id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
53973816
https://www.bbc.com/amharic/53973816
ቻይናና አውስትራሊያ፡ ቤይጂንግ የሲድኒን ወይን መመርመሯ አገራቱን እያጣላ ነው
ቻይና ለሁለተኛ ጊዜ ከአውስትራሊያ የሚገቡ ወይኖች ላይ ምርመራ መጀመሯ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን ፍጥጫ አክርሮታል።
ቻይና ከሁለት ሳምንት በፊት የአውስትራሊያ ወይኖችን እመረምራለሁ ማለቷን ተከትሎ ሌላ አንድ ዓመት የሚወስድ ምርመራ እንደምትከፍትም አስታውቃለች። አውስትራሊያ በበኩሏ ቻይና ውስጥ ወይን ስለማራገፏ እንዲሁም እርዳታ ስለመስጠቷ የቀረበባትን ክስ አጣጥላለች። በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ፖለቲካዊ ውጥረት ተከትሎ፤ ቻይና አውስትራሊያ ላይ የምጣኔ ሀብት ጫና እያሳደረች እንደሆነ ትወነጀላለች። የኮሮናቫይረስ መነሻን በተመለከተ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ ምርመራ አውስትራሊያ ቻይና ላይ ጣት መጠቆሟ፤ የቻይናን ሕዝብ ስሜት እንደጎዳ አንድ ከፍተኛ የቻይና ዲፕሎማት ባለፈው ሳምንት ተናግረዋል። ባለፉት ወራት ቻይና የአውስትራሊያ ገብስ፣ ስጋና ወይን ላይ ያነጣጠሩ እርምጃዎች ወስዳለች። ተማሪዎችና ጎብኚዎች ዘረኛነት እንዳይገጥማቸው ወደ አውስትራሊያ እንዳይሄዱ እየተነገራቸውም ነው። ባለፈው ሳምንት፤ የአውስትራሊያ መንግሥት ከሌሎች አገራት መንግሥታት ጋር የሚገባውን ውል መሰረዝ የሚያስችል ሕግ ሊተገብር መሆኑ ተሰምቷል። ይህም ቻይናን ኢላማ ያደረገ ነው ተብሏል። የአውስትራሊያ ትልቅ ገበያ ያለው ቻይና ነው። ይህም ከአገር አቀፍ የውጪ ምርቱ 32.6 በመቶ ነው። ቻይና የአውስትራሊያ ገብስ ላይ 80 በመቶ ቀረጥ የጣለችው ለአንድ ዓመት ከዘለቀ ምርመራ በኋላ ነው። በዓለም ንግድ ድርጅት መርህ መሠረት መሰል ምርመራዎች በአውስትራሊያ ወይን ምርቶች ላይ እየተካሄደ እንደነበር ቻይና አስታውቃለች። አዲሱ “ጸረ ድጎማ” የተባለው ምርምራ ተግባራዊ የሚሆነው ሁለት ሊትርና ከዛ በታች በያዙ ጠርሙሶች ላይ ነው። የአውስትራሊያው የንግድ ሚንስትር ክሱን አጣጥለዋል። የአገሪቱ የወይን ተክል እና ወይን አምራቾች ወኪል፤ ምርታቸው በቻይና ተፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። ወደ ቻይና ከምትልካቸው ምርቶች መካከል ብረትና ጋዝ ይጠቀሳሉ። እነዚህ ዘርፎች በወቅታዊው ችኩቻ ተጽዕኖ ስር አልወደቁም። አውስትራሊያ ወደ ቻይና ከምትልከው ወይንና የባህር እንስሳት ምግብ በተጨማሪ ትምህርትና ቱሪዝምም ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ናቸው።
news-54612591
https://www.bbc.com/amharic/news-54612591
ኮሮናቫይረስ፡ ዶናልድ ትራምፕ በፍጥነት ያገገሙበት መድሃኒት እውቅና ተሰጠው
አሜሪካ በኮቪድ-19 ታምመው ሆስፒታል ለሚገቡ ግለሰቦች ሬምዴስቪር የተሰኘውን ፀረ ቫይረስ መድሃኒት ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቀደች።
የአሜሪካ ምግብና መድሃኒት አስተዳደር (ኤፍዲኤ) እንዳለው መድሃኒቱ በክሊኒክ ውስጥ ሙከራ ላይ ባለበት ወቅት በቫይረሱ የተያዙ ሕሙማንን ማገገሚያ ጊዜ በአምስት ቀናት ውስጥ ያሳጥራል። በቅርቡ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ በኋላ መድሃኒቱ የተሰጣቸው ሲሆን በፍጥነትም እንዲያገግሙ ረድቷቸዋል መባሉ ይታወሳል። ይህ ቬክለሪ በሚል የብራንድ ስያሜ የሚታወቀው መድሃኒት የአሜሪካ መድሃኒትና ምግብ አስተዳደር ፈቃድ ሲያገኝ የመጀመሪያው መድሃኒት መሆኑን በመግለጫው ላይ ተመልክቷል። ባለፈው ሳምንት የዓለም ጤና ድርጅት ሬምዴሲቪር በቫይረሱ ተይዘው የታመሙ ግለሰቦች ላይ ያለው ውጤት አነስተኛ ነው ብሎ ነበር። የዓለም ጤና ድርጅት በሰራው ጥናት እዚህ ድምዳሜ ላይ መድረሱን ቢናገርም የመድሃኒት አምራቹ ገሌድ ግን ውጤቱን ሊቀበለው አልፈለገም። ሬምዴሲቪር በአሜሪካ ከግንቦት ወር ጀምሮ ለድንገተኛ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ እንዲውል ተፈቅዶ ነበር። እንደ አሜሪካ መድሃኒት እና ምግብ ቁጥጥር ባለስልጣን ከሆነ መድሃኒቱ ለአዋቂዎችና እድሜያቸው 12 ለሞላ ሕጻናት እንዲሁም ክብደታቸው 40 ኪሎ ግራም ለሆነ ግለሰቦች በሆስፒታል የኮቪድ-19 ሕክምና በሚከታተሉበት ወቅት ለማከም ጥቅም ላይ መዋል ይችላል። የባለስልጣኑ ኮሚሽነር የሆኑት ስቴፈን ሃሃን እንዳሉት ተቋሙ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ተደጋጋሚ የክሊኒክ ሙከራዎችን ካደረገ እና በሚገባ ከፈተሸ በኋላ ነው። ከተደረጉ የተለያዩ ጥናቶች መካከል አንዱ የማገገሚያ ቀናቱ ከ15 ቀናት 10 ማድረሱ ተገልጿል።
57318951
https://www.bbc.com/amharic/57318951
የሕፃን ሰውነት በአሲድ ያሟሟው 'ማፊያ' ከእስር መፈታቱ ቁጣ አስነሳ
የሲሲሊው የወንጀል ቡድን (ማፊያ) አለቃ ጆቫኒ ብሩስካ ከእስር መፈታቱ በርካቶችን አስቆጣ።
ጆቫኒ ከተከሰሰባቸው ወንጀሎች መካከል የሕፃን ሰውነትን በአሲድ ማሟሟት ይገኝበታል። 'ፒፕል ስሌየር' ወይም ሰው በላው በሚል ቅጽል ስሙ የሚታወቀው ጆቫኒ፤ ከ100 በላይ ግድያዎች ውስጥ እጁ እንዳለበት አምኗል። ይህም ታዋቂው የጸረ ማፊያ ዓቃቤ ሕግ ጆቫኒ ፋልኮን መግደልን ይጨምራል። ጆቫኒ የወንጀል ጓዶቹን በመጠቆም ዓቃቤ ሕግን ተባብሯል። ከ25 ዓመታት እስር በኋላ መፈታቱ ጉዳት ያደረሰባቸው ሰዎችን ወዳጅ ዘመዶች አስቆጥቷል። ጆቫኒ ብሩስካ ማነው? የ64 ዓመቱ ጆቫኒ፤ ኮስታ ኖስትራ የተባለ የሲሲሊ የወንጀል ቡድን አባል ውስጥ ቁልፍ ሰው ነበር። እአአ በ1992 የወንጀል ቡድኖችን ጉዳይ በመመርመር የሚታወቀው ዳኛ ጆቫኒ ፋልኮን የተገደለበትን ቦንብ አፈንድቷል። በፍንዳታው የዳኛው ባለቤትና ሦስት ጠባቂዎቹም ተገድለዋል። ከሁለት ወር በኋላ ደግሞ የዳኛው ባልደረባ የሆነው ፓውሎ ብሮሴሊኖ ተገድሏል። እነዚህ ግድያዎች መላው ጣልያንን ያስደነገጡና ወንጀለኛ ቡድኖችን በተመለከተ ጥብቅ ሕግ እንዲወጣ ያደረጉም ናቸው። ጆቫኒ ፈጽሜያቸዋለሁ ካላቸው ግድያዎች እጅግ አሰቃቂው የ11 ዓመት ታዳጊ ነው። ጁሴፒ ዲ ማቶ የተባለው ታዳጊ የሌላ ወንጀል ቡድን አባል ልጅ ነበር። ጆቫኒ ልጁን ለመግደል የወሰነው አባቱ ከድቶኛል ብሎ ነው። ልጁን አሳግቶ ካሰቃየው በኋላ አንቆት ሰውነቱን አሲድ ውስጥ አሟምቶታል። የታዳጊው ቤተሰቦች ልጃቸውን መቅበር አልቻሉም ነበር። ጆቫኒ እአአ በ1996 ከታሰረ በኋላ የእስር ጊዜውን ለመቀነስ የዓቃቤ ሕግ ምስክር ሆኗል። ከ1980 እስከ 1990 ድረስ በወንጀል ቡድኖች ከተፈጸሙ ወንጀሎች ጀርባ ያሉ በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ እገዛ አድርጓል። ከእስር ሲለቀቅ ምን ተባለ? ጆቫኒ መፈታቱ ጉዳት ያደረሰባቸው ሰዎችን ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች አስቆጥቷል። በጆቫኒ ከተገደሉ ጠባቂዎች የአንዱ ባለቤት ቲና ሞንትሪዎ፤ ለሪፐብሊካ ጋዜጣ "መፈታቱ ፍትሐዊ አይደለም። አበሳጭቶኛል" ብላለች። "ከ29 ዓመታት በኋላም ጆቫኒ ስለፈጸመው ግድያ አናውቅም። መንግሥት ከኛ ጎን አልቆመም። ቤተሰቤን ያመሰቃቀለው ሰው ነጻ ወጥቷል" ስትልም አክላለች። የተገደለው ዳኛ እህት ማርያ ፋልኮን ጆቫኒ ከእስር በመለቀቁ ማዘኗን ገልጻለች። በርካታ የጣልያን ፖለቲከኞች ጆቫኒ ከእስር መለቀቁን ኮንነዋል። የቀኝ ዘመሙ ሊግ ፓርቲ መሪ ማቶ ሳልቪኒ "የወንጀል ቡድን አለቃው ጆቫኒ ከ25 ዓመት በኋላ ከእስር ተለቋል። ይህ ለጣልያናውያን አይገባም" ብለዋል። የዴሞክራቲክ ፓርቲ መሪ ኤንሪኮ ሌታ ደግሞ "ሆድን በቡጢ የመታት ያህል ትንፋሽ የሚያሳጥር ውሳኔ ነው" ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
43985855
https://www.bbc.com/amharic/43985855
አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጋዜጠኞች ተስፋ
የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀንን ስናስብ የኢትዮጵያ የፕሬስ ይዞታ ከዓመት ዓመት ያለመሻሻል ጉዳይ የሚዘነጋ አይሆንም። የጋዜጠኝነት ሙያ ተሟጋቾችም ሃገሪቱን ለመገናኛ ብዙሃን ሥራ አስቸጋሪ ከሆኑ ቦታዎች መካከል ይመድቧታል።
በዚህ ዓመት ግን በእስር ላይ የነበሩ ጋዜጠኞች መፈታትና ከአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የተሰሙት ቃላት በዚህ ወቅት ለበርካቶች ተስፋ የሰጠ ይመስላል። ፍሬው አበበ አሁን በህትመት ላይ ካሉት ጥቂት ጋዜጦች መካካል የምትገኘዋ 'ሰንደቅ' ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ነው። ኢህአዴግ ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ ቅድመ ሳንሱርን ማንሳቱና የወጡት ሕጎች ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት እውቅና እንዲያገኝ በማድረግ በሃገሪቱ ነፃ ፕሬስ እንዲፈጠር አመቺ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ማድረጉን ይናገራል። አሁን ባለው ሁኔታ ዋነኛው ችግር ብሎ የሚያስበው የመንግሥት አስፈፃሚ አካላት የአመለካከት ችግርን ነው። በተለይ ፕሬሱን በተመለከተ ያለው አመለካከት እንደ ጠላት የመፈረጅ እንደሆነ ይናገራል። በዚህም ባለፉት 26 ዓመታት ብቅ ብለው የነበሩት ጋዜጦች እንዳለ ጠፍተው "በሚያሳዝን ሁኔታ ኢትዮጵያን የምታክል ትልቅ ሃገር ሦስት ብቻ በአማርኛ የሚታተሙ ጋዜጦች የቀሩባት ሆናለች" ይላል። በፈቃዱ ሞረዳ ደግሞ ለ15 ዓመታት የጦማር ጋዜጣ አዘጋጅና አሳታሚ ሆኖ ሰርቷል። በመጀመሪያዎቹ የፕሬስ ነፃነት ዘመን አስቸጋሪና ተግዳሮቶች የበዙበት እንደነበር የሚያስታውስው በፈቃዱ፤ ሥራውን ስለሚወደው ፈተናውን ተቀብሎ የሙያውን ስነ-ምግባር በተቻለ መጠን አክብሮ እውነትን ለማቅረብ ይጥር እንደነበር ይናገራል። የነበሩት አንዳንድ ጋዜጦች ፕሬሱን ለጥቃት የሚያጋልጡ ሥራዎችን ይሰሩ እንደነበር የሚናገሩ ሰዎች እንደነበሩ የሚያስታውሰው በፈቃዱ ነገር ግን "መንግሥት ፕሬሱን ስለማይፈልገው ምንም መልካም ነገር ብንሰራ ከማጥቃት ወደኋላ አይልም። እንዲያውም በሸሸነው እርምጃ መጠን ይከተለን ነበር" ሲል ይደመጣል። በወቅቱ የተለያዩ ወከባዎችና ክሶች ይቀርቡበት እንደነበር የሚዘክረው በፈቃዱ ሥራዉን በሚሰራበት ወቅት ዘወትር የሚያሳስበው ነገር እንዳልሆ ግን ይናገራል። በጋዜጠኝነት ሥራው ውስጥ በስድስት ወር ጊዜ ለዘጠኝ ጊዜ ታስሮ የተፈታው በፈቃዱ ይህ ሁኔታ ሙያዉን እንዲተው ባያደርገውም መጨረሻ ላይ ግን ነገሮች እየጠነከሩ ሲመጡ በተለይ የቤተሰቡ ሁኔታ ያሳስበው ጀመር። አምስት ያህል ክሶች ከጋዜጠኝነት ሥራው ጋር በተያያዘ ሲከታተል የነበረው በፈቃዱ በዚህ ሁኔታ መቀጠሉ መጨረሻውን እስር ቤት ሊያደርገው እንደሚችል በማሰብ ከሃገር መውጣትን የጨረሻው አማራጭ አደረገ። "እስራት ሰለቸኝ፤ ፈሪ ሆንኩ። ሃገሬን ጥዬ ስወጣ ያለተዘጉ ክሶችና የእስር ትዕዛዞች ወጥተውብኝ ነበር። ስለዚህ በእነዚህ ክሶች የእኔ እስር ቤት መግባት የሚያስገኘው ትርፍ ስላልታየኝ መሰደድና ሌላ አማራጭ መፈለግን" ምርጫው አደረገ። የአዲስ ነገር ጋዜጣ ማኔጂን ኤዲተር የነበረው መስፍን ነጋሽ፤ የጋዜጠኝነት ሥራን የተለያዩ ነገሮችን ለመማር ዕድልን ያገኘበትና ይነስም ይብዛ ለሃገር አስተዋፅኦ ያደረገበት የህይወቱ አካል እንደሆነ ይናገራል። መስፍን በፕሬስ ሥራዉ ውስጥ በተለይ የመንግሥትን ትኩረት የሚስቡ ጉዳዮች ላይ ሲሰሩ ህጋዊና መዋቅራዊ እንቅፋቶች ይገጥሟቸው እንደነበር ያስታውሳል። ከመንግሥት በኩል በአዘጋጆቹ ላይ ክስ ለመመስረት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የሚገልፅ መረጃ ከታማኝ ምንጮች ስላገኙ በግል በደረሱበት ውሳኔ መሰረት አብዛኞቹ ጋዜጠኞች ከሃገር እንደተሰደዱ ይናገራል መስፍን። ነገር ግን ማሳደዱ ከሃገር ከወጡ በኋላም አላበቃም ነበር። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በደረ-ገፅ በኩል የጋዜጣዋን ሥራ ለማስቀጠል ያደረጉትን ጥረት ተከትሎ በአንዳንዶቹ የጋዜጣዋ አዘጋጆች ላይ በሌሉበት ክስ ተመሰረተባቸው። አዲሱ መሪ. . . በቅርቡ ወደጠቅላይ ሚኒስትርነት መንበሩ የመጡት ዶክተር አብይ አህመድ ከቀድሞዎቹ መሪዎች በተለየ ለውጦችን ለማምጣት እንደሚፈልጉ ሲናገሩ እየተደመጡ ነው። ፍሬው አበበ እንደሚለው አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር በንግግራቸው የሃሳብ ብዝሃነትን በተመለከተ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ተናግራዋል። "ይህ ማለት ደግሞ በቀጥታ ፕሬስን የሚመለከት በመሆኑ፤ በገቡት ቃል መሰረት ይህንን ተግባራዊ ያደርጋሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ" ይላል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በውጪ ያሉ ጋዜጠኞች ወደሃገራቸው መጥተው እንዲሰሩ እንደሚፈልጉ የተናገሩትን ነገር መልካምና በበጎ መታየት እንዳለበት የሚያምነው በፈቃዱ፤ ነገር ግን በቅድሚያ መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች እንዳሉ ይጠቁማል። ከውጪ የሚተላለፉ ስርጭቶችን ማፈን ማቆምና አሳሪ የሆኑት ሕግ ላይ መሻሻሎችን ማድረግ ቃልን በተግባር ለማሳየት አንድ እርምጃ መሆኑን የሚጠቅሰው በፈቃዱ፤ እንደሱ በስደት ላይ ያሉ ጋዜጠኞች ላይ የተከፈቱ ክሶችና ውሳኔዎች መሰረዛቸው በይፋ እንዲነገር ይጠብቃል። ይህ ከተደረገና በሩ በቀና ልቦና ከተከፈተ "ወደሃገሬ ተመልሼ "ጦማር' ጋዜጣን መልሶ ለማሳተምና እንዲሁም በሌሎች የሚዲያ ሥራዎች ለሀገሬ የበኩሌን አስተዋፅኦ ለማድረግ የሚቀድመኝ የለም" ይላል። "ኢትዮጵያ በተግባር ብቻ ሳይሆን በቃልም የቆሰለች ሃገር ስለሆነች በቃል መታከም አለባት" የሚለው መስፍን አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የሚቀበለውን አይነት መልዕክት እያስተላለፉ ነው ይላል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፕሬስ ነፃነት ማክበርን በተመለከተ በተዘዋዋሪ መንገድ ከተናገሩት ባሻገር ግልፅ ባለሁኔታ የተናገሩት ነገር እንደሌለ የሚጠቅሰው መስፍን "ሃሳብን የመግለፅ ነፃነት ለዜጎች ሳይከበር፤ ለጋዜጠኞች ብቻ የሚከበር መብት አይሆንም" ይላል። ያለውን ሁኔታ ለማስተካከል ፍላጎቱ ካለ፤ በእስር ላይ ያሉትን ጋዜጠኞች መልቀቅና የተከሰሱትንም ክሳቸው እንዲሰረዝ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ከበፍቃዱ ጋር ይስማማል። በተጨማሪም "የፕሬስ ህጉንና የፀረ-ሽብር ህጉን መሰረዝ ካልሆነም አፋኝ የሆኑትን ክፍሎቻቸውን እንዲለወጡ ማድረግ እንዲሁም ጋዜጠኞች ሥራቸውን እንዲያከናውኑ በሁሉም መስኩ አመቺ ሁኔታን መፍጠር በጣም ያስፈልጋል" ባይ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እያቀረቡት ያለው ግብዣ ከልብ ከሆነ ከንግግር ባሻገር መንገዱን የሚያመቻች ተጨባጭ ተግባራትን ከወዲሁ መጀመራቸውን የሚያመለክቱ ሥራዎችን መሬት ላይ ማሳየት አለባቸውም ሲል ያክላል። መስፍን መሬት ላይ ያለው ሁኔታ እስከተቀየረ ድረስ በራሱ በኩል ወደ ሃገሩ ተመልሶ የጋዜጠኝነት ሥራውን ለመጀመር ፍላጎቱ እንዳለውም ይናገራል። "ከሃገር የመውጣቱ ውሳኔ ከባድ እንደነበረው ሁሉ ወደ ሃገር የመመለሱ ውሳኔም ቀላል አይሆንም" የሚለው መስፍን ነገር ግን ሁኔታዎች እስከተቀየሩና የሚፈልገውን ለመሥራት አመቺ ሁኔታ እስከተፈጠረ ድረስ ለመመለስ አያመነታም። የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ንግግር ወደ ተግባር የሚሻገር ከሆነ በበርካቶች ዘንድ የፈጠረው መልካም ስሜት የተዳከመውን የፕሬስ ሥራ እንዲያንሰራራ በር ሊከፍት ይችላል የሚለው የበርካቶች እምነት ይመስላል።
news-54612588
https://www.bbc.com/amharic/news-54612588
እርቀ ሰላም ኮሚሽን የፌደራልና የትግራይ ክልል መንግሥታት ለማስታረቅ ምን እየሰራ ነው?
እርቀ ሰላም ኮሚሽን የፌደራልና የትግራይ ክልል መንግሥታት ለውይይት ፈቃደኛ ከሆኑ ለማስታረቅ ዝግጁ መሆኑን አሰስታወቀ።
የኢትዮጵያ እርቀ ሰላም ኮሚሽን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተፈጠሩ 21 ግጭቶችን እያጠና መሆኑን ትናንት በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ገልጿል። የኮሚሽኑ ምክትል ሊቀመንበር የትነበርሽ ንጉሴ "ግጭቶችን የመለየት ሥራ ሰርተናል፤ ከእነዚህ ውስጥም በናሙና መልክ በመምረጥ እንዴት መፍታት እንችላለን በሚለው የግጭቶችን መንስዔና ምንነት የማጣራት ሥራ እየሰራን ነው" ብለዋል። እነዚህ ለዕርቅና ሰላም ፈታኝ ናቸው የተባሉ 21 ግጭቶች በአገሪቱ የተለያዩ ክልሎች ውስጥ የተፈጠሩ መሆናቸው ተነግሯል። ከእነዚህ ግጭቶች መካከል የተወሰኑት አሁንም ተመልሶ በሚፈጠር ግጭት ለሕይወት መጥፋት ምክንያት መሆናቸውን የተናገሩት የትነበርሽ ንጉሴ፣ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ከተውጣጡ ሽማግሌዎች ጋር ምክክር እንደሚደረግበትም ተናግረዋል። የፌደራል መንግሥትና የትግራይ ክልል ጉዳይ የእርቅና ሰላም ሥራ በሕዝቦች መካከል የሚሰራ መሆኑን የተናገሩት የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ሊቀመንበሩ ካርዲናል ብርሃነ እየሱስ ሱራፌል ከዚህ ቀደም የአገር ሽማግሌ ሆነው ሁለቱን መንግሥታት ለማሸማገል በተሳተፉበት ወቅት ያጋጠማቸውን እንዲህ ተናግረዋል "ወደ ክልሎች ሄደን ስናወያያቸው፣ የክልሉ አመራር እኛ ለውይይት ዝግጁ ነን ይሉናል። ለውይይት መድረክ አዘጋጅተናል ስንላቸው ደግሞ አንዳንድ ቅድመ ሁኔታዎችን የማስቀመጥ ሁኔታ አለ" በማለት መልሰዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ኮሚሽኑ የተቋቋመበትን አዋጅ በመጥቀስ "የእኛ ትልቁ ኃላፊነት ያለፉትን አለመግባባትና ጉዳቶች ላይ በማተኮር፣ በእነዚህ አለመግባባቶች የተጎዱ ስሜቶችን በመጠገን ስለነገ ሃሳብ እንዲኖራቸው ማድረግ ነው" ሲሉ የኮሚሽኑ ምክትል ሊቀመንበር የትነበርሽ ንጉሴ ተናግረዋል። "በፌደራል መንግሥትና በክልል ችግር ሲፈጠር የመፍታት ኃላፊነት የእርቅና ሰላም ኮሚሽን አይደለም" በማለት በፌደራል እና በትግራይ ክልል መካከል የተፈጠረው አለመግባባትን የመፍታት ኃላፊነት ለኮሚሽኑ በአዋጅ ከተሰጡት ሥልጣኖች መካከል አለመሆኑን በመጥቀስ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ኃላፊነት እንደሆነ ተናግረዋል። "እንደ ገለልተኛ ኮሚሽን ማድረግ የምንችለው ተረጋግተው አብረው እንዲያወሩ መጠየቅ ነው" በማለት ውይይት እንዲያደርጉ ገለልተኛ አካል የሚያስፈልግ ከሆነ፣ ኮሚሽኑ ዝግጁ መሆኑን የኮሚሽነሩ ምክትል ሊቀመንበር የትነበርሽ ንጉሴ ይናገራሉ። ሁለቱ አካላት ለውይይት ፈቃደኛ ከሆኑ ለማስታረቅ ዝግጁ መሆናቸውንም ጨምረው አስታውቀዋል። ሌሎች ጉዳዮች በአገሪቱ ውስጥ እርቅና ሰላም አስፈላጊ መሆኑን የሚያሳዩ ነገሮች ቢኖሩም፣ የሰላም አለመኖር ስራቸው ላይ ችግር እየፈጠረ መሆኑን የተናገሩት የኮሚሽኑ ምክትል ሊቀመንበር የትነበርሽ ንጉሴ፣ መንግሥት የሕዝቡን የእለት ተዕለት ሰላም መጠበቅ እንዳለበትም ተናግረዋል። በዚህ ዓመት ሥልጣን ላይ ያለውን ጨምሮ ከተለያዩ ፓርቲዎች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን የተናገሩት ምክትል ሊቀመንበሯ፣ ከወጣቶች ጋር እየሰሩ መቆየታቸውንና በሚመጡት ወራትም የኢትዮጵያ አስታራቂ ወጣቶች ፎረምን ለማቋቋም ዝግጅታቸውን መጨረሳቸውን ተናግረዋል። ሴቶች በእርቅ ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግም፣ የኢትዮጵያ ሴት በጎ ፈቃደኞች እርቅ መድረክ ለማቋቋም ዝግጁ መሆናቸውንም ተናግረዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ኮሚሽኑ ለሥራ እንዲዘጋጅ በቂ ጊዜ በመንግሥትም ሆነ በሌላ አካል አለመሰጠቱን የተናገሩት ኃላፊዎቹ፣ ይህም ደግሞ ሥራቸውን እያስተጓጎለ እንደሆነ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ እርቀ ሰላም ኮሚሽን በኢትዮጵያ ሕዝቦች መካከል ሰላም፣ ፍትህ፣ አንድነት፣ እና የብሔራዊ መግባባት እንዲሁም እርቅ እንዲወርድ ለመስራት አልሞ በ2011 ዓ.ም ላይ የተቋቋመ መሆኑ ይታወሳል። ሰላም
news-52217130
https://www.bbc.com/amharic/news-52217130
ታይዋን ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም ላቀረቡት ክስ ምላሽ ሰጠች
የታይዋን ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ዶክተር ቴድሮስ ትናንት የሰጡትን መግለጫ ተከትሎ የቀረበው ዘረኝነትን መሰረት ያደረገ ክስ መሰረተ ቢስ ነው ሲል ተቃወመ።
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ የግድያ ዛቻ እንደደረሰባቸውና ዘረኛና ጸያፍ ስድቦችን ሳይቀር እያስተናገዱ እንደሆነ ለዓለም ሚዲያ መናገራቸውን ተከትሎ ታይዋን ኃላፊው ይቅርታ ሊጠይቁኝ ይገባል ማለቷ ተዘግቧል። ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም የግድያ ዛቻና የዘረኛ ንግግር ጥቃት እየተሰነዘረባቸው መሆኑን የተናገሩ ሲሆን "ከሁለትና ከሦስት ወር በላይ ዘረኛ ጥቃቶች ተሰንዝረውብኛል። ጥቁር፣ ባርያ ተብያለሁ። እውነቱን ለመናገር እኔ በጥቁርነቴ እኮራለሁ። የሚባለው ነገርም ግድ አይሰጠኝም" ብለዋል። ቻይና እንደ እራሷ ግዛት ስለምትመለከታትና በዓለም አቀፍ ተቋማት ዘንድ እውቅና እንዳታገኝ በምታሳርፈው ተጽእኖ ምክንያት የዓለም ጤና ድርጅት አባል ያልሆነችው ታይዋን ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ከድርጅቱ አስፈላጊውን መረጃ አላገኘሁም በሚል ወቀሳ ስትሰነዝር ቆይታለች። በዶ/ር ቴድሮስ ትናንት በሰጡት መግለጫ ላይ የዘረኝነት ቃላት እንደተሰነዘረባቸው የተናገሩ ሲሆን ይህም ከታይዋን በኩል እንደሆ ማመልከታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። "ሰውየው ያሉት ነገር መሠረተ ቢስ ነው፤ ታይዋን ምራቋን የዋጠች፣ የሰለጠነችና ተራማጅ አገር ናት፤ እንዲህ ዓይነት ነገር ውስጥ አትገባም" ብላለች ታይዋን፤ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል የወጣ መግለጫ። የታይዋን 23 ሚሊዮን ሕዝብ በዓለም ጤና ድርጅት የተተበተበ ፖለቲካ ምክንያት ጉዳት ደርሶበታል ሲልም መግለጫው ጠቅሷል። የዶ/ር ቴድሮስ በታይዋን ላይ የሰነዘሩት ክስ መሰረተ ቢስ ብቻ ሳይሆን ቅዠትም ጭምር ነው ያለው የታይዋን መግለጫ ለዚህ ኃላፊትነት ለጎደለው አነጋገር ሰውየው በአፋጣኝና በይፋ ይቅርታ ሊጠይቁን ይገባል ብለዋል። ታይዋን ቫይረሱን መቆጣጠር ከቻሉ ጥቂት አገራት የምትመደብ ናት። በበሽታው የተያዙባት ሰዎች ብዛት 379 ሲሆን ሟቾች 5 ብቻ ናቸው። ታይዋን የዓለም ጤና ድርጅት ቫይረሱ በተከሰተበት የሰጠሁትን የጥንቃቄ መረጃ ቸል ብሎታል ስትል ትከሳለች።
news-56416068
https://www.bbc.com/amharic/news-56416068
ስደተኞች፡ የመን ውስጥ ኢትዮጵያውያን በሚበዙበት የስደተኞች መጠለያ ላይ በእሳት ከሞቱት መካከል 43ቱ መቀበራቸው ተነገረ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በየመን የካቲት 29/2013 ዓ.ም በእሳት አደጋ ቃጠሎ ምክንያት ሕይወታቸው ካለፉ ስደተኞች መካከል የ43ቱ ቀብር መፈፀሙን አስታወቀ።
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ላይ እንደተናገሩት በእሳት አደጋው ከሞቱ መካከል 43 የተቀበሩ ቢሆንም ከእነዚህ ውስጥ ምን ያህሉ ኢትዮጵያውያን ስለመሆናቸው የታወቀ ነገር የለም። አምባሳደር ዲና አክለውም ከየመን 150 ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ ተናግረዋል። ሂዩማን ራይትስ ዎች በየመን በስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ላይ ስለደረሰው የእሳት አደጋ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው በጣቢያው ላይ የእሳት አደጋ ያደረሰው በሁቲ አማፂያን የተተኮሰ መሳሪያ ነው ብሏል። "የሁቲዎች ግዴለሽነት የተሞላበት የጦር መሳሪያ አጠቃቀም በርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ለሞት መዳረጉ፣ በጦርነት በምትታመሰው የመን የሚገኙ ስደተኞች ሕይወት ምን ያህል በአደጋ የተከበበ መሆኑን አስታዋሽ ነው" ሲል በመግለጫው ላይ ጠቅሷል። የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ጉዳዩን በተመለከተ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር በሚገኘው የስደተኞች ማቆያ የሚገኙ አምስት ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን እንዲሁም በየመን የተባበሩት መንግሥታት ባለሥልጣናትን ማናገራቸውን ገልጿል። 550 ስደተኞች የማቆያ ጣቢያው ያለበትን የጽዳት ችግርና መጨናነቁን በመቃወም የረሃብ አድማ ላይ መሆናቸውን ሂማን ራይትስ ዋች አመልክቷል። እነዚህ ስደተኞች እንደሚሉት ከሆነ በማቆያው ውስጥ ለረዥም ጊዜ የኖሩ ሲሆን ከማቆያው ለመውጣት ለጥበቃ አባላቱ እስከ 70 ሺህ የየመን ሪያል ወይንም 280 ዶላር መክፈል ይጠበቅባቸዋል። ስደተኞቹ ለሰብዓዊ መብቱ ተቆርቋሪ ድርጅቱ እንደተናገሩት ጥበቃ አባላቱ የተለያዩ አፀያፊ ዘር ጠቀስ ስድቦችንም በየጊዜው እንደሚሰነዝሩባቸው ተናግረዋል። በወቅቱ የእሳት አደጋውን በተመለከ የሁቲ ታጣቂዎች ባወጡት መግለጫ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅትና የተባበሩት መንግሥታት ለስደተኞቹ መኖሪያ ባለማቅረብ እና ከየመን እንዲወጡ ለማድረግ ባለመተባበራቸው ለደረሰው አደጋ ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ ናቸው ሲሉ ወቅሰዋል። ከአደጋው የተረፉት በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የጠቀሰው የሰብዓዊ መብት ድርጅቱ የደረሰባቸውን ቃጠሎ በሰንዓ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ እየታከሙ ነው ተብሏል። እነዚህ ስደተኞች ሕክምና በሚያገኙበት ሆስፒታል አካባቢ ከፍተኛ የፀጥታ ኃይል ተሰማርቶ እንደሚገኝ የገለፀው የሰብዓዊ መብት ድርጅቱ ይህም ሰብአዊ እርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች እና ቤተሰቦች ለመጠየቅ እንዲሁም ክትተል ለማድረግ አስቸጋሪ ሁኔታ መፍጠሩን ተናግሯል። የሁቲ አማፂያን ለሰብዓዊ እርዳታ ቡድኖች ፈቃድ እንዲሰጡም ጥሪ አቅርቧል። የተባበሩት መንግሥታት ቡድን ክስተቱን በአገሪቱ ከተካሄዱ የሰብዓዊ መብቶት ጥሰቶች ተካትቶ ምርመራ እንዲያደርጉ ጠይቋል። የሁቲ አማፂያን ሰንዓን ጨምሮ በርካታ የየመን ክፍሎችን ይቆጣጠራል። የዓለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) በየመን 6000 ያህል ስደተኞች በማቆያ ውስጥ እንደሚገኙ ገልፆ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ በሕገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች ጭምር ታግተው ይገኛሉ ብሏል። አይኦኤም እንደሚገምተው በኮሮናቫይረስ ምክንያት የተጣለውን የመንቀሳቀስ ገደብ ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች የመን ውስጥ ወደየትም መሄድ ሳይችሉ እየተጉላሉ ነው። ምንም እንኳ የመን ማብቂያ ባላገኘ ጦርነት ውስጥ ብትሆንም በተለይ ደግሞ መነሻቸው ከአፍሪካ ቀንድ የሆኑ በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ድንበሯን እያቋረጡ ወደ ጎረቤት አገር ሳዑዲ አረቢያ ለመግባት በመፍለስ ላይ ናቸው። የመን ውስጥ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ ሳዑዲ አረቢያ ድንበሯን በመዝጋቷ አብዛኞቹ ስደተኞች በጦርነት፣ በረሃብና በበሽታ እየተሰቃዩ በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ይገኛሉ። የመን ውስጥ በሳዑዲ መራሹ ኃይልና በኢራን በሚደገፉት የሁቲ ታጣቂዎች መካከል ስድስት ዓመት የሆነውና አሁንም እየተካሄደ ያለው ጦርነት ከስደተኞቹ በተጨማሪ የአገሪቱን ዜጎች ህይወት አመሰቃቅሎታል። የመን ውስጥ ከሚኖሩ ሰዎች መካከል 80 በመቶ ያህሉ እርዳታ ላይ ጥገኛ ሲሆኑ፤ በርካቶች አገራቸውን እየለቀቁ ጦርነቱን ሽሽት ይሰደዳሉ።
news-47177340
https://www.bbc.com/amharic/news-47177340
እነ አቶ በረከት በማረሚያ ቤቱ ኢንተርኔት የለም ሲሉ ለፍርድ ቤት ተናገሩ
በጥረት ኮርፖሬት የሃብት ብክነት የተጠረጠሩት አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሣ ዛሬ በባህር ዳርና አካባቢዋ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
የአማራ ክልል ፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ባለፈው በተሰጠው የጊዜ ቀጠሮ ማስረጃዎችን ማየቱንና የምስክሮችን ቃል መቀበሉን አሳውቋል። ሆኖም ጉዳዩ ከባድ፣ ውስብስብና ድንበር ተሻጋሪ ከመሆኑም በላይ ምስክሮች እና ሰነዶች በሃገር ውስጥ እና ከሃገር ውጪ መገኘታቸውን አስታውሶ ምርመራውን አለማጠናቀቁን አስታውቋል። • በረከት ስምኦን ከየት ተነስተው እዚህ ደረሱ ከዚህ ተጨማሪ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል። የሕግ ሥልጣን በሌለው አካል መከሰሰሳቸውን የጠቀሱት አቶ በረከት ሰምኦን ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮው ውድቅ አንዲሆን ጠይቀው ነበር። የዳሽን ቢራ ሁሉም ሰነዶች ተሟልተው እንደሚገኙ የተናገሩት አቶ ታደሰ ካሣ በበኩላቸው መነግሥት አስረን አናጣራም፤ አጣርተን ነው የምናስረው ማለቱን ጠቅሰው የተጠየቀው የጊዜ ቀጠሮ አነሱን በእስር ለማቆየት ብቻ መሆኑን በመጠቆም ውድቅ አንዲሆን ጠይቀዋል። የግራ ቀኙን የተመለከተው ፍርድ ቤቱ የጉዳዩን ውስብስብነትና መረጃዎች በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ መገኘታቸውን ከግምት በማስገባት የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮውን ፈቅዷል። • አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ ወደ ባህር ዳር ተወሰዱ • አቶ በረከት ስምኦን ከብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት ታገዱ አቶ በረከት ስንገባም ስንወጣም አየተሰደብንና ስማችን እየጎደፈ ነው ብለዋል። ጠበቃ ማግኘት ባለመቻላቸው ፍርድ ቤቱ እንዲያቆምላቸውና ከቤተሰባቸው ጋር የመገናኘት ዕድል እንዲመቻችላቸው ጠይቀዋል። በተጨማሪም ተከሳሾቹ በማረሚያ ቤት ለመፃፍ የሚያስችላቸው ኮምፒዩተር እንዲገባላቸው ጠይቀዋል። አቶ በረከት በማረሚያ ቤት ውስጥ ኢንተርኔት የለም ሲሉም ተደምጠዋል። የሚደርስባቸውን ዘለፋ በተመለከተ ፍርድ ቤቱ ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን የሚደርስባቸውን ዘለፋ ለማስቆም እንደሚሰራ አስታውቋል።
news-45285848
https://www.bbc.com/amharic/news-45285848
ኡጋንዳዊው ሙዚቀኛና ተቃዋሚ የፓርላማ አባል በሃገር ክህደት ክስ ተመሰረተበት
ኡጋንዳዊው ተቃዋሚ የፓርላማ አባልና ታዋቂው ሙዚቀኛ ቦቢ ዋይን የሃገሪቱ ወታደራዊ ፍርድ ቤት በነጻ ካሰናበተው በኋላ በድጋሚ በሃገር ክህደት ክስ ቀርቦበት በመደበኛ ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ተወስኗል።
ቦቢ ዋይን ትክክለኛ ስሙ ሮበርት ክያጉላኒ ሲሆን፤ ወታደራዊ ፍርድ ቤቱ ካሰናበተው በኋላ ወዲያው ነው በድጋሚ በቁጥጥር ስር የዋለው። ጠበቃዎቹ በቁጥጥር ስር በዋለበት ሰዓት ድብደባ ደርሶበታል ቢሉም፤ ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒም ሆነ የመከላከያ ሃይላቸው ውንጀላውን አልተቀበሉትም። ቦቢ ዋይንን ጨምሮ ሌሎች 30 ሰዎችም ከባለፈው ሳምንት የማሟያ ምርጫ ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ስር ውለዋል። የእነዚህ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋል በሃገሪቱ ውጥረትን አንግሷል። ፖሊስም ከፍተኛ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን ከቤት እየወሰደ ነው። • የኡጋንዳ ወታደሮች ጋዜጠኛ በመደብደባቸው ሰራዊቱ ይቅርታ ጠየቀ • አፍሪካዊው ወጣት ለወባ በሽታ መፍትሄ ይዞ መጥቷል • የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዙማን የሙስና ቅሌት የሚያጋልጥ ምርመራ ተጀመረ የኡጋንዳው ታዋቂ ጋዜጣ '' ኒው ቪዥን'' በፊት ገጹ ይዞት እንደወጣው ከሆነ ቦቢ ዋይን በወታደራዊ ፍርድ ቤት ከመቅረቡ በፊት የመዳከም ምልክት ታይቶበት ነበር። በወቅቱ ህገወጥ የጦር መሳሪያ በመያዝ ነበር ክስ የቀረበበት። ጠበቃው ደንበኛቸው አስቸኳይ የህክምና እርዳታ ያስፈልጋቸውል ማለታቸውንም ጋዜጣው ገልጿል። የሃገሪቱ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም ብሎ በነጻ ካሰናበተው በኋላ በጥቂት ሰዓታት ልዩነት ከባለቤቱ ጋር በፖሊስ መኪና ተጭነው ተወስደዋል። ባለፈው ማክሰኞ የቦቢ ዋይን ደጋፊዎች የተቃውሞ ሰልፍ ባደገረጉበት ወቅት የመከላከያ ሃይሎች እርምጃ ወስደውባቸዋል። በወቅቱ አንድ ጋዜጠኛ ድበዳባ ሲደርስበት የሚያሳይ ምስል በማህበራዊ ሚዲያዎች ከተሰራጨ በኋላ የኡጋንዳ ሰራዊት ይቅርታጠይቋል።
news-45334252
https://www.bbc.com/amharic/news-45334252
በሶማሌ ክልል በተከሰተው ቀውስ በአንድ ቀን 96 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ
በሶማሌ ክልል በተከሰተው ቀውስ በአንድ ቀን 96 ሰዎች መገደላቸውን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ዘይኑ ጀማል ለቢቢሲ ገልፀዋል።
ሰዎቹ የተገደሉት ቀውሱ በተነሳበት የመጀመርያው ቀን ሐምሌ 27፣ 2010 ዓ. ም. ሲሆን፤ በሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ጅግጅጋን ጨምሮ በክልሉ የተለያዩ ከተሞች ግድያው መፈጸሙን ተናግረዋል። • በሶማሌ ክልል በተከሰተ ቀውስ ህይወት ሲጠፋ አብያተ-ክርስትያናት ተቃጠሉ ሰዎቹ የተገደሉት በአሰቃቂ ሁኔታ መሆኑን ተናግረው፤ ሀይማኖትና ብሔርን ለይቶ የተሰነዘረ ጥቃት እንደሆነ አክለዋል። "ከዘር ጭፍጨፋ አይተናነስም" ብለዋል። መነሻው የክልሉ አመራሮች አቅደው፤ ተግባሩን የሚፈጽሙ ሰዎች አሰልጥነውና አሰማርተው መሆኑን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል። እስከ አሁን የክልሉን የቀድሞ ፕሬዘዳንት አቶ አብዲ ሞሀመድ ኡመርን ጨምሮ ሰባት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል። • አብዲ ሞሃመድ ያለመከሰስ መብታቸው ተገፈፈ 'ሄጎ' በመባል የሚታወቀው ቡድን በግድያው እጁ ስለመኖሩ ቢቢሲ ላቀረበላቸው ጥያቄ፤ "በዋናነት በግጭቱ ተሳትፈዋል የሚባሉት ሄጎ በሚባለው ቡድን አባላት ናቸው። ሄጎ የሚባለውን የፈጠሩ፣ እቅዱን ያቀነባበሩ የክልሉ የፖለቲካ አመራሮች፣ የክልሉ የካቢኔ አባላትና ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣኖችን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ እየሰራን ነው" ብለዋል። ልዩ ፖሊስ በግድያው ተሳትፎ ስለመሆኑ ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ "ማን በምን ደረጃ ተሳተፈ የሚለው ተጣርቶ ለህዝብ ይፋ ይደረጋል" ሲሉ ኮሚሽነሩ አስረድተዋል። በጅግጅጋ የሚኖሩ የተለያዩ አካባቢዎች ተወላጆች ስጋት እንዳላቸው የሚናገሩት ጄኔራል ዘይኑ፤ የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት የክልልሉን ዋና ዋና ከተማዎች መቆጣጠሩ አንጻራዊ ሰላም ማስፈኑን ገልጸዋል። • ሙስጠፋ ኡመር የሶማሌ ክልል ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ በአሁን ወቅት አዲሱ የክልሉ ፕሬዘዳንት አቶ ሙስጠፋ ኡመር በተለያዩ አካባቢዎች እየተዘዋወሩ ህብረተሰቡን እየጎበኙ መሆኑን ተናግረዋል። የተፈናቀሉ ሰዎችን ወደ አካባቢው መመለስ ቀጣዩ ስራ መሆኑን ተናግረው፤ በዚህ ረገድ የአካባቢው ማህበረሰብ እየተባበራቸው እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
news-51147561
https://www.bbc.com/amharic/news-51147561
የሌሴቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ከቀድሞ ባለቤታቸው ግድያ ጋር በተገናኘ ከሥልጣናቸው ሊለቁ ነው
የሌሴቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶማስ ታባኔ ከሥልጣናቸው እንደሚለቅቁ ፓርቲያቸው መግለጹን ኤ ኤፍ ፒ የዜና ወኪል ዘግቧል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት ገዢው ፓርቲ ' ኦል ቦሳቶ ኮንቬንሽን' ቃል አቀባይ የሆኑ አንድ ግለሰብ እንደገለጹት፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶማስ ታባኔ የፊታችን ማክሰኞ ለካቢኔ አባላት የሥራ መልቀቂያቸውን እንደሚያስገቡ ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሥራቸው የሚለቁበት ምክንያት በይፋ ባይገለጽም፤ ባለፈው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀድሞ ባለቤታቸው በተገደለችበት አካባቢ ከነበረ ተንቀሳቃሽ ስልክ ጋር የተደዋወሉበት ማስረጃ እንዳለው በመግለጽ፤ ፖሊስ ለጥያቄ እንደሚፈልጋቸው ማስታወቁ ምክንያቱ እንደሆነ ተገምቷል። • የሌሶቶ ቀዳማዊት እመቤት በፖሊስ እየተፈለጉ ነው • "ዕፀ ፋርስ በመሸጥ ልጆቼን አሳድጋለሁ" የሌሴቶዋ አምራች ጠቅላይ ሚኒስትር ቶማስ ታባኔ በጉዳዩ ላይ እስካሁን ምንም ያሉት ነገር የለም። የሌሶቶ ፖሊስ ከሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የቀድሞ ባለቤት ግድያ ጋር በተያያዘ የአሁኗን ቀዳማዊ እመቤት ለጥያቄ እንደሚፈልጋቸው ቢገልጽም ቀዳማዊት እመቤት ማይሲያህ ታባኔ ግን የት እንደሚገኙ አልታወቀም። ፖሊስ እንዳለው ቀዳማዊት እመቤት ማይሲያህ ክስ ባይቀርብባቸውም ለጥያቄ ይፈለጋሉ። የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ሊፖሌሎ ታባኔ እንቆቅልሽ በሆነ መልኩ መሞታቸው ከተሰማ በኋላ የሃገሬው ዜጎች ሆነ ተብሎ የተሸፋፈነ ጉዳይ እንደሆነ ሲገልጹ ቆይተዋል። በአውሮፓውያኑ 2017 የተገደሉት የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ጉዳይን ለማጣራትና የአሁኗ ቀዳማዊት እመቤት የት እንደሚገኙ ለማወቅ የሌሴቶ ፖሊስ የዓለም አቀፍ ሕግ አስከባሪ ተቋማትን እርዳታም ጠይቋል። • እግራቸው አሜሪካ ልባቸው አፍሪካ ያለ የሆሊውድ ተዋንያን ሟች ቀዳማዊት እመቤት ከባለቤታቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ታባኔ ጋር በወቅቱ ተለያይተው የነበረ ቢሆንም ፍቺ ግን አልፈጸሙም። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ከአሁኗ ቀዳማዊት እመቤት በወቅቱ እጮኛቸው ከነበሩት ማይሲያህ ታባኔ ጋር ግንኙነት መስርተው ነበር። ሁለቱም ሴቶች እኔ ነኝ ቀዳማዊት እመቤት በሚል ፍርድ ቤት እስከ መካሰስ ደርሰው ነበር። ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን ካጣራ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቀድሞ ባለቤታቸው ጋር ይፋዊ ፍቺ እስካልፈጸሙ ድረስ ሊፖሌሎ ታባኔ ቀዳማዊት እመቤት ሆነው እንዲቀጥሉ ብይን አስተላልፏል።
47315037
https://www.bbc.com/amharic/47315037
ሳምሰንግ እንደ መጽሐፍ የሚገለጥ ስልክ አመረተ
የሳምሰንግ አዲሱ ምርት ዋጋው ከ50ሺህ ብር በላይ ነው። የተንቀሳቃሽ ስልክ አምራቹ ሳምሰንግ ሦስት በዓይነታቸው ልዩ ያላቸውን የስልክ ናሙናዎች ይፋ አድርጓል።
ከነዚህ ውስጥ አነጋጋሪ የሆነው እንደ መጽሐፍ ይገለጣል የተባለለት ስልክ ነው። በሁለት ወር ውስጥ ለገበያ ይቀርባል ተብሏል። በኅዳር 2010 "ጋላክሲ ኤስ" ምርቶችን ለገበያ ማቅረብ የጀመረው ሳምሰንግ 10ኛው ኤስ ሰፊ ገበያ ያስገኝልኛል ሲል ተልሞ ነው የተነሳው። ከዚሁ ታጣፊ ስልክ ጋር አብሮ የቀረበው "ጋላክሲ ኤስ10 5ጂ" ታጣፊ ያልሆነ ቢሆንም ፈጣን ኢንተርኔንትን ለመጠቀም ግብ አድርጎ የተፈበረከ ነው ተብሏል። • ሞባይል ስልክዎ ላይ መከራን አይጫኑ • ጃፓን ከቀበሌ መታወቂያ ያነሰች ሞባይል ሠራች • ሞባይል ለኢትዮጵያ እናቶችና ህፃናት ጤና ከነዚህ በኤስ10 ስም ከሚቀርቡ ሦስት ምርቶች አንዱ ደግሞ በዋጋ ደረጃ የደንበኞችን ኪስ የማይጎዳ እንዲሆን ታስቧል። የሳምሰንግ የመጨረሻ ምርት የነበረው 'ኤስ-9" በዋጋው መናር ምክንያት ሽያጩ ከተጠበቀው በታች ስለነበረ ድርጅቱ ትምህርት ወስጃለሁ ብሏል። ይህ እንደ መጽሐፍ ይገለጣል የተባለለት ቅንጡ ስልክ የሁለት መጠነኛ ስልኮች ስፋት ሲኖረው ወደ ጎን 18.5 ሴ.ሜ ይረዝማል። ሲዘረጋም ታብሌት እንጂ ስልክ አይመስልም። ዋናው አገልግሎቱ ደንበኞች በአንድ ጊዜ ሦስት መተግበሪያዎችን መጠቀም እንዲችሉ ነው። • የኢንተርኔት ገበያ በሶማሊያ • በሞባይልዎ የኢንተርኔት ወጪ ተማረዋል? አንድ ሰው በዚህ ታጣፊ ስልክ ዩቲዩብ ቪዲዮ እያየ፣ ማየቱን ሳያቋርጥ ስለፊልሙ ከወዳጁ ጋር በአጭር መልዕክት እየተላላከ ከጎን ሌላ ተጨማሪ መተግበሪያን ከፍቶ ያሻውን ማድረግ ያስችለዋል። ይህ ታጣፊ ስልክ 6 ካሜራዎች ሲኖሩት ሦስቱ ከጀርባ፣ ሁለት ከጎን አንድ ደግሞ ከፊት ለፊት ይገኛሉ። ይህም ስልኩን በየትኛውም ሁኔታ ይዞ ፎቶ ማንሳት ያስችላል ተብሏል። ከዚህም ባሻገር አንድን ምሥል አቅርቦና አርቆ ፎቶ ለማንሳት የሚያስችሉ መተግበሪያ ቁልፎች ተዘጋጅተውለታል። ሳምሰንግ "ኤስ 10" ገመድ አልባ ቻርጀር ስላለው አብረው የሚሸጡትን የጆሮ ማዳመጫዎችንና ሌሎች ባትሪ የሚሹ ቁሶችን ቻርጅ ማድረግ ይችላል። ይህ ስልክ ዋጋው በብር እስከ 56 ሺህ ይጠጋል። ቁርጥ ያለው ዋጋው በዶላር 1ሺህ 9መቶ 80 እንደሆነ ሲነገር በአዳራሹ የነበሩ ታዳሚዎችን አስደንግጧል።
news-52212362
https://www.bbc.com/amharic/news-52212362
ኮሮናቫይረስ፡ ከዚህም በላይ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚችል ተገለጸ
የኢትዮጵያ መንግሥት በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ነው ሲል በማስታወቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደነገገ።
በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጻፈው ይህ መግለጫ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ ግልጽ አላደረገም። መግለጫው መንግሥት ችግሩን በደረሰበት ልክ ለመቋቋም ተዘጋጅቷል ያለ ሲሆን ውሳኔውንም በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 93 መሰረት መታወጁን ገልጿል። "አገርን ለማዳንና ትውልድን ለመታደግ ከዚህ በላይ እርምጃ ልንወስን እንደምንችልም መታወቅ አለበት" ያለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ፣ ዜጎችንም ከዚህ በላይ ግዴታቸውን ለመወጣት መዘጋጀት እንዳለባቸው አሳስቧል። በዚህ ወቅት ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል ችግሩን ለመቋቋም ከሚሠሩት አካላት ጋር አብሮ እንዲቆም የጠየቀው ይህ መግለጫ ከዚህ በተቃራኒ ችግሩን ለማባባስ የሚሠሩ ካሉ ግን፣ "በሕጉ መሠረት የማያዳግም ርምጃ እንወስዳለን" ሲል ያስጠነቅቃል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ መግለጫቸው ላይ አክለውም ለተቸገሩ ወገኖች እገዛ እንዲደረግ እንዲሁም የቤት አከራዮች የተከራዮችን እዳ እንዲከፍሉ ጥሪ አቅርበዋል። "ከቻልን አናስከፍላቸው፤ ካልቻልን ቅናሽ እናድርግላቸው። ያም ካልሆነ ይህ ጊዜ እስኪያልፍ እንታገሣቸው። በዚህ ወቅት ተከራዮችን ከቤት ማስወጣት ፈጣሪም፣ ታሪክም ሕግም ይቅር የማይሉት ወንጀል ነው።" በማለት "ማናችን አልፈን ማናችን እንደምንተርፍ ለማናውቅበት ጊዜ ከመተባበር የተሻለ መሻገሪያ የለንም" ብለዋል። በተጨማሪም ለግል ባለሀብቶች የሠራተኞቻቸው ሕይወት እንዳያስጨንቁ አደራ ብለዋል። መንግሥት የኢኮኖሚ ችግሮችን ለመፍታት አስፈላጊውን ሁሉ እየወሰነ አብሯችሁ እንደሚሆን በዚህ አጋጣሚ እገልጥላችኋለሁ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተለያዩ አካላት እያደረጉ ስላሉት አገልግሎት ምስጋና እንደሚገባቸው ገልፀዋል። ለሕክምና ባለሞያዎች ተገቢውን ሁሉ አለማድረግ እጅን በእጅ እንደመቁረጥ በማለትም እነዚህን ባለሞያዎች በሚቻለው ሁሉ መርዳት እንደሚገባ ገልፀዋል። ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐብይ፣ ያለ እነርሱ ግንባር ቀደምነት ትግሉን ልናሸንፍ አንችልም ብለው፤ "የሕክምና ባለሞያዎችን ማክበር፣ ማመስገንና በጉዟቸው ሁሉ መተባበር ከእያንዳንዳችን ይጠበቃል።" አክለውም የመከላከያ አባላት፣ የፖሊስ ሠራዊት አባላት፣ የኤሌክትሪክ ኃይልና የውኃ አቅርቦት እንዳይስተጓጎል የሚሠሩ ባለሞያዎች፣ የሚዲያ ባለሞያዎች፣ የመገናኛ መሥመሮቻችን ላይ 24 ሰዓት የሚያገለግሉ ዜጎች፣ ተገቢው ምስጋናና ድጋፍ ከቤተሰባቸውም፣ ከማኅበረሰባቸውም ያስፈልጋቸዋል ብለዋል። ከቫይረሱ ባልተናነሰ የእርሻ ምርት መቀነስና የእርሻ ምርት አለመኖር ሀገራችንንና ሕዝቧን ይጎዳል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግብርና ስራ ላይ ለተሰማሩ አርሶ አደሮች "እናንተ ሀገር መጋቢዎች ስለሆናችሁ፣ እየተጠነቀቃችሁ ካለፈው የተሻለ ምርት ለማምረት ትጉ" ሲሉ መክረዋል። እንዲሁም የኢንዱስትሪ ምርቶቻችንም ፈጽመው መቆም የለባቸውም ሲሉ አረጋግጠዋል። በተለይም ከውጭ የምናመጣቸውን ምርቶች ለመተካት ለሚደረገው ጥረት መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግላችሁ እገልጥላችኋለሁ በማለትም ለአጠቃላእ ማህበረሰብ የሚሰጤጡ ምክሮችን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ አስታውሰዋል። በመጨረሻም "በኮሮና አይቀለድም፤ ጉዳዩ ከመኖርና ካለመኖር ጋር የተያያዘ ነው" በማለት አጠናቅቀዋል።
news-45261257
https://www.bbc.com/amharic/news-45261257
አፍሪካዊው ወጣት ለወባ በሽታ መፍትሄ ይዞ መጥቷል
"ይህ ፕሮጀክት የተጀመረው እንደ ቀልድ ነበር። ጓደኛሞች በጋራ ሰብሰብ ብለን የሆነ የሚያስደስት ነገር መስራት ፈለግን።" ይላል የ26 ዓመቱ ብሪየን ጊታ።
''ከአመት በኋላ ጓደኞቼን 'መልካም ጊዜ እያሳለፍን ነው። እየተዝናናን ነው። በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለንም የሰዎችን ህይወት መቀየር እንችላለን' አልኳቸው''። ይላል። ብሪየን የወባ በሽታ መመርመሪያ መሳሪያ ግኝቱን አስመልክቶ ከሮያል አካዳሚ ኦፍ ኢንጅነሪንግ አፍሪካ ሽልማት ከመቀበሉ ሳምንታት በፊት ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርጎ ነበር። ከአራት ዓመት በፊት ብሬን ከማከሬሬ ዩንቨርስቲ ጓደኞቹ ጋር በመሆን የደም ናሙና መውሰድ ሳያስፈልግ በፍጥነት የወባ በሽታን የሚመረምረውን ''ማቲባቡ'' ሲሉ የሰየሙትን በአነስተኛ ዋጋ እና መልሶ ጥቅም ላይ ሊውል የሚችለውን የፈጠራ ውጤት እንካችሁ አሉ። ምንም እንኳ ይህ ግኝት በሙከራ ደረጃ ላይ ያለ ቢሆንም ዳኞች ግን የወባ በሽታ መመርመሪያ መሳሪያውን ገዳዩን በሽታ በመዋጋት ሂደት ውስጥ በቀላሉ ታሪክ ቀያሪ ብለውታል። ማግኔቶች እና ማቲስኮፕ ማቲባቡ ማለት በስዋሂሊ ቋንቋ ''ህክምና'' ማለት ሲሆን፤ ማግኔት እና ማቲስኮፕ የተሰኘ ተንቀሳቃሽ መሳሪያን ይጠቀማል። መሳሪያው ቀይ የብርሃን ሞገድ የተጠቃሚው እጣት ላይ የሚያበራ ሲሆን የወባ ጥገኛ የሆነ ሄሞዞን ክርስቲያልስ የተሰኘ ንጥረ ነገርን ይለያል። ፈጣሪዎቹ ማቲባቡ የደም ናሙና መውሰድን የማይጠይቅ በመሆኑ የምርመራ ጊዜን ከማሳጠሩም በተጨማሪ ህጻናት የሚፈሩትን መርፌ መወጋት ስለሚያስቀር ሁኔታውን ወደላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ያመናሉ። በሰሜን ዩጋንዳ የሚገኘው ኪትጉም ሆስፒታል የህጻናት መታከሚያ ክፍል የወባ በሽታ ባሳሰባቸው ወላጆች ተሞልቷል፡፡ በዩጋንዳ ባለፈው ዓመት በበሽታው የሞቱትን 5100 ሰዎች ጨምሮ 9.5 ሚሊዮን ሰዎች በወባ በሽታ ተጠቅተዋል። ከእነዚህም መካከል አብዛኞቹ ህጻናት ናቸው። "ልጄ በድንገት ማንቀጥቀጥ ጀመረው፤ ምግብም መብላት አቆመ። ደህና ይጫወት ነበር። ትምህርት ቤትም ይሄድ ነበር። ወዲያው ግን ታመመ።" ትላለች አቻን ናይቲ በሰሜን ዩጋንዳ በሚገኘው ኪጉሙ ሆስፒታል ውስጥ የስድስት ዓመት ልጇ ከተኛበት አልጋ ጎን ተቀምጣ። "የምንኖረው ከክሊኒኩ በጣም ሩቅ በሆነች ትንሽዬ የእርሻ ቦታ ላይ ነው። ሌሎች ሶስት ትንንሽ ልጆቼን መንከባከብ አለብኝ። ገንዘብም የለኝም። እዚህ ለመምጣት ሶስት ቀን ፈጅቶብኛል። በመዘግየቴ ልጄ ተጎድቶ እንዳይሆን ሰል እፀልያለሁ።" ትላለች። የ40 ዓመቷን አቻን ኒየቲንን እና ወንድ ልጇ ኦፒዮ ኢኖሰንትን የመሳሰሉ በርካታ ሰዎች የሚኖሩት ከህክምና ተቋማት በጣም ርቀው ነው። ብሪየን መጀመሪያ ይሄን የፈጠራ ሀሳብ ያመጣው በወባ እና ታይፎይድ በሽታ በተመሳሳይ ጊዜ በታመመበት ወቅት ነበር። በሆስፒታል አልጋ ላይ ሳለም፤ መርፌ የማይፈልግ ፈጣን እና ህመም የለሽ ተንቀሳቃሽ የመመርመሪያ መሳሪያን አሰበ። በምህንድስና፣ በኮምፒውተር ሳይንስ እና ተላላፊ በሽታዎች ክህሎት ካላቸው ምሩቆች ጋር ተጣመረ። ማይከሮስኮፕ የወባ በሽታን ለመመርመር 30 ደቂቃ ወይም ከዚያ በላይ ይፈልጋል። በተቃራኒ የመጨረሻው የማቲባቡ ስሪት ግን ሁለት ደቂቃዎች ብቻ በቂ ናቸው። ራፒድ ዳይግኖስቲክ ቴስትስ የተሰኘው ሌላው እና በአሁኑ ወቅት ተቀባይነት ያለው የናሙና መውሰጃ ዘዴ እስከ 15 ደቂቃ የሚወስድ ሲሆን የደም ናሙና ያስፈልገዋል። ነገር ግን የጥገኛ ትሎችን ብዛት ማሳየት ስለማይችል ከልክ ሊያሳልፍው ይችላል። ማቲባቡ ምንም የደም ናሙና ስለማይፈልግ የተለየ ባለሙያ አያስፈልገውም ። በመሆኑም የማህበረሰብ አባላቱ በራሳቸው ሊያከናውኑት ይችላሉ። የሀብት ምንጭ እጥረት በተጨማሪም ማቲባቡ ከስማርት ስልክ ጋር የተገናኘ ነው። ይህም ማለት መረጃ ለመሰብሰብ እና የጤና ቡድኖች የወባ ወረርሽኝ በሚኖርበት ጊዜ ጥቆማ ለመስጠት ያስችላል። "በርካታ ሰዎች የሚኖሩት በገጠር አካባቢዎች ሲሆን መንገዶችም አስቸጋሪ ናቸው። በመሆኑም ወደጤና አገልግሎቶች ለመድረስ ይቸገራሉ።" ይላሉ የኪትጉም ሆስፒታል ዳይሬክተር ዶ/ር ጎፍሬይ አኬና። "ይህንን ችግር ለመፍታት ጥረት ለማድረግም በአካባቢው ሰዎችን የሚያክሙ የጤና ቡድኖችን አሰማርተናል። ነገር ግን መረጃ ስለሌለን እየተንቀሳቀሱ ያሉት በጭፍን ነው።" እንደ ሮያል አካዳሚ ኦፍ ኢንጅነሪንግ ከሆነ የማቲባቡ መሳሪያ ጨዋታ ቀያሪ ሊሆን ይችላል፡፡ እንደ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከሆነ፤ በመላው ዩጋንዳ በየዓመቱ ወደ ተባባሰ በሽታ የሚሸጋገሩ 1.5 ሚሊዮን ከባድ የወባ በሽታ ጉዳቶች ይከሰታሉ። ይህም ማለት በሽታው የተደረሰበት ዘግይቶ ነው ማለት ነው። የወባ በሽታ በ24 ሰዓት ውስጥ ህክምና ከተደረገ በጣም በፍጥነት እና በተሰካ ሁኔታ ሊታከም ይችላል። ለአገልግሎት ዝግጁ የሆነው እና በፍጥነት ለሚፈልጉት የሚደርሰው ማቲባቡ ይህንን ክፍተት ለመሙላት እና የተረጋገጠ ህክምናን ለማግኘት ያግዛል። ታሪክ ቀያሪ ግኝት? ነገር ግን ሁሉም ነገር ግልጽ ነው ማለት አይደለም። የአሁኑ ማቲባቡ መሳሪያ መፈለግ የሚችለው 80 በመቶው ያህሉን የወባ በሽታ ጉዳቶችን ነው፡፡ ይህም ብራየንም እንደሚያውቀው በአለም አቀፍ ተቀባይነት ካለው የ99 በመቶው አሰራር በእጅጉ የራቀ ነው። "የእኛ መሳሪያ ከበፊቶቹ ስሪቶች ጋር ሲነጻጸር የገዘፈ ነው። ከግለሰብ ኮምፒዩተር ጋር የተገናኘ ነው። እናም ብርሃኑ የደም ናሙናው ላይ ስለሚያንጸባርቅ ጣትህን ወደ ውስጥ መክተት አትችልም። ነገር ግን አሁን የእኛ ትኩረት በ300 ህሙማን ላይ የምናደርገው ቀጣይ የቤተሙከራ ምርመራዎች እና መሳሪያውን ፍጹም ማድረግ ላይ ነው። ዲዛይኑን በኋላ እናሻሽለዋለን።" ሲል ብሪየን ይናገራል። ለዶክተሮቹ ገለጻ ከሚያደርግባቸው በርካታ ክሊኒኮች አንዱ በሆነው እና ከካምፓላ ወጣ ብሎ በሚገኘው ክሊኒክ ውጪ ላይ ትንሽ ሻንጣ የምታክለውን መሳሪያውን ይዞ እንደቆመ። ተግዳሮቶቹ እንዳሉ ሆነው ብራየን አሁንም ማቲባቡ እንደሚሰራ እርግጠኛ ነው። ለወደፊቱ መሳሪያው የደም ማነስን ለመሳሰሉ ሌሎች በሽታዎች መመርመሪያ እንደሚሆን ተስፋ በማድረግ በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ገበያውን ለመያዝ 600 መቶ ሺህ ዶላር እየፈለገ ነው። የወባ በሽታ በየዓመቱ ግማሽ ሚሊዮን ያህል ሰዎችን እንደሚገድልና ከእነዚህም የሚበዙት ከሰሃራ በታች የሚገኙ ትናንሽ ልጆች መሆናቸው ሲታሰብ አደጋው ከብራየን የስራ ህይወት እና መልካም ስምም በላይ ነው። ይህ የቢቢሲ ተከታታይ ክፍል የተዘጋጀው ከቢል እና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ነው።
news-46218896
https://www.bbc.com/amharic/news-46218896
በሞያሌ በሶማሌና በኦሮሞ ተወላጆች መካከል በተከሰተ ግጭት የ19 ሰዎች ህይወት አለፈ
ካለፈው እሁድ ጀምሮ ሞያሌ ከተማ ሰላም እርቋታል። ከአካባቢው ነዋሪዎች እና ባለስልጣናት እንደሰማነው፤ በይዞታዎች ይገባኛል ምክንያት በኦሮሞ እና ሶማሌ ታጣቂ ሚሊሻዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ የ19 ሰው ሕይወት አልፏል፣ 102 ሰው ቆስሏል።
የሞያሌ ወረዳ ጤና ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ቦሮ ሆቃ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በኦሮሚያ ወገን 6 ሰዎች ሲሞቱ 72 ደግሞ ቆስለዋል። በሶማሌ ክልል በደህንነት አማካሪነት የሚሰሩት አቶ ሸኑ ጎደኖ ደግሞ ከሶማሌ ወገን 13 ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ 30 መቁሰላቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ቦሩ እንደሚሉት ከሆነ በግጭቱ ከፍተኛ የጦር መሳሪያ በጥቅም ላይ ውሏል። • የብሔር ግጭት የሚንጣት ሀገር • የውጪ ሀገር ጥሪዎች ለምን በኢትዮጵያ ቁጥር ይወጣሉ? • የዓመቱ ሐሰተኛ ዜናዎች በአፍሪካ የሞያሌ ወረዳ የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ጠቼ ግጭቱ መነሳቱን አምነው ግጭቱ ግን የጎሳ ሳይሆን በሶማሌ በኩል የመሬት መስፋፋት ፍላጎት ስለነበረ ነው ሲሉ ከሰዋል። እንደ እርሳቸው ገለፃ የሶማሌ ክልል ሞያሌን ወደ ዞን ለማሳደግና የዞኑ ከተማ መቀመጫም ለማድረግ ፍላጎት አለው ሲሉ ይከሳሉ። ይህንንም ለክልልና ለፌደራል መንግስት አመልክተው ምላሽ እንዳላገኙ ይናገራሉ። አቶ አሊ ጠቼ ጨምረውም በግጭቱ የአንድ ትምህርት ቤት ሁለት ክፍሎች እና የጤና ኬላ መቃጠሉን ተናግረዋል። አቶ ሸኑ ጎደኖ በበኩላቸው የግጭቱ መንስዔ በኦሮሞዎች በኩል የመሬት መስፋፋት ፍላጎት በመኖሩ ነው ሲሉ ይናገራሉ። እንደ እርሳቸው አባባል ከዚህ በፊት ሁለቱ ህዝቦች የይገባኛል ጥያቄ ያነሱባቸው በነበሩ አካባቢዎች የኦሮሞ ተወላጆች መጥተው ባንዲራ መትከላቸው እንደሆነ ጨምረው አስረድተዋል። ባንዲራውን የተከሉት በሶማሊያ መሬት ላይ ጭምር እንደሆነ የገለፁት አቶ ሸኑ 'ባንዲራ ንቀሉ አንነቅልም' በሚል እሰጥ አገባ ግጭቱ መነሳቱን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
news-56144583
https://www.bbc.com/amharic/news-56144583
ኮሮናቫይረስ፡ የትኞቹ የአፍሪካ ሃገራት ክትባት ጀመሩ? ሌሎቹስ መች ይጀምራሉ?
በአህጉረ አፍሪካ ቢያንስ 100 ሺህ ያክል ሰዎች እስካሁን በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል። አህጉሪቱ የኮሮናቫይረስ ክትባትን በተገቢው መንገድ እየሰጠች አይደለም እየተባለች ትታማለች።
ለመሆኑ የትኞቹ የአህጉሪቱ ሃገራት ናች ክትባት መስጠት የጀመሩት? የዓለም ሃገራት የኮቪድ-19 ክትባት ለማግኘት ፉክክር ላይ ናቸው። የአፍሪካ ሃገራት ግን ሃብታም ከሚባሉት ሃገራት ጋር ሲነፃፀር ወደኋላ የቀሩ ይመስላሉ። "በጣም ተጋላጭ የሆኑ የአፍሪካ ሃገራት ክትባት የማግኘት ተራቸው እስኪደርስ ድረስ እየጠቁ ነገር ግን እምብዛም ተጋላጭ ያልሆኑ ሃብታም ሃገራት ክትባቱን ሲያገኙ ማየት ፍትሃዊ አይደለም" ይላሉ በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ማትሺዲሶ ሞዬቲ። የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማኽሮ የአውሮፓና ሃገራትና አሜሪካ ከክትባቶቻቸው ቀንሰው ለአፍሪካ ሃገራት መስጠት አለባቸው ሲሉ ምክረ ሐሳብ አመንጭተው ነበር። የተወሰኑ ክትባቶች ለአፍሪካ ሃገራት በፍጥነት ሊዳረሱ ይገባል ይላሉ ፕሬዝደንቱ። አፍሪካ ውስጥ እስካሁን ድረስ ክትባት ማግኘት የቻሉት ከፋብሪካዎች በቀጥታ መግዛት የቻሉና ከሩስያ፣ ቻይና፣ ሕንድና ዩናይትድ አራብ ኤሜሬትስ በእርዳታ መልክ ያገኙ ሃገራት ናቸው። የአፍሪካ ሃገራት በዓለም አቀፍና ቀጣናዊ ፕሮግራሞች ክትባት ለማግኘት ተስፋ አድርገዋል። አንደኛው ፕሮግራም ኮቫክስ የተሰኘው ነው። ይህ ፕሮግራም ሁሉም ሃገራት ክትባት ያገኙ ዘንድ ያለመ ነው። የዓለም ጤና ድርጅት ከያዝነው የፈረንጆች ወር መጨረሻ ጀምሮ የአፍሪካ ሃገራት ክትባት ማግኘት ይጀምራሉ ብሎ ይገምታል። በዚህ ወቅት የሚሠራጩ 90 ሚሊዮን ክትባቶች የአህጉሪቱን 3 በመቶ ሕዝብ ይከትባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይህ ክትባት በጣም ተጋላጭ ለሆኑና በቫይረሱ ምክንያት የበለጠ አደጋ ለሚደርስባቸው እንደ ጤና ባለሙያዎች ላሉ የሕብረተሰብ አካላት የሚከፋፈል ነው። የኮቫክስ ዓላማ 600 ሚሊዮን ክትባት ማግኘት ነው። ይህ የክትባት መጠን በፈረንጆቹ 2021 መጨረሻ ባለው የአህጉሪቱን 20 በመቶ ሰው ይከትባል። የአፍሪካ በሽታ ቁጥጥርና መከላከል ማዕከል ኃላፊ ጆን ንኬንጋሶንግ ግን ይህ የክትባት መጠን በሽታውን ከአፍሪካ ነቅሎ ለማስወጣት በቂ ነው ብለው አያምኑም። እሳቸው እንደሚሉት የአፍሪካ ሃገራት ቢያንስ 60 በመቶ የሚሆነውን ሕዝባቸውን መከተብ አለባቸው። የአፍሪካ ሕብረትም በሃምሳ አምስቱ የአፍሪካ ሃገራት ስም ክትባት ለማግኘት ደፋ ቀና እያለ ነው። የአፍሪካ ሞባይል ኔትወርክ አቅራቢ ድርጅት የሆነው ኤምቲኤን 25 ሚሊዮን ዶላር በማዋጣት ለአፍሪካ የጤና ባለሙያዎች የሚሆን ሰባት ሚሊዮን ክትባት ለማግኘት እየጣረ ነው። የበሽታ ቁጥጥር ማዕከሉ እንደሚለው በኤምቲኤን በኩል የተገኘ አንድ ሚሊዮን ክትባት ለ20 ሃገራት በያዝነው ወር መጨረሻ ይከፋፈላል። የትኞቹ ሃገራት ቀድመው ክትባቱን እንደሚያገኙ ግን የተባለ ነገር የለም። ዜጎቻቸውን መከተብ የቻሉ ሃገራት የትኞቹ ናቸው? ምንም እንኳ ጥቂት ሃገራት ባለፈው ወር ክትባት መስጠት ቢጀምሩም አብዛኛዎቹ ሃገራት ግን ገና አልጀመሩም። በሰሜን አፍሪካ ክትባት መስጠት የጀመሩት ሃገራት ሞሮኮ፣ አልጄሪያና ግብፅ ናቸው። ከሰሃራ በታች ባሉ አፍሪካ አገራት ደግሞ ደቡብ አፍሪካ፣ ሲሼልስ፣ ሩዋንዳ፣ ሞሪሺዬስና ዚምባቡዌ ይገኛሉ። እንደ ኢኳቶሪያል ጊኒና ሴኔጋል ያሉ ሃገራት የመጀመሪያውን ዙር የሳይኖፋርም ክትባት ተቀብለዋል፤ መከተብ ግን አልጀመሩም። በአህጉሪቱ በወረርሽኙ ክፉኛ የተጠቃችው ደቡብ አፍሪካ አስትራዜኔካ የተሰኘውን ክትባት ለመከተብ ዕቅድ ይዛ ነበር። ነገር ግን ክትባቱ በአዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ላይ ያለው ኃያልነት አናሳ ነበው በሚል ሰርዛዋለች። ነገር ግን አሁን ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ከተሰኘው ፋብሪካ የተገኘው ክትባት ለአዲሱ ዝርያ ፍቱን ነው በሚል መከተብ ጀምራለች። ደቡብ አፍሪካ ከሕንዱ አቅራቢ ያገኘችውን አድን ሚሊዮን የአስትራዜኔካ ክትባት ሌሎች የአፍሪካ ሃገራት መጠቀም ከፈለጉ በሚል ለአፍሪካ ሕብረት ሰጥታለች።
news-42746352
https://www.bbc.com/amharic/news-42746352
''በቂ መጠለያ ባለመገኘታችን ዛፍ ሥር እያደርን ነው''
በኦሮሚያ እና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አዋሳኝ የድንበር አካባቢዎች በተፈጠረው ግጭት ከሶማሌ ክልል በመሸሽ ባሌ ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ ዜጎች የውሃ እና የምግብ እጥረት አጋጥሞናል በአጠቃላይ በቂ ትኩረት አልተሰጠንም ሲሉ እያማረሩ ነው።
የባሌ ዞን ተፈናቃዮች ለዘርፈ ብዙ ችግር ተጋልጠው ይገኛሉ። ከአምስት ወራት በፊት ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ሸሽተው በኦሮሚያ ክልል በባሌ ዞን ጉራ ዳሞሌ በሚባል ወረዳ ውስጥ ተጠልለው ከሚገኙ ዜጎች አንዱ የሆኑት ሼህ አህመድ ኢያ መንግሥት እና ህዝቡ ድጋፍ ቢያደርግልንም አሁንም በርካት ችግሮች አሉብን ይላሉ። በሌሎች መጠለያ ካምፕ እንደሚታየው በቂ የሆነ መጠለያ እንደሌላቸው የሚናገሩት ሼህ አህመድ፤ በሰጠን የሸራ መጠለያ ውስጥ ነው እየኖርን የምንገኘው ይላሉ። ''ዋነኛው ችግራችን መጠለያ ነው። አሁን ዛፍ ሥር ነው እያደርን ያለነው። ቅያር ልብስም የለንም። ቀይ መስቀል ብርድ ልብስ ቢሰጡንም በቂ አይደለም'' ሲሉ ይናገራሉ። ከ16 ሺ በላይ ተፈናቀዮች የሰፈሩባት ወራዳ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ችግሮች እንዳሉባት የወረዳዋ ነዋሪዎች ይናገራሉ። ለ19 ዓመታት ከኖሩበት ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ግጭት በመሸት ቤት እና ንብረታቸውን ጥለው ወደ ጉራ ዳሞሌ ወረዳ እንደመጡ የሚናገሩት ደግሞ ወይዘሮ ፋይዳ ናቸው። ወይዘሮ ፋይዳ ''የ10 ወር ጨቅላ፣ የሦስት እና የስድስት ዓመት ልጆቼን ይዤ ነው ወደእዚህ የመጣሁት። በዚህ የመጠለያ ጣቢያ ውስጥ መኖር ስለማይቻል ወደ ከተማ ሄጄ በሰው ቤት ተቀጥሬ ልጆቼን ለማሳደግ ጥረት ላይ ነኝ'' ሲሉ ይናገራሉ። ''በምግብ እጥረት የተራበ የለም'' የባሌ ዞን የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ቢሮ ሃላፊ የሆኑት አቶ አብረሃም ኃይሉ በበኩላቸው ተፈናቅለው ለመጡ ዜጎች መንግሥት እና ህዝቡ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረጉላቸው ነው ይላሉ። አቶ አብረሃም ''ተፈናቃዮቹ በረሃማ ስፍራ ላይ ተጠልለው ስለሚገኙ የውሃ እጥረት አጋጥሟል፤ ለዚህም ተጨማሪ የውሃ ማመላለሻ መኪናዎች እንዲሰጡን ለሚመለከተው የክልሉ ቢሮ ጥያቄ አቅረበን እየተጠባበቅን ነው'' ይላሉ። ይሁን እንጂ ''በምግብ እጥረት የተራበ የለም'' ሲሉ አቶ አብረሃም ይናገራሉ። ''የእርዳታ ሥራውን ለማስተባበር ተፈናቃዮች የሚገኙባቸውን ወረዳዎች ተመልክቻለሁ፤ እስካሁን ድረስም በምግብ እጥረት ምክንያት የተራበ ወይም ህይወቱ አደጋ ላይ የወደቀ ዜጋ የለም። እንደውም ተፈናቃዮች የሚደረግልን ድጋፍ ይቀጥል የሚል በጎ አስተያየት ነው የሚሰጡን'' ይላሉ። የተፈናቃዮች ድጋፍ አስተባባሪና መልሶ ማቋቋም ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ዶክተር አበራ ዴሬሳ ''እኔ እስከማውቀው ድረስ ለተፈናቃዮች የምግብ እና ቁሶች ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው'' ይላሉ። ''የእርዳታ ምግብ በየሁለት ሳምንቱ እየተጓጓዘ ነው። የተፈናቃዮች ቁጥር ከፍተኛ ስለሆነ እና ተበታትነው ስለሰፈሩ እርዳታውን በሚፈለገው መጠን እና ፍጥነት ማድረስ ላይ ችግር አለ'' ሲሉም ጨምረው ተናግረዋል። አጠቃላይ ሁኔታ ከባሌ ዞን የአደጋ መከላለክለ እና ዝግጁነት ቢሮ የተገኘው አሃዝ እንደሚያሳየው በዞኑ በሚገኙ 8 ወረዳዎች ውስጥ 111 ሺህ በላይ ተፈናቀዮች ይገኛሉ። ከእነዚህ መካከል 64 ሺ የሚሆኑት ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ ሲሆን የተቀሩት ደግሞ በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ ድንበረ ላይ ይኖሩ የነበሩ ነገር ግን ግጭቱን በመሸሽ የመጡ ናቸው።
news-50143191
https://www.bbc.com/amharic/news-50143191
ወንዶች የወሊድ መቆጣጠሪያ ክኒና ለመዋጥ ዝግጁ ናቸውን?
ሳይንቲስቶች ለወንዶች የተስማማ የወሊድ መቆጣጠሪያ ክኒና ለመፈበረክ ደፋ ቀና ማለት ከጀመሩ ግምሽ ክፍለ ዘመን አለፋቸው።
ምንም እንኳ በጀ የሚያስብሉ ዜናዎች በአለፋ ገደም ቢሰሙም በቀላሉ መድኃኒት ቤት መደርደሪያው ላይ የምናገኘው ክኒና መፈብረክ ግን አልቀለለም። የፈንድ እጥረት እና የወንዶች ክኒናውን ለመውሰድ ብዙም ፈቃደኛ ሆኖ አለመገኘት መድኃኒቱ በቶሎ እንዳይመረት እንቅፋት ሆነዋል። ጥናቶች ግን ይህንን ይጠቁማሉ፡ ክኒናው ለገበያ ቢውል ለመዋጥ የተዘጋጁ በርካታ ወንዶች አሉ። ለምሳሌ እንግሊዝ ውስጥ ከሚገኙ ወንዶች [ወሲብ ማድረግ ከሚችሉ] አንድ ሶስተኛ የሚሆኑቱ አማራጭ የወሊድ መቆጣጠሪያ ከተገኘ ለመውሰድ ምን ገዶን? ሲሉ ለተሰጣቸው መጠይቅ ምላሽ ሰጥተዋል። ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ደግሞ የወሊድ መቆጣጠሪያ መንገዶችን መጠቀም ሴቶችና ወንዶች በእኩሌታ ሊጋሩት የሚገባ ኃላፊነት ነው ብለው ያምናሉ። ወደ አሜሪካ ስናቀና መጠይቁን ከሞሉ ወንዶች [ወሲብ መፈፀም የሚችሉ እና ዕድሜያቸው ከ18-44 የሆነ] መካከል 77 በመቶ የሚሆኑት የወንድ ወሊድ መቆጣጠሪያን ከመሞከር እንደማይቦዝኑ አሳውቀዋል። የወንዶች የወሊድ መቆጣጠሪያ ክኒናውን ለመዋጥ ዝግጁ መሆን ምናልባት በስተመጨረሻ የወንዶች ወሊድ መቆጣጠሪያ መድኃኒት ፋርማሲ እንዲገባ አብረታች ምክንያት ይሆን? አሁን ወንዶች በዋናነት የሚጠቀሟቸው የወሊድ መቆጣጠሪያ መንገዶች ሁለት ናቸው፡ ኮንደም እና የዘር ቱቦን መቁረጥ ተመራጩ የወሊድ መቆጣጠሪያ የተባበሩት መንግሥታት ያወጣው አንድ መረጃ በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ መውለድ ከሚችሉ ጥንዶች 3/4ኛ የሚሆኑት የወሊድ መቆጣጠሪያ በፍፁም አይጠቀሙም ይላል። ያም ሆኖ እጅግ በብዛት የወሊድ መቆጣጠሪያ የሚወስዱት ሴቶች መሆናቸውን ጥናቱ ያክላል። ትዳር ወይንም ግንኙነት ውስጥ ካሉ ሴቶች 19 በመቶዎቹ የዘር ቱቦን ማስቋጠር፣ 14 በመቶ ቆዳ ውስጥ የሚቀበር፣ 9 በመቶ የሚዋጡ ክኒናዎችን እንዲሁም 5 በመቶዎቹ ደግሞ መርፌን ይመርጣሉ። የወንድ የወሊድ መቆጣጠሪያ የሚባሉት በዋነኝነት ሁለት ናቸው፤ ኮንደም እና የዘር ቱቦን ማስቆረጥ። 8 በመቶ ኮንደም ሲጠቀሙ፤ 2 በመቶ ብቻ የዘር ቱቦ ማስቆረጥን ይመርጣሉ። የሴቶች የወሊድ መቆጣጠሪያ መድኃኒት በገፍ መመረት የጀመረው በ1960ዎቹ ነበር። ዛሬ ከ100 ሚሊዮን በላይ ሴቶች የወሊድ መቆጣጠሪያ ኪኒና ይውጣሉ። ይህ መድኃኒት በአውሮጳ፣ አውስትራሊያ እና ኒው ዚላንድ አንደኛ ተመራጭ የወሊድ መቆጣጠሪያ መንገድ ነው። በአፍሪካ፣ ደቡብ አሜሪካ እና ሰሜን አሜሪካ ሁለተኛ በእስያ ደግሞ ሶስተኛው ተመራጭ መንገድ ነው። መድኃኒቱ ከ20ኛው ክፍለ ዘመን ብርቱ ፈጠራዎች አንዱ ተደርጎ ይቆጠራል። ለሴቶች መብት ትልቅ አበርክቶ አድርጓል ተብሎም ይታመናል። ሴቶች ከወንድ አጋራቸው ጫና ተላቀው በራሳቸው ሕይወት ራሳቸው እንዲወስኑ አስችሏል ይባልለታል። ነገር ግን የፆታ እኩልነት ከቀን ቀን ለውጥ እያሳየ ቢመጣም የወሊድ መቆጣጠሪያ እና ወንዶች ብዙም ያለመቀራረባቸው ነገር አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል። የወንድ ልጅ ዘር [ስፐርም] ፍሬ ጎልቶ ሲታይ ወሊድ መቆጣጠሪያ ለወንዶች መሥራት ከባድ ነው? የወሊድ መቆጣጠሪያ ለሴቶች አምርቶ መሸጥ የወሰደው ጊዜ 10 ዓመት ገደማ ነው። እና ለምን ይሆን ለወንዶች የሚሆን የወሊድ መቆጣጠሪያ ሠርቶ መሸጥ እንዲህ የከበደው? አንዳንድ ሳይንቲስቶች የወሊድ መቆጣጠሪያዎችን ለወንዶች እንዲሆን አድርጎ ማምረት እንደ ሴቶቹ ቀላል አይደለም ይላሉ። ወንዶች የወሊድ መቆጣጠሪያ የዘር ፍሬን [ስፐርም] በመቆጣጠር ላይ የተመሠረተ ስለሆነ ከሴቶች በላቀ ውስብስብ እና የጎንዮሽ ጉዳት ያለው ነው ሲሉ ይሞግታሉ። ለወንዶች የወሊድ መቆጣጠሪያን ለመሥራት ሙከራ ማድረግ የተጀመረው የሴቶቹ ከተፈበረከ ዓመታት በኋላ መሆኑ አንሶ ሙከራው በገንዘብ እጥረት ብዙ ጊዜ ይቋረጣል። ለዚህ ደግሞ እንደ ምክንያት የሚጠቀሰው ደግሞ ፋርማሲዎች፣ ተቆጣጣሪዎች እና ወንዶች ራሳቸው ለክኒናው ያላቸው አሉታዊ አመለካከት ነው።
54790644
https://www.bbc.com/amharic/54790644
አቶ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ የደህንነት ስጋት አለን በሚል ከፍርድ ቤት ቀሩ
በሽብር ወንጀል ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ የደህንነት ስጋት አለን በሚል ምክንያት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ።
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ችሎት የተከሳሾች የንብረት እግድ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ነበር ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው። ይሁን እንጂ ከተከሳሾች መካከል አቶ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ ፍርድ ቤት አልተገኙም። ፍርድ ቤቱም አቶ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ ለምን ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ በጠየቀበት ወቅት፤ የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ተከሳሾቹ የደህንነት ስጋት አለብን በሚል ምክንያት አለመቅረታቸውን ለፍርድ ቤቱ አስታውቋል። . የአቶ በቀለ ገርባ ቤተሰቦች ጤናቸው አሳስቦናል አሉ . ፍርድ ቤቱ የእነ አቶ ጃዋርን የዋስትና መብት ጥያቄ ውድቅ አደረገ በእነ አቶ ጀዋር መሐመድ የክስ መዝገብ ውስጥ የተከሰሱት አቶ ሐምዛ ቦረና፤ "አቶ ጀዋር እና አቶ በቀለ 'አገሪቱ አሁን ያለችበት ተጨባጭ ሁኔታ ላይ ከፍተኛ ስጋት ስላለን በዚህ ቀጠሮ መገኘት አንችልም' ብለዋል" ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል። "አሁን ባለው ሁኔታ አይደለም ጉዳት ይቅርና ሙከራ [የግድያ] ቢደረግብን አገሪቱ ወደ ከፋ አደጋ ውስጥ ስለሚያስገባት ለአገሪቱ በማሰብ ወደ ፍርድ ቤት ከሚደረግ ጉዞ እራሳችንን ቆጥበናል" ስለማለታቸው አቶ ሐምዛ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም አሁን አገሪቱ ውጥረት ውስጥ እያለች በንብረት ጉዳይ ላይ ለመከራከር ፍርድ ቤት መመላለስ 'ለእኛ ሃፍረት' ነው በሚል ምክንያት ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን አቶ ሐምዛ፤ አቶ ጀዋር እና አቶ በቀለን ወክለው ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል። በእነ አቶ ጀዋር መዝገብ ስር ተከሰው ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡ ተከሳሾችም አገሪቱ አሁን ያለችበት ሁኔታ አሳስቦናል በማለት ለፍርድ ቤቱ መናገራቸውን ከእነ አቶ ጀዋር ጠበቆች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ከድር ቡሎ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ፍርድ ቤቱ በንብረት እግዱ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለሕዳር 15 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥተዋል።
news-46998889
https://www.bbc.com/amharic/news-46998889
ተቃውሞ የሚንጣት ድሬዳዋ
ሰኞ የእግዜርአብ ታቦት ገብቶ ሲመለስ ፖሊስ መሬት በሚባል አካባቢ በተፈጠረ ግጭት የጀመረው የድሬዳዋ ውጥረት ዛሬም ቀጥሏል።
ደውለን ያነጋገርናቸው የድሬዳዋ ነዋሪዎች እንደነገሩን ከሆነ አርብ ዕለት ከማለዳ ጀምሮ ወጣቶች ሰልፍ ሲያካሄዱ፣ የተቃሞው ድምጾችን ሲያሰሙ፣ አልፎ አልፎም ድንጋይ ሲወራወሩ ነበር። • የድሬዳዋ ቀለማት • መስታወት መፃዒውን ጊዜ ለማየት እንደሚያስችል ያውቃሉ? የወጣቶች ጥያቄ እየሰፋ መጥቶ የሥራ አጥነት፣ የመልካም አስተዳደር፣ የፍትህና የእኩልነት ጥያቄዎች ጎልተው መውጣት ጀምረዋል። በተለይም የድሬዳዋን ፍቅር አታደፍርሱ፣ በብሔር አትከፋፍሉን፣ «40/40/20» የተሰኘው የአስተዳደር ቀመር ይውደም፣ የሚሉ ተቃውሞዎች ሲሰሙ ነበር። ረፋድ ላይ ድሬዳዋ ራስ ሼል አካባቢ «ከንቲባው ይውረድ! ድምጻችን ይሰማ!» የሚሉ ድምጾችም ከፍ ብለው ይሰሙ ነበር። በዚያ ያልፉ የነበሩ ሦስት መቶ የሚገመቱ ወጣቶች ባንዲራዎችን ከመያዝ ውጭ ተቃውሟቸውን በሰላማዊ መንገድ ያቀርቡ እንደነበር አቶ ሰለሞን ኃይሌ የተባሉ የድሬዳዋ ነዋሪ ነግረውናል። • የጂግጂጋ ነዋሪ ጥንዶች ስጋት ላይ ነን እያሉ ነው ትናንትናና ከትናንት በስቲያ ረቡዕ ባንኮች ተዘግተው መዋላቸውንና የከተማዋ እንቅስቃሴ በአመዛኙ ታውኮ እንደነበረም ሰምተናል። ተቃውሞው ሙሉ ከተማውን ያካለለ ባይሆንም ተቃውሞወቹ ዋና ዋና የንግድ እንቅስቃሴዎች በከፊል እንደተስተጓጎለም ነዋሪዎች ነግረውናል። «ወጣቶቹ ሆ ብለው ሲመጡ ሱቆች ይዘጋሉ፣ በረድ ሲል ደግሞ መልሰው ይከፈታሉ ብለዋል» አቶ ሰለሞን ለቢቢሲ። ዛሬ ከዚራ፣ በዋናነት ደግሞ «ጂቲዜድ» የሚባል ሰፈር፣ እንዲሁም ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የሚገኝበት አካባቢ ፖሊስና ወጣቶች ተፋጠው ማርፈዳቸውን የዓይን እማኞች ነግረውናል።
45623503
https://www.bbc.com/amharic/45623503
የወጣቶች ጅምላ እሥር በአዲስ አበባ
ዕለተ ረቡዕ መስከረም 8/2011፤ ወ/ሮ መሠለች ተክሌ እና ቤተሰቦቻቸው የ12 ቀን ልጅ ልጃቸውን ትንሽ አመም አርጓት ኖሮ ወደ ሆስታል ያቀናሉ።
ቤተሰቡ ሃገር ሰላም ብሎ፤ ከሆስፒታል ተመልሶ ምሳ ለመብላት ሲሳናዳ ግን ያልታሰበ ነገር ተከሰተ። «የደንብ ልብሳቸውን በወጉ የታጠቁ አራት አምስት የሚሆኑ የፀጥታ ኃይሎች ልጄን አቶ መኮንንን ፍለጋ በክፍት መኪና መጡ» ይላሉ። «አንድ ጉርሻ እንኳን ይጉረስ ብላቸው እምቢ አሉኝ» ይላሉ ወ/ሮ መሠለች። • በሃገሪቱ የተከሰቱት ቀውሶችና አዲስ አበባ የፀጥታ ኃይሎቹና ልጃቸው መኮንን ወደ አሥር ሰዓት ገደማ ወደቤት መጥተው ፖሊሶቹ ፍተሻ እንዳደረጉ ወ/ሮ መሠለች ያስታውሳሉ። «ለጥያቄ ነው የምንፈልገው ይመለሳል ብለው ነው የወሰዱት» የሚሉት እናት መሠለች ልጃቸው መኮንን ግንቦት 7 ወደ ሃገር ቤት ሲገባ ለማስተባበር የተሰለፈው ኮሚቴ አባል እንደሆነ ያወሳሉ። ነገር ግን ልጃቸው መኮንን ፍርድ ቤት በቀረበ ወቅት 'ከቡራዩ እና አሸዋ ሜዳ ግርግሮች' ጋር በተያያዘ እንደተያዘ ተነግሮታል ይላሉ። • "ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ተገንጥሎ የሚወጣ አካል የለም"-ኤፍሬም ማዴቦ «እናቴ እና እህት ወንድሞቼ ቡራዩ የተከሰተውን ግድያ በመሸሽ እኔ ጋር ተጠልለው ነው ያሉት፤ እኔ እንዴት እንዲህ ዓይነት ነገር አደርጋለሁ፤ ብሎ ተክራክሯል» በማለት የፍርድ ቤት ውሎውን ያስታውሳሉ ወ/ሮ መሠለች። 3ኛ ፖሊስ ጣብያ መጀመሪያ ላይ ታስረውበት የነበረው ቦታ ለጤና ምቹ ያልሆነ፣ ጨለማ እና የሽንት ሽታ የነበረው እንደሆነ ወ/ሮ መሰለች ነግረውናል። «አሁን ግን. . .» ይላሉ፤ «አሁን ግን የተሻለ ሁኔታ ላይ ነው ያሉት» በማለት ያክላሉ። እንደሳቸው ልጅ ላለ የልብ ህመም እና የሳይነስ አለርጂ ላለበት ቀርቶ ለማንም የሚመች እንዳልሆነም ይጨምራሉ። ከኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦነግ) ወደ ሃገር ቤት መመለስ ዋዜማ ጀምሮ ሰላም ርቋት የቆየችው አዲስ አበባ ከሰሞኑ ደግሞ በየቦታው በሚስተዋሉ ጅምላ እሥሮች ድንጋጤ ላይ ያለች ትመስላለች። • የአርበኞች ግንቦት 7 አቀባበል ኮሚቴ አባል ፍርድ ቤት ቀረበ በፌስቡክ ስሙ Ab Bella የሚታወቅ ሰው ከፈረንሳይ አካባቢ ኳስ በመመልከት ላይ ሳለ ከምሽቱ አራት ሰዓት ገደማ ከሌሎች ሰዎች ጋር በጅምላ እንደታሰረ በገፁ ፅፏል። ከእሥር በኋላ ነው ሁሉም ከየተያዘበት በቡድን በቡድን ሆኖ እንዲሰለፍ የተደረገው የሚለው አቤል የእሥሩ ዓላማ ሰውን ማስደንበር ሳይሆን አይቀርም ይላል። ዛሬ ከሰዓት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባወጣው መረጃ መሠረት ከመስከረም 2 - 7 ባሉት ቀናት 28 ሰዎች ተገድለዋል፡፡ ከእነዚህም መሀከል 7ቱ በፖሊስ የተገደሉ ሲሆኑ አንድ ሰው በስህተት የተገደለ ነው ብሏል ፖሊስ፡፡ ከዚው ውጭ የሚወጡ መረጃዎች ፖሊስ የሚያውቃቸው አይደለም ሲሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሜጀር ጄነራል ደግፌ በዲ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ፖሊስ ሁከቱን ለማስቆም ባደረገው ሙከራም በህገ ወጥ ተግባራት ላይ ተሰማርተው የተገኙ በርከት ያሉ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉንም ኮሚሽነሩ አብራርተዋል። በአሁኑ ወቅትም በሁከቱ ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ የነበሩ 1 ሺህ 204 የሚሆኑ ግለሰቦችን ከተለያዩ አካባቢዎች በመሰብሰብ በቀጣይ ሌላ ጥፋት ላይ እንዳይሳተፉ ለማድረግ ሰንዳፋ እንዲቆዩ ከተደረገ በኋላ ለተሃድሶ ስልጠና ወደ ጦላይ እንዲገቡ መደረጉንም ኮሚሽነሩ አክለዋል። ኮሚሽነሩ 174 ሰዎች በህግ ይጠየቃሉ፤ ሌሎች ከ1400 በላይ ደግሞ ከሺሻ ቤት እና ቁማር ቤቶች የተያዙና በርካታ ገንዘቦች ያሏቸው ናቸው ብለዋል። ወ/ሮ መሠለች ልጃቸው በቁጥጥር ሥር ሲውልም ሆነ ፍተሻ ሲደረግበት የፍርድ ቤት ማዘዣ እንዳልነበር ይናገራሉ። «እግዚአብሔር ካለ መስከረም 24 ገደማ ይፈታል ብለን እንጠብቃለን» ሲሉ ወ/ሮ መሠለች ተሰፋ ያደርጋሉ። • ፓርላማው የኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7 የሽብርተኝነት ፍረጃ መነሳትን አፀደቀ
news-55445100
https://www.bbc.com/amharic/news-55445100
ኮሮናቫይረስ ፡ የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ክትባት ጥያቄ እንዴት ይመለሳል?
ኢትዮጵያ በቀጣይ ወራት ቢያንስ 20 በመቶ ለሚሆኑ ዜጎች የኮሮናቫይረስ ክትባት እንድታገኝ ለማስቻል እየተሠራ እንደሆነ የጤና ሚንስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ለሕዝም ተወካዮች ምክር ቤት ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ፤ የዓለም አገራት ክትባቱን እንዲያገኙ የሚያስተባብረው ኮቫክስ የተባለው ጥምረት አባል እንደመሆኗ፤ እንደሌሎች አገራት ሁሉ ክትባቱን እንዲደርሳት ይደረጋል ብለዋል ሚንስትሯ። "በበጀት እና በክትባት ተደራሽነት ላይ እየተሠራ ስለሆነ እንደ ሌሎች አገራት ኢትዮጵያ ቢያንስ 20 በመቶ ለሚሆነው ዜጋ ክትባት እንድታገኝ ይደረጋል" ሲሉ አስረድተዋል። ኢትዮጵያ ባላት አቅም ከምትገዛው ክትባት ባሻገር በልገሳ ተጨማሪ ጠብታ እንድታገኝ እንደሚደረግም ሚንስትሯ ተናግረዋል። የጤና ሚንስትሯ፤ ኢትዮጵያም ለኮቫክስ የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት ጥያቄ እንዳቀረበች ከሳምንታት በፊት መናገራቸው አይዘነጋም። ዶ/ር ሊያ ጨምረውም፤ ለአገልግሎት ብቁ ከሆኑ የክትባት አይነቶች መካከል ኢትዮጵያም እንድታገኝ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። በኮቫክስ በኩል ክትባቱን በፍጥነት ለማግኘትና በቅድሚያ መከተብ ለሚገባቸው ወገኖች እንዲደርስ ለማድረግ እንደሚሰራም መግለጻቸው ይታወሳል። እስካሁን በተደረጉ ምርምሮችና ሙከራዎች በርካታ ተስፋ ሰጪ ክትባቶች ተገኝተዋል። ለበሽታው ተጋላጭ ለሆኑና ለጤና ባለሙያዎችም እየተሰጠም ነው። ቅድሚያ ከሚሰጣቸው መካከል የእድሜ ባለጸጎችና የቀደመ ህመም ያለባቸው በዋነኛነት ይጠቀሳሉ። እስካሁን ቀዳሚውን የተጠቃሚነት ዕድል ያገኙት ባለ ጸጋ አገራት ሲሆኑ፤ የዓለም ጤና ድርጅት ደግሞ ክትባቱ ለሁሉም እንዲዳረስ ጥረት እያደረገ መሆኑን አመልክቷል። አገራትም ለዜጎቻቸው ክትባቱን ለማቅረብ ባላቸው አማራጮች ሁሉ እየሞከሩ ነው። "አላማቸው ፍትሐዊ ስርጭት እንዲኖር ነው" በስዊድን ማላርጋለን ዓለም አቀፍ የጤና ተቋም ውስጥ መምህርና የሕብረተሰብ ጤና ሳይንስ ተመራማሪ የሆኑት በንቲ ገለታ እንደሚሉት እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አቅመ ደካማ አገሮች ክትባቱን ሊያገኙ የሚችሉት በኮቫክስ አማካኝነት ነው። ኮቫክስ ስብስብ ውስጥ የዓለም ጤና ድርጅት፣ ክትባት ላይ የሚሰራው ጋቪ እና የወረርሽኝ ምላሽ የሚያስተባብር ተቋምም ይገኛሉ። በጋራ የሳይንሳዊ ፈጠራና የክትባት ስርጭትን ያስተባብራሉ። "የክትባት ክፍፍል ስሌቱ በዓለም ጤና ድርጅት ነው የሚሠራው። በእድሜ እና በጤና ባለሙያ ስብጥር የሚወሰን ይሆናል" ሲሉ ያስረዳሉ። አቅመ ደካማ አገሮች ክትባቱን ከማግኘት እንዳይገለሉ አቅምን የማስታበባር ስራ ይኖራል ሲሉም ያክላሉ። "ዓለም አቀፉ የአጤና ድርጅት ገንዘብ ያላቸው አገሮች ምርቱን እንዲያግዙም ያደርጋል" ይላሉ። በክትባት ሥራው 172 አገሮች እንደተሳተፉ ጠቅሰው፤ የቀለም፣ የእድሜ እና መሠራቱን ያስረዳሉ። "የዚህ አገር ነው የሚባል አይደለም። አላማቸው ፍትሐዊ ስርጨት እንዲኖር ነው። ኮቫክስ ይህንን ይሰራል" ሲሉም ያክላሉ። ከዚህ ቀደም የኮቪድ-19 ቁጥር ሪፖርት ሲደረግ ቻይና እና አሜሪካ መካከል ፉክክር እንደነበር እንደ ምሳሌ የሚጠቅሱት አቶ በንቲ፤ "ዓለም አቀፍ ፖለቲካው የክትባት ስርጭቱን ሊጎዳ ይችላል የሚል ፍርሀት አለ። ቢሆንም ግን ፍትሐዊ ስርጭት ይኖራል የሚል እምነት አለኝ" ሲሉ ያስረዳሉ። በሌላ በኩል ክትባት ተገኝቷል በሚል ማሕበረሰቡ መዘናጋት እንደሌለበት ያሳስባሉ። "ኮልድ ቼይን ወይም የቅዝቃዜ ሰንሰለት ክትባቱ ከተመረበት አንድ ቦታ እስከሚደርስ ያለው ሰንሰለት ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ በየጊዜው መብራት ይጠፋል። የትራንስፖርት ችግርም አለ። እነዚህን አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ከግምት በማስገባት ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ጥንቃቄ ነው።" እስከሚመጣው ዓመት መጨረሻ ድረስ በዓለም ሁለት ቢሊዮን የክትባት ጠብታ የማከፋፈል እቅድ አለ። ከዚህ ቅድሚያ የሚሰጠው ለሽታው በጣም ተጋላጭ ለሆኑ አረጋውያን እና የጤና ባለሙያዎች ነው። "አገራችን የወጣት አገር ናት። የእድሜ ባለጸጋዎች ቁጥር ትንሽ መሆኑ ከሚመደበው የክትባት ስሌት ሊያጎድል ይችላል" የሚሉት ባለሙያው፤ ክትባቱ ጥሩ መረጋጋት ቢያመጣም መዘናጋት እንዳይኖር ካሁኑ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ያሰምሩበታል። እስካሁን ድረስ ውጤታማ የተባሉ ክትባቶችን ዝርዝር እንመልከት። ፋይዘር/ባዮንቴክ ኮሮናቫይረስን በመከላከል 90 በመቶ ውጤታማ ነው የተባለው ይህ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ይፋ የሆነው በፈረንጆቹ ሕዳር 9/2020 ነበር። በወቅቱ ክትባቱን ይፋ ያደረጉት ፋይዘር እና ባዮንቴክ ኩባንያዎች ግኝቱ ለሳይንስና ለሰው ልጅ ትልቅ እድል ነው ብለዋል። የአሜሪካ እና የጀርመን ኩባንያ የሆኑት ፋይዘር እና ባዮንቴክ በስድስት የተለያዩ አገራት 43 ሺህ 500 ሰዎች ላይ መሞከራቸውን የገለጹ ሲሆን አንድም ጊዜ አሳሳቢ የጤና ችግር አልታየም ብለዋል። አስትራዜኒካ እና ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ አስትራዜኒካ እና ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ እያበለፀጉ ያሉት ክትባት ከፍተኛ ተስፋ ከተጣለባቸው ክትባቶች መካከል ነው። ይሄው ክትባት በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በሙከራ መልክ ተሰጥቷል። ደቡብ አፍሪካ ለዚህ የክትባት ሙከራ የተመረጠችው በዘርፉ ባሏት ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆን ከአፍሪካ በርካታ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ያሉባትና ወረርሽኙም በፍጥነት እየተስፋፋባት በመሆኑ ነው። ይህ የክትባት ሙከራ ኦኤክስ1ኮቪድ-19 ክትባት የሚባል ሲሆን፤ ኮሮናቫይረስን የሚያስከትለው ሳርስ-ኮቪ-2 በተባለው ቫይረስ ሰዎች እንዳይያዙ ለመከላከል የታለመ ነው። ሞደርና የዩናይትድ ስቴትስ መድኃኒት አምራች ኩባንያ የሆነው ሞደርና ከኮሮናቫይረስ 95 በመቶ የሚከላከል አዲስ ክትባት ማግኘቱን ይፋ ካደረገ ሰነባብቷል። ሞደርና የምርምር ውጤቱን ይፋ ያደረገበትን ዕለት "ታላቅ ቀን" በማለት ሐሴቱን ገልጿል። ስፑትኒክ-5 ይህ ሩሲያ ሰራሽ ክትባት ይፋ በተደረገ ጊዜ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በአገር ውስጥ በተደረገ ምርምር አገር በቀል ክትባት አግኝተናል፤ ለሰዎች አገልግሎት እንዲውልም ይፋዊና ብሔራዊ ፍቃድ ሰጥተናል ብለው ነበር። በዓለም የመጀመርያው የተባለው ይህ ስፑትኒክ-5 ክትባት ሞስኮ የሚገኘው ጋማሊያ ኢንስቲትዩት ነው ያመረተው። ክትባቱ ይፋ የተደረገውም ነሀሴ ወር ላይ ነበር። ኢንስቲትዩቱ እንደሚለው ክትባቱ አስተማማኝ የመከላከል አቅም ይሰጣል። ሲኖቫክ መላው ዓለም ለኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት ደፋ ቀና ሲል ቻይናም እጇን አጣጥፋ አልተቀመጠችም። ሲኖቫክ የተባለ ክትባት መስራት ከጀመረች ሰነባብታለች። እንደውም በጎ ፈቃደኞችን መከተብ ከጀመረች ቆየት ብላለች። በቻይና በሙከራ ላይ የሚገኘው የኮቪድ-19 ክትባት አመርቂ የሚባል ውጤት እያስገኘ ነውም ተብሏል። ሆኖም ክትባቱ አመርቂ ውጤት ያስገኘው በረዥም የሙከራ ሂደት ውስጥ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ሳይሆን፤ መካከለኛ ምዕራፍ በሚባለው ክፍል ነው።
news-54627450
https://www.bbc.com/amharic/news-54627450
የክራይሲስ ግሩፕ አጥኚ ዊሊያም ዳቪሰን በቅርቡ በመቀለ በነበረው ቆይታ ምን አስተዋለ?
የዓለም አቀፉ ክራይሲስ ግሩፕ ከፍተኛ አጥኚ ዊሊያም ዳቪሰን በፌደራል መንግሥት እና በትግራይ ክልል መካከል ያለው ውዝግብ ለመገምገም ወደ መቀለ ከተጓዘ በኋላ ለድርድር ፍላጎት እንዳለ የሚያሳይ ነገር የለም ሲል ለቢቢሲ ገልጿል።
የክራይሲስ ግሩፕ አጥኚ ዊሊያም ዳቪሰን በአይሲጂ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ከፍተኛ አጥኚ የሆነው ዊሊያም ዳቪሰን፤ ከሰሞኑ ወደ መቀለ ያቀናው ክልሉ ከፌደራል መንግሥት ጋር ስለገባበት ውዝግብ ያለውን አቋም ለመገምገም እና ከገቡበት አጣብቂኝ የሚወጡበትን መፍትሄው ለማፈላለግ መሆኑን ይናገራል። በመቀለ ቆይታውም የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን ጨምሮ ከበርካታ የክልሉ ኃላፊዎች ጋር መነጋገሩን የሚያስረዳው አጥኚው፤ በቆይታው ለድርድር ፍላጎት መኖሩን የሚያሳይ ነገር የለም ብሏል። ከሁለት ወራት በፊት ዓለም አቀፉ ክራይሲስ ግሩፕ (አይሲጂ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ አስታራቂና የሚያቀራርቡ ንግግሮቻቸውን ወደ ተግባር እንዲለውጧቸው መጠየቁ ይታወሳል። አይሲጂ ጨምሮም በሁለቱ አካላት መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ አስፈላጊ ከሆነም የአፍሪካ ሕብረት ወይም የአፍሪካ መሪዎች በማሸማገሉ በኩል ተሳትፎ ሊያደርጉ ይችላሉ ከማለት በተጨማሪ በተለይ የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበር የሆኑት የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ቁልፍ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ ብሏል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ ላይ ከትግራይ ክልል ጋር የተከሰተው አለመግባባት "በሕግ እና ሕግ ብቻ የሚመለሰው ይሆናል" ያሉ ሲሆን የፌዴሬሽን እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚሰጡት ውሳኔ ላይ ብቻ በመመሠረት ጉዳዩ በሕግ የሚመለስ መሆኑን ተናግረዋል። የአይሲጂ አጥኚ ዊሊያም ዳቪሰን "በክልሉ እና በፌደራል መንግሥት መካከል ያለው ፍጥጫ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ነው። በፓርቲዎቹ መካከል ያለው ትስስር እየቀነሰ ነው። የፌደራል መንግሥት የትግራይን በጀት ካቋረጠ ነገሮች ሊባባሱም ይችላሉ" ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። ዊሊያም ጨምሮም፤ የፌደራል መንግሥት ለትግራይ ክልል የሚሰጠውን በጀት ካቋረጠ "ክልሉ ይህንን እንደ ጦርነት ትንኮሳ እና ከፌደሬሽኑ እንደመገፋት አየዋለሁ ብሏል። ይሄም አሳሳቢ ነው" ሲል ተናግሯል። ዊሊያም "ሁለቱም ወገኖች ወደ ጠረጴዛው መጥተው የሚወያዩበት መንገድ ማግኘት አለባቸው። ይህ ካልሆነ ቀውስ ይከተላል" ብሏል። "በኢትጵያ ያሉ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች መወያየት ይፈልጋሉ ብዬ አስባለሁ። ብልጽግና ፓርቲ፣ የኦሮሞ፣ የሶማሌ፣ በደቡብ የሚገኙ ፓርቲዎች፣ ሕወሓትና የትግራይ ተቃዋሚዎችም መወያየት ይፈልጋሉ። ችግሩ ግን ምን አይነት ድርድር ማድረግ እንዳለባቸው፣ ግባቸው ምን እንደሚሆን፣ ቅድመ ሁኔታዎቹ ምን መሆን እንዳለባቸው የተለያየ አመለካከት ነው ያላቸው። ይህም ፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ መድረክ መጥተው ውይይት እንዳያደርጉ እክል ይሆናል" ይላል። በትግራይ በነበረው ቆይታ የተረዳውንም ሲያስረዳ፣ የትግራይ ክልል መንግሥት ወደ መሰል ድርድር ወይም ውይይት ሊገባ የሚችለው ጠንከር ያሉ ቅድመ ሁኔታዎች ሲጠበቁ ነው። "ለምሳሌ ምርጫውን የሚመራ ባለአደራ መንግሥት ይቋቋም የሚል ነጥብን አላቸው። አሁን ላይ የፌደራል መንግሥቱ ወይም ገዢ ፓርቲው ይህን ቅድመ ሁኔታ የሚቀበልበት ሁኔታ ያለ አይመስልም።" ዊሊያም በጉዳዩ ላይ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ጋር ተገናኝቶ የመነጋገር ፍላጎት ቢኖረውም እድሉ ግን እስካሁን እንዳልተመቻቸ ይናገራል። የክራይሲስ ግሩፕ ከፍተኛ አጥኚ የሆነው ዊሊያም ዳቪሰን፣ ድርጅታቸው አሸማጋይ አለመሆኑን ይናገራል። "ሁለቱንም አካሎች የምናነጋግረው ግንዛቤያችንን ለማዳበር ነው። ትንታኔያችን የሁሉንም አካላት አስተያየት የያዘ እንዲሆን የተሟላ ጥናት እየሠራን ነው። ከዛ ምክረ ሐሳባችን ለሁሉም አካል ትርጉም የሚሰጥ ይሆናል" ብሏል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የትግራይ ክልልን በሚያስተዳድረው ሕውሓት እና በፌደራል መንግሥቱ መካከል አለመግባባቶች እየተካረሩ መጥተዋል። ባለፈው ዓመት ለማካሄድ ታስቦ የነበረው አገራዊ ምርጫ በኮሮናቫይረስ ስርጭት ስጋት እንዲራዘም ተደርጎ የትግራይ ክልል የራሱን ክልላዊ ምርጫ ማከናወኑ በሁለቱ አካላት መካከል ያለውን ውጥረት ከፍ አድርጎታል።
51253939
https://www.bbc.com/amharic/51253939
የታገቱት ተማሪዎች፡ የቤተሰብ ሰቀቀን፤ የማሕበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ጩኸት፤ የመንግሥት ዝምታ
ከሚማሩበት የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ለደህንነታቸው በመስጋት ወደ ቤተሰቦቻቸው እየተመለሱ ሳለ ማንነታቸው ባልታወቀ ወጣቶች የታገቱ ተማሪዎች ጉዳይ አሁንም ምላሽ አላገኘም።
ተማሪዎቹ ከታገቱ 50 ቀናት አልፏቸዋል። ወላጆች ልጆቻቸው መታገታቸውን ከሰሙ አንስቶ ለሚመለከታቸው አካላት ልጆቻቸውን እንዲመለሱላቸው ሲጠይቁ ቆይተዋል። ይሁን እንጂ መንግሥት በጉዳዩ ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ አልሰጠም። የተማሪዎችን መታገት ተከትሎ ከቀናት በፊት ወደ አዲስ ዘመን ያቀናው የቢቢሲ ዘጋቢ ከተማዋ ሃዘን እንዳጠላባት ይናገራል። የታጋች ቤተሰቦች ፊታቸው ጠቁሮ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሆነው ነው ያገኘኋቸው የሚለው ዘጋቢያችን ቤተሰቦችን ማነጋገር እጅግ አሳዛኝ እንደነበር ያስረዳል። መሪጌታ የኔነህ አዱኛ መሪጌታ የኔነህ አዱኛ የተማሪ ግርማሽ የኔነህ አባት ናቸው። መሪጌታ የኔነህ ''በጥር 2 ተለቀዋል ስንባል ደስ ብሎን ነበር፤ ነገር ግን እስካሁን ከልጆቻችን ጋር አልተገናኘንም። መንግሥትም ያለን ነገር የለም። ገድለውብን ይሆናል ብለን እየፈራን ነው። በዚያ ላይ ልጆቹ አይተውት የማያውቁትን ነገር ሲያዩ ይደነግጣሉ ብለን እናስባለን። ሞተውም ከሆነ እውነቱን ነግረውን ቤተሰብ ጋር ተሰባስበን አልቅሰን እርማችንን ብናወጣ ይሻለናል፤ እንዲህ በየቀኑ ምን ሆነው ይሆን እያልን በሰቆቃ ከምንኖር" ይላሉ። መሪጌታ እንደሚሉት የልጃቻቸው መታገት በቤተሰባቸው ላይ ከፍተኛ ጭንቀት ማሳደሩን ይናገራሉ። "ባለቤቴ ጨንቅላቷ ተጨንቆ ጸበል ወስጄ ነው ያከረምኳት" በማለት ይናገራሉ። ወ/ሮ ማሬ አበበ የተማሪ በላይነሽ መኮንን ወላጅ ወ/ሮ ማሬ አበበ የተማሪ በላይነሽ መኮንን ወላጅ ወ/ሮ ማሬ አበበ የተማሪ በላይነሽ መኮንን ወላጅ ናቸው። ወ/ሮ ማሬ የእጅ ስልክ ስለሌላቸው በላይነሽን በስልክ ካገኙ ሰነባባተዋል። "ስልክ ስለሌለኝ የሆነው ሁሉ የምሰማው ከሰው ነው" ይላሉ። ''እህል አልበላ። ሌተ ተቀነ አይ ጉድ እያልኩ ነው። እግዜር ቢሰማን፤ መንግሥትም ቢራራልን፣ ልጆቻችን ቢሰዱልን እያልን ነው . . . አሳድጌ አሳድጌ ልጅ የለኝም ማለት ነው?" ሲሉም መልሰው ይጠይቃሉ። ተማሪዎቹን መንግሥት እንዳስለቀቃቸው ሲሰሙ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቷቸው እንደነበረ የሚያስታውሱት ወ/ሮ ማሬ፤ "ወሬ ሆኖ ቀረ እንጂ" በማለት ተማሪዎቹ ተለቀዋል ቢባልም ከልጃቸው ጋር ሳይገናኙ እንደቀሩ ያስረዳሉ። አቶ ሃብቴ እማኙ የተማሪ ግርማ ሃብቴ ወላጅ አባት አቶ ሃብቴ እማኙ የተማሪ ግርማ ሃብቴ ወላጅ አባት ናቸው። ልጃቸው ግርማ ከታገተ በሶስተኛው ቀን በአጋቾቹ ስልክ ደውሎላቸው እንደነበረ ያስታውሳሉ። "የነበረበትን አልነገረኝም። ብቻ ደህና ነኝ ነው ያለኝ።" "ተስፋዬ የነበረው እሱ ነው" የሚሉት አቶ ሃብቴ፤ "እናቱ ቤተ-ክርስቲያን እየተንፏቀቀች እኔም የምሰራው ቅጡ ጠፋኝ። ልጄ የሚያውቀው ነገር የለም፤ የቤት ልጅ ነው። እንኳን የሰው አገር የራሱንም አያውቀው። . . . እናቱም የእሱን ሁኔታ አይታ በቤት ውስጥ የሉትን ልጆች ልትመራልኝ አልቻለችም" ይላሉ። አቶ ሃብቴ "የማደርገው ጠፋኝ፤ ከፍ ብል ሰማይ ዝቅ ብል መሬት ሆኖብኝ፤ የእሱን መከራ ሳላይ ብሞት አይነደኝም ነበር" ይላሉ። የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ላቀ አያሌው ከታገቱ ተማሪዎች ወላጆች መካከል የተወሰኑትን አነጋግሬአለሁ ይላሉ። ምክትል ርዕሰ-መስተዳድሩ፤ እንደ አገር ተማሪዎችን ለማስለቀቅ የሚደረገው ጥረት አናሳ በመሆኑ ፈጥኖ መፍትሔ ማግኘት አልቻለም ባይ ናቸው። «በተለይም አካባቢውን የሚያስተዳድረው የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና የፌዴራሉ መንግሥት ትኩረት መስጠትና ተማሪዎችን ማስለቀቅ አለባቸው» በማለት ለክልሉ የቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግረዋል። የማሕበራዊ ሚድያ ጩኸት የተማሪዎች መታገት ከተሰማ ወዲህ ጀምሮ በማሕበራዊ ሚድያዎች በተለይም በፌስቡክና ትዊተር አለፍ ገደም ያሉ ዘመቻዎች መካሄድ ጀምረው ነበር። ከጥቂት ቀናት በፊት ጀምሮ ግን የማሕበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ጩኸታቸውን በሰፊው ማሰማት ጀምረዋል። ታዋቂ ኢትዮጵያዊያን የማሕበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎችም ዘመቻውን ተቀላቅለዋል። በተለይ ትዊተር በተሰኘው ማሕበራዊ መድረክ ላይ #Bringourgirlsback #Bringourstudentsback #WhereAreTheStudents? #ተማሪዎችየትገቡ? የተሰኙ ዘመቻዎች በመካሄድ ላይ ናቸው። ፌስቡክ ላይም ያሉ ታዋቂና በርካታ ተከታይ ያሏቸው ኢትዮጵያውያን ድምፃቸውን ስለታገቱት ተማሪዎች ለመናገር እየተጠቀሙበት ነው። ስለታገቱት ተማሪዎች መንግሥት ከጥር 2/2012 ውጭ በይፋ ያለው የለም። የቤተሰቦች ሰቀቀንና የኢትዮጵያውያን ጩኸት ግን ቀጥሏል። የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የሚገኝበት ምዕራብ ኦሮሚያ በኮማንድ ፖስት ትዕዛዝ ሥር ነው የሚገኘው። አልፎም የቴሌኮም ኔትወርክ ከራቀው ሰነባብቷል። ተማሪዎቹን ያገታቸው ማነው? ምንም እንኳ የጠቅላይ ሚንስትሩ የፕሬስ ሴክሬታሪ ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን በጥር 2 ቃለ-ምልልሳቸው ታግተው ከነበሩ አብዛኞቹ ተለቀዋል ቢሉም፤ ተማሪዎቹን ያገታቸው ማነው? ከተለቀቁ የት ነው የሚገኙት? ከወላጆቻቸው ጋር ለምን እንዲገናኙ አልተደረገም? ለሚሉ እና ለሌሎች ጥያቄዎች የሰጡት ምላሽ አልነበረም። ከዚህ በተጨማሪ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ታግተዋል ያሉት የተማሪዎች ቁጥር እና የፌደራል መንግሥት ከእገታው አስልቅቄያለሁ የሚለው ቁጥር ልዩነት፤ በመንግሥት መካከል በራሱ የመረጃ መጣረስ መኖሩን ያሳያል የሚሉ በርካቶች ናቸው። አስምራ የታገቱበትን ሁኔታ ስታስረዳ "ደምቢ ዶሎ እና ጋምቤላ መካከል 'ሱድ' የምትባል ቦታ ላይ ስንደርስ መኪናውን አስቁመው፤ ወጠምሻ ወጣቶች መጥተው አፈኑን። የአፋኞቹ ቁጥር ከእኛ ቁጥር በላይ ነበር" ትላለች። ወጣቶቹ በወቅቱ የጦር መሣሪያ እንዳልታጠቁም ነው የምታስረዳው። ተማሪዎቹን ያገታቸው የትኛው አካል እንደሆነ በይፋ ባይነገርም፤ የጃል መሮ ነው የሚመራው ኃይል ስለመሆኑ ብዙዎች ግምታቸው አላቸው። ከተማሪዎቹ መታገት በኋላ ከቢቢሲ ጋር ቃለ-ምልልስ አድርጎ የነበረው በምዕራብ ኦሮሚያ የሚንቀሳቀሰው የቀድሞ የኦነግ ጦር አዛዥ ዲሪባ ኩምሳ ወይም ጃል መሮ "ይህን ለመጀመሪያ ጊዜ እየሰማሁ ያለሁት ከእናንተ ነው። የትግል ዓላማችን ከተማሪዎች ጋር አይገናኝም። በተማሪዎቹ ላይም ይህን የተባለውን አይነት ተግባር አልፈጸምንም። እንደተለመደው የእኛን ስም ለማጉደፍ የተወራ ነው እንጂ በፍጽም እንዲህ አይነት ተግባር አሁንም ወደፊትም እንፈጽምም'' ሲል አስተባብሏል። ቢቢሲ የተማሪዎቹን መታገት ከሰማበት ጊዜ አንስቶ የተለያዩ የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎችን ለማግኘት ጥረት እያደረገ ነው። ይሁን እንጅ የተሰጠው ውል ያለው ምላሽ የለም። የጠቅላይ ሚኒስትር ፕሬስ ሴክሬታሪ ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁንም ሆኑ ቢልለኔ ስዩም፤ ዝርዝር መረጃ እንዲሰጡን በተደጋጋሚ ብንደውልም ስልካቸው ባለመነሳቱ ልናገኛቸው አልቻልንም። የአማራ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌትነት ይርሳውን፣ የሰላም ግንባታና ሕዝብ ደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ አገኘሁ ተሻገርን ለማግኘት በተደጋጋሚ ያደረግነው ሙከራ ምላሽ አላገኘም። ስለታገቱት ተማሪዎች በድጋሚ የጠየቅናቸው የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ መልሳችሁ ደውሉልኝ ካሉ በኋላ ስልክ ሊያነሱ ፈቃደኛ አልሆኑም። ስለታገቱት ተማሪዎች ተጨማሪ ዘገባዎችን ለማንበብ፡
news-53282952
https://www.bbc.com/amharic/news-53282952
በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ11 ሚሊዮን በላይ ሲደርስ ግማሹ አገገሙ
በዓለም ዙሪያ በፍጥነት እየተስፋፋ ባለው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ11 ሚሊዮን በላይ ደረሰ።
በሽታው ከቻይና ውጪ ወደ ሌሎች አገራት መዛመት ከጀመረ ስድስት ወራትን ያስቆጠረ ቢሆንም የመከላከያ ክትባትም ሆነ የሚፈውስ መድኃኒት ሳይገኝለት በየዕለቱ በዓለም ዙሪያ በ10 ሺህዎች እየተያዙ ይገኛሉ። አስከ ዛሬ ቅዳሜ ጠዋት ድረስ ያለው የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ አሃዝ እንደሚያመለክተው 11 ሚሊዮን 074 ሺህ 878 ሰዎች በዓለም ዙሪያ በበሽታው መያዛቸው ተረጋግጧል። ይህ ቁጥርም አገራት በዜጎቻቸው ላይ እያደረጉት ያለውን ከፍተኛ መጠን ያለው ምርመራን ተከትሎ በየደቂቃው እየጨመረ የሚሄድ ሲሆን፤ የበሽታው የመዛመት ፍጥነትም እየጨመረ መሆኑን ባለሙያዎች ይረናገራሉ። በዓለማችን በበሽታው መያዛቸው ከታወቁት ከ11 ሚሊዮን ከሚበልጡት ሰዎች መካከል ከፍተኛው ቁጥር ያላቸው ህሙማን የሚገኙት አሜሪካ ውስጥ ሲሆን ቁጥራቸውም 2 ሚሊዮን 794 ሺህ 153 ነው። በሁለተኝነት ደግሞ ብራዚል 1 ሚሊዮን 539 ሺህ 081 በበሽታው የተያዙ ሰዎች እንዳገኘች ያረጋገጠች ሲሆን ሩሲያ ደግሞ በ666 ሺህ 941 ህሙማን ሦስተኛዋ አገር ሆናለች። በሽታው የተረጋገጠ ፈዋሽ መድኃኒት ባይኖረውም በርካቶች በተለያዩ መንገዶች ከበሽታው ማገገማቸው ታውቋል። የጆንስ ሆፕኪንስ መረጃ እንደሚያመለክተውም እስካሁን በበሽታው መያዛቸው ከተረጋገጡት ከ11 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ውስጥ ከግማሽ የሚበልጡት ማገገማቸውን ያመለክታል። በዚህም መሰረት እስከ ቅዳሜ ጠዋት ድረስ 5 ሚሊዮን 863 ሺህ 847 ሰዎች በዓለም ዙሪያ ከወረርሽኙ ያገገሙ ሲሆን ከፍተኛው ቁጥር የተመዘገበባት አገር ደግሞ ብራዚል ናት። በብራዚል 984 ሺህ 615 ሰዎች፣ በአሜሪካ 790 ሺህ 404 ሰዎች እንዲሁም በሦስተኛ ደረጃ ሩሲያ ውስጥ 437 ሺህ 115 ሰዎች ከኮሮናቫይረስ አገግመዋል። በተጨማሪም በበሽታው ሰበብ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 525 ሺህ 121 ሰዎች በዓለም ዙሪያ ህይወታቸውን ሲያጡ፤ ከፍተኛው የሟቾች ቁጥር የተመዘገቡባት አገር አሜሪካ ናት። በአሜሪካ በኮሮናቫይረስ ሰበብ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 129 ሺህ 434 ሆኖ በመጀመሪያው ደረጃ ላይ ስትገኝ በሁለተኛዋ ብራዚል ውስጥ ደግሞ 61 ሺህ 884 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። ሦስተኛዋ አገር ደግሞ ዩናይትድ ኪንግደም ስትሆን የሟቾች ቁጥር 44 ሺህ 216 ነው። የዓለም የጤና ድርጅት በየዕለቱ በሚያወጣው መረጃ መሰረት አስፈላጊው ጥንቃቄ ካልተደረገ በበሽታው የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ መጠን እየጨመረ ሊሄድ እንደሚችል አስጠንቅቋል።
45748282
https://www.bbc.com/amharic/45748282
የብሔር ግጭት የሚንጣት ሀገር ኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ ከ2 ሚሊየን በላይ ዜጎች ከቀያቸው ጨርቄን ማቄን ሳይሉ ተፈናቅለዋል። እነዚህ ዜጎች ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ብሔርን መሠረት ያደረገ ጥቃትን ሸሽተው ነው የተሰደዱት። በሌላ በኩል ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የተለያዩ ተሀድሶዎችን እያደረጉ ነው።
አብዛኞቹ በየአካባቢው የተካሄዱ ግጭቶች መነሻቸው የሀብት እጥረትና የመሬት የይገባኛል ጥያቄ ሲሆን ሌሎቹ ግን በአገሪቱ ሰፍኗል በሚባለው የብሔር አድልዎና መገለል የተነሳ ነው። • ''ከቤታችን ሸሽተን ስንወጣ ጉረቤቶቻችን ያለቅሱ ነበር'' ይህ የብሔር ጥቃት በሀገሪቷ ዋና መዲና በአዲስ አበባና ዙሪያም የ58 ሰዎችን ሕይወት ከቀጠፈ በኋላ ብዙዎች ሀገሪቱ የገባችበት ብሔር ተኮር ጥቃት አስደንግጧቸዋል። ይህ ብሔር ተኮር ጥቃትና ግጭት ወደ ሥልጣን ከመጡ ስድስት ወር የሆናቸውንና በርካታ ለውጦችን ላደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አስተዳደር ዋነኛ ተገዳዳሪ ጉዳይ ነው። ባለፉት ወራት ብቻ በአገሪቱ ካሉት ዘጠኝ ክልሎች በአምስቱ ግጭት ተከስቷል። እነዚህ ግጭቶች አንዳንዶቹ ብሔር ተኮር ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ በግጦሽ መሬት፣ በውኃ ሀብት፣ በድንበር አስተዳደር መነሻነት የተቀሰቀሱ ናቸው። ባለንበት የፈረንጆቹ 2018 የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት በርካታ ኢትዮጵያዊያን ለደህንነታቸው በመስጋት የመኖሪያ ቀያቸውን ጥለው ለመሰደድ ተገደዋል። ሹቦ ቤክሶ ከምዕራብ ጉጂ ከተፈነቀሉት መካከል አንዷ ነች። • በተፈናቃዮች ብዛት ኢትዮጵያ ከዓለም ቀዳሚ ሆነች የብሔር ፌደራሊዝም ኢትዯጵያ ዘጠኙን ክልላዊ መንግሥቶች ስትመሠርት መነሻ ሐሳብ የነበረው በክልሎች መካከል ያለውን ዕድገት ለማሳለጥና ተገቢውን ውክልና ለማስፈን ነው ቢባልም የሥርዓቱ ተቺዎች ግን የአንድ ብሔር የበላይነትን ለማስፈን ነበር ይላሉ። ይህ የአንድ ብሔር የበላይነት አለበት ተብሎ ሲተች የነበረው ሥርዓት ለብሔርተኝነት መንሰራፋት እና በብሔሮች መካከል ግጭት ለመቀስቀስ ሰበብ ሆኗል በሚል ይተቻል። • በአዲስ አበባ ከጸጥታ ኃይሎች ጋር ባጋጠመ ግጭት 5 ሰዎች ተገደሉ ከአራት ዓመት በፊት በኦሮሚያ እና በአማራ ብሔሮች የተመራው ፀረ መንግሥት ተቃውሞ የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን በገዛ ፈቃዳቸው ከሥልጣን እንዲለቁ ምክንያት ሳይሆን አልቀረም። የብሔሮች መፈናቀልና ስደት የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት ድርጅት (ዩኒሴፍ) በነሐሴ ወር 2.8 ሚሊየን ሰዎች ከቀያቸው ተፈናቀለዋል ብሎ ያወጣው ሪፖርት የአብዛኞቹ የመፈናቀል ምክንያት በግጭትና በድርቅ ነው ሲል አስፍሯል። መቀመጫውን በጄኔቫ ያደረገውንና ሀገር ውስጥ የሚኖርን መፈናቀል የሚከታተለው ድርጅት ከ1.4 ሚሊየን በላይ ኢትዮጵያውያን ከባለፈው ታኅሣሥ ወር እስከ ሰኔ ወር ድረስ መፈናቀላቸውን አስቀምጧል። አብዛኞቹ የተፈናቀሉ ሰዎች ከሶማሌ፣ ከኦሮሚያና ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ናቸው። የቡራዩው ጥቃት የኦነግን ወደ ሀገር ውስጥ መግባትን በማስመልከት በተደረገ የአቀባበል ዝግጅት ወቅት በተፈጠረ ግጭት በአዲስ አበባና በቡራዩ 58 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። • በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች ድንበር ግጭት የገዳ ስርዓት መፍትሔ ለምን አላመጣም? በቡራዩ በነበረው ጥቃት "መሬታችንን ለቃችሁ ውጡ" የተባሉ እንዳሉ ተሰምቷል። ጥቃቱም የደረሰባቸው አብዛኞቹ ግለሰቦች የአንድ ብሔር ተወላጅ መሆናቸው በወቅቱ ተዘግቦ ነበር። ይህንንም ተከትሎ በአዲሳ አበባ ጥቃቱን የሚያወግዝ ሰልፍ ተካሄዷል። የኦሮሞና ሶማሌ ግጭት በሀገሪቱ ከተስተዋሉ ግጭቶች ባጠቃላይ የከፋው በኦሮሚያና በሱማሌ ክልል ተወላጆች መካከል የተነሳው ነው። ግጭቱን ለማርገብ እንደ አውሮፓውያኑ በ2004 የሕዝብ ውሳኔ ላይ ቢደረሰም፤ በሁለቱ ክልል ነዋሪዎች መካከል የድንበር ግጭቱ ተባብሷል። በሕዝበ ውሳኔው መሠረት 80 በመቶው የመሬቱ ክፍል ወደ ኦሮሚያ ክልል እንዲጠቃለል ተወስኖ ነበር። ሆኖም የድንበር ወሰን አልተከለለም ነበር። ይህን ተከትሎም በአካባቢው በየጊዜው ግጭት ሲከሰት ቆይቷል። • መቋጫ ያልተገኘለት የኦሮሚያ ሶማሌ ጉዳይ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ግጭቱ በተቀሰቀሰበት ወቅት 173 ሰዎች እንደተገደሉ ሲገልጽ፤ በአንጻሩ ተቃዋሚ ፓርቲው የኢትዮጵያ ሶሻል-ዴሞክራቲክ ፓርቲ የተገደሉት 400 ሰዎች እንደሆኑ ያትታል።። በዩኒሴፍ መረጃ መሠረት ግጭቱ ለ141,410 ሰዎች መፈናቀል ምክንያት ሆኗል። የጌድዮና ጉጂ ግጭት እንደ አውሮፓውያኑ በ2018 ላይ በደቡብ ክልል ጌድዮና በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ግጭት ዳግመኛ ሲቀሰቀስ 642,152 ሰዎች ለመፈናቀላቸው ምክንያት መሆኑ ተመልክቷል። ነሐሴ ወር ላይ መንግሥት ባወጣው መረጃ መሠረት፤ ለተፈናቃዮች 1,000 ጊዜያዊ መጠለያዎች ተዘጋጅተዋል። በዚሁ ወር የኖርዌይ የስደተኞች ካውንስል ወደ አንድ ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች በግጭቱ ሳቢያ እንደተፈናቀሉ አስታውቋል። • በጉጂ እና ጌዲዮ ግጭት ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቀሉ • "የጌዲዮና ጉጂ ተፈናቃዮች ቸል ተብለዋል" የዓለም ቀይ መስቀል ማኀበር እንደ አውሮፓውያኑ 2017 ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት በቦረና፣ ሞያሌ፣ ጉጂ እንዲሁም ባሌ ዞኖች ከ20 በላይ ሰዎች በግጭት ሳቢያ አንደሞቱ አሳውቋል። ከ10,000 የሚበልጡ ሰዎች ደግሞ ወደ ጎረቤት ሀገር ኬንያ ተሰደዋል። በሐዋሳ ና ወላይታ የጉራጌና ቀቤና ብሔረሰቦች ግጭት የ 15 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው እንደ አውሮፓውያኑ በ2018 ሰኔ ወር ላይ ነበር። የአማራና ትግራይ ግጭት የአማራና ትግራይ ክልሎች የድንበር ግጭት ከሁለቱም ክልሎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለመሞታቸው ምክንያት ሆኗል። እንደ አውሮፓውያኑ በ2016 የወልቃይት ጠገዴ ማኅበረሰብ መሬታችን ያለፍቃዳችን በትግራይ ተካሏል በሚል የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄድ ጀመሩ። የወልቃይት ጠገዴ ማኅበረሰብን በመደገፍ የተቃውሞ ሰልፉ በጎንደርና ባሕር ዳርም ቀጠለ። • በመቱ ዩኒቨርስቲ ብሔር ተኮር ውጥረት ነግሷል የቅማንት የማንነት ጥያቄን ተከትሎ በአንድ ቀን ውስጥ ከ50 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። ሪፖርተር ጋዜጣ እንደ አውሮፓውያኑ በ2016 በነሐሴ ወር 97 ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ዘግቧል። የብሔር ግጭቶች በአፋር እንደ አውሮፓውያኑ በሚያዝያ 2015 በአፋር አብሌክ አዳሊና ሲዲ ሀቡራ ጎሳዎች መካከል በተነሳው የብሔር ግጭት 15 ሰዎች ተገድለዋል። የቤኒ ሻንጉል ጉሙዝና የጋምቤላ ጥቃቶች እንደ አውሮፓውያኑ መስከረም 2018 ላይ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዐሥር ሰዎች በብሔር ተኮር ጥቃት ተገድለዋል። ሟቾቹ የትግራይና የአማራ ክልሎች ተወላጆች ናቸው። 2016 መግቢያ ላይ በጋምቤላ በብሔር ግጭት 20 ሰዎች ተገድለዋል። በዩኒሴፍ መረጃ መሠረት በጥር 2018 ወደ 14,000 ልጆች ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተለያይተዋል። በሀገሪቱ በየጊዜው እዚህም እዚያም ብሔርን መሠረት ያደረጉ ግጭቶች ይቀሰቀሳሉ። በሀገሪቱ የብሔር ፌደራሊዝም ሥርዓት ላይም ጥያቄ አጭሯል። ኢትዮጵያ ወደፊት ልትከተለው የሚገባት የአስተዳደር ሥርዓት ላይም ትኩስ ውይይትን ቀስቅሷል።
53627279
https://www.bbc.com/amharic/53627279
ኮሮናቫይረስ፡ አውሮፕላኖች እንዴት ነው በፀረ- ተህዋሲያን የሚፀዱት?
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ ቀጥ ብሎ የነበረውን የአለም የንግድ እንቅስቃሴን ለመመለስ በርካታ ጥረቶች እየተደረገ ነው።
በተለያዩ አገራትም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ጥለዋቸው የነበሩ መመሪያዎችን እያላሉ ይገኛሉ። የወረርሽኝ ስርጭቱን ለመግታት አገራት አስተላልፈዋቸው ከነበሩ መመሪያዎች መካከል ዓለም አቀፍ በረራዎችን ማቆም፣ አየር ማረፊያዎቻቸውንና ድንበሮቻቸውን መዝጋት ይገኙበታል። በዚህም የተነሳ በርካታ የኢንዱስትሪ ዘርፎች በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱ ሲሆን በተለይም የአየር ትራንስፖርት ዘርፉ እንዲሽመደመድ ምክንያት ሆኗል። ከሰሞኑ አገራቱ ዘግተዋቸው የነበሩ ድንበሮቻቸውን ከፍተዋል፤ አለም አቀፍ አየር መንገዶቹም በረራዎችን ጀምረዋል። የአለም አቀፉ አቪየሽን ድርጅት የአየር ትራንስፖርቱ ዘርፍ እንዲያንሰራራና ተጓዦችም ደህንነታቸቸው በተጠበቀ መልኩ እንዲጓዙ ለማድረግ እንደ መመሪያነት የሚያገለግል አንድ ሰነድ አውጥቷል። በዚህም መመሪያ ውስጥ ከተካተቱት ጉዳዮች መካከል አውሮፕላኖች በምን መንገድ በፀረ- ተህዋሲያን መፀዳት እንዳለባቸውና የፅዳት ድግግሞሽንም ይመለከታል። እንዲሁ ከላይ ከላይ ሲታይ የአየር በረራና አካላዊ ርቀትን መጠበቅ የሚጣጣሙ አይመስሉም ። ነገር ግን ተቆጣጣሪ አካላት የተለያዩ ፕሮቶኮሎችን በማውጣት አስፈላጊ የሚባሉ የፅዳት መመሪያዎችን ለመተግበር ቀን ተሌት ደፋ ቀና በማለት ላይ ናቸው። ለአየር በረራዎች በዋነኝነት የሚያስፈልገው ፈጣንና፣ በቅልጥፍና የተሞላ ውጤታማ ፀረ- ተህዋሲያን የፅዳት ስርዓት መዘርጋት ነው። ከዚህም ጋር ተያይዞ ፍቃድ ያላቸው የፀረ- ተህዋሲያን ፅዳት በሚታዩና፣ ተደራሽ በሆኑ አካላት ላይ ጨርቅን እንዲሁም ተንቀሳቃሽ መርጫን በመጠቀም ማፅዳት ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛሉ። ነገር ግን ሁለቱም የማፅጃ መንገዶች በሰዎች አማካኝነት የሚካዱ ከመሆናቸው አንፃር ውጤታማነታቸውን የሚቀንስ ሲሆን መደረስ የማይችሉ የአውሮፕላኑ አካላትም ላይ ክፍተትን ይፈጥራሉ ተብሏል። ኦክስጅንና ኦዞን በሌላ መልኩ "አቶሚክ ኦክስጅንን" እንደ ፀረ-ተህዋሲያነት በመጠቅም አካባቢን ለማፅዳት ተጀምሯል። ከዚህም በተጨማሪ አምቡላንሶችን ለማፅዳት የሚጠቀሙበትን ፀረ ተህዋሲያንንም ለአውሮፕላን የውስጥ ክፍል ለማፅዳት እየታሰበበት ነው። ነገር ግን እነዚህ ማፅጃዎች ባላቸው የንጥረ ነገር በተለይም 'ኦክሳይድ' ባለው ባህርይ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች ላይ ጉዳት ሊፈጥሩ ይችሉ ይሆን በሚለው ስምምነት ላይ አልተደረሰም። መቶ በመቶ ውጤታማ የፀረ ተህዋሲያን ማፅጃ በሌለበት ሁኔታ ሌላኛው አማራጭ "የኦዞን" ንጥረ ነገሮችን መጠቀም ነው። በአሁኑ ወቅት ኦዞን በአውሮፕላን አካላት ላይ አገልግሎት ላይ ባይውልም በመጠጥ ቤቶችና በተለያዩ የንግድ ተቋማት ላይ በፀረ-ተህዋሲያን ማፅጃነት እያገለገለ ይገኛል። አካባቢውን የኦዞን ንጥረ ነገሮችን በመርጨት ውጤታማ የሆነ ፅዳትን ማግኘት ይቻላል። ነገር ግን ይህ ንጥረ ነገር በከፍተኛ መጠን ሲሆን ለሰዎች ጎጅ በመሆኑ ባለሙያን በመጠቀም መንገደኞች በሌሉበት ሁኔታ ሊረጭ ይገባል። ነገር ግን አሁንም ቢሆን ኦዞን ላይ ያለው ዋነኛ ጥያቄም የኦክሳይድ ንጥረ ነገር መጠኑ ነው፤ 'በአውሮፕላን የውስጥ አካልና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ላይ ያለው ተፅእኖ ላይ መስማማት አልተቻለም። 'አየኖችና የአልትራቫዮሌት ጨረር ' በላብራቶሪ ውስጥ ተሞክሮ ውጤታማ የሆነው ከከባቢ አየር የሚለቀቀውን የውሃ ትነት ውስጥ የኦክስጅንና ሃይድሮጅን ንጥረ ነገሮችን ለይቶ በማውጣት ፀረ ተህዋሲያንን መፍጠር ነው። ይህ የፀረ ተህዋሲያን ማፅጃ መንገድ በጣም አድካሚና ለሁለት ሰዓታት ያህልም የሚወስድ ጊዜን ይፈጃል። ሆኖም ይሄ መንገድ በከፍተኛ ሁኔታ ውጤታማና መቶ በመቶ የሚተማመኑበት ነው። ከዚህም በተጨማሪ ፀረ ተህዋሲያኑ ቀላልና ተንቀሳቃሽ በሆነ መልኩ ትልልቅ የአውሮፕላን አካሎችን ማፅዳት ቢቻልም ለማፅዳት ግን ረዘም ያለ ጊዜ መውሰድ ያስፈልጋል። ሌላኛው ደግሞ ሲ የሚባለው የአልትራቫዮሌት ጨረር ሲሆን ይህ ጨረር ሳርስ የተባለውን የኮሮናቫይረስ አይነት ማጥፋት ይችላል። ለዚያም ነው ከፍተኛ ወጪ የሌላቸው ጨረሮች የአውሮፕላን አካላትን ለማፅዳት እየተነደፉ እንዲሁም እየተመረቱ ያሉት። ይህንም ተከትሎ በገበያው ላይ የነዚህ ጨረሮች ፍላጎት በመጨመሩ ምክንያት የአልትራቫዮሌት ጨረሮችን የሚያመርቱ ኩባንያዎች ምርታቸው በሚቀጥሉት አራት አመታት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጨምርም ግምታቸውን አስቀምጠዋል። በርካታ አማራጮች በርካታ የፀረ ተህዋሲያን ማፅጃ አማራጮች ከመኖራቸው አንፃር በተለያየ ሂደትም ላይ ናቸው። አሁንም ቢሆን የትኛው የበለጠ ተስማሚ እንደሆነም እስካሁንም አይታወቅም። የትኛው የፀረ ተህዋሲያን ስርአት የበለጠ ውጤታማ እንደሚሆን መለየት ከተቻለ በኋላ ምን ያህል ጊዜም ይወስዳል የሚለውን ማየት አስፈላጊ እንደሆነም እየተነገረ ነው። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ አሁንም ስጋት ሆኖ ባለበት ወቅት በርካታ አየር መንገዶች በረራ መጀመራቸው ጋር ተያይዞ ቫይረሱ እንዳይሰራጭ የማድረግ ከፍተኛ ኃላፊነትና ሸክም ተጥሏባቸዋል። የአውሮፕላኑ ሰራተኞች፣ መንገደኞችን ደህንነት በሚያስጠብቅ መልኩ አውሮፕላኖቹ በፀረ ተህዋሲያን መፀዳትም ግዴታ ነው። እነዚህ የፀረ ተህዋሲያን ማፅጃ ዘዴዎች ቫይረሱን መግታት ብቻ ሳይሆን የአየር መንገድ ኃላፊዎችም ሆነ ተቆጣጣሪዎች የሚያስወጣቸውን ዋጋና እንዲሁም ቀልጣፋና ውጤታማ በሆነ መንገድ መፅዳት የሚችሉበትን ሁኔታ መገምገም ይጠበቅባቸዋል። በአንድ መልኩ የአየር ትራንስፖርቱ ወደቀደመ ሁኔታ እንዲመለሱ ግፊት እያደረጉ ሲሆን በሌላ መልኩ በዚህ ወረርሽኝ መካከል የተጓዦች ደህንነት በተጠበቀ መልኩ አገልግሎታቸውን መመለስና በወረርሽኙ ምክንያት ያጡትን ገቢ ለማግኘትም አጣጥመው መሄድ ይጠበቅባቸዋል። በተለይም አውሮፕላኖቹ የሚፀዱበትን ደረጃና ያለውን የስጋት መጠንን መቀነስና፤ የሚፀዳበትን ጊዜ አጣጥመው መሄድም ይጠበቅባቸዋል። የመንገደኞችን ጤንትና ደህንነት ቅድሚያ በመስጠትም አየር መንገዶቹ እነዚህን ተግባራት እንዲያከናውኑም አለም አቀፉ አቪየሽንም መመሪያ ሰጥቷል። ከአለም አቀፉ አቪየሽን ቡድንና፣ የትራንስፖርት ዘርፍ ተመራማሪዎች የተውጣጡ ግለሰቦችም ውጤታማ የሆኑትን የፀረ ተህዋሲያን የማፅጃ ዘዴዎችንም ለመቀየስ ከፍተኛ ምርምሮችን እያደረጉም ነው፤ የተለያዩ መመሪያዎችንም በማውጣትም ላይ ይገኛሉ።
news-41330086
https://www.bbc.com/amharic/news-41330086
ማሪያ አውሎ-ንፋስ ፖርቶ ሪኮና ቨርጅን ደሴቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ
ማሪያ ተብሎ የተሰየመው አውሎ-ንፋስ ፖርታ ሪኮና ቨርጅን ደሴቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ
በባህር ዳርቻ አካባቢ የሚገኙ ከተሞችን ሃይለኛ ንፋስ ዛፎችን ሲነቀንቅ ነበር መድብ አምስት የተባለው ከባድ አውሎ-ንፋስ በካረቢያን ዶሚኒካ ደሴት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ካደረሰ በኋላ ነው ወደ ፖርቶ ሪኮና ቨርጅን ደሴቶች የተሻገረው። ከባድ አውሎ-ንፋሱ በሰዓት 280 ኪ.ሜ እየነፈሰ ይገኛል። የማሪያ አቅጣጫ ኤርማ የተባለው አውሎ-ንፋስ የነፈሰበትን አቅጣጫ ይዞ እየተጓዘ ነው። የአሜሪካ ግዛት የሆነችው የፖርታ ሪኮ አስተዳዳሪ 3.5 ሚሊዮን ለሚሆኑት የግዛቷ ነዋሪዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል። የቀደመው ኤርማ አውሎ-ንፋስ ትቶት የሄደውን ስብርባሪ ማሪያ የተባለው ከባድ ነፋስ አንስቶት ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል የሚል ስጋት አለ። ከዚህ በተጨማሪም እየጣለ ያለው ከፍተኛ ዘናብ የመሬት መንሸራተት ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት አለ። የእንግሊዝ ቀኝ ግዛት በነበረችውና 72 ሺህ ህዝብ እንዳላት በሚነገርላት ዶሚኒካ በአውሎ-ንፋሱ ምክንያት ሰባት ሰዎች ሞተዋል፤ የመሬት ናዳም ተከስቷል። ጠቅላይ ሚንስትር ሩዝቨልት ስኬሪት ''እስካሁን ያናገርኳቸው ሰዎች በጠቅላላ የቤታቸው ጣሪያ በንፋስ እንደተወሰደ ነግረውኛል'' ብለዋል። የጠቅላይ ሚንስትሩም የቤት ጣሪያ በአውሎ-ንፋሱ መወሰዱ ይታወሳል። በዶሚኒካ የመገናኛ ዘዴዎች ከጥቅም ውጪ ሆነዋል።
49916461
https://www.bbc.com/amharic/49916461
10 ሚሊዮን ሕዝብ ይታደምበታል የተባለው ኢሬቻ በአዲስ አበባ
በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ እና የተለያዩ ሃይማኖቶችን የሚከተሉ ኦሮሞዎችን የሚያገናኘው የኢሬቻ በዓል በመጪው ቅዳሜ በአዲስ አበባ፤ እሁድ ደግሞ በቢሾፍቱ በድምቀት ለማክበር የተለያዩ ዝግጅቶች መደረጋቸው ተገልጿል።
ይህ የኢሬቻ ክብረ በዓል በኦሮሞዎች ዘንድ ከሚከበሩ የተለያዩ ክብረ በዓላት መካከል አንዱ ሲሆን፣ በትውልዶች መካከል ሲወርድ እንደመጣ ይነገራል፡፡ በዓሉ በአዲስ አበባ መከበር ካቆመ 150 ዓመታት እንዳለፉት የሚናገሩት አባገዳዎች ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በከተማዋ ላይ ሊከበር መሆኑ ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረባቸው ገልፀዋል። • ኔታኒያሁ ከጠ/ሚ ዐብይ ጋር ስለኤርትራዊያን ስደተኞች መወያየታቸውን ተናገሩ • "የሰለጠነና በሙሉ አቅም የሚዋጋ ኃይል ነው ችግሩን የሚፈጥረው" የማዕከላዊ ጎንደር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ • "ተጨማሪ የፌደራል የሥራ ቋንቋዎች እንዲኖሩ እየተሠራ ነው" ጠ/ሚኒስትር ዐብይ ከ150 ዓመት በኋላ በአዲስ አበባ የሚከበረውን ኢሬቻ ለማክበርም ከኦሮሚያ ከልል ሁሉም ዞኖች ታዳሚዎች ወደ አዲስ አበባ እየተመሙ መሆኑነን ቢቢሲ ያነጋገራቸው ግለሰቦች ይገልፃሉ። ከእነዚህም መካከል አንዱ የሆነው የሐረሩ ነገዎ መገርሳ ከሚኖርባት ጃርሶ ወረዳ፣ አፍረን ቀሎ ከተማ ተነስቶ ነጭ ባንዲራ በመያዝ ወደ አዲስ አበባ መጥቷል። ነገዎ ከሚኖርባት ከተማ መስከረም 10/2012 ዓ.ም የተነሳ ሲሆን ዘጠኝ ቀንና ለሊት በእግሩ ተጉዞ አዳማ ከደረሰ በኋላ ቢቢሲ አግኝቶ አነጋግሮታል። ነገዎ አዲስ አበባ ድረስ በእግሩ ለመጓዝ የፈለገው ኢሬቻ ከ150 ዓመት በኋላ በሀገሪቱ መናገሻ ከተማ አዲስ አበባ መከበሩን በማስመልከት እንደሆነ ይገልፃል። በየደረሰበት ከተማ ነዋሪው መልካም አቀባበል እንዳደረገለት የሚናገረው ነገዎ፤ አዲስ አበባ ሲደርስ አምስት የኦዳ (ዋርካ) ዛፍ ችግኝ እንደሚተክል ተናግሯል። ነገዎ ከዚህ ቀደም 30 ሺህ የዛፍ ችግኞችን በማፍላት በተለያዩ ክልሎች መትከሉን ገልጾ አሁን ደግሞ በአዲስ አበባ አምስቱም የመግቢያ በሮች ለመትከል ማቀዱን ይናገራል። ዝግጅቱ ምን ይመስላል? ዕረቡ ዕለት የኦሮሚያ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ እሬቻን በአዲስ አበባ (ሆረ ፊንፊኔ) በደመቀ ሁኔታ ለማክበር የሚያስችል ቅድመ ሁኔታ መጠናቁቅን በማስመልከት መግለጫ ሰጥቷል። ከ150 ዓመት በኋላ በአዲስ አበባ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል የኢሬፈና (ምስጋና የማቅረብ ሥነ ሥርዓት) ስፍራ በፍል ውሃ አካባቢ እንደሚሆን ተለይቶ አካባቢውን የማስተካከል ሥራ መሰራቱንም ጨምሮ ገልጿል። • አሥመራን አየናት፡ እንደነበረች ያለችው አሥመራ በዚህ በዓል ላይ ለመታደም ከአማራ፣ ከትግራይ፣ ከአፋር፣ ከሱማሌ፣ ከደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል፣ ከቤንሻንጉል ጉሙዝና ሌሎች ክልሎች የሚመጡ ተሳታፊዎች እንደሚኖሩም ተገልጿል። በዋዜማው መስከረም 23፤ የተለያዩ ዝግጅቶች የይኖራሉ ያለው ቢሮው ከእነዚህ መካከል አራት ሺህ ሜትር የሚረዝም ጭኮ፣ የሙዚቃ ድግሶች በሚሌኒየም አዳራሽና በስታዲየም፣ እንዲሁም የሲዳማ የቄጠላ ባህል (ባህላዊ ጭፈራ) ይቀርባል ሲሉ ጨምረው አስረድተዋል። አክለውም በመስቀል አደባባይ የጭኮ ዐውደ ርዕይ፣ የቄጠላ ጭፈራ፣ የፈረስ ጉግስ እንዲሁም ሌሎች የባሕላዊ ምግቦችና አልባሳት ትርዒት እንደሚኖር በመግለጫው ላይ ተጠቅሷል። ክብረ በዓሉ ላይ ከሁሉም የኦሮሚያ ዞኖች ተሳፈታፊዎች ወደ አዲስ አበባ መጓዝ የጀመሩት ከቀናት በፊት መሆኑን በማስታወስም በአጠቃላይ 10 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ ይታደማል ተብሎ እንደሚጠበቅ በመግለጫው ወቅት ተነግሯል። በዓሉ በሰላማዊ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ከ15 እስከ 20 ሺህ የሚሆኑ ወጣቶች [ፎሌዎች] እንደሚሳተፉ የተገለፀ ሲሆን የሰላም ማስከበሩን ሥራ በኃላፊነት የሚሰራ ኮሚቴም ተዋቅሯል ተብሏል። በትናንትናው ዕለትም የኢሬቻ በዓልን ምንነት ማስረዳት ላይ ያተኮረ ፎረም በሸራተን አዲስ ተካሂዷል። • እንቅስቃሴ አልባዋ ምጽዋ በፎረሙ ላይ የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ ምሁራንና አባገዳዎች ጥሪ ከተደረገላቸው እንግዶች ጋር የታደሙ ሲሆን የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል። የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር የሆኑት ሒሩት ካሳው ባደረጉት ንግግርም "የብሔር ብሔረሰቦች ባህል ከሌለ የኢትዮጵያ ባህል የምንለው አይኖርም" ሲሉ ተናግረዋል። አክለውም የሕዝቦችን መቀራረብ ለማጠናከርና የሀገሪቱን ቱሪዝም ለማበረታታት ይህንን መሰሉ ባህላዊ ፌስቲቫሎች ትልቅ ድርሻ እንዳላቸው ጠቅሰዋል። አባ ገዳዎችና አደ ሲንቄዎች የኢሬቻ ባህልን ጠብቀው ወደዚህ ትውልድ በማስተላለፋቸው አመስግነው፤ ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ ደግሞ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤታቸው የድርሻውን እንደሚወጣ ተናግረዋል። 4000 ሜትር የሚረዝም ጭኮ የኦዳራ ኢንተርናሽናል ካፌ ባለቤት የሆኑት አቶ ድንቡ አብደላ፤ የኢሬቻ ክብረ በዓል ወደ አዲስ አበባ መመለሱን አስመልክተው "የድርሻዬን ልወጣ ብዬ ነው" በማለት እስካሁን 'ረዥሙ ነው' የተባለውን ጭኮ ለማዘጋጀት መነሳታቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል። ጭኮን ለምን እንደመረጡ ሲያስረዱም "ይህ ትልቅ ሕዝብ ምን ባህላዊ ምግብ አለው? በምን ይታወቃል? ብለን አምስት ባህላዊ ምግቦችን ከዘረዘርን በኋላ ጭኮ በድሮ ጊዜ በጦርነት ወቅት እንደ ስንቅ ተይዞ የሚኬድ ስለነበር፣ ከዚያ አንጻር መርጠነዋል" ብለዋል። • "የማራቶን ሯጮቹ ላይ የተላለፈው እገዳ አይደለም" ዱቤ ጂሎ ይህን 4 ኪሎ ሜትር የሚረዝም ጭኮ ለማዘጋጀት 49 ኩንታል ገብስ፣ 3538 ኪሎ ግራም ቅቤ ጥቅም ላይ መዋሉን አቶ ድንቡ ነግረውናል። በቀን 300 ሜትር ያህል ጭኮ ሲሰራ መሰንበቱን የሚናገሩት ባለሀብቱ፤ በሥራው 18 ሰዎች የተሳተፉ ሲሆን ሥራውም 29 ቀናት እንደፈጀ ገልፀዋል። ይህንን ረዥም ጭኮ በዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ለማስመዝገብ መታሰቡንም የሚናገሩትወ አቶ ድንቡ፤ ይህን ጭኮ መንግሥት ወጪውን ሸፍኖ ለተሳታፊዎች በነፃ የማያቀርብ ከሆነ እነርሱ በተመጣጣኝ ዋጋ በእለቱ ለመሸጥ ማሰባቸውን ገልጸዋል። ይህንን ጭኮ ለማዘጋጀት ምን ያህል ገንዘብ እንዳወጡ ባለሀብቱ አልተናገሩም። ባንዲራና ኢሬቻ በአዲስ አበባም ሆነ በቢሾፍቱ በሚከበረው የኢሬቻ ክብረ በዓል ላይ ከአባ ገዳ ባንዲራ ውጪ የየትኛውም ፖለቲካ ፓርቲ ባንዲራ እንዳይያዝ የበዓሉ አስተባባሪ ኮሚቴ እና የቱለማ አባ ገዳ የሆኑት ጎበና ሆላ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አባ ገዳው አክለውም ባንዲራው የግጭት መንስዔ እንዳይሆንና ኢሬቻ ከፖለቲካ እና ከፖለቲካ ፓርቲዎች በላይ ስለሆነ እንዳይቀላቀል ሲሉ ውሳኔውን ማሳለፋቸውን በቃለ መጠይቁ ወቅት አብራርተዋል። • የአማራ ክልል ፖሊስ ረዳት ኮሚሽነር በቁጥጥር ስር ዋሉ • "የአማራ ልዩ ኃይል ከማዕከላዊ ጎንደር አይወጣም" የክልሉ የሰላምና ሕዝብ ደህንነት ቢሮ ኃላፊ ከዚህ ቀደም የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ባንዲራ የኦሮሞ ሕዝብ የትግል ዓርማ ተደርጎ ይወሰዳል። ከዚህ በፊትም ቢሾፍቱ ላይ ሲካሄድ በነበረው የኢሬቻ ክብረ በዓል ላይ ክልክል ሆኖ ይዞ የተገኘ ግለሰብ በሕግ ይጠየቅ እንደነበር ይታወሳል። በጉዳዩ ላይ የበዓሉ ተሳታፊዎች ባንዲራውን መያዝ በመከልከላቸው ደስተኛ አለመሆናቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል። በበዓሉ ወቅት የሚደረጉ የሰላም ማስከበር ሂደቶችን በተመለከተ የአዲስ አበባና ኦሮሚያ ፖሊስ እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩ ቀደም ብለው መግለጫ ሰጥተዋል።
news-45135018
https://www.bbc.com/amharic/news-45135018
ልደቱ አያሌው:- ''ወደ ፖለቲካ ትግሉ ልንመጣ የምንችለው ያፈረሰን የምርጫ ቦርድ እራሱ ከፈረሰ ብቻ ነው''
የኢዴፓ የቀድሞ ሊቀመንበር አቶ ልደቱ አያሌው ማስፈራሪያም እየደረሰብኝ በመሆኑ ከፖለቲካ ሕይወት ወጥቻለሁ ማለታቸውን ተከትሎ ብዙ ሰዎች አስተያየታቸውን እየሰጡ ነው። ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የቢቢሲ አማርኛ ባልደረባ ቃልኪዳን ይበልጣል አንኳር ጥያቄዎችን አንስቶላቸው ነበር።
"አብዛኛዎቹ የኢዴፓ አጀንዳዎች ቤተ መንግሥት ገብተዋል" "በደጉ ጊዜ" ከፖለቲካው ራስን ማግለል ለምን? አገር ውስጥ መንግሥትን በሰላማዊ መንገድ የሚገዳደሩ ፓርቲዎች ይቅርና ጎረቤት አገር ተጠልለው፣ ነፍጥ አንግበው ሲታገሉ የነበሩ ወደ አገር ቤት በሚገቡበት ወቅት አቶ ልደቱ ከዚህ ውሳኔ ለምን ደረሱ? ይህ ብዙዎች ሲያነሱት የነበረ ቁልፍ ጥያቄ ነው። አቶ ልደቱ ይህንኑ አንጻራዊ መሻሻል ያለበትን የፖለቲካ አውድ ባያብሉም ለምን ራሳቸውን በዚህ ጊዜ ማግለል እንደፈለጉ የተብራራ መልስ አይሰጡም። እንዲያውም በዚህ መልካም ጊዜ ፓርቲያቸው በምርጫ ቦርድ እንዲፈርስ መደረጉ እንዳሳዘናቸው ይገልጻሉ። •በሃገሪቱ የተከሰቱት ቀውሶችና አዲስ አበባ • ዐብይ አሕመድ ለኖቤል ታጭተዋል? • ሰመጉ በወልዲያ እና አካባቢው የመብት ጥሰት ተፈጽሟል አለ "ፓርቲ ከሌለኝ በግለሰብ ደረጃ የማደርገው ተሳትፎ ብዙም ጥቅም ይኖረዋል ብዬ አላስብም" በማለት ለምን በግላቸው ይህን ውሳኔ ለመውሰድ እንደበቁ ለማስረዳት ይንደረደራሉ። መቀሌ ተዘጋጅቶ በነበረ ጉባኤ መሳተፋቸው ያላስደሰታቸው ወገኖች ዛቻና ማስፈራሪያ እንዳደረሱባቸውና ይህም ለውሳኔ እንዳበቃቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። "...ለምን መቀሌ ሄዶ ስብሰባ ተካፈለ ብለው ከፍተኛ የሆነ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍተውብኝ፤ እንገድልሃለን፤ ንብረትሀን እናቃጥላለን የሚሉ መልእክቶች እደረሱኝ ነው።" ብለዋል። በድርጅት ደረጃ የሚያደርጉት አስተዋጽኦ እስከሌለ ድረስ፤ ነጻ ሐሳባቸውን ለመግለጽ በመሞከራቸው ብቻ እንደዚህ ዓይነት ለሕይወት የሚያሰጋ ማስፈራራት የሚደርስባቸው ከሆነ፤ "ነገሮች ትንሽ እስኪሰክኑ ድረስ ከየትኛውም ዓይነት የፖለቲካ ተሳትፎ ራሴን መቆጠብ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለው" ሲሉ ራሳቸውን ከፖለቲካ ያገለሉበትን ምክንያት ለቢቢሲ ጨምረው አስረድተዋል። "ፖለቲካ ነፍሴ ደስ ብሏት የማካሄደው ሥራ ነው" ያም ሆኖ አቶ ልደቱ ብዙዎቹ እንደጠረጠሩት እስከወዲኛው ራሳቸውን ከፖለቲካ ያገለሉ አይመስልም። ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ "ሁኔታዎች ከተለወጡ" ወደ ፖለቲካው እንደሚመለሱ ፍንጭ ሰጥተዋል። ''...ከፖለቲካ ለዘልዓለም እወጣለው ማለት አይደለም። ፖለቲካ በጣም ነው የምወደው፤ ፈልጌ ነብሴ ደስ ብሏት የማካሂደው ሥራ ነው። ስለዚህ በሕይወቴ ከፖለቲካ እወጣለው ብዬ አላስብም።'' • በጂግጂጋ የህክምና ቁሳቁሶች እጥረት አሳሳቢ ሆኗል • ፓርላማው የኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7 የሽብርተኝነት ፍረጃ መነሳትን አፀደቀ ይህ በግል ለፖለቲካ ተሳትፏዋቸው የሰጡት የ "እመለስ ይሆናል" ፍንጭ ነው። እንደ ድርጅት ወደ ፖለቲካ ለመመለስ ግን አንድ ቁርጥ ቅድመ ሁኔታን አስቀምጠዋል፤ ምርጫ ቦርድ ፈርሶ መሠራት እንዳለበት። "ወደ ፖለቲካ ትግሉ ልንመጣ የምንችለው ያፈረሰን የምርጫ ቦርድ እራሱ ከፈረሰ ብቻ ነው" ኢዴፓን ማን አፈረሰው? ኢዴፓን ለማፍረስ 1 ዓመት ከ8 ወር የፈጀ ጥረት ተደርጎ ነበር የሚሉት አቶ ልደቱ ይህንንም ጥረት ለማክሸፍ ከፍተኛ ትግል ውስጥ እንደነበሩ ተናግረዋል። "አምስት ጊዜ ሙከራ የተደረገብን ሲሆን፤ አምስቱንም ማክሸፍ ችለናል።" ይላሉ። ፖርቲያቸውን በማፍረሱ ሂደት የምርጫ ቦርድን ተሳትፎ ሲያጎሉም ከፖርቲያቸው በሐሳብ ተሸንፈው የወጡ ሰዎችን ጭምር በመያዝ ሸፍጥ እንደተፈጸመባቸው ያብራራሉ። እነዚህን ሰዎች የሐሰት ክስ ፍርድ ቤት እንዲያቀርቡ በማድረግ፤ ምርጫ ራሱ ምስክር በመሆን ፍርድ ቤት እየቀረበ፤ ደብዳቤ እየጻፈ፣ "ፓርቲውን ከሕዝብ ወደ ግለሰብ እንድናስረክበው አድርጎናል" ሲሉ ምርጫ ቦርድን ክፉኛ ይተቻሉ። አቶ ልደቱ ምርጫ ቦርድ ጣልቃ ገብቶ ፓርቲውን ያፈረሰው ስለመሆኑም በቂ መረጃ አጠራቅመው መያዛቸውን፣ ይህንን ሰነድም ለጋዜጠኞች ማሳየት እንደሚችሉ ተናግረዋል። "እንደማልፈራማ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያውቅ ይመስለኛል" ከፖለቲካ ራሳቸውን የማግለል ውሳኔ የወሰኑት አቶ ልደቱ እንዴት በዛቻ ምክንያት ራሳቸውን አገለሉ የሚለው ነጥብ የርሳቸውን የፖለቲካ ጉዞ በሚከታተሉት ሁሉ የሚዋልል ጥያቄ ነው። • ኦነግ ጊዜያዊ ተኩስ አቁም ማወጁን ገለፀ • «የሠራዊታችን አባላት በክብር ይሸኛሉ» ግንቦት 7 "ማስፈራራትና ዛቻ ፈርቼ አይደለም ይህን የወሰንኩት" ያሉት አቶ ልደቱ "እንደማልፈራማ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያውቅ ይመስለኛል" ይላሉ፤ ከዚህ የከፉ ሁኔታዎች ማሳለፋቸውን በማውሳት። ይህን ካሉ ዘንድ እንዴት በዛቻና ማስፈራሪያ የፖለቲካ ማራቶንን ለማቋረጥ ወሰኑ? "ከፖለቲካ ውጪ ሆኜ የምኖር ዓይነት ሰው አይደለሁም።" ''በመጀመሪያ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ትግል የሚባለውን ነገር እስከ መጨረሻው አላቋርጥም።'' ያሉት አቶ ልደቱ "ከፖለቲካ ውጪ ሆኜ የምኖር ዓይነት ሰው አይደለሁም።" ይላሉ። የፖለቲካ ግባቸውን ሲጠየቁም ''ለሕዝብ ወይም ለሃገር ብዬ ነው ፖለቲካን የማራምደው ብዬም አልመጻደቅም።እንደዚያ ብዬም አላውቅም" ካሉ በኋላ፣ "ፖለቲካን የማካሂደው ለማንም ብዬ ሳይሆን ለራሴ ብዬ ነው" ይላሉ። "የኢዴፓ አጀንዳዎች ወደ ቤተ መንግሥት ገብተዋል" አቶ ልደቱ የፖለቲካ ስኬትን ሥልጣን በመጨበጥ ብቻ እንደማይለኩት፣ ከዚያ ይልቅ የፖለቲካ ባሕልን በመቀየር ረገድ እንደሚመለከቱት ያትታሉ። ከዚህ አንጻር ፓርቲያቸው በርካታ ውጤቶችን እንዳስመዘገበም ያምናሉ። ለዚህ እምነታቸው በዓመታት ውስጥ ሲታገሉላቸው የነበሩና ውግዘትን ያስከተሉባቸው ጉዳዮች አሁን የሕዝብ መሆናቸውን እንደ ማስረጃ ያቀርባሉ። ለምሳሌ "ኢህአዴግን የችግሩ አካል ብቻ ሳይሆን የመፍትሄውም አካል አድርገን መሥራት አለብን" ብለው ገና ድሮ መነሳታቸውን ያስታወሱት አቶ ልደቱ ያን በማለታቸው በጊዜው ከፍተኛ ተቃውሞ እንዲደርስባቸው ማድረሱን ያስታውሳሉ። "አሁን ግን ሕዝቡ ይህንን ሐሳብ ተቀብሎ ከጠቅላይ ሚኒስተር ዐብይ አሕመድ ጎን ሲቆምና ከኢህአዴግ መፍትሄ ሲጠብቅ ማየት ለኛ ትልቅ ድል ነው።" ይህ ብቻም ሳይሆን ገዢው ፓርቲም ቢሆን የኢዴፓን አጀንዳዎች ወስዶ በመጠቀሙ ትግላቸው ፍሬ ማፍራቱን ይከራከራሉ። ''...አሁን ደግሞ ኢህአዴግ የፖለቲካ አጀንዳችንን እወሰደ ነው።...በእኔ እምነት አብዛኛዎቹ የኢዴፓ አጀንዳዎች ቤተ መንግሥት ገብተዋል።''
53852371
https://www.bbc.com/amharic/53852371
ኦሮሚያ፡ የኦሮሚያ አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ "የተወሰደው እርምጃ ተመጣጣኝ ነው" አለ
ከሰሞኑ በኦሮሚያ ክልል የተከሰተው አለመረጋጋት ለመቆጣጠር የተወሰደው እርምጃ ተመጣጣኝ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል አስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ።
ከሰሞኑ ግጭት ከተከሰተባቸው ከተሞች መካከል ድሬዳዋ፣ ጭሮ እና ሻሸመኔ ከሞች ተጠቃሽ ናቸው በኦሮሚያ ለተቃውሞ በተጠሩ ሰልፎች ምክንያት የሰዎች ህይወት መጥፋቱን ተከትሎ የፀጥታ ኃይሎች "ተመጣጣኝ ያልሆነ ኃይል" ከመጠቀም እንዲቆጠቡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል። በክልሉ በአሳሳ፣ አሰቦት፣ አወዳይ፣ ባሌ ሮቤ፣ ጭሮ፣ ደንገጎ፣ ድሬ ጠያራ፣ ዶዶላ፣ ገለምሶ፣ ጊኒር፣ ሀሮማያ፣ ሂርና እና ሻሸመኔ ባሉ ከተሞች የሰዎች ህይወት ማለፉን ኮሚሽኑ ከተለያዩ ምንጮች መረጃ እንደደረሰውም በትናንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ አስፍሯል። የሰዎች ህይወት ያለፈውም የኦሮሞ ተቃዋሚ ፓርቲ ፖለቲከኞች እንዲለቀቁ በተጠራ የተቃውሞ ሰልፍ መሆኑንም ጠቅሷል። በኦሮሚያ ክልል የአስተዳርና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጂብሪል መሐመድን ስለተፈጠረው አለመረጋጋትና በጸጥታ ኃይሎች ተመጣጣኝ ያልሆነ እርምጃ ተወስዷል መባሉን አስተባብለዋል። "ኮሚሸኑ ያወጣው መግለጫ ብዙ ስህትት አለው" ያሉት አቶ ጂብሪል መግለጫው "ሰላማዊ ሰልፍ በወጡ ሰዎች ላይ" ማለቱን በማንሳት ሰላማዊ ሰልፍ የሚባል ነገር እንደማያውቁ ገልፀዋል። እንደ አስተዳደርና ጸጥታ ኃላፊው የተካሄደው "ሁከት" ነው። ሁለተኛው ስህተት ይላሉ አቶ ጂብሪል፣ "ሰልፍ የወጡ ሰዎች የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ይፈቱ ይላሉ። የፓርቲ አመራር ስለሆነ የታሰረ የለም። በወንጀል ስለተጠረጠሩ ነው የታሰሩት" ሲሉ ያስረዳሉ። በሶስተኝነትም መግለጫውን ለማስተባበል የጠቀሱት "ምንጫቸው ፌስቡክ ነው። ጉዳዩ ከሚመለከተው አካል ምላሽ አልጠየቁም" የሚል ነው። የተወሰደው እርምጃ ተመጣጣኝ አይደለም የሚለውን ክስ ሲመልሱ "ተመጣጣኝ ያልሆነ እርምጃ ከተወሰደ ማየት ይቻላል። እስካሁን ባለው የተወሰደው እርምጃ ተመጣጣኝ ነው።" ብለዋል። አቶ ጂብሪል የተደረገው ነገር ሰላማዊ ሰልፍ ሳይሆን ሁከት ነው ካሉ በኋላ፣ የመንገድ የመዝጋት ሙከራ፣ ንብረት ለመዝረፍ፣ የትራንስፖርት መስጫ ተሽከርካሪዎችን ለመሰባበር፣ መንገደኞች ላይ ጠርሙስ ውስጥ ቤንዚን ጨምሮ ክብሪት ለኩሶ ለማቃጠል መሞከሩን እና ባንክ ለመዝረፍ የተሞከረበት ቦታም መኖሩን ገልፀዋል። በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ይላሉ የኦሮሚያ አስተዳደርና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊው፣ "መኪና ሁሉ ተጓዥ 30 ሰው ከሚሞት አንድ ሰው መሞቱ ግድ ይላል። እንደዚህ አይነት እርምጃ ነው የተወሰደው። ይህም ይቀጥላል።" ዶዶላ የቆሰለ ፖሊስ፣ የሞተ የመንግሥት ካቢኔ አባል አለ ያሉት አቶ ጂብሪል፣ የገደለው ሰውዬ እንዲቆም ተነግሮት እምቢ በማለቱ ፀጥታ ኃይሎች እርምጃ መውሰዳቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። አክለውም "ይህ ሲሆን እንደዚህ አይነት እርምጃዎች የማይወሰዱ ከሆነ የሕግ የበላይነት የሚባለው የት አለ ታዲያ?" ሲሉ ጥያቄ ያቀርባሉ። "ሐረር ላይ ከወታደር መሣሪያ ቀምቶ ከሌላው ሊቀማ ሲል ነው እርምጃ የተወሰደው። . . . በአጠቃላይ የሚጣራ ነገር ሊኖር ይችላል። አልፎ አልፎ ስህተት የተፈጸመባቸው ቦታዎች ሊኖሩ ይችላሉ። በመቶኛ ግን ስናየው አብዛኛው ቦታ የተወሰዱት እርምጃዎች ተመጣጣኝ ናቸው።" የሞቱና የቆሰሉ ሰዎች ቁጥርን ተጠይቀውም፣ "መረጃ እየተጠናቀረ ነው። ሲያልቅ እንናገራለን" ብለዋል። ከሰኞ እለት ጀምሮ በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች የሆነው ምንድን ነው? በክልሉ በተለያዩ ከተሞች ከሰኞ ጀምሮ አለመረጋጋት መኖሩን መዘገባችን ይታወሳል። ሰኞ እለት በድሬ ጥያራ ከተማ የባለቤቷ ወንድም እንደተገደለ እና ትናንት ሥርዓተ ቀብሩ እንደተፈጸመ ለደህንነቷ ሲባል ስሟ ያልተገለፀ ወጣት ለቢቢሲ ተናግራናለች። የሞተው ወጣት 30 ዓመቱ መሆኑን ገልፃ፣ በቅርቡ ያገባ ሙሽራ እንደነበር ነግራናለች። እርሱና ሶስት ጓደኞቹ በፀጥታ ኃይሎች በጥይት የተመታን ግለሰብ፣ በባጃጅ ወደ ሆስፒታል በመውሰድ ላይ ሳሉ፣ ሌሎች የፀጥታ ኃይሎች በማስቆም እንደ ደበደቧቸውና የአጎቷ ልጅም በጥይት ተመትቶ መሞቱን ትናገራለች። በድሬ ጥያራ የሚሠሩ የጤና ባለሙያ ደግሞ "በ12 በነበረው ሰልፍ ላይ ከባድ ተኩስ ነበር። ሲተኮስ እኛ ጤና ጣቢያ ነበርን። ከዛ መከላከያዎች ወደ እኛ መጡና አስክሬን የምትሰበስቡበት አምቡላንስ ይዛችሁ ኑ አሉን" በማለት የተፈጠረውን ሁናቴ ያስታውሳሉ። በቦታው በተገኙበት ወቅትም በርካታ ሰዎች በጥይት ተመትተው፣ ሌሎች ተደብድበው፣ ሌሎች ደግሞ ሕይወታቸው አልፎ ሜዳ ላይ መመልከታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። "በሕይወት ለነበሩት እርዳታ ሰጥተን ወደ ሆስፒታል ሪፈር አደረግን። የሞቱትን ወደ ጤና ጣቢያው ወሰድን። ሁለት ልጆች ሞተዋል። አንደኛው ማዲ ኡመር ሁለተኛው ደግሞ ፈሪድ አብዲ ይባላል። በወቅቱ ተደብድበው የነበሩትን መቁጠር አልቻልኩም። በጥይት የተመቱት ግን ወደ 12 የሚሆኑ ሰዎች ናቸው" ሲሉ የተመለከቱትን ለቢቢሲ አስረድተዋል። በጭሮ ሆስፒታል የጤና ባለሙያም ስላለው ሁኔታ ሲናገሩ "በቀደም [ሰኞ] 24 ሰዎች ተመትተው ነበር እኛጋ የመጡት። ከዛ በኋላ ቁጥሩ 30 ደርሷል" ካሉ በኋላ ሰኞ እለት ተመትቶ ወደ ጭሮ ሆስፒታል ህክምና ሲደረግለት የነበረ ጉማ የሚባል የ19 ዓመት ወጣት ሐሙስ እለት ሕይወቱ ማለፉን ተናግረዋል። ". . .ሌላ ወጣት ዶባ ከሚባል ወረዳ በጥይት ተመትቶ መጥቶ ነበር። ትናንት ወደ ቀዶ ሕክምና ክፍል እየወሰድነው ሳለ ሞተ። በአጠቃላይ በኛ ሆስፒታል አራት ሰዎች ሞተዋል። አራቱም በጥይት ነው የተመቱት።" በሐረር ሕይወት ፋና ሆስፒታል የሚሠሩ ባለሙያ እንደነገሩን ከሆነ ደግሞ፣ ከአወዳይና ከሌሎችም ከተሞች 23 ሰዎች ተመትተው ሆስፒታል ገብተዋል። ሦስት ሰዎች ሆስፒታል ከደረሱ በኋላ እንደሞቱም ነግረውናል። ባለሙያው እንዳሉት አብዛኞቹ በሆስፒታላቸው የሚገኙት ሰዎች ጭንቅላታቸው እና ከጀርባቸው የተመቱ ናቸው። አብዛኞቹ በአስጊ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙም አክለዋል።
news-52230763
https://www.bbc.com/amharic/news-52230763
ኮሮና ቫይረስ፡የቤት እንስሳት ኮሮናን ያመጡብናል ብላችሁ እንዳትሰጉ ተባለ
በዙሪያችን ያለው ሁሉ ስጋት የሚያጭር እንጂ ልብን የሚያሳርፍ አይመስልም። በተለይ በዚህ በኮሮና ወረርሽኝ ዘመን ትክክለኛ መረጃ ከሌለዎች ሁሉም ነገር ስጋት ያጭራል።
ርቀትዎን ጠብቀው፣ እጅዎን ታጥበው ከማንም ጋር ሳይጨባበጡ ቤትዎ ሲገቡ ጭራዋን እያወዛወዘች የምትተሻሽዎ ውሮ ወይም እየዘለለ የሚቀበልዎ ቡቺ በኮሮና ተጠቅተው ይሆን? ኮሮናስ ሊያሲዝዎት ይችላሉ? የእንስሳት ሕክምና ተመራማሪዎች ኮሮና በቤት እንስሳቶታችሁ በኩል ይመጣብኛል ስትሉ ስጋት አይግባችሁ እያሉ ነው። •በኮሮናቫይረስ ከተያዙት ኢትዮጵያዊያን ሦስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው •የወባ መድኃኒቶች ኮሮናን ለመፈወሳቸው ምን ማስረጃ አለ? ነገር ግን የድመት ባለቤቶች በእንስሳት መካከል የሚኖረውን የኮሮና ወረርሽኝ ለመከላከል ሲባል በቤት ውስጥ ብቻ እንዲቆዩ አድርጉ ሲሉ መክረዋል። ይህ "የድመቶቻችሁን እሰሩ" ምክር የመጣው ያለምክንያት አይደለም፤ በሆንክኮንግ የሲቲ ዩኒቨርስቲ ምሁሩ ዶ/ር ኤንጅል አልሜንድሮስ " አንድም ውሻ ወይንም ድመት ወደ ሰው ኮቪድ-19 አስተላለፈ የሚል ማስረጃ የለም" ይላሉ። በርግጥ ይላሉ ተመራማሪው ድመቶች ከሌላ ድመት በቫይረሱ ሊያዙ ይችላሉ። ስለዚህ በማለት ዶ/ር ሳንቶስ "በዚህ በወረርሽኝ ወቅት ራሳችሁን ብቻ ሳይሆን ድመቶቻችሁን በቤታችሁ ብትይዙ መልካም ነው" ዳንኤላ ዶስ ሳንቶስ የብሪታኒያ የእንስሳት ሐኪሞች ማህበር ፕሬዝዳንት ናቸው። ቢቢሲ በዘህ ጉዳይ ላይ አነጋግሯቸው ሲመልሱ በዶ/ር ኤንጅል ሃሳብ እንደሚስማሙ ገልፀዋል። አክለውም "ከቤተሰብ አባላቶቻችን መካከል አንዱ የኮሮና ምልክት ካሳየ ድመቶችን በቤት ውስጥ መያዝ ተገቢ ነው ብለዋል"። ለምን? ይህም ቫይረሱ ለሌሎች ድመቶችም እንዳይተርፍ በማለት ይመስላል። በተጨማሪም የቤት እንስሳቶችን የሚንከባከቡ ባለቤቶች እጃቸውን በሚገባ መታጠብ እንዳለባቸው መክረዋል። " እንስሳቶቹ በኮቪድ-19 ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ካላቸው በፀጉራቸው ውስጥ ቫይረሱን ሊይዙ ይችላሉ" በሆንክ ኮንግ አንድ የ17 ዓመት ውሻ በኮሮና ተይዞ የነበረ ሲሆን የተያዘው ደግሞ ከባለቤቱ ነው ተብሏል። " ነገር ግን ምንም እንኳ እንስሳቱ ቫይረሱ ቢገኝባቸውም አይታመሙም" ይላሉ ሐኪሞቹ። " በ2003 በሆንክኮንግ በነበረው የሳርስ-ኮቭ ወረርሽኝ ወቅት እንደየው በርካታ እንስሳት በሳርስ ቫይረስ ተይዘው ነበር። ነገር ግን አልታመሙም፤ ውሻ ወይንም ድመት ይታመማሉ ወደ ሰውም ያስተላልፋሉ የሚል ማስረጃ የለም" •በአማራ ክልል በቫይረሱ የተያዙ ግለሰቦች ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሰዎችን ለመለየት ክትትል እየተደረገ ነው •የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ምንድናቸው? መቼ ነው ሐኪም ቤት መሄድ ያለብኝ? ታዲያ ቫይረሱ ከሰው ወደ እንስሳ እንዴት ይተላለፋል? ድመቶች ሰዎች ሲያስሉ፣ ሲያስነጥሱ ወይንም ሲተነፍሱ ከአፍንጫ ለሚወጡ ፈሳሾችና ለመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽኖች ተጋላጭ ሳይሆኑ አይቀሩም ተብሎ ይታመናል። በቤልጂየም አንድ ግለሰብ የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ማሳየት ከጀመረ ከሳምንት በኋላ ድመቱ መያዟ ተረጋግጧል። በቻይና በተደረገ ጥናት ደግሞ አንድ ድመት ለሌላ ድመት ቫይረሱን ያስተላልፋል። " በላብራቶሪ የተደረገ ሙከራ እንደሚያሳየው ከሆነ ድመቶች በቫይረሱ ሊያዙ ይችላሉ" ይላሉ በዩናይትድ ኪንግግደም ፒርብራይት ኢንስቲትዮት ዳይሬክተር የሆኑትና ተላላፊ በሽታዎች ላይ ነው የሚመራመሩት ፕሮፌሰር ብሪያን ቻርልስተን። ፕሮፌሰሩ በቅርብ በኮሮና ተይዞ የነበረውን ነብር በመጥቀስ "ከድመት ወደ ድመት ተላላፊ መሆኑም ማስረጃ አለን" ብለዋል። •ታይዋን ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም ላቀረቡት ክስ ምላሽ ሰጠች አክለውም የሰው ልጅ ለጦጣ የመተንፈሻ አካል ሕመም እንደሚያስተላልፍ ማስረጃ አለ ብለዋል። ይህም ከምድራችን ላይ በመጥፋት ላይ ላሉ እንደ ጎሬላ ያሉ የዱር እንስሳት ስጋት መሆኑን አልሸሸጉም። እስካሁን ባለው ምርምርና በተገኘው ማስረጃ የሰው ልጅ ብቻ ነው ወደ ሌሎች እንስሳት ቫይረሱን የሚያሰራጨው። ይህ ወረርሽኝ ሲጀምር ቫይረሱ ከእንስሳ ወደ ሰው መተላለፉን እናውቃለን የሚሉት ዶ/ር አልሜንድሮስ ደግሞ ነገር ግን ይህ የሚሆነው እንስሳውን በሚመገቡ ሰዎች አማካኝነት ነው ብለዋል። ስለዚህም የቤት እንስሳት ወደ ባለቤቶቻቸው ቫይረሱን ስለማስተላለፋቸው ምንም ማስረጃ የለም ሲሉ ያረጋግጣሉ። "የቤት እንስሳዎቻችሁን ከቤታችሁ እንዳለ እንደ አንዱ አድርጋችሁ ተንከባከቡ፤ ስለዚህ ከታመማችሁ ከእነርሱ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት አይኑራችሁ" ዶ/ር አልሜንድሮስ።
news-54223314
https://www.bbc.com/amharic/news-54223314
ኮሮናቫይረስ፡በእንግሊዝ የለይቶ ማቆያን መመሪያ የጣሱ ሰዎች 13 ሺህ ዶላር ይቀጣሉ ተባለ
ራሳቸውን ለይተው እንዲቆዩ የተነገራቸው እንግሊዛውያን መመሪያውን ካላከበሩ 13 ሺህ ዶላር እንደሚቀጡ መንግሥታቸው ከሰሞኑ አስታውቋል።
በአዲሱ መመሪያ መሰረት የኮሮናቫይረስ ተመርምረው ፖዘቲቭ መሆናቸው ከተረጋገጠ ወይንም በኮሮናቫይረስ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነት መኖራቸው የታወቀ ሰዎች ራሳቸውን ለይተው እንዲቆዩ የሚያዝ መመሪያ ወጥቷል። በአገሪቷ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እንደገና ማገርሸቱን ተከትሎም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠበቅ ያለ መመሪያ እንዲወጣ ያዘዙት። በትናንትናው ዕለት፣ መስከረም 9፣ 2013 ዓ.ም 4 ሺህ 422 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን 27 ግለሰቦችም ህይወታቸው አልፏል። ከዚህም በተጨማሪ በስኮትላንድ 350 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተዘገበ ሲሆን፣ ከግንቦት ወር በኋላም ከፍተኛ ነው ተብሏል። በዌልስ 212 ና በሰሜን አየርላንድ 222 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተገልጿል። መመሪያውን ለተላለፉ በመጀመሪያ 1 ሺህ 300 ዶላር የሚያስቀጣ ሲሆን በተደጋጋሚ መመሪያውን ለሚጥሱት እስከ 13 ሺህ ዶላር ያስቀጣል። ከዚህም በተጨማሪ ጥሰቱ ከፍተኛም መሆኑ ከተረጋገጠ በመጀመሪያም ቢሆን መመሪያውን ለሚጥሱ 13 ሺህ ዶላር ቅጣት ይጠብቃቸዋል። በእንግሊዝ እስካሁን ድረስ ግለሰቦች ራሳቸውን እንዲያገሉ የምክር አገልግሎት ብቻ ነበር የሚሰጣቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን አዲሱን መመሪያ ባወጁበት እለትም ቫይረሱን ለመታገል ሁሉም መመሪያውን ማክበር አለበት ብለዋል። "ሁሉም ቢሆን ይሄ አዲሱ መመሪያ ጠቃሚ እንደሆነ ሊረዳ ይገባል። መመሪያውን ሁሉም ሊያከብረው ይገባል። የብሄራዊ ጤና አገልግሎት በሚያዛችሁ መሰረት ቫይረሱ ተገኝቶባችሁም ከሆነ በቫይረሱ ከተያዘ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ካላችሁ ራሳችሁን ለይታችሁ ልታቆዩ ይገባል። ካለበለዚያ ግን እነዚህን መመሪያዎች ተላልፋችሁ ከተገኛችሁ ጠበቅ ያለ ቅጣት ይጠብቃችኋል" በማለት ተናግረዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ስርጭት ለመግታት እንዲሁም ተጋላጭ ማህበረሰቦቹን ከቫይረሱ ለመታደግና ህይወት ማዳንም እንደሚገባም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምክር ቢጤ አዘል መልእክታቸውንም አስተላልፈዋል። እስካሁን ድረስ 19 ሺህ ሰዎች መመሪያውን የጣሱ ሲሆን ከግማሽ በላይ የሚሆኑትም የተጣለባቸውን ቅጣት እንዳልከፈሉም ከጠቅላይ አቃቤ ህግ የተገኘው መረጃ ያስረዳል። ከዚህም በተጨማሪ አቅማቸው ደካማ ለሆኑ ሰዎች በአንድ ጊዜ የሚሰጥም 650 ዶላር ይኖራል ተብሏል።
news-52059936
https://www.bbc.com/amharic/news-52059936
ኮሮናቫይረስ፡ ሴንጋፖር አካላዊ እርቀትን የማይጠብቁ ሰዎችን በገንዘብና በእስር ልትቀጣ ነው
ሴንጋፖር የኮሮናቫይረስን ለመከላከል ከሚመከሩት መንገዶች አንዱ የሆነውን በሰዎች መካከል መኖር ያለበትን አካላዊ እርቀት መጠበቅን ተግባራዊ የማያደርጉ ሰዎችን በገንዘብና በእስር ልትቀጣ ነው።
ትናንት እኩለ ሌሊት ላይ ተግባራዊ በተደረገው በዚህ ውሳኔ መሰረት አካላዊ እርቀታቸውን ሳይጠብቁ የተገኙ ሰዎች እስከ 7 ሺህ ዶላር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት፣ አስከ ስድስት ወራት የሚደርስ እስር ወይም በሁለቱም ሊቀጡ ይችላሉ ተብሏል። መንግሥት ከዚህ በተጨማሪ አዲስ መመሪያ ተግባራዊ እንደሚያደርግም እየተነገረ ነው፤ ይህም ከሰዎች ከአንድ ሜትር ባነሰ እርቀት ላይ ሆነው ሆነ ብለው የሚያስሉ ሰዎች ደንብ እንደጣሱ ተቆጥረው ሊቀጡ እንደሚችሉም ተነግሯል። ነገር ግን አንድ ሰው ሆነ ብሎ ማሳሉን በሚመለከት እንዴት ሊታወቅ እንደሚችል አጠያያቂ ሆኗል። በሴንጋፖር ሕዝቡ መንግሥት ያዘዘውን እንዲፈጽም እንዲህ ያለውን ከበድ ያለ ቅጣት የተለመደ ሲሆን፤ ዜጎችም ያለምንም ማመንታት ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ይነገራል። ሴንጋፖር በሽታው አሳሳቢ ደረጃ ካልደረሰባቸው አገራት መካከል ስትሆን ምግብ ቤቶችና ካፌዎች ክፍት ሲሆኑ እዚያም አካላዊ እርቀትን መጠበቅ የግድ ነው። በተጨማሪም መስሪያ ቤቶችና ትምህርት ቤቶች መደበኛ ተግባራቸውን እያከናወኑ ይገኛሉ ተብሏል። ምንም እንኳን ሴንጋፖር የኮሮናቫይረስን በመቆጣጠር በኩል ላደረገችው ጥረት በዓለም አቀፍ ደረጃ አድናቆትን ያገኘች ሲሆን፤ ዜጎች ግን ትምህርት ቤቶች እስካሁን ድረስ ክፍት ሆነው በመቆየታቸው ደስተኞች አይደሉም ተብሏል። በአንዳንድ አጸደ ህጻናትና በዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ባሉ ሰራተኞች ላይ የበሽታው ፍንጮች በመታየታቸው ወረርሽኙ በሕዝቡ ውስጥ በስጋት ሊሰራጭ ይችላል የሚል ስጋት ተፈጥሯል።
news-55281922
https://www.bbc.com/amharic/news-55281922
ፖሊስ ሜ/ጄ ጻድቃንን ጨምሮ ከ40 በላይ መኮንኖች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ አወጣ
የፌደራል ፖሊስ በአገር ክህደት እና ትግራይ ውስጥ የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አባላት እንዲታገቱ አድርገዋል ብሎ የጠረጠራቸውን ከአርባ በላይ የቀድሞ ከፍተኛ መኮንኖች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ማውጣቱን አስታወቀ።
ፖሊስ አርብ ምሽት ላይ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፤ የእስር ማዘዣው ቁጥራቸው ከአርባ በሚልቁ ከፍተኛ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ኃይል፣ የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አመራሮች መውጣቱን ገልጾ የተጠረጠሩትም በአገር ክደትና በሠራዊት አባላት ላይ በተፈጸመ ወንጀል ነው ብሏል። የመያዣ ትዕዛዙ ከወጣባቸው ከፍተኛ መኮንኖች መካከል የቀድሞው የአገሪቱ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም የነበሩት ሜጀር ጄኔራል ጻድቃን ገብረተንሳይ እንደሚገኙበት የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል። በተጨማሪም ኮሎኔል በርሄ ወልደ ሚካኤልና ኮሚሽነር ይህደጎ ስዩምን ጨምሮ ሌሎቹም ጥቅምት 24/2013 ዓ. ም በትግራይ ክልል "በመከላከያ ሠራዊትና በፌዴራል ፖሊስ አባላት ላይ የተካሄደውን እገታ እንደመሩና እንዳስተባበሩ በምርመራ የተደረሰባቸው" መሆኑን የፌደራል ፖሊስ ገልጿል። የመያዣ ትዕዛዙ የወጣባቸው ከፍተኛ መኮንኖች የተጠረጠሩበት ድርጊት በአገር ላይ ጥቃት ለመፈፀም በማቀድና በመሳተፍ መሆኑን አመልክቶ፤ ተፈላጊዎቹ ሠራዊቱን የከዱና በጡረታ የተገለሉ እንደሆነ መግለጫው አመልክቷል። የፌደራል ፖሊስ አክሎም አሁን የመያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸውንና ሌሎችን ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ ወደ መቀለ ከተማ የኮማንዶና የወንጀል ምርመራ ቡድን አሰሳ እንደሚያደርግና ውጤቱንም ይፋ እንደሚያደርግ ገልጿል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከአሁኑ የመያዣ ትዕዛዝ ቀደም ብሎ ኅዳር 9/2013 ዓ. ም ላይ በ76 ጄኔራሎች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የበታች ሹማምንቶች ላይ "ከህወሓት ጋር በመተባበር የአገር ክህደትን ፈፅመዋል" በሚል የእስር ትዕዛዝ እንደወጣባቸው ይታወሳል። በህወሓትና በፌደራል መንግሥቱ መካከል ለወራት የቆየው አለመግባባት በትግራይ ክልል በተናጠል የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ እየናረ በሄደበት ጊዜ አንደኛው ወገን ለሌላኛው የሕጋዊነት ዕውቅና በመንፈግ በተካረረ ውዝግብ ውስጥ ቆይተው ነበር። ይህ ፍጥጫ ጥቅም 24/2013 ዓ. ም የህወሓት ኃይሎች በትግራይ ክልል በሚገኘው የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ካዘዙ በኋላ በሦስት ሳምንት ውስጥ የክልሉ ዋና ከተማ በመንግሥት ሠራዊት ቁጥጥር ስር መግባቷ ይታወሳል። የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ አሁንና ከዚህ ቀደም በፌደራል ፖሊስ የመያዣ ትዕዛዝ ከወጣባቸው ወታደራዊና የፖሊስ መኮንኖች በተጨማሪ ዐቃቤ ሕግ በተለያዩ ከባድ ወንጀሎች በጠረጠራቸው የህወሓት አመራሮች ላይ ጭምር የእስር ማዘዣ አውጥቷል። እስካሁን በቁጥጥር ስር የዋሉ ጦር ሠራዊትና የፖሊስ መኮንኖች የሚገኙ ሲሆን፤ ከህወሓት ፖለቲካዊ አመራሮች መካከል ደግሞ የቀድሞዋ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂምና የትግራይ ክልል የቀድሞ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አዲስዓለም ባሌማ (ዶ/ር) ይገኙባቸዋል። የጦር ሠራዊትና የፖሊስ መኮንኖቹ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ አዲስዓለም ባሌማ (ዶ/ር) ለመጀመሪያ ጊዜ ፈርድ ቤት ቀርበው ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ጠይቆባቸዋል።
news-56596280
https://www.bbc.com/amharic/news-56596280
በምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ገንቤል ወረዳ ስለተፈፀመው ጥቃት ነዋሪዎች ምን ይላሉ?
በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ገንቤል ወረዳ ማክሰኞ መጋቢት 21/2013 ዓ.ም በዞኑ ውስጥ በሚገኘው በቦኔ ቀበሌ ውስጥ በሚገኙ ሰዎች ላይ "አሰቃቂና ዘግናኝ" መፈፀሙን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አስታውቋል።
ክልሉ ትናንት ባወጣው መግለጫ ላይ ጥቃቱን ያደረሱት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ናቸው ሲል ወንጅሏል። መጋቢት 21/2013ዓ.ም ከምሽቱ 1፡30 ጀምሮ ጥቃቱ መፈፀሙን የሰባት ልጆች አባት የሆኑት የቦኔ ቀበሌ ነዋሪ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ስማቸው እንዳይጠስ የጠየቁት እኚህ የአካባቢው ነዋሪ እንዳሉት ተኩስ ሲሰሙ ልጆቻቸውን ይዘው ወደ ጫካ በመሸሽ መትረፋቸውን የተናገሩ ሲሆን ጨምረውም ቤቶች መቃጠላቸውን፣ ሴቶች፣ አዛውንቶችና ሕጻናት መገደላቸውን ተናግረዋል። ሌላኛው ቢቢሲ ያነጋገራቸው ግለሰብ ደግሞ ወደ አካባቢው በ1977 ዓ.ም መምጣታቸውን ገልፀው ጥቃቱ እርሳቸው እና ቤተሰባቸው ከሚኖሩበት ስፍራ አቅራቢያ መፈፀሙን፣ አራት ልጆቻቸውን ይዘው በመሸሽ መትረፋቸውን ተናግረዋል። 28 ሰዎች በትናንትናው ዕለት መቅበራቸውን የሚናገሩት የሰባት ልጆች አባት የሆኑት ግለሰብ፣ በጥቃቱ ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል 18 ሰዎች ወደ ነጆ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ገልፀዋል። የአራት ልጆች አባት የሆኑት የአካባቢው ነዋሪ ደግሞ በጥቃቱ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 30 መሆን ይናገራሉ። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ረቡዕ ምሽት ላይ ይፋ እንዳደረገው በምዕራብ ወለጋ ውስጥ በሚገኘው በዚህ ወረዳ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የተገደሉት ሰዎች 28 መሆናቸውንና ጉዳት የደረሰባቸው 12 መሆኑን ገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይም ዛሬ፣ ሐሙስ ዕለት በምዕራብ ወለጋ የደረሰውን ጥቃት አውግዘው፣ በሁሉም ቦታ በደርሰው ጥቃት የአጸፋ እርምጃ በክልልና በፌዴራል መንግሥት ቅንጅት እየተወሰደ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው እነዚህ የቦኔ ቀበሌ ነዋሪዎች ከእነዚህም በተጨማሪ በአካባቢው ከብቶቻቸውን በመያዝ ለግጦሽ በአቅራብያ ወደ ሚገኝ ቀበሌ ይዘው ሄደው የነበሩ 15 ታዳጊዎችም በታጣቂዎች መገደላቸውን ገልፀዋል። ሁለቱም ግለሰቦች ማክሰኞ ምሽት የተከሰተውን ለቢቢሲ ሲያስረዱ፣ ታጣቂዎቹ ግለሰቦቹን ከየቤቱ በማውጣት አንድ ቦታ በመሰብሰብ በጥይት መግደላቸውን ገልጸዋል። ከጥቂት ወራት በፊት በተመሳሳይ በምዕራብ ኦሮሚያ ውስጥ በሚገኝ ሌላ ስፍራ ላይ ታጣቂዎች ነዋሪውን በአንድ ቦታ ላይ በመሰብሰብ በፈጸሙት ጥቃት በርካታ ሰዎችን መገደላቸው ይታወሳል። የሰባት ልጆች አባት የሆኑት ግለሰብ ጎረቤቶቻቸውን እና ዘመዶቻቸውን በጥቃቱ ማጣታቸውን ተናግረው፣ ከየቤቱ ተጠርተው መንገድ ላይ አውጥተው በጥይት ከተገደሉት መካከል አዛውንቶች፣ ታማሚ፣ የአንድ እና ሁለት ዓመት ሕጻናት የታቀፉ እናቶች እንደሚገኙበት አስረድተዋል። ጥቃት አድራሾቹ በከፈቱት ተኩስ ቤቶች መቃጠላቸውን የሚገልፁት እኚህ ግለሰብ ከተደበቁበት ጫካ የተመለሱት ሲነጋ መሆኑን ይናገራሉ። ጥቃቱን ተከትሎ የክልል የጸጥታ አካላት በአካባቢ በመድረስ በጥቃት ፈጻሚዎቹ ላይ የአጸፋ እርምጃ መውሰዱን የተገለፀ ቢሆንም፤ የአካባቢው ነዋሪዎች ግን የኦሮሚያ ልዩ ኃይል መጋቢት 22/2013 ዓ.ም ማለዳ ከረፈደ መድረሱን ተናግረዋል። የሰባት ልጆች አባት የሆኑት ግለሰብ ከእረኞቹ መካከል በየጫካው ሞተው የቀሩ ይኖራሉ የሚል ስጋት እንዳላቸው ይናገራሉ። የአራት ልጆች አባት የሆኑት ግለሰብ ከዚህ በፊት በአካባቢው የሚገኙ ታጣቂዎች እነርሱ ላይ ጥቃት እንደማይደርስባቸው እና ስጋት እንዳይገባቸው በመግለጽ ከአካባቢው እንዳይሄዱ ሲነግሯቸው እንደነበር ይናገራሉ። አሁንም ቢሆን ለደኅንነታቸው እንደሚሰጉ የሚናገሩት እነዚህ ግለሰቦች "ቤታችን ገብቶ ለማደር ስለምንሰጋ አዳራችን ከጫካ ነው" ብለዋል። በአሁኑ ጊዜ ጥቃት በተፈጸመበት አካባቢ የክልሉ ልዩ ኃይል መሰማራቱን ጨምረው አስረድተዋል። ቢቢሲ ጥቃቱ የተጸፈመበት አካባቢ አስተዳዳሪን ምላሽ ለማግኘት ወደ ተንቀሳቃሽ ስልካቸው በተደጋጋሚ ቢደውልም ባለመነሳቱ ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል። የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የተፈጸመውን ግድያ በተመለከተ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ እንዳሰፈረው "በምዕራብ ወለጋ በነዋሪዎች ላይ የተፈፀመው ጥቃት በአካባቢው የፀጥታ ሁኔታ አለመሻሻሉንና ይልቁንም ወደ አዋሳኝ አካባቢዎች እየተስፋፋና ተያያዥ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እያስከተለ መሄዱን ያሳያል" ብሏል። ወደ ሰላሳ ለሚደርሱ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነውን ጥቃት የተፈጸመው ኦነግ-ሸኔ በተባለው ቡድን እንደሆነ የክልሉ መንግሥትና ከጥቃቱ የተረፉ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ኦነግ-ሸኔ የተባለው ቡድን ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር አፈንግጦ የወጣ መሆኑ የሚነገር ሲሆን ባለፉት ሁለት ዓመታት በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙ አካባቢዎች በተደጋጋሚ በሰላማዊ ሰዎች ላይ በመፈጸም ስሙ ይተቀሳል። በተጨማሪም ቡድኑ የጸጥታ አካላትን፣ የአካባቢ አስተዳዳሪዎችንና የመንግሥት ሠራተኞችን ኢላማ በማድረግ ግድያዎችን መፈጸሙ በተደጋጋሚ ተዘግቧል። ቡድኑ በሚፈጽመው ጥቃት የቀበሌና የክልል አመራሮችን ጨምሮ በርካታ ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን ያመለከተው የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ረቡዕ እለት ባወጣው መግለጫ፤ በጥቃቶቹ የግልና የመንግሥት ንብረቶች መውደማቸውንም ገልጿል። የታጣቂ ቡድኑ እንቅስቃሴ በተለይ በምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች እጠነከረ በመጣበት ጊዜ የፌደራልና የክልሉ የጸጥታ ኃይሎች ተከታታይ እርምጃዎችና ዘመቻ ማካሄዳቸው ይታወሳል። በዚህም መንግሥት ታጣቂ ቡድኑን ከአካባቢው ለማስወገድ በተለያዩ ጊዜያት በወሰዳቸው እርምጃዎች በርካታ አባላቱን መግደሉንና መማረኩን ሲገልጽ መቆየቱ ይታወሳል። የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር እንዳሉት ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ የጸጥታ አካላት በኦነግ-ሸኔ ላይ በተወሰዱት እርምጃ 1947 አባላቱ ሲገደሉ 489ቱ ደግሞ መማረካቸውን ተናግረዋል። ቡድኑ በሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ የሚፈጽመው ጥቃት በተለይ በዚህ ዓመት እተደጋገመና የሚገደሉ ሰዎች ቁጥርም እየበረከተ መጥቷል።
news-54233764
https://www.bbc.com/amharic/news-54233764
ጓደኛው ራሱን ሲያጠፋ በፌስቡክ በቀጥታ የተመለከተው ግለሰብ ትግል
ጆሽ ስቲን የቅርብ ጓደኛው ሮኒ መክነት ራሱን ሲያጠፋ በፌስቡክ ቀጥታ የተመለከተው ከሦስት ሳምንት በፊት ነበር።
ጆሽ ስቲን (ቀኝ) ፌስቡክ የጓደኛውን ሞት በቀጥታ ማስተላለፍ ማቆም ይችል ነበር ይላል። ፌስቡክን ጨምሮ ጓደኛው ራሱን ሲያጠፋ ከሚያሳዩ ሌሎች ማኅበራዊ ሚዲያዎች ጋርም እየታገለ ነው። “ላለፉት ሁለት ሳምንታት የሮኒ ፊት በየኢንተርኔት ገጹ እየታየ ነው። ማኅበራዊ ሚዲያዎቹ ቁጥጥር እናደርጋለን ቢሉም ምንም አልተደረገም” ይላል። ጆሽ ጓደኛው ራሱን ሲያጠፋ በቀጥታ ማሰራጨት በጀመረ በሁለት ሰዓት ውስጥ ለፌስቡክ ጠቁሟል። ይህም ከጓደኛው ህልፈት ከግማሽ ሰዓት በፊት ነው። ሆኖም ግን ጥቆማ አድርጎ እስከ ለሁለት ሰዓት ገደማ ምላሽ እንዳላገኘና ፌስቡክ እየተሰራጨ የነበረው ተንቀሳቃሽ ምስል የድርጅቱን ደንብ እንደማይጥስ እንደገለጸለት ጆሽ ይናገራል። “ፌስቡክ ሮኒ ከመተኮሱ በፊት ስርጭቱን መግታት ይችል ነበር” ጆሽ እንደሚለው ከሆነ ፌስቡክ ስርጭቱን ማቆም ይችል ነበር። “ፌስቡክ ሮኒ ከመተኮሱ በፊት ስርጭቱን መግታት ይችል ነበር። የጓደኛዬን ሕይወት ማትረፍ ባይቻልም ቪድዮው በማኅበራዊ ሚዲያ አይሰራጭም ነበር።” ሮኒ 33 ዓመቱ ነበር። ኢራቅ ውስጥ ወታደር ነበር። ከአስደንጋጭ አጋጣሚ በኋላ የሚከሰት የአዕምሮ ጤና መዛባት ገጥሞተም ነበር። በቅርቡ ከሴት ጓደኛው ጋር የተለያየው ሮኒ፤ ራሱን ያጠፋ እለት ሲጠጣ ነበር ያመሸው። ራሱን ስለማጥፋት ሲያወራ ሊያስቆሙት ከሞከሩ ሰዎች ጋር ሲጋጭ ነበር። ፖሊሶችም ቤቱ ተገኝተው ነበር። ሮኒ ራሱን ሲያጠፋ ከ200 በላይ ሰዎች በቀጥታ ተመልክተዋል። ሞቱ በነጋታው ራሱን ሲያጠፋ የሚታይበት ተንቀሳቃሽ ምስል ተቆራርጦ መሰራጨት ጀመረ። “ቪድዮው ማንም ማየት የሚችለው (ፐብሊክ) ነበር። ቪድዮውን እየቆረጡ ያሰራጩ ሰዎች ስለ ሮኒ የተሳሳተ ነገር እየተናገሩ ነበር። ይህም ቪድዮው የበለጠ እንዲሰራጭ አድርጓል” ይላል ጆሽ። የሮኒ ፌስቡክ ላይ ተገቢ ያልሆኑ መልዕክቶች ይላኩ ነበር። ጆሽ ጉዳዮን ለፌስቡክ ቢያመለክትም፤ የገጹ ባለቤት እሱ ስላልሆነ ምንም ማድረግ እንደማይቻል ገልጸውለታል። በሌላ በኩል ለሮኒ ማስታወሻ በሚል የገንዘብ ማሰባሰቢያ ገጾች ተከፍተዋል። የሮኒ ቤተሰቦች ስለነዚህ ገጾች የሚያውቁት ነገር የለም። “ከቁጥጥራችን ወጥቷል። አውስትራሊያ ውስጥ ያለ ሰው የዘጠኝ ዓመት ልጁ የሮኒን ቪድዮ ቲክቶክ ላይ እንዳየ ተናግሯል” ይላል ጆሽ ስለሁኔታው ሲያስረዳ። ሮኒ ራሱን ሲያጠፋ ቪድዮ በመቅረጹ የሚወቅሱት አሉ። ቪድዮው ላደረሰባቸው ሥነ ልቦናዊ ጫና ሮኒን ተጠያቂ የሚያደርጉም አሉ። ጆሽ ግን በዚህ አይስማማም። “የቀጥታ ስርጭቱን ሲጀምር ያሰበው ይህን አይመስለኝም። ገጹ ላይ ብዙ ደስ የሚሉ ነገሮች አሉ። በቀጥታ እያሰራጨ ከሰዎች ጋር ያወራ ነበር።” ከማኅበራዊ ሚዲያ አልጠፋ ያለው ቪድዮ ጆሽ ጓደኛው ራሱን ሲያጠፋ የሚታይበት ተንቀሳቃሽ ምስል ከማኅበራዊ ሚዲያዎች ባለመጥፋቱ አዝኗል። ቪድዮው እየተሳጨ ያለው በሰው ሰራሽ የሐሰት ገጾች (ቡትስ) እንደሆነ ያምናል። “አንድ ገጽን በተመለከተ ለፌስቡክ ቅሬታ ስናቀርብ ገጹ ተዘግቶ ሌላ ገጽ ይከፈትና ተመሳሳይ መረጃ በስፋት ያሰራጫል።” ፈርስት ድራፍት ኒውስ ውስጥ የሚሠሩት ክሌር ዋርድል እንደሚሉት፤ ምስሎች ከሚሰራጩበት ምክንያት አንዱ ምስሉ ሰዎችን የሚያስቆጣ ነው ተብሎ ሲታመን ነው። እንደ ምሳሌ የሚጠቅሱት በኒው ዚላንድ ውስጥ የተከሰተውን የክራይስትቸርች ተኩስ ነው። ፌስቡክ ሰው ሰራሽ ሐሰተኛ ገጾች በተመለከተ የቀረበለት ጥያቄ ላይ ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። ባወጣው መግለጫ ግን “ቪድዮው በተሰራጨበት ቀን ዋናውን ቪድዮ ከገጹ አውርደናል። ቅጂዎቹንም ለማስወገድ ሞክረናል። ከዚህ በኋላ የቀጥታ ስርጭትን እንዴት በፍጥነት ማስቆም እንደምንችል እናጠናለን። ለሮኒ ቤተሰቦችና ጓደኞች ሀዘናችንን እንገልጻለን” ብሏል። የጆሽ ትግል ጆሽ ኢንስታግራም ላይ በጓደኛው ስም የተከፈቱ ሐሰተኛ ገጾች ገጥመውታል። ዩቲዩብ ላይም ከ500,000 በላይ ሰዎች የተመለከቱት ተንቀሳቃሽ ምስል ይገኛል። ቲክ ቶክ ላይ ቪድዮው ተቆራርጦ እየተሰራጨ ነው። ዩቲዩብ ሰዎች ራሳቸውን ሲጎዱ የሚያሳይ ቪድዮ የማስወገድ መርህ እንዳለው ይናገራል። ቲክቶክም እነዚህን ቪድዮዎች ተከታትሎ እንደሚያስወግድ አስታውቋል። ጆሽ ግን የሮኒ ቤተሰቦች በደረሰባቸው ነገር ልቡ ተሰብሯል። ሰዎች ጭንቅ ውስጥ ሲገቡ እንደ ሮኒ የቀጥታ ስርጭት ከመጀመራቸው በፊት አንዳች እርምጃ መወሰድ እንዳለበትም ያምናል። “በማንም ቤተሰብ ላይ ይህ እንዲደርስ አልፈልግም። እነዚህ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች ሀያላን ናቸው። ለሰዎች ግን ግድ የላቸውም” ይላል።
news-50627311
https://www.bbc.com/amharic/news-50627311
በማርገዛቸው ከትምህርት ቤት የተባረሩት ተማሪዎች ተመረቁ
ታንዛኒያ ውስጥ ተማሪ እያሉ በማርገዛቸው የተነሳ ከትምህርት ቤት ተባረው የነበሩ ሴቶች ጡረታ በወጡ አንዲት መምህር ድጋፍ አማካይነት ትምህርታቸውን አጠናቀቁ።
ከሁለት ዓመት በፊት የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ ያረገዙ ተማሪዎች ከትምህርት ቤት መባረር አለባቸው ብለው ከተናገሩ በኋላ በአገሪቱ እየተበራከተ የመጣው የታዳጊዎች እርግዝና ጉዳይ በዓለም አቀፍ ደረጃ የውዝግብ ርዕስ ሆኖ ነበር። ማርቲና ሳይመን ሲያራ የተባሉት የ72 ዓመት ጡረተኛ መምህር በሰሜናዊ ታንዛኒያ በምትገኘው የአሩሳ ከተማ ውስጥ ለእናቶቹ በከፈቱት ትምህርት ቤት ውስጥ ለተባረሩት ተማሪዎች የመማር ዕድልን ፈጥረውላቸዋል። ፋራጃ በተባለው ማዕከል ውስጥ ሴቶቹ የምግብ ዝግጅትና የልብስ ስፌት ሥልጠናዎችን የሚያገኙ ሲሆን ከሁሉ የበለጠው ደግሞ ትምህርታቸውን ሳያቋርጡ በትኩረት እንዲከታተሉ ሥራዎቻቸውን የሚያሳዩበትና የሚሸጡበት ቦታም ተዘጋጅቶላቸዋል። • በታንዛንያ አርግዘው የተገኙ ተማሪዎችና ወላጆቻቸው ታሰሩ • ታንዛኒያ ያጋጠማትን የኮንዶም እጥረት ለመቅረፍ 30 ሚሊዮን ኮንዶሞች ከውጭ አስገባች • ታንዛኒያ በዊግና ሰው ሰራሽ ጸጉር ላይ ከፍተኛ ቀረጥ ጣለች ከተማሪዎቹ መካከል አንዷ የሆነችውና የመንታ ልጆች እናት የሆነችው የ23 ዓመቷ ዴብራ ኢማኑኤል በ17 ዓመቷ በማርገዟ ቤተሰቦቿ ያባረሯት ሲሆን ከትምህርት ቤትም ተባራ ነበር። "ልጆቼን ለማሳደግና ለማስተማር ገንዘብ የሚያስገኝልኝ የራሴ የሆነ ሥራ እጀምራለሁ" ስትል በምግብ ዝግጅት የተከታተለችውን ሥልጠና ጨርሳ ስትመረቅ ለቢቢሲ ተናግራለች። የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት ከሁለት ዓመት በፊት በተካሄደ አንድ ሥነ ሥርዓት ላይ "ካረገዛችሁ፤ አለቀላችሁ" በማለት ተማሪ ልጃገረዶችን ካስጠነቀቁ በኋላ ከፍተኛ ወቀሳና ትችት ቀርቦባቸው ነበር። በወቅቱ ፕሬዝዳንቱ አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩት ያለውን የአገሪቱን ሕግ ጠቅሰው ነበር። እንደ አውሮፓዊያኑ በ2002 የጸደቀው ሕግ ተማሪ ልጃገረዶች አርግዘው ከተገኙ ከትምህርት ቤት ማባረርን ይፈቅዳል።
50371714
https://www.bbc.com/amharic/50371714
ዚምባብዌ አዲስ የባንክ ኖቶችን ማሰራጨት ልትጀምር ነው
በኢኮኖሚያ ቀውስ እየተናጠች ያለችው ዚምባብዌ አዲስ የገንዘብ ኖቶችን ማሰራጨት ልትጀምር ነው።
በሃገሪቱ የተከሰተውን ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ እጥረት ይቀርፋል በማለት ነው የዚምባብዌ ማዕከላዊ ባንክ ከዛሬ ጀምሮ አዲሱን መገበያያ ገንዘብ ማሰራጨት የሚጀምረው። ከፍተኛ የዋጋ ንረት ባለባት ሃገር አዲስ መገበያያ ገንዘብ ወደ ገብያው ማስገባት ያለውን የዋጋ ንረት እንዲጨምር ያደርጋል የሚል ስጋት በምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ዘንድ በስፋት እየተሰማ ነው። ይሁን እንጂ ማዕከላዊ ባንኩ የሚያሰራጫቸው አዲሶቹ ባለ ሁለት እና ባለ አምስት የባንክ ኖቶች የሚያስከትሉት ተጽእኖ እምብዛም ነው እያለ ነው። ይልቁንም በሃገሪቱ የተከሰተውን የጥሬ ገንዘብ እጥረት ያቃልላሉ ይላል ማዕከላዊ ባንኩ። በርካታ የሃገሪቱ ዜጎች የጥሬ ገንዘብ አቅርቦት እጥረት መከሰቱን ተከትሎ በባንክ ያላቸውን ገንዘብ ወጪ ማድረግ ተስኗቸው ቆይተዋል። መንግሥት አዲስ የባንክ ኖቶችን ማሳተም አማራጭን ይፋ ካደረገ በኋላ በሃገሪቱ የነበረው የዋጋ ንረት ከአንድ ወደ ሶስት አሃዝ ከፍ ብሏል። አሁን ላይ መንግሥት ይፋዊ የዋጋ ንረት መጠኑን ማሳወቅ አቁሟል። ይሁን እንጂ አሁን ላይ ያለው የዋጋ ንረት ከ300% በላይ እንደሆነ ይገመታል። የዚምባብዌ ዶላር የመግዛት አቅም እጅጉን መዳከሙን ተከትሎ እ.አ.አ. ከ2009 ጀምሮ ዜጎች በአሜሪካ ዶላር መገበያየት ጀምረው ነበር። ይሁን አንጂ መንግሥት ዜጎች በዚምባብዌ ገንዘብ መገበያየት እንዲጀምሩ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል።
news-51410600
https://www.bbc.com/amharic/news-51410600
በዚምባብዌ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ተደርምሶ ሰዎችን ገደለ
በዚምባብዌ የወርቅ ማዕድን ሲያወጡ የነበሩ ሰዎች የመደርመስ አደጋ ደርሶባቸው ሕይወታቸውን አጡ።
በዚምባብዌ የደረሰ የማዕድን ቦታ አደጋ የአገሪቱ ሄራልድ ጋዜጣ እንዳስነበበው ከሆነ በደረሰው የመሬት መደርመስ ምክንያት ሁለት ሰዎች ወዲያውኑ ሕይወታቸው አልፏል። 20 የሚሆኑት ደግሞ በተደረመሰው አፈር ተቀብረው እስካሁን መውጣት አልቻሉም። ማዕድን አውጪዎቹ ከመዲናዋ ሐረሬ በስተምዕራብ በኩል 120 ኪሎ ሜትር አካባቢ ርቃ በምትገኘው ክዌክዌ ከተማ ነው ማዕድን ሲያወጡ የነበረው። የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣንን ውሳኔን ተከትሎ የማዕድን ማውጫ ስፍራው በ2007 እ.አ.አ እንዲዘጋ ተደርጎ ነበር። ነገር ግን ሰዎች በሕገ ወጥ መልኩ ወደቦታው በማምራት በምሽት ማዕድን ሲያወጡ ቆይተዋል። "ከምሽቱ 4 ሰዓት አካባቢ እየሰራን እያለ በሌላኛው የማዕድን ማውጫ አካባቢ ከፍተኛ የሆነ የጩኸት ድምጽ ሰማን፤ ከዚያ ወጥተን ስንመለከት የተደረመሰ ድንጋይ ጓደኞቻችን ላይ እየተጫነ መሆኑን አየን" በማለት በቦታው የነበረ አንድ የማዕድን ሠራተኛ ምስክርነቱን ሰጥቷል። "አንዱን ጓደኛችንን ተረባርበን በሕይወት ማትረፍ ብንችልም ሁለቱ ግን ወዲያው ነበር የሞቱት። ከተቀበሩበት ለማውጣት ብንሞክርም የተጫናቸው አለት ከባድ በመሆኑ እርሱን ማንሳት አልቻልንም። ከሟቾቹና በሕይወት ከተረፉት ተጎጂዎች በተጨማሪ 20 የማዕድን ሠራተኞች ከመሬት በታች መውጫ አጥተዋል" ብሏል። ከአደጋው የተረፉት ተጎጂዎች ወደ አካባቢው ሆስፒታል ተወስደው ህክምና እየተደረገላቸው ነው። ባለፈው ዓመት 22 የማዕድን ሠራተኞች በተመሳሳይ አደጋ በዚምባብዌ ሕይወታቸውን አጥተዋል። የአገሪቱ መንግሥትም በአሁኑ ወቅት በሕገ ወጥ ማዕድን ማውጣት ሥራ ተሰማርተዋል ያላቸውን ግለሰቦች በብዛት እያፈሰ በማሰር ላይ ይገኛል።
news-48508692
https://www.bbc.com/amharic/news-48508692
በተቃውሞ እየተናጠች ባለችው ሱዳን ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ ቀረበ
የሱዳን ወታደራዊ ኃይል እስካሁን ከተቃዋሚዎች ጋር የተደረጉ ስምምነቶችን ወደ ጎን በመተው በዘጠኝ ወር ውስጥ ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ አቀረበ።
ይህ ጥሪ የተደረገው ወታደራዊ ኃይሉ በተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ እየወሰደ ያለው ኃይል የተቀላቀለበት እርምጃ ከዓለም አቀፍ መንግሥታት ተቃውሞ ከደረሰበት በኋላ ነው። በሱዳን ካርቱም ከመንግሥት ኃይሎች ጋር የተጋጩት ሰልፈኞች ላይ በተወሰደ እርምጃ እስካሁን 30 ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል። አሜሪካ ድርጊቱን "ጨካኝ እርምጃ" ስትል ኮንናዋለች። ወታደሩ እርምጃውን የወሰደው ተቃዋሚዎች ጋር ወደ ሲቪል አስተዳደር ለመሄድ የሶስት አመት የሽግግር ጊዜ ከተስማማ በኋላ ነው። • በአዲስ አበባ የኮሌራ በሽታ ምልክት ታየ • አሜሪካ የቪዛ አመልካቾችን የማህበራዊ ሚዲያ ዝርዝር ልትጠይቅ ነው • የቦይንግ 737 ማክስ ደህንነት ስለ ማሻሻል ያለው እሰጣ ገባ ቀጥሏል ፕሬዝዳንት ኦማር አል በሺር ከስልጣን ከተወገዱ ጀምሮ ሀገሪቱን እያስተዳደረ የሚገኘው የወታደራዊ ሽግግር ምክር ቤቱ ከተቃዋሚ ኃይሎች ጋር በመደራደር አዲስ አስተዳደር በሚመሰረትበት ጉዳይ ላይ መግገባባት ላይ ደርሰው ነበር። ነገር ግን የሽግግር መንግሥቱ መሪ ጄነራል አብደል ፋታህ አል ቡራሀን ለሀገሪቱ ቴሌቪዥን በላኩት መግለጫ " ከተቃዋሚዎች ጋር የምናደርገውን ድርድርም ሆነ እስካሁን ስምምነት የደረስንባቸውን አቋርጠናል" ብለዋል። አክለውም በዘጠን ወራት ውስጥ "አለም አቀፍና አህጉራዊ" ታዛቢዎች በተገኙበት ምርጫ ይካሄዳል ብለዋል። ይህ መግለጫ የመጣው የሲቪል አስተዳደር እንዲመሰረት የሚደራደሩት ተቃዋሚዎች ሀገሪቱን መምራት ያለበት ሲቪሉ ነው በማለት የሚደረገውን ድርድር በማቋረጥ ሀገር አቀፍ አድማ ከጠሩ በኋላ ነው።
41718655
https://www.bbc.com/amharic/41718655
የዓለም ጤና ድርጅት የሮበርት ሙጋቤን የበጎ ፈቃድ አምባሳደርነት ሰረዘ
የዓለም ጤና ድርጅት ሮበርት ሙጋቤን የበጎ ፈቃድ አምሳደር ብሎ ከሾመ በኋላ በተሰነዘረበት ትችት ለሙጋቤ የሰጠውን ሚና ለመሰረዝ ተገዷል።
የድርጅቱ ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም (ዶ/ር) ''የተነሱትን ቅሬታዎች በሙሉ ከግምት ውስጥ አስገብቻለሁ'' ብለዋል በሰጡት መግለጫ። ከዚህ በፊት ዶ/ር ቴድሮስ የዙምባብዌን የህብረተሰብ ጤና አገልግሎትን አድንቀው ነበር። ይሁን እንጂ ባለሙያዎች የዙምባብዌን የህብረተሰብ ጤና ሥርዓት ደካማ ነው ሲሉ ይነቅፋሉ። ሙጋቤ ስልጣን በያዙ በመጀመሪያዎቹ 20 ዓመታት የጤና አገልግሎቶችን ማስፋፋት ቢችሉም፤ እአአ ከ2000 ጀምሮ የዙምባብዌ ምጣኔ ሃብታዊ አቅሟ በመጎዳቱ የጤና ሥርዓቱም እጅጉን ተዳክሟል። በዙምባብዌ ለጤና ባለሙያዎች ለወራት ክፍያ ሳይፈፀምላቸው እንደሚቆይ ይነገራል። የመድሃኒት እጥረትም በሃገሪቱ አለ። ከዜጎቻቸው አማካይ የህይወት ጣሪያ ከ30 ዓመት በላይ የኖሩት ሙጋቤ በተደጋጋሚ ለህክምና ወደ ውጪ ሃገራት ይጓዛሉ። ዶ/ር ቴድሮስ የሙጋቤን የበጎ ፍቃድ አምባሳደርነት መሰረዝ ''ለዓለም ጤና ድርጅት የሚበጅ ሆኖ ስለተገኝ ነው'' ይህንም ከዙምባብዌ መንግሥት ጋር መክረናል ብለዋል። ለሙጋቤን የተሰጠውን ሚና ከተቃወሙት መካከል የእንግሊዝ መንግሥት፣ የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስተር፣ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች፣ በርካታ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና የዙምባብዌ የህግ-ባለሙያዎች ማህበር ይገኙበታል። ይህ የውሳኔ ለውጥ የአዲሱ የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተርን አመራር ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው ተብሏል። የጤና ሥርዓቷ የተዳከመ በመሆኑ እና በሰብዓዊ መብት አያያዟ የምተወቀሰውን ሃገር መሪ የዓለም ጤና ድርጅት የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ሆኖ መሾም አወዛጋቢ ሆኖ ቆይቷል። የዓለም ጤና ድርጅት ስር-ነቀል የሆነ ለውጥ ያመጣል ተብሎ በሚጠበቅበት ወቅት ገፅታውን የሚያበላሽ ሁኔታ ተፍጥሮበታል።
sport-45145455
https://www.bbc.com/amharic/sport-45145455
ማርክ ላውረንሰን ዛሬ የሚጀመረውን የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ውጤቶች ግምቱን አስቀምጧል
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ተመልሷል። የትኞቹ ቡድኖች የዓመቱ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በድል ይጀምራሉ? የትኞቹስ ሽንፈትን ይቀምሳሉ? እነዚህ ጥያቄዎች ዛሬ ምሽትና ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ ምላሽ ያገኛሉ።
• ቀጣዩ የፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ማን ይሆን? • የአፍሪካ እግር ኳስ ቅሌት • ቢጫና ቀይ ካርዶች እንዴት ወደ እግር ኳስ ሜዳ መጡ? የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ማርክ ላውረንሰን ዛሬ የሚጀምረውን የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት 10 ጨዋታዎች ውጤት ግምቱን አስቀምቷል። ላውሮ ዓመቱን ሙሉ በፕሪምር ሊጉ የሚደረጉትን የ380 ጨዋታዎች ውጤት የሚገምት ሲሆን፤ ዛሬ ምሽት ማንቸስተር ዩናይትድ ከሌስተር ሲቲ በሚያደርጉት ጨዋታ ግምቱን ይጀምራል። አርብ ማንቸስተር ዩናይትድ ከሌስተር (ምሽት 2 ሰአት) በኦልድ ትራፎልድ የሚገኙ የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች ይህን የዓመቱ የመጀመሪያ ጨዋታ ለመመልከት በጉጉት እንደሚገቡ ምንም ጥርጥር የለውም። በቅድመ ውድድር ጨዋታቸው ብዙም የሚያስደስት ውጤት ያላስመዘገቡት ዩናይትዶች ደጋፊዎቻቸውን ለመካስ የማይቆፍሩት ድንጋይ አይኖርም ይላል ላውሮ። አሰልጣኙ ሞሪንዮ ለማስፈረም ሲፈልገው ነበረው የመሃል ተከላካዩ ሃሪ መጓየር አሁንም በሌስተር ማልያ የሚጫወት ይሆናል። ማንቸስተሮች ያለ ምንም ጥርጥር ከባለፈው የውድድር ዓመት የተሻለ ቡድን ይዘው ይቀርባሉ የሚለው ላውሮ፤ በዚህ ዓመት ፈተና ሊሆንባቸው የሚችለው የፖል ፖግባ ጉዳይ ብቻ ነው ። በወኪሉ ሚኖ ራዮላ አማካይነት ወደ ባርሴሎና ለማምራት ተዘጋጅቷል ከተባለ በኋላ ፖግባ የተረጋጋ አይመስልም። ምናልባትም የአለም ዋንጫ አሸናፊው ፖግባ በማንቸስተር ደስተኛ ካልሆነ፤ ለሞሪንዮ የመሃል ክፍል ከባድ ፈተና ሊሆንባቸው እንደሚችል ጠቅሷል። ሌስተሮች በበኩላቸው በክረምቱ የዝውውር መስኮት ተጫዋች ለማስፈረም ሲሯሯጡ ነበር። ምንም እንኳን የአጥቂ መስመራቸው በጄሚ ቫርዲ ላይ ብቻ የተንተለጠለ ቢሆንም የፊት መስመር ተጫዋች ግን ማስፈረም አልቻሉም። ሌስተር ሲቲዎች ባለፈው ዓመት ካደረጓችው የመጀመሪያ 10 ጨዋታዎች በ7ቱ የተሸነፉ ሲሆን፤ ይህንን ጨዋታ በጥንቃቄ ያደርጋሉ ብሏል። በላውሮ ግምት መሰረት ማንቸስተር ዩናይትዶች 1- 0 ያሸንፋሉ። ቅዳሜ ኒውካስል ከቶተንሃም ምንም ተጫዋች ያላስፈረሙት ቶተንሃሞች፤ ይህ የውድድር ዓመት እጅግ ወሳኝ እንደሚሆላቸው አስባለው ብሏል ላውሮ። ምን ያህል ውጤታማ ይሆናሉ የሚለው ግን አሁንም አጠራጣሪ ነው። ኒውካስሎች አስቸጋሪ ክረምት ነበር ያሳለፉት። ደጋፊዎቻቸውም ቢሆኑ ለተጫዋቾች ብዙ ገንዘብ ፈስስ እየተደረገ አይደለም እያሉ ነው። ኒውካስሎች የመጀመሪያ ነጥባቸውን ለማግኘት ትግል ስለሚያደርጉ ጨዋታው 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ይጠናቀቃል፤ የላውሮ ግምት ነው። ቦርንማውዝ ከካርዲፍ ፕሪምየር ሊጉን ዘንድሮ የተቀላቀሉት ካርዲፎች ጥሩ ጥሩ የሚባሉ ተጫዋቾችን አስፈርመዋል። አብዛኛዎቹ ግን ከቻምፒየንሺፑ የመጡ ናቸው። ቦርንማውዞች በፕሪምየር ሊጉ ሲሳተፉ ይህ የውድድር ዓመት አራተኛቸው ሲሆን፤ የአማካይ ስፍራቸውን ለማጠናከር በ25 ሚሊዮን ፓውንድ ኮሎምቢያዊውን ጄፈርሰን ሌርማን አስፈርመዋል። የላውሮ ግምት፤ 1-1 • ጅማ አባጅፋር የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ሆነ • ያለእድሜ ጋብቻን በእግር ኳስ የምትታገለው ታዳጊ ፉልሃም ከክሪስታል ፓላስ ምንም እንኳን ክሪስታል ፓላሶች ለክንፍ ስፍራ ተጫዋቻቸው ዊልፍሬድ ዛሃ ከፍተኛ የሚባል ገንዘብ ቢቀርብላቸውም በዚህ ዓመት አብሯቸው የሚቆይ ይሆናል። አዲስ ፈራሚያቸው ማክስ ሜየር ደግሞ ለቡድኑ ትልቅ ጥንካሬ ይሆናል ተብሎ ይታሰባል። ፉልሃሞች በዚህ ክረምት ነው ወደ ፕሪምር ሊጉ ያደጉት። ብዙ ተጫዋቾችንም አስፈርመዋል። በዚህ ጨዋታም ስብስባቸውን ተጠቅመው ክሪስታል ፓላስን 2-1 እንደሚያሸንፉ ገምቷል። ሃደርስፊልድ ከቼልሲ ሃደርስፊልዶች ባለፈው ዓመት ላለመውረድ ሲታገሉ የነበረ ሲሆን፤ በዚህ የውድድር ዓመትም የተሻለ ነገር ይዘው የቀረቡ አይመስልም። ነገር ግን የመጀመሪያ ጨዋታቸው ችግር ውስጥ ከገባው ቼልሲ ጋር መሆኑ ምናልባት ነጥብ ይዘው እንዲወጡ ሊረዳቸው እንደሚችል ላውሮ ገምቷል። ቼልሲዎች የሚተማመኑበት ግብ ጠባቂያቸው ቲቦት ኮርቱዋ ወደ ማድሪድ መሄዱን ተከትሎ ተተኪ በማፈላለግ ተተምደው የቆዩ ሲሆን፤ አሁን ግን አዲስ በረኛ አግኝተዋል። አዲሱ የቼልሲ አሰልጣኝ ማውሪዚዮ ሳሪ ገና ያልተረጋጉ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ምርጥ አራት ውስጥ እንኳን መግባት ይከብዳቸዋል ብሏል። በጨዋታው ግን ቼልሲዎች ሁለት ለባዶ እንደሚያሸንፉ ገምቷል። ዋትፎርድ ከብራይተን ዋትፎርዶች ከዓመት ዓመት ከባድ የውድድር ዘመነ እንደሚሆንባቸው ብገምትም ሁሌም ጥሩ ዓመት ያሳልፋሉ ያለው ላውሮ፤ በዚህ ዓመት ግን ጠንካራ እንደሚሆኑ አስባለው ብሏል። ብራይተኖች በበኩላቸው ባለፈው ዓመት ከወራጅ ቀጠናው ለመውጣት ባለቀ ሰአት ያደረጉት ተጋድሎ የሚያስገርም ነበር። በዚህ ዓመትም ያንኑ ብቃታቸውን ደግመው ያሳዩናል ብሏል። ጥሩ የሚባሉ ተጫዋቾችንም አስፈርመዋል። በላውሮ ግምት ዋትፎርድ 1-0 ያሸንፋል። ዎልቭስ ከኤቨርተን በክረምቱ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያደጉት ዎልቭሶች ብዙ የፖርቹጋል ታዳጊ ተጫዋቾችን አስፈርመዋል። በውድድር ዘመኑም ብዙ ግቦችን እንደሚያስቆጥሩ አስባለው ብሏል። ኤቨርተኖች ባለፈው ዓመት ያጋጠማቸው አስቸጋሪ የውድድር ዘመን ዘንድሮ የሚደገም አይመስለኝም ያለው ላውሮ፤ በጨዋታው ግን ዎልቭስ 2-1 እንደሚያሸንፍ ገምቷል። እሁድ ሊቨርፑል ከዌስትሃም ሁለቱም ቡድኖች በዝውውር መስኮቱ ቁልፍ ቁልፍ ተጫዋቾችን ያስፈረሙ ሲሆን፤ አዝናኝ ጫዋታ ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል። ዌስትሃሞች ከአንድ እስከ አስር ባለው ውስጥ ለመጨረስ ተስፋ እንዳላቸውም አስባለው ብሏል ላወሮ። ሊቨርፑሎች ደግሞ ድሮም የነበራቸው ቡድን ላይ ዘንድሮ ያስፈረሟቸው ተጫዋቾች ሲደመሩ እጅግ አስፈሪ ይሆናሉ። እንደውም ለዋንጫው ማንቸስተር ሲቲን ሊገዳደሩ ይችላሉ። ይህንንም ጨዋታ በቀላሉ 2-0 እንደሚያሸንፉ አልጠራጠርም ብሏል። ሳውዝሃምፕተን ከበርንሌይ ሳውዝሃምፕተኖች ባለፈው የውድድር ዘመን በ38 ጨዋታዎች 37 ግቦችን ያስቆጠሩ ሲሆን፤ በዚህ ዓመትም ይህን አቋም የሚደግሙ ከሆነ አሳሳቢ ሊሆንባቸው ይችላል። በርንሌይ በበኩሉ ባለፈው ዓመት ለአውሮፓ ሊግ የመሳተፊያ እድል የሚሰጣቸው ውጤት ቢያስመዘግቡም፤ ሃሙስ ምሽት ጨዋታ አድርጎ እሁድ በፕሪምየር ሊጉ መጫወት ዓመቱን አስቸጋሪ ሊያደርግባቸው ይችላል። የላውሮ ግምት ሳውዝሃምፕተን 2-1 በርንሌይ አርሰናል ከማንቸስተር ሲቲ እጅግ አጓጊ እና ለክብርም ለነጥብም የሚደረግ ወሳኝ ጨዋታ። አዲሱ የአርሰናል አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሪ ኮከብ የሚባል ተጫዋች ማስፈረም ባይችሉም፤ የቀድሞው ቡድን ብቻውን ግን የሚናቅ አይደለም። በሌላ በኩል ግን የተከላካይ እና የአማካይ መስመሩ ብዙም ተስፋ የሚጣልበት እንዳልሆነ ብዙዎች አስተያየታቸውን እየሰጡ ነው። ማንቸስተር ሲሰቲዎች አሁንም ቢሆን አስፈሪ የሚባል አቋማቸው ላይ ነው የሚገኙት። ይህንንም ጨዋታ ያለምንም ጥርጥር ያሸንፋሉ ብሏል። አርሰናሎች ከ20 ዓመት በላይ የቆዩትን አሰልታን አርሰን ቬንገር ማሰናበታቸውን ተከትሎ ብዙ ለውጦች ሊኖሩ ይችላሉ። ይህ ደግሞ ውጤታቸው ላይ ከፍተኛ ተጽህኖ ይኖረዋል። የላውሮ ግምት፤ አርሰናል 0-2 ማንቸስተር ሲቲ
news-52306307
https://www.bbc.com/amharic/news-52306307
"ያስጨንቀኝ የነበረው ከእኔ ጋር ንክኪ የነበራቸው ሰዎች ጤንነት ነበር" የኮሮናቫይረስ ታማሚዋ ከባህር ዳር
በባህር ዳር ከተማ የኮሮናቫይረስ ታማሚ የሆነች ግለሰብ መገኘቷ የተረጋገጠው ቫይረሱ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ከታወቀ ሁለት ሳምንት በማይበልጥ ጊዜ ውስጥ ነበር። ቫይረሱ የተገኘባት ግለሰብ በወቅቱ ከዱባይ የተመለሰች እንደነበር ተገልጿል።
ባህር ዳር ከተማ በአሁኑ ወቅት በባህር ዳር የለይቶ ህክምና ማዕከል ውስጥ የምትገኘው በክልሉ የመጀመሪያዋ በሽታው እንዳለባት የተረጋገጠው ግለሰብ በቫይረሱ መያዟን ካወቀች ሃያ ቀን ሊሆናት ነው። አሁን ስላለችበት ሁኔታና ለቫይረሱ የተጋለጠችበትን አጋጣሚ በተመለከተ ቢቢሲ ያነጋገራት ሠናይ [ስሟ ለዚህ ታሪክ ሲባል ተቀይሯል] ስለበሽታው ከሰማችበት ጊዜ አንስቶ በቫይረሱ እንዳትያዝ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረጓን ታስታውሳለች። ነገር ግን ወደ አገሯ ከተመለሰች በኋላ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ በተለይ ጉምሩክ አካባቢ "ከበርካታ የውጪ አገር ዜጎች ጋር ተቀራርበን እንድንቆም በመደረጋችን ያኔ በተፈጠረው ንክኪ ቫይረሱ እንደያዘኝ እጠረጥራለሁ" ትላለች። ከዚያ ጊዜ ቀደም ብሎ የፊት መሸፈኛ ጭምብልና ጓንት ታጠልቅ እንደነበር አስታውሳ፤ ከሰዎች ጋርም ሆነ ከሌሎች ነገሮች ጋር የነበረኝን ርቀት በሚገባ ጠብቄያለሁ ትላለች። ከዱባይ ወደ ኢትዮጵያ የገባችው መጋቢት 10/2012 ዓ.ም መሆኑን የተናገረችው ሠናይ፤ በዚያው ዕለት በግል መኪና ተሳፍራ ባህር ዳር መግባቷን ተናግራለች። መኪና ስትሳፍርም አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ "ከውጪ መምጣቴን ተናግሬ ከመኪናው የኋላ መቀመጫ ከሻንጣ ጋር እንድቀመጥ ተሳፋሪዎቹን ጠይቄ፤ 'አንችን ከተመቸሽ ተቀመጭ' ብለውኝ ባህር ዳር ድረስ በዚህ ሁኔታ መጣሁ" በማለት አስፈላጊውን ጥንቃቄ አድርጌያለሁ ትላለች። ባህር ዳር ከደረሰች በኋላ አብሯት የሚኖረውን ልጇን ሌላ ቦታ እንዲሄድና ለጊዜው ራሷን ማግለል እንዳለባት ብትነግረውም ልጇ ባለመስማማቱ በቤቷ ውስጥ አንድ ክፍል አዘጋጅታ ራሷን ማግለሏንና ከዱባይ መመለሷንም ለማንም አለመናገሯን ታብራራለች። ከዚያ በኋላ በነበሩት ቀናት ውስጥ ለእራሷም ሆነ ለሌሎች ጥንቃቄ ለማድረግ "የፊት መሸፈኛ ጭምብልና የእጅ ጓንት አድርጌ ስለነበር፤ ሰው በጥርጣሬ ይርቀኝ ነበር" በማለት ከሰዎች ጋር የነበራት ግንኙነት የተገደበ እንደነበር። ከዱባይ ከተመለሰች በኋላ በስፋት የሚታወቁት እንደ ደረቅ ሳል፣ ትኩሳትና የሰውነት ድካም የመሳሰሉት የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ባይታዩባትም "የምግብ ጣዕም መለየት አለመቻሌና ነገሮችን ማሽተት ሲሳነኝ፤ እራሴን ተጠራጥሬ ወደ ሆስፒታል ሄድሁ።" በወቅቱ ወረርሸዕኙን በተመለከተ የነበረው ግንዛቤና ዝግጅት ከዚህ ግባ የሚባል ስላልነበረ የምርመራ ናሙና ለመስጠት ከስድስት ሰዓታት በላይ መጉላላቷን ታስታውሳለች። በመሆኑም አርብ ቀን [መጋቢት 18/2012 ዓ.ም] የተደረገላት ምርመራ ሰኞ [መጋቢት 21/2012ዓ.ም] ውጤቱ ሲመጣ በበሽታው መያዟ አረጋገጠ። ሠናይ የተደረገላት ምርመራ ይዞት ሊመጠ ስለሚችለው ውጤቱ እራሷን አዘጋጅታ ነበር። "በበሽታው ብያዝም ሆነ ከዚያ በኋላ በማህበራዊ ሚዲያ ሳይቀር ምን ሊባል እንደሚችል ቀድሜ የሥነ ልቦና ዝግጅት አድርጌ ስለነበር ሳልደናገጥ ወደ ማገገሚያ ማዕከል ሂጃለሁ" ብላለች። በሽታው እንዳለባት ካወቀችበት ጊዜ ጀምሮ በእርሷና በልጇ በኩል ቀጥተኛ ግንኙነት የነበራቸው ሰዎችን አድራሻ በመስጠት ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ አስደርጋለች። "ያንን ሁሉ ጥንቃቄ ያደረግሁት በእኔ ምክንያት አንድም ሰው መጎዳት ስለሌለበትና ከዚያም በተጨማሪ በዙሪያዬ የሚገኙ ቤተሰቦቼም ስኳር፣ የደም ግፊትና ሌሎች በሽታዎች ያሉባቸው በመሆናቸው በሽታውን እኔ ባስተላልፍባቸው መጀመሪያ የሚያልቀው የእኔ ቤተሰብ መሆኑን በመረዳትና ለከተማዬም እኔ መነሻ መሆን ስለሌለብኝ ነው" ብላለች ሠናይ። በመሆኑም ከእርሷና ከልጇ ጋር ግንኙነት ነበራቸው የተባሉ ሰዎች ልጇን ጨምሮ አብዛኛዎቹ ሁለት ጊዜ ምርመራ አድርገው ከቫይረሱ ነጻ ሆነው እንደተገኙ የባህርዳር ከተማ ከንቲባ መሃሪ ታደሰ (ዶ/ር) ለክልሉ ቴሌቪዥን ገልጸዋል። ሠናይ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ነዋሪነቱ በሌላ ቦታ የሆነና የማታውቀው ሰው ከእርሷ ጋር ንክኪ እንደነበረው ተጠቅሶ ወደቤቱ ከተመለሰ በኋላ በጠና ታሞ ወደ ጎንደር ሆስፒታል መግባቱ ሲነገር ነበር። ሠናይ ግን ከተባለው ሰው ጋር እንዳልተገናኘች፤ እንደማታውቀውም ገልጻ፤ ከእርሷ ጋር የቀረበ ግንኙነትና ንክኪ የነበራቸው ሰዎችን ለደኅንነታቸው ሲባል ክትትል እንዲደረግላቸው ወደለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ማስደረጓን ትናገራለች። አሁን "በመልካም ጤንነት ላይ ነኝ" የምትለው ሠናይ፤ በቅርቡ አገግማ እንደምትወጣ ተስፋዋን ገልጻለች። ትኩሳቱና ሳሉ ሙሉ በሙሉ እንደቆመና የጤና ባለሙያዎችም አቅማቸው በፈቀደው መልኩ እየረዷት መሆኑን የምትናገረው ሠናይ፤ በእርግጥም ከቢቢሲ ጋር በነበራት ከ25 ደቂቃ በላይ የቆየ የስልክ ቆይታም ምንም አይነት ሳልም ሆነ ማስለጠስ አልነበረባትም። ነገር ግን የበሽታው ምልክቶች ቢወገዱላትም ለበሽታው ማስታገሻነት የምትወስደው መድኃኒት ግን ጨጓራ ላይ ጉዳት እያደረሰ በተወሰነ መልኩ በጨጓራ ህመም መሰቃየቷን ትናገራለች ። "ከእኔ ጋር ንክኪ የነበራቸው ሰዎች ውጤት ነጻ መሆኑ ደግሞ ተጨማሪ አቅም ሆኖኝ በሽታውን በፍጥነት ድል እየነሳሁት ነው" ብላለች። የእነዚህ ሰዎች ውጤት ከመታወቁ በፊት ግን በጭንቀት እንቅልፍ እንደማትተኛና ይህም በሽታውን ያባብስባት እንደነበር ታስታውሳለች። በሽታው በባህሪው እረፍትና መረጋጋትን ስለሚፈልግ የውጤቱ መታወቅ አቅም እንደጨመረላት ታምናለች። በአማራ ክልል ሁለተኛው የኮሮናቫይረስ ታማሚ የተገኘው በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር አዲስ ቅዳም ከተማ ውስጥ ነው። ግለሰቡ ወደ ኢትዮጵያ እንደመጣ ወደ አዲስ ቅዳም ከተማ በገባ በተወሰኑ ቀናት ውስጥ በተደረገለት ምርመራ ቫይረሱ እንዳለበት ተረጋግጧል። ይህ ታማሚም ወደ ባህርዳር የለይቶ ማከሚያ ማዕከል ተወስዶ በአሁኑ ወቅት በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኝ የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አዲሱ ጋሻዬ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከግለሰቡ ጋር ንክኪ የነበራቸው ሰዎችን የመለየት ሥራ መሰራቱን የተናገሩት ኃላፊው፤ ቢያንስ 63 ሰዎች ተለይተው በእንጅባራ ሆስፒታል የለይቶ ማቆያ ውስጥ እንደሚገኙና አብዛኞቹ ምርምራ ተደርጎላቸው ነጻ መሆናቸው ቢረጋገጥም ሁለተኛ ምርመራ እሰከሚደረግላቸው በለይቶ ማቆያ ውስጥ ናቸው። ከእነዚህ ሰዎች መካከል የታማሚው ባለቤትና ልጅን ጨምሮ ቀጥተኛ ግንኙነት የነበራቸው የ8 ሰዎች የምርመራ ውጤት በቅርቡ የታወቀ ሲሆን አንደኛው ግለሰብ ብቻ ቫይረሱ እንዳለበት መረጋገጡን አቶ አዲሱ አስረድተዋል። በመሆኑም ከሁለተኛውም ሰው ጋር ንክኪ ይኖራቸዋል የተባሉ ግለሰቦችን በመለየት እስካሁን 91 ሰዎችን በለይቶ ማቆያ ማስገባታቸውንና በአጠቃላይም 154 ሰዎች በእንጅባራ ሆስፒታል በለይቶ ማቆያ ውስጥ እንደሚገኙ ተናግረዋል። ከዚህ ባሻገርም ከመጀመሪያው ሰው ጋር ንክኪ የነበራት የቤተሰቡ አባል ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አምርታ ስለነበር መረጃ በመለዋወጥ ወደ በለይቶ ማቆያ ገብታ ምርመራ ተደርጎላት ነጻ መሆኗን አቶ አዲሱ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል።
news-45518225
https://www.bbc.com/amharic/news-45518225
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተመልሷል፤ የጨዋታዎቹ ግምትም እንዲሁ
አምስተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ፍልሚያ ሲቀጥል ሊቨርፑል ከቶተንሃም የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል። ውጤት ገማቹ ማርክ ላውረንሰን እንዲህ ይላል።
ቅዳሜ ቶተንሃም ከሊቨርፑል ምንም እንኳ ሊቨርፑል ዌምብሌይ ላይ የነበረውን ጥላ ቢገፍም ይሄኛው ጨዋታ ቀላል ይሆናል ብዬ አላስብም ይላል ላውሮ። ለዚህ ነው ፍልሚያው በአቻ ውጤት ይጠናቀቃል ብዬ የማስበው ሲል ያክላል። ሁለቱም ቡድኖች በጥሩ አቋም ላይ ናቸው፤ ውጤቱም የሚያስከፋቸው አይመስለኝም። ግምት፡ 1 - 1 ቦርንማውዝ ከሌይስተር ቦርንማውዝ የዚህን ዓመት የመጀመሪያ ሽንፈታቸው ቀምሰዋል፤ በቼልሱ 2 ለምንም በመሸነፍ። ለይስተርም እንዲሁ ያለፈው ጨዋታቻውን በሽንፈት ፈፅመዋል። ቦርንማውዝ የማጥቃት ጨዋታን እንደሚመርጡ ባውቅም ሌይስተርም ለዚህ አያንስም የሚል እምነት አለኝ። ግምት፡ 1 - 1 ቼልሲ ከካርዲፍ እንደሊቨርፑልና ዋትፎርድ ሁሉ ቼልሲም እስካሁን ያደረጋቸውን ፍልሚያዎች በሙሉ ማሸነፍ ችሏል። ካርዲፍ ደግሞ በተቃራኒው አንድም ጨዋታ ማሸነፍ አልቻለም። ካርዲፎች ቀላል ይሆናሉ ብዬ ባላስብም ቼልሲ እንደሚረታ ግን አልጠራጠርም። ግምት፡ 3 - 0 • አወዛጋቢው የእግር ኳስ ዳኞች ማስመሪያ ሃደርስፊልድ ከክሪስታል ፓላስ ለክሪስታል ፓላስ አንድ ያለው መልካም ዜና ዊልፍሬድ ዛሃ ከደረሰበት ጉዳት ማገገሙ ነው። ፓላስ ያለ ዛሃ ጨዋታዎችን ለማሸነፍ እየከበደው የመጣ ይመስላል። ሃደርስፊልድ እስካሁን አንድም ጨዋታ ማሸነፍ ካልቻሉ አምስት ቡድኖች መካከል ናቸው። ግምት፡ 1 - 2 ማንቸስተር ሲቲ ከፉልሃም ፉልሃም ከብራይተን ጋር በነበራቸው ጨዋታ ሁለት ለዜሮ መምራት ቢችሉም የኋላ ኋላ ነጥብ ተጋርተዋል። ከሲቲ ጋር የሚኖራቸው ፍልሚያ እንደሚከብዳቸው አልጠራጠርም። ግምት፡ 3 - 0 • ቢጫና ቀይ ካርዶች እንዴት ወደ እግር ኳስ ሜዳ መጡ? ኒውካስትል ከአርሴናል የኒውካስትሉ አሠልጣኝ ራፋኤል ቤኒቴዝ የቡድኑ የመከላከል ስታይል ቢያስተቻቸውም ደጋፊዎቻቸው አሁንም ከእርሳቸው ጎን ናቸው። በዚህ ጨዋታ እንደሚሳካላቸው አስባለሁ። ቤኒቴዝ አምና በሜዳቸው አርሴናልን ማሸነፍ ችለዋል፤ ዘንድሮም ይደግሙታል ብዬ አስባለሁ። ግምት፡ 2 - 1 ዋትፎርድ ከማንቸስተር ዩናይትድ ዋትፎርደ አስገራሚ አቋም ላይ ናቸው። የዩናይትድ የመከላከል ብቃት የሚፈተነው አሁን ነው። በርንልይን በጥሩ ሁኔታ ያሸነፉት ዩናይትዶች አሁንም ይደግሙታል የሚል ግምት አለኝ። ግምት፡ 0 - 2 ዕሁድ ዎልቭስ ከበርንሌይ ዎልቭስ የመጀመሪያ ሶስት ነጥባቸውን ከዌስትሃም ማግኘት ችለዋል። በርንሌይ ግን እስካሁን ሶስት ነጥብ እንደራቃቸው ይገኛል። ግምት፡ 0 - 2 ኤቨርተን ከዌስትሃም ዌስትሃም እስካሁን ምንም ነጠብ ማምጣት ያለቻለ ብቸኛው ቡድን ነው፤ አሰልጣኝ ማኑዌል ፔሌግሪኒም ቡድኑን ለማዋቀር ጥረታቸውን ቀጥለዋል። በሌላ በኩል ኤቨርተን እስካሁን ሽንፈት አልቀመሱም፤ ይሄንንም ጨዋታ ከማሸነፍ ወደኋላ አይሉም ባይ ነኝ። ግምት፡ 2 - 1 ሰኞ ሳውዝሃምፕተን ከብራይተን ሁለቱም ቡድኖች ከአራት ጨዋታ አራት አራት ነጠብ መሰብሰብ ችለዋል። ይህኛውን ጨዋታ አቻ በመውጣት አንድ አንድ ነጠብ ያክላሉ የሚል እምነት አለኝ። ግምት፡ 1 - 1
52454422
https://www.bbc.com/amharic/52454422
ኮሮናቫይረስ፡ስደተኞች የኮቪድ-19 ምርመራን በነፃ እንዲያገኙ የሚተጋው ኢትዮጵያዊ
አትላንታ ክላርክስተን በሚባል ስፍራ የኮቪድ-19 ምርመራ እና የሌሎች ህክምናዎችን በነፃ የሚሰጥ ክሊኒክ መዘጋጀቱን ኢትዮጵያዊው ዶ/ር ደራራ ጢሞቲዎስ ለቢቢሲ ገለፁ።
ዶ/ር ደራራ ጢሞቲዎስ ክሊኒኩ ኤትኔ የሚል ስም ያለው ሲሆን ማንኛውም በአትላንታ አካባቢ የሚኖርና የጤና መድን ዋስትና ያለውም ሆነ የሌለው ሰው መጥቶ አገልግሎቱን በነፃ ማግኘት ይችላል ሲሉ ያስረዳሉ። ላለፉት 14 ዓመታት በአሜሪካ የኖሩት ዶ/ር ደራራ ጢሞቲዎስ፤ የአሜሪካ ዜግነታቸውን ያገኙት በቅርቡ ነው። • በርካታ ሰዎች ከጂቡቲ ወደ ኢትዮጵያ እየተሻገሩ መሆኑ አሳሳቢ ሆኗል • ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ አገሮችን እየረዳ ያለው ቢሊየነር ጃክ ማ ማነው? • በአዲስ አበባ ሁለት ወጣቶች በጥይት የተመቱበት ክስተት ምንድን ነው? ከዚህ ቀደም በጆርጂያ ግዛት አትላንታ ከተማ አቅራቢያ በምትገኘው የክላርክስተን ከተማ የምክር ቤት አባል ለመሆን ተወዳድረው ነበር። እንደ ዶ/ር ደራራ ገለፃ ክላርክስተን 13 ሺህ ሰዎች የሚኖሩበት ትንሽ ከተማ ብትሆንም አብዛኞቹ ነዋሪዎች ስደተኞች ናቸው፤ ከተማውም የሚታወቀውም በዚሁ ነው። አብዛኞች ኢትዮጵያውያን፣ ኤርትራውያን እና ከተለያዩ አገራት የመጡ ስደተኞች የሚሰሩት ስራ የታክሲ ሹፌር፣ ፋብሪካ እና ሌሎች ለቫይረሱ የሚያጋልጡ ስፍራዎች በመሆኑ መረዳዳት እንደሚያስፈልግ አቶ ደራራ አጽንኦት ሰጥተው ይናገራሉ። "ማንኛውም በአትላንታ አካባቢ የሚኖርና ችግር ያለበት ሰው መጥቶ ሊያነጋግረን ይችላል።" ኤትኔ ክሊኒክ እርሳቸው በቦርድ አባልነት የሚመሩት ሲሆን ከሌሎች ምግባረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት አትላንታ አካባቢ የኮሮናቫይረስ ምልክት የሚታይባቸውን ሰዎች በነፃ እንደሚመረምር ተናግረዋል። የአትላንታ አካባቢ ነዋሪዎች ሲመረመሩ ኢንሹራንስ ባይኖራቸውም ችግር የለውም የሚሉት አቶ ደራራ፣ በአሁኑ ሰዓት በጣም በርካታ ሰዎች መጥተው አገልግሎቱን እያገኙ መሆኑን ገልፀዋል። "አሜሪካ ውስጥ አንድ ሰው የጤና ኢንሹራንስ ከሌለው በጣም ይቸገራል። ይህ የአሜሪካ አስቀያሚ ገጽታ ነው። ለኮሮና ብቻ ሳይሆን ለተለያዩ በሽታዎችም ጭምር" አቶ ደራራ በቦርድ አባልነት የሚመሩት ክሊኒክ ግን የጤና መድህን ዋስትና የላችሁም ብሎ እንደማይመልስ ያስረዳሉ። ማንኛውም ሰው የኮሮና ምልክት ከታየበት፣ የጤና መታወክ ከገጠመው የክልኒካቸውን ደጃፍ ቢያንኳኳ ያለችግር እንደሚከፈትለት ይናገራሉ። "ኢንሹራንስ ካለው ጥሩ ። ከሌለውም ችግር የለውም።" የ40 ዓመቱ ዶ/ር ደራራ በዚህ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት የምግብ እጥረት ለሚያጋጥማቸውና ለሚራቡ ሰዎች ደግሞ ኢንቪዥን አትላንታ ከሚባል ድርጅት ጋር በመሆን የምገባ አገልግሎት ላይ እየሰሩ መሆኑን ለቢቢሲ ገልፀዋል። የምግብ ችግር ያጋጠመው ካለ እነርሱንም መርዳት እንችላለን ብለዋል።
news-43821004
https://www.bbc.com/amharic/news-43821004
ካለሁበት 29 ፡ እዚህ ሰው በሰውነቱ ብቻ ትልቅ ክብር አለው፤ ሃሳቡን በመናገርም ሆነ በሌላ ነገር ለመግለጽ ቢሻ ገደብ አይበጅለትም።
ለሚ ተክሌ እባላለሁ። አሁን የምኖረው አምየን በምትባል የፈረንሳይ ከተማ ሲሆን የምትገኘው ከፓሪስ 120 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ነው።
ለሚ በትምህርት ቤት ከኢትዮጵያ ስወጣ በኬንያ አድርጌ ነበር። ከዚያም ኬንያ ትምህርቴን አጠናቅቄ ሁለተኛ ዲግሪዬን ጀምሬ አንድ ዓመት እንደጨረስኩኝ ችግር ገጥሞኝ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ ግድ ሆኖብኝ ነበር። ሆኖም ግን ያሰብኳቸውን ነገሮች መሥራት ባለመቻሌ ወደ ናይሮቢ ተመልሰኩኝ። የነበርኩበት ሁኔታ ትምህርቴን የሚያስቀጥል ባለመሆኑ አስቸጋሪና ውስብስብ የስደት ጉዞ ለማድረግ ተገደድኩኝ። ከአፍሪካ ወደ አውሮፓ ከኬንያ ወደ ኡጋንዳ ከዚያም በደቡብና ሰሜን ሱዳን ቆላማው ክፍል አድርጌ ሰሃራ በረሃን አቋርጬ ግብፅ መዲና ካይሮ ገባሁ። ካይሮ ትንሽ ከቆየሁኝ በኋላ በሜዲቴራንያን ባሕር አድርጌ ወደ ጣልያን ለመግባት ወሰንኩኝ። ጉዞው አስቸጋሪና አስፈሪ ስለሆነ ከባድ ውሳኔ ላይ እንደደረስኩኝ አውቅያለሁ። ሆኖም ግን እራሴን አጠንክሬ ጉዞዬን ማድረግ ነበረበኝ። ሁለት ሳምንት በባሕር ላይ ስንቆይ አስፈሪነቱ እየተገለጠልኝ መጣ። በቅብብሎሽ የሚደረግ ጉዞ በመሆኑ በመጀመሪያ ትናንሽ መርከቦች ከካይሮ ወሰዱንና ወደ ጥልቅ ባሕር እንደደረስን ወደ ትልቅ መርከብ አስተላለፉን። ቀሰ በቀስ ወደ ጣሊያን ተጠግተን የውሃ ድንበሯን እንዳቋረጥን በጣሊያን ድንበር ጠባቂ ፖሊሶች ቁጥጥር ሥር ዋልን። ከዚያ ግን ፈረንሳይ ለስደተኞች ጥሩ ሃገር ናት ሲባል እሰማ ስለነበር እንደምንም ብዬ ወደዚያ ለመሄድ ወሰንኩኝ። በመጨረሻም ተሳካልኝና ፈረንሳይ ገባሁ። የባሕር ላይ ፈተና ባሕር ላይ በርካታ ችግሮች ያጋጣማሉ። የምግብና ውሃ እጥረት፣ የመርከብ ሞተር መበላሸትና መርከቡ ወዳልተፈለገበት አቅጣጫ በንፋስ መወሰድ የመሳሰሉት ችግሮች ሲያጋጥሙን ነበር። እኔም የነበርኩበት መርከብ ሞተር መሃል ውቅያኖስ ላይ ብልሽት ደረሰባት። ብዙ ጥረት ተደርጎ ከተሠራች በኋላ ከአንድ ቀን በኋላ መንገዳችንን ቀጠልን። በተመሳሳይ ሁኔታ ደግሞ ጓደኞቼ የነበሩበት መርከብ ሞተሩ ተበላሽቶ መሃል ውቅያኖስ ላይ ቆሞ ደረስንበትና በእኛ መርከብ እየተጎተተ የሄደበትን አጋጣሚ አልረሳውም። በጣም የሚያሳዝነው ከእኛ አንድ ሳምንት ዘግይቶ ይነሳ የነበረ መርከብ ጓደኞቻችንን እንደያዘ የት እንደገባ ሳይታወቅ እንደጠፋ መቅረቱ ነው። ስንገምት ወይ መርከቡ ሰጥሞ ነው ለበለዚያ ደግሞ ኩላሊት በሚሰርቁት ሰዎች በግዳጅ ተወስዶ ሊሆን ይችላል። በሌላ ባሕር ዳርቻ ደርሶ በቁጥጥር ሥር ወድቆም ሊሆን ይችላል፤ እኛ ግን ምንም ማወቅ አልቻልንም ነበር። ይህን ሳስብ ሁልጊዜ ያበግነኛል። እስከ መቼ ነው ወገኖቼ በባሕር እየተሰደዱ እስከመቼ እንደረገፉ ይቀራሉ ብዬ እራሴን እጠይቃለሁ። በተለይ ይህን እንዳስብ ሁሌም የሚያስገድደኝ እራሴው በዚህ መንገድ ማለፌ ነው። የዚህ ሃገር ሥልጣኔና እድገት እንዳለ ሆኖ፤ በፈረንሳይና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ትልቁ ልዩነት ሰላም፣ ዲሞክራሲና የሰብዓዊ መብት አጠባበቅ ነው። እዚህ ሰው በሰውነቱ ብቻ ትልቅ ክብር አለው፤ ሃሳቡን በመናገርም ሆነ በሌላ ነገር ለመግለጽ ቢሻ ገደብ አይበጅለትም። እዚህ ከመጣሁ አንስቶ መመገብ የሚያስደተኝ ፒዛ ነው። የሚጣፍጥ ፒዛ ያዘጋጃሉ። መቼም ከእራስ ሃገር ሁሉም ነገር ይናፍቃል። ዛፉ፣ ሰዉ፣ ከብቱ፣ ባህሉና ወጉ፣ ማሕበራዊ ኑሮው የእርስ በእርስ መከባበሩ፤ በተለይ ደግሞ አብሮ መብላቱ፣ በዓላቱን አብሮ ማሳለፉ። ምክንያቱም የእኛ ሃገር ሰው ብቻውን አይበላም፤ እንደዚህ ዓይነት ነገሮች በጣም ይናፍቁኛል። የአምየን ከተማ ጥንታዊና ታሪካዊ ከተማ በመሆኗ በብዙዎች ዘንድ ትታወቃለች። በተለይ በትልቁ የጎቲክ ካቶሊክ ካቴድራሏ የበርካቶችን ቀልብ የሚስብ ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን ለሃገሪቱ በተዋጉ የጥንት አርበኞች የተመሠረተች ከተማ ነችም ይባልላታል። እዚህ የምትገኘው ትልቋ የካቶሊክ ካቴድራል 3000 ዓመታትን አስቆጥራለች ይባላል። ይህ በጣም ትልቅ ቤተክርስቲያን ታሪካዊ ከመሆኑም ባሻገር በጣም የሚያምርም ስለሆነ በጣም የምንወደው ሥፍራ ነው። እዚህ ሃገር ከመጣሁ ቀልቤ አርፏል፤ ብዙ ነገሮች ተሳክተውልኛል። ትልቁ ነገር ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ ጉዳዬ በመንግሥት ተቀባይነት አግኝቶ የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ ማግኘቴ በጣም ካስደሰቱኝ ነገሮች አንዱ ነው። በአምየን የምትገኘው የካቶሊክ ካቴድራል ብዙ ሰዎች ይህንን ሳያገኙ ከአሥር ዓመታት በላይ የኖሩ አሉ፤ እኔን እግዚአብሔር በጣም እንደረዳኝ ይሰማኛል። የፈረንሳይ አረንጓዴ መሆን ያደግኩበትን ምዕራብ ወለጋን ያስታውሰኛል። ወደዚህ ሃገር እንደመጣሁ ቋንቋውን አለመቻሌ ትልቅ ችግር ሆኖብኝ ነበር። አሁን ግን የተወሰነውን ለመማር ችያለሁ። በርትቼም መማሬን እቀጥላለሁ። በአንዴ ወስዶ ሃገሬ ላይ ሚጥለኝ ሁኔታ ቢፈጠር ድንገት እራሴን ሃገሬ ላይ ማግኘት እሻለሁ። እንደው ተወልጄ ያደግኩበትና ቤተሰቦቼን፣ ዘመዶቼና ጓደኞቼ የሚገኙበት ምዕራብ ወለጋ ዱብ ብል ደስ ይለኛል። ለጫሊ ነጋሳ እንደነገረው የ'ካለሁበት' ቀጣይ ክፍሎችን ለማግኘት ፦ ካለሁበት 30፡ መስቀል እና አረፋን ሳስታውስ ውስጤ ይረበሻል ካለሁበት 31፡ ''ብዙ ትውስታዎቼ ከዛፍና ከጭቃ አያልፉም''
news-50163993
https://www.bbc.com/amharic/news-50163993
ኑስራት ጃሃን ራፊ፡ ወሲባዊ ትንኮሳን ሪፖርት ያደረገችውን አቃጥለው የገደሉ 16 ግለሰቦች ሞት ተበየነባቸው
የባንግላዴሽ ፍርድ ቤት በመምህሯ ወሲባዊ ትንኮሳን እንደተፈፀመባት ሪፖርት ያደረገችውን ተማሪ በእሳት አቃጥለው የገደሉ 16 ግለሰቦች ላይ የሞት ፍርድ አስተላለፈ።
ኑስራትን የገደሏት በላይዋ ላይ ነጭ ጋዝ አርከፍክፈው በማቃጠል ነበር ኑስራት ጃሃን የተባለችው ተማሪ፤ የትምህርት ቤቷ ርዕሰ መምህር ፆታዊ ትንኮሳ እንዳደረሰባት ሪፖርት ማድረጓን ተከትሎ ነበር ጋዝ አርከፍከው እሳት በመለኮስ አቃጥለው የገደሏት። • ወሲባዊ ትንኮሳን ሪፖርት በማድረጓ ተቃጥላ የተገደለችው • ወሲባዊ ትንኮሳ ያደረሰባት አለቃዋን በማጋለጧ የታሠረችው ሴት በትንሽ መንደር የተወለደችው የአስራ ዘጠኝ ዓመቷ ኑስራት የመድረሳ ወይም የእስልምና ትምህርትን ትከታተል ነበር። የተገደለችውም ከባንግላዴሽ ዋና መዲና ድሃካ 160 ኪሎ ሜትር በምትርቅ ፌኒ በተባለች ትንሽ ከተማ ነው። ግድያዋ በአገሪቷ ከፍተኛ ድንጋቴን የፈጠረ ሲሆን ለኑስራት ፍትህ በመሻትም ተከታታይ የሆኑ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል። ተመሳሳይ ጥቃቶች ላይ ፍትህ ለመስጠት ዓመታትን ይፈጅ የነበረው የፍርድ ሂደት አሁን ግን በጣም በፍጥነት ከተሰጡት ፍርዶች ይህ አንደኛው ነው ተብሏል። አቃቤ ሕግ ሃፌዝ አሕመድ ለጋዜጠኞች "ፍርዱ በባንግላዴሽ አንድን ሰው ገድሎ ማምለጥ እንደማይቻል ያረጋገጠ ነው" ብለዋል። የተከሳሾች ጠበቃ በበኩላቸው ይግባኝ እንደሚጠይቁ ተናግረዋል። በኑስራት ሞት ላይ የተደረገው ምርመራ፤ የክፍል ጓደኞቿን ጨምሮ በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ ሌሎች ወንዶች እርሷን ዝም ለማሰኘት ሙከራ ማድረጋቸው አመላክቷል። ፖሊስ ግድያው እንዲፈፀም አዘዋል ያላቸውን ርዕሰ መምህር ሲራጅ ኡድ ዶዩላን ጨምሮ ሦስት መምህራን በፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ ተብለዋል። የአዋሚ ሊግ ፓርቲ የአካባቢ መሪዎች የሆኑ ሌሎች ሁለት ተከሳሾች፤ ሩሁል አሚንና ማክሱድ አላም ጥፋተኛ ሆነዋል። በርካታ የአካባቢው ፖሊሶችም በኑስራት ላይ የተፈፀመው ግድያ አስመልክቶ ራሷን እንዳጠፋች ተደርጎ ሲነዛ የነበረው ሀሰተኛ መረጃ በማሠራጨት ተባብረዋል። ፖሊስ ጥበቃ እንደሚያደርግላት ከተነገራቸው በኋላ ለፖሊስ ሄዳ ሪፖርት እንድታደርግ እንዳበረታቷት የኑስራት ቤተሰቦች ለአገሪቷ መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል። በአስቸኳይ ፍትህ እንዲሰጣቸውም ሲጠይቁ ቆይተዋል። ለኑስራት ቤተሰቦች ልባቸውን የሰበረ ሐዘን ነው በኑስራት ላይ የሆነው ምን ነበር? ከመሞቷ በፊት ኑስራት በሰጠችው መግለጫ "የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ባልተገባ መልኩ ሰውነቴን ነክቶኛል፤ ወሲባዊ ትንኮሳ ፈፅሞብኛል" ስትል ሪፖርት ካደረገች ከ11 ቀናት በኋላ ባሳለፍነው ሚያዚያ ወር በትምህርት ቤቱ ጣሪያ ላይ ተወስዳ ነበር። አንዲት ሴት ተማሪ አንድ ጓደኛዋ እንደተጎዳ ነግራት ነበር ጣሪያው ላይ የወሰደቻት። ጣሪያው ላይ ስትደርስ ግን አምስት ተማሪዎች እንደከበቧትና በርዕሰ መምህሩ ላይ ያቀረበችውን ክስ እንድትተው ጫና ሊያደርጉባት ሞክረዋል። እምቢ ስትልም በእሳት እንደለኮሷት ተናግራለች። እንደተጎዳችና እንደማትተርፍ ስታውቅ ስለተፈጠረው ነገር በዝርዝር የተናገረች ሲሆን፤ ወንድሟም ንግግሯን በስልኩ ቀረጾታል። "መምህሩ ወሲባዊ ትንኮሳ ፈፅሞብኛል፤ እስከ መጨረሻዋ እስትንፋሴ ድረስ ይህንን ወንጀል እጋፈጣለሁ" በማለት ድርጊቱን የፈፀሙባትን ጥቂት ሰዎች ስም ጠርታለች። • በጋና በቢቢሲ ዘጋቢ ፊልም ላይ ወሲባዊ ትንኮሳ ሲፈፅሙ የታዩ መምህራን ከሥራቸው ታገዱ • የሥራ ቦታ ወሲባዊ ትንኮሳ የቱ ነው? የወንጀል መርማሪ ፖሊስ ኩማር ማጁምደር እንደገለፀው ገዳዮቿ ራሷን ያጠፋች ለማስመሰል ቢሞከሩም እቅዳቸው ሳይሳካም ለጥቂት ቀናትም ቢሆን በሕይወት ተርፋ መግለጫ መስጠት ችላለች። ይሁን እንጅ 80 በመቶ የሆነው የሰውነት ክፍሏ የተቃጠለው ኑስራት፤ ከአራት ቀናት በኋላ በሚያዚያ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች። አክሽን ኤድ የተባለ ድርጅት በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ባወጣው ሪፖርት፤ በባንግላዴሽ የልብስ ፋብሪካ የሚሠሩ 80 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ወሲባዊ ትንኮሳ ሲፈፀም አይተዋል አሊያም ራሳቸው ላይ ተፈፅሞባቸዋል ይላል። ይሁን እንጅ እንደ ኑስራት የደረሰባቸውን ወሲባዊ ትንኮሳ ሪፖርት ማድረግ የሚያስከትለው መዘዝ ስላለ መናገሩ የተለመደ አይደለም። የተለያየ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች ከማህበረሰቡ በአካል፣ በተለያዩ ድረገፆች ከቃል ዘለፋ ጀምሮ አካላዊ ጥቃት ይደርስባቸዋል። ኑስራትም ከዚህ አላመለጠችም። ለፖሊስ ሪፖርት ካደረገች በኋላ ርዕሰ መምህሩ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ተከትሎ ለኑስራት የከፋ ነበር። ግለሰቡ እንዲለቀቅ የሚጠይቁ ሰዎች አደባባይ ወጡ። ተቃውሞውን ያደራጁት ሁለት ወንድ ተማሪዎች ሲሆኑ የአካባቢውም ፖለቲከኞችንም ድጋፍ ማግኘት እንደቻሉ ተገልጿል። ምንም እንኳን ተጠቂዋ እሷ ብትሆንም ብዙዎች እሷን መወንጀል ጀመሩ። ቤተሰቧም የደህንነቷ ሁኔታ እንዳስጨነቃቸውም መናገራቸው ተዘግቧል። ጥቃቱን ሪፖርት ካደረገች ከአስራ አንድ ቀናት በኋላ ፈተና ልትፈተን ትምህርት ቤት ሄደች። "እህቴን ትምህርት ቤት የወሰድኳት እኔ ነኝ። ወደ ግቢው ለመግባት ስጠይቅ እንደማይፈቀድልኝ ነገሩኝ" በማለት የሚናገረው ወንድሟ ማህሙዱል ሃሰን ኖማን " ከመግባት ባያስቆሙኝ ኖሮ እንዲህ አይነት ሰቅጣጭ ጉዳይ በእህቴ ላይ አይፈፀምም ነበር" ብሏል። በኑስራት ግድያ ሕዝቡ ስሜቱን እንዴት ገለፀ? የኑስራት ሞት ከፍተኛ ተቃውሞን የቀሰቀሰ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦችም ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ንዴታቸውን ገልፀዋል። ኑስራት የደረሰባትን ትንኮሳ በመናገሯ ድፍረቷን ብዙዎች ቢያደንቁትም ከቀናት በኋላ ግን ሰቅጣጭ የሆነው አገዳደሏ ብዙዎችን አስደንግጦ ነበር። ፆታዊ ትንኮሳን ሪፖርት የሚያደርጉ ሰዎች ምን ያህል ለጥቃት ተጋላጭ እንዳደረጋቸውም የሚያሳይ ነው ተብሎም ከፍተኛ ቁጣ ተቀስቅሶ ነበር።። "ሴቶች የደረሰባቸውን ፆታዊ ትንኮሳ ሪፖርት ማድረግ ማለት ሌላ ትንኮሳን ማስተናገድ ማለት ነው። ጉዳዩ ለዓመታት ይጓተታል፤ ማህበረሰቡ ያሸማቅቃቸዋል። ከፖሊስ በኩል ጉዳዩን ለመርመር ፍቃደኝነት አያሳዩም። ወንጀለኞቹም ሳይቀጡ ይቀራሉ፤ ተጠቂዎቹም ፍትህ አያገኙም" በማለት የሰብአዊ መብት ጠበቃና የቀድሞ የሴቶች የሕግ ባለሙያ ማህበር ዳይሬክተር ሳልማ አሊ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ ሀሲናም ጥፋተኞቹ ሁሉ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው "ጥፋተኛ የሆነ ሁሉ ከሕግ አያመልጥም" ሲሉም በአደባባይ ተናግረው ነበር። መጀመሪያ ላይ ኑስራት ያቀረበችውን ወሲባዊ ትንኮሳ ክስ የሰረዘው ፖሊስ ግንቦት ወር ላይ በ16 ግለሰቦች ላይ ክስ መስርቷል፤ አቃቤ ሕግም የሞት ቅጣት እንዲበየንባቸው ሲከራከር ቆይቷል።
news-53364762
https://www.bbc.com/amharic/news-53364762
በኮሮናቫይረስ ምክንያት የኤምሬትስ አየር መንገድ 9ሺህ ሠራተኞችን ሊቀንስ ነው
ኤምሬትስ አየር መንገድ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ባስከተለው ተጽእኖ ምክንያት ዘጠኝ ሺህ የሚደርሱ ሠራተኞቹን ሊቀንስ መሆኑን ፕሬዝዳንት ተናገሩ።
የረጅም ርቀት ጉዞዎችን በማድረግ በዓለማችን ግዙፍ ከሚባሉት አየር መንገዶች አንዱ የሆነው ኤምሬትስ ይህን ያህል ሠራተኞችን ሊቀንስ መሆኑን ሲያስታውቅ የመጀመሪያ ጊዜው ነው። የኮሮናቫይረስ ተከስቶ የአየር ትራንስፖርቱን ዘርፍ ክፉኛ ከመጉዳቱ በፊት ኤምሬትስ 60,000 ሰራተኞች ነበሩት። ፕሬዝዳንቱ ሰር ቲም ክላርክ አየር መንገዱ እስካሁን አንድ አስረኛ የሚሆኑትን ሠራተኞቹን መቀነሱን ጠቅሰው "ከዚህም በኋላ እስከ 15 በመቶ የሚሆኑ ተጨማሪ ሠራተኞችን ልንቀንስ እንችላልን" ሲሉ ተናግረዋል። የአየር መንገዱ ፕሬዝዳንት ለቢቢሲ እንደገለጹት ኮሮናቫይረስ በፈጠረው ችግር ምክንያት ኤምሬትስ "እንደ ሌሎቹ አየር መንገዶች በከፋ ሁኔታ አልተጎዳም" ብለዋል። በአየር ትራንስፖርቱ ዘርፍ ውስጥ እየተወሰደ ያለው ሠራተኞችን የመቀነስ እርምጃ የኤምሬትስ ተቀጣሪዎችን ያሳሰባቸው ሲሆን ከዚህም ሊከፋ የሚችል እንደሆነም ሰግተዋል። በኤምሬትስ ሠራተኞች በአየር መንገዱ ውስጥ ደካማ የመረጃ ልውውጥና የግልጽነት መጓደል አለ በሚል ቅሬታዎች እንዳሉ ቢቢሲ ተገንዝቧል። እስካሁን ኤምሬትስ ካሉት 4,500 አብራሪዎች ውስጥ ቢያንስ 700 ለሚሆኑት ቅጥራቸው እንደሚቋረጥ በዚህ ሳምንት አሳውቋል። ይህም የኮሮናቫይረስ ቀውስ ከተከሰተ በኋላ ቢያንስ 1,200 የሚደርሱት ከሥራ እንደሚቀነሱ ተነግሯቸዋል ማለት ነው። በአብራሪዎቹ ላይ የተደረገው ከሥራ የመቀነስ ውሳኔ ያተኮረው ከቦይንግ አውሮፕላኖች ይልቅ በዋነኝነት ኤርባስ የተባሉትን አውሮፕላኖች በሚያበሩ ፓይለቶች ላይ ነው ተብሏል። ከአብራሪዎቹ በተጨማሪ ኤምሬትስ በሺህዎች የሚቆጠሩ የበረራ ሠራተኞችንም እንደቀነሰ ተነግሯል። ኤምሬት እጅግ ግዙፍ ከሆነውና 500 የሚደርሱ ሰዎችን ከሚያሳፍረው ሱፐርጃምቦ ኤርባስ ኤ380ኤስ አንስቶ የተለያየ ቁጥር ያላቸውን መንገደኞች እስከሚይዙት ቦይን 777 አውሮፕላኖች ድረስ አሉት። 290 አየር መንገዶች በአባልነት ያሉበት ዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር እንደተነበየው በዚህ ዓመት ብቻ አየር መንገዶች ከ84 ቢሊየን ዶላር በላይ ኪሳራ የሚገጥማቸው ሲሆን አንድ ሚሊዮን ሠራተኞችም ሥራቸውን ያጣሉ።
news-43368391
https://www.bbc.com/amharic/news-43368391
በርካታ ሰዎች ከሞያሌ በመሸሽ ወደ ኬንያ ገብተዋል
ባለፈው ቅዳሜ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በተከፈቱት ተኩስ ቢያንስ አስር ሰላማዊ ሰዎች ከተገደሉ በኋላ በርካታ የአካባቢው ሰዎች ድንበር አቋርጠው ወደ ኬንያ መሸሻቸውን ከሥፍራው ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈፃፀም በበላይነት የሚቆጣጠረው ግብረ ኃይል ሴክሬታሪያት ተወካይ የሆኑት ሌተናል ጄኔራል ሃሰን ኢብራሂም በመንግሥታዊው ቴሌቭዥን ቀርበው በሰጡት ማብራሪያ አምስት የሠራዊቱ አባላት በደረሳቸው የተሳሳተ መረጃ ምክንያት ተኩስ ከፍተው ዘጠኝ የሞያሌ ከተማ ነዋሪዎችን ሲገድሉ አስራ ሁለት ግለሰቦች ደግሞ ማቁሰላቸውን ገልፀዋል። አንድ ተጨማሪ ግለሰብ ሕይወቱ ያለፈው ተወካዩ ይህን ከነገሩን በኋላ ነው። የሠራዊቱ ከፍተኛ አዛዦች የሚገኙበት ቡድን ወደ ሥፍራው ማቅናቱን እና ጥቃቱን ያደረሱት የሠራዊቱ አባላት ትጥቃቸውን እንዲፈቱ ተደርገው ምርምራ እየተካሄደባቸው መሆኑን ተወካዩ ጨምረው ተናግረዋል። በሞያሌ አካባቢ አንድ ሻለቃ ጦር ሰፍሮ እንደሚገኝ እና ይህም ጦር የተሰጠው ግዳጅ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር እንደማይገናኝ የገለፁት ሌተናል ኮሎኔል ሃሰን የጦሩ አባላት ወደ አካባቢው የሚዘልቁ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አባላትን የመቆጣጠር ግዳጅ እንዳለው አስረድተዋል። ወደ ሥፍራው ያቀኑት የሠራዊቱ አዛዦች የአካባቢውን ነዋሪዎች የማረጋጋት ሥራ ያከናውናሉ የተባለ ቢሆንም በርካቶች ቀያቸውን ለቅቀው ድንበር በማቋረጥ ወደ ኬንያ እየሸሹ መሆኑን ያነጋገርናቸው የአካባቢው ባለስልጣናት ይገልፃሉ። የሞያሌ ከተማ ከንቲባ አቶ አስቻለው ዮሃንስ በርካታ ቁጥር ያላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች በተለይም ሸዋ በር እና ዜሮ አንድ የሚባሉ ቀበሌዎች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ከአካባቢው ሸሽተው ወደኬንያ መዝለቃቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። በትናንትናው ዕለት የሞቱትን ሰዎች ሲቀብሩና ከሌሎች አካባቢዎች የመጡ ሟቾችን ወደቀያቸው ሲልኩ እንደዋሉ የገለፁት አቶ አስቻለው ጥቃቱ የተፈፀመባቸው የከተማዋ አካባቢዎች የንግድ እና የአገልግሎት ሰጭ ተቋማት ተዘግተው ጭርታ ነግሶባቸው እንደዋሉ ገልፀዋል። በከተማዋ የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ በኃላፊነት የሚሰሩ አንድ ግለሰብ ከሞያሌ ከተማ እና ከአጎራባች ቀበሌዎች ሸሽተው ወደ ኬንያ ያመሩ ነዋሪዎች ቁጥር አስር ሺህ እንደሚደርስ ግምታቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል። የሞያሌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ በገጃ በበኩላቸው በትናንትናው ዕለትም ጫሜ በምትባልውና ከከተማዋ ጥቂት ኪሎሜትሮች ርቀት ላይ በምትገኝ አካባቢ ተኩስ እንደነበረና ቢያንስ አንድ ሰው መቁሰሉን እንደሚያውቁ ተናግረዋል። አቶ በገጃ ጉዳዩን በተመለከተ ከመከላከያ ሠራዊት አባላት ጋር መነጋገራቸውን ገልፀዋል::
news-54196676
https://www.bbc.com/amharic/news-54196676
እግር ኳስ፡ ሊዮኔል ሜሲ ስሙ የንግድ ምልከት መለያ እንዲሆን ተፈቀደለት
አርጀንቲናዊው የእግር ኳስ ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ ስሙን የንግድ ምልክት መለያ እንዲሆን ለማድረግ ፍርድ ቤት ሲከራከር ቆይቷል።
የፍርድ ቤት ክርክሩ የተጀመረው አንድ የስፔን የሳይክል ኩባንያ ከእኔ የንግድ ምልክት ጋር ይመሳሰላል በማለቱ ነበር። ኩባንያው ማሲ ነው የሚባለው። ታዲያም ሜሲ ከሚለው ጋር ተመሳሳይነት ስላለው በሕዝቡ ዘንድ ውዥንብር ይፈጥራል ሲል ነበር መከራከሪያ ያቀረበው። የባርሴሎና እግር ኳስ ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ ለስፖርት አልባሳት መለያ ስሙን እንደ ንግድ መለያ አድርጎ ለማስመዝገብ ያመለከተው ከ9 ዓመታት በፊት ነበር። እነዚህን ሁሉ ዓመታትም በክርክር አሳልፏል። በመጨረሻም ጉዳዩን የተመለከተው የአውሮፓ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እግር ኳስ ተጨዋቹ ሊዮኔል ሜሲ ስሙን እንደ ንግድ ምልክት መለያ ማስመዝገብ እንደሚችል ዛሬ ብይን ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱ የስፔን የሳይክል ኩባንያ ማሲ እና የአውሮፓ ህብረት የአዕምሮ ንብረት ጽ/ቤት ያቀረቡትን ይግባኝ ውድቅ አድርጓል። የአውሮፓ የፍትሕ ፍርድ ቤት ሕዝቡ የሁለቱን የንግድ ምልክት መለያዎች ልዩነት መለየት ይችል እንደሆነ በሚመዘንት ጊዜ፤ የኮከብ ተጨዋቹ ዝና ከግምት መግባቱ አይቀርም ብሏል። በመሆኑም ፍርድ ቤቱ የአውሮፓ ሕብረት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሁለት ዓመታት በፊት እግር ኳስ ተጨዋቹ ዝነኛ በመሆኑ ውዥምብር ሊፈጥር አይችልም ሲል ያስተላለፈውን ውሳኔ ተቀብሎ ብይን ሰጥቷል።
news-47638631
https://www.bbc.com/amharic/news-47638631
እሌኒ ገብረመድህን፡ ዋና የደስታ አስፈፃሚ ሥራቸው ምንድን ነው?
ዋና የደስታ አስፈፃሚ የተሰየመውን የሥራ መደብ ፈጥረው እራሳቸው ባቋቋሙት ድርጅት ውስጥ እራሳቸውን የመደቡት ዶ/ር እሌኒ ገብረመድህን ይህ ሃላፊነታቸው ምን እንደሆነና ምንስ ውጤት እንዳለው ይናገራሉ።
የብሉ ሙን ዋና የደስታ አስፈፃሚ ዶ/ር እሌኒ ገብረመድህን ዶ/ር እሌኒ ገብረመድህን በብዙ ሰዎች ዘንድ የሚታወቁት በሥራ ፈጠራቸው ወይም ለሥራ ፈጣሪዎች ዕድል በመስጠታቸው አሊያም ደግሞ የኢትዮጵያን የምርት ገበያን በማስጀመራቸው ነው። ሆኖም ግን ብዙ ሰው ላያውቀው የሚችለው በአሁኑ ሰዓት ዶ/ር እሌኒ ገብረመድህን ዋና የደስታ አስፈፃሚ ወይም በእንግሊዘኛ 'ቺፍ ሃፒነስ ኦፊሰር' መሆናቸውን ነው። ለመሆኑ የደስታ አስፈፃሚ ሥራ ምንድን ነው? ምንስ ማለት ነው? ብሉ ሙን የብሉ ሙን ዋና ዓላማ "ወጣ ያሉ፤ ለየት ያሉ የፈጠራ ሃሳቦችን ለመገፋፋት ታስቦ" የጅማሮ ሥራ ፈጠራንና በፈጠራ ሃሳቦች ላይ የተመሠሩቱ ሥራዎችን በገንዘብና በተለያየ መልኩ ድጋፍ ለማበርከት የተቋቋመ እንደሆነ ያስረዳሉ። • ደስታን ለመፍጠር የሚረዱ አምስት መንገዶች በዚህ ዓይነት የሥራ አካባቢ ደግሞ "አንድ ሥራ አስኪያጅ ለየት ባለ መልኩ ነገሮችን ማየት ይኖረበታል" የሚሉት ዶ/ር እሌኒ የብሉ ሙን ሥራ አስኪያጅ መሆን ማለት ደስታ አስፈፃሚ ከመሆን ጋር ትርጉሙ ተመሳሳይ ሆኖ ሊታሰብ እንደሚችል ይጠቁማሉ። "እራሴን ዋና የደስታ አስፈፃሚ ብዬ የሰየምኩትም ከድሮም ጀምሬ የምንሠራው በሙሉ መጨረሻው ደስታ መሆን አለበት ብዬ ስለማምን ነው" ይላሉ። "አንድ ሰው የማያስደስተውን ነገር መሥራት የለበትም። የሚያስደስተውን ደግሞ መሥራት አለበት" ብለው አንድ ሥራ አስኪያጅ ሥራው ወረቀት ማገላበጥ ወይም ለሰው ትዕዛዝ መስጠት ብቻ ሊሆን አይችልም ይላሉ። የዋና ደስታ አስፈፃሚ ሥራ ደግሞ የሁሉንም ሰው ደስታ ከእሳቤ አስገብቶ ጥሩ ውጤት ለማምጣት መነሳት ማለት እንደሆነ ይናገራሉ። የሥራ ድርሻቸው በሦስት የመሥሪያ ቤቱ ዘርፍ ውስጥ እንደሚንፀባረቅ ዶ/ር እሌኒ ይናገራሉ። • ደስታን አጥብቀን ስለፈለግን ለምን አናገኘውም? በድርጅት ውስጥ ተቀጥረው የሚሠሩት ሠራተኞች በሙሉ ደስታ የሚሰጥ ሥራ በመሥራትና በስሜት እንዲሠሩ ማመቻቸት ጠቀሜታው ከሠራተኛው በተጨማሪ ተገልጋዩ እራሱ 'በሚሰጠው አገልግሎት ድስተኛ ሆኖ እንዲሄድ ያስፈልጋል' በማለት የሥራ ድርሻቸውን ያስረዳሉ። ከተጠቃሚዎቹ ባሻገር ደግሞ ኢንቬስተሮቹ ገንዘባቸውን በሚለግሱበት ወቅት 'አምነውበት ብቻ ሳይሆን ደስተኛ ሆነው እንዲሰጡ' ማድረግም በአጠቃላይ የደስታን አስፈላጊነት ያስረዳሉ። "በጥልቀት አስቤበት ሳይሆን የሚሰማኝንና የማምንበት ስለሆነ የአንድ መሪ ዋና ዓላማ በሁሉም አቅጣጫ ደስታ መፍጠር ይመስለኛል" ይላሉ። ደስተኛ መሥሪያ ቤት ሃሳብን ማመንጨት፣ መፍጠር፣ ሃሳብን ማጋራትና በሙሉ የእራስ መተማመን ሃሳብን መግለፅ ለብዙ የማህበረሰቡ አባላት ከባድ እንደሆነ የሚያስረዱት ዶ/ር እሌኒ እነዚህን የሚያበረታቱ አካባቢዎች አስፈላጊ መሆናቸውን ይገላፃሉ። "ያለንብት ማህበረሰብ ለየት ያሉ ሃሳቦችን ብዙ ጊዜ በንቀት 'ከየት አመጣሽው? ከየት አመጣኸው?' የሚል ስለሆነ እኛ ለእንደዚህ ዓይነት ሃሳቦች ቦታ መፍጠር ነበረብን።" "ሁሌም ጠዋት ጠዋት ወደ ብሉ ሙን የፈጠራ ሃሳባቸውን ይዘው የመጡትን አባላት ምን እንደሚያስደስታቸው የመጠየቅ ልማድ አለኝ" የሚሉት ዶ/ር እሌኒ፤ እርሳቸውም የእራሳቸውን ስሜትና የሚያስደስቷቸውን ነገሮች እንደሚያካፍሏቸውም አጫውተውናል። • «ስጦታ ከመቀበል፤ መስጠት ያዋጣል» ከሚሰሟቸው ምላሾች መካከል አልፎ አልፎ የሚሳፈሩበትን ታክሲ በሰዓቱ ማግኘታቸው የሚያስደስታቸው እና የተመገቡት ምግብ እንዳስደሰታቸው የሚነግሯቸው እንዳሉና እሳቸውም በዚያን ዕለት የለበሱት ልብስ እንዳስደሰታቸው እንደሚነግሯቸው ይጠቅሳሉ። የደስታ የሚያስደስቱ ውጤቶች "እኛ የሰው ማንነት ላይ ነው የምናተኩረው። ሲያወሩ ሳቅ ብለው እንዲያወሩ፣ በእራሳቸው መተማመን እንዲያዳብሩና ደስተኛ እንዲሆኑ ነው የምንተጋው" በማለት በሥራ ቦታ ደስታ እንዲኖር ማድረግ ውጤታማ እንደሚያደርግ ያስረዳሉ። ከብሉ ሙን የሚወጡት ግለሰቦች ውጤታማ መሆናቸውን በደስታ የሚናገሩት ዶ/ር እሌኒ፤ በቅርብ ጊዜ ቶታል ያዘጋጀውን ውድድር ጠቅሰው "በተለያዩ ውድድሮችም ላይ ሲሳተፉ አሸናፊዎች ናቸው። በሥራቸው ብቻ ሳይሆን መንፈሳቸው እራሱ አሸናፊ ነው። በዚህ ዓመት አንደኛም፣ ሁለተኛም፣ ሦስተኛም የወጡት የብሉ ሙን ወጣቶች ናቸው። የረዳቸው ደግሞ በሥራቸው ደስተኛ መሆናቸው ይመስለኛል" በማለት ይናገራሉ።
news-52074361
https://www.bbc.com/amharic/news-52074361
ኮሮናቫይረስ፡ የኮሮናቫይረስ መነሻ የነበረችው የቻይናዋ ዉሃን ከተማ በከፊል ለእንቅስቃሴ ክፍት ሆነች
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የጀመረባት የቻይናዋ ዉሃን ከተማ ለሁለት ወር ያህል ከእንቅስቃሴ ታግዳ ከቆየች በኋላ በከፊል ክፍት ሆነች።
ወደ ዉሃን የመጡ ሰዎች ቤተሰቦቻቸው ለረዥም ጊዜ ያላዩ ሲሆን ከተማዋን ለቅቀው መውጣት የሚፈቀድላቸው ከሳምንት በኋላ ነው ተብሏል ዛሬ በርካታ መንገደኞች በዉሃን ባቡር ጣቢያ ሲተራመሱ ታይተዋል። ከስፍራው እንደሚወጡት ዘገባዎች ከሆነ ሰዎች ወደ ዉሃን ከተማ መግባት ቢፈቀድላቸውም መውጣት ግን አልተፈቀደም። የሁቤይ ግዛት ዋና ከተማ የሆነችው ዉሃን ከ50 ሺህ በላይ ኮሮናቫይረስ ያለባቸው ሰዎች የተገኙባት ሲሆን 3 ሺህ ያህል ሰዎች ደግሞ ሞተዋል። • ፕሬዝዳንት ትራምፕ የመኪና አምራቹን የመተንፈሻ መሳሪያ እንዲያመርት አዘዙ • የህክምና ባለሙያዎቻቸውን ለመከላከል የሚተጉት ቱኒዚያውያን እንደ ቻይና መንግሥት መረጃ ከሆነ በግዛቲቱ ያለው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እየቀነሰ ነው። ግዛቲቱ ቅዳሜ ዕለት 54 ሰዎች ብቻ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የገለፀች ሲሆን ሁሉም ሕሙማን ከሌላ አካባቢ የመጡ ናቸው ተብሏል። ቻይና በአሁኑ ሰዓት ከሌላ አካቢቢ የሚመጡ ህሙማንን ለመከላከል በሚል የመኖሪያ ፈቃድም ሆነ ቪዛ የያላቸው መንገደኞች ቢሆኑ እንኳ ከአገር ውጪ የሚመጡ የማንኛውንም አገር ዜጎች እንዳይገቡ አግዳለች። የቻይናንም ሆነ የሌላ አገራትን በረራ በሳምንት አንድ ቀን ብቻ እንዲሆን በተጨማሪም አውሮፕላኑ ካሉት መቀመጫዎች 75 በመቶውን ብቻ መንገደኞች መያዝ እንደሚችል አስታውቃለች። የኮቪድ-19 ቫይረስ በቻይናዋ ዉሃን የባህር አሳ ምግቦች በሚሸጥበት ገበያ እንደጀመረ የሚገመት ሲሆን ይህም ሊሆን የቻለው "ሕገ ወጥ የዱር እንስሳት ንግድ ላይ በተሰማሩ ሰዎች አማካኝነት ነው" ተብሏል። በከተማዋ የሚኖሩ 11 ሚሊየን ሰዎች በቤታቸው ተቀምጠው ያሳለፉ ሲሆን ከከተማዋ የሚያስወጡ የተለያዩ መንገዶችም ተዘግተው ነበር። ነገር ግን ከአርብ ጀምሮ ወደ ከተማዋ የሚያስገቡ መንገዶች ለእንቅስቃሴ ክፍት መሆናቸው ታውቋል። የከተማዋ 17 የባቡር መንገዶችም ቢሆኑ አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል። ዉሃን ከታሕሳስ ወር አጋማሽ ጀምሮ ከማንኛውም እንቅስቃሴ ታግዳ ቆይታ ነበር ማንኛውም ዉሃን የሚደርስ መንገደኛ በተንቀሳቃሽ ስልኩ ላይ ጤነኛ መሆኑን የሚያሳይ በመተግበሪያ ላይ የተጫነለትን አረንጓዴ ምልክት ማሳየት ይጠበቅበታል። ከዉሃን መውጣት የሚፈቀደው የአገር ውስጥ በረራ ሲጀምር ከአንድ ሳምንት በኋላ እንደሆነ የከተማዋ ባለስልጣናት ገልፀዋል። በቻይና ባለፈው ሕዳር ወር ላይ ወረርሽኙ የጀመረ ሲሆን በዚህም የተነሳ 3300 ሰዎች ሞተዋል። ከዚያ በኋላ ወረርሽኙ የተስፋፋባቸው ጣሊያንና ስፔን ግን ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር አስመዝግበዋል።
news-50944033
https://www.bbc.com/amharic/news-50944033
ጃዋር መሃመድ ኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስን መቀላቀሉን ፓርቲው አረጋገጠ
የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ሥራ አስኪያጅ የሆነው አክቲቪስት ጃዋር መሐመድ ኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስን (ኦፌኮ) መቀላቀሉን የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ለቢቢሲ ገለፁ።
ቀደም ሲል ፖለቲካ ውስጥ የመግባት ፍላጎት እንደሌለው ይልቁንም ከዳር ሆኖ በአገሪቱ ለተጀመረው ለውጥ ድጋፍ ማድረግን እንደሚመርጥ ተናግሮ የነበረው ጃዋር በቅርቡ የሃሳብ ለውጥ ማድረጉን እና ፖለቲካ ውስጥ ለመግባት መወሰኑን እንደተናገረ ይታወሳል። ፖለቲካውን ለመቀላቀል ቢወስንም ተሳትፎው በየትኛው ፓርቲ እንደሚሆን አለመወሰኑንም በወቅቱ ገልፆ ነበር። ጃዋር ፓርቲያቸውን እንደተቀላቀለ ከቢሯቸው መረጃ የተሰጣቸው ትናንት እንደሆነ የሚናገሩት ፕሮፌሰር መረራ "ኦፌኮ እገባለሁ ብሎ ለቢሯችን ነግሯል" ብለዋል። ከሦስት ወይም ከአራት ቀናት በፊት ፕሮፌሰር መረራ ባሉበት የፓርቲያቸውን ጽህፈት ቤት መጎብኘቱንም ገልፀዋል። • ኃይሌ ገብረሥላሴ ለ78 ሰዎች ሞት ፌስቡክን ወቀሰ • "ክስተቱ 'የግድያ ሙከራ' እንደሆነ ነው የምረዳው" ጀዋር መሐመድ • "በመንግሥትም በፖሊስም በኩል ምንም ዓይነት እርምጃ አልተወሰደም" ፌደራል ፖሊስ ጃዋር ወደ ኦፌኮ ለመቀላቀል ከመወሰኑ ቀደም ብሎ ከአመራሩ ጋር ያደረገው ንግግር እንደነበረ የተጠየቁት ሊቀመንበሩ "አባላት ስንመለምል ንግግር የለም፤ እሱ ራሱም እኮ እዚህ ገብቻለሁ ሊል ይችላል። እኛም ስብሰባ ላይ እኛን ተቀላቅሏል ብለን ልንናገር እንችላለን" የሚል መልስ ሰጥተዋል። ቢቢሲ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ የጃዋርን አባል የመሆን ጥያቄ ተቀብሎት እንደሆነም ለፕሮፌሰር መረራ ጥያቄ አቅርቦላቸው በሰጡት ምላሽ "ማንም ኢትዮጵያዊ የእኛ አባል ሊሆን ይችላል የምንከለክልበት የተለየ መንገድ የለንም። ወንጀል የሠራ ወይም በሕዝብ ላይ ወንጀል የሠራ እስካልሆነ ድረስ" በማለት መልሰዋል። ጃዋር መሐመድ ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ በመንግሥት ተመድበውለት የነበሩ ጥበቃዎች "እኔ ሳላውቅ ለማንሳት ሙከራ ተደርጓል" በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ መልዕክት ካሰፈረ በኋላ የተፈጠረውን ውዝግብና አለመረጋጋትን ተከትሎ ነበር ለምርጫ እንደሚወዳደር ፍንጭ የሰጠው። ወደ ፖለቲካው ለመግባት መወሰኑን ተከትሎ አሜሪካዊ ዜግነቱን መሰረዝ የሚያስችለውን ሂደት በቶሎ እንደሚጀምር ጃዋር በተደጋጋሚ በተለያዩ ቃለ ምልልሶቹ ጠቅሶ እንደነበር የሚታወስም ነው። አንዳንድ የዜና ምንጮች ጃዋር ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲን ማነጋገሩንም ጭምር ገልፀዋል። በፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ሊቀመንበርነት የሚመራው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)፤ በፕሮፌሰሩ ይመራ በነበረው የኦሮሞ ሕዝብ ኮንግረስና (ኦሕኮ) በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ይመራ በነበረው የኦሮሞ ፌደራሊስት ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኦፌዴን) ውህደት የተመሰረተ ፓርቲ ነው።
52505566
https://www.bbc.com/amharic/52505566
ኮሮናቫይረስ፡ የቤት ውስጥ ጥቃት ሰለባ ለሆኑ ሴቶች ከለላ የሚሰጠው ምክር ቤት
ብራሰልስ የሚገኝ የአውሮፓ ምክር ቤት ህንጻ ለ100 ሴቶች መጠለያ ሆኗል። ከሴቶቹ አብዛኞቹ የቤት ውስጥ ጥቃት ሰለባ ናቸው። ቤልጄም ዜጎቿ ከቤት እንዳይጡ ማወጇን ተከትሎ የቤት ውስጥ ጥቃት ተበራክቷል።
በመጠለያው ቤት አልባ ሴቶችም ይገኙበታል። ሄልሙት ኮሁል የተባለው ህንጻ ለሴቶች ማቆያ የሆነው ባለፈው እሮብ ነበር። በህንጻው ያሉ ቢሮዎች ወደ መኝታ ክፍልነት ተለውጠዋል። ምግብና የህክምና አገልግሎትም ይሰጣል። ሳሙሶሻል የተባለ የተራድኦ ድርጅት እንደሚለው፤ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ዜጎች ከቤት እንዳይወጡ መወሰኑን ተከትሎ የቤት ውስጥ ጥቃት ጨምሯል። በቤልጄም መዲና ብራሰልስ የሚገኘው ምክር ቤት ከሳሙሶሻል ጋር ተጣምሮ ነው ለሴቶች ከለላ የሚሰጠው። የተራድኦ ድርጅቱ ኃላፊ ሰባስሽን ሮይ፤ “የእንቅስቃሴ ገደብ ከተጣለ ወዲህ በቤት ውስጥ ጥቃት ሳቢያ ብዙ ሴቶች ጎዳና ወጥተው አግኝተናል” ብለዋል። የብራሰልስ ባለሥልጣኖች የጎዳና ተዳዳሪዎች በሆቴሎች እንዲጠለሉ አድርገዋል። በአሁን ወቅት አብዛኞቹን የአውሮፓ ምክር ቤቶች የሚጠቀምባቸው የለም። በምክር ቤቶቹ ጥቂት የሕዝብ እንደራሴዎች ለስብሰባ ሲገኙ፤ አብዛኞቹ ግን ስብሰባውን የሚከታተሉት በቪድዮ ነው። የምክር ቤቱ ፕሬዘዳንት ዴቪድ ሳሎሶ፤ ብራሰልስ ከመቼውም በላይ ችግር ውስጥ መውደቋን ገልጸው፤ “ችግሩ ሁላችንንም ይነካል” ብለዋል። “አሁን ያለንበት ውጥንቅጥ ሁላችንም በጎ ነገር እንድናደርግ ሊገፋፋን ይገባል” ሲሉም አክለዋል። ምክር ቤቱ ቤት አልባ ሰዎችን ለሚረዱ ድርጅቶች በየቀኑ 1,000 ምግብ ያከፋፍላል። የሳሙሻል ኃላፊ ሮይ እንደሚሉት፤ የእንቅስቀሴ ገደቡ ከተነሳ በኋላ ቤት አልባ የሆኑት ሴቶች እጣ ፈንታ ምን እንደሚሆን አጠያያቂ ነው። ኮሮናቫይረስ ያስከተለው ቀውስ፤ ለአደጋ እጅግ ተጋላጭ ለሆኑ የማኅበረሰቡ አካላት ከለላ የሚሰጥበት መሆኑንም አክለዋል። በመጠለያው ካሉ ሴቶች አንዷ አድሊን፤ “በእንደዚህ አይነት ወቅት ቤት አልባ ሰዎችን የሚያስታውስ የለም” ትላለች። ማቆያው እፎይታ እንደሰጣትም ትናገራለች። የእንቅስቃሴ ገደብ ሲጣል እሷና ባለቤቷ ከቦታ ቦታ ለመዘዋወር ተገደው ነበር። “ወደ 15 ኪሎ ሜትር በእግር ተጉዘናል። አንድ ቦታ ስናርፍ ፖሊሶች ተነሱ ይሉን ነበር። በስተመጨረሻ አቅማችን ተሟጠጠ” ትላለች። በሌሎች ማቆያዎች በአንድ ክፍል እስከ ስድስት ሴቶች እንደሚኖሩ በመጥቀስ፤ ምክር ቤቱ ውስጥ በአንድ ክፍል ሁለት ሴቶች ብቻ እንዲቆዩ መደረጉ ምቹ መሆኑንም ታስረዳለች። እሷ መጠለያ ብታገኝም ባለቤቷ እንደአብዛኞቹ ቤት አልባ ወንዶች አሁንም ጎዳና ላይ በመገኘቱ ግን ታዝናለች።
news-47043452
https://www.bbc.com/amharic/news-47043452
አሜሪካዊው ዶክተር ለአራት አመት ህፃን ዕፀ ፋርስ አዘዘ
አሜሪካዊው ዶክተር ለአራት አመት ህፃን ልጅ የእፀ ፋርስ ብስኩት ማዘዙን ተከትሎ የሙያ ፍቃዱ እንዳይሰረዝ በመከራከር ላይ ነው።
የተፈጥሯዊ መድኃኒት ባለሙያ የሆነው ዶ/ር ዊልያም ኤይደልማን እንደሚናገረው በጥቂቱ እፀ ፋርስን መውሰድ ህፃኑ ያለበትን ከፍተኛ የሆነ ግልፊተኝነት ቀዝቀዝ እንዲያደርግለት ነው። የዶክተሩ ምርመራ ልጁ የስሜት መዋዠቅን የሚያስከትለው ባይፖላር ዲስኦርደርና የትኩረት እጥረት ችግሮች እንዳለበት የሚያሳይ ቢሆንም ይህ ግን ስህተት እንደሆነ ተገልፆ ነበር። ይህንንም ተከትሎ ህክምናን የሚቆጣጠሩ የቦርድ አባላት የስነልቦና ባለሙያዎችን ባለማማከርና በቸልተኝነት ወንጅለውታል። •"ዕፀ ፋርስ በመሸጥ ልጆቼን አሳድጋለሁ" የሌሴቶዋ አምራች የልጁ አባት የልጁ ባህርይ ነውጠኛ በመሆኑ ከጥቂት አመታት በፊት ዶክተሩን ባማከሯቸው ወቅት ነው ዕፀ ፋርሱን ያዘዘወ። ዶክተሩም በመጠኑ ዝቅተኛ የሆነ እፀ ፋርስ ያዘዘለት ሲሆን ይህም ይፋ የወጣው የትምህርት ቤቱ ነርስ በምሳ ሰዓት ላይ ከእፀ ፋርስ የተሰራውን ብስኩት እንድትሰጠው በመጠየቋ ነው። ቦርዱ የዶክተሩ ፍቃድ እንዲሰረዝ የጠየቀው ዕፀ ፋርስን በማዘዙ ሳይሆን የምርመራው ውጤት ቸልተኝነት የተሞላበት በመሆኑ ነው ተብሏል። •ካናዳ ዕፀ ፋርስን ህጋዊ አደረገች የልጁ አባት በበኩሉ ህፃን እያለ የስሜት መዋዠቅን የሚያስከትለው ባይፖላር ዲስኦርደርና የትኩረት እጥረት ችግሮች አለው በመባሉ ብዙ መድኃኒቶችን ይወስድ እንደነበር ተናግሯል "መሞከሪያ እንደሆንኩ ይሰማኝ ነበር" ብሏል። በኋላም እፀ ፋርስን መጠቀም የጀመረ ሲሆን መረጋጋትን እንዳመጣለትና፣ ባለቤቱ ላይ ያሳየው የነበረው ግልፍተኝነት ሙሉ በሙሉ እንደተቀየረም ይናገራል። •"ኢትዮጵያዊ ታሪኮችን ወደ ዓለም አቀፍ የፊልም መድረክ ማምጣት ፈታኝ ነው" ዘረሰናይ መሐሪ ከዚህ ቀደምም የስሜት መዋዠቅን የሚያስከትለው ባይፖላር ዲስኦርደርና የትኩረት እጥረት ችግሮች ላሉበት ለትልቁ ልጁም እፀ ፋርስን እንደሚሰጠው አባትየው አሳውቋል። አባትየው እንደሚናገረውም ዕፀ ፋርስ በሁለቱም ልጆቹ ላይ በጎ የሆነ አስተዋፅኦ እንዳለው ነው። ዶ/ር ኤይደልማን ውሳኔውን ተቃውሞ የህክምና ሙያቸውን እንደሚቀጥል ተናግሯል። ጠበቆቹ በበኩላቸው ፍቃዱ እንዳይሰረዝ ማድረግ መቻላቸውንና ጉዳዩም በቀጠሮ እንደተያዘ ገልፀዋል። ለመድኃኒትነት የሚውለው ዕፀ ፋርስ በካሊፎርኒያ ከአውሮፓውያኑ 1996 ጀምሮ ፍቃድ ያገኘ ሲሆን ዶ/ር ኤይደልማንም በሺዎች ለሚቆጠሩ ህመምተኞችም ዕፀ ፋርስን አዟል።
news-55292088
https://www.bbc.com/amharic/news-55292088
በናይጄሪያ ትምህርት ቤት ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ጠፍተዋል ተባለ
በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ በሚገኝ ትምህርት ቤት ጥቃት መድረሱን ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች መጥፋታቸው ተገልጿል።
ታጣቂዎች በሞተርሳይክል ተጭነው በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱ ከደረሱ በኋላ ወደ ሰማይ መተኮስ እንደጀመሩና በርካቶችም በፍራቻ ብትንትን ብለው ከአካባቢው እንደጠፉ የአይን እማኝ ተናግሯል። ካትሲና ግዛት የሚገኘው የመንግሥት አዳሪ ትምህርት ቤት 800 ተማሪዎች ያሉበት ሲሆን ከበባውም የደረሰው አርብ አመሻሹ ላይ ነው። በትናንትናው ዕለት የናይጄሪያ ጦር ታጣቂዎቹ የተደበቁበትን ስፍራ እንዳገኘውና ከሰራዊቱ አባላትም ጋር የተኩስ ልውውጥ እንደነበርም ተገልጿል። በትምህርት ቤቱ ደረሰ በተባለው ከበባም ሆነ ጥቃት የደረሰው ጉዳት ግልፅ ባይሆንም ባለስልጣናቱ ግን ጉዳት ደርሶበት የመጣ ተማሪ የለም ብለዋል። የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ጥቃቱን አውግዘው የመማር ማስተማሩ ሂደት እንዲቀጥልና ምን ያህል ተማሪዎችም በትክክል እንደጠፉ ቆጠራ እንዲካሄድም ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። ጥቃቱን ተከትሎ ልጆቻቸውን በአፋጣኝ ከትምህርት ቤት የወሰዱ ወላጆችም የትምህርት ቤቱን ባለስልጣናት እንዲያሳውቁም ተብለዋል። የወንዶች ብቻ አዳሪ ትምህርት ቤት በሆነው ትምህርት ቤት አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎችም ተኩስ ከምሽቱ አምስት ሰዓት አካባቢ እንደሰሙና ለአንድ ሰዓትም የዘለቀ እንደነበር ለቢቢሲ ተናግረዋል። በትምህርት ቤቱ ውስጥ የሚገኙ የፀጥታ ኃይሎች ፖሊስ በቦታው ከመድረሱ በፊት ታጣቂዎቹን መግታትም እንደቻሉ ባለስልጣናቱ አስረድተዋል። በትናንትናው ዕለትም በነበረው መግለጫ ፖሊስ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር ገልፆ የተወሰኑትም ታጣቂዎች መሸሻቸውም ተነግሯል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ተማሪዎቹ ለደህንነታቸው በመስጋት አጥር እየዘለሉ ከግቢው ወጥተዋል። ሸሽተው ከነበሩት መካከል 200ዎቹ ቢመለሱም በርካታ ተማሪዎች በታጣቂዎቹ ታግተው እንደተወሰዱ የአይን እማኞቹ ተናግረዋል። አንድ ፖሊስም ቆስሎ ሆስፒታል ገብቶ ህክምና እየተደረገለት መሆኑንም መግለጫው አክሏል። የአካባቢው ነዋሪዎች ከፖሊስ ጋር በመጣመር የጠፉትን ተማሪዎች እየፈለጉ ሲሆን አብዛኛዎቹ ወላጆች ግን ልጆቻቸውን ከትምህርት ቤቱ አስወጥተዋል። "ትምህርት ቤቱ ባዶ ሆኗል፣ ሁሉም ተማሪዎችም ግቢውን ለቀው ወጥተዋል" በማለት ኑራ አብዱላሂ የተባለ የአይን እማኝ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪል ተናግሯል። "ከግዛቲቷ ወጥተው የነበሩ አንዳንድ ተማሪዎች ዛሬ ቢመለሱም በርካቶቹ በአውቶብስ ተሳፍረው ወደ መኖሪያ ቀያቸው አምርተዋል" ብሏል። የካትሲና አስተዳዳሪ አሚኑ ቤሎ ማሳሪ በግዛቲቷ የሚገኙ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በሙሉ እንዲዘጉ ወስነዋል። በጎሮጎሳውያኑ 2014 ከቺቦክ ግዛት 270 ሴት ተማሪዎች በፅንፈኛው ቦኮ ሃራም ታግተው መወሰዳቸው ይታወሳል። ካትሲና ትምህርት ቤት ላይ ለደረሰው ከበባም ሆነ ጥቃት ኃላፊነቱን የወሰደ አካል የለም። አካባቢው ቦኮ ሃራም ከሚንቀሳቀስበት ራቅ ያለም ነው ተብሏል።
news-53761492
https://www.bbc.com/amharic/news-53761492
ሊባኖስ፡ የቤይሩት ፍንዳታን ተከትሎ በርካታ የህክምና ማዕከላት ጥቅም አልባ ሆነዋል
ባለፈው ሳምንት በቤይሩት ከፍተኛ የሚባለውን ፍንዳታ ተከትሎ የጤና ማዕከላት ከጥቅም ውጭ ሆነዋል ተብሏል።
የአለም ጤና ድርጅት በከተማዋ አደረግኩት ባለው ግምገማ ከ55ቱ ውስጥ ግማሹ ጥቅም አልባ መሆናቸውን ተረድቷል። ትልልቅ የሚባሉ ሶስት ሆስፒታሎች የተዘጉ ሲሆን ተጨማሪ ሌሎች ሶስት ሆስፒታሎች ደግሞ የሰራተኞቻቸውን ቁጥር ቀንሰዋል። የድርጅቱ አሰሳ እንደጠቆመው በጤና ማዕከላቱ ውስጥም የኮሮናቫይረስን ለመግታት የወጡ መመሪያዎች ተግባራዊ እየሆኑ አይደለም። ቤይሩትን ባንቀጠቀጣት በዚህ ፍንዳታ 200 ዜጎቿን ያጣች ሲሆን 6 ሺህ ያህል ደግሞ መጎዳታቸውንም የከተማዋ አስተዳዳሪ ማርዋን አቡድ አስታውቀዋል። ለፍንዳታው ምክንያት ደግሞ በስፋት ለግብርና ማዳበሪያነት የሚውለው የአሞኒየም ናይትሬት ኬሚካል በወደብ አካባቢ ደህንነቱ ባልተጠበቀ ሁኔታ በመቀመጡ ነው። ከፍተኛ ክምችት የተባለው ይህ ኬሚካል ወደ 2 ሺህ 700 ቶንም ይመዝናል። ፍንዳታው ሳምንቱን በትናንትናው ዕለት የደፈነ ሲሆን ይህን ያህል ተቀጣጣይ ኬሚካል ደህንነቱ ባልተጠበቀ ሁኔታ በወደብ ላይ መቀመጡ ቁጣን ቀስቅሷል። ይህ የገነፈለው ቁጣም የሊባኖስ መሪን ከስልጣናቸው እንዲለቁ አድርጓቸዋል። የሆስፒታሎቹ ሁኔታ እንዴት ነው? በምስራቅ ሜድትራንያን የአለም ጤና ድርጅት ቅርንጫፍ ዳይሬክተር ዶክተር ብሬናንን በቤይሩት የሚገኙ 55 ዋነኛ የጤና ማዕከላትን ሁኔታ ገምግመዋል። ከነዚህም ውስጥ ግማሹ ጥቅም አልባ የሆኑ ሲሆን በዚህም ምክንያት በአገሪቷ 500 ለህሙማን የሚሆኑ አልጋዎችን እጥረት አስከትሏል። ሆስፒታሎቹ በፍንዳታው በተጎዱ ሰዎች በመጨናነቃቸው ሌሎች ህመምተኞችን ማከም አልቻሉም ብለዋል። የአለም ጤና ድርጅትም የተዘጉት ሆስፒታሎችና ክሊኒኮችን መክፈትና አገልግሎት እንዲሰጡ ማስቻል ቅድሚያ የሚሰጠው ስራ መሆን እንዳለበት እያሳሰበ ነው። ድርጅቱ የተለያዩ የህክምና ቁሳቁሶች ለሚያስፈልጋቸው የጤና ማዕከላትም እያሰራጨ ይገኛል። የኮሮናቫይረስ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ባለባት ሊባኖስ የጤና ማዕከላቱ ከጥቅም ውጭ መሆን ራስ ምታት ሆኖባታል። በቫይረሱ 7 ሺህ 121 ሰዎች መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን 87 ሰዎችም ህይወታቸው ማለፉን ከጤና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያስረዳል። ሊባኖስ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት እያደረገች የነበረውን ጥረት ያመሰገኑት ዶክተር ብሬናን ፍንዳታውን ተከትሎ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች መጨመሩ ስጋት አጥሏል ብለዋል። አገሪቷም ከፍተኛ የሚባለውን ቁጥር የመዘገበችው በዚህ ሳምንት ሲሆን ዳይሬክተሩ ከፍተኛ ጥንቃቄና ቁጥጥር እንደሚያስፈልግም አሳሳስበዋል። ፍንዳታው ከፍተኛ ጉዳት ያስከተለባት ቤይሩት ታሪካዊ ቦታዎችን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ህንፃዎች ፈራርሰዋል። ከተማዋን የጦር አውድማ አስመስለዋታል።
news-54936674
https://www.bbc.com/amharic/news-54936674
የሲሲሊ ማፊያዎችን የሚገዳደሩት ናይጄሪያውያን ሴቶች
አፍሪካውያን ጋዜጠኞች ለቢቢሲ በሚጽፉት ሳምንታዊ ደብዳቤ ላይ ናይጄሪያዊው ጋዜጠና ኢስማኤል ኢናሼ በጣልያኗ ሲሲሊ ከተማ ስለሚገኙ አስገራሚ ሴቶች ተከታዩን ጽፏል።
በጣልያኗ ተራራማ ከተማ ሲሲሊ የሚገኙ ናይጄሪያውያን ሴቶች በአስገዳጅ የወሲብ ንግድ ውስጥ እንዲገቡ የተደረጉ ሴቶችን የሚፈልግና የሚረዳ ማዕከል በአንዲት ሴት አማካይነት ተቋቁሟል። ኦሳስ ኢግቦን በሕወጥ አዘዋዋሪዎች ወደ ጣልያኗ ደሴት ለመጡ ሴቶች መቆያ የሚሆነውን ማዕከል የከፈተችው ባሳለፍነው ጥር ወር ላይ ሲሆን ለናይጄሪያውያን በናይጄሪያዊ የተቋቋመ የመጀመሪያው መጠለያ ማዕከል ነው። በአሁኑ ሰአት ማዕከሉ በሀያዎቹ እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ አራት ሴቶች የሚገኙ ሲሆን አንደኛዋ የልጅ እናት ናት። እስከያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት መጨረሻ ድረስ ደግሞ ሌሎች ተጨማሪ ሁለት ሴቶች እንደሚመጡ እጠብቃለው ትላለች። በአንዲት ሞቃታማ የመስከረም ከሰአት ላይ እንቅስቃሴ ወደማይታይባትና ማዕከሉ ወደሚገኝበት መንደር ተጓዝኩ። ከደሴቲቱ ዋና ከተማ ፓሌርሞ በብዙ ርቀት ላይ ነው የሚገኘው ማዕከሉ። ሴቶቹን ከሕገወጥ አዘዋዋሪዎቹና ማፊያ ቡድን አባላት ለመደበቅ። ማዕከሉ ሰፋ ያለ ወጥ ቤት ያለውና በአረንጓዴው ኮረብታዎች ላይ እይታ ያለው ሰገነት ነው። አሰራሩ የተለመደ የሲሲሊ መንደር የቤት አይነት ነው። ሴቶቹ እያንዳንዳቸው የራሳቸው ክፍሎች ያላቸው ሲሆን ወጥ ቤት እና መታጠቢያ ቤት ግን በጋራ ይጠቀማሉ። ይህ ቤት በአንድ በጣሊያናዊ ጓደኛዋ የተሰጣት ነው። በርካታ ጣሊያናውያን የናይጄሪያ ሴቶችን መርዳት ይፈልጋሉ ትላለች፤ ችግሩ ግን ፀረ-ስደተኞች ስሜት እየጨመረ በሄደበት ወቅት ሌሎች ጣሊያናውያን ይህንን እንዲያደርጉ አይፈልጉም። አሰቃቂ ግድያዎች ኦሳስ ኢግቦን ለመጀመሪያ ጊዜ የተዋወቅኳት 2018 ላይ ሲሆን ይህ ደገሞ እሷ እና ሌሎች ሴቶች ናይጄሪያውያንን የሚረዳ ማዕከል በቤኒን ሲቲ ከቋቋሙ ከሶስት ዓመታት በኋላ ነበር። ማዕከሉ በሲሲሊ የህገወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባ የሆኑ ሴቶችን ይረዳል። አብዛኛዎቹ ሴቶች ደግሞ የሚመጡት ኤዶ ከምትባለው የናይጄሪያ ግዛት ሲሆን ዋና ከተማዋ ደግሞ ቤኒን ሲቲ ናት። አሳስ ኢግቦን ከ18 ዓመት በፊት ነበር በሕገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ከቤቷ ተወስዳ በአስገዳጅ የወሲብ ንግድ ውስጥ እንድትገባ የተደረገችው። ለሲሲሊ አዘዋዋሪዎቿ እዳዋን ከፍላ ከጨረሰች በኋላ በአሁኑ ሰአት ከቤተሰቦቿ ጋር ፓሌርሞ ውስጥ በደስታ እየኖረች ነው። ነገር ግን ልክ እንደሷ መከራ የሚገጥማቸው ሴቶችን መርዳት ትፈልጋለች። እሷና ጓደኞቿ በአውሮፓውያኑ 2011 መጨረሻ እና በ 2012 መጀመሪያ ላይ በሁለት ወጣት የናይጄሪያ ሴቶች ላይ ከተፈፀመው ዘግናኝ ግድያ በኋላ እርምጃ ለመውሰድ ተነሳስሱ። ሟቾቹ የ20 ዓመትና የ22 ዓመት ወጣቶች ነበሩ። ግድያው በሲሲሊ የሚገኙ ሰዎችን ያስደነገጠ ሲሆን የናይጄሪያ ሴቶች በአስገዳጅ የወሲብ ንግድ ውስጥ እንዲገቡ እየደረጉ መሆኑና በርካታ መከራዎች እንደሚያጋጥማቸው ማሳያ ሆኖ ማለፍ ችሏል። እንደ የዓለም ስደተኞች ድርጅት መረጃ ከሆነ በአውሮፓውያኑ 2016 ብቻ 11 ሺ ናይጄሪያውያን ሴቶች ሲሲሊ መግባታቸው የተረጋጋጠ ሲሆን ከነዚህ ሴቶች መካከል 80 በመቶ የሚሆኑት በሕገወጥ አዘዋዋሪዎች ተጭነው መጥተው የወሲብ ንግድ ውስጥ እንዲሰማሩ ተደርገዋል። እነዚህ ሴቶች ሲሲሊ ከደረሱ በኋላ ደግሞ ለአዘዋዋሪዎቹ ክፍያ መፈጸም ግዴታቸው ነው። ሴቶቹም ለአዘዋዋሪዎቹ እስከ 35 ሺ ዶላር ድረስ የሚከፍሉ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ከወሲብ ንግድ የሚያገኙትን ገንዘብ በክፍያ መልክ ይወስዱባቸዋል። ሴቶቹ ጣልያን ከመድረሳቸው በፊት የሚፈጸሙት ሐይማኖታዊ ቃለ መሀላ መሰል ነገር አለ። ስነስርአቱ ሲካሄድ ቄሶች ጭምር የሚገኙ ሲሆን ከአዘዋዋሪዎቹ ቃል የሚወጡ ከሆነና እዳቸውን የማይከፍሉ ከሆነ ሴቶቹ እንዲሁም የሚወዷቸው ቤተሰቦች ጉዳት እንደሚደርስባቸው ይነገራቸዋል። አብዛኛዎቹ ከገጠራማ ክፍል የሚመጡት ሴቶች ይህንን ፍራቻ ምንም አይነት እርምጃ አይወስዱም። አብዛኛውን ጊዜም ገንዘባቸውን ለመጠየቅ እንኳን ድፍረት አይኖራቸውም። ኦሳስ ኢግቦን እንደምትለው ሴቶቹን ከማፊያ ቡድኖቹ ለማላላቀቅ ከፍተኛ ፈተና የሚፈጥረው ይህ የሚገቡት ቃል ነው። በቤኒን ሲቲ የሚገኘው መጠለያ ማዕከል ሴቶቹ ወደ ጣልያን ከመሄዳቸው በፊት ስለሚጠብቃቸው መከራና ስቃይ ቀድሞው እንዲያውቁ የሚሰራ ሲሆን ወደ አገራቸው ለሚመለሱ ሴቶች ደግሞ የስነልቦና ድጋፍና ምክር ይሰጣል። ''በፓሌርሞ የሚገኘው ማዕከል ደግሞ ከዚህ መሰል መከራ ያመለጡ ሴቶች የትምህርት ዕድል እንዲሁም ጣልያንኛ እንዲማሩና ሌላ ስራ እንዲያገኙ ይመቻችላቸዋል'' ትላለች ኦሳስ ኢግቦን። ሴቶቹ በማዕከሉ እስከ አንድ ዓመት ድረስ እንዲቆዩ የሚደረገ ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ያጋጠማቸውን መጥፎ ትዝታ እንደሚረሱና ለወደፊቱ ሕይወታቸው ለመዘጋጀት እንደሚያስችላቸው ይገመታል። ምንም እንኳን ማዕከሉ በበጎ ፈቃደⶉች የሚታገዝ ቢሆንም ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ለማሟላት ግን በሌሎች በጎ አድራጊዎች ድጋፍ ላይ የተመሰረተ ነው። በፓሌርሞ የሚኖሩ ናይጄሪያውያንም ቢሆኑ የተቻላቸውን እርዳታና ድጋፍ እንደሚያደርጉ ኦሳስ ትገልጻለች።
news-52892998
https://www.bbc.com/amharic/news-52892998
አሜሪካ ሕግን በመጠቀም ጥቁር ዜጎቿ ላይ ግፍ ትፈፅማለች?
ከሰሞኑ አሜሪካዊው ነጭ ፖሊስ ጥቁር አሜሪካዊውን ጆርጅ ፍሎይድን አንገቱን ከመሬት አጣብቆ ትንፋሽ እስኪያጥረው ድረስ ለአስር ደቂቃዎች ያህል ተንበርክኮበት በመቆየቱ ህይወቱ አልፏል።
ዓለምም ጆርጅ ፍሎይድ ህይወቱ እንድትተርፍ ሲማፀን፣ የሞቱ እናቱን እንዲደርሱለት ሲጣራ፣ የመጨረሻ እስትንፋሱን እንዲሁም ህይወት አልባ ሰውነቱን ተመልክቷል። በሚኒያፖሊስ እንደ እንስሳ የተገደለው ጆርጅ ፍሎይድ አሟሟት አሜሪካን ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም የሚገኙ ጥቁሮችን እንዲሁም የመብት ታጋዮችን ቁጣና ተቃውሞ አቀጣጥሏል። የጆርጅ ፍሎይድ ሞት በአገሪቷ ውስጥ ያለውን ለመቶዎች ዓመታት የቆየውን መዋቅራዊ ጭቆና፣ ታሪካዊ ኢ-ፍትሐዊነት፣ የፖሊስ ጭካኔና ሌሎችም መሰረታዊ ችግሮች ፍንትው አድርጎ አሳይቷል። ብዙዎችም ጥቁር አሜሪካውያን በባርነት ንግድ በግዞት ከመጡ ጀምሮ እየደረሰባቸው ያለውን ግፍም፣ ለነፃነት የተደረጉ ትግሎችን እንዲሁም እንዴት አሜሪካ ጥቁር ዜጎቿ ላይ አሁንም ቢሆን እንዴት አይነት ግፍ እንደሚፈፀምባቸው እየተናገሩ ነው፤ እየፃፉም ነው። ሚሊዮን ጥቁር አሜሪካውያን በማረሚያ ቤቶች በሚማቅቁባት፤ አገሪቱ ያወጣቻቸው ሕግና ሥርዓቶች መዋቅራዊ ጭቆና ያደርሳሉ ወይ? እስቲ አገሪቱ ፍትህን በማስፈንና ወንጀልን በመቆጣጠር ዘርፍ ረገድ በጥቁር አሜሪካውያን ላይ የሚፈፀሙ መድሎዎችን እንመልከት ከታዳጊዎች ጀምሮ በተለያዩ እድሜ የሚገኙ ላይ ጥቁር አሜሪካውያን በፖሊስ ጥይት ቆስለዋል እንዲሁም ተገድለዋል። በአስራዎቹ የሚገኙ ጥቁር ታዳጊዎችም በፖሊስ በተገደሉባቸው ወቅቶችም ፖሊሶች "ለህይወታችን ፈርተን ነው፤ ሽጉጥ ሊያወጡ መስሎን ነው" የሚሉ ምላሾች ሲሰጡም ተሰምተዋል። ይህንንም መሰረት በማድረግ የአሜሪካ ፖሊሶች ተጠርጣሪ ናቸው ብለው ጥይት የተኮሱባቸውን ሰዎች በምናጤንበት ወቅት ጥቁር አሜሪካውያን በፖሊሶች በጥይት መመታት ወይም የመገደላቸው እድል ከፍተኛ ነው። ከጥቁር አሜሪካውያን በመቀጠልም ከነጭ ሕዝቦች በበለጠም ቀደምት ሕዝቦች፣ እንዲሁም ላቲን አሜሪካውያንም በፖሊሶች ይተኮስባቸዋል እንዲሁም ይገደላሉ። በአሜሪካ ከዓመት በፊት የነበረውን የሕዝብ ቁጥር ብናይ ጥቁር አሜሪካውያን አስራ አራት በመቶ ቢሸፍኑም፤ ፖሊስ ክፉኛ ካቆሰላቸው ወይም ከገደላቸው አንድ ሺህ ሰዎች ውስጥ 23 በመቶውን ይሸፍናሉ። ይህም ቁጥር ከጎርጎሳውያኑ 2017 ዓመት ጀምሮ በተመሳሳይ መልኩ እየሄደ ሲሆን፤ በተቃራኒው በፖሊሶች በሽጉጥ የሚተኮስባቸው ወይም የሚገደሉ ነጮች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን መረጃዎች ያመላክታሉ። በአሜሪካ ውስጥ የአደንዛዥ ዕፅን መጠቀም በነጮችና በጥቁር አሜሪካውያን ተመሳሳይ ሁኔታ ቢኖረውም፤ ጥቁር አሜሪካውያን አደንዛዥ ዕፅ ይዘው ከተገኙ ዘብጥያ ይወርዳሉ። ለምሳሌ በጎርጎሳውያኑ 2018 የተደረጉ እስሮችን እንደ ማጣቀሻ ብናይ፤ በጥቁር አሜሪካውያን ዘንድ ያለው እስር 750 ከመቶ ሺህ ሲሆን ለነጭ አሜሪካውያን ደግሞ 350 ከመቶ ሺህ ነው። ነገር ግን ብሔራዊ የአደንዛዥ ዕፅ አጠቃቀም ላይ ከጎርጎሳውያኑ 2018 በፊት በተደጋጋሚ የወጡ ቁጥሮችን ብናይ በነጭ አሜሪካውያንና በጥቁር አሜሪካውያን ዘንድ የዕፅ አጠቃቀም ልማድ ተመሳሳይ ነው። ሆም የአሜሪካ የሲቪል መብቶች ህብረት ባደረገው ጥናት ጥቁር አሜሪካውያን ድንገት ዕፀ ፋርስ ይዘው ቢገኙ ያለምንም ምህረት በቁጥጥር ስር እንደሚውሉ ይፋ ያደረገ ሲሆን ይህም ከነጮች ጋር ሲወደዳር 3.7 እጥፍ እንደሆነም መረጃው አመላክቷል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አሜሪካውያን በጥቃቅን ወንጀሎች እስር ላይ እንደሚገኙ የተለያዩ መረጃዎች ያሳያሉ። በተለያየ ጊዜያትም አሜሪካ ጥቁርና ላቲን ሕዝቦቿን ወደ እስር ቤት በመወርወር ለነፃ የጉልበት ሥራ ዳርጋቸዋለች እንዲሁም የተለያዩ ኩባንያዎችም የእስር ቤት ጉልበትን በመጠቀም ላይ እንደሚገኙ የሚኣመለክቱ በርካታ ፅሁፎች ወጥተዋል። በእስር ላይ የሚገኙ ጥቁር አሜሪካውያን ከነጮች ጋር ሲወዳደር አምስት እጥፍ እንዲሁም ከላቲን አሜሪካውያን ጋር ሲወዳደር ደግሞ በእጥፍ ይበልጣል። በጎርጎሳውያኑ 2018 ያለውን የህዝብ ቁጥር ስንመለከት የጥቁር አሜሪካውያን ቁጥር አስራ ሦስት በመቶ ቢሆንም በእስር ቤት ካሉት ደግሞ ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል። በተቃራኒው ነጭ አሜሪካውያን የአገሪቱን የሕዝብ ቁጥር 60 በመቶ ቢሆኑም በእስር ቤት ካሉት ግን 30 በመቶው ብቻ ናቸው። ይህም ማለት ከመቶ ሺህ ጥቁር አሜሪካውያን መካከል አንድ ሺህዎቹ በማረሚያ ቤት የሚገኙ ሲሆን፤ የነጭ አሜሪካውያን ደግሞ 200 ከመቶ ሺህ ነው። ይህ ቁጥር በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ከአንድ ዓመት በላይ እስር ከተፈረደባቸው የተወሰደ ነው። ምንም እንኳን ባለፉት አስር ዓመታት በእስር ላይ የሚገኙት ጥቁር አሜሪካውያን ቁጥር ቢቀንስም፤ አሁንም ከሌሎች ዘሮች በበለጠ ጥቁር አሜሪካውያን በእስር ይገኛሉ።
news-49394919
https://www.bbc.com/amharic/news-49394919
አማራ ክልል፡ መተማ ዮሐንስ በተያዙት ተሽከርካሪዎች ላይ ምርመራ እየተደረገ ነው
የመከላከያ ሠራዊት ንብረት ናቸው የተባሉና በመተማ ዮሐንስ በኩል ጭነት ይዘው ወደ ሱዳን ሊሻገሩ ሲሉ እንዲቆሙ በተደረጉ አምስት ከባድ ተሽከርካሪዎች ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን የአካባቢው ፖሊስ ለቢቢሲ ገለጸ።
ትናንት ከሰዓት ከዘጠኝ ሰዓት በኋላ አምስት የመከላከያ ሠራዊት ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ሱዳን ለመሻገር ሲሞክሩ መተማ ዮሐንስ ላይ በአካባቢው ማኅበረሰብ ታግደው እንዳያልፉ መደረጋቸውን በስፋት እያነጋገረ ይገኛል። ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎችና ፎቶግራፎች እንደሚጠቁሙት ጭነት የያዙት ከባድ ተሽከርካሪዎች ጥቂት በማይባሉ ሰዎች ተከበው መንገድ ዳር እንደቆሙና የአካባቢው ባለስልጣናትም ስለጭነቱ ህጋዊነት ለማወቅ የማጣራት ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ያመለክታሉ። • ባሕር ላይ ያለምግብና መጠጥ 11 ቀናት ያሳለፈው ኢትዮጵያዊ ቢቢሲ ስለክስተቱ ለማወቅ ባደረገው ጥረት የመተማ ዮሃንስ ሁሉን አቀፍ የወንጀል ምርመራ ኦፊሰር የሆኑትን ሳጅን እንዳልካቸው ተሰማን በማናገር እንደተረዳው አምስቱ ከባድ ተሽከርካሪዎች እሁድ ከሰዓት በኋላ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ ወደ ሱዳን ለመሻገር ሲሞክሩ የኢሚግሬሽን ሰራተኞች አሽከርካሪዎቹን ፓስፖርት እንዲያሳዩ መጠየቃቸውንና ማሳየት እንዳልቻሉ ተገልጿል። ሳጅን እንዳልካቸው አክለውም "ይህንን ተከትሎ አለመግባባት መፈጠሩንና በዙሪያው የነበሩት የአካባቢው ነዋሪዎች የተሽከርካሪዎቹ ጭነት በሕገ ወጥ መልኩ ሊሻገር ነው በሚል ጥርጣሬ እንዳይንቀሳቀሱ አድርገው በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርገዋቸዋል" ብለዋል። ምንም እንኳ ፖሊስ ተሽከርካሪዎቹን ባገኘበት ጊዜ እንደተባለው ሆኖ ባያገኘውም "ሌላኛው የጥርጣሬ መነሻ ደግሞ የተሽከርካሪዎቹ የሰሌዳ ቁጥር በግሪስ ተቀብቶ እንዳይታይ ተደርጓል" የሚል እንደነበርም ሳጅን እንዳልካቸው ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት አምስቱም ተሽከርካሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሆነው የአካባቢው የመስተዳድር አካላት ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመሆን ማጣራት እየተደረገ መሆኑን የገለጹት የወንጀል ምርመራ ኦፊሰሩ ተሽከርካሪዎቹ የጦር መሳሪያ የጫኑ መሆናቸውን ማረጋገጣቸውን ተናገረዋል። • ''ውጤቱ ለእኔ ደመወዜ ነው" ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበው ብሩክ እናት ከባድ ተሽከርካሪዎቹ የተወሰነ ቁጥር ባላቸውና የመከላከያ ሠራዊት የደንብ ልብስና መለዮን የለበሱ ጠባቂዎች አጅበዋቸው እንደነበር ቢነገርም እስካሁን ግን ሙሉ መረጃ የሌላቸው መሆኑን ሳጅን እንዳልካቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ክስተቱን ተከትሎ መተማ ላይ ተይዘው እንዳያልፉ የተደረጉት ከባድ ተሽከርካሪዎች ላይ ዘረፋ እንደተፈጸመ እየተነገረ መሆኑን ጠቅሰን የጠየቅናቸው የፖሊስ ኃላፊው በሰጡን ምላሽ "በተፈጠረው ግርግር የጸጥታ ችግርም ሆነ ዘረፋ አላጋጠመም" ሲሉ አረጋግጠዋል። ፖሊስ ስለተያዙት ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች ምንነትና ወደየት እያመሩ እንደሆነ ለማወቅ ምርመራ እያደረገ መሆኑን የገለጹት ሳጅን እንዳልካቸው እስካሁን ከከፍተኛ የመከላከያ ሠራዊት ባለስልጣናት የተባሉት ነገር እንደሌለ ጠቅሰው "በዚሁ አካባቢ የሚገኘው የመከላከያ ሠራዊትም ስለጉዳዩ የሚያውቀው ነገር እንደሌለው ነግሮናል" ብለዋል። ስለጉዳዩ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የመተማ ዮሐንስ ከተማ የአስተዳደርና ጸጥታ ኃላፊ ኢንስፔክተር ይናገርን ብንደውልላቸውም ለጊዜው ያላቸው መረጃ ከዚህ የተለየ አለመሆኑን ገልጸው በአሁኑ ወቅት ሁሉም ተሽከርካሪዎች በአንድ ቦታ ሆነው ጥበቃ እየተደረገላቸው ሲሆን ጉዳዩን ለማጣራት የዞንና የክልል የሥራ ኃላፊዎች ወደ ስፍራው መጓዛቸውን ገልጸዋል። • በባሕር ዳር ለበቀል የተነሳች ሴት በአንድ ኃላፊ ላይ የአሲድ ጥቃት ፈጸመች አክለውም የተያዙት ከባድ መኪኖች አሽከርካሪዎች ሕጋዊ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ደብዳቤ እንዳላቸው መናገራቸውንና እስካሁን ግን የደብዳቤውን ሕጋዊነት ማረጋገጥ አለመቻሉን የአስተዳደርና ጸጥታ ኃላፊው ለቢቢሲ ገልጸዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሁለቱም የአካባቢው የፀጥታ ኃላፊዎች እንዳሉት ክስተቱን ተከትሎ በአካባቢው ምንም አይነት የፀጥታም ሆነ የትራንስፖርት መስተጓጎል እንደሌለና ከሱዳን ወደ መተማ ዮሐንስና ከመተማ ዮሐንስ ወደ ሱዳን ገላባት የሚደረገው እንቅስቀሴም እንደቀጠለ ነው ሲሉ አረጋግጠዋል። ስለተሽከርካሪዎቹ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከመከላከያ ሠራዊት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ስልክ ባለመነሳቱ ለጊዜው አልተሳካልንም።
news-46860124
https://www.bbc.com/amharic/news-46860124
ትራምፕ፡ ቱርክ በኩርድ ታጣቂዎች ላይ ጥቃት ከፈጸመች ኢኮኖሚዋ እንዳልነበር ይሆናል
አሜሪካ ጦሯን ከሶሪያ የማስወጣት ያላትን ዕቅድ ተከትሎ ቱርክ በሶሪያ የሚንቀሳቀሱ የኩርድ ታጣቂዎች ላይ ጥቃት ብትሰነዝር ከፍተኛ የኢኮኖሚ ውድቀት ያጋጥማታል ሲሉ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቱርክ መንግሥትን አስጠነቀቁ።
ትራምፕ እሁድ ዕለት በትዊተር ገጻቸው ላይ የኩርድ ታጣቂዎችም ቢሆኑ ከቱርክ መንግሥት ጋር እሰጣ ገባ ውስጥ እንዳይገቡ አስጠንቅቀዋል። የአሜሪካ ጦር ከኩርድ ሚሊሻዎች ጋር በመጣመር በሶሪያ የሚንቀሳቀሰውን ኢስላሚክ ስቴት (አይኤስ) ሲወጋ ከርሟል። • የሳዑዲው ጋዜጠኛ ለመገደሉ ቱርክ አሳማኝ ማስረጃ እንድታቀርብ አሜሪካ ጠየቀች • በሶሪያ ግጭት የቱርክ ኃይሎች ላይ ከባድ ጥቃት ተሰነዘረ • «ካሾግጂ ወዲያው ነበር የታነቀው» ቱርክ ቱርክ በበኩሏ የኩርድ ሚሊሻ ስብስብን አሸባሪ ስትል ፈርጃለች። የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ታየር ኤርዶጋን አሜሪካ ለኩርድ ታጣቂዎች የምታደርገውን ድጋፍ አምረረው ይቃወማሉ። ኤርዶጋን ከዚህ ቀደም የአሜሪካንን ድጋፍ ለማስቆም የተቻላቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ተናግረው ነበር። ትራምፕ በትዊተር ገጻቸው ላይ ጨምረው እንዳሰፈሩት አሜሪካ በሶሪያ ውስጥ በነበራት ተሳትፎ፤ ሩሲያ፣ ኢራን እና ሶሪያ ተጠቃሚዎች ሆኖዋል ብለዋል። ትራምፕ የአሜሪካ ጦርን ከሶሪያ የማስወጣት እቅዳቸውን ከአንድ ወር በፊት ይፋ ባደረጉበት ወቅት ከአጋር ሀገሮች ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟቸው ነበር። በመካከለኛው ምስራቅ ይፋዊ የሥራ ጉብኝነት እያደረጉ የሚገኙት የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፔዎ፤ ከቱርክ አቻቸው ጋር በስልክ እንደተወያዩ ተናግረው፤ ለኩርድ ታጣቂዎች ከለላ ለመስጠት ከቱርክ መንግሥት ጋር ስምምነት ላይ ሊደረስ እንደሚቻል ተናግረዋል። የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፔዎ እና የሳዑዲው አቻቸው አደል አል-ጁቤር ሪያድ ሳዐዲ ፖምፔዎ አቡ ዳቢ ላይ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ የቱርክ ሕዝብ እና ኤርዶጋን ሃገራቸውን ከአሸባሪዎች የመከላከል መብታቸውን የአሜሪካ መንግሥት ያከብራል ሆኖም ግን ከአሜሪካ ጎን ሆነው ሲፋለሙ የነበሩ ታጣቂዎች ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል ብለዋል። አሜሪካ ወደ ሰሜናዊ ሶሪያ ወደ 2ሺህ የሚጠጉ ወታደሮችን ማሰማራቷ ይነገራል። የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ከአራት ዓመታት በፊት ለኩርድ ታጣቂዎች ስልጠና የሚሰጡ ልዩ ኃይል ወደ ሶሪያ ልከው ነበር። ባለፉት ዓመታት በሶሪያ የተሰማራ የአሜሪካ ጦር ቁጥር በፍጥነት ጨምሯል።
news-50350132
https://www.bbc.com/amharic/news-50350132
የአንበጣ ወረራ፡ የተባበሩት መንግሥታት ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ኤርትራና ሱዳንን አስጠነቀቀ
በኢትዮጵያ የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ በቁጥጥር ሥር መዋል ካልተቻለ፤ ሰብል አውዳሚ የሆነው የአንበጣ መንጋ ጎረቤት አገራት ሊዛመት እንደሚችል የተባበሩት መንግሥታት አስታውቋል።
የአንበጣ መንጋው በቀን በቶን የሚገመት እፅዋትን ያወድማል የተባበሩት መንግሥታት በኢትዮጵያ አራት ክልሎች የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ መንግሥት ጥሪ ማቅረቡን በመግለጫው አስታውሷል። • ከሶማሌላንድና የመን የመጣው አንበጣ በአምስት ክልሎች ተከስቷል • የአንበጣ መንጋው እስካሁን በሰብል ላይ ጉዳት አላደረሰም መግለጫው አክሎም በአካባቢው ያሉ አርሶ አደሮችን ጠቅሶ እንደገለፀው አርሶ አደሮቹ በሰሜን አማራ አካባቢ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ጤፍና ሌሎች ሰብሎች ማጣታቸውን አትቷል። ባሳለፍነው ሳምንት አንበጣው ወደ የተከሰተባቸው ቦታዎች የኬሚካል ርጭት ለማካሄድ አውሮፕላን መላኩን መንግሥት አስታውቆ ነበር። ይሁን እንጅ ወረራውን ለመከላካል የሚደረገው ጥረት ውጤታማ አለመሆኑ ተገልጿል። እንደ የተባበሩት መንግሥታት የምግብና የእርሻ ድርጅት (ፋኦ) ከሆነ መንግሥት አንበጣውን ለመከላከል የሚያደርገው ጥረት በአንዳንድ አካባቢዎች ያለው የፀጥታ ችግር ተግዳሮት ሆኖበታል። "የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራውን ለመሥራት በአፋጣኝ ያለውን አቅምና ሐብት ተጠቅሞ ተግባር ላይ ማዋል ያስፈልጋል" ሲሉ በፋኦ የኢትዮጵያ ተወካይ የሆኑት ፋጡማ ሰይድ አሳስበዋል። በአጠቃላይ የበረሃ አንበጣ መንጋው በትግራይ፣ አማራ፣ ኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልል በሰብል እና በግጦሽ ላይ ጉዳት አስከትሏል። የአንበጣ መንጋው 350 ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት ባለው ቦታ በቀን 1.8 ሚሊየን ቶን እፅዋት ሲያወድም እንደነበር ፋኦ ግምቱን አስቀምጧል። የመከላከል ሥራው ከተዳከመም አንበጣው በኢትዮጵያ ውስጥ ወደ ሌሎች ቦታዎች እንዲሁም ወደ ሰሜን ምሥራቅ ኬንያ፣ የኤርትራን የተወሰኑ አካባቢዎች ፣ የሱዳን ደቡባዊ የባህር ዳርቻ ሊዛመት እንደሚችል ፋኦ አስጠንቅቋል። የአንበጣ መንጋው ከሦስት ወራት በፊት ከየመን እንደመጣ ይነገራል።
news-53260525
https://www.bbc.com/amharic/news-53260525
አቶ ጃዋር መሐመድና አቶ በቀለ ገርባ እንዲሁም በሃጫሉ ግድያ የተጠረጠሩ ሦስት ሰዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ
በድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ የተጠረጠሩ ሦስት ግለሰቦች እንዲሁም አቶ ጃዋር መሐመድና አቶ በቀለ ገርባ ፍርድ ቤት ቀረቡ።
በግድያው ተጠርጥረው ፍርድ ቤት የቀረቡት ሁለቱ ወንዶች አንዲት ሴት ሲሆኑ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ እንደተጠየቀባቸው ተገልጿል። በተያያዘ ዜናም የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ ባለፈው ማክሰኞ ከሰዓት በቁጥጥር ስር መዋላቸው የተገለጸው አቶ ጃዋር መሐመድና አቶ በቀለ ገርባ ዛሬ ጠዋት ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተነግሯል። ከድምጻዊው የቀብር ሁኔታ ጋር በተያያዘ የተፈጠረ ውዝግብን ተከትሎ በፖሊስ የተያዙት ሁለቱ ግለሰቦች ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ቀርበው ተጨማሪ ቀጠሮ እንደተሰጠ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኀን ዘግበዋል። ሁለቱ ግለሰቦች ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት ለሰዎች ሞት ምክንያት የሆነን ሁከት በመቀስቀስና በሰው ሕይወት ማጥፋት ተጠርጥረው መሆኑ ተገልጿል። በዚህም መሰረት አቶ በቀለ ገርባ ለሐምሌ 6 ሲቀጠሩ አቶ ጃዋር መሐመድ ደግሞ ለሐምሌ 9 ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ቀጠሮ ተሰጥቷቸው ወደ ማረፊያ ቤት መመለሳቸው ተነግሯል። • የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ የቀብር ሥነ ሥርዓት አምቦ ውስጥ ተፈጸመ • ከሃጫሉ ግድያ በኋላ ቢያንስ የ67 ሰዎች ህይወት መጥፋቱ ተገለጸ • የ የሰኔ 15ቱ አይነት ግድያን ለመድገም ታቅዶ እንደነበር የፌደራል ፖሊስ ገለፀ ከድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ የአስከሬን ሽኝት መስተጓጎልና ከአንድ የፖሊስ አባል ግድያ ጋር በተያያዘ አቶ ጃዋር መሐመድን ጨምሮ ሌሎች 35 ሰዎች በቁጥጥር መዋላቸውን የፌደራልና እና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽኖች አስታወቀው ነበር። ፖሊስ ጨምሮም ግለሰቦቹ በተያዙበት ጊዜ የጃዋር መሐመድ ጠባቂዎች ይዘውት የነበረው የጦር መሳሪያዎች እና መገናኛ ሬዲዮችንም መያዙንም ገልጿል። አቶ ጃዋር መሐመድና አቶ በቀለ ገርባ የተቃዋሚው የኦሮሞ ፌደራሊስት ፓርቲ (ኦፌኮ) አባላት ሲሆኑ ፓርቲው የአባሎቹ መታሰር እንዳሳሰበው ትላንት ለቢቢሲ ገልጾ ነበር። የሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በነበሩት ሁለት ቀናት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በተከሰተ ግጭት ቢያንስ ከ70 በላይ ሰዎች መሞታቸውን የክልሉ የኮምዩኒኬሽን ኃላፊ ለቢቢሲ ገልጸዋል። በዋና ከተማዋ አዲስ አበባም ሁለት የጸጥታ ኃይል አባላትን ጨምሮ የ10 ሰዎች ህይወት ማለፉን የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቋል።
news-45662600
https://www.bbc.com/amharic/news-45662600
የ7 ዓመቷ ታዳጊ ሬስቶራንት ውስጥ መደፈሯ ደቡብ አፍሪቃውያንን አስቆጥቷል
ደቡብ አፍሪቃውያን አንዲት የሰባት ዓመት ታዳጊ ሬስቶራንት ውስጥ ተደፍራለች መባሉን ተከትሎ ቁጣቸውን በመግለፅ ላይ ናቸው።
በአስገድዶ መድፈር የተጠረጠረው የ20 ዓመት ግለሰብ ወደ ሴቶች መፀዳጃ ቤት ተከትሏት በመግባት ልጅቱን ወደ ወንዶች መፀዳጃ ቤት ይዟት በመግባት ደፍሯታል ተብሏል። ተጠርጣሪው ወንጀሉ ከተፈፀመበት ቦታ ተይዞ በአስገድዶ መድፈር እና አደንዛዥ ዕፅ ይዞ በመገኘት ተከሷል። ደቡብ አፍሪቃ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል በከፍተኛ ሁኔታ ከሚከሰትባቸው ሃገራት መካከል ትመደባለች። • የታክሲ ሾፌሮች ላይ በተፈፀመ ጥቃት ሕይወት አለፈ • አዳኞቹ በአንበሳ ተበሉ የሃገሪቱ ፖሊስ ከመጋቢት በፊት በነበሩ 12 ወራት ብቻ ከ40 ሺህ በላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎችን መመዝገቡን አስታውቋል። ይህ ማለት በቀን ከ110 በላይ የአስገድዶ መድፈር አደጋዎች በደቡብ አፍሪቃ ይከሰታሉ ሲል 'አፍሪቃ ቼክ' የተሰኘ መሥሪያ ቤት ያትታል። በርከታ ደቡብ አፍሪቃውያን የታዳጊዋን ተገዶ መደፈር ተከትሎ ልጆቻችን አደጋ ላይ ናቸው ሲሉ ቁጣቸውን እየገለፁ ነው። ዕለተ ቅዳሜ ፕሪቶሪያ በተሰኘችው የሃገሪቱ ከተማ በሚገኝ አንድ መመገቢያ ሥፍራ የተከሰተው ይህ ድርጊት ጉዳዩ ወዴት እየሄደ ነው በሚል ብዙዎች እንዲጠይቁ አስገድዷል። የቢቢሲው ፑምዛ ፊህላኒነ ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ዘወትር ማለዳ ከሚሰሙ ዜናዎች መካከል አስገድዶ መድፈር አንዱ ነው ሲል ሁኔታውን ያስረዳል። ከታዳጊዋ መደፈር ሌላ ዶክተር ነኝ በማለት የ17 ዓመቷን አራስ የደፈረው ግለሰብ ሌላኛው መነጋገሪያ ሆኗል። ቁጥራቸው እጅግ የላቀ ደቡብ አፍሪካውያን ፌስቡክና ትዊተር ወደመሳሰሉ ማህበራዊ ድር አምባዎች በመዝለቅ ሃዘናቸውንና ስጋታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ። • 6 ሚሊዮን ብር፡ በማንዴላ እሥር ቤት ለማደር
news-54821423
https://www.bbc.com/amharic/news-54821423
የእስራኤል እና የአረብ አገራት እርቅ የጦር መሣሪያ ገበያውን ይለውጣል?
ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለመካከለኛው ምሥራቅ ፀሐይ ወጣ ሲሉ ተደምጠዋል።
እስራኤል ከሦስት የአረብ አገራት ጋር የሰላም ስምምነት ለማድረግ ወስናለች። ይህ ታሪካዊ ውሳኔ በርካታ ጉዳዮች ላይ ለውጥ ያመጣል። እስራኤል መጀመሪያ ላይ ሰላም ያወረደችው ከተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ጋር ነው። አገሪቱ ከአሜሪካ ተዋጊ ጀቶች ለመግዛት በዝግጅት ላይ ነበረች። የቀጠናው ዘመነኛ የጦር መሣሪያ ባለቤት የሆነችው እስራኤል የተሻለ መሣሪያ ልታቀርብ ትችላለች። . የአረብ አገራት እስራኤልን ኮነኑ . እስራኤልና ባህሬን ስምምነት ላይ ደረሱ . እስራኤል እና አረብ ኤሜሬቶች ታሪካዊ ከተባለለት ስምምነት ደረሱ የቀጠናው አገሮች መሣሪያ ከእስራኤል መግዛት ከጀመሩ፤ ኢራን እንደምትጎዳ የምታምነው አሜሪካ ተጠቃሚ ትሆናለች ማለት ነው። አሜሪካ ኢራንን ከተቀረው ዓለም የመነጠል ግብ አላት። የጦር መሣሪያ ሽያጭ ኤፍ-35 ላይትኒንግ በአሜሪካ መከላከያ የተሠራ የጦር አውሮፕላን ነው። በመላው ዓለም ካሉ መሣሪያዎች የላቀ ቦታ ይሰጠዋል። የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ይህን መሣሪያ ለመግዛት ለስድስት ዓመታት ጠብቃለች። ከተሳካላት መሣሪያው ያላት የመጀመሪያዋ የአረብ አገር ትሆናለች በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኝ ተቋም ውስጥ የሚሠሩት ጀስቲን ብሮንክ፤ “ኤፍ-35 በሚቀጥሉት 20 ዓመታት እስካሁን በአየር ኃይል ታሪክ ያልታየ መሣሪያ ይሆናል። የመሣሪያው ባለቤት መሆን ያስከብራል” ይላሉ። ባለፈው ሳምንት ትራምፕ 50 ኤፍ-35፣ በ10.4 ቢሊዮን ዶላር ለዩናይትድ አረብ ኤምሬቶች የመሸጥ እቅድ እንዳላቸው ለምክር ቤት መግለጻቸውን የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ለእስራኤል በቀጠናው አገሮች እውቅና ማግኘት ታሪካዊ ነው። ኤምሬቶች ደግሞ ለምጣኔ ሀብት እድገትና በቀጠናው ኃያል ለመሆን ይረዳታል። በሌላ በኩል የአረቡ አገራትን ውሳኔ ፍልስጤም “ክህደት ነው” ብላለች። ፍልስጤም ራሷን የቻለች አገር መሆኗን በተመለከተ የአረቡ አገራትን ድጋፍ ትፈልጋለች። ኤምሬቶች አሜሪካ ሠራሹን ኤምኪው-9 ሰው አልባ አውሮፕላን ለመግዛት ለዓመታት ሞክራለች። ነገር ግን የጦር መሣሪያ የውጪ ንግድን በተመለከተ የወጣው ስምምነት አግዷት ቆይቷል። የቻይናን የሰው አልባ አውሮፕላን ሽያጭ መቀልበስ የሚፈልጉት ትራምፕ መሣሪያውን የሚሸጡበት መንገድ ሲያፈላልጉ ነበር። የእስራኤል መሪዎች ጥያቄ በእስራኤል አስተዳደር ካሉ ጥቂቱ ለአረብ ኤምሬቶች ኤፍ-35 መሸጡን አይደግፉም። እስራኤል በቀጠናው ያላትን ወታደራዊ የበላይነት ያሳጣታል ብለው ይሰጋሉ። በአሜሪካ ሕግ መሠረት ለመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች የሚሸጥ መሣሪያ እስራኤል በቀጠናው ያላትን ስፍራ መገዳደር የለበትም። እስራኤል የቀጠናው ብቸኛ የኤፍ-35 ባለቤት የሆነችውም በዚህ መርህ መሠረት ነው። የእስራኤል አየር ኃይል እንደ ጎርጎሮሳውያኑ 2018 ላይ ኤፍ-35ን ለውጊያ የተጠቀመ የመጀመሪያ ሠራዊት መሆኑን ገልጿል። ይህም በሶርያ ላይ የተሰነዘረ ጥቃት ነው ሊሆን የሚችለው። የእስራኤል ኤፍ-35 በሊባኖስ መዲና ቤሩት ሰማይ ሲበር የሚያሳይ ፎቶ ውዝግብ አስነስቶ ነበር። ከዛም የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ኤፍ-35 ለዩናይትድ አረብ ኤምሬቶች እንዲሸጥ በሚስጥር መስማማታቸውን የአሜሪካ መገናኛ ብዙሀን ዘገቡ። የጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ ዘገባውን አጣጥሏል። የኔታንያሁ ተቀናቃኙ የመከላከያ ሚንስትር ቤኒ ጋንዝ ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ዋሽንግተን አቅንተው ነበር። እስራኤል ቪ-22፣ ኤፍ-15 ተዋጊ ጀት እንዲሁም ሌሎች እንዲሸጡላት የሚፈልጓቸውን መሣሪያዎች ዝርዝር ይዘው መጓዛቸው ተዘግቧል። “ለገልፍ አገሮች መሣሪያ መሸጥ ድርጊታቸውን መደገፍ ነው” ዋሽንግተን ውስጥ በዓለም አቀፍ ግንኙነት ዙርያ የሚሠሩት ዊልያም ሀርተግ፤ “አሜሪካ በመካከለኛው ምሥራቅ የጦር መሣሪያ ንግድ ከራሷ ጋር እየተሽቀዳደመች ነው” ይላሉ። ሳዑዲ አረቢያ፣ ባህሬን እና ሱዳን ከእስራኤል ጋር ሰላም ካወረዱ ከአሜሪካ የጦር መሣሪያ የመግዛት እድላቸው ይሰፋል። “ለገልፍ አገሮች መሣሪያ መሸጥ የሰብዓዊ መብት ጥሰታቸውን ጨምሮ ሌላም ድርጊታቸውን መደገፍ ነው” ሲሉ ያስረዳሉ። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የኢራን ጉዳይ እንደሚያሳስባቸውም ይናገራሉ። ኢራን በሁቲ አማጽያን እና በመንግሥት ደጋፊዎች እንዲሁም ሳዑዲ በምትደግፈው ኃይል ግጭት እየተናጠች ነው። ሰንአ ውስጥ የሰብዓዊ መብት ድርጅት ያቋቋሙት ራድያ አልሙታክወል “በቀጠናው መሣሪያ መሸጥ ድርጊቱን ግፉበት ማለት ነው። ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት ያደረሱ ከ500 በላይ የአየር ጥቃቶች መዝግበናል። አብዛኞቹ መሣሪያዎች የተሠሩት አሜሪካ የተቀሩት ደግሞ ዩኬ እና ጣልያን ሠራሽ ናቸው” ይላሉ። የወታደራዊ ጉዳይ ተንታኙ ጀስቲን ብሮንክ እንደሚናገሩት፤ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፤ የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን የመን ላይ መጠቀም ትፈልጋለች። የመንን የሰው አልባ አውሮፕላን ውጊያ “መሞከሪያ” እንዳደጓትም ያስረዳሉ። ኢራንን የሚደግፉት ወገኖች ለዩናይትድ አረብ ኤምሬቶች ኤፍ-35 ከተሸጠ ሌሎች የአረብ አገሮችም ሊከተሉ ይችላሉ። አሜሪካ የጦር መሣሪያዎቹን ለገልፍ አገሮች በመሸጥ ገበያዋን የማሳደግ እቅድ አላት። ትራምፕ የአስቸኳይ ጊዜ ድንጋጌን ተጠቅመው ከምክር ቤቱ የሚገጥማቸውን ተቃውሞ በማለፍ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር የሚያወጡ መሣሪያዎችን ለሳዑዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና ጆርዳን ሸጠዋል። በእስራኤል የአሜሪካ አምባሳደር ዴቪድ ፊደርማን ኤምሬቶች የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ኤፍ-35 ሊያገኙ ይችላሉ የሚለውን ስጋት አጣጥለው ነበር። እስራኤል ወታደራዊ የበላይነቷን እንደማታጣ እና እንዲያው ጠንካራ አጋሮች በቀጠናው ልታገኝ እንደምትችል ለጀሩሳሌም ፖስት ተናግረው ነበር። ተንታኞች የኢራን አየር ኃይል እድሜው ቢገፋም አቅሙ እያደገ እንደመጣ ይናገራሉ። ባለፉት አሠርታት ቴህራን የባለስቲክ ሚሳኤልን ጨምሮ በተለያየ ዘርፍ ኃይሏን ስታጠናክር ቆይታለች ሲሉ የአሜሪካ አየር ኃይሉ ሌ/ኮለኔል ክርስትን ማክቪን ይናገራሉ። የሰላም ስምምነቱ ኤምሬቶች ኤፍ-35 የመግዛት ጥያቄያቸውን ያፋጥነዋል? የሚለው ላይ የተለያየ ሐሳብ አለ። ምክር ቤቱ ሊያጓትተው ወይም ሊገታው ይችላል። ጆ ባይደን ፕሬዘዳንት ሆነው ከተመረጡ ነገሮች ሊለዋወጡም ይችላሉ።
news-52147214
https://www.bbc.com/amharic/news-52147214
ኮሮናቫይረስ፡ እስካሁን የኮሮናቫይረስ ያልደረሰባቸው አገራት እነማን ናቸው?
የዛሬ ሦስት ወር አካባቢ ኮሮናቫይረስ የሚባል ነገር በቻይና ተገኘ ተባለ። አንድም ሰው ከቻይና ውጭ አልተያዘም ነበር ያኔ።
በፓሲፊክ ውቅያኖስ ላይ ያለችው የቱቫሉ ደሴት አንድ ክፍል ከጃንዋሪ 13 ወዲህ ከቻይና ውጭም አለ ተባለ። መጀመርያ በታይላንድ፣ ከዚያም በደቡብ ኮሪያ እንዲሁም በአሜሪካ ተገኘ ተባለ። አሁን አንድ ሚሊዮን ሰዎች በዓለም ዙርያ በወረርሽኙ ተይዘዋል። ከኔፓል እስከ ኒካራጓ፣ ከኢኳዶር እስከ ኢትዮጵያ በሽታው ያልገባበት የለም ማለት ይቻላል፡። የሆስፒታል አልጋዎች ሞልተዋል፤ አገሮች ለደቂቃ አስበውት የማያውቁት የፊት ጭምብል እንኳ አንሷቸዋል። የምር ግን ኮሮናቫይረስ ያልገባበት አገር ይኖር ይሆን? በሚገርም ሁኔታ መልሱ "አዎ" ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል አገራት 193 ናቸው። ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ዕለት ድረስ 19 አገራት ኮሮናቫይረስ የሚባል ነገር በአገራችን አይተንም ሰምተንም አናውቅም ይላሉ። እነዚህን አገራት መዘርዘር ይቻላል። ብዙዎቹ ስማቸው ለጆሮም ለአይንም እንግዳ ነው። ኮሞሮስ፣ ኪሪባቲ፣ ሌሶቶ፣ የማርሻል ደሴቶች፣ ሜክሮኒሺያ፣ ናዉሩ፣ ሰሜን ኮሪያ፣ ፓላዉ፣ ሳሞዋ፣ ሳዎ ቶሜና ፕሪንሲፔ፣ ሶሎሞን ደሴቶች፣ ደቡብ ሱዳን፣ ታጃኪስታን፣ ቶንጋ፣ ቱርክሜኒስታን፣ ቱቫሉ፣ ቫኑዋቱና የመን ናቸው። አንዳንድ ተመራማሪዎች ምናልባት እነዚህ አገራት በቂ ፍተሻ አላደረጉ ይሆን? ሲሉ ይጠረጥራሉ። ወይም ደግሞ ሙልጭ አድርገው እየካዱ ይሆን? ወይም ደግሞ ሪፖርት ተደርጎ አያውቅባቸውም ማለት ነው። የሚገርመው ብዙዎቹ አገሮች ትንንሽ ደሴቶች መሆናቸው ነው። እነዚህ አገሮች ደግሞ እምብዛምም የውጭ አገር ጎብኚ የማይሄድባቸው አይደሉም። እንደተባበሩት መንግሥታት መረጃ ከሆነ በዓለም በጎብኚ ቁጥር የመጨረሻዎቹ 10 አገራት (ማለትም በዓመት ጥቂት ሰዎች ብቻ የሚጎበኟቸው አገራት) በኮሮናቫይረስ አልተያዙም። በቂ ርቀትን መጠበቅ ኮሮናቫይረስን ለመከላከል አንዱ መንገድ ነው ሲባል ሰምተናል። እነዚህ ደሴቶች በአፈጣጠራቸውም ነጠል ብለው ነው የተወለዱት። ለምሳሌ በፓሲፊክ ውቅያኖስ የሚገኘው ናዉሩ ደሴት በአቅራቢያው ከሚገኝ አገር በ320 ኪሎ ሜትር ይርቃል። ባናባ ደሴት ነው ለናዉሩ ቅርቡ ጎረቤት አገር። ናውሩ ደሴት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል አገራት ተርታ ከሞናኮ ቀጥሎ ሁለተኛው ትንሹ ደሴት ሲሆን ጠቅላላ ሕዝቡ ከ10ሺህ አይበልጥም። ድሃዋ ናውሩ የኮሮናቫይረስ ከተከሰተባት ከባድ አደጋ እንደሚሆን ተሰግቷል በዓለም ጎብኚዎች ድርሽ ከማይሉባቸው አገራት አንዱ ነው ናዉሩ። አንድ በአስጎብኚነት የተሰማራ መኮንን በዚያች ደሴት ባለፈው ዓመት የጎብኚዎች ቁጥር 160 ብቻ ነበር ብሏል፤ ይህ ቁጥር በሌላ ይፋዊ ጥናት ባይደገፍም ቅሉ። ታዲያ እንዲህ ያለ አገር ራሱን በተፈጥሮ ቀድሞውኑ አርቆ ሳለ ምን መጠንቀቅ ያሻዋል ይባል ይሆናል። ሆኖም ነገሩ ወዲህ ነው። በዚህ ደሴት አይበለውና የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ቢገባ ጉድ ነው የሚፈላው። አንድ ሆስፒታል ነው ያላቸው፣ አንድም የመተንፈሻ መርጃ መሣሪያ ቬንትሌተር ላይኖራቸው ይችላል። የነርሶች ቁጥር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። ስለዚህ ኮሮናቫይረስ ምናልባት ብዙ ጥፋት ሊያደርስ ይችላል ማለት ነው። የሆነስ ሆነና ይህቺ ናውሩ ደሴት ራሷን እንዴት ጠበቀች? ከአንድ ወር በፊት ከቻይና፣ ከደቡብ ኮሪያና ከጣሊያን ማንም አይምጣብኝ አለች። ድሮም የሚመጣ አልነበረም ለነገሩ። በመጋቢት ወር አጋማሽ ደግሞ ናውሩ ወደ ፊጂ ደሴት ወደ ኪሪባቲና ማርሻል ደሴቶች መብረር አቁሚያለሁ አለች። ወደ ጎረቤት ብሪስበን ብቻ በ15 ቀን አንድ ጊዜ እበራለሁ አለች። ከዚያ በኋላም ከአውስትራሊያ ተመላሽ የሆኑ ሁሉ የ14 ቀናት ራስን የማግለል የውዴታ ግዴታ መመሪያን አወጣች። እነዚህ ናዉሩን የመሰሉ ትንንሽ ደሴቶች እንኳንም ኮሮናቫይረስ በራቸውን አላንኳኳ ይላሉ ዶ/ር ኮሊን። ዶ/ር ኮሊን የቀድሞው የዓለም ጤና ድርጅት ባልደረባ ናቸው። "እነዚህ አገሮች አንዳችም ሁነኛ የጤና ጥበቃ መዋቅር የላቸውም። ኮሮናቫይረስ ቢገባ ይንኮታኮታሉ፤ ቬንትሌተር እንኳ የላቸውም"› ይላሉ ዶክተሩ። በዚያ ላይ በእነዚህ ደሴቶች የሚኖሩ አብዛኞቹ ዜጎች ስኳር፣ ደም ግፊትና ሌሎች ተዛማጅ በሽታዎች አሉባቸው። ኮሮናቫይረስ በሽታ ያለበትን ሰው ምን እንደሚያደርግ ይታወቃል። እንደ ዶ/ር ኮሊን ገለጻ እነዚህ ትንንሽ አገራት ሰው ሲታመምባቸው ወደ ውጭ አገር ነው የሚልኩት። አሁን ደግሞ ውጭ አገራት በራቸውን ከርችመዋል። በሽታው በእነዚህ ደሴቶች ገባ ማለት ሕዝባቸውን ጨረሰው እንደማለት ነው ይላሉ። ስለዚህ የእነዚህ ደሴቶች ብቸኛ ተስፋ ተፈጥሮ ፈንጠር አድርጎ ፈጥሯቸዋልና ፈንጠር ብለው በራቸውን ከርችመው መኖር ብቻ ነው። የናዉሩ ደሴት ፕሬዝዳንት ሊዮኔል አንጊሚያ አጥባቂ ሃይማኖተኛ ናቸው። "ስለበሽታው ስሰማ ወደ እግዚያብሔር እጄን ዘረጋሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስን አቀበለኝ። ወደ ደረቴ ጥብቅ አድርጌ ያዝኩት፡፡ መዝሙር ዳዊት አንቀጽ 147፣ ምን ይላል። "ጽዮንም ሆይ፥ ለአምላክሽ እልል በይ፤ የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቷልና፥ ልጆችንም በውስጥሽ ባርኳልና። በወሰንሽም ሰላምን አደረገ" ፕሬዝዳንቱ ቀጠሉ፤ "በየጊዜው የዓለምን ካርታ ከፍቼ የበሽታውን ስርጭት ስመለከት አገሩ ምድሩ ሁሉ በፈንጣጣ የተያዘ ይመስል ቀይ በቀይ ሆኗል። ስለዚህ እኛ ናዉሩዎች ለተቀረው ዓለም መጸለይ እንዳለብን ይሰማናል። ጸሎታችን እንደሚረዳችሁም ተስፋን እናደርጋለን።" የኮሮናቫይረስን ሽሽት ሻንጣችንን እንሸክፍ ይሆን? ወደ ናዉሩ ደሴት!
news-53855435
https://www.bbc.com/amharic/news-53855435
ሊቢያ: ግብጽ ስለምን ጄነራል ሃፍታርን ለመደገፍ ጦሯን ወደ ሊቢያ ላከች?
እስቲ የጎረቤትዎ ቤት በእሳት እየነደደ ማንም እሳቱን ለማጥፋት የሚመጣ ሰው አልያም እሳት አጥፊ ቡድን ባይመጣና እሳቱ ወደ እርስዎ ቤትም ተዛምቶ ቤተሰብዎን ሲያቃጥል ያስቡት።
ግብጽ በሊቢያ እየሆነ ያለውን ነገር ከዚህ አይነት እሳት ለይታ አታየውም። ምክንያቱም የቀድሞው የሊቢያ መሪ ሙአመር ጋዳፊና በእርሳቸው የሚመራው መንግስታቸው በአውሮፓውያኑ 2011 ካበቃላቸው በኋላ አገሪቱ እንዳልነበረች ሆናለች። በሊቢያ የሚታየው አለመረጋጋትና የሰላም እጦት ደግሞ ወደ ግብጽም እንዳይጋባ ስጋት አለ። ሊቢያ እስካሁን ድረስ በአግባቡ ስራቸውን የሚሰሩ መስሪያ ቤቶችም ሆነ ማንኛውም አይነት የደህንነት እና ወታደራዊ አካላት የሌሏት ሲሆን 1100 ኪሎሜትር የሚሆነው ድንበሯም እየተጠበቀ አይደለም። በተጨማሪም አገሪቱ የጦር መሳሪያ ማከማቻ እየሆነች ነው። ሊቢያ ችግር ውስጥ መግባት የጀመረችው ዜጎቿ እንዴት ወደፊት መጓዝ እንዳለባቸው መስማማት ሲያቅታቸውና አክራሪ ታጣቂዎች እስላማዊ ሊቢያን እንፈጥራለን ብለው መንቀሳቀስ ሲጀምሩ ነው። በግብጽ 2013 ላይ እስላማዊው መሪ ፕሬዝደንት ሞሀመድ ሙርሲን ከስልጣን ከተባረሩ ወዲህ አገሪቱ የነዚህ ታጣቂዎች የመጀመሪያ ኢላማ ሆናለች። በተባበሩት መንግስታት አደራዳሪነት በሊቢያ ጊዜያዊ መንግስት ለመመስረትና ታጣቂዎችን ትጥቅ ለማስፈታት በተደጋጋሚ ተሞክሯል። በሊቢያ በእስላማዊ ፅንፈኛ አክራሪዎች በተሞላው ምዕራባዊ ክፍል እና ጸረ ኢስላማዊ አቋም ያላቸው በምስራቅ በኩል ለስልጣን እየተሻኮቱ ሲሆን ግብጽም በዚህ ሰአት ጎራዋን እየለየች ነው። የሙስሊም ወንድማማቾች ቡድንን አሸባሪ በማለት የፈረጀችው ግብጽ በሊቢያ ኢስላማዊ አቀንቃኞች ላይ ጦርነት ያወጁት ጀነራል ካሊፋ ሀፍታርን መደገፏ ሳይታለም የተፈታ ነው። ጀነራል ካሊፋ በስተምዕራብ በኩል ድጋፍ ያላቸው ታጣቂዎችን በመዋጋት ቤንጋዚን እና ሌሎች ትልልቅ ከተማዎችን እየተቆጣጠሩ ይገኛሉ። ላለፉት ስድስት ዓመታት ደግሞ የግብጽ ዋናኛ አላማ በሊቢያ ያለውን እሳት በሊቢያ እንዲቆይና ወደ ድንበሯ እንዳይገባ ማድረግ ነው። ለዚህም ነው ጀነራል ካሊፋ ሀፍታርን መደገፍ የመረጠችው። ነገርግን ልክ በአካባቢው ትልቅ ተሰሚነትና ኃይል ያላት ቱርክ በሊቢያ የሚገኙ ኢስላማዊ ቡድኖችን መደገፍ ስትጀምር ነገሮች ወደ ሌላ አቅጣጫ መሄድ ጀምረዋል። የጀነራል ካሊፋ ሀፍታርን ግስጋሴ ለማስቆምና ዋና ከተማዋ ትሪፖሊ በጀነራሉ ቁጥጥር ስር እንዳትወድቅ በማሰብ ቱርክ ቴክኒካዊና ወታደራዊ ድጋፍ ማድረግ ጀምራለች። ከቱርክ በተደረገለት ድጋፍ በመነሳሳት ትሪፖሊ የሚገኘው አስተዳደር ወደ ጦርነት በመግባት ሌሎች የአገሪቱ ክፍሎችን ከጀራል ካሊፋ ሀፍታር ለማስለቀቅ ቆርጦ መነሳቱን አስታውቋል። ቱርክ በሺዎች የሚቆጠሩ የሶሪያ ወታደሮችን እና ጂሃዳዊ ታጣቂዎችን ወደ ትሪፖሊ በማስገባት በጦርነቱ እንዲረዱ ማድረጓ ግብጽ ዝም ብላ ነገሮችን እንዳትመለከት አስገድዷታል። ሰኔ ወር ላይ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ በርካቶችን ያስደነቀ የግብጽ ወታደራዊ ትዕይንት ከታደሙ በኋላ አንድ ነግ ብለዋል። ''የግብጽና የሊቢያን ታሪካዊ ግንኙነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ግብጽ በሊቢያ እየሆነ ባለው ነገር ላይ ጣልቃ እንድትገባ በቂ ምክንያት አላት። ከውጭ አገራት የሚመጡ ተጽህኖዎችን በመቋቋም አገራዊ ጥቅሟንም ማስጠበቅ ግድ ይላታል'' ሲሉ ተደምጠዋል። በሜዲትራኒያን ባህር እና ሰርጥ በኩል ማንኛውም አይነት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ለግብጽ ሉአላዊነቷን እንደ መጣስ ነው የሚቆጠረው። ለትሪፖሊ ታማኝ የሆኑ ሚሊሻዎች በዚህ በኩል ለማቋረጥ የሚሞክሩ ከሆነ ግብጽ ብሄራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ እንደምትንቀሳቀስና ቀይ መስመር እንደሆነ ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል። ፕሬዝዳንቱ ይህንን ካሉ ከጥቂት ቀናት በኋላ ደግሞ የግብጽ ፓርላማ ሃሳባቸውን ሙሉ በሙሉ ደግፎታል። የአገሪቱ መከላከያ ኃይሎች ዋና አዛዥ የሆኑት ፕሬዝዳንት አብዱልፋታህ አልሲሲ አስፈላጊ ነው ብለው ባመኑት አካባቢ ወታደሮችን እንዲኣዘምቱም ጭምር ፈቃድ አግኝተዋል። መቀመጫውን ትሪፖሊ ያደረገው አስተዳደር ደግሞ ፕሬዝደንቱ ባስተላለፉት ወታደራዊ ማስፈራራት ደስተኛ እንዳልሆነና ጉዳዩን 'ጦርነት እንደማወጅ' እንደሚመለከው አስታውቋል። የግብጽ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ደግሞ ፕሬዝዳንታቸውን በማሞካሸት የመከላከያ ሰረዊቱ ከዓለም ጠንካራ ከሚባሉት እንደሆነ በመግለጽ አድናቆታቸውን ገልጸዋል። ሌላው ቀርቶ የግብጽን ወታደራዊ ብቃት ከቱርክ ጋር በማነጻጸርም የግብጽን ጦር ሲያሞካሹ ነበር። ነገር ግን አንዳንድ የአካባቢው ተንታኞችና ፖለቲከኞች ግብጽ ብሄራዊ ጥቅሜን አስጠብቃለው በማለት በምታደርገው እንቅስቃሴ መሀል በሊቢያ እሳት ውስጥ ገብታ ያልታሰበ ጉዳትና ኪሳራ እንዳያጋጥማት እያስጠነቀቁ ይገኛሉ። በተጨማሪም ተንንታኞቹ የግብጽ ወታደሮች ከእስራኤል ጋር ከተዋጉበት የአውሮፓውያኑ 1973 ጦርነት ወዲህ እዚህ ግባ የሚባል የጦርነት ልምድ አለመኖሩ ነገሮችን ከባድ ሊያደርግባቸው እንደሚችል ጠቁመዋል። ስለዚህ ግብጽ ያሏት ሁለት አማራጮች አሉ። አንደኛው ጁፍራ እና ሰርጥ ላይ ሊፈጸሙ የሚችሉ ጥቃቶችን ለመከላከል ቀደም ብላ እርምጃ መውሰድ ሲሆን ይህ እርምጃ ግን ጦርነት ሊቀሰቅስ የሚችልበት እድሉ ከፍተኛ እንደሆነ ይታመናል። ሁለተኛው አማራጭ ማንኛውም አይነት ቡድን ግብጽ ያስቀመጠችውን ቀይ መስመር እስከሚያልፍ ድረስ መጠበቅ ነው። ይሄኛውም አማራጭ ቢሆን ግን ከዘገየ በኋላ ሊወሰድ የሚችል እርምጃ በመሆኑ ለራሷ ግብጽና ሊቢያ ላሉ ወዳጆቿ አስጊ ነው። ወጣም ወረደ ግብጽ ሊቢያን በተመለከተ ግራ የሚያጋባ አጣብቂኝ ውስጥ የወደቀች ትመስላለች።
news-56742302
https://www.bbc.com/amharic/news-56742302
የ20 አመቱ ጥቁር አሜሪካዊ ግድያን ተከትሎ የፖሊስ ኃላፊው ከስራቸው ለቀቁ
ዳውንቴ ራይት የተባለ የ20 አመት ወጣት በሚኒያፖሊስ ከተማ ከፖሊስ በተተኮሰበት ጥይት መገደሉን ተከትሎ የከተማዋ የፖሊስ ኃላፊ ከስራቸው ለቀዋል።
ከኃላፊው በተጨማሪ የተኮሰችበት ፖሊስም እንደለቀቀች ተዘግቧል። የፖሊስ ኃላፊ ቲም ጋኖንና የተኮሰችበት ፖሊስ ኪም ፖተር ከብሩክሊን ሴንተር ኃይል ስራቸው የለቀቁት ዳውንቴ መገደሉን ተከትሎ ለሁለት ቀናት ያህል ከፍተኛ አለመረጋጋትና ሁከት በመነሳቱ ነው። ፖሊሷ ዳውንቴን ጥይት የተኮሰችበት በስህተት እንደሆነና ዋነኛ አላማዋ ማደንዘዣ መተኮስ እንደነበር ተናግራለች። ግድያው የተፈፀመው ከሚኒያፖሊስ ወጣ ብላ በምትገኝ አካባቢ ሲሆን በባለፈው አመት ጆርጅ ፍሎይድ አንገቱን መሬት አጣብቆ የገደለው ፖሊስ የፍርድ ሂደትም የሚታይበት አካባቢ ነው። በያዝነው ሳምንት ማክሰኞ የብሩክሊን ማዕከል ከንቲባ ማይክ ኤሊየት ለሪፖርተሮች እንደተናገሩት ስራቸውን በለቀቁት የፖሊስ ኃላፊ ቦታ ለ19 አመት በሰራዊቱ ያገለገሉትን ቶኒ ግሩይንግን መሾማቸውን ነው። በሳምንቱ መጀመሪያ ሰኞ ከስራቸው የለቀቁት የፖሊስ ኃላፊ ጋኖን ፖሊሷ ዳውንቴን የተኮሰችበት "በስህተት እንደሆነና" ሽጉጧንና የማደንዘዣ መሳሪያዋን በማሳሷቷ እንደሆነ ተናግረው ነበር። "ኃላፊው ከስራቸው መልቀቃቸው መልካም ነገር ነው" ያሉት ከንቲባው ዳውንቴ ላይ የተኮሰችበት ፖሊስ እንዲሁ ከስራ መልቀቋ በተወሰነ መልኩ "በማህበረሰቡ መረጋጋትን እንደሚያመጣ ተስፋ አደርጋለሁ" ብለዋል። ዳውንቴ ላይ የተኮሰችበት ፖሊስ እንዲሁም የፖሊስ ኃላፊው ከስራቸው መልቀቃቸውን ዜና በሚኒያፖሊስ ሳልቬሽን አርሚ የምግብ ማመላለሻ አስተባባሪ ሆና ለምትሰራው አምበር ያንግ የተቀላቀለ ስሜትን ፈጥሮባታል። ምንም እንኳን ዜናው ቢያስደስታትም ከዚህ ፈጠን ብሎ ሊደረግ በተገባ ነበር ብላ ታምናለች። ብሩክሊን ሴንተር ፖሊስ ቢሮ ውጭ ቆማ በፖሊሶቹ ድርጊት ምን ያህል እንደተንገበገበችና እንደተቆጨች ትናገራለች። "ከስራዋ መባረር ነበረባት። ተኩሳ የገደለችው ፖሊስ እስከምትለቅ ሊጠበቅ አይገባም ነበር" ትላለች። የፖሊስ ኃላፊውን አስመልክቶም "ለማህበረሰቡ ምንም ግድ የሚሰጠው ሰው አልነበረም። እንኳን ተሰናበተ" በማለት ታስረዳለች። ዝናብና በረዶ እየደበደባቸው ተቃውሟቸውን ለማሰማት ከመጡት ውስጥ አንዷ ነች አምበር።
news-48166894
https://www.bbc.com/amharic/news-48166894
አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ፡ ትምህርት ቤት ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ አስቀመጠ
አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ በአማራ ክልል፤ በዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ፃግብጅ ወረዳ የዳስ ትምህርት ቤት በመገኘት ትምህርት ቤት ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ማስቀመጡን የዋግ ኸምራ አስተዳደር የትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሽታው አዳነ ለቢቢሲ ገለፁ።
• ወላጆች ለልጆቻቸው የሚመኟቸው ኢትዮጵያዊ መምህር በዳስ ትምህርት ቤቱ 159 ተማሪዎች የሚማሩ ሲሆን የሚገነባው ትምህርት ቤትም በአትሌት ሻለቃ ኃይለ ገ/ሥላሴ ሥም እንደተሰየመም ገልፀውልናል። የሚገነባው ትምህርት ቤት በቀጣይ 5 ወራት እንደሚጠናቀቅም ይጠበቃል። አትሌት ኃይለ ገ/ሥላሴ የዳስ ትምህርት ቤቶችን በቴሌቪዥን ተመልክቶ እንዲህ ዓይነት ትምህርት ቤት በዚህ ዘመን መኖር የለበትም የሚል ሃሳብ እንዳደረበት በመገናኛ ብዙሃን መግለፁ የሚታወስ ሲሆን ቦታዎቹን ለመጎብኘት ትናንት ወደ ሥፍራው አቅንቷል። በአስተዳደሩ በርካታ የዳስ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን የሚናገሩት ኃላፊው የመንግስት ትኩረት አናሳ መሆኑ እና የትምህርት መሠረተ ልማቶች ሳይሟሉ ትምህርት ቤት መክፈት ለዳስ ትምህርት ቤቶች መበራከት አንዱ ምክንያት እንደሆነ ይናገራሉ። "ችግሮቹ ተደጋግመው ቢነሱም ትኩረት የሰጠው የለም፤ እንዲያውም ትንሽ እንቅስቃሴ የተጀመረውና በማህበራዊ ሚዲያዎች መረጃውን በመልቀቅ ትኩረት ማግኘት የቻሉት ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ነው" ይላሉ። በእነዚህ የዳስ ትምህርት ቤቶች ዝናብ በሚዘንብበት ጊዜ ትምህርት የሚቋረጥ ሲሆን ፀሐይን ግን በቅጠል በመሸፈን ለመከላከል ጥረት እንደሚደረግ ተናግረዋል። "በአስተዳደሩ የሚገነቡት ትምህርት ቤቶች በጣም ጠባብና በውል የማያንቀሳቅሱ ከዳስ ያልተሻሉ ናቸው" የሚሉት ኃላፊው በዋግ ኸምራ ከሚገኙት 264 ትምህርት ቤቶች ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው የትምህርት ጥራት ቁጥጥር መሠረት 154ቱ (85 በመቶው) ከደረጃ በታች መሆናቸውን ይገልፃሉ። • የዘንድሮ ተመራቂዎች እንዴት ሥራ ያገኛሉ? በመደበኛ ትምህርት ቤት 324 የዳስ መማሪያ ክፍሎች ሲኖሩ ህፃናት በእግራቸው ተጉዘው ትምህርት ቤት መድረስ ስለማይችሉ በአቅራቢያቸው የተሰራ 550 የሳተላይት ትምህርት ቤቶችም የዳስ መሆናቸውን አቶ ሽታው ይጠቅሳሉ። በዋግ ኸምራ አስተዳደር በአጠቃላይ 874 የዳስ መማሪያ ክፍሎች የሚገኙ ሲሆን ከ1500 በላይ ተማሪዎች የሚማሩበትም ነው። አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴም ከታላቁ ሩጫ በሚሰበሰብ ገቢ ሁለት ተጨማሪ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባትም ቃል መግባቱንም ኃላፊው አክለዋል።
42914331
https://www.bbc.com/amharic/42914331
ህገወጡ የአረብ አገራት ጉዞ በአዲሱ አዋጅ ይገታል?
በቤት ሰራተኝነት ወደ ተለያዩ አረብ አገራት የሚሄዱ ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚደርሰው የአካል ጉዳት፣ስቃይና እንግልት ለዓመታት የማህበረሰብ ራስ ምታት ነበር።
በአሰሪዎች መደብደብ፣ መደፈር፣የጉልበት ብዝበዛ ፣ክፍያ መከልከልና ሌሎችም አስከፊ ስቃዮች ወደ አረብ አገራት የሄዱ በርካታ ኢትዮጵያዊያን እጣ ነበር። የኢትዮጵያዊያኑን ስቃይ የሚያሳዮ ቪዲዮዎች በማህበራዊ ድረ ገፅ ሲለቀቁ ደግሞ የህብረተሰቡ ቁጣና ቁጭት ያይል ነበር። ከአራት ዓመት በፊት ሳውዲ ህገወጥ ያለቻቸውን በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንን ማስወጣትዋን ተከትሎ መንግስት ወደ ተለያዩ አረብ አገራት በቤት ሰራተኝነት የሚደረጉ ጉዞዎችን አገደ። ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት ደግሞ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዲሱን የኢትዮጵያ የውጭ አገር ሥራ ስምሪት አዋጅ 923/2008 አፀደቀ። አዋጁ ዜጐች ደህንነታቸውና መብታቸው ተጠብቆና ተረጋግጦ በውጭ አገር በሥራ እንዲሰማሩ የሚያስችሉ ሁኔታዎች መመቻቸትን በሚመለከት ዝርዝር ሁኔታዎችን ያስቀምጣል፡፡ አዋጁ ምን ይላል? አዋጁ ማን መሄድ ይችላል? ምን ዓይነት ሥልጠናና መሥፈርቶችን አሟልቶ? የኤጀንሲዎችና የአሠሪዎች ግዴታና ኃላፊነትስ ምን ድረስ ነው? የሚሉ ጉዳዮችን ይዘረዝራል፡፡ አዋጁ ከሚያስቀምጣቸው አንኳር ጉዳዮች መካከል ኤጀንሲዎች ወደ ሥራ ለመግባት በግል ከሆነ የአንድ ሚሊዮን ብር፣ በቡድን ከሆነ ደግሞ አምስት ሚሊዮን ብር ካፒታል እንዲኖራቸው በተጨማሪም መቶ ሺሕ ዶላርም ተቀማጭ እንዲያደርጉ የሚሉት ይገኙበታል፡፡ በተጨማሪም መድህን እንደሚቋቋምና ኤጀንሲዎችም በሚልኩት ሰው ብዛት መሠረት ለመድህኑ እንዲያዋጡ የሚለውም ሌላው ጉዳይ ነው፡፡ አዋጁ ኤጀንሲዎች ላይ የሚያስቀምጠው የገንዘብ መስፈርት ከባድ መሆን ብዙዎቹን ከጨዋታ ውጭ ያደርጋቸዋል የሚል ስጋት ያላቸው አሉ። በሌላ በኩል አዋጁ ለሥራ ወደ ውጭ አገር የሚሄድ ማንኛውም ሠራተኛ ቢያንስ የስምንተኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቀና በብቃት ማረጋገጫ የተመሰከረ የሙያ ስልጠና መውሰድ እንዳለበት ያስቀምጣል። አሰሪዎች የሚያስቀምጡትን መስፈርት ማሟላት እነደሚገባም አዋጁ ያስቀምጣል። ወደ አረብ አገራት በብዛት የሚሄዱት ከገጠሪቱ የአገሪቱ ክፍል የሚመጡና ከሶስት ከአራተኛ ክፍል በላይ ያልገፉ ከመሆናቸው አንፃር መስፈርቱ የመሄድ ፍላጎት ያላቸውን በርካቶች ይገድባል የሚል እምነት ያላቸው አሉ። እገዳው ምን ለውጥ አመጣ? ነገር ግን እገዳው ተጥሎ በነበረባቸው ባለፉት አራት ዓመታት በህገወጥ መንገድ ብዙዎች ወደ ተለያዩ አረብ አገራት ይሄዱ እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ። ጉዞው በሱዳንና በኬንያ በኩል በደላሎች እርዳታ ሲደረግ እንደነበርም፤ በቱሪስት ቪዛ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስተው በሚሄዱባቸው አገራት በሕገወጥ ደላሎችና ኤጀንሲዎች ሥራና የሥራ ፈቃድ አግኝቶ ለመቅረት የሞከሩም በርካታ እንደሆኑ ይነገራል። በአንድ ወቅት በዚህ መንገድ በዱባይ አየር መንገድ በአንድ በረራ ዱባይ ሄደው ለመቅረት የሞከሩ 30 ኢትዮጵያውያን በአየር መንገዱ ኢሚግሬሽን ተይዘው ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸው ለዚህ አንድ ማሳያ ነው። ባለፈው ሳምንት ማብቂያም አንድ የቢቢሲ ጋዜጠኛ በተጠቀሰው መንገድ ወደ ዱባይ ሄደው ሳይሳካላቸው በኬንያ አየር መንገድ ወደ ኢትዮጵያ እየተመለሱ የነበሩ ከአስር በላይ የሚሆኑ ሴቶችን አግኝቶ ነበር። ወ/ሮ ጥሩ ብርሃን ጌትነት በቤት ሰራተኝነት እንጀራ ለማግኘት ወደ ተለያዩ አራብ ሃገራት ሄደው ነገሮች እንዳሰቡት ሳይሆን አእምሯዊና አካላዊ ጉዳት ደርሶባቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያዊያትን የሚያስጠልለውና የሚረዳው ጉድ ሳማሪታን ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ናቸው። መንግስት እግዱን ጥሎ እያለም ብዙዎች በህገወጥ በመንገድ ወደ አረብ አገራት ይሄዱ እንደነበር ይናገራሉ። ባለፈው የአውሮፓውያኑ ዓመት እንኳን ጉድ ሳማሪታን በህገወጥ መንገድ ሄደው ጉዳት ደርሶባቸው የተመለሱ ከ120 በላይ የሚሆኑ ከአረብ አገር ተመላሾችን እንዳስተናገደ ገልፀዋል። "መንግስት እገዳ ቢጥልም የቆመ ነገር የለም።ምናልባት የደላላ ቁጥር ቀንሶ ሊሆን ይችላል እነጂ።"የሚሉት ወ/ሮ ጥሩ ብርሃን ተጎድተው የሚመለሱት ሴቶች በደላላ በሱዳን፣ጅቡቲና የመን ወደ ተለያዩ አረብ አገራት ሄደው የነበሩ እንደሆኑ ያስረዳሉ። እሳቸው እንዳሉት በደላላ በቀጥታ በአውሮፕላንም የሚሄዱ አሉ። መንግስት ቢዘጋውም ጉዞው በብዙ መልኩ ሲደረግ የቆየ ሲሆን በሁሉም ሂደት ውስጥ የደላሎች ተሳትፎ አለ። ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ጉድ ሳማሪታን የሚሄዱት ብዙዎቹ ከቤሩት የሚመለሱ ናቸው።በርካቶቹም በሄዱ ሶስት ወር በማይበልጥ ጊዜ የሚመለሱ እነደሆኑ ከወ/ሮ ጥሩብርሃን ንግግር መረዳት ይቻላል። መስፈርቶቹ ከነባራዊ እውነታ አንፃር እንዴት ይታያሉ? የኢትዮጵያ የውጭ አገር ሥራ ስምሪት አገልግሎት ሰጪ ኤጀንሲዎች አሠሪ ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ መዝገቡ አሰፋ ኤጀንሲዎቹ ላይ ወደ 12 የሚሆኑ መስፈርቶች መቀመጣቸውን ይጠቅሳሉ። አንዳንዶቹ መስፈርቶች ስነምግባር በጎደለው መንገድ የሚሰሩና እንዲሁ ያለዝግጅት ወደ ስራው ዘው ብለው የሚገቡ ኤጀንሲዎችን ለመገደብ ታስበው የወጡ ቢሆንም ከባድና ተፈፃሚነታቸው እንደሚያስቸግር ይናገራሉ አቶ መዝገቡ። እሳቸው እንደሚሉት መቶ ሺህ ዶላር ማስያዝ ለብዙዎቹ ኤጀንሲዎች ከባድ ነው። በሌላ በኩል የዜጎች መብት የሚጣሰው የት ጋር ነው የሚለውን በደንብ መመልከት ያስፈልጋል። አዋጁ ላይ ስለተቀመጡ ብቻም ሳይሆን በተቀባይ አገር ላይ ያሉ በተግባር መታየት ያለባቸው ነገሮችም አሉ። "ችግር ቢያጋጥማቸው በተቀባይ አገር ማን ይደርስላቸዋል?ከኤምባሲ ጋር ያላቸው ግንኙነትስ ምን መሆን አለበት?የሚሉና መሰል ጉዳዮች ተግባራዊነት በጥንቃቄ ሊታይ ይገባል። ነገሩ በኤጀንሲዎች ላይ ብቻ የሚጣል አይደለም።''ይላሉ። ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ግን የገንዘብ መስፈርቱ ችግር እንዳልሆና እስካሁን 980 ኤጀንሲዎች ፎርም እንደወሰዱና ማመልከቻ እንዳስገቡ አስታውቋል። የሚኒስቴር መስሪያቤቱ የውጭ አገር ስራ ስምሪት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ አበራ መስፈርቱን አሟልተው የተገኙ 20 ኤጀንሲዎች የብቃት ማረጋገጫ እንዳገኙ ተናግራዋል። እስካሁን ከ980 ፍቃድ ያገኙት 20 ብቻ መሆን በራሱ ግን የሚናገረው ነገር ለመኖሩ አያጠራጥርም። የአገሪቱን የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ተደራሽነትን ታሳቢ በማድረግ የተጓዦችን የትምህርት ደረጃ የሚመለከተው መስፈርትም ችግር እንደማይሆን አቶ ብርሃኑ ይናገራሉ። ነገር ግን ባለፉት አመታት በገፍ ወደ አረብ አገራት ሲሄዱ የነበሩት ማንበብ እነኳ የማይችሉ የመሆናቸው እውነታ ደግሞ የሚናገረው ተቃራኒውን ነው። እገዳው ተጥሎ ህገወጡ ጉዞ እንደቀጠለ ነበር። ኤጀንሲዎችና ተጓዦች አዲሱ የስራ ስምሪት አዋጅ የሚጠይቃቸውን መስፈርቶች ማሟላት ካልቻሉ ህገወጡ ጉዞ ተጠናክሮ ይቀጥላል የሚለው ስጋት የብዙዎች ነው።
news-53769072
https://www.bbc.com/amharic/news-53769072
አማራ ክልል፡ በደሴ ማረሚያ ቤት 13 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ
በደሴ ማረሚያ ቤት በተደረገ የኮቪድ-19 ምርመራ 13 ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው ማረጋገጡን የከተማው ጤና መምሪያ አስታወቀ።
የመምሪያው ኃላፊ አቶ አብዱልሃሚድ ይመር በተለይ ለቢቢሲ እንዳስታወቁት 12ቱ የህግ ታራሚዎች ሲሆኑ ሌላኛው ደግሞ የማረሚያ ቤቱ ባልደረባ ናቸው። እንደ አቶ አብዱልሃሚድ ገለጻ ከሆነ ከማረሚያ ቤቱ ጋር በመነጋገርም አዲስ የሚገቡ ታራሚዎች ለ14 ቀናት ለብቻቸው እንዲቆዩ ከማድረግ በተጨማሪ በመጨረሻዎቹ ቀናት ላይ ምርመራ ሲደረግላቸው ቆይቷል። ከሐምሌ 20 በኋላ ማረሚያ ቤቱ የገቡ 46 ታራሚዎች ላይ በተደረገ ምርመራ 10 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንዳለባቸው ለማረጋገጥ ተችሏል። “ታራሚዎቹ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ናቸው። ከተለያዩ ከደቡብ ወሎ ወረዳዎች እና ከደሴ ከተማም የተገኙ ናቸው” ብለዋል። በሁለተኛ ዙር 60 ሰዎች ላይ በተደረገ ምርመራ ሦስቱ ቫይረሱ እንዳለባቸው ተረጋግጧል። በሁለተኛው ዙር ቫይረሱ ከተገኘባቸው መካከል በመጀመሪያው ዙር እንዳለባቸው ከታወቁ ሰዎች ጋር ንክኪ የነበራቸው እና አንድ ማረሚያ ቤቱ ባልደረባ ይገኙበታል። የማረሚያ ቤቱን የሕግ ታራሚዎች እና ባልደረባዎችን በሙሉ ለመመርመር መቻሉንም አቶ አብዱልሃሚድ አስታውቀዋል። ቫይረሱ የተገኘባቸው ቦሩ ሜዳ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የተላኩ ሲሆን፤ ተጓዳኝ ህመም ያለበት አንድ ታራሚ ካሳየው የህመም ምልክት ውጭ ሁሉም በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል። በማረሚያ ቤቱ የቫይረሱ ስርጭት እንዳይስፋፋ አዲስ የሚገቡትን እና ነባር ታራሚዎችን ከመመርመር ባለፈ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ፣ የኬሚካል ርጭት፣ ርቀትን ማስጠበቅ እና ንጽህና የማስጠበቅ ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል። ባለፉት ወራት በአማራ ክልል በተደረገ የኮሮናቫይረስ ምርመራ 83 አሽከርካሪዎች እና ረዳቶቻቸው ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። በክልሉ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካካል 23 የህክምና ባለሙያዎች እንደሚገኙበትም ከአማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያገኘነው መረጃ ያሳያል። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር 25,118 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 463 ደርሷል። እንዲሁም አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 11,034 ደርሰዋል።
news-49481120
https://www.bbc.com/amharic/news-49481120
በአውሮፕላን ውስጥ ለቀልድ "ቦምብ" ያለው ኢትዮጵያዊ ለእስር ተዳረገ
በአውሮፕላን ውስጥ ሆነው ቀልድ ቢናገሩ እንዲያው መዘዝ የሚያስከትልብዎት መስሎዎት ያውቃል? 'በለፈለፉ ይጠፉ' እንዲሉ አንድ ኢትዮጵያዊ አውሮፕላን ውስጥ ሆኖ በቀልድ መልኩ ቦምብ ማለቱ ለአራት ወራት እስር ዳርጎታል።
ጪፍራየ በቀለ ሚያዝያ ወር ላይ ከናይሮቢ ወደ ጆሃንስበርግ ለመብረር "ቦምብ" ብሎ በመቀለዱ የጆሞ ኬንያታ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለሦስት ሰዓታትም ያህል ተዘግቷል። •ፖሊስ አንድን ወጣት ሲደበድብ በተንቀሳቃሽ ምስል ያስቀረው የዐይን እማኝ •ኢትዮጵያውያን 'የሌሉበት' ስለ ኢትዮጵያ የሚዘክረው ሬድ ሲ ዳይቪንግ ሪዞርት ፊልም ቢቢሲ ከውሳኔው እንደተረዳው ጪፍራየ በቀለ አውሮፕላን ውስጥ የበረራ አስተናጋጆች እየተቆጣጠሩ ባሉበት ሰዓት "ምን ያስፈራል? ቦምብ መሰለሽ ወይ" በማለት ለበረራ አስተናጋጇ በመቀለድ ተናግሯል። የበረራ አስተናጋጇም የሥራ ባልደረቦቿን ካዋየች በኋላ ለአብራሪው በመናገር አውሮፕላኑ ሌላ ቦታ ተወስዶ ሁሉም መንገደኞች እንዲወርዱ ከተደረጉ በኋላ አውሮፕላኑ ተፈትሿል። በረራውም ተሰርዟል። ለወራት ማረፊያ ቤት በእስር ላይ የቆየው ኢትዮጵያዊ አርብ እለት ፍርድ ቤት ቀርቦ እስር ተበይኖበታል። የኢትዮጵያዊው ንግግር አዲስ ክስተት አይደለም፤ ከዚህ ቀደምም እንዲህ አይነት ሁኔታዎች አጋጥመው ያውቃሉ። ከስድስት ዓመታት በፊትም በጆን ኤፍ ኬኔዲ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አንድ ግለሰብ ለጓደኛው "ቦምብ" ሲል የሰማው የደህንነት ሰራተኛ ግለሰቡን በቁጥጥር ሥር አውሎታል። ግለሰቡ የጠራው 'ቦምብ' የሚል መጠሪያ ስላለው ታዋቂ ሳንድዊች ነበር። በጎርጎሳዊያኑ አቆጣጠር 2004ም እንዲሁ እንግሊዛዊ ተማሪ ቦርሳዋ ውስጥ 'ቦምብ' እንዳለ በመቀለዷ በአሜሪካ አየር ማረፊያ ውስጥ በቁጥጥር ሥር የዋለች ሲሆን ለቀልዱም ይቅርታ ጠይቃለች። እንደ ጎርጎሳውያኑ 2003ም እንዲሁ የኢራቅ የባህር መርከበኛ ሁለት ቦምቦችን በሻንጣው ይዣለሁ ማለቱን ተከትሎ የፀጥታ ችግር ተፈጥሮ እንደነበር ተዘግቧል።
news-53010370
https://www.bbc.com/amharic/news-53010370
የጀርመኑ አየር መንገድ ሉፍታንዛ 22 ሺህ ሠራተኞቹን ሊቀንስ ነው
በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት ምክንያት ኪሳራ ያጋጠመው የጀመርኑ ሉፍታንዛ አየር መንገድ 22ሺህ ሠራተኞቹን ሊቀንስ መሆኑን አስታወቀ።
ሉፍታንዛ ከሚቀንሳቸው ሠራተኞቹ ገሚሱ ጀርመን የሚገኙ ናቸው። አየር መንገዱ ባስቀመጠው ግምት ከወረርሽኙ በኋላ የበረራው ኢንዱስትሪ ለማገገም ረዥም ጊዜ ይወስድበታል። በዚህም አየር መንገዱ እስከ 100 አውሮፕላኖቹን ሊያጣ ይችላል። ኩባንያው ይህን እርምጃ መውሰድ ያስፈለገው፤ የኩባንያውን ሥራ ለማስቀጠል እና በተቻለ መጠን የበርካታ ሰዎችን ስራ ለማስቀጠል ነው ተብሏል። ኩባንያው ከ135ሺህ በላይ ሠራኞች ያሉት ሲሆን ከእነዚህም መካከል ግማሽ ያክሉ የሚገኙት በጀርመን ነው። ባሳለፍነው ዓመት ሉፍታንዛ ኩባንያውን ለመታደግ ከጀመርን መንግሥት 9 ቢሊዮን ዩሮ መቀበሉ ይታወሳል። በዚህም የጀርመን መንግሥት የኩባንያው የ20 በመቶ ድርሻ ይኖረዋል። ይህ የጀመርን መንግሥት እና የሉፍታንዛ ስምምነት በአውሮፓውያን ኮሚሽን እና በኩባንያው የድርሻ ባለቤቶች ፍቃድ ማግኘት ይኖርበታል። ሉፍታንዛ የቫይረሱ ስርጭት ባስከተለበት ኪሳራ ጀርመን ዊንግስ የተባለውን ርካሽ አየር መንገዱን ለመዝጋት ተገዷል። ከሉፍታንዛ በተጨማሪ በርካታ አየር መንገዶች ሠራተኞቻቸውን ለመቀነስ ተገደዋል። ከእነዚህም መካከል ብሪቲሽ ኤርዌይስ ከ12ሺህ እስከ 45ሺህ ሠራተኞቹን ለማሰናበት አማራጮቹን እያጤነ መሆኑ ተነግሯል። ራይንኤር በበኩሉ ወደ 3ሺህ የሚሆኑ ሠራተኞቹን ለመቀነስ ዝግጅቱን አጠናቋል። የአየር መንገዱ ኃላፊዎች እንዳሉት ከሆነ አየር መንገዱ ከገበያው ሳይወጣ ለመቆየት የሚፈልገው 15 በመቶ የሚሆኑ ሠራተኞቹን ብቻ ነው። ኢዚ ጄት በበኩሉ 30 በመቶ የሚሆኑ ሠራተኞቹን ይቀንሳል። ይህም 4500 ሠራተኞች ገደማ ማለት ነው። 10ሺህ ሠራተኞች ያሉት ቨርጅን አትላንቲክ በበኩሉ 3ሺህ ሠራተኞቹን እንደሚያሰናብት አስታውቋል። የአውሮፕላን በረራ የሚጀመረው መቼ ይሆን?
sport-45365210
https://www.bbc.com/amharic/sport-45365210
ሳሙኤል ኤቶ ለቀድሞው የብሄራዊ ቡድን አምበል ቤት ሊገዛ ነው
የቀድሞው የካሜሩን ብሄራዊ ቡድን አምበል ኖርበርት ኦዎና በከባድ የኑሮ ጫና ምክንያት ላለፉት ሁለት ዓመታት ቤት አልባ ሆኖ ቢቆይም፤ ታዋቂው እግር ኳሰኛና የሃገሩ ልጅ የሆነው ሳሙሴል ኤቶ አለሁልህ፤ እኔ አዲስ ቤት እሰጥሃለው ብሎታል።
ኤቶ ለቢቢሲ እንደተናገረው በቅርቡ ወደ ሃገሩ በተመለሰበት ወቅት ነው ኖርበርትን ያገኘው። የቀድሞው የባርሴሎና እና ቼልሲ አጥቂ ሳሙኤል ኤቶ በአሁን ለኳታር ስፖርትስ ክለብ የሚጫወት ሲሆን፤ የ67 ዓመቱን የቀድሞ ብሄራዊ ቡድን አምበል የጎዳና ህይወት የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም በሃገሪቱ ቴሌቪዥን ከተመለከተ በኋላ ነው ሃሳቡ የመጣለት። • አፍሪካውያን በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውስጥ • የጀግና አቀባበል ለአትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ኦዎና ሆስፒታል ውስጥ የአንጀት ቀዶ ጥገና ለማድረግ እየተጠባበቀ ሲሆን፤ ቢቢሲ በስልክ ባነጋገረው ወቅትም ኤቶ በጣም ሩህሩህና ቅን ሰው እንደሆነ ተናግሯል። የአፍሪካ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ አራት ጊዜ የተመረጠው የ37 ዓመቱ ሳመኑኤል ኤቶ 1000 ዶላር እንደሰጠውና በተጨማሪም አዲስ የመኖሪያ ቤት ለመስጠት ቃል እንደገባለት አክሏል። የኦዎናን ህይወት በሚያሳየው ዘጋቢ ፊልም ላይ የቀድሞ እግር ኳሰኛ የነበረውን ጥሪት በሙሉ አሁን በህይወት የሌሉትን ልጁን እና ባለቤቱን ለማሳከም እንዳዋለው ተናግሯል። በመጨረሻም ወደ ጎዳና ህይወት ለመውጣት እንደተገደደና የሚበላው እስከማጣት እንደደረሰ ይናገራል። ዘጋቢ ፊልሙ አየር ላይ ከዋለ በኋላ ግን የሃገሪቱ ቀዳማዊ እመቤት ቻንተል ቢያን ጨምሮ ብዙ ካሜሮናውያን ሆስፒታል ገብቶ ህክምና እንዲከታተል ረድተውታል። • ቀጣዩ የፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ማን ይሆን? ሌላኛው የቀድሞ የካሜሩን ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች ጆሳፍ ካምጋ እንደሚለው ኦዎና ብቻ ሳይሆን ለሃገራቸው ታሪክ የሰሩ ብዙ ካሜሩናውያን እግር ኳስ ተጫዋቾች ተረስተዋል። በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ። የካሜሩን እግር ኳስ አካዳሚ በበኩሉ የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋቾችን ወደ አሰልጣኝነትና ወደ አመራር ቦታ ለማምጣት እቅድ ነድፎ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
news-50626137
https://www.bbc.com/amharic/news-50626137
የአየር ጸባይ ለውጥ ላይ የሚመክረው ስብሰባ ምን ይዞ ይሆን?
የፖለቲካ መሪዎች እና የአየር ጸባይ ለውጥ ላይ የሚሰሩ ዲፕሎማቶች እየተባባሰ ስለመጣው የአየር ጸባይ ለውጥና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ለመምከር ለሁለት ሳምንታት በስፔኗ ዋና ከተማ ማድሪድ ይወያያሉ።
እንደ ተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገለጻ '' ወደኋላ የማፈግፈጊያ ጊዜ አይደለም፤ ቆራጥ መሆን አለብን'' ብለዋል። • ብራዚል ሌዎናርዶ ዲካፓሪዮ አማዞን ጫካ እንዲቃጠል አድርጓል ስትል ከሰሰች • የተትረፈረፈ የሚመስለው አሸዋ እጥረት እያጋጠመው ነው 'ሴቭ ዘ ቺልድረን' በበኩሉ ተለዋዋጭ የአየር ንብረት በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ አፍሪካውያ ለረሀብ መጋለጥ ምክንያት እንደሆነ ገልጿል። አክሎም በከባድ አውሎ ነፋስና ድርቅ ምክንያት 33 ሚሊዮን ሰዎች እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን አስቸኳይ የምግብ እርዳታም ያስፈልጋቸዋል ብሏል። በቺሊ ሊካሄድ ታስቦ የነበረው ይህ ስብሰባ በሃገሪቱ ባጋጠመው ከፍተኛ አለመረጋጋት ምክንያት ወደስፔኗ ማድሪድ እንዲዘዋወር ሆኗል። በዚሁ ስብሰባ 29 ሺ የሚደርሱ የሃገራት መሪዎች፣ የአየር ንብረት ጥበቃ ተሟጋቾችና ሌሎችም ለሁለት ሳምንታት መፍትሄ በሚሆኑ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ ይጠበቃል። ከስብሰባው አስቀድመው መልእክታቸውን ያስተላላፉት የተባባሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ "የአየር ንብረት ለውጥ አሳሳቢ የሚባል ደረጃ ላይ ደርሷል የሀገራት መሪዎችም ቆራጥ መሆን አለባቸው" ብለዋል። አክለውም '' በጣም ወሳኝ የሆኑ 12 ወራት ከፊታችን ይጠብቁናል፤ በተለይ ደግሞ ዋነኞቹ በካይ ጭሶችን የሚለቁ ሀገራት ትልቅ ሃላፊነት አለባቸው። የግሪንሃውስ ጋዝ ልቀትን መቀነስ ላይም ከፍተኛ የሆነ ቆራጥነት ያስፈልጋል።'' ''ዝም ብለን ከመቆፈርና ያለውን ሀብት ያለአግባብ ከመጠቀም ይልቅ ታዳሽ የሆኑ ሃይሎችን ተፈጥሮአዊ በሆነና የወደፊቱን ትውልድ በማይጎዳ መልኩ ልንጠቀምባቸው ይገባል'' ብለዋል። ዛፍ መትከል የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ይረዳል? የፓሪሱን የአየር ንብረት ስምምነት ጥቂት ከሚባሉ ሃገራት በስተቀር ሁሉም ሀገራት ተስማምተው የፈረሙ ሲሆን ከፈረንጆቹ 2020 በፊት ተጨባጭ ሆነ የአየር ንብረት ለውጥን የሚከላከል መፍትሄ ማቅረብ አለባቸው። አምሳ የሚደርሱ የዓለም መሪዎች በስፔኗ መዲና እንደሚገኙ የሚጠበቅ ሲሆን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግን በስብሰባው እንደማይካፈሉ አስታውቀዋል።
news-55715149
https://www.bbc.com/amharic/news-55715149
የሜክሲኮው ፕሬዚዳንት አሜሪካ የስደተኞች ፖሊሲዋን እንድታሻሽል ጠየቁ
በሺዎች የሚቆጠሩ የመካከለኛው አሜሪካ ስደተኞች ቡድን በጓቲማላ ፖሊስ እንዳይወጡ በታገዱበት በአሁኑ ወቅት የሜክሲኮው ፕሬዚዳንት አንድሬ ማኑኤል ሎፔዝ ኦብራዶር አሜሪካ የስደተኛ ፖሊሲዋ ላይ መሰረታዊ ለውጥ እንድታደርግ ጠይቀዋል።
ፕሬዚዳንት አንድሬ በነገው ዕለት፣ ጥር 12/2013 ዓ.ም ስልጣን የሚረከቡት ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በሰደተኞች ጉዳይ ላይ ከሜክሲኮም ሆነ ከሌሎች አገራት ጋር በቅርበት እንደሚሰሩ ያላቸውን ተስፋ አስቀምጠዋል። በአሁኑ ወቅት ወደ አሜሪካ የሚጓዙ በአብዛኛው መነሻቸውን ሆንዱራስ ያደረጉ 7 ሺህ የሚሆኑ የመካከለኛው አሜሪካ ስደተኞች ቡድን ወደ ጓቲማላ ገብተዋል። በመቀጠልም ሜክሲኮን በመሻገር ወደ አሜሪካም ለመግባት ሰንቀዋል። በየአመቱም ከመካከለኛው አሜሪካ የሚነሱ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ካራቫን ተብሎ በሚታወቀው የጅምላ ቡድን የሚጓዙ ስደተኞች አብዛኛው በእግራቸው ወደ አሜሪካ በአንድ ላይ ይገባሉ። ስደተኞቹ በአገራቸው ግጭት፣ ፖለቲካዊ መሳደድ፣ ጭቆናንና ድህነትን ሸሽተው እንደሚመጡ ይናገራሉ። በተለይም እነዚህ አገራት በህዳር ወር ላይ ከፍተኛ ዝናብና አውሎ ንፋስ በቀላቀለው የሆሪኬን ማዕበል መመታታቸው የአገሬውን ዜጎች ሁኔታ አክፍቶታል። በትናነትናው ዕለት፣ ጥር 10/2013 ዓ.ም የሜክሲኮው ፕሬዚዳንት ባደረጉት ንግግር አሜሪካ የስደተኞች ፖሊሲዋን እንድታሻሽል በጥብቅ ጠይቀዋል። "ወቅቱ በስደተኞች ፖሊሲ ላይ የተገባው የማሻሻያ ቃል የሚተገበርበት ነው፤ እሱንም ነው ተስፋ የምናደርገው" ብለዋል። አክለውም "በ ጆ ባይደን የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የስደተኞች ፖሊሲን ማሻሻያ እንደሚያጠናቅቁ ተመራጩ ፕሬዚዳንት ሲናገሩ ሰምቻለሁ። ተስፋም የማደርገው ይህንንኑ ያሳካሉ ብዬ ነው" ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ በተጨማሪም መንግሥታቸው ስደተኞች ወደ ሜክሲኮ እንዳይገቡ ተፅእኖ ለማድረስ እንደሚሞክር ቢናገሩም በማስከተልም የስደተኞቹ መብትም ሊከበር ይገባል የሚል መልዕክትም አስተላልፈዋል። ሰኞ እለት በአብዛኛው ከሆንዱራስ የተነሱ ካራቫን ተብሎ በሚታወቀው የጅምላ ቡድን የሚጓዙ 4 ሺህ ስደተኞችን የፀጥታ ኃይሎች ለመበታተንም ሙከራ አድርገው ነበር። ስደተኞች ቫዶ ሆንዶ በምትባል አካባቢም ሰፍረዋል። ፖሊሶቹ ስደተኞቹን ከመጠለያቸው እንዲወጡና ወደመጡበት 50 ኪሎሜትር ርቀት ወዳለው የሆንዱራስ ድንበርም እንዲመለሱ እያስፈራሩዋቸውም እንደነበር የአይን እማኞች አሳውቀዋል። ስደተኞቹ በተወሰነ መልኩ ቢበታተኑም በርካቶቹ ግን ድንጋይ ወደ ፖሊስ በመወርወር ምላሽ ሰጥተዋል። ፖሊስም አስለቃሽ ጋዝ ረጭቷል። ቡድኑ ከቅዳሜ ጀምሮ መንገዳቸው ቢዘጋቸውም እነሱም ዋነኛ ጎዳናዎችን በመዝጋት የትራፊክ መጨናነቅ ፈጥረዋል። አንዳንድ ስደተኞች የከበቡባቸውን የፀጥታ ኃይሎች በኃይል ለማለፍ በሚሞክሩበት ወቅት ግጭቶች ተከስተዋል። ተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከደቡባዊ አሜሪካ ድንበር በሜክሲኮ በኩል የሚገቡ ስደተኞችን ህገወጥ በማለት ከፍተኛ ቁጥጥር እንዲደረግ አዘው ነበር። ከዚህም በተጨማሪ በሜክሲኮ፣ ጓቲማላ፣ ሆንዱራስና ኤልሳልቫዶርም አገራት ላይ የስደተኞችን እንቅስቃሴ እንዲቆጣጠሩ ከፍተኛ ጫና እያሳረፉባቸው ነበር። ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የትራምፕን ጥብቅ የስደተኞች ፖሊሲ አስተዳደራቸው እንደሚያሻሽል ቃል ቢገቡም፤ ፖሊሲዎች በአንድ ምሽት ስለማይቀየሩ ስደተኞች ጉዟቸውን እንዳይጀምሩ አስጠንቅቀዋል።
news-51506712
https://www.bbc.com/amharic/news-51506712
የአሜሪካው ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ዊሊያም ባር በትራምፕ ትዊት ተማረርኩኝ አሉ
የአሜሪካ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ዊሊያም ባር የፕሬዝደንት ትራምፕ የማያባሩ ትዊቶች ሥራዬን እያስተጓጎሉ ነው ሲሉ አማረሩ።
ባር ይህን የተናገሩት የቀድሞ የትራምፕ አማካሪ የነበሩትና የተከሰሱት ሮጀር ስቶን የፍርድ ሂደት ጋር በተያያዘ የአገሪቱ የፍትህ ሥርዓት ላይ ከፍተኛ ትችት እየተሰነዘረ ባለበት በዚህ ወቅት ነው። አሁን ባልተለመደ መልኩ በትራምፕ ተማርሬአለሁ ያሉት አቃቤ ሕጉ ባር የትራምፕን ትዊት ሊያባራ ይገባል ሲሉ ለኤቢሲ ተናግረዋል። ጨምረውም "ትራምፕ ስለ ፍትህ ተቋሙ የወንጀል ጉዳዮች ትዊት ማድረግ ማቆም ያለባቸው ጊዜ ይመስለኛል" ሲሉ ተናግረዋል። ትራምፕ ከስር ከስር እየተከተሉ በትዊተር ገጻቸው በሚሏቸው ነገሮቸ ምክንያት ፈፅሞ ሥራ መሥራት እያቃተን ነው ብለዋል። የአሜሪካ ሴኔት መሪ ሚች ማክኮኔል "ትራምፕ ለሥራዬ እንቅፋት እየሆኑብኝ ነው የሚለውን የጠቅላይ አቃቤ ሕጉ የባርን ቅሬታ ማድመጥና መቀበል አለባቸው" ብለዋል። በዚህ ሳምንት የአሜሪካ የፍትህ ተቋም የትራምፕ የረዥም ጊዜ ወዳጅ የነበሩት ሮጀር ስቶንን የእስራት ጊዜ ለማሳጠር እቅድ እንዳለው ማሳወቁን በብዙዎች ዘንድ ቁጣ ቀስቅሷል። የትራምፕ የቀድሞ አማካሪ ስቶን እአአ በ2016 በአሜሪካ በተካሄደው ምርጫ የሩሲያ ጣልቃ ገብነት ነበር በሚል ሲደረግ የነበረውን ምርመራ በማደናቀፍና በሐሰት መስክረዋል በሚል ነው የተከሰሱት። የፌደራል አቃብያነ ሕግ ስቶን መጀመሪያ ላይ ምርመራውን ለማደናቀፍ በመሞከራቸው ከሰባት እስከ ዘጠኝ ዓመት እስር ይገባቸዋል ሲሉ የፍርድ ሐሳብ ሰጥተው ነበር። ይህን ውሳኔ ተከትሎ ትራምፕም "ይህ እብደት ነው፤ ኢፍትሃዊ ሁኔታ ነው" ሲሉ ትዊት አድርገው ነበር። እናም የፍትህ ተቋሙ የርሳቸውን ትዊት ተከትሎ የራሱ አቃብያነ ሕጎች የሰጡትን ብይን ውድቅ አደረገ። ይህም አቃቤ ሕጉ ሚስተር ባር የትራምፕን ፍላጎት ለማስፈፀም ተንቀሳቀሱ የሚል ከባድ ጥያቄን አስነሳ። አራት አቃብያነ ሕጎችም የፍትህ ተቋሙን ውሳኔ በመቃወም ሥራቸውን ለቀቁ።
news-51813028
https://www.bbc.com/amharic/news-51813028
ኮሮናቫይረስ ሰዎችን ከእምነታቸው እየለየ ይሆን?
ኮሮናቫይረስ የዓለም ራስ ምታት መሆኑን ተከትሎ የሰዎች እንቅስቃሴ በእጅ ተገቷል። ጉዞዎች እየተሰረዙ ነው፤ አብሮ መሳቅ መጫት ቀርቶ የሞተን ሰብሰብ ብሎ መቅበር ፈተና ሆኗል።
የእግዜር ሰላምታን ከእጅ ወደ እግር ለማውረድ የተገደዱ ብዙ አገሮች ናቸው። የእንግሊዝ ፓርላማም ሆነ የፕሪምየር ሊግ ተጫዋቾች ከተጨባበጡ ሰነባበቱ። ኮሮና ቀስ በቀስ በሃይማኖትም እየገባ ነው። የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር አብያተ ክርስትያናት፣ መስጂዶችና እና ሌሎች ቤተ እምነቶች የፀሎትና የሃይማኖት በዓላት አከባበር ላይ ለውጥ ለማድረግ ተደገደዋል። • ከኮሮናቫይረስ ጋር የሚደረገውን ፍልሚያ የሚመሩት ሰው አምልኮዎች የሚደረጉበት ሁኔታ እንዲህ እየተቀየረ ባለበት ሁኔታ እምነት እንዴት ይፀናል? የሚል ጥያቄ የሚያነሱ አሉ። እስልምና በታላቁ የመካ መስጂድ ለወትሮ የሚታደሙት በሺህዎች የሚቆጠሩ የነበሩ ቢሆንም የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ተከትሎ የምእመኑ ቁጥር በእጅጉ ቀንሷል። በመስጂዱ ምእመናን በእጃቸው እንዳይነኳቸው የታጠሩ ቦታዎችም አሉ። ከውጭ መካንም ሆነ መዲናን ለመጎብኘት የሚደረግ ጉዞ ላይ የተጣለው ገደብም እንዳለ ነው። ከሃጅ ጉዞ በተለየ መልኩ በየዓመቱ የትኛውም ጊዜ ላይ መደረግ ለሚችለው ለኡምራ ጉዞ ቢያንስ በዓመት ስምንት ሚሊዮን የሚሆኑ ወደ መካ ያቀኑ ነበር። ናይጂሪያ ውስጥ ወደ መካ የሚደረጉ መንፈሳዊ ጉዞዎችን የሚያመቻቸው አንድ የጉዞ ወኪል ኃላፊ የሆኑት ሃዚዳ ታኒሙ ዳኑ "ሰዎች አዝነዋል፣ የኡምራህ ነበር ጊዜው እና ሁሉም የማምለክ ጉዞውን ይወደዋል" በማለት ነገሩ ተፅእኖ የሚያሳድረው የኡምራህ ጉዞ ላይ ብቻም ላይሆን እንደሚችል ይናገራሉ። እገዳው እስከ ረመዳን፣ ከዚያም እስከ ሃጅ ጉዞ ቢራዘምስ በሚል ብዙዎች መጨነቃቸውን አልቀረም። የሳዑዲ ባለስልጣናት እገዳው ጊዜያዊ መሆኑን ከመጠቆም ውጭ እገዳው እስከ ሃጅ ድረስ ሊረዝም ስለ መቻል አለመቻሉ የሰጡት ፍንጭ የለም። • እውን ነጭ ሽንኩርት የኮሮናቫይረስ ጠር ነው? የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ሊጨምር የሚችል ሃይማኖታዊ ሁነቶች አሁንም የሚስተዋሉበት ሁኔታ አለ። ምንም እንኳ ቫይረሱ አገራቸውን እየናጠ ቢሆንም በቅርቡ ኢራናዊያን በተለይም የሺአ እምነት ተከታዮች 'ኮሮናቫይረስ የሚባል ነገር የለም' በሚመስል መልኩ መቅደስ ውስጥ ግድግዳዎችን በምላሳቸው ሲልሱ የሚታይበት ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ በሰፊው እየተጋራ ነበር። እዚህ ተንቀሳቃሽ ምሥል ላይ አንድ ሰው ኮሮናቫይረስ እንደማያስፈራውና የአምልኮ ስፍራው ፈውስ እንዳለው እየተናገረ የመቅደስ በርና ግድግዳዎችን ሲልስ ይታያል። ይህና ሌሎችም ቪዲዮው ላይ የሚታዩ ነገሮች ብዙዎችን ሊረብሹ ይችላሉ። በቪዲዮው ከሚታዩት ሁለቱ ግለሰቦች ሲታሰሩ ጥቂት የማይባሉ ኢራናዊያን የእምነት ተቋማት በእንዲህ ያለው ጊዜ ሙሉ ለሙሉ መዘጋት ነበረባቸው ብለዋል። በሌላ በኩል በቫይረሱ የተያዘ አንድ ሰው ብቻ በተገኘባት ደቡብ አፍሪካ ሼኮች የአርብን ጁምአ ስለኮሮናቫይረስ እንዲጠነቀቁ ለማስተማር እንደተጠቀሙበት የቢቢሲ አፍሪካው ሞሃመድ አሊዬ ታዝቧል። በዚህም አማኞችን እንዳይጨባበጡ መክረዋል። ምእመናን ምክሩን ቢቀበሉም በቀላሉ መተው የሚችሉት ልማድ ባለመሆኑ መጨባበጥ መቀጠላቸውንም ዘጋቢው ተመልክቷል። ሂንዱዎች ይህ ወቅት ለሂንዱ እምነት ተከታዮች የቀለም በዓላቸው ሆሊን የሚያከብሩበት ሲሆን በዓሉ ጥሩ መንፈስ መጥፎውን ማሸነፉ የሚዘከርበት ነው። ብዙዎች አደባባይ ወጥተው ራሳቸውን እንዲሁም ሌሎችን የሚያቀልሙበት ነው። የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ህዝብ የሚታደምበትን ይህን በዓል እንደማይታደሙ ተናግረዋል። ዜጎች እንዲህ ባለው ብዙ ሰዎች በሚገኙበት ስርዓት እንዳይገኙም አሳስበዋል። ምንም እንኳ እንደ አፍ መሸፈኛ ያሉን በማድረግ አንዳንዶች ጥንቃቄ ለማድረግ ቢሞክሩም ቅዳሜና እሁድ የነበረውን በዓል ብዙዎች ተሰባስበው አክብረዋል። ይህ እጅግ አደገኛ ነው ብለው ራሳቸውን ከበዓሉ ያቀቡም ጥቂት አልነበሩም። በህንዷ አርሚስታር የሚኖረው ኒኪ ሲንግ በስልክ መልካም ምኞትን መለዋወጥን እንደመረጠ ይናገራል። የአይሁድ እምነት በምእራብ ለንደን የአይሁድ እምነት ራቢ የሆኑት ጃኪ ታቢክ ነገሩ እጅግ አስቸጋሪ መሆኑን ለማስረዳት ሲሞክሩ " ባለቤቷን በሞት የተነጠቀችን ሚስት ቀብር ላይ እንዴት አቅፈህ አታፅናናም? በጣም ከባድ ነገር ነው" ይላሉ። • የኮሮናቫይረስ ህመም ምልክቶችና እንዳይዘን ማድረግ ያለበን ጥንቃቄ ቢሆንም ግን ሰዎች መነካካትን ትተው እንዲህ ዓይነት ሃዘን ላይ ያሉ ሰዎችን በጥንቃቄ ቀረብ ብሎ በማናገር ማፅናናት እንደሚችሉ ይናገራሉ። በእስራኤል ቀዳሚ የአይሁዶች ራቢ ዳቪድ ላው ሰዎች እንዳይነካኩና እንዳይሳሳሙ መልክታቸውን አስተላልፈዋል። ብዙዎቹ ራቢዎችም እንደ እርሳቸው እየመከሩ ነው። ክርስትና በመቶዎች የሚቆጠሩ በሚታደሙበት በዋሽንግተን ዲሲው ጆርጅታውን ክራይስት ቤተክርስትያን አገልጋይ የሆኑት ግለሰብ ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው መታወቁን ተከትሎ በዚያ ቤተ እምነት የሚታደሙ ራሳቸውን አግልለው እንዲቆዩ ተነግሯቸዋል። ቄስ ቲሞቲ ኮሌ ቫይረሱ የተገኘባቸው ቅዳሜ ዕለት ሲሆን ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን ተለይተው እንዲቆዩ ተደርጓል። ቄስ ቲሞቲ በመሩት የአምልኮ ስነስርዓት ላይ 550 ምዕመናን ታድመው ነበር ተብሏል። • ወደ እስራኤል የሚገቡ መንገደኞች በሙሉ ለ14 ቀን ራሳቸውን ለይተው እንዲያቆዩ ተወሰነ • በኮሮናቫይረስ ተያዙ ከተባሉት ኢትዮጵያዊያን አንዱ ነጻ ሆነ በጣሊያንም ቦሆን ፖፕ ፍራንሲስ እንደተለመደው በመስኮት ብቅ ብለው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይን እየተመለከቱ ቡራኬ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም። ለዚህም ምክንያታቸው በቫቲካን ሊፈጠር የሚችለውን መጨናነቅ ለማስቀረት በማሰብ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የዕለቱን ቡራኬም በኢንተርኔት የቀጥታ ስርጭት ሰጥተዋል። ከጋና እስከ አሜሪካ እንዲሁም አውሮጳ የሚገኙ የካቶሊክ የእምነት አባቶች የቫይረሱን ወረርሽኝ ለማስቀረት በሚል በሕብረት የማምለክ ስርዓታቸውን ቀይረዋል። የቅዱስ ቁርባን አሰጣጥም ሆነ የእምነት አባቶችን እጅ ጨብጦ መሳም ከቀሩት ስርዓቶች መካከል ይገኙበታል። ይህ ተግባር ግን ሁሉንም ምዕመን አላስደሰተም።
news-48585211
https://www.bbc.com/amharic/news-48585211
ከወለደች ከ30 ደቂቃዎች በኋላ የ10ኛ ክፍል ፈተና የወሰደችው እናት
የ10ኛ ክፍል ተማሪዋ አልማዝ ደረሰ ዛሬ የጀመረውን የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና፤ ከወለደች ከ30 ደቂቃዎች በኋላ እዚያው ሆስፒታል ውስጥ ሳለች ተፈትናለች።
የኢሉ አባ ቦራ ዞን መቱ ከተማ ነዋሪ የሆነችው አልማዝ ደረሰ የ21 ዓመት ወጣት ስትሆን ዛሬ ሰኞ ጠዋት 2 ሰዓት ላይ የመጀመሪያ ልጇን ከተገላገለች በኋላ 2፡30 ላይ ደግሞ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቅያ ፈተና መፈተኗን ለቢቢሲ ተናግራለች። ''የፈተናው ቀን እንዲራዘም መደረጉ ከምወልድበት ቀን ጋር እንዲጋጭ ሳያደርገው አልቀረም'' የምትለው አልማዝ ወንድ ልጅ በሰላም ተገላግላለች። ነብሰ ጡር ሆና የ10ኛ ክፍል ትምህርቷን ስትከታተል እንደነበረች የምታስታውሰው አልማዝ፤ እርግዝናዋ በትምህርቷ ላይ ያሳደረው ጫና እንዳልነበረ ትናገራለች። ፈተናው ላይ ለመቀመጥ በቂ ዝግጅት ማድረጓን የምታስረዳው አልማዝ፤ ዛሬ ፈተና በሚጀምርበት ዕለት ጠዋት ምጥ ሲይዛት ባለቤቷ ወደ ሆስፒታል ከወሰዳት በኋላ ለትምህርት ቢሮ ሰዎች ጉዳዩን በማሳወቅ ሆስፒታል ድረስ መጥተው እንደፈተኗት ታስረዳለች። ''ፈተናውን ለመፈተን ተጣድፌ ስለነበረ፤ ምጡ ምንም አልከበደኝም። ምንም ሳይመስለኝ ነው የወለድኩት'' ''ፈተናውም በጣም ጥሩ ነበር'' ብላለች አልማዝ። ''መጀመሪያ ላይ ሊፈትናት የሚችል ሰው የለም ብለውኝ ነበር'' የሚለው ባለቤቷ አቶ ታደሰ ቱሉ ''መደበኛ ተማሪ መሆኗን ሲረዱ ግን በፍጥነት ሆስፒታል ድረስ ፈተና እንድትወስድ አመቻቹልን'' በማለት ሁኔታውን ያስረዳል። አልማዝ በሆስፒታል ውስጥ ፈተናውን ስትወስድ በፌደራል ፖሊስ ታጅባ ነበር። አልማዝ እና ታደስ ያለፉትን ጥቂት ዓመታት በፍቅር አብረው መኖራቸውን ይናገራሉ። ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ ባይራዝም ኖሮ ነብሰ ጡር እያለች ነበር የምትወልደው ይላል አቶ ታደሰ። አልማዝ በመምህሮቿ ዘንድ ተወዳጅ ተማሪ መሆኗን እና መምህሮቿም በእርግዝናዋ ምክንያት ፈተናው እንዳያመልጣት ክትትል ሲያደርጉ እንደነበረ ሰምተናል። ''ነብሰ ጡር ስለነበረች ወደ መጨረሻ ላይ ሆዷ እየገፋ ሲሄድ ከበዳት እንጂ ጎበዝ ተማሪ ነች'' ይላል ባለቤቷ አቶ ታደሰ። አጠቃላይ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና በቀጣዮቹ ቀናት መሰጠቱ የሚቀጥል ሲሆን፤ አልማዝም ''የተቀሩትን ፈተናዎች እዛው ትምህርት ቤት ሄጄ እፈተናለሁ'' እያለች ነው።
news-53441803
https://www.bbc.com/amharic/news-53441803
ሱዳናውያን ጥብቅ የእስልምና ሕግጋት መሻሻል የለባቸውም ሲሉ ለተቃውሞ ወጡ
በቅርቡ በአንዳንድ ጥብቅ እስላማዊ ሕጎቿ ላይ ማሻሻያዎችን ያደረጉት የሱዳን ባለስልጣናት ተቃውሞ ገጠማቸው።
በርካታ የሸሪአ ሕግጋት ተግባራዊ እንዲሆኑ የሚፈግፉ ሱዳናውያን በቀርቡ የአገሪቱ የሽግግር መንግሥት ጥብቅ የእስልምና ሕግጋትን ማሻሻሉን ተቃውመው አደባባይ ወጥተዋል። በቅርቡ የሱዳን መንግሥት ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች የአልኮል መጠጥ እንዲጠጡ ከመፍቀዱ በተጨማሪ ሐይማኖት የመቀየር መብትን ጨምሮ በርካታ ለውጦችን ይፋ አድርጎ ነበር። የሱዳን ፍትህ ሚንስቴር ባለስልጣናት ሰዎች ለፈጸሙት 'ኢ-ሞራላዊ ተግባር' በአደባባይ እንዲገረፉ የሚያዘው ትዕዛዝ እንዲቆም መታወጁንም ተናግረው ነበር። ትናንት ከአርብ ጸሎት በኋላ ግን መንግሥት ያስተዋወቀውን ማሻሻያዎች ለመቃወም የወጡ ሰልፈኞች፤ "የፈጣሪ ሕግ መቀየር የለበትም" እንዲሁም "መንግሥት በሐይማኖት ጣልቃ መግባት የለበትም" የሚሉ መፈክሮችን ይዘው መውጣቻቸውን ኤኤፍፒ የዜና ወኪል ዘግቧል። ተቃዋሚዎቹ የሱዳን የሽግግር መንግሥት መሪ የሆኑትን ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሃምዶክን በስም እየጠሩ "ሃምዶክ፤ ካርቱም ኒው ዮርክ አይደለችም" ሲሉም ተደምጠዋል። የሽግግር መንግሥቱ ያሻሻላቸው ሕጎች የትኞቹ ናቸው? በተሻሻለው ሕግ መሠረት ከአሁን በኋላ ሱዳናውያን ሴቶች ጉዞ ለማድረግ ከወንድ የቤተሰብ አባል ፍቃድ ማግኘት አይጠበቅባቸውም። ከዚህ ቀደም በሱዳን የአልኮል መጠጥ መጠጣት አይፈቀድም ነበር። አሁን ግን ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች አልኮል በቤታቸው መጠቀም ይችላሉ። ይሁን እንጂ ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች ሙስሊሞች ባሉበት ቦታ አልኮል ሲጠጡ ቢገኙ ቅጣት እንደሚጣልባቸው ተነግሯል። የእስልምና እምነት ተከታዮች ግን አሁንም ቢሆን አልኮል መጠጣት አይፈቀድላቸውም ሲሉ የፍትህ ሚንስትሩ ተናግረዋል። ሙስሊም ያለሆኑ ግሰቦች አልኮል ከመጠቀም ባሻገር፤ መሽጥ እና ከውጪ ማስገባት ይችላሉ ተብሏል። የሱዳን መንግሥት ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰኩት 3 በመቶ የሚሆኑ ሙስሊም ያልሆኑ ሱዳናውያንን መብትን ለመጠበቅ ነው ብሏል። በሱዳን እስካሁን ድረስ የእስልምን ሐይማኖትን የሚቀይሩ ሰዎች የሞት ቅጣትን ጨምሮ ከባድ ቅጣት ይጣልባቸው ነበር። የሽግግር መንግሥቱ ሰዎች ሐይማኖታቸውን የመቀየር መብት አላቸው ሲል ደንግጓል።
news-47493137
https://www.bbc.com/amharic/news-47493137
ተማሪውን የገደለው ታንዛንያዊው መምህር በስቅላት ሊቀጣ ነው
ታንዛኒያ ውስጥ ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ላይ ተማሪውን በከባድ ሁኔታ ደብድቦ ለሞት ያበቃው መምህር በስቅላት እንዲቀጣ ተፈርዶበታል።
ብይኑን ያስተላለፉት ዳኛ ላሜክ ምላቻ እንደተናገሩት የ51 ዓመቱ መምህር ሬስፒሸስ ምታዛንጊራ በዱላ የ14 ዓመት ታዳጊውን በተደጋጋሚ መትቶት ነበር። • የተማሪውን ልጅ አዝሎ ያስተማረው መምህር አድናቆት ተቸረው • ወላጆች ለልጆቻቸው የሚመኟቸው ኢትዮጵያዊ መምህር ታዳጊውም ከደረሰበት ከባድ ጉዳት ማገገም ሳይችል ቀርቶ ህይወቱ አልፋለች። መምህሩ ታዳጊውን የደበደበው የአንዲት ሴት መምህርን የእጅ ቦርሳ ሰርቀሃል በሚል ምክንያት እንደሆነ ለፍርድ ቤቱ ተገልጿል። በታንዛኒያ ህግ መሰረት ትምህርት ቤት ውስጥ አካላዊ ቅጣት የተከለከለ ሲሆን ቅጣቱ የሚፈቀድባቸው አንዳንድ ሁኔታዎች ግን አሉ። በዚህም ወቅት ተማሪዋ ወይንም ተማሪው አራት ጊዜ እንዲገረፍ የሚፈቀድ ሲሆን የትምህርት ቤቱ ሃላፊ ወይም ሃላፊው ስልጣን የሰጠው መምህር ግን በቦታው መኖር አለበት ይላል። ባለፈው ዓመት በኪቤታ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ይማር የነበረው ታዳጊ ህይወት ማለፉ ሲሰማ ሃገር አቀፍ ተቃውሞና ቁጣ አስነስቶ ነበር። የታዳጊው ቤተሰቦችም ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር እስኪውል ድረስ የልጃችንን ሬሳ አንቀብርም ብለው ነበር። • የ7 ዓመቷ ህፃን መፀዳጃ ቤት አልሰራልኝም ስትል አባቷን ከሰሰች ምንም እንኳን መምህሩ የሞት ቅጣት ቢፈረድበትም ታንዛኒያ ከአውሮፓውያኑ 1994 ወዲህ ምንም አይነት የሞት ቅጣት አከናውና አታውቅም። የእጅ ቦርሳዋ ተሰረቀባት የተባለችው መምህርም ክስ ቀርቦባት የነበረ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ምንም ጥፋት አልሰራችም ብሎ በነጻ አሰናብቷታል።
news-52586468
https://www.bbc.com/amharic/news-52586468
በአቶ በረከት ስምኦን እና ታደሠ ካሣ ላይ የፍርድ ውሳኔ ተላለፈ
በእነ አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሠ ካሣ ላይ የፍርድ ውሳኔ ተላለፈ።
የአማራ ክልል ፍርድ ቤት በቀድሞ ባለስልጣናቱ በአቶ በረከት ስምኦን ላይ ስድስት ዓመት እንዲሁም በአቶ ታደሰ ካሳ ላይ የስምንት ዓመት የእስር ውሳኔ አስተላልፏል። ፍርድ ቤቱ የከሳሽንና የተከሳሾችን ክርክር ሲያዳምጥ ከቆየ በኋላ ዛሬ በዋለው ችሎት በ1ኛ እና 2ኛ የክስ መዝገቦች ላይ ጥፋተኛ በተባሉት በ1ኛ ተከሳሽ አቶ በረከት ስምኦን ላይ የስድስት ዓመት እስር እና የ10 ሺህ ብር የቅጣ ውሳኔ አስተላልፏል። •በረከት ስምኦን ስለራሱ ይናገራል •በረከት ስምኦን ከየት ተነስተው እዚህ ደረሱ ከዚህም በተጨማሪ በ1ኛ፣ 2ኛ እና 4ኛ የክስ መዝገቦች ላይ ጥፋተኛ በተባሉት 2ኛ ተከሳሽ አቶ ታደሰ ካሳ ላይ ደግሞ የስምንት ዓመት የእስር ቅጣትና የ15 ሺህ ብር የቅጣት ውሳኔ መበየኑን የአማራ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል። ችሎቱ ሁለቱ ግለሰቦች ይግባኝ የማለት መብት እንዳላቸው የገለጸ ሲሆን ችሎቱ ፍርዱ በሕግ ቁጥጥር ስር ከዋሉበት ጊዜ ጀምሮ ይሰላልም ተብሏል። አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሠ ካሣ በጥረት ኮርፖሬሽንን በቦርድ ሰብሳቢነትና በዋና ሥራ አስፈፃሚነት ሚናቸው ጋር በተያያዘ ወንጀል ፈፅመዋል በሚል ጥር 2011 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ መቆየቱ ይታወሳል። ከቀናት በፊት በሁለቱ የቀድሞ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል። አቶ በረከት ስምኦን ማናቸው? አቶ በረከት ስምኦን ከኤርትራዊያን ቤተሰቦቻቸው ጎንደር ውስጥ ተወልደው እንዳደጉ ይነገራል። ቤተሰቦቻቸው ያወጡላቸው ስም መብራህቱ ሲሆን የአባታቸው ስም ደግሞ ገብረሕይወት እንደሆነ በቅርብ የሚያውቋቸው ሰዎች ይናገራሉ። በቀዳሚነት የታላቅ ወንድማቸውን ፈለግ በመከተል የኢህአፓ አባል ሆነው ወደ ትግሉ ከገቡ በኋላ የስም ለውጥ እንዳደረጉም እነዚሁ ሰዎች ያስታውሳሉ። ስማቸውን ለምን እንደለወጡ የሚታወቅ ነገር ባይኖርም የሌላ ታጋይ ስም እንደወሰዱ ግን ይነገራል። ይህም በረከት ስምኦን የሚባል የኢህአፓ ታጋይ እንደነበርና በትግሉ ወቅት ባልታወቀ ምክንያት ከትግሉ ሜዳ ድንገት በመሰወሩ በርካታ የኢህአፓ አባላት የተገደለ መስሏቸው ነበር። በነበረው ልምድም ይህን ታጋይ ለማስታወስ መብራህቱ ገብረህይወት በረስምኦን የሚለውን ሙሉ ስም እንደወሰዱም የቅርብ ሰዎቻቸው ያወሳሉ። •አቶ በረከት ስምኦን ሥልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ •«ወይዘሮ ጎሜዝ፤ እርስዎ አያገባዎትም! አርፈው ይቀመጡ በልልኝ» አቶ በረከት ከየት ወደየት? አቶ በረከት ስምኦን ወደ ትግል የገቡት በመጀመሪያ የኢህአፓ አባል ሆነው ሲሆን ድርጅቱ በዋናነት ከደርግና ከሌሎች ተቀናቃኝ ድርጅቶች በገጠመው ጥቃት በተዳከመበት ወቅት በውስጡ የተፈጠረውን መከፋፈል ተከትሎ ከሌሎች ጓዶቻቸው ጋር ድርጅቱን ጥለው ወጡ። ከኢህአፓ የተለዩት አቶ በረከት ከትግሉ ጠቅልለው ግን አልወጡም ከጓዶቻቸው ጋር ብዙም ያልቆየውን ኢትዮጵያ ኮሚኒስት ፓርቲ (ኢኮፓ) አቋቁመው የነበረ ሲሆን ቀጥለውም አሁን የአማራ ክልል ገዢ ፓርቲ የነበረው አማራ ዲሞክራቲክ ፓርቲ መነሻ የሆነውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄን (ኢህዴን) በመመሥረት ከህወሓት ጋር ግንባር ፈጥረው ደርግን ታግለዋል። ከደርግ ውድቀት በኋላ አቶ በረከት በብአዴን ውስጥ ቁልፍ ሚና ከነበራቸው ሰዎች መካከል ቀዳሚው በመሆን ቆይተዋል። አቶ በረከት የነበሩባቸው ቁልፍ የመንግሥት ኃላፊነቶች
news-41299480
https://www.bbc.com/amharic/news-41299480
በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች መካከል የተከሰተውን ግጭት የሚያብራሩ አምስት ነጥቦች
በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች በተቀሰቀሱ ግጭቶች ምክንያት የሰዎች ህይወት ጠፍቷል፤ ከሃምሳ አምስት ሺ በላይ የሚቆጠሩ ዜጎችም ከመኖሪያቸው እንዲፈናቀሉ ተገደዋል።
የኦሮሚያ ክልል መንግሥት፤ የሶማሌ ልዩ ፖሊስን እንዲሁም ሚሊሻዎች ወደ ኦሮሚያ ዘልቀው በመግባት ጥቃት አድርሰዋል ሲል የሚከስ ሲሆን፤ የሶማሌ ክልል በበኩሉ አጥቂዎቹን በኦሮሚያ ክልል የሚደገፉ ናቸው ሲል በኮሚኒኬሽን ቢሮው በኩል አሳውቋል። መወነጃጀሉና የቃላት ምልልሱ መካረር የክልሎቹ መንግስታት ግንኙነት ያለበትን ደረጃ ከማሳበቁም ባለፈ የግጭቶቹን መረር ማለትም አመላካች ነው። ይሁንና በሁለቱ ክልሎች መካከል ውዝግብ፣ ግጭት፣ ሲያልፍም ደም መፋሰስ ሲያጋጥም የአሁኑ የመጀመሪያው አይደለም። 1.አጨቃጫቂ ወሰን በቆዳ ስፋቱ ከአገሪቱ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዘው የኦሮሚያ ክልል፤ ከሁለተኛው ሰፊ የሶማሌ ክልል ጋር የሚያዋስነው 1410 ኪሜ ድንበር አለው። ይህ ድንበር ግን ክልሎቹ አሁን ያሉበትን ቅርጽ ይዘው ከተመሰረቱበት ጊዜ አንስቶ ውዝግብ አያጣውም። ውዝግቡን ፈትቶ ወሰኖቹን መልክ ለማስያዝ ታስቦም ሕዝበ ውሳኔ ከ400 በሚበልጡ ቀበሌዎች በጥቅምት ወር 1997 ዓ.ም ተደርጓል። በሕዝበ ውሳኔው መሰረት ከ80 በመቶ በላይ የሚሆኑ ቀበሌዎች በኦሮሚያ አስተዳደር ሥር እንዲጠቃለሉ የተወሰነ ቢሆንም የወሰን ማካለል ሥራው ተግባራዊ ሳይሆን ቆይቷል። ይህም በየጊዜው ለሚነሱ ግጭቶች አባባሽ ምክንያት መሆኑ አልቀረም። ባለፈው ሚያዝያ ግን የሁለቱም ክልሎች ፕሬዚዳንቶች ሕዝበ ውሳኔውን ተግባራዊ ለማድረግ ያስችላል የተባለ ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱ በተፈረመበት ወቅት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ "ትልቅ ድል" መገኘቱን ሲገልፁ፥ የሶማሌ ክልል አቻቸው አብዲ መሃመድ በበኩላቸው "በሁለቱ ወንድማማች ሕዝቦች መካከል ዳግመኛ ግጭት አይኖርም።'' ብለው ነበረ። የኦሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ አቶ አዲሱ አረጋም የችግሩ ምንጭ ''የድንበር ጉዳይ እንዳልሆነ የሚያረጋግጥልን፤ ድንበር በማንጋራባቸው አካባቢዎች ጭምር ጥቃት ሲፈፀም የነበረው። የድንበሩን ጉዳይ በ1997 ሕዝበ-ውሳኔ መሰረት ለመፍታት በተደረሰው ስምምነት መሰረት እየሰራን ነው።ሥራውም ሰባ በመቶ በላይ ተጠናቋል።'' ሲሉ ሌላ ምክንያት ሊኖር እንደሚችል ይጠቁማሉ። 2.የተፈጥሮ ሃብት ፉክክር በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር የሚገኙ የኦሮሞ እና የሶማሌ ክልል አርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አድር ሕዝቦችን ግንኙነት ያጠኑት የማኅበረሰባዊ ሥነ-ሰብ ተመራማሪው ፈቃዱ አዱኛ እንደሚሉት ፉክክርና ግጭት በተለይ የቦረና ኦሮሞዎችና የአካባቢው ሶማሌ ጎሳዎች መገለጫዎች ሆነው ቆይተዋል ይላሉ። ፉክክርና ግጭቶቹ በብዛት ውሃ እና የግጦሽ መሬትን በመሳሰሉ የተፈጥሮ ሃብቶች ተጠቃሚነት ዙርያ የሚያጠነጥኑ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ አንስቶ የብሔር መልክ እየያዙ መምጣታቸው ይወሳል። በአገሪቱ ፖለቲካዊ አወቃቀር የብሄር ድንበሮች የፖለቲካ ድንበሮች ጭምርም በመሆናቸው፤ በማኅበረሰቦቹ ዘንድ ያለውን የፉክክር መንፈስ ክልላዊ ገፅታ አላብሶታል ሲሉ ይከራከራሉ አቶ ፈቃዱ። ለዚህም በማሳያነት የሚጠቅሱት ከዚህ ቀደም በአንፃራዊነት ሰላማዊ ግንኙነት የነበራቸው የአርሲ ኦሮሞና አጎራባች የሶማሌ ጎሳዎች ደም ወዳፋሰሰ ግጭት መግባታቸውን ነው። አካባቢዎቹ ለድርቅ ተጋላጭነታቸው ከፍ ያለ መሆኑ በተፈጥሮ ሃብት ፍላጎቶች ላይ ለሚነሱ ቅራኔዎች ተጨማሪ ነዳጅ የሆኑ ይመስላል። 3.የሕዝበ-ውሳኔ ራስ ምታት ለተመራማሪው ፈቃዱ አዱኛ፤ መንግሥት ለአካባቢዎቹ ወሰን ተኮር ግጭቶች ፖለቲካዊ መፍትሄ ለመስጠት ባደረገው እንቅስቃሴ ሕዝበ-ውሳኔ ማከናወኑ የአካባቢዎቹን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ ነው። የአካባቢው ኗሪዎች በአብዛኛው አርብቶ አደሮች እንደመሆናቸው ከሥፍራ ሥፍራ ይንቀሳቀሳሉ። ይህም ወሰኑን ቁርጥ ባለ ሁኔታ ማስቀመጥን አዳጋች ያደርገዋል። የህዝበ-ውሳኔው ውጤት በሁለቱ ክልሎች መካከል የተነሳውን ጥያቄ ምላሽ ሰጥቷል ቢባልም የተካሄደበትን ወቅት መሰረት ያደረገ ሌላ ጉዳይ አሁን እንደተነሳ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር "ከሶማሌ ክልል በኩል የሚነሳው ጥያቄ ሕዝበ-ውሳኔው የተካሄደበት ወቅት የሶማሌ ክልል የራሱን ግዛት ሊያስጠብቅ በማይችልበት አቅም ላይ በነበረበት ጊዜ በመሆኑ ብዙ ግዛት ተወስዶብኛል የሚሉ ጥያቄዎች እያነሳ ነው።" ይላሉ። 4.ሞትና መፈናቀል ባለፈው ነሐሴ የተካረሩ ግጭቶችን ያስተናገደው የሚኤሶ አካባቢ ለወትሮውም ለዚህ መሰል ፍጭቶች ባይታወር አይደለም። ሕዝበ ውሳኔን ባስተናገደው የ1997 ዓ.ም በመኢሶና በቦርደዴ አካባቢዎች በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን እንዲፈናቀሉ ያስገደዱ ግጭቶች ተከስተዋል ይላል የአይ ዲ ፒ ፕሮጄክት ሪፖርት። በ2005 ዓ.ም ደግሞ በሞያሌ አካባቢ በተቀሰቀሰ የሁለቱ ብሔር አባላት ግጭት ከ20ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች ሸሽተው ኬንያ መግባታቸውን የኬንያ ቀይ መስቀል ማህበር በዚሁ ወቅት አስታውቆ ነበር። በወቅቱ ለግጭቱ መቀስቀስ ምክንያት ተደርጎ የተጠቀሰው በግጦሽ መሬት ይገባኛል ቢሆንም ግጭቶቹ ብሄር ተኮር ይዘት እንዳላቸውም አብሮ ተዘግቧል። ባለፈው ዓመት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር የሚከሰቱት ግጭቶች መንስዔ የብሄር ይዘት አለው ባይሉም፤ በግጦሽ መሬትና በውሃ የተቀሰቀሰ ነውም አላሉም። ከዚያ ይልቅ ለጉዳዩ ቅርበት አላቸው ያሏቸውን የአካባቢውን አስተዳዳሪዎችን ወቅሰዋል። 5.ማኅበረ-ባህላዊ ልዩነቶችና አንድነቶች የኦሮሞና ሶማሌ ሕዝቦች ከምስራቅ ኩሽ የቋንቋ የዘር ግንድ የሚመዘዙ ሲሆን በኢትዮጵያ ሶማሌዎችና በተለይም እስልምና በገነነባቸው የኦሮሞ አካባቢዎች መካከል መልካም የሚባል ግንኙነት ተመስርቶ መቆየቱን የሚያነሱት አቶ ፈቃዱ፤ ባሌ ውስጥ የሚገኘው የሼክ ሁሴን መስጊድ በሁለቱም ሕዝቦች እንደ ቅዱስ ቦታ መቆጠሩን ያስታውሳሉ። የሶማሌና የኦሮሞ ሕዝብ አብሮ ከመኖሩ አንፃር በርካታ አንድ የሚያደርጓቸው ነገሮች እንደሉ የሚጠቅሱት የፖለቲካል ሳይንስ መምህሩ፤ ምንም እንኳን እነዚህ ግዛቶች በወሰን ቢከፋፈሉም አሁንም የሁለቱ ህዝቦች የሚንቀሳቀሱባቸው ከተሞች አሉ፤ በማለት የሁለቱ ሕዝቦች አብሮነት እንደማይቋረጥ ይናገራሉ።
54336433
https://www.bbc.com/amharic/54336433
በቤንሻንጉል ክልል መተከል ዞን ዘላቂ ሰላም ማምጣት ለምን አልተቻለም?
በመተከል ዞን በተከሰተው የፀጥታ ችግር ውስጥ እጃቸው አለበት የተባሉ እና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ባለመወጣት የተጠረጠሩ ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮች ላይ ፖለቲካዊ እርምጃ መወሰዱን የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይስሃቅ አብዱልቃድር ለቢቢሲ ተናገሩ።
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን የተለያዩ ወረዳዎች አመራር የነበሩ 45 ግለሰቦች ሙሉ በሙሉ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ መደረጉን የተናገሩት ኃላፊው እጃቸው አለበት በሚል ጥቆማ የቀረበባቸው በሕግ እንዲጠየቁ እንደሚደረግ ተናግረዋል። አጠቃላይ በተደረገው በወረዳ አመራር ግምገማ "በተለያየ መንገድ ከፀረሰላም ኃይሎች ጋር እጃቸው አለበት" ተብለው የተጠረጠሩ አመራሮች ላይም እርምጃው መወሰዱን ተናግረዋል። ስራቸውን በአግባቡ አልተወጡም፣ የሕዝብን ደህንነት ማስጠበቅ አልቻሉም፣ መረጃ እያላቸው ቸልተኛ ሆነዋል በሚል ተገምግመው ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ከተደረጉ 45 አመራሮች መካከል በወንጀል ውስጥ በመሳተፍ እጃቸው አለበት የሚል ጥቆማ የቀረበባቸው አስር የወረዳ አመራሮች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል ከኃላፊነታቸው ከተነሱ የክልል አመራሮች መካከል የክልሉን ፖሊስ በምክትል ኮሚሽነርነት እየመሩ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም በሚል ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን አቶ ይስኃቅ ተናግረዋል። በዞን ደረጃ ስድስት አመራሮች፣ በዳንጉር፣ ቡለን፣ ወንበራ ወረዳ ዋና እና ምክትል አስተዳዳሪዎች እንዲሁም ቁልፍ አመራሮችም ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ባለመወጣታቸው የተነሳ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ጨምረው ገልፀዋል። እነዚህ ኃላፊዎች ላይ በወንጀል መሳተፋቸውን የሚያሳይ መረጃ ከተገኘ በሕግ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እንደሚደረግ አክለው ተናግረዋል። ግምገማው እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ እንደሚቀጥል የተናገሩት አቶ ይስኃቅ፣ ኅብረተሰቡን የማረጋጋትና የተፈናቀሉትን ወደ ቀያቸው የመመለስ ስራ እየተሰራ ከኃላፊነት የተነሱት አመራሮች የነበራቸው ተሳትፎ ላይ መረጃ ከተገኘ በሕግ የመጠየቁ ስራ እንዲቀጥል መወሰኑን ተናግረዋል። በክልልና በዞን ደረጃ የሚገኙ አመራሮች የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ባለመወጣታቸው ሲገመገሙ፣ በወረዳ ደረጃ በቀጥታ ተሳትፎ አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ አመራሮች መገኘታቸውንም ገልፀዋል። በወረዳ ደረጃ አመራር የነበሩና ቀጥታ ተሳትፎ ኖሯቸው በሕግ ቁጥጥር ስር ከመዋላቸው በፊት የሸሹ መኖራቸውን ኃላፊው አስረድተዋል። በቀበሌ ደረጃ በቀጣይ ቀናት ግምገማው እንደሚቀጥል አስረድተዋል። ዘላቂ ሰላም በዞኖቹ ማምጣት ለምን አልተቻለም? ጥቃቱን እያደረሱ የሚገኙት ታጣቂዎች ከሌላ ቦታ የመጡ አለመሆናቸውን የሚገልፁት አቶ ይስሃቅ፣ በአብዛኛው ባለፈው ዓመት ጃዊ አካባቢ በነበረው ጥቃት "መንግሥት ሊከላከለን አልቻለም" በሚል ቅሬታ የገባቸው ወጣቶች ሸፍተው ጫካ መግባታቸውን ይናገራሉ። በወቅቱ ጥቃቱ ሲደርስ በአመራርነት ቦታ ላይ የነበሩ ግለሰቦች አልተጠየቁም የሚል ቅሬታ በወጣቶቹ ዘንድ መፈጠሩን ያነሱት አቶ ይስሃቅ፣ ነገር ግን የክልሉንና የአገሪቱን ሰላም የማይፈልጉ ኃይሎች በተለይ "ከሕዳሴ ግድቡ ጋር በተያያዘ" ወጣቶቹን በሱዳን ጠረፍ አካባቢ አስታጥቀው አሰልጥነው ወደ አካባቢው እንዲገቡ ማድረጋቸውን ገልፀዋል። በማህበራዊ መገናኛ ብዙኀንም "መተከል የኛ ነው" የሚል ቅስቀሳ መኖሩ እና ይህም የአካባቢዎቹን ወጣቶች ላይ 'የእኛ እጣ ፈንታ ምንድን ነው?' የሚል ቅሬታ መፈጠሩን ተናግረዋል። በቡለንና ወንበራ ወረዳዎች ላይ በደረሱ ጥቃቶች ሕይወታቸውን ያጡ ግለሰቦች የአንድ ብሔር ብቻ ተወላጆች እንደሆኑ ተደርጎ በማህበራዊ መገናኛ ብዙኀን የሚደረግ ቅስቀሳም አካባቢው እንዳይረጋጋ ማድረጉን ተናግረዋል። ክልሉ መሬት ወስደው ሳያለሙ በተቀመጡ ባለሃብቶች ላይ በወሰደው እርምጃ ቅሬታ የገባቸው የተለያዩ ኃይሎችም የሚነሱ ግጭቶችን በመደገፍ ተሳትፎ ማድረጋቸውን ገልፀዋል። ጥቃቱን ከፈፀሙ እና በተወሰደው እርምጃ በቁጥጥር ስር ከዋሉት በተገኘው መረጃ መሰረት በክልሉ የሚንቀሳቀስ አንድ ተፎካካሪ ፓርቲ ተልዕኮ እንደሰጣቸው የተናገሩ ወጣቶች መኖራቸውንም ጨምረው ተናግርዋል። ይህ አቶ ይስሃቅ በስም የሚጠቅሱት ተቃዋሚ ፓርቲ፣ ግልጽ ቅስቀሳ የሚያደርግ እንደነበር አንስተው፣ በተጨማሪ ደግሞ የአካባቢው መልከአምድር፣ እንዲሁም መሰረተ ልማቶች አለመሟላታቸው ለታጣቂ ኃይሎች እንቅስቃሴ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ገልፀዋል። ክልሉ ምን እርምጃ እየወሰደ ነው? የክልሉ ልዩ ኃይል እና መከላከያ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን በተለያየ ወቅት ርምጃ እንደሚወሰድ ኃላፊው ተናግረዋል። በአጠቃላይ ክልሉ በወሰደው ሰላም የማስከበር እርምጃ እስከ እሁድ ድረስ በጥቃቱ ላይ በቀጥታ የተሳተፉ 391 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ያሉት አቶ ይስሃቅ፣ በቁጥጥር ስር የዋሉት ታጣቂዎቹን በመቀለብ ሲረዱ የነበሩ፣ የተለያየ ግንኙነት የነበራቸውና በቀጥታ ታጣቀው ጥቃት የፈፀሙ መሆናቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በመተከል ዞን በተለያየ ወቅት በደረሱ ጥቃቶች እጃቸው አለበት ወይንም ኃላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም በሚል ኃላፊዎችና ታጣቂዎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ሲውሉ አዲስ አለመሆኑን ያነሱት አቶ ይስሃቅ፣አሁንም በዞኑ ማረሚያ ቤት የሚገኙ እና ሁለት ዓመት ሙሉ ክስ ያልተመሰረተባቸው ግለሰቦች እንደሚገኙ አስረድተዋል። ይህም ቅሬታን ፈጥሯል የሚሉት አቶ ይስሃቅ ይህ የሆነበት ምክንያትን ሲያስረዱ የእነዚህ ተጠርጣሪዎች ጉዳይ የተያዘው በፌደራል መርማሪ ቡድን በመሆኑ እንደሆነ ይገልፃሉ። የፌደራል መርማሪ ቡድኑ በየጊዜው በተዘዋዋሪ ችሎት በመምጣት ጉዳዩን እንደሚመለከት የሚናገሩት ኃላፊው የተፋጠነ ፍትህ አለማግኘት ቅሬታዎችን መፍጠሩን ይናገራሉ። ይህ በመተከል ዞን ብቻ የሚታይ ሳይሆን ካማሼ ዞንም አንድ አመት እና ከዚያ በላይ ክስ ሳይመሰረትባቸው በማረሚያ ቤት የሚገኙ ተጠርጣሪዎች መኖራቸውን ገልፀዋል። እነዚህ ሰዎች የተፋጠነ ፍርድ እንዲያገኙ ክልሉ ከአቃቤ ሕግ ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል።
news-53985095
https://www.bbc.com/amharic/news-53985095
አሜሪካ፡ ሰባት ጊዜ በጥይት የተመታው አሜሪካዊ አባት ትራምፕን ማግኘት አልፈልግም አሉ
በፖሊስ በተደጋጋሚ በጥይት የተመታው ጥቁር አሜሪካዊ ጄኮብ ብሌክ አባት 'በልጄ ሕይወት የፖለቲካ ቁማር አልጫወትም' ብለዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከሰዓታት በኋላ ዊስኮንሰን የምትገኘው ኬኖሻ ከተማን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ጄኮብ ብሌክ በኬኖሻ ፖሊስ ነው በጥይት የተመታው። ይህን ተከትሎ በከተማዋና በሌሎች የአሜሪካ ክፍሎች ተቃውሞ ተቀስቅሶ ነበር። ጄኮብ በሕይወት ይትረፍ እንጂ መራመድ እንደማይችል ሐኪሞች ተናግረዋል። ትራምፕ የከተማዋን አስተዳዳሪዎች ያናግራሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከጉብኝቱ በፊት የጄኮብን በተሰቦች እንደማይገኙ ምክንያቱ ደግሞ ቤተሰቡ በጉብኝቱ ወቅት ጠበቃ እንዲኖር እንፈልጋለን ማለታቸው እንደሆነ ተናግረዋል። ከሲኤንኤን ጋር ቆይታ የነበራቸው የጄኮብ አባት ጄኮብ ሲኒዬር፤ የልጃቸው ሕይወት ትራምፕን ከማግኘት በላይ ዋጋ እንዳለው ተናግረዋል። "ፖለቲካ ውስጥ መግባት አልፈልግም። ይህ ጉዳይ የልጁ ጉዳይ ነው። ፎቶ ከመነሳት ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም።" የከተማዋ አስተዳዳሪዎች በአካባቢው ዳግም ተቃውሞና ረብሻ እንዳይነሳ በመፍራት ፕሬዝደንቱ ኬኖሻን ባይጎበኙ ይሻላል ቢሉም ዶናልድ ዛሬ ከሰዓቱን መገኛዬ እዚያ ነው ብለዋል። ትራምፕ ዴሞክራቶቹ የዊስኮንሰን ሃገረ ገዥና የከተማዋ ከንቲባ ሰላም ማስከበር አልቻሉም ሲሉ ይወቅሳሉ። ትራምፕ በመጪው ኅዳር ለሚከናወን የአሜሪካ ምርጫ ዋነኛ አጀንዳቸው አድርገው የያዙት ሕግና ሥርዓትን ማስከበር እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ይደመጣሉ። በቅርቡ ደግሞ የ29 ዓመቱ ጄኮብ ብሌክ በነጭ ፖሊስ ሰባት ጊዜ በጥይት መመታቱን ተከትሎ በርካታ ከተማዎች ተቃውሞ ሲያስተናግዱ ነበር። የጄኮብ አባት ከትራምፕ ጋር በመጨባበጥ ልጃቸውን ላይ የደረሰውን ጥቃት በፖለቲካ ለመሸፈን እንደማይሞክሩ ነው ለሲኤንኤን የተናገሩት። "ልጄ ከጥቂት ሳምንታት በፊት እየተሯሯጠ ከልጆቹ ጋር ይጫወት ነበር። ስልክ ደውሎልኝ እያወራን እንሳሳቅ ነበር። አሁን ግን እግሮቹን እንኳ ማንቀሳቀስ አይችልም።" ጄኮብ ብሌክን በጥይት በተደጋጋሚ መቶታል የተባለው ነጩ ፖሊስ ረስተን ሼስኪ ምርመራ እየተካሄደበት ስለሆነ በግዳጅ እረፍት እንዲወጣ ተደርጓል። ምንም እንኳ ትራምፕ የተጎጂውን ቤተሰብ አያግኙ ከተማዋን ይጎበኛሉ ተብሏል። ፕሬዝደንቱ በሰሞኑ ግርግር የወደሙ ንበረቶችን ይጎበኛሉ ይላል ከቤተ መንግሥታቸው የተለቀቀው መረጃ። በግርግሩ ወቅት ዘረኝነትን ተቃውመው ሰልፍ ከወጡ ሰዎች ጋር የትራምፕ ደጋፊዎች ተጋጭተዋል። በወቅቱ ሁለት ሰዎችን ገድሏል የተባለ አንድ ታዳጊን ድርጊት ፕሬዝደንቱ መከላከላቸው እያስወቀሳቸው ነው። ያለፉት ወራት አሜሪካ በፀረ-ዘረኝነት ተቃውሞ ከጥግ እስከ ጥግ የተናጠችበት ነው። ተቃውሞቹ የተቀሰቀሱት ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ በፖሊስ እጅ ከተገደለ በኋላ ነው።
news-50922447
https://www.bbc.com/amharic/news-50922447
በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንቅስቃሴ ላይ ጊዜያዊ ገደብ ተጣለ
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ከማደሪያ ክፍላቸው ውጪ የሚኖራቸው ቆይታ ከምሽቱ አራት ሰዓት እንዳያልፍ ይህም በተቆታጣሪዎች (ፕሮክተሮች) በየዕለቱ ክትትል እንዲደረግ መገለፁ ተሰምቷል።
እንዲሁም ዩኒቨርስቲዎቹ ተማሪዎች ከንጋት 12:00 ሠዓት በፊትና ከምሽት 1:00 ሰዓት በኋላ ከግቢ ውጪ እንዳይገኙ የተወሰነ ሲሆን፤ ይህንንም በግቢዎቹ ጥበቃ የፈረቃ ኃላፊዎች፣ የፌደራል እና የክልል ፀጥታ አካላት በዚህ ላይ መረጃ ተሰጥቷቸው እንዲያስፈፅሙ መወሰኑን በትናንትናው ዕለት የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቀወል። በሚኒስቴሩ የኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ደቻሳ ጉርሙ ይህ ውሳኔ "ጊዜያዊ ነው" በማለት ችግር ያጋጠማቸው የትምህርት ተቋማት ሰላም ከተረጋጋ እንደሚነሳ ለቢቢሲ ተናግረዋል። • ዩኒቨርስቲዎች በፌደራል ፖሊስ እንዲጠበቁ መወሰኑ ተገለፀ • ተማሪዎች በተመደቡበት ዩኒቨርስቲ ብቻ ነው መማር የሚችሉት- የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስቴሩ ያስቀመጠው የሰዓት ገደብ ለጥንቃቄ የተደረገ ነው ያሉት አቶ ደቻሳ ጉርሙ፤ በደብረ ብርሃንና በወለጋ ዩኒቨርስቲዎች የተገደሉ ሁለት ተማሪዎች ከዩኒቨርስቲዎቹ ቅጽር ግቢ ውጪ መሆኑን ያስታውሳሉ። ወለጋ ዩኒቨርስቲ ሞቶ የተገኘው ተማሪ የተገደለው አሳቻ ሰዓት መሆኑን በመጥቀስ፤ ጥፋተኛ ተብለው ከዩኒቨርስቲው የሚታገዱ ወይም የሚባረሩ ተማሪዎች ሌሎች አማራጮችን እንዳይጠቀሙ በሚቻለው አቅም ሁሉ ለተማሪዎቹ ሕይወት ሙሉ ጥንቃቄ ለማድረግ በሚል የተወሰነ መሆኑን ለቢቢሲ አብራርተዋል። በዚህ ዓመት በዩኒቨርስቲ ውስጥ በተነሳ ግጭት ከሞቱት ተማሪዎች መካከል አብዛኞቹ በግቢው ውስጥ እንዲሁም በማደሪያ ክፍላቸው አካባቢ መሆኑን የተጠየቁት አቶ ደቻሳ "ግቢ ውስጥ ያሉ ችግሮችን ለማሻሻል የፀጥታውን ሁኔታ አጠናክረናል፤ ውጪ ደግሞ እንዳይከሰት የተሻለ ጥንቃቄ ለማድረግ ይህ ውሳኔ ተወስኗል" ሲሉ መልሰዋል። በዩኒቨረስቲ ግቢ ውስጥ የተሻለ ጥበቃ አለ የሚሉት አቶ ደቻሳ የዩኒቨርስቲዎችን ሰላም ለማረጋገጥ በዩኒቨርስቲዎች በፌደራል ፖሊስ የሚካሄደው ጥበቃ ለውጥ እያመጣ ነው በማለት ለዚህም በአስረጅነት አዳዲስ ግጭቶች እየተነሱ አለመሆኑን ይጠቅሳሉ። በአማራና በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎችን ሰላም ለማጠናከር የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሚያስተባብረው የዩኒቨርስቲ የቦርድ አመራሮችና ባለስልጣናት ከአካባቢ ኃላፊዎችና የአገር ሽማግሌዎች የተካተቱበት ኮሚቴ ተዋቅሮ ሁሉንም የሚመለከታቸውን አካላት በማወያየት በዩኒቨርስቲዎች ዘላቂ ሰላም ማምጣት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል። ከዚህ ጎን ለጎን ሰላሙን ማስጠበቅና ጸጥታውን አስተማማኝ በማድረግ ተማሪዎችም ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ በሚል የፌደራል ፖሊስ ወደ ዩኒቨርስቲዎች መግባቱን አስታውሰው አሁን ያለው ሁኔታ ጥሩ መሆኑን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። • "ሙስና ለመጣው ፖለቲካዊ ለውጥ አንድ ምክንያት ነው" • አቶ ለማ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጎልተው የወጡባቸው አጋጣሚዎች "ግቢ ውስጥ ያለውን የፀጥታ ሂደት ስናጠናክር ከግቢ ውጪ እንዳይከሰትና የተኘው ሰላም እንዳይደፈርስ ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው" ብለዋል። በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ በየትኛውም ደረጃ ያለ ግለሰብ የፀጥታ ችግርና ተጠያቂ የሚሆን ከሆነ ተጠያቂ እናደርጋለን ያሉት አቶ ደቻሳ፤ ሰላማዊ የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ አባላት ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ከዩኒቨርስቲ ለቅቀው ወደቀያቸው የሄዱ ተማሪዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ነበሩባቸው ተቋማት እንዲመለሱ እንፈልጋለን ሲሉ ገልፀዋል። አክለውም ተማሪዎች ተመልሰው ትምህርታቸውን እንዲጀምሩ ጥሪ ቀርቧል ያሉት አቶ ደቻሳ፣ በሚኖሩበት አካባቢ በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ረብሻ ለማነሳሳት መሞከር ወንጀል ነው ሲሉም ተናግረዋል። የፀጥታ ችግር የታየባቸው 22 ዩኒቨርስቲዎች ተለይተው እየተሰራ ነው ያሉት አቶ ደቻሳ በእነዚህ ዩኒቨርስቲዎች የተወሰዱ የማስተካከያዎች እርምጃዎችን በተመከለተ የተጠቃለለ መረጃ እጃቸው ላይ እንደገባ እንደሚያስታውቁ ተናግረዋል። በተያያዘ ዜናም በግጭቶች ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ትምህርት በሁሉም የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከሚቀጥለው ሳምንት አንስቶ ይጀመራል ተባሏል። በሚኒስትሩ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ደቻሳ ጉርሙ ከግጭቶች ጋር ትምህርት ተቋርጦባቸው ከነበሩት ዩኒቨርስቲዎች አብዛኞቹ ትምህርት ጀምረዋል፤ ቀሪዎቹ ደግሞ ከሚቀጥለው ሳምንት አንስቶ ሙሉ በሙሉ ወደመደበኛ ትምህርት ይመለሳሉ ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
news-43207880
https://www.bbc.com/amharic/news-43207880
በአፍሪካ መዋዕለ-ንዋይ የማፍሰስ ዕድሎችና ፈተናዎች
በመገናኛ ብዙሃን ብዙ ጊዜ ስለ አፍሪካ ሲዘገብ የሚነገረው ረሃብ፣ ጦርነትና እልቂት የሞላባት ክፍለ ዓለም መሆንዋ ብቻ ነው።
እውነቱ ግን በአሁኑ ወቅት አፍሪካ፤ በውጪ ለሚኖሩ የብዙ ባለሃብቶች ትልቅ ኢንቨስትመንት ማዕከል መሆኗ ነው። ዶክተር ሓርነት በክረጽዮን አፍሪካውያኖች ይህን ዕድል በደንብ እንዲጠቀሙበት የሚያስችል 'አፍሪካ ቢዝነስ ጃምፕስታርት' የተሰኘ ፕሮጀክት በመንደፍና ተግባራዊ በማድረግ ብዙዎች ወደ አህጉሪቱ እንዲመጡ ለማድረግ ተግታ እየሰራች እንደሆነ ትገልፃለች። "የአፍሪካ ቢዝነስ ጃምፕስታርት ዋና ዓላማ በተለይም በአሜሪካና አውሮፓ የሚኖሩ አፍሪካውያን በተለያዩ ዘርፎች በአህጉሪቱ እንዲሰማሩ ለማበረታታትና ስልጠና ለመስጠትም ነው" ትላለች ዶከተር ሃርነት። ስልጠናዎቹና የንግድ ዕድሎቹ አፍሪካ ውስጥ ለሚኖሩም ጭምር ክፍት መሆኑን ገልጻለች። በአሁኑ ወቅት ንግድና ኢንቨስትመንት በአፍሪካ እያደገ መሆኑን በመጠቆም፤ አፍሪካውያን ታዛቢ ብቻ ከመሆን አልፈው በተፈጠረው ዕድል ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ በር መከፈቱን ዶክተር ሓርነት በአፅንኦት ትናገራለች። አፍሪካ ቢዝነስ ጃምፕስታርት የአፍሪካውያንን ዕውቀት በኢንቨስትመንት ዘርፍ ለማሳደግ ዋነኛና መሰረታዊ ዓላማው አድርጎ በመስራት ላይ ይገኛል። እስከ ዛሬ ይደረግ የነበረው የኤርትራዊያንና የኢትዮጵያዊያን ኢንቨስትመንት ተሞክሮንና ጥናትን መሠረት ያደረገ እንዳልነበረ ዶክተር ሃርነት ይገልፃሉ። "ኤርትራውያንና ኢትዮጵያውያንን ስንመለከት በፊት የነበሩትን ሃበሾች ዱካ በመከተል በአንጎላ፣ በደቡብ ሱዳን ወይም በኡጋንዳ መነገድ ነው የሚወዱት።" ሆኖም ግን እንደ አንጎላና ደቡብ ሱዳን ያሉት ሃገራት ውስጥ ንግድና የኢንቨስትመንት ዋስትና የሌለውና ለአደጋ የተጋለጠ ነው። በማለት ዶክተር ሓርነት በተነፃፃሪ ዋስትና ያላችው ሃገሮችን ጠቅሳለች። "እንደታንዛኒያ፣ ሩዋንዳ፣ ቦትስዋናና ጋናን የመሳሰሉ ሃገራት የተሻለ ዕድልና ዝቅተኛ ስጋት ያለባቸው ናችው። ስለዚህ አስፈላጊ ጥናት በማካሄድ ከአንጎላና ከደቡብ ሱዳን የተሻለ አማራጭ አለ።" በኤርትራና በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሁኔታ በሚመለከት ደግሞ፤ በተለይ ኤርትራ ውስጥ ለንግድ የሚመች ሁኔታ የሌለ መሆኑን የምትገልፀው ሓርነት የንግድ ፈቃድም እንደማይሰጥ አመልክታለች። በተመሳሳይ ኢትዮጵያ ውስጥም በቀላል መንገድ ንግድ መጀመር አይቻልም። ምክንያቱም የንግድ ፍቃድ በቀላሉ ስለማይገኝ። በተለይ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ለሌላቸው ሰዎች የሚታሰብ አይደለም። እንደ እርሻ፣ የውጭ ንግድና ማምረት በመሳሰሉ አንዳንድ ኢንዳስትሪዎች በኩል ግን ብዙ ዕድል እንዳለ ትናገራለች። ላለፉት 4 ዓመታት አፍሪካ ቢዝነስ ጃምፕስታርት ብዙ ሰዎችን በአንድነት በማሰባሰብ ሩዋንዳ ውስጥ የጥናታዊ ጉዞ እንዲያደርጉና ሃገሪቱ ውስጥ ያሉትን ዕድሎች በቅርብ እንዲዳስሱ አድርጓል። "ከእኔ ጋራ የተጓዙ ኤርትራውያንና ኢትዮጵያውያንን በጣም ነው የተገረሙት። ምክንያቱም ከዚህ በፊት የነበራቸው ተሞክሮ አንጎላ ወይም ደቡብ ሱዳን ብቻ በመሆኑ ነው።" "በሩዋንዳ ንግድ መክፈት በጣም ቀላል ነው። በ24 ሰዓታት ውስጥ የንግድ ፍቃድ ያለችግር ማግኘት ይቻላል። ሰለዚህ ሩዋንዳ ለመላው አፍሪካ ምሳሌ መሆን ትችላለች።" ዶክተር ሓረነት ጀርመን ተወልዳ ያደገች የሁለት ልጆች እናት ስትሆን በምግብ ዋስትናና የገጠር ዕድገት ዘርፍ ምሩቅ ነች። ለ13 ዓመታት በተባበሩት መንግሥታትና የአውሮፓ ህብረት እንደዚሁም በኦክስፋም ውስጥ የበላይ አማካሪ በመሆን በታላቋ ብሪታንያ፣ በኤርትራ፣ በሱዳንና በጀርመን ሰርታለች። አሁን ደግሞ የአፍሪካ ያልተነካ ሃብት ጥቅም ላይ ለማዋል በሚል ሃሳብ ነው ትኩረትዋን ወደ አፍሪካ ያደረገች።
news-46629557
https://www.bbc.com/amharic/news-46629557
ኮሚሽኑ ለምን አስፈለገ? ስልጣን እና ተግባሩስ?
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽንን ለማቋቋም የወጣውን ረቂቅ አዋጅ ከአምስት ሳምንታት በፊት ማጽደቁ ይታወሳል።
ከሁለት ቀናት በፊት ደግሞ የትግራይ ክልላዊ ምክር ቤት የኮሚሽኑን ማቋቋሚያ አዋጅ ውድቅ እንዲሆን የሚጠይቅ የውሳኔ ሐሳብ አጽድቋል። ምክር ቤቱ የኮሚሽን ማቋቋምያ አዋጁን ኢ-ሕገመንግስታዊ ነው ብሎታል። መንግሥት በበኩሉ የኮሚሽኑ መቋቋም፤ በክልሎች የአስተዳደር ወሰን፣ ራስን በራስ ማስተዳደርና በማንነት ጥያቄዎች ዙሪያ የሚታዩ ተደጋጋሚ ችግሮችን በማያዳግም መንገድ ለመፍታት ያስችላል ይላል። ታኅሣሥ 11 2011 ዓ.ም ረቂቅ አዋጁ የ313 የምክር ቤት አባላትን የይሁንታ ድምጽ አግኝቶ የነበረ ሲሆን 33 አባላት ደግሞ ተቃውመውታል። በተጨማሪም አራት ተወካዮች ድምጸ ተአቅቦ አድረገው ነበረ። •"በኢትዮጵያ ፖለቲካ የኦነግ ስም ቅመም ነው" የኦነግ የፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ 1. የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽንን ምንድነው? የአባላቱ ቁጥር በመንግሥት የሚወሰነው ይህ ኮሚሽን፤ ከአስተዳደር ወሰን እና ከማንነት ጥያቄዎች ጋር በተያየዘ ለሚነሱ ጥያቄዎች የመፍትሄ ሃሳቦችን ይሰነዝራል እንጂ ውሳኔ የማስተላለፍ ስልጣን የለውም። ኮሚሽኑን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ መሰረት ኮሚሽኑ ሥራውን በነጻነትና በገለልተኝነት ያከናውናል ተብሏል። 2. ኮሚሽኑ ለምን አስፈለገ? በሃገሪቱ ከአስተዳደር ወሰን እና ከማንነት ጥያቄዎች ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጥያቄዎች በተለያዩ አካባቢዎች ለአለመረጋጋት መንስዔ መሆናቸው በስፋት ይነገራል። መንግሥት የኮሚሽኑ መቋቋም፤ በክልሎች የአስተዳደር ወሰን፣ ራስን በራስ ማስተዳደርና በማንነት ጥያቄዎች ዙሪያ የሚታዩ ተደጋጋሚ ችግሮችን በማያዳግም መንገድ ለመፍታት ያስችላል ይላል። • "ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ ተስፋና ስጋት አለ" ኦባንግ ሜቶ ኮሚሽኑም ግልጽ እና ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ከአሰተዳደር ወሰኖች፣ ራስን በራስ ከማስተዳደር እንዲሁም ከማንነት ጋር የተያያዙ ግጭቶችን መንስዔ በመመርመር የመፍትሄ ሃሳቦችን ለህዝብ፣ ለሁለቱ ምክር ቤቶች እንዲሁም ለሥራ አስፈጻሚው አካል እንዲያቀርብ ነው የሚቋቋመው። 3. የኮሚሽኑ ስልጣን እና ተግባር ምንድነው? ከአስተዳደራዊ ወሰኖች አከላለል፣ ራስን በራስ ከማስተዳደር እንዲሁም ከማንነት ጥያቄ ጋር የተገናኙ ማናቸውንም አይነት ግጭቶችን በጥናት ለይቶ አማራጭ የመፍትሄ ሃሳቦችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት በሪፖርት መልክ ያቀርባል። ከአስተዳደራዊ ወሰኖች እና ከማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የተነሱ ግጭቶች ተፈተው፣ በአጎራባች ክልሎች መካከል ያለው መልካም ግንኙነት የሚታደስበትና የሚጠናከርበትን መንገድ የማመቻቸት ግዴታ ይኖርበታል ተብሏል። • ''የሚፈርስ የግድቡ አካል የለም'' የግድቡ ዋና ሥራ አስኪያጅ 4. የኮሚሽኑ አባላት እነማን ናቸው? ''በሥራ ልምዳቸው በማህበረሰቡ የተመሰገኑና መልካም ስም ያተረፉ ይሆናሉ'' ይላል አዋጁ፤ ስለ ኮሚሽኑ አባላት አሰያያም ሲዘረዝር። የኮሚሽኑ አባላት ቁጥር በመንግሥት የሚወሰን ሲሆን የኮሚሽኑ ሰብሳቢ፣ ምክትል ሰብሳቢ እና ሌሎች አባላት በጠቅላይ ሚንስትሩ አቅራቢነት በሕዝብ ወካዮች ምክር ቤት ይሰየማሉ። 5. በኮሚሽኑ መቋቋም ላይ የተነሱ ጥያቄዎች ምንድናቸው? የአዋጁን መጽደቅ የተቃወሙ የምክር ቤቱ አባላት፤ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው ክልሎች እና ባለድርሻ አካላት በረቂቅ አዋጁ ላይ በስፋት ሳይመክሩበት እና ሳይወያዩበት በጥድፊያ መጽደቁ ትክክል አይደለም በለዋል። ከዚህ በተጨማሪም ሕገ-መንግሥቱን ይጥሳል፤ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ስልጣንን ይጋፋል ብለዋል። • መፈናቀልና ግድያን የተቃወሙ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ግጭት በተቃራኒው የረቂቅ አዋጁን መጽደቅ የደገፉት በበሉላቸው፤ አዋጁ በሁለት ቋሚ ኮሚቴዎች ተመርምሮ ከሕገ-መንግሥቱ ጋርም ሆነ ከሌሎች አዋጆች ጋር እንደማይጋጭ ተረጋግጧል፤ ኮሚሽኑ ውሳኔ የማስተላለፍ አቅም ስለሌለው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ስልጣንን አይጋፋም ብለዋል።
news-52131803
https://www.bbc.com/amharic/news-52131803
ከኮሮናቫይረስ እያገገሙ ያሉ ምን ይላሉ? የ2 ወጣት ሴቶች ታሪክ
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በዓለም ላይ ተስፋፍቶ የብዙ ሰዎችን ህይወት እየቀጠፈ ቢሆንም የዚያኑ ያህል ቁጥራቸው በርካታ የሆኑት ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል። ነገር ግን በሽታው በአብዛኛው በእድሜ የገፉ ሰዎችን እንደሚያጠቃ ቢነገርም በርካታ ወጣቶች እየተያዙ እንደሆነ ዘገባዎች ያመለክታሉ።
ጄሲ ክላርክ ሆስፒታል ውስጥ እያለች ከእነዚህም ውስጥ በበሽታው ክፉኛ ታመው ወደ ሆስፒታል በመግባት ያገገሙ ሁለት ወጣቶች ስለበሽታውና ስላለፉበት ሁኔታ እንደሚከተለው ይተርካሉ። "ለነፍሴም ለልጄም ተጨነቅኩ" ካረን እባላለሁ፤ እንግሊዝ ኬንት ነው የምኖረው። የ6 ወር እርጉዝ ነ ነኝ። በየካቲት ወር 2ኛ ሳምንት ድንገት ሳል ጀመረኝ። ቀጥሎ ደግሞ አተነፋፈሴ ተቀየረ። ቶሎ ብዬ 999 ደወልኩ። በደቂቃዎች ውስጥ አምቡላንስ ቤቴ ደጅ ደረሰ። ለመተንፈስ ስለተቸገርኩ ወደ ሆስፒታል የደረስኩት አምቡላንስ ውስጥ በኦክሲጂን ታግዤ ነበር። ምርመራ ሲደረግልኝ ኮቪድ-19 እንደሆነ ደረሱበት። ሁለቱም ሳምባዎቼ በሳምባ ምች ተጠቅተዋል። ለብቻዬ ተነጥዬ አልጋ ያዝኩ። ማንም አይጎበኘኝም። ማንም እንዲያየኝ አይፈቀድም። ይህ ቀላል አይደለም። እንዴት ከባድ ጊዜ እንዳሳለፍኩ! በወቅቱ ከአልጋዬ ጋ ተጣብቄ መጸዳጃ ቤት እንኳ መሄድ አልችልም ነበር። የአልጋውን አንሶላ የሚቀይሩልኝ ራሱ እኔን ወደ ሌላ አቅጣጫ በጎኔ ገልብጠው ነው። ትንፋሽ ደጋግሞ ያጥረኝ ነበር፤ የምሞት የምሞት ስለሚመስለኝ ልክ መተንፈስ ሲያቅተኝ ቶሎ ጤና ረዳቶቹን ድረሱልኝ እላለሁ። እነሱ ለባብሰውና በሽታው እንዳይተላለፍባቸው ጭምብላቸውን በጥንቃቄ አጥልቀው እስኪመጡ ጭንቅ ነው። ሻል ባለኝ ቁጥር ከቤተሰቤ ጋር በስልክ ለረዥም ደቂቃዎች አወራለሁ። ያን የማደርገው ፍርሃትን ለማሸነፍ ስል ነው። ልሞት እንደምችል ስለተረዳሁ ይህንኑ እነግራቸዋለሁ፤ ቤተሰቤቦቼ ለማይቀረው ክፉ ቀን መዘጋጀታቸውን ይነግሩኛል፤ በዚያ መጠን ግን ተስፋንም ይሰጡኛል። ለእያንዳንዷ እስትንፋሴ እታገል ነበር፤ በዚያ ላይ ሁለት ነፍስ ነበርኩ፤ ለሁለት ነፍስ ነበር የምታገለው። ልጄ እንዳይሞትብኝ አብዝቼ እጨነቅ ነበር። በሂደት እያገገምኩ ስመጣ ከሆስፒታል መውጣትና ቤቴ ውስጥ ራሴን አግልዬ ማገገም እንደምችል ተነገረኝ። መጀመሪያ ከሆስፒታሉ በር ወጥቼ ንፋስ ፊቴን ሲገርፈኝ የተሰማኝን ደስታ በቃላት ልገልጸው አልችልም። አስታውሳለሁ ከባሌ ጋር ነበርኩ። የፊት ጭንብል አጥልቀናል። የመኪናው መስኮት ክፍት ነበር። ድንገት ነፋሱ ሲመታኝ አቤት እንዴት ደስ እንዳለኝ! ለእያንዳንዷ ጥቃቅን ስጦታ ማመስገን እንደጀመርኩ ያወቅኩት ያኔ ነበር። ካረን ከባለቤቷ ጋር እየፈራሁት ነው የያዘኝ… ጄሴ ክላርክ እባላለሁ። 26 ዓመቴ ነው። አገሬ እንግሊዝ፤ ሼፍልድ ነው። ኮሮናቫይረስ ቢይዘኝ ችግር ላይ እንደምወድቅ ገና ከመጀመርያው ታውቆኝ ነበር። ምክንያቱም ከአምስት ዓመት በፊት ኩላሊቴን ታምሜ አስወጥቻለሁ። ኮሮናቫይረስ ደግሞ ተጨማሪ ህመም ባለበት ሰው እንደሚበረታ ስለማውቅ… ምን ዋጋ አለው ታዲያ! ድንገት ያስለኝ ጀመር። ቀጠለና ለመተንፈስ ያዳግተኝ ጀመር። ሆዴ አካባቢና ጎንና ጎኔ ሕመም ተሰማኝ። እውነት ለመናገር የሆነ ሰው በዱላ የደበደበኝ ያህል ነበር የሚሰማኝ። ጠቅላይ ሚኒስራችን ቦሪስ ጆንሰን 'ቤት አርፋችሁ ተቀመጡ' ያለ ቀን እጮኛዬ ወደ ድንገተኛ ክፍል ወሰደኝ። እዚያ እንደደረስን ቶሎ ተለያየን፤ ምክንያቱም ተራራቁ ስለተባለ። አብሮኝ ሊገባም አይችልም። በእውነቱ ብቻዬን መሆን በጣም ነበር ያስፈራኝ፡፡ የሆነ ሰው አብሮኝ እንዲሆን፤ አለሁልሽ እንዲለኝ ነበር ፍላጎቴ። በድንገተኛ ክፍል አረንጓዴ የፊት ጭንብል ተሰጠኝ። ከዚያ ለኮሮናቫይረስ ታማሚዎች ወደተዘጋጀ ስፍራ ወሰዱኝ። እዚያ ለደህንነታችን ሲባል አልጋችን ተራርቆ ነበር የተዘረጋው። እስከዚያ ሰዓት ድረስ ኮቪድ-19 እንዳለብኝ አልታወቀም። ምክንያቱም አልተመረመርኩማ። ሐኪሜ እንደነገረኝ ሁሉንም ድንገተኛ ክፍል የመጣን ሰው ለመመርመር በቂ መሣሪያ የለም። በዚያ ሰዓት ሳምባዬ አካባቢ የማቃጠል ስሜት ነበር የሚሰማኝ። የህመም ማስታገሻ ተሰጠኝ። ለ6 ሰዓት ድንገተኛ ክፍል ቆየሁ። እጮኛዬ ያን ሁሉ ሰዓት መኪና ውስጥ ደጅ እየጠበቀኝ ነበር። በመጨረሻ ኮሮናቫይረስ ተገኘብኝ። እጮኛዬ ሥራው ከህመምተኞች ጋር ስለሚገናኝ ምናልባት እሱ አስተላልፎብኝ እንደሆነ እገምታለሁ። ምክንያቱም እሱ ምልክት የማያሳይ የኮሮናቫይረስ ተጠቂ (asymptomatic) እንደሆነ ተደርሶበታል። ከቀናት ህክምና በኋላ ከሆስፒታል ብወጣም አሁንም ራሴን ለይቼ በማገገም ላይ ነው ያለሁት። የተረዳሁት ነገር ቢኖር እኛ ወጣቶችም ለኮሮናቫይረስ ተጋላጭ እንደሆንን ነው። ኮሮናቫይረስ የአዛውንቶች በሽታ ነው የሚለው አመለካከት ፉርሽ ነው።
news-45120745
https://www.bbc.com/amharic/news-45120745
በኤሌክትሪክ ኃይል ታሪፍ ላይ ጭማሪ ሊደረግ ነው
በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚዎች ላይ የታሪፍ ጭማሪ ለማድረግ አስፈላጊው ሂደት መጀመሩን የኢትዮጵያ ኢነርጂ ባለስልጣን ሲያስታውቅ፤ ማሻሻያው ዝቅተኛ የኃይል ተጠቃሚዎችን እንደማይነካ ባለስልጣኑ ገልጿል።
ይህንን ለቢቢሲ የተናገሩት የኢትዮጵያ ኢነርጂ ባለስልጣን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጌታሁን ሞገስ ሲሆኑ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ጭማሪው በተለያዩ ደረጃዎች አልፎ ተቀባይነት ሲያገኝ ተግባራዊ እንደሚሆን ተናግረዋል። አቶ ጌታሁን የታሪፍ ጭማሪ ማድረግ ያስፈለገበትን ምክንያት ሲያብራሩ፤ ለመጨረሻ ጊዜ የታሪፍ ጭማሪ ተደርጎ የነበረው ከ12 ዓመታት በፊት እንደነበረ አስታውሰው ''በየዓመቱ ከ10-15 በመቶ ድረስ የዋጋ ግሽበት ነበር፤ የውጪ ምንዛሬ ዋጋ ላይም ከፍተኛ ለውጥ አለ" ብለዋል። እንደዳይሬክተሩ "ከዚህ በተጨማሪ መስሪያ ቤቱ እስከ 60 በመቶ የሚሆኑ የካፒታል ዕቃዎችን ገዝቶ ነው የሚያስገባው በውጪ ምንዛሬ ነው። ከዚህ በተጨማሪ መስሪያ ቤቱ በስፋት የሚጠቀምባቸው ብረት እና የምህንድስና ዕቃዎች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ስላለ የዋጋ ማሻሻያ እንደናደርግ ግድ ብሎናል።'' ይላሉ። • የብርሃን ዋጋ ስንት ነው? • ኢትዮ-ቴሌኮም፡ አንድ ወደፊት ሁለት ወደኋላ? • በሞባይልዎ የኢንተርኔት ወጪ ተማረዋል? ይህ ጭማሪ ሳይሆን ማስተካከያ ነው የሚሉት ዳይሬክተሩ ''መስሪያ ቤታችን በቂ ገንዘብ ከተጠቃሚዎች መሰብሰብ ባለመቻሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ላይ ተደጋጋሚ ቅሬታን ሲያስነሳብን ነበር'' ብለዋል። ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ጋር ሲነጻጸር ኢትዮጵያዊያን ለኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚጠይቁት ገንዘብ አነስተኛ እንደሆነ የሚናገሩት አቶ ጌታሁን፤ ''በሌሎች ሃገራት በየሦስት እና አራት ዓመቱ የዋጋ ማሻሻያ ማድረግ የተለመደ ነው እኛ ሃገር ግን ላለፉት 12 ዓመታት አልተደረገም'' ይላሉ። ብሔራዊ የኤሌትሪክ ታሪፍ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጎ የሚሰጡ ግብረ መልሶችን ካካተተ በኋላ የተጠቃለለ የውሳኔ ሃሳብ ለሚመለከተው የመንግሥት አካል ቀርቦ ይጸድቃል እንደሚፀድቅ አቶ ጌታሁን ለቢቢሲ ተናግረዋል። አዲሱ ታሪፍ መቼ ወደ ሥራ ሊገባ እንደሚችል ለቀረበላቸው ጥያቄም ትክክለኛ ቀኑን መናገር እንደማይችሉ ነገር ግን አዲሱ ታሪፍ በአስቸኳይ ወደ ሥራ እንዲገባ የኢነርጂ ባለስልጣን ፍላጎት መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል። ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉት የመስሪያ ቤቱ ደንበኞች ከፍጆታ መጠናቸው አንጻር ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች በመሆናቸው፤ በእነዚህ ደንበኞች ላይ የሚጣል ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ እንደማይኖር ያስረዱት አቶ ጌታሁን፤ ከፍተኛ የኤሌትሪክ ፍጆታ የሚጠቀሙ አነስተኛ ኃይል የሚጠቀሙትን እንዲደግፉ የሚያደርግ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለውን አሰራር እንደሚዘረጋ ተናግረዋል።
news-49982798
https://www.bbc.com/amharic/news-49982798
ትዊተር በስህተት ኢሜል አድራሻዎችን ለማስታወቂያ በመጠቀሙ ይቅርታ ጠየቀ
ትዊተር በስህተት ደንበኞቹ ለአካውንታቸው ደህንንት በሚል ያስገቡትን ኢሜል አድራሻና የስልክ ቁጥር ለማስታወቂያ በመጠቀሙ ይቅርታ ጠየቀ።
ኩባንያው እንዳለው ሶስተኛ ወገን ማስታወቂያ ድርጅቶች የተለዩ የትዊተር ተጠቃሚዎችን ዝርዝር መረጃዎች በመጠቀም፣ ተጠቃሚው መረጃው በዚህ መልክ ጥቅም ላይ እንዳይውል ፍላጎት ሳይኖረው፣ ማስታወቂያ ልከውላቸዋል። ትዊተር በመግለጫው "ምን ያህል ሰው በዚህ ምክንያት እንደተጎዳ ማረጋገጥ አልቻልንም" ያለ ቢሆንም ቢቢሲ ግን በመላው ዓለም ያሉ የትዊተር ተጠቃሚዎች በዚህ ጉዳይ ሰለባ መሆናቸውን አረጋግጧል። • እየበረታ በመሄድ ላይ ያለው የዋጋ ንረት አዙሪት • የጨለቆት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የተዘረፈው ዘውድ ይመለስልኝ እያለች ነው • በአፍሪካ የመጀመሪያው ስማርት ስልክ ማምረቻ ፋብሪካ በሩዋንዳ ተከፈተ ብዙ ጊዜ ኩባንያው ደንበኞቹን በቀጥታ ለማግኘትና እንዲህ ዓይነት መረጃዎችን ለማስተላለፍ ፈጣን አይደለም። ኩባንያው ችግሩ መቼ እንደተፈጠረ ያለው ነገር የለም። ነገር ግን እኤአ ከመስከረም 17 (ከ21 ቀን በፊት) ጀምሮ መሆኑን ገልጧል። ድርጅቱ አክሎም ለደህንንት ሲባል የተሰበሰቡ የስልክና የኢሜል አድራሻዎችን ለማስታወቂያ ከአሁን በኋላ እንደማይጠቀም አስታውቋል። ትዊተር በመላውዓለም በየቀኑ 139 ሚሊየን ተጠቃሚዎች ሲኖሩት ማስታወቂያ በገፃቸው ላይ እንደሚለቀቅም ይናገራል። ትዊተር ለማስታወቂያ አስነጋሪዎች በግላቸው ተሰብስቦ በእጃቸው የሚገኙ የኢሜል አድራሻዎችን እርሱ ጋር ካሉ አድራሻዎች ጋር በማመሳከር ማስታወቂያ በገፃቸው ላይ ይለቅቃል። ይህ አሰራር በማህበራዊ መገናኛ ብዙኃን ኩባንያዎች ዘንድ የተለመደ ሲሆን በዚህ ከምርቶች ጋር የበለጠ ቅርበትና ትስስር ያላቸውን የተመረጡ ደንበኞችን ታላሚ ያደረገ የማስተዋወቂያ ስልት ተደርጎ ይወሰዳል። አሁን ግን ትዊተር በመግለጫው ላይ እንዳሰፈረው ከማስታወቂያ ድርጅቶች ጋር ያላቸውን ኢሜል አድራሻ ከማመሳከር ይልቅ በቀጥታ ተጠቃሚዎች ለአካውንታቸው ደህንነት የተጠቀሙትን ስልክና ኢሜል አድራሻ በጅምላ ለማስታወቂያ አገልግሎት መዋሉን ነው። "የማስታወቂያ ድርጅቶች የገበያ ዝርዝራቸውን ሲያስገቡ እኛ ትዊተር ላይ ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ፍላጎት ያላቸውን ደንበኞች ለደህንነት ማስጠበቂያ ያስገቡትን ስልክ ወይንም ኢሜል አድራሻ እናዛምዳለን። ይህ ደግሞ ስህተት ነው፤ ለዚህም ይቅርታ እንጠይቃለን" ብሏል ኩባንያው። ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ፌስቡክ ደንበኞቹ ለደህንነታቸው ሲሉ የተጠቀሙትን የኢሜል አድራሻ ለማስታወቂያ ተጠቅሞበታል በሚል ጠንከር ያለ ትችት ተሰንዝሮበት ነበር። ፌስቤቡክ ግን ጉዳዩን በስህተት ነው ሲል አልገለፀውም።
52378022
https://www.bbc.com/amharic/52378022
ኮሮናቫይረስ፡ ፌስቡክ ከእንግሊዛውያን የኮቪድ-19 ምልክቶች ከታዩባቸው መረጃ ሊሰበስብ ነው
በዩናይትድ ኪንግደም ፌስቡክ የተመረጡ ተጠቃሚዎቹን የኮቪድ-19 ምልክት እንደታየባቸውና እንዳልታየባቸው ዛሬ ሊጠይቅ መሆኑ ተሰማ።
ፌስቡክ ይህንን የሚያደርገው ከካርኒጌ ሜለን ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ሲሆን የቫይረሱን ስርጭት ለማወቅ ይረዳል ተብሏል። ፌስቡክ የተጠቃሚዎቹን የጤና መረጃ እንደማይዝና በቀጥታ ወደ ዩኒቨርስቲው እንደሚያስተላልፍ አስታውቋል። • የበርሊን ማራቶን መቼ እንደሚካሄድ አልታወቀም • ኢትዮጵያን ጨምሮ አስር የዓለም አገራት ከፍተኛ የረሃብ አደጋ ተደቅኖባቸዋል-የዓለም ምግብ ድርጅት • አሜሪካ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ መስጠት ልታቆም ነው አንድ ባለሙያ የሚገኘው መረጃ ለተመራማሪዎች ጠቃሚ ነው ያሉ ሲሆን ነገር ግን በራሱ ምልክቱ መታየቱ ብቻ ሳይሆን ስለ በሽታው የበለጠ በመግለጽ መሆን አለበት ብለዋል። የዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ፌስቡክ በአሜሪካ እንዲህ አይነት የዳሰሳ ጥናት ያደረገ ሲሆን በሳምንት ውስጥ በሚሊየን የሚቆጠር ምላሽ አግኝቷል። የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ስለጤንነታቸውና መሰረታዊ የሆኑ የኮቪድ-19 ምልክቶችን እንደ ሳልና ትኩሳት ያሉ ታይቶባቸው ከሆነ ይጠየቃሉ። የካርኒጌ ሜለን ዩኒቨርስቲ ምሁራን በሳምንት ውስጥ መረጃውን ከወሰዱ በኋላ ደግሞ በየአካባቢው ያሉ ኮቪድ-19 የሚያክሙ ሆስፒታሎችና የጽኑ ሕሙማን ክፍሎች ምን ያህል ሕሙማን ሊጎበኟቸው እንደሚችሉ ትንበያ ይሰራሉ። ፌስቡክ በአሜሪካ በየአካባቢው ምልክቱን ያሳዩ ሰዎችን የሚያሳይ ካርታ አትሟል። በሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪ የሆኑት ማሪቺዮ ሳንቲላና ፕሮጀክቱ " በጣም ጠቃሚ ነው" ብለዋል። " ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በህብረተሰቡ ውስጥ ያለውን የስርጭት መጠን በመገመት ረገድ ትልልቅ ተግዳሮቶችን ከፊታችን እየደቀነ ነው" ሲሊ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "በርካታ መረጃ ባገኘን ቁጥር እጅግ የተሻለ ይሆናል" ሲሉም ያክላሉ። ነገር ግን አንድን የመረጃ ምንጭ ብቻ ማመን መልካም አለመሆኑን በመጥቀስ የፌስቡክ መረጃንም ለሌሎች መረጃዎች እንደ ግብዓት ብንጠቀመው ይሻላል ይላሉ። ዶ/ር ሳንሪላና ህብረተሰቡን ስለጤናው የሚጠይቁ መተግበሪያዎችና የዳሰሳ ጥናቶች ሰፊ ምላሽ አያገኙም ሲሉ ያስጠነቅቃሉ። "በየሳምንቱ ስለጤንነታችን የሚጠይቀን መተግበሪያ አይተናል። መጀመሪያ ላይ ሁሉም ሰው በንቃት ይሳተፋል፤ ከዚያም ቀናት እየጨመረ ሲሄዱ የተሳታፊዎቹ ቁጥር እየቀነሰ ይሄዳል" ብለዋል። ስለዚህም ቫይረሱ በህብረተሰቡ ውስጥ በቆየ ቁጥር መተግበሪያዎቹን የመሰልቸት ስሜት ኣዳብራል ሲሉ ተናግረዋል።
news-56440710
https://www.bbc.com/amharic/news-56440710
የቢል ጌትስን፣ የኦባማንና የኤለን መስክን ትዊተር ገጽ የመነተፈው ወጣት ተፈረደበት
አሜሪካዊው የ17 ዓመት ወጣት የሥመ ጥር ሰዎችን የትዊተር ገጽ ሰርስሮ በመግባት የማጭበርበር ወንጀል በመፈጸሙ ጥፋተኛ ተባለ፡፡
ወጣቱ ግራሐም ኢቫን ክላርክ ይባላል፡፡ ይህንን ወንጀል ሲፈጽም እድሜው 17 ነበር፡፡ አሁን 18ኛ ዓመቱን ይዟል፡፡ ወጣቱ ከቢትኮይን የዲጂታል ገንዘብ ጋር በተያያዘ ነው የማጭበርበር ወንጀሉን የፈጸመው፡፡ መጀመርያ የሥመጥርና ገናና ሰዎችን የትዊተር አካውንቶች በመጥለፍና ሰርስሮ በመግባት ገንዘብ ለማሰባሰብ ሞክሯል፡፡ የትዊተር ገጻቸው በወጣቱ ከተመነተፈባቸው ሥመጥሮች መካከል የቲቪ ዝነኞች ቁንጮ ኪም ካርዳሺያን ዌስት፣ ቢሊየነሮቹ ኤለን መስክና ቢልጌትስ፣ እንዲሁም የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ይገኙበታል፡፡ ይህ ወጣት ምንተፋውን ካቀነባበረ በኋላ በዝነኞቹ የትዊተር ገጽ ላይ ተከታዮቻቸው ገንዘብ እንዲረዱ የሚጠይቅ ጽሑፍ ለጥፏል፡፡ ለምሳሌ የቢሊየነሩን ቢልጌትስ አካውንት ሰርስሮ ከገባ በኋላ እንዲህ ሲል ሐሰተኛ መልእክት አስተላልፏል፡፡ ‹‹ሰዎች ከሐብቴ እየቀነስኩ በቢትኮይን ለኮቪድ ተጠቂዎች እርዳታ እንዳደርግ ጠይቀውኛል፡፡ እነሆ እናንተ 1ሺ ዶላር ስትልኩልኝ እኔ በአድራሻችሁ 2ሺ ዶላር እልካለሁ›› በዚህ ሐሳዊ ዘዴ ወጣቱ 117ሺ ዶላር የሚገመት የክሪፕቶከረንሲ ገንዘብ መመንተፍ ችሏል፡፡ ወጣቱ በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ ግን ያጭበረበረውን ገንዘብ በማመኑ ገንዘቡ ወደተመዘበረባቸው ሰዎች እንዲመለስ ሆኗል፡፡ የ17 ዓመቱ ወጣት አሁን በፍሎሪካ ፍርድ ቤት ለ3 ዓመት ዘብጥይ እንዲወርድ ተወስኖበታል፡፡ ከዚህ በኋላም ኮምፒውተር ሲጠቀም ከተቆጣጣሪ/ከጸጥታ ኃይሎች ጋር እንጂ ብቻውን ድርሽ እንዳይል ፍርድ ቤቱ በይኗል፡፡
news-56899180
https://www.bbc.com/amharic/news-56899180
ደቡብ ሱዳን ወደለየለት ጦርነት ልትገባ እንደምትችል የተባበሩት መንግሥታት አስጠነቀቀ
የተባበሩት መንግሥታት ደቡብ ሱዳን ወደ ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር እያደረገች ያለው ጉዞ ቀርፋፋ መሆኑ ከፍ ወዳለ ግጭት ሊያመራ ይችላል ሲል ስጋቱን ገለጸ።
በፕሬዝደንት ሳልቫ ኪርና ድርጅቱ እንዳለው ደቡብ ሱዳን ወደ ሰላማዊ መንገድ መምጣት ካልቻለች ወደ ቀድሞው ዓይነት ግጭት ልትመለስ ትችላለች። አንድ አዲስ የወጣ ሪፖርት እንደሚያሳየው የጦር መሣሪያ ዝውውር ማዕቀብ እንዲጣልና የሰላም ሂደቱን የሚያደናቅፉ ሰዎች እንዲቀጡ ሐሳብ አለ። የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት የተፈረመው ከሦስት ዓመት በፊት ነበር። ነገር ግን ከዚህ ስምምነት በኋላ በፕሬዝደንት ሳልቫ ኪርና በተቀናቃኛቸው ሪዬክ ማቻር ደጋፊዎች መካከል በርካታ ግጭቶች ተካሂደዋል። ከሰላም ስምምነት በፊት የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝደንት የነበሩት ሪዬክ ማቻር ከስምምነቱ በኋላ ይህን ሥልጣናቸውን መልሰው ማግኘታቸው አይዘነጋም። ነገር ግን ደጋፊዎቻቸው አሁንም ከሳልቫ ኪር ኃይሎች ጋር መፋለማቸውን እንደቀጠሉ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት እንደሚያሳየው ይህ ግጭት ሰብዓዊ እርዳታዎች በሰላም እንዳይደርሱ እያደናቀፈ ነው። በሁለቱ ኃይሎች መካከል በሚከሰቱ ግጭቶች ሳቢያ በርካታ ደቡብ ሱዳናውያን እርዳታ ጠባቂ ለመሆን ተገደዋል። ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ደቡብ ሱዳን ላይ ተጥሎ የሚገኘው የጦር መሳሪያ ማዕቀብ ለአንድ ዓመት እንዲራዘመ ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል። የአሜሪካ መንግሥት በተመረጡ የደቡብ ሱዳን መንግሥት ባለስልጣናት ላይ ማዕቀቦችን ጥሎ ይገኛል። ማዕቀብ ከተጣለባቸው መካከል የቀድሞ ምክትል ፕሬዝደንት ታባን ዴንግ ጋይ ይገኙበታል። የቀድሞው ፕሬዝደንት ንብረቶቻቸውን እንዳያንቀሳቅሱ በአሜሪካ እግድ ተጥሎባቸዋል። ደቡብ ሱዳን ከየት ወዴት? ስምምነቱ ስድስት ዓመት የዘለቀውንና ከ400 ሺህ በላይ ሰላማዊ ዜጎችን ሕይወት የቀጠፈው እንዲሁም ከ12 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ያፈናቀለውን የደቡብ ሱዳናውያን የእርስ በእርስ ጦርነት ያስቆማል የሚል ተስፋ ተጥሎበት ነበር። ደቡብ ሱዳን ረዥም ዓመት ከወሰደው ደም አፋሳሽ የእርስ በእርስ ጦርነት በኋላ ከሱዳን ተለይታ ራሷን የቻለች አገር የሆነችው እኤአ በ2011 ነው። ፕሬዝዳንት ኪር ምክትል ፕሬዝዳንታቸው የነበሩትን ማቻርን ከስልጣናቸው ካነሱ በኋላ ደቡብ ሱዳን በወርሃ ታኅሣሥ 2013 ወደለየለት የእርስ በእርስ ጦርነት ገብታለች። በወቅቱ ፕሬዝዳንት ኪር፣ ማቻር መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ እያሴሩ ነው ብለው የወነጀሏቸው ቢሆንም ማቻር ግን አስተባብለዋል። በደቡብ ሱዳን የተካሄደው የእርስ በእርስ ጦርነት ፖለቲካዊ አለመግባባት የፈጠረው ቢሆንም የጎሳና የኃይል ክፍፍል መልክም አለው። የደቡብ ሱዳን ሁለት ትልልቅ ጎሳዎች ዲንካና ኑዌር ሁለቱ የፖለቲካ አመራሮች የተገኙባቸው ሲሆን አንዳቸው ሌላኛቸውን ወገን ማጥቃታቸውን በመጥቀስ ይወነጃጀላሉ።
47972744
https://www.bbc.com/amharic/47972744
የጌዲዮ ተፈናቃዮች የከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት አጋጥሟቸዋል
ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን በደቡብ ኢትዮጵያ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች በአሳሳቢ የምግብ እጥረት ውስጥ ይገኛሉ አለ።
በመጠለያዎቹ ውስጥ በርካታ ነብሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች ይገኛሉ በመጋቢት ወር የድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን በአንድ መጠለያ ስፍራ ብቻ በሚገኙ ሕፃናት ላይ ያየውን የምግብ እጥረት "ድንገተኛ ከሚባለው ወለል በላይ ያለፈ" ነው ብሎታል። አክሎም ቡድኑ በምግብ እጥረት እጅጉን የተጎዱ ነብሰ ጡር እናቶችንም መመልከቱን አትቷል። • ጌዲዮ በዐቢይ ጉብኝት ማግስት • በጉጂ እና ጌዲዮ ግጭት ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቀሉ "የመጠለያ ጣቢያዎቹ እጅጉን የተጨናነቁ መሆናቸውን በአስከፊ የኑሮ ሁኔታ ላይ መገኘት እንዲሁም ተፈናቃዮቹ ወረርሽኝ ሊከሰት በሚችልበት ሁኔታ ውስጥ መኖራቸውን ተመልክተናል። ተፈናቃዮቹ በተደጋጋሚ ቀያቸውን እንዲለቁ መሆኑ ጤናቸው አስጊ በሆነበት ሁኔታ እንዲኖሩ አድርጓቸዋል።" ብለዋል በስፍራው ያሉት የድንበር የለሽ ሐኪሞች ማህበር የመስክ ባለሙያና አስተባባሪ ማርከስ ቦይኒንግ። ድንበር የለሽ የሐኪሞች ከአካባቢው አስተዳደር ጋር የተፈናቃዮቹን የሚያገኙትን ምግብ ለማሻሻል እየሰራ ይገኛል። የመፈናቀሉ መንስዔ ምንድን ነው? ለአሁኑ ሰብአዊ ቀውስ ምክንያት የሆነው መፈናቀል የጀመረው፤ ባለፈው ዓመት በጉጂ እና በጌዲዮ ተወላጆች መካከል ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ ነው። ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር ላይ፤ በሁለቱም ማህበረሰቦች መካከል በተነሳ ግጭት ሰዎች መሞታቸው፣ ቤቶች መቃጠላቸው እና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቀዬያቸውን ጥለው መሰደዳቸው ተዘግቦ ነበር። • በጉጂ እና ጌዲዮ ግጭት ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቀሉ ይህን ተከትሎም ሰዎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው ተሰደዱ። ብዙ የጌዲዮ ተወላጆችም ከምዕራብ ጉጂ ዞን ተፈናቅለው ጌዲዮ ዞን ወደሚገኙ አካባቢዎች ገብተው መጠለል ጀመሩ። ከጉጂዎች በኩልም የተፈናቀሉ እንዳሉም ይነገራል።
news-53791654
https://www.bbc.com/amharic/news-53791654
ሐሰተኛ ዜና፡ አነጋጋሪው የሩሲያ የኮሮናቫይረስ ክትባትና የፑቲን ጉዳይ
ሩሲያ ላለፉት ወራት ሙከራ ስታደርግበት የነበረው ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ፍቃድ መስጠቷን ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን ካሳወቁ በኋላ፤ በርካቶች ክትባቱ ላይ ጥያቄ አንስተዋል።
በዓለም ዙሪያ ክትባቶች ላይ ሙከራ እየተደረገ ነው ስለ ክትባቱ ሐሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ቀልድ አዘል አስተያየቶች እየሰነዘሩ ነው። ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ብዙዎች ከተጋሯቸው ሐሳቦች ጥቂቱን እንመልከት። ‘ጀግናው ፑቲን’ ፑቲንን በተመለከተ በተለያዩ ቋንቋዎች የለበጣ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ነው። በሆሊውድ ፊልሞች የሚታወቁ እንደ ስፓይደርማን እና አይረንማን ያሉ ልቦወለዳዊ ጀግኖችን ከፑቲን ጋር ያነጻጸሩ አሉ። በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት ከተሰራጩ ፎቶዎች አንዱ ፑቲን ትልቅ የክትባት መርፌ ጀርባቸው ላይ አድርገው ድብ ሲጋልቡ ያሳያል። ይህንን ፎቶ ፑቲን ራሳቸው አጋርተውታል የሚል ሐሰተኛ ወሬም ሲናፈስ ነበር። ፑቲንን የሚደግፍ የፌስቡክ ገጽ ላይ ክትባቱን የሚደግፍ ጽሁፍ 200 ሺህ ጊዜ ተሰራጭቷል። ይፋዊ የፑቲን ገጽ ባይሆንም በርካቶች የፕሬዘዳንቱ እንደሆነ ያምናሉ። በእርግጥ ፑቲን እምብዛም ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ አይገኙም። በገጹ ላይ በርካታ ተመልካች ያገኘው ፎቶ የመጀመሪያውን የሶቪየት ኅብረት ሳተላይት ከኮቪድ-19 ክትባት ጋር ያነጻጽራል። ሳተላይቱ “በሕዋ ለሰው ልጆች መንገድ የጠረገ ነው”፣ ክትባቱ ደግሞ “የሰው ልጆችን ከአፍና አፍንጫ መሸፈኛ እንዲሁም ከአካላዊ ርቀት የሚታደግ ነው” ተብሏል። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የክትባቱ አስተማማኝነት ላይ ጥያቄ ከማንሳቱ ባሻገር፤ የዓለም ጤና ድርጅት ሩሲያ ዓለም አቀፍ ሕግጋትን እንድታከብር አሳስቧል። የተጋነነ ዜና አንድ ፌስቡክ ላይ የወጣ ጽሁፍ “ሩሲያ በተደጋጋሚ በክትባት ዓለምን ታድጋለች” ይላል። የቀዝቃዛው ጦርነት የበሽታ ቁጥጥር የታሪክ ምሁሩ ዶ/ር ዶራ ቬራጋ አስተያየቱ “የተጋነነ” ነው ሲሉ ሐሳባቸውን ገልጸዋል። ጽሁፉ የልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) እና የኮሌራ ክትባት ሩሲያ ውስጥ እንደተሠሩ ያትታል። ሆኖም ግን ዶሮ ላይ የሚሠራ የኮሌራን ክትባት ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኘው ፈረንሳዊው ተመራማሪ ሉዊስ ፓስተር ነው። ከዚያም እአአ 1885 ላይ ጄሚ ፈር የተባለ ስፔናዊ ሐኪም ሰዎችን ከበሽታው መከላከል እንዲቻል አደረገ። ለልጅነት ልምሻ የመጀመሪያውን ውጤታማ ክትባት ያገኙት አሜሪካዊው የቫይረስ ተመራማሪ ዶ/ር ጆናስ ሳልክ ናቸው። በመቀጠልም በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት የመጀመሪያው የልጅነት ልምሻ የጠብታ ክትባት የተገነ ሲሆን፤ እስካሁን ጥቅም ላይ የሚውለውም ይህ ክትባት ነው። ክትባቱ የአሜሪካ እንዲሁም የሩሲያ (ሶቪየት) ጥምር ግኝት በመባል ይታወቃል። ዶ/ር ዶራ እንደሚሉት፤ ክትባቱ የተሠራው በአሜሪካዊው ዶ/ር አልበርት ሳቢን እና በሶቪየቱ ሚኻይሊ ቾማኮቭ ጥምረት ነው። የክትባቱ ዜና በሩሲያ ክትባቱ ከኮቪድ-19 ጋር የሚደረገውን ትግል ለማሸነፍ ትልቅ እርምጃ እንደሆነ በሩሲያ ብሔራዊ ጣቢያ መገለጹ ይታወሳል። ክትባቱ አስተማማኝ መሆኑ በብሔራዊው ቴሌቭዥን ከመገለጹ ባሻገር፤ ክትባቱ ‘ሱፑቲንክ’ ከተባለችው ሳተላይት ጋር እየተነጻጸረ ይገኛል። ሳተላይቷ ሕዋ ላይ በማረፍ ግንባር ቀደሟ ናት። ምዕራባውያን ክትባቱ ላይ ጥርጣሬ አለን ማለታቸውን ብሔራዊ ጣቢያው አጣጥሎታል። “ቅናት ነው” እንዲሁም “ሩስያ ላይ የተቃጣ የመረጃ ጦርነት ነው” ሲልም ምላሽ ሰጥቷል። የዚህ ሳምንት የመገናኛ ብዙሃን ዘገባ፤ ከ2016ቱ የኢቦላ ክትባት ዘገባ ጋር ይመሳሰላል። ክትባቱ ሩሲያ ውስጥ መመዝገቡ፤ ለአገሪቱ የመድኃኒት አቅርቦት ዘርፍ ድል መሆኑ ተገልጾ ነበር። ማስረጃ ባይቀርብም ክትባቱ ከሩሲያ ውጪ ከተሠሩ ክትባቶች በበለጠ ውጤታማ መሆኑም ተገልጾ ነበር። የፑቲን ልጅ ፎቶ ነው የተባለው ምስል መድኃኒት አምራቾች ላይ የተሰነዘረ ትችት አንድ ከጣልያን የወጣ የማኅበራዊ ሚዲያ ጽሁፍ፤ ፑቲንን በማጣቀስ የተጻፈ ነበር። በእርግጥ ጽሁፉ የሚያጣቅሰው ንግግር የሩሲያን መገናኛ ብዙሃንን ጨምሮ የትም ቦታ አልተኘም። ከ35 ሺህ ጊዜ በላይ በፌስቡክ የተሰራጨው ጽሁፉ፤ “መድኃኒት አምራቾች ክትባቱን እንድናዘገየው ጠይቀውናል። ይሄ የምጣኔ ሀብት ጉዳይ አይደለም። ሩሲያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ትታ ስለ ገንዘብ አታስብም" ይላል። ጽሁፉ በፑቲን አድናቂዎች ገጽ ላይ የወጣ ጽሁፍ የተሳሳተ ትርጓሜ ሊሆን ይችላል። በፑቲን ወዳጆች ገጽ ላይ መድኃኒት አምራቾችን የሚተችና ፕሬዘዳንቱን የሚያወድስ ጽሁፍ አለ። በሁለቱም ጽሁፎች እንደተመለከተው፤ ሩሲያ ለክትባቱ በፍጥነት ፍቃድ የሰጠችው በመድኃኒት አምራቾች ተገፋፍታ ነው የሚል ትችት ሰፍሯል። የሳይንቲስቶች ዋናው ስጋት ሩሲያ ስለ ክትባቱ አስተማማኝነት የሚያስረዳ ጽሁፍ አለማሳተሟ ነው። ፑቲን ክትባቱን ልጃቸው እየወሰደች መሆኑን ተናግረዋል። ይህም የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች መነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል። ፕሬዘዳንቱ የትኛዋ ልጃቸው ክትባቱን እንደወሰደች ይፋ ባያደርጉም፤ ክትባቱ ያስከተለው ብቸኛ የጎንዮሽ ጉዳት ተወሰነ ጊዜ መጠነኛ የሙቀት መጨመር መሆኑንም አብራርተዋል። ሕንድ ውስጥ በስፋት የተሰራጨ ተንቀሳቃሽ ምስል፤ ክትባት ስትወስድ የምትታይ ሴት የፑቲን ልጅ እንደሆነች ይጠቁማል። ወጣቷ የክትባት ምርምሩ አካል ብትሆንም፤ የፑቲን ልጅ ሳትሆን የወታደራዊ ሕክምና ተቋም ተማሪ ናት። ሩሲያ አገኘሁት ያለችውን ክትባት በተመለከተ እነዚህና ሌሎችም ያልተረጋገጡ ዜናዎች፣ ምስሎችና ቪዲዮዎች በማኅበራዊው ሚዲያ መድረክ ላይ በስፋት እየተሰራጩ ነው።
news-54190243
https://www.bbc.com/amharic/news-54190243
የትግረይ ምርጫ ፡ ባይቶና ፓርቲ የተሰጠን አንድ ወንበር አይገባንም አለ
በቅርቡ በተካሄደው የትግራይ ክልል ምርጫ ላይ ከተሳተፉት ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆነው ባይቶና አባይ ትግራይ የተሰጠን ወንበር አይገባንም አለ።
ፓርቲው ዛሬ [ሐሙስ] ባወጣው መግለጫ "የምርጫው ፍትህዊነትና ዴሞክራሲያዊነት ተበላሽቷል" ብሏል። ምርጫውን ገዢው ፓርቲ ህወሓት ከ98 በመቶ በላይ የመራጮችን ድምፅ በማግኘት እንዳሸነፈ መገለጹ ይታወሳል። በአዲሱ የክልሉ ምክር ቤት የመቀመጫ ድልድል ሕግ መሠረት ህወሓት ካገኛቸው 152 የምክር ቤት መቀመጫዎች በተጨማሪ 38 ወንበሮች ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ይከፋፈላሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር። ነገር ግን የምርጫ ኮሚሽኑ ባወጣው ውጤት መሠረት ህወሓት 189 ወንበሮች ሲያገኝ 1 ወንበር ደግሞ ባይቶና ማግኘቱ ተነግሯል። ነገር ግን ባይቶና ዛሬ ባወጣው መግለጫ "ውሳኔው ባንቀበለውም ሕግን እናከብራለን። በሕጉ መሠረት ደግሞ ይህ ወንበር ለእኛ ይገባናል ብለን አናምንም" ብሏል። ከትግራይ ክልል ምርጫ በፊት የወጣው ሕግ 20 በመቶ ወንበሮች በተፎካካሪ መካከል የሚከፋፈል ነው ይላል። ነገር ግን ይህ ሕግ በጊዜው ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ተቃውሞ ገጥሞት ነበር። ፓርቲው በመግለጫው "የትግራይ የምርጫ አዋጅ ከመጀመሪያውም ህወሓትን ለማገልገል የወጣ ነው ብለን እናምናለን" ብሏል። "ይሁን እንጂ በቀመሩ መሠረት እኛ የደርስንበት የተሰጠን የሕዝብ ድምፅ ወንበር ለማግኘት የሚበቃ እንዳልሆነ ነው" ይላል መግለጫው አክሎ። ይሁን እንጂ ባይቶና፤ ለእኛ እንደሚገባ የሚያረጋግጥ የሕግ አገባብ ወይም ስሌት ካለ የተሰጠንን ወንበር በፀጋ ለመቀበል ዝግጁ ነን ይላል። ፓርቲው የትግራይ ሕዝብ ምርጫውን ለማሳካት ላደረገው አስተዋፅዖ ክብር እንዳለው በመግለጫው አትቷል። አክሎም ለምርጫ ኮሚሽኑ ለክልሉ የፀጥታ ኃይሎችም ምስጋናውን አቅርቧል። ፓርቲው በምርጫው ቀንና ከምርጫው በኋላ አጋጠመ ያለውን እንቅፋት በተመለከተም መልዕክት አስተላልፏል። "ማንን እንደመረጣችሁ እናውቃለን"፤ "ከምርጫው በኋላም የት እንደምትገቡ እናያለን"፤ "ምርጫው እስኪያልቅ ድረስ ከተቃዋሚ ፓርቲ ዕጩዎች ጋር እንዳትታዩ" የሚሉ ኢ-ሕገ መንግሥታዊ ማስፈራራቶች ደረሱባቸው ሰዎች እናዳሉ ገልጿል። አልፎም የህወሓት መዋቅር ቤት ለቤት እየዞሩ ባይቶና ላይ የሠሩት ስም ማጥፋት በምርጫው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳሳደረበት ፓርቲው ገልጿል። ጳጉሜ 04/2012 ዓ.ም በትግራይ ክልል ምርጫ የተካሄደው ምርጫን በተመለከተ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሕጋዊ ያልሆነ እና ተፈጻሚነት የሌለው እንዳለው ይታወሳል።
news-56343932
https://www.bbc.com/amharic/news-56343932
ትግራይ፡ ከ130 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ገለጸ
ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) ባደረገው ቅኝት በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ከ131 ሺህ በላይ የተፈናቀሉ ሰዎች እንዳሉ አመለከተ።
ድርጅቱ እንዳለው ተፈናቃዮቹ በትግራይና ተጎራባች በሆኑት የአፋር እንዲሁም የአማራ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ 39 በሚሆኑ ተደራሽ ስፍራዎች ላይ እንደሚገኙ ገልጿል። ይህ የተፈናቃዮች መረጃ የተሰበሰበው አዲስ በሆነው 'ዲስፕሌስመንት ትራኪን ማትሪከስ' በተባለ ዘዴ ሲሆን በዚህም የሕዝብ ቁጥርን በተመለከተ መረጃ በመሰብሰብና የሰዎችን ተጋላጭነት እንዲሁም የተፈናቃዮችን ፍላጎቶችን መሠረት በማድረግ መረጃን በመሰብሰብ የሚተነትን ነው። አይኦኤም እንዳለው በዚህ የቅኝት ተግባሩ 30,383 ተፈናቀሉ ቤተሰቦችን መለየት ችሏል። ሴቶችና ህጻናትን ጨምሮ አብዛኞቹ ተፈናቃዮች የአስቸኳይ ጊዜ መጠለያ፣ ምግብና ንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦቶችን እንደሚያስፈልጋቸው ተገልጿል። ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት እናዳለው "ይህ መረጃ በተከሰተው ቀውስ ምክንያት የተፈናቀሉትን አጠቃላይ ሰዎች የሚያመለክት አይደለም። ከዚያ ይልቅ መረጃውን ለማሰባሰብ አመቺ በሆኑ ስፍራዎች በአገር ውስጥ የተፈናቀሉትን ሰዎች ብቻ የሚወክል ነው።" በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ በትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኘው የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ላይ የቀድሞው የክልሉ አስተዳዳሪ በነበረው በህወሓት ኃይሎች የተሰነዘረበትን ጥቃት ተከትሎ ወታደራዊ ግጭት መጀመሩ አይዘነጋም። በዚህም ሳቢያ ጦርነቱን በመሸሽ ከ60 ሺህ የሚልቁ ሰዎች ድንበር ተሻግረው ወደ ሱዳን ሲሰደዱ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ነዋሪዎች ደግሞ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በእዚያው በክልሉ የተለያዩ ስፍራዎች እንደሚገኙ የእርዳታ ድርጅቶች አመልክተዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት በግጭቱ ሳቢያ የተፈናቀሉትን ለመርዳትና መልሶ ለማቋቋም ከፍተኛ ገንዘብ መድቦ የሰብአዊ እርዳታዎችን እያቀረበ መሆኑን ገለጸ ሲሆን፤ ሌሎች ግብረ ሰናይ ድርጅቶችና ዓለም አቀፍ ተቋማት እርዳታ ለማቅረብ ፈቃድ አግኝተው ተሳትፎ እያደረጉ ነው።
news-44948949
https://www.bbc.com/amharic/news-44948949
ቫያግራ የወሰዱ ኔዘርላናዳውያን እናቶች ልጆቻቸውን አጡ
ኔዘርላንድ ውስጥ እየተሰራ የነበረ ጥናት ተሳታፊ የነበሩ እርጉዝ ሴቶች ቫያግራ እንዲወስዱ ከተደረገ በኃላ የተወለዱት 11 ጨቅላዎች ህይወታቸው አልፏል።
ቫያግራ የወሰዱ እናቶች ልጆቻቸውን በሞት ተነጥቀዋል እንክብሉ ለሴቶቹ የተሰጠው የጽንስ እድገት ለማፋጠን ነበር። መድሀኒቱ የደም ዝውውርን ስለሚያፈጥን የተረገዙትን ልጆች ሳንባ ከጥቅም ውጪ አድርጓል። እናቶቹ የእንግዴ ልጅ እድገት መዘግየት ገጥሟቸው ነበር ወደ ሙከራዊ ህክምና ያመሩት። የእንግዴ ልጅ እድገት መዘግየት መድሀኒት ያልተገኘለት የጽንስ ወቅት እክል ነው። •ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር የተለቀቁ ግለሰቦች ለዳግም እስር እየተዳረጉ ነው ተባለ •አሥመራ፡ የአዛውንቶች ከተማ •የቤተ ክርስትያኗ የክፍፍል እና የውህደት ጉዞ ጽንስ መወለድ ካለበት ጊዜ ቀድሞ እንዲወለድ ከማድረጉም በላይ ጨቅላዎች በቶሎ እንዲቀጩም ምክንያት ይሆናል። በሙከራው ወቅት ምንም ስህተት እንዳልተሰራ ቢገለጽም ችግሩ እንዴት እንደተከሰተ ለማወቅ ምርመራ እየተካሄደ ነው። ከዚህ በፊት በእንግሊዝ፣ በአውስትራሊያ እና በኒው ዚላንድ ተመሳሳይ ሙከራዎች ተድርገው ነበር። ሙከራዎቹ ጥቅምም ጉዳትም አላስከተሉም። በ 11 የኔዘርላንድ ህክምና መስጫዎች ውስጥ ይካሄድ የነበው ጥናት እንደ ፈረናጆቹ በ 2020 ይጠናቀቃል ተብሎ ነበር። ከሴቶቹ መሀከል 93ቱ ሲልደፊል የተሰኘ የቫያግራ አይነት 90ው ደግሞ ተመሳሳይ የሙከራ መድሀኒት ወስደው ነበር። ከተወለዱት ልጆች መሀከል 20ው የሳንባ ህመም ገጥሟቸዋል። እናቶቻቸው ሲልደፊል የተሰኘ የቫያግራ አይነት የወሰዱት 11 ጨቅላዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል። ፕሮፌሰር ዛሮክ አልፌሪክ የተባሉ የእንግሊዙን የዛያግራ ምርምር የመሩ ባለሙያ ከደቹ ጥናት በኃላ የተከሰተው የጨቅላዎች ህልፈት ያልተጠበቀ መሆኑን አስደርተዋል። በሌሎች ሀገሮች ሞት ያላስከተለው እንክብል ለምን ኔዘርላንድ ውስጥ ህይወት እንደቀጠፈ መጠናት አለበትም ብለዋል።