የኤሌክትሪክ ምሶሶዎችን ደርምሶ ሚሊዮኖችን በጨለማ አስውጧል። አንዳንድ የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሉት፤ ኢትዮጵያ እየገነባች ያለችው ግደብ ሙሉ በሙሉ ሥራ ላይ ውሎ ቢሆን ኖሮ ጎርፉ ሱዳን ላይ ይህን ያክል ጉዳት ባልደረሰ ነበር። በአባይ ወንዝ 85 በመቶ ድርሻ ያላት ኢትዮጵያ፤ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድቡን መገንባት ከጀመረች ዓመታት ተቆጥረዋል። በዚህ ዓመት ደግሞ ግድቡ በውሃ መሞላት ተጀምሯል። ግድቡ በሙሉ አቅሙ ውሃ መያዝ ሲጀምር በአፍሪካ ትልቁ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ኃይል ይሆናል። ይሁን እንጂ የታችኛው የተፋሰስ አገር የሆነችው ግብጽ፤ ግድቡ የውሃ ድርሻዬን ይቀንስብኛል ስትል ትሰጋለች። ግድቡ በምን ያክል ጊዜ ይሞላ? የሚለው እስካሁን መግባባት ላይ አልተደረሰም። የዓለም አቀፍ የውሃ ሕግ እና ፖሊስ ባለሙያ የሆኑት ሱዳናዊው ሳልማን ሞሐመድ (ዶ/ር)፤ የግብጹ አስዋን ግድብ የጎርፍ ውሃን እንዴት አድርጎ በአግባቡ መጠቀም እንደሚቻል ያሳያል ይላሉ። “ዘንድሮ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ እኛ ሱዳናውያን ብዙ ሕይወት እና ንብረት አጥተናል። ግብጽን ስንመለከት ግን ምን ችግር አልገጠማቸውም። ምክንያቱም የጎርፉን ውሃ ወደ ትልቁ አስዋን ግድብ ስለሚያስገቡት ነው። እኛም እንደዚህ አይነት ግድብ ቢኖረን አንጎዳም ነበር። የኢትዮጵያ ግድብ ያድነን ነበር” ይላሉ። ይህ በእንዲህ አንዳለ ሱዳን በናይል ወንዝ ላይ 8 የኃይል ማመንጫ ገድቦች እንዳሏት መዘንጋት የለብንም። “የእኛ ግድቦች በጣም ትናንሽ ናቸው” ይላሉ ሳልማን ሞሐመድ (ዶ/ር)። “ግብጽ የጎርፍ ውሃውን በአስዋን ግድብ አጠራቅማ በበረሃ ላይ እያካሄደች ላለችው የግብርና ሥራ ውሃን ትጠቀማለች። የደህንነት ስጋቶች በቅርቡ በአፍሪካ ሕብረት አደራዳሪነት እየተካሄደው ባለው ድርድር፤ ግድቡ ምን ያህል ውሃ መያዝ አለበት? ምን ያህል መጠን ያለው ውሃ መለቀቅ አለበት? በሚሉት ጉዳዮች ላይ ሱዳን ወደ ግብጽ ያጋደለች ትመስላለች። ይህ አቋም በቀድሞ የሱዳን ፕሬዝደንት ኦማር አል-በሽር ይንጸባረቅ ነበር። አሁን በስልጣን ላይ ያሉት የሱዳን የጦር መኮንኖች ጠንካራ የግብጽ አጋር ናቸው። በፕሬዝደንት አል-በሽር የሥልጣን ዘመን ወቅት የሱዳን ተደራዳሪ የነበሩት አሕመድ ኤል-ሙፍቲ በግድቡ ላይ የደህንነት ስጋት እንዳላቸው ከዚህ ቀደም ገልጸው ነበር። ግድቡ በአንዳች ምክንያት ጉዳት ቢደርስበት የሱዳን መዲናን ጨምሮ በቀጠናው ባሉ አገራት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል ብለው ነበር። የሱዳን ባለስልጣናት ከግድቡ ግንባታ ጋር ተያይዞ ሊከሰት የሚችልን ግጭት ለመቅረፍ ከፍተኛ ጥረት እየደረጉ ነው። ባሳለፍነው ሳምንት ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የሰጡት አስተያየት ግን ሱዳን እያደረገች ካለችው ጥረት ጋር የሚጻረር ነው። ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ሱዳን እና እስራኤል የሰላም ስምምነት መድረሳቸውን በማስመልከት የሁለቱን አገራት ጠቅላይ ሚንስትሮች በስልክ እያነጋገሩ ባሉበት ወቅት፤ “ግብጽ ግድቡን ልታፈነዳው ትችላለች” ማለታቸው ይታወሳል። እስከ ባለፈው ሐምሌ ወር ድረስ የሱዳን የሽግግር መንግሥት የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሆነው ያገለገሉት አስማ አብደላ ለሶስቱ አገራት የሚበጀው ምክክር ብቻ ነው የሚል ጠንካራ አቋም ይዘው ነበር። ሱዳን ግድቡ ጎርፍን ከመቆጣጠር በላይ ሌሎች ጥቅሞችን ይዞ እንደሚመጣ ስለምትረዳ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲኖር ትሻለች። ‘የአፍሪካ የኩራት ምንጭ’ እንደ ዶ/ር ሞሐመድ ከሆነ፤ የኢትዮጵያ ግድብ ሱዳን ከራሷ ግድቦች ከፍ ያለ ኤሌክትሪክ እንድታመነጭ ይረዳታል። ይህም ብቻ ሳይሆን ሱዳን ከኢትዮጵያ ርካሽ የሆነ ኤሌክትሪክ እንድትገዛ ይረዳታል። ዶ/ር ሞሐመድ ግድቡ ለሱዳን ይዞ የሚመጣው ጥቅም ይህ ብቻ አይደለም ይላሉ። የሱዳን ገበሬዎች እርሻ የሚያከናውኑት ጥቅምት እና ሕዳር ወራት ላይ መሆኑን ያስታውሳሉ። የአባይ ወንዝ ውሃ ፍሰት ላይ ቁጥጥር ማድረግ የሚቻል ከሆነ ግን ገበሬዎች በዓመት ከአንድ ግዜ በላይ ዘር ሊዘሩ እንደሚችሉ ያስረዳሉ። በድርቅ ዓመታትም ግድቡ ተጨማሪ ውሃን በመልቀቅ የሚኖረውን የዝናብ ውሃ እጥረት ሊቀርፍ ይችላል። በሱዳን መዲና ሰዎች ስለ ግድቡ ያላቸው አቋም ምን እንደሆነ ሲጠየቁ ድጋፋቸው ለኢትዮጵያ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። “እንደግፋቸዋለን ምክንያቱም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ርህራሄ አለን” ሲል የ44 ዓመቱ ሳላ ሃሰን ይናገራል። ሳላ የሚኖርበት ኦማዱሩማን ከተማ በቅርቡ በጎርፍ ከተጠቅለቀለቁት ከተሞች አንዷ ነች። ነዋሪነቱ በካርቱም የሆነው የ37 ዓመቱ ሞሐመድ አሊ ግድቡን እንደ የአፍሪካ ኩራት እና ለበርካቶች የሥራ እድልን ይዞ እንደሚመጣ ፕሮጀክት ነው የሚመለከተው። “በሱዳን የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን አሉ። ግድቡ ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያውያኑ ከሱዳናውያን ጋር ወደ ኢትዮጵያ ሄደው ሥራ የሚሰሩ ይመስለኛል” ይላል። “ፕሮጅከቱ በርካታ አፍሪካውያንን እንደመጥቀሙ ግድቡን መቶ በመቶ ነው የምደግፈው። በአፍሪካ ቀንድ ያሉ አገራት በርካታ ችግሮችን አሳልፈዋል። እንዲህ አይነት የልማት ፕሮጀክት ያስፈልጋቸዋል” ብሏል ሌላው የካርቱም ነዋሪ።
news-53394391
https://www.bbc.com/amharic/news-53394391
በብራዚል የሳኦ ፖሎ ፖሊስ አንዲት ሴት አንገት ላይ ቆሞ በመታየቱ ቁጣ ተቀሰቀሰ
በብራዚል ሳኦፖሎ ፖሊስ የአንዲት ጥቁር ሴት አንገት ላይ ቆሞ የሚያሳይ ምሰል በአገሪቱ ቴሌቪዥን ከተላለፈ በኋላ ሁለት ፖሊሶች በወንጀል ሊጠየቁ መሆኑ ተገልጿል።
ግለሰቧ እድሜዋ በሰላሳዎቹ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን አንዲት አነስተኛ ግሮሰሪ እንዳላትና ከመጠጥ ቤቷ ውስጥ ተጎትታ ወጥታ እጆቿ በካቴና እንደታሰሩ በመንገድ ላይ መጎተቷ ተገልጿል። ይህ ክስተት በግንቦት ወር መፈፀሙ የተገለፀ ሲሆን የዓይን ምስክር የሆነ ሰው በስልኩ መቅረፁ ታውቋል። የግዛቲቱ አስተዳዳሪ ዶሪያ እንዲህ አይነት የመብት ጥሰትን እንደማይታገሱ ገልጸው፣ ግለሰቧን በመያዝና በማንገላታት የተሳተፉ ሁለቱም ፖሊሶች ከስራቸው መሰናበታቸውን አስታውቀዋል። የፖሊሶቹ ማንነት እስካሁን ይፋ አልተደረገም። አገረ ገዢው አክለውም በሳኦ ፖሎ 2ሺህ ፖሊሶች አካላቸው ላይ ካሜራ ተገጥሞላቸው ለስራ እንደሚሰማሩ ገልጸዋል። ግለሰቧ በፖሊስ እንግልትና ስቃይ ሲደርስባት የሚያሳየው ምሰል የሳምንቱ መጨረሻ ላይ በፋንታስቲኮ ቴሌቪዥን ጣብያ ተላልፏል። ምስሉ በብራዚል ውስጥ ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን ክስተቱን በአሜሪካ በግንቦት ወር መጨረሻ ላይ ጆርጅ ፍሎይድ ላይ ከደረሰው ጋር በማመሳሰል ንዴታቸውን ገልጸዋል። ነጭ ፖሊስ ጆርጅ ፍሎይድ አንገት ላይ በመቆም መተንፈስ ከልክሎት ለሞት መዳረጉ ይታወሳል። የፍሎይድ ሞት በአሜሪካ እና አውሮፓ ሰፊ ህዝባዊ ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን በአንዳንድ ስፍራዎች ሰልፈኞች ከፖሊሶች ጋር ሲጋጩ ተስተውሏል።
news-44009903
https://www.bbc.com/amharic/news-44009903
የእንግሊዝኛ ፈተና ጀርመናዊ ተማሪዎችን አስቆጣ
ከ30ሺ በላይ የጀርመን ተማሪዎች ከሰሞኑ የወሰዱትን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ፈተና በመቃወም የበይነ መረብ የተቃውሞ ዘመቻ ጀምረዋል።
ቤደን ዌርትምበርግ በተሰኘችው የጀርመን ግዛት የትምህርት ሚኒስቴር በተዘጋጀው የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ውስጥ የሚገኙ ጥያቄዎች 'ፍትሃዊ ያልሆኑ' እና ያረጁ ያፈጁ ቃላት የታጨቁባቸው ናቸው ሲሉ ተፈታኞች አማረዋል። ለግዛቷ ባለስልጣናት ባስገቡት አቤቱታ ተማሪዎች ፈተናው ፍትሃዊ አለመሆኑ እንዲሁም አስቸጋሪነቱ ጠቅሰው በእርማት ወቅት ግምት ውስጥ እንዲገባ አሳስበዋል። የዘንድሮ ፈተና ከቀደምቶቹ ጋር ሊወዳደርም 'አይገባም 'ሲሉ ተሟግተዋል። የግዛቷ ባለስልጣናት በበኩላቸው የተካተቱት ጥያቄዎች 'አግባብ ያላቸው ናቸው' በማለት ፈተና አውጪውን አካል ደግፈዋል። በዘንድሮው ፈተና ተፈታኞች የእንግሊዝን ከአውሮፓ ህብረት መውጣት መሰረት ያደረጉ የካርቱን ስዕሎችን እንዲያነፃፅሩ እንዲሁም ሄነሪ ሮስ በ1934 እኤአ ከፃፉት መፅሃፍ ላይ የተመሰረቱ ጥያቄዎችን እንዲመልሱ ተጠይቀዋል። ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ በሌላኛው የጀርመን ግዛት ሰሜን ራይን ዌስትፋሊያ ውስጥ የተፈተኑ ተማሪዎች በእንግሊዝኛ ፈተና ላይ ቅሬታ አቅርበው በድጋሚ እንዲከለስ ተደርጓል።
news-56506498
https://www.bbc.com/amharic/news-56506498
የእስራኤል ምርጫ፡ ኔታንያሁ መንግሥት መመሥረት የሚያስችላቸውን ድምጽ ሳያገኙ ቀሩ
በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ለአራተኛ ጊዜ በሚካሄደው የእስራኤል ምርጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ አዲስ መንግሥት ለመመሥረት የሚያስፈልጋቸውን ድምጽ የማግኘት ዕድላቸው ዝቅተኛ እንደሚሆን ተገለጸ።
የኔታንያሁ ሊኩድ ፓርቲ እና አጋሮቻቸው 120 መቀመጫ ካለው የእስራኤል ፓርላማ 52 ወይም 53 መቀመጫዎችን ብቻ እንደሚያገኙ ተገምቷል። ጠቅላይ ሚኒስትሩን በኃላፊነት መቆየታቸውን የሚቃወሙ ፓርቲዎች 60 ወንበሮችን እንደሚያሸንፉ ተገምቷል። በዚህም የያሚና ፓርቲን ድጋፍ ቢያገኙም ኔታንያሁ አብላጫ ድምፅ አይኖራቸውም ማለት ነው። በቀድሞው የኔታንያሁ ደጋፊ ናፍታሊ ቤኔት የሚመራው ያሚና ፓርቲ ሰባት ወንበሮችን እንደሚያገኝ ቅድመ ግምት ቢሰጠውም የትኛውን ወገን እንደሚደግፍ እስካሁን በግልፅ አልታወቀም። የቅድመ ምርጫ ውጤቶች ከተለቀቁ በኋላ ቤኔት በሰጡት መግለጫ “ለእስራኤል መንግሥት የሚጠቅመውን ብቻ አደርጋለሁ” ብለዋል። ከቀጣይ እርምጃዎች በፊት ያሚና የመጨረሻ ውጤቱን እንደሚጠብቁ ለኔታንያሁ መናገራቸውን ገልጸዋል። ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዙ ገደቦች ምክንያት ሁሉም ድምጾች ከረቡዕ ከሰዓት በፊት ይቆጠራሉ ተብሎ እንደማይጠበቅ የእስራኤል ማዕከላዊ የምርጫ ኮሚቴ አስታውቋል። ኔታንያሁ ማክሰኞ ዕለት በትዊተር ገፃቸው ደጋፊዎቻቸውን አመስግነዋል። “በአመራሬ ቀኝ ዘመም እና ሊኩድ ከፍተኛ ድል አስመዝግበዋል። ሊኩድ እስካሁንም ድረስ ትልቁ ፓርቲ ነው” ብለዋል። ዋነኛው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ያይር ላፒድ ፓርቲ የሽ አቲድ ከኔሴት ተብሎ በሚጠራው ከእስራኤል ፓርላማ መቀመጫዎች ውስጥ ከ 16 እስከ 18 የሚሆኑትን ያሸንፋል ተብሎ ተገምቷል። በፓርቲያቸው “እጅግ ትልቅ” ስኬት “ኩራት ይሰማኛል” ብለዋል። “ከአንዳንድ የህብረቱ አመራሮች ጋር ለለውጥ የሚረዳ ውይይት ዛሬ አመሻሽ ጀምሬያለሁ። በቀጣዮቹ ቀናትም እቀጥላለሁ። በእስራኤል ጤናማ መንግስት ለማቋቋም የተቻለውን ሁሉ አደርጋለሁ” ሲሉ አስታውቀዋል። በኔታንያሁ አመራር ላይ እንደ ህዝበ ውሳኔ በታየው ምርጫ ላይ ለመምረጥ ብቁ ከሆኑት መካከከል ከ 67.2% በላይ የሚሆኑት ድምጽ ሰጥተዋል፡፡ የ71 ዓመቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከጎርጎሮሳዊያኑ 2009 ጀምሮ በስልጣን ላይ ይገኛሉ። በ1990ዎቹ መገባደጃ ላይም ለሦስት ዓመታት በጠቅላይ ሚንስትርነት አገልግለዋል። የምርጫ ዘመቻው ያተኮረው እስራኤል በዓለም ቀዳሚ ባደረጋት የኮቪድ -19 የክትባት መርሃግብር እና ከአንዳንድ የአረብ አገራት ጋር በፈጠሩት ዲፕሎማሲያዊ ስኬት ላይ ነበር። ተቃዋሚዎቻቸው ግን በሙስና ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው በሥልጣን መቆየት እንደሌለባቸው ተከራክረዋል። ኔታንያሁ ግን ጥፋት አልፈጸምኩም በሚል ይከራከራሉ። ባለፉት ሶስት ምርጫዎች ኔታንያሁም ሆኑ ተቀናቃኞቻቸው የተረጋጋ ጥምረት መመስረት አልቻሉም።
news-55211959
https://www.bbc.com/amharic/news-55211959
ሕንድ ውስጥ በርካቶች ምንነቱ ባልታወቀ በሽታ ታመው ሆስፒታል ገቡ
በሕንድ ውስጥ በሚገኝ አንድ ግዛት ነዋሪ የሆኑ ሰዎች ምንነቱ ባልታወቀ በሽታ ታመው ሆስፒታል መግባተቸው ተነገረ።
የአገሪቱ ባለስልጣናት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ 140 ሰዎችን ሆስፒታል እንዲገቡ ያደረገው በሽታን ምንነት ለማወቅ ምርምራ እያካሄዱ ነው። የህክምና ተመራማሪዎችም የዚህን በሽታ ምንነት ለመለየት እና የሕመሙን መንስኤ ለማወቅ ጥረት መጀመራቸው አስታውቀዋል። አንድራ ፕራዴሽ ከሚባለው ግዛት የመጡት ታማሚዎች በርካታ የተለያዩ የሕመም ምልክቶች ሲያሳዩ የነበረ ሲሆን፤ ከምልክቶቹ ውስጥም ማቅለሽለሽ እና እራስን ስቶ ተዝለፍልፎ መውደቅ ደግሞ አብዛኛዎቹ ላይ የተስተዋለ እንደሆነ ዶክተሮች ገልጸዋል። ኢሉሩ የተባለው የመንግሥት ሆስፒታል ደግሞ ምናልባት ተጨማሪ ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ታማሚዎች ከመጡ በሚል በርካታ አልጋዎች ነጻ ሆነው እንዲጠባበቁም ተደርጓል ተብሏል። ሕንድ የኮሮናቫይረስ ተጽእኖን ለመቀነስ እና ስርጭቱን ለመቆጣጠር ደፋ ቀና በምትልበት በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ምንነቱ ያልታወቀ ሕመም መከሰቱ በርካቶችን አሳስቧል። የአካባቢው መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ደግሞ ሁሉም ወደ ሆስፒታል የተወሰዱ ታማሚዎች የኮሮናቫይረስ ምርምራ የተደረገላቸው ሲሆን ማናቸውም ግን በቫይረሱ አልተያዙም። በኢሉሩ የመንግሥት ሆስፒታል የሚሰራ አንድ የጤና ባለሙያ ለኢንዲያን ኤክስፕረስ ሲናገር '''አይናችን አካባቢ ማቃጠል ይሰማናል' ብለው ወደ ሆስፒታላችን ከመጡት መካከል በተለይ ደግሞ ሕጻናቱ ወዲያው ማስመለስ ጀመሩ። አንዳንዶቹ እራሳቸውን የሳቱ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ ቅዝቃዜ ተሰምቷቸው ይንቀጠቀጡ ነበር'' ብሏል። ወደ ሆስፒታል ከተወሰዱት ሰዎች መካከል አብዛኛዎቹ በአሁኑ ሰዓት በጥሩ ጤንነት ላይ የሚገኙ ሲሆን አንዳንዶቹም ተሽሏቸው ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ መደረጉ ተገልጿል። የአንድራ ፕራዳሽ የጤና ሚኒስትር አላ ካሊ ካሊ ክሪሽና እንዳሉት ደግሞ ከሁሉም ታማሚዎች ላይ የደም ናሙና የተወሰደ ቢሆንም ምንም አይነት የቫይረስ ኢንፌክሽን ምልክት ግን አልታየባቸውም። ''ባለሙያዎቻችን የሰዎቹን መኖሪያ አካባቢ ከጎበኙ በኋላ በምርመራችን የአየር እና የውሃ ብክለት አለመሆኑን ደርሰንበታል። ምስጢራዊ የሆነ ሕመም ይመስላል፤ የትኛውም የላብራቶሪ ምርመራ ምክንያቱን ሊያውቀው አልቻለም'' ብለዋል የጤና ሚንስትሩ።
56547521
https://www.bbc.com/amharic/56547521
ንግድ፡ በኢትዮጵያ አንድ ግለሰብ ብቻውን ኩባንያ እንዲያቋቁም ተፈቀደ፤ አዲሱ የንግድ ሕግ ምን ይዟል?
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 16/2013 ዓ.ም ላለፉት 62 ዓመታት ሲያገለግል የቆየውን የአገሪቱን የንግድ ሕግ በመሻር በአዲስ እንዲተካ በሙሉ ድመጽ ወስኗል።
ይህን አዲሱ የንግድ ሕግ ከዚህ በፊት ከነበረው አንጻር በርካታ ለውጦች የተደረጉበት እንደሆነ ይነገራል። ለማዘጋጀትም ረጅም ጊዜ የወሰደና በርካታ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ነበር። ከቢቢሲ ጋር ቆይታ የነበራቸውና አዋጁን በማርቀቅ ሂደት የተሳተፉት ከፍተኛ የሕግ አማካሪ ታደሰ ሌንጮ (ዶ/ር) የሕጉ መውጣት የኢትዮጵያን የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴን በአወንታዊ መንገድ ለመቀየር ከፍተኛ አስተዋጾ እንዳለው ይናገራሉ። ባለሙያው የሕጉን መውጣት አስፈላጊነት ሲያስረዱ የሚጠቅሱት ላለፉት 62 ዓመታት ሲያገለግል የቆየው ሕጉ ከወቅታዊው የዓለም ሁኔታ ጋር አለመሄዱን ነው። "የንግድ ሕጉ በወጣበት የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ የኢንቨስትመንት፣ አገራዊና ዓለም አቀፋዊ አውድ የ1952ቷ እና የ2013ቷ ኢትዮጵያ በጣም የተለያዩ ናቸው" የሚሉት ታደሰ (ዶ/ር) ይህ መሆኑ ደግሞ ኢትዮጵያ ለንግድ ከሚመቹ አገራት ዝርዝር ውስጥ በዝቅተኛ ደርጃ ላይ እንድትቀመጥ እንድርጓታል ሲሉ ገልጸዋል። የዚህ ውጤት ደግሞ አገሪቱን በተለያየ መልክ ዋጋ አስከፍሏታል። "ኢንቨስተሮች ይሄ አገር እንዴት ቀላል ነው? እንዴት ለንግድ አመቺ ነው? የሚሉትን ነገር ሰለሚያዩ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣው ኢንቨስመንት ይቀንሳል ማለት ነው። ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ያለውን ካፒታል የመሳብ አቅሟንም በጣም አሳንሶታል" በማለት የሚያስርዱት ባለሙያው፤ ይህም የሥራ ፈጠራንና የውጭ ንግድን እንዲሁም የምጣኔ ሀብት ዕድገቷን የሚገታ ነው ሲሉ አብራርተዋል። በ1952 ዓ.ም የወጣውን ይህን ሕግ ለመቀየር ከ30 ዓመት በፊት ጀምሮ ጥረት ሲደረግ እንደቆየ ተገልጻል። 825 አንቀጾች ያሉት አዲሱ አዋጅ በርካታ ማሻሻያዎችን የያዘ ነው። ከእነዚህ ጥቂቶቹን እንመልከት። አንድ ግለሰብ ለብቻው ኩባንያ መክፈት እንዲችል ተፈቅዷል በቀድሞው የንግድ ሕግ መሠረት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ለማቋቋም ቢያንስ ሁለት ሰዎች ያስፈልጋሉ። "ለምሳሌ የውጭ ኩባንያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት ሲያደርጉ አንድ ሌላ ሰው ማምጣት ይጠበቅባቸዋል ማለት ነው። ይህ ብዙ ወጪ ነው የሚያስወጣቸው። ከፍተኛ ጥርጣሬም ይፈጥራል" ይላሉ የሕግ ባለሙያው። ከዚህም በላይ አብሮ ኩባንያውን የመሰረተውን ሰው ባለመስማማት ወይም በሞት ምክንያት ለመቀየር ሲፈለግ ያለውን ሒደት "አበሳ ነው" ሲሉ ከባድነቱን ይገልጹታል። ይህም የኩባንያውን ቀጣይነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባና አላስፈላጊ ለሆኑ ወጪዎች የሚዳርግ ነው ሲሉም አክለዋል። እንደ ታደሰ (ዶ/ር) ገለጻ፣ በአገር ውስጥ ያሉ በርካታ ኃላፊነታቸው የተወሰኑ የግል ኩባንያዎች በተግባር የአንድ ሰው ሆነው ሳለ፤ ለሕጉ ሲባል ግን ተጨማሪ ሰው በባለቤትነት ይመዘግባሉ። አዲሱ የንግድ ሕግ ይህን ግዴታ አንስቶ አንድ ግለሰብ ብቻውን ኩባንያን እንዲከፍት ፈቅዷል። ይህም ሰዎች በቀላሉ ወደ ሥራ እንዲገቡና ባለቤትነትን በተመለከተ ስጋት እንዳይኖራቸው ያግዛቸዋል ብለዋል። የንግድ ትርጓሜን መቀየር በተሻረው ሕግ የተዘረዘሩት የንግድ አይነቶች 21 ብቻ ናቸው። ከነዚህ ውጪ ያሉት ንግድ አይደሉም ተብለው እንደሚገመቱ ባለሙያው ያስረዳሉ። አሁን ግን ሕጉ የንግድ አይነቶችን ወደ 38 አሳደጓቸዋል። "ያም ብቻ ሳይሆን በአዲሱ ሕግ የንግድ ትርጉም ክፍት ነው። በግልፅ ካልተከለከለ በስተቀር ማንኛውም ሰው ከፀሐይ በታች ባለን ሥራ ንግድ ነው፤ ያተርፋል ብሎ እንደሙያ የያዘውን ሥራ አስመዝገቦ መቀጠል ይችላል" ሲሉ አስረድተዋል። ይህ መሆኑ ደግሞ አዳዲስ የንግድ አይነቶችንና የፈጠራ ሐሳቦችን እንደሚያበርታታ አክለዋል። ኃላፊነታቸው የተወሰኑ የሙያ ሽርክና ማኅበራት መፈቀድ ከቀደመው ሕግ በተቃራኒው አዲስ የጸደቀው አዋጅ ግለሰቦች በሙያቸው ተደራጅተው እንዲሠሩ በግልጽ ድንጋጌ አስቀምጧል። አዋጁን በማርቀቅ ሒደት የተሳተፉት ከፍተኛ የሕግ አማካሪው፤ እያንዳንዱ ሙያ የሚጠይቀውን ሥነ ምግባር ይዘው ደንበኞቻቸውን የሚያስተናግዱ የሽርክና የሙያ ማኅበራት እንዲስፋፉ ያስችላል ብለዋል። በሌላው ዓለም በስፋት የሚሠራበት ቢሆንም ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው ሕግ በግልጽ ባለመፍቀዱ ዘርፉን አዳክሞታል። በሌላ በኩል የቀድሞው ሕግ የአክስዮን ማኅበራት የዳይሬክተሮች የቦርድ አባላት ሁሉም የአክሲዮን ባለድርሻ እንዲሆኑ ግዴታ የጣለ ነበር። ነገር ግን በአዲሱ ሕግ ባለድርሻ መሆን ሳይጠበቅባቸው፤ ባለ ድርሻ ያልሆኑ ሰዎች በሙያቸው እስከ አንድ ሦስተኛ ድረስ የሚሆነውን የዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት ቦታን እንዲይዙ ይፈቃዳል። በተጨማሪም ከተሻረው ሕግ በተቃራኒ ምክንያታዊ በሆነ መንገድ የሚከስሩ የንግድ ሰዎች ነጻ የሚሆኑበትን መንገድ እንዳመቻቸም ገልጸዋል። የሕግ ባለሙያው ታደሰ (ዶ/ር) እነዚህን ጨምሮ ለንግድ እንቅስቃሴው የማይመቹ ሕጎችን ያሻሻለው የአዲሱ አዋጅ መውጣት "በአገር ውስጥ ያለውን እንቅሰቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል" ብለዋል። በአዲሱ አዋጅ ያልተካተቱት የባንክ፣ የኢንሹራንስና፣ የማጓጓዣ ዘርፎችን የሚመለከቱ ጉዳዮች በቀድሞው አሠራር መሠረት የሚቀጥሉ ሲሆን፤ በቀጣይ ራሳቸውን ችለው እንዲወጡ እየተሠራ መሆኑ ተጠቁሟል። አዲሱ የንግድ ሕግ በነጋሪት ጋዜጣ ወጥቶ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ሥራ ገብቶ የቀድሞውን ሕግ ይተካል ተብሎ ይጠበቃል።
news-43749541
https://www.bbc.com/amharic/news-43749541
የቤት ሰራተኞችን ለመላክ ከኩዌት ጋር ድርድር እንደሚያስፈልግ ኢትዮጵያ አስታወቀች
በቤት ሰራተኝነት ወደ ተለያዩ አረብ አገራት የሚሄዱ ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚፈፀመውን ከባድ አካላዊ ጥቃትና ሌሎች ችግሮችንም ተከትሎ መንግሥት በቤት ሰራተኝነት ወደእነዚህ ሃገራት የሚደረግ ጉዞን አግዶ ነበር።
አዲስ የውጭ ሃገር የሥራ ስምሪት አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፀደቀ በኋላ ከጥቂት ሳምንታት በፊት መንግስት እገዳውን ማንሳቱ ይታወቃል። የ29 ዓመቷ ፊሊፒናዊት በአሰሪዎቿ መገደሏን ተከትሎ ባለፈው ሳምንት ፊሊፒንስ ዜጎቿ ወደ ኩዌት ሄደው በቤት ሠራተኝነት እንዳይሰማሩ ህግ አውጥታለች። ይህ ከተሰማ ሰዓታት በኋላ ነው የኩዌት ባለሥልጣናት ሃገሪቱ የገጠማትን የቤት ሠራተኛ እጥረት ለመቅረፍ ኢትዮጵያውያንን ለመቅጠር ዝግጁ መሆናቸውን ያስታወቁት። ጉዳዩ የሚመለከተው የማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የውጭ ሃገር ስራ ስምሪት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ብርሃኑ አበራ ግን የኩዌትን ፍላጎት በተመለከተ ጉዳዩ ገና ነው ይላሉ። በቤት ሰራተኝነትና በተለያዩ የጉልበት ስራዎች የተሰማሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያን የሚገኙባትና ቀደም ሲል በቅርቡም በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንን ከግዛቷ ጋር ካስወጣችው ሳውዲ አረብያ ጋር ስምምነት ተደርጓል። በአዲሱ አዋጅ መሠረት የቤት ሰራተኞችን የመላክ ስምምነቱ ያለቀለት ቢሆንም በኢትዮጵያ በኩል የሚቀር ነገር እንዳለ አቶ ብርሃኑ ይናገራሉ። በሃገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ነገሮች መዘግየታቸውንና ወደ ተግባር ለመግባት ስምምነቱ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መፅደቅ እንደሚጠበቅበትም ያስረዳሉ። "ሰነዱ አሁን ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ደርሷል፤ አዋጁ ወደ ተግባር የሚገባው ስምምነቱ ሲፀድቅ ነው።" ይላሉ። ቀደም ሲል ኢትዮጵያ ከኩዌት ጋር የተፈራረመችው ሰነድ ቢኖርም አሁን ስምምነቱ መሻሻል እንደሚኖርበት አቶ ብርሃኑ ይናገራሉ። በዋነኛነትም ከኩዌት ጋር "የሁለትዮሽ ድርድር ያስፈልጋል" ይላሉ።። በአሁኑ ወቅት በምዕራባዊ እስያና በምስራቅ አረብ መካከል በምትገኘው ኩዌት 15 ሺህ ኢትዮጵያዊያን እንደሚገኙ ይገመታል።
news-47974564
https://www.bbc.com/amharic/news-47974564
ኢትዮጵያዊው የኡጋንዳ አየር ኃይል ፊታውራሪ
ለዓመታት የኢትዮጵያ አየር ኃይልን በጦር አውሮፕላን አብራሪነት አገልግለዋል። ሌተናንት ኮሎኔል ጌታሁን ካሳ በፈፀሟቸው ጀብዶች እና በወታደራዊ ስነምግባራቸው ከኢትዮጵያ መንግሥት ትልቅ የጀግንነት ሽልማት አግኝተዋል።
ከእናት አገራቸው ብቻም ሳይሆን ሌተናንት ኮሎኔል ጌታሁን ከጎረቤት አገር ኡጋንዳ መንግሥትም ትልቅ ወታደራዊ ሽልማት የተበረከተላቸው የሁለት አገር ጀግና ናቸው። • የካቢኔው ሽግሽግ ምን ያመላክታል? የአየር ኃይሏ ፊታውራሪ በመሆን ለዓመታት ያገለገሏትና ከጥቂት ቀናት በፊት ህይወታቸው ያለፈው፤ ሌ/ኮ ጌታሁን ሽኝትን በከፍተኛ ወታደራዊ ስነ ስርዓት በማድረግም ነው ኡጋንዳ ለባለውለታዋ ምስጋናዋን የገለፀችው። ሌ/ኮ ጌታሁን ለዓመታት የሙሴቬኒ አውሮፕላን አብራሪም ሆነው አገልግለዋል። "የሙሴቪኒ ታናሽ ወንድም ወደ ኡጋንዳ ወሰዷቸው..." በደርግ ስርዓት ውድቀት ዋዜማ በርካታ የኢትዮጵያ ወታደሮች ድንበር አቋርጠው እንደ ኬንያ ወዳሉ ጎረቤት አገራት ተሰደዋል። ሄሊኮፕተር ይዘው እንደ የመን እና ሳዑዲ አረብያ ወዳሉ አገራት የሄዱ የአየር ኃይል አብራሪዎችም ነበሩ። ሌ/ኮ ጌታሁን ግን እስከ መጨረሻዎቹ ማለትም ኢህአዴግ አዲስ አበባን እስከተቆጣጠረበት ዕለት ድረስ በአየር ኃይል ቅጥር ቆይተው ነው በመጨረሻ ራሳቸውን ቀይረው በስውር በሞያሌ በኩል ወደ ኬንያ ያቀኑት። • ዩጋንዳ ሰራዊቷ የቻይና የንግድ ቦታዎችን እንዲጠብቅ አዘዘች ለተወሰነ ጊዜ በኬንያ የስደተኞች ካምፕ ከቆዩ በኋላ በካምፑ መቆየታቸው ለደህንነታቸው እንደሚያሰጋ ስለታመነ ወደ መዲናዋ ናይሮቢ እንዲዘዋወሩ ተደረገ። በወቅቱ ስልጣኑን በማደራጀት ላይ የነበረው የኢህአዴግ መንግሥት እሳቸውና ሌሎችም የአየር ሃይል ሰዎች ተላልፈው እንዲሰጡት እየጠየቀ እንደነበርና በመጨረሻም በልዩ ድርድር እሳቸውና ጓደኞቻቸው አስር ሆነው ወደ ኡጋንዳ እንዲሄዱ ተደረገ። እነ ሌ/ኮ ጌታሁንን ናይሮቢ ድረስ መጥቶ ወደ ኡጋንዳ የወሰዷቸውም የኡጋንዳው ፕሬዘዳንት ዩዎሪ ሙሴቬኒ ታናሽ ወንድም ጀነራል ሳሊም ሳለህ እንደነበሩ ወንድማቸው አቶ ተሾመ ካሳ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሌ/ኮ ጌታሁን መጀመሪያ ሶሮቲ በተሰኘ አካባቢ ቆይተው ኋላ ቋሚ ኑሯቸውን በኢንቴቤ አደረጉ። ከዚያም የኡጋንዳ አየር ኃይልን በማደራጀት፣ በርካታ ፓይለቶችን በማሰልጠንና የስልጠና መመሪያዎችን በመቅረፅ ለኡጋንዳ አየር ኃይል ትልቅ አስተዋፅኦ አድርገዋል። በጆሴፍ ኮኔ የሚመራው የሎርድ ሬዚስታንስ እንቅስቃሴ ኤል አር ኤ ሰሜናዊ ኡጋንዳ ላይ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ለአገሪቱ ራስ ምታት በሆነበት ወቅት ትልልቅ ወታደራዊ ተልእኮዎችን እንደፈፀሙ የሕይወት ታሪካቸው ያሳያል። ዜግነት እንደ ሽልማት የኤል አር ኤ መፈንጫ የነበረውን ሰሜናዊ ኡጋንዳ ወደ ሰላም ለመመለስ ላበረከቱት ተሳትፎ ኡጋንዳዊ ዜግነት ሲሰጣቸው የአገሪቱን ከፍተኛ የጀብድ ኒሻን ከፕሬዝዳንት ዩዎሪ ሙሴቬኒ እጅ መቀበልም ችለዋል። • የኢትዮጵያ አየር ኃይል አልሸባብ ላይ ጥቃት ፈጸመ እንደ አውሮፓውያኑ ከ1996 እስከ 2005 የኡጋንዳ መከላከያ ሰራዊት ባካሄዳቸው እና አየር ኃይሉ በተሳተፈባቸው ተልእኮዎች ሁሉ ሌ/ኮ ጌታሁን እንደነበሩም በሕይወት ታሪካቸው ላይ ሰፍሯል። ከስልጠና፣ ከበረራ፣ የአደረጃጀት መመሪያዎችን ማዘጋጀትና የሄሊኮፕተር ግዥዎችን ማማከርን ጨምሮ እሳቸው ያልተሳተፉበት የኡጋንዳ አየር ኃይል እርምጃ አልነበረም ማለት ይቻላል። ሌ/ኮ ጌታሁን ከልብ ጋር በተያያዘ ችግር ለአንድ ሳምንት ያህል ታምመው መጋቢት 30 ቀን 2011 ዓ.ም በህክምና ሲረዱ በነበሩበት የካምፓላው ናካሴሮ ሆስፒታል ሕይወታቸው አልፏል። ህልፈታቸው እንደተሰማ ቤተሰባቸው ወደ ኡጋንዳ ያቀናው፤ አስክሬናቸውን ወስዶ በኢትዮጵያ ለመቅበር የነበረ ቢሆንም ኡጋንዳ ባለውለታዋ ሌ/ኮ ጌታሁንን ለመሸኘት እያደረገች ያለውን የሽኝት ዝግጅት ሲመለከቱ አስከሬናቸው ማረፍ ያለበት እዚያው በኡጋንዳ ምድር እንደሆነ ማመናቸውን የታላቅ ወንድማቸው ልጅ ዮናታን መንክር ካሳ ገልፆልናል። • ኢትዮጵያ ሳተላይት ማምጠቅ ለምን አስፈለጋት? አጎቱን 'የሁለት አገር ጀግና' ብሎ የሚገልፀው ዮናታን አጎቱ የኢትዮጵያ አየር ኃይል አብራሪ በነበሩበት ወቅት ከባድ የሚባሉ የጦር ጀብዱዎችን መፈፀማቸውን፤ በአንድ አጋጣሚም ጓደኛቸው ያበር የነበረው ሄሊኮፕተር በጠላት ቀጠና ውስጥ ተመትቶ በወደቀ ወቅት ምንም እንኳ እሳቸው እንዲመለሱ ትዕዛዝ ቢተላለፍላቸውም በተኩስ ልውውጥ ውስጥ ሄሊኮፕተር አሳርፈው የቆሰለ ጓደኛቸውን ይዘው እንደተነሱ ብዙ ጓደኞቻቸው እንደሚመሰክሩም ይናገራል። እሱ እንደገለፀልን ራሳቸው ያስተማሯቸውና የአሁኑ የኡጋንዳ አየር ኃይል አዛዥ ተገኝተው የሕይወት ታሪካቸውን ባነበቡበት በከፍተኛ ወታደራዊ ሽኝት በኡጋንዳ ወታደራዊ መቃብር ስፍራ ስርዓተ ቀብራቸው ሰኞ ሚያዝያ ሰባት ቀን ተፈፅሟል። ፍታታቸው የተፈፀመውም ከምስረታው ጀምሮ ትልቅ ተሳትፎ ባደረጉበት በካምፓላው የኢትዮጵያ መካነ ሰላም መድሃኒዓለም ቤተ ክርስትያን ነው። ፕሬዘዳንት ሙሴቪኒ የሌ/ኮ ጌታሁንን ሕልፈተ ዜና እንደሰሙ በርግጥም ህልፈታቸው ተፈጥሯዊ መሆኑ እንዲረጋገጥ ማድረጋቸውንና የቀብር ስነስርዓቱን በሚመለከትም ነገሮችን እየጠየቁ መከታተላቸውንም ወንድማቸው አቶ ተሾመ ነግረውናል። • ሕይወትን ከዜሮ መጀመር ሌ/ኮ ጌታሁን ከጥቂት አመታት በፊት በረራ ቢያቆሙም ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ የኡጋንዳ አየር ኃይል ከፍተኛ አማካሪ ሆነው ሲሰሩ ነበር። ከእሳቸው ጋር የኡጋንዳ አየር ኃይልን የተቀላቀሉ ኢትዮጵያዊ ጓደኞቻቸው ጥቂት ከሰሩ በኋላ የተሻለ ሕይወት ፍለጋ ወደ አሜሪካና አውሮፓ ሲሄዱ እሳቸው ግን እስከ ሕይወታቸው ፍፃሜ ኡጋንዳን አገራቸው ማድረጋቸው በኡጋንዳዊያን ዘንድ ክብርን እንዳተረፈላቸው ይነገራል። ከቤተሰቦቻቸው እንደተረዳነው የ69 ዓመቱ ሌ/ኮ ጌታሁን ትዳር አልመሰረቱም፤ ልጅም የላቸውም። ብዙ ጓደኛም የሌላቸውና ብቸኛ የሚባሉ ዓይነት ሰው ነበሩ። ኡጋንዳን መኖሪያ ቤታቸው ቢያደርጉም በየዓመቱ በቋሚነት ኢትዮጵያ ለሚገኙ 23 የቤተሰባቸው አባላትና ልጅ ሳሉ ላገለገሉባቸው የገጠር አብያተ ክርስትያናት በየዓመቱ ከፍተኛ ገንዘብ ይልኩ እንደነበርም ያነጋገርናቸው ቤተሶቦቻቸው ገልፀውልናል።
news-54791218
https://www.bbc.com/amharic/news-54791218
የዶናልድ ትራምፕ ሕይወት፡ ከሆቴል እስከ ቤተ መንግሥት
ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ምርጫ ዕጩ ሆነው ከመቅረባቸው በፊት እጅግ የታወቁ ቢሊዮነር ነበሩ።
አንድ ቀን ፕሬዝደንት እሆናለሁ ብለውም ይናገሩ ነበር። ይኸው አሁን አሜሪካን እየመሩ ይገኛሉ። ፕሬዝደንቱ በዕጩነት ሲቀርቡ 'አሁንስ እኒህ ሰውዬ አበዙት' ያላለ አልነበረም። ምክንያቱ ደግሞ ሰውዬው ከዚያ በፊት የሚታወቁበት ባህሪያቸው ነው። ነገር ግን የ70 ዓመቱ የንግድ ሰው የሪፐብሊካን ፓርቲ ዕጩ ሆነው ወደ መድረክ ወጡ። በአሜሪካ ታሪክ እጅግ አነጋጋሪውና አከራካሪው ነው የተባለውን የ2016 ምርጫ ረትተው መንበረ ሥልጣን ተቆናጠጡ። አሁን ድጋሚ ለመመረጥ ሌላ አወዛጋቢ ምርጫ ውስጥ ይገኛሉ። የልጅነት ሕይወት ዶናልድ ኒው ዮርክ ውስጥ በመኖሪያ ቤት ሽያጭ እጅግ የናጠጡት ፍሬድ ትራምፕ አራተኛ ልጅ ናቸው። በአባታቸው ኩባንያ ውስጥ አንድ አነስተኛ የሚባል ሥራ ተሰጥቷቸው እንዲሠሩ ቢጠበቁም ትምህርት ቤት ውስጥ በጥባጭ ፀባይ በማሳየታቸው ወደ ወታደራዊ አካዳሚ ተላኩ። . ነገ ጠዋት ስለ አሜሪካ ምርጫ ምን ዜና ልንሰማ እንችላለን? . በአሜሪካ ፕሬዘዳንት የሚመረጠው እንዴት ነው? . ትራምፕ እና ባይደን የመጨረሻ ሰዓት ቅስቀሳ እያደረጉ ነው ታላቅ ወንድማቸው ፍሬድ ፓይለት ሲሆኑ ጊዜ የአባታቸውን ንብረት ለመቆጣጠር ዶናልድ ያኮበክቡ ጀመር። ታላቅ ወንድሜ ፍሬድ በ43 ዓመታቸው በአልኮል መጠጥ ምክንያት ሲሞት ነው አልኮልና ትምባሆ ንክች ላለማድረግ የወስንኩት ይላሉ ትራምፕ። ትራምፕ ወደ 'ሪል ስቴት' ዘርፍ የገቡት ከአባታቸው አንዲት ሚሊዮን ብር ተበድረው እንደሆነ ይናገራሉ። ቀስ በቀስ የአባታቸውን ትላልቅ 'ፕሮጀክቶች' ማንቀሳቀስ ያዙ። በአውሮፓውያኑ 1971 የአባታቸውን ድርጅት ስም 'ትራምፕ ኦርጋናይዜሽን' ሲሉ ሰየሙት። የትራምፕ አባት የሞቱት በ1999 [በአውሮፓውያኑ] ነበር። ትራምፕ 'አባቴ ለኔ መነቃቃቴ ነው' ብለው ነበር በወቅቱ። የቢዝነስ ሕይወት ትራምፕ የቤተሰባቸውን ቢዝነስ ከአነስተኛ ከተሞች ጀምሮ እስከ ትላልቆቹ ድረስ በማስፋፋት ይታወቃሉ። አሜሪካ ውስጥ ባሉ ትላልቅ ከተሞች ትራምፕ ህንፃ የሚል ማየት እንግዳ አይደለም። ሙምባይ፣ ፊሊፒንስና ኢስታንቡል ውስጥም ትራምፕ ታወር የተሰኙ ሕንፃዎች አሏቸው። ትራምፕ ሆቴሎችና ቁማር ቤቶችም ገንብተዋል። ነገር ግን ይህ ማስፋፋት የባንክ ዕዳ ውስጥ እንደከተታቸው ይነገራል። አልፎም አሜሪካና የተቀረው ዓለም የሚዘጋጁ የቁንጅና ውድድሮች ባለቤት ነበሩ። ወይዘሪት ዓለም፣ ወይዘሪት ዩኤስኤ፣ እንዲሁም ወይዘሪት ታዳጊ ዩኤስኤ የቁንጅና ውድድሮች ባለቤት የእሳቸው ድርጅት ነበር። በ2003 ኤንቢሲ የተሰኘው ጣቢያ ላይ 'ዚ አፕሬንቲስ' የተሰኘ ኢ-ልቦለዳዊ የቴሌቪዥን ቅንብር ጀመሩ። የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ሆነው ለ14 ዓመታት ሠርተዋል። ትራምፕ 213 ሚሊዮን ዶላር ለዚህ ተግባሬ ተከፍሎኛል ይላሉ። ትራምፕ በርካታ መፃሕፍትንም ፅፈዋል። ድርጅቶቻቸው ከክራባት ጀምሮ እስከታሸገ ውሃ ድረስ ያመርታሉ፤ ይሸጣሉ። ፎርብስ መፅሔት የትራምፕ ሃብት 3.7 ቢሊዮን ዶላር ነው ቢልም እሳቸው ግን 10 ቢሊዮን ዶላር ነው ይላሉ። አባትና ባል ትራምፕ ሶስት ጊዜ አግብተዋል፤ ሁለት ጊዜ ፈትተዋል። ታዋቂዋ የቼክ አትሌት ኢቫና ዜልኒኮቫ የመጀመሪያ ሚስታቸው ነበረች። ከኢቫና ጋር ሶስት ልጆች አሏቸው። ዶናልድ ትንሹ፣ ኢቫንካና ኤሪክ። ከኢቫና በመቀጠል ተዋናይት ማርላ ማፕልስን አገቡ። ከ6 ዓመት ትዳራቸው ቲፋኒ የተሰኘች ሴት ልጅ አግኝተዋል። ከዚያ በመቀጠል የአሁኗ ባለቤታቸው ቀዳማዊ እመቤት ሜላኒያን አገቡ። ይህ የሆነው 2005 ላይ ሲሆን በወቅቱ ሜላኒያ ሞዴል ነበረች። ሜላኒያና ትራምፕ ባሮን ዊሊያም የተሰኘ ልጅ አላቸው። ትራምፕ አሁንም የድርጅታቸው ዋና ሥራ አስኪያጅ ቢሆኑም ከመጀመሪያ ትዳራቸው ያፈሯቸው ልጆች ድርቶቻቸውን ያስተዳድሩላቸዋል። ዕጩ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዝደንት የመሆን ህልም እንዳለቸው መናገር የጀመሩት ከ1987 ጀምሮ ነው። በ2000 በተካሄደው ምርጫ ላይ የሪፎርም ፓርቲ አባል ሆነው ተወዳድረው ነበር። በ2008 ባራክ ኦባማ ሥልጣን ከያዙ በኋላ ትራምፕ፤ 'ኦባማ የተወለዱት አሜሪካ' አይደለም ሲሉ ተደመጡ። ነገር ግን ይህ የትራምፕ ፅንሰ ሐሳብ ሃሰት ነበር። ትራምፕ ይቅርታ ባይጠይቁም ፅንሰ ሐሳባቸው ሃሰት መሆኑን አምነዋል። ትራምፕ በይፋ የምርጫ ዘመቻውን የተቀላቀሉት ሰኔ 2015 ነበር። 'አሜሪካን ድጋሚ ታላቅ አደርጋታለሁ' ሲሉ ነበር ዘመቻቸውን የጀመሩት። የሰውዬው የምረጡኝ ዘመቻ እጅግ አነጋጋሪ ነበር። 'በሜክሲኮና በአሜሪካ ድንበር ላይ የግንብ አጥር እዘረጋለሁ፤ ሙስሊሞች ወደ ሃገሬ እንዳይገቡ አግዳለሁና የአሜሪካን ምጣኔ ሃብት አጠናክራለሁ' በሚሉ ንዑስ ሐሳቦች ነበር ደጋፊዎቻቸውን መግዛት የቻሉት። ትራምፕ በዚህ አቋማቸው ብዙ ተቃውሞዎች ገጥሟቸው ነበር። እሳቸው ግን 'ፍንክች' አላሉም። ትራምፕ የምርጫውን ዘመቻውን ከመቀላቀላቸው በፊት አድርገዋቸዋል የተባሉ እኩይ ተግባሮቻቸው በሚድያ ቢናፈሱም ለደጋፊዎቻቸው ግን ይህ የኔን ስም ለማጥፋት የተወጠነ ነው በማለት ያስተባብሉ ነበር። ለአንዳንድ ሰዎች ትራምፕ ያለፈውን ምርጫ ማሸነፋቸው አሁንም ያስገርማቸዋል። ትራምፕ ያለ ምንም የፖለቲካ ልምድና የውትድርና ሥልጠና መንበር የጨበጡ የመጀመሪያው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ናቸው።
news-43625963
https://www.bbc.com/amharic/news-43625963
አዲስ የሞባይል ቀፎ በኢትዮ ቴሌኮም ኔትዎርክ ላይ ለማሰመዝገብ ማወቅ ያለብዎት
ኢትዮ ቴሌኮም ከመስከረም 2009 ዓም ጀምሮ የደንበኞችን የሞባይል ቀፎ የመመዝገብ (Equipment Identity Registration System - EIRS) አገልግሎት መጀመሩ ይታወሳል።
ይህም ምዝገባ ዘመናዊ የቴሌኮም አገልግሎት መስጠት፤ ደህንነትን ማስጠበቅ እና ለአገሪቱ ገቢ ማስገባትን ዓላማ ያደረገ እንደነበር ድርጅቱ አስታውቆ ነበር። በተጨማሪም በሕገወጥ መንገድ የገቡና ጥራታቸው ድርጅቱ የሚያቀርበውን አገልግሎት የማይመጥኑ ስልኮችን ለመከላከል ታስቦ የተጀመረ መሆኑንም ጨምሮ ገልጾ ነበር። በአሁኑ ሰዓትም አዲስ ቀፎ ገዝቶ ለመጠቀም ምን ማድረግ እንዳለባቸው ባለማወቅ በኢትዮ ቴሌኮም ኔትዎርክ ላይ መሥራት የማይችሉ ስልኮችን ተታለው በመግዛት ለኪሳራ እየተዳረጉ እንደሆነ ተጠቃሚዎች ያማርራሉ። ይህን ለማሰቀረት ምንድነው መደረግ ያለበት ብለን የኦሮሞ አይሲቲ መስራችና ዳይሬክተር የሆነውን አቶ አብዲሳ በንጫን ጠይቀን ነበር። አዲሰ ቀፎ ሲገዛ ምን መደረግ አለበት? አንድ ስልክ ሲመረት 15 አሃዝ ያሉት አይኤምኢአይ('IMEI') ሚስጥር ቁጥር ጋር ነው የሚሠራው። ይህን አይኤምኢአይ('IMEI) ቁጥር ለማወቅም *#06# በመደወል ማወቅ ይቻላል። ሆኖም አስመስለው የሚመረቱ ቀፎዎቸ የትክክለኞቹን ስልኮች መለያ ቁጥር በማስመሰል ሊሠሩ ስለሚችሉ በኢትዮ ቴሌኮም ኔትዎርክ ላይ ከጥቅም ውጭ ይሆናሉ ማለት ነው። ድርጅቱ ገና ይህን አገልግሎት ሲጀምር ሁለት ሚሊዮን የሚሆኑ በማስመሰል የተሠሩ የሞባይል ቀፎዎች አገልግሎት መዋላቸውን ለይቻለሁ ብሎ ነበር። በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥም እነዚሀ ስልኮች ከአገልግሎት ዉጭ እንደሚሆኑ እና ደንበኞቹም በቶሎ እንዲያሰመዘግቡ አሰታዉቋል። ስለዚህ አዲሰ ቀፎ ሲገዛ አስመስለው የተሠሩ አለመሆናቸውን በማወቅ ካልተገባ ኪሳራ መዳን እንደሚቻል ባለሙያው ያስረዳሉ። ትክክለኛዎቹን ቀፎዎች ለማወቅ እነዚህን ቅደም ተከተሎች ይከተሉ 1- ሊገዙት ያሰቡት ቀፎ ውስጥ ሲም ካርድ ያስገቡ 2- *868# በመተየብ ይደዉሉ። ከዚያም 3 አማራጮች ይመጣሉ እነዚህም አማራጮች፡ 1- ፎን አንሎክ( Phone Unlock) 2- ስዊች አንሎክ (Switch Unlock) 3-ቼክ ስታተስ (Check Status) የሚሉ ናቸው። በመጣልን የቁጥር መጻፍያ ቦታ ላይ 3ኛውን ቼክ ስታተስ (Check Status) የሚለውን በማሰገባት መላክ ወይም ሴንድ የሚለውን (SEND) ቁልፍ መጫን። ከዚያም 2 አማራጮች ይመጣሉ። እነዚህም አማራጮች፡ 1- ባይ አይኤምኢአይ (By IMEI) 2-ባይ ፎን ነምበር (By Phone number) የሚሉ ናቸው። 1- ባይ አይኤምኢአይ (By IMEI) የሚለውን በማስገባት ስንልከው ወይም ሴንድ (SEND) ስንለው ወዲያውኑ አይኤምኢአይ ቁጥር አስገቡ (Enter IMEI number) የሚል መልዕክት ይመጣል። ከዚያም በማስገባት *#06# የምናገኘውን የ አይኤምኢአይ 'IMEI' ሚስጥር ቁጥር አስገብተን መልእክቱን መላክ ወይም ሴንድ (SEND) እንለዋለን። ከዚህ በኋላ ወዲያዉኑ በኢትዮ-ቴሌኮም ኔትዎርክ ላይ የሚሠራና የማይሠራ ቀፎ መሆኑን ያውቃሉ። መደረግ የሌለባቸው ከላይ በተጠቀሱት መሠረት ትክክለኛውን ስልክ ማግኘት ካልቻሉ፤ ቀፎው አዲስ ነውና ገና ከእሽጉ ስላልተፈታ ነው ተብሎ መገዛት እንደለሌለበት ባለሙያው ይመክራሉ። እንዲሁም በተጨማሪ ሳይከፈት በፊት ለ 3 ሰዓታት ቻርጅ መደረግ አለበት በማለት ሻጮች ሊሸጡ ቢሞክሩ ኪሳራ ሊያስከትል እንደሚችልም ተናግረዋል። ከውጭ አገር የሚመጡ ስልኮችን አስመልክቶ ከውጭ አገር የሚመጡ ስልኮችን በተመለከተ ስልኩን ያመጣው ሰው ካለ አንድ ስልክ በነፃ ማሰመዝገብ የሚችል ሲሆን፤ ከዚያ በላይ ቁጥር ላላቸው ቀፎዎች 45% ግብር በመክፈል ማስመዝገብ የሚቻል መሆኑን ነው የተገለጸው።
news-45755906
https://www.bbc.com/amharic/news-45755906
የ2018 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ዛሬ ረፋድ ይፋ ይደረጋል
የ2018 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ዛሬ ረፋድ ይፋ ይደረጋል። ምርጫውን የሚያከናውነው 5 አባላት ያሉት ኮሚቴ የዘንድሮ የኖቤል የሰላም ሽልማት ዕጩዎች ቁጥር 331 መሆኑን አሳውቋል።
ከእነዚህም መካከል 216 ግለሰቦች ሲሆኑ 115ቱ ደግሞ ቡድኖች መሆናቸውን ኮሚቴው ጠቁሟል። በኖቤል ሽልማት አሰራር መሰረት ዕጩዎች ለህዝብ ይፋ የሚደረጉት ከ50 ዓመታት በኋላ ነው። ዕጩዎቹ እነማን እንደሆኑ ባይታወቅም በርካቶች የዘንድሮውን የኖቤል ሽልማት ማን ሊያሸንፍ እንደሚችል የራሳቸውን ግምት እየሰጡ ይገኛሉ። የሁለቱ ኮሪያ መሪዎች የአሸናፊነቱ ቅደሚያ ግምት ከተሰጣቸው ግለሰቦች መካከል ይገኙበታል። የሰሜን ኮሪያው መሪ በሰብዓዊ መብት አያያዘቸው በተደጋጋሚ ቢወቀሱም ከደቡብ ኮሪያው አቻቸው ጋር በመሆን በሁለቱ ሃገራት መካከል የቆየውን ውጥረት ለማርገብ የወሰዷቸው እርምጃዎች የሽልማቱ ተመራጭ ያደርጋቸዋል የሚሉት በርካቶች ናቸው። • ዐብይ አሕመድ ለኖቤል ሽልማት ታጭተዋል? ሌላው ሽልማቱን ሊያሸንፉ ይችላሉ ተብለው ቅድሚያ ግምት ከተሰጣቸው መሪዎች መካከል እንዱ ዶናልድ ትራምፕ ናቸው። ትራምፕ በኮሪያ ባህረሰላጤ ሰላም ለማስፈን እንዲሁም ሰሜን ኮሪያ ኒኩለር ቦንም ከማበልጸግ እንድትቆጠብ ላደረጉ ያላሰለሰ ጥረት ሽልማቱን ሊያሸንፉ ይችላሉ ተብሏል። በእስር ላይ የሚገኘው ጸሃፊው ራኢፍ ባዳዊ፣ ሊቀ ጳጳስ ፈራንሲስ እና የካታሎንያ የነጻነት መሪ ካርለስ ፑይግዴሞንት ሽልማቱን ያሸንፋሉ ተብሎ ግምት ከተሰጣቸው መካከል ይገኙበታል። የዘንድሮውን የኖቤል የሰላም ሽልማት ያሸንፋሉ ተብለው ግምት ከተሰጣቸው ሌሎች ግለሰቦች መካከል እስር ላይ የሚገኘው ጸሃፊው ራኢፍ ባዳዊ፣ ሊቀ ጳጳስ ፈራንሲስ እና የካታሎንያ የነጻነት መሪ ካርለስ ፑይግዴሞንት ይገኙበታል። የሳውዲ ዜግነት ያለው ጸሃፊው ራኢፍ ባዳዊ ፣ ''የመገናኛ አውታሮችን በመጠቀም እስልምናን ዘልፏል'' በሚል ክስ ላለፉት 6 ዓመታት በሳውዲ እስር ቤት ውስጥ ይገኛል። በስፔን መንግሥት ሕጋዊ እውቅና ባልነበረው ሕዝበ ውሳኔ ካታላኖች በካርለስ ፑይግዴሞንት እየተመሩ ከስፔን ተገንጥለው ሃገር ለመመስረት ሙከራ አድርገው ነበር። ሕዝበ ውሳኔውን ተከትሎም ካርለስ ከስፔን ሸሽተው በቤልጅም እየኖሩ ይገኛሉ። • "ካታሎንያ ከስፔን ተገንጥላ አገር የመሆን መብቷን አሸነፈች" ከግለሰቦቹ በተጨማሪ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ሽልማቱን ሊያሸንፍ ይችላል ከተባሉ ድርጅቶች መካከል አንዱ ነው። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድስ ከዕጩዎቹ መካከል እንዱ ሊሆኑ አይችሉም? ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ከፍተኛ የሕዝብ ድጋፍ ማግኘት ብቻም ሳይሆን የኖቤል ሽልማት እንዲያገኙም ጭምር ዘመቻ ተከፍቶ ነበር። ይሁን እንጂ የኖቤልን የሰላም ሽልማትን የጊዜ ሰሌዳ ስንመለከት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የ2018 የኖቤል ሽልማት እጩ የመሆናቸው ነገርን አጠያያቂ ያደርገዋል። የኖቤል ኮሚቴ የጊዜ ሰሌዳ እንደሚከተለው ነው። መስከረም፡- በፈረንጆች መስከረም (ሴፕቴምበር) የኖርዌይ ኖቤል ኮሚቴ እጩዎችን ለመቀበል ይሰናዳል። እጩ የመቀበሉ ሥራ ለቀጣይ ስድስት ወራት ይጸናል። እጮዎቹን መጠቆም የሚችሉት ከላይ የተዘረዘሩት ብቁ ጠቋሚ የተባሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ብቻ ናቸው። የካቲት፡- በየካቲት የእጩዎች መቀበያ ጊዜ ያበቃል። ከየካቲት 1 በፊት ያልተጠቆመ በዚያ ዓመት እጩ መሆን አይችልም። መጋቢት፡-ኮሚቴው የእጮዎችን ዝርዝር ያቀርባል። ከእጮዎቹ ውስጥ ከ20 እስከ 30 የሚሆኑትን ብቻ ለተጨማሪ ማጣሪያ ይቀርባሉ። ጥቅምት፦ በጥቅምት መጀመርያ ኮሚቴው አሸናፊውን በድምጽ ብልጫ ይመርጣል። ይግባኝ የማይባልበት ምርጫ ነው ታዲያ። በታኀሳስ፦ 10 (በፈረንጆቹ) በኦስሎ ኖርዌይ የሽልማት ሥነ ሥርዓቱ ይካሄዳል። የኖቤል ሽልማት ከአንድ ዓመት ዘለግ ያለ ጊዜን የሚወስድ ሂደት ነው። ኾኖም ጥቆማ የመቀበያ ጊዜ ከፈረንጆች መስከረም ጀምሮ ለ6 ወራት የሚዘልቅ ነው። ይህ እንግዲህ መጪውን የመስከረም ወር ሳይሆን የ2017ቱን ወር አንድ ብሎ የሚጀምር ነው። የእጩ መስኮቱ ከተዘጋ ከሁለት ወራት በኋላ ወደ ሥልጣን የመጡት ዐብይ አሕመድ ቢያንስ የ2018 የኖቤል ሽልማት እጩ የመሆናቸው ዐድል ጠባብ ያደርገዋል። ምናልባት የኖቤል ኮሚቴው በመጨረሻዎቹ ጊዜያት እጩ የመጨመር ሥልጣን ስላለው ያ ተግባራዊ ከሆነ ጠባብ እጩ የመሆን እድል ሊኖራቸው ይችላል።
news-55444741
https://www.bbc.com/amharic/news-55444741
በላቲን አሜሪካ የኮቪድ-19 ክትባት ዘመቻ ተጀመረ
በላቲን አሜሪካ አገሮች የኮቪድ-19 ክትባትን ለመጀመርያ ጊዜ በዘመቻ መስጠት ተጀምሯል። በተለይ ሜክሲኮ በዚህ ረገድ ቀዳሚ ሆናለች።
ሜክሲኳዊቷ ነርስ የፋይዘር ባዮንቴክ ክትባትን ለመወጋት የመጀመርያዋ የላቲን አሜሪካ ዜጋ ሆናለች። ይህ ዘመቻ የተጀመረው ትናንት ሐሙስ ሲሆን ሜክሲኮ 3ሺህ ብልቃጥ ክትባት ወደ አገሯ እንደገባ ነው ዘመቻውን የጀመረችው። ሜክሲኮ ተህዋሲው በርካታ ዜጎችን ከገደለባቸው የዓለም አገራት ተርታ ትመደባለች። በዓለም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ በተህዋሲው ያለቀባቸው አገራት በቅደም ተከተል አሜሪካ፣ ብራዚል ሕንድና ሜክሲኮ ናቸው። ሜክሲኮን ተከትሎ ቺሌ እና ኮስታሪካ የጀርመን/አሜሪካ ሰራሹን ፋይዘር ባዮንቴክ ክትባትን ለዜጎቻቸው መስጠት ጀምረዋል። አርጀንቲናም በተመሳሳይ ከቀናት በኋላ ክትባት መስጠት ልትጀምር እንደሆነ ይፋ አድርጋለች። ሆኖም አርጀንቲና የመረጠችው የክትባት ዓይነት ራሺያ ሰራሹን ሰፑንትኒክቪ ሲሆን 300ሺህ ብልቃጥ ቦነስ አይረስ መድረሱ ተሰምቷል። ከደቡብ አሜሪካ አገሮች ከፍተኛ ሕዝብ በተህዋሲው የሞተባት ብራዚል ግን እስከ አዲሱ የፈረንጆች ዓመት የካቲትድረስ ክትባቱን መስጠት እንደማትጀምር ተዘግቧል። አወዛጋቢው ፕሬዝዳንቷ ቦልሴናሮ ክትባቱን እንደማይወስዱ ተናግረዋል። ምክንያቱም እኔ በቫይረሱ ተይዤ ስለነበረ የመከላከል አቅም አዳብሪያለሁ ብለዋል። ረቡዕ ሜክሲኮ የደረሱበት 3ሺህ ብልቃጥ ክትባቶች የተመረቱት ቤልጂየም ውስጥ ነው። የመጀመርያዋ ተከታቢ ነርስ ክትባቱን ስትወስድ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሎፔዝ ኦፕራዶር በተገኙበት ለሕዝብ በቀጥታ ተላልፏል። የሜክሲኮ መንግሥት በቀጣይ ሁሉንም የጤና ባለሙያዎች ቅድሚያ ሰጥቶ ክትባቱን ለማዳረስ እንደሚሞክር ቃል ገብቷል። ሜክሲኮ 1 ሚሊዮን 300ሺህ ዜጎቿ በተህዋሲው ተይዘው 120ሺህ የሚሆኑት ሞተውባታል። ቺሊ 600ሺህ ሰዎች ተይዘውባት 16ሺ የሚሆኑት ሞተውባታል። አርጀንቲና 1 ሚሊዮን 600ሺ ሰዎች ተይዘው 42ሺ የሚሆኑት ሞተዋል። የቺሌው ፕሬዝዳንት ሰባስቲያን ፓኔራ የክትባቱ መጀመር የአዲስ ተስፋ ዘመን መምጣትን ያመላክታል ሲሉ ለሕዝባቸው ንግግር አድርገዋል።
news-53576991
https://www.bbc.com/amharic/news-53576991
2 ሚሊዮን ሰዎች የሚሳተፉበት የሐጅ ሥነ ሥርዓት ዘንድሮ በ10ሺ ሰዎች ብቻ ይፈጸማል
ሳኡዲ አረቢያ መንፈሳዊ ተጓዦች ወደ አገሯ እንዳይገቡ አግዳለች፡፡ የሐጅ ቪዛም ዘንድሮ አላተመችም፡፡
ዛሬ በሚጀመረው ሥነ ሥርዓት የሚሳተፉት የሌላ አገር ዜጎች በሳኡዲ የመኖርያ ፈቃድ ያላቸው ብቻ ናቸው ተብሏል፡፡ በግምት ከ10ሺ የማይበልጡ ሰዎች ብቻ ሐጅ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ መኖርያ ፈቃድ ኖሯቸው በሳኡዲ የሚገኙ የሌላ አገር ዜጎችም ቢሆኑ ወደ ቅድስት አገር መካ ሲገቡ ሙቀታቸው መለካት ይኖርባቸዋል፡፡ የኮቪድ-19 ቫይረስ ምርመራም ማድረግ ይገደዳሉ፡፡ ሐጅ ፈጻሚዎቹ ከሥነ ሥርዓቱ በፊትም ሆነ ሥርዓቱን ከፈጸሙ በኋላ ራሳቸውን ለተወሰነ ጊዜ ማግለልም ይጠበቅባቸዋል፡፡ በሳኡዲ የሐጅ ጉዳዮች ሚኒስትር መሐመድ ሳለህ ቢንተን ለአል አረቢያ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃለ ምልልስ ሐጅ አድራጊዎች ወደ መካ ከመግባታቸው በፊት በቤታቸው ራሳቸውን ለአራት ቀናት ገለል አድርገው መቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚያም መካ ከተማ ከገቡ በኋላ በሆቴላቸው ለሌላ አራት ቀናት የጤና ወሸባ መግባት አለባቸው፡፡ በዘንድሮ ሐጅ ተሳታፊዎች መካከል 30 እጁን የሚይዙት የራሷ የሳኡዲ አረቢያ ዜጎች ናቸው፡፡ ሳኡዲ አረቢያ በቫይረሱ የተያዙባት ሰዎች ቁጥር 270,000 ሲሆን 3,000 ሰዎች ሞተውባታል፡፡ በኢስላም እምነት ከአምስቱ የሃይማኖቱ መሠረቶች አንዱ አቅም ያለው ሰው በሕይወት ዘመኑ ቢያንስ አንድ ጊዜ የሐጅ ሥነ ሥርዓት እንዲያደርግ ይጠበቅበታል፡፡አመታዊው የሐጂ ሥነ ሥርዓት ዛሬ ረቡዕ ነው የሚጀምረው፡፡ ወትሮው ከመላው ዓለም ሁለት ሚሊዮን ሰዎች በዚህ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት የሚሳተፉ የነበረ ሲሆን ዘንድሮ ግን በኮሮና ምክንያት ቁጥሩ ተገድቧል፡፡
news-53125900
https://www.bbc.com/amharic/news-53125900
"በታቃውሞው የተገደለውን የልብ ጓደኛዬን ፍትህን በመሻት ነው ሰልፍ የወጣሁት"
"ጓደኛዬ ልቡ ሰፊ ነበር፤ ሁሉን መውደድ የሚችል" ትላለች ዳይመንድ
በኔብራስካ፣ ኦማሃ ነዋሪነቷን ያደረገችው ዳይመንድ ትምህርት ቤት ውስጥ የነበራትን ስራ ስታጣ ከጎኗ የነበረውም ጓደኛዋ ጄምስ ስከርሎክ ነበር። እሱም ሆነ ቤተሰቦቹ ወደ ቤታቸው ጋበዟት፤ የሚበሉትን በልተው፤ ቤት ያፈራውንም እንደቀማምሱም የቤተሰባችን አካል ነሽ አሏት። በህይወቷ ትልቅ ውለታ ውሎልኛል የምትለው ጄምስ ቤት አልባ ከመሆን አዳናት። "መኖሪያ አጥቼ እሱም ሆነ ቤተሰቦቹ አለንልሽ ሲሉኝ፤ ከጓደኛዬ በላይ መሆኑን ተረዳሁኝ" በማለት ለሬዲዮ ዋን ኒውስ ቢት የተናገረችው ዳይመንድ "ወንድሜ ነበር" ብላለች። ዳይመንድና የ22 አመቱ ጄምስ ጎረቤቶች ነበሩ። የተገናኙትም በጋራ መኖሪያ ቤቶቻቸው (አፓርትመንታቸው) ግቢ ውስጥ በሚገኘው የመዋኛ ገንዳ ከሁለት አመታት በፊት ነበር። ጄምስ ስራ ቦታ ይሸኛታል፤ የትምህርት ቤት ስራዎቿንም ያግዛታል። እስካሁንም ቢሆን ደብተሮቿ ላይ የሳላቸው ስዕሎች አሉ። በሚወዱት ጓደኞቹ ጁጁ የሚል ቅፅል ስም የተሰጠው ሲሆን በታናናሽ ወንድሞቹና እህቶቹ የሚወደድ፤ ከሁሉ ጋር የሚቀልድ እንደነበርም ዳይመንድ ትናገራለች። በግንባታ ሰራተኝነት ተቀጥሮ ይሰራ የነበረ ሲሆን የሰባት ወር ልጁንም ለመንከባከብና አትኩሮትም ለመስጠት በሚል ስራውን አቆመ። በአባትነቱም ይኮራ ነበር ትላለች ዳይመንድ የህፃን ልጁን የወደፊት ሁኔታ ምን ሊሆን ይችላል? የሚለውም ሁኔታ ስለሚያስጨንቀውም ነበር ጄምስ ለማህበራዊ ፍትህ መታገልን የመረጠው። በተለይም በነጭ ፖሊስ ተደፍቆ የተገደለውን ጆርጅ ፍሎይድን ሞት ተከትሎ የተነሱ የ'ብላክ ላይቭስ ማተር' ተቃውሞዎች ላይም በከፍተኛ ሁኔታ ድምፃቸውን ካሰሙት መካከል አንዱ ነው። ነገር ግን ግንቦት 22፣ 2012 ዓ.ም ጄምስ እንደወጣ አልተመለሰም። የአንድ መጠጥ ቤት ባለቤት የሆነው ነጩ ጃኮብ ጋርድነር በሽጉጥ ተኩሶ እንደገደለውም የሚያሳይ ቪዲዮ ወጣ። ጃኮብ ጋርድነር መጠጥ ቤቱ በር ላይ እየጠበቀ የነበረ ሲሆን፣ ጄምስ ከኋላው መጥቶ ሲይዘውም ሁለት ጊዜ በአየር ላይ ተኩሶ በማስከተል ጄምስን እንደመታው ታውቋል። ጄምስም በደረሰበት ጉዳት ህይወቱ አልፏል። የግዛቱ አቃቤ ህግ የመጠጥ ባለቤቱ ራሱን ለመከላከል በሚል ነው የተኮሰው ስለዚህ ክስ አልመሰርትበትም ብሏል። ነገር ግን የአይን እማኞች ጃኮብ ጋርድነርና አባቱ ተቃዋሚዎችን የዘረኛ ስድብ ሲሳደቡ እንደነበርና ሲያስፈራሩም በማየቱ ጄምስ ለመከላከል ነው ከኋላ የገባው ብለዋል። የህዝቡንም ቁጣ ተከትሎ አቃቤ ህጉ ከማህበረሰቡ የተውጣጣ ኮሚቴ ያዋቀረ ሲሆን ግለሰቡ ይከሰስ አይከሰስ በሚለውም ጉዳይ ላይ የሚወስኑ ይሆናል። የመጠጥ ቤቱ ባለቤት ጥፋተኛ ሆኖ ካገኙትም በግድያ ወንጀል እንዲሁም ፈቃዱ ያለፈበት የጦር መሳሪያ በመያዝ ክስ ይመሰረትበታል። "ለውጥ መምጣት አለበት" የኔብራስካዋ ኦማሃ የባለፈው ዓመት የህዝብ ቁጥር እንደሚያሳየው 77 በመቶ የሚሆነው ህዝቧ ነጭ ነው። የጄምስ መሞትንም ተከትሎ የኔብራስካ አስተዳዳሪ ፒት ሪኬትስ ጥቁሩን ማህበረሰብ ባናገሩበትም ወቅትም ስሜት አልባ ንግግር ነው በሚል ብዙዎች አቋርጠው ወጥተዋል። ጓደኛዋ ሲሞት ዳይመንድ በቦታው አልነበረችም፤ ከዚያ በፊትም በነበሩት የተቃውሞ ሰልፎችም እንዲሁ አልተሳተፈችም። የፖሊስ ጭካኔን ብትረዳም ፖለቲካዊ ተሳትፎዋ ግን የቀዘቀዘ ነበር። ይህ ሁሉ ግን ጄምስ ሲሞት ተቀየረ። " ጄምስን እንደ ወንድሜ ነው የምወደው። እሱን ማጣት ማለት ተሰምቶኝ የማያውቅ ኃዘንና ህመም እንዲሰማኝ ሆኗል" በማለትም ተናግራለች። የቅርብ ጓደኛዋንም ሞት ተከትሎ የኮሮናቫይረስ መመሪያዎች ሳያስጨንቋት ከጓደኞቿ ጋር ተቃውሞውን ተቀላቀለች። "መንግሥት በራሱ ህዝብ ላይ ተነስቷል" የምትለው ዳይመንድ "ህዝቡ ግን ከተባበረ በመንግሥትም ላይ ቢሆን ለውጥ ማምጣት እንችላለን" ትላለች። "ተቃውሞዬን እቀጥላለሁ፤ ምርጡ ጓደኛዬ አሁንም ቢሆን ፍትህ አላገኘም" በማለትም ለኒውስ ቢት አስረድታለች። የጆርጅ ፍሎይድን ግድያ ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ ከተገደሉት አስራ ዘጠኝ ሰዎች መካክለ ጄምስ አንዱ ነው። አብዛኛዎቹ እንደ ጄምስ ምንም መሳሪያ ያልያዙ ጥቁር ወጣቶች ናቸው። አንዳንዶቹ በተተኮሰባቸው ጥይት ሲሞቱ፣ አንደኛው ደግሞ ሰልፈኞቹን የሚቃወም ግለሰብ በተሰበሰው ህዝብ መካከል መኪናውን በመንዳቱ ህይወቱ አልፏል። ዳይመንድ ሌሎች ወጣቶች የብላክ ላይቭስ ማተር እንቅስቃሴን እንዲቀላቀሉና ተቃውሞቹም ሰላማዊ እንዲሆኑ ጥሪዋን አቅርባለች። "ሁኔታው የከፋ ቢሆንም፤ ቤታችንን ማፍረስ የለብንም። ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተቃውሟችንን እያሰማን ደህንነታችንን እንጠብቅ" በማለት መልዕክቷን አስተላልፋለች። ዳይመንድ ቢቢሲን ባናገረችበት ወቅት ከጄምስ ቤተሰብ ጋር በመሆን ህይወቱን ለመዘከር የሚደረገውን የሃዘን ስርአት ለመካፈል እየተዘጋጀች ነበር። ጄምስን የገደለው ወደ ፍርድ እንደሚቀርብ ተስፋን የሰነቀችው ዳይመንድ አጠቃላይ ለተገደሉትም "ፍትህን እንሻለን" ትላለች። ጄምስ የወደፊቱን ብሩህ ነበር ብሎ ነበር የሚያስበው፤ ልክ እንደ ወንድሙ የንቅሳት አርቲስት እንዲሁም ኮሌጅ ገብቶም የማጥናት እቅድ ነበረው። ልጁም ሕይወቱ ነበረች ትላለች። ሞቱንም ተከትሎ ብዙዎች በትዊተር ህይወቱን የዘከሩት ሲሆን ለመታሰቢያነቱም እንዲውል ትልቅ ቅርፅ ቆሞለታል። "ሲሞት ታላቅ ስራ ሰርቶ እንደሚሞት ይነግረኝ ነበር" የምትለው ዳይመንድ ጄምስ በሕይወት እያለም የራፕ ሙዚቃም ይጫወት፤ ለልጁ አርዓያ መሆንም ይፈልግ ነበር። በስተመጨረሻም "ለትልቅ አላማ ነው የሞተው፤ ስሙም ከመቃብር በላይ ነው" ብላለች።
news-56372139
https://www.bbc.com/amharic/news-56372139
የሞስኮ ፖሊስ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጉባኤን በመክበብ 200 ፖለቲከኞችን በቁጥጥር ስር አዋለ
የሩሲያ ፖሊስ የተቃዋሚ ፖርቲዎች እያደረጉ ያለውን ጉባኤ ሰብሮ በመግባት 200 ፖለቲከኞችን በቁጥጥር ስር አውሏል።
ከታሰሩት መካከል ታዋቂ አመራሮች ይገኙበታል ተብሏል። ለሁለት ቀናት ያህል ይካሄዳል ተብሎ የነበረው ጉባኤ ገና ከጅማሮው ነው ፖሊስ ያቋረጠው። ፖሊስ የሞስኮ ሆቴልን ከብቦ ተሳታፊዎቹን በሙሉ በቁጥጥር ስር አውሏል። ፖሊስ እንደሚለው ፖለቲከኞቹ ስብሰባ በማካሄድ የኮሮናቫይረስ መመሪያዎችን ጥሰዋል እንዲሁም ይህንን ጉባኤ ያዘጋጀው "የማይፈለግ ድርጅት" ነው ብሏል። አገሪቷ የምታደርገው ምርጫ እየተቃረበ በመጣበት ወቅት ባለስልጣናቱ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ የሚያደርጉት ጫና ከፍተኛ ነው ተብሏል። ባለፈው ወር ዋነኛ ተቃዋሚና ቭላድሚር ፑቲንን በሰላ ትችቱ የሚታወቀው አሌክሴ ናቫልኒ ለእስር ተዳርጓል። ተመርዞ የነርቭ ጉዳት ያጋጠመው አሌክሴ ህክምና አድርጎ ጀርመን ከተመለሰ በኋላ ነው ለእስር የተዳረገው። ባለስልጣናቱ በይደር የቆየውን የፍርድ ቤት እስር ውሳኔ ጥሷል ተብሏል። አሌክሴ መርዘውኛል የሚላቸው የክሬምሊን ቤተ መንግሥት ባለስልጣንን ነው። በአጠቃላይ በሩሲያ የሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በዚህ ሞስኮ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ነበር። የዚህ ጉባኤ ዋነኛ አላማ በመጪው መስከረም ላይ አገሪቷ የምታደርገው ብሄራዊ ምርጫ ላይ ያሉ ስትራቴጂዎችን ለመወያየት ነበር የተዘጋጀው። የአገሪቱ ቴሌቪዥን እንዳሳየው የጉባኤው ተሳታፊዎች በፖሊስ በቁጥጥር ስር ሲውሉ ነው። ፖሊስ "በርካታ ተሳታፊ ፖለቲከኞች ጭምብል አላጠለቁም" ያለ ሲሆን እንዲሁም ሌሎች የኮሮናቫይረስ መመሪያዎችንም ጥሰዋል ይላል። ጉባኤውን አዘጋጅቷል የተባለውና "ያልተፈለገ ድርጅት" ተብሎ የተጠራው ኦፕን ሩሲያ እንደሆነ ፖሊስ አስታውቋል። ኦፕን ሩሲያ የተቋቋመው የሩሲያ ዋነኛ ተቃዋሚ በሚባሉት ሚክሃይል ኮዶሮኮቭስኪ በእንግሊዝ ውስጥ ነው። ሚክሃይል ኮዶሮኮቭስኪ በእስር ለአስር አመታት የቆዩ ሲሆን ጠበቆቻቸው በፈጠራ ክስ ነው የታሰሩት ብለዋል። ፖለቲከኛው ከእስር በኋላ ውጭ አገር በስደት መኖር ጀምረዋል። የሩሲያ ባለስልጣናት የውጭ አገር ድርጅቶች ሆነው በፖለቲካ ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች በአገሪቱ መንቀሳቀስን ያግዳል። በአገሪቱም ውስጥ "የማይፈለጉ" ከተባሉ ድርጅቶች አንዱ ነው። በጉባኤው ተሳታፊ የሆኑት አንደኛው የተቃዋሚ መሪ አንድሬይ ፒቮቫሮቭ በበኩላቸው ዩናይትድ ዲሞክራትስ በሚባል ድርጅት ጉባኤው እንደተካሄደ ተናግረዋል። የፖሊስ ከበባ "እኛን ማስፈራራት" ላይ ያነጣጠረ ነው ይላሉ።
41514081
https://www.bbc.com/amharic/41514081
ስለኢትዮጵያ የቤተ ክርስቲያን ስዕሎች ምን ያህል ያውቃሉ?
ኢትዮጵያ ከሶስት ሺ አመታት የሚሻገር የስነ ጥበብ ታሪክ እንዳላት አጥኝዎች ያወሳሉ።
ጎንደር የሚገኘው የደብረብርሀን ስላሴ ቤተክርስቲያን ስዕሎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስትና ከፍ ያለ ሚና እንደተጫወተ የሚመሰክሩ በየአብያተ ክርስትያናቱና በየገዳማቱ ግድግዳዎች ላይ ፤ በኃይማኖታዊ ድርሳናት ውስጥ እንዲሁም በእንጨት ላይ የተሰሩ በርካታ ስዕሎች ለዘመን መደራረብ እጅ ሳይሰጡ ይገኛሉ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አለ የስነጥበብና ዲዛይን ትምህርትቤት የስነ ጥበብ ታሪክ መምህርና ተመራማሪው አበባው አያሌው 'ኧ ግሊምስ ኦፍ ኧ ስሪ ሚሊኒያ ኦፍ ኢትዮፒያን አርት' በተሰኘ ፅሁፋቸው እንደሚያስረዱት በሶስተኛው እና በአራተኛው ክፍለ ዘመን መባቻ አካባቢ የቅድመ ክርስትና ስነ ጥበባዊ ስኬት ተመዝግቦ ነበር። በወቅቱ የአክሱም ስርወ መንግስት በአገር ውስጥና ከሌሎች የውጭ አገራትም ጋር የሚደረጉ የንግድ እንቅስቃሴዎች እጅጉን ስኬታማ መሆኑ በተለይም ለኪነ ሕንፃና ለቅርፃ ቅርፅ ባለሞያዎች ከፍተኛ ድጋፍ ችሮታል። በ4ኛው ምዕተዘመን ክርስትና የአክሱም መንግስታዊ ኃይማኖት ሊሆን ከበቃ በኋላ ግን ለሙታን መታሰቢያ የሚሆኑ ምስለ-ቅርፆችን እና ግዙፍ ሃውልቶችን ማቆም አንድም ከእምነቱ አስተምህሮ ጋር የሚፃረር ሆኖ በመታየቱ፤ በተጨማሪም የአረማዊ ዘመን ልማድ ተደርጎ በመቆጠሩ የቅርፃ ቅርፅ ጥበብ እየከሰመ ሲመጣ በፋንታው ክርስቲያናዊ ስነ-ስዕል አብቧል። ነገር ግን በአክሱም ዘመን ከተሰሩት ክርስትያናዊ ስዕሎች ብዙዎቹ በተደጋጋሚ የአብያተ ክርስትያናትና የገዳማት እድሳት ምክንያት ጠፍተዋል። ከቅድመ ክርስትያናዊ የጥበብ ስራዎች መካከል እስካሁን ያለው ትክክለኛነቱ የተረጋገጠው ብቸኛ ስዕል የአቡነ ገሪማ የወንጌሎች የድርሳን ውስጥ ምስል ነው። ጎንደር የሚገኘው የደብረብርሀን ስላሴ ቤተክርስቲያን ስዕሎች (እ.ኤ.አ ከ1150 እስከ 1270)የነበረው የዛግዌ ስርወ መንግስት በስነ ጥበብ፣ በኪነ ሕንፃ እንዲሁም በስነ ፅሑፍ የላቀ ደረጃ ላይ መድረሱን የታሪክ ሊቃውንት እንዲሁም የተለያዩ ድርሳናት የሚመሰክሩ ሲሆን፤ ክርስትያናዊ ስዕል አብሮ በልፅጎ እንደነበርም ከመውደም የተራረፉ የግድግዳ ላይ ስዕሎች እንደሚመሰክሩ የአበባው ፅሁፍ ያሳያል። በተለይም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትና ይበልጡኑ እየተስፋፋ በመጣበት ከ14ኛው ክፍለ ዘመን አንስቶ የቁም ጽሕፈት፣ ክርስትያናዊ ስነ ጽሑፍ እንዲሁም ስነ ስዕል አብረው ዳብረዋል። የኢትዮጵያ ስነ ጥበባዊ ትውፊት ባልተቋረጠ ቅብብሎሽ ከዘመን ዘመን ለመቀጠሉ አንደኛው ምክንያት በየጊዜው የሚነሱትን ፈተናዎች ተቋቁማ ኢትዮጵያ እንደአገር መቀጠል መቻሏ ነው ሲሉ ፖላንዳዊው የስነ ጥበብ ታሪክ እና የስነ ስብ ተመራማሪ ስታኒስላቭ ኮይናትስኪ 'ኢትዮፒያን አይከንስ' በተባለው መጽሐፋቸው ያትታሉ። ምንም እንኳ ከቀረው ዓለም ክርስትያናዊ ስነ ስዕል ጋር የይዘትና የቅርፅ ተመሳሳይነትን መያዙ ባይቀርም፤ የኢትዮጵያ ክርስትያናዊ ስነ ስዕል የራሱ ልዩ መገለጫዎችም አሉት። ኮይናትስኪ በየጊዜው ከምዕራባዊውም ከምስራቃዊውም ዓለም ጋር ያዳበረቻቸው የቻለ ግንኙነት አሻራውን የቤተ ክርስቲያን ስነ ስዕል ላይ ማሳረፉን ይጠቅሳሉ። ለዚህም በምሳሌነት የግሪክ፣ የኮፕት (የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን)፣ የኑቢያ እንዲሁም የአርመን ዱካዎች መስተዋላቸውን በአስረጅነት ይጠቅሳሉ። ይሁን እንጅ የኢትዮጵያ መልክዓ ምድራዊ እውነታ እና በከፊልም በእርሱ ላይ ተመስርቶ ለምዕተ ዓመታት ያህል ከቅርብ የአፍሪካ አገራት እንኳ ተነጥላ መቆየቷ በመሰረታዊነት የራሷ የሆነ ልዩ ቤተ ክርስቲያናዊ የአሳሳል ጥበብን ታዳብር ዘንድ አስችሏታል። ለምሳሌም በምዕራብ፣በመካከለኛውና በደቡባዊ አፍሪካ የስነ ቅርጽ ጥበብ በዋናነት ተመራጭ የስነ ጥበብ ዘርፍ ሲሆን የኢትዮጵያ ክርስትያናዊ ስነ ጥበብ ግን ዐብይ መገለጫው ስነ ስዕል ነው። ጎንደር የሚገኘው የደብረብርሀን ስላሴ ቤተክርስቲያን ስዕሎች ቅዱስ ቀለማት ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ስነ ስዕል ልዩ መልኮች አንደኛው አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ቀለማት ግልጋሎት ላይ መዋላቸው ነው። ከጥቁርና ነጭ ቀለማት በተጨማሪ ሰማያዊ፣ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማት ብቻ ለስዕል ስራ ይውላሉ። የአበባው ጽሑፍ እንደሚያስረዳው እነዚህ ቀለማት እንደቅዱስና መለኮታዊ ቀለማት ይቆጠራሉ። እስከ 17ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ቀይ፣ ቢጫና አረንጓዴ ቀለማት በየአካባቢው ከሚገኙ ዕፆች ተጨምቀው ይሰሩ የነበረ ሲሆን ሰማያዊ ደግሞ ከውጭ አገራት እንዲመጣ ይደረግ ነበር። ጥልቀት አልባነት እና የጀርባ ከባቢ ያለመኖር በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ስነ ስዕል ውስጥ ጥልቀት፣ ርቀትና ቅርበት እንዲሁም የጀርባ ከባቢን የሚያሳይ ገጽታ ማየት ያልተለመደ ሲሆን ስዕሎቹም ባለ ሁለት አውታር ብቻ ናቸው። ኢትዮጵያዊያን "ቅርጽን ሳይሆን ኃሳብን" ነው የሚስሉት ሲሉ በሌላኛው 'ሜጀር ቲምስ ኢን ኢትዮፒያን ፔይንቲንግ ' መጽሐፋቸው የሚያስረዱት ኮይናትስኪ እንዲህ የሆነበትን ምክንያት ሲተነትኑ ለግለሰባዊ ስብዕና በአውሮፓዊያን የሚቸረውን ያህል አፅንዖት ስለማይሰጥ ነው ይላሉ። ደብረማርቆስ የሚገኙ የቤተክርስቲያን ስዕሎች የእይታ ቅብብሎሽ በኦርቶዶክሳዊው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የስዕል ጥበብ ተመልካቹ ስዕሉን የሚያየውን ያህል ስዕሉም ተመልካቹን ያያል ተብሎ ይታመናል። ይህም ሁኔታ ስዕሎች ኃይል እንዳላቸው እንዲታሰብ አስችሎታል። የሌሎች ምስራቃዊ አብያተ ክርስትያናትን ያህል የቅዱሳን ምስሎች አምልኮ ባይኖርም በኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንም ውስጥ ምስሎች ለጸሎት እንደሚያገለግሉ ኮይናትስኪ ይገልፃሉ። ለቅዱሳን ስዕል የሚሰጥ የገዘፈ ክብር ከሚስተዋልባቸው መንገዶች አንዱ ምስሎቹ የሚቀመጡበት ሁኔታ ነው፤ እንደአብነት ከቅድስት ማርያም ወይንም ከስቅለት ስዕሎችን ጨርቅ የሚደረግ መሆኑን ልብ ማለት ይቻላል። ደብረማርቆስ የሚገኙ የቤተክርስቲያን ስዕሎች የሰው ፊት አቀማመጥ የቤተ ክርስቲያን ምስሎች ባለሶስት አውታር ካለመሆናቸውም በላይ እንቅስቃሴ አይኖራቸውም። ብዙ ጊዜ ሰዎች፣ ቅዱሳን እና የመሳሰሉት ሲሳሉ እንቅስቃሴ አልባ ሆነው ነው። አልፎ አልፎ ብቻ ፈረስ ጋላቢ ቅዱሳን በተወሰነ ድርጊት ውስጥ ሆነው ይታያሉ። እንቅስቃሴንና አቅጣጫ በዓይን ውርወራ ወይንም የምልከታ አቅጣጫ ብቻ ይመላከታሉ። የሰው ልጅ ፊት ሶስት ዓይነት ብቻ አቀማመጦች ይኖሩታል። ቅዱሳን እና ፃድቃን ሙሉ በሙሉ ፊት ለፊት ሆነው ወይንም ሁለት ሶስተኛው ፊታቸው እየታየ ይሳላሉ። ይህ የሚሆንበት ምክንያት ምስሉ በተመልካቹ ላይ ኃይሉን እንዲፈነጥቅ ከማሰብም በመነሳት ነው። ኃጥኣን እና እርኩሳን ደግሞ ፊታቸው የጎንዮሽ ወይም አንድ አይናችው ብቻ እንዲታይ ይደረጋል። ደብረሲና ጎርጎራ የሚገኙ የቤተክርስቲያን ስዕሎች ያልታወቁ ሰዓሊያን በድርሳናት ውስጥ የሚሳሉ ስዕሎች ላይ የሰዓሊያን ስም ሰፍሮ የሚገኝባቸው አጋጣሚዎች አሉ። ይሁንና ኃይማኖታዊ ስዕሎችን መስራት እንደኃይማኖታዊ ተግባር ስለሚቆጠር የሰዓሊያን ስም እምብዛም አይገኝም። ብዙ ጊዜም ሰዓሊያን የአብያተ ክርስትያናትን ግድግዳዎች በኃይማኖታዊ ስዕሎች እንዲያስውቡ ስራ ሲሰጣቸው ተግባራቸውን ከመጀመራቸው አስቀድሞ ሱባዔ ገብተው መንፈሳዊ አመራርን ይሽታሉ።
53511869
https://www.bbc.com/amharic/53511869
ከኢትዮጵያ ለጂቡቲ ተላልፎ የተሰጠው አብራሪ በረሃብ አድማ ላይ ነው ተባለ
ኢትዮጵያ ውስጥ ተይዞ ለጂቡቲ ተላልፎ የተሰጠውና በአገር ክህደት የተከሰሰው ጂቡቲያዊው የአየር ኃይል አውሮፕላን አብራሪ እስር ላይ እያለ ለሁለተኛ ጊዜ የረሃብ አድማ እያደረገ መሆኑ ተነገረ።
በጂቡቲ የተለያዩ አገራት ጦር ሰፈሮች ይገኛሉ በእስር ላይ የሚገኘው የፉዐድ ዩሱፍ ጠበቃ ለፈረንሳይ ሬዲዮ እንደገለጹት የአብራሪው የጤና ሁኔታ ችግር ላይ ቢሆንም ምግብ ለመብላት ፈቃደኛ አይደለም። በተጨማሪም ላለበት የጤና ችግር ህክምና እንዲያገኝ ወደ ሆስፒታል ቢወሰድም ልመረዝ እችላሁ በሚል ምክንያት ህክምና ለማግኘት እንደማይፈልግ ገልጿል ተብለዋል። አብራሪው ወታደራዊ አውሮፕላን ይዞ ከአገር ለመውጣት ሙከራ አድርጓል በሚል የቀረበበትን ክስ ውድቅ አድርጎታል። የጂቡቲ ወታደራዊ ባለስልጣናትን በሙስና በመክሰስ ባለፈው መጋቢት ወር ወደ ኢትዮጵያ በመሸሽ ጥገኝነት ለማግኘት ቢሞክርም ተይዞ በሚያዚያ ወር ላይ ለአገሩ መንግሥት ተላልፎ መሰጠቱ ተነግሯል። ፉዐድ ለጂቡቲ ተላልፎ ከተሰጠ በኋላ በአገር ክህደት ተከሶ በእስር ላይ የሚገኝ ሲሆን ቀደም ሲል ያለበት እስር ቤት ኃላፊዎች በአግባቡ እንዳልያዙት የከሰሰ ሲሆን ቤተሰቦቹም መንግሥት እያንገላታቸው መሆኑን በመግለጽ ተናግረው ነበር። ነገር ግን የጂቡቲ መንግሥት የቀረበበትን ክስ ሐሰት መሆኑን በመግለጽ አስተባብሏል። ይህንን ተከትሎም የሰብአዊ መብት ተከራካሪው ድርጅት ሂማን ራይትስ ዋች የጂቡቲ መንግሥት የቀረበበትን ክስ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል። አብራሪው ሰቆቃ እንደተፈጸመበት የሚገልጽ ቪዲዮ ከእስር ቤት ሾልኮ ከወጣ በኋላ ባለፈው ሰኔ ወር ላይ ጂቡቲ ውስጥ ድርጊቱን የሚቃወሙ ዜጎች አደባባይ ወጥተው እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል። በኢትዮጵያ የጂቡቲ አምባሳደር ሞሐመድ ኢድሪስ ፋራህ ከዚህ ቀደም ለሮይተርስ ፓይለቱ የታየዘው ሚያዝያ ወር ላይ አዲስ አበባ ውስጥ እንደሆነ ገልጸው፤ ወደ ኢትዮጵያ የሸሸው አውሮፕላን ይዞ ወደ ኤርትራ ለመጓዝ ሙከራ ካደረገ በኋላ እንደሆነ አመልክተው ነበር።
52138509
https://www.bbc.com/amharic/52138509
ኮሮናቫይረስ፡ ኢትዮጵያ የሞባይል ባንኪንግን ዘርፍ ለአገር በቀል ኩባንያዎች ክፍት አደረገች
በባንኮችና በጥቃቅን የገንዘብ ድርጅቶች ተይዞ የነበረውን የሞባይል ባንኪንግ ዘርፍ ለሌሎችም ድርጅቶችም ክፍት እንዲሆን ብሔራዊ ባንክ ባወጣው አዲስ መመሪያ ወሰነ።
ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የጥሬ ገንዘብን በመጠቀም የሚፈጠረው ግንኙነት ለመቀነስ ኢትዮጵያ በሞባይል ባንኪንግ ያላትን ህግ በማላላት የአገር ውስጥ ባለኃብቶች እንዲሰማሩበት ክፍት አድርጋለች። ይህም ንክኪን ለመቀነስና ህዝቡ ሙሉ በሙሉ ጥሬ ገንዘብ መጠቀምን ያቆማል ተብሏል። •ኢትዮጵያ፡ ሁለት ሰዎች ከኮቪድ-19 መዳናቸው ተገለፀ •በአማራ ክልል ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የትምህርት ተቋማት ለመጠለያነት ተዘጋጁ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው አዲስ መመሪያ መሰረትም ፈቃድ ለማውጣት የሚፈልጉ አምሳ ሚሊዮን ብር፣ ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆን እንዲሁም 10 ባለድርሻ ያሉት አክሲዮን መሆን እንዳለባቸው አስታውቋል። መመሪያውም ከትናንትና መጋቢት 24፣2012 ዓ.ም ጀምሮ በተግባር ላይ የዋለ ሲሆን በቀን ስምንት ሺ ብር ያህል እንዲሁም በወር 60ሺ ብር ማውጣት ይቻላል። የሞባይል ባንኪንግ ፈቃድ ያላቸው ኩባንያዎችም ገንዘብ የማስቀመጥ፣ ብድር፣ ኢንሹራንስ እንዲሁም ሌሎች አገልግሎት መስጠት ያስችላቸዋል። በመንግሥት ይዞታ ስር ያሉ ተቋማትም የሞባይል ባንኪንግ ፈቃድ መጠየቅ እንደሚችሉም ባንኩ በመመሪያው አስቀምጧል፥ ይህ ውሳኔም እንደ ኢትዮ ቴሌኮምም ሆነ ሌሎች ድርጅቶች እንዲወዳደሩ በር ይከፍትላቸዋል። •"ከቤት አትውጡ የሚሉን ልጆቼን ምን እንዳበላቸው ነው?" •በኮሮናቫይረስ የወረርሽኝ 'ዘመን' ተስፋ የሚሰጡ 5 ነገሮች በርካታ ኢትዮጵያውያን ግብይይት የሚፈፅሙት በጥሬ ገንዘብ ሲሆን የሞባይል ባንኪንግ እንደ ሌሎች አገራት የተለመደ አይደለም። በተለያየ ደረጃ የሚገኙ ባለስልጣናት ብዙዎች ቤታቸው እንዲቀመጡና በተጨናነቁ ስፍራዎች መገኘት እንዲቆጠቡ ምክርም ቢለግሱም ብዙዎች ወደ ባንኮች የሚያደርጉትን ጉዞ አልቀነሱም፤ በጥሬ ገንዘብ የሚደረጉ ንክኪዎችም አልቀነሱም። አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ከትራንስፖርት ጀምሮ የተለያዩ ክፍያዎችን የሚፈፅመው በጥሬ ገንዘብ ነው።
53477383
https://www.bbc.com/amharic/53477383
ኮሮናቫይረስ፡ ውጤታማ የተባለው የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ የኮቪድ-19 ክትባት የሚሰራው እንዴት ነው?
በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ተሰርቶ ሙከራ እየተደረገበት ያለው የኮሮናቫይረስ ክትባት የሰውነትን የመከላከል ሥርዓትን እንደሚያጎለብትና ደኅነነቱ የተጠበቀ መሆኑ ተገለፀ።
በክትባቱ ሙራ ላይ በበጎ ፈቃደኝነት የተሳተፉ 1,077 ሲሆኑ የተሰጣቸው ክትባት ጸረ ተህዋሲ [አንቲቦዲ] እንዲያዳብሩና ነጭ የደም ህዋሳታቸው ኮሮናቫይረስን መከላከል እንዲችል ሆኗል ተብሏል። የዚህ ምርምር ውጤት ግኝት በጣም ተስፋ ሰጪ የተባለ ሲሆን፤ ነገር ግን ይህ በሽታውን የመከላከያ አቅምን ለማግኘት በቂ መሆን አለመሆኑ ያልታወቀ ሲሆን ሰፊ ሙከራ እየተካሄደም ይገኛል። ይህ ምርምር የተደረገው በቅድሚያ ክትባቱ ለበርካታ ሰዎች ቢሰጥ ደኅንነቱ የተጠበቀ ይሆናል ወይ የሚለውን ለማረጋገጥ ነው ተብሏል። ክትባቱ የሚሰራው እንዴት ነው? ይህ ባልተጠበቀ ፍጥነት የተሰራው ክትባት ሲኤችኤዲ0ኤክስ1 ኤንኮቪ-19 (ChAdOx1 nCoV-19) ይባላል። የተሰራው ቺምፓንዚዎች ላይ ጉንፋን ከሚያስከትል ቫይረስ ዘረመል ተፈበርኮ ነው። ቫይረሱ በጥንቃቄ በላብራቶሪ ውስጥ የተሰራ ሲሆን በቅድሚያ በሰዎች ላይ ኢንፌክሽኖች እንዳያስከትል እንዲሁም ደግሞ "ኮሮናቫይረስ እንዲመስል" ተደርጓል። • በኮሮናቫይረስ ሰበብ ትኩረት የተነፈጉት የዓለማችን ገዳይ ችግሮች • ሩሲያ የኮሮናቫይረስ ክትባት መረጃዎችን ለመመንተፍ ሞክራለች መባሏን ውድቅ አደረገች • የሩሲያ የመረጃ መረብ ሰርሳሪዎች የኮቪድ-19 ክትባት ምርምርን ኢላማ ማድረጋቸው ተነገረ ተመራማሪዎች ይህንን ያደረጉት ኮሮናቫይረስ የሰው ልጅ ህዋሶች በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚጠቀምበትን የ"ስፓይክ ፕሮቲን" ጄኔቲክ መመሪያዎችን በመውሰድ ለሚያመርቱት ክትባት ተጠቅመው ነው። ይህም ማለት ክትባቱ ኮሮናቫይረስን የሚመስል ሲሆን የመከላከል ሥርዓቱም እንዴት አድርጎ ማጥቃት እንዳለበት ይለማመዳል ማለት ነው። ጸረ ተህዋሲዎችና ቲ ህዋሳት ምንድን ናቸው? እስካሁን ድረስ ስለ ኮሮናቫይረስ ሲወራ ትኩረቱ በአብዛኛው ያለው አንቲቦዲዎች ላይ ነው፤ ነገር ግን እነዚህ የመከላከያ ኃይላችን አንድ ክፍል ብቻ ናቸው። አንቲቦዲዎች ትንንሽ ፕሮቲኖች ሲሆኑ የተሰሩትም ቫይረሱ ላይ በሚጣበቁት የመከላከል ሥርዓታችን ነው። አንቲቦዲዎችን እንዳይሰሩ ማድረግ ከተቻለ ኮሮናቫይረስን እንዳይሰራ ያደርገዋል። ቲ ሴል ደግሞ የነጭ የደም ሴሎች ዓይነት ሲሆኑ፤ የመከላከል ሥርዓታችንን በማስተባበር እና የትኞቹ ህዋሶች እንደተጠቁና እንደወደሙ ለመለየት ያገለግላሉ። ሁሉም ውጤታማ የሆኑ ክትባቶች አንቲቦዲን እና ቲ ሴልን ምላሽ ያካተቱ ናቸው። የቲ ሴሎች ቁጥር ክትባቱን ከወሰዱ ከ14 ቀናት በኋላ ከፍ ያለ ሲሆን የአንቲቦዲዎች ደግሞ ከክትባቱ ከወሰዱ ከ28 ቀን በኋላ ከፍ ብሎ ታይቷል። ምርምሩ የረዥም ጊዜ የመከላከል አቅም ምን እንደሚመስል ለመለየት በቂ ጥናት አላደረገም። ደህንነቱ የተጠበቀ ነው? አዎ፤ ነገር ግን የጎንዮሽ ጉዳት አለው። ክትባቱን በመውሰድ የሚመጣ አደገኛ የሆነ የጎንዮሽ ጉዳት የለውም፤ ነገር ግን ክትባቱን ከወሰዱ 70 በመቶ ያህል ሰዎች ትኩሳት አልያም ራስ ምታት አዳብረዋል። ተመራማሪዎቹ ይህ ደግሞ በፓራሳታሞል የሚድን ነው ሲሉ ተናግረዋል። ፕሮፌሰር ሳራ ጊልበርት "ክትባታችን የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመቆጣጠር ያገለግላል ከማለታችን በፊት በርካታ ሥራ መሰራት አለበት፤ ነገር ግን ይህ የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት ተስፋ ሰጪ ነው" ብለዋል። ክትባቱ ውጤታማ ሆኖ ለአገልግሎት የሚበቃ ከሆነ ዩናይትድ ኪንግደም አስቀድማ 100 ሚሊዮን ክትባቶችን አዛለች። የምርምሩ ቀጣይ ሥራ ምንድን ነው? እስካሁን ድረስ ያለው የክትባቱ ምርምር ውጤታማ ነው። ነገር ግን ክትባቱ ለሌሎች ቢሰጥ ደኅንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ጥናቱ እስካሁን ድረስ ሰዎች በኮሮናቫይረስ እንዳይታመሙ ይከላከላል ወይስ በኮቪድ-19 ቢያዙ የሚያሳዩትን ምልክት ይቀንሳል የሚለውም አልታወቀም። በዩናይትድ ኪንግደም ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች በሚቀጥለው ሙከራ ላይ ይሳተፋሉ። ይሁን እንጂ ሙከራው ወደ ሌሎች አገራትም እየተስፋፋ ሲሆን ለዚህም ምክንያት ነው የተባለው በዩናይትድ ኪንግደም ያለው የቫይረሱ ስርጭት መጠን እየቀነሰ በመሆኑ የክትባቱ ውጤታማነትን ለማወቅ አስቸጋሪ ስለሚያደርገው ነው። በአሜሪካ 30 ሺህ ሰዎች፣ በደቡብ አፍሪካ 2000 ሰዎች እንዲሁም በብራዚል 5000 ሰዎች የሚሳተፉበት ሙከራ ይደረጋል። ከዚህ በኋላም "ተግዳሮታዊ ሙከራ" በመባል የሚታወቀው የምርምር ደረጃ የሚካሄድ ሲሆን በዚህም ወቅት ክትባቱን የተከተቡ ሰዎች ሆን ተብሎ በኮሮናቫይረስ እንዲያዙ ይደረጋሉ። ምንም እንኳ መድኃኒቱ ስላልተገኘ የሙያ ሥነ ምግባር ጥያቄ ቢነሳም ይህ ግን መከናወኑ አይቀርም ተብሏል። ክትባቱን መቼ አገኛለሁ? ከተሳካ የኮሮናቫይረስ ክትባት ውጤታማ መሆኑ የሚረጋገጠው በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ ነው። ነገር ግን ለሕዝብ በስፋት ጥቅም ላይ በዚህ ወቅት አይውልም። የጤና ባለሙያዎች ባላቸው የሥራ ሁኔታና ተጋላጭነት፣ በእድሜ በመለየት ክትባቱን በቅድሚያ እንዲያገኙ ይደረጋል። ይሁን እንጂ ሁሉም ነገር በእቅዱ መሰረት ከሄደ ክትባቱ ለተለያዩ ማኅበረሰብ ክፍሎች በሚቀጥለው የፈረንጆች ዓመት መጀመሪያ ወራት ላይ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። ቦሪስ ጆንሰን እንዳሉት "በጣም ተስፋ አለኝ፣ ነገር ግን መቶ በመቶ እርግጠኛ ሆኜ በዚህ ዓመት ወይንም በሚቀጥለው ዓመት ክትባቱን እናገኛለን ማለት ማጋነን ነው። ገና እዚያ አልደረስንም" ብለዋል። የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ክትባት እዚህ ደረጃ ሲደርስ የመጀመሪያው አይደለም።፤ በቻይናና በአሜሪካ የሚገኙ የተመራማሪዎች ቡድኖችም ተመሳሳይ ውጤት ለህትመት አብቅተዋል።
50052016
https://www.bbc.com/amharic/50052016
አሜሪካ ቱርክ ላይ ማዕቀብ ጣለች
አሜሪካ ቱርክ በሶሪያ ድንበር ላይ እየወሰደችው ላለው የጦር ጥቃት ምላሽ ሁለት የቱርክ ሚኒስትር መሥሪያ ቤቶችንና ሶስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ ጣለች።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለቱርኩ አቻቸው ጣይብ ኤርዶጋን ስልክ የደወሉ ሲሆን የስልክ ልውውጡም በፍጥነት ተኩስ የሚቆምበት ላይ እንደነበር ምክትል ፕሬዝዳንቱ ማይክ ፔንስ ተናግረዋል። ማይክ ፔንስ አክለውም ወደ ቱርክ " በተቻለ ፍጥነት" እንደሚሄዱ ተናግረዋል። • ትራምፕ ቱርክን አስጠነቀቁ • ቱርክ ከሶሪያ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ላይ በፈፀመችው ጥቃት በርካቶች ተገደሉ • በአፋር ክልል በተፈፀመ ጥቃት 17 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች ቆስለዋል የሶሪያ ጦር ወደ ሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል የገባ ሲሆን ይህም በቱርክ ከሚረዱ አማፂያን ተግዳሮት ገጥሞታል። የሶሪያ ጦር ወደ አካባቢው የተሰማራው እስከ ባለፈው ሳምንት ድረስ የአሜሪካ አጋር ከነበረው በኩርዶች ከሚመራው ጦር ጋር ከተደራደረ በኋላ ነው። ቱርክ ከሶሪያ ጋር በሚያዋስናት አካባቢ ጦሯን አሰማርታ ውጊያ የጀመረችው በአካባቢው "ደህንነቱ የተጠበቀ ቀጠና" ለመፍጠር መሆኑን ደጋግማ ትናገራለች። ይህ "ደህንነቱ የተጠበቀ ቀጠና" ስፍራ በሶሪያ ግዛት ውስጥ 30 ኪሎ ሜትርን የሚሸፍን ሲሆን፣ በዚሁ ቦታ ቱርክ በአሁን ሰዓት በግዛቷ ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ 2 ሚሊየን የሶሪያ ስደተኞችን የማስፈር ሃሳብ አላት። እነዚህ ስደተኞች አብዛኞቹ ኩርዶች ስላልሆኑ ይህንን የቱርክ ሀሳብ የሚተቹ አካላት ጉዳዩ አንድ ብሔር ላይ ያተኮረ ጥቃት ነው ሲሉ የአንካራን መንግሥት ይተቻሉ። ሰኞ ዕለት ከዋሺንግተን ለጋዜጠኞች ቃላቸውን የሰጡት የገንዘብ ሚኒስትሩ ስቴቨን ማንቺን ማዕቀቡን "በጣም ጠንካራ" በማለት የቱርክ ኢኮኖሚን እንደሚጎዳ ተናግረዋል። የአሜሪካ ገንዘብ ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ ላይ ማዕቀቡ ሁለት የቱርክ ሚኒስትር መስሪያ ቤቶችን የሚመለከት ሲሆን እነዚህ ተቋማትም የመከላከያና የኃይል እንዲሁም የሀገር ውስጥ ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች ናቸው ብለዋል። " የቱርክ መንግሥት ባህሪ ንፁኃንን ለአደጋ ያጋለጠ እንዲሁም ቀጠናውን የሚያተራምስ ነው። በተጨማሪም አይኤስን ለማሽመድመድ የሚደረገውን ጥረት ፍሬ ቢስ የሚያደርግ ነው" ይላል መግለጫው። ማይክ ፔንስ በበኩላቸው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከቱርክ አቻቸው ጋር በስልክ ማውራታቸውን ገልጠዋል። አሜሪካ የቱርክ ያልተገባ ባህሪ በሶሪያ በእስር ላይ ይገኙ የነበሩ የአይ ኤስ ጦር አባላት እንዲለቀቁ ምክንያት ሆኗል ስትል ተናግራ ነበር። የአውሮፓ ሕብረትም የሕብረቱ አባል ሀገራት ወደ ቱርክ የሚላኩ የጦር መሳሪያዎችን እንዳይልኩ ሀሳብ እንዳለው ገልጾ ነበር። በምላሹም ቱርክ ከአውሮጳ ሕብረት ጋር ያላትን የትብብር ማዕቀፍ " አድሏዊና የሕግ መሠረት በሌለው ርምጃው የተነሳ" ዳግመኛ ለመፈተሽ እንደምትገደድ አስታውቃ ነበር። • "የተርባይኖች መቀነስ በሚመነጨው ኃይል ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም" የህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ • በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ የሞቱ ሰዎች አጽም ለቤተሰቦቻቸው እየተሰጠ ነው በግጭቱ እስካሁን ድረስ 160 ሺህ ሰዎች ቀያቸውን ጥለው መሸሻቸውን የተባበሩት መንግሥታት ያስታወቀ ሲሆን 50 ንፁኃን በሶሪያ ውስጥ 18 ደግሞ በደቡብ ቱርክ ድንበር ላይ መገደላቸውን መረጃዎች ያሳያሉ። የኩርድ ኃይሎች 56 ተዋጊዎቻቸው መገደላቸውን የተናገሩ ሲሆን ቱርክ በበኩሏ 3 ወታደሮቿና 16 አፍቃሪ ቱርክ አማፂያን መሞታቸውን ገልጣለች። ቱርክ ወደ ሶሪያ ጦሯን ያዘመተችው ፕሬዝዳንት ትራምፕ በድንገት በስፍራው የነበረ የአሜሪካ ጦር እንዲወጣ ካዘዙ በኋላ ነው። ይህ የአሜሪካ እርምጃ ቱርክ በአካባቢው በሚገኙ በኩርዶች የሚመራው ጦር ላይ ጥቃት ለመክፈትና የድንበር ከተሞችን በእጇ ለማስገባት ሰበብ ሆኗታል።
51087785
https://www.bbc.com/amharic/51087785
ጃፓናዊው ቢሊዬነር ወደ ጨረቃ አብራው የምትጓዝ 'ውሃ አጣጭ' እየፈለገ ነው
ጃፓናዊው ቢሊዬነር ዩሳኩ ማይዛዋ በስፔስ ኤክስ መንኩራኩር ወደ ጨረቃ አብራው የምትጓዝ ሴት ጓደኛ እየፈለገ እንደሆነ አሳውቋል።
በፋሽን ኢንዱስትሪ ላይ የተሰማራው የ44 ዓመቱ ዩሳኩ ወደ ጨረቃ የሚጓዝ የመጀመሪያው ሲቪል ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ጉዞው የዛሬ ሁለት ዓመት በግሪጎሪ አቆጣጠር 2023 ላይ የሚከናውን ሲሆን ከ1972 በኋላ ወደ ጨረቃ የሚደረግ የመጀመሪያው ጉዞ ሊሆን ይችላል። በመረጃ መረብ አማካይነት ፍላጎቱን ይፋ ያደረገው ጎልማሳው ቱጃር ይህንን 'ልዩ ጉዞ' አብራኝ የምትጓዝ ልዩ እንስት ከወዴት አለች? እያለ ነው። ከ27 ዓመቷ ተዋናይት ፍቅረኛው ጋር በቅርቡ የተለያየው ዩሳኩ በድረ-ገፁ ላይ ባለ መረጃ መስበስበያ ላይ ሴቶች መስፈርታቸውን እንዲያስቀምጡ አቤት ብሏል። «ብቸኝነትና ባዶነት ሊጠናወቱኝ እየሻቱ ስለሆነ መፍትሄው አንዲት ሴትን ማፍቀር ነው» ሲል በድረ-ገፁ አሥፍሯል። «የሕይወት አጋር እፈልጋለሁ፤ ከወደፈቷ አጋሬ ጋር ከውጭው ምህዋር ሆኜ የዓለም ሰላምን እሰብካለሁ» ሲል አክሏል። ሶስት ወራት የሚቆይ የዩሳኩ ውሃ አጣጭ ፍለጋ ሂደት ብዙ መስፈርቶችን አዝሎ በድረ-ገፁ ላይ ሰፍሯል። በፍቅር ግንኙነት ውስጥ ያልሆነች፣ ዕድሜዋ ከ20 በላይ፣ ቅን አስተሳሰብ ያላትና ወደ ሕዋ ለመብረር ዝግጁ የሆነች የዩሳኩ መስፈርቶች ናቸው። የማመልካቻው ቀን መዝጊያ ጥር 8/2012 ሲሆን አሸናፊዋ ሴት በመጋቢት ወር መጨረሻ ይፋ ትሆናለች። አንድ ባንድ ውስጥ በከበሮ መቺነት ያገለግል የነበረው ዩሳኩ ወጣ ባሉ ድርጊቶቹ ይታወቃል። በዚህ ወር መጀመሪያ እንኳ በትዊተር ገፁ ላይ የሚሰፍሩ መልዕክቶቹን ለሌሎች ያጋሩ 100 ሰዎችን መርጬ 925 ሺህ ዶላር አከፋፍላለሁ ማለቱ አነጋጋሪ ነበር። ዞዞ የተባለ የልብ ዲዛይን ባለቤት የሆነው ዩሳኩ የተጣራ ትርፉ 3 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ ይገመታል።
news-55079318
https://www.bbc.com/amharic/news-55079318
ቴክኖሎጂ፡ ስለምን ፌስቡክ እና አፕል አይስማሙም ?
የኩባንያዎች የንግድ ውድድር ትልልቅና ተፎካካካሪ የሆኑት ኮካ ኮላ እና ፔፕሲን፣ ቦይንግ እና ኤርባስን፣ ማክዶናልድ እና በርገር ኪንግን አንድ የጋራ ነገር እንዲኖራቸው አድርጓል።
የአፕሉ ቲም ኩክና የፌስቡኩ ማርክ ዙከርበርግ ይህም በልጦ ለመገኘት የሚደረግ ፍልሚያ፤ ለዚያም ነው የፌስቡክ እና የአፕል ውዝግብ በጣም ሳቢ የሆነው። ሁለቱም ትልልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያ መሆናቸው ላይ ነው ተመሳሳይነታቸው የሚያበቃው። ከሞላ ጎደል ሁሉም የፌስቡክ ገቢዎች የሚገኙት ከማስታወቂያ ሲሆን አፕል ደግሞ በአብዛኛው ከቁሳቁስ እና ከመተግበሪያ ሽያጭ ነው ገቢው። እንደ እውነቱ ከሆነ ሁለቱ ኩባንያዎች እርስ በርሳቸው አይወዳደሩም፣ ግን ደግሞ አይዋደዱም።ለዓመታት የአፕሉ አለቃ ቲም ኩክ ፌስቡክ ተጠቃሚዎቹን እንደ ምርት በመቁጠር ከማስታወቂያ ገንዘብ ከማግኘቱም በላይ በፍጥነት የግል ሚስጢርን ያባክናል ይላሉ። የፌስቡኩ አቻቸው ማርክ ዙከርበርግ በበኩላቸው የአፕል ምርቶች ውድ በመሆናቸውና ፌስቡክን ለመተቸት ድብቅ ዓላማ አለው በማለት ይተቻሉ።እንደ ኒው ዮርክ ታይምስ ዘገባ ባለፈው ዓመት አፕል የፌስቡክ ማበልጸጊያ መሣሪያዎችን እስከማቋረጥ ደርሷል። ባለፈው ሳምንት አዲስ እሰጣ አገባ ተፈጥሮ ግንኙነቶችን የበለጠ የከፋ አድርጎታል፡፡ በቁስል ላይ እንጨት መስደድ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ አፕል ሰዎች መረጃዎቻቸውን ይበልጥ እንዲቆጣጠሩ የሚያደርግ 'አፕ ትራኪንግ ትራንስፓረንሲ' የተሰኘ መተግበሪያ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ይህም ቀደም ሲል የነበረውን አሠራር በመቀየር ደንበኞች እንደ ፌስቡክ ያሉ መተግበሪያዎቻቸውን እየመረጡ መረጃዎችን እንዲጠቀሙ ያግዛል። ከፍተኛ ትርፍ ለማግኘት ያለሙ ማስታወቂያዎችን ለሚሸጠው ፌስቡክ ይህ ትልቅ ችግር ነው። ይህም ንግዳቸውን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጎዳ በግልፅ ይናገራሉ። አፕል መተግበሪያዎችን የሚሠሩ እንዲዘጋጁ ጊዜ ለመስጠት የታቀዱትን ለውጦች እስከሚቀጥለው ዓመት ድረስ ላለመተግበር ወስኗል።ጄን ሆቫርት ባለፈው ሳምንት ለውጡ ለምን እንደዘገየ በሚገልጽ ደብዳቤ ላይ ዙከርበርግን ከመውቀስ ወደ ኋላ አላሉም። "የፌስቡክ ሥራ አስፈፃሚዎች በተቻለ መጠን ብዙ መረጃዎችን መሰብሰብ ዓላማቸው መሆኑን ግልፅ አድርገዋል" በማለት።"ይህም የተጠቃሚዎች ግላዊ ምስጢርን አለማክበር ተስፋፍቶ መቀጠሉን ያሳያል" ብለዋል። ፌስቡክም ለዚህ ምላሽ ሰጥቷል። "ዋናውን የገቢ ጉልበታቸውን ተጠቅመው ለራሳቸው መረጃ እየሰበሰቡበት ተፎካካሪዎቻቸውም ተመሳሳይ መረጃን እንዳይጠቀሙ በሚባል እየከለከሉ ነው" ብለዋል። "የሚናገሩት ስለ ግላዊ መረጃ ቢሆንም ዋናው ነገር የገቢ ትርፍ ነው" ሲሉ ገልጸዋል። ይህም ከፌስቡክ የበለጠ የንግድ አምሳያ አለው በሚል ኩራት ለሚሰማው አፕል በቁስሉ ላይ እንጨት መስደድ ነው። እስከ 2010 ድረስ የአፕል መስራች የሆነው ስቲቭ ጆብስ ፌስቡክን በግላዊ መረጃ ዙሪያ ማስጠንቀቁ ተዘግቧል። ፌስቡክ ማስታወቂያዎችን ለመሸጥ መረጃዎችን መጠቀም ይችል ነበር ነገር ግን "ያንን ላለማድረግ መርጠናል" ብለዋል የአፕል የወቅቱ አለቃ ኩክ እ.አ.አ በ 2018። የሲሊከን ቫሊው ባለሃብት እና የዙክድ መጽሐፍ ደራሲ ሮጀር ማክናሚ የፌስቡክ አድናቂ አይደሉም።"የአፕል አንዱ ባህል ደንበኞቹን ማብቃት ነው። የፌስቡክ ባህል ደግሞ ተጠቃሚዎቹን መበዝበዝ ነው" ብለዋል።"ከታሪክ አኳያ እንኳን ቢታይ አፕል ሌሎች ሰዎችን ለመንቀፍ ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩትም ይህን ላለማድረግ መርጧል። የፌስቡክ አሠራር ምን ያህል አናዳጅ እንደሆነ ይህ ማሳያ ይመስለኛል" ሲሉም ተናግረዋል።ፌስቡክስ ምክንያት አለው? እውነት አፕል ተወዳዳሪዎችን ለማፈን የገበያ የበላይነቱን ለመጠቀም እየሞከረ ነውን? የአፕል የማስታወቂያ ገቢ በአንፃራዊነት አነስተኛ ቢሆንም ሞርጋን ስታንሊ እንደሚሉት በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ይህ ገቢው በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያድግ ተተንብይዋል።ስለዚህ የፌስቡክ የተጠቃሚዎች መረጃን በመያዝ ለራሱ ገቢ ማግኛ ለማድረግ እየሞከረ ነው?ይህ እንግዳ ነገር ሊሆን ይችላል። ማደብዘዝ አሁን አሁን በጣም ከተለመዱት የአሜሪካ የቴሌቪዥን ማስታወቂያዎች አንዱ የአፕል የግላዊ መረጃ ጥበቃ ዘመቻ ነው።"አንዳንድ ነገሮች መጋራት የለባቸውም። አይፎን በዚህ በኩል እንድትጠብቁ ያግዛችኋል" የሚል ነው የማስታወቂያ ዘመቻ አለው።አፕል የግል ምስጢራዊነት ተወዳጅ መሆኑን እና ይህንንም ቀለል አድርጎ ማየት እንደማይገባ ያምናል። ኢ-ፍትሃዊነትአፕል ግን በሁሉም ዘርፍ ገበያውን በብቸኝነት /ሞኖፖሊ/ እንደተቆጣጠረ ይነገርለታል።አፕ ስቶርን በመጠቀም መተግበሪያ የሚሠሩት ላይ ኢ-ፍትሃዊ ሕግን ይጭናል ከተባለ በኋላ በተከታታይ ሕዊ ሂደት ውስጥ ገብቷል።በተጨማሪም ኩባንያው ተገቢውን የግብር ክፍያን አይከፍልም የሚሉ ክሶች ቢነሱበትም ደርጅቱ ግን ያስተባብላል። የግላዊነት እና ከምንም ጋር ያለመነካካት ክርክር በእርግጥ ከዙከርበርግ ጋር ይመደባል።እ.አ.አ በ2014 ኩክ ደንበኞቹን እንደ ምርት በመቁጠር ፌስቡክን ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ ሲተቹ የፌስቡክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ለታይም መጽሔት ምላሽ ሰጥተው ነበረ። "የሚያበሳጨኝ ብዙዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ የማስታወቂያ ንግድ አሠራርን ከደንበኞች ጋር የማይስማሙ እንደሆነ አደርገው የሚያመሳስሉት ናቸው።" "እንደምታስቡት ለአፕል እየከፈላችሁ ስለሆነ ከእነሱ ጋር እንደምትስማሙ ነው? ከእነሱ ጋር ብትስማሙ ኖሮ ምርቶቻቸውን በጣም ርካሽ ያደርጉ ነበር" ብለዋል። ይህ ምናልባት አንድ አሳማኝ ነጥብ አለው፤ በዚህም አፕል በዓለም ላይ በጣም ሀብታም ከሆኑ ኩባንያዎች አንዱ ነው። የስልክ ጦርነት የዚህ የጋራ ውጥረት ሌላው እንግዳ ነገር የሁለቱ ኩባንያዎች አንዱ በአንዱ ላይ ጥገኛ መሆናቸው ነው። አይፎን ላይ ፌስቡክ (ከዋትስአፕ እና ከኢንስታግራም ጋር) የማይገኝ ቢሆን ኖሮ ስልኩ ለብዙ ደንበኞች ዝቅ ያለ ደረጃ ይኖረው ነበር። በተቃራኒው ደግሞ ሰዎች ፌስቡክን በአይፎን ላይ መጠቀም ባይችሉ ኖሮ ሰዎች ሌሎች የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮችን ይፈልጉ ነበር?ሁለቱም ኩባንያዎች ጤናማ እና ጠንካራ የሥራ ግንኙነት ቢኖራቸው ትርጉም ይሰጣል የሚሉ በርካቶች ናቸው። ግን እንደዛ አይደለም። የአፕል ባለሙያ የሆኑት ካሮላይና ሚላኔሲ እንደሚሉት ሁለቱ ኩባንያዎች ዓለምን በተለየ መንገድ ከማየት ባለፈ በመካከላቸው ያለው ጥላቻ ባህላዊና ግላዊ ነው።"በፍልስፍና ረገድ የተለያዩ ናቸው" ይላሉ።"አፕልን እንመልከት። ፌስቡክ በደንበኞቻቸው ላይ ስላለው ጠባይ የሚያሳስባቸው ከሆነ በአፕል መሳሪያዎች ላይ ለምን ፌስቡክን እንደመተግበሪያ እንዲኖር ይረፈቅዳሉ?"ይህም ወደ ጉዳዩ ጫፍ ይደርሳል። እስካሁን እኒህ ሁለት ኩባንያዎች የማይስማሙ ናቸው።ይህ የስልክ ጦርነት ነበር ቢሆንም እውነታው ግን ግንኙነታቸው ስሜታዊ ነበር።አፕል አሁን እያቀረበ ያለው መተግበሪያ ግን ከዚህ ጦርነት አለፍ ያለ ነው። በዚህ ጉዳይ ግላዊ መረጃ ላይ ያላቸው አባዜ ለፌስቡክ ጥሩ አይደለም። አዳዲሶቹ ሕጎች ማኅበራዊ ድረ-አምባውን ይጎዱታል እየተባለ ነው።በትላልቅ ቴክኖሎጂዎች ውስጥ ከሚኖሩ ተወዳዳሪዎች መካከል የፌስቡክ እና የአፕል ከፊት ሲታይ በጣም አናሳ ሊሆን ይችላል። ጉግል የፌስቡክ ግልጽ ተወዳዳሪ ሲሆን ማይክሮሶፍት እና ጉግል ደግሞ የአፕል ተቀናቃኞች ናቸው።ግን የግላዊ መረጃ ጉዳይ በፌስቡክ እና በአፕል መካከል የማይጠፋ እሳት አስነስቷል። እናም እ.አ.አ 2021 ተፎካካሪነቱን ይበልጥ ያቀጣጥለዋል።