id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
53180025
https://www.bbc.com/amharic/53180025
ከኮሮና ያገገሙት የ114 ዓመቱ አዛውንት ሕክምናቸውን ጨርሰው ቤታቸው ገቡ
ከኮሮናቫይረስ አገግመው ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል ለተጨማሪ ሕክምና ተልከው የነበሩት የ114 ዓመት አዛውንት ሕክምናቸውን ጨርሰው መውጣታቸውን በየካቲት ሆስፒታል የውስጥ ደዌ ህክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ሊያ ፋንታሁን ለቢቢሲ ተናገሩ።
ዶ/ር ሊያ በየካቲት ሆስፒታል ለግለሰቡ ሕክምና ሲያደርጉ እንደነበር ለቢቢሲ ገልፀው፣ ግለሰቡ ያለ መሳሪያ ድጋፍ መተንፈስ በመቻላቸውና የነበሩባቸውን ኢንፌክሽኖች በመታከማቸው ከሆስፒታል መውጣታቸውን ገልፀዋል። ግለሰቡ እድሜያቸው 114 ይሆናል ተብለው የተጠየቁት ዶክተሯ " የ114 ዓመት አዛውንት ናቸው። ልጆቻቸውም የልጅ ልጆቻቸውም አብረዋቸው አሉ" ሲሉ መልሰዋል ዶ/ር ሊያ ፋንታሁን። የልጅ ልጃቸው ቢንያም ልኡልሰገድም ለቢቢሲ እንደገለፀው አያቱ እድሜያቸው 114 ነው። ሳል ይዟቸው መኖሪያ ሠፈራቸው በሚገኘው ጤና ጣብያ ሲታከሙ እነደነበር ገልጾ ከእርሳቸው በተወሰደው ናሙና ኮቪድ-19 እንዳለባቸው በመታወቁ ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል መግባታቸውን ይናገራል። ግለሰቡ በቅድሚያ በኤካ ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው የቆዩት ለአስራ አራት ቀን ነው። ከዚያም በሕክምናው ጋር በተያያዘ ኢንፌክሸን ስለነበረባቸው ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል ተዘዋውረው ነበር። ከኮቪድ-19 ነጻ መሆናቸው ከተረጋገጠ በኋላ በየካቲት ሆስፒታል የጀመሯቸውን አንቲባዮቲክ መድኃኒቶችና ኦክስጅን ይወስዱ እንደነበር ዶ/ር ሊያ አክለው ገልፀዋል። የካቲት 12 ሆስፒታል ከገቡ ቀናት እንዳለፏቸው የገለፁት ዶ/ር ሊያ፣ ቀስ በቀስ ያለ መሳሪያ ድጋፍ መተንፈስ በመቻላቸው ወደ ቤታቸው ዛሬ መሸኘታቸውን ተናግረዋል። የልጅ ልጃቸው ቢንያምም ዛሬ ተሽሏቸው ወደ ቤታቸው ገብተዋል ሲል ለቢቢሲ አረጋግጧል። በኮሮናቫይረስ ተይዘው በአዲስ አበባ በሚገኘው ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ሕክምና ሲከታተሉ የነበሩ የ114 የእድሜ ባለጸጋ ከበሽታው አገግመው መውጣታቸውን የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ያሬድ አግደው በፌስቡክ ገጻቸው ያስታወቁት ትናንት ነበር። አዛውንቱ ለተጨማሪ ህክምና የካቲት 12 ሆስፒታል ገብተው ለአራት ቀናት ያህል ቆይተዋል። በኢትዮጵያ እስካሁን የተደረገው የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ 232,050 ሲሆን 5,175 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። 81 ሰዎች ከቫይረሱ ጋር በተገናኘ ህይወታቸው ሲያልፍ 1,544 ሰዎች ደግሞ ማገገማቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ይገልፃል። በአሁን ሰዓት ቫይረሱ ያለባቸው 3 ሺህ 548 ሰዎች ሲሆኑ 30 ሰዎች በፀና ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የጤና ሚኒስቴር ሪፖርት ጨምሮ ያሳያል።
news-45516506
https://www.bbc.com/amharic/news-45516506
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጉዳት ለማድረስ የሚሞክሩትን እንደማይታገሱ አስጠነቀቁ
ዛሬ ረፋድ ላይ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ በሚገኙት ሽሮሜዳ፣ አዲሱ ገበያ፣ ሾላ እና እንቁላል ፋብሪካ አካባቢዎች በወጣቶች መካከል መጠነኛ ግጭት እንደረበረ እማኞች ለቢቢሲ ተናገሩ።
ኮሚሽነር ጄኔራል ዘይኑ ጀማል በግጭቱም የቤት እና መኪና መስኮቶች ተሰባብረዋል፣ የትራንስፖርት አገልግሎት ለተወሰኑ ሰዓታት ተቋርጧል። የፌዴራል ፖሊስ አባላት ግጭቱን ለማስቆም በስፍራው ሲንቀሳቀሱ እንደነበር እና ይህ ዘገባ በታተመበት ሰዓት ነገሮች እየተረጋጉ እንደሆነ እማኞች ጨምረው ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ ግንኙነት ቢሮ ም/ሃላፊ ወ/ሮ ሃይማኖት ዘለቀ በበኩላቸው ለአዲስ ቴሌቭዥን እንደገለፁት ግጭቱን ወደ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ለማሸጋገር ሙከራ መደረጉን ጠቅሰው ተገቢ ያልሆኑ ነገሮች ካሉ መስተካከል ያለባቸው በኃይል እና በፀብ አጫሪነት ሳይሆን በከተማ አስተዳደሩ አማካይነት በህግ አግባብ እንደሆነ ሲናገሩ ተሰምተዋል። • የሕዝብ ፍላጎት ካለ ባንዲራን መቀየር ይቻላል፡ ጠ/ሚ ዐብይ • "የሰንደቅ ዓላማ ጉዳይ የህዝቡን ውይይት መጠየቁ አይቀሬ ነው" - አቶ ንጉሡ ጥላሁን • የቀድሞው የሶማሌ ክልል ሰንደቅ አላማ እንዲመለሰ ተደረገ የኦነግ የሥራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት እና ከፍተኛ አመራሮችን ለመቀበል የተቋቋመው ኮሚቴ አስተባባሪ አቶ ኢብሳ ነገዎ ለቢቢሲ እንደተናገሩት እየታየ ያለው «ጠብ አጫሪነት» ሊቆም እንደሚገባ መክረው የቄሮ ወጣቶች በሚታወቁበት ሰላማዊ ትግል እንጂ በንብረት ማውደም እና ጠበኝነት ውስጥ እንዳይሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል። «ይሄንን አቀባበል ለማደፍረስ ለሚፈልጉ ኃይሎች መጠቀሚያ ከመሆን ታቀቡ» ሲሉም አሳስበዋል። በቅዳሜው አቀባበል ከ2ሚሊየን በላይ ሰዎች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የተናገሩት አስተባበሪው አቀባበሉን ሰላማዊ ለማድረግ ከአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ጋር በቅርበት እየሰሩ እንደሆነ ተናግረዋል። ሁኔታዎች እንዲረጋጉ በማሰብ ድርጅታቸው ከግንቦት ሰባት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን መግለጫ እና የሰላም ጥሪ እንዳስተላለፉም አብራርተዋል። የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀኔራል ዘይኑ ጀማልም ለሀገር ውስጥ የዜና ተቋማት በሰጡት መግለጫ «ማንም ሰው፣ ጉልበተኛ ነኝ ብሎ በህዝብ ላይ፣ በህዝብ እና ሀገር ተቋማት ላይ ጉዳት ሲያደርስ ቁጭ ብለን የምናይበት ሁኔታ ሊኖር አይችልም» ሲሉ አስጠንቅቀዋል። አክለውም የአዲስ አበባ ወጣቶች ማንንም የመከልከል ሃላፊነት እንዳልተሰጣቸው፣ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ጎዳናዎች ወጥተው ከኦሮሚያ ወጣቶች ጋር መጋጨታቸውን ማቆም እንዳለባቸው ተናግረዋል ። «የአሮሚያ ወጣቶችም በሰላማዊ ሁኔታ ባንዲራቸውን መስቀል ይችላሉ» ያሉት ኮሚሽነር ጄኔራሉ ጎዳናዎች እና የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች ግን የህዝቡ የጋራ ንብረት ስለሆኑ የራስን አርማ ቀለም ለመቀባት መሞከር ተገቢ እንዳልሆነ አሳስበዋል።
55127132
https://www.bbc.com/amharic/55127132
አውስትራሊያ ሐሰተኛ ምስል በመለጠፉ ቻይና ይቅርታ ትጠይቀኝ አለች
በቻይና መንግሥት የትዊተር ገጽ ላይ አንድ አውስትራሊያዊ ወታደር አፍጋኒስታናዊ ታዳጊን ሲገድል የሚያሳይ ነው የተባለ ሐሰተኛ ምስል በመለጠፉ ቻይና ይቅርታ እንድትጠይቅ አውስትራሊያ አሳሰበች።
የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚንስትር ስኮት ሞሪሰን በቴሌቭዥን ቀርበው "ቤጂንግ እንዲህ ያለ አስቀያሚ ምስል በመለጠፏ ልታፍር ይገባል" ብለዋል። በአሁኑ ወቅት ሁለቱ አገራት ከፍተኛ ፖለቲካዊ ውጥረት ውስጥ ናቸው። ምስሉም ነገሮችን የሚያባብስ ነው ተብሏል። ይህ ምስል የአውስትራሊያ ወታደሮች የጦር ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ክስ የሚያቀርብ እንደሆነም ተገልጿል። በያዝነው ወር መባቻ ላይ የወጣ ሪፖርት፤ እአአ ከ2009 እስከ 2013 ባሉት ዓመታት 25 አውስትራሊያውያን ወታደሮች 39 ንጹሀን የአፍጋን ዜጎችን ገድለዋል ብሏል። የአውስትራሊያ መከላከያ ኃይል ሪፖርት ከፍተኛ ወቀሳ ያስከተለ ሲሆን፤ ፖሊስ ጉዳዮ ላይ ምርመራ ከፍቷል። የቻይና የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ቃል አቀባይ ሊያን ዛሆ፤ አውስትራሊያዊ ወታደር አንድ ጠቦት ያቀፈ ታዳጊ አጠገብ በደም የተነከረ ስለት ይዞ የሚያሳይ የተቀናበረ ምስል ለጥፈዋል ተብሏል። የአውስትራሊያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፤ ምስሉ የአውስትራሊያ ወታደሮች ሁለት የአፍጋን ወጣቶችን በስለት ገድለዋል የሚለውን በመረጃ ያልተደገፈ ወሬ የተመረኮዘ ነው ብሏል። ሆኖም ግን የተካሄደው ምርመራ ወሬውን የሚደግፍ አንዳችም መረጃ አላገኘም። የቻይናው ቃል አቀባይ በትዊተር ገጽ ምስሉን የለጠፉት "የአፍጋን ንጹሀን ዜጎች እና እስረኞች በአውስትራሊያ ወታደሮች መገደላቸው ያስደነግጣል። ድርጊቱን እናወግዛለን። ተጠያቂ መሆን አለባቸው" ከሚል ጽሁፍ ጋር ነበር። ጠቅላይ ሚንስትር ስኮት ሞሪሰን በበኩላቸው ትዊተር ላይ የተለጠፈውን ምስል እና ጽሁፍ "በጣም አስቀያሚ እና እጅግ የሚያበሳጭ። የቻይና መንግሥት በትዊቱ ሊሸማቀቅ ይገባል" ሲሉ ኮንነዋል። አውስትራሊያ፤ ምስሉ "ሐሰተኛ" ስለሆነ ትዊተር ከመተግበሪያው ላይ እንዲሰርዘው ጠይቃለች።
40973519
https://www.bbc.com/amharic/40973519
ጥበብን ከቆሻሻ
ልጅ ያሬድ እና ጓደኛው እስጢፋኖስ በከተማችን ውስጥ ያለ አንድ ጉዳይ እጅጉን ያሳስባቸዋል፤ ይህም በየቦታው ተጥለው የሚታዩት ላስቲኮች እና አጥንቶች !
''ላስቲክ እና አጥንት በአከባቢና በሰው ልጆች ላይ የሚያስከትለውን ከፍተኛ ጉዳት እንረዳለን ለዚህም በቆሻሻ አወጋገድ ላይ ህብረተሰቡን ለማስተማር ይህን እያደርግን ነው'' ብለዋል። የተፍጥሮ አከባቢ ተቆርቋሪ የሆኑት ጓደኛሞች ከቆሻሻ አዲስ ጥበብን እየፍጠሩ ነው! የቆሻሻ አያያዝ፣ አጓጓዝና አወጋገድ ሥርዓት ደካማ በሆነባቸው እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ ሃገራት ውስጥ የሚፍጠሩት ቆሻሻዎች በሰው ልጆች፣ በአካባቢና በእንስሳት ደህንነት ላይ ከፍተኛ አደጋን ያሰከትላሉ። የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም ሪፖርት እንደሚያሳየው በቆሻሻ ምክንያት የሚከሰተው ብክለት ለአካባቢ ደህንነት አንዱና ዋነኛው አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን አርጋግጧል፡፡ በመዲናችን አዲስ አበባም የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ሂደት ላይ የሚታየው ደካማ ሥርዓት በከተማዋ ነዋሪዎችና እንስሳት ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተጽዕኖን ፈጥሯል። የከተማዋ የአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የከተማዋን ጽዳት ለመጠበቅ የተለያዩ ጥረቶችን እያደረገ ቢሆንም የማህበረሰቡ የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ልማድ ደካማ በመሆኑ ከተማችን ለነዋሪዎቿም ሆነ ለእንስሳት ደህንነት ምቹ አይደለችም። ልጅ ያሬድና ጓደኛው እስጢፍኖስ የአካባቢን ንጽህና መጠበቅ የሁሉም ሃላፊነት እንደሆነ ይስማማሉ። ለዚህም ህብረተሰቡም የሚጠበቅበትን በመወጣት የአካባቢ ብክለትን እንዲቀርፍ ለማስተማር በጥበብ ሙያቸው አንድ ተግባር በመፍጸም ላይ ይገኛሉ። ልጅ ያሬድና እስጢፍኖስ ከወዳደቁ ላሰቲኮች፣ አጥንቶችና የብረት ቁርጥራጮች የተለያዩ ስዕሎችንና ቅርጻ-ቅርጾችን ይሰራሉ። ልጅ ያሬድ እንደሚለው ከቆሻሻና ከአጥንት የተለያዩ ቅርጻ ቅርጾችን እየሰሩ ሰዎች ቆሻሻን በአግባቡ እንዲያስወግዱ ለማስተማር ጥረት እያደርጉ ነው። ይህ የሞተር ሳይክል ቅርፅ ከአጥንትና ተጥለው ከተገኙ ብረቶች የተሰራ ነው እስጢፋኖስ በበኩሉ ከወዳደቁ ላስቲኮችና የብስኩት ማሸጊያዎች የሚሰራቸው ስራዎች ህብረተሰቡ ለአጭር ጊዜ ተጠቅሞ የሚጥላቸው ላሰቲኮች የዕድሜ ልክ ችግር ሊሆኑ እንደሚችሉ እንዲገነዘቡ ሊያደርጋቸው ይችላል ይላል። ይህ ስዕል ከተጣሉ የብስኩት መጠቅለያ ላሰቲኮች የተሰራ ነው ''በእነዚህ ስራዎች ምንም አይነት የገንዘብ ጥቅም አናገኘም። ይህን የምናደርገው በቆሻሻ ምክንያት የሚመጣ የአካባቢ ብክለት ሰለሚያሳስበንና ጥቅም የላቸውም ተብለው የሚጣሉ ቁሶችን መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል በማሰብ ነው። ገንዘብ ብንፈልግ ሌሎች ብዙ ገንዘብ ሚያሰገኙ ነገሮችን መስራት እንችላለን'' ይላል ልጅ ያሬድ። ልጅ ያሬድ ለሥራው ግብዓት የሚሆን አጥንት ሲለቅም በሥራቸው ላይ የሚሰጧቸው አስተያየቶች አበረታች አለመሆናቸው ልጅ ያሬድን ቅር ያሰኘዋል። ''ይህን ሥራ ስንሰራ መልካም አስተያየት የምናገኝ ይመስላል፤ የሚያሳዝነው ግን ብዙ ውጣ ውርዶችን እያለፍን ነው የምንሰራው። ሰዎች አላማዬን ሳይገነዘቡ ለምን አጥንት ትለቃቅማለህ? ከቴሌቪዥን ጠፍተህ ቆሻሻ ውስጥ ለምን ትዞራለህ? መቼ ነው እንደሰው የምትሆነው ይሉኛል? ቆሻሻውን አፅድቼ ነው ንፁህ የሆነ ጥበብ የምሰራው። ሰዎች ይህንን ሊገነዘቡልኝ ይገባል። በተጨማሪም አይረቡም ከተባሉ ነገሮች ብዙ ጠቃሚ ነገር መስራት እንደሚቻል ነው ማሳየት የፈለኩት።'' ብሏል። ልጅ ያሬድና እስጢፋኖስ እንደሚሉት ለዚህ ሥራቸው ከየትኛውም ወገን ምንም አይነት ድጋፍም ሆነ የሞራል ማበርታቻ ስለማያገኙ ተሰፋ ቆርጠው ስራቸውን ሊያቆሙ እንደሆና ተናግረዋል። ልጅ ያሬድ ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ በአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ ላይ መስራት የጀመረ ሲሆን በ2003 ዓ.ም በሃገር አቀፍ ደርጃ የሚሰጠውን የአካባቢ ጥበቃ ሽልማት የሆነውን 'ግሪን አወርድ' አሸንፏል።
news-53544127
https://www.bbc.com/amharic/news-53544127
"አገሬ ነች፣. . .ሞትም ቢመጣ እዚሁ ነው የምጋፈጠው"- ኃይሌ ገብረሥላሴ
በዘመናዊው ዓለም የኢትዮጵያ ስም በበጎ እንዲነሳ ካደረጉ ሰዎች መካከል ኃይሌ ገብረሥላሴ በቀዳሚነት የሚጠቀስ ሰው ነው። ኃይሌ በአገሪቱ ውስጥ ከህጻን እስከ አዋቂ የሚታወቅና ስሙ ዘወትር የሚነሳ ድንቅ አትሌት ነው።
ኃይሌ በሩጫው መስክ የአገሩን ገጽታ በታላላቅ የዓለም መድረኮች ላይ በአውንታዊ መልኩ ሲያስነሳና ሲያስወድስ ቀይቶ ጎን ለጎንም በተለያዩ የኢንቨሰትመንት ዘርፎች ላይ በመሰማራት በጥረቱ ያገኘውን ሐብት አፍስሶ ለእራሱና ለወገኖቹ ጠቃሚ የሆኑ ምጣኔ ሃብታዊ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል። ከሳምንታት በፊት በአንዳንድ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ተከስቶ የነበረው አለመረጋጋት ለበርካታ ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት መሆኑ ይታወሳል። ከዚህ ባሻገርም በርካታ ተቋማትና መኖሪያ ቤቶች ላይ በተፈጸመው ጥቃትም ከፍተኛ ውድመት መድረሱም ተገልጿል። በተለይ በሻሸመኔና በባቱ ከተሞች ውስጥ በተፈጸመው ጥቃት በንብረት ላይ የደረሰው ውድመት ከፍተኛ መሆኑን ቢቢሲ ያናገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎችና ባለንብረቶች እማኝነታቸውን ሰጥተዋል። በእነዚህ ከተሞች ከወደሙ ንብረቶች መካከል በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በዓለማችን የሩጫ ታሪክ ውስጥ ስማቸው ከሚጠቀሱ ጥቂት ብርቅዬ አትሌቶች መካከል አንዱ የሆነው የኃይሌ ገብረሥላሴ ሁለት ትልልቅ ሆቴሎች ይገኙበታል። ኃይሌ ገብረሥላሴ በከተሞቹ ውስጥ የአገር ውስጥም ሆነ የውጪ እንግዶችን ከሚያስተናግዱ ደረጃቸውን የጠበቁ ጥቂት ሆቴሎች መካከል ቀዳሚ በሆናቸው በሁለቱ ሆቴሎቹ የደረሰው ውድመት በገንዘብ ቢሰላ ከሁለት መቶ ሚሊዮን ብር ሊበለጥ እንደሚችል ለቢቢሲ ግምቱን ገልጿል። "ትክክለኛ ቁጥሩን አላወቅንም፤ እስከ 290 ሚሊዮን [ሊደርስ ይችላል]። እንዲሁ ከሁለት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ብለን ነው የያዝነው" የሚለው ኃይሌ ስሌቱ ሲሰራ የወደሙ ወይንም የጠፉ ዕቀዎችን ለመመልሰ ቢሞከር ዛሬ ገበያው ላይ ባላቸው ዋጋ መሰረት መሆኑን ይገልፃል። የጉዳት መጠን "ሻሸመኔ የነበረው ሆቴላችን ባለሦስት ኮከብ ነው፤ እርሱ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ወድሟል። በጣም ብዙ የለፋንበት ቤት ነበር" ይላል ኃይሌ የእርሱ ንብረት በሆኑ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ የደረሱትን ጉዳቶች ለቢቢሲ ሲዘረዝር። "የዝዋዩ ሪዞርት ደግሞ . . . እንዲያውም ዝም ብሎ ቀፎው ቆሟል፤ መስታወቶቹ ረግፈዋል፤ ስፓው ተቃጥሏል፤ የአካል ብቃት ማዕከሉ ተቃጥሏል። ግምጃ ቤቱ፣ የልብስ ማጠቢያ ክፍሉ፣ የምግብ ማብሰያ ክፍሉ በሙሉ ተቃጥለዋል። እንግዳ መቀበያ ክፍሉን ጨምሮ አንዳንዶቹ ደግሞ ተርፈዋል፤ ግን ብዙዎቹ ዕቃዎች ተዘርፈዋል።" በሁለቱ ከተሞች ወደሥራ ተመልሶ የመግባት ሐሳብ ስለመኖር ያለመኖሩ የተጠየቀው ኃይሌ ቁርጥ ያለ ውሳኔ ላይ ያለመደረሱን የሚጠቁም ምላሽ ሰጥቷል። "የሻሸመኔውን ሆቴል የምንሰራው ከሆነ እንደገና ከመሬቱ ጀመረን ቆፍረን ነው የምንሰራው። የዝዋዩን እንኳ ማደስ ይቻላል፤ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ወደሥራ መመለስ ይቻላል" ሲል ግምቱን ይናገራል። በሁለቱ ሆቴሎች ቁጥራቸው ወደ አራት መቶ የሚጠጉ ሠራተኞች ተቀጥረው ይሰሩ ነበር፤ እንደ ኃይሌ ገለፃ። "እነርሱ ከሥራ ውጪ ሆነዋል።" ሥራቸውን ያጡት እነዚህ ግለሰቦች በከተሞቹ በሚገኙ ሌሎች ሆቴሎችና ሪዞርቶች ተቀጥረው እንዳይሰሩ እንኳ እነርሱን ሊቀጥሩ የሚችሉ ተመሳሳይ ተቋማት በአብዛኛው የጉዳት ሰለባ ሆነዋል እንደሆኑ ይናገራል ኃይሌ። "ይህ ትልቅ ቀውስ ነው፤ በአገሪቱ የሥራ አጡ ቁጥር በበዛበትና ብዙ ወጣቶች ሥራ በሌላቸው በአሁኑ ጊዜ ተጨማሪ ሥራ አጥ መፍጠር ነው" የሚለው ኃይሌ፤ በሌሎች ተቋማትም ላይ በደረሰው ተመሳሳይ ጉዳት የእንጀራ ገመዳቸው የተበጠሰ ወይንም የሳሳ ግለሰቦች ቁጥር ሲታሰብ ችግሩን ይበልጡኑ ያገዝፈዋል ሲል ያስረዳል። የዋስትና ዕጦት ኃይሌ በሻሸመኔ እና ዝዋይ ከተሞች እንዲሁም በሌሎች የኦሮሚያ አካባቢዎች በንግድና በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ የደረሱት ጥቃቶች የሥራ መቋረጥን ማስከተላቸው በመንግሥትን በግብር የሚሰበሰብን ዳጎስ ያለ ገቢ ከማሳጣታቸው ባሻገር ሌሎች መዋዕለ ነዋያቸውን ለማፍሰስ ለሚያስቡ ባለሐብቶች የማስጠንቀቂያ ደወል የሚያሰሙ ናቸው ይላል። "ሌላው [ጥያቄ] የሚቀጥለው ባለሐብት የተቃጠለች ከተማ እያየ ምን ዓይነት ተነሳሽነት ኖሮት ገንዘቡን ያፈሳል? የሚለው ነው። ፋብሪካዎች ተቃጥለዋል፤ ሆቴሎች ተቃጥለዋል፤ ሕንፃዎች ተቃጥለዋል፤ የንግድ ተቋማት ተቃጥለዋል፤ የአበባ እርሻ. . . ብዙ ነገሮች ተቃጥለዋል። [. . . ] እንደአገር አጥተነዋል የምለው እርሱንም ነው።" ኃይሌ በጥቃቱ ለመወደሙት ንብረቶቹና ተቋማቱ የመድን ዋስትና ክፍያ አገኛለሁ የሚል እምነት የለውም። "እኔ ምናልባትም እዚህ ያጣሁትን በሌሎች የንግድ ድርጅቶቼ አካክሰው ይሆናል፤ ግን አንዲት ነገር የነበረችውና እርሷንም በአንድ ቀን ያጣ ስንት አለ። የአንዳንዶቹን ስትሰማ ሰቅጣጭ ነው፤ በሌሊት ልብስና በነጠላ ጫማ፥ መቀየሪያ ልብስ እንኳን ሳይዙ ወጥተው በየሰው ቤት የቀሩ አሉ።" በንብረቱ ላይ ስለተፈጸመው ውድመት በአካባቢው ካሉ የማኅበረሰብ መሪዎችና ባለስልጣናት ጋር የስልክ ውይይቶችን ማድረጉን ኃይሌ ለቢቢሲ ተናግሯል። "ብዙ ሠራተኞች ከሥራ ውጪ ሆነዋል፤ መንግሥት ቶሎ መልስ እንዲሰጥ እንፈልጋለን፤ እየተነጋገርንም ነው" ይላል። "ብዙ ሰዎች አልቀሰዋል፤ አርባ ስምንትና ሃምሳ ዓመት የለፉበትን ሥራቸውን ያጡ ሰዎች እንባቸውን አፍስሰዋል፤ እነርሱም ፍትሕ ይፈልጋሉ።" ምላሹ ያለው በዋናነት በመንግሥት እጅ ነው ሲል አጥብቆ የሚከራከረው ኃይሌ ነገሮች እንዲስተካከሉ ከተፈለገ "ፍትሕና ለወደፊቱ ዳግም ተመሳሳይ ጥቃቶች እንደማይደርሱ ዋስትና ያሻል" ይላል። "በመጀመሪያ ፍትህ እፈልጋለሁ" ሲል ለቢቢሲ ያስረዳል ኃይሌ። "ይሄንን የፈፀሙ ሰዎች ወደ ሕግና ፍትህ መቅረብ አለባቸው።" ከዚህ ባሻገር የሚጠብቀው ዋስትና ግን ከመንግሥትም ብቻም ሳይሆን ከሕዝብም ጭምር መምጣት አለበት ባይ ነው ኃይሌ፤ ላንጋኖ አካባቢ ጥቃት ለማድረስ የተደረገ ሙከራ በአካባቢው ነዋሪዎችና ሠራተኞች መክሸፉን በማውሳት በሌሎችም ስፍራዎች ተመሳሳይ ነገር ሊኖር ይገባ እንደነበር ይናገራል። "የግለሰብን ንብረት እያጠቃህ ሌላ ግለሰብ መጥቶ ሥራ ይሰራል ማለት ከባድ ነው።" የፀጥታ ኃይሎችም ይህን መሰሉን ድርጊት መከላከል ነበረባቸው፤ "እርሱን አላደረጉም" ሲልም ኃይሌ ቅሬታውን ገልጿል። ኃይሌ ለደረሰው ጉዳት ካሣ እንደሚያስፈልግም ይሞግታል። በቅርቡ በአዳማ በሚከፍተው አዲስ ሆቴሌ በባቱ እና በሻሸመኔ ጥቃቶች ሥራቸውን ያጡና መኖሪያቸውን መቀየር የሚችሉ የተወሰኑ ሰዎችን ለመቅጠር መታሰቡን የሚናገረው ኃይሌ፤ የሰሞኑን መሪር ዜናዎች ግን በጥቅሉ በአገሩ ላይ ያለውን ተስፋ እንዳላሳጡት ይለፃል፦ "አገሬ ነች፣ ኢትዮጵያ ነች፣ የትም አልሄድም። ሞትም ቢመጣ እዚሁ ነው የምጋፈጠው።"
news-53852369
https://www.bbc.com/amharic/news-53852369
ኢትዮጵያ፡ በደረሰው የጎርፍ አደጋ 130 ሺህ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል
በኢትዮጵያ እስከ ነሐሴ ወር አጋማሽ ድረስ የጣለው ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የተነሳ 170 ሺህ ያህል ነዋሪዎች ጉዳት ሲደርስባቸው 130 ሺህ ሰዎች ደግሞ ከቀያቸው መፈናቀላቸውን የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ምክትል ኮሚሽነር ለቢቢሲ ገለፁ።
ኮሚሽነሩ አቶ ዳመነ ዳሮታ ከዚህ በፊት የነበረውን ልምድ ከግንዛቤ በማስገባት በዚህ ዓመት ክረምት ወቅት በጎርፍ ምክንያት ወደ 2 ሚሊየን ያህል ሰዎች ሊጎዱ እንዲሁም 434 ሺህ ያህሉ ደግሞ ሊፈናቀሉ ይችላሉ ተብሎ ግምት መያዙን ተናግረዋል። እንደ ኮሚሽነሩ ገለፃ ከሆነ እስካሁን ድረስ በአዋሽ ወንዝ ሙላት የተነሳ በአፋር ክልል የተጎዱ ሰዎች ቁጥር ወደ 67 ሺህ 885 አካባቢ ሲሆን፣ 40 ሺህ 130 አካባቢ ደግሞ መፈናቀላቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ኮሚሽነር ዳመነ አክለውም ደቡብ ኦሞ ዳሰነች አካባቢ በኦሞ ወንዝ ሙላትና የግቤ 3 የኃይል ማመንጫ ግድብ ውሃ በተወሰነ መልኩ መልቀቁን ተከትሎ በደረሰ የጎርፍ አደጋ በኦሞ በሚገኙ ከ15 ሺህ በላይ ሰዎች እንዳይጎዱ ከሚኖሩበት አካባቢ የማውጣት ሥራ መከናወኑን ገልፀዋል። እነዚህ ሰዎች በጊዜያዊ መጠለያ እንዲቆዩ መደረጉን ገለፀው ከ10ሺህ በላይ ለሚሆኑት የተለያዩ ድጋፎች ደርሷል ብለዋል። ለቀሪዎቹ 5ሺ ሰዎች ደግሞ ድጋፍ ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን አክለዋል። ዘንድሮ በጎርፍ የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ለቢቢሲ የገለፁት ኮሚሽነሩ፣ ነገር ግን ኮሚሽኑም ሆነ መንግሥት ከሌሎች ጊዜያት በተሻለ ሁኔታ ዝግጅት ያደረጉበት ዓመት እንደነበር ለቢቢሲ አብራርተዋል። በዚህ ዓመት በልግ ወቅት በደረሰው የጎርፍ አደጋ ምክንያት 470 ሺህ ያህል ነዋሪዎች ጉዳት ሲደርስባቸው ከ300 ሺህ በላይ ደግሞ መፈናቀላቸውን ኮሚሽነሩ ጨምረው አስረድተዋል። ኮሚሽኑ ይህን የበልግ ወቅት አደጋን በመቋቋም ላይ ባለበት ወቅት የክረምቱ ዝናብ ከበልጉ ዝናብ ጋር ተያይዞ በመምጣቱ ወንዞችና ግድቦች በመሙላታቸው በርካቶች ለአደጋ መጋለጣቸውን ተናግረዋል። ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ከነበረው ልምድ በተለየ ሶስት ጊዜ የጎርፍ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ማውጣቱን ገልፀው ሁለቱ ማስጠንቀቂያዎች የወጡት በዚህ ክረምት ወቅት መሆኑን አብራርተዋል። እስከ መስከረም መጨረሻ ተከታታይ ዝናብ ስለሚኖር ጎርፍና የመሬት መንሸራተት ሊከሰት እንደሚችል የገለፁት ኮሚሽነሩ ነሐሴ መጨረሻዎቹ ላይ የተንዳሆ ግድብ ሊሞላ ስለሚችል ቀጣይም ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ፣ እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስም የከሰምና፣ የቆቃ ግድቦች እየሞሉ እንደሚሄዱ በመግለጽ ሁሉም አካላት አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል። በመከላከኛውና፣ የታችኛው አዋሽ ላይ ከፍተኛ የመከላከል ስራ እየተሰራ መሆኑን ጨምረው በመግለፅ በዚህም የተነሳ በአዋሽ ወንዝ ሙላት የተነሳ በዚህ የክረምት ወቅት የደረሰው ጉዳት መቀነሱን ተናግረዋል።
news-52081144
https://www.bbc.com/amharic/news-52081144
ኮሮናቫይረስ፡ በኮሮናቫይረስ ከተያዙት ኢትዮጵያዊያን ሦስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው
በኢትዮጵያ ተጨማሪ ሦስት በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች በመገኘታቸው አጠቃላይ ቁጥሩ አስራ ዘጠኝ መድረሱን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዛሬ ዕሁድ አስታወቀ።
በሽታው እንዳለባቸው ከተረጋገጡት ሰዎች መካከል ሁለቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ የ14 እና የ48 ዓመት እድሜ ያለቸው የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ናቸው። ከእነዚህ ሁለት ታማሚዎች በተጨማሪም ባለፈው አርብ በሽታው እንደተገኘባቸው የተገለጸው የ61 ዓመት ግለሰብም የዚሁ ቤተሰብ አባል እንደሆኑ ቢቢሲ ማረጋገጥ ተችሏል። ባለፈው ሳምንት እንደተገለጸው የአዳማ ከተማ ነዋሪ የሆኑት የ61 ዓመቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ግለሰብ ወደ ውጪ አገር የተደረገ የጉዞ ታሪክ ያልነበራቸው ቢሆንም ከውጭ አገር ዜጋ ጋር ግንኙነት እንደነበራቸው ተገልጿል። በዚህም ሳቢያ ግለሰቡ በበሽታው ሊያዙ መቻላቸውንና ዛሬ መያዛቸው ይፋ የተደረጉት ሁለቱ የግለሰቡ የቤተሰብ አባላት ምናልባትም ቫይረሱ ከግለሰቡ ሳይተላለፍባቸው እንዳልቀረ ተገምቷል። ሁለቱ ሰዎች የበሽታው ምልክት ባያሳዩም ቀደም ሲል በቫይረሱ ከተያዘ ግለሰብ ጋር የቅርብ ንክኪ ስለነበራቸው በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገላቸው ቆይተው ትናንት በመጋቢት 19 በተደረገላቸው የላቦራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። አዲስ በበሽታው መያዛቸው ዛሬ ከታወቁት ሦስት ሰዎች መካከል አንደኛዋ የ26 ዓመት ኢትዮጵያዊት ስትሆን መጋቢት 8/2012 ዓ.ም ወደ ቤልጅየም ብራስል እንዲሁም መጋቢት 10/2012 ዓ.ም ደግሞ ወደ ካሜሮን ተጉዛ እንደነበር ታውቋል። ግለሰቧ የበሽታው ምልክት ስለታየባት ወደ ጤና ተቋም በመሄድ በተደረገላት የላብራቶሪ ምርመራ ቅዳሜ መጋቢት 19/2012 ዓ.ም በቫይረሱ መያዟ ተረጋግጧል። እስካሁን በሚመለከታቸው አካላት በበሽታው መያዛቸው ተረጋግጦ ኢትዮጵያ ውስጥ ከተመዘገቡት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ህሙማን መካከል ኢትዮጵያዊያን 12፣ ጃፓናዊያን 4፣ አንዲት እንግሊዛዊት፣ አንድ ኦስትሪያዊና አንድ ሞሪሸሳዊ ናቸው። ከአስራ ሁለቱ የኮሮናቫይረስ ተጠቂ ኢትዮጵያዊያን መካከል አንድ አራተኛው የሚሆኑት የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው። በኢትዮጵያ ውስጥ ተመርምረው ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ከተረጋገጡት ሰዎች መካከል ሁለቱ ጃፓናዊያን ወደ አገራቸው የሄዱ ሲሆን አንደኛው ከበሽታው ሙሉ ለሙሉ ማገገሙ ተነግሯል። ምንም እንኳን በሽታው እንደተገኘባቸው ዛሬ ከተገለጹት ሰዎች ጋር የታማሚዎቹ አጠቃላይ ቁጥር 19 ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 16 ነው።
48552479
https://www.bbc.com/amharic/48552479
አፍሪካውያን ስደተኞች በደቡብ አሜሪካ አድርገው አሜሪካ ለመግባት ተሰልፈዋል
ቴክሳስ የሚገኙ የአሜሪካ ድንበር ጠባቂዎች ባለፉት ሳምንታት ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ አፍሪካውያንን ድንበር ሊያቋርጡ ሲሉ መያዛቸውን ገልፀዋል።
የአሜሪካ ጉምሩክና ድንበር ተቆጣጣሪ መሥሪያ ቤት ድንበር ላይ የሚደርሱ አፍሪካውያን ቁጥር "በከፍተኛ ቁጥር እየጨመረ"መሆኑን ገልፆ ሁኔታውም "ሰብዓዊ ቀውስ" ነው ብሎታል። ባለፉት ስምንት ቀናት ብቻ ከ500 በላይ አፍሪካውያን ስደተኞች ዴል ሪዮ ድንበር ላይ በቁጥጥር ስር ውለዋል። አብዛኞቹ ስደተኞች ከአንጎላ፣ ካሜሮንና ከሪፐብሊክ ኮንጎ የመጡ ቤተሰቦች መሆናቸውን የድንበር ተቆጣጣሪው መሥሪያ ቤት አስታውቋል። ባለፈው ሳምንት 116 አፍሪካውያን ስደተኞች በአሜሪካ ደቡባዊ ድንበር ላይ መድረሳቸው ታውቋል። • እግር ኳስ ተጫዋቹ ወንድወሰን ዮሐንስ እንዴት ተገደለ? • የአክሱም ሙስሊሞች ጥይቄ መቼ ምላሽ ያገኝ ይሆን? • የደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ስጋት ላይ ነን ይላሉ የዴል ሪዮ ድንበር ተቆጣጣሪ የበላይ ኃላፊ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት ከስደተኞቹ ጋር ባለው የባህልና የቋንቋ ልዩነት ምክንያት መግባባት አልቻሉም። ይህም "ተጨማሪ የቤት ስራ" እንደሆነባቸው አስረድተዋል። አብዛኞቹ ስደተኞች ከዴል ሪዮ ተነስተው ቴክሳስ ወደምትገኘው ሳን አንቶኒዮ ለመድረስ 240 ኪሎ ሜትር መጓዝ ይጠበቅባቸዋል። የሳን አንቶኒዮ ከተማ አስተዳደር ቃል አቀባይ ለቢቢሲ እንደገለፁት ከበጎ አድራጎት ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን ለስደተኞቹ ሁሉን አቀፍ አገልግሎት የሚሰጥ ማዕከል እያቋቋሙ ነው። የአካባቢው ባለስልጣናት ፈረንሳይኛ ተናጋሪ በጎ ፈቃደኞችን እየፈለጉ ሲሆን በሚቀጥሉት ቀናት ብቻ 300 ስደተኞች ወደ ከተማቸው ይደርሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። አፍሪካውያኑ እንዴት አሜሪካ ድንበር ደረሱ? አፍሪካውያኑ እስካሁን ድረስ የትኛውን መስመር ተከትለው አሜሪካ ደጃፍ እንደተገኙ በግልፅ የታወቀ ነገር የለም። ነገር ግን በቅርቡ በተደረገ አንድ ቃለምልልስ አፍሪካውያን ቤታቸውን ጥለው በቅድሚያ ወደ ብራዚል እንደሚጓዙ መረጃ አለ። ከዛም ወደ ሰሜናዊ ኮሎምቢያ እና ማእከላዊ አሜሪካ በመሄድ ወደ አሜሪካ ድንበር እግራቸውን ያስጠጋሉ። ይህ ግን በርካታ ሳምንታት የሚፈጅና አድካሚ ጉዞን ይጠይቃል። ከዚህ በኋላ ያለው መላ ምት አሜሪካን ከሜክሲኮ የሚለየውን ሪዮ ግራንዴ ወንዝን ተጠቅመው አሜሪካ ይገባሉ የሚል ነው። እስካሁን ድረስ 19 ሺህ ስደተኞች ድንበር ሊያቋርጡ ሲሉ መያዛቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ይናገራሉ። "በማረሚያ ቤት 4ሺህ ስደተኞች ሲኖሩን ከፍተኛ ቁጥር እንዳለን ይሰማን ነበር" ያሉት ኃላፊዎቹ "6 ሺህ ሲኖሩን እንደ ቀውስ እንቆጥረዋለን፤ አሁን ግን 19 ሺህ አሉን ይህ ደግሞ ከአቅማችን በላይ ነው" ሲሉ ተደምጠዋል። በግንቦት ወር 144 ሺህ 278 ስደተኞች የአሜሪካ ድንበርን የረገጡ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 100 ሺዎቹ ቤተሰቦችና ህፃናት ናቸው። ከባለፈው አመት መስከረም ወር ጀምሮ በአሜሪካ ድንበር ተቆጣጣሪዎች በቁጥጥር ስር ከዋሉ መካከል ስድስት ህፃናት በማቆያ እያሉ መሞታቸው ይታወቃል።
news-56144442
https://www.bbc.com/amharic/news-56144442
ትራምፕ ኪምን "በኤር ፎርስ ዋን ልሸኝህ" ሲሉ ጠይቀዋቸው ነበር
ትራምፕ በሥልጣን ላይ እያሉ ከፈፀሟቸው ድርጊቶች መካከል ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ-ኡን ጋር የተገናኙበት ዕለት የሚረሳ አይደለም።
ቢቢሲ ይህንን ግንኙነት በተለመከተ ከሰሞኑ አዳዲስ መረጃዎች አግኝቷል። በውይይቱ ወቅቱ ነበሩ የተባሉ ሰዎችንም አናግሯል። ዕድሜ ጠገብ ዲፕሎማቶችን ጨምሮ ብዙዎችን ያስደነገጠው ግን ትራምፕ ኪምን "በኤር ፎርስ ዋን ልውሰድህ" ሲሉ የጋበዙበት ቅፅበት ነው። ትራምፕ ለሁለተኛ ጊዜ ከኪም ጋር የተገናኙት በቪዬትናም ከተማ ሃኖይ ነበር። ይህ ግንኙነት ውጤቱ የሰመረ አልነበረም። ትራምፕ ለጋዜጠኞች "አንዳንድ ጊዜ የሚያዋጣው ሹልክ ብሎ መውጣት ነው ብለው ተናግረው ነው ከስብሰባው የወጡት። ነገር ግን ስብሰባው ጥለው ከመውጣታቸው በፊት የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝደንት አንድ አስደናቂ ጥያቄ ለኪም አቅርበው ነበር። በትራምፕ ዘመን በእስያ ከፍተኛ አማካሪ የነበሩት ማቲው ፖቲንጀር "ትራምፕ ኪምን 'በኤር ፎርስ ዋን ወደቤትህ ልሸኝህ' ሲሉ ጋብዘዋቸው ነበር" ሲሉ ለቢቢሲ ይናገራሉ። ፕሬዝደንቱ ኪም በቻይና በኩል አድርገው በባቡር እንደመጡ ያውቁ ነበር። 'በሁለት ሰዓት ውስጥ ወደ ሃገርህ ላደርስህ እችላለሁ' ቢሏቸውም ኪም ግን አሻፈረኝ አሉ።" የቀድሞው የብሔራዊ ደህንነት አማካሪው ጆን ቦልተን ይህ ክስተት በትራምፕና ኪም ፍቅር ወቅት ካይዋቸው አስገራሚ ነገሮች መካከል አስደናቂው እንደሆነ ለቢቢሲ ሹክ ብለዋል። አማካሪው "ትራምፕ አዲስ የቅርብ ጓደኛ ያገኙ መስሏቸው ነበር" ይላሉ። ትራምፕ በዚህ ምክክራቸው ወቅት የገዛ ዲፕሎማቶታቸውን ሳይቀር ያስደነገጥ አንድ ሌላ ነገር አድርገው ነበር። የቀድሞው ፕሬዝደንት በኪም ጥያቄ መሠረት አሜሪካ ከደቡብ ኮሪያ ጋር የምታደርገውን ወታደራዊ ልምምድ ለማቆም ተስማሙ። ቦልተን እንደሚሉት "ኪም ጁንግ ልክ እንደከዚህ በፊቱ በአሜሪካና ደቡብ ኮሪያ መካከል ለ60 ዓመታት ያክል የዘለው ወታደራዊ ልምምድ እንዲቆም ነበር ፍላጎታቸው።" "ትራምፕ ድንገት ተነስተው "ትራምፕ 'የጦርነት ጨዋታውን [ትራምፕ የተጠቀሙት ቃል] አስቆመዋለሁ። ምንም አስፋላጊ አይደለም፤ በዚያ ላይ ገንዘብ አባካኝ ነው። ይህ ደስተኛ እንደሚያደርግህ አምናለሁ' ሲሉ ማመን አቅቶኝ ነበር።" "የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፖምፔዬ፤ የፕሬዝደንቱ ፅ/ቤት ኃላፊ ኬሊ እንዲሁም እኔ ክፍሉ ውስጥ ተቀምጠን ነበር። ስለዚህ ጉዳይ ማንም አላማከረንም። ቀጥታ ከትራምፕ ጭንቅላት የመጣ ነገር ነው። ደግሞ በምትኩ ምንም ነገር አላገኘንም።" ትራምፕ ለኪም የላኩት ምስጢራዊ መልዕክት ኪምና ትራምፕ የተገናኙበት መድረክ ለብዙዎች ድንገቴ የሆነው ነበር። ይህ ከመሆኑ ከወራት በፊት ትራምፕ ኪምን 'የሮኬቱ ሰውዬ' እያሉ ሲጠሩት፤ ሰሜን ኮሪያን ደግሞ 'እሳት አለብሳታለሁ' እያሉ ሲዝቱ ነበር። የተባበሩት መንግሥታት ባለሥልጣን የሆኑት ጄፍ ፌልትማን በዚህ ውጥረት ወቅት ከትራምፕ የተላከ ሚስጥራዊ መልዕክት ወደ ኪም እንዳደረሱ ይናገራሉ። የፖለቲካ ጉዳዮች ምክትል ፀሐፊ የሆኑት ጄፍ በሰሜን ኮሪያዎች ግብዣ ወደ ፒዮንግያንግ ሊያቀኑ ነበር። ነገር ግን የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰውዬው ወደዚያ ማቅናታቸው ትክክለኛ ውሳኔ እንዳይደለ ሲናገር ነበር። ከጥቂት ሳምንታት በኋላ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ወደ ዋይት ኃውስ መጡ። ፌልትማን እንደሚሉት "በዚህ ወቅት ትራምፕ ወደ ጉቴሬዝ ጠጋ ብለው ጄፍ ፌልትማን ወደ ፒዮንግያንግ ቢያቀና መልካም ነው። ለሰሜን ኮሪያዎች እኔ ከኪም ጋር ለመጋናኘት ፈቃደኛ መሆኔን ይንገራቸው" ብለው ነበር። ፌልትማን ወደ ፒዮንግያንግ ባቀኑ ወቅት ለሰሜን ኮሪያዊያን ሁኔታው ምን ያህል ከባድ እንደሆነ እንዳስረዷቸው ይናገራሉ። የተመድ ባለሥልጣን ከትራምፕ የተሰጣቸውን መልዕክት ለኪም እንዲያደርሱሏቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ጠየቋቸው። "ከዚያ በክፍሉ ፀጥታ ሰፈነ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፀጥታውን ሰብረው 'እኔ አንተን አላምንህም። ለምንስ አምንሃለሁ? አሉኝ። እኔ እንዲያምኑኝ አልጠየቅኩም። ድርጅታችን ከትራምፕ መልዕክት ተልኮለታል። እኔ የመጣሁት መልዕክቱን ለማድረስ ነው አልኳቸው።" ዲፕሎማቱ ወደ ፒዬንግያንግ ሲሄዱም ሆነ ሲመለሱ ጦርነት መነሳቱ አይቀሬ ነው እያሉ ይፈሩ እንደነበር ለቢቢሲ ተናግረዋል። ኪም ለትራምፕ ቀጥተኛ ምላሽ አልሰጡም። ከወራት በኋላ ለደቡብ ኮሪያ ባለሥልጣናት ከአሜሪካው ፕሬዝደንት ጋር ለመገናኘት ዝግጁ መሆናቸው ነገሯቸው። የደቡብ ኮሪያው የደህንነት አማካሪ መልዕክቱን ለማድረስ ሳይውሉ ሳያድሩ ወደ ዋይት ኃውስ መጡ። ትራምፕ ኪምን ለማግኘት 'እስማማለሁ' ባሉ ጊዜ የደቡብ ኮሪያው አምባሳደር ቹንግ በድንጋጤ ከወንበራቸው ሊወድቁ ትንሽ ነበር የቀራቸው ሲሉ የወቅቱ የአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ማክማስተር ሁኔታውን ያስታውሳሉ። ልክ እንደ አብዛኛዎቹ የዋይት ኃውስ ሰዎች ማክማስተር ኪምና ትራምፕ መገናኘታቸው አልተዋጠላቸውም ነበር። ነገር ግን ልክ እንደ አብዛኛዎቹ የውጭ ጉዳይ ውሳኔዎች ትራምፕ በራሳቸው መንገድ ነበር የተጓዙት ይላሉ አማካሪው። "እኛ ሐሳባችን የነበረው ኪም ከመንግሥታት የሚመጣው ጫና ትንሽ እንዲከብድባቸው ነበር። ትራምፕ ግን ይህን ዕድል መቋቋም አልቻሉም"
news-53469905
https://www.bbc.com/amharic/news-53469905
ሙዚቀኛው ካኒዬ ዌስት ለቀጣዩ የአሜሪካ ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳውን ጀመረ
እውቁ አሜሪካዊ ሙዚቀኛ ካኒዬ ዌስት ከ4 ወራት በኋላ በሚካሄደው የአሜሪካ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ይፋዊ የምረጡኝ ቅስቀሳውን ትናንት ምሽት በደቡብ ካሮላይና ጀመሯል።
የ43 ዓመቱ ካኒዬ ዌስት ‘በርዝደይ ፓርቲ’ የተሰኘ ፓርቲውን ይዞ ነው ወደ ምርጫ ውድድሩ የሚገባው። አሁንም ቢሆን ግን በርካታ ደጋፊዎቹ ካኒዬ ዌስት የእውነቱን ለፕሬዝደንታዊ ምርጫ የመወዳደሩ ነገር ጥርጣሬን አላቸው። በቻርልስተን ውስጥ ያካሄደው የምርጫ ቅስቀሳ ካኒዬ ዌስት የእውነት ለአሜሪካ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ለመወዳደሩ ማረጋገጫ ሊሆን አይችልም ተብሏል። ካኒዬ ዌስት ትናንት ምሽት ባደረገው የምረጡኝ ዘመቻ ጭንቅላቱ ላይ “2020” የሚል ምልክት አድርጎ እና የጥይት መከላከያ ልብስ ለብሶ ታይቷል። በአዳራሹ ለተሰበሰቡ ደጋፊዎቹም ያለ ማይክራፎን ወይም ድምጽ ማጉያ ንግግር ሲያደርግ አምሽቷል። ስለ ጽንስ ማቋረጥ እየተናገረ ሳለ ማልቀስም ጀምሮ ነበር። ካኒዬ ዌስት ወላጆቼ ጽንስ ማቀወረጥ ሊፈጽሙብኝ ነበር ሲል በስሜት ሆኖ ተናግሯል። ካኒዬ ዌስት እአአ 2007 በሞት ስለተለዩት ወላጅ እናቱም ስሜታዊ ሆኖ ብዙ ነገር ተናግሯል። ካኒዬ ዌስት በዚህ ወር መጀሪያ ላይ ነበር በ2020 የአሜሪካ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ተወዳዳሪ እንደሚሆን ያስታወቀው። ይሁን እንጂ የምርጫው ተወዳዳሪ ለመሆን በበርካታ ግዛቶች በቂ የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብ ይኖርበታል።
news-48494202
https://www.bbc.com/amharic/news-48494202
የአንጎላ አማፂ ቡድን መሪ ከሞቱ ከ17 ዓመታት በኋላ ድጋሚ ተቀብረዋል
ዩኒታ የተሰኘው የአንጎላ አማፂ ቡድን መሪ የነበሩት ጆናስ ሳቪምቢ ከሞቱ 17 ዓመታት ቢሆናቸውም ከሰሞኑ እንደ አዲስ ግብዓተ መሬታቸው ተፈፅሟል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ፀዓዳ የለበሱ የአማፂ ቡድኑ አባላት የቀድሞ መሪያቸውን ዳግማዊ ግብዓተ መሬት ሲያደምቁት ታይተዋል። የእርስ በርስ ጦርነት ሲያምሳት የነበረችው አንጎላ ከጆናስ ሞት በኋላ ወደ ቀልቧ የተመለሰች መሰለች፤ ሰውዬው የሞቱት በግሪጎሪሳውያን አቆጣጠር 2002 ላይ ነበር። • መስቀል እና አረፋን ሳስታውስ ውስጤ ይረበሻል የጆናስ አፅም ከ17 ዓመታት በኋላ ለቤተሰቦቹ ተሰጥቷል። የዩኒታ አባላትም የመሪያቸው ዳግመኛ መቀበር ለሃገራዊ መግባባት ይረዳል ሲሉ ተሰምተዋል። ኤኤፍፒ የተሰኘው የዜና ወኪል አንድም የመንግሥተ መሪ በሥርዓተ ቀብሩ ላይ እንዳልተገኘ አስተውያለሁ ሲል ዘግቧል። የአንጎላ እርስ በርስ ጦርነት ለ27 ዓመታት ሲዘልቅ ቢያንስ ግማሽ ሚሊዮን ሕዝብ እንደቀጠፈ ይነገርለታል። • "ድርጅቴ ከሩስያ ጋር ጦርነት ገጥሟል" የፌስቡክ አለቃ 'ጥቁሩ አውራ ዶራ' በተሰኘ ቅፅል ስሙ የሚታወቀው ጆናስ ለበርካቶች እንደ ጠንካራ መሪ ቢታይም ጨካኝ ነበር የሚሉ አልጠፉም። 2002 ላይ ነበር የመንግሥት ወታደሮች ጆናስን ከገደሉት በኋላ በፍጥነት አፈር እንዲለብስ ያደረጉት። የጆናስ ቤተሰቦችም ሆኑ የአማፂ ቡድኑ አባላት መሪያቸው አፅሙ ወጥቶ ድጋሚ እንዲቀበር መንግሥትን ለዓመታት ሲጎተጉቱ ከርመዋል። ከጆናስ ጋር ዓይንና ናጫ የነበሩት የአንጎላው ፕሬዝደንት ኤድዋርዶ ዶስ ሳንቶስ 2017 ላይ ከሥልጣን መውረዳቸው የአማፂ ቡድኑ አባላት ጉትጎታ እንዲሰማ አስተዋፅኦ ሳያደርግ እንዳልቀረ ይነገራል። • ሰሜን ኮሪያ አሜሪካንን ጦርነት በማወጅ እየወነጀለች ነው
news-51569212
https://www.bbc.com/amharic/news-51569212
ከ33 ዓመት በፊት የተዘረፈው ዘውድ ለጨለቆት ሥላሴ ቤተክርስቲያን እንደሚመለስ ተገለጸ
ለ21 ዓመታት በኔዘርላንድስ አቶ ሲራክ አስፋው በተባሉ ግለሰብ እጅ የቆየው ጥንታዊ ዘውድ ዛሬ የካቲት 12 ቀን 2012 ዓ. ም. ለኢትዮጵያ ተመልሷል።
በ18ኛው ክፍለ ዘመን እንደተሰራ የሚነገርለት ዘውድ፤ በኔዘርላንድስ ኤምባሲ በኩል ለኢትዮጵያ የተመለሰ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ቅርሱን ተረክበዋል። ከመቐለ 16 ኪሎ ሜትር በደቡብ ምሥራቅ አቅጣጫ ከሚገኘውና ረዥም ዕድሜ ካስቆጠረው ሥላሴ ጨለቆት ቤተ ክርስትያን እንደተሰረቀም ይታመናል። የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሙሉጌታ ፍስሐ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ዘውዱ ለተወሰነ ጊዜ በብሔራዊ ሙዝየም ቆይቶ ለጨለቆት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ይሰጣል። "የተሰረቀው ከጨለቆት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ነበር። የሚመለስበትን ቀን ገና ባንወስንም በአድዋ በዓል ላይ ለማስረከብ አስበናል" ሲሉ ገልጸዋል። • የጨለቆት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የተዘረፈው ዘውድ ይመለስልኝ እያለች ነው • ለ21 ዓመታት የኢትዮጵያን ቅርስ ደብቀው ያቆዩት ኢትዮጵያዊ ቅርሱ ነሀሴ 26፣ 1979 ዓ. ም. እንደተሰረቀ የሚናገሩት ዶ/ር ሙሉጌታ፤ ከቅርሱ ዝርፊያ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ግለሰቦች ቢኖሩም፤ ቅርሱ በምን መንገድ ከአገር እንደወጣ እስካሁን አልታወቀም ብለዋል። ቅርሱን ለ21 ዓመት በቤታቸው ያቆዩት አቶ ሲራክ ስለ ዘውዱ ለኔዘርላንድስ መንግሥት ካሳወቁ በኋላ ጉዳዩ በውጪ ጉዳይ ሚንስትር በኩል ወደ ባህልና ቱሪዝም ሚንስትር ከዛም ወደ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን መመራቱን ዶ/ር ሙሉጌታ ገልጸዋል። "ቅርሱ የጨለቆት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን መሆኑን በፎቶ ማስረጃዎች ካረጋገጥን በኋላ እንዲመለስ ተወስኗል" ሲሉ አስረድተዋል። የትግራይ ክልል ቅርሱ ከተሰረቀ በኋላ ለማስመለስ ደብዳቤዎች ይጻጻፍ እንደነበር እንዲሁም ቅርሱ ከመዘረፉ በፊት የነበረበትን ሁኔታ የሚያሳዩ የፎቶግራፍ ማስረጃዎች እንዳሉም አክለዋል። • ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ስለተዘረፉ ቅርሶች ምን እናውቃለን? • የሠላም ተጓዧ ሉሲ (ድንቅነሽ) ምን ደረሰች? "ጠቅላይ ሚንስትሩ የዳያስፖራው ምሳሌ ነህ አሉኝ" ላለፉት 41 ዓመታት ኔዘርላንድስ ውስጥ የኖሩትና የአገሪቱን ዜግነት ያገኙት አቶ ሲራክ፤ ቅርሱን ለ21 ዓመታት ደብቀው ማቆየታቸውን ይፋ ባደረጉበት ወቅት ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ "ለቅርሱ ደህንነት እምነት የምጥልበት ሥርዓት ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲህ በአጭር ጊዜ ይመጣል ብዬ አልጠበቅኩም ነበር" ማለታቸው የሚታወስ ነው። አሁን ባለው አስተዳደር እምነት በመጣላቸው ቅርሱን ለኢትዮጵያ ለማስረከብ መወሰናቸውን በወቅቱ ገልጸው ነበር። አቶ ሲራክ፤ ስደተኞች የጥገኝነት ጥያቄያቸው ተቀባይነት እስኪያገኝ የስደተኞቹን ቁሳ ቁስ ተረክበው ቤታቸው በአደራ ያስቀምጡ ነበር። ቤታቸው ይመላለሱ ከነበሩ ሰዎች አንዱ፤ ቅርሱን እሳቸው ቤት ትተውት እንደሄዱም ተናግረዋል። አቶ ሲራክ ቅርሱን ለጠቅላይ ሚንስትሩ ካስረከቡ በኋላ ከቢቢሲ ጋር አጭር ቆይታ ያደረጉ ሲሆን ደስታቸውንም ገልፀዋል። "ዛሬ የተሰማኝን ለመግለጽ ቃላት ያጥረኛል፤ በሕይወት እያለሁ ኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ መጠቶ ዘውዱን ለኢትዮጵያ አስረክባለሁ ብዬ አልሜ አላውቅም ነበር" ብለዋል። ለጠቅላይ ሚንስትሩ ዘውዱን ማስረከብ "ለኔ ታላቅ ክብር ነው" ያሉት አቶ ሲራክ፤ "ከ20 ዓመታት በላይ ይዤ የከረምኩትን ሸክም ከጀርባዬ አውርደውልኛል" በማለት ስሜታቸውን ገልጸዋል። ዘውዱን ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ በአደራና በጥንቃቄ አስቀምጠው በማስረከባበቸውም ጠቅላይ ሚንስትሩ "የዳያስፖራው ምሳሌ ነህ" እንዳሏቸው ተናግረዋል። ከቀደመው ትውልድ የተሸጋገረን ቅርስ ለቀጣዩ ትውልድ ማስረከብ እንዳስደሰታቸውም አክለዋል። "ዘውዱን ለ21 ዓመታት ቤቴ ውስጥ አይቼዋለሁ። ዛሬ ቤተ መንግሥት ውስጥ ሳየው ግን ልዩና ገናና ሆኖ ታየኝ" ሲሉም አቶ ሲራክ ተናግረዋል። የዘውዱ ታሪካዊ ዳራ በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር ከ1745-1865 በወቅቱ የእንደርታ ዙሪያ የሚባለውን ሰፊ ግዛት ያስተዳደሩት ራስ ወልደሥላሴ በአራት ቦታዎች ማለትም በጨለቆት፣ በአንጣሎ፣ በፈለግዳሮና በመቐለ ቤተ መንግሥቶችን ገንብተው ነበር። በአንድ ወቅትም ጨለቆትን ዋና ከተማቸው አድርገዋታል። ለአሥራ ስድስት ዓመታት መንነው በቤተ ክርስቲያኗ የሚኖሩት የ82 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ አባ ገብረሥላሴ፤ ሦስት ዘውዶችን ራስ ወልደሥላሴ ለቤተ ክርስቲያኗ መስጠታቸውን ለቢቢሲ መግለፃቸው የሚታወስ ነው። ራስ ወልደሥላሴ ካበረከቷቸው ዘውዶች መካከል በኔዘርላንድስ ተገኝቶ ዛሬ ለኢትዮጵያ የተመለሰው ዘውድ አንዱ ነው። ዘውዱን አንዳንዶች በላሊበላ እንዲሁም በፋሲለደስ ወቅት የነበረ ነው ቢሉም፤ ኒው ዮርክ ታይምስ ያናገራቸው በኢትዮጵያ ቅርሶች ላይ ከፍተኛ ጥናት ያደረጉት ጃኮፖ ጊንስቺ፤ ዘውዱ ከሥላሴ ጨለቆት ቤተ ክርስቲያን የተሰረቀ ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል። በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪ የሆኑት ጃኮፓ እንደሚሉት፤ ዘውዱ ከመጥፋቱ በፊት በ1980ዎቹ መጨረሻ ላይ አንድ የቤተ ክርስቲያን ቄስ ዘውዱን ራሳቸው ላይ ጭነው ፎቶ ተነስተዋል። ዘውዱ በአይነቱ የተለየ እንደሆነ የሚናገሩት ተመራማሪው፤ ዋጋውንም 55 ሺህ ዶላር ወይም 1.76 ሚሊዮን ብር ይገመታል ብለዋል። • ድሬ ዳዋ ስለሚገኙት የለገ ኦዳ የዋሻ ሥዕሎች ያውቃሉ? • አደጋ የተጋረጠበት የአፄ ፋሲለደስ ቤተ መንግሥት በተለያዩ ዘመናት የኢትዮጵያ ቅርሶች ተዘርፈው ከአገር ወጥተዋል። የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ከተለያዩ አገሮች ጋር ስምምነት በማድረግ ቅርሶችን ለማስመለስ ቢሠራም፤ ቅርሶች እንዳይዘረፉ መከላከል ጉልህ ቦታ እንደሚሰጠው የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሙሉጌታ ተናግረዋል። "ቅርስ ህልውና ነው፤ ለዘመናት የሰው ልጅ ያለፈበትን ታሪክና ባህል የሚገልጽ ቅርስ እኛነታችንን ይገልጻል" የሚሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ቅርሶች ከማንነት መገለጫነታቸው ባሻገር የቱሪስት መስህብ እንደሆኑ በማከልም ማኅበረሰቡ ቅርሶቹን መጠበቅ እንዳለበት ገልጸዋል።
news-50114248
https://www.bbc.com/amharic/news-50114248
ተማሪዎች የካርቶን ሳጥን አጥልቀው ፈተና እንዲፈተኑ ያደረገ የህንድ ትምህርት ቤት ይቅርታ ጠየቀ
ተማሪዎች ጭንቅላታቸው ላይ የካርቶን ሳጥን አጥልቀው ፈተና እንዲፈተኑ ያደረገው የህንድ ትምህርት ቤት ባለሥልጣን ይቅርታ ጠየቀ።
ትምህርት ቤቱ ይቅርታ የጠየቀው ያልተለመደውና ተማሪዎች የካርቶን ሳጥን አጥልቀው የሚያሳየው ፎቶ በርካታ ሰዎችን ካነጋገረ በኋላ ነው። ፎቶው የተነሳው በካርናታካ ግዛት በባጋት ቅድመ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የኬሚስትሪ ፈተና ሲፈተኑ ነበር። • ለተማሪ ሲፈተኑ የተያዙት ርዕሰ-መምህር 5 ዓመት ተፈረደባቸው • ክፍያ ባልከፈለ ተማሪ እጅ ላይ ማህተም የመታው ትምህርት ቤት ተወገዘ በፎቶግራፎቹ ላይ እንደሚታየው ተማሪዎቹ በአንድ በኩል የተሰነጠቀ የካርቶን ሳጥኖች አጥልቀው የነበረ ሲሆን እንዳይኮራረጁ ለማድረግ ታስቦ የተደረገ ነው። ይህንን ተከትሎ የትምህርት ቤቱ አስተዳዳሪ በተፈጸመው ድርጊት የግዛቷ ባለሥልጣናትን በይፋ ይቅርታ ጠይቀዋል። የትምህርት ቤቱ አስተዳዳሪ ሳቲሽ፤ ኩረጃን ለመከላከል ያልተለመደ መንገድ በመጠቀማቸው ይቅርታ መጠየቃቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። እርሳቸው እንዳሉት ተማሪዎችን እንዳይኮራረጁ ለማስቻል ይህንን ዘዴ የተጠቀሙት የሆነ ቦታ ስለ ጠቀሜታው በመስማታቸው ለመሞከር በማሰባቸው ነው። ተማሪዎቹ ፈቃደኛ በመሆናቸው የራሳቸውን የካርቶን ሳጥን ይዘው በመምጣት ውሳኔውን ተግባራዊ እንዳደረጉም አስተዳዳሪው አክለዋል። "በምንም ዓይነት መልኩ አልተገደደዱም፤ በፎቶግራፉ ላይ ጥቂት ተማሪዎች ካርቶኑን ሳያጠልቁ ይታያሉ። ካርቶኑንም ከ15 ደቂቃ በኋላ፤ አንዳንዶች ደግሞ ከ20 ዲቂቃ በኋላ አውልቀውታል፤ እኛ ራሳችን ከአንድ ሰዓት በኋላ እንዲያወልቁት ጠይቀናቸዋል።" ብለዋል። የግዛቷ ባለሥልጣናት ፎቶግራፉን እንዳዩ በፍጥነት ወደ ትምህርት ቤቱ በመሄድ ቅሬታቸውን አሰምተዋል። • 1550 ተማሪዎች ለኩረጃ ሲሉ ስማቸውን ለውጠዋል • ህንዳዊቷ ተማሪ ራሷን በማጥፋቷ ተማሪዎች ዩኒቨርስቲውን አቃጠሉ የቅድመ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት የቦርድ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ፒርጃደ፤ ድርጊቱን "ሰብዓዊነት የጎደለው ነው" ሲሉ አውግዘውታል። "በዚህ ጉዳይ ላይ መልዕክት ሲደርሰኝ፤ ወዲያውኑ ነበር ወደ ኮሌጁ ስከንፍ የደረስኩት። ከዚያም የኮሌጁ አስተዳደር ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ነግሬያቸዋለሁ" ብለዋል። "ለኮሌጁ አስተዳደር አሳውቄያለሁ፤ በተማሪዎቹ ላይ ይህንን ድርጊት በመፈፀማቸውም ሥነ ምግባር በመጣስ እንዲቀጡ እናደርጋለን" ማለታቸውን ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ እርሳቸውን ጠቅሶ ዘግቧል። የትምህርት ቤቱ ባለሥልጣን በበኩላቸው ድርጊቱን እንዳቆሙ ገልጸው፤ በትምህርት ቤቱ ቦርድ መርህ በመከተል በትብብር እየሠሩ እንደሆኑ ገልጸዋል።
44072605
https://www.bbc.com/amharic/44072605
የድሬዳዋ ቀለማት
በስምጥ ሸለቆ ምሥራቃዊ ዳርቻ ላይ የምትገኘው የድሬዳዋ ከተማ ምሥረታዋ በ19ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን መደምደሚያ ላይ ከተዘረጋውና መዲናይቱ አዲስ አበባን ከጅቡቲ ጋር ከሚያገናኘው የባቡር መስመር ጋር ይያያዛል።
የባቡር መስመሩ እና ከእርሱም ጋር ተያይዞ በከተማዋ እምብርት የተቋቋመው ጣቢያ ለንግድ መጧጧፍ ትልቅ በር ከመክፈቱም ባሻገር በሺህዎች ለሚቆጠሩ የአካባቢው ኗሪዎች ሥራን ፈጥሮ ነበር። ከጥቂት ዓመታት አንስቶ ግን መስመሩ ለዕድሜ ጫና እጅ ሰጥቶ የወትሮ አገልግሎቱን መስጠት ተስኖታል። ቀድሞ ይታወቅበት የነበረው ግርግር እና ሞቅታ ርቆት ድብታ ተጭኖታል። ሁለቱን ራስ ገዝ የከተማ አስተዳደሮች፤ አዲስ አበባ እና ድሬዳዋን ማገናኘቱ ቢቀርም ግን ወደ ጅብቲ በየሳምንቱ የተወሰኑ ጉዞዎችን ያደርጋል። የአዲሱ የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር እውን መሆን ተስፋቸውን እንዳወገገው ሰራተኞች ይናገራሉ። የተዘጋ የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የተዘጋ የአርመን ቤተ ክርስትያን የተቃጠለ የቀድሞ የአውሮፓውያን የንግድ ቦታ የቀድሞ አውሮፓዊያን መኖሪያ ከዚራ የተዘጋ የአርመን ቤተ ክርስትያን በ1920ዎቹ መጨረሻ የጣልያን ወራሪ ኃይሎች ድሬዳዋ ከተማ እና የባቡር መስመሩን ይዘዋቸዋል። በከተማዋ ውስጥ በነበሩት ከፍተኛ ቁጥር ባላው አውሮፓውያን ምክንያት የጣልያን ኃይሎች በከተማዋ ላይ የበረታ ዱላ ከማሳረፍ እንደተቆጠቡ የሚያትቱ ፀሐፍት አሉ። ከተማዋ ከጣልያን ኃይሎች ነፃ ከወጣች በኋላ የብሪታንያ ተፅዕኖ ጎላ ብሎ ቆይቷል። "ነምበር ዋን" ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ለዚህ ምስክር ሲሆን፥ አካባቢው ከጣልያን ኃይሎች ጋር ሲፋለሙ ህይወታቸውን ላጡ 73 አፍሪካዊ ወታደሮች እና 3 የብሪታንያ ዘውዳዊ አየር ኃይል መኮንኖች መካነ መቃብር ይገኝበታል። የአፍሪካ እና የብሪታንያ ወታደሮች መካነ መቃብር የአፍሪካ እና የብሪታንያ ወታደሮች መካነ መቃብብ በር ላይ አነስተኛ የንግድ ሥራ የምታከናውን ሴት በ1999 ዓ.ም የተከናወነው የሕዝብ ቆጠራ ድሬዳዋ ከ340 ሺህ በላይ ኗሪዎች እንዳሏት አሳይቷል። ይህ ቁጥር በእርግጥ በከተማዋ አስተዳደር ስር የሚገኙ አጎራባች የገጠር ቀበሌዎችንም የሚጨምር ነው። አሁን ቁጥሩ ግማሽ ሚሊዮን እንደደረሰ ይገመታል። ድሬዳዋ ለዘመናት በንግድ ማዕከልነት ባለፉት ጥቂት ዓመታት የንግድ እንቅስቃሴ መፋዘዝ እንዳጋጠመው ቢቢሲ በከተማዋ ተገኝቶ ያነጋገራቸው ነጋዴዎች ይገልፃሉ። አሁንም ግን ልዩ ልዩ አሻራ ያረፈባቸው ዝብርቅርቅ ቀለማቷን እና ጣፋጭ ምግቦቿን አቅፋ ይዛ ትገኛለች። ቀፊራ ገበያ የታይዋን ገበያ መግብያ አንድ ገፅታ ወደ መስጊድ የሚወስደው ታዋቂው የኮኔል መንገድ ኮኔል ያለው ታዋቂው የሐሺሜ ሙሸበክና ጣፋጭ መሸጫ መደብር
news-42228635
https://www.bbc.com/amharic/news-42228635
''ኢትዮጵያዊያንን የባሕር ላይ አደጋ መሞከሪያ ያደርጉ ነበር''
የ20 ዓመቱ ሌንጮ በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ እስከ መሰናዶ ትምህርት ድረስ ተምሯል። "ብዙ ታሪክ አሳልፌያለሁ" የሚለው ሌንጮ አሁን ጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ ነው የሚኖረው።
እንዴት ከሐገር ወጣ? እ.ኤ.አ በ2014 በነበረው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞ ሰልፍ ላይ በመሳተፉ እስር ቤት ገባ። ከእስር ከወጣም በኋላ ለዳግም እስር ላለመዳረግ በማለት ከሀገር እንደወጣ ይናገራል። ከባሌ ሮቤ አዲስ አበባ ከዛም ባህር ዳር ተጓዘ። በመቀጠልም መተማ በመግባት የኢትዮጵያ ድንበርን አቋረጠ። "ሱዳን እንደደረስን እስር ቤት አስገብተው ፀጉራችንን ላጩን፤ ከቤተሰቦቻችንም ብር እንድናስልክ አስገደዱን " ይላል ሌንጮ። የተጠየቀውን ገንዘብ ከፍሎ ከእስር ቤት ከወጣ በኋላ በደላላ በሰሃራ በረሃ ውስጥ ለስድስት ቀናት ተጉዞ ሊቢያ ገባ። ደላላውም ለሚቀጥለው ደላላ አሳልፎ ሸጠው። "ሶስት ጊዜ ለተለያዩ ነጋዴዎች ተሽጫለሁ" "ሬሳና አፅም እያዩ መራመድ" ከሱዳን የተነሱት 87 ኢትዮጵያውያን ነበሩ። "በአንድ መኪና እስከ 50 የምንሆን ሰዎችን ጭነውን በሚሄዱበት ወቅት ከመኪናው ላይ የሚወድቁ ሰዎች ነበሩ፤ ሰው ወድቋል ብሎ ማቆም አይታሰብም። ዝም ብለው ይነዳሉ።" ከዚህ በተጨማሪ ይላል ሌንጮ "በሰሃራ በረሃ ውስጥ በምንሄድበት ወቅት የብዙ ሰዎች ሬሳ እና አፅም እየተመለከትን ነበር" በማለት ሐዘኑን ይገልፃል። በሊቢያ አይዳቢያ በምትባል ከተማ ይዟቸው የመጣው ደላላ ሸጧቸው ሄደ። እነዚህም ደላሎች "ገንዘብ አልተከፈለላችሁም በማለት በትንሽዬ ኮንቴይነር ውስጥ ከተቱን" ይላል፤ ". . .ኮንቴይነሩ በጣም ትንሽ በር እንጂ መስኮት የሌለው ሲሆን ከአንድ መቶ በላይ የምንሆን ሰዎችን እዛ ውስጥ ከተቱን። የከፈሉ ሰዎች ከኮንቴይነሩ ሲወጡ ያልከፈልነው ግን እዛ ውስጥ ቀረን።" በማለት ያስታውሳል። ከሱዳን የተነሱት 87 ኢትዮጵያውያን ነበሩ። "ቀን በሐሩሩ የተነሳ መቆምም ሆነ መቀመጥ አስቸጋሪ ነው። ሌሊት ደግሞ ብርዱ አጥንትን ዘልቆ ይሰማል" ከዚህ በተጨማሪም ይላል ይህ ሌንጮ "ከሁለት እና ከሦስት ቀን በላይ እዛ ውስጥ ቆይተህ ስትወጣ ሰውነትህ ነጭ ይሆናል" በተጨማሪም በዚያ በረሃ ውስጥ ውሃ ማግኘት ህልም ነው ይላል። "ውሃ ፊት ለፊትህ ያስቀምጡና ልጠጣ ስትል ይደፉታል። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ተጨንቀን ከቤተሰቦቻችን ገንዘብ እንድናስልክ ነው።" ሌንጮም ብር ሞልቶለት ከኮንቴይነሩ ውስጥ በህይወት መውጣት ቻለ። እድለኛ ያልሆኑ አራት ወጣቶች ግን ከነሌንጮ ተለይተው እዛው ቀሩ። ከዛም በኋላ ሌላ ደላላ መጥቶ በሜዲትራንያን ዳርቻ በምትገኘውና የሊቢያ ዋና ከተማ ወደ ሆነችው ትሪፖሊ ጉዞ ጀመሩ። በላንድ ክሩዘር መኪና ላይ 'እንደ ሸቀጥ በመደራረብ' ለሌላ ደላላ አሳልፈው ሰጧቸው። እነዚህም ደላሎች የሱዳን፣ የኤርትራ እና የሱማሌ ወጣቶችን በመጨመር ከ200 በላይ የሚሆትን በጭነት መኪና ላይ አሳፈሯቸው። የተጫኑበት መንገድ በጣም ዘግናኝ እንደነበር ሊንጮ ያስታውሳል። "ጭነት መኪናው ላይ ካሳፈሩን በኋላ ከላያችን ላይ እንጨት ረበረቡብን ከዛም እጆቻችንን ከተረበረበው እንጨት ጋር አሰሩት። ከዚያም በኋላ መኪናውን ሸራ አለበሱት። በዚህ ሁኔታ ውስጥ መተንፈስ ከባድ ነበር። አጠገቤ የነበረ ልጅ አረፋ ደፍቆ ሲሞት አይቻለሁ።" በመሃል እነዚህ ወጣቶች ተጨንቀው ሸራውን በመበጣጠስ ጮሁ። ኬላ ላይም የሃገሪቱ ፖሊሶች ይዘዋቸው ወደ እስር ቤት አስገቧቸው። በዚህ እስር ቤትም ለአስራ አምስት ቀናት ቆዩ። "ፈጣሪ ልባቸውን አራርቶልን ከእስር ተለቀቅን" ይላል ሌንጮ። ከዚያ ከወጡ በኋላ በባህር ላይ በማሻገር ወደ አውሮፓ የሚያደርሱ ደላሎች ጋር ተወሰዱ። እነዚህም ከሌሎቹ ደላሎች በምንም አይለዩም ነበር። 32ሺህ የኢትዮጵያ ብር እንዲከፍሉ ጠየቋቸው ። "ቤተሰብ ደግሞ ልጆቻችን ከሚሞቱ ብለው ያላቸውን ጥሪት አሟጠው ይልኩልናል።" "በሰሃራ በረሃ ውስጥ በምንሄድበት ወቅት የብዙ ሰዎች ሬሳ እና አፅም እየተመለከትን ነበር።" ባርነት በእርሻ ቦታ ከዚህ ጉዞ በኋላ ሌንጮ እና ሌሎች ወጣቶች አውሮፓ ለመግባት ያላቸው ህልም የቀረበ መሰላቸው። ተስፋቸው ግን ለረጅም ጊዜ አብሯቸው አልቆየም፤ በመሃል ያልታሰበ ነገር ተከሰተ። "ወደ ባህር ጭነውን እየሄድን በነበረበት ወቅት እንደ ወታደር የለበሱ እና የታጠቁ ሰዎች መሃል መንገድ ላይ አስቆሙን።" ከነበሩበት መኪናም አስወርደዋቸው ወደሌላ መኪና ተዛወሩ። በበረሃ ውስጥ በግምት ከ30 ኪሎ ሜትር በላይ እንደሄዱ የሚናገረው ሌንጮ ለሁለት ቀናት በአንድ ክፍል ውስጥ ቆይተው ወደ እርሻ ቦታ እንደወሷቸው ያስታውሳል። "ቀኑን ሙሉ በእርሻ ውስጥ ሲያሰሩን ውሃ ስናጠጣ እንዲሁም ቆሻሻ ስንለቅም ውለን ማታ ገብተን ነው ምግብ የሚሰጡን።" "አንድ ቀን ማሳው ውስጥ ደክሞኝ ብቆም በፌሮ መጥቶ ወገቤን መታኝ። ለብዙ ቀናት ታመምኩ" በማለት ያሳለፈውን ስቃይ ያስታውሳል። ከ 15 ቀን በኋላ እነዚሁ የያዟቸው ሰዎች መጀመሪያ ያስቆሟቸው ቦታ መለሷቸው። በመጨረሻም ባህር ዳርቻ ደረሱ። "መሞከሪያ አደረጉን" እዚህም ክፉ ክፉ ነገር አይቻለሁ ይላል ሌንጮ። የሜዲትራኒያን ባህር ሞገዱ ፀጥ የሚልበት እና ለጉዞ ተስማሚ የሚሆንበት ወቅት አለ። በሌላ ጊዜ ደግሞ ሞገዱ የሚበረታበት እና ለጉዞ አስፈሪ ይሆናል። ያኔ መርከብም ሆነ ጀልባ ይገለብጣል የሰው ሕይወትም ይጠፋል። አብዛኞቹ ስደተኞች ጉዞ የሚያደርጉት ባህሩ ሲረጋጋ እና ሞገዱ ፀጥ ሲል ነው። ሌንጮ አየሁ የሚለው ግን "ሞገዱ በሚያይልበት እና ለጉዞ አዳጋች በሚሆንበት ወቅት 85 የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ተመርጠው ለሙከራ ብለው ጀልባ ላይ ጫኗቸው።" ሌንጮ በድምሩ ከ103000 የኢትዮጵያ ብር ( 4000 ዶላር ) በላይ ለህገወጥ አዘዋዋሪዎችና ደላሎች ከፍሏል ከሁለት ቀናት በኋላ እነ ሌንጮ ሲሰሙ እነዛ ልጆች ሁሉ ውሃ በልቷቸዋል። "የማውቃቸው ጓደኞቼም እዛ ውስጥ ነበሩ" ይላል ሌንጮ። ለአራት ቀናትበባህር ላይ መንከራተት ይህንን አሳዛኝ እና አሰቃቂ ዜና ከሰሙ በኋላ እነ ሌንጮ ለመሄድ በዝግጅት ላይ ነበሩ። ከእንጨት በተሰራች አንድ አነሰተኛ ጀልባ ላይ 410 ሰዎች በምሽት የባህር ላይ ጉዟቸውን ጀመሩ። ሴቶችና ህፃናቶችም በጀልባዋ ላይ አብረው ነበሩ። ከብዙ መከራ በኋላ ተጉዘው ዓለም አቀፍ የውሃ ድንበር ላይ ሲደርሱ የነፍስ አድን ሰራተኞች በአካባቢው አልነበሩም። ሌንጮ "ቀኑ እሁድ ስለነበር የነፍስ አድን ሰራተኞቹ ሥራ ላይ አልነበሩም። ጉዟችንን በመቀጠል አንድ መርከብ ስናይ ያድነናል ብለን ተስፋ ብናደርግም የአሳ አጥማጆች መርከብ ነበር" በማለት ያስታውሳል። እንደዚህ እያሉ አራት ቀናትን በባህር ላይ አሳለፉ። በአራተኛው ቀን የነፍስ አድን ሰራተኞች መርከብ በመምጣት ወደ ጣልያን ወሰዷቸው። ከጥቂት ጊዜያት በኋላም ወደ ጀርመን ተሻገረ። አሁን ላይ መለስ ብሎ ሲያስታውሰው "የሚሰቀጥጠኝ ሴቶች ላይ የሚደርሰው እንግልት ነው " ይላል። ከተለያዩ ቦታዎች የመጡ ወጣት ሴቶች አብረዋቸው እንደነበሩ የሚናገረው ሌንጮ፤ እነዚህን ሴቶች ወስደው የፈለጉትን ነገር ያደርጓቸዋል። ተዉ ብሎ መሃል የሚገባ ካለ ይደበደባል። በማለት ከሰው ልጅ የማይጠበቅ ነገር እንደሚፈፅሙ በሐዘን ስሜት ውስጥ ሆኖ ያስረዳል። ሌንጮ ከሃገር ወጥቶ የጣልያንን መሬት እስከሚረግጥበት ድረስ በድምሩ ከ103000 የኢትዮጵያ ብር (4000 ዶላር) በላይ ለህገወጥ አዘዋዋሪዎችና ደላሎች ከፍሏል።
news-45166885
https://www.bbc.com/amharic/news-45166885
የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር የተኩስ አቁም ማድረጉን አስታወቀ
የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) የተኩስ አቁም ማድረጉን አስታወቀ።
ኦብነግ በመንግሥት በኩል ለንግግርና ለሰላም እየተወሰዱ ያሉትን አዎንታዊ እርምጃዎችን በመገንዘብ ከእሁድ ሐምሌ 06፣ 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ተኩስ አቁም ማወጁን ገልጿል። ግንባሩ በሶማሌ ክልል ከመንግሥት አንፃር የሚያካሄደውን ወታደራዊና የደህንነት ተልዕኮዎችን በድርድር ስምምነት ላይ እስኪደረስ ድረስ ማቆሙን አሳውቋል። • አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው ኦብነግ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር እየተደራደረ ነው • «ኦነግ ሀገር ለመገንጠል ነው የምሠራው ብሎ አያውቅም» ሽጉጥ ገለታ (ዶ/ር) የኦብነግ ቃል-አቀባይ የሆኑት አብዱልቃድር ሃሰን ሄርሞጌ ''በሶማሌ ክልል ውስጥ ሰላም ሰፍኖ ማየት እንፈልጋለን። የክልሉ ህዝብ ለረዥም ዓመታት በጭቆና ውስጥ ነው የቆየው። የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እና በክልሉ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ውይይት ማድረግ ያስፈልገናል'' ብለዋል። በቃ-አባዩ አብዱልቃድር ሃሰን ሄርሞጌ የሚመራ የኦብነግ ልዑክ ትናንት ማምሻውን አዲስ አበባ ገብቷል። ኦብነግ በተጨማሪም በአንድ ወገን ላወጀው የተኩስ አቁም የኢትዮጵያ መንግሥት ተመሳሳይ እርምጃ በመውሰድ የተጀመረው የሰላም ሂደት እንዲፋጠን ጠይቋል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኦብነግን ጨምሮ ኦነግ እና ግንቦት 7ን ሽብርተኛ መባላቸው ይሰረዝ ዘንድ ሚኒስትሮች ምክር ቤት የላከለትን ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ከተወያየበት በኋላ ማጽደቁ ይታወሳል። • ፓርላማው የኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7 የሽብርተኝነት ፍረጃ መነሳትን አፀደቀ በተያያዘ ዜና የመንግሥት ኮሚኬሽን ጉዳዮች ጸ/ቤት ሃላፊ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) ሊቀመንበር ሆነው ተሹመዋል። ፓርቲው ያለፉትን ሶስት ቀናት በክልሉ ተከስቶ የነበረውን ሁከት በተመለከተ ጥልቅ ግምገማ ካደረኩ በኋላ አህመድ ሺዴን የፓርቲው ሊቀመንብር በማድግ በሙሉ ድምጽ መርጫለው ብሎዋል። የክልሉ ፕሬዝዳንት የነበሩት አብዲ ሙሃመድ ኡመር ከክልሉ ፕሬዝዳንትነታቸው ቢነሱም በበፓርቲ ሊቀመንበርነታቸው ይቀጥላሉ ተብሎ ነበር።
news-49341234
https://www.bbc.com/amharic/news-49341234
ከቤትዎ እና ከመሥሪያ ቤትዎ የሚወጣ በካይ ድምፅ ስሜትዎን እንደሚያጨፈግግ ያውቃሉ?
ቤትዎ አሊያም መሥሪያ ቤትዎ ሆነው ድንገት ደርሶ 'ሙድዎ ከተበከለ'፤ ቀንዎ ከጨለመ፤ አንድ ነገር ያስተውሉ ይላሉ ሳይንቲስቶች፤ በዙሪያዎ ያለ ድምፅን።
ከቢሮ ሊሆን ይችላል ወይም ከመመገቢያ ሥፍራዎች [ሬስቶራንት] እንዲሁም ሰው ከሚበዛባቸው ቦታዎች የሚወጡ ድምፆች ከመሬት እና ጣራ ጋር ሲጋጩ የሚፈጥሩት ሌላ ዓይነት ድምፅ አለ። • ስለድምጻችን ልናውቃቸው የሚገቡ ሰባት ነገሮች በተቃራኒው ወለላቸው በእንጨት የተሠራ ሕንፃዎች ድምፅን የማፈን ባሕርይ ስላላቸው ለአእምራችን ውስጣዊ ሰላም ይለግሳሉ። ድምፅ እንደሚያገኘው ነፃነት ባሕሪው የሚለዋወጥ እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች ተናግረው አይጠግቡም። ሕንፃ ሲገነባ ሰው ወይም ሌላ ቁስ እንዲኖርበት አሊያም እንዲከማችበት ብቻ ሳይሆን፤ ምን ዓይነት ድምፅ ሊያስተናግድ ይችላል የሚለውም ከግምት ውስጥ እንዲገባ የሥነ ሕንፃ ሰዎች ይመክራሉ። ባለሙያዎች ሕንፃን ሲገነቡ ምን ዓይነት ቁስ ነው የሚጠቀሙት ምን ዓይነት ቅርፅስ እንዲኖረውስ ይፈለጋል? ሊዘነጋ የሚገባው ጥያቄ አይደለም። ትሬቨር ኮክስ የአኩስቲክ ኢንጅነር ናቸው። ብዙ ጊዜ ዙሪያችንን ለማስተዋል ዓይናችንን እንጠቀም እንጂ ጆሯችን ሁሌም አሰሳ ላይ እንደሆነ የሚናገሩት ባለሙያው «ጆሯችን መረጃን ከመልቀም ቦዝኖ አያውቅም» ይላሉ። • ራስዎን ካላስፈላጊ የስልክ ጥሪ እንዴት ይታደጋሉ? «ዓይናችን ተሸፍኖ አንድ ወና ቤት ብንገባ በምንሰማው ነገር ብቻ የቤቱን ስፋት፣ የጣራውን ልክ፣ የወለል ንጣፍ ተደርጎለት እንደሁ ማወቅ እንችላለን» የሚሉት ደግሞ ኤሌክትሪካል ኢንጅነር ቤሪ ብለሰር ናቸው። «በጣም በርካታ ነገር ወደ ጆሯችን ይገባል፤ ትኩረት ስለማንሰጠው ነው እንጂ።» የድምፅ ብክለት ምንድነው? ያልተፈለገ ድምፅ፤ በጉዞ፣ በእንቅልፍ፣ በሥራና ትምህርት፣ በንግግር እና በመሰል የሰው ልጅ የተለመዱ እንቅስቃሴዎች ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድር እና ጤናማ ከባቢን በመበከል በሥነ ልቦናዊ እና አካላዊ ጤንነት ላይ ጉዳት የሚያደርስ ነው-የድምፅ ብክለት። ሆኖም ግን የድምፅ መጠን እንደ ሰሚው ዕድሜ፣ የጤንነት ሁኔታ፣ እንደ ድምፁ ዓይነት፣ ቆይታና ድግግሞሽ የሚለያይ ነው። ለአንዱ መደበኛ ድምፅ ለሌላው የሚረብሽ፤ ለአንዱ የሚረብሽ ድምፅ ለሌላው ሙዚቃ ሊሆን ይችላል። • "የት ይቀርልሃል!? አፈር ድሜ ትበላለህ...!" ጋሽ አበራ ሞላ ኢትዮጵያ የድምጽ መጠን ለመወሰን መመሪያ አውጥታለች። ሕጉ ለመኖሪያ አካባቢዎች፣ ከንግድ አካባቢዎችና ከኢንዱስትሪ ዞኖች መውጣት የሚገባው የድምጽ መጠን ቀን ቀን 55፣ 65 እና 75 ዲሲቢል እንዲሁም ሌሊት 45፣ 57 እና 70 ዲሲቢል መሆን እንዳለበት በቅደም ተከተል ያስቀምጣል፡፡ ነገር ግን በተለይ አዲስ አበባ የድምፅ ብክለት እጅጉኑ የሚበዛባት ከተማ እንደሆነች ለመናገር መስካሪ አያሻም። ይህ ከኒው ዮርክ ባቡር ጣቢያዎች አንዱ ከምድር በታች የሚገኝ ሕንፃ ሲሆን ምን ዓይነት ምስጢር መደበቅ አይችልም። ሹክሹክታዎች ሳይቀር ከአንዱ ጥግ ወደ አንዱ ይጓዛል ድምፅ፣ ሙድ እና የአእምሮ ጤና ድምፅ እና ሕንፃዎች ያላቸው ግንኙት 'ሙዳችንን' ሊወስኑት ይችላሉ። ሰዎች መታጠቢያ ቤት ሲገቡ ማንጎራገር የሚወዱት ለምን ይመስልዎታል? ምክንያቱ ድምፃችንን ቅላፄ ይኑረውም አይኑረው ኩልል አድርጎ ስለሚያወጣው ነው። ታድያ ከምንወስደው 'ሻወር' ባልተናነሰ ዘና ያለ ስሜት እንዲኖረን ያደርጋል። ኒው ዮርክ ከተማ የሚገኝ አንድ የባቡር ጣቢያ ከምድር በታች የሚገኝ ሲሆን፤ ይህ ከምድር በታች የሚገኝ ሕንፃ ምን ዓይነት ምስጢር መደበቅ አይችልም። ሹክሹክታዎ ሳይቀር ከአንዱ ጥግ ወደ አንዱ ይጓዛል። በተቃራኒው የሚረብሽ ድምፅ ለጭንቀት እንደሚዳርግ፣ ቀናችንን ሊያበላሸው እንደሚችልና በሥራችን ላይ ተፅፅኖ እንደሚኖረው ይነገራል። • ዘሩባቤል ሞላና በአነቃቂ መንፈስ የታሸው 'እንፋሎት' አልበሙ ጫጫታ በበዛበት፣ ሰው ተጨናንቆ በሚኖርበት አካባቢ መኖር እርዳታ የማጣት ስሜት እንደሚፈጥር፤ በተቃራኒው ድምፅ ባልበዛባቸው አካባቢዎች መኖር ደግሞ ጥልቅ የመመራመር ስሜት እንደሚያጎናፅፍ አንድ ጥናት ያሳያል። ድምፅን ያጠኑ ሰዎች አንዲት ነጠላ ድምፀት [ቶን] ያላት ተፅዕኖ ከፍተኛ ነው፤ በርካታ ድምፀቶች የሚኖራቸውን ተፅዕኖ ደግሞ አስቡት ይላሉ። ለዚህም ነው ሕንፃ ሲገነቡ ወይም ሲያስገነቡ አሊያም መሥሪያ ቤትዎ ወይም መኖሪያ ቤትዎን ከድምፅ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ያጢኑበት የሚል ምክር ባለሙያዎቹ የሚሰጡት።
news-52794754
https://www.bbc.com/amharic/news-52794754
ኮሮናቫይረስ፡ ማኅበራዊ ርቀትን መጠበቅ የሚያስችሉ ቀላል ተግባራዊ ስልቶች
እራሳችንን ከኮሮናቫይረስ ከምንከላከልባቸው መንገዶች አንዱ ማኅበራዊ ርቃታችንን በመጠበቅ ነው።
አገራት እና ግለሰቦች ሰዎች ማኅበራዊ ርቀታቸውን መጠበቅ የሚያስችሏቸውን ተግባሯዊ ዘዴዎችን አምጥተዋል። ይህ አሜሪካ ኒው ዮርክ ግዛት ነው። ሰዎች እራሳቸውን ዘና ለማድረግ ወደ መናፈሻዎች ሲሄዱ መቀመጥ ሚችሉት በክቦቹ ውስጥ ነው። በስሪ ላንካ ሰዎች በአሳንስር (ሊፍት) ውስጥ በዚህ መልኩ ርቃታቸውን በመጠበቅ እራሳቸውን ከቫይረሱ ይከላከላሉ። ሲድኒ አውስትራሊያ በሚገኝ ምግብ ቤት መመገቢያ ጠረጴዛ ላይ ካርቶን ላይ የተሳሉ ስዕሎት ይቀመጣሉ። ተጠቃሚዎች መቀመጥ የሚችሉት በባዶ ወንበሮች ላይ ነው። የስዕሎቹ መኖር ምግብ ቤቱ በሰው የተሞላ አይነት ስሜት እንዲፈጥር ያደርጋል ተብሎለታል። ሰዎች ታይላንድ ባንኮክ በሚገኝ በዚህ ምግብ ቤት ውስጥ ምሳ እየተመገቡ ነው። በሰዎች መካከል የተዘረጉት የላስቲክ መከለያዎች ሰዎች በቫይረሱ የመያዝ እድላቸውን ዝቅ ያደርጋሉ። የአልባኒያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ማኅበራዊ ርቀታቸውን በመጠበቅ የተቀመጠላቸውን አቅጣጫ በመከተል ወደ ህንጻ ሲገቡ። ይህ ደግሞ ሂውስተን ቴክሳስ ነው። ይህ የሴቶች የውበት ሳሎን በዚህ መልኩ ደንበኞቹን ከቫይረሱ ለመጠበቅ ይጥራል። ይህ ምስል ብራሰልስ ቤልጄም የሚገኙ ተማሪዎች ርቀታቸውን በመጠበቅ ሲነጋገሩ ያሳያል። በፈረንሳይ ሰዎች ባቡር ሲጠብቁ ርቀታቸውን ጠብቀው ነው። የአሜሪካ መንግሥት በሳን ፍራንሲስኮ ቤት አልባ ለሆኑ ዜጎች ያዘጋጀው ጊዜያዊ ማረፊያ ቦታ ርቀትን በጠበቀ መልኩ የተዘጋጅቷል ነው። በባንኮክ ታይላንድ የሚገኝ ምግብ ቤት፤ ሰዎች ርቀታቸውን እንዲጠበቁ ለማስገደድ 'ፓንዳ' አሻንጉሊት በየወንበሮቹ ላይ አስቀምጧል። ሰዎች አሻንጉሊቱን አንስተው መቀመጥ አይችሉም። በዚህም ማኅበራዊ ርቀንት ማስጠበቅ ተችሏል። በስፔን ማድሪድ ሚገኝ ቤተ-ክርስቲያን ቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ ምዕመናን ብቻ ወደ ውስጥ እንዲገቡ ይፈቅዳል። በሚላን ጣሊያን በሚገኝ ምግብ ቤት ውስጥ አስተናጋጁ የደንበኛውን የሰውነት ሙቀት ሲለካ። በሌባኖስ ቤይሩት በሚገኝ መስጅድ ውስጥ፤ ሙስሊሞች ጸሎት ሲያካሂዱ በዚህ መልኩ ርቀታቸውን በመጠበቅ ነው። በመስገጃ ምንጣፉ ላይ የተቀረጸው ስዕል ሰዎች ርቀታቸውን በቀላሉ እንዲያውቁ ያስችላል። የሁሉም ፎቶግራፎች የባለቤትነት መብት በሕግ የተጠበቀ ነው።
news-55984267
https://www.bbc.com/amharic/news-55984267
ሱዳን ኢትዮጵያ ላይ ጦርነት መክፈት እንደማትፈልግ ገለፀች
ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ባላት የድንበር ውዝግብ የተነሳ ጦርነት እንደማተከፍት ገለፀች።
የሱዳን የሽግግር መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር አብደላህ ሐምዶክ እሁድ እለት ሱዳን ኢትዮጵያ ላይ ጦርነት የመክፈት ፍላጎት እንደሌላት ገልፀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሁለቱ አገራት መካከል አለመግባባት በፈጠረው የድንበር ጉዳይ ሱዳን ጦርነት ውስጥ ያለመግባት "የፀና አቋም" እንዳላት ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዶክ ይህንን ያሉት እሁድ ዕለት በፊንላንድ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር የተመራውን የአውሮጳ ልዑካን ቡድን ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው። ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ሁለቱ አገራት ይገባኛል የሚሉትን የድንበር አካባቢ ጉዳይ ለመፍታት፣ ሱዳን በኃይል ከያዘችው አካባቢ ለቅቃ መደራደር እንደሚያስፈልግ ስትናገር ቆይታለች። እንዲሁም ኢትዮጵያ በሱዳን ድንበር ያለውን ውጥረት ለመፍታት የሶስተኛ አካል ጣልቃ ገብነትን እንደማትፈልግ አቶ ውሂብ ሙሉነህ በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ከድንበር ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ቴክኒካል አማካሪና በኢትዮጵያ ሱዳን ድንበር ኮሚሽን አባል ለቢቢሲ መግለጻቸው ይታወሳል። ከአንድ ምዕተ ዓመት በላይ ሁለት አገሮችን ያወዛገበው ድንበር፤ ከፍ ያለ የእርሻ ልማትና ተያያዥ ኢንቨስትመንቶች የሚደምቁበት አካባቢ ነው። በሁለቱም አገሮች የሚገኙ የአካባቢው ነዋሪ ድንበርተኞች የይገባናል ጥያቄን ያነሱበታል፡፡ እሁድ እለት ሱዳን ካርቱም የገባውን የአውሮፓ ልዑካንን ቡድን የመሩት የፊንላንድ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ፔካ ሃቪስቶ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትርንና የተለያዩ የአገሪቱ ባለስልጣናት ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት ሱዳን በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ላይ ስላላት አቋም እና በአገሪቱ ላይ ስለሚኖረው ተጽዕኖ መነጋገራቸውን የአገሪቱ ዜና ወኪል ዘግቧል። ሱዳን በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ ስምምነት ላይ ሳይደረስ የግድቡን ሁለተኛ ዙር ሙሌት ካከናወነች በብሉ ናይል ዳርቻ በሚኖሩ ከ20 ሚሊዮን በላይ ሱዳናውያን ሕይወት አደጋ ውስጥ ይወድቃል ስትል ማስረዳቷን የሱዳን ዜና አገልግሎት፣ ሱና ዘግቧል። የሱዳን ካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር የአውሮፓ ልዑክ የሁለት ቀን የሥራ ጉብኝትን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ላይ ልዑኩ የአውሮፓና ሱዳን ትብብርን በአገሪቱ ውስጥ ያለውን ዲሞክራሲያዊ ሽግግርን ባገናዘበ መልኩ እንዲሁም የሱዳን እና ኢትዮጵያ ድንበር ውጥረትን ስደተኞችን እንዲሁም የሕዳሴውን ግድብ በተመለከተ መወያየታቸውን የዜና ወኪሉ ዘግቧል። የአውሮፓ ልዑክ ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።የአውሮፓ ልዑክ ቡድንም ከሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ያደረገው ውይይት ውጤታማ እንደነበር መግለፁ ተመልክቷል። ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስናት ምሥራቃዊው የአል-ቀዳሪፍ ግዛት ላይ ማንኛውንም የአየር በረራ እንዳይካሄድ ማገዷ ይታወሳል። ለመሆኑ ከዚህ ድንበር ጋር በተያያዘ ያለው ታሪክ ምንድነው? ኢትዮጵያና ሱዳን የሚጋሩት ድንበር ርዝመት 750 ኪሎ ሜትር ያካላል። ነገር ግን ይህ ድንበር አብዛኛው ርቀት ግልጽ በሆነ መንገድ መሬት ላይ አልተመላከተም። ይህን ለማሳካት ተደጋጋሚ ንግግሮች ተጀምረው በተደጋጋሚ ተቋርጠዋል። ዶ/ር ወንድወሰን ተሾመ የተባሉ ተመራማሪ፤ "የአፍሪካ ቅኝ ግዛት ዘመን ድንበሮች በተለይም የሱዳንና ኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ" በተሰኘና በእንግሊዝኛ በተጻፈ ጥናታቸው እንደገለጹት የሁለቱ አገሮች ድንበር የአሁን ጊዜ ወሰን እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ1902 እና በ1907 የተደረጉ የአንግሎ-ኢትዮጵያ የካርታ ላይ ምልከታ ስምምነቶችን መሠረት ያደረጉ ናቸው። በቅኝ ግዛት ወቅት በሱዳንና በኢትዮጵያ መሬት ላይ ለተመላከቱ ድንበሮች ኃላፊነቱ ተሰጥቶት የነበረው ሁነኛ ሰው የአይሪሽ ተጓዥና አሳሽ የነበረው ቻርለስ ግዊይን ነበር። የሱዳን ገዳሪፍና ብሉ ናይል ግዛቶች ከአማራ ክልል ጋር ይዋሰናሉ። በ1908 ነበር በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ድንበር የተሰመረው።። የአልፋሽቃ ማዕዘን ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በይገባኛል የምትወዛገብብት አካባቢ ረዥም የግዛት ድንበር ነው ያላት። ሁለቱም አገሮች ለም ነው የሚባለውን ፋሽቃ አካባቢን እጅጉኑ ይፈልጉታል።ይህ በሁለቱ አገሮች ዓይን ውስጥ ያለው አካባቢ የአልፋሽቃ ማዕዘን ወይም የአልፋሽቃ ጥግ ተብሎ ይጠራል። በዚህ ድንበር ሁለቱም አቅጣጫ የሚገኙ ገበሬዎች ባሻገራቸው ያሉ ለም መሬቶች ላይ ያማትራሉ። አልፋሽቃ ማዕዘን በደቡብ ምሥራቅ ሱዳን ምሥራቃዊ ገዳሪፍ የሚገኝ ለም መሬት ነው።አልፋሽቃ መሬት 250 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሸፍንና 600 ሺህ ኤክር ለም መሬትን የሚሸፍን ነው። ለለምነቱ ምክንያት የሆኑት እንደ አትባራ፣ ሰቲት እና ባስላም ወንዞችም በቅርብ ይገኛሉ። ሁለቱ መንግሥታት ከዚህ ቀደም ይህንን አወዛጋቢ ድንበር በድጋሚ ለማስመር፣ የጋራ ፕሮጀክቶችን ለመጀመር እና የአካባቢው ሕዝብ ተጠቃሚ ለማድረግ ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር። ቀደም ካለው አስተዳደር ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግሥት በአገሬው ሕዝብ ሉአላዊ መሬቱን ቆርሶ እየሰጠ ነው በሚል ተደጋጋሚ ወቀሳ ሲቀርብበት ነው የቆየው። እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2014 የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እና የወቅቱ ሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር ሐሰን አልበሽር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸውን ድንበሩ መሬት ላይ የሚመላከትበትን የመጨረሻ ቀን እንዲያሳውቁ መመርያ አስተላልፈውላቸው ነበር።ሆኖም አወዛጋቢውን ድንበር መሬት ላይ የማመላከቱ ሥራ እስከዛሬም አልተሳካም፡፡
news-48116598
https://www.bbc.com/amharic/news-48116598
“ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ከደወሉልን በኋላ ተረጋግተናል” የናዝራዊት አበራ እህት
ናዝራዊት አበራ በቻይና በእፅ ዝውውር ተጠርጥራ በቁጥጥር ሥር መዋሏ ከተሰማ አራት ወራቶች ተቆጥረዋል።
አንድ ሰው እፅ ሲያዘዋውር ከተገኘ የሞት ፍርድ እንዲበየንበት የሚያዘው የቻይና ሕግ በናዝራዊት ላይ ተግባራዊ ይሆናል በሚል በቤተሰቦቿ፣ በቅርብ ዘመዶቿ እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ስጋትን ፈጥሯል። በመሆኑም ናዝራዊት ጥፋተኛ አለመሆኗን ለመግለፅ የፊርማ ማሰባሰብ ዘመቻ አሁንም እየተካሄደ ነው፤ ጉዳዩም የታዋቂ ሰዎችንና የባለሥልጣናትን ትኩረት መያዝ ችሏል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተሉት እንደሆነም ተገልጿል። • በቻይና የተደረሱት ስምምነቶች የትኞቹ ናቸው? የናዝራዊት ታላቅ እህት ቤተልሔም አበራ እንደሚሉት በወቅቱ ናዝራዊት ላይ የሞት ፍርዱ በአፋጣኝ ተወስኖ ወደ ተግባር ይገባል የሚል ስጋት ነበራቸው፤ ለቤተሰቡም ከባድ ሃዘን ያጠላ ጭንቀት ሰፍኖ ነበር። ታዲያ በዚህ ጊዜ ነበር የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ስልክ ያንቃጨለው። "ጠቅላይ ሚንስትሩ በእጃችን ስልክ ላይ ነበር የደወሉልን፤ መጀመሪያ ሞት እንደሌለ ነው ያረጋጉን ፤ በቅርቡም ወደ ቻይና እንደሚያቀኑና ከያዟቸው ጉዳዮች አንዱ በመሆኑ የሚኖረውን ሂደት እንደሚያሳውቁን በራሳቸው አንደበት ነግረው ነበር" ይላሉ አጋጣሚውን ሲያስታውሱ። ይህም በተወሰነ መልኩም ቢሆን ለቤተሰቡ እፎይታ እንደሰጣቸው የናዝራዊት ታላቅ እህት ቤተልሔም ይናገራሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የገቡላቸው ቃል ባይኖርም የኢትዮጵያ መንግሥት ጉዳዩን እንደሚከታተለውና ለቻይና መንግሥትም ጥያቄውን እንደሚያቀርብ ነግረውናል ይላሉ። ከቀናት በፊት ለሮድ ኤንድ ቤልት ኢንሼቲቭ ፎረም ወደ ቻይና ያቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በቻይና ቆይታቸው የናዝራዊት አበራ ጉዳይ አንዱ ጉዳያቸው እንደሆነ አስታውቀው ነበር። ጉባዔው ከተጠናቀቀ በኋላ የእርሳቸውን ወደ ኢትዮጵያ መመለስ ተከትሎ 'ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ናዝራዊትን አስፈትተዋት መጡ' የሚሉ መረጃዎች በተለያዩ ማህበራዊ ድረ ገፆች እየተናፈሱ ነው። • ተስፋዬ ገብረአብ ስለ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ምን ይላል? ይሁን እንጂ ያነጋገርናቸው የናዝራዊት ታላቅ እህት ቤተልሔም አበራ "ናዝራዊት አልተፈታችም፤ እስካሁን ቻይና በሚገኘው ጉዋንዡ በእስር ላይ ነው የምትገኘው፤ የሚናፈሰው ወሬም ሀሰት ነው" በማለት ሀሰተኛው መረጃው እየተካሄዱ ያሉትን ዘመቻዎች እንዳያስተጓጉል ስጋታቸውን ይገልፃሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ከቻይና ከተመለሱ በኋላ ባይደውሉላቸውም በጠቅላይ አቃቤ ሕግ በኩል ሥራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ማረጋገጥ እንደቻሉ ይናገራሉ። "ቻይና ከሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንፅላና ከተለያዩ አካላት ጋር ሆነን በቅርበት እየተከታተልን ነው" የሚሉት ቤተልሔም የኢትዮጵያ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ቢሮ ቻይና ከሚገኘው አቃቤ ሕግ ጋር የመረጃ ልውውጥ እያደረጉ መሆናቸውንም ለቢቢሲ ገልፀዋል። በዚህም መሰረት ፍርድ ቤት እስከምትቀርብ ድረስ ናዝራዊትን በአካል ማግኘት ባይቻልም በቆንጽላው በኩል መረጃዎች እንደሚለዋወጡ የሚናገሩት ቤተልሔም ሒደቱ ቀላል እንደማይሆን ቢገምቱም በተስፋ ተሞልተው የእርሷን መፈታት እየተጠባበቁ ነው። "ናዝራዊት በተፈጥሮዋ ጠንካራ ናት" የሚሉት እህቷ እስር ቤት ከባድ ቢሆንም አሁን ተረጋግታ ከሙያዋ ጋር ግንኙነት ያላቸውንና የቋንቋ መጻህፍትን እያነበበች እንደምትጠባበቅ ይገልፃሉ። ናዝራዊት የተለያዩ መጻህፍት እንዲገቡላት የጠየቀች ሲሆን እስር ቤት ያሉትን ቻይናውያን የእንግሊዝኛ ቋንቋ እያስተማረች ነው፤ የቻይና ቋንቋ ተምራ መውጣትም እንደምትፈልግ መልዕክት አስተላልፋላቸዋለች። ለአንዳንድ ወጪዎች የሚሆናት በወር 100 የአሜሪካ ዶላር (3000 ሺህ ብር ገደማ) በቆንጽላው በኩል እንደሚልኩላት ነግረውናል። በሌላ በኩል ለናዝራዊት ሻምፖ መሳዩን እፅ ሰጥታለች ተብላ የተጠረጠረችው ጓደኛዋ ስምረት ካህሳይ አዲስ አበባ በሚገኘው ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በቁጥጥር ሥር ውላ የነበረ ቢሆንም በማግስቱ በ20 ሺህ ብር ዋስትና እንደተለቀቀች ያስታውሳሉ። • «በስልክዎ ታካሚና አካሚ እናገናኛለን» ሥራ ፈጣሪው ወጣት ይሁን እንጂ አቤቱታቸውን በማቅረባቸው በድጋሚ በዚያው ፖሊስ ጣቢያ ከጓደኛዋ ጋር በቁጥጥር ሥራ ውላ ጉዳዩ በፍርድ ሂደት ላይ ይገኛል። በናዝራዊት ላይ የተፈጠረው ምን ነበር? ኢትዮጵያዊቷ ናዝራዊት አበራ በእፅ ዝውውር ባለፈው ታህሳስ 14 ቀን 2011 ዓ.ም በቻይና በቁጥጥር ሥር ውላ በእስር ላይ እንደምትገኝ ይታወሳል። የምህንድስና ሙያ ያላት ናዝራዊት ወደ ቻይና ስትሄድ ከጓደኛዋ የተሰጣት ሻምፖ መሳይ እቃ 1 ኪሎ ግራም ኮኬይን የተባለ እፅ መሆኑ የታወቀው ቻይና በደረሰችበት ጊዜ ነበር። • በዕጽ በማዘዋወር የተጠረጠረችው ናይጄሪያዊት ከሳኡዲ እስር ቤት ተለቀቀች "እንዴት እንደተያዘች አናውቅም፤ በጓደኛዋ ጋባዥነት አብረው እንደሚሄዱ እናውቃለን፤ ጓደኛዋ አባቴ ሞተ ብላ እርሷን ብቻዋን እንደላከቻት ነግራናለች" ይላሉ የናዝራዊት ታላቅ እህት የተያዘችበትን አጋጣሚ ሲያስታውሱ። ሐሙስ ቀን ወደ ቻይና ያቀናችው ናዝራዊትም ለሁለት ተከታታይ ቀናት ድምጿ ሲጠፋባቸው የአሁኗ ተጠርጣሪ ጓደኛዋን ይጠይቋታል። እርሷም ለጓደኛዋ እንድትሰጥላት የሰጠቻት ሻምፖ ምክንያት ሳይሆን እንደማይቀር እንደነገረቻቸው ያስረዳሉ። በወቅቱ የነበረው ሁኔታ ቤተሰቡን ያስደነገጠ ቢሆንም በተለይ ለእናታቸው የጤና እክል ምክንያት ሆኗል። እናቷ ናዝራዊት እስካሁን የትና በምን ሁኔታ እንዳለች አያውቁም። ባጋጠማቸው ስትሮክ ግማሽ ጎናቸው መንቀሳቀስ እንደማይችልም ሰምተናል። ዕለት በዕለትም ስለ እርሷ መጠየቃቸውን ቀጥለዋል።
news-41919875
https://www.bbc.com/amharic/news-41919875
የቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት ትውስታዎች በኢትዮጵያውያን ዓይን
ሶስትና አራት አስርት ዓመታትን ወደ ኋላ ብንሄድ የኢትዮጵያን የስነ-ፅሁፍ ስራዎች በሩሲያ ወይም በቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት ፀሀፊያን የትርጉም ስራዎች የተሞላ ነበር።
አያልነህ ሙላቱ ከቀድሞው መሪ መንግስቱ ኃይለማርያም በማስተርጎም ስራ ላይ ከነዚህም ውስጥ የፊዮዶር ዶስቶቭስኪ 'ክራይም ኤንድ ፐኒሽመንት' የሚለው ፅሁፍ ወንጀልና ቅጣት በሚል ርዕስ በሩሲያ አምባሳደር በነበሩት ካሳ ገብረ-ህይወት ተተርጉሟል። የዚሁ ደራሲ ስራ የሆነው 'ኖትስ ፍሮም አንደርግራውንድ' የስርቻው ስር መጣጥፍ በሚል የማክሲም ጎርኬይ እናት እንዲሁም የሊዮ ቶልስቶይ ስራዎች ተጠቃሽ ናቸው። በፅሁፋቸውም ስለ ሩሲያ አብዮት፤ ስለ ጭቆናና መደብ ትግል፤ ወይም ታዋቂ ስለሆነው ሬድ ስኩዌር (አደባባይ)ም ይሁን ስለ አጠቃላይ ባህሉ ጠቅሰዋል። በአድዋ ጦርነትም ይሁን ለሁለተኛ ጊዜ ጣልያን ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት ድጋፍ ወደሰጠቻት የቀድሞ ሶቭየት ህብረት ብዙ ተማሪዎች በ1960ዎቹና በ1970ዎቹ ሄደዋል። በተለይም ዓለም አቀፍ ሶሻሊዝም በተስፋፋበት ወቅት የሶቭየት ህብረትና የኢትዮጵያ ግንኙነት ጠንካራ ነበር። የሶሻሊዝምን ርዕዮተ-ዓለም የሚያንፀባርቁት የካርል ማርክስ፣ የቭላድሚር ሌኒን ሀውልቶች፤ የኮሚዩኒስት ማኒፌስቶ ትርጉም በከፍተኛ ሁኔታ የሚጠቀሱ ናቸው። በዚያን ወቅት የቀድሞ ሶቭየት ህብረት ሄደው ከተማሩት ውስጥ ታዋቂው ፀሐፊ-ተውኔት አያልነህ ሙላቱ ይገኙበታል። አያልነህ የትያትር ድርሰትን ለመማር ወደ ሞስኮ ያቀኑት በንጉሱ ዘመን በ1962 ዓ.ም ነበር። በወቅቱ በአሜሪካ የትምህርት ዕድል የነበረ ቢሆንም ከደራሲያን ማህበር መንግስቱ ለማ "ገንዘብን ለማካበት ከሆነ በካፒታሊዝም ወደ ምትመራዋ አሜሪካ ብሄድ ጥሩ እንደሆነ ነገር ግን ስነ-ፅሁፍን ለመማር ከሆነ ወደ ሶቭየት ህብረት ብሄድ ጥሩ እንደሆነ መከሩኝ" በማለት ይናገራሉ። ቦታው ላይ ሲደርሱ የአሌክሳንደር ፑሽኪን አያት ኢትዮጵያዊ/ኤርትራዊ ከመሆን ጋር ተያይዞ በክብር እንደተቀበሏቸው ያስታውሳሉ። ፀሀፊና ገጣሚ መሆናቸውም ከእሱ ጋር በከፍተኛ ሁኔታ በመያያዙ ሞስኮ በሚገኝ ሬድዮ በሳምንት ሁለት ጊዜ "የደራሲው ደብተር" በሚል ርዕስ በአማርኛ የሬድዮ ፕሮግራም ያቀርቡ ነበር። ፑሽኪን ስለ አያቱ "ዘ ኒግሮ ኦፍ ፒተር ዘ ግሬት" በሚለውም ፅሁፉ አስቀምጧል። በኢትዮጵያ የተማሪዎች እንቅስቃሴ በሶሻሊዝም፣ኮሚዪኒዝምና ማኦይዝም ርዕዮተ-ዓለም በተዋጠበት ወቅት የሶሻሊዝም ሀገራት የኑሮ ሁኔታ ምን እንደሆነ መሬት ላይ ያሳያቸው ሁኔታ እንደሆነ ይናገራሉ። "የሶቭየት ህብረት ሶሻሊዝም ሰዎችን የማያበላልጥ፤ የሰዎችንም ክብርም ከፍ የሚያደርግ ስርአት ነው" በማለት ይናገራሉ። በቦታው ሲደርሱ በጣም ያስደነቃቸውም የማህበራዊ አኗኗራቸው ነው። እንደ ኢትዮጵያ አይነት ከፍተኛ የማህበራዊ ኑሮ ትስስር ካለበት ቦታ ቢመጡም የሩሲያ ከማስደነቅም በላይ ነበር የሆነባቸው። "የግል ንብረት የሚባል የለም" የሚሉት አያልነህ በመጀመሪያ በመጡበትም ወቅት ሸሚዛቸውን ያለሳቸው ፈቃድ ለብሶ ያገኙትን ተማሪ ተናደው ሊጣሉት ባሉት ወቅት "ለምን እንደተናደድኩ አልገባውም፤ የኔ ልብስ እኮ ስላልታጠበ ነው፤ ሲታጠብ ትለብሳለህ" ብሏቸዋል። የካፒታሊዝም ዋና ፅንሰ-ሀሳብ የሆነውን "የሀብት ክምችትን" በመቃወም "ለነገ የሚያስቀሩት ነገር የለም" ይላሉ። ማንኛውም የሰው ልጅ መሰረታዊው ነገር ሊሸፈን ይገባል በሚለው መርሀቸው መሰረት ምግብ ርካሽ ከመሆኑ በተጨማሪ ህክምናና ትምህርት በነፃ እንደነበር ይናገራሉ። ኑሮ በሞስኮ ቀላል አልነበረም ምክንያቱም እንደ አቶ አያልነህ ሀይማኖት አጥባቂና ከፊውዳሊዝም ስርዓት የመጣ ሰው መደብ የሌለበትና እምነት እንደ ማርክስ አባባል ኦፒየም (ማደንዘዣ) የሚታይበት ሁኔታ ቀላል አልነበረም። በወቅቱም የሩሲያ አብዮት አመላካች የሆነችውን የቀይ ኮከብ አርማን "ኮከቧ ወደ እግዚአብሄር እያመላከተች ነው" በማለታቸው ብዙዎችን እንዳስደነገጠም አይዘነጉትም። ምንም ባይደርስባቸውም እምነትን እንዲህ ባደባባይ ላይ መናገር ፍፁም ክልክል እንደነበር ይናገራሉ። በወቅቱም ብዙ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ስለነበሩ ማህበር የነበራቸው ሲሆን የአውሮፓ ተማሪዎች ማህበር አባል ነበሩ። "የሶሻሊዝሙ ዕምብርት ላይ ስለነበርን ማዕከልም ነበርን" ይላሉ። ሞስኮ ውስጥ እንጀራም ይሁን የኢትዮጵያ ሬስቶራንት ባይኖርም አብዛኛውን ጊዜ ከማርክስ ሀውልት አጠገብ ያለው ሬድ ስኩዌር የተባለ አደባባይ እንዲሁም ፑሽኪን አደባባይ እንደሚሄዱም ይናገራሉ። ስለ ደግነታቸው አውርተው የማይጠግቡት አያልነህ ልጃቸው ሩሲያ ከተወለደ በኋላ ይንከባከቡላቸው የነበሩት "ባቡሽካ" (የሩሲያ አያቶችንም) በእጅጉ ያስታውሳሉ። አሁንም የእርጅና ጊዜያቸውን እዛው ቢያሳልፉ ደስ እንደሚላቸው ይገልፃሉ። ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን ከአቶ አያልነህ በ20 ዓመታት ልዩነት የሄዱት የስነ-ጥበብ መምህርና ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን ልምድ ከዚህ በተቃራኒው ነው። የሶቭየት ህብረት መፈራረስ ዋዜማ ላይ የሄዱት በቀለ መኮንን ታላቅ እየተባለ ሲሞካሽ የነበረው ሶሻሊዝም በከፍተኛ ደረጃ በሚተችበት፤ "የግራ ፖለቲካ ጣኦቶቻቸውን መደርመስ የጀመረበት ጊዜ ነበር" በማለትም ይገልፃሉ። ራሱን ሶሻሊስት ብሎ የሚጠራው የደርግ መንግስት "ብዙ ሰዎችን በማፈስ፣ በማሰር፣ በማንገላታት ላይ ስለነበር ወደ ሩሲያ መሄዱም አማራጭ ከማጣት ጋር ወይም ሽሽት ነው" ይላሉ። መጀመሪያ ሞስኮ የገቡበትን ቀን የማይረሱት በቀለ "አጥንት ድረስ የሚሰማው ብርድ ሲሰማኝ፤ ብረት የማሸት ነው የመሰለኝ" ይላሉ። በጊዜው ሶሻሊስት ተብላ ብዙ ጥፋት ካለባት አገር ወደ ሌላ ሶሻሊስት ሀገር መሄድ የነበረውን ስሜት ሲገልፁ "ሁሉን ነገር በጥርጣሬና በጥላቻ ነበር የምመለከተው፤ ሩስኪ በምማርበት ወቅት እንኳን የነበረኝን የእንግለዚዝኛ ቋንቋ ለማስጠፋትና ለማደናበር ይመስለኝ ነበር" ይላሉ። "ህዝቡ በፍርሀት ከተሸበበት እየወጣ በነበረበት ሁኔታ ላይ ነው የደረስኩት" የሚሉት በቀለ ሶሻሊዝም የተተረጎመበት መንገድም ትክክል ነው ብለው እንደማያስቡም ይናገራሉ። "ቤተ-ክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች ነፃ ህክምናም ሆነ ነፃ ትምህርት አያገኙም፤ ስለዚህ ሰዎች ተደብቀው ይሄዱ ነበር" ይላሉ። መሰረታዊ ነገሮች የተሟሉበት ሁኔታ እንዲሁም ምግብ እንደ ሰብዓዊ መብት ታይቶ የሚራብ ሰው ባይኖርም ስርዓቱን መቃወም አይቻልም ነበር በማለት በቀለ ያወሳሉ። "የተቃወሙ ብዙዎች ወደ ሳይቤሪያ ይጋዛሉ፤ ነፃነት አልነበረም" ይላሉ። የነበረውን ስርኣት ከጆርጅ ኦርዌል "አኒማል ፋርም" ከተሰኘ ድርሰት ጋር የሚያመሳስሉት በቀለ በወቅቱ ይሰበክ የነበረውን የመደብ እኩልነትም ጥያቄ ውስጥ ይከቱታል። "ባቡር ውስጥ ስንገባ ሰዎች ይገላመጣሉ፤ ስታሊን በዘረጋው የጠበቀ ስለላ መሰረት ሚስቶች ባሎቻቸውን የሚሰልሉበት መረብም ነበር። ብዙዎችም ወደ ሳይቤሪያም ተግዘዋል" ይላሉ። የጅምላ አስተሳሰብ የሰፈነበት ስርዓት ነው ቢሉም የሥነ-ፅሁፍ ባህላቸው በጣም የመጠቀና የማንበብ ባህላቸው አስደናቂ እንደነበር ግን ሳያወሱ አያልፉም። የሩስያ የአብዮት ፖስተሮች የቦሪስ የልሰንን መሪነትን ተከትሎ የሶሻሊዘም ዓለም አቀፍነት ተደምስሶ በጥቁር ህዝብ ላይ ያለው ዘረኝነት ጎልቶ ቢወጣም በዛን ጊዜ ግን በአደባባይ ዘረኝነት እንዳልነበር ይናገራሉ። "ጥቁር ሰው አይተው የማያውቁ ወይም አንዳንዶች በግዴለሽነት ቢያደርጉትም ብዙዎች ከሩሲያ ወዳጅ ስለመጣን ማስቀየም ይፈሩ ነበር" ይላሉ። ምንም እንኳን በ6 አመት ቆይታቸው ሞስኮን ብዙ ባይወዱዋትም የሌኒን ግራድ፤ ዊንተር ፓላስ የመሳሰሉ አካባቢዎች ትዝታ አሁንም እንዳለ ነው።
53981838
https://www.bbc.com/amharic/53981838
ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ፡ በርካቶች ስብሰባ የሚያካሂዱበት ዙም ሚሊዮን ዶላሮች አተረፈ
በኮሮናቫይረስ ምክንያት በርካቶች ስብሰባ የሚያካሂዱበት ዙም በከፍተኛ ሁኔታ ትርፉ ጨመረ።
ድርጅቱ በሦስት ወራት 355 በመቶ ማለትም 663.5 ሚሊዮን ዶላር አትርፏል። ይህም ከተጠበቀው በላይ ነው። የዙም ተጠቃሚዎች ቁጥር ከአምና ጋር ሲነጻጸር ወደ 458 በመቶ አድጓል። የድርጅቱ ሼር ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ጨምሮ 325.10 ዶላር ሆኗል። ዓመታዊ ገቢው ከ2.37 ቢሊዮን ዶላር እስከ 2.39 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል። ይህም ከተጠበቀው 30 በመቶ እጥፍ ነው። ዙም ትርፋማነቱ እየጨመረ የመጣው በነፃ መተግበሪያውን ከሚጠቀሙ ሰዎች በተጨማሪ ገንዘብ የሚከፍሉ ትልልቅ ተቋሞችም ደንበኞቹ ስለሆኑ ነው። ከ100 ሺህ ዶላር በላይ የሚያስገቡለት ተቋሞች ባለፉት ስድስት ወራት በእጥፍ አድገው 988 እንደደረሱ ድርጅቱ አስታውቋል። በበይነ መረብ ስብሰባ ማካሄድ ከሚቻልባቸው መተግበሪያዎች መካከል ሲስኮ ዌቤክስ እና ማይክሮሶፍት ቲምስ ይጠቀሳሉ። የኮሮናቫይረስ ስርጭት መባባሱን ተከትሎ ትርፋቸው እየናረ ይገኛል። ሆኖም ግን እንደ ዙም የተዋጣለት፣ ትርፉ የጨመረ፣ ዝነኛ የሆነም የለም። በሌላ በኩል መረጃ ሰርሳሪዎችም መተግበሪያውን ኢላማ አድርገዋል። ዙም የተጠቃሚዎችን መረጃ በሚስጥር እይዛለሁ ቢልም የግለሰቦችን መረጃ ለፌስቡክ እንደሚያስተላልፍ መረጃ ሰርሳሪዎች አጋልጠዋል። ዙም፤ ስብሰባ የሚጠሩ ተቋሞች ወይም ሰዎች ተሰብሳቢዎችን እንዲከታተሉ እንደሚፈቅድም ተገልጿል። ተቋሙ ከቻይና ጋር ባለው ቅርብ ትስስር ይተቻል። ወደ 700 ያህል ሠራተኞቹ ያሉት ቻይና ሲሆን፤ የአገሪቱ መንግሥት ሊጠቀምበት እንደሚችልም ስጋት አለ።
55837366
https://www.bbc.com/amharic/55837366
ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር የሚያወዛግባትን መሬት እንደማትለቅ አስታወቀች
ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ያለውንና በቅርቡ መልሳ የወሰደችውን መሬት እንደማትለቅ አስታወቀች።
የሱዳኑ ሱና ከፍተኛ የመከላከያ ኃላፊን ጠቅሶ፤ ሱዳን በምዕራባዊ ድንበሯ ላይ የሚገኘውንና ከኢትዮጵያ ጋር ያወዛግባት የነበረውን መሬት እንደማትመልስ ዘግቧል። "ሱዳን ከአልፋሻጋ ይዞታ ቅንጣት ታህል እንደማትሰጥ ሜጀር ጀነራል ሀይደር አልቲራፊ አረጋግጠዋል። ለወታደራዊ ኃይል ምልመላ እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል" ይላል የመንግሥታዊው ሱና ዘገባ። ኢትዮጵያ በበኩሏ አለመግባባቱን በድርድር ለመፍታት ሱዳን የያዘችውን መሬት እንድትለቅ እንደ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጣለች። የሱዳኑ ጄነራል ግን አልገዳሪፍ ውስጥ ፋላታ ከተባለው ጎሳ ድጋፍ በተቀበሉበት ወቅት ባደረጉት ንግግር "ሁሉም ዜጎች ልጆቻቸው ወታደራዊ ኃይሉን ተቀላቅለው የአገራቸውን ዳር ድንበርና ክብር እንዲያስጠብቁ እንዲያነሳሱ እጠይቃለሁ" ብለዋል። የሱዳን ወታደራዊ ኃይል ድንበር ላይ ያለውን ቀጠና ለማሳደግ የመንገድና የድልድይ ግንባታ ላይ እንደተሰማራ ተናግረዋል። "በቀጠናው የአገልግሎት ዘርፍ በመገንባት እንቅስቃሴን ምቹ ለማድረግም እየሠሩ ነው" ሲሉ አክለዋል። የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ፤ ከቀናት በፊት በሰጡት መግለጫ ሱዳን ወደቀደመ ይዞታዋ ካልተመለሰች ለድርድር መቀመጥ እንደማይቻል ተናግረዋል። ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር አልፋ እንድትጠብቅም ሆነ መሬት እንድትይዝ የተደረሰ ስምምነት እንደሌለም ቃል አቀባዩ አምባሳደር ዲና መናገራቸው ይታወሳል። ሱዳን የያዘችውን መሬት እንድትለቅ ኢትዮጵያ በቅድመ ሁኔታ ማስቀመጧንና ይህ ከተሳካ ሁለቱ አገራት በዋናነትም ችግራቸውን ተነጋግረው መፍታት እንደሚችሉም አስረድተዋል። ሱዳን እና ኢትዮጵያን የሚያወዛግበው አልፋሽጋ የግብርና ሥራ እየተከናወነበት የሚገኝ ሲሆን፤ ባሳለፍነው ጥቅምት ሱዳን አካባቢውን ሙሉ በሙሉ እንደምትቆጣጠር አስታውቃለች። ይህም ከኢትዮጵያ ጋር የሚያወዛግባትንና በኢትዮጵያ ሚሊሻ ተይዞ የነበረውን የድንበር አካባባቢ ይጠቀልላል።
41823285
https://www.bbc.com/amharic/41823285
''የራሴን ሳይሆን የመንግሥትን አቋም ነው የማንፀባርቀው'' ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ
በየትኛውም አጋጣሚ የሚሰጡት መግለጫና አስተያየት የግላቸው ሳይሆን የወከሉት መንግሥትን አቋምን የሚያንፀባርቅ እንደሆነ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ ገለጹ።
በተለያዩ ስፍራዎች ያጋጠሙ ግጭቶችን ተከትሎ የመገናኛ ብዙሃን ያቀረቧቸው ዘገባዎች መረጋጋት የሚያመጡ አልነበሩም፤ ስለዚህም መንግሥት አስፈላጊው ማጣራት ካደረገ በኋላ እርምጃ ይወስዳል ሲሉ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ ሚኒስትር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ለንደን በሚገኘው የቢቢሲ ዋና መሥሪያ ቤት ተገኝተው በሰጡት ቃለ-ምልልስ ገልዋል። ''ስለሆነም የሕዝብም ይሁን የግል መገናኛ ብዙሃን ተጠያቂ የሚያደርጋቸው ጥፋት ውስጥ ገብተው ከተገኙ መጠየቃቸው አይቀርም'' ብለዋል ሚኒስትሩ። ከተከሰቱት ግጭቶች አንፃር የመገናኛ ብዙሃን የሃገሪቱን ሰላምና የሕዝቡን አብሮ የመኖር ልምድ የሚንድ ደርጊት ውስጥ መሳተፍ የለባቸውም ያሉት ዶ/ር ነገሪ፤ ሕዝብን የሚያጋጭ ሥራ የሚሰሩ የመንግሥትም ሆነ የግል የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ሕግን እየጣሱ መሆኑ መታወቅ አለበት ብለዋል። ይህም የግል አስተያየታቸው እንደሆነ የተጠየቁት ዶክተር ነገሪ ''በአሁኑ ጊዜ በየትኛውም ሁኔታ መንግሥትን ወክዬ ነው የምናገረው፤ የመንግሥት ሃላፊነትን ከተረከብኩ ጊዜ ጀምሮ የማንፀባርቀው የመንግሥትን አቋም ነው'' ብለዋል። ሚኒስትሩ እንዳሉት ''ጋዜጠኞችን የምንጠራው የግል አስተያየታችንን ልንሰጥ አይደለም። ጉዳዩም የህዝብ ጉዳይ ነው። አንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን ህዝብን ከህዝብ ሊያጋጭ ሚችል ዘገባዎችን ሲያስተላልፉ ነበር። የግል አስተያየቱን ነው የሰጠው ብለው የሚያምኑ የራሳቸው ስህተት ለመሸፈን ወይም ከተጠያቂነት ለመሸሸ ያደረጉት ከሆነ ወደፊት አጣርተን የምንደርስበት ጉዳይ ነው የሚሆነው'' ብለዋል። በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ውስጥ ተደጋጋሚ ግጭቶች ቢስተዋሉም መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲያወጣ የሚያስገድድ ሁኔታ እንደሌለ የተናገሩት ዶክተር ነገሪ፤ "መንግሥት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሃገሪቱን የመምራት ፍላጎት የለውም። በአሁኑ ጊዜ አስቸኳይ ጊዜ እንዲታወጅ የሚያደርግ ችግር የለም" ብለዋል። በሃገሪቱ እየታዩ ያሉ ግጭቶቹና አለመረጋጋቶች ከመደበኛው የፀጥታ ኃይል ቁጥጥር ውጪ አይደለም ያሉት ሚኒስትሩ፤ ክልሎች በራሳቸው ሊወጡት የሚችሉትና ካስፈለገም ከፌደራል መንግሥቱ ጋር በጋራ የሚቆጣጠሩት ጉዳይ ነው ብለዋል። ስለዚህም አሁን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚያስፈልግበት ጊዜ አይደለም ሲሉ አስረግጠዋል። ከተቃውሞዎችና ከግጭቶች ጀርባ ኪራይ ሰብሳቢዎችና በኮንትሮባንድ ንግድ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች ናቸው ተብለው የተጠቀሱት እነማን እንደሆኑ የተጠየቁት ዶክተር ነገሪ፤ ማንነታቸውን ለመለየትና ወደ ህግ ለማቅረብ ክልሎችና የፌደራል መንግሥቱ በጋራ እየሰሩ ነው፤ ማንነታቸውም በሂደት የሚገለፅ ይሆናል ብለዋል። መንግሥት በውጪ ካሉ ተቃዋሚዎች ጋር እየተደራደረ ነው ስለሚባለው በሰጡት ምላሽ ''እየተደረገ ያለ ምንም ዓይነት ድርድር የለም'' በማለት ነገር ግን የመንግሥት በር ለድርድር ዝግ እንዳልሆነ ተናግረዋል።
news-44302816
https://www.bbc.com/amharic/news-44302816
ካለሁበት 34፡ በአሜሪካ የህግ አስከባሪዎች ከማንም ሰው በበለጠ ህግን ይጠብቃሉ፤ ያከብራሉ።
ገመቹ አቡጋሬ በዱኬ እባላለው። በምዕራብ ሸዋ ዞን አዳሚ ቱሉ ወረዳ፤ ጊዶ ኮምቦልቻ ባቱ አካባቢ ነው ተወልጄ ያደግኩት። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን እዛው ነው ተከታተልኩት።
የከፍተኛ ትምህርቴን ለመከታተል ደግሞ ወደ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሄድኩ። የመጀመሪያ ዲግሪዬን እዛው አገኘሁ። ትምህርቴን ጨርሼ ከተመረቅኩኝ በኋላ በተለያዩ የመንግሥት እና የግል ድርጅቶች ውስጥ በሂሳብ ሰራተኝንት ስሰራ ቆየሁ። ከዚም ዲቪ ደርሶኝ ወደ አሜሪካ መጣሁ። አሁን የምኖረው በሳውዝ ዳኮታ ግዛት ሲ ፎልስ በምትባል ከተማ ነው። ይቺ ከተማ በጣም የተዋበች እና ዘመናዊ ናት። ከፍ ካለ ስፍራ የሚፈሰውና ከተማዋን አቋርጦ የሚሄደው ወንዝ ደግሞ ልዩ ውበት ሰጥቷታል። ሃገሬን እና አሜሪካን ማወዳደር ይከብደኛል። አሜሪካ በቴክኖሎጂ የመጠቀች ናት፤ ኢትዮጵያ ግን ገና በማደግ ላይ ያለች ሃገር ነች። እዚህ አገር ሁሉም ነገር በተግባር ነው የሚገለጸው። ህጎች እንኳን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ይደረጋሉ። ኢትዮጵያን ከአሜሪካ የሚለያት ዋናው ነገር ብዬ የማስበው የህግ አተገባበር ሥርዓቱ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ትልልቅ ህጎች አሉ፤ ነገር ግን ልዩነቱ ወደ ተግባር መቀየሩ ላይ ነው። እዚህ አገር ህጎች ተግባራዊ የሚደረጉት በሰዎች ብቻ ሳይሆን በቴክኖሎጂም ጭምር ታግዘው ነው። የተለያዩ ካሜራዎች እና የቴክኖሎጂ ውጤቶች ህግን ለማስከበር ጥቅም ላይ ይውላሉ። ህግ አስከባሪዎቹም ቢሆኑ ለህጉ ተገዢዎች ናቸው። የእኛን ሃገር ስንመለከት ግን ከታች ካለው የህግ አስከባሪ ጀምሮ እስከ ትልቅ ባለስልጣን ድረስ ሁሉም ከህግ በላይ እንደሆኑ ነው የሚያስቡት። እዚህ አገር ግን ከኢትዮጵያ ተቃራኒ ነው። ህግ አስከባሪዎቹ በግንባር ቀደምነት ለህግ ተገዢ ናቸው። ይሄ ለኔ በጣም ልዩ ነው። ወደ አሜሪካ በመምጣቴ አተረፍኩ ብዬ የማስበው ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ብቻ አይደለም፤ ተግባራዊ እና መፍትሄ ላይ ያተከረ የትምህርት ማግኘቴም ጭምር ነው። የተለየ ስልጣን ወይም ችሎታ ቢኖረኝ በምኖርባት ከተማ ያለውን ከፍተኛ የጤና አገልግሎት እና ለትምህርት የሚደረግ ክፍያ መለወጥ እፈልጋለው። ምክንያቱም ለትምህርት እና ለጤና አገልግሎት የሚከፈለው ክፍያ በጣም የተጋነነ ነው። እኔ የምኖርበት አካባቢ ብዙ የምግብ አይነቶች አሉ፤ እንደ እንጀራ ግን የሚያስደስተኝ የለም። እዚህ ካሉት ምግቦች የምመርጠው ግን ፒዛ ነው። ከሃገሬ ደግሞ ከሚናፍቁኝ ነገሮች መካከል የሰዉ የእርስ በርስ መከባበር እና ባህል አክባሪነት ሁሌም ከልቤ አይጠፉም። የምኖርባት ከተማ ብዙ ተፈጥሮአዊ መስህቦች አሏት፤ ለኔ የተለየ ስሜት የሚሰጠኝና የምወደው በከተማዋ መሃል የሚፈሰው ሲ ፎልስ ወንዝ ነው። ከተማዋ ስሟን ያገነችውም ከዚሁ ወንዝ ነው። አካባቢው ለአይን ስለሚማርክ ብዙ ሰዎች መጥተው ይጎበኙታል። ሁሌም ቢሆን እዚህ ያለውን የተራቀቀ ቴክኖሎጂ እና የተቀናጀ ሥርዓት ስመለከት ሃገሬ ትዝ ትለኛለች። ምናለ ኢትዮጵያም እንደዚህ ብትሆን እላለሁ። እዚህ ሃገር ለመጀመሪያ ጊዜ እንደመጣሁ ያስደነገጠኝ ነገር የሃገሬ ልጆች በተለያዩ ሱሶች እና አደንዛዥ እጾች ተጠምደው ስመለከት ነበር። ያንን ሁሉ ችግር አልፎ እዚህ ደርሶ፤ የመጣበትን ምክንያት ረስቶ ሰው እንዴት ሱስ ውስጥ ይገባል ብዬ በጣም አዘንኩ። እራስን ለማሻሻል ዋናው ነገር የግል ጥረት እና ውሳኔ እንጂ ከሃገር መውጣቱ ብቻ እንዳልሆነ አስተምሮኛል። በሆነ ተአምር አንድ ኃይል ሃገሬ ቢወስደኝ በታላቁ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ በሻሸመኔ መንገድ ላይ የምትገኘው የትውልድ ቦታዬ ብሄድ ደስ ይለኛል። ይህች ከተማ በትንንሽ ሃይቆች የተከበበች በመሆኗ ለኑሮ ምቹ እና ተስማሚ መልከዓ-ምድር አላት። የ'ካለሁበት' ቀጣይ ክፍል ለማግኘት ፦ ካለሁበት 35፡ አቧራ እንደ ዝናብ ሲዘንብ አይቼ ስለማላውቅ ሁሌም ያስገርመኛል
49983007
https://www.bbc.com/amharic/49983007
"ሙሰኛ አይደለሁም" የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ ልጅ
የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ ልጅ "ሙሰኛ አይደለሁም" እያለ ነው።
ዱዱዜን ዙማ ይህንን ያለው በአባቱና በሱ ጉዳይ ላይ የተወነጀሉበትን የሙስና ሂደቶችን እያጣራ ላለው ኮሚቴ ነው። እንደ አባቱ ዙማ ዱዱዜንም የቀረበበትን የሙስና ጉዳዮች ውንጀላ ናቸው በማለት አጣጣጥሏል። •የጨለቆት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የተዘረፈው ዘውድ ይመለስልኝ እያለች ነው •"መንግሥት የዋጋ ንረቱን ለመቆጣጠር መሰረታዊ የምግብ ሸቀጦችን ያስገባል"ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ "እንደ ወንጀለኛ ነው እየታየሁ ያለሁት፤ የሙስና መመሰያ ሆኛለሁ። የሃገሪቷን ትሪሊዮን አንጡራ ሃብት እንደመዘበርኩ ተደርጎ ነው እየቀረበ ያለው፤ ይህ ግን ከእውነታ የራቀ ነው" ብሏል። አክሎም " ለህዝቡ ማለት የምፈልገው እኔ ሙሰኛ አይደለሁም። ከማንም ገንዘብ ወስጄ አላውቅም የመውሰድም እቅዱ የለኝም" ብሏል። በአባቱ የፖለቲካ ፍትጊያዎችም ተጠቂ እንደሆነ ገልጿል። •እየበረታ በመሄድ ላይ ያለው የዋጋ ንረት አዙሪት "ከዚህ ቀደምም ብየዋለሁ፤ አሁንም ደግሜ እናገረዋለሁ። በሚያሳዝን ሁኔታ በፖለቲካው ማዕበል ውስጥ ተይዣለሁ" ብሏል። የሙስና ጉዳዩን እየመሩ ያሉት ዳኛ ሬይመንድ ዞንዶ በበኩላቸው የሚፈለገው እውነቱን ብቻ ነው ብለዋል። "ሁሉንም ጉዳዮች እያየናቸው ነው፤ እያጣራንም ነው። በመረጃ ተመስርተን ነው የምንሄደው፤ የምንፈልገው እውነቱን ነው፤ ፤ሌላ የተደበቀ አላማ የለንም" ብለዋል። አጣሪ ቡድኑ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ፈፀሟቸው የተባሉ የሙስና ተግባራትን በመመርመር ላይ ነው። ውንጀላዎቹ ጃኮብ ዙማ በስልጣን በነበሩበት ወቅት ከጉፕታ ቤተሰብ ጉቦ በመቀበል የመንግሥት ካቢኔዎች ላይ ተፅእኖ በመፍጠርና የመንግሥት ጨረታዎችን ያለአግባብ ሰጥተዋል የሚለው አንዱ ነው። የቀድሞው ፕሬዚዳንትም ይሁን የጉፕታ ቤተሰብ በጭራሽ በማለት ክደዋል።
news-52526791
https://www.bbc.com/amharic/news-52526791
ፖሊስ በመምሰል በፈረንሳይ ሰዎችን ሲያጭበረብሩ የነበሩ የተባሉ ኢራናውያን በቁጥጥር ሥር ዋሉ
ፖሊስ በመምሰል በፈረንሳይ ሰዎችን ሲያጭበረብሩ የነበሩ የተባሉ ኢራናውያን በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተነገረ።
አንዲት ሴት እና ሦስት ወንዶች ፖሊስ በመምሰል የእንቅስቃሴ ገደብ በተጣለበት ወቅት ሰዎች ከቤታቸው ለመውጣት ምክንያታቸው የተዘረዘረበትን ወረቀት እንዲያሳዩ ሲጠየቁ ነበር። አራቱ አጭበርባሪዎች እስከ 25 ሺህ ዩሮ (27 ሺህ ዶላር) ሳያጭበረብሩ አይቀርም ተብሏል። ላለፉት 7 ሳምንታት ፈረንሳይዊያን ከቤት መውጣት የሚችሉት ወደ ሥራ ለመሄድ፣ ምግብ ለመሸመት፣ አካላዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ፣ የህክምና እርዳታ ለማግኘት ወይም አስቸኳይ የቤተሰብ ጉዳይ ሲያጋጥማቸው ብቻ ነው። ከቤት ውጪ በሚገኙበት ወቅት ዜጎች ከቤት የወጡበትን ምክንያት የሚያትት ወረቀት መያዝ ይኖርባቸዋል። ፖሊስ እንዳለው እነዚህ አራት አጭበርባሪዎች የፖሊስ ዩኒፎርም እና የአፍ እና የአፍንጫ ጭምብል አጥልቀው ሰዎችን በሁኔታቸው እየለዩ ያስቆማሉ። ከዚያም ከቤት የወጡበትን ምክንያት የሚያስረዳ ወረቀት እየጠየቁ የሰዎችን ኪስ እና ቦርሳ በመበርበር ያገኙትን ጥሬ ገንዘብም ይሁን ወድ ንብረት ሲዘርፉ ቆይተዋል። ፖሊስ ኮሚሽነሩ ናታን ባዎር እንዳሉት አራቱ ኢራናውያን "ጥሩ ፈረንሳይኛ ተናጋሪዎች አይደሉም" ትኩረት ሲያደርጉ የነበሩትም ስደተኞች ላይ ነው። ኮሚሽነሩ ጨምረው እንዳሉት በአጭበርባሪዎች ከተታለሉ ሰዎች መካከል 7 ሰዎችን ለይተዋል። ከእነዚህም መካከል ከአንዱ 12 ሺህ ዩሮ ተዘርፏል።
news-53595984
https://www.bbc.com/amharic/news-53595984
ኬንያ በሊባኖስ በቆንስላዋ በደል ስለሚፈጸምባቸው ዜጎቿ ምርመራ ልታደርግ ነው
ኬንያ በሊባኖስ በሚገኙ ዜጎቿ ላይ የደረሰውን ማንገላታት የሚያጣራ ቡድን ወደ መካከለኛው ምሥራቋ አገር ልትልክ ነው።
ኬንያውያን በቤይሩት ቆንስላ ውስጥ መንገላታት እንደደረሰባቸው የሚያሳይ ዘገባ የቀረበው በሲኤንኤን ነው። የሴኤንኤን የምርመራ ዘገባ በሊባኖስ በቤት ሠራተኝነት የሚሰሩ ኬንያውያን በአገራቸው ቆንስላ ባለስልጣን እና ረዳቱ የሚደርስባቸውን ብዝበዛ ወይንም ጥቃት ይዞ ቀርቧል። በዚህ የሲኤንኤን ዘገባ ላይ በርካቶች የተጠየቁ ሲሆን እንደሚመቱ፣ እንደሚሰደቡና እንደሚዘለፉ፤ ለቆንስላው አገልግሎት ከተገቢው በላይ ክፍያ እንደሚጠየቁ እንዲሁም ወደ አገራቸው ለመመለሻ የሚሆን ገንዘብ እንዲያገኙ በወሲብ ንግድ ላይ እንዲሰማሩ እንደሚመክሯቸው ጠቅሰው አስረድተዋል። የጉዳዮን እውነትነት አንድ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅትም እማኝነቱን በመስጠት አረጋግጧል። ነገር ግን የቆንስላው ባለስልጣናት ሁለቱም ሊባኖሳዊያን ሲሆኑ፤ የቀረበባቸውን ክስ አስተባብለዋል። የኬንያ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ከሆነ በኩዌት የሚገኘው የኬንያ ኤምባሲ፣ በሊባኖስ የሚገኘውን ቆንስላ በኃላፊነት የሚመራ በመሆኑ ወደ ቤሩት በመጓዝ ጉዳዩን ያጣራል ብለዋል። በኩዌት የኬንያ አምባሳደር ሃሊማ ሞሐመድ ለዴይሊ ኔሽን "በአሁኑ ሰዓት በረራ ዝግ በመሆኑ በሚቀጥለው ሳምንት ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ሊባኖስ ለመጓዝ አቅደናል" ብለዋል። በቅርቡ በሌባኖስ ውሰጥ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በመባባሱ እና በምጣኔ ሃብቱ ድቀት የተነሳ ከ100 በላይ ኢትዮጵያውያን በቆንስላቸው በር ላይ አሰሪዎቻቸው ጥለዋቸው መሄዳቸው ይታወሳል።
news-42276294
https://www.bbc.com/amharic/news-42276294
አሜሪካ ከፍልስጤም ጋር ልታካሂድ አስባ የነበረውን ውይይት አቋርጣለሁ ስትል አስጠነቀቀች
ምክትል ፕሬዚደንት ማይክ ፔንስ ከፍልስጤሙ መሪ መሐሙድ አባስ ጋር ሊያደርጉት ያሰቡትን የሰላም ድርድር ልትሰርዝ እንደምትችል አሜሪካ አስጠነቀቀች።
አንድ የፍልስጤም ከፍተኛ ባለሥልጣን ማይክ ፔንስ በፍልስጤም ተቀባይነት የላቸውም ማለታቸውን ተከትሎ ነው ማስጠንቀቂያው የመጣው። ትራምፕ አሜሪካ ለዘመናት ስትከተል የነበረውን ፖሊሲ በመሻር እየሩሳሌም የእስራኤል ዋና መዲና ናት በማለት እውቅና መስጠታቸው ይታወሳል። ከእወጃው በኋላ ጋዛ ሰርጥ እና ዌስት ባንክ አካባቢ በተነሳ ግጭት ቢያንስ 31 ፍልስጤማውያን መቁሰላቸውም ታውቋል። የተቃውሞ ሰልፉ እንደሚቀጥልም ነው እየተነገረ ያለው። የፍልስጤሙ እስላማዊ ቡድን 'ሃማስ' ከትራምፕ እወጃ በኋላ እንደ አዲስ አመፅ እንዲነሳ ቅስቀሳ ማካሄዱን ተያይዞታል። እስራኤል በበኩሏ በመቶ የሚቆጠሩ ወታደሮቿን ወደ ዌስት ባንክ አሰማርታለች። በርካታ የአሜሪካ አጋር ሃገራት የትራምፕን ውሳኔ የተቃወሙት ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምከር ቤት እንዲሁም የአረብ ሊግ በውሳኔው ላይ መክረው አቋማቸውን በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። ምክትል ፕሬዚደንት ማይክ ፔንስ ወደ ፍልስጤም በማቅናት ከአባስ ጋር በቀጣናው ሰላም በማስፈን ዙሪያ እንደሚመክሩና እስራኤልና ግብፅንም እንደሚጎበኙ ተነግሮ ነበር። ነገር ግን ጂብሪል ራጆብ የተባሉ የፋታህ ፓርቲ ነባር አባል "ፔንስን ለመቀበል በራችን ክፍት አይደለም" ሲሉ ተደምጠዋል። ሙሐሙድ አባስ በጉዳዩ ዙሪያ እስካሁን ምንም ያሉት ነገር የለም። እየሩሳሌም በክርስትና፣ እስልምና እንዲሁም አይሁድ እምነቶች ትልቅ ሥፍራ የሚሰጣት ቦታ ስትሆን፤ እስራኤል ከስድስት ቀናቱ ጦርነት በኋላ ከተማዋ የእኔ ናት ብትልም ዓለም አቀፍ እውቅና ሳታገኝ ቀርታለች። በእስራኤል ኤምባሲ ያላቸው ሁሉም ሃገራትም መቀመጫቸውን ቴል አቪቭ ማድረግ መርጠዋል። አሜሪካ እየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ ናት ስትል ያወጀች የመጀመሪያዋ ሃገር ሆናለች።
52320884
https://www.bbc.com/amharic/52320884
አፍሪካ ቀጣይዋ የኮቪድ-19 ወረርሽኘ ማዕከል ልትሆን ትችላለች-የዓለም ጤና ድርጀት
አፍሪካ ቀጣይዋ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኘ ማዕከል ልትሆን ትችላለች ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ።
ባለፈው ሳምንት በአፍሪካ አንዳንድ አገራት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮ ታይቷል። በአፍሪካ እስካሁን ድረስ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ወደ 18000 ሰዎች ገደማ ሲኖሩ ከእነዚህ መካከል ወደ 1000 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል። በርግጥ ይህ ቁጥር በአሜሪካና በአውሮፓ ከታዩት አንፃር አነስተኛ መሆኑ ነው የተነገረው። የዓለም ጤና ድርጀት ቫይረሱ በአፍሪካ በዋና ከተሞች ብቻ ተወስኖ አልተቀመጠም ብሏል። አክሎም አህጉሪቱ በሽታው ለጠናባቸው ታማሚዎች ለመተንፈስን የሚያግዙ በቂ መሳሪያዎች የሏትም። የድርጅቱ የአፍሪካ ዳይሬክተር ዶ/ር ማቲዲሶ ሞይቲ ለቢቢሲ እንዳሉት ድርጅታቸው ቫይረሱ ከዋና ከተሞች ወደ ክልል ከተሞች እየተስፋፋ መሆኑን ገምግሟል። በደቡብ አፍሪካ፣ ናይጄሪያ፣ አይቮሪኮስት፣ ካሜሮንና ጋና ከከተማ በራቁ ስፍራዎች ቫይረሱ መሰራጨቱን ገልፀዋል። አክለውም የአፍሪካ አገራት የኮሮናቫይረስ ህሙማንን ለማከም የሚያስችል አቅም ስለሌላቸው መከላከል ላይ ማተኮራቸውን ይናገራሉ። "የጽኑ ህሙማን ክፍል ክትትል የሚያስፈልጋቸውን ሕሙማንን ቁጥር ለመቀነስ እየሰራን ነው፤ ምክንያቱም እንደዚህ አይነት የህክምና ክፍሎች በበርካታ የአፍሪካ አገራት በበቂ እንደማይገኙ እናውቃለን" ብለዋል። "አህጉሪቱ ከምትጋፈጣቸው ነገሮች መካከል ቀዳሚው የቬንትሌተሮች እጥረት መሆኑን መናገር እችላለሁ" ያሉት ዳይሬክተሯ፣ በኮሮናቫይረስ በጽኑ ለታመሙ ሰዎች ቬንትሌተር የማግኘት ጉዳይ የሞትና የሕይወት መሆኑን ተናግረዋል። ይህ መሳሪያ በጽኑ ታመው በራሳቸው መተንፈስ ለተቸገሩ ህሙማን ወደ ሳንባቸው ኦክስጅን በማድረስና ካርቦን ዳይኦክሳይድን በማስወጣት ቁልፍ ሚና አለው። በአፍሪካ በኮሮናቫይረስ ተይዘው ከሞቱ ሰዎች መካከል ቀዳሚው ዚምቧቤያዊው ጋዜጠኛ ሲሆን በወቅቱ በዋና ከተማዋ ሐራሬ የሚገኙ ባለስልጣናት እርሱን ለማከም ቬንትሌተር እንዳልነበራቸው ተናግረው ነበር። በአፍሪካ ሌላው ቫይረሱ በስፋት ይሰራጭባቸዋል ተብሎ ከተሰጉ ስፍራዎች መካከል አንዱ ከፍተኛ ጥግግት ያለባቸው ቦታዎች ሲሆኑ በእነዚህ ስፍራዎች የሚኖሩ የማህበራዊም ሆነ አካላዊ ርቀታቸውን ለመጠበቅ ፈታኝ እንደሚሆን እንዲሁም በርካቶቹ እጃቸውን የሚታጠቡበት ውሃና ሳሙና ላይኖራቸው ይችላል ተብሏል።
53245475
https://www.bbc.com/amharic/53245475
በድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት የተቆጡ ወጣቶች በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ ጥቃት አደረሱ
በድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት የተቆጡና ብረትና ተቀጣጣይ ነገር ያዙ ወጣቶች በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን በእንግሊዝ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የዳያስፖራና የሚዲያ ኃላፊ የሆኑት አቶ ያለው ከበደ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የለንደን ከተማ አቶ ያለው ከበደ ለቢበሲ እንደገለፁት በትናንትናው እለት በድምጻዊ ሃጫሉ ሞት የተቆጡ በርከት ያሉ ወጣቶች ተሰባስበው ወደ ኤምባሲው በመምጣት የተለያዩ ጉዳቶችን አድርሰዋል ብለዋል። ወጣቶቹ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በማውረድ ለማቃጠል መሞከራቸውን በምትኩ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሰንደቅ አላማ መስቀላቸውንና በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን ጨምረው አስረድተዋል። ወጣቶቹ ወደ ኤምባሲው የመጡት ከሰዓት ስምንት ሰዓት ላይ ነው ያሉት ኃላፊው ወደ ኤምባሲው ለመግባት መሞከራቸውንም ገልፀዋል። በኤምባሲው የቆንስላር ክፍል ውክልና ለመስጠት መጥቶ የነበረ አንድ ተገልጋይን ሲወጣ በማግኘት መደብደባቸውንም ጨምረው ተናግረዋል። የወጣቶቹ ዋና አላማ ኤምባሲው በመግባት ጉዳት ማድረስ እንደነበር ያመላከቱት አቶ ያለው ተቀጣጣይ ነገርና ብረት ይዘው እንደነበር አስረድተዋል። አቶ ያለው አክለውም በወቅቱ የኤምባሲው ሠራተኞች በሙሉ በሥራ ገበታቸው ላይ ነበሩ በማለት ንብረት ላይ ጉዳት ከማድረስና አንድ ተገልጋይ ከመደብደቡ ውጪ ሌሎች ሰዎች ላይ ጉዳት አለመድረሱን ገልፀዋል። ኤምባሲው ጉዳዩን ለፖሊስ ማመልከቱን ገልፀው በንብረት ላይ ያደረሱት ጉዳት፣ ተገልጋይን በመደብደባቸው በሕግ ለመጠየቅ የሚያስችል መረጃ ወስደዋል። ወጣቶቹ የፈቃድ ሠልፍ ሳይጠይቁ በድንገት በመምጣታቸው ምክንያት ማንነታቸውን ለመለየት ከሲሲቲቪ ካሜራ ላይ መረጃ መውሰዳቸውን አስረድተዋል። እስካሁን ድረስ ግን ከጥፋት አድራሾቹ መካከል የተያዘ አለመኖሩን አቶ ያለው ተናግረዋል። ከዚህ በኋላ ግን ፖሊስ ክስ እንደሚመሰርት መናገራቸውን ተናግረዋል። ኤምባሲው ላይ ጥቃት ከደረሰ በኋላ በለንደን የሚገኘው የአጼ ኃይለስላሴ ሃውልት መፍረሱን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተሰራጨው ፎቶ ያሳያል። አቶ ያለው ኃውልቱ ከኤምባሲው ርቆ እንደሚገኝና እርሳቸውም በፌስቡክ ላይ ማየታቸውን በመግለጽ ከዚህ ውጪ ተጨማሪ መረጃ እንደሌላቸው ገልፀዋል። አቶ ያለው አክለውም ወጣቶቹ አሁን በድንገት በመምጣታቸውና የከፋ ጉዳት ባለማድረሳቸው እንጂ ኤምባሲውም ላይ ሆነ ሠራተኞቹ ላይ የከፋ ጉዳት ሊደርስ የሚችልበት እድል መኖሩን አስታውሰው፣ በቪየና ስምምነት መሰረት ኤምባሲውን የመጠበቅ የእንግሊዝ መንግሥት ግዴታ እንዳለበት አስታውሰው ፖሊስ አስፈላጊውን ጥበቃ እንደሚያደርግላቸው መናገሩን ገልፀዋል። "የኤምባሲው ሠራተኞች በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት ሀዘን ውስጥ በነበሩበትና መንግሥት ወንጀሉን ፈጻሚዎች አድኖ ለፍርድ ለማቅረብ ቁርጠኝነቱን በተናገረበት ሰአት ይህ መድረሱ አሳዝኖናልም" ብለዋል።
news-44787107
https://www.bbc.com/amharic/news-44787107
የ "ጥርስ አልባው" ማዕቀብ መነሳት ፖለቲካ?
የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የኤርትራ ጉብኝታቸውን ተከትሎ ኢትዮጵያ ኤርትራ ላይ የተጣለው ማእቀብ እንዲነሳ ከጥቂት ቀናት በፊት አዲስ አበባ ለተገኙት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉትሬዝ ይፋዊ ጥያቄ አቅርባለች።
ሰላምና ጦርነት በሌለበት ሁኔታ ተፋጠው የነበሩት ኢትዮጵያና ኤርትራ ተቃዋሚዎቻቸውን ከመደገፍ በተጨማሪ ከዘጠኝ ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ ኤርትራ ላይ ማዕቀብ እንዲጣልባት በከፍተኛ ሁኔታ ግፊት ማድረግ ጀመረች። በአፍሪካ ህብረት በኩል ቀጥተኛ ጥያቄና በምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) በኩል ደግሞ በተዘዋዋሪ ግፊት ማድረጓንም ተንታኞች ይናገራሉ። ወሳኝ ምጣኔ ሃብታዊ እርምጃዎች በ100 ቀናት የጠቅላይ ሚኒስትሩ 100 ቀናት ከጦርነቱ በኋላ የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው የሚል አቋም ያራምዱ ነበር የሚሉት የግጭት አፈታት ባለሙያ የሆኑት አቶ ኤልያስ ኃብተ-ስላሴ የኢትዮጵያ መንግስት በወቅቱ ስልጣን የነበረው የሶማሊያ ፌደራላዊ የሽግግር መንግስት ግብዣ ተከትሎ ወደ አካባቢው ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ያካሄደ ሲሆን፤ ሁለቱም ባላንጣዎች በሶማልያ ተቃራኒው ቡድኖችን ሲደግፉ ነበር። የኤርትራና የኢትዮጵያ መንግስታት በአካባቢው የሚያደርጉት ጣልቃ ገብነት፤ በብዙ የፖለቲካ ተንታኞች እንደ የውክልና ጦርነት ተደርጎ ነበር የተወሰደው። "ኢትዮጵያ የራሷን ጥቅም ለማስከበር ስትሯሯጥ የነበረ ሲሆን፤ ኤርትራም በበኩሏ ኢትዮጵያን የሚጣሉ ኃይሎች እደግፋለሁ" የሚል አመለካከት ነበራት ይላሉ። ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን አሜሪካን የመሳሰሉ አገራት ኤርትራ እስላማዊ አክራሪነትና አሸባሪነትን ትደግፋለች የሚል ምክንያት አቅርበዋል። ይህንንም ተከትሎ የኤርትራ መንግሥት አልሸባብን እንደሚደግፍ የተባበሩት መንግስታት አጣሪ ኮሚቴ ባቀረበው ሪፖርት መሠረት፣ የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ ማዕቀብ የጣለ ሲሆን፣ ለሁለተኛና ለሦስተኛ ጊዜ ማራዘሙ ይታወሳል፡፡ በእርግጥም ኤርትራ አልሻባብን በገንዘብና በትጥቅ ትደግፋለች የሚለውን ክስ ኢትዮጵያ በበላይነት የምትቆጣጠረው ኢጋድ እና የአፍሪካ ህብረት በቀጥታ ያቀረቡት ጥያቄ ተከትሎ የሆነ ነበር። ኤርትራ የሚቀርብባት ውንጀላ ያልተቀበለች ሲሆን የተጣለባትን ማእቀብም መሰረት አልባ ስትል ኣጣጥላው ነበር። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ እርምጃዎች የት ድረስ? ኤርትራና ኢጋድ ሁለቱም አገሮች በድንበር ሳቢያ ወደ ጦርነት ማምራታቸውን ተከትሎ እንደ አገናኝ ድልድይ መድረክ ሆኖ ያገለግል እንደነበር የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ። ይሁን እንጂ ሶማሊያ ላይ የተከሰተው ፖለቲካ ቀውስ ሁለቱም በውክልና ለተለያዩ ቡድኖች መደገፋቸውን ተከትሎ በድርጅቱ ውስጥ አለመግባባት መፈጠሩ መረጃዎች ያመላክታሉ። በዚህም ምክንያት ድርጅቱ በሶማሊያ ጉዳይ ላይ የሰጠው ውሳኔ ጋር ተያይዞ ኤርትራ በአውሮፓውያኑ 2007 ላይ ከድርጅቱ ራሷን ማግለሏ ይታወሳል። ራሷን ከኢጋድ ካገለለች ግዜ ጀምሮ ከአካባቢው አገራትና ከዓለም ዓቀፍ ማህበረሰቡ ጋር የነበራት ግንኙነት እየተቋረጠና እየተነጠለች የመጣች መሆኑንን፤ በተለይም ማእቀቡ ኤርትራን ከሌላው አለም እንድትነጠል አድርጓታል ቢሉም ተፅእኖው ከፍተኛ እንዳልሆነ አቶ ኤልያስ ይናገራሉ። የማዕቀቡ ፋይዳ "ማዕቀቡ የተገደበ ነበር፤ ኢኮኖሚያዊ ሳይሆን የጦር መሳሪያ ለኤርትራ ዝውውርን መገደብ፣ ከፍተኛ የኤርትራ ባለስልጣናት እንቅስቃሴያቸው እንዲገደብ" የሚያትት እንደሆነ የሚናገሩት አቶ ኤልያስ የኤርትራ ህዝብና ኢኮኖሚን በጭራሽ የሚነካ እንዳልነበር ይናገራሉ። በለንደን ተቀማጭነታቸው ያደረጉት የምስራቅ አፍሪካ ፖለቲካ ተንታኝ አብዱልራህማን ሰይድ በበኩላቸው ማእቀቡ ተግባራዊ ሆኖ አልቆየም ይላሉ። "የጦር መሳሪያም ዝውውር ይሁን የባለስልጣናቱ ከአንድ ወደ ሌላ ቦታ መዘዋወርና ክፍት ሆኖ ነው የቆየው፤ ማዕቀቡ ድሮም ጥርስ አልባ ነበር" ይላሉ። ከዚያም በተጨማሪ የተባበሩት ኤምሬትስ ኤርትራ ላይ የጦር ሰፈር መስርታ የመንን ስትመታም ነበር ይላሉ። "ማዕቀቡ ከተነሳ ለኤርትራ መንግሥት ስርዓት የሞራል ብርታት ይሰጠው ይሆናል" ይላሉ። ተፅእኖውም እዚህግባ የማይባል በመሆኑም የተለያዩ ሀገራት ማዕቀቡን ለማስነሳት ጅማሮ ላይ የነበሩ መሆናቸውንም አቶ ኤልያስ ይናገራሉ። ወሳኝ ምጣኔ ሃብታዊ እርምጃዎች በ100 ቀናት ማዕቀቡ ይነሳ ይሆን? የኢትዮጵያና የኤርትራ ግንኙነት መሻሻል ጋር ተያይዞ ኢትዮጵያ ማእቀቡ እንዲነሳ የጠየቀች ሲሆን፤ ኢትዮጵያስ ይህንን ማድረግ ትችላለች ወይ ለሚለው ጥያቄም፤ ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት አባል ስለሆነች ጥያቄውን ማቅረብ የምትችል መሆኑን የሚናገሩት አቶ ኤልያስ የመጨረሻው ውሳኔ የፀጥታ ኃይሉ ነው ይላሉ። የኤርትራ ወዳጆች የሆኑ ሀገራት የማዕቀቡን እርባና ቢስነትና ውጤታማ አለመሆኑን ጠቅሰው ግፊት ሲያደርጉ የነበሩ አካላት እንደነበሩም ይናገራሉ። "በየትም አለም ቢሆን እገዳ አይሰራም፤ በእጅ አዙር እየሰራ ነው" የሚሉት አቶ ኤልያስ በአፓርታይድ ስርዓት ወቅት ማዕቀብ ተጥሎባት የነበረችው ደቡብ አፍሪካ እንዴት ከእስራኤል የጦር መሳሪያ በእጅ አዙር ታገኝ እንደነበር በምሳሌነት ያነሳሉ። አሜሪካ የተለየ ፍላጎት አላት የሚሉት አቶ ኤልያስ የኤርትራ ስትራቴጂካዊ አቀማመጥና የሶማሊያን ኢስላማዊ ቡድን ለመምታት የአሰብ ወደብን በመስጠት መተባበሯ በምዕራባውያን ዘንድ እንደበጎ አስተዋፅኦ ሊታይ እንደሚችልም ይጠቅሳሉ። "ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ለምዕራቡ አለም ያደረጉት አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው፤ ለህዝቡ አልጠቀመመም እንጂ፤ ከነበረው አስተሳሰብ ተቀይሯል" ይላሉ። ያለውን ለውጥ በማየት አሜሪካና የአውሮፓ ህብረት ፈቃድ ከተጨመረበት በቀላሉ ማዕቀቡ እንደሚነሳ የሚናገሩት አቶ ኤልያስ የቀድሞ አምባሳደርና በአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ኃላፊ ዶናልድ ያምማቶ ከኤርትራ ባለስልጣናት ጋር መወያየት አንድ ጠቋሚ ነገር ነው ይላሉ። በሌላ በኩል አልሸባብን ለመደገፍ የኤርትራ መንግሥት አቅም የለውም የሚሉት አቶ አብዱልራህማን "ኢትዮጵያ ማዕቀቡ ይነሳ ማለቷ በአፍሪካም ሆነ በቀጠናው ካላት ትልቅ ቦታ እንዲሁም በአለም ዓቀፍ ዲፕሎማሲ ተሰሚ መሆኗ ከፍተኛ ተፅእኖ ሊኖረው ይችላል፤ በፍጥነትም ይነሳል" ይላሉ። ማእቀቡም በቅርብ እንደሚነሳ አቶ ኤልያስ ተስፋ አላቸው።
news-56898167
https://www.bbc.com/amharic/news-56898167
የኢራኑ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር በድብቅ በተቀዳ ድምፅ የመንግሥታቸውን ጉድ አወጡ
አንድ ሾልኮ የወጣ የድምፅ ቅጂ የኢራኑ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጃቫድ ዛሪፍ አይነኬ የሚመስለውን አብዮታዊ ዘብ ሲተቹ አሰምቷል።
ሚኒስትሩ አብዮታዊው ዘብ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲውን እንደተቆጣጠረ እንዲሁም ኢራንን ወደ ሶሪያ ጦርነት እንዳስገባት ያወራሉ። በርካቶች 'አፋቸውን በመዳፋቸው ይዘው' ባደመጡት የድምፅ ቅጂ ሚኒስትሩ በሶሪያ ጦርነት ኢራን የሩስያን ዱካ እየተከተለች እንዳለ ይናገራሉ። በበርካታ ኢራናዊያን ዘንድ አምባገነናዊ ባሕርይ የላቸውም ከሚባሉት ጉምቱው ዲፕሎማት ዛሪፍ አፍ ይህ መውጣቱ ብዙዎችን አስደንቋል። ድምፁን ማን ቀድቶ እንደለቀቀው ባይታወቅም ኢራን ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ለማካሄድ ደፋ ቀና በምትልበትና ፖለቲካዊ ጨዋታው በደራበት ወቅት መለቀቁ ጥርጣሬ ጭሯል። ሚኒስትር ዛሪፍ ፕሬዝደንት ሀሳን ሩሃኒን የመተካት ሐሳብ እንደሌላቸው ተናግረዋል። ነገር ግን ወግ አጥባቂ ፖለቲከኞች የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩን እንደማያምኗቸው ይነገራል። ወጣም ወረደ የድምፅ ቅጂውን ተከትሎ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አደጋ ላይ ሊወድቁ እንደሚችሉ ሳይታለም የተፈታ ይመስላል። የአገሪቱ ቁጥር አንድ የፀጥታ ኃይል የሆነው አብዮታዊው ዘብን ጨምሮ ሁሉንም የመንግሥት ጉዳዮች በበላይነት የሚቆጣጠሩት አያቶላ አሊ ካሚኒ ምን ዓይነት ፍርድ እንደሚሰጡ አይታወቅም። የሦስት ሰዓት ርዝማኔ ያለው የድምፅ ቅጂ ለቢቢሲና ለሌሎች የዜና ተቋማት ተልኳል። ቅጂው የፕሬዝደንት ሩሃኒን የሥልጣን ዘመን አስመልክቶ ከሁለት ወራት በፊት ከተሠራ አንድ የታሪክ ፕሮጀክት ላይ እንደተወሰደ መረዳት ተችሏል። ዛሪፍ በተደጋጋሚ ለዓመታት ሐሳብ አስተያየታቸው ሰሚ እንደሌለውና እንደማይታተም ሲናገሩ ይደመጣሉ። ሚኒስትሩ አብዮታዊው ዘብ ዲፕሎማሲና የኢራን ውጭ ጉዳይ ፖሊሲን ቀጠናዊ የኃይል ግፊያን ለመቆጣጠር እየተጠቀመበት እንደሆነ ሲያማርሩ ይሰማሉ። ሚኒስትሩ እንደሚሉት በአሜሪካ የድሮን ጥቃት የተገደሉት የቀድሞው የአብዮታዊው ዘብ የኩድስ ኃይል አዛዥ ጄኔራል ቃሲም ሱሊማኒ ናቸው የሩስያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ስለፈለጉ ብቻ ኢራንን ወደ ሶሪያ ጦርነት የከተቷት። አክለው ሱሊማኒ የኢራን ብሔራዊ አየር መንገድ የሆነው ኢራን ኤርን ይዘው ወደ ሶሪያ ጦርነት አምርተዋል በማለት በሶሪያው ጦርነት የመንገደኞች አውሮፕላን ጥቅም ላይ መዋሉን አረጋግጠዋል። ዛሪፍ አክለውም፤ የሩስያው ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ኢራን በፈረንጆቹ 2015 ሩስያን ጨምሮ ከስድስት ኃያላን አገራት ጋር የኒውክሌር ስምምነት እንዳትደርስ የተቻላቸውን ሁሉ አድርገዋል ብለዋል። እንደ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከሆነ ኢራን ከምዕራቡ ዓለም ጋር ሰላም እንድትፈጥር ሩስያ አትሻም። ሚኒስትሩ ከሩስያው አቻቸው ላቭሮቭ እንዲሁም አገራቸው ኢራን የሩስያ አጋር እንደሆነች ቢታሰብም የዛሪፍ ሐሳብ ብዙዎችን አስደንቋል። ኢራን እና ዩናይትድ ስቴትስ የኒውክሌር ስምምነቱን በሚያንሰራሩበት መንገድ ዙሪያ ቪዬና ውስጥ እየመከሩ ይገኛሉ። አሜሪካ በዶናልድ ትራምፕ ዘመን ኢራን ላይ ማዕቀብ መጣሏን ተከትሎ ኢራን ስምምነቱን ማፍረሷ የሚዘነጋ አይደለም። ሚኒስትር ዛሪፍ እንደሚሉት አብዮታዊው ዘብ ስምምነቱን በፍፁም አይፈልገውም፤ ተግባራዊ እንዲሆንም አይሻም። ለዚህ እንደ ምሳሌ የጠቀሱት አንድ ሚሳዔል በሚሞከርበት ወቅት አብዮታዊው ዘብ "እስራኤል ከምድረ-ገፅ መጥፋት አለባት" የሚል ፅሑፍ በሂብሪው ማስፃፉንና በ2016 በባሕረ ሰላጤው ላይ 10 የአሜሪካ የውቅያኖስ አሳሾችን ማገቱን ነው። አብዮታዊው ዘብ በበርካታ ጉዳዮች የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩን እንደማያማክሯቸው ሚኒስትሩ አጋልጠዋል። አሜሪካ ሱሌማኒን ከገደለች በኋላ ኢራን በአፀፋው ኢራቅ ውስጥ አሜሪካዊያን ያሉበት ወታደራዊ ካምፕን ማጥቋቷን አውስተው ስለ ጉዳዩ የሰሙት ከጥቃቱ ሁለት ሰዓት ቀደም ብሎ እንደሆነ ይናገራሉ። የኢራን ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የዛሪፍ አስተያየት ከአውድ ውጭ እንደተወሰደ ተናግረው አስፈላጊ ከሆነ ሙሉ ቃለ ምልልስ እንደ አዲስ እንደሚለቀቅ ተናግረዋል።
news-46299511
https://www.bbc.com/amharic/news-46299511
ደቡብ ኮሪያዊው ፓስተር አማኞችን አስገድዶ በመድፈር ወንጀል ታሰሩ
አንድ ደቡብ ኮሪያዊ ፓስተር ስምንት የቤተክርስቲያኑ አማኞችን አስገድዶ በመድፈር ወንጀል ተከሰው 15 ዓመት ተፈረደባቸው።
ሊ ጃኢ ሮክ የተባሉት የ75 ዓመት 'ማሚን ሴንትራል ቸርች' የተሰኘ ቤተክርስቲያን አገልጋይ 130 ሺ ተከታዮች ያሏቸው ሲሆን፤ የቀረበባቸውን ክስ አልፈጸምኩም በማለት ሲከራከሩ ነበር። ተጎጂዎቹ ሴቶች ፓስተር ሊ ቅዱስ መንፈስ በእኔ ውስጥ አለ ስለሚሉን የታዘዝነውን ነገር ሁሉ እንፈጽም ነበር ብለዋል፤ ''አምላክ እኔ ነኝ'' ይሉም ነበር ብለዋል። አብዛኛዎቹ ደቡብ ኮሪያውያን በትልልቅና ብዙ ገንዘብ እንዲሁም ተጽዕኖ መፍጠር በሚችሉ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ይጠቃለላሉ። ነገር ግን እዚም እዚያም ከዋናዎቹ ቤተክርሰቲያኖች ተገንጥለው የራሳቸውን አገልግሎት የሚሰጡ ቤተክርስቲያኖችም አሉ። • የቦርዱ ማሻሻያና የብርቱካን ሹመት ምንና ምን ናቸው? • የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አመፅን በፎቶ አብዛኛዎቹ ተገንጣይ ቤተክርስቲያኖች ደግሞ በማጭበርበርና ገንዘብ በመሰብሰብ ላይ ያተኮሩ ናቸው። የፓስተር ሊ ቤተክርስቲያንም ከእነዚህ መካከል አንዱ ነው ተብሏል። ቤተክርስቲያኑ እ.አ.አ በ1982 ሲሆን የተቋቋመው፤ በመጀመሪያ 12 አባላት ብቻ ነበሩት። በአሁኑ ሰአት ግን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተከታዮች ያሉት ሲሆን፤ የራሱ ዋና መስሪያ ቤትና ታዋቂ የበይነ መረብ ፈውስ አገልግሎት መስጫም አለው። አነጋጋሪው የአስገድዶ መድፈር ጉዳይ ለህዝብ ጆሮ መድረስ የጀመረው ባለፈው ዓመት አንዳንድ ሴቶች ፓስተሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው እንዲመጡ እየጠየቁ ግብረ ስጋ ግንኙነት ከእሳቸው ጋር ካልፈጸሙ እንደማይፈወሱ እንደተነገራቸው ይፋ ሲያደርጉ ነው። ''እሳቸውን እምቢ ማለት ከባድ ነው። እሳቸው ማለት ንጉስ ናቸው። እንደ አምላክም ናቸው። ከልጅነቴ ጀምሮ የቤተክርስያኑ ተከታይ ነበርኩ'' ብላለች አንዲት ሴት። ተመሳሳይ ጥቃት ደርሶብናል ያሉ ስምንት ሴቶች ጉዳዩን ለፍርድ ቤት አቀረቡ። ባለፈው ግንቦት ወር ላይም ፓስተሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ። • ወሎ በነዳጅ 'ልትባረክ' ይሆን? የፍርድ ውሳኔው በዋናው ዳኛ ሲነበብ ፓስተር ሊ አይናቸውን ጨፍነው ነበር ተብሏል። እስከ መጨረሻው ውሳኔ ድረስም ሴቶቹ ያልተገባ ባህሪ በማሳየታቸው ከቤተክርስቲያኑ የተወገዱ ናቸው በማለት ሲከራከሩ ነበር፤ ፓስተሩ።
57318950
https://www.bbc.com/amharic/57318950
የግድያ ሙከራ የተደረገባቸው የኡጋንዳው የትራንስፖርት ሚንስትር ቆሰሉ
የኡጋንዳ የትራንስፖርት ሚንስትር በታጣቂዎች የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው የቆሰሉ ሲሆን የሚንስትሩ ልጅና ሹፌር ግን በጥቃቱ መገደላቸው ተገለጸ።
የቀድሞው የመከላከያ ኃላፊና የአሁኑ የትራንስፖርት ሚንስትር ጄነራል ካቱምባ ዋማላ የግድያ ሙከራ የተደረገባቸው ካምፓላ የሚገኘው ቤታቸው አቅራቢያ መሆኑን የአይን እማኞች ገልጸዋል። በሞተርሳይክል ይጓዙ የነበሩ ታጣቂዎች የሚንስትሩ መኪና ላይ ደጋግመው መተኮሳቸው ነው የተነገረው። ከግድያ ሙከራው ጋር የተያያዙ ናቸው የተባሉ የስልክ ጥሪዎች ላይ ምርመራ እየተካሄ እንደሆነ መከላከያ ኃይሉ አስታውቋል። ጄነራል ካቱምባ የደረሰባቸው ጉዳት ለሕይወታቸው አስጊ እንዳልሆነና ሕክምና እያገኙበት ያለው ሆስፒታል በወታደሮች እየተጠበቀ እንደሆነ ተገልጿል። ኡጋንዳ ውስጥ እጅግ ከሚከበሩ ፖለቲከኞችና ወታደራዊ ግለሰቦች አንዱ ናቸው። የአገሪቱ መከላከያ ኮማንደር እንዲሁም የፖሊስ ኃላፊም ሆነው አገልግለዋል። የቢቢሲዋ የኡጋንዳ ዘጋቢ ፔሸንስ አቲሬ እንደምትለው፤ መሰል ጥቃቶች የተለመዱ ቢሆኑም የግድያ ሙከራው አስደንጋጭ ነው። ዛሬ ጥቃት ሲፈጸምባቸው በወታደር መኪና ውስጥ ነበሩ። መኪናው ላይ ከጎን እና ከፊት ተተኩሶበታል። ልጃቸው ብሬንዳ ዋማላ እና ሹፌራቸው ሀሩና ካዮንዶ ሕይወታቸው አልፏል። ጄነራሉ ደም በደም ሆነው፣ በፍርሀት ሲንቀጠቀጡና ከዚያም በሞተርሳይክል ወደ ሆስፒታል ሲወሰዱ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ወጥቷል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት በሞተርሳይክል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ተኩስ እየከፈቱ አገሪቱን እየናጧት እንደሆነ የቢቢሲ ዘጋቢ ትናገራለች። እአአ ሰኔ 2018 ላይ ኢብራሒም አቢርጋ የተባለ ፖለቲከኛና የፕሬዘዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ቀንደኛ ደጋፊ ቤቱ አቅራቢያ ተተኩሶበት ተገድሏል። የቀድሞው የፖሊስ ቃል አቀባይ አንድሪው ፌሊክስ ካውሲም በሚያዝያ 2017 ተገድሏል። የእስልምና መምህራንም በተመሳሳይ ሁኔታ ተገድለዋል። እስካሁን ድረስ ግድያዎቹ ተመርምረው ውጤት ሲገኝ ወይም ተጠያቂዎች ለፍርድ ሲቀርቡ አልታየም።
news-49668659
https://www.bbc.com/amharic/news-49668659
በወር አበባ ምክንያት መምህሯ ያንጓጠጣት ተማሪ ራሷን አጠፋች
የ14 አመቷ ኬንያዊት ተማሪ የትምህርት ቤቷ ደንብ ልብስ በወር አበባ ርሶ ከታየ ከሰዓታት በኋላ ራሷን ማጥፋቷ ተሰምቷል።
እናቷ ቢያትሪስ ቺፕኩሩይ ልጇ ካቢያንጌክ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በምትማርበት ወቅት አስተማሪዋ የደንብ ልብሷ ደም መራሱን ተመልክቶ አርብ ዕለት ከክፍል እንድትወጣ ብቻ ሳይሆን አንጓጥጧታል ይህ ከሆነ ከሰዓታት በኋላም ልጄን በሞት ተነጥቄያለሁ ብለዋል። ይህንን ተከትሎም የልጅቷ ራሷን ማጥፋት ትክክለኛው ምክንያት መምህሩ መሆኑ አለመሆኑን ፖሊስ እያጣራሁ ነው ብሏል። •"የሴቶች የንፅህና መጠበቂያን ከቀረጥ ነፃ እናደርጋለን" ዶ/ር አሚር አማን •"ለመጨረሻ ጊዜ ያየሁት በትንሳኤ በዓል ነበር" የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌ እናት "የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ ለመግዛት አቅሙ አልነበራትም። የወር አበባዋ ሲፈስ የተመለከተው አስተማሪ ግን ከክፍል አስወጥቶ ውጭ እንድትቆም አድርጓታል" በማለት እናት ይከስሳሉ። ከናይሮቢ በምዕራብ በኩል 270 ኪ/ሜ በሚገኘው የሃገሪቱ ክፍል እናቷን ጨምሮ ከ200 በላይ ወላጆች መምህሩ እንዲታሰር ትናንት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። ትምህርት ቤቱ በዚሁ ምክንያት የተዘጋ ሲሆን የተዘጋውን መንገድ ለማስከፈትም ፖሊስ አስለቃሽ ጋዝ ተኩሷል። •ወደ ጫካነት የተቀየረው ስታዲየም ከሁለት አመታት በፊት የወጣውን የኬንያ ሕግ ተከትሎ መንግሥት ለሁሉም የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የንፅህና መጠበቂያ ለማቅረብ ወስኗል። የሃገሪቱ የፓርላማ አባላት 4.5 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣው የተማሪዎቹ አመታዊ የንፅህና መጠበቂያ ፍጆታ በሚገባ በየትምህርት ቤቱ ስለመድረሱ እያጣሩ ይገኛሉ።
news-53135328
https://www.bbc.com/amharic/news-53135328
በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ህሙማን ላይ የአንቲቦዲ ምርመራ መደረግ ተጀመረ
በኢትዮጵያ ከኮቪድ-19 አንጻር ተፈጥሯዊ በሽታን የመከላከል ህዋሳት (አንቲቦዲ) ምርመራ በህሙማን ላይ ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ሳምንታት እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ተቋም አስታወቀ።
ተቋሙ እንዳለው ምርመራው የኮቪድ-19 በሽታ ያለበት ሰው ቫይረሱን ለመለየት የሚረዳ ሳይንሳዊ ሲሆን በተጨማሪም በማኅበረሰብ ውስጥ ያለውን የበሽታን ስርጭት ለመረዳትና ምላሽ ለመስጠት እንደሚያገለግል ገልጿል። በተጨማሪም ለወረርሽኙ ይበልጥ ተጋላጭ በሆኑት የኅብረተሰቡ ክፍሎች ውስጥ ያለውን የኮቪድ-19 በሽታ ስርጭት ለማወቅ የሚደረገው የአንቲቦዲ ምርመራ አስፈላጊ መሆኑን ተቋሙ አስታውቋል። ይህ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 15 ድረስ ለሦስት ተከታታይ ሳምንትት የሚካሄደው በአገሪቱ ውስጥ በሚገኙ እየተስፋፋ ባለው ወረርሽኝ በተያዙ ሰዎች ላይ ነው ተብሏል። ይህ የቅኝት ምርመራ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የኮሮናቫይረስ በሽታ ስርጭት ለማወቅ የሚያግዝ ሲሆን ምርመራው በሁሉም ክልሎችና የከተማ መስተዳደሮች ውስጥ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል። • ከባድ የጤና ችግር ኖሮባቸው ከኮቪድ-19 ያገገሙ ሰዎች ታሪክ • ዴክሳሜታዞን ምን ያህል አስተማማኝ ነው? ኢትዮጵያ ውስጥስ ይገኛል? • ከባድ የጤና ችግር ኖሮባቸው ከኮቪድ-19 ያገገሙ ሰዎች ታሪክ የአንቲቦዲ ምርመራው የሚደረገው ከሰዎች ላይ በሚወሰድ እስከ አምስት ሚሊ ሊትር በሚደርስ የደም ናሙና ላይ ሲሆን፣ የበሽታው ተከላካይ ህዋሳቱ እንደየበሽታው ዓይነት እንደሚለያዩ ተገልጿል። ይህ ምርመራ የኮሮናቫይረስን ለመካላከልና ለመቆጣጠር ለሚደረገው የቅኝት ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተቋሙ አመልክቷል። አንቲቦዲ አካላችን የሚገጥሙትን የተለያዩ ህመሞች ለመቋቋምና ለመከላከል በተፈጥሮ የሚያዘጋጀው መከላከያ ሲሆን ሰውነታችን ለበሽታው ከተጋለጠ በኋላ በሚኖሩ ጥቂት ሳምንታት ውስጥ በበሽታ ተከላካይ ህዋሳቱን ያመርታል። ይህንን ተፈጥሯዊ የበሽታ መከላከያ አቅም ምርመራን ውጤት በማወቅ ብቻ ሕክምና መስጠት እንደማይቻል የጠቀሰው ተቋሙ፣ ነገር ግን በቀጣይ ሊወሰዱ በሚገባቸው እርምጃዎች ላይ ጠቃሚ ግብዓት ሆኖ እንደሚያገልግል ባለሙያዎች ይናገራሉ። የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ተቋም ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ የሚገኘው በሽታን የመከላከል ህዋስ (አንቲቦዲ) የመመረት ሁኔታ በእድሜ፣ በአመጋገብ፣ በሚጠቀማቸው መድኃኒቶች፣ በሚያጋጥመው በሽታ ከባድነት እና ባሉበት ተጓዳኝ በሽታዎች ላይ ይወሰናል ብሏል።
sport-44851168
https://www.bbc.com/amharic/sport-44851168
ጅማ አባጅፋር የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ሆነ
እስከ መጨረሻዎቹ ሁለት ሳምንታት ድረስ ሶስት ክለቦችን ያፎካከረውና አሸናፊውን ለመለየት እስከ ዛሬው ጨዋታ ድረስ በጉጉት ያስጠበቀው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፍጻሜውን አግኝቷል።
ፕሪምየር ሊጉን ዘንድሮ የተቀላቀሉት ጅማ አባጅፋሮች በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ የ2010 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ሆነዋል። ጅማ አባጅፋር ከአዳማ ከተማ ጋር በሜዳቸው ጅማ ላይ ዛሬ በ8 ሰዓት ደረጉትን ጨዋታ 5 ለባዶ በማሸነፍ ነው ሻምፒዮን መሆናቸውን ያረጋገጡት። ከ30 ጨዋታ 55 ነጥብ መሰብሰብ የቻሉት ጅማ አባጅፋሮች ቀላል የሚባል አመት አላሳለፉም። ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ጣራ ለምመጣት ከፍተኛ ትግል አድርገው ነበር። ''ብሔርተኝነት'' እያጠላበት ያለው እግር ኳስ ዛሬ በተመሳሳይ 8 ሰዓት በተደረገው የሰላሳኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጨረሻ ጨዋታ ሌላኛው ለዋንጫው የተጠበቁትን ቅዱስ ጊዮርጊሶች ከሃዋሳ ከተማ አገናኝቷል። በጨዋታው 2 ለባዶ ያሸነፉት ጊዮርጊሶች የጅማ አባጅፋርን ውጤት እስኪሰሙ ድረስ በአዲስ አበባ ስታዲየም የተቀመጠውን ዋንጫ እንደሚያነሱት ተስፋ አድርገው ነበር። ከጨዋታው በፊት ቅዱስ ጊዮርጊሶች ከ29 ጨዋታዎች 52 ነጥብ በመሰብሰብ ከጅማ አባጅፋር ጋር ተመሳሳይ ነጥብና የግብ ልዩነት ይዘው፤ ብዙ ባገባ በሚለው ህግ በፕሪምየር ሊጉ ሰንጠረዥ አናት ላይ ተቀምጠው ነበር። ከጨዋታዎቹ መጠናቀቅ በኋላ ግን ጅማ አባጅፋር በ55 ነጥብና 24 የግብ ልዩነት አንደኛ ሆኖ ሲጨርስ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ በተመሳሳይ ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ ሁለተኛ ሆኖ ጨርሷል። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ቡና ባለፈው አርብ መቐለ ከተማን 3 ለ 1 በማሸነፍ በ50 ነጥብ ሶስተኛ ሆኖ የጨረሰ ሲሆን፤ አርባምንጭ ከተማ፤ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እንዲሁም ወልዲያ ከነማ ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መውረዳቸውን አረጋግጠዋል። ቅዳሜ ዕለት የመውረድ አደጋ ተጋርጦበት የነበረው ድሬዳዋ ከተማ በፕሪሚየር ሊጉ ሰንጠረዥ 13ኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ያረጉት ጨዋታ በዝናብ ምክንያት ቢቋረጥም፤ ጨዋታው እሁድ በድጋሚ ተካሂዶ ድሬዳዋ ከተማ 2 ለባዶ በማሸነፍ 35 ነጥብ በመያዝ በፕሪምየር ሊጉ መቆየቱን አረጋግጧል። የጅማ አባጅፋሩ አጥቂ ኦኪኪ አፎላቢ ዛሬ ያስቆጠራቸውን 4 ግቦች ጨምሮ በ23 ግብ የአመቱ ኮከብ ጎል አግቢ ሆኖ ጨርሷል። የኢትዮጵያ ቡናው ሳሙኤል ሳኑሚ በ13 ግብ ሁለተኛ እንዲሁም የኢትዮ ኤሌክትሪኩ አል ሃሰን ካሉሻ በ13 ግብ ሶስተኛ ሆነው ጨርሰዋል።
50272640
https://www.bbc.com/amharic/50272640
ጎርፍ ባጠቃቸው የምሥራቅ አፍሪካ አገራት ተጨማሪ ዝናብ ሊጥል ይችላል ተባለ
ካለፉት ሳምንታት ጀምሮ ከባድ የጎርፍ አደጋ ባጋጠማት ሶማሊያ በቀጣይ ቀናትም ተጨማሪ ዝናብ ሊጥል እንደሚችል የአየር ሁኔታ ትንበያ ሙያተኞች ገለጹ።
በጎርፉ ሳቢያ ወደ 273,000 የሚጠጉ ሰዎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው እንደሸሹ 'ኢንተርናሽናል ሬስኪው ኮሚቴ' የገለጸ ሲሆን፤ 'አክሽን አጌንስት ሀንገር' የተባለው ድርጅት ደግሞ የጎርፍ አደጋው ከዚህ ቀደም ከደረሱት እጅግ የከፋ ነው ብሏል። • መሬት መንሸራተትና ጎርፍ በደቡብ ኢትዮጵያ ጥፋት አደረሰ • ጎርፍ የመቶ ሰዎችን ሕይወት ቀጠፈ በጎርፉ የኬንያ እና የደቡብ ሱዳን አንዳንድ ቦታዎችም ጉዳት ደርሶባቸዋል። ደቡብ ሱዳን ውስጥ ከ600,000 የሚበልጡ ሰዎች ከቤታቸው ተፈናቅለዋል። ባለፈው ረቡዕ ፕሬዘዳንት ሳልቫ ኪር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጃቸውም የሚታወስ ነው። ፒቦር የተባለችው የአገሪቱ ግዛት ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ እንደምትገኝም የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ገልጸዋል። "ከተማዋ ሙሉ በሙሉ በውሀ ተውጣለች። ሁኔታው እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል" ሲሉ 'ሜዲካል ሳን ፍሮንቴይርስ' የተባለው የደቡብ ሱዳን የአደጋ ጊዜ አስተባባሪ ወኪል ኢድ ፈርዲናንድ አቴ ተናግረዋል። • በፌስቡክ የሐሰት ዜና ለማሰራጨት ሲል ፖለቲካኛ ለመሆን ያሰበው ግለሰብ በደቡብ ሱዳን የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ እርዳታ ኮሚቴ ኃላፊ አንድርያ ኖይስ እንዳሉት፤ በጎ አድራጊዎች ሰዎችን ለመርዳት በጎርፍ የተሞሉ ጎዳናዎች ማለፍ ይጠበቅባቸዋል። "ሰዎችን የምንረዳው እስከ ጉልበታችን እና ታፋችን የሚደርሰውን ውሀ አልፈን ነው"ሲሉ ያለውን ሁኔታ ገልጸዋል። በጎርፍ አደጋ ከፍተኛ ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች መቼ፣ ምን ያህል ዝናብ ሊጥል እንደሚችል አስተማማኝ መረጃ የለም። ሆኖም ኬንያ ውስጥ ጥቅምት ወር ላይ ኃይለኛ ዝናብ እንደጣለ ታውቋል። በኬንያዋ ሞምባሳ ጥቅምት 16 ላይ 100 ሚሊ ሜትር ዝናብ ጥሏል። ይህም በወሩ ከተመዘገበው የዝናብ መጠን የላቀ ነው። ባለሙያዎች እንደሚሉት፤ የዝናብ መጠን ለመጨመሩ ምክንያቱ 'ፖዘቲቭ ኢንድያን ኦሽን ዲፖል' በመባል የሚታወቀው የአየር ሁኔታ ነው። ይህ የሚፈጠረው ምዕራባዊው የህንድ ውቅያኖስ ከምሥራቃዊው ክንፍ በላይ ሲሞቅ ነው። ዛሬና ነገ እንዲሁም በቀጣዩ ሳምንት ጭምር በሶማሊያ ከፍተኛ ዝናብ እንደሚጥል ይጠበቃል።
news-45557284
https://www.bbc.com/amharic/news-45557284
አሜሪካ ከቻይና የሚገቡ እቃዎች ላይ አዲስ ታሪፍ ጣለች
የአሜሪካና የቤጂንግ የንግድ ጦርነት እየተካረረ ባለበት በአሁኑ ወቅት አሜሪካ 200 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ የቻይና እቃዎች ላይ አዲስ ታሪፍ መጣሏ ተሰማ።
ሩዝ በዚህኛው የታሪፍ ዙር አሜሪካ ያነጣጠረችበት የቻይና ምርት ነው ከእነዚህ መካከል የእጅ ቦርሳዎች፣ ሩዝና ጨርቃጨርቅ ይገኙበታል።በአጠቃላይ በዚህኛው ዙር አሜሪካ ከቻይና የሚገቡ ስድስት ሺህ የሚሆኑ እቃዎች ላይ ታክስ ጥላለች። ቻይና ቀደም ሲል አሜሪካ ተጨማሪ ታሪፎችን ልትጥል ብትሞክር አፀፋውን እንደምትመልስ አስታውቃ እንደነበር ይታወሳል። አዲሱ ይህ የአሜሪካ ታሪፍ ከአንድ ሳምንት በኋላ በ አስር በመቶ ጀምሮ ከዚያም እስከ ሃያ አምስት በመቶ ጨምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልጿል። . ስለተፈፀመው ጥቃት እስካሁን የምናውቀው . ሞትና መፈናቀል በአዲስ አበባ ዙሪያ . አቶ ዳውድ ኢብሳ ማናቸው? ሁለቱ አገራት ስምምነት ላይ ምድረስ እስካልቻሉ ድረስ ይህ ነገር እንደ አውሮፓውያኑ እስከ መጭው ዓመትም ሊዘልቅ ይችላል።. የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይህ የታሪፍ ዙር ቻይና እያሳየች ላለችው ኢፍትሃዊ የንግድ አሰራር አፀፋ ነው ብለዋል። ኢፍትሃዊ ከሚሏቸው የቻይና የንግድ ተግባራት መካከል ኩባንያዎቿን መደጎም እና ቻይና ውስጥ በተወሰኑ ዘርፎች የሚሰማሩ የውጭ ኩባንያዎች የግድ አንድ የአገር ውስጥ አጋር እንዲኖራቸው ማስገደድ ይገኙበታል። " መደረግ ስላለበት ለውጥ በግልፅ አስቀምጠናል።ቻይና ለኛ ፍትሃዊ እንድትሆንም ብዙ እድል የሰጠናት ቢሆንም ቻይና አካሄዷን ለመለወጥ ፍቃደኛ ሳትሆን ቀርታለች "ብለዋል ትራምፕ። አሁንም ለዚህ እርምጃ ቻይና አፀፋ እመልሳለው ብትል አገራቸው 267 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት እቃ ላይ ሶስተኛውን ዙር ታሪፍ ተግባራዊ ለማድረግ እንደምትገደድ በመግለፅ ቻይናን አስጠንቅቀዋል። እርምጃው በንድፈ ሃሳብ ደረጃ የአሜሪካ ምርቶች ዋጋ ከምታስገባቸው ቁሶች ዋጋ ጋር ሲነፃፀር ርካሽ እንደሆን በማድረግ ተጠቃሚዎች ዋጋው የሚቀንሰውን የአሜሪካን እቃ እንዲገዙ ያደርጋል።
news-54451983
https://www.bbc.com/amharic/news-54451983
በኢትዮጵያ የጦር መሳሪያ ምዝገባ በቅርብ ጊዜ እንደሚጀመር ተገለፀ
ከጥቂት ወራት በፊት በፓርላማ የፀደቀው የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ተግባራዊ ለማድረግ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ እንዳሉ የሰላም ሚኒስቴር አስታውቋል።
በአፍሪካ ሕገወጥ የጦር መሳሪያ ያላቸው ሰዎች የሚያሳውቁበት ወይንም ለሕጋዊ አካላት የሚያስረክቡበት ወርን በማስመልከት የሰላም ሚኒስቴር ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመሆን የጦር መሳሪያ ቁጥጥርና አስተዳደርን በማስመልከት ዛሬ መግለጫ በሰጡበትም ወቅት ነው ይህ የተገለፀው። በአፍሪካ ውስጥ የሕገወጥ መሳሪያዎች ከቀላል ወንጀሎች እስከ ሽብር ተግባር የሚፈፀምባቸው እንደሆነ የሰላም ሚኒስቴሯ ሙፈርያት ካሚል ተናግረዋል። ባለፉት ሁለት ዓመታትም ሕገወጥ የጦር መሳሪያ በመቆጣጠር እንዲሁም ሰላም ለማስፈን ኅብረተሰቡን እና ጉዳዩ የሚመለከታቸውን በማሳተፍ እየተሰራ እንደነበር ጠቁመዋል። "እስካሁን ባለው አሰራር የሕገወጥ መሳሪያ ዝውውርን መቆጣጣር ያለባቸው ተቋማት የሚፈለገው የቴክኖሎጂ እገዛ የላቸውም" ያሉት ሚኒስትሯ፣ መንግሥት ለጉዳዩ ትልቅ ትኩረት በመስጠት በፌደራል ደረጃ ያሉ ባለሙያዎችን አሰልጥኖ በቅርብም ምዝገባ የሚጀመር መሆኑን ተናግረዋል። በተጨማሪም ስልጠናውን በክልል እና በከተማ አስተዳደሮች ላሉ ባለሙያዎች በመስጠት አዋጁን በአገር አቀፍ ደረጃ ስራ ላይ ለማዋል እንደሚሰራም ተገልጿል። አዋጁ በአገሪቱ የሕግ የበላይነት ተከብሮ ሰላማዊ እና መረጋጋት የሰፈነበትን ኅብረተሰብ ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ሚኒስትሯ ጨምረው ተናግረዋል። የሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር የሚቀጥል ከሆነ "ሰላም ጠፍቶ አንዱ በአንዱ ላይ እንዲነሳ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር" የተናገሩት ሚኒስትሯ ኅብረተሰቡም ከመንግሥት ጎን እንዲቆምም በዚሁ አጋጣሚ ጥሪ አቅርበዋል። ምን እየተሰራ ነው? የሰላም ሚኒስቴር አማካሪ አሆኑት አቶ ሚናስ ፍሰሃ ኢትዮጵያ እኤአ በ2004 የአነስተኛ ጦር መሳሪያዎች መከላከልና ቁጥጥር (ናይሮቢ ፕሮቶኮል) መፈረሟን አስታውሰው፣ ለረዥም ዓመታት ሕግ ሳይኖራት እንደቆየች ተናግረዋል። ይሁንና መንግሥት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለጉዳዩ በሰጠው ትኩረት በታሕሳስ 2012 የጦር መሳሪያ አስተዳደር ቁጥጥር አዋጅ 1177/2012 እንዲወጣ መደረጉን ተናግረዋል። ይህንንም አዋጅ ወደ ተግባር ለመቀየር ደንቦችና መመሪያዎች ተዘጋጅተው መጠናቀቁን አማካሪው ጨምረው ገልፀዋል። "የሕዝብን ደህንነት የማስጠበቅ ግዴታና ኃላፊነት ያለበት መንግሥት እንደሆነ ይታመናል" ያሉት አቶ ሚናስ ይሁንና ዜጎች ባላቸው የማኀበራዊና ባህላዊ እሴቶች፣ ለደህንነታቸው እንዲሁም በስራቸው ምክንያት ጦር መሳሪያ እንዲይዙ ግዴታ ሲሆንባቸው በሕጉ ላይ በተቀመጠው መሰረት የጦር መሳሪያ እንዲይዙ ይፈቀድላቸዋል ሲሉም በመግለጫው ላይ ተናግረዋል። የጦር መሳሪያ ቁጥጥርና ምዝገባ ስራውን በበላይነት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እንዲሰራ መታቀዱት የተናገሩት አቶ ሚናስ፣ የክልሎች እና የከተማ አስተዳር ፖሊስ ኮሚሽኖች በፌደራል ፖሊስ በሚሰጣቸው ውክልና መሰረት እንደሚሰሩ ተነግሯል። ይሁን እንጂ ዛሬ በተሰጠው መግለጫ ላይ በአገሪቱ ውስጥ ስላለው የሕገወጥ መሳሪያ ሁኔታ እንዲሁም ምዝገባው መቼ እንደሚጀመር የተባለ ነገር የለም። ጦር መሳሪያን መታጠቅ የሚችለው ማን ነው? አዋጁ ማን የጦር መሳሪያ መታጠቅ እንደሚችል እና እንደማይችል በግልፅ እንዳስቀመጠ የሚናገሩት አቶ ሚናስ ፍሰሃ ሙሉ ለሙሉ ወይንም በከፊል የሕግ ብቃት የሌላቸው ሰዎች፣ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወይንም ባለባቸው የአካል ጉድለት ምክንያት የተከለከሉ የጦር መሳሪያ መጠቀም እንደማይችሉ ሕጉ ላይ ሰፍሯል ብለዋል። ሌላኛው አዋጁ የጦር መሳሪያ ያላቸው አስመዝግበው ፈቃድ እንዲኖራቸውና እንዲጠቀሙ ከማስቻል ጎን ለጎን ከአንድ የጦር መሳሪያ በላይ ያላቸው ሰዎችም በአካባቢያቸው በሚገኘው የፖሊስ ጽህፈት ቤት አማካኝነት እንዲመልሱ የሚያደርግ መሆኑንም አቶ ሚናስ ይናገራሉ። የጦር መሳሪያ ምዝገባው የሚካሄደው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በሚያወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እንደሚሆንም ተናግረዋል።
news-42513472
https://www.bbc.com/amharic/news-42513472
ቤተ-ክርስቲያን ላይ በተፈፀመ ጥቃት በርካቶች ተገደሉ
ከግብፅ መዲና ካይሮ በስተደቡብ በምትገኘው ሄልዋን አካባቢ በኮፕቲክ ክርስቲያኖች ላይ በተፈፀሙ ሁለት ጥቃቶች 12 ሰዎች መገደላቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ።
አስር ሰዎች የተገደሉት አንድ ታጣቂ ወደ ቤተክርስቲያ ለመግባት በሞከረበት ጊዜ ሲሆን ፖሊሶች ዘልቆ እንዳይገባ አድርገውታል። ከዚህ ጥቃት ከአንድ ሰዓት በኋላ በተመሳሳይ አካባቢ በሚገኝ የአንድ ክርስቲያን መደብር ላይ በተፈፀመ ጥቃት ሁለት ሰዎች ተገድለዋል። ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ከ100 የሚበልጡ ክርስቲያኖች የአይኤስ የግብፅ ቅርንጫፍ እንደሆነ በሚነገርለት ታጣቂ ቡድን ተገድለዋል። የተፈፀሙትን ጥቃቶች ተከትሎ የፀጥታ ሠራተኞች በዋና ከተማዋ ካይሮ ዙሪያ ኬላዎችን አቁመው ቁጥጥር እያደረጉ ነው። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የፀጥታ ባለሥልጣናት ፈጥኖ ደራሽ ኃይልን ጨምሮ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም በአዲስ ዓመት እና በኮፕት ክርስቲያኖች የገና በዓል ሰሞን ጥበቃ እንደሚያደርጉ አሳውቀው ነበር። በቤተ ክርስቲያኑ ላይ የተፈፀመው ጥቃት ፖሊሶች ጥበቃ እያደረጉ ሳለ ጥርጣሬ የሚያጭር እንቅስቃሴ ከተመለከቱ በኋላ መሆኑን የቢቢሲ ዘጋቢ ገልጿል። ተጠርጣሪዎቹ ፖሊሶች በቀረቧቸው ጊዜ ነበር ተኩስ ከፍተው ጉዳቱን ያደረሱት። ከሟቾቹም መካከል በቤተክርስቲያኑ ጥበቃ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሦስት ፖሊሶች ይገኙበታል። በጥቃቱ ሁለት ሰዎች በፅኑ የቆሰሉ ሲሆን ሌሎች በርካቶች እንደቆሰሉም ተዘግቧል። የቢቢሲ ዘጋቢ እንደገለፀው አንድ ሟች ላይ ፈንጂ የተገኘ ሲሆን ይህ ደግሞ ይበልጥ ከባድ የሆነ ጥቃት ተቀነባብሮ እንደነበር ያረጋግጣል። ፈንጅውም በጥንቃቄ እንዲከሽፍ ተደርጓል። ሌላው ታጣቂ አምልጦ የነበረ ቢሆንም ኋላ ላይ ከታተቀው ጦር መሳሪያና ቦምቡ ጋር ተይዟል። በአካባቢው በሚገኝ አንድ መደብር ላይ ጥቃት መፈፀሙም ታውቋል። የግብፅ ኮፕቲክ ቤተ-ክርስትያን የአገሪቱ ባለስልጣናት ተገቢውን ጥበቃ እንደሚያደርጉ ከማውራት በዘለለ በተግባር እርምጃ አልወሰዱም ሲሉ መውቀሳቸውን የቢቢሲ ዘጋቢ ገልጿል። እንደዚህ ያለው ጥቃት ውጥረትን እንደሚያከርም ቤተ ክርስትያኗ ገልፃለች። ግብፅ ሙስሊሞች ብዙሃን የሆኑባት አገር ስትሆን አነስተኛ ቁጥር ካላቸው ክርስትያኖቿ አስር በመቶ የሚሆኑት የኮፕቲክ ክርስትና እምነት ተከታዮች ናቸው። ሚያዝያ ላይ አሌክሳንደሪያና ታንታ በተሰኙ ከተሞች በሚገኙ የኮፕት አብያተ-ክርስትያናት ላይ በተፈፀሙ ጥቃቶች 45 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል። ግንቦት ላይ ደግሞ ወደ ገዳም እየሄደ የነበረ አውቶቡስ ላይ በተፈፀመ ጥቃት 29 ክርስትያኖች ህይወታቸውን አጥተዋል። ጥቅምት ላይ ደግሞ ካይሮ ውስጥ አንድ የኮፕቲክ ቄስ በስለት ተወግተው መገደላቸው ይታወቃል። ለጥቃቶቹ ሃላፊነት የወሰዱት ከአይ ኤስ ጋር ግንኙነት አለን የሚሉ አክራሪ ሙስሊም ቡድኖች ናቸው።
47439061
https://www.bbc.com/amharic/47439061
የቢቢሲ አማርኛ የመጀመሪያ ዝግጅት በኢትዮጵያ ምድር
ከየካቲት 25 እስከ መጋቢት 07/2011 ዓ.ም ድረስ የቢቢሲ አማርኛ፣ ኦሮምኛ እና ትግርኛ አዘጋጆች በየአካባቢው ያሉ ታዳሚዎችበሚኖሩባቸው ከተሞች በመገኘት በቀጥታ ለማግኘትና ለመወያየት ወደ ተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች አቅንተዋል።
ለቢቢሲ በአይነቱ የመጀመሪያው በሆነው በዚህ ልዩ ዝግጅት ህብረተሰቡ የሚሳተፍባቸው ውይይትና ክርክሮች እንዲሁም አዳዲስ መሰናዶዎች በየዕለቱ ለታዳሚው የሚቀርብ ይሆናል። በ2010 ዓ.ም የተጀመሩት እነዚህ የቢቢሲ አገልግሎቶች ለታዳሚዎቻቸው ቅርብ የሆኑ በርካታ ታሪካዊ ክስተቶች ሲዘግቡ ቆይተዋል። •ያልተጠበቁ ክስተቶች የታዩበት ዓመት ይህ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደው ዝግጅትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ አንድ ዓመት ሊሆናቸው በተቃረበበት ጊዜ በመሆኑ፤ የተገኙ ውጤቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ለመቃኘት አጋጣሚውን ፈጥሯል። በተጨማሪም የመጀመሪያዋ ሴት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት የሆኑት ወ/ሎ መዓዛ አሸናፊና የቀድሞ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር የነበሩትና አሁን የመጀመሪያዋ የምርጫ ቦርድ ሊቀመንበር ከሆኑት ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳን ጨምሮ የሃገሪቱ ተጠቃሽ ከሆኑ ግለሰቦች ጋር የተደረጉ ቃለምልልሶች ይቀርባሉ። •የቢቢሲ አማርኛ በአንድ ዓመት ውስጥ ያቀረባቸው ተነባቢ ዘገባዎች ለ11 ቀናት በሚዘልቀው በዚህ ዝግጅት በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ለሚገኙት ታዳሚዎች ቁልፍ የሆኑ ጉዳዮችን የሚዳስሱ ተከታታይ መሰናዶዎች ይቀርባሉ። ወጥ ዝግጅቶቻችንን በሬዲዮ፣ በፌስቡክና በቢቢሲ አማርኛ ድረ ገፃችን ላይ ታገኟቸዋላችሁ። የዚህ ዝግጅት ማጠቃለያ የሚሆነውም ሦስቱም ቋንቋዎች በጋራ ቅዳሜ መጋቢት 07/2011 ዓ.ም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በሃሰተኛ ዜና (ፌክ ኒውስ) ላይ በሚያዘጋጁት ውይይት ይሆናል። •"የጠቅላይ ሚኒስትሩ ትልቁ ስኬት ብዙ ሰው በተስፋ እንዲኖር ማድረጋቸው ነው" ዶ/ር ዮናስ አዳዬ የቢቢሲ የምሥራቅ አፍሪካ ሃላፊ ሬቼል አኪዲ እንደምትለው "የጋዜጠኝነት ሥራችንን በአፍሪካ በህዝብ ብዛት ሁለተኛ በሆነችውና በርካታ ወጣቶች በሚገኙባት ኢትዮጵያ ውስጥ ማስተዋወቅ እንፈልጋለን። በዚህ ዝግጅትም በሃገሪቱ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ ለመቃኘትና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ለመዳሰስ እንችላለን። ይህም ታዳሚዎቻችን ስለኢትዮጵያ የተሟላ መረጃ እንዲኖራቸው ያደርጋል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።" //Ends ሃሽታግ: #ቢቢሲአማርኛወደእናንተ መጥቷል/#ቢቢሲኒውስአማርኛ/ #ሙሉታሪኩንያግኙ የፌስቡክ ገጻችን: BBC News Amharic ተጨማሪ መረጃ: ለቃለመጠይቅና ማወቅ የሚፈልጉት ነገር ካለ ከቢቢሲ ወርልድ ሰርቪስ ግሩፕ ኮምዩኒኬሽ [email protected] ቢቢሲ ኒውስ አፍሪካ በተለያዩ ቋንቋዎች አህጉሪቱን የሚመለከቱ ዝግጅቶችን በሬዲዮ፣ በቴሌቪዥንና በድረ ገጽ ያቀርባል። ቢቢሲ ካሉት የቋንቋ አገልግሎቶች መካከል አማርኛ፣ ኦሮምኛና ትግርኛ ይገኙበታል።
news-51368390
https://www.bbc.com/amharic/news-51368390
ኮሮናቫይረስና የነዳጅ ዘይት ምን አገናኛቸው?
ኮሮናቫይረስ የማይነካው ነገር እንደሌለ እየታየ ነው። በየሰበብ አስባቡ እያሻቀበ የነበረውን ነዳጅ ዘይትን ሊነካው ዳርዳር እያለ ነው።
በሽታው አሳሳቢ ደረጃ ላይ በደረሰበት በአሁኑ ጊዜ የዓለማችን ትልልቆቹ የነዳጅ አምራች አገራት በሽታው ካስከተለው ችግር ለመቋቋም በሚያደርጉት ጥረት ውስጥ ምርታቸው ሊቀንስ ይችላል እየተባለ ነው። የነዳጅ ዋጋን ለመደገፍ እርምጃ እንዲወሰድ እየተጠየቀ ባለበት በአሁኑ ወቅት የነዳጅ አምራች አገራት ማህበር የሆነው ኦፔክ እና አጋሮቹ በዚህ ሳምንት ስብሰባ እንደሚቀመጡ እየተጠበቀ ነው። • ኮሮናቫይረስ፡ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች በቻይና • አባቱ በኮሮናቫይረስ የተጠረጠረው አካል ጉዳተኛ ታዳጊ ሞተ በጥር ወር መጀመሪያ ላይ የነዳጅ ዋጋ በዓመት ውስጥ ከታየው ከፍ ብሎ በ20 በመቶ ካሻቀበ በኋላ አሽቆልቁሎ ዝቅተኛው ዋጋው ላይ ይገኛል። ስለምን ይህ የቫይረስ ወረርሽኝ እንዲህ ያለው ከፍተኛ ተጽእኖን በዓለም አቀፉ የኃይል ገበያ ላይ ሊያስከትል ቻለ? የነዳጅ ዋጋ ለምን በከፍተኛ ሁኔታ ቀነሰ? የቻይናዊያን አዲስ ዓመት የበዓል ጊዜ በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍል በበሽታው ምክንያት በመራዘሙና የጉዞ እገዳ በመደረጉ ፋብሪካዎች፣ ቢሮዎችና መደብሮች ዝግ ሆነው ይገኛሉ። ይህም ማለት አስከ 14 ሚሊዮን በርሜሎችን በቀን ውስጥ የምትጠቀመውና የዓለማችን ትልቋ የድፍድፍ ነዳጅ ገዢ አገር የሆነችው ቻይና ማሽኖቿን ለማንቀሳቀስ፣ ለተሽከርካሪዎችና ለኤሌክትሪክ ኃይል ወትሮ ከምትፈልገው ነዳጅ ዘይት በእጅጉ የቀነሰውን እንድትጠቀም አድርጓታል። በወረርሽኙ ምክንያት በርካታ አየር መንገዶች ወደ ቻይና የሚያደርጓቸውን በረራዎች በማቋረጣቸው የተነሳና በቻይና ውስጥ ባለው የጉዞ እገዳ ሳቢያ በረራዎች በመቀነሳቸው ለአውሮፕላን ነዳጅ ያለው ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሰዋል ተብሎ ይታሰባል። • ኮሮናቫይረስ፡ ምን ያህል አሳሳቢ ነው? • ካሜሮናዊው በኮሮናቫይረስ በመያዝ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሆነ ብሉምበርግ በዚህ ሳምንት እንደዘገበው የቻይና ዕለታዊ የድፍድፍ ነዳጅ ፍጆታ በ20 በመቶ ቀንሷል። ይህም ማለት ብሪታኒያና ጣሊያን በአንድ ላይ በቀን የሚያስፈልጋቸውን ነው። በዚህም ሳቢያ በቻይና መንግሥት የሚተዳደረው የእስያ አህጉር ትልቁ የነዳጅ ማጣሪያ ሲኖፔክ በየቀኑ የሚያጣራውን የድፍድፍ ነዳጅ መጠን በ600 ሺህ በርሜሎች ቀንሷል። ይህም ከሥራው 12 በመቶው አቁሟል ማለት ሲሆን ከ10 ዓመታት በላይ ባለው ጊዜ ውስጥ ከፍተኛው ቅናሽ ነው። በነዳጅ ዘይት ላይ የታየው ከፍተኛ ቅናሽ የኃይል ኢንዱስትሪውን በከፍተኛ ደረጃ እንዳሳሰበው የዘርፉ ባለሙያዎች እየተናገሩ ነው። የወረርሽኙ ተጽእኖ በዓለም ኢኮኖሚ ላይ በነዳጅ ፍላጎት ላይ የተከሰተው ከፍተኛ ቅናሽ በቻይና ውስጥ የተከሰተውን የሥራ መቀዛቀዝን የሚያሳይ ግልጽ ምልክት ነው። በተጨማሪም ባለፉት 30 ዓመታት ውስጥ ቻይናን ካጋጠማት የኢኮኖሚ ዕድገት መቀነስ ክስተት ውስጥ ዝቅተኛው ማጋጠሙ ደግሞ የነዳጅ ፍጆታዋን የበለጠ ይቀንሰዋል ተብሏል። የተባሉት በቻይና የሳይንስ አካዳሚ ውስጥ ተመራማሪ የሆኑነት ዣንግ ሚንግ እንደሚሉት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በዓመቱ መጀመሪያ ላይ ባሉት ሦስት ወራት የአገሪቱን ዓመታዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ከ5 በመቶ በታች ሊያወርደው ይችላል። • "ኮሮናቫይረስ በአሜሪካ የሥራ ዕድልን ሊያሳድግ ይችላል" ያደጉት አገራት እድገታቸውን ለማጠናከር ትግል በሚያደርጉበት ጊዜ ቻይና የዓለማችን ሁለተኛዋ ግዙፍ ኢኮኖሚና ለዓለም የኢኮኖሚ ዕድገት አንቀሳቃሽ ሞተር ናት። የዓለም ገንዘብ ድርጅት ዳይሬክተር የሆኑት ክሪስታሊና ጆርጂዮቫ ባዚህ ሳምንት እንዳሉት ወረርሽኙ ቢያንስ ለአጭር ጊዜ የዓለም ኢኮኖሚ ዕድገትን ያቀዛቅዘዋል፤ ነገር ግን የወደፊቱን ለመናገር አሁን ጊዜው ገና እንደሆነም አመልክተዋል። ነዳጅ አምራቾች ምን ማድረግ አለባቸው? እያሽቆለቆለ ያለውን የነዳጅ ዋጋ ለማሳደግ ታላላቆቹ የዓለም ነዳጅ ዘይት አምራቾች ለገበያ የሚያቀርቡትን ምርት በከፍተኛ መጠን ለመቀነስ በሚያደርጉት ስብሰባ ላይ እንደሚወያዩ እየተነገረ ነው። የኮሮናቫይረስ ክስተት ለነዳጅ የለውን ፍላጎት እንዲቀንስ በማድረጉ ምክንያት የነዳጅ አምራችና ላኪ አገራት ማኅበር የሆነው ኦፔክ አባል የሆነችው ኢራን ሰኞ ዕለት እየወደቀ ያለውን የነዳጅ ዋጋ ለመደገፍ እርምጃዎች እንዲወሰዱ በይፋ ጠይቃለች። የኦፔክ አባል አገራትና ሩሲያ በዚህ ሳምንት ያደርጉታል ተብሎ በሚጠበቀው ስብሰባ ላይ በቀን ለገበያ ከሚያርቡት የነዳጅ ምርት ከ500 ሺህ እስከ 1 ሚሊዮን በርሜል የሚደርሰውን ለመቀነስ ይወያያሉ ተብሏል።
news-45803364
https://www.bbc.com/amharic/news-45803364
ኤልቲቪ ብሮድካስት ባለስልጣን ማስጠንቀቂያ እንዳልሰጠው ገለፀ
በቅርቡ በኤልቲቪ ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ሊቀ መንበር ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ከቤተልሄም ታፈሰ ጋር ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ለቴሌቭዥን ጣቢያው ማስጠንቀቂያ እንደሰጠ በማህበራዊ ሲነገር ነበር።
የኤልቲቪ የሰው ኃይል አስተዳደር አዲስ ብርሃኑ ግን ማስጠንቀቂያ እንዳልተሰጣቸው ለቢቢሲ በመግለፅ፤ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን ከሚዲያዎች ጋር ተደርጎ በነበረው የመገማገሚያ ውይይት ቃለ መጠይቁ ተነስቶ "ካለው የፖለቲካ ሁኔታ ጋር የማይጣጣምና ሁኔታውንም የሚያጋግል ስለሆነ ትክክል አይደለም" የሚል አስተያየት እንደተሰጣቸው ገልፀዋል። •በመኪና አደጋ የሞቱ የደምህት ወታደሮች ቁጥር አራት ደረሰ •መቀመጫቸውን ለማስተለቅ የሚታትሩ ሴቶች እየሞቱ ነው •የፍስሀ ተገኝ የቤተሰብ ፍለጋ ጉዞ ስብሰባው ላይ ተገኝተው እንደነበር የሚናገሩት አዲስ ኤልቲቪን ለብቻ ጠርቶ ማስጠንቀቂያ የሰጠ አካል እንደሌለ ገልፀዋል። ጉዳዩን እንደ ማስጠንቀቂያ እንደማይወስዱት የተናገሩት አዲስ ቃለ-መጠይቁ ከማህበራዊ ሚዲያ ላይ የወረደበት ምክንያት ከብሮድካስት ባለስልጣን አስተያየት ጋር የተገናኘ አይደለም ብለዋል። "ከማህበራዊ ሚዲያ ላይ ቃለመጠይቁን ያወረድነው በራሳችን ፍቃድ ነው። ጋዜጠኛዋን የግል ህይወት የሚነካና ስድብ ስለበዛ ጉዳዩን ለማቀዝቀዝ አውርደነዋል።" ብለዋል። በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ቤተልሄም ሥራ እንደለቀቀች ተደርጎ የሚነገረውም ፍፁም እውነት እንዳልሆነ ተናግረዋል። በሌላ በኩል ቤተልሄም ታፈሰ ከቢቢሲ ጋር በነበራት ቆይታ ብሮድካስት ባለስልጣን ቃለ መጠይቁ ከዩቲዩብ እንዲወርድ ቴሌቪዥን ጣቢያውን እንዳስጠነቀቀ እንዲሁም ''እኔም ከአሁን በኋላ አስተካክዬ እንደሰራ'' ነው ከቢሮዬ የተነገረኝ ትላለች። ቤቴሌሄም ትናንት ምሽት ቢቢሲ በጉዳዩ ላይ ያነጋገራቸው የኤልቲቪ የሰው ኃይል አስተዳደር አዲስ ብርሃኑ አስተያየት ትክክል አይደለም ትላለች። ''የግል አሰተያየታቸው እንደሆነ ነው የሚገባኝ'' ብላላች። ቤተልሄም አክላ እንደተናገረችው ''በጉዳዩ ላይ እኔን ሳትጠይቁኝ በሰራተኛ ቅጥር ላይ ያለችን ጉዳዩ ብዙም የማይመለከታትን ግለሰብ ማነጋጋራችሁ በዘገባው ቅር እንድሰኝ አድርጎኛል።'' ብላለች። ቢቢሲ በወቅቱ አዲስን ባናገራት ወቅት ስብሰባው ላይ መገኘታቸውንና ኤልቲቪ በስራው እንደሚቀጥል የተናገሩ ሲሆን ጨምረውም "ጋዜጠኛዋ ስራ ለመልቀቅ ብታስገባ ቀጥታ የሚመለከተው እኔን ነው" ብለዋል። ትናንት ምሽት ነዋሪነቱን አሜሪካን ሃገር ካደረገው የቅርብ አለቃዬ ነው ከምትለው የቴሌቪዥን ጣቢያው ባለቤት ጋር በጉዳዩ ላይ መነጋገሯን የምትናገረው ቤቲ ከአለቃዋ ጋር''በሥራዬም እቀጥላለሁ'' ብላለች። ኤልቲቪ የቴሌቪዥን ጣቢያም በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መልዕክት የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ሃላፊዎችን ጠርቶ እንዳናገረ ገልፀው፤ ባለስልጣኑ እንዲያስተካክሉም አስተያየት እንደተሰጣቸው አስፍረዋል። " ባለስልጣኑ ይስተካከሉ ባላቸው ጉዳዮች ማለት የቃላት አጠቃቀም፣ ወደ ብሄር ብሄረሰቦች ያዘነበሉ የሚመስሉ ጥያቄዎችና አስተሳሰቦች እንዲሁም መሰል ችግሮችን እንድናስተካከል ምክር አዘል ማሳሰቢያ ተሰጥቶናል" የሚል ፅሁፍ ሰፍሯል። በዩቲዩብ የሚገኘውን ፕሮግራም ከገፃቸው ላይ እንዲያነሱ ማሳሰቢያ እንደተሰጣቸው ገልፀው በትዕዛዙም መሰረት በትናንትናው እለት ማንሳታቸውን አስታውቀዋል። በማህበራዊ ሚዲያ የሚራገቡት ጣቢያው ሊዘጋ ነው፣ ጋዜጠኛዋ ተባራለች የሚሉት ትክክለኛ መረጃም እንዳልሆነ አስፍረዋል። እስካሁን በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን እንዲሰጡን የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ኃላፊዎችን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ባይሳካም ጥረት ማድረጋችንን እንቀጥላለን።
49340956
https://www.bbc.com/amharic/49340956
የስኮላስቲክ አፕቲቲዩድ ፈተና ውጤትን የሚያጣራ ኮሚቴ ተዋቀረ
በዘንድሮው የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ አንዳንድ ተማሪዎች የ ስኮላስቲክ አፕቲቲዩድ (ሳት) ፈተና ውጤታቸው ላይ ቅሬታ እያሰሙ ነው።
በድሬዳዋ ከተማ የተለያዩ የመሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የነበሩና ውጤታቸው ላይ ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎችና ወላጆች ዛሬ ወደ ትምህርት ቢሮ ማምራታቸውን ገልጠው የትምህርት ቢሮ ኃላፊዋ ቅሬታቸውን ለበላይ ኃላፊዎች በአካል በመሄድ እንደሚያቀርቡ እንደነገሯቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። በድሬዳዋ ቅድስት ቤዛ የመሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆነችውና ለቢቢሲ ቅሬታዋን ያቀረበችው ተማሪ አጠቃላይ ሌሎች የትምህርት አይነቶች ላይ ቅሬታ ቢኖራትም የስኮላስቲክ አፕቲትዩድ ውጤቷ ግን ከሚጠበቀው በታች እንደሆነ ታስረዳለች። • በአገር ውስጥ ያለው መፈናቀል ሕገ ወጥ ስደትን አባብሷል? • የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት የምግብ ምርት ከውጪ እንዳይገባ አዘዙ • ዕፅ በማዘዋወር የተጠረጠረው ኬንያዊ ቱጃር ቤት በፖሊስ እየተበረበረ ነው "የእኔ 35 ነው ከመቶ፤ የጓደኞቼም ሐያ እና ከዚያ በታች ነው" በማለት በአጠቃላይ ውጤት 400ና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎችን ውጤት በማጣቀስ ያለውን ልዩነት ታሳያለች። ዛሬ በድሬዳዋ ትምህርት ቢሮ ተገኝተው ቅሬታቸውን ያቀረቡት ወላጆችና ተማሪዎች የሮትቶዳም፣ ብስራተ ገብርዔል፣ እና የቤዛ መሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች እንደሆኑ ለማወቅ ችለናል። የመቀሌ ከተማ ነዋሪ የሆነችው ተማሪ በበኩሏ በሌሎች የትምህርት አይነቶችም ባመጣችው ውጤት ጭምር ደስተኛ አለመሆንዋን ትናገራለች። የአፕቲትዩድን ውጤቷም ቢሆን ከጠበቀችው በታች መሆኑን በመናገር "አፕቲትዩድ ላይ ተሸላሚ ተማሪ ሳይቀር ነው ዝቅተኛ ውጤት ያመጣው። እንዴት ብሎ ነው አንድ ተማሪ 6፣ 7፣ 0 ከ100 የሚያገኘው?" ስትል ትጠይቃለች። "እኔ ለፈተናው ካደረግኩት ዝግጅት አንጻር ያገኘሁት ውጤት ፈጽሞ አይመጥነኝም" በማለትም ቅሬታዋን ለቢቢሲ ገልጣለች። ተማሪዎቹ ያቀረቡትን ጥያቄ መስማታቸውን የሚናገሩት የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አርአያ ገ/እግዚአብሔር ቅሬታው እንደደረሳቸው ለቢቢሲ አረጋግጠው ለማጣራት ኮሚቴ ማዋቀራቸውን ተናግረዋል። አሁን እያስተናገድን ነው ያሉት አቶ አርአያ ማንኛውም ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች ቅሬታቸውን በግል ቅሬታቸውን ማቅረብ እንደሚችሉ ተናግረዋል። ውጤቱ በኢንተርኔት የተለቀቀው ማንኛውም ቅሬታ ያለው አካል አይቶ ቅሬታውን ማቅረብ እንዲችል ነው የሚሉት አቶ አርአያ የመጨረሻ የሚሆነው በወረቀት ታትሞ የሚሰጠው ውጤት መሆኑን ይጠቅሳሉ። ቅሬታውን በአካል፣ በስልክ ካልሆነም በድርጅቱ ድረገፅ ላይ ማቅረብ እንደሚቻል ገልፀው ቅሬታ አቅራቢው የፈተና መለያ ቁጥሩን፣ ትምህርት አይነቱን አሟልተው ጥያቄ ቢያቀርቡ ከሰርትፍኬት ሕትመት በፊት ይስተናገዳሉ ብለዋል።
news-54145138
https://www.bbc.com/amharic/news-54145138
ኮሮናቫይረስ ፡ ከአንዲት ዶክተር በስተቀር ሁሉም ዶክተሮች የተሰደዱባት ከተማ
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የመን ሲገባ በከተማዋ አደን አገልግሎት የሚሰጠው ሆስፒታል አንድ ብቻ ነበር። በአደን ከተማ ከአንድ ሚሊየን በላይ ሰዎች እንደሚኖሩ ይገመታል።
ዶክተር ዞሃ ታዲያ በዚህ ወቅት በሽታውን በመፍራትና የሕክምና ግብዓቶች ባለመኖራቸው አብዛኞቹ ዶክተሮች ከተማዋን ጥለው ወጥተዋል። በዚህ ጊዜ በከተማዋ የኮቪድ-19 ታማሚዎችን ለማከም በፈቃዷ የቀረችው ዶክተር ዞሃ ብቻ ናት። በጦርነት በፈራረሰችውና ምንም በሚባል ደረጃ በሥራ ላይ ያለ ሆስፒታል በሌላት ከተማ፤ የወረርሽኙ ስርጭት ሲጨመር ምን ልትሆን እንደምትችል ማሰብ ቀላል ነው። እዚህ ላይ የአብዱልከሪም ያለፈበትን ፈተና እናንሳ። አብዱልከሪም አሊ የዚህችው ከተማ ነዋሪ ነው። ታዲያ አንድ ቀን አባቱ አሊ በጠና ታመሙበት። ሰውነታቸው እየደከመ መምጣቱን ተመለከተ። ለክፉ የማይሰጣቸው ቀላል ጉንፋን ያዳከማቸው ነበር የመሰለው። ከዚያ ግን እየባሰባቸው ሲመጣ ወደ ሆስፒታል ይዟቸው ሄደ። ያን ጊዜ ሌሎች ጥቂት ሆስፒታሎች ነበሩ። ራጅ ከተነሱ በኋላ አባቱ የደረት ኢንፌክሽን እንዳጋጠማቸው ተነገረው። በወቅቱ ፅኑ ሕሙማን ክፍል መግባት ያስፈልጋቸው ነበር። ይሁን እንጂ ዶክተሮቹ ሆስፒታሉ እንደዚህ ዓይነት የጤና እክሎችን እንዳማይስተናግድ ገልጸው፤ ኮሮናቫይረስ ሊኖርባቸው ይችላል በሚል አባቱ በሆስፒታሉ መቆየት እንደማይችሉ አረዱት። አብዱልከሪም አባቱን ይዞ አምስት ሆስፒታሎችን አዳረሰ። ግን ቫይረሱን በመፍራትና የበሽታ መከላከያ የሕክምና ግብዓት ስለሌለ የትኛውም ሆስፒታል ተቀብሎ ሊያክምለት አልቻለም። በዚህም ሳቢያ አብዛኞቹ ዶክተሮች ጥለው በመሰደዳቸው ከአንድ ሆስፒታል በስተቀር አብዛኞቹ ሆስፒታሎች ዝግ ነበሩ። በሆስፒታሉ የኮቪድ-19 ታማሚዎችን ለማከም ፈቃደኛ የሆነች ብቸኛዋ ዶክተር ዞሃ ነበረች። አብዱልከሪም ዶ/ር ዞሃን ያገኛት ለአንድ ሳምንት ያህል ሲያፈላልጋት ቆይቶ ነው። ዶ/ር ዞሃ፤ አብዱልከሪም ሲያገኛት "አባቴ ሊሞት ነው! እባክሽ!" እያለ እንደተማፀናት ትናገራለች። እርሷም አልጋም ሆነ ኦክስጅን እንደሌለ ነገረችው። በእርግጥ አባቱ ተጎድተው ነበር፤ ለመተንፈስም ይቸገሩ ነበር። አብዱልከሪም "አባቴ ሊሞት ነው. . . እባክሽ ዶክተር" እያለ በተማጽኖ ከመጮህ በዘለለ ሌላ የሚያደርገው ነገር አጣ። ዶ/ር ዞሃም ሁኔታውን አይታ ምንም የምትረዳቸው ነገር ባይኖርም አባቱ ሆስፒታሉ እንዲገቡ አደረገች። ያለውን የኦክስጅን ጭምብል አጠለቁላቸው። ይሁን እንጅ ሊተርፉ አልቻሉም። ሆስፒታል ከገቡ ከ15 ደቂቃ በኋላ ሕይወታቸው አለፈ። የየመን መንግሥት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመዋጋት ምንም ያደረገው ቅድመ ዝግጅት አልነበረም። በሁለት የጦርነት ግንባሮች አጣብቂኝ ውስጥ ነበር ያለው። በሰሜን ለስድስት ዓመታት በዘለቀው ከሁቲ አመፂያን ጋር የሚያደርገው ፍልሚያ፤ በሌላ በኩል አደንን ለመቆጣጠር በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከሚደገፈው ኃይል ጋር የሚያደርገው ጦርነት። በዚህም ሳቢያ ኮሮናቫይረስ በአገሪቱ ሲሰራጭ ጉዳቱን የከፋ አድርጎታል። አንድ በከተማዋ የሚገኝ የመቃብር ቆፋሪም እንዲህ ዓይነት ነገር ገጥሞት እንደማያውቅ ተናግሯል። "ከጦርነት በላይ አስከፊ ነው" ሲል ነበር ሁኔታውን የገለጸው። መቃብር ቆፋሪው ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከመግባቱ በፊት በአማካይ በቀን 10 ሰዎችን ነበር የሚቀብረው። "አስክሬን ወደ እኛ ይመጣል፤ ነገር ግን እንደ አሁኑ አይደለም" ብሏል። በአንድ ወር ውስጥ 1 ሺህ 500 አስክሬን እንደቀበረ በመግለጽ። ወሩን ሙሉ ዶክተር ዞሃ ካለችበት ሆስፒታል መግባት የቻሉ ሰዎች ፍፃሜም ይኽው ነበር። አሁን ግን ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን በአካባቢው ገብተዋል። "ቡድኑ ከመድረሱ በፊት እያንዳንዱ ታማሚ ከሆስፒታሉ የሚወጣው አስክሬኑ ነበር። አሁን አንዳንዶቹ ታማሚዎች አገግመው በእግራቸው መውጣት ችለዋል" ትላለች ዶ/ር ዞሃ። ልዩነቱም የገሃነምና የገነት ያህል እንደሆነ በመግለጽ።
news-51396099
https://www.bbc.com/amharic/news-51396099
በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሙሽሮች ያልታደሙበት የሠርግ ድግስ
ሁሌም የሠርግ ዝግጅቶች እንደታቀዱት አይከናወኑም፤ እየጨመረ የመጣው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ደግሞ አንድ የሠርግ ሥነ ሥርዓትን ሙሽራውና ሙሽራዋ በሌሉበት እንዲካሄድ አስገድዷል።
ሙሽሮቹ ጆሴፍ ይውና ባለቤቱ ካንግ ቲንግ ሙሽሮቹ ጆሴፍ ይውና ባለቤቱ ካንግ ቲንግ ከሠርጋቸው ቀን ጥቂት ቀናት ቀደም ብለው ነበር ከቻይና ወደ አገራቸው የተመለሱት። በዚህም ሳቢያ ሠርጉ ላይ እንዲገኙ የተጋበዙት ሰዎች በሥነ ሥርዓቱ ለመታደም ስጋት እንዳላቸው በመግለጻቸው፤ ሙሽሮቹ የእንግዶቹን ፍርሃት ለማስወገድ አንድ ዘዴ ፈጠሩ። በዚህም ሙሽሪትና ሙሽራው የደስታቸውን ዕለት አብረዋቸው እንዲያሳልፉ የጋበዟቸው እንግዶች ከሚገኙበት አዳራሽ ርቀው ምስላቸውን በቀጥታ በማስተላለፍ የጋብቻ ሥነ ሥርዓታቸውን ፈጽመዋል። • ኮሮናቫይረስ፡ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች በቻይና • የኮሮናቫይረስ ስጋትና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጥንዶቹ ከወዳጅ ዘምድ ርቀው በሥነ ሥርዓቱ ላይ ማድረግ የሚጠበቅባቸውን በሙሉ ሲያከናውኑና ንግግር ሲያደርጉ በቪዲዮ አማካይነት በአዳራሽ ውስጥ ተቀምጠው ለጠበቋቸው ታዳሚዎች ታይተዋል። ሴንጋፑር ውስጥ እስካሁን በበሽታው የተያዙ 28 ሰዎች የተገኙ ሲሆን ይህም ከቻይና ውጪ ከፍተኛ ተጠቂዎች ካለባቸው አገራት መካከል ከጃፓን ቀጥላ ሁለተኛ እንድትሆን አድርጓታል። ምን አማራጭ አለ? ከቻይና ሁናን ግዛት የመጣችው ሙሽሪት ካንግ ከቤተሰቧ ጋር አዲስ ዓመትን ለማክበር ከሳምንታት በፊት ወደ አገሯ ስትሄድ ሙሽራው ይውም ተከትሏት ሄዶ ነበር። ሁናን ግዛት ደግሞ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ተነስቶባታል የምትባለው ግዛት ጎረቤት ናት። ሙሽራው ይው ለቢቢሲ እንደተናገረው በተለይ የሄዱበት የሁናን ግዛት አካባቢ በጣም ገጠር በመሆኑ የተነሳ ስለበሽታው ምንም አይነት ፍርሃት አልነበረም። ከዚያም ጥንዶቹ ለጥቂት ቀናት በመቆየት በዓሉን አክብረው በሁለት ቀናት ውስጥ በማዕከላዊ ሴንጋፑር ውስጥ በሚገኘው ኤም ሆቴል ውስጥ በደገሱት ሠርጋቸው ላይ ለመገኘት ተመለሱ። • በሽታውን ለመደበቅ ባለስልጣናት ዶክተሮችን ያስፈራሩ ነበር • ኮሮናቫይረስ፡ ምን ያህል አሳሳቢ ነው? በእርግጥ ጥንዶቹ ጋብቻቸውን የፈጸሙት በጥቅምት ወር ላይ በሙሽሪት አገር ቻይና ውስጥ ሲሆን እዚያም ደግሰው እንግዶቻቸውን ጋብዘዋል። ይህ ሴንጋፑር ውስጥ ያዘጋጁት ሁለተኛው ትልቁ የዕራት ግብዣ በመጀመሪያው ላይ ወደ ቻይና ሄደው ሠርጉን ለመታደም ያልቻሉ የሙሽራውን ቤተሰብ አባላት ለመጋበዝ የተዘጋጀ ነበር። በእስያ ውስጥ ሁለት የሠርግ ሥነ ሥርዓቶችን ማዘጋጀት ብዙም ያልተለመደ አይደለም። በተለይ ደግሞ ጥንዶቹ ከሁለት የተለያዩ አገራት የመጡ ከሆነ በተለያዩ ቦታዎች ድግስ ይኖራል። ጥንዶቹ ከወላጆቻቸው ጋር በ'ስክሪን' ላይ ሲታዩ የታዳሚው ስጋት በሠርጉ ላይ እንዲታደሙ የተጠሩት ሰዎች ሁለቱ ጥንዶች ከቻይና መመለሳቸውን ሲሰሙ በሥነ ሥርዓቱ ላይ የመገኘታቸው ነገር እያሳሰባቸው መጣ። "አንዳንድ ጥሪ የተደረገላቸው ሰዎችም እንደማይመጡ መናገር ጀምረው ነበር።" ይላል ሙሽራው። "እኛም የሠርጉን ሥነ ሥርዓት ለሌላ ጊዜ ለማስተላለፍ ፈልገን የነበረ ቢሆንም፤ ሆቴሉ ሁሉም ነገር መዘጋጀቱንና ምንም ድርድር እንደማይኖር በመግለጽ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀረ። በዚህም ምንም አማራጭ ስለሌለን በዕቅዳችን መሰረት ሠርጋችንን ለማከናወን ወሰንን።" • ኮሮናቫይረስና የነዳጅ ዘይት ምን አገናኛቸው? • ለመከላከል ብቻ ሳይሆን ስም ለማውጣት ያስቸገረው አዲሱ ቫይረስ የሠርጉን ታዳሚዎች ፍርሃት ለማስወገድም ጥንዶቹ እንግዶቹ በሚገኙበት ሥፍራ ላይ ላለመገኘት ወሰኑ። "ይህንን ለታዳሚዎቹ ገልጸን በቪዲዮ ኮንፈረንስ አማካይነት ሠርጉን እንደምንታደም ስንነግራቸው አንዳንዶቹ ደነገጡ" የሚለው ሙሽራው ያው፤ "አዳራሹ ውስጥ ብንሆን ኖሮ የሚኖረው ድባብ የተለየ ይሆን ነበር፤ ታዳሚዎቹ ስለበሽታው በማሰብ ይጨነቁ ነበር" ብሏል። "መጀመሪያ ላይ ቤተሰቦቼ በሃሳቡ ደስተኛ አልነበሩም፤ ነገር ግን ቆይተው ተስማምተውበታል።" ከቻይና መምጣት የነበረባቸው የሙሽሪቷ ካንግ እናት በቫይረሱ መስፋፋት ምክንያት በተፈጠረ ስጋት ምክንያት በተጣለ ተደራራቢ የጉዞ እገዳ ሳቢያ በሠርጉ ላይ መገኘት ሳይችሉ ቀርተዋል። ጥንዶቹ የሠርግ ሥነ ሥርዓታቸውን የታደሙበት ክፍል ውስጥ ሠርግ በቪዲዮ ኮንፈረንስ በመጨረሻም ለሠርጉ ከተጋበዙት 190 ሰዎች መካከል 110ሩ በዝግጅቱ ላይ ለመታደም የቻሉ ሲሆን፤ ሌሎቹ በተለያዩ ምክንያቶች ሳይገኙ ቀርተዋል። በሠርጉ ዕለት ምሽት የተጠሩት ከአንድ መቶ በላይ እንግዶች በሆቴሉ አዳራሽ ውስጥ ሆነው ሙሽሮቹ ደግሞ በሆቴሉ አንድ ክፍል ውስጥ በመሆን በቪዲዮ ኮንፈረንስ አማካይነት ምስላቸው በትልቅ የሸራ ስክሪን ላይ እየታየ አስፈላጊውን ሥነ ሠርዓት ሁሉ አከናውነው ከታዳሚው ጋር ደስታቸውን ተጋርተዋል። "ጠሪ አክብረው የመጡትን እንግዶች አመስግነን የተዘጋጀውን እራት እየበሉ እንዲዝናኑ ጋብዘናቸዋል" ይላል ሙሽራው ይው። • አውስትራሊያ ከቻይና ተመላሾችን ራቅ ወዳለች ደሴት ማጓጓዝ ጀመረች ሆቴሉም ለጥንዶቹ ሻምፓኝ ያቀረበላቸው ሲሆን እነሱም ክፍላቸው ውስጥ ሆነው ክዳኑን አፈናጥረው በመክፈት ጽዋቸውን አንስተው ለታዳሚው የምስጋና ንግግር አድርገዋል። ይህ ሙሽሮቹ በአንድ ክፍል ውስጥ ሆነው ያከናወኑት ሥነ ሥርዓት በሙሉ በአዳራሽ ውስጥ ሆነው ሠርጉን ለታደሙት እንግዶች በቪዲዮ በቀጥታ ተላልፏል። "በዚህ ሁኔታ አላዘንንም፤ ነገር ግን ቅር ብሎናል" ሲል ሙሽራው ይው ለቢቢሲ ተናግሯል። አክሎም "ምንም አይነት ምርጫ አልነበረንም፤ ስለዚህም የሚጸጽተን ነገር የለም።"
news-55984272
https://www.bbc.com/amharic/news-55984272
ኤለን መስክ 1.5 ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ ቢትኮይን መግዛቱን ተከትሎ መገበያያው ከፍተኛ ጭማሪ አሳየ
የኤለን መስክ የመኪና ኩባንያ ቴስላ 1.5 ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ ቢትኮይን በታህሳስ ወር መግዛቱን አስታወቀ። ኩባንያው ገንዘቡን ወደፊት መቀበል እንደሚጀምርም ጨምሮ ይፋ አድርጓል።
ይህ ዜና እንደተሰማ የቢትኮይን ዋጋ በ 17 በመቶ ወደ 44 ሺህ 220 አሻቅቧል ተብሏል። ቴስላ ኩባንያው በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴው የማይጠቀምበትን ጥሬ ገንዘብ ዳጎስ ያለ ትርፍ ለማግኘት በማሰብ ይህንን ማድረጉን ገልጿል። መስክ በትዊተር ገፁ ላይ "#bitcoin" የምትል ቃል ማኖሩን ተከትሎ ዋጋው ማሻቀቡ ተሰምቷል። ከቀናት በኋላ ከሰሌዳው ላይ ያጠፋው ቢሆንም ስለ ቢትኮይን እና ሌላ ክሪፕቶከረንሲ፣ ዶጅኮይንን ጨምሮ፣ ግን ማውራቱን ቀጥሎበታል። መስክ ስለ ዶጅኮይን ማውራቱን ተከትሎ ዋጋው በ50 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ቴስላ በታሕሳስ ወር ላይ " የኢንቨስትመንት ፖሊሲዬ ላይ ማሻሻያ አድርጌያለሁ" ያለ ሲሆን ማንም ግለሰብ "በተቀማጭ ንብረቶች (digital assets)" ማለትም ዲጂታል ከረንሲዎች (የመገበያያ መንገዶች)፣ በወርቅ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት የለውም ብሎ ነበር። ኩባንያው 1.5 ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ ቢትኮይን መግዛቱን ያስታወቀ ሲሆን ወደፊትም " ዲጂታል ንብረቶችን ሊገዛ እና ሊያስተዳድር" እንደሚችል ገልጿል። "በተጨማሪም ወደፊት በሥራ ላይ ባሉ ሕጎች ላይ ተመስርተንና መጀመሪያ ላይ ውሱን በሆነ መልኩ ምርቶቻችንን በቢትኮይን መሸጥ እንጀምራለን ብለን አንጠብቃለን" ብሏል። መስክ ከሳምንት በፊት በትዊተር ሰሌዳው ላይ ቢትኮይን በኢንቨስተሮች ከፍተኛ ተቀባይነት ለማግኘት "ጫፍ ላይ ደርሷል" ብሎ ጽፎ ነበር። ይህ የቴስላ እርምጃ ለክሪፕቶከረንሲ "ማርሽ ቀያሪ" ነው ሲሉ ባለሙያዎች ተናግረዋል። ክሪፕቶከረንሲ ላይ ምርምር የሚያደርገው ሜሳሪ የተሰኘው ተቋም ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ኤሪክ ተርነር " የቴስላ ወደ ቢትኮይን መግባትን ተከትሎ ኩባንያዎች ቢትኮይን ለመግዛት ሲሽቀዳደሙ ልናይ እንችላለን" ብለዋል። "አሁን በዓለም ላይ ትልቁ ኩባንያ ቢትኮይን አለው ማለት ቴስላ ላይ ኢንቨስት ያደረገ ባለሃብት በሙሉ . . .ተጋልጦ አለው ማለት ነው።" ነገር ግን የMarkets.com አናሊስት የሆነው ኒይል ዊልሰን ግን ቢትኮይን "በጣም የሚዋዥቅ" ክሪፕቶከረንሲ ነው ሲል ያስጠነቅቃል። "ቴስላ አሁን ከፍተኛ የሆነ አደጋን ሊወስድ ነው፤ ይህ በርካታ ባለሃብቶችን ላያስጨንቃቸው ይችላል። ነገር ግን አንዳንድ ወግ አጥባቂዎችን ግድ ይላቸዋል" ብሏል። ከቅርብ ወራት ወዲህ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ያሳየው ቢትኮይን በዚህ ዓመት ከፋይናንስ ተቋማት ድጋፍ እያገኘ መጥቷል። የዓለማችን ግዙፉ የገንዘብ አስተዳዳሪ ብላክሮክ የተወሰኑ ፈንዶቹ በከረንሲው (በመገበያያው) ኢንቨስት እንዲያደርጉ ውሳኔ አሳልፏል። ነገር ግን አሁንም ማዕከላዊ ባንኮች ክሪፕቶከረንሲን በአይነ ቁራኛ ነው የሚመለከቱት። በጥቅምት ወር የባንክ ኦፍ ኢንግላንድ ገዢ አንድሪው ቤይሊ፣ ቢትኮይንን እንደ ክፍያ ለሚጠቀሙ አካላት ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል። ቢትኮይንን በክፍያ የሚጠቀሙ ሰዎችንም ሲመክሩ ዋጋው በጣም የሚዋዥቅ መሆኑን ባለሃብቶች ሊያውቁ ይገባል ብለዋል። ቢትኮይን ምንድነው? ቢትኮይን ማለት በቀላል ቋንቋ፤ ዲጂታልገንዘብ+መገበያያ በማለት ማጠቃለል ይቻላል። ይህ መገበያያ በኪሳችን ተሸክመን እንደምንዞረው የብር ኖት ወይም ሳንቲም ሳይሆን 'ኦንላይን' የሚቀመጥ ዲጂታል ገንዘብ ነው። • በአሁኑ ወቅት በጣም ተፈላጊ የሆኑ የዲጂታል ዘርፍ ሥራዎች የትኞቹ ናቸው? ሌላው የቢትኮይንና የተቀሩት የክሪይፕቶከረንሲዎች ልዩ ባህሪ በመንግሥታት እና በባንኮች አለመታተማቸው እንዲሁም ቁጥጥር አለመደረጉ ነው። ቢትኮይን የሚፈጠረው 'ማይኒንግ' በሚባል ሂደት ነው። በመላው ዓለም በኔትወርክ በተሳሰሩ ኮምፒውተሮች ቁጥጥር ይደረግበታል። ቢትኮይንን የፈጠረው ግለሰብ/ቡድን በዓለም ላይ 21 ሚሊዮን ቢትኮይኖች ብቻ እንዲፈጠሩ ገደብ እንዳስቀመጡ ይታመናል። የብሎክቼይን መረጃዎች እንደሚያሳዩት እስካሁን 17 ሚሊዮን ያህል ቢትኮይኖች ማይን ተደርገዋል።
news-46395979
https://www.bbc.com/amharic/news-46395979
ዓለማችን "ክትባቱ ቸል በመባሉ ምክንያት" የኩፍኝ ወረርሽኝ ያሰጋታል ሲል አለም አቀፉ ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ
በአለም አቀፍ ደረጃ የኩፍኝ ወረርሽኝ እንዳለ የጠቀሰው የአለም አቀፉ የጤና ድርጅት ዘገባ ባለፈው አመት ብቻ አንዳንድ ሀገራት "ረዘም ላለና ለከፋ ወረርሽኝ" ተጋልጠው ነበር ብሏል።
የአለም ጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነ በሁሉም የአለማችን ሀገራት በ2016 ከታየው በ2017 ሰላሳ በመቶ ጨምሯል። ባለሙያዎች ለቁጥሩ መጨመር እንደምክንያት ያነሱት ስለ ክትባቱ ያለው የተሳሳተ መረጃንና የህክምና አገልግሎት ስርአቶች መውደቅን ነው። የኩፍኝ ክትባት የሚሊየኖችን ህይወት ይታደጋል ሲሉም ያስረዳሉ። • 'ቆሞ የቀረው' የተቃውሞ ፖለቲካ? • በአዲስ አበባ አፍላ ወጣቶች በከፍተኛ መጠን በኤች አይቪ እየተያዙ ነው • የታገቱት ሕንዳውያን ድረሱልን እያሉ ነው ኩፍኝ ከሰው ወደ ሰው በከፍተኛ ሁኔታ የሚተላለፍ ሲሆን በወቅቱ ካልታከመም የአይን ብርሃንን እስከማጣት ሊያደርስ፣ ለሳንባ ምች፣ ለአንጎል እብጠትና ለኢንፌክሽን ያጋልጣል። የአለም አቀፉ ጤና ድርጅትና የአሜሪካ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል በጋራ ያወጡት ጥናት ኩፍኝን ላለፉት 17 ዓመታት ሲከታተሉ እንደነበር ያሳያል። ባለሙያዎቹ እንደሚሉት ከ17 ዓመት ወዲህ የኩፍኝ ወረርሽኝ በከፍተኛ መጠን የጨመረ ነው። ይህ የመጀመሪያው አመት ሲሆን 110 ሺህ ከኩፍኝ ጋር ተያያዥ የሆኑ ሞቶችም ተመዝግበዋል። ባለሙያዎቹ በዚህ አመትም ያለው እንቅስቃሴ በተመሳሳይ መልኩ መቀጠሉ ያሳሰባቸው ሲሆን ይህም በአውሮጳ የክረምት ወራት ተመሳሳይ የታማሚዎች ቁጥር አእንዲመዘገብ አድርጓል ይላሉ። ከዚህ በፊት በሽታው ጠፍቶባት የነበረችው ቬንዚዌላ የጤና ስርዓቷ በምጣኔ ሀብትና የፖለቲካ ቀውስ ምክንያት ከወደመ በኋላ ከፍተኛ የተጠቂዎች ቁጥር ተመዝግቦባታል። በአሁኑ ወቅት ከሀገር ሀገር በርካታ ሰዎች መንቀሳቀሳቸው በሽታው በፍጥነት ሊዛመት ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል። ባለፈው ዓመት በዩክሬን፣ ጣሊያን፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመንና ግሪስ የኩፍኝ ወረርሽኝ መጨመር ታይቷል። “ወደ ሃገራችን ጤነኛ ሰው ይዘን እንመለሳለን ወይ የሚል ስጋት አለኝ”
news-42645131
https://www.bbc.com/amharic/news-42645131
የካሊፎርኒያ መሬት መንሸራተት አደጋ ተጎጂዎች ቁጥር እየጨመረ ነው
የካሊፎርኒያ የመሬት መንሸራተት እስካሁን የ17 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈ ሲሆን አሁንም በአስራዎቹ የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በፍርስራሽ ውስጥ እንዳሉ እየተዘገበ ይገኛል።
ሳንታ ባርብራ በተሰኘው ወረዳ 28 ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው የአካቢቢው ባለሥልጣናት ተናግረዋል። ከ100 በላይ መኖሪያ ቤቶች ከጥቅም ውጭ ሲሆኑ ሌሎች 300 የሚሆኑት ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። በርክሊ ጆንሰን የተባለ የአደጋ ጊዜ ሠራተኛ አንዲት የሁለት ዓመት ህፃን ከፍርስራሽ ስር በሕይወት ብትገኝም ከባድ አደጋ ስለደረሰባት ወደ ሕክምና መስጫ ቦታ መወሰዷን ተናግሯል። "በሕይወት መገኘቷ በራሱ ለእኔ ተዓምር ነው" ሲል እንባ የተናነቀው በርክሊ ለሳንታ ባርብራ ጋዜጠኞች ተናግሯል። አክሎም የገዛ ቤቱ ከጥቅም ውጪ እንደሆነና ከባለቤቱ ጋር በመሆን ህፃን ልጃቸው ሊያድኑ እንደቻሉ አሳውቋል። የወረዳዋ ጥበቃ ኃላፊ ቢል ብራውን እንዳሳወቁት ምንም እንኳ 50 የሚሆኑ ሰዎችን ሕይወት መታደግ ቢቻልም 13 ሰዎች የት ይግቡ የት ምን ዓይነት ፍንጭ የለም። መሬት መንሸራተቱ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰባት የካሊፎርንያ ግዛት ደቡባዊ ክፍል ታዋቂ አሜሪካውያን ለመኖሪያነት የሚመርጧት ናት። ከእነዚህም መካከል የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢዋ ኤሌን ዲጀነረስ እና አፍሪካ-አሜሪካዊቷ የሚድያ ሴት ኦፕራ ዊንፍሬይ ይገኙበታል። ባለፈው ወር በካሊፎርንያ ግዛት የደረሰው ሰደድ እሣት መሬቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረሱ ምክንያት አሁን የጣለው ከፍተኛ ዝናብ ለመሬት መንሸራተቱ እንዳጋለጠ ባለሙያዎቹ እየዘገቡ ይገኛሉ። የአሜሪካ አደጋ ጊዜ መስሪያ ቤት እንዳስታወቀው አካባቢው ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ለመሰል አደጋዎች የተጋለጠ ነው። በመሬት መንሸራተቱ ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ የካሊፎርንያ ግዛት ነዋሪዎች አካባቢውን በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ለቀው ለመውጣት ተገደዋል።
news-54595826
https://www.bbc.com/amharic/news-54595826
በፈረንሳይ አንገቱን ለተቀላው መምህር በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ድጋፋቸውን አሳዩ
በመላው ፈረንሳይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አንገቱን ተቀልቶ ለተገደለው መምህር ድጋፋቸውን ለመስጠት አደባባይ ወጡ።
ሳሙኤል ፓቲይ የተባለው መምህር በክፍሉ ውስጥ አወዛጋቢ የነብዩ መሐመድ የካርቱን ስዕሎችን ለተማሪዎቹ ካሳየ በኋላ ከትናንት በስቲያ አንድ የ18 ዓመት ወጣት ትምህርት ቤት አቅራቢያ አንገቱን መቅላቱ ይታወሳል። ሳሙኤል ፓቲይ የሚያስተምርበት ትምህርት ቤት መምህራንን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች “እኔም መምህር ነኝ” “እኛ ፈረንሳይ ነኝ” የሚሉ መፈክሮችን ይዘው አደባባይ ወጥተዋል። ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን መምህሩ አንገቱ ተቀልቶ የተገደለው "በእስላማዊ የሽብር ጥቃት ነው" ብለው ነበር። ጥቃት ያደረሰው ሩሲያ ውስጥ የተወለደው ወጣት አብዱላክ ሲሆን ጥቃቱን ባደረሰበት ስፍራ በፖሊስ በጥይት ተመትቶ ተገድሏል። ከዚህ ጥቃት ጋር በተያያዘ የፈረንሳይ ፖሊስ 11 ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ይፋ አድርጓል። ከእነዚህም መካከል 4ቱ ከጥቃት አድራሹ ጋር የቅርብ ዝምድና የነበራቸው ናቸው። ለ47 ዓመቱ መምህር ድጋፋቸውን ለመግለጽ አደባባይ ከወጡት መካከል “ለሪፐብሊኩ ጠላቶች ትዕግስት አያስፈልግም” “እኔም መምህር ነኝ፤ ፓቲይ አንተን አስብሃለሁ” የሚሉ መፈክሮችም ታይታዋል። የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚንሰትር ጄን ካስቴክስ በትዊተር ገጻቸው ላይ “እኛ ፈንሳይ ነን። . . . አታሸብሩንም” ሲሉ ጽፈዋል። በጥቃቱ የተገደለው መምህር አርብ ዕለት የሆነው ምን ነበር? ጥቃቱ አድራሹ ከሚኖርበት ከተማ 110 ኪ.ሜትር ተጉዞ ትምህር ቤቱ ጋር ከደረሰ በኋላ ሳሙኤል ፓቲይ የተባለው መምህር የትኛው እንደሆነ እንዲጠቁሙት ተማሪዎችን ጠይቋል። ጥቃት አድራሹ ከዚህ ቀደም ከትምህር ቤቱ ጋርም ይሁን ከመምህሩ ጋር ግንኙነት አልነበረውም። መምህሩ ከትምህርት ቤት ወደ መኖሪያ ቤቱ ሲጓዝ ጥቃት አድራሹ ሲከተለው ነበር። ከዚያም በቢላዋ ጭንቅላቱን መትቶ ከጣለው በኋላ አንገቱን ቀልቶታል። ፖሊስ እንደሚለው ጥቃቱን ሲያደርስ "አላሁ አክበር" ሲል የአይን እማኞች ሰምተውታል። ጥቃቱን ካደረሰ በኋላ ለመሰወር ቢጥርም ጥሪ የደረሰው ፖሊስ በፍጥነት በስፍራው ተገኝቷል። ከዚያም 12 ጊዜ በጥይት ተመትቶ ተገድሏል። ፖሊስ 30 ሴንቲ ሜትር የሚረዝም ቢላዋ ከጥቃት አድራሹ ጎን ማግኘቱንም አስታውቋል። በፈረንሳይ መሰል ጥቃት ሲፈጸም ይህ የመጀመሪያው አይደለም። ከሶስት ሳምንት በፊት ትውልደ ፓኪስታናዊ የ18 ዓመት ወጣት በስጋ መከትከቻ ትልቅ ቢላ ሁለት ሰዎች ላይ ጉዳት አድርሶ ነበር። እአአ 2015 ላይ ሁለት ሙስሊም የፈረንሳይ ዜጎች የቻርሊ ሄብዶ መጽሔት ቢሮን ሰብረው በመግባት በሰራተኞቹ ላይ ተኩስ ከፍተው ሰራተኞቹን ጨምሮ በጠቅላላው 12 ሰዎች መግደላቸው የሚታወስ ነው።
news-48494174
https://www.bbc.com/amharic/news-48494174
ቦይንግ 737 ማክስ 8፤ የቱሉ ፈራ ደጋግ ኢትዮጵያዊ ልቦች
መጋቢት 1/2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ቦይንግ 737 ማክስ 8 ማለዳ ወደ ናይሮቢ ጉዞውን ማድረግ ቢጀምርም ከስድስት ደቂቃ በላይ አየር ላይ መቆየት አልቻለም። ከ35 ሀገራት የተሰባሰቡ 157 ሰዎችን እንደጫነ እየተምዘገዘገ ጊምቢቹ ወረዳ ቱሉ ፈራ አካባቢ ወደቀ።
ከአደጋው አንድም ሰው አልተረፈም። በአደጋው ሁሉም ሰው እኩል አዘነ። ከሁሉም ግን የቱሉ ፈራ አካባቢ ነዋሪዎች ይለያል። በተለይ የእማማ ሙሉ። ከወጭ ወራጁ ጋር፣ ከኢትዮጵያዊው ኬኒያዊው ጋር ነጠላቸውን አዘቅዝቀው፣ እርጅና ያደከመው አይናቸው እንባ ያዘንባል። ሁሌም ደረታቸውን እየደቁ፣ የእንባ ጅረት ፊታቸውን ያርሰዋል። የቢቢሲ ባልደረቦች የእኚህን እናት ደግ ልብ በቪዲዮም በጽሑፍም አስነበቡ። ማህበራዊ ሚዲያውም 'ኢትዮጵያዊነት በጠፋበት በዚህ ዘመን፣ አንዱ ሌላውን በሚያሳድድበት፣ አገር ከብጥብጥና ከመፈናቀል ዜና ውጪ በማትሰማበት ወቅት ኢትዮጵያዊ ደግ ልብ ተገኘ' ሲሉ ተቀባበሉት። • "አደጋውን ስሰማ በረራው ጠዋት እንዳልሆነ ራሴን አሳመንኩኝ" የረዳት አብራሪው ጓደኛ • ስለ አደጋው እስካሁን የምናውቀው • 'መጥፎ ዕድል' አውሮፕላኑ የወደቀበት ስፍራ ስያሜ እንደሆነ ያውቃሉ? አንድ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ የጊምቢቹ ወረዳ ቱሉ ፈራ አካባቢ እና የሀማ ቀበሌዎች ነዋሪዎችን ደግነት በማሰብ "ለምን አናመሰግናቸውም?" ሲል በፌስቡክ ገጹ መጠየቁን ያስታውሳሉ ኢንጂነር ስንታየሁ ደምሴ። ኢንጂነር ስንታየሁ ደምሴ ትናንት በቱሉ ፈራ የተካሄደው የምስጋና ፕሮግራም አስተባባሪ ናቸው። ታዲያ እሳቸው ሀሳቡን ለሚቀርቧቸው እና ለማህበራዊ ድረ-ገፅ ተጠቃሚዎች አብራርተው በማካፈል 'ጎበዝ ኢትዮጵያዊ ደግ ልብ ተገኝቷል እስቲ አበጃችሁ እንበላቸው' አሉ። ሀሳቡ ፋፍቶ በጎ ፈቃደኞችን አሰባሰበ። ስምንት አባላት ያሉት ኮሚቴ ተዋቅሮና ከአካባቢው ነዋሪ ጋር ምክክር ተደርጎ በትንትናው እለት አውሮፕላኑ በወደቀበት አካባቢ ለሚገኙ ነዋሪዎች የምሥጋና ፕሮግራም ተካሄደ። ምስጋናውን ለማድረስ ከአዲስ አበባ ሁለት አውቶቡስ ተንቀሳቅሷል። አንዱ የጋዜጠኞች ቡድንን የያዘ ነው። ሌላው ደግሞ አመስጋኝ አንደበትና ልባቸውን የያዙ ሰዎችን። አቅም ያለው የግል መኪናውን እያሽከረከረ ስፍራው ላይ ተገኝቷል ይላሉ የኮሚቴው አባል የሆኑት አቶ ነፃነት ተስፋዬ። እንደው ለመሆኑ ከምናውቃቸው መካከል እነማን ተገኙ? ስንል የተለመደ ጥያቄ አከልን። ከሀገር ሽማግሌዎች ተባባሪ ፕርፌሰር አህመድ ዘካርያ እና አቶ ኃይሌ ገብሬ አሉ አቶ ነፃነት ተስፋዬ፣ ኢንጂነር ስንታየሁ አክለውም ሙሐዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት እና አርቲስት አብርሃም ወልዴም ምስጋና አቅራቢዎች ነበሩ አሉን። • አደጋው ስፍራ በየቀኑ እየሄዱ የሚያለቅሱት እናት ማን ናቸው? • "ምርኩዜን ነው ያጣሁት" የካፒቴን ያሬድ አባት ኢንጂነሩ በማከልም ለህዝቡም ከፍ ያለ ግብዣ እና የማስታወሻ ስጦታ ተበርክቷል አሉን። ስጦታው ምን ነበር? የወ/ሮ ሙሉ ፎቶ የእኚህ ደግ እናት ምስል ለቱሉ ፈራ አዲስ ስም፣ አዲስ መለያ ሸማ ሆኗታል። እናም ፎቶው ጥሩ ተደርጎ ተለብጦ አካባቢው ነዋሪዎች ለመጡበት የቀበሌ አስተዳደር ተሰጥቷል። አቶ ደቻሳ ጉተማ በትናንትናው የምስጋና መርሀ ግብር ላይ ከታደሙ አባወራዎች መካከል አንዱ ናቸው። "እኛ ያለቀስነው ሟቾቹ ሰው በመሆናቸው" ነው ይላሉ። ሰው ሆነው፣ ለሰው ልጅ ሕይወት መጥፋት በማዘናቸው፣ በባህል በወጋቸው መሰረትም ተዝካር በማውጣታቸው ብቻ "ገለታ ይድረሳችሁ" መባላቸው ደንቋቸዋል። 'እንዳከበራችሁን ክበሩ' የእርሳቸው ምርቃት ነው። ኢንጂነር ስንታየሁ "በጎ ነገር፣ ፍቅር ብርቅ በሆነበት፣ መተሳሰብ በጠፋበት በዚህ ዘመን የቱሉ ፈራ አካባቢ ሰዎችን ማግኘት መታደል ነው" ይላሉ። ኢንጂነሩም አክለው እናቶቻችን ሁሉ እማማ ሙሉን ይመስላሉ። እሳቸውን ማመስገን ደግ እንዲበረክት፣ ደግነትም ነፍስ እንዲዘራ ማድረግ ነው ሲሉ አክለዋል። የእማማ ሙሉን ደግነት ያየች አሜሪካ የምትኖር ኢትዮጵያዊት፣ ገነት በቀለ ትባላለች፣ ለእማማ ሙሉ ስጦታ መስጠት የምፈልገው ልክ ለእናቴ እንደማደርገው ነው በማለት ጃንጥላ፣ ሻርፕ፣ ቅባት ልካላቸዋለች። እማማ ሙሉ በበኩላቸውም "እኔ ኢትዮጵያውያን በመንደራችን አደጋ ስለደረሰባቸው ወገኔ ተጎዳብኝ ብዬ አዘንኩ እንጂ እንዲህ ያለ ሽልማት አገኝበታለሁ ብዬ አይደለም። እናንተ ግን ይገባሻል ብላችሁ ሽልማት የላካችሁልኝን ፈጣሪ ዋጋችሁን አብዝቶ ይስጣችሁ። ይህንን ሁሉ ሽልማት ብቻዬን ምን አደርገዋለሁ? ሠፈር ስመለስ የአንገት ልብሱን ለጎረቤቶቼ አከፋፍለዋለሁ። ቅባቱንም ልጆቻችን አንድ ላይ ይቀቡታል" ማለታቸውን ሰምተናል። ኢንጂነር ስንታየሁ እኛ ልናመሰግናቸው ስለሆነ የሄድነው ከኪሳችን ሳንቲም አዋጥተን ሁለት ሰንጋ አርደን ነበር። የአካባቢው ሰው ግን በአገልግል ፈትፍቶ፣ ቆሎ አዘጋጅቶ ጠበቀን በማለት ደጋግሞ ስለሚዘረጋውና ደግነት ስለማይነጥፍበት የቱሉ ፈራ አካባቢ ነዋሪ ይመሰክራሉ። አቶ ነፃነት በበኩላቸው ይህ የምስጋና መርሀ ግብር የበጎ ፈቃደኞችን ኪስ ብቻ እንዲዳስስ ነው የፈለግነው ይላሉ። የየትኛውም ድርጅት ድጋፍን በዋናነት አልጠየቅንም። በርግጥ ውሃና ቢራ ያቀረቡ አሉ ሌላው ግን ሀሳቡን ከደገፉ አመስጋኝ ኢትዮጵያውያን የተሰበሰበ ብር ነው ይላሉ። ኢንጂነር በበኩላቸው ከ100 ሺህ እስከ 150 ሺህ ሳናወጣ አልቀረንም ብለውናል።
news-48200815
https://www.bbc.com/amharic/news-48200815
በስህተት ከባንክ የተሰጣቸውን 1 ሚሊየን ብር የመለሱት መምህር
አቶ ዓለሙ ተስፋዬ (ዶ/ር) ባህርዳር በሚገኘው የአቢሲኒያ ባንክ በተንቀሳቃሽ ደብተራቸው የገባውን ገንዘብ ለማውጣት በጣና ቅርንጫፍ የተገኙት ሚያዝያ 29 ቀን 2011 ዓ. ም. ነበር።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፤ ማኅበረ ቅዱሳን በሚያስተባብረውና አቶ ዓለሙ በሚሳተፉበት ፕሮግራም የአብነት ትምህርት ቤቶችና ገዳማትን ለማደራጀት የተሰበሰበ አንድ ሚሊየን ሁለት መቶ ሦስት ሺ ብር በስማቸው ገብቶ ነበር። • 360 ብር ለአንድ ሕጻን በገበያ አካባቢ በሚገኘውና የሥራ ጫና በሚበዛበት የጣና ቅርንጫፍ ያሉ ሠራተኞች የተለመደ የዕለት ከዕለት ሥራቸውን በማከናወን ላይ ሳሉ አቶ ዓለሙ ከፍጠኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለማውጣት መጠየቃቸውን የጣና ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ ቢራራ መላኩ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ደንበኛው የጠየቁት የገንዘብ መጠን አንድ ሚሊየን ሁለት መቶ ሦስት ሺ ብር ነበር። አቶ ቢራራ እንደሚሉት፤ የገንዘቡ መጠን ከፍ ያለ ስለነበረ ፊትለፊት የነበረው ገንዘብ ከፋይ ለደንበኛው 3000 ብሩን ብቻ እንዲሰጣቸው ተደርጎ፤ ቀሪውን 1.2 ሚሊየን ብር ወደ ውስጥ ገብተው እንዲወስዱ ተደርጓል። ''ወደ ውስጥ ከገቡ በኋላ ብሩን አብረን ቆጥረን እንዲረከቡ አደረግን። ደንበኛው ከጠየቁት አንድ ሚሊየን ብር ጭማሪ ተሰጥቷቸው ገንዘቡን ገቢ ወደሚያደርጉበት ቦታ ሄዱ።'' አቶ ቢራራ እንደሚሉት፤ ለአቶ ዓለሙ አንድ ሚሊየን ብር ተጨማሪ መሰጠቱንና ከባንኩ ብር መጉደሉን አላወቁም ነበር። አቶ ዓለሙ በስህተት የተሰጣቸውን ገንዘብ በጆንያ ጭነው እስከተመለሱበት ጊዜ ድረስ ምንም እንዳልጠረጠሩ ያስረዳሉ። የተፈጠረውን ነገር "እጅግ አስገራሚ'' ሲሉም ይገልጹታል። ''ደንበኛው በመጀመሪያ ገንዘቡን ይዘው ሲመለሱ ትርፍ ብር ሊመልሱልን እንደሆነ አላወቅኩም ነበር። ሀሳባቸውን ቀይረው ብሩን ገቢ ሊያደርጉት እንደሆነ ነበር ያሰብነው።'' • ሁለት እምነቶችን በአንድ ጣራ ለአስርታት ያሳደሩ ጥንዶች አቶ ዓለሙ ግን የራሳቸውን ገንዘብ ገቢ ሊያደርጉ ሳይሆን ባንኩ በስህተት የሰጣቸውን ተጨማሪ አንድ ሚሊየን ብር ሊመልሱ ነበር ወደ ቅርንጫፉ የተመለሱት። በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የኬሚስትሪ ትምህርት ክፍል ኃላፊ የሆኑት አቶ ዓለሙ ተስፋዬ፤ ''ወደ ውስጥ ከገባን በኋላ ብሩ ሲቆጠር አጠገቡ ቁጭ ብዬ ስለነበር መጠኑ ትክክል መሆኑን እያረጋገጥኩ ወደ ጆንያ ውስጥ አስገባ ነበር'' ሲሉ ይናገራሉ። አቶ ዓለሙ ብሩን ከተረከቡ በኋላ አብሯቸው ከነበረ ግለሰብ ጋር ለሥራ ማስኬጃ ብሩን ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ ለማድረግ ተንቀሳቀሱ። ንግድ ባንክ ሲደርሱ ግን ፈጽሞ ያልጠበቁት ነገር አጋጠማቸው። የባንኩ ሠራተኛ ብሩን እንደተመለከተው ከመቁጠሩ በፊት "2.2 ሚሊየን ነው አይደል?" ብሎ ጠየቃቸው። ''እንደዛ ብሎ ሲጠይቀን፤ የብሩ መጠን 1.2 ሚሊየን ነው ብለን መለስንለት። ብሩን አብረነው በድጋሚ ስንቆጥረው እውነትም 2.2 ሚሊየን ብር ሆኖ አገኘነው'' በማለት አቶ ዓለሙ ስለሁኔታው ያስረዳሉ። ''የራሳችን የሆነውን 1. 2 ሚሊየን ብር ገቢ ካደረግን በኋላ ቀሪውን ብር ለመመለስ ወደ አቢሲኒያ ባንክ ጣና ቅርንጫፍ ተመለስን'' የባንኩ ሥራ አስኪያጅ የቀን ገቢ ሂሳብ የሚሠራበት ሰአት ባለመድረሱ ገንዘቡ መጉደሉን እንዳላወቁ ይናገራሉ። ''ብሩ ይጉደል አይጉደል ለማወቅ ሂሳብ መዝጋት ነበረብን'' ይላሉ። • የፍስሀ ተገኝ የቤተሰብ ፍለጋ ጉዞ አቶ ቢራራ እንደሚሉት፤ አቶ ዓለሙ ብር በስህተት ሰጥታችሁኛልና ልመልስ ሲሏቸው፤ በመጀመሪያ ነገሩ ቀልድ መስሏቸው ነበር። ኋላ ላይ ነገሩ እውነት ሆኖ ሲገኝ ግን ግርምትም ድንጋጤም እንደፈጠረባቸው ይናገራሉ። አቶ ዓለሙ ገንዘቡን ባይመልሱ ምን ይፈጠር ነበር? የሚል ጥያቄ ያቀረብንላቸው አቶ ቢራራ፤ የሥነ ምግባር እርምጃዎች ሊያስከትል ይችል ነበር ይላሉ። ''ስህተቱ በሥራ ጫና ምክንያት ወይም ባለማወቅ የተፈጠረ እንደሆነ በምንም አይነት መንገድ ማረጋገጥ ስለማይቻል ሆነ ተብሎ እንደተፈጸመ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።'' ደንበኛው የሰሩት ስህተት ባለመኖሩና ባንኩ ክፍያ ፈጽሞላቸው ወደጉዳያቸው ስለሄዱ ገንዘቡን ለመመለስ የሚያስገድዳቸው የሕግ አሰራር አልነበረም። ''የአቶ ዓለሙን ስብዕና በቃላት ለመግለጽ እጅግ ከባድ ነው፤ ከህሊና በላይ ነው፤ ፈጣሪ በላባቸው ሠርተው ያገኙትን ገንዘባቸውንና ትዳራቸውን እንዲባርክላቸው እመኝላቸዋለሁ'' ብለዋል አቶ ቢራራ። • ምግብ ማብሰልና ማጽዳት የቤት ውስጥ ጥቃቶችን ለመቀነስ አቶ ቢራራ "ይህ ለትውልድ አርአያ የሚሆን ተግባር ነው። እድሜ ልካቸውን ሊኮሩበት የሚገባ ተግባር ነው። እኔም ብሆን እድሜ ዘመኔን በሙሉ አስታውሰዋለሁ። የመልካም ሥራ አርአያ አድርጌ የማስታውሳቸው ሰው ይሆናሉ'' በማለት የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። አቶ ዓለሙ በበኩላቸው፤ ተግባሩ ብዙ ሰዎች ሊያደርጉት የሚችሉት ነው በማለት፤ የባንኩን ሠራተኛ ከብዙ እንግልት በማዳናቸው ደስተኛ እንደሆኑና የህሊና እርካታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል።
news-53422734
https://www.bbc.com/amharic/news-53422734
ኬንያ፡ በአንድ ወር ሁለት ጊዜ ለማግባት የተገደደችው የ12 ዓመት ታዳጊ ነጻ ወጣች
በአንድ ወር ውስጥ ሁለት ወንዶችን እንድታገባ የተገደደችው የ12 ዓመት ታዳጊ የኬንያ ባለስልጣናት ጣልቃ ገብተው እንዳስጣሏት ተዘገበ።
ከኬንያ ዋና ከተማ በስተምዕራብ በምትገኘው ናሮክ በተባለችው ግዛት ውስጥ ነዋሪ የሆነችው ታዳጊ አባት ልጁን መጀመሪያ የ51 ዓመት አዛውንት ለሆኑ ግለሰብ ድሯት ነበር። ከዚያም በኋላ ከመጀመሪያው 'ጋብቻ' ማምለጥ ብትችልም ተመልሳ ከሌላ የ35 ዓመት ጎልማሳ ጋር ለመኮብለል መገደዷ ተነግሯል። ይህንንም ተከትሎ ጉዳዩ በአካባቢው ወዳሉ የህጻናት መብት ተከራካሪዎችና የመንግሥት ባለስልጣናት ዘንድ በመድረሱ ታዳጊዋ ያለዕድሜዋ እንድትገባበት ከተደረገው ጋብቻ እንድትወጣ ተደርጓል። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች እንዲያገቡ ማድረግ በኬንያ ሕግ መሰረት ወንጀል ነው። ታዳጊዋ ከገባችበት ያለዕድሜ ጋብቻ እንድትወጣ የተደረገችው አንድ የህጻናት መብት ተከራካሪ በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ የነበረች ሌላ ታዳጊን ጉዳይ እየተከታተለ ባለበት ጊዜ ባገኘው መረጃ መሰረት ነው። "አባቷ መጀመሪያ ለአንድ አዛውንት ድሯታል። ከዚያም ምንም አማራጭ ስላልነበራት በድጋሚ ከሌላ ጎልማሳ ጋር ለመሆን ተገደደች" ሲል በናሮክ ግዛት ውስጥ ያለው የህጻናትን ጉዳይ የሚከታተለው ማኅበር ባልደረባ ጆሽዋ ካፑታህ ለቢቢሲ ተናግሯል። ስታንዳርድ የተባለው ጋዜጣ እንደዘገበው የመጀመሪያው ግለሰብ አራት ላሞችን በጥሎሽ ያቀረበ ሲሆን፣ ታዳጊዋ ጋብቻውን በብትቃወምም በአጎቷ ልጆች መመታቷ ተገልጿል። "ከመጀመሪያው ጋብቻ አምልጬ ወደ አባቴ ቤት ብመለስ መልሰው ሊሰጡኝ ይችላሉ ብዬ ስለፈራሁ፤ ከ35 ዓመቱ ሰው ጋር አብሬ ኮበለልኩ" ስትል ከሌላ ባለትዳር ሰው ጋር እንደጠፋች መናገሯን ጋዜጣው ጠቅሷል። ነገር ግን መኮብለሏን ያወቀው አባት ታዳጊዋን አግኝቶ መጀመሪያ ለተዳረችለት ሰው መልሶ እንደሰጣት የህጻናት መብት ተከራካሪው ካፑታህ ተናግሯል። ካፖታህ ጨምሮም በአካባቢው ያለው ድህነትና በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው ህጻናት ያለዕድሜያቸው እንዲዳሩ የማድረጉን ሁኔታ እንዳባባሰው ገልጿል። "አንዳንድ ቤተሰቦች ይራባሉ፤ በዚህም ለሴት ልጆች ወላጆች በጥሎሽ መልክ የሚሰጡት ሁለት ወይም ሦስት ላሞች ስለሚያጓጓቸው በችግር ምክንያት ታዳጊ ልጆቻቸውን ያለዕድሜያቸው እንዲዳሩ ያደርጋሉ" ብሏል። በናሮክ ግዛት ውስጥ በሚገኙት በማሳይ ማኅበረሰቦች ዘንድ ሴት ልጆች በቤት ውስጥ እንደ ሃብት የሚታዩ ሲሆን፣ ሲያገቡም በሚያመጡት የከብቶች ጥሎሽ ምክንያት በአካባቢው ታዳጊ ህጻናትን ያለዕድሜያቸው እንዲዳሩ ይደረጋል። የመንግሥት ባለስልጣናትና የህጻናት መብት ተከራካሪዎች ታዳጊዋን ከገባችበት ሕገወጥ ጋብቻ ለማስጣል ወዳለችበት ሄደው ቢያገኟትም ግለሰቦቹ ግን መሰወራቸው ተገልጿል። የአካባቢው መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ታዳጊዋ ከተገኘች በኋላ ፖሊስ ተደብቀዋል የተባሉትን አባቷንና ሁለቱን ግለሰቦች ለመያዝ ፍለጋ ላይ ነው። ተፈላጊዎቹ ተይዘው ጥፋተኛ መሆናቸው ከተረጋገጠ በአገሪቱ ሕግ መሰረት እስከ አምስት ዓመት የሚደርስ የእስር ቅጣት ወይም አንድ ሚሊዮን ሽልንግ ማለትም 10 ሺህ ዶላር የገንዘብ ቅጣት ይጠብቃቸዋል።
news-55036276
https://www.bbc.com/amharic/news-55036276
የዓለም አትሌቲክስ ሽልማት፡ ሁለት አፍሪካዊያን ለዓመቱ ምርጥ ሴት አትሌቶች ሽልማት ታጩ
የዓለም አትሌቲክስ በየዓመቱ በሚያዘጋጀው ምርጥ ሴት አትሌቶች ሽልማት ኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ እና ኬንያዊቷ ፔረስ ጀፕቺርቺር ከመጨረሻዎቹ አምስት እጩዎች ዝርዝር ውስጥ መግባታቸው ተገለፀ።
የዓለም አትሌቲክስ ማክሰኞ እለት በአስሩ ዝርዝር ውስጥ ገብተው ከነበሩ አትሌቶች አምስት ለመጨረሻው ዙር መመረጣቸውን አስታውቋል። ሌሎች ሦስት አፍሪካዊያን አትሌቶች አስሩ ዝርዝር ውስጥ ተካተው የነበረ ቢሆንም 5ቱ ዝርዝር ውስጥ ግን መግባት ሳይችሉ ቀርተዋል። እነዚህ አትሌቶች ኢትዮጵያዊቷ አባበል የሻነህ፣ ኬንያዊያኖቹ ዶ ፌዝ ኪፕየጎን እና ሔለን ኦቢሪ ናቸው። ለ ሌሎቹ በአምስቱ ዝርዝር ውስጥ መካተት ያልቻሉት አትሌቶች ደግሞ የኔዘርላንዷ ፌምኬ ቦል እና እንግሊዟ ላውራ ሙር ናቸው። የዘንድሮው ዓመት የዓለም አትሌቲክስ ሽልማት ሥነ ሥርዓት በቨርቹዋል [ኢንተርኔት] በአውሮፓዊያኑ ታህሳስ 5 የሚካሄድ ሲሆን በማኅበራዊ ሚዲያም በቀጥታ ይሰራጫል ተብሏል።የዓመቱ ምርጥ ሴት አትሌት 5ቱ እጩዎች ለተሰንበት ግደይ በ5000 ሜትር በ14፡06፡62 በመግባት የዓለም ክብረ ወሰንን ሰብራለች። ቫሌንሺያ በተደረገው በዚህ ውድድር በጥሩነሽ ዲባባ ለአስራ ሁለት ዓመታት ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን አሻሽላለች ተብሏል። የ22 ዓመቷ ሯጭ የገባችበት ሰዓትም 14 ደቂቃ ከ6.62 ሰኮንዶች ሲሆን የጥሩነሸ ደግሞ 14 ደቂቃ ከ11.15 ሰከንዶች ነበር። በሞናኮ በተካሄደው በዋንዳ ዲያመንድ ሊግም 5000 ሜትር ሩጫ በሁለተኛ ደረጃነት አጠናቃለች። ሲፋን ሐሰን 18,930 ሜትር በአንድ ሰዓት ጊዜ በመሮጥ የዓለም ክብረ ወሰን ይዛለች። በ10 ሺህ ሜትር በ29፡36፡67 በማጠናቀቅም የአውሮፓ ክብረወሰን ያስመዘገበች ሲሆን በታሪክ አራተኛዋ ፈጣኗ ሯጭ ተብላለች። የዓለም ግማሽ ማራቶን አሸናፊ ናት። በሴቶች ውድድር 1፡ 05፡34 እና 1፡ 05፡ 16 ሰዓት በመግባት የግማሽ ማራቶን ክብረወሰንን ሁለት ጊዜ ሰብራለች። በቤት ውስጥና ከቤት ውጭ በተደረጉ አራት የርዝመት ዝላይ ውድድሮች አሸንፋለች። በቤት ውስጥ በተካሄደ የርዝመት ዝላይ ውድድር 15.43 ሜትር በመዝለል የዓለም ክብረ ወሰን ሰብራለች። በሰባት የ100 ሜትር ውድድሮች አሸንፋለች። በዓለም መሪነት 100 ሜትር በ10.85 ሰከንድ ሮጣለች። ከእነዚህ እጩዎች አሸናፊውን ለመለየት ሦስት የድምፅ አሰጣጥ መንገዶች አሉ። የዓለም አትሌቲክስ ምክር ቤት እና የዓለም አትሌቲክስ ቤተሰቦች ድምፃቸውን በኢሜይል የሚሰጡ ሲሆን አድናቂዎቻቸው ደግሞ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ድምፅ ይሰጣሉ። ከአጠቃላይ ድምፁ የምክር ቤቱ ድምፅ 50 በመቶ ይይዛል። የአትሌቲክስ ቤተሰቦችና የሕዝብ ድምፅ ደግሞ እያንዳንዳቸው 25 በመቶ ይይዛሉ።
news-55400119
https://www.bbc.com/amharic/news-55400119
“ፈጣሪ ይቅር ሊለኝም ላይለኝም ይችላል” ሕገ ወጥ ሰው አዘዋዋሪው
ሻፊላህ አፍጋኒስታናዊ ነው። በ16 ዓመቱ ወደ ቱርክ እየሄደ መሆኑን ለቤተሰቦቹ በስልክ አስታውቆ ነበር።
ኤልሀም ኑር ያኔ ከሱ ጋር ድንበር የሚያቋርጡ 100 ሰዎች ነበሩ። በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ አፍጋኒስታናውያን ልክ እንደሱው ወደ አውሮፓ ይሰደዳሉ። ወደ ኢስታንቡል እንዲወስዱት የከፈላቸው ሰው አዘዋዋሪዎች ፖሊሶች እንዳይዟቸው ቫን በተባለ ሀይቅ ምሽት ላይ ለመጓዝ ወሰኑ። በምሽት እየተጓዙ ሳለ ጀልባቸው ሰጠመ። 32 አፍጋኒስታናውያን፣ ሰባት ፓኪስታናውጣን እና አንድ ኢራናዊ ጭኖ ነበር። ከአደጋው በኋላ የ61 ሰዎች አስክሬን ተገኝቷል። ሻፊላህን ጨምሮ የት እንደደረሱ ያልታወቁ ስደተኞችም አሉ። ስደተኞቹን ያጓጓዘው ካቡል ውስጥ ያለ ሕገ ወጥ አዘዋዋሪ ነው። ቢቢሲ ይህንን ግለሰብ አነጋግሮት ነበር። “የሰው ዝውውር ለብቻ የሚሠራ አይደለም” ኤልሀም ኑር (ስሙ ተቀይሯል) ስደተኞችን ወደ ፈረንሳይ፣ ጣልያን እና ዩናይትድ ኪንግደም በመላክ ይታወቃል። አብረውት የሚሠሩ ሰዎች ብዙ ናቸው። “የሰው ዝውውር ለብቻ የሚሠራ አይደለም። ሁላችንም አዘዋዋሪዎች ትስስር አለን” ይላል። ብዙ አፍጋኒስታንን ጥለው የሚወጡ ደንበኞች አሉት። የተባበሩት መንግሥታት እንደሚለው፤ አሁን ላይ ከአፍጋኒስታን የወጡ ዜጎች 2.7 ይሆናሉ። በከፍተኛ ሁኔታ ሰው ከሚሰደድባቸው ሶርያ እና ቬንዝዌላ ቀጥሎ ያለችው አገር አፍጋኒስታን ናት። ስለዚህም ኤልሀም ሁሌም የሚያጓጉዘው ሰው አያጣም። ብዙ አፍጋኖች ከአገራቸው የሚወጡት እንደ ኤልሀም ባሉ አዘዋዋሪዎች አማካይነት ነው። ወደ አውሮፓ ለመድረስ ወጥነው ከአገራቸው ከሚወጡት የሚሳካላቸው ጥቂቱ ናቸው። የሻፊላህ አጎት አሸር አፍዘል ጉዞው ከባድ እንደሆነ ያውቃሉ። ሆኖም ግን ሻፊላህ ደብዛው ይጠፋል ብለው አልጠበቁም። ቤተሰቡ ሻፊላህ የት እንደደረሰ አለማወቁ ሀዘኑን አብሶባቸዋል። አስክሬናቸው የተገኘ ስደተኞች ቀብር ተፈጽሟል። ለሻፊላህ ግን ምንም ማድረግ አልተቻለም። “ይኖራል ብለን አንጠብቅም። አስክሬኑን ብናገኝ ነው የምንለው” ይላሉ አጎቱ። ሻፊላህ 1,000 ዶላር ለኤልሀም ከፍሎ ነበር ከአገር የወጣው። ከሌሎች ስደተኞች ጋር በእግርም በጭነት መኪናምተጉዘው በኢራን አልፈው ቱርክ ደርሰው ነበር። ሆኖም ቫን ሀይቅ ላይ ህልማቸው ተቀጨ። ኤልሀም ከሻፊላህ ተቀብሎ የነበረውን ገንዘብ ለቤተሰቡ እንደመለሰ ይናገራል። “እስከ ጣልያን ለመሄድ 8,500 ዶላር ይከፈላል” ከአፍጋኒስታን ቱርክ 1,000 ዶላር፣ ከቱርክ ወደ ሰርቢያ 4,000 ዶላር፣ ከሰርቢያ እስከ ጣልያን 3,500 ዶላር ያስከፍላሉ። ባጠቃላይ 8,500 ዶላር ማለት ነው። ኤልሀም በእያንዳንዱ ስደተኛ ከ3,000 እስከ 3,500 ዶላር ያገኛል። የማያውቃቸውን ወይም እሱን ከሚያውቁ ሰዎች ጋር የማይተዋወቁ ሰዎችን አያገኝም። ሰነድ ለሌላው ስደተኞች ጉዞው ከባድ እንደሆነ ያውቃል። ቀን ተደብቀው ማታ ማታ ብቻ ነው የሚጓጓዙት። በቴህራን፣ ቫን እና ኢስታንቡል ስደተኞቹ ስውር ቤቶች እንዲያርፉ ይደረጋል። ስደተኞቹ በሌቦች ኢላማ እንዳይደረጉ ሲባል ጌጣጌጥ፣ የእጅ ሰዓትና ሌላ ውድ ቁሳቁስ አይዙም። ከ100 ዶላር በላይ እንዳይዙ ኤልሀም ይመክራቸዋል። ቱርክ ለመድረስ አንድ ሳምንት እና ከዛም በላይ ሊወስድ ይችላል። ብዙውን ጊዜ ስደተኞች የሚመርጡት በቱርክ ወደ ግሪክ የሚወስደውን መንገድ ነው። የአውሮፓ ድንበር ኤጀንሲ በዚህ ዓመት በአስር ወር ውስጥ 17,000 ሰዎች ወደ አውሮፓ እንደተሻገሩ ይገምታል። ከስደተኞቹ አንዱ ሻህ እንደሚለው ከግሪክ ወደ ቦስንያ መጓዝ ከባድ ነበር። በተደጋጋሚ ወደ አገሩ እንዲመለስ ከተደረገ በኋላ በስተመጨረሻ ድንበር መሻገር ችሏል። “ድንበር ለመሻገር ስሞክር ፖሊሶች ደብድበውኛል። ብዙ እንግልት ደርሶብኛል” ይላል። ሻህ ጣልያን ስለመድረሱ እርግጠኛ አይደለም። ግን አፍጋኒስታን ወዳሉ ስደተኛ አዘዋዋሪዎች መደወል አይፈልግም። ብዙም እርዳታ እንደማይሰጡ ይናገራል። “ልትሞት፣ ልትታፈን፣ ልትጎዳ ትችላለህ። ማንም አይረዳህም። ሰው አዘዋዋሪዎች ፖሊሶችን ስለሚፈሩ ሊረዱህአ ይችሉም” ይላል ሻህ። በቂ ምግብና ውሃ የለም። በረሀብና ጥም ምክንያት ሰዎች ሲሞቱም አይቷል። ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት እንደሚለው፤ ዘንድሮ ሜድትራኒያን ባህርን ለማቋረጥ ሲሞክሩ 1,000 ሰዎችሞተዋል። በርካታ ስደተኞች አንድ ላይ በጀልባ ተጭነው ሲሄዱ አደጋ ይገጥማቸዋል። ሕይወታቸውንም ያጣሉ። ከስደተኛነት ወደ ሰው ዝውውር ኤልሀም በአንድ ወቅት ስደተኛ ነበር። አባቱ የ14 ዓመት ታዳጊ ሳለ 5,000 ዶላር ለሰው አዘዋዋሪዎች ከፍለው ከአገር አስወጥተውታል። “ጉዞዬ ከባድ ነበር። በተለይ ቡልጋርያ ባቡር ውስጥ ተደብቀን ነበር። ከባቡር እንድዘል ተገድጄም ነበር” ይላል። ወደ ሰው ዝውውር የገባው 90 ዶላር እየተከፈለው ነበር። ዩኬ ከደረሰ በኋላም ከሰው አዘዋዋሪዎች ጋር መስራቱን ቀጥሏል። 21 ዓመቱ ላይ ፖሊሶች እያፈላለጉት እንደሆነ ሲሰማ ወደ አፍጋኒስታን ተመለሰ። አውሮፓ የደረሱ ስደተኞች ስለሱ ስለሚያወሩ ደንበኞቹ ተበራክተው ነበር። “ሰዎች ከአገር እንደማስወጣቸው ያምኑብኛል” ይላል። አሁን ላይ በሱ አማካይነት 100 ሰዎች ወደ አውሮፓ እየተጓዙ ነው። ሻፊላህ የደረሰበት ጉዳት እጅግ ስላዛነው ከዚህ በኋላ ዝውውሩን እንደሚተወው ይናገራል። “ቤተሰቦቻቸውን ደጋግሜ ይቅርታ ጠይቄያለሁ። ጉዞው ላይ ብዙ ነገር ሊገጥማቸው እንደሚችል አስቀድሜ ነግሬያቸዋለሁ። ፈጣሪ ይቅር ሊለኝም ላይለኝም ይችላል” ሲል የተሰማውን ተናግሯል። እሱ ሰው ማዘዋወር ቢያቆምም ባያቆምም ሂደቱ መቀጠሉ አይቀርም። በሺዎች የሚቆጠሩ አፍጋኒስታናውያን የተሻለ ሕይወት ፍለጋ ድንበር ማቋረጣቸው ይቀጥላል።
news-52613715
https://www.bbc.com/amharic/news-52613715
ኮሮናቫይረስ፡ ሳኡዲ ለዜጎቿ የምትሰጠውን ድጎማ በማቋረጥ ተጨማሪ ዕሴት ታክስን በሦስት እጥፍ ጨመረች
የሳኡዲ አረቢያ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የደቀቀውን ኢኮኖሚዋን ለመደገፍ በተጨማሪ እሴት ታክስ ላይ ሦስት አጥፍ ጭማሪ ልታደርግ መሆኑን አስታወቀች።
የአገሪቱ መንግሥት ከዚህ በተጨማሪም ለዜጎቹ ይሰጠው የነበረውን የኑሮ መደጎሚያ ገንዘብ እንደሚያቋርጥም አስታውቋል። የኮሮናቫይረስ ባስከተለው ዓለም አቀፍ ቀውስ ምክንያት የነዳጅ ዋጋ በመቀነሱ በነዳጅ ሀብት የበለጸገችው ሳኡዲ አረቢያ የገቢ መጠኗ በእጅጉ አሽቆልቁሏል። ሳኡዲ አረቢያ ከሁለት ዓመታት በፊት ነበር ኢኮኖሚው በነዳጅ ላይ ብቻ እንዳይንጠለጠል በሚል ተጨማሪ እሴት ታክስን ያስተዋወቀችው። የሳኡዲ አረቢያ ዜና ተቋም እንደዘገበው ተጨማሪ እሴት ታክሱ ከፈረንጆቹ ሰኔ ወር ጀምሮ ከ5% ወደ 15% ከፍ ይላል። "እነዚህ እርምጃዎች በጣም ከባድ ነገር ግን አሁና ካለው ሁኔታ አንጻር እጅግ አስፈላጊ ናቸው። የአገሪቱን የገንዘብና ኢኮኖሚያዊ ደኅንነትን ለማረጋገጥ ነው እርምጃዎቹ የተወሰዱት" ብለዋል የገንዘብ ሚኒስትሩ ሞሐመድ አል ጃዳን። ይህ ውሳኔ የተላለፈው አገሪቱ የምታወጣው ወጪ ከምታስገባው ገቢ በማነሱ ምክንያት መንግሥት ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ የ9 ቢሊዮን ዶላር የበጀት ጉድለት ማጋጠሙን ተከትሎ ነው። ይህም ሊሆን የቻለው በተጠቀሰው የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ከነዳጅ የሚገኝ ትርፍ 22 በመቶ በመቀነሱ አገሪቱ ማግኘት የቻለችው 34 ቢሊዮን ዶላር ብቻ በመሆኑ ነው። በነዚሁ ሦስት ወራትም የሳኡዲ አረቢያ ማዕከላዊ ባንክ እንዳስታወቀው የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ገንዘብ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ዝቅ ብሏል። ልዑል ሞሐመድ ቢን ሳልማን የሳኡዲ አረቢያ ኢኮኖሚን ለማነቃቃትና አጠቃላይ የአገሪቱን ገጽታ ለመቀየር እየወሰዱት የነበረውን እርምጃ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ፈተና እንደሚሆንበት ይጠበቃል።
news-55298650
https://www.bbc.com/amharic/news-55298650
የጆ ባይደን ባለቤት "ዶ/ር" ተብለው መጠራታቸው እያጨቃጨቀ ነው
የተመራጩ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ባለቤት እና አዲሲቱ ቀዳማዊ እመቤት ለስማቸው ቅጽል "ዶክተር" የሚለውን መጠቀም አለባቸው ወይ የሚለው በአሜሪካ ማህበራዊ የትስስር መድረክ አነጋጋሪ ጉዳይ ሆኗል።
የተመራጩ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ባለቤት ጂል ባይደን ጉዳዩ ማነጋገር የጀመረው ጆሴፍ ኤፒስቴን የተባለ አምደኛ በዎልስትሪት ጆርናል ጋዜጣ አንድ ጽሑፍ ማሳተሙን ተከትሎ ነው። ይህ አምደኛ በጋዜጣው ባሰፈረው ሐሳብ ጂል ባይደን ራሳቸውን "ዶክተር ጂል ባይደን" እያሉ መጥራታቸው አሳፋሪ ነው፤ ትክክልም አይደለም፤ እናም 'ክብርት ቀዳማዊት እመቤት እባክዎ ራሱን አደብ ያስገዙ' የሚል ይዘት ያለው ጽሑፍ ጽፏል። ይህ ሐሳብ ያስቆጣቸውና አሉታዊ ጾተኝነት ነው ያሉ ጉዳዩን ወደ ማኅበራዊ የትስስር መድረክ ወስደውታል። አምደኛው የመጪዋን ቀዳማዊት እመቤት በትምህርት ያገኙትን ዶክትሬት ከክብር ዶክትሬት ጋር በማመሳሰል ጽፏል። "ዶ/ር ጂል ባይደን ቀልደኛ ናቸው። ራሳቸውን በግድ ዶክተር ብለው የሚጠሩ ኮሚክ ሴትዮ" ሲል ተሳልቆባቸዋል ይህ ጎምቱ የአካዳሚክ ሰው በዎልስትሪት በጻፈው ሐሳብ። ይህ የአምደኛው ሐሳብ ያበሳጫቸው ሰዎች አምደኛውን በአሉታ ጾተኝነት ከሰውታል። ይህ ለሴቶች ያለውን ንቀት ብቻ የሚያሳይ ነው፤ አሳፋሪም ነው ብለዋል ብዙዎች። ጂል ባይደን ዶክተር የሚለውን የአካዳሚክ ቅጽል በትዊተር ገጻቸው በይፋ ይጠቀሙታል። ይህ ዶ/ር ወይም ፕሮፌሰር መባባሉ ከዩኒቨርስቲዎች አውድ ውጭ እምብዛምም የተለመደ አይደለም። ጂል ዶክትሬታቸውን ያገኙትም ከደላዌር ዩኒቨርስቲ እአአ 2007 ላይ ነበር። የመመረቂያ ጽሑፋቸውን የጻፉትም በማኅበረሰብ ኮሌጆች ውስጥ ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ተማሪዎችን እንዴት መታደግ ይቻላል በሚል ርእስ ነበር። ከዚህም በላይ ጂል ባይደን ሁለት የማስተርስ ዲግሪ ያላቸው ሲሆን በአሜሪካ ታሪክ ብዙ ርቀት በትምህርት ከገፉ ቀዳማዊት እመቤቶች ተርታ በቅርቡ ይመደባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ያም ሆኖ በዎልስትሪት ጆርናል ሐሳቡን ያሰፈረው አምደኛው ጂል ባይደን ላይ ተዘባብቶባቸዋል። "አንድ ብልህ ሰው ምን አለ መሰለሽ? አንድ ሰው አንድ ልጅ እንኳ ሳያዋልድ ራሱን ዶክተር ብሎ ባይጠራ እመክረዋለሁ!" አምደኛው ኤፕስቴይን የ83 ዓመት ሰው ሲሆን በአካዳሚክ ዘርፍ ትልቅ ቦታ ከሚሰጣቸው ሰዎች የሚመደብ ነው። "እባክዎ ዶ/ር ጂል ራስዎን ዶ/ር እያሉ ማቄል ያቁሙ" ብሏቸዋል መጪዋን ቀዳማዊት እመቤት። የአምደኛውን ሐሳብ ካጣጣሉት ሰዎች መካከል የጥቁሮች መብት ተሟጋች የነበረው የማርቲን ሉተር ኪንግ ጁንየር ትንሽ ልጅ በርኒስ ኪንግ ትገኝበታለች። "አባቴ ዶክተር ኪንግ ተብሎ ይጠራ የነበረው ሐኪም ስለነበረ አይደለም፤ ነገር ግን ተግባሮቹ ብዙዎችን ፈውሰዋል" ስትል በትዊተር ሰሌዳዋ ላይ ጽፋለች። ተመራጭዋ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሐሪስ በበኩሏ "ዶ/ር ጂል ዶክትሬቷን ያገኘቸው ገዝታ ሳይሆን በጥረት ነው። ለኔም ለተማሪዎቿም ሆነ ለአሜሪካዊያን ትልቅ አርአያ ናት" ብላለች። ብዙዎች የአምደኛውን ሐሳብ "ዶ/ር ጂል ሴት በመሆናቸው የተሰነዘረ ንቀት እንጂ ሌላ አይደለም ሲሉ" ከአሉታ ጾተኝነት ጋር አስተሳስረውታል። ሐኪም ሳይሆኑ በሌላ ዘርፍ ራስን "ዶ/ር" ብሎ መጥራት በአሜሪካ እምብዛምም የተለመደ ባይሆንም ከዚህ ቀደም በኒክሰን ጊዜ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ሄንሪ ኪሲንገር ባልታወቀ ምክንያት ራሳቸውን ዶ/ር ኪሲንገር ብለው ይጠሩ ነበር። ብዙ ሚዲያዎችም ይህንኑ አጠራር ይከተሉ ነበር። "ዶክተር" የሚለው ቃል ከስም ቅጥያ ጋር አብሮ አገልግሎት የሚውልበት አግባብ በብዙ አገራት በሕክምና ለተመረቀ ሰው ብቻ ነው የሚውለው። ሆኖም በትምህርት ተቋማት የሚሰሩ መምህራንና ተመራማሪዎች ሦስተኛ ዲግሪ ከሰሩ በኋላ በትምህርታዊ አውድ ብቻ ይህንኑ ቅጽል ይጠቀማሉ። ሆኖም በይፋ በሌላ አውድ ላይ ዶክተር ሲሉ ራሳቸውን አይጠሩም። የጂል ባይደን ጉዳያ አነጋጋሪ የሆነውም ከሕክምና ውጭ ባሉ ዘርፎች በሦስተኛ ዲግሪ ስለተመረቁ ብቻ ራሳቸውን ዶክተር ብለው በትዊተር ሰሌዳቸው ላይ መሰየማቸው ነው። ቢቢሲ የውስጥ የስም አጠራር ደንብ እንደሚለው አንድ ግለሰብ "ዶ/ር" የሚል መጠርያ በዜናዎች ላይ ከስሙ ጋር አብሮ ለመጠቀም በሕክምና ወይም ደግሞ በአንዳንድ ቤተክርስቲያን አገልግሎት ዘርፍ የዶክትሬት ዲግሪ የያዘ መሆን ይኖርበታል ይላል።
49415393
https://www.bbc.com/amharic/49415393
የሃገሪቱ ፖለቲካዊ ሁነቶች በአልባሳት አሰያየም ላይ
ከሰሞኑ ምናልባት ትግራይ ሄደው በአንደኛው ልብስ መሸጫ መደብር ውስጥ 'ደብረጽዮን' አለ? ሲባል ሲሰሙ ምናልባት የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት እዚህ ሱቅ ውስጥ እንዴት ይኖራሉ? የሚል ስሜት ሊፈጥርብዎት ይችላል።
ነገር ግን የሃገር ባህል ልብስ መሆኑን ሲሰሙ ይገረሙ ይሆን? እንዴት ነው ስያሜውን ያገኘውስ የሚል ጥያቄን ይጭርብዎት ይሆናል። በየአመቱ ከነሐሴ 14 ጀምሮ ለሶስት ቀናት በአማራ ክልል በሰቆጣና በላሊበላ ሻደይ፣ አሸንድየ፤ በትግራይ ክልል አሸንዳ ክብረ በዓል ሴቶችን ማዕከል በማድረግ ይከበራል። በዚህም ክብረ በዓልም ዋነኛው ትኩረት አልባሳት ሲሆን በየአመቱም አዳዲስ የልብስ ዲዛይኖችም የሚታዩበት ነው። በዚህ አመትም በትግራይ ክልልና በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ህብረ ቀለም ያሸበረቁ ልብሶች ቀርበዋል። ከዚህም በተጨማሪ የሃገሪቱ ወቅታዊና የፖለቲካ ግለቶች የተንፀባረቁባቸው የአልባሳት ስያሜዎችም ተሰጥተዋቸዋል። በመቐለ ከተማ የሃገር አልባሳትን በመስፋት ሽርጉድ ሲል ቢቢሲ ያገኘው የማነ ለቢቢሲ እንደገለፀው በዚህ አመት ዋነኛ ተፈላጊው ልብስ ደብረፅዮን የሚል ስም ተሰጥቶታል። ደብረፅዮን የሚባለው ልብስ የትግራይ ክልል ሰንደቅ አላማ በዋነኝነት ይዟል። "ዘንድሮ በጣም ተፈላጊ የሆነው ይሄው 'ደብረጽዮን' የሚባለውነው። ብዙዎቹም እየሸመቱት ነው። የትኛው ነው ደብረጽዮን እያሉ ይጠይቁንና ይወስዱታል" ብሏል። ትግራይ በዚህ አመት ህይወታቸውን ያጡ ጄኔራሎችን በአልባሳት ስምም እየዘከረቻቸው ነው። ከዚህ በተጨማሪ በቀድሞው የመረጃና ደህንነት ኃላፊ ጌታቸው አሰፋ፣ በዚህ አመት ህይወታቸውን ባጡት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም የተሰየመው ሰዓረ መኮንን እንዲሁም ሜጀር ጄኔራል ገዛኢ አበራ እና ጌታቸው ረዳ በመሳሰሉት የተሰየሙ አልባሳትም ለገበያ ቀርበዋል። በባለፉት ስምንት አመታት የአሸንዳን በዓል ያከበረችው መርሂት ገብረ አሸንዳ "የነጻነት ቀኔ ናት" ትላለች ለአሸንዳ ለየት ያለ ፍቅር ያላት መርሂት በተለይ ደግሞ አሸንዳ ስትመጣ በየዓመቱ አዳዲስ አልባሳትና ዲዛኖች ይዛም ስለምትመጣ፤ እንዲሁም ከጓደኞቿ ጋር በደስታ ፈንጥዘው የሚያሳልፉባቸው ቀናት በመሆኑ እንድትናፍቃት አድርጓታል። በየአመቱም ከጓደኞቿ ጋር ዋነኛ መወያያቸው በዓሏ ምን አይነት አዲስ ዲዛይን ይዛ ትመጣ ይሆን የሚለው ነው። • ሻደይ፦ለሴቶች፣ በሴቶች ፌስቲቫል በዓሏ በቡድን በቡድን ተለይተው የምትከበር በመሆኑ ደግሞ፤ የእያንንዱ የቡድኑ አባላት አንድ ዓይነት ምርጫ ላይ ለመድረስ ሁሌም እንደሚቸገሩ መብርሂት ትናገራለች። ምንም እንኳን በመጨረሻ አንድ ዓይነት ቀለም እና አሰራር ምርጫ ላይ መድረሳቸው እንደማይቀር መብርሂት ትናገራለች። አሁን አሁን ይሄው ምርጫቸውን የሚያወሳስበው ደግሞ ሌላ ጉዳይ ታነሳለች። "በተለይ በቅርቡ ዓመታት የምንመርጠው ጨርቅና አሰራር ዘዴ ብቻ ሳይሆን ለአልባሳቱ የሚሰጠው ስያሜም ፤ 'ይሔ ይሻለናል' 'ይሄ ይሻላል' ስንባባል ክርክሩ እንደሚቀጥል" ትናገራለች። የአሸንዳ ልብስ ስያሜውን ከማን ነው የሚያገኘው? በመቐለ ከተማ ዓዲ ሓቂ ለረዥም ዓመታት በልብስ ስፌት ስራ የተሰማራው ጀማል ወሃቢ ረቢ የአሸንዳ በዓል ከፍተኛ ገበያ የሚያገኝበት ጊዜ ነው። በልጃገረዶቹ ምርጫ የተለያዩ ልብሶች ሰርቶ የሚያቀርብ ሲሆን የአልባሳቱ ስያሜዎች ብዙዎቹ ከአምጪዎች እንደሚያገኝ ይገልፃል። • ሜድ ኢን ቻይና- የሀገር ባህል አልባሳቶቻችን አንደኛው ደረጃ ልብስም በሜትር 170 ብር እየተሸጠ እንደሆነ ሪፖርተሮቻችን ታዝበዋል። ቀደም ሲል የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ የመጡበት ወቅት ስለ ነበር 'ኦባማ' የሚባል ልብስ አንደኛ ሆኖ ሲሸጥ ነበር። ከእሱ በኋላም በቃና የቴሌቪዥን ጣብያ 'ቃና' የሚል ልብስ ተወዳጅ ሆኖ ገበያውን ተቆጣጥሮት እንደነበርም ቢቢሲ ያናገራቸው ግለሰቦች ተናግረዋል። ልጃገረዶቹ ብቻ ሳይሆን በሚዲያዎችም ባህላዊ ልብሳቸውን አሸንዳን እንዲያከብሯት በሚድያ ቅስቀሳ ሲደርግ ተስተውሏል። የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ምክትል ሐላፊ ወ/ሮ ዘነቡ ሓለፎም ገበያው በየዓመቱ 'ዘንድሮ ምን ተባለ' በሚል ወቅታዊ ሁኔታዎች ከፍተኛ ተፅእኖ ውስጥ እንደሚወድቅ ተናግረዋል። "አሸንዳ ባህላዊ ትውፊት አላት። በየዓመቱ የምትቀያየር ባህል መሆን የለባትም። በተለመደውና የቀደመው አለባበስ ዘይቤን ጠብቃ ነው መከበር ያለበት"ይላሉ። • ፊቼ ጨምበላላ፦ የሲዳማ ሕዝብ አዲስ ዓመት "አሸንዳ ፋሽን አይደለችም። በየዓመቱ ልብሱ መቀያየር አለበት ብለን አናምንም። የልብሱ አሰራርና ዲዛይን በየግዜው ሊለያይ ይችላል። መከበር ያለባት ግን በአገር በቀል ጥበብ ልብስ ነው። ምክንያቱም አንደኛ ጥበቡ የራሳችን ለስንት ዘመን ከተውልድ ትውልድ እየተሸጋገረ የመጣ ነው። ሁለተኛ በርካታ የስራ ዕድልም ይፈጥራል።" ይላሉ "ዘንድሮ ለኪሳራ ተዳርገናል" በልብስ ስፌት የተሰማሩት ጀማልና የማነም በዓሏ ባህሏን ጠብቃ ብትከበር ያምናሉ።። ሆኖም፤ ባለፉት ዓመታት በአሸንዳ ጥሩ ትርፍ ያገኙ እንደነበር ዘንድሮ ግን ለኪሳራ እንደተዳረጉ ነው የሚናገሩት። "ጨርቁ አምጥተኗል። የሚድያ ቅስቀሳ መደረግ የነበረበት መጀመርያ ነበር። እኛም አንከስርም ነበር። ይዘነው ቁጭ ብለናል። ቀድመው ይህንን በሚድያ ቢያደርጉት ጥሩ ነበር" ይላል የማነ።
news-56708099
https://www.bbc.com/amharic/news-56708099
የጃክ ማ ኩባንያ አሊባባ በቻይና የ2.75 ቢሊዮን ዶላር ቅጣት ተጣለበት
የአለማችን ግዙፉ የበይነ መረብ የንግድ ኩባንያ አሊባባ በቻይና የ2.75 ቢሊዮን ዶላር ቅጣት ተጥሎበታል።
ይህ የገንዘብ መጠን ክብረወሰን ነው ተብሏል። የቻይና ተቆጣጣሪዎች አሊባባ የገበያውን ስርዓት ለአመታት ያህል በበላይነትና በብቸኝነት የተቆጣጠረበት መንገድ ክፍተት አግኝተንበታል ብለዋል። ኩባንያው በበኩሉ ባወጣው መግለጫ ውሳኔውን እንደሚያከብርና እንደሚፈፅም አስታውቋል። የገበያ ስርዓት ተንታኞች በበኩላቸው ይህ ቅጣት ቻይና በኢንተርኔት የግብይት ስርዓት የሚፈፅሙና ፤ አይነኬ ነን ብለው ለሚያስቡ ግዙፍ ኩባንያዎችን እንደማትተው ማሳያ ነው ተብሏል። ኩባንያው ከቻይና ውጭ እውቅና እምብዛም ባይኖረውም በቻይና ግን አድራጊና ፈጣሪ እንደሆነ የቢቢሲው ዘጋቢ ሮቢን ብራንት ከሻንጋይ ይናገራል። አሊባባ አማዞንና ኢቤይ የተሰኙት ኩባንያዎች በጥምረት እንደማለት እንደሆነ የቢቢሲ ዘጋቢ አክሏል። የኢንተርኔት ንግድ ላይ በዋነኝነት የሚሰራው ይህ ኩባንያ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ዘርፉን በማስፋት ብድር፣ እንዲሁም የቴክኖሎጂ ክፍያ አፈፃፀሞችና ሌሎች ጉዳዮች ላይ እየተሳተፈ ነው ተብሏል። ኩባንያው ቻይና የጣለችበት ቅጣት ከሁለት አመት በፊት ያገኘው ገቢ አራት በመቶ ያህል ይሆናል እንደሆነም ተዘግቧል። የቻይና የገበያ ስርዓት ተቆጣጣሪዎች እንደሚሉት አሊባባ ውድድርን ለመግታትና ለማስቆም በሚል የተለያዩ ሁኔታዎችን ይጠቀም ነበር እንዲሁም ሌሎች ተወደዳዳሪዎች ከገበያው እንዲወጡ ሆን ብሎ ሰርቷል ይሉታል። የኩባንያው መስራች ታዋቂው ጃክ ማ በአንድ ዝግጅት ላይ የቻይና ተቆጣጣሪዎች ፈጠራን እየገቱ ነው በማለት ትችት ያዘለ ንግግር አድርገው ነበር። ከዚህም ጋር የተገጣጠመ በሚመስል መልኩ መንግሥት የባለሃብቱን የቢዝነስ አሰራር እየፈተሸና ጠበቅ ያለ ምርመራ መክፈቱን አሳወቀ። ጃክ ማ በቻይና ውስጥ የተሳካላቸው ባለሃብትና የስራ ፈጣሪ ናቸው። "ይህ ቅጣት በገበያው ላይ በበላይነትና በብቸኝነት የተቆጣጠረውን ኩባንያ አሰራር የሚያስቀር ይሆናል" በማለት ቦኮም ኢንተርናሽናል የተባለው ድርጅት ከፍተኛ ተመራማሪ ሆንግ ሃዎ ተናግረዋል። "በቻይና ከፍተኛ ስፍራ የተሰጠው ጉዳይ ነው። ገበያው በብቸኝነትና በበላይነት መቆጣጠሩ ጋር በተያያዘ ቅጣት እንዲጣልበት ብዙ ግፊቶች ነበሩ" ይላሉ። ሌሎች የአገሪቷ ግዙፍ ትልልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እንዲሁ ከፍተኛ ጫና እየደረሰባቸው ነው ተብሏል። በባለፈው ወር አገሪቷ ያወጣችው ገበያ በብቸኝነት መምራትና መቆጣጠር ህጎች ጥሰዋል ያለቻቸውን 12 ኩባንያዎች ቀጥታለች። ከነዚህም ኩባንያዎች መካከል ቴንሰንት፣ ባይዱ፣ ዲዲ ቹክሲንግ፣ ሶፍት ባንክ፣ ባይት ዳንስ ይገኙበታል።
news-57278891
https://www.bbc.com/amharic/news-57278891
በኢትዮጵያ ከ1.8 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት ወሰዱ
ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ መከላከያ መስጠት በጀመረች በሁለት ወራት ውስጥ ከ1.8 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ክትባት መስጠቷ ታወቀ።
የሐይማኖት አባቶች በተከተቡበት ጊዜ በአፍሪካ በርካታ ሰዎች በኮሮናቫይረስ ከተያዙባቸው አምስት አገራት መካከል አንዱ የሆነችው ኢትዮጵያ የበሽታውን መከላከያ ክትባት መስጠት መጋቢት 04/2013 ዓ.ም ነበር የጀመረችው። ከሁለት ወራት በፊት በኢትዮጵያ በቀዳሚነት ለህክምና ባለሙያዎች መሰጠት የጀመረው የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት እስከ ትናንት ድረስ ለ1 ሚሊየን 801 ሺህ 175 ሰዎች ደርሷል። የአገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ባወጣው ቅደም ተከተል መሠረት ክትባቱ ለበሽታው በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ ለሆኑና በበሽታው ቢያዙ ከባድ ጉዳት ሊደርስባቸው ለሚችሉ ሰዎች ነው ክትባቱ በቀዳሚነት እንዲሰጥ የተደረገው። በዚህም መሠረት የጤና ባለሙያዎች፣ ዕድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ ለሆኑና ዕድሜያቸው ከ50 እስከ 60 ሆኖ ተጓዳኝ ህመም ላለባቸው ሰዎች ቅድሚያ በመስጠት ክትባቱ እየተሰጠ መሆኑም ተገልጿል። ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት መስጠት ዘመቻዋን የጀመረችው ኮቫክስ ከተሰኘውና የኮቪድ-19 ክትባት ለደሃ አገራት እንዲደርስ ከተመሰረተው ዓለም አቀፍ የድጋፍ ጥምረት ባገኘችው 2.2 ሚሊዮን ብልቃጥ የአስትራዜኒካ ክትባት ነበር። በአገሪቱ በአገልግሎት ላይ እንዲውል ከአስትራዜንካ በተጨማሪ በኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ፍቃድ የተሰጠው የኮሮናቫይረስ ክትባት የቻይናው የሲኖፋርም የተባለው ይገኝበታል። በኢትዮጵያ ከተለያዩ ምንጮች እስከ መጪው ዓመት ኅዳር 2014 ዓ.ም ድረስ 20 ሚሊዮን ክትባት በማስገባት በመላዋ አገሪቱ ተሰራጭቶ ለሕዝቡ እንዲዳረስ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ቀደም ሲል ተነግሯል። የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው መረጃ መሠረት ለክትባቱ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ባለሙያዎችና የሕብረተሰብ ክፍሎች የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባቱን ማግኘታቸው የተገለጸ ሲሆን፤ የክትባቱ ሥርጭት ወደ ቀሪው ሕዝብ እንዲደርስ እየተደረገ ነው ተብሏል። የኮሮናቫይረስ ክትባት የመጀመሪያው ዙር ከተሰጠ በኋላ በሳምንታት ጊዜ ውስጥ ሁለተኛው ክትባት የሚሰጥ ሲሆን፤ የመጀመሪያውን ክትባት የወሰዱ ሰዎች ሁለተኛውን ክትባት መውሰድ ይጠበቅባቸዋል። የአፍሪካ በሽታዎች መቆጣጠሪያ ማዕከል መረጃ እንደሚያመለክተው ኢትዮጵያ 2.5 ሚሊዮን ብልቃጥ የአስትራዜኒካና የሲኖፋርም ክትባቶችን ያገኘች ሲሆን ይህም ከአጠቃላይ ሕዝቧ 1.09 በመቶውን ብቻ የሚሸፍን ነው። ኢትዮጵያ ከናይጄሪያ ቀጥላ በአፍሪካ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ያላት ስትሆን በበሽታው የተያዙ በርካታ ሰዎች ካሉባቸው የአህጉሪቱ አምስት አገራት መካከልም ትገኛለች። በዚህም ኢትዮጵያ ከደቡብ አፍሪካ፣ ከሞሮኖና ከቱኒዚያ ቀጥላ በአፍሪካ በርካታ በበሽታው የተያዙ ሰዎች የተገኙባት አገር ናት። ወረርሽኙ በኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱ ከታወቀበት ከመጋቢት 2012 ዓ.ም አንስቶ አስከ ትናንት ቅዳሜ ግንቦት 21/2013 ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ ከ2.7 ሚሊዮን በላይ የኮሮናቫይረስ ምርመራዎች የተደረጉ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥም ከ271 ሺህ በላይ ሰዎች ላይ በሽታው ተገኝቷል። በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ አብዛኞቹ ማለትም ከ230 ሺህ የሚበልጡት ከበሽታው ማገገመቻው የተነገረ ሲሆን 4 ሺህ 143 ሰዎች ደግሞ በበሽታው ሰበብ ለህልፈት መዳረጋቸውን የጤና ሚኒስቴርና የሕብረተሰብ ጤና ተቋም መረጃ ያመለክታል። ኢትዮጵያ የበሽታውን መስፋፋት ለመቆጣጠር ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብ ካልጣሉ የአፍሪካ አገራት መካከል አንዷ ስትሆን፤ ነገር ግን በርካታ ታማሚዎች ከተገኘባቸው አገራት መካከል ትገኛለች። በተጨማሪም ካላት የሕዝብ ብዛት አንጻር ቁጥሩ ዝቅተኛ ነው ቢባልም ከአህጉሪቱ አገራት መካከል በርካታ ክትባት አግኝታለች። አስካሁንም 1,801,175 ሰዎች የወረርሽኙን መከላከያ ክትባት ማግኘታቸው ተነግሯል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽን በዓለም ዙሪያ ከተስፋፋበት ጊዜ ጀምሮ ከ169 ሚሊዮን 598 ሺህ በላይ ሰዎች በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥም 3 ሚሊዮን 526 ሺህ በላይ ሰዎች ለሞት ተዳርገዋል። በሽታው ዓለምን ካዳረሰ ከአንድ ዓመት በኋላ በሽታውን ይከላከላሉ የተባሉ በርካታ ክትባቶች ይፋ ደርገው ጥቅም ላይ እየዋሉ ሲሆን አስካሁን ድረስ ከ1 ቢሊየን 834 ሚሊዮን ሰዎች በላይ ተከትበዋል።
47302367
https://www.bbc.com/amharic/47302367
'የተሳመው ከንፈር' ጥቃት ደረሰበት
ነገሩ የሆነው የዛሬ 74 ዓመት ነው። አንድ መርከበኛ አንዲትን ኮረዳ ከመንገድ ዳር ሳብ አድርጎ ከንፈሯን ጎረሰው።
ይህ ሲሆን አልፍሬድ አይዠንስታድ የሚባል ዕድለኛ ፎቶ አንሺ ድንገት በቦታው ነበር። ቀጭ፣ ቀጭ፣ ቀጭ አደረገው፤ ካሜራውን። ያ ፎቶ ሳር ቅጠሉን አነጋገረ። ዓለም ይህንን 'ድንገቴ መሳሳም' ወደደው። ሀውልትም ሠራለት። ስሙንም "የማያዳግም ፍቅር" ሲል ጠራው። ትናንት ታዲያ በዚያ ፎቶ ላይ የልጅቱን ከንፈር ሲስም የሚየታው የያኔው ጎረምሳ 95 ዓመት 'ሞልቷቸው' ሞቱ። ዓለም አዘነ። ስለዚያ ቅጽበታዊ ስሞሽም ይበልጥ መነጋገር ያዘ። • የዛሬ 74 ዓመት የተሳመው 'ከንፈር' ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ • ዓለም ሁሉ የሚያወራለት ክሪይፕቶከረንሲ ምንድነው? ለካንስ አንዳንዶች ያን ሀውልት ሲያዩ ደማቸው ይፈላ ኖሯል። ለካንስ መሳሳሙንም እንደ ጾታዊ ጥቃት ነበር የሚመለከቱት። ሌሊቱን አድብተው ጥቃት አደረሱበት። ሀውልቱ ላይ። ምነው ቢባሉ ያ 'መርከበኛ የልጅቱን ከንፈር የሳመው አስፈቅዶ ስለመሆኑ ምንም መረጃ የለም' አሉ። ነሐሴ 14፤ 1945፤ ኒውዮርክ የ2ኛው የዓለም ጦርነት በአሜሪካ ድል አድራጊነት መጠናቀቁ በተበሰረበት ወቅት ነበር እነዚህ ሁለት ተአምረኛ ከንፈሮች የተገናኙት። እርግጥ ነው አይተዋወቁም። ተያይተውም ተደባብሰውም አያውቁም፣ ከዚያ በፊት። ያን ዕለት ግን ድንገት ተገናኙ። ያገናኛቸው ደግሞ የጃፓን በጦርነቱ እጅ መስጠት ነው። የአቶ ጆርጅ ማንዶሳ እና የወይዘሪት ዚመር ፈሬድማን ከንፈሮች ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ይኸው እስከዛሬ ዓለምን ጉድ አሰኝተዋል።። ይህን ቅጽበታዊ ክስተት በፎቶ ካሜራ የቀለበው ዕድለኛ ሰው አልፍሬድ አይዠንስታድ ነው። እሱም "አረ እኔ ድንገት ነው፣ አስቤበትም አይደለም ያነሳኋቸው" ብሏል። • በካናዳ 7 ሕፃናት በእሳት ቃጠሎ ምክንያት ሞቱ ፎቶው እጅግ ዝነኛና ዓለምን በአውደ ርዕይ ያዳረሰ ሲሆን ላለፉት 74 ዓመታት ዝናውን የነጠቀው የለም። ይህ ሁሉ የሆነው ነሐሴ 14፣ 1945 ዓ.ም ነበር። ታዲያ የትናንቱ ልብ የሚሰብረው ዜና በዚያ ፎቶ ላይ ይታይ የነበረው ያ የያኔው መርከበኛ በተወለደ በ95 ዓመቱ ከዚህ ዓለም መለየቱ ነበር። ጥቃት አድራሾቹ ምን አሉ? በፍሎሪዳ ሳራሶታ የሚገኘው ይህ ሀውልት "አንኮንዲሽናል ሰሬንደር" የሚል ስም አለው። "ለማይናወጽ ፍቅር እጅ መስጠት" እንበለው? ወይስ "የማያዳግም ፍቅር"? ይህን ሀውልት ያልታወቁ ሰዎች ሌሊቱን በቀለም አበለሻሽተውታል። በሀውልቱ ላይ በጎረምሳው መርከበኛ እየተሳመች ያለችው ወይዘሪት ዚመር እግሮቿ ላይ "ሚቱ"(Me too) የሚል ጽሑፍ በቀይ ቀለም ተጽፎባት ታይቷል። ይህም ምናልባት ድርጊቱ በ'አክራሪ ጾተኞች' የተፈጸመ እንደሆነ ጥርጣሬን አሳድሯል። ፖሊስ የደረሰውን ጥፋት በገንዘብ አንድ ሺህ ዶላር ተምኖታል። ለብዙዎች የነዚህ ጥንዶች 'ድንገቴ ስሞሽ' በወቅቱ የነበረውን መጠን ያለፈ ደስታና ፈንጠዚያ የሚወክል ነው። ነገር ግን ክስተቱ በ'ጽንፈኛ ጾታ' ተሟጋቾች ዘንድ የተወደደ አይመስልም። የወቅቱን ፈንጠዚያ ከማሳየቱ ይልቅ ጾታዊ ጥቃትን ነው የሚዘክረው ብለው የሚሟገቱ አልጠፉም። ይህን እንዲሉ ያስቻላቸው መርከበኛው መንዶሳ የወይዘሪት ፍሬድማንን ስምምነት ሳያገኝ ነው ከንፈሩን ከንፈሯ ላይ ያሳለፈው በሚል ነው። እርግጥ ነው ከዓመታት በፊት (በ92 ዓመታቸው) የያኔዋ ኮረዳ ወይዘሪት ዚመር ፍሬድማን በሰጠችው (በሰጡት) ቃል "በ1945 ያ መርከበኛ የሳመኝ እኮ በፍቃዴ ሳይሆን እንዲያው ድንገት ደርሶ ጎተት አድርጎ ነበር ከንፈሬን የጎረሰው" ሲሉ የወቅቱን ሁኔታ አስታውሰው ነበር። ነገር ግን ይህን ቃል ሰጥተው በ2016 ሕይወታቸው ካለፈ በኋላ ልጃቸው ለኒውዮርክ ታይምስ እንደተናገረው እናቱ የያን ጊዜውን ድንገቴ ስሞሽ ያን ያህልም በአሉታዊ መንፈስ እንደማያዩት ተናግሯል። የሳሮሳታ ፍሎሪዳ ፖሊስ በሀውልቱ ላይ የደረሰውን ድርጊት በማኅበራዊ ሚዲያ ካሰራጨ ወዲህ በ'ጽንፈኛ ጾተኞች' ላይ ሰፊ ውግዘት መዝነብ ጀምሯል። "ጸታዊ ጥቃት በጥቅሉ የሚወገዝ ነው። ነገር ግን ይህ ፎቶ ያንን አያሳይም። በጭራሽ ከጥቃት ጋር የሚተሳሰር አይደለም። በእርግጠኝነት የምነግራችሁ ኮረዳዋን የሳሟትና ትናንት የሞቱት ሰው በዚያ ወቅት ድርጊቱን ሲፈጽሙ ጥቃት እየፈጸሙ አልነበረም።" ብላለች አንዲት አስተያየት ሰጪ። ሌሎች ደግሞ ይህን የአክራሪ ጾተኞችን ድርጊት ጸያፍና መጠን ያለፈ ብለውታል። "ይህን ያደረጉ ሰዎች ያሳዝናሉ። መርከበኛው በ95 ዓመታቸው ባረፉበት ማግስት ይህ መሆን አልነበረበትም" ብለዋል ሌላ አስተያየት ሰጪ። ሌሎች በአንጻሩ ሀውልቱ የሴቶችን ጥቃት የሚያንጸባርቅ በመሆኑ የሳራሶታ ከተማ ሀውልቱን እንዲያፈርሰው ጠይቀዋል። ሀውልቱም ስሙ "የማያዳግም ፍቅር" ሳይሆን "የማያዳግም ጥቃት" ነው መባል ያለበት ብለዋል።
48159597
https://www.bbc.com/amharic/48159597
በዲሞክራቲክ ኮንጎ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች በኢቦላ ሞቱ
በዲሞክራቲክ ኮንጎ በኢቦላ ወረርሽኝ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከአንድ ሺህ በላይ መድረሱን የሀገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር አስታወቀ።
በሀገሪቱ እጅግ አደገኛ የተባለለት የኢቦላ ወረርሽኝ ለሁለተኛ ጊዜ የተከሰተው ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ላይ ነበር። የዓለም የጤና ድርጅት ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ማይክል ራያን እንዳሉት ከሆነ በሀኪሞች ላይ እምነት ማጣት እና አመፅ ወረርሽኙ ወደ ሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል የሚያደርገውን ስርጭት ለመግታት የሚደረገውን ጥረት እክል ውስጥ ጥሎታል። ዶክተር ራያን አክለውም ከታሕሳስ ወር ጀምሮ በጤና ተቋማት ላይ የደረሱ 119 ጥቃቶች ተመዝግበዋል ብለዋል። • ዓለማችን የኩፍኝ ወረርሽኝ ያሰጋታል • ሕይወት ከኢቦላ ወረርሽኝ በኋላ • አለማችን የኩፍኝ ወረርሽኝ እንደሚያሰጋት አለም አቀፉ ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ የዓለም ጤና ድርጅት ባለሙያዎች የወርሽኙ ስርጭት ሊቀጥል እንደሚችል መተንበያቸውን በጄኔቫ በሰጡት መግለጫ ላይ አስታውቀዋል። የጤና ባለሙያዎች በርካታ ክትባቶች በእጃቸው ላይ እንደሚገኝ የተናገሩት ኃላፊው፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የህክምና ክትትሉን ጀምረዋል ብለዋል። ነገር ግን የታጠቁ አማፂያን የሚፈፅሟቸው ጥቃቶች እንዲሁም በሕክምና ባለሙያዎች ላይ እምነት ማጣት የመከላከል ጥረቱን እንዳይጎዳው ዶ/ር ራያን አስታውቀዋል። "አሁንም የማህበረሰብቡን ቅቡልነትና እምነት የማግኘት ፈተና አለብን" ብለዋል። በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኢቦላ ብቻ ሳይሆን በኩፍኝ ወረርሽኝም ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ፤ 50 ሺህ ሰዎች መታመማቸው ተመዝግቧል። የዓለም አቀፉ ጤና ድርጅት ኩፍኝ በሀገሪቱ ካሉ 26 ግዛቶች በ14ቱ መከሰቱን አስታውቋል። ይህ ደግሞ ከተማና ገጠርን ሳይለይ መሆኑን አስምረውበታል። ኢቦላ በሀገሪቱ ሁለት ግዛቶች ብቻ የተከሰተ ሲሆን ስርጭቱን ለመግታት ግን ባለው ግጭት ምክንያት አዳጋች ሆኗል። እንደ ዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ከሆነ ወደ ቀሪው የዓለም ክፍል የመሰራጨት እድሉ የመነመነ ቢሆንም የኮንጎ ጎረቤት ሀገራትን ግን ያሰጋል። ኢቦላ ከ2013 እስከ 2016 በምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ተከስቶ ከ 11 ሺህ ሰዎች በላይ መሞታቸው ይታወቃል።
44756709
https://www.bbc.com/amharic/44756709
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከ20 ዓመታት በኋላ አዲስ ምዕራፍ ከፈቱ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከሃያ ዓመታት በኋላ ኤርትራን ለመጎብኘት በመጓዝ ወደ አሥመራ ከገቡ በኋላ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ መሪ ሆኑ።
ለዚህ ጉብኝት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጋር የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)፣ የተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ የፌዴሬሽም ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂምና የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮ ሃላፊው አቶ አህመድ ሽዴ አብረዋቸው ተጉዘዋል። ለጉብኝቱ የኤርትራ መንግሥት ከፍ ያለ ትኩረት ሰጥቶ ዝግጅት ሲያደርግ የቆየ ሲሆን በተለያዩ ከተሞች ከባለፈው ሳምንት ማብቂያ ጀምሮ ደማቅ አቀባበል ለማድረግ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል። • የኤርትራ ልዑካን ቡድን አባላት አዲስ አበባ ደርሰዋል • ኢትዮጵያና ኤርትራ፦ ከእራት በኋላ ምን ተወራ? ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሥመራ ሲደርሱ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና ከፍተኛ የኤርትራ ባለስልጣናት በአየር ማረፊያው ተገኝተው አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች ጎዳና ላይ የዘንባባ ዝንጣፊ በመያዝ ለጠቅላይ ሚኒስትሩን ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ለጠቅላይ ሚኒስተሩ አቀባበል ለማድረግ በአስመራ ጎዳናዎች ላይ ከወጡት ተሳታፊዎች መካከል አንዱ "የኤርትራ ህዝቦች ለሰላም ብዙ መሰዋዕትነት ከፍለዋል። ከ20 ዓመታት ድካምና ትዕግስት በኋላ የመሰዋዕታችንን ውጤት በዲፕሎማሲ፤ በሰላም ጥሪ እና በእድገት መልክ እያየነው ነው።'' በማለት የነበረውን ስሜት ገልጿል። ሌላኛው የአስመራ ነዋሪ በበኩሉ "ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ወንድሞቻቸውና ወደ ሃገራቸው ነው የመጡት። እኛ ለብዙ ዘመናት ስናልመው የነበረውን ሰላም እውን አድርገዋል። በብዙ ምክንያት ሳይሳካ የቀረውን ሰላም እንድናየው ረድተውናል። እንኳን ወደ አስመራ በደህና መጡ።'' ብሏል። ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አቀባበል በአሥመራ ጎዳና ላይ በጃፓን የኤርትራ አምባሳደር የሆኑት እስጢፋኖስ አፈወርቂ የጠቅላይ ሚኒስትሩን አቀባበል ደማቅነትን በተመለከተ ባሰፈሩት መልዕክት "በኤርትራ ታሪክ የዛሬውን ያህል ለየትኛውም የሃገር መሪ ጉብኝት የሞቀ አቀባበል ተደርጎ አያውቅም" ብለዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጽህፈት ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ ፍፁም አረጋ በበኩላቸው በትዊተር ገፃቸው ላይ እንዳሉት "ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለታሪካዊው ጉብኝት አሥመራ ሲደርሱ በፕሬዝዳንት ኢሳያስና በበርካታ ሕዝብ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል" ሲሉ አስፍረዋል። በናይሮቢ ከተማ የሚኖር መአሾ ሃበቴ ተስፋ ሚካኤል የተባለ ኤርትራዊ ''ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት ነው። ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ሁሌም ቢሆን ጎረቤታሞች ናቸው፤ ጎረቤታሞች ሆነውም ለዘልአለም ይቀጥላሉ።'' ሲል ያለውን ተስፋ ገልጿል። አክሎም በኤርትራ አንድ አባባል አለን፤ ''የምትተኛ ከሆነ ጎረቤትህም መተኛት አለበት''። በተፈጠረው ነገር ደስተኛ ነኝ። ለሁለቱም ሃገራት ሰላምን እመኛለው።'' ብሏል። • የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት ኢኮኖሚያዊ ትርፍ? ኢትዮጵያ የአልጀርሱን የድንበር ኮሚሽን ውሳኔን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ መወሰኗን ተከትሎ የተጀመረው የሁለቱን ሃገራት ግንኙነትን ለማሻሻል እየተደረገ ያለው ጥረት አንድ አካል የሆነው ይህ ጉብኝት ትልቅ እርምጃ እንደሆነ እየተገለፀ ነው። በዚህ ጉብኝት የሁለቱ ሃገራት መሪዎች ቀደም ሲል የተጀመሩ ንግግሮችን በመቀጠል ወደፊት ስለሚኖረው ግንኙነትና ትብብርን በተመለከተ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጋር በአሥመራ አየር ማረፊያ
news-47991048
https://www.bbc.com/amharic/news-47991048
ደስታና እንቅልፍ- የፀሃይ ብርሃን ለህይወት አስፈላጊ የሆነባቸው ምክንያቶች
እንደምትገኙበት የዓለም ክፍል ቀን ሊረዝምና ሊጨልም ቢችልም የሚያገኙት ብርሃን አስፈላጊነት ግን ጥያቄ የሌለው ነገር ነው። በሰሜናዊ ንፍቀ ክበብ አካባቢ የሚኖሩ ከሆነ ሌሊቶች በደቂቃዎች አጠር እያሉ ቀናት ደግሞ በተመሳሳይ መልኩ ረዘም ይላሉ።
በአንፃሩ ደግሞ በደቡባዊው ክፍል ለሚኖሩ በተቃራኒው ይሆናል። በደመናማና ጨለምለም ባሉት ወራትም ቤት ሞቅ ሞቅ አድርጎና ደረብረብ አድርጎ ሞቅ የሚያደርግ ምግብ መብላትም ደስ የሚል ነገር አለው። ነገር ግን የፀሃይ ብርሃን ለጤና ወሳኝ ነው። • በፀሐይ የሚሰራው የሕዝብ ማመላለሻ ጀልባ ብዙዎች ፀሃይ የምትፈነጥቅበትን ጊዜ በፍንጥዝያ ነው የሚቀበሉት። ይህ ጊዜ ሰዎች በደስታ ተሞልተው የሚጠብቁት የሚናፍቁትም ነው። ሰዎች በደስታና በልዩ ስሜት ሆነው ለምን ይጠብቃሉ? ለሚለው ሳይንስ መልስ ያለው ይመስላል። 1. ብርሃን ሰዓት ቆጣሪ ነው ቀናችን በ24 ሰዓት ዑደት የተወሰነ ነው። ይህ ዑደት መሬት በራሷ ዛቢያ ለመዞር የሚወስደው 24 ሰዓትን የተከተለ ሲሆን ሰርካዲያን ሰዓት ይባላል። ይህ የሰዎች የሰዓት ዑደት ያለምንም ሌላ ተፅእኖ ሁሌም የሚቀጥል ቢሆንም ሰውነት ግን ከምንም በላይ ብርሃንን ይከተላል። • የመይሳው ካሳ የልጅ ልጆች ይህ የሰውነት የውስጥ ክፍል ስርዓቶች ብርሃንን ይከተላሉ ማለት ነው። 2. ብርሃንን ተከትሎ መተኛትና መንቃት ብርሃን የመኝታና የመንቃትን ጊዜ ጠቋሚ ነው። ይህ የሚሆነው ብርሃን አእምሯችን የመተኛትና የመንቃት ጊዜን እንዲያውቅ በማድረግ ነው። በዚህ መልኩ መሸት ሲል አእምሯችን ለመተኛት የሚረዳንን ሜላቶኒን የተሰኘው ሆርሞን እንዲመረት መልእክት ያስተላልፋል። የተወሰኑ አየር መንገዶች ይህን የተፈጥሮ ዑደት ለመከተል መንገደኞች ሲሳፈሩ እራት ላይ ዘና የሚያደርግ ብርሃን ከዚያም ፀሃይ መጥለቂያ በሚመስል መልኩ ብርሃን በመልቀቅ መንገደኞቻቸው እንዲያሸልቡ ለማድረግ ይሞክራሉ። 3. ብርሃን እንቅልፍ ማጣትን ይከላከላል የኮምፒውተር፣ ታብሌትና ስልክ ስክሪኖች የሚለቁት ሰማያዊ ብርሃን ለመተኛች የሚረዳው ሆርሞን እንዳይለቀቅ ያደርጋል። በቅርቡ እየወጡ ያሉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከእንቅልፍ በፊት እነዚህ ነገሮችን ማስወገድን ይመክራሉ። እንዲያውም እነዚ ነገሮች በእንቅልፍ ሰዓት መኝታ ክፍል ሁሉ እንዳይገኙ ሁሉ ይመከራል። • ማህበራዊ ሚዲያዎችን መጠቀም የሌለብዎት ሰአት መቼ ነው? እንቅልፍ የመተኛት ችግር ካለብዎት የጠዋት ፀሃይን ማግኘት እንደሚረዳ ጥናቶች ያመለክታሉ። 4. ብርሃን ስሜታችን ላይ ተፅእኖ ያደርጋል በቀን የተወሰነ ብርሃን ማግኘት ለእንቅልፍ ብቻም ሳይሆን ለስሜታችንም ወሳኝ ነው። ከሰዎች ደስተኝነት ጋር በቀጥታ ይገናኛልና። ብርሃን ላይ ስንሆን አእምሯችን መልእክት ስለሚደርሰው ጥሩ ስሜት እንዲሰማን የሚያደርገው ሴሮቶኒን የተባለው ሆርሞን በደንብ እንዲመረት ያደርጋል። በተቃራኒው አነስተኛ የብርሃን የሚያገኙ ለድብርት የመጋለጥ እድላቸው ሰፊ እንደሆነ ይታመናል። ቀናት በሚያጥሩበት ወቅት የብርሃን እጥረት በሚያሳድረው ተፅእኖ ብዙዎች በተመሳሳይ የስሜት ችግር ይጠቃሉ። 5. የፀሃይ ብርሃን አጥንትን ያጠነክራል ሰውነት ከምግብ የሚገኘውን ካልሲየምና ፎስፈረስ መጠቀም እንዲችል የፀሃይ ብርሃን ወሳኝ ነው። እነዚህ ንጥረ ነገሮች ደግሞ ለአጥንት፣ ለጥርስና ጡንቻ መጠንከር እጅግ አስፈላጊ ናቸው። • እርቀ-ሰላም እና ይቅርታ፡ ከደቡብ አፍሪካ እስከ ኢትዮጵያ በተቃራኒው ከፀሃይ ብርሃን የሚገኘው ቫይታሚን ዲ (የፀሃይ ቫይታሚን) እጥረት የአጥንት ደካማነትንና የአጥንት መጣመምን ያስከትላል። በርግጥ በከፍተኛ ሁኔታ ለፀሃይ መጋለጥም ችግር እንደሚያስከትል አይዘነጋም።
50312800
https://www.bbc.com/amharic/50312800
የአጋላጩ መረጃ የቦይንግ ኦክስጅን አቅርቦት ላይ ጥያቄ አስነሳ
የቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላን በጉዞ ላይ ሳለ አደጋ ቢደርስ ተጓዦች ኦክስጅን ላያገኙ እንደሚችሉ አንድ የድርጅቱ የቀድሞ ሠራተኛ አጋለጠ።
ቦይንግ 787 ድሪምላይነር ጆን ባርኔት የተባለው ግለሰብ የሠራው ጥናት፤ አውሮፕላኑ ውስጥ በአደጋ ጊዜ ኦክስጅን የሚያሰራጨው መሣሪያ የተበላሸ ወይም የማይሠራ መሆኑን እንዳሳየው ይፋ አድርጓል። በአንድ የቦይንግ ማምረቻ ፋብሪካ ውስጥ ሆን ተብሎ የማይሠሩ መሣሪያዎች እንደሚገጠሙም አጋላጩ ተናግሯል። • ቦይንግ ትርፋማነቴ ቀንሷል አለ • ቦይንግ 737 ወንዝ ውስጥ ገባ ቦይንግ የጆን ባርኔትን ክስ አጣጥሎ፤ ሁሉም አውሮፕላኖቹ በጥራት እንደተሠሩና በደህንነት ረገድም አስተማማኝ እንደሆኑ ገልጿል። የድርጅቱ የቀድሞ የጥራት ተቆጣጣሪ ኢንጂነር ጆን፤ በጤና እክል ምክንያት ቦይንግን እስከለቀቀበት ጊዜ ድረስ ለ32 ዓመታት ሠርቷል። ቦይንግ በኢትዮጵያና በኢንዶኔዥያ 737 ማክስ አውሮፕላኖቹ ላይ የደረሰውን አደጋ ተከትሎ ከየአቅጣጫው ውርጅብኝ በዝቶበታል። ጆን ባርኔት 787 ድሪምላይነር በመላው ዓለም ረዥም ርቀት በመጓዝ የሚታወቅ አውሮፕላን ነው። ቦይንግ ለተለያዩ አየር መንገዶች ሸጦትም ትርፋማ ሆኗል። ጆን እንደሚለው ግን አውሮፕላኑን ለማምረት ጥድፊያ ስለነበር ለጥራቱ በቂ ትኩረት አልተሰጠውም። ቦይንግ በበኩሉ ይህ መረጃ ስህተት እንደሆነና ድርጅቱ ለጥራት ቅድሚያ እንደሚሰጥ ገልጿል። አጋላጩ ጆን፤ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር 2016 ላይ ለቢቢሲ እንደገለጸው፤ አደጋ ሲከሰት ኦክስጅን የሚያሰራጨው መሣሪያው ላይ ችግር አስተውሏል። ይህ መሣሪያ በአግባቡ ካልሠራ፤ የአውሮፕላኑ ተሳፋሪዎች ሕይወት አደጋ ውስጥ ይወድቃል። አውሮፕላኑ በ35,000 ጫማ ከፍታ እየበረረ ከሆነና የኦክስጅን ማሰራጫ መሣሪያው ካልሠራ፤ ተሳፋሪዎች በአንድ ደቂቃ ራሳቸውን ይስታሉ። በ40,000 ጫማ ከፍታ ደግሞ በ20 ሰከንድ ራሳቸውን ይስታሉ። ይህ ሞት ወይም የአዕምሮ ጉዳት ሊያስከትልም ይችላል። • ቦይንግ የ737 ማክስ ሶፍትዌርን አሻሽያለሁ አለ • ቦይንግ የአደጋውን የምርመራ ውጤት ተቀበለ ጆን 300 የኦክስጅን ማሰራጫዎች ላይ ምርመራ አድርጎ 75ቱ በተገቢው ሁኔታ እንደማይሠሩ ማረጋገጡን ይናገራል። ጉዳዩ በጥልቅ እንዲፈተሽ ለማድረግ ቢሞክርም የቦይንግ አመራሮች እንዳስቆሙትም አክሏል። በ2017 ለአሜሪካው የበረራ ተቆጣጣሪ ኤፍኤኤ ችግሩን ቢያሳውቅም አንዳችም እርምጃ አልተወሰደም። ኤፍኤኤ እንደሚለው ከሆነ ግን በወቅቱ ቦይንግ ይህንን ጉዳይ እየፈተሸ መሆኑን ተናግሯል። 2017 ላይ ኦክስጅን በአግባቡ የማያስተላልፉ መሣሪያዎች ከአገልግሎት ውጪ መደረጋቸውን ቦይንግ ገልጿል። ከእያንዳንዱ ተሳፋሪ ወንበር በላይ የሚገኘው የኦክስጅን ማስተላለፊያ በተደጋጋሚ መሞከሩንም አክሏል። ጆን ችግሮቹን ሲያጋልጥ፤ ቦይንግ በአንጻሩ የጆን ሙያዊ ታማኝነት ላይ ጥያቄ እንዲነሳ በማድረጉ፤ ጆን ቦይንግ ላይ ክስ መስርቷል። ቦይንግ በበኩሉ ሠራተኞቹ ማንኛውንም አይነት አስተያየትና ቅሬታ ለድርጅቱ እንዲያሳውቁ እንደሚያበረታታ እንዲሁም አስፈላጊውን ምርመራ እንደሚያካሂድም ተናግሯል። • ቦይንግ ለተጎጂ ቤተሰቦች 100ሚ. ዶላር ሊሰጥ ነው • ቦይንግ ለሟች ቤተሰቦች ካሳ ሊከፍል ነው ቦይንግ ውስጥ ስላለው አሠራር ያጋለጠ ሠራተኛ ጆን ብቻ አይደለም። ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ አየር መንገድ 737 ማክስ አውሮፕላን መከስከሱን ተከትሎ አራት የቦይንግ ሠራተኞች (የቀድሞ ወይም አሁንም ያሉ) ለኤፍኤኤ ጥቆማ አድርሰዋል። በቦይንግ 737 ማክስ ግንባታ ከተሳተፉ የቀድሞ ሠራተኞች አንዱ የሆነው አዳም ዲክሰን፤ ቦይንግ ውስጥ በፍጥነት በርካታ ምርቶች እንዲገባደዱ ጫና እንደሚደረግ ይናገራል። ይህንን ቅሬታ ጆንም ይጋራል። ባለፈው ወር የዴሞክራቶች የኮንግረስ አባል አልቢኖ ሲረስ፤ ከ737 ማክስ ዋና ኃላፊዎች አንዱ የላኩትን ኢሜል በማጣቀስ፤ የቦይንግ ሠራተኞች ከመጠን በላይ እንሚሠሩ መናገራቸው ይታወሳል። ቤተሰባቸው በቦይንግ ሊሳፈሩ ሲሉ ጥርጣሬ እንደሚገባቸውም ተናገረው ነበር። ቦይንግ አውሮፕላኖቹ አስተማማኝ እንደሆኑና ከኤፍኤኤ ጋር ሆኖ ጥልቅ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ገልጿል። መስከረም ላይ አዳዲስ ለውጦች ማድረጉን እንዲሁም የምርትና የአገልግሎት አስተማማኝነት ክፍል ማቋቋሙንም ተናግሯል።
48687056
https://www.bbc.com/amharic/48687056
ኢትዮጵያና ሌሎች ድሃ የአፍሪካ ሀገራት ለመድኃኒት ከዋጋው 30 እጥፍ ይከፍላሉ
እንደ ኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ፣ ጋና፣ ኬኒያ ያሉ ሀገራት አንድ መድሀኒት ከሚያወጣው ዋጋ 30 እጥፍ እንደሚከፍሉ በቅርቡ ይፋ የሆነ ጥናት አስታወቀ።
የምጣኔ ሀብታቸው ከዝቅተኛ እስከ መካከለኛ የሆኑ የአፍሪካ ሀገራት ፍትኑነታቸው ዝቅተኛ ለሆነ መድሀኒቶች ከፍተኛ ገንዘብ ይከፍላሉ ሲሉ የተናገሩት የሲዲጂ ከፍተኛ የጤና ባለሙያ ናቸው። እንደ ዛምቢያ፣ ሴኔጋል፣እና ቱኒዚያ ያሉ ሀገራት የሕመም ማስታገሻ የሆነውን ፓራሲታሞል ለመግዛት እንኳ አሜሪካና እንግሊዝ ከሚሸጥበት 30 እጥፍ ይከፍላሉ ብለዋል። ጥናቱን ያካሄደው ሲዲጂ የተባለ መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገ ድርጅት ሲሆን ከዝቅተኛ እስከ መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት 'ብራንድ' የሆኑና ተመሳስለው የተሰሩ መድሀኒቶችን ለመግዛት ከፍተኛ ገንዘብ እያወጡ ነው ሲል ተናግሯል። • ክትባት ከየት ተነስቶ የት ደረሰ • በኬንያ ከኢቦላ ጋር የሚመሳሰሉ ምልክቶች ያለባት ታማሚ ተገኘች ጥናቱን ካደረጉት ባለሙያዎች መካከል አንዷየሆነችው አማንዳ ግላስመን እንዳለችው በርካታ ሀገራት 'ብራንድ' የሆኑ መድሀኒቶች ለመግዛት ከፍተኛ ገንዘብ እያወጡ ሲሆን ነገር ግን በተቃራኒው ጥራታቸው የተረጋገጠ 'ብራንድ' ያልሆኑ ጄኔሪክ ተብለው የሚጠሩ መድሀኒቶችን በርካሽ ዋጋ ማግኘት ይችላሉ ብላለች። 'ብራንድ' የሆኑ መድሀኒቶች ሲባል ከፍተኛ ስምና ዝና ያላቸው የመድሀኒት አምራች ድርጅቶችን ስም ያዙ ማለት ብቻ ሲሆን መድሀኒቱን በማምረት ሂደትም ሆነ መድሀኒቱ በያዘው ፈዋሽ ንጥረ ነገር ላይ ምንም አይነት ድርሻ የለውም ስትል ታክላለች። የመድሀኒት ገበያ በድሀ ሀገራት "እየሰራ አይደለም" ያሉት ከሴንተር ፎር ዴቬሎፕመንት የመጡት ካሊፕሶ ቻልኪዶ ናቸው። እርሳቸው እንደሚሉት "የገበያ ውድድር የለም" ይህ ደግሞ የሆነው "የአቅራቢዎች ቅብብሎሹ በተወሰኑ ድርጅቶች ስለታጠረ ነው።" በሚሰሩበት ድርጅት የአለም አቀፍ ጤና ፖሊሲ ዳይሬክተር የሆኑት ቻልኪዶ በቅርቡ አንድ ጥናት ከባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን ይፋ አድርገዋል። • ሞሐመድ ሙርሲ ፍርድ ቤት ውስጥ ሞቱ በጥናቱ ላይ ገቢያቸው ዝቅተኛና መካከለኛ የሆነ ሀገራት የመድሀኒት ፍጆታቸው የተወሰኑ ላይ ብቻ የሚያተኩር ነው። ይህም ደካማ የሆነ የገበያ ወድድር፣ ቁጥጥርና ጥራት እንዲኖር አድርጓል። የበለጸጉ ሀገራት የህዝብ ገንዘብ እንዲሁም መድሀኒት ለመሸመት ያለው ውጣ ውረድ ጠንካራ ስለሆነ ርካሽ መድሀኒቶች ገበያው ላይ ይገኛሉ ሲሉ ይናገራሉ። ድሀ ሀገራት ግን ውድ መድሀኒቶችን ገዝተው ይጠቀማሉ ነገር ግን በአሜሪካና በእንግሊዝ ያየን እንደሆነ ርካሽና ብራንድ የሌላቸው ጄኔሪክ ተብለው የሚጠሩ የመድሀኒት ውጤቶች በገበያው ላይ 85 በመቶ ድርሻ አላቸው። በጣም ድሃ ሀገራት ለጋሽ ሀገራት መድሀኒት ሲገዙላቸው ተጠቃሚ ይሆናሉ፤ ምክንያቱም ያለ ማዘዣ የሚሸጡ መድሀኒቶች ዋጋቸው ዝቅ እንዲል ስለሚያደርግ ነው። ቻልኪዶ እንደሚሉት ከድሃ እስከ መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት "ዝቅተኛ ዋጋ ለማግኘት መደራደርና ጥራቱ የተጠበቀ ምርት ለማግኘት ይቸገራሉ" እንዲሁም በርካታ ዋጋውን የሚያንሩ ጉዳዮች አሉ የሚሉት ባለሙያዋ አንዳንዴ በግብርና እንዲሁም በሙስና ምክንያት ሊሆን ይችላል ሲሉ ያስቀምጣሉ። የቁጥጥር ደረጃው በላላ ቁጥር የመድሀኒቱም ጥራት እየወረደ እንደሆነ ይገመታል ሲሉ ባለሙያዋ ያብራራሉ። "የቁጥጥር አለመኖር ሰዎች መድሀኒቱ እንደማይሰራ እንዲሰማቸው ያደርጋል ስለዚህ ይሰራል ብለው ላሰቡት፣ ባይሰራም እንኳ፣ ተጨማሪ ገንዘብ ይከፍላሉ።" የወጣው ጥናት የማጠቃለያ ሀሳብ ብሎ ያቀረበው አለም አቀፉ ማህበረሰብ ከሌላው ጊዜ በተለየ ትብብር እንዲያደርግ እና የዓለም አቀፉ ጤና ድርጅት የፖሊሲ ማሻሻያ እንዲደረግ ነው። ይህም በተመረጡ ሀገራት ላይ የመድሀኒት ግዢና አስተዳደር ላይ ማሻሻያ ለማድረግ ይረዳል።
news-57217336
https://www.bbc.com/amharic/news-57217336
'ጥቁር ፈንገስ'፡ በሕንድ 9 ሺህ ገደማ ሰዎች በሚዩኮማይኮስስ በሽታ መያዛቸው ተረጋገጠ
ሕንድ ገዳይ በሆነው እና እየተስፋፋ ባለው የ'ጥቁር ፈንገስ' በሽታ የተያዙ ከ8 ሺህ 800 በላይ ሰዎች መዘገበች።
ሕንድ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከኮቪድ-19 ያገገሙ እና እያገገሙ ያሉ ህሙማንን በሚያጠቃው 'ጥቁር ፈንገስ' መያዛቸውን አረጋገጠች እምብዛም ያልተለመደውና ሚዩኮማይኮስስ የተባለው ይህ በሽታ 50 በመቶ ገዳይ ሲሆን አንዳንዶችን ደግሞ የዓይን ብርሃናቸውን ያሳጣል። ከቅርብ ወራት ወዲህ ሕንድ ከኮቪድ-19 ያገገሙ እና እያገገሙ ያሉ ህሙማንን የሚያጠቃውን በሽታ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ላይ አግኝታለች። ሐኪሞች እንደሚሉት በሽታው ኮቪድን ለማከም ከሚጠቀሙት ስቴሮይድ መድሃኒቶች ጋር ይያያዛል። የስኳር ህሙማንም ለዚህ በሽታ ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው። ሐኪሞች ለቢቢሲ እንደተናገሩት በሽታው ሰዎች ከኮቪድ 19 ካገገሙ ከ12 እስከ 18 ባሉት ቀናት ይከሰታል። በሕንድ በበሽታው ከተያዙት ሰዎች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የተመዘገበው በምዕራባዊ የሕንድ ግዛቶች ጉጃራት እና ማሃራሽትራ ነው። ቢያንስ 15 ተጨማሪ ግዛቶች ከ8 እስከ 900 በበሽታው የተያዙ ሰዎችን መዝግበዋል። የበሽታው ሥርጭት መጨመሩን ተከትሎም የሕንድ 29 ግዛቶች በሽታውን በወረርሽኝነት ሊያውጁ እንደሆነ ተነግሯል። በአገሪቷ በበሽታው የተጠቁ ህሙማንን ለማከም አዲስ የተከፈቱ ማዕከላት በፍጥነት እየሞሉ ነው። በማዕከላዊ ሕንድ ከተማ ኢንዶር በሚገኘውና 1 ሺህ 100 አልጋዎች ባሉት በማሃራጃ የሽዋንትሮ የመንግሥት ሆስፒታል ከሳምንት በፊት በቁጥር ስምንት የነበሩት ህሙማን ቅዳሜ ምሽት ቁጥራቸው ወደ 185 ከፍ ብሏል። የሆስፒታሉ የሕክምና ክፍል ኃላፊ ዶክተር ቪፒ ፓንደይ ከእነዚህ ህሙማን ከ80 በመቶ በላይ የሚሆኑት አፋጣኝ ቀዶ ሕክምና እንደሚያስፈልጋቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሆስፒታሉ በ'ጥቁር ፈንገስ' የተጠቁ ህሙማንን ለማከም 200 አልጋዎች ያሉት 11 ክፍል ማዘጋጀቱንም ኃላፊው አክለዋል። ከዚህ ቀደም በዓመት አንድ ወይም ሁለት በበሽታው የተያዙ ሰዎችን እንደሚያክሙ የተናገሩት ዶክተር ፓንደይ፤ አሁን ግን የበሽታው ሥርጭት መጨመሩ ያልተጠበቀ እንደሆነ ተናግረዋል። የጥቁር ፈንገስ በሽታው ከኮቪድ-19 በበለጠ ፈታኝ ነውም ብለዋል ዶክተር ፓንደይ። ህሙማኑ በሚገባና በቶሎ ሕክምናውን ካላገኙ የሞት ምጣኔው ወደ 94 በመቶ ከፍ ሊል እንደሚችል ተነግሯል። የሕክምናው ዋጋም ውድ እንደሆና በቂ የመድሃኒቱም አቅርቦት እንደሌለ ዶክተር ፓንደይ አክለዋል። ዶክተር ፓንደይ ከአራት ሆስፒታሎች 201 ህሙማን መረጃ ሰብስበው ነበር። ከእነዚህ መካከል አብዛኞቹ ከኮቪድ-19 ያገገሙ እና ወንዶች መሆናቸውን አመልክተዋል። አብዛኞቹም በስቴሮይድ መድሃኒቶች የታከሙና እንደ ስኳር በሽታ ያሉ ተጓዳኝ ህመሞች ያሉባቸው ነበሩ። በአራት ሕንዳውያን ዶክተሮች የተሠራ ጥናትም በሚዩኮማይኮስስ የተያዙ ከ100 በላይ የኮቪድ-19 ህሙማንን ተመልክቶ ነበር። ከእነዚህ መካከል 79 የሚሆኑት ወንዶች ሲሆኑ 83 የሚሆኑት ደግሞ የስኳር ህመም ያለባቸው ናቸው። በሁለት የሙምባይ ሆስፒታሎች በ45 የጥቁር ፈንገስ በሽታ ሕሙማን ላይ የተሠራ ሌላ ጥናትም በበሽታው የተጠቁት ሁሉም የስኳር ያለባቸው እንደነበሩ ወይም በስኳር ህመም ሳቢያ ተኝተው የሚታከሙ እንደነበሩ አመልክቷል። በርካታ ሕሙማንን ያከሙ የዐይን ቀዶ ሕክምና ዶክተር አክሻይ ናያር "በሚዩኮማይኮስስ ከተጠቁ ህሙማን በደማቸው ውስጥ ጤናማ የስኳር መጠን ያላቸው አልነበሩም" ሲሉ ለቢበሲ ተናግረዋል። ሚዩኮማይኮስስ ምንድን ነው? ሚዩኮማይኮስስ ያልተለመደና በፈንገስ የሚመጣ በሽታ ነው። በሽታው በአፈር ፣ በእፅዋት፣ በእንስሳት ጽዳጅ እና በበሰበሱ ፍራፍሬዎችና አትክልቶች ውስጥ ለሚፈጠረው 'ሚዩኮር' የተባለ ፈንገስ በመጋለጥ ይከሰታል። የዐይን ቀዶ ሕክምና ባለሙያው ዶ/ር አክሻይ ኔር እንደሚሉት ሚዩኮማይኮስስ በማንኛውም ቦታ፣ በአፈርና በአየር እንዲሁም በጤማና ሰዎች አፍንጫና ንፍጥ ውስጥ ይገኛል። በሽታው የፊትና የራስ ቅል መገጣጠሚያ አጥንቶች፣ አንጎል እና ሳንባ ላይ ጉዳት ያስከትላል። የስኳር በሽታ አሊያም እንደ ካንሰርና ኤች አይቪ በደማቸው የሚገኝ ሰዎች ያሉ በሽታ የመከላከል አቅማቸው ደካማ የሆኑ ሰዎችን እስከሞት ሊያደርስ ይችላል።
news-55968658
https://www.bbc.com/amharic/news-55968658
ኩባ ኢኮኖሚዋን ለግሉ ዘርፍ ክፍት ልታደርግ ነው
ኢንዱስትሪዎች በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ብቻ በሚንቀሳቀሱባት ኩባ አንዳንድ ዘርፎች ከመንግሥት እጅ ወጥተው በግሉ ዘርፍ ለባለሀብቶች ክፍት ሊደረጉ ነው።
የሥራና ሠራተኞች ሚኒስትር ማርታ ኤሌና እንዳሉት አሁን የግል ባለሀብት ሊገባባቸው የሚችሉ የኢንዱስትሪ ዘርፎች ከ127 ወደ 2000 እንዲሆኑ ተደርጓል። ይህም ማለት ጥቂት ዘርፎች ብቻ ናቸው በመንግሥት ይዞታ ሥር የሚቆዩት። የኮሚኒስቷ አገር ኩባ ባለፉት ዓመታት ምጣኔ ሀብቷ ክፉኛ መጎዳቱ ይታወሳል። ይህም የሆነው አንድም በወረርሽኝ ምክንያት ሲሆን ሁለተኛው የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በኩባ ላይ ጥሎት በነበረው ማዕቀብ ነው። ባለፈው የአወሮፓውያኑ ዓመት ብቻ የኩባ ኢኮኖሚ 11% ቁልቁል ተንሸራቷል። ይህም በ30 ዓመት ውስጥ የከፋው ነው ተብሏል። ኩባዊያን ለኑሮ መሠረታዊ የሚባሉንት እንኳ ለመሸመት ተችግረዋል። ሚኒስትሯ ማርታ 124 ኢንዱስትሪዎች ብቻ ናቸው ለግል ዘርፍ ክፍት የማይደረጉት ብለዋል። ሆኖም እነዚህ የትኞቹ እንደሆኑ ከመዘርዘር ተቆጥበዋል። አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ምናልባት እነዚህ በመንግሥት እጅ ብቻ ይቆያሉ የተባሉት ሚዲያ፣ ጤናና መከላከያ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ይሆናሉ ሲል ግምቱን አስቀምጧል። በኩባ በሺህ የሚቆጠሩ በግል ከተያዙ አነስተኛና ጥቃቅን እርሻዎች ሌላ በመንግሥት ያልተያዘው ዘርፍ በባለቤትነት የሚይዙት እንደ የነጋዴዎች ማኅበር፣ የእጅ ሙያ ባለቤቶች ማኅበር እንዲሁም የታክሲ አሽከርካሪዎች ማህበርና የመሳሰሉት ናቸው። የአገሪቱ 40 ከመቶ የሚሆነው የግል ቢዝነስ ከቱሪዝም ጋር የተያያዘ በመሆኑ ወረርሽኙን ተከትሎ ከፉኛ ተጎድቷል። ላለፉት 60 ዓመታት በአሜሪካና በኩባ መካከል የነበረው ቅራኔ መሻሻል አሳይቶ የነበረው በአውሮፓውያኑ 2015 ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማና የኩባው ራውል ካስትሮ ግንኙነታቸውን ጤናማ ለማድረግ መስማማታቸውን ተከትሎ ነበር። ይህን ተከትሎ የአሜሪካ ዜጎች ኩባን እንዲጎበኙ፣ አገር በቀል ኢንዱስትሪዎችም እንዲያብቡ የሚያስችሉ ሁኔታዎች ተፈጥረው ነበር። ሆኖም ይህ የትራምፕ ግንኙነቱን የማሻሻል ጥረት በተተኪያቸው ዶናልድ ትራምፕ ውድቅ ተደርጓል። የትራምፕ ደጋፊ የሆኑ የኩባ አሜሪካዊያን የኦባማን ከራውል ካስትስሮ ጋር መገናኘት የኮሚኒስት አገሯን የመለማመጥ ያህል ነው ብለው ሲቃወሙ ነበር። ትራምፕም የደጋፊዎቻቸውን ቅሬታ ሰምተው ኩባ ላይ ማእቀብ ጥለዋል። አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በምርጫ ቅስቀቸው ወቅት አገራቸው ከኩባ ጋር ያላትን ግንኘኙነት ለማደስ እንደምትፈልግ መናገራቸው የሚታወስ ሲሆን ነገር ግን ይህ አጀንዳ ምን ያህል ቅድሚያ የሚሰጡት ይሆናል የሚለው ግልጽ አይደለም።
news-51455090
https://www.bbc.com/amharic/news-51455090
በኮሮናቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1ሺህ ደረሰ
ቻይና ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን በአግባቡ አልያዙም ያለቻቸውን ከፍተኛ ባለስልጣናት ከሥልጣን ያነሳች ሲሆን በበሽታው ተይዘው የሞቱ ሰዎች ቁጥርም 1 ሺህ መድረሱ ተሰምቷል።
የቻይና ባለስልጣናት የኮሮና ቫይረስን ወረርሽኝን የያዙበት መንገድ በተደጋጋሚ ሲያስተቻቸው ነበር የሁቤይ ጤና ኮሚሽን የፓርቲው ጸሐፊ እንዲሁም የኮሚሽኑ የበላይ ኃላፊ ከሥራቸው ከተነሱት ባለስልጣናት መካከል ናቸው። እነዚህ ከፍተኛ ሹማምንት በቻይና ከበሽታው ጋር በተያያዘ ከስልጣናቸው የተነሱ የመጀመሪያዎቹ ከፍተኛ ባለስልጣናት ናቸው። • የአውስትራሊያ ሳይንቲስቶች ኮሮና ቫይረስን 'ሊያመርቱ' ነው የአካባቢው የቀይ መስቀል ምክትል ኃላፊም የመጣውን እርዳታ በአግባቡ ካለማድረስ ጋር በተያያዘ "ኃላፊነትን በተገቢው ሁኔታ አለመወጣት" በሚል ከሥራቸው ተሰናብተዋል። ሰኞ እለት በሁቤይ አውራጃ ብቻ 103 ሰዎች የሞቱ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገሪቱ ደግሞ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1,016 ደርሷል። ነገር ግን በቻይና በበሽታው አዲስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መሆኑ የተነገረ ሲሆን የሁቤይ አውራጃ የጤና ኮሚሽን በግዛቱ 2,097 ሰዎች መያዛቸውን ሰኞ ዕለት አስታውቋል። እንደ ሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኀን ዘገባ ከሆነ በሁቤይና በሌሎች ግዛቶች በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከኮረናቫይረስ ወረርሽን ጋር በተገናኘ ከሥራቸው የተሰናበቱ ሲሆን ምርመራ እየተደረገባቸው ያሉና ማስጠንቀቂያ እንዲደርሳቸው የተደረጉም መኖራቸው ተገልጿል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የቻይና ባለስልጣናት ወረርሽኙን የያዙበት መንገድ እያስተቻቸው ይገኛል። የኮረናቫይረስን አስቀድሞ በመለየት ያስጠነቀቀው ዶክተር መሞቱን ተከትሎ ከፍተኛ ቁጣ ተቀስቅሶ እንደነበር ይታወሳል። • ስለአዲሱ ኮሮና ቫይረስ ማወቅ የሚገባዎ ነጥቦች • ከሞት የታደገው ጎሽ ከቤት አልወጣም ብሎት የተቸገረው ኢትዮጵያዊ በአሁኑ ሰዓት በቻይና 42,200 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው የታወቀ ሲሆን ይህም ከዚህ ቀደም ከነበረው የሳርስ ወረርሽን ቀጥሎ ከፍተኛ የጤና ቀውስ መሆኑ ተገልጿል። የሁቤይ ጤና ኮሚሽን እንዳለው ከሆነ በአውራጃዋ ብቻ 31,728 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው የተመዘገበ ሲሆን ከእነዚህም መካከል 974 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል። አብዛኛው ሞት በሁቤይ ግዛት ዋና ከተማ ዉሃን ውስጥ የተከሰተ ነው። ይህች 11 ሚሊየን ነዋሪዎች ያሉባት ከተማ አሁን ድረስ እንቅስቃሴ ተገድቦባት ትገኛለች። ከቻይና ውጪ በዩናይትድ ኪንግደም ስምንት ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን መንግሥትም ይህንን የጤና ስጋት በሚመለከት ማስጠንቀቂያ ለዜጎቹ አስተላልፏል። የኮሮና ቫይረስ ከቀላል እስከ ከባድ የመተንፈሻ አካል ሕመም የሚያስከትል የቫይረስ ዝርያ ሲሆን ሞትን ሊያስከትል የሚችል ህመም ነው። ወረርሽኙ በሽታው ያለበት ሰው ሲያስነጥስ፣ ባልበሰሉ ምግቦች፣ ከታማሚው ሰው ጋር በሚደረግ የቅርብ ንክኪ ይተላለፋሉ። በበሽታው የተያዙ ሰዎች ትኩሳት፣ ሳል፣ የትንፋሽ መቆራረጥ እና የመተንፈስ ችግር ምልክቶች ይታይባቸዋል። በሽታው የጠናባቸው ሰዎች ላይ ደግሞ እንደ ሳምባ ምች እና ከባድ የመተንፈሻ አካላት ህመም ይስተዋላል።
48591303
https://www.bbc.com/amharic/48591303
አፍሪካ ቴክኖሎጂ በፍጥነት ሊጣጣሙ የቻሉ አይመስሉም፤ ሌላ አማራጭ ግን የላቸውም
ያልበለፀገ መሠረተ-ልማት የአህጉረ አፍሪካ ዕድገት ማነቆ መሆኑ አያጠራጥርም። ሎጅስቲክስ [ለጊዜው አቻ የአማርኛ ፍቺ ባናገኝለትም] ደግሞ ለዚህ አንዱ ምክንያት እንደሆነ ሲነገር እነሰማለን።
አፍሪካ ውስጥ የሚገኙ ኩባንያዎች ከምግብ እስከ አልባሳት በርካታ ቁሳቁሶችን ያመርታሉ፤ ወደ ገበያ ወስዶ መሸጥ ግን እንደሚታሰበው ቀላል አይደለም። ናይት ፍራንክ የተሰኘ አንድ አጥኚ እና አማካሪ ድርጅት የትራንስፖርት ዋጋ የአንድን ሸቀጥ ከ50 እስከ 75 በመቶ ያለውን ድርሻ ሊወስድ ይችላል ሲል ይተነትናል። • አምስቱ የአፍሪካ ቴክኖሎጂ ጎዳናዎች በ2018 ናይጄሪያ ውስጥ የሚገኝ ኮቦ360 የተሰኘ ድርጅት ግን አንድ መላ አመጣ፤ ድርጀቱ የፈጠረው የሞባይል መተግበሪያ [አፕ] ከአምራች እስከ ጫኝና አውራጅ ድረስ ያሉትን በአንድ ገመድ የሚያስተሳስር ነው። እርስዎ አምራች ቢሆኑ ከምርትዎ ጋር እስከ ወደብ መንከራተት አይጠበቅብዎትም፤ ስልክ እየደወሉ መጨነቅም ቀርቷል። እኒህን ተግባራት የሚከውነው እንግዲህ ይህ የሦስት ዓመት ጨቅላ ድርጅት ነው። ናይጄሪያ ውስጥ ያሉ ገበሬዎች ከእርሻቸው ከሚልኩት ምርት 50 በመቶው እንኳ በሰላም ነጋዴዎች ደጃፍ ከደረሰ አምላካቸውን ያመሰግናሉ። ታድያ ይህን የተረዳው መተግበሪያው የምርቶችን ደህንነት የሚያስጠብቅ መስመርም ዘርግቷል። የሴኔጋሏ ከተማ ዳካር ነዋሪዎች ወደ ገበያ መውጣት ቀንሰዋል። ኦንላይን መሸመት እየተቻለ ደግሞ የምን ጉልት ለጉልት መንከራተት ነው ያሉ ይመስላሉ። የኬንያዋ መዲና ናይሮቢም ብትሆን ከራስ ምታት መድሃኒት እስከ ዘይት ድረስ 'ኦንላይን' ሸምተው ቤት ድረስ ማስላክ ይችላሉ። ለዚያውም በግማሽ ሰዓት። ዕድሜ ጁሚያን [ምንም እንኳ ድርጅቱ አፍሪካዊ አይደለም እየተባለ ቢታማም] ለመሳሰሉ ድርጅቶች። • የሰዎችን ማንነት የሚለየው ቴክኖሎጂ እያከራከረ ነው 'ክዊኬሪ' የተሰኘ የሴኔጋል ኩባንያ እርስዎ ከየትኛውም ዓለም የገዙትን ዕቃ ቤትዎ ድረስ መጥቶ፤ አንኳኩቶ ያስረክብዎታል። የድርጅቱ ዋነኛ ተጠቃሚዎች ደግሞ ወጣቶች ናቸው። ለምሳሌ ያህል ኬንያንና ሴኔጋል አነሳን እንጂ በርካታ ሃገራት ቴክኖሎጂን ተጠቅመው ከጊዜ ጊዜ የዜጎቻቸውን ሕይወት ለማቅለል እየሞከሩ ነው። በቂ ነው ማለት ግን አይደለም። ተጀመረ እንጂ ገና ብዙ ርቀት መጓዝን ይጠይቃል ይላሉ በዘርፉ 'ጥርስ የነቀሉ' ባለሙያዎች። ለምሳሌ ለመሰል ቴክኖሎጂዎች የሚሰጠው ብድር ወለድ ከ12-20 በመቶ ያክል ነው። ይህ ደግሞ ድርጅቶቹ አትራፊ እንዳይሆኑ ማነቆ ሆኗል፤ ይላል የአፍሪካ ልማት ባንክ ዘገባ። • የኢንተርኔት ገበያ በሶማሊያ ናይጄሪያ እኛ በተለምዶ ባጃጅ የምንላቸው ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎች ኬኬ የተሰኘ ስያሜ አላቸው። እንደተመረቀ ሥራ ብርቁ የሆነው ሳሙኤል ኦጉንዳሬ 'ኬኬ ጋይ' የተሰኘ ድርጅት በማቋቋም አሽከርካሪዎች በድንቡ ለበሰው ደንበኛን እንደንጉስ እየተንከባከቡ እንዲያስተናግዱ ማድረግ ያዘ። «ሰዎች እኔን ተመልክተው ከትንሽ ነገር ተነስተው ስኬታማ ሊሆኑ እንደሚችሉ እንዲያምኑ እፈልጋለሁ» ይላል። ኢትዮጵያም ውስጥ እንደሌሎቹ ሃገራት አርኪ ባይሆንም መሰል ፈጠራዎችን ማየታችን አልቀረም። የበይነ-መረብ ጠንካራ አለመሆን ነገሮችን ሱሪ በአንገት ቢያደርጋቸውም። ኢትዮጵያም ትሁን አፍሪካ ይላሉ ባለሙያዎች. . . ኢትዮጵያም ትሁን አፍሪቃ ከቴክኖሎጂ ውጭ አማራጭ ያላቸው አይመስልም።
news-51797886
https://www.bbc.com/amharic/news-51797886
ሂዩማን ራይትስ ዋች ቡድኑ መንግሥት በምዕራብ ኦሮሚያ ኢንተርኔትና ስልክን እንዲከፍት ጠየቀ
ለሁለት ወራት በምዕራብ ኦሮሚያ ተዘግቶ የቆየውን የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲከፍት ሂዩማን ራይትስ ዎች ጠየቀ።
የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳለው የአገልግሎቶቹ መቋረጥ ቤተሰቦች መካከል ያለውን ግንኙነትንና ለኑሮ አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶችን ከማስተጓጎሉ በተጨማሪ መንግሥት በአካባቢው በታጣቂዎች ላይ እያካሄደ ያለውን ዘመቻ በተመለከተ የመረጃ ግርዶች እንዲፈጠር አድርጓል ብሏል። ከታኅሳስ 23/2012 ዓ.ም ጀምሮ የሞባይል ስልክ፣ የመደበኛ ስልክና የኢንተርኔት አገልግሎቶች በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙት የቄለም ወለጋ፣ የምዕራብ ወለጋና ሆሮጉድሩ ዞኖች ውስጥ ተቋርጦ መቆየቱን ያመለከተው ሪፖርቱ፤ በምሥራቅ ወለጋ ደግሞ በከተሞች አካባቢ ብቻ የጽሑፍ መልዕክትና የሞባይል አገልግሎት ቢኖርም የኢንተርኔትና የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎቶች ዝግ እንደሆኑ ነዋሪዎች ተናግረዋል ብሏል። የአገልግኦቶቹ መዘጋት የተከሰተው የመንግሥት ኃይሎች የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ታጣቂ ኃይል በሆነው ቡድን ላይ ዘመቻ በከፈተባቸው አካባቢዎች ሲሆን በቦታዎቹ "ግድያና የጅምላ እስርን ጨምሮ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች" መዘገባቸውን ሂዩማን ራይት ዋች ገልጿል። የድርጅቱ የአፍሪካ ቀንድ ዳይሬክተር ላይቲታ ባደር፤ የግንኙነት አገልግሎቶቹ መቋረጥ በአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ችግርን እያስከተለ በመሆኑ መንግሥት በአስቸኳይ በመክፈት እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል። የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ቡድኑ፤ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አስተዳደር ስር ማኅበራዊና ፖለቲካዊ አለመረጋጋቶች በሚያጋጥሙበት ወቅት ካለምንም ምክንያት የኮሚዩኒኬሽን አገልግሎቶችን ማቋረጥ እየተለመደ መጥቷል ብሏል። ማዕከላዊው መንግሥት ስለአገልግሎቶቹ መቋረጥ ምንም አይነት ማብራሪያ ባይሰጥም ጠቅላይ ሚኒስርቱ ፓርላማ ቀርበው እንዳረጋገጡት እርምጃው የተወሰደው "በጸጥታ ምክንያት ነው።" የገዢው ፓርቲ ቃል አቀባይ እርምጃው ከሚካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ ጋር ግንኑነት የለውም ነገር ግን ለዘመቻው መሳካት አስተዋጽኦ አድርጓል ማለታቸውን ድርጅቱ በመግለጫው ላይ ጠቅሷል። "ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ሕጎች ሰዎች ኢንተርኔትን ጨምሮ በየትኛውም አማራጭ በነጻነት መረጃን ማግኘትና ማስተላለፍን ይደግፋሉ። ከጸጥታ ጋር የተገኛኘ ክልከላም ሕግን መሠረት ማድረግና ለተባለው ችግርም ተመጣጣኝ መሆን ይገባዋል። ግልጽነት በጎደለው ሁኔታ የግኙነት መስመሮችን ማቋረጥና የሚቆይበት የጊዜ ርዝመት የመብት ጥሰትን ሊጋብዝ ይችላል" ብሏል ድርጅቱ። መግለጫው አክሎም ባጋጠመው የግንኙነት መስመሮች መቋረጥ ሳቢያ አራት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በሥራቸው ላይ እንቅፋት እንደገጠማቸው መናገራቸውን በመግለጽ፤ ሁኔታው በአካባቢዎቹ ባለው የጤና አገልግሎት አቅርቦትም ላይ ጫና መፍጠሩን ሰራተኞችን ጠቅሶ በሪፖርቱ ላይ አመልክቷል። በተጨማሪም በእርምጃው ሳቢያ ቤተሰብ መካከል ያለው ግንኙነት እንዲቋረጥ ማድረጉናና ተማሪዎችም መቸገራቸውን ገልጿል። ቀደም ሲል ተቃውሞዎች በተቀሰቀሱበት ወቅት፣ በፈተናዎች ጊዜና የሰኔ 15ቱ ግድያ ወቅት የኢንትርኔት አገልግሎት የተቋረጠ ሲሆን በእነዚህ ጊዜያት "መንግሥት ስለአገልግሎቱ መቋረጥም ሆነ መቼ እንደሚመለስ ምንም አይነት ማብራሪያ አልሰጠም" ሲል ሂዩማን ራይትስ ዎች ገልጿል። ወታደራዊ ዘመቻው በሚካሄድባቸው የምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢዎች ስላለው የስልክ አገልግሎት መቋረጥን በተመለከተ በአካባቢው የአገር መከላከያ ሠራዊት እየወሰደው ካለው ኦፕሬሽን ጋር የተያያዘ መሆኑን ከሁለት ሳምንት በፊት የጦር ኃይሎች ምክትል ኢታማዦር ሹም የሆኑት ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ለቢቢሲ አረጋግጠው ነበር። ኤታማዦር ሹሙ አክለውም "የስልክ አገልግሎት እንዲቋረጥ መደረጉ በአካባቢው በታጣቂዎቹ ላይ የሚወሰደውን እርምጃ ስኬታማ አድርጎታል" ብለውም ተናገረዋል። መንግሥት ታጣቂዎች ለማደን ያደርገው የነበረው ዘመቻ እንቅፋት ገጥሞት እንደነበረና የስልክ አገልግሎት እንዲቋረጥ መደረጉ "በጣም ነው የጠቀመን" ያሉት ጀነራል ብርሃኑ፤ ታጣቂዎቹ "የሞባይል ስልክ በመጠቀም ነው የመንግሥትን እንቅስቃሴ ለሁለት ዓመት ሲያከሽፉ የቆዩት" ብለው ለቢቢሲ ተናግረው ነበር።
news-44920707
https://www.bbc.com/amharic/news-44920707
በባሌ ዞን ጎባ ከተማ በተፈጠረው ግጭት የስድስት ሰዎች ሕይወት መጥፋቱ ተገለፀ
በባሌ ዞን በጎባ ከተማ ባለፉት ቀናት በተፈጠረ ግጭት የስድስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የከተማዋ ከንቲባ ዘይነባ ጣሀ ተናግረዋል። በርከት ያሉ ሰዎች ደግሞ በአቅራቢያ በሚገኝ የጤና ተቋም የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ነውም ብለዋል።
ግጭቱ የተጀመረው በባሌ የኦሮሞ ገበሬዎች ትግል ወቅት ግንባር ቀደም ታጋይ የነበሩት የሀጂ አደም ሳዶን ሐውልት በከተማዋ በሚገኝ አደባባይ መገንባትን በመቃወም ነው ያሉት ከንቲባዋ፤ ሐውልት የመገንባት ጥያቄው በአካባቢው ነዋሪዎች እና ሽማግሌዎች የቀረበ ነው ሲሉ ያስረዳሉ። ይህንን ጥያቄም መንግሥት ተቀብሎት ወደ እንቅስቃሴ መገባቱን ከንቲባዋ ለቢቢሲ ተናግረዋል። • በአዲስ አበባ የሚኖሩ የጎባ ተወላጆች ከኦሮሚያ ባለሥልጣናት ጋር ተወያዩ • ''የኤርትራ ኢኮኖሚያዊ ዕቅድ የተነደፈው በኢትዮጵያ ሃብት ላይ ነበር'' አምባሳደር አውዓሎም ወልዱ ሐውልቱ ሊቆም በታሰበበት አደባባይ ላይ ቀድሞ የነበረ የቀይ ቀበሮ ሐውልት አይፈርስም፤ የታሰበው ሐውልትም ሌላ ቦታ ላይ ይተከል የሚሉ ነዋሪዎች ቅሬታ ያቀረቡ መሆኑን ያስታወሱት ከንቲባዋ ይህ ቅሬታም ዞን ድረስ መድረሱን ተናግረዋል። በከተማዋ ነዋሪ የሆነና ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ግለሰብ ለቢቢሲ ሲያስረዳ በተፈጠረው ሁኔታ ላይ ከከንቲባዋ ሀሳብ ጋር ይስማማል። "የቀይ ቀበሮው ሐውልት ቀይ ቀበሮ እንኳን አይመስልም" ሲል የተቃውሞው ወደ አላስፈላጊ አቅጣጫ መሄዱን ያስረዳል። እንደ እርሱ እምነት በዚህ ግጭት ሌሎች ኃይሎች እጃቸው አለበት ይላል። ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ዕለት የባሌ ዞን አመራሮች በዚህ ጉዳይ ላይ ከህብረተሰቡ ጋር መወያየታቸውን የተናገሩት ከንቲባዋ በስብሰባው ላይ የተሳተፉት አካላት አብዛኛዎቹ የሐውልቱን መተከል ይቃወሙት እንደነበር ያስታውሳሉ። የሚቃወሙበትም ምክንያትም ከሐይማኖት ጋር እንደማይገናኝ አስረድተው ሀውልቱ መቆም እንደሌለበት በደፈናው ተቃውመዋል ብለዋል ከንቲባዋ። ከንቲባ ዘይነባ ጣሀ ሐሙስ ዕለት በከተማዋ የግጭት ምልክቶች መታየታቸውን ሰዎች በየፊናቸው በመሆን ይዝቱ አንደነበር ያስታውሳሉ። • የቻይና ግዙፍ ማሽኖች •ማንዴላን ውትድርና ያሰለጠኑት ኢትዮጵያዊ አርብ ዕለት በርከት ያሉ ከገጠር ቀበሌዎች ዱላ ይዘው የመጡ ነዋሪዎች ወደ ከተማዋ እንደገቡ፤ እንዲሁም አስተዳደሩ የመጣችሁት ለሰላም ከሆነ ዱላችሁን ጣሉ በማለት በርካቶች ዱላቸውን መጣላቸውን የተወሰኑም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል። "እነዚህ ወደ ከተማዋ የገቡ ሰዎች ቅዳሜ ዕለት መንግሥት ሳያውቅ ማለዳ ወጥተው የቀይ ቀበሮውን ሐውልት አፈራረሱት። ይህ ሲሆን ምንም አይነት ግጭት አልተፈጠረም። ሐውልቱን አፈራርሰው ከከተማዋ እየወጡ እያለ በአቅራቢያው ከሚገኝ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የደወል ድምፅ ተሰማ" የሚሉት ከንቲባዋ ይህንን የደወል ድምፅ የሰሙ የከተማዋ ነዋሪዎች መሳሪያ ታጥቀው ወጡ በማለት ግጭቱ መልኩን መቀየሩን ያስረዳሉ። ከዚህ በኋላም ከተማዋን ለቅቀው እየወጡ ከነበሩ ሰዎች ጋር ግጭት ተፈጥሮ የሰው ህይወት ላይ አደጋ ደርሷል ሲሉ የነበረውን ሁኔታ ተናግረዋል። ከተማዋ ውስጥ የታጠቁ ኃይሎች ነበሩ የሚሉት ከንቲባዋ የኦሮሚያ ፖሊስ ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ እስከ 12 ሰዓት ድረስ ከእነዚህ ኃይሎች ጋር ሲታኮሰ መዋሉን ሁኔታውን ለመቆጣጠር ግን ከአቅም በላይ እንደሆነበት ይናገራሉ። በዕለቱ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች አብዛኞቹ በጥይት ተመትተው እንደሆነ ለቢቢሲ ያስረዱት ከንቲባዋ አሁን መረጋጋት እንደታየም ጨምረው ተናግረዋል። ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገው የጎባ ከተማ ነዋሪ ወደ ከተማዋ በርካታ መሳሪያ ገብቷል የሚል ወሬ በሰፊው ይናፈስ እንደነበር ያስታውሳል። ነገር ግን እርሱ በዓይኑ ያየው ምንም አይነት ነገር እንደሌለ ለቢቢሲ ገልጿል። ከንቲባ ዘይነባ የከተማው አስተዳደር በነገው ዕለት ነዋሪዎችን ለማነጋገር እቅድ እንደያዘ ገልፀዋል። ሐጂ አደም ሳዶ በባሌ የኦሮሞ ገበሬዎች ትግል ወቅት ግንባር ቀደም የነበሩ ግለሰብ ሲሆኑ በኋላ ላይም በእነ ጄነራል ታደሰ ብሩ የሚመራው ሜጫና ቱለማ ማህበር የቦርድ አባል ነበሩ።
news-49792736
https://www.bbc.com/amharic/news-49792736
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ 300ሺህ ተማሪዎችን ለመመገብ እየተዘጋጀ ነው
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማው ትምህርት ቢሮ በተያዘው የትምህርት ዘመን ከ300 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ለመመገብ በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታወቀ።
የትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ወደ 300ሺህ የሚጠጉ በመጀመሪያ ደረጃ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎችን ለመመገብ ዝግጅት እየተደረገ ነው። • “ከተማ አስተዳደሩ የወሲብ ንግድን በህግ ወንጀል የማድረግ ስልጣን የለውም” የህግ ባለሙያ • በአዲስ አበባ ተማሪዎች በዲዛይነሮች የተዘጋጀ የደንብ ልብስ ሊለብሱ ነው "ከዚህ በፊት 70ሺህ ተማሪዎችን ስንመግብ ነበር። የምገባ ፕሮግራሙ የተማሪዎች የትምህርት ቅበላ አቅምን ከፍ ማድረጉን ስለተመለከትን ቁጥሩን ከፍ አደረግነው እንጂ፤ ምገባው የነበረ ነው።" ሲሉ አቶ ዘላለም ተናግረዋል። "በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ተማሪዎችን ስንመግብ ቆይተናል፤ አሁን ግን መርሃ ግብሩ በሁሉም ትምህርት ቤት ነው የሚከናወነው'' የሚሉት አቶ ዘላለም፤ የመመገቢያ አዳራሽ እና ማብሰያ ቦታዎች እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቁመዋል። በመንግሥት የመጀመሪያ ደረጃ ትምሀርት ቤቶች ውስጥ የሚማሩት አብዛኛዎቹ የተማሪዎች ወላጆቻቸው አነስተኛ ገቢ ያላቸው መሆኑን ያነሱት አቶ ዘላለም፤ "ልጆቻቸውን መግበው ወደ ትምህርት ቤት መላክ የማይችሉት በርካቶች ናቸው" ይላሉ። መርሃ ግብሩ የተማሪዎችን የትምህርት መቀበል አቅም ከፍ ከማድረጉ በተጨማሪ፤ በምግብ እጥረት ከትምህርት ቤት ይቀሩ የነበሩ ተማሪዎችን ቁጥር እንደሚቀንስ ይናገራሉ። • 360 ብር ለአንድ ሕጻን • በአሁኑ ወቅት በጣም ተፈላጊ የሆኑ የዲጂታል ዘርፍ ሥራዎች የትኞቹ ናቸው? የምገባ ፕሮግራሙን ወጪ የከተማ አስተዳደሩ እንደሚሸፍነው የሚናገሩት አቶ ዘላለም፤ ግብዓቶችን በማቅረብ እና በማብሰል ደግሞ የተማሪ ወላጆች ተደራጅተው እንደሚሳተፉ አክለዋል። "ይህ ፕሮግራም ለወላጆችም የሥራ እድል እየፈጠረ ነው" ሲሉ የተቀናጀ ስራ እየተሰራ ስለመሆኑ ማሳያ ይጠቅሳሉ። አቶ ዘላለም ጨምረው እንደተናገሩት በመንግሥት ትምህርት ቤቶች እየተካሄዱ የሚገኙት እድሳቶች ስላላለቁ የዘንድሮ ትምህርት ዘመን የፊታችን ሰኞ ላይጀምር ይችላል ብለዋል። "እድሳቶቹ ባለመጠናቀቃቸው፤ እስከ ዓርብ ድረስ አይተን ትምህርት የሚጀመርበት ቀን ልናራዝም እንችላለን " ብለዋል።
50272646
https://www.bbc.com/amharic/50272646
በማሊ ታጣቂዎች 53 ወታደሮችን ገደሉ
በሰሜን ምሥራቅ ማሊ ታጣቂዎች 53 ወታደሮች መግደላቸውን የአገሪቱ መንግሥት አስታወቀ። ባለፉት አሥር ዓመታት ከደረሱ ጥቃሮች ይህኛው የከፋ መሆኑም ተገልጿል።
የአገሪቱ ወታደራዊ ኃይል የደረሰው "የሽብር ጥቃት ነው" ሲል በትዊተር በኩል ገልጿል። • በማሊ በምትገኝ አንድ መንደር ውስጥ '100 ሰዎች ተገደሉ' • በማሊ 37 ሰዎች ገደማ በታጣቂ ተገደሉ እስላማዊ ታጣቂዎች እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር 2012 ላይ ሰሜናዊ ማሊን ሲቆጣጠሩ ማሊ ሰላሟን አጥታ ነበር። የማሊ ወታደሮች ከፈረንሳይ ወታደሮች ጋር በመተባበር አካባቢውን ከታጣቂዎቹ ቢያስለቅቁም አሁንም የደህንት ጥያቄዎች ይነሳሉ። ከጥቃቱ አሥር ሰዎች ቢተርፉም፤ ከፍተኛ የንብረት ውድመት እንደገጠማቸው የማሊ ቃል አቀባይ ያያ ሳንጋሬ ተናግረዋል። መናካ በተባለው አካባቢ ለደረሰው ጥቃት እስካሁን ኃላፊነቱን የወሰደ አካል የለም። • ታዳጊዎች ለ17 ቀናት መውጣት አቅቷቸው የቆዩበት ዋሻ ለጎብኚዎች ክፍት ሆነ • ታዳጊዎች ለ17 ቀናት መውጣት አቅቷቸው የቆዩበት ዋሻ ለጎብኚዎች ክፍት ሆነ መስከረም መጨረሻ ላይ ከቡርኪና ፋሶ ጋር ባለው የድንበር አካባቢ የሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ ላይ በደረሰው ጥቃት 38 ወታደሮች መገደላቸው ይታወሳል። ፈረንሳይ የምትደግፈው 'ጂ5 ሳሀል' የተባለው የጸረ ሰላም ኃይሎች መካች ቡድን ውስጥ ማሊ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ቻድ፣ ኒጀር እና ሞሪታንያ ይገኙበታል። አምስቱ አገራት መስከረም ላይ ለደረሰው ጥቃት ተጠያቂ ያደረጉት 'አናሳሩል ኢስላም' የተባለው ቡድን አባላትን ነው። ቡድኑ 2016 ላይ የተመሰረተው በጽንፈኛው ሰባኪ ኢብራሂም ማላም ዲኮ ሲሆን፤ ሰባኪው 2012 ላይ በሰሜን ማሊ ከታጣቂዎች ጋር መዋጋቱ ይነገራል።
news-49982797
https://www.bbc.com/amharic/news-49982797
በአፍሪካ የመጀመሪያው ስማርት ስልክ ማምረቻ ፋብሪካ በሩዋንዳ ተከፈተ
ሩዋንዳ በአፍሪካ የመጀመሪያውን ስማርት ስልክ ማምረቻ ከፈተች። ፋብሪካው በዋና ከተማዋ ኪጋሊ የሚገኝ ሲሆን በምረቃው ላይ ፕሬዚደንት ፓል ካጋሜ ተገኝተዋል።
በማራ ግሩፕ በተሰኘ የቴክኖሎጂ ኩባንያ፣ ማራ ኤክስና ማራ ዜድ ስማርት ስልኮችን የሚያመረተው ይህ ፋብሪካ ስልኮቹ የጎግልን አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም እንደሚጠቀሙ ተናግሯል። ስልኮቹ 5500 ብርና 3700 ብር አካባቢ ዋጋ ተተምኖላቸዋል። • እየበረታ በመሄድ ላይ ያለው የዋጋ ንረት አዙሪት • ራስዎን ካላስፈላጊ የስልክ ጥሪ እንዴት ይታደጋሉ? ሰኞ ዕለት ፋብሪካውን ጋዜጠኞች ተዟዙረው እንዲጎበኙ ከተደረገ በኋላ "ይህ በአፍሪካ የመጀመሪያው ስማርት ስልክ ማምረቻ ነው" ብለዋል የማራ ግሩፕ የበላይ ኃላፊ አሺሽ ታካር ለሮይተርስ። ታካር አክለውም ፋብሪካው ዒላማው ያደረገው ጥራት ላይ መሠረት አድርገው ለመክፈል የተዘጋጁ ግለሰቦችን ነው። በአፍሪካ ውስጥ ከሚሸጡ በርካታ ስልኮች መካከል አብዛኞቹ የሚመጡት ከቻይና ነው። እነዚህ ስልኮች ሁለት ሲም የሚወስዱ እንዲሁም ማራ ግሩፕ ከተመነው ዋጋ ባነሰ ለቀበያ የሚቀርቡ ናቸው። በኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ አልጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ የተለያዩ መለዋወጫዎችን ከቻይና በማስመጣት የሚገጣጠሙ ስማርት ስልኮች እንዳሉ ሚስተር ታከር ይናገራሉ። "እኛ በማምረት ደረጃ የመጀመሪያዎቹ ነን። ማዘር ቦርዱን፣ እንዲሁም በአጠቃላይ ንዑሳን ክፍሎቹን የምናመርተው እዚሁ ነው። በእያንዳንዱ ስልክ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ጥቃቅን ነገሮች አሉ" ሲሉ ተናግረዋል። በቀን 1200 ስልኮችን ያመርታል የተባለው ይህ ፋብሪካን ለማቋቋም 24 ሚሊየን ዶላር እንደወጣበት ተነግሯል። ፕሬዝዳንት ካጋሜ ፋብሪካው የሩዋንዳውያንን ስማርት ስልክ ተጠቃሚነት እንደሚጨምር ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል። በአሁኑ ሰዓት በሩዋንዳ ከሚገኙ ተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚዎች 15 በመቶው ብቻ ስማርት ስልክ ይጠቀማሉ።
news-56282077
https://www.bbc.com/amharic/news-56282077
አማራ ክልል፡ "የትግራይ ክልል ጥያቄ ካለው ለፌደራል መንግሥት ማቅረብ ይችላል"
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የወልቃይትና የራያ አካባቢዎችን በተመለከተ ያሚያቀርበው ጥያቄ ካለ በሕጋዊ መንገድ ማቅረብ ይችላል ሲል የአማራ ክልል አስታወቀ።
አቶ ግዛቸው ሙሉነህ የአማራ ክልል የመንግሥት ጉዳዮች ኮምዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ለቢቢሲ እንደተናገሩት "የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሚያነሳው ጥያቄ ተገቢነት የሌለው ክስ እና ውሃ የማይቋጥር ነው" ብለዋል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገብረ መስቀል ካሳ በአማራ ክልል ኃይሎች የክልሉ ግዛቶች መያዛቸውን ገልጸው፤ አካባቢውን ለቅቀው እንዲወጡ በተደጋጋሚ መጠየቃቸውን ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። በአማራ ክልል በኩል በወልቃይትና በራያ አካባቢዎች ቀደም ሲል አንስቶ የወሰንና የማንነት ጥያቄዎች ሲነሱ የቆዩ መሆናቸውን ያስታወሱት አቶ ግዛቸው፣ ለዚህ የሕዝብ ነው ላሉት ጥያቄ "በሕገ-መንግሥቱ መሠረት ምላሽ ሳይሰጥ መቆየቱን" ይናገራሉ። በጥቅምት ወር መጨረሻ በትግራይ ክልል የተቀሰቀሰውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ ከፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ጋር የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ተሰማርቶ እንደነበር የሚታወስ ነው። ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የህወሓት ኃይሎች በቅራቅር እና በሶሮቃ በኩል የከፈቱትን ጥቃት ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመሆን የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ "በተደራጀ መልኩ" መመከት ችለዋል ሲሉ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ አስታውሰዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የኤርትራ ሠራዊት እና የአማራ ክልል ኃይል ከትግራይ ክልል እንዲወጡ በቅርቡ ባወጣው መግለጫ ላይ ጠይቋል። ኃላፊው የክልሉ መንግሥት እነዚህን የራያና የወልቃይት አካባቢዎች በጊዜያዊነት እያስተዳደረ መሆኑን ገልፀው ሕግ የማስከበሩ ሥራ መቀጠሉን፣ የዕለት እርዳታ ማቅረብ እና የመንግሥት ተቋማትን መልሶ ማደራጀትና ሥራ እንዲጀምሩ እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል። እንደ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ገለጻ ከሆነ በአካባቢው አሁንም የሕግ ማስከበር ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸው የመንግሥት ተቋማት ወደ ሥራ እንዲገቡም ጥረት እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል። ኃላፊው አካባቢዎቹን በኃይል መያዝ ሕገ-መንግሥቱን አይጻረርም? ተብለው ተጠይቀው በየትኛውም ዓለም አቀፍ ሕግ ቢለካ ሕገ መንግሥቱን የሚጻረር ተግባር አይደለም ሲሉ መልሰዋል። ይህንንም ሲያስረዱ "ከመጀመሪያው በሕገ-መንግሥት ወይንም በአዋጅ የተወሰዱ ቦታዎች አይደሉም" በማለት በአሁኑ ወቅት የትግራይ ክልል "ጥያቄ ካለው በሕጋዊ መልክ ማቅረብ ይችላል" ብለዋል። ጨምረውም የአማራ ክልል አካባቢውን በጊዜያዊነት እያስተዳደረው መሆኑን ገልፀው የፌደራል መንግሥቱ በዘላቂነት መፍትሄ እንዲሰጠው ጥያቄያችን ይቀጥላል ብለዋል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የጽህፈት ቤት ኃላፊ በአማራ ክልል ኃይሎች የክልሉ ግዛቶች መያዛቸውን ገልጸው፤ "አስተዳደሩ ህወሓት ያስተዳድረው ከነበረው ግዛት በሴንቲሜትር የቀነሰ ክልልን አያስተዳድርም" ብለዋል። አቶ ገብረ መስቀል እንዳሉት ጊዜያዊ አስተዳደሩ በሕገ መንግሥቱ ላይ የተገለጸውን የትግራይ ክልልን እንደሚያስተዳድር ገልጸው፤ "እነዚህን ቦታዎች ከሕግ ውጪ የያዙ ኃይሎች የአገሪቱን ሕገ መንግሥት እየተጻረሩ ነው" ብለዋል። እንደ አማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ደግሞ "በሕግ ማስከበሩ ሂደት" ውስጥ እነዚህ የማንነት እና የወሰን ጥያቄዎችን "እግረ መንገዱን መልስ ሰጥቷል" ብለዋል። "በጉልበት ተወስዷል፤ በጉልበት ተመልሷል፤ በኃይል ተነጥቀናል በኃይል አስመልሰናል" ባሉት በዚህ እርምጃ "የተጠቀሱት አካባቢዎች የአማራ እንጂ የትግራይ አይደሉም፤ በዚህ ጉዳይ ላይ የውጭ ኃይልም ሆነ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ጣልቃ ሊገባብን አይገባም" ብለዋል። አጠቃላዩ ምዕራባዊ የትግራይ ክፍል እንዲሁም በደቡብ አላማጣ፣ ኮረምና ሌሎች የገጠር አካባቢዎች በአሁኑ ጊዜ በአማራ ክልል ስር መሆናቸውን ያመለከቱት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ፤ ይህም ለፌደራል መንግሥቱ ሪፖርት ተደርጎ ኃይሎቹ ከአካባቢዎቹ እንዲወጡ በተደጋጋሚ መጠየቃቸውን ገልጸዋል። "ግፊት የምናደርገው የተሰማራው ኃይል እንዲወጣ ብቻ ሳይሆን በአካባቢዎቹ የሚፈጸሙ ወንጀሎች እንዲቆሙና ፈጻሚዎቹ በሕግ እንዲጠየቁ ነው" ሲሉ አቶ ገብረ መስቀል ተናግረዋል። አቶ ግዛቸው "የትግራይ ክልል ቦታዎቹ የእኔ ናቸው፣ ይገባኛል የሚል ከሆነ አሰራሩን ተከትሎ በሕጋዊ መንገድ ይጠየቅ" በማለት የአማራ ክልልም "ሕጋዊ አካሄዱን ይቀጥላል" ብለዋል። ወልቃይት፣ ጠለምት፣ ሰቲት ሁመራ፣ ራያ፣ አላማጣ፣ ኮረም አካባቢዎች በአማራ ክልል መንግሥት ስር መሆናቸውን ኃላፊው አረጋግጠው፤ "በእነዚህ አካባቢዎች ያለው ሕዝብ ነጻነቱን በኃይል አውጇል" ብለዋል። በተጠቀሱት አካባቢዎች ባሉ የትግራይ ተወላጆች ላይ በደል ተፈጽሟል እንዲፈናቀሉም ተደርጓል በሚል ለቀረበው ክስም አቶ ግዛቸው ሲመልሱ "የትግራይ ተወላጆችም ከአማራ ሕዝብ ጋር አብረው የኖሩ አብረውም የሚኖሩ ናቸው። አንድም የትግራይ ተወላጅ እንዲገፋ አልተደረገም" በማለት በአካባቢው ባሉ የሥራ እድሎች ማንንም ሳይለዩ ቅጥር መፈፀማቸውን ተናግረዋል። ነገር ግን ግጭት ሲከሰት መፈናቀል የማይቀር ነው ያሉት ኃላፊው፤ ከአካባቢው ተፈናቅለው የነበሩት ነዋሪዎች እንዲመለሱ የክልሉ መስተዳደር አስፈላጊውን ሥራ እያከናወነ ነው ብለዋል። የአማራ ክልል እነዚህን የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባቸው አካባቢዎች "በህወሓት የአስተዳዳር ዘመን በኃይል የተወሰዱ ናቸው ይመለስልኝ ሲል ለዓመታት ጥያቄ ሲያቀርብ መቆየቱን" አቶ ግዛቸው ገልጸዋል። ጨምረውም በወቅቱም በአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ላይ መፈናቀልና ከዚያም ያባሱ በደሎች ተፈጽመዋል በማለት "አሁን ሕዝቡ ከዚህ አፈና ነጻ ወጥቷል" ብለዋል። በመሆኑም ጥያቄውን ሕጋዊ ለማድረግ ከፌደራል መንግሥት ጋር እየተነጋገሩ እንደሆነ የገለፁት ኃላፊው፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ ክልሉ በሕዝቡ ጥያቄ ላይ እንደማይደራደር ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የህወሓት ኃይሎች ትግራይ ውስጥ በሚገኘው የአገሪቱ ሠራዊት ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወታደራዊ ዕርምጃ እንዲወሰድ ማዘዛቸው ይታወሳል። ለሦስት ሳምንታት በተካሄደ ወታደራዊ ዘመቻ የፌደራሉ ሠራዊት የክልሉን ዋና ከተማ መቀለን ሲቆጣጠር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተካሄደው "ሕግ የማስከበር ዘመቻ" መጠናቀቁን አውጀው ነበር። ነገር ግን ከዚያ በኋላም ባለፉት ሦስት ወራት በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶች እየተካሄዱ መሆናቸውን ከክልሉ የሚወጡ ሪፖርቶችና የዓለም አቀፍ ተቋማት የገለጹ ነው። በጦርነቱ ምን ያህል ሰዎች እንደሞቱ በትክክል የታወቀ ነገር ባይኖርም በሺዎች የሚቆተሩ ሊሆኑ እንደሚችል ይገመታል። ከዚህ ባሻገር ግጭቱን በመሸሽ ከ60 ሺህ በላይ ሰዎች ወደ ሱዳን መሰደዳቸው የተነገረ ሲሆን፤ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ደግሞ የሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብ መንግሥትና ረድኤት ድርጅቶች ጥረት እያደረጉ ነው።
news-53873019
https://www.bbc.com/amharic/news-53873019
ካሊፎርኒያ የሰደድ እሳቱን ለማጥፋት የአውስትራሊያን እርዳታ ጠየቀች
የአሜሪካዋ ካሊፎርኒያ ግዛት ራስ ምታት የሆነባትን ሰደድ እሳት ለመዋጋት 12ሺህ የሚደርሱ የእሳት አደጋ ሰራተኞችን ብታሰማራም እስካሁን እሳቱ በቁጥጥር ሥር አልዋለም።
ካሊፎርኒያ ይልቁን የስድስት ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል። እሳቱ ጫካዎችንና እና ቤቶችን እያወደመ እንደሆነ የገለጹት የካሊፎርኒያ ግዛት አስተዳዳሪው ጋቪን ኒውሰም አደጋውን መቆጣጠር ከብዶናል ብለዋል። ከተለያዩ የአሜሪካ ክፍሎች እርዳታ እየመጣ እንደሆነም ገልጸዋል። አክለውም አውስትራሊያ እና ካናዳም ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። ''እሳቱ የሰው ኃይል አቅማችንን እያዳከመብን ነው'' ብለዋል ገዢው። እዚም እዚያም እየተከሰቱ የሚገኙት 560 የሰደድ እሳቶች ግዛቲቱ ከዚህ ቀደም ካስተናገደቻቸው መካከል ይህ መጠኑ ሰፊ መሆኑ ተገልጿል። በካሊፎርኒያ ያለው ከፍተኛው ሙቀት የሰደድ እሳቱን እያባባሰ መሆኑ ተነግሯል። አርብ ዕለት የድንገተኛ አደጋ ክፍል ኃላፊዎች እንደገለጹት በአንዳንድ አካባቢዎች የእሳቱ መጠን በእጥፍ እየጨመረ ሲሆን በዚህም ምክንያት 175ሺህ ነዋሪዎች ቤታቸውን ጥለው ለመሸሽ ተገደዋል። የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችን ጨምሮ እስካሁን በሰደድ እሳቱ 43 ሰዎች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን በመቶዎች የሚቆጠሩ ግንባታዎች ደግሞ እንዳልነበሩ ሆነው መውደማቸው ተገልጿል። በተጨማሪም በሺዎች የሚቆጠሩ ህንጻዎች አደጋ ላይ ናቸው። እሳቱ የተከሰተባቸው አካባቢዎች ተፈጥሮአዊ አቀማመጥ ምቹ አለመሆኑ ደግሞ የማጥፋትና የመከላከል ስራውን በእጅጉ ፈታኝ አድርጎተል። በተጨማሪም በአካባቢው ያለው ከፍተኛ ንፋስ ነገሮችን ከባድ አድርጎባቸዋል። እሳቱን ለመቆታጠር እስካሁን በርካታ እሳት አደጋ ሰራተኞች፣ መኪናዎችና አውሮፕላኖች ወደ አካባቢው የተንቀሳቀሱ ሲሆን እንደ ኦሪጎን፣ ኒው ሚክሲኮ፣ እና ቴክሳስ ያሉ ግዛቶችም ድጋፋቸውን እያደረጉ ይገኛሉ። የካሊፎርኒያ ገዢው ባስተላለፉት የእርዳታ ጥሪ ላይ ''በዓለማችን ቁጥር አንድ የሰደድ እሳት ተከላካይ ሠራተኞች'' ያሏት አውስትራሊያ ድጋፍ ታድርግልን ሲሉ ተማጽነዋል። ከዚህ በተጨማሪ የግዛቲቱ ነዋሪዎች የአየሩ ደህንነት እስካሁን ስላልተረጋገጠ ከቤታችሁ ባትወጡ ይሻላችኋል እየተባሉ ነው። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ግዛቲቱ የኤሌክትሪክ ኃይል ችግርም አጋጥሟታል። በካሊፎርኒያ በሚነሳው ተደጋገሚ እሳት እስካሁን በርካቶች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ከሁለት ዓመት በፊት በተከሰተው የሰደድ እሳት ቢያንስ 25 ሰዎችን መሞታቸው የሚታወስ ነው። ባሳለፍነው ዓመት ጥቀምት ላይ ደግሞ በሺዎች የሚቆጠሩ የሎስአንጀለስ ኗሪዎች መኖሪያቸውን ጥለው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ነበረ።
news-54291347
https://www.bbc.com/amharic/news-54291347
በፊንላንድ አውሮፕላን ማረፊያ ውሾች በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎችን በሽታ መለየት ጀመሩ
በመላው ዓለም በሚገኙ አውሮፕላን ማረፊያዎች ውስጥ አነፍናፊ ውሾችን መመልከት የተለመደ ነገር ነው።
እነዚህ ውሾች ሕገ-ወጥ ቁሶችን እና ኮንትሮባንድ አነፍንፈው ይጠቁማሉ። በፊንላንዱ ሄልሲንኪ-ቫንታ አውሮፕላን ማረፊያ ግን ለአነፍናፊ ውሾች የተሰጣቸው ኃላፊነት ለየት ይላል። አነፍናፊ ውሾች በኮሮናቫይረስ የተያዘን ሰው አሽትተው እንዲለዩ ለሙከራ ሥራ ተሰማርተዋል። 10 አሰልጣኞች 15 ውሾችን በአውሮፕላን ማረፊያው የሙከራ ሥራ አስጀምረዋል። የዚህ ግብረ ኃይል መሪ የሆኑት አና ሄለም-በጆርክማን፤ ውሾቹ ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተይዘው ምልክት ከማሳየታቸው ከአምስት ቀናት በፊት በበሽታው መያዛቸውን ይለያሉ ብለዋል። “በበሽታ የተያዙ ሰዎችን በመለየት ረገድ አስደናቂ ውጤት አስመዝገበዋል። ወደ 100 ፐርሰንት ተጠግተናል” ብለዋል። ውሾቹ መንገደኞችን የሚመረምሩት እንዲህ ነው። መንገደኞች በአውሮፕላን ማረፊያው እንደደረሱ አንገታቸውን በጨርቅ ይጠርጋሉ። ከዚያም ያ ጨርቅ በኒኬል ኩባያ ውስጥ ተደርጎ ውሾቹ እንዲያሸቱት ይደረጋል። በዚህም ውሾቹ ጨርቁን በማሽተት አንድ መንገደኛ በሽታው ይኑርበት፤ አይኑርበት በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ መለየት ይችላሉ። በአየር መንገዱ እስካሁን ሲተገበር የቆየው ይህ ሙከራ አመርቂ ውጤት ቢያሳይም በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎችን ለመለየት አነፍናፊ ውሾችን የመጠቀሙ ጉዳይ ተጨማሪ ምርመራ ያስፈልገዋል ተብሏል። በአሁኑ ወቅትም መንገደኞች አነፍናፊ ውሾቹ ቫይረሱ እንዳለባቸው ወይም እንደሌለባቸው ቢጠቁሙም ለተጓዦች የኮሮናቫይረስ ምርመራ እየተደረገላቸው ይገኛል። የአገሪቱ ባለስልጣናት ግን ውሾቹ በቅርቡ ልክ ሕገ-ወጥ ቁሶችን አነፍንፈው እንደሚለዩት ሁሉ፤ በኮቪድ-19 የተያዘን ሰው ለመለየት እንደሚሰማሩ ተስፋ አላቸው።
news-47731453
https://www.bbc.com/amharic/news-47731453
በሕዝብ ቆጠራው መራዘም የትግራይ ክልል ቅሬታና የኮሚሽኑ ምላሽ
የሕዝብና ቤት ቆጠራ ኮሚሽን በሃገሪቱ መፈናቀልና ግጭቶች መኖራቸው እንዲሁም ቆጣሪዎችን በመልመል ረገድ በሚጠበቀው ደረጃ በቂ ዝግጅት አልተደረገም በሚሉና ሌሎች ምክንያቶች ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም የውሳኔ ሃሳብ ከሳምንት በፊት ማሳለፉ የሚታወስ ነው።
ይህንኑ ተከትሎ በዚህ ሳምንት የትግራይ ክልል መንግሥት የሕዝብና ቤት ቆጠራው ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ ተገቢ አይደለም ሲል ምክንያቶቹን በመጥቀስ መግለጫ ሰጥቷል። የትግራይ ክልል መንግሥት ካነሳቸው ምክንያቶች አንዱ "ጉዳዩ በምክክር ላይ ያለ እንጂ ውሳኔ የተላለፈበት አለመሆኑ ነው" ሲሉ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር አብራሃም ተከስተ ለቢቢሲ ተናግረዋል። • አምስት ነጥቦች ስለቀጣዩ የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ ''መጋቢት ዘጠኝ ላይ ነው አስአኳይ ስብሰባ የተጠራው። በመሃል በነበሩት ጊዜያት አዲስ የተከሰተ ነገር የለም። አብዛኞቹ ክልሎችም በተቀሩት ጊዜያት የቆጠራ ዝግጅቱን አጠናቀው ቆጠራ ማካሄድ እንደሚቻል ነው ሃሳብ ያቀረቡት፤ ስለዚህ የግልጽነት ችግር አለ'' ብለዋል። "የሕዝብ ቆጠራውን ወደሌላ ጊዜ ለማስተላለፍ የውሳኔው ሃሳብ የተላለፈው በቆጠራ ኮሚሽኑ እንጂ በሕዝብ ተወካዮችና በፌደሬሽን ምክር ቤቶች ውሳኔ አላገኘም" የሚሉት የብሔራዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተርና የሕዝብ ቆጠራ ኮሚሽን ዋና ጸሃፊ አቶ ቢራቱ ይገዙ፤ "ኮሚሽኑ ለብቻው ያስተላለፈው ውሳኔ አይደለም" በማለት ይከራከራሉ። እሳቸው እንደሚሉት የክልሎች ተወካዮች የሆኑ ከፍተኛ ኃላፊዎችና የፌደራል ከፍተኛ አመራሮች ባሉበት ውይይት ስለተደረገ፤ ከተገለጹት ምክንያቶች ውጪ ሌላ ሰበብ የለም። • ኢትዮጵያዊያን ቶሎ አያረጁም? • በአንድ ቦታ የተሰበሰቡ ሰዎችን ቁጥር እንዴት ማወቅ ይቻላል? የሕዝብና ቤት ቆጠራው እንዲራዘም የውሳኔ ሃሳብ የቀረበው ከሳምንት በፊት እንደመሆኑ፤ በተደጋጋሚ መረዘሙ ተአማኒነትን አያሳጣም ወይ ለሚለው ጥያቄ አቶ ቢራቱ መልስ ሲሰጡ ''በችግር ውስጥ ተሁኖ ሲሰራ ነበር፤ ትክክለኛ ቆጠራ ተካሂዷል ወይ የሚል ጥያቄ ሊቀርብበት የሚችለው፤ ነገር ግን ችግሮች ከተቀረፉ በኋላ ቆጠራን ማካሄድ ተአማኒነቱን ይጨምራል እንጂ አይቀንስም'' ብለዋል። አቶ ቢራቱ ይህንን ይበሉ እንጂ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ "ቆጠራው መራዘሙ በሕገ መንግሥቱ ላይ ያሉ ድንጋጌዎችንም የጣሰ ነው" ብለዋል። ''በየአስር ዓመቱ ቆጠራው እንዲካሄድ ነው ሕገ መንግሥቱ የሚደነግገው። ስለዚህ መንግሥት ሥራውን ስላልሰራ ቆጠራው ይተላለፍ ብሎ መወሰን የሕገ መንግሥቱ ድንጋጌ እንዲከበር ያለውን ቁርጠኝነት በተመለከተ ችግር እንዳለ ነው የሚያሳየው።'' ሲሉም ያክላሉ ዶ/ር አብርሃ ተከስተ። አቶ ቢራቱ በበኩላቸው "የሕገ መንግሥቱን ድንጋጌ አልጣስንም፤ እየሰራን ያለነው ሕጉ በሚፈቅደው መንገድ ነው" በማለት ያስረዳሉ። ''ሕገ መንግሥታችን የህዝብና ቤት ቆጠራው በየአስር ዓመቱ ይካሄዳል ይላል፤ ይሄ በግልጽ የተቀመጠ ነው። ነገር ግን አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ ለሚመለከተው አካል ቀርቦ በጉዳዩ ላይ ተወያይቶና ከህግ አንጻር ገምግሞ አቅጣጫ የሚያስቀምጥ ይሆናል'' በማለት የአሰራር ሂደቱን ያብራራሉ። ለቆጠራው ቅድመ ዝግጅት ክልሉ ወጪ በማውጣቱ የማራዘም ውሳኔው ተገቢ ላለመሆኑ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ዶክተር አብርሃም ያነሱት ሌላኛው ምክንያት ነው። "ለቅድመ ዝግጅቱ ብዙ ወጪ ስለተደረገበትና መተላለፉ ደግሞ ኪሳራ ስላስከተለ በቀጣይ ቆጠራው ሲካሄድ ክልሉ ላልተፈለገ ወጪ ይዳረጋል" በማለት ምክንያታቸውን አስቀምጠዋል። ከዚህ አንጻር ኃላፊነት የሚወስድ አካልና ተጠያቂነትም መኖር አለበት ብለዋል ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ። • ጌዲዮ በዐቢይ ጉብኝት ማግስት ከዚህ ጋር በተያያዘ አቶ ቢራቱ ምላሽ ሲሰጡ ምንም እንኳን አንዳንድ የልማት ድርጅቶ የቆጠራውን ወጪ የሚሸፍኑ ቢሆንም እስካሁን በነበሩትም ሆነ አሁን ወጪውን የሚሸፍነው የፌደራል መንግሥት ስለሆነ የክልሎች ወጪ እምብዛም ነው ይላሉ። ''60 በመቶ በመንግሥት ቀሪው 40 በመቶ ደግሞ በልማት አጋሮች የሚሸፈን ነው ብለን ነበር የተነሳነው፤ ነገር ግን አሁን ባለው ሁኔታ ወጪውን እየሸፈነ ያለው የፌደራል መንግሥት ነው። ከዚህ ውጪ ክልሎች ምናልባት ወደታች ማህበረሰቡ ጋር ወርደው የማስረዳትና የመቀስቀስ ሥራ ስለሚሰሩ ወጪ ሊያወጡ ይችላሉ ግን ብዙ አይደለም'' ይላሉ የኮሚሽኑ ዋና ፀሐፊ አቶ ቢራቱ። • ሰማይ ላይ ወልዳ አሥመራ የምትታረሰው ኢትዮጵያዊት ከዓመት በፊት ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ በተወሰኑ ክልሎች በነበረ የፀጥታ ችግር መራዘሙ የሚታወስ ነው፡፡ ይሁንና የፀጥታ ችግሮቹ ተቀርፈው በዚህ ዓመት እንደሚካሄድ ተጠብቆ የነበረና ሰፊ ቅድመ ዝግጅት የተደረገ ቢሆንም የሕዝብና ቤት ቆጠራው በድጋሚ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል።
news-48419945
https://www.bbc.com/amharic/news-48419945
የአሃዱ ኤፍ ኤም ጋዜጠኛ ታምራት አበራ ፍርድ ቤት ሳይቀርብ በመታወቂያ ዋስ ተለቀቀ
አርብ አመሻሽ ላይ በሠንዳፋ ፓሊስ በሥራ ገበታው ላይ እያለ በቁጥጥር ሥር የዋለው የአሀዱ ኤፍኤም ጋዜጠኛ ታምራት አበራ ዛሬ በመታወቂያ ዋስ መለቀቁን የጣቢያው ምክትል አዘጋጅ ሊዲያ አበበ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
ጋዜጠኛው ዛሬ ፍርድ ቤት ሳይቀርብ የዋስ መብቱ እንደተከበረለት የተናገሩት ምክትል አዘጋጅዋ እርሳቸው፣ የዜና ክፍል ኃላፊውና ምክትል ኤዲተሩ ረቡዕ ዋስ ይዘው መጥተው ቃላቸውን እንዲሰጡ እንደተነገራቸው ለማወቅ ችለናል። አርብ ከምሽቱ 11፡00 አካባቢ ሁለት የኦሮሚያ ሰንዳፋ አካባቢ ፖሊስ አባላት ከአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ፖሊስ መምሪያ ባልደረባ ጋር በመሆን በአሃዱ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ቢሮ በመምጣት ጋዜጠኛ ታምራት እና የሬዲዮ ጣቢያው ሥራ አሥኪያጅ አቶ ጥበቡ በለጠ እንደሚፈለጉ በመግለፅ መጥሪያ ማሳየታቸውን የጣቢያው ምክትል አዘጋጅ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በወቅቱ ጋዜጠኛ ታምራት የተፈለገበት ጉዳይ ምን እንደሆነ ጠይቀው ፖሊስ አስሮ እንዲያመጣቸው መታዘዙን ቀሪውን ፍርድ ቤቱን ትጠይቃላችሁ በማለት ወደ ፖሊስ ጣቢያ ወስደውታል። • የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይቅርታ ጠየቀ • የጄል ኦጋዴን እስር ቤት ኃላፊ ተይዞ ለኢትዮጵያ ተሰጠ • አይስላንድ አንድ ተማሪ ብቻ የቀረውን ትምህርት ቤት ልትዘጋ ነው በእለቱ እስከ ምሳ ሰዓት የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ አቶ ጥበቡ በሥራ ገበታቸው ላይ የነበሩ ቢሆንም ከሰአት ግን እንዳልነበሩ ያስረዱት ምክትል አዘጋጇ የዛኑ እለት አመሻሽ ላይ ከሀገር ውጪ ለሥራ ወጥተው እንደሚገኙ አረጋግጠዋል። ፖሊስ ወደ አሀዱ ቢሮ በመጣበት ወቅት በመጥሪያው ላይ ተጠርጣሪዎች ተብለው አራት ሰዎች ስማቸው ሰፍሮ ማየታቸውን የሚናገሩት አዘጋጇ አንደኛዋ የፍርድ ባለ እዳዋ ሲሆኑ ሌሎቹ ሦስቱ የእርሳቸው ቤተሰቦች መሆናቸውን ገልፀዋል። እነዚህ የፍርድ ባለ እዳ እና ተጠርጣሪዎቸ ክሱ የተመሰረተበት ሰንዳፋ አካባቢ ነዋሪ መሆናቸውንና አሁንም በመኖሪያ ቤታቸው እንደሚገኙ የሚናገሩት ሊዲያ እነርሱ ፍርድ ቤትም ሆነ ፖሊስ ጣቢያ እንዲቀርቡ እንዳልተደረገ ይናገራሉ። ጋዜጠኛ ታምራት በቁጥጥር ስር በዋለበት ወቅት ጉዳዩ በሽምግልናና በንግግር የሚፈታ ከሆነ በማለት የሬዲዮ ጣቢያው የሚገኝበት ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ፖሊስ መምሪያ እንደተወሰደ የሚናገሩት ሊዲያ የጣቢያውን አዛዥ በማነጋገር ሠንዳፋ ነው የምንወስደው በማለት ወደዚያው እንደወሰዱት ያስረዳሉ። በአሁኑ ሰዓት ሠንዳፋ በኬ 02 የሚባል የከተማው ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ የሚገኘው ጋዜጠኛ የአሀዱ ሬዲዮ ጠበቃ አቁሞለት እንዲከራከርለት እንዳደረገ ተናግረዋል። ይህ ዘገባ እስከተጠናቀበት ድረስ ፖሊስ ሁለት ጊዜ የጋዜጠኛውን ቃል መቀበሉን የተናገሩት ሊዲያ ሁለት አቃቢያነ ሕጎች የጣቢያውን ባልደረቦች ቃል መቀበላቸውንም ለማወቅ ችለናል። ጋዜጠኛ ታምራት በሠንዳፋ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር የዋለው በሰራው ዘገባ ምክንያት ነው የሚሉት የጣቢያው ምክትል አዘጋጅ ዘገባው ለጣቢያው የተሰራ ስለሆነ በብሮድካስት አዋጁ መሰረት ሊጠየቅ የሚገባው ጣቢያው ነው በማለት ከዚህ በፊት ፍርድ ቤቱ የዘገባውን ቅጂ ጠይቆ መውሰዱን ያስታውሳሉ። በዘገባው ምክንያት የተከሰሱት ሥራ አስኪያጅና ሪፖርተሩ ብቻ መሆናቸውን አስረድተዋል። ጉዳዩ ምን ነበር? ዘገባው በሠንዳፋ ከተማ የገጠር ቀበሌዎች አካባቢ ባሉ ቀበሌዎች በሁለት ተከራካሪ ቤተሰቦች መካከል ያለ የውርስ ጉዳይ ነው። ወደ አሀዱ ቢሮ የመጡት አንዲት ግለሰብ ከአባታቸው መሬት ወርሰዋል። ወራሽ ነን የሚሉ የወንድሞቻቸው ልጆች ከስሰው በ2001 ዓ.ም ወደ አሀዱ ቢሮ ለመጡት እናት ተፈርዶላቸው ነበር። • ፌስቡክ የአፍሪካ የዴሞክራሲ ሥርዓት ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው? አያት ለልጅ ልጅ ማውረስ አይችልም በሚል ፍርድ ቤቱ ክሱን ዘግቶት ነበር። ነገር ግን በ2009 ከሳሽ የነበሩት ልጆች በተከሳሽ አባት ስም የአባታቸውን ስም አስቀይረው መጥተው በ2009 ይገባቸዋል ተብሎ ተፈርዶላቸው ነበር። እኚህ እናት ከይግባኝ ሰሚ ቤት እስከ ሰበር ሰሚ ችሎት ድረስ ሄደው የታችኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ ይፅና የሚል ውሳኔ ለልጆቹ ተፈረደ። እኝህ እናት ሕጋዊ ወራሽ እኔ ሆኜ ሳለሁ የአስተዳደር በደል ደርሶብኛል ሲሉ ወደ አሀዱ ሬዲዮ ጣቢያ መጡ። ጣቢያውም የሚመለከተውን አካል ግራ ቀኝ አነጋግሮ ዘገባ ሰርቷል ይላሉ ምክትል አዘጋጇ። ጋዜጠኛ ታምራት ላይ የተለያዩ ማስፈራሪያዎች እየደርሱበት እንደነበር የሚገልፁት አዘጋጇ አሀዱ ኤፍ ኤም ከዚህ በፊት በብሮድካስት ባለሰልጣንም ሆነ በሌላ አካል ቅሬታ ቀርቦበት እንደማያውቅ ተናግረዋል። የኦሮሚያንም ሆነ የሰንዳፋ ፖሊስን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። የሚዲያ ሕጉ ምን ይላል? የሕግ ባለሙያና የኢትዮጵያ ሚዲያ ሕግ ማሻሻያ የጥናት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ሰለሞን ጎሹ አንድ ጋዜጠኛ ለሚሠራው ሥራ ኃላፊነት አለበት ያሉ ሲሆን፣ "ተላለፈ በተባለው የሕግ ማዕቀፍ የሚወሰን ቢሆንም እንደተላለፈው ሕግ ግለሰቡም ሆነ የሚዲያ ተቋሙ የሚጠየቅበት አግባብ አለ" ይላሉ። ይሁን እንጂ እርሳቸው እንደሚሉት አንድ ጋዜጠኛ ለሚሰራው ስህተት የማረሚያ ዕድል ሊሰጠው ይገባል። የወንጀል ጉዳይ ከሆነ ግለሰቡም ሆነ ተቋሙ ተጠያቂ የሚሆኑበት አግባብ ሲኖር በፍትሃብሄር ሲሆን የጋዜጠኛው ኃላፊነት ተትቶ ተቋሙ የሚጠየቅበት አግባብ ይኖራል ብለዋል። ነገር ግን እንደ ሁኔታው ጋዜጠኛውም የሚጠየቅበት አግባብ አለ በማለት ያክላሉ። አቶ ሰለሞን የመገናኛ ብዙሃኑን ሕግ 590ን ጠቅሰው " ጋዜጠኛ በሥህተት አይከሰስም፤ ከተሳሳተ ማረሚያ ያወጣል እንጂ አይከሰስም" ይላሉ። ባለሙያው እንደሚያስረዱት ከተጠየቀም በሕግ የተቀመጡ የተለያዩ አንቀፆች ላይ ተመስርቶ ነው ሲሉ ያብራራሉ። የጋዜጠኛ ታምራት ጉዳይን ያነሳንላቸው ባለሙያው የጉዳዩን ዝርዝር ባያውቁትም "ጋዜጠኛ ስህተት መስራት አንዱ የሕይወቱ አካል ነው፤ የሠራቸውን ወንጀሎች አሊያም የሕግ ጥሰቶች ተጠቅሶ ነው መጠየቅ ያለበት" በማለት ያብራራሉ። አክለውም ጋዜጠኛ ተጠርጥሮ እንኳን ቢታሰር "ሲከራከር ታስሮ አይደለም፤ የዋስትና መብቱን አቅርቦ ፍርድቤቱን የሚጠይቅ ሳይሆን ጋዜጠኛ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ራሱ ወጥቶ እንዲከራከር እንዲፈቀድለት የሚዲያ ሕጉ ያዛል" ይላሉ። የሚዲያ ሕጉ የተለያዩ ችግሮች ቢኖሩበትም በዚህ ጉዳይ ግን ግልፅ የሆነ ድንጋጌ ነው ያለው ብለዋል። አንድ ጋዜጠኛ ስህተት ቢሰራ ማረሚያና ማስተካካያ እንዲያወጣ የሚገደድ ሲሆን የሠራው ስህተት ታስቦበትና ታቅዶበት ነው ከተባለም የወንጀል ሕግ ስለሚሆን ያኔ በጋዜጠኛው ላይ ክስ መመስረት ይቻላል ሲሉ ሀሳባቸውን ይቋጫሉ።
news-54521488
https://www.bbc.com/amharic/news-54521488
ፖሊሶች ከፈረስ ላይ በገመድ አስረው የወሰዱት ጥቁር አሜሪካዊ 1 ሚሊዮን ዶላር ይገባኛል ሲል ከሰሰ
ሁለት ነጭ ፖሊሶች በፈረስ ላይ ተቀምጠው በቴክሳስ፣ ጋልቭስቶን ጎዳናዎች ላይ በገመድ አስረው የወሰዱት ጥቁር አሜሪካዊ የከተማዋን አስተዳደርና ፖሊስን ከሷል። አንድ ሚሊዮን ዶላርም ይገባኛል ብሏል።
የ44 አመቱ ዶናልድ ኒሊ ያለ ፈቃድ የእግረኞች መረማመጃ ላይ ተኝቶ ተገኝቷል በሚል ወንጀልም ተጠርጥሮ በገመድ አስረው ፖሊሶች ሲወስዱት የታየው። ይህም ቪዲዮ መውጣቱን ተከትሎ ፖሊስ ይቅርታ ጠይቆ ነበር። በዚህ ሳምንት የቀረበው ክስ የሚያስረዳው ፖሊሶቹ የፈፀሙት ድርጊት" ፅንፈኛና አሰቃቂ ነው" በማለት ዶናልድ ኔሊም ለስነ-ልቦናዊ ቁስልና የአዕምሮ ጤንነቱም ላይ ጉዳት አድርሰውበታል ይላል። ቤት አልባ የሆነው ዶናልድ በእግረኞች መረማመጃ ላይ ተኝቶ በመገኘቱም ነው ፖሊሶች በቁጥጥር ስር እንዳዋሉት የአሜሪካ ሚዲያዎች የዘገቡት። ፖሊስ ፍቃድ የሌለው ቦታ ላይ ተገኝቷል ብሎ ያቀረበበትም ወንጀል ፍርድ ቤቱ በነፃ አሰናብቶታል። በገመድም ታስሮ ሲወሰድ ያዩ በርካቶችም ከባርነት ዘመን ጋርም በማነፃፀር ቁጣቸውን ገልፀዋል። በክሱም ላይ ይሄው ሁኔታ ተገልጿል። ክሱ እንደሚያትተውም " በገመድ ታስሮ በጎዳናዎች ላይ ባርያ ይመስል መውሰድ አፀያፊ ነው" ይላል። የከተማዋን እንዲሁ የጋልቭስቶን ፖሊስን ተጠያቂ ያደረገው ክሱ ዶናልድ በታሰረበት እጅ ሰንሰለት ምክንያት ጉዳት ደርሶበታል፤ በጎዳናው ላይ ይዘውትም ሲሄዱ በከፍተኛ ሙቀት ተለብልቧል እንዲሁም በሁኔታውም ፍርሃትና ውርደት እንደደረሰበትም ያትታል። የከተማው አስተዳዳሪዎች ለሚዲያዎች አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል። በመጀመሪያ ዶናልድ በገመድ ታስሮ ሲወሰድ የሚያሳየው ምስል መውጣቱን ተከትሎ በተቀሰቀሰው ቁጣ በገመድ አልታሰረም በማለት ፖሊስ ለማስተባበልም ሞክሮ ነበር። ከምርመራ በኋላ የወጣው ቪዲዮ እንደሚያሳየውም ፖሊሶች በዚህ መንገድ አስረው በማዋረዳቸውም ሲዘባበቱበት ተሰምተዋል። የጋልቭስተን ፖሊስረ ኃላፊ ቬርኖን ሃሌ እንዳሉም በዚህ መንገድ ተጠርጣሪዎችን መውሰድ በአንዳንድ ሁኔታዎች ተቀባይነት ያለው ቢሆንም "በዚህ ወቅት ግን ፖሊሶቹ ያልተገባ ባህርይ ነው ያሳዩት" በማለት ተችተዋል። ይህንን ለመፈፀም "የተደበቀ ሴራ አልነበረም" ያሉት ኃላፊው ዶናልድ ለደረሰበት "አላስፈላጊ ውርደት" ይቅርታ ጠይቀዋል። ያንንንም ተከትሎ በዚህ መንገድ ተጠርጣሪዎችን ማሰር አይገባም በሚልም እግድ ተጥሎበታል።
news-56471328
https://www.bbc.com/amharic/news-56471328
የኮሮናቫይረስ ክትባትና ሐሰተኛ ሰነድ በድብቅ እየተሸጠ ነው
የኮሮናቫይረስ ክትባት፣ መከተብን የሚያሳዩ ሰነዶችና ሐሰተኛ ከኮቪድ-19 ነጻ የምስክር ወረቀቶች በስውሩ የበይነ መረብ መድረክ [ዳርክኔት] ላይ እየተቸበቸቡ ነው።
በአሁኑ ጊዜ እየተሰጡ ያሉት የተለያዩ የክትባት አይነቶች ዋጋ ወጥቶላቸው ለሽያጭ የቀረቡ ሲሆን፤ የአስትራዜኒካ፣ ስፑትኒክ፣ ሲኖፋርም ወይም ጆንሰን ኤንድ ጆንስን ክትባቶች ከ500 አስከ 750 ዶላር እየተሸጡ መሆኑ ተነግሯል። በተጨማሪም በዚህ ድብቅ የኢንተርኔት የግብይት መድረክ ላይ ለጉዞና ለሌሎች ምክንያቶች የሚፈለገው የኮሮናቫይረስ ክትባት መውሰድን የሚያመለክተውን ሰነድ አስከ 150 ዶላር በሆነ ወጪ መግዛት ይቻላል። ቢቢሲ ለሽያጭ የቀረቡት ክትባቶች ትክክለኛ ስለመሆናቸው ማረጋገጥ ባይችልም፤ ተመራማሪዎች እንደሚሉት ግን በዚህ ስውር የግብይት መድረክ ላይ ከክትባት ጋር የተያያዙ ማስታወቂያዎች በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል። ይህ ዳርክኔት ወይም ዳርክ ዌብ የሚባለው ድብቅ የኢንተርኔት የግብይት መድረክ በተወሰኑ የበይነ መረብ ማሰሻ መጠቀሚያዎች በኩል ብቻ ሊደረስበት የሚችል ነው። የበይነ መረብ ደኅንንት ምርምር ተቋሙ 'ቼክ ፖይንት' ካለፈው ጥር ጀምሮ የክትባት ሽያጭ ማስታወቂያዎች መታየት እንደጀመሩ አመልክቷል። የክትባት ሽያጩን በተመለከተ በተከታታይ ጭማሪ አሳይቶ በሦስት እጥፍ በማደግ ከ1,200 በላይ ማስታወቂያዎች ቀርበዋል። ይህንን የክትባት ሽያጭ የሚያካሂዱት ከአሜሪካ፣ ከስፔን፣ ከጀርመን፣ ከፈረንሳይና ከሩሲያ ሲሆኑ፤ በርካቶቹ ማስታወቂያዎች በሩሲያ ቋንቋና በእንግሊዝኛ የቀረቡ ናቸው። በክትባቶቹ ማስታወቂያዎቹ ላይ ለተለያዩ ክትባቶች የተለያየ ዋጋ የወጣላቸው ሲሆን፤ በኢትዮጵያ እየተሰጠ ያለው የኦክስፎርድ-አስትራዜኒካ ክትባት 500 ዶላር፣ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን እና ስፑትኒክ ክትባት እያንዳንዳቸው በ600 ዶላር እንዲሁም ሲኖፋርም ደግሞ 750 ዶላር ይሸጣሉ ተብሏል። አንድ የክትባት አቅራቢ ማስታወቂያ እንደሚለው ክትባቱን የሚፈልግ ሰው ትዕዛዝ በሰጠ በቀጣዩ ቀን በአስቸኳይ እንሚያቀርብ ገልጿል። ሐሰተኛ የኮቪድ-19 የምርመራ ውጤት የሚሰጥ አንድ አስተዋዋቂ ደግሞ ለገዢዎች እንዲህ ሲል ማበረታቻ እንደሚሰጥ ገልጿል። "ለተጓዦች፣ ለአዲስ ሥራ ተቀጣሪዎችና ለሌሎችም ከኮሮናቫይረስ ነጻ ስለመሆናቸው የምርመራ የምስክር ወረቀት እንሰጣለን። ሁለት የምስክር ወረቀቶችን ለሚገዙ ሦስተኛውን በነጻ እናዘጋጃለን" ይላል። ከምርመራ ውጤት ጎን ለጎን የክትባት የምስክር ወረቀት አስፈላጊ እየሆነ ነው። በተለይ የክትባት ምስክር ወረቀት ወደ ቡና ቤቶች ወይም የስፖርት ስታዲየሞች ለመግባት ይጠየቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። ሐሰተኛ የክትባት ማረጋገጫ ሰነድና የምርመራ ምስክር ወረቀት በበይነ መረብ ስውር የግብይት መድረክ ላይ የሚሸጥ ሲሆን፤ ክፍያውም ለይቶ ለማወቅ አስቸጋሪ በሆነ መንገድ የኢንተርኔት የክፍያ መንገድ ቢትኮይን አማካይነት የሚፈጸም መሆኑን በሽያጩ ላይ ምርመራ ያደረጉት ባለሙያዎች ተናግረዋል። ይህንን ሽያጭ ከሚከታተሉት ባለሙያዎች መካከል አንዱ የሆኑት ኦዲድ ቫኑኑ ሲናገሩ "የክትባትም ሆነ የምርመራ ሐሰተኛ ሰነዶችን እንዲሁም ክትባትን በዚህ መንገድ ለመግዛትመሞከር አደገኛ ነው" በማለት ምክንያቱን ሲያስረዱ "የበይነ መረብ መረጃ መዝባሪዎች በዚህ መንገድ የሰዎችን ግላዊ መረጃዎችን በመውሰድ ለዝርፊያ ሊዳርጉ ይችላሉ" ብለዋል። ባለሙያው ከቡድናቸው ጋር በሽያጩ ላይ ምርመራ ሲያደርጉ 750 ዶላር ከፍለው የሲኖፋርም ምርት የሆነውን ክትባት ያዘዙ ቢሆንም እስካሁን ክትባቱ እንዳልደረሳቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። የጥናት ቡድኑ እንደሚለው ክትባቶቹን እናቀርባለን በማለት ማስታወቂያ የሚያስነግሩት የሚሸጡት ክትባት ትክክለኛ ይሁን አይሁን እርግጠኛ መሆን አይቻልም። ጨምረውም አገራት ከክትባትና ከምርመራ ጋር በተያያዘ ለማረጋገጫነት የሚሰጧቸው ሰነዶች ተመሳስለው እንዳይዘጋጁ የሚያስችል ዘዴን እንዲቀይሱ አሳስበዋል።
news-51569575
https://www.bbc.com/amharic/news-51569575
ኬንያዊውን ገርፈዋል የተባሉት ቻይናውያን አሰሪዎች ከሃገር እንዳይባረሩ ፍርድ ቤቱ አዘዘ
ኬንያዊውን ገርፈዋል የተባሉት ቻይናውያን አሰሪዎች ከሃገር እንዲወጡ የተላለፈውን ትዕዛዝ ፍርድ ቤቱ ማገዱ ተዘግቧል።
ከሰሞኑ አንድ ኬንያዊ በቻይናውያን አሰሪዎች በመዲናዋ በናይሮቢ በሚገኝ ሬስቶራንት ውስጥ ሲገረፍ የሚያሳይ ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተሰራጭቶ ከፍተኛ ቁጣና ንዴት አስከትሏል። ይህንንም ተከትሎ ፍርድ ቤቱ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ለፖሊስ በሰጠው ትእዛዝ መሰረት አራቱ ቻይናውያን በቁጥጥር ስር ውለዋል። • የህዳሴው ግድብ ድርድር ትኩረቱን ስቶ የውሃ ድርሻ ክፍፍል ላይ ሆኗል ተባለ • ከማዕከላዊ ስልጣን የተገፋው ህወሓት ከዬት ወደዬት? የሃገር ውስጥ ሚኒስትር ፍሬድ ማቲያንጊ በአስቸኳይ ከሃገር እንዲባረሩ ትእዛዝ አስተላልፈው ነበር። ፍርድ ቤቱ ለተጨማሪ 15 ቀናት በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲቆዩም ትእዛዝ ቢያስተላልፍም ክስ አልተመሰረተባቸውም። አራቱ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የዋሉት ከአስር ቀናት በፊት በመዲናዋ ናይሮቢ በተለምዶ ኪለለሽዋ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ቼዝ ው ተብሎ በሚጠራው ሬስቶራንት ውስጥ ነው። • ቻይና ዘረኝነት ተንፀባርቆበታል ባለችው ፅሁፍ ምክንያት ጋዜጠኞችን ከሃገሯ አባረረች አንደኛው አሰሪ በተለይም በሬስቶራንቱ ተቀጥሮ የሚሰራውን ኬንያዊ አርፍደሃል በሚል በዱላ ደብድቦታል ተብሏል። ይህንን የሚያሳይ ቪዲዮ ብዙዎች ማጋራታቸው ቁጣን በከፍተኛ ሁኔታ እንዳባባሰው ተዘግቧል።
news-53260521
https://www.bbc.com/amharic/news-53260521
በአዲስ አበባ ባለፉት ሁለት ቀናት ሁለት ፖሊሶችን ጨምሮ የ10 ሰዎች ህይወት አለፈ
በአዲስ አበባ ውስጥ ባለፉት ሁለት ቀናት ውስጥ ተከስቶ በነበረው አለመረጋጋት የስምንት ነዋሪዎችና የሁለት ጸጥታ አስከባሪዎች ህይወት ማለፉን የከተማዋ ፖሊስ አስታወቀ።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ በብሔራዊው ቴሌቪዥን ቀርበው እንደተናገሩት ከማክሰኞ ጀምሮ በመዲናዋ የጸጥታ መደፍረስ እንዳጋጠመ አስታውቀዋል። ኮሚሽነር ጌቱ በከተማዋ ውስጥ በዜጎች ላይ ደረሰ ባሉት ጉዳት "ማክሰኞና ረቡዕ የ8 ሰዎች ህይወት አልፏል" ካሉ በኋላም፣ ነዋሪዎች ህይወታቸው ያለፈው "በቦምብ፣ ጥይት፣ በድንጋይ እና በመሳሰሉት ነው" ብለዋል። የተከሰተውን የጸጥታ ችግር ለማረጋጋት ተልዕኮ ተሰጥቷቸው ተሰማርተው የነበሩ የፖሊስ አባላት ላይ ከቀላል የአካል ጉዳት እስከ ሞት የደረሰ ጉዳት መድረሱንም ገልጸዋል። ኮሚሽነሩ ጨምረውም "ማክሰኞ እና ረቡዕ 57 የሚሆኑ የፌደራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ላይ ጉዳት ደርሷል" በማለት ሁለት የፖሊስ አባላት ደግሞ ህይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል። በከተማዋ አንዳንድ አካባቢዎች በነበረው አለመረጋጋትም "የግል እና የመንግሥት ተሽከርካሪዎችን መሰባበር እና ማቃጠል፣ የዜጎችን ያፈሩትን ሃብት እና ንብረት የመዝረፍ እንቅስቃሴ ነበር" ኮሚሽነሩ ጌቱ አርጋው። ንብረትነታቸው የግለሰብ እና የመንግሥት የሆኑ 250 ተሽከርካሪዎች ተሰባብረዋል፣ 20 ተሽከርካሪዎች ተቃጥለዋል ሲሉም አክለዋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ትናንት ምሽት በሰጠው መግለጫ ላይ ጨምሮ እንዳለው አብን እና ባልደራስ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የብሔር ግጭት ለመቀስቀስ ሞክረዋል ብሏል። በዚህም የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት መሳተፋቸውን ገልጸው በተለይ የባልደራስ እና አብን አመራሮች እና አባላት በግልጽ ቲሸርት በመልበስ እና የፓርቲያቸውን አርማ በመያዝ፤ በከተማዋ የተለያየ አካባቢዎች እተንቀሳቀሱ "የብሔር ግጭት ለመፈጥር እንቅስቃሴ ሲደረጉ ነበር" ብለዋል። "በተለያዩ የከተማው አቅጣጫ በመንቀሳቀስ አንዱ ብሔር ሌላውን ሊያጠቃ እንደመጣ፤ እየተወረረ እንደሆነ" በመግለጽ "እንዲከላከል" ቅስቀሳ ሲያደርጉ ነበር ብለዋል። ጨምረውም ይህን አጋጣሚ በመጠቀም በከተማዋ ሁከት እና ብጥብጥ በመፍጠር ኅብረተሰቡ እርስ በእርሱ እንዲጋጭ እንቅስቃሴዎች ሲካሄዱ እንደነበር አመልክተዋል።
news-44856158
https://www.bbc.com/amharic/news-44856158
ትራምፕ ከፑቲን ጋር በተያያዘ ወቀሳ እየዘነበባቸው ነው
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩስያው አቻቸው ቭላዲሚር ፑቲን ተገናኝተው መክረዋል። በውይይታቸው ወቅት ትራምፕ የተናገሩት ግን አሜሪካውያን በሳቸው ላይ ያላቸው እምነት ይበልጥ እንዲሸረሸር እያደረገው ይመስላል።
«ሩስያ በአሜሪካ ምርጫ ጣልቃ የምትገባበት ምንም ምክንያት የላትም» በማለት ከደህንነት መሥሪያ ቤታቸው ተቃራኒ የሆነ ድምፅ ትራምፕ አሰምተዋል። የአሜሪካ ፓርላማ አፈ ቀላጤ እና ዋነኛው ሪፐብሊካን ፖል ራያን በበኩላቸው «ትራምፕ ሩስያ የአሜሪካ አጋር አለመሆኗ አልገባቸውም መሰል» ሲሉ ወርፈዋቸዋል። "ዘረኛ አይደለሁም" የዛሬ 10 ዓመት ገደማ ኦባማን በመቀናቀን ምርጫ ያካሄዱት ሌላኛው ታዋቂ ፖለቲከኛ ጆን ማኬይንም «አሳፋሪ ተግባር» ሲሉ ተደምጠዋል። ፕሬዝደንት ፑቲን «ከደሙ ንፁህ ነኝ» በማለት ወቀሳውን አጣጥለውታል። እለተ ሰኞ በፊንላንድ መዲና ሄልሲንኪ የተገናኙት ሁሉቱ መሪዎች ከሁለት ሰዓታት በላይ የወሰደ ዝግ ስብሰባ አካሂደዋል። ከዚያ በኋላ ባካሄዱት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው ትራምፕ መዘዘኛውን ንግግር ያድረጉት። አዲስ ዕቅድ ስደተኞችን ለማባረር «ሩስያ የዛሬ 2 ዓመት ገደማ በተደረገው ምርጫ ጣልቃ ገብታለች በማለት የደህንነት መሥሪያ ቤትዎ ይወቅሳል፤ እውን በዚህ ይስማማሉ?» ተብለው የተጠየቁት ትራምፕ «ኧረ በጭራሽ፤ ምን ሲደረግ ሩስያ በሃገሬ ምርጫ ጣልቃ ትገባለች» በማለት ታሪካዊ ተቀናቃኝ ሃገራቸውን ወግነው ምላሽ ሰጥተዋል። በዚህ አልበቃ ያላቸው ትራምፕ «ባይሆን ከሩስያ ጋር ያለን ጠብ ያለሽ በዳቦ ሊቀረፍ ይገባል» ብለዋል። ኪም፡ 'እብዱ' ትራምፕ ለንግግሩ ዋጋ ይከፍላል የአሜሪካ ደህንነት መሥሪያ ቤቶች ሩስያ በፈረንጆቹ 2016 በተደረገው ምርጫ ጣልቃ በመግባት ሂላሪ ክሊንተን እንዲረቱ ትልቅ ሚና ተጫውታለች በማለት የፑቲንን ሃገር መውቀስ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ትራምፕ ዘግየት ብለው በትዊተር ገፃቸው «በደህንነት መሥሪያ ቤቴ እተማመናለሁ» በማለት ነገሩን ለማቀዛቀዝ ጥረዋል። ቢሆንም ከትችት መዓት አልተረፉም፤ በዘርፉ አሉ የተባሉ ፖለቲከኞች «አሳፋሪ ድርጊት» እያሉ ሁኔታውን እስኪያብጥለጥሉት ድረስ። የዴሞክራት ፓርቲ አባል የሆኑ ቻክ ሹመር የተባሉ ግለሰብ «ትራምፕ እኛን እየከፋፈሉ አቅማችንን በማዳከም አጋሮቻችንንም እያስቀየሙ ነው» የሚል መግለጫ አውጥተዋል። ትራምፕ ወቅቱ "የአሜሪካ አዲስ ዘመን ነው" አሉ በአሜሪካ አሉ የተባሉ አውራ የደህንነት ሰዎችም ሁኔታው እንዳሳዘናቸው አልሸሸጉም። የቀድሞው የሲአይኤ ኃላፊ ጆን ብሬናን «የትራምፕ ምላሽ የማይረባ መሆኑ ሳያንስ ሰውየው የፑቲን ኪስ ውስጥ እኮ ነው ያሉት» ሲሉ ነው ሃሳባቸውን ያሰፈሩት። የትራምፕ ምክትል ማይክ ፔንስ ግን «አለቃዬን አትንኩብኝ» የሚል ሃሳብ ሰንዝረዋል።
44804027
https://www.bbc.com/amharic/44804027
የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሉ አቶ አብዲ በአቶ ጌታቸው ላይ ያቀረቡትን ክስ ኢህአዴግ እንደማያውቀው ገለፀ
የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርዕሰ መሰተዳደር የሆኑት አቶ አብዲ ሞሃመድ ከክልላቸው የመገናኘ ብዙሃን ጋር በነበራቸው ቆይታ የተናገሯቸው ነገሮች አነጋጋሪ ሆኗል።
አቶ አብዲ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን የመጀመሪያዎቹን 100 ቀናት አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፤ የጠቅላይ ሚንስትሩ የለውጥ ውሳኔዎች እንደሚደግፉ ገልጸው፤ ''ባለፉት ዓመታት ለክልሉ ህዝብ ልማት የተለያዩ ሥራዎችን ሰርተናል። በሥራዎችችን ውስጥ ደግሞ ስህተት ፈጽመናል። ጊዜው የይቅርታ ነው። ስለዚህ ስለሰራነው ስህተት ይቅርታ እንጠይቃለን። ስህተትን የማይቀበል ሴጣን ብቻ ነው'' ሲሉ ተደምጠዋል። ከአቶ አብዲ መግለጫ ውስጥ የበርካቶችን ትኩረት የሳበው የቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋን በሚመለከት የሰጡት አስተያየት ነው። ''ጌታቸው ሙሰኛ፣ ሌባ እና ራሰ ወዳድ ነው'' ሲሉ አቶ አብዲ ተደምጠዋል። • "ከሞቱት አንለይም" የሶማሌ ክልል እስረኞች • የደኅንነት መሥሪያ ቤቱ ኃላፊ ከሥልጣናቸው ተነሱ አቶ አብዲ ''የክልል አስተዳዳሪ ሆኜ ወደ ጌታቸው ቢሮ መግባት የቻልኩት ከ10 ዓመታት በኋላ ነው። አቶ ጌታቸው ለላፉት 27 ዓመታት ለምን ከሚዲያው ተደብቆ ቆየ? የአሜሪካው የስለላ ተቋም ሃላፊ እንኳ ህዝብ ፊት ወጥቶ መግለጫ ይሰጣል። እሱ ተንኮል እየሰራ ካልሆነ በቀር ለምን ተደበቀ?'' ብለዋል። የብሔር ብሔረሰቦች በዓል በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል ጅግጅጋ ላይ ህዳር 29/2006 ዓ.ም በተካሄደው ሥነ-ሥርዓት ላይ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ወደ ጅግጅጋ እንዳይሄዱ የከለከለው አቶ ጌታቸው ነው በማለት አቶ አብዲ ተናግረዋል። ''አዲስ አበባ ላይ ተቀምጦ የክልል መስተዳድሮችን ይሾማል'' ያሉት አቶ አብዲ ''አቶ ጌታቸው አሁን ለመጣው ለውጥ እንቅፋት ይሆናል'' ሲሉም ተደምጠዋል። የአቶ አብዲክስ አሁን ለምን? አቶ አብዲ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ለተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በርካቶች ተጠያቂ ያደርጓቸዋል። ከዚህ በተጨማሪም ለእሳቸው ተጠሪ በሆነው በሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ ለሚፈጸመው ኢሰብዓዊ ድርጊቶች አቶ አብዲ ተጠያቂ መሆን እንዳለባቸው ሂዩማን ራይስት ዎችን ጨምሮ የተለያዩ አካላት ያሳስባሉ። በቅርቡ ሂውማን ራይትስ ዎች ''ዊ አር ላይክ ዘ ዴድ" (ከሞቱት አንለይም) በሚል ርዕስ ባወጣው ሪፖርት በሶማሌ ክልል የሚገኙ እስረኞች የዘፈቀደ እስራት፣ ድብደባ፣ መደፈርና የሰው ልጅ ማሰብ ከሚችለው በላይ እንግልት እንደሚደርስባቸው አትቷል። በሪፖርቱ መሰረት ይህንን ሲፈፅሙ የነበሩት የእስር ቤቱ ኃላፊዎችና የፀጥታ ኃይሎች፤ የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ ናቸውም ብሏል። አቶ አብዲ በቅርቡ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተርነት እንዲነሱ የተደረጉትን አቶ ጌታቸው አሰፋን በከፍተኛ ደረጃ መውቀስ ለምን አስፈለጋቸው? የሚለው የበርካቶች ጥያቄ ነው። የሶማሌ ክልል የፖለቲካ ምህዳር እና የአቶ አብዲን አስተዳደር ጠንቅቄ አውቃለው የሚሉት የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቹ አቶ ሙስጠፋ ኡመር ሁለት ምክንያቶችን በዋናነት ያስቀምጣሉ። እንደ አቶ ሙስጠፋ ከሆነ አቶ አብዲ ይህን መሰል ወቀሳን መሰንዘር ያስፈለጋቸው፤ "የአዲሱ የፖለቲካ ለውጥ አካል ሆነው ስልጣን ላይ መቆየት ስለሚፈልጉ ነው። አቶ ጌታቸው እና ሌሎች ግለሰቦች ይፈጽሙ የነበሩትን በይፋ ማውጣት 'ታዓማኒነትን ያተርፍልኛል' የሚል ስሌትን በመያዝ ያደረጉት ነገር ነው'' ይላሉ። ''ከቀናት በፊት የክልሉ ምክር ቤት ተሰብስቦ ባለበት ሰዓት አቶ አብዲ አንድ ጥቁር ቦርሳ ይዘው መጡ። ከዚያም 'በዚህ ሻንጣ ውስጥ በርካታ ሚስጥሮች አሉኝ። የክልሉ ባለስልጣናት እና የፌደራል መንግሥት ባለስልጣናት ሚስጥር እዚህ ውስጥ አለ። ገንዘብ የከፍልኳቸው ባለስልጣናት አሉ። እኔን ቢነኩ ይህን ሚስጥር አወጣለሁ' በማለት ሲያስፈራሩ ነበር'' በማለት ተናግረዋል። የአቶ ሙስጠፋ ሌላኛው ምክንያት ''አቶ ጌታቸው አቶ አብዲን ከስልጣናቸው በተደጋጋሚ ለማንሳት ሙከራ አድርጓል። ይህንንም ለመበቀል ያደረገው ሊሆን ይችላል'' በማለት ግምታቸውን ያስቀምጣሉ። አቶ አብዲ በቴሌቪዥኝ በተላለፈው መግለጫቸው ላይ 'አብዲ ጌታቸው ከተባረረ በኋላ ነው ስለሱ የሚያወረው ሊለኝ የሚችል አመራር የለም። ለሁሉም የኢህአዴግ ማዕከላዊ የኮሚቴ አባላት አቤት ብያለው'' ብለዋል። በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡን የኢህአዴግ ጽ/ቤት ኮሚኬሽን ኃላፊ ሆኑትን አቶ ሳዳት ጠይቀን ነበር። ''አቶ አብዲ የሰጡትን መግለጫ ተመልክቻለሁ። አቶ አብዲ በጽሁፍም ሆነ በስብሰባዎች ላይ ይፋ በሆነ መልኩ ያቀረቡት ጥያቄ ስለመኖሩ የምናውቀው ነገር የለም። ለከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ያላቸውን ቅሬታ አንስተው ሊሆን ይችላል። በጽ/ቤት ደረጃ ግን የምናውቀው ነገር የለም'' ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል። የህወሓት ምክትል ሊቀ-መንበርና የኢህዴግድ ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረ እግዚአብሔርም ''ስለ ጉዳዩ የማውቀው ነገር የለም። ለእኔም በግሌ የነገረኝ ነገር የለም፤ ሊነግረኝም አይችልም። እንዲህ አይነት ቅሬታም ካለ ህግ እና ሥርዓትን በመከተል ለሚመለከተው የመንግሥት አካል ማቅረብ ነው ያለባቸው። ስለዚህ ጉዳይ የማውቀው ነገር የለም። ይህ አይነት አቤቱታ ለማዕከላዊ ኮሚቴ የሚቀርብ አይደልም። የማውቀው ነገር የለም'' ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ጌታቸው አሰፋ ማናቸው? አቶ ጌታቸው አሰፋ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትን ለበርካታ ዓመታት በዋና ዳይሬክተርነት ይምሩት እንጂ ስለማነነታቸው እና ሥራቸው በይፋ የሚታወቅ ነገር የለም። ትውልዳቸው መቀሌ ከተማ ስለመሆኑ እና በወጣትነት ዘመናቸው ዊንጌት ስለመማራቸው በስፋት ይነገር እንጂ ይህም ቢሆን እውነትነቱ የተረጋጋጠ አይደለም። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ከቦታቸው እንዲነሱ ከተደረጉ ግለሰቦች መካከል አቶ ጌታቸው አንዱ መሆናቸው ይታወሳል። ከሳምንታት በፊት የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ባውጣው መግለጫ ጄነራል አደም መሃመድ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው አቶ ጌታቸውን ተክተዋል።
news-47634988
https://www.bbc.com/amharic/news-47634988
አሜሪካ የቦይንግ 737 ማክስ ፈቃድ ላይ ምርመራ ልታደርግ ነው
የአሜሪካ መንግሥት ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ለመብረር እንዴት ፈቃድ እንዳገኘ እንዲጣራ ትዕዛዝ አስተላለፈ።
በአምስት ወራት ውስጥ ሁለቴ የተከሰከሰው ይህ አውሮፕላን በሁለቱ አደጋዎቹ ውስጥ "ተመሳሳይነት" አለ ተብሏል። የትራንስፖርት ሚንስትር ኤሊን ቻኦ የአሜሪካ ምርመራ ክፍል የአውሮፕላኑን የበረራ ፈቃድ እንዲያጣራ ጠይቀዋል። • ሁለቱን የአውሮፕላን አደጋዎች የሚያመሳስላቸው ነገር አለ • ቦይንግ 737-8 ማክስ አውሮፕላኖቹ በሙሉ እስከ ግንቦት እግድ ተጣለባቸው የአደጋው መርማሪዎች አንዱ ትኩረታቸውን ያደረጉት የአውሮፕላኑን ሞትር በድንገት ከመቆም የሚጠብቀውን ሥርዓት ማጥናት ሲሆን፤ አውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ደግሞ ሶፍትዌሩ መሻሻል አለበት ብሏል። ቻኦ ለምርመራው ቡድን መሪ ካለቪን ስኮቭል በላኩት መልዕክት ምርመራው "የአሜሪካ ፌደራል የአየር ትራንስፖርት አስተዳደር አውሮፕላኑ የበረራ ደህንነት ማረጋገጫ ምርመራ በትክክል እንደተካሄደበት ለማረጋገጥ እንዲረዳ ነው" ብለዋል። የጥቅምት ወሩን የላየን ኤር አውሮፕላን አደጋን ተከትሎ ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ከተከሰከሰ በኋላ የአሜሪካ ፌደራል የአየር ትራንስፖርት አስተዳደር ለምን 737 ማክስ አውሮፕላንን ከበረራ ለማገድ ይህን ያህል ዘገየ የሚል ጥያቄ ፈጥሯል። ሬውተርስ እንደዘገበው የአሜሪካ ፍትህ ቢሮ የፌደራል የአየር ትራንስፖርት አስተዳደሩ የቦይንግ አውሮፕላንን የደህንነት ሁኔታ ለምን ችላ እንዳለ ምርመራ ጀምሯል። • ኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬም ስኬታማ ነው በአሁኑ ደረጃ አውሮፓና ካናዳ የአውሮፕላኑን ደህንነት በእራሳቸው ለማረጋገጥ መወሰናቸውን አሳውቀዋል። ይህ ውሳኔም የአውሮፕላኑን ተመልሶ በዓለም አቀፍ ደረጃ የመብረር አቅሙን ጥያቄ ውስጥ ከትቶታል። አውሮፓውያንና ካናዳውያን መርማሪዎች ብዙ ጊዜ የአሜሪካን ፌደራል የአየር ትራንስፖርት አስተዳደር የምርመራ ውጤትን ይከተሉ ነበር። የአውሮፓ ሕብረት የአየር ትራንስፖርት ደህንነት ኤጀንሲ (ኢሳ) በሚደረጉት ማንኛውም አይነት የንድፍ ማሻሻያን በጥልቀት ለመከታተል ቃል ገብቷል። "ሁሉንም ጥያቄዎቻችንን በበቂ ሁኔታ መልስ የሚሰጡ ነገሮችን ካላገኘን አውሮፕላኑ ተመልሶ እንዲበር ፈቃድ አንሰጥም" የኢሳ ኃላፊ ፓትሪክ ኪ ለአውሮፓ ሕብረት የተናገሩት ማረጋገጫ ነው። ከአሜሪካ ቀድማ አውሮፕላኑን ከበረራ ያገደችው ካናዳ፤ የአሜሪካን ፌደራል የአየር ትራንስፖርት አስተዳደር ማረጋገጫን ከመቀበል ይልቅ ወደፊት በእራሷ መርምራ 737 ማክስ አውሮፕላንን የበረራ ፈቃድ እንደምትሰጥ አሳውቃለች። የአሜሪካ ፌደራል የአየር ትራንስፖርት አስተዳደር በካናዳና አውሮፓ ሕብረት ውሳኔ ላይ አስተያየት ከመስጠት ቢቆጠብም በሰጠው መግለጫ "አሁን በአሜሪካና በዓለም ላይ የሚታየው የበረራ ደህንነት እዚህ ስኬት ላይ የደረሰው በእኛ ጠንካራ ሥራና ከሌሎች የዓለም አየር መንገዶች ጋር በምናደርገው ትብብር ነው" ብለዋል። • አቶ ተወልደ አየር መንገዶች ሁሉ ለጊዜው ቦይንግ 737-8 ማክስን እንዳይጠቀሙ ጠየቁ ባለፉት ሁለት አደጋዋች በአጠቃላይ 356 ሰዎች ሞተዋል። እስካሁን ሁለቱ አደጋዎች የተያያዙ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ባይገኝም የኢትዮጵያን አውሮፕላን ጥቁር ሳጥን እየመረመሩ ያሉ የፈረንሳይ ባለሙያዎች እስካሁን ባላቸው ግኝት በሁለቱ አደጋዎች መካከል "ተመሳሳይነት" አለ ብለዋል። ባለሙያዎች እንደሚሉት በቦይንግ አውሮፕላን ላይ አውሮፕላኑ ቁልቁል በአፍንጫው እንዳይከሰከስ ለማድረግ የተገጠመው አዲስ ቴክኖሎጂ ሁለቱም አደጋዎች ላይ ተፅዕኖ ሳይኖረው አይቀርም ይላሉ። ቦይንግ ከኢንስፔክተር ጀነራሉ ጋር የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን የበረራ ማረጋገጫ ለመፈተሽ እንደሚተባበር ተናግሯል።
news-50039748
https://www.bbc.com/amharic/news-50039748
በአፋር ክልል በተፈፀመ ጥቃት 17 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች ቆስለዋል
በአፋር ክልል፣ አፋንቦ ወረዳ፣ ኦብኖ ቀበሌ ሳንጋ የሚባል ጣቢያ ላይ አርብቶ አደሮች በሰፈሩበት አካባቢ ታጣቂዎች ፈፀሙት ባሉት ጥቃት የበርካታ ሰዎች ሕይወት ማለፉን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሁሴን አሊ ለቢቢሲ ገለፁ።
ባሳለፍነው አርብ ከሌሊቱ 10 ሰዓት እስከ ቅዳሜ ከቀኑ 10 ሰዓት ድረስ ተፈፅሟል ባሉት ጥቃት፤ 17 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን የስድስት ወር ህፃንን ጨምሮ ሴቶችና አረጋዊያን ይገኙበታል። በ34 ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ ደርሷል። አራቱ ከ7 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት ሲሆኑ፤ ዘጠኙ ደግሞ ሴቶች መሆናቸውን አቶ ሁሴን ተናግረዋል። የመቁሰል አደጋ ያጋጠማቸውም በአሳይታና በዱብቲ ሆስፒታሎች ሕክምና እየተከታተሉ ሲሆን የከፋ ጉዳት ያጋጠማቸው ወደ መቀሌ ሆስፒታል መላካቸውን ገልጸዋል። የነዋሪዎቹ ንብረት የሆኑ በርካታ እንስሳትም ተገድለዋል፤ በንብረትም ላይ ጉዳት ደርሷል። • በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ የሞቱ ሰዎች አስከሬን ለቤተሰቦቻቸው እየተሰጠ ነው አቶ ሁሴን የጥቃቱን ምክንያት በውል ባያውቁትም ከዚህ በፊት ከሚደርሱ አንዳንድ ግጭቶች በመነሳት የመሬት ወረራ ሳይሆን እንደማይቀር ይገምታሉ። "የመሬት ወረራ ነው፤ ወረዳው በሶማሌ ክልል ስር መሆን አለበት የሚሉ ይኖራሉ ብዬ እገምታለሁ፤ ስለዚህ የመሬት ወረራ ነው እንጂ ሌላ ምክንያት የለም " ብለዋል። መሬት ወረራ ለመሆኑ ምን ማስረጃ እንዳለቸው በቢቢሲ የተጠየቁት አቶ ሁሴን፤ ከአሁን በፊት የአርብቶ አደሮችን እንስሳት እየዘረፉና ግለሰቦችን እየገደሉ ይሄዱ እንደነበር ጠቅሰዋል። ታጣቂዎቹ በቁጥጥር ሥር አለማዋላቸውን የገለፁልን አስተዳዳሪው ካገኟቸው መታወቂያዎችና ሌሎች ማስረጃዎች ግን የጥቃት አድራሾቹን ማንነት መረዳት እንደቻሉ አስረድተዋል። • "ለእናንተ ደህንነት ነው በሚል እንዳሰሩን ተገልፆልናል" የባላደራ ምክር ቤት አስተባባሪ ጥቃቱን ከፈፀሙ በኋላም በአፋር ክልል በአብዛኛው የኢሳ ጎሳ አባላት ወደሰፈሩበት 'ሃሪሶ' የተባለ ቦታ መግባታቸውን ይናገራሉ። "ጥቃት ፈፃሚዎቹ እንደ መትረየስ እና ቦምብ ያሉ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ተጠቅመዋል" የሚሉት ዋና አስተዳዳሪው በጥቃቱ ሕፃናት፣ ሴቶች፣ አረጋዊያን እና ወጣቶች ሰለባ ሆነዋል። በወቅቱ የአካባቢው ነዋሪዎች ጥቃቱን ለመከላከል ካደረጉት ጥረት ውጪ "ጥቃት አድራሾቹ ያሰቡት ከፈፀሙ በኋላ ወደ መጡበት ተመልሰዋል" ሲሉ የክልሉ መንግሥት የወሰደው እርምጃ እንደሌለ ይናገራሉ። የክልሉ አመራሮች ወደ ሥፍራው አቅንተው የደረሰውን ጉዳት የተመለከቱ ሲሆን አካባቢውን ለማረጋጋት እየሠሩ እንደሆነ አክለዋል። እርሳቸው እንደሚሉት ከዚህ ቀደም በምሽት ወደ ሥፍራው በመሄድ እንስሳት መስረቅና አንዳንድ ሰዎችን ገድሎ መሄድ ካልሆነ በስተቀር እንደ አሁኑ በከባድ መሣሪያ የታገዘ ጥቃት ተፈፅሞ እንደማያውቅም ገልፀውልናል። "በወረዳው 400 የሚጠጉ አርብቶ አደሮች ይኖራሉ" የሚሉት የአካባቢው ነዋሪ አቶ አሎ ያዩ በበኩላቸው፤ በርካታ አርብቶ አደሮች በሚገኙበት ኦብኖ ቀበሌ ጥቃት መፈፀሙን ይናገራሉ። በጥቃቱም በሰው ሕይወት ላይ ብቻ ሳይሆን የንብረት ውድመትም አስከትሏል። በአካባቢው በሚኖሩ ማህበረሰቦች ላይ በተለያዩ ጊዜያት ጥቃት እንደሚደርስ ያስረዳሉ። አቶ አሎ ቦታው ድንበር በመሆኑ ከአዋሽ እስከ ጅቡቲ ያለው መንገድ ተመሳሳይ ጥቃቶችን እንደሚያስተናግድ ገልፀው፤ ከዚህ ቀደም ነፍሰ ጡሮች ሳይቀሩ የተገደሉበት አጋጣሚ መኖሩን አስታውሰዋል። • በአፋር ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት አንድ ሰው ተገደለ የአፋር ክልል የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሕመድ ካሎይታ፤ በክልሉ ዞን አንድ፣ አፋንቦ ወረዳ ላይ በአርብቶ አደሮች ላይ ድንገተኛ ጥቃት መፈፀሙን ይናገራሉ። ጥቃቱም ከጅቡቲ በመጡ ከባድ መሳሪያ በታጠቁ ኃይሎች መፈፀሙንም ያስረዳሉ። በጥቃቱ ሴቶችና ህፃናትም ሰለባ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። "የደረሰው ጥቃት አሳዛኝና የሚያሳምም ነው" የሚሉት ኃላፊው አካባቢው ድንበር በመሆኑ ሕገ ወጥ ኮንትሮባንዲስቶች መንቀሳቀሻ መሆኑን አመልክተው፤ ታጣቂዎቹ ይህንን ሕገ ወጥ ድርጊት እንደልባቸው ለማንቀሳቀስ በማሰብ አርብቶ አደሮቹ ላይ ጥቃት እንደፈፀሙ ያስረዳሉ። በጥቃቱም ከጂቡቲ የገቡ እና የኢሳ የታጠቁ ኃይሎች መሳተፋቸውን ይናገራሉ። "በዋናነት ሕፃናትና ሴቶች ላይ ትኩረት አድርገው ነው ጥቃቱን የፈፀሙት" የሚሉት ኃላፊው ሕይወታቸው ያለፉ እንዲሁም ጉዳት ደርሶባቸው ሕክምና ላይ የሚገኙ እንዳሉ ተናግረዋል። በአካባቢው ከክልሉ አልፎ ለአገር ስጋት የሆኑና ሕገወጥ የጦር መሣሪያዎችን ንግድ የሚያንቀሳቅሱ ግለሰቦች አሉ፤ ብዙ ጊዜም ሕገ ወጥ መሣሪያዎች በአካባቢው ይያዛሉ" ሲሉ ያስረዳሉ። በመሆኑም የሚመለከተው አካል አስቸኳይ መፍትሔ ሊወስድ ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። የክልሉ ባለሥልጣናት የአካባቢውን ሰላም ለማረጋጋጥ እየሠሩ መሆናቸውን አክለዋል። በተያያዘ ዜናም አንዳንድ ወገኖች የጅቡቲ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግሮ አፋር ክልል በመግባት ጥቃት ፈጽሟል በሚል ያቀረቡት ክስ ሀሰት መሆኑን የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር መግለጹን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። የዜና ተቋሙ የመከላከያ ሚኒስትር ምክትል ኤታማዦር ሹም ጽ/ቤት ኃላፊ ኮሎኔል ተስፋዬ አያሌውን ጠቅሶ እንደዘገበው በአፋር ድንበር በኩል የጅቡቲ ጦር የኢትዮጵያ ድንበር ገብቶ በአርብቶ አደሮች ላይ ጉዳት አደረሰ የሚለው መረጃ ሃሰት መሆኑን ገልጿል። አክሎም በአካባቢው አልፎ አልፎ በግጦሽ፣ በውሃ እና በሌሎች ምክንያቶች ከሚከሰቱ ግጭቶች ውጪ በሁለቱ አገሮች መካከል ለግጭት የሚዳርግ ምንም ምክንያት አለመኖሩን አስረድተዋል። በክልሉ በዜጎች ላይ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተም የመከላከያ ሠራዊት በሥፍራው ተገኝቶ ጉዳዩን እያጣራ መሆኑን ተናግረዋል።
51830174
https://www.bbc.com/amharic/51830174
የዲያቆን ዳንኤል ክብረት የቦርድ አባልነት ውዝግብ አስነሳ
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባው የሚኒስትሮችን፣ የኮሚሽነርና የቦርድ አባላት ሹመትን አጽድቋል።
በዕለቱ አንዳንድ የምክር ቤቱ አባላት ምክር ቤቱ ሹመት በመስጠትና በመንፈግ ላይ መጠመዱን በማንሳት ቅሬታ ያቀረቡ ሲሆን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ቦርድ አባልነት የቀረቡት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ላይ ያላቸውን ተቃውሞ አሰምተዋል። ለኢትዮጵያ የፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባል ሆነው ከቀረቡ ዘጠኝ ሰዎች መካከል አንዱ የሆኑት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ላይ ቅሬታ ያቀረቡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እንዳሉት ከሆነ ግለሰቡ የሀይማኖት እኩልነት ላይ የማያምኑ፣ በዜጎች መካከል ክፍፍል እንዲፈጠር የሚሰሩ፣ በማለት በሕዝብ የሚነሱባቸው ቅሬታ ወደ ጎን በመተው መቅረብ አልነበረባቸውም በሚል አባልነታቸውን ተቃውመዋል። የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት መላውን ኢትዮጵያ የሚያገለግል በመሆኑ በእርሳቸው የቦርድ አባልነት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባል ሆነው ከቀረቡት አባላት መካከል ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ላይ ቅሬታ በመቅረቡ ለብቻው ጉዳያቸው ታይቶ ድምጽ እንዲሰጥ ከተደረገ በኋላ በ148 ድጋፍ በ126 ተቃውሞ እና 24 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ የዲያቆን ዳንኤል የቦርድ አባልነት ፀድቋል። ከዚህ በኋላ በቀሩት አባላት ላይ ድምጽ የተሰጠ ሲሆን በአብላጫ ድጋፍ ድምጽ በመመረጣቸው በሕዝብ ተወካዮቹ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል። ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባል የነበሩትና አሁንም በአባልነት እንዲቀጥሉ የቀረቡት ዲያቆን ዳንኤል በአብላጫ ድምጽ ከተመረጡ በኋላ በምክር ቤቱ ቀርበው ቃለ መሀላ ከፈፀሙ የቦርድ አባላት መካከል አልተገኙም ነበር። ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አቅራቢነት የቀረበለትን የተለያዩ የሚኒስትሮች ሹመትንም ተቀብሎ አጽድቋል። በዚህም መሰረት ምክር ቤቱ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ፣ ዶክተር ሊያ ታደሰ የጤና ሚኒስትር፣ አቶ ላቀ አያሌው የገቢዎች ሚኒስትር፣ ወይዘሮ ፊልሰን አብዶላሂ የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር በማድረግ በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል። በዛሬው እለት የተሾሙት ሚኒስትሮችም ሆኑ የፕሬስ ድርጅት ቦርድ አባላት በምክር ቤቱ ቀርበው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል። በተጨማሪም ምክር ቤቱ የፌደራል የሥነ ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሹመት አጽድቋል። አቶ ፀጋ አራጌ የፌደራል የሥነ ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን ተሾመዋል። በምክር ቤቱ ውሎ ከቀረቡት ሌሎች ቅሬታዎች መካከል የብልጽግና ፓርቲ ሕጋዊነት ጉዳይ ከአንዳንድ አባላት የተነሳ ሲሆን ሌሎች የሕዝብ እንደራሴዎች ደግሞ የምርጫ ቦርድ ሕግን በመጥቀስ የፓርቲውን ሕጋዊነት ተከራክረዋል።
news-52197187
https://www.bbc.com/amharic/news-52197187
ኮሮናቫይረስ፡ በኢኳዶር ሬሳ-ሳጥን በመጥፋቱ ሬሳ-ካርቶን ታደለ
በደቡብ አሜሪካዋ ኢኳዶር የጣውላ ሬሳ ሳጥን እጥረት በመከሰቱ ባለሥልጣናት ለጊዜው የካርቶን ሬሳ ሳጥን እየተጠቀሙ ነው።
በኢኳዶር ሕዝብ እጭቅ ባለባት ከተማ ጓያኪውል እጥረቱ ከፍተኛ በመሆኑ መንግሥት 4 ሺህ የሬሳ "ሳጥኖችን" (የሬሳ ካርቶኖችን) ለማከፋፈል ተገዷል። የሬሳ መርማሪዎች ምርመራ ከጨረሱ በኋላ የሬሳ ሳጥን ያለህ እያሉ ሲሆን የቀብር አስፈጻሚዎችም ምን ማድረግ እንዳለባቸው ተቸግረው ቆይተዋል። በዚች የኢኳዶር ትልቅ ከተማ ከሦስት ሚሊዮን ሰዎች በላይ ይኖራሉ። በርካታ ሰዎች በኮሮናቫይረስ እየሞቱም ነው። ምንም እንኳ ይፋዊው የሟቾች ቁጥር 180 ብቻ ነው ቢልም ይህ አሐዝ ትክክል እንዳልሆነ ብዙዎች ያምናሉ። ፕሬዝዳንት ሌኒን ሞሬኖ ይህ ቁጥር ተመርምረው ኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸው የሞቱትን ብቻ የሚመለከት ነው ብለዋል። የአገሪቱ በቀን የመመርመር አቅም ዝቅተኛ በመሆኑ ዜጎች በቫይረሱ መያዛቸው ሳይታወቅ እየሞቱ እንደሆነ ይገመታል። ይህቺ ጓያኪውል የምትባለው ከተማ የወደብ ከተማ ስትሆን በሽታው የተነሳባት የኢኳዶር ከተማ ናት። የከተማዋ ነዋሪዎች በየመንገዱ ሬሳ እየተጣለ እንደሆነና መንግሥት ቶሎ ቶሎ ሬሳዎችን እያነሳ እንዲቀብር ሲጠይቁ ነበር። በርታ ሳሊናስ የተባለች አንዲት ነዋሪ ለቢቢሲ-ስፓኒሽ ክፍል በቅርቡ እንተናገረችው የእህቷ እንዲሁም የእህቷ ባል ሬሳ ከቤት ለማውጣት አራት ቀናት ወስዷል። ለጊዜው በፕላስቲክ አንሶላ ሬሳዎቹን ጠቅልለን ለማቆየት ተገደን ነበር ብላለች ሳሊናስ ለቢቢሲ። ኢኳዶር የሕዝቧ ብዛት 17 ሚሊዮን ሲሆን እስካሁን 3ሺህ 465 ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው ተረጋግጧል። የጓያኪውል ከተማ ከንቲባ ራሳቸው በቫይረሱ ተይዘው የአልጋ ቁራኛ ናቸው።
news-56817115
https://www.bbc.com/amharic/news-56817115
በኦሃዮ ግዛት ፖሊስ የ16 አመት ጥቁር ታዳጊ ሴትን በጥይት ገደለ
በአሜሪካዋ ኦሃዮ ግዛት ፖሊስ የ16 አመት ጥቁር ታዳጊ ሴት በጥይት ተኩሶ መግደሉ ተዘግቧል።
ፖሊስ በአካባቢው የቢላ መውጋት ሙከራ ተደርጓል በሚል አስቸኳይ የስልክ ጥሪ ደርሶት ነው ወደ አካባቢው የደረሰው ተብሏል። ከፖሊስ በተተኮሰባት ጥይት የተገደለችው ታዳጊ ማኪያ ብሪያንት ትባላለች። በኦሃዮ፣ የየኮሎምበስ ፖሊስ በበኩሉ ታዳጊዋ ላይ ጥይት ከመተኮሱ በፊት ሌሎች ሰዎች ላይ በቢላ ጥቃት ለማድረስ እየሞከረች አለኝ በማለት እንደ ማስረጃነት ከመኪና የተቀረፀ ቪዲዮ አሳይቷል። በአሁኑ ወቅት በግድያው ላይ ምርመራ የተከፈተ ሲሆን ባለስልጣናቱም የአካባቢውን ነዋሪ ተረጋጋጉ በማለት በመጠየቅ ላይ ናቸው። በግድያው ላይ ተሳትፏል የተባለው ፖሊስ ከደመወዙ ጋር እረፍት እንዲወስድ ተደርጓል። በኦሃዮ ግዛት በምትገኘው ኮሎምበስ ከተማ በያዝነው ሳምንት ማክሰኞ በአንድ ሰፈር አካባቢ ረብሻ በመነሳቱ ፖሊስ እንዲደርስ ጥሪ የቀረበለት ከሰዓት 10፡45 አካባቢ ነበር። ከፖሊስ መኪና የተቀረፀው ቪዲዮ እንደሚያሳየው ከአንድ ቤት ውጭ በተሰበሰቡ ግለሰቦች መሃል ጭቅጭቅ መነሳቱንና ማኪያ ብሪያንት የተባለችው ታዳጊ በአንደኛው ቡድን አባል የጩቤ ጥቃት ስትሰነዝር ያሳያል። ፖሊስ ቡድኑን ተጠግቶ መሬት ላይ ተንበርከኩ በማለት በርካታ ጥይት ተኩሶ ታዳጊዋንም ክፉኛ ተኩሶ አቁስሏታል። በቪዲዮውም ላይ ፖሊሱ "ቢላ ይዛለች፤ ተኩስ" የሚለው ድምፁ የሚሰማ ሲሆን በአካባቢው ሁኔታውን ሲታዘብ የነበረ ግለሰብ ህፃን ልጅ ናት ሲል ይሰማል። ባለስልጣናቱ ፖሊስ ታዳጊዋ ላይ የተኮሰባት የሌሎቹን ታዳጊዎች ህይወት ለማዳን ነው ብለዋል። የማኪያ አክስት በበኩሏ ለአካባቢው ሚዲያ እንደተናገረች የእህቷ ልጅ ጥቃት ደርሶባት ራሷን እየተከላከለች ነበር ብላለች። ሃዜል ብሪያንት የተባለችው የታዳጊዋ አክስት ለአንደኛው ቴሌቪዥን እንደተናገረችው "በጣም ጥሩ ልጅ ነበረች። አዎ እንደ ሁሉም ታዳጊ ልጆች ረባሽ ልትሆን ትችላለች ነገር ግን እንደ ውሻ በጎዳና ላይ መሞት አይገባትም" ብላለች። የማኪያ እናት ፓውላ ብሪያንት በበኩላቸው "ተጎድቻለሁ፣ ተሰብሬያለሁ" በማለት በልጃቸው ሞት ሃዘናቸውን የገለፁ ሲሆን ልጃቸው "ሰው ወዳጅ ነበረች" ብለዋል። "ይሄ መፈጠር አልነበረበትም፤ መልሶች እፈልጋለሁ" በማለት በኃዘን በተሰበረ ድምፃቸው ተናግረዋል።
news-54054557
https://www.bbc.com/amharic/news-54054557
"ቻይና በአፍሪካ የጦር ሰፈር ለመክፈት አራት አገራትን እያማረጠች ነው" አሜሪካ
የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር ቻይና በአፍሪካ ወሳኝ የጦር ሰፈር አስፈልጓታል አለ። አራት አገራትንም ለዚሁ ዓላማ በቻይና ታጭተዋል ብሏል።፡
ከአሜሪካ መከላከያ ሚንስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ኬንያ፣ ሲሼልስ፣ ታንዛኒያና አንጎላ ናቸው ቻይና የጦር ሰፈር ልትከፍትባቸው ያሰበቻቸው አገራት። ሆኖም ግን ሌሎችም አገራትም በቻይና እቅድ ውስጥ ቢኖሩም ለጊዜው ስማቸውን አልተገለም። ይህን የአሜሪካንን መግለጫ በተመለከተ አራቱ አገራት ምላሽ አልሰጡም። ይህ ሪፖርት የወጣው ባለፈው ሳምንት ሲሆን በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት በስፋት ሪፖርቱ በየአገራቱ ሚዲያዎች ሲናፈስ ቆይቷል። ዘገባው እንደሚለው ቻይና አሁን በጂቡቲ ካላት የጦር ሰፈር ሌላ በሌሎች ቢያንስ አራት አገራት፣ የአየር፣ የባሕር፣ የእግረኛ ጦር ማቀነባበርያ የጦር ሰፈር ለመክፈት ከጅላለች፣ ንግግርም ጀምራለች። ከአፍሪካ ውጭ ደግሞ በማያንማር፣ በታይላንድ፣ በሲንጋፖር፣ በኢንዶኒዢያ፣ በፖኪስታን፣ በሲሪላንካ፣ በዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ፣ በአንጎላና በታጃኪስታን ሌሎች ጦር ሰፈሮችን ለመክፈት ቻይና ስለማሰቧ ተነግሯል።
news-55019336
https://www.bbc.com/amharic/news-55019336
ሕዋ ፡ ከአሜሪካ ተባሮ ቻይናን ወደ ሕዋ እንድትመጥቅ ያስቻላት ሰው
ቻይናዊው ሳይንቲስት አንድ ብቻ ሳይሆን ሁለት ኃያል አገራትን ወደ ሕዋ እንዲመጥቁ አድረጓል። ነገር ግን ታሪኩ የሚወሳው በአንደኛዋ አገር ውስጥ ብቻ ነው።
ለዚህ ሰው መዘከሪያ ሻንጋሃይ፣ ቻይና ውስጥ አንድ ሙሉ ሙዚዬም ቆሟል። በዚህ ሙዚዬም ውስጥ 70 ሺህ የሚደርሱ ቁሳቁሶች ቻይና 'የሕዝብ ሳይንቲስት' እያለች የምትጠራውን ኩዊያን ዙሴንን ለማስታወስ ተሰድረዋል። ኩዊያን የቻይና ሚሳኤልና የሕዋ ፕሮግራም አባት ነው። ቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሕዋ ያመጠቀችውን የመጀመሪያ ሳተላይትን ገንብተው ዕውን ካደረጉት መካከል ነው። አገሪቱ ላደረገችው የሚሳኤል ግንባታ ያበረከተው ጥናትም ቻይናን ኒውክሌር ታጣቂ አድርጓታል። ሰውዬው ቻይና ውስጥ ስሙ ሁሌም ሲታወስ ይኖራል። ነገር ግን ከአስር ዓመት በላይ በተማረባትና በሠራባት ሌላኛዋ ኃያል አገር እምብዛም አይታወስም። ኩዊያን የተወለደው በጎሮጎሳውያኑ በ1911 ነበር። ቤተሰቦቹ የተማሩ ናቸው። አባቱ የቻይናን ዘመናዊ ትምህርት ሥርዓት ከዘረጉት ሰዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ኩዊያንም እጅግ ጎበዝ ተማሪ ነበር። ከሻንግሃይ ጂያዎ ቶንግ ዩኒቨርሲቲ በማዕረግ ተመርቆ የአሜሪካው ማሳቹሴትስ የቴክኖሎጂ ተቋም ውስጥ የመማር ዕድል አገኘ። በ1935 ፀጉሩን በመስመር የተቆረጠ፤ ቦላሌ በልኩ የታጠቀ ቻይናዊ ለትምህርት ቦስተን ደረሰ - ማሳቹሴትስ የቴክኖሎጂ ተቋም ለመማር። ትምህርቱን እንደጨረሰ ካልቴክ እየተባለ ወደ ሚቆላመጠው ዝነኛው የካሊፎርኒያ የቴክኖሎጂ ተቋም አቀና። በወቅቱ ተቋሙ አሉ የሚባሉ መምህራን የሚያስተምሩበት ነበር። ቢሮውን ደግሞ የሚጋራው ታዋቂው ሳይንቲስት ፍራንክ ማሊና ነበር። ጊዜው የሮኬት ሳይንስን በተመለከተ ጥቂት ተማሪዎች ላይ ብቻ ፍላጎት የሚያሳዩበትና የሚወያዩበት ርዕስ ነበር። የትኛውም ተማሪ ኒውክሌር ሳይንስ የወደፊቱ ዐብይ ርዕስ ይሆናል ብሎ ደፍሮ አይናገርም። ይህ የተቀየረው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ነው። ፍራንክ ማሊና እና ሌሎች ሳይንቲስቶች 'ሳይንስ ስኳድ' ተብለው ነው የሚጠሩት። ይህ ቡድን በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ወቅት የአሜሪካ መከላከያ መስሪያ ቤትን ቀልብ መሳብ ጀመረ። መከላከያው ለቡድኑ ድጋፍ በማድረግ ትናንሽ ክንፍ ያላቸውና በአጭር ርቀት መንደርደሪያ የሚነሱ አውሮፕላኖች እንዲሠሩ ማድረግ ጀመር። በዚህ ፕሮጀክት ተሳታፊ ከነበሩ ሳይንቲስቶች መካከል አንዱ ቻይናዊው ኩዊያን ነው። በወቅቱ ቻይና ሪፐብሊክ የአሜሪካ አጋር ነበረች። ስለዚህ የኩዊያን በፕሮጀክቱ ላይ መሳተፍ እምብዛም አሳሳቢ አልነበረም። ይህን ዕድል የተጠቀመው ኩዊያን ድብቅ የሆኑ ጥናቶችን ሳይቀር የማግኘት እድልን አገኘ። ለአሜሪካ ሳይንስ አማካሪ ቦርድም ይሠራል ነበር። ጦርነቱ ሲያበቃ ኩዊያን ዓለም ውስጥ አሉ ከሚባሉ የጄት ሳይንቲስቶች መካከል አንዱ ለመሆን ችሎ ነበር። ወደ ጀርመን አቅንቶም በጊዜያዊነት ሌፍተናንት ኮሎኔል ሆኗል። ቻይናዊው ሳይንቲስት አድራሻውን አሜሪካ ባደረገ በአስር ዓመቱ ነገሮች ይወሳሰቡ ጀመር። በ1949 ሊቀ-መንበር ማኦ አገራቸው ቻይና የኮሚኒስት ሪብሊክ ሆናለች ሲሉ አወጁ። በዚህ ጊዜ ቻይናዊያን አሜሪካ ውስጥ እንደ ጠላት መታየት ጀመሩ። በተመሳሳይ ወቅት አሜሪካ ውስጥ ሰላዮች እንዳሉ ይነገር ጀመረ። ከተጠርጣሪዎቹ አንዱ ደግሞ ሊቁ ኩዊያን ሆነ። ምንም እንኳ ሳይንቲስቱ ሰላይ ስለመሆኑ ማስረጃ ባይቀርብበትም የይለፍ ወረቀቱን ተነጥቆ የቁም እሥረኛ እንዲሆን ተፈረደበት። የካሊፎርኒያ ቴክኖሎጂ ተቋም [ካልቴክ] ባልደረቦቹ እሱ ንፁህ ነው ብለው ቢከራከሩለትም የሚሰማ ጆሮ ጠፋ። ከአምስት ዓመት የቁም እሥርና እንግልት በኋላ ፕሬዝደንት አይዘንአወር ወደ ቻይና እንዲባረር ወሰኑ። ሳይንቲስቱም ከባለቤቱና አሜሪካ ከተወደሉ ሁለት ልጆቹ ጋር በመሆን በጀልባ ከአሜሪካ ወጣ፤ ወደዚያች አገር ላይመለስም ቃል ገባ። ቃሉንም አላጠፈም። ሳይንቲስቱ ቻይና ሲገባ የጀግና አቀባበል የተደረግለት ሲሆን የቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ አባል እንዲሆን ጥሪ ቀረበለት። ከዚያም ከጥቂት ጊዜ በኋላ አሁን ድረስ አገሪቱን በብቸኝነት እያስተዳደረ ያለው ኮሚዩኒስት ፓርቲ አባል ሆነ። ቻይና ሲገባ የሮኬት ሳይንስ ጉዳይ ብዙም የሚታወቅ አልነበረም። ነገር ግን ከ15 ዓመታት በኋላ ቻይና የመጀመሪያውን ሳተላይት ስታመጥቅ ምርመሩን የመራው እሱ ነበር። ኩዊያን ለዘመናት ቻይናዊያንን ስለ ሮኬት ሳይንስ አስተምሯል። የቻይና ሉናር ኤክስፕሎሬሽን ፕሮግራም የተሰኘው ተቋም እንዲቋቋም አስተዋፅዖ አድርጓል። የሚገርመው ቻይና በእሱ አጋዥነት ያበለፀገችውን መሣሪያ አሜሪካ ላይ መተኮሷ ነው። ይህ የሆነው በባሕረ ሰላጤው ጦርነት ወቅት በፈረንጆቹ 1991 ነበረ። ዛሬ ቻይናና አሜሪካ መልሰው ፍጥጫ ውስጥ ናቸው። የአሁኑ ፍጥጫ የንግድ ነው፤ የቴክኖሎጂ ደኅንነት ጉዳይም ያጨቃጭቃቸዋል፤ ሌላው ደግሞ ፕሬዝደንት ትራምፕ እንደሚሉት ቻይና ኮቪድ-19ኝ ወደሌሎች አገራት እንዳይዛመት አላደረገችም በሚል ነው። ምንም እንኳ አሜሪካውያን ኩዊያን ማን እንደሆነ ባያውቁትም በርካታ ቻይናዊ አሜሪካዊያን ይህንን ሊቅ በደንብ ያውቁታል። ምናልባትም አሜሪካ በግዛቷ ተምሮ ታላቅ ሥራዎችን ማከናወን ያቻለውን ኩዊያንን ወደ ትውልድ አገሩ ቻይና ባታባርረው ኖሮ 'ታላቅ አሜሪካዊ ሳይንቲስት' እተባለ ሥራው ሊወሳ ይችል ነበር። ኩዊያን አንድ ክፍለ ዘመን ለሚጠጋ ጊዜ እዚህች ዓለም ላይ ኖሯል። በዚህ ጊዜ ቻይና ከድህነት ወደ ዓለም ኃያልነት ተሸጋግራለች። ከመሬት አልፋ ሕዋ ላይ የበላይ ከሚባሉ አገራት ተርታ ተሰልፋለች።
news-56398440
https://www.bbc.com/amharic/news-56398440
ኮሮናቫይረስ፡ በኢትዮጵያ ኮቪድ-19 በጽኑ የሚታመሙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር "በአስደንጋጭ ሁኔታ" ጨመረ
በኢትዮጵያ ከጥቂት ሳምንታት ወዲህ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የሚያዙ፣ ወደ ጽኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡና በበሽታው ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር "በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ" መሆኑን የሕብረተሰብ ጤና ኢነስቲቲዩት አስታወቀ።
ቀደም ሲል በጽኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ህክምና እያገኙ የነበሩ ሰዎች ቁጥር በአራት መቶዎች ውስጥ የቆየ ሲሆን ይህ አሃዝ ባለፉት ቀናት ውስጥ አምስት መቶን ተሻግሮ ወደ ስድስት መቶ መጠጋቱን በየዕለቱ የሚወጣው የበሽታው የዕለት ሁኔታ ሪፖርት ያመለክታል። ሰኞ ዕለት በጽኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ይገኙ የነበሩት ሰዎች ቁጥር 531 የነበረ ሲሆን ትናንት ማክሰኞ ቁጥሩ በ60 ጨምሮ 591 በመድረሱ በህክምና ተቋማቱ ላይ ጫና መፈጠሩ ተነግሯል። በዚህም ሳቢያ የጽኑ ህሙማን ክትትል ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች በሚውሉት የሰው ሰራሽ መተንፈሻ መርጃ (ቬንትሌተር) እና ኦክስጂን አቅርቦት ላይ እጥረት አጋጥሟል የሕብረተሰብ ጤና ተቋም ትናንት እናደለው የሰውሰራሽ መተንፈሻ ድጋፍ ከሚያስፈልጋቸው ሰዎች መካከል ስምነቱ በመጠባበቅ ላይ ነበሩ። ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በነበሩ ቀናት የተደረጉ የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤቶች እንደሚያመለክቱት በየዕለቱ በአማካይ ከ1300 በላይ ሰዎች ላይ በወረርሽኙ መያዛቸውን ያመለክታል። አጠቃላይ የምርመራው ውጤት በመቶኛ ሲሰላ ከተመረመሩት 100 ሰዎች ውስጥ በአማካኝ 19 ሰዎች ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። በዚህም በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከ32 በመቶ በላይ ጨምሯል። በበሽታው ሰበብ ለህልፈት የሚዳረጉ ሰዎችን ቁጥር ስንመለከትም ከዕለት ዕለት ዕየጨመረ በአማካይ ከ15 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ህይወት እያለፈ ነው። ይህም ቀደም ካሉት ሳምንታት ጋር ሲነጻጸር በ89 በመቶ መጨመሩን ባለሙያዎቹ ተናግረዋል። ወረርሽኙ ከቁጥጥር ውጪ እንዳይሆን ተሰግቷል የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ማክሰኞ ዕለት፣ በሰጡት መግለጫ "ወረርሽኙ ከቁጥጥር ውጭ ከመሆኑ በፊት ሁሉም ኃላፊነቱን መወጣት አለበት" ሲሉ አሳስበዋል። የበሽታው ስርጭት ባለፉት ወራት በተለይም ባለፉት ሳምንታት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ጠቅሰው፤ ቀደም ሲል በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ከ10 በመቶ በታች የነበረው ከፍ ብሎ አዲስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአማካይ 17 በመቶ ማሻቀቡን ተናግረዋል። በዚህም እስካሳለፍነው ቅዳሜ ድረስ በነበሩት 10 ቀናት ውስጥ "ከ12 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ፣ የ149 ሰዎች ህይወትም በወረርሽኙ ሳቢያ አልፏል" ብለዋል። የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን እንዲሁም የጽኑ ህሙማን ህክምና የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥርም በባለፉት ቀናት ለመጀመሪያ ጊዜ ከ450 መብለጡን ተናግረዋል። በዚህም ሳቢያ የጽኑ ህሙማን ክፍሎች መሙላታቸውን፣ ያሉ የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያዎች (ቬንትሌተር) በህሙማን ሙሉ ለሙሉ መያዛቸውን እንዲሁም የኦክስጅን እጥረት ማጋጠሙን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ እስከ መጋቢት 06/2013 ዓ.ም ድረስ በተደረገ የኮሮናቫይረስ ምርመራ 176,618 ሰዎች በወረርሽኙ መያዛቸው የተረጋጠ ሲሆን 2,555 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። በተጨማሪም 531 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ምክንያት በጽኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፤ ይህ ቁጥርም በሽታው ኢትዮጵያ ውስጥ ከተገኘ በኋላ ከፍተኛው ነው። የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ተቋም እንዳለው ከእነዚህም ውስጥ 66ቱ ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ (ቬንትሌተር) ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው። የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ተቋም ዛሬ ባወጣው መረጃ መሰረት ያሉት የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያዎች በመያዛቸው በጽኑ የታመሙ 8 ያህል ግለሰቦች የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ። "ክትባት መሰጠቱ ይቀጥላል" የጤና ሚኒስትሯ በአገሪቷ እየተሰጠ ያለውን የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት አስመልክቶ የአስትራዜኒካ ክትባትን መስጠት እንደሚቀጥል ተናግረዋል። አንዳንድ አገራት ከአስትራዜኒካ የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል ባሉት ችግር ምክንያት ክትባቱን መስጠት ቢያቆሙም በኢትዮጵያ ክትባቱ መሰጠት እንደሚቀጥል የጤና ሚኒስቴር ገልጿል። ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ዴንማርክ፣ ኖርዌይ እና ስፔንን ጨምሮ ስምንት የአውሮፓ አገራት ክትባቱ ከደም መርጋት ጋር የተያያዘ ችግር ሊኖረው ይችላል በሚል የአስትራዜኔካ ክትባት ለጊዜው እንዲቆም አድርገዋል። የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ዛሬ ማክሰኞ፣ በሰጡት መግለጫ ላይ እንዳሉት በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ውስጥ እየተሰጠ ያለው የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ጋር በተያያዘ እስካሁን ያጋጠመ ችግር እንደሌለ ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ መሰጠት የተጀመረው ወረርሽኙ በአገሪቱ ውስጥ መገኘቱ ይፋ በተደረገ በዓመቱ ባለፈው ቅዳሜ መጋቢት 04/2013 ዓ.ም ነበር። በአገሪቱ እየተሰጠ የሚገኘው የአስትራዜኔካ ምርት የሆነው 2.2 ሚሊየን ብልቃጥ ክትባት ኮቫክስ ከተሰኘው ዓለም አቀፍ የክትባት አቅርቦት ጥምረት የቀረበ ነው። ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ እስካሁን ባለው መረጃ ተከሰተ የተባለው ችግር "ከአስትራዜኒካ ክትባት ጋር ግንኙነት እንደሌለውና ክትባቱ መቀጠል እንዳለበት የዓለም የጤና ድርጅት፣ የአውሮፓና የእንግሊዝ የመድኃኒት ጥናትና ቁጥጥር ባለስልጣን በይፋ አስታውቀዋል" ብለዋል። በአውሮፓ ሕብረት አባላት አገራትና በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ እስካሁን 17 ሚሊዮን ሰዎች የአስትራዜንካ ክትባትን መከተባቸውና ከእነዚህ ውስጥም 40ዎቹ የደም መርጋት ችግር እንዳጋጠማቸው የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። የዓለም ጤና ድርጅት በርካታ የአውሮፓ አገራት የአስትራዜኒካ ክትባት እንዳይሰጥ ማገዳቸውን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ ክትባቱ የደም መርጋት ስለማስከተሉ ምንም አይነት ማስረጃ የለም ብሏል። ዶ/ር ሊያ ታደሰም ክትባቱ በበርካታ አገራት ውስጥ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች መዳረሱንና በኢትዮጵያም መሰጠቱ እንደሚቀጥል ተናግረው ጉዳዩ "በሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በኩል ጥብቅ ክትትል ይደረግበታል" ብለዋል። በዚህም መሠረት ክትባቱን በተመለከተ አዲስ ነገር የሚኖር ከሆነ ሕብረተሰቡ እንዲያውቀው እንደሚደረግ ገልጸው "ከክትባቱ ጋር ተያይዞ እስካሁን የገጠመ ችግር ባለመኖሩ ክትባቱን መስጠታችንን እንቀጥላለን" ብለዋል። በዚህም መሠረት ክትባቱ ለጤና ባለሙያዎች፣ ተጓዳኝ በሽታ ላለባቸው ሰዎችና ለአረጋዊያን በተከታታይ የሚሰጥ መሆኑን በመግለጽ እስከሚቀጥለው ዓመት ታኅሣስ ድረስ ከአገሪቱ ሕዝብ 20 በመቶውን እንዲከተብ ይደረጋል ብለዋል።
news-56493093
https://www.bbc.com/amharic/news-56493093
አሜሪካ ኮሎራዶ ውስጥ አንድ ታጣቂ በከፈተው ተኩስ 10 ሰዎች ገደሉ
በኮሎራዶ አንድ ግለሰብ ፖሊስን ጨምሮ አስር ሰዎችን በገበያ ሥፍራ ተኩሶ መግደሉን ፖሊስ አስታወቀ።
ጥቃት ፈጻሚው ቆስሎ መያዙም ተሰምቷል። በገበያ ሥፍራው የደረሰው ጥቃት በዩቲዩብ ቀጥታ መተላለፉም ታውቋል። ጥቃቱ የደረሰው በአገሪቱ አቆጣጠር ቀን 8፡30 ላይ ሲሆን ግለሰቡ ወደ ገበያ አዳራሹ እንደገባ መተኮስ ጀምሯል። ጥቃቱ የደረሰበት አካባቢ፣ ቦውልደር ፖሊስ ከ20 ደቂቃ በኋላ በትዊተር ገፁ ላይ "በኪንግ ሱፐርስ የገበያ ስፍራ ተኩስ የከፈተ ግለሰብ አለ" ሲል ጽፎ ነበር። ከሁለት ሰዓት በኋላ ፖሊስ ሰዎች ከአካባቢው እንዲርቁ አስጠንቅቋል። አክሎም "ምንም ዓይነት ቴክኒካዊ መረጃ ካያችሁ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ አታሰራጩ" ሲል ትዊትር ሰሌዳው ላይ ነዋሪዎቹን ጠይቋል። ነገር ግን አንዳንድ በአካባቢው የነበሩ ግለሰቦች በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸውን ግለሰቦች ምስል በማኅበራዊ ሚዲያዎቻቸው ላይ ሲያጋሩ ነበር። በዩቲዩብ የተላለፈው ቪዲዮ ላይ "ምን እንደተከሰተ አላውቅም. . . የተኩስ ድምጽ ሰማሁ። የሆነ ሰው ተመትቶ ወደቀ" የካሜራ ባለሙያው "የሚተኩስ ሰው አለ ዞር በል" ብሎ ሲጮህ ይሰማል። ከዚያ በኋላም እርሱ ሲሮጥ ከገበያ አዳራሹ ውስጥ የተኩስ ድምጽ ይሰማ ነበር። በቪዲዮው ላይ ፖሊስ ደርሶ የገበያ አዳራሹን ሲከብ ይታያል። በትዊተር ላይ የኮሎራዶ አገረ ገዢ ዣሬድ ፖሊስ "በዚህ ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸው እና ወዳጆቻቸውን ላጡ መጽናናትንና ብርታትን እመኛለሁ" ብለዋል። ዋይት ሐውስ በበኩሉ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ስለ ጥቃቱ መረጃው እንዲደርሳቸው መደረጉን ገልጿል።
news-57251121
https://www.bbc.com/amharic/news-57251121
ከሽረ መጠለያዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በወታደሮች መወሰዳቸው ተነገረ
ከምዕራብ ትግራይ ተፈናቅለው በሽረ ከተማ በሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች ከተጠለሉት ተፈናቃዮች መካከል በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በኤርትራና ኢትዮጵያ ሠራዊት ተወስደው መታሰራቸውን የዓይን እማኞች ለቢቢሲ ገለጹ።
በሽረ በአንድ ትምህርት ቤት የሚገኙ ተፈናቃዮች ወታደሮቹ ሰኞ ምሽት አራት ሰዓት አካባቢ ተፈናቃዮች ወደሚገኙባቸው ትምህርት ቤቶች በመሄድ ነበር ወጣት ወንዶችን መውሰዳቸውን የገለጹት። በተለይ ፀሐየና ወንፊቶ በሚባሉ ትምህርት ቤቶች ወንዶችን ከነበሩባቸው ክፍሎች በማስወጣት፤ አንዳንዶቹን በመኪና ሌሎቹን ደግሞ በእግር አሰልፈው እንደወሰዱዋቸውና ድብደባ እንደፈጸሙባቸው የዓይን እማኞቹ ይናገራሉ። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ተፈናቃዮቹን የማሰር "ተግባር ሊፈጽም እንደማይችል" በመግለጽ የተባለውን "ፈጠራ" ሲል አጣጥሎታል። የሠራዊቱ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ በሰጡት ምላሽ "ሠራዊታችን በታሪክ እንዲህ አያደርግም። ይሄንን የሚገልጽ ዜናም የለም። ይህ ሊሆን የሚችልበት አግባብም የለም፤ ምን ፈልጎ ነው እንደዚህ የሚያደርገው?" ሲሉ ጉዳዩን እንደማይቀበሉት ተናግረዋል። ስለ ጉዳዩ ቢቢሲ ያነጋገራቸው በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የሰሜን ምዕራብ ዞን አስተዳዳሪ ዶክተር ቴድሮስ አረጋዊ እስሩን በተመለከተ ማክስኞ ጠዋት መረጃ እንደደረሳቸው በመግለጽ "ሁኔታው ለምን እንደተፈጸመ እያጣራሁ ነው" ብለዋል። "አካባቢው ላይ ካሉ አንዳንድ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ግለሰቦች መረጃው ደርሶኛል። አስፈላጊ ማስተካከያ እንዲደረግም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንነጋገራለን" ሲሉ ዶ/ር ቴድሮስ ገልጸዋል። ባለፈው ጥቅምት ወር ማብቂያ ላይ የህወሓት ኃይሎች በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ በትግራይ በተከሰተው ግጭት ከ60 ሺህ በላይ ሰዎች ወደ ሱዳን ሲሰደዱ፤ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩት ደግሞ በክልሉ ውስጥ ተፈናቅለው በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተጠልሉ ይገኛሉ። የኢትዮጵያና የኤርትራ ወታደሮች በክልሉ ውስጥ ግድያና ጾታዊ ጥቃቶችን ጨምሮ የተለያዩ በርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ፈጽመዋል በመባል የተከሰሱ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግሥት ክሱን በተመለከተ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ አካላት ጋር ምርመራ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን መግለጹ ይታወሳል። በሽረ ከተማ ያጋጠመው ምንድን ነው? ወይዘሮ ለምለም በጦርነቱ ምክንያት ከሞቀው ቤታቸው ተፈናቅለው በሽረ ፀሐየ ትምህርት ቤት ተጠልልው ከሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች መካከል አንዷ ናቸው። ወታደሮቹ ሰኞ ምሽት 4፡30 አካባቢ እንደመጡ የሚናገሩት ወይዘሮ ለምለም "ሦስት ልጆቼን ወስደውብኛል። ብዙ ወጣት ናቸው በኃይል የተወሰዱት" በማለት የ18፣ 23ና 25 ዓመት ወጣት ልጆቻቸው መወሰዳቸው ተናግረዋል። ወታደሮቹ የሁለቱ አገራት እንደሆኑና ወጣት ወንዶችን ብቻ ለይተው መውሰዳቸውንም ያስረዳሉ። "ዓይነ ስውር ሳይቀር ደብድበዋል፤ ሴቶችን አንፈልግም ብለው ወንዶቹን ብቻ በሰባት መኪና ጭነው ወሰዱ። ተመልሰውም በእግር ብዙ ወጣቶች ወስደዋል" ብለዋል። ወጣቶቹ የተወሰዱበትን ምክንያት በሚመለከት "የተነገረን ነገር የለም፤ ስናለቅስ ነው ያደርነው" ይላሉ። የ78 ዓመት ባለቤታቸው እንደታሰሩ የሚናገሩት ሌላ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉትና ከዳንሻ የመጡ ተፈናቃይ በበኩላቸው፤ ወታደሮቹ ከፀሐየ ትምህርት ቤት ባለቤታቸውን መውሰዳቸውንና ጉና በሚባል መጋዘን ውስጥ መታሰራቸውን ይናገራሉ። "የታሰሩበትን ምክንያት ለመጠየቅ ወደ ቀይ መስቀል ሄደን ነበር። አካባቢው ላይ ያገኘናቸው ወታደሮች እራሳችን ነው የወሰድናቸው፤ እዚህ ፎቶ በመነሳት የምታመጡት ነገር የለም። እራሳችን ለይተን እንለቃቸዋለን፤ ወደዚህ አትምጡ አሉን" ብለዋል። በተጨማሪም "500 የሚሆኑ ሰዎች ነው የወሰዱት። ወጣት ይሁን አዛውንት እየደበደቡ ነው የወሰዱት፤ ብዙ ሰው ተደብድቧል" ሲሉም አስረድተዋል። መንፊቶ ሌላው ተፈናቃዮቹ የሚገኙበት ቦታ ሲሆን በተመሳሳይ ሰዓት ሰዎች ተለይተው መወሰዳቸውን አንድ የዓይን ምስክር ገልጻል። "መኪኖች መጥተው ግቢውን ከበቡት። ሰበሰቡን፤ አንዳንዶቹን በብትር መቱዋቸው። ጤነኞቹን በሙሉ ወሰዷቸው፤ ሁለት ሰዎች ብቻ ነው የቀረነው። እኛም አካል ጉዳተኞች ስለሆንን ነው" ብሏል። "ትንሽ ይሁን ትልቅ ወንድ የሆነው ሁሉ ተወስዷል" የሚሉት የ60 ዓመቱ ተፈናቃይ አቶ ዘርአይ በበኩላቸው፤ ተመለሰው እንዳይመጡ በሚል ስጋት ስምንት የቤተሰብ አባሎቻቸውን ይዘው ከማቆያው የወጡ እንዳሉ ተናግረዋል። አንድ የ70 ዓመትና ሌሎች ከ50 ዓመት በላይ የሆኑ የሚያውቋቸው ሰዎች መታሰራቸውም ገልጸዋል። ባለሥልጣናት ምን አሉ? በሽረ ከተማ 16 የስደተኞች መጠለያ እንዳለ የገለጸው የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የሰሜን ምዕራብ ዞን አስተዳዳሪ ዶክተር ቴድሮስ አረጋይ "ትምህርት ቤቶች ላይ የነበሩ ተፈናቃዮች ማታ መወሰዳቸው መረጃው አለኝ" ብለዋል። "ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር ከዲስፕሊን ጋር የተያያዘ ከሆነ ወይም ያለመግባባት ካለ በማጣራት ይፈታሉ" በማለት፤ ምን ያህል ሰዎች እንደታሰሩ እንደማያውቁና በጉዳዩ ላይ ክልሉን ከሚያስተዳድረው 'ኮማንድ ፖስት' ጋር እንደሚነጋገሩ አስታውቀዋል። የመከላከያ ሠራዊት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ግን መረጃው "የፈጠራ" ነው በማለት አጣጥለውታል። "የኢትዮጵያ ሠራዊት እንደዚህ አይነት ተግባር ሊፈጽም የማይችል፤ ሰላም በማስከር በዓለም አንደኛ ደረጃ ሆኖ የሚቀጥል ነው" በማለት ተፈናቃዮችን የሚያስርበት ምክንያት የለውም ብለዋል።
44920708
https://www.bbc.com/amharic/44920708
በአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑ የባሌ ጎባ ተወላጆች የኦሮሚያ ባለሥልጣናትን አነጋገሩ
ቅዳሜ ሐምሌ 14 በባሌ ዞን ጎባ ከተማ በተፈጠረ ግጭት 6 ሰዎች ሕይወታቸውን ካጡ በኋላ ዛሬ ማለዳ በአዲስ አበባ የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች ወደ ኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት አምርተዋል።
በመቶዎች የሚቆጠሩት እኚህ ግለሰቦች ጥያቄያቸውን ይዘው የኦሮሚያ ክልል የፍትህ ቢሮ የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊን እና ሌሎች ባለሥልጣናትን አነጋግረዋል። የኮሚቴው ተወካዮች ለቢቢሲ እንደገለፁት ዋና ጥያቄያቸው የኦሮሚያም ሆነ የፌደራል መንግሥት በጎባ የተፈጠረውን ችግር በሚገባ ያውቀዋል ወይ? የሚል እንደነበር ገልፀው ኃላፊዎቹም በአከባቢው የነበረውን የተለየ እንቅስቃሴ ከ15 ቀን በፊት ጀምሮ እየተከታተሉት እንደነበር ገልፀዋል። • በጎባው ግጭት የስድስት ሰዎች ሕይወት ጠፋ • ከምዕራብ ኦሮሚያ ከተሞች ጥቃት ጀርባ ያለው ማን ነው? • ኦሮሚያ በአዲስ አበባ በምታገኘው ልዩ ጥቅም ላይ ሊመክር የነበረው ስብሰባ ተበተነ ኃላፊዎቹ አክለውም በመሃል የቅዳሜው ግጭት እንደተፈጠረ እንደነገሯቸው የኮሚቴው አባላት ለቢቢሲ አስረድተዋል። ጨምረውም በአካባቢው ከፍተኛ የገንዘብ መጠን መሰራጨቱን የክልሉ የደህንነት መሥሪያ ቤትም እንደሚያውቅ፤ ገንዘቡ ከማን እንደመጣ ለእነማን እንደተበተነ የማጣራት ሥራ እየሰራ እንደሆነ እንደተነገራቸው ለቢቢሲ ገልፀዋል። ግጭቱ የብሔርም ሆነ የሐይማኖት እንዳልነበር የሚናገሩት እነዚህ የኮሚቴ አባላት ይህ ግጭት በሌሎች የፖለቲካ ፍላጎት ባላቸው ኃይሎች በገንዘብ የሚደገፍ እንደሆነ እንደሚያምኑ የክልሉ ባለስልጣናትም ይህንን እንዳረጋገጡላቸው ይናገራሉ። በአሁን ሰዓትም በቂ የመከላከያ ኃይል በስፍራው እንደገባ፣ እነርሱም በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተፈጠረውን ነገር በማረጋጋት ሂደት የበኩላቸውን እንዲወጡ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ገልፀዋል። ጎባ ሙስሊምና ክርስቲያኑ ተዋዶ የኖረባት ከተማ ናት የሚሉት እነዚህ የኮሚቴ አባላት እነርሱም በግጭቱ ዙሪያ የተለያዩ መረጃዎች እንዳሏቸው ገልፀዋል። የጎባ የቀድሞ ሰላሟ እንዲመለስ እንፈልጋለን ያሉት በአዲስ አበባ የሚኖሩት የከተማዋ ተወላጆች ይህንን ለማሳየት ዛሬ ወደ ፕሬዝዳንቱ ጽ/ቤት ከመጡት ሰዎች መካከል ሙስሊሞችም እንደሚገኙበት ይናገራሉ። • ሃይ ባይ ያጣው ብሔር ተኮር መፈናቀል የኮሚቴ አባላቱ ከባለሥልጣናቱ ጋር በነበራቸው ውይይት የኦሮሚያ ክልል የደህንነት ፀጥታ ዋና ኃላፊ እና የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርን የያዘ የልዑካን ቡድን ወደ ጎባ እንዳመራ እንደተነገራቸው እነርሱም የማረጋጋት ሥራውን እንዲሰሩ መንግሥትም ተሳታፊ የነበሩ ኃይሎችን ህግ ፊት እንዲያቀርብ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ገልፀዋል። የኮሚቴው አባላት አሁን ያለውን የመደመር ስሜት የጎባ ልጆችም ማስተጋባት ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን በአካባቢው ያሉ ባለስልጣናት የተለያዩ ጫናዎችን እንደሚያደርጉባቸው ተናግረዋል።
news-50198592
https://www.bbc.com/amharic/news-50198592
ንሥሮችን ሲከተሉ የነበሩ አጥኚዎች የሞባይል እዳ ውስጥ ተዘፈቁ
ከአገር አገር የሚሰደዱ ንሥሮችን እየተከተሉ የሚያጠኑ ሩሲያዊያን ሳይንቲስቶች ወደ ኢራንና ፓኪስታን ተጉዘው ገንዘባቸውን ከመጨረሳቸው በተጨማሪ በሞባይል የኢንትርኔት አገልግሎት ከፍተኛ እዳ ውስጥ ገቡ።
አጥኚዎቹን ለእዳ የዳረጓቸውን ንሥሮች ከደቡባዊ ሩሲያና ከካዛኪስታን የተነሱ ናቸው ተብሏል። በተለይ ሚን ተብሎ የሚጠራው ንሥር ከካዛኪስታን ተነስቶ ወደ ኢራን ስለሚጓዝ እሱን መከተሉ ነው ለአጥኚዎቹ እዳ መናር ምክንያት የሆነው። አጥኚዎቹ ከሚከታተሏቸው አእዋፋት ላይ የሚሰበስቡት አጭር የጽሁፍ መልዕክት እንዳሉበት አገር የክፍያ ተመን ሁኔታ የተለያየ በመሆኑ ንሥሮቹ በሚሄዱባቸው አገራት ብዛት ክፍያው ከፍ እያለ ይሄዳል። ሳይንቲስቶቹ የዱር እንስሳት ጥበቃን በተመለከተ ጥናት የሚያደርግ ሩሲያ ውስጥ የሚገኝ የአንድ ማዕከል የበጎ ፈቃድ ተሳታፊዎች እንደሆኑም ተነግሯል። አጥኚዎቹ የገቡበትን ችግር የተገነዘበው የሩሲያው የሞባይል ስልክ አገልግሎት አቅራቢ ሜጋፎን የተባለው ድርጅት እዳቸውን ሰርዞ ከዚህ በኋላ የሚጠቀሙትን የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት በቅናሽ እንዲከፍሉ ወስኗል። • የስልክዎን ባትሪ ለረዥም ጊዜ ለመጠቀም • ድካምና የአቅም ማነስ ይሰማዎታል? እነሆ ምክንያቱና መፍትሄው • በርካታ ኤርትራዊያን ታዳጊዎች ሰሜን አየርላንድ ውስጥ ተገኙ ሳይንቲስቶቹ የገቡበትን የስልክ ዕዳ ለመክፈል በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያሉ ተከታዮቻቸው ገንዘብ እንዲለግሷቸው ጠይቀው ነበር። አጥኚዎቹ በሞባይል የኢንተርኔት አገልግሎት እዳ ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ በማህበራዊ መገናኛ ብዙህን ላይ ድጋፍ ለማግኘት ባቀረቡት የድጋፍ ጥሪ መሰረት ከ1500 ዶላር በላይ ለመሰብሰብ ችለው ነበር። ሳይንቲስቶቹ እዳ ውስጥ የከተታቸው ንሥሮቹ የት እንዳሉ በሚያመለከተው አጭር መልዕክት አማካይነት አእዋፋቱ ለደህንነታቸው አመቺ የሆነ ስፍራ መድረስ አለመድረሳቸውን በሳይንሳዊ መንገድ ለማወቅ ያስችላቸዋል። ለየት ያለ የንሥር ዝርያ እንደ ሆኑ ከሚነገርላቸው ሚን ከተባሉት ንሥሮች መካከል አጥኚዎቹ 13ቱን በአሁኑ ጊዜ የት እንዳሉና ያሉበትን ሁኔታ እየተከታተሉ ሲሆን፤ በዚህ ወቅት ከሚራቡበት የሳይቤሪያና የካዛኪስታን አካባቢዎች ወደ ደቡብ እስያ ይሄዳሉ። የሞባይል ስልክ አገልግሎት አቅራቢው ሜጋፎን የሳይንቲስቶቹን እዳ መሰረዙ የጀመሩትን ንሥሮቹን የመከታተል ሥራ እንዲቀጥሉ ከማስቻሉ በተጨማሪ ለደህንነታቸው የሚያስፈልግ በጣም ጠቃሚ መረጃን ለመሰብሰብ ያግዛል ተብሏል።