id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
news-41440979
https://www.bbc.com/amharic/news-41440979
ኢትዮጵያ ኢንተርኔትን በመዝጋቷ ከ130 ሚሊዮን ዶላር በላይ አጣች
ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ዓመታት ለ36 ቀናት ያህል ኢንተርኔትን (በይነ-መረብ) በዘጋችበት ጊዜ ከ130 ሚሊዮን ዶላር በላይ አጥታለች ሲል የምሥራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ዓለም አቀፍ የመረጃ ቴክኖሎጂ ፖሊሲ ትብብር የተሰኘው ተቋም ገለፀ።
የተቋሙ ጥናት የኢንተርኔን መዘጋት በሃገራት ምጣኔ ሐብት ላይ ያደረሰውን ጉዳት በተለያዩ መለኪያዎች የገመተ ሲሆን፤ በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ ለ36 ቀናት ያህል ኢንተርኔትን በዘጋችበት እንዲሁም ለሰባት ቀናት ያህል በነበረው የማኅበራዊ ሚዲያ መናወጥ ወቅት በጥቅሉ ከ130 ሚሊዮን ዶላር በላይ አጥታለች ይላል። ኢንተርኔት በተዘጋበት እያንዳንዱ ቀን ከ3.4 ሚሊዮን ዶላር በላይ የመልክዕት ማስተላለፊያ መተግበሪያዎች (አፕ) በታወኩበት አንድ ቀን ደግሞ ከ870 ሺህ ዶላር በላይ አገሪቷ ታጣለች ሲል ጥናቱ ይገምታል። እ.ኤ.አ ከ2015 ጀምሮ ከሰሃራ በታች ያሉ አገራት በተለያየ ምክንያት ኢንተርኔትን መዝጋታቸው ንፍቀ አህጉሩን ከ237 ሚሊዮን ዶላር በላይ አስጥቶቷል። ተቋሙ ባጠናቀረውና ይፋ በሆነ ጥናት እንደተመላከተው ባለፉት ሁለት ዓመታት ኢንተርኔት ለቀናት እንዲዘጋ ባደረጉ የአፍሪካ ሃገራት የእርምጃው ምጣኔ ሐብታዊ ጠባሳ ረዘም ላለ ጊዜ የሚቆይ ነው። ጥናቱ ቢያንስ በአስራ ሁለት ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሃገራት ኢንተርኔትን የመዝጋት መንግሥታዊ እርምጃ መወሰዱን ያወሳ ሲሆን ከእነዚህም መካከል አስሩን መርምሯል። እርምጃው በተለያዩ ምክንያቶች መነሻነት የተወሰደ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ በብሔራዊ ፈተና ወቅት የፈተናን ሾልኮ መውጣት ለመከላከል በሚል ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ ተዘግቶ ነበር። ቻድ፣ ጋቦን፣ ጋምቢያ፣ የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ እና ኡጋንዳ ደግሞ ምርጫን አስታክከው ኢንተርኔትን የዘጉ ሃገራት ናቸው። ሕዝባዊ ፀረ-መንግሥት ተቃውሞዎች ለኢንተርኔት በመንግሥት መዘጋት ምክንያት ከሆኑባቸው አገራት መካከል ኢትዮጵያ በድጋሚ የምትገኝ ሲሆን፤ ተመሳሳዩን እርምጃ የወሰዱ ሌሎች ሃገራት ብሩንዲ፣ መካከለኛው የአፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ካሜሩን፣ የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ፣ ማሊ፣ ኒጀር እንዲሁም ቶጎ ናቸው። ካሜሩን እ.ኤ.አ ከ2015 እስከ 2017 ባሉት ዓመታት ለ93 ቀናት ኢንተርኔትን ስትዘጋ ኢትዮጵያ ደግሞ ለ36 ቀናት ያህል ኢንተርኔን ዘግታለች። ኢንተርኔትን መዝጋት የመረጃ ተደራሽነትን እና የመናገር ነፃነትን በማወክ የዜጎችን መሰረታዊ መብቶች ይጥሳል ያለው ተቋሙ፤ ቁርጥ ያለ መረጃ እንደልብ የማይገኝ መሆኑ የእርምጃውን ምጣኔ ሐብታዊ ዋጋ ማስላትን አዳጋች እንደሚያደርገው ያምናል። ይሁንና የቱንም ያህል ለአጭር ቀናትም ቢሆን የኢንተርኔት መዘጋት የምጣኔ ሐብታዊ እንቅስቃሴዎችን ውጤታማነት ያስተጓጉላል፣ በንግድ እንቅስቃሴ ላይ ያለ መተማመንን ይቀንሳል፣ እርምጃውን የወሰደችውን አገር የአደጋ ተጋላጭነቷ ከፍ ያለ እንደሆነ የሚያስገምት ገፅታንም ይሰጣል። እንዲሁም የዜጎችን የዕለት ተዕለት አኗኗርን ያውካል ይላል ተቋሙ። ጥናቱን ያከናወነው የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ዓለም አቀፍ የመረጃ ቴክኖሎጂ ፖሊሲ ትብብር የተሰኘው ተቋም ልማትን እና ድህነት ቅነሳን ለማሳለጥ የመረጃ እና የኮምፒውተር ቴክኖሎጂን መጠቀም ላይ የሚሰራ ነው።
54637487
https://www.bbc.com/amharic/54637487
ሶማሌ ክልል፡ ኦብነግ የከፍተኛ አመራሮቹ እስር በድርድር ሊፈታ እንደሚችል ገለፀ
የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) ሶስት ከፍተኛ አመራሮቹ መታሰራቸውን የፓርቲው ቃለ አቀባይ አብዱልከድር ሀሰን ኢርሞጌ አዳኒ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በሶማሌ ክልል ፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉትም የቆራሄ ዞን ሊቀመንበር መሃመድ ጂግሬ ገመዲድ፣ ምክትላቸው ተማም መሃመድ ማህሙድና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባሉና ለረዥም አመታት በፓርቲው በስራ አስፈፃሚነት የሰሩት መሃመድ ኢብራሂም ሙርሳል ናቸው። የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ኡመር ፋሩቅ ወርፋም ለቢቢሲ ሶማሊኛ በሰጡት ቃል ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አረጋግጠዋል። ፓርቲው በትዊተር ገፁም ላይ እንዳሰፈረው በትናንትናው ዕለት፣ ጥቅምት 11/2013 ዓ.ም ልዩ ፖሊስና የቀብሪ ደሃር ፖሊስ መሃመድ ኢብራሂም ሙርሳልን በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል። ሌሎቹ አመራሮች ደግሞ ጥቅምት 10/2013 ዓ .ም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስፍሮ "ኦብነግ ሰላሙን እያከበረ መሆኑ ክልሉን አበሳጭቷል" ብሏል። ሶስቱ የፓርቲው ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አስመልክቶ "ህገወጥ ነው" በማለትም ቃለ አቀባዩ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ከሶስት አስርት አመታት በላይ በትጥቅ ትግል ላይ የነበረው ግንባሩ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ከመንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት የተፈረመው ከሁለት አመት በፊት ጥቅምት 11፣ 2010 ዓ.ም በአስመራ ነበር። ይህንንም በማስመልከት በቀብሪዳሃር ከፍተኛ የደስታና የድጋፍ ሰልፍ ከሰሞኑ ተካሂዷል። ከዚህም በተጨማሪ በቀብሪዳሃር በተከታታይ ኮንፍረንሶችና ስብሰባዎችን ፓርቲው እያካሄደ ሲሆን እነዚህን ስብሰባዎችንም ለማካሄድም ከከተማዋ ምክር ቤት ፈቃድ ማግኘታቸውን ቃለ አቀባዩ ይናገራሉ። አቶ ኡመር በበኩላቸው ስብሰባው እንደሚደረግ የአካባቢው መስተዳድር እውቅና እንዳልነበረው ተናግረዋል። ከዚህም በተጨማሪ በአሁኑ ወቅት የኮሮናቫይረስ ስርጭት እየተስፋፋበት ባለበት ወቅት አስፈላጊው የመከላከል ጥንቃቄ ሳይደረግ በርካታ ሰዎችን በመጥራታቸው ስብሰባው እንዲበተን መደረጉን ገልፀዋል። ኃላፊው አክለውም ለተሰብሳቢዎቹና አመራሮቹ የሚያደርጉት ውይይት "ሕገወጥ" መሆኑ ሲነገራቸውም ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተናግረዋል። እንዲሁም ወደ መሰብሰቢያ አዳራሹ እንዳይገቡ በሚከለከሉበት ወቅትም በኃይል ጥሰው ለመግባት መሞከራቸውን ገልፀዋል። ቃለ አቀባዩ በኃላፊው አባባል አይስማሙም በወቅቱም ህገወጥ የሆኑ እንቅስቃሴዎች እንዳልተፈጠሩ እንዲሁም የደረሱ ችግሮችም ሆነ ጉዳቶች አለመኖራቸውን አስረድተዋል። በአሁኑ ወቅት በፓርቲያቸው፣ በክልሉ መንግሥትና በፌደራል መንግሥት መካከልም ውይይቶች እየተካሄዱ መሆኑን ገልፀው በድርድርም እንደሚፈታም ተስፋ እንደሚያደርጉ ለቢቢሲ ገልፀዋል። ኦብነግ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ስምምነት ከተፈረመ በኋላ በምርጫ ቦርድ ህጋዊ ሰውነት አግኝቶ "የህዝቡን ጥቅም ቅድሚያ በመስጠት" በክልሉ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝም ተናግረዋል። በባለፉት ጊዜያትም ውስጥ ከክልሉም ሆነ ከፌደራል መንግሥት ጋር ተባብረው እየሰሩ እንደሚገኙም ገልፀዋል። ሆኖም በባለፉት ሶስት፣ አራት ወራት ግን ከክልሉ መንግሥት በኩል ፓርቲያቸውን ኢላማ ያደረጉ ትንኮሳዎች እንዳሉ ገልፀው በአጠቃላይ በክልሉ ውስጥ ያለው የመንግሥትና ፓርቲያቸው ሰላማዊ ቢሆንም በአንዳንድ አካባቢዎች ፍጥጫና ትንኮሳ መኖሩንም አስረድተዋል። "በሰላማዊ መንገድ እየታገልን ነው ያለነው፤ ክልሉም ሆነ ከፌደራል መንግሥት ጋርም ተባብረን መስረት እንፈልጋለን። ማንኛውም አይነት ትንኮሳም ሆነ ሆነ ጥቃት በምንም መንገድ አስፈላጊ አይደለም። እኛ ሁሌም ቢሆን ለመተባበርና ለመደራደር ዝግጁ ነን ። " ይላሉ በፓርቲያቸውና በክልሉ መንግሥት ላለው አለመግባባት ዋነኛ ምክንያቶች የሚሏቸወም የክልሉ መንግሥት የመንግሥት ተቋማትን ህገወጥ በሆነ መንገድ በመጠቀም ኢላማ አድርገውናል ይላሉ። ኦብነግ የአመራሮቹና የአባላቶቹ መታሰር በድርድር ሊፈታ እንደሚችል ገልፆ ጉዳዩ በሰላም መቋጨት ካልቻለ ግን ወደ ፌደራል መንግሥቱ ሊወስደው እንደሚችል አሳውቋል። ፓርቲያቸው ከክልሉም ሆነ ከፌደራል መንግሥት ጋር በሰላማዊ መንገድ ተባብሮ ለመስራት፣ ያሉትን ችግሮች ህጋዊና በሰለጠነ መንገድ ለመፍታት ፅኑ ቁርጠኝነት እንዳለውና በዚህ መንገድ እየሰራም እንደሆነ ይናገራሉ። በአሁኑ ወቅት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ኢትዮጵያ ያራዘመችው ምርጫ ላይ ለመሳተፍ እየተዘጋጁ መሆኑን የገለፁት አቶ አብዱልከድር በሰላማዊ ሁኔታ መታገል እንደሚፈልጉና መፍታትም እንደሚቻል ገልፀዋል። ግንባሩ በክልሉ ብቻ ሳይሆን በአገር አቀፍ ሁኔታ በዲሞክራሲያዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድ እየተንቀሳቀሰ የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማድረግም ዝግጁነት እንዳለውም አፅንኦት በመስጠት ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ የታዩ መሻሻሎች በጎ እንደሆነ የሚናገሩት ቃለ አቀባዩ በአሁኑ ወቅት በአገሪቷ ውስጥ የተንሳራፋውን ግጭቶች በሰላማዊ መንገድና በድርድር መፍታት ይቻላል ብሎ ፓርቲያቸው እንደሚያምንና የብሄራዊና የብሄሮች ውይይትም አስፈላጊነትን አስምረዋል። ኦብነግ ከኢትዮጵያ ለመገንጠል ትግል ያደርጉ ከነበሩ አማፂ ቡድኖች መካከል አንዱ ሲሆን የተመሰረተው በጎሮጎሳውያኑ 1984 ነው። ቡድኑ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ መንግሥት ሽብርተኛ ተብለው ከተሰየሙ ቡድኖች ዝርዝር ውስጥ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ሦስት የፖለቲካ ቡድኖች ከሽብር ቡድን ዝርዝር ውስጥ በፓርላማው ውሳኔ እንዲወጡ ከተደረገ በኋላ በውጪ የሚገኙ የታጠቁ ተቃዋሚዎች ወደ ሃገር ቤት መመለሳቸው ይታወቃል።
news-55270526
https://www.bbc.com/amharic/news-55270526
ቴክኖሎጂ ፡ የጉግል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ትምኒት ገብሩን ይቅርታ ጠየቁ
የጉግል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሱንድራ ፒቻኢ ትምኒት ከሥራዋ የለቀቀችበትን ሁኔታ በማስመልከት ይቅርታ ጠይቀዋል።
ትምኒት ገብሩ ይሁን እንጂ የጎግል አለቃው ትምኒት እንዴት ልትባረር እንደቻለችም ይሁን ከጉግል መባሯሯን አላረጋገጡም። ባሳለፍነው ሳምንት የአርቴፌሻል ኢንተለጀንስ- ኤኤይ (የሰው ሰራሽ ልህቀት) ተመራማሪ እና በጉግል የኤአይ የሥነ ምግባር ተመራማሪ ቡድን አጋር መሪ የነበረችው ትምኒት፤ ከጎግል መባረሯን አስታውቃ ነበር። ትምኒት እንዳሳወቀችው ጉግል ከሥራዋ ያባረራት "ድርጅቱ ትኩረት የተነፈጋቸው ድምጾችን ያፍናል" በማለት ለሥራ ባልደረቦቿ የኢሜል መልዕክት ከላከች በኋላ ነው። ኩባንያው "ከአመራር ውጪ ለሆኑ ተቀጣሪዎች የላክሽው ኢሜል የጉግል አስተዳደር ከሚፈቅደው አሠራር ውጪ ነው" የሚል ኢሜል እንደላከላት ተናግራለች። በትውልድ ሕንዳዊ የሆኑት የጎግል አለቃ ሱንድራ ፒቻኢ ኩባንያው ትምኒት “ከጉግል የተለየችበትን ሁኔታ መመርመር ይኖርበታል” ብለዋል። ለጉግል ሠራተኞች በላኩት የኢሜይል መልዕክት ላይ ሱንድራ “ተጽእኖ ፈጣሪ እና ባለ ብዙ ተሰጥኦ ጥቁር ሴት ጉግልን በሃዘን ስለተሰናበተች ኃላፊነት መውሰድ ይኖርብናል” ብለዋል። ትምኒት በበኩሏ ለሥራ አስፈጻሚው የኢሜል መልዕክት “ይህ ይቅርታ መጠየቅ አይደለም” ስትል ምላሽ ሰጥታለች። ትምኒት ከጉግል ከመባሯ በፊት ከሌሎች የኩባንያው ተመራማሪዎች ጋር የጻፈችው የጥናት ጽሑፍ እውቅና እንድትነፍግ እና በጥናት ጸሑፉ የተሳተፉ ሰዎችን ስም ዝርዝር ከጥናት ወረቀቱ እንድታነሳ ተነግሯት እንደነበረ ገልጻለች። በሰው ሠራሽ ልህቀትና ተያያዥ የቴክኖሎጂ ዘርፎች የሚሠሩ እውቅ ባለሙያዎች የትምኒትን መባረር በመቃወም ትዊተር ላይ ድምጻቸውን ሲያስሙ ቆይተዋል። ከዚህ በተጨማሪም በሺዎች የሚቆጠሩ የጉገል ሠራተኞችን ትምኒት ገብሩን የሚደግፈው ደብዳቤ ላይ በመፈረም ከጓኗ መቆማቸውን ሲገልጹ ነበር። የትምኒት መባረርንም እንደ ዋሽንግተን ፖስት፣ ብሉምበርግ እና ኒው ዮርክ ታይምስ ያሉት ግዙፍ የአሜሪካ የሚዲያ ተቋማት ይዘውት ወጥተዋል።
news-52989984
https://www.bbc.com/amharic/news-52989984
በናይጄሪያ በቦኩ ሃራም ሳይፈጽሙት አልቀረም በተባለ ጥቃት ቢያንስ 59 ሰዎች ተገደሉ
በሰሜን ምሥራቅ ናይጄሪያ ጸንፈኛ ጂሃዲስቶች ሳይፈጽሙት አልቀረም በተባለ ጥቃት ቢያንስ 59 ሰዎች ተገደሉ።
ታጣቂዎች በቦርኖ ግዛት ውስጥ በምትገኝ መንደር ውስጥ በወሰዱት እርምጃ ነው ሰዎቹ የተገደሉት። የአካባቢ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ከሆነ ጥቃቱ በነዋሪዎቹ ላይ ከተሰነዘረ በኋላ መንደሯ ሙሉ በሙሉ እንድትወድም ተደርጓል። ኤኤፍፒ እንደዘገበው ከሆነ ጥቃቱ ከተሰነዘረበት ስፍራ ቢያንስ የ59 ሰዎች አስክሬን ተሰብስቧል። ሬውተርስ በበኩሉ 69 ሰዎች ተገድለዋል ሲል ዘግቧል። የአካባቢው መገናኛ ብዙሃን ጨምረው እንደዘገቡት ከሆነ ጥቃቱ የተሰነዘረው የበቀል እርምጃ ለመውሰድ ነው። ሬውተርስ እንደሚለው ከሆነ፤ ምንም እንኳ ለዚህ ጥቃት ኃላፊነቱን የወሰደ ቡድን ባይኖርም፤ የመንደሯ ነዋሪዎች በአካባቢው ስለሚንቀሳሱት ሚሊሻዎች መረጃ ለናይጄሪያ መንግሥት መረጃ ያቀብላሉ ተብለው በጂሃዲስቶች ይወነጀላሉ። ኤኤፍፒ የመንደሯ ነዋሪዎች ከብቶቻቸውን ከዘራፊዎች ለመጠበቅ ሲሉ የሚሊሻው አባላት የሆኑትን ገድሏል ሲል ዘግቧል። ምንም እንኳ ለዚህ ጥቃት ኃላፊነቱን የወሰደ አካል ባይኖርም ጂሃዲስቱ ቦኮ ሃራም በሰሜን ናይጄያ ግዛት ለሚፈጸሙ ተመሳሳይ ጥቃቶች ኃላፊነቱን ሲወስድ ቆይቷል። እአአ 2014 ከቦርኖ ግዛት ከ270 በላይ ሴት ተማሪዎችን አፍኖ ከወሰደ በኋላ የበርካቶች መነጋጋሪያ ሆኖ የቆየው ቦኩ ሃራም፤ ከናይጄሪያ በተጨማሪ በቻድ፣ ኒጀር እና ካሜሩን በስፋት ይንቀሳቀሳል። ከሁለት ወራት በፊትም የቡኩ ሀራማ ታጣቂዎች አሳቻ ቦታ ላይ ጠብቀው 47 የናይጄሪያ እና ወደ 100 የሚጠጉ የቻድ ወታደሮችን መግደላቸው ይታወሳል። ለዓመታት ናይጄያን እና ጎረቤት አገራትን ሲያስጨንቅ በቆየው ቦኮ ሃራም፤ በሚያደርሳቸው ጥቃቶች በሺዎች የሚቆጠሩ ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን፤ ቁጥራቸው በውል የማይወታወቅ በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ቤት ንብረታቸውን ጥለው ለመሰደድ ተገደዋል።
news-49960041
https://www.bbc.com/amharic/news-49960041
ሁለት ሜትር ከሃያ አምስት ሴንቲ ሜትር የሚረዝመው ሴኔጋላዊ ቅርጫት ኳስ ተጫዋች
ሴኔጋላዊው ታኮ ፎል ወደ ቅርጫት ኳሱ ዓለም የተቀላቀለው ገና ከሰባት ዓመታት በፊት ቢሆንም የ2.25 ሜትር ርዝማኔ ያለው ይህ ተጫዋች በአሜሪካ ቅርጫት ኳስ (ኤንቢኤ) ከፍተኛ ስፍራ እያገኘ ነው።
ከዓለም ረዥሙ የቀድሞው የእግር ኳስ ተጫዋች ሮማኒያዊው ጆርጅ ሙሬሳን በ6.3 ሴንቲ ሜትር የሚያጥረው የ23 አመቱ ታኮ፤ የታዋቂው የቦስተን ሴልቲክስ ከቋሚዎቹ አስራ አምስት ተጫዋቾች አንዱ ለመሆንም ጥረት ላይ ነው። • የደቡብ አፍሪካ ባሕር ጠላቂዎች በኬንያ አስክሬን ፍለጋ ላይ ሊሰማሩ ነው • የካቶሊክ ቄሶች ማግባት ይፈቀድላቸው ይሆን? • በአሜሪካዊቷ ፖሊስ የፍርድ ሂደት ምስክርነት የሰጠው የዐይን እማኝ ተገደለ ሴልቲክስ ታኮ ፎልን የመረጠበት ምክንያትም ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገቡ እንደሆነም ተገልጿል። በሴኔጋሏ መዲና ዳካር የተወለደው ታኮ፤ ወደ አሜሪካ የሄደው በ16 ዓመቱ ሲሆን፤ በዩኒቨርስቲ ኦፍ ሴንትራል ፍሎሪዳ ቅርጫት ኳስ ይጫወት ነበር። ታኮ ለቢቢሲ እንደተናገረው፤ ዩኒቨርስቲው ውስጥ ብዙዎች ሙያውን እንዲያሳድግ ድጋፍ አድርገውለታል። ታዳጊ ሳለ ብዙም ስለ ቅርጫት ኳስ እንደማያውቅ ይናገራል። ጊዜውን ያሳልፍ የነበረው ካርቱን ፊልሞች በማየት ነበር። የአያቱ ቅርጫት ኳስ መውደድ ስፖርቱ ላይ ፍቅር እንዲያሳድር አድርጎታል። ወደ አሜሪካ ከሄደ በኋላ ሙሉ ትኩረቱን ወደ ቅርጫት ኳስ አድርጓል። ጉዞው ግን አልጋ በአልጋ አልነበረም። "ቅርጫት ኳስ መጫወት አልችልም ነበር። ብዙ ነገር መማር ይጠበቅብኝ ነበር። እድለኛ ሆኜ ብዙ ሰዎች ራሴን እንዳሻሽል ረድተውኛል" ይላል። ሂውስተን አንድ ዓመት ከቆየ በኋላ ወደ ቴኒሲ፣ ጂዎርጂያ እና ፍሎሪዳ አቅንቷል። በዩኒቨርስቲ ኦፍ ሴንትራል ፍሎሪዳ ሁለት ዓመት ቆይቷል። "አንድ ሴኔጋላዊ ታዳጊ ነበርኩ። ቅርጫት ኳስ መጫወት የጀመርኩትም ከስድስት ዓመት በፊት ነበር። ኤንቢኤ ውስጥ ለመጫወት ብዙ ለፍቻለሁ። በጣም እድለኛ እንደሆንኩ ይሰማኛል። ቅርጫት ኳስ ሕይወቴ ነው። አንድ ቀን እንኳን ሳልጫወት ባልፍ አዝናለሁ" ሲል ይናገራል።
news-53915679
https://www.bbc.com/amharic/news-53915679
እግር ኳስ፡ ሊዮኔል ሜሲ 'የልቀቁኝ ደብዳቤ' ለባርሴሎና አስገባ
አርጀንቲናዊው የእግር ኳስ እንቁ ሊዮኔል ሜሲ የልቀቁኝ ደብዳቤ ለባርሴሎና ኃላፊዎች ማስረከቡ ተነገሯል።
የ33 ዓመቱ የባርሴሎና ኮከብ አጥቂ ባለፈው ማክሰኞ የልቀቁኝ ማመልከቻ የተተየበበት ፋክስ ልኳል፤ በደብዳቤውም በዚህ የዝውውር መስኮት ባርሴሎናን መልቀቅ እንደሚፈልግ አሳውቋል። ባርሴሎና በቻምፒዮንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ ባየርን ሚዩኒክን ገጥሞ 8-2 መረታቱ ይታወሳል። የባለን ደኦር [የዓለም ኮከብ ተጫዋች] ሽልማትን ስድስት ጊዜ ማንሳት የቻለው ሜሲ ለስፔኑ ክለብ ባርሴሎና ከፈረንጆቹ 2004 ጀምሮ ተጫውቷል። የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን አራት ጊዜ ማንሳትም ችሏል። ሜሲ ከባርሴሎና ጋር የገባው ውል የሚያበቃው በቀጣዩ ዓመት [2021] ነው። ከዚያ በፊት ተጫዋቹን መግዛት የፈለገ ክለብ 700 ሚሊየን ዩሮ ማውጣት ይኖርበታል። ሜሲ ግን ስምምነቱ ላይ 'ካሻሁ በነፃ እንድሰናበት የሚያትት አንቀፅ አለ፤ እሱን ተግባራዊ ማድረግ እፈልጋለሁ' ብሏል። የክለቡ ቦርድ አባላት አስቸኳይ ስብሰባ ያደርጋሉ እየተባለ ነው። ሜሲ የክለቡ ፕሬዝደንት ጆሴፕ ማርያ ባርቶሜዩ ካልተሰናበቱ እንደማይቆይ ቢነገርም ተጫዋቹ ክለቡን ለመልቀቅ የቆረጠ ይመስላል። ይህ ዜና ከተሰማ በኋላ የባርሳ ደጋፊዎች ኑ ካምፕ ስታድየም ተሰብስበው በክለቡ ቦርድ አባላት ላይ ያላቸውን ተቃውሞ አሰምተዋል። ሜሲና ባርሴሎና ጉዳያቸውን በሕግ ፊት ሊፈቱ ይችላሉ እየተባለ ነው። ስምምነቱ ላይ ሜሲ የልቀቁኝ ደብዳቤ ከሰኔ አስቀድሞ ካስገባ በነፃ ወዲያውኑ ሊለቅ ይችላል የሚል አንቀፅ አለ። ነገር ግን ይህ ቀን አልፏል። ሜሲና ወኪሎቹ ግን የዘንድሮው ዓመት ውድድር በኮሮናቫይረስ ምክንያት ስለተራዘመ አንቀፁ አሁንም ተግባራዊ መሆን አለበት ይላሉ። ነገር ግን የሕግ ባለሙያዎች ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ከሄደ ባርሴሎና የተሻለ ተጠቃሚ ነው ይላሉ። ሜሲ ባርሴሎናን መልቀቅ የፈለገው በተለያዩ ምክንያቶች ነው ይላል ስፔናዊው ፀሐፊ ጉለም ባላግ። አንደኛው ምክንያት ከሰሞኑ የተከናነቡት ሽንፈት ነው። ነገር ግን ክለቡ ሜሲ እንዲለቅ ይፈልጋል ሲል ጉለም ይፅፋል። ሊዮኔል ሜሲ ባርሴሎናን የተቀላቀለው የ13 ዓመት ታዳጊ እያለ ነበር። ሜሲ ለዋናው ክለብ 731 ጊዜ ተሰልፎ 634 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል። 10 የላ ሊጋ ዋንጫ ጨምሮ 34 ዋንጫዎችን ማንሳት ችሏል።
52423332
https://www.bbc.com/amharic/52423332
ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ግርፋት እንዲቆም ጠቅላይ ፍርድ ቤት አዘዘ
ሳኡዲ አረቢያ ግርፋትን መቀጣጫ ማድረግ ልታቆም እንደሆነ አንድ ለመገናኛ ብዙሃን የተላከ ሕጋዊ ሰነድ ጠቆመ።
ከሃገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ያጠፉ ሰዎች ከግርፋት ይልቅ በእሥራት ወይም በገንዘብ እንዲቀጡ ይደረጋል። ሰነዱ፤ ይህ የንጉሥ ሰልማንና ልጃቸው አልጋ ወራሽ ልዑል ሞሐማድ ቢን ሰልማን የሰብዓዊ መብት ለውጥ እርምጃ አካል ነው ይላል። ሳኡዲ መንግሥትን የተቃወሙ ሰዎችን በማሠርና በጋዜጠኛ ጃማል ኻሾግጂ ግድያ ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ትችት ሲደርስባት ቆይቷል። የሳኡዲ እርምጃዎች የሚቃወሙ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፤ ሃገሪቱ ሰብዓዊ መብት በመርገጥ ወደር የላትም ሲሉ ይወነጅላሉ። ሐሳብን በነፃነት መግለፅ በእጅጉ የታፈነ ነው፤ መንግሥትን መቃመው ደግሞ ለምክንያት የለሽ እሥር ይዳርጋል ይላሉ። መጥፎ ገፅታ በግሪጎሪ አቆጣጠር 2015 ላይ ሳኡዲ አራቢያዊው ጦማሪ ራይፍ ባዳዊ በአደባባይ መገረፉ አይዘነጋም። 'የሳይበር' ወንጀል ፈፅሟል፤ እስልምናን አንቋሿል ተብሎ ነበር የተቀጣው። ሳዑዲ አራቢያዊው ጦማሪ ራይፍ ባዳዊ በአደባባይ መገረፉ አይዘነጋም ጦማሪው በየሳምንቱ አንድ አንድ ሺህ ልምጭ እንዲገረፍ ነበር የተወሰነበት። ነገር ግን ግለሰቡ በግርፋሩ ምክንያት ሊሞት ደርሶ ነበር መባሉን ተከትሎ ተቃውሞ የበረታባት ሳኡዲ ግርፋቱ እንዲቆም አዘዘች። ተንታኞች ግርፋት ለሳኡዲ መጥፎ ገፅታ እየሰጣት ስለሆነ ነው ለማቆም የወሰነችው ይላሉ። ቢሆንም ንጉሡንም ሆነ አልጋ ወራሹን የሚቃወሙ ሰዎች አሁንም እየታሠሩ እንደሆነ ይዘገባል። ባለፈው አርብ ሳኡዲ ውስጥ ስለሰብዓዊ መብት በመከራከር የሚታወቅ አንድ ግለሰብ እሥር ቤት ውስጥ ያለ በስትሮክ መሞቱ ተነግሯል። የሙያ አጋሮቹ የሕክምና እርዳታ ቢያገኝ ኖሮ ይድን ነበር ይላሉ።
news-44242222
https://www.bbc.com/amharic/news-44242222
የወባ ትንኝ አደገኛ የሆነችው በሂደት ነው
የዓለም የጤና ድርጅት እንደሚለው በዓመት ከ 200 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወባ ይያዛሉ።
እንደ አውሮፓውያኑ በ2016 በወባ ከተያዙ ሰዎች መሀከል ግማሽ ሚሊዮኑ ህይወታቸው አልፏል። ከሟቾቹ አብላጫውን ቁጥር የሚይዙት እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ናቸው። የወባ ትንኝ ሁሌም አደገኛ ነፍሳት አልነበረም። የወባ ትንኝ የአደገኛነት መጠን አሁን ካለበት ደረጃ የደረሰው በአዝጋሚ ሂደት መሆኑን ያውቁ ኖሯል? ካምብሪጅ ውስጥ የሚገኘው ዌልካም ሳንገር ኢንስቲትዩት በቅርቡ ይፋ ያደረገው ጥናት የወባ ትንኝ የሰው ልጆችን ህይወት የሚቀጥፍ ነፍሳት ለመሆን ያለፈበትን የእድገት ደረጃዎችን ያሳያል። ጥናቱ የተሰራው ሰባት የወባ ትንኝ ዝርያዎችን በናሙናነት በመውሰድ ሲሆን ከ50 ሺህ ዓመታት በፊት ትንኙ አንድ አይነት ዝርያ ብቻ እንደነበረው ተመራማሪዎቹ ደርሰውበታል። በጥናቱ መሰረት የትንኝ ዝርያው ከጊዜ ወደ ጊዜ ሰዎችን ወደሚያጠቃ አደገኛ ነፍሳትነት ተሸጋግሯል። ከተመራማሪዎቹ አንዱ ዶ/ር ማት በርማን እንደሚለው ትንኞች ከጊዜ በኋላ ያሳዩት የዘረ መል ለውጥ የሰዎችን ቀይ የደም ህዋስ ማጥቃት የሚችሉበት ደረጃ ላይ አድርሷቸዋል። "ጥናታችን ጥገኛ ህዋሳት ሰውነት ውስጥ ከገቡ በኋላ የሚቆዩበትን እንዲሁም እየተከፈሉ በመባዛት ሰውነት ውስጥ በወባ ትንኝ የሚሰራጩበትን ሂደት ይዳስሳል" ሲል ያስረዳል። ከጥገኛ ህዋሳቱ መሀከል ፕላስሞድየም ፋልሲፓረም የተባለው ከፍተኛ የጤና እክልን ያስከትላል። ለህልፈት የምትዳርገው ሴት የወባ ትንኝ ሰዎችን ስትነድፍ የቺምፓንዚና ጎሬላ ዝርያዎችን የሚያጠቁ ነፍሳትም አሉ። አጥኚዎቹ ጋቦን ወደሚገኝ የጦጣ ማቆያ አቅንተው ከእንስሳቱ የደም ናሙና ወስደዋል። "ጤነኛ በሆኑት እንስሳት ደም ውስጥ ጥገኛ ህዋሳት ተገኝቷል" ሲል ዶክተሩ ይናገራል። ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት የደም ናሙናዎቹ የወባ ትንኝን ዘረ መል ለማወቅና በዝግመተ ለውጥ ያሳዩትን ለውጥ ለመገንንዘብ ችለዋል። የወባ ትንኝ አደገኛ የሆነበትን ሂደትም ደርሰውበታል። በጥናቱ ከተካተቱት ሰባት የወባ ትንኝ አይነቶች ሦስቱ ቺምፓንዚን፣ ሦስቱ ደግሞ ጎሬላ የሚያጠቁ ናቸው። ፕላስሞድየም ፋልሲፓረም የሚባለው አደገኛ የትንኝ ዝርያ ከ 50 ሺህ ዓመታት በፊት ቢገኝም የሰው ልጆችን ወደማጥቃት የተሸጋገረው ከ 3,000 እና ከ 4,000 ዓመት በፊት ነው። "የወባ ትንኝ ሰዎችን ወደሚያጠቃ ነፍሳትነት ለማደጉ የሰዎች ከቦታ ቦታ መዘዋወር ምክንያት ነው" ሲል ዶ/ር ማት ያስረዳል። የሊቨርፑሉ ስኩል ኦፍ ትሮፒካል ሜዲሲን ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ጃኔት ሄሚንግዌይ "የወባ ትንኝ አደገኛ የሆነበትን ጊዜና ሁኔታ ስለሚያሳይ ጠቃሚ ነው" ትላለች። የትንኙ አደገኛ የሆነበትን ሂደት መገንዘብ ችግሩን ለመቅረፍ እንደሚያስችልም ተናግራለች። "ብዙ ሰዎች ወባ ከእንስሳት ወደ ሰዎች የሚተላለፍ መሆኑን አያውቁም። የሰው ሰውነትን ተዋህደው ወደ አደገኛነት የተሸጋገሩትም በጊዜ ሂደት ነው" ስትል ትገልጻለች።
news-54117001
https://www.bbc.com/amharic/news-54117001
ፌስቡክ “ከጥላቻ ትርፍ እያገኘ ነው”
አንድ የቀድሞ የፌስቡክ ባልደረባ ድርጅቱ “ከጥላቻ ትርፍ እያገኘ ነው” በሚል የድርጅቱ አካል መሆን አልሻም ሲል በገዛ ፍቃዱ ከስራው ተሰናብቷል።
በተመሳሳይ ከዚህ ቀደም ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ የፌስቡክ ሰራተኞ ድርጅቱ የጥላቻ ንግግርን ለማስወገድ በቂ እርምጃ አልተጓዘም በሚል ሥራቸውን በገዛ ፈቃዳቸው ለቀዋል። የቀድሞ የፌስቡክ ቅጥረኛ የነበረው ኢንጅነሩ አሾክ ቻንደዋይን “የተሳሳተው የታሪክ አካል መሆን አልሻም” ብሏል። ፌስቡክ በሌሎች ጉዳዮች ላይ አፋጣኝ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውሶ ከጥላቻ ንግግሮች ጋር በተያያዘ ግን ጠንከር ያለ እርምጃ ከመውሰድ ተቆጥቧል ብሏል። ፌስቡክ በበኩሉ ከጥላቻ ንግግር ጋር የተያያዙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ፖስቶችን ከገጹ ስለማጥፋቱ አስታውቋል። ቻንደዋይን እንደሚለው ከሆነ ግን የፌስቡክ መተግበሪያን ፍጥነት የሚቀንስ አንዳች እክል ሪፖርት ከተደረገ፤ ችግሩ በአስደናቂ ፍጥነት ይቀረፋል። ከጥላቻ ጋር የተያያዙ መልዕክቶች ላይ ግን ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ፍላጎት የለም ብሏል። በወረሃ ሐምሌ ላይ ፕሬዝደንት ትራምፕ ከ “ብላክ ላይቭስ ማተር” የተቃውሞ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ያሰፈሩትን መልዕክት ፌስቡክ እንዲያጠፋው በርካቶች ጠይቀው ነበር። ትዊተር በወቅቱ ይህንኑ ተመሳሳይ የፕሬዝደንቱ መልዕክት እውነተኝነቱ ያልተረጋገጠ ስለሆነ ተጠቃሚዎች እውነታ እንዲያመሳክሩ ምልክት አኑሮ ነበር። ፌስቡክ ግን በፕሬዝደንቱ መልዕክት ላይ ምንም አይነት እርምጃ ባለመውሰዱ በርካታ የድርጅቱ ሠራተኞች ስራቸውን በግል ፍቃዳቸው ለቀዋል። ተቃውሟቸውን ለማሰማትም በርካታ ሰራተኞች ከመስሪያ ወንበራቸው ተነስተው ወደ ደጅ በመውጣት ድምጻቸውን አሰምተዋል። ትራምፕ በወቅቱ ለጥፈውት የነበረው የትዊተር መልዕክት ተቃውሞን ለመቆጣጠር ተጨማሪ የፖሊስ ኃይል እንደሚልኩ እና “ዘረፋ ሲጀመር፤ ተኩስ ይከፈታል” የሚል ነበር።
49181404
https://www.bbc.com/amharic/49181404
ከአራት ቢሊዮን በላይ ችግኞችን ለማፍላት አርባ ቢሊዮን የሚጠጋ ብር ወጥቶበታል ተባለ
ከጥቂት ቀናት በፊት በተካሄደው የችግኝ መትከል ዘመቻ ላይ ከ23 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን ኢትዮጵያ እስከ ጳጉሜ መጨረሻ በምታደርገው የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ 4.7 ቢሊዮን ችግኞችም መፈላታቸው ተገልጿል።
በአጠቃላይ ችግኞቹን ለማፍላት ወደ አርባ ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብም መውጣቱን የብሔራዊ ደን ልማት ፕሮግራም አስተባባሪ ዶ/ር ተፈራ መንግሥቱ ለቢቢሲ ገልፀዋል። የዘንድሮውን የችግኝ ተከላው ፕሮግራም ባለፉት ሶስት ወራት መርኃ ግብር ተዘርግቶ እንደተሰራ ጠቅሰው፤ ዝግጅቱ ግን አመቱን ሙሉ ነው ተሰርቷል ብለዋል። ለዚህ ተከላ ሲባል አዳዲስ አይነት ችግኞች ያልተፈሉ ሲሆን ተከላው የተከናወነው ባለው ክምችት መሆኑን ጠቅሰዋል። • የጠቅላይ ሚኒስትሩ 200 ሚሊዮን ችግኞች • በአስር ወራት አማርኛ ማንበብና መፃፍ የቻለው ጀርመናዊ በኃገሪቱ ካሉ የችግኝ ጣቢያ ክምችት ችግኞቹ ከመሰራጨታቸው አንፃር ለእያንዳንዱ ስነ ምህዳር፣ አካባቢ የትኛው ይጠቅማል የሚል ጥናት አለመደረጉንም አቶ ተፈራ ጠቅሰዋል። ይህ ማለት ግን ችግኞቹ የጎንዮሽ ችግር አለባቸው ማለት እንዳልሆነ ያስረዳሉ። "ለኢትዮጵያ መልክአ ምድር የማይሆኑ ችግኞች አልተፈሉም።" የሚሉት አቶ ተፈራ አንዳንድ ችግኞች ግን ካላቸው የአካባቢ መስተጋብር ጋር የተሻለ የሚፀድቁበት ሁኔታ ይኖራል ይላሉ። ችግኞቹን ከሰሜን ወደ ደቡብ በማሰባጠርና በሚስማማባቸው አካባቢ ለመትከል በቂ ጊዜም እንዳልነበረ አስረድተዋል። ካሉት ችግኞች ሁሉም ይፀድቃሉ ተብለው የማይጠበቁ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ተፈራ እስካሁን ባለው ልምድ ከአምሳ ፐርሰንት በታች የፀደቀበት ሁኔታም ስለነበር አሁን ባለው እስከ 70% የሚሆነው ከፀደቀ ትልቅ ውጤት ነው ብለው ያስባሉ። ተከላው በበቂ ዝግጅት ካለመሆኑ፣ በስፋትና፣ በዘመቻ ከመሆኑ አንፃር፤ የህዝቡን መነቃቃት መፍጠር፣ ተቋማት በተቀናጀ ሁኔታ መምራታቸው የዘንድሮው ተከላ ሂደት ትርፉ መሆኑን ይናገራሉ። የክትትል ስርአት ለመዘርጋት ጥረት መደረጉ እስካሁን ከነበረው የተሻለ ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል አቶ ተፈራ ያምናሉ። ከዚህም በተጨማሪ የተተከሉት ዛፎች ሃገር በቀል እና የውጪ ዝርያ ያላቸው ችግኞች እንደሚገኙበት የጠቀሱ ሲሆን ዝርዝር የችግኞቹ አይነት ወደፊት ይገለጻል ብለዋል። ሰኞ ዕለት የተተከሉት ችግኞች በሙሉ በሃገር ውስጥ የተፈሉ መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር ተፈራ ከሰኔ 26 ወዲህ 3.5 ቢሊዮን ችግኞች በመላው ሃገሪቱ መተከሉን ጨምረው ተናግረዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አነሳሽነት የተጀመረው ይህ ዘመቻ ባሳለፍነው ሰኞ በአንድ ቀን 200 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፤ በዕለቱ አመሻሽ ላይ መንግሥት በመላው ሃገሪቱ የተተከሉት የችግኞች ብዛት ከ350 ሚሊዮን በላይ መሆኑን መግለጹ ይታወሳል። አንዳንድ ቦታዎች የሚተከሉ ችግኞች እጥረት አጋጥሞ እንደነበር ቢነገርም ዶ/ር ተፈራ ግን "ዝግጁ የተደረጉት የችግኞች ብዛት 4.7 ቢሊዮን ስለነበሩ የችግኝ እጥረት አላጋጠመም" በማለት የክልል መንግሥታት ለዘመቻው ከፍተኛ ዝግጅት በማድረጋቸው ከተጠበቀው በላይ ከፍተኛ ስኬት መመዝገቡን አብራርተዋል። • "በኤችአይቪ የምሞት መስሎኝ ልጄን ለጉዲፈቻ ሰጠሁ" • የተተከሉት ችግኞች እንዴት ተቆጠሩ? በአንድ ቀን ብዙ ችግኞችን በመትከል በህንድ ተይዞ የነበረው ክብረ ወሰን መሰበሩን እየተነገረ ሲሆን፤ ይህም በጊነስ በይፋ ስለመመዝገቡ የተጠየቁት ዶ/ር ተፈራ ይህን ጉዳይ የሚከታተለው የጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ መሆኑን ጠቁመዋል። ስለጉዳዩ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃም ትክክለኛው ቁጥር የሚረጋገጥበት ሥርዓት እንዳለው አመልክቶ በአጭር ጊዜ የሚጠናቀቅ ባለመሆኑ የማስመዝገቡ ሥራ በሂደት ላይ መሆኑ ተገልጿል። ባለፈው ሰኞ በመላዋ ሃገሪቱ በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ ሁለት ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ ከ350 ሚሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውን መንግሥት አሳውቋል። በዚህም በዓለም በተመሳሳይ ተግባር ተይዞ የነበረው ክብረ ወሰን ወደ ስድስት እጥፍ በሚደርስ ቁጥር ተሻሽሏል።
news-51247654
https://www.bbc.com/amharic/news-51247654
ስለአዲሱ ኮሮና ቫይረስ ማወቅ የሚገባዎ ነጥቦች
በቻይናዋ ዉሃን ግዛት የተከሰው ኖቭል ኮሮና ቫይረስ ከቻይና ውጪ ወደ በርካታ አገራት እየተዛመተ ይገኛል።
አሜሪካ፣ ፈረንሳይ፣ ጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ታይዋን፣ አውስትራሊያ በሽታው መታየቱን ሪፖርት ካደረጉ አገራት መካከል ይገኙበታል። የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ቫይረሱ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይዛመት እየወሰደ ስላለው እርምጃ እና ስለ ቫይረሱ የሚከተለውን መረጃ አስተላልፏል። ኮሮና ቫይረስ ምንድነው? የኮሮና ቫይረስ ከቀላል እስከ ከባድ የመተንፈሻ አካል ሕመም የሚያስከትል የቫይረስ ዝርያ ሲሆን ሞትን ሊያስከትል የሚችል ህመም ነው። የቫይረሱ መተላለፊያ መንገዶች በሽታው ያለበት ሰው ሲያስነጥስ፣ ባልበሰሉ ምግቦች፣ ከታማሚው ሰው ጋር በሚደረግ የቅርብ ንክኪ ይተላለፋሉ። የበሽታው ምልክቶች በበሽታው የተያዙ ሰዎች ትኩሳት፣ ሳል፣ የትንፋሽ መቆራረጥ እና የመተንፈስ ችግር ምልክቶች ይታይባቸዋል። በሽታው የጠናባቸው ሰዎች ላይ ደግሞ እንደ የሳምባ ምች እና ከባድ የመተንፈሻ አካላት ህመም ይስተዋላል። በበሽታው መያዛቸውን የጠረጠሩ ሰዎች ምን ማድረግ አለባቸው? ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ካለብዎ ወዲያውኑ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የጤና ተቋም ይሂዱ። የበሽታው ስሜት ከመፈጠሩ አስራ አራት ቀናት በፊት በሽታውን ሪፖርት ወዳደረጉ አገራት ሄደው ከነበረም ይህንንም ለጤና ባለሙያ ያሳውቁ። በሚያስሉበት እና በሚያስነጥሱበት ጊዜ በሽታው ወደ ጤነኛ ሰው እንዳይተላለፍ አፍና አፍንጫን በክንድ፣ በመሃረብ ወይም በሶፍት ይሸፍኑ። አፍን አፍንጫን ለመሸፈን የተጠቀምንበትን ሶፍት በአግባቡ በቆሻሻ መጣያ ውስጥ ማስወገድ እና እጅን ሁልጊዜ በውሃ እና በሳሙና መታጠብ ያስፈልጋል። በበሽታው መያዝዎን ሪፖርት ለማድረግ በነጻ የስልክ መስመር 8335 ወይም የመደበኛ ስልክ 0112765340 መጠቀም ይችላሉ። በሽታው ወዳለባቸው ሃገራት ሲጓዙ ሊወሰዱ የሚገቡ ጥንቃቄዎች ትኩሳት እና የሳል ምልክት ከሚያሳዩ ሰዎች ጋር ንክኪ አለማድረግ በተለይ ደግሞ ከታመሙ ሰዎች ወይም ከአካባቢያቸው ጋር ንክኪ ከፈጠሩ እጅን በሳሙናና ውሃ መታጠብ ያልበሰሉ የእንስሳት ተዋጽኦዎችን አለመመገብ በሕይወት ካሉም ሆነ ከሞቱ የቤት እና የዱር እንስሳት ጋር ንክኪ አለማድረግ ስለ በሽታው በቂ መረጃ እንዲኖረዎ የሚመለከታቸውን ይጠይቁ የመከላከልና የዝግጁነት ሥራዎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቤጂንግ፣ ሆንግ ኮንግ፣ ሻንጋይ፣ ቸንዱ እና ጓንዡ እንደሚበር ይታወቃል። ይህ ቫይረስ ከተሰራጨባቸው ከተሞች መካከል ደግሞ ቤጂንግ እና ሆንግ ኮንግ ተጠቃሽ ናቸው። ከዚህ በተጨማሪም ቦሌ ዓለም አቀፍ አየርማረፊያ በርካታ መንገደኞች አቋርጠውት የሚያልፉት በርካታ ናቸው። የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በዓለም ጤና ድርጅት ምክረ ሀሳብ መሠረት ለሁሉም መንገደኞች የሰውነት ሙቀት የመለካት ሥራ መጀመሩን አስታውቋል።
news-44388828
https://www.bbc.com/amharic/news-44388828
“መሸ መከራዬ”፡ የታዳጊዎች ስቃይ
በኢትዮጵያ በሦስት ክልሎች የተከሰተው የእከክ በሽታ አሁን ደግሞ በአማራ ክልል የተወሰኑ ወረዳዎች ማገርሸቱ ተሰምቷል።
የጥቂቶች ጉዳይ አይደለም። በዓለም 130 ሚሊዮን ሰዎች ቆዳቸውን ያካሉ። እከክ ቀላል የሚመስል ግን ደግሞ ምቾት የሚነሳ የቆዳ ችግር ነው። በዚያ ላይ እረፍት ይነሳል። ብዙውን ጊዜ የሚኾነው ታዲያ እንዲህ ነው፤ ድርቅን ተከትሎ የውሃ እጥረት ይከሰታል። የውሃ እጥረት ደግሞ ለእከክ መዛመት በር ይከፍታል። በኢትዮጵያም የሆነው ይኸው ነው። በቅርብ ዓመታት የተከሰተ ድርቅን ተከትሎ በትግራይ፣ ደቡብና አማራ ክልሎች እከክ በተለይም ብላቴናዎችን እያሰቃየ ነው። ባለፈዉ ዓመት በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የዚህ በሽታ ስርጭት 5.5 በመቶ ነበር። ትግራይ ክልል በበኩሉ ከጥቅምት 2015 እስከ መጋቢት 2016 ባሉት ወራት ብቻ 27ሺህ ነዋሪዎች በዚህ በሽታ ተጠቅተዋል። በተመሳሳይ ዓመት በአማራ ክልል 373 ሺህ ሰዎች በዚህ በሽታ ተጠቅተው እንደነበር የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ያመለክታል። በዚህ ዓመትም የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ በዳባት ወረዳ ባካሄደዉ አንድ ጥናት በወረዳዉ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ 10 በመቶ ሕጻናት የበሽታዉ ተጎጂ እንደሆኑ ያሳያል። ቦርቀዉ ያልጠገቡ ሕጻናት ሲያኩ ማየት በራሱ ያማል። የነገ ተስፋቸዉ እዉን ለማድረግ ረጅም ርቀት እየተጓዙ የሚማሩ ሕጻናት ቀላል የሚመስለዉ፤ ግን ደግሞ ማኅበራዊና ሥነ-ልቦናዊ ጉዳቱ የጎላው የእከክ በሽታ ጠምዶ ይዟቸዋል። ስሙን የማንጠቅሰው የዳባት 03 ትምህርት ቤት ተማሪ የሆነው ታዳጊ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እጁ ላይ የታየዉ የእከክ በሽታ እንቅልፍ እየነሳው ነው። ቀን ላይም ቢኾን መማር እንደተቸገረ ይናገራል። "ቆሻሻ ዉሃ ስነካ እጄን ማሳከክ ጀመረኝ። እናቴ ለሕክምና የሚሆን ገንዘብ ስለሌላት ሐኪም ቤት አልወሰደችኝም" ይላል በሚያባባ የልጅ አንደበቱ። "አስተማሪዋ ደግሞ በሌሎች ተማሪዎች እንዳላስተላልፍባቸው ለብቻዬ አስቀመጠችኝ። ተማሪዎችም ሰላም አይሉኝም፣ አብሬያቸዉ መጫወት አልቻልኩም። ታጋባብናለህ ይሉኛል" ሲል ይህ በሽታ ያሳደረበትን መገለል ይናገራል። "መሸ መከራዬ!" የእከክ በሽታ ከ15 ዓመት በታች የሚገኙ ሕጻናትን በብዛት የሚያጠቃ ሲሆን በንጽህና ጉድለት እንደሚመጣ የሕክምና ባለሞያዎች ይናገራሉ። ዳባት ወረዳ ላይ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች 50 በመቶ ተማሪዎቹ ከገጠር አካባቢ ነው የሚመጡት። ገጠር ደግሞ በቂ ውሃ የለም። በሽታው በባህሪው ከፍተኛ የሆነ ንክኪ በሚኖርበት አካባቢ ቶሎ ይሰራጫል። ማታ ላይ የማሳከኩ ሁኔታ ስለሚጨምር ነው የአካባቢዉ ማኅበረሰብ በሽታውን "መሸ መከራዬ" እያለ የሚጠራው። እከክን ከማከክ ሌላ...? ይሄንን ችግር ለማጥናት ባለሞያዎቹን ወደ ወረዳዉ የላከ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ባደረገዉ የጤና እርዳታ የተወሰኑ ተማሪዎች መድኃኒት ማግኘት እንደጀመሩ የዳባት 03 ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ርስቄ ረታ ወርቁ ይገልጻሉ። "አብዛኛዎቹ ልጆት እጃቸዉ ላይ ነዉ እየታየ ያለዉ። የተወሰነ ተማሪዎች መድኃኒት አግኝተዋል" ብለዋል። ሆኖም ግን ተማሪዎች ላይ የሚያደርሰውን መሸማቀቅ ሳይጠቅሱ አያልፉም። ሰላምታ መለዋወጥ እና መተቃቀፍ በደቂቃዎች ውስጥ በሽታው ለመተላለፍ እድል የሚሰጡ በቂ ምክንያቶች ናቸው። ልብስ መዋዋስና የንጹህ ዉሃ አቅርቦት ችግር የመተላለፍ ዕድሉን በእጥፍ ይጨምሩታል። አብዛኛዎቹ የገጠር ትምህርት ቤቶች በቂ የዉሃ አቅርቦት እንደሌላቸዉ የሚናገረው በጎንደር ዩኒቨርሲ የአካባቢ ጤና አጠባበቅ መምህር ዶክተር ሄኖክ ዳኜ፤ ኅብረተሰቡ ዘንድ ያለዉ የዚህን በሽታ የተሳሳተ ግንዛቤ በመቀየር ረገድ ብዙ መሠራት እንዳለበት ይገልጻል። "የቆየ ምግብ በመብላት የሚመጣ ነው፤ እርግማን ነው እያሉ ሰዎች ሕክምና አይሄዱም። ከዚህ አልፎም በዚህ በሽታ የተጠቁት ሕጻናት ተማሪዎች ሌሊት ስለሚያሳክካቸው በቂ እንቅልፍ ስለማያገኙ ቀን እንቅልፍ ስለሚጥላቸው በአግባቡ ለመማር እየተቸገሩ ነው" ይላል ዶክተር ሄኖክ።
51655635
https://www.bbc.com/amharic/51655635
ኮሮናቫይረስን በተመለከተ ከሚሰራጩ ሃሰተኛ መረጃዎች እንዴት እራስዎችን መጠበቅ ይችላሉ?
በቅርቡ በኮሮናቫይረስ የተያዘ በኢትዮጵያ ተገኘ የሚሉ ሐሰተኛ ዜናዎች በስፋት ሲሰራጩ ተሰተውሏል።
የቫይረሱን ስርጭት እና እየተወሰዱ ስላሉ እርምጃዎች በተመለከተ በመንግሥት ተቋማት እና ተዓማኒ ምንጮች የሚሰጡ መረጃዎችን ብቻ መቀበል ይመከራል። ስለ ቫይረሱ የጠራ ግንዛቤ ይኑርዎ፡ የቫይረሱ ምልክቶች በትኩሳት እና ደረቅ ሳል ይጀምራል። ከሳምንት በኋላ የመተንፈስ ችግር ያጋጥማል። በበሽታው የተያዘ ሰው እስከ 14 ቀናት ምንም አይነት ምልክት ላያሳይ ይችላል። አንዳንድ ሰዎች የበሽታ ምልክት ሳያሳዩ በሽታውን ሊያስተላልፉ ይችላሉ። ኮሮናቫይረስ መድሃኒት አለው? ቫይረሱን ከሰውነት ውስጥ የሚያስወግድ መድሃኒት የለም። ሃኪሞች በሽተኞችን እያከሙ የሚገኙት የታማሚዎችን የበሽታ የመከላከል አቅምን ከፍ በማድረግ ነው። ለመተንፈስ የሚረዱ ቁሶችም ጥቅም ላይ ይውላሉ። እራሴን ከቫይረሱ እንዴት ነው መጠበቅ የምችለው? በቫይረሱ እርሶ ወይም ሌሎች መያዛቸውን ከተጠራጠሩ እራሰዎን ያግልሉ፤ በቤትዎ ይቆዩ ሌሎችም ተመሳሳይ እንዲያደርጉ የበኩልዎን ይወጡ። 8335 ላይ በመደወል ለማሕብሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በፍጥነት ያሳውቁ።
45886117
https://www.bbc.com/amharic/45886117
ኢትዮጵያ ካሏት ሚኒስትሮች ግማሾቹ ሴቶች እንዲሆኑ አደረገች
በትናንትናው የህዝብ እንደራሴዎች ውሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የሚኒስትሮችን ሹመት ሲያፀድቁ ሴቶች ግማሽ ያህሉን ሹመቶች አግኝተዋል።
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሔር በአዲሱ ሹመት ቀዳሚው ተግባርዎት የሚሆነው ምንድን ነው የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር። እሳቸው በመጀመሪያ ቢሮው ውስጥ ያለውን ሁኔታ በሚገባ ማጥናት ውጤታማ ሥራ መስራት የሚያስችሉና በሌላ በኩል ደግሞ እንቅፋት የሚሆኑ ሁኔታዎችን በመለየት የአሰራር፣ የመመሪያና የፖሊሲ ለውጥ የሚያስፈልጋቸው ነገሮች ካሉ ጥናት ላይ በመመስረት ለውጦችን አድርጎ ህብረተሰቡ ጥሩ የሚባል አገልግሎት እንዲያገኝ ማድረግ እንደሆነ አስረድተዋል። እሳቸው በሚመሩት በዚህ ተቋም ውስጥ በቀጣይ በርካታ ሴቶች ወደ ሃላፊነት ይመጡ እንደሆ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፤ ብቃት ኖሯቸው ነገር ግን በተለያየ ምክንያት የሚገባቸውን ሃላፊነት የማያገኙ ሴቶች ስላሉ በርግጥም ወደ ሃላፊነት እንዲመጡ የተቻላቸውን እንደሚያደርጉ ነገር ግን ሴቶች ሴት በመሆናቸው ብቻ ሃላፊነት ቦታ ላይ እንደማይቀመጡ አረጋግጠዋል። •የአዲስ አበባ ወጣቶች በሳምንቱ መጨረሻ እንደሚለቀቁ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ •ከጄኔራሎቹ ሹመት ጀርባ? • ኢንጅነር አይሻ መሃመድ የሃገር መከላከያ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ የነበሩትና አሁን ደግሞ የትራንስፖርት ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የከተማ ህዝብን ከማገልገል ወደ አገርን ማገልገል መምጣታቸው ትልቅ ሃላፊነትና ትልቅ እድልም እንደሆነ ይናገራሉ። "እድሉንም በአግባቡ መጠቀም እንዳለብኝ አምናለውም" ይላሉ። እሳቸው እንደሚሉት አጠቃላይ የሴቶች ሹመቱ በህግ አውጭው በኩል ነገሮች እየተሻሻሉ ቢመጡም በአስፈፃሚው በኩል ግን ከፍተኛ ጉድለት እንዳለ ሲነሳ መቆየቱንና ይህ አዲስ ሹመት ሴቶችን በተለይም በከፍተኛ ደረጃዎች ላይ ማሳተፍን በሚመለከት ያለውን የአፈፃፀም ክፍተት ከመሰረቱ የቀየረና ትልቅ ትርጉም ያለው እርምጃ ነው። የአዲሱን ሹመት ሃምሳ በመቶ ሴቶች ማግኘታቸውን ብዙዎች በተለያየ መንገድ ተመልክተውታል። የሴታዊት መስራች ዶ/ር ስህን ተፈራ "ሃምሳ በመቶ ሹመት ከጠበቅነውና ማንም መጠየቅ ከሚችለው በላይ ነው" ይላሉ። በተለይም ትልልቅ የሆኑና ከዚህ ቀደም በወንዶች ይያዙ የነበሩ የሚኒስትር ሃላፊነቶች ለሴቶች መሰጠቱ አስደሳች እንደሆነ ይናገራሉ። ይህ እርምጃ በደንብ ታስቦቦት የተወሰደ እንደሆነም ያምናሉ ዶ/ር ስህን። ነገር ግን የሴቶችና የህፃናት ሚኒስቴር የተለያዩ እንዲሆኑ ይፈልጉ እንደነበርና ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ሲያብራሩ "የህፃናትና የሴቶች ጥያቄ በጣም ይለያያል ስለዚህ አንድ ላይ እንዲሆኑ ማድረግ ሁሉንም እንደ ተጎጂና ተረጂ የማየት ነገር ነው" የሚል ነው። በሴቶቹ ሹመት ደስተኛ ቢሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ሴት ተሿሚዎች የተናገሩት ቅር መሰኘታቸውን ግን ይናገራሉ። "እንደ ዜጋ ሚሰርቁም ማይሰርቁም ስላሉ ዋናው ነገር መሆን ያለበት ሴቶች ይሰርቃሉ፤ አይሰርቁም ሳይሆን ሃምሳ በመቶ ውክልና ስላለን ነው ሹመቱን ያገኙት መሆን ያለበት" ይላሉ።
news-55717273
https://www.bbc.com/amharic/news-55717273
ኢትዮጵያ በወታደራዊ ኃይል ጥንካሬ ከአፍሪካ 6ኛ ከዓለም 60ኛ ሆነች
በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት በወታደራዊ ኃይል ጥንካሬ ዝርዝር ውስጥ ከገቡት የአፍሪካ አገራት መካከል ኢትዮጵያ የስድስተኛነትን ቦታ ስትይዝ በዓለም 60ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣላች።
የተለያዩ መረጃዎችን መሠረት በማድረግ በየዓመቱ የአገራትን ወታደራዊ ጥንካሬ የሚያሳይ ደረጃን የሚያወጣው 'ግሎባል ፋየር ፓወር' የተባለው ተቋም ለዚህ ዓመት ባወጣው ዝርዝር ውስጥ 35 የአፍሪካ አገራት የተካተቱ ሲሆን ኢትዮጵያ የ6ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። በደረጃው ሰንጠረዥ መሠረት ግብጽ ከአፍሪካ ቀዳሚዋ ስትሆን፣ በመከተል ደግሞ አልጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጄሪያ፣ ሞሮኮና ኢትዮጵያ በቅደም ተከተል ተቀምጠዋል። የኢትዮጵያ ጎረቤት ሱዳን ደግሞ በ10ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ግሎባል ፋየር ፓወር በዓለም ዙሪያ ካሉ አገራት መካከል ባደረገው የወታደራዊ ጥንካሬ ምዘና፣ ከ50 በላይ መመዘኛዎችን የተጠቀመ ሲሆን በዚህም አገራት ያላቸውን የወታደራዊ ኃይል ጥንካሬ በዝርዝር ይፋ አድርጓል። ድርጅቱ የ138 አገራት ወታደራዊ ጥንካሬን የመዘነ ሲሆን፣ በዓለም በወታደራዊ ኃይላቸው ኃያላን ተብለው በቀዳሚነት የተቀመጡት አሜሪካ፣ ሩሲያ፣ ቻይና፣ ሕንድ፣ ጃፓንና ደቡብ ኮሪያ ከአንድ አስከ ስድስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል። በዚህ ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያ በ60ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን ግብጽ በ13ኛ ደረጃ፣ ሱዳን ደግሞ በ77ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። ደረጃውን ያወጣው ግሎባል ፋየር ፓወር የየአገራቱን ወታደራዊ የሰው ኃይል፣ ከታጠቁት መሳሪያዎች ጋር በማቅረብ አነጻጽሮ ነው የዓለም አገራትን ወታደራዊ ኃይል ደረጃን ይፋ ያደረገው። በያዝነው አዲሱ የፈረንጆች ዓመት በዝርዝሩ ውስጥ የ138 አገራት ወታደራዊ ኃይል የተገመገመ ሲሆን፤ የእያንዳንዱ አገር ወታደራዊ አቋም ከተራዘመ የማጥቃትና የመከላከል ወታደራዊ ዘመቻ አቅም አንጻር በተለያዩ መመዘኛዎች ተግምግሞ ነው በግሎባል ፋየር ፓወር ደረጃ የተሰጠው። የዓመቱ የአገራት ወታደራዊ አቅም ደረጃ ዝርዝር ሲወጣ፣ የሕዝብ ብዛት፣ የሠራዊት መጠን፣ የታጠቁት መሣሪያ፣ የገንዘብ አቅም፣ የአቅርቦት ብቃትና መልክአ ምድራዊ አቀማመጥን ጨምሮ ከ50 በላይ መመዘኛዎችን ተጠቅሟል ተብሏል። በዚህ ዓመቱ የአገራት ወታደራዊ አቅም አመላካች ዝርዝር ውስጥ ከ35 የአፍሪካ አገራት 6ኛ፣ ከ138 የዓለም አገራት መካከል ደግሞ በ60ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ኢትዮጵያ፣ ካላት 108 ሚሊዮን ሕዝብ አንድ በመቶው ወይም 162 ሺህ የሚሆነው በሠራዊት አባልነት ታቅፏል ተብሏል። በሠራዊት ብዛት የኢትዮጵያ ሠራዊት 162 ሺህ ወታደሮች ሲኖሯት፣ 24 ተዋጊ አውሮፕላኖች፣ 8 ተዋጊ ሄሊኮፕተሮች፣ 365 ታንኮች፣ 130 ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎች፣ 480 ከባድ መድፎች፣ 180 የሮኬት መተኮሻዎች እንዲሁም 65 ቀላል መድፎች ሲኖሩት የአገሪቱ ዓመታዊ ወታደራዊ በጀት ደግሞ 520 ሚሊዮን ዶላር እንደሆነ ግሎባል ፋየር ፓወር ገልጿል። ከዚህ አንጻር በአህጉረ አፍሪካ በወታደራዊ ኃይል ቀዳሚ የሆነችው ግብጽ ከ104 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት ሲሆን፣ አጠቃላይ የወታደር ብዛቷ ደግሞ 930 ሺህ፣ ታዋጊ አውሮፕላን 250፣ ተዋጊ ሄሊኮፕተር 91፣ ታንኮች 3735፣ ከባድ መድፍ 2200፣ ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎች 11ሺህ ሲኖራት፣ 10 ቢሊዮን ዶላር የመከላከያ በጀቷ እንደሆነ የደረጃው ሰንጠረዥ አመልክቷል። ከ138 አገራት መካከል በ77ኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ሱዳን ከ45 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ሲኖራት፣ አጠቃላይ ያላት ወታደር ብዛት 190 ሺህ ነው። በትጥቅ በኩል 45 ተዋጊ አውሮፕላኖች፣ 43 ተዋጊ ሄሊኮፕተሮች፣ 830 ታንኮች፣ 450 ብረት ለበስ ተሽከርካሪ አላት። የአገሪቱ ዓመታዊ የመከላከያ በጀት 4 ቢሊየን ዶላር ነው። በአፍሪካ አህጉር ግብጽ በወታደራዊ ኃይል የመጀመሪያውን ደረጃ ስትይዝ፣ ኢትዮጵያ 6ኛ፣ ሱዳን ደግሞ 10ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። በዚህ ዝርዝር ውስጥ ከኢትዮጵያ ጎረቤት አገራት መካከል ኬንያ ከአፍሪካ 12ኛ፣ ደቡብ ሱዳን 22ኛ፣ ሶማሊያ ደግሞ 34ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። በግሎባል ፋየር ፓወር የአገራት ወታደራዊ ጥንካሬ የደረጃ ዝርዝር ውስጥ ከ54ቱ የአፍሪካ አገራት የተካተቱት 35 ብቻ ናቸው። በዚህም ምክንያት በወታደራዊ የጥንካሬ አመላካች የደረጃ ሰንጠረዡ ውስጥ 19 የአፍሪካ አገራት ያልተካተቱ ሲሆን የኢትዮጵያ ጎረቤት የሆኑት ኤርትራና ጂቡቲ በዚህ ውስጥ ካልገቡት መካከል ናቸው። የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ውስጥ፣ በአፍሪካ ሕብረት እና በተባበሩት መንግሥታት ስር የሠላም ማስከበር ተልዕኮን ተቀብሎ በመሰማራት ከሌሎች የአህጉሪቱ አገራት የበለጠ ሚና እንዳለው የሚነገር ሲሆን፤ ለተባበሩት መንግሥታት የሠላም ማስከበር ስራ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮችን በማቅረብ ቀዳሚ መሆኑ ይጠቀሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በአገሪቱ ሠራዊት አደረጃጀት ላይ ለውጦች እየተደረጉ መሆናቸው፣ እንዲሁም ሠራዊቱን በሥልጠናና በትጥቅ የማዘመን ሥራ እተካሄደ መሆኑ መገለጹ ይታወቃል።
news-49068333
https://www.bbc.com/amharic/news-49068333
የሱዳን አማጺ መሪ አዲስ አበባ ላይ እየተደረገ ካለ ድርድር ተይዘው ሊባረሩ እንደነበር ተነገረ
በሱዳን ለተከሰተውን ፖለቲካዊ ቀውስ መፍትሄ ለማግኘት ዓላማ አድርጎ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ባለው ድርድር አንድ የሱዳን አማጺ ቡድን መሪን አዲስ አበባ ላይ በቁጥጥር ስር ለማዋል ሙከራ መደረጉ ተነገረ።
የሱዳን ፍትህና እኩልነት የተሰኘው ተቃዋሚ ቡድን መሪ የሆኑትን ጂብሪል ኢብራሂምን ከበርካታ ባልደረቦቻቸው ጋር ወደ ሱዳን ተላልፈው ሊሰጡ ነበር። በዳርፉር ዋነኛው አማጺ ቡድን የሆነው የፍትህና እኩልነት እንቅስቃሴ መሪ የሆኑት ጂብሪል ኢብራሂም የተባሉት ግለሰብ ናቸው ተይዘው ከኢትዮጵያ እንዲባረሩ ሊደረግ የነበረው ተብሏል። • የኢትዮጵያን አደራዳሪነት የሱዳን ህዝብ እንዴት ይመለከተዋል? • የሱዳን አለመረጋጋት በኢትዮጵያ ላይ የሚያስከትለው ተጽእኖ ምንድነው? • ኦማር አል-በሽር ከወራት በኋላ ታዩ ቢቢሲ ክስተቱን ለማጣርት የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሆኑትን አቶ ነቢያት ጌታቸውን ያናገረ ሲሆን ቃል አቀባዩ ስለጉዳዩ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል። በሱዳን ታጣቂ ቡድኖችና በተቃዋሚዎቹ ጸረ መንግሥት እንቅስቃሴ መካከል እየተደረገ ያለው ድርድር የተጀመረው ሃገሪቱ ውስጥ ለወራት የዘለቀውን ፖለቲካዊ ቀውስ ለማብቃት ያስችላል የተባለው ስምምነት በጊዜያዊው ወታደራዊ አስተዳደርና በተቃዋሚዎች መካከል ከተደረሰ ከቀናት በኋላ ነው። ትናንት ዕሁድ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ምንም ዓይነት መረጃ ሳይሰጡ የሱዳን ፍትህና እኩልነት የተሰኘው ተቃዋሚ ቡድን መሪ የሆኑትን ጂብሪል ኢብራሂምን ከበርካታ ባልደረቦቻቸው ጋር ነጥለው በመያዝ ወደ ቦሌ አየር ማረፊያ ወስደዋቸው እንደነበር በድርድሩ ላይ ተሳታፊ ከሆኑ ተቃዋሚዎቹ መካከል አንዱ ለቢቢሲ ተናግሯል። ነገር ግን የአፍሪካ ሕብረት አደራዳሪዎች በክስተቱ ውስጥ ጣልቃ ገብተው በድርድሩ ላይ መጥፎ ውጤት ሊኖረው ይችል የነበረውን የቃዋሚዎቹን ከአዲስ አበባ የማባረር ድርጊትን አስቁመውታል። በሱዳን ያጋጠመውን ቀውስ ለመፍታት የአማጺ ቡድኑን ጨምሮ ሁሉም አካላት በወደፊቱ የሃገሪጡ እጣ ፈንታ ላይ መስማማት እንዳለባቸው ይታመናል። በሱዳን ሠራዊት ጄነራሎችና በተቃውሞ እንቅስቃሴው መሪዎች መካከል ባለፈው ሳምንት የተደረሰው ሥልጣንን የመጋራት ስምምነት ረገድ ለውጦች ታይተዋል። ሆኖም ግን ዋነኛው ተቃዋሚ ኃይል የሆኑት የሱዳን አብዮታዊ ግንባር በስምምነቱ ባለመካተቱ ከሕዝቡ ጋር የሱዳንን የሰላም ጥረት ወደፊት ለማራመድ እነዚህ ተቃዋሚዎች የሚሳተፉበት ድርድር ለማደረግ ነው አዲስ አበባ ላይ የተገናኙት።
news-54642320
https://www.bbc.com/amharic/news-54642320
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ 'በሰብዓዊነት ላይ በሚፈፀሙ ወንጀሎች' በስዊድን ክስ ቀረበባቸው
ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን (አርኤስኤፍ) የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን በሰብዓዊነት ላይ በሚፈፀሙ ወንጀሎች ክሱን ስዊድን ለሚገኘው አቃቤ ህግ አቅርቧል።
ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ በተጨማሪ ሰባት ከፍተኛ ባለስልጣናትንም በሰብዓዊነት ላይ በሚፈፀሙ አለም አቀፍ ወንጀሎች ቡድኑ ወንጅሏቸዋል። ለዚህም እንደ መነሻ የሆነው ለሁለት አስርት አመታት በእስር ላይ የሚገኘው ኤርትራዊ-ስዊድናዊ ጋዜጠኛ ዳዊት ይስሃቅ ጋር በተያያዘ ነው። ባለስልጣናቱ ጠንከር ያለ ምርመራ እንዲከፈትባቸው፣ ጋዜጠኛውን በማገት፣ በማንገላታትና ያለበትንም ደብዛ በማጥፋት ክስ ይመሰርትባቸዋል ብሎም እንደሚያንም ቡድኑ በድረ-ገፁ አስፍሯል። በአለም ላይ ለረዥም አመታት በእስር ላይ የሚገኝ ጋዜጠኛ እንደሆነም ቡድኑ በድረገፁ አስፍሯል። ቡድኑን በመወከል ክሱን ያቀረቡት ሁለት ስዊድናዊ ጠበቆች ሲሆኑ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን ጨምሮ፣ የውጭ ጉዳይ፣ የፍትህና የማስታወቂያ ሚኒስትሮችና ሌሎች አራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ተካትተውበታል። "ባለስልጣናቱ ምንም እንኳን ደረጃቸው ከፍ ያለ ቢሆንም ዳዊትን ይስሃቅን አስረው ለሃያ አመታት እንዲበሰብስ ያደረጉት ግለሰቦች ለወንጀላቸው ኃላፊነት ሊወስዱ ይገባል" በማለት በክሱ ላይ ፊርማቸውን ካስቀመጡት አንዱ የሆኑት ጠበቃና የኖቤል የሰላም አሸናፊ ሽሪን ኢባዲ ናቸው ስዊድናዊ ኤርትራዊ ጋዜጠኛ ዳዊት ይስሃቅ "እነዚህ ግለሰቦች በፍፁም ማን አለብኝነት የፈለጉትን እንዲያደርጉና መክሰስ የሚችሉም አገራት ከተዋቸው ፍትህ በኤርትራ ሊሰፍን አይችልም" ብለዋል ጠበቃው ጋዜጠኛና ገጣሚው ዳዊት ይስሃቅ ነፃ ኤርትራን አገለግላሁ በማለት ወደ ትውልድ አገሩ ተመልሶም የለውጥ ደጋፊ የሆነ ጋዜጣም አቋቁሞም ነበር። ኤርትራም የግል ጋዜጦችን ዘጋች እንዲሁም የሚቀርቡበትን ትችት ዝም ለማሰኘት የኤርትራ መንግሥት በጀመረው ዘመቻም ፖለቲከኞችን፣ ጋዜጠኞችንና ተማሪዎችን ለእስር ዳርጓል። ዳዊትን ጨምሮ በርካታ የግል ጋዜጣ አዘጋጆችም በጎሮጎሳውያኑ 2001 ለእስር ተዳረጉ። ጋዜጠኛው ቤተሰቡን፣ ጠበቃውን እንዲሁም በተደጋጋሚ ከተባበሩት መንግሥታትም ሆነ የስዊድን ተወካዮች እንዲያገኙት ጥያቄ ቢቀርብም ማንም ጎብኝቶት አያውቅም። በህይወት እንዳለ የተጠረጠረው በጎሮጎሳውያኑ 2005 ሲሆን በእስር ላይ በፈታኝ ሁኔታ እንደሚገኝም የቡድኑ ድረ-ገፅ ጠቁሟል።
news-51500322
https://www.bbc.com/amharic/news-51500322
ኡጋንዳ ተማሪዎቿን ከቻይና ለማስወጣት ገንዘብ የለኝም አለች
የኡጋንዳ መንግሥት በኮሮናቫይረስ ክፉኛ በተጠቃችው የቻይናዋ ዉሃን ከተማ ወስጥ የሚገኙትን ተማሪዎች ወደ አገራቸው ለመመለስ የሚያስችል ገንዘብ የለኝም አለ።
ቁጥራቸው 105 ይሆናሉ የተባሉት ኡጋንዳዊያን ተማሪዎችን አውሮፕላን ተከራይቶ ከዉሃን ለማስወጣት ከፍተኛ ወጪን የሚጠይቅ በመሆኑ አዳጋች መሆኑን መንግሥት ገልጿል። ነገር ግን ተማሪዎቹ የመዒኣስፈልጋቸውን ነገሮች እንዲያሟሉ የሚያግዝ የተወሰነ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ተጠቅሷል። በኡጋንዳ ፓርላማ ውስጥ በተካሄደ ክርክር ላይ እንደተናሳው በአሁኑ ጊዜ ተማሪዎቹን ወደ አገራቸው ለመመለስ ዕቅድ የለም። ይህም ለሳምንታት በሰቆቃና በበሽታው የመያዝ ስጋት ውስጥ ለቆዩት ተማሪዎች አሳዛኝ ውሳኔ ነው ተብሏል። የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ጄን ሩት አቼንግ ትናንት ለፓርላማው እንደገለጹት ኡጋንዳ የበሽታውን ወረርሽኝ ለመቆጣጠር የሚያስችል ዕውቀትም ሆነ የተለየ ተቋም የላትም። በተጨማሪም ሚኒስትሯ ውሃን ውስጥ ለሚገኙት ለተማሪዎቹ መደገፊያ የሚሆን 61 ሺህ ዶላር በስልካቸው በኩል እንደሚላክላቸው የተናገሩ ቢሆንም እያንዳንዱ ተማሪ ምን ያህል ገንዘብ እንደሚደርሰው ግልጽ አይደለም። ከተማሪዎቹ መካከልም የተወሰኑት ገንዘብ፣ ምግብና የአፍንጫና አፍ መሸፈኛ ጭንብል እንዳለቀባቸው በመግለጽ እያማረሩ ነው። ተማሪዎቹ እራሳቸው ከዉሃን እንዲወጡ እንዲደረግ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ሲያካሂዱ ቆይተዋል። ከቻይና ወደ ኡጋንዳ ትናንት ሐሙስ የገቡ ከ260 በላይ የሚሆኑ ኡጋንዳዊያንና ቻይናዊያን ለሁለት ሳምንት እራሳቸውን ከሌሎች ሰዎች አግልለው እንዲቆዩ መንግሥት ጠይቋል። ባለፈው ሳምንት በኢንቴቤ አየር ማረፊያ በኩል ከቻይና የገቡ 100 የሚሆኑ ሰዎች በለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲቆዩ ተደርጓል። ተገቢው ምርመራ ሳይደረግ ሰዎች ወደ አጋንዳ እየገቡ ባለበት በአሁኑ ወቅት መንግሥት የወሰደው ይህ እርምጃ በሽታውን ለመቆጣጠር ምን ያህል ውጤታማ ይሆናል በሚል ጥያቄ እየቀረበ ነው።
news-52604644
https://www.bbc.com/amharic/news-52604644
ኮሮናቫይረስ፡ ባራክ ኦባማ አሜሪካ ለወረርሽኙ የሰጠችውን ምላሽ "ቅጥ አምባሩ የጠፋው" ሲሉ ተቹ
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ቀውስ ለመቆጣጠር በሰጡት ምላሽ ላይ ተተኪያቸውን ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕን በከፍተኛ ሁኔታ ተችተዋል።
ባራክ ኦባማ ከጎርጎሳውያኑ 2009 እስከ 2017 ድረስ አሜሪካን በፕሬዚደንትነት አስተዳድረዋል ባራክ በግል ባደረጉት የስልክ ስብሰባ ላይ አሜሪካ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የምታደርገው ጥረት " ቅጥ አምባሩ የጠፋው" ነው ሲሉ ተናግረዋል። የቀድሞ ፕሬዚደንቱ ይህን ያሉት የቀድሞ የሥራ ባልደረቦቻቸው ለጆ ባይደን ፕሬዚደንታዊ ምርጫ እንዲሰሩ ባበረታቱበት ወቅት እንደሆነ ሲኤንኤን ዘግቧል። •ቤታቸው እስር ቤት የሆነባቸው ጥቃት የሚደርስባቸው ሴቶች •በኮሮናቫይረስ ከተቀጠፉ ኢትዮጵያውያን መካከል ጥቂቶቹ "ለወረርሽኙ ጥሩ የሚባሉ መንግሥታትንም ሊፈትን ይችላል። ነገር ግን ይሄ ወረርሽኝ ለኔ ምንድነው የሚል የግለኝነት ስሜት በዳበረበት ሁኔታና የሁሉንም ፍላጎት አሽቀንጥሮ የጣለ አሰራር በመንግሥታችን ላይ መታየቱ ከፍተኛ ቀውስ ነው" ብለዋል። ዋይት ሃውስ በምላሹ ፕሬዚደንት ትራምፕ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የወሰዱት እርምጃ የአሜሪካዊያንን ሕይወት ታድጓል ብሏል። ኦባማ በስልክ ውይይታቸው ወቅት፤ የሪፐብሊካኑ ተተኪያቸው ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የወሰዱት ምላሽ ላይ መንግሥታቸው ተጠያቂ እንደሚሆን አሳስበዋል። ኦባማ አክለውም በቀድሞ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ማይክል ፍልይን የወንጀል ክስ ለማንሳት የተደረገውን ውሳኔም በጥብቅ ተችተዋል። ኮሮናቫይረስ በአሜሪካ እስካሁን ባለው መረጃ በአሜሪካ ከ77 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸው ሲያልፍ 1.2 ሚሊየን ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ይህም ከዓለም አገራት ከፍተኛው ነው። አብዛኞቹ የአገሪቷ ግዛቶች ባለፈው ወር የእንቅስቃሴ ገደብ የጣሉ ሲሆን አሁን ላይ ግን የተጣሉ ገደቦችን እያላሉ እና ሰዎች ወደ ሥራ እንዲመለሱ እየፈቀዱ ነው። ይሁን እንጅ የጤና ባለሥልጣናት ውሳኔው የቫይረሱን ሥርጭት ሊያባብሰው ይችላል በማለት እያስጠነቀቁ ነው። የትራምፕ አስተዳደር ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የሚከተለው ዘዴ ወጥነት የጎደለው ነው። በፈረንጆቹ የካቲት ወር 'ይጠፋል' በሚል የወረርሽኙን አስከፊነት ያጣጣሉት ሲሆን ባለፈው ወር አጋማሽ ላይ ደግሞ ወረርሽኙ አስከፊ መሆኑን ተናግረዋል። ባሳለፍነው የፈረንጆቹ ሚያዚያ ፀረ ተህዋስያን ኬሚካል መውሰድ በሽታውን ሊከላከል ይችላል ሲሉ አስተያየት የሰጡ ሲሆን፤ ባለሙያዎች ሃሳባቸውን ውድቅ አድርገውታል። ባለፈው ሳምንት ደግሞ መንግሥታቸው ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ያቋቋመውን ግብረ ኃይል እንደሚበትኑ አስታውቀው ነበር። በኋላ ላይ ደግሞ ሃሳባቸውን ለውጠው ግብረ ኃይሉ ሥራውን እንደሚቀጥል በመግለፅ፤ አኮኖሚውን መክፈት ላይ ትኩረት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
50792400
https://www.bbc.com/amharic/50792400
የአብዲሳ አጋ ጀብዱ በሥዕል መጽሐፍ
የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ ሚናስ ኃለፎም ካህሳይ ከፒያሳ ወደ አዲሱ ገበያ በታክሲ ሲሄድ አንዳች አስደናቂ ታሪክ በራድዮ ይሰማል። ስለ አብዲሳ አጋ የጀግንነት ታሪክ።
ተራኪው አብዲሳ ጣልያን ሳሉ የሠሩትን ጀብዱ ያወሳል። ይህ ታሪክ ለሚናስ አዲስ እንደነበረ ይናገራል። የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪ ሳለ በአማርኛ መጽሐፍ ላይ ስለ አብዲሳ አጋ አንብቧል፤ ተምሯል። በራድዮ የሰማው ታሪክ ግን ዝርዝር መረጃ የያዘ ነበር። "አማርኛ መጽሐፍ ላይ አብዲሳ ከጣልያን እሥር ቤት በመስኮት ከማምለጣቸው ያለፈ መረጃ አልነበረም።" • ለኢትዮጵያዊያን የንባብ ወዳጆች ምርጡ መጽሐፍ የትኛው ነው? • ኮሎኔል መንግሥቱን ትግል ለመግጠም ቤተ መንግሥት የሄደው ደራሲ • ማንችስተር ዐይኑን የጣለባቸው የአቶ ምሥጢረ ኃይለሥላሴ ልጆች የራድዮው ትረካ፤ አብዲሳ ከእሥር ቤት አምልጠው የራሳቸውን ጦር መልምለው፣ እሥር ቤቱን ሰብረው ገብተው፣ እሥረኞችን ካስመለጡ በኋላ ፋሺስቶችን እና ናዚዎችን መዋጋታቸውን ይዳስሳል። "ይሄን ታሪክ ጭራሽ አላውቀውም ነበር። ስሰማው በጣም ተመሰጥኩ፤ ታሪኩ ልብ ወለድ ፊልም ነው የሚመስለው፤ ከሰማሁ በኋላ ጥናት ማድረግ ጀመርኩ።" ሚናስ ጥናቱን ጨርሶ፣ የአብዲሳን የጣልያን የተጋድሎ ታሪክ ወደ መጽሐፍ ለውጦታል። "አጋ" የተሰኘው በሥዕል የተደገፈው ይህ መጽሐፍ (ግራፊክ ኖቭል) የተመረቀው ባለፈው ሳምንት ነበር። መጽሐፉ መነሻ ያደረገው አብዲሳ ጣልያን ውስጥ ሲዋጉ ይመዘግቡት የነበረውን የዕለት ውሎ ማስታወሻ (ዳያሪ) እንደሆነ ሚናስ ይናገራል። መጽሐፉ በብዛት ገበያ ላይ ስለሌለ ከአሮጌ ተራ በውድ እንደገዛው ያስታውሳል። ይህ ብዙዎች ስለ አብዲሳ ጥልቅ መረጃ እንዲያገኙ የረዳው መጽሐፍ የ "አጋ" መነሻም ሆነ። "የአብዲሳን ታሪክ ወደ ኮሚክ ሥዕሎች ቀይሬ ነው የሠራሁት፤ ታሪኩ ጣልያን ለሁለተኛ ጊዜ ኢትዮጵያን ከወረረችበት ጊዜ ኢትዮጵያ ነፃ እስክትወጣ ያለውን ጊዜ ይሸፍናል" ሲል ያስረዳል። በአብዲሳ የሕይወት ታሪክ እጅግ የሚገረመው ሚናስ፤ ለመጽሐፉ የሚያስፈልገውን ጥናት ካጠናቀቀ በኋላ በስድስት ወር ውስጥ ሥዕሉንና ጽሑፉን ቢጨርስም ስፖንሰር ለማግኘት ስለተቸገረ መጽሐፉን ቶሎ ማሳተም አልቻለም ነበር። መጽሐፉ በኢትዮጵያ የሰርቢያ ኢምባሲ ድጋፍ መታተሙን ጠቅሶም፤ በቀጣይም የሚደግፈው ካገኘ መጽሐፉን በተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የማሳተም እቅድ እንዳለው ገልጿል። ሚናስ እንደሚለው፤ የአብዲሳን የጀብዱ ታሪክ ከኢትዮጵያውያን ባሻገር ሌሎችም እንዲረዱት በማሰብ "አጋ"ን በ500 ቅጂ በእንግሊዘኛ ጽፎ አሳትሞታል። "የኢትዮጵያን ታሪክ ባህር እንደማሻገር አስበዋለሁ" ሲልም ይገልጻል። "አብዲሳ አጋ ብዙ ሊደረጉ የማይችሉ የጀግንነት ተግባሮች ፈጽመዋል፤ ሰው ከጠላት አገር እሥር ቤት አምልጦ ሊያስብ የሚችለው የራሱን ሕይወት ስለማዳን ነው። አብዲሳ ይህን አላደረጉም። ወደ እሥር ቤቱ ተመልሰው ዩጎዝላቪያን ጨምሮ ጣልያን ስትወራቸው የነበሩ አገሮችን ታሣሪዎች አስፈትተው ተዋጉ" ሲል የሚያስደንቀውን የአብዲሳ ጀብዱ ያስረዳል። የኢትዮጵያውን ጀግኖች ታሪክ በስፋት በታዳጊዎችና በወጣቱ ትውልድ ዘንድ አለመታወቁን ሚናስ ይገልጻል። "ዓላማዬ ታዳጊዎችና ወጣቶች ታሪካቸውን እንዲያውቁና የኢትዮጵያም ታሪክ ድንበር ተሻግሮ በመላው ዓለም እንዲሰራጭ ማድረግ ነው" ሲልም ግቡን ያስረዳል።
news-51780956
https://www.bbc.com/amharic/news-51780956
የኮሮናቫይረስ ህመም ምልክቶችና በበሽታው ላለመያዝ ማድረግ ያለብን ጥንቃቄ
የኮሮናቫይረስ በዓለም ዙሪያ ባሉ ከሰማኒያ በላይ አገራት ውስጥ ተዛምቶ 130 ሺህ ያህል ሰዎች በበሽታው የተያዙ ሲሆን ከ4 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ለሞት ተዳርገዋል።
በዚህም ሳቢያ ወረርሽኙ የወቅቱ የዓለም ሕዝብ ስጋት ሆኗል። ስለዚህ ስለበሽታው ምንነትና እራስን ለመከላከል መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ ጠቃሚ መረጃዎችን እነሆ። የኮሮናቫይረስ በሽታ ምልክቶች የትኞቹ ናቸው? የኮሮናቫይረስ የመተንፈሻ አካላት በሽታ ሲሆን ሲጀምር በትኩሳት ሲሆን በማስከተልም ደረቅ ሳል ይነረዋል። ከሳምንት በኋላ ደግሞ የትንፋሽ ማጠርን ያስከትላል፤ በዚህ ሳቢያም አንዳንድ በበሽታው የተያዙ ሰዎች የህክምና እርዳታ ሊያስፈልጋቸው ይችላል። የእነዚህ ምልክቶች መታየት ግን በበሽታው የመያዝ ምልክት ላይሆን ይችላል። ምክንያቱም ምልክቶቹ ከተለመዱት የጉንፋንና የኢንፍሉዌንዛ ምልክቶች ጋር ተመሳሳይ ነው። ኮሮናቫይረስ የከፋ በሚሆን በት ጊዜ ኒሞኒያን፣ ሳርስን፣ የውስጥ አካላት ሥራ ማቆምን እንዲሁም ሞትን ሊያስከትል ይችላል። በዕድሜ የገፉና አስም፣ የስኳር በሽታ፣ የልብ ህመምን የመሳሰሉ ቀደም ሲል የነበሩ የጤና ችግሮች ያሉባቸው ሰዎች በበሽታው ሲያዙ በጠና የመታመም ዕድላቸው ከፍተኛ ነው። ሰዎች በበሽታው ከተያዙ በኋላ ምልክቶችን እስከሚያሳዩ ድረስ እስከ 14 ቀናትን ሊወስድ እንደሚችል የዓለም የጤና ድርጅት ገልጿል። ነገር ግን አንዳንድ አጥኚዎች ምልክት የማየቱ ነገር አስከ 24 ቀናት ድረስ ሊቆይ እንደሚችል ጠቁመዋል። እንዴት እራሴን መጠበቅ እችላለሁ? የጤና ተቋማት እንደሚሉት በሽታውን ለመከላከል እጅን በመደበኝነት በደንብ መታጠብ እጅግ ጠቃሚ ነው። እስካሁን በሽታው እንዴት እንደሚተላለፍ በእርግጠኝነት የሚታወቅ ነገር የለም። ነገር ግን የኮሮና አይነት ቫይረሶች በበሽታው የተያዙ ሰዎች በሚያስሉበትና በሚያስነጥሱበት ወቅት በሚያወጧቸው ጥቃቅን ጠብታዎች አማካይነት ነው። ስለዚህም ስናስልና ስናስነጥስ አፍንጫና አፋችንን በሶፍት ወይም በክርናችን እንሸፍን፤ ፊታችንን እጃችንን ሳንታጠብ አንንካ። በተጨማሪም ከታመሙ ሰዎች ጋር የቀረበ ንክኪ ከማድረግ መቆጠብ በሽታውን ለመከላከል ያግዛል። የህክምና ባለሙያዎች እንደሚሉት የፊት መሸፈኛ ጭንብሎች የሚፈለገውን ያህል በሽታውን ለመከላከል አያስችሉም። 'የኮሮናቫይረስ አለብኝ ብዬ ካሰብኩ ምን ማድረግ አለብኝ?' በበሽታው ተይዣለሁ ብለው የሚያስቡ ሰዎች አስፈላጊውን ምክርና የህክምና ድጋፍ ለማግኘት ለሚመለከታቸው የጤና ተቋማት ማሳወቅ አለባቸው። በበሽታው ተያዞ ይሆናል ተብሎ ከሚታሰብ ሰው ጋር የቀረበ ንክኪ ከነበረዎት፤ እራስዎን ለተወሰነ ጊዜ ከሌሎች ሰዎች አግልለው እንዲቆዩ ሊነገርዎት ይችላል። ስለዚህ በበሽታው ከተያዙ ሰዎች ጋር የሚኖርን የቀረበ ንክኪ ማስወገድ ይኖርብዎታል። በሽታው ከተከሰተባቸውና ከሌሎች አገራት የተመለሱ ከሆነ ምናልባትም ለተወሰነ ጊዜ እራስዎን አግልለው መቆየት ሊያስፈልግዎት ይችላል። ኮሮናቫይረስ ምንያህል አደገኛ ነው? ሊድንስ ይችላል? የዓለም ጤና ድርጅት ከ56 ህሙማን ላይ በሰበሰበው መረጃ መሰረት በኮሮናቫይረስ ከተያዙ አምስት ሰዎች መካከል አራቱ ቀለል ያሉ የበሽታውን ምልክቶች ብቻ ያሳያሉ። በዚህም መሰረት፡ ምንም እንኳን አሃዞቹ አስተማማኝ ባይሆኑም በበሽታው ከተያዙት መካከል የሚሞቱት ሰዎች ብዛት ዝቅተኛ እንደሆነ ተስተውሏል፤ ይህም ማለት በበሽታው ከተያዙ ሰዎች መካከል ከመቶው አንድ ወይም ሁለቱ ብቻ የሚሆኑት ናቸው ለሞት የሚዳረጉት። በአሁኑ ጊዜ በሺዎች የሚቆጠሩት በህክምና ላይ ያሉ ሲሆን ሊሞቱ ይችላሉ። በዚህም ሳቢያ የሞት መጠኑ በመቶኛ ከፍ ሊል ይችላል።
news-46589150
https://www.bbc.com/amharic/news-46589150
ሳዑዲ የአሜሪካ 'ጣልቃ ገብነትን' አወገዘች
አሜሪካ ሳዑዲ በየመን እያደረገች ላለችው ጦርነት የምታደርገውን ወታደራዊ ድጋፍ እንድታቆም ሴኔቱ ውሳኔ ማስተላለፉን ሳዑዲ አውግዛለች።
ትራምፕ አሜሪካ ከሳዑዲ ጋር ስላላት የንግድና ወታደራዊ ግንኙነት ቀጣይነት ሲሟገቱ ቆይተዋል በጋዜጠኛ ኻሾግጂ ግድያም ሴኔቱ የሳውዲው ልዑል ሞሃመድ ቢን ሳልማን ተጠያቂ በማድረጉም ነው ሳዑዲ አሜሪካን የወቀሰችው። የሳዑዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሴኔቱን ውሳኔ እውነተኛ መረጃ ላይ ያልተመሰረተና ጣልቃ ገብነት የታየበት ብለውታል። ባለፈው ሳምንት ሴኔቱ ያስተላለፈው የውሳኔ ሃሳብ የመፅደቅና ህግ የመሆን እድሉ እጅግ አነስተኛ ነው ቢባልም ሳውዲ የሴኔቱን እርምጃ አውግዛ ብቻ አላረፈችም። ይልቁንም ለትራምፕ ቁጣዋን ማሳወቅን መርጣለች። • ''የሚፈርስ የግድቡ አካል የለም'' የግድቡ ዋና ሥራ አስኪያጅ • የአለማየሁ ተፈራ ፖለቲካዊ ካርቱኖች የሳዑዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያወጣው መግለጫ ይህን የአሜሪካ እርምጃ አገሪቱ እንደምትቃወም አስታውቋል። የሳዑዲ መግለጫን ተከትሎ እስካሁን አሜሪካ የሰጠችው ይፋዊ ምላሽ የለም። ሴኔቱ ሃሙስ እለት ያስተላለፈው ውሳኔ በአገሪቱ የ1973 የጦርነት ህግ መሰረት፤ የአሜሪካ ኮንግረስ አካል የሆነ ክፍል አገሪቱ የወታደራዊ ድጋፏን እንድታቋርጥ ውሳኔ ሲያስተላልፍ ይህ የመጀመሪያው ነው ተብሏል። • ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን? አስገዳጅ ያልሆነው የሴኔቱ ውሳኔ ሃሳብ እስላማዊ ፅንፈኞችን እየተዋጉ ከሚገኙት ውጭ አሜሪካ በየመን ግጭት ያሳተፈቻቸው ሃይሎቿን እንድታስወጣ ለትራምፕ ጥሪ የሚያስተላልፍ ነው። ሴኔቱ በጋዜጠኛ ሃሾግጂ ግድያም የሳውዲው ልዑል ሞሃመድ ቢን ሳልማንን ተጠያቂ ያደረገው በሙሉ ድምፅ ነው። አሜሪካ ባለፈው ወር ለሳዑዲ የጦር አውሮፕላኖች ነጃጅ መሙላት አቁማ ነበር። አሁን ደግሞ ይህ የሴኔቱ የውሳኔ ሃሳብ ህግ መሆን ከቻለ ክልከላው የሚፀና ይሆናል ማለት ነው።
news-50218736
https://www.bbc.com/amharic/news-50218736
እሷ ማናት? #4፡ ከሒሳብ ጋር በአጋጣሚ ነው የተዋደድነው
በሒሳብ ትምህርት የዶክትሬት ዲግሪዋን (ፒኤች ዲ) ለማግኘት እየሰራች ነው። ሰዎች እምብዛም ገፍተው በማይሄዱበት የትምህርት ዓይነት እንዴት ውጤታማ ልትሆን እንደቻለች አጫውታናለች።
ስሜ ኤቢሴ አዱኛ ይባላል። ተወልጄ ያደኩት በነቀምት ከተማ ነው። የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርቴን በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ፣ ሁለተኛ ዲግሪ ደግሞ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተምርያለሁ። በአሁን ሰዓት ደግሞ የሦስትኛ ዲግሪ ትምህርቴን በዴንማርክና በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች እየተከታተልኩ ነው። • የኮምፒዩተር ትምህርት ለኬኒያ ሴት እስረኞች ሁለተኛ እድል ይሰጣቸው ይሆን? • አንድም ሴት የፓርላማ አባል የሌላት ሃገር ሒሳብ መረጠሽ ወይንስ መረጥሽው ? የሙያ ሕይወቴ ከሒሳብ ጋር የተቆራኘ ይሆናል ብዬ አልገመትኩም ነበር። ለመጀመሪያ ዲግሪ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በተመደብኩበት ወቅት የሒሳብ ትምህርት ሳልመርጥ በአጋጣሚ ደረሰኝ። ከዚያ በኋላ ግን እኔና ሒሳብ በጣም ተዋደድን። እኔ ልምረጠው ሒሳብ ይምረጠኝ የሚታወቅ ነገር የለም። የሒሳብ ትምህርትን ከድሮም ፈርቼው አላውቅም። ዩኒቨርሲቲ ገብቼ ትምህርቱ ሲደረሰኝ ጥሩ ነጥብ ማስመስገብ ጀመርኩኝ፤ እየወደድኩትም መጣሁ። በዚያ ላይ ይህ ትምህርት ለሴት ይከብዳል ለወንድ ደግሞ ይመቻል የሚል አመለካከት የለኝም። ማንም ሰው ፍላጎት ካለው፣ ከጣረና በሥራ ካስደገፈው ይሳካል ብዬ ስለማስብ የሒሳብ ትምህርትን አጥብቄ ይዤ ቀጠልኩበት፤ እዚህም ደረስኩኝ። አሁንም ቢሆን ከምወዳቸው ትምህርቶች መካከል ትልቁን ቦታ የያዘው ሒሳብ ነው። የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪ እያለሁ 'ጊዜ ቤት' ላይ ሌሎች ልጆች ሸምድደው በፍጥነት እንደሚሉት አልነበርኩም፤ ነገር ግን በልጅነቴ በተወሰነ ደረጃ ይህንን 'የጊዜ ቤት' እሠራ ነበር። በዚያ ወቅት ተማሪ እያለሁ አባቴ የሒሳብ መምህር ስለነበረ በሒሳብ ጥሩ መረዳት እንዲኖረኝ አድርጓል። በጭንቅላቴ ሸምድጄ ከመያዝ ይልቅ ተረድቼ ማስላት ይቀለኝ ነበር። የሒሳብ ጥቅም የተለያየ ነው። ለምሳሌ ሒሳብ በሁለት ይከፈላል፤ 'ፕዩር ማቴማቲክስና አፕላይድ ማቴማቲክስ' ተብለው ይለያሉ። • ሴት ተመራቂዎች ለምን ሥራ አያገኙም? • ሚሼል ኦባማ በአሜሪካ እጅግ ተወዳጇ ሴት ተባሉ እኔ የምማረው 'አፕላይድ ማቴማቲክስ' በተጨባጭ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚጠቅም ነው። ለምሳሌ የምመረምራቸው ስሌቶች ኤች ሲቪ ለተባለው የጉበት ቫይረስ መፍትሔ ለማግኘት የሚረዳ ነው። ስለዚህ ሒሳብ በሕይወታችን ያሉን ተጨባጭ ችግሮች መፍትሔ ለመስጠት የሚረዳ የትምህርት ዓይነት ነው። ነገ የሚሆንን ነገር ለመተንበይ ሒሳብ ችግሮቻችንን በቁጥር አስልተን ለማስቀመጥ ይረዳናል። የሒሳብ ምሁሮች ከስሌቱ በኋላ ቀመሩን ከነመፍትሔው ያስቀምጡልናል። የምህድስና ሙያ ያላቸው ሰዎች ደግሞ እንዲህ ዓይነት ቀመሮችን በሥራ ላይ ያውላሉ። ስለዚህ ከሒሳብ ሙያተኞች ይልቅ በምህንድስና ውስጥ የተሰማሩ ሰዎች በይበልጥ ማስረዳት ይችላሉ። ውጣ ውረዶችን ለማለፍ በሥራም ሆነ በኑሮ እንደማንኛውም ሰው የተለያየ መሰናክል ይገጥመኛል። ነገር ግን የችግሩን ያህል ሳይሆን ነገሮችን ከአቅሜ አንፃር ነው የምገመግማቸው። ችግር እንደሚያበረታኝና እንደሚያጠነክረኝ ስለማውቅ ሁሌም መውጫ ቀዳዳ ነው የምፈልገው። አንዳንዴ ሰዎች ፊቴንና ዕድሜዬን አይተው ይገምቱኛል። አንዳንዴ ጊዜ እንዲያውም በሴትነቴ ጭምር ለመመዘን ይሞክራሉ። እንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች ሲገጥሙኝ ደግሞ እራሴን በደንብ አስተዋውቃለሁ። ምን ማድረግ እንደምችል፣ ማን እንደሆንኩ እና ፍላጎቴ ምን እንደሆነ አስፈላጊ በሆነበት ቦታ ሁሉ እናገራለሁ። ይህ ደግሞ በሕይወቴ የምፈልገውን ነገር በሙሉ እንዳገኝ አድርጎኛል በዚያ ላይ ተግባቢ ሰው ነኝ። ሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪ መማር ጊዜን ስለሚፈልግ የጊዜ እጥረት ያጋጥማል። የፒኤች ዲ ትምህርት ምግብ የምበላበት ጊዜ እንኳን አይሰጥም፣ ያስጨንቃል ደግሞም ድብርት ያስከትላል። ቢሆንም ግን ያለኝን ጊዜ አብቃቅቼ ከጓደኞቼም ሆነ ከቤተሰቦቼ ጋር ጊዜ አሳልፋለሁ። ከዚህ ሁሉ ግን ያለንን ጊዜ በደንብ ከተጠቀምንበት የምንፈልገውን ማሳካት ይቻላል ብዬ አስባለሁ። • ሴት አስገድዳ ከወንድ ጋር ወሲብ ብትፈጽም፤ አስገድዶ መድፈር ይባላል? • ከመጀመሪያው 'የብላክ ሆል' ምስል ጀርባ ያለችው ሴት ፍቅር እና ፒኤች ዲ እንደሚታወቀው በአገራችን ሴት ልጅ ስትበልጥ ወንዶች ብዙ ደስተኛ አይደሉም፤ ሁሉም እንዲዚህ ናቸው ማለቴም አይደልም ነገር ግን እንዲህ ዓይነት አስተሳብ አለ። በሁሉም መንገድ ወንድ የበላይ ሆኖ አንዲታይ የሚፈልጉ አሉ። እንደእኔ አመለካለከት የትምህርት ደረጃ እና ፍቅር የተለያዩ ናቸው። ለመጀመሪያ ዲግሪ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በተመደበችበት ወቅት የሒሳብ ትምህርት ሳትመርጥ በአጋጣሚ ደረሳት። በኋላ ግን ሒሳብና እርሷ በፍቅር ወደቁ። ስኬቴ ችግር የሚሆንበት ካለ ለማስተናገድ አልችልም። የቤተሰቤ አባላት በማደርገው ጥረት ላይ በጣም የደግፉኛል። ጓደኛና የምወደው ሰው የምለውም ሰው ልክ እነደዚህ የሚደግፈኝ መሆን አለበት። ለምን ትበልጠኛለች ካለ ግን ይህ ፍቅር ነው ወይንስ ቅናት? ብዙ ሴቶች ያለንን አቅም የተረዳነው አይመስለኝም። እንችላለን ብለን ካመንን ማድረግ አያቅተንም። ይህን ከተረዳን ደግሞ በውበት፣ በጋብቻ እና በገንዘብ መወሰን የለብንም። እራሳችን ያለምነው ትልቅ ቦታ ላይ መድረስ እንደምንችል ማሰብና መጣር ነው ያለብን። ስለዚህም የሚያጋጥሙንን መሰናክሎች በእራሳችን ማለፍ መቻል አለብን። እንደዚህ ወደፊት ከተራመድን አገራችንን ወደፊት ለመምራት አያቅተንም። ያለንን አቅማችንንና መላ የማበጀት ጥበባችንን እንጠቀምበት ብዬ ለሴቶች ምክሬን እሰጣለሁ።
news-46683709
https://www.bbc.com/amharic/news-46683709
በ2018 ጎልተው የታዩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ
የቢቢሲ 'ሌተርስ ፍሮም አፍሪካ' የአፍሪካውያን ጸሐፍት መልእክት ማስተላለፊያ መድረክ ነው። በቅርቡ ከተነበቡ ጽሑፎች አንዱ የጋናዊቷ ጋዜጠኛ ኤልዛቤት ኦሄን ነው።
ጠቅላይ ሚንስትሩ ወታደሮችን ፑሽ-አፕ ሲያሰሩ ጋዜጠኛዋ ሊገባደድ ቀናት የቀረውን የአውሮፓውያን 2018 ስትቃኝ በጉልህ የምታነሳው ኢትዮጵያን እንዲሁም መሪዋን ነው። ጋዜጠኛዋ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ዓመቱን አይረሴ አድርገውታል ትላለች። • የዶክተር ዐብይ አሕመድ 'ፑሽ አፕ' በዋነኛነት የምታነሳው ጠቅላይ ሚንስትሩ ወታደሮችን ፑሽ-አፕ ያሰሩበትን እለት ነው። ወታደሮች በጉልበት ወደ ቤተ መንግሥት ከገቡ መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ የሚሆንበት እድል ሰፊ ቢሆንም፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ ሁኔታውን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ጠቁማ፤ "ጠቅላይ ሚንስትሩ ሥልጣን ከያዙ በኋላ ሊሆኑ ይችላሉ ተብለው የማይታሰቡ ነገሮችን አድርገዋል። ስለሳቸውም ሆነ ሥራቸውን ስለሚያከናውኑበት መንገድ ለመገመት አስቸጋሪ ነው" ብላለች። ከኤርትራ ጋር እርቀ ሰላም ወርዷል የኢትዮጵያና የኤርትራ እርቀ ሰላም ተለያይተው ለነበሩ ቤተሰቦች ብስራት ነበር ኢትዮጵያ በአምባገነናዊ አስተዳደር ትችት ሲሰነዘርባት ቆይቷል። ከኤርትራ ጋር ለዓመታት መኳረፏም ያሳማታል። ጋዜጠኛዋ፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ ሥልጣን በጨበጡ በወራት ዕድሜ ከኤርትራ ጋር እርቀ ሰላም መውረዱን፤ ከዓመቱ ጉልህ ክንውኖች አንዱ ትለዋለች። • የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት ኢኮኖሚያዊ ትርፍ? የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መነሳቱ፣ ብዙ የፖለቲካ እስረኞች መፈታታቸው፣ የፖለቲካ ስደተኞች ወደ ሀገር ቤት መመለሳቸው፣ እገዳ ተጥሎባቸው የነበሩ ድረ ገጾችና የቴለቭዥን ጣቢያዎች ነጻ መውጣታቸውም አይዘነጋም። በኢትዮ-ኤርትራ እርቀ ሰላም፤ ተለያይተው የነበሩ ቤተሰቦች በአይነ ስጋ ለመተያየት በቅተዋል። የአውሮፕላንና የመኪና እንቅስቃሴ ወደነበረበት ተመልሷል። ስልክ መደዋለም ይቻላል። ሴቶች በአመራር የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት ሳሕለወርቅ ዘውዴ ጠቅላይ ሚንስትሩ ከካቢኔ አባላቾቻቸው ግማሹን ሴቶች አድርገዋል። ሴት ፕሬዘዳንትም ተሹሟል። የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊን ጨምሮ ሌሎችም ሴቶችም ወደ አመራር የመጡበት ዓመት መሆኑን ጋዜጠኛዋ ታስረግጣለች። • የሴቶች መብት ታጋይዋ ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ማን ናቸው? ጋዜጠኛዋ ኤልዛቤት ኦሄን ስለ አመራር ለውጥ ስታነሳ ደቡብ አፍሪካንም ትጠቅሳለች። ፕሬዘዳንት ጃኮብ ዙማ ሥልጣን እንዲለቁ ከተደረገ በኋላ ሲሪል ራማፎሳ ወደ አስተዳደር መጥተዋል። የሀገሪቱ ራስ ምታት የሆነወን ሙስና ይዋጋሉ ተብሎም ተስፋ ተጥሎባቸዋል። ጋዜጠኛዋ አዲሶቹን የደቡብ አፍሪካና የኢትዮጵያ መሪዎች ስታነጻጽር "ራማፎሳ ሥራቸውን በፑሽ-አፕ ባይሆንም በዱብ ዱብ ጀምረዋል" በማለት ነው። •"ገዳ የወደፊቱ የፖለቲካ ስርዓት መሆን ይችላል" ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ ዓመቱ በአፍሪካ ምን ይመስል ነበር? የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ አፍሪካን የሚያንጓጥጥ ዘረኛ ቃል ከአፋቸው መውጣቱን ተከትሎ ተቺዎቻቸው በእጥፍ ጨምረዋል። ባለቤታቸው ሜላኒያ ትራምፕ ደግሞ ጋና፣ ማላዊ፣ ግብጽና ኬንያን መጎብኘታቸው ይታወሳል። ጋዜጠኛዋ ትራምፕ ለስደተኞች ያላቸውን የተዛባ ምልከታ፤ ፈረንሳይ ከሚኖረው ማሊያዊ ስደተኛ ማማዶ ጋሳማ ስኬት ጋር ታነጻጽረዋለች። ጨቅላ ህጻንን ከፎቅ ከመውደቅ የታደገው ስደተኛ፤ ከፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የክብር ዜግነት ማግኘቱ ይታወሳል። ስደተኞች በበጎ እንዲታዩ ያስቻለ የዓመቱ ክስተት ነበር። በሌላ በኩል ዩጋንዳዊው ሙዚቀኛና የሕዝብ እንደራሴ በዓመቱ ጎልተው ከወጡ ግለሰቦች መካከል ይጠቀሳል። • ቦቢ ዋይን፦ ኡጋንዳዊው እንደራሴ እንደገና ታሠረ ሀገር በመክዳት ተከሶ ታስሮ የነበረው፤ ቦቢ ዋይን የዩጋንዳን መንግሥት በመተቸት ይታወቃል። በእስር ላይ ሳለ ከደረሰበት እንግልት ካገገመ በኋላ በአንድ መድረክ ማቀንቀኑንም ይታወሳል። ኮንጓዊው ዶክተር ዴኒስ ሙክዌጌ የኖቤል የሰላም ተሸላሚ የሆኑት በዚሁ በ2018 ነበር። በተለይም ለተደፈሩ ሴቶች በሚሰጡት ህክምና ዶክተሩ ተመስግነዋል። • ዐብይ አሕመድ ለኖቤል ሽልማት ታጭተዋል? የላይቤሪያው ፕሬዘዳንት ጆርጅ ዊሀ የቀድሞ አሰልጣኛቸው አርሰን ቬንገርን ወደ ትውልድ ሀገራቸው መጋበዛቸውን ጋዜጠኛዋ በጽሁፏ አካታለች። "ቬንገር የዊሀን የእግር ኳስ ህይወት ስኬታማ በማድረጋቸው የላይቤሪያ ትልቅ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል" ኔልሰን ማንዴላ በህይወት ቢኖሩ ዘንድሮ 100ኛ ዓመታቸውን ያከብሩ ነበር። ልደታቸው ታስቦ በዋለበት እለት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ወደ ደቡብ አፍሪካ ማቅናታቸው ይታወሳል። • ዊኒ ማንዴላ ሲታወሱ • ማንዴላን ውትድርና ያሰለጠኑት ኢትዮጵያዊ በጸረ አፓርታይድ ትግሉ የሚታወቀው ታዋቂው ጃዝ ሙዚቀኛ ሂዊ ማሳኬላ እንዲሁም ዊኒ ማንዴላም ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩበት ዓመት ነው። የኮፊ አናን የቀብር ስርዐት በ2018 የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊና ዲፕሎማት ኮፊ አናን በ80ኛው አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። • ታላቁ ዲፕሎማት ኮፊ አናን ሲታወሱ የቀብር ስነ ስርዐታቸው በትውልድ ሀገራቸው ጋና ውስጥ ተከናውኗል "የቻይናና አፍሪካ ፍቅር እንደቀጠለ ነው" ትላለች ጋዜጠኛ ኤልዛቤት ኦሄን። ቤዢንግ ውስጥ በተካሄደ ኮንፈረንስ ላይ የቻይናው ፕሬዘዳንት ዢ ዢፒንግ ለአፍሪካ 60 ቢሊዮን ዶላር ለመለገስ ቃል መግባታቸውንም ታጣቅሳለች።
49470848
https://www.bbc.com/amharic/49470848
መንታ ጠብቃ አምስት የተገላገለችው ኡጋንዳዊት እናት
መንታ ለመውለድ የጠበቀችው እናት ሶስት ሴቶችና ሁለት ወንዶች በድምሩ አምስት ልጆችን በመገላገሏ ድንጤ ላይ እንደወደቀች የሃገሪቷ ሚዲያ ደይሊ ሞኒተር ዘግቧል።
በሃገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል ነዋሪ የሆነችው ሶፊያት ሙቴሲ ከዚህ ቀደም መንታ እንዲሁም ሶስት ልጆችን በአንዴ ተገላግላ የነበረ ሲሆን አንድ ልጅም እንዳጣች ጋዜጣው ዘግቧል። •ለኃይማኖት እኩልነት የሚታገሉት የሰይጣን አምላኪዎች •ኢትዮጵያውያን 'የሌሉበት' ስለ ኢትዮጵያ የሚዘክረው ሬድ ሲ ዳይቪንግ ሪዞርት' ፊልም "አምስት ልጆች መገላገሌ በጣም ነው ያስገረመኝ፤ ምክንያቱም ከዚህ ቀደም ለምርመራ የጤና ማእከል ሄጄ በታዬሁበት ወቅት የህክምና ባለሙያዎች መንታ እንዳረገዝኩ ነው የነገሩኝ" በማለት አግራሞቷን ለጋዜጣው አጋርታለች የሚረዳትም አካል ባለመኖሩ ልጆቿንም እንዲያሳድጉላትም እርዳታን እየሻተች ነው። •ፀረ-መውለድ ፍልስፍናን ያውቁታል? እንደ ሞኒተር ዘገባ ከሆነ የመጀመሪያ ባሏን በሞት ያጣች ሲሆን የአሁኑ አጋሯ ደግሞ ሃያ ልጆች አሉት ተብሏል። በኢጋንጋ ናካቩሌ ሆስፒታል አዋላጅ የሆነችው ሞውሪን ባቢን በበኩሏ አራሷም ሆነ ጨቅላዎቹ በሙሉ ጤንነት ላይ እንዳሉ ገልፃለች። "በሆስፒታል በሰራሁባቸው አመታት አምስት ልጅ የወለደች እናት አጋጥሞኝ አያውቅም፤ አብዛኛውን ጊዜ መንታ ወይም ሶስት ልጆች ናቸው የሚያጋጥሙን፤ ህፃናቱ በሙሉ ጤና ቢወለዱም እንክብካቤንና ክትትልን ይሻሉ" ብላለች።
51772675
https://www.bbc.com/amharic/51772675
'ኮሮናቫይረስ አለብህ' በሚል ቡጢ የቀመሰው የኦክስፎርድ ተማሪ
ኢሲያዊያን ከዚህ ኮሮናቫይረስ ወዲህ በየአካባቢው መገለል እየደረሰባቸው ነው። በቅርቡ በትዊተር የተሰራጨ አጭር ቪዲዮ 'ኮሮናዎች መጡ" በሚል ቻይናዎች በኬንያ ናይሮቢ ውስጥ ሰዎች ሲሸሽዋቸው ያሳይ ነበር።
በቡጢ የተነረተው ጆናታን ቀዶ ጥገና ያስፈልገኛል ብሏል አሁን ደግሞ በእንግሊዝ ሎንዶን በጎብኚዎች በሚዘወተረው የኦክስፎርድ ጎዳና አንድ የ23 ዓመት ወጣት ከበድ ያለ ድበደባ ደርሶበታል። ጆናታን ሞክ አደጋው የደረሰበት በምሽት ወደ ቤቱ እየሄደ ነው። 4 ወጣቶች "ቁም! ኮሮና አለብህ" በሚል ፊቱ እስኪያባብጥ ደብድበውታል። ጆናታን ሞክ ትውልዱ ከሲንጋፖር ነው። ከአራቱ ደብዳቢዎቹ ሁለቱ ገና የ16 እና 15 ዓመት ልጆች ሲሆኑ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ ካደረገ በኋላ ለቋቸዋል። • ከኮሮናቫይረስ ጋር የሚደረገውን ፍልሚያ የሚመሩት ሰው • በቲቪ የምናያቸው ፑቲን እውነተኛው ናቸው ወይስ ቅጂ? • በኮሮናቫይረስ ፍራቻ በእግር ሰላምታ የሰጡት ፕሬዚዳንት ጆናታን ሞክ በዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ለንደን ተማሪ ነው። የተደበደበውም በቶተንሃም ኮርት ሮድ አጠገብ ነው። እሱ እንደሚለው መጀመርያ የደበደበው ሰው 'ሲያየኝ በጣም ተናዶ ነበር' ይላል። እየደበደበኝ ጮክ ብሎ "ያንተን ኮሮናቫይረስ ወደ አገሬ እንዲገባ አልፈልግም፤ ውጣልን" ሲል ይጮኽ ነበር ብሏል። ሁለተኛው ደብዳቢም በቡጢ አፍንጫዬን ነርቶኛል። ጆናታን ሞክ ለቢቢሲ እንደተናገረው ቀኝ ዐይኑ ሥር ያለ አጥንት በድብደባው በመሰበሩ በቅርቡ ቀዶ ጥገና ያደርጋል። ኮሮናቫይረስ ተነስቶባታል ተብላ የምትገመተው ሁቤ ግዛት፣ ውሃን ከተማ በቻይና የምትገኝ በመሆኑ በመልካቸው ቻይናዊያንን የሚቀርቡ ኢሲያዊያን በተቀረው ዓለም ለተለያዩ መገለል፣ መንጓጠጥና ጥቃት እየተዳረጉ እንደሆነ መረጃዎች እየወጡ ነው። ይህ ዜና እስኪዘገብበት ሰዓት ድረስ በመላው ዓለም 100ሺ 598 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። 3410 ሰዎች ሞተዋል። 55ሺ 991 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።
news-48530979
https://www.bbc.com/amharic/news-48530979
የኦሮምኛ ድምጻዊ ዳዲ ገላንን ገድሏል የተባለው የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት
ድምጻዊ ዳዲ ገላንን ገድሏል የተባለው ተከሳሽ፣ ከተማ ረጋሳ፣ የእድሜ ልክ እስራት ተበየነበት።
የኦሮምኛ ዘፋኙ ዳዲ ገላን የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ ግንቦት 28 2011ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ከተማ ረጋሳ ድምጻዊ ዳዲ ገላንን ለመግደል ሆነ ብሎና አቅዶ የካቲት 4 2011 ዓ.ም. ከምሽቱ 5፡30 ላይ በሊበን ጩቃላ ወረዳ በሽጉጥ ሁለት ግዜ ተኩሶ ደረቱን መትቶ መግደሉ ተረጋግጧል ብሏል። ድምጻዊ ዳዲ ገላን በጥይት ተመትቶ የሞተ ዕለት አሟሟቱ ለደስታ በተተኮሰ ጥይት እንጂ ሆነ ተብሎ የተደረገ አይደለም የሚል እምነት ነበር። በወቅቱ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የድምጻዊው ጓደኛ እና የሊበን ጩቃላ ወረዳ ፖሊስ ፅፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ግርማ ሚደቅሳ ድምጻዊው ለደስታ በተተኮስ ጥይት መገደሉን ገልጸው ነበር። • ኦሮምኛ ዘፋኙ ለደስታ በተተኮሰ ጥይት ህይወቱን አጣ • የኢትዮጵያ ተፈናቃዮች አይንና ጆሮ እንደተነፈጋቸው ተገለፀ የአስክሬን የምረመራ ውጤት አርቲስቱ ሁለት ግዜ በሽጉጥ ጥይት ተመትቶ መገደሉን ያረጋገጠ ሲሆን አንድ ጥይት የሟች አስክሬን ውስጥ ተገኝቷል ተብሏል። ፍርድ ቤቱ በተጨማሪም ከሟች አስክሬን ውስጥ የወጣው ጥይት አይነት ተከሳሽ ከሚይዘው ሽጉጥ የተተኮሰ መሆኑ ተረጋግጧል ብሏል።ተከሳሹ ግድያውን አልፈጸምኩ ሲል ቢከራከርም የቀረበበትን ማስረጃ መከላከል ግን አልቻለም። አቃቤ ሕግ በተከሳሹ ላይ የቅጣት ማክበጃ ሃሳብ የለኝም በማለት ፍርድ ቤቱ ውሳኔ እንዲያስተላልፍ ጠይቋል። የተከሳሽ ጠበቃ በበኩላቸው ደንበኛቸው ከዚህ በፊት ተከስሰው እንደማያውቁ፣ የተመሩ ሰው አለመሆናቸውን፣ የጦር መሳሪያ አጠቃቀም ላይ ያላቸው ግንዛቤ አነስተኛ መሆኑን እንዲሁም የበርካታ ቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውን በመጥቀስ ቅጣቱ እንዲቀንስ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል። ተከሳሹም አቅመ ደካማ የሆኑ ሰዎችን ጨምሮ 9 የቤተሰብ አባላት አስተዳዳሪ መሆናቸውን በመጥቀስ ፍርድ ቤቱ ቅጣቱን እንዲቀንስላቸው ተማጽነዋል። የግራ ቀኙን ክርክር ያደመጠው የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሸ ከተማ ረጋሳ ድምጻዊ ዳዲ ገላንን መግደሉ በመረጋገጡ የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት በይኖበታል። ድምጻዊ ዳዲ ገላን ፓለቲካዊ ይዘት ያላቸውን የኦሮምኛ ሙዚቃዎችን በመጫወት የሚታወቅ ሲሆን በዘፈኖቹ በተደጋጋሚ ለእስር ተዳርጎ ነበር።
41465741
https://www.bbc.com/amharic/41465741
"ካታሎንያ በሕዝበ-ውሳኔ አገር የመሆን መብቷን አሸነፈች"
እሁድ በተካሄደው የካታሎንያ ህዘበ-ውሳኔ ካታላን ከስፔን ተገንጥላ ራሷን የቻለች አገር የመሆን መብቷን አሸንፋለች።
ካታሎናውያን ባንዲራቸውን በማውለብለብ ብሄራዊ መዝሙር ሲዘምሩ የካታሎንያ መሪ ካርለስ ፑይግዴሞንት እንደተናገሩት የስፔን አንድ ግዛት የነበረቸው ካታሎንያ አገር የመሆን መብቷን አነጋጋሪና ግጭት ከተቀላቀለበት ከተባለው ሕዝበ-ውሳኔ በኋላ አሸንፋለች። ከአንድ ወገን በኩል ነፃነትን ለማወጅ በሩ ክፍት ነበርም በሚል አስተያየተቸውን ሰጥተዋል። ከዚህም በተጨማሪ የካታሎንያ ኃላፊዎች እንደተናገሩትም በእሁዱ ምርጫ ላይ የመረጡት 90% ነፃነትን የሚደግፉት ናቸውም ብለዋል። ምንም እንኳን የመጣው የህዘብ ቁጥር 42.3 ቢሆንም የስፔን ህገ-መንግስታዊ ፍርድ ቤት የምርጫ ጣቢያዎችን ህገወጥ ናቸው በሚል ያወጀ ሲሆንም ፖሊስም ምርጫውን ለማገድ ኃይልን በመጠቀሙ ብዙ መቶዎች ቆስለዋል። የፖሊስ ኃይል በምርጫ ጣቢያዎቹ ላይ የመምረጫ ካርዶቹንም በኃይል ወስደዋቸዋል።በሌላ በኩል በዚህ ጭካኔ በተሞላበት የመብትና የነፃነት ጥሰት የተነሳ 40 የሚሆኑ የካታሎንያ የንግድና ሌሎች ማህበራት በግዛቱ ትልቅ የሚባለውን ሕዝባዊ አመፅ ማክሰኞ ቀን ጠርተዋል። እሁድ ማታ ቁጥራቸው ብዙ የሚባል የነፃነት ደጋፊዎች በባርሴሎና ባንዲራቸውን እያውለበለቡ እንዲሁም የካታሎንያ ብሄራዊ መዝሙር ሲዘምሩ አምሽተዋል። ትይዩ በሆነ መልኩ የነፃነት ተቃዋሚዎችም በባርሴሎና እንዲሁም በሌሎች የስፔን ግዛቶች የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል። ግጭቱ ምን ያህል የከበደ ነበር? የካታሎንያ መንግስት እንደሚለው ከ800 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በግጭቱ ምክንያት አደጋ ደርሶባቸዋል። የ ስፔን የአገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር በበኩሉ ግጭቱን ተከትሎ 12 ፖሊሶች እንደቆሰሉና ሶስት ሰዎችም እንደታሰሩ ተናግረዋል። ይህንንም ተከትሎ 92 የምርጫ ጣቢያዎች ተዘግተዋል። በጊሮና ግዛት የተደራጀ የፖሊስ ኃይል ካርለስ ፑይጅዲሞንት የሚመርጡበት የምርጫ ጣቢያ ላይ በኃይል ሰብረው በመግባት ሊመርጡ የተዘጋጁትን በኃይል እንዲወጡ አስገድደዋቸዋል። ፑይጅዲሞንትም ሌላ የምርጫ ጣቢያ ሄደው እንዲመርጥ ተገደዋል። በተለያዩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የታዩ ቪዲዮዎችም እንደሚያሳዩት በጊሮና ግዛት ህዘቡን ይከላከሉ የነበሩ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ሳይቀሩ በፖሊስ ድብደባ ደርሶባቸዋል። የባርሴሎና ከንቲባ አዳ ኮላው ምንም መከላከያ በሌለው ህዘብ ላይ ፖሊስ ያደረሰውን ጥቃት ያወገዙ ቢሆንም የስፔን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ሶራያ ሳንዘ ደ ሳንታማሪያ በተቃራኒው ፖሊስ ስርአት ባለውና በተመጣጣኝ መልኩ የአፀፋ ምላሽ እንደሰጠ ተናግረዋል።
news-51633957
https://www.bbc.com/amharic/news-51633957
የኢራን ምክትል ጤና ጥበቃ ሚንስቴር ኮሮናቫይረስ እንደያዛቸው ተገለጸ
የኢራን ምክትል ጤና ጥበቃ ሚንስትር ኢራጅ ሀሪርቺ ኮሮናቫይረስ እንዳለባቸው ተገለጸ።
በአገሪቱ 15 ሰዎችን የገደለውን በሽታ በቁጥጥር ሥር ለማዋል እየተጣጣረች ሲሆን፤ ኢራጅ ሀሪርቺ ራሳቸውን አግልለው አስፈላጊውን ህክምና መውሰድ እንደጀመሩ ተናግረዋል። ምክትል ጤና ጥበቃ ሚንስትሩ ሰኞ እለት ስለ ኮቪድ-19 ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ፤ ግንባራቸውን በተደጋጋሚ ሲጠራርጉ ታይተው ነበር። በእለቱ የአገሪቱ ባለሥልጣናት የበሽታውን የስርጭት ስፋት በተመለከተ ሀሰተኛ መረጃ ሰጥተዋል መባሉን አስተባብለው ነበር። እስካሁን 95 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል ቢባልም፤ ትክክለኛ ቁጥሩ ከዚህ ሊጨምር እንደሚችል ተገልጿል። • ስለአዲሱ ኮሮና ቫይረስ ማወቅ የሚገባዎ ነጥቦች • ኮሮና ቫይረስ መጠሪያ ስሙን አገኘ • በአፍሪካ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ህመምተኛ ተገኘ የዓለም ጤና ድርጅት እንዳለው፤ በአገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ድንገት ማሻቀቡ አሳሳቢ ነው። የተባበሩት መንግሥታት የቀጠናው ዋና ዳይሬክተር ወደ ኢራን ሊያደርጉት የነበረው ጉዞ የተሸጋገረ ሲሆን፤ የዓለም ጤና ድርጅት ቃል አቀባይ እንዳሉት፤ የቴክኒክና የጤና ባለሙያዎች ቡድን እንዲሁም የምርመራ መሣሪያ በቀጣይ ሁለት ቀናት ወደ ኢራን ይደርሳል። እስካሁን በመላው ዓለም በኮቪድ-19 እንደተያዙ የተመዘገበው ሰዎች ቁጥር ከ80,000 በላይ ሲሆን፤ 2,700 ሰዎች ሞተዋል። ከኢራን የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፤ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በኢራን መንግሥት ይፋ ከተደረገው አሀዝ ይበልጣል። ኢራን በሽታው በተሰራጨባቸው አካባቢዎች ሰዎች ተለይተው የሚቆዩባቸው ሥፍራዎች እንደማታዘጋጅ አሳውቃለች። የኢራን ባለስልጣኖች ማቆያ ሥፍራዎችን "ኋላ ቀር ናቸው፤ አናምንባቸውም" ብለዋል።
news-54400083
https://www.bbc.com/amharic/news-54400083
ኮሮናቫይረስ፡ ከትራምፕ በፊት በኮቪድ የተያዘችው የትራምፕ አማካሪ ሆፕ ሂክስ ማነች?
ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እና ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጠው የፕሬዝደንቱ የቅርብ ረዳታቸው ሆፕ ሂክስ በኮሮናቫይረስ መያዟ ከተረጋገጠ በኋላ ነው።
ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እና አማካሪያቸው ሆፕ ሂክስ ከፕሬዝደንቱ ለወራት ሲያጣጥሉት በቆዩት ቫይረስ መያዛቸው ከተነገረ በኋላ በተደጋጋሚ ስሟ እየተነሳ ያለችው ሆፕ ሂክስ ለበርካቶች አዲስ ናት። የ31 ዓመቷ ወጣት የቀድሞ ሞዴል ስሟ በአደባባይ እንዲነሳ ብዙም ፍላጎት የላትም። የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር የነበሩት አንቶኒ ስካራሙቺ በ2017 ላይ ከሥራቸው ሲሰናበቱ ነበር ሆፕ ሂክስ በቦታቸው ተተክታ የፕሬዝደንቱ የቅርብ ረዳት የሆነችው። ሆፕ በዚህ የሥራ መደብ ላይ ስትመደብ ምንም አይነት የፖለቲካ ልምድ አልነበራትም። ታዲያ በወቅቱ የ28 ዓመት ወጣት እና የፖለቲካ ልምድ የሌላት ሆፕ እንዴት በአሜሪካ መንግሥት ውስጥ ለፕሬዝደንቱ የቀረበ ከፍተኛ ሥልጣንን ልትይዝ ቻለች? ሆፕ፣ ኢቫንካ እና ትራምፕ ሆፕ 2017 ላይ የፕሬዝደንቱ ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ሆና ከመሾሟ አምስት ዓመታት በፊት ከትራምፕ ቤተሰብ ጋር ትውውቅ እንደነበራት ይነገራል። ሆፕ፤ የዶናልድ ትራምፕ የመጀመሪያ ልጅ የሆነቸው ኢቫንካ ለምትመራው የፋሽን ኩባንያ የሕዝብ ግንኙነት ሥራን በመስራት ነበር ከፕሬዝደነቱ ልጅ ጋር የቀረበ ግንኙነት ነበራት። በተጨማሪም ሆፕ ሞዴል ነበረች። ራልፍ ሎውረን ለተሰኘው እውቅ የፋሽን ኩባንያ በሞዴልነት ሰርታለች። ለኢቫንካ የፋሽን ኩባንያ የሕዝብ ግንኑነት ባለሙያ ሆና በሰራችበት ወቅትም ስኬታማ ነበረች። ከኢቫንካ ትራምፕ ጋር በቅርበት መስራቷና በሥራዋም ስኬታማ መሆኗ የዶናልድ ትራምፕን ትኩረት እንድታገን እድል ከፍቶላታል። በመጀመሪያ ላይም እአአ 2014 ትራምፕ ለሚያንቀሳቅሱት የሪል ስቴት ኩባንያቸው የሕዝብ ግንኙነት ሥራ እንድትከውን እራሳቸው መርጠው ሾሟት። ሚሊየነሩ ትራምፕ ሆፕ ሂክስ በምታከናውነው ሥራ ደስተኛ ስለነበሩ "አስደናቂ ሰው ናት" ሲሉ ለአንድ መጽሔት ተናግረው ነበር። ሆፕ ሂክስ ሆፕ ወደ ፖለቲካው እንዴት ገባች? ሆፕ ከአሜሪካ ባሻገር ዓለምን ወደሚያሽከረክረው የአሜሪካ የፖለቲካ መድረክ የተሳበችው በድንገት ነበር። ይህም አለቃዋ ለፕሬዝደንትነት እጩ ሆነው እአአ በ2015 መግቢያ ላይ የመጀመሪያ የምርጫ ቅስቀሳቸውን ለማድረግ ጉዞ ሲያደርጉ እንደ በአጋጣሚ ሆፕ ሂክስ አብራቸው ነበረች። በአሜሪካ ፕሬዝደንታዊ ፉክክር ውስጥ ከትራምፕ ጎን የመሆን እድል የገጠማት ሆፕ ከፖለቲካው ይልቅ እያከናወነችው በነበረው ሪል ስቴት ኩባንያው የሕዝብ ግንኙነት ሥራ ላይ የማተኮር ፍላጎቷ ነበር። ነገር ግን የምርጫ ቅስቀሳው እየተጠናከረ ሲሄድ ሆፕ የእጩ ፕሬዝደንቱ የምርጫ ቅስቀሳ አካል መሆን ወይም የትራምፕ ሪል ስቴት ኩባንያ ሕዝብ ግነኙነት ኃላፊ ሆኖ መቀጠል በሚለው ላይ መወሰን ነበረባት። በሥራዋ የሚተማመኑባት ዶናልድ ትራምፕም ለፕሬዝደንትነት በሚያደርጉ ፉክክር ውስጥ እንድታግዛቸው በፖለቲካ ውስጥ አብራቸው እንድትቆይ ጠየቋት። እሷም ጥያቄውን ተቀብላ ሙሉ ትኩረቷን በፖለቲካው መድረክ የሕዝብ ግንኙነት ላይ አደረገች። ትኩረት የማትሻው ሆፕ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሲሰጡ ወይም ቃለ መጠይቅ ሲያደርጉ ሆፕ ሂክስ ከጎናቸው አትታጣም። እሷ ግን ከማይክራፎን ፊት ሆና ማውራትን አትመርጥም። የፕሬዝደንቱ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን አባል በሆነችበት ወቅትም እራሷን ከማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች አርቃለች። በዚህም የትዊተር ገጿን የዘጋች ሲሆን የኢንስታግራም ገጿም ለሌሎች ዝግ ነው። ዶናልድ ትራምፕ ብዙ በተባለለት ምርጫ አሸንፈው ፕሬዝደንት ሲሆኑ በጽህፈት ቤታቸው ውስጥ ባዋቀሩት አዲስ ክፍል ውስጥ የዋይት ሐውስ ስትራቴጂክ ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር በመሆን በአሜሪካ መንግሥት ውስጥ መስራት ጀመሩ። ትራምፕ "ሆፕስተር" እያሉ የሚጠሯት ሆፕ ሂክስ ትራምፕ ከሚያምኗቸው የቅርብ ረዳቶቻቸው መካከል አንዷ እንደሆነች እና የፕሬዝደንቱን አመለካከት ማስቀየር ከሚችሉ በዙሪያቸው ካሉ ጥቂት አማካሪዎች መካከል ሆፕ አንዷ እንደሆነች ይነገራል። ሆፕን የሚያውቋት ሰዎች የፕሬዝደንቱን ሃሳብ ወይም አመለካከት ማስቀየር ሳይሆን፤ ፕሬዝደንቱ ማድረግ የሚሹትን በቀላሉ መፈጸም የሚችሉበትን አማራጭ ነው የምታቀርበው ይሏታል። 'ፖለቲኮ' የተባለው ገጽ በአንድ ዘገባው እንደጠቀሰው ሆፕ ሂክስ የትራምፕ ቤተሰብን በጥልቀት ከሚያውቁት መካከል አንዷም ነች ብሏል። ሆፕ ሂክስ ፕሬዝደንቱ በሚሄዱባቸው ቁልፍ ቦታዎች ሁሉ የምትገኝ ሲሆን በዋይት ሐውስ ውስጥ ከትራምፕ ጋር በየዕለቱ የቀረበ የሥራ ግንኙነት ካላቸው ሰዎች መካከል አንዷ ነች። ይህም ነው ፕሬዝደንቱ ትኩረት ነፍገውት ለሚሊዮኖች አሜሪካዊያን መታመምና ከ200 ሺህ ለሚልቁት ደግሞ ሞት የሆነው የኮሮናቫይረስ ከእሷ እንደተጋባባቸው የተነገረው። ፕሬዝደንት ትራምፕ በወረርሽኙ መያዛቸው ዓለምን በማስደንገጥ የምድራችን ዋነኛ ርዕስ ሲሆን የመገናኛ ብዙሃን ትኩረት መሆን የማትሻውንም ሆፕ ሂክስን ይፋ እንድትወጣ አድርጎ መነጋገሪያ አድርጓታል።
43840175
https://www.bbc.com/amharic/43840175
ከሃገር እንዳይወጣ ተከልክሎ የነበረው እስክንድር ነጋ እገዳው ተነሳለት
ጋዜጠኛና የዲሞክራሲ አቀንቃኝ እስክንድር ነጋ ከሃገር እንዳይወጣ መከልከሉን ለቢቢሲ ገልፆ የነበረ ሲሆን እንደገና ፓስፖርቱ ተመልሶለት እንዲጓዝ እንደተፈቀደለት ተናግሯል።
እስክንድር እንደሚለው ወደ ሆላንድ ጉዞ ሊያደርግ ትናንት ለሊት ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኘቶ የነበረ ቢሆንም ጉዞ እንዳያደርግ ተከልክሎ ፓስፖርቱን ተነጥቆ ወደ መኖሪያ ቤቱ ተመልሷል። ''አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዓመታዊ ክብረ በዓል ላይ ተጋብዤ ወደ ሆላንድ ልሄድ ነበር ይሁን እንጂ ፓስፖርቴን ተቀምቼ ለመመለስ ተገድጃለው'' ብሏል። ወደ ሆላንድ የሚያደርገውን ጉዞ ሃሙስ ምሸት ለመጀመር ፤ እስክንድር ለሊት 7፡30 ገደማ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረሰ ይናገራል። ''ሻንጣዎቼን በሙሉ አስገብቼ ቦርዲንግ ፓስ (አውሮፕላን መሳፈሪያ ወረቀት) ተቀብዬ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ወዳለው ኢሚግሬሸን ተመራሁ። እዛ ከደረስኩ በኋላ ኢሚግሬሽን ኦፊሰሯ ፓስፖርቴን ከተመለከተች በኋላ ቆሜ እንደጠብቃት ነግራኝ ወደ ውስጥ ገባች። ለግማሽ ሰዓት ካስጠበቀችኝ በኋላ ሌላ ሰው መጥቶ መጓዝ እንደማልችል እና የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ ቢሮ ቁጥር 9 ሄጄ እንዳነጋግር ተነገረኝ'' በማለት የተፈጠረውን ነገር ያስረዳል። የሚሄድበትን ጉዳይ በማስረዳት ፓስፖርቱን መልሰውለት እንዲጓዝ እንዲፈቅዱለት ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርግም እንዳልተሳካለት ገልጿል። 'ትዕዛዙ ከአለቆቻችን የመጣ ነው' የሚል መልስ ሲሰጠው ምንም ማድረግ አለመቻሉን ይናገራል። ለምን ከአገር መውጣት እንደተከለከለ እስካሁን እርግጠኛ ባይሆንም እስክንድር በሶስት ምክንያቶች ሊሆን እንደሚችል ግምቱን አስቀምጧል። የመጀመሪያው ምክንያት ወደ ሆለንድ የሚሄደው ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል የ50ኛ ዓመት ዝግጅት ላይ ለመሳተፍ ከመሆኑ ጋር ይገናኛል። እስክንድር እንዳለው ከሰዓታት በኋላ እዚያው ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከሚገኘው ኢሚግሬሽን ቢሮ ተደውሎለት ፓስፖርቱ ሲመለስለት ጉዞውን ማድረግ እንደሚችልም ተገልፆለታል። ''ይህ ድርጅት ደግሞ በኢትዮጵያ መንግሥት ስለማይወደድ በዝግጅቱ ላይ እንዳልሳተፍ ሊሆን ይችላል። ሌላው በሆለንድ በሚገኙ የኢትዮጵያ ማህብረሰብ አባላት ለእኔ የተዘጋጀ የእራት ግብዣ ነበር እዛ ላይም እንዳልሳተፍ ታስቦ ሊሆን ይችላል። ከዚህ በተጨማሪ ሌላው ግምቴ ከእስር መፈታታችንን የማይደግፉ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት አሉ እና የእነሱም ትዕዛዝ ሊሆን ይችላል"የሚለው እስክንድር እንደተባለው ከተባለው ቢሮ ሄዶ ምክንያቱን በርግጠኝነት ከማጣራት ውጭ ምንም አማራጭ እንደሌለው ይናገራል። ባለፉት ቅርብ ዓመታት በኢትዮጵያ መንግሥት ከሃገር እንዳይወጡ ከታገዱት መካከል የዞን 9 አባላት ይገኙበታል። የዞን 9 አባል የሆነው ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ አራት የዞን 9 አባላት ጓደኞቹ በተደጋገሚ ከሃገር እንዳይወጡ ተደርገዋል ይላል። ''በአየር መንገድ በሚገኘው ኢሚግሬሽን ከሃገር እንዳይወጡ ተብሎ የስም ዝርዝራቸው ከተቀመጠ ሰዎች መካከል የጓደኞቼም መኖሩን ለተለያዩ ጉዳዮች ከአገር ሊወጡ ሞክረው ሲከለከሉ አረጋግጠናል"ይላል። የአምንስቲ ኢንተርናሸናል የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ አጥኚ የሆኑት አቶ ፍሰሃ ተክሌ፤ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሆላንድ 50ኛ አመት የምስረታ በዓሉን ሲያከብር እስክንድርን የክብር እንግዳ አድርጎ ሊጋብዘው እቅድ እንደነበረው ይናገራሉ። "ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መንግስት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማስቆም ቃል በገባ ማግስት ይህ መሆኑ ያሳዝናል። አምነስቲም እገዳው ቶሎ ተነስቶለት እስክንድር ለቅዳሜው ዝግጅት መጓዝ እንዲችል እንጠይቃለን " ብለው ነበር አቶ ፍስሃ። እስክንድር ከቀናት በፊት ከቢቢሲ ጋር ባደረገው ቆይታ ''የዲሞክራሲ ጥማት የማይቀለበስበት ደረጃ ላይ መድረሱን ተመልክቻለሁ'' ብሎ ነበር።
news-53761489
https://www.bbc.com/amharic/news-53761489
ኮሮናቫይረስ፡ ሁለት ጊዜ ከቡራዩ የኮቪድ-19 ህክምና ማዕከል ያመለጡት እስረኞች እየተፈለጉ ነው
የምስራቅ ሸዋ ቦራ ወረዳ የሕግ ታራሚዎችና በኮሮናቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሁለት ወጣቶች ቡራዩ ወደሚገኘው የኮቪድ-19 የህክምና ማዕከል ከተወሰዱ በኋላ፤ ከህክምና ማዕከሉ ለሁለተኛ ጊዜ ማምለጣቸው እና ፖሊስ እየፈለጋቸው እንደሆነ ተነገረ።
ሻሎ ፊታላ እና ኢሳቾ አበበ የተባሉት ሁለት ወጣቶች እና ሌሎች 3 ታራሚዎች በምስራቅ ሸዋ ዞን ቦረ ወረዳ ባለ በእስር ቤት ሳሉ በኮሮናቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን ተከትሎ ለህክምና ወደ ቡራዩ ከተማ መወሰዳቸውን የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ሚሊዮን ታፈሰ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ከላይ ስማቸው የተጠቀሰው ሁለቱ ወጣቶች፤ ወደ ቡራዩ በተወሰዱ በጥቂት ቀናቶች ውስጥ ከለይቶ ህክምና ማዕከሉ ማምለጣቸውን ኢንስፔክተር ሚሊዮን ተናግረዋል። ሁለቱ ወጣቶች ከለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከሉ ካመለጡ በኋላ ወደ ቤተሰቦቻቸው መኖሪያ ቀዬ መመለሳቸውን ኢንስፔክተሩ ተናግረዋል። "ወጣቶቹ ከህክምና መስጫው አምልጠው ወደ ወረዳችን ነው የመጡት። በደረሰን ጥቆማ መሠረት ህዝቡን አስተባብረን አንድ የገጠር መንደር ውስጥ ከያዝናቸው በኋላ ወደ ቡራዩ መልሰናችዋል" ብለዋል። ወጣቶቹ ወደ ለይቶ ማቆያ ማዕከሉ እንዲመለሱ ከተደረጉ ከአራት ቀናት በኋላ ማለትም ቅዳሜ ነሐሴ 2 ለሁለተኛ ጊዜ ከማዕከሉ ማምለጣቸውን የፖሊስ አዛዡ ተናግረዋል። "ለሁለተኛ ጊዜ ማምለጣቸውን ከሰማን በኋላ ፍለጋችንን አጠናክረን እየሰራን ነው። ቤተሰቦቻቸው ጋር የሉም። ገጠር ድረስ የህብረሰብ ክፍል መረጃ አድርሰናል። እስካሁን ግን አለገኘናቸውም። ምናልባት ወደ ሌላ ወረዳዎች ውስጥ ተደብቀው ሳይቀሩ አይቀርም" ብለዋል። የቦራ ወረዳ ምክትል የጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ፍጹም ወርቅነህ፤ በኮሮናቫይረስ ተይዘው "ከለይቶ ማከሚያ ማዕከል ያመለጡት ወጣቶች ጉዳይ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሮብናል" ብለዋል።
news-43961048
https://www.bbc.com/amharic/news-43961048
የሕይወትን ክር ጫፍ ፍለጋ
በልጅነቱ ቤት ውስጥ የነበሩ አሻንጉሊቶችን ደብተሩ ላይ እያስመሰለ ለመሳል ይሞክር እንደነበር ቤተሰቦቹ ያስታውሳሉ፤ ሰዓሊ ዮሴፍ ሰቦቅሳ። "ስዕልን ከልጅነቴ ጀምሮ ውስጤ እንደነበር ይሰማኛል" የሚለውም ለዚህ ነው።
ዮሴፍ ሰቦቅሳ እርሱ እንደሚለው እስከ ስድስተኛ ክፍል ድረስ ስዕልን ትኩረት ሰጥቶ የሚከታተለው የትምህርት ዓይነት አልነበረም። እንደማንኛውም የከተማ ልጅ የእንቁጣጣሽ ስዕሎችን እየገዛ ደግሞ እየሳለ በመሸጥ አሳልፏል። በ13 ዓመቱ ወደ ሰባተኛ ክፍል ሲሸጋገር ግና ስዕል የሕይወት ጥሪው፤ የወደፊት የኑሮ ዘይቤው መሆኑ ይገለጥለት መጣ። "ያኔ ነው ወደ ሩሲያ የሳይንስና የባህል ማዕከል በመሄድ የስዕል ትምህርትን መከታተል የሻትኩት" ይላል። ለጥቆም ወደ አቢሲኒያ የስነጥበብ ትምህርት ቤት ዘለቀ፤ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱንም ሲያጠናቅቅ ደግሞ ወደ አዲስ አበባ የስነጥበብ ትምህርት ቤት በመግባት ተሰጥኦውን በትምህርት ያዳብር ያዘ። ፍለጋው አያልቅም. . . ዮሴፍ ስለስዕሎቹ ሲናገር "መጀመሪያዬም መጨረሻዬም ይመስለኛል" ይላል። ሸራ ወጥሮ ሃሳቦቹን በወጉ በብሩሽ ማስፈር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ እንዲሁም ወደፊትም ስራዎቹ አልፋ እና ኦሜጋቸውን ፍለጋ ላይ እንዳደረጉ ሲናገር በምስጠት ነው። ፍለጋ ላይ ማተኮሩን የተያያዘው በ2006 ወደ ከፍተኛ ትምህርት ቀጣና ካቀና በኋላ እንደሆነ የሚናገረው ዮሴፍ ወደ ዩኒቨርስቲ ከገባ በኋላ የስዕል ሃሳቦችን ሲያሰላስል ያሳለፋቸውን ሕይቶች መሳል መፈለጉ ትዝ ይለዋል። በዛ ወቅት በልጅነቱ ይወደው የነበረው ትኩስ እንጀራ አእምሮው ውስት የትዝታ ማህደሩን ዘረጋ። "ትኩስ እንጀራ ብቻ ሳይሆን ድርቆሽም ከምወደው መካከል ነው" ይላል ዮሴፍ፤ ያንን ሲያስታውስ ደግሞ እንጀራውም ሆነ ማሰሻው ተነጣጥለው አልታዩትም፤ ማሰሻ እና ምጣድ መልኩ ያማረ እንጀራ ለማውጣት ያላቸውን ዝምድና በማሰብ ወደ እይታዊ ጥበብ የመቀየር ሃሳብ አእምሮውን ወጥሮ ያዘው። ማሰሻ በዩኒቨርስቲ ቆይታው ስራዎችን እንዲሰራ ሲታዘዝ ማሰሻን በመውሰድ ማሰስ የሚል ነገር በማፍለቅ ትኩረቱን አደረገ። ማሰስ መፈለግ የሚለውን የህይወት ትርጉም ከዚህ በመውሰድ ምንድን ነው የምናስሰው? ምንስ ነው የምንፈልገው? የሚለውን በስእል ስራዎቹ ውስጥ ለማሳየት እንደሚጥር ይናገራል። የማሰሻ እና የምጣድ መገናኘት ጥሩ እንጀራ ለማግኘት ዋስትና መሆኑን በማየት ምጣድን የዓለም ተምሳሌት አድርጎ በመውሰድ በርካታ ስራዎችንም ሰርቷል። ''የሰው ልጅ በዚህች ክብ ዓለም ሲኖር የተለያዩ ነገሮችን ለማሳካት፣ ሕልሙን እውን አድርጎ ለመጋገር እና ቆርሶ ለመብላት የተለያዩ ነገሮችን ያስሳል" የሚለው ዮሴፍ ይህ ሃሳብ ከትናንቱ ጀምሮ የስዕል ስራው ማጠንጠኛ ተምሳሌት በመሆን እያገለገለው እንደሆነ አበክሮ ይናገራል። በመቀጠልም የተለያዩ ጤፍ እንጀራ አይነቶችን በመጠቀም፣ ማሰሻውንና፣ እንደማሰሻ የምንገለገልበት የጎመን ዘርን በምሳሌነት በመጠቀም ስራዎቹን እንደሚሰራ ያስረዳል። እኛና ቴክኖሎጂ ዛሬ ፍለጋውን ከዚህ ባሻገርም እንዳሻገረ የሚያስረዳው ዮሴፍ ያለንበትን የመረጃ ዘመን የፍለጋው አካል እንደሆነ ለማሳየት የተጠቀመበትን እና ስራዎቹን ለህዝብ ያቀረበበትን አውደ ርዕይ በምሳሌነት ያነሳል። በ2008 ድንቅ አርት የስነ-ጥበብ ውጤቶች ማሳያ 'ሪፍሌክሽን ቁጥር 2' ላይ ያቀረበውና የሰው ልጅ በድረ-ገፆች ውስጥ በፍለጋ እንዴት እንደተወሰደና እንደሚማስን ለማሳየት የተለያዩ የኮምፒውተር ቁሶችን በመጠቀም ያቀረበውን ስራ ለአብነትም ይጠቅሳል። የሰው ልጅ እና ቴክኖሎጂ ምን ያህል እንደተሳሰሩ ያሳየበትና የዩኒቨርስቲ ትምህርቱን ሲያጠናቅቅም ለመመረቂያ ስራው የሆነውን ስራ በመሆኑም ከየትኛውም ስራው በበለጠ ያስታውሰዋል። ስራው ይላል ዮሴፍ "ስራው የማዘር ቦርድን በመጠቀም የተሰራ ነው። ማዘር ቦርድ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለማንቀሳቀስ የምንጠቀምበት ነው። የሰው ልጅ በህይወት ለመኖር የደም ዝውውሩን ወዲህ ወዲያ የሚያደርጉ የደም ስሮች እንዳሉት ሁሉ በማዘር ቦርዶቹም ላይ የተለያዩ መስመሮች፣ ቅርፆች፣ መነሻዎች አሉ። እነዚህን ማዘር ቦርድ ላይ ያሉ መስመሮች፣ መነሻዎችና ነጥቦችን እንደ የጥበብ አላባ በመውሰድ ግማሽ የሰው ፊት ግማሽ ማዘር ቦርዱን በማድረግ የሰው ልጅና ቴክኖሎጂ ያላቸውን ዝምድና ያሳየሁበት አውደ ርዕይ ትልቅ ቦታ የምሰጠው ስራዬ ነው" ይላል። ከፊል የአብስትራክት አይነት ስዕሎች ሰዓሊ ዮሴፍ ከስነጥበብ ትምህርት ቤት ተመርቆ ከወጣ በኋላ 15 ያክል የስዕል አውደ ርዕዮችን ለብቻውም ሆነ ከሙያ አጋሮቹ ጋር በመሆን አቅርቧል። በአሁኑ ሰአት ከፊል ረቂቅ ወይም 'አብስትራክት' ስዕሎች ላይ እንሚያተኩር የሚናገረው ዮሴፍ አብዛኞቹ ስራዎቹ ግን ተምሳሌታዊ መሆናቸውንም ይገልፃል። በታህሳስ ወር 'ሪፍሌክሽን ቁጥር 3' ብለው ከሙያ አጋሮቹ ጋር ያሳዩት የስዕል አውደ ርዕይ ድጋፍም ነቀፋም ያገኘበት እና ትልቁ መድረክ እንደሆነ የሚናገረው ዮሴፍ በዚህ አውደ ርዕይ ላይ በርካታ ሰዎች መምጣታቸው ፍሰሃ እንዳላበሰው ያስታውሳል፤ "ይህ ትልቁ መድረኬ እና ስኬቴ ነው" በማለትም ይገልፀዋል። ስዕል እና ገቢ ሰዓሊ ዮሴፍ ስዕልን ገቢው አድርጎ እንደሚኖር ይናገራል። አሁን በከተማችን ስዕልን እንደገቢ ምንጭ አድርጎ ለመጠቀም ለሚፈልጉ ጥሩ ጊዜ እንደሆነም ይመሰክራል። "አሁን በቅርቡ እንኳ የሸጥኩት ስዕል 32000 ብር ያወጣ ነው" ይላል ከገቢ አንፃር ያለውን ትርፍ ሲያስረዳ። ዮሴፍ ለወደፊት የስዕል ስራዎችን ይዞ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ላይ የማሳየት ሕልም አለው፤ "ቢያንስ በዓመት ሁለት ጊዜ እንኳ ስራዎቼን ለህዝብ ባቀርብ፣ በዓለም ዙሪያ ተዘዋውሬ ስራዎቼን ባሳይና እኔም ሀገሬም ብንጠቀም ስል አልማለሁ።"
news-55170434
https://www.bbc.com/amharic/news-55170434
ሚሊዮን ዶላሮች የሚያስታቅፈው የደቡብ አፍሪካ ሎቶሪ ተጭበርብሯል ተባለ
የደቡብ አፍሪካ ሎቶሪ 5-6-7-8-9-10 ተከታታይ ቁጥር ሆኖ መውጣቱ እያነጋገረ ነው
የደቡብ አፍሪካ ሎቶሪ የአሸናፊው ቁጥር አስገራሚ ሆኖ ወጥቷል፡፡ ከ5 ጀምሮ እስከ 10 ቁጥሮች በተርታ መውጣታቸው አገሬውን ጉድ አሰኝቷል፡፡ ቁጥሮቹ ተከታታይ መሆናቸው ብቻ አይደለም ግርታን የፈጠረው፡፡ በአንድ ጊዜ የናጠጠ ሚሊዮነር የሚያደርገው አንደኛ እጣ ያሸነፈው ሰው አንድ ሰው አለመሆኑ ነው፡፡ 20 ሰዎች አሸናፊ ነን ብለው መቅረባቸው ሌላ ጥርጣሬን ፈጥሯል፡፡ እንዴት 20 ሰዎች ይህንን ተከታታይ ቁጥር ሊገምቱ ይችላሉ ነው ተጭበርብሯል የሚል ጥርጣሬን የፈጠረው፡፡ የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ሎቶሪ እጣውን ያወጣሁት በሕዝብ ፊት በቴሌቪዥን በቀጥታ ሥርጭት ነው፣ ይህ የዕድል ጉዳይ ነው ቢሉም ፖሊስ ግን ነገሩን ስላላማረው ምርመራ እጀምራለሁ ብሏል፡፡ አንድን የአሸናፊ ቁጥር 20 ሰዎች ማግኘታቸው በፍጹም ያልተመለደና የመከሰት ዕድም በጣም አነስተኛ የሚባል ነው፡፡ በዚያ ላይ የአሸናፊ ቁጥር ከ5 ጀምሮ ተከታታይ አሀዝ መያዙ አጋጣሚ ብቻ ተብሎ የሚታለፍ አልሆነም፡፡ ብሔራዊ ሎቶሪው እንደሚለው 20 ሰዎች ቁጥሩን በትክክል በመገመታቸው እያንዳንዳቸው 370 ሚሊዮን ዶላር ይሰጣቸዋል፡፡ አንድ ሰው የደቡብ አፍሪካ ‹ፓወርቦል› ሎተሪን የማሸነፍ ዕድሉ ከ42 ሚሊዮን 375ሺ 200 ሰዎች መካከል 1 ብቻ ነው፡፡ የሎቶሪ አስተዳደሩ በትዊተር ሰሌዳው ላይ ‹‹እንኳን ደስ ያላችሁ፤ 20 አሸናፊዎች የቁጥሮቹን ቅደም ተከተል በትክክል ስለገመታችሁ ደስ ይበላችሁ!›› ሲል የደስታ መግለጫ አስተላልፏል፡፡ ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት የወጣው ሎቶሪ ቁጥርና የአሸናፊዎች ብዛት ግራ የተጋባው አገሬው በማኅበራዊ የትስስር ገፆች በመውጣት ቧልትና ፌዝ ሲጋራ አምሽቷል፡፡
45589043
https://www.bbc.com/amharic/45589043
ግንቦት ሰባትና አርበኞች ግንባር አልተለያዩም ተባለ
ከሰሞኑ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነት እና ለዲሞክራሲ ንቅንቄ አካል የሆነው እና የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር ከፓርቲው ሊለያይ መሆኑ ሲነገር ቆይቷል።
የፓርቲው ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ግን ይህንን "የተለመደ የማኅበራዊ ሚዲያ" አሉባልታ ነው ብለውታል። "ወደአገር ቤት ስንመጣ የመጣው ፓርቲ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነት እና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ ነው። አርበኞች ግንቦት ሰባት የሚባል ነገር የለም፤ የኢትዮጵያ አርበኞች ንቅናቄ የሚባል የለም። ከውስጥ ተገንጥሎ ሊወጣ የሚችል አካል የለም። ተዋኽደናል" ሲሉ አቶ ኤፍሬም ለቢቢሲ ገልፀዋል። • "ሰው እየሳቀ መሞት እንደሚችል አሳያችኋለሁ ነበር ያልኳቸው'' አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ • ስለተፈፀመው ጥቃት እስካሁን የምናውቀው • ኦህዴድ አብዮታዊ ዴሞክራሲንና ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነትን ታሪክ ሊያደርጋቸው ይሆን? ለበርካታ አመታት በኢትዮጵያ መንግስት የሽብር ዝርዝር ውስጥ ተቀምጦ የነበረው የአርበኞች ግንቦት ሰባት መቀመጫውን በጎረቤት ኤርትራ አድርጎ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል። ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደስልጣን መምጣት በኋላ በአገሪቱ የተከናወኑ ለውጦችን ተከትሎ ቡድኑ የትጥቅ ትግሉን ማቆሙን ይፋ ካደረገ በኋላ ከሌሎች መሰል ቡድኖች ጋር ከሽብር ዝርዝር መሰረዙ ይታወሳል። የቡድኑ ከፍተኛ አመራሮች በቅርቡ ወደአገር ቤት ሲመለሱ በመዲናዋ አዲስ አበባ ሞቅ ያለ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን፥ አቶ ኤፍሬም ፓርቲያቸው ወደኢትዮጵያ ከተመለሰ በኋላ ከዚህ በፊት በህቡዕ ይንቀሳቀሱ የነበሩ አባሎቻቸውን ከአመራሩ ጋር በማስተዋወቅ ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል። "እንኳን መለያየት ይቅርና፥ አርበኞች ግንቦት ሰባት ከዛሬ ሁለት ወር በፊት ከነበረውም በተሻለ ጥንካሬ ላይ ይገኛል" ብለዋል። በስልክ ያነጋገርናቸው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑትና ይህንን ውሳኔ ለማሳለፍ በጎንደር የተካሄደውን ስብሰባ መምራታቸውን ያስረዱት አርበኛ መንግስቱ ወ/ስላሴ ጉዳዩን በተመለከተ በሚቀጥለው እሁድ ይፋዊ መግለጫ እንደሚሰጡ ገልፀው መለያየቱ ግን ዕውን መሆኑን ነግረውናል።
44843673
https://www.bbc.com/amharic/44843673
"ኢትዮጵያና ኤርትራን የሚለያቸው የለም" ኢሳያስ አፈወርቂ
በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተፈጠረው አዲስ የሰላምና የወዳጅነት ምዕራፍ ማብሰሪያ ሥነ-ሥርዓት በሚሊኒየም አዳራሽ ትላንት ተካሂዷል። የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ እና የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ዝግጅቱን ታድመውታል።
በዝግጅቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ "ኢትዮጵያና ኤርትራን የሚለያቸው የለም" ሲሉ ተደምጠዋል፤ "የሁለቱ ሃገራት ሰላም ጠቃሚነቱ ለቀጣናው ጭምርም ነው" ሲሉም አክለዋል። "ለውጡን ማንም ሊያቆመው አይችልም፤ ኢትዮጵያ 100 ሚሊዮን ዐብይ አላት፤ አንዱ ቢያልፍ አንዱ ይተካል" የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ መልዕክት ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሚሊኒየም አዳራሽ ተገኝተው የነበሩ ታዳምያንን 'ይደግምልን' ያስባለ መስመርም ተናገርረዋል፤ "እኔ ኢሳያስ አንድ ላይ ስንሆን አሰብን እንጋራለን" በማለት። "የኢትዮጵያና የኤርትራ ሰላም ለቤተሰብና ለጎረቤት ትምህርት ይሆናል ብዬ አምናለሁ። ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደ ኢትዮጵያ ሊተያይ ይገባል" ሲሉ አስረግጠዋል። "ነጻነት፣ ሰላም፣ ዴሞክራሲና ፍቅር ብርሃን እንጂ ጨለማ አያመነጨውም፤ ጨለማም ከእነዚህ ጋር ስምምነት የለውም። ስለሆነም የተገኘውን ሰላም፣ ዴሞከራሲና ነጻነት መጠበቅ ያሰፈልጋል" ሲሉ በጭብጨባ የታጀበ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በበኩላቸው "የኤርትራን ህዝብ ሰላምታና ፍቅር ለኢትዮጵያ ህዝብ ይዤ መጥቻለሁ" ሲሉ ነበር ንግግራቸውን የጀመሩት። "በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የተፈጠረውን ሰላምና የሚታሰበውን የጋራ ልማት ማንም ኃይል አንዲፈታተነው አንፈቅድም" ሲሉም አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል። "ጥላቻን አስወግደን ልማትና ብልፅግና ለማምጣት በሁሉም መስኮች ተባብረን ወደፊት ለመራመድ ቆርጠን ተነስተናል" የኢሳያስ ድምፅ ነበር። ፕሬዝደንቱ በአማርኛ መልዕክታቸውን ባስተላለፉበት ወቅት በርካቶች በጭብጨባ ሲያጅቧቸውም ተስተውለዋል። • የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አዲስ አበባ ገቡ • ፕሬዝዳንት ኢሳያስ የኢትዯጵያና የኤርትራ ሕዝቦች አንድ ናቸው አሉ • ስለ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ምን ያህል ያውቃሉ? ይህን ተከትሎም በኬንያ የኤርትራ አምባሳደር የሆኑት በየነ ርዕሶም "ኢሳያስ እንባ እየተናነቃቸው ለኢትዮጵያ ሕዝብ በአማርኛ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። አኔ ኢሳያስን ለ40 ዓመታት አውቃቸዋለሁ፤ በአማርኛ ሲያወሩ ሰምቼ ግን አላውቅም" ሲሉ በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል። በርካታ ሺዎች ታድመውበታል በተባለው ዝግጅት ላይ ታዋቂ ድምፃዊያን ሥራዎቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን ተወዳጁ ድምፃዊ ማሃሙደ አሕመድ 'ሰላም' በተሰኘ ሥራው ታዳሚውን አስፈንጥዟል። ኢትዮያዊያንና ኤርትራውያን ዘርና ሃይማኖት ሳይለያቸው የታደሙበት ይህ 'የሰላም ማብሰሪያ' ዝግጅት የተሳካ እንደነበርም በሥፍራው የነበረው የቢቢሲ ጋዜጠኞች ቡድን ታዝቧል። ለቢቢሲ ድምፃቸውን የሰጡ ታድምያን የመሰል ዝግጅት ተሳታፊ መሆናቸው ውስጣዊ ፍስሃ እንዳደላቸው አልሸሸጉም። በፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመራው የኤርትራ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ እያካሄደ ያለውን የሦስት ቀናት ጉብኝትን አጠናቆ ዛሬ ወደ ኤርትራ ይመለሳል ተብሎ ይጠበቃል።
news-54498317
https://www.bbc.com/amharic/news-54498317
ኮሮናቫይረስ፡ አፍሪካ በወረርሽኙ ሳቢያ ከተጎዳው ምጣኔ ሐብት ለማገገም 1.2 ትሪሊየን ዶላር ያስፈልጋታል ተባለ
አፍሪካ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ካጋጣት የኢኮኖሚ ውድቀት ለማገገም እንዲሁም የጤና ወጪ 1.2 ትሪሊየን ዶላር እንደሚያስፈልጋት ዓለም አቀፉ ገንዘብ ተቋም [አይኤምኤፍ] አስታወቀ።
ገንዘቡ ያስፈልጋታል የተባለው ለሚቀጥሉት 3 ዓመታት መሆኑ ተገልጿል። የተቋሙ ዳሬክተር ክርስታሊና ጆርጂቫ እንዳሉት ዓለም አፍሪካ ከገባችበት ቀውስ እንድታገግም ለመደገፍ ዓለም ብዙ መስራት አለበት ብለዋል። በአፍሪካ በኮሮናቫይረስ የተያዙ እንዲሁም የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከሌሎች አህጉራት ያነሰ ነው፤ ነገር ግን የዓለም ባንክ በወረርሽኙ ሳቢያ ተጨማሪ 43 ሚሊዮን የሚሆኑ አፍሪካዊያን ለከፋ ድህነት የመጋለጥ አደጋ ተጋርጦባቸዋል ብሏል። በወረርሽኙ ሳቢያ የሥራ እድሎች በመታጠፋቸው እና የቤተሰብ ገቢ በ12 በመቶ በመቀነሱ የደረሰው የኢኮኖሚ ተፅእኖ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአፍሪካ እየታየ የነበረውን ጠንካራ እድገት እየቀለበሰው መሆኑን የገንዘብ ተቋሙ ዳሬክተር በበይነ መረብ በነበራቸው የተቋሙ ስብሰባ ላይ ተናግረዋል። ችግሩንም ለማቃለል በርካታ አፍሪካ አገራት መንግሥታት ከልማት እቅዳቸው 2.5 በመቶ ያስወጣቸውን ፖሊሲዎች አስተዋውቀዋል። አይኤም ኤፍ የአፍሪካ አገራት ከደረሰባቸው ተፅዕኖ እንዲያገግሙ 26 ቢሊዮን ዶላር የለገሰ ቢሆንም፤ የግል አበዳሪዎች እና በሌሎች አገራት ድጋፍ ቢኖርም፤ አሁንም ግን ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ እጥረት አለ ብለዋል። "አንዳንድ አገራት ከብድር አግልግሎትና ተጨማሪ የማህበራዊና ጤና ወጪዎች መካከል እንዲመርጡ የሚያስገድዳቸውን የዕዳ ጫናዎች እየተጋፈጡ ነው" ብለዋል ኃላፊዋ። ይህንን ችግር ለመፍታትም ተበዳሪዎች ብድራቸውን የሚከፍሉበት ጊዜ እንዲራዘም ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፤ ለብድር የሚሆን ተጨማሪ ገንዘብ ማቅረብ እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል። በአፍሪካ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን፤ ወደ 37 ሺህ የሚጠጉት ሕይወታቸውን አልፏል።
52555291
https://www.bbc.com/amharic/52555291
በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ምክንያት የመናገር ነፃነት አደጋ ላይ ነው- ሂዩማን ራይትስ ዎች
የኢትዮጵያ መንግሥት የኮቪድ-19ን ለመከላከል ያስተላለፋቸው ገደቦችና ለአምስት ወራት የደነገገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመናገር ነፃነትን ለመገደብ እየተጠቀመበት ነው ሲል የሂዩማን ራይትስ ዎች ተቸ።
ድርጅቱ በመግለጫው ባለፈው ወር ጠበቃ ኤልሳቤጥ ከበደና ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ አስተያየት በመስጠታቸው መታሰራቸውን ጠቀሷል። ሪፖርቱ እንዳለው ኮሮናቫይረስ በአገሪቱ እንዳይስፋፋ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋዜጠኞችንና መንግሥትን የሚተቹትን ለማሰር እየዋለ ነው። "ስለቫይረሱ የሚሰራጩ የተሳሳተ መረጃዎች ስጋት ቢሆኑም የመናገር ነፃነትን ለመገደብ ግን ሰበብ ሊሆኑ አይገባም" ያሉት የድርጅቱ የአፍሪካ ቀንድ ዳይሬክተር ላይቲቲያ ባደር፣ መንግሥት ያየሰው ሽመልስ ላይ የከፈተውን ክስ ውድቅ ማድረግ፣ ኤልሳቤጥ ከበደንም ከእስር መልቀቅ አለበት እንዲሁም ሰዎች በሰላማዊ መንገድ ሃሳባቸውን ስለገለፁ ብቻ ማሰር ማቆም ይገባዋል ሲሉ ተናግረዋል። • በስልጤ ዞን ኮቪድ-19 ያለባቸው ሴት እንዴት ሊገኙ ቻሉ? • አቅመ ደካሞችን እያማለለ የሚገኘው የማፊያዎች ገንዘብ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው በኮቪድ-19 ተያዘ ሰው ከተገኘ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የወረርሽኙን ስርጭት ለመከላከል ይረዳል ያሉትን እርምጃ ያስተላለፉ ሲሆን በወቅቱ መገናኛ ብዙኀንም "ለህብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃ" እንዲያደርሱ አሳስበው ነበር። ከዚህ በኋላም በትግራይ ቴሌቪዥን ጣብያ ፖለቲካዊ ፕሮግራሞች የሚያቀርበው ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ በግል የፌስ ቡክ ገፁ ላይ መንግሥት በኮቪድ-19 ምክንያት ለሚሞቱ ሰዎች 200 ሺህ ጉድጓዶች እንዲቆፈሩ አዝዟል ሲል ጽፏል። በወቅቱ መንግሥት መረጃው ስህተት ነው ሲል አስተባብሏል። በሚቀጥለው ቀን ጋዜጠኛው ለገጣፎ አካባቢ ከሚገኘው ቤቱ በፖሊስና በደህንነት ሰዎች ተይዞ መታሰሩ ይታወሳል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ሐሰተኛ መረጃ በማሰራጨት በሚል ካሰረው በኋላ ለሶስት ሳምንት ክስ ሳይመሰርት እንዳቆየው የገለፀው መግለጫው፣ በኋላም በቂ ማስረጃ ባለመቅረቡ በዋስ እንዲለቀቅ ቢወሰንም የፌደራል ፖሊስ በመካከል ጣልቃ ገብቶ ይግባኝ በማለት ማሻሻያ የተደረገበትን የፀረ ሽብር ሕግ በመጣስ ከስሶታል ብሏል። ለሁለተኛ ጊዜ የፌደራል ፍርድ ቤት ለጋዜጠኛ ያየሰው የዋስትና መብቱን አስጠብቆለት ሊለቀቅ መቻሉን መግለጫው አክሎ አስፍሯል። የሂይማን ራይትስ ዎች እንዳለው ከሆነ ያየሰው የተከሰሰው በአዲሱ የጥላቻና ሐሰተኛ መረጃ ሕግ መሆኑን ገልጿል። የኢትዮጵያ ህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር በጎ ፈቃደኛ ጠበቃ የሆነችው ኤልሳቤጥ በሐረሪ ክልላዊ መንግሥት በቁጥጥር ስር መዋሏን ድርጅቱ ጨምሮ አስታውቋል። ድርጅቱ ከምትሰራበት ተቋም አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት ኤልሳቤጥ እስካሁን ድረስ ክስ ያልተመሰረተባት ሲሆን ነገር ግን " ግጭት የሚያነሳሳ" ሀሰተኛ መረጃ በፌስ ቡክ በማሰራጨት ተወንጅላለች ብሏል። ግለሰቧ በኮሮናቫይረስ ተይዘዋል ያለቻቸውን ሰዎች በስም ጠቅሳ በፌስቡክ ገጿ ላይ መፃፏ ተገልጿል። የክልሉ ባለሰልጣናት በቫይሱ ተይዘዋል ተብለው በስምና በብሔር የተጠቀሱ ሰዎችን እንዲሁም ከእነሱ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሰዎች በአጠቃላይ ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ መደረጉን ገልፀዋል። በበወቅቱ በግለሰቧ የተፃፈው መረጃ ተሰርዞ ማስተካከያ ተደርጎበታል። ሂዩማን ራይትስ ዎች እንዲህ አይነት መረጃዎች ግለሰቦችን ደህንነት የሚጋፋ መሆኑን ገልጿል። የግለሰቦችንም የህክምና መረጃ ይፋ ማድረግ ለማግለልና መድልዖ ያጋልጣል ሲል አስፍሯል። ነገር ግን እንዲህ አይነት ድርጊቶች በወንጀል መታየት የለባቸውም ሲል በመግለጫው ላይ አስቀምጧል። • መኪና ለመግዛት የወላጆቹን መኪና አስነስቶ የሄደው የ5 ዓመት ህጻን ተያዘ • “ያልተፈተነ መድኃኒት አትውሰዱ” የአለም ጤና ድርጅት በኢትዮጵያ የአስቸኴይ ጊዜ አዋጁ ከተደነገገ በኋላ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ህጉን የሚጥሱ ሰዎችን ያስጠነቀቁ ሲሆን ሐሰተኛ ዜናዎችን የሚያሰራጩ ግለሰቦችና ሚዲያ ተቋማትንም አስጠንቅቀዋል። ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ሁለት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጆችን ያሳለፈች ሲሆን በእነዚህ ወቅቶች በርካታ ሰዎች መታሰራቸው ይታወሳል። ሂዩማን ራይትስ ዎች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወቅት የሚደርሱ ጥሰቶችን ለመከላከል ገለልተኛ አካል ምልከታ ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስቧል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈፃፀም የሚከታተል ቡድን ያቋቋመ ሲሆን የሰብኣዊ መብት ኮሚሽንና የሲቪል ሶሳይቲ ድርጅቶችም ሊሳተፉ እንደሚገባ ድርጅቱ በመግለጫው ላይ አትቷል። " የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የከዚህ ቀደሙን ስህተት እንዳይደግሙት" ያሉት ባደር " በቀጣዮቹ አምስት ወራት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ዜጎች በአዋጁ ወቅት የተጣሉ ድንጋጌዎችን በመጠቀም የመብት ጥሰት እንደዳይኖር ከዚያም በኋላ እንዳይቀጥል" ሊከታተሉ ይገባል ብለዋል።
news-48597773
https://www.bbc.com/amharic/news-48597773
የአላባማ ግዛት ህጻናትን የደፈሩ እንዲኮላሹ የሚያዝ ሕግ አሳለፈች
በአሜሪካ የምትገኘው አላባማ ግዛት ህጻናትን የደፈሩ በኬሚካል እንዲኮላሹ የሚያዝ ሕግ አሳለፈች።
በሕጉ መሠረት፤ እድሜያቸው ከ13 ዓመት በታች በሆኑ ህጻናት ላይ ወሲባዊ ትንኮሳ ፈጽመው በእስር ላይ የሚገኙ ወንጀለኞች ፍርዳቸውን ሳይጨርሱ ከእስር የሚለቀቁ ከሆነ፤ ከአንድ ወር በፊት የወሲብ ፍላጎታቸውን የሚቀንስ መድሃኒት እንዲወስዱ ይደረጋል። መድሃኒቱ በእንክብል ወይም በመርፌ መልክ የሚሰጥ ሲሆን በሰውነት ውስጥ የሚገኘውን የቴስቴስትሮን መጠንን ዝቅ በማድረግ የወሲብ ፍላጎንትን በከፍተኛ መጠን ይቀንሳል። • "በወንድሜ ለአምስት ዓመታት ተደፍሬአለሁ" • "ደላላው ወደ ቤቱ ወሰደኝ፤ በዚያው ቀን አስገድዶ ደፈረኝ" ይሁን እንጂ መድሃኒቱ መወሰድ ሲቆም የወሲብ ፍላጎት ወደነበረበት ይመለሳል። ከአላባማ ግዛት በተጨማሪ ሉዚያና፣ ፍሎሪዳ እና ሌሎች 4 የአሜሪካ ግዛቶች ይህን መሰሉን ሕግ ተቀብለው ተግባራዊ ያደርጋሉ። የአላባማ ግዛት አስተዳዳሪ ኬይ ኢቪይ ነች ሰኞ ዕለት በፊርማዋ ሕጉን ያጸደቀችው። ''ይህ በአላባማ የሚገኙ ህጻናትን ለመታደግ አንድ እርምጃ ነው'' ብላለች አስተዳዳሪዋ። በወንጀል ድርጊቱ ጥፋተኛ የተባሉት ግለሰቦች ለመድሃኒቱ ወጪውን ይሸፍናሉ። ይህን የሕግ ማዕቀፍ ሥራ ላይ እንዲውል ጫና ያሳደሩት የሪፓብሊካኑ ተወካይ ስቲው ሃረስት ሲሆኑ፤ ጾታዊ ትንኮሳ የደረሰባቸው የሕጻናት ማቆያ ማዕከል ውስጥ ከሚገኙ ልጆች የሰሟቸው ታሪኮች እጅጉን እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል። ይህ ሕግ ተቃውሞ አላጣውም። የአላባማ አሜሪካ ሲቪል ሊብሪቲስ ማህበር ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ራንዳል ማርሻል ለAL.com ሲናገሩ፤ ''ይህን መድሃኒት ሊያስከትለው የሚችለው ጉዳት ምን እንደሆነ አይታወቅም። ግዛቱ በምርምር ደህንነቱ የልተረጋገጠን መድሃኒት በሰዎች ላይ መጠቀም ሲጀምር፤ ከሕገ-መንግሥቱ ጋር የሚጻረር ይመስለኛል።'' ብለዋል። እ.አ.አ. 2009 ላይ እንግሊዝ ውስጥ በኬሚካል የማኮላሸት የምረምር ፕሮጄክት ላይ ፍቃደኛ የነበሩ እሰረኞች ተሳታፊ ነበሩ። ''ከፍተኛ የሆነ የወሲብ ፍላጎት ወይም ወሲባዊ ምኞት'' አለባቸው የተባሉት እስረኞች፤ መድሃኒቱን ከወሰዱ በኋላ ''በህይወታቸው ላይ አዎንታዊ ለውጥ ተመዝግቧል'' ሲሉ የአዕምሮ ጤና ባለሙያ ዶን ግሩኒን ተናግረዋል። ደቡብ ኮሪያ እና ኢንዶኔዥያ ይህን መሰል ሕግ ተግባራዊ ያደርጋሉ።
news-55829689
https://www.bbc.com/amharic/news-55829689
አፍሪካ በ2020 ኢንተርኔትን በማቋረጧ ብቻ 237.4 ሚሊዮን ዶላር አጥታለች
ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2020 ለ1536 ሰዓታት ወይም በቀናት ሲሰላ ለ64 ቀናት ያህል ኢንተርኔት ማቋረጧንና በዚህም የተነሳ 11̄1.3 ሚሊዮን ዶላር ማጣቷን አንድ ጥናት አመለከተ።
ጥናቱ የተሰራው የአገራትን ኢንተርኔት ፍሰትን በሚከታተለው ኔት ብሎክስ በተሰኘው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት እንዲሁም የኢንተርኔት መብትን በሚያቀነቅነው 'ዘ ኢንተርኔት ሶሳይቲ' ጥምረት ነው። ሪፖርቱ በዓለማችን ላይ የተከሰቱ የኢንተርኔት መዘጋትና እና የማህበራዊ ሚዲያ መቋረጦች ያስከተሏቸውን የምጣኔ ኃብት ቀውሶች የሚገመግም ነው ተብሏል። ይህ ጥናት ኢትዮጵያ፤ የፖለቲካ ትኩሳት በጋለባቸውና አለመረጋጋቶች በተከሰተባቸው ወቅቶች ኢንተርኔት መዝጋቷን ገልጿል። የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን መገደል ተከትሎ በተቀሰቀሰ ሕዝባዊ ተቃውሞ የተነሳ፣ ከሰኔ እስከ ሐምሌ ባሉት ወራቶች ውስጥ፣ ከሶስት ሳምንት በላይ ኢንተርኔት ተቋርጦ እንደነበር ጥናቱ አመልክቷል። እንደ ተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት ከሆነ በዚህ ግጭት 166 ሰዎች ሲገደሉ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን ጨምሮ 2ሺህ ያህል ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል። በወቅቱ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት 9ሺህ ያህል ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ገልጾ ነበር። ጥቅምት 24 2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል የሕወሓት ኃይሎች በክልሉ በሚገው የሰሜን እዝ ላይ ጥቃት መክፈታቸው ከተገለፀ በኋላ መንግሥት ሕግ የማስከበር ዘመቻ ያለውን እርምጃ ተከትሎ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦ መቆየቱ ይታወሳል። ከሁለት ወራት በፊት በክልሉ በተከሰተው ወታደራዊ ግጭት ሳቢያ ተቋርጠው የነበሩት የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎቶች በከፊል የተመለሱባቸው አካባቢዎች ቢኖሩም፤ በበርካታ ከተሞች ውስጥ እስካሁን ስልክም ሆነ ኢንተርኔት አለመመለሳቸውን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ ፍሬሕይወት ታምሩ በአንድ ወቅት ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ አረጋግጠዋል። የአገልግሎቱ መቋረጥ የሰብዓዊ እርዳታ የሚሰጡ ድርጅቶችም ሆነ የክልሉ ነዋሪዎች ላይ ያለውን የመረጃ ፍሰት ማደናቀፉን በተለያየ ጊዜ የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ። ሂውማን ራይትስ ዎች ይህንን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ላይ በክልሉ ያለው የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ ለሰብዓዊ ድርጅቶችና ለጋዜጠኞች የሚካሄዱ እንቅስቃሴዎችን ለመከታተል እና ለመዘገብ አዳጋች ማድረጉን አመልክቷል። ከክልሉ ውጪ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆችም ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመገናኘትና መረጃ ለመለዋወጥ በዚህ ምክንያት መቸገራቸውን ገልጾ ነበር። በ2020 የኢንተርኔት መዘጋት ያስከተለው ኪሳራ በቀሪው የዓለማችን ክፍል የኢንተርኔት መቋረጥ ምን ይመስላል? በፈረንጆቹ 2020 ዓ.ም ዓለማችን ለ27 ሺህ ሰዓታት ያህል ኢንተርኔት ማቋረጥ አጋጥሟት በአጠቃላይ 4.01 ቢሊየን ዶላር አክስሯታል ሲል ይኸው ጥናት አመልክቷል። ይህ ቁጥር በ2019 ከነበረው የ8.05 ቢሊየን ዶላር ኪሳራ ጋር ሲነጻጸር በግማሽ ቀንሶ ታይቷል። በአፍሪካ በ2020 ብቻ ለ6ሺህ 929 ሰዓታት ኢንተርኔት መቋረጡን ይፋ ያደረገው ይህ ጥናት፣ በዚህም የተነሳ አህጉሪቱ 237.4 ሚሊዮን ዶላር አጥታለች ሲል አትቷል። በአፍሪካ በነበረው የኢንተርኔት ማቋረጥ ምክንያት 56.3 ሚሊዮን ያህል ሰዎች አገልግሎት ሳያገኙ መቅረታቸውን ጥናቱ ይፋ አድርጓል። ጥናቱ እንደሚያሳው ከሆነ ይህ የምጣኔ ኃብት ቀውስ ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ካስከተለው ቀውስ ጋር ተደምሮ አገራቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አስከትሏል። በ2020 በመላው ዓለም በ21 አገራት 93 የኢንተርኔት መቋረጦች ማጋጠማቸውንም ይኸው ሪፖርት አመልክቷል። በመላው ዓለም ኢንተርኔት ለ27 ሺህ 165 ሰዓታት መቋረጡን የዘገበው ይኸው ሪፖርት ኢንተርኔት ማቋረጥ ለ10 ሺህ 693 ሰዓታት፣ ማህበራዊ መገናኛ ብዙኀንን መዝጋት ደግሞ ለ5 ሺህ 552 ሰዓታት፣ እንዲሁም ኢንተርኔት ፍጥነትን እንዲዘገይ ማድረግ ለ10 ሺህ 920 ሰዓታት ተመዝግቧል። በዚህም የተነሳ በዓለማችን ላይ በዚህ ምክንያት 268 ሚሊዮን ያህል ሰዎች የኢንተርኔት አገልግሎት ሳያገኙ መቅረታቸውን አስታውቋል። በዓለማችን ላይ በኢንተርኔት መቋረጥ ክፉኛ ከተጎዱ የዓለማችን አገራት መካከል ሕንድ ቀዳሚውን ስፍራ ትይዛለች ተብሏል። ሕንድ እና ምያንማር ለተከታታይ ሁለት ዓመታት ኢንተርኔትን በማቋረጥ ስማቸው በቀዳሚነት ተጠቅሷል። ቻድ በበኩሏ ዋትስአፕን ከ2018/19 ጀምሮ በግዛቷ ላይ መጠቀም እንዳይቻል ያደረገች ሲሆን፣ ይህንንም ውሳኔዋን በ2020 መቀጠሏ ተመልክቷል። በዓለማችን ላይ የኢንተርኔት መቋረጥ የተከሰተባቸው ምክንያቶች ሲዘረዘርም፣ ምርጫን በማስመልከት 15 በመቶ፣ የፕሬስ ነጻነትን ለማፈን 12 በመቶ፣ 29 በመቶ ደግሞ የመሰብሰብ ነጻነትን ለማስተጓጎል እንደሆነ በሪፖርቱ ላይ ተመልክቷል። ይህ ሪፖርት በዓለማችን ላይ የተከሰቱ የኢንተርኔት እና የማህበራዊ መገናኛ ብዙኀን መቋረጦች ያስከተሏቸውን የምጣኔ ኃብት ቀውሶች የሚገመግም ነው። የኢንተርኔት ማቋረጥ ማለት ይኹነኝ (ሆን) ተብሎ የመረጃ ፍሰትን በአንድ የተወሰነ አካባቢ ለመግታት በሚል ኢንርኔትን ወይንም የኤሌክትሮኒክስ ግንኙነትን ማቋረጥ፣ ፍጥነቱ እንዲዘገይ ማድረግ መሆኑን አክሰስ ናው የተሰኘው ድርጅት ይገልጻል። አምባገነን መንግሥታት የተቃውሞ ሰልፍን ለማደናቀፍ፣ በይበልጥ ደግሞ በምርጫ በሚካሄድበት ወቅት የሚኖሩ ሰልፎችን ላይ ቁጥጥር ለማጥበቅ ኢንተርኔትን እንደሚዘጉ ተገልጿል። ይህ ሪፖርት በ2021 ኢንተርኔት መቋረጥ በእነዚህ መንግሥታት ሊቀጥል ይችላል ሲሉ ተንብየዋል።
44544719
https://www.bbc.com/amharic/44544719
የካናዳ ፓርላማ ዕፀ-ፋርስን ለመዝናኛነት ህጋዊ አደረገ
የካናዳ ምክር ቤት ዕፀ-ፋርስን ለመዝናኛነት ህጋዊ አድርጓል።
ምክር ቤቱ ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈው ማክሰኞ ሲሆን ህጉ ዕፀ-ፋርስ እንዴት እንደሚበቅል፣ እንደሚሰራጭና እንደሚሸጥም ይወስናል። ይህ ህግም ካናዳውያን ከመጪው መስከረም ጀምሮ ዕፀ-ፋርስን በህጋዊ መንገድ መገበያት ያስችላቸዋል። ዕፀ-ፋርስን ለመዝናኛነት ህጋዊ ስታደርግ ካናዳ ሁለተኛ አገር ናት። ኡራጓይ በአውሮፓውያኑ 2013 ተክሉን ለመዝናኛነት ህጋዊ ያደረገች ሲሆን ፤ በተቃራኒው የአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች ተቃውመውታል። በካናዳ ዕፀ-ፋርስን መጠቀም ወንጀል የሆነው በአውሮፓውያኑ 1923 ሲሆን ለህክምና አገልግሎት ፈቃድ ካገኘ 17 ዓመታትን አስቆጥሯል። አዋጁ በዚህ ሳምንት ህግ ሆኖ ከፀደቀ በኋላ መንግሥት ህጉ ተግባራዊ የሚሆንበትን ኦፊሴላዊ ቀንም ይወስናል። የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ በትዊተር ገፃቸው እንዳሰፈሩት "ለልጆቻቸችን ዕፀ-ፋርስን ማግኘት ቀላል ነበር፤ ወንጀለኞችም ትርፍ በማጋበስ ላይ ናቸው" ብለዋል። በተቃራኒው አንዳንድ ቡድኖች ይህንን አዋጅ የተቃወሙ ሲሆን በተለይም ተቃዋሚ ወግ አጥባቂ ቡድን በጉዳዩ ላይ ያላቸውን ድምፅ አሰምተዋል። መንግሥት ግዛቶቹን እንዲሁም ለአስተዳደሮቹ ከ8-12 ሳምንታት በመስጠት ለዕፀ-ፋርስ የገበያ ቦታ እንዲያመቻቹ ጊዜ እንደሚሰጥም አሳውቀዋል። ይህ ጊዜም ለኩባንያዎች ብቻ ሳይሆን ለፖሊስ ኃይልም አዲሱን ህግ ተግባራዊ እንዲያደርጉት ጊዜ እንደሚሰጥም ተገልጿል። ከሶስት ዓመታት በፊት የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው ካናዳውያን ለዕፀ-ፋርስ ስድስት ቢሊዮን ዶላር እንዳወጡ ተገልጿል።
news-53320573
https://www.bbc.com/amharic/news-53320573
የኮሮናቫይረስ "መድኃኒቶች" በጥቁር ገበያ እየተቸበቸቡ ነው
የቢቢሲ የምርመራ ጋዜጠኞች ቡድን እንዳረጋገጠው ሁለት ነብስ አድን የኮሮናቫይረስ መድኃኒቶች ሕንድ ውስጥ ጥቁር ገበያ ላይ በውድ ዋጋ እየተቸበቸቡ ነው።
ረምደሲቪር እና ቶሲሊዙማብ የተሰኙት መድኃኒቶች በኮሮናቫይረስ ክፉኛ የታመሙ ሰዎችን ለማከም ጥቅም ላይ የሚውሉ ናቸው። ነገር ግን ጥቁር ገበያው ላይ እጅግ በናረ ዋጋ እየተሸጡ በመሆኑ እጥረት እያጋጠመ መሆኑን የጤና ባለሙያዎች ይናገራሉ። የአቢናቭ ሻርማ አጎት ኮቪድ-19 ተገኝቶባቸው ደልሂ ውስጥ የሚገኝ ሆስፒታል ሲገቡ ከፍተኛ ትኩሳትና የትንፋሽ እጥረት እያሰቃያቸው ነበር። ይሄኔ ነው ዶክተሮች ቤተሰቦቹ ሬምደሲቪር እንዲገዛ ያዘዙት። መደኃኒቱ ሕንድ ውስጥ ለኮሮናቫይረስ በሽተኞች እንዲሰጥ ፈቃድ አግኝቷል። • በኢትዮጵያ የመተንፈሻ ቀዳዳ ያላቸው ጭምብሎች ለምን ጥያቄ ውስጥ ገቡ? • በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ11 ሚሊዮን በላይ ሲደርስ ግማሹ አገገሙ • አስራ አንድ አባላቱ በኮሮናቫይረስ የተያዙበት ቤተሰብ ጭንቀትና ደስታ ነገር ግን አቢናቭ መድኃኒቱን እንዲህ በቀላሉ ሊያገኘው አልቻለም። የአጎቱ ጤና ሁኔታ ደግሞ ከጊዜ ጊዜ እያሽቆለቆለ መጣ። ከብዙ ሙከራና የስልክ ጥሪዎች በኋላ መድኃኒቱን ሰባት እጥፍ ከፍሎ ማግኘቱን አቢናቭ ይናገራል። ይህ የአሚናቭ ብቻ ሳይሆን የበርካታ ሕንዳውያን ታሪክ እየሆነ መጥቷል። ምንም እንኳ አንዷ ብልቃጥ መድኃኒት ዋጋዋ 5 ሺህ ሩጲ ቢሆንም ጥቁር ገበያ ላይ እስከ 30 ሺህ ሩጲ እና ከዚያ በላይ እየተቸበቸበ እንደሆነ ቢቢሲ ማረጋገጥ ችሏል። ረምደሲቪር የተሰኘው መድኃኒት ተፈላጊነቱ እየጨመረ የመጣው በኮቪድ የተያዙ ሰዎችን ሕመም መቀነስ በመቻሉ ነው። በጥናት እንደተረጋገጠው መድኃኒቱ የበሽታውን ምልክት ቀናት ከ15 ወደ 11 ዝቅ አድርጎታል። ምንም እንኳ ባለሙያዎቹ መድኃኒቱ የመጨረሻው ፍቱን መድኃኒት አይደለም ቢሉም ኮሮናቫይረስን የሚገታ መድኃኒት እስካሁን ባለመገኘቱ ዶክተሮች መድኃኒቱ ጥቅም ላይ እንዲውል እያዘዙ ይገኛሉ። ቢቢሲ ያነጋገራቸው በሕንዷ መዲና ደልሂ እንዲሁም አካባቢዋ የሚኖሩ ሰዎች መድኃኒቱን ለማግኘት በርካታ ሺህ ሩጲዎች መክፈላቸውን ይናገራሉ። አንዳንዶች ዕድሜ ልካቸውን ያጠራቀሙትን ገንዘብ መድኃኒቱ ለመግዛት አውለናል ይላሉ። መድኃኒቱ በጥቁር ገበያ ዋጋው እንዲህ ንሮ እንዲሸጥ ያደረገው በቂ አቅርቦት ባለመኖሩ ነው። መቀመጫውን ዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው ጊሊያድ ሳይንስስ የተሰኘው ተቋም ነው ረምደሲቪር የተሰኘውን መድኃኒት ለኢቦላ በሽታ እንዲውል ነው የሰራው። ድርጅቱ አራት የሕንድ ኩባንያዎች መድኃኒቱን እንዲያመርቱ ፈቃድ ሰጥቷል። ነገር ግን እስካሁን ድረስ መድኃኒቱን ማምረት የጀመረው አንድ ድርጅት ብቻ ነው። ይህ ድርጅት 20 ሺህ ብልቃጦችን አምርቶ ለገበያ ማቅረቡን አሳውቆ መድኃኒቱ እንዴት የጥቁር ገበያ ነጋዴዎች እጅ ላይ ሊወድቅ እንደቻለ መረጃው የለኝም ሲል ለቢቢሲ አሳውቋል። ድርጅቱ ምርቶቹን ለሆስፒታሎች አከፋፍያለሁ ቢልም ሆስፒታሎች ምርቱ የለንም እያሉ ነው። መድኃኒት መሸጫ መደብሮችም መድኃኒቱን መደርደሪያቸው ላይ አይታይም። እጥረት ያጋጠመው ረምደሲቪር ብቻ ሳይሆን ቶሲሊዙምባ የተሰኘው ሕይወት አድን መድኃኒትም ከገበያ እየጠፋ ነው። ይህ መድኃኒት በኮሮናቫይረስ ተይዘው የሚማቅቁ ሰዎችን ስቃይ በመቀነስ ረገድ ውጤታማ ነው ተብሎለታል። የሕክምና ባለሙያዎች መድኃኒቱ ተጨማሪ ምርመራ ያሻዋል ይላሉ። ነገር ግን በዓለም ዙሪያ በርካታ ሆስፒታሎች መድኃኒቱ በጎ ውጤት እንዳሳየ ይናገራሉ። ነገር ግን ይህን መድኃኒት በቀላሉ ማገኘት የማይታሰብ ነው። ሕንድ ውስጥ ያሉ በርካታ ሆስፒታሎች መድኃኒቱ ስለሌላቸው የታካሚ ቤተሰቦች ፈልገው እንዲያመጡ ነው የሚያዙት። የሁለቱም መድኃኒቶች አምራችና አከፋፋይ ድርጅቶች መድኃኒቶቹ እንዴት ጥቁር ገበያው ሊገኙ እንደቻሉ አናውቅም ይላሉ። በመሃሉ ግን በርካታ ቤተሰቦች መድኃኒቱን ለመግዛት ጥሪታቸውን እያሟጠጡ ይገኛሉ።
42136998
https://www.bbc.com/amharic/42136998
ዚምባብዌ ለሙጋቤ ብሔራዊ ቀን ሰየመች
ዚምባብዌ የካቲት 14ን የሮበርት ጋብርኤል ሙጋቤ ብሔራዊ የወጣቶች ቀን በማለት ሰየመች።
የሃገሪቱ ጋዜጣ እንደዘገበው የቀድሞው ፕሬዝደንት ሙጋቤ የልደት ቀን ብሔራዊ የህዝብ በዓል እንዲሆን ታወጇል። ሙጋቤ የሃገሪቱ ሠራዊት ጣልቃ መግባቱን እና ለቀናት የዘለቀ ህዝባዊ ተቃውሞን ተከትሎ ባለፈው ሳምንት ሥልጣን መልቀቃቸው ይታወሳል። 'ዘ ሄራልድ' የተባለው ጋዜጣ እንደዘገበው የቀድሞው ፕሬዝዳንት የልደት ቀን ብሔራዊ በዓል እንዲሆን የፓርቲያቸው ዛኑ-ፒፍ የወጣት ሊግ ከፍ ያለ ግፊት ሲያደርግ ቆይቶ ተቀባይነት ያገኘው ባለፈው ነሐሴ ወር ነበር። ውሳኔው ግን በይፋ እንዲመዘገብ የተደረገው አርብ ዕለት እንደሆነ ጋዜጣው ጨምሮ ዘግቧል። ባለፈው ሳምንት አዲሱ የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ እንደተናገሩት፤ ሙጋቤ ከሃገሪቱ መስራቾች እና መሪዎች መካከል አንዱ እንደመሆናቸው ተገቢው ዕውቅናና ክብር ሊሰጣቸው ይገባል። "በግሌ ሙጋቤ አባት፣ መምህር፣ የትግል ጓድ እና መሪ እንደሆኑ ይቆያሉ" ሲሉ ምናንጋግዋ በበዓለ ሲመታቸው ላይ ባደረጉት ንግግር ገልፀው ነበር። ሮበርት ሙጋቤ ሥልጣን እንዲለቁ ለማግባባት 10 ሚሊዮን ዶላር ተሰጥቷቸዋል የሚለውን ሪፖርት እስካሁን ማረጋገጥ አልተቻለም። ሙጋቤና ባለቤታቸው ግሬስ በአሁኑ ጊዜ በዋና ከተማዋ ሐራሬ ውስጥ በሚገኘው ቤታቸው ውስጥ እንደሚገኙ የተነገረ ሲሆን ሃገራቸውን ለቀው የመውጣት ዕቅድ የላቸውምም ተብሏል።
news-56156450
https://www.bbc.com/amharic/news-56156450
ኮሮናቫይረስ፡ የሟቾች ቁጥር 500,000 መድረሱ ‘ልብ ሰባሪ ምዕራፍ ነው’- ባይደን
አሜሪካ በኮሮናቫይረስ ምክንያት 500,000 ዜጎቿን ማጣቷን ተከትሎ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለህዝቡ ንግግር አድርገዋል።
"እንደ አንድ ህዝብ እንዲህ ዓይነቱን ጭካኔ የተሞላበት ዕጣ ፈንታ መቀበል አንችልም። በሀዘኑ መቆዘምን መከልከል አለብን" ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ፣ ምክትል ፕሬዚዳንቱ እና የትዳር አጋሮቻቸው ከንግግሩ በኋላ በኋይት ሃውስ በነበረው የሻማ ማብራት ሥነ-ስርዓት ወቅት የህሊና ፀሎት አድርገዋል፡፡ አሜሪካ ከ 28.1 ሚሊዮን በላይ ዜጎቿ በቫይረሱ በመያዛቸውም በዓለም አቀፍ ደረጃ ቀዳሚ ሆናለች። ፕሬዝዳንቱ "ዛሬ ሁሉም አሜሪካውያን እንዲያስታውሱ እጠይቃለሁ፡፡ ያጣናቸውን እና ወደ ኋላ የተውናቸውን ዳግም አስታውሱ" ሲሉ አሜሪካኖች ኮቪድን በጋራ እንዲዋጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በፌደራል መንግሥቱ ሥር የሚገኙ ሁሉም ቦታዎች ላይ ለሚቀጥሉት አምስት ቀናት የአገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ባይደን አዝዘዋል፡፡ ጆ ባይደን በኋይት ሃውስ ተገኝተው ንግግራቸውን የከፈቱት፣ በኮቪድ-19 የደረሰው አሜሪካውያን ሞት ከአንደኛው በዓለም ጦርነት፣ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት እና በቬትናም ጦርነት ከሞቱት ሰዎች ድምር ቁጥር የበለጠ መሆኑን በመጥቀስ ነው። "ዛሬ በእውነት አስከፊ እና ልብ ሰባሪ ምዕራፍ ነው- 500,071 ሰዎች ሞተዋል" ብለዋል፡፡ በመቀጥለም "ብዙ ጊዜም እንደ ተራ አሜሪካዊ ሰዎች ሲገለጹ እንሰማለን። እንደዚህ ዓይነት ነገር የለም። ምንም ተራ ብሎ ነገር የለም፡፡ ያጣናቸው ሰዎች እጅግ የተለዩ ነበሩ፡፡ በአሜሪካ የተወለዱ ወደ አሜሪካ የተሰደዱ ናቸው" ብለዋል። "ብዙዎቹም የመጨረሻ እስትንፋሳቸውን በአሜሪካ ወስደዋል" ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ጆ ባይደን ሚስታቸው እና ሴት ልጃቸው በጎርጎሮሳዊያኑ 1972 በመኪና አደጋ የተገደሉ ሲሆን ወንድ ልጃቸው ደግሞ በ 2015 በካንሰር ህይወቱ ማለፉን በማንሳት የራሳቸውንም የሃዘን ተሞክሮ ጠቅሰዋል። "ለእኔ በሀዘን ውስጥ ያለው መንገድ ዓላማን መፈለግ ነው" ብለዋል። ባይደን በወረርሽኙ ላይ የወሰዱት እርምጃ ከቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የተለየ ነው። ትራምፕ በአደገኛው ቫይረስ ተጽዕኖ ላይ ጥርጣሬ ያሳደሩ እና የቫይረሱ ስርጭትን ለመከላከል ጭምብሎችን መልበስ እና ሌሎች እርምጃዎችን ፖለቲካዊ አድርገውት እንደነበር ይነገራል፡፡ ባይደን ስልጣኑን ከመረከባቸው ከአንድ ቀን በፊት 400,000 አሜሪካውያን በቫይረሱ ምከንያት የሞቱበትን ክስተት አስበው ውለዋል፡፡ በሌላ በኩል በዋሽንግተን በብሔራዊ ካቴድራል ደወሎች 500 ጊዜ ተደውሏል- በወረርሽኙ ህይወታቸው ላለፈው ለአንድ ሺህ አሜሪካዊ አንድ ጊዜ ማለት ነው፡፡ በአሜሪካ ምን እየሆነ ነው? በኮሮቫይረስቫይረስ የተያዙት አሜሪካውያን ቁጥር በሁለተኛ ደረጃ ከያዘች ህንድ (11 ሚሊዮን) እና ብራዚል (10.1 ሚሊዮን) ጋር ሲነፃፀር በእጥፍ የሚበልጥ ነው፡፡ ብራዚል በ 244,000 የሟቾችን ቁጥር ሁለተኛ ስትሆን ሜክሲኮ 178,000 ሰዎችን አጥታ በሦስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ "ከአስርተ ዓመታት በኋላ በመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽን ምክንያት የደረሰውን የብዙዎች ሞት በሃገሪቱ ታሪክ ውስጥ እንደ ታላቅ ታሪካዊ ምዕራፍ ይገልጹታል" ሲሉ የበሽታ መከላከያ ባለሙያው ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ ለሲ.ኤን.ኤን ገልጸዋል። "አስገራሚ ቁጥር ነው። ከአንድ ዓመት በፊት ግማሽ ሚሊዮን አሜሪካውያን በዚህ በሽታ ሕይወታቸውን ያጣሉ የሚል ግምት አልነበረኝም" ብለዋል በብራውን ዩኒቨርሲቲ የኅብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት ዲን የሆኑት ዶ/ር አሺሽ ጅሃ። "በዚህች ሀገር ውስጥ ብዙ አቅም፣ ብዙ ሀብት አለን ... የምንከላከለው ስለነበር መከሰት አልነበረበትም፡፡ አሁን እዚህ ደርሰናል፡፡ የምንሰጠው ምላሽ የተሳሳተባቸውን መንገዶች ሁሉ ማንፀባረቅ ያለብን ይመስለኛል" ሲሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል፡፡ የዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ከሰሞኑ ይፋ ባደረገው ትንበያ መሠረት ቢያንስ 90,000 የሚሆኑ ተጨማሪ አሜሪካውያን እስከ ሰኔ 1 ቀን ድረስ በቫይረሱ ይሞታሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በግምቱ መሠረት በግንቦት መጨረሻ ቫይረሱ በየቀኑ 500 ገደማ አሜሪካውያንን እንደሚገድል ይገምታል። በአሁኑ ወቅት በየቀኑ ወደ 2,000 የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ እንደሚሞቱ ይገመታል። በየቀኑ ወደ 1.6 ሚሊዮን የሚጠጋ ክትባት ለአሜሪካዊያን እየተሰጠ በመሆኑ ሆስፒታል የሚገቡ ሰዎች መጠን ለ40ኛ ተከታታይ ቀናት ቀንሷል፡፡ ሆኖም ባለሙያዎች በአገሪቱ ውስጥ እየጨመረ በሄደው አዲስ የኮሮናቫይረስ ዝርያ የሟቾችን ቁጥር ሊጨምር ይችላል በሚል አሳስቧቸዋል፡፡ አኃዞች ቢሻሻሉም በኮሮናቫይረስ ምክንያት የአሜሪካኖች በሕይወት የመኖር ዕድሜን በአንድ ዓመት ቀንሷል ሲል የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማዕከል ባለፈው ሳምንት አስታውቋል፡፡ በቫይረሱ እጅግ በተጎዱትና በቁጥር አናሳ በሆኑት ማህበረሰቦች ዘንድ ደግሞ ለውጡ ከፍተኛ ነው ተብሏል። በህይወት የመኖር ዕድሜያቸው በከፍተኛ ደረጃ የቀነሰባቸው ጥቁር ወንዶች ሲሆኑ ከጥር እስከ ሰኔ 2020 ባለው ጊዜ ብቻ በሦስት ዓመት ቀንሷል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ የሂስፓኒኮች በህይወት የመኖር ዕድሜ በ 2.4 ዓመት ቀንሷል፡፡
news-53044859
https://www.bbc.com/amharic/news-53044859
የሐይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ወደ ምዕራብ ኦሮሚያም ይሄዳሉ
የሐይማኖት መሪዎችና የአገር ሽማግሌዎች በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥትና በትግራይ ክልል መስተዳደር መካከል ያለውን አለመግባባት በሽምግልና መፍትሔ እንዲያገኝ ለማገዝ ዛሬ ወደ መቀለ እንደሚሄዱ ተነግሯል።
መቀለ ከተማ የሽምግልና ቡድኑ ከመቀለ ጉዞው ባሻገር ለረጅም ጊዜ ግጭቶችና የሰላም መደፍረስ እንዳጋጠመው ወደሚነገርልት የምዕራብ ኦሮሚያ እካባቢዎች በመንቀሳቀስ ሰላም እንዲወርድ እንደሚጥር የቡድኑ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ለቢቢሲ ጨምረው ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ በፌደራል መንግሥቱና በትግራይ ክልል መካከል ያለው አለመግባባት ከጊዜ እየተካረረ በመሄድ ከኢህአዴግ መክሰም በኋላ የነበራቸው ግንኙነት ተቋርጦ አሁን ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ይሰማል። ይህ አለመግባባት ያሳሰባቸው የሐይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ሁለቱን ወገኖች ለማቀራረብ ወደ ትግራይ ዛሬ ማክሰኞ እንደሚያቀኑ የኢትዮጵያ ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መስኡድ አደም ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። • "አምባገነናዊ መንግሥት ሲመሰረት ተባባሪ ላለመሆን ኃላፊነቴን ለቅቄያለሁ" ወ/ሮ ኬሪያ • "የዋልታ ዘገባ ሆነ ተብሎ የተፈጸመ ሴራ ነው" የትግራይ ክልል የሽምግልና ቡድኑ ወደ መቀለ የሚሄድበት ዋና ዓላማ በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለው አለመግባባት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተካረረ መሄዱ እና ችግሩ እንዲፈታ ደግሞ መቀራረብና መነጋገር አስስፈካጊ በመሆኑ እንደሆነ ተገልጿል። አቶ መስኡድ እንዳሉት የሽምግልና ቡድኑ በሁለቱ ወገኖች ፖለቲካዊ አመለካከት የሚያነሳው ነገር እንደሌለ ጠቅሰው፤ መግባባትን በመፍጠር አገራዊ ኃላፊነትን ለመወጣት እንደሚጥሩ አመልክተዋል። "እንደ ሐይማኖት አባትም እንደ አገር ሽማግሌም በዚህ ጉዳይ ላይ ተነጋገሩ እንላለን። ከዚያም በሚያደረጉ ውይይቶች ላይ በሚደረጉ ድርድሮች ላይ መፍትሄዎች ይመጣሉ ብለን እናስባለን" ሲሉ ተናግረዋል። እንደ ሽምግልና ቡድኑ እምነት ለሚታየው አለመግባባት ዋነኛው ችግር ያጋጠሙ ቅራኔዎችን ተቀራርቦ መነጋገር አለመቻል ነው። ስለዚህም እነዚህ የሐይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ይህንን ሚና በመውሰድ ሁለቱን ወገኖች በማቀራረብ እንዲነጋገሩና ለገጠማቸው ችግር በእራሳቸው መንገድ መፍትሔ እንዲኣገኙ መርዳት የቡድኑ ቀዳሚ ሐሳብ ነው ተብሏል። "የመጀመሪያውን እርምጃ በመውሰድ አገራዊ ኃላፊነታችንን እንወጣ። እናቀራርባቸው፤ እነሱ ይነጋገሩ" የሚል መነሻ በሽማግሌዎቹ መኖሩ ተገልጿል። አቶ መስኡድ እንዳሉት ይህንን የሽምግልን ለማከናወን ተነሳሽነቱ ከማንም ግፊት የመጣ እንዳልሆነ ጠቅሰው ይህ ተግባር "እንደ ሐይማኖት መሪም ሐይማኖታዊ ግዴታ ነው። የተጣሉን ማስታረቅ ሰዎችን ማቀራረብ ሐይማኖታዊ የተቀደሰ ምግባር ነው። እንደ አገር ሽማግሌም ትልቅ የሞራል ግዴታም ጭምር ነው" ሲሉ በእራስ ተነሳሽነት የተጀመረ እንቅስቃሴ መሆኑን ተናግረዋል። የሽምግልና ቡድኑ በፌደራል መንግሥቱና በትግራይ ክልል መካከል ያለው አለመግባባት መፍትሔ እንዲያገኝ "እንደ አማኝ ፈጣሪ ያግዘናል ብለን ነው የምናስበው። ሐይማኖት መሪዎች በፀሎት ያግዛሉ፣ የአገር ሽማግሌዎች ያነጋግራሉ፣ ያደራድራሉ፥ ያቀራርባሉ" በማለት ጥረታቸው በስኬት እንደሚጠናቀቅ ያላቸውን ተስፋ አመልክተዋል። • በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ለምን ተስፋፋ? • የኮሮናቫይረስ ውጤት መዘግየት ስጋት እየፈጠረ ነው የሽምግልና ቡድኑ በሁለቱ ወጎች መካከል ያለው ትልቁ ችግር ያለመነጋገር ነው ብሎ እንደሚያምንና ለዚህ ደግሞ ቁልፉ መነጋገር በመሆኑ በመነጋገር መፍትሔ ይገኛል ብሎ እንደሚያምን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ላለመግባባትም እኮ መግባባት ያስፈልጋል። በዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ አንግባባም፤ በዚህ በዚህ ጉዳይ ተግባብተን አብረን እንቀጥላለን ማለትም አንድ ነገር ነው። ተቀራርበው እንዲነጋገሩ ካደረግን ከዚያ በኋላ ችግሮቻቸውን በመነጋገር፣ በውይይት ይፈታሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን።" የሽምግልና ቡድኑ የዛሬ ወደ ትግራይ የሚደረገው ጉዞ የመጀመሪያው እንደሆነና በዚህ ጉዞ ብቻ ተወስኖ እንደማይቀር የተናገሩት አቶ መስኡድ ሌሎች መቀራረብና መግባባት ይኖርባቸዋል በሚባሉ ወገኖች መካከል ተመሳሳይ ሥራዎች እንደሚከናወን ተናግረዋል። በዚህም "ወደ ምዕራብ ኦሮሚያ፣ ወደ አማራም፣ ወደ ሶማሌም፣ ወደ ሌሎቹ የአገሪቱ ክፍሎችም በመሄድ በአጠቃላይ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ጥረት ይደረጋል። የዛሬው የመቀሌ ጉዞ የእዚያ ጥረት ማስጀመሪያ ነው የሚሆነው" ብለዋል። በአገሪቱ የለውጥ እርምጃዎች መወሰድ ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ የትግራይ ክልል ገዢ ፓርቲ ህወሓት በአንድ ግንባር ስር ለ25 ዓመታት በአንድ ላይ ሲሰሩ ከነበሩት ድርጅቶች ጋር የነበረው ትስስር ላልቶ ቅራኔ በአደባባይ ሲነገሩ ቆይተዋል። በተለይም የአራት ክልላዊ ፓርቲዎች ጥምረት የነበረው ኢህአዴግ ከስሞ በብልጽንና ፓርቲ ሲተካና ህወሓት እራሱን ሲያገል ነገሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ ተካረው አሁን ካለበት ደረጃ ላይ መድረሱ ይታወሳል።
news-52703735
https://www.bbc.com/amharic/news-52703735
የአሜሪካ ኢኮኖሚ በኮሮናቫይረስ ሰበብ በ30 በመቶ ያሽቆለቁላል ተባለ
የአሜሪካ ኢኮኖሚ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ከ20 እስከ 30 በመቶ ሊያሽቆለቁል እንደሚችል የፌደራል መንግሥቱ ግምጃ ቤት ሊቀ መንበር ተናገሩ።
ጄሮም ፓውል ለሲቢሲ በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ እንዳመለከቱት የኢኮኖሚ መቀዛቀዙ በወራት ውስጥ የሚያበቃ ብቻ ሳይሆን እስከ ቀጣዩ የፈረንጆች ዓመትም ሊዘልቅ እንደሚችል ገልጸዋል። ምናልባትም የአገሪቱ ኢኮኖሚ ከወደቀበት ተነስቶ ወደነበረበት ለመመለስ ለወረርሽኙ ክትባት እስኪገኝ ድረስ መቆየት ሊያስፈልገው እንደሚችልም ጠቁመዋል። በዚህም ምክንያት የግምጃ ቤት ሊቀመንበሩ ፓውል ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ የአሜሪካ ሕግ አውጪዎች ተጨማሪ የኢኮኖሚ ማነቃቂያና እርዳታ እንዲያጸድቁ ጥሪ አቅርበው ነበር። የኮሮናቫይረስ ባስከተለው ጫና ምክንያት ከመጋቢት ወር አጋማሽ ወዲህ ከ36 ሚሊዮን በላይ አሜሪካዊያን ሥራቸውን በማጣታቸው ምክንያት የመንግሥትን ድጋፍ ለማግኘት አመልክተዋል። ጄሮም ፓውል ጨምረውም "የአሁኑ ወቅት ከባድ ችግር ያጋጠመን ጊዜ ነው። ዜጎች ያሉበትን ስቃይ በቃላት ለመግለጽ ያስቸግራል። ቢሆንም ግን ጊዜ ሊወስድ ይችላል እንጂ ኢኮኖሚው ማገገሙ አይቀርም" በማለት እስከ ቀጣይ ዓመት ድረስ ችግሩ ሊቀጥል እንደሚችል አመልክተዋል። እስካሁን ያለው የሥራ አጦች ቁጥር እስከ 25 በመቶ ሊድረስ እንደሚችልና ተጎጂዎቹም "ዝቅተኛ ክፍያ የሚያገኙ ሰዎች" እንደሚሆኑና በተለይ ደግሞ ሴቶች በኢኮኖሚ ቀውሱ ክፉኛ ተጎድተዋል ብለዋል። ነገር ግን የአገሪቱ የፋይናንስ ሥርዓት ጤናማ በመሆኑና ወረርሽኙም ከኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውጪ ያጋጠመ "ውጫዊ ክስተት" በመሆኑ አሜሪካ የኢኮኖሚ ድቀት እንደማይገጥማት ተናግረዋል። ሊቀ መንበሩ አክለውም ባለፉት ሦስት ወራት ኢኮኖሚው እስከ 30 በመቶ ቢያሽቆቁልም፤ ወረርሽኙ ለሁለተኛ ዙር ተመልሶ ጉዳት ካላስከተለ በቀጣዮቹ ሦስት ወራት ውስጥ "በፍጥነት የማገገም ዕድል አለ" ብለዋል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ክፉኛ የተመታችው አሜሪካ ከዓለም አገራት ሁሉ የላቀ ቁጥር ያለቸው ሰዎች በሽታው ከመያዛቸው በተጨማሪ ከፍተኛውን የሟቾች ቁጥር መዝግባለች። በአንዳንድ ግዛቶቿ በእንቅስቃሴ ላይ ተጥሎ የነበረው ዕገደ ከመላላቱ ጋር ተያይዞ በሸታው ተመልሶ ለሁለተኛ ጊዜ ሊያገረሽ ይችላል የሚል ስጋት ተፈጥሯል።
news-56156452
https://www.bbc.com/amharic/news-56156452
ኮሮናቫይረስ፡ ቻይና ለኮቪድ-19 ምርመራ ከአሜሪካ ዲፕሎማቶ ላይ ተወሰደ በተባለ ናሙና ተወዛገቡ
ቻይና ከአሜሪካ ዲፕሎማቶች ፊንጢጣ ላይ ለኮሮናቫይረስ ምርመራ በሚል ናሙና እንዲወሰድ አላደረኩም ስትል ተናገረች።
የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዲፕሎማቶች በዚህ መንገድ ናሙና እንዲሰጡ መደረጋቸውን በመግለጽ ቅሬታ ማሰማታቸውን ዘግበው ነበር። የተወሰኑ የቻይና ከተሞች ባለሙያዎች "በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን በተሻለ መለየት ያስችላል" በማለታቸው የተነሳ ከፊንጢጣ ናሙና ይወስዳሉ። ቻይና የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በስፋት መቆጣጣር ከቻሉ ውሱን የዓለም አገራት መካከል አንዷ ነች። የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዣሆ ሊዢን ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የቀረበውን መረጃ መሰረተ ቢስ ነው ሲሉ አጣጥለውታል። "ቻይና በአገሯ ተቀማጭነታቸውን ያደረጉ ዲፕሎማቶችን ከፊንጢጣቸው ናሙና እንዲሰጡ በጭራሽ አላደረገችም" ብለዋል። ባለፈው ሳምንት ዋሺንግተን ፖስት የተወሰኑ ሠራተኞች ለአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት እንዲህ ዓይነት ምርመራ እንዲያደርጉ መገደዳቸውን መግለጻቸውን ዘግቧል። ናሙናው የሚወሰደው ከ3-5 ሴንቲሜትር ርዝመት ያለው መሳሪያ በጥንቃቄ በማሽከርከር ነው። እንዲህ ዓይነት ምርመራ ምን ያህል ዲፕሎማቶች እንዳደረጉ የታወቀ ነገር የለም። ረቡዕ ዕለት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት "የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዲህ ዓይነት ምርመራ እንዲያደርጉ አልተስማማም፤ ጉዳዩ መፈፀሙን እንዳወቅን ተቃውሟችንንም [ለቻይና] የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አቅርበናል" ብሏል። የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምርመራው "በስህተት" መከናወኑን እንደተገለፀለት አክሎ አስረድቷል። ቻይና ይህንን የምርመራ ዓይነት ያስተዋወቀችው በታኅሣስ ወር ሲሆን ከተለመደው በአፍንጫና ከአፍ ከሚወሰድ ናሙና በተለየ ቫይረሱን ለመለየት ያስችላል ሲሉ ባለሙያዎች ተናግረዋል። ነገር ግን ይህ ምርመራ የሚያስፈልገው ለተወሰኑ ሰዎች መሆኑን ባለሙያዎቹ ገልፀው በለይቶ ማቆያ ላሉ ሰዎች ብቻ ነው ሲሉ ምክራቸውን ለግሰው ነበር።
news-48898987
https://www.bbc.com/amharic/news-48898987
ሊብራ፡ አዲሱ የፌስቡክ ዲጅታል ገንዘብ እና አፍሪካ
ከቀጣዩ የፈረንጆቹ ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ ፌስቡክ ወደ ሁለት ቢሊዮን ለሚጠጉ ተጠቃሚዎቹ በዋትስአፕ፣ ኢንስታግራም እና በፌስቡክ መተግበሪያዎቹ አማካኝነት ግብይትን እንዲፈጽሙ ለማስቻል እየሰራ ይገኛል።
ሊብራ ተብሎ በሚጠራው ክሪፕቶ-ከረንሲ 139 ሚሊዮን በአፍሪካ የሚገኙ የፌስቡክ ተጠቃሚዎችም ግብይት መፈጸም ይችላሉ ተብሏል። ከምዕራባውያን ሃገራት ከወዳጅ ዘመዶች በገንዘብ አስተላላፊዎች ከፍተኛ ገዘንብ የምትቀበለው አፍሪካ፤ ፌስቡክ ይህን መሰል ቀላል እና ቀልጣፍ የገንዘብ ዝውውር ማድረጊያ አማራጭን ማምጣቱ ለአፍሪካ አህጉር ጠቀሜታው ላቅ ያለ ነው ተብሏል። • ዓለም ሁሉ የሚያወራለት ክሪይፕቶከረንሲ ምንድነው? • በአሁኑ ወቅት በጣም ተፈላጊ የሆኑ የዲጂታል ዘርፍ ሥራዎች የትኞቹ ናቸው? • አምስቱ የአፍሪካ ቴክኖሎጂ ጎዳናዎች በ2018 የቴክኖሎጂ ጋዜጠኛው አንዲሌ ማሱኩ ''በደቡብ አፍሪካ ነው የምኖረው። ከውጪ ሃገር የተላከልኝን ገንዘብ ተቀብዬ ወደ ዚምባብዌ ለመላክ ያለኝ ስጋት ከፍተኛ ነው። የተቀበልኩትን ገንዘብ በጠራራ ጸሐይ ልዘረፍ እችላለሁ'' በማለት ይናገራል። ጋዜጠኛ አንዲሌ የፌስቡክ እቅድ ይህን መሰል ስጋቶችን ከመቅረፍም አልፎ ሰዎች ወደ ትውልድ ሃገራቸው ገንዘብ ለመላክ ከገንዘብ አስተላላፊዎች የሚጠየቁትን ከፍተኛ የማስተላለፊያ ዋጋ መቀነስ ያስችላል ይላል። ባሳለፍነው ዓመት የዓለም ባንክ ያወጣው ሪፖርት እንደጠቆመው ከሰሐራ በታች ወዳሉ ሃገራት ገንዘብ መላክ ከየትኛው የዓለማችን ከፍል ብዙ የማስተላለፊያ ወጪን ይጠይቃል። እንደምሳሌም 200 የአሜሪካ ዶላር በዌስተርን ዩኒያን ወይም በመኒግራም ለመላክ 19 ዶላር መላኪያ ገንዘብ ያስከፍላል። የደቡብ አፍሪካ ራንድ በሌላ በኩል በርካታ የአፍሪካ መንግሥታት በክሪብቶ-ካረንሲዎች ላይ የላቸው የደህንነት ጥርጣሬ የፌስቡክም ሆነ የሌሎች ዲጅታል ከረንሲዎች ውጤታማነትን ጥያቄ ውስጥ መክታቱ አልቀረም። በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ የክሪፕቶ-ካረንሲ መጠቀሚያነትን ካገዱ ሃገራት መካከል ናይጄሪያ እና ዚምባብዌ ይጠቀሳሉ። ክሪፕቶ-ካረንሲዎችን በመጠቀም የግዢው ማንነት ይፋ ሳይደረግ ግብይት መፈጸም ይቻላል። በዚህም ሕገ-ወጥ ቡድኖች የጦር መሳሪያዎች እና እጾችን ሊገዙ እና ሊሽጡ ይቻላሉ፣ ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና አሸባሪዎችን ለመደገፍ ያስችላል በማለት ቢትኮይንን ጨምሮ ሌሎች ክሪይፕቶከረንሲዎች ላይ ያላቸውን ስጋት የሚያነሱ ሃገራት አሉ። ክሪይፕቶ-ከረንሲን ምንድነው? ኦክስፎርድ መዝገበ ቃላት 'ክሪይፕቶ-ከረንሲን'፤ የገንዘብ ልውውጦችን ደህንነት የሚያረጋግጥ፣ የተጨማሪ አሃዶችን መፈጠርን የሚቆጣጠር እና ገንዘብ መተላለፉን የሚያረጋግጥ ጠንካራ ክራፕቶግራፊ የሚጠቀም መገበያያ እንዲሆን ተደርጎ የተቀረጸ ዲጂታል ገንዘብ ሲል ይገልጸዋል። ቢትኮይን ምንድነው? ቢትኮይን ማለት በቀላል ቋንቋ፤ ዲጂታል+ገንዘብ+መገበያያ በማለት ማጠቃለል ይቻላል። ይህ መገበያያ በኪሳችን ተሸክመን እንደምንዞረው የብር ኖት ወይም ሳንቲም ሳይሆን 'ኦንላይን' የሚቀመጥ ዲጂታል ገንዘብ ነው። ሌላው የቢትኮይንና የተቀሩት የክሪይፕቶከረንሲዎች ልዩ ባህሪ በመንግሥታት እና በባንኮች አለመታተማቸው እንዲሁም ቁጥጥር አለመደረጉ ነው። ቢትኮይን የሚፈጠረው 'ማይኒንግ' በሚባል ሂደት ነው። ሊብራ ከቢትኮይን በምን ይለያል፡ ሊብራ ልክ እንደ ቢትኮይን የሚፈጠረው 'ማይኒንግ' በሚባለው ሂደት ነው። ልዩነታቸው ሊብራ በሚታወቁ ኩባንያዎች ቁጥጥር ይደረግበታል። ቢትኮይን እና ሌሎች ክሪፕቶ-ከረንሲዎች በመንግሥታት እና በባንኮች አይታተሙም፤ ቁጥጥርም አይደረግባቸውም። የፌስቡኩ ሊብራ ግን በመንግሥታት እና በማዕከላዊ ባንኮች ቁጥጥር ይደረግበታል በተጨማሪም በጥሬ ገንዘብ ተቀማጭ ይኖረዋል። ሊብራ ከአሁኑ ከቪዛ፣ ማስተርካርድ፣ ኡበር እና ሰፖቲፋይ ተቀባይነትን አግኝቷል። የፌስቡክ ዲጂታል ገንዘብ ለአፍሪካውን ሁነኛ የመገበያያ አማራጭን ይዞ ይመጣል የሚሉ በርካቶች እንዳሉ ሁሉ፤ የአፍሪካ መንግሥታት ዜጎች የፌስቡክ ዲጅታል ገንዘበ አጠቃቀም ካልተዋጠላቸው በቀላሉ አገልግሎቱን ማቋረጥ መቻላቸው ስጋትን ፈጥሯል። የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢ አገልግሎቱን ሆነ ብሎ ቢያቋርጥ በፌስቡክ፣ ዋትስአፕ እና በሌሎች መተግበሪያዎች የሚደረጉ የገንዘብ ዝውውር ወዲያው ይቋረጣል። በዚህም ምክንያት ሊብራ ላይ መሞርኮዝ እንደማይቻል ባለሙያዎች ስጋታቸውን ያስቀምጣሉ።
news-53386933
https://www.bbc.com/amharic/news-53386933
በቡራዩ በጎርፍ አደጋ 9 ሰዎች ሲሞቱ የደረሱበት ያልታወቁ እየተፈለጉ ነው
ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ በምትገኘው ቡራዩ አካባቢ ቅዳሜ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ ቢያንስ 9 ሰዎች መሞታቸውን እና የደረሱበት ያልታወቁ ሰዎች እየተፈለጉ መሆኑን የከተማው ኮሙኒኬሽን አቶ አብደላ ቲቤሶ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
አቶ አብደላ ቲቤሶ ገፈርሳ ኖኖ የሚባል ቀበሌ እና ገፈርሳ ጉጄ የሚባሉት ቀበሌዎች ውስጥ ባጋጠመው የጎርፍ አደጋ እስካሁን የ9 ሰዎች አስክሬን መገኘቱንና የደረሱበት ያልታወቁ ሰዎች እየተፈለጉ መሆኑን ገለጸው፤ በንብረት ላይም ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን አስታውቀዋል። በጎርፍ አደጋው ህይወታቸውን ያጡት አብዛኛዎቹ ሰዎች ለሥራ ከሌላ አካባቢዎች የመጡ ሰዎች መሆናቸውንም ተናግረዋል። የሟቾችን አስክሬን ማንነት የመለየት ሥራ ላይ መሆናቸውን የገለጹት አቶ አብደላ እስካሁን ማንነታቸው የታወቁ ሰዎች አስክሬን ወደ ትውልድ መንደራቸው እየተሸኘ መሆኑን ተናግረዋል። ኃላፊው እንዳመለከቱት በጎርፍ አደጋው እስካሁን በንብረት ላይ የደረሰው የጉዳት መጠን ባይታወቅም ነገር ግን ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን መገመት እንደሚቻል ለቢቢሲ ገልጸዋል። ግዙፍ ፋብሪካዎች፣ መኖሪያ ቤቶች፣ ሱቆች፣ የመንግሥት ተቋማት እና ቤተ-እመነቶች ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል ተጠቃሽ ናቸው። "አንድ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እና በግቢው ውስጥ የነበረ ትምህርት ቤት ሙሉ በሙሉ በጎርፉ ተወስዷል" ያሉት አቶ አብደላ፤ በጎርፉ ምክንያት የወደሙ መኖሪያ ቤቶች በቁጥር እስካሁን ባይለዩም በርካታ መሆናቸውን ተናግረዋል። ጎርፉ ሳቢያ በርካታ ቁጥር ያላቸው የቤት እንስሳት የሞቱ ሲሆን "የሞቱ ከብቶች፣ ፍየሎች፣ በጎች እና ፈረሶች አሁንም ሜዳ ላይ እንዳሉ ናቸው" ሲሉ ተናግረዋል። አንድ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪም በጎርፍ ተወስዶ ሜዳ ላይ ወድቆ እንደሚገኝም አቶ አብደላ ተናግረዋል። በአካባቢው ይህን መሰል አደጋ ከዚህ ቀደም ተከስቶ እንደማያውቅ አቶ አብደላ ቲቤሶ ለቢቢሲ ገልፈዋል።
news-42265018
https://www.bbc.com/amharic/news-42265018
የግሉ ዘርፍ ሠራተኞች ለመውለድ ምን ያህል ይጠብቁ?
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ረቡዕ ህዳር 26 ቀን 2010 ዓ.ም ባካሄደው የሶስተኛ ዓመት 7ኛ መደበኛ ስብሰባ የተሻሻለውን የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ በማፅደቅ የመንግሥት ሰራተኞችን የወሊድ ፈቃድ ከሦስት ወደ አራት ወር ከፍ እንዲል አድርጓል።
አዋጁ በብዙዎች እሰይ የተባለለት ቢሆንም የአዋጁን መፅደቅ ተከትሎ በግሉ ዘርፍ ያሉ እናቶችስ? የሚል ጥያቄ እየተነሳ ነው። አንድ አገር ላይ እየሰሩና እኩል ግብር እየከፈሉ እንዴት የዚህ ዓይነት ልዩነት ይኖራል በሚል አስተያየታቸውን የሰነዘሩ ብዙዎች ናቸው። በግሉ ዘርፍ ያሉ ሴቶችን ጉዳይ በተመለከተ ከቢቢሲ ጥያቄ የቀረበላቸው የፌደራል የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር ህግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ተክይበሉ በግሉ ዘርፍና በመንግሥት በጀት በማይተዳደሩ የልማት ድርጅቶች የአሰሪና ሠራተኛ ግንኙነትን የሚመለከት ሌላ አዋጅ መኖሩን በማስታወስ ይህ አዋጅም ተሻሽሎ ተመሳሳይ ውጤት እንደሚኖር ገልፀዋል። "የአሰሪና ሠራተኛ አዋጁ በመሻሻል ላይ ነው። በመሰረታዊነት የሚታየው ወሊድ ሴት ልጅ ትውልድን የመተካት ሃላፊነት የምትወጣበት ተፈጥሯዊ ነገር መሆኑ ነው። ስለዚህ ተመሳሳይ የሆነ የፖሊሲ አቋም ይኖራል ተብሎ ነው የሚጠበቀው። እስከዛሬም የነበረው ነገር ተመሳሳይ ነው" ብለዋል አቶ ደረጀ። ነገር ግን ይህ በግሉ ዘርፍ ያሉ ሴቶች የወሊድ ፈቃድን የሚመለከተው አዋጅን የማሻሻል ሂደት ገና በጅምር ላይ ነው። አቶ ደረጀ እንደሚሉት በአሁኑ ወቅት ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ማሻሻያውን እያየውና እየመከረበት ሲሆን ለውሳኔ አልደረሰም። እዚህ ጋር ሊነሳ የሚችለው ጥያቄ ለግል ዘርፍ ሠራተኞች የተዘጋነው አዋጅ በትክክል መቼ ይፀድቃል የሚለው ነው። ለመንግሥት ሠራተኞች የፀደቀው አዋጅ በተጨማሪም የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የህፃናት ማቆያ እንዲያዘጋጁም ይደነግጋል። ያነጋገርናቸው እናቶች እርምጃው በጣም ጥሩ እንደሆነ ሲገልፁ ስድስት ወር ጡት ከማጥባት አንፃር አሁንም የወሊድ ፈቃድ ሊሻሻል እንደሚገባ የሚናገሩም አሉ። በተመሳሳይ የኢትዮጵያ የማህፀንና ፅንስ ሃኪሞች ማህበር ፕሬዚዳንት ዶክተር ደረጀ ንጉሴ ከእናቶች ከወሊድ ማገገም እንዲሁም ስድስት ወር ከማጥባት አንፃር ማህበራቸው የወሊድ ፍቃድ መርዘምን እንደሚደግፍ ይናገራሉ። ይህ ማለት ፍቃዱ ከዚህም በላይ ከፍ ቢል እንደ ህክምና ባለሙያ የሚደግፉት ነው። በተቃራኒው በአገሪቱ ነባራዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ የወሊድ ፍቃድን መጨመር የሴቶችን ሥራ የመቀጠር እድል ይቀንሳል የሚል አስተያየት የሰጡን ሴቶችም አሉ። በፌስቡክና በተለያዩ ገፆች ሴቶችን የሚመለከቱ ነገሮችን የምትፅፈው ቤተልሄም ነጋሽ ቀደም ሲል የወሊድ ፈቃድ እንዲጨመር በማህበራዊ ድረ ገፆች ቅስቀሳ እናድርግ የሚል ጥያቄ ቀርቦላት የነበረ ቢሆንም፤ መጀመሪያ የኢኮኖሚው ሁኔታና የቀጣሪዎች አመለካከት ከግምት ውስጥ መግባት አለበት ብላ በማመን በቅስቀሳው ከመሳተፍ መቆጠቧን ትናገራለች። "ማህበረሰቡ መጀመሪያ መውለድ ዘር መተካት መሆኑን በመረዳት በወሊድ ምክንያት እናቶች ላይ የሚፈጠረውን ጫና ለመካፈል ፈቃደኛ መሆን አለበት። የድርጅት ባለቤቶች የወሊድ ፍቃድ ሲሰጡ ቀጣዩን ትውልደ እየተንከባከቡና እያሳደጉ መሆኑን ማወቅ አለባቸው" ትላለች። የቀድሞዋ ጋዜጠኛ ሮዝ መስቲካ ሥራዋን ያቆመችው የመጀመሪያ ልጇን ስትወልድ እንደነበር ታስታውሳለች። የወሊድ ፍቃድ ስድስት ወር መሆን አለበት በማለት በማህበራዊ ድረ ገፅ ቅስቀሳ ስታደርግ በመቆየቷ በአዋጁ መሻሻል ደስተኛ መሆኗን ትናገራለች። "ስድስት ወር ይጨመር የምለው አንድም ስድስት ወር ለማጥባት፤ ሌላው ደግሞ እናት በቂ እረፍት እንድታደርግ ነው። ቢሆንም ግን የተገኘው አንድ ወርም ቀላል ባለመሆኑ ደስተኛ ነኝ። ብዙ እናቶች እንደሚያደርጉት ከራሳቸው ፍቃድ ጨምረው ስድስት ወር ሊያጠቡ ይችላሉ" ብላለች። በመጀመሪያው የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ 515/1999 መሰረት የወሊድ ፍቃድ ሦስት ወር ነበር።
news-55169354
https://www.bbc.com/amharic/news-55169354
የእስራኤል ምክር ቤት አባላት ፓርላማውን ለመበተን የድጋፍ ድምፅ ሰጡ
የእስራኤል ምክር ቤት አባላት ፖርላማውን ለመበተን የሚያስችለውን ከፍተኛ የድጋፍ ድምፅ ሰጥተዋል።
ፓርላማው እንዲበተንም የመጀመሪያ ዙር ከፍተኛ ድምፅ ተገኝቷል ተብሏል። ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ናታንያሁ ጋር ስልጣን የመጋራት ስምምነት የገቡት የአገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር ቤኒ ግራንትዝ ድጋፍም ነው ውሳኔው ያለፈው። በትናንትናው ዕለት ውሳኔ የተላለፈበት የፓርላማ ይበተን ረቂቅ እንደገና ክንሴት ተብሎ ለሚጠራው የአገሪቷ ፓርላማ ለግምገማ መቅረብ አለበት። ፓርላማውም ገምግሞ በአዲሱና ቀጣዩ ምርጫ ላይ ውሳኔ ያሳልፋል፤ በዚህም መሰረት እስራኤል በሁለት አመት ውስጥ አራተኛ ምርጫዋንም ልታካሂድም እቅድ ይዛለች። የእስራኤል የፖለቲካ ፓርቲ አባላት የአገሪቱን በጀት በተመለከተ መስማማት አቅቷቸው ለረዥም ጊዜ በማያፈናፍን አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል። በትናንትናው ዕለት በነበረው የድምፅ መስጫ ስነ ስርአት 61 ለ54 በሆነ ብልጫ ፓርላማው እንዲበተን ውሳኔ ተላልፏል። ከምርጫው በፊት የአገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር ቤንያሚን ናታንያሁ የአገሪቱን በጀት ስምምነት አዘግይተዋል በማለት "የምጣኔ ኃብት የሽብር ጥቃት" እየፈፀሙ ነው ሲሉ በቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ ወቅሰዋቸዋል። ቤኒ ግራንትዝ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የበጀቱን ስምምነት ያዘገዩት ሆን ብለውና የስልጣን ጊዜያቸውንም ባልተገባ ሁኔታ ለማራዘም ነው ይላሉ። "ኔታንያሁ እኔን ብቻ አይደለም የዋሸኝ፤ እናንተንም ዋሽቷችኋል። የእስራኤልን ህዝብ አጭበርብሯል" በማለትም ወርፈዋቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ በበኩላቸው ወቅቱ "የምርጫ አይደለም። የአንድነት ጊዜ ነው" ብለዋል። በስልጣን የመጋራቱ ስምምነት መሰረት ናታንያሁ በጠቅላይ ሚኒስትርነት 18 ወራት ካገለገሉ በኋላ ለቤኒ ግራንትዝ ማስተላለፍ አለባቸው። ነገር ግን በአሁኑ ወቅት የበጀቱ ስምምነት ወደየትም ባለመሄዱ ስልጣናቸውን ለማስረዘም ክፍተት እየፈለጉ ናቸው በማለት ተንታኞች መናገራቸውን ታይምስ ኦፍ እስራኤል ዘግቧል። አገሪቷ በአውሮፓውያኑ 2018 በፀደቀ በጀት እየሰራች ያለች ሲሆን ከዚያም በኋላ ሶስት ምርጫዎችን አካሂዳለች። የቀኝ ክንፉ ሊኩዊድ ፓርቲ መሪ የሆኑት ናታንያሁ በሙስና ወንጀልም የፍርድ ሂደታቸው እየታየ ነው። ጉቦ በመክፈል፣ በማጭበርበርና እምነት በማጉደል ውንጀላ የቀረበባቸው መሪው በጭራሽ እንዳልፈፀሙ ይናገራሉ።
48442484
https://www.bbc.com/amharic/48442484
'መንፈስ ቅዱስ' ከቅጣት የጋረደው አሽከርካሪ
ጀርመን ውስጥ ነው። አንድ ሾፌር መንዳት ከሚገባው ፍጥነት በላይ እየከነፈ ሲጓዝ፤ በትራፊክ ፖሊስ ካሜራ እይታ ውስጥ ይገባል።
ጀርመን ውስጥ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር 105 ዩሮ (2600 ብር ገደማ ) ያስቀጣል። ትራፊክ ፖሊሶችም ግለሰቡን ለመቅጣት የደህንነት ካሜራውን ሲመለከቱ ያልጠበቁት ገጠማቸው። የግለሰቡ መኪና ፊት ለፊት አንዲት ነጭ እርግብ ትበራለች። እርግቧ ትበር የነበረው በሾፌሩ መቀመጫ ትክክል ስለነበረ የግለሰቡን ማንነት መለየት አልተቻለም። ፖሊሶቹም እርግቧ "የመንፈስ ቅዱስ አምሳያ ናት" ብለው፤ ግለሰቡን ላለመቅጣት ወሰኑ። ፖሊሶቹ እርግብ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መንፈስ ቅዱስን መወከሏን አጣቅሰው፤ ለግለሰቡ ከለላ ስለሰጠችው ከቅጣት ተርፏል ብለዋል። • ተዓምራዊቷ ቅድስት ማርያም ውቕሮ ገዳም • ደቡብ ኮሪያዊው ፓስተር በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ታሰሩ "ግለሰቡ በእርግብ አምሰያ የተላከለትን መልዕክት ተረድቶ ከዚህ በኋላ የፍጥነት ወሰን አይጥስም ብለን ተስፋ እናደርጋለን" ሲሉም ፖሊሶች ተናግረዋል። ግለሰቡ ያሽከረክር የነበረበት ጎዳና የፍጥነት ወሰን በሰዓት 34 ኪሎ ሜትር ሲሆን፤ እሱ ግን በ54 እየነዳ ነበር። ፖሊሶቹ መቅጣት ፈልገው የነበረው ግለሰቡን ብቻ ሳይሆን እርግቧንም ጭምር ነበር። "እርግቧ እጅግ በፍጥነት በመብረሯ ልንቀጣት ፈልገን ነበር። ግን የት ለመድረስ እንደምትከንፍ ስላላወቅን ይቅር ብለናታል" ብለዋል።
news-52586895
https://www.bbc.com/amharic/news-52586895
ኮሮናቫይረስ በአፍሪካ እስከ 190 ሺ ሰዎችን በመጀመሪያው ዓመት ሊገድል ይችላል- የዓለም ጤና ድርጅት
ኮሮናቫይረስ በአፍሪካ እስከ 190 ሺ ሰዎችን በመጀመሪያው ዓመት ሊገድል ይችላል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ።
የዓለም ጤና ድርጅት ትናንት ማምሻውን በሰጠው መግለጫ ኮሮናቫይረስ በመጀመሪያው ዓመት ብቻ በአፍሪካ ከ 83 ሺ እስከ 190 ሺ ሰዎችን ሊገድል እንደሚችል አስታውቋል። በተጨማሪም ቫይረሱ በቶሎ በቁጥጥር ስር የማይውል ከሆነ ከ29 ሚሊየን እስከ 44 ሚሊየን ሰዎች በቫይረሱ ሊጠቁ ይችላሉ ብሏል ድርጅቱ። ‘’የዓለም ጤና ድርጅት ይህንን ግምት የሰራው አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገራት ቫይረሱን ባለበት ለማስቆም እየወሰዱት ያለው እርምጃ በቂ አለመሆን ብቻ ሳይሆን ከሚገባው በታች በመሆኑ ነው’’ ብለዋል የድርጅቱ አፍሪካ ኃላፊ ማትሺዶ ሞዌቲ። በርካታ አፍሪካ አገራት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ህዝባዊ ስብሰባዎችን ከልክለዋል፤ ዓለማ አቀፍ በረረዎችን አቁመዋል፤ የሰዓት እላፊ ጥለዋል፤ የእንቅስቃሴ ገደብም አበጅተዋል። ነገር ግን አሁን እየተወሰዱ ያሉት እርምጃዎች በቂ አይደሉም፤ ያሉትም ሕጎች በአግባቡ ተግባራዊ እየተደረጉ አይደለም ብሏል የዓለም ጤና ድርጅት። ቫይረሱ ከሌላው ዓለም ዘግይቶ አፍሪካ በመድረሱ የስርጭቱ መጠን በአሁኑ ወቅት ዝቅተኛ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ለዓመታት የሚቆይ ወረርሽኝ ሊሆን እንደሚችልም ድርጅቱ ስጋቱን ገልጿል። ‘’ይህ ቫይረስ ለሚቀጥሉት ዓመታት አብሮን ሊቀጥል የሚችልበት እድል ሰፊ ነው። መንግስታት ከአሁኑ ተገቢውን ስራ ካልሰሩ ይህ መሆኑ አይቀርም። በርካታ ሰዎችን መመርመር፣ ንክኪ ያለበትን ቦታ በፍጥነት መለየትና ለታማሚዎች በለይቶ ማቆያ ውስጥ ህክምና መስጠት ወሳኝ ናቸው’’ ብለዋል ማትሺዶ ሞዌቲ። ድርጅቱ አክሎም እንደ ደቡብ አፍሪካ፣ አልጄሪያና ካሜሩን ያሉ አገራት በቫይረሱ ክፉኛ ሊጠቁ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል። ይህ የዓለም ጤና ድርጅ የሰራው ጥናት በአህጉሪቱ አባል የሆኑ 47 አገራት ላይ የተሰራ ሲሆን ጂቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ ግብጽ፣ ሊቢያ፣ ቱኒዚያና ሞሮኮን አያካትትም። እስካሁንም በነዚሁ 47 አገራት ከ 35 ሺ በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ከ1200 በላይ ደግሞ ሕይወታቸውን አጥተዋል ብሏል ድርጅቱ። አሁን ባለው አካሄድ ከ3.5 ሚሊየን እስከ 5.5 ሚሊየን የሚደርሱ ሰዎች ሆስፒታል ሊገቡ እንደሚችሉ የተነበየው ድርጀቱ ከእነዚህ ውስጥ ከ82 ሺ እስከ 167 ሺ የሚሆኑት ከባድ የጤና እክል ያጋጥማቸዋል ብሏል። በተጨማሪም ከ52ሺ እስከ 107 ሺ የሚደርሱት ደግሞ የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ (ቬንትሌተር) ሊያስፈልጋቸው እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጀት አሳስቧል።
news-54708505
https://www.bbc.com/amharic/news-54708505
ኢትዮጵያ፡ የዩኒቨርሲቲዎች መከፈት እና የተማሪዎች ስጋት
በኮሮናቫይረስ ስርጭት ስጋት ለበርካታ ወራት ተቋርጦ የነበረው የዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማሩ ሂደት በቅርቡ ይጀመራል።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ከጥቅምት 23 እስከ 30/2013 ዓ.ም. ድረስ የመጀመሪያ ዙር የተማሪዎች ቅበለ እንዲጀምሩ መወሰኑ ይታወሳል። ይህን ተከትሎ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከዚህ ቀደም ተስተውሎ የነበረው የጸጥታ ስጋት ከግምት በማስገባት የተማሪዎች ደህንነት ሁኔታ ስጋት ውስጥ የከተታቸው በርካቶች ናቸው። ተማሪዎች ምን ይላሉ? የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ለሆነችው ቃልኪዳን አባይነህ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ መወሰኑ ደስታን ፈጥሮላታል። ላለፉት ስምንት ወራት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምከንያት ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅላ ስትኖር የተለየ ጥንቃቄ ባለማየቷ ጊዜዋ እንደባከነ ተሰምቷታል። እርሷ በምትማርበት ዩኒቨርስቲ ባለፉት ዓመታት ይህ ነው የሚባል የፀጥታ ችግር ተፈጥሮ ስላልነበረ የደህንነት ስጋት ባይገባትም፤ የሌሎች ዩኒቨርስቲዎች ሁኔታ ግን "አሁን ካለው የፖለቲካ ሁኔታ አንጻር ከዚህ በፊት ችግር ይፈጠርባቸው የነበሩ ዩኒቨርስቲዎች ላይ ስጋት አለኝ" ትላለች። ሊቀሠራዊቱ ይመር ደግሞ የአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ነው። ወደ ዩኒቨርሲቲ የመመለሱ ነገር ስጋት አሳድሮበታል። ስጋት የሆነበት ነገር ደግሞ ባለፉት ዓመታት በተማሪዎች መካከል ችግር የፈጠሩ ጉዳዮች ምላሽ ሳያገኙ ወደ ዩኒቨርሲቲ መመለሱ ነው። በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚከሰቱ ችግሮችን የሚቀሰቅሱና የሚዘውሩት በአገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ ተዋናይ በሆኑ አካላት መሆኑን የሚናገረው ሊቀሠራዊቱ፤ እነዚህ ባለድርሻ አካላት ቁጭ ብለው ሳይወያዩና ልዩነቶቻቸውን ሳይፈቱ ወደ ዩኒቨርስቲ መመለሱ ስጋት ሆኖበታል። የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲም በተመሳሳይ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ከማቅናታቸው በፊት የተማሪዎች ደህንነትን ለማረጋገጥ እና ግጭት እንዳይከሰት የሚመለከታቸው አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠይቋል። ፓርቲው የተቋረጠውን ትምህርት መልሶ ለማስጀመር በሚደረገው ዝግጅት የመማር ማስተማሩ ሥራ አመቺ የሆነ እና በአንጻራዊነትም ከግጭት ነጻ የሆነ ሁኔታን ለመፍጠር እንዲሰራ ጠይቋል። የኦፌኮ ፓርቲ ሊቀመንበር እና ለበርካታ ዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና መንግሥት ከዚህ ቀደም በዩኒቨርሲቲዎች የጸጥታ ችግር አደረሱ የተባሉ ሰዎች ላይ የተወሰዱ እርምጃዎች ምን እንደሆኑ ማሳወቅ አለበት ይላሉ። ፕሮፌሰር መረራ "አምና ከአማራ ክልል የመጡ ተማሪዎች ደምቢ ዶሎ ታግተዋል ተብሎ ሲወራ ነበር። እስከ አሁን ምንም የተባለ ነገር የለም። አሁንም ከዚያ ክልል የሚመጡ ተማሪዎች ወደዚያ መሄድ ይሰጋሉ። ከዚህም ወደዚያ ለመሄድ እንደዚያው" ይላሉ። እንደ ፕሮፌሰር መረራ ከሆነ ዘንድሮ መንግሥት በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የጸጥታ ችግር እንዳይከሰት ምን አይነት ዝግጅት እንዳደረገ ማሳወቅ አለበት። ፕሮፌሰር መረራ አክለውም ዘንድሮ ምርጫ ስለሚካሄድ የፖለቲካ ትኩሳቱን እንደሚባባስ ገልጸው መንግሥት ከአሁኑ ቢያስብበት መልካም ነው ብለዋል። መንግሥት በበኩሉ የዩኒቨርሲቲ ደህንነቶችን ለማረጋገጥ ከፌደራል ፖሊስ ጋር እንደሚሰራ አስታውቋል። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደቻሳ ጉርሙ በዩኒቨርስቲዎች አካባቢ የሚፈጠሩ የፀጥታ መደፍረሶች በተቋማቱ የፀጥታ ኃይል ብቻ የሚፈታ ባለመሆኑ ከፌደራል ፖሊስ ጋር እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል። በያዝነው ወር መጨረሻ ላይ ተማሪዎች ተቀብለው ሥራቸውን የሚጀምሩትን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ስልጠና መሰጠት እንደተጀመረም አቶ ደቻሳ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች እና የፖሊስ አባላትን ያካተተው ስልጠናው የመማር ማስተማር ሂደት ሊያውኩ ይችላሉ የተባሉ ስጋቶች ላይ ውይይት መደረጉን ተናግረዋል። ለበርካታ ወራት ተቋርጦ የነበረው ትምህርት ያለምንም መስተጓጎልና ችግር እንዲቀጥል ከወዲሁ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የገለፁት አቶ ደቻሳ፤ በጥበቃ እንዲጠናከሩና በቴክኖሎጂ እንዲታገዙ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። በዩኒቨርሲቲ ጊቢዎች ውስጥ የጥበቃ ስራውንም ለማጠናከር የደህንነት ካሜራ ለመጠቀምም ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ደቻሳ የፌደራል ፖሊስ ለዩኒቨርሲቲዎች ጥበቃ ሳይሆን የሚያደርገው የዩኒቨርስቲዎችን ጥበቃ ያጠናክራል ብለዋል። ዩኒቨርስቲዎች በቁጥር ብዙ መሆናቸው እና አንድ ዩኒቨርስቲም በርከት ያሉ ካምፓሶች እንደሚኖሩት አስታውሰው የፌደራል ፖሊስ የእነዚህን ዩኒቨርስቲዎች ጥበቃ ሁኔታ እንደሚያጠናክር ይናገራሉ። "አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እገዛ ያደርጋሉ አላስፈላጊ ሲሆን ወደ መደበኛ ስራቸው ይመለሳሉ" ሲሉም የፌደራል ፖሊስ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፀጥታ ሁኔታ ውስጥ የሚኖረውን ተሳትፎ ተናግረዋል።
54637494
https://www.bbc.com/amharic/54637494
የአፍሪካ ህብረት በናይጄሪያ ተቃዋሚዎች ላይ የደረሰውን ጥቃት አወገዘ
የፖሊስ ጭካኔን በመቃወም የወጡ ናይጄሪያውያን ላይ የደረሰውን ጥቃት የአፍሪካ ህብረት በፅኑ አውግዞታል።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ በአገሪቱ ውሰጥ ላሉ የፖለቲካና ማህበራዊ ባለድርሻ አካላት "ሰብዓዊ መብት እንዲጠበቅና ሕግም እንዲከበር" የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ሰዎችን በማሰር፣ በማሰቃየትና ግድያም ይፈፅማል በሚል ከፍተኛ ውግዘት እየቀረበበት ያለውና ዘረፋን ለማስቆም የተመሰረተው ልዩ የፌደራል ፖሊስ ኃይል ወይም ሳርስ እንዲበተን ጠይቀዋል ። ከዚህም በተጨማሪ ወንጀል ፈፅመዋል ተብለዋል የሚባሉ የፖሊስ አባላትም ምርመራ እንዲከፈትባቸውና ወደ ፍርድ እንዲቀርቡም አሳሳስበዋል። ናይጄሪያ አባል የሆነችበትና አስራ አምስት አባላት ያሉት የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ) በበኩሉ ተቃዋሚዎችና የናይጄሪያ መንግሥት በውይይት ሊፈቱት ይገባል ብሏል። ኢኮዋስ ተቃውሞው በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት ሁለቱም አካላት ኃይል መጠቀም እንደማይገባቸው አሳውቋል። "ተቃዋሚዎቹ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ሰልፋቸውን እንዲያካሂዱና የናይጄሪያም የፀጥታ ኃይሎች ሰልፈኞቹ ላይ ኃይልን ከመጠቀም እንዲታቀቡ ጥሪያችንን እናቀርባለን" ይላል ኢኮዋስ ያወጣው መግለጫ በናይጄሪያ የፖሊስን የጭካኔ በትር ተማርረው የወጡ ተቃዋሚዎች ጎዳና ላይ መውጣታቸውን ተከትሎ በፀጥታ ኃይሎች የተገደሉ ሰዎችን አስመልክቶ የአፍሪካ ህብረትም ሆነ ኢኮዋስ ዝምታን መርጠዋል ተብለው ተተችተዋል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት አምነስቲ ማክሰኞ እለት፣ ጥቅምት 10/ 2013 በንግድ ማዕከሏ ሌጎስ በፀጥታ ኃይሎች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 12 መድረሱን አሳውቋል። የናይጄሪያ ጦር በበኩሉ ሪፖርቱ ሃሰተኛ ዜና ነው በማለት አጣጥሎታል። ከፍተኛ ተቃውሞ የቀረበበት ሳርስ እንዲበተን ቢደረግም የሳርስ አባላት በሌሎች የፖሊስ ክፍሎች እየተሰማሩና እየተመደቡ ነው የሚሉ ጉዳዮች መሰማታቸውን ተከትሎም እንደገና ተቃውሞቹ የቀጠሉት። ሰልፈኞቹ እነዚህ የሳርስ አባላት ለፈፀሙት ወንጀል ህግ ፊት መቅረብ አለባቸውም እያሉ ነው። ከሰሞኑ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት "ስር ነቀል" የፖሊስ ማሻሻያ እንደሚደረግና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈፅመዋል የተባሉትም የሳርስ አባላት ወደ ፍርድ ይቀርባሉ ብለው ነበር።
news-55825409
https://www.bbc.com/amharic/news-55825409
ጃዋር መሐመድ፡ በቢጫ ለባሾቹ ምክንያት የእነ ጃዋር ችሎት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠበት
ቢጫ ቀለም ልብስ በለበሱ ግለሰቦች ምክንያት የእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የዛሬ ችሎት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠበት።
ጀዋር መሐመድ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የፀረ ሽብርና ሕገመንግሥታዊ አንደኛ ችሎት ዛሬ ማለዳ የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሊቀበል ቀጠሮ ይዞ ነበር። ይህን ተከትሎ አቶ ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባን ጨምሮ በዚህ የክስ መዝገብ የተከሰሱ ተከሳሾች ፍርድ ቤትየቀረቡ ቢሆንም ችሎቱ ግን ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት አሰናብቷቸዋል። ይሀህ ሊሆን ቻለው የፍርድ ሂደቱን ለመከታተል ቢጫ ልብስ ለብሰው በፍርድ ቤት የተገኙ ሰዎች ወደ ፍርድ ቤቱ እንዳይገቡ በፖሊስ መከልከላቸውን ተከትሎ ተከሳሾች እና ጠበቆች ባሰሙት አቤቱታ ነው። ከተከሳሾች መካከል አቶ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ እና ሐምዛ አዳነ ሰዎች ቢጫ ቀለም ያለው ልብስ በመልበሳቸው ወደ ፍርድ ቤት እንዳይገቡ መደረጉ አግባብ አይደለም፤ ቢጫ ልብስ በመልበሳቸው ብቻ ለእስር የተዳረጉ አሉ ሲሉ ቅሬታቸውን ለፍርድ ቤት አቅርበዋል። ባለ ቢጫ ቀለም ልብስ የመልበስ ዘመቻ ከሰሞኑ በማሕበራዊ ሚዲያዎች ላይ በርካቶች ቢጫ ልብስ የመልበስ ዘመቻ ሲያከናውኑ ቆይተዋል። ይህም ተከሳሾች በማረሚያ ቤት እና ፍርድ ቤት ሲቀርቡ የሚለብሱትን ባለ ቢጫ ቀለም ቱታ ለመወከል ነው። ተከሳሾች ፍርድ ቤት ሲቀርቡ፤ ለተከሳሾች የሞራል ድጋፍ ለመስጠት ቢጫ ቀለም ያላቸውን ልብሶች በመልበስ በፍርድ ቤት እንደሚገኙ የዘመቻው አካል የሆኑት ይናገራሉ። ባለፉት ሁለት ቀጠሮዎች በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የክስ መዝገብ ሥራ የተከሰሱ ተከሳሾች ፍርድ ቤት በቀረቡብት ወቅት ቢጫ ቀለም ያለው ልብስ ለብሳ ከፍርድ ቤት የተገኘችው መሠረት ዳባ፤ ይህ ዘመቻችንን ለተከሳሾች የሞራል ብርታትን ለመስጠት ነው ትላለች። "እነሱ ከሚለብሱት የልብስ ቀለም ጋር ተመሳሳይ ልብስ በመልበስ 'እኛም ከእናንተ ጋር ነን'፣ 'ከእናንተ ጋር ታስረናል' የሚል መልዕክት ማስተላለፍ ፈልገን ነው" ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች። ባለ ቢጫ ቀለም ልብስ የመልበስ ዘመቻ አስተባባሪ የሆነው ወቢ ቡርቃሳ የጀመሩት ዘመቻ በርካቶችን በማሳተፍ ከታሰበው በላይ ብዙ ሰዎች ጋር መድረሱን ይናገራል። በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ #oromoyellowmovement የሚል መሪ ቃል ሲጠቀሙ ቆይተዋል። በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ላይ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ የቤተሰብ አባላቶቻቸው እና ሌሎች ሰዎች በለበሱት የልብስ ቀለም ሳቢያ ወደ ፍርድ ቤት እንዳይገቡ መደረጋቸውን እና ለእስር መዳረጋቸውን በመጥቀስ፤ በዚህ ምክንያት ሰዎች ወደ ፍርድ ቤት እንዳይገቡ ተደርጎ ባሉበት ሁኔታ ምንም ዓይነት አስተያየት መስጠት እንደማይችሉ ተናግረዋል። አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ሐመዛ አዳነ ሰዎች ወደ ፍርድ ቤት እንዳይገቡ መከልከላቸው እንዳሳዘናቸው እና ቢጫ በመልበሳቸው የታሰሩት ይፈቱ ሲሉ ጠይቀዋል። የተከሳሾች ጠበቆችም ችሎቱ ለሕዝብ ክፍት ሆኖ ሳለ ሰዎች በለበሱት የልብስ ቀለም ሳቢያ ወደ ችሎት እንዳይገቡ መከልከላቸው አግባብ አይደለም በማለት የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጥ ፍርድ ቤቱን ጠይዋል። ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ ሌላ ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠት የፍርድ ሂደቱን ያጓትታል ሲል ተከራክሯል። የግራ ቀኙን ክርክር ያደመጠው ፍርድ ቤቱ የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ለመስማት ለጥር 27፣ 2013 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱ ሰዎች በለበሱት የልብስ ቀለም ፍርድ ቤት እንዳይገቡ መደረጉ አግባብ አይደለም ያለ ሲሆን፤ ታዳሚዎች በሙሉ ግን ቢጫ ቀለም ያለው ልብስ ለብሰው በፍርድ ቤት የሚገኙ ከሆነ በችሎቱ ላይ ጫና ሊፈጥር እንደሚችል ከግምት ማስገባት አለበት ብሏል። በሰኔ ወር፣ 2012 ዓ.ም ከሙዚቀኛው ሃጫሉ ግድያ በኋላ በቁጥጥር ሥር የዋሉት አቶ ጃዋር መሐመድና በክስ መዝገባቸው ውስጥ የሚገኙ ሌሎች 24 ሰዎች ተደራራቢ አስር ክሶች እንደተመሰረተባቸው ይታወሳል። በእነ አቶ ጃዋር መሃመድ ከቀረቡ ተደራራቢ አስር ክሶች ስድስቱ እንዲቋረጡ ፍርድ ቤት ጥር 14/2013 ዓ.ም ውሳኔ አስተላልፏል። አቶ ደጀኔ ጉተማ፣ ዶ/ር ብርሃነ መስቀል አበበና ፀጋዬ ረጋሳ አገር ውስጥ የሌሉና በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ መዝገብ ውስጥ ከተከሰሱት መካከል ናቸው። የድምጻዊ ሃጫሉ ግድያን ተከትሎ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ተከስቶ ከነበረ ሁከት ጋር ተያይዞ ነበር እነ አቶ ጃዋር መሐመድ በቁጥጥር ሥር የዋሉት።
50794973
https://www.bbc.com/amharic/50794973
ምዕራብ አውስትራሊያ የፍቃድ ሞትን ሕጋዊ አደረገች
ምዕራብ አውስትራሊያ በህክምና ባለሙያዎች የታገዘ የፍቃድ ሞትን ሕጋዊ በማድረግ ሁለተኛዋ የአውስትራሊያ ግዛት ሆናለች።
የሕዝብ እንደራሴዎች ሕጉን ሲያጸድቁ በርካቶች ሀሴታቸውን ገልጸዋል። ሕጉ ሲጸድቅ በደስታ የተቃቀፉ የሕዝብ ተወካዮችም ነበሩ። • ኒውዚላንድ የፈቃድ ሞት ላይ ሕዝበ ውሳኔ ልታደርግ ነው • ሙሽሪት በሰርጓ ቀን ዋዜማ ጉድጓድ ውስጥ ገብታ ሞተች • የተባበሩት መንግሥታት የቺሊ ፖሊሶች ሰብዓዊ መብት ጥሰዋል አለ በአውስትራሊያ ቪክቶሪያ በተባለችው ግዛት ከሁለት ዓመት በፊት የፍቃድ ሞት ሕጋዊ ሲደረግ፤ በግንባር ቀደምነት ለመሞት የወሰኑት ጽኑ የካንሰር ህመም ያለባቸው ሴቶች ነበሩ። አወዛጋቢው ሕግ በፐርት ግዛት ከመጽደቁ በፊት ለሳምንታት የጦፈ ክርክር ተደርጎበታል። የጤና ጥበቃ ሚንስትሩ ሮጀር ኩክ ዜናውን ሲሰሙ የደስታ እንባ ተናንቋቸው ነበር። አንዳንዶች አደገኛ ሲሉ የፈረጁት ይህ ሕግ 100 ቅድመ ሁኔታዎች አሉት። በፈቃዱ ለመሞት የወሰነ ሰው በሕጉ ከለላ ከማግኘቱ በፊት በጠና እንደታመመና ከስድስት ወር እስከ አንድ ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ሕይወቱ ሊያልፍ እንደሚችል ማስረጃ ማቅረብ አለበት። የሁለት ገለልተኛ ሀኪሞች ፊርማም ያስፈልጋል። የህክምና ተቋሞች ሕጉን ለማስተግበር እስኪዘጋጁ 18 ወር የተሰጣቸው ሲሆን፤ ከዛ በኋላ ሕጉ በተግባር ይውላል።
news-44693402
https://www.bbc.com/amharic/news-44693402
ሬሳ ማቀዝቀዣ ክፍል ውስጥ እየተነፈሰች የተገኘችው ሴት
ደቡብ አፍሪቃዊቷ ሴት ሞታለች ተብላ ከተገነዘችበት የሬሳ ማቀዝቀዣ ክፍል በሕይወት ተገኝታለች። አሁን ላይ የህክምና እርዳታ እየተደረገላት እንደሆነም ታውቋል።
በደቡብ አፍሪቃዋ ጉዋቴንግ ግዛት ነዋሪ የሆነችው ይህች ሴት በትራፊክ አደጋ ምክንያት ሞታለች ተብሎ በባለሙያዎች ከታወጀ በኋላ ነው ወደ ሬሳ ማቀዝቀዣ ክፍል የተወሰደችው። በአደጋው ወቅት እርዳታ ሲሰጥ የነበረ የአምቡላንስ ኩባንያ "እስትንፋሷ እንዳላለፈ የሚያሳይ ምንም ዓይነት ምልክት አልነበራትም" ሲል ቃሉን ሰጥቷል። ነገር ግን የሬሳ ክፍል ሠራተኛ የሆነ ሰው ትንፋሽ ወደማይደመጥበት ክፍል ሲገባ ያጋጠመው ሌላ ነው፤ ተአምረኛዋ ሴት ትንፋሽ ዘርታ። ስሟ እንዲጠቀስ ያልተፈለገው ይህች ሴት አሁን ላይ ጆሃንስበርግ በሚገኝ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላት እንደሆነ ታውቋል። የግለሰቧ ቤተሰቦች ሁኔታው እንዲጣራላቸው በጠየቁት መሠረት ምርመራ እየተከናወነ እንደሆነ ቢቢሲ ተገንዝቧል። "እኛ ስለዚህ ጉዳይ ከፖሊስ፣ የአደጋ ጊዜ ሠራተⶉችና የሬሳ ክፍል ሠራተኞች እውቅና ውጭ የምንለው ነገር የለንም። ምላሽ ግን እንፈልጋለን" ሲሉ የቤተሰቡ ተወካይ የሆኑ ሰው ለቢቢሲ ተናግረዋል። በክስተቱ የቤተሰቡ 'ቆሌ እንደተገፈፈ' ግን ተወካዩ አልሸሸጉም። የሕክምና ባለሙያዎቹ ግን ምንም ዓይነት ስህተት እንዳልፈፀሙ ነው እየተናገሩ ያሉት። ከሞት ክፍል በሕይወት የወጣችውን ግለሰብ ጨምሮ ሌሎች ሰዎች በተጎዱበት የትራፊክ አደጋ ሁለት ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል። ወርሃ መስከረም ላይ አንድ ስፔናዊ ግለሰብ ሕይወቱ ካለፈ በኋላ ሞቱን እንዲያጣሩ የተመደቡ ባለሙያዎች በሕይወት እንዳገኙት የሚዘነጋ አይደለም። በዚህች የጉድ ሃገር ደቡብ አፍሪቃ አንድ የ50 ዓመት ጎልማሳ ከሬሳ ማቀዝቀዣ ከፍል ውስጥ እየጮኸ መውጣቱም ይታወሳል።
news-41011746
https://www.bbc.com/amharic/news-41011746
ተመራማሪዎች፡ ትዳር "ጤናን ይጠብቃል"
ትዳር ለጤና እንደሚበጅ እና ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠንን የመሰለ ለከባድ የልብ ሕመም የሚያጋልጥ የጤና እክል በሚያጋጥም ወቅት ይህንን ተቋቁሞ የመዳን ዕድልን ከፍ እንደሚያደርግ ተመራማሪዎች ገልፀዋል።
የሚያፈቅሯቸው የትዳር አጋር ያላቸው ሰዎች ራሳቸውን በሚገባ እንዲንከባከቡ ሊያበረታቱዋቸው እንደሚችሉ ያስረዳሉ። ተመራማሪዎቹ ውጤቱ ላይ የደረሱት አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ በእንግሊዝ ነዋሪ የሆኑ አዋቂ ሰዎችን በማካተት በተሰራ ጥናት ላይ ተመርኩዘው ሲሆን የገለፁትም የልብ ጤና አጠባበቅ ማህበር ላይ በተደረገ ጉባኤ ነዉ ። በጥናቱ የተካተቱት ሰዎች ከፍተኛ የደም ግፊት፣ ኮሌስትሮል ወይንም የስኳር በሽታ ያለባቸው ናቸው። የጥናቱም ውጤት እንደሚያሳየው በሽታን በመቋቋም ረገድ ባለትዳሮቹ ከላጤዎቹ የበለጠ ወውጤትን አሳይተዋል። የትዳር በረከት? ጥናቱን ያከናወኑት ዶክተር ፖል ካርተርና የአስተን ሜዲካል ትምህርት ቤት አጋሮቻቸው ከዚህ ቀደምም ትዳር ከልብ ህመም ለማገገም ጋር ከፍተኛ አስተዋፅኡ እንዳለው አሳይተው ነበር። በብሪታንያ የልብ ጤና አጠባበቅ ማህበር ጉባኤ ላይ የቀረበው የቅርብ ጊዜው ምርምራቸውም ይህ ለምን እንዲህ ሊሆን እንደቻለ የሚጠቁም ነው። ትዳር ኮሌስትሮል እና ከፍተኛ የደም ግፊትን የመሳሰሉ አደገኛ የልብ ሕመም አጋላጭ ሁኔታዎች እንደ መከላከያ እንደሚሆን መላ ምት አላቸው። በተጨማሪ ጥናቱ የልብ ህመምን ጨምሮ በሁሉም መንስኤዎች ያጋጠሙ ሞቶችን አጢኗል። 14 ዓመት በፈጀው ጥናት መጠናቀቂያ ላይ በ50ዎቹ፣ በ60ዎቹ እና በ70ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ባለትዳሮች በህይወት የመቆየት ዕድላቸው ላጤ ከሆኑት በ16 በመቶ ከፍ ያለ ሆኖ ተገኝቷል። ይህ እውነታ ለስኳር በሽታ እና ለከፍተኛ የደም ግፊትም የሚሰራ ሲሆን ባለትዳሮችም በከፍተኛ ፍጥነት ማገገምን አሳይተዋል። ከትዳር ውጪ አብረው የሚኖሩ፣ የተለያዩ፣ የደተፋቱ ወይንም የትዳር አጋራቸውን በሞት ወዳጡ ሰዎች ሲመጣ ግን ቁልጭ ያለ ምስልን ማግኘት ጥናቱ አዳግቶታል። ከዚህ በተጨማሪም ጥናት አድራጊዎቹ ባለትዳሮቹ በደስተኛ ትዳር መገኘት ያለመገኘታቸውን ጉዳይ ከግምት ውስጥ አላስገቡም። የጥናቱ ማጠቃለያ ግን ማግባትን እንደ ግዴታ ሳይሆን በሕይወታችን ውስጥ አጋር መኖሩ በጤና ላይ ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው ነው። "ምክንያቶቹ ላይ የበለጠ ጥናት ቢያስፈልገውም ባለትዳርነት ከልብ በሽታ ህመምም ሆነ ለልብ ሕመም ሊያጋልጡ ከሚችሉ ጉዳዮች እንደሚጠብቅ ጥናቱ ያሳያል።" በማለት ዶክተር ካርተር የሚያስረዱ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም "ሁሉም ሰው ትዳር መመስረት አለበት እያልን ግን አይደለም፤ የትዳርን አዎንታዊ ፋይዳዎችን ኮርጀን በጓደኞች፣ በቤተሰብ አባላት እና በማህበራዊ የድጋፍ መረቦችም ልንተገብረው ያስፈልገናል።" የብሪታንያ የልብ ፋውንዴሽን ሃላፊው ዶክተር ማይክ ናፕተን በበኩላቸው "ከዚህ የምንወስደው መልዕክት ማህበራዊ ግንኙነቶቻችን ከፍተኛ የደም ግፊትን ከመሳሰሉ በሽታዎች ጋር ትስስር እንዳላቸውና ለጤናችንም ሆነ ለደህንነታችን ወሳኝ ጉዳዮች መሆናቸውን ነው" ብለዋል። የልብ ሕመም አጋላጮች ናቸዉ ተብለው በተመራማሪዎቹ ከተጠቀሱት መካከል ማጨስ፣ ከፍተኛ የደም ግፊት፣ ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠን፣ የስኳር በሽታ፣ ከመጠን ያለፈ ውፍረት፣ አካላዊ እንቅስቃሴ ያለማድረግ፣ በቤተሰብ ውስጥ ያለ የልብ ሕመም ታሪክ ይገኙበታል። "ባለትዳር ሆናችሁም አልሆናችሁ፣ ከልብ ሕመም አጋላጮች መካከል አንዱም ካለባችሁ፣ እነርሱን ለመቆጣጠር ወደምትወዷቸው ሰዎች ፊታችሁን ማዞርና ድጋፍ መሻት ትችላላችሁ" ሲሉም አክለዋል።
news-57248762
https://www.bbc.com/amharic/news-57248762
ኢሞጂዎች ተርጓሚ የማያስፈልጋቸው የዓለም ቋንቋ ይሆኑ ይሆን?
😊 ይህ ኢሞጂ ቢላክልዎት ምን ያስቅሃል/ሻል ሊሉ ይችላሉ። 😫 በዚህኛዋ ኢሞጂ እያንቀላፋሁ መሆኔን ላሳይ እችላለሁ።
ይሁን እንጂ እነዚህን ኢሞጂዎች በአጭር መልዕክትዎ መካከል ከመጠቀም አልፈው ዘለግ ያለ አረፍተ ነገር መመስረት ይችላሉ? እኤአ በ2018 ላይ የብሪታኒያ ግንባር ቀደም የቴኒስ ተጫዋቹ አንዲ ሞሬ በሠርጉ ዕለት የተሰማውን ስሜት አንድም ቃል ሳይጠቀም በኢሞጂ ብቻ መልዕክቱን ትዊትር ሰሌዳው ላይ በማስፍር ዓለምን አስደንቆ ነበር። ከሠርግ ዝግጅት ወደ ቤተ ክርስቲያን የተደረገው ጉዞ፣ የቀለበት ሥነ ሥርዓቱ፣ የፎቶ ፕሮግራሙ፣ ደግሱ፣ ፍቅር እና እንቅልፍ የተካተቱበት የሞሬ መልዕክት በኢሞጂ የታዩበት ነው። ይህም አዲስ የዓለማችን መግባቢያ ቋንቋ እየተወለደ መሆኑን ያሳየ ነበር። የምትስቀዋን ኢሞጂ የፈጠሩት እነ ቪቪያን ኢቫንስ ኢሞጂ ዓለም ሊግባበት የሚችል ቋንቋ ነው ይላሉ። ኬቲ ብሮኒ የገበያ ጥናት የሥነልቦና ባለሙያ ናት። በአውሮፓውያኑ በ2017 ለአንድ የትርጉም ድርጅት ኢሞጂዎችን ለመተርጎም ተቀጠረች። ኢሞጂዎች ዓለም ሊግባባቸው የሚችል ቋንቋ ከሆኑ ለምን አስተርጓሚ አስፈለገ? ብሮኒ አንደምትለው አሁን ወረት ሆኖብን በኢሞጂ እንጠቀም እንጂ የዓለም ቋንቋ መሆን አይችሉም። እንደውም እንደማሟያነት ነው ሊጠቅሙን የሚችሉት ስትል ታስረዳለች። ኢሞጂዎች አጭር መልዕክት ስንልክ፣ በአካል ስናወራ የፊታችን ገጽታ ሊቀየር እንደሚችለው ሁሉ ስሜታችንን ለመግለጽ ይጠቅሙናል። አንዳንዴ በአጫጭር መልዕክቶቻችን ውስጥ ኢሞጂዎችን ካልቀላቀልን የጻፈው ሰው ጥሩ ባልሆነ ስሜት ወይንም ደግሞ በትዕዛዝ መልክ የተናገረን ሊመስለን ይችላል። ይሁን እንጂ ይህንን ለማስቀረት የምንጠቀማቸው ኢሞጂዎች አሉታዊ ጎን ሊኖራቸው ይችላል። ሁላችንም ስልካችን ውስጥ ተመሳሳይ ኢሞጂዎች ቢኖሩንም ስንጠቀም ልንል የምንፈልገው ጉዳይ ግን በባህል፣ በቋንቋ በእድሜ እና በመሳሰሉት ጉዳዩች የተለያየ ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ የአውራ ጣት ምልክትን ማሳየት በምዕራባውያን ባህል አንድ ንግግር ትክክል ወይንም አግባብ መሆኑን ሊያሳይ ይችላል። ነገር ግን በግሪክና በመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ይህ ምልክት ስድብ ነው። የመላዕክ ኢሞጂን ማሳየት አሁንም ለምዕራብውያኑ የዋህነትን ሲያሳይ፣ ቻይና ውስጥ ግን የሞት ፍርሃት ምልክት ሆኖ ነው የሚያገለግለው። የማጨብጨብ ምልክት የደስታን፣ ማበረታታትን እና ጎሽ የማለት መልዕከትን የሚያስተላልፍ መሆኑን በርካቶቻችን ብንቀበለውም ለቻይናውያን ግን ወሲብ የመፈፀም ምልክት ነው። በ2017 በተደረገ ጥናት በረመዳን ወቅት ሙስሊሞች ስሜታቸውን ለመግለጽ ምን ዓይነት ኢሞጂ ይጠቀማሉ የሚለውን በማየት ፕሪስሞጂ ኢሞጂ የዓለም ቋንቋ መሆኑን አመላካች ለማግኘት ሞክሯል። ትዊተር ላይ ከተጻፉ አጫጭር መልዕክቶች ሙስሊሞች በረመዳን ወቅት እንግሊዘኛ፣ ጀርመንኛ፣ ስፓኒሽና የቱርክ ቋንቋ የሚናገሩ ሙስሊሞች ቀይ የልብ ቅርጽ ያለው ኢሞጂ ሲጠቀሙ፤ አረብኛ፣ ኡርዱ እና ፋርስ ቋንቋዎችን የሚናገሩ ደግሞ የግማሽ ጨረቃን ምልክት ሲጠቀሙ ተስተውለዋል። 'አመሰግናለሁ' ለማለት የምንጠቀመው የእጅ ምልክት ደግሞ ከእነዚህ ኢሞጂዎች በይበልጥ ጥቅም ላይ ውሎ ነበር። ይሁን እንጂ አረብኛ የሚናገሩ ሰዎች በዘጠነኛ ደረጃ ላይ ነው የተጠቀሙት። በኡርዱ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ደግሞ ጨርሶውኑ አልተጠቀሙትም። በሙስሊም ባህል ውስጥ እጅን በዚህ መልኩ ለምስጋና ማጋጠም ፀሎትን ለማሳየት ላይጠቅም ይችላል። በምዕራባውያን ዘንድ ግን ትልቅ የሆነ ሐይማኖታዊ ጠቀሜታ አለው። ጃፓን ውስጥ ግን ከሐይማኖት ጋር ሳይሆን፣ 'አመሰግናለሁ' 'እባክዎን' የሚለውን ቃል ይተካል። ስለኢሞጂ ማስተማር አያስፈልገውም ኢሞጂ ስሜትን የምንገልጽበት ቋንቋ ስለሆነ ለመልመድ በጣም ቀላል ነው። ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ከ45 ዓመት ሰው ይልቅ የስድስት ዓመት ልጅ ይህንን የቴክኖሎጂ ቋንቋ መጠቀም ይችላል። ለወደፊት ሰዎች ቋንቋን ትተው በኢሞጂ መነጋገር ይችሉ ይሆን? እነደ ፕሮፌሰር ቪቪያንስ ኢቫንስ ከሆነ ኢሞጂ መጥቶ የሚሄድ ፋሽኑ የሚያልፍበት ሳይሆን የዲጂታል ተግባቦትን ሙሉ ያደረገ ቋንቋ ነው። በተግባቦታችን መካከል ኢሞጂዎችን መጠቀም ግንኙነታችንን መልካም ያደርገዋል። በአሁኑ ጊዜ የአሜሪካ የቴክኖሎጂ መንደር ሲሊከን ቫሊ እኛን የሚመስል የሮቦት ኢሞጂ እየሰራ ነው። ይህ ኢሞጂ ወደ ሌሎቹ ሲላክ ስሜታችንን በእንቅስቃሴ ጭምር ለሌሎች ያሳያል። አሁንም ታድያ የባህል ልዩነቱ እንዳለ ሆኖ ኢሞጂዎች የዓለምን ሕዝብ ከማራራቅ ይልቅ የማቀራረብ አገልግሎትን ይሰጣሉ ብላ ታምናለች ብሮኒ። ስለ ኢሞጂዎች በጥቂቱ ማወቅ ይፈልጋሉ? የትኞቹ አገራት የትኛውን ኢሞጂ አዘውትረው ይጠቀማሉ? የዓለማችን የመጀመሪያው የፈገግታ ምልክት 35 ዓመት ሆነው። ከዚህ ፈጠራ በስተጀርባ ያለውን የኮምፕዩተር ሳይንቲስት ስኮት ፋልማንን ይተዋወቁ።
news-53573123
https://www.bbc.com/amharic/news-53573123
ሕዝብ፡ የዓለም የሕዝብ ቁጥር ቢቀንስ ምን ሊፈጠር ይችላል?
የወሊድ መጠን እየቀነሰ ይሄዳል ማለት በምዕተ ዓመቱ መጨረሻ ላይ የበርካታ አገሮች የሕዝብ ቁጥር ያንሳል ማለት ነው።
ጥቂት ሕዝብ እንዲሁም አረጋውያን የሚበዙባቸው አገሮች መፈጠራቸውም አይቀርም። ተከታዮቹ ስድስት ነጥቦች ከዓለም ሕዝብ ቁጥር መቀነስ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ናቸው። 1. ለድሃ አገራት መልካም ዜና ነው የወሊድ ቁጥር እና የምጣኔ ሀብት እድገት ጎን ለጎን ይሄዳሉ። ሴቶች በአማካይ ጥቂት ልጆች ብቻ የሚወልዱት፤ በተሻለ ሁኔታ ትምህርትና ሥራ ሲያገኙ፣ የእርግዝና መቆጣጠሪያ ተደራሽ ሲሆን፣ ማስወረድን የሚከለክል ሕግ ሲላላ እንዲሁም የጨቅላዎች ሞት ሲቀንስ ነው። አነስተኛ ገቢ ባላቸው አገሮች የወሊድ መጠን ሲቀንስ፤ በርካቶች የተሻለ ሕይወት የማግኘት እድላቸው ይሰፋል። ጥቂት ልጆች ብቻ ሲወለዱ፤ እያንዳንዳቸው የተሻለ ትምህርትና የጤና አገልግሎትም ያገኛሉ። ባለፉት ዓመታት የወሊድ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰባቸው አገሮች ግን እምብዛም አይጠቀሙም። በእነዚህ አገሮች አረጋውያን የሚንከባከባቸው ያጣሉ። የምርታማ ወጣቶች ቁጥርም ይቀንሳል። 2. ብዙዎች ጡረታ መውጣትን በጉጉት መጠበቅ ይጀምራሉ ብዙዎች ጡረታ መውጣትን በጉጉት የሚጠባበቁበት ዓለም ይፈጠራል። በሥራ ላይ የሚያሳልፏቸው ዓመታት ቁጥርም ይጨምራል። የአረጋውያን ቁጥር ሲጨምር የጤና ሥርዓት ችግር ውስጥ ይገባል የሚል ፍርሀት ቢኖርም፤ ሁሉም አዛውንቶች ስለማይታመሙ ያን ያህል አስጊ ላይሆን ይችላል። ዓለም ላይ የሰዎች እድሜ ከመጨመሩ ጎን ለጎን ጤናማ ሆነው የሚያረጁ ሰዎች ቁጥርም ከፍ እያለ መጥቷል። በኦክስፎርድ ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ሣራ ሀርፐር እንደሚሉት፤ የአረጋውያን ቁጥር ይጨምራል የሚለው ስጋት አንዳንድ እውነታዎችን ከግምት ማስገባት አለበት። “ከአስር ዓመታት ወዲህ የአረጋውያን የጤና ሁኔታ እየተሻሻለ መጥቷል። ስለዚህም አረጋውያን ጤናማ ሆነው መንቀሳቀስ ይችላሉ” ይላሉ። በአሁን ወቅት የሚወለዱ ልጆች ከ20 ዓመታት በፊት ከተወለዱት ጋር ሲነጻጸሩ፤ ለአምስት ተጨማሪ ዓመታት ጥሩ ሕክምና ያገኛሉ። በእርግጥ ይህ በሶርያ የሚወለዱ ሕፃናትን አይጨምርም። ሁለተኛው ምዕተ ዓመት ከተጀመረ ወዲህ በሩዋንዳ የሚወለዱ ልጆች 22 ተጨማሪ ዓመታት መኖር ጀምረዋል። በገቢ ባደጉት እንደ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ጀርመን እና አሜሪካ ያሉት አገራት፤ የዜጎች ዕድሜ ከአንድ እስከ ሦስት ዓመት ጨምሯል። 3. መንግሥታትድንበራቸውንመክፈትይጠበቅባቸዋል ሦስተኛው ነጥብ የስደተኞች ጉዳይ ነው። የወሊድ መጠን በመቀነሱ ሳቢያ አነስተኛ ወጣት ያላቸው አገራት፤ የሌሎች አገሮች ወጣት ተወላጆችን ወደ ግዛታቸው ለማስገባት መሞከር አለባቸው። ይህም ዓለም ላይ ያሉ ዘሮች እንዲሁም ባህላቸውም እንዲዋሀድ መንገድ ይፈጥራል። 4. ቤተሰብን የመንከባከብ ጉዳይ በስካንድኔቪያን አገሮች መንግሥት ልጅ መውለድን ያበረታታል። ለወላድ እናቶች የሚሰጠው ጊዜና ለልጅ እንክብካቤ የሚደረገው ድጋፍ ሴቶች ከተጠበቀው በላይ እንዲወልዱ አበረታቷል። ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ የሚሠሩት ዶ/ር ሃና ሪቺ እንደሚሉት፤ የሀብታም አገራት መንግሥታት ማበረታቻ የወሊድ ቁጥርን ይጨምራል። በድሃ አገራት ሴቶች ከሚፈልጉት በላይ ልጆች ሊወልዱ ይችላሉ። በሌላ በኩል ኑሮ ውድ በሆነባቸው አገሮች ልጆችን ማሳደግ ከባድ ስለሆነ ጥንዶች ብዙ አይወልዱም። ይህን ተከትሎ መንግሥታት ሰዎች ጡረታ የሚወጡበትን እድሜ ሊያራዝሙ ይችላሉ። ፕሮፌሰር ሣራ እንደሚሉት፤ ቤተሰብን ለመንከባከብ ሰፊ ጊዜ ተሰጥቶ፤ የሥራ ዘመን ግን እንዲጨመር በመንግሥታት ሊወሰንም ይችላል። 5. አሳሳቢው የሥራ ጉዳይ በለንደን የምጣኔ ሀብት ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ቲዚና ሊዎን እንደሚሉት፤ አረጋውያን ምንም ያህል ጠንካራ ቢሆኑም ወደ እድሜ ዘመናቸው መገባደጃ አካባቢ አጋዥ ያስፈልጋቸዋል። የአረጋውያን ቁጥር ከፍተኛ በሆነባቸው አገሮች የጤና እንዲሁም የማኅበረሰባዊ መዋቅር ቀውስ ሊገጥም እንደሚችልም ባለሙያው ያሳስባሉ። ስለዚህም ከአሁኑ ሠራተኞችን በዘርፉ ማሰልጠን መጀመር እንዳለበት ዶ/ር ቲዚና ያስረዳሉ። “ለወደፊቱ የሕፃናት ወይም የማህጸን ሀኪሞች ብዙም ላያስፈልጉን ይችላሉ” ይላሉ። 6. ተፈጥሮልታገግምትችላለች የሕዝብ ቁጥር ሲቀንስ ተፈጥሮ እንደምታገግም ፕ/ር ሣራ ያስረዳሉ። ዶ/ር ሃና በበኩላቸው ከሕዝብ ቁጥር ይልቅ የምጣኔ ሀብት እድገት ተፈጥሮ ላይ ጫና እንደሚያሳድር ያምናሉ። አገራት በምጣኔ ሀብት በልጽገው ተፈጥሮን የሚበዘብዙ ከሆነ የሕዝብ ቁጥር መቀነሱ ለውጥ አያመጣም። ባለፉት አስርታት የምጣኔ ሀብት እድገት እና የአካባቢ ብክለት ቀጥተኛ ግንኙነት ነበራቸው። አሁን ግን ሀብታም አገሮች የካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀታቸውን ቀንሰው ቴክኖሎጂ ላይ ገንዘባቸውን እያፈሰሱ ነው።
news-54962886
https://www.bbc.com/amharic/news-54962886
ኮሮናቫይረስ ፡ 95 በመቶ አስተማማኝ ነው የተባለ አዲስ የኮቪድ-19 ክትባት ተገኘ
ሞዴርና የተባለ ድርጅት ከኮሮናቫይረስ 95 በመቶ የሚከላከል አዲስ ክትባት ማግኘቱን ይፋ አደረገ።
የዩናይትድ ስቴትስ መድኃኒት አምራች ኩባንያ የሆነው 'ሞዴርና' ያሰራጨው መረጃ ፋይዘር የተባለው ድርጅት ተመሳሳይ ይዘት ያለው መረጃ ካወጣ ከቀናት በኋላ ነው። ሁለቱም ድርጅቶች የረቀቁ መንገዶችን ተጠቅመው ነው ክትባቶችን ያገኙት። ሞዴርና የምርምር ውጤቱን ያደረገበትን ዕለት 'ታላቅ ቀን' በማለት ሐሴቱን የገለፀ ሲሆን፤ በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ክትባቱን ለመጠቀም ፈቃድ እንደሚያገኝ አስታውቋል። ነገር ግን ድርጅቱ ያወጣው የመጀመሪያ ዙር ውጤት ስለሆነ ያልተመለሱ ጥያቄዎች እንዳሉ እየተነገረ ነው። የክትባቱ ሙከራ አሜሪካ ውስጥ ያሉ 30 ሺህ ሰዎችን ያሳተፈ ሲሆን ግማሾቹ በየአራት ሳምንቱ ክትባቱ ሲሰጣቸው ግማሾቹ ደግሞ ጥቅምና ጉዳት የሌለው መርፌ ተወግተዋል ውጤቱን ለመለየት ተሞክሯል። ከዚህ ሙከራ በተገኘ ውጤት መሠረት 94.5 በመቶ ሰዎች በክትባቱ ምክንያት ለኮሮናቫይረስ ሳይጋለጡ ቀርተዋል ተብሏል። ስለክትባቱ ውጤቱ የቀረበው ዘገባ ጨምሮም፤ ሙከራ ከተደረገባቸው መካከል 11 በኮቪድ-19 ክፉኛ የታመሙ ሰዎች የመከላከል አቅም አዳብረዋል ይላል። የሞዴርና ዋና የሕክምና ኃላፊ ታል ዛክስ "በጠቅላላው የክትባቱ ውጤታማነት ድንቅ ነው. . . ታላቅ ቀን" ነው ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። እስካሁን የማናውቀው የክትባቱ ዘላቂነት ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ እስካሁን አልታወቀም። ይህን ለማወቅ ተሳታፊዎች ላይ የሚደረገው ክትትል ይቀጥላል። ክትባቱ በዕድሜ ለገፉ ሰዎች የተሻለ መከላከል እንደሚሰጥ ቢጠቆምም ሙሉ መረጃ ግን ያሻል ተብሏል። ዛክስ ለቢቢሲ እንደተናገሩት "እስካሁን ባለው መረጃ ክትባቱ በጊዜ ብዛት አቅሙን አያጣም።" ሌላው የማይታወቀው ነገር ክትባቱ ሰዎች በጣም እንዳይታመሙ ከማድረግ ያግዳል ወይ የሚለውና ወደ ሌሎች ሰዎች እንዳያስተላልፉስ ያደርጋል የሚለው ነው። ደኅንነቱስ? ክትባቱ እስካሁን በደኅንነት ጉዳይ ይህ ነው የሚባል ነገር አልተነሳበትም። ነገር ግን የትኛውም መድኃኒት 100 በመቶ እንከን አልባ ሊሆን አይችልም። አንዳንድ ተሳታፊዎች ክትባቱ የወሰዱ ሰሞን መጠነኛ ድካም፣ ራስ ምታትና ሕመም እንደተሰማቸው አስታውቀዋል። የሞዴርና እና የፋይዘር ክትባት ከ90 በመቶ በላይ ውጤታማ መሆናቸው ተነግሯል። ነገር ግን የሁለቱም ድርጅቶች ውጤት የመጨረሻ ደረጃ ላይ አልደረሰም። ውጤታማነቱም ሊቀየር ይችላል ተብሏል። ቢሆንም የሞዴርና ክትባት ማቀዝቀዣ ውስጥ ለማስቀመጥ ከሌሎቹ ክትባቶች በተለየ ቀላል እንደሆነ ተነግሯል። የሞዴርና ክትባት ማቀዝቀዣ ውስጥ እስከ አንድ ወር መቆየት ሲችል የፋይዘር ግን ለአምስት ቀናት ብቻ ነው የሚቆየው። ሩስያ የለቀቀችው ስፑትኒክ 5 የተሰኘው ክትባትም 92 በመቶ የመከላከል አቅም እንደላው ተነግሯል። መቼ ልናገኘው እንችላለን? ይህ የሚወሰነው ባለንበት ቦታና በዕድሜያችን ነው ተብሏል። ሞዴርና ክትባቱን ለአሜሪካ የመድኃኒት ቁጥጥር ኃላፊዎች በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት እንደሚያቀርብ አስታውቋል። 20 ሚሊዮን ክትባቶች ለአሜሪካውያን ዝግጁ እንደሚያደርግም ድርጅቱ አስታውቋል። ድርጅቱ በሌሎች አገራትም ፈቃድ ለማግኘት እየሞከረ እንዳለና በሚቀጥለው ዓመት 1 ቢሊዮን ክትባቶች አምርቶ ለማዘጋጀት ማቀዱን አስታውቋል።
news-45318975
https://www.bbc.com/amharic/news-45318975
የብአዴን መግለጫ፡- ከስያሜ መቀየር እስከ ኢትዮ ሱዳን ድንበር
የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) በ12ኛ መደበኛ ድርጅታዊ ጉባኤው የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የአማራ ክልል ርዕሰ-መስተዳደር እና የብአዴን መክትል ሊቀመንበር ነሃሴ 17 እና 18 /2010 የተደረገውን ስብሰባ ተከትሎ ድርጅቱ በኦፊሳላዊ ገፁ በክልሉ ያለውን ወቅታዊ መንፈስ «ወሳኝና ታሪካዊ » ሲል የገለፀው ሲሆን ይሄን ታሳቢ ያደረጉ ባለ 12 ነጥብ ውሳኔዎችን ማስተላለፉን አትቷል። • ትራምፕ በማኬይን ቀብር ላይ አይገኙም • የመዋቢያ ምርቶች ውስጥ መርዛማ ንጥረ-ነገሮች ተገኙ • እነ አንዷለም አራጌ ህይወት እንደገና በውሳኔዎቹ ድርጅቱ ፣ • የስያሜ፣ የፖለቲካ ፕሮግራም እና መተዳደሪያ ደምብ ማሻሻያ እንደሚያደርግ ይፋ አድርጓል፤ • የጥረት ኮርፖሬት እና የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም (አብቁተ) የተባሉት የልማት ድርጅቶች ተጠሪነታቸው ለክልሉ መንግስት እንዲሆን ፖለቲካዊ ውሳኔ አስተላልፏል፤ • ቀደም ብሎ የተደረገውን በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል ያለውን የድንበር ማካለል በተመለከተ የተገባውን ስምምነት «መብታችንን ያላስጠበቀ፣ የሚመለከታቸውን አካላት ያላሳተፈና የጋራ አቋምም ያልተያዘበት ውሳኔ » ሲል ከተቸው በኋላ፤ ውሳኔው በፌዴራል መንግስት በኩል አስቸኳይ ማስተካከያ እንዲደረግበት ጠይቋል። በተጨማሪም የሱዳን ጦር ያለአግባብ ሰፍሮበታል ካለው በቋራ ወረዳ ከሚገኘው ነፍስ ገበያ ከተባለው ስፍራ ለቆ እንዲወጣ የፌዴራል መንግስትም ይሄንን እንዲያስፈፅም ጠይቋል። • ከእነዚህ ውሳኔዎች በተጨማሪ የግለሰብ እና የቡድን መብት ተጣጥመው እንዲጓዙ እንደሚተጋ፣ በስደት ቆይተው ከተመለሱ «ተፎካካሪ ፓርቲዎች» ጋር ተከባብሮ ለመስራት እና ዲሞክራሲን ለማስፋት ፅኑ ፍላጎት እንዳለው አስታውቋል። • «የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ መንግስት አባላት የሆኑ ክልሎች አከላለል በህዝቦች እውነተኛ ፍላጎትና ንቁ ተሳትፎ፣ ብዝሃነትንና ሃገራዊ አንድነትን በሚያጠናክር አግባብ ሕገ መንግስቱን መሰረት አድርጎ እንዲከለል እንታገላለን፡፡» በማለትም አክሏል። የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አቶ በረከት ስምኦንን እና አቶ ታደሰ ካሳን ከማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት ማገዱም ይታወሳል። የአቶ በረከት እና የአቶ ታደሰ እገዳ "በጥረት ኮርፖሬት ላይ ከሰሩት ጥፋት ጋር የተያያዘ ነው" ተብሏል። ስለዚህም እስከ ቀጣዩ የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ጉባኤ ድረስ ከኮሚቴው አባልነት ተግደው ይቆያሉ ተብሏል። • አቶ በረከት ስምኦን ከብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት ታገዱ
52483723
https://www.bbc.com/amharic/52483723
የልጄ ገዳይ ኮሮናቫይረስ እንዳይዘው ከእስር ልቀቁልኝ ያሉት አርጀንቲናዊ እናት
ሲልቪያ ኦንቲቫሮ የተባሉ አርጀንቲናዊት፤ የአስም ታማሚ የሆነው የልጃቸው ገዳይ በኮሮናቫይረስ እንዳይያዝ፣ ከእስር ቤት እንዲለቀቅ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለባለሥልጣኖች ጽፈዋል።
የሲሊቪያ ልጅ አሌሆ ሁናው ሲልቪያ ከሁለት ወር በፊት የልጃቸው ገዳይ ከእስር ቤት ለመለቀቅ ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ እንዲሆን አቤቱታ አሰምተው ነበር። ሆኖም ግን ወቅታዊው ሁኔታ ሀሳባቸውን እንዲቀይሩ አስገድዷቸዋል። “እጅግ ተበሳጭቼበታለሁ፤ በጥላቻ ተሞልቼም ነበር፤ ቢሆንም እንዲሞት አልፈልግም” ሲሉ በደብዳቤያቸው ተማጽነዋል። ባለፈው ማክሰኞ የአርጀንቲናው ፕሬዘዳንት አልቤርቶ ፈርናንዴዝ ታራሚዎች ከእስር ቤት ተለቀው በቤታቸው የቁም እስር እንዲገቡ የቀረበውን ሐሳብ ተቀብለዋል። የፕሬዘዳንቱ ውሳኔ ፍትህ ያዛባል የሚሉ ወገኖች፣ በተቃራኒው ታራሚዎች ይፈቱ የሚሉም አሉ። ታራሚዎች በተጨናነቁባቸው እንዲሁም ንጽህናቸው ባልተጠበቀ ማረሚያ ቤቶች ውስጥ ኮሮናቫይረስ በፍጥነት ሊሰራጭ ይችላል በሚል ስጋት፤ ባለፉት ሳምንታት በማረሚያ ቤቶች ተቃውሞ ሲካሄድ ነበር። “ታራሚዎች ምን ያህል እንደፈሩ መገመት እችላለሁ” የሲሊቪያ ልጅ አሌሆ ሁናው የተገደለው እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ2004፣ በሜንዶዝራ ግዛት ነበር። ገዳዩ ዲዬጎ አርዱኢኖ የ16 ዓመት እስራት ተፈርዶበታል። ባለፈው ማክሰኞ ማሪያና ጋርዲ የተባሉ ዳኛ፤ ዲዬጎ አስም ስላለበት ለበሽታው ሊጋለጡ ከሚችሉ 400 ታራሚዎች አንዱ ነው ብለው ነበር። ሲልቪያ በጻፊት ግልጽ ደብዳቤ፤ የቁም እስርን እንደሚደግፉ ተናግረዋል። “ወረርሽኝ ገጥሞናል፤ ማረሚያ ቤቶች ደግሞ የተጨናነቁ ናቸው፤ ታራሚዎች ምን ያህል እንደፈሩ መገመት እችላለሁ” ብለዋል። ቲኤን ለተባለ የቴሌቭዝን ጣቢያ፤ ዲዬጎን ከእስር አለመፍታት እንደ ሞት ፍርድ ይቆተራል ሲሉ ተናግረዋል። ይህንን እንደማይቀበሉም አክለዋል። ሲልቪያ ከ1976 እስከ 1983 በነበረው ወታደራዊ አገዛዝ ስር ለሰባት ዓመታት የፖለቲካ እስረኛ ነበሩ። ማረሚያ ቤት የማሰላሰያ ጊዜ እንደሰጣቸው የሚናገሩት እናት፤ ዲዬጎ ከዚህ ቀደም ሊፈታ ሲል የተቃወሙት በቂ ማሰቢያ ጊዜ ማግኘቱንና የተሻለ ስብእና ማዳበሩን እርግጠኛ ስላልሆኑ ነበር። ጋዜጠኛና የሜንዶዝና አስተዳደር አማካሪ የነበረው ልጃቸው ቤቱ ውስጥ በወይን ጠርሙስ ተመቶ ነበር ሕይወቱ ያለፈው። ተቃውሞ በማረሚያ ቤቶች በሊማ ከተማ ማረሚያ ቤት በተካሄደ ተቃውሞ ዘጠኝ ሰዎች ሞተዋል። በወቅቱ ሁለት ታራሚዎች በኮቪድ-19 ሳቢያ መሞታቸውን ተከትሎ ታራሚዎች ለማምለጥ ሞክረው እንደነበርበ እስር ቤቱ አስተዳዳሪዎች ተገልጿል። የቀድሞው የቺሊ ፕሬዘዳንትና የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ሚሼል ባቼሌት የላቲን አሜሪካ ማረሚያ ቤቶች ፅዱ መሆን እንዳለባቸው አሳስበዋል። ብዙም አደገኛ ያልሆኑ ታራሚዎች እንዲፈቱም ጥሪ አቅርበዋል። ቺሊ እና ኮሎምቢያ በሺዎች የሚቆተሩ ታራሚዎችን ፈተዋል። ባለፈው ሳምንት የሜክሲኮ ምክር ቤት ታራሚዎች እንዲፈቱ ውሳኔ አስተላልፏል። በተቃራኒው ኤል ሳልቫዶር የአመጽ ቡድን አባሎች ወረርሽኙን ሰበብ በማድረግ ከማረሚያ ቤት ለመውጣት እየሞከሩ ነው ብላለች። ባለፈው እሮብ አርጀንቲና ውስጥ ሰብአዊ መብት በመጣስ ታስሮ የነበረው የ 70 ዓመቱ ካርሎስ ካፕዲቪላ ተለቆ ወደ ቁም እስር መግባቱ ውዝግብ አስነስቷል። ደም ግፊትን ጨምሮ ሌሎችም ህመሞች ስላሉበት ለኮሮናቫይረስ እንዳይጋለጥ ተብሎ መፈታቱ ተገልጾ ነበር።
45060062
https://www.bbc.com/amharic/45060062
በድሬዳዋ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አልታወጀም ተባለ
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከጥቂት ቀናት በፊት ከተማዋን የጸጥታ ስጋትና የኮማንድ ፖስት መቋቋምን በማስመልከት መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ ጉዳዩ እያነጋገረ ይገኛል።
ከዚራ ኮማንድ ፖስት ከተቋቋመ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል ማለት ነው በሚል ግራ መጋባትም የተፈጠረ ይመስላል። ነገር ግን የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ አብደላ አህመድ ለቢቢሲ ዛሬ በስልክ እንደተናገሩት ባለፉት ቀናት በታዩ የግጭት ዝንባሌዎች የተነሳ ኮማንድ ፖስት ተቋቁሞ የከተማዋን ጸጥታና ደህንነት ለመጠበቅ እየተሞከረ እንደሆነና እንደወትሮው ሁሉ አስተዳደሩ ከመከላከያ ሰራዊት እና ከፌዴራል ፖሊስ በጸጥታ ካውንስል በኩል በቅንጅት እየሰራ እንደሆነ አብራርተዋል። "አዲስ ነገር አይደለም። በመደበኛነት አብረን ነው የምንሰራው" ሲሉም የጸጥታ ካውንስል አዲስ እንዳልሆነ ተናግረዋል። ባለፉት ሁለት ሶስት ቀናት አስጊ የነበሩ ነገሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የጠቀሱት ምክትል ከንቲባው "ምንም የከፋ ነገር የለም።" ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል። ስጋት ያሳደሩት ጉዳዮች በዝርዝር ምን እንደነበሩ ከቢቢሲ የተጠየቁት አቶ አብደላ ከመሬት ጋር ተያይዞ የተነሱ ጥያቄዎች ነበሩ ሲሉ በደምሳሳው አልፈውታል። የድሬዳዋ ቀለማት በሶማሊያና በኦሮሚያ የተከሰተው የድንበር ግጭት ወደ ድሬዳዋ እየተዛመተ እንደሆን የተጠየቁት ምክትል ከንቲባው "በዚያ ደረጃ የሚገለጽ ነገር የለም። ይሄ የውስጥ ችግር ነው፤ ኮሚቴ አቋቁመን እየፈታነው ነው።" ሲሉ ችግሩ ምንም የብሔር መልክ እንደሌለው አጭር አስተያየታቸውን ለቢቢሲ ሰጥተዋል።
52709940
https://www.bbc.com/amharic/52709940
ኮሮናቫይረስ፡ ትራምፕ ለዶ/ር ቴድሮስ የ30 ቀን ጊዜ ገደብ ሰጡ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጀነራል ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የ30 ቀን ማስጠንቀቂያ ሰጡ።
ፕሬዝዳንቱ ዶ/ር ቴዎድሮስን በሰላሳ ቀናት በድርጅታቸው ውስጥ "መሰረታዊ ለውጥ" እንዲያመጡ ያሳሰቡ ሲሆን አለበለዚያ ግን አሜሪካ ሙሉ በሙሉ ለድርጅቱ የምታደርገውን ድጋፍ ታቋርጣለች ሲሉ ለዶ/ር ቴድሮስ በጻፉት ደብዳቤ አስጠንቅዋል። ፕሬዝዳንቱ ለዶ/ር ቴዎድሮስ የጻፉትን ደብዳቤ በትዊተር ገፃቸው ላይ ያሰፈሩ ሲሆን የዓለም ጤና ድርጅት የሚጠበቅበትን በሚገባ ስላለመወጣቱ ሲናገሩ ቫይረሱ ከቻይናዋ ዉሃን በተነሳበት ወቅት "በተደጋጋሚ ስለ ቫይረሱ ስርጭት አስመልክቶ ይቀርቡ የነበሩ ተጨባጭ መረጃዎችን ችላ ብሏል" ሲሉ ወቅሰዋል። አክለውም የዓለም ጤና ድርጅት በተደጋጋሚ ቻይናን "ሲያንቆለጳጵስ" ነበር በማለት የዓለም ጤና ድርጅት "መሰረታዊ የሆነ ማሻሻያ ካላደረገ" በማለት በጊዜያዊነት ያቋረጡትን የአሜሪካ ድጋፍ በቋሚነት ለማድረግና "አባልነታችንንም እናስብበታለን" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። • የሌሴቶ ጠቅላይ ሚንስትር ከሥልጣናቸው ለቀቁ • የኮሮናቫይረስ ክትባት ቢገኝ አፍሪካ ከሃብታም አገራት እኩል ተጠቃሚ ትሆን ይሆን? • የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እና የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ዶናልድ ትራምፕ የዓለም ጤና ድርጅትን መወንጀል ብቻ ሳይሆን ድርጅቱ "የቻይና አሻንጉሊት" ነው ሲሉም ጠንከር ያለ ወቀሳም ሰንዝረዋል። ይህ አስተያየታቸው የተሰማው ድርጅቱ በወረርሽኙ ላይ የሁለት ቀናት ጉባዔ እያካሄደ ባለበት ወቅት ነው። አክለውም የዓለም ጤና ድርጅት "የተለያዩ መጥፎ ምክሮችን ሲሰጠን ነበር" ካሉ በኋላ ምክሮቹ "በጣም ስህተት የነበሩና ሁሌም ወደ ቻይና ያደሉ ነበሩ" ብለዋል። በጉባዔው ፕሬዝዳንቱ ራሳቸው ያልተገኙ ሲሆን የጤና ሚኒስትራቸው ግን ስብሰባውን በቪዲዮ ተካፍለዋል። ሚኒስትሩ ድርጅቱ ወረርሽኙን የያዘበት የተሳሳተ መንገድ "ለበርካቶች ህይወት መቀጠፍ" ምክንያት ሆኗል ብለዋል። ትራምፕ በአገራቸው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የሰጡት ምላሽ የሚኮነኑ ሲሆን እርሳቸው ደግሞ የዓለም ጤና ድርጅትን ስለወረርሽኙ የዓለም ሕዝብን ቀድሞ አላሳወቀም፤ በቂ አላደረገም እንዲሁም በቻይና ላይ ከበቂ በላይ እምንት አለው በማለት ይተቹታል። አሜሪካ ለዓለም ጤና ድርጅት የምታደርገውን ድጋፍ ማቋረጧ ይታወሳል። የዓለም ጤና ድርጅት ለሁለት ቀናት እያካሄደ ያለው አመታዊ ጉባዔውን 194 አባል አገራት የሚሳተፉበት ሲሆን የድርጅቱን ስራዎችም መለስ ብለው ይገመግማሉ ተብሏል። ዓለምን የናጣት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ልዕለ ኃያላኑ አሜሪካና ቻይናን ጠብ ያለሽ በዳቦ እያሰኘ ነው። የዶ/ር ቴድሮስ መሥሪያ ቤት እንዲህ በዓለም ፖለቲካ ትንቅንቅ መሃል እገኛለሁ ብሎ ያሰበ አይመስልም። አሜሪካን ቻይናን ትከሳለች፤ ቻይና ደግሞ ያለስሜ ስም አትስጭኝ ትላለች። የአውሮፓ ሕብረት በበኩሉ ቫይረሱ ከየት ተነስቶ የት ደረሰ የሚለው በገለልተኛ ወገን ይጣራ ይላል። የትኛው እንሰሳ ኮሮናቫይረስን ወደ ሰው ልጅ አስተላለፈ የሚለው አንቀፅ ላይ የአውሮፓ ሕብረት የቻይናን ስም ከመጥቀስ ተቆጥቧል። 300 ሺህ ሕዝብ በጥቂት ወራት የቀጠፈው ቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው ቻይና ውስጥ ነው። ሌሎች ደግሞ ገለልተኛ የሆነ የዓለም ጤና ድርጅት አጣሪ ቻይና ገብቶ መነሾውን ቆፍሮ ያውጣ ይላሉ። እስካሁን ድረስ ባለው ማጣራት ቻይና ገለልተኛ ወገኖች እንደልባቸው እንዲሆኑ አልፈቀደችም። አሜሪካና አውስትራሊያ ደግሞ እንዴት ተኩኖ እያሉ ነው። ቻይና አቋሟን ትቀይራለች ብሎ መጠበቅ የዋህነት ሳይሆን አይቀርም። ጉባዔውን 'መርቀው' የከፈቱት የቻይናው ፕሬዝደንት ዢ ጂፐንፒንግ 'ሃገሬ በሽታውን ግልፅ በሆነ መንገድ ነው የተቆጣጠረችው' ይላሉ። 'አይሆንም እናጣራ የምትሉ ከሆነ ደግሞ መጀመሪያ በሽታውን በቁጥጥር ሥር እናውለው' ባይ ናቸው። የኮሮናቫይረስ ህመም ምልክቶችና እንዳይዘን ማድረግ ያለብን ጥንቃቄ
news-50640646
https://www.bbc.com/amharic/news-50640646
ሜሲ ለስድስተኛ ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊ ሆነ
የባርሴሎና እና የአርጀንቲናው የፊት መስመር ተጫዋች ሊዮኔል ሜሲ የዓለማችን ምርጥ ተጫዋች በመባል ለስድሰተኛ ጊዜ የባሎንዶር ሽልማት አሸናፊ ሆነ።
የ32 ዓመቱ ሜሲ ባሎንዶርን ሲያሸንፍ እ.አ.አ. ከ 2015 በኋላ የመጀመሪያው ሲሆን ለክለቡና ለአገሩ 54 ግቦችን በማስቆጠር ባለፈው ዓመት ደግሞ ከባርሴሎና ጋር የላሊጋው አሸናፊ መሆን ችሏል። • ማንችስተር ዐይኑን የጣለባቸው የአቶ ምሥጢረ ኃይለሥላሴ ልጆች • ተሰናባቹ ኡናይ ኤምሪን ሊተኳቸው የሚችሉ 7 አሰልጣኞች የሊቨርፑሉ ተከላካይ ቨርጂል ቫን ዳይክ ደግሞ በዚህ ዓመት ሁለተኛውን ቦታ መያዝ ችሏል። አምስት ጊዜ ባሎንዶርን ማሸነፍ የቻለው የጁቬንቱስና የፖርቹጋር አጥቂው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሦስተኛ መሆኑ ታውቋል። በሴቶች ደግሞ ከአሜሪካ ጋር የዓል ዋንጫን ማሸነፍ የቻለችው ሜገን ራፊኖ የባሎንዶር አሸናፊ ስትሆን እንግሊዛዊቷ ሉሲ ብሮንዝ ሁለተኛ ሆናለች። የሊቨርፑሉ ግብ ጠባቂ ብራዚላዊው አሊሴን ቤከር ምርጥ በረኛ ሲባል ጀርመናዊው የባርሴሎና ግብ ጠባቂ ማርክ ቴር ስቴገን እና ብራዚላዊው የማንቸስተር ሲቲ በረኛ ኤደርሰን ሁለተኛና ሦስተኛውን ቦታ ይዘዋል። የጁቬንቱሱ የመሀል ተከላካይ ደ ሊክት ከ21 ዓመት በታች ምርጥ ተጫዋች ተብሎ በቀድሞ ባሎንዶር አሸናፊዎች ተመርጧል። ሜሲ ዘንድሮ የባሎንዶር አሸናፊ ሲሆን ውድድሩን ለ11ኛ ተከታታይ ጊዜ ከስፔን ላሊጋ የመጡ ተጫዋቾች እንዲያሸንፉ አድርጓል። • ከመጠጥ ቀጅነት ወደ እንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ሜሲ በሽልማቱ ወቅት ''ምንም እንኳን ባሎንዶርን ያሸነፍኩት ለስድስተኛ ጊዜ ቢሆንም በጣም የተለየ ደስታ ተሰምቶኛል። ባለቤቴ ሁሌም ቢሆን ትልቅ ህልም እንዲኖረን ትነግረኛለች፤ ለዚህም እራሴን በጣም ዕድለኛ አድርጌ ነው የምቆጥረው።'' ሜሲ ለባርሴሎና እስካሁን 700 ጊዜ ተሰልፎ የተጫወተ ሲሆን በስሙም 614 ግቦችን አስቆጥሯል። ከቡድኑም ጋር 10 የላሊጋና አራት ቻምፒየንስ ሊግን ጨምሮ 34 ዋንጫዎችን ማንሳት ችሏል።
news-51529787
https://www.bbc.com/amharic/news-51529787
የህወሓት ነባር ባለስልጣናት ኢሳያስ በኢትዮጵያ ጉዳይ ጣልቃ መግባታቸውን እንቃወማለን አሉ
በቅርቡ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከኤርትራ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ጉዳይ መቋጫ እንዳያገኝ ህወሓት እንቅፋት ሆኗል ሲሉ በመተቸት ተናግረው ነበር።
አቶ ስዩም መስፍን ፕሬዚዳንቱ ስለ ኢትዮጵያ እና አፍሪካ ቀንድ ዘርዘር ያለ ማብራሪያ በሰጡበት በዚህ ቃለ መጠይቅ፤ የኢትዮጵያና የኤርትራ ግንኙነትም በተመለከተ "በድንበርና በባድመ ጉዳይ ላይ ብቻ ሳንታጠር በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ሪፎርም (ለውጥ) በሙሉ አቅማችን እንደግፋለን" ብለውም ነበር። ፕሬዚዳንት ኢሳያስ "የኢትዮጵያን ጉዳይ እጃችንን አጣጥፈን የምንመለከተው አይደለም" በማለት መረር ባለ ቃል መናገራቸውን ተከትሎም የህወሓት ነባር ታጋዮችና የቀድሞ ከፍተኛ ባለስልጣናት አልወደዱትም። "በውስጥ ጉዳያችን ጣልቃ ገብተዋል" በማለት ፕሬዚዳንት ኢሳያስን ተችተዋል። የቀድሞ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ስዩም መስፍን እና የቀድሞ የትግራይ ፕሬዝዳንት አቶ ፀጋይ በርኸ ለየካቲት 11 ክብረ በዓል በተዘጋጁ መድረኮች ላይ ፕሬዚዳንት ኢሳያስን በግልፅ ተችተዋል። አቶ ፀጋይ በርኸ ባለፈው ሳምንት በማይ ፀብሪ ከተማ ተገኝተው ሲናገሩ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በኢትዮጵያ ጉዳይ "እጁን ካስገባ እጁ ይሰበራል እንጂ የሚያመጣው አንዳች ነገር የለም" ብለዋል። "ይህ የኢትዮጵያውያን የውስጥ ጉዳይ ነው፤ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አያገባቸውም" ያሉት አቶ ፀጋይ የፕሬዝደንት ኢሳያስን ጣልቃ ገብነት "ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ መንግሥት ሊቃወሙት ይገባል" ሲሉ ተደምጠዋል። አቶ ጸጋይ በርኸ "ሃገራችንን ለማፍረስ ነው ይህን እያደረገ ያለው" ሲሉም ፕሬዚዳንት ኢሳያስን የወቀሱ ሲሆን "ሁለት ሶስቴ ያስቡበት" ሲሉም የኤርትራውን ፕሬዚዳንት አስጠንቅቀዋል። በትናንትናው ዕለት የካቲት 8፣2012 ዓ.ም አክሱም ሲከበር በነበረው የህወሓት 45ኛ አመት ምስረታ በዓል የተገኙት አቶ ስዩም መስፍንም በንግግራቸው ጠንከር ያለ ትችት አሰምተዋል። ''ኢሳያስ አፈወርቂ 'ወያኔን እና ወያኔ የገነባውን ሕገ-መንግሥት አፈርሳለሁ' ማለታቸው ነውር" ብለዋል። "ይሄንን ሕገ-መንግሥት ለማፍረስ የሚመጣ ካለ እሱ ሞሶሎኒ ነው። ሂትለር ነው" በማለት ነው መረር ያለ ትችት ያሰሙት። አክለውም "ኢሳያስ ግማሹን የኤርትራ ህዝብ በትኖ ሲያበቃ፤ የኤርትራን ህዝብ ማስተዳደር ሳይችል ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ልማት ሊያመጣ አይቻልም" ብለዋል። የኤርትራ ህዝብም፤ ኢትዮጵያውያን እያደረጉት እንዳሉት ሁሉ ፕሬዝዳንት ኢሳያስን "መጀመርያ የውስጥ ችግራችንን እንፍታ ሊሏቸው ይገባል" ሲሉ ምክር አዘል መልእክት ያስተላለፉት አቶ ስዩም "ከዚያም እንደ ህዝብ፣ እንደ ሀገራት እንደ መንግሥታት አንዱ ሌላኛው ላይ ጣልቃ ሳይገባ መስራት እንችላለን" ብለዋል አቶ ስዩም መስፍን። ቀደም ሲል የህወሐት ፅህፈት ቤት በጉዳዩ ላይ የሚሰጠው ይፋዊ መግለጫ እንደሌለው ለቢቢሲ ገልጾ ነበር።
news-46678528
https://www.bbc.com/amharic/news-46678528
የዓመቱ የአፍሪካ አነጋጋሪ የኢንስታግራም ፖስቶች
ኢንስታግራም ላይ አንድ ቪድዮ መልቀቅ ከመላው ዓለም ለመተዋወቅ አቋራጭ መንገድ ከሆነ ሰነባበተ። ግሩም ድምጽ ያላቸው ታዳጊዎች፣ ምርጥ ተወዛዋዥ ወጣቶች በኢንስታግራም አማካኝነት ዝናን ተቆናጥጠዋል። በአንድ ጽሁፍ ወይም በአንድ ፎቶ ዝነኛ የሆኑትንም ቤቱ ይቁጠራቸው።
• የዓመቱ ሐሰተኛ ዜናዎች በአፍሪካ • "ሕዝብ እንዲጠይቅ አድርገናል" ዋና ኦዲተር ገመቹ ዱቢሶ ሊገባደድ ቀናት በቀሩት የአውሮፓውያኑ 2018 አፍሪካ ውስጥ አነጋጋሪ የነበሩ የኢንስታግራም ፖስቶች የሚከተሉት ናቸው። 1. የሪሀና ኢንስታግራም ገጽ ዝና ያቀዳጃቸው ታዳጊዎች የ Instagram ይዘት መጨረሻ, 1 ድምጻዊቷ ሪሀና አራት ታዳጊ ናይጄሪያውያን ሲደንሱ የሚያሳይ ቪድዮ በኢንስታግራም ገጿ ያጋራችው በመጋቢት ወር ነበር። ቪድዮው ሦስት ሚሊዮን ወዳጆች ሲያገኝ፤ 'ታዳጊዎቹ እነማን ናቸው?' የሚል ጥያቄ የሚጠይቁ ተበራከቱ። ታዳጊዎቹ 'ኢኮሮዱ ታለንትድ ኪድስ' ይባላሉ። ሌጎስ ውስጥ ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ቤተሰቦች የተወለዱ ታዳጊዎች ሲሆኑ፤ የሪሀና ፖስት ከብዙዎች ህሊና እንዳይረሱ አድርጓቸዋል። 2. የ 11 ዓመቷ ዲጄ 'ዲጄ ስዊች' የ 11 ዓመቷ ታዳጊ ኤሪካ ታንዶህ የመድረክ ስም ነው። በመላው ጋና እውቅ የሆነችው በወርሀ ሰኔ ነበር። ኢንስታግራም ላይ 140,000 ተከታዮች ያሏት ታዳጊ፤ ሥራዎቿን የምታስተዋውቀውም በኢንስታግራም ገጿ ነው። • መገረዝ የቀጠፈው ህይወት ኤሪካ በጋና ታሪክ የዲጄዎች ውድድርን ያሸነፈች በእድሜ ትንሿ ልጅ ናት። 3. የኬንያው ፊልም በካንስ ፊልም ፌስቲቫል በዋኑሪ ካዩ የተሰራው 'ራፊኪ' ፊልም ካንስ ፊልም ፌስቲቫል ላይ በመታየት ግንባር ቀደሙ ኬንያዊ ፊልም ሆኗል። ፊልሙ 'የተመሳሳይ ጾታ የፍቅር ግንኙነትን ያስተዋውቃል' ተብሎ በኬንያ መንግሥት እገዳ ተጥሎበት ነበር። ፊልም ሰሪዋ ዋኑሪ ስለ ፊልሙ ኢንስታግራም ገጿ ላይ ስትጽፍ፤ ኬንያዊቷ የሆሊውድ ተዋናይት ሉፒታ ኒዮንጎ የ'እንኳን ደስ አለሽ' መልእክት በኢንስታግራም ገጿ አስተላልፋለች። የኬንያ መንግሥት ፊልሙ ላይ የጣለው እገዳ ለአንድ ሳምንት አንስቶ፤ ፊልሙ የኦስካር እጩ ሲሆን ብዙዎች ደስታቸውን የገለጹትም በኢንስታግራም ነበር። 4. የናኦሚ ካምቤልና የቡሀሪ ጉዳይ መጋቢት ላይ እንግሊዛዊቷ ሞዴል ናኦሚ ካምቤል የናይጄሪያው ፕሬዘዳንት ሙሀመዱ ቡሀሪ በግሏ ጥሪ እንዳደረጉላት ገልጻ ከፎቶ አባሪ ጋር በኢንስታግራም ገጿ ለጥፋለች። • የገና እለት ወደ ሀገሩ እንዲመለስ የተገደደው ስደተኛ ሆኖም የመንግሥት ቃል አቀባይ፤ በግል ጥሪ እንዳልተደረገላት ገልጸው ፖስት አደረጉ። ሞዴሏ ብዙም ሳትቆይ የፋሽን ትርኢት ለመታደም ሌጎስ መገኘቷን ገልጻ ፖስት ያደረገችውን አስተካከለች። ይህ ፖስት የማኅበራዊ ሚዲያ ተከታታዮችን ትኩረት የሳበ ነበር። 5. 'ሹዱ' ደቡብ አፍሪካዊቷ ዲጂታል ሞዴል እንግሊዛዊው ፎቶ አንሺ ካሜሩን-ጄምስ 'ሹዱ' የተባለች ዲጂታል ሞዴል ያስተዋወቀው የካቲት ላይ ነበር። ሞዴሏ በቀጭን፣ ረዥም አፍሪካዊ ሴት ቅርጽ የተሰራች ስትሆን፤ ፎቶ አንሺው በሥራው ትችት ተከትሎታል። 'ሺዱ' በ20ዎቹ መጨረሻ ያለች ዲጂታል ሞዴል ስትሆን፤ ከ150,000 በላይ የኢንስታግራም ተከታዮች አሏት። • ታዋቂው የሆሊውድ ተዋናይ በፆታዊ ትንኮሳ ክስ ተመሰረተበት ፎቶ አንሺውን ያሞገሱት እንዳሉ ሁሉ፤ 'ሹዱ' እንደ ነጭ ወንድነቱ ለአፍሪካውያን ሴቶች ያለው የተዛባ አመለካከት ነጸብራቅ ናት ብለው የተቹም ነበሩ። 6. ስዊድናዊቷ ቱሪስትና ኬንያዊቷ ታዳጊ ጆሳ ጆንሰን የተባለች ስዊድናዊት ቱሪስት በናይሮቢ የተጨናነቁ መንደሮች ያገኘቻትን ታዳጊ ፎቶ ኢንስታግራም ላይ ለጠፈች። ከፎቶው በበለጠ ብዙዎችን ያስቆጣው ከፎቶው ጋር አያይዛ የጻፈችው ነበር። "ታዳጊዋ በህይወት ዘመኗ እጅግ የተደሰተችበት ቅጽበት እኔና ጓደኞቼን ስታገኝ ነው" ብላ ነበር። ታዳጊዋ ለወደፊት በእድሜ የሚበልጣት ሰው አግብታ በድህነት እንደምትማቅቅ፤ ባሏ ጥሏት ሲሄድ ልጇን ለማሳደግ ሴተኛ አዳሪ እንደምትሆንም ጽፋ ነበር። • የሪፐብሊኩ ጠባቂ ሃይል መቋቋም ምን ያመለክታል? በአጸያፊ ንግግሯና ዘረኛ አስተያየቷ ተተችታለች። ጽሁፏ በአጭር ጊዜ ከበርካቶች አሉታዊ ምላሽ አሰጥቷታል። 7. ደቡብ አፍሪካውያኑ ፖሊሶች የደቡብ አፍሪካ የፖሊስ ሀላፊ ሳኔል ሶጺዝ ኢንስታግራም ላይ ፖስት በምታደርጋቸው ፎቶዎች ምክንያት ብዙ ተከታይ አላት። ከራሷ ፎቶ በተጨማሪ አንዲት የደርባን ኮንስታብል ፎቶዎችን ፖስት ስታደርግ ደግሞ አነጋጋሪነቷ ጨመረ። ሶዌቶ ውስጥ ያለ አንድ ጋዜጣ 'ሁለት ቆንጆ ፖሊሶች' የሚል ጽሁፍ ሲያስነብብ የማኅበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሆኑ። የፖሊሷ ዝና በአጭር ጊዜ ናኝቶ፤ በሥራ ቦታዋ፣ መንገድ ላይም ሰዎች "እሷ ነች! እሷ ነች!" እያሉ ይነጋገሩም ጀመር። 8. የአምስት አመቷ ታዳጊ ፎቶ ሀምሌ ላይ ናይጄሪያዊቷ ፎቶ አንሺ ሞፊ ባሙይዋ፤ በኢንስታግራም ገጿ ጄር የተባለች የአምስት ዓመት ታዳጊ ፎቶ ፖስት አደረገች። ብዙ ሺ አድናቂዎችም ጎረፉላት። ልጅቷ 'የዓለም ቆንጆ' የሚል መጠሪያ ተሰጣት። ፎቶ አንሺዋ "በልጅነትና በታዳጊነት መካከል ያለውን ሽግግር ያሳየሁበት ሥራ ነው። ሁለቱም ዘመን የማይገድባቸው እንዲሆኑ እፈልጋለሁ" ስትል ስለ ፎቶው ተናግራለች። የአምስት ዓመት ልጅን መዋዋቢያ ቀብቶ፣ ዊግ ቀጥሎ ፎቶ ማንሳት ተገቢ አይደለም ብለው ተቃውሞ ያሰሙ ነበሩ። ሆኖም የልጅቷ እናት ለጄር እንዲሁም ለሁለት እህቶቿ ጆሚና ጆባ የኢንስታግራም ገጽ አውጥታለች። 'ዘ ጄ ስሪ ሲስተርስ' የተባለው ይህ ገጽ 108,000 ተከታዮች አሉት።
news-53906345
https://www.bbc.com/amharic/news-53906345
አሜሪካ፡ ጥቁር አሜሪካዊው በ7 ጥይት መመታቱን ተከትሎ ተቃውሞ ተቀስቅሷል
ባለፈው እሁድ ዊስኮንሲን ውስጥ አንድ ጥቁር አሜሪካዊ በጥይት መመታቱን ተከትሎ ተቃውሞ በርትቷል።
ኬኖሻ ውስጥ ሕንጻዎችና መኪናዎች ተቃጥለዋል ፖሊስ፤ ጄኮብ ብሌክ የተሰኘውን የ29 ዓመት ጥቁር አሜሪካዊ ቢያንስ ሰባት ጊዜ በጥይት መቶታል ተብሏል። ኬኖሻ የተባለችው በዊስኮንሲን ግዛት የምትገኘው ከተማ ነዋሪ የሆነው ግለሰብ ከፖሊስ ጋር በተፈጠረ አተካራ መካከል ወደ መኪናው ሲገባ ፖሊስ አከታትሎ ሲተኩስበት የሚያሳይ ተንቃሳቃሽ ምስል ተሰራጭቷል። ይህን ተከትሎ በግዛቲቱ ለሁለተኛ ቀን የዘለቀ ተቃውሞ ተቀስቅሷል። ሕንፃዎች ወድመዋል፤ መኪናዎች ተቃጥለዋል። የግዛቲቱ አገረ ገዢ ቶኒ ኤቨርስ ብሔራዊው ክቡር ዘብ እንዲረዳቸው ጥሪ አቅርበዋል። ባለፈው ግንቦት ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ በአሰቃቂ ሁኔታ በፖሊስ መገደሉን ተከትሎ ለሳምንታት የዘለቀ ተቃውሞ አሜሪካን እንደናጣት አይዘነጋም። ተቃዋሚዎች ፖሊስ ዜጎች በተለይ ጥቁር አሜሪካውያን ላይ የሚያደርሰውን በደል ያቁም ይላሉ። የኬኖሻ ከተማ አስተዳደር ከምሽት 2 ሰዓት እስከ ጥዋት 1 ሰዓት የሚቆይ ሰዓት እላፊ ቢጥልም ተቃዋሚዎች ገደቡን ጥሰው ድምፃቸውን ሲያሰሙ አምሽተዋል። በርካታ ወጣት ተቃዋሚዎች የከተዋማ ፍርድ ቤትን ሊጠብቁ ከቆሙ የፀጥታ ኃይሎች ጋር ተጋጭተዋል። ተቃዋሚዎች 'ፍትህ ለጄኮብ' በማለት ድምፃቸውን እያሰሙ እንዳሉ ከሥፍራው የሚወጡ ዘገባዎች ያሳያሉ። ጄኮብ ብሌክ ቢያንስ ሰባት ጊዜ በጥይት ቢመታም በሕይወት እንዳለና ሕክምና እያገኘ እንደሆነ ተሰምቷል። አገረ ገዢው ኤቨርስ "ብሔራዊው ክቡር ዘብን የጠራሁት ሰልፈኞች ድምፃቸውን ሥርዓት ባለው መልኩ እንዲያሰሙና የሕዝብ ንብረት እንዳያወድሞ ነው" ሲሉ ተደምጠዋል። ለተቃውሞ የወጡ ነዋሪዎች ግለሰቡን በጥይት የመቱት ፖሊሶች በሕግ ጥላ ሥር ይዋሉ ያሉ ተቃዋሚ ሰልፈኞች ወደ ከተማዋ ሕዝብ ደኅንነት ቢሮ ሰብረው ለመግባት ሙከራ አድርገዋል። ፖሊስ ይህን ለመከላከል አስለቃሽ ጭስ ተኩሷል። ዴሞክራቱ አገረ ገዢ ጥቁር አሜሪካዊው በፖሊስ በጥይት መመታቱን አውግዘዋል። ነገር ግን ይህ አስተያየታቸው ትችት አስከትሎባቸዋል። የከተማዋ ፖሊስ ማኅበር ኃላፊ ፒት ዲተስ "አስተያየቱ ኃላፊነት የጎደለው ነው። ቢያንስ የተፈጠረው ነገር እስኪጣራ አስተያየት መስጠት አልነበረባቸውም" ሲሉ ይወቅሳሉ። ሰውዬው በሁለቱ ነጭ ፖሊሶች ጥቃት ሲደርስበት የቀረፀው ግለሰብ ፖሊሶቹ ጥቁር አሜሪካዊውን በቡጢ እንደመቱት ለሲኤንኤን ተናግሯል። ብሌክ ወደ መኪናው አቅንቶ በሩን ከፍቶ ዝቅ ሲልና አንዱ ነጭ ፖሊስ ካናቴራውን ይዞ አከታትሎ ሲተኩስበት በምስሉ ላይ ይታያል። የዊስኮንሲን ፍትህ ቢሮ ጉዳዩን እየመረመርኩ ነው ቢልም ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል። የብሌክ አጋር የሆነችው ሴት ሦስት ልጆቻቸው መኪናው ውስጥ ከኋላ ተቀምጠው እንደነበርና አባታቸው በጥይት ሲመታ እንደተመለከቱ ተናግራለች። የ29 ዓመቱ ግለሰብ ከቀዶ ህክምና ክፍል ወጥቶ አሁን በማገገሚያ ክፍል እንደሚገኝ ተዘግቧል። ሰውዬው በጥይት መተዋል የተባሉት ሁለቱ ነጭ ፖሊስ የግዳጅ እረፍት ላይ ሲሆን እንዲከሰሱ ጥሪ እየቀረበ ነው። ዴሞክራቱ ፕሬዝደንታዊ ዕጩ ጆ ባይደን የብሌክ ጉዳይ ግልፅ በሆነ መንገድ እንዲጣራ ሲሉ ሰኞ መግለጫ አውጥተዋል።
43918191
https://www.bbc.com/amharic/43918191
ከባድ ዝናብና የጎርፍ አደጋ በአንዳንድ አካባቢዎች ጉዳት አስከተለ
ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በደቡብ፣ በደቡብ ምሥራቅና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የጎርፍ አደጋ ተከስቷል። በዚህም በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ከመድረሱ ባሻገር መንገዶች በመዘጋታቸው በአካባቢዎቹ የሚገኙ ነዋሪዎች ለችግር መጋለጣቸውን ይናገራሉ።
አሁን እየጣለ ያለው ዝናብ ለእርሻና ለተለያዩ ተግባራት የሚጠቀምና የተጠበቀ ቢሆንም መጠኑ ከፍተኛ በመሆኑ ግን የተለያዩ ጉዳቶችን እያስከተለ መሆኑን የሚናገሩት የጉጂ ዞን የአደጋ ስጋት አመራር ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አበበ አባቡልጋ ናቸው። ይህንን ዝናብ ተከትሎ በተለያዩ የኢትዮጵያ ደቡብና ደቡብ ምዕራብ አካባቢዎች "መንገዶች የመቆረጥ፣ ፀረ-ሰብል ተባዮች መከሰት፣ በንብረት ላይ ጥፋት መድረስና የመሳሰሉ ጉዳቶች ተከስተዋል" ይላሉ አቶ አበበ። የሚጥለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ ጎርፍ ጉዳት ካደረሰባቸው አካባቢዎች መካከል አንዱ በሆነው በባሌ ዞን መደ ወላቡ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አቶ አህመድ ጁንዳ እንደሚሉት አደጋው የተከሰተው በዝናቡ ምክንያት ብቻ ሳይሆን በመሰረተ-ልማት ጉድለት ጭምር እንደሆነ ይጠቅሳሉ። በፌደራል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የአቅርቦትና ሎጂስቲክስ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አይድሮስ ሃሰን እንደሚሉት መንግሥት ለአደጋ ተጋላጭ በሆኑ ቦታዎች ላይ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን፤ ነገር ግን ከጎርፍ አደጋ ጋር በተያያዘ ከሶማሌ ክልል ውጪ ከሌሎች ቦታዎች ምንም ሪፖርት እንዳለቀረበ ይናገራሉ። የሚደርሱ አደጋዎችን ለመቋቋም በአንዳንድ አካባቢዎች ቀደም ተብሎ አስፈላጊ የሆኑ ድጋፎችን የማቅረብ ሥራ እንደተከናወነ የሚናገሩት አቶ አይድሮስ "በዚህ መሰረትም በቅርበት ድጋፍ የሚሰጥ ሲሆን፤ ከዚያ በላይ ከሆነ ደግሞ በሚቀርብ ጥያቄ መሰረት ከፌደራል መንግሥቱ አስቸኳይ ምላሽ ይሰጣል።" ጨምረውም ከኦሮሚያ ክልል ከጎርፍ አደጋ ጋር ተያይዞ የቀረበ ጥያቄ እንደሌለ ነገር ግን በሶማሌ ክልል አፍዴርና በሌሎች በተወሰኑ ወረዳዎች ላይ የጎርፍ አደጋ እንደነበርና መንግሥት አስፈላጊውን ምላሽ እየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞም የብሔራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ፈጠነ ተሾመ እንደሚናገሩት አሁን አደጋው በደረሰባቸው አካባቢዎች "ከመደበኛው በላይ የሚሆን ዝናብ ሊጥል እንደሚችል ተተንብዮ ነበር" ሲሉ አስታውሰዋል።
news-48488784
https://www.bbc.com/amharic/news-48488784
የቦይንግ 737 ማክስ ደህንነት ስለ ማሻሻል ያለው እሰጣ ገባ ቀጥሏል
የአውሮፓ ሕብረት የትራንስፖርት ባለስልጣናት የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ደህንነትን ለማሻሻል እየተሰራ ያለውን ሶፍትዌር እውቅን ለመስጠት ከሌሎች የትራንስፖርት ባለስልጣናት ጋር አብረው እንደሚሰሩ አስታወቁ።
ቻይና ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖችን ቀድመው ካገዱ ሃገራት መካከል ተጠቃሽ ነች የአውሮፓ ሕብረት የትራንስፖርት ባለስልጣናት፤ አውሮፕላኖቹን በራሳቸው የአየር ክልል ውስጥ መልሶ ስለማብረር ውሳኔ የሚሰጡት በራሳቸው ጊዜ እንደሚሆን ተናግረዋል። በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ላይ የተጫነው ኤምካስ የተሰኘው ስርዓት በኢንዶኔዢያው ላየን እና ኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኖች ላይ ለደረሰው አደጋ እንደ ምክንያትነት በርካቶች ሲያቀርቡት ቆይተዋል። • ቦይንግ ትርፋማነቴ ቀንሷል አለ • ቦይንግ የ737 ማክስ ሶፍትዌርን አሻሽያለሁ አለ በኢትዮጵያ የደረሰውን አደጋ ተከትሎ ነበር ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች እንዳይበሩ ዓለም አቀፍ እገዳ የተጣለባቸው። የዓለማችን አየር መንገዶች የተለያዩ የትራንስፖርት ባለስልጣናት በአውሮፕላኖቹ ላይ ያላቸው መተማመን ልዩነት መፍጠር፤ በደንበኞች እና በኢንዱስትሪው ላይ አሉታዊ ጫና ያሳድራል ሲሉ ስጋታቸውን ይገልጣሉ። የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች የበረራ ፍቃድ ከአሜሪካ ቀድመው ቻይና እና የአውሮፓ ህብረት መሰረዛቸው በትራንስፖርት ባለስልጣናት መካከል ባልተለመደ መልኩ ልዩነት እንዳለ አሳይቷል። የቦይንግ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኩባንያቸው ማክስ 737 አውሮፕላኖችን ወደ በረራ ለመመለስ ጥረት እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል። የአውሮፓ ሕብረት የትራንስፖርት ኮሚሽነር ቫዮሌታ በልክ እንዳሉት፤ የአውሮፓ የበረራ ደህንነት ኤጀንሲ ቦይንግ ማክስ 737 አውሮፕላኖቹን ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያቀርበውን አማራጭ በትኩረት ያጤነዋል ብለዋል። አውሮፕላኖቹን ወደ በረራ መቼ ይመለሱ በሚለው ላይ የተቆረጠ ቀን ባይኖርም፤ ዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበር ግን ከሐምሌ ወር በፊት የሚሳካ አይመስለኝም ይላል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም የኢትዮጵያ አየር መንገድ 737 ማክስ 8 አውሮፕላኖቹን ወደ ሥራ መቼ ሊመልስ ይችላል ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፤ ''737 ማክስ አውሮፕላኖችን ወደ በረራ ቢመለሱ፤ እኛ አውሮፕላኖቹን ለማብረር የመጨረሻው አየር መንገድ ነው የምንሆነው'' ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተው ነበር። የኢቲ 302 ስብርባሪ። ከቀናት በፊት የካናዳ የአየር ትራንስፖርት ባለስልጣናት የአውሮፕላኖቹን ደህንነት በተመለከተ ከአሜሪካ ፌደራል የአቪዬሽን አስተዳደር ጋር ይልቅ ከአውሮፓ ሕብረት የትራንስፖርት ባለስልጣናት ጋር መስራትን እንደሚመርጡ ጠቁመዋል። የትራስፖርት ባለስልጣናት የአንድን አውሮፕላን የበረራ ደህነንት ፍቃድን የሚያረጋግጡት አውሮፕላኑ ከሚመረትበት የመንግሥት አካል በሚሰጥ ማረጋገጫ ነው። በዚህም መሰረት የቦይንግ አውሮፕላኖች ደህንነት የሚያረጋግጠው የአሜሪካው የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር ነው። ይሁን እንጂ በኢንዶኔዢያ እና በኢትዮጵያ የደረሱትን አደጋ ተከትሎ የተደረጉ ማጣሪያዎች እንዳጋለጡት የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር የአውሮፕላኖችን የደህንነት የማረጋገጥ የተወሰነውን ክፍል ለአውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ሰጥቷል። ይህም በአቪዬሸን አስተዳደሩ ላይ ከፍተኛ ጫናን ፈጥሯል። • 'መጥፎ ዕድል' አውሮፕላኑ የወደቀበት ስፍራ ስያሜ እንደሆነ ያውቃሉ? አሁንም ቢሆን ይሻሻላል የተባለው ሶፍትዌር መቼ እንደሚጠናቀቅ፣ በምን አይነት መልኩ መግባባት ላይ እንደሚደረስ እንዲሁም አውሮፕላኖቹ በረራ መቼ እንደሚጀምሩ የጠራ ነገር የለም።
news-52046300
https://www.bbc.com/amharic/news-52046300
ሶማሊያ በዓለም አቀፍ አበዳሪዎች ከፍተኛ የብድር ስረዛ ተደረገላት
የዓለም ባንክና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ሶማሊያ ብድር እንዲቃለልላት የሚያስችሉ እርምጃዎችን መውሰዷን ማስታወቃቸውን ተከትሎ የአበዳሪዎችን ድጋፍ አግኝታለች።
የሶማሊያ ሴቶች የፊት ጭምብል አድርገው እንደ መግለጫው ከሆነ ሶማሊያ አጠቃላይ ብድሯ ከ5.2 ቢሊዮን ዶላር በከፍተኛ ደረጃ ዝቅ ይደረግላታል። ይህም የሚሆነው በሦስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ነው። በሶማሊያ የዓለም ባንክ ተወካይ ሁግ ራይደል ለቢቢሲ እንደገለጹት የሶማሊያን የብድር መጠን ለማቃለል ከሚወሰደው የተቀናጀና ሰፊ ሂደት መካከል ይህ የመጀመሪያው እርምጃ ነው ብለዋል። ሶማሊያ ከ30 ዓመት በፊት ከነበረው የእርስ በርስ ጦርነት ጀምሮ ብድሯን ከፍላ አታውቅም፤ በዚህ ምክንያትም ሶማሊያ ከተለያዩ አበዳሪ ተቋማት እንደገና ብድር ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት ከባድ አድርጎባታል። አሁን ግን ይህ የብድር ስረዛ ስለተደረገላት መንግሥት በመላ አገሪቱ ለሚያከናውናቸው አገልግሎቶች ብድር ለመጠየቅ ያስችለዋል። የሶማሊያው ጠቅላይ ሚንስትር ሃሰን አሊ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት "ይህ ከነጻነት በኋላ ያገኘነው ሁለተኛው ነጻነት ነው" ብለዋል፤ ከቅኝ ግዛት ነጻ የወጡበትን ሁኔታ በማጣቀስ። "አሁን ያለንበት ጊዜ በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ በመሆኑ በአበዳሪ ተቋማቱ በተወሰደው እርምጃ መሰረት ልናገኘው የምንችለው የበጀት ድጋፍ በመላ አገራችን ለሕዝቡ አገልግሎት ለመስጠት ትልቅ እገዛ ያደርጋል። ከሁሉም በላይ ደግሞ ሁላችንንም እያሸበረን ያለውን ኮሮናቫይረስን ለመዋጋት ይረዳናል" ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሩ። እንደ ሶማሊያ ባለ በሽብርተኞች በተደጋጋሚ ጥቃት ለሚደርስበት አገርም ሽብርተኝነትን ማሸነፍ የሚቻለው ምጣኔ ሃብትን በማሳደግ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ ወጣቶችንና ሴቶችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል። አክለውም ፍትሃዊና ግልጽ የሃብት ክፍፍል በመፍጠር ሽብርተኝነትን ማሸነፍ ስለሚቻል የብድር ቅነሳ ውሳኔው ለሶማሊያ ዘርፈ ብዙ ጥቅም የሚያመጣ መሆኑን ጠቅላይ ሚንስትር ሃሰን ተናግረዋል። ሶማሊያ፡ በደም የተሸፈነችው ምድር
news-50120799
https://www.bbc.com/amharic/news-50120799
ከልክ በላይ በወፈሩ ሰዎች ሳንባ ውስጥ ስብ እንደሚፈጠር ተደረሰበት
ላልተመጣጠነና ከመጠን በላይ ለሆነ ውፍረት የተጋለጡ ሰዎች ሳንባ ውስጥ ስብ ለመጀመሪያ ጊዜ መገኘቱ ተገለፀ።
አውስትራሊያዊያን ተመራማሪዎች ከ52 ሰዎች የተወሰደ ናሙና ላይ ተመስርተው ባካሄዱት ምርምር በሳምባቸው ውስጥ የተገኘው የስብ ክምችት መጠን እንደ ሰውነታቸው የክብደት መጠን መጨመሩን ያመለክታል። • "ወፍራም ሴቶች ለአገርም ለቤተሰብም ሸክም ናቸው" የግብፅ የቴሌቪዥን ጋዜጠኛ • ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን? አጥኚዎቹ እንዳሉት ግኝቱ ላልተመጣጠነና ከመጠን በላይ ለሆነ ውፍረት የተጋለጡ ሰዎች፤ እንደ አስም ላሉ የመተንፈሻ አካል የጤና ችግሮች የመጋለጣቸው እድል ሰፊ እንደሆነ ያስረዳል። የመተንፈሻ አካል ባለሙያዎች በበኩላቸው ሰዎቹ ክብደት ሲቀንሱ ችግሩ ይስተካከል እንደሆነ ጥናቱ ቢመለከተው መልካም ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። በአውሮፓ ሪስፓራቶሪይ ጆርናል ላይ የታተመው ይህ ጥናት፤ ተመራማሪዎቹ ለምርምራቸው ከሞቱ ሰዎች የተለገሱ ሳንባዎችን በናሙናነት ተመልክተዋል። በዚህም መሠረት 15 የሚሆኑት አስም ያልታየባቸው ሲሆን 21ዱ የጤና ችግሩ ታይቶባቸዋል። ይሁን እንጂ ሕይወታቸው ያለፈው በሌሎች ምክንያቶች ነበር። 16 የሚሆኑት ግን በዚሁ ችግር ሕይወታቸው ማለፉን ጥናቱ አሳይቷል። ተመራማሪዎቹ በዝርዝር ለማጥናት ከተወሰዱ የሳንባ ናሙናዎች 1400 የሚሆኑ የአየር ማስተላለፊያ ቧንቧዎች ላይ በማይክሮስኮፕ ጥልቅ ምርመራ አድርገዋል። በዚህም መሠረት ተመራማሪዎቹ በአየር ማስተላላፊያ ቧንቧዎች ግድግዳ ላይ የስብ ክምችት ያገኙ ሲሆን ችግሩ በተለይ ከመጠን በላይ የወፈሩ ሰዎች ላይ ታይቷል። በመተንፈሻ ቧንቧው ላይ የስብ ክምችቱ እየጨመረ መምጣቱም፤ ጤናማ ለሆነው የአተነፋፈስ ሥርዓት መዛባትና የሳንባ መቆጣት እንደሚከሰት የማስጠንቀቂያ ደወል ነው ተብሏል። በጥናቱ ላይ የተሳተፉት በምዕራብ አውስትራሊያ ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር ፒተር ኖቤል "ያልተመጣጠነ ወይም ከመጠን በላይ ውፍረት ከአየር ቧንቧ ከሚከሰት የጤና ችግር ጋር የተያያዘ ሲሆን በጣም ከባድ የሆነ የጤና ችግር ሊያስከትል ይችላል" ብለዋል። የጤና እክሉ ከመጠን በላይ በሆነ ውፍረት ምክንያት በሳንባ ላይ በሚፈጠር ጫና ወይም ከውፍረቱ ጋር ተያይዞ በሚመጣ የሳንባ መቆጣት ጋር ሊያያዝ ይችላል። ይሁን እንጂ ዶክተር ፒተር እንደሚሉት ሌላ ምክንያትም ሊኖረው እንደሚችል በጥናቱ ተጠቁሟል። "በአየር ቧንቧ ግድግዳ ላይ ያለው የስብ ክምችት፤ የአየር መተላለፊያ ቦታን በመያዝ በሳንባ ላይ መቆጣትን እንደሚያስከትል በጥናቱ ደርሰንበታል" ብለዋል ዶክተር ኖቤል። • ሳናውቀው በሰውነታችን ውስጥ የሚከማች አደገኛ ስብ • በፈረንሳይ ክብደት ይቀንሳል በተባለ መድሃኒት እስከ 2ሺህ ሰዎች ሞተዋል ተባለ ይህም የአየር ቧንቧው እንዲወፍር በማድረግ ወደ ሳንባችን የሚገባውንና የሚወጣውን አየር መጠን በመገደብ፤ የመተንፈሻ አካል የጤና ችግር አመላካች ነው ብለዋል። የአውሮፓ የመተንፈሻ አካላት ጤና ማህበር አባል የሆኑት ፕሮፌሰር ቴሪ ትሩስተር እንዳሉት በክብደት መጠን መጨመርና በመተንፈሻ አካል የጤና ችግሮች መካከል ያለውን ግንኙነት ለማሳየት ጥናቱ ጠቃሚ ነው፤ ምክንያቱም ከልክ በላይ ውፍረት ለእንደዚህ ዓይነት የጤና ችግሮች ምልክት መሆኑን ሲያመላክት በተለይ አስም ላለባቸው ሰዎች ችግሩ የከፋ ይሆናል። ጉዳዩ በጣም ወፍራም ሰዎች ሥራ ሲሠሩና ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ቶሎ ቶሎ መተንፈስ እንደሚፈልጉ ከመመልከትም በላይ ነው ይላሉ። በመሆኑም ክብደት ሲቀነስ የስብ ክምችቱም እየቀነሰ ይመጣ እንደሆነ ለማወቅ ሌላ ጥናት መሥራት ቢያስፈልግም፤ በተለይ የአስም ታማሚዎች ጤናማ የሰውነት ክብደት እንዲኖራቸውም ጥረት ማድረግ ይኖርባቸዋል ሲል ጥናቱ አሳስቧል። በእንግሊዝ ቶራሲስ ሶሳይቲ ኮሚቴ ኃላፊ የሆኑት ዶክተር ኦልሳቤት ሳፔይ በበኩላቸው የሰውነት ክብደት ከአየር ቧንቧ ችግር ጋር መገናኘቱን ያሳየ የመጀመሪያው ጥናት መሆኑን ገልፀዋል። "በአገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ የሚታየውን ከልክ በላይ ለሆነ ውፍረት የሚጋለጡ ሰዎች ቁጥር መጨመርን ስንመለከት፤ የአስም ሕመም ምን ያህል ከባድ የጤና እክል እንደሆነ ለመረዳት ያስችላል" የሚሉት ዶክተር ኤልሳቤት፤ የአስም ሕመምን ለማከምም የሚረዱ ዘዴዎችን ለመለየት ጥናቱ ያግዛል ብለዋል። "ጥናቱ በተወሰነ መልኩ የተሠራ ነው፤ ነገር ግን ሰፊ ቁጥር ባላቸው ህሙማን ላይ እና በሌሎች የመተንፈሻ አካል የጤና ችግሮች ጋር በስፋት መመልከት አለብን" ሲሉ አክለዋል።
news-45860240
https://www.bbc.com/amharic/news-45860240
የአውሮፓ አገራት የተገደለው የሳዑዲ ጋዜጠኛ ምርመራ እንዲቀጥል አሳሰቡ
እንግሊዝ፣ ጀርመንና ፈረንሳይ በቅርቡ ደብዛው የጠፋውን ታዋቂውን የሳዑዲ ጋዜጠኛ ጀማል ካሹጊን አስመልክቶ ጠበቅ ያለ ምርመራ እንፈልጋለን አሉ።
በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው መልዕክቱን ያስተላለፉት አገራቱ ኃላፊነቱን የሚወስድ አካል ካለም ተጠያቂ ሊሆን እንደሚገባና ከሳዑዲ ባለስልጣናትም ዘርዘር ያለ መልስ እንፈልጋለን ብለዋል። የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ጄሬሚ ሀንት እንዳሉት ለተፈጠረው ነገር በሙሉ የሳዑዲ አረብያ ኃላፊነት መሆኑንም አስረድተዋል። ሳዑዲ በበኩሏ ጀማል ካሹጊ ቱርክ፣ ኢስታንቡል በሚገኘው ቆንሱላቸው ውስጥ መገደሉን ክደዋል። •ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን ለመግደል በመሞከር የተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ ቀጠሮ ተጠየቀ •የዓለምፀሐይ፣ የፍስሃ እና የካሳሁን አዲስ ተስፋ •"ለወታደራዊ ደኅንነቱ የማንቂያ ደወል ነው" የሳዑዲ የሀገሪቱ ሚዲያ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው ሀገሪቷ ማንኛውንም አይነት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ማስፈራሪያዎችን በፍፁም እንደማትቀበልና በግዛቷ ላይ ለሚፈፀሙ ማንኛውም ድርጊቶች ምላሹ የከፋና ፈጣን ነው ብለዋል። ነገር ግን በትናንትናው ዕለት ንጉስ ሳልማን አቋማቸውን አለሳልሰው የቱርኩን ፕሬዚዳንት ጣይብ ኤርዶጋንን ሁለቱን መንግሥታት ያጣመረ የምርመራ ቡድን ማቋቋማቸውን አመስግነዋል። ጨምረውም ከቱርክ ጋር ያላቸውን ጠንካራ ግንኙነት ምንም እንዳያበላሸው ገልፀዋል። የሳዑዲ መንግሥት የሰላ ተቺ የሆነው ጋዜጠኛው ጀማል ካሹጊ ኢስታንቡል ቆንሱላ ግቢ ውስጥ ከገባ በኋላ ደብዛው ከጠፋ አስር ቀናት አልፈውታል። የቱርክ ባለስልጣናት በበኩላቸው ጀማል ካሹጊ በቆንሱላው ውስጥ በሳዑዲ ወኪሎች እንደተገደለ የተናገሩ ሲሆን ሳዑዲ "ውሸት" በማለት ክዳዋለች። ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ጀማል በቆንሱላው ጋብቻን በተመለከተ የሚያስጨርሰው ጉዳይ ስለነበረው ቦታው ላይ እንደተገኘ ተጠቅሷል። የቱርክ የፀጥታ ኃይሎች ለበቢሲ እንደተናገሩት ለዋሽንግተን ፖስት ይፅፍ የነበረው ጀማል ካሹጊ በቆንሱላው ውስጥ እንደተገደለ የድምፅና የቪዲዮ ማስረጃ እንዳላቸው ነው። ከቱርክ በኩል የተኙ ምንጮች እንዳስረዱት ጀማል 15 በሚሆኑ የሳዑዲ ወኪሎች እንደተገደለ ነው። ከአውሮፓ አገራት በተጨማሪ ዶናልድ ትራምፕ የጀማል ጉዳይ እንዳሳሰባቸው ገልፀው ሳዑዲ አጥጋቢ መልስ ልትሰጥ እንደሚገባም መናገራቸው የሚታወስ ነው። ትራምፕ ጨምረውም ጀማል ካሹጊ ቆንሱላው ውስጥ ተገድሎ ከሆነ ሳዑዲ የከፋ ቅጣት እንደሚጠብቃትም አስጠንቅቀዋል።
news-46733754
https://www.bbc.com/amharic/news-46733754
የአውሮፕላን አደጋዎች የበዙበት 2018
በባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት በአውሮፕላን አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ2017 ጋር ሲወዳደር ከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ቢያሳይም፤ የአውሮፕላን ጉዞ ዝቅተኛ አደጋ ከሚያጋጥማቸው የመጓጓዣ ዘዴዎች መካከል ዘጠነኛው ነው ተብሏል።
በ2017 ከአውሮፕላን አደጋዎች ጋር በተያያዘ 44 ሰዎች ብቻ የሞቱ ሲሆን፤ ባሳለፍነው 2018 ግን 556 ሰዎች በአውሮፕላን አደጋ ህይታቸውን አጥተዋል። • መከፋፈል ያጠላበት ጉዞ አድዋ ከሁሉም የከፋው የተባለለት አደጋ ደግሞ የኢንዶኔዢያው አየር መንገድ አውሮፕላን ተከስክሶ 189 ሰዎች የመሞቱበት ነው ተብሏል። በአንጻሩ 2017 በአውሮፕላን አደጋዎች በታሪክ ትንሽ ሞት የተመዘገበበት ሆኖ ነበር ያለፈው። • መከላከያ በዛላምበሳ ድንበር እንዲቆይ ስምምነት ተደረሰ የኔዘርላንዱ 'ኤኤስኤን' የተባለው ድርጅት እንዳስታወቀው ባሳለፍነው ዓመት የብዙ ሰዎችን ህይወት የቀጠፉ 18 የአውሮፕላን አደጋዎች ተከስተዋል። ከእነዚህም መካከል ደግሞ 189 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈበት የኢንዶኔዢያው ቦይንግ 737 አደጋ፣ 112 ሰዎች የሞቱበት የኩባው አውሮፕላን አደጋ፣ በኢራን ዛግሮስ ተራሮች ላይ ተከስክሶ 66 ሰዎች የሞቱበት አደጋ እንዲሁም የ51 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው የኔፓሉ አየር መንገድ አደጋ ይጠቀሳሉ። • ስልክዎ እንደተጠለፈ የሚያሳዩ ሰባት ምልክቶች ምንም እንኳን የዓለም አቀፍ ኤቪዬሽን ድርጅቶች ከባለፉት ሃያ ዓመታት ጀምሮ አደጋዎችን ለመቆጣጠር እየሰራን ነው ቢሉም፤ የሟቾች ቁጥር ግን እምብዛም መቀነስ እያሳየ አይደለም።
42942014
https://www.bbc.com/amharic/42942014
አስጊነቱ እየጨመረ ያለው ካንሰር
አቶ ወንዱ በቀለ የሁለት ዓመት ልጃቸውን በካንሰር ምክንያት በሞት ሲነጠቁ የህይወት መስመራቸው የተቀየረው እስከወዲያኛው ነው ።
ላለፉት አስራ አራት ዓመታት በልጃቸው ስም ባቋቋሙት "ማቴዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ"ለታማሚዎች እንክብክካቤ ማቀረብ እንዲሁም ስለበሽታው ግንዛቤ መፍጠርን የህይወታቸው ግብ ከማድረጋቸውም ባለፈ ተቋሙን ማስተዳደር አሁን የሙሉ ጊዜ ሥራቸው ነው። ማቴዎስ ያልተጠበቀና በእርጅና የመጣ ልጅ ቢሆንም አዲስ በረከትን ይዞላቸው እንደመጣ የሚናገሩት አቶ ወንዱ " የማቴዎስ መወለድ ህይወታችንን በጣም ነው የቀየረው" ይላሉ። በሁለት ዓመቱ ህመም ሲሰማው ወደ ህክምና ይዘውት በሄዱበት ወቅት ነው የደም ካንሰር እንዳለበት የተነገራቸው። ህክምናውም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተጀመረ። አቶ ወንዱ እንደሚናገሩት መድሃኒቶቹ ኃገር ውስጥም ስለሌሉ ከውጭ ነበር የሚያስመጡት። ከሁለት ከሶስት ወር በኋላ ታክሞ ይድናል የሚል ተስፋን ቢሰንቁም እያገረሸበት መጣ እናም ከህክምና ማዕከሉም የተሰጣቸውም ምላሽ " ህክምናው እዚህ ሀገር የለም ውጭ አገር ይዛችሁት ሂዱ የሚል ነው" በማለት አቶ ወንዱ ይናገራሉ። በኬሞ ቴራፒው ምክንያት ማቴዎስ ስለተዳከመ አውሮፕላን ላይ መውጣት እንዳልቻለ አቶ ወንዱ ይናገራሉ። "ማቲ የተሻለ ህክምና ማግኘት እየቻለ ህክምናው ኢትዮጵያ ባለመኖሩ ብቻ አይናችን እያየ ከዚህ አለም በሞት ተለየ" ይላሉ። ህክምናው በጣም ውስብስብና አስቸጋሪ እንደነበር የሚናገሩት አቶ ወንዱ በአፉም ደም ይተፋና ተስፋ አስቆራጭም እንደነበር ነው። "ከዚህም የተነሳ ራሴን ለማጥፋት ያሰብኩበት ጊዜ ነበር" ይላሉ። ከአስራ ዓመታት በኋላ የሀገሪቱን የካንሰር የጤና ሽፋን በሚመለከቱበት ጊዜ ለውጥ እንዳለ የሚመለከቱት አቶ ወንድ በመንግሥት ደረጃ የተቋቋመው የአገር አቀፍ የካንሰር መቆጣጠሪያ እቅድ ከሁለት አመት በፊት መውጣቱ እንዲሁም ጎንደር፣ መቀሌና ጅማ ትልልቅ የካንሰር የግንባታ ማእከል እየተሰራ መሆኑ ነው። አሁንም ክፍተቶች እንዳሉ የሚናገሩት አቶ ወንዱ ከነዚህም ውስጥ መድሃኒቶች በበቂ አለመገኘት፣የባለሙያዎች ከፍተኛ እጥረትን ይጠቅሳሉ። በተለይም ከህፃናት የካንሰር ህክምና ጋር ተያይዞ ሶስት የህክምና ባለሙያዎች ብቻ እንዳሉ ይናገራሉ። አሁን በሚሰሩት ስራ ከፍተኛ እርካታ የሚሰማቸው አቶ ወንዱ "ሰው በረዳን ቁጥር ልጃችንን እንደረዳን ወይም ወደ ልጃችን እንደቀረብን ነው የምናስበው" ይላሉ። ካንሰር በኢትዮጵያ በኢትዮጵያካንሰር በርካቶችን በዋናነት ለህልፈት ከሚያበቁ ተላላፊ ያልሆኑ አራት በሽታዎች አንዱ መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ይገልፃል። በኢትዮጵያ ምዝገባ ባለመኖሩ በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ትክክለኛ ቁጥር ለማወቅ የሚያዳግት መሆኑን የሚናገሩት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የካንሰር ህክምና ስፔሻሊስቱ ዶ/ር ማቴዎስ አሰፋ ናቸው። በአዲስ አበባ ውስጥ ባለ የካንሰር ምዝገባ ወደ 8500 አዳዲስ የካንሰር ህሙማን የሚመጡ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 2/3ኛው ሴቶች መሆናቸውን ዶ/ር ማቴዎስ ይናገራሉ። ከዚህም የተነሳ የዓለም ጤና ድርጅት በየዓመቱ 60ሺ አዳዲስ የካንሰር ህመምተኞች እንደሚኖሩ መጠቆሙን ዶ/ር ማቴዎስ ጨምረው ያስረዳሉ። በሴቶች ላይ 30% የሚሆነው የጡት ካንሰር አንደኛ ደረጃን ሲይዝ፣ የማህፀን ጫፍ ካንሰር ከዚያ ቀጥሎ ደግሞ የአንጀት ካንሰር እንደሆነ ዶ/ር ማቴዎስ ለቢቢሲ ገልፀዋል። በወንዶች ላይ ደግሞ በአንደኛ ደረጃ የትልቁ አንጀት ካንሰር፣ በሁለተኛ ደረጃ የፕሮስቴት ካንሰር እና ከተለያዪ እጢዎች የሚነሱ የካንሰር አይነቶችን ይጠቀሳሉ። ዶክተር ማቴዎስ ለካንሰር ከሚያጋልጡ ጉዳዮች መካከል ብለው የሚጠቅሷቸው የእድሜ መጨመር፣ ጤናማ ያልሆነ የአኗኗር ሁኔታ ይህም ብዙ ቅባት ያለው ምግብና ስጋን መመገብ፣ ትምባሆ ማጨስ፣ መጠን ያለው አልኮል መጠጣት እንዲሁም ኢንፌክሽንና ከቫይረስ ጋር የተያያዙ ናቸው። ምንም እንኳን በሀገሪቱ ውስጥ ያለው የካንሰር ህሙማን ቁጥር በየአመቱ እየጨመረ ቢሆንም የህክምና አቅርቦቱ አመታት የሚጠበቅበትና ብዙዎች ያሰላቸ መሆኑም ይነገርለታል። የካንሰር ህክምና ተደራሽነት የህክምና ተደራሽነቱን በተለመለከተ ለዶክተር ማቴዎስ ቢቢሲ ጥያቄ አቅርቦላቸው ነበር የትኛውም ሀገር ቢሆን የካንሰር ቁጥጥር ፕሮግራም ሊኖረው ይገባል የሚሉት ባለሙያው የመጀመሪያው ቀዳሚ ነገር መከላከል እንደሆነ ይናገራሉ። " አልኮል መጠጥን መቀነስ፣ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ በአጠቃላይ የአኗኗር ዘይቤን መቀየር ዋነኛው ነገር ነው። ከዚህም በተጨማሪ ከኢንፌክሽን ጋር የተያያዙ ካንሰሮችንም መቀነስ ይቻላል። ይህም አዋጭና ብዙ ዋጋ የማይጠይቅ ነገር ነው። "በማለት ባለሙያው ይናገራሉ። ከዚህም በተጨማሪ ካንሰሩ ወደ ከፍተኛ ደረጃ ሳያድግ ቅድመ-ካንሰር ምርመራ ማድረግ ይሄም ለጡትና ለማህፀን ጫፍ ካንሰር ሳይብስ በፍጥነት ህክምና ማድረግን እንደሚያስችል ዶክተር ማቴዎስ ይናገራሉ። ከቅድመ-ምርመራ ጋርም በተያያዘ ክፍተቶች እንዳሉም ያስረዳሉ። ከፍተኛ ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ ህክምናው የተወሳሰበ እንደሆነ የሚናገሩት ዶክተር ማቴዎስ የቀዶ ጥገና፣ የጨረር፣ የሆርሞንና የኬሞ ቴራፒ ህክምና ደረጃ በደረጃ የሚሰጡና በዋጋም የማይቀመሱ መሆናቸውንም ይገልፃሉ። በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አንድ የካንሰር የህክምና ማዕከል ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ውስጥ ሲሆን ሁለት የጨረር ህክምና መስጫ ብቻ መሆኑ የህክምናው ተደራሽነት ያለውን ክፍተት ማሳያ መሆኑን ዶክተር ማቴዎስ ይናገራሉ። ከዚህም በተጨማሪ የባለሙያዎች እጥረት ሌላው ችግር እንደሆነ ይገልፃሉ። ይህንንም ሁኔታ ለማሻሻል አንዳንድ ጅምሮች እንዳሉ የሚናገሩት ዶክተር ማቴዎስ ከነዚህም ውስጥ በተለያዩ ከተሞች በአዋሳ፣ በመቀሌ፣ በጅማ፣ በሀረማያ እንዲሁም በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የካንሰር ህክምና ማዕከላት እየተገነቡ መሆናቸው ነው። የባለሙያዎችንም እጥረት ለመቅረፍ እንዲሁ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በካንሰር ህክምና ተማሪዎችንም እያሰለጠኑ ነው። በተጓዳኝም የሜዲካል ፊዚክስ፣ የጨረር ህክምና ስፔሻሊስት ትምህርቱ በሀገር ውስጥ ያልነበረ ቢሆንም በቅርቡ እንደሚጀመርም ዶክተር ማቴዎስ ይናገራሉ።
news-53523370
https://www.bbc.com/amharic/news-53523370
ቻይና በቼንግዱ የሚገኘው የአሜሪካ ቆንስላ እንዲዘጋ አዘዘች
አሜሪካ በሂውስተን የሚገኘውን የቻይና ቆንስላ እንዲዘጋ ውሳኔ ማስተላለፏን ተከትሎ፤ ቻይናም በተመሳሳይ ሁኔታ በቼንግዱ ከተማ የሚገኘውን የአሜሪካ ቆንስላ እንዲዘጋ አዛለች።
ከሁለት ቀናት በፊት አሜሪካ የቻይናን ቆንስላ ለመዝጋት መወሰኗን ይፋ ስታደርግ፤ ቤጂንግ የአሜሪካ ውሳኔ “ፖለቲካዊ ፍላጎት የታየበት” ነው ብላለች። የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ቆንስላውን ለመዝጋት የወሰንኩት “የአሜሪካን አዕምሯዊ ንብረት ለመጠበቅ ሲባል ነው” ማለቱ ይታወሳል። አሜሪካ ቆንስላው እንዲዘጋ ስለመወሰኗ የተነገረው፤ ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች በቆንስላው ቅጥር ግቢ ውስጥ ቆሻሻ መጣያ ቅርጫት ውስጥ ወረቀት ሲያቃጥሉ መታየታቸውን ተከትሎ ነው። በወቅቱ የቻይና የውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን አሜሪካ ቆንስላው እንዲዘጋ መወሰኗ “እጅጉን የሚያስቆጣ ነው፤ ለውሳኔው ትክክለኛነት መከራከሪያ ማቅረብ እንኳ አያስችልም” ካሉ በኋላ ቻይና የመልስ መት እንደምትሰጥ ተናግረው ነበር። ይህንንም ተከትሎ ቻይና የአሜሪካን ቆንስላ ለመዝጋት ወስናለች። የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከቤጂንግ መንግሥት ጋር በንግድ፣ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እና በሆንግ ኮንግ ጉዳዮች በተደጋጋሚ ሲነታረክ ይስተዋላል። በቅርቡ ድግሞ ቻይና የኮቪድ-19 ክትባት ምርምር የሚያካሂዱ ቤተ ሙከራዎች ላይ ስለላ እያደረገች ነው ሲል የአሜሪካ የፍትህ ተቋም ከሷል። በኮሮናቫይረስ ላይ የሚደረግ ምርምርን ሰልለዋል የተባሉ ሁለት ቻይናውያን ላይም ክስ ተመስርቷል። በክሱ ላይ በስም የተጠቀሱት ሁለት ግለሰቦች በአሜሪካ ኩባንያዎች ላይ ስላላ ሲያካሂዱ፤ የቻይና መንግሥት የደህንነት ተቋም ድርጋፍ አድርጎላቸዋል ተብሏል።ቻይና በበኩሏ አሜሪካ ከመሰል ተግባሯ እንድትቆጠብ ጠይቃለች።
50313540
https://www.bbc.com/amharic/50313540
ወንድማማቾች አግብተው የነበሩ ፓኪስታናውያን በጋራ ራሳቸውን አጠፉ
ፓኪስታን ውስጥ በጋራ ራሳቸውን ያጠፉ ሁለት ሴቶችን ጉዳይ ፖሊስ እየመረመረ ይገኛል።
በአገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው ድህነት የተንሰራፋባት አካባቢ ራሳቸውን ያጠፉት ናታሁ ቤይ እና ቬሩ ቤይ ከወንድማማቾች ጋር ትዳር መስርተው ነበር። ወንድማማቾቹ አርሶ አደሮች ሲሆኑ፤ የሟቾቹ አስክሬን የተገኘውም በሚኖሩበት የእርሻ መሬት ላይ ነው። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደተናገሩት፤ ወንድማማቾቹ እና ባለቤቶቻቸው የበቆሎ ምርት ለመሰብሰብ እርሻው አቅራቢያ እየኖሩ ነበር። • ፓኪስታን ክርስትያኗን ቢቢን ከእስር ለቀቀች • የአጋላጩ መረጃ የቦይንግ ኦክስጅን አቅርቦት ላይ ጥያቄ አስነሳ ሴቶቹ ለምን ራሳቸውን እንዳጠፉ እስካሁን የታወቀ ነገር ባይኖርም፤ በአካባቢው ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ቁጥር እየተበራከተ መምጣቱ ይነገራል። ታሀር የሚባለው አካባቢ በተፈጥሮ ኃብት የበለጸገ ቢሆንም፤ በፓኪስታን እጅግ ከደኸዩ ስፍራዎች አንዱ ነው። በአካባቢው ከህሪ በምትባለው መንደር ውስጥ ይኖሩ የነበሩት ናታሁ እና ቬሩ ለምን ራሳቸውን እንዳጠፉ አለማወቁን ፖሊስ ገልጿል። ካብር ካህን የተባሉ የፖሊስ ኃላፊ ወቅቱ ሰብል የሚሰበሰብበት በመሆኑ በረሀብ ምክንያት ራሳቸውን አጠፉ ማለት እንደማይቻል ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ከሥራ ጫና ወይም ቸል ከመባል ጋር የተያያዘ ሊሆንም ይችላል" ብለዋል። አስክሬናቸውን የመረመሩት ዶ/ር ፑሻ ራሜሽ፤ ሰውነታቸው ላይ ጉዳት አለመኖሩን እና መላው ቤተሰባቸው በሀዘን መሰበሩን ገልጸዋል። በሀያዎቹ መጀመሪያ ላይ ስለሚገኙት ናታሁ እና ቬሩ እምብዛም ባይታወቅም፤ ቬሩ የአንድ ዓመት ልጅ እንዳላት የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። • በግድያ የተጠረጠሩት 22 ኢንች በምትሰፋ ቀዳዳ ሾልከው አመለጡ • የሆንግ ኮንግ 'የተቃውሞ' ኬክ ከውድድር ታገደ በአካባቢው የሚኖር አላህ ጆዲዮ የተባለ ግለሰብ እንደሚለው፤ ሁለቱን ሴቶች ራሳቸውን እንዲያጠፉ የሚያስገድድ ምክንያት ነበር ወይ? ሲል ባለቤቶቻቸውን እና አባታቸውን ጠይቆ፤ ምንም የተለየ ነገር አለመከሰቱን ነግረውታል። ምናልባትም በአካባቢው ነዋሪዎች መካከል ያለ አለመግባባት ለሞት እንደዳረጋቸው አላህ ይጠረጥራል። "ኑሯችን ከእጅ ወደ አፍ ነው። ላለፉት ወራት የእርሻ መሬቱ ላይ ሲሠሩ ስለነበር አለመግባባቶች ተፈጥረው ይሆናል። ወጣቶች ስለሆኑ በንዴት ተገፋፍተው፣ ባልበሰለ አዕምሮ የወሰኑት ውሳኔ ሊሆን ይችላል" ብሏል። ዘንድሮ፤ ታሀር በሚባለው አካባቢ ቢያንስ 59 ሰዎች ራሳቸውን አጥፍተዋል። ከነዚህ 38ቱ ሴቶች፣ ሁለቱ ደግሞ ህጻናት ናቸው። በዚህ ስፍራ ባለፈው ዓመት 198 ሰዎች ራሳቸውን ማጥፋታቸውን 'አዋሬ ዶት ኦርግ' የተሰኘ ድርጅት ያወጣው መረጃ ያመለክታል። ድርጅቱ ራስ ለማጥፋት ምክንያት ያለው ድህነትና በነዳጅ ቁፋሮ ፕሮጀክት ከቤት ንብረት መፈናቀልን ነው። የመብት ተሟጋቾች በሠራተኞች መካከል የሚፈጠር እሰጣ ገባን እንደምክንያት ያስቀምጣሉ። መንግሥት አቅመ ደካሞችን የሚደጉምበት አሠራር አለመኖሩ ችግሩን እንዳባባሰውም ይገልጻሉ። ፓኪስታን ውስጥ አብላጫውን ቁጥር የሚይዙት ሙስሊሞች ሲሆኑ፤ በአካባቢው የሚኖሩት የተገለሉ ሂንዱዎች ናቸው። ከፍተኛ ቦታ የተሰጣቸው ሂንዱዎች እንዲሁም ሙስሊሙ ማኅበረሰብም ነዋሪዎቹን ያንቋሽሻቸዋል።
42389738
https://www.bbc.com/amharic/42389738
የሰሀራ በረሐን በክራች ያቋረጡት ስደተኞች
ወቅቱ ከ13 አመታት በፊት ነው።በ1970ዎቹ ለነጻነት በተካሄደዉ ትግል የዘመቱና በጦርነቱ ጊዜ አንዳንድ እግራቸዉን ያጡት አበደ ተስፋይና የማነ ጊላጋብርን ለደህንነታቸዉ በመስጋት በሕገ ወጥ መንገድ የአገራቸዉን ድንበር በክራንች አቋርጠዋል።
በከባድ ፈተናም ሱዳን መግባት ችለዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰዎች ለተሻለ የትምህርት እድል፣ ስራ እና ህይወት ይሰደዳሉ ቢልም እንኳ አብዛኛዎቹ በድህነት፣ ጦርነት፣ ግጭትና የሰብአዊ መብቶች ጥሰት፣ አለመረጋጋትና የመልካም ኣስተዳደር እጦት፣ የማህበራዊ ኣገልግሎት እጦትና ሌሎች ምክንያቶች እንደሚሰደዱ አስቀምጧል። ለነዚህ የቀድሞ ታጋዮች የተሰደዱበት ምክንያትም በሀገራቸው ነፃነት ማጣትና በፖለቲካው አለመረጋጋት ነው። በአውሮፓውያኑ 1998 እስከ 2000 በተካሄደዉና የ20 ሺ ወጣቶችን ህይወት ያስከፈለዉ የኢትዮጵያና ኤርትራ የድንበር ጦርነት በአልጀርስ የሰላም ስምምነት መጠናቀቁ የሚታወስ ነው። ጦርነቱንም ተከትሎ ሚኒስትሮች እና ጀነራሎች የሚገኙበት ከፍተኛ የመንግሥት ሃላፊዎች ህገ-መንግሥቱን ተግባራዊ ለማድረግ ማሻሻያዎችንም በአገሪቷ ውስጥ ለማካሄድ ውይይቶች ተጀመሩ። "ጉዟችንን ገምግመን አካሄዳችን እናስተካክል በሚል በ1997 በብሄራዊ ምክር ቤት ያጸደቅነዉ አቋም ተግባራዊ እናድርግ" የሚሉ ጥያቄዎችም መነሳት ጀመሩ። በወቅቱም አበደ እና የማነም ማሻሻያ መደረግ አለበት እንዲሁም ህገ-መንግሥቱ ይከበር የሚሉት ሃሳብ ደጋፊዎች ነበሩ። ምላሹ ግን የከፋ ነበር "እነዚህ ዴሞክራሲያዊ ጥያቄዎች በሃይል ተጨፈለቁ። በብዙ ተቋማትና ኃላፊነት ያሉ የመንግስት ካድሬዎችን ማደንና ማሰር ከተጀመረ በኋላ፤ ለህይወታችን በመስጋት ነዉ ያመለጥነው" በማለት ከአገራቸው የወጡበትን ምክንያት ይናገራሉ። በአውሮፓውያኑ መስከረም 2001 ዓ.ም ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችን በማሰር የተጀመረዉ ጉዳይ የዚህ ሃሳብና አመለካከት አራማጅ ናቸዉ ተብለዉ የተጠረጠሩ ሁሉ እስር ቤት ገቡ። ለነፍሱ የሰጋው ሁሉ ከዚህ ውርጅብኝ ለማምለጥ ስደትን ምርጫቸው አደረጉ ፤ በዚህም ወቅት ነው አበደ ቤተሰቡን ትቶ አቅሙ የፈቀደለትን ዝግጅት አድርጎ ለሚያውቁትም ሰዎች ሳይናገር ተደብቆ የወጣው። በእግሩ ፈታኝ የሚባለውን የኤርትራ በረሃዎችን በማቋረጥ ከስንት ድካም እና እንግልት በኋላ ከባድ የወባ በሽታን ሸምቶ ካርቱም ገባ። የማነም አንጀቱን አሰር አድርጎ የ3 ወር ህጻን ልጁን ጨምሮ ሶስት ልጆቹ እና ባለቤቱን ይዞ ስደትን ጀመረ። በአንድ እግሩም እያነከሰ፣ እየወደቀና እየተነሳ በክራንቹ ታግዞ ወደ ሱዳን ገባ። በመጀመሪያ ሃሳባቸው የነበረው ሁኔታዎች እስኪረጋጉ ሱዳን ላይ ሊቆዩ ነበር ፤ ነገር ግን ሱዳንም ላይ ከፍተኛ እክል ስለገጠማቸው ከባዱ የሰሃራ በረሃንና ባህርን አቋርጠው ለመጓዝ ወሰኑ። ሁለቱም የበረሃ ጉዟቸውን በምሬት ያስታውሳሉ።አበደ ሰዎች በሰዎች ላይ ተደራርበው ከተጫኑ ወጣቶች ጋር ነዉ የተጓዘዉ። አምስት ቤተሰቡን ይዞ የወጣዉ የማነ ደግሞ ከ10 ኤርትራዉያን ጋር እቃ መጫው ላይ ተጭኖ ነው በረሃውን ያቋረጠው። ሁለቱም ፈታኝና አሰቃቂ የሚባለውን ጉዞ ገጥሟቸዋል። በውሃ ጥም መንገድ ላይ የሞቱትን አስከሬን እያዩ ተጉዘዋል። ከ20 ዓመታት በላይ የታገሉለትም አላማ ነፃነትን ሳይሆን ለስደትና እንግልት ምንጭ መሆኑ አሳዝኗቸዋል። አጋጣሚዎቻቸው አሰቃቂ ከመሆናቸውም አንፃር ለመናገር ከባድ ናቸው። አበደ በጉዞው ላይ ብዙ ምስላቸዉ የማይለይ በዉሃ ጥም የሞቱ አስከሬኖች መሃከል የአንድ ዘመዱን መታወቂያ አግኝቷል። ይህ ክፉ አጋጣሚም ልቡን ሰብሮታል። የማነም በጉዞዉ በአንዲት የተበላሸች መኪና ዉስጥ በርካታ የሞቱ ሰዎች እንዳየ ይናገራል። አበደ የሰሃራ በረሃን ለማጠናቀቅ ሁለት ሳምንታት ሲፈጅበት ለየማነ አንድ ወር ወስዶበታል። መዘግየቱም ያጋጠመው መኪኖቹ መንገድ ላይ ስለተሰበሩ ሲሆን ከሁለቱ መኪኖች ለቅያሪ የሚሆን እቃ አዉጥተዉ ለአንደኛዋ ለመግጠም ሱዳን ስለተመለሱ ነዉ። መጨረሻ ላይ ሊቢያ ለመግባት አንድ ቀን ሲቀራቸዉ ሁለቱም መኪኖች ተሰብረዉ መንቀሳቀስ አልቻሉም። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ያኔ የመኪኖቹ መንቀሳቀስ ብቻ ሳይሆን ምግብና ነዳጅም አልቆ ነበር። አብረዋቸዉ የነበሩ አዘዋዋሪዎች መልካም ስለነበሩ መኪኖችን ለማስተካከል የተቻላቸዉን ሞክረዉ የሚረዳቸዉን ሰዉ ለማምጣት ወደ ሊቢያ አቀኑ። መንገድ ላይ ሌሎች ስደተኞች አድርሰዉ የሚመለሱ መኪኖች አግኝተዉ ሲመለሱ ገንዘብ ከፍለዉ መሄድ የሚችሉ ካሉ ብለዉ በጠየቁበት ወቅት የማነ ቤተሰቡን ይዞ ከጥቂት ስደተኞች ጋር ሊቢያ ገቡ። ሌሎቹ ግን ተስፋ ቆርጠዉ በእግር እንደሞኮሩና መንገድ ላይ እንደቀሩ የተረፉ አንድ ሁለት ሰዎች አጫውተውታል። ከዛ ሁሉ የበረሐ ጉዞ የከፋ የሚለውም አጋጣሚም የደረሰበት አንድ ቀን ጉዞው መሐል በፍተሻ ምክንያት ከመኪና አስወርደዋቸው በክራንቹ በመታገዝ 20 ኪሎ ሜትር ያክል የተጓዘውን ነው። የባህር ወጀቡ እስኪረጋጋ ሊቢያ ለአራት ወራት ያህል ከቆየ በኋላ የማይቀረውን ሁለተኛዉን ፈታኝ ጉዞ ለመጀመር ተነሳሱ። በመጀመሪያዎቹ ባህርን የማቋረጥ ጉዟቸው አልቀናቸውም። ሁለት ሶስት ጊዜም ከባህር ተመልሰዋል። ከ72 ሰዓታት ጉዞ በኋላ እና ጭንቀት በሰላም ጣልያን ገቡ። ጉዟቸውንም ቀጥለው አበደ ወደ ሆላንድ የማነ ደግሞ ስዊዘርላንድ ገቡ። ዛሬ ታህሳስ 9 በየዓመቱ በዓለም አቀፍ ዘንድ "የስደተኞች ቀን" በሚከበርበት በተለያየ ምክንያት ለተሰደዱ ህዝቦች በተለይም ከባዱ የሰሃራ በረሃንና ባህርን ተሻግረዉ የሚያርፉበት አገር የደረሱ ኤርትራውያንና ኢትዮጵያውያን በስደት ያገኙትን አጋጣሚ በኣግባቡ እንዲጠቀሙ መማር የሚችሉ እንዲማሩና ሰርተዉ ሊቀየሩ እንደሚገባ ይመክራሉ። ይሄንን ቀን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ አገራትና መንግስታት እና ተቋማት ውይይት የሚያደርጉ ሲሆን ፤ በሊቢያ በረሃ በጨረታ የተሸጡትን ስደተኞች ትኩረት እንዲሰጡና መፍትሄ እንዲተገብሩ ጥሪያቸዉን አቅርበዋል። በአውሮፓውያኑ ታህሳስ 4 2000 ዓ.ም በስደተኞች ጉዳይ የመከረዉና ታህሳስ 9 ዓለምአቀፋዊ ቀን ሆና እንድትከበር የወሰነዉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በ1990 የሰራተኞችና ቤተሰቦቻቸዉን መብት የሚከላከል ስምምነት ኣጽድቋል። እየጨመረ የመጣዉን ዓለምአቀፋዊ ስደት በጠንካራ ፖሊሲ እንዲደገፍ፣ መሰረታዊ ሰብአዊ መብቶች እንዲረጋገጡ እና ለስደተኞች የመንቀሳቀስ ነጻነት እንዲፈቀድ እና አህጉራዊና ከባቢያዊ መደጋገፍ እንዲሰፍንም 132 የድርጅቱ አባል ሃገራት የተቀበሉት ስምምት ነዉ። ይሄንንም ተግባራዊ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ባለታሪኮቻችን አፅንኦት ይሰጣሉ።
news-47867211
https://www.bbc.com/amharic/news-47867211
ከ28 ዓመታት በኋላ ለዕይታ የበቃው ኢትዮጵያዊ ተውኔት
የተውኔቱ ጭብጥ በሕክምና ተቋማት ላይ የሚታዩ ሙያዊ ደባዎች ላይ የሚያጠነጥን ሲሆን ሙያቸውን ለግል ጥቅማቸው የሚያውሉትን የሚተችና የሚያስተምር ታሪክ ነው። በአስክሬን ሽያጭ፣ በመድሃኒት አቅርቦት፣ ከአስክሬን ላይ ስለሚደረጉ ዘረፋዎች ገልጦ ያሳያል- ነቃሽ።
• "ፍቅር እስከ መቃብር"ን በአይፎን 7? ነቃሽ በዮሐንስ ብርሐኑ ተደርሶ ለዕይታ የበቃው ከዛሬ 28 ዓመታት በፊት በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የባህልና ቲያትር አዳራሽ ነበር። ይህ ተውኔት ከዓመታት በኋላ በተስፋ የኪነጥበብ ኢንተርፕራይዝ በአርቲስት ተፈራ ወርቁ አዘጋጅነት ዳግም ለዕይታ በቅቷል። በአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑት አቶ የማነ ታዬ ተውኔቱን የተመለከቱት በሃያዎቹ መጀመሪያ የዕድሜ ክልል ላይ እያሉ በአንድ ጓደኛቸው ጋባዥነት ነበር። "በወቅቱ ከፍተኛ ተወዳጅነት ነበረው" የሚሉት አቶ የማነ በአዲስ አበባ ማዘጋጃ የነበረውን ረጅም ሰልፍ ተቋቁመው እንዳዩት ያስታውሳሉ። ከተውኔቱ በተለይ አልአዛር ሳሙኤል የተጫወተው እኩይ ገፀ ባህሪ (ሊቀረድ) ከአዕምሯቸው አልጠፋም። "ከአስክሬን ላይ የወርቅ ጥርሶችን የሚሰርቅ ገፀባህሪ ነበር እና በዚያ ዘመንና እድሜ እንዲህ ዓይነት ነገር ይፈጠራል ብዬ ስለማላምን በአግራሞት በአዕምሮዬ ተቀርፆ ቀርቷል" ይላሉ። አሁንም ተውኔቱ በድጋሚ በመቅረቡ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው በድጋሜ ለማየት እንደጓጉ ነግረውናል። ዓመታትን ያስቆጠሩ ተውኔቶች ተመልሰው ለተመልካች ዕይታ ሲበቁ እንዲሁም ተመልካች ኖረውም አልኖረውም ለዓመታት ከመድረክ ሳይወርዱ የሚቆዩበት አጋጣሚ ይስተዋላል። ለዚህም የተውኔት ጸሐፊዎች ብዕር ነጥፏል፣ ገንዘብ ወዳድ ስለሆኑ የተሻለ ገንዘብ የሚያስገኝላቸውን ፊልም ይመርጣሉ፣ የቀደሙትን ቲያትሮች በብስለትም በሃሳብም የሚስተካከላቸው ስለሌለ ተደጋግመው ቢታዩም ይወደዳሉ፤ የሚሉ የተለያዩ አስተያየቶችን የሚሰጡ በርካቶች ናቸው። • ትንሳኤን "አድማቂ" ገጣሚያን በእነዚህ ሃሳቦች መካከል ባቢሎን በሳሎን፣ የጠለቀች ጀምበር የሚሉና ሌሎች ተውኔቶችም በድጋሚ ለተመልካች ቀርበዋል። 'አሉ' የተሰኘ ትርጉም ተውኔትም ከ20 ዓመታት በኋላ በድጋሚ ሊወጣ መሆኑን ሰምተናል። በቅርቡ በሀገር ፍቅር ቲያትር የተከፈተው 'ነቃሽ' ተውኔትም አንዱ ሆኗል። "ነቃሽ በወቅቱ እንደ ሼክስፔር ሥራዎች ያህል ተወዳጅ ስለነበር ከወቅቱ ጋር አስማምተን በድጋሚ ለዕይታ እንዲበቃ ሆኗል" የሚለው አዘጋጁ፣ በተውኔቱ ላይ ከዛሬ 28 ዓመታት በፊት ከተወኑት ተዋናዮች ሁለቱ አሁንም የቀደመውን ገፀ ባህሪያቸውን ወክለው ተጫውተዋል- አልአዛር ሳሙዔልና ፋንቱ ማንዶዬ። በድጋሜ በተውኔቱ ላይ የመተወን ዕድሉን ያገኘው አርቲስት ፋንቱ ማንዶዬ ቲያትሩን በድጋሚ ለመጫወት ጥያቄ ሲቀርብለት ደስታው ወደር አልነበረውም። "በዚያን ጊዜም ሲሰራ ወቅቱን የጠበቀ ቲያትር ነበር፤ አሁንም ተሻሽሎ በመቅረቡ ተመልካች ይወደዋል" ይላል የቀደመውን በማስታወስ። እርሱ እንደሚለው የድርሰቱ ሃሳብ ዘመን የሚሽረው አይደለም፤ በተለይ የተነሳው የህክምናው ዘርፍ ከመድሃኒት አቅርቦት ጋር በተየያዘ የሚሰሩ ደባዎችን የሚያጋልጥና ለመንግስት አቅጣጫ የሚያሲዝ ነው። በተውኔቱ ላይ የሆስፒታሉ የጥበቃ ክፍል ሆኖ የሚተውነው አርቲስት ፋንቱ አሁንም ተመሳሳይ ገፀ ባህሪይ ይዞ ይጫወታል። 28 ዓመታት ወደ ኋላ ተጉዘው ቃለ ተውኔቱን ሙሉ በሙሉ ባያስታውስም ዋናውን ገፀ ባህሪ ውድነህን በተመለከተ "ውድነህ ለድሃ ገንዘቡን የሚሰጥ እንጂ እሱ ከድሃ አይዘርፍም" የሚለውን ንግግር አይረሳውም። • ዳንስን በሁለተኛ ዲግሪ • “ከወጡት ስራዎቼ ይልቅ ገና የሚወጡት ናቸው ትልቅ ቦታ ያላቸው” አለማየሁ ገላጋይ አርቲስት ፋንቱ ተውኔቶች በድጋሜ ወደ መድረክ መምጣታቸው መልካም ቢሆንም ደራሲያን ወደ ፊልሙ ማዘንበላቸው ግን አዳዲስ ተውኔቶች እንዳይቀርቡ እንደ አንድ ምክንያት ያነሳል። የቀደሙት አንጋፋና ዘመን አይሽሬ ድርሰቶችን የሚያበረክቱት አንጋፋ ደራሲያን ዛሬ በሕይወት አለመኖራቸውም ሌላኛው ተያያዥ ምክንያቱ ነው። "እኛ በፊት የምንሰራውም፣ የምንተውነውም ፤ በአብዛኛው ህዝቡ እንዲያይልን ፣ እንዲወድልን ፣ እንዲያጨበጭብልን ነው" የሚለው አርቲስቱ ትምህርት ለኑሮ፤ ሙዚቃ ለአዕምሮ በሚል በነፃ ሜዳው ላይ የሚያቀርቡት ዝግጅት እንደነበር ያስታውሳሉ። ዘመኑ ያለ ገንዘብ ለመኖር አዳጋች ቢሆንም፣ ሁሉ ነገር ወደ ገንዘብ መቀየር አለበት ማለቱ ተገቢ እንዳልሆነ ያሰመረበት ጉዳይ ነው። አርቲስት አልአዛር ሳሙዔልም ከዚህ የተለየ ሃሳብ የለውም። "ተውኔቱ በድጋሚ እንዲመጣ ፍላጎቱ ነበረኝ" የሚለው አልዓዛር አሁንም አዳዲስ ተውኔቶች እየተፃፉ ነው የሚል አቋም አለው። ነቃሽ በዛን ጊዜ የነበረውን የተውኔት ተመልካችን ፍላጎት ያሟላ ስለነበር አሁንም ያንን በድጋሚ ማሳየቱ ጥሩ ነው" ይላል። የቆዩ ተውኔቶች ለምን በድጋሜ ይመጣሉ? የተውኔቱ አዘጋጅ አርቲስት ተፈራ ወርቁ በተለያየ ጊዜ በአዘጋጃቸው ተውኔቶች በመጠይቅ ከተሰበሰቡ የተመልካች ምርጫ ውስጥ አንዱ ነቃሽ ሆኖ በማግኘታቸው በድጋሚ እንደተዘጋጀ ይናገራል። አዘጋጁ እንደሚለው እነዚህ ተመልካቾች ተውኔትን በቋሚነት የሚያዩ ሲሆን ዕድሜያቸው ከ28 እስከ 45 የሚገመቱ ናቸው ብሏል። "አሁንም አዳዲስ ተውኔቶች ይወጣሉ፤ ነገር ግን የድሮዎቹም በድጋሚ መሰራታቸው ያላየው ትውልድ እንዲመለከተው ዕድል የሚሰጥ ነው" የሚለው አዘጋጁ አዳዲስ ተውኔቶች ቢፃፉና ለዕይታ ቢበቁ ምርጫው እንደሆነ ይናገራል። ይሁን እንጂ አንዳንድ ተውኔቶች ለዓመታት መድረክ ተፈናጠው የሚቆዩበትን ምክንያቶች የተውኔት ፅሁፍ አለማግኘት፣ ደራሲዎች ከሚያገኙት ክፍያ ጋር በተያያዘ ከተውኔት ይልቅ ፊልምን መምረጣቸውና ከተውኔት መሸሻቸውን ከብዙ በጥቂቱ ይዘረዝራል። የተውኔት ዘርፉ ከድርሰት ጋር በተያያዘ ካለበት ፈተና በተጨማሪ ሌሎች በርካታ ተግዳሮቶችን እንደሚያስተናግድም ተደጋግሞ ይነሳል። "አበረታች አይደለም፤ ለባለሙያዎች ጥሩ ክፍያ መክፈል አልተቻለም፤ ቢሮክራሲው፣ የትኬት ቀረጥ፣ የመግቢያ ዋጋ አነስተኛ (30 /40ብር) መሆኑ ኢንዱስትሪውን ቁልቁል እንዲሄድ አድርጎታል" ሲል ያስረዳል። በተለይ በግል ተውኔትን ለሚያቀርቡት ፈተናው ያይላል። "ፊልሞች በተውኔት ላይ ተፅእኖ አሳድረው ነበር፤ አሁን ግን እየተመለሰ ነው" የሚለው አርቲስት አልአዛር፤ ለዚህም የቀደመው ትውልድ የሚያስታውሰውን መድገሙ አስተዋፅኦ ሳይኖረው አይቀርም ይላል። በመሆኑም የቀደሙት ተውኔቶች ድጋሚ መቅረባቸው ሊበረታታ እንደሚገባ ይናገራል። ነቃሽ ተውኔት ዘወትር ማክሰኞ ከ11፡00 ሰዓት ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት ከትናንት ሚያዚያ 1/2011 ዓ.ም መታየት ጀምሯል።
news-41330382
https://www.bbc.com/amharic/news-41330382
ትራምፕ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያደረጉት የመጀመሪያ ንግግር ትችት ገጠመው
ዶናልድ ትራምፕ ለመጀመሪያ ጊዜ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተገኝተው ያደረጉት ንግግር ከተለያዩ ሃገራት ትችት ገጥሞታል።
በተለይ የትራምፕ ትችት የደረሰባቸው ሃገራት የፕሬዝዳንቱን ንግግር ተገቢ ያልሆነ ሲሉ ወቀሳ አቅርበዋል። ዶናልድ ትራምፕ ኢራንን "አነስተኛ ቁጥር ካላቸው በጥባጭ ሃገራት አንዷ" ሲሏት፤ አሜሪካ ተገዳ ወደ ጦርነት ከገባች ሰሜን ኮሪያን "ሙሉ ለሙሉ ታጠፋለች" ብለዋል። የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር የትራምፕ የማንአለበኝነት ንግግር ኋላ ቀር በሆነው ዘመን የሚደረግ እንጂ በተባበሩት መንግስታት መሆን እንደሌለበት ጠቁመዋል። ለዜጎቻቸው ህይወት መሻሻል የሚጥሩ ሉዓላዊ ሃገራትን በመፍጠር ዙሪያ ያተኩራል በተባለው ንግግራቸው ትራምፕ አብዛኛውን ጊዜ ዓለም አሁን ላለችበት ችግር መንገድ ከፍተዋል ባሏቸው "በጥባጭ ሃገራት" ዙሪያ ትኩረት አድርገዋል። አሜሪካ ከተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ውሳኔ በተቃራኒ የሚሳኤል ሙከራ የምታደርገውን ሰሜን ኮሪያ ስታስጠነቅቅ ቆይታለች። "የሚሳኤሉ ሰው ራሱን በማጥፋት ተልዕኮ ላይ ነው" ሲሉ ትራምፕ የሰሜን ኮሪያውን መሪ ኪም ጆንግ ኡንን ተችተዋል። "አሜሪካ ራሷን ወይንም አጋሮቿን ለመከላከል ከተገደደች ሰሜን ኮሪያን ሙሉ ለሙሉ ከማጥፋት ውጭ አማራጭ የላትም" ብለዋል። የእስራኤል፣ ሶሪያ፣ ኢራንና ሳዑዲ አረቢያ ተወካዮች የትራምፕን ንግግር ሲሰሙ አንድ የስብሰባው ተሳታፊ ፊቱን በእጆቹ ሸፍኖ በማጉረምረም ምላሽ ሰጠ ሲል ሬውተርስ ዘግቧል። የስዊዲን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማርጎት ዋልስቶርም "ተገቢ ላልሆነ ተሳታፊ፥ ተገቢ ባልሆነ ጊዜ የተደረገ ተገቢ ያልሆነ ንግግር" ሲሉ ለቢቢሲ አስረድተዋል። ኢራን "በዴሞክራሲ ሽፋን በሙስና የተጨማለቀች አምባገነን" ነች ካሉ በኋላ "የብጥብጥ፥ ደም መፋሰስ እና የረብሻ ዋና መሠረት ናት" ሲሉ ትራምፕ ተናግረዋል። ትራምፕ በንግግራቸው "የሶሻሊዝም አምባገነን" ናት ያሏትን ቬንዙዌላን እርምጃ ሊወስዱባት እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል። ቬንዙዌላ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሆርጌ አሪዬዛ "ማስፈራሪያ" ያሉትን ንግግር አጣጥለዋል። "ትራምፕ የዓለም ፕሬዝዳንት አይደለም። የራሱን መንግስት አንኳን ማስተዳደር አቅቶታል" ሲሉ የቬንዙዌላ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ገልጸዋል።
news-54430779
https://www.bbc.com/amharic/news-54430779
ኮሮናቫይረስ ፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመንገደኞቹ የኮቪድ-19 ኢንሹራንስ ሽፋን ጀመረ
በአፍሪካ ትልቁና ፈር ቀዳጅ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመንገደኞቹ የኮቪድ-19 ኢንሹራንስ ከመስከረም 21/2013 ዓ.ም መጀመሩን አስታውቋል።
የኢንሹራንስ ሽፋኑ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሚጓዙ ዓለም አቀፍ መንገደኞች በሙሉ ሲሆን፤ መንገደኞችን መመለስ፣ ለይቶ ማቆያና ሌሎችም የህክምና ወጪዎችን እንደሚሸፍን አየር መንገዱ ባወጣው መግለጫ አስፍሯል። 'ሼባ ኮምፎርት' የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ኢንሹራንስ መንገደኞች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተሳፍረው በጉዟቸው ወቅት በኮቪድ-19 ቢያዙ የህክምና ወጪያቸው እስከ አንድ መቶ ሺህ ዩሮ ድረስ ይሸፈንላቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ ለለይቶ ማቆያም በየቀኑ 150 ዩሮ፣ ለአስራ ቀናትም ያህል እንደሚሸፈንላቸው ከአየር መንገዱ የተገኘው መረጃ ያስረዳል። አየር መንገዱ የመንገደኞቹን ጤናና ደኅንነት ለመጠበቅና ያለምንም ሃሳብ በሰላም እንዲጓዙ ለማድረግም ይህንን የኢንሹራንስ ሽፋን መጀመሩን አስታውቋል። ዓለም አቀፉ የኢንሹራንስ ሽፋኑንም በተመለከተ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተወልደ ገብረ ማርያም እንዳሉት "በዓለም ላይ ጥብቅ የደኅንነት መከላከያን በማስተወቅ ቀዳሚ ከሆኑት አየር መንገዶች አንዱ በመሆኑ ደስተኞች ነን። የኮቪድ-19 ዓለም አቀፉን ኢንሹራንስ ሽፋን በመስጠት የመንገደኞቻችንም በራስ መተማመንን እንጨምራለን" ማለታቸውንም መግለጫው አስፍሯል። በአሁኑ ወቅት ከኮሮናቫይረስ ስጋት ጋር ተያይዞም የመንገደኞች ደኅንነት ስጋት በሆነበትም ወቅት አየር መንገዱ አስፈላጊውን ለውጦች በማካሄድ የመንገደኞች ደኅንነትን ማስጠበቅ ዋናና ቀዳሚ ተግባሩ መሆኑንም አሳውቋል። ሼባ ኮምፎርት ኢንሹራንስ ከአክሳ ፓርትነርና አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ ጋር በመጣመር ሽፋኑን የሚሰጥ ሲሆን፤ ኢንሹራንሱም ለደርሶ መልስ ቲኬት ለ92 ቀናት አንድ ጉዞ 31 ቀናትን የሚሸፍን ይሆናል። ይህ አየር መንገዱ ለተጓዞቹ ያቀረበው ኢንሹራንሱ ሽፋንም ከመስከረም 21/2013 ዓ.ም እስከ መጋቢት ድረስ የሚቆይ ይሆናል። የኮሮናቫይረስ ክፉኛ ከጎዳቸው ዘርፎች መካከል የአየር ትራንስፖርት አንዱ ሲሆን፤ በዓለም ዙሪያ ያሉ በርካታ አየር መንገዶች ሠራተኞቻቸውን ከመቀነስ አንስቶ ከበረራ ውጪ አስኪሆኑ ድረስ ጉዳት አድርሷል። በአፍሪካ ውስጥ የሚገኙ አየር መንገዶች ባለፉት ስድስት ወራት ቀውስ ውስጥ የገቡና ሥራ ለማቆም የተገደዱ ያሉ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን ጭነቶችን በማመላለስ አስቸጋሪውን ጊዜ ለማለፍ እንደቻለ ተነግረዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አገራት ለአየር ትራንስፖርት በራቸውን እከፈቱ ቢሆንም የኮሮናቫይረስ ስጋት የፈጠረው ተጽእኖ እስካሁን አልተቃለለም።
news-42631640
https://www.bbc.com/amharic/news-42631640
ከእስራኤል የሚባረሩ ስደተኞች ለአደጋ እየተጋለጡ ነው
ከእስራኤል የተባረሩ ስደተኞች ወደ አውሮፓ ለመግባት ሲሉ ህይወታቸውን አደጋ ላይ እየጣሉ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን አስጠነቀቀ።
አንዳንድ ስደተኞች ከእስራኤል ባገኙት ገንዘብ ወደ አውሮፓ ለመሻገር እየሞከሩ ነው እንደኮሚሽኑ ገለፃ ከሆነ ሮም ላይ ካነጋገራቸው 80 ኤርትራዊን መካከል አብዛኛዎቹ የመካከለኛዋ ምሥራቅ ሃገርን ለመልቀቅ ከእስራኤል መንግሥት የሚሰጠውን ገንዘብ ተጠቅመው በሰሜን አፍሪካ በኩል ወደ አውሮፓ አደገኛ የሚባለውን ጉዞ አድርገዋል። ስደተኞቹ 3500 ዶላር ተሰጥቷቸው ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ወይም ወደተስማሙበት ሶስተኛ ሃገር እንዲሻገሩ ይደረጋል። ሆኖም አብዛኛዎቹ ወደ ሰሜን በማቅናት በሊቢያ በኩል ወደ አውሮፓ ለመግባት ሜድትራኒያንን ያቋርጣሉ። በጉዟቸው ወቅትም ሁሉም መጎሳቆል፣ እንግልትና ማስፈራሪያ እንደደረሰባቸው የኮሚሽኑ መግለጫ አመልክቷል። እስራኤል በዕቅዷ መሠረት አብዛኛዎቹ ከኤርትራ እና ከሱዳን የሆኑትን ከ30 ሺህ በላይ ስደተኞችን አስገድዳ ከሀገር እንዲወጡ የምታደርግ ከሆነ ብዙዎች ህይወታቸውን አደጋ ላይ ሊጥሉ ይችላሉ ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስጠንቅቋል። ሁሉም ስደተኞች እስከመጪው ሚያዝያ ድረስ ሃገሪቱን ለቀው የማይወጡ ከሆነ እስር እንደሚጠብቃቸው እስራኤል ባለፈው ሳምንት ገልጻለች። እስራኤል "ኤርትራዊያንና ሱዳናዊያንን ከሰሃራ በታች ወደሚገኙ የአፍሪካ ሃገራት የማስፈር ፖሊሲዋን እንድታቆም" ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል። ዕቅዱ"ወጥነት" የሌለው እና ግልጽ ያለሆነ ነው ያሉት የተባበሩት መንግሥታት ስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ዊሊያም ስፒንድለር፤ እስራኤል ሌላ መፍትሔ እንድታቀርብም ጠይቀዋል።
news-46176349
https://www.bbc.com/amharic/news-46176349
የጣና ቂርቆስ ገዳም መነኮሳትና መናኞች በእምቦጭ ምክንያት ገዳሙን ለቀው እየወጡ ነው
በደቡብ ጎንደር ዞን ገደራ ወረዳ የሚገኘውና ከጣና ገዳማት አንዱ የሆነው የጣና ቂርቆስ ገዳም መነኮሳት በእምቦጭ አረም ምክንያት ገዳሙን ለቀው እየወጡ ነው።
ከመነኮሳቱ አንዱ የሆኑት አባ ወልደመድህን ገ/ማሪያም እምቦጭ በገዳሙ ላይ ፈተና ሆኗል ይላሉ። • የጣና ዕጣ ፈንታ ለገዳማቱ መነኮሳት አሳሳቢ ሆኗል • ጣና ሐይቅ የተጋረጡበት ፈተናዎች "መነኮሳት ከመንፈሳዊ ስራቸው ውጭ ለተግባረ ስጋቸው ስራ ይሰራሉ፤ ነገር ግን እምቦጩ ለስራቸው ተግዳሮት ሆኖባቸዋል" የሚሉት አባ ወልደመድህን የገዳሙን ጀልባም ለስራ እንዳይንቀሳቀስ አድርጎታል፤ እንስሳትን ለማደለብ የሚጠቀሙበትን ሳር ይዞታል፤ ገዳሙ እንዳይጎበኝም እንቅፋት ሆኗል ይላሉ። ገዳሙ ከባህር ዳር ከተማ በጀልባ ሶስት ሰዓት ያስጉዛል። አሁን ግን ጀልባው መጠጋት ባለመቻሉ በእግራቸው ሊጓዙ ግድ ሆኗል። በተለይ የገዳሙ የእርሻ መሬት በአረሙ በመወረሩ ላለፉት ዓመታት ችግር ላይ እንደነበሩና ባለፈው ዓመት አሜሪካ አገር በሚኖሩ ግለሰቦች እርዳታ አረሙ ተለቅሞ አልቆ እንደነበር ያስታውሳሉ። ይሁን እንጂ በማዕበል ተገፍቶ ከሌላ አካባቢ የሚመጣው አረም እንደገና መዛመት እንደጀመረ ይገልፃሉ። መነኮሳቱ ገዳሙን ለቀው እየወጡ ነው የሚባለው የማይመስል ነው የሚሉት አባ ወ/መድህን የእርሻ መሬታቸው በአረሙ በመያዙ ከምዕመናኑ በምፅዋት የሚመጣ ምግብን እየተቃመሱ መቆየታቸውን ግን ተናግረዋል። "ቅርስ ጠባቂ ነን፤ እርዱን ብለን እንማፃናለን እንጂ ፈተና ሲመጣ ጥሎ መውጣት አይቻልም። ለማን አስረክበን ነው ጥለን የምንወጣው?" ሲሉ ይጠይቃሉ። የገዳሙ አስተዳዳሪ (አበምኔት) አባ ገብረፃድቅ ወልደቂርቆስ ግን የገዳሙ መውጫ መግቢያም በአረሙ መያዙን፣ ጎብኝዎች ገዳሙን ለመጎብኘት እንዳልቻሉና በተለይ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ መነኮሳቱ ሰብል ማምረት እንዳልቻሉ ጠቅሰው በእምቦጩ ምክንያት ገደሙን ለቀው የወጡ እንዳሉ ይናገራሉ። ለገዳሙ ዕቃ የጫነች ጀልባ በእንቦጩ አረም በመያዟ ተገፍታ መውጣቷ ለገዳሙ አስተዳዳሪ የቅርብ ጊዜ ትውስታቸው ነው። • የጣና ሐይቅን ሌሎችም አረሞች ያሰጉታል •"ቀጣዩን ምርጫ ከዳር ሆኜ ባልታዘብም ተወዳዳሪ ግን አልሆንም" ብርቱካን ሚደቅሳ በገዳሙ የሚገኘው መንፈሳዊ ጉባዔ አባላት የገዳሙ መነኮሳት የሚያመርቱትን ይመገቡ እንደነበርና ጉባዔው በእምቦጩ ምክንያት መበተኑንም ለንግግራቸው ዋቢ ያደርጋሉ። ቤተክርስቲያኑ ውስጥ አገልግሎት የሚሰጡ ካህናትም እየወጡ መሄዳቸውን አስተዳዳሪው (አበምኔቱ) ለቢቢሲ ገልፀዋል። "መነኮሳት ብንሆንም በቀን አንድ ጊዜ ምግብ ያስፈልጋል፤ የጣፈጠም ባይሆን፣ ሆድም የሚሞላ ባይሆን ፤ ዋና ዓላማው ፀሎት፣ ምናኔና ታሪኩን ለትውልድ ማስተላለፍ ቢሆንም ይህን ለማድረግ ምግብ ማስፈለጉ አያጠያይቅም" ይላሉ። ነገር ግን ከሁለት ዓመታት ወዲህ ገዳሙ ምንም ማምረት ባለመቻሉ እስካሁን በምዕመናን ድጋፍ እንደቆሙ ያስረዳሉ። "ርሃቡንና ጥሙን ተቋቁሞ የሚቆይ እንዳለ ሁሉ አልችል ብለው የሚወጡም አሉ" የሚሉት አስተዳዳሪው (አበምኔቱ)፤ በሌላም በኩል የገዳሙንና የሐይቁን ፈተና ላለማየት፣ እንዲሁም ከግለሰብም ሆነ ከመንግስትም የሚደርስላቸው ሲያጡ በብስጭት ጥለው የሄዱ እንዳሉ ይናገራሉ። በዚህም ምክንያት የመነኮሳትና የመናኞች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱንም ያስረግጣሉ። ለነፍስ ያደሩ መነኮሳትና መናኞች በእምቦጭ ምክንያት ገዳሙን ጥለው እየወጡ መሆናቸው ከመንፈሳዊነቱ ጋር አይቃረንም ወይ ያልናቸው አባ ገ/ፃድቅ "መነኮሳቱ ለፈጣሪ አላድር ብለው ፤ ስጋችን ጎደለብን ብለው እየሸሹ አይደለም" ይላሉ። እርሳቸው እንደሚሉት እየሸሹ ያሉት ወደ ከተማ አሊያም የተሻለ ነገር ፍለጋ ሳይሆን በርሃ ነው። • በኦሮሚያ እና ሶማሌ አዋሳኝ ድንበር ላይ የጅምላ መቃብር ተገኘ • የሴት ልጅ ግርዛት በማይታመን መልኩ ቀነሰ በመንፈሳዊ ሕይወትም ቢሆን ቁጭት አለ የሚሉት አስተዳዳሪው "ከብዝሃ ሕይወትነቱ ባሻገር የጣና ሐይቅ እነ አቡነ ሰላማ፣ ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ፣ ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ የፀለዩበትና ብዙዎችን የፈወሱበት፣ ብዙ አራዊቶች በውስጡ የሚገኙበት፣ በርካታ ሰዎች ጥማቸውን የሚቆርጡበት ነው ብሎ በማሰብ ቁጭት አድሮባቸዋል" ሲሉ ያብራራሉ። ቁጭቱ ለሌላውም ሰው የሚሰማው ቢሆንም በተለይ መሃል ሃይቁ ላይ ለሚገኙት ለእነሱ ይብሳል። አረሙ የገዳሙን ይዞታ ሙሉ በሙሉ ወሮታል፤ በግምት 6 ሄክታር የሚሆነውን የእርሻ መሬትም ሸፍኖታል ይላሉ -አባ ገብረፃድቅ። ገዳሙ ከሁለት ዓመታት በፊት አባቶችና እናቶች እንዲሁም የመንፈሳዊ ጉባዔ ተማሪዎችን ጨምሮ 200 መናኞች ይገኙበት የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ግን ቁጥራቸው ቀንሶ 165 መነኮሳት እንደሚገኙ አስተዳዳሪው ተናግረዋል።
news-52229256
https://www.bbc.com/amharic/news-52229256
ኮሮናቫይረስ፡ የፈረንጆቹ በጋ የቫይረሱን ሥርጭት ይገታው ይሆን?
ኮቪድ-19 የጀመረ ሰሞን ይሄ ቫይረስ ሙቀት አይስማማውም ሲባል ነበር። ከጤና አማካሪዎቻቸውም በላይ በኅብረተሰብ ጤና ጉዳይ እንደ ሳይንቲስት የሚያደርጋቸው ዶናልድ ትራምፕ እንዲያውም "በጋ ይግባ እንጂ ሙቀት ቫይረሱን አፈር ድሜ ያበላዋል" ሲሉ ነበር።
እውን የቫይረሱ ሥርጭት በሙቀት ወራት ይገታ ይሆን? ሳይንቲስቶች ይህን ጥያቄ አፍ ሞልቶ ለመመለስ ጊዜው ገና ነው ይላሉ። ይህ ቫይረስ ወቅት ይመርጣል አይመርጥም ጥናት ይሻል። ጥናቱን ለማድረግ ገና ወቅቶቹ ራሳቸው አልገቡም፤ በተለይ በአንድ አካባቢ በተለያየ ወቅት ኮቪድ-19 ምን የተለየ ባህሪ አለው የሚለውን ለማጥናት። ምልክቶችን ለማየትም በተለያዩ አካባቢዎች በሽታው ያሳየው ባሕሪ በስፋት መጠናት ይኖርበታል። ይህ ማለት ግን እስካሁን በዚህ ረገድ የተገኙ ምንም መረጃዎች የሉም ማለት አይደለም። አንጀት የሚያርሱ ባይሆኑም ኮቪድ-19 ለቀዝቃዛና ደረቅ አየር እጅ እንደማይሰጥ ከወዲሁ ምልክቶች ታይተዋል። አንድ ጥናት አማካይ ሙቀታቸው ዝቅ ያሉ አካባቢዎች ቫይረሱ ሥርጭቱ ብርቱ እንደነበር አመላክቷል። ሌላ የጥናት ወረቀት ደግሞ በመቶ የቻይና ከተሞች የቫይረሱን ባህሪ የተመለከተ ሆኖ ውጤቱም ከፍተኛ የአየር ሙቀትና የእርጥበት መጠን (ሂሙዩዲቲ) ያለባቸው ቦታዎች ሥርጭቱ አዝጋሚ ሆኖ ታይቷል። ተጨማሪ የጥናት ወረቀት (ምንም እንኳ ይህኛው ጥናት የተጓዳኝ ባለሞያ ግምገማ ገና ያልተደረገበት ቢሆንም) የሚከለተውን የድምዳሜ አንቀጽ ይዟል። "ኮቪድ-19 በሁሉም የዓለም ክፍል በተለያዩ የአየር ጠባዮች መሠራጨቱ እሙን ቢሆንም ቀዝቃዛና ደረቅ የአየር ሁኔታ ባለባቸው ቦታዎች ግስጋሴው ኃያል ነበር።" እርግጥ ነው የስርጭት ፍጥነቱና ስፋቱ ቢለያይም ኮቪድ እስካሁን ባሳየው ጉልበት በየትኛውም የወበቅ/እርጥበት (ሂይሙዩዲቲ) ሁኔታ፣ በየትኛውም የአየር ንብረትና በየትኛውም የዓለም ክፍል ከሰው ወደ ሰው መተላለፍ እንደሚችል ተረጋግጧል። በሌላ ቋንቋ ቫይረሱን ይህ የአየር ንብረት ይበግረዋል፤ አይበግረውም የሚለው ጉንጭ አልፋ ክርክር ነው የሚሆነው። ለጊዜው ቫይረሱንና የአየር ንብረትን ጉዳይ አድርገን ስናወራ የምናወራው ስለ ሥርጭት ፍጥነት ብቻ የሚሆነውም ለዚሁ ነው። በሰሜንና በደቡብ እኩል አይሰራጭ ይሆን? ጉንፋንን ጨምሮ በርካታ የቫይረስ በሽታዎች በሰሜንና በደቡብ ንፍቀ ክበብ እኩል የሥርጭት መልክና ባህሪ እንደሌላቸው ከዚህ ቀደም የተረጋገጠ ጉዳይ ነው። ነገር ግን በምድር ወገብ አካባቢ ያሉትና በተለይም ቆላማ አካባቢዎች ከሌሎች የትሮፒካል አየር ከሌላቸው አካባቢዎች ተመሳሳይ የሥርጭት መልክ ኖሯቸው አያውቅም። ያም ሆኖ እንደ ማሌዢያና ዲሞክራቲክ ኮንጎ ያሉ በምድር ወገብ ቀበቶ ሥር ያሉ አገራት ሞቃትና ወበቃማ-እርጥበት አዘል አየር ቢኖራቸውም ኮቪድ-19 ደፍሯቸዋል። የስርጭት መጠናቸው ስለሚለያይ ሁለቱ አገራትን ብቻ ወስዶ ድምዳሜ ላይ መድረስ ያዳግታል። ወደ ደቡብ ንፍቀ ክበብ ስናማትር የምናገኘው አውስትራሊያንና ኒውዚላንድን ነው። ቫይረሱ ሲገባ እነሱ የበጋ ወራቸውን በማገባደድ ላይ ነበሩ። በዚያ ወቅት ከሰሜኑ ንፍቀ ክበብ በተነጻጻሪ በኒውዚላንድ እና አውስትራሊያ አካባቢ የወረርሽኙ ሥርጭት የተገደበ ነበር ማለት ይቻላል። ነገር ግን የአየር ንብረትና የአገሮቹ መገኛ ብቻውን ሁሉን ነገር አይወስንም። ለምሳሌ ወደዚያ አገር የገቡ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ብዛትና የሰዎች የጥግግት መጠን፣ እንዲሁም የአኗኗር ሁኔታ፣ የጤና አጠባበቅ ወዘተ ወሳኝ ነገሮች ናቸው። በተለይም ቫይረሱ ሰዎች ከአገር አገር እየተዘዋወሩ ስላሰራጩት የአየር ንብረት ከቫይረሱ ጋር ያለውን ተዛምዶ ነጥሎ ለማጥናት ፈታኝ ያደርገዋል። ከዚህ ቀደም የነበሩ ቫይረሶች ባሕሪ ምን ያሳያል? ኮሮናቫይረስ የቫይረሶች የወል ስም ነው። ኮቪድ-19 በሽታው ነው። ይህንን በሽታ የሚያመጣው ደግሞ ሳርስ-ኮቭ-2 የተባለ ቫይረስ ነው። ኮቪድ-19 ከነሳርስ እና ሜርስ ጋር ተቀራራቢ ባህሪ ያለው ቫይረስ ነው። እነዚያ የኮሮናቫይረስ አባላት ያሳዩት ባህሪ ስለ ኮቪድ-19 የሚነግረን ነገር ይኖር ይሆናል። የለንደን ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ሳይንቲስቶች ከዚህ ቀደም የተከሰቱ ኮሮናቫይረሶች በክረምት ስርጭታቸው ከፍተኛ እንደነበር ደርሰውበታል። ከ2 ሺህ በላይ ሰዎችን ባካተተው በዚህ ጥናታቸው ከጉሮሮ በሚወሰድ ናሙና የደረሱበት ነገር ቢኖር ኮቪድ-19 ከመከሰቱ በፊት በነበሩ ኮሮናቫይረሶች የበሽታው የክረምት ስርጭት ከበጋው በእጅጉ የፈጠነ እንደሆነ አውቀዋል። ከሳይንቲስቶቹ አንዷ ኤለን ፍርንጋዚ እንደምትለው ከዚህ በመነሳት ኮቪድ-19 በበጋው ወቅት ትንሽ እፎይታ ሊሰጠን ይችል ይሆናል ስትል ግምቷን ለቢቢሲ ተናግራለች። ሆኖም ግን ትላለች ዶ/ር ኤለን፤ ምናልባት ኮቪድ-19 ባህሪው ከዚህ ቀደም ካሉት ተመሳሳይ ቫይረሶች በአንዳንድ ነገሩ የተለየ ሊሆን እንደሚችል መዘንጋት የለብንም። በሌላ በኩል በሽታው በስፋት በመላው ዓለም ስለተሰራጨና የተያዙ ሰዎች ቁጥር ሲታይ ብዙም ተስፋ ማድረግ ላያስፈልግ ይችላል ስትል ትደመድማለች። በሳውዝሀምፕተን ዩኒቨርስቲ ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ማይክል እንደሚሉት ደግሞ ኮቪድ-19 በአፈጣጠሩ ከሌሎች የኮሮናቫይረስ ዝርያዎች ተቀራራቢ ይሁን እንጂ የሚያድግበትና የሚሰራጭበት ፍጥነት እንዲሁም ያደረሰው ጥፋት ከሌሎች ኮሮናቫይረሶች ጋር አያገናኘውም። ሆኖም ለአየር ንብረት ወቅቶች የሚያሳየው ባህሪ በጉጉት የሚጠበቅ ነው። የጥናት ወረቀቶች እየወጡ ነው። ዞሮ ዞሮ ኮቪድ-19 በአየር ንብረት መለወጥ አልያም በፈረንጆች በጋ ሊገታ ይችል እንደሆነ በጥቂት ወራት ውስጥ የምናየው ይሆናል።
41815451
https://www.bbc.com/amharic/41815451
እውነተኛ ውበትን ፍለጋ
ፎቶግራፈር ሚሃኤላ ኖሮክ ''አሁን ወደ ጉግል ሄደው Beautiful women (ውብ ሴቶች) ብለው ጉግል ያድርጉ'' ትላለች። እጅግ በርካታ ምስሎችን ይመለከታሉ። ያገኟቸውን ምስሎች በትኩረት ይመልከቱ።
ከግራ ወደ ቀኝ ፎቶግራፎቹ የተነሱት ፓሪስ ፈረንሳይ፣ ደቡብ ኦሞ ኢትዮጵያ እና ግሪክ ነው። ሚሃኤል የምትመለከቷቸው ምስሎቹ ''የሴት ልጅን ውበት መወከል የማይችሉ እና እጅግ በጣም ወሲብ ቀስቃሽ የሚባሉ አይነት ምስሎች ናቸው'' ትላለች። እውነት ነው። በምስሉ ላይ የሚታዩት አብዛኛዎቹ ሴቶች ባለተረከዝ ጫማ የተጫሙ እና ስስ ልብሶችን የለበሱ ናቸው። ከዚህ በላይ ደግሞ ''ውብ ሴቶች'' የተባሉት የሰውነት ቅርፃቸው የተስተካከለ፣ ነጭ፣ ወጣት እና ቆዳቸው እንከን የሌለሽ ሆነው ይታያል። ሚሃኤላ ''የሴት ልጅ ውበት ማለት ይህ ነው?'' ስትል ትጠይቃለች። አለመታደል ሆኖ የሴት ልጅን ውበት በዚያ መልክ የሚገልጹ አሉ። ''አለመታደል ሆኖ ውበ ሴቶችን ከቁስ ጋር የሚያዛምዱ እና በወሲብ እይታ ውስጥ የሚከቷቸው በርካቶች ናቸው'' ትላለች። ከግራ ወደ ቀኝ ፎቶግራፎቹ የተነሱት በጀርመን፣ ጣሊያን እና ፈረንሳይ ነው። ''ሴቶች ግን እንደዛ አይደሉም። የራሳችን የሆነ ታሪክ አለን፣ የራሳችን ተጋድሎ እና ኃይል አለን። በርካቶች ግን በሌላ መልክ ቀርበዋል።'' ሚሃኤላ በቅርቡ እሷ የነሳቻችውን የአምስት መቶ ሴቶች ፎቶግራፍ የያዘ እና ''አትላስ ኦፍ ቢዩቲ''' የተሰኘ መጽሃፍ አስመርቃለች። ፑሽካር ህንድ። ሚሃኤላ በመላው ዓለም ሴቶች የጸጥታ ኃይል አስከባሪ አባል ሆነው ሳይ ደስታ ይሰማኛል ትላለች። ሮማኒያዊቷ ፎቶግራፍ አንሺ ለ'ውበት' ምንም አይነት ትርጉም አትሰጥም። በተለያየ የእድሜ ክልል ላይ የሚገኙ፣ በተለያየ የሥራ መስክ ላይ የተሰማሩ እና የተለያየ የኋላ ታሪክ ያላቸውን ሴቶች ውበትን ሊለኩ የሚችሉበት ተመሳሳይ መመዘኛ ሊኖር አይችልም ትላለች። ''ሰዎች ፎቶግራፎቼን ማየት ያስደስታቸዋል። ለዚህም ምክንያቱ ፎቶ የማነሳቸው ሴቶች በአከባቢያችን የሚገኙትን ነው ብዬ አምናለው'' ስትል ታስረዳለች። የማነሳቸው ፎቶግራፎች በጣም ቀላል እና ተፍጥሯዊ ሊባሉ የሚችሉ ናቸው። ይህም ውብ ሴቶችን በዚህ መልክ ስለማናያቸው ፎቶግራፎቼን የተለዩ ያደርጋቸዋል ስትል ስለ ሥራዎቿ ትናገራለች። ከ500 በላይ ፎቶግራፎችን የያዘው መጽሃፏ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ13 ሃገራት ወስጥ ተዘዋውራ ያነሳቻቸው ፎቶዎች አካቷል። ካፕቴን ቤሪኒስ ቶሬስ የሜክሲኮ ፌደራል ፖሊስ ሄሊኮፕተር አብራሪ ነች። በአንዳንድ ሃገራት ሴቶችን ፎቶግራፍ ማንሳት በጣም ከባድ ነው። ''ወግ አጥባቂ በሆኑ ማሕብረሰቦች ውስጥ ሴቶች እንደፍላጎታቸው መሆን አይችሉም። ከዚህ በላይ ደገሞ ሁሉንም እንቅስቃሴያቸውን በቅርብ የሚከታተል አይጠፋም። በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ የምትኖር ሴት ፎቶግራፍ ለመነሳት ፍቃደኛ ልትሆን አትችልም። ፍላጎት ቢኖራት እንኳን የወንድ አጋሯን ፍቃድ ማግኘት ይኖርባታል'' ስትል በስራዋ ላይ ስለሚያጋጥሟት ችግሮች ታስረዳለች። አቢ እና አንጄላ የተባሉት እህትማማቾች በኒው ዮርክ አሜሪካ የወታደራዊ ሙዚየም አስጎብኚ፤ ፕዮንግያንግ ሰሜን ኮሪያ እናት እና ሁለት ልጆች ሶሪያ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ሸሽተው ግሪክ በሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ይኖራሉ። ሚሃኤላ የዓለማችን ተዋቂ እና ባለፀጋ ግለሰቦች ለውበት እውነተኛ ያልሆነ መገለጫዎች ከመስጠታቸውም በላይ የማይጨበጥ አድረገውታ ትላለች። ይሁን እንጂ በጊዜ ሂደት ውስጥ ተፍጥሯዊ የሆነው ውበት በዓለም ተቀባይነቱ እየጨመረ መምጣቱ አይቀርም ስትል ሚሃኤላ ትናገራለች። ከግራ ወደ ቀኝ ሚሃኤላ ፎቶግራፎች ያነሳችው ኔፓል ካትማንዱ እና በአይስላንድ ዋና ከተማ ሬኬጂቨ ነው።
45126495
https://www.bbc.com/amharic/45126495
በጂግጂጋ የህክምና ቁሳቁሶች እጥረት አሳሳቢ ሆኗል
ሰሞኑን በሶማሌ ክልል ጂግጂጋ የተከሰተውን ብጥብጥ ተከትሎ የህክምና ቁሳቁሶች እጥረት እንዳለ በክልሉ ቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ በበጎ ፈቃደኛነት የሚያገለግሉ ጠቅላላ ሐኪም ዶ/ር እዮብ መኮንን ለቢቢሲ ገልፀዋል።
በወቅቱ አገልግሎት እየሰጡ ያሉት በጅግጅጋ ከተማ ከጥቂት ቀናት በፊት አንስቶ በተቀሰቀሰው ግጭት ምክንያት ከቤታቸው ተፈናቅለው በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስትያን ውስጥ ለተጠለሉ እና አካላዊ ጉዳት ለደረሰባቸው ነው። •የጂግጂጋ ነዋሪዎች የምግብና የውሃ ችግር አሳስቧቸዋል •በሶማሌ ክልል በተከሰተ ቀውስ ህይወት ሲጠፋ አብያተ-ክርስትያናት ተቃጠሉ •አብዲ ሞሃመድ ኡመር በቁጥጥር ስር ዋሉ ትናንትና ከእኩለ ቀን ትንሽ ቀደም ብሎ በቤተ ክርስትያኒቱ ቅፅር ግቢ ውስጥ ድንኳን ተክለው የህክምና አገልግሎቱን መስጠት መጀመራቸውን የሚናገሩት ዶክተር እዮብ ቢቢሲ እስካናገራቸው የዛሬ ረፋድ ድረስ ባለው ጊዜ ከመቶ በላይ ለሚሆኑ ጉዳተኞች እርዳታ መስጠታቸውን ይናገራሉ። ይሁንና ከግጭቱ በፊት አንስቶ ረዘም ላለ በሽታ ተከታታይ ህክምና በመውሰድ ላይ የሚገኙ ተፈናቃዮች ችግር ላይ መውደቃቸውን ያሰምሩበታል። እነዚህ በሽተኞች "በዚህ በአደጋው ምክንያት መድኃኒታቸውንም አጥተዋል፤ ከቤታቸው ሲወጡ ሁሉንም ነገር ነው ያጡት" ይላሉ። "እዚህ በቂ የመድኃኒት አቅርቦት የለም። የተቻለው እየተደረገ ነው፤ ግለሰቦችም እርዳታ እያደረጉ ነው። ግን በቂ አቅርቦት የለም። እዚህ የስኳር፥ የደም ግፊት በሽተኞች አሉ።"ብለዋል የቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ማኅበር በቤተ ክርስትያኑ ያሰማራው የበጎ ፈቃደኞች ቡድን አምስት ሐኪሞች፣ አምስት ነርሶች እና የመድኃኒት ባለሞያ እንዳለው ዶክተር እዮብ ጨምረው ለቢቢሲ ገልፀዋል። ከግጭቱ ጋር በተገናኘ በከተማዋ የተፈናቀሉት ሰዎች ቁጥር ከሃያ ሺህ እንደሚበልጥ መረጃ እንዳላቸው የሚናገሩት ዶክተር እዮብ፥ ገረባሳ በተሰኘ የወታደሮች ካምፕ ውስጥ የተጠለሉ ሁለት ሺህ አካባቢ የሚሆኑ ተፈናቃዮችን በትናንትናው ዕለት መጎብኘታቸውን ይናገራሉ። በካምፑ ውስጥ ያሉት ተፈናቃዮች ሜዳ ላይ ፈስሰው እንደሚገኙ እና ከወታደሮች ጋር ከመጋራታቸው በስተቀር ሌላ የምግብ ምንጭ እንደሌላቸው ማስተዋላቸውንም ለቢቢሲ ተናግረዋል። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ መምህር በርካታ ሰዎች ከተማዋን ለቅቀው ለመውጣት መኪኖችን ሲማፀኑ መመልከታቸውን እንዲሁም በጭነት መኪና ከመጠን በላይ ታጭቀው ወደሃረር በማቅናት ላይ ያሉ በርካቶች መኖራቸውን በወሬ መስማታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። መምህሩ የኢንተርኔት አግልግሎት መቋረጥ ችግሩን እያባባሰ ነው ባይ ናቸው። በአንድ በኩል ከየት እንደሚመጡ የማይታወቁ መረጃዎች ለሰዎች ዘንድ በስልክ መድረሳቸው ያለውን ስጋት ያናረው ሲሆን፥ ትክክለኛ እና ተጨባጭ መረጃ ከማግኘት እንደታቀቡ ይገልፃሉ። "ህዝቡ ምንም መረጋጋት አልቻለም። ለምሳሌ ትናንትና መነሻ የማይታወቅ መረጃ ተነዝቶ፤ ትጥቅ የማስፈታት ሂደት ስለሚኖር የተኩስ ልውውጥ መፈጠሩ አይቀርም በሚል ሰዎች ሁሉ እየተደዋወሉ በስጋት ሲናጡ ነው ያመሹት"ብለዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ያለውን ችግር ጥልቀት በአገሪቱ ዙርያ ለማሳወቅ እና አፋጣኝ እርዳታ እንዲሁም መፍትሔ እንዳይመጣ ደንቃራ ፈጥሯል ይላሉ። "የኢተርኔቱ መቋረጥ ትልቅ ተፅዕኖ ፈጥሯል። ቢያንስ ያለውን ነገር፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አልፎም ለዓለም ሕዝብ ማሳየት ይቻል ነበር።" ይላሉ።
news-42021875
https://www.bbc.com/amharic/news-42021875
ሙጋቤ አሁንም በእምቢተኝነታቸው እንደጸኑ ነው
የዚምባብዌ የረጅም ጊዜ መሪ ሮበርት ሙጋቤ ሥልጣናቸውን በፍጥነት እንዲለቁ የቀረበላቸውን ጥያቄ አልቀበልም ማለታቸው እየተዘገበ ነው።
የ93 ዓመቱ ሙጋቤ ባለፈው ረቡዕ በመከላከያ ኃይላቸው ቁጥጥር ሥር ከወደቁ በኋላ ተተኪያቸውን በተመለከተ የስልጣን ትግል ተፈጥሯል። እስካሁን ሙጋቤ ከአካባቢያዊ ልዑካኑና ከጦሩ አለቃ ጋር ያካሄዱት ውይይት ውጤቱ ምን እንደነበረ በይፋ አልተገለጸም። ሆኖም የመረጃ ምንጮች ስልጣናቸውን የማስረከብ ጥያቄውን አሻፈረኝ ማለታቸውን እየገለጹ ነው። የተቃዋሚው መሪ ሞርጋን ሻንጋራይ ሙጋቤ 'የህዝባቸውን ፍላጎት ለማሟላት አሁኑኑ ከሥልጣናቸው መውረድ አለባቸው'' ብለዋል። ጦሩ እርምጃውን የወሰደው ሙጋቤ ምክትላቸውን ኤመርሰን ምናንጋግዋን አባረው ባለቤታቸው ግሬስ ሙጋቤ የፓርቲያቸው ዛኑ-ፒኤፍና የፕሬዝዳንትነት መንበሩን ሊረከቡ እንደሚችሉ ፍንጭ መስጠታቸውን ተከትሎ ነው። ''ሮበርት ሙጋቤ በቁጥጥር ስር ውለዋል፤ ደህንነታቸውም ይጠበቃል'' በዚምባብዌ የሚገኘው የቢቢሲው አንድሪው ሃርዲንግ እንደሚለው ሙጋቤ ሥልጣናቸውን ለመልቀቅ ከተገደዱ ለወታደራዊ ጦሩን ጣልቃገብነት በሂደት ህጋዊ እውቅና ለመስጠት መንገድ ይከፍታሉ። በእርግጥ በዚምባብዌ ጎዳናዎች ሙጋቤ በሥልጣን እንዲቆዩ የሚፈልጉ ሰዎችን ማግኘት ይከብዳል ይላል አንድሪው። ሆኖም ከሥልጣናቸው የሚያርፉበትን ሁኔታዎች የማመቻቸቱና የሽግግር ስምምነቱን የማካሄዱ ሂደት ጊዜ መውሰዱ አይቀርም። አሁን በሃራሬ ምን እየተካሄደ ነው? እስካሁን ምንም ግልጽ አይደለም። የዚምባብዌው ሄራልድ ጋዜጣ ሙጋቤ የጦሩን መሪ ጀነራል ኮንስታኒቲኖ ቺዌንጋንና የደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ(ሳድክ) ተወካዮች ጋር በቤተመንግሥት ሲነጋግሩ የሚያሳዩ ፎቶዎችን አውጥቶ ነበር። ከእነርሱ ጎን ደግሞ ከሙጋቤ ጋር ለዓመታት የሚተዋወቁት የሮማው ካቶሊክ ቄስ ፊደሊስ ሙኮኖሪ የድርድሩ አካል ሆነዋል። ለውይይቱ ቅርብ የሆኑ ምንጮች እንደሚናገሩት የነጮችን የበላይነት ከረቱበት ከአውሮፓውያኑ 1980 ጀምሮ ዚምባብዌን የመሩት ሙጋቤ በቀጣዩ ዓመት ለማካሄድ ከታቀደው ምርጫ በፊት ሥልጣናቸውን ለመልቀቅ አልተባበርም ብለዋል። ለጦሩ ቅርበት ያለቸው የመረጃ ምንጭ ለአጃንስ ፈራንስ ፕሬስ(ኤ ኤፍ ፒ) ሲገልጹ '' ጊዜ ለመውሰድ እየሞከሩ ይመስለኛል '' ብለዋል። አንዳንድ ታዛቢዎችም ሙጋቤ ሥልጣን ለመልቀቅ የእርሳቸውና የቤተሰባቸው ደህንነት እንደሚጠበቅ ዋስትና እንዲሰጣቸው ለመጠየቅ ይሞክራሉ ይላሉ። የዛኑ-ፒ ኤፍ ባለሥልጣናት በመጪው ታህሳስ የፓርቲው ጉባኤ እስከሚካሄድ ድረስ ሙጋቤ የመሪነት ስማቸውን ይዘው መቆየት እንደሚችሉና ያኔ ግን ምናንጋግዋ በይፋ የፓርቲውና የሀገሪቱ መሪ እንደሚሆኑ ገልጾ ነበር። መጋቤ በቤተ መንግሥት ከተለያዩ ኃላፊዎች ጋር መክረዋል የዚምባብያውያን ሃሳብ ምንድን ነው? በርካታ የዚምባብዌ ዜጎች ሙጋቤ በመኖሪያ ቤታቸው መወሰናቸውንና ጦሩም እርምጃ መውሰዱን ይደግፉታል። '' ጦሩ ጥሩ ነገር ነው ያደረገው'' ይላል አንዱ መጽሃፍ ሻጭ '' የሽግግር መንግስት እንዲኖረን ያደርጋል'' እርሱ አሁን የሙጋቤ የ37 ዓመታት የመሪነት ጊዜ እንደተጠናቀቀ ያምናል። ሌሎችም ቢሆኑ የለውጥ ፍላጎት እንደነበረ በሚያሳይ መልኩ አሁን ሃሳባቸውን በግልጽ መናገር ጀምረዋል። ስለ ሙጋቤ እና ዚምባብዌ ምን እየተባለ ነው? ደቡብ አፍሪካም ሆነ አካባቢው ምንን ይፈልጋሉ? ደቡብ አፍሪካ በአውሮፓውያኑ 2008 የዚምባብዌ ኢኮኖሚ በከፍተኛ ሁኔታ ከማሽቆልቆሉ ጋር ተያይዞ የተሰደዱ ሚሊዮን የዚምባብዌ ስደተኞችን ተቀብላለች። በዚህም ምክንያት መረጋጋት እንዲፈጠር ልዩ ፍላጎት አላት። የደቡብ አፍሪካ መከላከያ ሚኒስትር ኖሲቪዌ ማፊሳ ንካኩላና እንዲሁም የሀገሪቱ የፀጥታና ደህንነት ሚኒስትር ቦንጋኒ ቦንጎ የ ደቡብ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብን (ሳድክ) ወክለው ከሙጋቤ ጋር በመነጋገር ላይ ናቸው። በተጨማሪ ሳድክ በቦትስዋና ስብሰባ አድርጎ የነበረ ሲሆን ክልሉ ዚምባብዌ ላይ ያለውን ቀውስ አስመልክቶም ጉባዔ እንዲካሄድ ጠርቷል። " ያለውን የፖለቲካ ችግሮች በሰላም እንዲፈቱ " ጥሪ ማቅረባቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በዘገባው አትቷል። የአፍሪካ ህብረት በበኩሉ ስልጣንን በወታደራዊ ኃይል መቆጣጠርን እንደሚቃወም ተናግሯል። የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ-መንበር የጊኒው ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴም በበኩላቸው ጦሩ ተመልሶ ወደ ሰፈራው እንዲመለሱና ሀገሪቱም ወደህገ-መንግሥታዊ ስርዓት እንድትመለስ መልዕክት አስተላልፈዋል። የዚምባብዌ ተቃዋሚስ? የስርዓቱ ተቃዋሚ ፓርቲ ሙቭመንት ፎር ዲሞክራቲክ ቼንጅ መሪ ሞርጋን ሻንጋራይ በበኩላቸው ሙጋቤ በአስቸኳይ ሥልጣን እንዲለቁና "ሁሉንም የሚያሳትፍና የሚስማሙበት የሽግግር መንግስት" የሚቋቋምበት መንገድ እንዲመቻች ጠይቀዋል። እነዚህም ማሻሻያዎች በነፃና ፍትሀዊ ምርጫ የሚመሩ መሆን እንዳለባቸው ጨምረው ተናግረዋል። ግሬስ ሙጋቤ በምን ሁኔታ ላይ ናቸው? በቅርቡ የወጡ መረጃዎች የሚያሳዩት ግሬስ ሙጋቤ ወደ ናሚቢያ እንደሄዱ ነው ነገር ግን ምንጮች አሁን የሚሉት በግቢያቸው ውስጥ እንዳሉ ነው። የደገፏቸው የዛኑ ፒኤፍ ፓርቲ ወጣት ክንፍም አብረዋቸው አሉ። በዚሁ ሳምንት ረቡዕ ዕለት ቁልፍ ደጋፊያቸው የሆኑት ኩድዛይ ቺፓንጋ የጦሩን መሪ ከተቹ በኋላ የቃል ጦርነቱ ተጋግሎ ጦሩ ሀገሪቷን እንዲቆጣጠሩ ማድረጉን በማስመልከት የተቀረፀ የይቅርታ መልዕክታቸውን በቴሌቪዥን አስተላልፈዋል። ምንም እንኳን ኩድዛይ ቺፓንጋ በጦሩ ቁጥጥር ስለሆኑ ይሆናል ይህንን መግለጫ የሰጡት የሚል አስተሳሰብ ቢኖርም በፍቃደኝነት የተሰጠ እንደሆነ ተናግረዋል። የፓርቲው ወጣት ክንፍ ታላላቅ አባላትም በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የወጡ ሪፖርቶች አሉ። ጦሩ ሀገሪቷን እንዴት ተቆጣጠረ? በዚህ ሳምንት ረቡዕ ጥዋት ላይ የዚምባብዌ ጦር የሀገሪቱን የቴሌቪዥን ጣቢያ (ዜድቢሲ)ን በመቆጣጠር "ሙጋቤ አካባቢ ያሉትን ወንጀለኞችን ዒላማ" እንዳደረገ መግለጫ ሰጥቷል። ሠራዊቱ እንዲሁም የጦሩ መኪኖች ፓርላማውን እንዲሁም ቁልፍ የሚባሉ ህንፃዎችን ከበው ነበር። ሰኞ ዕለት ጄኔራል ቺዋንጋ ለነፃነት የተደረገውን ትግል በመጥቀስ የዛኑ ፒ ኤፍ ፓርቲ አባላት ባለስልጣናቱን ማስወገዳቸውን ከቀጠሉ ጦሩ ጣልቃ እንደሚገባ ጠቅሰው ነበር። ኤመርሰን ምናንጋግዋ በአውሮፓውያኑ 1970ዎቹ ለነፃነት በተደረጉ ጦርነቶች ላይ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ታጋይ ናቸው።
44299246
https://www.bbc.com/amharic/44299246
ከሚሊዮን ብር በላይ ያወደመችው ተማሪ ክስ ቀረበባት
ተማሪ ደግሞ ይህን ያህል ገንዘብ ከየት ሊያመጣ ይችላል የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል።
ተማሪዋ የባንክ ደብተር ውስጥ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ በስህተት ገቢ ተደርጓል ይህቺ ተማሪ ቦርሳ ውስጥ የገባው ሲሳይ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ነው። ለዚያም በአንድ ቀን። ሲቦንጊሊ ማኒ የ28 ዓመት የዩኒቨርስቲ ተማሪ ናት። ለዚያም የአካውንቲንግ ተማሪ። በስህተት የባንክ ደብተሯ ውስጥ ከገባው 1.1 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ 63ሺ ዶላሩን እንዳልነበረ አድርጋ አውድማዋለች። እጇ ውስጥ ከገባው 30 ሚሊዮን ብር ውስጥ ያጠፋቸው ገንዘብ ወደኛ ሲመነዘር ከ2 ሚሊዮን ብር አይበልጥም። በዋልተር ሲሱሉ ዩኒቨርስቲ የአካውንቲንግ ተማሪ ወደሆነችው ሲቦንጊሊ ማኒ ይህ ሁሉ አዱኛ እንዴት በአንድ ጊዜ ሊገባ እንደቻለ የደቡብ አፍሪካ መገናኛ ብዙኃንን እያነጋገረ ነው። አሁን በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሆና ክስ የተመሠረተባት ሲቦንጊኒ የድሀ ድሀ ተማሪዎች የሚረዱበት ማኅበር ውስጥ በወር 110 ዶላር የገንዘብ ድጎማ እየተደረገላት ነበር የምትማረው ተብሏል። የዕድል ጉዳይ ሆኖ ግን ከዕለታት በአንዱ የባንክ ደብተሯ ውስጥ 30 ሚሊዮን ብር ገባላት። ማመን አልቻለችም። ወዲያውኑ 63 ሺህ ዶላሩን መንዝራ ለፈንጠዚያና ውድ ጌጣ ጌጦችን ለመግዛት አውላዋለች። ትናንት ፍርድ ቤት ቀርባ ማስጠንቀቂያ ከተሰጣት በኋላ ለሐምሌ 2 ተቀጥራለች ተብሏል። ደቡብ አፍሪካውያን በትዊተር ገጻቸው እልፍ ሐሳቦችን እየተለዋወጡ ሲሆን በርካቶች "እሰይ ደግ አረግሽ! አበጀሽ!" እያሏት ነው።
52290169
https://www.bbc.com/amharic/52290169
ኮሮናቫይረስ፡ ደቡብ ኮሪያውያን ጭምብልና ክሊኒኮች በተዘጋጁበት ሁኔታ ምርጫ እያካሄዱ ነው
ደቡብ ኮሪያ በኮሮና ወቅትም ቢሆን ምርጫው ይካሄዳል ብላ በመወሰኗ መራጮች ወደየጣቢያው እየመጡ ነው።
ነገር ግን ዝም ብሎ በዘፈቀደ መምጣት የለም። ሁሉም የፊት ጭምብል ማድረግ እንዲሁም በአንድ ሜትር ተራርቀው መሰለፍ አለባቸው። ከዚያም የሙቀት መጠናቸው ይለካል፣ እጃቸውንም በሳኒታይዘር እንዲያፀዱ ይደረግና የእጅ ጓንት ያጠልቃሉ። እነዚህን ሁሉ ሂደቶች ካለፉ በኋላ ነው ድምፃቸውን ለመስጠት ወደተከለለው ሚስጥራዊ ቦታ የሚወሰዱት። • ትራምፕ ለዓለም ጤና ድርጅት የሚሰጠው ገንዘብ እንዲቋረጥ አዘዙ • የኮሮናቫይረስን በመቆጣጠር በኩል እየተሳካላት ያለችው አገር በዚህ የኮሮና ወረርሽኝ እየተዛመተ ባለበት ወቅት የብሔራዊ ጉባኤው ምርጫ በተያዘለት እቅድ መሰረት እንዲካሄድ እነዚህ ቅድመ ጥንቃቄዎች በመከናወን ላይ ናቸው። ብሔራዊ ጉባኤው (ፖርላማው) ሶስት መቶ መቀመጫዎች ያሉት ሲሆን፣ ሰላሳ አምስት ፓርቲዎችም ተፎካካሪዎቻቸውን አቅርበዋል። ነገር ግን በአብዛኛው ውድድሩ የሚሆነው በገዥው ፓርቲ ሚንጆ ዲሞክራቲክ ፓርቲና በተቀናቃኙ ወግ አጥባቂው ዩናይትድ ፊውቸር ፓርቲ መካከል ነው። በምርጫው ላይ መንግሥት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ለመቆጣጠር እያደረገው ያለው ጥረት የምርጫ ውይይቶችን የበላይነት ስፍራ ይዞ ነበር። ኮሮና ሊያስከትለው የሚችለውን ከፍተኛ የኢኮኖሚ መሽመድመድ እንዲሁም ከፕሬዚዳንቱ የእርዳታ እቅዶች ጋር ተያይዞ ያሉ የሙስና ቅሌቶችም በብዙዎች ዘንድ ፍራቻን አንግሰዋል። የብሔራዊ ጉባኤው ምርጫ ተመራጮች እንዲሁም የፓርቲዎች እውቅና የሚመዘንበት ሲሆን፤ ዋናው ምርጫ ግን የሚደረገው ከሁለት ዓመታት በኋላ ነው። 'የመምረጥ መብት' የኮሮና ቫይረስ ፍራቻ በነገሰበት ሰአት ምርጫው ይካሄዳል መባሉ ከፍተኛ ቀውስ ሊያስከትል እንደሚችሉ ትችቶች እየተሰሙ የነበረ ቢሆንም እኔ ግን ያስተዋልኩት በተረጋጋ ሁኔታ የተደረገ ምርጫ ነው። መራጮች በተሰጣቸው ቦታ ላይ በፀጥታ ቆመው ተራቸውንም እየጠበቁ ነበር። "ምናልባት ብዙ መራጭ ስለማይመጣ ምርጫው ቢራዘም የሚል ሃሳብ ነበረኝ። ነገር ግን እኔም መጥቻለሁ ብዙ ሰውም ለመምረጥ መጥቷል። የሚያስጨንቅ ነገር የለም" በማለት አንዲት ወጣት መራጭ ለቢቢሲ ተናግራለች። የቫይረሱ የመዛመት ሁኔታ መራጮችንም ያሰጋ አይመስልም። ከአስራ አንድ ሚሊዮን በላይ የሚበልጥ መራጭ፣ 26 በመቶ የሚሆነው አገሬው መርጧል። አንዳንዶች በፖስታ ምርጫቸውን ሲልኩ አብዛኞቹ ደግሞ ማልደው መጥተው መርጠዋል። የተያዘው ህዝብ ቁጥርም ከፍተኛው ነው ተብሏል። ከዚህ በተጨማሪ የ18 ዓመት እድሜ ያላቸው ሰዎችም ሲመርጡ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። የመጀመሪያ መራጮችም በመዲናዋ ሴዉል በደስታ ሲመርጡ ታይተዋል። "መምረጥ መብታችን ነው። ማድረግ ያለብንም ነገር ነው" በማለት የምትናገረው የመጀመሪያ ጊዜ መራጭ ምንም እንኳን ከፕላስቲክ የተሰሩ የእጅ ጓንቶች ለመምረጥ ባይመቹም፤ "ዋናው ደህንነት" ነው ብላለች። በለይቶ ማቆያ ክሊኒኮች ላይ ሆኖ መምረጥ ደቡብ ኮሪያ በታሪኳ ውስጥ ምርጫን አራዝማ አታውቅም። በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር በ1950ዎቹ በነበረው የኮሪያ ጦርነት እንኳን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተካሂዷል። በዚህ ወቅት ለባለስልጣኖቹ ዋነኛ ፈተና የነበረው ምናልባት ቫይረሱ ቢዛመትስ የሚል ነበር። እናም የሙቀት መለኪያው ጣቢያዎቹ ላይ አስገዳጅ የሆነበትም ምክንያት መከላከል ያስችል ዘንድ በሚል ነው። መራጮች የሙቀት መጠናቸው ከ37.5 ሴንቲግሬድ በላይ ከሆነ ከሌላው መራጭ ተነጥለው በተዘጋጀው ለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲመርጡ ይደረጋሉ። የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች የምርጫ ውጤታቸውን በፖስታ እንዲልኩ ተጠይቀዋል። • የኮሮናቫይረስን በመቆጣጠር በኩል እየተሳካላት ያለችው አገር ነገር ግን የኮሮና መካከለኛ ምልክት ለሚያሳዩ ሰዎች ከመኖሪያ ሰፈሮች ራቅ ባለ ሁኔታ አንድ የምርጫ ጣቢያ ተዘጋጅቷል። አንዲት ሴትዮ የሆስፒታል ጋወኗን እንደለበሰችና፣ የፊት ጭምብል አጥልቃ ስትመርጥ ቢቢሲ ተመልክቷል። "መጀመሪያ መምረጥ አልችልም ብዬ አዝኘ ነበር፤ ነገር ግን ኮሮና ቢይዘንም መምረጥ እንደምንችል ስሰማ በጣም ተደሰትኩ" በማለት ለሮይተርስ ተናግራለች። ምንም እንኳን ደቡብ ኮሪያ ምርጫ ይካሄድ ብትልም አሁንም የሰአት እላፊ አዋጅ እግዱ እንዳለ ነው። እንዲሁም መራጮች የህዝብ ትራንስፖርት መጠቀም አይችሉም። ወደ ምርጫ ጣቢያዎቹ ሲመጡ በእግራቸው ወይም በራሳቸው መኪና መሆን አለበት። ቤታቸውም ሲመለሱ የጤና ባለሙያዎች ጋር መደወል አለባቸው ካለበለዚያ ለእስር ሊዳረጉ ይችላሉ። ይህንንም ለማሳለጥ 550 ሺ ሰራተኞች በአገሪቷ ባሉ የምርጫ ጣቢያዎች ተመድበዋል።
44106540
https://www.bbc.com/amharic/44106540
የውድድር ዘመኑ ምርጥ 11
ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ከ10 ወራት ቆይታ በኋላ ሊጠናቀቅ ግድ ሆኗል። የፕሪሚዬር ሊጉን ምርጥ ተጫዋቾች በየሳምንቱ የሚመርጠው ጋርዝ ክሩክስ እነሆ የወድድር ዘመኑን ምርጥ አስራ አንድ ተጫዋቾች እኚህ ናቸው ይላል።
ወርሃ ነሐሴ ላይ የጀመረው የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ በማንችስተር ሲቲ አሸናፊነት ተጠናቋል። ዌስትብሮም፣ ስቶክና ስዋንሲ ደግሞ ከሊጉ ሲወርዱ፤ አርሴናል ደግሞ ከዌንገር ጋር የነበረው የ22 ዓመታት ቁርኝት ቋጭቷል። እነዚህ ሁሉ እንዳሉ ሆነው የውድድር ዘመኑ ምርጥ አስራ አንድ ውስጥ መካተት የቻሉት ምርጥ 11 ተጫዋቾች እነማን ናቸው? ግብ ጠባቂ ዳቪድ ዴ ሂያ (ማንቸስተር ዩናይትድ) ሆዜ ሞሪኖ ዴ ሂያ ወደ ሪያል ማድሪድ ከመሄድ ይልቅ ዩናይትድ እንዲቆይ ያሳመኑት ጊዜ ትልቅ ነገር እንደሰሩ እሙን ነበር። ዴ ሂያ በዚህ የውድድር ዘመን ያሳየው ብቃት እጅግ ማራኪ ነበር። ምንም እንኳ ሞሪኖ ለዚህ ድንቅ በረኛ የሚመጥን ተከላካይ መስመር ሊሰሩ ባይችሉም። ትዝ የሚላችሁ ከሆነ ሞሪኖ ከቼልሲ ጋር ዋንጫ ሲያነሱ ፒተር ቼክ በረኛ ነበር፤ ዊሊያም ጋላስ፣ ጆን ቴሪና ሪካርዶ ካርቫልሆ ደግሞ ተከላካዮች። ዴ ሂያ እነዚህን የመሳሰሉ ተከላካዮች ቢኖሩት ኖሮ ዩናይትድ ዋንጫ የማንሳት አቅም ነበረው። ያም ሆነ ይህ ዴ ሂያ በ18 ጨዋታዎች ምንም ጎል ያልተቆጠረበት ግብ ጠባቂ ሆኖ የወርቅ ጓንቱን መውሰድ ችሏል። ተከላካይ መስመር ዎከር፣ ዳንክ፣ ኦታሜንዲ እና ያንግ ካይል ዋከር (ማንቸስተር ሲቲ) - ፔፕ ጋርዲዮላ ዎከርን ከቶተንሃም በ50 ሚሊየን ዩሮ ሲገዛው ጥርጣሬ ገብቶኝ ነበር። ነገር ግን በመጀመሪያ ጨዋታው ያሳየውን ብቃት ስመለከት ሲቲዎች ለተጫዋቹ ያወጡት ወጭ የማያስቆጭ እንደሆነ ገባኝ። በምርጥ የመከላከል አቋም ላይ በመገኘት ቡድኑ ዋንጫ እንዲያነሳ ከማገዙም በላይ ለጎል የሚሆኑ ኳሶችንም ሲያቀብል ነበር። ሊዊ ዳንክ (ብራይተን) - ይህ ተጫዋች በቻምፒንሺፕ ደረጃ ሲጫወት ተመልክቸዋለሁ፤ በፕሪሚዬር ሊጉ ያየሁት ግን ፍፁም ሌላ ሆኖ ነው። የቶተንሃሙ ጆን ቬርቶኸንን መርጬ መገላገል እችል ነበር፤ ነገር ግን ብራይተብ ጥሩ ይሁንም አይሁን ዳንክ በዚህ ዓመታ ያሳየው ብቃት ያለምንም ጥርጥር ሊያስመርጠው ይገባል። 56 ጎል ሊሆኑ የሚችሉ ኳሶችን ጠራርጎ በማስወጣትም ከሁሉም የላቀ መሆኑን አሳይቷል። ኒኮላስ ኦታሜንዲ (ማንቸስተር ሲቲ) - ይህ ልጅ አቋሙ የሚዋዥቅ ነበር፤ ነገር ግም በዚህ ዓመት ዘላቂ የሆነ ብቃት አሳይቶናል። ቨንሴንት ኮማፓኒ በተጎዳብት ሰዓትም እጅግ ወሳኝ ተጫዋች ሆኖ መገኘት ችሏል። አልፎም ከማንኛውም የሊጉ ተጫዋች በበለጠ ስኬታማ ኳሶችን ለቡድን አጋሮቹ ማቀበል ችሏል። አሽሊ ያንግ (ማንቸስተር ዩናይትድ) - ያንግ በዩናይትድ ያበቃለት ተጫዋች መስሎኝ ነበር። ከአንቶኒዮ ቫልንሲያ በመቀጠል ከክንፍ ተጫዋችነት ወደ ተመላላሽ ተከላካይነት የተቀየረ መሆንም ችሏል። በዚህ የወድድር ዘመን ባሳየው ብቃትም በ32 ዓመቱ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን እንዲጠራ ሆኗል። አማካዮች ደ ብረይን፣ ፈርናንዲኖ እና ሲልቫ ኬቭን ዴ ብረይን (ማንቸስተር ሲቲ) - በዚህ የውድድር ዘመን ካየኋቸው ተጫዋቾች ሁላ እንደ ኬቭን አንጀቴን ያራሰው የለም። እንደው ሞሃመድ ሳላህ የሚገርም ብቃት ላይ መገኘቱ እንጂ የውድድር ዘመኑ ምርጥ መሆን ይገባው የነበረ ልጅ ነው። እንግዲህ እግር ኳስ እንዲህ ነው። ይህን ተጫዋች የውድድር ዘመኑ ምርጥ ተጫዋቾች መሃል ከማካተት ያለፈ ነገር ማድረግ ብችል አደርግ ነበር። ፈርናንዲንሆ (ማንቸስተር ሲቲ) - ክሎውድ ማኬሌሌ ከሪያል ማድሪድ፤ ጋርካምቢያሶ ደግሞ ከኢንተር ጋር መሰል ድል መጋራት ችለዋል። ፈርናንዲኖ ደግሞ ከሲቲ ጋር ስኬትን ማጣጣም ችሏል። እኒህ ተጫዋቾች ራሳቸውን ከእነ ዚነዲን ዚዳን እኩል ባይመድቡም ለቡድናቸው ድል የማይቆፍሩት ድንጋይ የለም። ዳቪድ ሲልቫ (ማንቸስተር ሲቲ) - ሲልቫ ለሲቲ በጣም ለየት ያለ ግልጋሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ተጫዋች ነው። ዘጠኝ ጎል አስቆጥሮ 11 ማቀበልም የቻለ ተጫዋች ነው ሲልቫ። አጥቂዎች ሳላህ፣ ኬን እና አጉዌሮ ሞሃመድ ሳላህ (ሊቨርፑል) - ይህ ግብፃዊ ለሃገሩም ሆነ ለቡድኑ እያደረገ ያለው በቃላት ሊገለፅ የማይችል ነው። የዚህ ውድድር ዘመን ብቃቱ ደግሞ በአግራሞት አፍ የሚያስከድን ነው። የሊቨርፑል ደጋፊዎች ሞ ሳላህ...ሞ ሳላህ እያሉ ቢዘምሩ የሚገርም አይደለም። በ32 ጎሎችም በአንድ የውድድር ዘመን ብዙ ያገባ የሚለውን ክበረ-ወሰን መስበር ችሏል። ሃሪ ኬን (ቶተንሃም) - አነሆ ሌላ ድንቅ የውድድር ዘመን ለሃሪ ኬን። አኔ ይህ እንግሊዛዊ ሌሎች የሃገሩ ልጆች በየቦታው ዋንጫ ሲያነሱ እያየ እዛው ቶተንሃም መቆየት እስከመቼ እንደሚቆይ አላውቅም። በሁሉም የወድድር ዓይነቶች 42 ጎሎች በማስቆጠር የክለቡን ክብረ-ወሰን መስበርም ችሏል። ሰርጂዮ አጉዌሮ (ማንቸስተር ሲቲ) - የየሳምንቱን ምርጥ አስራ አንድ የሚከታተሉ ሰዎች መቼም ለአጉዌሮ ያለኝን አድናቆት ያውቃሉ። ሲቲ ዋንጫውን እንዲበላ የአጉዌሮ ጎሎች ትልቅ ሚና መጫወታቸው ሊዘነጋ አይገባም። የሲቲ የምን ጊዜም ጎል አግቢ ክብረ-ወሰነንም መጨበጥ ችሏል። የወድድር ዘመኑ ምርጥ አሰልጣኝ ራፋኤል ቤኒቴዝ - ኒውካስል ዩናይትድ የውድድር ዘመኑ ምርጥ ሶስት አሰልጣኞች እንነማ ናቸው ተብዬ በተጠይቅኩ ጊዜ ያለማንገራገር ራፋ ቤኒቴዝ፣ ሾን ዳይሽ እና ክሩስ ሑቶን ብዬ ነበር። በርንሌይ ለአውሮፓ ሊግ ይበቃል፤ ብራይተን በሊጉ ይቆያል፤ ኒውካስል ደግሞ 44 ነጥብ መሰብሰብ ይችላል የሚል እምነት ፈፅሞ አልነበረኝም። ቤኒቴዝ ኒውካስልን ለቻምፒዮንሺፕ ዋንጫ ከማብቃታቸውም ባሻገር ሊጉን የሚመጥን ቡድን አድርገውታል። ልጆቹን ለሽንፈት እምቢ እንዲሉ አድርጎም ቀርጿቸዋል።
news-50806684
https://www.bbc.com/amharic/news-50806684
ቲፋኒ ሃዲሽ፡ ጥቁርነትና ይሁዳዊነት
የዘር ግንዷ ከኤርትራና ከአሜሪካ የሚመዘዘው ተዋናይቷ ቲፋኒ ሃዲሽ በአይሁዳውያን እምነት ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ባት ሚትዝቫህን አክብራለች።
ባት ሚትዝቫህ የሚባለው አንዲት ታዳጊ አስራ ሁለት አመት ሲሞላትና፤ በእምነቱም ዘንድ ነፍስ ማወቋ ሲረጋገጥ፤ መፅሀፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሱትን የሃይማኖቱን ህግጋትም ሆነ ትእዛዝ መፈፀም የሚያስችላትን እድሜ ማረጋገጥ የምትችልበትን ቀን የሚከበርበት ነው። •ኢትዮጵያውያን 'የሌሉበት' ስለ ኢትዮጵያ የሚዘክረው ሬድ ሲ ዳይቪንግ ሪዞርት ፊልም •"ወደ እናት ሃገራችን እስራኤል ውሰዱን" ለቲፋኒ ሃዲሽ ግን በአርባኛ አመቷ ሲሆን ይህንን እለት ያከበረችው፤ በኔትፍሊክስም ለእይታ በበቃው ብላክ ሚትዝፋህ (የጥቁር ሚትዝፋህ) የይሁዳዊነት መሰረቷን ስታከብር የሚያሳይ ነው። ጉዞዋ ብዙ ጥቁር አይሁዳውያን ትልቅ ከሆኑ በኋላ ዘራቸው ከዛ መሆኑን ሲያውቁ የሚያደርጉትን እንዲሁም የአይሁድ እምነትን በትልቅነታቸው ሲቀበሉ የሚያደርጉትን ጉዞ ያንፀባርቃል። ቲፋኒ ኤርትራዊና አይሁዳዊ አባቷን ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኘችው በ27 አመቷ ነው። ነገር ግን ወዲያው ይሁዳዊነቷን አልተቀበለችም፤ የዲኤንኤ ምርመራ ማድረጓን ተከትሎ ነው ስረ መሰረቷን የተቀበለችው። የእብራይስጥ ቋንቋን እንዲሁም መፅሃፈ ቶራህን ማጥናት ጀመረች፤ ባት ሚትዝቫህን ያከበረችበትንም ምክንያት ስትናገር አፍሪካዊነቷን እንዲሁም ይሁዳዊነት መሰረት ለማክበር ነው። ቲፋኒ ይህንን ማድረጓም ብዙ አፍሪካዊ አሜሪካውያን የዘር ግንዳቸውን እንዲፈልጉ ሊያበረታታቸው እንዲሁም ሊያነሳሳቸው እንደሚችል ነው። •በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ወደ ፅዮን ውሰዱን ተማፅኖ የአይሁዳዊነት መንገዶች በተለምዶ ይሁዳዊነት በዘር የሚተላለፍ፤ አንድ ሰው አያቱ ወይም ቤተሰቡ የዘር ግንድ ከዛ የሚመዘዝ ከሆነ ከእምነቱ ጋር ብዙዎች ግንኙነት ይፈጥራሉ። አንዳንዶች ደግሞ የዘር ግንዳቸው ከዛ የሚመዘዝ ባይሆንም ይሁዳዊነትን በራስ በመነሳሳት የሚቀበሉ አሉ። በአፍሪካ ውስጥ ያሉ የአይሁዳውያንን ቁጥር ማወቅ ከባድ እንደሆነ የብላክ ጂውስ ኦፍ አፍሪካ መፅሃፍ ደራሲ ዶ/ር ኤዲት ብሩደር ይናገራሉ። "በአፍሪካ ውስጥ ከሌላው አለም ጋር አንድ አይነት የሆነ ይሁዳዊነት አይደለም፤ በተፃራሪው የሚቀያየር ነው" ብለዋል። በአፍሪካ ውስጥ ከፍተኛ የይሁዲውያን የህዝብ ቁጥር ያለው በደቡብ አፍሪካ ሲሆን ብዙዎቹም ቤተሰቦቻቸው ከአውሮፓ የተሰደዱ ናቸው። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያንንም በሌላው አለም ማንነታቸው ሳይታወቅ ለዘመናት የኖሩ ሲሆን በጎርጎሳውያኑ 1975 በእስራኤል መንግሥት እውቅና ተሰጥቷቸዋል። አብዛኛዎቹ ወደ አርባ ሺ የሚገመቱት በጎርጎሳውያኑ 1970-1991 ባለው ጊዜ በምስጢራዊ ዘመቻዎች ወደ እስራኤል እንዲመጡ ተደርገዋል። አሁንም ቢሆን በአህጉሪቷ የተለያዩ ክፍሎች ጥቁር ይሁዳውያን የሚገኙ ሲሆን፤ አንዳንዶቹም ማህበረሰቦች በተለያየ ደረጃ እውቅና አግኝተዋል። እንደ ቲፋኒ ያሉት የዘር ግንዳቸውን በዲኤንኤ ማረጋገጥ የቻሉ ሲሆን እንደ ሚካኤል ሎሞቴ ያሉት ደግሞ የይሁዲነት ማንነታቸውን በሌላ መንገድ ነው ማወቅ የቻሉት። በጎርጎሳውያኑ 1960ዎቹ ነው በእንግሊዝ ሰሜናዊ ምስራቅ በምትገኘው የሁል ከተማ ያደገው፤ ሚካኤል ሎሞቴ ስለ ጉዞው ለቢቢሲ ተናግሯል። ከነጭ እንግሊዛዊ እናትና ከጥቁር ጋናዊ አባት የተወለደው ሚካኤል ሁለቱም ወላጆቹ ይሁዳውያን ናቸው። ስለ ቤተሰቦቹ ማንነትም ሆነ መሰረት ጎርመስ እስኪል ድረስ የሚያውቀው ታሪክ አልነበረም። •"ማርታ፣ ለምን ለምን ሞተች?" "ቤታቸው ውስጥ የሚከናወኑ ተግባራት ከጋና መሰረቱ የተመዘዙ ባህሎች ይመስሉኝ ነበር" በማለት ለቢቢሲ ተናግሯል። አባቱ ጭንቅላታቸው ላይ ትንሽ ቆብ ያደርጉ ነበር፤ በእብራይስጥ ቋንቋም ያወሩ ነበር። "ስለ ይሁዳውያንም ሆነ አይሁዶች ምንም ተብለን አናውቅም" ብሏል። ወላጆቹ ስለ ይሁዳዊነት ምንም ብለው ለምን እንደማያውቁ ባይረዳም ከቤት ሲወጣ በአስራ ስምንት አመቱ መፅሀፈ ቶራህን አባቱ ሰጥተውታል። "መፅሀፉን በጥልቀት ሳነበውና ስረዳው የሁሉም ነገር መነሻ እንደሆነ ተረዳሁኝ፤ ብርሃን እንደተፈነጠቀልኝ ነው የተሰማኝ" ብሏል። በዛን ወቅትም ነው የማንነቱን መሰረት ፍለጋ የገባው፤ በዚህም ፍለጋ ላላ ካሉ በጣም አጥባቂ ይሁዲዎች አጋጥመውታል። ሚካኤል በሰሜናዊ ለንደን በሚገኝ አጥባቂ ባልሆነ ምኩራብም ያመልካል። ወደዛም ያመራው ከተለያዩ ዘር፣ ባህል የመጡ ለምሳሌም ጥቁር፣ እስያውያን፣ ነጮች ይሁዳውያን መኖራቸው ነው። ሚካኤል የቲፋኒን ይሁዳዊ ማንነቷን የመቀበል ዜና ሲሰማ ደስታ ተሰምቶታል። "ሰዎች በማንነታቸውና በመሰረታቸው ኩራት እንዲሰማቸው ልናበረታታቸው ይገባል" የሚለው ሚካኤል እንዲህ በአደባባይ ስለ ማንነቷም መናገሯ ኩራት እንደፈጠረበት አልደበቀም። ይሁዳዊ መሆን ይሁዳዊ ማንነታቸውን በተለያየ መንገድ ፈልገው የሚያረጋግጡ ሰዎች አሉ። ማንነትንም ሆነ እምነትን መቀየር ግላዊና ምስጢራዊ እንደመሆኑ መጠን ብዙዎችም ይህንኑ ጉዟቸውን ይፋ አያደርጉም። ከነዚህም መካከል ቤዛ አበበ አንዷ ናት ከሃይማኖት ገለል ካሉ ቤተሰቦች የተወለደችው ቤዛ ይሁዳዊነትን መጀመሪያ ያወቀችው በቀድሞ የወንድ ጓደኛዋ ነው። እምነቱን ማጥናት፤ እብራይስጥ ቋንቋን መማር ነበረባት። ለስድስት ወራት ያህልም ፈታኝ የሚባለውን ጥናት በፅናት አድርጋለች። "በአጠቃላይ አራት አመታት ያህል ወስዶብኛል። ትንሽ የተወሳሰበ ሂደት ነበረው፤ ነገር ግን ተወጥቸዋለሁ። ቁርጠኛነቴንም ያዩ ሰዎች ረድተውኛል" ብላለች። ብዙዎችም እንዲህ በአስቸጋሪ ሁኔታ ለምን ማለፍ እንደፈለገች ሲጠይቋት ቤዛም በምላሹ " ነፍስ የምትፈጠረው ይሁዳዊ ሆና ነው። ብትቀየርም በሆነ መንገድ እዚህ መንገድ ላይ ብትደርስ፤ ራስን የማግኘት ጉዞ ነው" በማለት ታስረዳለች። •ከኮርኔል በኮምፒውተር ሳይንስ ፒኤችዲ በማግኘት የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት የሆነችው ረድኤት አበበ በሌላ ቋንቋ ነፍስ ማን እንደሆነች፤ጉዞዋ የት እንደሆነች ታውቃለች፤ ያንን መንገድ መፈለግ ብቻ ነው የሚያስፈልገው። በዓለም ላይ የሚገኙ የይሁዳውያን እምነት ተከታዮች የቲፋኒ ሐዲሽ ባት ሚትዝፋህን ማክበር ዜና በደስታ ነው የተቀበሉት " የምስራች" መልዕክቶችም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ተዥጎድጉደዋል። ቤዛም በዚህ ዜና ከተደሰቱት መካከል ናት " በዚህ መንገድ ማንነቷን መቀበሏ በጣም ነው ያስደሰተኝ" ብላለች።
54341611
https://www.bbc.com/amharic/54341611
ቅርሶች ፡ የተዘረፉ ቅርሶች ሊመለሱ ይገባል ብሎ የተቃወመው የኮንጎ ተሟጋች በፈረንሳይ ፍርድ ቤት ቀረበ
ፈረንሳይ በቅኝ ግዛት ወቅት የዘረፈቻቻቸውን ቅርሶች ልትመልስ ይገባል በማለት በፈረንሳዩ ሙዝየም ተቃውሞ ሲያሰማ የነበረ የኮንጎው ተሟጋች ፍርድ ቤት ቀርቧል።
ከእርሱ በተጨማሪ እንዲሁ አራት ተሟጋቾችም በመዲናዋ ፓሪስ በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት በተጨማሪ መቅረባቸው ተዘግቧል። ኤምሪ ምዋዙሉ ዲያባንዛና አራቱ ተሟጋቾች ቅርሶቹን ሊሰርቁ ሞክረዋል በሚልም ውንጀላ ነው ፍርድ ቤት የቀረቡት። ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙም የአስር አመት እስራትና 176 ሺህ ዶላር ቅጣት ይጠብቃቸዋል። ክስተቱ የተፈጠረው ሰኔ ወር ላይ ሲሆን የአርባ አንድ ዓመቱ ተሟጋች ኳይ ብራንሊ በሚባለው ሙዝየም ውስጥ ገብቶ ከቻድ የተዘረፈ የሥርዓተ ቀብር ማስፈፀሚያ ቅርስ አንስቶ በህንፃው ውስጥ ማሳየት ጀመረ። ቅርሱ የ19ኛው ክፍለ ዘመን ወቅት የተገመተ ሲሆን ከቻድም በቅኝ ግዛት ተዘርፎ የተወሰደ ነው። ከዚያም በመቀጠልም በሌሎች ሙዝየሞችም እንዲሁ ተመሳሳይ ድርጊቶችን ፈፅሟል ተብሏል። ቫይስ መፅሄት ተሟጋቹን "እውነተኛ ኪሊሞንገር" ብሎታል። ኪሊሞንገር በብላክ ፓንተር ፊልም አንድ ገፀ ባህርይ ሲሆን ከአፍሪካ የተዘረፉ ሃብቶች በአውሮፓ ሙዝየም መከማቸት አጥብቆ የሚቃወም ነው። ሆኖም የፈረንሳይ ባለስልጣናት ድርጊቱን አውግዘውታል። "ቅርሶችን የመመለስ ጉዳይ ንግግርና ክርክር የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው" በማለት የሙዝየሙ ዳይሬክተር ኢማኑኤል ካሳርሄሩ መናገራቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በዘገባው አስነብቧል።
news-43619932
https://www.bbc.com/amharic/news-43619932
በአማርኛ የሚያንጎራጉረው ፈረንሳያዊ
'ልጅ ሊዮ' በሚለው በመድረክ ስሙ የሚታወቀው ሌዮናር በተለያዩ መድረኮች ላይ ከብዙ ታዋቂ ዘፋኞችም ጋር ተጫውቷል።
አማርኛ አቀላጥፎ የሚናገረው ልጅ ሊዮ የፈረንሳይ ዜግነት ያላቸው ቤተሰቦቹ አዲስ አበባ ለሥራ ሲመደቡ እሱም አዲስ አበባን ረገጠ። ምንም እንኳን የተማረው 'ሊሴ ገብረ ማሪያም' የፈረንሳይ ትምህርት ቤት ቢሆንም ለአማርኛ ቋንቋ ፍቅር ያደረበት በልጅነቱ ነው። በቤታቸው ከነበሩት ሠራተኞችና ከትምህርት ቤት ጓደኞቹ ጋር እየተነጋገረ ቀስ በቀስ አማርኛ ለመደ። አባቱ በኢትዮጵያ የነበራቸውን የ7 ዓመት የሥራ ቆይታ ጨርሰው ወደ ሌላ ሃገር ቢሄዱም ሊዮ ግን ለአማርኛና ለኢትዮጵያ የነበረው ፍቅር አልጠፋም። ከአባቱ ጋር ከሀገር ሀገር እየተዘዋወረ ያደገው ሊዮ ቋንቋ ለማወቅ ፍላጎት ብቻ ሳይሆን ፈጣንም ነበር። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ ዩኒቨርሲቲ ገብቶ አማርኛን ለመማር ወሰነ። አማርኛ ቋንቋን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ታሪክም የተማረው ሊዮ ሁለተኛ ዲግሪውን ቢይዝም ቋንቋውን በደንብ ለማወቅና አቀላጥፎ ለመናገር 10 ዓመታት እንደፈጀበት ይናገራል። ሊዮ በየ10 ዓመቱ ወደ ኢትዮጵያ የሚመላለስ ሲሆን ከሙዚቃው በተጨማሪም የተለያዩ ሥራዎችን ይሠራል። "ኢትዮጵያ ለኔ ሃገሬ ነች፤ ልቤም ኢትዮጵያዊ ነው" ይላል። ኢትዮጵያ ውስጥ ረዘም ላለ ጊዜ መኖሩና በምግብ ቤቱ ከሚያስተዳድራቸው ሠራተኞች ጋር በአማርኛ ብቻ መግባባቱ ቋንቋውን እንዲያዳብር እንደረዳው ይናገራል። ይህም አማርኛውን ለማሻሻል ከመጥቀሙም ባሻገር ለሙዚቃዬም አስተዋጽዖ አድርጓል ይላል። በተለይም ልጅ እያለ ከእኩዮቹ ጋር አብሮ ማሰለፉ አማርኛውን እንዲያሻሽል እንደረዳው ያስታውሳል። ''ከግቢ መውጣት ባይፈቀድልንም እንኳን በምኖርበት የሾላ ሰፈር ልጆች ብዙ ተምሬያለሁ፤ ከዚያም በተጨማሪ ብዙ ጊዜዬን ከዘበኛው ጋር አሳልፍ ነበር። ሬድዮ ሲያዳምጥም ካጠገቡ አልርቅም ነበር። ይሄም ብዙ ረድቶኛል '' ይላል አድጎ ዩኒቨርሲቲ ከገባም በኋላ ከልጆች ጋር ወደ ጭፈራ ቤት በሚሄድበትም ወቅት በባህላዊ ሙዚቃ ይወዛወዝ እንደነበር ይናገራል። ትናንቱን መለስ ብሎ በማስታወስም ''እኔ ከኢትዮጵያ ብወጣ እንኳን ኢትዮጵያ ግን ከሰውነቴ አትወጣም'' ይላል። ነዋሪነቱን በፈረንሳይ መዲና ያደረገው ልጅ ሊዮ የሙዚቃ አልበሙን በመሥራት ላይ ነው። "በፈረንሳይም ቢሆን አማርኛን የሚያናግሩኝ ሐበሾች አላጣም፤ ከአማርኛ አልፎ ክትፎ የሚጋብዙኝ ጓደኞችን አፍርቼያለሁ" በማለት በሳቅ ታጅቦ ይናገራል። አማርኛ እንዳይጠፋበትም በስካይፕም ሆነ በቫይበር ከኢትዮጵያዊ ጓደኞቹ ጋር እንደሚያወራ የሚገልጸው ልጅ ሊዮ አልፎ አልፎ ደግሞ በዩ ቲዩብ ላይ የተለያዩ የአማርኛ ዝግጅቶችን ፊልሞችንና ሌሎችንም በአማርኛ የተሠሩ ቪድዮዎችን ይከታተላል። ለሙዚቃ ለየት ያለ ፍቅር እንዳለው የሚናገረው ሊዮ ሰሜቱን ማንፀባርቅም ሆነ ማስረዳት የሚችለው በሙዚቃ ብቻ እንደሆነ ይናገራል። ''በተፈጥሮዬ ዜማ በውስጤ ይሽከረከራል። ብዙ ጊዜ መጀመሪያ ዜማው ነው የሚመጣልኝ'' ይላል። ዜማው አንዴ መስመር ከያዘለት በኋላ ግጥሞቹን ከኢትዮጵያዊ ጓደኛው ጋር አብሮ በመሆን እያስተካከሉ ሙዚቃውን ያቀናብራሉ። የሙዚቃ ፍቅሩ የተፀነሰው በልጅነቱ እንደሆነ የሚናገረው ሊዮ ሙዚቃ ለእርሱ ትልቅ ስፍራ እንዳለው ይናገራል። ''ለሰውነት ምግብ እንደሚያስፈልግ ሁሉ ለአዕምሮም ምግብ ያስፈልጋል፤ ለእኔ ደግሞ ሙዚቃ እንደ ምግብ ነው'' ይላል። ሬጌ ሙዚቃ ማዳመጥ የሚወደው ሊዮ እራሱን በአንድ ሙዚቃ አይወስንም በተቃራኒው የተለያዩ ሃገራት የመኖር ልምዱን የሚገልጽበት አንዱ መንገድ በሙዚቃ ነው። ''ይህች ዓለም የተለያዩ ሃገራት አላት። እኔ ደግሞ በብዙ ሃገራት ነው ያደኩትና ያንን ሁሉ ማንፀባርቅ የምችለው በሙዚቃዬ ነው'' በማለት ያብራራል። አሁን ሙዚቃ ላይ ብቻ እያተኮረ እንዳልሆነ የሚያስረዳው ሊዮ የተለያዩ ሥራዎችን በመሥራት እንደ ማንኛውም ሰው መኖር እንደሚፈልግ ተናግሯል። የሚወደውን ሙዚቃም ለመሥራትም በዚሁ ምክንያት ጊዜ እንደፈጀበት ያስረዳል። ሙዚቃን ተገዶ ሳይሆን እሱ ሲያሰኘው የሚሠራው ሊዮ ለወደፊቱ በየሃገራቱ እየዞረ ሙዚቃውን የማቅረብ ዕቅድ አለው። አሁንም ቢሆን በሚኖርበት አካባቢ በተለያዩ መድረኮች ላይ እየተገኘ ሙዚቃውን ይጫወታል። ታዲያ በእነዚህ መድረኮች በአማርኛ ሲያንጎራጉር የሰሙ ታዳሚዎቹ አማርኛ በመናገሩም ይደነቃሉ። በተደጋጋሚም ''ይህ ፈረንጅ ከየት አመጣው ይሄን አማርኛ'' ሲሉ ሰምቷቸው ያውቃል። ለኢትዮጵያ ያለውን ጥልቅ ፍቅር ከመናገር ወደኋላ የማይለው ሊዮ ''ከኢትዮጵያ ጋር ያለኝ ግንኙነት መቼም አይቋረጥም። ኢትዮጵያ መኖር በጣም ብወድም እንኳን አንድ ቦታ ግን ስላላደኩኝ በየተወሰነ ጊዜ መቀየር ግድ ይለኛል'' ይላል። ከልጅ ሊዮ ጋር ያደረግነውን ቆይታ ለማዳምጥ ከታች ያለውን ቪድዮ ያጫውቱ። ከልጅ ሊዮ ጋር ቆይታ
news-56755324
https://www.bbc.com/amharic/news-56755324
ኮሮረናቫይረስ፡ በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ጽኑ ህሙማን ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት አሻቀበ
የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱ ከታወቀ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የጽኑ ታማሚዎች ቁጥር ከአንድ ሺህ ማለፉን ተገለጸ።
የጤና ሚኒስቴርና የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ሐሙስ ሚያዝያ 07/2013 ዓ.ም ባወጣው ዕለታዊ የወረርሽኙ መግለጫ ላይ እንዳመለከተው በበሽታው በጽኑ የታመሙ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 031 መድረሱን አመልክቷል። ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱ ከታወቀ ከአንድ ዓመት በኋላ ባሉት ሦስት ወራት፤ ማለትም ባለፉት ጥር፣ የካቲትና መጋቢት ውስጥ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ቀስ በቀስ እያሻቀበ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እየደረሰ መሆኑን የኢትዮጵያ የጤና ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ ሲገልጹ ነበር። የወረርሽኙ በማኅበረሰብ ደረጃ መስፋፋቱ አሳሳቢ ከመሆኑ በተጨማሪ በወረርሽኙ ሳቢያ በጽኑ የሚታመሙና ለሞት የሚዳረጉ ሰዎችም ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። ከወራት በፊት ምርመራ ከሚያደርጉ ሰዎች መካከል ቫይረሱ ይገኝባቸው የነበሩት ከአምስት መቶ ብዙም ሳይርቅ በመቶዎቹ የሚቆተሩ የነበረ ሲሆን አሁን ግን በየቀኑ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች በበሽታው ተይዘው ይገኛሉ። ከዚህ በተጨማሪም በበሽታው ክፉኛ ታመው የጽኑ ህሙማን ክትትልና ድጋፍን የሚሹ ሰዎች ቁጥር ከአምስት መቶ በታች ሆኖ ለረጅም ጊዜ የቆየ ሲሆን፤ ባለፉት ሁለት ወራት ግን አሃዙ ከአምስት መቶ አልፎ አሁን ከአንድ ሺህ በላይ ደርሷል። በተመሳሳይ በየቀኑ በበሽታው ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በአስራዎቹ የሚቆጠር ሆኖ ለረጅም ጊዜ ቆይቶ አሁን ግን ከሃያዎቹ አስከ ሰላሳዎቹ የሚደርሱ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ እየተመዘገበ ነው። በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሚያዙና የጽኑ ህሙማን ህክምናና ክትትል የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ የሰው ሰራሽ መተንፈሻ መሳሪያና የኦክስጂን እጥረት እያጋጠመ መሆኑ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገልጾ የነበረ ሲሆን ቁጥሩ በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩ ችግሩን የበለጠ ያባብሰዋል። ተቋሙ በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ ውስጥ በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከዕለት ዕለት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በመምጣቱ የባለሙያ ድጋፍና እንክብካቤ የሚሹ ሰዎች ቁጥር "የህክምና ማዕከላት ማስተናገድ ከሚችሉት አቅም በላይ" እየሆነ መምጣቱን ጨምሮ ገልጿል። በዚህም ሳቢያ በኮሮናቫይረስ በጽኑ ታምመው በህክምና ተቋማት ድጋፍ ለማግኘት ለሚመጡ ህሙማን አገልግሎት የሚውሉ "የሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ (ቬንትሌተር) እና የኦክስጅን እጥረት እያጋጠመ ነው" ሲል ገልጿል። የኮሮናቫይረስ የመተንፈሻ አካላትን በተለይም ሳንባን የሚያጠቃ ሲሆን በበሽታው ክፉኛ ለተጠቁ ጽኑ ህሙማን ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መርጃ (ቬንትሌተር) እና ኦክስጂን ህይወታቸውን ለመታደግ ለሚደረገው ጥረት በእጅጉ አስፈላጊ ናቸው። በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ በጽኑ የታመሙ ሰዎችን ህይወት ለመታደግ በአሁኑ ወቅት በአገልግሎት ላይ የሚገኙት የሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መርጃ ቬንትሌተሮች ቁጥር ከ500 ብዙም የበለጡ እንዳልሆኑ ሲገለጽ ቆይቷል። በየዕለቱ በበወረርሽኙ በጽኑ ታመው ድጋፍ የሚሹት ህሙማን ቁጥር በመቶዎች ከመቆጠር አልፎ በአሁኑ ጊዜ ከአንድ ሺህ በላይ መድረሱ የጤና ተቋማት ለህሙማኑ እንክብካቤና ድጋፍ ለመስጠት ችግር እየገጠማቸው መሆኑ ቀደም ሲል መገለጹ ይታወሳል። በተለይም በወረርሽኙ በጽኑ ታመው የቬንትሌተርና የኦክስጂን ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ህሙማን ቁጥር እየጨመረ በመሆኑ የነፍስ አድን አገልግሎቱን መስጠት ከማይቻልበት ደረጃ ላይ ከደረሰ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ሊያሻቅብ ይችላል። በአሁኑ ወቅት በመላው አገሪቱ በየዕለቱ የሚመዘገበው በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የገለጸው ኢንስቲትዩቱ፤ ከዚሁ ጋር ተያይዞም በወረርሽኙ ሳቢያ የጽኑ ህሙማን የህክምና አገልግሎት የሚፈልጉ ህሙማንና ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር "አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል" ይገኛል ብሏል። ሐሙስ ዕለት በወጣው የበሽታው ዕለታዊ ሪፖርት መሠረትም 33 ሰዎች በኮቪድ-19 በሽታ ምክንያት መሞታቸው ተገልጿል። በዕለቱ 8 ሺህ 878 ሰዎች ምርመራ ተደርጎላቸው 2 ሺህ 149ኙ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን፤ ቀደም ሲል በበሽታው ተይዘው ከነበሩት መካከል ደግሞ 1 ሺህ 288 አገግመዋል። አስካሁን በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ውስጥ 236 ሺህ 554 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3 ሺህ 285 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 175 ሺህ 879 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
news-51232348
https://www.bbc.com/amharic/news-51232348
ቻይና ኮሮናቫይረስ፡ በመቶ ሚሊዮኖች በሚደረጉ ጉዞዎች ሥርጭቱ ሊስፋፋ እንደሚችል ተሰግቷል
ቻይና በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎቿ በሚያከብሩት ሉናር አዲስ ዓመት ተከትሎ በሁቤ ግዛት የተከሰተውን ገዳይ ቫይረስ ሥርጭት ለመቆጣጠር ግብ ግብ ገጥማለች።
ሉናር የቻይናውያን አዲስ ዓመት ሲሆን በድምቀት የሚከበር በዓል ነው። ይህ በዓል በዓለማችን በርካታ ሰዎች ጉዞ የሚያደርጉበት ወቅት ሲሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በዓሉን ለማክበር ወደ አገራቸው ይገባሉ። ባለሥልጣናት በቤጂንግ እና ሆንግ ኮንግ የሚደረጉ ትላልቅ ዝግጅቶች እንዳይካሄዱ ሰርዘዋል። ሆንግ ኮንግ ዓለም አቀፍ 'ካርኒቫሎችን' እና ዓመታዊ የሆነውን የእግር ኳስ ውድድር እንዳይደረግ ከልክላለች። • ቻይና የተከሰተው ገዳይ ቫይረስ በርካቶችን ሳይበክል አልቀረም • ቻይና ውስጥ የተከሰተው ቫይረስ አሜሪካ ደረሰ ቫይረሱ ከተከሰተበት ውሃን ግዛት አውሮፕላን ወይም ባቡር እንዳይገባም እንዳይወጣም ተከልክሏል፤ መንገዶች መዘጋታቸው ተነግሯል። በዉሃን ግዛት ሰዎች የፊት ጭምብል አድርገው መንቀሳቀሳቸው ግድ ሆኗል። ዉሃንን ጨምሮ በሁቤ ግዛት የሚገኙ ሌሎች ከተሞች የሕዝብ የመጓጓዣ አገልግሎቶችን ከልክለዋል። የቻይና ባለሥልጣናት እንዳሉት በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 25 ከፍ ያለ ሲሆን 830 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በቫይረሱ እንደተያዙ ከተረጋገጡት ሰዎች መካከል 177ቱ በአስጊ ሁኔታ የሚገኙ ሲሆን፤ 34 ከበሽታው ድነው ከህክምና ተቋም መውጣታቸውን የአገሪቷ የጤና ኮሚሽን አስታውቋል። ከዚህም ባሻገር 1,072 በቫይረሱ ሳይያዙ እንዳልቀሩ የተጠረጠሩ ሰዎች መኖራቸውንም ኮሚሽኑ አክሏል። የዓለም ጤና ድርጅት ከቻይና ውጭ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 13 መሆናቸውና ቁጥራቸው አነስተኛ በመሆኑ ቫይረሱ 'ዓለም አቀፍ የጤና ቀውስ' ነው ሲል አልፈረጀውም። ይሁን እንጅ "ምን አልባት አስቸኳይ ትኩረት ከሚያስፈልጋቸው አንዱ ሊሆን ይችላል" ሲሉ የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጀነራል ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ተናግረዋል። ባሳለፍነው ማክሰኞ አሜሪካ ሁለተኛውንና በቫይረሱ ሳይያዝ እንዳልቀረ የተጠረጠረ ሰው ምርመራ እያደረገች እንደሆነ ገልጻለች። ሌሎች የዓለም አገራትስ ? ታይላንድ፣ አሜሪካ፣ ታይዋን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ቬየትናምና ሲንጋፖር ባሳለፍነው ማክሰኞ በበሽታው የተያዙ ሰዎች መገኘታቸውን አስታውቀዋል። ጃፓንና ደቡብ ኮሪያ በቫይረሱ የተያዘ ሁለተኛ ሰው ማግኘታቸውን አረጋግጠዋል። እስካሁን ከቻይና ውጭ 13 በበሽታው የተያዙ ሰዎች የተገኙ ሲሆን ከቻይና ቀጥሎ ታይላንድ በብዛት በበሽታው የተያዙ ሰዎች የተገኙባት አገር ሆናለች። ዩናይትድ ኪንግደምና ካናዳን ጨምሮ በበሽታው ሳይያዙ እንዳልቀሩ የተጠረጠሩ ሰዎችን እየመረመሩ ነው። የአሜሪካ ባለሥልጣናት በቴክሳስ ግዛት ሁለተኛውን በቫይረሱ የተጠረጠረ ሰው ላይ ምርመራ እያደረገች እንደሆነ ያሳወቀችው ባለሰፈው ማክሰኞ ነበር። ታማሚው ከቻይናዋ ዉሃን ወደ ቴክሳስ ያቀናና የቴክሳስ ኤ ኤንድ ኤም ዩኒቨርሲቲ ተማሪ መሆኑ ታውቋል። • የኢቢሲ ጋዜጠኞች ለምን ይጠፋሉ? በአሜሪካ እስካሁን በቫይረሱ እንደተያዘ የተረጋገጠው በዋሽንግተን ግዛት ሲያትል ሲሆን ግለሰቡ አገግሞ ከሆስፒታል መውጣቱ ተገልጿል። በርካታ ባለሥልጣናት ዱባይና አቡዳቢ አየር መንገዶችን ጨምሮ ከቻይና ለሚመጡ መንገደኞች የጤና ምርመራ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። ታይዋን ከውሃን የሚመጡ መንገደኞች እንዳይገቡ እገዳ ጥላለች። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወደ ቻይና የሚያቀኑ አሜሪካዊያን ተጓዦች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አስጠንቅቋል።
53237142
https://www.bbc.com/amharic/53237142
ፌደራል ፖሊስ ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ በጥይት የተመታው መኪናው ውስጥ መሆኑን ገለፀ
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል እንደሻው ጣሰው የድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን አሟሟት በተመለከተ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን አመሻሹ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።
ኮሚሽነሩ በመግለጫው ላይ እንደተናገሩት ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ከመኪናው ወርዶ እንደተመለሰና ፤ ወደ መኪናው ከገባ በኋላ ተጠርጣሪዎቹ የመኪናውን በር ከፍተው በጥይት መትተውታል ብለዋል። ድምፃዊው ከመኪናው ለምን ወርዶ እንደተመለሰ ኮሚሽነሩ ያሉት ነገር የለም። ኮሚሽነር ጄነራል እንደሻው በወንጀል ድርጊቱ ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሰዎች መኖራቸውን አስታውሰው "በክትትል ሥር ያሉም አሉ" ብለዋል። የፌደራል ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን የምርመራ ቡድን በጋራ ማዋቀራቸውን የገለፁት ኮሚሽነሩ ቀን ከማታ መረጃዎች ሳይጠፉ ከወንጀል ሥፍራ አስፈላጊ መረጃዎችን ለመውሰድ እየሰሩ መሆናውን ገልፀዋል። አክለውም "ከእሱ ጋር የተያያዙ ኬዞችን በማጣራት በአጭር ጊዜ ለህብረተሰቡ የበሰለ መረጃ እናቀርባለን ብለን እናምናለን" ብለዋል ኮሚሽነር ጄነራሉ። "የወንጀሉ አፈጻጸም የተደራጀ እና የረቀቀ ስለሆነ ትዕግስት የሚጠይቅ ነው" ያሉት ኮሚሽነር ጄነራሉ፤ ተጽእኖ ፈጣሪ የሆኑ ግለሰቦች ላይ ግድያ ከሚፈጸምባቸው ምክያቶች አንዱ "አገር ወደ ትርምስ እንድትገባ ነው" ብለዋል። "ስለዚህ ይህን የምርመራ አካላችን አድርገን በጥንቃቄ ጠንካራ መርማሪዎች መድበን የማጣራት ሥራው በስፋት እየተሰራ ነው የሚገኘው" በማለት አስረድተዋል። ኮሚሽነሩ "በድርጊቱ የተቆጡ ወጣቶች የሰላማዊ ዜጎች ንብረትን በአዲስ አበባ ከተማ ጨምሮ በተለያየ የአገራችን ክፍሎች እንዳወደሙ መረጃ ደርሶናል" በማለት መሰል ድርጊቶች ስህተት መሆናቸውን ጠቁመው "እያንዳንዱ እርምጃችን ኃላፊነት በተሞላበት መልኩ መሆን አለበት" በማለት መልዕክት አስተላለፈዋል።
48836208
https://www.bbc.com/amharic/48836208
ማጤስ እንደሳንባችን ሁሉ ዓይናችንንም ይጎዳል
በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዩናይትድ ኪንግደም ዜጎች በማጨስ ብቻ እይታቸውን አደጋ ላይ እየጣሉ መሆኑን የሕክምና ባለሙያዎች ተናገሩ።
የዓይን ሕክምና ባለሙያዎች እንደሚሉት ከአምስት ሰዎች መካከል አንዱ ብቻ ነው ትምባሆ ማጨስ የዓይን ብርሀንን እንደሚያሳጣ እውቀት ያለው። ከማያጨሱ ሰዎች ይልቅ ይላሉ ባለሙያዎቹ፤ የሚያጨሱ ሰዎች በሁለት እጥፍ የዓይን ብርሃናቸውን የማጣት እድላቸው ከፍ ያለ ነው። የዓይን ህክምና ባለሙያ የሆኑት አይሻ ፋዝላኒ እንደሚሉት "ሰዎች ማጨስና ካንሰር ያላቸውን ግንኙነት በሚገባ ያውቃሉ፤ ነገር ግን ማጨስ የአይን ብርሃን ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት አይረዱትም።" ትምባሆ ማጨስ የዓይን ብርሃንን በከፍተኛ ሁኔታ ለጉዳት ይዳርጋል ይላሉ ባለሙያዎቹ። • ኢትዮጵያ ከዓለም ጥቂት አጫሾች ያሉባት አገር ናት • የሰሞኑ የአዲስ አበባ እስርና ሕጋዊ ጥያቄዎች • "ኢህአዴግ ነፃ ገበያም፣ ነፃ ፖለቲካም አላካሄደም" ፀደቀ ይሁኔ (ኢንጂነር ) የሲጋራ ጭስ አይንን የሚያቃጥልና እይታን የሚጎዳ መራዥ ኬሚካል በውስጡ ይዟል። ባለሙያዎቹ አክለውም ማጨስ ከስኳር ጋር ተያይዞ የሚመጣ የዓይን ህመምን በማባባስ የደም ስሮችን ይጎዳል ይላሉ። አጫሾች ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚመጡ የእይታ መቀነሶች ከማያጨሱት ይልቅ በሶስት እጥፍ ተባብሶ የሚታይባቸው ሲሆን ጥቃቅን ነገሮች ለመለየት ያላቸው ችሎታም ይደክማል። ዶ/ር አይሻ "ማጨስ ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚመጣን የእይታ መድከም በማባባስ ለዓይነስውርነት የማጋለጥ እድሉ ከፍተኛ በመሆኑ አጫሾች ማጤስ ለማቆም መወሰን ይኖርባቸዋል" ሲሉ ምክራቸውን ይለግሳሉ። ከማያጨሱ ሰዎች ይልቅ የሚያጨሱ ሰዎች በድንገተኛ የዓይን ብርሃን መጥፋት የመጋለጣቸው እድል 16 እጥፍ የላቀ ነው የሚሉት ባለሙያዎች፤ ይህ የሚሆነው ወደ ዓይን የሚሄደው የደም ፍሰት በድንገት ሲቋረጥ መሆኑን ይናገራሉ። ባለሙያዎቹ አክለውም ማጨስን ማቆም አልያም ማቋረጥ የአይን ብርሃናን ከአደጋ ለመከላከል ሁነኛ መፍትሄ መሆኑን ጠቅሰው በየጊዜው ምርመራ ማድረግንም ይመክራሉ።
news-49463976
https://www.bbc.com/amharic/news-49463976
ዘረኝነት ሽሽት ጋና የከተመው አሜሪካዊ
አፍሪቃ አሜሪካዊው ኦባዴሌ ካምቦን ጋና የገባው 2000 ዓ.ም. ላይ ነበር፤ ከዚያ በኋላ ዞር ብሎ ወደ ትውልድ ሃገሩ አሜሪካ ማየት አላስፈለገውም።
ለዚህ ደግሞ ምክንያት የሆነኝ በቆዳ ቀለሜ ምክንያት ለእሥር መብቃቴ ነው ይላል ካምቦን። አንድ ወቅት ከፍተኛ ባሪያዎች የተሸጡባትና የተለወጡባት ጋና አሁን ለካምቦን የነፃነት ምድሩ ነች፤ የተደላደለ ሕይወት እየመራም ይገኛል። ወደ ኋላ ማየት አይሻም፤ የአሜሪካ መንገዶች ላይ በፖሊስ መገላመጥን ጠልቷል፤ ልጆቹ በቀለማቸው ምክንያት ብቻ የፖሊስ ቀለሃ ሲሳይ እንዲሆኑም አይፈልግም። ልጆቹን አሜሪካ ውስጥ ስለማሳደግ ሲያስብ ታሚር ራይስ ድቅን ይልበታል። ክሊቭላንድ በተሰኘችው ከተማ መጫወቻ ሽጉጥ ይዞ እንደወጣ የቀረው ራይስ፤ 'ትክክለኛ ሽጉጥ የያዘ መስሎን ነው ተኩስን የገደልነው' ባሉ ፖሊሶች በ14 ዓመቱ ምድርን የተሰናበተው ራይስ። ገምዳላ ፍርድ የ14 ዓመቱ ታዳጊ ሞት ተቃውሞን ቀስቅሶ ነበር፤ 'ብላክ ላይቭስ ማተር' የተሰኘው እንቅስቃሴም ጉዳዩን እጅጉን አጡዞት ፍትህ ፍለጋ ብዙ ጮኋል። ካምቦን 'ሕይወቴን ቀያሪ' ያላት አጋጣሚ የዛሬ 12 ዓመት ገደማ ተከሰተች። በሚኖርባት ቺካጎ ያሉ ፖሊሶች በቁጥጥር ሥር አውለው ፍርድ ቤት ገተሩት። 'መኪናው ውስጥ የጦር መሣሪያ ይዞ አግኝተነዋል፤ ጥፋት ሊፈፅምም ነበር' ሲሉ ለዳኛው አቤት አሉ። እርግጥ ነው ካምቦን የጦር መሣሪያ ይዞ ነበር። ጥይት ያልጎረሰ ፍቃድ ያለው ሽጉጥ። ፍርድ ቤት ቆሞ ክሱን ሲሰማ ግን ደነገጠ። «የዛኔ ነው ለራሴ አንድ ቃል የገባሁት። ሁለተኛ አእምሯቸው የሞሰነ ነጭ አሜሪካዊ ፖሊሶች ያሉበት ፍርድ ቤት መቆም አልፈልግም ያልኩት።» ቺካጎ ውስጥ ዩኒቨርሲቲዎችና ሌሎች ትምህርት ቤቶች በማስተማር ሕይወቱን ይገፋ የነበረው ካምቦን በነፃ ተለቀቀ። አእምሮው ግን እረፍት አላገኘችም። ለአንድ ዓመት ያክል ያጠራቀማትን 30 ሺህ ዶላር [863 ሺህ ብር] ይዞ ጉዞ ወደ አክራ፤ ጋና። ባለቤቱ ካላ አብራው ወደ ጋና መጣች። ጥንዶቹ አሁን የሶስት ልጆች ወላጅ ናቸው። አማ፣ ኩዋኩ እና አኮስዋ። አፍሪቃዊ መንፈስ ካምቦን፤ አሁን የዶክትሬት ድግሪውን በቋንቋ ጥናት ከጋና ዩኒቨርሲቲ አግኝቷል። እዚያው ዩኒቨርሲቲ 'አፍሪቃን ስተዲስ' በተሰኘው ትምህርት ክፍል ውስጥ በአስተማሪነት ያገለግላል። ወደ ጋና ከተመሰለ ወዲህ አንድም ቀን በቆዳው ቀለም ምክንያት የዘረኝነት ጥቃት ደርሶበት አያውቅም። «የሚገርም ነው! ነጭ አሜሪካውያን ዩኤስ ውስጥ እንዲህ ነው የሚኖሩት ማለት ነው። 'የሆነ ነገር ያጋጥመኝ ይሆን?' ሳይሉ በነፃነት መንቀሳቀስ።» ነገር ግን ጋና ውስጥ ሕይወት ፍፁም ናት ማለት አይደለም ይላል ካምቦን። «ስለ አፍሪቃዊ መንፈስ ስታወራ ሰዎች ራስታ ነው ብለው ያስባሉ፤ ነጮች ያስተቀዋወቁን እምነት ነው አሁንም ጎልቶ የሚታየው። አፍሪቃውያን የራሳቸው ኃይማኖት ሊኖራቸው እንደሚችል ብዙም አይንፀባረቅም።» በሚኖርበት አፓርታማ ያሉ ጋናውያን ሕፃናት አንድም ሃገር አቀፍ ወይንም አፍሪቃዊ ቋንቋ መናገር አለመቻላቸው እንዳስደነቀው አይሸሽግም። አቶ ካምቦን ወደ ጋና ከመጣ ወዲህ ሁለት የምስራቅ አፍሪቃ ቋንቋዎችን ለምዶ ቅኔ መዝረፍ ጀምሯል። አካን እና ዮሩባ ቋንቋዎችን አቀላጥፎ ይናገራል። ዎሎፍ የተሰኘውን ቋንቋም ተክኖበታል። ስዋሂሊ እና ኪኮንጎ ቋንቋዎችንም በበቂ ሁኔታ ይረዳቸዋል። የጋንዲ ሃውልት ይፍረስ ካምቦን፤ የቅኝ ግዛት አዳፋ አሻራዎች እንዲፋቁ የበኩሉን አስተዋፅኦ ያደርጋል። ባለፈው ዓመት የሕንድ ነፃነት መሪ የሚባለው ማሕትማ ጋንዲ ሃውልት ከጋና ዩኒቨርሲቲ እንዲወገድ ቅስቀሳ አካሂዷል፤ ተሳክቶለታልም። ደቡብ አፍሪቃዊያንን ዘረኝነት በተጠናወተው ስድብ ያንቋሸሸና ሕንዶች ከጥቁር ሕዝቦች የተሻሉ ናቸው ሲል የተናገሩ ነው ይሉታል ጋንዲ። «ለገዛ ጀግኖቻችን ክብር የሌለን እና ሌሎችን ከፍ ከፍ የምናደርግ ከሆነ ችግር አለ ማለት ነው።» ወደ ሃገር ቤት የጋናው ፕሬዝደንት ናና አኩፎ አዶ የያዝነው የጎርጎሮስውያን ዓመት 2019 'የመመለሻ ዓመት' ነው ሲሉ ይፋ አድርገዋል። በባሪያ ንግድ ምክንያት እናት ሃገራቸውን ጥለው የሄዱ አፍሪቃውያን ሲመለሱ እጅ ዘርግቶ መቀበል ግዴታችን ነው ይላሉ ፕሬዚዳንቱ። የጋና ቱሪዝም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤትም ይህንን አጋጣሚ ተጠቅሞ ጋናን ለማስተዋወቅ ደፋ ቀና እያለ ነው። ካምቦን እንቅስቃሴው የሚደገፍ ነው ይላል። ግን አትርሱ ሲል ያስጠነቅቃል. . . ውጭ ሃገራት የሚኖሩ አፍሪቃውያን 'ኤቲኤም' አይደሉም።