id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
news-50915346
https://www.bbc.com/amharic/news-50915346
ሁሉን ነገር ወደ አፌ የሚያሰኘው ሕመም ታዳጊዎችን ሊገል ነው
እነ ሄክታር ፈርናንዴዝ ቤት ያለው ማቀዝቀዣ ሁሌም ይቆለፋል። የጓዳው በርም እንዲሁ ተከርችሟል።
ሄክተር እና ልጁ ክርስቲያን በመኖሪያቸው የሚገኘውን የመድኃኒት መደርደሪያ ጨምሮ ማንኛውም ሊበላ የሚችል ነገር የተቀመጠበት ቁም ሳጥን ባጠቃላይ ጥርቅም ተደርጎ ይቀረቀራል፤ ይከረቸማል። ቁልፉም በሄክተር ትራስ ስር ይቀመጣል። ሄክተር ቤቱ ውስጥ የሚቆልፋቸው ሳጥኖች እና ክፍሎች የበዙት ሌባ ስለሚፈራ አይደለም። ልጁ ክርስቲያን 'ፕሬደር-ዊል' የሚባል የማይፈወስ ህመም ስላለበት እንጂ። በሽታው ያለባቸው ሰዎች ምንም ያህል ቢመገቡ በማያቆም ረሀብ ይጠቃሉ። በሽታው መጠሪያውን ያገኘው እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ1965 ህመሙን ባገኙት ተመራማሪዎች ስም ነው። • የአገልግል ምግብ አምሮዎታል? ያለማቋረጥ መራብ የሄክተር ልጅ ክርስቲያን የ18 ዓመት ወጣት ነው። አባቱ እንደሚናገረው፤ ክርስቲያን ሁልጊዜም ከፍተኛ ክትትል ካልተደረገለት ማንኛውንም ነገር በልቶ፣ ከጥጋብ የተነሳ ሊሞት ይችላል። "ልጄ ማንኛውም ሊበላ የሚችል ነገርን በልቶ ያውቃል። አንድ ጊዜ ከቆሻሻ መጣያ ውስጥ ሲመገብ ነበር። ሙሉ የጥርስ መፋቂያ በልቶ ጨርሶም ያውቃል። የውሻ ምግብ የተመገበበትም ጊዜ ነበር።" ሄክተር ሁሌም አናናስ ቆራርጦ አጠገቡ ያስቀምጣል። ክርስቲያን ምግብ ሲጠይቀው አንድ የአናናስ ክፋይ ብቻ ይሰጠዋል። ልጁ ከሚያስፈልገው በላይ የስኳር መጠኑ ካለፈ ችግር ውስጥ ስለሚወድቅ፤ ደጋግሞ ምግብ ሲጠይቀው አናናሱን መጥኖ መስጠት ግድ ሆኖበታል። ፕሬደር-ዊል፤ ክሮሞዞም 15 የተባለው በሰውነት ውስጥ ሲደጋገም ወይም ሲጠፋ የሚከሰት ህመም ነው። ህመምተኞችን እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውን በእጅጉ የሚፈታተን በሽታ ነው። በበሽታው የሚጠቁ ታዳጊዎች ከመጠን ያለፈ ውፍረት፣ ስኳር፣ የአዕምሮ እድገት ውስንነት እና የባህሪ ችግርም ይገጥማቸዋል። • ጨቅላ ልጅዎትን ከአቅም በላይ እየመገቡ ይሆን? ክርስቲያን አመለ ሸጋ ልጅ ቢሆንም፤ ምግብ ፈልጎ ካጣ ግን በጣም ይቆጣል፤ ከቁጥጥርም ውጪ ይሆናል። አባቱ ልጁ ምግብ ካላገኘ የሚሆነውን፤ "እንደ ኃይለኛ አውሎ ንፋስ ማንኛውንም ነገር ይደመስሳል" ሲል ይገልጻል። ክርስቲያን ራሱን እንዳይጎዳ ሌሎች ላይም ጉዳት እንዳያደርስ ከወንበር ጋር አስሮ ለማስቀመጥ ተሞክሮ እንደነበርም ሄክተር እንባ እየተናነቀው ይናገራል። የአባትየው ትልቁ ስጋት እሱ ከሌለ ልጄ ምን ሊውጠው ይችላል? ብሎ መስጋቱ ነው። በተለይም ኩባ ውስጥ እንዲህ አይነት ህመም ያለባቸው ልጆችን መንከባከብ በጣም ፈታኝ ነው። ሄክተር የልጁ ክብደትና የስኳር መጠን ከልኩ እንዳያልፍ፤ የአመጋገብ ስርዓቱን ለማስተካከል ይሞክራል። ሆኖም ለልጁ የሚያስፈልገውን ምግብና መድሀኒት ኩባ ውስጥ ማግኘት ፈታኝ ነው። • ልጆችዎ ጤናማ ምግብ እንዲመገቡ ማድረጊያ መላዎች የኩባ መንግሥት የጤናው ዘርፍ አስተማማኝ ነው ቢልም፤ የክርስቲያን አይነት ህመም ያለባቸው ልጆችን ማከም የሚችሉ ሀኪሞች እምብዛም እንዳልሆኑ ሄክተር ይገልጻል። "በሽታው ያለባቸው ሰዎች ጥቂት ስለሆኑ ሀኪሞቹ እንዲህ አይነት ህመም ያለበት ሰው የሚገጥማቸው በ20 ዓመት አንዴ ሊሆን ይችላል። እስከነ አካቴው ታማሚ አይተው የማያውቁም አሉ።" ፕሬደር-ዊል ያለባቸው ልጆች የአመጋገብ ሥርዓት፣ የሥነ ልቦና እና የሌሎችም ባለሙያዎች ክትትል ያስፈልጋቸዋል። ህሙማኑን የመርዳት ጅማሮ ባለፈው ወር ኩባ አስረኛውን የፕሬደር-ዊል ውይይት አካሂዳለች። ተመራማሪዎች፣ ሀኪሞች፣ ታማሚዎችና ቤተሰቦቻቸውም ውይይቱን ተካፍለዋል። የፕሬደር-ዊል ማኅበር ፕሬዘዳንት ፕሮፌሰር ቶኒ ሆላንድ እንደሚሉት፤ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን በአጠቃላይ በአንድ መድረክ ማገናኘት እጅግ ጠቃሚ ነው። በበሽታው ዙርያ ልምድ ያላቸውና የሌላቸው ተሞክሮ መለዋወጥ እንደሚችሉ ያስረዳሉ። ቤተሰቦች ለልጆቻቸው የተሻለ የህክምና አገልግሎት ለማግኘት እንዲታገሉ እንደሚያነሳሳም ያክላሉ። ኩባ በህክምናው ዘርፍ ብዙ ቢቀራትም ተስፋ ሰጪ ጅማሮዎች እንዳሉ ፕሮፌሰር ቶኒ ይናገራሉ። ሀኪሞች ስለ በሽታው ያላቸው ግንዛቤ እያደገ መምጣቱን፣ የህሙማኑ ቤተሰቦች እርስ በእርስ መረዳዳት የሚችሉበት ክበብ መፈጠሩንም እንደ በጎ ጅማሮ ይጠቅሳሉ። 2010 ላይ በሽታው ያለባቸው ልጆች ቤተሰቦች ለስብሰባ ሲጠሩ የተገኙት ስድስት ወላጆች ብቻ ነበሩ። ዛሬ ላይ ግን ከ100 በላይ ኩባውያን ቤተሰቦች ተሰባስበዋል። • የሼፎች የበዓል ምግብ ምርጫ፡ ሼፍ ዮሐንስ፣ ጆርዳና እና ዮናስ ሄክተር ልጁን አትክልትና የሩዝ ኬክ ለምሳ ያበላል። በእርግጥ ኩባ ውስጥ የሩዝ ኬክ ማግኘት ቀላል አይደለም። የኩባ ነባራዊ ሁኔታ ሄክተር ለልጁ የሚያደርገው እንክብካቤ ላይ ተጽዕኖ ቢያሳድርም የተቻለውን እያደረገ ነው። እንዲያውም ልጆቻቸው በበሽታው ለተጠቁ ቤተሰቦች ልምዱን ማካፈል ጀምሯል።
news-44315035
https://www.bbc.com/amharic/news-44315035
ልጅነቴን ያያችሁ? በተለያዩ የኢትዮጵያ ስደተኛ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ሕፃናት ሁኔታ
በኢትዮጵያ ሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች በሚዋሰኑ አካባቢዎች በሚኖሩ ሰዎች መካከል ያጋጠሙ ግጭቶችና በጸጥታ ኃይሎች ሳቢያ ሲደርስ በነበረዉ ጥቃት በርካቶች ከቀዬቸዉ በመፈናቀል እስከ ወደ ጎረቤት አገር ኬኒያ ድረስ ተሰድደዋል።
ህፃናት በሰሜን ሶማሊያ የሚገኝ የተፈናቃዮች ካምፕ ውስጥ (2012) በሁለቱም ክልሎች የነበረዉ ግጭት 93ሺ የሚጠጉ ሰዎችን ከቤት ንብረታቸዉ ሲያፈናቅል እድሜያቸዉ ለትምህርት የደረሱ ሕጻናት ደግሞ ትምህርታቸዉ እንዲያቋርጡ ተገደዋል ይላል ጥር ወር 2018 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያወጣዉ ሪፖርት። ሌሎች ከ1ሺ 500 በላይ ህጻናት ደግሞ ከቤተሰቦቻቸዉ ተለያይተዋል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችም በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ጊዜያዊ መጠለያዎች እንዲሰፍሩ ሆኗል። ልጅነትና መፈናቀል ግጭቶች ሕጻናቱን ትምህርታቸውን እንዳይከታተሉ፣ በወላጆቻችው የቅርብ ክትትልና ክብካቤ እንዳያገኙ እንዲሁም እንደልጅ ቦርቀው እንዳያድጉ እያደረገ ነው። ወይዘሮ ፈቲሃ አደም ተወልደዉ ከአደጉባት ከተማ ጅግጅጋ የስምንት ወር ሕጻን ይዘው ነው መስከረም ሁለት ግጭቱን ሸሽተው ወደ ሐመሬሳ መጠለያ የመጡት። እኚህ ወይዘሮ ከኑሯቸው መፍረስ ከገቡበት ጉስቁልና ይበልጥ የልጃቸው ጤንነት ያሳስባቸዋል። "ይህ ነዉ ብዬ ለመግለጽ በሚያስቸግረኝ ሁኔታ ነው ከቤት ንብረቴ ሕጻን ልጄን ይዤ የተፈናቀልኩት፤ ያለ ምግብ ያለ ውሃ ጅግጅጋ ካምፕ ለሁለት ቀናት ካሳለፍን በኋላ ሕጻናት እየተቸገሩ እላያችን ላይ እየታመሙ ወደ ሐማሬሳ መጣን፤ ቆይቶ ደግሞ በየወረዳችሁ ግቡ ተብለን በድሬ-ጥያራ ገባን" ይላሉ። እኚህ እናትን ጨምሮ ከ8 እስከ 10 ቤተሰብ የያዙ በርካቶች ለጤንነታቸዉ አስጊ በሆነ ቦታ ሕጻናት ልጆችን ይዘው እየኖሩ ነው። "ምንም የጤና አገልግሎት ስለሌለ ልጆቻችን በጣም ችግር ላይ ናቸው" የሚሉት ወይዘሮ ፈቲሃ "ያለንበት ቦታ በደን የተሸፈነና ከሸክላ የተሰራ በመሆኑ ልጄ እስካሁን ድረስ እየታመመ ነው፤ እዚህ ብዙ ህጻናት አሉ፤ መጥቶ የሚያየን ሰው ግን የለም" ሲሉ ያማርራሉ። በግጭቶቹ ምክንያት ተፈናቅለው መጠለያ ውስጥ የነበሩ አብዛኛዎቹ እንደወጡ የሚናገሩት የአደጋና ስጋት አመራር ኮሚሽነሩ አቶ ምትኩ ካሳ ለቀሩት ምላሽ የመስጠት ሥራው እየተሰራ እንደሆነ ነው የሚገልጹት። "እስከ አሁን መጠለያ ውስጥ ለሚገኙ እናቶችና ሕጻናት የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ታች ካሉ የጤና ሴክተሮች በመተባበር የጤና እንክብካቤ እያደረገ ነው የሚገኘው። ከዚህ ባለፈ ኮሚሽኑ ሕጻናት እንዳይጎዱ አልሚ ምግብን ያቀርባል" ይላሉ። መጠለያ ሰርተን እናስገባችኋለን ተብሎ እስከ አሁን ተስፋ ያለዉ ነገር ለማየት አልታደልንም የሚሉት ወይዘሮ ፈቲሃ ግን የተሻለ የህክምና አገልግሎት ማግኘት አልቻልንም ሲሉ የኮሚሽነሩን ኃሳብ ይሞግታሉ። አያይዘውም "ልጆቻችን የሚበሉት ነጭ ሩዝ ብቻ ነው፤ የተሻለ የጤና አገልግሎት እዚህ መጠለያ ውስጥ ማግኘት አስቸጋሪ በመሆኑ መፍትሄ እንፈልጋለን" ይላሉ። በኢትዮጵያ ሴቭ ዘ-ችልድረን የሰብዓዊ ምላሽ ኃላፊ የሆኑት ሀሰን አብዱላሂ እነዚህ ተፈናቃዮች ያላቸውን ነገር ስላጡ ከአቅማቸው በላይ በሆኑ ሥራዎች ላይ ለመሰማራት የተገደዱበት አጋጣሚ አለ ይላሉ። አክለውም "ግጭት በተነሳባቸዉ አካባቢዎች መጀመርያውንም ድርቅ ስለነበረ የአመጋገብ ሁኔታቸው ወርዶ የታየበት፣ ለአካልና ጾታዊ ጥቃት የተዳረጉበትና ቤተሰባቸውን ለመርዳት ያለ እድሜያቸው እንዲያገቡ የተገደዱበት ሁኔታም እንዳለ ያካሄድነው ጥናት ያሳያል" ሲሉ ገልጸዋል። መልሶ የማቋቋም ሥራ እስካሁን ድረስ 300 ሺህ የሚጠጉ ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ ቦታቸዉ ተመልሰዋል የሚለት የአደጋና ስጋት አመራር ኮሚሽነር መመለስ ያልፈለጉትን በኦሮሚያ ክልል 11 አካባቢዎችን በመምረጥ መልሶ ለማቋቋም እየሰሩ መሆኑን ይናገራሉ። ባቀዱት መሰረት እስከ አሁን ድረስ ከ30 ሺ በላይ መጠለያ ጣብያ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ወደተሰራላቸው መጠለያ እንዲገቡ ተደርጓል ሲል ይገልጻሉ። ሶማሌ ክልል ውስጥ ደግሞ 8 አካባቢዎች ተመርጠዉ በአራቱ መጠለያው ተገንብቶ የተፈናቀሉትን የማስገባት ሥራ ብቻ እንደሚቀርም ገልፀዋል። መጠለያ ውስጥ ለተቀሩት ሰዎች አገልግሎት በመስጠት ረገድ ግን ክፍተቶች እንዳሉ ኮሚሽነሩ ይቀበላሉ። "ሰዎች ከመጠለያ ጣቢያ አውጥቶ በዘላቂነት በማቋቋም ክፍተቶች አሉ።" በኢትዮጵያ ሴቭ ዘ-ችልድረን የሰብዓዊ ምላሽ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሀሰን በበኩላቸው በቀጣይነት የሕጻናትን ሁኔታ ለመጠበቅ፣ ግጭትን ለመከላከልና ለግጭት ተጋላጭ የሆኑትን ቦታዎች ላይ ግጭት የመከላከል ስራዎች መሰራት አለበት ሲሉ ይመክራሉ።
news-55501952
https://www.bbc.com/amharic/news-55501952
ዝውውር ፡ ፖግባ ወደ ዩቬንቱስ? አሊ ወደ ፒኤስጂ?
የዘንድሮው የአውሮፓ ኳስ እረፍት አልባ ነው። የክረምት እረፍት ያላገኘው ይህ ተወዳጅ እግር ኳስ ወደ ጥር ወር የዝውውር መስኮት እያመራ ነው።
የሚደግፉት የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ክለብ ለዋንጫ እየተፎካከረም ይሁን ለአውሮፓ ውድድሮች እየተሰናዳ፤ አሊያም ላለመውረድ እየታገለ፤ የውድድር ዘመኑን እያጋመሰ ይገኛል። ቀጣዩ ወር ደግሞ ጥር ነው። ክለቦች ተጫዋች አስፈርመው ቀዳዳ የሚሸፍኑበት፤ ካልሆነም ሸጠው ገንዘብ የሚያተርፉበት። በዚህኛው ዙር መስኮት ስማቸው አብዝቶ እየተነሳ ያሉ የፕሪሚዬር ሊግ ተጫዋቾችን እንዳስሳለን። ፖል ፖግባ - ማንቸስተር ዩናይትድ [ዕድሜ - 27] ፈላጊ ክለብ - ዩቬንቱስ ፖግባ ዩናይትድን ለቅቆ ይሄዳል? አይሄድም? ይሄ የሁል ጊዜ ጥያቄ ነው። የዘንድሮውም የዝውውር መስኮት ያለ ፖግባ የሚያምርበት አይመስልም። የዓለም ዋንጫ አሸናፊው ፈረንሳዊ ፖል ፖግባ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ለዩናይትድ 19 ጊዜ ተሰልፎ ተጫውቷል። ነገር ግን የተጫዋቹ ወኪል [አወዛጋቢው ሚኖ ራዮላ] ፖግባ በዩናይትድ ቤት ያለው ቆይታ አብቅቶለታል እያለ ነው። ወኪሉ እንደሚለው ከሆነ ፖግባ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት 'ደስተኛ አይደለም'፤ 'ክለብ መቀየርም አለበት' ይላል። ሜሱት ኦዚል - አርሴናል [ዕድሜ - 32] ፈላጊ ክቦች - ፌኔርባቼ፣ ዲሲ ዩናይትድ፣ ኤልኤ ጋላክሲ፣ ኢንተር ማያሚ ኦዚል በአርሴናሉ አሠልጣኝ ማይክል አርቴታ ተፈላጊነት ካጣ ቆይቷል። በእንግሊዝም ሆነ በአውሮፓ ውድድሮች ላይ ከሚሳተፉ የክለቡ ተጫዋቾች ስም ዝርዝር ስሙ ተፍቋል። በፈረንጆቹ 2014 ከጀርመን ጋር የዓለም ዋንጫ ያነሳው መድፈኛ የአርሴናል ከፍተኛው ተከፋይ ነው። ነገር ግን በሚቀጥለው ክረምት የውል ፊርማው ይገባደዳል። ተጫዋቹ ከአርሴናል ጋር ስምምነት ላይ መድረስ ከቻለ ውሉን ቀድሞ ቀዶ ክለቡን ሊለቅ ይችላል እየተባለ ነው። ዴሊ አሊ - ቶተንሃም [ዕድሜ 24] ፈላጊ ክለቦች - ፓሪስ ሴይንት ዠርሜይን፣ ኤቨርተን እንግሊዛዊው አሊ ከቶተንሃም ጋር ይዘልቃል ወይ የሚለው ጉዳዩ ከጊዜ ወደ ጊዜ አጠራጣሪ እየሆነ መጥቷል። በጆዜ ሞውሪንሆ አስተዳደር ብዙም ተሰላፊነት እያገኘም አይደለም። በያዝነው የፕሪሚዬር ሊግ ውድድር ዘመን አንድ ጊዜ ብቻ ነው መሰለፍ የቻለው። ፒኤስጂ ባለፈው ክረምት ተጫዋቹን ለማስፈረም ቢሞክርም የክለብ ባለቤት ዳንኤል ሌቪ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። የፈረንሳይ ሊግ ባለድሎቹ በሚቀጥለው ወር ተጫዋቹን ለማስፈረም ድጋሚ ሙከራ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ኢሊቪዬር ዥሩድ - ቼልሲ [ዕድሜ - 34] ፈላጊ ክለቦች - ዌስት ሃም፣ አትሌቲኮ ማድሪድ፣ ማርሴይ ኢሊቪዬር ዥሩድ ከቼልሲ ጋር ያለው ቆይታ እየተገባደደ ይመስላል። ይህ እውን እየሆነ የመጣው የክለቡ አሠልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ ቲሞ ቬርነርን የመሳሰሉ አጥቂዎች ካስፈረመ በኋላ ነው። ነገር ግን ነባሩ ፈረንሳዊ አጥቂ በ23 ጨዋታዎች 14 ጎሎች በማስቆጠር አሁንም ወሳኝ መሆኑን አሳይቷል። ቼልሲ ከሴቪያ ጋር በነበረው የቻምፒዬንስ ሊግ ጨዋታ 4 ጎሎች በማስቆጠር ስሙን ተክሏል። ከዚህ ጨዋታ በኋላ ነው በርካታ ክለቦች ፈላጊ ነን ማለት የጀመሩት። ከላይ ከተጠቀሱት ተጫዋቾች በተጨማሪ የሊቨርፑሉ ዲቮክ ኦሪጊ በዎልቭስ፣ በኒውካስትልና በሊድስ እየተፈለገ ነው። ተጫዋቹ በሊቨርፑል ቤት ባስቆጠራቸው ጎሎች ታሪክ ሠርቷል። ዎልቨርሃምተን ዎንደረርስ ምናልባት ኦሪጊን ሊያስፈርሙ ይችላሉ እየተባለ ነው። የ22 ዓመቱ የቼልሲው ፊካዮ ቲሞሪም በሊድስ የሚፈለግ ሌላኛው ተጫዋች ነው። ተጫዋቹ ባለፈው ውድድር ዘመን 22 ጊዜ ለቼልሲ ተሰልፎ ቢጫወትም በዚህኛው ግን እምብዛም እየታየ አይደለም። ሌላኛው ስሙ ከዝውውር መስኮቱ ጋር እየተነሳ ያለው ተጫዋች የዎልቭስ አጥቂ አዳማ ትራዎሬ ነው። የ24 ዓመቱ ስፔናዊ አጥቂ አዳማ፤ ዘንድሮ ወደ ፕሪሚዬር ሊጉ ባደጉት ሊድስ ዩናይትድ ይፈለጋል። ባለፈው ውድድር ዘመን እጅግ ድንቅ አቋም በማሳየት ለስፔን ብሔራዊ ቡድን መጠራት የቻለው አዳማ፣ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ጎል ማስቆጠር ተስኖታል። ቢሆንም ተፈላጊነቱ አልቀነሰም። አዳማን ለመሸጥ እየተሰናዱ ያሉት ዎልቭሶች የማንቸስተር ሲቲው ዚንቼንኮን ለማስፈረም ደፋ ቀና እያሉ ነው። ተጫዋቹ ከዎልቭስ በተጨማሪ በሳውዝሃምፕተን፣ ሌይስተርና ዌስት ሃም ይፈለጋል። የጥር ወር ዝውውር መስኮት በሚቀጥለው ቅዳሜ ተከፍቶ ለአንድ ወር የሚቆይ ይሆናል።
news-49494316
https://www.bbc.com/amharic/news-49494316
ከአርባ የሚበልጡ ስደተኞች በሊቢያ ባህር ዳርቻ ሰመጡ
ከአርባ የሚበልጡ ስደተኞች በሊቢያ ባህር ዳርቻ እንደሰመጡ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ተራድዖ ድርጅት (ዩኤንኤችሲአር) አስታውቋል። ስደተኞቹን አሳፍራ የነበረችው ጀልባ መስመጧንና ስልሳ የሚሆኑትን ማዳን እንደተቻለም የየኤንኤችሲአር ቃል አቀባይ ቻርሊ ያክስሌይ ገልፀዋል።
ስደተኞቹንም ከትሪፖሊ 100 ኪ.ሜትር ርቀት በምትገኘው የባህር ዳርቻ ከተማ አል ኮምስ መጥተዋል። •ኢትዮጵያውያን 'የሌሉበት' ስለ ኢትዮጵያ የሚዘክረው ሬድ ሲ ዳይቪንግ ሪዞርት ፊልም የሃገሪቷ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ከአካባቢው አሳ አጥማጆች ጋር በመተባበር ግለሰቦቹን በማትረፍ ሂደቱ በመረባረብ ላይ እንደቀጠሉም ዩኤንኤችሲአር በድረገፁ አስታውቋል። "አይቀሬ አደጋዎች ናቸው የሚለው አስተሳሰብ ማስወገድ አለብን፤ በባህር ህይወታቸውን እየቀጠፉ ያሉትን ማዳን ብቻ ሳይሆን ከመጀመሪያውም ህይወታቸውን እንዲህ አደጋ ላይ ጥለው የሚያሰድዳቸው ጉዳይ ምንድን ነው የሚለውን መፍትሔ ልናበጅለት ይገባል" በማለት በማዕከላዊ ሜድትራንያን የዩኤንኤችሲአር ልዩ መልዕክተኛ ተናግረዋል። የዩኤንኤችሲአር ቡድንም ከአደጋው ለተረፉት የህክምናና ሰብአዊ እርዳታዎችን በመለገስ ላይ ናቸው። •ዘረኝነት ሽሽት - ከአሜሪካ ወደ ጋና በያዝነው አመትም በሜድትራንያን ባህር ስደተኞችን አሳፍራ የነበረች ጀልባ ሰምጣ አሰቃቂ የሚባል አደጋ ደርሶ 150 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። አሁን የደረሰውን አደጋ ጨምሮ ከጥር ወር ጀምሮ ባለው አውሮፓ ለመድረስ በሚል ተስፋ የሜድትራንያን ባህር ሲያቋርጡ 900 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። የበርካታ ሰዎችን ህይወት መቀጠፍ ተከትሎም ዩኤንኤችሲአር የተባበረ እርዳታ እንደሚያስፈልግ አፅንኦት በመስጠት ለአውሮፓ ህብረት ሃገራትም ነፍስ አድን መርከቦች እንዲዘጋጁ ጥሪ አቅርቧል። • ባንግላዴሽ የጋብቻ መመዝገቢያ ቅፅ ላይ "ድንግል" የሚለው ቃል እንዲወጣ ወሰነች ከዚህም በተጨማሪ በባህርም ላይ ሆነ በአየር የነፍስ አድን የተሰማሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ላይ የተጣለው ህጋዊም ገደብ ሊነሳ ይገባል ብሏል ድርጅቱ። በወደብ አካባቢ የሚገኙ ሃገራት በፍቃደኝነት ላይ የሚስሩ የነፍስ አድን ሰራተኞችን ማበረታታት እንጂ መከልከል እንደማይገባ ድርጅቱ ድረገፁ ላይ ባወጣው መግለጫ ገልጿል። •ፖሊስ አንድን ወጣት ሲደበድብ በተንቀሳቃሽ ምስል ያስቀረው የዐይን እማኝ ከዚህም በተጨማሪ ስደተኞችን ከሊቢያ አውጥቶም ወደተሻለ ስፍራ በመውሰድ የተደላደለ ህይወት እንዲኖሩ መስራት ያስፈልጋል ተብሏል። የዩኤንኤችሲአር ምክትል ኮሚሽነር ኬሊ ክሌመንትስ ከሰሞኑ በሊቢያ የሚገኘውን ሰብአዊ ቀውስ ተገኝተው የተከታተሉ ሲሆን በእስር ላይ ያሉ ስደተኞችም ሊለቀቁ ይገባል ብለዋል። ምክትል ኮሚሽነሯ አክለውም 4800 የሚሆኑ ስደተኞችን ለማስለቅ ከሊቢያ ባለስልጣናት ጋር እየተነጋገሩ መሆናቸውን ገልፀዋል።
news-56380481
https://www.bbc.com/amharic/news-56380481
ጠፍቶ የነበረው ሚሊዮኖች የሚያስገኘው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ትኬት እንዴት ተገኘ?
ላለፉት ስድስት ወራት ሲጠበቅ የነበረው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ አንደኛ ዕጣ አሸናፊው ወጣት ክንዴ አስራት ሦስት ትኬቶችን ይዞ መቅረቡን የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር የኮምዩኒኬሸን ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ነዋይ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
ክንዴ አስራት አቶ ቴዎድሮስ አክለውም ወጣት ክንዴ ያቀረባቸው ሦስት ትኬቶችን ብቻ በመሆኑ 12 ሚሊዮን ብሩ ተሸላሚ ይሆናል ሲሉ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። የአንዱ ትኬት ባለዕድል ባለመቅረቡ የተነሳም ቀሪው ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል ብለዋል። የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ዕጣ ባለ ዕድሎች የታወቁት ባለፈው ዓመት ማብቂያ ላይ ጳጉሜ 5/2012 ዓ.ም ነበር። የዚህ ዕጣ አሸናፊዎች ሽልማቶቻቸውን ወስደው የሚጠናቅቁበት የጊዜ ገደብ የካቲት 30/2013 ዓ.ም እንደነበር የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚህም መሰረት የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር የዚህን እንቁጣጣሽ ሎተሪ እድለኞች ሲሸልም መቆየቱን አስታውሰዋል። ሁለተኛውን ዕጣ መርሐቤቴ መራኛ ከተማ ለሦስት ሰዎች መከፋፈሉን ያስታወሱት አቶ ቴዎድሮስ፣ አንድ ግለሰብ ስድስት ሚሊዮን፣ ሌሎቹ ሁለት ግለሰቦች ደግሞ ሁለት ሁለት ሚሊዮን ብር መሸለማቸውንም ይናገራሉ። የሦስተኛው ዕጣ አሸናፊም ዝዋይ ከተማ ነዋሪ መሆናቸውንም አስታውሰዋል። የእንቁጣጣሽ ሎተሪ አንደኛ እጣ አሸናፊ ግን ሳይሸለም በመቆየቱ የተነሳ የዛሬ ሦስት ወር ድርጅቱ ባለዕድለኛው እስከዚህ ቀን ድረስ አለመቅረቡን በመግለጽ በማስታወቂያ ጥሪ መቅረቡን ተናግረዋል። የዛሬ አስራ አምስት ቀንም በተመሳሳይ 20 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው እንቁጣጣሽ ሎተሪ 0216884 የሆነ ቁጥር መሆኑን እና በደቡብ ክልል አካባቢ መሸጡን በመግለጽ እድለኛው አለመቅረቡን ድርጅቱ ገልጾ ነበር። ከዚህ በኋላ ግን እድለኛው አርብ የካቲት 26/2013 ዓ.ም ቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ ሦስት ቲኬቶችን ይዞ መቅረቡን ይናገራሉ። ወጣት ክንዴ አስራት ሦስት ትኬቶችን ያቀረበ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ሽልማቱን አለመረከቡን ገልፀዋል። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ትኬቱ ተጣርቶ ትክክለኛው አሸናፊ መሆን አለመሆኑ የመለየት ሥራ በቅድሚያ ስለሚሰራ መሆኑንም አብራርተዋል። ብሔራዊ ሎተሪ ማንኛውም አሸናፊ ቲኬቶቹን ይዞ ሲመጣ ማጣራት እንደሚያደርግም ጨምረው ገልፀዋል። "የሙሉ ዕጣው አሸናፊ እኔ ነኝ" ክንዴ አስራት በጋሞ ዞን የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪ ነው። አርባ ምንጭ ላይ በበጎ ፈቀደኛነት ያገለግላል። አሁን አሸናፊ ያደረገውን የሎተሪ ትኬት በትክክል የቆረጠው የት እንደሆነ አያስታውስም። "ወይ ሻሸመኔ ወይ አርባ ምንጭ ይሆናል የቆረጥኩት" ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። በእርግጥ ክንዴ ሐዋሳም የሎተሪ ትኬት የቆረጠ ቢሆንም እርሱ ግን ጎዶሎ ቁጥር በመሆኑ ባለዕድል ካደረጉት ትኬቶች መካከል አለመሆኑን በልበ ሙሉነት ያስረዳል። ይህንን ያለበትንም ምክንያት ሲያስረዳ "በአጠቃላይ የ360 ብር ትኬት ነው የቆረጥኩት" በማለት ነው። ክንዴ ሙሉ ዕጣውን የሚያስገኙ አምስት ትኬቶችን በመቶ ብር መግዛቱን በማስታወስ "የሙሉ ዕጣው አሸናፊ እኔ ነኝ" ሲል ይናገራል። ሁሌም ሙሉ ዕጣ ነው የምቆርጠው የሚለው ክንዴ፣ ሁለቱ ትኬቶች በእርሱ ቸልተኝነት እና በጊዜው መርዘም የተነሳ መጥፋታቸውን ይናገራል። ትኬቶቹን ቆርጦ የተወሰኑትን በኪስ ቦርሳው ቀሪዎቹን ደግሞ ቤት ማስቀመጡን የሚናገረው ክንዴ ለሥራ ወደ ድሬዳዋ ሄዶ ስለነበር መርሳቱን ይናገራል። ክንዴ አሁንም ቢሆን ሎተሪውን መቁረጡን ያወቀው የልጁን ትምህርት ቤት ክፍያ በባንክ በኩል ከፍሎ አልከፈልክም በመባሉ ማረጋገጫ ደረሰኝ ሲፈልግ ነው። ሎተሪውን ሲያገኝ አዟሪዎች ጋር ሄዶ ማውጫ ቢፈልግም በመቆየቱ የተነሳ ማውጫ የያዘ አዟሪ ማግኘት ተቸግሮ እነደነበርም ያስታውሳል። ክንዴ የአንደኛ እጣ አሸናፊ የሚያደርጉትን ሦስት ትኬቶች ያገኘው የካቲት 22/2013 ዓ.ም መሆኑን ይናገራል። ሁለት ቀን ሙሉ የጠፉትን ሁለት ትኬቶች ሲፈልግ ቆየ። "የት ጣልኩት?" በሚል በየስርቻው ፈልጓቸዋል፤ ብዙ ሐሳብ አውጥቷል አውርዷል። ነገር ግን እነዚህን ሁለት ትኬቶች በመጣሉ ዛሬም ይቆጫል። ክንዴ ፌስቡክ ተጠቃሚ መሆኑን ሲናገር "ፌስቡክ ላይ ተጥጄ ነው የምውለው" በማለት ነው። ታዲያ በፌስቡክ ላይ የእንቁጣጣሽ ሎተሪ አንደኛ እጣ አሸናፊ እየተፈለገ መሆኑን አንብቧል። እኔ እሆናለሁ የሚል ሃሳብ ግን አልነበረውም። በቴሌቪዥን የእንቁጣጣሽ ሎተሪ አንደኛ እጣ ባለ እድለኛ እየተፈለገ መሆኑን ሲሰማ፣ በፌስቡክ ሰዎች መልዕክቱን ሲቀባበሉ ሲያይ 'ባለዕድለኛው ከትግራይ ክልል ነው' አልያም 'ሞቷል' በሚል ከጓደኞቹ ጋር ያወራ እነደነበር ያስታውሳል። ክንዴ፣ የካቲት 24/2013 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በየካቲት 26/2013 ዓ.ም ለብሔራዊ ሎተሪ ሪፖርት ማድረጉን ተናግሯል። አዲስ አበባ ሲመጣ አክስቱ ጋር ማረፉን የሚናገረው ክንዴ፣ የአክስቱን ልጅ ወደ ብሔራዊ ሎተሪ ይዞት ሲሄድ የ20 ሺህ ብር ሎተሪ ደርሶኛል ሲል መዋሸቱን ይናገራል። ክንዴ የ12 ሚሊዮን ብር አሸናፊ የሚያደርገውን ትኬቶች በእጁ ይዞ መገኘቱ አስደንግጦታል። "ደንግጬ ስለነበር መረጋጋት ያስፈልገኝ ነበር" ሲል ሁኔታውን ይገልጻል። ብሔራዊ ሎተሪ ደርሶ ባለዕድሉ እርሱ መሆኑን እስኪያሳውቅ ድረስ በርካታ ነገሮችን ፈርቶ እንደነበር የሚናገረው ክንዴ፣ "እንቅልፍ እምቢ ብሎኝ፤ ተረብሼ ነበር" ይላል። "ብሩ ከፍተኛ በመሆኑ ትንሽ ያስደነግጣል፤ ከማንም ጋር ሳላወራ ከራሴ ጋር ብቻ ሳወራ ነበር።" አሁን ሎተሪውን ለብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አስረክቦ፣ አሻራውን ሰጥቶ እስኪጠሩት ድረስ እየጠበቀ ይገኛል። ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደርም ትኬቱ ትክክለኛ መሆኑን እያጣራ መሆኑን በመግለጽ በቅርቡ ባለእድል መሆኑ እንደተረጋገጠ ብሩ እንደሚሸለም ተናግሯል። ሙሉ እጣውን የቆረጥኩት እኔ ነኝ የሚለው ክንዴ፣ ቀሪው ስምንት ሚሊዮን ብር በትግራይ ክልል ለተፈናቀሉ ስጡልኝ ሲል ጠይቋል። ወጣት ክንዴ ያቀረበው ሦሰት ትኬት ብቻ መሆኑን የገለፁት አቶ ቴዎድሮስ የአንዱ ትኬት ባለዕድል ስላልቀረበ ገንዘቡ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል ብለዋል። ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር 60 ዓመት ሊሞላው የቀረው አንድ ዓመት ብቻ ሲሆን፣ በእነዚህ ዓመትታት በሙሉ ባለእድሎችን ሲሸልም የቆየ ድርጅት መሆኑን አስታውሰው፣ ምን ጊዜም የሎተሪ ባለዕድሎች ተገኝተውለት መሸለም እንደሚፈልግ ኃላፊው ገልፀዋል።
news-54130919
https://www.bbc.com/amharic/news-54130919
ከባለቤቱ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት 4 ሰዎችን የገደለው ፖሊስ ተያዘ
ከባለቤቱ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት 4 ግለሰቦችን በጦር መሳሪያ ተኩሶ የገደለው የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
ፖሊስ ወንጀሉ በተፈጸመበት ስፍራ ምርመራ ሲያደርግ ተጠርጣሪው የግድያ ወንጀሉን የፈፀመው መስከረም 1 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡30 በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ጨርጨር ጊርጎስ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነው ብሏል ኮሚሽኑ በፌስቡክ ገጹ ባሰፈረው መረጃ። ተጠርጣሪው ረዳት ሳጅን መልህቁ መኪ የተባለ የፖሊስ አባል ሲሆን ከባለቤቱ ጋር በትዳር ለሁለት ዓመት አብረው ሲኖሩ በመካከላቸው በተፈጠረ አለመግባባት ከ15 ቀን በፊት ባለቤቱ ወደ ቤተሰቦቿ ቤት መሄዷን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ጄላን አብዲ ገልጸዋል። ከባለቤቱና ከቤተሰቦቿ ጋር የተፈጠረውን አለመግባባት ምክንያት በማድረግ ተጠርጣሪው የፖሊስ አባል ለስራ የታጠቀውን መሳሪያ ይዞ ወደ ባለቤቱ ቤተሰቦች ቤት በመሄድ የሚስቱን እናት ፣የእንጀራ አባቷን፣ የእህቷን ባል እና የቤት ሰራተኛን በአጠቃላይ 4 ግለሰቦችን ተኩሶ በመምታት ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርጓል ብሏል ፖሊስ። ግለሰቡ ወዲያውኑ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን የተለያዩ ማስረጃዎችን በማሰባሰብ የምርመራ ሂደቱ የተጀመረ መሆኑን እና ምርመራውንም በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ ለሚመለከተው የፍትህ አካል እንደሚላክ ዳይሬክተሩ ገልፀዋል። ''የአዲስ ዓመት የበዓል አከባበር በሰላም እንዲከናወን መላው የፖሊስ አባላትና የፀጥታ ሃይሉ ሌት ከቀን ሃላፊነታቸውን በቁርጠኝነት ሲፈፅሙ ብለሹ ስብዕና ባለው አንድ የፖሊስ አባል የተፈፀመው ተግባር ኮሚሽኑን በእጅጉ ያሳዘነ ከመሆኑም ባሻገር የፖሊስ አባላቱን እና የፀጥታ ሃይሉን የማይወክል ነው'' ሲሉ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ጄላን አብዲ ገልጸዋል።
news-41751630
https://www.bbc.com/amharic/news-41751630
ከእግር ኳስ ሜዳ ወደ ኮኛክ ጠመቃ
እንደሌሎች እግር ኳስ ተጫዋቾች ለስራ የሚነሳሳው ስታዲየም ውስጥ ደጋፊዎችን ሲመለከት አይደለም። እሱን የወይን ዘለላዎች የበለጠ ለስራው ያለውን ፍላጎት ከፍ ያደርጉለታል።
ኦሊቪዬ ቴቢሊ ለበርሚንግሃም ከ80 በላይ ጨዋታዎችን ተጫውቷል እግር ኳስ እና አልኮል አብረው የማይሄዱ ቢሆንም የቀድሞው የበርሚንግሃም ሲቲ ተከላካይ ኦሊቪዬ ቴቢሊ ግን ኮኛክ ማምረትን መርጧል። የቀድሞው የሴልቲክና የበርሚንግሃም ተከላካይ አሁን በዓለማችን ታዋቂ በሆነው የፈረንሳይ የወይን እርሻ ውስጥ ኮኛክ ያመርታል። ኮኛክ ከሻምፓኝ ጋር ተመሳሳይ ቢሆንም ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያለው የአልኮል መጠጥ ነው። የመጀመሪያውን የወይን እርሻ ገና ዕድሜው በአስራዎቹ መጨረሻ ላይ እያለ መግዛቱ ብዙዎች እንደሚያስቡት የቀድሞው እግር ኳስ ተጫዋች ቴቢሊ ገንዘቡን አነስተኛ ፕሮጀክት ላይ አለማፍሰሱን ያሳያል። "የመጀመሪያ የፕሮፌሽናል ተጫዋችነት ውሌን ስፈርም ነው ሁለት ሄክታር መሬት የገዛሁት" ሲል በደቡብ ምዕራብ ፈረንሳይ በሚገኘው ሳልስ ደ ኤንጅል በተባለች መንደር በሚገኘው እርሻ ውስጥ ሆኖ ነው ኦሊቪዬ ኃሳቡን ለቢቢሲ ያካፈለው። " ለራሴ ጉዳት ቢያጋጥመኝና እግር ኳስን ባቆም ልሰራው የምችለው ነገር ሊኖረኝ ይገባል ስል እነግረው ነበር። ግዢውን የፈጸምኩት ፕሮፌሽናል ተጫዋች ከመሆኔ በፊት ለእረፍት ጊዜዬ የሚያስፈልገኝን የኪስ ገንዘብ የማገኘው እርሻዎቹ ላይ በመስራት ስለነበር ነው። ፕሮፌሽናል ተጫዋች መሆን ከባድ በመሆኑ ነበር ፊርማዬን እንዳኖርኩ እርሻውን ለመግዛት የወሰንኩት" ሲል ይገልጻል። እ.አ.አ በ1993 ነበር ቴቢሊ በፈረንሳይ ሁለተኛ ሊግ ለሚጫወተው እና ቤተሰቦቹ ከአቢጃን መጥተው ከከተሙባት ከተማ ብዙም ለማይርቀው ኒዮር የፈረመው። አዳዲስ የጠመቃ ዘዴዎችን እየተማረ ያለው ቴቢሊ ይህ ጉዞ ወደ ሻቶሩ እና ሼፊልድ ዩናይትድ እንዲያመራ ዕድል ከፍቶለታል። እኤአ በ2000 በተካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ የተሳተፈ ሲሆን በ2001 ደግሞ በስኮትላንዱ ሴልቲክ በአንድ የውድድር ዓመት የሶስት ዋንጫ ባለቤት ለመሆን በቅቷል። ከበርሚንግሃም ጋርም ለአራት ዓመታት በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለመጫወት ችሏል። ለካናዳው ቶሮንቶ እግር ኳስ ክለብ አራት ዓመት ተኩል ለመጫወት ተስማምቶ ፊርማውን ቢያኖርም በደረሰበት ጉዳት ምክንያት ከሳምንታት በላይ ለክለቡ ሳይጫወት ጫማውን ሰቅሎ ወደ እርሻው እንዲያተኩር አስገድዶታል። ሆኖም ስራውን ለመጀመር ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ አልነበረም። ለኮኛክ እርሻ የሚሆን መሬት ውድ እና በቀላሉ የማይገኝ መሆኑ ስራውን እንዳይጀምር ችግር ሆኖበት ነበር። ይህን እስኪያሟላም ሁለት ምግብ ቤቶችን ከፍቶ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል። ብቸኛ ልጃቸውን በሞት ያጡ አንድ ጎረቤቱ የእርሻ መሬታቸውን የሚሸጡለት ሰው ሲያፈላልጉ ቆይተው "ልጁ ጓደኛዬ ከመሆኑም በላይ ስማችንም ተመሳሳይ በመሆኑ ይህ ገፋፍቶት ይመስለኛል እርሻውን ለኔ ሊሸጥልኝ ወሰነ" ሲል ኦሊቪዬ እርሻ ያገኘበትን አጋጣሚ ያስታውሳል። እርሻውን የሸጡለት ዦን ሚሼል ለፒን በበኩላቸው "እዚህ ሁሉም ወይን ጠማቂ ተመሳሳይ ነው። እግር ኳስ ስለምወድ፥ ቴቢሊ ስለሚያስደስተኝና በችግሬ ወቅት ከጎኔ ስለነበር ለሱ ለመሸጥ ወሰንኩኝ። ጥቁር ሰው እርሻዬን ቢገዛዉስ? እግር ኳስ ተጫዋች ቢሆንስ? ምንድነዉ። ብዙዎች ሊያስቆሙኝ ቢፈልጉም እኔ ግን ውሳኔዬን አልቀየርኩም" ብለዋል። የግዢ ውሉን ተከትሎም መጀመሪያ ላይ እንደባዳ ሲታሰብ የነበረው የመጀመሪያው አፍሪካዊ የኮኛክ ጠማቂ አይን በሆነ ቦታ ላይ 22 ሄክታር የእርሻ ባለቤት ለመሆን በቃ። ከእርሻው በተጨማሪም የመጥመቂያ ባለቤት የሆነ ሲሆን የአጠማመቅ ሂደቱን በደንብ ባያውቀውም መሬቱን የሸጡለት ዦን ሚሼል አሁን አማካሪው ሆነዋል። ኳስ ካቆመ ከአምስት ዓመት በኋላ የመጀመሪያውን የኮኛክ ጠርሙስ አምርቷል የበርሚንግሃምን ቱታ ለብሶ በእርሻ ውስጥ ሲሰራ የሚታየው ቴቢሊ በእግር ኳስ ተጫዋችነቱ ዘመን በጠንካራነቱ ይታወሳል። በአንድ ወቅት በጨዋታ የመጀመሪያ አጋማሽ ከባድ ጉዳት ቢገጥመውም ጨዋታውን ከማጠናቀቁም በላይ በሌላ ጊዜ ደግሞ በአንድ እግር ጫማ ብቻ በተጫዋች ላይ ሸርተቴ ሲገባ ተስተውሏል። "የአካባቢው ነዋሪዎች አንድ አፍሪካዊው ተጫዋች እነሱ የሚሰሩትን ለመስራት በመምረጡ በጣም ይገረማሉ። ከሰኞ እሰከ እሁድ በመስራቴም ጭምር ይደመማሉ። አግራሞታቸው የሚጨምረው ደግሞ ከባድ ስራ የሚሉትን በመስራቴ ነው። እኔ ግን የምሰራው ሰዎችን ለማስገረም አይደለም። ስራውን ስለምወደው እስከምችለው ድረስ እሰራለሁ" ሲል እኤአ ከ1999 እስከ 2004 ለአይቮሪኮስት የተጫወተው ቴቢሊ ይገልጻል። እንደአብዛኛዎቹ የአካባቢው የኮኛክ አምራቾች የምርቱን 90 በመቶ ለትልልቅ ኩባንያዎች የሚሸጥ ሲሆን ቀሪውን ደግሞ ኮኛኮችን ሰብስቦ በሚያስቀምጥበት ቦታ ያኖራቸዋል። የመጀመሪያ ኮኛኩን እአአ በ2013 ያመረተው የቀድሞው ተጫዋች ምርቶቹን ለአፍሪካ ብቻ የመሸጥ ፍላጎት አለው። "ይህ ህልሜ ነው፤ ከአሁኑ ለአንዳንድ የአፍሪካ በተለይም የአይቮሪኮስት ምግብ ቤቶች ኮኛኬን እየሸጥኩ ነው። በምፈልገው መጠን ባይሆንም በጅምሩ ደስተኛ ሆኛለሁ" ሲል ይገልጻል። ቴቢሊ ከኮኛክ ጠመቃው ጡረታ ሲወጣ እርሻውን ለልጆቹ ማስተላለፍ ይፈልጋል፤ እስከዛ ድረስ ግን ብቸኛው አፍሪካዊ የኮኛክ አምራች ሆኖ ይቀጥላል።
news-42617047
https://www.bbc.com/amharic/news-42617047
ሶማሊላንድ አስገድዶ መድፈርን በተመለከተ የመጀመሪያ ሕግ አወጣች
ሶማሊላንድ ከተመሠረተች ለመጀመሪያ ጊዜ አስገድዶ መደፈርን የሚያወግዝ ሕግ አርቅቃለች።
በቀደመው ጊዜ አስገድዶ መድፈር የፈፀመ ግለሰብ ቢበዛ በደል የፈፀመባትን ሴት ማግባት ይኖርበታል እንጂ በሕግ አይጠየቅም ነበር። አዲስ የወጣው ሕግ ግን አስገድዶ የመድፈር ወንጀል የፈፀመ ሰው እስከ 30 ዓመት የሚደርስ የእሥራት ቅጣት ሊበይንበት ይችላል። በፈረንጆቹ 1991 ነበር ሶማሊላንድ እንደ ራስ ገዝ አስተዳደር ከሶማሊያ ራሷን ነፃ ብታደርግም፤ በዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ዘንድ እውቅ አላገኘችም። የሃገሪቱ ፓርላማ አፈ-ጉባዔ ባሼ ሞሐመድ ፋራህ ለቢቢሲ ሲናገሩ አስገድዶ የመድፈር ወንጀል ከጊዜ ወደ ጊዜ አየተባባሰ በመምጣቱ ሕጉ አስፈላጊ ነው ብለዋል። "አሁን አሁን እስከ ሰባት የሚደርሱ ሰዎች አንዲት ሴት ላይ አስገድዶ የመድፈር ወንጀል እየፈፀሙ ይገኛሉ። አዲስ የወጣው ሕግ ወንጀሉን ሙሉ በሙሉ ያስወግድልናል ብለን እናምናለን" ብለዋል። ሕጉ የሕፃናትና ሴቶች መብት ተሟጋቾችን ዓመታት የዘለቀ ጉትጎታ ተከትሎ የመጣ ነው። የሴቶች አጀንዳ ከተሰኘ ተቋም የመጣችው ፋይሳ አሊ ዩሱፍ ለቢቢሲ እንተናገረችው የሕጉን መውጣት ለዘመናት በጉጉት ሲጠብቁት የነበረ ጉዳይ ነው። የሕጉ ተግባራዊ መሆን ሶማሊላንድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን ተቀባይነት እንደሚጨምረው ይጠበቃል ስትል የቢቢሲዋ አን ሶይ ዘግባለች።
news-49224739
https://www.bbc.com/amharic/news-49224739
ኡጋንዳዊቷ ፕሮፌሰር ፍርድ ቤቱ የወሰነባትን እስር በመቃወም እርቃኗን ወጣች
ኡጋንዳዊቷ ምሁር ፕሮፌሰር ስቴላ ንያንዚ የአገሪቷን ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒን አፀያፊ ቃል በመሰንዘር አዋርደሻል በሚል የአስራ ስምንት ወራት እስር ተፈረዳባት።
የኢንተርኔት ትንኮሳ በሚል ወንጀል ፍርድ ቤቱ እስር መወሰኑን ተከትሎ ፍርዱን የኡጋንዳ ሐሳብብ በነፃነት የመግለፅ መብትን የሸረሸረ በሚል የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እየተቹት ነው። አርብ እለት የተካሄደውን የፍርድ ሂደት በቪዲዮ የታደመችው ፕሮፌሰር ስቴላ ውሳኔውን ስትሰማ ጡቶቿን በማውጣት ተቃውሞዋን ገልፃለች። • "ማንም መብታችንን ሊሰጠን ስለማይችል፤ ሴቶች ማንንም ሳይጠብቁ በራሳቸው መታገል አለባቸው" •ሻደይ፦ለሴቶች፣ በሴቶች ፌስቲቫል "አፀያፊ ኮሚዩኒኬሽን" በሚልም ክስ ቀርቦባት የነበረ ሲሆን እሱ ግን ውድቅ የተደረገው ከዚህ ውሳኔ በአንድ ቀን ቀደም ብሎ ሐሙስ እለት። ይህ ውሳኔ ከተሰማ በኋላ በስሜት የተሞላ ንግግር ያደረገችው ፕሮፌሰሯ በውሳኔው ማዘኗን ስትገልፅ ደጋፊዎቿም ድጋፋቸውን ገልፀዋል። "ሙሴቪኒን የማበሳጨት እቅድ አለኝ፤ አምባገንነቱ አድክሞናል፣ በቃን" ብላለች። የመናገር ነፃነትን በተመለከተ ኡጋንዳ ብዙም የማያወላዳ አካሄድ እንዳላት ሪፖርተርስ ዊዝ አውት ቦርደርስ የገለፀ ሲሆን ሙሴቪኒንም ምንም አይነት ትችትን አይቀበሉም ብሏቸዋል። በዚህ አመት መጀመሪያ ህገወጥ የመንግሥት መድኃኒት ሽያጭ ላይ የምርመራ ጋዜጠኝነት እየሰሩ የነበሩ የቢቢሲ ጋዜጠኞችም መታሰራቸው የሚታወስ ነው። የ44 አመቷ ስቴላ በምርምሩ ዘርፍ የላቀች ስትሆን በምስራቅ አፍሪካ ውስጥ አንቱታን ከተቸራቸው ዩኒቨርስቲዎች አንዱ በሆነው ማኬሬሬ ዩኒቨርስቲም ታስተምር ነበር። ፌስቡክ ላይ በፀረ መንግሥት ፅሁፎቿ የምትታወቀው ፕሮፌሰሯ፤ ፅሁፎቿም የግጥምን መልክ የያዙ ሲሆን "በስድብ" የተሞሉ ናቸው የሚሉም አስተያቶች ይሰማሉ። "በዚህ ፍርድ ቤት እንደ ተጠርጣሪና እስረኛ መቅረቤ የሰፈረውን አምባገነንነት ማሳያ ነው። ስርአቱ ምንያህል አምባገነን እንደሆነ አጋልጫለሁ" በማለት ከፍርድ ውሳኔው በኋላ ፌስቡክ ገጿ ላይ የፃፈች ሲሆን አክላም "አምባገነኖችን ለማስወገድ በሚደረገው ትግል ታዛቢ ብቻ መሆን አልፈልግም" ብላለች። በኢንተርኔት ትንኮሳ የሚለው ክስ የቀረበባት ባለፈው አመት ፌስቡክ ገጿ ላይ የ74አመቱን አዛውንት ፕሬዚዳንት "ከእናቱ ማህፀን ሲወጣ ምነው በፈሳሹ ተቃጥሎ ቢሆን" የሚል ነገር መፃፏን ተከትሎ ነው። •ኢንጅነር አይሻ መሃመድ የሃገር መከላከያ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ አምነስቲን ጨምሮ ብዙ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የፍርዱ ውሳኔ ተቀልብሶ ለሰባት ወራት እስር የቆየችው ስቴላ ነፃ እንድትወጣ ጠይቀዋል። "የፍርድ ቤቱ ውሳኔ በፍፁም ተቀባይነት የሌለው ነው። የኡጋንዳ መንግሥት ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ የማስከበር ግዴታውን አልተወጣም፤ ይህም የሚያሳየው ምንያህል መንግሥት ለትችቶች ቦታ እንደሌለው ነው" በማለት የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ጆአን ንያንዩኪ ገልፀዋል። ከዚህ ቀደምም ፕሬዚዳንቱን "ጥንድ ቂጥ" በማለት በፌስቡክ ገጿ ላይ ፅፋ ለእስር ተዳርጋ የነበረ ሲሆን የፍርድ ሂደቱም እስካሁን አላለቀም።
news-41720665
https://www.bbc.com/amharic/news-41720665
የቺቦክ ማስታወሻ ደብተሮች፡ የቦኮ ሃራም እገታ የጽሑፍ ቅጂዎች
ባለፈው ግንቦት ከቦኮ ሃራም እገታ ከተለቀቁት ልጃገረዶች መካከል አንደኛዋ ለጋዜጠኛ አዳዎቢ ትሪሻ ንዋኡባኒ ለሶስት ዓመታት በታሰረችበት ወቅት ስላስቀመጠችው የማስታወሻ ደብተር አጫውታታለች።
የ24 ዓመቷ ናዖሚ አዳሙ አብረዋት ይማሩ ከነበሩት መካከል በእድሜ ትልቋ ነበረች። እ.አ.አ በ2014 እርሷን ጨምሮ በአብዛኛው ክርስቲያን የነበሩ ከ200 በላይ ሴት ተማሪዎች ታግተው በሰሜን ናይጄሪያ ወደሚገኘው ሳምቢሳ የተሰኘ የቦኮ ሃራም መደበቂያ ደን ተወሰዱ። በእስር በነበሩበት ጊዜ ሴቶቹ ቁርዓን እንዲቀሩ ይደረግ ስለነበር ማስታወሻ የሚይዙበት ደብተር ተሰጥቷቸው ነበር። ከመካከላቸው ግን አንዳንዶቹ ሴቶች የእገታውን ማስታወሻ ለመያዝ ተጠቀሙባቸው። ታጣቂዎቹ ባገኟቸውም ጊዜ ደብተሮቹን አቃጠሉባቸው። ናዖሚ ግን የራሷን መደበቅ ችላለች። አሁን 20 የሞላት የቅርብ ጓደኛዋ ሳራ ሳሙኤልና ሶስት ሌሎች ልጃገረዶችም እንዚህን ደብተሮች ገጠመኞቻቸውን ለመመዝገብ ተጠቀሙባቸው። ለማስታወሻ የተጠቀሙበት 2 ባለ 40 ገጽ ደብተሮች ተርፈዋል የተገኙትም ማስታወሻዎች በመለስተኛ እንግሊዘኛና በደካማ ሃውሳ የተጻፉ ሲሆኑ ያለ ቀናት የተመዘገቡ ቢሆንም በታገቱባቸው የመጀመሪያ ወራት አካባቢ የተጻፉ መሆናቸው ግልጽ ነው። ከመዘገቧቸው ብዙ ትውስታዎች መካከል አሥሩን መርጠን በሚቀጥሉት 10 ቀናት ይዘንላችሁ እንመጣለን። 1) ለማገት አላሰቡም ነበር በአውሮፓውያኑ ሚያዚያ 14, 2014 ዓ.ም የቺቦክ ትምህርት ቤት ላይ ጥቃት ያደረሱት ታጣቂዎች አመጣጣቸው ሞተር ለመስረቅ እንጂ ልጃገረዶቹን ለማገት አልነበረም ። የፈለጉትም ሞተር የትኛው እንደነበር ግልጽ ባይሆንም የመኪና ይሁን ሌላ ለማወቅ አዳጋች ሆኗል። ሆኖም በአካባቢው የግንባታ ሥራ እየተካሄደ ስለነበረ ድንገት ሲሚንቶ የሚያቦካውን ሞተር ፈልገው ሊሆን ይችላል፤ ይህም ሞተር ደረቅ መሣሪያዎችን ለመሥራት መጠቀም ስለሚቻል ሊሆን ይችላል። ሞተሩን በአካባቢው ማግኘት ሲያቅታቸው ግን ሰብሰበዋቸው የነበሩትን ልጃገረዶች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሲነጋገሩ ግን መስማማት አልቻሉም ነበር። "እርስ በርሳቸው መጣላት ጀመሩ። አንድ ትንሽ ልጅ ከመካከላቸው 'ማቃጠል አለብን' አላቸው። 'አይሆንም ወደ ሳምቢሳ መውሰድ አለብን' አለ ሁለተኛው። ሌላኛው ሰው ደግሞ 'አይ አይሆንም እንደሱ አናድርግ' አለና 'እንምራቸውና ከዚያ ወደ ቤተሰቦቻቸው ቤት እንሂድ' አለ። እየተከራከሩም ሳለ አንደኛው 'አይሆንም ባዶ መኪና ይዤ መጥቼ ባዶ መኪና ይዤ አልመለስም፣ ባይሆን ወደ [አቡባከር] ሼኮ [የቦኮ ሃራም መሪ] ይዘናቸው ከሄድን ምን ማድረግ እንዳለበን ያውቃሉ። " አሰቃቂ የሆኑትን አማራጮች ካወጡ ካወረዱ በኃላ ሴቶቹን ይዘዋቸው ለመሄድ ወሰኑ ... ከዚያስ?
47319711
https://www.bbc.com/amharic/47319711
ሦስት ጊዜ ከሞት ቅጣት ነፍሱ የተረፈችው ጎልማሳ
ባይሶን ካውላ 'ሞት እምቢ' ነው። አንዳንዱ ትረፍ ሲለው የመታነቂያው ገመድ ይበጠስበታል። አንዳንዱ ትረፍ ሲለው የገዳዩ ሽጉጥ ጥይት ይነክሳል። እንደ ባይሶን ካውላ ዓይነቱ ደግሞ አንቆ ገዳዩ ደግሞት ከሞት ይተርፋል።
የነ ካውላ ገዳይ ሞት የተፈረደባቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር ይዞ አንድ በአንድ እያነቀ ከዚህ ምድር ያሰናብታል። ልክ ባይሶን ካውላ ጋ ሲደርስ ይደክመወና ያርፋል። 'በቃ ሌላ ጊዜ አንቃችኋለሁ፤ ሂዱ' ይላቸዋል። ይህ የተከሰተው አንድ ጊዜ ቢሆን አይገርምም። ይህ የሆነው ሦስት ጊዜ ነው። አሁን አገሩ ማላዊ አንቆ መግደልን በሕግ ከልክላለች። • ብቻቸውን ወደ መዝናኛ ስፍራ የሚሄዱ ሴቶች ፈተና • አር ኬሊ ሴቶችን አስክሮ በመድፈር ውንጀላ ቀረበበት • "ከ[እኛ] የተለየን ጦር 5 በመቶ እንኳ አይሆንም" መሮ የኦነግ ጦር አዛዥ ትረፊ ያላት ነፍስ ባውሰን ካውሎን ለእስር የዳረጉት ቀናተኛ ጎረቤቶቹ ናቸው። ሰው ገድለኻል ተብሎ ተሰከሰሰ። የገደለ ይገደል ነበር፤ ያን ጊዜ። ዘመኑ 1992 ነው፤ እንደ ፈረንጆቹ ቀን አቆጣጠር። ማላዊ ተወልዶ ያደገው ባይሶን ካውላ ደቡብ አፍሪካ ነዳጅ ማደያ ሠርቶ ያጠራቀማትን ጥሪት ይዞ ወደ አገሩ ተመለሰ። መሬት ገዝቶ አምስት ሰዎችን ቀጥሮ ፍራፍሬ፣ ስንዴና በቆሎ ማምረት ጀመረ። "ከዚህ በኋላ ነበር ሕይወቴ ምስቅልቅል ውስጥ የገባችው"ይላል ካውላ። ከዚህ በኋላ የሆነውን አሳዛኝ ታሪክ እንዲህ ይተርክልናል። የሞት ፍርድን እንደመጠበቅ የሚያስጨንቅ ምን ነገር አለ? "ጎሬቤቶቼ አንዱ ሠራተኛዬ ላይ ጥቃት አደረሱበት። ያለ ረዳት መንቀሳቀስ ሁሉ አቅቶት ነበር። ሽንት ቤት እንኳ በኔ እርዳታ ነበር የሚንቀሳቀሰው። አንድ ቀን ታዲያ ከባድ ዝናብ ጥሎ ነበርና ጭቃ አዳልጦኝ ወደቅኩ። ስወድቅ ታዲያ እሱም እኔን ተደግፎ ነበረና አደገኛ አወዳደቅ ወደቀና ሆስፒታል ገባ። የቀን ነገር ኾኖ በዚያው ሕይወቱ አለፈች። እኔ ያኔ 40 ዓመቴ ነበር። በጭራሽ ባላሰብኩት ሁኔታ ሰው በመግደል ተከሰስኩ። እነዚሁ ክፉ ጎረቤቶቼ በሐሰት መሰከሩብኝና ፍርድ ቤት ጥፋተኛ አለኝ። ሰው ለገደለ ወዲያው ሞት ነበር ፍርዱ። እናቴ ሉሲ ፍርድ ቤቱ ሞት እንደወሰነብኝ ስትሰማ ከሐዘኗ ብዛት እንባዋ ደረቀ። በዚህ ወቅት ማላዊ በአምባገነኑ ሃስቲንግስ ባንዳ ሥር ነበረች። በቃ አቤት የማይባልበት ዘመን። የሞት ቅጣቴ ተፈጻሚ እንዲሆን ወረፋ መጠበቅ ነበረብኝ። አንቆ መግደያ ማሽኑን የሚያንቀሳቅሰው አንድ ሰው ነበር። ሞትን በወረፋ መጠበቅ እጅግ ከባድ ነገር ነው። • የቻይና ዓይን ያረፈበት የባህል ልብሳችን • በለገጣፎ-ለገዳዲ 'ህገወጥ' ናቸው የተባሉ ቤቶች ፈረሱ ከዕለታት አንድ ቀን ወረፋህ ደርሷል ተባልኩ። ወደ መታነቂያው ስሄድ የሞትኩ ያህል ደንዝዤ ነበር። የሚገርመው በዚያ ዘመን ሁሉንም ፍርደኛ አንቆ የሚገድል ሰው ነበር። ደቡብ አፍሪካም ሌሎች አገሮችም እየሄደ እዚህ ማላዊም እየመጣ ይህንን ሥራ ለመንግሥት ይሠራል። በዚያ ዘመን እሱ ነበር የተዋጣለት አንቆ ገዳይ። ማላዊ የሚመጣው ታዲያ በሁለት በሦስት ወር አንድ ጊዜ ነበር። ከ21 ፍርደኞች መካከል ስሜ እንዳለና በዚያ ቀን ልገደል እንደሆነ ተነገረኝ። ልክ ከቀኑ ሰባት ሰዓት የኔ ተራ እንደሆነና እንድዘጋጅ ተነገረኝ። በመኾኑም መጸለይም ተፈቀደልኝ። 7፡00 ሰዓት የተባልኩ እስከ ዘጠኝ ሰዓት አስጠበቁኝ። እውነት እውነት እላችኋለሁ ሞትን መጠበቅ ከባድ ነው። ልክ ዘጠኝ ሰዓት ሲል አናቂያችን [አንቆ ገዳያችን] ሥራ አቆመ። ሦስት የሞት ፍርደኞች ሌላ ቀን እንድንመለስ ተነገረን። የመግደያ ማሽኑን እሱ ብቻ ነው ማንቀሳቀስ የሚችለው ይባል ነበር። ያን ቀን "በቂ ሰው ገድያለሁ፤ ለዛሬ ይበቃል በሚቀጥለው ወር እንቀጥላለን" አለና ሄደ። በሚቀጥሉት ጊዜያትም እንዲሁ ሆነ። የአጋጣሚ ወይም የዕድል ጉዳይ ኾኖ አንቆ ገዳያችን እየደከመው ወይም እየሰለችው በሚቀጥለው እመለሳለሁ እያለ የመሞቻችንን ቀን አራዘመው። ይህ የሞት ቅጣት መዘግየት በብዙዎች እንደ ዕድለኛ ያስቆጥረኝ ይሆናል። ነገር ግን እጅግ የሚያሰቃይ ነገር ነው። በዚህም ምክንያት ሁለት ጊዜ ራሴን ለማጥፋት ሞክሬ ከሸፈብኝ። ከሞት አፋፍ መልስ እንዲህ እንዲህ እያለ በማላዊ የመንግሥት ለውጥ ተካሄደ። በዚያው የሞት ፍርደኞች ጉዳይ ቀስ በቀስ ተዘነጋ። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ግን የሞት ፍርድ ይሰጣል። ኾኖም ላለፉት 25 ዓመታት ተፈጻሚ ኾኖ አያውቅም። ፕሬዝዳንቱም በሞት ፍርደኛ ላይ አይፈርሙም። ዛሬም ድረስ የሞት ፍርደኞች አሉ፤ መንግሥት መጥቶ በገዳይ ማሽን እንዲያስቀምጣቸው የሚጠባበቁ። ኾኖም ግን ተፈጻሚ ኾኖ አያውቅም። የብዙ ሞት ፍርደኞች ውሳኔ ወደ ዕድሜ ልክ ይቀየራል። • ተፈራ ነጋሽ፡ "በነገራችን ላይ ሙዚቃ አልተውኩም" ይኸው ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እኔም እስር ቤት ነበር የቆየሁት። እርግጥ ነው ከነበርኩበት ወደ ዞምባ ማእከላዊ እስር ቤት ተዘዋውሬያለሁ። እስር ቤት ውስጥ ትምህርት ላይ አተኩራለሁ። በእስር ቤት ውስጥ አስተማሪ ሆኜ አገለግላለሁ። ሩብ ምዕተ ዓመት እስር ቤት ካሳለፍኩ በኋላ ድንገት በ2007 ዓ.ም አንድ አስገራሚ ነገር ተፈጠረ። የእንጀራ ልጁን የገደለ አንድ አደገኛ እጽ ተጠቃሚ ወደ እስር ቤት መጣ። ነገር ግን ድርጊቱን የፈጸመው የአእምሮ በሽተኛ ስለነበረ እንደሆነ ተከራከረ። በዚህም የሞት ፍርደኛ መሆን እንደሌለበት ፍርድ ቤት በይግባኝ ተሟገተ። ፍርድ ቤቱ በሚገርም ሆኔታ ልክ ነህ አለው። በዚህ አጋጣሚ የሞት ፍርድ እንዲቀለበስ ሐሳብ ቀረበ። ከ170 የሞት ፍርደኞች ውሰጥ 139ኞቻችን ጉዳያችን በድጋሚ እንዲታይ ተባለ። ፍርድ ቤት ትፈለጋለህ ስባል እንደተለመደው በአንድ ወንጀለኛ መስክር ሊሉኝ ነው ብዬ ነበር። ዳኛው ያሉትን ነገር ማብላላት እንኳን አልቻልኩም። ነጻ ሰው ነህ ነው የሚሉኝ። እስር ቤቱን ለቀህ ውጣ ነው የሚሉኝ። ሕጻን እያሉ የማውቃቸው 6ቱ ልጆቼ ከእስር ስወጣ ትልልቅ ልጆች ኾነው ነበር። ባለቤቴ ግን እኔ ሞትን በምጠባበቅበት ወቅት ሞታለች። አሁን ነጻ ሰው ነኝ። ብቻዬን ነው የምኖረው። • "ከሷ ጋር የምኖረው እንዳትገድለኝ ስለምፈራ ብቻ ነው" • ከተለያየ አባት የተወለዱት መንትዮች እስር ቤት እየተመላለሰች ያን ሁሉ የእስር ዓመት ስትጠይቀኝ የነበረችው እናቴን እየተንከባከብኩ እኖራለሁ። 80 ዓመቷ ነው። እናቴ የመጀመርያ ልጇ ነኝ። በእኔ ምክንያት ተንከራትታለች። በዚያ ሁሉ የሞት ፍርደኝነት ዘመን መከራን ብቻዋን ተቋቁማለች። አሁን ወደ እርሻ እንድትሄድ አልፈልግም። ቤት ቁጭ አድርጌ እንከባከባታለሁ። ቀጣዩ አላማዬ የሸክላ ቤት ለውዷ እናቴ መቀለስ ነው።
54159838
https://www.bbc.com/amharic/54159838
ጎርፍ፡ በኢትዮጵያ በመቶ ዓመታት ይከሰታል በተባለ ጎርፍ ግማሽ ሚሊዮን ሰው ተጎዳ
በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች በደረሰው የጎርፍ አደጋ፣ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች መጎዳታቸውን መንግሥት ገለፀ።
የሰላም ሚኒስትር ሙፈርያት ካሚል እና የውሃ መስኖና ኤነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ለጋዜጠኞች በትናንትናው ዕለት በሰጡት መግለጫ የዘንድሮ ክረምት ዝናብ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ በቤቶችና መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል። የሰላም ሚኒስትሯ ሙፈርያት ካሚል በሶስት ክልሎች እና 23 ወረዳዎች የጎርፍ አደጋ መከሰቱን ገልፀው፣ 580 ሺህ ዜጎች መጎዳታቸውንና ከእነዚህም ውስጥ 217 ሺህ የሚሆኑት ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸው ተገልጿል። በ100 ዓመታት መካከል አንዴ የሚከሰት እንደ ውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ገለፃ ከሆነ ሰሞኑን የተከሰተው የጎርፍ አደጋ ከአዋሽ ወንዝ መነሻ እስከ መድረሻው ፣ በኦሞ ወንዝ፣ በስምጥ ሸለቆ ውስጥ በሚገኙ እንደ ባቱ (ዝዋይ) እና መቂ ባሉ ከተሞች፣ በአባይ ተፋሰስ አካባቢ እና ጣና ሐይቅን ጀምሮ እስከ ሱዳን እንደዚሁም ደግሞ በባሮ ወንዝ መሆኑን ተናግረዋል። ሰሞኑን በአንዳንድ ቦታዎች የተከሰተው የጎርፍ አደጋ በመቶ አመታት ውስጥ አንዴ የሚከሰት መሆኑን ዶ/ር ስለሺ ጨምረው አስረድተዋል። በአዋሽ ወንዝ የተከሰተው ደግሞ ባለፉት 30 ዓመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ መሆኑን አክለዋል። ዘንድሮ ከባድ ዝናብ መተንበዩን የተናገሩት ሚኒስትሩ፣ ቅድመ ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱንም አብራርተዋል። እንደምሳሌም በኦሮሚያና በአፋር ክልል ውስጥ 134 ኪሜትር ርዝመት ያለው የውሃ መውረጃ መስመር ጥገና መሰራቱን ተናግረዋል። በተጨማሪም የተፋሰሱ ምክር ቤት ከክልሎች ፕሬዝዳንቶች እና ጉዳይ የሚመለከታቸው ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች ጋር መወያየታቸውንና ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን ይናገራሉ። አደጋው የደረሰበት ስፍራ "በሄሊኮፕተር በመታገዝ በሰው ሕይወት ላይ አደጋ ሳይደርስ የተሳካ ስራ መስራት ተችሏል፤ ጎርፉ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ በተወሰኑ ከብቶች ላይ አደጋ ደርሷል፤ የተወሰኑ ቤቶችም በጎርፍ ተውጠዋል" ብለዋል። ከነፍስ ማዳን ስራ ባሻገር ሰዎች ለችግር እንዳይጋለጡ ማድረግ እና የምግብና ሌሎች ቁሳቁስ አቅርቦቶች እየተሰራ መሆኑን የሚናገሩት የሰላም ሚኒስትሯ፣ ጎርፉ ካለፈ በኋላ የመልሶ ማቋቋም ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል። አስከ ጳጉሜ 1/2012 ድረስ የተሰበሰበ መረጃን መሰረት ያደረገ
news-52954466
https://www.bbc.com/amharic/news-52954466
በአሜሪካ ፀረ-ዘረኝነት ተቃውሞዎች የቀጠሉ ሲሆን ታላቅ የተባለውም ሰልፍ ተካሄደ
በአሜሪካ ሚኒያፖሊስ ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ እጁ ከኋላ እንደተጠፈረ ከመሬት ላይ ተጣብቆ ነጭ ፖሊስ አንገቱን በጉልበቱ ለዘጠኝ ደቂቃ ተጭኖት ህይወቱ ማለፉን ተከትሎ በበርካታ ግዛቶች እየተካሄዱ ያሉ ተቃውሞ 12ኛ ቀኑን ይዟል፡
ዘረኝነትንና የፖሊስ ጭካኔን በመቃወም እየተደረገ ያለው ህዝባዊ አመፅ ቀጥሎም በመላው አሜሪካም ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል፡፡ በዋሽንግተን ዲሲ ትልቅ በተባለው ተቃውሞ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አደባባይ በመውጣት ቁጣቸውን የገለጹ ሲሆን ፖሊስ ተቃዋሚዎች ወደ ዋይት ሃውስ እንዳይቀርቡ ከልክሏል፡፡ በኒውዮርክ፣ ችካጎ ፣ ሎስ አንጀለስ እና ሳን ፍራንሲስኮም በርካታ ሰዎች ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ጆርጅ ፍሎይድ በተወለደባት ሰሜን ካሮሊና ግዛት ከመታሰቢያ ሥነ ሥርዓቱ በፊት ሰዎች ለፍሎይድ ያላቸውን ክብር ገልጸዋል፡፡ በዩናይትድ ኪንግደም ምንም እንኳን መንግሥት በወረርሽኙ ሳቢያ ሰዎች እንዳይሰባሰቡ ቢያሳስብም የለንደን ፓርላማ አደባባይ በሰዎች ተሞልቶ ነበር፡፡ በአውስትራሊያ በሲድኒ፣ ሜል ቦርን እና ብሪስቤን የአውስትራሊያ ቀደምት ህዝቦች (አቦርጂኖች) አያያዝ ላይ ትኩረት ያደረጉ ተቃውሞዎች ተካሂደዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በፈረንሳይ፣ ጀርመን እና ስፔንም የተቃውሞ ሰልፎች ነበሩ፡፡ መሳሪያ ያልታጠቀው ፍሎይድ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር በአሰቃቂ ሁኔታ በሚኒያፖሊስ ከተማ የተገደለው ከሁለት ሳምንታት በፊት ነበር፡፡ አሟሟቱን የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስልም አንድ ነጭ ፖሊስ ለዘጠኝ ደቂቃዎች የፍሎይድን አንገት በጉልበቱ ተጭኖ ፍሎይድም መተንፈስ እንዳልቻለ እየተናገረ ሕይወቱ ሲያልፍ ያሳያል፡፡ የጆርጅ ፍሎይድ አንገት ላይ በጉልበቱ ቆሞ የነበረው ዴሪክ ቾቪን የተባለ ነጭ ፖሊስ በዚህ ድርጊቱ ከሥራ የተባረረ ሲሆን ክስም ተመስርቶበታል፡፡ ድርጊቱ ሲፈጸም በሥፍራው የነበሩ ሦስት ፖሊሶችም በተመሳሳይ ከሥራ የተባረሩ ሲሆን በግድያው ተባብረዋል በሚል ተከሰዋል፡፡
news-56596285
https://www.bbc.com/amharic/news-56596285
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና እንዴት በፍጥነት ሊታረም ቻለ?
የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተናን ከዚህ ቀደም ባልነበረ ፍጥነት ከሦሰት ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ አርሞ ውጤቱን በዚህ ሳምንት አስታውቋል።
የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ2012ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና በተመዝጋቢ፣ በተፈታኝም እንዲሁም በውጤትም ደረጃ ከፍተኛ መሆኑ አስታውቋል ቀደም ባሉት ዓመታት የፈተናውን ውጤት ለማሳወቅ ወራት ይጠይቅ የነበረ ሲሆን የአሁኑ ከየትኛውም ጊዜ በፍጥነት ተጠናቅቋል። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? የሚለው ብዙዎች ጥያቄ ነው። ቢቢሲ የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዴላሞ ኦቶሬን (ዶ/ር) ይህንን ጠይቋቸው ሲመልሱ፤ ፈተናው መጋቢት 2/2013 ዓ.ም መጠናቀቁን አስታውሰው ከመጋቢት 3/2013 ዓ.ም ጀምሮ መረከብ መጀመራቸውን ይናገራሉ። በቅድሚያም 20 ሺህ አካባቢ የሚሆኑ የአዲስ አበባ ተፈታኞችን እርማት መጋቢት 4/2013 ዓ.ም ማጠናቀቃቸውን ገልፀዋል። አጠቀላይ ፈተና የማረሙን ሂደት በአንድ ሳምንት ማጠናቀቃቸው የሚናገሩት ኃላፊው፣ ቀሪው ሥራ መረጃ ማጥራት ስለነበር እርሱን ሲሰሩ መቆየታቸውን አስረድተዋል። ስለሚጠቀሙበት ቴክኖሎጂም ሲናገሩም "የብሪቲሽ ዲ አር ኤስ ቴክኖሎጂን ነው፤ አዲስ የተቀየረ ቴክኖሎጂ የለም" ብለዋል። ማሽኑ በ24 ሰዓት ውስጥ በአማካኝ 420 ሺህ ፈተና ወረቀቶችን ያርማል ሲሉ ያስረዳሉ። ይህ ቴክኖሎጂ የእያንዳንዱን ተፈታኝ መልስ መስጫ ወረቀት ስካን በማድረግ ወደ ኮምፒውተር እንደሚያስገባ በመግለጽ ይህንንም ለማድረግ 24 ማሽኖች እንዳሉ አብራርተዋል። ፈተናው በፈረቃ ለ24 ሰዓት ሲታረም መቆየቱን የሚናገሩት ኃላፊው፣ ተማሪዎች በፈተና መራዘም ምክንያት በስነልቦና በመጎዳታቸው ይህንን ለማካካስ ቶሎ ውጤቱን ለመግለጽ ጠንክረው መስራታቸውን ይናገራሉ። ፈተናውን በፍጥነት አርሞ ለማጠናቀቅ ሶስት ነገሮች ምክንያት ሆነዋል ያሉት ኃላፊው የመጀመሪያው ፈተናው በሰላም መጠናቀቁ መሆኑን ያስረዳሉ። በሰላም ባይጠናቀቅ ኖሮ የሚጣራ ጉዳይ፣ በፖሊስ እጅ የተያዙ ጉዳዮች፣ የእርማት ጊዜውን እንዲዘገይ ያደርገዋል ሲሉ ያስረዳሉ። ሁለተኛው የሰዓት አጠቃቀም ነው በማለት፣ በፈረቃ 24 ሰዓት መታረሙን ያስታውሳሉ። ይህም ፈተናውን አርሞ ለማጠናቀቅ የሚወስደውን ጊዜ ለማጠናቀቅ አጭር ጊዜ መውሰዱን ይናገራሉ። ሶስተኛው ስራውን ለመምራት የተጠቀምንበት የአደረጃጃት እና አመራር ስርዓት ነው ሲሉ ተናግረዋል። እነዚህ ሶስቱ ጉዳዮች ተቀናጅተው እንደተባለው በፍጥነት እንዲያልቅ አድርጓል ብለዋል። በእርማት ወቅት ማሽኑ ስህተት የሚሰራበት እድል በጣም አነስተኛ መሆኑን የሚናገሩት ኃላፊው ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች ቅሬታቸውን በማቅረብ እንደሚስተናገዱ ተናግረዋል። ተማሪዎች ቅሬታ በሚያቀርቡበት ወቅት መከተል ያለባቸው ነገሮችን ሲያስረዱም በያሉበት ኦንላየን ሆነው የተዘጋጀውን ቅጽ መሞላት አልያም በአካል በጽሑፍ ማቅረብ እንደሚችሉ ይናገራሉ። ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት ካለው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተየያዘ ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች በኦንላየን እንዲያስገቡ ይመክራሉ። የተማሪዎችን ቅሬታ ለመመልከት ብቻ የተቋቋመ ኮሚቴ እንዳለ የሚናገሩት የኤጀንሲው ዳይሬክተር በፍጥነት ምላሽ እንደሚሰጥ ገልፀዋል። ቅሬታውን በፍጥነት ምላሽ የሚሰጥበት ምክንያት ወደ ዩኒቨርስቲ መግቢያ ነጥብ ከመገለፁ በፊት ለማስታወቅ ስለሚሰራ አእንደሆነም አብራርተዋል። አንድ ተማሪ ዩኒቨርስቲ መግቢያ ከተነገረ በኋላ ቅሬታውን ቢያቀርብ ጉዳዩ ታይቶ የሚደረግ ማስተካካያ ካለ እንደሚሰራ ጨምረው ገልፀዋል። የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ2012ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና በተመዝጋቢ፣ በተፈታኝም እንዲሁም በውጤትም ደረጃ ከፍተኛ መሆኑ አስታውቋል። እንደ ኤጀንሲው መረጃ ከሆነ ከ350ሺ ተማሪዎች በላይ ተመዝግበው፤ ተፈትነው ውጤታቸውን ማወቅ ችለዋል። ኤጀንሲው የተፈታኞች ቁጥር ከሌሎች ዓመታት በተለየ ከፍ ያለ ነው ማለቱን ተከትሎ በዚህ በኮቪድ ወረርሽኝ ጊዜ እንዴት ሊጨምር ቻለ በማለት የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዳይሬክተር ይህ መረጃ ተያይዞ የሚመጣው 10ኛ ክፍል ለመሰናዶ መግቢያ ተፈትነው ካለፉ ጋር መሆኑን ያስረዳሉ። የእነዚህ የመሰናዶ መግቢያ ፈተና ወስደው ባለፈው ዓመት ለመፈተን ሲጠባበቁ የነበሩ ተማሪዎች ቁጥር ሲታይ መቀነስ እንደማያሳይ አብራርተዋል። ዘንድሮ ፈተናውን የወሰዱ 350ሺህ ተማሪዎች መፈተን የነበረባቸው ባለፈው ዓመት ቢሆንም የኮቨድ-19 ወረርሽኝ በዓለም አቀፍ ደረጃ በመከሰቱ ወደ 2013 ዓም እንዲገፋ አድርጎታል። የኤጀንሲ ዳይሬክተር ለሆኑት ዴላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) ዘንድሮ ስላጋጠመ ኩረጃ ጥያቄ ቀርቦላቸው በአገር አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ደረጃ ኩረጃን መቀነስ መቻሉን ተናግረዋል። ፈተናው በሚሰጥበት ወቅት በአንዳንድ ክልሎች ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ክፍል ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው መግባት እንደሌለባቸው እየታወቀ ይዘው መግባታቸውን ገልፀዋል። ይህ ያጋጠመው የመጀመሪያዎቹ ፈተናዎች፣ ሒሳብ እና እንግሊዘኛ ፈተናዎች ከተጠናቀቁ በኋላ እና አፕቲትዩድ እየተሰጠ በነበረበት ወቅት መሆኑንም ያስታውሳሉ። ኩረጃው ያጋጠመው ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ክፍል ከገቡ በኋላ በመሆኑ ለመቆጣጠር መቻሉን የገለፁት ኃላፊው ከዚህ ቀደም አጋጥሞ አንደነበረው ያለ አስቀድሞ ስርቆት አለመኖርን አስረድተዋል። በዚህም የተነሳ በፈተና ክፍል ውስጥ የተሰጣቸውን ፈተና ወረቀት ፎቶ በማንሳት ውጪ ላለ ሰው በቴሌግራም ልኮ ማሰራት እንዳጋጠመ ይናገራሉ። በዚህ ዓመት በዚህ መንገድ የኮረጁ ከ20 በላይ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ውጤታቸው ሲሰረዝ፣ 10 ያህል ተፈታኞች ደግሞ አንድ ትምህርት ሲኮርጁ በመገኘታቸው በዚያ ትምህርት ውጤት እንዳያገኙ መደረጉን አስታውቀዋል።
43890290
https://www.bbc.com/amharic/43890290
የቢንላደን የቀድሞ ጠባቂ በጀርመን
በአንድ ወቅት የኦሳማ ቢን ላደን ጠባቂ የነበረው የቱኒዝያ ዜግነት ያለው ሰው ከአውሮፓውያኑ 1997 ጀምሮ በጀርመን መጠለያ ጣቢያዎች መኖሪያውን እንዳደረገ ተገለፀ።
የጀርመኑ የቀኝ አክራሪ አማራጭ ፓርቲ፤ ሳሚ ኤ ስለሚባል ሰው ማንነት ያቀረበውን ጥያቄ ተከትሎም የሰውየው ምስል በክልሉ መንግሥት ይፋ ሆኗል። የጀርመን መገናኛ-ብዙሃን የሰውየውን ሙሉ ስም የግል መረጃውን ለመጠበቅ ሲባል እንዳልዘገቡ ተገልጿል። የጂሃድ አራማጆች ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም ብሎ የካደ ሲሆን፤ የጀርመን መንግሥትም ግለሰቡን ወደ ቱኒዝያ ለመመለስ ይዞት የነበረውን እቅድ እንግልትና ስቃይ ይደርስበታል በሚል ስጋት እንደሰረዘው አስታውቋል። ቢንላደን አልቃይዳ ተብሎ የሚጠራውን የጂሃድ አራማጅ ቡድንን ይመራ የነበረ ሰው ሲሆን በአውሮፓውያኑ 2001ም አሜሪካ ምድር ላይ ለደረሰው የሽብር ጥቃት ተጠያቂ ነው ተብሎ ነበር። በ2011 ደግሞ በአሜሪካ ልዩ ኃይል ፓኪስታን ውስጥ ታድኖ ተገድሏል። አሜሪካ ላይ በተፈፀመው የመስከረም 11ዱ የሽብር ጥቃት ተሳታፊ ከነበሩት አጥፍቶ ጠፊ ፓይለቶች መካከል ሦስቱ በሰሜናዊ ጀርመን በምትገኘው ሀምቡርግ የአልቃይዳ ህዋስ አባል ነበሩ። በአውሮፓውያኑ 2005 የጀርመን ፀረ-ሽብር ፍርድ ላይ አንድ ምስክር በሰጠው ቃል ይህ ሳሚ ኤ የተባለው ሰው በአውሮፓዊያኑ 2000 በአፍጋኒስታን ውስጥ የቢንላደን ጠባቂ ሆኖ እንደሰራ መስክሯል። ምንም እንኳን በጊዜው ሰውየው ቢክድም የወቅቱ ዳኛ የነበሩት ዱሴልዶርፍ ምስክሩን አምነውታል። በአውሮፓውያኑ 2006ም ሳሚ ኤ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት አለው በሚል ምርመራ ተደርጎበት የነበረ ሲሆን ክስ ግን አልተመሰረተበትም። ሳሚ ኤ ከጀርመናዊ ሚስቱና ከአራት ልጆቹ ጋር በምዕራባዊ ጀርመን በምትገኘው ቦቹም በምትባል ከተማ ነዋሪ ነው። ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ አግኝቶ የተለያዩ ቴክኖሎጂ ስልጠናዎችንም ወስዷል። የጥገኝነት ጥያቄውን ባለስልጣናቱ ለደህንነት ጠንቅ ነው በሚል አልተቀበሉትም። በየቀኑም ወደ ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ ሪፖርት እንደሚያደርግ ተገልጿል። ተጠርጣሪ የሆኑ የጂሃድ አራማጆች በሰሜን አፍሪካ ባሉ ሀገራት ስቃይ እንደሚደርስባቸው የጀርመን መንግሥት መረጃ ያሳያል። በዚህም ምክንያት ቱኒዝያም ሆነ ጎረቤት አረብ ሀገራት ስደተኞችን ለመመለስ ደህንነታቸው የተጠበቁ አገሮች አይደሉም ተብሏል።
48525914
https://www.bbc.com/amharic/48525914
በኦሮሚያ ክልል ብክለት አስከትለዋል በተባሉ 22 ፋብሪካዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ
በዚህ አመት በኦሮሚያ ክልል የአፈር፣ የውሃና የአየር ብክለት አስከትለዋል በተባሉ 22 ፋብሪካዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ።
የክልሉ የተፈጥሮ ሃብት ደንና የአየር ንብረት ባለስልጣን አቶ ቦና ያዴሳ እርምጃ ከመውሰድ በተቃራኒ በዘርፉ በጎ አስተዋጽኦ ላበረከቱ 18 ፋብሪካዎች የማበረታቻ ሽልማት ተሰጥቷል ብለዋል። እርምጃ የተወሰደባቸው ፋብሪካዎች አብዛኞቹ የቆዳ፣ የብረታብረት፣ የሲሚንቶ ፋብሪካዎችና የቡና ማጠብ ስራ ላይ የተሰማሩ ናቸው ያሉን ኃላፊው ለጊዜው ፋብሪካዎቹ ስራቸውን አቁመው የቆሻሻ ማስወገድ ስርዓታቸው ላይ ማስተካከያ እስኪያደርጉ ተዘግተዋል ብለዋል። ከእነዚህም መካከል 18 የሚሆኑት የሚጠበቅባቸውን ማስተካከያ አድርገው ወደ ስራ መግባታቸውን አቶ ቦና ተናግረዋል። • የኢትዮጵያ ተፈናቃዮች አይንና ጆሮ እንደተነፈጋቸው ተገለፀ • በአክሱም ዩኒቨርስቲ አንድ ተማሪ ሲሞት በርካቶች ቆሰሉ • ''ወደ ኢትዮጵያ የምናደርገውን ጉዞ አንሰርዝም'' ከዚህም በተጨማሪ ሕዝቡ ቅሬታ የሚያሰማባቸው ፋብሪካዎች ላይ ጠንከር ያለ ክትትል እንደሚያደርጉ ኃላፊው ጨምረው ለቢቢሲ ተናግረዋል። በአለም አቀፍ ደረጃ ዛሬ እየተከበረ የሚገኘውን የአካባቢ ጥበቃ ቀን በማስመልከት ያነጋገርናቸው የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ፍቃዱ በበኩላቸው የኢትዮጵያ የአየር ብክለት ተጽዕኖ የአየር ብክለት ተጋላጭነት እየጨመረ ነው ብለዋል። በአለም አቀፍ ደረጃ ዛሬ የአካባቢ ጥበቃ ቀን "አየር ብክለትን" ዋና ጉዳዩ አድርጎ በቻይና እየተከበረ ይገኛል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም ከአየር ብክለት ጋር በተያያዘ በሚከሰት የጤና ችግር ምክንያት በአለም 7 ሚሊዮን ሰዎች ያለ እድሜያቸው እንደሚሞቱ ያትታል። ከእነዚህ መካከል 4 ሚሊዮን የሚሆኑት በእስያ ፓስፊክ የሚገኙ ናቸው። ኢትዮጵያ በአየር ብክለት ከሌሎች ሃገራት ጋር ስትነጻጸር የተሻለች ብትሆንም በትልልቅ ከተሞችና በከተሞች አቅራቢያ ከፋብሪካዎች መስፋፋትና ከተሽከርካሪዎች ብዛት ጋር በተያያዘ የአየር ብክለት እየጨመረ መምጣቱን ጠቅሷል። ፕሮፌሰር ፍቃዱ ከአየር ብክለት የሚያስከትለው ጉዳትና ህብረተሰቡ ሊያደረግ በሚገባው ጥንቃቄ ላይ መሥሪያ ቤታቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ላይ አትኩሮ እየሰራ መሆኑን ነግረውናል። ኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ቀንን በመጭው ቅዳሜ በአዳማ ስታከብር ዋናው ትኩረት በጉዳዩ ላይ ግንዛቤ መፍጠር እንደሆነም ጨምረው አስረድተዋል። በአየር ብክለት ከሚከሰቱ የጤና ችግሮች መካከል የሳምባ በፍጥነት ማርጀት፤ አስም፤ ብሮንካይት፤ ካንሰር ይገኙበታል።
news-43412024
https://www.bbc.com/amharic/news-43412024
ሊቢያ በ205 ህገ ወጥ አዘዋዋሪዎች ላይ የእስር ትዕዛዝ አወጣች
ስደተኞችን ከአፍሪካ ወደ አውሮፓ በህገ-ወጥ መንገድ የሚያዘዋውሩ 205 የሊቢያ እና የሌሎች ሃገራት ዜጎች ላይ ሊቢያ የእስር ትዕዛዝ አወጣች።
ከስሃራ በታች ካሉ ሃገራት ለሚመጡ ስደተኞች ወደ መዳረሻቸው ለሚያደርጉት ቦታ ሊቢያ ቁልፍ መሸጋጋሪያ ሃገር ናት በእስር ትዕዛዙ ላይ እንደተጠቀሰው፤ 205ቱ ህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች፤ ስደተኞችን በማሰቃየት፣ አስገድዶ በመድፈር እንዲሁም ነፍስ በማጥፋት የተከሰሱ ናቸው። የሊቢያ ጠቅላይ አቃቢ ህግ እንደገለጹት የእስር ትዕዛዙ ከተቆረጠባቸው መካከል የሃገሪቱ የደህንንት ሃላፊዎች፣ በሊቢያ የሚገኙ የአፍሪካ ሃገራት ኤምባሲዎች እና የስደተኞች ማቆያ ጣቢያ አለቆች ይገኙበታል። በአውሮፓውያኑ 2011 የቀድሞ የሊቢያ መሪ ሙዓመር ጋዳፊ ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ ሊቢያ ከገባችበት ቀውስ መውጣት ተስኗት ትገኛለች። ስልጣን በተለያዩ ሚሊሻዎች እና በሁለት ተቀናቃኝ መንግሥታት እጅ ስለሚገኝ ህገ-ወጥ እንቅስቃሴዎች እንዲኖሩ እድል ከፍቷል። ከስሃራ በታች ካሉ ሃገራት ለሚመጡ ስደተኞች በቀይ ባህር አድርገው አውሮፓ ለመግባት ለሚያደርጉት ጥረት ሊቢያ ቁልፍ መሸጋጋሪያ ሃገርም ነች። የህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎቹ መረብ ላይ ምርመራው የተጀመረው ከአንድ ዓመት በፊት ሲሆን የጣሊያን አቃቢ ህግም በምርመራ ስራው ላይ ተሳትፎ እያደረገ ነው። የሊቢያ ጠቅላይ አቃቢ ህግ ምረመራ ቢሮ ዳይሬክተር ሴዲቅ አል-ኑር እንዳሉት ከሆነ በህገ-ወጥ ስራው ላይ በርካት የኢሚግሬሽን ሰራተኞች ይገኙበታል። ከዚህ በተጨማሪም ዳይሬክተሩ እንዳሉት አዘዋዋሪዎቹ እና ጽንፈኛው ኢስላሚክ እስቴት ቀጥተኛ ግኑኘነት አላቸው።
48552480
https://www.bbc.com/amharic/48552480
የሱዳን አለመረጋጋት በኢትዮጵያ ላይ የሚያስከትለው ተጽእኖ ምንድነው?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ፍጥጫ ላይ ያሉትን የሱዳን መንግሥት ወታደራዊ መሪዎችና ሕዝባዊ ተቃውሞውን የሚመሩትን ተቃዋሚዎች ለማነጋገር ዛሬ ጠዋት ሱዳን መዲና ካርቱም ገብተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው፣ የኢታማዦር ሹሙ ጄነራል ሰዓረ መኮንን፣ አምባሳደር ሙሐመድ ድሪር ከልኡክ ቡድኑ አባላት መካከል ይገኙበታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ካርቱም ያቀኑት ሰሞኑን የተከሰተውን ደም አፋሳሽ ግጭት ተከትሎ ነው። በጉዟቸውም በሃገሪቱ የነገሰውን ውጥረት ለማብረድ አልበሸርን ከስልጣን አንስተው ጊዜያዊውን አስተዳደር የሚመሩትን ወታደራዊ ባለስልጣናት አነጋግረዋል። ወታደራዊው አስተዳደር ስልጣኑን በቶሎ ለሲቪሎች እንዲያስረክብ ግፊት እያደረጉ ያሉትና በርካታ ደጋፊዎቻቸው እንደተገደሉባቸው የሚናገሩትን የተቃዋሚውን ቡድን መሪዎችን ያናግራሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጋር የግብፅ መንግሥት ተወካዮችም ውጥሩቱን ለማርገብ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ሱዳን ግብተዋል። በተጨማሪም የአፍሪካ ህብረት ሰላምና ደህንነት ኮሚሸነር ስማሊ ቼሩጉኢ አብረው አብረው እንደሚሆኑ ተነግሯል። • የአክሱም ሙስሊሞች ጥይቄ መቼ ምላሽ ያገኝ ይሆን? • አፍሪካውያን ስደተኞች በአሜሪካ ድንበር ደጅ እየጠኑ ነው • ካፍ የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ድጋሚ እንዲካሄድ አዘዘ የሱዳን አለመረጋጋት በኢትዮጵያ የሚያስከትለው ተጽእኖ ምንድነው? በኪል ዩኒቨርሲቲ መምህር ለሆኑት አዎል አሎ (ዶክተር) የሱዳን አለመረጋጋት በኢትዮጵያ ላይ ሊፈጥር የሚችለው ቀጥተኛ ተጽእኖ ምንድነው ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ መስጠት የጀመሩት ሁለቱ ሃገራት ሰፊ ሊባል የሚችል ድንበር እንደሚጋሩ በማስታወስ ነበር። ''ሁለቱ ሃገሮች ሰፊ እና ብዙ ህዝብ የሚመላለስበት ድንበር ይጋራሉ። ሰላም እና ጸጥታ በሁለቱም ሃገራት ድንበር ላይ የማይኖር ከሆነ፤ የተለያዩ ችግሮች ወደ ኢትዮጵያ ሊመጡ ይችላል።'' ይላሉ። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር እንዳለ የሚያስታውሱት ዶክተር አወል አሎ፤ ''የሱዳን አለመረጋጋት ይህንን የሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ሰፋ ባለ ሁኔታ ሊያበረታታ ይችላል'' ይላሉ። ዶክተር አዎል አሎ፤ በኢትዮጵያ አለመረጋጋት እያለ የጎረቤት ሃገር መንግሥስትም ሃገሩን መቆጣጠር ካልቻለ፤ ኢትዮጵያን ችግር ውስጥ መክተት ለሚፈልጉ ኃይሎች የሱዳን ምድርን ጥቅም ላይ ሊያውሉ እንደሚችሉ ያስረዳሉ። ዶ/ር አወል ኢትዮጵያ ሱዳንን በተመለከተ ሌላው ያላት ፍላጎት የአባይ ግድብን በተመለከተ እንደሆነ ይጠቁማሉ። ''በኢትዮጵያ እና በግብጽ መካከል ያለችው ሃገር ሱዳን ነች። በኢትዮጵያ እና በግብጽ መካከል አለመግባባቶች ተፈጥረው ወደ ሌላ ደረጃ ቢሸጋገር እንኳ ሱዳን የምትጫወተው ሚና ቀላል አይደለም'' ይላሉ። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በሱዳን ምን ይገጥማቸው ይሆን? የአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካን በቅረበት የሚከታተለው የቢቢሲው ጋዜጠኛ ፈረጌል ኬን ''የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር ከእርሱ በእጅጉ የተለዩ ከሆኑት የሱዳን አጋሮቹ ጋር ነው የሚገናኘው'' ይላል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይን ''የቀድሞ የጦር መሪ፤ አሁን ግን በርካታ ላውጦችን ያስመዘገበ መሪ'' ሲል የሚገልጽ ሲሆን፤ የሱዳን ጊዜያዊ ወታደራዊ የሽግግር መንግሥት መሪዎችን ደግሞ ''ወታደራዊ የሆነ መንግሥታዊ ስርዓትን ለመዘርጋት ቆረጠው የተነሱ'' ሲል ይገልጻቸዋል። ፈረጌል ኬን በሱዳን ጉዳይ ያገባኛል የሚሉት አካላት ብዛት እና የፍላጎት መለያየትን ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ ሁሉንም አካላት ማግባባት ቀላል ሊሆን እንደማይችል ግምቱን ያስቀምጣል። የአፍሪካ ህብረት ሱዳን ወደ ሲቪል አስተዳደር እስክትመለስ ድረስ ከየትኛውም የህብረቱ እንቅስቃሴ ማገዱ ተገቢ የሚያደርጉ ምክንያቶች አሉ የሚለው ፈረጌል ኪን፤ አፍሪካዊ ያልሆኑት ሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች በሱዳን ላይ እያሳደሩ ካሉት ተጽእኖ በላይ የአፍሪካ ህብረት ፈላጭ ቆራጭ መሆን ይጠበቅበታል። ምክንያቱም በሱዳን ነገሮች ቢባባሱ ችግሩ የሚተርፈው ለአህጉሪቱ አገራት እንጂ ለሳዑዲ እና ለአረብ ኢሚሬቶች አይደለምና ይላል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጉዞ የሚደረገው 108 ተቃዋሚ ሰልፈኞች መሞታቸው ከተነገረና ትናንት አፍሪካ ህብረትም ሱዳን ወደ ሲቪል አስተዳደር እስክትመለስ ድረስ ከየትኛውም የህብረቱ እንቅስቃሴ እንዳገዳት ካስታወቀ በኋላ ነው። በኪል ዩኒቨርሲቲ መምህር ለሆኑት አዎል አሎ (ዶክተር) የጠቅላይ ሚንስትሩን ጉብኝት ወቅታዊ ነው። ነገሮች ተባብሰው የተለያዩ ኃይሎች ከመፈጠራቸው በፊት ኢትዮጵያ የአስታራቂነት አስተዋጽኦዋን መወጣት ያለባት አሁን ላይ ነው ባይ ናቸው። ሰሞኑን በተካሄደው ደም አፋሳሽ ተቃውሞ ውስጥ የሀገሪቱ ልዩ ኃይል በተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ እርምጃ መውሰዱ የተነገረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በሱዳን ከተሞች በስፋት ተሰማርተው ይገኛሉ ተብሏል። የሱዳን ጤና ጥበቃ ሚኒስትር የተገደሉት ተቃዋሚ ሰልፈኞች 61 ብቻ ናቸው ያሉ ሲሆን፤ ከተቃዋሚ ሰልፈኞች ጋር ግንኙነት ያላቸው የሐኪሞች ቡድን ግን ሟቾቹ 100 እንደሆኑ መግለፃቸው ይታወሳል። ለወራት የዘለቀው ተቃውሞ ወደ ብጥብጥ ያደገው ሰኞ ዕለት የደህንነት ኃይሎች ለወራት ከመከላከያ ኃይሉ ዋና መሥሪያ ቤት ፊት ለፊት በመቀመጥ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ የነበሩ ሰልፈኞችን ማዋከብ ከጀመሩ በኋላ ነው። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኦማር አል በሺር ከስልጣን ከወረዱ በኋላ ይሄኛው ወታደሩ የወሰደው እርምጃ ከፍተኛ ሟቾች የተመዘገበበት ነው። ከሰኞ ጀምሮ በተቃዋሚዎች እና በወታደራዊ ምክር ቤቱ መካከል ሲደረግ የነበረው ንግግር የተቋረጠ ሲሆን በርካታ ምዕራባውያን ሃገራትም በሱዳን ጉዳይ ያላቸውን ስጋት ገልጠዋል።
news-53963770
https://www.bbc.com/amharic/news-53963770
ኢላን መስክ በአሳማ ጭንቅላት ላይ የኮምፒወተር ቅንጣት የገጠመው ምን አስቦ ነው?
የሕዋ ታክሲ (ስፔስ ኤክስን) ፈጥሯል፡፡ ቴስላን አስተዋውቋል፡፡ ፔይፓልም የሱ ሥራ ነው፡፡ የዓለም 31ኛው ሀብታም ነው፡፡ 97 ቢሊዮን ዶላር ይገመታል፣ ሀብቱ፡፡
ገርትሩድ የተሰኘችው አሳማ ጭንቅላት ውስጥ የኮምፒውተር ቅንጣት ተገጥሟል አሁን ደግሞ በአንዲት አሳማ ጭንቅላት ውስጥ የኮምፒውተር ቅንጣት (computer chip) ገጥሞላታል፡፡ ይህን ያደረገው በኮምፒውተር የሚታገዝ የሰው ልጅ ጭንቅላት ለመፍጠር ያለውን ሕልም እውን ለማድረግ ነው፡፡ ከደቡብ አፍሪካ ወደ ካናዳ በልጅነቱ ከሄደ በኋላ በተማሪነት ወደ አሜሪካ አቀና፡፡ አሁን ዓለማችንን በምድርም በሰማይም በቴክኖሎጂ እየናጣት ይገኛል፡፡ ዕድሜው ገና 50 አልደፈነም፡፡ የሚኖረው በሎስ አንጀለስ፣ ካሊፎርኒያ ነው፡፡ 7 ልጆች አሉት፡፡ ሰሞኑን ስሙ የተነሳው አዲስ የፈጠራ ሙከራ በመጀመሩ ነው፡፡ ሳንቲም የምታህል የኮምፒውተር ቅንጣት የእንሰሳ ጭንቅላት ውስጥ ገጥሟል፡፡ አሳማ ናት፡፡ ስሟ ገርትሩድ ይባላል፡፡ ሐሳቡ የሰው ልጅ ወደፊት ጭንቅላቱ በኮምፒውተር እንዲታገዝ ማስቻል ነው፡፡ ‹‹ልክ አእምሮ ላይ ትንሽዬ የእጅ ሰዓትና ኤሌክትሪክ የማስቀመጥ ያህል ነው›› ብሏል ቢሊየነሩ ፈጣሪ ኢላን መስክ በዌብካስት፡፡ ኒውራሊንክ የሚባለው የቴክኖሎጂ ፈጠራ ኩባንያው ይህንን አሁን በአሳማ የሞከረውን ቀጥሎ በሰዎች ላይ ሙከራ ለማድረግ እንዲፈቀድለት ባለፈው ዓመት ማመልከቻ ማስገባቱ ይታወቃል፡፡ ሐሳቡ ተግባራዊ ሲደረግ የነርቭ ችግር ያለባቸው ሰዎች ስልክና ኮምፒውተርን እንዲሁም ሌሎች ማናቸውም ተግባራትን በአእምሯቸው በማሰብ ብቻ እንደ ማንኛውም ጤነኛ ሰው ማዘዝ ይችላሉ፡፡ ቢሊየነሩ ፈጣሪ ኢላን መስክ ተስፋ የሚያደርገው ወደፊት የሰው አእምሮ ውስጥ የሚገጠመው ኮምፒውተር-ቅንጣት፣ ሕይወትን ከማቅለሉም በላይ ፓርኪንሰንና ህብለ ሰረሰር ጉዳት ያለባቸው ሰዎችን ያድናል፡፡ የቢሊየነሩ ኢላን መስክ የረዥም ጊዜ ህልሙ የሰው ልጅን የላቀ ፍጡር ወይም ልዕለሰብ ማድረግ ነው፡፡ መስክ እንሚያስበው የሰው ልጅ ወደፊት የሚጠፋው በሰው ሰራሽ ክህሎት (አርተፊሻል ኢንተለጀንስ) መወሳሰብ ነው፡፡ ይህንን መቋቋም የሚቻለው ደግሞ ልዕለ-ሰብ በመፍጠር ነው፡፡ ልዕለ-ሰብ የሚፈጠረው ደግሞ በኮምፒውተር በሚታገዝ አእምሮ ብቻ ነው፡፡ ግርቱሩድ የተሰኘቸው አሳማ ሳንቲም መጠን ያለው ኮምፒውተር ፍላሽ ከተገጠመላት በኋላ በካሜራ ክትትል ተደርጎላታል፡፡ መጀመርያ ትንሽ የመወዛገብ ነገር ቢታይባትም በኋላ ግን ሕይወቷን ቀጥላለች፡፡ ገለባ አሽትታ ስትቀምስ የነርቭ እንቅስቃሴዋና ስሜቷ በተገጠመላት ኮምፒውተር አማካኝነት ክትትል ሲደረግለት ነበር፡፡ አሳማዋ ምግብ ስትሻ በጭንቅላቷ የተገጠመላት ማሽን ቀድሞ ምልክቶችን ማሳየት ችሏል፡፡ ይህ ኒውትራሊንክ የሚባለው ቅንጣት እጅግ ደቂቅ የሆኖ ክሮች እንዲኖርት ተደርጎ ነው የተመረተው፡፡ ከፀጉር ውስጥ ቢሰካ መለየት አይችልም፡፡ ከጸጉርም የቀጠኑ ክሮችን ነው የተደረጉለት፡፡ ይህ ቅንጣት 3ሺህ ኤሌክትሮድሰን የያዘ ሲሆን ከሰው ጸጉር የቀጠኑ ተጣጣፊ ክሮች አንድ ሺህ የአእምሮ ኒውሮንስን መቆጣጠር ይችላሉ ተብሏል፡፡ ባለሙያዎች የሰው ልጅ አእምሮ መጀመርያ እንዴት ይሠራል የሚለውን ጠንቅቀን ሳናውቅ አእምሮ ላይ ቅንጣት መግጠም ያለውን ፋይዳ በጥርጣሬ ይመለከቱታል፡፡ አሳማዋ የኮምፒውተር ቅንጣት ተገጥሞላት ሳለ ከሌሎች አሳማዎች በተለየ ምንም የሆነችው ነገር ባለመኖሩ አንድ የሳይንስ እርምጃ ተደርጎ ታይቷል፡፡ ይህም ምናልባት ወደፊት የሰው ልጆች አንጎል ተከፍቶ ሳንቲም የምታክል ቅንጣት ቢጨመርበት አደጋ አይፈጥር ይሆናል የሚል ተስፋን አሳድሯል፡፡ የሰው ጭንቅላት ውስጥ ኒውሮሲግናሎችን ማንበብ የሚችል ቅንጣት ተገጠመ ማለት ሰዎች ቴሌቪዥን ቻናል ለመቀየር፣ እጅ የሌላቸው ሰዎች ማሸን የተገጠመላቸውን ማሽን ለማዘዝ፣ ወይም በኮምፒውተር ለመተየብ ጣቶች አያስፈልጉ ይሆናል፡፡ ፍላጎቱን ማሰብ ብቻ በቂ ነው፡፡
news-49232316
https://www.bbc.com/amharic/news-49232316
ደቡብ አፍሪካዊያን ታዳጊ አብራሪዎችን ሲረዱ የነበሩት ፓይለቶች በአውሮፕላን አደጋ ሞቱ
ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ ሃገራት አየር ላይ ከበረሩት ደቡብ አፍሪካዊያን ታዳጊ አብራሪዎች ጀርባ ሆነው ፕሮጀክቱን ሲያስተባብሩ የነበሩ ሁለቱ ደቡብ አፍሪካዊያን ፓይለቶች ቅዳሜ ዕለት ታንዛንያ ውስጥ ባጋጠማቸው የመከስከስ አደጋ ህይወታቸው አለፈ።
ከጥቂት ሳምንታት በፊት ደቡብ አፍሪካዊያኑ ታዳጊዎች በገጣጠሟት አውሮፕላን ከደቡብ አፍሪካ ተነስተው ካይሮ መዲና ግብፅ መግባታቸው የሚታወስ ነው፤ ከታዳጊዎቹ ጀርባ ደግሞ ሁለት ፓይለቶች ፕሮጀክቱ እንዲሳካ ጥረዋል። •ታዳጊዎቹ በገጣጠሟት አውሮፕላን ከደቡብ አፍሪካ ተነስተው ካይሮ ገቡ •ታዳጊዎች በገጣጠሟት አውሮፕላን የመጀመሪያ በረራቸውን አደረጉ ዴስ ዌርነርና ዌርነት ፍሮንማን የተባሉት ፓይለቶች ታዳጊዎቹ የሚያበሯትን አውሮፕላን ከኋላ አጅበው በመቆጣጠር በጉዟቸው ይከተሏቸው ነበር። ደቡብ አፍሪካ በዛሬው ዕለት እንደሚደርሱ ይጠበቅ የነበረ ቢሆንም ከታንዛንያ ታቦራ አየር ማረፊያ የተነሱት አብራሪዎቹ ቅዳሜ ዕለት መከስከሳቸውን የታንዛንያ ባለስልጣናት ተናግረዋል። ፓይለቶቹ ከእይታ ከመጥፋታቸው በፊት የሞተር ችግር እንዳጋጠማቸው መልዕክት ማስተላለፋቸውን የታንዛንያ የአየር ትራንስፖርት ባለስልጣን አስታውቋል። አውሮፕላኗ ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ የሆነች ሲሆን ማግኘት የተቻለውም ጥቂት አካሏን መሆኑንም ባለስልጣናቱ አክለው ተናግራዋል። አውሮፕላኗ ባለቤትነቷ ዩ ድሪም ግሎባል የሚባል ድርጅት ሲሆን ይህም ከታዳጊዎቹ ፓይለቶች አንዷ ሜጋን ዌርነርና አሁን ህይወቱ ያለፈው አባቷ ዴስ ዌርነር ነው። "ከኬፕታውን ካይሮ ታዳጊዎቹን አጅባ ስትበር የነበረችው አውሮፕላን መከስከሷን መስማት ያሳዝናል፤ የፕሮጀክቱ ጠንሳሾች ዴስ ዌርነርና ዌርነር ፍሮምናንም ህይወታቸውን አጥተዋል። ሌላ አደጋ የደረሰበት ሰው የለም" ሲል ድሪም ግሎባል በፌስቡክ ገፁ ይህንን መልዕክት አስፍሯል። •በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን ፌስቲቫል፡ ሙዚቃ፣ ኳስ፣ ፍቅርና ቡጢ.. ሁለቱ ፓይለቶች የታዳጊዎቹን አብራሪዎች አውሮፕላን ፕሮጀክት ከጅምሩ የጠነሰሱት ሲሆን በዳይሬክተርነትም እየመሩት ነበር ተብሏል። ታዳጊዎቹ የሚያበሯት አራት መቀመጫ ያላት አውሮፕላን ከተለያየ ስፍራ በተውጣጡ 20 ተማሪዎች ነው የተገጣጠመችው። ይህንን ፕሮጀክት የጀመረችው የ17 ዓመቷ ሜጋን ስትሆን አንድ ሺ የሚሆኑ ተማሪዎች ፍላጎታቸውን ቢያሳዩም ባደረጉት ማጣራት20 ተማሪዎች ተመርጠዋል። ስድስቱም ታዳጊዎች የአብራሪነት ፍቃድ ያገኙ ሲሆን 12 ሺህ ኪሎ ሜትር ርቀት በረራም በስድስቱ ትከሻ ላይ ወድቆ ነበር። በሦስት ሳምንት ጉዟቸውም ናሚቢያ፣ ኢትዮጵያ፣ ማላዊ፣ ዛንዚባር፣ ዩጋንዳ የመሳሰሉ አገራትን አካልለዋል። ታዳጊዎቹ አውሮፕላኗን ሰርቶ ለማጠናቀቅ ሦስት ሳምንታት የፈጀባቸው ሲሆን፤ የውስጥ አካሏን ከደቡብ አፍሪካ አውሮፕላን አምራች ኩባንያ በመግዛት እንዲሁም በሺህዎች የሚቆጠሩ የውስጥ አካሏን መገጣጠም ችለዋል። አንዳንድ የአውሮፕላኑ ክፍሎችና ሞተሩ በሰለጠኑ ሰዎች የተገጠሙ ሲሆን አጠቃላይ አውሮፕላኑ የተገጣጠመው በታዳጊዎቹ ነው።
news-52533113
https://www.bbc.com/amharic/news-52533113
ኢትዮጵያ ሰው ሠራሽ የዘረ-መል ለውጥ የተደረገባቸው የእህል ዘሮችን ለማምረትና ለመጠቀም አልተስማማችም
ኢትዮጵያ ሰው ሰራሽ የዘረ-መል ለውጥ የተደረገባጋቸው ሕያዋን (ጄኒቲካሊ ሞዲፋይድ ኦርጋኒዝም) የእህል ዘሮችን ለማምረትም ሆነ ለመጠቀም እንዳልተማማች ተገለጸ።
የግብርና ሚኒስቴር ለቢቢሲ፤ ሰሞኑን ኢትዮጵያ ልውጥ ሕያዋንን ለማምረትና ለመጠቀም በሯን ለመክፈት ተስማምታለች በሚል የሚነገረው ትክክል እንዳልሆነ ገልጿል። ከጥቂት ሳምንታት ወዲህ ኢትዮጵያ ልውጥ ሕያውን (ጀኒቲካሊ ሞዲፋይድ ኦርጋኒዝምስ፤ ጂኤምኦ) በሚመለከት ከእራሷ ባሻገር ሌሎች አገራትም የሚከተሉት ጠንከር ያለ አቋሟን አለዝባ እንደተቀበለች ሲዘገብ እና በጉዳዩም ላይ ሚናዎች ተለይተው ክርክሮች ሲደረጉ ተስተውሏል። በወርሃ የካቲት የአሜሪካ መንግሥት የግብርና መስሪያ ቤት የውጭ አገራት ግብርና አገልግሎት እና በዓለም አቀፉ የግብርና መረጃ መረብ የታተመ የግብርና ሥነ- ሕይወት ቴክኖሎጂ ግምገማ የኢትዮጵያ መንግሥት በግብርና ሥነ ሕይወት ዘርፍ ያሉ ቴክኖሎጂዎችን የመጠቀም ፍላጎት በግልፅ ማሳየቱን አመልክቶ ነበር። የአሜሪካ የግብርና መስሪያ ቤት ሠራተኞችን ግምገማ ቢያካትትም የአገሪቱን አቋም ግን አይገልፅም በተባለው በዚህ ዘገባ ላይ እ.ኤ.አ በ2018 የኢትዮጵያ መንግሥት የሥነ ሕይወት ለውጥ የተደረገለትን የጥጥ ዝርያ (ቢቲ-ኮተን) መቀበሏን፤ ድርቅን እና ፀረ ሰብል ተባይን የሚቋቋም የበቆሎ ዝርያ ላይም በቦታ የተከለለ የመስክ ላይ ጥናት እንዲደረግ መፍቀዷን ጠቅሷል። ስለጉዳዩ ለማጣራት ቢቢሲ ያነጋገራቸው በግብርና ሚኒስቴር የሰብል ምርት ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኢሳያስ ለማ "ኢትዮጵያ በሰፋፊ እርሻዎች በባለሃብቶች ብቻ ለማምረት ሁለት ጂኤምኦ የጥጥ ዝርያዎችን ብትመዘግብም፤ ይህ በጥቅሉ አገሪቱ እነዚህን ምርቶች ተቀብላለች ወደሚል ድምዳሜ መድረስ አይቻልም" ይላሉ። "ሁለት ዝርያዎችን ከህንድ አምጥተን ሞክረን፤ ስኬታማ ናቸው ተብሎ በዝርያ ደረጃ ተመዝግበዋል። ሌሎች አገራት እንደሚያደርጉት ለእህል ግን አልፈቀድንም" ብለዋል አቶ ኢሳያስ። እ.ኤ.አ በ2018 የተመዘገቡት ሁለት ሰው ሰራሽ የዘረ መል ለውጥ የተደረገባቸው የጥጥ (ቢቲ-ኮተን) ዝርያዎች ተቀባይነት አግኝተው ምዝገባ ይደረግላቸው እንጂ ወደሥራ ለመግባት ገና የሚቀሩ ደረጃዎች እንዳሉ አቶ ኢሳያስ ጨምረው ገልፀዋል። እነዚህ ዝርያዎች ጥጥን በሚያጠቃ አንድ ተባይ ምክንያት የተሻለ የመቋቋም አቅም ካላቸው ተብሎ እንደተሞከረና ምርምሩ አብቅቶ የተባሉት ዝርያዎቹ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መመዝገባቸውን ጠቅሰዋል። "ቀጥሎ ያለው ዘሩ እንዴት ነው በታጠረ፥ ማለትም በባለሃብት ብቻ እንዲለማ የሚደረገው ወደሚለው ቀጣይ እርምጃ ለመሄድ ዘር መግባት ነበረበት። ይሄን የዘር ሒደት ተስማምተን አልጨረስንም፤ ገና ነው። ዘር አልገባም፣ ዝርያዎቹ እንዴት ይሰራሉ የሚለው መመርያም አልፀደቀም" ይላሉ። ዝርያዎቹን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት እንቅፋት ከሆኑ ጉዳዮቹ አንዱ ዝርያዎቹን የሚያመርተው የህንድ ኩባንያ የብቸኛ አቅራቢነት (ሞኖፖሊ) አሠራር ያለው መሆኑን ዳይሬክተሩ ለቢቢሲ ተናገረዋል። በሰፋፊ እርሻዎች ለንግድ አገልግሎት ብቻ ይውላሉ የተባሉት እነዚህን ዝርያዎች ሥራ ላይ ከማዋል ጋር በተገናኘ፥ "ከሕንዱ ኩባንያ ጋር መስማማት አለብን፤ አንደኛ ዝርያዎቹ እዚህ መባዛት አለባቸው። ዝርያዎቹ ከተመዘገቡ በኋላ እኔ ዘሩን በየዓመቱ አቀርባለሁ ከሚለው [የኩባንያው ሐሳብ] ጋር አልተስማማንም። ከሌላው የጥጥ ዝርያ ጋር እንዳይቀላቀል የማድረጉን ሒደትም ገና አልተሄደበትም። በዚያ ላይ ተንጠልጥሎ ነው የቀረው።" ኢትዮጵያ በ2001 ዓ.ም ያፀደቀችው የደኅንነተ ሕይወት አዋጅ ሰው ሰራሽ የዘረ መል ለውጥ የሚደረግባቸው ሕያዋን ላይ የሚደረጉ ምርምሮች ላይ በሮችን ጠበብ ያደረገ ነበር። አዋጁን ሆን ብሎ ጂኤምኦን ወደ ከባቢ መልቀቅን ይከለክላል በሚል በዘረ መል ብዝሃነት የዳበረ ከባቢዋን ከዝርያ መበከል ለመታደግ ችላለች በሚል ያሞካሿት ነበሩ። ይሁንና ከስድስት ዓመታት በኋላ በአዋጁ ላይ ማሻሻያዎችን አድርጋ በሩን ሰፋ አድርጋለች እየተባለ ነው። አዋጆቹ በሚፀድቁባቸው ጊዜያትም ቢሆን በጂኤምኦ ዝርያዎች ዙርያ ጥቅም እና ጉዳት እየዘረዘሩ ሐሳባዊ ሙግቶችን ያደረጉ የዘርፉ ባለሞያዎች ነበሩ። እነዚህ ሙግቶች አሁንም ሲያስነሰራሩ እየተስተዋለ ነው። ጂኤምኦን የሚቃወሙ ወገኖች ሰው ሰራሽ የዘረ መል ለውጥ የሚደረግባቸው ዝርያዎች ቀድሞ ያልታሰበ ጉዳት ሊያመጡ ይችላሉ፤ ከዚህም በዘለለ ዝርያዎቹ ላይ ምርምር የሚያደርጉ ትልልቅ የግል ኩባያዎች የባለቤትነት መብት ስለሚኖራቸው፥ ገበሬዎች የእነርሱ ጥገኞች እንዲሆኑ ያደርጋሉ ይላሉ። በሌላ በኩል የጂኤምኦ ዝርያዎች ከትንሽ መሬት ብዙ ምርትን ያሳፍሳለሉ፥ ለተፈጥሯዊ ጫናዎች እና ጉዳት አማጭ ተባዮች በቀላሉ አይበገሩም ሲሉ ያሞግሷቸዋል ደጋፊዎቻቸው።
sport-45443693
https://www.bbc.com/amharic/sport-45443693
የሃገራት ሊግ ምንድነው?
የሁሉንም እግር ኳስ አፍቃሪ ቀልብ ይዞ ከቆየው የዓለም ዋንጫ መጠናቀቅ በኋላ ቀንሶ የነበረው የእግር ኳስ ተመልካች ቁጥር የአውሮፓ ሊጎች ሲጀመሩ እንደገና አንሰራርቷል።
እስካሁን አራተኛ ሳምንት ጨዋታዎች የተደረጉበት እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ገና ከአሁኑ ፉክክሩ ተጧጡፏል። ሊቨርፑል፣ ቼልሲና ዋትፎድ ከአራት ጨዋታ 12 ነጥቦችን በመሰብሰብ ከአንድ እስከ ሦስት ያለውን ቦታ ይዘዋል። በሁሉም ጨዋታ ሽንፈትን ያስተናገደው ዌስት ሃሞ ደግሞ የመጨረሻውን ሃያኛ ቦታ ይዟል። በስፔን ላሊጋ ባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ ከሦስት ጨዋታ ሦስቱንም በማሸነፍ የላሊጋው አሸናፊ ለመሆን የሚያደርጉትን ትንቅንቅ ከጅምሩ ተያይዘውታል። • ጥቁር አሜሪካዊው ኮሊን ኬፐርኒክ የናይክ ኩባንያ መሪ አስተዋዋቂ ሆነ • ሞሃመድ ሳላህ በፊፋ ምርጥ የወንድ ተጫዋች የመጨረሻ ሶስት ውስጥ ገባ በአዲሱ የፊፋ አሰራር መሰረት በዚህ ሳምንት ሁሉም የአውሮፓ ሊጎች የውስጥ ውድድር አያካሂዱም። ይህም የሚሆነው ትርጉም የለሽ ያላቸውን የወዳጅነት ጨዋታዎችን ለማስቀረት በማለት ፊፋ ያዘጋጀው የሃገራት ሊግ ሐሙስ ዕለት ስለጀመረ ነው። በመክፈቻው ዕለትም የዘንድሮው የአለም ዋንጫ አሸናፊ ፈረንሳዮች ከ2014 አሸናፊዎቹ ጀርመኖች ጋር የተገናኙ ሲሆን፤ ጨዋታውም ምንም ግብ ሳይቆጠርበት አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል። በዚህኛው የዓለም ዋንጫ ከፈረንሳይ ጋር ለፍጻሜ ደርሳ 4 ለ 2 በሆነ ውጤት የተሸነፈችው ክሮሺያም ከፖርቹጋል ያደረገችውን ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ የአቻ ውጤት አጠናቃለች። በአዲሱ አሰልጣኝ ሪያን ጊግስ የሚመሩት ዌልሶች በበኩላቸው ከአርላንድ ያደረጉትን ጨዋታ 4 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፈዋል። አሰልኙኙ ጊግስም በዚህ ጨዋታ የመጀመሪያ ሦስት ነጥብን ማግኘት ችሏል። • አፍሪካውያን በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውስጥ ፊፋ ሃገራት የቅድመ ዝግጅት ጨዋታዎችን ትኩረት ሰጥተው በደንብ እንዲጫወቱ ይረዳል ብሎ ያዘጋጀው አዲሱ የሃገራት ሊግ ውድድር 55 ሃገራትን ያሳትፋል። የሃገራቱ ምድቦችም የሚወሰኑት ፊፋ በሚያወጣው ዓመታዊ የዓለም ሃገራት ብሔራዊ ቡድን ደረጃ ሲሆን፤ ሦስት ወይንም አራት አባላት ይኖሩታል። በዚህ መልኩ የሚካሄደው ውድድር እ.አ.አ በወርሃ ሰኔ 2019 ፍጻሜውን የሚያገኝ ሲሆን፤ አሸናፊው ብሄራዊ ቡድን የሃገራት ሊግ ሻምፒዮን የሚባል ይሆናል። ቅዳሜና እሁድ ከሚደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች መካከል እንግሊዝን ከስፔን የሚያገናኘው ጨዋታ ተጠባቂ ከሚባሉት መካከል ነው።
news-50792431
https://www.bbc.com/amharic/news-50792431
ሙሽሪት በሰርጓ ቀን ዋዜማ ጉድጓድ ውስጥ ገብታ ሞተች
በሰሜን ናይጄሪያ ፋቲማ አቡባካር የተባለች የ16 ዓመት ሙሽራ ድንገት ጉድጓድ ውስጥ ገብታ ሞታለች።
የፋቲማ አቡበከር ሰርጓ ሐሙስ ለታ ነበር። ከሰርጉ ቀን በፊት በነበረ ዝግጅት ነው ድንገት ጉድጓድ ውስጥ የገባቸው። አባቷ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ረቡዕ ለታ ፈቲማ በአክስቷ ቤት ግቢ በነበረ ጉድጓድ በቅርበት ቆማ ነበር። • በበዴሳ ከተማ ታዳጊውን ለመታደግ የሞከሩ 4 ሰዎች የውሃ ጉድጓድ ውስጥ ገብተው ሞቱ • ዐይነ ስውሩ በአቃቂ ክፍለ ከተማ ሕንፃ ከሰባተኛ ፎቅ የአሳንሰር ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ ሞተ "ልጄ በሰርጓ እጅግ ተደስታ ነበር። ትጫወትና ትስቅ ነበር ከጓደኞቿ። ከእጮኛዋ ጋርም እጅግ ይዋደዱ ነበር" ብለዋል። ሙሽራው ለጊዜው በሐዘን ምክንያት ጤናው ተቃውሶ መናገር አቅቶታል። የሟች ፋጢማ አባት ለቢቢሲ እንደተናገሩት ለሰርግ የጣሉት ድንኳን ለለቅሶ እንዲሆን ሆኗል። • በጫጉላ ሥነ ሥርዓት ላይ የፈነዳው ቦምብ ሙሽራውን ገደለ
news-55570796
https://www.bbc.com/amharic/news-55570796
የአሜሪካ ምክር ቤት፡ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች በአሜሪካ ምክር ቤት ላይ የፈፀሙት ወረራ በምስል
የአሜሪካ ሕዝብ እንደራሴዎች ተሰብስበው ጆ ባይደን ለፕሬዝዳንትንት የተመረጡበትን የምርጫ ውጤት ለማፍደቅ በመነጋገር ላይ ሳሉ ነው በድንገት በሺህ የሚቆጠሩ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች ምክር ቤቱን ጥሰው የገቡት።
በዚህም ምክንያት የምክር ቤቱ ስብሰባ ለሰዓታት እንዲቋረጥ የተደረገ ሲሆን በዋሽንግተን የሰዓት እላፊ ገደብ ተጥሏል። ካፒቶል ሒል የአሜሪካ መንግሥት መቀመጫ ሲሆን የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት በቀኝ፣ የሕግ መምሪያው ምክር ቤት መሰብሰቢያ ደግሞ በግራ በኩል የሚገኝበት፣ በርካታ ቢሮዎች ያሉበት ታሪካዊ ሕንጻ ነው። ተቃዋሚ ሰልፈኛው በአሜሪካ ካፒቶል ሂል ሕንጻ ውስጥ የኮንፈደሬት ባንዲራን አንግቦ የተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች የአሜሪካ ካፒቶል ሕንጻ ጥሰው ገብተው ፎቶዎችን ሲነሱ አንድ ተቃዋሚ ሰልፈኛ ከአሜሪካ ካፒቶል ሂል ምስባክ ይዞ ሲወጣ ከሴኔት ምክር ቤት ውስጥ ከውጪ ለመግባት የሚታገሉ የዶናልድ ትራፕድ ደጋፊዎች ላይ ፖሊስ ሽጉጥ ደቅኖ ሰልፈኛው ከባልኮኒ ላይ ወደ ሴኔት ምክር ቤት ወለል ሲዘል ፖሊስ ሰልፈኞቹን ለመቆጣጠር ሲሞክር፣ የአሜሪካ የሕዝብ እንደራሴዎች እና የምክር ቤቱ ሠራተኞች የጭስ መከላከያ ጭምብል ለብሰው በተቃዋሚ ሰልፈኞች "ትራምፕ ፕሬዝዳንቴ ነው" የሚል ባንዲራ ሲውለበለብ የትራምፕ ደጋፊ በአፈጉባኤዋ ጠረጴዛ ላይ ከተቀመጠ በኋላ "አናፈገፍግም" የሚል መልዕክት ትቶ ሄዷል በርካታ ተቃዋሚ ሰልፈኞች በካፒቶል ሂል ውስጥ በቁጥጥር ስር ውለዋል የዶናልድ ትራምፕ ነውጠኛ ደጋፊዎች በአሜሪካ ምክር ቤት ውስጥ ከፖሊስ ጋር ተፋጠው የአሜሪካ ምክር ቤት ፖሊስ የካፒቶል ሂልን መስኮት ሰብሮ የሚገባ ተቃዋሚ ሰልፈኛን ሲከላከል ተቃዋሚዎች በሕንጻው ውስጥ የትራምፕ ደጋፊዎች በምክር ቤቱ ፎቶዎችን ሲነሱ ከተቃዋሚዎቹ አንዱ
news-53004400
https://www.bbc.com/amharic/news-53004400
በወጣቷ ጥያቄ የአሜሪካ ትልቁ መዝገበ ቃላት የ"ዘረኝነት" ትርጉምን ሊያሻሽል ነው
የአሜሪካው ሜሪየም ዌብስተር መዝገበ ቃላት እንደ ኦክስፎርድ መዝገበ ቃላት ሁሉ ታዋቂና ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ነው።
ኬኔዲ ሚችሀም አንዲት ወጣት ጥቁር አሜሪካዊት ታዲያ ለዚህ መዝገበ ቃላት አሳታሚ በጻፈቸው ደብዳቤ ምክንያት መዝገበ ቃላቱ ዘረኝነት ወይም (racism) ለሚለው የእንግሊዝኛ ቃል የትርጉም ፍቺ ማሻሻያ ለማድረግ ወስኗል። ለቃሉ ትርጉም ፍቺ መሻሻል ምክንያት የሆነችው ወጣት ኬኔዲ ሚችሀም ትባላለች። 22 ዓመቷ ሲሆን ከአዮዋ ግዛት ደሬክ ዩኒቨርስቲ ገና መመረቋ ነው። ያደገችው በፈርጉሰን ሚዙሪ ሲሆን፤ ይህ አካባቢ ደግሞ በጸረ ዘረኝነት ትግል ላይ ብዙ ታሪክ ያለው ቦታ ነው። ምናልባት አስተዳደጓና ያደገችበት ሰፈር ስለ ዘረኝነት ብዙ እንድታውጠነጥን ሳያደርጋት አልቀረም። ወጣቷ ሚችሀም ለአሳታሚዎቹ በጻፈችው ደብዳቤ ዘረኝነት ለሚለው ቃል የተሰጠው ትርጉም "አንድ የጎደለው ነገር አለ" ስትል አስገንዝባለች። ይህም 'መዋቅራዊ ዘረኝነት' የሚለውን ጽንሰ ሐሳብ መግደፉ ነው። አንድ በድርጅቱ በአርታኢነት በከፍተኛ ኃላፊነት የሚሰሩ ሰው ልጅቱ ያነሳቸው ነጥብ መሠረታዊ በመሆኑ ማሻሻያው ይደረጋል ብለዋል። የመዝገበ ቃላቱ አሰናጆችም ይህንኑ አረጋግጠዋል። አሳታሚው እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በአሜሪካ ሜኔሶታ ግዛት፣ በሚኒያፖሊስ ከተማ ባለፈው ወር ጆርጅ ፍሎይድ የተባለ ጥቁር በአንድ ነጭ ፖሊስ የተፈጸመበት አሰቃቂ ግድያን ተከትሎ ተቃውሞ በመቀጣጠሉ ነው። ሚችሀም ለዚህ ያነሳሳት ዘረኝነትን በተለየ መንገድ ስትመለከትና ሰዎች ዘረኛ ስለመሆናቸው ስትነግራቸው ወደ መዝገበ ቃላቱ በመሄድ እንዴት ዘረኛ እንዳልሆኑ ሊያስረዷት እየሞከሩ ስላስቸገሯት ነው። ከእነዚህ አጋጣሚዎች በኋላ ሚችሀም የመዝገበ ቃላቱ አሰናጆች ለዘረኝነት ሰፋ ያለ ትርጉም ሊሰጡት እንደሚገባ በማመኗ ደብዳቤውን ለመጻፍ ተነሳስታለች። አሁን ለጊዜው ዘረኝነት በሜርየም ዌብስተር መዝገበ ቃላት ሦስት ትርጉሞች ብቻ ተሰጥቶት ይገኛል፤ 1ኛ. ዘረኝነት ማለት አንድ ማኅበረሰብ በቆዳ ቀለሙ የበላይ ነው፤ አንዱ ከሌላው ይበልጣል ብሎ ማሰብ 2ኛ. ዘርን መሰረት ባደረገ ሁኔታ የተቋቋመ የፖለቲካ ፕሮግራም ወይም አስተሳሰቡን በዚሁ በዘር ልዩነት ላይ መሰረት አድርጎ ማደራጀት 3ኛ. የዘር ልዩነት እና መድልዎ ናቸው ሚችሀም ለቢቢሲ እንደተናገረቸው ከላይ የተዘረዘሩት የቃሉ ብያኔዎች ያላካተቷቸው ሕያው የዘረኝነት ልማዶችና ከሃይል አሰላለፍ ጋር ያለውን ቁርኝቶች አሉ። ይህንንም ያስተዋለችው ከዛሬ አራት ዓመት በፊት እንደሆነ ሚችሀም ለቢቢሲ ተናግራለች። "በማኅበራዊ ሚዲያ ገጼ ላይ ሰዎች ስለ ዘረኝነት ሀሳባቸውን እንዲያጋሩኝ ጠይቄ ነበር፤ እኔ በኮሌጅም ይሁን በዩኒቨርስቲ የሚደርስብኝን ዘርን መሰረት ያደረገ ረቂቅ መድልዎ እምብዛምም የሚያስተውለው የለም" ብላለች። ይህን ረቂቅ ዘረኝነት ጉዳይ ስታነሳ ግን ሰዎች ቶሎ ብለው መዝገበ ቃላቱን በማንሳት እሷ እንደተሳሳተች ሊያሳምኗት ሲሞክሩ ቆይተዋል። አንዳንድ ሰዎች "ስለ ዘረኝነት ምንም የምታውቂው ነገር የለም፤ ዝም ብለሽ አትዘባርቂ" እያሉ ሲያንቋሽሹኝ ነበር ብላለች ሚችሀም። አንዳንዶች በተለይ የዚህን መዝገበ ቃላት ትርጓሜን እየቀዱ በእኔ ማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ ላይ በመለጠፍ አንዱ ዘር ከሌላው ይበልጣል ብለው እስካላመኑ ድረስ በፍጹም ዘረኛ ሊባሉ እንደማይገባ ይሟገቷት ነበር። አንዳንዶችማ ጭራሽ "ይኽው ጥቁር ሆነሽ ዩኒቨርስቲ ገብተሻል፤ ከእኛው እኩል ጥቅሞችሽ ተከብረውልሻል፤ ምን ይሁን ነው የምትይው?" ይሏት ነበር። እሷ በበኩሏ የተሰጡኝ ዕድሎች እንዳሉ ሆነው በቆዳ ቀለሜ ምክንያት ብቻ ከፊቴ የሚደነቀሩብኝን መሰናክሎች ሰዎች ሊያይዋቸው አልቻሉም ትላለች። ሊያይዋቸው ያልቻሉት ደግሞ እነዚያ መሰናክሎች በእነርሱ ሕይወት ውስጥ ስለሌሉ ነው። በዚህም ምክንያት ነገሩን ስታብሰለስለው ቆይታ በግንቦት 28 ለመዝገበ ቃላቱ አርታኢያን ደብዳቤ ልካለች። በዚህ ደብዳቤዋ ላይ አጽንኦት የሰጠችው ዘረኝነት ሲባል "ማኅበራዊና ተቋማዊ" ረቂቅ ቅርጽ ሊኖረው እንደሚችልና በቆዳ ቀለም የተነሳ አንዱ ለሌላው የሚሰጠው የአስተሳሰብ ብያኔም ዘረኝነት እንደሆነ አብራርታለች። "ባልጠበቅኩት ሁኔታ ለዚህ ደብዳቤዬ በቀጣዩ ቀን ምላሽ ተላከልኝ" ትላለች ሚችሀም። ከተከታታይ የደብዳቤ ልውውጦች በኋላ የመዝገበ ቃላት አሳታሚው ይህ ጉዳይ በአፋጣኝ ሊስተካከል እንደሚገባና የቃላት ብያኔው እርሷ እንዳለችው ሆኖ መታተም እንዳለበት ይፋ አድርጓል። የሜሪየም ዌብስተርስ መዝገበ ቃላት የአርታኢያን ሥራ አስኪያጅ ፒተር ሶኮሎውስኪ ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት ማሻሻያው "ረቂቅና ተቋማዊ ዘረኝነቶችን የሚይዝ ትርጓሜ እንዲያካትት ይደረጋል። ይህን የተመለከተ አንድ ሁለት ምሳሌም አብሮ ተካትቶ ይታተማል" ብለዋል። አዲሱን ማሻሻያ የተደረገበትን ቅጽም በነሐሴ ወር ታትሞ ይወጣል ብለዋል ሥራ አስኪያጁ። ምንጊዜም ቢሆን "ሰዎች ዘረኝነትን በተመለከተ ያላቸው ትርጉም ተመሳሳይ ሊሆን ይገባዋል፤ መግባባት ይኖርብናል" ይላሉ ፒተር ሶኮሎዉስኪ። ዘረኝነት የሚጨበጥ፣ የሚዳሰስ ወይም በገቢር የሚፈጸም ብቻ ሳይሆን በአስተሳሰብ ውስጥ የሚቀበር ረቂቅ መልክ እንዳለው ለዘመናት ቸል ሲባል የቆየ ጉዳይ ነው። ይህ በመዝገበ ቃላት ደረጃ መቀመጡ ሰዎች ዘረኝነትን በተቀራራቢ ትርጉም እንዲረዱት ያግዛቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።
news-55026902
https://www.bbc.com/amharic/news-55026902
ዩቲዩብ ክፍያ ሳይፈጽም ማስታወቂያዎችን በቪዲዮዎች ላይ ሊያስገባ ነው
ዩቲዩብ ብዙ ቪዲዮዎች ላይ ማስታወቂያዎችን ማሳየት እንደሚጀምር እና ለሁሉም ግን ክፍያ ላይፈጽም እንደሚችል አስታወቀ፡፡
ኩባንያው በአሁኑ ወቅት የማስታወቂያ ገቢውን በሽርክና መርሃ ግብሩ ላይ ከተመዘገቡ ቪዲዮ ሠሪዎች ጋር ይጋራል። ከዚህ በኋላ ግን ዩቲዩብ የሽርክና መርሃ ግብሩ አካል ያልሆኑ አንዳንድ ቪዲዮዎች ላይም ማስታወቂያዎችን ማስገባት እጀምራለሁ ብሏል። በአገልግሎት ውሉ ላይ በተደረጉ ለውጦች ምክንያት ዩቲዩብ ከማስታወቂያዎቹ የሚገኘውን ገቢ ለቪዲዮ ሠሪዎች አያጋራም ማለት ነው። በተጨማሪም ተመልካቾች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ማስታወቂያዎችን እንዲያዩ ሊገደዱ ይችላሉ ተብሏል። የዩቲዩብ የሽርክና መርሃ ግብር አካል ለመሆን ጥያቄ ማቅረብ የሚያስፈልግ ሲሆን፤ 1000 በላይ ተከታይ ላላቸው እና በአንድ ዓመት ውስጥ ለ4000 ሰዓታት ቪዲዮዎቻቸው ለታዩላቸው ብቻ የሚሰጥ ነው። ዩቲዩብ በመርሃ ግብሩ ውስጥ የሌሉ ቪዲዮ ሠሪዎች "ከእነዚህ ማስታወቂያዎች የገቢ ድርሻ አይወስዱም" ቢልም ቪዲዮ ሠሪዎች በመደበኛ መንገድ የሽርክና መርሃ ግብር አካል ለመሆን ጥያቄ ማቅረብ ዕድል ይኖራቸዋል ተብሏል። እንደ ዩቲዩብ የማመልከቻ ሂደት ገለፃ ጥያቄዎች በሰዎች እንዲገመገሙ ወረፋ ተራቸውን እንዲጠብቁ እንደሚደረግ ገልጾ ይህም ከአንድ ወር በላይ ሊፈጅ ይችላል ብሏል። ጋዜጠኛና ደራሲው ክሪስስቶከል-ዎከር "ይህ ማለት የሽርክና መርሃ ግብሩ አካል ያልሆነ አነስተኛ የቪዲዮ ሠሪ ምንም ዓይነት የማስታወቂያ ገቢ ሳያገኝ ብዙ ተመልካች ያገኛል ማለት ነው" ሲል ያስረዳል። "አንድ የቪዲዮ ሠሪ ስኬቱን ተጠቅሞ እንደ ስፖንሰር ባሉ ሌሎች ገቢዎች ሊጠቀም ቢችልም ውሳኔው ግን እንግዳ ይመስላል" ሲል ጥያቄ አንስቷል። "ዩቲዩብ ቀድሞውንም ትኩረቱ እጅግ በጣም ብዙ ገንዘብ በማግኘት ላይ ነው" ሲልም አብራርቷል። "በበቂ ሁኔታ ሳይክሳቸው ወይንም ላደረጉት አስተዋጽኦ ተገቢውን እውቅና ሳይሰጣቸው ዩቲዩብ በሥራቸው ይበልጥ ተጠቃሚ ለመሆን የፖሊሲ ለውጥ ማድረጉ ቪዲዮ ሠሪዎችን ይበልጥ የሚያበሳጭ ነው" ብሏል። ለውጦቹ በአሜሪካ ውስጥ እየተጀመሩ ሲሆን አዲሱ ውል በሚቀጥለው ዓመት በሌሎች ቦታዎችም "ተግባራዊ ይሆናሉ" ሲል ዩቲዩብ አስታውቋል። ይህ የዩቲዩብ ውሳኔ ተቃውሞ ቢገጥመውም ሀሳቡን የመቀየር ዕድሉ ጠባብ መሆኑን ስቶከል-ዎከር ገልጿል።
44213348
https://www.bbc.com/amharic/44213348
ሳናውቀው በሰውነታችን ውስጥ የሚከማች አደገኛ ስብ
በጤናማ የሰውነት ክብደት ውስጥ የስብ ክምችት ሊኖር ይችላል? የ29 ዓመቷ የቢቢሲ ጋዜጠኛ መጠነኛ የሰውነት አቋም ያላትና ጤናማ የምትባል ናት።
የምትለብሰው 12 ቁጥር ልብስ ሲሆን ጤናማ የህይወት ዘዬ እንደምትከተል ታምናለች። በፀደይ ወቅት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ብትሰራም በዝናብ ወቅት ብዙም እንቅስቃሴ አታደርግም። "የውስጤን ባላውቅም ከላይ ጤነኛ ሆኖ መታየትን እፈልጋለው" ትላለች። ሱሺ ለንደን በሚገኝ አንድ ክሊኒክ ያደረገችው ምርመራ ውጤት ግን አስደናቂ ሆነ። ምርመራው የሚደረገው በተለየ የኤክስ ሬይ ምርመራ ነው። ይህ ምርመራ በሰውነት ውስጥ ያለ የስብ መጠንንና ስርጭትን እንዲሁም የጡንቻዎች ሁኔታን ለማጤን ያስችላል። ለሆድ አካባቢ የስብ ክምችት ከሴቶች ይልቅ ወንዶች ተጋላጭ ሲሆኑ በንፅፅር በሴቶች ላይ ስብ በመላ አካል ተሰራጭቶ እንደሚገኝ ጥናቶች ይጠቁማሉ። "ጥሩ ስሜት ሊኖርና ጥሩ አቋም ያለው ሆኖ መታየት ይቻል ይሆናል። ነገር ግን በሰውነት ውስጥ የስብ ክምችት ሊኖር ይችላል። ይህ ደግሞ አደገኛ ነው። ምክንያቱም የሰውነት ውስጥ የስብ ክምችት የተለያዩ የውስጥ አካላትን ከቦ ሊገኝ ይችላልና። ይህ እንደ አይነት ሁለት ካሉ የስኳር በሽታ ጋር ይገናኛል" ይላሉ የህክምና ባለሙያው ፊል ቻንት። ከዓለም አቀፉ የቦዲ ማስ ኢንዴክስ (አጠቃላይ የሰውነት ክብደት አመላካች) ልኬት አንፃር ሲታይ ሱሺ ትንሽ ክብደቷ መሆን ከሚጠበቅበት አለፍ ያለ ነው። በዚህ ዓለም አቀፍ ልኬት የቦዲ ማስ ኢንዴክሳቸው በ18.5 እና 24.9 መካከል የሆኑ ሰዎች ጤናማ ክብደት እንዳላቸው ይታመናል። ቢሆንም ግን የቦዲ ማስ ኢንዴክስ ልኬት የሰውነት ስብ መጠንን ወይም ስርጭትን የሚመለከት መረጃ አይሰጥም። ስለዚህም የሱሺን ድብቅ የውስጥ ስብ መጠን ያጤኑት ፊል በእሷ እድሜ የምትገኝ ሴት ሊኖራት ከሚገባው የስብ መጠን ከሁለት እጥፍ በላይ እንዳላት ነግረዋታል። ከሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው 90 በመቶ የሚሆነው የሰውነት ስብ የሚገኘው ከሰውነት ቆዳ ስር ነው። የወገብና የአጠቃላይ ቁመት ስሌትን በመስራት ከልክ በላይ ስብ በሰውነት ውስጥ መኖሩን ማወቅ ይቻላል። አስር በመቶ የሚሆው ስብ ደግሞ ሰዎች ሊመለከቱት ከሚችሉት ውጭ እና ውስጣዊ ሲሆን እንደ ጉበትና አንጀት ያሉ ክፍሎችን ከብቦ ይገኛል። ይህ ሁለተኛው አይነት ስብ መጠኑ አነስተኛ ቢሆንም ለጤና ግን አደገኛ ነው። ይህ ስብ ለምን እንዲህ አደገኛ ሆነ? ይህ ስብ የልብ ችግርን እንዲሁም አይነት ሁለት የስኳር ህመምን ያስከትላል። በቅርብ ጊዜ የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ደግሞ ይህ ስብ ለካንሰር የመጋለጥ አደጋንም ይጨምራል። ይህ የስብ ክምችት በተለይም ሆድ አካባቢ ከሚገኝ ውፍረት ጋር ይያያዛል። ጥናቶች እንደሚያሳዩት እግር ወይም ዳሌ ላይ ከሚኖር ስብ ይልቅ የወገብ አካባቢ ስብ ክምችት አደገኛ ነው። በሌላ በኩል ሆድ አካባቢ የሚኖር ስብም ለስኳር በሽታ እንዲሁም ለኮሌስትሮል ሊያጋልጥ ይችላል። ማን ይበልጥ የዚህ አደገኛ ስብ ክምችት ይኖረዋል? የስብ ክምችትና ስርጭት በፆታ ይለያያል። በጥቅሉ ወንዶች በይበልጥ ሆድ አካባቢ ለሚኖር ለዚህ የስብ ክምችት የተጋለጡ ናቸው። ነገር ግን ይህ አደገኛ የስብ አይነት በአካል ብቃት እንቅስቃሴና አመጋገብን በማስተካከል በቁጥጥር ስር ሊውል ይችላል። ቅባት ምግቦች፣ አልኮል፣ ቀይና የታሸጉ ስጋዎችና ስኳር የበዛባቸው መጠጦች ለዚህ አይነቱ የስብ ክምችት ሊያጋልጡ እንደሚችሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
49575650
https://www.bbc.com/amharic/49575650
የማዉ ጫካን ለማዳን 60 ሺ ኬንያውያን ከመኖሪያቸው ተባረሩ
በኬንያ ተፈጥሯዊ ሃብቶች ዝርዝር ውስጥ እጅግ በጣም ወሳኝ ከሚባለው የማዉ ጫካ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ከ60ሺ በላይ ዜጎችን መንግስት ማባረር ጀምሯል።
የኬንያ ዋነኛ የውሃ ምንጭ እንደሆነ የሚነገርለት ይህ ጫካ የዝናብ ውሃን ለረጅም ጊዜ ይዞ የሚያቆይ ሲሆን በደረቅ ወራት ደግሞ ውሃውን ወደ ሃገሪቱ ብዙ ወንዞች መልሶ ይለቀዋል። ባለስልጣናት እንደሚሉት ሰዎቹ በሕገ-ወጥ መንገድ የሰፈሩ ሲሆን የእርሻ ቦታ ለማዘጋጀት በማሰብ ጫካውን እየመነጠሩት ነው። • 'በእርግማን' የተፈጠረው የኮንሶው 'ኒው ዮርክ' • በክረምት ሲዘንብ የመሬት ሽታ ለምን ያስደስተናል? ከሰኞ ጀምሮ አንዳንድ ፍቃደኛ ቤተሰቦች ጫካ ውስጥ የሰሩትን ቤትና ያዘጋጇቸውን የእርሻ ቦታዎች በገዛ ፍቃዳቸው ለቅቀው መሄድ የጀመሩ ሲሆን መንግሥት በኃይል ንብረታችን ከሚያወድም በሰላም ለመልቀቅ መርጠናል ብለዋል። በአካባቢው የሚገኙ 31 ትምህርት ቤቶችም በዚሁ ምክንያት ከሰኞ ጀምሮ ዝግ ሆነዋል። በዚህም ከ10 ሺ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ቀርተዋል። የኬንያ የደን አገልግሎት መስሪያ ቤት በመቶዎች የሚቆጠሩ የታጠቁ ጠባቂዎቹን ከፖሊስ ጎን ሆነው ነዋሪዎቹን ከማዉ ጫካ የማስወጣት ስራውን እንዲያግዙ በማለት አሰማርቷቸዋል። ነዋሪዎቹን የማስወጣት ስራውን እጅግ አስፈላጊ ያደረገው አካባቢው ትልቅ ውሃ የመቋጠር አቅም ስላለውና የዝናብ ዑደትን በእጅጉ ስለሚወስን ነው ብለዋል የሃገሪቱ የአካባቢ ሚኒስትር ካሪያኮ ቶቢኮ። ከዚህ በተጨማሪ ብዙ ጎብኚዎችን የሚስበውና ብዙ የዱር እንስሳት ወደ ታንዛንያ ሲሄዱ አቋርጠውት የሚያልፉት የማራ ወንዝ ቋሚ የውሃ ምንጭ ነው። ነገር ግን ይህ የመንግሥት እርምጃ ከአንዳንድ የግዛት አስተዳዳሪዎች ወቀሳን አስከትሏል። መንግሥት ጉዳዩን በድርድርና በጠረጴዛ ዙሪያ መፍታት ሲገባው በኃይል እርምጃ መውሰዱ ተገቢ አይደለም ብለዋል። • ብዝኀ ሕይወት ምንድን ነው? ለምንስ ግድ ይሰጠናል? • ኢትዮጵያ ሀይቆቿን መጠበቅ ለምን ተሳናት? ጫካው የሚገኝበት ክልል አስተዳዳሪ የሆኑት ኪፕቹምባ ሙርኮመን በበኩላቸው ነዋሪዎቹ ከጫካው ወጥተው እንዳይሄዱ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። በቅርብ የሚገኝ አዋሳኝ ክልል አስተዳዳሪ ሌዳማ ኦሌ ኪና ደግሞ በእሱ በኩል ያሉት የማሳይ ማህበረሰብ ነዋሪዎች በሰላም መውጣታቸውን በመግለጽ የማዉ ጫካን የመታደግ ስራው በመጨረሻም ተጀመረ ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። እንደ ዓለማቀፉ የዱር እንስሳት ጥናት ፈንድ መረጃ መሰረት ከሆነ ኬንያ ነጻነቷን ካገኘችበት እ.አ.አ. 1963 ጀምሮ የማዉ ጫካ 37 % የሚሆነውን ሽፋኑን በሰዎች ምክንያት አጥቷል።
news-51830171
https://www.bbc.com/amharic/news-51830171
በሞረትና ጅሩ ወረዳ እነዋሪ ከተማ ነጻ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት የሄደ ቡድን ላይ ጥቃት ደረሰ
በአማራ ክልል ሞረትና ጅሩ ወረዳ፣ እነዋሪ ከተማ ነጻ የሕክምና አገልግሎት ሊሰጡ የመጡ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች የሐይማኖት ስብከት ለምን ያካሂዳሉ በሚል ጥቃት እንደደረሰባቸው የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ለቢቢሲ ተናገሩ።
ወደ ከተማዋ ያቀናው የሕክምና ቡድን 18 የውጪ አገር ዜጎች የተካተቱበት ከ200 በላይ አባላት ያሉት መሆኑን ዋና ኢንስፔክተር ወጋየሁ ቦጋለ ለቢቢሲ ገልፀዋል። የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስትያን ፕሬዝዳንት የሆኑት መጋቢ ይልማ ሙሉጌታ በበኩላቸው በእነዋሪ ከተማ ለ20 ዓመት የነበረ ቤተ እምነት ላይ ጥቃትና ዘረፋ መፈፀሙን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። መጋቢ ይልማ አክለውም ጥቃቱ የተፈፀመው በሐይማኖት አክራሪዎች ነው ያሉ ሲሆን ንብረቶች መዘረፋቸውን፣ ሦስት ሰዎች ተደብድበው ሆስፒታል እንደሚገኙ እና ቃጠሎ መፈፀሙን ተናግረዋል። የተደበደቡት የቤተክርስቲያኒቱ ምዕመናን ብርሃኑ ተስፋ፣ አያሌው ማሞ እንዲሁም ተፈራ ሊያስብሸዋ የሚባሉ መሆናቸውን በመጥቀስ፤ አክራሪ ያሏቸው ጥቃት አድራሾች የቤተ ክርስቲያኒቱን ጥበቃ ደብድበው መሳሪያውን በመንጠቅ ቤተ እምነቱ ላይ ውድመት ማድረሳቸውን አረጋግጠዋል። ዋና ኢንስፔክተ ወጋየሁ እንዳሉት የሕክምና ቡድኑ በከተማዋ ነጻ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት የመጣው ባለፈው ቅዳሜ እለት ነው። ቡድኑ ከእሁድ ጀምሮ በእነዋሪ ጤና ጣቢያ በመገኘት ነፃ የሕክምና አገልግሎት ሲሰጥ የነበረ ሲሆን፤ ለሕክምናው አገልግሎት ጎን ለጎን ከገጠር ቀበሌዎችና ከከተማው ለሚመጡ ተገልጋዮች የሐይማኖታዊ ስብከት ይደረግ እንደነበር ተገልጿል። • የቀድሞው የደኅንነት መስሪያ ቤት ምክትል ይናገራሉ • "ሞተዋል ወይም በሕይወት አሉ ይበሉን'' የታጋች ተማሪዎች ቤተሰብ • በመሐል ሜዳ ሚስቱን ለመግደል የሞከረው ግለሰብ የሦስት ሰዎችን ህይወት አጠፋ መጋቢ ይልማ በከተማዋ ለነጻ ሕክምና አገልግሎት ለመስጠት መጡ የተባሉትን ቡድኖች በተመለከተ እንደተናገሩት ከእነርሱ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነትም ሆነ እውቅና እንደሌላቸው አስረድተዋል። ቡድኑ የሕክምና አገልግሎቱን ሊሰጥ የመጣው ከእሁድ እስከ አርብ ድረስ ሲሆን ከጤና ጣቢያው ጎን ድንኳን በመጣል ሐይማኖታዊ ስብከት ሲያካሄዱ እንደነበር ይናገራሉ። የከተማው ነዋሪ ይህ ለምን ይሆናል ብሎ ተቃውሞ ነበር ያሉት በሰሜን ሸዋ ዞን የሞረትና ጅሩ ወረዳ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ዳኜ አምታታው ሲሆኑ፤ የሕዝቡን ቅሬታ ይዘው ስብከቱን እንዳያደርጉ ለማነጋገር መሞከራቸውን አስታውሰዋል። ዋና ኢንስፔክተሩ በበኩላቸው ሕዝቡ የሐይማኖት ስብከቱ በከተማዋ በሚገኘው የፕሮቴስታንት የእምነት ተቋም ቅጽር ግቢ ውስጥ ቢሰጥ ችግር የለብንም ማለቱን በማነሳት፤ ከጤና ጣቢያው ጎን ድንኳን ጥለው ስብከት ማካሄዳቸውና የሐይማኖት መጻህፍት ማደላቸው ቁጣን እንደቀሰቀሰ አመልክተዋል። ዋና ኢንስፔክተር ወጋየሁ አክለውም ከእሁድ ጀምሮ እስከ ትናንት ድረስ አገልግሎቱ በሰላም ሲሰጥ የቆየ ቢሆንም በኋላ ግን ከገጠር ቀበሌዎችና ከከተማው ተቆጥተው የመጡ ወጣቶች በድንኳኑ እንዲሁም በሙሉ ወንጌል ቤተ እምነት ላይ የድንጋይ ድብደባና ቃጠሎ ጉዳት ማድረሳቸውን ገልፀዋል። አቶ ዳኜ በበኩላቸው "የተቆጣው ሕዝብ ከቁጥጥር ውጪ ነበር የሆነው" በማለት በወቅቱ ጉዳት ሳይደርስ ችግሩን ለመቆጣጠር የተደረገው ጥረት አለመሳካቱን ይገልፃሉ። ዋና ኢንስፔክተር ወጋየሁ አክለውም ዋነኛ ትኩረታችን የነጻ ሕክምና አገልግሎት ለመስጠት ወደ ከተማችን የመጡ ባለሙያዎችና ባልደረቦቻቸው ምንም አይነት ጉዳት እንዳይደርስባቸው መከላከል ነበር፤ ያንንንም ማድረግ ችለናል በማለት ቡድኑን እስከ ደብረብርሃን ድረስ አጅበው በመሸኘት እንዲሄዱ ማድረጋቸውን ይገልፃሉ። በጥቃቱ የቤተክርስቲያኒቱ ማምለኪያ አዳራሽ እንዲሁም ስድስት ለቢሮነት የሚያገለግሉ ክፍሎች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን የገለፁት የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ፕሬዝዳንት መጋቢ ይልማ ሙሉጌታ የተዘረፉባቸውና የተቃጠሉ ንብረቶች ግምት አንድ ሚሊየን ብር እንደሚደርስ ለቢቢሲ ገልፀዋል። መጋቢ ይልማ በተፈጸመው ጥቃት ሦስት ሰዎች ላይ ጉዳት እንደደረሰ ቢናገሩም ዋና ኢንስፔክተሩ ወጋየሁ ግን አንድ የጥበቃ ሰራተኛ ብቻ በድንጋይ መጎዳቱን ገልጸዋል። በተጨማሪም ከንብረት አንጻር ስብከት ሲካሄድነበት የነበረ ድንኳን፣ እንግዶቹ ለመቆያ የሰሩት ካምፕና ልብስ እንዲሁም የሙሉ ወንጌል የቀድሞ ቢሮዎች መቃጠላቸውን ፖሊስ አረጋግጧል። ዋና ኢንስፔክተሩ አክለውም እስከአሁን ድረስ በጉዳዩ ተጠርጥሮ የተያዘ አንድም ግለሰብ እንደሌለ በመግለጽ ክትትል እያደረጉና መረጃ እያሰባሰቡ መሆኑነን ተናግረዋል። በተያያዘ ዜና የካቲት 25 እና 26/2012 ዓ.ም በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ጉራጌ ዞን ኮኪር ገደባኖ ጉታዘር ወረዳ፤ መሃል አምባ ከተማ የሚገኝ የሙሉ ወንጌል አጥቢያ ላይ ጥቃት መድረሱን መጋቢ ይልማ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ቤተክርስቲያኒቷ በአካባቢው ከ25 ዓመት በላይ የኖረች መሆኗን ጠቅሰው "በአካባቢው የሚገኙ የሐይማኖት አክራሪዎች ከምሽቱ 3፡30 ላይ አፍርሰዋታል" ሲሉ ገልጸዋል። በተጨማሪም በወቅቱ በቦታው ላይ የነበሩ ምዕመናን ላይም ድብደባ መፈፀሙንና ሰባት ምዕመናን መታሰራቸውን ጠቁመዋል። ከዚህ ባሻገርም ቀደም የነበረው የአምልኮ ቦታ ሙሉ በሙሉ መቃጠሉንና የነበረው ንብረት መውደሙን ተናግረዋል። ታስረው ከነበሩት ሰባት ምዕመናን መካከል ስድስቱ ትናንት መፈታታቸውን የሚናገሩት መጋቢ ይልማ፣ አንዱ ግን አሁንም በእስር ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል። በከተማው የሚገኙ ከ40 በላይ የቤተክርስቲያኒቷ አባላት ለደህንነታቸው በመስጋት ወደ ጎረቤት ወደ ሆነው የኦሮሚያ ክልል በመሸሽ በሀርቡ ጩልሌ ሙሉ ወንጌል ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ጠቅሰዋል። ከተሰደዱት መካከል ሕፃናትና ሴቶች እንደሚገኙበት የሚናገሩት ፕሬዝዳንቱ አንዳንዶቸቹ ወደ ወልቂጤ ዞን መሰደዳቸውን ጨምረው አስረድተዋል። መጋቢ ይልማ አክለውም በጥቃቱ 500 ሺህ ብር በማውጣት እየተገነባ የነበረው አዲስ የማምለኪያ ስፍራ መውደሙን በመጥቀስ በቤተክርስቲያኒቷ ላይ በተለያየ ቦታዎች የሚደርሰውን ጥቃት መደጋገመ መምጣቱን አመልክተዋል።
43207916
https://www.bbc.com/amharic/43207916
"ልጄ ከአሁን አሁን ነቅቶ ይጠራኛል እያልኩ ስጠብቅ 12 ዓመት ሆነኝ"
ወ/ሮ ሀሊማ ሙዘይን እና ባለቤቷ ኑሮን ሳኡዲ አረቢያ ሲያደርጉ ሰርቶ መኖርን ወልዶ መሳምን አስበው ነው። ከ 30 ዓመት በላይ በዚህ ሀገር ሲኖሩም ሁለት ልጆች አፍርተዋል።
ኑሯቸውን መካ ያደረጉት ሀሊማና ባለቤቷ ሁለተኛ ልጃቸው በአራተኛ አመቱ ላይ ባጋጠመው መጠነኛ የጤና እክል ጅዳ ወደሚገኝ ሆስፒታል አመሩ። "ሲተነፍስ ይቸገር ነበር በተለይ ሲተኛ መተንፈስ ያቅተው ነበር" ትላለች ወ/ሮ ሃሊማ ስለነበረው ሁኔታ ስታስታውስ። መካ የተወለደው ልጃቸው እንደማንኛውም ሕፃን ሮጦ የሚጫወት ስቆ የሚቦርቅ ነበር። በአራተኛ አመቱ ላይ ግን የመተንፈስ ችግር ስላጋጠመው ወደ ጅዳ ለህክምና ይዘውት ሄዱ። ጅዳ ይዘውት ሲመጡ በእርሷም በባለቤቷም ዘንድ ያለው ሃሳብ ምርጡን የህክምና ክትትል አግኝቶ ወደቤቱ በሰላም ይመለሳል የሚል ነበር። ሆስፒታሉም ይህንን ነው ያረጋገጠላቸው። አፍንጫው ውሰጥ ስጋ መብቀሉን እና እሱን ለማስወገድ የ10 ደቂቃ ቀላል ቀዶ ህክምና እንደሚያካሄዱ ተነገራቸው። ይህንን የቀዶ ህክምና ለማድረግም ከግብፃዊ ዶክተር ጋር ቀን ቆረጡ። በቀጠሯቸው እለት ለ10 ደቂቃ የቀዶ ህክምና በሆስፒታሉ ደርሰው ሳቂታው ልጃቸውን ለዶክተሩ አስረክበው መጠባበቅ ጀመሩ። ልጃቸው ግን ከአስር ደቂቃ በኋላ ህክምናውን አጠናቆ አልመጣም። ለሰዓታት ጠበቁ ልጃቸው ከተኛበት አልነቃም። አንድ ቀን ጠበቁ ለውጥ የለም፣ አንድ ሳምንት ከዚያም ወር ከዚያም ዓመት በልጃቸው ስጋ ውስጥ ከምትላወስ ነፍስ በቀር የጤናው ሁኔታ ሳይሻሻል ቀረ። የ 10 ደቂቃው ቀዶ ህክምና ህይወታቸውን ባላሰቡት መልኩ አናወጠው። ከህክምናው በኋላ በሰላም ይወጣል ያሉት ልጅ ከአልጋ መነሳት አልቻለም። አይናገርም አይሰማም። ስለዚህ ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል ተዛወረ። በገዛ ራሱ መተንፈስ ስላልቻለ የመተንፈሻ መሳሪያ እርዳታ አስፈለገው። በባለቤቷ መጠነኛ ገቢ የሚኖሩት እነሃሊማ ኑሯቸው መካ እና ጅዳ ተከፈለ። እናት እና ሴት ልጇ መሀመድን ለማስታመም ጅዳ ሲቀሩ አባት ደግሞ የቤተሰቡን የእለት ጉርስ ለማሸነፍ ወደ ሥራው መካ ተመለሰ። ኑሮ ግን በዚህ መልኩ መቀጠል አልቻለም። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ሴት ልጃቸው ወደ አባቷ ዘንድ ተመለሰች። ሐሊማ ልጄ ከአሁን አሁን ነቅቶ የቀድሞ ፈገግታውን አያለሁ እያለች ብቻዋን ማስታመም ቀጠለች። ''ቀሪው የቤተሰብ አባላት በሳምንት አንዴ እየመጡ ያዩታል'' የምትለው ሃሊማ ልጇ ትምህርት ቤት እየሄደ ከእኩዮቹ ጋር እየቦረቀ በአካልም በመንፈስም ያድጋል ብላ ብታስብም እርሱ ግን በታመመበት አልጋ ላይ 17 ዓመት ሊሞላው ነው። ልጃቸውን ለ10 ደቂቃ ቀዶ ህክምና ወደ ሆስፒታል ይዘው የሄዱት እናት 12 ዓመታት በሆስፒታል ቆዩ። በአራት ዓመቱ ለቀላል ቀዶ ጥገና ወደ ሆስፒታል የገባው መሀመድ የ17 ዓመት የልደት በአሉን በማይሰማበትና በማይለማበት የሆስፒታል አልጋ ላይ ሊያከብር ነው። ''ሆስፒታል ለቀላል ቀዶ ጥገና ከመግባቱ በፊት ሙሉ ምርመራ ተደርጎለት ጤነኛ ነው ብለዋል'' የምትለው ሃሊማ ዛሬ ግን የተፈጠረውን የህክምና ስህተት የሚያስተካክል አካል ጠፍቷል። ሆስፒታሉም ውስጥ ቀን እየገፋ ሲሄድ ልጁን ይዛ ወደቤቷ እንድትሄድ ተነግሯት ያውቃል። እርሷ ግን ልጄ በእግሩ እየተራመደ ገብቶ አልጋ ላይ የቀረው እዚሁ ስለሆነ ሳይሻለው አልሄድም በማለት እዛው እንደቀረች ትናገራለች። ልክ እንደማንኛዋም እናት ዛሬም ልጄ ድኖ ከጓደኞቹ እኩል ወጥቶ ይገባል እያለች ተስፋ የምታደርገው ሐሊማ በአሁኑ ሰዓት ሙሉ ተስፋዋን ያደረገችው ግን በፈጣሪዋ ላይ ነው። የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከልጇ ጋር ሆስፒታል ላለፉት 12 አመት ማሳለፏን እያነባች የምትናገረው ሃሊማ የልጇን ነፍስ ለማቆየት የተሰካኩለት የህክምና መሳሪያዎች የተሻለ ህክምና አግኝቶ ጤናው አለመስተካከሉ እና ጉዳዩን በዲፕሎማሲም ሆነ በህጋዊ መንገድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሊረዳት ባለመቻሉ ሀዘኗን እንዳበረቱት አልሸሸገችም። የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሚገኘው ሪያድ እንደሆነ የምትናገረው ሃሊማ ሪያድ ድረስ ሄዳ ጉዳይዋን አቤት ማለቷን እንዲሁም ጅዳ ለሚገኘው ቆንስላም ማሳሰቧን ታስታውሳለች። ነገር ግን እኔ ዞር ስል ይረሱታል ስለዚህ ምንም ሊፈይዱልኝ አልቻሉም ብላለች። በተደጋጋሚ አቤቱታ እና ውትወታ ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ጉዳይዋን ለሀገሪቱ ጤና ጥበቃ ያቀረበችው ሃሊማ የልጇ ጤንነት አሁን ያለበት ሁኔታ ላይ የደረሰው ሙሉ በሙሉ በህክምና ስህተት እንደሆነ አረጋግጠውላታል። የመሃመድን ህክምና ስህተት የመረመረው የሳኡዲ አረቢያ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሀኪሞች ቦርድ ለልጇ ጤና ካሳ ይሆን ዘንድ በማለት 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሪያል እንዲከፈላት ወስኖላት ነበር። በወቅቱ ሃሊማ ከብሩ ይልቅ የልጇን ጤና ስላስቀደመች አልቀበልም ማለቷን ትናገራለች። የዚህን ውሳኔ ማህተም ያረፈበት ደብዳቤ እንኳ የኢትዮጵያ ቆንስላ መውሰድ እንዳልቻለ የምትናገረው ሃሊማ የኔ ጉዳይ በቆንስላ ውስጥ አመድ ለብሷል ስትል ታማርራለች። ይህ ውሳኔ ከተሰጠ ሦስት ዓመት ቢሆነውም ቆንስላው ተከታትሎ ማስፈፀም እንዳልቻለ እንዲሁም የሚገባትን ካሳ ማግኘት እንዳልቻለች ትናገራለች። በሳኡዲ አዲስ ህግ ወጥቷል የምትለው ሃሊማ በዚህ ህግ መሰረት ለልጇ ህክምና መክፈል ይጠበቅባታል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ለልጇ መክፈልም ሆነ የጤናውን ሁኔታ መከታተል ስላልቻለች የተወሰነላትን ክፍያ አግኝታ ወደ ሃገሯ መግባት ትፈልጋለች። "ዓለም መከራ ናት" የምትለው ሃሊማ አሁን ልጇን ዶ/ር አይከታተለውም ነርስም አልተመደበለትም። ሕልሜ በሌላ ሀገር የተሻለ ህክምና እንዲያገኝ እና እንዲድን ነበር ትላለች። ''ከዚህ ውጭ ግን የልጄን ጤንነት የነጠቀው ዶ/ር ተቀጥቶ፣ ያወጣሁት ወጪ ተከፍሎኝ እና ለደረሰብኝ ስቃይ ተክሼ ወደ ሀገር ቤት ብገባ እና ልጄን ለሀገሬ አፈር ባበቃው ምኞቴ ነው'' ትላለች ከማያቆመው እንባዋ ጋር እየታገለች። በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው ኑሯቸውን በሳኡዲ ያደረጉት አቶ ነብዩ ሲራክ የሃሊማን ልጅ ታሪክ ከሰሙ መቆየታቸውን ይናገራሉ። የሃሊማ ታሪክ በህግ በአግባቡ ቢያዝ እና የሚከታተልላት አካል ቢኖር 12 ዓመት ሥራ መፍታቷ፣ ያወጣችው ወጪ ተሰልቶ እስከ 15 ሚሊዮን የሳኡዲ ሪያል ሊከፈላት ይችላል ይላል። ነገር ግን ብቸኛ መሆኗ እና የሚከታተልላት ወገን መጥፋቱ ፈተናዋን እንዳበረታባት ይናገራል።
news-46675590
https://www.bbc.com/amharic/news-46675590
የሪፐብሊኩ ጠባቂ ሃይል መቋቋም ምን ያመለክታል?
ህገመንግስቱንና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ሊሰነዘሩ ከሚችሉ ጥቃቶች እንዲጠብቅ የተቋቋመው የሪፐብሊኩ ጠባቂ ሃይል ምስረታ ይፋ ሆኗል።
እሁድ ታህሳስ 14 ቀን 2011 ዓ.ም የጥበቃ ሃይሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ትርኢት አሳይቷል። ይህ የሪፐብሊኩ ጠባቂ ሃይል ከፍተኛ ባለስልጣናትንና ቤተሰቦቻቸውን ከተለያዩ ጥቃቶች እንደሚጠብቅም ተገልጿል። የዚህ አይነቱ የሪፐብሊክ ጠባቂ ሃይል በአፍሪካ የተለመደ እንዳልሆነ በደረግ የኤርትራ ገዥ የነበሩት ከዚያም ከስምንት በላይ የሚሆኑ የአፍሪካ አገራትን በፀጥታ ጉዳይ ያማከሩት ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ ይናገራሉ። ሻለቃ ዳዊት ከ33 ዓመታት ስደት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት ከጥቂት ቀናት በፊት ነው። • "ሕዝብ እንዲጠይቅ አድርገናል" ዋና ኦዲተር ገመቹ ዱቢሶ • በምዕራብ ኦሮሚያ በታጠቁ ኃይሎች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 41 መድረሱ ተገለፀ ቢሆንም ግን የዚህ አይነት ተቋማት በአንዳንድ አገራት መኖራቸውን ይገልፃሉ። በዚህ ረገድ በግርማዊ ቀዳማዊ ሃይለ ሥላሴ ክቡር ዘበኛ ተብሎ የተቋቋመውን ቡድን በቀዳሚነት ይጠቅሳሉ። መደበኛ ሰራዊት ስራውን ሲሰራ ክቡር ዘበኛ ደግሞ የመንግስትንና የንጉሱን ደህንነት ይጠብቅ እንደነበር ፤ በተመሳሳይ በኢራን የገዥው ፓርቲንና መንግስትን የሚጠብቅ የሪፐብሊክ ጠባቂ ቡድን እንዳለ ይናገራሉ። የኢራኑ የሪፐብሊክ ጠባቂ ሃይል ግን በብዙ ውጊያዎች ላይ እንደሚሰማራ ገልፀዋል። የእንግሊዙን የንጉሳዊያን ጠባቂ ሃይልን በምሳሌነት ይጠቅሳሉ። እነዚህ የጥበቃ ሃይላት ዋንኛ ስራቸው መንግስትንና ባለስልጣናትን መጠበቅ ነው። ትናንት ትርኢቱን ያሳየው የኢትዮጵያው የሪፐብሊክ ጠባቂ ቡድንም ከዚህ የተለየ ተልዕኮ እንደማይኖረው ነግረውናል። በሌላ በኩል የአሜሪካ ፌደራል መንግሥት ሕግ አስከባሪ ኤጀንሲዎች መካከል ልዩ ኃይል የሆነው ሴክሬት ሰርቪስ ከሪፐብሊኩ ጠባቂ ኃይል ጋር ተመሳሳይ ተግባራት አለው። የአሜሪካው ሴክሬት ሰርቪስ ፕሬዝዳንቱን እና ቤተሰቦቻቸውን ብቻ ሳይሆን ምክትል ፕሬዚዳንት፣ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶችን፣ ዕጩ ፕሬዝዳንቶችን እና ቤተሰቦቻቸውን እንዲሁም በአሜሪካ ጉብኝት የሚያደርጉ የሃገራት መሪዎች ደህንነትን ይጠብቃል። የሪፐብሊኩ ጠባቂ ሃይል መቋቋም ምን ይጠቁማል? ከለውጡ በፊት በዚሁ መንግስት ተቋቁሞ የነበረው የአጋዚ ጦር ከሞላ ጎደል መሰል ተልዕኮ ይወጣ እንደነበር ሻለቃ ዳዊት ይናገራሉ። "አጋዚ ግን እነ መለስን እና ሌሎች የህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ ባለስልጣናትን ነበር የሚጠብቀው" የሚሉት ሻለቃ ዳዊት፤ የአጋዚ አደረጃጀት ከአንድ የፖለቲካ አመለካከት ብቻ የሚቀዳ ፤ የተልኮ ትኩረቱም አንድ ወገን ላይ ብቻ ስለነበር እሱን ከማቆየት መሰል ጦር የማቋቋም ፍላጎት እንደመጣ ይገልፃሉ። • ኦነግ ከመንግሥት ጋር ያደረኩት ስምምነት አልተከበረም አለ በአጠቃላይ በፌደራል ደረጃ የተቋቋመው ጦር ሃይል አመራሩ በአብዛኛው ከአንድ ወገን የመጣ በመሆኑ ይለወጥ ቢባል እንኳን ጊዜ ይወስዳል ፤ ከዚህ ባሻገርም ለውጡን ያለመቀበል ነገር መኖሩም ሌላ የማያስኬድ ነገር እንደሆነ ያስረዳሉ። ስለዚህም በዚህ ሁኔታ ውስጥ ይህን የሪፐብሊክ ጠባቂ ሃይል ማቋቋም አስፈላጊና ተገቢ እንደሆነ ያምናሉ። ውሳኔው በአጠቃላይ "ለመንግስትና ለባለስልጣናት የግል ጥበቃ ጦሩ እንደማያስተማምን" ማሳያ ሊሆን እንደሚችልም ምልከታቸውን አስቀምጠዋል።
news-43284714
https://www.bbc.com/amharic/news-43284714
ፍቅር እና ግንኙነት ከቲንደር አብዮት በኋላ
ምን ያህል ጥንዶች በበይነ-መረብ በዘንድሮው የፍቅረኞች ቀን ተገናኙ? 'ከዚህ ቀደሙ የሚበልጥ' የሚለው ምላሽ ችግር የሌለው መልስ ነው። ምክንያቱም በበይነ-መረብ ፍቅረኛን የማፈላለግ ሥራ በመላው ዓለም በመጠናከሩ ነው።
ግን በይነ-መረብ የፍቅር ጓደኛን ለማግኘት ምርጡ መንገድ ነው? በቀጣይ የኮምፒውተር መረጃ ከማን ጋር በፍቅረኛነት አብረው እንደሆኑ እና ምን ያህል ጊዜ አብረው እንደቆዩ ማወቅ ይቻላል። ይህ እንደሚሆን ከወራት በፊት ብላክ ሚረር በተሰኘው የቴሌቪዥን ተከታታይ ፕሮግራም ተገልጿል። ከወዲሁ ግን ቴክኖሎጂ ፍቅርን ቀይሮታል። በ1990ዎቹ አጋማሽ ማች ዶት ኮም ከጀመረው በኋላ በበይነ-መረብ ፍቅረኛን መፈለግ በከፍተኛ ደረጃ ተስፋፍቷል። እንደቲንደር ያሉ መተግበሪያዎች ደግሞ እንደአዲስ ለመቀላቀል ቀላል በመሆናቸው እና ፍቅረኛ የመፈለግን አካሄድ በማቅለላቸው ወደሌላ ደረጃ አድርሰውታል። ቲንደር የስማርት ስልኮች መምጣትን ተከትሎ በአውሮፓዊያኑ 2012 ነበር የተጀመረው። ከሁለት ዓመት በኋላ በቀን ሁለት ቢሊዮን ጎብኚዎችን ማግኘት ችሏል። ባለፈው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዴሞክራቶች ለምርጫ ቅስቀሳም ይህንኑ ተጠቅመውበታል። የ24 ዓመቷ ጦማሪ ጆርዳን ብራውን እንደምትለው በአውሮፓዊያኑ 2016 በይነ-መረብን በመጠቀም ነበር ከምትኖርበት አካባቢ ብዙም የማይርቀውን ፍቅረኛዋን ያገኘችው። ይህ ባይሆን ኖሮ ላይገናኙ እንደሚችሉ ጠቅሳ ሁለቱም ዲዝኒን መውደዳቸው ደግሞ ይበልጥ እንዳቀራረባቸው አስታውቃለች። የ30 ዓመቷ ሳራ ስካረሌት በአውሮፓዊያኑ 2015 ወደ ዱባይ ስታቀና ከአዳዲስ ሰዎች ጋር ለመገናኘት ነው የቲንደር አባል የሆነችው። የቀድሞ የወንድ ፍቅረኛዋንም ከአንድ ወር በኋላ ነበር ያገኘችው። ከምታወራቸው ሰዎች ጋር መገናኘት ግን አስቸጋሪ መሆኑን ጠቅሳለች። "ለረዥም ጊዜ ከእነሱ ጋር የጽሑፍ መልዕክት ብትለዋወጥም ተገናኝቶ ቡና ለመጠጣት እንኳን ፍላጎት የላቸውም" ትላለች። ሌሎችም አስቸጋሪ ሁኔታዎች እንዳሉ ጆርዳን ትናገራለች። "በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዓታቸውን ለማጥፋት የሚፈልጉ እና ሥራ ፈቶች ስላሉ ኑሮህን ከማዘበራረቅ ውጭ ምንም አይሰሩም" ብላ የታዘበችውን ትገልጻለች። ከእነዚህ ሁሉ ችግሮች ጋርም ቢሆን ፍቅረኛን ማፈላለጊያ በይነ-መረቦች በከፍተኛ ደረጃ እያደጉ ነው። አፕ አኒ እንደተባለ ተቋም ጥናት ከሆነ በአውሮፓዊያኑ 2016 በእነዚህ በይነ-መረቦች 234 ቢሊዮን ፓውንድ ወጪ የተደረገ ሲሆን ይህ አሃዝ በ2017 ወደ 448 ከፍ ብሏል። 59 በመቶ የሚሆኑ አዋቂዎች ፍቅረኛን ማፈላለጊያ በበይነ-መረቦች አዳዲስ ሰዎችን ለማግኘት ጥሩ ናቸው ብለው እንደሚያምኑ የፒው ጥናት ይጠቁማል። በበይነ-መረብ ጥንዶችን ማፈላለጊያ መንገዶች በተለይም የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በሞት በሚያስቀጣባቸው ሃገራት ላሉ የተመሳሳይ ጾታ ጥንድ ፈላጊዎች ጠቃሚ መሆኑን ግራይነደሩ ጃክ ሃሪሰን-ኩይታና አስታውቀዋል። በአፕ አኒ ውስጥ ዳይሬክተር በመሆን በማገልገል ላይ የሚገኙት ፖል ባርነስ እንደሚሉት እንግሊዝ ውስጥ ባለፈው ዓመት ተገልጋዮች በብዛት ከተጠቀሟቸው 10 መተግበሪያዎች ውስጥ ሶስቱ የፍቅረኛ ማፈላለጊያ መተግበሪያዎች ናቸው። "እዚህ በጣም ብዙ ገንዘብ ስላለ አሁን በጣም ብዙ ፉክክርም አለ" ይላሉ ባርነስ። "ስለዚህ መተግበሪያ ሰሪዎች ተጠቃሚዎቻቸውን በደንብ ማወቅ እና በይበልጥ የሚሳተፉበትን መንገድ ሊፈጥሩ ይገባል" ብለዋል። ቀደም ሲል የፍቅረኛ የማፈላለግ አገልግሎት ሰጪዎች አባል መሆን የሚፈልጉ በጣም ብዙ ጥያቄዎችን እንዲመልሱ ይጠብቁባቸው ነበር። አሁን ግን ማሽኖች የበለጠ ሊስማሙ የሚችሉ ተፈላላጊዎችን በማገናኘቱ በኩል ይሰራሉ። ትዊተር ላይ አንድ ሰው የሚጽፈውን ከ300 እስከ 400 የሚደርስ ቃል ያለውን ነገር በማገናዘብ ማሽኑ ምን ያህል ሁለት ሰዎች የጋራ ነገር እንዳላቸው ለማወቅ ይችላል ይላሉ የላቭፍላተር ተባባረሪ መስራች ዲያጎ ስሚዝ። ላቭፍላተር መቀመጫውን ቶሮንቶ ካደረገ እና ሪሲፕቲቪቲ ከተሰኘ የቋንቋ ጥናት ተቋም ጋር በመቀናጀት የሚመሳሰሉ ሰዎችን ለመለየት የሚያሰችላቸውን አዲስ ዘዴ ፈጠሩ ሲሆን በዘንድሮው ዓመትም ተግባራዊ ይደረጋል። ይህም በኦስቲን ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊ ስነልቦና ፕሮፌሰር የሆኑት ጀምስ ፔንቤከር ጥናት እንዲያደርጉ አነሳስቷቸዋል። ፕሮፌሰር ፔንቤከር በ86 ጥንዶች ላይ ባደረጉት ጥናት ተመሳሳይ ቃላትን፣ ሀረጎችና እና ሌሎች የቋንቋ አጠቃቀሞችን የሚጋሩት ከሶስት ወራት በላይ አብረው የመቆታቸው ዕድል ከፍተኛ ነው። ሌላኛው ዘዴ ደግሞ ስማርት ስልኮችን ቦታ ጠቋሚ በመጠቀም ጥንዶችን የማገናኘት ስራ ነው። መቀመጫውን ፓሪስ ያደረገው ሃፕን የተሰኘ የመተግበሪያ ተቋም ቀኑን ያሳለፉበትን አካባቢ ያጣናል። ከዚም ከእርሶ በ250 ሜትር ርቀት ውስጥ ያለፉ ሰዎችን ማንነት ያሳይዎታል። እነዚህን ሰዎች በእውኑ ዓለም ማግኘት በጣም ቀላል መሆኑን የተቋሙ ባልደረባ የሆኑት ክሌይር ሰርቴይን ይገልጻሉ። "ዋናው ነገር መገናኘት እና መሞከር ነው። የተገናኙት ሰዎች መጣጣም ወይም አለመጣጣማቸው ምስጢራዊ እና በጣም አስገራሚ ነገር ነው።" ሆኖም በቅርብ ርቀት መኖር የትዳር አጋርን መፈለግን ችግር ሚፈታው ከሆነ ባለን ማህበራዊ አካባቢ ብቻ እንድንታጠር ያደርገናል ሲሉ የሶሶሊጂ ባለሙያው ጁስዉ ኦርቴጋ ያስጠነቅቃሉ። በበይነ-መረብ ፍቅረኛን ማፈላለግ ከተለያየ ዘር የመጡ ሰዎችን እያገናኘ መሆኑን ጠቁመዋል። በካምብሪጅ ዩኒቨርሰቲ የማስተርስ ተማሪ እያለች ስለቲንደር ያጠናችው ራቼል ካትዝ አሁን ደግሞ ለዶክተሬት ዲግሪዋ በግራይነደር ዙሪያ እያጠናች ሲሆን በሃሳቡ ትስማማለች። "በአንድ ወቅት ሰዎች በአቅራቢያቸው ከሚገኙ ሰዎች ጋር ብቻ ነበር የሚጋቡት። በይነ-መረብ ከመስፋፋቱ ጋር ተያይዞ ይህ ነገር ከየትኛውም ዓለም ክፍል ካሉ ሰዎች ጋር ሊሆን ችሏል።" በ2018 ደግሞ የመኖሪያ አካባቢ አሁንም በድጋሚ ወሳኝ ጉዳይ ሆኗል ይላሉ ካትዝ። "ስለዚህ በጣም ከሚቀርብዎት ሰው ጋር ይገናኛሉ ማለት ነው። ይህ ደግሞ የደረጃ ልዩነትንም ያካትታል።" እንደባለሙያዎች ከሆነ የትዳር አጋርን የሚያገናኙ በይነ-መረቦች ከፍተኛ የቴክኖሎጂ አሠራሮችን ያካተቱ ይሆናሉ ይላሉ። አስቡት እስኪ በመዝናኛ ስፍራ ያሉትን ሰዎች በስልክዎ ስካን በማድረግ በይነ-መረብ ፍቅረኛ ለመፈለግ መመዝገብ አለመመዝገባቸውን ማወቅ ይችላሉ ሲሉ ክሌር ሰርቴይን ይገልጻሉ። በእነዚህ የበይነ-መረብ ፍቅረኛ ማፈላለጊያ መተግበሪያዎች ላይ ከሚነሱት ችግሮች መካከል ለሴቶች ምቹ አይደሉም መባሉ ነው። የዋንስ ዴቲንግ መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ ጂን ሜየር እንደሚሉት በፍቅረኛ ማፈላለጊያ በይነ-መረቦች ላይ የሚገኙ ሴቶች ቁጥር ከ35 በመቶ በጭራሽ በልጦ አያውቅም ይላሉ። ወንዶችም አንዳንድ ጊዜ እንደወንዶች ራሳቸውን አያቀርቡም። በእነሜየር መተግበሪያ ላይ ሴቶች ስለሚገጥሟቸው ሴቶች ግብረ-መልስ ይሰጣሉ። ወንዶች ከእነዚህ ምላሾች ሊማሩ ይችላሉ ሲሉ ይገልጻሉ። ቀድሞ የቲንደር ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ዎልፍ ሄርድ የመጀመሪያ ግንኙነታቸውን ከወንድ ጋር ባደረጉ ሴቶች ዙሪያ የሚሰራ በምብል የሚል መተግበሪያ ይፋ አድርገዋል። ከ85 በመቶ በላይ የሚሆኑት የድርጅቱ ሠራተኞች ሴቶች ሲሆኑ እንደፎርብስ ምጽሔት ከሆነ የድርጅቱ ዋጋ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ተገምቷል። ስለዚህ በበይነ-መረብ ፍቅረኛን ከመፈለግ ቀጠሎ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ተጨምረውበት ቢያስደምሙንም ወደ ፍቅር ስንመጣ ግን ምንም ዋስትና አይሰጡም።
news-46354439
https://www.bbc.com/amharic/news-46354439
ናሳ የማርስን ውስጣዊ አወቃቀር ለማጥናት ሮቦት ላከ
የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ኤጀንሲ ናሳ ከሰባት ደቂቃ መንጠር በኋላ የላካት ሮቦት በቀይዋ ፕላኔት ወይም ማርስ ላይ በሰላም አርፋለች።
ዘ ኢንሳይት ፕሮብ የተባለችው ይህች ሮቦት አላማ አድርጋ ያነገበችውም የማርስን ውስጣዊ አወቃቀር ጥናት ለማድረግ ነው። ማርስ ላይ ጥናት ሲደረግ ከመሬት ቀጥሎ ሁለተኛ ፕላኔት ያደርጋታል። የሮቦቷም ማርስ ላይ ማረፍ የተሰማው ከምሽቱ አምስት ሰዓት አካባቢ ሲሆን ይህም በጭንቀት ሲጠብቁ ለነበሩት ከፍተኛ እፎይታን ፈጥሯል። •ወ/ሪት ብርቱካን በወዳጆቻቸው አንደበት •በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ወደ ፅዮን ውሰዱን ተማፅኖ •የጋና ቅንጡ የሬሳ ሳጥኖች በናሳ ካሊፎርኒያ ጄት ፕሮፐልሺን ላብራቶሪ ተሰስብበው የነበሩ ሳይንቲስቶችም ሮቦቷ ማርስ ላይ በሰላም ማረፏን ሲያዩ በደስታ እንደፈነጠዙ ተዘግቧል። የናሳ ዋና አስተዳዳሪ ጄምስ ብሪደንስታይን "የሚያስገርም ቀን ነው" ባሉት በዚህ ዕለት ደስታቸው ከፍተኛ እንደሆነም ገልፀዋል። ፕሬዚዳንት ትራምፕም እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንደደወሉላቸውም ጨምረው ገልፀዋል። የካሊፎርኒያ ጄት ፕሮፐልሺን ላብራቶሪ ዳይሬክተር ማይክ ዋትኪንስ በበኩላቸው "ይህ ስኬት ሁላችንንም ሊያስታውሰን የሚገባው ደፋርና የተለያዩ ቦታዎችን ልናስስ እንደሚገባን ነው" ብለዋል። ኢንሳይት ሮቦት በአሁኑ ወቅት ኤልሲየም ፕላኒሺያ በተባለው ሰፊ ሜዳማ ቦታ ያረፈች ሲሆን ይህም ከቀይዋ ፕላኔት (ማርስ) ምድር ወገብ ተጠግታ መሆኑም ተገልጿል። ሮቦቷ ከማረፏም በፊት ናሳ ቦታውን በማርስ ትልቁ የፓርኪንግ ቦታ ሲል ጠርቶታል። ወዲያው ሮቦቷ እንዳረፈች በደቂቃ ውስጥ በሮቦቷ የተነሳው ፎቶ ደብዘዝ ያለ ቢሆንም በኋላ ግን ጥርት ያለ ፎቶ መላኳ ተዘግቧል። ሮቦቷ የመጀመሪያዋ ምርምር የሚሆነው የማርስ ውስጣዊ አወቃቀርን ማጥናት ይሆናል። በዚህም ጥናት ድንጋዮች ከምን እንደተሰሩ፣ የፕላኔቷን የሙቀት መጠንና እንዲሁም ማርስ በፈሳሽ ወይም በጠጣር የተሞላች ፕላኔት ነች ለሚለው ምላሽ የሚሰጥ ይሆናል።
news-47550396
https://www.bbc.com/amharic/news-47550396
"ማብረርን ወደላቀ ደረጃ የማድረስ ህልም ነበረው"የረዳት አብራሪው አህመድ ኑር ጓደኛ
በቅርቡ የተከሰከሰው ቦይንግ 737 ማክስ 8 ረዳት አብራሪ የነበረው አህመድ ኑር ፓይለት ከመሆኑ በፊት በልደታ ህንፃ ኮሌጅ በአርክቴክቸር የትምህርት ክፍለ ዘርፍ እንደተመረቀ የሚናገረው በተቋሙ ሲማር በነበረበት ወቅት የዩኒቨርስቲ ጓደኛው የነበረው ፈክሩዲን ጀማል ነው።
ከጓደኝነት በተጨማሪ በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው ለሶስት አመታት ያህል በአንድ ዶርም ውስጥ አድረዋል። አህመድ ኑርን ለመግለፅ ቃላት ያጠረው ፈክሩዲን "አህመድ ኑርን ለመግለፅ ይከብዳል። በጣም የተረጋጋ ሰው ነበር። ምንም ነገር ሲያደርግ በጣም ተረጋግቶ ነው። ትዕግስተኛ ነው" ይላል። •"የሞተው የኔ ያሬድ ነው ብዬ አላሰብኩም" የካፕቴን ያሬድ የ11 አመት ጓደኛ ፈክሩዲን እንደሚናገረው የአርክቴክቸር ትምህርት ፈታኝ ቢሆንም "አህመድ ኑር በተረጋጋ መንፈስ ነገሮችን ስለሚያከናውን ትምህርቱ እንደፈተነው መገመት ይከብዳል።" ይላል። ለጓደኞቹ ፈጥኖ ደራሽ ነበር የሚለው የሰባት አመት በላይ ጓደኛው ፈክሩዲን "ማብረርን እንደ ጥናት ሳይሆን ወደላቀ ደረጃ የማድረስም ህልም ነበረው" ብሏል። አብዛኛውን ጊዜም ስለበረራ ለጓደኞቹ ሲያስረዳ በአይነ ህሊናቸው እንዲታያቸው አድርጎ በጥልቀት እንደሚተነትንም ይገልፃል። •ለ60 ዓመታት የዘለቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድና የቦይንግ ግንኙነት "በሕይወቱ አቋራጭ ነገር ሲጠቀም አይቼው አላውቅም" ሁልጊዜም በአንድ ጉዳይ ላይ የጠለቀ እውቀት እንዲኖረው ስለሚፈልግም ጊዜውን እንደሚሰጥ ይናገራል። ልደታ ተማሪ በነበረበትም ወቅት ለማብረር ከፍተኛ ፍቅር እንደነበረው የሚናገረው ፈክሩዲን በህይወቱ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች አትኩሮት ሰጥቶም እንደሚከታተል ይገልፃል። በማያጠናበት ወቅት እግር ኳስ ይጫወት የነበረ ሲሆን፤ ለቀድሞ የአማርኛ ሙዚቃዎች ለየት ያለ ፍቅር ነበረው። " እኩል እድሜ ላይ ብንሆንም እኛ የማናውቀውን ሙዚቃ ይዘፍንና ይሄ ልጅ ግን መቸ ነው የተወለደው ያስብለን ነበር።" በማለት ፈክሩዲን ይናገራል። ድሬዳዋ ተወልዶ ያደገው የ26 አመቱ አህመድረ ኑር ወደ አዲስ አበባ የመጣውም በዩኒቨርስቲ ድልደላ በምህንድስና የትምህርት ዘርፍ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተመድቦ ነው። •ኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬም ስኬታማ ነው ተማሪ ሳሉ አዘውትሮ ቤተሰቦቹን ሊጎበኝ ድሬዳዋ ይመላለስ እንደነበር ያስታውሳል። ከትምህርት ቤት ተመርቆ ከወጣ በኋላና የበረራ ትምህርቱን ከጀመረም ሆነ ማብረር ከጀመረ በኋላ በተቻለ መጠን ይገናኙ እንደነበር የሚናገረው ፈክሩዲን "ገና ጎጆ መውጣቱም ስለነበር፤ አብዛኛውን ጊዜ ወደኛ ቤትም ይመጣል። ከትምህርት አለም ወደስራ መግባቱም ስለነበር ብቻውን ነበር የሚኖረው።" ብሏል። ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት ከበረራው አንድ ቀን ቀደም ብሎ ቅዳሜ እለት ሲሆን የህንፃ አጨራረስ ቀለምና ጂፕሰም ላይ የሚሰራ ሌላ ጓደኛውን ከነ ፈክሩዲን ጋር ለማገናኘት ነበር። "ቆይና ነገ ትሄዳለህ ብንለውም ነገ ወደ ኬንያ እበራለሁ ብሎን ወደ አመሻሹ 12 ሰአት ላይ ወደ ሰሚት ሊሄድ ተለያየን።" ይላል። ከዚያም በኋላ ዜናውን የሰማው ኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሚሰራ ትልቅ ወንድሙ ጋር እሁድ እረፋፈዱ ላይ ቁጭ ብለው ቴሌቪዥን በመመልከት ላይ በነበሩበት ወቅት ነው። ወንድሙ የአደጋውን ዜና በኢንተርኔት ሲያይ በጣም ደነገጠ መጀመሪያ ያየውም ካፕቴን ያሬድን ነው። "ካፕቴን ያሬድን አቀዋለሁ፤ ልጅ ነው። አብሬው ሁሉ በርሬ አውቃለሁ፤ ደስ የሚል ሰው ነው ብሎ ነገረኝ" ፈክሩዲን ቀጥሎም በረራው የት ነበር ብሎ ሲጠይቀው ወንድሙም ኬንያ ብሎ መለሰለት "በጣም ብደነግጥም በረራው ጠዋት እንዳልሆነ ራሴን አሳመንኩኝ፤ እሱ አለበት የሚለውንም ላለማመን ምክንያት ለራሴ ፈለግኩኝ። በቀን የተለያዩ በረራዎች ስላሉ በሌላኛው ይሆናል አልኩኝ" የሚለው ፈክሩዲን በዛው ሳያቆምም ለማጣራት ብዙ ጥረቶችን ማድረግ ጀመረ። በመቀጠልም ጓደኞቹ ደዋውለው የበረራ ሰዓቱ ጥዋት መሆኑን ተረዱ። በዛም መንገድ ነው አስደንጋጭ ዜናውን የሰማው። "ያው አምላክ ያመጣውን ነገር ምን ማድረግ ይቻላል፤ ለጓደኞቹ ብዙ ነገር ነው። በጣም እንደ አባት፣ ጓደኛ ፣ ወንድም የሚያዩት ነበሩ።" በማለት በሃዘን ገልጿል።
news-54164769
https://www.bbc.com/amharic/news-54164769
ጀርመን፡ የተመረዘው ሩስያዊ አሌክሲ ናቫልኒ ወደ ሩስያ ሊመለስ ነው
ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲንን አጥብቆ በመተቸት የሚታወቀው ሩስያዊው አሌክሲ ናቫልንሊ ወደ ሩስያ ሊመለስ መሆኑን ቃል አቀባዩ ተናገሩ።
አሌክሲ መመረዙን ተከትሎ ጀርመን ውስጥ ሕክምና ሲደረግለት ነበር። ቃል አቀባዩ ኪራ ያርሚሽ “ወደ ሩስያ አይመለስም ብሎ ማሰብ አስገራሚ ነው” ብለው ትዊት አድርገዋል። አሌክሲ ከተመረዘ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተነሳውን ፎቶግራፍ በኢንስታግራም ገጹ ላይ ለጥፏል። ፎቶው ላይ አሌክሲ በሀኪሞች ተከብቦ ይታያል። ያለ ቬንትሌተር ድጋፍ መተንፈስ መጀመሩንም ኢንስታግራሙ ላይ ጽፏል። አሌክሲ ነሐሴ 20 በረራ ላይ ሳለ ነበር ራሱን የሳተው። የተደረገለት ምርመራ እንደሚያሳየው፤ የተመረዘው ኖቪቾክ በተባለው ኬሚካል ነው። መመረዙ እንደታወቀ በርሊን ወደሚገኝ ቻርቴ የተባለ ሆስፒታል ተወስዷል። ከአሌክሲ ጋር የሚሠራው ቡድን እንደሚለው ከሆነ እንዲመረዝ ትእዛዝ ያስተላለፉት ፑቲን ናቸው። የፕሬዘዳንቱ አስተዳደር ግን እጄ የለበትም ብሏል። ከዚህ ቀደም የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ሩስያ ስለ ኖቪቾክ ፕሮግራሟ ለዓለም አቀፍ ተቆጣጣሪዎች መረጃ መስጠት ማለቱ ይታወሳል። የመብት ተሟጋቹ አሌክሴ ናቫልኒ መመረዙን ተከትሎ ሩስያ ስለ ኖቪቾክ ነርቭ ኤጀንት (መርዛማ ኬሚካል) መረጃ እንድትሰጥ ተጠይቃ ነበር። የኔቶ ጸሐፊ ጄንስ ስቶልበርግ አባላቱ ጥቃቱን አውግዘዋል ብለዋል። የመብት ተሟጋቹ በኖቪቾክ እንደተመረዘ “ማስረጃ አለ” ሲሉም አክለዋል። ሩስያ ግን ለአሌክሴ ሕክምና እያደረገ የነበረው ሆስፒታል የሰጠውን ማብራሪያ አጣጥላለች።
42743088
https://www.bbc.com/amharic/42743088
የካንሰር የደም ምርመራ "አሰደናቂ ውጤት" አስገኘ
ተመራማሪዎች በሕክምና ሳይንስ ትልቅ እመርታ ነው ያሉትን ለካንሰር አለም አቀፍ የደም ምርመራ እርምጃ ወሰዱ።
በጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ ስምንት ተመሳሳይ ጠባይ ያላቸውን በሽታዎች መለየት የሚያስችል ሙከራ አድርጓል። አላማቸው ካንሰርን ቀድሞ ማወቅና ሕይወትን ማዳን ነው፤ ምርምሩን የእንግሊዝ ባለሙያዎች "እጅግ በጣም አስደናቂ" ሲሉ ገልፀውታል። እጢዎች አነስተኛ የሆነ የዘረመልና የፕሮቲን አሻራቸውን በደማችን ውስጥ ትተው ያልፋሉ። የካንሰር ፍለጋው ምርመራ የሚመለከተው በተደጋጋሚ በካንሰር ወቅት የሚነሱ 16 ጅኖችንና ስምንት ፕሮቲኖችን ነው። በዘር እንቁላል፣ ጉበት፣ ሆድ ጣፊያ፣ ጉሮሮ፣ ትልቁ አንጀት፣ ሳንባ፣ ጡት ካንሰር ባለባቸው እና ወደ ሌሎች ቲሹዎች ባልተዛመተባቸው 1005 ሕሙማን ላይ ሙከራው የተደረገ ሲሆን፤ በአጠቃላይ 70 በመቶ የሚሆነው ምርመራ ካንሰር መኖሩን ያሳያል። የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የሕክምና ትምህርት ቤት ዶ/ር ክርስቲያን ቶማስቲ ለቢቢሲ እንደተናገሩት "ይህ ቀድሞ የመለየት ምርመራ ወሳኝ ነው፤ ውጤቱም በጣም አስደናቂ ነው" ብለዋል። "እንደሚመስለኝ ይህ ካንሰርን በማጥፋት ላይ ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል።" ካንሰር ቀድሞ ከተገኘ ለማከም ያለው እድል ሰፊ ነው። ምርመራ ከተደረገባቸው ከስምንት ካንሰሮች አምስቱ ቀድሞ የመለየት ምርመራ ፕሮግራም አልነበራቸውም። የጣፊያ ካንሰር አነስተኛ ምልክት ብቻ ስላለው ማወቅ የሚቻለው ከዘገየ በኋላ ስለሆነ ምርመራውን ካደረጉ አምስት ሕሙማን መካከል አራቱ በዛው አመት ይሞታሉ። በቀዶ ጥገና ሊወገዱ የሚችሉ እጢዎችን ማግኘት ለህሙማኑ "የቀን እና የለሊት ያህል ልዩነት አለው" ይላሉ ዶ/ር ቶማስቲ። "አሁን ካንሰር ሕመምን የመፈለግ ሙከራው የካንሰር ምርመራ አድርገው በማያውቁ ሰዎች ላይ ተሞክሯል። "ይህ ከጠቃሚዎቹ ምርመራዎች መካከል አንዱ ይሆናል። ተስፋ የሚደረገው ለጡት ካንሰር የሚደረገውን ማሞግራም እና ለአንጀት ካንሰር የሚደረገውን ኮሎኖስኮፒ አይነት ሌሎች ምርመራዎችን ያግዛል ተብሎ ነው።" ዶ/ር ቶማስቲ ለቢቢሲ እንደገለፁት "የደም ምርመራ በአመት አንዴ ይደረጋል ብለን ነው የምናስበው" በካንሰር ላይ በርካታ ምርምር የሚያደርጉትና የቡድን መሪ የሆኑት ዶ/ር ገርት አታርድ ለቢቢሲ እንዳሉት "ይህ በጣም ትልቅ አቅም ነው። በጣም ተደንቄያለሁ። ያለ ስካን ወይንም ያለኮሎኖስኮፒ በደም ምርመራ ብቻ ካንሰርን መለየት መቻል ትልቅ ሚስጥርን እንደመፍታት ነው።" አክለውም ""በጣም ተቃርበናል"ካንሰርን ለመመርመር የደም ናሙናን መፈተሽ የሚያስችል"ቴክኖሎጂውም አለን።" ነገር ግን አሁንም ካንሰሩ ከተገኘ በኋላ ምን መደረግ አለበት የሚለው ላይ ጥያቄ አላቸው። በአንዳንድ ሕመሞች የካንሰር ሕክምናው ከህመሙ ጋር ከመኖር የበለጠ በጣም ፈታኝ ነው። ለምሳሌ ወንዶች የዘር ፍሬ ካንሰር ሲኖርባቸው ቀስ በቀስ ስለሚያድግ ከሚታከም ይልቅ በቅርበት የህክምና ክትትል ማድረግ ይመከራል። "ካንሰርን በተለየ መልኩ ስናገኘው ሁሉም ሕክምና ያስፈልገዋል ብለን አንወስድም " ይላሉ ዶ/ር አታርድ።
news-46106683
https://www.bbc.com/amharic/news-46106683
በግብጻዊው የሊቨርፑሉ አጥቂ ሞሐመድ ሳላህ ቅርጽ የተሰራው ሃውልት መሳለቂያ ሆኗል
ምትሃተኛው የሊቨርፑል እና የግብጽ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጫዋች ሞሃመድ ሳላህ ቅርጽ ተሰራ የተባለው ሃውልት የበርካቶች መቀለጃ ሆኗል።
በስተግራ የሊቨርፑል እና የግብጽ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጫዋች ሞሐመድ ሳላህ በስተቀኝ በሞ ሳላህ ቅርጽ ተሰራ የተባለው ሃውልት ይህ የጥበብ ሥራ በግብጽ ሻርም አል-ሼክህ ስታዲየም ባሳለፍነው እሁድ ነበር ለህዝብ ይፋ የተደረገው። የፊት መስመር ተጫዋቹ ጎል ካስቆጠረ በኋላ ደስታውን የሚገልጽበትን ሁኔታን ያሳያል ተብሏል። ቅርጹ ሞ ሳላን ስለመምሰሉ ግን ብዙዎች እየተጠራጠሩ ነው። • የውድድር ዘመኑ ምርጥ 11 • ሊቨርፑል ሞ ሳላህን ለፖሊስ አሳልፎ ሰጠ በሞ ሳላህ ምስል ተሰራ የተባለው ሃውልት ከዚህ ቀደም በክርስቲያኖ ሮናልዶ ቅርጽ ተሰራ ከተባለው ሃውልት ጋር ሰዎች እያነጻጸሩት ይገኛሉ። ይህን የጥበብ ሥራ የሰራችው ቀራጺዋ ማያ አብደላህ ለግብጽ መገናኛ ብዙሃን ''ይህን ልዩ የሆነ'' የጥበብ ሥራ የሰራሁት ሞሐመድ ሳላህ ለግብጻውያን ወጣቶች የስኬታማነት ምልክት አድርጌ ስለምወስደው ነው ብላለች። ማያ በፌስቡክ ገጿ ላይ ባሰፈረችው ጽሑፍ የቅርጹ የመጨረሻ ውጤት ከመጀመሪያ እንደተለየ ገልጻ ''ሰዎች የሚሰጡት አስተያየት ትህትናና ክብር የተሞላበት እንደሚሆን ተስፋ አለኝ'' ብላለች። ሞ ሳላህ በትዊተር ገጹ ላይ ቅርጹን በተመለከተ ተሳልቋል። የሞ ሳላህ ቅርጽ ይፋ የተደረገው የግብጽ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታ አልሲሲን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳሚዎች በተገኙበት ነው።
50093599
https://www.bbc.com/amharic/50093599
በአውስትራሊያ የውድድር ፈረሶች እየታረዱ ነው በሚል የቀረበው ውንጀላ ላይ ምርመራ ተጀመረ
በአውስትራሊያዋ ኩዊንስላንድ ግዛት ውስጥ በሚገኝ የእርድ አገልግሎት መስጫ- ቄራ ውስጥ ፈረሶች ሲጉላሉና ሲጎሳቆሉ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በኤቢሲ የቴሌቪዥን ጣቢያ ከተላለፈ በኋላ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል።
በቴሌቪዥን ጣቢያ የተሰራ ዘገባ እንደሚያሳየው ከግልቢያ ውድድር የሚገለሉ ፈረሶች እየታረዱ መሆናቸውን ነው። በአውስትራሊያ ፈረሶችን ማረድ ሕጋዊ ቢሆንም በአንዳንድ ግዛቶች ግን ከውድድር በጡረታ የተገለለ ፈረሶች ወደ ሌላ የእንስሳት ማቆያ እንዲዛወሩ ብቻ ይፈቅዳሉ። በአውስትራሊያ የፈረስ ግልቢያ ተወዳጅ ስፖርት ሲሆን ከፍተኛ ገንዘብም ይገኝበታል። • የትግራይ ክልል አዲስ ገቢ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ወደ አማራ ክልል አንደማይልክ አስታወቀ • ሜክሲኮ ውስጥ የኤል ቻፖን ልጅ ለመያዝ ከባድ ውጊያ ተደረገ • "አሁን ያለው ሁኔታ ከቀጠለ ነገ ወደ እርስ በርስ ጦርነት እንደሚገባ ግልጽ ነው" አቦይ ስብሃት ባለስልጣናት በቅርቡ ከሚካሄደው የፈረስ ግልቢያ ውድድር አስቀድሞ የቀረበውን ይህንን ውንጀላ አስመልክተው በሰጡት ምላሽ "አስደንጋጭ" ብለውታል። "እንስሳትን ማጎሳቆልና ማንገላታት አስነዋሪ ተግባር ነው" ያሉት የኪዊንስላንድ የግልቢያ ውድድር ሚኒስትር ስተርሊንግ ሂንቺልፍ ናቸው። የአካባቢው አስተዳደር በኤቢሲ ዘገባ ላይ ወደ ተጠቀሰው የእርድ አገልግሎት መስጫ ባለሙያዎችን ወዲያውኑ መላካቸውን አስታውቀዋል። የእርድ አገልግሎት በሚሰጠው በዚህ ቄራ ውስጥ በ22 ቀን ብቻ 300 የውድድር ፈረሶች መታረዳቸው በቴሌቪዥን ጣቢያው ዘገባ ላይ ተጠቅሷል። ዘገባው አክሎም ፈረሶች በዚህ ቄራ ውስጥ ይመታሉ፤ ይንገላታሉ ሲል ይጠቅሳል። የአውስትራሊያ የፈረስ ግልቢያን የሚያስተዳድረው አካል ፈረሶች ጡረታ ወጥተው ከውድድር ከራቁ በኋላ እምጥ ይግቡ ስምጥ ማወቅ አልቻልኩም ሲል ተናግሮ ነበር። ይህንን መዝግቦ በመያዝ የሚከታተል አካል በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲቋቋምም ሃሳብ አቅርቦ ነበር። የፈረስ ግልቢያ ውድድር የሚያካሂደው አካል በእንስሳት መብት ተሟጋቾች ለዓመታት ይብጠለጠል ነበር። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በቅርቡ የሚካሄደውን የፈረስ ግልቢየያ ውድድር ይታደሙታል ተብሎ ይጠበቃል።
44896314
https://www.bbc.com/amharic/44896314
ዶናልድ ትራምፕ ፑቲን አሜሪካን እንዲጎበኙ ጋበዟቸው
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሩሲያው መሪ ቭላድሚር ፑቲን በፀደይ ወቅት አሜሪካን እንዲጎበኙ እንደጋበዟቸውን የዋይት ሀውስ አፈ ቀላጤ አስታወቁ።
በሩሲያ በኩል እስካሁን ምንም የተባለ ነገር የለም ሳራ ሳንደርስ ጉብኝቱን በተመለከተ ንግግሮች መጀመራቸውንም ገልፀው ሁለቱ መሪዎች ከጥቂት ቀናት በፊት በፊንላንድ ሄልሲንኪ ተገናኝተው የተወያዩ ሲሆን የተወያዩባቸውን ዝርዝር ጉዳዮች ይፋ ሳያደርጉ ቀርተዋል። ሁለቱ መሪዎች መገናኘታቸውን ተከትሎ ትራምፕ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተናገሩት ነገር ውዝግብ አስነስቶ የነበረ ቢሆንም ሰውየው ግን በመጨረሻ ውይይቱ በስኬት መጠናቀቁን ተናግረዋል። ከዚያም በቀጣይ እንደገና እንደሚገኛኙ ቢያመለክቱም እስካሁን በሩሲያ በኩል ትራምፕና ፑቲን ዳግም ሊገናኙ ስለመሆኑ የተባለ ነገር የለም። የፑቲን 'አሜሪካን ጎብኙ' ግብዣን በተመለከተ የተለያዩ የአሜሪካ ባለሥልጣናት በተለያየ መልኩ ስሜታቸውን እየገለፁ ነው። የቀጥታ ስርጭት ቃለ ምልልስ ላይ ሳሉ ዜናውን የሰሙት የአሜሪካው ብሄራዊ ደህንነት ፎረም ዳይሬክተር ዳን ኮትስ "ነገሩ ልዩ ይሆናል"ሲሉ በመሳቅ ነበር መልስ የሰጡት። • ትራምፕ ከፑቲን ጋር በተያያዘ ወቀሳ እየዘነበባቸው ነው ጨምረውም አስተርጓሚዎቻቸው ብቻ በተገኙበት የትራምፕና የፑቲን ውይይት ምን እንደተወራ ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለም ገልፀዋል። በአሜሪካ ምክር ቤት የዲሞክራቲክ ፓርቲ መሪ የሆኑት ቻክ ሹመር ሁለት ሰዓታት በወሰደው የትራምፕና የፑቲን ውይይት ምን እንደተወራ ትራምፕ እንዲናገሩ ጥሪ አስተላልፈዋል። "ምን እንደተነጋገሩ እስካላወቅን ድረስ ፕሬዝዳንት ትራምፕ አሜሪካ፣ ሩሲያም ይሁን ሌላ ቦታ እንደገና ከፑቲን ጋር ለብቻቸው ዳግም እንዲወያዩ መፈቀድ የለበትም" ብለዋል።
news-54207954
https://www.bbc.com/amharic/news-54207954
ጎርፍ ፡ ጣና ሐይቅ ሞልቶ በዙሪያው ያሉ ከ12 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ለጉዳት አጋለጠ
ባለፈው ዓመት የክረምት ወራት በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት የጣና ሐይቅ ከመጠን በላይ በመሙላቱ በሐይቁ ዙሪያ የሚገኙ የመኖሪያ አካባቢዎችን ጨምሮ ሰፊ ቦታ በውሃ ተጥለቅልቋል።
የፎገራ ጎርፍ የጣና ሐይቅ በየዓመቱ የክረምት ወራት ወቅት ዝናብ በሚጥልበት ጊዜ የሚሞላ ቢሆንም የዘንድሮው ግን መጠኑ በጣም ከፍተኛ እንደሆነና ምናልባትም ከ30 ዓመት ወዲህ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እንደሞላና ሰፊ ቦታን ማጥለቅለቁን ቢቢሲ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። ቀሲስ ሙሉዬ ተገኘ ነዋሪነታቸው የጣና ሐይቅን ተጎራብቶ በሚገኘው በፎገራ ወራዳ ናበጋ ቀበሌ ነው። የስድስት ልጆች አባት የሆኑት ቄስ ሙሉዬ፤ የጣና ሐይቅ ውሃ ሞልቶ ካፈናቀላቸው አርሶ አደሮች መካከል አንዱ ናቸው። እንደ እርሳቸው ገለጻ የሐይቁ ውሃ መስኩን አልፎ ቤታቸውን ስላጥለቀለቀው የቤተሰቦቻቸውን ሕይወት ለመታደግ መኖሪያቸውን ለቀው ወደ ሌላ ቦታ ለመሄድ ተገደዋል። በቤት ውስጥ ከነበራቸው ንብረት መካከል ለዕለት ምግብ የሚሆንና እንስሳትን ብቻ ይዘው ራቅ ብለው ወደሚገኙ ቤተሰቦቻቸው በመሄድ ተጠግተው እየኖሩ መሆናቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። አራት ጥማድ መሬት እንዳላቸው የሚናገሩት ቄስ ሙሉዬ፤ ቢያንስ ሦስት ጥማድ የሩዝ ማሳቸው ከጣና ሐይቅ ተገፍቶ በመጣው የእምቦጭ አረም ተሸፍኖ ከጥቅም ውጪ በመሆኑ በአሁኑ ብቻ ሳይሆን በቀጣይ ሕይወታቸው ላይ ከባድ ችግር እንደተደቀነ አመልክተዋል። "የውሃ ሙላቱ ያስከተለው ጉዳት ጊዜያዊ ብቻ ሳይሆን በቀጣይ ሕይወታችንን የምንመራበትን አዝመራም አውድሞብናል" ይላሉ። በተመሳሳይ በጣና ሐይቅ የውሃ ሙላት ከተጥለቀለቁት አካባቢዎች አንዱ በሆነው በፎገራ ወረዳ ዋገጠራ ቀበሌ የሚኖሩት ዲያቆን ድምጸ በዚሁ ሳቢያ ሥራቸውና ሕይወታቸው መስተጓጎል እንደገጠመው ይናገራሉ። ዲያቆን ድምጸ ኑሯቸውን በንግድ የሚመሩና የተለያዩ ሸቀጣሸቀጦችን ለአካባቢው ነዋሪ በማቅረብ የችርቻሮ ንግድ እያካሄዱ ጎን ለጎን ደግሞ የእርሻ መሬት ተከራይተው ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ለማግኘት የግብርና ሥራን ነበር። ባለፈው ዓመትም አንድ ሄክታር ተኩል መሬት ከግለሰብ 45 ሺህ ብር ከፍለው ለአንድ ዓመት ተከራይተው ሩዝ ተክለው፣ ከሩዙ መነሳት በኋላ ደግሞ በበልጉ ወቅት ደግሞ ጤፍ ለማምረት አቅደው ነበር። ነገር ግን ሁሉም ነገር እንደ ዕቅዳቸው ሳይሆን የጣና ሐይቅ ሞልቶ በዙሪያው ያሉ አካባቢዎችን በከፍተኛ መጠን በማጥለቅለቁ ብዙ ብርና ጉልበታቸውን ያፈሰሱበት የእርሻ መሬት በውሃው ተሸፍኗል። በዚህም ሩዝ የተከሉበት ማሳ ከሐይቁ በመጣው የእምቦጭ አረም ተሸፍኖ ማሳው ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጪ እንደሆነባቸው በሐዘን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይህ ጉዳትም ከዲያቆን ድምጸ በተጨማሪ ቢያንስ 180 የሚሆኑ ጎረቤቶቻቸው ላይ እንደደረሰና ብዙዎቹ ከሚኖሩበት አካባቢ ተፈናቅለው ወደ ሌላ ቦታ ለመሄድ መገደዳቸውን ተናግረዋል። እሳቸው ግን ለንግድ ያመጧቸውን የሸቀጦችን ይዘው መውጣት ባለመቻላቸው ሁለት ሕጻናት ልጆቻቸውን ይዘው ከውሃ ሙላት ጋር እየኖሩ ነው። በመሆኑም መንግሥት ፈጥኖ እንዲደርስላቸውና ሕይወታቸውን እንዲያተርፍላቸው ተማጽነዋል። የፎገራ ጎርፍ የውሃ መጥለቅለቁ የጣና ሐይቅን በሚጎራበቱት በደቡብ ጎንደር ዞን ሊቦ ከምከም ወረዳ ውስጥ ሦስት ቀበሌዎች፣ በፎገራ ወረዳ ሁለት ቀበሌዎችና በደራ ወረዳ አንድ ቀበሌ በድምሩ 6 ቀበሌዎች ውሃ መዋጣቸውን በደቡብ ጎንደር ዞን የአደጋ መከላከል መምሪያ ውስጥ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ስዩም አስማረ ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም በነበሩት ዓመታት በሚያጋጥም የውሃ መጥለቅለቅ ሳቢያ እነዚህ ቀበሌዎች እንዳሁኑ ሙሉ በሙሉ ባይሆንም በመጠኑም ቢሆን ችግር ይደርስባቸው እንደነበር የገለጹት ቡድን መሪው የዘንድሮው ግን የተለየና ከፍተኛ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል። የውሃ መጥለቅለቁ ባጠቃቸው በእነዚህ ስድስት ቀበሌዎች ውስጥ ከ12,500 በላይ ሰዎች በአደጋው ተጠቂ በመሆናቸው ወደ ሌላ ቦታ ለመውሰድ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የተናገሩት አቶ ስዩም፤ እስካሁን ከ2,500 በላይ ነዋሪዎችን ከነበሩበት አካባቢ አውጥቶ ወደ ሌላ ቦታ መውሰድ መቻሉን ተናግረዋል። "የዘንድሮውን የውሃ ሙላት የከፋ ያደረገው የእምቦጭ አረም ከሐይቁ ውሃ ጋር አብሮ መምጣቱ ነው" ያሉት አቶ ስዩም፤ በዚህም ምክንያት ችግር ከገጠማቸው ሰዎች በተጨማሪ በ10 ሺህዎች የሚቆጠሩ እንስሳትም የሚመገቡት አጥተው ችግር ላይ እንደሆኑ ገልጸዋል። ከጣና ሐይቅ አልፎ በመጣው ውሃ የተጥለቀለቁት አካባቢዎች በአብዛኛው የሩዝ ምርት በማምረት የሚታወቁ ሲሆን በእዚህ ወቅትም የአርሶ አደሮቹ ማሳ በሩዝ ምርት ሙሉ በሙሉ የሚሸፈንበት ጊዜ ነበር። ነገር ግን የሩዝ ማሳው ለሐይቁ ህልውና ትልቅ ስጋት ሆኖ በቆየውና በውሃው ሙላት ተገፍቶ በመጣው የእምቦጭ አረም በመሸፈኑ የአርሶ አደሮቹ ማሳ ከጥቅም ውጪ መሆኑን እንደሆነና በዚህ ምክንያትም እስከ 6 ሺህ ሄክታር የሩዝ ማሳ በእምቦጭ አረም ሊወድም እንደሚችል ቡድን መሪው ለቢቢሲ ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት የአደጋው ተጠቂዎችን ካሉበት በውሃ የተሸፈነ አካባቢ የማውጣቱ ሥራ ተጠናክሮ እንደቀጠለ የተናገሩን አቶ ስዩም ጀልባ፣ ጋሪ እና ሌሎች ዘዴዎችን በመጠቀም ሰዎችን እና እንስሳትን ወደ ኮረብታማ ቦታ በማዘዋወር አስፈላጊ የምግብ እና የጤና ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን አቶ ስዩም ገልጸዋል።
news-51734125
https://www.bbc.com/amharic/news-51734125
በኮሮናቫይረስ፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና የሚያደርገውን በረራ እንደማያቋርጥ ገለጸ
በአፍሪካ ትልቁ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምንም እንኳን ግፊት ቢደረግበትም ወደቻይና የሚያደርገውን በረራ እንደማያቋርጥ በድጋሚ አሳወቀ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም እንደተናገሩት የኮሮናቫይረስ መስፋፋትን ለመቆጣጠር ወደ ቻይና የሚደረጉ በረራዎችን ማቋረጥ መፍትሄ አይሆንም ሲሉ ተናግረዋል። አክለውም በቫይረሱ ምክንያት ቻይናን ማግለል ፍትሃዊ አይደለም ብለዋል። "የቀጥታ በረራዎችን ማቋረጥ ቫይረሱን አይገታውም፤ ምክንያቱም ተጓዦች ከቻይና ከሌሎች አገራት በኩል ኢትዮጵያን ጨምሮ ወደሌሎቹ የአፍሪካ አገራት ይገባሉ። በዚህም ነው ዓለም እርስ በርሷ ተሳስራላች የሚባለው" ሲሉ መናገራቸውን የቻይናው ዢንዋ የዜና ወኪል ዘግቧል። አቶ ተወልደ በተጨማሪም እንደጠቀሱት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እንደሌሎቹ አየር መንገዶች ሁሉ የገቢ መቀነስ አጋጥሞታል። በዚህም የተጓዦች ቁጥር በ20 በመቶ ቀንሷል ብለዋል። ስለዚሁ ጉዳይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማሪያም ከሳምንታት በፊት በሰጡት ምላሽ "አሁን ጊዜያዊ ችግር ስላጋጠማቸው በረራ ማቋረጥ በሞራልም በሥነ ምግባርም ተቀባይነት የለውም" በማለት የተከሰተውን ችግር ለመከላከልም "ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንጂ፤ በረራዎችን ማቋረጥ ግን ካሉ አማራጮች ውስጥ አይደለም" ሲሉም ተናግረዋል። ባለፈው ሳምንት በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ የካቲት ወር ላይ ብቻ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የአፍሪካ አየር መንገዶች 400 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማጣታቸውን ዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት የበላይ ተቆጣጣሪ አስታወቀ። ምንም እንኳን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እንደሌሎቹ አህጉራት አፍሪካን ክፉኛ ባያጠቃም ያስከተለው ተጽእኖ ግን ቀላል የሚባል እንዳልሆነ እየተነገረ ነው። የወረርሽኙን መከሰት ተከትሎ የታንዛኒያ፣ የሞሪሺየስ፣ የማዳጋስካር፣ የሩዋንዳ፣ የሞሮኮ፣ የግብጽና የኬንያ አየር መንገዶች ወደ ቻይናና ከቻይና ወደ የአገራቸው የሚደረጉ ሁሉንም በረራዎች እንዲቋረጡ አድርገዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና የሚያደርገውን በረራ እንደማያቋርጥ ገለጸ ዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር እንደሚለውም ከኮሮናቫይረስ መስፋፋት ጋር በተያያዘ አየር መንገዶቹ 400 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ኪሳራ እንዳጋጠማቸው አመልክቷል። ለዚህም እንደ ምክንያት የተጠቀሰው አየር መንገዶቹ ወደ ቻይና የነበሯቸውን የበረራ መስመሮች በማቋረጣቸውና በረራዎችን በመሰረዛቸው እንደሆነ ተገልጿል። የዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር ምክትል ፕሬዝዳንት ለቢቢሲ እንደተናገሩት በተለይ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት 100 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ ላጋጠማቸው የአፍሪካ አየር መንገዶች የኮሮናቫይረስ ክስተት የገጠማቸውን ችግር የበለጠ የከፋ ያደርግባቸዋል። እስካሁን ድረስ በግብጽ፣ በቱኒዚያ፣ በሞሮኮ፣ በአልጄሪያ፣ በናይጄሪያና በሴኔጋል በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸው የተዘገበ ቢሆንም በየትኛውም የአፍሪላ አገር ውስጥ በሽታው በወረርሽኝ ደረጃ አልተከሰተም ተብሏል። የዓለም የጤና ድርጅት እንዳስጠነቀቀው ደካማ የጤና አገልግሎት ሥርዓት ያላቸው ድሃ አገራት ወረርሽኙን ለመቋቋም አቅም የላቸውም፤ ከእነዚህ ውስጥም አብዛኞቹ የሚገኙት በአፍሪካ ውስጥ መሆኑ አሳሳቢ ነው ብሏል። በተያያዘ ዜና የኬንያ መንግሥት ከኮሮናቫይረስ የመስፋፋት ስጋት ጋር በተያያዘ ከሰሜናዊ የጣሊያን ሁለት ከተሞች የሚመጡ በረራዎች እንዲቋረጡ አዟል። ኬንያ ይህንን እርምጃ የወሰደችው በአውሮፓ ውስጥ በርካታ ቫይረሱ የተገኘባቸው ታማሚዎች ካሉባት አገራት አንዷ ከሆነችው ጣሊያን የመጡ መንገደኞች አፍሪካ ውስጥ በበሽታው ተይዘው በመገኘታቸው ነው። በቱኒዚያ፣ በሞሮኮና ናይጄሪያ ውስጥ በቫይረሱ ተይዘው የተገኙት ሰዎች ከጣሊያን የመጡ መሆናቸው ስጋት መፍጠሩን ተከትሎ ነው የኬንያ መንግሥት ናይሮቢ ከሚገኘው የጣሊያን ኤምባሲ ጋር በመመካከር ነው የተወሰኑ በረራዎችን ከማቋረጡ ውሳኔ ላይ የደረሰው። የኬንያ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሙታሂ ካግዌ እንደተናገሩት ጣሊያን ውስጥ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች ቁጥር ከፍ ማለቱ እዚህ ውሳኔ ላይ እንዲደርሱ አድርጓቸዋል። ጣሊያን ውስጥ ቢያንስ 1800 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን 52 ሰዎች ደግሞ በበሽታው ህይወታቸው አልፏል።
54094330
https://www.bbc.com/amharic/54094330
ኮንጎ፡ የነፃነት ታጋዩ ፓትሪስ ሉሙምባ ጥርስ ለቤተሰቦቹ እንዲሰጥ ተወሰነ
የኮንጎ የነጻነት አባት ፓትሪስ ሉሙምባ ጥርስ ለቤተሰቦቹ እንዲሰጥ የቤልጂየም ፍርድ ቤት ወሰነ።
ውሳኔውን የፓትሪስ ሉሙምባ የወንድም ልጅ ዤን ዣኪዌስ ሉሙምባ "መልካም እርምጃ ነው" በማለት ተቀብለውታል። " ሉሙምባ አልቅሰን ያልቀበርነው ጀግና ነው፤ ውሳኔው [በቤልጂየም ፍርድ ቤት የተሰጠው] እውነታውን ለማወቅ ጥሩ ጅምር ነው. . . እዚያ የምንደርስበት መንገድ ይኖራል" ብሏል ዤን ዣኪዌስ። ዤን እንደሚለው ከሆነ ከፓትሪስ ሉሙምባ ጋር አብረው የተገደሉ ሁለት ሰዎች፣ ጆሴፍ ኦኪቶ እና ማውሪስ ምፖሎ " እነርሱም የኮንጎ ጀግኖች ናቸው" በማለት ግለሰቦቹ እንዴት እንደተሰዉ እውነታው ግልጽ መሆንና መነገር አለበት ሲል ተናግሯል። የቤልጂየም ፍርድ ቤት ከፓትሪስ ሉሙምባ አስከሬን ላይ የተወሰደው ጥርስ ለልጃቸው ጁሊያና እንዲመለስ ወስኗል። ልጃቸው ጁሊያና ለቤልጂየም ንጉሥ ጥርሱ እንዲሰጣት የሚጠይቅ ደብዳቤ ጽፋ ነበር። ኮንጎ ከቤልጂየም ነፃነቷን እኤአ በ1960 ካገኘች በኋላ የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ሉሙምባ በ1961 በተገንጣይ አማፂያን ታግተው ተገድለዋል። የቤልጂየም መንግሥት በግድያው ላይ እጁ እንደነበረበት ገልፆ በ2002 በይፋ ይቅርታ ጠይቋል። በግድያው የእንግሊዝ እና የአሜሪካ የስለላ ተቋማት መሳተፋቸው ይታመናል። የሉሙምባ ጥርስ በቤልጂየም ፖሊስ መወሰዱ ይታመናል ሲል የፈረንሳዩ የዜና ወኪል የዘገበ ሲሆን አክሎም፣ በኋላም በቤልጂየም ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር ውሏል ብሏል።
news-45109053
https://www.bbc.com/amharic/news-45109053
የአእምሮ መታወክን በሚያስከትሉ ህመሞች ላይ በኢትዮጵያ ጥናት እየተደረገ ነው
ብዙ ገንዘብ ታጠፋለች፤ በሯን ዘግታ ትቀመጣለች ፤ ከሰው በላይ የሆነች ይመስላታል፤ የእንቅልፍ ጊዜዋ በጣም አጭር ነው፤አለባባሷ የተለየ ነው፤ ወሲባዊ ስሜቷ በጣም ከፍተኛ ደረጃ ላይ ይደርሳል፡፡
የህመሙ መጠን እየጨመረ በመጣ ቁጥር ራሷን መቆጣጠር ይሳናታል፡፡ ቅሽለቱ ቢያንስ በዓመት አንዴ ወይም ሁለቴ ይከሰትባታል። አስፈላጊው የምክር አገልግሎትና መድኃኒት ሲሰጣት ብቻ መለስ ይልላታል። ቤተሰብ የተስፋ ጭላንጭል ዐይቶ፤ በፊታቸው ላይ የበራው ደስታ ሳይገለጥ ቅጭም ይላል፡፡ እንደገና ከፍተኛ ድብርት ይወርሳታል፡፡ ራሷን ትጠላለች ፤ ራሷን ታወግዛለች ፤እሷነቷ ያንገሸግሻታል፡፡ እነዚህ ስሜቶቿ ከመጠን በላይ ይሆኑና ራሷን የማጥፋት ፍላጎት ላይ ያደርሳታል ። ሌት ተቀን እርሷን መጠበቅ የቤተሰብ ሥራ ሆነ፡፡ • በኢትዮጵያ የአዕምሮ ህሙማን ሰብዓዊ መብት እየተጣሰ ይሆን? • ጭንቀት እርጅናን ያፋጥናል • የሙዚቃ ሕክምና በኢትዮጵያ ስሜቷን የሚያወርድ መድኃኒት ሲሰጣት ወደ ቀደመው ማንነቷ ትመለሳለች። በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ለተከታታይ ሦስት ዓመታት ሕክምናዋን ተከታተለች፡፡ በጤናዋም ላይ ቀስ በቀስ ለውጥ መታየት ጀመረ፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአእምሮ ሕክምና ትምህርት ክፍል መምህርና ሐኪም የሆኑት ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ካከሟቸው ሰዎች መካከል የዚችን ወጣት የጤና ጉዳይ እንደ አብነት ያነሳሉ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ትዳር መሥርታ፣ ልጅ ወልዳ፣ ልጇን እያሳደገች፤ ሕይወቷን በተገቢው መልኩ እየመራች እንደሆነ ለቢቢሲ የገለፁት ፕሮፌሰር መስፍን መልካም አጋጣሚውን ያስታውሱ እንጂ ለባሰ የአእምሮ ህመም ተዳርገው ራሳቸውን ያጠፉ እንዳሉም አይዘነጉም፡፡ ቅሽለት ምንድነው? ቅሽለት አንዳች የአእምሮ ጤና መጓደል ነው። በሕክምና ስሙ ሀይፖማኒያ (Hypomania) በመባል ይታወቃል። መገናኛ ብዙኃን በስፋት የሚያወሷቸው የስሜት መዋዠቅ (Bipolar) እና የአስተሳሰብ መዛባት (Schizophrenia)፣ በዚሁ ቅሽለት (Hypomania) በተሰኘው የአእምሮ ሕመም ሥር የሚጠቀሱ ከባድ የአእምሮ ጤና ችግሮች ናቸው። አንድ ሰው ራሱን ሲያገል፣ ከሰው ጋር ለመቀላቀል ሲፈራ ፣ ትካዜ ሲያበዛ፣ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴውን ሲጠላ፣ ቤት መቀመጥ ሲጀምር፣ ለድብርት እየተጋለጠ መሆኑንና ይህም እያደገ ሲሄድ የአስተሳሰብ መዛባት (Schizophrenia) ወደተባለው የአእምሮ ህመም እየተጠጋ ለመሆኑ አመላካች ነው ። ለዚህ ሕመም የተጋለጡ ሰዎች ከእውነታ ጋር ያላቸው ግንኙነት የተዛባ ነው፡፡ ምክንያታዊ ያልሆነ ጥርጣሬንና ሐሳብን ሊያስቡ ይችላሉ፤ በስሜት ህዋሶቻቸው አማካኝነት በገሃዱ ዓለም የሌሉ ስሜቶች ሊቀበሉ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ ምንም ሰው በሌለበት ሁኔታ የለሆሳስ ድምጽ ሊሰሙ ይችላሉ፤ ዕይታ ውስጥ የሌለን ነገር ይመለከታሉ፡፡ ማኅበራዊ ሕይወታቸው ይቃወሳል፣ ሥራ መሥራት ይሳናቸዋል፡፡ በስሜት ወጀብ ይናጣሉ፡፡ ወጀቡ ቅሽለት (Hypomania) የተሰኘው ሕመም ላይ ይጥላቸዋል ይላሉ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ። ሌላኛው የአእምሮ ጤና እክል የስሜት መዋዠቅ ነው፡፡ Bipolar! ይህም የሁለት ስሜቶች መዛነፍ ውጤት ሲሆን ታማሚው ምክንያታዊ ያልሆነ ደስታ፣ ሐዘንና እንዳንዴም ከባድ ድብታን ያስተናግዳል፡፡ በዚህ ህመም የተጠቁ ሰዎች ከመሬት ተነስተው በሳቅ ሊንከተከቱ ይችላሉ፤ አሊያም ምንም ሰበብ አስባብ በሌለበት በእንባ ይታጠባሉ፡፡ ስሜታቸው ምክንያታዊነትና ሚዛናዊነት ይጎድለዋል። ይህ ደግሞ ለታማሚም፣ ለአስታማሚም ፣ ለሐኪምም ፈተናው ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ እነዚህ የአእምሮ ሕመሞች ከ0.5 እስከ 1 በመቶ ሥርጭት እንዳለው የሚናገሩት ፕሮፌሰሩ አንደ ቀላል የሚታይ አይደለም ይላሉ። በመሆኑም በአንድ ቤተሰብ ውስጥ እንደዚህ ዓይነት የጤና ችግር ሲያጋጥም ሌሎች የቤተሰቡ አባላት አሊያም የትዳር አጋር እገዛ ከፍተኛ መሆን እንዳለበት ይመክራሉ ። ኢትዮጵያ፤ የጥናቱ መዳረሻ በቅርቡ ለእነዚህ ከባድ የአእምሮ ሕመሞች ዘላቂ መፍትሔ ለመፈለግ ያለመ ዓለም አቀፍ ሰፊ የጥናት እቅድ በኢትዮጵያ ይፋ ተደርጓል። ዶክተር ሰለሞን ተፈራ በአዲስ አበባ የኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር እንዲሁም በኢትዮጵያ የጥናቱ አስተባባሪ ናቸው፡፡ ጥናቱ ከባድ የአእምሮ ህመም የሚባሉትን የአስተሳሰብ መዛባት (Schizophrenia)፣ እንዲሁም የስሜት መዋዠቅ (Bi-polar) ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ይላሉ፡፡ ዓላማውም የእነዚህን የጤና ችግሮች የዘር መሠረታቸውን ፣ አጋላጭ ዘሮችን(Genes) ፣ የሚከሰትባቸውን ምክንያቶችንና የሕክምና ዘዴዎችን በመለየት ሕክምናውን ማፈላለግ ነው፡፡ በዚህ ዓለም አቀፋዊ ጥናት ከአፍሪካ አህጉር ኢትዮጵያን ጨምሮ ኬንያ፣ ኡጋንዳና ደቡብ አፍሪካ የጥናቱ አካል ሆነዋል፡፡ "ከፍተኛ የሆነ የዘር ስብጥር ያላቸው በመሆኑ፣ ልዩ ልዩ የዘር መዋቅሮችን ለማግኘት ያስችላል፤ በባህሪው ነባር ሕዝብ በመሆኑ ለጥናቱ ጠቃሚ መረጃ ሊገኝበት ይችላል" ይላሉ የጥናቱ አስተባባሪ ዶክተር ሰለሞን። ካሁን ቀደም በኢትዮጵያ ውስጥ የዘር ጥናቶች የተካሄዱ ሲሆን የተወሰዱት ናሙናዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ናቸው፡፡ ይህም የአእምሮ ጤና ችግሮቹን በስፋት ያሳዩ እንዳልነበሩ ይገልጻሉ፡፡ "የአእምሮ ጤና እክሎቹ ሁሉንም የሰው ዘር የሚያጠቁ በመሆናቸው በአገራት መካካል ያለው ሥርጭትም ተመሳሳይነት አለው" የሚሉት ዶክተር ሰለሞን በኢትዮጵያ ከመቶ ሰዎች አንዱ ለእነዚህ የአእምሮ ህመሞች ይጋለጣል ይላሉ፡፡ ሰማኒያ በመቶ በዘር የሚተላላፍ በመሆኑ በአገራት መካከል ያለው ሥርጭት ያን ያህል ልዩነት እንደሌለው ይናገራሉ፡፡ በመሆኑም ዓለምአቀፋዊ የሆነ መፍትሄ ለመፈለግ ኤዥያ፣ አውሮፓ፣ አውስትራሊያ፣ሰሜን አሜሪካም ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ ከእነዚህ ክፍለ ዓለማት የተሰባሰቡ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ በዓለም ላይ የሰው ዘርን ይወክላሉ የተባሉ የዘረ መል ናሙናዎች ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ እና ኤም አይ ቲ በጋራ በሚመሩት ቤተ-ሙከራ ጥናት ይደረግባቸዋል፡፡ ይህም ከአራት እስከ አምስት ዓመታት ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል ተገምቷል፡፡ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ ይብቀል እንደዚህ ያሉ ጥናቶችን ለማካሄድ የገንዘብ አቅም የሚጠይቁ በመሆናቸው በስፋትና በጥልቀት ለማጥናት የማይደፈር መሆኑ ተደጋግሞ ይጠቀሳል፡፡ ይህ ጥናት በአንድ በጎ ፈቃደኛ አሜሪካዊ ቢሊየነር ቴድ ሰታንሊ የኑዛዜ ገንዘብ የሚደገፍ ነው፡፡ ለጥናትና ምርምሩ ግማሽ ቢሊዮን ዶላር ሐብታቸውን ነው ተናዘው ያለፉት። ለዚህ በጎ ተግባር ያነሳሳቸው ደግሞ ልጃቸው የስሜት መዋዠቅ (Bi-polar) ህመም ተጠቂ መሆኑ ነበር። እርሱን ለማዳን ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበረም፤ ይሁን እንጂ ልጃቸውን መታደግ አልቻሉም፡፡ በልጃቸው ላይ የደረሰው በሌላ ላይ አይድረስ ሲሉ "ስታንሊ ሴንተር"ን መሥርተው በአእምሮ ጤና ችግሮች ላይ አብዝተው ይሠሩ ነበር፡፡ እርሳቸውም በቅርቡ ሕይወታቸው አልፏል፡፡ ዘለቄታ ያለው መድኃኒት ለእኔ ልጅ ባይደርስ እንኳን ለሌሎች ይድረስ ሲሉ ጠቅላላ ሐብታቸውን ለዚህ በጎ ተግባር እንዲውል ተናዘዙ፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚሠራው ይህ ጥናት የሚደገፈው ቢሊየነሩ ቴድ ስታንሊ በተናዘዙት ገንዘብ መሆኑን ዶክተር ሰለሞን ጨምረው ተናግረዋል፡፡
news-56439798
https://www.bbc.com/amharic/news-56439798
ኮሮናቫይረስ፡ ታዳጊ አገራት ክትባት እንዲያመርቱ የቀረበውን ሃሳብ ሀብታም አገራት መቃወማቸው ተነገረ
ታዳጊ አገራት ክትባት የማምረት አቅማቸውን ለማጎልበት ድጋፍ ለማድረግ የቀረበውን ሃሳብ ሀብታም አገራት እንዳይሳካ እያደረጉ መሆናቸውን የቢቢሲ ኒውስናይት ፕሮግራም ያገኛቸው ሰነዶች አመለከቱ።
በርካታ ደሃ አገራት የዓለም የጤና ድርጅት በክትባት ማምረት በኩል ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጥያቄ ያቀረቡ ቢሆንም፤ ባለጸጋ አገራት ግን ከዓለም አቀፍ ሕግ በተቃራኒ የደሃ አገራቱ ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ እንዳያገኝ እየገፉት ይገኛሉ። ይህ መረጃ የተገኘው በዓለም ጤና ድርጅት የተዘጋጀና ሾልኮ ከወጣ በጉዳዩ ላይ ከተዘጋጀ የድርድር ሰነድ ቅጂ ላይ ነው። ሃሳቡን ከተቃረኑት ባለጸጋ አገራት መካከል ዩናይትድ ኪንግደም፣ አሜሪካ እና የአውሮፓ ሕብረት ይገኙበታል። በዚህ ጉዳይ ላይ ምላሽ የሰጡት የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ቃል አቀባይ "አለም አቀፍ ወረርሽኝ ዓለም አቀፍ ምላሽ ይፈልጋል" በማለት "የኮሮናቫይረስ ክትባትና ህክምና በዓለም ዙሪያ በፍትሃዊነት እንዲዳረስ በሚደረገው ጥረት አገራችን ቀዳሚ ናት" ብለዋል። ጨምረውም ለታዳጊ አገራት ከአንድ ቢሊየን ብልቃጥ በላይ የኮሮናቫይረስ ክትባት እንዲቀርብ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ዩናይትድ ኪንግደም ከፍተኛውን ገንዘብ ካበረከቱት አገራት መካከል አንዷ መሆኗን ገልጸዋል። በርካታ ባለሙያዎች እንደሚሉት የክትባቶች ፍትሃዊ ክፍፍል ወረርሽኙንና ሞትን በመከላከል በዓለም ዙሪያ ያለውን በሽታውን የመከላከል አቅምን ያጎለብተዋል። ነገር ግን ዓለም ያላት ክትባቱን የማምረት አቅም ከሚስያስፈልገው አንድ ሦስተኛ የሚሆነውን ብቻ እንደሆነ የህክምና ፖሊሲና የአእምሯዊ ንብረት ሕግ ባለሙያ የሆኑት ኤለን ቲሆን ይናገራሉ። "እነዚህ ክትባቶች በሀብታም አገራት ተመርተው በእነሱ ቁጥጥር ስር የሚቆዩ ናቸው። ስለዚህም በማደግ ላይ ያሉ አገራት ክትባቱን ብቻ ሳይሆን ክትባቱን በማምረት በኩል ተገቢው ድርሻ እንዲኖራቸው እየጠየቁ ነው" ብለዋል። ክትባት ለማምረት በሌሎች በባለቤትነት የተያዙትን የክትባቶችን ግብአቶች የመጠቀም መብት ማግኘት ብቻ በቂ አይደለም፤ ከዚህ በተጨማሪ ክትባቶቹ እንዴት እንደሚሰሩ ዕውቀት ሊኖር ይገባል ምክንያቱም ቴክኖሎጂው ውስብስብ ሊሆን ስለሚችል። የዓለም ጤና ድርጅት በዚህ ረገድ የባለቤትነት መብቶችን ችላ ሊላቸው አይችልም። ነገር ግን አገራትን በማግባባት የክትባት አቅርቦት ከፍ እንዲል ለማድረግ እየጣረ ነው። ውይይቱም ከዓለም አቀፍ ሕጎች አንጻር የባለቤትነት መብትን በተመለከተ መግባባትን በመፍጠር አገራት ቴክኒካዊ አቅም አግኝተው ክትባቶችን እንዲያመርቱ ለማድረግ የሚያስችሉ አማራጮችን በመፈለግ ላይ አተኩረዋል። ነገር ግን የመድኃኒት ኢንዱስትሪው ይህ የባለቤትነት መብትን የሚሸረሽር እርምጃ ወደፊት ኮቪድንና ሌሎች ህመሞችን ለማከም በሚያስፈልገው ገንዘብ አቅርቦት ላይ የራሱ የሆነ እንቅፋትን ይፈጥራል ሲል ይከራከራል። በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የአሜሪካ የመድኃኒት አምራቾች ተወካዮች ይህንን ስጋታቸውን በሚመለከት ለፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በጻፉት ደብዳቤ ገልጸዋል። በደብዳቤያቸው ላይ ለባለቤትነት መብት የሚደረገው ጥበቃን ማንሳት አዲስ የቫይረስ ዝርያዎችን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጨምሮ በወረርሽኙ ዙሪያ የሚደረገውን ጥረት ይጎዳዋል ብለዋል። ክትባት በስፋት እንዲመረት በቀረበው ሃሳብ ዙሪያ የተለያዩ ተቃራኒ አቋሞች እየተንጸባረቁ ሲሆን ባለጻጋ አገራትም ይህንን ሃሳብ እንደተቃወሙት ቢቢሲ ያገኘው ሾልኮ የወጣ ሰንድ ያመለክታል።
news-54261909
https://www.bbc.com/amharic/news-54261909
በኢንተርኔት አማካኝነት እጽ ይሸጡ የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተያዙ
የአውሮፓ እና የአሜሪካ ፖሊስ በጥምረት ባካሄዱት ኦፐሬሽን ማንነታቸውን በመደበቅ በኢንተርኔት አማካኝነት አደንዛዥ እጽ ሲሸጡ የነበሩ 179 ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋላቸው ተገለጸ።
ከግለሰቦቹ በተጨማሪ ፖሊስ ከ6.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ግምት ያለው ጥሬ ገንዘብ እና ዲጂታል ገንዘብ የያዘ ሲሆን እጽ እና የጦር መሳሪያ ከግለሰቦቹ ጋር መያዙም ተነግሯል። እነዚህ ሰዎች በቁጥጥር ሥር የዋሉት ከበርካታ የአውሮፓ አገራት እና አሜሪካ ሲሆን የተደራጁ ወንጀሎች ተከላካይ ኃይል ዩሮፖል፤ “ማንነትን በመደበቅ የሚደረገው ሕገ-ወጥ ግብይነት ጊዜው አብቅቷል” ሲል መግለጫ አውጥቷል። የዩሮፖል የኢንተርኔት ወንጀል ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ኤድቫራዳስ ሲሌሪስ “ድብቁ ኢንተርኔት ከአሁን በኋላ ሚስጥር አይሆንብንም” ብለዋል። “ዲስራፕትቶር” የሚል ስያሜ የተሰጠው ኦፕሬሽንን የአሜሪካው የፍትሕ ቢሮ እና ዩሮፖል በቅንጅት ያስፈጸሙት ሲሆን በኦፕሬሽኑ እንደ ፌንታኒ፣ ሄሮይን፣ ኮኬን እና ኤክስቴሲ የተሰኙ እጾች ተይዘዋል። በቁጥጥር ሥር ከዋሉት 179 ሰዎች መካከል 119 በአሜሪካ፣ 2 በካናዳ፣ 42 በጀርመን፣ 8 በኔዘርላንድ፣ 4 በዩኬ፣ 3 በኦስትሪያ እና 1 ግለሰብ ደግሞ ስዊድን ውስጥ መያዛቸው ተገልጿል። ሰዎች ማንነታቸው እና መገኛቸው ሳይታወቅ ልዩ መተግበሪያዎችን በመጠቀም “ዳርክ ዌብ” ተብሎ በሚጠራው የኢንተርኔት ክፍል ላይ በርካታ ሕገ-ወጥ ተግባራትን ያከናወናሉ። “በዳርክ ዌብ” ላይ ሰዎች ማንነታቸውን መደበቅ ስለሚችሉ እንደ ኩላሊት ካሉ የሰው ልጆች አካላት እስከ አደንዛዥ እጽ መገበያየት ይቻላል ይላሉ የኢንፎሜሽን መረብ ደህንነት ባለሙያዎች። ፖሊስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መሰል ወንጀለኞችን በቁጥጥር ሥር እያዋለ ይገኛል። ኤድቫራዳስ ሲሌሪስ ሕግ አስከባሪ አካላት በቅንጅት መስራት ከቻሉ ወንጀለኞችን መቆጣጠር የማይቻልበት ምክንያት የለም ብለዋል። እነዚህ ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውም “የዳርክ ዌብ ወርቃማ ዓመታት” እያለፉ መምጣታቸውን ያሳያል ተብሏል።
news-49902868
https://www.bbc.com/amharic/news-49902868
የሩሲያዊያን የአልኮል መጠጥ ፍጆታ መቀነሱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ
የሩሲያዊያን የአልኮል መጠጥ ፍጆታ ከአውሮፓዊያኑ 2003 እስከ 2016 ባሉት ዓመታት ውስጥ 43 በመቶ ያህል መቀነሱን የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል።
በሩሲያ አልኮል መጠጥ ለሞት ከሚዳርጉ ዐብይ ምክንያቶች መካከል በዋናነት ይጠቀሳል ለአልኮል ፍጆታቸው መቀነስ ምክንያት ነው የተባለው የሩሲያ መንግሥት የወሰደው ጥብቅ ቁጥጥርና ዜጎቹ ወደ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ በመሸጋገራቸው እንደሆነ ተነግሯል። • አልኮል የማይሸጥባቸው መጠጥ ቤቶች • ለአንድ ወር ከአልኮል መታቀብ የሚኖረው አስደናቂ ውጤት የዓለም የጤና ድርጅት እንዳስታወቀው የአልኮል ፍጆታ መጠን የሰው ልጅ በዚህች ምድር ላይ ከሚኖረው እድሜ ጋር ከፍተኛ ግንኙነት አለው። ከዚህ ቀደም ሩሲያ በዓለማችን በጣም በርካታ ጠጪዎች ካሉባቸው አገራት አንዷ ነበረች። በሩሲያ የአልኮል መጠጥ ፍጆታ በተለይ አምራች ለሆኑ ወጣት ወንዶችን ሞት ከሚያፋጥኑ ምክንያቶች መካከል አንዱ ተደርጎም ይወሰድ እንደነበር ሪፖርቱ ያስረዳል። ይሁን እንጂ ከ2003 እስከ 2018 ድረስ ባሉት ጊዜያት የአልኮል ፍጆታና የሞት መጠን ቀንሷል። ከአልኮል መጠጥ ጋር በተያያዘ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥርም እንዲሁ። ባለፈው ዓመት በአገሪቷ ታሪክ በአስገራሚ ሁኔታ የሩሲያዊያን የመኖሪያ አማካይ እድሜ ለወንዶች 68 ዓመት ለሴቶች ደግሞ 78 ዓመት እንደደረሰ ተገልጿል። የአልኮል ቁጥጥር እርምጃዎችን ያስተዋወቁት የቀድሞ የአገሪቷ ፕሬዝደንት ድሚትሪ ሜድቬዴቭ ሲሆኑ የማስታወቂያ ሕጎችን በማውጣት፣ በአልኮል ምርቶች ላይ ግብር በመጨመር እና አልኮል መጠጥ የሚሸጥበትን ሰዓት በመገደብ ቁጥጥር ሲደረግ ቆይቷል።
51147389
https://www.bbc.com/amharic/51147389
ከኢትዮጵያ ለአረብ አገራት በሕገ ወጥ የሚሸጡት አቦ ሸማኔዎች
በየወሩ ቢያንስ አራት የአቦ ሸማኔ ግልገሎች በሕገ ወጥ የዱር እንስሳት አዘዋዋሪዎች አማካኝነት ከሃገር ሊወጡ ሲሉ ደንበር ላይ እንደሚያዙ ተነገረ።
አቦ ሸማሌ ከግልገሏ ጋር የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን እንዳስታወቀው፤ ግልገሎቹ በቅደሚያ ከኢትዮጵያ ወደ ሶማሊላንድ ሃርጌይሳ ከተወሰዱ በኋላ በየመን በኩል ወደ ሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ተወስደው ይሸጣሉ። በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን የእንስሳት እና የእንስሳት ውጤቶች ሕገ-ወጥ ዝውውር እና ቁጥጥር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዳንኤል ጳውሎስ፤ አቦ ሸማኔዎቹን ባለጸጋ አረቦች የቤት እንስሳ አድርገው ያሳድጓቸዋል። በህገ ወጥ አዘዋዋሪዎች እጅ ከተያዙት አቦ ሸማኔዎች አንዱ አቶ ዳንኤል ጨምረው እንደተናገሩት፤ አቦ ሸማኔዎቹ ግብይት የሚፈጸመው በጥቁር ገብያ ላይ ስለሆነ የተተመነ ቋሚ ዋጋ የላቸውም። ይልቁንም ገዥን እና ሻጭ በተስማሙበት ዋጋ ግልገሎቹ ይሸጣሉ። አብዛኛውን ጊዜ ከኢትዮጵያ በሕገ-ወጥ መንገድ የሚያወጡት ሰዎች አንድ የአቦ ሸማኔ ግልገልን ከ10ሺህ እስከ 15ሺህ የኢትዮጵያ ብር ይሸጣሉ። ግለገሎቹ አረብ ሃገራት ከደረሱ በኋላ ግን ዋጋቸው እጅጉን ከፍ እንደሚል አቶ ዳንኤል ገልጸዋል። ከአሾ ሸማኔ በተጨማሪ የአንበሳ ደቦሎችም የሕገ-ወጥ እንስሳት አዘዋዋሪዎች ሰለባ ናቸው። አቶ ዳንኤል ከወራት በፊት አንድ ኢትዮጵያዊ ሶማሊላንድ ላይ የአንበሳ ደቦል ይዞ መገኘቱን ተናግረዋል። "የአንበሳ ደቦሏን ከሶማሊላንድ አምጥተን በእኛ መጠለያ ውስጥ እንድትቆይና እንድታገግም አድርገናል" ብለዋል። በተያያዘ ዜና ከሁለት ቀናት በፊት የሳዑዲ ባለስልጣናት የአቦ ሸማኔ ግልገሎችን በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለማስገባት የሞከሩ በርካታ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን አስታውቃል። የሳዑዲ ፖሊስ ግልገሎቹ መነሻቸው የአፍሪካ ቀንድ ሃገራት በተለይም ኢትዮጵያና ሶማሊያ ናቸው ብሏል። የእንስሳት መብት ተከራካሪዎች እንደሚሉት ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ እንስሳት በሕገ-ወጥ ዝውውሩ ወቅት በሚደርስባቸው እንግልት ህይወታቸው ያልፋል። በተጨማሪም ሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች በኢትዮጵያ እና በምስራቅ አፍሪካ ሃገራት ውስጥ ለሚገኙት እንስሳት ከፍተኛ ስጋት ናቸው ተብሏል።
news-54022871
https://www.bbc.com/amharic/news-54022871
ሊባኖስ፡ በቤይሩት የነፍስ አድን ሰራተኞች "በፍርስራሽ ውስጥ የልብ ምት " መስማታቸውን ገለፁ
በቤይሩት የነፍስ አድን ሰራተኞች በሊባኖስ ዋና ከተማ የደረሰው ከባድ ፍንዳታ አንድ ወር ከሞላው በኋላ በህንጻዎች ፍርስራሽ ውስጥ ህይወት መኖሩ የሚያሳይ ምልክት በመታየቱ ፍለጋ መጀመራቸው ተገለፀ።
የነፍስ አድን ሰራተኞች በፍርስራሽ ውስት በህይወት ያለ ሰው መኖሩን ትቆማ የሰታቸው አነፍናፊ ውሻ ነው ማር ሚካዔል በመባል በሚታወቀው ስፍራ በሚገኘው ህንጻ ፍርስራሽ ውስጥ የልብ ምት ተሰምቷል የሚለው ያልተረጋገጠ ዜና ከተሰማ በኋላ በህይወት ያለን ነገር የሚለይ መሳሪያ ወደ አካባቢው መላኩ ተገልጿል። ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ፍለጋው ምሽት ላይ የተቋረጠ ቢሆንም በጎ ፈቃደኞች ግን በእጃቸው ፍለጋውን መቀጠላቸው ተሰምቷል። በሊባኖሱ ፍንዳታ 2 ሺህ 750 ቶን አሞኒየም ናይትሬት ሲፈነዳ ከ200 በላይ ሰዎች ሲሞቱ 300 ሺህ ያህል የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ቤት አልባ መሆናቸው ተገልጿል። በከተማዋ ወደብ፣ በርካታ የመኖሪያ ቤቶች የሚገኙበት አቅራብያ፣ በርካታ ለአደጋ የሚያጋልጡ ቁሳቁሶች ያለ ተገቢው ጥንቃቄ ተቀምጠዋል በሚል ተቃውሞ ተነስቶ ነበር። ተቃዋሚዎችን ማረጋጋት ያልቻለው መንግሥት፣ በከተማዋ በርካታ ምሽቶች ተቃዋሚ ሰልፈኞች ከፖሊስ ጋር ከተጋጩ በኋላ ስልጣኑን ለቅቋል። በተያያዘ ዜና ከቤሩት የባህር ወደብ ውጪ በሚገኝ ስፍራ ሐሙስ እለት አራት ኮንቴይነር (ማከማቻ) ውስጥ የተቀመጠ 4.3 ቶን አሞኒየም ናይትሬት መገኘቱን የወታደራዊ ኃይሉ አስታውቋል። ባለሙያዎች ኮንቴይነሮቹን (ማከማቻዎቻቸውን) መመርመራቸው የተገለፀ ቢሆንም ተጨማሪ መረጃ ከመስጠት ግን ተቆጥበዋል። የህይወት አድን ሰራተኞች በተደጋጋሚ በህይወት ያለ ሰው መኖሩን ለማረጋገጥ እየሞከሩ ነው ሐሙስ እለት በአንድ በፈራረሰ ህንጻ አካባቢ የተሰባሰቡ ከቺሊ የመጡ የህይወት አድን ሰራተኞች ፍለጋ ሲጀምሩ በርካቶች የሚፈጠረውን ተዓምር ለማየት ተሰባስበው ነበር። በፍርስራሹ ውስጥ በህይወት ያለ ሰው መኖር አለመኖሩ አሁንም አልተረጋገጠም። የነፍስ አድን ሰራተኞች ፍርስራሹን የሚያነሳላቸው ክሬን ማግኘት ስላልቻሉ እንዲሁም ህንጻው ሊደረመስ ይችላል የሚል ስጋት በመፈጠሩ ምሽት ላይ ፍላጋቸውን አቋርጠዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች ግን በእጃቸው ፍለጋቸውን ለማካሄድ ቆርጠው እየፈለጉ የነበረ ሲሆን ግለሰቦች ክሬን በማምጣት ፍለጋው እንዲቀጥል መደረጉን በአካባቢው ያለ የቢቢሲ ጋዜጠኛ ተመልክቷል። ከዚህ በኋላም ከቺሊ የመጡ የነፍስ አድን ሰራተኞችም ወደ ስፍራው መመለሳቸው ታውቋል። ረቡዕ እለት በፍርስራሹ አጠገብ አነፍናፊ ውሻ ይዘው የሚያልፉ የነፍስ አድን ሰራተኞች፣ ውሻው በህይወት ያለ ሰው መኖሩን ምልክት እንደሰጣቸው ተናግረዋል። ሐሙስ እለት በድጋሜ ውሻው በተመሳሳይ ስፍራ በህይወት ያለ ሰው መኖሩን ምልክት ሰጥቷል። ቡድኑ ፍለጋውን ለማካሄድ የልብ ምት ወይንም ትንፋሽ መኖሩን ለማረጋገጥ ስካነር (መመርመሪያ) ከተጠቀመ በኋላ ፍርስራሹን ለማንሳት መሳሪያዎችን ይዞ መጥቷል። የነፍስ አድን ሰራተኞች በፍርስራሽ ውስት በህይወት ያለ ሰው መኖሩን ትቆማ የሰታቸው አነፍናፊ ውሻ ነው የነፍስ አድን ሰራተኞቹ በሰባት ቡድን በመከፋፈል ህንጻው ዳግም እንዳይደረመስ በመስጋት ፍርስራሹን አንድ በአንድ ማንሳት ጀምረዋል። በስፍራው የነበረው የቢቢሲ ጋዜጠኛ እንደተመለከተው በህይወት ያለ ሰው ለመፈለግ ተደጋጋሚ ጥሪ ቢደረግም ምንም ምላሽ የሚሰጥ አካል የለም። የቀይ መስቀል ባልደረቦች፣ የመከላከያ ኃይሉ፣ የእሳት አደጋ ሰራተኞች እንዲሁም የበጎ ፈቃደኛ ሰራተኞች በስፍራው ተገኝተዋል። የቺሊ የነፍስ አድን ሰራተኞች ሊባኖስ የደረሱት ከሶስት ቀን በፊት ነው። እንደ መረጃ ምንጮች ከሆነ ፍርስራሽ ውስጥ 15 ሜትር ድረስ ጠልቆ ትንፋሽን የሚያደምጥ መሳሪያ ይዘው መጥተዋል። እስካሁን ድረስ በፍርስራሹ ውስጥ በህይወት ያለ ሰው መኖሩ አልተረጋገጠም። ነገር ግን በስፍራው የተሰባሰቡ ሰዎች በህይወት በተአምር ተርፎ የሚወጣ ሰው ለማየት ጓጉተዋል። የአልጀዚራ ባልደረባ በበኩሉ በትዊተር ገፁ ላይ ፍለጋውን እያካሄደ የሚገኘው ቡድን የሰው አካል ማግኘታቸውን ጠቅሶ " በፍርስራሽ ውስጥ የልብ ምቱ የተሰማው ሰው ይሆናል" ብሏል። ማር ሚካዔል በፍንዳታው ክፉኛ ከተጎዱ ስፍራዎች መካከል አንዱ ነው። ከፍንዳታው በፊት ወደቡ ፊት ለፊት በሚገኝ ስፍራ ደማቅ የምሽት ህይወት ይታይ ነበር።
news-46480757
https://www.bbc.com/amharic/news-46480757
ከስም ፊት የሚቀመጡ መለያዎና አንድምታቸው
ከሰሞኑ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪ ቢልለኔ ስዩም ወ/ሮም ወ/ሪትም አትበሉኝ በስሜ ብቻ ጥሩኝ ስትል ያስተላለፈችው መልዕክት የብዙዎች መነጋገሪያ ሆኗል።
ሃሳቡን የተጋሩት ቢኖሩም የማህበረሰቡን እሴት ማፍረስ ነው ሲሉ የተቃወሙም አልታጡም፤ የጋብቻ ሁኔታን የማይገልፁ አማራጭ ቃላትን ያዋጡ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ታይተዋል። በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የባህል መምህር ዋልተንጉስ መኮነን (ዶ/ር) በየማህበራዊ እርከኑ፣ በሽግግር ጊዜ የሚሰጡ፣ በሐይማኖታዊ ሥርዓት፣ በአስተዳደራዊ ሥርዓት፣ በሙያ የሚሰጡ ማዕረጎችና ሌሎችም የሚና መገለጫ ማዕረጎች እንዳሉ ያስረዳሉ። 'ልጅ' የመኳንንትና የመሳፍንት ልጆች መጠሪያ እንደነበር እንደምሳሌ ያነሳሉ ለማሳያም ልጅ እያሱን ይጠቅሳሉ። • ታሪክ እየቀየሩ ያሉት ሴቶች • ኢንጅነር አይሻ መሃመድ የሃገር መከላከያ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ በማህበረሰቡ ዘንድ ያላቸውን ሚናና ሁኔታ ለማሳየት ተብሎ በዕድሜ ደረጃ ለልጆች የሚሰጥ ስያሜም መኖሩን ይናገራሉ፤ ነገርግን በዘመን፣ በአስተዳደር፣ በማኅበረሰብ አስተሳሰብ ልዩነት ምክንያት የሚሰጡት ማዕረጎች (መለያዎች) ሊሻሻሉ አሊያም ሊለወጡ ይችላሉ። ሲወርድ ሲወራረድ የመጣው ላላገባች ሴት የሚሰጠው 'ወይዘሪት' የሚለው መለያ እንዲሁም ላገባች ሴት የሚሰጠው 'ወይዘሮ' የሚለው ማዕረግ አሁንም ሰዎች ይጠቀሙበታል። ከአንድ በላይ የሆኑ ያላገቡ ሴቶችም 'ወይዛዝርት' ሚል መጠሪያ ይሰጣቸዋል። ይህም የማኅበረሰብ ደረጃና ሚናቸውን ለማሳየት ተብሎ የሚሰጥ ማዕረግ እንደሆነ ይገልፃሉ። በተጨማሪም መለያዎች በቃላት ባይገለጹም እንደየማኅበረሰቡ ባህል የአካል ክፍሎች ለውጥን፣ የአለባበስ ሥርዓትን፣ አካሄድን፣ የሚይዟቸውን ቁሳቁሶች፣ የፀጉር አሰራርን (አቆራረጥን) በማየት ብቻ የግለሰቦችን የጋብቻ ሁኔታ ማወቅ እንደሚቻል ያስረዳሉ - የባህል መምህሩ ዋልተንጉስ። በቆየው አባዊ ሥርዓት (ፓትሪያርኪ) የሴቶች ሚና ትዳር መስርቶ ልጅ ማሳደግ አንድ የማህበራዊ ደረጃ ማሳያ መንገድ ነበር ይላሉ፤ ማዕረጉም ይህንን ሙያዋን አመላካች ሆኖ ይመጣል። በተቃራኒው አሁን ባለው ሥርዓት ደግሞ አንዲት ሴት ተምራ ተመራምራ የሙያ ማዕረግ አግኝታ ሚናዋም እየተለየ አሊያም እየተቀየጠ ይሄዳል። • "ፓስፖርት መስጠት አልተከለከለም" የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች ተቋም "አንዳንድ ጊዜ እነዚህ ማዕረጎች የነበረውን ርዕዮተ ዓለምና ያለፍንበትን መንገድ ያሳያል" የሚሉት ዋልተንጉስ (ዶ/ር) እነዚህ መገለጫዎች ከወንዶች ይልቅ ሴቶች ላይ ጎልተው መታየታቸውን ይናገራሉ። እነዚህ ማዕረጎች ያላቸው ትርጓሜና ሚና እየተለወጠ ሲመጣ መምታታትን ያመጣሉ፤ አሁንም የሆነው ከዚህ ዘለለ እንዳይደለ ይገልፃሉ። ካላቸውና ከሚኖራቸው ሚና ጋር በተያያዘም ማዕረጉ ሥነ ልቦናዊና ማህበራዊ ተፅዕኖዎች ማሳደራቸው አይቀርም የሚሉት መምህሩ "ለምሳሌ ፆታዊ ግንኙነት መስርተው ላያገቡ ይችላሉ ነገር ግን ሊወልዱ ይችላሉ መለያቸውም ወ/ሪት ይሆናሉ። ከዚህም ባሻገር ፈጥናም ሆነ ዘግይታ ብታገባ አሊያም ከነጭራሹ ጋብቻ ምርጫዋ ባይሆን ተፅእኖ ይኖረዋል።" ማዕረጎቹ ይፋዊ የጋብቻ ሥነ ሥርዓትን የተንተራሱ በመሆናቸውም ይፋዊ ባልሆነ መልኩ ጋብቻ የሚመሰርቱትን ለመጥራት መደናገርን ይፈጥራሉ። "አግብተሻል? አላገባሽም?" የሚሉ መጠይቆች መዘውተራቸውም በማህበራዊ ግንኙነትም ሆነ በሥነ ልቦናዊ ሥርዓት የሚያሳድረው ተፅእኖ ቀላል የሚባል አይደለም። በመሆኑም ቃሉና ሚናውም ከዘመኑ ጋር እየተለወጠ በመምጣቱ የሚያስማማና የሚገልፃቸው አዲስ ቃል ማውጣት ሳያስፈልግ አይቀርም ይላሉ ። በሌላ በኩል በወሎ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋ መምህርና የባህልና ኪነጥበብ ዳሬክተር የሆኑት አፀደ ተፈራ (ዶ/ር) እንደሚሉት ችግሩ ያለው ማዕረጉ ጋር ሳይሆን ማዕረጉን ተከትሎ ከሚመጣው ኋላ ቀር አስተሳሰብ ነው ሲሉ ይሟገታሉ። መገለጫዎቹ እንደ ማዕረግ የሚሰጡ ሲሆኑ በአካባቢው ባህልም የአንድ ሴት የጋብቻ ሁኔታ ሽግግርን ለማመላከት "እንኳን ከወ/ሪት ወደ ወ/ሮነት አሻጋገረሽ" እንደምትባል ጠቅሰው ማዕረጉም አግብታ በፈታች ቁጥር የሚቀየር እንዳልሆነ ይናገራሉ። ምን አልባት ያች ሴት በትምህርትና በሙያ በሚሰጡ ማዕረጎች ልትተካው ትችላለች ምክንያቱም ሁለት ማዕረግ በአንድ ጊዜ መጠቀም ስለማይቻል ነው ይላሉ። ወይዘሪት ለማን የሚሰጥ ማዕረግ ነው? ወይዘሪት ላላገቡ ሴቶች የሚሰጥ የጋብቻ ሁኔታ ማዕረግ ቢሆንም በቀደመው ዘመን ከጋብቻ በፊት የወሲብ ግንኙነት ያልፈፀመች ሴት መጠሪያነትም ይውል እነደነበር ዶ/ር አፀደ ያስረዳሉ። በእርግጥም ያች ሴት ድንግል እንደሆነች ያመላክት ነበር። ይሁን እንጂ በአሁኑ ዘመን የፍቅር ጋብቻ የሚል ልማድ በመኖሩ አንዲት የ'ወ/ሪት'ማዕረግ የተሰጣት ሴት የወሲብ ግንኙነት አልፈፀመችም ማለት አይቻልም ይላሉ። ምንም እንኳን ማዕረጉ የቀደመውን አባዊ ሥርዓት የሚያሳይ ቢሆንም ማዕረጉ በማህበረሰቡ ዘንድ ያላትን የጋብቻ ሁኔታ የሚያመለክት ከመሆኑ የዘለለ ሌላ ተፅዕኖ የለውም ሲሉ ዶ/ር አፀደ የራሳቸውን ተሞክሮ ያነሳሉ። ቃሉን ማስወገድም፤ ሌላ ቃል ለመፍጠር መባዘኑም ከንቱ ነው ሲሉ ያክላሉ። • ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ስለተዘረፉ ቅርሶች ምን እናውቃለን? እርሳቸው በማህበረሰቡ ዘንድ የተቀመጠውን የጋብቻ እድሜ ቢያልፉትም ትዳር አልመሰረቱም ለዚህም የራሳቸው ምክንያትና እምነት አላቸው፤ ወ/ሪት ተብለው ቢጠሩም የተለየ ትርጉም አይሰጣቸውም። ለማዕረጉ ትርጉም ሰጥቶ ማብሰልሰሉም ሆነ መጠቀሙ እንደ ሴቷ ፍላጎትና እምነት የሚወሰን ነው ይላሉ-ዶ/ር አፀደ። አንዲት ሴት ያለችበት የጋብቻ ሁኔታ የራሷ ምርጫና ውሳኔ እስከሆነና እስካመነችበት ድረስ ከማህበረሰቡ ለሚመጣው አመለካከት ራሷን እንደ ተበዳይ መቁጠሩ ተገቢ እንዳልሆነ ይገልፃሉ። ስለ ማዕረጉ ሳይሆን እንደ 'ቁሞ ቀር' የሚባሉ የማህበረሰቡን አመለካከቶች መሞገት ያስፈልጋል ሲሉም ያክላሉ።
53075610
https://www.bbc.com/amharic/53075610
በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የሚደረገው ድርድር፡ የግብፅ ፍላጎትና የኢትዮጵያ ውሳኔ
በአሜሪካና በዓለም ባንክ አሸማጋይነት ሲደረግ የነበረው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር ፍሬ አለማፍራቱን ተከትሎ ዳግም የሦስትዮሽ ድርድሩ በበይነ መረብ የቪዲዮ ኮንፈረንስ ለአምስት ቀናት ያህል ተካሂዷል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የውሃ ሙሌትና ዓመታዊ የውሃ አለቃቅን በተመለከተ ሦስቱ አገራት የሚያደርጓቸው ውይይቶች ከመቋጨታቸው በፊት ኢትዮጵያና ግብፅ ለድርድሩ አለመሳካት ምክንያት እርስ በርስም እየተወነጃጀሉ ነው። ሰኞ ዕለትም ድርቅ በሚከሰትበት ወቅት የሦስቱ አገራት ጥቅም በምን መልኩ ይሆናል የሚለው ላይ የተወያዩ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ የግድቡን ሙሉ አቅም እየተጠቀመች ድርቅ ቢያጋጥም ችግሩ የሦስቱም አገራት ኃላፊነት ነው የሚል አቋም ላይ መድረሷንም የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር መግለጫ አስረድቷል። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ትናንት አመሻሽ ላይ በሰጡት መግለጫ ግብፅ ግትር ያለ አቋም በመያዟ ድርድሩ ወደተፈለገው ደረጃ ሊሄድ እንዳልቻለ አስታውቀዋል። ግብፅ በአንድ በኩል ታሪካዊ ተጠቃሚነት በሚል መርህ የወንዙን ውሃ ሙሉ በሙሉ በበላይነት ለብቻዋ የመጠቀም ፍላጎት እንዳለ አፅንኦት በመስጠትም ተናግረዋል። "የተለያየ መንገድ ፈልገው ድርድሩን ለማቋረጥ ነው ሃሳባቸው። ለመስማማት የፈለግነውን ስጡን ይላሉ። ካልሰጣችሁን አንስማም ይላሉ። የሚፈልጉትን በሙሉ ካላገኙ አንስማማም ይላሉ። ካልተስማማን ደግሞ ውሃ አትሞሉም ይሉናል" ብለዋል። በድርድሩ ላይ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌትና ዓመታዊ አለቃቅና አስተዳደርን የተመለከተ ሰነድ ያቀረበች መሆኑን የገለፁት ሚኒስትሩ፤ በቀረበው ሰነድ ላይ ውይይት አድርጎ ውጤት ከማምጣት ይልቅ ድርድሩን የማፋረስና ኢትዮጵያን የማጠልሸት ሥራዋን ቀጥላለች በማለት ወንጅለዋል። "ድርድር በባህርዩ ሰጥቶ መቀበል ነው። እኛ እየተደራደርን ያለነው ምንም መስጠት ከማይፈልጉ ነገር ግን ሁሉንም መውሰድ የሚፈልጉ ኃይሎች ጋር ነው። "ከእንዲህ አይነቱ ኃይል ጋር መደራደር በጣም አስቸጋሪ ነው። ሁሉንም ልውሰድ ከሚል ኃይል ጋር መደራደር ምንም አይነት ስምምነት ላይ ሊደረስ አያስችልም" የሚሉት አቶ ገዱ በግብፅ በኩል የሚታየው "ስስታምነት" ነው ብለውታል። አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ኢትዮጵያ የአባይን ውሃን በፍትሐዊና ምክንያታዊ ተጠቃሚነት መርህ የመጠቀም እንጂ የታችኞቹ ተፋሰስ አገራትን በፍጹም የመጉዳት ፍላጎት እንደሌላትም አረጋግጠዋል። ነገር ግን በግብፅ በኩል የሚታየው በድርድሩ ችግሮችን የመፍታት አካሄድ ሳይሆን በተለያዩ አቅጣጫዎች በመሄድ ኢትዮጵያ ላይ ጫና የመፍጠር አካሄድ ነው ብለዋል። "በድርድሩ የተለመደ አቀራረብ ይዘው ነው የመጡት፤ በአንድ በኩል ከእኛ ጋር ይደራደራሉ በሌላ በኩል ደግሞ ወደተለያዩ ዓለም አቀፍ አካላት በተለይም ለፀጥታው ምክር ቤት ጉዳዩን ለማቅረብ ጥረት ያደርጋሉ። አሁንም በድርድሩ ሂደት አንድ እግራቸውን ኒውዮርክ (የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት) ሌላ እግራቸውን ድርድሩ ውስጥ አድርገው ቀጥለዋል። ሁለት መንታ መንገድ ይዘው ነው እየተደራደሩ ያሉት" ብለዋል። ግብፅ ለዘመናትም ኢትዮጵያ በአባይ ላይ ያላትን ጥቅም እንዳታስከብር ሴራ ስትጎነጉን ኖራለች በማለት የወነጀሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ግድቡን ለመስራት አቅም እንዳይኖር፣ እንዳይሰራ እንዲሁም ኢትዮጵያን በማዳከም ግብፅ እየሰራች ነው ብለዋል። በተለይም ከሰሞኑ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሽኩሪህ እየተደረገ ባለው የሦስትዮሽ ድርድር ምንም ለውጥ እንዳያመጣና ስምምነት ላይ ሳይደረስ የግድቡ የመጀመሪያ የውሃ ሙሌት ሥራ ለመጀመር ኢትዮጵያ መወሰኗ የግብፅን ጥቅም የሚጋፋ በመሆኑ አቤቱታዋን ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደምታስገባ አስታውቀዋል። ይህንንም አስመልክቶ በዚህ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ አቋም ምንድን ነው ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄም አቶ ገዱ ምላሽ ሰጥተዋል። "ለተባበሩት መንግሥታትም ይውሰዱት። የትም ቦታ ይውሰዱት ፤ የፈለገውን ነገር ይበሉ። ኢትዮጵያንም ስሟን ያጥፉ አንዳንድ ጊዜም ያስፈራሩ። የራሳችንን ከአገራችን የሚመነጨውን ውሃ፣ በራሳችን ግዛት የሚገነባውን ግድብ የአባይ ውሃ የመጠቀም መብታችንን በምንም ተአምር አሳልፈን ልንሰጥ አንችልም። ይሄንን ማወቅ አለባቸው፤ ለግብፅ ሕዝብም ማሳወቅ ኦለባቸው" ብለዋል። ግብፅ የሦስትዮሹን ድርድር አቋርጣ ከወጣች ሦስቱ አገራት ተቀምጠው የሚነጋገሩበት ጉዳይ ይፈርሳል፤ ኢትዮጵያም ከዚህ በኋላ ለድርድር የምትቀመጥበት ምንም ዓይነት መንገድ የለም ብለዋል። ለድርድር ወደ ኋላ እንደማትመለስም አስታውቀዋል። በውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ የሚካሄደው ድርድር የሚቀጥል ሲሆን በደቡብ አፍሪካ፣ የአውሮፓ ሕብረት እና አሜሪካ ታዛቢነትም እየተካሄደ ነው ያለው። ከሰሞኑ የኢትዮጵያ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሦስቱ አገራት ድርድር የግድቡ የመጀመሪያ ሙሌት እና ዓመታዊ አለቃቅ ላይ ብቻ የተወሰነ እንደሚሆን ገልፆ በግብጽ በኩል ድርድሩ ከሕዳሴው ግድብ ውሃ አሞላልና አለቃቀቅ አልፎ በውሃ ድርሻና አጠቃቀም ላይም እንዲሆንና የኢትዮጵያን የወደፊት በአባይ ውሃ የመጠቀም መብትን የሚገድብ ዓይነት ስምምነት ላይ እንዲደረስ ፍላጎቶች ያሉ መሆናቸውንም ጠቁሟል። ይህንንም ተከትሎ ከየግብፅ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ የሦስቱ አገራት ድርድር እንደተፈለገ መካሄድ ያልቻለው በኢትዮጵያ ችግር ነው ማለታቸው ውንጀላ መሆኑን የገለፀው ሚኒስቴሩ፤ በተቃራኒው ስምምነቶቹ ውጤታማ መሆን ያልቻሉት ግብፅ የቅኝ ግዛትን የውሃ ስምምነት ሙጥኝ ብላ በመያዟ እንደሆነ ገልጿል። ይህ ስምምነት ኢትዮጵያንም ሆነ የላይኛው ተፋሰስ አገራትን የተፈጥሮና ተገቢ የውሃ መብታቸውን የሚከለክል ነው ብሏል። ሚኒስቴሩ አክሎም የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብንም ግራ ለማጋባትም ሆነ ኢትዮጵያ የቅኝ ግዛት ስምምነትን እንድትቀበል የሚደረግ ጫና፣ ግፊትም ሆነ ዘመቻ ተቀባይነት የለውም ብሏል። ኢትዮጵያ በሌለችበት የተፈረመ ስምምነት እንዲሁም ሕጋዊ ከሆነው የአባይን ወንዝ መጠቀም መብት ለመካለከል ግብፅ የምትሄድበት መንገድንም እንደሚቃወም አስታውቋል። አገራቱ የግድቡን ደኅንነት ሕጎች፣ አካባቢያዊና ማኅበራዊ ግምገማ ጥናት እንዲሁም መመሪያዎችና ሕጎች አጠቃቀም ላይም የጋራ መግባባት ላይ እንደተደረሰም ገልጿል።
news-50654807
https://www.bbc.com/amharic/news-50654807
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ኢትዮጵያ ከኤርትራ የሚያደርጉት ጨዋታ አይካሄድም
የምስራቅና መካከለኛው አፍሪቃ የእግር ኳስ ውድድር ወይም በቅፅል ስሙ ሴካፋ ከቀጣዩ ቅዳሜ ጀምሮ በዩጋንዳ ይካሄዳል። በውድድሩ ምድብ ሀ ላይ የተመደቡት ኢትዮጵያ እና ኤርትራ እርስ በርስ ይገናኛሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን እንደገለጸው የእግር ኳስ ቡድኑ አባላት ወደ ውድድሩ አይሄዱም። • ሜሲ ለስድስተኛ ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊ ሆነ • ማንችስተር ዐይኑን የጣለባቸው የአቶ ምሥጢረ ኃይለሥላሴ ልጆች ስለዚህ በርካቶች በጉጉት ሲጠብቁት የነበረው የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ብሄራዊ ቡድን አባላት የሚያደርጉት ግጥሚያ አይደረግም ማለት ነው። ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ከአዘጋጇ ኡጋንዳ እና ቡሩንዲ ጋር በአንድ ምድብ ተደልድለው ነበር። ብሄራዊ ቡድኑ ለምን ወደ ኡጋንዳ እንደማይሄድ የጠየቅናቸው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን '' ምንም እንኳን የሴካፋ ውድድር ለብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች የሚፈሩበት ቢሆንም ከገንዘብ ጋር የተያያዘ ችግር ስላለብን ትልልቅ የሚባሉ የወዳጅነት ጨዋታዎች ላይ ወጪ ብናደርግ ይሻላል ብለን ወስነናል። በተጨማሪም ሊጉ ተቋርጦ ስለሆነ ውድድሩን የምንሳተፈው፤ ይህንን ከግምት ውስጥ አስገብተን ነው ውሳኔ ላይ የደረስነው'' ብለዋል። አክለውም '' በርግጥ አወዳዳሪው አካል የሚሸፍነው ነገር ቢኖርም፣ ከ 15 ዓመት በታችና የሴቶች ብሄራዊ ቡድን ውድድሮች ላይ ተሳትፈን ነበር፤ ከዚህም ጋር በተያያዘ ያነሳናቸው የራሳችን ጥያቄዎች ነበሩ። በውድድሩም ያልተስማማንባቸው ነገሮች አሉ'' ብለዋል። በሌላ በኩል በኡጋንዳ አዘጋጅነት በሚካሄደው የሴካፋ የሴቶች ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ውድድርም ኢትዮጵያ እንደማትሳተፍ የእግር ኳስ ፌደሬሽኑ አስታውቋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ከፊፋ እና ከካፍ ከሚያገኛቸው ድጋፎች እንዲሁም ከድጋፍ ሰጪ አካላት ከሚመጡ ገቢዎች ውጪ ምንም አይነት የበጀት ድጋፍ እንደማይደረግለት የገለጹት አቶ ጥላሁን ''ብሄራዊ ቡድን የትም ሲሄድ ወጪውን በሙሉ የሚሸፍነው ፌደሬሽኑ ነው፤ በዚህ ምክንያት እንቸገራለን በማለት ሁኔታውን ያስረዳሉ። ''ለካፍም ኢትዮጵያ በውድድሩ እንደማትሳተፍ ቀድመን በደብዳቤ አሳውቀናል።'' • ተሰናባቹ ኡናይ ኤምሪን ሊተኳቸው የሚችሉ 7 አሰልጣኞች ኢትዮጵያና ኤርትራ በድንበር ምክንያት ጦርነት ውስጥ ከገቡ ጀምሮ በብሄራዊ ቡድን ደረጃ በየትኛውም ውድድር ተገናኝተው የማያውቁ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አሕመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ግን ነገሮች ተቀይረዋል። በርካታ የሁለቱም ሀገራት ደጋፊዎችም በውድድሩ የሁለቱን ሀገራት ብሄራዊ ቡድኖች ጨዋታ ለማየት በጉጉት እየተጠባባቁ ነበር። በኡጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ የፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ በሚካሄደው የሴካፋ ውድድር ሀገራት በሶስት ምድቦች ተከፍለው ይፋለማሉ።
news-53525198
https://www.bbc.com/amharic/news-53525198
አቶ ልደቱ አያሌው በፖሊስ ተይዘው ወደ ቢሾፍቱ ከተማ ተወሰዱ
የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) የብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት ፖለቲካኛው አቶ ልደቱ አያሌው በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፓርቲያቸው አስታወቀ።
አቶ ልደቱን ፖሊስ የያዛቸው በቅርቡ በቢሾፍቱ ከተማ ተከስቶ የነበረውን አለመረጋጋት በማስተባበርና በመደገፍ ተጠርጥረው እንደሆነ አቶ አዳነ ታደሰ የኢዴፓ ፕሬዝዳንት ለቢቢሲ ገልጸዋል። ዛሬ አርብ ረፋድ ላይ አዲስ አበባ ውስጥ በፌደራል ፖሊስ ተይዘው መኖሪያቸው ወደሚገኝበት የቢሾፍቱ ከተማ እንደተወሰዱ ተገልጿል። የፓርቲው ፕሬዝዳንት አቶ አዳነ የኦሮሚያ ፖሊስ አቶ ልደቱን ለመያዝ የመያዣ ትዕዛዝ ያወጣው ሐምሌ 03/2012 ዓ.ም እንደሆነና እስከ ዛሬ ሊያገኛቸው እንዳልቻለ መግለፁን ለቢቢሲ ተናግረዋል። የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ ባቀረበው ክስ ምክንያት በአቶ ልደቱ ላይ የእስር ማዘዣው በቢሾፍቱ ከተማ ፍርድ ቤት የወጣ እንደሆነ አቶ አዳነ በመጨመር ገልጸዋል። አቶ ልደቱ ነዋሪነታቸው ከአዲስ አበባ 40 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው በቢሾፍቱ ከተማ ውስጥ ሲሆን፣ ዛሬ ረፋድ ላይ የፌደራል ፖሊስ ስልካቸው ላይ በመደወል እንደሚፈለጉ በመግለፁ፣ ወደ ፌደራል ፖሊስ ቢሮ በመሄድ እዚያ በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና ፌደራል ፖሊስም ለሚፈልጋቸው የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ ለማስረከብ እንደወሰዳቸው አቶ አዳነ ገልጸዋል። አቶ ልደቱ የኢዴፓ መስራችና አባል አመራር ሆነው ለረጅም ዓመታት የቆዩ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ የድርጅቱ የብሔራዊ ምክር ቤት አባልና አብሮነት በሚባለው የፓርቲዎች ጥምረት ውስጥ የኢዴፓ አስተባባሪ ተወካይ ናቸው። አቶ ልደቱ በአወዛጋቢው የ1997 ምርጫ ላይ ተሳትፈው በማሸነፍ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የነበሩ ሲሆን በራሳቸው ፖለቲካዊ ህይወትና በአገሪቱ ፖለቲካ ዙሪያ መጽሐፍትን ጽፈዋል።
news-45218135
https://www.bbc.com/amharic/news-45218135
የሜክሲኮ ተማሪዎች ወሲባዊ ትንኮሳን የሚከላከል ካፖርት ፈለሰፉ
አራት ሜክሲኳውያን ተማሪዎች ከጾታዊ ጥቃት የሚከላከል ካፖርት ፈልስፈዋል። የካፖርቱ እጀታ የተሰራው ከሚነዝር ኤሌክትሪክ ሲሆን፤ ጥቃት የሚሰነዝር ሰው ካፖርቱን የለበሰን ሰው ክንድ ሲይዝ እንዲነዝረው ያደርጋል።
የካፖርቱ እጀታ ከነዛሪ ኤሌክትረክ የተሰራ ነው ተማሪዎቹ ካፖርቱን የፈለሰፉት ሀገራቸው ውስጥ የተንሰራፋውን ወሲባዊ ትንኮሳ ለመከላከል ሲሆን፤ "ውሜን ዌረብል"ወይም "እንስቶች የሚለብሱት" የተሰኘ ስያሜ ተሰጥቶታል። • ሴቶች እንዲደፈሩ ያበረታታው ግብጻዊ የህግ ባለሙያ ተፈረደበት • ካይሮ፡ ለሴቶች በጣም አደገኛ ከሆኑ ከተሞች አንዷ ከአራቱ ተማሪዎች ሁለቱ አናይድ ፓራ ኮሬዝ እና ኤስቴላ ጎሜዝ የሜካትሮኒክስ ኢንጅነሪንግ ተማሪዎች ናቸው። የሮቦቲክስ ተማሪዋ ግዌን ፓርክ እንዲሁም የህግ ተማሪ ጉዋዱልፔ ማርቲኔዝም ተሳትፈዋል። አራቱ የካፖርቱ ፈልሳፊዎች ፈልሳፊዎቹ የፈጠራ ኃሳቡ ብልጭ ያለላቸው ለአንድ የትምህርት ክፍለ ጊዜ ፕሮጀክት ሲያውጠነጥኑ ነበር። አናይድ ፓራ "ብዙ ሴት ጓደኞቻችን የሀይል ጥቃት ይደርስባቸዋል። ጾታን መሰረት ስላደረገ ጥቃት ጥናት ከሰራን በኃላ ካፖርቱን ለመስራት ወሰንን" ትላለች። በሚኖሩበት የሜክሲኮዋ ፑቤላ ግዛት በየቀኑ ወሲባዊ ትንኮሳ ይደርሳል። ካፖርቱ የተሰራው ከጥጥ ሲሆን፤ ዘጠኝ ቮልት የኤሌክትሪክ ሀይል የሚያመነጭ ባትሪ ውስጡ ተቀብሯል። የኤሌክትሪክ ገመዱ በካፖርቱ ውስጥ ለውስጥ ይዘዋወራል። ካፖርቱ ኤሌክትሪክ እንዲያመነጭ መዝጊያው (ዚፕ) ላይ ማብሪያና ማጥፊያ ተገጥሞለታል። ካፖርቱ የሚሰራው ቀልፉን በመጫን ነው አንድ ሰው ካፓርቱን የለበሰ ሰውን ለማጥቃት አስቦ የተጠቂውን ክንድ ቢይዝ የኤሌክትሪክ ንዝረት ይከተላል። አጥቂው በኤሌክትሪክ ንዝረቱ ሲንዘፈዘፍ ተጠቂው ከአካባቢው ርቆ ለመሸሽ ጊዜ ያገኛል። የህግ ተማሪው ጉዋዱልፔ ማርቲኔዝ፤ ካፖርቱን ጥቅም ላይ ማዋል የህግ ጥያቄ እንደማያስነሳ ሲያስረግጥ "አላማው ራስን መከላከል ብቻ ነው" በማለት ነው። ካፖርቱ የሚያመነጨው የኤሌክትሪክ ንዝረት ለህይወት ስለማያሰጋ እንደ መሳሪያ ሊቆጠር እንደማይቻልም ያስረዳል። • ሞርጋን ፍሪማን በፆታዊ ትንኮሳ ለቀረበባቸው ውንጀላ ይቅርታ ጠየቁ • ቢል ኮዝቢና ፖላንስኪ ከኦስካር አካዳሚ ተባረሩ የካፖርቱን ንድፈ ሀሳብ የሚያሳይ የሙከታ ስራ (ፕሮቶታይፕ) ለማጠናቀቅ ሶስት ወር ወስዶባቸወሰል። በቀጣይ የኤሌክትሪክ ኃይሉን ከካፖርቱ እጀታ በዘለለ በሌሎች የካፖርቱ ክፍሎችም የመግጠም እቅድ አላቸው። ተማሪዎቹ ተመሳሳይ መንገድ በመጠቀም ነዛሪ ካናቴራ፣ ቀሚስና ሱሪም ለመስራት አስበዋል። ካፖርቱ ገበያ ላይ ከዋለ 50 ዶላር የሚሸጥ ይሆናል።
49724501
https://www.bbc.com/amharic/49724501
ዋሾዎችን ለመለየት የሚረዱ መንገዶች
እውነቱን ተናግሮ የመሸበት ማደር የሚሉ ዓይነት ሰው ነዎት? ወይስ ዋሽቶ ማስታረቅ በሚለው ሀሳብ የሚያምኑ?
ብዙም ጉዳት የማያስከትሉ ውሸቶች ለማኅበረሰብ በጋራ መቀጠል አስፈላጊ እንደሆኑ ይታመናል። ሰዎች የሚናገሩት ነገር ውሸት ይሁን ወይም እውነት ማወቅ ቀላል ላይሆን ይችላል። ነገር ግን ሰዎች ሲዋሹ ለማወቅ የሚረዱ መንገዶች አሉ። • ኤርትራ ፖለቲከኞችን እና ጋዜጠኞችን እንድትለቅ ተጠየቀ • በሳዑዲ የደረሰው ጥቃት እጅጉን እንዳሳሰባቸው የኔቶ ኃላፊ ገለፁ በመዋሸት ሰላምን ማስጠበቅ ለመሆኑ ውሸት ምንድን ነው? አንድ ሰው ሆነ ብሎ፣ ለማታለል አቅዶ፣ ከእውነታ የራቀ መረጃ ሲሰጥ እየዋሸ ነው እንላለን። ግን ምን ያህሎቻችን ሙሉ በሙሉ እውነት እንናገራለን? ከአንድ ሰው ጋር ሲያወሩ፤ ያ ሰው ስለእርስዎ የሚያስበውን ነገር አንዳችም ሳያስቀር የሚነግርዎ ይመስልዎታል? ሰዎች ስለእርስዎ ያላቸውን አመለካከት አንድም ሳያስቀሩ ቢዘረግፉት፤ አብሮነታችሁ ጥያቄ ውስጥ ሊገባ ይችላል። ብዙዎቻችን መቶ በመቶ ሀቀኛ መሆን አዋጭ እንዳልሆነ እናምናለን። ስለዚህ አንድን ሰው 'ውይ ጸጉርህ ሲያስጠላ' አንለውም። ምንም እንኳን ጸጉሩን ባንወደውም፤ እውነታውን እንደብቃለን። እውነታውን በመደበቃችንም ከሰውየው ጋር ያለን ግንኙነት ጤናማ ይሆናል። ከሦስት ሰው አንዱ በየቀኑ ይዋሻል የሥነ ልቦና ተመራማሪው ሪቻርድ ዊስማን እንደሚናገሩት፤ ከሦስት ሰዎች አንዱ በየቀኑ ቢዋሹም፤ ወደ አምስት በመቶ የሚሆኑ ሰዎች 'ዋሽተን አናውቅም' ይላሉ። ሰዎች በቀላሉ መዋሸት ቢችሉም ሌላ ሰው ሲዋሽ ለማወቅ እንደማይችሉ ተመራማሪው ያስረዳሉ። ተመራማሪው ቤተ ሙከራ ውስጥ የሚዋሹ ሰዎች የሚታይበት ቪድዮ ከፍተው 'እነዚህ ሰዎች እየዋሹ ነው?' ብለው ብዙ ሰዎችን ጠይቀው ነበር። ከተጠያቂዎቹ መካከል ቪድዮው ላይ ከሚታዩት ሰዎች ዋሾዎቹን መለየት የቻሉት 50 በመቶው ብቻ ናቸው። ተመራማሪው እንደሚናገሩት፤ ፖሊሶች፣ ጠበቆች እና ዳኞችም ዋሾዎችን ለመለየት ይቸገራሉ። ጥናቶች እንደሚያሳዩት፤ ውሸታም ሰዎችን በማወቅ ረገድ ውጤታማ ሆነው የተገኙት ታራሚዎች ናቸው። • ሶስት ሚሊየን ሶሪያውያን ወደ ሃገራቸው ሊመለሱ ነው • የምዕራብ ኦሮሚያ ነዋሪዎች ስጋትና ሰቆቃ ሰው ሲዋሽ ለማወቅ አይንዎን ሳይሆን ጆሮውን አስልተው ይጠብቁ ብዙ ጊዜ ሰዎች ሲዋሹ ማወቅ የማንችለው ትኩረታችን እይታ ላይ ስለሆነ ነው። አዕምሯችንም ለእይታ ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣል። በርካቶች ዋሾዎችን ለመያዝ የሚጠቀሟቸው መንገዶች አነዚህ ናቸው፦ ግለሰቡ ሲያወራ ይቁነጠነጣል? ፊቱ ላይ ዋሾነት ይነበባል? ተመራማሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ግን እይታ ብቻውን በቂ አይደለም። እንዲያውም የሰዎችን ንግግር አትኩሮ በማዳመጥ እየዋሹ መሆን ወይም አለመሆኑን መረዳት ይቻላል፥ ውሸታም ሰዎች ለአንድ ጥያቄ መልስ ከመስጠታቸው አስቀድመው ዘለግ ላለ ሰዓት ያሰላስላሉ። ራሳቸውን ከወሬው ለማራቅ ስለሚሞክሩ 'እኔ'፣ 'የኔ' የሚሉ አገላለጾችን አብዝተው አይጠቀሙም። ግንባርዎ ላይ 'ኪው' በመስራት ዋሾ መሆን አለመሆንዎ ሊታወቅ ይችላል የሥነ ልቦና ተመራማሪው ሪቻርድ ዊስማን፤ ሰዎች በጣታቸው የኪው ምልክት ሠርተው ግንባራቸው ላይ እንዲያሳዩ በማድረግ ውሸታም ናቸው ወይስ ሀቀኛ? ለሚለው ጥያቄ መልስ ማግኘት እንደሚቻል ይናገራሉ። "Q" የተባለቸውን የእንግሊዘኛ ፊደል በጣትዎ ከሠሩ በኋላ ግንባርዎ ላይ ሲያሳርፉት የፊደሉ ጭራ ያደላው ወደ ግራ አይንዎ ነው ወይስ በስተቀኝ ወዳለው አይንዎ? የፊደሉን ጭራ ወደግራ አይንዎ ካደረጉ የለየልዎ ውሸታም ነዎት ማለት ነው። የ 'ኪው' ጭራ ወደቀኝ አይንዎ ካደላ ደግሞ ሀቀኛ የመሆን እድልዎ ሰፊ ነው። ተመራማሪው ከዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሱት ያለምክንያት አይደለም። አንድ ሰው 'ኪው' ሠርቶ ግንባሩ ላይ ሲያሳርፍ ሰው ጭራውን ማየት በሚችልበት አቅጣጫ ካደረገ፤ ለሰዎች አመለካከት ከፍተኛ ቦታ ይሰጣል ማለት ነው። ስለዚህም በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ይዋሻል። በተቃራኒው የፊደሉ ጭራ ለተናጋሪው በሚታይበት አቅጣጫ ከሆነ፤ ተናጋሪው ሰዎች እንዴት ያዩኛል? ብሎ ብዙም ሳይጨነቅ እቅጭ እቅጩን እንደሚያወራ ያሳያል። • አል-ቃይዳ ከቢን ላደን ልጅ መገደል በኋላ • አውስትራሊያዊው ተናካሽ ቁራ ሲሸሽ ከብስክሌት ወድቆ ሞተ ሰው ብቻ ሳይሆን እንስሳትም ይዋሻሉ እዚህ ምድር ላይ የሚዋሹት የሰው ልጆች ብቻ አይደሉም። እንስሳትም አጭበርባሪ ናቸው። ለምሳሌ ስክዊድ የተባለው የአሳ ዝርያ ራሱን ከአጥቂ ወንድ ለመከላከል ሴት መስሎ ይንቀሳቀሳል። ወንድ ዶሮ ምግብ በአካባቢው ባይኖርም፤ ምግብ ሲያገኝ የሚያወጣውን ድምጽ ተጠቅሞ ሴት ዶሮ ይጠራል። ጥሪው ውሸት ላይ የተመሰረተ ነው። የሰው ልጅ መዋሸት የሚጀምረው መቼ ነው? ተመራማሪው ሪቻርድ እንደሚናገሩት፤ ሰዎች ከልጅነታቸው አንስቶ ሊዋሹ ይችላሉ። ለምሳሴ አንድን ህጻን 'ከኋላህ የምትወደውን መጫወቻ አስቀምጬልሀለሁ፤ ነገር ግን ዞር ብለህ እንዳታይ' ብለነው ከአንድ ክፍል ብንወጣ፤ ልጁ መጫወቻውን ዞሮ መመልከቱ አይቀርም። ተመራማሪው በሠሩት ጥናት መሰረት፤ 50 በመቶው ልጆች 'መጫወቻውን አላየሁም' ብለው ዋሽተዋል። በጥናቱ ውስጥ የተካተቱት ህጻናት ከሦስት ዓመት አይበልጡም። ጥናቱ ሰዎች በለጋ እድሜያቸው መዋሸት እንደሚጀምሩ ማሳያ ነው። የሰው ልጅ ከጥንትም ይዋሻል የሰው ልጅ በስልት መዋሸትን የተካነበት ከጥንት ጀምሮ ነው። ለምሳሌ ቺምፓንዚዎች ምግብ ለማደን ሲሉ ብዙ ስልቶች ይጠቀማሉ። ቺምፓንዚዎች ምግብ ለማግኘት እርስ በእርስ የሚጣሉ ከሆነ ጸቡ ማቆሚያ አይኖረውም፤ ስለዚህ አንዳቸው ሌላቸውን የሚያታልሉበት መንገድ ይዘይዳሉ። ጥናቶች እንደሚያሳዩት፤ ዘመናዊ ሰው ይህንን ስልት እያሳደገ መጥቷል። መዋሸት ለሰው ልጆች አብሮነትና፣ ለማኅበረሰቡ በጋራ መቀጠል አስፈላጊ እንደሆነ ተመራማሪዎች ይናገራሉ።
news-54431822
https://www.bbc.com/amharic/news-54431822
ኮሮናቫይረስ ፡ ጽኑ ህሙማንን ያለንክኪ ገላቸውን የሚያጥብ አልጋ የሰሩት ኢትዮጵያዊ
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በዓለማችን ከ1 ሚሊየን በላይ ሚሆኑ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል። የወረርሽኙ ሥርጭት አሁንም በአንዳንድ አገራት እያገረሸ ነው።
በሽታው እጅግ አስከፊ ነው። የታመሙ ሰዎች እንደየባህላቸው በወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዳይጠየቁ፤ በሽታው የበረታባቸው ሰዎች ሲሞቱ ደግሞ ቀብራቸው ላይ ሰው እንዳይቆም የገደበ በሽታ ነው። በተለይ በሽታው የተከሰተ ሰሞን በቀብር ላይ የሚገኙ ጥቂት ሰዎች ብቻ ነበሩ። የሚወዷቸውን ሰዎች የቀብር ሥነ ሥርዓት በርቀት በኢንትርኔት አማካይነት ተከታትለው 'እርማቸውን ያወጡ' በርካቶች ናቸው። ይህ ሁሉ የሚደረገው የበሽታውን ሥርጭት ለመቆጣጠር ነው። በኮሮናቫይረስ በጽኑ የታመመ የቤተሰብ አባልን ማጉረስ፣ ማጠብ፣ ከተኙበት ማገላበጥ፣ መደገፍማ የማይታሰብ ነው። ታዲያ በሆስፒታል ውስጥ ከሐኪሞች ጋር ብቻ ተፋጠው ያሉ ራሳቸውን መደገፍ የማይችሉ ጽኑ ህሙማን ስቃዩን እንዴት እያሳለፉ ይሆን? በዚህ ወረርሽኝ ታመው ነገር ግን የቤተሰብና የወዳጆቻቸውን ድጋፍና እንክብካቤ ማግኘት ያልቻሉ ጽኑ ህሙማን ጉዳይ ያሳሰባቸው አንድ ኢትዮጵያዊ ችግራቸውን በተወሰነ ደረጃም ቢሆን የሚያቃልል አንድ የፈጠራ ሥራ ይዘው ብቅ ብለዋል። ይህ የፈጠራ ሥራ በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከሚያስችሉና በኢትዮጵያ ባሳለፍነው 2012 ዓ.ም በአዕምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤት ከተመዘገቡ ስምንት የፈጠራ ሥራዎች መካከል አንዱ መሆኑን የተቋሙ የፓተንት መርማሪ አቶ ጌታቸው ጣፋ ለቢቢሲ ገልፀዋል። ያለንክኪ ገላን የሚያጥበው ሁለገቡ አልጋ አልጋው ሁለገብ ነው። ሁለገብ ስንል ለተለያየ አገልግሎት ይውላል ማለታችን ነው። ሲያስፈልግ እንደ ፍራሽ አልጋ ላይ ማስቀመጥ ይቻላል። እንደ ቃሬዛ፣ እንደ ብርድ ልብስ፣ እንደ የአስክሬን ሳጥንም መጠቀም ይቻላል። ብርድ ከሆነ ማሞቂያ፤ ሙቀት ከሆነ ደግሞ ማቀዝቀዣ ተገጥሞለታል። እዚያው ውስጥ ሆኖ ያለማንም ረዳት ገላን መታጠብ ያስችላል። የፈጠራ ሥራ ባለቤቱ ብርሃኔ የኋላእሸት ይባላሉ። በሙያቸው የኤሌክትሪክ ባለሙያ ናቸው። በላውንደሪ እጥበት ንግድ ላይም ተሰማርተው ይገኛሉ። ከሙያቸው ጋር የተያያዙ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎችን የመስራት ልምድ አላቸው። አቶ ብርሃኔ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ይህንን የፈጠራ ሥራ የሰሩት ኮቪድ-19 ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱ በተረጋገጠ በሁለተኛው ሳምንት ነበር። ለዚህ ፈጠራቸው መነሻ ነበራቸው። አንድ ጊዜ የኤሌክትሪክ ጥገና ባለሙያ በመሆናቸው የቴክኒክ ሥራ ለመስራት አዲስ አበባ ውስጥ ወደሚገኘው ኮቪድ-19 ሕሙማን ማዕከል ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ያመራሉ። እዚያም ጽኑ ህሙማንን የማየት አጋጣሚው ነበራቸው። ጽኑ ህሙማኑ በበሽታው ምክንያት ስለሚዳከሙና አጋዥ የመተንፈሻ መሳሪያ ስለሚገጠምላቸው መንቀሳቀስ አይችሉም። በሽታው ደግሞ ንክኪን ስለማይፈቅድ እንደልባቸው ቶሎ ቶሎ ሰውነታቸውን እንዲታጠቡ የሚረዳቸው የቅርብ ሰው የላቸውም። ይህን ጊዜ ነበር የፈጠራ ሥራው ሃሳብ ብልጭ ያለላቸው። ከዚያም ህሙማኑ እዚያው በተኙበት ሆነው በ'ስቲም' [እንፋሎት] እና ለብ ባለ ውሃ ገላቸውን የሚያጥባቸው አልጋ ሰሩ። አልጋው የተሰራው ቆዳ ከሚመስል ፕላስቲክ ሲሆን ልክ እንደ 'ስሊፒንግ ባግ' [በዚፕ የሚዘጋ የመተኛ ሻንጣ] ዓይነት ነው። ይህን ፈጠራ አልጋ ላይ በማስቀመጥም እንደ ፍራሽና ብርድልብስ ጠቅም ላይ ሊውል ይችላል። ጋላ መታተብ የሚፈልግ ህመምተኛ በዚፕ ወደ ሚዘጋው መታጠቢያው ውስጥ ይገባል። ሻንጣው የንፁህ ውሃ ማስገቢያና የቆሻሻ ውሃ ማስወገጃ ቱቦ ተገጥሞለታል። እዚያው ውስጥ ሆነው ገላቸውን በውሃ ግፊት ይታጠባሉ። ከታጠቡ በኋላም ቆሻሻ ውሃውን በተገጠመለት የማስወገጃ ቱቦ በመልቀቅ በተገጠመለት ፋን [በማድረቂያ] ሳይንቀሳቀሱ ሰውነታቸውን ማደራረቅ ይችላል። በአልጋው ላይ የተገጠመው የእንፋሎት [ስቲም] ማሽን ብርድ ብርድ ሲላቸው ያሞቃቸዋል። ሰውነታቸው እንዲፍታታም እንደ ውሃ ገንዳ ሊጠቀሙበት ይችላሉ። ሙቀት ሲሰማቸው ቀዝቃዛ አየር፤ ሲበርዳቸው ሙቀት መጨመርና ያለውን የአየር ሁኔታ ማስተካከልም ያስችላል። "አልጋው እንደ ማንኛውም አልጋ ምቹ ነው" የሚሉት አቶ ብርሃኔ፤ የተገጠመለት የአየር ሁኔታ ማስተካከያው ምን አልባት ንዝርት ሊያመጣ ይችላል የሚል አስተያየት እንደተሰጣቸውና ያን አሻሽለው ለመስራት እየሞከሩ መሆኑን ገልፀዋል። ጽኑ ህሙማኑ ሕይወታቸው ካለፈም የሻንጣውን ዚፕ በመዝጋት አስከሬናቸው በሙቀት እንዲደርቅ በማድረግ፤ ቱቦዎቹን በማላቀቅ ያለምንም ንክኪ ወደ ቀብር ለመሸኘትም ያስችላል። "አልጋም፣ የሬሳ ሳጥንም፣ ብርድ ልብስም ነው" ይላሉ አቶ ብርሃኔ፤ በተላላፊው የኮሮናቫይረስ ምክንያት በጽኑ የታመሙ ሰዎችን ለመንከባከብ የሚረዳውን የፈጠራ ሥራቸውን ሲገልጹት። የዚህ ፈጠራ ሥራ አገልግሎቱ ግን ይህ ብቻ አይደለም። ከገጠር አካባቢ የሚመጡ ህሙማንን እንደ ቃሬዛ በመጠቀም የበሽታውን ስጋት በሚያስወግድ ሁኔታ ያለ ንክኪ ወደ ህክምና ተቋማት ለመድረስም ጥቅም ላይ መዋል ይችላል። በአንቡላንሶች ውስጥም ህሙማኑን በምቾት ለማውረድና ለማንቀሳቀስ በሚያስችል መልኩ የተሰራ ሲሆን፤ እንዲሁም በገጠር አካባቢ በሜዳ ላይ፣ በትምህርት ቤትም ሆነ በስፖርት ሜዳ በቀላሉ የሚጎተት ሆኖ ተዘጋጅቷል። "በአንድ ቀን ከ500 እስከ 600 አልጋዎች ሊመረት ይችላል" የሚሉት አቶ ብርሃኔ፤ ነገር ግን በዚህ ዘመን አስፈላጊ ነው የተባለውን ፈጠራቸውን ወደ ምርት እንዲያስገቡ አስተያየት ቢሰጣቸውም፤ ድጋፍ በማድረግ አብሯቸው የሚሰራ አካል እንዳላገኙ ተናግረዋል። የፈጠራውን ሃሳብ ወደ ተግባር በመለወጥ ባለፉበት ሂደት ውስጥ እስካሁን ድረስ ለሙከራ ሥራቸው ወደ 200 ሺህ ብር ገዳማ እንዳወጡም ገልፀዋል። አቶ ብርሃኔ ከዚህ በተጨማሪም በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ጉዳት እያደረሰ ያለውን የአንበጣ ለመከላከል ያስችላል ያሉትን ፈጠራቸውን ባለፈው ዓመት አበርክተው እንደነበር ያስታውሳሉ። ለዚህም በባትሪና በፀሐይ ኃይል ቻርጅ ተደርጎ አንበጣን የሚገድል በእጅ የሚያዝና መኪና ላይ የሚገጠም መሳሪያ ቢሰሩም ፈጠራቸውን ሥራ ላይ ለማዋል ቀርቶ ለማት ፈቃደኛ የሆነ ጉዳዩ የሚመለከተው አካል ማግኘት እንዳልቻሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚህም ሳቢያ "የፈጠራ ሥራን የሚደግፍና የሚያበረታታ አሰራር የለም" ሲሉም ቅሬታቸውን አቅርበዋል። ነገር ግን በዚህ ተስፋ ያልቆረጡት አቶ ብርሃኔ የፈጠራ ሥራቸው ወደ ምርት ከገባ ለአገር ውስጥና ለውጭ ገበያ የማቅረብ እቅድም አላቸው።
news-45911041
https://www.bbc.com/amharic/news-45911041
በአውስትራሊያ ገንዘብ ለማግኘት ካንሰር ታምሜያለሁ ብላ ያጭበረበረችው ክስ ተመሰረተባት
በአውስትራሊያ የምትገኝ አንዲት ሴት ካንሰር ታምሜያለሁ ብላ በማጭበርበር እርዳታ ከሚያሰባስብ ድረገፅ 55 ሺ ዶላር በመቀበሏ ክስ ተመስርቶባታል።
የ27 ዓመቷ ሉሲ ዊይላንድ የማህበራዊ ሚዲያንም በመጠቀም የማህፀን ካንሰር በሽታ ጋር እንዴት እየታገለች እንዳለችም በተደጋጋሚ ትፅፍ እንደነበር ፍርድ ቤቱ ገልጿል። ፖሊስ ጨምሮ እንደገለፀውም የገንዘብ እርዳታንም ለመጠየቅ የህዝቡን ዕምነትም ጥያቄ ውስጥ ከታዋለች ብሏል። ለእስር የበቃችውም በአንድ ግለሰብ ጥቆማም እንደሆነ ተገልጿል። •አምነስቲ ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉና ሚካኤል መላክ እንዲለቀቁ ጠየቀ •"የመከላከያ ሚኒስቴርን በተሻለ መልኩ መምራት ይቻላል" ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በኢንስታግራም ላይ በለጠፈችው ፎቶ ሉሲ ዊይላንድ የኦክስጅን ጭምብልን ጨምሮ በተለያዩ የህክምና ቁሳቁስ ተከባ ታይታለች። በሌሎች ፎቶዎችም ላይ በህክምና ቦታ ላይ ፀጉሯ ሙሉ በሙሉ ተላጭቶ የሚሰሟትን ስሜቶችም አጋርታለች። "ከመጠን ያለፈ ድካም ይሰማኛል፤ እንደተለመደው ድጋፋችሁን ለምትሰጡኝ ሁሉ አመሰግናለሁ" ብላለች። በአንዳንድ ፎቶዎቿ ላይ የሚታየው የህይወት አጋሯ ስለማጭበርበሯ ይወቅ አይወቅ ግልፅ አይደለም ተብሏል። ጉዳዩን በዋነኝነት የያዘው መርማሪ ክሪስ ላውሰን ለሪፖርተሮች ሐሙስ እለት እንደተናገረው " በጣም አሳዛኝ ነው። በማህበረሰባችን የሚገኙ ትክክለኛ ታማሚዎችና እሷን የረዷት ናቸው በዚህ ወንጀል ተጠቂ የሆኑት" ብለዋል። ጥርጣሬዎች የተነሱት የማህበረሰቡ አባላት እርስ በርስ የሚጣረሱ ነገሮችን ከሰሙ በኋላ መሆኑን ኤቢሲ የተባለው የሚዲያ ወኪል ዘግቧል። ሉሲ ዊይላንድ ዋስትናዋን ባትከለከልም ፓስፖርቷ እንደተወሰደባት ተገልጿል። ፍርድ ቤቱ ለታህሳስ ቀጠሮ ሰጥቷታል። ጎ ፈንድ ሚ ተብሎ የሚታወቀው ድረ ገፅ ምርመራውን እንደሚያግዙ ገልፀው ገንዘቡም ለለጋሾቹ እንደሚመለስ ገልፀዋል።
news-48456159
https://www.bbc.com/amharic/news-48456159
ኩምሳ ዲሪባ (መሮ)፡ የኦነግ ጦር መሪ በትግላችን እንቀጥላለን አለ
በምዕራብ ኦሮሚያ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የጦር መሪ የሆነው ኩምሳ ዲሪባ ወይም መሮ፤ በምዕራቡ ክፍል የሚገኘው የኦነግ ጦር የትጥቅ ትግል ማድረጉን እንደሚቀጥል ለቢቢሲ ተናገረ።
የምዕራብ ኦሮሚያ የኦነግ ጦር መሪ መሮ (ግራ) እና የኦነግ ሊቀመንበር ዳውድ ኢብሳ (ቀኝ)። መንግሥትን እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባርን ለማስታረቅ ተዋቅሮ የነበረው ኮሚቴ ትናንት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ባቀረበበት መድረክ ላይ የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከአሁን በኋላ ኦነግ ታጥቆ የሚንቀሳቀስ የጦር ኃይል አይኖረውም ማለታቸውን ተከትሎ ነው የጦሩ መሪ ይህን የተናገረው። • በምዕራብ ኦሮሚያ ስድስት ሰዎች መገደላቸው ተሰማ በምዕራብ ኦሮሚያ የጦር መሪ የሆነው ኩምሳ ዲሪባ ወይም መሮ፤ ''የተለወጠ ነገር የለም'' በማለት ከኦነግ ሊቀ መንበር በተለየ መልኩ የኦነግ ጦር የትጥቅ ትግል ማድረጉን እንደሚቀጥል ለቢቢሲ ተናግሯል። መሮ መከላከያው፣ ፖሊስ እና የደህንነት አካሉ ሙሉ በሙሉ የፓርቲ ወገንተኝነቱን አቁሞ የሕዝብ ወገንተኝነቱን እስካላረጋገጠ ድረስ የመንግሥትን ጥሪ አንቀበልም ብሏል። ''እኛ ለፓርቲ ወግኖ ሕዝብን የሚጎዳ የመከላከያ አካል መሆን አንሻም'' ሲል ከዚህ በፊት ከመንግሥት ጋር በተደረሰው ስምምነት የግንባሩ ታጣቂዎች ከመንግሥት የጸጥታና የመከላከያ ኃይል ጋር ለማካተት የቀረበውን ሃሳብ መሮ ውድቅ አድርጎታል። • በጦላይ የኦነግ ሠራዊት አባላት ላይ የተከሰተው ምንድን ነው ? ጨምሮም ''ለጊዜያዊ ጥቅም ተብሎ በንግግር ተሸፋፍኖ የሚያልፍ ነገር አያዛልቅም። ነገ እሳት መነሳቱ አይቀርም። ዘላቂ መፍትሄ በሚሰጡ ምክክሮች ላይ ለመወያየት ግን ዝግጁ ነን'' በማለት ለድርድር ዝግጁ መሆኑን ጠቁሟል። መንግሥትን እና ኦነግን ለማስታረቅ ተዋቅሮ የነበረው ኮሚቴም ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት መሣሪያ አንገበው ጫካ ገብተው የነበሩ የኦነግ ወታደሮች በሰላማዊ መንገድ ትግላቸውን እንዲቀጥሉ ወይም ወደሚዘጋጅላቸው ስፍራ ለስልጠና እንዲገቡ ጥረት ሲያደርግ እንደቆየ አስታውሷል። ኮሚቴው የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በተገኙበት ነው ሪፖርቱን ያቀረበው። • «ኦነግ ሀገር ለመገንጠል ነው የምሠራው ብሎ አያውቅም» ሽጉጥ ገለታ (ዶ/ር) ሪፖርቱ በቀረበበት ወቅት የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ፤ ኦነግ ከአሁን በኋላ ጦር አንግቦ የሚንቀሳቀስ ሠራዊት አይኖረውም፤ መንግሥት ሕግ ለማስከበር የሚወስደውን እርምጃም እንደግፋለን ብለዋል። የኮሚቴው ሪፖርት ቁልፍ ነጥቦች የአስታራቂ ኮሚቴውን ሪፖርት ያቀረቡት አቶ በቀለ ገርባ ሲሆኑ፤ ባቀረቡት ሪፖርት ውስጥ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አንስተዋል። ኦነግ ከአሁን በኋላ ታጥቆ የሚንቀሳቀስ ጦር ስለማይኖረው ኮሚቴው የተቋቋመበትን ዓላማ ማሳካቱን ጠቅሰው፤ ኮሚቴው በኦነግ እና በመንግሥት መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት ታስረው የነበሩ ሰዎች ከእስር እንዲለቀቁ ጠይቋል። • ከተገደሉት አንዱ የማዕድን ኩባንያው ባለቤት ነበር በተጨማሪውም ኮሚቴው ኦነግ በሰላማዊ መንገድ ፖለቲካዊ ትግሉን ለመቀጠል በሚያደርገው እንቅስቃሴ የመንግሥት ድጋፍ እንዳይለይ እና የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ወደተዘጋጀላቸው ስፍራ የገቡ የኦነግ ጦር አባላት ቃል የተገባላቸው ሁሉ ተፈጻሚነት እንዲኖረው ኮሚቴው ጠይቋል።
news-57188715
https://www.bbc.com/amharic/news-57188715
እነ አቶ ጃዋር መሀመድ የፍርድ ቤት ቀጠሯቸው ከሁለት ዓመት በኋላ እንዲሆን ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ተደረገ
እነ አቶ ጃዋር መሐመድ የፍርድ ቤት ቀጠሯቸው ከሁለት ዓመት በኋላ እንዲሆን ያቀረቡትን ጥያቄ ፍርድ ቤት ውድቅ አደረገ።
የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር የሆኑት ጃዋር መሐመድ እና ሌሎችም በፀረ ሽብር አዋጅ እና በሌሎችም የተከሰሱ ሲሆን ቀጠሯቸው ከሁለት ዓመት በኋላ እንዲያዝ ቢጠይቁም ፍርድ ቤት ጥያቄቸውን ውድቅ አድርጓል። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የእነ ጃዋርን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉን ጠበቃቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ መዝገብ ስር የተከሰሱት በዛሬው ዕለት ግንቦት 12፣ 2013 ዓ.ም የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀርበዋል። ከተከሳሾቹ ጠበቆች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ቱሊ ባይሳ ለቢቢሲ እነደተናገሩት የዛሬ ችሎቱ የተሰየመው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ መሰረት በማድረግ ጉዳያቸውን ለማየት ነበር። ትናንት ረቡዕ ዕለት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእነ አቶ ጀዋር መሐመድ መዝገብ የምስክሮች አሰማም ሂደት በዝግ ችሎት ወይስ ከመጋረጃ ጀርባ ይካሄድ የሚለውን የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በድጋሚ እንዲመረምር ውሳኔ አስተላልፎ ነበር። ፍርድ ቤቱ ዐቃቤ ህግ በምስክሮች ላይ ሊደርስባቸው ይችላል ያላቸውን በቂ እና አሳማኝ አደጋዎች በዝርዝር ለከፍተኛው ፍርድ ቤት እንዲያቀርብም አዝዟል። የተከሳሾች ጠበቆች ደግሞ ይህንን ውሳኔ በመቃወም አቤቱታቸውን ለሰበር ሰሚ ችሎት አቤት እንደሚሉ ተናግረው ነበር። ይሁን እንጂ በዛሬው ዕለት የዚህ ትዕዛዝ ግልባጭ ፍርድ ቤቱ ስላልደረሰው ጉዳዩን ሳያየው ቀርቷል። በዛሬው ቀጠሮ ላይም አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 20 ተከሳሾች ልደታ የሚገኘው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ችሎት በአካል ቀርበው ነበር። በዚሁ መሰረት ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ግንቦት 18 2013 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል። በዛሬው ዕለት ከተከሳሾች አቶ ጃዋር መሐመድ አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ደጀኔ ጣፋ ችሎቱን በማስፈቀድ ለፍርድ ቤቱ ሃሳባቸውን ማቅረባቸውን ጠበቃቸው አቶ ቱሊ ተናግረዋል። እነዚህ ተከሳሾችም ጉዳያቸው በፍርድ ቤት የሚታይ ሳይሆን የፖለቲካ ውሳኔ የሚፈልግ መሆኑን በመግለጽ፣ ፍርድ ቤት በመመላለስ የተከሳሾችን፣ የሕግ ባለሙያዎችን፣ የጠቅላይ አቃቤ ሕግን እና የጠበቆችን ጊዜ ከማጥፋት ረዥም ቀጠሮ ለሁለት ዓመት እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል ብለዋል። "ምርጫ አልፎ መንግሥት ከተረጋጋ በኋላ በ2015 ወይንም ደግሞ በ2016 ጉዳያችን ይታይ ሲሉ ተናግረዋል።" የኮሎኔል ገመቹ እና የሌሎችን ተከሳሾችን ጉዳይ እንደማስረጃ ያቀረቡት እነ አቶ ጃዋር፣ ይህ ፍርድ ቤት ነጻ ቢለቀን እንኳ መንግሥት አይለቀንም ሲሉ መናገራቸውን አቶ ቱሊ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በያዝነው ሳምንት ማክሰኞ እለት እነ ኮሎኑል ገመቹ አያናን ፍርድ ቤት በነጻ ቢያሰናብታቸውም፣ የፌደራል ጸጥታ ኃይሎች ከማረሚያ ቤቱ በራፍ ላይ በቁጥጥር ስር እንዳዋሏቸው ጠበቃቸው ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። እነ አቶ ጃዋር መሐመድ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት የሚታይ ሳይሆን የፖለቲካ ውሳኔ የሚፈልግ መሆኑን ሲናገሩ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም። የሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ ፖሊስ በወንጀል ጠርጥሮ በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው ቢናገርም እነ ጃዋር ግን ምርጫ ላይ እንዳንሳተፍ ነው በቁጥጥር ስር የዋልነው ሲሉ ለችሎቱ ሲናገሩ ቆይተዋል። እን አቶ ጃዋር መሐመድ በተከሰሱበት ወንጀል በአሁኑ ጊዜ ፍርድ ቤት ጉዳያቸውን እያየ ያለ ሲሆን የተጠረጠሩበትን ወንጀል አልፈጸምንም ሲሉ ቃላቸውን ለፍርድ ቤቱ ሰጥተዋል። ከዚህ በኋላ አቃቤ ሕግ ማስረጃውን እንዲያቀርብ የታዘዘ ሲሆን ማስረጃ የሚቀርብበት አኳኋን ላይ ግን ክርክር እየተካሄደ ይገኛል። ዛሬ ተከሳሾቹ ለፍርድ ቤት ባቀረቡት ጉዳይ ላይ አቃቤ ሕግ፣ የሌላን ጉዳይ መዝገብ ከዚህ መዝገብ ጋር ማያያዝ ትክክል አይደለም፤ እያደረጉት ያሉት ክርክር የፖለቲካ ክርክር ስለሆነ ፍርድ ቤቱ ሊፈቅድላቸው አይገባም ሲል ተከራክሯል። ፍርድ ቤቱም ከሁለቱም ወገን ያለውን ሃሳብ ካደመጠ በኋላ ተከሳሾች ከሁለት ዓመት በኋላ እንዲሰጣቸው የጠየቁትን ቀጠሮ ውድቅ በማድረግ ለግንቦት 18 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መያዙን አቶ ቱሊ ተናግረዋል። በ2012 ሰኔ ወር ላይ ከድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ በቁጥጥር ስር የተያዙት አቶ ጃዋር መሐመድ እና በመዝገባቸው ስር የሚገኙ ሌሎች የፀረ ሽብርን አዋጅን የቴሌኮም ወንጀል አዋጅን የጦር መሳሪያ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅን እና የአገሪቷን የወንጀል ሕግ የተለያየ አንቀጽ በመተላለፍ ነው የተከሰሱት። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ከጦር መሳሪያ ቁጥጥር አዋጅ ጋር የተያያዙ ክሶች እንዲቋረጡ ማድረጉ ይታወሳል። አቶ ደጀኔ ጉተማ ዶ/ር ብርሃነ መስቀል አበበ ሰኚ፣ ፀጋዬ ረጋሳ አራርሳ፣ በአገር ውስጥ የሌሉት እና በእነ ጃዋር መሐመድ የክስ መዝገብ ስር ከተከሰሱት ውስጥ ናቸው።
news-42410304
https://www.bbc.com/amharic/news-42410304
ዩቲዩብን እንዴት የገቢ ምንጭ ማድረግ ይችላሉ?
ዩቲዩብ ለብዙዎቻችን ተንቀሳቃሽ ምስሎችን በነፃ የምንኮመኩምበት ድረ-ገፅ ነው።
ነገር ግን ዩቲዩብ ከዚህም አልፎ ለብዙዎች የገቢ ምንጭ መሆን ከጀመረ ሰነባብቷል፤ ታዋቂነት ከማትረፍም በላይ ሚሊዬነር መሆን የቻሉ ጥቂት አይደሉም። አብዛኛው ተጠቃሚ በነፃ ከሚመለከተው ተንቀሳቃሽ ምስል እንዴት ገቢ ሊገኝ ይችላል? የሚለው ግን የብዙዎች ጥያቄ ነው። እነሆ አምስት መንገዶች... 1• ማስታወቂያዎች የመጀመሪያው ዩቲዩብን የገቢ ምንጭ ማድረጊያው መንገድ ማስታወቂያ ነው። አንድ ምስል ከመመልከትዎ በፊት የሚመጣው ማስታወቂያ ለዩቲዩበኞች አንደኛው የገቢ ምንጫቸው ነው። አንድ ሺህ ተጠቃሚዎች ማስታወቂያውን በተመለከቱ ቁጥር ጉግል ለዩቲዩበኛው ከ1 ዶላር 5 ዶላር ድረስ ሊከፍል ይችላል። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዩቲዩብ 50 በመቶውን ገቢ መውሰድ በመጀመሩ ምክንያት ከማስታወቂያ የሚገኘው ገቢ እጅግ ቀንሷል። እርስዎ አንድ ምስል ዩቲዩብ ላይ ሰቅለው የእርስዎን ምስል ለማየት የሚመጡ አንድ ሚሊዮን ሰዎች ማስታወቂያውን ከተመለከቱ ከ1ሺህ ጀምሮ እስከ 5ሺህ ዶላር ሊያገኙ ይችላሉ ማለት ነው። 2•ለሚከፍሉ/ለሚለግሱ ማሳየት ዩቲየበኞች ሰው ብዙም የማያውቀው የገንዘብ መሰብሰቢያ መንገድ በመጠቀምም ገቢ ያገኛሉ። ታዋቂው እንግሊዛዊ ዩቲዩበኛ ኢቫን ኤዲንገር እንደሚናገረው "በይነ-መረብን በመጠቀም ሳንቲም ማሰባሰብ የሚቻልበት መንገድ እንደሆነ አስቡት" ይላል። "ተጠቃሚዎች ቪዲዎችን ተመልክተው ከወደዷቸው ከ1 ዶላር ጀምሮ በወር እርዳታ እንዲለግሱ የሚያደርግ ሂደት ነው" ሲል ይተንትናል። አንዳንድ ዩቲዩበኞች መሰል ሂደት ያለውን ጥቅም በመረዳት እርዳታ የሚለግሱ ተጠቃሚዎች ብቻ ምስሎቹን የሚመለከቱበት ድረ-ገፅ ይዘረጋሉ። 3• ተያያዥ ድረ-ገፆች ይህ መላ በተለይ ፋሽንና የመዋቢያ ውጤቶችን በተመለከተ ተንቀሳቃሽ ምስል ሰርተው ዩቲዩብ ላይ ለሚሰቅሉ በጣም ተመራጭ ነው። ለምሳሌ ዩቲዩበኞቹ አንድ የመዋቢያ ውጤት የሆነ የምርት ዓይነትን ጥቅምና ጉዳት ከተነተኑ በኋላ ያንን ምርት መሸመት የሚፈልጉ ሰዎች ተያይዞ በተቀመጠው ድረ-ገፅ አማካይነት ምርት መግዛት እንደሚችሉ ይጠቁማሉ። በዚህ መንገድም የመዋቢያ ምርቱን ከሚሸጠው ድርጅት ጋር ባላቸው ስምምነት መሠረት ጥቅም ያገኛሉ ማለት ነው። 4• ምርት ጥቆማ ፖስተሮች፣ ቲሸርት እንዲሁም የተንቀሳቃሽ ስልክ አካላት ዩቲዩበኞች ገቢ የሚያገኙባቸው ሌሎች መላዎች ናቸው። ለምሳሌ አንዲት ዩቲዩበኛ በድረ-ገፁ በምታስተላልፈው መልዕክት ላይ አንድን ምርት የሚጠቁም ቲሸርት ለብሳ ወይም ስልክ ይዛ ብትታይ ይህ ማለት ተዘዋዋሪ ምርት ማስተዋወቅ በመሆኑ ሌላ የገቢ ምንጭ ሆኖ ያገልግላል። የምርት ምልክት (ብራንድ) ነገር በዚህ ብቻ የሚያበቃ አይደለም። 5• የምርት ምልክት (ብራንድ) ማስታወቂያ ኤዲንገር እንደሚናገረው የምርት ምልክት ለዩቲዩበኞች ዋነኛ የገቢ ማግኛ መላ ነው። ብዙ ጊዜ ኩባንያዎችና አምራቾች ብዙ ተከታይ ባላቸው ዩቲዩበኞች አማካይነት ምርቶቻቸውን ያስተዋውቃሉ፤ ለዚህም በርካታ ገንዘብ ይከፍላሉ። "ሉክ የተባለ ባልንጀራዬ ከአንድ የአሜሪካ ኩባንያ ጋር የ26 ሺህ ዶላር ስምምነት እንደተፈራረመ አውቃለሁ" ይላል ኤዲንገር። ብዙ ተከታይ (ሰብስክራይበር) ያላቸው ዩቲዩበኞች ከላይ በተጠቀሱት መንገዶች የትየለሌ ትርፍ ሊያገኙ ይችላሉ፤ እያተረፉም ይገኛሉ።
news-54064529
https://www.bbc.com/amharic/news-54064529
ፑቲን 'አስመርዘውታል' የተባለው አሌክሴ ከገባበት ሰመመን ነቃ
የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲንን በድፍረት በመተቸት የሚታወቀው አሌክሴ የነርቭ ስርዓትን በሚያውክ መርዝ ከተመረዘ በኋላ ከገባበት ሰመመን መንቃቱን የሕክምና ባለሙያው አስታወቀ።
ፑቲን እንዳስመረዙት የሚጠረጠረው ተቀናቃኛቸው አሌክሴ ናቫልኒ ወደ ጀርመኑ ዝነኛ ሻርሌት ሆስፒታል ከተዛወረ በኋላ ላይሞት ይችላል የሚሉ መረጃዎች እየወጡ ነበር። የሕክምና ቡድኑ በሰጠው መግለጫ ፖለቲከኛው የተመረዘው ናቪቾክ’ በሚሰኝ የነርቭ ስርዓትን በሚያውክ መርዝ እንደሆነ ገልጸው ነበር። በፀረ-ሙስና ዘመቻቸው የሚታወቁት አሌክሲ በበረራ ላይ እያሉ ነው በአውሮፕላን ውስጥ ተዝለፍልፈው የወደቁት። አውሮፕላኑን በድንገተኛ ሁኔታም ኦምስክ የሚባል ቦታ ለማረፍ መገደዱንም ቃለ አቀባይዋ ኪራ ያርሚሽ በትዊተር ገፃቸው አስታውቀዋል። የጀርመን መንግሥት አሌክሴ ላይ የተፈጸመውን ድርጊት አጥብቆ እንደሚያወግዝ ገልጾ፤ ሩሲያ በአስቸኳይ ማብራሪያ እንድትሰጥ ጠይቆ ነበር። መራሂተ መንግሥት አንጌላ መርክልም በጉዳዩ ላይ ከካቢኔ አባላቶቻቸው ጋር አስቸኳይ ስብሰባ መቀመጣቸው ይታወሳል። በርሊን ውስጥ የሚገኘው የሕክምና ቡድኑ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሌክሴ ለመተንፈስ እገዛ ከሚያደርግለት ሜካኒካል ቬንትሌተር ቀስ በቀስ እንዲላቀቅ መደረጉን አስታውቋል። '' ለሚደረግለት ህክምና ጥሩ ምላሽ እየሰጠ ነው። በመርዙ ምክንያት ሊደርስበት የሚችለውን የረጅም ጊዜ ጉዳት ግን አሁን ላይ ሆነን ማወቅ አንችልም'' ብሏል የህክምና ቡድኑ። በተጨማሪም ዶክተሮች ከአሌክሴ ባለቤት ጋር በቅርበት እየተነጋገሩ መሆኑንም ገልጸዋል። የአሌክሴ ቃል አቀባይ ኪራ ያርማይሽ በትዊተር ገጿ ላይ ባሰፈረችው መልዕክት '' ስለ አሌክሲ አዲስ ዜና፤ ዛሬ አሌክሲ ከሰመመን እንዲነቃ ተደርጓል። ቀስ በቀስ ሙሉ በሙሉ ከቬንትሌተር እንዲላቀቅ ይደረጋል። ሰዎች ሲያናግሩትም ምላሽ መስጠት ጀምሯል'' ብላለች። አሌክሴ ናቫልኒ ነሐሴ 15፣ ቶምስክ ከምትሰኝ የሩሲያ ከተማ ወደ ዋና መዲናዋ ሞስኮ እየበረረ ሳለ ከፍተኛ ሕመም ስለተሰማው አውሮፕላኑ በድንገት ኦምስክ፣ ሳይቤሪያ እንዲያርፍ ተገድዶ ነበር። አሌክሴ አውሮፕላኑን ከመሳፈሩ በፊት በቶምስክ አውሮፕላን ጣቢያ ቁጭ ብሎ ሻይ ሲጠጣ የሚያሳይ ፎቶ ተለቆ ነበር። ይህም ለህመሙ ምክንያት መመረዙ ነው የሚሉ ግምቶች በስፋት ተዛምቷል። የሩሲያ መንግሥት ግን ይህን ወቀሳ በተደጋጋሚ ሲያስተባብል ቆይቷል። የተቃዋሚው አሌክሴ መመረዝ ከተሰማ በኋላ የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ መርከልና የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አገሮቻቸው ለአሌክሴ ሕክምና ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸው በይፋ ገልጸው ነበር። ሆኖም የሩሲያ መንግሥት በሆስፒታሉ በኩል ሰውየው ወደ አምቡላንስ ለመግባት አቅም የለውም በሚል ሕክምናውን ሲከላከሉ ነበር። የአሌክሴ ሚስት በበኩሏ የሳይቤሪያው ሆስፒታል ታማሚው ባሏ ወደ ጀርመን እንዳይወሰድ እያዘገየ ያለው ወደሞት አፋፍ ከተጠጋ በኋላ እንደማይተርፍ ሲያውቁ ለመስጠት ነው በሚል ከፍተኛ ተቃውሞ ስታሰማ ነበር። የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) በበኩሉ ሩስያ ስለ ኖቪቾክ ፕሮግራሟ ለዓለም አቀፍ ተቆጣጣሪዎች መረጃ መስጠት አለባት ማለቱ የሚታወስ ነው። የመብት ተሟጋቹ አሌክሴ ናቫልኒ መመረዙን ተከትሎ ነው ስለ ኖቪቾክ ነርቭ ኤጀንት (መርዛማ ኬሚካል) መረጃ እንድትሰጥ የተጠየቀው። የኔቶ ጸሐፊ ጄንስ ስቶልበርግ አባላቱ ጥቃቱን አውግዘዋል ብለዋል። የመብት ተሟጋቹ በኖቪቾክ እንደተመረዘ “ማስረጃ አለ” ሲሉም አክለዋል። ሩስያ ግን ለአሌክሴ ሕክምና እያደረገ ያለው ሆስፒታል የሰጠውን ማብራሪያ አጣጥላለች። ከጥቂት ወራትም በፊት የህገ መንግሥት ማሻሻያ ላይ ድምፅ ይሰጥ መባሉን ተከትሎ ህገ መንግሥቱን የጣሰ ነው በማለት ከመፈንቅለ መንግሥት ጋር አመሳስለውታል። ፖለቲከኛው ይህንን ያሉት ማሻሻያው የአገሪቱን የፕሬዚዳንትነት ስልጣን ከሁለት ጊዜ በላይ መመረጥ እንዲያስችላቸው የሚያደርግ በመሆኑ ነው። በተለይም በአገሪቱ ውስጥ ያለ ቅጥ የተንሰራፋውን ሙስና በማጋለጥ የህዝብ ቀልብ የሳቡት ፖለቲከኛው የፕሬዚዳንት ፑቲን ዩናይትድ ራሺያ (የተባበረች ሩሲያ) ፓርቲን "ሌቦችና ቀማኞች" ሲሉም ይጠሯቸዋል። በጎርጎሳውያኑ 2011 የፑቲን ፓርቲ ምርጫን አጭበርብሯል በማለት ከፍተኛ ተቃውሞ ማስተባበራቸውን ተከትሎም ለአስራ አምስት ቀናት ታስረዋል። ከዚህም በተጨማሪ በ2013ም ገንዘብ አጭበርብረዋል በሚል ክስ ለአጭር ጊዜ ታስረው የነበረ ቢሆንም እስሩ ፖለቲካዊ ነው በሚል በከፍተኛ ሁኔታ ተወግዟል።
news-56795573
https://www.bbc.com/amharic/news-56795573
በአማራ ክልል፡ በሰሜን ሸዋና የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከለከለ
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ለቀናት የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ የተቋቋመው የዕዝ ማዕከል በአንዳንድ የጸጥታ ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስን መከልከሉን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።
አጣዬ ከተማ ውስጥ ንብረት በተቃጠለበት ጊዜ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ውስጥ ያለውን የጸጥታ ሁኔታ በተመለከተ ባወጣው መግለጫ፣ በተለይ በአማራ ክልል ምሥራቃዊ ክፍል ውስጥ ያለውን የሠላም መደፍረስ ለመቆጣጠር የዕዝ ማዕከል [ኮማንድ ፖስት] መመመስረቱን ገልጿል። የመከላከያ ሚኒስቴር በሰሜን ሸዋ፣ በደቡብ ወሎ እና የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን ወረዳዎች በተለይም ባለፉት ቀናት በአጣዬ ከተማና በአካባቢው በታጠቁ ኃይሎች በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ውድመት መድረሱን አመልክቷል። በዚህም መሠረት የዕዝ ማዕከሉ ከደብረ ሲና እስከ ኮምቦልቻ ባለው መስመር አዋሳኝ ወረዳዎች ከመንገድ ግራና ቀኝ ባለው 20 ኪሎ ሜትር ውስጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እንደማይቻል አሳውቋል። በተጨማሪም በአካባቢዎቹ መንገድ መዝጋት፣ አብያተ ክርስቲያናት፣ የመንግሥት ተቋማት፣ የግለሰብ መኖሪያና ንብረት ማውደም ወይም "ለዚህ ተግባር በተናጥልም ይሁን በቡድን መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ" መሆኑን ገልጿል። ጥቃት በተፈጸመባቸውና የተቋቋመው የዕዝ ማዕከል መረጋጋትን ለማስፈን በሚንቀሳቀስባቸው በእነዚህ አካባቢዎች የተጣሉትን ክልከላዎች ተላልፎ የተገኘ ማንኛውም አካል ላይ "ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድበት" ጨምሮ አስታውቋል። የመከላከያ ሚኒስቴር በመግለጫው ላይ እንዳለው ከተጠቀሱት በተጨማሪ "ቀጣይ በኮማንድ ፖስቱ ለኅብረተሰቡ የሚገለጹ ክልከላዎች" ሊኖሩ እንደሚችሉም አመልክቷል። ካለፈው ሳምንት ማብቂያ ጀምሮ በሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ በሚገኙት በአጣዬ፣ በካራቆሬ፣ በሸዋሮቢት፣ በማጀቴ፣ በአላላ፣ በአንጾኪያና የታጠቁ ናቸው በተባሉ ኃይሎች ለቀናት በተፈጸሙ ጥቃቶች ከባድ ጉዳት መድረሱን የክልሉ ባለሥልጣናት ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። ቢቢሲ አርብና ቅዳሜ ያናገራቸው የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ጥቃቱ አስፈሪና በከባድ የጦር መሳሪያ የታገዘ መሆኑን ገልጸው በርካታ ሰዎች መሞታቸውን፣ ቤቶችና የእምነት ቤቶች መውደማቸውን ገልጸዋል። ቅዳሜ ዕለት ጥቃቱ ከአጣዬ ባሻገር ወደ ሌሎች ከተሞች በመሸጋገሩ በአቅራቢያ ባሉ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች ወደ ደብረ ብርሃንና እና መሃል ሜዳ ለመሸሽ መገደዳቸውን ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የጸጥታ ኃላፊ አቶ አበራ መኮንን ለቢቢሲ እንደገለፁት ጥቃቱ የተፈፀመው በዞኑ በሚገኙ አምስት ወረዳዎች ውስጥ ሲሆን "በጣም ከፍተኛ" ቁጥር ያለው የታጠቀ ኃይል "ወረራ" መፈፀሙን ተናግረዋል። ኃላፊ አቶ አበራ ቅዳሜ ዕለት "ችግሩ በአጠቃላይ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ" እንደነበር ገልጸው፤ በአካባቢው ከባድ ጉዳት ቢደርስም በወቅቱ ዋነኛ ሥራ አድርገው እየሰሩ ያሉት ሕዝቡን ከጉዳት መጠበቅና ማረጋጋት ላይ መሆኑን ተናግረዋል። የአማራ ክልልና የዞኑ ባለሥልጣናት በተጠቀሱት ጥቃት በተፈጸመባቸው አካባቢዎች ከባድ ጉዳት እንደ ደረሰ ከመናገር ውጪ በሰውና በንብረት ላይ ስለደረሰው ጥፋት ዝርዝር መረጃ አልሰጡም። ጥቃቱን ለማስቆምና ለመቆጣጠር የመከላከያ ሠራዊት፣ የፌደራል ፖሊስና የክልሉ ልዩ ኃይል በአካባቢዎቹ መሰማራታቸው የተነገረ ሲሆን የጸጥታ ኃይሉ ከባድ ውድመት የደረሰባትን የአጣዬ ከተማን ቅዳሜ ዕለት መቆጣጠሩ ተገልጿል። የአማራ ክልል የሰላምና የሕዝብ ደኅንነት ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሲሳይ ዳምጤ ለክልሉ መገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት "በሰሜን ሸዋ ዞን በተፈጸመው ጥቃት ንጹሃን ተገድለዋል፣ የአካል ጉዳት ደርሷል፣ ሀብትና ንብረት ወድሟል" ብለዋል። የታጣቂ ኃይሉ ጥቃት ቀዳሚ ኢላማ በሆነችው በአጣዬ ከተማ ላይ የተፈጸመውን ከባድ ጥቃት ተከትሎ በስፍራው በሚገኘው ማረሚያ ቤት ውስጥ የነበሩ እስረኞች እንዲወጡ መደረጉም ተነግሯል። ለቀናት የዘለቀው በዚህ የታጣቂዎች ጥቃት ከአጣዬ አቅራቢያ የሚገኙትን ካራቆሬ፣ ማጀቴ፣ አንፆኪያ፣ መኮይና ሸዋሮቢትንም የነካ ሲሆን የእነዚህ ከተሞች ነዋሪም ከባድ ስጋት ውስጥ ወድቆ እንደነበር አቶ ሲሳይ ገልጸው ነበር። የዞኑም የሆነ የክልሉ ባለሥልጣናት እንደተናገሩት በተፈጸመው ጥቃት የጸጥታ ኃይሎችን ጨምሮ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ በርካታ ሰዎች ሳይገደሉ እንዳልቀረ ገልጸዋል። ነዋሪዎችና የክልሉ ባለሥልጣናት ለተፈጸመው ጥቃት "ኦነግ-ሸኔ" የተባለውን ቡድን ተጠያቂ አድርገዋል። ይህ አሁን የተከሰተውና ለቀናት የዘለቀው ከባድ ጥቃት በዚህ ዓመት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ መከሰቱ ሲሆን፣ በሰሜን ሸዋና በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞኖች ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት የበርካታ ሰዎችን ህልፈት ያስከተሉ ተመሳሳይ ጥቃቶች ከዚህ ቀደምም በተደጋጋሚ ማጋጠማቸው አይዘነጋም። ከሦስት ሳምንት በፊት በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋና የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞኖች ውስጥ ተከስቶ በነበረ ተመሳሳይ አለመረጋጋት ከ300 መቶ በላይ ሰዎች መሞታቸውን ኤኤፍፒ የዜና ወኪል የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋምን ጠቅሶ ዘግቦ ነበር።
47466513
https://www.bbc.com/amharic/47466513
የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ኬንያና ሶማሊያን በማሸማገል ለነበራቸው ሚና አመሰገኑ
በምስራቅ አፍሪካ በሚገኙት የተለያዩ ሃገራት ላይ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከሶማሊያ መንግሥት ምስጋና ተችሯቸዋል።
በጠቅላይ ሚኒስት ዐብይ አህመድ አስተባባሪነት ፕሬዚዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ መሐመድ ፋርማጆና ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ዛሬ ጥዋት በኬንያዋ መዲና ናይሮቢ የተገናኙ ሲሆን በሃገራቱ ላይ ለተፈጠረው የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሻከርን መፍትሄ ማምጣት ላይ ተወያይተዋል። •"የጠቅላይ ሚኒስትሩ ትልቁ ስኬት ብዙ ሰው በተስፋ እንዲኖር ማድረጋቸው ነው" ዶ/ር ዮናስ አዳዬ ይህንንም ተከትሎ የሶማሊያ መንግሥት ባወጣው መግለጫም " የሶማሊያ መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የሁለቱን መንግሥታት ስብሰባ በማሳለጥ ለነበራቸው ሚና እናመሰግናለን" የሚል ነው። በትናንትናው ዕለት ናይሮቢ የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሶማሊያው ፕሬዚዳንት ጋር አብረው ሲሆን የሁለቱ ሃገራት መንግሥታትም እንዲወያዩ ጫና ሳያደርጉ እንዳልቀረም ተዘግቧል። የሁለቱ ሃገራት ዲፕሎማሲያዊ ፍጥጫ ላይ የነበሩ ሲሆን ይህም ሁለቱ ሃገራት በሚጋሩት የባህር ድንበር ላይ ያለው አወዛጋቢው የጋዝ ክምችት ይገባኛል ጥያቄ ነው። •የድኅረ ዐብይ ሚዲያ በምሁራኑ ዕይታ በዚህ እግድ በተጣለበት የጋዝ ስፍራ ነዳጅ እያወጣች ሸጣለች በማለት የምትከሰው ኬንያ ባለፈው ወርም አምባሳደሯን ከሞቃዲሾ አስወጥታለች። ይህንንም ተከትሎ በሁለቱ ኃገራት መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ተቋርጦ ነበር። የሁለቱ ኃገራት መሪዎችን ስብሰባ ተከትሎ በተላከው ጋዜጣዊ መግለጫም ሁለቱ ፕሬዚዳንቶች ግንኙነታቸውን ለማደስ መስማማታቸው ተገልጿል። •በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት "ሁለቱ መሪዎች ፍሬያማ የሆነ ስብሰባን አከናውነዋል። ሃገራቱ ግንኙነታቸውን ለማደስና ለማጠናከርም ከስምምነት ላይ ደርሰናል" በሚልም ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት የተሰጠው መግለጫ ያትታል። ሶማሊያ በባህር ድንበሩ ላይ የሚገኘውን የጋዝ ክምችት ይገባኛል ጥያቄ ለአለም አቀፉ ፍትህ ፍርድ ቤት ያቀረበች ሲሆን ጉዳዩም እየታየ ነው። የየሃገራቱ አምባሳደሮች መቸ እንደሚመለሱም ቀነ ገደብ አልተጠቀሰም።
news-51276516
https://www.bbc.com/amharic/news-51276516
በአዲሱ ቫይረስ የሟቾች ቁጥር አሻቀበ
ከቻይና የዓሣ ጉሊት እንደተነሳ የሚገመተው ኮሮና ቫይረስ እስከ ትናንት የሟቾች ቁጥር 81 የነበረ ቢሆን በአጭር ሰዓታት ውስጥ 106 መድረሱ ድንጋጤን ፈጥሯል።
ቻይናዊያን የአፍ-አፍንጫ ጭምብል አጥልቀው ነው የሚውሉት እስከዛሬ የተረጋገጡ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር 4 ሺህ 515 ደርሷል። ይህ ቁጥር ከቀናት በፊት 2835 ነበር። የተያዦች ቁጥር ማሻቀቡን ተከትሎ ቻይና የጉዞ እቀባዋን አጠናክራለች። • 24 ሺህ ፖስታዎችን ማደል የታከተው ስልቹው ፖስተኛ ተያዘ • የታገቱት ተማሪዎች፡ የቤተሰብ ሰቀቀን፤ የማሕበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ጩኸት የቫይረሱ መነሻ ናት የምትባለው የዉሃን ከተማ በሁቤት ክፍለ ግዛት የምትገኝ ትልቅ ከተማ ስትሆን 11 ሚሊዮን ሕዝብ ይኖርባታል። ወደ 700ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ተማሪዎች ናቸው። ከተማዋ ለጊዜው በጉዞ እቀባ ላይ ናት። ኮሮናቫይረስ የመተንፈሻ አካላትን ዕለታዊ ተግባራቸውን የሚያስተጓጉል ቫይረስ ሲሆን እስከዛሬም ፈውስም ሆነ ክትባት አልተገኘለትም። ብዙዎቹ እየሞቱ ያሉት ግን ቀድሞመው መተንፈሻ አካላት ጋር በተያያዘ ችግር ያለባቸው እና በእድሜ ገፋ ያሉ ሰዎች መሆናቸውን የሕክምና ሰዎች መታዘብ ችለዋል። ቻይና ምን እያደረገች ነው? የቻይና አዲስ ዓመት ላይ የተከሰተው ይህ ቫይረስ ለቁጥጥር እጅግ አስቸጋሪ ሆኗል። ምክንያቱ ደግሞ ይህ የቻይናዊያን አዲስ ዓመት በመቶ ሚሊዮኖች የሚገመተው ቻይናዊ ከከተማ ከተማ፣ ከግዛት ግዛት፣ ከአገር አገር የሚጓጓዝበት ሁነኛው ወቅት በመሆኑ ነው። የቻይና መንግሥት በዓሉን ከግምት ውስጥ በማስገባት አብዛኛዎቹን የበዓል መርሃ ግብሮች ሰርዟ። ዜጎቿ ባሉበት እንዲቆዩ በማሰብም ክብረ በዓሉን በሦስት ቀናት ገፍታለች። ይህም በመሆኑ አርብ ያበቃ የነበረው በዓል እስከ እሑድ ይዘልቃል። ቤይጂንግ ከሁቤይ ክፍለ ግዛት የሚነሱ አውቶቡሶችን ያስቆመች ሲሆን ቤይጂንግም ሆነ ሻንጋይ ከሁቤት ወደ ሌሎች ከተሞች የሚገቡ ሰዎች በትንሹ ለ14 ቀናት ክትትል እያደረግችላቸው ነው። ከ106 ቻይናዊያን ሟቾች 100 የሚሆኑት ከዚሁ የሁቤይ ክፍለ ግዛት የመጡ ናቸው። • ሴትየዋ ኬክ በፍጥነት በመብላት ውድድር ላይ ሳሉ ሞቱ በዓለማቀፍ ደረጃ ያሉ እውነታዎች አሜሪካ ዜጎቼ "እባካችሁ ወደ ቻይና መሄድ ይቅርባችሁ" የሚል ምክር ሰጥታለች። በተለይ ደግሞ ወደ ሁቤይ ክፍለ ግዛት "በፍጹም እግራችሁን እንዳታነሱ" ብላለች። በሚቀጥሉት ቀናትም ዜጎቿንና የኤምባሲ ሰዎቿን ከዉሃን ከተማ ለማስወጣት አቅዳለች። ሌሎችም የአውሮፓ አገሮች ተመሳሳይ ተግባር እየፈጸሙ ይገኛሉ። ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የሚመሩት የዓለምአቀፉ የጤና ድርጅት ባወጣው መረጃ በትንሹ 47 የቫይረሱ ተጠቂዎች የሚገኙት ከቻይና ውጭ ነው። በዚህም መሠረት 8ቱ ከታይላንድ ሲሆኑ፣ አሜሪካ ሲንጋፖርና ታይዋን እያንዳንዳቸው 5 ታማሚዎች ተመዝግበውባቸዋል። ማሌዢያ፣ ደቡብ ኮሪያና ጃፓን እያንዳንዳቸው 4፣ ፈረንሳይ 3፣ ቬትናም 2 ዜጎቻቸው ታመውባቸዋል። ኔፓል፣ ካናዳ፣ ካምቦዲያ፣ ስሪላንካና ጀርመን እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ዜጋ በቫይረሱ መያዙን አረጋግጠዋል። እስካሁን ከቻይና ውጭ በቫይረሱ ተይዞ የሞተ ግን አልተመዘገበም።
49637714
https://www.bbc.com/amharic/49637714
በጋምቤላ የተራድኦ ድርጅት ሰራተኞችን በመግደል የተጠረጠሩ አለመያዛቸው ተገለፀ
ባለፈው ሳምንት ሐሙስ አክሽን ኤጌይንስት ሃንገር የተባለው የተራድኦ ድርጅት ሁለት ሰራተኞች በማይታወቁ ታጣቂዎች ከጋምቤላ አርባ አምስት ኪ.ሜትር ርቀት ላይ በምትገኝ ቦታ ተገድለዋል።
ግድያው ከተፈፀመ በኋላ ድርጅቱ ድረገፁ ላይ ባወጣው መግለጫ በግድያው የተሰማውን ኃዘን አስፍሮ ከነፍስ አድን ስራዎች ውጭ ሌሎች የግብረ ሰናይ ድርጅቶች በጋምቤላ ማቋረጡን ገልጿል። •ከጋምቤላ እስር ቤት በርካታ ታራሚዎች አመለጡ እስካሁን ድረስ ተጠርጣሪ እንዳልተያዘና ምርመራው እንደቀጠለ የጋምቤላ ክልል የሰላምና የፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶማስ ቱት ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ኃላፊነታቸውን አልተወጡም ብለን ጥቃቱ የደረሰበት አካዶ ቀቦሌ ሶስት የስራ ኃላፊዎች አስረናል። የስራ ኃላፊዎቹ በቁጥጥር ስር ሆነው ተጠርጣሪዎችን ማግኘት ስለሚያስቸግር ከህዝቡ ጋር ሆነን ጥቆማ ለመንግሥት እንሰጣለን በማለታቸው በዋስ ተለቀዋል" ይላሉ አቶ ቶማስ •"ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ ተስፋና ስጋት አለ" ኦባንግ ሜቶ አክለውም "የምንጠረጥራቸው ሰዎች አሉ ነገር ግን መረጃው ሙሉ እንዲሆን ከህዝብ ጥቆማ ያስፈልገናል" ያሉት አቶ ቶማስ ኃላፊዎቹ ከማህበረሰቡ ጋር ተመካክረው ተጠርጣሪዎችን እንዲያጋልጡ ስምምነት ላይ ተደርሷል። አቶ ቶማስ ግድያው የተፈፀመ እለት ዝናብ ዘንቦ በመጨቅየቱ የተጠርጣሪዎች ዱካ መገኘቱንና የፀጥጣ ኃይሎችም ዱካውን ተከትለው ቢሰማሩም ውጤት ላይ መድረስ አልቻሉም። ግድያው እንዴት ተፈፀመ? ግድያው የተፈፀመበት በጋምቤላ ክልል ይታንግ የምትባል ወደ ስደተኞች መጠለያ ጣቢያ በቅርብ እርቀት የምትገኝ ቦታ ናት። አቶ ቶማስ እንዳሉት የተገደሉት የኃገር ውስጥ ሰራተኞች ሲሆኑ በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸው ማለፉን አስረድተዋል። "አንደኛው ሟች የመኪናው አሽከርካሪ ከመኪናው ውጭ ሞቶ የተገኘ ሲሆን ሌላኛው ሟች መኪና ውስጥ የአደጋ መከላከያ ቀበቶ እንደታጠቀ ተገድሏል" ብለዋል። መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው የተራድኦ ድርጅት እንዳስታወቀው ሟቾቹ ወደ ዊኜል ስደተኞች መጠለያ ጣብያ እየተጓዙ ነበር። .በዓመቱ አነጋጋሪ ከነበሩ ጉዳዮች ጥቂቱ በተባበሩት መንግሥታት የተራድኦ ድርጅት የኢትዮጵያ አስተባባሪ ስቴቨን ዌሬ ኦማሞ በሰጡት መግለጫ በኢትዮጵያ ውስጥ በሰብዓዊ እርዳታ የሚሳተፉ ተቋማትንም ሆነ ሰራተኞች ደህንነትና ጥበቃ መንግሥት እንዲያረጋግጥ ጠይቀዋል። "የኢትዮጵያ መንግሥት ስራ ኃላፊዎች ግድያውን የፈፀሙትን ግለሰቦች ወደ ህግ እንደሚያቀርቡ ሙሉ እምነት አለኝ" ብለዋል። ድርጅቱ በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር 1ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ ኢትዮጵያ ውስጥ እየሰራ እንዳለ ከድረገፁ የተገኘው መረጃ ያሳያል።
news-50963122
https://www.bbc.com/amharic/news-50963122
#9 እሷ ማናት? ከበለስ ማርማላታ በማምረት ወደ ውጪ የምትልከው ኢትዮጵያዊት
ጸጋ ገብረኪዳን እባላለሁ፤ ባለትዳርና የሁለት ሴት ልጆች እናት ነኝ። በትግራይ ሐውዜን ከተማ ተወልጄ ሰባት ዓመት ሲሞላኝ ከቤተሰቦቼ ጋር ወደ አስመራ ሄድኩኝ። እስከ 10ኛ ክፍልም እዛው አስመራ ተማርኩኝ።
ከበለስ ችፕስ፣ ማርማላታ ጭማቂ የምታመርተው ጸጋ ገብረኪዳን በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ምክንያት ግን፤ በ1993 ዓ.ም ከቤተሰቦቼ ጋር ወደ ኢትዮጵያ ተመለስን። በዚህ ወቅት ትምህርቴንም አቋርጬ፤ ትልቅ ሰውም ሆኜ ስለነበር ሥራ እየሠራሁ ቤተሰቦችን መርዳት ግድ ይለኝ ነበር። ከሁለት ዓመት በኋላ፤ 'እናቶች ለእናቶች' በተባለው ማኅበር ውስጥ [በ1993 ዓ.ም የተቋቋመ ማኅበር ሆኖ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ያለባቸው እናቶችን ይረዳል]፤ ጽዳትና ተላላኪ ሆኜ ተቀጠርኩኝ። በ2005 ዓመተ ምህረት መጨረሻ አካባቢ፤ አሁን ላለሁበት ደረጃ አጋጣሚ የፈጠረልኝን ዕድል አገኘሁ። በማኅበሩ ውስጥ እየሰራሁኝ ሳለ፤ አንዲት ሜክሲኳዊት ለሴቶቹ ሥልጠና ለመስጠት መጣች። የበለስ ተክል ከሚታወቅበት ሃገር የመጣችው ባለሙያ፤ ከዚህ ፍሬ እንዴት የተለያየ ምግብ ማዘጋጀት ይቻላል የሚል ሥልጠና ለአንድ ሳምንት ሰጠችን። • "ማርታ፣ ለምን ለምን ሞተች?" • እሷ ማናት፡ "አፍሪካዊያንን ሚሊየነር ለማድረግ አስባለሁ"- ሐና ተክሌ ራሴን መቀየር የዘወትር ህልሜ ስለነበር፤ ሥልጠናውን በሚገባ ወሰድኩ። ሥልጠናውን ተግባራዊ አድርጌ መሻሻል አለብኝ የሚል ውሳኔ ላይ ደርሼ ስለነበር፤ የተለያዩ ችግሮች እየገጠሙኝም ቢሆን ቀጠልኩበት። በዚህ መሠረት ከበለስ የሚዘጋጅ ጭማቂ፣ ኩኪስና ሌሎችን ነገሮችን እያዘጋጀሁ ሰዎች እንዲያውቁት ለማድረግ ብዙ ዋጋ ከፈልኩ። ሰው በተፈጥሮው አዲስ ነገር ቶሎ መቀበል ስለሚከብደው፤ በተለይ ማርማላታውን ማምረት ስጀምር ማመን የሚያቅታቸው፣ መቀበል የሚያስቸግራቸው በርካታ ሰዎች ይገጥሙኝ ነበር። "የበለስ ማርማላታ ደግሞ ምንድን ነው!?" የሚሉኝ ብዙዎች ነበሩ። በወቅቱ የገንዘብ አቅምም ስላልነበረኝ በቀላሉ ከሚያጋጥሙኝ ፈተናዎች ለመውጣት እቸገር ነበር። • አፍጋናዊቷ ስደተኛ በኢትዮጵያ በለስ በቅርብ የሚገኝ ሃብታችን በመሆኑ በየቀኑ ተስፋ በማድረግ ገፋሁበት፤ እየከሰርኩም ሰው እንዲያውቀው አደረግኩኝ። በዚህ ሁሉ ተስፋ ቆርጨ አላውቅም። አሁን? በለስ ወርቃማ አረንጓዴ ሃብት ነው ብዬ ነው የማምነው። እስከአሁን በአግባቡ ሠርተን ጥቅም ላይ አውለነዋል ብዬ አላስብም። በመሆኑም፤ ከበለስ የሚሠራው ማርማላታም ሆነ ጭማቂ እንዴት ቢሠራ ሰው ሊወደው ይችላል? ምን ዓይነት ጥረትና ታታሪነት ይፈልጋል? በሚሉት ጉዳዮች ላይ ብዙ ጊዜ አጥፍቻለሁ። በለስ፤ እሾሁን በአግባቡ በማስወገድ ሰላጣ፣ ጥብስ፣ ዱለት ማዘጋጀትም ይቻላል። አልፎ አልፎ በሚዘጋጁ ዐውደ ርዕዮች ላይ እየቀረብኩኝ፤ የዚህን ምርት ጥቅምና ይዘት ለማስረዳት ረጅም ጊዜ ወሰደብኝ። ቢሆንም በጽናት ቀጠልኩ። እንዲህ ዓይነት ሥራ ብዙ ሰው ደፍሮ ስላልገባበት፤ እኔ የምችለውን ሰርቼ ራሴን በመቀየር ኀብረሰተቡን መጥቀም የምችልበት ደረጃ ላይ ደርሻለሁ። • የ29 ዓመቷ የህክምና ዶክተርና ኢንጅነር ዕልልታ ጉዞ • ከሞት መንጋጋ ያመለጠችው የሐመሯ ወጣት ለብቻዬ ከምሆን ደግሞ ሌሎች አራት ሰዎች ጨምሬ "ጸጋና ንርአያ የሽርክና ማህበር" የሚል የማኑፋክቸሪግ ማኅበር በመመስረት እየሠራሁ ነው። በዚህ ማኅበር አራት ሴቶችና አንድ ወንድ አለን። ማኅበሩን በ2007 ዓ.ም ነው ያቋቋምነው። ቀደም ብሎ፤ የዓለም ምግብ ፕሮግራም (ፋኦ) እና የግብርና ሚኒስቴር በመተባበር ከአንድ የጣልያን ሃገር ትልቅ ሱፐርማርኬት ጋር የገበያ ትስስር ፈጠሩልኝ፤ በዚህ አጋጣሚ 4ሺህ ጠርሙስ ማርማላታ ልኬያለሁ። እነሱም፤ የምርቱን ብቃት በማረጋገጥ ለአንድ አመት መቆየት የሚችል ተፈጥሮአዊ ምርት መሆኑን መስክረውልኝ ገንቢ አስተያየት ሰጥተውኛል። በቅርቡ ኳታር ከሚገኘው አንድ ትልቅ ሱፐርማርኬት ጋር ተነጋግሬያለሁ፤ እንደሚቀበሉኝም ነግረውኛል። በአገር ውስጥም እንደ ሸዋ ሱፐርማርኬት ባሉ ትልልቅ የገበያ አዳራሾች ምርቱን አስገብቼ ነበር። በዚህ አጋጣሚም ህብረተሰቡን አውቆት መጠቀም እንደሚፈልግ ተረድቻለሁ። • የዩኒቨርስቲ መምህርቷ ሞዴል፡ "ውበት ባመኑበት ነገር ጠንክሮ መሥራት ነው" • ኢትዮጵያዊያን ለምን ሥጋ አይመገቡም? ግን፤ የምናመርታቸውን ምርቶች የምናሽግበት ጠርሙስ እጥረት ስለሚገጥመን፤ በምንፈልገው ልክ ገበያው ላይ ገብተን መወዳደር አልቻልንም። የማምረት አቅማችን አንሶ ሳይሆን፤ የጠርሙሱ መግዣ ዋጋ እኛ ለምርቱ ከገመትነው በላይ ስለሚሆንብን ነው። ከአሁን በኋላስ? በኢንተርኔት ላይ እንገኛለን። አሁን ላይ የፈጠርኩት ካፒታል ወይም ሃብት ይህ ነው ማለት ባልችልም፤ ራሴን የምችልበት ሥራ በመፍጠር ግን አዲስ ነገር ህብረተሰቡን ማስተዋወቅ ችያለሁ። ምርቱን የምናመርተው በሰው ጉልበት ብቻ በመሆኑ፤ በቅርቡ አቅማችንን አሳድገን ዘመናዊ ግብዓት በመጠቀም ብዙ ምርት ማምረት የምንችልበት አቅም እንደምንፈጥር ተስፋ አደርጋለሁ። ሥራችን ለማስፋት ከመንግሥት ብድር ስንጠይቅ፤ መኪናና ቤት ይጠይቁናል። ይህ ለእኛ ትልቁ ፈተናችን ነው። ሴት ልጅ በሕይወቷ የሚፈትኗት ነገሮች ብዙ ቢሆኑም፤ ሥራን መምራት፣ ልጅ ማሳደግ፣ ቤተሰብ ማስተዳዳር አንድ ላይ ይበልጥ ይፈትኗታል። ብዙ ጊዜ ወደ ተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ስንቀሳቀስ፤ ልጆችን ትቼ ስለምወጣ፤ በእነሱ ሃሳቤ ወደ ኋላ ይወሰዳል፣ እሳቀቃለሁ፤ እናፍቃለሁ። ጠንክሬ ባመንኩበት እንድቀጥል አድርጎኛል የምለው አንድ ነገር ቢኖር ያለኝ ጽናት ቢሆንም፤ ባለቤቴም በነጻነት እንድንቀሳቀስ ስለሚያግዘኝ ከስኬት ሳልደርስ ግን አልቀረሁም። በሚቀጥሉት ዓመታት፤ የተሻሉ የበለስ ምርቶች የሚሠሩበት ኢንዱስትሪ እንዲኖረኝ እጥራለሁ። ይህ ለብዙ ሰዎች [በተለይም ለሴቶች] የሥራ ዕድል በመፍጠር ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ እንዲሆን፤ እንዲሁም ልጆቼ ጥንካሬን የሚማሩበት ቦታ እንዲሆን እፈልጋለሁ። ሴቶች ጠንካራና ሥራ ፈጣሪ ነን ብዬ አምናለሁ። ጊዜው ደግሞ ሴት ልጆችን የተሻለ ዕድል እንዲያገኙ የሚፈቅድ ስለሆነ፤ ተስፋ ሳንቆርጥ፣ ቸልተኝነት ሳናበዛ "እንዴት ግን እችለዋለሁ?" የሚል አስተሳሰብ አስወግደን ራሳችን እንድናሳድግና እንድንቀይር እማጸናለሁ። እሷ ማናት? የሚለው ጥንቅራችን ያሰቡበትን ዓላማ ለማሳካት ብዙ ውጣውረዶችን ያሳለፉ ሴቶችን ታሪክ የምናስቃኝበት ነው።
50059200
https://www.bbc.com/amharic/50059200
ህወሓት: "እሳትና ጭድ የሆኑ ፓርቲዎች ሊዋሃዱ አይችሉም"
የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ለሰባት ቀናት ሲያካሄድ የነበረውን ስብሰባ በማጠናቀቅ መግለጫ አውጥቷል።
ዘለግ ባለው በዚህ መግለጫ ህወሓት የኢህአዴግ መዋሃድ እርምጃን በተመለከተ ያለውን አቋም አንጸባርቋል። የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር -ኢህአዴግ መስራች እና ዋነኛ አባል የሆነ ህወሓት ፤ የኢህአዴግ የውህደት እንቅስቃሴን አጥብቆ ኮንኗል። ህወሓት በመግለጫው "ከኢህዴግ ርዕዮተ ዓለም እና መተዳደሪያ ደንብ ውጪ አንድ ውህድ ፓርቲ ለመመስረት እየተደረገ ያለው ሩጫ ሕገ-ወጥ ነው" ብሏል። • "ለስልጣን ተብሎ የሚፈጠር ውህደትን ህወሓት ፈጽሞ አይቀበለውም" አቶ ጌታቸው ረዳ • "አገሪቷ አሁን ለምትገኝበት የፖለቲካ ብልሽት ህወሓት ተጠያቂ ነው" አዴፓ "እንዲፈጠር እየተፈለገ ያለው ፓርቲ በቅርጽ ብቻም ሳይሆን በይዘትም፤ ከነበረው ኢህአዴግ ፕሮግራም በመሰረቱ የተለየ አዲስ ፓርቲ የመመስረት ጥረት ነው" ያለ ሲሆን፤ . . . "የኢትዮጵያ ህዝብ ኢህአዴግን የመረጠው በያዘው ፕሮግራም መሰረት ነው። አገር እንዲመራ በህዝብ ኃላፊነት ያልተሰጠው አዲስ ፓርቲ ለመመስረት እየተሞከረ ነው ያለው።" ሲል መግለጫው ይቀጥላል። "ይመሰረታል የተባለው ውህድ ፓርቲ በህዝብ ስልጣን ላይ እንዲቆይ ፍቃድ ያልተሰጠው ፓርቲም ብቻ ሳይሆን፤ ስልጣን ለመያዝ መወዳደር የማይችል ፓርቲ ይሆናል" ብሏል። "እሳት እና ጭድ የሆኑ ፓርቲዎች በውስጥ የተሸከመው ግንባር፤ አይደለም ውህደት ፓርቲ በግንባርነት አብሮ የሚያቆይ የጋራ አስተሳሰብ እንኳን የላቸውም" ሲል ጠንከር ያለ እገላለጽን በመግለጫው ላይ አስፍሯል። የህወሓትና የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ለቢቢሲ ሲናገሩ፤ ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ተዋህዶ አንድ ወጥ ሃገራዊ ፓርቲ ይሆናል እየተባለ የሚነገረውን ጉዳይ ህወሓት ዘንድ ፈጽሞ ተቀባይነት እንደማይኖረው መናገራቸው ይታወሳል። "በየእለቱ እርስ በርስ እየተናቆሩ የሚውሉ አባል ፓርቲዎችን ይዘን የሃገር ችግርን በመረዳትም ሆነ ችግርን ለመፍታት በምንከተለው መንገድ ጭምር እርስ በእርሱ በሚጋጩበት ሁኔታ ውሁድ ፓርቲ ለመመስረት መሯሯጥ፤ የጥቂት ግለሰቦች የስልጣን ጥማት ለማርካት ካልሆነ በስተቀር የሃገሪቷን ችግር የሚፈታ ሃገራዊ ፓርቲ ይፈጠራል ብሎ ህወሓት አያምንም" በማለት አቶ ጌታቸው ገልጸው ነበር። ከዚህ በተጨማሪም ህውሓት ለትግራይ፣ ለኢትዮጵያ እና ለኤርትራ ህዝብ መልዕክት አስተላልፏል።ህውሓት በመግለጫው፤ "የተከበርክ የትግራይ ህዝብ፤ አሁንም ቢሆን ሁኔታዎች እየከበዱና እየባሱ በመምጣታቸው ደህንነትህንና ህልውናህን ለማስጠበቅ የምታደርገው ትግል ይበልጥ አጠናክረህ ልትቀጥልበት ይገባል" የሚል መልዕክት ለሚያስተዳደርው ክልል ህዝብ መልዕክት አስተላልፏል::አክሎም "ህገ መንግስታችንና ህብረ ብሄራዊ ፌደራላዊ ስርዓታችን የሚሸረሽሩና የሚጥሱ ተግባራት በየቀኑ ማየት የተለመደ ተግባር ሆኗል። . . . መላው የሀገራችን ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦችም ህብረ-ብሄራዊ ፌዴራላዊ ስርዓታችንን ለማዳን በሚደረገው ወሳኝ ትግል ከማንኛውም ጊዜ በላይ አገራችንን ለማዳን ሊረባረብ ይገባል" በማለት ለኢትዮጵያ ህዝብ ያለውን ጥሪ አቅርቧል።በመጨረሻም ህውሓት በመግለጫው፤ ለኤርትራ ህዝብ "የትግራይና የኤርትራ ህዝብ ለጋራ መብትና ጥቅም በጋራ የታገሉ ወንድማማች ህዝቦች ናቸው። የነበረውና አሁንም ያለው ዝምድናና መደጋገፍ ወደ ዘላቂ አስተማማኝ ደረጃ ለማድረስ ባለፈው ዓመት የተጀመረው የሰላም ጭላንጭል በዚህ ዓመትም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል" ብሏል።
47302287
https://www.bbc.com/amharic/47302287
በካናዳ 7 ሕፃናት በእሳት ቃጠሎ ምክንያት ሞቱ
ሰባት ታዳጊዎች በአንድ ቤት ውስጥ የእሳት እራት መሆናቸው ከካናዳዋ ሃሊፋክስ ተሰምቷል። እነዚህ ታዳጊዎች የአንድ ቤተሰብ አባላት ይሆናሉ ተብሎም ተገምቷል።
አንድ ወንድና ሴትም በእሳቱ ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸዋል። የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በቤቱ ውስጥ የተነሳው እሳት የመጀመሪያውንና ሁለተኛውን ፎቅ ወዲያው እንደተቆጣጠረው ገልጿል። ፖሊስ የሟቾቹን ማንነት እስካሁን ድረስ ባይገልፅም አንድ የዜና ተቋም ግን ሟቾቹ የሶሪያ ስደተኞች ናቸው ሲል ዘግቧል። • ሶሪያውያን ስደተኞች በአዲስ አበባ ጎዳናዎች • ፓስፖርት፡ የሰዎችን እንቅስቃሴ የወሰነ ሰነድ • ምን ያህል እንደምንኖር የሚያሳዩ ዘጠኝ እውነታዎች ቤተሰቡ ወደ ካናዳ ከመጣ አንድ ዓመት ከስድስት ወር ገደማ ቢሆነውም ወደ ሐሊፋክስ ከተዘዋወሩ ግን ስድስት ወር እንደሆናቸው የአካባቢው ኢማም ለቢቢሲ ተናግረዋል። እሳቱ ሕይወታቸውን ከነጠቃቸው ታዳጊዎች መካከል ትንሹ የአራት ወር ሕፃን ሲሆን ትልቁ ደግሞ የ15 ዓመት ጎረምሳ ነው። በአካባቢው የሚገኝ ስደተኞቹን መልሶ በማቋቋም ላይ የተሰማራ አንድ ድርጅት በፌስ ቡክ ገፁ ላይ እንዳሰፈረው ቤተሰቦቹ የባርሆ ናቸው ብሏል። የተጎዳው ግለሰብ ሕይወቱ በአስጊ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝና በሆስፒታል የፅኑ ህሙማን ክፍል ክትትል እየተደረገለት እንደሆነ ተዘግቧል። የእሳት አደጋ ሰራተኞች በስፍራው ደርሰው እሳቱን ለመቆጣጠር አንድ ሰዓት ያህል እንደፈጀባቸው ተገልጿል። ባለ ሁለት ፎቅ ህንፃው ሙሉ በሙሉ የወደመ ሲሆን ለእሳቱ መንስዔ የሆነውን ነገር ለመለየት ጥናት እየተደረገ መሆኑም ተነግሯል። የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር የከተማው ከንቲባ በደረሰው አደጋና ሕይወታቸውን ባጡት ታዳጊዎች የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልፀዋል።
news-44302196
https://www.bbc.com/amharic/news-44302196
በደቡብ አፍሪካ ዝቅተኛው የሠራተኛ ወርሃዊ ክፍያ 7ሺ ብር ሊሆን ነው
ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ የደቡብ አፍሪካ ፓርላማ ለሠራተኞች ዝቅተኛውም የክፍያ መጠን የሚወስን ረቂቅ ሕግ ማጽደቁ ተዘግቧል።
ደቡብ አፍሪካ በዓለም ላይ ከፍተኛ የክፍያ ልዩነት ከሚታይባቸው አገሮች አንዷ ናት። የፓርላማውን ይሁንታ ያገኘው ይህ ሕግ በሰዓት ትንሹ የክፍያ ልክ 20 የደቡብ አፍሪካ ራንድ መሆኑን ይደነግጋል። ይህም በሰዓት አንድ ዶላር ከስድሳ ሳንቲም ወይም 45 ብር ይጠጋል። ምንም እንኳ ፕሬዚዳንት ራማፉሶ ረቂቁን ወደ ሕግ የሚቀይረውን ፊርማ እስከ አሁን ባያኖሩም የክፍያው ማደግ በትንሹ 6 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎችን ኑሮ ያሻሻል ተብሎ ይጠበቃል። ገዢው ፓርቲ ኤኤንሲ ረቂቁን ታሪካዊ ብሎታል። የሠራተኛ ጉዳዮች ሚኒስትር የሆኑት ኦሊፋንታ በበኩላቸው ማሻሻያው በመጠኑ ትንሽ ቢሆንም መልካም ጅምር ነው ብለውታል። "ረዥም ጉዞ ከእርምጃ ይጀምራል። የጉልበት ሠራተኞች እዚህ ግባ የሚባል ክፍያ ሳያገኙ አስቸጋሪ ሕይወትን አሳልፈዋል፤ ተበዝብዘዋል። የአሁኑ እርምጃ የረዥሙ ጉዞ መጀመርያ ነው" ብለዋል ሚኒስትሯ። ዲኤ የሚባለው ሁነኛው ተገዳዳሪ ፓርቲ በበኩሉ ባወጣው መግለጫ እርምጃውን ተቃውሞታል። "ረቂቅ ሕጉ በቂ ሕዝባዊ ውይይት አልተደረገበትም፤ በርካቶችንም ለሥራ አጥነት ያጋልጣል" ሲል ኮንኖታል። በዝነኛው ጁሊየስ ማሌማ የሚመራው ግራ ዘመሙ ኢኮኖሚክ ፍሪደም ፋይተርስ ረቂቅ ሕጉን ተቃውሞታል። ይህ ሕግ በፕሬዚደንቱ ፊርማ ሲጸድቅ የደቡብ አፍሪካ ሠራተኞች ወርሃዊ የክፍያ ወለል በወር 3500 የደቡብ አፍሪካ ራንድ ይሆናል። ይህ ወደ ብር ሲመነዘር ከ7ሺ ብር ይልቃል።
48523608
https://www.bbc.com/amharic/48523608
የኬንያ ፖሊስ የልጇን አፍ የሰፋችውን እናት እያደነ ነው
የኬንያ ፖሊስ የልጇን ከንፈሮች አጋጥማ የሰፋችውን እናት እየፈለገ እንደሆነ አንድ የመንግሥት ኃላፊ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
የናኩሩ ግዛት ኮሚሽነር ጁሊየስ ንያጋ እንደገለፁት የተሰፋው ህፃን የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነው። ኮሚሽነሩ አስገራሚው ሁኔታ እንዴት እንደተፈፀመ ሲናገሩም አንድ መምህር ህፃኑን እርሳስና ላጲስ እናቱን እንዲያስገዛ ትእዛዝ ይሰጡታል። •ኬንያ ሳንቲሞቿ ላይ የነበሩ መሪዎችን በእንስሳት ቀየረች •ኬንያ ሳተላይት ልታመጥቅ ነው •ስደተኞችን የረዳው ኢማም ዘብጥያ ወረደ ልጁም እናቱን በጠየቀበት ወቅት መምህሩ ራሱ ይግዛልህ የሚል ምላሽ በመስጠቷ ተማሪውም የተባለውን ሄዶ ለትምህርት ቤቱ እንደተናገረ ይኼው ኮሚሽነሩ ገልፀዋል። ትምህርት ቤቱም ወላጅ እናቱን ጠርቶ ስለ ጉዳዩ ሲጠይቅ አላልኩም ብላ ከመካዷ በተጨማሪ በቀጣይነት የወሰደችው እርምጃ የልጆቿን ከንፈሮች አገጣጥማ መስፋትን እንደሆነ ኮሚሽነር ጁሊየስ ገልፀዋል።
news-46389817
https://www.bbc.com/amharic/news-46389817
የህጻናትን ዘረ መል ማስተካከል ክልክል ነው?
የሰው ልጆች ተክሎችን ማዳቀልና እንደገና መፍጠር ይችላል። ይህ ብቻም ሳይሆን የእንስሳትን ተፈጥሮ መቀየርና የሰው ልጅ የዘረ መልን እስከ ማስተካከልም ተደርሷል።
በቅርቡ አንድ ቻይናዊ ተመራማሪ የመንትዎችን ፅንስ ኤች አይ ቪ ኤድስ እንዳይዛቸው አድርጎ ውስጣዊ አወቃቀራቸውን አስተካክያለው ማለቱም የሰሞኑ ዜና ነው። ነገር ግን የሰው ልጅን ተፈጥሮአዊ የዘረ መል አወቃወር መቀየርና ማስተካከል በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት የሌለውና እንደውም እንደ ወንጀል የሚቆጠር ነው። ቻይናዊው ፕሮፌሰር እንደሚለው ከመንትዮቹ ሽል ውስጥ ለተለያዩ በሽታዎች ተጋላጭ ሊያደርጓቸው የሚችሉ ንጥረ ነገሮችን በማስወገድ ብቻ ኤች አይቪ በሽታ እንዳይዛቸው ማድረግ ችሏል። • ሳይንቲስቱ መንትዮች ኤች አይ ቪ እንዳይዛቸው ዘረ መላቸውን አስተካከለ • እውን እንጀራ ሱስ ያስይዛል? እንደዚህ አይነቶቹ የዘረ መል ጥናቶች አንዳንድ ከቤተሰብ የሚተላለፉ በሽታዎችንም ለማስቀረት ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው። ነገር ግን ገና ባልተወለዱ ህጻናት ላይ የሚከናወነው የዘረ መል ማስተካከልና መቀየር ሂደት ለሚቀጥለው ትውልድ የሚተላለፍ ችግር ሊሆን እንደሚችል የሚሰጉ ብዙዎች ናቸው። በገዛ እራሳችን ምርምር በሽታን ብንፈጥርስ የሚሉም አልጠፉም። ብዙዎቹ ሙከራዎችም በሰዎች ላይ ባይደረጉ ይመርጣሉ። እንግሊዝ ውስጥ ተመራማሪዎች መወለድ የማይችሉ ጽንሶች ላይ የዘረ መል ማስተካከል እንዲያደርጉ የሚፈቀድላቸው ሲሆን፤ ምንም አይነት ችግር የሌለባቸውና ያለምንም ችግር መወለድ የሚችሉ ጽንሶች ላይ ግን ምርምሩን ማካሄድ ክልክል ነው። አሜሪካ ከዚህ ጋር በተያያዘ ቀለል ያለ ህግ ያላት ሲሆን፤ ጃፓን ደግሞ ምረምሩን ለመፍቀድ እያሰበች ነው ተብሏል። ቻይናዊው ሳይንቲስት የሚሰራበት ሸንዘን የሚገኘው ሳውዘርን ዩኒቨርስቲ ኦፍ ሳይንስ ኤንድ ቴክኖሎጂ ስለ ምርምሩ ምንም እንደማያውቅ ጠቅሶ በአስቸኳይ ምርመራ እንደሚጀምርም አሳውቋል። • ልባችን ከእድሜያችን ቀድሞ ሊያረጅ እንደሚችል ያውቃሉ? በቻይና ህግ መሰረት ገና ባልተወለዱ ህጻናት ላይ የዘረ መል ማስተካከያ ምርምሮችን ማድረግ ክልክል ነው። የሃገሪቱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምክትል ሚኒስተር ዡ ናንፒንግ እንደተናገሩት ዜናውን ሲሰሙ በጣም ደንግጠዋል። ሰውዬው የሰራው ምርምርም የቻይናን ህግ የጣሰ ህገወጥ ተግባር ነው ብለዋል። በለንደኑ ሴንት ጆርጅ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚሰሩት ዶክተር ያልዳ ጃምሺዲ እንደሚሉት የዘረ መል ማስተካከል የተደረገባቸው ህጻናት ወደፊት ምን አይነት ችግሮች ሊገጥሟቸው እንደሚችል ማወቅ ከባድ ነው። ከዚህ ለየት ያለ ሃሳብ ያላቸው ደግሞ ምርምሩ ሊያመጣ የሚችለውን ችግር ካለማወቃችን በተጨማሪ ይላሉ፤ የዘረ መል ማስተካከል የተደረገባቸው ህጻናት ከሌሎች የተለዩ ተደርገው ሊቆጠሩ ይችላሉ ይላሉ። ይህ ደግሞ ከሌሎች የተለየ ጥቅም እንዲያገኙ አልያም እንዲገለሉ ሊያደርጋቸው እንደሚችል በመጥቀስ መቅረት አለበት በማለት ይከራከራሉ። • አዲስ የፀረ-ተህዋስ ዝርያ በአፈር ውስጥ ተገኘ ፅንሱ ላይ የተቀየረው የዘረ መል አይነት ወደፊት ለሚቀጥለው ትውልድ የሚተላለፍ እንደሆነ በመስጋትና በተፈጥሮ ጣልቃ መግባት መሆኑን በማሰብ ብዙዎች መከልከል አለበት ቢሉም፤ ቻይናዊው ሳይንቲስት ግን በሽታ ሳይከሰት በፊት ማስቀረት ምንድነው ችግሩ ባይ ነው። እ.አ.አ. በ2012 የተጀመረው የዘረ መል ማስተካከል ምናልባት ሃያላን ሰዎችን ለመፍጠር ጥቅም ላይ ውሎ በዓለማችን ያለውን የአቅምና የጉልበት ልዩነት ይበልጥ እንዳያሰፋው የሚሰጉም አልጠፉም።
news-57196960
https://www.bbc.com/amharic/news-57196960
በአሜሪካ ኢሲያዊያን ላይ የሚደርሰው ጥቃት ለምን ጨመረ?
ኢሲያዊያን ዝርያ ያላቸው ሰዎች በአሜሪካ ጥቃት በርክቶባቸዋል፡፡ ይህም የሆነው ከኮቪድ ወረርሽኝ መከሰት በኋላ ነው፡፡
ዛሬም ድረስ ነገሩ እየባሰበት እንጂ እየተሻሻለ አልመጣም፡፡ በዚህም የተነሳ ጆ ባይደን አዲስ ረቂቅ ሕግ እንዲወጣ አድርገዋል፤ ፊርማቸውንም አኑረውበታል። የፈረሙበት ረቂቅ ሕግ ኢሲያዊያን ጥቃት እየጨመረ በመምጣቱ ይህንኑ ለመግታት ካስቻለ በሚል ነው፡፡ መቼ ለታ አንድ የታይላንድ ጎልማሳ መሬት ላይ ተገፍትረው ተጥለው ሞተዋል፡፡ በቀደም አንድ የፊሊፒንስ ዝርያ ያለው አሜሪካዊ በሴንጢ ፊቱ ተቆራርጧል፡፡ ባለፈው አንዲት ቻይናዊት ሴት በጥፊ ተመትታ እሳት ተለኩሶበታል፡፡ የዛሬ ዓመት ገደማ በአንድ ምሽት በኢሲያዊያን የውበት ሳሎን ውስጥ ስምንት የኢሲያ ዝርያ ያላቸው ሰዎች ተገድለዋል፡፡ እነዚህ በሙሉ በቅርብ ጊዜ በተለይም የኮቪድን ወረርሽኝ ተከትሎ በአሜሪካ ምድር የደረሱ ጥቃቶች ናቸው፡፡ በቅርብ ወራት ደግሞ ፖሊስ በርካታ ክሶች ደርሰውታል፡፡ በተለይም በቃላት ዝርጠጣና ማንጓጠጥ፣ በድብደባ፣ እንዲሁም መንገድ ላይ በአደባባይ ጭምር የተተፋባቸው ኢሲያዊ መልክ ያላቸው አሜሪካዊያን ለፖሊስ አቤት ብለዋል፡፡ የመብት ተቆርቋሪዎች ይህ የጥላቻ ወንጀል ነው ይላሉ፡፡ በኢሲያዊያን ላይ ጥላቻው የበረታው ደግሞ ኮቪድ ወረርሽኝን ያመጣችሁብን እናንተ ናችሁ ከሚል እሳቤ ስለሚመነጭ ነው፡፡ የአሜሪካ የምርመራ ቢሮ ወረርሽኙ የመጣ ሰሞን በኢሲያዊ መልክ ባላቸው ዜጎች ላይ ጥቃት ሊበረታ እንደሚችል አስጠንቅቆ ነበር፡፡ የ2020 የጥላቻ ጥቃቶች ሪፖርት ለጊዜው ይፋ ባይሆንም በ2019 የጥላቻ ጥቃት አሐዝ ባለፉት 10 ዓመታት ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ከፍ ብሏል፡፡ ስቶፕ አፒሄት የተባለ አንድ በመብት ላይ የሚሠራ ቡድን ባለፈው ዓመት ብቻ 3ሺ የሚጠጉ ሪፖርቶች እንደደረሱት ይፋ አድርጓል፡፡ እነዚህ ሁሉ አቤቱታዎች የደረሱት ከኢሲያዊያን ሲሆን መልከ ብዙ ጥቃቶች ከተሰነዘረባቸው በኋላ ለተቋሙ አቤት ያሉ ናቸው፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም በኢሲያዊያን ላይ የጥላቻ ጥቃቶች አሳሳቢ በሚባል ደረጃ እየጨመሩ ነው ሲል ዘገባ አውጥቷል፡፡ አንዳንድ ግዛቶች ችግሩን ለመቅረፍ የተናጥል እርምጃ ጀምረዋል፡፡ ኒውዮርክ ከተማ ይህን የሚከታተል ልዩ ኃይል ያቋቋመች ሲሆን ባለፈው ዓመት ብቻ 27 ከፍተኛ ጥቃቶች መድረሳቸውን ሰንዳለች፡፡ በኦክላንድ፣ ካሊፎርኒያ ፖሊስ ‹ቻይናታውን› በሚባለው ሰፈር ልዩ ዕዝ (ኮማንድ ፖስት) እስከማቋቋም ደርሷል፡፡ ነገሩ እየተስፋፋ በመሄዱ ዕውቅ አሜሪካዊያን ይህ ዘረኝነት ጥቃት እንዲቆም ጥሪ ማቅረብም ጀምረዋል፡፡ እንዴት በአንድ ጊዜ በኢሲያዊያን ላይ ይህ ሁሉ የጥላቻ ጥቃት ሊደርስ ቻለ? ነገሩስ ለምን እያደገ መጣ ለሚለው ብዙ መላምቶች እየተሰነዘሩ ነው፡፡ አሜሪካዊያን በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት ሕይወታቸው ስለተመሰቃቀለ ይህን ወረርሽኝ ያመጡት ደግሞ የኢሲያ ሰዎች ናቸው ብለው በተሳሳተ መልኩ መረዳታቸው አንዱ ምክንያት እንደሆነ ይገመታል፡፡ ሌሎች ጥናቶች ደግሞ ነገሩን ያባባሱት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ናቸው ይላሉ፡፡ ትራምፕ በንግግራቸው ጸረ ቻይና አመለካከቶችና ዘረኝነቶች ይንጸባረቁ ስለነበር፣ በተለይም ወረርሽኙን ‹የቻይና ተህዋሲ› እያሉ ይጠሩት ስለነበር ደጋፊዎቻቸው ኢሲያዊያንን ሲያዩ ደማቸው መፍላት እንደጀመረ ይናገራሉ፡፡ ባይደን በበኩላቸው እንዲህ ያሉ ቃላት ጥላቻን ስለሚያነግሱ ማንም ሰው ኮቪድን ‹የቻይና ተህዋሲ› ወይም ‹ኩንግ ፍሉ› በሚል ቃል እንዳይጠቀም የሚከለክል ሕግ ላይ ፈርመዋል፡፡ ይህን ያደረጉትም ነጩ ቤተ መንግሥት በገቡ በመጀመርያው ሳምንት መሆኑ ለነገሩ የሰጡት ቦታ የሚያሳይ ነበር፡፡ በግንቦት 20 ደግሞ ኮቪድ19 ክራይም አክት የተሰኘ ረቂቅ ላይ ፈርመዋል፡፡ ይህ ረቂቅ ለፌዴራል አቃቢ ሕግ በዚህ የኢሲያዊያን ጥላቻ ዙርያ የተሻለ ሥራ እንዲሠራ በጀት የሚፈቅድ ሲሆን ግዛቶችም የጥላቻ ጥቃቶችን እንዲከላከሉና ሰፊ ሥራ እንዲሠሩ የሚያግዝ ድጎማን ይሰጣል፡፡ ከዚህ ሁሉ በኋላም ግን ነገሩ መሻሻል አልታየበትም፡፡ በአሜሪካ ኢሲያዊያን አሁንም ይንጓጠጣሉ፤ ይደበደባሉ፣ ተገድለው ይጣላሉ፡፡ ምናልባት ትልቁ ሥራ መሠራት ያለበት አስተሳሰብ ላይ ሳይሆን አልቀረም፡፡
news-52621423
https://www.bbc.com/amharic/news-52621423
ኮሮናቫይረስ፡ ከቤት መውጣት ሊያስጨንቀን ይገባል?
አንዳንድ አገራት የእንቅስቃሴ ገደብ እያላሉ ነው። የሥነ ልቦና ባለሙያዎች በበኩላቸው የእንቅስቃሴ ገደብ ከተነሳ በኋላ ሕይወት ምን ሊመስል ይችላል? የሚለው በርካቶችን እያስጨነቀ ነው ይላሉ።
የ25 ዓመቷ ጸሐፊና የአዕምሮ ጤና እንዲሁም የሴቶች መብት ተሟጋች አካንክሻ ባሂታ፤ “ለብዙዎቻችን ሕይወት ምቹ አይሆንም” ትላለች። የእንቅስቃሴ ገደቡ ከመጣሉ በፊትም ጭንቀት ውስጥ የነበረችው ጸሐፊ፤ ጭንቀት ያለባቸው ሰዎች ተገልለው ሲኖሩ ምን አይነት ተጽዕኖ እንደሚያድርባቸው በማኅበራዊ ሚዲያ ትገልጻለች፤ ከተከታዮቿ ጋርም ትወያያለች። ደልሂ ትኖር የነበረው አካንክሻ፤ ሕንድ እንቅስቃሴ ስትገታ ወደ ቼናይ አቅንታ ከቤተሰቦቿ ጋር ተቀላቅላለች። የአንድ ወር ቆይታዋ ቀላል አልነበረም። በጣም የከፋት ቀን ታለቅሳለች። አብዛኛውን ጊዜ በግሏ መሆንን ትመርጣለች። “ይህም ያልፋል እያሉ ለራስ መንገር ብቻ ነው የሚቻለው” ትላለች። “ጭንቀት ላለበት ሰው ከቤት መውጣት በራሱ ስቃይ ነው” ማኅበራዊ መስተጋብሮች የሚያስጨንቋት ጸሐፊቷ፤ የቤተሰቦቿ ድጋፍ አልተለያትም። ከቤተቦቿ ጋር መሆን ያስደስታታል። የእንቅስቃሴ ገደብ ሲነሳ እንዴት ወደቀደመ ሕይወቷ እንደምትመለስ ስታስብ ግን ትጨነቃለች። “ጭንቀት ላለበት ሰው ከቤት መውጣት በራሱ ስቃይ ነው” ትላለች። ቤት ውስጥ ብዙ ጊዜ ማሳለፍ ከተለመደ በኋላ ዳግመኛ ወደ ውጪ መውጣት አስፈሪ መሆኑን ታስረዳለች። ከህክምና ባለሙያዎች እስከ ነጋዴዎች ድረስ በርካቶች ጭንቅ ውስጥ ናቸው። በአጭር ጊዜ ውስጥ የብዙዎቻችን ሕይወት እንዳልነበረ መሆኑም እሙን ነው። ካናዳ ውስጥ የሚሠሩት የሥነ ልቦና ምሁር ዶ/ር ስቲቨን ቴይለር፤ “ሰዎች እንቅስቃሴ አልባ ሕይወትን ለመላመድ እየሞከሩ ነው” ይላሉ። ይህን ሕይወት መላመድ እንቅስቃሴ ሲጀመር ውዝግብ ውስጥ ሊከት ይችላል። “ሰዎች እንቅስቃሴ መቆሙን ተላምደው፣ ከወደዱት ከቤት መውጣት ሊያጨንቃቸው ይችላል” ይላሉ ዶ/ር ስቲቨን። ዓለም ስለ ኮሮናቫይረስ ከመስማቱ ከሳምንታት በፊት ስለ ወረርሽኝ እና ሥነ ልቦና መጽሐፍ ያሳተሙት ባለሙያው፤ የቫይረስ ሥርጭት እንዲሁም በቁጥጥር ሥር የመዋሉ ነገር ከሥነ ልቦና ጋር ይተሳሰራል ይላሉ። ዜጎችን ለድሕረ ወረርሽኝ ሕይወት ማዘጋጀት አገራት እንቅስቃሴ ላይ የጣሉትን ገደብ ሲያላሉ ዜጎች ደህንነት እንዲሰማቸው መደረግ እንዳለበት ዶ/ር ስቲቨን ያስረዳሉ። “ዜጎች ለድሕረ ወረርሽኝ ሕይወት እንዲዘጋጁ መደረግ አለበት። አሁን ከሰዎች ጋር መተቃቀፍ፣ ሬስቶራንት ሄዶ መመገብ ይቻላል መባል አለበት” ይላሉ። ሰዎች በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያቸው ስጋት ውስጥ እንዳይወድቁ መመሪያ መሰጠት አለበት። አንዳንዶች ከቤት የመውጣት ፍርሀት እያደረባቸው እንደሆነም ባለሙያው ይናገራሉ። “በበሽታው እያዝ ይሆን ብለው ይፈራሉ፤ ሆኖም ግን በሳምታት ወይም በወራት እድሜ ይህ ጭንቀት ይወገዳል።” በሌላ በኩል ጭንቀቱ የረዥም ጊዜ የሥነ ልቦና ጠባሳ የሚጥልባቸውም አሉ። ለምሳሌ ጸሐፊቷ አካንክሻ፤ ሕንድ እንቅስቃሴ ላይ የጣለችውን ገደብ ስታነሳ ምን ዓይነት ሕይወት ይጠብቀኝ ይሆን? ብላ እየተጨነቀች ነው። “ብዙዎች የእንቅስቃሴ ገደቡ የሚነሳበትን ቀን በጉጉት እየጠበቁ ነው፤ እነሱ ያሉበትን ስሜት ግን እኔ አልረዳም” ትላለች። የሥነ ልቦና ባለሙያዎች እንደሚመክሩት፤ አመጋገቧን አስተክላለች። የአካል ብቃት እንቅስቃሴም ትሠራለች። “ሁሉም ነገር ቀለል አርገን መጀመር አለብን። በየቦታው ድግስ ተጥሎ አዕምሮዬን መሳት አልፈልግም” ስትልም ትናገራለች። የእንቅስቃሴ ገደብ ከተነሳ በኋላ ከሚኖረው ለውጥ ጋር ለመላመድም ራሷን እያዘጋጀች ነው።
46106625
https://www.bbc.com/amharic/46106625
በካሜሮን ከ70 በላይ ተማሪዎችና መምህራን ታገቱ
በምዕራብ ካሜሮን በርካታ ተማሪዎችና መምህራን ታግተው መወሰዳቸው ተነገረ።
ሰኞ ዕለት 79 ተማሪዎችና ርዕሰ መምህሯን ጨምሮ ሶስት መምህራን በካሜሮን ከምትገኘው ባሜንዳ ታፍነው መወሰዳቸውን የመንግስት ባለስልጣናት ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ከታገቱት ተማሪዎች መካከል ዕድሜያቸው ከ10 - 14 የሚደርሱ ህፃናት የሚገኙበት ሲሆን ይማሩበት የነበረው ትምህርት ቤትም ፕሪስቤቴሪያን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይሰኛል። የካሜሮን ጦር ሰራዊትን ያካተተ የፍለጋ ቡድን ልጆቹን ለማግኘት አሰሳ ላይ ነው። የአካባቢው አስተዳደር የሆኑት አዶልፍ ሌሌ ላአፍሪክ ልጆቹን ያገቱት ተገንጣየይ ቡድኖች ናቸው ሲሉ ከስሰዋል። ሁለቱ የእንግሊዘኛ ተናጋሪ ክልሎች ነፃነታቸውን እንዲያገኙ የሚፈልጉ አማፅያን ትምህርት የማቆም አድማ ጠርተው ነበር። ነገር ግን አንድም አማፂ ቡድን ልጆቹን ያገትኩት እኔ ነኝ ሲል ኃላፊነቱን አልወሰደም። • ግብፅ የኮፕቲክ ክርስቲያኖች ላይ ጥቃት ያደረሱትን በሞት ቀጣች ከአጋቾቹ በአንዱ እንደተቀረፀ የተገመተ ተንቀሳቃሽ ምስል በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ላይ እየተንሸራሸረ ይገኛል። በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ በአንድ ጠባብ ክፍል ተፋፍገው የቆሙ ወንድ ህፃናት ተደናግጠው ካሜራውን የያዘው ግለሰብ ስማቸውን እና የመጡበትን አካባቢ እንዲናገሩ ሲጠይቃቸው ይሰማል። እንዲሁም "ትናንት ማታ በአምባ ቦይስ ነው የተወሰድኩት። የት እንዳለሁ አላውቅም" የሚል አረፍተ ነገርም ያስደግማቸዋል። አምባ የሚለው መጠሪያ ተገንጣዮቹ ቡድኖች ሊፈጥሩት የሚፈልጉት አምባዞኒያ የተሰኘው ሀገር በአጭሩ ሲጠራ ነው። ከተማሪዎቹ አንዱ የሆነው አልጋ ስር ተደብቆ ሳይያዝ የቀረው ልጅ ለቢቢሲ እንደተናገረው አጋቾቹ ትምህርት ቤቱ ውስጥ ከገቡ በኋላ ነገሮች በፍጥነት ነው የተከናወኑት። "አንድ ጓደኛዬን ያለርህራሄ ሲደበድቡት ነበር። ድምፄን አጥፍቼ መቆየት ብቻ ነበር የፈለግሁት። አንዳንዶቹን እንደሚተኩሱና እንደሚመቷቸው ይናገሩ ነበር። ትልልቆቹን ልጆች ከበቧቸው ትንንሾቹን ከኋላ ነበር ያደረጓቸው።" በትምህርት ቤቱ መምህርት የሆነችው ደግሞ "ወታደሮቹ ወደ ትምህርት ቤቱ ከገቡ በኋላ በቀጥታ ወደ ርዕሰ መምህርቷ ቢሮ አመሩ፤ ከዛም በሩን በኃይል በመገንጠል ገቡ። አሁንም ስብርባሪው አለ" ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች። • "ምንም ከህዝብ የሚደበቅ ነገር አይኖርም" አዲሱ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሽመልስ አብዲሳ በትምህርት ቤቱ እና በአማፂያኑ መካከል አሸማጋይ የሆኑት ግለሰብ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ "አጋቾቹ ምንም አይነት ነገር አይፈልጉም። የጠየቁን ትምህርት ቤቱን እንድንዘጋ ብቻ ነው። ስለዚህ ትምህርት ቤቱን እንደምንዘጋ ቃል ገብተንላቸዋል" ብለዋል። "ተማሪዎቹንና መምህራኖቹን ይለቋቸዋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን" ሲሉም አክለዋል። አማፂያኑ በሚንቀሳቀሱባቸው ስፍራዎች ተማሪዎች ሲታገቱ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በቅርብ ጊዜ ውስጥ ከአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ 5 ተማሪዎች ታግተው የተወሰዱ ሲሆን አስካሁን ድረስ የደረሱበት አልታወቅም። የካሜሮን አማፅያን እንደሚሉት የሀገሪቱ የትምህርት ስርዓት እንግሊዘኛ ተናጋሪ የሆኑትን ይጨቁናል ሲሉ ይከሳሉ። • "ሌሎች ሴቶች ላይ የአሲድ ጥቃት ሳይ ይረብሸኛል፤ ህመሜን ያስታውሰኛል" ካሚላት መህዲ
news-51749412
https://www.bbc.com/amharic/news-51749412
የኦጋዴን ጦርነት፡ የሲያድ ባሬ ወረራ ሲታወስ
ኩባዊው ወታደር ካርሎስ ኦርላንዶ - በወቅቱ ዕድሜው 20 ነበር። ካርሎስ ኦርላንዶ ጥር 1970 ዓ.ም. የሶማሊያ ወታደሮች እጅ ላይ ወደቀ።
ከቀኝ ወደግራ - መንግሥቱ ኃይለማርያም፣ ፊደል ካስትሮ እና ራውል ካስትሮ የዓለም መገናኛ ብዙሃን በተሰበሰቡበት የኢትዮጵያንና ኩባን ወታደራዊ ምስጢር እንዲያወጣ ተደረገ። የኦጋዴን ጦርነት ተብሎ የሚታወቀው በኢትዮጵያና ሶማሊያ መካከል የተደረገው ጦርነት የዛሬ 42 ዓመት የካቲት 26/1970 ዓ.ም. ነበር የተጠናቀቀው። በ1966 ዓ.ም ሶማሊያ የአረብ ሊግን ተቀላቀለች። በወቅቱ የሶማሊያ መሪ የነበረው ሜጀር ጄኔራል ሲያድ ባሬ ኢትዮጵያን ወረረ። ጦርነቱ የተጀመረ ሰሞን የሲያድ ባሬ [ዚያድ ባሬ] ጦር በሶቪዬት ኅብረት ይደገፍ ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥት ደግሞ ከዩናይትስ ስቴትስ ጋር ወዳጅነት አለው። በወቅቱ በቀዝቃዛ ጦርነት ውስጥ የነበሩት ሶቪዬት ኅብረትና አሜሪካ ምሥራቅ አፍሪካ ገቡ። ፕሬዝደንት አብዲራሺድ አሊ ሸርማርኬን በመንፈቅለ-መንግሥት ፈንግሎ ሥልጣን የጨበጠው የዚያድ ባሬ መንግሥት ድንበር ማስፋፋት ዋነኛ ዓላማው አደረገ። ወሳኟ ቦታ ደግሞ - ኦጋዴን። ኦጋዴን ሠፍሮ የሽምቅ ውጊያ ያካሂድ የነበረው የምዕራብ ሶማሌ ነፃ አውጭ ግንባር የኢትዮጵያ ጦር ላይ ጥቃት ሠነዘረ። የጦርነቱ መባቻ ተደርጎ የሚቆጠረውም ይህ ጥቃት ነበር። በመቀጠል የዚያድ ባሬ ጦር በሶቪዬት ኅብረት የጦር መሣሪያ ታግዞ ወደ አጋዴን ገሰገሰ። በወቅቱ ከንጉሡ አገዛዝ ወደ ወታደራዊው ደርግ የተሻጋገረችው ኢትዮጵያ በይፋ ራሷን ማርክሲስት ስትል አወጀች፤ ወዳጅነቷም ከሶቪዬት ኅብረት ጋር ሆነ። አሜሪካ ደግሞ ድጋፏን ለሶማሊያ አደረገች። ሁለቱ አገራት ወደ ቀለጠ ጦርነት ገቡ። በወቅቱ የሲያድ ባሬ መንግሥት ኩባውያን የኢትዮጵያውን ጦር ደግፈው እየተዋጉ ነው ሲል ወቀሰ። ይህንንም ለማሳመን ሲሉ የኩባ ወታደሮች መያዝ ጀመሩ። የዚያኔ ነው ኩባዊው ወታደር ካርሎስ ኦርላንዶ ተይዞ ለጋዜጠኞች መግለጫ እንዲሰጥ የተገደደው። ኩባዊው ወታደር ካርሎስ ኦርላንዶ [በስተቀኝ] የዚያድ ባሬ መንግሥት ወራራውን አጠናክሮ በጅግጅጋ በኩል ደንበር አልፎ ገብቶ ብዙ ጥፋት አደረሰ። የንፁሃን ዜጎች ሕይወት ተቀጠፈ። አልፎም ወደ ሐረር ገሰገሰ። ይሄኔ ነው የኢትዮጵያ ክተት የታወጀው። ሐረር ላይ 40 ሺህ ገደማ የኢትዮጵያ ጦር ኃይል ጠበቀው። ተጨማሪ 10 ሺህ የኩባ ጦረኞች ከኢትዮጵያ ጎን ነበሩ። የኢትዮጵያ ጦር የዚያድ ባሬን ጦር አሳዶ ከመሬቱ አስወጣ። የመጨረሻው ውጊያ የነበረው ካራማራ ላይ ነበር። በወቅቱ በዘመናዊ የጦር መሣሪያ የታገዘው የኢትጵያ ጦር በሰማይ በምድር ጥቃቱን በማጠናከር የሶማሊያ ጦርን ድባቅ መታ። ጦርነቱ ሲጀመር ኢትዮጵያ 10 በመቶ ብቻ የኦጋዴን መሬት በእጇ ነበር። ጦርነቱ ካራማራ ተራራ ላይ ሲያበቃ ኦጋዴን ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ተያዘች። በካራማራ ጦርነት በርካቶች ተሰውተዋል። በቀጣናው ያለውን ድርሻ ለማስፋት ኢትዮጵያን የወረረው ሜጀር ጄነራል ሲያድ ባሬ ከሽንፈቱ በኋላ ተቀባይነቱ እየሟሸሸ መጣ። ታላቋ የሚል ቅጥያ የነበራት ሶማሊያም ከኦጋዴን ጦርነት በኋላ በእርስ በርስ ጦርነት መታመስ ጀመረች። ሲያድ ባሬ 1983 ዓ.ም ከሥልጣን ተወግዶ ወደ ናይጄሪያ ሸሸ። ሕልፈተ ሕይወቱም ለአራት ዓመታት በስደት በቆየባት ናይጄሪያ ሆነ። በጦርነቱ ኩባ፣ ሰሜን ኮሪያ፣ የመንና ምሥራቅ ጀርመንን ጨምሮ ሌሎች አገራት አጋርነታቸውን ለኢትዮጵያ አሳይተዋል። ከ16ሺህ በላይ የኩባ ወታደሮች በውጊያው እንደተሳተፉ መዛግብት ያሳያሉ። የኢትዮ-ሶማሊያ የኦጋዴን ጦርነት የብዙሃን ሰላማዊ ዜጎችን ቢቀጥፍም፤ ኢትዮጵያዊያን ወታደሮች ጅግንነታቸውን ያሳዩበት እንደሆነ በታሪክ ይወሳል።
news-52965329
https://www.bbc.com/amharic/news-52965329
የጆርጅ ፍሎይድ ሞት በአሜሪካ አዲስ ሕግ እንዲረቀቅ ምክንያት ሆነ
በአሜሪካ የሕግ መምሪያ ምክር ቤት በዲሞክራት ፓርቲ አባላት አመንጪነት አዲስ የሕግ ረቂቅ ቀርቧል። ረቂቁ የአሜሪካንን ፖሊስ የሚመለከት ነው።
ከፍተኛ የዴሞክራቲክ ፓርቲ ባለስልጣናት ተንበርክከው ጆርጅ ፍሎይድን ሲያስቡ ይህ የሕግ ረቂቅ በፍጥነት እንዲቀርብ ያደረገው የጆርጅ ፍሎይድ በሜኔሶታ ግዛት፣ ሚኒያፖሊስ ከተማ ውስጥ በፖሊስ በግፍ መገደሉ ሲሆን ይህን ተከትሎ በመላው አሜሪካ የተቀሰቀው ተቃውሞ ሌላ ምክንያት ሆኗል። የሕግ ረቂቁ በአሜሪካ እጅግ ከባድ ሆኖ የቆየውን ፖሊስን የመክሰስ ጉዳይ ቀላል ያደርገዋል ተብሎ ይጠበቃል። የተጠርጣሪዎችን አንገት በክንድ ጠምልሎ መያዝ እና ተጠርጣሪ ትንፋሽ እንዲያጥረው ማድረግን ያስቀራል ተብሏል። በተለይም ረቂቁ ዘርን ማዕከል ያደረጉ የፖሊስ እርምጃዎችን ይቀንሳል ተብሎለታል። ይህ ረቂቅ የሚኒያፖሊስ ሕግ አውጪዎች የከተማዋን ፖሊስ ኃይል ለመበተን መዛታቸውን ተከትሎ ነው የቀረበው። የጆርጅ ፍሎይድ በነጭ ፖሊስ በግፍ መግደል ይህ ረቂቅ በቶሎ እንዲረቀቅ ምክንያት ሳይሆን አልቀረም። ነገር ግን ረቂቁ በሁለቱም ምክር ቤት ዲሞክራቶች ዘንድ ከፍ ያለ ድጋፍ ያግኝ እንጂ በሕግ መወሰኛው ምክር ቤት የሚገኙ ሪፐብሊካኖች ይደግፉታል ወይ የሚለው አጠያያቂ ሆኗል። የሟች ጆርጅ ፍሎይድ ወንድም በዚህ ሳምንት መጨረሻ በሕግ መምሪያው ምክር ቤት ቀርቦ ምስክርነት ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ "ጀስቲስ ኢን ፖሊሲንግ አክት-2020" የተሰኘው ሪቂቅ ለሕግ መምሪያ ምክር ቤት የቀረበው ትናንት ሰኞ ሲሆን ረቂቁን ያስተዋወቁት ዝነኛዋ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ናንሲ ፒሎሲ፣ እንዲሁም ቸክ ሹመር፣ እና ጥቁሩ የምክር ቤት አባል ካማላ ሀሪስ ናቸው። አፈ ጉባኤዋ ናንሲ ፒሎሲ ይህን ረቂቅ የሕግ ሐሳብ ለምክር ቤቱ ከማስተዋወቃቸው በፊት በቅርብ ጊዜ በፖሊስ ግፍ የተገደሉ ጥቁር ሴትና ወንድ አሜሪካዊያንን ስም ዝርዝር ለሸንጎው አሰምተዋል። ይህ ረቂቅ የሕግ ሐሳብ ወደፊት ሕግ ሆኖ ከጸደቀ የፌዴራል ፖሊስ ኃይልን ሳይሆን እንደ ረቂቅ ካሜራ ያሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን እንዲጠቀም ያስገድደዋል። ማጅራትን ጠምልሎ መያዝ፣ በተጠርጣሪዎች ላይ ድንገቴ አሰሳና አፈሳ ማድረግንም ይገድባል። ከዚህም በላይ ፖሊስ ለሚፈጽማቸው ጥፋቶችና የመብት ጥሰቶች ተጠያቂ የሚሆንበትን ዕድል ያመቻቻል። ይህን በማይተገብሩ የፖሊስ ኃይሎች ላይ የፌዴራል ፈንድ እንዳይለቀቅላቸው ያደርጋል። "የጆርጅ ፍሎይድ በዚያ መንገድ መሰዋት ለበርካታ አሜሪካዊያን በስቃይና በግፍ መሞት ምን እንደሚመስል ለቅጽበት እንዲያስቡት እና ብሔራዊ የጋራ ስሜት እንዲያገኙም ጭምር አድርጓል" ብለዋል ናንሲ ፒሎሲ በንግግራቸው። "ዛሬ ይህ ብሔራዊ የመጠቃት ስሜት ወደ ብሔራዊ ሕግ የሚሸጋገርበት ዕለት ነው" ሲሉም የሕጉን አስፈላጊነት አስምረውበታል። ይህ ሕግ ሲጸድቅ ተጠርጣሪዎችን በግፍ መግደልን ይከላከላል፣ ፖሊሶች የሚገዟቸውን የጦር መሣሪያዎች ዓይነት ይወስናል፣ የፍትሕ ሚኒስትር በፌዴራልና በአካባቢ ፖሊስ የሚፈጸሙ ዘር ተኮር በደሎችን እንዲመረምር ስልጣን ይሰጣል። ከዚህም በተጨማሪ የፖሊስን የሕግ ጥሰቶች የሚመዘገብ ትልቅ ብሔራዊ ቋት እንዲኖር ያስችላል። አንዳንድ ሪፐብሊክን የራሳቸውን የሕግ ረቂቅ ሐሳብ ለመጻፍ እንደሚያስቡ ፍንጭ የሰጡ ቢሆንም በአመዛኙ የዶናልድ ትራምፕ ፓርቲ ግን ለናንሲ ፒሎሲ ረቂቅ ድጋፍ ስለመስጠት አለመስጠቱ አልታወቀም። ከዶናልድ ትራምፕ መስመር አፈንግጠዋል የሚባሉት የሪፐብሊካኑ ሴናተር ሚት ሮምኒ ባለፈው እሑድ በትዊተር ሰሌዳቸው ከሰልፈኞች ጋር ወደ ዋይት ሐውስ ሲያቀኑ የሚያሳይ ፎቶግራፍ የሰቀሉ ሲሆን ከፎቶግራፉ ስር "የጥቁሮች ሕይወት ግድ ይለኛል" (ብላክ ላይቭስ ማተር) የሚል ጽሑፍ አስቀምጠዋል። በሕግ መምሪያ ምክር ቤት ውስጥ የዲሞክራቲክ ፓርቲ ተወካዮች ቁጥር ስለሚያይል ይህ ረቂቅ በከፍተኛ ድምጽ የማለፍ ዕድል ቢኖረውም በሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ግን እንቅፋት ሊገጥመው ይችላል የሚል ስጋት አለ። በተለይም ዶናልድ ትራምፕ ከናንሲ ፒሎሲ ጋር ያላቸው የሻከረ ግንኙነት እንቅፋት ሊፈጥር እንደሚችል ተሰግቷል። ረቂቅ ሕጉ በአሜሪካ ሕግና ሥርዓት እንዲሸረሸር ሊያደርግ ይችላል በሚል ዶናልድ ትራምፕ ተቃውሞ ሊያቀርቡበት ይችላሉ ተብሎም ተሰግቷል። ዶናልድ ትራምፕ ተቃውሞ ካቀረቡበት ደግሞ የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ውድቅ ሊያደርገው የሚችለበት ዕድል ሰፊ ይሆናል።
50697934
https://www.bbc.com/amharic/50697934
በኔፓል የወር አበባ የሚያዩ ሴቶች ጽዩፍ ተደርገው ይታያሉ
በኔፓል ገጠራማ አካባቢዎች "የወር አበባ ጎጆ" የሚባል ነገር አለ። "የወር አበባ ጎጆ" ማለት ሴቶች ከወለዱ በኋላ ወይም ደግሞ የወር አበባ በሚያዩበት ሰዓት ከኅብረተሰቡ ተገለውና ራቅ ተደርገው የሚመቀመጡበት እልፍኝ ነው።
በቅርቡ የ21 ዓመቷ ወጣት ፓርባቲ ራዋት የወር አበባ ላይ ነሽ በሚል ራቅ ተደርጋ በዚህ "የወር አበባ ጎጆ" እንዲቆለፍባት ኾና ነበር። በዚያው ታፍና ሞታለች። ከርሷ ሞት ጋር በተያያዘ አንድ የቤተሰብ አባል በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውሏል። ይህ ሴቶችን የማግለለ ተግባር በሕግ የተከለከለ ቢሆንም ፖሊስ ተጠርጣሪን ለመያዝ ሲሞክር ግን ይህ የመጀመርያ ነው። በአገሬው ባሕል ሴቶች የወር አበባ ላይ ከሆኑ እንደቆሸሹ ተደርጎ ይታሰባል። • ፍርድ ቤት እየሄደች ሳለ በእሳት የተቃጠለችው ሕንዳዊት ሞተች • የወር አበባ ለምን በአንዳንድ ሴቶች ላይ ህመም ያስከትላል? • ኔፓላዊቷ ለወር አበባ በተገለለ ጎጆ ሕይወቷ አለፈ ሴቶችን ጽዩፍ አድርጎ የማየቱ ነገር በወር አበባ ጊዜ ብቻ አይደለም። ልጅ ከወለዱ በኋላም ለተወሰነ ጊዜ ተገለው ራቅ ባለች ጎጆ ይቆለፍባቸዋል። ፖሊስ ያዝኩት ያለው የሟች ቤተሰብ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ የሚቀጣው 26 ዶላር ብቻ ነው። ምዕተ ዓመት ባለፈው የሂንዱ ባሕል ሴቶች በወር አበባ ጊዜያቸው ከእንሰሳት ጋር ጋጣ ውስጥ እንዲያድሩ ይደረጋሉ። በወር አበባ ላይ ሳሉ የሚነኩት ነገርም እንደረከሰ ይታሰባል። ምግብንም ሆነ ወንድን እንዳይነኩ ጥብቅ መመሪያ አለ። በዚህ ዘመንም ቢሆን በወር አበባ ጊዜ ራቅ ወዳለ ጎጆ ተወስደው እዚያው እንዲኖሩ ይደረጋል። የሚኖሩባቸው ጎጆዎች እጅግ ቅዝቃዜ ስለሚኖራቸው ሴቶቹ በወሊድ ጊዜ ለሞት ይዳረጋሉ። በቅርቡ በእባብ ተነድፋ የሞተች ሴትም እንዳለች ፖሊስ ገልጧል። ኔፓል ይህን ኋላ ቀር አስተሳሰብና ድርጊት እንዲቆም ጥረት ማድረግ የጀመረችው እንደ ጎርጎሮሲያዊያኑ በ2005 ቢሆንም ወንጀል ሆኖ የተደነገገው ግን ከሁለት ዓመት በፊት ነው። ያም ሆኖ ይህ አጉል ባሕል ስር የሰደደ በመሆኑ ወንጀል መደረጉ እምብዛምም ለውጥ አላመጣም። በዚህ ዓመት ብቻ ሦስት ሴቶች የወር አበባ ላይ ናችሁ ተብለው ራቅ ወዳሉ ጎጆዎች ተወስደው በመጣላቸው ሞተዋል። አንዲት ሴት በዚህ እጅግ ጠባብ በሆነ "የወር አበባ ጎጆ" ውስጥ ከሁለት ልጆቿ ጋር ለመታሰር በመገደዷ እርሷም ልጆቿም ታፍነው መሞታቸው ተዘግቧል።
news-51367629
https://www.bbc.com/amharic/news-51367629
አባቱ በኮሮናቫይረስ ተጠርጣሪነት ወደ ለይቶ ማቆያ የገባበት ቻይናዊ አካል ጉዳተኛ ታዳጊ ሞተ
በራሱ መንቀሳቀስም ሆነ ምንም አይነት ነገሮችን ማከናወን የተሳነው ቻይናዊ ታዳጊ፤ አባቱ በኮሮናቫይረስ ተጠርጣሪነት ተለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲገባ በተደረገ በሳምንቱ ህይወቱ አልፏል።
አባትየው ለታዳጊው ብቸኛው አሳዳጊ እንዲሁም ተንከባካቢው ነበር ተብሏል። ይህንንም ተከትሎ ቻይና ሁለት ባለስልጣኗቿን ከሥራ አባራለች። የአስራ ስድስት ዓመቱ ታዳጊ ሞቶ የተገኘው ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ዕለት ሲሆን አባቱ እንዲሁም ወንድሙ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ከገቡ ከሳምንት በኋላ ነው። •ቻይና አሜሪካን ኮሮናቫይረስን አስመልክቶ ፍራቻ እየነዛች ነው ስትል ወነጀለች •ከቻይና ውጪ የመጀመሪያው ግለሰብ በኮሮና ቫይረስ ሞተ የታዳጊው ህይወት ከማለፉ በፊት በሳምንት ውስጥ ሁለት ጊዜ ብቻ እንደተመገበም የወጡ ሪፖርቶች ያሳያል። የአካባቢው የኮሚዩኒስት ፓርቲ ፀሐፊ እንዲሁም ከንቲባ ሁጃሄ ከስልጣናቸው እንዲወርዱ ተደርገዋል። የታዳጊውም ታሪክ በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል። ቤተሰቡ የኮሮና ቫይረስ መነሻ ናት በምትባለው ሁቤይ ግዛትም ይኖሩ ነበር። •ቻይና ለኮሮና ቫይረስ ህሙማን በስምንት ቀናት ሆስፒታል ገነባች •በኮሮናቫይረስ ከተጠረጠሩ አራት አዲስ ሰዎች አንዱ በአክሱም እንደሚገኝ ተገለፀ አባትየው ለይቶ ማቆያ ውስጥ ከገባ በኋላ ዌይቦ ተብሎ በሚጠራው የቻይና ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ልጁ ብቻውን እንደሆነ፣ ምግብም ሆነ ውሃ ቤት ውስጥ እንደሌለ በመግለጽ እርዳታ እንዲሰጠው መማፀኑን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። 'ሰረብራል ፐልሲ' ተብሎ በሚጠራውና ገና በጨቅላነት በሚከሰት በሽታ ይሰቃይ የነበረው ታዳጊ የእይታ ችግር፣ የመስማትና የመናገር እክል፣ የጡንቻ መዛል በአጠቃላይ አካላዊ እንቅስቃሴን ማድረግ አይችልም ነበር ተብሏል። ታዳጊው መሞቱ ከተሰማ በኋላ ባለስልጣናቱ ምርመራ እንደሚጀምሩ አሳውቀዋል። እስካሁን ባለው መረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 17 ሺህ የደረሰ ሲሆን ለ361 ሰዎች ህይወት መቀጠፍም ምክንያት ሆኗል። ከቻይና ውጭ 150 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውም የተረጋገጠ ሲሆን በፊሊፒንስም አንድ ሞት ተከስቷል። የዓለም ጤና ድርጅት ቁጥሩ ከዚህ በላይ እንደሚያሻቅብም ያስጠነቀቀ ሲሆን፤ የቻይና ባለስልጣናት ቫይረሱ እንዳይዛመት የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ናቸው።
news-57058614
https://www.bbc.com/amharic/news-57058614
በአፍሪካ ሕብረት ለሚመራው ድርድር አሜሪካ ድጋፍ አደርጋለሁ አለች
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፈሪ ፌልትማን አገራቸው በአፍሪካ ሕብረት መሪነት ሦስቱ አገራት ለሚያደርጉት ድርድር አሜሪካ ድጋፏን ለማድረግ ቁርጠኛ ነኝ አሉ።
አምባሳደሩ ይህን ስለማለታቸው የተሰማው ዛሬ ከውሃ፣ ኢነርጂ እና መስኖ ሚንስትሩ ዶ/ር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ጋር ከተወያዩ በኋላ ነው። በቀጠናው በሚገኙ አገራት ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት አምባሳደር ፌልትማን ዛሬ ከኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ተደራዳሪ ቡድን አባላት ጋር ውይይት ማድረጋቸው ተዘግቦ ነበር። ዶ/ር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ከአምባሳደር ፌልትማን ጋር መወያየታቸውን በትዊተር ገጻቸው ላይ ገልጸው፤ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ደረጃን በተመለከተ እና በአፍሪካ ሕብረት ስለሚመራው የድርድር ሂደት ዙሪያ ግልጽ ውይይት ማድረጋቸውን አስፍረዋል። አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን አገራቸው አድልዎ የሌለበት ድጋፍ እንደምታደርግ እና ሦስቱ አገራት በአፍሪካ ሕብረት መሪነት ሁሉን ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት እንዲደርሱ ቁርጠኛ መሆኗን መናገራቸውን ገልጸዋል። የአባይ ወንዝ ለኢትዮጵያ እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል እና ወደፊት በድርድሩ እንዴት ከስምምነት መድረስ እንደሚቻል ማብራሪያ መስጠታቸውን ገልጸዋል። አምባሳደር ፌልትማን በተለያዩ በቀጠናው በሚገኙ አገራት ከሚያደርጉት ኦፌሴላዊ ጉብኝት በተጨማሪ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቢሮዎች፣ የአፍሪካ ህብረት የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም ከፖለቲካ አመራሮችና ከሰብአዊ እርዳታ ተቋማት ሃላፊዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል። ልዩ መልዕክተኛው በአፍሪካ ሃገራት ጉብኝት እያደረጉ ያሉት ሃገራቸው በአፍሪካ ቀንድ የፖለቲካ፣ የጸጥታና ሰብአዊ ችግሮች በዲፕሎማሲያዊ ጥረት እንዲፈቱ ያላትን ቁርጠኝነት ለማረጋገጥና በቀጠናው ያላትን የፖሊሲ ትብብር ለማጠናከር ነው ተብሏል። አምባሳደር ፌልትማን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው በፕሬዝደንት ጆ ባይደን በቅርቡ መሾማቸው ይታወሳል። ልዩ መልዕክተኛ አዲስ አበባ ከመግባታቸው በፊት በግብጽ፣ ሱዳን እና ኤርትራ ተገኝተው ከየአገራቱ መሪዎች ጋር መወያየታቸው አይዘነጋም። አምባሳደር ፌልትማን ለሁለት ቀናት ሱዳን ከቆዩ ወደ አስመራ አቅንተው ከፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ረዘም ላለ ሰዓት መወያየታቸውን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስትር የማነ ገብረመስቀል አስታውቀው ነበር። አራት ሰዓት በቆየው ውይይት ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ኤርትራ ከአሜሪካ ጋር አብራ ለመሥራት ቁርጠኛ መሆኗን ተናግረዋል ሲሉ የማስታወቂያ ሚንስትሩ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። አምባሳደሩ ከዚህ በተጨማሪ ወደ ግብጽ አምርተው ከፕሬዝደንት አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ፣ ከውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ ሳሚህ ሽኩሪ እና ከሃገሪቱ የውሃ ሚንስትር ጋር ስለመገናኘታቸው ተዘግቧል። በውይይታቸው ወቅት አል-ሲሲ ግብጽ ከአባይ ውሃ የምታገኘው ድርሻ መቀነስን አትታገስም በማለት ስለመናገራቸው ዋሽግተን ፖስት ዘግቧል። አምባሳደር ፌልትማን ከግብጽ ባለስልጣናት ጋር በነበራቸው ቆይታ የጆ ባይደን አስተዳደር በቀጠናው ላሉ አንገብጋቢ ጉዳዮች መፍትሄ ለመስጠት ትኩረት ያደርጋል ሰለማለታቸው ዋሽንግተን ፖስት ምንጮቹን ጠቅሶ ጨምሮ ዘግቧል። ጄፍሪ ፌልትማን ፌልትማን ማን ናቸው? ጄፍሪ ፌልትማን በሹመታቸው ወቅት በተለይ በኢትዮጵያና በዙሪያዋ ስላሉ ሁኔታዎች የተለየ ትኩረት እንደሚሰጡ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ አስታውቆ ነበር። ፌልትማን በድርድርና የሽምግልና ጉዳዮች ላይ ጥናትን በማካሄድና በአደራዳሪነትም ከፍ ያለ ልምድ እንዳላቸው ይነገራል። ፌልትማን በፖለቲካዊና በውጭ ጉዳይ ፖሊሲዎች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቀድሞውንና የአሁኑን ዋና ጸሐፊዎች ባን ኪሙን እና አንቶኒዮ ጉቱሬዝን ያማከሩ ሲሆን፤ ለጸጥታው ምክር ቤት በሠላምና በደኅንነት ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያዎችን በመስጠት ይታወቃሉ። በተባበሩት መንግሥታት ቆይታቸው ወቅትም በልዩ መልዕክተኝነት አገልግለዋል፤ በተጨማሪም በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ውስጥ ለ26 ዓመታት ያገለገሉት ፌልትማን በሊባኖስ፣ በኢራቅ፣ በእስራኤል፣ በቱኒዚያ፣ በሃንጋሪና በሄይቲ ከፍተኛ ዲፕሎማት ሆነው አገልግለዋል።
news-48488782
https://www.bbc.com/amharic/news-48488782
ኔይማር የቀረበበትን ወሲባዊ ትንኮሳ ክስ አጣጣለ
ብራዚላዊው ዕውቅ እግር ኳሰኛ ኔይማር በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ በአንዲት ሴት ላይ ወሲባዊ ትንኮሳ አድርሰሃል ተብሎ ክስ ቀረበበት።
በሳኦ ፖሎ ብራዚል የተመሰረተበት የክስ ሪፖርት እንደሚያሳየው ከሆነ፤ ከሳሿ ሴት ኔይማር በሚጫወትበት ፓሪስ መሃል ከተማ በሚገኝ አንድ ሆቴል ውስጥ ወሲባዊ ትንኮሳውን ፈጽሞብኛል ብላለች። • ሮናልዶ "ደፍሮኛል" ያለችው ሴት ከመብት ተሟጋቾች ድጋፍ አገኘች • የምሥራቅ ሸዋ ፖሊስ የተዘረፈውን ቡና እየፈለገ ነው የቀረበውን ክስ በማስመልከት የኔይማርም ወኪሎች ''ሙሉ በሙሉ የተሳሳተ'' ሲሉ አሳጥለውታል። ኔይማር በአሁኑ ሰዓት ለኮፓ አሜሪካ ውድድር ከብሄራዊ ቡድኑ ጋር በብራዚል ልምምድ እያደረገ ይገኛል። የቀረበበት ክስ ምንድነው? የፖሊስ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፤ ከሳሿ ኔይማርን የምታውቀው ኢንስታግራም ላይ ሲሆን፤ ኔይማር ፓሪስ ከተማ እንዲገናኙ እንደጠየቃት ቃሏን ሰጥታለች። ከዚያም ከብራዚል ፈረንሳይ የአየር ቲኬት እንደገዛላት እና ሆቴል ሶፊትል ፓሪስ አርክ ዲ ቲሪየምፍ በተሰኘ ቅንጡ ሆቴል እንድታርፍ እንዳደረገ ጨምራ ለፖሊስ ተናግራለች። ኔይማርም ወደተጠቀሰው ሆቴል ግንቦት 7 ሲመጣ ''በግልጽ ሰክሮ'' ነበር ትላለች። ለጥቂት ደቂቃዎች ከተነጋገሩ በኋላ ኔይማር ይህቺን ሴት ወደ ራሱ አስጠግቶ በመያዝ ''ያለሴቲቱ ፍቃድ በኃይል ወሲብ ፈጽሟል'' ይላል የፖሊስ የክስ መዝገብ። • የወሲብ ቪዲዮ ህይወቷን ያሳጣት ወጣት ከዚያም ጥቃቱ የተፈጸመባት ሴት ከሁለት ቀናት በኋላ የደረሰባትን ጥቃት ለፈረንሳይ ፖሊስ ሳታሳውቅ ወደ ብራዚል ተመለሰች። "በደረሰባት ጥቃት እጅጉን ተደናግጣ እና ፈርታ ስለነበረ በሌላ ሃገር የደረሰባትን እውነታ ማሳወቅ አልተቻላትም'' ይላል ለፈረንሳይ ፖሊስ ለምን ሪፖርት እንዳላደረገች የክስ ሪፖርቱ ሲገልፅ። የኔይማር አባት ምን ይላሉ? የእግር ኳሰኛው አባት፣ ኔይማር ዶስ ሳንቶስ፣ ቅዳሜ ዕለት ለብራዚል ቴሌቪዝን ሲናገሩ ''ይህ ግልጽ የሆነ ወጥመድ ነው።'' ብለዋል። ''በጉዳዩ ላይ የሕዝብ አመለካከት ካልጠራ እና እውነታውን በፍጥነት ማሳየት የማንችል ከሆነ፤ ይህ ጉዳይ እየተባባሰ ነው የሚሄደው። ኔይማር ከዚህች ሴት ጋር በዋትስአፕ ያደረጋቸውን ግንኙነቶች ብንመለከት እውነታው ይታወቃል'' ይላሉ የኔይማር አባት። የ27 ዓመቱ አጥቂ የሥነምግባር ጉድለት የብራዚል ብሔራዊ ቡድን አምበልነትን አሳጥቶታል። ከአንድ ወር በፊት ክለቡ ፒኤስጊ በሌላ ክለብ መሸነፉን ተከትሎ ኔይማር ደጋፊን በመማታቱ የፈረንሳይ የእግር ኳስ ኃላፊዎች በሦስት ጨዋታዎች ላይ እንዳይሰለፍ ውሳኔ አስተላልፈውበታል። ኮፓ አሜሪካ የደቡብ አሜሪካ ሃገራት ውድድር ሲሆን ከ12 ቀናት በኋላ በአዘጋጇ ሃገር ብራዚል ይከናወናል።
52475576
https://www.bbc.com/amharic/52475576
ኮሮናቫይረስ: አማራ ክልል ሠርግ ላይ በፈነዳ ቦንብ ህይወት ጠፋ
በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን እናርጅና እናውጋ ወረዳ እናርጅ ሲማ ቀበሌ ትላንትና ምሽት ሲካሄድ በነበረ የሠርግ ሥነስርዓት ላይ በቦንብ ፈንድቶ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ።
ህይወታቸው ካለፉት በተጨማሪ አራት ሰዎች ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን አራቱ ደግሞ ቀላል ጉዳት እንደደረሰባቸው የእናርጅና እናውጋ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ጥሩ ሴት መንግስት ለቢቢሲ ገልጸዋል። ከሟቾቹ አንዱ የሆኑት እና ቦንቡን ይዘውት የነበሩት ግለሰብ የሠርገኞቹ ቤተሰብ ሲሆኑ በአጋጣሚ የደረሰ ጉዳት እንጂ ሆን ተብሎ አለመሆኑን ኃላፊዋ ተናግረዋል። ጉዳት ደረሰባቸው ግሰቦች የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል። መንግስት የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ ከአራት በላይ ሰዎች የሚሰበሰቡባቸው እንደ ሠርግ ያሉ ዝግጅቶች እንዳይካሄዱ መከለከሉን ኃላፊዋ አስታውሰው በወረዳው ሠርግ እንዳይደገስ ርብርብ እየተየተደረገ ነው ብለዋል። “ግለሰቦች ተነግሯቸው አይደገስም አሾልከን ዳርን በሚሉበት ወቅት ነው እንግዲህ ጉዳት የደረሰው። [ሠርጉ ላይ] ብዙ ሰው አልነበረም። ቦንብ የያዘውና ህይወቱ የጠፋው ግለሰብም አማች ነው። ሰርጉ እንዲቆም ትዕዛዝ ከተሰጠ በኋላ ነው ይህንን ድርጊት ሲፈጽም ጉዳት የደረሰው”ብለዋል። “ቀደም ሲል የግንዛቤ ስራ ሰርተናል እምቢተኛውን ደግሞ በህግ ፊት እያቀረብን ነው። ለዚህ ወረዳው ትኩረት ሰጥቶ እየሠራበት ነው። በርካታ ግለሰቦች አቅርበን ጠይቀን በርካታ ሠርግ አቋርጠናል። ብዙዎችንም ተጠያቂ አድርገናል። ለበሽታው ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል በሚል አዋጁን በመጣስ ሰርግ እና ተስካር ደግሰው ከ41 በላይ ክስ የተመሰረታቸው ሰዎች አሉ” ሲሉ ገልጸዋል። ከጉዳቱ ጋር ተጠርጣሪ በተያያዘ በቁጥጥር ስር ስለመዋሉ መረጃ የለኝም ያሉት ወይዘሮ ጥሩሰው “ቦንቡም የያዘው ህይወቱ አልፏል። ይህንን [ሠርጉን] የፈጸመውም ተጠያቂ የማይሆንበት ምክንያት የለም” ብለዋል። የእናርጅና እናውጋ ወረዳ ፖሊስ በበኩሉ መርማሪዎችን ወደቦታው በማሰማራት ስለጉዳይ እየመረመረ መሆኑን ነግሮናል።
news-55829615
https://www.bbc.com/amharic/news-55829615
ፓኪስታን፡ አሜሪካዊውን ጋዜጠኛ ቀልተው ገድለዋል የተባሉት ግለሰቦች በነፃ ተሰናበቱ
አሜሪካዊውን የዋል ስትሪት ጋዜጠኛ ዳንኤል ፐርልን ገድለዋል የተባሉት አራት ግለሰቦችን የፓኪስታን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከወንጀሉ ነፃ ናችሁ ብሎ አሰናብቷቸዋል።
የዋል ስትሪት ጆርናል ጋዜጠኛ ዳንኤል ፐርል ዳንኤል ፐርል የተገደለው በአውሮፓውያኑ 2002 ነው። በደቡብ እስያ የነበረው የዋል ስትሪት ጆርናል ኃላፊ የነበረው ዳንኤል በፓኪስታን ፅንፈኛ ቡድኖች ላይ አንድ ሪፖርት እያዘጋጀ በነበረበት ወቅት ነው ታግቶ፣ ከዚያንም አንገቱ ተቀልቶ የተገደለው። ግድያውን በዋነኝነት በማቀናበር ተከሶ የነበረው ትውልደ እንግሊዛዊ ታጣቂ ሲሆን በዚህ ጠለፋና ግድያ ሌሎች ሶስት ተባባሪዎች እንዲሁ ተከሰው ነበር። ነገር ግን የፓኪስታን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግለሰቦቹን በነፃ አሰናብቷቸዋል። የጋዜጠኛው ቤተሰቦች ጠበቃ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ በከፍተኛ ሁኔታ እንዳስደነገጣቸውና "ለፍትህ አሳዛኝ ቀን" ሲሉ ጠርተውታል። ነገር ግን የአሜሪካ ባለስልጣናት እጃችን አጣጥፈው እንደማይቀመጡ ያስታወቁ ሲሆን የግድያው አቀነባባሪ ነው የተባለው ኦማር ሼክን በአሜሪካ ክስ እንደሚከፍቱበት አስጠንቅቀዋል። ዳንኤል ፐርል እንዴት ተገደለ? በአውሮፓውያኑ 2001 መስከረም ላይ በአሜሪካ በደረሰው ሽብር ጥቃት ማግስት የዋል ስትሪቱ ጆርናል ጋዜጠኛ ዳንኤል ፐርል ፅንፈኛ ታጣቂ ቡድኖችን በተመለከተ አንድ ሪፖርት ለማጠናቀር ወደ ፓኪስታን አቀና። ነገር ግን ያልተጠበቀው ሆኖ ራሱ ሰለባ ሆነ። በመጀመሪያ በሰንሰለት ታስሮና ሽጉጥ ተደግኖበት ፎቶዎች ወጥቶ የነበረ ሲሆን በኋላም ተቀልቶ ተገደለ። አሰቃቂ ግድያው በቪዲዮ የተቀረፀ ሲሆን አልቃይዳና አይኤስ በሚያደርጓቸው የፕሮፓጋንዳ ቪዲዮዎች ተመሳሳይ ቪዲዮ እንዲጠቀሙ ምክንያት የሆነው ይኸው የዳንኤል ፎቶ ነው። በግድያው ተከሶ የነበረው ኦማር ሼክ የተወለደው በእንግሊዝ ሲሆን በለንደን በሚገኘው የስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ ትምህርቱን ተከታትሏል። በጎሮጎሳውያኑ 1995 ምዕራባውያን ቱሪስቶችን በማገት በህንድ ለእስር ተዳርጎ ነበር። እሱም ሆነ ሁለት ታጣቂዎች ከአምስት አመት በኋላ በነፃ ተለቀዋል።በነፃ የተለቀቁበት ምክንያት ታጣቂዎች ታሊባን በሚቆጣጠሩት አፍጋኒስታን አውሮፕላን ጠልፈው መንገደኞቹን ነፃ ለማውጣት እነ ኦማር እንዲፈቱና በልውውጥ እንዲሆን መጠየቃቸውን ተከትሎ ነው። ኦማርና ዳንኤል የተገናኙት በፓኪስታኗ ከተማ ራዋንፒንዲ በጎሮጎሳውያኑ 2002 ነው። ኦማር ሃሰተኛ ስም ሰጥቷታል የተባለ ሲሆን ዳንኤል ለሪፖርቱ ማናገር የሚፈልገው ፅንፈኛ የሚባል ታጣቂ ተከታይ እንደሆነ ኦማር ነገረው። ኦማር ከሰውየው ጋር አገናኝሃለሁ እንዳለውና ነገር ግን ጋዜጠኛውን ወጥመድ ውስጥ እንዳስገባው ተነግሯል። ዳንኤል ካራቺ ወደምትባለው የወደብ ከተማ ባቀናበት ወቅት ታገተ። የአጋቾቹ ጥያቄ የነበረው በአሜሪካ ኃይሎች በጓንታናሞ ቤይ እስር ላይ ላሉ የተሻለ አያያዝ እንዲኖር፣ በጓንታናሞ የታሰሩ ፓኪስታናውያን እንዲለቀቁ የሚል ነበር። ከዚህ በተጨማሪ አሜሪካ ለፓኪስታን ቃል ገብታው የነበረውን ተዋጊ ጄቶች አንድትሰጣት ወይም ገንዘቧን እንድትመልስ የሚለውም ሌላኛው ጥያቄያቸው ነበር። በመጨረሻ ዳንኤል ፐርል የሞሳድ ሰላይ ነህ በሚል ተገድሏል። ግድያውን አቀነባብረሃል ተብሎ የተከሰበሰው ኦማር ሼክ ለምን በነፃ ተሰናበቱ? ምርመራ ከተካሄደ በኋላ ነበር ኦማርና ሶስት ተባባሪ የተባሉት የታሰሩት፤ ክስም ተመሰረተባቸው። ኦማር ሼክ እገታውን ስለማቀናበሩና በራዋልፒንዲ በሚገኝ ሆቴል ጋዜጠኛውን ማግኘቱን ሁለት የአይን እማኞች መስክረዋል። ነገር አቃቤ ህግ ያቀረበው ክስ ከፍተኛ ችግር የተስተዋለበት ነው ተብሏል። ምንም እንኳን ብዙዎች ኦማር ለፓኪስታን የደህንነት ሰራተኞች ራሱን አሳልፎ ነው የሰጠው ቢሉም ፖሊስና አቃቤ ህግ በበኩላቸው በካራቺ አየር ማረፊያ ከሳምንት በኋላ በቁጥጥር ስር ነው የዋለው ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ ኦማር ሼክ ራሱ ግድያውን እንዳልፈፀመ መረጃዎች መውጣት ጀመሩ። በአሁኑ ወቅት የሚታሰበው የአልቃይዳ ከፍተኛ ኃላፊና በአሁኑ ወቅት በጓንታናሞ ቤይ ያለ ካሊድ ሼክ መሃመድ የተባለ ግለሰብ ለግድያው ጥፋተኛ እንደሆነ ነው። ነገር ግን የፓኪስታን ባለስልጣናት ሆን ብለው የምስክሮችን እማኝነት ውድቅ አድርገውታል ተብሏል። ስማችን አይጠቀስ ያሉ በምርመራው ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ የነበራቸው ሁለት ግለሰቦች ለቢቢሲ እንደተናገሩት ክሱ የተያዘበት መንገድ አሳዛኝ ነው ብለዋል። በግድያው ወቅት የተፈጠሩ ሁኔታዎችን አለማጤን እንዲሁም ግድያው ተፈፀመ በተባለበት ወቅት ኦማር በቦታው አለመገኘቱ ክሱን ውሃ እንዳይቋጥር አድርጎታል ይላሉ። ነገር ግን መርማሪዎቹ ኦማር ግድያውን አቀናብሯል ብለው ያምናሉ። በባለፈው አመት በሲንድ የሚገኝ የፓኪስታን ፍርድ ቤት ኦማርና ሶስቱ ተባባሪ የተባሉትን ግለሰቦች በነፃ አሰናብቶ ነበር። የፍርድ ቤቱ ውሳኔ በተለያዩ ሚዲያዎች ከፍተኛ ውግዘት በማስከተሉ የዳንኤል ቤተሰቦችና አቃቤ ህግ ውሳኔው እንዲቀለበስ ይግባኝ እስኪጠይቁ ግለሰቦቹ በእስር ላይ እንዲቆዩ ተደርገው ነበር። ነገር ግን የፓኪስታን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኙን ውድቅ አድርጎ ውሳኔው እንዲፀና አድርጓል።
48279045
https://www.bbc.com/amharic/48279045
ናይጄሪያ፡ በረመዳን ምግብ የበሉ 80 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
በናይጄሪያዋ ካኖ ግዛት በረመዳን ጾም ወቅት በአደባባይ ምግብ የበሉ 80 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የግዛቲቱ እስላማዊ ሸሪያ ፖሊስ አስታውቀ።
ሂስባህ የሚል ስያሜ ያላቸው እነዚህ የሸሪያ ፖሊሶች በግዛቲቱ በተለያዩ አካባቢዎች ባለፉት ቀናት ቁጥጥር ሲያደርጉ ነው ግለሰቦቹን የያዙት። በፈረንጆቹ 2000 የሸሪያ ህግ እንደገና ተግባራዊ ከተደረገባቸው በርካታ የናይጄሪያ ግዛቶች መካከል አንዷ በሆነችው ካኖ ግዛት የሚኖሩ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ጸሃይ ወጥታ እስትክጠልቅ ድረስ ምግብ በአፋቸው እንዳይዞር ህጉ ያዛል። • በፆም ወቅት ሰውነታችን ውስጥ ምን ይካሄዳል? • የቢላል አዛን የናፈቃቸው ሀበሾች የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ያልሆኑ ሰዎች በቤታቸው እንደፈለጉት መመገብ የሚችሉ ሲሆን የእስልምና ተከታዮች ግን በጾም ወቅት በአደባባይ መመገብ አይችሉም። በግዛቲቱ የሸሪያ ህጉም ከመንግሥታዊ ህጉ ጋር ጎን ለጎን በመሆን ይሰራል። በካኖ ግዛት የሂስባህ ቃል አቀባይ የሆኑት አዳሙ ያህያ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በአደባባይ በመመገባቸው በቁጥጥር ስር የዋሉት ሁሉም ሙስሊሞች ሲሆኑ የሸሪያ ህጉ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ያልሆኑት ላይ ተግባራዊ አይሆንም። በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል አንዳንዶቹ ምግብ የበሉት የረመዳን ጨረቃን እራሳቸው ባለማየታቸው እንደሆነ ሲገልጹ፤ ሌሎቹ ደግሞ የጤና እክልን እንደ ምክንያትነት ቢያቀርቡም ባለስልጣናቱ ግን ተቀባይነት የሌለውና ምክንያት ነው ብለዋል። • ቴምር በረመዳን ለምን ይዘወተራል? በቁጥጥር ስር የዋሉት ሰማንያዎቹ ግለሰቦች ተግባሩን ሲፈጽሙ የመጀመሪያቸው በመሆኑ በከባድ ማስጠንቀቂያ መለቀቃቸውን ቃል አቀባዩ አክለዋል። ከዚህ በኋላ በረመዳን ወቅት ከማፍጠሪያ ሰዓት ውጪ ምግብ ሲበሉ ቢገኙም ወደ ፍርቤት ተወስደው ለመዳኘት ቃል ገብተዋል። የሂስባህ አባላቱም በረመዳን የጾም ቀናት ከተማዋን በማሰስ ተመሳሳይ ተግባር የሚፈጽሙ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን እንደሚቀጥሉበትም ተገልጿል።
news-54367341
https://www.bbc.com/amharic/news-54367341
አርሜንያ -አዘርባጃን ግጭት፡ ሩሲያ በናጎርኖ ካራባህ ጉዳይ የሰላም ውይይት ልታዘጋጅ ነው
ሩሲያ በናጎርኖ-ካራባህ ግዛት ይገባኛል ወደ ግጭት ያመሩት የቀድሞ የሶቪየት ሪፐብሊክ አካል በነበሩት አርሜንያና አዘርባጃን መካከል ያለውን ግጭት ለማስቆም የሰላም ውይይት ልታዘጋጅ መሆኑን አስታወቀች።
የአገሪቷ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰረጌ ላቭሮቭ ለሁለቱ አገራት መንግሥታት ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፤ መሥሪያ ቤታቸው እንደገለፀው ሚኒስትሩ፤ አገራቱ 'ለጦርነት መቋመጣቸውን' እንዲያቆሙ አሳስበዋል።. ረቡዕ ዕለት የሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ መሥሪያ ቤት እንደገለፀው፤ ሩሲያ የሰላም ውይይቱን ለማዘጋጀት ፈቃደኛ መሆኗን ለመግለፅ የሁለቱን አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጠርተው ነበር። የሩሲያው ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲንም ግጭቱን አስመልክተው ከፈረንሳዩ ፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በስልክ ተወያይተዋል። ሁለቱ መሪዎች የተኩስ አቁም ጥሪ አቅርበዋል። ሩሲያ ከአርሜንያ ጋር የጦር ሕብረት ያላት ሲሆን በአገሪቷም የጦር ሰፈር አላት። ይሁን እንጅ ከአዘርባጃን መንግሥት ጋርም የቅርብ ግንኙነት እንዳላት ይነገራል። አርሜንያ ራስገዝ የሆነችውን ናጎርኖ- ካራባክህን የምትደግፍ ቢሆንም ይፋዊ እውቅና ግን አላገኘችም። በሁለቱ አገራት መካከል እሁድ እለት በተቀሰቀሰው ግጭት ከ100 በላይ ሰዎች የሞቱ ሲሆን፤ በዓመታት ውስጥ በግዛቷ ሳቢያ የተቀሰቀሰው ከባድ ግጭት ነውም ተብሏል። የአዘርባጃን አካል እንደሆነች የምትታወቀው ናጎርኖ-ካራባህ የምትተዳደረው ግን በአርሜንያ ነው። አርሜንያና አዘርባጃን በግዛቷ ሳቢያ ከጎርጎሮሳዊያኑ 1988-1994 ድረስ ተዋግተዋል። አሁንም ዓለም አቀፍ ኃይሎች በግጭቱ ጣልቃ ይገባሉ የሚል ስጋት እየጨመረ መጥቷል። ሰሞኑን የተቀሰቀሰው ግጭት መነሻው ግልፅ አይደለም። ረቡዕ ዕለት የአዘርባጃኑ ፕሬዚደንት ኢልሃም አሊየቭ የአርሜንያ ወታደሮች ግዛቷን ለቀው እስኪወጡ ድረስ እንደሚዋጉ ዝተዋል። " አንድ ቅድመ ሁኔታ ብቻ ነው ያለን፤ ይህም የአርሜንያ ወታደሮች ያለምንም ማቅማማት፣ ሙሉ ለሙሉ እና በአፋጣኝ መሬታችንን ለቀው መውጣት አለባቸው" ሲሉ ነበር ፕሬዚደንቱ የተናገሩት። አዘርባጃን በበኩሏ ሁለት የጠላት የጦር ታንኮች መውደማቸውን የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ያጋራች ሲሆን፤ የአርሜንያ ብርጌድ በቶናሸን መንደር ያለውን አካባቢ ጥለው መውጣታቸውን ገልፃለች። ረቡዕ ዕለት አዘርባጃን በማርታከርት ከተማ ላይ በፈፀመችው የአየር ድብደባ ሦስት ሰላማዊ ዜጎች መገደላቸውን የአርመኒያ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። የመንግሥት የዜና ወኪሉ 'አርመንፕረስ' ደግሞ ግጭቱ ከተቀሰቀሰ ጀምሮ ሰባት ሰላማዊ ሰዎች እና 80 ወታደሮች ተገድለዋል ብሏል። በሌላ በኩል የአርሜንያ መከላከያ ሚኒስቴር በቱርክ ኤፍ-16 ተመትቶ እንደተጣለ የተነገረው የአርመኒያ ኤስዩ-25 የጦር ጀትን ምስል አውጥቷል። የአዘርባጃን ታማኝ ወዳጅ የሆነችው ቱርክ ግን የቀረበባትን ክስ 'ርካሽ ፕሮፖጋንዳ' ስትል ውድቅ አድርገዋለች። ይሁን እንጅ አንድ ተዋጊ ባለፈው ሳምንት ከሰሜን ሶሪያ እንደተመለመለ እና ለውጊያው በቱርክ በኩል እንደተላከ ለቢቢሲ አረብኛ ተናግሯል። የቱርክ ፕሬዚደንት ሬሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን አማካሪ ኢልኑር ሴቪክ ግን ዘገባውን 'ሙሉ ለሙሉ መሰረተ ቢስ' ብለውታል። ግጭቱ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት -ኔቶ አባል አገራት በሆኑት ፈረንሳይና ቱርክ መካከል ውጥረትን ፈጥሯል። ፈረንሳይ ለበርካታ አርሜንያዊያን መኖሪያ ስትሆን ቱርክ ደግሞ በአዘርባጃን የሚገኙ ቱርካዊያንን ትደግፋለች። ረቡዕ ዕለት የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰተር ሜቭሉት ካቩሶግሉ ፈረንሳይ "አርሜንያዊያንን ትደግፋለች" ሲሉ ከሰዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዚዳነት ኢማኑኤል ማክሮንም ለዚህ የአፀፋ ምላሽ የሰጡ ሲሆን ከቱርክ የሚመጡ 'ጦርነት ቀስቃሽ' መልዕክቶችን ተችተዋል። ፕሬዚደንት ፑቲንና ማክሮን በስልክ ውይይት ካደረጉ በኋላ ቀጣይ እርምጃዎች ላይ መነጋገራቸውንና የአውሮፓ የፀጥታና ትብብር ድርጅት-ሚንስክ ግሩፕ ግጭቱን ለመፍታት እንደሚሞክር የፑቲን መሥሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ሚንስክ ግሩፕ በጎርጎሮሳዊያኑ 1992 የተመሰረተ ሲሆን የሚመራው በፈረንሳይ፣ ሩሲያ እና አሜሪካ ነው።
news-56884283
https://www.bbc.com/amharic/news-56884283
የወር አበባ ፈቃድ የከለከሉት የአየር መንገድ ኃላፊ ተፈረደባቸው
የቀድሞ የደቡብ ኮሪያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሴት የአየር መንገዱ ሠራተኞች በሕግ የተፈቀዳላቸውን የወር አበባ ፈቃድ በመከልከላቸው ተቀጡ።
የእስያን አየር መንገድ የቀድሞው ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት ኪም ሶ ቼዎን ከ15 የበረራ አስተናጋጀች የቀረበላቸውን 138 የእረፍት ጥያቄዎችን እኤአ ከ2014 እስከ 2015 ባለው ግዜ ውስጥ ከልክለዋል። ባለሥልጣኑ ተቋሙ ሴት ሠራተኞች በወር አበባ ጊዜያቸው ሊያገኙ የሚገባውን ፈቃድ በመከልከላቸው ጉዳዩ ፍርድ ቤት ቀርቦ 1800 ዶላር እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል። ኪም በበኩላቸው ፈቃድ ያልሰጡት የበረራ አስተናጋጆቹ በወር አበባ ላይ እንደነበሩ ማስረጃ አላቀረቡም ሲሉ የመከራከሪያ ሃሳብ አቅርበዋል። በደቡብ ኮሪያ ሴቶች በወር አበባ ወቅት ከፍተኛ ህመም ከተሰማቸው በወር አንድ ቀን እረፍት የመውሰድ መብት ከ1953 ጀምሮ ተረጋግጦላቸዋል። ነገር ግን በርካታ አጠራጣሪ የእረፍት ጥያቄ ማመልከቻዎች እንደነበሩ ጠቅሰው ሲከራከሩ የነበሩት ኪም፤ ሠራተኞች የወር አበባ እረፍትን ከዓመት በዓሎች እና ከሌሎች ረፍቶቻቸው ጋር አቀራርበው ይጠይቁ ነበር ሲሉም ተናግረዋል። በጉዳዩ ላይ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ብይን በይግባኝ የተመለከተው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሴቶች በወር አበባ ላይ እንደሚገኙ ማስረጃ መጠየቅ አይገባም ብሏል። ማስረጃ መጠየቅ የሰብአዊ መብቶቻቸውን ብሎም የግል ምስጢራቸውን የመጠበቅ መብታቸውን ይጋፋል ሲል የስር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አጽንቷል።
news-55476037
https://www.bbc.com/amharic/news-55476037
ኮሮናቫይረስ፡ በሩሲያ በኮቪድ-19 የሞቱ ሰዎች መንግሥት ከገለፀው ሦስት እጥፍ ይበልጣል ተባለ
የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ታቲያና ጎሊኮቫ በዚህ የፈረንጆች ዓመት በአገሪቱ ከተከሰቱት ሞቶች 80 በመቶ ያህሉ በኮቪድ-19 ምክንያት የመጡ መሆናቸውን ተናገሩ።
ይህም ማለት ከዚህ ቀደም መንግሥት በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሞተውብኛል በማለት ሪፖረት ካደረገው ቁጥር ሦስት እጥፍ ይሆናል ማለት ነው። ሩሲያ 55,827 ዜጎቿ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሞተዋል በማለት ሪፖርት ያደረገች ሲሆን፤ የአሁኑ የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ መረጃ ይህንን ቁጥር ወደ 186,000 ከፍ ያደርገዋል ተብሏል። ጎሊኮቫ በ2020 የመጀመሪያዎቹ 11 ወራት በአገሪቱ ያጋጠመው የሟቾች ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ13.8 በመቶ ይበልጣል ብለዋል። የሩሲያ ስታትስቲክስ ባለሥልጣን በበኩሉ በዚህ ዓመት ተጨማሪ 229,700 ዜጎች መሞታቸውን አስታውቋል። ስለዚህ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ መሰረት 186,057 ሞቶች በቀጥታ ከኮሮናቫይረስ ጋር የተያያዙ ናቸው ማለት ነው። ይህ ቁጥር የሩሲያ የስታትስቲክስ ባለሥልጣን ይፋ አድርጎት ከነበረው ቁጥር የበለጠ ነው ተብሏል። በዓለም ላይ እስካሁን ድረስ በከፍተኛ ሁኔታ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ዜጎቻቸውን በሞት መነጠቃቸውን ሪፖርት ያደረጉት አሜሪካ እና ብራዚል ናቸው። ሩሲያ በኮሮናቫይረስ የሞቱ ሰዎችን ቁጥርን የምታሰላው የአስከሬን ምርመራ ተደርጎ የሞታቸው መንስዔ በትክክል ኮሮናቫይረስ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ ነው። ይሁን እንጂ ከኮቪድ-19 ጋር የተያያዙ ሌሎች ሞቶች በኮሮናቫይረስ ባስከተለው ተያያዥ ምክንያት የሞቱ በሚል አይካተትም ነበር። ነገር ግን በኅዳር ወር ብቻ ከኮሮናቫይረስ ጋር የተያያዙ ሞቶች በሩሲያ ከፍተኛ መሆናቸውን የአገሪቱ ስታትስቲክስ ባለሥልጣን መረጃ ያሳያል። በሩሲያ ዋና ከተማ ሞስኮ ባለፈው ወር የተከሰቱ ሞቶች ከአስሩ አንዱ ከኮሮናቫይረስ ጋር የተያያዘ ነበር ተብሏል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጎሊኮቫ መንግሥታቸው በኮሮናቫይረስ ምክንያት የተከሰቱ ሞቶችን ቁጥር አልደበቀም ሲሉ ፍርጥም ብለው ተከራክረዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኅዳር እና ታህሣስ ወራት አገሪቱ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተጠቃችባቸው ጊዜያት ሁሉ የከፉት ነበሩ ብለዋል። ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የአገራቸውን የጤና ሥርዓት ያንቆለጳጰሱ ቢሆንም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ሆስፒታሎች ግን በኮቪድ-19 ምክንያት ታመው እርዳታ በሚሹ ሰዎች ተጨናንቀዋል ተብሏል። ሩሲያ ምንም እንኳ በአውሮፓ ኅብረት የመድኃኒቶች ኤጀንሲ ባይረጋገጥም ስፑትኒክ 5 በማለት የሰየመችውን የኮሮናቫይረስ ክትባት አምርታ ለዜጎቿ መከተብ እንዲሁም ወደ ቤላሩስ፣ አርጀንቲናና ሃንጋሪ መላክ ጀምራለች። በቤላሩስ ማክሰኞ እለት ክትባቱ መሰጠት የተጀመረ ሲሆን በሩሲያ ደግሞ በአጠቃላይ 700,000 ክትባቶች ተሰራጭተዋል ተብሏል።
news-54216634
https://www.bbc.com/amharic/news-54216634
3.2 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡት የተሰረቁ ጥንታዊ መጻሕፍት ተገኙ
ለንደን ውስጥ ከሚገኝ መጋዘን የተሰረቁ፣ 3.2 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ወደ 200 የሚጠጉ መጻሕፍት ሮሜንያ ውስጥ እንደተገኙ ፖሊስ ገለጸ። ከመጻሕፍቱ መካከል በጋሌሊዮና አይዛክ ኒውተን የተጻፉ ይገኙበታል።
መጻሕፍቱ ከሦስት ዓመታት በፊት ነበር የተሰረቁት። ከዚያም በሮሜንያ ገጠር ውስጥ በሚገኝ አንድ መጋዘን ውስጥ ተደብቀው ተገኝተዋል። ዘራፊዎቹ የሮሜንያ የወንጀል ቡድን አባላት መሆናቸው ተገልጿል። 13ቱ ላይም ክስ መመስረቱ ተነግሯል። ኔሜት በምትባል የሮሜንያ ግዛት ውስጥ በተደረገ አሰሳ መጻሕፍቱ ከመጋዘን በታች ተቀብረው ነው የተገኙት። መርማሪዎች እንዳሉት፤ መጻሕፍቱን ለማግኘት ከባለፈው ዓመት ጀምሮ በዩናይትድ ኪንግደም፣ በሮሜንያ እና በጣልያን 45 ቤቶች ላይ አሰሳ አካሂደዋል። ከተሰረቁት መጻሕፍት ውስጥ ለማግኘት አስቸጋሪ የሆኑት የዳንቴ፣ ፍራቸስኮ ደ ጎያ እና ሌሎችም የ16ኛው እና የ17ኛው ክፍለ ዘመን ሥራዎች ይጠቀሳሉ። መርማሪ አንዲ ዱርሀም “በጣም ውድ መጻሕፍት ናቸው። ሊተኩ አይችሉም” ብለዋል። መጻሕፍቱ ላስ ቬጋስ የሚካሄድ ጨረታ ላይ ከመቅረባቸው በፊት ሂትሮው አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ ያለ መጋዘን ውስጥ እንዲቆዩ ተደርገው ነበር። ዘራፊዎቹ 12 ሜትር ጉድጓድ ቆፍረው ነበር የቀበሯቸው። አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው፤ መጻሕፍቱ ተቀብረው ስለነበር የት እንዳሉ ለማወቅ የሚረዳን የመለያ መሣሪያ (ሴንሰር) ማለፍ ችለዋል። የሮሜንያ የወንጀል ቡድኖች ከዚህ ቀደምም ከዩናይትድ ኪንግደም የዘረፏቸውን ቁሳቁሶች ሳይታወቅባቸው ከአገር ማስወጣት ችለዋል። የተለያዩ የሟጓጓዣ አማራጮችንም እንደሚተቀሙ ተነግሯል።
news-46744322
https://www.bbc.com/amharic/news-46744322
ሶማሊያ የተባበሩት መንግሥታት መልዕክተኛ ኒኮላስ ሃይሶምን አባረርች
ሶማሊያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መልዕክተኛ የሆኑትን ኒኮላስ ሃይሶም እራሳቸውን እንደ ሶማሊያ መሪ በመቁጠር ዓለም አቀፉን ድርጅት ''አዋርደዋል'' በማለት ከሃገሯ አባረረች።
ኒኮላስ ሃይሶም የቀድሞ የአልሸባብ መሪ ለነበሩት ሙክታር ሮቦው አጋርነታቸውን ያሳዩ ሰልፈኞች ግድያ አሳስቦኛል ብለው ነበር። የሶማሊያን ደቡብ ምዕራብ ግዛት ለማስተዳደር ተወዳድሮ የነበረው የቀድሞ የአልሸባብ መስራች እና አባል ሙክታር ሮቦው በሶማሊያዋ ባይዶዋ ከተማ የአሚሶም የሰላም አስከባሪ ኃይል አባል በሆኑ የኢትዮጵያ ወታደሮች በቁጥጥር ሥር ውሎ ከምርጫ ሳይሳተፍ መቅረቱ ይታወሳል። • የቀድሞ የአልሸባብ መሪ በኢትዮጵያ ሠራዊት በሶማሊያ በቁጥጥር ሥር ዋለ • አልሸባብ አይኤስ ላይ ጦርነት አወጀ • አልሸባብ በኬንያ ጥቃት አደረሰ የሚሉና ሌሎች አጫጭር ዜናዎች የሙክታር ሮቦው እስር እና በምርጫ እንዳይሳተፍ መደረጉን ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ፤ 15 ሰዎች መገደላቸውን እና ወደ 300 የሚጠጉ ደግሞ ለእስር መዳረጋቸውን የተባበሩት መንግሥታት አስታውቋል። የተባበሩት መንግሥታት አልሸባብን እየተዋጉ ለሚገኙት የሶማሊያ መንግሥት ጦር ስልጠናዎችን፣ የደንብ ልብስ እንዲሁም ክፍያ ይሰጣል። ትናንት ከአል-ቃይዳ ጋር ጥምረት ያለው አልሸባብ በሞቃዲሹ ወደ ሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ቅጥር ግዚ ውስጥ ሞርታር ተኩሻለሁ ብሎ ነበር። በጥቃቱ ሶስት ሰዎች መጎዳታቸውን የተባበሩት መንግሥታት አስታውቋል። የአልሸባብ ምክትል መሪ የነበሩት ሙክታር ሮቦው ቡድኑን እ.አ.አ. 2017 ላይ ነበር ክደው የተለዩት። ሙክታር ሮቦው 'ሉዓላዊነት ተጥሷል' ሙክታር ሮቦው ከአልሸባብ እራሱን ካገለለ ከአንድ ዓመት በኋላ የሶማሊያን ደቡብ ምዕራብ ግዛት ለማስተዳደር ከሳምንታት በፊት በተካሄደ ምርጫ ለመሳተፍ ፍላጎቱን አሳይቶ ነበር። ሆኖም ምርጫው ከመከናወኑ ጥቂት ሳምንታት በፊት ሙክታር ሮቦው በሶማሊያ መንግሥት በቁጥጥር ሥር ውሎ በምርጫው እንዳይሳተፍ ተደርጓል። የሶማሊያ መንግሥት ሙክታር ሮቦው ''ከጽንፈኛ አስተሳሰቡ አልተላቀቀም'' ብሎታል። • አሜሪካ 62 የአልሸባብ ታጣቂዎችን ገደልኩ አለች • በጎሳ ታጣቂዎች እና በአልሸባብ ወታደሮች መካከል ግጭት ተቀሰቀሰ በሶማሊያ የተባበሩት መንግሥታት መልዕክተኛ ኒኮላስ ሃይሶም ከአራት ቀናት በፊት ሙክታር ሮቦው ለምን እንደተሳረ፤ እንዲሁም በደጋፊዎቹ ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ እንዲመረመር የሚጠይቅ ደብዳቤ ለሶማሊያ መንግሥት ጽፈው ነበር። የሶማሊያ መንግሥት ለተመድ መልዕክተኛው ምላሽ ስለመስጠቱ ባይታወቅም፤ የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ አህመድ ኢሴ አዋድ የተመድ መልዕክተኛው እኛ ሃገር ተቀባይነት የላቸውም ብለዋል። ''ኒኮላስ ሃይሶም ዲፕሎማሲያዊ አሰራሮችን ጥሰዋል፣ እራሳቸውንም የሶማሊያ መሪ አድርገው ቆጥረዋል። ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምግባር ውርደት ናቸው። የሶማሊያን ሉዓላዊነት እና ነጻነት ተጋፍተዋል'' በማለት የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ ለቢቢሲ ሶማልኛ ተናግረዋል። ኒኮላስ ሃይሶም ደቡብ አፍሪካዊ ሲሆኑ፤ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኔልሰን ማንዴላ የሕግ አማካሪ ነበሩ። ከዚያም አፍጋኒስታን፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግሥታት መልዕክተኛ በመሆነ አገልግለዋል።
55285172
https://www.bbc.com/amharic/55285172
ኦስትሪያ ትምህርት ቤት ውስጥ ሂጃብ ማድረግ የሚከለክለውን ሕግ ሰረዘች
የኦስትሪያ ፍርድ ቤት በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሂጃብን ጨምሮ የተለያዩ ሐይማኖት መገለጫዎችን ማድረግ የሚከለክለውን ሕግ ሰረዘ።
ሕጉ የሐይማኖት ነፃነትን የሚጋፋ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ አስታውቋል። ሕጉ የተላለፈው ወግ አጥባቂው 'ፒፕልስ ፓርቲ' ከግራ ዘመሙ 'ፍሪደም ፓርቲ' ጋር ጥምር መንግሥት መስርቶ በነበረበት ወቅት ነው። ፍርድ ቤቱ ሕጉ ሴት ሙስሊሞችን አግላይ እንደሆነ ተናግሯል። መንግሥት ሕጉን ሲያወጣ ሙስሊም ተማሪዎች በክፍል ጓደኞቻቸው ጫና እንዳይድርባቸው ለመጠበቅ ነው ቢልም፤ ፍርድ ቤቱ ግን "ሕጉ ወንጀለኛ አድርጎ ያስቀመጠው ትክክለኛውን ሰው አይደለም" ብሏል። ፍርድ ቤቱ አክሎም፤ መንግሥት ሙስሊም ተማሪዎችን መከላከል ከፈለገ ሐይማኖት እና ፆታን መሠረት አድርገው መድልዎ የሚያደርሱ ሰዎችን የሚቀጣ ሕግ ነው ማውጣት ያለበት ብሏል። ሕጉ ተግባራዊ የተደረገው አምና ነበር። ሂጃብ ማድረግ ክልክል ነው ብሎ በግልጽ ባያስቀምጥም፤ "እስከ 10 ዓመታቸው የሆኑ ልጆች ራስ ላይ የሚጠመጠሙ ሐይማኖታዊ ልብሶችን ማድረግ አይችሉም" ይላል። የሲክ እና የአይሁድ እምነት ተከታይ ልጆችን ሕጉ እንደማያካትት መንግሥት ተናግሯል። ስለዚህም ሕጉ ሂጃብ ላይ ያነጣጠ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ተናግሯል። የፍርድ ቤቱ ፕሬዘዳንት ክሪስቶፍ ግራቤንዋርተር "ሕጉ ክልከላ የጣለው ሙስሊም ተማሪዎች ላይ ነው። ይህ ሕግ ከሌሎች ተማሪዎች ነጥሎ ያገላቸዋል" ብለዋል። የትምህርት ሚንስትር ሄንዝ ፋስማን "ሴቶች ያለ ጫና በትምህርት ሥርዓቱ ማለፍ አለመቻላቸው ያሳዝናል" ብለዋል። የኦስትሪያ የሙስሊም ማኅበረሰብ ተቋም ሕጉ መሻሩን በደስታ ተቀብሎታል። "ሴቶችን እኩል እድል ማግኘታቸውን ማረጋገጥ እና በራሳቸው የሚወስኑትን መቀበል የሚቻለው ክልከላ በመጣል አይደለም" ሲል መግለጫ አውጥቷል። ሕጉ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲረቅ፤ መራሔ መንግሥት ሰባስሽን ከርዝ "ሕጉ የኦስትሪያ ማኅበረሰብ ውስጥ ተነጥሎ የሚወጣ ማኅበርን ያስወግዳል" ብለው ነበር። የፍሪደም ፓርቲ ምክትል መራሔ መንግሥት ሄንዝ ክርስትን ስትራቼ፤ መንግሥት ታዳጊ ሴቶችን "ከፖለቲካዊ እስልምና" ለመጠበቅ እየሞከረ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ከዚያም ሕጉ እአአ 2019 ላይ ተግባራዊ እንዲሆን ተድርጓል። አሁን ላይ ፒፕልስ ፓርቲ ከግሪን ፓርቲ ጋር ተጣምሯል። ሂጃብ የሚከለከለውን ሕግ እስከ 14 ዓመት በደረሱ ታዳጊዎች ላይ ተግባራዊ የማድረግ እቅድ ነበረ።
news-45054701
https://www.bbc.com/amharic/news-45054701
በምዕራብ ጎጃም ታራሚ አስገድዶ የደፈረው ፓሊስ የእስራት ጊዜ ተጨመረበት
ለእስር የተዳረገችው ጓደኛዋ 'በአደራ የሰጠኋትን እቃ ሰውራለች' በማለቷ ተጠርጥራ ነው፡፡ ጉዳዩ እስከሚጣራ በአዴት ፖሊስ ጣቢያ እንድትቆይ ይደረጋል፡፡
የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር "በጊዜው ሴት እስረኛ እሷ ብቻ ነበረች" ይላሉ የአዴት ከተማ አስተዳዳር ፖሊስ ጽህፈት ቤት የወንጀል ምርመራ ባለሙያ የሆኑት ዋና ኢንስፔክተር መልካሙ ወርቁ፡፡ አንድ ምሽት ያላሰበችው ሆነ፡፡ ተረኛ ጥበቃ የነበረ ፖሊስ ይህችን በህግ ከለላ ስር የነበረች ወጣት በር ከፍቶ በግድ እንድትወጣ በማድረግ፣ በመሳሪያ በማስፈራራትና በመደብደብ በጥበቃ ማደሪያ ክፍል ውስጥ አስገድዶ ደፈራት፡፡ አቤቱታ አሰማች። ከጎን ታስረው የነበሩ ወንድ እስረኞችም ሌሊት ላይ በር ሲከፈት ሰምተናል ሲሉ ምስክርነታቸውን ሰጡ፡፡ ክስ ተመሰረተ፡፡ ጉዳዩን ግራና ቀኝ አይቻለሁ ያለው የወረዳው ፍርድ ቤት ተጠርጣሪው ላይ ሁለት ዓመት ከሶስት ወር እስር አስተላለፈ፡፡ ውሳኔውም በርካቶችን አስቆጣ፡፡ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች መነጋገሪያ አጀንዳ ሆነ። ፍርድ ተጓደለ ተባለ፡፡ አሲድን እንደ መሳሪያ የግሉ ዘርፍ ሠራተኞች ለመውለድ ምን ያህል ይጠብቁ? "ማንም መብታችንን ሊሰጠን ስለማይችል፤ ሴቶች ማንንም ሳይጠብቁ በራሳቸው መታገል አለባቸው" የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ጆሮ እንዴት ደረሰ? የፍርድ ውሳኔው በወረዳው ፍርድ ቤት የፌስቡክ ገጽ ላይ ይፋ ከተደረገ በኋላ መስማታቸውን የማህበሩ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሜሮን አራጋው ይናገራሉ፡፡ የማህበሩ የባህር ዳር ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ፍርድ ቤቱንና ክሱን ይከታተሉ የነበሩትን አቃቤ ህግ በማነጋገር ክትትሉን ጀመረ፡፡ ወ/ሮ ሜሮን "ወጣቷ የአስገድዶ መድፈር ጥቃት ተፈጽሞባት ሳለ ፍርድ ቤቱ በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የግብረ ስጋ ግንኙነትን በተመለከተ የሚያስረዳውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 213ን ጠቅሶ ውሳኔ ማሳለፉ ጥያቄ ፈጠረብን" ይላሉ። በወቅቱ የተጠርጣሪውን የመከላከያ ምስክር ሳይሰማና፣ የተጠቂዋን የህክምና ማስረጃ ሳያይ ብይን መስጠቱ ፍርዱ እንዲዛባ አድርጓል ይላሉ፡፡ ስለዚህም ማህበሩ ክትትሉን አጠናክሮ ቀጠለ፡፡ ጉዳዩ ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ተባለ። መዝገቡ ይታይበት ወደነበረው ፍርድ ቤት ተመልሶ በድጋሚ እንዲታይም ተወሰነ፡፡ በወረዳው ፍርድ ቤት ሲታይ የቆየው ይሄው የክስ መዝገብ ሰኔ 16፣ 2010 ዓ. ም. ስምንት ዓመት ከአምስት ወር እስር በተከሳሹ ላይ ወሰነ፡፡ በዚህ ሁሉ ሂደት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንትን ጨምሮ ሌሎች ዳኞች ትብብር በማድረጋቸው የእሷን ጉዳይ በተመለከተ ይህ ነው የሚሉት ተግዳሮት እንዳልገጠማቸው ገልጸዋል፡፡ ይግባኝ? የፍርድ ውሳኔው ይሻሻል እንጂ አሁንም ፋይሉ አልተዘጋም የሚሉት ዳይሬክተሯ ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ሲያሳልፍ የተከተላቸው የክስ ማቅለያና ማክበጃ ምክንያቶች፣ ያየው ማስረጃ፣ የቀረበበት ጊዜም ወሳኝነት ስላለው ይህንን የሚያጣራ ባለሙያ ወደ ስፍራው እንደላኩ ይናገራሉ፡፡ "አሁንም የህግ ክፍተት ካገኘንበት ይግባኝ ከማለት የሚያግደን ምክንያት የለም" ይላሉ ፡፡ ማህበራዊ ድረገጾች ማህበራዊ ሚዲያ ትክክለኛ መረጃን መሰረት በማድረግ በአዎንታዊና በሃላፊነት መጠቀም ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን ለመከላከል ያለውን አስተዋጽኦ ጥቃቱ የተፈጸመባትን ወጣት ጉዳይ የሰሙበትን አጋጣሚ ለአብነት በማንሳት ያስረዳሉ፡፡ መረጃ ለመለዋወጥ፣ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን ለማውጣትና ትኩረት እንዲያገኙ ለማድረግ ብሎም ማስረጃዎች ቅርብ እንዲሆኑ ለማድረግ የማህበራዊ ድረ ገጾችን አስፈላጊነትን ያነሳሉ፡፡ የማህበሩ ተግዳሮቶች ማህበሩ በስድስት የክልል ከተሞች ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች ያሉት ሲሆን 53 ማዕከላትም አሉት ፡፡ ማህበሩ በተለያየ ጊዜ በሴቶች ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶችን አደባባይ በማውጣትና ለህግ በማድረስ ፍትህ እንዲያገኙ አስችሏል፡፡ ይሁን እንጂ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የወጣው የበጎ አድራጎትና ማህበራት አዋጅ ባሰቡት መጠን ስራቸውን እንዳይሰሩ እየተፈታተናቸው እንደሆነ ያነሳሉ፡፡ "ህጉ በመሻሻል ሂደት ላይ በመሆኑ ፈተናችን ይቀየራል የሚል ተስፋ አለኝ" ብለውናል ዳይሬክተሯ፡፡ ማህበሩ በዓመት 10,000 የሚሆኑ ኬዞችን ይቀበላል፡፡ ከእነዚህ መካከል 1,000 የሚሆነው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ነው፡፡
news-51188559
https://www.bbc.com/amharic/news-51188559
ሴቶች የኮረንቲ ገመድ እንዲጨብጡ ያደረገው ጀርመናዊ ሃሰተኛ ዶክተር ተፈረደበት
ጀርመናዊው የዶክተር ለምድ የለበሰ ግለሰብ ወሲባዊ ፍላጎቱን ለሟሟላት ሲል ሴቶች የኮረንቲ ገመድ እንዲጨብጡ በማድረጉ 11 ዓመት ተፈረደበት።
ዴቪድ በመባል የሚታወቀው የ30 ዓመቱ ግለሰብ ለሴቶች ብር እየከፈለ የስቃይ ማስታገሻ አለኝ በማለት አታሏል፤ ይህንን ያደረገው ደግሞ ወሲባዊ ፍላጎቱን ለሟሟላት ነው ተብሏል። ግለሰቡ ተጠቂዎች ቤቱ ውስጥ ያለ የኮረንቲ ገመድ ሲጨብጡ ስካይፒ በተባለው የቪድዮ መደዋወያ ተመልክቷል እንዲሁም ቀርጿል። የጀርመኗ ከተማ ሚዩኒክ የሚገኝ አንድ ፍርድ ቤት ዴቪድ በ13 የግድያ ሙከራዎች ጥፋተኛ ሆኖ አግኝቼዋለሁ ብሎ ነው ፍርድ የበየነው። አቃቤ ሕግ፤ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምሩቁ ወንጀለኛ፤ ዶክተር ነኝ በማለት በይነ-መረብ ላይ ያገኛቸውን ሰዎች ለሳይንሳዊ ጥናት እንደሚፈልጋቸው አስመስሎ ኮረንቲ እንዲጨብጡ አድርጓል ይላል። ግለሰቡ ሴቶችን በበይነ-መረብ ከመለመለ በኋላ በሳይንሳዊ ጥናቱ ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኛ ከሆኑ 3325 ዶላር [106 ሺህ ብር] እየከፈለ እንደሚያታልል ተደርሶበታል። ተጠቂዎቹ ብረት ነክ ዕቃዎችን ከኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጋር እያገናኙ ሲሰቃዩ በስካይፒ ተመልክቷል። ከጠቂዎቹ መካከል አንዲት የ13 ዓመት ታዳጊ ትገኝበታለችም ብሏል አቃቤ ሕግ። ዳኛ ቶማስ ቦት፤ ዴቪድ የተሰኘው ግለሰብ ተጠቂዎቹ ብረት ከኮረንቲ እንዲያገናኙ አድርጓል፤ ይህ ማለት ደግሞ ሰዎችን በኤሌክትሪክ ማሰቃየት ነው ብለዋል ብሎ የዘገበው የጀርመኑ ዶች ቬሌ ጋዜጣ ነው። አቃቤ ሕግ ግለሰቡ ወሲባዊ ፍላጎቱን ለማርካት ነው ይህንን ወንጀል የከወነው ሲል ለፍርድ ቤቱ አቅርቦ፤ ፍርደ ቤቱም ግለሰቡ ለ11 ዓመታት ከርቸሌ ይውረድ ሲል በይኗል።
52196304
https://www.bbc.com/amharic/52196304
ምርጫ ቦርድ የተራዘመ ቀን ቆርጦ እንዳላቀረበ አሳወቀ
ከኮሮና ቫይረስ ስጋት ጋር በተያያዘ ምርጫው በተያዘበት ቀን ነሐሴ 23፣ 2012 ማካሄድ እንደማይችል ያሳወቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔውን ለተወካዮች ምክር ቤት ማሳወቅ እንጂ የተራዘመ ቀን ቆርጦ እንዳላቀረበ አስታውቋል።
ቦርዱ ተጠሪነቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደመሆኑ መጠን በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ተይዘው የነበሩ ተግባራት ማከናወን እንደማይችል ጠቅሶ ወሳኔውን ለምክር ቤቱ ማሳወቁን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስፍሯል። •"ከቤት አትውጡ የሚሉን ልጆቼን ምን እንዳበላቸው ነው?" •በአማራ ክልል ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የትምህርት ተቋማት ለመጠለያነት ተዘጋጁ በዚህም መሰረት በጊዜ ሰሌዳው ሲከናወኑ የነበሩ ተግባራት እንዲቆሙ፣ የወረርሽኙ ስጋት ሲወገድ እንደገና ተገምግሞ እንቅስቃሴ እንዲያስጀምር የሚሉ ውሳኔዎች ማስተላለፉንም ለምክር ቤቱ ሪፖርት አድርጓል። ቦርዱ በተሰጠው ሃላፊነት መሰረት ችግሩን ለተወካዮች ምክር ቤት ከማቅረብ እና በጥናት ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ከማድረግ ውጨ ከስልጣኑ ውጪ የሰራው ወይም ስልጣኑ ኖሮት ሳይወጣ የቀረው ሃላፊነት የለምም ብሏል። በህገ መንግስቱ በተቀመጠው መሰረት በስራ ላይ የሚገኘው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስልጣን ጊዜው ከሚያበቃበት አንድ ወር አስቀድሞ ቦርዱ አጠቃላይ ምርጫውን ማድረግ የማይችል መሆኑን ምክር ቤቱ ተገንዝቦ፣ ከዚህ አንጻር የሚሰጠው ውሳኔ ቢኖር ለመነሻነት ያገለግለው ዘንድ ይህ ውሳኔ እንዲሁም ቦርዱ ያደረገው የዳሰሳ ጥናት ሰነድ ለህዝብ ተወካዮች እንዲተላለፍለት ማድረጉን ጠቅሷል። ከዚህም በተጨማሪ እንዲህ አይነት ውሳኔዎች ላይ ሲደረስ ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በሁለት ዙር ውይይት መደረጉን ጠቅሶ በመግባባትም ተጠናቋል ብሏል። የፖለቲካ ፓርቲዎቹም የወረርሽኙ አሳሳቢነት በተለይም እንደ ኢትዮጵያ አይነት ላለ አገር ሊያስከትል የሚችለውን ቀውስ ጠቅሰው ከተለያዩ የመንግሥት አካላትም ጋር በመመካከር እንዲሰራ ጠይቀዋል።
news-55000105
https://www.bbc.com/amharic/news-55000105
ትግራይ ፡ ኤርትራ በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ ዝምታዋን ሰበረች
በሰሜናዊ ኢትዮጵያ የተከሰተውን ግጭት በተመለከተ ምንም አይነት አስተያየት ሳትሰጥ የቆየችው ኤርትራ በማስታወቂያ ሚኒስትሯ በኩል ዝምታዋን ሰብራለች።
በዚህም ኤርትራ በዋና ከተማዋ አሥመራ ላይ የሚሳኤል ጥቃት ከተፈጸመ ከቀናት በኋላ የኢትዮጵያ ሰሜናዊ ግዛት የሆነችውን የትግራይ ክልልን የሚያስተዳድረውን ህወሓትን በ"ክፉ ዓላማና ድርጊት" ወቅሳለች። በፌደራል መንግሥትና በትግራይ ክልል ኃይሎች መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት ወደ ሦስተኛ ሳምንቱ በተሸጋገረበት በአሁኑ ወቅት የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል ትናንት ህወሓት ላይ ወቀሳ ሰንዝረዋል። ሚኒስተሩ በትዊተር ገጻቸው ላይ ያሳፈሩት ጥቅምት 25/ 2013 ዓ.ም መንግሥት በህወሓት የሚመሩት የክልሉ ኃይሎች ላይ ወታደራዊ እርምጃ መውሰድ ከጀመረ በኋላ ስለግጭቱ ከኤርትራ በኩል የተሰማ ይፋዊ አስተያየት ነው። ሚኒስትር የማነ ጨምረውም ብዙም ግልጽ ባልሆነው ሁኔታ ባሰፈሩት መልዕክት ላይ፤ የህወሓትን "ተገማች የሆነ ገነር ግን ውጤት አልባ የመጨረሻ መፍጨርጨርን ማጉላት አስፈላጊ አይደለም" ብለዋል። የማስታወቂያ ሚኒስትሩ መልዕክታቸው ላይ ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ከኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ወደ አሥመራ ከተማ ስለተተኮሱት ሚሳኤሎችም ሆነ የኢትዮጵያ ሠራዊት እያካሄደ ስላለው ወታደራዊ ዘመቻ ምንም ሳይሉ ቀርተዋል። የማነ ገብረ መስቀል ኤርትራን በሚመለከት አገራዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በፍጥነት በትዊተር ገጻቸው ላይ ተደጋጋሚ መልዕክቶችን በማጋራት ይታወቁ የነበረ ቢሆንም፤ በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ የኤርትራ ስም በተደጋጋሚ ቢነሳም ምንም ሳይሉ ቆይተዋል። በተጨማሪም በኤርትራ ከተማ ላይ የሚሳኤል ጥቃትን ተከትሎ በእሳቸው በኩል ማብራሪያ ይሰጣል ተብሎ በበርካቶች ዘንድ ቢጠበቅም አስከ ትናንት ድረስ ምንም ሳይሉ ቆይተዋል። ግጭቱ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ የትግራይ ባለስልጣናት በተደጋጋሚ ኤርትራ የኢትዮጵያ ሠራዊትን እየደገፈች ነው በማለት ሲከስሱ ቆይተዋል። የደርግን መንግሥት ለመጣል በተደረገው የትጥቅ ትግል ወቅት አጋር የነበሩት አሁን ኤርትራን የሚያስተዳድረው ህዝባዊ ግንባር ለዴሞክራሲና ለፍትህ (ህግዴፍ) እና ህወሓት ዓመታትን በዘለቀ መቃቃር ውስጥ ቆይተዋል። ከሃያ ዓመታት በፊት በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ተካሂዶ ከነበረው ደም አፋሳሽ የድንበር ጦርነት በኋላ በኢትዮጵያ መንግሥት ውስጥ ቁልፍ ሚና የነበረው ህወሓት እና በኤርትራ መንግሥት መካከል የነበረው ቁርሾ አስካሁን ድረስ ዘልቋል። ትናንት [ረቡዕ] የኤርትራ ባለስልጣናት ወደ ግብጽ ተጉዘው ከግብጽ ከፍተኛ ባለስልጣንት ጋር በነበራቸው ውይይት በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ሁኔታ መነጋገራቸው ተገልጿል። ጥቅምት 24 2013 ዓ.ም የትግራይ ልዩ ኃይል በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መሰነዘሩን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የመከላከያ ኃይል በክልሉ መንግሥት ላይ እርምጃ እንዲወስድ ማዘዛቸው ይታወሳል። ሁለት ሳምንታት ያስቆጠረው የፌደራል መንግሥቱና በትግራይ ልዩ ኃይሎች መካከል እየተደረገ ያለው ግጭት ከተቀሰቀሰ ጀምሮ በክልሉ ውስጥ ያለው የግንኙነት መስመር በመቋረጡ ዝርዝር መረጃዎችን ለማግኘት አዳጋች ሆኗል። ነገር ግን ክልሉን እያስተዳደሩ ያሉት ዶ/ር ደብረፂዮን እንዲሁም መከላከያ በሰጧቸው መግለጫዎች የፌደራል መንግሥቱ ኃይሎች ሽሬን እና ራያን ተቆጣጥረው ወደ አክሱም እያመሩ መሆኑ ተነግሯል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ደብረፂዮንን (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የህወሓት ነባር አመራሮችን በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚያስችል የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ በ96 ግለሰቦች ላይ ማውጣቱን አስታወቋል። በትናንትናው ዕለትም ህዳር 9/2013 ዓ.ም ኮሚሽኑ በድጋሜ 76 ጄኔራሎች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የበታች ሹማምንቶች "ከህወሓት ጋር በመተባበር የአገር ክህደትን ፈፅመዋል" በሚል የመያዣ ትዕዛዝ እንደወጣባቸው አስታውቋል። የተለያዩ የዓለም አቀፍ መንግሥታት የፌደራልና የክልሉ መንግሥታት የገቡበትን ግጭት በንግግር እንዲፈቱ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ግን ጉዳዩ "ህግ ማስከበር ነው" በሚል ሳይቀበሉት ቀርተዋል። እንደ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት መግለጫ ከሆነ በአሁን ሰዓት 30 ሺህ ሰዎች በላይ ግጭቱን በመሸሽ ወደ ሱዳን መሸሻቸውን አስታውቋል።
news-56398463
https://www.bbc.com/amharic/news-56398463
ቢዮንሴ እና ቴይለር ስዊፍት በ2021 የግራሚ ሽልማት ታሪክ ሰሩ
ቢዮንሴ ለ28ኛ ጊዜ የግራሚ ሽልማትን በማግኘት እንዲሁም ቴይለር ስዊፍት ለሦስት ተከታታይ ዓመታት የዓመቱ ምርጥ አልበም ሽልማትን በመውሰድ ታሪክ አስመዘገቡ።
በአሁኑ ጊዜ ቢዮንሴ በግራሚ ሽልማት ታሪክ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ሽልማት ያሸነፈች ሴት ድምጻዊት በመሆን ቀዳሚነቱን ይዛለች። ከዚህ ቀደም ይህንን ክብረወሰን ጨብጣ የነበረችው አሊሰን ክራውስ ነበረች። 63ኛው የግራሚ ሽልማት በሎስ አንጀለስ የተካሄደ ሲሆን በተለምዶ "የሙዚቃ ትልቁ ምሽት" በመባል ይታወቃል። በዚህ ዓመት በኮሮናቫይረስ ወርሽኝ የተነሳ ከዚህ ቀደም ከነበሩት የሽልማት ሥነ ሥርዓቶች በተለየ ምንም ዓይነት እንግዳ ሳይገኝ ዝግጅቱ ተካሂዷል። ቢዮንሴ በምርጥ የአር ኤንድ ቢ ሙዚቃ አቀራረብ ተመርጣ ሽልማቱን ስትቀበል "ታላቅ ክብርና ደስታ ይሰማኛል" ብላለች። ቴይለር ስዊፍትም እንዲሁ ሦስት ግዜ የዓመቱ ምርጥ አልበምን በማሸነፍ የመጀመሪያዋ ሴት በመሆን ታሪክ ሰርታለች። ድምጻዊቷ ሽልማቱን ያገኘችው በኮሮናቫይረስ ውሸባ ውስጥ ሆና በሰራችውና "ፎክሎር" የሚል መጠሪያ በሰጠችው አልበሟ ነው። ከዚህ ቀደም ፊርለስ በተሰኘው አልበሟ በ2010 እና 1989 የሚል መጠሪያ ባለው አልበሟ ደግሞ በ2016 ማሸነፏ ይታወሳል። ከዚህ ቀደም ሦስት ድምጻውያን፤ ፍራንክ ሴናትራ፣ ፖል ሳይመን እንዲሁም ስቲቪ ወንደር ብቻ የዓመቱ ምርጥ አልበምን ሦስት ጊዜ አሸንፈው ያውቃሉ። ቢዮንሴ 28ኛዋን የግራሚ ሽልማት ያሸነፈችበት ሥራዋ ለጥቁሮች ኃያልነትና ጽናትን ለማሰብ ባለፈው ዓመት ሰኔ 10 ያቀረበችው ነው። "እንደ የጥበብ ሰው ያለሁበትን ዘመን ማንፀባረቅ ሥራዬ ነው ብዬ አምናለሁ፤ እናም ደግሞ አስቸጋሪ ጊዜ ነበር" ብላለች ቢዮንሴ ሽልማቷን በተቀበለችበት ወቅት። "ስለዚህ ሁሉንም ጥቁር ንግሥቶችና ንጉሦች እኔን እንዲያነሳሱ፣ ዓለምን እንዲያነቃቁ ማበረታታና ሞራላቸውን ከፍ ማድረግ ፈለግሁ" ብላለች ከሥራዋ ጀርባ የነበረውን ምክንያት ስታስረዳ። በሌላ ዜና ናይጄሪያውያኑ በርና ቦይና ዊዝ ኪድ የ2021 ግራሚ አዋርድን አሸንፈዋል። በርና ቦይ በምርጥ ዓለም አቀፍ ሙዚቃ አልበም ዘርፍ ሲያሸንፍ፣ ዊዝኪድ በበኩሉ በምርጥ የሙዚቃ ቪዲዮ ተሸልሟል። ዊዝኪድ ቪዲዮውን የሰራው ከቢዮንሴ ጋር ሲሆን፣ ሙዚቃውም ብራውን ስኪን ገርል ይሰኛል። የቢዮንሴ ልጅ የሆነችው ብሉ አይቪ በዚህ ሙዚቃ አሸናፊ ሆናለች። የበርና ቦይ ትክክለኛ ስሙ ዳሚኒ ኦጉሉ ሲሆን ለሁለት ተከታታይ ዓመታት ዕጩ ነበር። በዘንድሮው የግራሚ ሽልማት የኮሮናቫይረስ ምክንያት አካላዊ ርቀትን ለመጠበቅ ሲባል የሙዚቃ ሥራዎች የቀረቡት በአምስት የተለያዩ መድረኮች ላይ ነው። የጥቁሮች ሕይወት ዋጋ አለው በሚል ስሜት ከተቀነቀኑ መካከል ሌላ ሽልማት ያገኘው ሥራ በአር ኤንዲ ቢ አቀንቃኟ ኸር (H.E.R.) የተዘፈነው ነው። ድምጻዊቷ ስለሥራዋ ስትናገር ሙዚቃውን እናቷ ቤት ሆና ራሷ እንደቀረፀችው ተናግራለች። ይህ ሙዚቃ ባለፈው ዓመት ጆርጅ ፍሎይድ የተባለው ጥቁር አሜሪካዊ አንገት ላይ አንድ ነጭ ፖሊስ ቆሞበት ሕይወቱ ከማለፉ በፊት 'መተንፈስ አልቻልኩም' ሲል የተናገረውን በመውሰድ የተሰራ ነው። ኸር ትክክለኛ ስሟ ጋብሬላ ዊልሰን ሲሆን ባለፈው ዓመት ከሪያራ ቶማስ ጋር በመሆን ሙዚቃውን መጻፋቸው ይታወሳል። ድምጻዊቷ በዚህ ሥራዋ አሸናፊ ሆና ሽልማት ስትቀበል "ፍርሃቴ እና ብሶቴ እንዲህ ተጽዕኖ ይኖረዋል ብዬ አስቤ አላውቅም" ስትል ተናግራለች። አክላም "ለዚያ ነው ሙዚቃ የምጽፈው፤ ደግሞ በጣም አመሰግናለሁ" ብላለች።
news-47276072
https://www.bbc.com/amharic/news-47276072
በምዕራብ እና በማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች የአስቸኳይ ጊዜ ወይስ የመሣሪያ እገዳ?
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በምዕራባዊና ማዕከላዊ ጎንደር በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለውን አለመረጋጋትና የህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመቆጣጠር እርምጃ መውሰድ መጀመሩ ተገለጸ።
የሃገር መከላከያ ሠራዊትና የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እሁድ ዕለት እንዳስታወቁት ከጎንደር፣ መተማ፣ ሁመራ መስመርና በጎንደር ከተማ ውስጥ ግለሰቦች የጦር መሳሪያ ታጥቀው እንዳይንቀሳቀሱ ገደብ መጣሉንና ይህንን ትላልፈው በተገኙ ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገልጿል። በተጠቀሱት አካባቢዎች በተለያዩ ጊዜያት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳትን ያስከተሉ ግጭቶች መከሰታቸውና ግጭቱን ለመቆጣጠር ከክልሉ አቅም በላይ በመሆኑ እና የጸጥታው ችግር ከመሻሻል ይልቅ በየጊዜው እየተባባሰ በመምጣቱ ተጨማሪ ኃይል አስፈላጊ መሆኑ እንደታመነ በመግለጫው ተመልክቷል።በዚህም ምክንያት የአማራ ብሔራዊ ክልልዊ መንግሥት ለፌዴራል መንግሥት ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ውሳኔውን ተግባራዊ ለማድረግና ሠላም ለማስከበር ከእሁድ የካቲት 10/2011 ዓ.ም ጀምሮ በተጠቅሱት አካባቢዎች ላይ እንደተሰማራ ተነግሯል። • ደቡብ ጎንደር መካነ እየሱስ ውስጥ ምን ተፈጠረ? • የጦር መሳሪያዎቹ ምንጫቸው የት ነው?የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘላለም ልጃለም ለቢቢሲ እንደተናገሩት ይህን እርምጃ መውሰድ "መንግዶች እየተዘጉ ነው፣ ሰዎች እየተፈናቀሉ፣ ዝርፊያ እየተፈጸመ፣ ሰዎች እየተገደሉ እና ንብረት እየተዘረፈ በመሆኑና የመንግሥት አገልግሎት መስጠት ባለመቻሉ ሰላም የማስከበር ሥራ በፍጥነት ለማከናወን ነው" ብለዋል። ኮሚሽነሩ ጨምረውም እርምጃው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አለመሆኑን አመልክተው፤ ክልከላው ለፀጥታ ሥራ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ሲባል የተተደረገ እንጂ የዜጎችን ሕገ መንግሥታዊ መብት በአዋጅ የመገደብ እርምጃ አይደለም ብለዋል። "ከመቼውም ጊዜ በላይ የፀጥታ ኃይሉ ከፍትኛ ስምሪት የሚያደርግበት በመሆኑ ለዚህ የሚመች ሁኔታ ለመፍጠር እንጂ ዜጎች ህጋዊ እስከሆኑ ድረስ ከተከለከሉት አካባቢዎች ውጪ ባሉት ቦታዎች መሳሪያ ይዘው መንቀሳቀስ ይችላሉ" በማለት አብራርተዋል። የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በተከሰተባቸው አካባቢዎች መኪና አስቁሞ ዝርፊያ፣ ግድያ፣ ሰዎችን አፍኖ የመውሰድ ወንጀል የሚፈጽሙ ቡድኖች መኖራቸውን ኮሚሽነር ዘላለም ልጃለም ተናገግረዋል። • እነ አቶ በረከት በማረሚያ ቤቱ ኢንተርኔት የለም አሉ • ኦሮምኛ ዘፋኙ ለደስታ በተተኮሰ ጥይት ህይወቱን አጣ "ክልከላው የሚቆየው የአካባቢውን ሰላም አስከብረን መደበኛ የልማት እንቅስቃሴ እስኪጀመር ይሆናል። የክልልና የፌዴራል የጸጥታ አካላት ከሕብረተሰቡ ጋር በትብብር እየስሩ ነው ክልከላውም ይህን ስራ ለማሳለጥ ነዉ። ስለዚህ ስራችንን ስንጨርስ የሚነሳ ይሆናል" ብለዋል።የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ በአካባቢዎቹ አስተማማኝ ሰላም እስኪሰፍን ድረስ መሆኑን በማመልከት ክልከላው የሚመለከታቸውን ቦታዎች በዝርዝር አስቀምጧል።በዚህም መሠረት ከጎንደር ወደ መተማ በሚያመራው መስመር ከመንገድ ግራና ቀኝ በአምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ በቡድንም ሆነ በግል ትጥቅ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ሲሆን በሁመራ መስመርም በተመሳሳይ ክልከላ ተጥሏል። • ሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር መበራከት ምንን ያመለክታል? • በደቡብ ወሎ ሙሽራና ሚዜውን የገደለው ቦምብበጎንደር ከተማ ውስጥም በመንግሥት ከተፈቀደላቸው ፀጥታ አካላት ውጪ ማንኛውም ሰው መሣሪያ ታጥቆ መንቀሳቀስ እንደማይችልም በመግለጫው ላይ ተመልክቷል። ክልከላውን በመተላለፍ በፀጥታ ማደፍረስ ተግባር ውስጥ ተሳትፎ ያደረገ ኃይል እርምጃ እንደሚወሰድበትና 'ሰላም ለማስከበር' በሚል ሰበብ ማንኛውም ግለሰብ ከፈቃድ ውጪ መሣሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እንደማይቻል እገዳ ተጥሏል። ውሳኔውን ጥሰው በተገኙ ሰዎች ላይ የሚወሰድ እርምጃን በተመለከተም ኮሚሽነሩ ሲናገሩ "ክልከላው ተግባራዊ ሆኗል። የክልል እና ፌደራል መንግሥታት የሚያዉቁት ክልከላ ነው። ክልከላውን በተላለፉ ሰዎች ላይ በህግ የመጠየቅና በያዙት መሳሪያ ላይም ውሳኔ የማስወሰን ሥራ ይሰራል" ብለዋል።በተጠቀሱት አካባቢዎች የተጣለው የጦር መሳሪያ ይዞ የመንቀሳቀስ እገዳ ከእሁድ ጀምሮ ተፈጻሚ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ዘላለም ልጃለም ገልጸው ክልከላውን ተላለፈው በሚገኙ አካላት ላይ የፀጥታ ኃይሎች ተመጣጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ መታዘዛቸውን አመልክተዋል። በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚኖረው ህዝብ ካለው የጦር መሳሪያን ይዞ ከመንቀሳቀስ ልምድ አንጻር ክልከላውን ለማስፈጸም አስቸጋሪ አይሆንም ወይ? ተብለው የተጠየቁት ኮሚሽነሩ "ክልከላው በተጣለባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች ውሳኔውን እንዲረዱት በተለያዩ አካላት ሥራ እየተሰራ ነው። ነገር ግን በሌሎች አካባቢዎች ሰላማዊ በሆነ መልኩ ህጋዊ መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ይቻላል። አላማውም ከትጥቅ ማስፈታት ጋር የሚያያዝ አይደለም" ብለዋል። በቅርቡ በምዕራብና ማዕከላዊ የጎንደር አካባቢዎች በተከሰቱ የሰላም መደፍረስ ችግሮች ምክንያት በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ከደረሱ ጉዳቶች በተጨማሪ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን ክልሉ መግለጹ ይታወሳል። • ድብቅ የህጻናት ጋብቻዎች • የሴት ልጅ ግርዛት ምንድነው? የት እና ለምን ይፈጸማል? ከዚህ አንጻርም ኮሚሽነሩ ባለፉት ሳምንታት በተከሰቱ ግጭቶች ጥፋት ያደረሱ ግለሰቦች ተፈልገው በህግ እንዲጠየቁ እንደሚደረግና በአጠቃላይ እስካሁን በዚህ የብጥብጥ ሂደት ውስጥ የተሳተፉ ግለሰቦችን በቁጥጥር የሚያውል የምርመራ ቡድን ተቋቁሞ አስፈላጊውን ተግባር እያከናወነ መሆኑንና "አጠቃላይ የጥፋቱ መጠን፣ የጠፋዉ ንብረት፣ የተሳታፊዎች ዝርዝር፣ የተጎዱ ሰዎችን በተመለከተ በቀጣይ ይፋ ይደረጋል" ብለዋል። ይህንን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግም የሃገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የክልሉ ፖሊስና የጸጥታ ሃይሎች እንደተሰማሩም ተገልጿል።
news-56156446
https://www.bbc.com/amharic/news-56156446
በአሜሪካ አዲስ የሚወለድ ልጅን ጾታ ይፋ ለማድረግ የተገጣጠመ መሳሪያ ፈንድቶ አባትየውን ገደለ
በኒውዮርክ የልጅ አባት ለመሆን ጥቂት ጊዜ የቀረው አባት የልጁን ጾታ ይፋ ለማድረግ የገጣጠመው መሳሪያ ፈንድቶ ሕይወቱን መቅጠፉን ፖሊስ አስታወቀ።
እሁድ ዕለት የኒውዮርክ ከተማ ነዋሪ የሆነው ግለሰብ በቅርቡ የልጅ አባት በመሆኑ የተሰማውን ደስታ ለመግለጽ ወዳጅ ዘመዶቹን ጠርቶ ተፍ ተፍ እያለ እንደነበር ቤተሰቦቹ ተናግረዋል። ይህንንም አስመልክቶ ለወዳጅ ዘመድ የጽንሱን ጾታ ለመንገር መለስተኛ ድግስ ሲያዘጋጅ አብረውት ወንድሞቹም ነበሩ። በዚህ ድግስ ላይ የሚወለደውን ልጅ ጾታ ይፋ ለማድረግ የሚያስችለውን መሳሪያ አባት የገጣጠመው ሲሆን፤ ነገር ግን በድንገት ፈንድቶ ለሞት ሲያበቃው ወንድሙን ደግሞ አቁሱሎታል ይላል የፖሊስ ዘገባ። ፖሊስ እንዳለው የ28 ዓመቱ ክርስቶፈር ፔክኒ የገጣጠመው መሳሪያ ፈንድቶ የገደለው ሲሆን የ27 ዓመቱን ወንድሙን ማይክል ፔክኒን ደግሞ አቁስሎታል። ጾታን ይፋ ለማድረግ የሚዘጋጁ ድግሶች በአሜሪካ አደጋ ሲያደርሱ ይህ አዲስ አይደለም ተብሏል። ፖሊስ እሁድ እለት ፍንዳታውን ያስከተለው ምን ዓይነት መሳሪያ እንደሆነ እስካሁን ድረስ ይፋ አላደረገም። የኒው ዮርክ ከተማ ፖሊስ እና የፈንጂ አምካኝ ቡድኖች ግን በጋራ ምርመራ እያደረጉ መሆኑ ግን ታውቋል። የከተማዋ ፖሊስ ቃል አቀባይ ለኒውዮርክ ታይምስ እንደገለፁት የተገጣጠመው መሳሪያ ቱቦ መሰል ነገር ይዞ ነበር በማለት ተናግረው ዝርዝረር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል። አንድ ወንድሙን በሞት ያጣውና ሌላኛው ወንድሙ ቆስሎ ሆስፒታል የገባው ፒተር ፔክኒ ጁኒየር፣ የተከሰተውን ለጋዜጣው ሲያስረዳ "ከማስበውና ከምገምተው በላይ አስፈሪ አደጋ ነበር" በማለት ፍንዳታውን ምን እንዳስከተለው እንደማያውቅ ተናግሯል። ከዚህ ቀደም ጾታን ይፋ ለማድረግ ተብለው በተዘጋጁ ድግሶች ላይ በደረሱ አደጋዎች ሞት ተመዝግቦ ያውቃል። በአሜሪካ ጾታን ይፋ ለማድረግ የተለያዩ ዝግጅቶች የሚኖሩ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የመገመት ጨዋታ በኋላም ርችት እና በቀለም የተሞላ ጭስ ያለበት ፍንዳታ ይከተላል። ነገር ግን በርካታ ትልልቅ ድግሶች ላይ አደጋዎች ከዚያም ሞቶችም ይከሰታሉ። በዚህ ወር በሚቺጋን አዲስ ለሚወለድ ልጃቸው በተዘጋጀ የእንኳን ደስ አለን ድግስ ላይ ከተተኮሰ ርችት የተፈናጠረ ሹል ነገር ለአንድ ሰው ሕይወት ማለፍ ምክንያት መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል። በካሊፎርኒያ ደግሞ ባለፈው ዓመት መስከረም ወር እና በ2017 ሚያዚያ ወር ላይ ለተነሳ ሰደድ እሳት ሁለት የተፀነሰውን ልጅ ጾታ ይፋ ለማድረግ የተደገሱ ድግሶች ሰበብ መሆናቸው ተመዝግቦ ይገኛል። በወቅቱ በካሊፎርኒያ ኤል ዶራዶ የደረሰው የእሳት አደጋ ከ19 ሺህ ኤከር በላይ መሬት አቃጥሎ በርካቶች ቤት ንብረታቸውን ጥለው እንዲሰደዱ በርካታ ቤቶች እንዲቃጠሉ አድርጓል።
57146507
https://www.bbc.com/amharic/57146507
ኢዜማ የምርጫው መራዘም 'ምክንያታዊ' ነው ሲል ባልደራስ በበኩሉ 'ማብራሪያ እፈልጋለሁ' አለ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የምርጫው መረዘም ምክንያታዊ ነው ሲል ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ( ባልደራስ) በበኩሉ ቦርዱ ምርጫውን በሚያራዝምባቸው ቀናት ውስጥ የሚያከናውናቸውን ተግራት በዝርዝር ማሳወቅ አለበት አለ።
የኢዜማ እና ባልደራስ አርማ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከቀናት በፊት ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ለማካሄድ የሚየስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች በወቅቱ ሊጠናቀቁ ሚችሉበት ሁኔታ ስለሌለ ምርጫው በሳምንታት ሊራዘም ይችላል ማለቱ ይታወሳል። ሰኔ 5 በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ እንዲሁም ከትግራይ በስተቀር በተቀረው የአገሪቱ ክፍል ደግሞ ግንቦት 28 የድምጽ መስጫ ቀን ይሆናል ተብሎ እቅድ ተይዞ ነበር። ምርጫ ቦርድ ከሎጂስቲክ ሥራዎች መጓተት ጋር በተገናኘ ምክንያት ነው የታቀደው ምርጫ በሁለት ወይም በሦስት ሳምንታት ማራዘም ሊያስፈልግ ይችላል ያለው። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ትናንት ምንም እንኳ አስተዳደራቸው በመጀመሪያው ዕቅድ መሠረት ለመቀጠል ፍላጎት ቢኖረውም፤ በምርጫ ቦርድ በኩል ምርጫውን ለአጭር ጊዜ ለማዘግየት ያቀረበው ሐሳብ "ምክንያታዊ በመሆኑ በዚያው ተስማምተናል" ሲሉ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።፡ የምርጫው መራዘም ምክንያታዊ ነው የኢዜማ ፓርቲ የሕዝብ ግነኙነት ኃላፊ ናትናኤል ፈለቀ፤ የድምጽ መስጫው ቀን እንዲራዘም የቀረበው ሐሳብን "በእኛ አመለካከት ምክንያታዊ ሆኖ ነው ያገኘነው" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ምርጫውን አጣድፈን ተገቢ የሆነው ዝግጅት ሳይደረግ ተከናውኖ ችግር ውስጥ ከምንገባ ተጨማሪ ጊዜ ተወስዶ እነዚህን ሥራዎች አጠናቆ ምርጫውን ማካሄድ የተሻለ ውጤት አለው" ብለዋል። የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ቢሮ ኃላፊ አቶ ገለታው ዘለቀ ደግሞ ምርጫ ቦርድ ምርጫውን በሁለት ወይም በሦስት ሳምንት አራዝማለሁ ሲል በሚራዘሙት ሳምንታት ምን እንደሚያከናውን በዝርዝር መታወቅ አለበት ብለዋል። "ምርጫ ቦርድ ምርጫ አራዝማለሁ ሲል ምን ሊሰራ እንደሆነ በዝርዝር ማሳወቅ አለበት። አሁን ላይ ምን እንደሚሰራ ግልጽ የሆነ ነገር የለም" ሲሉ ገለታው ተናግረዋል። "ምርጫ ቦርድ ጊዜ እፈልጋለሁ ሲል ለምንድነው የሚፈልገው? የሚል አቋም ነው ያለን" ብለዋል። ፓርቲያቸው የምርጫው ተሳታፊ እንደመሆኑ ምርጫ ቦርድ ጊዜ ለማራዘም ሲጠይቅ ምርጫ ለምን እንደሚያራዝምና በተጨማሪው ጊዜ ውስጥ የሚከናወኑ ተግባራት በዝርዝር መቅረብ እንዳለበት ገልፈዋል። "ለምሳሌ የሎጂስቲክ እጥረት በእነዚህ ስፍራ አጋጥሞኛል ካለ፤ የሚሰራውን ሥራ እና የሚያስፈልገውን ጊዜ ግልጽ ካደረገ እንስማማለን" ብለዋል። አቶ ናትናኤል ምርጫው በአገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ነጻ እና ፍትሃዊ የሆነ ምርጫ የሚካሄድበት ይሆናል ብለው እንደሚያምኑና ከዚህ ቀደም እንዲህ አይነት ምርጫ ለማካሄድ ተሞክሮ ካለመኖሩ አንጻር ችግሮች ሊኖሩ እንደሚችሉ ፓርቲያቸው ቀድሞ ከግምት ያስገባው ጉዳይ ነው ብለዋል። አክለውም "ምርጫው መራዘሙ ያን ያህል በምርጫው ላይ የሚኖረንን ምልከታ የሚቀይር አይደለም" ሲሉ የፓርቲያቸውን አቋም አንጸባርቀዋል። ምርጫው በድጋሚ እንዲራዘም የሚደረግ ከሆነ ግን በሕዝብ ያልመረጠን መንግሥት በስልጣን ላይ ማቆየት ስለሚሆን ምርጫው ከሁለት ወይም ሦስት ሳምንት በኋላ መካሄድ አለበት የሚል አቋም ፓርቲያቸው እንዳለው አቶ ናትናኤል ተናግረዋል። "ከዚህ በላይ ከተራዘመ በሕዝብ ያልተመረጠ መንግሥት በስልጣን ላይ እንዲቆይ የሚያደርግ ነው" ይላሉ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለስድስተኛው አገራዊ ምርጫ እስከ 50 ሚሊዮን የሚደርሱ መራጮች ይሳተፋሉ ብሎ እንደሚጠብቅ ይፋ ቢያደርግም ቦርዱ በቅርቡ ይፋ ባደረገው አሃዝ መሠረት እስካሁን ድምጽ ለመስጠት የተመዘገቡት ድምጽ ሰጪዎች ቁጥር 36 ሚሊዮን ተሻግሯል። የምርጫ ካርድ ከወሰዱት መካከል 16.6 ሚሊዮኑ ሴቶች ሲሆኑ ፤ 19.5 ሚሊዮኑ ደግሞ ወንዶች ናቸው፡፡ እንደ ምርጫ ቦርድ መረጃ ከሆነ ጋምቤላ፣ አዲስ አበባ፣ ሶማሌ እና አፋር ክልሎች ከተገመተው በላይ የመራጮች ካርድ ከተወሰደባቸው መካከል ናቸው። በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአንጻራዊነት ዝቅተኛ የመራጮች ምዝገባ መከናወኑን የምርጫ ቦርድ መረጃ ያሳያል።
news-49341232
https://www.bbc.com/amharic/news-49341232
ዕፅ በማዘዋወር የተጠረጠረው ኬንያዊ ቱጃር ቤት በፖሊስ እየተበረበረ ነው
የኬንያ ፖሊስ ዕፅ በማዘዋወር ወንጀል ጠርጥረነዋል ያሉትን አሊ ፑንጃኒ በመርመር ላይ ናቸው፤ ሞምባሳ የሚገኘው መኖሪያ ቤቱንም ትላንት ሲያስሱ ውለዋል።
ሚስቱ ነኝ የምትል አንድ የኔፓል ዜግነት ያላት ሴት እና ሌሎች ሁለት ወንዶች ከአሰሳው ጋር በተያያዘ ሶስት ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል። ግለሰቦቹ የተያዙት ኒያሊ በተሰኘችው የሞምባሳ መንደር ውስጥ በሚገኘው የፑንጃኒ መኖሪያ ቤት ውስጥ መሆኑ ታውቋል። • ታዳጊዎችን በወሲብ ንግድ በማሰማራት ተከሶ የነበረው ቱጃር አሟሟት ጥያቄን ፈጥሯል አሊ ፑንጃኒ፣ ሁለቱ ኬንያውያን ወንድማማቾች ባክታሽ እና ኢብራሂም አካሽ፣ እንዲሁም ቪጄ ጎስዋሚ የተባለ ግለሰብ ከዕፅ ዝውውር ጋር በተያያዘ በአሜሪካ መንግሥት ይፈለጋሉ። ፑንጃኒ፤ እሳከሁን በዕፅ ዝውውር ስለመጠርጠሩ ምንም የሰጠው አስተያየት የለም። ወንድማማቾቹ ባለፈው ዓመት ዕፅ ታዘዋውራላችሁ፤ 100 ኪሎ ግራም ሄሮይን የተባለ ዕፅ ወደ አሜሪካ ለማስገባትም አቅዳችኋል ተብሎ የቀረበባቸውን ክስ ማመናቸው አይዘነጋም። • የዓለማችን ቱጃር 2 ቢሊየን ዶላር ለድሆች ሊለግሱ ነው የወንድማማቾቹ ክስ እስከ ዕድሜ ልክ ሊያስቀጣ ይችላል ቢባልም የተባባሪዎቻቸውን ስም በማጋለጥ ቅጣታቸውን ለማስቀለል አስበዋል የሚሉ መረጃዎች እየወጡ ነው። የአሊ ፑንጃኒ የግል ጠበቃ ሰኞ ዕለት በሰጡት መግለጫ ደንበኛው የሕክምና እርዳታ ለማገኝት ወደ ሕንድ እንዳቀኑ አስታውቀዋል። የአሊ ፑንጃኒ ቤተሰቦች ቱጃሩ የሆስፒታል አልጋ ላይ ተኝቶ ሕክምና ሲከታተል የሚያሳይ ፎቶ ለቀዋል። የጉምቱው ቱጃር ክስ ኒው ዮርክ ውስጥ በሚገኝ ፍርድ ቤት እየታየ ይገኛል። • የአውሮፓን እግር ኳስ የሚዘውረው ሃብታሙ 'ደላላ'
news-55751444
https://www.bbc.com/amharic/news-55751444
ኮሮናቫይረስ፡ ስለኮቪድ-19 ክትባት ማወቅ ያለብን ወሳኝ ነጥቦች
ብዙ አገራት ሩጫ ላይ ናቸው፡፡ መጀመርያ ክትባቱን እጃቸው ለማስገባት ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ቶሎ ብለው ለሕዝባቸው ለማደል፡፡
በተለይ ያደጉት አገራት ትንፋሽ አጥሯቸዋል፡፡ ለድል ጓጉተዋል፡፡ ኮሮና የሚባል ጠላት ምጣኔ ሀብታቸውን ብቻ ሳይሆን ሕዝባቸውን እየጨረሰ ነው፡፡ ፖለቲከኞች በዚህ ጦርነት ውጤት ካላመጡ ሕዝባቸው አንቅሮ ይተፋቸዋል፡፡ ለክትባት ‹መስገብገባቸው› ከዚህ የሚመነጭ ነው፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት ‹እንተሳሰብ እንጂ ጎበዝ› የሚል ይዘት ያለው መግለጫ ለማውጣት የተገደደውም ለዚሁ ነው፡፡ ድሀ አገራት ለጊዜው የበይ ተመልካች ሆነዋል፡፡ ቢሆንም ግን ክትባቱ ወደነሱም እየመጣ ነው፡፡ ዓለም አንድ መንደር በሆነችበት ሁኔታ እንዴት ነው አንድ አገር ሕዝቡን ብቻ ስላስከተበ ከስጋት ነጻ የሚሆነው? እስራኤል 9 ሚሊዮን ሕዝቧን ለማስከተብ የጀመረችው ፈጣን እርምጃ እስከአሁን ግማሽ ሚሊዮን ሕዝቧን አዳርሷል፡፡ ሆኖም ግን ወረርሽኙ ጋብ አላለም፡፡ ገና ከአሁኑ ለምን የሚሉ ጥያቄዎች መነሳት ጀምረዋል፡፡ ውጤት ለማየት ግን ጊዜ ይፈልጋል፡፡ ክትባቱን አንድ ሰው በተወጋበት ቅጽበት ለኮቪድ ተህዋሲ ራሱን ተከላካይ ያደርጋል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው፡፡ የሚከተሉት ነጥቦችን መረዳት ለክትባቱ ይበልጥ እናድናውቅ ይረዳል፡፡ ክትባት ምንድነው? ክትባት ማለት ለአንድ ኢንፌክሽን፣ በሽታ ወይም ተህዋሲ ሰውነታችን እንዲከላከል ሰራዊት የሚያዘጋጅ ጠብታ ነው፡፡ ክትባት በይዘቱ ሙትት ያለ፣ ወይም የተዳከመ የተህዋሲ ቅንጣትን የያዘ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህም ማለት በሽታውን፣ ተህዋሲውን ራሱ ነው የምንወጋው ማለት ነው፡፡ ወይም ደግሞ በሽታው በሽታ እንዳያስከትል በሚያስችል ደረጃ ራሱን ለሰውነታችን ብቻ እንዲያጋልጥ አድርጎ ማንነቱን ማሳጣት ማለት ነው፡፡ በዚህ ሂደት የሰውነታችን በሽታ ተከላካይ ሰራዊት ለጠላት ኃይል እንዳያሸረግድ፣ እጅ እንዳይሰጥ፣ እንዲነቃ፣ የማንቃት ትጥቅና ስንቅን የማቀበል ያህል ነው የክትባቱ ሁነኛ ተግባር፡፡ ክትባት ለሕመም አያጋልጥም፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ሰዎችን ሊያዳክማቸው፣ ወይም መጠነኛ የጎንዮሽ ጉዳት ሊያደርስባቸው ይችላል፡፡ ከነዚህም ምልክቶች መሀል ክንድ ላይ ቁስለት ወይም ደግሞ ጊዝያዊ ትኩሳት የተለመዱ ናቸው፡፡ የጎንዮሽ ጉዳቱ ተፈርቶ መቼስ ከሞት ጋር የሚፋጠጥ አይኖርም፡፡ መልካሙ ዜና ከክትባት በኋላ ለተህዋሲ የማይበገር ሰው መሆን መቻሉ ላይ ነው፡፡ ክትባት ከመድኃኒትም በላይ የሚሆነውም ለዚህ ነው፡፡ መድኃኒት የተከሰተን በሽታ ለማጥፋት ነው ቀን ተሌት የሚተጋው፣ ክትባት ግን በሽታውን መጀመርያውኑ ያመክናል፡፡ ሲዲሲ ክትባቶች ችግር የለባቸውም ባይባልም ትሩፋታቸው ከችግራቸው እጅግ የበዛ ነው ይላል፡፡ ክትባቶች ከመሰራጨታቸው በፊት በእንሰሳት ላይ ይሞከራሉ፣ በቤተ ሙከራ ይሞከራሉ፣ በጥቂት ሰዎች ይሞከራሉ፣ በብዙ ሰዎች ይሞከራሉ፤ በጊዜ ሂደት ይጠናሉ፡፡ ይህን ሁሉ ሂደት እንዲያልፉ የሚደረጉት የሰው ልጅ ላይ የሚያደርጉትን ጉዳት በትክክልና በይበልጥ ለመረዳት ነው፡፡ ኮቪድ ጊዜ አልሰጥ በማለቱ ግን ይህ ረዥምና ዓመታትን የሚወስድ የሕክምና ምርመራ ሒደት እንዲያጥር ሆኗል፡፡ የስጋቱ ምንጭም ይኸው ነው፡፡ ክትባት እንዴት ሊሰራ ይችላል? ክትባቶች አስጊ አይደሉምን? ክትባቶች የተጀመሩት በ10ኛው ክፍለ ዘመን በቻይናዊያን እንደሆነ ይነገራል፡፡ ነገር ግን እስከ 1796 ዓ/ም የአሁኑን ሳይንሳዊ ቅርጽ አልያዘም፡፡ ኤድዋርድ ጀነር ፈንጣጣ ላይ ሲመራመር የተወሰነ የፈንጣጣ ቅንጣት ሰውነትን የመከላከል አቅም አንቅቶ በተሻለ እንደሚያዘጋጅ ተረዳ፡፡ ይህንኑ አረጋገጠና ከ2 ዓመት በኋላ ግኝቱን አሳተመው፡፡ ከዚህ በኋላ በላቲን ቫካ የሚለው ቃል (ትርጉሙ ላም ማለት ነው) ቫክሲን ወደሚል ቃል ተለወጠና ክትባት የዓለም መድኅን ሆነ፡፡ የሰው ልጅ ከፈጠራቸው ድንቅ የሕክምና ግኝቶች ውስጥ ክትባት ዋናው ነው፡፡ ክትባት ባይኖር ኖሮ በዓመት 3 ሚሊዮን ሕዝብ እንደ ቅጠል ይረግፍ ነበር፡፡ የዓለም ሕዝብ ቁጥር ምናልባት አሁን ካለው ግማሽ ሊሆን ይችልም ነበር፡፡ 20 የሚሆኑ በሽታዎችን ቀጥ አድርጎ ያቆማቸው ክትባት ነው ይላል የዓለም ጤና ድርጅት፡፡ ክትባቶችን እንዴት ነው አንዱን ከሌላው የምናወዳድረው? ፋይዘር ባዮንቴክ እና ሞደርና ሁለቱም አሰራራቸው ከተህዋሲው የተወሰነ የጄኔቲክ ኮድ በመቅዳት የተቀመሙ ናቸው፡፡ ይህም ማለት ደካማና ሙትት ያለ አንቲጀን ወስዶ ክትባት ከመስራት ይልቅ ሰውነታችንን በጄኔቲክ ኮድ አማካኝነት በተህዋሲው የላይኛው ክፍል የሚገኙ በሽታ አምጪ ተህዋስ ክፍሎችን እንዲያውቅና እነሱን ድምጥማጣቸውን የሚያጠፋ ፕሮቲን እንዲያመርት ነው ያደረጉት፡፡ የኦክስፎርዱ አስትራዜኒካ ትንሽ አሰራሩ ይለያል፡፡ ሳይንቲስቶች ይህን ክትባት የቀመሙት ትንሽ የተለወጠ ቺምፓንዚን የሚያጠቃ የጉንፋን ተህዋሲን በቤተሙከራ አዘጋጅተው ከዚያ የኮቪድ 19 የጄኔቲክ ኮድ ላይ ጨመሩት፡፡ በውጤት ደረጃ ሁሉም ተቀራራቢ ናቸው፡፡ አሜሪካና ብሪታኒያ ፈቅደዋቸዋል፡፡ ሜክሲኮ፣ ቺሌ፣ ኮስታሪካ ፋይዘርን ለሕዝባቸው እየሰጡ ነው፡፡ ብራዚል ደግሞ ለአስትራዜኒካ እና ለሲኖቫክ ፍቃድ ሰጥታ ሕዝቧን እየከተበችው ነው፡፡ ሌሎች የኮቪድ ክትባቶች አሉ? ከአስትራዜኒካና ሞደርና እንዲሁም ፋይዘር ሌላ ክትባቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ የቻይናው ሲኖቫክ የሚያመርተው ኮሮናቫክ አለ፡፡ በቻይና፣ በሲንጋፖር፣ በማሊዢያ፣ በኢንዱኒዢያ፣ በፍሊፒንስ ተግባር ላይ ውሏል፡፡ ሕንድ ደግሞ ኮቫክሲን የሚባል ባራት ባዮቴክ የሰራው አገር በቀል ክትባት ጀምራለች፡፡ ሩሲያ ስፑትኒክ የሚባል የራሷን ክትባት ለሕዝቧ እየሰጠች ነው፡፡ በአርጀንቲና 300ሺህ የስፑትኒክ ቅንጣት ለሕዝብ እየተከፋፈለ ነው፡፡ የአፍሪካ ኅብረት 270 ሚሊዮን ቅንጣት ደርሶታል፡፡ ክትባቱ ፋይዘር፣ አስትራዜኔካ እና ጆንሰን ጆንሰንን ያካተተ ነው፡፡ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ገና ሙከራውን ያላገባደደ ክትባት ነው፡፡ ይህ 270 ሚሊዮን ቅንጣት ባለፈው ከተሰጠ 600 ሚሊዮን ቅንጣት ተጨማሪ መሆኑ ነው፡፡ ይህን የሚያስተባብረው ኮቫክስ ዓለም አቀፍ የትብብር ጥምረት ነው፡፡ ይህ ጥምረት ለድሀ አገራት ክትባቱ እንዲደርስ ከዓለም ጤና ድርጅትና ከቫክሲን አሊያንስ ጋር በጥምረት የሚሰራ ነው፡፡ ክትባቱን መውሰድ ይኖርብናል? ክትባቱን ግዴታ ያደረገ አገር እስከአሁን የለም፡፡ ነገር ግን ክትባቱን መውሰድ ካለመውሰድ እጅጉኑ ይመከራል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ግን በጤና ምክንያት ክትባቱን ባይወስዱ የሚመከሩ ይኖራሉ፡፡ ሲዲሲ ክትባቱን ወስዶ ኮቪድን ማቆም ይቻላል ሲል አትስጉ የሚል መልእክት አስተላልፏል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት ይህ ተህዋሲን ለማሽመድመድ የዓለም 70 ከመቶ ሕዝብ መከተብ ይኖርበታል ብሏል፡፡ ይህም ማለት ድርጅቱ ሕዝብ ክትባቱን እንዲወስድ እያበረታታ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ይህ ክትባት እንዲቀመም የሄደበት መንገድና ፍጥነት ያሳስባቸዋል፡፡ ይህ ተገቢ አይደለም አይባልም፡፡ ነገር ግን ሂደቱ እንዲፈጥን የሆነው ከፈጠረው አደጋ በመነሳት ነው፡፡ አሜሪካ 400 ሺህ ዜጎቿን አጥታለች፡፡ በርካታ አገራት በሺ የሚቆጠር ዜጎችን አጥተው ሚሊዮኖች በሞት ስጋት ላይ ናቸው፡፡ በዚህ ሁኔታ ክትባቱ እንዲፈጥን አለማድረግ አይቻልም፡፡ ያም ሆኖ ሳይንሳዊ ሂደቶች እንዳይጣሱ ሁሉን አቀፍ ጥረት መደረጉን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡ በአጭሩ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ክትባቱን ሲወስዱ የወል ተህዋሲ የመከላከል አቅም ይፈጠራል፡፡ ያን ጊዜ ብቻ ዓለም ወደነበረችበት ጤና ትመለሳለች፡፡ የኮሮናቫይረስ ክትባት ዝግጁ የሚሆነው መቼ ነው?
news-54078491
https://www.bbc.com/amharic/news-54078491
በትግራይ ምርጫ መራጮች ድምጽ መስጠት ጀመሩ
የትግራይ ክልል እያካሄደ በሚገኘው ክልላዊ ምርጫ ዛሬ ከንጋት ጀምሮ መራጮች ድምጽ መስጠት ጀምረዋል።
መራጮች ከንጋት 12፡00 ጀምሮ በ2ሺህ 672 የምርጫ ጣቢያዎች ድምጻቸውን እየሰጡ ይገኛሉ። መቀለ የሚገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ መራጮች ድምጻቸውን ለመስጠት ከንጋት 10፡30 ጀምሮ ምርጫ ጣቢያዎች ፊት ለፊት ተሰልፈው መመልከቱን ገልፆልናል። በክልሉ 38 የምርጫ ክልሎች እንዳሉ የትግራይ ክልል ምርጫ ኮሚሽን መግለጹ ይታወሳል። በክልላዊ ምርጫው ክልሉን የሚያስተዳድረውን ህወሓትን ጨምሮ 5 ፓርቲዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ። በኢትዮጵያ በነሐሴ መጨረሻ ላይ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው አገራዊ ምርጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ ከተላለፈ በኋላ፤ በትግራይ በተናጠል እየተካሄደ የሚገኘው ክልላዊ ምርጫ ሕገ-ወጥና ተቀባይነት የሌለው ነው በማለት የፌደሬሽን ምክር ቤት መወሰኑ ይታወሳል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድም ትናንት ምሽት በኢቢሲ በተላለፈው ቃለ መጠይቃቸው ምርጫው ሕጋዊ አይደለም ብለዋል። "ሕጋዊ አይደለም [ክልላዊ ምርጫው]። ምክንያቱም በኢትዮጵያ ምርጫ ማከናወን የሚችለው የምርጫ ቦርድ ብቻ ነው" ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዲረዱት የምፈልገው ነገር ህውሓት ክልሉን ለዓመታት አስተዳድሯል። ክልሉን የማስተዳደር ስልጣኑም እስከ ቀጣዩ ምርጫ ድረስ እንዲራዘም ተደርጓል ብለዋል። "አሁን በዚህ ሰዓት የሚደረጉ የእቁብ ስብስቦች ወይም ጉባኤዎች የእኛ ትልቅ እራስ ምታት መሆን የለባቸውም" ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ። "በእኔ በኩል ለኢትዮጵያ ውጊያ ያስልጋል ብዬ አላምንም። እኔ በፍጹም ውጊያ ከሚደግፉ ሰዎች ጎን መመደብ አልፈልግም። እኔ የምፈልገው ለትግራይ አንድ ጥይት መላክ ሳይሆን አንድ የኮሮና አፈ መሸነኛ መላክ ነው የምፈልገው" ሲሉ ተናግረዋል።
44249347
https://www.bbc.com/amharic/44249347
ሞርጋን ፍሪማን በፆታዊ ትንኮሳ ለቀረበባቸው ውንጀላ ይቅርታ ጠየቁ
ዝነኛው አሜሪካዊ የፊልም ተዋናይ ከስምንት ሴቶች በላይ ፆታዊ ትንኮሳ አድርሶብናል የሚለውን ውንጀላ ተከትሎ ይቅርታ ጠይቀዋል።
"ጎይንግ ኢን ስታይል" የተሰኘው ፊልም ቀረፃ አስተባባሪ የነበረች አንዲት ሴት ለወራት ያህልም ትንኮሳ እንዳደረሰባት ሲኤንኤን በዘገባው አስነብቧል። የ80 ዓመቱ ዕድሜ ባለፀጋ በተደጋጋሚ ያለፍቃዷ እንደነኩዋት፣ ቀሚሷን ሊገልቡ እንደሞከሩና የውስጥ ልብስም አድርጋ እንደሆነ ይጠይቋት እንደነበር አስታውቃለች። ሞርጋን ፍሪማን በበኩላቸው "ምቾት ለተነሱና ክብር ለተነፈጉት" ይቅርታን ለግሰዋል። በመግለጫቸው ጨምረው " የሚያውቀኝ ሰው ሁሉ የሚመሰክረው እኔ አውቄ ሰዎችን ማስቀየምም ሆነ ምቾት እንዲነሱ አላደርግም" ብለዋል። "ሴቶችን ምቾት መንሳት መቼም ቢሆን አላማየ አይደለም" ብለዋል። በሆሊውድ ውስጥ በፆታዊ ትንኮሳ ሲወነጀሉ ከሀርቬይ ዌይንስቴይን ቀጥሎ ሞርጋን ፍሪማን ሌላኛው ዝነኛ ሰው ሲሆኑ በተለይም የብዙ ፊልሞች ባለቤት የሆኑት ሀርቬይ ዌይንስተን ያደረሱትን ወሲባዊ ጥቃትም ተከትሎ በዓለም አቀፍ ዘንድ ሚቱ (#Me Too) የሚል ዘመቻዎች እየተካሄዱ ነው። ይህች የፊልም ቀረፃ አስተባባሪ የፆታዊ ትንኮሳ ደርሶብኛል ብለው ለሲኤኤን ከተናገሩት ከስምንቱ ሴቶች አንዷ ናት። በወቅቱም አለን አርኪን የተባለው ሌላኛው ተዋናይ ለሞርጋን ፍሪማን "ትንኮሳቸውን እንዲያቆሙ በነገሯቸው ወቅት እንደደነገጡና ምንም ማለት እንዳልቻሉ" ተናግራለች። ከዚህም በተጨማሪ እንደ አውሮፓውያኑ 2013 በወጣው "ናው ዩ ሲ ሚ' (Now You See Me) በሚቀረፅበት ወቅት "ሴቶች ጡታችንን እንዲሁም ሌሎች የሰውነት ክፍሎቻቸችን የሚያጋልጥ ልብስ እሳቸው ባሉበት እንዳንለብስ ሰራተኞቹ ይነግሩን ነበር" ብላለች። በተቃራኒው ሲኤኤን የስራ ባልደረቦቻቸውን አናግሮ ሞርጋን ፍሪማን ሁልጊዜም ለስራቸው የሚተጉና ባህርያቸውም ባለሙያነትን የተላበሰ እንደሆነ ዘግቧል።