id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
49561141
https://www.bbc.com/amharic/49561141
በደቡብ አፍሪካው ዝርፊያ ከአርባ በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
ደቡብ አፍሪካውያን ሥራችንን ወስደበውናል ያሏቸውን ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪቃ ሃገራት ዜጎች ላይ ጥቃት አድረሰዋል። አመፀኞቹ የውጭ ሃገር ዜጎች ሱቆችንና ንብረቶችን በመዝረፍ እና በማቃጠል ላይ እንዳሉ ከሥፍራው የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ።
ይህንን ተከትሎም ከአርባ በላይ ደቡብ አፍሪካውያን ትናንት ማምሻውን ጀምሮ በቁጥጥር ስር ውለዋል። ፖሊስ አመጸኞቹን ለመቆጣጠር አስለቃሽ ጭስ የተጠቀመ ሲሆን ነገሮች ከቁጥጥር ውጪ መሆን ሲጀምሩ ደግሞ የጎማ ጥይቶችንም ጭምር ተጠቅሞ ነበር ተብሏል። • በደቡብ አፍሪካ እስር ላይ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ተለቀቁ • ደቡብ አፍሪካ በወሮበሎች ላይ የጦር ሠራዊቷን አዘመተች ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጂፒ በተሰኘው የደቡብ አፍሪቃ ግዛት የሬስቶራንት ባለቤት የሆነው አቶ ተከስተ ሹምዬ ስለሁኔታው ጠይቀነው ነበር። ''የሌላ ሃገር ዜጎች የሆኑ አፍሪካውያን ላይ ነው ጥቃቱ የተሰነዘረው። በተለይ ደግሞ የመኪና ሽያጭ ላይ የተሰማሩ ናይጄሪያውያን ላይ ከእሁድ ጀምሮ ጥቃት ተፈጽሟል። እስካሁን በሰማሁት ዜና ከ50 በላይ መኪና ተቃጥሏል''በማለት ሁኔታውን ያስረዳል። እሁድ ጠዋት ላይ ሶስት ሰዎች መገደላቸውን እና አንድ ህንጻ እንደተቃጠለ ሁኔታው እስካሁን እንዳልተረጋጋ ተከስተ ይናገራል። ተከስተ እንደሚለው በግምት ከአስር ቀናት በፊት ፕሪቶሪያ በተባለችው ከተማ የሃገሬው ታክሲ ሾፌሮች ከናይጄሪያውያን ሾፌሮች ጋር ተጋጭተው በናይጄሪያውያን በተተኮሰ ጥይት አንድ ደቡብ አፍሪካዊ መሞቱን ተከትሎ ትልቅ ብጥብጥ ተነስቶ ነበር። በዚህም ምክንያት ላለፉት ቀናት ናይጄሪያውያንን ጨምሮ ከሌላ ሃገራት የመጡ ዜጎችን ንብረት መዝረፍና ማቃጠል ተበራክቶ እንደነበር ተከስተ ይናገራል። ''ይህ ዝርፊያና አመጽ ወደ ጆሃንስበርግ ተዛምቶ መጥቷል። እሁድ ዕለት ዝርፊያና ማቃጠሉ ተጀመረ። ቀደም ብሎ ግን ከሌላ ሃገራት የመጡ ዜጎችን እናስወጣለን የሚል ማስፈራሪያና ማስጠንቀቂያ ደርሶን ነበር''። • ትሬቨር ኖዋ የዓለማችን አራተኛው ቱጃር ቀልደኛ ሆነ ብዙ ኢትዮጵያውያን በሚገኙበት ጂፒ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በኢትዮጵያን ላይ የደረሰ ጉዳት አለ ወይ? ተብሎ ለቀረበለት ጥያቄ ተከስተ ሲመልስ፤ '' ጂፒ አካባቢ እስካሁን ምንም የደረሰ ነገር የለም። ግን ፕሪቶሪያ ውስጥ ሱቆች ሲቃጠሉ የአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ሱቆችም አብረው ወድመዋል። ግን እዚህ ጆሃንስበርግ የፖሊስ ቁጥሩ ከፍ ስላለ ብዙ ደፍረው አልመጡም'' ብሏል። በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም በበኩላቸው ደቡብ አፍሪካውያን ወጣቶች ከሌላ ሃገራት የመጡ ዜጎች ስራችንን ቀምተውናል በሚል መነሻ እራሳቸውን በማደራጀት ሱቆች ላይ የመዝመት ሁኔታ ታይቷል ይላሉ። ''ከዚህ ጋር በተያያዘ ዜጎቻችን በስነልቦናም ይሁን ከዝርፊያው ጋር በተገናኘ የሚያጋጥማቸው ችግር አለ፤ ይህንንም ለመፍታት ከሃገሪቱ የጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር የሚቻለውን ሁሉ እየተደረገ ነው''። አክለውም ''በእኛ ማህበረሰብ በኩል በቂ የሆነ ከለላ በማድረግ ላይ እና የዜጎች ንብረት እንዳይዘረፍ በመከላከል በኩል የተሟላ አይደለም በሚል ቅሬታ አለ'' ብለዋል። • ደቡብ አፍሪቃዊቷን የቦክስ ቻምፒዮን የገደለው ተያዘ ብዙ ናይጄሪያውን እና የናይጄሪያውያን ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ የናይጄሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆፍሪ ኦንዬማ ''ማሰብ የተሳናቸው ወንጀለኞች'' የፈጸሙት ተግባር ነው በማለት መሰል ተግባራት በአስቸኳይ እንዲቆም አሳስበዋል። የውጭ ሃገር ዜጎች ንብረት የሆኑ ሱቆች መዘረፍና ማቃጠል የደቡብ አፍሪካ የዕለት ተዕለት አጋጣሚ እየሆነ መጥቷል። በቅርቡም መፍትሄ የሚያገኝ አይመስልም። ብዙዎችም እንዴት ደቡብ አፍሪካውያን የሌላ አፍሪካ ሃገር ዜጎች ላይ ጥቃት ያደርሳሉ? ብለው ቢጠይቁም ጉዳዩ በቀላሉ ምላሽ የሚያገኝ ነገር አይደለም። ምናልባት ስራ አጥ የሆነው የደቡብ አፍሪካ 28 በመቶ የሚሆነው ወጣት ስራ ቢያገኝ ይሄ ሁሉ ነገር በአንዴ ይቆም ነበር የሚሉም አልጠፉም።
news-55226711
https://www.bbc.com/amharic/news-55226711
ትግራይ ፡ መንግሥት የእርዳታ አቅርቦት ሥራን ሙሉ ለሙሉ እንደሚመራ አስታወቀ
ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተደረሰው ስምምነት የሚደረጉት የእርዳታ አቅርቦት ሥራዎች ሙሉ ለሙሉ በመንግሥት እንዲመራ ታሳቢ በማድረግ መሆኑ ተገለጸ።
ይህ የተነገረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይ የሆኑት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሲሆን በዚህ ሂደት የመንግሥት ሚና በማንም የሚተካ እንዳልሆነ አስረድተዋል። ይህንንም በተመለከተ አምባሳደር ሬድዋን በሰጡት ማብራሪያ ከተባበሩት መንግሥታት ጋር የተደረሰው ስምምነት የሚካሄዱት የእርዳታ አቅርቦት ሥራዎች በሙሉ በኢትዮጵያ መንግሥት እንዲመሩ የሚያደርግ መሆኑን ጠቅሰው "የትኛውም አካል የመንግሥትን ቦታ የሚተካ አይሆንም" ብለዋል። አምባሳደር ሬድዋን ጨምረውም በስምምነቱ የኢትዮጵያ መንግሥት የእርዳታ አቅርቦቱን ሥራ በመምራት የሚያስተባብር ሲሆን የእርዳታ ድርጅቶቹ በሚንቀሳቀሱባቸው ቦታዎች ሁሉ ስላለው ሁኔታ መንግሥት የሚሰጠውን መመሪያ ተቀብለው ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው አመልክተዋል። "ኢትዮጵያ ኃላፊነቱን የሚወጣ መንግሥት ያላት አገር በመሆኗ ሞግዚት አያስፈልጋትም" ያሉት አምባሳደሩ መንግሥት አስፈላጊውን የምግብና የህክምና አቀርቦቶች እርዳታ አቅርቦት ለትግራይ ክልል የሚያቀርብ መሆኑን አማባሳደር ሬድዋን ገልጸዋል። በዚሁ መግለጫ ላይ የተባበሩት መንግሥታት ሰራተኞች እንደተተኮሰባቸውና በቁጥጥርም ስር እንደዋሉም አስታውቀዋል። ጨምረውም መደረግ የነበረበት ነገር ሳይደረግ ቀርቷል ብሎ መንግሥት በሚያስብባቸው ሁኔታዎች ላይ ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ ይፈቅዳልም ብለዋል። በትግራይ ክልል የተከሰተውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ በርካታ ሰዎች ከቤታቸው ሸሽተው ወደ ጎረቤት አገር እንደተሰደዱና ሌሎች ደግሞ እዚያው ሆነው ለችግር መጋለጣቸውን የተባበሩት መንግሥታትና ሌሎች የእርዳታ ድርጅቶች ሲገልጹ ቆይተዋል። አነዚህ በአገር ውስጥ በችግር ላይ የሚገኙትን ሰዎች ለመርዳት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ መንግሥት አመቺ ሁኔታ እንዲፈጥር መስማማቱን ባለፈው ሳምንት ተገልጾ ነበር። ይህ በእንዲህ እንዳለም ወታደራዊ ግጭቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ ተቋርጠው የሚገኙትን የኤሌክትሪክ ኃይልና የቴሌኮም አገልግሎቶች መልሶ ለማስቀጠል እየተሰራ መሆኑን አምባሳደር ሬድዋን ተናግረዋል። በዚህም መሠረት እነዚህን አገልግሎቶች መልሶ ለማስጀመር መቀለን፣ አክሱምና አዲግራትን ጨምሮ ወደ ሌሎች አካባቢዎች ቡድን መላኩን ጠቁመዋል። በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የተገኙት የብሔራዊው የአደጋ ስጋት መከላከልና ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ጨምረው እንደተናገሩት ከግጭቱ ቀደም ብሎ በትግራይ ክልል 1.8 የሚሆኑ የሰብአዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች እንደነበሩ ገልጸው፤ አሁንም እርዳታ ለማቅረብ ይኸው ቁጥር እንደመነሻ መያዙን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት በከተሞች አካባቢ ከሚገኙት ዝቅተኛ ነዋሪዎች መካከል ከ20 እስከ 30 በመቶ የሚሆኑት የግብይት ስፍራዎች በአግባቡ ሥራ እስኪጀምሩ ድረስ የእርዳታ ድጋፍ እንደሚፈልጉም ተናግረዋል። በፌደራል መንግሥቱና የትግራይ ክልልን ሲያስተዳድር በነበረው ህወሓት መካከል ወታደራዊ ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ ለሳምንታት የዘለቀ ውጊያ መካሄዱ ይታወቃል። በዚህ ወቅትም ግጭቱን በመሸሽ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቤት ንብረታቸውን ትተው በአገር ውስጥና በጎረቤት አገር መጠለላቸውን የእርዳታ ድርጅቶች ይገልጻሉ። የክልሉ ዋና ከተማ መቀለ በፌደራል መንግሥት ሠራዊት ቁጥጥር ስር ከገባች በኋላ መንግሥት በክልሉ የተጎዱ መሰረተ ልማቶችን መልሶ መጠገንና በግጭቱ የተፈናቀሉ ሰዎችን መልሶ በማቋቋም ላይ ከተለያዩ ተቋማት ጋር እንደሚሰራ መግለጹ ይታወሳል። ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም እና አዲስዓለም ባሌማ (ዶ/ር) በፌደራል መንግሥቱ ከሚፈለጉት የህወሓት አመራሮች መካከል የሚገኙት አዲስዓለም ባሌማ (ዶ/ር) በቁጥጥሩ ስር እንዳሉም በዛሬው ዕለት በነበረው መግለጫ ተገልጿል። አዲስዓለም ባሌማ (ዶ/ር) በፖሊስ ቁጥጥር ስር መሆናቸውን ከመግለጽ ውጪ ስለተያዙበት ሁኔታ ዝርዝር ማብራሪያ አልሰጡም። በጋዜጣዊው መግለጫ ላይ ሁለቱ ከፍተኛ አመራሮች የት እንደሚገኙ ባይጠቁሙም ለፖሊስ ቃላቸውን መስጠታቸውንና ሕዝቡ "በቅርቡ" ግለሰቦቹ የሚሉትን እንደሚሰማ አመልክተዋል። አምባሳደር ሬድዋን በጠቀሱት መሰረት አዲስዓለም (ዶ/ር) ባለፈው ሳምንት እጃቸውን እንደሰጡ ከተነገረው የቀድሞዋ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ኬሪያ ኢብራሂም በመቀጠል በመንግሥት ቁጥጥር ስር ያሉ ሁለተኛው የህወሓት ከፍተኛ አመራር ናቸው። አዲስዓለም ባሌማ (ዶ/ር) ከክልሉ ምክትል የርዕሰ መስተዳደርነት ስልጣን በተጨማሪ በተለያዩ የፌደራልና የትግራይ ክልል ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ያገለገሉ ሲሆን በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነውም ሰርተዋል። መንግሥት ከዚህ ቀደም በተለያዩ ወንጀሎች እፈልጋቸዋለሁ ያላቸውን ከፍተኛ የህወሓት አመራሮችን ለመያዝ የእስር ትእዛዝ መውጣቱን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
news-46340517
https://www.bbc.com/amharic/news-46340517
በአለም ላይ በየቀኑ 137 ሴቶች በህይወት አጋሮቻቸውና በቤተሰቦቻቸው ይገደላሉ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው በዓለም ላይ በአማካኙ 137 ሴቶች በህይወት አጋራቸው፣ በፍቅረኞቻቸውና በቤተሰቦቻቸው በየቀኑ እንደሚገደሉ ነው።
ፅሁፉ እንደሚያሳው በከፍተኛ ሁኔታ ሴት የምትገደልበት ቦታ ቤቷ እንደሆነ ነው። በባለፈው ዓመት ከተገደሉት 87 ሺ ሴቶች መካከል ግማሹ ህይወታቸው የጠፋው የቅርብ በሆኑ ቤተሰቦቻቸው ሲሆን 30 ሺዎቹ በህይወት አጋራቸው እንዲሁም 20 ሺዎቹ በዘመዶቻቸው እንደሆነ መረጃው ያሳያል። •የተነጠቀ ልጅነት •"ማንም መብታችንን ሊሰጠን ስለማይችል፤ ሴቶች ማንንም ሳይጠብቁ በራሳቸው መታገል አለባቸው" •"የመከላከያ ሚኒስቴርን በተሻለ መልኩ መምራት ይቻላል" ኢንጂነር አይሻ መሀመድ የወንዶች ግድያ ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ላይ ነው የተባበሩት መንግሥታት መረጃ ጨምሮ እንደሚያሳየው ከሴቶች በላይ በአራት እጥፍ ወንዶች በግድያ ህይወታቸውን ያጣሉ ይኼው መረጃ እንደሚያሳየው ከአስሩ ግድያዎች ስምንቱን የሚፈፅሙት ወንዶች መሆናቸውን ነው። ነገር ግን ሪፖርቱ እንደሚያሳየው ግድያ ከሚፈፀማባቸው አስሩ ስምንቱ ሴቶች ሲሆኑ ጥቃቱም የሚደርሰው በፍቅረኞቻቸውና በህይወት አጋሮቻቸው ነው። "በህይወት አጋሮቻቸውና በፍቅረኞቻቸው የሚገደሉ ሴቶች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን በሴቶችም ላይ ከፍተኛ ጫና እያደረሰ እንደሆነ" ሪፖርቱ ያትታል። አርባ ሴቶች፣ 21 ሃገራት፣ አንድ ቀን ከአውሮፓያኑ ጥቅምት 1 ጀምሮ የተለያዩ የሚዲያ ሽፋኖችን በመዳሰስ ከፆታቸው ጋር በተያያዘ በ21 ሃገራት ላይ የተገደሉ ሴቶች ቁጥር 47ነው። እነዚህ ግድያዎች አሁንም ምርመራ ላይ ናቸው። Women whose killings were reported by the media on 1 October 2018 በሀገሪቱ ሚዲያ ከተዘገቡና የሀገሪቱ ባለስልጣናትም ካረጋገጧቸው አምስት ግድያዎች እነሆ ጁዲት ቼሳንግ፣ 22፣ ኬንያ ጥቅምት ወር ላይ ጁዲት ቼሳንግና እህቷ ናንሲ የማሽላ እህላቸውን በማረስ ላይ ነበሩ። የሶስት ልጆች እናት የሆነችው ጁዲት ከባለቤቷ ላባን ካሙረን ጋር የተለያየች ሲሆን ወደ ቤተሰቦቿ መንደር ለመመለስም ወሰነች። እህትማማቾቹ የተለመደ ተግባራቸውን ማከናወን በጀመሩበት ወቅት የፈታችው ባለቤቷ ደርሶ ጁዲትን ገደላት። የአካባቢው ፖሊስ እንደገለፀው ግለሰቡ በአካባቢው ማህበረሰብ ተገድሏል። ይኸው ሪፖርት ጨምሮ እንደጠቀሰው አፍሪካም ውስጥ በትዳር አጋሮቻቸው ወይም በቤተሰቦቻቸው የሚገደሉ ሴቶች ቁጥር ከፍተኛ ሲሆን፤ ከ100 ሺ ሰዎች 3.1 እንደሆነም ተጠቅሷል። የባለፈው አመት መረጃ እንደሚያሳየው እስያ በሴቶች ግድያ ከፍተኛ ቁጥር መያዟን ነው። በባለፈው አመት 20 ሺ ሴቶች ተገድለዋል። ኔሃ ሻራድ ቻውዱሪ፣ 18፣ ህንድ ኔሃ ሻራድ ቻውዱሪ በ18 አመቷ የክብር ግድያ ተብሎ በሚጠራው ሳትገደል እንዳልቀረች ተገምቷል። በተገደለችበት ወቅት ከወንድ ጓደኛዋ ጋር የተገናኙበትን ዕለት እያከበረች የነበረ ሲሆን፤ ግንኙነታቸውንም ቤተሰቦቿ ይቃወሙ ነበር ተብሏል። በዛችው ዕለትም ወላጆቿና አንድ የወንድ ዘመድም ቤት እንደገባች በመግደል ተወንጅለዋል። ምርመራው የቀጠለ ሲሆን፤ ቢቢሲ ከቤተሰቦቿ ጠበቃ እንደተረዳው የቀረበባቸውን ክስ ሊክዱ እንደተዘጋጁ ነው። በመቶዎች የሚቆጠሩ ሴቶች ቤተሰብ ከማይፈቅደው ወንድ ጋር የፍቅር ግንኙነትና ትዳር በመመስረትና ይገደላሉ። ይህ የክብር (ኦነር ኪሊንግ) ተብሎ የሚጠራው ግድያ ሪፖርት ስለማይደረግም መረጃ ማግኘት አስቸጋሪ ነው። ዘይናብ፣ ሴካንቫን፣ 24፣ ኢራን ዘይናብ ሴካንቫን ባሏን ገድላለች በሚል በኢራን ባለስልጣኖች ተገድላለች። ዘይናብ በሰሜናዊ ምዕራብ ኢራን ወግ አጥባቂ ከሆኑ ቤተሰቦች ሲሆን የተወለደችው፤ ዝርያዋም ከኩርዲሽ ወገን ነው። ገና በህፃንነቷ ከቤተሰቦቿ ጠፍታ የሄደችው ዘይናብ፤ የተሻለ ህይወትንም ፍለጋ አገባች። አምነስቲ እንደገለፀው ባለቤቷ አካላዊ ጥቃትና ድብደባ ያደርስባት የነበረ ሲሆን ፍችም በተደጋጋሚ ብትጠይቅ ምላሽ አላገኘችም፤ ፖሊስ ጥያቄዋን ችላ ብሎታል። በ17 ዓመቷም ባሏን በመግደል ወንጀል ተከሰሰች። አምነስቲን ጨምሮ ደጋፊዎቿ እንደሚሉት ባለቤቷን መግደሏን እንድታምን ፖሊሶች ድብደባና እንግልት ያደረሱባት ሲሆን፤ ትክክለኛ ፍርድም አላገኘችም። ሪፖርቱ ጨምሮ እንደገለፀው የህይወት አጋሮቻቸውን የገደሉ ሴቶች ከፍተኛ የሆነ አካላዊ ጥቃት እንደሚደርስባቸው ነው። ወንድ ጥቃት አድራሾች በበኩላቸው "መቆጣጠር መፈለግ፣ ቅናትና መተው" ሴቶችን ለመግደል የተነሳሱባቸው ምክንያቶች እንደሆኑም ተጠቅሷል። ሳንድራ ሉሲያ ሐመር ሞራ፣ 39፣ ብራዚል ሳንድራ ሉሲያ ሐመር ሞራ ከአጉያር ሪቤይሮ በ16 ዓመቷ ተጋባች። ባሏም የገደላት ከተፋቱ ከአምስት ወራት በኋላ ነው። ፖሊስ ለቢቢሲ ብራዚል እንዳሳወቀው አንገቷ ላይ በጩቤ ተወግታ ነው የተገደለችው። ገዳዩነ ባለቤቱን መግደሉን በስልኩ ቪዲዮ በመቅረፅ ተናዟል። በቪዲዮውም ላይ እንደሚታየው ሳንድራ ሌላ ፍቅረኛ እንደያዘችና እንደካደችውም ተናግሯል። መታሰር እንደማይፈልግና " የአምላክን መንግሥት አብረው እንደሚወርሱ ጠቅሶ መኝታ ክፍላቸው ውስጥ ራሱን ገድሎ ተገኝቷል። የሳንድራ ጉዳይ "ገድሎ ራስን ማጥፋት" የሚባል ሲሆን፤ይህም አንድ ሰው ሰዎችን ገድሎ ራሱን የሚያጠፋበት ማለት ነው። ሜሪ አሚል፣ 36፣ ፈረንሳይ ሜሪ አሚ በቀድሞ ባለቤቷ ሴባስቲየን ቫይላት በጩቤ ተወግታ ተገደለች። ባልና ሚስቱ የተፋቱት ከአራት የጋብቻ አመታት በኋላ ነው። ለፖሊስ ከመናዘዙ በፊት በጩቤ የገደላት ሲሆን፤ ከጥቂት ቀናት በኋላም በእስር ቤት ራሱን ገድሎ ተገኘ። ሜሪ አሚል በምትነግድበት የልብስ ሱቅም አካባቢ የተለያዩ ግለሰቦች የማስታወሻ አበባ አስቀምጠዋል። ምንም እንኳን እነዚህ የግድያ ዜናዎች በሚዲያ ቢሰሙም ቁጥራቸው በውል የማይታቅ ሴቶች ግድያ ሪፓርትና ምርመራ ሳይደረግበት እንደዋዛ ያልፋል። ይህንንም በማየት የሴቶች ግድያ ምን ቢሆን ነው ሪፖርት ለመደረግ የሚበቃው የሚል ጥያቄ ያስነሳል። ሪፖረተር፦ ክሩፓ ፓዲ ፕሮዲውሰር፦ ጆርጊና ፔርስ ምርምር፦ ቢቢሲ ሞኒተሪንግ
45669200
https://www.bbc.com/amharic/45669200
በኢትዮጵያ ህግ ሺሻ ማጨስ ህገ- ወጥ ነውን?
ሰሞኑን በአዲስ አበባ በተከሰተው ቀውስ የሟቾች ቁጥር 28 መድረሱን ፖሊስ ገልጿል። ቀውሱንም ተከትሎ በአዲስ አበባ የተለያዩ መጠጥ ቤቶችን ጨምሮ የመዝናኛ ቦታዎች ወደ ሦስት ሺ ሁለት መቶ የሚሆኑ ሰዎች በጅምላ እንደታሰሩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት አምነስቲ አስታውቋል።
ፖሊስ በበኩሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፆው መቶ ሰባ አራት ለፍርድ እንደሚቀርቡ እንዲሁም አንድ ሺ ሁለት መቶ አራት ሰዎችን ለማነፅና ለማስተማር በሚል ወደ ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ ለተሐድሶ ስልጠና ተልከዋል። •ጅምላ እሥር በአዲስ አበባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር የሞከሩትን እንዳሰረ ቢገልፅም አምነስቲ በበኩሉ እስሩን አውግዞ በአሁኑ ሰዓት እየታዩ ያሉ ለውጦችን ወደ ኋላ የሚጎትት ነው ብሏል። በሺዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦች አዲስ አበባ ላይ መታስራቸው በተለይም ከሺሻ ቤቶችና ጫት ቤቶች መወሰዳቸው ጋር ተያይዞ ሺሻ ህገ ወጥ ነው? ከሆነስ ግለሰቦቹ ወደ ፍርድ ቤት ለምን አልቀረቡም? ወደ ተሐድሶ ካምፕ ለምንድን ነው? የሚላኩት የሚሉ ክርክሮች መነሳት ጀምረዋል። የኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድሃኒት እና የጤና ክብካቤ አስተዳደር ባለስልጣን የትምባሆ ቁጥጥር መመሪያ መጋቢት ወር 2007 ዓ.ም ያወጣ ሲሆን፤ በመመሪያውም መሰረት የትምባሆ ምርቶች በማለት የሚዘረዝራቸው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ከትምባሆ ቅጠል የተዘጋጁ በማጨስ፣ በመሳብ፣ በማኘክ፣ በማሽተት ወይም በሌላ መንገድ የሚወሰድ ማንኛውም ንጥረ ነገር ሆኖ የጋያ ወይም የሺሻ ትምባሆን፣ የኤሌክትሮኒክ ኒኮቲን ይጨምራል። የመመሪያው ዓላማም በዝርዝር የተቀመጠ ሲሆን ትምባሆን በመጠቀምና ለትምባሆ ጢስ በመጋለጥ በማህበረሰቡ ላይ የሚደርሰውን የጤና፣ የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና አካባቢያዊ ጉዳቶችን ለመከላከልና ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የፈረመማቻቸውን የትምባሆ ቁጥጥር ኮንቬንሽንም ለማስፈፀም ነው። •በእርጥብ ሳርና ቅጠል ጥቃትን ያስቆሙ አባቶች መመሪያው ከባለስልጣኑ ፈቃድ ሳያገኝ የትምባሆ ምርትን ለንግድ ተግባር ወደ ሃገር ውስጥ ማስገባት፣ ማከፋፈል ወይም በጅምላ መሸጥ እንደማይቻል ያስቀመጠ ሲሆን፤ የትምባሆ ምርትን ማስተዋወቅና ስፖንሰር ማድረግ በፍፁም የተከለከለ እንደሆነ በግልፅ አስቀምጧል። በዚህም መሰረት ማጨስ የተከለከለባቸው ቦታዎች ተብለው የተቀመጡት፤ በህዝብ መጓጓዣዎች፣ በጤናና በትምህርት ተቋማት፣ በምግብ ቤቶች፣ በመዝናኛ ቦታዎች፣ በአውሮፕላን ማረፊያ፣ በፋብሪካዎችና በህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሾች ናቸው። ምንም እንኳን በነዚህ ቦታዎች ቢከለከልም ከትምህርት ተቋማት፣ ከመንግሥት መስሪያ ቤትና ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት አገልግሎት ከሚሰጡ ተቋማት ውጭ ለማጨስ የተከለለ ወይም የተሰየመ ክፍል ለብቻው የአየር ማናፈሻ ( ventilation) የተገጠመለት ከሆነ በሌሎቹ ቦታዎች ማጨስ እንደሚቻል ተቀምጧል። በዩኒቨርስቲ፣ በኮሌጅና በሌሎች ተቋማት የተከለለ ክፍል ካለ ትምባሆንም ሆነ የትምባሆን ምርት መገልገል እንደሚቻልም መመሪያው ያትታል። ካለፉት አስር ዓመት ሺሻ ቤቶች ህገ-ወጥ ተብለው ሲታሸጉና እቃዎችም የተወሰዱ ሲሆን፤ በተመሳሳይም ጫት ቤቶችንም ጫት መሸጥ ነው እንጂ የማስቃም ፈቃድ የላችሁም በሚል ሲዘጉ እንደነበር የህግ ባለሙያና ጠበቃ የሆኑት አቶ ታምራት ኪዳነ ማርያም ይናገራሉ። ምንም እንኳን ብዙዎቹ ንግድ ቤቶች ፍቃድ አግኝተው በዛ መሰረት እየሰሩ ያሉ ሲሆን፤ "ሁልጊዜም የሚነሳው ጭቅጭቅ እንዲሸጡ ነው እንጂ እንዲያስቅሙ አልተፈቀደላቸውም" የሚል እንደሆነ ባለሙያው ይናገራሉ። "ትምባሆ ማጨስ የተፈቀዱባቸው ቦታዎች በመመሪያው በግልፅ የተቀመጡ ሲሆን፤ ስለ ጫት ግን የት መቃም እንደማይቻል የተደነገገ ደንብ የለም" ይላሉ። ምናልባትም ነጋዴ የተሰጠው ፈቃድ ለመቸርቸር ከሆነ ሰዎችን ሰብስቦ የሚያስቅም ከሆነ የተሰጠውን ፈቃድ በመተላለፍ ሊጠየቅ ይችላል። የደንብ መተላለፍ ወንጀሎች ቀላል ሲሆኑ ለምሳሌ ትምባሆ ተገቢ ባልሆነ ሁኔታ ማጨስ አብዛኛውን ጊዜ በገንዘብ ቅጣት የሚታለፉ ናቸው። የንግድ ቤቶቹ ግን ህገ-ወጥ (ከተፈቀደው ውጭ) ተግባር በማከናወን ጠንከር ያሉ ቅጣት ሊጣልባቸው ይችላል። •ስለተፈፀመው ጥቃት እስካሁን የምናውቀው እነዚህን ደንቦች ካልተከተሉ ከአስተዳደራዊ እርምጃ ጀምሮ፣ ከንግድ ፍቃድ መሰረዝ በወንጀል ተጠያቂ እስከማድረግ መመሪያው የሚጠቅስ ሲሆን፤ ተጠቃሚዎች ደንቡን ተላልፈው ቢገኙ ወይም ስለ ተጠቃሚዎች መመሪያው የሚያትተው ነገር የለም። መመሪያው ተጠቃሚዎችን ምንም ካላለ በምን የህግ ማዕቀፍ ነው የታሰሩትስ ወይም ተጠያቂ የሚሆኑት? ሰሞኑን አዲስ አበባ የታፈሱ ሰዎች ከሺሻ ማጨስ ጋር መያያዙንም አስመልክቶ ባለሙያው "ተጠቃሚዎቹ በምን አግባብ ነው የሚታሰሩት፤ ባለቤቶቹን በህገ-ወጥ (ያለ ፈቃድ) መነገድ በሚል ተጠያቂ ሊሆኑ ይችል ይሆናል" የሚሉት የህግ ባለሙያው "ተጠቃሚዎችን አጭሳችኋል ብሎ ለመያዝ በጣም ከባድ ነው" ይላሉ። በተከለከለ ቦታ ትምባሆ አጭሳችኋል በሚል ከሆነ በገንዘብ ቅጣት ወይም በመደበኛ ፍርድ ቤት ሳይሆን በከተማው ፍርድ ቤት ደንብን በመተላለፍ ሊጠየቁ እንደሚችሉም ይናገራሉ። "ለማፈስና ወስዶ ለማሰር ምንም መሰረት የለውም፤ ደንብ ተላልፈዋል የሚል አግባብ ካለ በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረብ ይኖርባቸዋል። ከከተማ አርቆ ወደ ሌላ ቦታ ለመውሰድ የሚያስችል ህግ የለም፤ ከፀጥታ ጋር የሚገናኝ ወይም ሌላ የፖለቲካ ምክንያት ከሌለው እንዲህ አይነት ህግ የለም" ይላሉ ባለሙያው። ለማነፅ፣ ለማስተማር የሚባለው ሃሳብ ባለሙያው እንደ በጎ ቢያዩትም ይህንን ለማድረግ ህግ ያስፈልጋል ማስተማርና መመለስ የሚችለው ፍርድ ቤት እንደሆነ አፅንኦት ሰጥተው ይናገራሉ። "ጥፋተኛ ብሎ ቀጥቶ፤ በዚህ አይነት መልኩ ይታረሙ የሚል የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ፍርድ ቤት ማዘዝ ይኖርበታል። ነገር ግን አስፈፃሚው አካል (መንግሥት) ፍርድ ቤቱ እንዲህ አይነት ውሳኔ ሳይወስን በራሱ ጊዜ ባለስልጣናት ተነስተው እነዚህን ልጆች እናርማቸው፣ እንኮትኩታቸው ብሎ ወስዶ ለማረም መሞከር ትክክል አይደለም። ህጋዊም አይደለም።"
news-52453522
https://www.bbc.com/amharic/news-52453522
ኮሮናቫይረስ፡ ህንድ ከቻይና ልትፈጽመው የነበረውን ፈጣን መመርመሪያ መሳሪያዎችን ግዥ ሰረዘች
ህንድ ከቻይና ልትፈጽመው የነበረውን ወደ ግማሽ ሚሊየን የሚጠጋ ፈጣን የመመርመሪያ መሳሪያ ግዢ ሰረዘች።
ምክንያቱ ደግሞ መሳሪያዎቹ በሥራ ላይ የጥራት ጉድለት ስለተገኘባቸው ነው። ዴልሂም በተለያዩ ግዛቶች በአገልግሎት ላይ ሲውሉ የነበሩ የመመርመሪያ መሳሪያዎች ሥራ እንዲያቋረጡ አድርጋለች። የመመርመሪያ መሳሪያዎቹ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ደም ውስጥ የሚገኘውን በሽታ መከላከያ (አንቲ ቦዲስ) የመለየት አቅም ሊኖራቸው ይገባ ነበር። ውጤቱንም ለማሳወቅ 30 ደቂቃ የሚወስድ ሲሆን ባለስልጣናት በተወሰነ አካባቢ ያለውን የቫይረሱን ስርጭት በፍጥነት ለመረዳት ያስችላል ተብሎ ነበር። ሆኖም ፈጣን መመርመሪያው የኮሮናቫይረስን መመርመር አልቻለም። በርካታ ተመራማሪዎችም መመርመሪያ መሳሪያዎቹን መጠቀም አሳስቧቸዋል። ይሁን እንጂ ቻይና በህንድ የቀረበውን ክስ ውድቅ አድርጋዋለች። "ከቻይና የሚመጡ የህክምና ምርቶች ጥራት ቅድሚያ ተሰጥቷቸዋል። የተወሰኑ ግለሰቦች የቻይና ምርቶችን ለማጣጣል እና ሐሰተኛ ለማድረግ መሞከር እንዲሁም በጭፍን ጥላቻ መመልከት ፍትሃዊ ያልሆነና ኃላፊነት የጎደለው ነው" ሲሉ የቻይና ኤምባሲ ቃል አቀባይ ጂ ሮንግ በሰጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል። ህንድ በቂ ምርመራ እያደረገች እንዳልሆነ ያሳሰባቸው በርካታ ግዛቶች ግን የህንድ የህክምና ጥናት ካውንስል (ICMR) የመመርመሪያ መሳሪያዎቹን ለመጠቀም እንዲፈቅድላቸው ግፊት ሲያደርጉ ነበር። ተቋሙ በመጀመሪያ ላይ አመንትቶ የነበረ ቢሆንም ከሁለት የቻይና ካምፓኒዎች መሳሪያዎቹ እንዲገቡ መንገድ አመቻችቷል። ከትንሽ ጊዜ በኋላ ግን ግዛቶቹ መሳሪያውን በኮሮናቫይረስ መያዙ የተረጋገጠ ሰው ላይ መሞከራቸውንና ውጤቱም ከቫይረሱ ነጻ መሆኑን (ኔጋቲቭ) ማሳየቱን በመግለጽ፤ የመመርመሪያ መሳሪያዎቹ ትክክለኛነት 5 በመቶ ብቻ ነው ሲሉ ቅሬታ ማቅረብ መጀመራቸው ተነግረወል። ከዚያም መመርመሪያ መሳሪያዎቹ በተቋሙ በተደረገ ፍተሻ ጥራት የሌላቸው መሆናቸው ሊታወቅ ችሏል። ሰኞ ዕለት የዴልሂ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወጣውን ገንዘብ በመጥቀስ መንግሥት ለመሳሪያዎቹ ከልክ በላይ ከፍሏል ካለ በኋላ ጉዳዩ የበለጠ ተወሳስቧል። ይሁን እንጅ ባለሥልጣናት የመመርመሪያ መሳሪያዎቹን ለመግዛት ቅድመ ክፍያ ስላልፈጸሙና የማጓጓዙም ሥራ በመሰረዙ መንግሥት ምንም አይከስርም ሲሉ ለአገሪቷ መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል።
55777882
https://www.bbc.com/amharic/55777882
የዩኬ አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ከቀደመው የከፋ ነው ተባለ
በዩናይትድ ኪንግደም የተገኘው አዲስ የቫይረስ ዝርያ ከቀደመው የከፋ እንደሆነ ተገለጸ።
ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን የምርምር ውጤትን አጣቅሰው እንደተናገሩት፤ አዲሱ ዝርያ የከፋ እንደሆነ ምልክቶች ታይተዋል። ምርምሩ የተካሄደው በቀደመው ኮሮናቫይረስ ሳቢያ የሞቱ ሰዎችን ቁጥር አዲሱ ዝርያ ከገደላቸው ጋር በማወዳደር ነው። በፍጥነት የሚተላለፈው ዝርያ በዩኬ እየተሰራጨ ይገኛል። "ቫይረሱ በፍጥነት ከመተላለፉም በላይ በከፍተኛ ሁኔታ ገዳይም ነው" ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሩ በሰጡት መግለጫ። ፐብሊክ ኸልዝ አንግላንድ፣ ኢምፔርያል ኮሌጅ ኦፍ ለንደን እና ሌሎችም ግዙፍ የሕክምና ተቋሞች አዲሱ ዝርያ ምን ያህል ገዳይ እንደሆነ ጥናት እየሠሩ ነው። የጥናቱ የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት፤ አዲሱ ዝርያ ቀድሞ ከነበረው የኮሮናቫይረስ አይነት በበለጠ አደገኛ መሆኑን ያሳያል። የዩኬ መንግሥት የጤና አማካሪ ሰር ፓትሪክ ቫላንስ መረጃው "ገና አልተጠናከረም" ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል። ስለ አዲሱ ዝርያ ግልጽ መረጃ ለማግኘት ተጨማሪ ምርምሮች እንደሚያስፈልጉ ጠቁመዋል። ቀደም ሲል የተሠራ ጥናት ቫይረሱ ከ30% እስከ 70% ተላላፊ እንደሆነ የሚያሳይ ሲሆን፤ አዲሱ ዝርያ ከዚህ 30 በመቶ በላቀ ሁኔታ እንደሚተላለፍ ተጠቅሷል። ይህ ማለት 1,000 በ60ዎቹ እድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎች በቀድሞው ኮሮናቫይረስ ቢያዙ የሚሞቱት 10ሩ ናቸው። ነገር ግን በአዲሱ ዝርያ ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 13 ከፍ ይላል። መስከረም ላይ የተገኘው አዲሱ ዝርያ አሁን በሰዎች ላይ በተደጋጋሚ የሚስተዋል ወረርሽኝ ሆኗል። የፋይዘር እንዲሁም የኦክስፎርድና አስትራዜኒካ ክትባቶች በዩኬ የተከሰተውን አዲስ ዝርያ ይከላከላሉ ተብሎ ይታመናል። ነገር ግን በብራዚል እና በደቡብ አፍሪካ የተገኙት አዲስ ዝርያዎች አሳሳቢ እንደሆኑ የጤና ባለሙያዎች ጠቁመዋል።
news-45795864
https://www.bbc.com/amharic/news-45795864
አፍሪካዊያን ሌሎች የአፍሪካ ሃገራትን መጎብኘት ለምን ይከብዳቸዋል?
ናይጄሪያዊው ቁጥር አንድ የአፍሪካ ባለሃብት አሊኮ ዳንጎቴ በአንድ ወቅት ሲናገሩ፤ በአህጉሪቱ ውስጥ ወደ ሚገኙ ሃገራት ለመጓዝ የ38 ሃገራት ቪዛ ግድ ይለኛል ብለው ነበር። አብዛኛው የአውሮፓ ሃገራት ዜጎች ግን ወደ ብዙ የአፍሪካ ሃገራት ያለ ቪዛ መጓዝ ይችላሉ።
እየተገባደደ ባለው የፈረንጆቹ ዓመት የአፍሪካ ህብረት የአባል ሃገራት ዜጎች ወደ አፍሪካ ሃገራት ጉዞ ሲያደርጉ ይጠየቁ የነበረውን ቪዛ ለማስቀረት ዕቅድ ነበረው። ከ5 ዓመታት በፊት የተደረሰው ስምምነት በቀጣዮቹ 50 ዓመታት ውስጥ ለማሳካት ከተሰበው ራዕይ እና ፍኖተ ካርታ መካከል ዋነኛው ነበር። • መቀመጫቸውን ለማደለብ የሚታትሩ ሴቶች እየሞቱ ነው • ሴቶችን እየቆራረጡ ሲሸጡ የነበሩ በቁጥጥር ሥር ዋሉ • የአስር ደቂቃ እንቅስቃሴ የማስታወስ ችሎታን እንዴት ይጨምራል? እስካሁን ግን በምስራቅ አፍሪካ በህንድ ውቅያኖስ ላይ የምትገኘዋ አፍሪካዊት ሃገር ሲሼልስ ብቻ ናት ሁሉም የአፍሪካ ሃገራት ዜጎች ያለ ቪዛ ሊጎበኟት የሚችሉት። በቅርቡ የአፍሪካ ህብረት ያደረገው ጥናት እንደሚያሳየው፤ አፍሪካዊያን ያለ ቪዛ ሊጓዙ የሚችሉት 22 በመቶ ወደሚሆኑ የአፍሪካ ሃገራት ብቻ ነው። ኢትዮጵያውያን ደግሞ ያለ ቪዛ ወይም በመዳረሻ ቪዛ ሊጎበኟቸው የሚችሏቸው ሃገራት ኬንያ፣ ሲሼልስ፣ ዩጋንዳ፣ ቶጎ፣ ሩዋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሞሪሺየስ፣ ሞሪታኒያ፣ ማደጋስካር፣ ጊኒ ቢሳሁ፣ ጂቡቲ፣ ኮሞሮስ፣ ኬፕ ቨርድ እና ቡሩንዲ ናቸው። የአፍሪካ ህብረት ልክ እንደ የአውሮፓ ህብረት ሃገራት ሁሉ ድንበር አልባ አፍሪካዊ አሃጉር በመፍጠረ 1.2 ቢሊዮን ህዝብ በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ ይፈልጋል። ይሁን እንጂ ይህን እቅድ ለማሳካት በርካታ ውጣውረዶች ተጋርጠውበታል። 55 የአፍሪካ ሃገራትን የጎበኘው ደቡብ አፍሪካዊው ጦማሪ ኬቺ ናዝማ ''መሪዎቻችን በቀኝ ግዛት ተሰምሮ የተሰጣቸውን ድንበር ላለማስደፈር ብዙ ርቀት ይጓዛሉ'' ሲል የአፍሪካን መሪዎች ይተቻል። ከአፍሪካ ሃገራት እንደ ደቡብ አፍሪካ ሌሎች አፍሪካውያን ወደ ሃገሯ እንዳይገቡ የሚከለክል፤ እንዲሁም ለተቀረው ዓለም በሩንን የሚክፈት የለም። 28 የአውሮፓ ሃገራት ዜጎች ወደ ደቡብ አፍሪካ ያለ ቪዛ መጓዝ ይችላሉ። ደቡብ አፍሪካ ለ15 አፍሪካውያን ሃገራት ብቻ ነው በሯን ክፍት ያደረገችው። የአፍሪካውያን ፓስፖርት ናሚቢያ፣ ሞሪሺየስ፣ ጋና፣ ሩዋንዳ፣ ቤኒን፣ ኬንያ እና እንዲሁም ኢትዮጵያ በቅርቡ ሌሎች አፍሪካውያን ዜጎች ወደ ሃገሮቻቸው እንዲገቡ የጉዞ መስፈርቶችን ቀንሰዋል። የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ሃገራትን ፓስፖርት የሚተካ ''አፍሪካን ፓስፖርት'' (የአፍሪካውያን ፓስፖርት) በተሰኝ አዲስ ፓስፖርት እ.አ.አ. በ2016 ለመቀየር እቅድ ነበረው። እቅዱ ባይሳካም የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ እና የቀድሞ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ኢድሪስ ዴይባ የፓስፖርቱ ባለቤት ለመሆን ችለዋል። የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ እና የቀድሞ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ኢድሪስ ዴይባ እ.አ.አ. 2016 ላይ የፓስፖርቱ ባለቤት ለመሆን ችለዋል። የጉዞወጪ መናር አፍሪካዊያን ሌሎች የአፍሪካ ሃገራትን እንዳይጎበኙ ተግዳሮት የሚሆንባቸው ሌላኛው ምክንያት ደግሞ በቂ የመንገደኞች የበረራ አገልግሎቶተች አለመኖራቸው ነው። ቢገኙም ዋጋቸው የሚቀመስ አይደለም። በዚህ ላይ ደግሞ በየመዳረሻቸው ለቪዛ የተጋነነ ዋጋ ይጠየቃሉ። ጅቡቲ ለአንድ ሰው ቪዛ 90 ዶላር ትጠይቃለች። የሸንገን ቪዛ ለማግኘት ግን ሚከፈለው 75 ዶላር ብቻ ሲሆን፤ 26 አውሮፓ ሃገራትን መጎብኘትም ያስችላል።
news-53374688
https://www.bbc.com/amharic/news-53374688
በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ የሚጫወተውን ኮከቧን የማታውቀው አገር
ኩባ በዓለማችን የኮሚዩኒዝም ሥርዓት ሙሉ በሙሉ ካልተወደገባቸው ጥቂት አገራት አንዷ ናት።
የኩባ ዜጎች ቀሪው ዓለም በስፋት የሚተቀምባቸውን መረጃና የግንኑነት ዘዴዎች በቀላሉ ኤኣገኙም። በዚህም በይነ መረብ እንደልብ ማግኘት አይታሰብም። ቢሆንም አንድ እናት ግን ይህ አላገዳትም፤ በአንድ ዶላር የገዛችውን ካርድ ፍቃ ወደ ጉግል በመክፈት በመፈለጊያው ሳጥን ውስጥ 'ኦኔል ኸርናንዴዝ' ስትል ትተይባለች። በፕሪሚዬር ሊግ ታሪክ የመጀመሪያው ኩባዊ የሆነው ተጫዋች እናት እንዲህ ነው ስለልጇ ሁኔታ የምታጣራው። የ27 ዓመቱ የኖርዊች ቡድን የክንፍ መስመር ተጫዋች ኸርናንዴዝ የተወለደው በኩባዋ ሞሮን ከተማ ውስጥ ነው። ከተማዋ 'ፌርማታ'ናት። ሰዎች ከአንድ ከተማ ወደ ሌላ ከተማ ሲያቀኑ አረፍ የሚሉባትና ሻይ ቡና የሚቀማምሱባት። ኸርናንዴዝም እትብቱን በቀበረባት ከተማ ብዙም መቆየት አልሻተም። ገና በስድስት ዓመቱ ነበር ይህችን ከተማ ጥሎ የወጣው። እናቱ አንድ ጀርመናዊ ቱሪስት ተዋወቀች። ከዓመት በኋላ ጋብቻ ፈጽማ ልጆቿን ኩባ ውስጥ በመተው ወደ ጀርመን አቀናች። በኀወላም ከሁለት ዓመት በኋላ ኸርናንዴዝና እህት ወንድሞቹም ወደ ጀርመን ሄዱ። ይህ ውሳኔ የ21 ዓመቷን እናትና የስድስት ዓመቱን ኸርናንዴዝ ሕይወት ቀየረ። የኸርናንዴዝ እንጀራ አባት የእግር ኳስ አሰልጣኝ ነበር። አንድ የሕፃናት ቡድን የተቀላቀለው በእናቱ የስፓኒስ ቁጣና ጩኸት እየታገዘ ኸርናንዴዝ ኳስ እየገፋ በክንፍ በኩል መብረሩን ቀጠለ። በአውሮፓውያኑ 2010 የ17 ዓመቱ ኸርናንዴዝ ለመጀመሪያ ጊዜ የፕሮፌሽናል እግር ኳስ ጉዞውን 'ሀ' ብሎ ጀመረ። ለጀርመን ከ18 ዓመት በታች ቡድንም መመረጥ ቻለ። የቀድሞው የባየርን ሚዩኒክ እና የሊቨርፑል ተከላካይ የነበሩት ክርስትያን ዚግ ታዳጊውን ኦኔልን አሰልጥነውታል። "ኦኔል ወጣት እያለ ጠንካራ ሠራተኛ ነበር" ይላሉ። ኦኔል ኸርናንዴዝ ከጀርመኑ ኢንትራክት ብሮንሽዌግ በ2.5 ሚሊዮን ዩሮ ኖርዊችን የተቀላቀለው በመስከረም ወር በ2018 ነበር። ኦኔል ለእንግሊዝኛ ባዕድ ነበር። ነገር ግን ልክ በልጅነቱ ከስፔንኛ ወደ ጀርመንኛ እንደተሸጋገረው ሁሉ እንግሊዝኛን መሽምደድ ያዘ። በመጀመሪያው ዓመት ብቻ 8 ጎሎችን አስቆጠረ፤ 10 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀበለ። የቻምፒዮንሺፑ ክለብ ኖርዊች፤ በኦኔልና በቡድን አጋሮቹ ታግዞ ጉዞ ሽቅብ ወደ ፕሪሚዬር ሊግ አደረገ። ኦኔል ኸርናንዴዝ ኖርዊች ከሊቨርፑል ጋር በነበረው ጨዋታ ተቀይሮ ሲገባ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግን ኳስ የነካ የመጀመሪያው ኩባዊ ሆነ። ነገር ግን ኩባውያን ስለ ኮከቡ የሚያውቁት እምብዛም ነው። የኸርናንዴዝ ኦኔል እናት እናቱ፤ ኸርናንዴዝ ከልጅነቱ ጀምሮ ለኩባ ብሔራዊ ቡድን መጫወት ይሻ እንደነበር ትናገራለች። እናቱ የኦኔል ወኪል በመሆኗ ከኩባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር ትወያያለች። "ወደ ሃቫና ሄጄ ብዙ ጊዜ ስብሰባ አድርጊያለሁ፤ እስካሁን ድረስ ለምን ለብሔራዊ ቡድን እንዳልመረጡት ግን አይገባኝም።" ኩባ ውስጥ ያሉ የስፖርት አፍቃሪዎች ስለ ኸርናንዴዝ ሰምተው አያውቁም። ኩባዊው ኦስካልዶ ሱዋሬዝ ሊቨርፑል ከናርዊች ሲጫወት ተመልክቷል። ጨዋታ አድማቂዎቹ ተንታኞች ኸርናንዴዝ ፕሪሚዬር ሊግ የተጫወተ የመጀመሪያው ኩባዊ ነው ሲሉም ሰምቷል። "ከዚያ በኋላ ግን አላየሁትም። ለትላልዎቹ ክለቦች ቢጫወት ኖር እናውቀው ነበር። እዚህ በይነ-መረብ ውድ ስለሆነ ዜና ከራድዮ እንጂ ከጉግል አይደለም የምናገኘው" ይላል። "ለትልቅ ሊግ መጫወቱ ያስደስተኛል። ነገር ግን ኩባ ውስጥ ኔይማርና ሜሲ እንጂ እሱ ብዙም አይታወቅም" ይላል ኦስካልዶ ሱዋሬዝ። ኸርናንዴዝ፤ እንኳን በኩባ ዋና ከተማዋ ሃቫና ይቅርና በትውልድ ስፍራው ሞሮንም ብዙም ታዋቂ አይደለም። "ችግሩ ኩባ ውስጥ እግር ኳስ ይህን ያህል ተወዳጅ ስፖርት አይደለም። ነገር ግን እግር ኳስ የሚመለከቱ ሰዎች ልጄን እንደሚያውቁት እርግጠኛ ነኝ" ትላለች እናቱ። ምንም እንኳ ኩባ ውስጥ ቡጢ እና ቤዝቦል ታዋቂ ቢሆኑም የእግር ኳስ አሰልጣኞች ስለኸርናንዴዝ ኦኔል መረጃው አላቸው። ሕፃናትን የሚያሰልጥነው ሉዊስ ኤንሪኬም ኳስ የሚወዱ ሰዎች ያውቁታል ይላል። ኩባ፤ በ1938 የዓለም ዋንጫ ላይ ተሳታፊ ነበረች። በውድድሩ ላይ ሮማኒያን መርታት ብትችልም በስዊድን 8 ለምንም ተሸንፋች። የቀድሞው የኩባ ፕሬዝደንት ፊደል ካስትሮ የአርሰናል ደጋፊ ነበሩ የሚል ወሬ በሃቫና ጎዳናዎች ላይ ይሰማል። ነገር ግን ፕሬዝደንቱ ከክለቡ ስም እንጂ ለኳስ ይህን ያህል ፍቅር የላቸውምም ይባላል። ኩባ ለእግር ኳስ ባትንገበገብም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እግር ኳስ እንደ አንድ መዝናኛ ይቆጠር ይዟል። ቡድኑ ኖርዊች ከፕሪሚዬር ሊግ እንዳይወርድ እየታገለ ያለው ኸርናንዴዝም አንድ ቀን በአገሩ ሰዎች ዘንድ በደንብ ታውቆ ይከበር ይሆናል።
news-45998150
https://www.bbc.com/amharic/news-45998150
በምዕራብ ጎጃም ጎንጂ ቆለላ ወረዳ ተመራማሪዎች በደቦ ጥቃት ሕይወታቸው አለፈ
በምዕራብ ጎጃም ዞን ጎንጂ ቆለላ ወረዳ ለምርምር የሄዱ ተመራማሪዎች ጥቅምት 13፣ 2011 ዓ.ም በተፈፀመባቸው የደቦ ጥቃት ሕይወታቸው አልፏል።
የጎንጂ ቆለላ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ደመቀ መላኩ እንደተናገሩት ግለሰቦቹ ጥቃቱ በተፈፀመበት ቀን ጥዋት በአዲስዓለም የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለተማሪዎች መረጃ ሰጥተው፤ ለጥናት የሚያስፈልገውን የምርምር ናሙና ሽንትና ሰገራ መሆኑን አስረድተው ከተመረጡ ልጆች ናሙናዎችን በመውሰድ ላይ ነበሩ። ዕለቱም የአዲስ ዓለም ገበያ ቀን ሲሆን ት/ቤቱም በዚያው አቅራቢያ ይገኛል። • አቶ ታደሰ ካሳ፡ "…ወሎዬ ነኝ፤ መታወቂያዬም አማራ የሚል ነው" • ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፡ በሚያውቋቸው ሰዎች አንደበት ዋና አስተዳዳሪ እንደሚናገሩት "በተሳሳተ መልኩ ልጆቻችን የጤና ክትባት እየተሰጣቸው ነው፣ እየተመረዙብን ነው፣ ሊገደሉብን ነው" በማለት ቁጥራቸው በርከት ያሉ ግለሰቦች ወደ ትምህርት ቤት አምርተዋል። በወቅቱ የነበሩ የትምህርት ቤቱ ጥበቃዎችም ከቁጥጥራቸው ውጭ በመሆኑ በአካባቢው በነበሩ ጥቂት ፖሊሶች ታግዘው ወደ ፖሊስ ጣቢያ በመወሰድ ላይ ሳሉ በወረዳው በሚገኝ አዲስ ዓለም የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት አቅራቢያ መናሃሪያ አካባቢ ጥቃቱ እንደደረሰባቸው አቶ ደመቀ ለቢቢሲ ገልፀዋል። ዋና አስተዳዳሪው ስለ ግለሰቦቹ ማንነትም አስመልክቶ እንደገለፁት አንዱ ግለሰብ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለሶስተኛው ዲግሪ ጥናት ወደ ቦታው ያመራ ሲሆን፣ ሌላኛው በሜጫ ወረዳ በሚገኝ ጤና ጣቢያ የሚሰራ የጤና መኮንን ናቸው። የወረዳው የጤና ባለሙያም ጉዳት ደርሶበት በአካባቢው የጤና ተቋም ህክምና እየተደረገለት እንደሆነ አስተዳዳሪው ይናገራሉ። የወረዳው የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ አንተነህ በላይ በበኩላቸው ከዚህ ቀደም ባህር ዳር ክትባት ሲሰጡ ሞቱ በሚል በተናፈሰ ወሬ ምክንያት መኪና መሰባበርና በሰዎችም ላይ ጉዳት መድረሱን አስታውሰው አካባቢው ለባህርዳር ቅርብ በመሆኑ ይሄው መረጃ በመናፈሱ ጥቃቱ ሊፈፀም እንደቻለ ያስረዳሉ። "ግለሰቦቹ ደብዳቤ ቢይዙም ወረዳውን አላሳወቁም" የሚሉት ኃላፊው ከሁለት ት/ቤት ናሙና ለመሰብሰብ ወረዳውን ጤና ፅ/ቤት እንደጠየቁና ደብዳቤ ተፅፎላቸው ቀጥታ ወደ ት/ቤት እንደሄዱ ይናገራሉ። በድንጋይና በዱላ በደረሰባቸው አሰቃቂ ጥቃት ህይወታቸው ወዲያው ማለፉን ኃላፊው አስረድተዋል። • ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፡ በሚያውቋቸው ሰዎች አንደበት • ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር የፍቅር ግንኙነት አለዎት? ጥቃቱ የተፈፀመው ከቀኑ 7፡30 ገደማ ሲሆን የፀጥታ ኃይሎች 10፡30 ገደማ ሁኔታውን ማረጋጋት እንደተቻለ ገልፀዋል። ግለሰቦቹ የአካባቢው ተወላጆች በመሆናቸው ማህበረሰቡ ፀፀት እንደተሰማው ገልፀው "እጃችንን በእጃችን ቆረጥን፤ አገር የሚጠቅሙ ምሁራንን አጣን!" በሚል በድርጊቱ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን አጋልጦ መስጠት የጀመረውም ራሱ ህብረተሰቡ እንደሆነ ባለሙያው ይናገራሉ። በተጨማሪም የአካባቢው ተወላጅ የሆኑና ቤተክርስቲያን ለማሰራት ድጋፍ እያደሩ የነበሩ ግለሰቦችም መኪናቸው የተመራማሪዎቹ ንብረት ነው በሚል ጥርጣሬ ጥቃት ቢሞከርባቸውም፤ በአካባቢው ይታወቁ ስለነበር ከጥቃት ሊድኑ እንደቻሉ የወረዳው አስተዳዳሪ ለቢቢሲ ገልፀዋል። ይሁን እንጂ መኪናቸውን እንደተቃጠለ ዋና አስተዳዳሪው ጨምረው ተናግረዋል። በጥቃቱ እጃቸው አለበት የተባሉ 27 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው የማጣራት ስራው እየተካሄደ ይገኛል ብለዋል።
41758438
https://www.bbc.com/amharic/41758438
ኳታር ለሠራተኞቿ ዝቅተኛውን የደሞዝ ክፍያ ገደብ አስቀመጠች
ኳታር የተለያዩ ሠራተኞችን የሚመለከቱ ሕጎች በማርቀቅ እና በማሻሻል ላይ ትገኛለች። ከእነዚህ መካከል ለመጀመሪያ ጊዜ ያፀደቀችው የዝቅተኛ ደሞዝ ክፍያ ገደብ አንዱ ነው።
ከ2022 የዓለም ዋንጫ ዝግጅት ጋር ተያይዞ በኳታር ታሪክ በቁጥሩ ከፍተኛ ነው የተባለ ሠራተኛ ዶሃ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ ሥራ ላይ ይገኛል። ይህንን ተከትሎም ዓለም አቀፍ የሠራተኞች መብት ተከራካሪ ድርጅቶች የኳታር ሠራተኛ አያያዝ ላይ ጥያቄ ሲያቀርቡ ቆይተዋል። ዓለም አቀፉ የሠራተኞች ድርጅት (አይኤልኦ) ኳታር ወርሃ ሕዳር ከማብቃቱ በፊት ባላት የሠራተኛ ሕግ ላይ ክለሳ ካላደረገች የከፋ ነገር ይከተላል ብሎ ካስጠነቀቀ በኋላ ነው ሃገሪቱ ማሻሻያ ያደረግችው። የዓለም አቀፉ የሠራተኞች ሕብረት ኮንፈደሬሽን ዋና ፀሓፊ የሆኑት ሻሮን ባሮው ለውጡ በኳታር ለዘመናዊ ባርነት ማክተም ምልክት ነው ሲሉ ተደምጠዋል። ኳታር ለረጅም ጊዜ 'ካፋላ' የተባለ ቀጣሪ ድርጅቶች ካልፈቀዱ በስተቀር ከውጭ ሃገር የሚመጡ ሠራተኞች ድርጅቱን ለቀው ወደሌላ ቀጣሪ ድርጅት ወይም ሃገሪቱን ለቀው መሄድ እንዳይችሉ የሚያደርግ አሠራር ስትከተል ቆይታለች። ኳታር ከታህሳስ 2016 ጀምሮ ካፋላ የተባለው አሰራር ተግባራዊ እንዳይሆን ማድረጓ ይታወሳል። በአዲሱ ማሻሻያ አብይ ለውጥ ያመጣሉ የተባሉ የሠራተኛ ሕግጋትን ያዘለ እንደሆነ ታውቋል። ከእነዚህም መካከል • ፆታ ሳይለይ ለሠራተኞች የሚከፈል ዝቅተኛ የደሞዝ መጠን ገደብ እንዲኖረው • ከወጭ ሃገር የሚመጡ ሠራተኞች ሃገሪቱን ለመልቀቅ የቀጣሪዎቻቸውን ፈቃድ መጠይቅ እንዳይሹ • መታወቂያ ካርዶች በቀጣሪ ድርጅቶች ሳይሆን በመንግሥት እንዲሰጥ እና መሰል ሕግጋትን ያዘለ ነው። የኮንፈደሬሽኑ ዋና ፀሓፊ ባሮው እንደሚሉት አሁንም ብዙ የሚቀሩ ጉዳዮች ቢኖሩም እርምጃው አውንታዊ የሚባል ነው። አዳዲሶች ማሻሻያዎች መቼ ሥራ ላይ መዋል እንደሚጀምሩ ግን አስካሁን የታወቀ ነገር የለም። ከ1.5 እስከ 2 ሚሊዮን የሚደርሱ እና በአብዛኛው ከእስያ እንደመጡ የሚነገርላቸው የጉልበት ሠራተኞች በኳታር የግንባታ ዘርፍ ተሰማርተው እንደሚገኙ ይገመታል። በ2013 የዓለም አቀፉ የሠራተኞች ሕብረት ኮንፈደሬሽን ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው 1200 ያህል ከውጭ ሃገራት የመጡ ሠራተኞች በ2022 ዓለም ዋንጫ ዝግጅት በሚካሄዱ ግንባታዎች ላይ ተሰማርተው ሳለ ሕይወታቸው አልፏል።
47442573
https://www.bbc.com/amharic/47442573
ደቡብ አፍሪካዊው ኮማኪ ትሬቨር ኖዋ እየተወገዘ ነው
የተወዳጁ "ዘ-ዴይሊ ሾው" አሰናጅና እውቁ ደቡብ አፍሪካዊ ኮማኪ ትሬቨር ኖዋ በማኅበራዊ የትስስር መድረክ ሚሊዯኖች ውግዘት እያዘነቡበት ነው።
ውግዘቱ በፓኪስታንና ሕንድ የሰሞኑ የካሽሚር ፍጥጫ ላይ የሰነዘረውን ቀልድ ተከትሎ የመጣ ነው። ለሴቶች የተከለከለ ተራራን የወጣችው የመጀመሪያ ሴት ይህንኑ የማሕበራዊ ትስስር መድረኩን የውግዘት ዘመቻ ተከትሎ ትሬቨር በይፋ አድናቂዎቹን ይቅርታ ጠይቋል። "ሕንድና ፓኪስታን ወደ ጦርነት ከገቡ በጣም አዝናኙ ጦርነት ይሆናል። በታሪክም ረጅሙ ጦርነት እንደሚሆን እገምታለሁ" በሚል ውጥረቱን ከቦሊውድ ፊልሞች ጋር በማስተሳሰር ነበር ቀልድ ለመፍጠር የሞከረው። አድናቂዎቹ ትሬቨር ኖዋን "ዘረኛ" እና "ጨካኝ" ሲሉ ነው የተቹት። ቀብሩን አዘጋጅቶ ራሱን ያጠፋው አርሶ አደር ኖዋ ለአድናቂዎቹ በጻፈው የትዊተር የይቅርታ ደብዳቤ "እኔ ቀልድን የምጠቀመው ሕመምንና ስቃይንም ለማስታገስም ጭምር ነው። ሕንድና ፓኪስታን ላይ የኮመኩት ነገር ከጦርነቱም በላይ ትኩረት መሳቡ ግን ገርሞኛል፤ ለማንኛውም ካስከፋኋችሁ ይቅርታ" ብሏል። የሰሞኑን የሕንድና ፖኪስታን የካሽሚር ግጭት ተከትሎ ሁለቱ የኒኩሌየር ታጣቂ ሃገራት ወደ ሙሉ ጦርነት እንዳያመሩ ስጋት አለ። ቢቢሲ አማርኛ ወደ እናንተ መጥቷል ፓኪስታን የሕንድን የጦር ሄሊኮፕተር መትታ ከጣለች በኋላ ውጥረቱን ለማርገብ በሚል የማረከችውን አብራሪ ለሕንድ አሳልፋ መስጠቷ ይታወሳል።
news-49902872
https://www.bbc.com/amharic/news-49902872
ግብፅ ከአሜሪካ ያስመለሰችውን ጥንታዊ የሬሳ ሳጥን ለዕይታ አቀረበች
ግብፅ ከአሜሪካ ያስመለሰቻቸውን ጥንታዊ ቅርሶች ተከትሎ 2100 ዓመታትን ያስቆጠረውን የአንድ ቄስ የአስክሬን ሳጥን ለዕይታ ማቅረቧን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።
ሬሳ ሳጥኑ ከግብፅ የተዘረፈው በ 'አረብ ስፕሪንግ' አብዮት ወቅት የነበረ ሲሆን ኒው ዮርክ ለሚገኘው ሜትሮፖሊታን ሙዚየም ቅርሱን ሲገዛ፤ ከግብፅ ተዘርፎ የተወሰደ መሆኑን እንዳላወቀ ተገልጿል። • አሜሪካ ከግብፅ የተሰረቀውን የወርቅ ሬሳ ሳጥን መለሰች • ላሊበላ፡ የመፍትሔ ያለህ የሚለው ብሔራዊ ቅርስ • 31 ኢትዮጵያውያን ከኖርዌይ ተባረሩ ሙዚየሙ፤ ከክርስቶስ ልደት በፊት በአንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን አካባቢ እንደተሠራ የሚገመተውን የሬሳ ሳጥን ለግብፅ ባለሥልጣኖች ማስረከቡ የሚታወስ ነው። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ2011 ግብፅ ውስጥ አብዮት ሲቀጣጠል፤ ሬሳ ሳጥኑ ሚንያ ከሚባለው አካባቢ ተዘርፎ፤ በዱባይ በኩል ወደ ጀርመን ከዛም ወደ ፈረንሳይ ተወስዷል። ከዚያም ሀሰተኛ መረጃዎችን በመጠቀም በዓለም አቀፉ የሥነ ጥበብ ደላሎች አማካኝነት አሜሪካ ኒዮርክ ለሚገኘው ሜትሮፖሊታን ሙዚየም መሸጡን ባለሥልጣናት ተናግረዋል። ሬሳ ሳጥኑ ውስጥ ኔደጅማንክህ የተባሉት እና ሔሪሻፍ የተባለው አማልክት ቄስ የደረቀ አስክሬን እንደሚገኝበት ተገልጿል። 'ኔጀማንክህ' በመባል የሚታወቀው እና በወርቅ የተለበጠው የሬሳ ሳጥን ተሰርቆ በሕገ ወጥ መንገድ ከግብፅ የወጣው በአውሮፓዊያኑ 2011 ነበር። የአስክሬን ሳጥኑ ከክርስቶስ ልደት በፊት በአንደኛው ክፍለ ዘመን በ4 ሚሊየን ዶላር ከፐርሺያኖች መገዛቱ ተነግሯል። ሙዚየሙ 1971 ሐሰተኛ የውጭ ንግድ ፈቃድ እና ሀሰተኛ መረጃዎች እንደቀረቡለት እና ሳያውቁ እንደተገዛ አቃቤ ሕግ ለአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል። ባለሥልጣናቱ እንዳሉት ጥንታዊ የሆነው የአስክሬን ሳጥን በአውሮፓዊያኑ 2011 ተሰርቆ እስከሚወሰድ ድረስ በግብፅ ሚንያ ክልል ከ2000 ዓመታት በፊት ተቀብሮ ነበር የቆየው።
news-56756413
https://www.bbc.com/amharic/news-56756413
የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር የሕዳሴ ውዝግብን ለመፍታት ለአስቸኳይ ስብሰባ ጥሪ አደረጉ
የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ውዝግብን ለመፍታት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲደረግ ለግብጽና ለኢትዮጵያ መሪዎች ጥሪ አደረጉ።
ለዓመታት ሲካሄድ የነበረው የሕዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር በኮንጎዋ መዲና ኪንሻሳ ውጤታማ አለመሆኑን ተከትሎ ይህ ውይይት የመጨረሻ ሙከራ ሊሆን ይችላል ተብሏል። በኪንሻሳ ላይ ሱዳን እና ግብጽ የሕዳሴ ግድብ ድርድር ታዛቢዎችን ሚና ለመቀየርና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ አሜሪካ እና የአውሮፓ ሕብረት በአደራዳሪነት እንዲገቡ ሃሳብ ቢያቀርቡም ኢትዮጵያ አልተቀበለችውም። ኢትዮጵያ ድርድሩ በአፍሪካ ሕብረት ጥላ ስር እንዲሆን ትፈልጋለች። ይህንን የኢትዮጵያ ሃሳብም ሰሞኑን ሩሲያ እንደምትደግፈው የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ሩሲያ የሕዳሴ ግድብ ውዝግብ በአፍሪካ ሕብረት ጥላ ስር እንዲፈታ ፍላጎት አላት በማለት የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ተናግረዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህንን ንግግር ያደረጉት በካይሮዋ መዲና ከግብጹ አቻቸው ሳሜ ሽኩሪ ጋር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሆነ ተዘግቧል። ኢትዮጵያ በመጪው ሰኔ ክረምት ሲገባ ሁለተኛ ዙር ሙሌቷን በእቅዷ መሰረት እንደምታከናውን አስታውቃለች። ነገር ግን ግብጽና ሱዳን ኢትዮጵያ ሁለተኛ ዙር ሙሌት ከማከናወኗ በፊት ስምምነት ላይ መደረስ አለበት ይላሉ። ኢትዮጵያ ከሰሞኑ የህዳሴ ግድብን ሁለተኛ ዙር ውሃ ሙሌት ከማካሄዷ በፊት ግብጽ እና ሱዳን ለመረጃ ልውውጥ ባለሙያዎች እንዲመድቡ ጠይቃለች። የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ስለሺ በቀለ ኢትዮጵያ በመጪው የክረምት ወቅት ለምታከናውነው የውሃ ሙሌት አገራቱ የግድብ ባለሙያዎችን ኢንዲመድቡ በይፋ መጋበዛቸውን ያስታወቀው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው። ኢትዮጵያ ይህን ጥሪ ያቀረበችው፣ ቀደም ሲል ሦስቱ አገሮች በተስማሙት ስምምነት መሠረት ነው። ሆኖም ከሰሞኑ በሕዳሴ ግድብ ውዝግብ ላይ የግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ ሁሉም አማራጮች ክፍት ናቸው በማለት ማስጠንቀቃቸውን ተከትሎ የግብጽ ፓርላማ ድጋፍ እንደሚሰጥ አስታውቋል። የፓርላማ አባል ታሪክ ሬድዋን በካይ በበኩላቸው በካይሮ በተደረገ የሰብዓዊ መብት ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርና የኢትዮጵያ ምክር ቤቱ ግብጽ ያደረገችውን ጥሪ ውድቅ አድርገዋል ብለዋል። የምክር ቤቱ አባል እንደሚሉት የሕዳሴ ግድብ በታችኛው ተፋሰስ ያሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮ ያለባቸውን ፍራቻና ተማፅኖ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት መስማት አይፈልጉም ይላሉ። "የግብጽ አርሶ አደሮች የኢትዮጵያን የምጣኔ ሃብት ልማት አይቃወሙትም። ልማታችን የሚሉት ውሃ ነው አርሶ አደሮቻችንና ሕዝባችንን የሚመግበው። የአባይ ውሃ ሊያስማማን በተገባ ነበር። የጦርነት መነሾ ሊሆን አይገባም" ብለዋል። በአምስት ዓመት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ የነበረው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እስካሁን ሲጓተት ቆይቶ በግንባታ ላይ አስር ዓመትን አስቆጥሯል። ተገንብቶ ሲያበቃ በግዝፈቱ ከአፍሪካ ቀዳሚ እንደሚሆን የተነገረው ግድቡ በአሁኑ ጊዜ ወደ 80 በመቶ የሚጠጋው የግንባታ ሥራው መጠናቀቁ የተገለጸ ሲሆን በሚቀጥለው ዓመት በከፊል የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል ተብሎ ይጠበቃል። ከአምስት ሺህ በላይ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እንደሚያመነጭ የተነገረለት ይህ ግድብ ተጠናቆ ሥራ ሲጀምር ከግማሽ በላይ ለሚሆነው የአገሪቱ ሕዝብ፣ ለኢንዱስትሪዎችና ለጎረቤት አገራት የኤሌክትሪክ ኃይል ያቀርባል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።
news-56192205
https://www.bbc.com/amharic/news-56192205
የመርከብ መሃንዲሱ የባህር ላይ "ቆሻሻን" የሙጥኝ ብሎ ከመስመጥ ዳነ
ከመርከብ ላይ በድንገት የወደቀው ዋና መሃንዲስ "በባህር ላይ ያለ ቆሻሻን ሙጥኝ" በማለቱ ህይወቱ ሊተርፍ እንደቻለ ልጁ አስታውቋል።
በፖስፊክ ውቅያኖስ ላይ ከመርከብ በድንገት የወደቀው ቪዳም ፔርቬርቲሎቭ በውሃ ውስጥ አስራ አራት ሰዓታትን አሳልፏል ተብሏል። የ52 አመቱ መሃንዲስ በወቅቱ የህይወት አድን ጃኬት አልለበሰም ነበር የተባለ ሲሆን፤ ድንገትም ከነበረበት በኪሎሜትሮች ርቀት ጥቁር ነጥብ በማየቱ ወደዚያው እየዋኘ አምርቷል። ያየው ነገር ግን አሳ አጥማጆች የጣሏትን እቃ ሲሆን እሱንም ሙጥኝ በማለት ህይወቱ ድኗል። "ከእነዚያ ሰዓታት በኋላ ስናገኘው ከነበረበት በ20 አመት ያረጀ መስሎና በጣም ደካክሞ ቢሆንም በህይወት በመኖሩ ደስተኞች ነን" በማለት ልጁ ማራት ለኒውዚላንድ የዜና አገልግሎት ተናግሯል። ቪዳም ፔርቬርቲሎቭ ዜግነቱ ከሉቴንያ ሲሆን ሲልቨር ሰፖርተን የተባለው መርከብ ዋነኛ መሃንዲስ ነው። በወቅቱም መርከቡ ከኒውዚላንድ የቱዋራንጋ ወደብ በብሪታንያ ግዛት ስር ወዳለችውና በተገለለችው ፒት ካሪን እቃዎችን እያመላለሰ ነበር ተብሏል። በመርከቡ የሞተር ክፍል ነዳጅ ቅያሬ ጋር ተያይዞ ሙቀትና መደንዘዝ የተሰማው ግለሰብ፤ ነፋስ ለማግኘትም ነው መርከቡ ጫፍ ላይ ቆሞ የነበረው። ሆኖም ከዚያ በኋላ መውደቁ ተሰምቷል። ማራት አባቱ ራሱን ስቶ እንደወደቀ የሚጠረጥር ሲሆን፤ አባትየው ግን እንዴት እንደወደቀ እንደማያስታውስና ራሱን ውሃ ውስጥ ማግኘቱን መናገሩን አስረድቷል። ዋና መሃንዲሱ ከመርከብ እንደወደቀ ያልተረዱት መርከበኞችም ትተውት መሄዳቸው ተሰምቷል። ራሱን ውሃ ውስጥ ያገኘው መሃንዲስ በውቅያኖሱ ውስጥ እየዋኘ ለሰዓታት የቆየ ሲሆን ድንገትም የተጣለ እቃ ከርቀት በማየቱ ወደዚያው አቅንቷል። ይህንንም እቃ ሙጥኝ ብሎ በመያዝ ህይወቱን ማትረፍ ችሏል። የመርከቧ ሰራተኞች መሃንዲሱ መጥፋቱን ያወቁት ከስድስት ሰዓታት በኋላ ሲሆን የመርከቧ ካፕቴይንም መርከቧን በማዞር ግለሰቡን ፍለጋ ጀመሩ። ቪዳም ፔርቬርቲሎቭ መርከቧን በርቀት ሲያያት እጁን በማውለብለብ ለመጣራት ምክሯል። እድለኛም ሆኖ አንደኛው መንገደኛ" ደከም ያለ የሰው ድምፅ ሰምቻለሁ" ማለቱን ተከትሎ እጁን የሚያውለበልበውን መሃንዲስ ሊያዩት ችለዋል። "በህይወት ለመቆየት የነበረው ፅናትና አልበገር ባይነት የሚገርም ነው ። እኔ ብሆን እስካሁን ሰጥሜ ሞቼ ነበር። እሱ አካላዊ እንቅስቃሴ የሚያዘወትርና ጤንነቱንም ይጠብቅ ስለነበር ነው መትረፍ የቻለው" ብሏል ልጁ ማራት።
46644150
https://www.bbc.com/amharic/46644150
የጭንቅላት ቀዶ ጥገና እየተደረገለት ጊታር የተጫወተው ግለሰብ
ደቡብ አፍሪቃዊው የጃዝ ሙዚቃ ተጫዋች ሙሳ ማንዚኒ የጭንቅላት ቀዶ ጥገና እየተደረገለት ጊታሩን ሲቃኝ ነበር፤ አሁን ላይ የሚገኝበት ሁኔታም እጅጉን መልካም እንደሆነ ተነግሯል።
ስድስት ሰዓታትን በፈጀው ቀዶ ጥገና ላይ ሙሳ ጊታር እንዲጫወት የሆነው ዶክተሮቹ ቀዶ ጥገናውን ሲያከናውኑ እንዲመቻቸው ነው ተብሏል። የዩኒቨርሲቲ አስተማሪ የሆነው ሙሳ የሙዚቃ ተጫዋች በመሆኑ የጭንቅላት ቀዶ ጥገናው የጣቶቹ እንቅስቃሴ ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ ለመየት ያስችል ዘንድ ነው ጊታር እንዲጫወት የተፈቀለደት። • «ሰው ሲበሳጭ ማስታወሻ እይዝ ነበር» አዲስ ዓለማየሁ ቀዶ ጥገናው በሙያው ጥርሳቸውን በነቀሉ የደቡብ አፍሪቃ የጭንቅላት ቀዶ-ጥገና ስፔሻሊስቶች ነው የተካሄደው። ሙሳ፤ በግሪጎሪ አቆጣጠር 2006 ነበር ከጭንቅላት ዕጢ ጋር በተያያዘ በሽታ ተጠቅቶ የነበረው፤ ሁኔታው ሲጠናበት ግን ወደ ቀዶ ጥገና ክፍል መግባት ግድ ሆነበት። ከቀዶ ጥገና ስፔሻሊስቶቹ አንዱ የሆኑት ዶክተር ኤኒከር እንዲህ ታካሚዎች ንቁ ሆነው ሳለ የሚካሄድ ሕክምና አንዳንዴ ተመራጭ ነው ይላሉ። • ቀዶ ህክምና በአፍሪካ ስጋት መሆኑ ከፍ ብሏል «ዕጢውን በቀለለ ዘዴ ማስወገድ እንድንችል ያግዘናል፤ አልፎም የትኛው የሰውነት ክፍል እየሠራ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን በግልፅ ማየት እንችላለን።» ምናልባት ሙሳ በማደንዘዣ እንዲተኛ ተደርጎ ቢሆን ኖሮ የተወሰነ የሰውነት ክፍሉ 'ፓራላይዝ' ሊሆን ይችል እንደነበር ባለሙያዎቹ ይናገራሉ። በሙዚቃ ሥራው ሽልማት ማግኘት የቻለው ሙሳ ለተደረገለት የተሳካ ቀዶ ጥገና ዶክተሮቹን ሳያመሰግን አላለፈም። • በርካቶች ከምጥ ይልቅ በቀዶ ህክምና መውለድን እየመረጡ ነው
news-53386932
https://www.bbc.com/amharic/news-53386932
ከሃጫሉ ግድያ ጋር ተያይዞ አቃቤ ሕግ እስካሁን ያነሳቸው አራት ቁልፍ ነጥቦች
የዛሬ ሁለት ሳምንት ሰኔ 22/2012 ዓ.ም ምሽት 3፡30 ገዳማ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ አዲስ አበባ ውስጥ በጥይት ተመትቶ መገደሉ ይታወሳል።
ከሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ ፖሊስ የተወሰኑ ተጠርጣሪዎችን መያዙን አስታውቆ በተከታታይ በነበሩት ቀናትም ተጨማሪ ሰዎች ከወንጀሉ ጋር በተገናኘ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ በተለይ በግድያው ውስጥ ቀጥተኛ ተሳትፎ አላቸው የተባሉ ተጠርጣሪዎችን በተመለከተ ፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በተለይ ባለፈው ሳምንት ተከታታይ መረጃዎች ሰትቷል። "ሃጫሉን ተኩሶ የገደለው ጥላሁን ያሚ ነው" ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሐምሌ 3/2012 ዓ.ም በሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በቀጥታ ተሳትፈዋል ያላቸውን የሦስት ግለሰቦችን ማንነት ይፋ አድርጓል። ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጓ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በሰጡጥ መግለጫ በድምጻዊ ሃጫሉ ግድያ በቀጥታ ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩትን ጥላሁን ያሚ፣ አብዲ አለማየሁ እና ከበደ ገመቹ (በወቅቱ በቁጥጥር ሥር አልዋለም ነበር) መሆናቸውን አስታውቀዋል። ሃጫሉ ሁንዴሳን ተኩሶ የገደለው ጥላሁን ያሚ አንደሆነም በዕለቱ ጠቅላይ አቃቤ ሕጓ ተጠርጣሪው የሰጠውን ቃል ጠቅሰው ይፋ አድርገዋል። መግለጫው ከተሰጠ ከሰዓታት በኋላም ሦስተኛው ተጠርጣሪ ከበደ ገመቹ ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ አደአ ውስጥ ድሬ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ዐቃቤ ሕግ አስታወቋል። ተጠርጣሪዎች "ተልዕኮ የተቀበሉት ከኦነግ-ሸኔ ነው" ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንዳሉት ተጠርጣሪዎቹ የግድያውን ተልዕኮ ኦነግ-ሸኔ ከተባለው ቡድን ተቀብለው ማስፈጸማቸውን በመግለጽ፤ ቡድኑ ከግድያው ጀርባ እጁ እንዳለበት ተናግረዋል። ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን ተኩሶ የገደለው ጥላሁን ያሚ የተባለው ግለሰብ ተልዕኮውን ከኦነግ-ሸኔ እንደተቀበለና ድምጻዊውን ኢላማ ማድረግ ለምን እንዳስፈልገ በሰጠው ቃል መግለጹንም ተናግረዋል። የግድያ ተልዕኮውን እንዲፈጽም ከሸኔ ቡድን በሰኔ ወር ውስጥ ሦስት ጊዜ መገናኘቱንም አሳውቀዋል። "ሃጫሉ ተደጋጋሚ ማስፈራሪያዎች ይደርሱት ነበር" ከሁለት ቀናት በፊት ማለትም ቅዳሜ ሐምሌ 4 ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና የፌደራል ፖሊስ በሰጡት የጋራ መግለጫ ለይ ሃጫሉ ተደጋጋሚ የግድያ ማስፈራሪያዎች ይደርሱት እንደነበረ አስታውቀዋል። በመግለጫው በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተደራጁ እና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ጸጋ፤ በሃጫሉ ሁንዴሳ የእጅ ሰልክ ላይ ተደጋጋሚ የግድያ ዛቻዎች ይደርሱት እንደነበረ አመልከተዋል። አቶ ፍቃዱ ጨምረውም ሃጫሉ ለጓደኞቹ ዛቻዎች እየተሰነዘሩበት እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲናገር እንደነበረ አስታውቀዋል። በቴሌግራም አማካንኝነት ደግሞ እራሱን የኦነግ-ሸኔ አስተባባሪ ከሚል ግለሰብ በድምጽ እና በጽሑፍ ማስፈራሪያዎች ሲደርሱት እንደነበረም አቶ ፍቃዱ ጨምረው አስረድተዋል። "ኦኤምኤን የሃጫሉን ቃለ መጠይቅ ቆርጦ አስተላልፏል" አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ከመገደሉ ከአንድ ሳምንት በፊት ከኦሮሞ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኦኤምኤን) ጋር ያደረገው ቃለ መጠይቅ አየር ላይ መዋሉ ይታወሳል። አቶ ፍቃዱ እንዳሉት ከሆነ ኦኤምኤን አርቲስቱ በቃለ መጠይቁ ከኦነግ-ሸኔ የግድያ ዛቻ በተደጋጋሚ እንደሚደርሰው የተናገረበትን የቃለ መጠይቅ ክፍል ተቆርጦ እንዲወጣ ተደርጓል። ሃጫሉ በቃለ መጠይቁ ላይ ከሌሎች ማኅበረሰቦች ጋር እንዲጋጭ የሚያደርጉ ሌሎች አመለካከቶቹን እንዲያጸባርቅ በጠያቂው በኩል ተደርጓልም ብለዋል አቶ ፍቃዱ። አቶ ፍቃዱ እንዳሉት አርቲስት ሃጫሉ ከኦኤምኤን ጋር ያደረገው ቃለ መጠይቅ 1 ሰዓት ከ 11 ደቂቃ እንደሚረዝም ተናግረው በኦኤምኤን የተላለፈው ግን 47 ደቂቃ በቻ ነው ብለዋል። ተቆርጦ እንዲቀር የተደረገው ክፍልም ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግም ተናግረዋል። ተቆርጦ እንዲቀር የተደረገው ከኦነግ-ሸኔ ይደርስበት የነበረው ዛቻ ብቻ ሳይሆን፤ "በዚህ አገር ለውጥ መምጣቱን፣ ይሄ ለውጥ እያደገ ሊሄድ እንደሚችል፣ ለውጡን መደገፍ አማራጭ የሌላው ነገር መሆኑን፣ አብሮ መቆም የሚያስፈልግ መሆኑን . . ደጋግሞ የሚያሰቀምጥባቸው ቦታዎች ናቸው ተቆርጠው እንዲቀሩ የተደረጉት" ሲሉ አቶ ፍቃዱ ተናግረዋል። ሃጫሉ ከዚህ ቀደም ምን ብሎ ነበር? ሃጫሉ ሁንዴሳ ከዚህ ቀደም ቢቢሲን ጨምሮ ከሌሎች መገናኛ ብዙሃን ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ተደጋጋሚ የግድያ ዛቻዎች ይደርሰው እንደነበረ ተናግሯል። ከግድያው ከሳምንት በፊት ሰኔ 15/2012 ዓ.ም በኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ላይ በተላለፈው ቃለ መጠይቁ፤ ሃጫሉ "እየታገልኩ እኮ ነው የምኖረው" በማለት ተደጋጋሚ የግድያ ዛቻ እንደሚደርስበት ተናግሮ ነበር።
news-53326841
https://www.bbc.com/amharic/news-53326841
ኮሮናቫይረስ: የብራዚሉ ፕሬዝዳንት በኮቪድ-19 መያዛቸው ተገለፀ
የብራዚል ፕሬዝዳንት ጃየር ቦልሶናሮ በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተገለፀ።
ፕሬዝዳንቱ ኮሮናቫይረስ በአገራቸው ከተከሰተ ጀምሮ ለአራተኛ ጊዜ ምርመራ ማድረጋቸው የተገለፀ ሲሆን፣ ሰኞ እለት ያደረጉት የአሁኑ ምርመራ ግን የሙቀት መጠናቸው ከፍ በማለቱና የኮሮናቫይረስ ምልክት በማሳየታቸው መካሄዱ ተገልጿል። ቦልሶናሮ በተደጋጋሚ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የሚከሰቱ የጤና አደጋዎችንና ቀውሶችን ሲያጣጥሉ የነበረ ሲሆን፣ " ቀላል ጉንፋን" በማለት ቢያዙ በጣም ሊጎዱ እንደማይችሉ ሲናገሩ ተደምጠው ነበር። ፕሬዝዳንቱ የክልል አስተዳዳሪዎችንም የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመግታት ጥለውት የነበረውን የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲያነሱ ተናግረው የነበረ ሲሆን፣ በወቅቱም የእንቅስቃሴ ገደቡ ምጣኔ ሃብትን ይጎዳል ብለው ነበር። ሰኞ እለትም በአፍና በአፍንጫ መሸፈኛ ላይ የተላለፈውን መመሪያ አጣጥለውት ሲናገሩ ተደምጠዋል። በሚያዚያ ወርም በቫይረሱ ቢያዙ እንኳ" አያስጨንቀኝም ቢሆን ቢሆን መጠነኛ ጉንፋን ነው" በማለት ተናግረው ነበር። ይህንን አስተያየት በሰጡበት ወቅት በኮቪድ-19 ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ3000 በታች የነበረ ሲሆን በቫይሩሱ የተያዙትም 40 ሺህ ብቻ ነበር። በብራዚል በአሁኑ ወቅት በኮሮናቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ65 ሺህ በላይ ሲሆን በቫይረሱ የተያዙም ከ1.6 ሚሊዮን በላይ ደርሰዋል። ምንም እንኳ በቫይረሱ የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ቢመጣም፣ ፕሬዝዳንቱ ግን የክልል አስተዳደሮች የጣሉት የእንቅስቃሴ ገደብ ምጣኔ ሃብቱን ከቫይረሱ በላይ እየጎዳው እንደሆነ ተናግረው፣ መገናኛ ብዙኀንም ስለቫይረሱ ፍርሃትና ውዥንብር እየነዙ ነው ሲሉ ኮንነዋል። ፕሬዝዳንቱ ሰኞ እለት ብራዚላውያን ህዝብ በተሰበሰበበት ስፍራ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ እንዲያደርጉ የሚደነግገውን ህግ መጠነኛ ለውጥ አድርገውበታል። ቦልሳኖሮ በተደጋጋሚ ህዝብ በበዛበት ስፍራ ሲገኙ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ ታይተዋል። በብራዚል የአሜሪካ አምባሳደር፣ በአሜሪካ የነጻነትን ቀንን አስመልክቶ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ፕሬዝዳንት ቦልሶናሮን ጋብዘው ነበር። በዚህም የተነሳ የፕሬዝዳንቱ በኮቪድ-19 መያዝን አስመልክቶ ምርመራ እንደሚያደርጉ ተገልጿል። ቅዳሜ እለት ፕሬዝዳንት ቦልሶናሮ በውጪ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ጋር የአሜሪካውን አምባሳደር ቶድ ቻፕማንንን አቅፈው የአሜሪካ የነጻነት በዓልን ሲያከብሩ የተነሱት ምሰል በትዊትር ላይ ታይቷል። ፕሬዝዳንቱ በቫይረሱ መያዛቸው እንደተሰማ ኤምባሲው በትዊትር ላይ አምባሳደሩ "ምልክት አልታየባቸውም ነገር ግን አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሁሉ ያደርጋሉ" የሚል መልእክት አስፍሯል። የአሜሪካ ኤምባሲ መልእክት አክሎም ምርመራ እንደሚያደርጉ ገልጾ" የምርመራ አሰራሮችን ይከተላሉ" ብሏል። ፕሬዝዳንቱ የኮሮናቫይረረስ ምርመራ ሲያደርጉ የመጀመሪያ ጊዜያቸው አይደለም፤ ከዚህ በፊት ሶስት ጊዜ ተመርምረው የሚያውቁ ሲሆን ሁሉም ነጻ መሆናችን የሚያሳዩ ነበር ተብሏል።
news-48144492
https://www.bbc.com/amharic/news-48144492
ስራቸው ለሞት የዳረጋቸው ጋዜጠኞች
ቢያንስ በሶስት ወይም በየአራት ወር ጊዜ ውስጥ አንድ ግለሰብ ከእናቴ ሞት ጋር በተያያዘ ምርመራ ለማድረግ ወደ ቤታችን ይመጣል። ቤተሰባችን ይህንን ግለሰብ ለመጀመሪያ ጊዜ ያየው ከስድስት ዓመት በፊት እናታችንን በቁጥጥር ስር ለማዋል ሲመጣ ነበር።
እናቴ በወቅቱ ማልታ ውስጥ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት እየተወዳደሩ ስለነበሩት ግለሰብ ቀልድ አዘልና ፖለቲካዊ መልእክት ያለው ጽሁፍ አቅርባ የነበረ ሲሆን አንድ ሰው ቅሬታውን ለፖሊስ አሳውቆ ነበር። • የጋዜጠኛው አስክሬን 'በአሲድ እንዲሟሟ ተደርጓል' • 'ለሼህ አላሙዲ መፈታት የጠቅላይ ሚንስትሩ አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነበር' በዛው ቀን ምሽትም ይሄ ሁሌም ወደቤታችን የሚመጣው ፖሊስ ከፍርድ ቤት የተጻፍ ደብዳቤ ይዞ በሌሊት መጣ። እናቴን በቁጥጥር ስር አውሎ ይዟት ሄደ። የቀረበባትም ክስ በህገወጥ መንገድ ሃሳብን መግለጽ ነበር። ከሰአታት በኋላም መለቀቋን የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ተመለከትኩ። በወቅቱ የአባቴን ቲሸርት ለብሳ የነበረ ሲሆን ጸጉሯም ቢሆን እንደተንጨባረረ ነበር። ነገር ግን ወደቤት እንኳን ሳትመጣ ስለደረሰባት ነገርና ስለጠቅላይ ሚኒስትሩ መጻፏን ቀጠለች። እናቴ በተገደለችበት ቀን አንድ የመንግስት ሚኒስትር የባንክ ደብተሯን እንዳታንቀሳቅስ አግዶባት ስለነበር እሱን ለማስተካከል ወደ ባንክ ቤት ሄደች። ነገር ግን ከባንክ ወጥታ ወደመኪናዋ ስትገባ ግማሽ ኪሎግራም የሚመዝን ተቀጣጣይ ፈንጂ ከመኪናዋ ስር ተቀምጦ ነበር። የ53 ዓመቷ ዳፍኒ ካሩዋና ጋሊዚያ የተጠመደው ቦምብ ፈንድቶ እዛው ህይወቷ አለፈ። ይህንን ታሪክ የሚተርከው ማቲውና ወንድሙ ፖል ያለእናት ቀሩ። በወቅቱ ስልጣን ላይ የነበረው መንግስት ደጋፊዎች በእናቴ መሞት የተሰማቸውን ደስታ በይፋ ይገልጹ ነበር ይላል ማቲው። ሌሎችቸ ደግሞ በገዛ ፈቃዷ ህይወቷን እንዳጣች ይናገሩ ነበር። እናቴ ግን ለማልታ ነጻነት እየታገለች ነው ህይወቷ ያለፈው። የዳፍኒ ካሩዋና ጋሊዚያ አሟሟት የዓለማቀፍ ፕሬስ ነጻነት ቀን ጋዜጠኝነትና በህይወት ላይ ስለሚደርስ አደጋ ሲወራ ደግሞ በሁላችንም ጭንቅላት ቀድሞ የሚመጣው በቅርቡ ቱርክ ውስጥ የተገደለው የሳኡዲ ዜግነት ያለው ጋዜጠኛ ጃማል ሃሾግጂ ነው። ጀማል በሳዑዲ ዝነኛ ጋዜጠኛ ነበር፤ የሶቪየት ሕብረት የአፍጋኒስታን ወረራን በዝርዝር ዘግቧል። እንደ ኦሳማ ቢን ላደን ከመሳሰሉ ግለሰቦች ጋር ቃለ መጠይቅ አድርጓል። በቅርቡ ለመጋባት እቅድ እንደነበራቸው የምትናገረው የኻሾግጂ እጮኛ ከባድ ሃዘን ውስጥ ናት። ለበርካታ አስርት ዓመታት ለሳዑዲ ንጉሳውያን ቤተሰብ የቅርብ ሰው ነበር፤ የሳዑዲ መንግሥት የመገናኛ ብዙሃን አማካሪ ሆኖም ሰርቷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ከሳዑዲ መንግሥት ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ሃገር ጥሎ ወደ አሜሪካ ተሰደደ። በጽሑፎቹም የሳዑዲ አረቢያውን ልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሰልማንን ይተች ነበር። • ዕጽ በማዘዋወር የተጠረጠረችው ናይጄሪያዊት ከእስር ተለቀቀች ኢስታንቡል በሚገኘው የሳዑዲ አረቢያ ቆንስላ ውስጥ እንደተገደለ የታመነው ሃሾግጂ ወደ ቅጥር ግቢው እንደገባ ነበር ታንቆ የተገደለው ይላል የቱርክ መንግስት የሰጠው መግለጫ። ከዚያም የጋዜጠኛው በድን አካል ተቆራርጦ እንዲጠፋ ተደርጓል። በወቅቱም የሳዑዲው አልጋ ወራሽ ልዑል ሞሐመድ ቢን ሰልማን «ሃሾግጂ እንደ አደገኛና አክራሪ ኢስላሚስት ነው የማየው» ብለው ተናግረው ነበር። የሃሾግጂ ቤተሰቦች ግን ጃማል የማንኛውም አክራሪ ቡድን አባል እንዳልነበር ገልፀዋል። «ጃማል ሃሾግጂ ምንም ዓይነት አደጋ ሊያመጣ የሚችል ሰው አልነበረም፤ እሱን አደገኛ ማለት እንደመሳለቅ ነው» የሚል መግለጫም አውጥተው ነበር።
56870718
https://www.bbc.com/amharic/56870718
ባለሙያዎች በኮቪድ ምክንያት የጠፋን የማሽተት ስሜት ለመመለስ 'የማሽተት ሥልጠና' ውሰዱ አሉ
በኮቪድ-19 መያዛቸውን ተከትሎ የማሽተት ስሜታቸውን በፍጥነት መመለስ ያልቻሉ ሰዎች የማሽተት ሥልጠና እንዲወስዱ ባለሙያዎች ምክረ ሃሳብ ሰጡ።
ባለሙያዎቹ የማሽተት ስሜትን ለመመለስ የስትሮይድስ ህክምና ከመከታተል ይልቅ 'የማሽተት ስልጠና' መውሰዱ የተሻለ እንደሆነ ገልጸዋል። ይህ የማሽተት ስልጠና ለወራት የተለያዩ ሽታዎችን በማሽተት አእምሮን እንደገና በማሰልጠን የተለያዩ ሽታዎችን እንዲለይ የማድረግ ሂደት ነው። የዓለም አቀፉ የባለሙያዎች ቡድን እንደሚለው የማሽተት ስልጠና ዋጋው ርካሽ እና ሂደቱም ቀላል ነው። ከስቴሮይድስ ሕክምና ጋር ሲነጻጸርም፤ የማሽተት ስልጠናው የጎንዮሽ ጉዳቶች የሉትም። ከትኩሳት እና ከማያቋርጥ ሳል በተጨማሪ የመሽተት እና የጠዓም ስሜት ማጣት ከኮሮናቫይረስ ዋና ዋና ምልክቶች መካከል ተጠቃሾች ናቸው። ማሽተት አለመቻል ብዙውን ጊዜ ሕመሙ ካለፈ በኋላ በፍጥነት ይመለሳል። ሆኖም ከአምስት ሰዎች መካከል አንዱ ከህመሙ ከስምንት ሳምንት በኋላም የማሽተት ችግር እያጋጠማቸው መሆኑን ሪፖርት አድርገዋል። የኢስት አንግሊያ ዩኒቨርሲቲ ኖርዊች የሕክምና ትምህርት ቤት ባልደረባው ፕሮፌሰር ካርል ፊልፖት እንደሚሉት ኮርቲኮስትሮይድስ ማሽተትን የመመለስ አቅሙ በጣም ጥቂት ነው። "የታወቁ የጎንዮሽ ጉዳቶች ስላሉት ከቫይረሱ በኋላ በሚመጣ የማሽተት ስሜት ማጣትን ለማከም መታዘዝ የለባቸውም ብለን እንመክራለን" ብለዋል። "እንደ ዕድል ሆኖ በኮቪድ-19 የተነሳ ሽታ ማጣት የሚገጥማቸው አብዛኛዎቹ ሰዎች በፍጥነት የማሽተት ስሜታቸውን መልሰው ያገኛሉ" ብለዋል። ከስቴሮይድ የጎንዮሽ ጉዳቶች መካከል የደም ግፊት እና የስሜት መለዋወጥ ተጠቃሽ ችግሮች ናቸው። ዓለም አቀፍ የአለርጂ እና ሪህኖሎጂ ኦረም መጽሔት ላይ በወጣው ጽሑፍ መሠረት ተመራማሪዎቹ "የማሽተት ሥልጠና"ን በአማራጭነት አቅርበዋል። ይህም ተለይተው የሚታወቁ እና በቀላሉ የሚለዩ ሽታ ያላቸውን አራት ነገሮችን ማሽተትን ያካትታል። ለምሳሌ ብርቱካን፣ አዝሙድ፣ ነጭ ሽንኩርት እና ቡናን በቀን ሁለት ጊዜ ማሽተት። ፕሮፌሰር ፊልፖት እንዳሉት ጥናቶች 90 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች ከስድስት ወር በኋላ የማሽተት ስሜታቸውን ሙሉ በሙሉ መልሰው ያገኛሉ። በዚህ ጊዜ ካልተመለሰ ግን አእምሮ ሽታ እንዲለይ እና የተለያዩ ሽታዎችን እንደገና እንዲያውቅ "የማሸተት ስልጠና" ይረዳል።
news-56121975
https://www.bbc.com/amharic/news-56121975
በአሜሪካ ማዕቀብ ምክንያት ፊቱን ወደ አሳማ እርባታ ያዞረው ሁዋዌ
ሁዋዌ በአሜሪካ ዘመናዊ ስልኮቹ ላይ ከባድ ማዕቀቦችን በመጣሉ ምክንያት ፊቱን ለአሳማ ገበሬዎች ቴክኖሎጂ ወደ ማቅረብ አዙሯል።
ግዙፉ የቻይናው የቴሌኮም ኩባንያ የትራምፕ አስተዳደር ለአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት አስጊ ነው ተብሎ በመፈረጁ አስፈላጊ ዕቃዎችን እንዳያገኝ ተደርጓል፡፡ ሁዋዌ የገጠመውን የስማርት ስልክ ሽያጭ ሊያካክስ በመፈለጉ ለቴክኖሎጂው ሌሎች የገቢ ምንጮችን እየተመለከተ ነው፡፡ ለአሳማ ገበሬዎች በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጅ ከመሥራት በተጨማሪ ሁዋዌ የከሰል ማዕድን ኢንዱስትሪ ጋርም ይሠራል፡፡ ሁዋዌ የደንበኞችን መረጃ ለቻይና መንግስት ሊያጋራው ይችላል ሲሉ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ክስ ቢያቀርቡትም ድርጅቱ በተደጋጋሚ አስተባብሏል፡፡ በዓለም ትልቁ የቴሌኮም መሣሪያዎች አምራቹ በዚህ ምክንያት የ 5ጂ ሞዴሎችን አካላት ለማስመጣት የአሜሪካ መንግሥት ፈቃድ ስለላልሰጠው የ 4ጂ ሞዴሎችን በመሥራት ተገድቧል፡፡ በብሔራዊ ደህንነት ላይ ስጋት ፈጥሮብናል ያሉ እንደ እንግሊዝ ያሉ ሌሎች ሃገራትም ሁዋዌ የሚያደርገውን የ 5ጂ ዝርጋታ አስቁመዋል፡፡ በዚህ ዓመት የስማርት ስልኮችን ምርቱን እስከ 60% ድረስ እንደሚቀንሰው ሪፖርቶች ጠቁመዋል፡፡ ይህን ግን ማረጋገጥ አልተቻለም። "ይህ የሚያሳየው የሁዋዌ ምርቶች ጥራትና ልምዳችን ምንም አይነት ችግር እንደሌለበት ነው፡፡ ሁዋዌ በጂኦፖለቲካዊ ውዝግብ መካከል የተያዘ በመሆኑ ለሁዋዌ የመጫወቻ ሜዳው አይደለም" ሲሉ የኩባንያው ቃል አቀባይ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ስለዚህ ሁዋዌ ፊቱን ወደ ሌሎች የገቢ ምንጮችን ያዞረ ይመስላል። እንደክላውድ ኮምፒውቲንግ፣ ስማርት ተሽከርካሪዎች እና ተለባሽ መሣሪያዎች እንዲሁም ስማርት መኪና የማምረትም ዕቅዶች አሉት። በጥቂት ተጨማሪ ባህላዊ ኢንዱስትሪዎች ላይ ዓይኑን ጥሏል፡፡ የአሳማ እርባታ ቻይና በዓለም ትልቁ የአሳማ እርሻ ኢንዱስትሪ ባለቤት ስትሆን፣ የአለማችን አሳማዎች ግማሽ ያህሉ መኖሪያ ናት፡፡ በሽታዎችን ለመለየት እና አሳማዎችን እንቅስቃሴ ለመከታተል በሚያስችለው አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አማካኝነት የአሳማ እርሻዎችን ለማዘመን ቴክኖሎጂው እየረዳ ነው፡፡ የፊት መለያ ቴክኖሎጂ እያንዳንዱን አሳማዎች መለየት ሲያስችል ሌሎች ቴክኖሎጂዎች ደግሞ ክብደታቸውን፣ አመጋገባቸውን እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎቻቸውን ይቆጣጠራሉ፡፡ ሁዋዌ የፊት ለይቶ የማወቅ ቴክኖሎጂ በማዘጋጀት ላይ ሲሆን ባለፈው ወር ግን ትችት ገጥሞታል። ምክንያቱ ደግሞ ከእግረኞች ምስል መካከል የኡሂጉር ተወላጅ የሆኑ የሚመስሉትን ሰዎችን ለይቶ በሚያሳውቀው ስርዓቱ ነው። እንደ ጄዲዳትኮም፣ አሊባባን ጨምሮ ሌሎች የቻይና ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ከአሳማ ከሚያረቡ አርሶ አደሮች ጋር አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለማስተዋወቅ እየሠሩ ነው፡፡ የሁዋዌ ቃል አቀባይ አክለውም "በ 5ጂ ዘመን ለኢንዱስትሪዎች የበለጠ እሴት ለመፍጠር አንዳንድ ባህላዊ ኢንዱስትሪዎችን በኢንፎርሜሽን እና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) እንደገና ለማነቃቃት የምንሞክርበት ሌላ ምሳሌ ነው" ብለዋል፡፡ የከሰል ማዕድን እና መረጃ የሁዋዌ መስራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሬን ዤንግፈይ በዚህ ወር መጀመሪያ በሰሜን ቻይና ሻንሺ ግዛት የማዕድን ፈጠራ ቤተ-ሙከራ በይፋ አስጀምረዋል። ዋና ሥራ አስፈጻሚው ለድንጋይ ከሰል ማዕድን አውጪዎች "አነስተኛ ሠራተኞችን፣ ከፍተኛ ደህንነትን እና ከፍተኛ ብቃትን የሚያመጣ እና ማዕድን አውጪዎቹ በሥራ ቦታቸው ሱፍ እና ከረቫት እንዲለብሱ" የሚያስችላቸውን ቴክኖሎጂን ለማዳበር ይፈልጋሉ፡፡ በዝግጅቱ ላይ በክብ ጠረጴዛ ዙሪያ በተደረገ ስብሰባ ላይ ሬን ኩባንያው ከሰል ማዕድን እና ከብረት እንደ ቴሌቪዥኖች፣ ኮምፒውተሮች እና ታብሌቶች ያሉ ምርቶች ላይ ትኩረት እያደረገ ይገኛል፡፡ "በስልክ ሽያጮች ላይ ሳንመሠረት እንኳን በመቀጠል እንችላለን" ያሉት ሬን የአሜሪካ ኩባንያዎች ያለፍቃድ ከሁዋዌ ጋር እንዳይሠሩ የሚያግደውን የጥቁር መዝገብ ያነሳል የሚል እምነት እንደሌላቸው ጨምረው ጠቅሰዋል፡፡
news-54053426
https://www.bbc.com/amharic/news-54053426
ኮሮናቫይረስ ፡ አውስትራሊያ 85 ሚሊዮን ክትባቶች ለዜጎቿ ልታቀርብ ነው
የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚንስትር አሁን እየበለጸጉ የሚገኙት ሁለቱ ክትባቶች ስኬታማ የሚሆኑ ከሆነ 85 ሚሊዮን ክትባቶችን መንግሥት ለሕዝቡ እንደሚያቀርብ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚንስትር ስኮት ሞሪሰን አገራቸው የኮሮናቫይረስ ክትባት ለዜጎቿ በነጻ ለማቅረብ ሁለት የኮሮናቫይረስ ክትባቶችን ለመግዛት ስምምነቶችን ፈርማለች ብለዋል። እንደ ጠቅላይ ሚንስትሩ ከሆነ አውስትራሊያ ክትባቶቹን ለመግዛት 1.24 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ታደርጋለች። "25 ሚሊዮን አውስትራሊያውያን ከየካቲት 2013 ጀምሮ ክትባቱን ማግኘት ይችላሉ ለዚህ ግን ማረጋገጫ የለም" ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ስኮት የካቲት ላይ ለዜጎች ክትባቱን በነጻ ማቅረቡ መቶ በመቶ እርግጠኛ ባይሆንም የአገሪቱ የጤና ባለሙያዎች ክትባቶቹ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ይሁንታቸውን የሚሰጡ ከሆነ፤ አውስትራሊያ ክትባቶቹን ቀድማ እንደምታገኝ ጠቁመዋል። አንደኛው ክትባት በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እና በመድኃኒት አምራቹ ኩባንያ አስትራዜኔካ ጥምረት እየበለጸገ የሚገኝ ሲሆን፤ ሌላኛው ደግሞ በአውስትራሊያው ኩዊንስላንድ ዩኒቨርሲቲ እና ሲኤስኤል የሚመረት ነው። አውስትራሊያ ለመግዛት ውል ከያዘችው መካከል 33.8 ሚሊዮን ክትባት ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን 51 ሚሊዮን የሚሆነው ደግሞ በኩዊንስላንድ ዩኒቨርሲቲ የሚመረተውን ነው። በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እየተዘጋጀ የሚገኘው ክትባት በሦስተኛ ደረጃ ክሊኒካዊ ሙከራ ላይ የደረሰ ሲሆን በ30ሺህ ሰዎች ላይ ክትባቱ ተሞክሯል። በመላው ዓለም የሚገኙ አገራት የኮሮናቫይረስ ክትባት እንዲደርሳቸው የተለያዩ አይነት ጥረቶችን ሲያካሂዱ ቆይተዋል። ሐምሌ ወር ላይ የዓለም ጤና ድርጅት 165 የዓለም አገራት፤ ድሃ አገራት ክትባቱን ለዜጎቻቸው እንዲያደርሱ ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎት ማሳየታቸውን አስታውቆ ነበር። በዓለም ዙሪያ በአሁኑ ወቅት 140 የኮሮናቫይረስ ክትባቶችን ለማበልጸግ ምርምሮች እየተከናወኑ ይገኛሉ። አውስትራሊያ እስካሁን ድረስ ከ26ሺህ በላይ ዜጎቿ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሲሆን 769 ደግሞ ህይወታቸው አልፏል።
news-45062153
https://www.bbc.com/amharic/news-45062153
ጀዋር መሐመድ ከ"ቲም ለማ" ጋር ምስጢራዊ ግንኙነት ነበረው?
ጀዋር መሃመድ ከአገር ከወጣ 15 ዓመታትን አስቆጥሯል። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያን መሬት ከረገጠ ዐስር ዓመታትን ደፍኗል።
ገጠር አካባቢ ተወልዶ እንዳደገ የሚናገረው ጀዋር ለአዲስ አበባ ብዙም ትውስታ ባይኖረውም ያደገበት ገጠር ወንዙ ተራራው ከህሊናው አልጠፉም። ልጅ ሳለ ባደገበት ቀዬ በኦነግና በኢህአዴግ መካካል ግጭት የነበረበት በመሆኑ "የልጅነት ትውስታዬ ከሌሎች ልጆች የተለየ ነው" ይላል። ትግል ውስጥ የገባውም ይህንን ሁነት ለመቀየር እንደሆነ ይናገራል። "ልጆቼ እኔ ባደኩበት ሁኔታ እንዲያድጉ አልሻም" በእርሱ ላይና በሚመራው ሚዲያ ላይ ተመሥርቶ የነበረው የሸብርተኝነት ውንጀላ ከተነሳ ጀምሮ የጃዋር ወደ አገር ቤት ማቅናት ሲጠበቅ ነበር። ያ ቀን ነገ ቅዳሜ ሆኗል። • ጀዋር እና ዐብይ ምን ተባባሉ? • በሰኔ 16ቱ ፍንዳታ የተጠረጠሩ 5 ግለሰቦች ላይ ክስ ሊመሰረት ነው ጉዞውን አስመልክቶ ብዙዎች ስለ ደኅንነቱ ስጋት ገብቷቸው "የአትመለስ" ማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ጭምር ከፍተው ነበር። ይህ የወዳጆቹ ሥጋት የኢንጂነር ስመኘውን ግድያ ተከትሎ እየተጋጋመ መጥቶ ነበር። "የእኔም ውሳኔ፣ የእነርሱም ስጋት ልክ ነው" የሚለው ጃዋር መንግሥት ለደኅንነቱ ዋስትናና ጥበቃ እንደሚያደርግለት አልሸሸገም። የእርሱን ወደ አገር ቤት የመመለስ ፋይዳ ሲያጠናክርም "በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ በመቃወም ኢትዮጵያ አሁንም ብጥብጥ ውስጥ እንዳለች በማሳየት በአመራርና በሕዝቡ ላይ ያለውን በራስ መተማመን ለመሸርሸር ጥረት የሚያደርጉ ቡድኖች እንዳሉ ይናገራል። ስለሆነም ይህንን አስተሳሰብ ለማዳከም የእርሱ ወደ አገር ቤት መመለስ አዎንታዊ ድርሻ እንደሚኖረው በጽኑ ያምናል። በሕይወቱ ላይ የሚደርስ አደጋ ካለ እስከዛሬ የለፋበት በጎ ዓላማ ማራመጃ በመሆኑ እንደኪሳራ እንደማያየው ያስረዳል። "ሕይወታችን በፈጣሪ እጅ እንጂ በፖሊስ እጅ ስላልሆነ፤ አደጋ ይመጣል ብለን ትግል አናቆምም" የሚለው ጀዋር ባለፉት አራት ዓመታት በእርሱ ላይ ሙከራዎች ተደርገው እንደነበርና አያሌ የሥራ ባልደረቦቹ እንደተሰው አስታውሶ የርሱ ነፍስ ከሌሎች የተለየች እንዳልሆነች ይጠቅሳል። ሐምሌ 30 ለጀዋር የዛሬ ሁለት ዓመት ሐምሌ 30 በኦሮሚያ የተጠራው የተቃውሞ ሰልፍ አቶ ለማ መገርሳ ሥልጣን እንዲይዙ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ነበረው ይላል። ያቺ ቀን ታሪካዊ እንደሆነች በመጥቀስ። በዚያች ዕለት ከሁለት መቶ በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ ይናገራል። ባለፉት አራት ዓመታት 5 ሺህ ሰው እንደተሰዋ ገልፆ ለሚመጣው ለውጥ ክብሩን እንደሚያገኝ ሁሉ ለጠፋውም ቢኾን ኃላፊነቱን እወስዳለሁ ብሏል። ወደ ኢትዮጵያ የሚመለስበት ቀን ሃምሌ 30 መሆኑም ለዚሁ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የታቀደ ነው። በዚሁ ዕለት የትግሉ እምብርት ሆና ወደምትወሰደው አምቦ፣ እንዲሁም ጊንጪና ጉደር አካባቢ በመሄድ በትግሉ ሕይወታቸውን ያጡ ቤተሰቦችን የማግኘትና የማወያየት ፕሮግራም፤ እንዲሁም በእስር ቤት የተጎዱትን የማቋቋምና የመርዳት ሥራ ለመሥራት እቅድ ይዟል። ጀዋር ትግራይን ያውቃታል? ከአገር ከመውጣቱ በፊት በአንድ ወቅት ለአፍታ አክሱም ይሂድ እንጂ የትግራይ ክልልን እንደማያውቀው ይናገራል። ላለፉት 27 ዓመታት ህወሓት በሠራው ስህተት በትግራይና በሌሎች ክልሎች መራራቅ ተፈጥሯል ብሎ የሚያምነው ጀዋር ጉዞው ህወሓት የበላይነቱን በማጣቱ በኢህአዴግም ሆነ በክልሉ የተፈጠረውን ውጥረት የማርገብ ዓላማ እንዳለው አስታውቋል። ከሕወሓት አመራሮች፣ ከክልሉ ምሁራንና አዛውንቶች ጋር በመወያየት የመፍትሄ ሐሳብ ለማቅረብ እንደሚፈልግም ጨምሮ ተናግሯል ። "ልባቸውን ከፍተው ካናገሩኝና ጆሯቸውን ሰጥተው ካዳመጡኝ፤ ጉዞዬ ከፍተኛ ስኬት እንደሆነ እቆጥረዋለሁ" ብሏል። ቁጭ ብሎ ከመነጋጋር በተለየ የማዳመጥ ሥራ መሥራት እፈልጋለሁ የሚለው ጀዋር "ሐሳባቸው ምንድን ነው" የሚለው ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ጠቅሷል። "በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የመስጋትና የመከፋት ስሜቶችን ስለማይ ስጋታቸው ምን እንደሆነ በማዳመጥ የመፍትሔ ሐሳብ ለማቅረብ እሞክራለሁ" ብሏል ጉዞው በዚህ ብቻ የሚጠናቀቅ ሳይሆን ከአማራ ሕዝብ ጋር የተጀመረው የእርቅ ብቻ ሳይሆን የትግል አጋርነት ለማጠናከር ከክልሉ አመራርና ምሁራን ጋርም ውይይት ያደርጋል። በምሥራቅ ኢትዮጵያ በሚኖረው ጉዞም በተለይ ባለፉት ሁለት ዓመታት በኦሮሚያና በሶማሌ ክልል ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት ለመፍታት ከአገር ሽማግሌዎችና ምሁራን ጋር ውይይት እንደሚያደርግም ገልጿል። ጃዋር ራሱን እንደ ነጻ አውጪ ይመለከታል? ሰላማዊ ትግልን በሚመለከት ውጭ አገር በሚገኙ በተለያዩ የትምህርት ተቋማት ለትግሉ የሚረዳውን ዕውቀት እንደቀሰመ ይናገራል። ወጣቶችንም በዚህ ጉዳይ ላይ በማሰልጠን ትግሉ ላይ እንዲሰማሩ አብቅቷል። ይሁን እንጂ ራሱን አንደለውጡ ቁልፍ መሪ ሳይሆን ሌት ተቀን በመሥራት ኃላፊነቱን እንደተወጣ አንድ ተራ ወጣት እንደሚቆጥር በጽኑ ይናገራል። "ለውጡን ያመጡት የታገሉት ወጣቶች ናቸው" ይላል፣ ደጋግሞ። ይህን የሚለው "ለፖለቲካዊ ትክክልነት" ፍጆታ ይሆን ወይስ በእርግጥም ይህ የሚያምንበት ሐሳብ እንደኾነ ከቢቢሲ የተጠየቀው ጃዋር ይህንኑ ደጋግሞ አረጋግጧል። የነለማ ወደፊት መምጣትና ከነ ገዱ ጋር በመቆራኘት የሠሩት ሥራ አገሪቷን እንዳዳነም ጨምሮ አብራርቷል። ከ "ቲም ለማ" ጋር ምስጢራዊ ግንኙነት? አሁን ካሉት አመራሮች ጋር በትግሉ ወቅት የቀደመ ትውውቅና ግንኙነት ስለመኖሩ የተጠየቀው ጀዋር ቀጥተኛ ምላሽ ለመስጠት ባይፈቅድም አሁን ያለው አመራር ወደፊት ገፍቶ እንዲመጣ ውስጥ ውስጡን ላለፉት ዐሥርታት በደኅንነትም በወታደራዊ ክንፍ በርካታ ሥራ ሲሠራ መቆየቱን ለቢቢሲ ተናግሯል። ነገር ግን ከእነርሱ ጋር ከመነጋገርና ከግንኙነቱ ይልቅ መናበቡ ያይል እንደነበር ያስታውሳል። ወደፊት ከመጣው አመራር በተለይም ከ"ቲም ለማ" ጋር በቀደመው ጊዜ እነማን ተሳትፎ እንደነበራቸው ጀዋር በስም መጥቀስ ባይፈቅድም ወደፊት ታሪክ የሚያወጣው ነገር ይኖራል ሲል ጥያቄውን በደምሳሳው አልፎታል። የጀዋር ገቢ ምንጭ ምንድን ነው? ጀዋር በምን ይተዳደራል? የገቢ ምንጩስ ምንድነው? የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር ኃ/ማሪያም ደሳለኝን የአንድ ወቅት ንግግር ጠቅሶ " መቼም በጆንያ የሚሰጠኝ የለም" ሲል ከቀለደ በኋላ ዲያስፖራው የኦሮሞ ማኅበረሰብ የሚያደርገውን ድጋፍ በስተቀር ከሌላ መንግሥትም ሆነ ቱጃር ግለሰብ የተገኘ ምንም ዓይነት ድጋፍ እንደሌለ ተናግሯል። ከአንዳንድ መንግሥታት ጭምር ችሮታዎች ይቀርቡ እንደነበር፣ ነገር ግን ለመቀበል ፍቃደኛ ሳይሆኑ መቆየታቸውን ያስታውሳል። ጀዋር ከቢቢሲ ጋር በነበረው ዘለግ ያለ ቆይታ አገር ቤት ከገባ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ በአማርኛ ፣ በኦሮምኛ፣ በእንግሊዝኛና በሌሎች ቋንቋዎች ዕለታዊ ጋዜጣ እንዲሁም የራዲዮ ጣቢያ ለመክፈት በመጨረሻው ምዕራፍ እንደሚገኝም ጠቁሟል።
news-55909547
https://www.bbc.com/amharic/news-55909547
የሚየንማር ወታደራዊ መሪዎች "አገሪቷን ለማረጋጋት" በሚል ፌስቡክን አገዱ
ከቀናት በፊት የሚየንማርን መንግሥት በኃይል የገረሰሰው ወታደራዊ ኃይል የማህበራዊ ሚዲያውን ፌስቡክ አግዶታል።
ወታደራዊ መሪዎቹ ፌስቡክን ለማገድ ምክንያት ነው ያሉት "አገሪቷ እንድትረጋጋ" ለማድረግ ነው ብለዋል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ የተነሳውን መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ በርካታ የአገሪቷ ዜጎች ተቃውሟቸውን እያሰሙ ያሉት በፌስቡክ ነው። ፌስቡክ ለተቃውሞው አጋርም ሆኗል እየተባለ ነው። ከዚህ ሰላማዊ አመፅ ጋር ተያያይዞ የአገሪቱ ምክር ቤት አባላት ከመዲናዋ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቶች ወደ ውጭ አንወጣም በማለት ተቃውሟቸውን እያሳዩ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በያንጎን ከተማ እንዲሁ ነዋሪዎች ከበሮ በመደብደብ የሰላማዊ አመፁን እንዳጠናከሩ እየተዘገበ ነው። የፌስቡክ ሚና ምንድን ነው? የአገሪቱ ኮሚዩኒኬሽንና መረጃ ሚኒስቴር እንዳሳወቀው ፌስቡክ ለቀናት ያህል ዝግ እንደሚሆን ነው። ነገር ግን ሚኒስቴሩ ውሳኔውን ካሳለፈ በኋላ ቢቢሲ ባገኘው መረጃ መሰረት አንዳንዶች ፌስቡክን እየተጠቀሙ እንደነበር ነው። በያንጎን የጉዞና የአስጎብኝ ድርጅት ያለው አንቶኒ አንግ ለቢቢሲ እንደተናገረው በዋይፋይ ፌስቡክን መጠቀም እንደሚችልና በዳታ ብቻ እንደታገደ ተናግሯል። በርካቶችም ፌስቡክን መጠቀም ያስችላቸው ዘንድ አማራጭ ቪኢኤን እየጫኑ እንደሆነም አስረድቷል። ነገር ግን ይህንን ከተናገረ ከሰዓታት በኋላ ሙሉ በሙሉ ፌስ ቡክ ተዘግቷል። በርካቶችም ሃሳብን የመግለፅ ነፃነትን የሚጥስ ነው በማለት እየተቹት ነው። ከሚየንማር 54 ሚሊዮን ዜጎች መካከል ግማሹ ፌስቡክን የሚጠቀሙ ሲሆን በተለይ በዚህ ወቅትም የአገሪቱ በርካታ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና አቀንቃኞች መፈንቅለ መንግሥቱን ለመቃወም የፌስቡክ ገፆችን በመፍጠር ድምፃቸውን እያሰሙ ነበር። ፌስቡክ መታገዱን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ "ባለስልጣናቱ እግዱን እንዲያነሱና የሚየንማር ዜጎች ከቤተሰቦቻቸው፣ ከወዳጅ፣ ዘመድና ጓደኞቻቸው ጋር በነፃነት መረጃ እንዲለዋወጡና እንዲገናኙ ማድረግ አለባቸው" በማለት ኩባንያው ጠይቋል። ቴሌኖር ሚየንማር የተባለው የቴሌኮም ኩባንያ በበኩሉ ፌስቡክን እንዲያግድ የተሰጠውን የመንግሥት ትዕዛዝ ተግባራዊ ቢያደርግም ይህ ሁኔታ የሰብዓዊ መብትን የሚጥስ ነው በማለት በመግለጫው አውጥቷል።
news-50204861
https://www.bbc.com/amharic/news-50204861
በፈረንሳይ ኩሽና ውስጥ ተሰቅሎ የተገኘ ስዕል በ24 ሚሊዮን ዩሮ ተሸጠ
በዕውቅ ጣሊያናዊ ሰዓሊ ተስሎ የነበረው እና ለረዥም ዓመታት ጠፍቶ የቆየው ስዕል በአንዲት አዛውንት ፈረንሳያዊ ሴት ኩሽና ውስጥ ከተገኘ በኋላ ሪኮርድ በሆነ በ24 ሚሊዮን ዩሮ ዋጋ በጨረታ ተሸጠ።
ስዕሉ ለበርካታ ዓመታት በኩሽና ውስጥ ከማብሰያ ምድጃ በላይ ግድግዳ ላይ ተንጠልጥሎ ቆይቷል። ይህ የስዕል ሥራ ከአንድ ወር በፊት ነበር በሰሜናዊ ፈረንሳይ የተገኘው። 6 ሚሊዮን ዋጋ ያወጣል ተብሎ ቢገመጥም፤ ከተገመተው አራት እጥፍ በሆነ ዋጋ በጨረታ ተሽጧል። • ለ21 ዓመታት የኢትዮጵያን ቅርስ ደብቀው ያቆዩት ኢትዮጵያዊ • የጨለቆት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የተዘረፈው ዘውድ ይመለስልኝ እያለች ነው አጫራጩ ድርጅት በሥም የልተጠቀሰው የስዕሉ ገዢ ከሰሜናዊ ፈረንሳይ እንደሆነ ጠቁሟል። ስዕሉ ለበርካታ ዓመታት በኩሽና ውስጥ ከማብሰያ ምድጃ በላይ ግድግዳ ላይ ተንጠልጥሎ ቆይቷል። አንድ የስዕል ባለሙያ እና አጫራች ስዕሉን ከተመለከተ በኋላ ባለቤቶቹ የስዕሉን ዋጋ ለማስተመን ባለሙያዎችን እንዲያማክሩ ሲወተውት ነበር ተብሏል። ባለቤቶቹ ግን ስዕሉ እድሜ ጠገብ ሃይማኖታዊ ምልዕክት ያለው ስዕል ከመሆን ባለፈ ብዙ ዋጋ ያለው የጥበብ ሥራ መስሎ አልታያቸውም። በስዕሉ ላይ የተደረጉ ጥልቅ ምርምሮች ስዕሉ የጣሊያናዊው ሰዓሊ ሶኒ ዲ ፔፖ መሆኑን አረጋገጥዋል። በጣሊያን ፍሎረንስ የተወለደው ሶኒ ዲ ፔፖ በ13ኛው ክፈለ ዘመን መጨረሻ ላይ እና በ14ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ የስዕል ሥራዎችን ሰርቷል። ይህ የጥበብ ሥራ በመጠን አነስተኛ ሲሆን 20 ሲ.ሜትር በ26 ሴንቲ ሜትር ያክላል። ስዕሉ የአንድ የስዕል ሥራ አካል ሲሆን የተቀሩት ስዕሎች ሎንደን እና ኒው ዮርክ በሚገኙ የሰዕል ማሳያ ማዕከል ውስጥ ይገኛሉ።
news-48306033
https://www.bbc.com/amharic/news-48306033
ፈረንሳይ፡ 17 ታካሚዎችን የመረዘው ዶክተር
ፈረንሳይ ውስጥ 17 ሰዎችን በመመረዝ የተጠረጠረው የህክምና ባለሙያ ምርመራ እየተደረገበት እንደሆነ ፖሊስ አስታወቀ።
ዶክተር ፍሬዴሪክ ፔሺዬ የማደንዘዣ ህክምና ባለሙያ ሲሆን፤ ከዚህ በፊትም ከሰባት ሰዎች መመረዝ ጋር በተያያዘ ምርመራ ሲደረግበት ነበር። በዚሁ ጉዳይ በአጠቃላይም 9 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል። አቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤት እንደገለጸው፤ ዶክተሩ ተግባሩን የፈጸመው በታካሚዎቹ ላይ ድንገተኛ ችግር የተከሰተ በማስመሰልና ባልደረቦቹ የሚጠቀሟቸው መሣሪያዎች ላይ ችግር በመፍጠር ችሎታውን ለማሳየት አስቦ ነው። • ጨው በየዓመቱ 3 ሚሊዮን ሰዎችን ይገድላል • 49 እናቶችን ያስረገዘው የህክምና ባለሙያ • ስለ እንቅልፍ የተሳሳቱ አመለካከቶች ዶክተር ፍሬዴሪክ ፔሺዬ ግን የቀረበበትን ክስ ሙሉ በሙሉ የካደ ሲሆን፤ ጥፋተኛ ሆኖ የሚገኝ ከሆነ እድሜ ልክ እስራት እንደሚጠብቀው ተገልጿል። የዶክተሩ ጠበቃ ጆን ይቭስ ለ'ኤኤፍፒ' የዜና ምንጭ እንደገለጹት፤ ምርመራው ዶክተሩ ጥፋተኛ ስለመሆኑ አያረጋገረጥም። ''ዶክተሩ ታካሚዎችን እንደመረዘ ሊገምቱ ይችላል፤ ነገር ግን ይህ ግምት ብቻ ነው'' በማለት ተከራክረዋል። የ47 ዓመቱ ፍሬዴሪክ ፔሺዬ በተመሳሳይ ክስ በአውሮፓውያኑ 2017 ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረ ሲሆን፤ ምንም ማስረጃ ባለመገኘቱ በነጻ ተሰናብቷል። ኋላ ላይ ግን የሥራ ፈቃዱ እንዲነጠቅ በፍርድ ቤት ተወስኖ ነበር። ፖሊስ በዚህ ሳምንት 66 ሰዎች ያልታሰበ የልብ ድካም አጋጥሟቸው ነበር በማለት በድጋሚ ለጥያቄ ወስዶታል። በድጋሚ በቀረበበት ክስ መሰረትም እድሜያቸው ከአራት እስከ ሰማንያ የሚደርሱ ታካሚዎች በዶክተሩ ግዴለሽ አሰራር ጉዳት ደርሶባቸዋል። • በሕይወት ከሌለች እናት የተወለደችው ሕፃን ፍሬዴሪክ ፔሺዬ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ '' የምርመራው ውጤት ምንም ይሁን ምን ሙያዬን አጥቻለሁ'' ብሏል። ''ከዚህ በኋላ ታካሚዎችን መርዟል የተባለ ዶክተርን ማን ሊያምን ይችላል? ቤተሰቦቼ በጣም አዝነዋል፤ ልጆቼ አንድ ነገር እንዳይሆኑም እሰጋለው" በማለት የደረሰበትን ጫና ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።
news-45080637
https://www.bbc.com/amharic/news-45080637
የደቡብ ሱዳን መንግሥትና አማፂ ቡድኑ የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ
የደቡብ ሱዳን መንግሥት በስልጣን ክፍፍል ላይ ከሀገሪቱ ዋነኛ አማፂ ጋር ስምምነት ላይ መድረሱ ተገለፀ።
ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር እና የአማፂ ቡድኑ መሪ ስምምነቱን የፈረሙት በጎረቤት ሀገር ሱዳን ነው። ስምምነቱ ማቻር ከአምስቱ ምክትል ፕሬዝዳንቶች አንዱ ሆነው ወደስልጣን መመለስ የሚያስችላቸው ሲሆን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት የሆነውንና ለአምስት አመታት የዘለቀውን የእርስ በእርስ ጦርነት ያስቆማል ተብሎ እምነት ተጥሎበታል። • ደቡብ ሱዳን ለመኪና መግዣ 16 ሚሊየን ዶላር አወጣች • የደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር አልተሳካም • የደቡብ ሱዳኑ ማቻር ሃገር ሊቀይሩ ነው ከዚህ በፊት የተሞከሩ የሰላም ስምምነቶች በሙሉ ሳይሳኩ መቅረታቸው ይታወሳል። " በመጀመሪያ በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ በመስማማት ሁሉም ወገኖች የተኩስ አቁም ለማድረግ ተፈራርመዋል" ሲሉ ስምምነቱ እንዲደረስ ከፍተኛ ሚና የተጫወቱት የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አል ዲርዲሪ ሞሐመድ ተናግረዋል። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አርብ ዕለት ይህ ስምምነት እንደሚሰራ ያላቸውን ዕምነት ሲገልፁ እንደሌሎቹ ስምምነቶች "የተጫነብን" ስላልሆነ ይሰራል ነበር ያሉት። "ይህ ስምምነት አይከሽፍም። የማይከሽፍበት ምክንያት ደግሞ የሱዳን ህዝቦች እራሳቸው በመካከላቸው ሰላም እንዲወርድ በመስማማታቸው ነው " ማለታቸውንም ሮይተርስ ዘግቧል። ደቡብ ሱዳን በ2011 ነፃነቷን ካወጀች በኋላ በእርስ በእርስ ጦርነት ስትታመስ ቆይታለች። ከዚያ በኋላም የብሔር ጥቃቶችና በርካታ ውድመቶችን እስከ 2013 ድረስ አስተናግዳለች። ግጭቱ የተከሰተው በሳልቫኪር እና በማቻር መካከል በተፈጠረው ልዩነት ነበር። ሳልቫኪር በወቅቱ ምክትላቸው የነበሩትን ማቻርን መፈንቅለ መንግስት ለማካሄድ አሲረዋል በሚል ከስልጣን ካሰናበቷቸው በኋላ ሲሆን በወቅቱ ማቻር ውንጀላውን አጣጥለውታል።
news-56506656
https://www.bbc.com/amharic/news-56506656
የግብፁ ሱዌዝ ቦይ 400 ሜትር በሚረዝም የጭነት መርከብ ምክንያት ተዘጋ
የግብፁ ሱዌዝ ካናል ቴክኒካዊ ችግር ባጋጠመው ግዙፍ የጭንት መርከብ መዘጋቱና መጨናነቁ ተዘገበ።
የአደጋ ጊዜ መርከቦች ወደ ሥፍራው ተልከው 400 ሜትር ርዝማኔና 59 ሜትር ስፋት ያለውን መርከብ ለማገዝ ደፋ ቀና እያሉ ነው። ነገር ግን መርከቡ በሥፍራው ለቀናት ቆይቶ በመተላለፊያው ላይ የትራፊክ መጨናነቅ ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት አለ። መርከቡ የትራፊክ መጨናነቅ የፈጠረው ባለፈው ማክሰኞ በሱዌዝ ቦይ በስተሰሜን በኩል ነው። የሱዌዝ ቦይ በመባል የሚታወቀው የግብፅ መተላለፊያ ቦይ የሜድትራኒያን እና ቀይ ባህርን በማገናኘት በእስያና አውሮፓ መካከል አጭሩ የሚባለውን የውቅያኖስ መንገድ ይፈጥራል። ኤቨር ግሪን የተሰኘው ግዙፍ መርከብ ከቻይና ተነስቶ ወደ ኔዘርላንድስ እያቀና ነበር። የግብፅ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት መርከቡ ባጋጠመው ቴክኒካዊ ችግር ምክንያት ነው መሃል ላይ ቆሞ የቀረው። በፈረንጆቹ 2018 የተሠራው ይህ የፖናማ መርከብ ኤቨርግሪን ማሪን በተሰኘው የትራንስፖርት ኩባንያ ባለቤትነት ነው የሚንቀሳቀሰው። መርከቡ የበርካታ የጭነት መርከቦች መተላለፊያ መንገድ ላይ በመቆሙ ምክንያት የመርከቦች እንቅስቃሴ ለጊዜው ተገትቷል። አንድ ከሌላ መርከብ ላይ ሆና ፎቶ ያነሳች ግለሰብ ፎቶውን በማሕበራዊ ድር አምባዎች ላይ አጋርታ ሁኔታው ምን እንደሚመስል ለማሳየት ሞክራለች። መርከቡ መሃል መንገድ ላይ በመቆሙ ምክንያት ከወዲህም ሆነ ከወዲያ የሚመጡ መርከቦች ቆመው ችግሩ እስኪፈታ ከመጠበቅ ውጭ አማራጭ የላቸውም። የግዙፉ መርከብ መንገድ መዝጋት በርካታ ዕቃዎች የጫኑ መርከቦችን በመግታቱ ምክንያት የምጣኔ ሃብት ቀውስ እንዳይመጣ ተንታኞች ይሰጋሉ። መርከቡ ከሥፋራው እንዲንቀሳቀስ ለመርዳት ምናልባት ከሥር ያለውን አሸዋ ቆፍሮ ማውጣት ስለሚጠይቅ ቀናት ሊወስድ ይችላል እየተባለ ነው። መርከቡ በምን ዓይነት ቴክኒካዊ ችግር ምክንያት መንቀሳቀስ እንዳልቻለ አልታወቀም። የሱዌዝ ቦይ 193 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ አለው።
51179305
https://www.bbc.com/amharic/51179305
የጥምቀት በዓል፡ ከበዓሉ አከባባር ጋር በተያያዘ ጎንደር እና ሐረር የተከሰተው ምንድነው?
በሐረር ከጥምቀት በዓል አከባበር ጋር በተያያዘ አለመረጋጋት ተፈጥሮ እንደነበር ተሰምቷል። በዚሁ ዙሪያ የሐረሪ ክልል የጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ናስር ይያ ስለተፈጠረው ነገር ማብራሪያ እንዲሰጡን ጠይቀናቸዋል።
ኃላፊውም ''የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ የእምነቱ ተከታዮች በዓሉን ለማክበርና አካባቢውን ለማስዋብ የተለመደ እንቅስቃሴያቸውን በሚያደርጉበት ወቅት በዓሉን የማይመለከትና ሕግ የማይፈቅደውን ባንዲራ ለመስቀል ሙከራ ያደረጉ በመኖራቸው አለመረጋጋት ተከስቶ ነበር'' ብለዋል። ''ይህንን ተከትሎም ትናንት የሀይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የአካባቢው ወጣቶችና ቄሮዎችን በማስተባበርና የጸጥታ ኃይሎችንም በማቀናጀት ችግር እንዳይፈጠር ማድረግ ችለናል'' ሲሉ አስረድተዋል። ኃላፊው እንዳሉት፤ አንድ ሁለት ሰዎች ሰንደቅ አላማውን ለመስቀል በሚሞክሩበት ወቅት ሌሎች ደግሞ 'ይህን አትሰቅሉም' በሚል ግርግር ተፈጥሮ ነበር። ''እነዚህ [ግርግሩን የፈጠሩት] ሰዎች እምነትን ከእምነት ማጋጨት፤ ሕዝብን ከሕዝብ ማጋጨት ነው እቅዳቸው። በሁሉም አካባቢዎች ታቦት በሰላም ወጥቶ ይገባል። ነገር ግን መስጂድና ቤተክርስቲያን በቅርበት በሚገኙባቸው አካባቢዎች ችግር ለመፍጠር ተሞክሯል'' ብለዋል። ትናንት በሐረር አለመረጋጋት እንደነበርና ተኩስም እንደተሰማ በስፋት እየተነገረ መሆኑን የጠቀስንላቸው ኃላፊው፤ ጠዋት ላይ አንዳንድ ግርግሮች ተፈጥረው የነበሩ ቢሆንም ከሰዓት ከተማው መረጋጋቱን መሆኑን ነግረውናል። ''ዛሬ ታቦት በሚገባበት ወቅት አራተኛ በተባለው አካባቢ ተገቢ ያልሆነ ጭፈራና ንብረት ላይ ድንጋይ መወርወር ጀምረው ነበር። አካባቢው ቤተ ክርስቲያንም መስጂድም ያለበት ከመሆኑ አንጻር በሀይማኖት ስም የተደረገው ነገር ተገቢ አይደለም። ነገር ግን ተፈጥሮ የነበረው ነገር በቁጥጥር ስር ውሏል'' ሲሉ አስረድተዋል። ንብረት ላይ ከደረሰው ጉዳት ውጪ እስካሁን የተጎዳ ሰው አለመኖሩን ኃላፊው ተናግረዋል። አቶ ናስር የጉዳት መጠኑን በትክክል ለመግለጽ ባይችሉም፤ ወደ ስምንት የሚጠጉ ቤቶች ድንጋይ ተወርውሮባቸው መስታወቶች እንደተሰባበሩ ያስረዳሉ። ትናንት ጠዋት ታቦት የሚሸኙ ሰዎች መንገድ ተዘግቶባቸዋል ስለመባሉ የተጠየቁት የጸጥታ ቢሮ ኃላፊው፤ '' ማንም መንገድ የተዘጋበት የለም፤ ማንም መንገድ የዘጋም የለም" ብለዋል። ''ታቦት እንዳያልፍ አልተከለከለም፤ መንገዱም ክፍት ነው። ይሄ ተግባር ውዥንብር ለመፍጠርና ሕዝቡን በእምነት ስም ለማነሳሳት የሚደረግ ጥረት ነው'' ሲሉም አብራርተዋል። ከሁለቱ ቀናት ክስተት ጋር በተያያዘ እስካሁን ሰባት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና ምዕመናን በዓሉን አክብረው ወደቤታቸው ገብተው፣ ከተማዋም ሰላማዊ እንቅስቃሴዋን እንደቀጠለች አቶ ናስር ነግረውናል። ጎንደር የጥምቀት በዓል ማዕከል እንደሆነች የሚነገርላት የጎንደር ከተማም ከጥምቀት በዓል ጋር በተያያዘ አሳዛኝ ክስተት አስተናግዳለች። በጎንደር ጥንታዊው የአፄ ፋሲል ገንዳ አካባቢ እየተካሄደ የነበረው የጥምቀት በዓል ታዳሚያንን እንዲያስተናግድ ተሰድሮ የነበረ የእንጨት ርብራብ ተደርምሶ ቢያንስ 10 ሰዎች ሕይታቸውን ማጣታቸው ተዘግቧል። ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውም አሉ። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በዓሉን ለመደታደም በሺዎች የሚቆጠሩ ጎብኝዎች ወደ ጎንደር አቅንተው ነበር ብሎ ዘግቧል። ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር የጥምቀት በዓልን ለማክበር የሄደው ሳሙዔል ባህሩ በአደጋው የተጎዱ ሰዎች በቃሬዛ ወደ ሆስፒታል ሲወሰዱ ተመልክቻለሁ ይላል። ከባለቤቱ ጋር ጥምቀትን ለማክበር የሄደው ሳሙዔል ከአደጋው በኋላ ከፍተኛ ድንጋጤ እንደነበር ይናገራል። የጎንደር ከተማ ሰላም እና ፀጥታ ኃላፊ አቶ ተስፋ መኮንን የእንጨት ርብራቡ በ'ባለሙያዎች' የተሠራ ነው፤ አደጋው የተከሰተው በእንጨት ርብራቡ ደካማነት አይመስለኝም ብለዋል። "ወጣቶች ወደ ላይ ወጥተው ማክበር ፈልገው ሲወጡ እንጨቱ መሸከም ከሚችለው በላይ ሆኖበት ነው የተደረመሰው።» የአማራ ክልል ፖሊስ ቃል-አቀባይ ኮማንደር መሠረት ደባልቄ 100 ያክል ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ አብዛኛው ቀላል ጉዳት ነው፤ የሞቱ ሰዎች ቁጥር የጠራ መረጃ የለኝም ሲሉ ሰኞ አመሻሹን ላይ ተናግረዋል። ተጎጂዎች ወደ ጤና ተቋማት ተወስደው ሁኔታው ከተረጋጋ በኋላ በዓሉ እንዲቀትል ተደርጓል።
55359558
https://www.bbc.com/amharic/55359558
ትግራይ፡ የመቀለ ከተማ በምን ሁኔታ ላይ ትገኛለች?
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከሾማቸው ኃላፊዎች መካከል አንዱ የሆኑት የመቀሌ ከተማ ከንቲባ አቶ አታኽልቲ ኃይለሥላሴ በከተማዋ የተለያዩ የመሠረታዊ አገልግሎቶች ሥራ መጀመራቸውን ለቢቢሲ ገለጹ።
አቶ አታኽልቲ ኃይለሥላሴ ግጭቱን ተከትሎ ለሳምንታት ተቋርጠው የነበሩት የውሃ፣ የኤሌክትሪክ፣ የጤናና የአየር ትራንስፖርት አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ መጀመራቸውን የገለፁት ከንቲባው፤ የባንክ አገልግሎት ግን በሁለት ቀን ውስጥ የሚያስፈልጋቸውን ዝግጅት አጠናቀው አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ሲሉ ተናግረዋል። ባንኮች ከዚህ ቀደም በወረቀት አገልግሎት የሰጡበት አሰራር ስለነበር እርሱን ወደ ሲስተም ውስጥ እስኪያስገቡ ድረስ የአገልግሎት መስጫ ጊዜው መዘግየቱንም አብራርተዋል። በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ በትግራይ ክልል የጸጥታ ኃይሎችና በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት መካከል የተቀሰቀሰውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ ለ40 ቀናት ያህል በክልሉ የኤሌትሪክ፣ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎቶች ተቋርጠው ቆይተዋል። በእነዚህ ጊዜያት በትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች የስልክ፣ መብራት፣ ኢንተርኔት ባንክና የመሳሰሉት ለዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ወሳኝ የሆኑ አገልግለቶች ከሥራ ውጪ ሆነው ነበር። የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ከአንድ ወር በላይ ከሥራ ገበታቸው ርቀው የነበሩ የመንግሥት ሠራተኞች፣ ከሰኞ ታህሳስ 05/2013 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ገበታቸው ላይ እንዲገኙ ባቀረበው ጥሪ መሰረት፣ በርካታ ግለሰቦች ወደ ሥራ ገበታቸው የተመለሱ ቢሆኑም በየቢሮው በርካታ የወደሙ ነገሮች በመኖራቸው እነዚያን የማስተካከል እና የመመዝገብ ሥራ እየሰሩ መሆናቸውን ከንቲባው ጨምረው አስታውቀዋል። ከመቀለ አዲስ አበባ በአውሮፕላን ለሚደረግ ጉዞ በኢንተርኔት አማካይነት ትኬት ለመቁረጥ አሁንም እንደማይቻል የተጠየቁት ከንቲባው ከኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ ጋር በተያያዘ ይህ መፈጠሩን ገልፀው ድርጅቱ የተለያዩ መፍትሄዎችን እያመቻቸ ነው ብለዋል። ከአዲስ አበባ ትኬት በማስቆረጥ መገልገል እንዲሁም ከእሁድ ጀምሮ ከመቀለ በሚዘረጋ ሲስተም አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ መሆኑንም ገልፀዋል። አቶ አታኽልቲ ከከተማዋ ነዋሪ ጋር በየደረጃው እየተወያዩ መሆኑን አመልክተው፣ በየደረጃው የክፍለ ከተማ እና የቀበሌ ምክር ቤቶችንም እያቋቋሙ መሆኑን ተናግረዋል። "በዋነኛነት የፀጥታው እንዲጠበቅ የምንፈልገው በማኅበረሰቡ ነው" ያሉት ከንቲባው፣ "ያ እስኪሆን ድረስ ግን የፌደራል ፖሊስ እና የመከላከያ ኃይል ከሚመለከተው የመስተዳድር አካል ጋር በመቀናጀት ፀጥታውን በማስከበር ላይ ነው" ብለዋል። በከተማዋ አልፎ አልፎ ዘረፋ እንደሚስተዋል የተናገሩት ከንቲባው ተጨማሪ የፀጥታ ኃይል የሚመደብበት እና ሕዝቡ ድጋፍ በሚፈልግበት ወቅት መረጃ የሚሰጥበትን መንገድ በማመቻቸት ላይ መሆናቸውን ይናገራሉ። በዋነኛነት ከፀጥታ አካሉ እና በኅብረተሰቡ መካከል እንደ ድልድይ ሆነው እንዲያገለግሉ ከኅብረተሰቡ ውስጥ በሥነ ምግባራቸው የተመሰከረላቸው እና ማኅበረሰቡ እኛን ሊጠብቁን እና ሊከላከሉ ይችላሉ ብሎ ላመነባቸው ወጣቶች በጎ ቃደኞች ምልመላ ተደርጎ ገለጻ በመሰጠት ላይ መሆኑን ገልፀዋል። "እስካሁን ድረስ በየዕለቱ መልካም የሚባል ለውጥ እየታየ ነው" የሚሉት ከንቲባው የንግድ ቤቶች፣ የመንግሥት የአገልግሎት ተቋማት እንዲሁም የሰዎች እንቅስቃሴ ወደ መደበኛው ሁኔታ እየተመለሰ መሆኑን አስረድተዋል። በመቀለ ከተማ የመንግሥት ወታደሮች በወሰዱት የሕግ ማስከበር እርምጃ ተገድለዋል ስለተባሉ የከተማዋ ነዋሪዎች የተጠየቁት አቶ አታኽልቲ፣ እርሳቸው ይህንን ኃላፊነት የተረከቡት በቅርቡ መሆኑ እና ከተረከቡበት ቀን አንስቶም ከዝርፊያ እና አለመግባባት ጥቆማዎች ውጪ የሞት መረጃ እንዳልመጣላቸው ጠቅሰው በተሻለ የክልሉን ፀጥታ የሚያስተባብሩ አካላት በጉዳዩ ላይ ምላሽ ቢሰጡ ተገቢ መሆኑን ገልፀዋል። የከተማዋ ነዋሪዎች ስልካችን ይጠለፋል የሚል ስጋት እንዳላቸው በተመለከተ ተጠይቀውም በዚህም ጉዳይም መረጃ እንደሌላቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ባለፈው ጥቅምት ወር ማብቂያ ላይ በትግራይ ክልል የተከሰተውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ የፌደሬሽን ምክር ቤት የክልሉ አስተዳደር እንዲፈርስ ከወሰነ በኋላ የተሰየመው የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ ሥራው ከጀመረ ቀናት ተቆጥረዋል። ክልሉን ያስተዳድር በነበረው ህወሓትና በፌደራል መንግሥቱ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ለወራት ከዘለቀ በኋላ በትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኘው የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ላይ በክልሉ ልዩ ኃይል ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ለሳምንታት የዘለቀ ወታደራዊ ግጭት መካሄዱ ይታወሳል። በዚህም ወቅት የስልክ፣ የመብራትና ሌሎች መሠረታዊ አገልግሎቶች ለሳምንታት ተቋርጠው የቆዩ ሲሆን የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት የክልሉን ዋና ከተማ መቆጣጠሩን ተከትሎ የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ክልሉ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ እንዲመለስ ጥረት እያደረገ መሆኑን ተገልጿል። በትናንትናው ዕለትም በአዲግራትና ውቅሮ ከተሞች ተቋርጦ የነበረው የመብራት አገልግሎት መመለሱን የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል በማኅበራዊ ድረገፁ ላይ አስታውቋል።ድርጅቱ አክሎም የሽሬ፣ አክሱምና አድዋ ከተሞች ኃይል እንዲያገኙም እየሰራ መሆኑንና በጥቂት ቀናት ውስጥ የኃይል አቅርቦቱ ሥራ እንደሚጀምር ይጠበቃል።
news-45764576
https://www.bbc.com/amharic/news-45764576
ጉርሻ፡ በዓለም ዙሪያ ምን ይመስላል?
ሰሞኑን የእንግሊዝ ፖለቲከኞች ስለ ብሬግዚት (ኢንግሊዝ ከአውሮፓ ህብረት የመለየት ጉዳይ) ከመነጋገር ውጪ ሌላ ጉዳይ ላይኖራቸው ይችላል ብለን ልናስብ እንችላል።
በእንግሊዝ ሃገር ጉርሻ ፖለቲካዊ ንግግሮችን አስነስቷል • 5 ሺህ ጉርሻዎች! • አንድ በሞቴ! ሆኖም ግን በዚህ ሳምንት ፖለቲከኞች ካፌዎች እና ምግብ ቤቶች ለሠራተኞቻቸው ጉርሻ እንዳይሰጡ ስለመከልከል ሲወያዩ ቆይተዋል። በዚህ ጉዳይ እንደ እንግሊዞች ነገሩን በጥሞና የተነጋገረበት ሃገር ግን የለም። በ17ኛው ክፍለ ዘመን እንግሊዞች ጉርሻ መስጠት እንደጀመሩ ይታመናል። ተግባሩም የተጀመረው ለዝቅተኛው የማህበረሰብ ክፍል ስጦታ የመለገሻ ተግባር ተደርጎ ነበር። አሁን ጉርሻ መስጠት በዓለም ዙሪያ ልማድ ሆኗል። ይሁን እንጂ በአንዳንድ ሃገራት ጉርሻ መስጠት እንደ ስድብ ሊቆጠር ይችላል። በአሜሪካ ለምሳሌ ጉርሻ ለአንድ ሠራተኛ ሌላኛው ትልቁ የገቢ ምንጭ ነው። አሜሪካ ጉርሻ ከመስጠት ቀጥሎ ግብር ሰነድ ቅጽ መሙላት ነው የሚያደናብረው እየተባለ መቀለድ በአሜሪካ የተለመደ ሆኗል። አሜሪካውያን ወደ አውሮፓ መጓዛቸውን ተከትሎ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ጉርሻ መስጠት በአሜሪካ ተለመደ። ይህ ልማድ ፀረ-ዲሞክራሲ ነው፤ ሠራተኞችንም እንደ ለማኝ ይቆጥራል ተብሎ ብዙም ድጋፍ አልነበረውም። 21ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ግን በአሜሪካ ጉርሻ የደመወዝ ዋና አካል ተደርጎ ይቆጠራል። ኦፈር አዛር የተባሉ የምጣኔ ሃብት ባለሙያ እ.አ.አ በ2007 ከምግብ ቤቶች ብቻ ሠራተኞች በጉርሻ መልክ 42 ቢሊየን ዶላር እንደተቀበሉ ይናገራሉ። ጉርሻ መስጠት በቻይና አሁን ያለው ልምድ እምብዛም ነው። ቻይና ልክ እንደ ብዙ እስያዊ ሃገራት ቻይና ውስጥ ጉርሻ የመስጠት ባህል እምብዛም ነው። እንዲያውም ለአስተናጋጆች የሚሰጠው ጉርሻ እንደ ጉቦ ተቆጥሮ ለዘመናት ተግባሩ የተከለከለ ነበር። ዛሬም ቢሆን ተግባሩ ብዙም አልተለመደም። የሃገሪቱ ነዋሪዎች በሚያዘወትሯቸው ምግብ ቤቶች ጉርሻ አይሰጥም። በውጪ ሃገር ዜጎች በሚጎበኙ ሆቴሎች ውስጥ ግን ልማዱ እየተስፋፋ ነው። በጃፓን ለአስተናጋጅ ጉርሻ መስጠት እንደ ስድብ ይቆጠራል ጃፓን ለሠርግ፣ ቀብር እና ለተለያዩ ሁነቶች ጉርሻ መስጠት የተለመደ ቢሆንም በሌላ ሃገራት በተለመደው መልኩ ገንዘብ መስጠት ግን ተቀባዩን የማሳነስ ስሜት ይፈጥራል። ፍልስፍናው ተጠቃሚው ጥሩ አገልግሎት እና መስተንግዶ ማግኘት የተለመደ መሆን አለበት የሚል ነው። ጉርሻ መስጠት ግድ ከሆነ ጉርሻው ሲሰጥ በፖስታ ተደርጎ አክብሮትን በሚያሳይ መልኩ መሆን አለበት። በጃፓን የሚገኙ የሆቴል ውስጥ አስተናጋጆች ፍጹም ጨዋ፣ ሰዓት አክባሪ እና ጉርሻ አክብሮት በተሞላበት መልኩ አልቀበልም ኢንዲሉ ስልጠና ይሰጣቸዋል። ፈረንሳይ አስተናጋጆች የተሻለ ደመወዝ እንዲያገኙ እና ጉርሻ ከመቀበል እንዲቆጠቡ በማሰብ ፈረንሳይ ምግብ ቤቶች በሂሳብ ላይ የአገልግሎት ክፍያን (ሰርቪስ ቻርጅ) እንዲጨምሩ የሚያስገድድ ሕግ አወጣች። ይህም በጊዜ ሂደት ውስጥ በሌሎች የአውሮፓ ሃገራት እየተለመደ መጣ። ወጣቶች ብዙውን ጊዜ ጉርሻ እንደማይሰጡ ቢነገርም ጉርሻ መስጠት ግን አልቀረም። እ.አ.አ በ2014 15% የሚሆኑት የፈረንሳይ ተጠቃሚዎች ጉርሻ እንደማይሰጡ ተናግረዋል። ይህም ቁጥር ከዓመት በፊት ከነበረው ቁጥር በሁለት እጥፍ ጨምሯል። ደቡብ አፍሪካ እ.አ.አ 2017 በደቡብ አፍሪካ በየቀኑ 140 መኪናዎች ተሰርቀዋል። የሥራ ፈላጊው ሕዝብ ቁጥር 25 በመቶ በሆነባት ደቡብ አፍሪካ፤ በሌሎች ሃገራት ባልተለመደ መልኩ ለመኪና ጥበቃ ጉርሻ ይሰጣል። ሹፌሮች የማቆሚያ ቦታ እንዲያገኙ ከመርዳት አንስቶ መኪናቸውን እስከመጠበቅን ያካትታል። ስዊዘርላንድ በስዊዘርላንድ ያሉ ተጠቃሚዎች ለምሳሌ ገንዘብ ጠቅልለው ለሆቴል ሠራተኞች ወይም ለፀጉር አስተካካዮች ይሰጣሉ ይባላል። ሆኖም ግን የሃገሪቱ ዝቅተኛው ክፍያ ከዓለም ዙሪያ ከፍተኛው ነው። ለምሳሌ የአስተናጋጅ ደመወዝ በወር ከ4000 ዶላር ይበልጣል። ሕንድ የሕንድ ምግብ ቤቶች እና ካፍቴሪያዎች በሚያስከፍሉት ዋጋ ላይ ተጨማሪ የአገልግሎት ክፍያ ስለሚጠይቁ ጉርሻ መስጠት ተጨማሪ ወጪ ነው። ከዚህ ውጪ በሕንድ ያለው ልማድ የሂሳቡን 15% ወይም 20% መተው ነው። እ.አ.አ በ2015 በተደረገ ጥናት መሰረት ከእስያ ሃገራት ሕንዶች ከባንግላዴሺ እና ከታይላንዶች ቀጥሎ ከፍተኛ ጉርሻ በመስጠት የታወቁ ናቸው። የሲንጋፖር መንግሥት ጉርሻን አያበረታታም ሲንጋፖር ለሆቴል ሰራተኛ ውይም ለታክሲ ሹፌር አንስተኛ ጉርሻ መስጠት አያስቆጣም። ይሁን እንጂ ጉርሻ መስጠት በራሱ በሲንጋፖር ብዙ የሚያነጋግር ጉዳይ ነው። በሃገሪቱ የመንግሥት ድረ-ገጽ ላይ 'ጉርሻ መስጠት የደሴቱ የኑሮ ዘይቤ አይደለም' የሚል ጽሑፍ አለ። ግብፅ ጉርሻ መስጠት በግብፅ ባህል ውስጥ በጣም የሰረፀ ሲሆን፤ ጉርሻ ባክሺሽ በመባል ይታወቃል። አቅም ያላቸው ግብፃውያን እንደ አስተናጋጅና ቤንዚን ቀጂ ላሉ ሠራተኞች በየጊዜው ጉርሻ ይሰጣሉ። ይህም ባህል የሥራ እጦት ቁጥር 10% በሆነበት ኢኮኖሚ ውስጥ በጣም ተመስጋኝ ነው። ጉርሻም የሃገሪቱን ጠቅላላ የሃገር ውስጥ ምርት 40% ያክላል። የግብፅ በጉርሻ ላይ መተማመን የባክሺሽን ባህል አፋጥኗል ኢራን ኢራንን ለመጎብኘት የሚሄዱ ሰዎች ታሩፍ የተሰኘውን ባህል ያገኛሉ። እሱም በኢራን ባህል ማንኛውንም ክፍያ በጨዋነት በመጀመሪያ እምቢ ማለት ሲሆን፤ የታክሲ ሹፌርም ጭምር በመጀመሪያ የሚሰጠውን ክፍያ አይቀበልም። ይህ ግን ለጉርሻ አይደረግም ምክንያቱም ጉርሻ የዕለት ተዕለት ኑሮ አካል ሆኗል። ታሩፍ የተሰኘው ግራ አጋቢ የኢራን ባህል ጉርሻን አያካትትም ሩስያ በሶቪየት ዘመን ጉርሻ መስጠት ጭራሽ አይቻልም ነበር። ምክንያቱም የሠራተኛውን ክፍል እንደማሳነስ ተደርጎ ስለሚቆጠር ነው። ሩስያውያን ግን ስም አላቸው እሱም 'ሻዬቪዬ' ሲሆን 'ለሻይ' እንደ ማለት ነው። ጉርሻ መስጠት እ.አ.አ በ2000ዎቹ ተመልሶ ቢመጣም በእድሜ የገፉ ሰዎች ግን አሁንም እንደ ስድብ ሊቆጥሩት ይችላሉ። አርጀንቲና ቆንጆ ምግብ ላቀረበ አስተናጋጅ ጉርሻ ቢሰጡ ችግር ውስጥ ባይከትዎትም እንኳን እ.አ.አ በ2004 በወጣው የሰራተኛ ሕግ መሠረት ግን ለምግብ አቅራቢና ለሆቴል ኢንዱስትሪ ጉርሻ መስጠት ሕጋዊ አይደልም ይላል። እንደዚያም ሆኖ ግን ጉርሻ አሁንም ይሰጣል ይህም የአንድን አርጀንቲናዊ አስተናጋጅ ውርሃዊ ገቢ 40% ያህላል።
news-54306940
https://www.bbc.com/amharic/news-54306940
ከፓሪሱ ጥቃት ጋር በተያያዘ 7 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
በፓሪስ ከተማ ከቀድሞ የቻርሊ ሄብዶ መጽሔት ቢሮ አቅራቢያ ከተፈጸመው ጥቃት ጋር በተያያዘ 7 ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ባለስልጣናት አስታወቁ።
ትናንት አንድ ግለሰብ በስጋ መከትከቻ ትልቅ ቢላ ሁለት ሰዎች ላይ ጉዳት አድርሶ ነበር። ትውልደ ፓኪስታናዊ የሆነው እና ድርጊቱን ሳይፈጽም አይቀርም የተባለው የ18 ዓመት ወጣት የወንጀል ድርጊቱ በተፈጸመበት ቦታ ላይ በቁጥጥር ሥር ውሏል። ከወጣቱ በተጨማሪ 6 ሰዎች በቁጥጥር ሥር እንደሚገኙ እና ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ የፈረንሳይ ፖሊስ አስታውቋል። ጥቃቱ የሽብር ጥቃት ተደርጎ ምርመራው እየተከናወነ እንደሆነ የአገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል። የአገር ውስጥ ጉዳዮች ሚንስትሩ ጄራልድ ዳርማኒን “ይህ በግልጽ ጽንፈኛ ኢስላማዊ ሽብርተኝነት ነው” ካሉ በኋላ፤ ፖሊስ በቀድሞ መጽሔት ቢሮ አካባቢ የነበረውን የጸጥታ ስጋት በቸልታ አልፎታል ብለዋል። እአአ 2015 ላይ ሁለት ሙስሊም የፈረንሳይ ዜጎች የቻርሊ ሄብዶ መጽሔት ቢሮን ሰብረው በመግባት በሰራተኞቹ ላይ ተኩስ ከፍተው ሰራተኞቹን ጨምሮ በጠቅላላው 12 ሰዎች ገድለው ነበር። ከዚያም ከፖሊስ ሲሸሹ የነበሩት ጥቃት አድራሾቹ በፖሊስ ተገድለዋል። ቧልት ቀመስ የሆነው ቻርሊ ሄብዶ በቀኝ አክራሪዎች ላይ በመዘባበት በርካታ ስራዎችን የሚያቀርብ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ በካቶሊክ፣ አይሁድና እስልምና እምነቶችም ላይ ፌዝና ቀልድ ማቅረቡ አወዛጋቢ አድርጎታል። በአንደኛው ካርቱን ላይ ነብዩ መሐመድ በተርባን ጥምጥም ፈንታ ቦምብ ጭንቅላታቸው ላይ አድገው ይታያል። ከአምስት ዓመታት በፊት በመጽሔቱ ሰራተኞች ላይ ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ መጽሔቱ የሚዘጋጀው ስፍራው ከማይታወቅ ቦታ ነው። ትናንት የፈጠረው ምንድነው? የአገሪቱ ባለስልጣናት እንደሚሉት ትናንት ከሰዓት ጥቃት የደረሰባቸው ሁለቱ ግለሰቦች የአንድ የዜና ወኪል ሰራተኞች ሲሆኑ ከመስሪያ ቤታቸው ደጃፍ ላይ ሆነው ሲጃራ እያጨሱ ነበር። “የሰዎች ጩኸት ሰምቼ ወደ መስኮቱ ጠጋ ብዬ ስመለከት ትልቅ ቢላ የያዘ ሰው ሁለት ባልደረቦቼን ሲያባርር ተመለከትኩ” ብሏል የዜና ወኪሎቹ ባልደረባ። ጥቃቱ የደረሰባቸው ሁለቱ ግለሰቦች ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ኤኤፍፒ የዜና ወኪል ዘግቧል። ተጠርጣሪው ወንጀሉ በተፈጸመበት ቦታ በቁጥጥር ሥር ከዋላ በኋላ ከሚኖርበት ቤትም አምስት ፓኪስታናውያን ተይዘዋል።
43538338
https://www.bbc.com/amharic/43538338
እስር በአዲስ አበባ እና በባህር ዳር
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ በቅርቡ ከእስር የተፈቱ ጋዜጠኞች፣ ጦማሪያንና ፖለቲከኞች አዲስ አበባ ውስጥ በፖሊስ ትናንት መያዛቸው ተዘገበ።
በተመሳሳይም በአማራ ክልል ዋና ከተማ ባህር ዳር ውስጥ በርካታ ምሁራንና ፖለቲከኞች ቅዳሜ ዕለት በፖሊስ እንደተያዙ መረጃዎች ያመለክታሉ። በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቤት በተዘጋጀ ማህበራዊ ሥነ-ሥርዓት ላይ ታዳሚ ከነበሩትና በፖሊስ ከተያዙት መካከል ከሳምንታት በፊት ከረዥም እስር በኋላ የተፈቱት ተመስገን ደሳለኝን ጨምሮ እስክንደር ነጋ፣ አንዷለም አረጌ እና ዘላላም ወርቃገኘሁ የሚገኙበት ሲሆን፤ ማህሌት ፋንታሁ፣ በፍቃዱ ኃይሉ፣ ወይንሸት ሞላ፣ አዲሱ ጌትነት፣ ይድነቃቸው አዲስ፣ ስንታየሁ ቸኮል እና ተፈራ ተስፋዬ የተባሉ ግለሰቦች ትናንት ምሽት ተይዘዋል። ፖሊስ የያዛቸውን ሰዎች በአቅራቢያው ወደሚገኝ ጣቢያ ወስዶ ምርመራ ያደረገላቸው ሲሆን፤ መሰብሰብ እንደማይቻልና ማስፈቀድ እንደነበረባቸው ለታሳሪዎቹ እንደተነገራቸው ከታሳሪዎቹ ቤተሰብ አንዱ ተናግሯል። በዝግጅቱ ስፍራ ተሰቅሎ ነበር የተባለው የኮከብ ምልክት የሌለው ባንዲራ ፖሊሶች በስፍራው እንደደረሱ ያለመግባባቱ መነሻ የነበረ ሲሆን በፖሊስ ጣቢያ ውስጥም እንደመጀመሪያ ክስ ቀርቧል። የተያዙት ጋዜጠኞች፣ ጦማሪያንና ፖለቲከኞች ቀድሞ በተወሰዱበት ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ቃላቸውን ከሰጡ በኋላ ወደሌላ ፖሊስ ጣቢያ ከመሸ በኋላ መዘዋወራቸውን የተመስገን ደሳለኝ ወንድም ገልጿል። ታሳሪዎቹ ሳይፈቱ በፖሊስ ጣቢያ ሌሊቱን እንዳሳለፉ ቤተሰቦቻቸውና ጓደኞቻቸው ገልፀዋል። በተመሳሳይ ባለፈው ሳምንት መጠናቀቂያ በባህር ዳር ከተማ የታሰሩት ከአስራ አምስት በላይ ግለሰቦች ህጋዊ ፓርቲ የማቋቋም ሒደት ላይ እንደነበሩ ተነግሯል። የፓርቲው መስራች ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ክርስትያን ታደለ ለቢቢሲ እንደገለፁት ኮሚቴው የምርጫ ቦርድ ይሁንታ አግኝቶ እንቅስቃሴ ከጀመረ ከአራት ወራት በላይ ተቆጥረዋል። ያለፉትን ጥቂት ወራት የፓርቲውን መርኃ ግብር እና መተዳደሪያ ደንብ ረቂቆች ሲያሰናዱ እንዲሁም የቅድመ-መስረታ ጉባዔ እንቅስቃሴዎችን ሲያከናውኑ እንደቆዩ የሚናገሩት አቶ ክርስትያን፤ መስራች ጉባዔውን መቼ እና የት እናከናውን በሚለው ጉዳይ ላይ ለመምከር ነበር በባህር ዳር ከተማ የተሰበሰቡት። በተያያዘም ሥራ ላይ ያለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለሚያስፈፅመው ግብረ ኃይል ጥያቄ የማቅረብ ዕቅድ እንደነበራቸውም ይገልፃሉ። ከፓርቲው መሥራቾች በተጨማሪ በስፍራው የነበረ የክልሉ ጋዜጠኛ መታሰሩን የሚገልፁት አቶ ክርስትያን፤ እርሳቸው ለሥራ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ውጭ የሚገኙ በመሆኑ በቦታው እንዳልተገኙ ሆኖም ከባልደረቦቻቸው ባገኙት መረጃ መሰረት ታሳሪዎቹ በሚያዙበት ወቅት ድብደባ እንደነበረ መረዳታቸውን ለቢቢሲ ጨምረው ተናግረዋል።
news-53591380
https://www.bbc.com/amharic/news-53591380
ኢትዮጵያውያን ጮቤ ሲረግጡ ግብፅን ያስከፋው የህዳሴ ግድብ ሙሌት
የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ምዕራፍ ሙሌት መከናወኑን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥትና የኢትዮጵያ ዜጎች በከፍተኛ ሁኔታ ደስታቸውን ሲገልጹ ግብጽ ግን በነገሮች አካሄድ ምንም ደስተኛ እንዳልሆነች እየታየ ነው።
ኢትዮጵያ ላለፉት በርካታ ዓመታት በአባይ ወንዝ ላይ እና ዙሪያ ምንም አይነት የልማት ስራዎችን እንዳትሰራ ከፍተኛ ጫና ሲደረግባት የነበረ ሲሆን ማንኛውም አይነት ከወንዙ ጋር የተገናኘ ስራ ደግሞ የውሃውን መጠን ሊቀንሰው ስለሚችል ግብጽ ጉዳዩ የመኖርና ያለመኖር ጥያቄ ነው በማለት ስትከራከር ቆይታለች። በአጎርጎሳውያኑ 2011 ግንባታው የተጀመረው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በአሁኑ ሰአት ለመጀመሪያ ዙር የታቀደለትን ውሃ መያዝ ችሏል። በዚህ ዓመት የክረምት ወቅት በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያትም ግድቡ 4.9 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ አጠራቅሟል። የውሃ ሙሌቱ የተጀመረው ደግሞ ግብጽ ሙሌቱን በተመለከተ ሁሉንም የሚያስማማ ሕጋዊ ስምምነት ላይ ሳይደረስ ነው ብላለች። ከመጀመሪያውኑም ስምምነት ላይ ሳይደረስ የውሃ ሙሌቱ መጀመር የለበትም በማለት ግብጽ ስትከራከር ነበር። በሚቀጥሉት ከአራት እስከ ስድስት ዓመታት በግድቡ እንዲኖር የሚፈለገው የውሃ መጠን 74 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ሲሆን ሙሉ በሙሉ ግንባታው ሲጠናቀቅና ስራ ሲጀምር በአፍሪካ ትልቁ የኃይል ማመንጫ ግድብ ይሆናል። ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን በአባይ ወንዝ አጠቃቀም ላይ በትንሹ ለአስር ዓመታት ሲያደርጉት የነበረው ድርድር እዚህ ግባ የሚባል ስምምነት ላይ መድረስ ባይቻልም ኢትዮጵያ ግን ላለፉት ሰባት ዓመታት የግድቡን ግንባታ ስራ አላቆመችም ነበር። ግብጽ ላለፉት ዓመታትም የተለያዩ ዓለማቀፍ ተቋማትና አገራትን በመጠቀም በግድቡ ዙሪያ በቻለችው መጠን ፖለቲካዊ ጫና ለማሳደር ሞክራለች። ነገር ግን ከሰሞኑ ግብጽ የተሸነፈች ይመስላል፤ ምክንያቱም ኢትዮጵያ ግድቡን መሙላት ጀምራለች። ከዚህ በኋላ ግብጽ ምን ማድረግ እንዳለባትና እንደምትችል ግራ የተጋባች ትመስላለች። ነገር ግን አሁንም ቢሆን ወታደራዊ መፍትሄ እንደ አማራጭ ሊቀርብ እንደሚችል ማሰብ ይቻላል። የግብጽ ባለስልጣናት እስከመጨረሻው በሰላማዊ ድርድር እንደሚያምኑ በተደጋጋሚ ገልጸዋል። ነገር ግን ሁሉም አይነት አማራጭ ከግምት ውስጥ ይገባል ሲሉም ተደምጠዋል። አሁን ግን ግድቡ መሞላት መጀመሩን ተከትሎ ግብጽ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ሲካሄድ የነበረው ውይይት ላይ እምነት እንዳላትና ኢትዮጵያ ለብቻዋ የምትወስነውን ውሳኔ እንደማትቀበለው ገልጻለች። ግብጽ በረሀማ ተፈጥሮአዊ አቀማመጥ እንዳላት በተደጋጋሚ በመግለጽ የታላቁ ሕዳሴ ግብድ ግንባታ የመኖርና ያለመኖር ጥያቄ ነው ብላለች። የአባይ ወንዝ ደግሞ ለግብጻውያን የመጠጥ እና የግብርና ውሃ ዋነኛ ምንጭ ነው። ኢትዮጵያም አባይን የህልውና መሰረቴ ነው በማለት ትከራከራለች። የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር የውኃ ሙሌት መጠናቀቁን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ባስተላለፉት መልዕክት ”በጋራ ጥረታችን ግድባችንን እዚህ ደረጃ ስላደረስነው መላው የሀገራችን ሕዝቦች እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ” ብለው ነበር። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገዱ አንዳርጋቸው ደግሞ አባይ ከወንዝነት አልፎ ሐይቅ መሆኑን በመግለጽ አባይ የእኛ ነው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። በዚህም ሰአት ነበር ግብጻውያን የፈሩት ነገር እንዳልቀረ የተገነዘቡት። አንድ ግብጻዊ ጋዜጠኛም ኢትዮጵያ በአገሩ ላይ የበላይነት እንደተቀዳጀች በመግለጽ ጨዋታው ግን አሁንም አለመጠናቀቁን ፅፏል። አክሎም '' ኢትዮያውያን እኛ ያለ አባይ መኖር እንደማንችል መቀበል አይፈልጉም። እነሱ ከተለያዩ ወንዞች በየዓመቱ እስከ 950 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ያገኛሉ። ይህ ቁጥር ደግሞ እኛ ከምንፈልገው ግማሹ ማለት ነው'' ሲል ጽፏል። አሁንም እንደሚቀጥል የሚገመተው ድርድር ፍሬ አልባ የሚሆን ከሆነ ግብጽ ጉዳዩን ወደ ተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ለመውሰድና የኢትዮጵያን እጅ ለመጠምዘዝ ታስባለች። ነገር ግን ጉዳዩ በአምስቱም ቋሚ የምክር ቤቱ አባል አገራት ተቀባይነት ማግኘቱ አጠራጣሪ ነው። ምክንያቱም ቻይና እና ሩሲያ እራሳቸው ያልፈቱት ድንበር ተሻጋሪ ወንዝ ጉዳይ አለባቸው። በዚህ ላይ ውሳኔ ሰጡ ማለት የእነሱም ጉዳይ ሊነሳባቸው ነው ማለት ነው፤ ይህንን ደግሞ አይፈልጉትም። ግብጽና ኢትዮጵያ መስማማት በሚችሉባቸው ቀላል ጉዳዮች ላይ እንኳን መስማማት አለመቻላቸው በቀጠናው አለመረጋጋትን ሊፈጥር እንደሚችል እሙን ነው። ግብጽ እንደምትለው በግድቡ ምክንያት ድርቅ ወይም ማንኛውም አይነት ውሃ እጥረት የሚያጋጥማት ከሆነ አብሮት የሚመጣው መዘዝ ከሰሜን አፍሪካ እስከ አውሮፓ ድረስ የሚሄድ ነው። በሁለቱ ትልልቅ የአፍሪካ አገራት መካከል ደግሞ ጦርነት ቢከሰት ኪሳራው ለሁሉም የአፍሪካ አገራትና ለመላው ዓለምም ነው።
49694873
https://www.bbc.com/amharic/49694873
ኬንያ ራስተፈሪያኒዝም ኃይማኖት ነው ስትል በየነች
የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ራስተፈሪያኒዝም ከሌሎች ኃይማኖቶች እኩል ኃይማኖት ነው ሲል በየነ።
አንድ ትምህርት ቤት አንዲት ልጅ ፀጉሯን በራስተፈሪያን እምነት መሠረት 'ድሬድሎክ' አድርጋለች ሲል ከትምህርት ማገዱን ተከትሎ ነው ክስ የተመሠረተው። ዳኛ ቻቻ፤ ልጅቱ እምነቷን ተከትላ ነውና ፀጉሯን 'ድሬድሎክ' ያደረገችው፤ የመማር መብቷን ልትከለከል አይገባም ሲል ፍርድ ሰጥተዋል። ራስተፈሪያኒዝም ጃማይካ ውስጥ እንደ ጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር 1930ዎቹ የተመሠረተ እምነት ነው። የልጅቱ ወላጆች ናቸው። «ልጃችን በኃይማኖቷ ምክንያት ትምህርት ተነፍጋለች፤ ፀጉሯ ደግሞ የእምነቷ ምልክት ነው፤ ልትላጨውም አትችልም» ሲሉ ነው ክሳቸውን ያሰሙት። የኬንያ ሕገ-መንግሥት ማንም ሰው በኃይማኖት፣ በሃሳብ፣ በእምነት እና አስተያየቱ ምክንያት መገለል ሊደርስበት አይችልም ቢልም ልጃችን ግን መገለል ደርሶባታል ሲሉም አክለው ክሳቸውን አሰምተዋል። ኬንያ ትምህርት ቤት ውስጥ መተግበር ያለበት አለባበስን የሚወስን ሕግ ባይኖራትም ትምህርት ቤቶች የትምህርት ሥርዓትን የማይውክ ሕግ እንዲያወጡ ይገደዳሉ። በኃይማኖት ምክንያት ግን ማንም እምነቱን ሊቀይር አይገባም የሚል ሕግ ተቀምጧል። «ወደ አህጉረ አፍሪካ ተመልከቱ! አንድ ጥቁር ይነግሣል፤ ነፃነትም ይሆናል» ጃማይካዊው የመብት ታጋይ ማርከስ ጋርቬይ ነበር ይህን 'የተነበየው'። ኢትዮጵያን ከአራት አሥርት ዓመታት በላይ የገዙት ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ በ1923 ዓ. ም. የንግሥና ዙፋናቸውን ጫኑ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አማኞች ቀዳማዊ ዐፄ ኃይለስላሴ ከአምላክነት ጀምሮ የተለያየ ስፍራ ተሰጥቷቸዋል።
50963340
https://www.bbc.com/amharic/50963340
ጓደኛ ጤና ላይ ያለው ተፅዕኖ እንዴት ያለ ነው?
አዲስ ዓመት ሲመጣ ዕቅድ ይወጣል፤ ውጥን ይወጠናል፤ መላ ይመታል. . . አዲስ ይለበሳል፤ አዲስ ይታሰባል።
ታድያ የግሪጎሪ ቀን ኦቆጣጠር 2020 መምጣቱን ተከትሎ ብዙዎች የአዲስ ዓመት ዕቅዴ ያሉትን ጤናማ ትልም ጀባ እያሉ ነው። አመጋገብን ጤናማ ከማድረግ ጀምሮ እንቅስቃሴ መጀመር ሰዎች ብዙ ጊዜ ሊተግብሯቸው ዕቅድ ከሚይዙላቸው ጉዳዮች መካከል ናቸው። ታድያ ለእነዚህ ዕቅዶች እውን መሆን ጓደኛ፣ ቤተሰብ እና ወዳጅ ዘመድ ትልቅ ቦታ አላቸው። የጓደኞቻችን እና የምናደንቃቸው ሰዎች ባሕሪይ ይጋባብናል። ሌላው ቀርቶ ለጤናችን አስጊ የሆኑ ባሕሪያትን ለምሳሌ ትምባሆ መሳብ እና ብዙ መመገብን ሳይቀር ከወዳጆቻችን እንኮርጃለን። • ቤተሰብና ጓደኛ የሚያከራየው ድርጅት • ጓደኛ ለማፍራት ማወቅ ያለብን ጠቃሚ ነጥቦች ይህ ማለት እንደ ካንሰር፣ የልብ ሕመም እና ስትሮክ የመሳሰሉ የማይተላለፉ በሽታዎች ከወዳጅ ዘመድ ይተላለፉብናል ማለት ነው። ጓደኞቻችን ያለልክ እንድንወፍር ምክንያት ናቸውን? በሥራ ቦታም ሆነ በምናዘውትራቸው ሥፍራዎች የምናገኛቸው ሰዎች ትልቅ ተፅዕኖ ፈጣሪ ናቸው። ፋርሚንግሃም የተሰኘ የልብ ጥናት ተቋም ማሕበራዊ መስተጋብሮች ጤና ያላቸውን ተፅዕኖ ለበርካታ ዓሥርት ዓመታት ሲያጠና ቆይቷል። ዓመታትን በዘለቀው ጥናት መሠረትም ከልክ ያለፈ ውፍረት ያለው ጓደኛ ካለዎት የእርስዎም ዕጣ ፈንታ ወደዚያው ነው የሚል መደምደሚያ አስቀምጧል። በተለይ ደግሞ ይላል ጥናቱ ሁለት ተመሳሳይ ፆታ ያላቸው ጓደኛሞች ተመሳሳይ ለሆነ የጤና መጓደል የመጋለጣቸው ዕድል የሰፋ ነው። ፍቺ፣ ትምባሆ ማጨስ እና አልኮል መጠጣት ከቤተሰብ ቤተሰብ እየወረዱ የሚሙ መሆናቸውን ነው የጥናቱ ውጤት የሚያሳየው። አልኮል፣ ትምባሆ፣ ያልተመጣጠነ አመጋገብ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ በዓለማችን ከ10 ሰው 7 ሰው ይቀጥፋሉ። ማሕበራዊ መስተጋብሮች ዘርፈ ብዙ የባሕሪይና የአመል መቀያየር ችግር ሊያመጡ ይችላሉ። ለምሳሌ አጫሽ አዋቂ ሰዎች የሚበዙበት ማሕበረሰብ ውስጥ የሚያድጉ ታዳጊዎች የማጨስ አዝማሚያቸው ከፍ ያለ ነው። • ትዳር ከባድ የጤና ችግሮችን ለመከላከል • የኢትዮጵያዊያንን ትዳር አከርካሪ እየሰበረ ያለው ምን ይሆን? ታድያ እንዴት አድርገን ከወዳጅ ዘመዶቻችን መልካም መልካሙን መቅሰም የምንችለው? አውሮጳውያን ከአልኮል የፀዳ ጥቅምት፤ ከሥጋ የፀዳ ጥር. . . በማለት ወራትን እየከፋፈሉ ጤናማ ሕይወት ለመኖር ይተጋሉ። ባለሙያዎች መሰል ክበባት ጤናማ ሕይወት ለመምራት 'አሪፍ መላ' መሆኑን ይጠቁማሉ። አልፎም ወዳጅ ዘመዶቻችን ጤናማ ሕይወት እንዲመሩ መገፋፋት አስፈላጊ መሆኑን ሳያሰምሩበት አያልፉም። እኛ ጎጂ ተፅዕኖ ከሚያድርብን፤ በጎ ተፅዕኖ ለምን አናሳድርም? ነው ዋናው ቁም-ነገር።
news-51262100
https://www.bbc.com/amharic/news-51262100
24 ሺህ ፖስታዎችን ማደል የታከተው የዓለማችን ስልቹው ፖስተኛ ተያዘ
በሥራው የተሰላቸው ፖስተኛ ማድረስ የነበረበትን በሺዎች የሚቆጠሩ ፖስታዎች ቤቱ ውስጥ ከምሮ በፖሊስ ተያዘ።
ፖስተኞች በጃፓን ዶቅዶቄ እየጋለቡ ፖስታ ሲያድሉ በዚህም የጃፓን ፖሊስ በሰውየው ላይ የምርመራ ዶሴ ከፍቶበታል። ጃፓናዊው ፖስተኛ ሲበዛ ስልቹ ነው። እንዲያደርስ ከተነገረው ፖስታ መሀል 24 ሺህ የሚሆነውን ቤቱ አስቀምጦታል። ክፋት አይደለም መታከት ነው ብሏል። ይህ ፖስተኛ ከቶኪዮ ወጣ ብላ በምትገኘው ካናጋዋ ቀበሌ ውስጥ በሚገኘው ቤቱ 24 ሺህ የፖስታ ጥቅሎችን ፖሊስ ባገኘበት ቅጽበት ታላቅ መገረምን ፈጥሮ ነበር። የ61 ዓመቱ ጎልማሳ ፖስተኛ የፖስታ ጥቅሎቹን ለምን አላደልክም ሲባል "ይሰለቻል" ብሏል። • የዓለማችን ቁጥር አንድ ሃቀኛዋ ሃገር • ሴትየዋ ኬክ በፍጥነት በመብላት ውድድር ላይ ሳሉ ሞቱ በዚያ ላይ ከእርሱ በዕድሜ የሚያንሱት ፖስተኞች ጋር መወዳደርና ሰነፍ ሆኖ መታየት እንዳልፈለገም ተናግሯል። የዮኮሃማ ፖስታ ቤት በሰውየው ስንፍና ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን "ችግር የለም ሁሉንም እኔ ራሴ አድላቸዋለሁ" ብሏል። ይህ ስልቹ ጃፓናዊ በሚሰራበት ፖስታ ቤት ቅርንጫፍ ከ2 ዓመት በፊት ፖስታዎች እየተሰወሩ ነው ምርመራ ይጀመር ብሎ ነበር። ነገር ግን በኋላ ይፋ የሆነው የፖሊስ ምርመራ እንዳመላከተው ይህ ስልቹ ፖስተኛ ከፈረንጆቹ 2003 ጀምሮ ነው ፖስታ ማደል አሰልቺ እንደሆነ ተሰምቶት ቤቱ መከመር የጀመረው። ይህ በስም ያልተጠቀሰው ጃፓናዊ ስልቹ ፖስተኛ በተከሰሰበት ወንጀል ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ካለው 3 ዓመት እስር እንዲሁም ግማሽ ሚሊዮን የን ሊቀጣ ይችላል። ቅጣቱ ወደ ብር ሲቀየር 150 ሺህ ብር ይጠጋል።
news-51410601
https://www.bbc.com/amharic/news-51410601
አፍሪካ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል አቅሙ አላት?
ቻይና ሁቤይ ግዛት የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ በመላው ዓለም ጭንቀትን ፈጥሯል። ቫይረሱ በርካታ የዓለማችን አካባቢዎችን በአጭር ጊዜ ማዳረሱና ለጊዜው ፈዋሽ መድሃኒት ያልተገኘለት መሆኑ ደግሞ አሳሳቢነቱን ከፍ አድርጎታል።
አፍሪካዊት እናት እስካሁን ባለው ሁኔታ ቫይረሱ ካልተገኘባቸው ሁለት አህጉራት መካከል አፍሪካ አንዷ ብትሆንም ባለሞያዎች ግን ይህ ማረጋገጫ ሊሆን አይችልም እያሉ ነው። ቫይረሱ በዉሃን ከተማ ከተከሰተ ጀምሮ ቢያንስ 600 በላይ ሰዎች ሲሞቱ ከ30 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ በበሽታው መጠቃታቸው ታውቋል። ከሟቾቹም ሆነ በበሽታው ከተያዙት ውስጥ ላቅ ያለውን ድርሻ የሚይዙት ቻይናዊያን ናቸው። ባለፈው ሳምንት የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮናቫይረስን የዓለም ከፍተኛ ስጋት ነው ብሎታል። ይህ ዓይነቱ ውሳኔ በድርጅቱ የሚወሰነው በጣም ኣሳሳቢ ጉዳይ ሲከሰት ሲሆን ይህም በታሪክ ለስድስተኛ ጊዜ የሆነ ነው። እስካሁን አፍሪካ ውስጥ ቫይረሱ የተገኘባቸው አገራት ባይኖሩም ዋናው ጥያቄ ግን አፍሪካዊያን አሁን በአህጉሩ ያሉትን ህሙማን በአግባቡ ማከም በማይችሉበት ደረጃ ላይ እያሉ ኮሮናቫይረስ ቢጨመር ምን ይሆናሉ የሚለው ነው። አሁን በሽታው አፍሪካ ውስጥ ቢከሰት ህክምናውን ለማድረግ ምን የተሟላ ነገር አለ? እስከዚህ ሳምንት መጀመሪያ ድረስ በአፍሪካ ቫይረሱን ለመለየት የነበሩት ቤተ ሙከራዎች ሁለት ብቻ ናቸው። አንዱ ደቡብ አፍሪካ፤ ሌላኛው ደግሞ ሴኔጋል የሚገኙ ናቸው። ሌሎች የአህጉሪቱ አገራትም ናሙናዎቻቸውን ወደ እነዚህ አገራት በመላክ ነው የቫይረሱን ውጤት ሲያረጋግጡ የነበሩት። በዚህ ሳምንት ደግሞ ጋና፣ ማዳጋስከር፣ ናይጄሪያና ሴራሊዮን ይህንን የቤተ ሙከራ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል። ለኮሮና ቫይረስ የአፍሪካ ዝግጅት የዓለም ጤና ድርጅትም በአህጉሩ ያሉ 29 ቤተ ሙከራዎች ቫይረሱን መለየት እንዲችሉ ድጋፍ ለማድረግ አጋዥ ቁሳቁስ የላከ ሲሆን አስፈላጊም ከሆነ ከሌሎች አገራት ተጨማሪ የድጋፍ ቁሳቁሶችን ለማምጣትም ዝግጁ ነኝ ብሏል። በመቀጠልም በዚህ ወር መጨረሻ ቢያንስ 36 የአፍሪካ አገራት የኮሮናቫይረስን ለመለየት የሚያስችል ቤተ ሙከራ ይኖራቸዋል ተብሎ ተስፋ ተደርጓል። አገራት የወሰዱት እርምጃ የናይጄሪያ የቀይ መስቀል ማኅበር 1 ሚሊዮን የበጎ አድራጎት ሠራተኞችን በተጠንቀቅ አዘጋጅቻለሁ ብሏል። ይህም በማንኛውም ወቅት የኮሮናቫይረስ በናይጄሪያ ምድር ተከሰተ ቢባል ተረባርበን ለመቆጣጠር ያስችለናል ብሏል። የታንዛኒያ የጤና ሚንስቴር የለይቶ ማቆያ አካባቢዎችን በምሥራቅ፣ በሰሜንና ምዕራብ የአገሪቱ አካባቢዎች አዘጋጅቷል። የሙቀት መጠን መለኪያ በበቂ ሁኔታ ያሟላ ሲሆን ቫይረሱን መከላከል አመቺ በሆነ መልኩ የሰለጠኑ 2 ሺህ የጤና ባለሞያዎችም ዝግጁ ተደርገዋል። የኡጋንዳ የጤና ሚንስቴር ከቻይና የመጡ ከ100 በላይ ሰዎች ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው እስኪረጋጥ ድረስ ለብቻቸው እንዲቆዩ አድርጓል። ከፊሎቹ በሁለት ሆስፒታሎች እንዲቆዩ የተደረገ ሲሆን የተወሰኑት ደግሞ ከማንም ጋር ሳይገናኙ በቤታቸው እንዲያሳልፉ ተርጓል። ከኢቦላ የተወሰደ ተሞክሮ ይኖር ይሆን? ዶክተር ሚካኤል ያኦ በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ድንገተኛ ህክምና ክፍል ኃላፊ ናቸው። እርሳቸው እንደሚሉት የኢቦላ ቫይረስ ከ2014 እ.አ.አ ጀምሮ በምዕራብ አፍሪካና አሁን በዴሞክራቲክ ኮንጎ የተከሰተ ቢሆንም ያስገኘው ተሞክሮ እምብዛም ነው። "ኮሮና ቫይረስ አፍሪካ ውስጥ ቢገባ ጉዳቱ ከፍ ያለ ሊሆን ይችላል" በማለትም ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል። "አገራትን የምንመክረው ቢያንስ ቫይረሱ ከመሰራጨቱ በፊት ከፍተኛ የሆነ የመለየት ሥራ ላይ እንዲረባረቡ ነው" ብለዋል ኃላፊው። በርካታ የአፍሪካ አገራት አየር ማረፊያቸው ላይ ተጓዦች እንደደረሱ የኢቦላ ምርመራ ያደርጋሉ። የኢቦላ ቫይረስ የተከሰተባቸው አገራትም እስካሁን የለይቶ ማቆያ ቦታዎች አሏቸው። በበሽታው የተያዙ ሰዎችን ለማከምም የሕክምና አሰጣጥ ብቃታቸውን አሳድገዋል። ነገር ግን አስቸጋሪው ነገር ኢቦላ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው የበሽታው ምልክት ከታየ በኋላ ሲሆን በሌላ በኩል ኮሮናቫይረስ ምንም ምልክት ሳያሳይ ቫይረሱ ከሰው ወደ ሰው ሊተላለፍ ይችላል። ይህም ከአፍሪካ ደካማ የጤና ሥርዓት ጋር ተዳምሮ የስርጭቱንና የቁጥጥር ሂደቱን ፈታኝ ያደርገዋል። በአፍሪካና በቻይና መካከል የሚደረገው ጉዞስ ለቫይረሱ ስርጭት ምን አስተዋጽዖ አለው? የአፍሪካና የቻይና የተጠናከረ የንግድ ልውውጥ ቫይረሱን ያሰራጨዋል ተብሎ ከሚፈራባቸው መንገዶች ቀዳሚው ነው። ቻይና የአፍሪካ ትልቅ የንግድ ሸሪኳ ስትሆን ከ10 ሺህ በላይ የቻይና ኩባንያዎች በአፍሪካ በተለያዩ ዘርፎች እየሰሩ ይገኛሉ። ከ1 ሚሊዮን በላይ ቻይናዊያንም አፍሪካ ውስጥ በተለያዩ አገራት ይኖራሉ። ይህም የቻይናንና የአፍሪካን የገዘፈ ቁርኝት ያሳያል። ነገር ግን በእንደዚህ አይነቱ አስቸጋሪ ወቅት ሌላ ጣጣ ሊያመጣ ይችላል ተብሎ ተሰግቷል። ጋርዲያን ባወጣው መረጃ መሰረት ደግሞ ከ80 ሺህ በላይ የአፍሪካ ተማሪዎች በቻይና የተለያዩ ግዛቶች ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ። በተመሳሳይ የቻይና ተማሪዎችም ወደ አፍሪካ ይመጣሉ። የ21 ዓመቱ ካሜሩናዊ ተማሪ በቻይና በነበረው ቆይታ በቫይረሱ ተይዟል ተብሎ በመጠርጠሩ በሆስፒታል ህክምና እየተደረገለት ይገኛል። በእስያ ያለው ከፍተኛ የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ የህዝብ እንቅስቃሴና በአየር ትራንስፖርት ምክንያት የተከሰተ ነው የሚሉት የዘርፉ ሙያተኞች ለአፍሪካም ይህ ተጨማሪ ስጋት እንደሚደቅን ያስረዳሉ። በ2002 እ.አ.አ በቻይና የተከሰተው የሳርስ ቫይረስ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በተገኘ አንድ የቫይረሱ ተጠቂ ግለሰብ ምክንያት፤ ቫይረሱ በአህጉሩ በከፍተኛ ሁኔታ ተስፋፍቶ ነበር። በዚያን ጊዜ ከነበረው ጋር ሲነጻጸር ደግሞ አሁን በቻይናና በአፍሪካ መካከል ያለው የአየር ትራንስፖርት በ600 በመቶ ጨምሯል። የሙቀት መጠን አየር መንገድ ላይ ሲለካ በርካታ የዓለም አገራት አየር መንገዶች ወደ ቻይና የሚያደርጉትን ጉዞ አቋርጠዋል። በአፍሪካም ተመሳሳይ ሥራ እርምጃ እንዲወሰድ ሕዝቡ ጫና እያደረገ ነው። ሩዋንዳና ኬንያ የአየር ጉዟቸውን ያቋረጡ የአፍሪካ አገራት ናቸው። ነገር ግን የአህጉሪቱ ግዙፍ አየር መንገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና የሚያደርገውን በረራ ያላቋረጠ በመሆኑ የአፍሪካዊያን ስጋት ብዙም አልተቀነሰም። የዓለም ጤና ድርጅት በተለይ ከቻይና ጋር ሰፊ ግንኙነት አላቸው ያለቸውን 13 አገራት ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል በማለት ለይቷል። እነዚህ አገራት ኮሮናቫይረስን የማስተናገድ እድላቸው ሰፊ ነው በመባል ነው የተለዩት። ለእነዚህ አገራትም የተለየ እገዛ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ድርጅቱ አስታውቋል። የዓለም ጤና ድርጅት ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ የተለየ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ያላቸው አገራት የሚከተሉት ናቸው።
47958654
https://www.bbc.com/amharic/47958654
አልሲሲ እስከ 2030 ግብጽን ሊመሩ ይችላሉ
የግብፅ ፓርላማ የቀረበለትን የሕገ መንግሥት ማሻሻያያ አፀደቀ። በተሻሻለው ሕገ-መንግሥት መሠረት አልሲሲ እስከ 2030 ድረስ በመንበራቸው ላይ ሊቆዩ ይችላሉ።
አልሲሲ የሁለተኛ የምርጫ ዘመን ስልጣናቸው የሚያበቃው በ2022 ነው። አሁን በተሻሻለው ሕገ-መንግሥት መሰረት በሰላሳ ቀናት ውስጥ ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ይጠይቃል። ይህ ደግሞ አራት ዓመት የነበረውን የስልጣን ዘመናቸውን ወደ ስድስት ዓመት ከፍ በማድረግ ለአንድ የስልጣን ዘመን እንዲወዳደሩ እድል ይሰጣቸዋል። የፓርላማው ውሳኔ የአልሲሲ የሥልጣን ዘመን ዘለግ ባለ ዓመታት መለጠጡ ብቻ ሳይሆን ዳኞችና አቃቤ ሕጉን የመሾም ልዩ ሥልጣንንም ሰጥቷቸዋል። ከአል-ሲሲ ባሻገር ለመከላከያ ሠራዊትም ተጨማሪ ኃላፊነቶችን ይሰጣል። • 138 ሰዎች ዜግነታቸውን ተነጠቁ • ሱዳን በህዳሴው ግድብ ጉዳይ አቋሟን ትቀይር ይሆን? • ሰባ ኢትዮጵያውያን ባህር ላይ መሞታቸው ተሰማ አልሲሲ እንደ ጎርጎሮሲያዊያኑ በ2013 በመፈንቅለ መንግሥት መሀሙድ ሙርሲን አስወግደው ሥልጣን ከያዙ በኋላ የተቃውሞ ድምጾችን ሁሉ በመደምሰስ ድጋሚ ምርጫን 97 በመቶ ድጋፍ አግኝቼ አሸንፊያለሁ ብለው ካወጁ ጥቂት ዓመታት ተቆጥሯዋል። የግብፅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሞላው በአልሲሲ ደጋፊዎች ሲሆን ሁል ጊዜም የአልሲሲን ቃል በማስፈፀም በተቃዋሚዎች ይከሰሳል። ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል አስተያየቱን የሰጠ አንድ የሕዝብ እንደራሴ እንዳለው "አልሲሲ ወሳኝ የሆኑ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የደህንነት እርምጃዎችን የወሰዱ ናቸው እናም የስልጣን ዘመናቸው ሊራዘምላቸውና የጀመሩትን የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሊቀጥሉ ይገባል" ብሏል። የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባሉ ኻሊድ ግን "እብደት ነው፤ ትልቅ የስልጣን ጥመኝነት" ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። የመረጃ መረብ ፍሰትን የሚከታተለው ተቋም የግብፅ መንግሥት ይህ ሕገ-መንግሥት እንዳይሻሻል የሚወተውቱና ፊርማ የሚያሰባስቡ 34 ሺህ ድረ ገፆችን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል ዘግቷል ሲል ይፋ አድርጓል። እነዚህ ወገኖች 250 ሺህ ፊርማ አሰባስበው ነበር። በ2014 በሕዝበ ውሳኔ ጸድቆ የነበረው የግብጽ ሕገ መንግሥት 'አንቀጽ-140' ተመራጩ ርዕሰ ብሔር ከሁለት የአራት ዓመት የአገዛዝ ምዕራፍ በላይ በሥልጣን እንዳይቆይ ያስገድዳል። ነገር ግን አሁን በፀደቀው ማሻሻያ ርዕሰ ብሔሩ ስድስት አመት በሥልጣን እንዲቆይ ያስችለዋል።
news-53290027
https://www.bbc.com/amharic/news-53290027
'ጀግናዬ" የሚለውን የወዳጁን ቀብር በቴሌቪዥን የተከታተለው የሃጫሉ ሁንዴሳ ጓደኛ
ታዋቂው ሙዚቀኛ ሃጫሉ ሁንዴሳ በጥይት ተመትቶ ከተገደለ በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ ለቀናት የቆየ አለመረጋጋት ተፈጥሮ የነበረ ሲሆን በወቅቱ በነበሩ ግጭቶችም ቢያንስ 80 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
ሃጫሉ ሁንዴሳ እና አመንሲሳ ኢፋ የሃጫሉ ሙዚቃዎች ብዙ ጊዜ ፍቅርና አንድነትን የሚሰብኩ የነበሩ ሲሆን በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ የነበሩ ብሶቶችንም በማቀንቀን ይታወቃል። የቢቢሲው የካሜራ ባለሙያ አመንሲሳ ኢፋ ከሃጫሉ ጋር የቅርብ ወዳጅ የነበረ ሲሆን ከዓመታት በፊት ሽልማቶችን ማሸነፍ የቻለ ሙዚቃው ላይ የቀረጻውን ሥራውን አብሮ አከናውኗል። ስለሞቱ እንዴት እንደሰማና ስለነበረው ሁኔታ ሲያስታውስ "አንዳንዴ ስለ ሃጫሉ ሞት ሳስብ ምናለ እሱ በሕይወት ተርፎ እኔ በሞትኩኝ እላለሁ። ለበርካቶች እሱ ጀግና ነበር፤ ገና ብዙ ከእሱ እጠብቅ ነበር" ይላል። ለሕዝቡ ተዋግቷል፤ በርካታ ሙዚቀኞች፣ አርቲስቶች፣ ተሟጋቾችና ፖለቲከኞች የነበረውን ሁኔታ ሸሽተው ከአገር ሲወጡ፣ ሃጫሉ ማንም የማያነሳቸውን ሀሳቦች እያነሳ አገር ውስጥ ነበር የቆየው። ‘ሃጫሉ ሆስፒታል ገብቷል’ ሰኞ ምሽት ላይ ሃጫሉ ምን ሆነ የሚሉ ጥያቄዎች በአጭር የጽሑፍ መልዕክቶች ለአመንሲሳ መድረስ ጀመሩ። በሰዓቱ ማንም ሕይወቱ አልፋለች የሚል አልነበረም፤ ነገር ግን የሆነ ነገር እንደተከሰተ ግልጽ ነበር። አንዳንድ ጓደኞቼን በስልክ ለማግኘት ሞከርኩኝ ነገር ግን አልተሳካልኝም። ከዚያም አንድ ሰው ሃጫሉ ሆስፒታል እንደሚገኝ መልዕክት ላከልኝ። ወዲያው ወደሚገኝበት ሆስፒታል እየሄድኩ ሳለ አንዱን ጓደኛዬን በስልክ ማግኘት ቻልኩ፤ እሱም በስልክ እንባ እየተናነቀው ከሃጫሉ አስከሬን አጠገብ እንደሚገኝ ነገረኝ። ልክ ሆስፒታል ስደርስ አስክሬኑ የሚገኝበት አካባቢ ብዙ ሰዎች ተሰብስበዋል፤ ከባድ የለቅሶ ድምጽም ይሰማ ነበር። የሆነ ሰው የተሸፈነበትን ጨርቅ ሲገልጥ ደረቱ ላይ በጥይት የተመታውን ተመለከትኩ። በቦታው ፖሊስም በርካታ ወዳጆችም ነበሩ። ስሙን እየጠራሁ አለቀስኩ። ሁሉም ሰው ይጮሀል፤ ሁሉም ሰው ያለቅሳል። የሃጫሉ አስከሬን ለተጨማሪ ምርምራ ወደ ሌላ ሆስፒታል ሲወሰድ አምቡላንሱን ተከተልነው። እስከ ሌሊቱ አስር ሰዓት ድረስ እየጠበቅን ነበር። ዜናውን የሰሙ በርካቶችም በሆስፒታሉ አቅራቢያ መሰባሰብ ጀምሩ። ሁሉም ስሙን እየጣራ እንባውን ያፈስ ነበር። የጠዋት ፀሐይ ከወጣች በኋላ ደግሞ አስክሬኑን ከአዲስ አበባ አስወጥተን 100 ኪሎሜትር በምትርቀውና ወደ ትውልድ ከተማው አምቦ ለመውሰድ ጥረት አደረግን። ከአዲስ አበባ ስንወጣ ነገሮች ተቀያይረው ነበር። እዚህም እዚያም ችግር ተፈጥሮ ነበር። በየመንገዱ ተቃውሞዎች የነበሩ ሲሆን ፖሊስ አስለቃሽ ጭስ ሲተኩስ የተኩስ ድምጽም እሰማ ነበር። ልክ ቡራዩ ስንደርስ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በሕዝብ ማመላሻዎችና በእግራቸው ወደ አዲስ አበባ ሲጓዙ አገኘናቸው። ሀዘናቸውን ለመግለጽና ያላቸውን ክብር ለማሳየት ነበር ያን ሁሉ መንገድ ተጉዘው የመጡት። ሁሉም ከተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች የመጡ ሲሆን፤ የሃጫሉን ሞት ከሰሙ በኋላ ሌሊቱን በሙሉ በእግራቸው ሲጓዙ የነበሩ በርካቶችም ናቸው። የቀብር ሥነ ሥርዓቱ አዲስ አበባ መሆነ አለበት የሚሉም ነበሩ። መኪናዬ ውስጥ ሆኜ ሰዎች "ሃጫሉ የአገራችን ጀግና ነው’’ ሲሉ አሰማለሁ። "በአዲስ አበባ የጀግና አቀባበር ሊደርገግለት ይገባል" የሚሉም ነበሩ። ለጥቂት ጊዜ ከቆምን በኋላ አስክሬኑን ይዘን ወደ አዲስ አበባ መመለስ ጀመርን። በኋላ ላይ መንግሥት ሃጫሉ አምቦ ነው መቀበር ያለበት ማለቱንና ቤተሰቡም የቀብር ሥነ ሥርዓቱ አምቦ ውስጥ እንዲሆን ፍላጎት አላቸው መባሉን ሰማን። ከዚያም አስክሬኑ በሄሊኮፕተር ወደ አምቦ ከተማ ተወሰደ። ነገር ግን ሐሙስ ዕለት ወደ አምቦ የሚወስደው መንገድ በመዘጋቱ የሃጫሉ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ መገኘት ሳልችል ቀረሁ። በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ በርካታ ሰዎች የተገኙ ሲሆን በቀጥታ ስርጭትም ይተላለፍ ነበር። እኔም ቀብሩን በቴሌቪዥን ለመከታተል ተገደድኩ፤ ሁኔታው ለእኔ በጣም አስቸጋሪ ነበር። በተገቢው መንገድ ለመሰናበት በቀብሩ ላይ መገኘት ነበረብኝ። ከቀጥታ ስርጭቱ እንደተመለከትኩ በቀብሩ ላይ እምብዛም በርካታ ሰዎች አልነበሩም። በእኛ ባህል አይደለም እንደዚህ አይነት የአገር ጀግና ይቅርና አንድ ተራ ሰው እንኳን ሕዝብ ተሰብስቦ ነው የሚቀብረው። ሁኔታውን በቴሌቪዥን እያየሁ አነባሁ። ከዚያም ለእናቴ ደወልኩላት እና "ዛሬውኑ መሞት እፈልጋለሁ" አልኳት። እሷም በጣም እያለቀሰች ነበር። ከዚያች ቀን በኋላ ማንም ሰው "እንዴት ነህ?" እያለ ሲጠይቀኝ ማልቀስ ነው የሚቀናኝ። ሌላው ቢቀር ሐሙስ ዕለት አንድ የሃጫሉ ጓደኛው የሆነ ነገር እንዳጋጠመው ስሰማ ለማጣራት ብዬ የደወልኩት ወደ ሃጫሉ ስልክ ላይ ነበር። ሁሉንም ነገር እስካሁን አልተቀበልኩትም። ለመጨረሻ ጊዜ ያገኘሁት ከህልፈቱ አንድ ሳምንት በፊት ነበር። ‘ኤሴ ጂርታ’ የሚል አዲስ ሙዚቃ እንዳዘጋጀና እንድሰማው እንደሚፈልግ ነግሮኝ ነበር። የሃጫሉ ሥራዎች በፖለቲካ ብቻ የታጠሩ አልነበሩም፤ ስለ ባህል፣ ማንነት፣ አንድነት፣ ሰብአዊ መብትና ፍቅርን በተመለከተ በርካታ ሥራዎችን ለአድናቂዎቹ አበርክቷል። ሃጫሉ ኩሩ የኦሮሞ ልጅ ነበር። አንዳንድ ሰዎች ሃጫሉ ከአዲሱ አስተዳደር ወይንም ከብልጽግና ፓርቲ ገንዘብ ተቀብሏል በሚል ይወነጅሉት ነበር። እሱ ግን "ማንም እኔን አይገዛኝም" ይል ነበር። ምንም እንኳን ከበርካታ ሰዎች ጋር አለመግባባት ውስጥ ቢገባም፤ እንዲሁም አዲስ አበባ ውስጥ ከሆኑ ሰዎች ጋር ጥሩ ያልሆነ ግንኙነት ቢኖረውም ለህይወቱ ፈርቶ አያውቅም። ሁሌም የሚለው አባባል ነበረው "ለሕዝብ ሲል የሚሞት ሰው ጀግና ነው" የሚል። "እኔ ከማንም የተለየሁ አይደለሁም" ብሎኝ ነበር በአንድ ወቅት።
50400828
https://www.bbc.com/amharic/50400828
ሂላሪ ክሊንተን "በሚቀጥለው ምርጫ በጭራሽ አልወዳደርም ማለት አይቻልም"
ሂላሪ ክሊንተን በሚቀጥለው ዓመት በሚካሄደው የአሜሪካ ምርጭ እንዲወዳደሩ የሚሹ ሰዎች ከፍተኛ ጫና እያሳደሩባቸው እንደሆነ አሳውቀዋል።
ሂላሪ ክሊንተን [ቀኝ] እንግሊዝ ውስጥ ከልጃቸው ቼልሲ ክሊንተን [ግራ] ጋር በጋራ የፃፉትን መፅሐፍ በማስተዋወቅ ላይ ናቸው ሂላሪ ክሊንተን እንግሊዝ ናቸው። ከልጃቸው ቼልሲ ክሊንተን ጋር በጋራ የፃፉትን መፅሐፍ በማስተዋወቅ ላይ ናቸው። የባለፈው ምርጫ የዴሞክራቶች ዋነኛ ተወካይ እና የዶናልድ ትራምፕ ተቀናቃኝ የነበሩት ሂላሪ እንደው በእርግጥ በሚቀጥለው ምርጫ ይሳተፋሉ ወይ? ተብለው በቢቢሲ ተጠይቀዋል። የ72 ዓመቷ ሂላሪ እሳቸው ባለፈው ምርጫ ቢመረጡ ኖሮ ነገሮችን እንዴት ሊከውኑ ይችሉ እንደነበር ሁሌም እንደሚያስቡ አልሸሸጉም። በግሪጎሪ አቆጣጠር 2020 ላይ ለሚካሄደው ምርጫ 17 ዕጩዎች ዴሞክራቲክ ፓርቲን ወክለው ለመወዳደር እየተፋለሙ ይገኛሉ። የቢቢሲ ራድዮ 5 ጋዜጠኛ የሆነችው ኤማ ባርኔት 'በሚቀጥለው ዓመት ምርጫ ይወዳደራሉ ወይ?' ስትል ለክሊንተን ጥያቄ አቅርባለች። «ባለፈው ምርጫ ብምረጥ ኖሮ ለአገሬም ሆነ ለዓለም የተሻለ ነገር አደርግ እንደነበር ሁሌም አስባለሁ። አላስብበትም ማለት አይቻልም። ማንም አሸነፈ ማን በሚቀጥለው ዘመን ከባድ ሥራ ይጠብቀዋል። ብዙ የተሸነቆሩ ቀዳዳዎችን መሸነፈን አለበት።» እርግጡን ምላሽ እንዲነግሯት ወጥራ ለያዘቻቸው ኤማ፤ ሂላሪ ክሊንተን እንዲህ ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋታል። «አንድ ነገር ልንገርሽ፤ በጣም ብዙ ሰዎች በሚቀጥለው ዓመት ምርጫ እንድሳተፍ ይወተውቱኛል። እኔም ሁሌም እላለሁ፤ በጭራሽ አልወዳደርም ማለት አልችልም። ግን አሁን ካንቺ ጋር ቁጭ ብዬ እያወራሁ ባለሁበት ቅፅበት ስለመወዳደር አላስብም።» ሂላሪ ክሊንተን የውጭ ጉዳይ በመሆን አገራቸውን አገልግለዋል። የኒው ዮርክ ግዛት እንደራሴም ነበሩ። ባለቤታቸው ቢል ክሊንተን አገሪቱን በፕሬዝደንትነት ሲመሩ ደግሞ ቀዳማዊ እመቤት። ለሚቀጥለው ምርጫ የዶናልድ ትራምፕ ተቀናቃኝ ይሆናሉ ተብለው ከሚጠበቁት መካከል ኤሊዛቤት ዋረንና ጆ ባይደን ቀዳሚዎቹ ናቸው። አዛውንቱ በርኒ ሳንደርስም የዋዛ ተቀናቃኝ ይሆናሉ ተብሎ አይጠበቀም።
news-54744137
https://www.bbc.com/amharic/news-54744137
140 ስደተኞች ሴኔጋል አቅራቢያ ሰጥመው ሞቱ
የተባበሩት መንግሥታት ወደ 200 የሚጠጉ ስደተኞችን ጭና ወደ አውሮፓ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ሴኔጋል አቅራቢያ ሰጥማ 140 ስደተኞች መሞታቸውን አስታወቀ።
140 ስደተኞች ሴኔጋል አቅራቢያ ሰጥመው ሞቱ ጀልባዋ ማቡር ከምትባለው የሴኔጋል ከተማ ከተነሳች በኋላ በእሳት ተያይዛ መስጠሟን ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አረጋግጧል። አደጋው የደረሳው ባለፈው ቅዳሜ ነበር። ከአደጋው 60 ሰዎች በሕይወት መትረፍ መቻላቸው ተጠቁሟል። ስደተኞቹ የስፔን ካናሪ ደሴትን በማቋረጥ መዳረሻቸውን አውሮፓ ለማድረግ የተነሱ ነበሩ ተብሏል። ከእአአ 2018 ጀምሮ በርካታ የምዕራብ አፍሪካ ስደተኞች አውሮፓ ለመድረስ ይህን አቅጣጫ አዘውትረው ይጠቀሙበታል። የተባበሩት መንግሥታት ይህ አደጋ በተያዘው የፈረንጆች ዓመት በየትኛውም የዓለማችን ክፍል በስደተኞች ላይ ከደረሱት አደጋዎች አስከፊው ነው ብሏል። በሴኔጋል የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ተወካይ ባካይ ዱምቢዓ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችን ለማጥፋት አገራት እና ድርጅቶች በጋራ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል። የስፔን መንግሥት በዚህ ዓመት ብቻ 11ሺህ ስተደኞች በካናሪ ደሴት መመዝገባቸውን አስታውቋል። ይህ አሃዝ ከአንድ ዓመት 2ሺህ500 ገደማ እንደነበረ የስፔን መንግሥት ጨምሮ አስታውቋል። ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በበኩሉ እስካሁን በዚህ አቅጣጫ አውሮፓ ለመድረስ በሚደረግ ጥረት ቢያንስ 414 ሰዎች መሞታቸውን ይፋ አድርጓል።
news-54575535
https://www.bbc.com/amharic/news-54575535
"የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝብ ዕጣፈንታ የተያያዘ ነው" አምባሳደር ዲና
የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ያደረጓቸው ተደጋጋሚ የስራ ጉብኝቶች አገራቱ መተባበር የሚችሉባቸውን መስኮች ያሳየ መድረክ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ ዲና ሙፍቲ ገልፀዋል።
ለሁለት አስርት አመታት ሰላምና ጦርነት በሌለበት ሁኔታ ተፋጠው የነበሩትን ኢትዮጵያና ኤርትራ ወደ ሰላም መድረኩን መምጣት ተከትሎ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ግንኙነት ምን ይመስላል? እንዲሁም በተደጋጋሚ ኢትዮጵያን የሚጎበኙት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ይዘቱ ምንድን ነው ለሚለው ጥያቄ ከጋዜጠኞችም ቀርቦላቸው ነው ይህንን ገለፃ የሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በየሁለት ሳምንቱ ለጋዜጠኞች በሚያደርገው መግለጫም የኢትዮ-ኤርትራ ግንኙነትን ጨምሮ፣ በውጭ አገራት ያሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጉዳይ፣ የኮሮናቫይረስና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክተውም ቃለ አቀባዩ በዛሬው ዕለት፣ ጥቅምት 6/ 2013 ዓ.ም ማብራሪያ ሰጥተዋል። በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የሁለትዮሽ ግንኙነት በሚመለከቱ ጉዳዮች ምላሽ የሰጡት ቃለ አቀባዩ ሁለቱ አገራት ደም አፋሳሽ በሆነው ጦርነት በርካታ ዜጎቻቸውን እንዳጡና ለሁለት አስርት አመታትም ያህል ጦርነትና ሰላም በሌለበት ሁኔታ የተፈጠረውን የሁለቱ የተሳሰሩ ህዝቦችን ግንኙነት ለማስቀጠልም እየተሰራ ነው ብለዋል። በሁለቱ አገራት መካከል የአየር በረራ፣ ቀጥታ የስልክ መስመሮች መቀጠላቸው የአገራቱንም ሆነ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን የማስቀጠል ስራ እንደሆነ አስምረው ግንኙነቱ የሁለቱም ህዝቦች በሚፈልጉት መጠን ላይሆን ይችላል ተብሏል። "የኢትዮጵያም ሆነ የኤርትራ ህዝብ በሚፈልገው መጠን ባይሆንም፤ የአየር በረራ፣ የስልክ መስመሮች በቀጥታ መስራታቸው፤ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ ቀጥሏል። የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝብ ዕጣፈንታ የተያያዘ ነው።" ብለዋል በቅርቡ በኢትዮጵያ የሶስት ቀናት የስራ ጉብኝታቸውን ያደረጉት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ስድስት ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል፤ ይህንንም ተከትሎ ጥያቄ ማጫሩንም ከጋዜጠኞቹ ጥያቄ ተወርውሯል። ፕሬዚዳንቱ በአሁኑ ጉብኝታቸውም የህዳሴ ግድብን ጨምሮ የልማት አካባቢዎችንም ጎብኝተዋል። የፕሬዚዳንቱ የስራ ጉብኝት ሁለቱ አገራት አብረው መስራት የሚችሉበትን ዘርፎች ከመቀየስ በተጨማሪ በመሪዎች መካከል የሚፈጠረው ቅርበትም ጠቃሚ እንደሆነ አምባሳደሩ ይናገራሉ። "በተደጋጋሚ በመሪዎች መካከል የሚፈጠረው ቅርበትና መቀራረብ በአገሮች መካከል ለሚፈጠረው መቀራረብ መሰረት ፣ መደላደል ይሆናል።" በማለትም በሁለቱ አገራት የተጀመረውን ግንኙነት የማስቀጠል ስራም መሆኑን አፅንኦት በመስጠት በቀናነት መታየት አለበት ብለዋል። የአለም ስጋት በሆነው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በሁለቱ አገራት መካከል ያሉ በረራዎችና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱም እንደተቋረጠ የገለፁት ቃለ አቀባዩ ሆኖም ለወደፊት ችግሩ ሲቀረፍ የበለጠ የኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝብ ግንኙነትም እንደሚዳብርም እምነታቸውን አስቀምጠዋል። በዚሁ መግለጫም ላይ በተደጋጋሚ ጥያቄ ከጋዜጠኞች የተነሳው በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን በተመለከተ ነው። በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ኢ-ሰብዓዊ በሆነ ሁኔታ በእስር ቤት ታጉረው ለተለያዩ በሽታዎችና ሞቶች መዳረጋቸው አሳዛኝ መሆኑንም በወቅቱ ቃለ አቀባዩ ገልፀዋል። ዜጎቿን ወደ አገራቸው ለመመለስም ከፍተኛ ጥረት እያደረገች ያለችው ኢትዮጵያም በባለፉት ሳምንታት 993 ኢትዮጵያውያን ዜጎች መልሳለች። ከነዚህም ውስጥ 955 ከሳዑዲ አረቢያ፣ 5 ከታንዛንያ 5፣ 35 ከጂቡቲ መሆናቸውንም አምባሳደር ዲና ጠቅሰዋል። ምንም እንኳን መንግሥት በፈታኝ ሁኔታ ያሉትን ዜጎች ለመመለስ ከፍተኛ ፍላጎት ቢኖርም የስደተኞችን የማንነት ሁኔታ የማጣራትና ደህንነት ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የመዘግየት ችግር እንዳለም ጠቅሰዋል። ከዚህም በተጨማሪ እዚህ ከመጡ በኋላ በገፋቸው ችግር ተመልሰው እንዳይሄዱም የሚሰሩ ስራዎች እንዳሉም ጠቁመዋል። የህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ ሚና እንዳለ ሆኖ በአገሪቷ ላይ የሰፈነው ዜጎችን ከአገር እንዲወጡ የሚገፉ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና የስራ አጥነትና የመሳሰሉት ምክንያቶች በዋነኝነት መቀረፍ እንዳለባቸውና መሰረታዊ መፍትሄ የሚባለውም ችግሩ ሙሉ በሙሉ ሲወገድ መሆኑንም አስረድተዋል። "የመመለሱ ስራ እሳት የማጥፋት ስራ ነው ሆኖም አሁን ባለው ሁኔታ ዜጎችን የመመለሱ ጉዳይ ተጠናክሮ ይቀጥላል" ብለዋል። ባለፉት ሳምንታት የእንግሊዙ ጋዜጣ ቴሌግራፍ በማጎሪያ ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን ታሳሪዎች በስልካቸው ከላኳቸው ፎቶዎች መካከል ከመስኮት ላይ ራሱን የገደለ ግለሰብና በብርድ ልብስ የተጠቀለለ አስከሬን መታየቱ ስደተኞቹ ያሉበትን ሰቆቃ አስደንጋጭ አድርጎታል። ያሉበት መከራና ስቃይ የምድር ሲኦል የሆነባቸው እነዚህ ስደተኞች ራሳቸውን ለማጥፋት የተገደዱና በመተፋፈጋቸውም ሞተዋል ተብሏል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ስደተኞች ምግብ፣ ውሃ እጥረትና ከሰው በታች ሆነው ህይወታቸውን ለመግፋት በመገደዳቸው ስቃያቸውን ለመግለፅ ቃል አጥተዋል። በስቃይ ያሉት ሰደተኞች ለባለፉት ስድስት ወራት በዚህ መልኩ ማሳለፋቸውን በምሬት ተናግረዋል። ከዚህም በተጨማሪ በውጭ ጉዳይ የተመራው ቡድን ወደ ሱዳን አቅንቶ በጎርፍ ለተጎዳችው ሱዳን የመድኃኒትና የምግብ እርዳታ መለገሱንም ቃለ አቀባዩ አውስተዋል። በዛሬው መግለጫ ላይ ከጋዜጠኞች በተጨማሪ ቀርቦላቸው የነበረው ጥያቄ የውጭ ጉዳይና የፌዴሬሽን ምክር ቤት በኢትዮጵያ ተቀማጭነታቸውን ላደረጉ የውጭ አገራት አምባሳደሮች የተሰጠውን መግለጫ በተመለከተ ነው። በውጭ ጉዳይ አማካኝነት ከፌዴሬሽን ምክር ቤትና ከከፍተኛ መንግሥት አካላት ጋር የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎች የኢትዮጵያ ምርጫ ለምን እንደተላለፈ እንዲሁም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ትግራይ ክልል ያደረገችውን ምርጫ ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች በሚመለከት ለአምባሳደሮቹ ማብራያ ተሰጥቷል። "አምበሳደሮቹ ስለ አገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ሪፖርት ሲያደርጉ የተሳሳተ መረጃ ያቀብላሉ ያም በኢትዮጵያና በአገራቱ መካከል ግንኙነት ስለሚያበላሽ ያንንም ለማስተካከል ነው" መግለጫው እንደተሰጠ ጠቅሰዋል። አምባሳደሮቹም በማጠቃለያቸው የኢትዮጵያ ሰላም፣ መረጋጋት፣ ብልፅግናና የኢትዮጵያ እድገትን እንደሚደግፉና የእነሱም ፍላጎት እንዳለበት መጥቀሳቸውን አምባሳደሩ ተናግረዋል።
news-43821012
https://www.bbc.com/amharic/news-43821012
ጥበብን ሰላም ለማስፈን መጠቀም የሚፈልገው ሙዚቀኛ
ኤርትራ ውስጥ ተወልዶ ያደገዉ ወጣት ድምፃዊ ፍሬሰላም ሙሴ የ15 ዓመት ልጅ እያለ ሙዚቃ እንደጀመረ ይናገራል።
"ሙዚቃ ለእኔ ምስጢር ነዉ። ከሰዎች ጋር ማዉራት ስጀምር ብቻ ነዉ ስለ ሙዚቃ ማሰብ የማቆመዉ። በቀላሉ የምተወዉና የምገልጸዉ አይደለም" ይላል። በተለያዩ የሙዚቃ ዝግጅቶች ላይ ሙዚቃ በመጫወት እራሱን ማሳደግ የጀመረዉ ፍሬሰላም ወላጅ አባቱ ይጫወቱበት የነበረውን ክራርና ጊታርን የመሳሰሉ የሙዚቃ መሣሪያዎችን እየተጫወተ እንዳደገ ነዉ የሚናገረዉ። "ቤተሰቤ ሙዚቃ የተማርኩበት ትምህርት ቤቴ ነዉ። ከኤርትራ እንደወጣሁ ከተለያዩ ኢትዮጵያዉያን ሙዚቀኞች ጋር በተለያዩ መድረኮች ላይ ሠርቻለሁ። ዱባይና ኡጋንዳም መሥራት ችያለሁ።" ጥበብን ለሰላም ሙዚቃ ለድምፃዊ ፍሬሰላም ቋንቋንና ባህልን ከመግለጽና ከማጉላት አንፃርም በአካልና በሥነ-ልቦና የተለያዩ ሕዝቦች አንድ ላይ እንዲዘምሩና እንዲገናኙ የማድረግ ኃይል አለዉ። "ሙዚቃ በጠባብ ጎሰኝነት ለተጠቁ ሰዎች ፈዉስ ነዉ። በኤርትራ ውስጥ አንድ ወግ ነበር። በመንግሥታት ግጭት ምክንያት የኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር ከተዘጋ በኋላ፤ ለሙዚቃ እንኳን የምትሆን ትንሽ ቀዳዳ ተዉሉን ይባል ነበር። ይሄ ለእኔ ትልቅ ትርጉም አለዉ። ሙዚቃ ልብ ዉስጥ የሚኖር ትልቅ ሃብት ነዉ።" ሙዚቃ ሥነ-ልቦናዊ መነቃቃትን በመፍጠር፣ ጭንቀትና ብስጭትን በመቀነስ ረገድና የባህሪ ለዉጥ እንዲመጣ አስተሳሰብን ከመቅረፅ አኳያ ትልቅ ፋይዳ አለዉ። በመሆኑም እኛ ወጣቶች የሕዝብን አንድነት በማሳደግ መትጋት አለብን ሲል ሃሳቡ ይቋጫል።
news-45649069
https://www.bbc.com/amharic/news-45649069
ኬንያዊው ጋዜጠኛ የ2018 የቢቢሲ ኮምላ ዱሞር ሽልማትን አሸነፈ
ኬንያዊው ጋዜጠኛና የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጁ ዋይሂጋ ምዋራ ቢቢሲ በየአመቱ የሚያዘጋጀውን የኮምላ ዱሞር ሽልማት አሸናፊ ሆኗል።
ጋዜጠኛው በኬንያ ''ሲቲዝን ቲቪ'' በተባለ የቴሌቪዥን ጣቢያ ውስጥ እጅግ በጣም ተወዳጅ የሆነ ''ኒውስ ቡሌቲን'' የተባለ ፕሮግራም አቅራቢ ነው። ከሚያገኘው ሽልማት በተጨማሪም ለንደን በሚገኘው የቢቢሲ ዋና መስሪያ ቤት ለሶስት ወራት ቆይታ የሚያደርግ ሲሆን፤ ወደ ሃገሩ ተመልሶም ስለነበረው ቆይታና ያገኘውን ልምድ የሚያካፍል ይሆናል። •በእርጥብ ሳርና ቅጠል ጥቃትን ያስቆሙ አባቶች •ኦህዴድ አብዮታዊ ዴሞክራሲንና ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነትን ታሪክ ሊያደርጋቸው ይሆን? •ስለተፈፀመው ጥቃት እስካሁን የምናውቀው ቢቢሲ ሽልማቱን በየዓመቱ ለማዘጋጀት የወሰነው ታዋቂው የቢቢሲ ጋዜጠኛ ኮምላ ዱሞር እ.አ.አ በ2014 በድንገት ከሞተ በኋላ እሱን ለማስታወስ ያለመ ነው። ዋይሂጋ ምዋራ ሽልማቱን ሲያሸንፍ አራተኛው ሰው ሲሆን፤ በ2015 የተዘጋጀው የመጀመሪያውን ሽልማት ዩጋንዳዊቷ ናንሲ ካቹንጊራ፤ በተከታዮቹ ሁለት ዓመታት ደግሞ ናይጄሪያውያኑ ዲዲ አኪንዬሉሬ እና አሚና ዩጉዳ አሸናፊ ሆነዋል። ዋይሂጋ በኬንያውያን ዘንድ ተወዳጅና ከፖለቲካ እስከ ስፖርት ድረስ ሁሉንም ዘገባዎች የሚያቀርብ ጋዜጠኛ ነው። ''ኮምላ ዱሞር ብዙ ነገር ያስተማረኝና የተዋጣለት ጋዜጠኛ ነበር፤'' እሱ በህይወቱ ማከናወን ከቻለው 20 በመቶ እንኳ የሚሆነውን ማሳካት ብችል በህይወቴና በጋዜጠኝነት ሙያ ብዙ እንደሰራሁ ነው የምቆጥረው።'' ብሏል ዋይሂጋ።
news-52414667
https://www.bbc.com/amharic/news-52414667
በጅማ ሰቃ ለእስር የተዳረጉት አቶ አብዶ አባ-ጆቢር ማናቸው?
ከትናንት ጀምሮ በማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ እጃቸው ወደኋላ ታስረው እና በበርካታ በታጠቁ ወታደሮች ተከበው የሚታዩ ሰው ምስል በስፋት ሲጋራና ስለምንነቱ የበርካቶች መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። ለመሆነ እኚህ ሰው ማናቸው?
በምስሉ ላይ የሚታዩት አቶ አብዶ አባ-ጆቢር ይባላሉ። ምስሉ የተነሳው ዕረቡ እለት በጅማ ዞን ሰቃ ጨቆርሳ ወረዳ ከመኖሪያ ቤታቸው በፀጥታ ኃይሎች ተይዘው ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሲወሰዱ የሚሳይ ነው። "ከሰዓት 11፡30 ላይ መጥተው መኖሪያ ቤታችንን ከበቡ። ከዚያ በሩን በርግደው ወደ ውስጥ ገብተው እጁን ወደኋላ አስረው እየደበደቡ ይዘውት ሄዱ" ሲሉ የአቶ አብዶ አባ-ጆቢር ባለቤት ወይዘሮ ጀሚላ አባራ ራያ ለቢቢሲ ተናግረዋል። እኚህ ሰው ማናቸው? ለምን በዚህ መልኩ ተያዙ? አቶ አብዶ አባ-ጆቢር የጅማ ዞን ሰቃ ጨቆርሳ ወረዳ ነዋሪ ናቸው። ባለትዳር እና የሦስት ልጆች አባትም ናቸው። አቶ አብዶ የሰቃ ጨቆርሳ ወረዳ ትምህርት ቢሮም ተቀጣሪ ናቸው። "የነበረውን ሁኔታ መግለጽ ከባድ ነው። ፊልም የሚሰሩ እንጂ አንድ ሰው ለመያዝ የመጡ አይመስሉም። መኖሪያ ጊቢያችን በፖሊስ ተሞልቶ ነበር" ይላሉ ወ/ሮ ጀሚላ የነበረውን ሁኔታ ሲያስረዱ ጨምረውም መኖሪያ ቤታቸውም ተፈትሿል። እንደ ወ/ሮ ጀሚላ ከሆነ ባለቤታቸው የየትኛውም ፓርቲ አባል አይደሉም። "አንድ ሰው በዚህ ወረዳ ውስጥ የወረዳውን አመለካከት ካልተከተለ፤ እንደ ተቃዋሚ ነው የሚታው" በማለት ባለቤታቸው ባላቸው የግል አመለካከት ብቻ ለእስር መዳረጋቸውን ይናገራሉ። በተመሳሳይ ቀን በሰቃ ጮቆርሳ ወረዳ በተመሳሳይ መልኩ ሌሎች ሰዎችም ስለመያዛቸው ለማወቅ ተችሏል። አራቡ ካሊፋ የተባለ አንድ ወጣት ለቢቢሲ እንደተናገረው ረቡዕ ጠዋት ላይ ቤታቸው በጸጥታ አስከባሪ ኃይሎች ከተከበበ በኋላ ወላጅ አባቱ እና ወንድሙ ተይዘው መወሰዳቸውን ይናገራል። "እኛ የየትኛውም የፖለቲካ አባል አይደለንም። በማንነታችን እንኮራለን፤ ለሕዝብ እንቆረቆራለን። እነሱ ግን 'ከኦነግ ጋር ግነኙነት አላችሁ' ይሉናል" ይላል አራቡ። ፍተሻ… ለአቶ አብዶ አባ-ጆቢር እስር እና መኖሪያ ቤቱ ለምን እንደተፈተሸ የተሰጣቸው ምክንያት "በመኖሪያ ቤታችሁ ውስጥ የተለያየ አይነት የጦር መሳሪያና ሰዎችን ለመግደል እቅድ የተያዘበት ቃለ-ጉባኤ አለ" የሚል መሆኑን ባለቤታቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። "'መኖሪያ ቤትህ ውስጥ የጦር መሳሪያ አለ። እሱን ሳንወስድ አንደሄድም' አሉት። እሱ ደግሞ 'ከፈለጋችሁ ቤቴን አፍርሳችሁ ፈልጉ። ምንም አታገኙም። የጦር መሳሪያ ካገኛችሁ ስቀሉኝ' አላቸው" በማለት ወ/ሮ ጀሚላ በባለቤታቸው እና በጸጥታ አስከባሪዎቹ መካከል የነበረውን ንግግር ያስታውሳሉ። በተደረገው ፍተሻ የጦር መሳሪያ አለመገኘቱን እና ልጆቻቸው ይጫወቱበት የነበረው የፕላስቲክ ሽጉጥ እና የታሪክ መጽሃፍ ይዘው መሄዳቸው ወ/ሮ ጀሚላ ተናግረዋል። አቶ አብዶ ለእስር የተዳረጉት ረቡዕ ከሰዓት እንደነበረ እና እስከ ትናንት (ሐሙስ) ምሽት ድረስ 12፡30 ድረስ ቃል እንዳልተቀበሏቸው ባለቤታቸው ይናገራሉ። "በጥሪ ወረቀት መጥራት ሲችሉ ልክ እንደሽፍታ እጁን ወደኋላ አስረው እየደበደቡ ይዘውት ሄዱ" የሚሉት ወ/ሮ ጀሚላ ፤ በአሁኑ ሰዓት ባለቤታቸው ታስረው የሚገኙት ከበርካታ ሰዎች ጋር መሆኑ ለኮቪድ-19 ይጋለጡ ይሆን ብለው እንደሚሰጉ ተናግረዋል። በጉዳዩ ላይ የሰቃ ጨቆርሳ ወረዳ አስተዳደር፣ የወረዳው ፀጥታ ጽህፈት ቤት እንዲሁም የወረዳውን ፖሊስ አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
news-44937202
https://www.bbc.com/amharic/news-44937202
ካለሁበት 40: "ካለ ቪዛ ወደ 127 አገራት መጓዝ እችላለሁ"
ለቲ ሂርጳ እባላለሁ። ምዕራብ ወለጋ ጊዳ አያና የምትባል ከተማ ውስጥ ነው ተወልጄ ያደግኩት።
'እዚህ የጸጥታ ችግር የለም' ከአገር ከወጣሁ 15 ዓመታት አልፉ፤ አሁን የምኖረው ካናዳ ኤድመንተን በምትባል ከተማ ውስጥ ነው። የመጀመሪያ ዕቅዴ አሜሪካ ወደሚኖረው ወንድሜ ጋር መሄድ ነበር። ወንድሜም አሜሪካ እንዲወስደኝ ዕድሎችን ለማመቻቸት 1996 ላይ ወደ ኬንያ አቀናሁ። ይሁን እንጂ የወንድሜ ጥረት ሳይሳካ ቀረ፤ እኔም ወደ ኢትዮጵያ አልመለስም ብዬ ኬንያ ጥገኘነት ጠይቄ መኖር ጀመርኩ። አንድ በር ሲዘጋ ሌላው ይከፈታል እንደሚባለው ሁሉ፤ ሌላ መልካም ዕድል አጋጥሞኝ ወደ ካናዳ መጣሁ። ኢትዮጵያን እና ካናዳ በሰፊው ከሚለያዩበት አንዱ ደህንነት ነው። እዚህ አገር ምን ሰርቼ እራሴን ላኑር የሚለው ነገር ነው ሰውን የሚያስጨንቀው እንጂ የግል ደህንነቱ አያሳስበውም። እዚህ ከመጣሁ በኋላ ብዙም የከበደኝ ነገር አልነበረም። የመጣሁ ሰሞን በረዶ የሚጥልበት ወቅት ስለነበር ቅዝቃዜው ከብዶኝ ነበር። ከአገር የሚናፍቀኝ ነገር ቢኖር ማህበራዊ ህይወቱ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዉ ተሰባስቦ አብሮ በልቶ መጨዋወት የተለመደ ነገር ነው። እዚህ አገር ግን ይህን አይነት ልማድ የለም። አገር ቤት ጎረቤት ዘመድ ነው። እዚህ አገር ግን ጎረቤቴ ማን እንደሆነ አንኳ አላውቅም። እዚህ አገር መልካም የሆነልኝ የካናዳ ዜግነት ማግኘቴ እና የአገሪቱ ዜጎች ያላቸውን መብት እኔም መጋራቴ ነው። የካናዳ ዜግነት ማግኘቴ ቪዛ ሳያስፈልገኝ 172 አገራትን መጎብኘት ያስችለኛል። ካለሁበት 38፡ ''ሳላስበው ወደ ትምህርት ዓለሙ የመቀላቀሉን ሕልሜን አሳካሁኝ'' ካለሁበት ልዩ መሰናዶ፡ ሎስ አንጀለስ ከዐብይ አህመድ በፊትና በኋላ የህንድ ምግብ በጣም እወዳለሁ። ከቤት ውጪ ከተመገብኩ 'ቺክን ብራይን' የተባለውን ምግብ መመገብ እመርጣለሁ። በልጅነቴ ወንዝ ውስጥ ስዋኝ እና ለጫካ ቅርብ ሆኜ በማደጌ እዚህ አገር ደን እና የውሃ አካል ባየው ቁጥር አገሬን ያስታውሰኛል። በተለይ ደግሞ የምኖርባትን ኤድመንተን ከተማ ለሁለት ከፍሎ የሚያልፍ ሳሰኬቹዋን የሚባለውን ወንዝ አገሬን ያስታውሰኛል። የካናዳ የአየር ጸባይ፤ በበጋ ወቅት እጅግ ሞቃታማ እንዲሁም በቅዝቃዜ ወቅት እጅግ ቀዝቃዛ ነው የሚሆነው። ለፊራፍኦሊ ዱጋሳ እንደነገራት የ'ካለሁበት' ቀጣይ ክፍሎችን ለማግኘት ፦ ካለሁበት 41: ከባሌ እስከ ቻድ የተደረገ የነጻነት ተጋድሎ
news-46616156
https://www.bbc.com/amharic/news-46616156
ሆዜ ሞሪንሆን የሚተካው የዩናትዶች ቋሚ አሰልጣኝ ማን ይሆን?
ማንችሰተር ዩናይትድ ኦሌ ጉናር ሶልሻየርን የቡድኑ ጊዜያዊ አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን አስታውቋል።
ራያን ጊግስ፣ ኦሌ ጉናር ሶልሻየር እና ዴቪድ ቤካም በፈረንጆቹ 2002 ዩናይትዶች ሊድስ ዩናይትድ ላይ ጎል አስቆጥረው ደስታቸውን ሲገልጹ ማክሰኞ ምሽት ላይ ክለቡ በድረ-ገጹ ላይ በስህተት ሶልሻየር ጊዜያዊ አሰልጣኝ ሆኖ መሾሙን ካሳወቀ በኋላ መልሶ መግለጫውን ከድረ-ገጹ ላይ ሰርዞት ነበር። ይሁን እንጂ ከደቂቃዎች በፊት ክለቡ በይፋዊ ድረ-ገጹ ላይ ሶልሻየር የክለቡ ጊዜያዊ አሰልጣኝ መሆኑን አስረግጧል። ማንችሰተር ዩናይትድ በግሪጎሪ አቆጣጠር 1999 ላይ የቻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ውድድር ላይ ሶልሻየር ጎል ሲያስቆጥር የሚያሳይ ቪዲዮ ከጫነ በኋላ ''ጊዜያዊ አሰልጣኛችን'' ሲል ገልጾት ነበር። የኖርዌይ ዜጋ የሆነው የቀድሞ የዩናይት የፊት መስመር ተጫዋች ቀያይ ሰይጣኖቹ ቋሚ አሰልጣኝ እስኪያገኙ ተጠባባቂ አሰልጣኝ ሆኖ ይቆያል። የዩናይትዶች ቋሚ አለቃ ማን ሊሆን ይችላል? የብዙዎች ጥያቄ ሆኗል። ከዚያ በፊት ግን ዩናይትዶች ቋሚ አድርገው ከሚቀጥሩት አሰልጣኝ ምን ይፈልጋሉ የሚለውን እንመልከት። ዩናይትዶች ቋሚ አድረገው የሚቀጥሩት አሰልጣኝ፤ ስለዚህ ማን ሊሆን ይችላል? 1. ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ ከፍተኛ ቅድመ-ግምት የተሰጠው ለቶተንሃሙ አሰልጣኘኝ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ ነው። ቶተንሃሞች ድንቅ ኳስ ይጫወታሉ። ቶተንሃምን የመሰለ ቡድን ያዋቀረው እሱ ባላስፈረማቸው ተጫዋቾች ነው። ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንም ጠንካራ ተጫዋቾችን ማምረት ችሏል። ከተጫዋቾች እና ከመላው የቶተንሃም ክለብ ሰራተኞች ጋርም መልካም ግነኙነት አለው። ፖቼቲኖ በሌላ ክለቦችም ተፈላጊ የሆነ አሰልጣኝ ነው። ሪያል ማድሪድ ይፈልገው ነበር። ማክሰኞ ዕለት በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ወደ አዲስ ስታዲያም ሊሄድ ስለመሆኑ ለቀረበለት ጥያቄ ፖቼቲኖ ሲመልስ፤ ''ብዙ እውነት ያልሆኑ መላምቶች ሊሰጡ ይችላሉ። በመሰል መላምቶች ላይ ተንተርሼ ምላሽ መስጠት አልፈልግም። እኔ ትኩረቴ እዚህ ባለው ስራዬ ላይ ብቻ ነው'' ብሏል። • የአፍሪካ እግር ኳስ ቅሌት 2. ዚነዲን ዚዳን ውጤታማ የእግር ኳስ ዘመን፣ ሶስት የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫዎች፣ ኃያሉን ሪያል ማድሪድን በማሰልጠን የሶስት ዓመታት ልምድ። ለማንችስተር ዩናይትድ አይመጥንም ይላሉ? ዚዳን ከማድሪድ ጋር ከተለያየበት ሰዓት ጀምሮ ቀጣዩ ክለብ ዩናይትድ ሊሆን እንደሚችል በስፋት ሲነገር ቆይቷል። ዚዳን ወደ ኦልድ ትራፎርድ ቢያቀና ከሃገሩ ልጆች ፖል ፖግባ እና አንቶኖዮ ማርሻል ጋር ጥሩ ግነኙነት ይፈጥራል ተብሎ ይገመታል። ይሁን እንጂ ዚዳን ወጣት ተጫዋቾችን የማብቃት አቅሙ እና የቴክኒክ አሰለጣጠን ክህሎቱ ጥያቄ ይነሳበታል። ይህ ብቻም አይደለም የዚዳን ደሞዝ ለዩናይትድ የማይቀመስ ሊሆን ይችላል። ዚዳን ወደ ዩናይትዶች ሜዳ የሚመጣ ከሆነ የውድድር ዘመኑ እስኪጠናቀቀ መጠበቅ አይኖርበትም። • ''ብሔርተኝነት'' እያጠላበት ያለው እግር ኳስ 3. ዲዬጎ ሲሚዮኒ ከዚህ ቀደም ዩናይትዶች አሰልጣኝ በሚፈልጉበት ወቅት ሲሚዮኒን አነጋግረውት ነበር። ሲሚዮኒ በታክቲክ እጅጉን የተደራጀ አሰልጣኝ ነው። በላሊጋው ስኬታማ ጊዜዎችን እያሳለፈ ነው። እንደ ዩናይትዶች ታላቁ አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ሁሉ ሲሚዮኒም የአሸናፊነት ስሜትን በማጫር ይታወቃል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ሲሚዮኒ ከሞሪንሆ ጋር ተመሳሳይ የእግር ኳስ ፍልስፍና እንዳላቸው በርካቶች ይስማሙበታል። ታዲያ ዩናይትዶች ሆዜን አሰናብተው ከተሰናባቹ ጋር ተመሳሳይ የኳስ ባህሪ ያለውን አሰልጣኝ ወደ ኦልድትራፎርድ ያመጣሉ? • አወዛጋቢው የእግር ኳስ ዳኞች ማስመሪያ
news-47461349
https://www.bbc.com/amharic/news-47461349
የቢጫ ወባ ካርድ በቦሌ ለሚወጡ ሁሉ ግዴታ ሊሆን ነው?
ቢጫ ወባ ክትባትን በርካታ ኤምባሲዎች ለተጓዦች በግዴታነት ያስቀምጣሉ። ኢትዮጵያም ይህንኑ ተግባራዊ የምታደርግባቸው ጎብኚዎች በርካታ ናቸው።
ለመሆኑ ከአገር የሚወጡ ተጓዦች በሙሉ ቢጫ ወባ ክትባትን ለመከተብ ይገደዳሉ? አንዳንድ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ባለፈው ሳምንታት ምንጭ ጠቅሰው እንደዘገቡት ከሆነ ማንኛውም በቦሌ ከአገር የሚወጣ ዜጋና ወደ ከየትም አገር ወደ አገር ቤት የሚገባ ጎብኚ የቢጫ ወባ ክትባት መውሰዱን ያሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት መያዝ እንዳለበትና ይህም ግዴታ ሊደረግ እንደሆነ ዘግበዋል። •በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት ይህ ምን ያህል እውነት ነው በሚል ዶ/ር በየነ ሞገስ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ም/ዋና ዳይሬክተርን ጠይቀናቸው ነበር። እርሳቸው እንደሚሉት ይህ በመገናኛ ብዙኃኑ የተሰራጨው መረጃ በመጠኑ የተፋለሰ ነው። በዚህና ተያያዥ ጉዳዮች ዙርያ የሰጡንን ማብራሪያ በአጭሩ እናቅርብላችሁ። ማን ይከተብ፣ ማን አይከተብ የሚወስነው ማን ነው? ይህን የመወሰን ሥልጣን የአገሮች እንጂ የማንም አይደለም። የዓለም ጤና ድርጅት ሚና ጠቅላላ ሕጎች መመሪያና ደንቦችን የማዘጋጀትና የመከታተል እንዲሁም የማማከር ሲሆን መዳረሻ አገራት ግን ግዴታን ይጥላሉ። ቢጫ ወባ ክትባት ሁሉም መንገደኞች እንዲይዙ ቢመከርም አስገዳጅነቱ እንደሚጓዙባቸው አገሮች ደንብና ግዴታ እንጂ ሁሉም ሰው ሲወጣና ሲገባ ይከተብ የሚል መመሪያ የለም። •በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት ክትባቱ የት ይሰጣል? በአዲስ አበባ ብቸኛው የክትባት መስጫ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሲሆን አሁን ግን በቦሌ አየር መንገድ የመዳረሻ ቪዛ አገልግሎት መጀመሩን ተከትሎ በአየር መንገድ ውስጥም ክትባት መስጫ ማእከል ለማዘጋጀት መሰናዶ አለ። ከጥቁር አንበሳ ሌላ አንድ የግል ሆስፒታልም ክትባት ለመስጠት ፍቃድ ወስዷል ብለዋል ዶ/ር በየነ። ወረርሽኝ ተከስቶ ያውቃል? በአገር ውስጥ ቢጫ ወባ የያገረሽበታል የሚባለው ቦታ በደቡብ ክልል በተለይም ደቡብ ኦሞና አካባቢው ነው። ኾኖም ወረርሽኙ አልፎ አልፎም ቢሆን መከሰቱ አልቀረም። ለአብነት ባለፈው መስከረም አካባቢ በወላይታ ወረርሽኝ መከሰቱ መዘገቡ ይታወሳል። ቢጫ ወባ ገዳይ ነው? ቢጫ ወባ ገዳይ ነው። ነገር ግን ክትባቱ እጅግ አስተማማኝ ነው። በሽታው የተያዘ ሰው ምልክት ሳይኖረው ለሞት የሚያበቃ ሁኔታ ሊገጥመው ይችላል። ሁሉንም የተያዘ ሰው ግን ይገድላል ማለት አይደለም። የበሽታው ምልክቶች ማቅለሽለሽ፣ ማስመለስ፣ መዛል፣ ከፍ ያለ ትኩሳትና የጡንቻ ህመም ናቸው። በሕይወታችን ስንት ጊዜ ነው መከተብ ያለብን? አንድ ጊዜ መከተብ ለዕድሜ ልክ ያገለግላል። ሆኖም የአንዳንድ ሰዎች በሽታ የመከላከል መጠን ዝቅ ያለ ስለሚሆን በየ 10 እና 15 ዓመቱ በድጋሚ መከተብ ጥቅም እንጂ ጉዳት የለውም። አንድ ሰው በቢጫ ወባ ተይዞ ካገገመ በኋላም በድጋሚ የመያዝ ዕድሉ የመነመነ የመነመነ የሚሆነውም ለዚሁ ነው። ክትባቱ በዘመቻ ለምን አይሰጥም? የኢትዮጵያ መንግሥት በፈረንጆች በ2020 (ከአንድ ዓመት በኋላ) የቢጫ ወባ ክትባትን በመደበኛነት በዘመቻ (Routine Vaccination) መልክ መስጠት ይጀምራል። ይህንንም ለማሳካት ከወዲሁ ዝግጅት ተደርጓል። •አዲሷ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ማን ናቸው? የሐሰተኛ (ፎርጅድ) የቢጫ ወባ ካርድ ነገር በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በር ላይ በርካታ ሐሰተኛ የቢጫ ወባ ካርዶች በጠራራ ጸሐይ ይቸበችባሉ። ሰዎች ክትባቱን ከመውሰድ ይልቅ ካርዱን ገዝተው መሄድ ይቀላቸዋል። ይህን ሁኔታ ለመግታት ጥፋተኞችን ሕግ ፊት የማቅረብ ሥራ ስንሠራ ቆይተናል ይላሉ ዶ/ር በየነ። "ሐሰተኛ ባለማኅተም ካርዶቹ ከሆስፒታሉ የሚወጡ ናቸው ወይ? በሚል ሲጠየቁም "የለም ሙሉ በሙሉ ውጭ ተመሳስለው የሚሠሩ ናቸው" ብለዋል። •'በእኔ በኩል ሒሳቤን ዘግቻለሁ ' አቶ ታምራት ላይኔ ዶ/ር በየነ ጨምረው ይህንን ችግር ሙሉ በሙሉ ለመቅረፍ «ባር-ኮድ» ማንበብ የሚችል ዲጂታል ካርድ በመዘጋጀት ላይ እንደሆነ ነግረውናል። ይህ ካርድ በኮምፒውተር መረጋገጥ የሚችል የራሱ መለያ ቁጥር ስለሚኖረው በዚህ ዓመት መጨረሻ ቢጫ ካርዱን ይተካል ተብሎ ይጠበቃል። ለዚህ የሚረዱ መሣሪያዎች ግዢ ተጠናቆ ከቴሌ የቪፒኤን ፍቃድ እየተጠበቀ ነው። ይህ ዲጂታል ካርድ ተግባራዊ ሲሆን በተጭበረበረ ቢጫ ወባ ካርድ ከአገር የሚወጡ ዜጎችን በቀላሉ መቆጣጠር እንደሚቻልም ኃላፊው ለቢቢሲ ተናግረዋል። •''አዝማሪዎቻችን የሙዚቃ ሳይንቲስቶች ናቸው" የካርድ ዋጋ ለምን 22 ብር ሆነ? ይህ ዋጋ የዛሬ 20 እና 30 ዓመት የወጣ ተመን ነው። አንዳንድ ሰዎች የብሩ ማነስ ክትባቱ የውሸት ነው ብለው እንዲያምኑ አድርጓቸዋል ይላሉ ዶ/ር በየነ። ለመድኃኒቱ የሚወጣው ገንዘብ ግን ከዚህ በብዙ እጥፍ የሚበልጥ ነው። ይህን ዝቅተኛ ተመን የመከለስ ሐሳብ እንዳለም ዶ/ር በየነ ተናግረዋል። የቢጫ ወባ ክትባትን በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ብቻ በዓመት ከ70ሺ የሚልቁ ሰዎች ይከተባሉ።
news-50969788
https://www.bbc.com/amharic/news-50969788
በጠገዴ ከታዳጊዎቹ ግድያ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ ተይዘዋል፤ ክትትሉ ቀጥሏል- የወረዳው ፖሊስ
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን፤ ጠገዴ ወረዳ ታግተው ከተወሰዱ ስምንት ታዳጊዎች መካከል ስድስቱ መገደላቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
ታዳጊዎቹ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ታግተው የተወሰዱት ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ከሰዓት አካባቢ ማይዳራ በሚባል ወንዝ አካባቢ ከብት በመጠበቅ ላይ ሳሉ ነበር። እድሜያቸው ከ10-16 የሚሆኑት ታዳጊዎች፤ ለቀናት ታግተው አጋቾቻቸው የጠየቁት ገንዘብ ሳይከፈል በመቅረቱ በጥይት ተገድለዋል። ከሟቾቹ መካከል አንዱ ጥጋቡ ደሳለኝ የተባለ የ10 ዓመት ታዳጊ ነው። ጥጋቡ ለቤተሰቦቹ ሦስተኛ ልጅ ሲሆን የመጀመሪያ ወንድ ልጅም ነው። አባቱን በመስክ ሥራዎች ለማገዝ በተለያየ ጊዜ ትምህርቱን ቢያቋርጥም ሁለተኛ ክፍል ግን ደርሶ ነበር። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የጥጋቡ አባት አቶ ደሳለኝ ማለደ "ልጄ በቤተሰቡም ሆነ በትምህርት ቤቱ የተወደደ፣ ታዛዥና ሰው አክባሪ ነበር'' ሲሉ በሀዘን በተሰበረ ልብ ይገልፁታል። ጥጋቡ ከቤት እንደወጣ ባልተመለሰበት ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ትምህርት ቤት አልሄደም ነበር። አባቱ ሰብል ለመሰብሰብ ወደ እርሻቸው ሄደው ስለነበር እርሳቸውን ለማገዝ እርሱም ከብቶቹን ይዞ ወደ መሥክ ሥራ ተሰማራ። ሰዓቱ ከቀኑ ከ8፡00 ገደማ ይሆናል። ጥጋቡ ግን ወደ ቤቱ አልተመለሰም። ማታ ወደ ቤት ይመለሳል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረውን ጥጋቡን ትተው፤ ከብቶቹ ወደ ቤታቸው አመሩ። እርሱ ግን የውሃ ሽታ ሆነ። በሁኔታው የተደናገጡት ቤተሰቦች አመሻሽ 12 ሰዓት ጀምሮ ፍለጋቸውን ጀመሩ። "ከዚህ በፊት ህፃናት ተይዘው ባያውቁም፤ በአካባቢው ሽፍቶች በመኖራቸው ይዘውት ይሆናል፤ ምን የበደልኩት ነገር ይኖር ይሆን?" በማለት ሰው እየጠየቁ፣ በርሃና ጥሻውን እያቆራረጡ ሲፈልጉ አደሩ። በማግስቱም ታህሳስ 11 ቀን 2012 ዓ.ም ልጆቹን ያገቷቸው ግለሰቦች ደውለው "አስረናቸዋል" ሲሉ ነገሯቸው። ልጃቸው ከማን ጋር በምን ሁኔታ እንዳለ ቁርጡ የተነገራቸው አባት ታዲያ፤ ለወረዳው ፖሊስ ጣቢያ "ልጄ ታግቷል" ሲሉ አመለከቱ። አመልክተውም ግን ዝም አላሉም። የወለደ አንጀት አይችልምና በወረዳው እና በአጎራባች ወረዳ፤ ምዕራብ አርማጭሆ ድረስ ሲፈልጉት ከረሙ። በተለያየ ቦታ ስልክ እየደወሉ፤ እየጠየቁ ማፈላለጉን ቀጠሉ። • ለጎንደር ጥልቅ ፍቅር ያለው ኬንያዊ ቤተ መንግሥት ሊገባ ሲል ተያዘ በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ ከአጋቾቹ ስልክ ተደወለ። 'ስምንት ሕፃናት ይዘናል፤ ለእያንዳንዳቸው 120 ሺህ ብር ይዛችሁ ኑ' ሚል ትዕዛዝ ደረሳቸው። "እኛ ድሆች ነን። ብር የለንም፤ ምንስ ተገኝቶ ነው? ፤ ምንስ በድለናችሁ ነው?" ሲሉ ይጠይቃሉ። "ብር ነው የምንፈልገው ሌላ ጉዳይ የለንም፤ ገንዘብ አላችሁ፤ ተካፍለን እንብላ" ሲሉ እቅጩን ነገሯቸው። በሁኔታው ግራ የተጋቡት ቤተሰቦች በተደወለበት ስልክ እየደወሉ "ብር አላገኘንም፤ እያሰባሰብን ነው፤ እባካችሁ ልጆቹን ስደዱልን" እያሉ ልጆቹ እንዳይጎዱና እንዳይገርፉ ሲለምኑ፤ አጋቾቹም ሲደውሉ ሰነበቱ። "ገንዘብ ይዛችሁ ካልመጣችሁ እርምጃ እንወስዳለን" እያሉ ያስፈራሯቸው እንደነበር አቶ ደሳለኝ ይናገራሉ። አጋቾቹ ለልጆቹም ስልክ እየሰጡ "ገንዘብ ይዛችሁ የማትመጡ ከሆነ፤ አታገኙንም" እንዲሉ ያደርጓቸው ነበር። "ልጆች ናቸው። ምን በደሏችሁ?፤ እኛ አልበደልናችሁ። እባካችሁ!" እያሉ እየተለማመጡ ነበር። ግን ይገድሏቸዋል የሚል ሃሳብ ፈፅሞ እንዳልነበራቸው አቶ ደሳለኝ ይናገራሉ። ያሳለፉትን ቀናትም "በአፋችን እሳት በሆዳችን እሳት እየወጣ ነው የሰነበትነው" ሲሉ ይገልፁታል። በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ ታህሳስ 19 ቀን ልጃቸው ከሌሎች ጓደኞቹ ጋር እንደተገደለ ከወረዳው ፖሊስ ተደውሎ ተነገራቸው። በልጃቸው ላይ ይህ ከሆነ በኋላ፤ እንኳን ለልጆቻቸው ለራሳቸውም ስጋት እንዳደረባቸው፤ ቀሪዎቹ ልጆቻቸውም ቤት ውስጥ እንደሚውሉ ይናገራሉ። የጠገዴ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት ተወካይ ኃላፊ ኢንስፔክተር እሸቴ ገ/ማሪያም ከግድያው ጋር በተያያዘ ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንና አሁንም ፍለጋው ተጠናክሮ መቀጠሉን ያስረዳሉ። እርሳቸው እንደሚሉት ከቤተሰብ የልጆቹ መጥፋት ጥቆማ እንደደረሳቸው፤ አጋቾቹ ደውለውበታል የተባለውን የስልክ መስመር ለማጣራት ወደ አካባቢው ኢትዮ ቴሌኮም መሥሪያ ቤት ደብዳቤ ፃፉ። ተጣርቶም የስልክ መስመሩ ባለቤት ማንነት ተነገራቸው። ግለሰቡ በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ ሲጠየቅ "ለአጎቴ ሸጨለታለሁ" ይላል። የስልክ መስመሩ የተሸጠላቸው አጎት የሚገኙበትን ሌላ ስልክ ፖሊስ ከተቀበለ በኋላ ባደረገው ማጣራት፤ ግለሰቡ መቀሌ ከተማ እንደሚገኙ ማወቅ ችለዋል። ግለሰቡን በቁጥጥር ሥር አውሎ ለመመርመር የሚገኙት በሌላ ክልል ውስጥ በመሆኑ ጉዳዩን የፌደራል መንግሥት ጸጥታ አስከባሪ ኃይል እንዲይዘው በማድረግ እየተሠራ መሆኑን ኢንስፔክተሩ ገልፀውልናል። በሌላ በኩል በአካባቢው 'ሽፍታዎች' አልፎ አልፎ አሽከርካሪዎችን፣ ግለሰቦችን በማገት ገንዘብ የመጠየቅ ልማድ እንዳለ የሚናገሩት ኢንስፔክተሩ፤ ከዚህ ቀደምም በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሽፍቶች መኖራቸውን ያስታውሳሉ። ኢንስፔክተር እሸቴ እንደሚሉት፤ ከህፃናቱ ግድያ ጋር በተገናኘም በአካባቢው ሽፍታ ተብለው የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ቤተሰቦች በስጋት ተሰውረዋል። በአካባቢው በቀል ስላለ እርሱን ሽሽት መሰወራቸው እንዲሁም ከግድያው ከተረፈው ልጅ ከሰሙት ቃል ግድያውን የፈፀሙት ሽፍታዎች ሳይሆኑ እንዳልቀሩ ሌላ ፍንጭ እንደሰጣቸው ተናግረዋል። እስካሁንም ስምንት የሚሆኑ የሽፍታ ቤተሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለዋል። በአካባቢው በተለያየ ምክንያት የሸፈቱ 'ሽፍታዎች' የሚታወቁ ቢሆንም፤ እነርሱን አድኖ ለመያዝ ግን የአካባቢው መልከዓ ምድራዊ ሁኔታና ግለሰቦቹ ከቦታ ቦታ ስለሚንቀሳቀሱ አዳጋች ሆኖ መቆየቱን ገልፀዋል።
news-56142077
https://www.bbc.com/amharic/news-56142077
ምርጫ 2013 ፡ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ መጀመራቸውን ይፋ አደረጉ
በመጪው ምርጫ የሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለምርጫው የሚያደርጉትን ቅስቀሳ መጀመራቸውን ይፋ አደረጉ።
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)፣ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክረሲና (ባልደራስ) እንዲሁም የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በጋራ ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ የምርጫ ቅስቀሳ መጀመራቸውን ባካሄዷቸው ሥነ ሥርዓቶች በይፋ አድርገዋል። ቅዳሜ የካቲት 13/2013 ዓ.ም "ንቁ ዜጋ፤ ምቹ አገር" በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ የግዮን ሆቴል የምርጫ ቅስቀሳ ጅማሬውን ይፋ ያደረገው ኢዜማ፤ "ይህ ምርጫ ከዚህ በፊት እንደነበሩት የይስሙላ ወይም የሙከራ ሳይሆን፤ በትክክል የመጀመሪያ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲሆን" ኃላፊነት እንዳለባቸው የፓርቲው መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሥነ ሥርዓቱ ላይ ተናግረዋል። የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋም ምርጫው ዜጎች ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ መሠረት የምንጥልበትና አገሪቱ ወደተረጋጋ ስርዓት የምትሸጋገርበት ሊሆን ይገባል ብለዋል። "ጊዜው አሁን ነው!" በሚል መሪ ቃል በምርጫው የሚሳተፈው አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)፤ በአዲስ አበባ ጉዳናዎች ላይ ባካሄደው መርሐ ግብር ከባልደራስና ከመኢአድ ጋር በመሆን የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻው መጀመሩን ይፋ አድርጓል። በሥነ ሥርዓቱ ላይ የአብን ሊቀ መንበር አቶ በለጠ ሞላ በምርጫው ስጋት ብቻ ሳይሆን እድልም እንደሚሚመጣ ጠቅሰው "ሁላችንም ከቀደመው የፖለቲካ አዙሪትና የምርጫ ተሞክሮ ተምረን ለአገራችን የመጀመሪያው የተሳካ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ልናደርገው እንችላለን" ብለዋል። አብን ከአዲስ አበባ ባሻገር በባሕር ዳር፣ በጎንደርና በደሴ ከተሞች የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻው መጀመሩን ባካሄዳቸው ሥነ ሥርዓቶች ይፋ አድርጓል። በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በወጣው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት የመራጮች ምዝገባና የምርጫ ቅስቀሳ ሰኞ የካቲት 08/2013 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን፤ ገዢው የብልጽግና ፓርቲ ባለፈው ሳምንት ሊቀመንበሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በተገኙበት ሥነ ሥርዓት ላይ የምርጫ ማኒፌስቶውንና የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቱን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። በዚህ ወቅት የፓርቲው ሊቀመንበር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) እንደተናገሩት "ዋናው ፍላጎታችን ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያንን አሸናፊ የሚያደርግ ምርጫ ማድረግ ነው። ይህም ማለት ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ሁሉም በነጻነት የሚሳተፍበት፣ በሀሳብ ልዕልና የሚመረጥ ወይንም የሚወድቅበትን ሁኔታ መፍጠር ነው" ብለዋል። ባለፈው ዓመት ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ወደዚህ ዓመት ከተሸጋገረ በኋላ በመጪው ግንቦት ማብቂያና በሠኔ ወር መጀመሪያ ላይ ለማካሄድ የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶለት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስፈላጊውን ዝግጅት እያካሄደ መሆኑ ይታወቃል። ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ከትግራይ ክልል በስተቀር በሌሎቹ የአገሪቱ ክፍሎች ይካሄዳል በተባለው ምርጫ ከአገሪቱ ሕዝብ ግማሽ ያህሉ በመራጭነት ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ምርጫ ቦርድ ገልጿል። በዚህ ምርጫ በመላው አገሪቱ ድምጽ የሚሰጡባቸው ከ50 ሺህ በላይ የምርጫ ጣቢያዎች፣ ከ152 ሺህ በላይ የመራጮች ምዝገባን የሚያከናውኑ ባለሙያዎችና ከ254 ሺህ በላይ ምርጫ አስፈጻሚዎ እንደሚሰማሩ ተገልጿል።
news-54915506
https://www.bbc.com/amharic/news-54915506
ትግራይ ፡ ከባድ የሮኬት ፍንዳታ በኤርትራ መዲና አሥመራ መሰማቱ ተነገረ
በኤርትራዋ መዲና አሥመራ ከተማ አየር ማረፊያ አካባቢ ቅዳሜ ምሽት የከባድ መሳሪያ ፍንዳታዎች መሰማታቸውን ነዋሪዎችና ዲፕሎማቶች ለቢቢሲ አረጋገጡ።
ፍንዳታው የተሰማው ከአንድ በላይ ተወንጫፊ ሮኬቶች በአስመራ ከተማ ውስጥ መውደቃቸውን ተከትሎ ሲሆን በዚህም ሳቢያ ስለደረሰ ጉዳትም ሆነ ስለምክንያቱ እስካሁን የተገለጸ ነገር የለም። ሮኬቶቹ ከትግራይ ክልል እንደተወነጨፉ ሚዲያዎችና ዲፕሎማቶች ተናግረዋል። አርብ ኅዳር 04/2013 ዓ.ም ምሽት በሰሜን ኢትዮጵያ በአማራ ክልል ውስጥ በሚገኙት በባሕር ዳርና በጎንደር አየር ማረፊያዎች ላይ ከትግራይ ክልል በኩል በተተኮሱ ሮኬቶች በተፈጸመ ጥቃት መጠነኛ ጉዳት መድረሱን የኢትዮጵያ መንግሥት ያስታወቀ ሲሆን ለዚህም ጥቃት የትግራይ ክልል ኃይሎች ኃላፊነት መውሰዳቸው ይታወቃል። ከኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት ጋር ወታደራዊ ግጭት ውስጥ የገባው የትግራይ ክልልን የሚመራው ህወሓት ከፍተኛ አመራር አባል የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ በክልሉ ቴሌቪዥን ላይ ቅዳሜ ዕለት ቀርበው ተጨማሪ ጥቃቶች ሊፈጽሙ እንደሚችሉና ይህም በኤርትራ ውስጥ የሚገኙ የተመረጡ ኢላማዎች እንደሚጨምር አስጠንቅቀው ነበር። የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) በተደጋጋሚ የኤርትራ ኃይሎች የኢትዮጵያ መንግሥትን በመደገፍ ጥቃት እየፈጸሙባቸው መሆኑን የከሰሱ ሲሆን፤ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር አቶ ዑስማን ሳልሕ ለሮይተርስ በሰጡት ቃል "በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አንገባም" ሲሉ ተናግረው ነበር። ኢትዮጵያና ኤርትራ ደም አፋሳሽ የድንበር ጦርነት ካደረጉ በኋላ ለሁለት አስርት ዓመታት ተፋጠው ከቆዩ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደስልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ ሰላም አውርደው ግንኙነታቸውን እያጠናከሩ ይገኛሉ። በፌደራል መንግሥቱና በትግራይ ክልል መካከል ለወራት የዘለቀው ውዝግብና ፍጥጫ ከሳምንት በፊት ወደ ወታደራዊ ግጭት ተሸጋግሮ በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ውጊያዎች እየተካሄዱ መሆናቸው ይታወቃል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንዳለው በትግራይ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ጦርነት እስካሁን ድረስ ቢያንስ 17 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ግጭቱን በመሸሽ ድንበር ተሻግረው ወደ ሱዳን ገብተዋል። ኤርትራ ውስጥ የተከሰተው የአሥመራ ከተማ ነዋሪዎች ቅዳሜ ምሽት ተደጋጋሚ ከባድ የፍንዳታ ድምጽ መስማታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። አንድ ስማቸው ያልተገለጸ ዲፕሎማት "ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በርካታ ሮኬቶች በከተማዋ በሚገኘው አየር ማረፊያ አቅራቢያ መውደቃቸውን ነው" ሲሉ ለፈረንሳይ ዜና ወኪል ኤኤፍፒ ተናግረዋል። የኤርትራ የዜና ድረገጽ የሆነው 'ተስፋ ኒውስ' በትዊተር ገጹ ላይ እንዳሰፈረው፤ "በህወሓት ቁጥጥር ስር ከሚገኘው የትግራይ አካባቢ የተተኮሱ ሁለት ሮኬቶች አውሮፕላን ማረፊያውን ስተው ከአሥመራ ከተማ ዳርቻ ላይ ወድቀዋል" ብሏል። ቀደም ሲል የህወሓት ቃል አቀባይ የኤርትራ ኃይሎች ድንበር ተሻግረው ወደ ኢትዮጵያ በመግባት የፌደራል መንግሥቱን ሠራዊት በጦርነቱ እየተደገፉ መሆናቸውን በመግለጽ ኤርትራ ላይ ጥቃት እንደሚፈጽሙ አስጠንቅቆ ነበር። የኤርትራ መንግሥት ግን በግጭቱ ውስጥ ምንም አይነት ሚና እንደሌለው የገለጸ ሲሆን፤ ከትግራይ ጋር በሚዋሰኑ የድንበር አካባቢዎች ውጊያዎች ስለመካሄዳቸውና የቆሰሉ ወታደሮች ኤርትራ ውስጥ በሚገኙ ሆስፒታሎች ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን የሚያመለክቱ ዘገባዎች እየወጡ ይገኛሉ። ጥቃት በባሕር ዳርና በጎንደር የኢትዮጵያ መንግሥት በባሕር ዳርና በጎንደር ከተሞች የሚገኙትን አውሮፕላን ማረፊያዎች ኢላማ ያደረገ የሮኬት ጥቃት ባለፈው አርብ መፈጸሙን ቅዳሜ ዕለት ይፋ አድርጓል። በዚህም አንድ ሮኬት በጎንደር አየር ማረፊያ ላይ በከፊል ጉዳት ያደረሰ ሲሆን፤ በተመሳሳይ ሰዓት የተተኮሰው ሌላኛው ሮኬት ግን በባሕር ዳር ከሚገኘው አየር ማረፊያ ውጪ መውደቁን አንድ ባለስልጣን ለሮይተርስ ተናግረዋል። ሁለቱም አየር ማረፊያዎች ለሲቪልና ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች አገልግሎት የሚሰጡ ሲሆን ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ በሰው ላይ የተደረሰ ጉዳትን በተመለከተ ወዲያው የተሰጠ መረጃ የለም። ጥቃቱ በቅርቡ ፌደራል መንግሥቱ አማካይነት ለተፈጸሙት የአየር ድብደባዎች የተወሰደ የአጸፋ እርምጃ መሆኑን አቶ ጌታቸው ረዳ ተናግረዋል። "በትግራይ ሕዝብ ላይ የሚፈጸሙት ጥቃቶች አስካልቆሙ ድረስ፤ ጥቃቱ ተጠናክሮ ይቀጥላል" ያሉ ሲሆን በትግራይ ቴሌቪዥን ላይ ባደረጉት ቃለምልልስም ተጨማሪ ጥቃቶች እንደሚኖሩ አስጠንቅቀዋል። የደረሰ ጉዳት በፌደራል መንግሥቱና በትግራይ ክልል መካከል ወታደራዊ ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ በመቶዎች ህይወታቸውን ማጣታቸው የተነገረ ሲሆን፤ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጭፍጨፋ መፈጸሙን የሚያመለክቱ ዘገባዎችም እየወጡ ነው። የሰብአዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅት የሆነው አምነስቲ ኢንትርናሽናል እንዳለው ባለፈው ሰኞ በማይካድራ ከተማ "በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በስለተማ ነገሮች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን" እንደረጋገጠ ሪፖርት አድርጓል። አምነስቲ እንዳለው "በከተማዋ ውስጥ በሚገኙ ጎዳናዎች ላይ የወዳደቁና ሰዎች በቃሬዛ ተሸክመዋቸው የሚታዩ አስከሬኖችን የሚያሳዩ እውነተኝነታቸው የተረጋገጡ ፎቶዎችን" ተመልክቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ለህወሃት አመራሮች ታማኝ የሆኑ ኃይሎችን ለጅምላ ግድያው ተጠያቂ ያደረጉ ሲሆን፤ የትግራይ ክልል በበኩሉ እጃችን የለበትም ብለዋል። በአገሪቱ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የተፈጸመውን ግድያ ለመመርመር አጣሪ ቢድን ወደ ስፍራው መላኩን ገልጿል። ከዚህም በተጨማሪ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን የተሰደዱ ሲሆን የሱዳን መንግሥትም በስደተኞች መጠለያ ካምፕ ውስጥ አስገባቸዋለሁ ብሏል።
news-53332012
https://www.bbc.com/amharic/news-53332012
የሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ የሟቾች ቁጥር መጨመሩን ፖሊስ አስታወቀ
የድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በተከሰተው አለመረጋጋት የሞቱ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን የፌደራልና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽኖች አስታወቁ።
ባለመረጋጋቱ ህይወታቸውን ያጡት ሰዎች ቁጥርን በተመለከተ የሚወጣው መረጃ ጭማሪ ቢያሳይም በፌደራል ፖሊስና በኦሮሚያ ፖሊስ በኩል እየወጣ ያለው አሃዝ ልዩነትን አንጸባርቋል። ኤኤፍፒ የዜና ወኪል የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ተጠባባቂ ኮሚሽነር ሙስጠፋ ከድር ለአገሪቱ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሰጡት ያለውን መግለጫ ጠቅሶ እንደዘገበው የሟቾች ቁጥር 239 ደርሷል። ነገር ግን ቢቢሲ ይህንን አሃዝ ለማጣራት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት የሆኑትን አቶ ጄይላን አብዲን ጠይቆ ባገኘው መረጃ መሰረት የጸጥታ ኃይል አባላትን ጨምሮ የሟቾች ቁትር 177 መሆኑን ለመረዳት ችሏል። በዚህም መሰረት 167 ሰዎቹ የሞቱት ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ሲሆን የቀሩት 10ሩ ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ደግሞ 229 መሆናቸውን አቶ ጄይላን ለቢቢሲ ገልጸዋል። በተጨማሪም ከአለመረጋጋቱ ጋር በተያያዘ ከተፈጸሙ ጥቃቶችና የንብረት ውድመት የተጠረጠሩ በርካታ ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌደራል ፖሊስ ገልጾ፤ በኦሮሚያ ክልል 3100 ሰዎች እንዲሁም 1600 ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ተይዘዋል። በሌላ በኩል ደግሞ የኦሮሚያ ፖሊስ ተጠባባቂ ኮሚሽነሩ እንዳሉት እንዳሉት ግን ቁጥሩ "በክልሉ በተከሰተው አለመረጋጋት 14 የፖሊስና የሚሊሽያ አባላትና 215 ሰላማዊ ሰዎች ሞተዋል" በማለት ተናግረዋል ሲል ኤኤፍፒ ዘግቧል። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 166 መድረሱን የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፖሊስ ኮሚሽነር ግርማ ገላን የገለጹ ሲሆን በወቅት 167 የሚሆኑ ግለሰቦችም ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ምክትል ኮሚሽነሩ ተናግረው ነበር። ከሰኞ ሰኔ 22 ሌሊት ጀምሮ በተቀሰቀሰው አለመረጋጋት በቀናት ውስጥ ይህ ቁጥር በከፍተኛ መጠን ጨምሮ 239 መድረሱም ተገልጿል። በባለስልጣኑ ለህይወት መጥፋት ምክንያት ያሉት ከፀጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት እንዲሁም በተለያያዩ ብሔሮች መካከል ከተፈጠረ ሁከት የተያያዘ ነው ተብሏል። ከዚህም በተጨማሪ ተጠባባቂ ኮሚሽነሩ በክልሉ "የመንግሥት እንዲሁም የግል ንብረቶች ላይ ከፍተኛ ውድመት እንዲሁም ዝርፊያ ተፈፅሟል" ብለዋል። መንግሥት ለደረሱት ጥፋቶች ተጠያቂ ናቸው ያላቸውን 3 ሺህ 500 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንዳዋሉም ተናግረዋል "እነዚህ ግለሰቦች ፀረ- ሰላም ኃይሎች ናቸው። የድምፃዊውን ሞት ሽፋን በማድረግ ሕገ መንግሥታዊውን ሥርዓት በኃይል ለማፈራረስ ጥረት አድርገዋል፤ ጥቃቶችንም ፈፅመዋል" ብለዋል። ፖሊስ ጨምሮም በግድያ፣ በሁከቱና በንብረት ማጥፋቱ ላይ ከተሳተፉት ሰዎች በተጨማሪ አለመረጋጋቶቹ ተከስተው ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች በተሰጣቸው ኃላፊነት መሰረት ነዋሪውን በመጠበቅ ኃላፊነታቸዉን ያልተወጡ የፀጥታ አባላትን የመለየት ሥራ እየተከናወነ ነው ብሏል። በፖለቲካ ግጥሞቹ ከፍተኛ ዝናን ያተረፈው ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ የተገደለው ሰኔ 22/2012 ዓ.ም አዲስ አበባ ውስጥ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ገላን ኮንዶሚኒየም ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ መኪናው ውስጥ ነበረ። በግድያው ተጠርጥረው ሁለት ወንዶችና አንዲት ሴት ፍርድ ቤት ባለፈው ሳምንት ቀርበው የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ እንደተጠየቀባቸው ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ከግድያው ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ሰዎች መያዛቸውን ገልጿል።
49862594
https://www.bbc.com/amharic/49862594
ናይጄሪያ፡ 500 የሚጠጉ ወንዶች ታጉረውበት ከነበረው ህንጻ ነፃ ወጡ
በሰሜን ናይጄሪያ በምትገኘው ካዱና ከተማ ውስጥ ታሥረው ወሲባዊ ጥቃት እና እንግልት ሲደርስባቸው ነበር የተባሉ 500 የሚደርሱ ወንዶች ነጻ መውጣታቸውን ፖሊስ አስታወቀ።
አምስት ዓመት ከሚሆናቸው ህጻናት አንስቶ እስከ ጎልማሶች ድረስ በአንድ ህንጻ ውስጥ ታጉረው ነበር አምስት ዓመት ከሚሆናቸው ህጻናት አንስቶ እስከ ጎልማሶች ድረስ በአንድ ህንጻ ውስጥ ታጉረው ነበር። ህንጻው የእስልምና ትምህርት መስጫ ነው የሚል ሽፋን ተሰጥቶት ነበር ተብሏል። • መሐመድ አሊ፡ የአልሲሲን ገመና አደባባይ ያሰጣው ግብጻዊ • ሙጋቤ በተወለዱበት ከተማ ሊቀበሩ ነው • አንጎላዊያኑ በደቡብ ኮሪያ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ዘጠኝ ወራትን አስቆጠሩ የካዱና ከተማ ፖሊስ ኃላፊ አሊ ጃንጋ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ስለ ህንጻው ጥቆማ ከደረሳቸው በኋላ ወንዶቹን ነፃ ማውጣት ችለዋል። አንዳንዶቹ አካላዊ ጉዳት ደርሶባቸው፣ የተቀሩት ደግሞ በቂ ምግብ ባለማግኘታቸው ምክንያት ተዳክመው ነበር። "ህንጻው ሰዎች የሚሰቃዩበት፣ የባርነት ቤት ነበር" ሲሉ ኃላፊው ተናግረዋል። በህንጻው ውስጥ ታግተው የነበሩት ወንዶች ለዓመታት ወሲባዊ ጥቃት ይፈጸምባቸው፣ ምግብም ይከለከሉ እንደነበረም ገልጸዋል። መምህራን ናቸው የተባሉ ስምንት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል። ከታጋቾቹ አንዱ የሆነው ቤል ሀምዛ "በዚህ ህንጻ ውስጥ ለሦስት ወር እግሬን ታሥሬ ቆይቻለሁ፤ የእስልምና ትምህርት ቤት ነው ይላሉ፤ ነገር ግን ከህንጻው ለመውጣት የሚሞክር ሰው ጣሪያ ላይ ተሰቅሎ ከባድ ቅጣት ይቀጣል" ብሏል። ህንጻው የእስልምና ትምህርት መስጫ ነው የሚል ሽፋን ተሰጥቶት ነበር አንዳንዶቹ ታዳጊዎች ለፖሊስ እንደተናገሩት፤ ቤተሰቦቻቸው ወደ ህንጻው የወሰዷቸው የእስልምና ትምህርት የሚሰጥበት ቦታ ነው ብለው በማመን ነበር። ከታዳጊዎቹ ሁለቱ የተላኩት ከቡርኪና ፋሶ ሲሆን፤ የተቀሩት የሰሜን ናይጄሪያ ተወላጆች ናቸው። በአካባቢው የእስልምና ትምህርት ከሚሰጥባቸው ትምህርት ቤቶች በጥቂቱ ውስጥ ታዳጊዎች እንደሚበዘበዙ፣ እንዲለምኑ እንደሚገደዱም ይነገራል። አንድ ወላጅ "ልጆቻችን እንዲህ ያለ ስቃይ እንደሚደርስባቸው አናውቅም ነበር" ሲሉ ለሮይተርስ ተናግረዋል። ነፃ የወጡት ወንዶች በጊዜያዊ መጠለያ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፤ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን የከተማዋ ባለሥልጣኖች ለቢቢሲ ገልጸዋል።
news-56318084
https://www.bbc.com/amharic/news-56318084
ስደተኞች፡ በየመን ኢትዮጵያውያን በሚበዙበት መጠለያ ውስጥ በተነሳ እሳት በርካቶች ሞቱ
በየመኗ ዋና ከተማ ሰንዓ በርካታ ኢትዮጵያውያን በነበሩበት አንድ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ በተነሳ እሳት በርካቶች መሞታቸው ተነገረ።
በርካታ ከአፍሪካ ቀንድ በተለይም ከኢትዮጵያ የሄዱ ስደተኞች በተጠለሉበት በዚህ ስፍራ የተነሳው እሳት 30 ሰዎችን ሲገድል 170 ሰዎች ደግሞ ተጎድተዋል ሲል ዓለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም (አይኦኤም} ገልጿል። የእሳት አደጋው የተነሳው የሁቲ ታጣቂዎች በሚሳዔልና ድሮን ሳዑዲ አራቢያ ውስጥ ያለ የነዳጅ ማከማቻ መምታቸውን ተከትሎ ሳዑዲ መራሹ ኃይል በሰንዓ ጥቃት ከፈጸመ በኋላ ነው። የእሳት አደጋው ከመድረሱ በፊት መጠለያ ጣቢያው በጦርነቱ ሳቢያ ምስቅልቅሉ ወጥቶ እንደነበር ተነግሯል። ከስደተኞቹ በተጨማሪ የመጠለያው ጠባቂዎችም በአደጋው ከሞቱ መካከል ናቸው። የአይኦኤም የመካከለኛው ምሥራቅና ሠሜን አሜሪካ ተወካይ የሆኑት ካርሜላ ጎዴ የድርጅቱ ሠራተኞች ከ170 በላይ ለሆኑ በእሣት አደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች እርዳታ እያደረጉ እንደሆነ በትዊተር ገፃቸው አሳውቀዋል። አደጋ ከደረሰባቸው 170 ሰዎች መካከል 90 ያክሉ በአስጊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ካርሜላ ጽፈዋል። የእሳት አደጋው መንስዔ እስካሁን ባይታወቅም የሳዑዲ መራሹ ኃይል ያደረሰው ጥቃት በአካባቢው ባሉ ሕንፃዎች ላይ ጉዳት ማድረሱ ከተነገረ በኋላ መሆኑ ተገልጿል። የእሳት አደጋውን በተመለከ የሁቲ ታጣቂዎች ባወጡት መግለጫ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅትና የተባበሩት መንግሥታት ለስደተኞቹ መኖሪያ ባለማቅረብ እና ከየመን እንዲወጡ ለማድረግ ባለመተባበራቸው ለደረሰው አደጋ ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ ናቸው ሲሉ ወቅሰዋል። ትናንት እሁድ በስደተኞቹ መጠለያ ውስጥ በደረሰው የእሳት አደጋ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችል ተሰግተወል። አይኦኤም እንደሚገምተው በኮሮናቫይረስ ምክንያት የተጣለውን የመንቀሳቀስ ገደብ ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች የመን ውስጥ ወደየትም መሄድ ሳይችሉ እየተጉላሉ ነው። ምንም እንኳ የመን ማብቂያ ባላገኘ ጦርነት ውስጥ ብትሆንም በተለይ ደግሞ መነሻቸው ከአፍሪካ ቀንድ የሆኑ በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ድንበሯን እያቋረጡ ወደ ጎረቤት አገር ሳዑዲ አራቢያ ለመግባት በመፍለስ ላይ ናቸው። የመን ውስጥ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ ሳዑዲ አረቢያ ድንበሯን በመዝጋቷ አብዛኞቹ ስደተኞች በጦርነት፣ በረሃብና በበሽታ እየተሰቃዩ በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ይገኛሉ። የመን ውስጥ በሳዑዲ መራሹ ኃይልና በኢራን በሚደገፉት የሁቲ ታጣቂዎች መካከል ስድስት ዓመት የሆነውና አሁንም እየተካሄደ ያለው ጦርነት ከስደተኞቹ በተጨማሪ የአገሪቱን ዜጎች ህይወት አመሰቃቅሎታል። የመን ውስጥ ከሚኖሩ ሰዎች መካከል 80 በመቶ ያህሉ እርዳታ ላይ ጥገኛ ሲሆኑ፤ በርካቶች አገራቸውን እየለቀቁ ጦርነቱን ሽሽት ይሰደዳሉ። ምንድን ነው የተከሰተው? ቢቢሲ ያነጋገራቸው እና በየመን ሰንዓ የእሳት አደጋ በደረሰበት ማቆያ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ስለእሳት አደጋው መንሰኤ ሲናገሩ "የተወረወረ የእጅ ቦንብ" ነው ይላሉ። ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት [አይኦኤም] የየመን ቢሮ እንዳለው ለበርካታ ሰዎች ምክንያት የሆነው ቃጠሎ የደረሰበት ማዕከል በአገሪቱ መንግሥት የሚተዳደር ማቆያ ሲሆን አደጋው በደረሰበት ወቅት 700 ያህል ስደተኞች በውስጡ ነበሩ። በወቅት በማቆያ ውስጥ የነበረ አንድ ስደተኛ የዓይን እማኝ ለቢቢሲ እንዳለው ከእሳት አደጋው ቀደም ብሎ በማቆያው ጠባቂዎችና በስደተኞች መካከል አለመግባባት ነበር። አለመግባባቱ ተባብሶ ስደተኞቹ ወደ አገራችን መልሱን ማለታቸውንና ካልሆነ ግን ምግብ እበላም በማለ ተቃውሟቸውን ማሰማታቸውን ይናገራል። ይህ አለመግባበት ተካርሮ "ጠባቂዎቹ የማቆያውን በር ዘግተው ከውጪ የእጅ ቦንብ በመወርወር" አደጋው መፈጠሩን ለቢቢሲ አስረድቷል። አደጋው በደረሰበት ወቅት በአካባቢው የነበረ ሌላ ኢትዮጵያዊ ስደተኛም ለደረሰው አደጋ ምክንያቱ "የተወረወረ የእጅ ቦንብ ነው" ብሏል። ጨምሮም አደጋው ከደረሰበት ስፍራ የሟቾችን አስከሬን ካነሱ ሰዎች አረጋገጥኩ በማለት እንደተናገረው "እስከ ትናንት እኩለ ለሊት ድረስ 182 ሰዎች መሞታቸውን" ገልጿል። በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ስደተኞች ሰንዓ ውስጥ ወዳሉ ትልልቅ የመንግሥት ሆስፒታሎች በአምቡላንስ መወሰዳቸውንም ጨምሮ ገልጿል። በየመን ማን ከማን ጋር እየተዋጋ ነው?
news-54874864
https://www.bbc.com/amharic/news-54874864
ኮሮናቫይረስ፡ በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሺህ አለፈ
በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሺህ ማለፉን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት ህዳር 2/2013 ዓ.ም አስታወቀ።
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በፌስቡክ ገፁ ላይ ይፋ እንዳደረገው በኢትዮጵያ ኮሮናቫይረስ መከሰቱ ከታወቀበት መጋቢት 4 /2012 ዓ.ም ጀምሮ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 100 ሺህ አልፏል። የኮቪድ-19 ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ በቫይረሱ የተያዘ ሰው የተገኘው መጋቢት 4/ 2012 ዓ.ም ሲሆን እስካሁን ድረስ ለ1,534,470 ምርመራ ተደርጎ 100 ሺህ 327 በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በኢትዮጵያ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 1ሺህ 537 መሆናቸውን የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ መግለጫ ያትታል። አክሎም 61 ሺህ 516 ህሙማንም ከበሽታው አገግመዋል ሲል ገልጿል። የጤና ሚኒስቴሩ አክሎም "ኮሮና የለም" ከሚል የተሳሳተ አመለካከት በመውጣት ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል በመከላከሉ ላይ ጠንክሮ እንዲሰራ ጥሪ አቅርቧል። የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትም "ማስክ ካልተደረገ አገልግሎት የለም" የሚለውን መርህ እንዲከተሉ አሳስቧል። በበርካታ አገራት በኮቪድ-19 የሚያዙ ከፍተኛ ቁጥር መመዝገቡን ተከለትሎ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሚሊዮን አልፏል። እንደጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ከሆነ ከ1.25 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል። በብዙ አገራት በቂ ምርመራ ባለመደረጉ እንጂ ይህን አሃዝ ከፍ ያለ ነው ተብሎ ይገመታል። በመላው አለም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁትር 51,554,166 መድረሱን የዩኒቨርስቲው መረጃ ያሳያል። በቫይረሱ በከፍተኛ ቁጥር ከተያዙት አገራት መካከል አሜሪካ፣ ሕንድ እና ብራዚል ከቀዳሚዎቹ ተርታ ይገኙበታል። እንደ አፍሪካ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር መረጃ ከሆነ እስካሁን ድረስ በአፍሪካ 1,904,820 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ 45,954 ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን ከዚሁ ጋር በተያያዘ አጥተዋል።
news-52980990
https://www.bbc.com/amharic/news-52980990
ኮሮናቫይረስ በቻይና ከተባለው ጊዜ ቀድሞ መከሰቱን የሳተላይት ምስሎች ጠቆሙ
ካለፈው ነሐሴ ወር ጀምሮ በቻይናዋ ዉሃን ከተማ ውስጥ በሚገኙ ሆስፒታሎች የታየው ከፍተኛ የሰዎች እንቅስቃሴ የኮሮናቫይረስ እንደተከሰተ ከተነገረበት ጊዜ ቀድሞ ሳይጀምር እንዳልቀረ እንደሚያመለክቱ አንድ ጥናት ጠቆመ።
በከተማዋ የሚገኙ አምስት ሆስፒታሎች አካባቢ ከነሐሴ እስከ ታኅሳስ ወር ድረስ ባሉት ጊዜያት በትራፊክ ተጨናንቀው መታየታቸውን የሳተላይት ምስል መረጃዎች ማመልከታቸውን ያስታወቁት የሃርቫርድ ተመራማሪዎች ናቸው። በጊዜው የታየው የትራፊክ ፍሰትም፤ ስለሳልና ተቅማጥ ምልክት ምንነት የተመለከቱ መረጃዎች ለማግኘት ወደ ድረ ገጾች ጎራ የሚሉ ከፍተኛ ተጠቃሚዎች ቁጥር ጋር መገጣጠሙንም ጥናቱ ያስረዳል። ቻይና ጥናቱ በተሳሳተ መረጃ ላይ የተመሰረተ እና እርባና ቢስ ነው ስትል አጣጥለዋለች። ቫይረሱ ለመጀመሪያ ጊዜ በቻይና የታየው በህዳር ወር እንደሆነ ይታመናል። ባለሥልጣናትም ባልታወቀ ምክንያት በሳንባ ምች በሽታ የተያዙ ሰዎች እንዳሉ ለዓለም ጤና ድርጅት ያስታወቁት ግን ታኅሳስ ወር መጨረሻ ላይ ነበር። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱ ከተገለጸበት ጊዜ አስቀድሞም በተወሰነ ደረጃ ማኅበራዊ መረበሾች እንደነበሩም የጥናቱ መሪ ዶ/ር ጆን ብሮውንስቴን ለኤቢሲ ኒውስ ተናግረዋል። በእርግጥ ጥናቱ በዘርፉ ባለሙያዎች አልተገመገመም። ጥናቱ ያሳየው ምንድን ነው? አጥኚዎቹ ከአምስት የዉሃን ሆስፒታሎች እንቅስቃሴን የሚያሳዩ የንግድ ሳተላይት የምስል መረጃን የመረመሩ ሲሆን መረጃውን ከዚህ ቀደም ከነበረው ተመሳሳይ ጊዜ ጋር አነጻጽረውታል። በዚህም በጎርጎሮሳዊያኑ ህዳር 2018 ቲያንዮ በተባለ በዉሃን በሚገኝ ትልቅ ሆስፒታል 171 መኪናዎች ቆመው የተመለከቱ ሲሆን፤ በ2019 በተመሳሳይ ጊዜና ቦታ 285 መኪናዎች ቆመው እንደነበር የሳተላይት ምስሉ አሳይቷል ተብሏል። ይህም ቀድሞ ከነበረው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የትራፊክ ፍሰቱ 67 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። በዚሁ ጊዜ የኮሮናቫይረስ ምልክቶችን በቻይና ባይዱ በተሰኘ የኢንትርኔት መፈለጊያ ዘዴ ላይ [ሰርች ኢንጅን] የሚያስሱ ሰዎች ታይተዋል። ይህም በዉሃን በወቅቱ የተከሰተ አንዳች ነገር ስለመኖሩ የሚያሳዩ ተጨባጭ መረጃዎች ናቸው ብለዋል ዶ/ር ብራውንስቴን። አጥኚዎቹ ከተጠቀሙበት የዉሃን ሆስፒታል እንቅስቃሴን ከሚያሳዩ ሳተላይት ምስሎች መካከል አንዱ የጥናቱ አንድምታዎች ምንድን ናቸው? በቤይጂንግ የሚገኘው የቢቢሲው ዘጋቢ ጆን ሱድወርዝ፤ ጥናቱ በተካተቱ መረጃዎች ላይ ውስንነት እንዳለ ያሳያል ብሏል። ጆን በምሳሌ ሲያስረዳም፤ አንዳንዶቹ ፎቶግራፎች በደመና የተሸፈኑ በመሆናቸው ለተከታታይ ዓመታት በተመሳሳይ ጊዜ የተነሱ የሳተላይት ምስሎችን ሁልጊዜ ማወዳደር አይቻልም ይላል። ከዚህም ባሻገር ጥናቱ በጠቀሰው ጊዜ ወረርሽኙ ቢኖር ምናልባት የተወሰኑ ሰዎች ዉሃንን ጥለው በመውጣት ወደ ሌሎች አገራት ይጓዙ ነበር፤ ልክ በሌሎች የዓለም አገራት ኮቪድ-19 ሲከሰት የነበሩና እያየነው ካለው አንዳንድ መረጃዎች ጋር ተመሳሳይ ይሆን ነበር ብሏል። ምንም እንኳን ቻይና ስለ ቫይረሱ ለማሳወቅ ዘግይታለች ለሚለው ሃሳብ ጥናቱን እንደ ማስረጃ መጠቀም ፍትሃዊ ባይሆንም፤ ምክንያቱ በውል የማይታወቅ በሽታ በማኅበረሰብ ውስጥ ሲከሰት በይፋ የበሽታው ምንነት ሳይታወቅ ሊስፋፋ ይችላል ሲል ሃሳቡን ሰንዝሯል። ቻይና መነሻው በውል ባልታወቀ የሳንባ ምች በሽታ ሰዎች መያዛቸውን ለዓለም ጤና ድርጅት ያሳወቀችው በጎርጎሮሳዊያኑ ታህሳስ 31/2019 ነበር። ከዘጠኝ ቀናት በኋላ የቻይና ባለሥልጣናት የሳንባ ምች በሽታ በተያዙ አብዛኞቹ ሰዎች የኖቨል ኮሮናቫይረስ ማግኘታቸውን አስታወቁ። በኋላም ቫይረሱ ኮቪድ-19 በሽታን የሚያስከትል ሳርስ-ኮቪድ-2 የሚል ስያሜ ተሰጠው። ከዚያም ጥር 23 /2020 ዉሃንና ሌሎች የቻይና ከተሞች ሙሉ በሙሉ እንቅስቃሴ ያቸውን ገደቡ። የዓለም ጤና ድርጅትም ከሰባት ቀናት በኋላ ከቻይና ውጪ ባሉ አገራት 82 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ተከትሎ በሽታውን ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ መሆኑን ማወጁ ይታወሳል።
news-55802354
https://www.bbc.com/amharic/news-55802354
የዓለም ምግብ ድርጅት የአንበጣ መከላከያ ርጭት ለማካሄድ የገንዘብ እጥረት ገጥሞኛል አለ
የተባበሩት መንግሥታት የዓለም ምግብ ድርጅት (ፋኦ) በምስራቅ አፍሪካ የአንበጣ ወረርሽኝን ለመዋጋት ያሰማራቸውን አውሮፕላኖች ሙሉ በሙሉ በገንዘብ እጥረት ምክንያት ሊያቆማቸው እንደሚችል አስጠነቀቀ።
የዓለም ምግብ ድርጅት እንዳለው ከሆነ አውሮፕላኖችን ለማንቀሳቀስ 38 ሚሊዮን ዶላር ይፈልጋል። አዲስ የአንበጣ ወረርሽኝ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ ተከስቶ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ገበሬዎችን ሕይወት ፈተና ውስጥ መጣሉ ተልጿል። እነዚህ በአንበጣ ወረርሽኝ የተጎዱ አካባቢዎች በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እንዲሁም በከባድ ጎርፍ ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ እንደሚገኙ ተገልጿል። እንደ ፋኦ ምዘና ከሆነ በኬንያ ብቻ በ11 ግዛቶች የአንበጣ ወረርሽኝ የተከሰተ ሲሆን መንጋው ወደ ታንዛንያ የባህር ዳርቻዎች እየተመመ መሆኑ ተገልጿል። በዚህ ዓመት በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ሰፊ የሆነ የእርሻ ማሳ በአንበጣ ወረርሽኝ የተነሳ መውደሙም ተገልጿል። በምስራቅ አፍሪካ በዚህ ዓመት ብቻ የአንበጣ ወረርሽኝ ሲከሰት ሶስተኛው ነው። አዲሱ የአንበጣ ወረርሽኝ የተራባው በሳይክሎን ጋቲ ታግዞ ሲሆን፣ በቀጠናው በአንድ ጊዜ የሁለት ዓመት ዝናብ በአጭር ቀናት ውስጥ አስከትሎ ነበር። ይህ ደግሞ ለአንበጣ መንጋ መራቢያነት ምቹ ሆኖ ማገለገሉን ባለሙያዎች ይናገራሉ። በሶማሊያ የዓለም ምግብ ድርጅት የድንገተኛ እርዳታ ማስተባባሪያ ኃላፊ የሆኑት ኢዛና ካሳ "የወረርሽኙ ተጽዕኖ ከዚህ ቀደምም ደካማ የምግብ ዋስትና የነበረው አርሶ አደር፣ ከፊል አርብቶ አደር እንዲሁም አርብቶ አደሩ ሕይወት ላይ፣ የበለጠ ጫና ያሳድራል።" ብለዋል። የተባበሩት መንግሥታት እንዳለው ከሆነ ከባለፈው ዓመት ታሕሳስ ወር ጀምሮ በመሬት እና በአየር የሚደረገው የፀረ ተባይ መድሃኒት ርጭት 1.2 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ምግብ እና የወተት ተዋጽኦ ከውድመት ታድጓል። "አፍሪካ ከዚህ ቀደም በዚህ መጠን የአንበጣ ወረርሽኝ ያየችው፣ በሳህል አካባቢ ሲሆን፣ ሙሉ በሙለ ለመቆጣጠርም ሁለት ዓመት እና 500 ሚሊዮን ዶላር ያህል ያስፈልጋል።" የዓለም ምግብ ድርጅት (ፋኦ) ምክትል ዳይሬክተር ጄነራል ላውረንት ቶማስ "ይህ ወረርሽኝ በጣም ከፍተኛው ነው፣ ነገር ግን በምስራቅ አፍሪካ ለመቆጣጠር ቁርጠኝነቱ አለ። መንግሥታት እነዚህ አውሮፕላኖች መብረር እንዲችሉ ማድረግ ይኖርባቸዋል።"
news-50597487
https://www.bbc.com/amharic/news-50597487
ቱርክ የፈረንሳዩን ፕሬዝደንት 'ሽብርን ይደግፋሉ' ስትል ከሰሰች
የቱርኩ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር፤ የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ሽብርተኝነትን ይደግፋሉ ሲሉ ተቹ።
የቱርኩ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ የፈረንሳይ ባለስልጣናት ቱርክ በሶሪያ የወሰደችውን እርምጃ መተቸታቸውን ተከትሎ ነው የቱርኩ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ ይህን ትችት የሰነዘሩት። የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ ማክሮን የአውሮፓ መሪ መሆን ቢፈልጉም፤ መረጋጋት እንኳ አልቻሉም በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ባለፈው ወር ማክሮን በኩርዶች የሚመሩትን የሶሪያ ዲሞክራቲክ ኃይል ተቀብለው ማነጋገራቸው ቱርክን እጅጉን አበሳጭቶ እንደነበረ ይታወሳል። የፕሬዝደንት ማክሮን ጽ/ቤት የሶሪያ ዲሞክራቲክ ኃይልን ተቀብለው ያነጋገሩት አይኤስን በመዋጋት ረገድ ለሚያሳዩት አጋርነት እውቅና ለመስጠት እና ቱርክ በሰሜን ሶሪያ ላይ ልትወስደው ስላሰበችው የጦር እርምጃ ለመምክር መሆኑን አስታውቆ ነበር። ኩርዶች በቱርክ፣ ኢራቅ፣ ኢራን እና ሶሪያ ውስጥ ተበታትነው የሚኖሩ ሲሆን፤ የራሳቸውን ሉዓላዊት፣ ነጻ አገር ለመመስረት ይታገላሉ። በቱርክ ብቻ ወደ 20 ሚሊዮን የሚጠጉ ኩርዶች እንደሚኖሩ የሚገመት ሲሆን፤ ቱርክ ነጻ አገርን ለመመስረት የሚታገሉትን ኩርዶች አሸባሪ ስትል ትፈርጃቸዋለች። የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ከሦስት ሳምንታት በፊት ባደረጉት ንግግር የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ቱርክ በሰሜን ሶሪያ ለጀመረችው ወታደራዊ እርምጃ ምላሽ መስጠት ባለመቻሉ ክፉኛ ኮንነውታል። ማክሮን ኔቶን "አዕምሮው ሞቷል" ሲሉም ገልጸውታል። በተጨማሪም የኔቶ አባል አገራት ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረግ እና ከውሳኔ መድረስ እንደተሳናቸው ተናግረዋል። የቱርክ እና ሩሲያ ጥምር ኃይል በሰሜናዊ ሶሪያ የምድር ቅኝት እያደረጉ ይገኛሉ። የቱርኩ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ፤ ትናንት ከአገሪቱ የሕዝብ እንደራሴዎች ፊት ቀርበው፤ "እሱ [ማክሮን] የአሸባሪ ደጋፊ ነው። በተደጋጋሚ ወደ ቤተ-መንግሥት እየጠራ ያስተናግዳቸዋል። ወዳጆቼ አሸባሪ ኃይሎች ናቸው ካለ ከዚህ በላይ ምንም ማለት አይቻልም" ብለዋል። ቱርክ ወደ ሰሜን ሶሪያ ዘልቃ በመግባት "ደህንነቱ የተረጋገጠ ቀጠና" ለመፍጠር ከ30 በላይ ኪሎ ሜትሮችን ዘልቃ በመግባት የጦር እርምጃዎችን ስትወስድ ቆይታለች። በዚሁ ቀጠና የቱርክ እና ሩሲያ ጥምር ኃይል የምድር ቅኝት እያደረጉ ይገኛሉ። ቱርክ ከወራት በፊት ዘመናዊ ሩሲያ ሰራሽ ኤስ-400 የተሰኙ ከምድር ወደ አየር ሚሳኤል ሥርዓቶችን ከክሬምሊን መግዛቷን ተከትሎ ከኔቶ አባል አገራት ጋር ያላት ወዳጅነት ሻክሯል።
news-57140213
https://www.bbc.com/amharic/news-57140213
የአሜሪካ የተራድኦ ድርጅት በኢትዮጵያ የረሃብ አደጋ ስጋት መኖሩን አመለከተ
የአሜሪካው የተራድኦ ድርጅት ዩኤስ አይዲ በኢትዮጵያ የረሃብ ስጋት መኖሩን ገለፀ።
ዶሚኒክ ራብ እና ሳማንታ ፓዎር የዩናይትድ ስቴትስ የዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ (ዩኤስአይዲ) መሪ እና የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በነበራቸው የጋራ ውይይት ላይ በኢትዮጵያ የረሃብ ስጋት አለ ስለማለታቸው ድርጅቱ በድረገፁ ላይ አስፍሯል። የዩኤስአይዲ መሪ ሳማንታ ፓወር ከዩኬው የውጭ፣ የኮመን ዌልዝና የልማት ጉዳዮች ሚኒስትሩ ዶሜኔክ ራብ ጋር በበይነ መረብ አማካይነት ሲወያዩ በኢትዮጵያና በየመን እየጨመረ ነው ስላሉት የረሃብ ስጋት መወያየታቸውን ዩኤስአይዲ አስታውቋል። ባለስልጣናቱ ስለ አሜሪካና ዩናይትድ ኪንግደም ግንኙነት መጠናከርን፣ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን፣ የሴቶች ትምህርት፣ የሰብአዊ እርዳታ በጀትና የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተ መወያየታቸውንም ድረ ገፁ አትቷል። ጨምሮም "እንደ በኢትዮጵያና የመን ባሉ አገራት እየጨመረ ስለመጣው የረሃብ ስጋት መክረዋል" ከማለት ውጪ በየትኛው የአገሪቱ ክፍል የረሃብ አደጋ ስጋት እንዳለ ያለው ነገር የለም። ይህ በእንዲህ እንዳለ የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም በትግራይ ያለው ሁኔታ "እጅግ አስከፊ" ነው ብለዋል። ዋና ዳይሬክተሩ ሰዎች በትግራይ ክልል በረሀብ ምክንያት ሰዎች እየሞቱ ነው፤ የምግብ እጥረትም እየተስፋፋ ነው ብለዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ቴድሮስ አድኃኖም በጄኔቭ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ "በትግራይ ያለው ሁኔታ ምናልባት ቃሉ ከገለጸው አስከፊ የሚባል ነው። እጅግ አስከፊ ነው" ብለው 4 ሚሊዮን ተኩል ወይም 5 ሚሊዮን ሕዝብ የሰብአዊ ድጋፍ እንደሚፈልግ ገልጸዋል። "91 ከመቶ የሚሆነው ሕዝብ የምግብ እርዳታን የሚጠባበቅ ነው። በርካታ ሰዎች በእርግጥም በረሃብ እየሞቱ ነው። አሳሳቢ የሆነ የተመጣጠነ ምግብ እጥረትም በስፋት አጋጥሟል" ብለዋል። በትግራይ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያሻቸው ሲገለጽ ቆይቷል። በትግራይ ክልል "በርካቶች በረሃብ ምክንያት ለሞት ሊዳረጉ እንደሚችሉ" ባለፈው ጥር አንድ የመንግሥት ባለስልጣን መናገራቸውን ከእርዳታ ሠራተኞች ጋር ከተደረገ ስብሰባ ላይ ሾልኮ የወጣ ማስታወሻ ላይ ሰፍሮ መገኘቱ መዘገቡ ይታወሳል። በፌዴራልና በክልሉ መንግሥት መካከል በተፈጠረ ግጭት ከገበያዎች የምግብ አቅርቦት መመናመን፣ በክልሉ ተከስቶ በነበረው የአንበጣ ወረርሽኝና በተያያዥ ምክንያቶች በርካቶችን ለአስቸኳይ የምግብ ርዳታ እንዳጋለጣቸው የተለያዩ ሪፖርቶች ጠቁመዋል። የተባበሩት መንግሥታት ደርጅት ደግሞ በትግራይ 4.5 ሚሊዮን ሕዝብ አስቸኳይ የምግብ ርዳታ ያስፈልገዋል ብሎ ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ የሰብዓዊ እርዳታ ለዜጎች ለማቅረብ የተቻለውን ሁሉ ሲያደርግ መቆየቱን በተደጋጋሚ ገልጿል። መንግሥት ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ርዳታ አቅራቢ ድርጅቶ በመላው ትግራይ ገብተው እንዲሰሩም ከመፍቀዱም በላይ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል።
news-50833024
https://www.bbc.com/amharic/news-50833024
ጃፓን፡ ጋዜጠኛዋን የደፈረው 30 ሺ ዶላር ተቀጣ
የጃፓን ፍርድ ቤት አንዲት ሴት ጋዜጠኛ ታዋቂው ጋዜጠኛ ደፍሮኛል ብላ ያቀረበችውን ክስ ተቀብሎ 3.3 ሚሊየን የን (30 ሾ ዶላር) ካሳ እንዲከፍል ብያኔ አስተላልፏል።
በአንድ የዜና ተቋም ውስጥ በጋዜጠኝነት የምትሰራው ሾሪ ኢቶ ኖሪዩኪ ያማጉቺ የተባለው ግለሰብ በአውሮፓውያኑ 2015 ራሷን በሳተችበት ወቅት እንደደፈራት በመግለጽ ክስ አቅርባ ነበር። ጉዳዩን ሲከታተል የነበረው አቃቤ ሕግ በእውነት ስለመደፈሯ ምንም ማስረጃ ማግኘት አልቻልንም ብለው ነበር። ሾሪ ኢዮ ግን ይግባኝ በመጠየቋ ክሱ እንደገና ሲታይ ቆይቷል። • በኢራቅ ጎዳናዎች ከፍ ያሉት ሴቶች • ለሁለት ዓመታት ልጁን በጓደኞቹ ያስደፈረው አባት ህንድን አስቆጣ የእሷ ጉዳይም ጾታዊ ጥቃቶች እምብዛም ወደ ሕግ በማይቀርቡባት ጃፓን በርካቶች ወደፊት እንዲመጡ አድርጓል። የፍርድ ሂደቱ ከተጠናቀቀ በኋላ'' በጣም ደስ ብሎኛል'' ብላለች የ30 ዓመቷ ሾሪ፤ 'ድል' የሚል ጽሁፍም በእጇ ይዛ ታውለበልብ ነበር። በጃፓን የመደፈር ጥቃት ከሚደርስባቸው ሴቶች መካከል 4 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ጉዳዩን ለፖሊስ እንደሚያሳውቁ በአውሮፓውያኑ 2017 የጃፓን መንግስት የሰራው ጥናት ያሳያል። ሾሪ እንደምትለው ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ጋር የቅርብ ግንኙት ያለው ታዋቂው ዘጋቢ ኖሪዩኪ ያማጉቺ በ2015 ስለአንድ የስራ ጉዳይ ለማውራት በማለት የእራት ግብዣ አድርጎላት ነበር። '' የበላሁት ወይም የጠጣሁት ውስጥ መድሀኒት ሳይጨመርብት አልቀረም፤ ራሴን ስቼ ነበር። ከቆይታ በኋላ ስነቃ ግን አንድ ሆቴል ውስጥ ተኝቼ ኖሪዩኪ ያማጉቺ ከላዬ ሆኖ አገኘሁት።'' ኖሪዩኪ ያማጉቺ በወቅቱ በጃፓን ታዋቂ የዜና ወኪል የሆነው 'ቶክዮ ብሮድካስቲንግ ሲስተም' የዋሽንግተን ቢሮ ዋና ሀላፊ ነበር። ጉዳዩን ለፖሊስ ካሳወቀች በኋላ ወደተደፈረችበት ሆቴል ተወስዳ ሁኔታው እንዴት እንደፈጠረ እንድታስረዳ መደረጓን ታስታውሳለች። '' ፖሊሶቹ ወደ ሆቴሉ ከወሰዱኝ በኋላ ሰው የሚመስል አሻንጉሊት እላዬ ላይ ጭነው የሆነውን ነገር በሙሉ አስረጂን እያሉ ያዋክቡኝ ነበር። ደግሞ ሁሉም ፖሊሶች ወንዶች ነበሩ። በጣም አስጨናቂና አስፈሪ ሁኔታ ነበር'' ብላለች። • እሷ ማናት?: ለነፃነትም ለጥበብም ያልታከቱ እጆች ሾሪ ለደረሰባት ጥቃት 11 ሚሊዮን የን (105 ሺዶላር) ካሳ ጠይቃለች። ተከሳሽ ደግሞ አልደፈርኩም በፈቃድ ላይ የተመሰረተ ነበር በማለት ስሜን ስላጠፋች 130 ሚሊዮን የን (1.1 ሚሊየን ዶላር) ካሳ ትክፈለኝ ብሎ ተከራክሯል። ግራ ቀኙን የተመለከተው ፍርድ ቤትም ተከሳሽ ለሾሪ 3.3 ሚሊየን የን (30 ሾ ዶላር) ካሳ እንዲከፍል ብያኔውን አስተላልፏል።
51740177
https://www.bbc.com/amharic/51740177
በጎንደር ጊዜ ያለፈባቸው መድኃኒቶች ሲያከፋፍሉ ነበር የተባሉ 13 ካናዳዊያን በዋስ ተለቀቁ
የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸውን መድኃኒቶች ሲያከፋፍሉ ነበሩ የተባሉ 13 ካናዳዊያን እና ሁለት ኢትዮጵያዊያን እያንዳንዳቸው በ20ሺህ ብር ዋስ መለቀቃቸውን በጎንደር የሦስተኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ደሳለኝ አበራ ለቢቢሲ ገለጹ።
15ቱ ግለሰቦች ትላንት የካቲት 25 ቀን 2012 ዓ. ም. በዋስ እንደተለቀቁ ገልጸዋል። 15ቱ ግለሰቦች ጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 አካባቢ በሚገኝ ትምህርት ቤት የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸውን መድኃኒቶች በመስጠት ላይ እያሉ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አየልኝ ታከለው ለቢቢሲ ገልጸዋል። ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት መድሃኒት የተሰጣቸው ሰዎች እና ትምህርት ቤቱ በሰጡት ጥቆማ ነው ተብሏል። "ጥቆማውን መነሻ አድርገን የህክምና ባለሙያዎች እንዲያዩት እና እንዲያረጋግጡ አድርገናል። በትክክልም ጊዜው ያለፈበት መድኃኒት ለተማሪዎቹ እየሰጡ መሆኑን ካረጋገጥን በኋላ ሰዎቹን በቁጥጥር ስር አውለናል" ሲሉ ኮማንደር አየልኝ ለቢቢሲ ገልጸዋል። • ከኮሮናቫይረስ ጋር የሚደረገውን ፍልሚያ የሚመሩት ሰው • በአማራ ክልል አንዳንድ ቦታዎች ዳኞች ጥቃት እየደረሰባቸው ነው • የተማሪዎቹ መታገት ከተሰማ 90 ቀናት አለፉ በርካታ መድኃኒቶች ጊዜ ያለፈባቸው ናቸው ያሉት ኮማንደር አየልኝ፤ "እነዚህ መድኃኒቶች እስከ ስድስት ዓመት ድረስ ጊዜ ያለፈባቸው ናቸው" ብለዋል። "ከዚህ በፊት በዋነኛነት እርዳታ የሚሰጡት አልባሳት እና የተለያዩ ነገሮችን ነበር። አመጣጣቸውም ይሄን ብለው ነው። ነገር ግን በተጨማሪ ይሄን ድርጊት አከናውነዋል" ሲሉም አክለዋል። ኮማንደር አየልኝ እንደተናገሩት፤ ተጠርጣሪዎቹ ተማሪዎቹ በሚነግሯቸው የህመም ምልክቶች እና 'እንዲህ ዓይነት ህመም አለብን' ሲሏቸው ያለምንም መመርመሪያ መሣሪያ እና ቴክኖሎጂ መድኃኒት ሰጥተዋል ተብሏል። መድኃኒቶቹን ወስደው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ስለመኖራቸው ሲጠየቁም "መድኃኒቱን የወሰዱ ሰዎችን የጤና ሁኔታ ምርመራ ማድረግ ያስፍልጋል። አሁን ባለው ሁኔታ ጉዳት ላይኖር ይችላል። ከጊዜ በኋላ ግን ጉዳት ሊያመጣ ይችላል። እሱን ሙያተኛ የሚያስቀምጠው ይሆናል" ሲሉ መልሰዋል።
51254053
https://www.bbc.com/amharic/51254053
ቻይና ተላላፊውን በሽታ ለመግታት በ6 ቀናት ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ ሆስፒታል ልትገነባ ነው
የቻይናዋ ዉሃን ግዛት በ6 ቀናት ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ ሆስፒታል ልትገነባ መሆኗን አስታውቃለች።
በ6 ቀናት የሚጠናቀቀው የቻይና ሆስፒታል የውሃን ግዛት ሆስፒታሉን በአስቸኳይ የምትገነባው ቻይና ውስጥ ተከስቶ መዳረሻውን ብዙ የዓለም አገራት እያደረገ ያለውን የኮሮና ቫይረስን ለማከም ነው። ቫይረሱ በግዛቷ ከተከሰተ ወዲህ 830 ሰዎች በቫይረስ መጠቃታቸው ታውቋል። 41 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ሞተዋል። 11 ሚሊዮን ዜጎች በሚኖሩባት ውሃን ግዛት በቫይረሱ በታመሙ ታካሚዎች ሆስፒታሎች ተጨናንቀው ከፍተኛ የመድኃኒተ እጥረትም ተከስቷል። የአገሪቱ ብሔራዊ ብዙሃን መገናኛ እንደዘገበው አዲሱ በ6 ቀናት ውስጥ የሚጠናቀቀው ሆስፒታል 1 ሺህ የመኝታ አልጋዎች እንዲኖሩት ተደርጎ የሚሰራ ነው። የተለቀቁ የተንቀሳቃሽ ምስሎች እንደሚያሳዩት ቆፋሪ ማሽኖች በቦታው የደረሱ ሲሆን በ25 ሺህ ሄክታር ላይ የሚያርፈውን ሆስፒታል መቆፈር ጀምረዋል። አሁን የሚሰራው ሆስፒታል በ2003 (እ.አ.አ) የሳርስ ቫይረስን ለማከም በቤጂንግ ከተሰራው ሆስፒታል ጋር ተመሳሳይ ነው ተብሏል። እንዴት በ6 ቀናት ብቻ ሆስፒታል መሥራት ይቻላል? ይህን ዜና ተከትሎ በርካቶች አስተያየት እየሰጡ ይገኛሉ። "ቻይና እንደዚህ አይነት ወቅታዊ ችግሮችን ለማለፍ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት በማጠናቀቅ የምትታማ አይደለችም" በማለት ያንዙንግ ሁዋንግ የተባሉ ዓለም አቀፍ የጤና ሞያተኛ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። እርሳቸው እንደሚሉት በቤጂንግ በ2003 የተሰራው ሆስፒታል በሰባት ቀናት ነበርና የጠተናቀቀው ይህኛውን ሆስፒታል በተባለው ቀን ለማጠናቀቅ የሚያስቸግር ነገር የለም። "ውሳኔው ከላይ ካሉት ባለስልጣናት የተሰጠ በመሆኑ የቢሮክራሲና የፋይናንስ ሰንሰለቶች ስለማይኖሩትና ሁሉም አቅርቦቶች በበቂ ደረጃ የሚሟላለት በመሆኑ ሆስፒታሉ በተባለው ጊዜ ይጠናቀቃል" የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት መሃንዲሶቹ ከመላው ቻይና ተሰባስበዋል። ቻይና በምህንድስናው ዘርፍ እጅግ የተዋጣላት ነች፤ ምናልባት ምዕራባዊያን ላያምኑ ይችላሉ፤ ነገር ግን ይህ ዕውን መሆኑን ለማረጋገጥ 6 ቀናትን ብቻ ይታገሱ በማለት የቻይናዊያንን የምህንድስና ፍጥነት አድንቃዋል። ይህ ከሆነ በኋላ ዉሃን ግዛት መድሃኒቶችን ከጎረቤት ሆስፒታል ታስመጣለች ወይም ደግሞ ቀጥታ ከፋብሪካዎች ታስመጣለች። ሳርስ ቫይረስ ሲከሰት ምን ነበር የሆነው? በ2003 በቻይና ተከስቶ የነበረውን የሳርስ ቫይረስ ለማከም ሲባል ዢያኦታንግሻን ሆስፒታል በቤጂንግ ተገነባ። የዓለማችን ፈጣኑ ግንባታ በመሆን በሰባት ቀናት ብቻ ነበር የተገነባው። በተባለው ቀን ለማጠናቀቅ 4 ሺ የሚሆኑ ሙያተኞች ሌትና ቀን በስራው ተሳትፈውበታል። በውስጡ የኤክስሬይ ክፍል፣ የሲቲ ስካን ክፍል፣ ከፍተኛ-እንክብካቤ የሚሰጥበት ክፍልና ላቦራቶሪ ነበረው። እያንዳንዱ ክፍል የራሱ የሆነ የመታጠቢያ ቤት አለው። በሁለት ወራት ውስጥ ሆስፒታሉ የሳርስ በሽታ በመላ አገሪቱ ከታየባቸው ቻይናውያን መካከል አንድ ሰባተኛ የሚሆኑትን በመፈወስ በህክምና ታሪክ ተዓምር የተሠራበት ነው ተብሏል።
53633841
https://www.bbc.com/amharic/53633841
ትራምፕ ቻይና ሰራሹ ቲክቶክ ላይ እርምጃ ሊወስዱ ነው
ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በመጪዎቹ ቀናት በቻይና ሰራሹ ቲክቶክ ላይ እርምጃ ሊወስዱ መሆኑን ማይክ ፖምፔፖ ገለጹ።
የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ ማይክ ፖምፔዮ፤ ፕሬዝደንቱ ቲክቶክ ላይ እርምጃ መውሰድ ያስፈለጋቸው የስልክ መተግበሪያው በአሜሪካ ላይ የብሔራዊ ደህንነት ስለጋረጠ ነው ብለዋል። ቻይና ስሪቱ የተንቀሳቃሽ ምሥል መጋሪያ ድር ቲክቶክ በመላው ዓለም በተለይም በወጣቶች ዘንድ ሰፊ ተቀባይነት ያገኘ ነው። የቪዲዮ መጋሪያው መተግበሪያ “ለቻይናው ኮሚኒስት ፓርቲ መረጃ በቀጥታ ከሚያስተላለፉት መካከል ነው” ብለዋል ፖምፔዮ። ዶናልድ ትራምፕም በቀጣዩ ጥቂት ቀናት የቲክቶክን እጣ ፈንታ ላይ ይወስናሉ ብለዋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዎ። ትራምፕ ከዚህ ቀደም ቲክቶክን በአሜሪካ እንዳይሰራ አግዳለሁ ሲሉ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል። ቲክቶክ ግን ለቻይና መንግሥት መረጃ እንደማያቀብል እንዲሁም ቁጥጥር እንደማይደረግበት በተደጋጋሚ ሲያስተባብል ቆይቷል። ፖምፔዮ ለፎክስ ኒውስ ሲናገሩ፤ አሜሪካ የሚሰሩ እና ለቻይና መንግሥት መረጃ የሚያቀብሉ በርካታ ኩባንያዎች አሉ ብለዋል። ኩባንያዎቹ ለአሜሪካ መንግሥት ከሚያቀብሏቸው መረጃዎች መካከል በሰዎች ሰልክ ቁጥር ውስጥ ተመዝግበው የሚገኙ አድራሻዎች እና ስልክ ቁጥሮች ይገኙበታል። ትራምፕ ባለፈው አርብ ነበር በአሜሪካ ብቻ 80 ሚሊዮን ወርሃዊ ደንበኞች ያሉትን ቲክቶክን ለመዝጋት ፍጹማዊ ፕሬዝዳንታዊ ሥልጣናቸውን እንደሚጠቀሙ ያስታወቁት። ባይትዳንስ በሚባል የቻይና ኩባንያ ባለቤትነት የተመዘገበው ይህ የቪዲዮ መጋሪያ በብዛት እድሜያቸው ከ20 ዓመት በታች በሆኑ ወጣቶች ዘንድ ይወደዳል። ይህ በእንዲህ እያለ የአሜሪካ ግዙፉ ኩባንያ ማይክሮሶፍት ቲክቶክን ለመግዛት እየተነጋገረ እንደሆነ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ተሰምቷል። የማይክሮሶፍት አለቃ ሳትያ ናዴላ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር በጉዳዮ ዙርያ ትናንትና እሑድ መወያየታቸውን ኩባንያው ይፋ አድርጓል። ቻይናና አሜሪካ ከቅርብ ወራት ወዲህ ከረር ወዳለ የንግድና የዲፕሎማሲ ጦርነት ውስጥ መግባታቸው ይታወሳል።
news-53561118
https://www.bbc.com/amharic/news-53561118
የእሁዱ ስብሰባና በኦነግ አመራር አባላት መካከል የተፈጠረው ተቃርኖ
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከመኖሪያ ቤታቸው እንዳይወጡ ተደርገዋል የሚለውን ዜና ተከትሎ፤ በግንባሩ ጽሕፈት ቤት የተካሄደው የድርጅቱ አመራሮች ስብሰባ “ሊቀ መንበሩን ለማንሳት ነው” የሚል መረጃ እንዲሰራጭ ምክንያት ሆኖ ነበር።
አቶ አራርሶ ቢቂላ ከዚህ በተጨማሪም የግንባሩ አመራር ለሁለት የመከፈሉ ጉዳይ መነጋገሪያ ከመሆኑ በተጨማሪ አቶ ዳውድ ኢብሳ ከሊቀ መንበርነታቸው ተነስተው በአቶ አራርሶ ቢቂላ እንዲተኩ ተደርጓል የሚል ወሬም በስፋት ሲነገር ቆይቷል። ይሁን እንጂ አቶ ዳውድ ኢብሳን እንዲተኩ ተመርጠዋል የተባሉት አቶ አራርሶ ቢቂላ ዜናው ፍጽም ሐሰት ነው ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ አራርሶ ትናንት በኦነግ ጽሕፈት ቤት የተካሄደው ምርጫ የሊቀ መንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ እውቅና የነበረው መሆኑን በመናገር አሁንም የድርጅቱ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ መሆናቸውን ገልጸዋል። አቶ አራርሶ ስለ ስብሰባው እንደተናገሩት፤ በዋና አጀንዳነት “ሕዝቡ ምን አይነት ሁኔታ ውስጥ ይገኛል? ድርጅታችንስ ምን ድረጃ ላይ ነው? በተለይ ደግሞ ወደ አገር ከገባን በኋላ ምን አገኝን፣ ምን አጣን? የሚለውን ገምግመናል” በማለት ለቢቢሲ አብራርተዋል። በተጨማሪም በአሁኑ ጊዜ በርካታ የግንባሩ አባላት እና አመራሮች መታሰራቸውን በተመለከተ የስብሰባው ተሳታፊዎች መወያየታቸውን አመልክተው “በዚህም ጉዳይ አንድ ሃሳብ ይዘን ተለያይተናል” ብለዋል። ነገር ግን የግንባሩ ሊቀ መንበር በከተማው ውስጥ እያሉ፣ በሚመሩት ድርጅት ስብሰባ ላይ ሳይገኙ ውይይቱን ስለማድረጋቸውና አቶ ዳውድ ስለስብሰባው የሚያውቁት ነገር ስለመኖሩ ከቢቢሲ ለተጠየቁት ጥያቄ አቶ አራርሶ መልስ ሰጥተዋል። “አቶ ዳውድ የተለየ ጉዳይ ስለገጠማቸው እየተንቀሳቀሱ የዕለተ ከዕለት ሥራቸውን ማከናወን አልቻሉም። ስለዚህም ስብሰባችን ላይ መገኘት አልቻሉም” ብለው፤ ይሁን እንጂ ስለ ጉዳዩ ከአቶ ዳውድ ጋር ተነጋግረውበት እንደነበር ገልጸዋል። ጨምረውም፤ ስብሰባው እንዲካሄድ የሊቀ መንበሩን ይሁንታ እንዳገኙ በመጥቀስ “ውይይታችንን ሳንጨርስ ኔትዎርክ ተቋርጦ ነበር። ነገር ግን የድርጅቱ ከፍተኛ አመራር [ጉሚ ሰባ] ተሰብስቦ እንዲመክር ተስማምተን ነበር” ብለዋል። ዋናው ሊቀ መንበር ባለመገኘታቸው በምክትሉ የሚመራ አይነት ሰብሰባ መካሄዱን በመግለጽ፤ በዚህም ሊቀ መንበሩን ጨምሮ “ምንም አይነት ሹም ሽር አልተካሄደም” ሲሉ አስረግጠው ተናግረዋል። አቶ አራርሶ ቢቂላ ይህንን ይበሉ እንጂ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ገዳ ኦልጅራ (ዶ/ር) ግን የተካሄደውን ስብሰባ በተመለከተ የተለየ ሃሳብ እንዳላቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ትናንት በአቶ አራርሶ ቢቂላ የተመራው ሰብሰባ የድርጅቱ እውቅና የለውም” በማለት ስብሰባው በግንባሩም ሆነ በሊቀ መንበሩ የማይታወቅ መሆኑን ለቢቢሲ ገልጸዋል። አቶ አራርሶ፤ ከአቶ ዳውድ ስብሰባ ለማካሄድ ፍቃድ እንደተሰጣቸው ተናግረው ስብሰባ ሲጠሩ፤ ገዳ (ዶ/ር) ወደ አቶ ዳውድ እንደደወሉና፤ አቶ ዳውድ ስለ ስብሰባው መረጃ እንዳልደረሳቸው እንደገለጹላቸው ተናግረዋል። ያለ ድርጅቱ ሊቀ መንበር እውቅና ስብሰባ ማካሄድ ተገቢ አይደለም ብለው ለስብሰባ የሄዱ ሰዎችን እንደከለከሉ ገልጸው፤ “ሲከለከሉ የታጠቁ የመንግሥት አካላትን ይዘው መጥተው፣ በጉልበት ገብተው ነው ስብሰባቸውን ያካሄዱት። ስብሰባው ሕጋዊ አልነበረም” ብለዋል። ገዳ (ዶ/ር) አያይዘውም ስብሰባው ላይ የተነሱ አጀንዳዎችን እንደማያውቁ ተናግረዋል። በስብሰባው ሹም ሽር ተካሂዶ፤ በአቶ ዳውድ ምትክ አቶ አራርሶ ሊቀ መንበር ሆነዋል የሚል ወሬ እንደተናፈሰ ጠቅሰን፤ እውነት ስለመሆኑ ሲጠየቁም እሳቸውም ተጨባጭ መረጃ እንዳልደረሳቸው አስረግጠው፤ “ከወሬ ያለፈ አይመስለኝም። ለዚያ የሚያበቃ ስብሰባ አይደለም” ብለው ምላሽ ሰጥተዋል። ቢቢሲ ካናገራቸው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራር አባላት በተጨማሪ ለተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ስለተፈጠረው ነገር የሚሰጡት ማብራሪያ እርስ በርሱ የሚቃረን ሲሆን ግለሰቦች ከሚሰጡት ምላሽ ውጪ እስካሁን ከግንባሩ ተሰጠ መግለጫ የለም። ሊቀመንበሩ ከአቶ ዳውድ ኢብሳ ከመኖሪያቸው መውጣት እንዳልቻሉ እንዲሁም የስልክ ግንኙነት ስለሌላቸው በድርጅቱ ውስጥ እተካሄደ ስላለው ነገር ቁርጥ ያለ ነገር ለመስማት አልተቻለም።
news-52212411
https://www.bbc.com/amharic/news-52212411
ኢዘዲን ካሚል፡ ኮሮናቫይረስ ለመቆጣጠር የፈጠራ ሥራዎቹን ያበረከተው ወጣት
ኢዘዲን ካሚል ይባላል። የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ነው። እስካሁን ከትምህርት ሰዓት ውጭ 30 የሚሆኑ የፈጠራ ሥራዎችን ጨምሮ 7 የሚሆኑ የአንድሮይድ መተግበሪያዎችንም እንደሰራ ይናገራል።
ከፈጠራ ሥራዎቹ ውስጥ ለ13ቱ የፈጠራ ሥራዎቹ ከ'ሴቭ አይዲያስ ኢንተርናሽናል' የባለቤትነት መብት እንዳገኘ ገልፆልናል። የኮሮናቫይረስ ኢትዮጵያ መግባቱ ከተረጋገጠ በኋላ ደግሞ ከጓደኛው ጋር በመሆን ቫይረሱን ለመከላከል የሚረዱ ሁለት የፈጠራ ሥራዎችን ሰርቷል። ከእጅ ንክኪ ነፃ የሆነ የእጅ መታጠቢያ የእጅ መታጠቢያው ሙሉ በሙሉ ከእጅ ንክኪ የፀዳ ሲሆን፤ በተገጠመለት ሴንሰር የሰዎችን እንቅስቃሴ በመረዳት ያለ ንክኪ ፈሳሽ ሳሙና ጨምቆ በመስጠት ውሃውን ከፍቶ ያስታጥባል። መታጠቢያው መብራት በሚኖርበት ጊዜ በዚህም መልክ መጠቀም ያስችላል። የኤሌክትሪክ ኃይል ከተቋረጠ ወይም ከሌለስ? ኢዘድን ለዚህ መላ ዘይዷል። ኢዘዲን እንደሚለው መብራት ሁልጊዜ አስተማማኝ ባለመሆኑና መታጠቢያውን ያለ ኤሌክትሪክ ኃይል መንገድ ላይ ማስቀመጥ ከተፈለገ ሌላ አማራጭ ዘዴ መጠቀሙን ይገልጻል። በእግር የሚረገጥ ፔዳል በመግጠም ከንክኪ በፀዳ መልኩ እጅን መታጠብ ያስችላል። ይህ የፈጠራ ሥራውም በማህበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት እንዳገኘለት ይናገራል። እስካሁን 35 የሚሆኑ ከእጅ ንክኪ ነፃ የእጅ መታጠበያዎች በወልቂጤ የተለያዩ ቦታዎች አገልግሎት እየሰጡ ነው። መጀመሪያ ሥራውን ሲጀምሩ ወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ድጋፍ እንዳደረገላቸው የሚገልፀው ኢዘዲን፤ ጠቃሚ መሆኑ ከታመነበት በኋላ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲና የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በጋራ በመሆን 35 የሚሆኑ እጅ መታጠቢያዎችን አዛጋጅተዋል። እነዚህን የእጅ መታጠቢያዎችም በወልቂጤ ከተማና በገብሪ ክፍለ ከተማ በተለይ ሰው የሚበዛባቸው፤ የባንክና ሆስፒታል መግቢያና መውጫ በሮች እንዲሁም ጤና ጣቢያዎች አካባቢ በማስቀመጥ ሰዎች እንዲገለገሉበት ተደርጓል። የተለያዩ ግለሰቦችም የእጅ መታጠቢያው እንዲሰራላቸው ትዕዛዝ እንደሰጡ ኢዘዲን ገልፆልናል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ወጣት ኢዘዲን ካሚል ከሠራቸው የፈጠራ ሥራዎቹ አንዱ ከእጅ ንክኪ ነፃ የሆነ የእጅ መታጠቢያ ነው። መካኒካል ቬንትሌር ወረርሽኙን ተከትሎ እያጋጠመ ያለውን የቬንትሌተር እጥረት ችግር ለመፍታትም ሁለት ነገሮችን አስቦ ነበር። አንደኛው ሜዴትሮኒክ የሚባል ህክምና እቃዎች የሚያመርት ካምፓኒ የለቀቀውን PB560 የተባለ ሞዴል ቬንትሌተር በመቅዳት በአገር ውስጥ ማምረት መቻል ሲሆን ሌላኛው የራሱን ፈጠራ የሆነ መካኒካል ቬንትሌተር መስራት ነው። በመሆኑም በአገር ውስጥ በሚገኙ ቁሳቁሶች ሜካኒካል ቬንትሌተር መስራቱን ነግሮናል። የህክምና እቃው ውድ መሆኑና አሁን ባለው ሁኔታ እጥረት መኖሩ ለፈጠራ ሥራው እንዳነሳሳው ይናገራል። በመሆኑ በቀላል ዋጋ በብዛት ቢመረት መንግሥት በሃገሪቷ በብዛት ተሰራጭቶ ጥቅም ላይ መዋል ይችላል ብሏል። "እነዚህ እቃዎች ከውጭ ነው የሚገቡት" የሚለው ኢዘዲን እነርሱም ጋር የቫይረሱ ወረርሽኝ ከፍተኛ በመሆኑ እጥረት ስለሚያጋጥም አገር ውስጥ በሚገኙ እቃዎች ማምረት እንደሚቻል ለማሳየት የፈጠራ ሥራውን እንደሰራው ገልጾልናል። • የ27 አስደናቂ ፈጠራዎች ባለቤት የ17 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ
news-55513637
https://www.bbc.com/amharic/news-55513637
በአንድ ጊዜ በሁለት ዲግሪ በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቀው ሙከረም
ሙከረም አሊ ኑር ይባላል። በኮምፒውተር ሳይንስ እና ኢንጂነሪንግ እንዲሁም በኤሌክትሮኒክስ እና ኮሙኒኬሽን ኢንጂነሪንግ ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተመርቋል።
3.93 በማምጣት የግቢውን ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቦ ዋንጫ ተሸልሟል። ሙከሪም በአንድ ጊዜ በሁለት ዲግሪ ነው የተመረቀው። በዩኒቨርስቲው አንድ ተማሪ የተሻለ ውጤት ካለው ሁለት ዲግሪዎችን በተመሳሳይ ጊዜ መማር ይችላል። 3.5 እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች ሁለተኛ የትምህርት ክፍል በመምረጥ መማር ይችላሉ። ሁለት ዲግሪ ሲወሰድ ትምህርቶቹ ተመሳሳይ እንዲሆኑ ይጠበቃል። ይህ ማለት ደግሞ የሚወሰደው ትምህርት ብዛት ስለሚቀንስ በአምስት ዓመት ውስጥ መጨረስ ይቻላል ማለት ነው። ከሙከሪም ጋር በሁለት ዲግሪ የተመረቁት 33 ተማሪዎች ናቸው። የመጀመሪያው ቢ... በኮምፒውተር ሳይንስ እና ኢንጂነሪንግ 170 የትምህርት ሰዓት (ክሬዲት አወር)፣ በኤሌክትሮኒክስ እና ኮሙኒኬሽን ኢንጂነሪንግ 23 የትምህርት ሰዓት (ክሬዲት አወር) ወስዶ ትምህርቶቹን በአምስት ዓመት ውስጥ እንዳጠናቀቀ ይናገራል። ሙከሪም አብዛኛውን ትምህር 'ኤ' አግኝቶ ነው የተመረቀው። "አንድ ሁለት ቢ ይኖራል። ሌላው ኤ እና ኤ ማይነስ ናቸው" ይላል። ኤ ማግኘት የለመደው ተመራቂው ቢ ሲያገኝ እንደሚያዝን ይናገራል። ለመጀመሪያ ጊዜ ቢ ያገኘበትን ጊዜም እንዲህ ያስታውሳል. . . "የመጀመሪያውን ቢ ያገኘሁት የመጀመሪያ ዓመት፣ ሁለተኛው መንፈቀ ዓመት ላይ ነበር። ከዚያ ትምህርት ውጭ የሁሉንም ውጤት አይቼ ነበር። ሁሉም ኤ እና ኤ ቻርጅ ነበሩ። እና የቀረችዋ አንድ ኮርስ ኤ ብትመጣ ኖሮ 4 ነበር የማመጣው። እሷን በጣም ጠብቄ ነበር። በእርግጥ ጫናዎች ስለበዙብኝ እንዳልሰራሁ ገብቶኝ ከኤ በታችም ጠብቄ ነበር። ቢ ሳመጣ በጣም ነው ውስጤ የተነካው። ያዘንኩበት ጊዜ ነው። ወደፊት እንደዚያ አይነት ነገሮች እንዳይደገሙ የተሻለ ለመሥራት ነበር ያቀድኩት።" ሁሌም ወደ ፈተና ከመግባቱ በፊት በጎ ነገር እንደሚያስብ ይናገራል። "ብዙ ጊዜ ነገሮችን የማቅለል ባህሉና ልምዱ አለኝ" የሚለው ሙከረም፤ ቀለል አድጎ የማንበብና ፈተናውን እንደሚሠራ እርግጠኛ የመሆን ልማድ እንዳዳበረ ያስረዳል። የሚያነበውና የሚያውቀው ሐሳብ ላይ ያተኩራል። ፈተና ከመጀመሩ በፊት ውጤቱ ጥሩ እንደሚሆን እርግጠኛ ሆኖ ይገባል። "ሳልገባም፣ ስገባም፣ ከወጣሁም በኋላ የተሻለ ውጤት እንደሚመጣ እጠብቃለሁ" የሚለው ተመራቂው ፈተና ላይ ሳለ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ የተሻለ ውጤትን ይጠብቃል። ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገቡ የዋንጫ፣ ሜዳሊያ እና ላፕቶፕ ሽልማቶች አግኝቷል። ከሁሉም በላይ ግን ከሰዎች ያገኘው ከበሬታ ያስደስተዋል። "የሰውን ምላሽ ሳይ ትልቅ ውጤት እንዳስመዘገብኩ ነው እየተሰማኝ"ያለው ሙከሪም፣ "ከሰዎች የምታገኘው ሞራል በጣም ደስ የሚል ነገር ነው" ሲል ያክላል። "ዩኒቨርሲቲው የማስተርስ ሙሉ ስኮላርስፕም ሰጥቶናል።" ከተመረቀ በኋላ ዋንጫውን ይዞ ኮምፒውተሩን ለመውሰድ ወደ ቤተ ሙከራ አምርቶ እንደነበር ያስታውሳል። ታዲያ ቤተሰቦቹ ሲደውሉት "ላብ ነኝ" ብሎ ሲመልስላቸው ለጥናት የሄደ መስሏቸው "በምርቃቱ ቀን ያጠናል" ብለው አስበው እንደነበርም አውግቶናል። "ላይብረሪ ብዙም አልጠቀምም" ሙከሪም ብዙም ቤተ መጻሕፍት ውስጥ ማጥናት አያዘወትርም። እንዲያውም ትኩረቱ የቡድን የቤት ሥራዎች ላይ ነው። "ዶርም ከጓደኞቼ ጋር እየተረዳዳሁ። ሁላችንም የየራሳችን አቅም አለን። እኔ ያለኝን አቅም ለሌሎች አሳያለሁ፤ አስረዳለሁ። እነሱም ደግሞ ከእኔ የተሻለ አቅም ስላላቸው ባላቸው አቅም እኔን ያስረዱኛል። ይህ የግሩፕ ጥናት ከአንደኛ ዓመት ጀምሮ እስከምንመረቅበት ድረስ ስናደርግ የነበረው ነው።" ከክፍል ከወጡ በኋላ ከማጥናት ይልቅ ክፍል ውስጥ የማተኮር ልማድ ያለው ሙከሪም፤ "ክፍል ውስጥ ያልተረዳሁትን ነገሮች እዚያው ነው ጨርሼ የምሄደው" ይላል። እሱና ጓደኞቹ ከእነርሱ በታች ያሉ ተማሪዎችን ያስተምራሉ። ይህም የበለጠ እንዲያነብ አግዞታል። ከዩኒቨርስቲው ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡን ተከትሎ እንቅጠርህ ያሉት ድርጅቶች እንደነበሩና እሱ ግን በትምህርቱ የመግፋት ሐሳብ እንዳለው ይናገራል። በዩኒቨርሲቲው የፌስቡክ ገጽ ላይ ውጤቱን አይተው ያደነቁት፣ ያበረታቱት እንዳሉም ያስታውሳል። ቀጣይ እቅዱ በአገር ውስጥና በውጪም ትምህርቱን ገፍቶበት በሙያው ማኅበረሰቡን ማገልገል ነው። "ኢትዮጵያውያኖች እንደ ማኅበረሰብ ብዙ ችግር አሉብን። እነዚያን ነገሮች ባለኝ እውቀት መፍታት እና ማኅበረሰቡን የመጥቀም ትልቅ ፍላጎት አለኝ። ግን እሱን ለማድረግ እራሴ ጠንካራ እውቀት ሊኖረኝ ይገባል በሚል አሁን ትምህርቱ ላይ ነው ያተኮርኩት። ከዚያ በኋላ ግን እነዛን ተጠቅሜ የመሥራት ሃሳቡ አለኝ።" ማኅበረሰቡን የሚጠቅሙ ሶፍትዌሮች መሥራት ህልሙ ነው። በኮምፒውተር ሳይንስ እና ኢንጂነሪንግ፣ በሰው ሠራሽ ክህሎት (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ)፣ በማሽን ለርኒንግ እና ዳታ ሴንስ ዘርፎች ብዙ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ያምናል። በአይሲቲ ዘርፍ ላለፉት አምስት ዓመታት በውድድር ሲሳተፍ እንደነበረና ይህንን በአዳማ ዩኒቨርስቲ እንደጀመረው ይናገራል። ወደ ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች የማስፋፋት እቅድም አለው። "አባቴ ነጋዴ እንድሆን ይፈልግ ነበር" የሙከሪም አባት ባለ ሱቅ ናቸው። እስከ 12ኛ ክፍል ሲማር ከትምህርት ሰዓት ውጪ ሱቅ ውስጥ ይሠራ ነበር። አባቱ ንግድ ላይ እንዲያተኩር ይፈልጉ እንደነበርም ይናገራል። "ያደግኩት ንግድ ላይ ነው። አባቴ ሱቅ ውስጥ እንድሠራ ይፈልግ ነበር። እስከ ስምንተኛና ዘጠነኛ ክፍል ድረስ ያሉትን ውጤቶች ሲያይ ግን ወደ ትምህርት ብታደላ የሚል ነገር አመጣ" ሲል ያስታውሳል። ቤተሰቡ የዩኒቨርስቲ ውጤቱን ሲያዩ ያሉትንም እንዲህ ያስታውሳል. . . "ደስታቸውን መግለጽ ነው ያቃታቸው። ያኔ ያሰብነው ነገር [ንግዱ] ትክክል እንዳልነበረ ነው ያሰቡት። አሁን ደስተኛ ናቸው። ቤተሰቦቼ የነበረውን ብዙ ጫና ተቋቁሜ በማለፌ ደስተኛ ናቸው።" "ቤተሰብን የመርዳት እና የእነርሱን ሃቅ የመጠበቅ ግዴታ ይኖርብኛል። ከሥራዬና ከትምህርቴ ጋር የማይጋጭብኝ ከሆነ ለማገዝ ፍቃደኛ ነኝ" የሚለው ተመራቂው፤ ከዚህ በኋላ ምናልባትም ከትምህርት ለእረፍት ወደቤት ሲሄድ እንደ ድሮው ቤተሰቦቹን በሱቅ ሥራው ያግዝ ይሆናል። በእርግጥ ከቤተሰቡ በተጨማሪ ሌሎችንም የሚያግዝ ሰው ነው። ዩኒቨርስቲ ከገባበት ጊዜ አንስቶ ለአምስት ዓመታት ተማሪዎችን አስተምሯል። "ያለኝን እውቀትና ልምድ ለሌሎች የማስተላለፍ ግዴታ አለብኝ ብዬ ስለማስብ ሁሌም አስተምር ነበር። በዚያ የተነሳ ከብዙ ሰዎች ጋር ግንኙነት ፈጥሬያለሁ። በተማሪዎች ዘንድ ትልቅ ተወዳጅነት ነው ያለኝ። ሁሉም ሰው እውቀቱን ለሌሎች ማካፈል አለበት ብዬ ነው የማስበው" ሲልም ምክሩን ያካፍላል። አብዛኛው ተመራቂ በቀላሉ ሥራ እንደማያገኝ ከግምት በማስገባትም፤ ተመራቂዎች መቀጠርን ብቻ ግብ ከማድረግ የራሳቸውን ሥራ መፍጠር አለባቸው ይላል። "ግዴታ ቅጥር መጠበቅ የለብንም። ባለኝ እውቀት ምን መሥራት እችላለሁ? ማኅበረሰቡ ላይ ምን ችግር አለ? ምን እድልስ አለ? የሚለውን በደንብ ካየን ያንን መፍታትና ወደ ሥራ መቀየር እንችላለን።"
news-46991059
https://www.bbc.com/amharic/news-46991059
በረከት ስምኦን ከየት ተነስተው እዚህ ደረሱ
አቶ በረከት ስምኦን ወታደራዊውን መንግሥት ከሥልጣን ያስወገደው የትጥቅ ትግል ውስጥ በተለያዩ ቡድኖች ውስጥ ከተሳተፉ አንጋፋ ታጋዮች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።
ከትጥቅ ትግሉ ማብቃት በኋላ በተለያዩ የፓርቲውና የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊነቶች ላይ ያገለገሉ ሲሆን ጎልተው መውጣት የጀመሩት ግን በ1993 የኢህአዴግ ዋነኛ አካል በነበረው ህወሓት ውስጥ የተከሰተውን ክፍፍል ተከትሎ በበላይነት የወጡት የወቅቱ የድርጅቱ ሊቀ መንበርን አቶ መለስ ዜናዊን ደግፈው ከቆሙ በኋላ ነበር። በወቅቱ ቁልፍ በፓርቲውና በመንግሥት ኃላፊነቶች ላይ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው አንጋፋ የህወሓት አመራር አባላት ይዘውት ከነበሩበት ቦታ ገለል ሲደረጉ ክፍተቱን ለመሸፈን ወደፊት ከመጡትና የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የቅርብ ሰው ለመሆን ከቻሉት ሰዎች መካከል አቶ በረከት ቀዳሚው ናቸው። • አቶ በረከት ስምኦን ሥልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ አቶ በረከት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀጥለው በፓርቲውና በመንግሥት ጉዳዮች ላይ በተለያዩ መድረኮች ላይ ወጥተው የሚናገሩ ሁለተኛው ሰው ናቸው። ሃሳባቸውን አደራጅተው በመናገርና የፓርቲውን የርዕዮተ ዓለም የመንግሥትን ፖሊሲዎች በመተንተን በኩልም ከሌሎች ባለሥልጣናት ጎልተው የሚታዩ መሆናቸውም ይነገርላቸዋል። ለፓርቲው ቅርበት ያላቸው ሰዎች እንደሚናገሩትም የኢህአዴግ የርዕዮተ ዓለም ልሣን በሆነችው "አዲስ ራዕይ" መጽሔት ላይ በብዕር ስም ከሚጽፉት ከአቶ መለስ ዜናዊ ቀጥለው ወቅታዊና ፖለቲካዊ ትንታኔዎችን ከሚያዘጋጁ ጥቂት ሰዎች መካከል አቶ በረከት አንዱ ናቸው። በ1997 የተካሄደውና ለበርካታ ሰዎች ሕይወት ማለፍና ሃገሪቱን ወደ ከባድ ቀውስ አድርሷት በነበርው ምርጫ ወቅት አቶ በረከት ዋነኛው የኢህአዴግ ፊት ነበሩ። በቅድመ ምርጫ ወቅት በተካሄዱ ክርክሮች ላይ ከሌሎቹ የፓርቲው ተወካዮች በተለየ የኢህአዴግን ፖሊሲዎች ይዘው ሲከራከሩ እንደነበር ይታወሳል። ከዚያም በኋላ በተከሰቱት አወዛጋቢ ጉዳዮች ዙሪያ በሁሉም መድረኮች ላይ ለማለት በሚያስደፍር መልኩ በረከት ከፊት ቀዳሚ ነበሩ። • በደብረማርቆስ 'ባለስልጣኑ አርፈውበታል' የተባለው ሆቴል ጥቃት ደረሰበት አቶ በረከት በ1997 ምርጫ ሰሜን ወሎ ቡግና ውስጥ ፓርቲያቸውን ወክለው የተወዳደሩ ሲሆን በቀዳሚው የምርጫ ውጤት በተቃዋሚ ተፎካካሪያቸው መሸነፋቸው ተነግሮ ቢሆንም ፓርቲያቸው ያቀረበውን ቅሬታ ተከትሎ በተደረገው የድጋሚ ምርጫ ወደ ምክር ቤት ለመግባት ችለዋል። ድርጅታቸውን ኢህአዴግንና እርሳቸውን ለሚተቹና ለሚቃወሙ ሰዎች ትዕግስት እንደሌላቸው የሚነገርላቸው አቶ በረከት በተለይ ጋዜጠኞችን ቢሯቸው ድረስ ጠርተው እንደሚያስጠነቅቁና ጠንከር ያሉ ቃላትን ይሰነዝሩ እንደነበር ችግሩ የደረሰባቸው ይናገራሉ። አንዳንዶች ደግሞ አቶ በረከት በሃገሪቱ የነፃ ፕሬስ እንቅስቃሴ እንዲዳከምና ለጋዜጠኞች መታሰርና ከሃገር መሰደድ ቁልፍ ሚና እንደነበራቸው በተለያዩ አጋጣሚዎች ስማቸውን ሲያነሱ ቆይተዋል። አቶ በረከት ማናቸው? አቶ በረከት ስምኦን ጎንደር ውስጥ ነዋሪ ከነበሩ ከኤርትራዊያን ቤተሰቦቻቸው ጎንደር ውስጥ ተወልደው እንዳደጉ ይነገራል። ቤተሰቦቻቸው ያወጡላቸው ስም መብራህቱ ሲሆን የአባታቸው ስም ደግሞ ገብረሕይወት እንደሆነ በቅርብ የሚያውቋቸው ሰዎች ይናገራሉ። በቀዳሚነት የታላቅ ወንድማቸውን ፈለግ በመከተል የኢህአፓ አባል ሆነው ወደ ትግሉ ከገቡ በኋላ የስም ለውጥ እንዳደረጉም እነዚሁ ሰዎች ያስታውሳሉ። ስማቸውን ለምን እንደለወጡ የሚታወቅ ነገር ባይኖርም የሌላ ታጋይ ስም እንደወሰዱ ግን ይነገራል። • አቶ በረከት ስምኦን ከብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት ታገዱ ይህም በረከት ስምኦን የሚባል የኢህአፓ ታጋይ እንደነበርና በትግሉ ወቅት ባልታወቀ ምክንያት ከትግሉ ሜዳ ድንገት በመሰወሩ በርካታ የኢህአፓ አባላት የተገደለ መስሏቸው ነበር። በነበረው ልምድም ይህን ታጋይ ለማስታወስ መብራህቱ ገብረህይወት በረከት ስምኦን የሚለውን ሙሉ ስም እንደወሰደ ይነገራል። አቶ በረከት ከየት ወደየት? አቶ በረከት ስምኦን ወደ ትግል የገቡት በመጀመሪያ የኢህአፓ አባል ሆነው ሲሆን ድርጅቱ በዋናነት ከደርግና ከሌሎች ተቀናቃኝ ድርጅቶች በገጠመው ጥቃት በተዳከመበት ወቅት በውስጡ የተፈጠረውን መከፋፈል ተከትሎ ከሌሎች ጓዶቻቸው ጋር ድርጅቱን ጥለው ወጡ። ከኢህአፓ የተለዩት አቶ በረከት ከትግሉ ጠቅልለው ግን አልወጡም ከጓዶቻቸው ጋር ብዙም ያልቆየውን ኢትዮጵያ ኮሚኒስት ፓርቲ (ኢኮፓ) አቋቁመው የነበረ ሲሆን ቀጥለውም አሁን የአማራ ክልል ገዢ ፓርቲ የሆነው አዴፓ መነሻ የሆነውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄን (ኢህዴን) በመመሥረት ከህወሓት ጋር ግንባር ፈጥረው ደርግን ታግለዋል። • "...ባለሐብቶችን ለቅመህ እሰር ብሎኝ ነበር" አቶ መላኩ ፈንታ ከደርግ ውድቀት በኋላ የብሔር ድርጅቶች ጎልተው በመውጣታቸው ኢህዴን የአማራ ሕዝብ ውክልናን ለመውሰድና ተቀባይነትን ለማግኘት እራሱን የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኢህዴን) በሚል ስያሜ እራሱን መልሶ አዋቅሮ ለረዥም ዓመታት የኢህአዴግ አባል ፓርቲ በመሆን ቆይቷል። አቶ በረከት ስምኦንም በብአዴን ውስጥ ቁልፍ ሚና ከነበራቸው ሰዎች መካከል ቀዳሚው በመሆን ቆይተዋል። በኢህአዴግ ውስጥም የብአዴን ዋነኛ ሰው በመሆን አድራጊ ፈጣሪ እንደነበሩ ይነገራል። አቶ በረከት የነበሩባቸው ቁልፍ የመንግሥት ኃላፊነቶች የአቶ በረከትና ፓርቲያቸው አቶ በረከት ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ በስፋት ይታዩበት ከነበረው የፖለቲካ መድረክ የራቁ ሲሆን በፖሊሲ አማካሪነትና በጥናትና ምርምር ከማዕከል ውስጥ ተገድበው ቆይተዋል። በ2010 ዓ.ም መጀመሪያ ወራት ውስጥም ሳይታሰብ ድንገት ምክንያታቸውን ባልገለጹበት ሁኔታ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ መልቀቂያ ማስገባታቸው ሲነገር ተመልሰው የመነጋገሪያ ርዕስ ለመሆን ችለው ነበር። ነገር ግን ከጥቂት ጊዜ በኋላ ያቀረቡትን መልቀቂያ በማንሳት ወደ ሥራ መመለሳቸውን አሳውቀው ነበር። • ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር የፍቅር ግንኙነት አለዎት? በሃገሪቱ ለዓመታት የዘለቀው ሕዝባዊ ተቃውሞ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት ጊዜ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሥልጣን መልቀቅ ተከትሎ በፓርቲያቸው ኢህአዴግ ውስጥ የተካሄደው ለውጥ በእናት ድርጅታቸው ብአዴን ውስጥም ለውጥን አምጥቷል። ይህ ለውጥ ግን ለአቶ በረከት አዎንታዊ ነገርን ይዞ የመጣ አልነበረም። ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ላይ የድርጅታቸው ማዕከላዊ ኮሚቴ አመራር በነበሩበት የጥረት ኮርፖሬት ላይ ፈጸሙት ባለው ጥፋት ከብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት አግዷቸዋል። ብአዴንም በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ባካሄደው ጉባኤ ፓርቲውን በድጋሚ መልሶ በማዋቀር ለሁለተኛ ጊዜ የስም ለውጥ አድርጎ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) የሚል ስያሜን ያዘ። አቶ በረከትም ከፓርቲው ከታገዱ በኋላ እራሳቸውን ያግልሉ አሊያ ይባረሩ በይፋ ሳይገለጽ በለውጡ ሂደት ከፓርቲው ወደ ጎን ተገፍተው ቆይተዋል። በመጨረሻም ፈጸሙት ከተባለው ጥፋት ጋር በተያያዘ አዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኘው ቤታቸው ጥር 15/2011 ዓ.ም ተይዘው ከድርጅቱ አብረዋቸው ታግደው ከነበሩት አቶ ታደሰ ካሳ ጋር ወደ ባህርዳር ተወስደዋል።
news-46998428
https://www.bbc.com/amharic/news-46998428
"አቶ ጌታቸው አሰፋን በተመለከተ ከክልሉ ጋር እየሰራን ነው" ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዛሬ አርብ ጥር 17 ቀን ከሰዓት በኋላ በሰጠው መግለጫ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ እና ሌሎችም አካባቢዎች ተነስቶ ከነበረው ሁከት እና ብጥብጥ ጋር በተያያዘ ሳከናውነው የቆየሁትን ምርመራ አጠናቅቄያለሁ ብሏል።
• "አብዲ ሞሃመድ ኡመር ስልጣን ለመልቀቅ በተደጋጋሚ ጠይቀው ነበር" አዲሱ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት በፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የተደራጁ፣ ድንበር ተሻጋሪ እና አገራዊ ጉዳት የሚያደርሱ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ተመስገን ላጲሶ በበኩላቸው ለምርመራው መነሻ የሆነው ከሐምሌ 28 እስከ 30 2010 ዓ.ም የተፈፀሙ ወንጀሎች ቢሆኑም በምርመራው ሂደት አቶ አብዲ የክልሉ ፕሬዚዳንት በነበሩበት ጊዜ የተፈፀሙ ወንጀሎችን እንድንመረምር የሚያስችሉ ማስረጃዎችን አግኝተናል ብለዋል። የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ የሆኑት አቶ ዝናቡ ቱኑ ምርመራውን ፌዴራል ፖሊስ፣ የክልሉ ፖሊስና የመረጃ ደህንነት ጽሕፈት ቤት በጋራ ሲያከናወኑ መቆየታቸውን ገልፀዋል። ኃላፊው ምርመራው አምስት ወራት የፈጀው የክልሉ የቀድሞ ከፍተኛ መሪዎች ሁሉ የተሳተፉበት በመሆኑ ይህ ወንጀሉን ውስብስብ ማድረጉን አስረድተዋል። ከሶማሌ ብሔር ውጭ የሆኑ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ ያነጣጠረ ነበሩ ባሏቸው ጥቃቶች የተሳተፉ ናቸው የተባሉ 46 ተጠርጣሪዎችን ሕገ መንግሥትን ለመናድ በመሞከር፣ በማነሳሳት፣ በአስቃቂ ግድያና በአስገድዶ መድፈር ከሰናል ብለዋል ኃላፊው። • አዲሱ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ማን ናቸው? ይሁን እንጂ ከተከሳሾቹ መካከል በቁጥጥር ስር ውለው የሚገኙት ስድስት ብቻ ናቸው። ሌሎቹ በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ ተደብቀው እንደሚገኙ ገልፀዋል። አቶ ዝናቡ በቀድሞው የክልሉ መንግሥት በተደራጀ እና በተጠና መልኩ ዕቅድ ተይዞ እና አስፈላጊ የሰው ኃይልም ቀርቦ የተከናወኑ ናቸው ባሏቸው ጥቃቶች በርካታ የሰው ሕይወት ጠፍቷል፣ አሰቃቂ ግድያ ተፈፅሟል፣ ከዚህም ውስጥ በእሳት በማቃጠል፣ አንገት በመቅላት መግደል፣ እንዲሁም በህይወት እያሉ መቅበር ተከናውኗል ሲሉ ተናግረዋል። "የቀድሞው የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሃመድ ዑመርን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ኃላፊዎች መሳተፋቸውን ከምርመራ ሪፖርቱ ተረድተናል" ያሉት አቶ ዝናቡ ከፌዴራል የሚመጣ ኃይልን እንመክታለን በሚል የክልሉ ኃላፊዎች ያስተባብሩ እንደነበርም ገልፀዋል። የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ቃል አቀባይ ጨምረው እንደተናገሩት የ58 ሰዎች ህይወት የጠፋ ሲሆን 50 ሰዎች በጅምላ ተቀብረው ተገኝተዋል ብለዋል። እርሳቸው እንዳሉት አርባ ሁለቱ አንድ ላይ፣ ስምንቱ ደግሞ ሌላ ቦታ በጅምላ ተቀብረው ተገኝተዋል። በተጨማሪ ሌሎች 200 ሰዎች በጅምላ ተቀብረው ቢገኙም የእርሱ ምርመራ ገና አልተጠናቀቀም። በምርመራ ተደረሰበት በተባለው ግድያም የኦርቶዶክስ እምነት ካህናት እና ምዕመናን በቤተ ክርስትያን ግቢ ውስጥ ተገድለዋል፤ ተቀብረዋል ተብሏል። እንደ አቶ ዝናቡ 266 ሰዎች የአካል ጉዳት ሲደርስባቸው 10 ሴቶች ሄጎ በሚባለው ጥቃት አድራሽ ቡድን እና በክልሉ ልዩ ኃይል ተደፍረዋል፤ ይሁንና ይህ ቁጥር መደፈራቸውን የደበቁ ሴቶች የሚኖሩ በመሆኑ ከፍ ሊልም ይችላል ተብሏል። የተዘረፈ እና የተቃጠለ ንብረት ከ421 ሚሊዮን ብር በላይ ይሆናል ብለዋል አቶ ዝናቡ። •"በረከትና ታደሰ በሙስና መጠርጠራቸው አስደንቆኛል" አቶ ጌታቸው ረዳ በቅርቡ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ስለዋሉት አቶ በረከትና አቶ ታደሰን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ "ምርመራውን የሚያከናውነው የአማራ ክልል ዐቃቤ ሕግ ነው፤ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አይደለም፤ ስለዚህ የምንለው የለም" ብለዋል። አክለውም የቀድሞ የደህንነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋን በተመለከተም ካልተያዙ ሰዎች መካከል እንደሚገኙ አመልክተው፤ በመሆኑም ይህንን በተመለከተ ከክልሉ መንግሥት ጋር እየሰራን ነው፤ ለመያዝ አስፈላጊ ሒደቶች እየተከናወኑ እንደሆነ አስረድተዋል። ከጅግጅጋ ብጥብጥ ተጠርጣሪዎች መካከል ደግሞ የተወሰኑት ያለመከሰስ መብት ያላቸው በመሆኑ እርሱን በተመለከተም ከክልሉ ጋር እየሰሩ መሆናቸውን አክለው ተናግረዋል። አሁን ባለው የምርመራ ሂደት አቶ አህመድ ሽዴ ከተጠርጣሪዎች መካከል እንደማይገኙበትም ጠቁመዋል።
54024259
https://www.bbc.com/amharic/54024259
የብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ የክረምቱ ዝናብ አሁንም የጎርፍ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል አስጠነቀቀ
የብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ የክረምቱ ዝናብ አሁንም የጎርፍ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል አስጠነቀቀ።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ አየር ትንበያ ዋና ክፍል ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ጫሊ ደበሌ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የክረምት ዝናብ በቀጣዮች ቀናትም የጎርፍ አደጋ ሊያስከትል ስለሚችል አስፈላጊው ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ በአርሲና በምስራቅ ሸዋ ዞኖች ዘጠኝ ወረዳዎችና 42 ቀበሌዎች ወደ 20 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ላይ ጉዳት አድርሷል። በአፋር ክልል በሚገኙ 14 ወረዳዎች ደግሞ በአዋሽ ወንዝ ሙላት የተነሳ ከ120 ሺህ በላይ ሰዎች በጎርፍ ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን የክልሉ የአደጋ መከላከል ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ እና ምላሽ ኃላፊ አቶ ማሂ አሊ በተለይ ለቢቢሲ ገልጸዋል። አቶ ማሂ አክለውም ቢያንስ 72 ሺህ ሰዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን ተናግረዋል። በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ እስከ ዛሬ ድረስ 43 ሺህ 670 ሰዎች በጎርፍ ምክንያት መፈናቀላቸው ተገልጿል። በኢትዮጵያ እስከ ነሐሴ ወር አጋማሽ ድረስ የጣለው ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የተነሳ 170 ሺህ ያህል ነዋሪዎች ጉዳት ሲደርስባቸው 130 ሺህ ሰዎች ደግሞ ከቀያቸው መፈናቀላቸውን የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ምክትል ኮሚሽነር ለቢቢሲ መግለፃቸው ይታወሳል። የኦሮሚያ የአደጋ ስጋት ኮሚሽነር አባድር አብዳ በዚሁ ጉዳይ ላይ ጠይቀናቸው እንደተናገሩት የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ ሰዎችን ከቀያቸው ማፈናቀሉንና ንብረት ማውደሙን ገልፀው " የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ በመፍሰሱ በአርሲና በምስራቅ ዞኖች ዘጠኝ ወረዳዎች 42 ቀበሌዎች ውስጥ የሚኖሩ ከ19 ሺህ 900 በላይ ሰዎች ጎድቷል" ብለዋል። በተጨማሪም በቤቶችና በደረሱ ሰብል ማሳዎች ላይ ጎርፉ ጉዳት ማድረሱን ገልፀዋል። ለተጎዱት ሰዎች የምግብ እህል፣ አልባሳት ድጋፍ እየተሰጣቸው መሆኑን አንስተዋል። ከቀያቸው የተፈናቀሉት ሰዎች ሌላ ስፍራ እንደሰፈሩና ቀሪዎቹ ደግሞ ወደ ዘመዶቻቸው በመሄድ እንደተጠለሉ ተናግረዋል። "አንዳንድ ሰዎች በውሃ በተከበቡባቸው አካባቢዎች በትራክተርና፣ በጀልባ በመታገዝ አውጥተናል" ሲሉ ገልፀዋል። አሁን በውሃ ተከብቦ እየተቸገሩ ያሉ አለመኖራቸውን የደረሰው አደጋ ከአቅም በላይ እንዳልሆነ ተናግረዋል። በፈንታሌ ወረዳ መተሃራ ከተማ ከአንድ ቀበሌ የተፈናቀሉት ሰዎች የምግብ እህልና እንደ ምንጣፍ ያሉ ድጋፎች መሰጠት መጀመራቸውን አንስተዋል። ሐሙስ ዕለት ከ3000 ፍራሽ በላይ 71 ኩንታል እህል፣ 170 ኩንታል ሩዝ እና ወተት ጭምር መሰጠቱን ተናግረዋል። ሞልቶ የፈሰሰው ውሃ ከቅርብ ቀናት ወዲህ እየቀነሰ እንዳለ አንስተው በሚቀጥሉት ሳምንታትም በተከታታይ እየቀነሰ ከሄደ ሰዎች ወደ ቀያቸው ሊመለሱ ይችላሉ ብለዋል። አሁንም ጎርፉ በቀነሰበት አካባቢዎች ሰዎች ወደቀያቸው እየተመለሱ መሆኑን ይናገራሉ። መተሃራ የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ የተበጀለትን ቦይ በማፍረስ የምስራቅ ሸዋ ዞን ከተሞች ወደ ሆኑት ወንጂና መተሃራ ከተሞች ላይ ጉዳትን አድርሷል። በመተሃራ ከረቡዕ ማታ ጀምሮ በከተማዋ ካሉት ሁለት ቀበሌዎች አንዱ ሙሉ በሙሉ በጎርፍ ተጥለቅልቋል። የከተማዋ ከንቲባ አቶ ታደለ ድሪብሳ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በመተሃራ የተከሰተው የጎርፍ አደጋ በከተማዋ ታሪክ ታይቶ አይታወቅም ብለዋል። "የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ ወደ ከተማችን ፈስሷል ይህ ደግሞ በዚህ ከተማ ታሪክ ትልቅ አደጋ ነው። " የደረሰው አደጋ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ ሰዎች በህይወታቸው ከመውጣት ውጪ ንብረታቸውን ሙሉ በሙሉ ማውጣት ሳይችሉ በመቅረታቸው እንደወደመባቸው ተናግረዋል። ይህ ጎርፍ ሁለቱን ቀበሌዎች የሚያገናኘው መንገድ እንዲሁም ከምዕራብ ሃረርጌ ዞን ሃንቸር ወረዳ ጋር የሚያገናኘውን መንገድ ሙሉ በሙሉ በመቁረጡ ሰዎችን የማውጣት ስራ ላይ እንቅፋት ፈጥሯል ሲሉ ከንቲባው ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚህም የተነሳ ከተማዋ ለሁለት ተከፍላ እንደምትገኝም ይገልጻሉ። አሳይታ አፋምቦ ዱብቲ እና ቀጠና 3 የሚባሉ አካባቢዎች ደግሞ የተጎዱ ሰዎች ከፌደራል፣ ከክልል መንግሥት እንዲሁም ከእርዳታ ድርጅቶች የምግብ እህልና ቁሳቁሶች ድጋፍ እየቀረበላቸው መሆኑን ሰምተናል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ አየር ትንበያ ዋና ክፍል ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ጫሊ "አሁንም ቢሆን፣ በመካከለኛ ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ አገሪቱ ክፍሎች እንዲሁም ደጋማ የደቡብ ክፍል ከፍተኛ ዝናብ ይጠበቃል" ሲሉ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። የሚዘንበው ዝናብ አፈሩ ውሃ መጥገቡ በቀላሉ ጎርፍ ማስከተል ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ዳይሬክተሯ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ወ/ሮ ጫሊ እንዳሉት ከዚህ በፊትም በሰኔ ወር ውስጥ ከፍተኛ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል የብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ አስቀድሞ ማስጠንቀቁን ተናግረዋል። በግንቦት ወር ውስጥም ከትልቁ ፓስፊክ ውቅያኖስ በሚመጣው የንፋስ እንቅስቃሴ ላይ በመመስረት የአየሩን ሁናቴ መተንበይ የሚያስችል መረጃ ሲያሰባስቡ እንደቆዩ አብራርተዋል። በተጨማሪም አደጋው ባስከተለው አዋሽ ወንዝ አካባቢ የመኸር እና ክረምት ወቅቶች ጎርፍ የሚያስከትል ዝናብ እንደሚኖርና የአፈር እርጥበት እንደሚከሰት መተንበያቸውን ጠቅሰዋል። ዘንድሮም ክረምት ዝናብ የሚያገኙ አካባቢዎች በአንዳንድ ስፍራዎች መደበኛውን መጠን የሚያገኙ ቢሆንም አንዳንዶች ደግሞ ከሚጠበቀው በላይ ማግኘታቸውን ዳይሬክተሯ ገልፀዋል። በሐምሌ ወቅት ዝናብ በተከታታይ በመዝነቡ፣ በነሐሴ ወር ደግሞ ከፍተኛ ዝናብ መኖር ለተከሰተው ጎርፍ አስተዋጽኦ ማድረጉን አንስተዋል።
news-46556015
https://www.bbc.com/amharic/news-46556015
የህዳሴ ግድብ ከአራት ዓመታት በኋላ ኃይል ያመነጫል፡ ዋና ሥራ አስኪያጁ
ትናንት ረፋድ ላይ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ያለበትን ደረጃ አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሂዶ ነበረ።
በውይይቱ ላይ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ክንውኖች ላይ ማስተካከያ በማድረግ ፕሮጀክቱ ከአራት ዓመታት በኋላ እንደሚጠናቀቅም ተገልጿል። ፕሮጅክቱ ሲጀመር የግድቡ ግንባታ ተጠናቆ ኃይል ማመንጨት ይጀምራል የተባለበትን ቀነ ገደብ ካለፈ ዓመታት ተቆጥረዋል። ትናንት በተካሄደው ውይይት የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከግንባታው በፊት ጥልቅ ምርምርና ጥናት ባለመደረጉ ግንባታው ሊዘገይ እንደቻለ የገለፀ ሲሆን የግድቡ ግንባታ መዘግየት ሃገሪቱ በየዓመቱ 800 ሚሊየን ዶላር እንድታጣ አድርጓታል ተብሏል። በአጠቃላይ ግድቡ አሁን የሚገኝበት ደረጃም 65በመቶ መሆኑ ተነግሯል። የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩትን የኢንጅነር ስመኘው በቀለን ህልፈት ተከትሎ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው መሾማቸው ይታወሳል። • ስለአዲሱ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ጥቂት እንንገርዎ • ስለኢንጂነር ስመኘው አሟሟት እስካሁን ምን እናውቃለን? ዋና ሥራ አስኪያጁ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ያለበትን ደረጃ፣ የግድቡ ግንባታ የተስጓተተበትን ምክንያት እንዲሁም ወደ ፊት በግንባታው ላይ ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ ችግሮ ከቢቢሲ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። ለግድቡ መጓተት በዋነኝነት የሚቀመጠው ምክንያት ምንድን ነው? ዋና ሥራ አስኪያጁ ለግንባታው ስራ መጓተት ዋነኛው ምክንያቶች የኤሌክትሮ መካኒካል እና የብረታ ብረት ስራዎች በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ መጓዝ ስላልቻሉ ነው ይላሉ። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የእነዚህ ስራዎችን ውል ሰጥቶ የነበረው ለመከላከያ ብረታብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ፤ ሜቴክ መሆኑን ያስታወሱት ኢንጂነሩ፤ ፕሮጄክቱ መዘግየቱን ተከትሎ እንዲሁም በፕሮጀክቱ ዙሪያ የህዝቡ አመኔታ እየቀነሰ በመምጣቱ መንግሥት ከሜቴክ ጋር የነበረውን ውል ከአንድ ወር ገደማ በፊት ሙሉ በሙሉ በማቋረጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚታወቁ ተቋራጮች ጋር ውል ለመግባት ድርድር ላይ እንዳለና ሥራ የጀመሩ ተቋራጭችም እንዳሉ ገልፀዋል። ''ከዚህ በፊት በተቆራረጡ ውሎች ነበር ስራዎች ሲከናወኑ የነበሩት። አንዱ የአንዱን ሥራ ካዘገየ ኃላፊነት የሚወስድ አልነበረም። ስለዚህ ሥራውን በወጥነት ለማከናወን በዓለም አቀፍ ደረጃ በሃይድሮ ኤሌክትሪክ ሥራ ልምድ ካላቸው የጀርመን እና ፈረንሳይ ሃገራት ኩባንያዎች ጋር ድርድር እያደረግን ነው። የተወሰኑትም ወደ ሥራ ገብተዋል'' ይላሉ። ለተርባይን እና ጄኔሬተር ጂኢ አልስቶም ከተሰኘ የፈረንሳይ ኩባንያ ጋር እንዲሁም ለተርባይን-ጄኔሬተር አቅርቦት እና ተከላ ከጀርመኑ ቮኢዝ ኩባንያ ጋር ውል ለማሰር እየተነጋገሩ እንደሆነም ገልፀውልናል። • ለህዳሴ ግድብ ግንባታ መዘግየት ምን አይነት መፍትሔዎች እየተሰጡ ነው? ፈርሶ እንደ አዲስ የሚሰራ ወይም ማስተካከያ የሚደረግበት የግድቡ አካል አለ? ኢንጂነር ክፍሌ ፈርሶ እንደ አዲስ የሚገነባ የግድቡ አካል የለም ይበሉ እንጂ ውል የሚገቡት የውጪ ኩባንያ የተሰሩት ስራዎች ደረጃቸውን ስለመጠበቃቸውና ትክክል ስለመሆናቸው በቂ ፍተሻ ያደርጋሉ ይላሉ። ''የብረታ ብረት ስራ ውልን ሙሉ ለሙሉ ለውጪ ኩባንያ እንሰጣለን። የውጪ ኩባንያ ይህን ውል ሲቀበል ከዚያ በፊት የተሰሩ ስራዎች ጥራት እንዳላቸው የማረጋገጥ ኃላፊነትን ጭምር ነው አብሮ የሚወስደው" ብለዋል። ቀደም ሲል በሜቴክ ፋብሪካዎች የተሰሩ የውሃ መዝጊያ እና የውሃ ማስተላለፊያ አሸንዳዎች አሉ። በግድቡ ላይ የተተከሉም አሉ። እነዚህ በትክክል ተተክለዋል ወይ? በትክክል ተበይደዋል ወይ? ብሎ የማጣራት ግዴታ አለባቸው። የጎደለ ወይም ስህተት ያለበት ካለ ፈትሾ የማስተካከል እንጂ ፈርሶ እንደ አዲስ የሚገነባ ነገር የለም።'' ይላሉ ኢንጂነር ክፍሌ። ህዳሴ ግድብ ከአራት ዓመታት በኋላስ እንዴት ይጠናቀቃል? ዋና ሥራ አስኪያጁ እንደሚሉት ከሆነ የህዳሴው ግድብ ከጅምሩ ዋነኛ ችግሩ ''ተግባራዊ ሊሆን የሚችል የጊዜ ሰሌዳ አልነበረውም።'' ይህ ይሁን እንጂ እሳቸው ''ተጨባጭ ነው'' በሚሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ግድቡ ከአራት ዓመታት በኋላ ተጠናቆ ኃይል ማመንጨት እንደሚችል ባለ ሙሉ ተስፋ ናቸው። ''ይህ ፕሮጀክት የበጀት ችግር ገጥሞት አያውቅም። ወደፊትም አይገጥመውም። መንግሥት ቅድሚያ ሰጥቶ የሚያከናውነው ፕሮጀክት ነው።'' የሚሉት ዋና ሥራ አስኪያጁ፤ ለግድቡ መጠናቀቅ ወሳኝ የሚባሉ ስራዎች ቅድሚያ ተሰጥቷቸው መሰራት በመጀመራቸው ግድቡ በፍጥነት እና በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ይጠናቀቃል። በግድቡ ግንባታ ላይ ወደፊት ሊኖሩ የሚችሉ ፈተናዎችስ? '"ህዳሴ ግድብ በጣም ውስብስብ የሆነ ፕሮጀክት ነው።" የሚሉት ዋና ሥራ አስኪያጁ ግድቡ ሲከናወን ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉ ስጋቶች ምንድናቸው? እነዚህን ችግሮች እንዴት ነው ማለፍ የሚቻለው? የሚሉትን ጥያቄዎች እና ምላሾች ቀድሞ ማወቅ የፕሮጅክቱ ሥራ አስኪያጅ ኃላፊነቶች መካከል ዋነኛው ነው። ግድቡ ውሃ እንዲይዝ ማድረግ በራሱ አንዱ ፈተና ሊሆን እንደሚችል ይናገራሉ። "በግድቡ ግንባታ ላይ እክል ሊሆኑ የሚችሉ ዝርዝር ጉዳዮችን ቀድሞ ለመለየት እንጥራለን፤ ለችግሮቹም መፍትሄ እየሰጠን እንሄዳለን" ይላሉ ኢንጂነር ክፍሌ።
news-53160669
https://www.bbc.com/amharic/news-53160669
በቄለም ወለጋ ዞን አምፊሎ ወረዳ ሸበል ቀበሌ ነዋሪዎችን ምን አፈናቀላቸው?
በቄለም ወላጋ ዞን አምፊሎ ወረዳ ሸበል ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ በርካታ ሰዎች በጸጥታ ችግር ምክንያት ተፈናቅለው በጋምቤላ ክልል 03 የሚባለው አካባቢ መጠለላቸውን ለቢበሲ ተናግረዋል።
በምዕራብ ኢትዮጵያ ከሚገኘው የመኖሪያ አካባቢያቸው እንደተፈናቀሉ የሚናገሩት እነዚህ ነዋሪዎቹ አሁን ተመልሰው በተጠለሉበት ስፍራ ለተለያዩ ችግሮች መጋለጣቸውንም ለቢቢሲ ገልጸዋል። ከአንድ ሳምንት በፊት በቀበሌያቸው ሸበል፣ በተከሰተው ግጭት የተነሳ የአምስት ሰዎች ሕይወት ካለፈ በኋላ ወደ ጋምቤላ ክልል እንደሸሹ የሚናገሩት ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ነዋሪ "አሁን ደግሞ የመንግሥት ኃላፊዎች በጉልበት ወደ መኖሪያ ቀያችን መልሰውናል" ይላሉ። የሁለት ልጆች አባት የሆነውና ሸራ ወጥሮ በጋምቤላ 03 እንዳለ የተናገረው ሌላ ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቀ ግለሰብ በበኩሉ አሁንም ቢሆን በፍርሃት እንደሚኖር ተናግሮ ወደ መኖሪያ አካባቢው የተመለሰው ያለው ሁኔታ ስለሚያሰጋው መሆኑን ለቢቢሲ ተናግሯል። • የሜዳ ቴኒሱ ኮከብ ሰርቢያዊው ጆኮቪች በኮሮናቫይረስ ተያዘ • ለ50 ዓመታት ሳይፈታ የቆየውን የሒሳብ እንቆቅልሽ በቀናት ውስጥ የፈታችው ተማሪ "ቅዳሜ ጠዋት ሸበል ውስጥ ከፍተኛ ተኩስ ሰሲማ ደንግጠን ተበታተንን" ያሉት ወደ ቀያቸው ከተመለሱት መካከል አንዱ ናቸው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ መሸሽ መጀመራቸውን በመግለጽ "የመንግሥት ወታደሮች የሚሉት ተኩሱ የተከፈተው የሸኔ ታጣቂዎች ላይ ነው። እኛ ወደ ጫካ የሸሸነው ተኩሱን ሰምተን ነው" ነው ብለዋል። ቡና ጫካችን ውስጥ ሆነን ስንሰማ በዚህ ተኩስ የተነሳ አምስት ሰዎች መሞታቸውን ሰምተናል በማለት የነበረውን ሁኔታ ያስረዳሉ። ይህንን ፈርተን በእግራችን ወደ ጋምቤላ አቅንተናል ያሉት ነዋሪው ችግሩ በተከሰተበት ዕለት ሁሉም ነዋሪዎች ደንግጠው መሸሻቸውን ይናገራሉ። "ተኩስ ሲከፈት እየሞተ ያለው ሰላማዊ ሰው ነው" በማለት እያጋጠመ ነው ያሉትን ለቢቢሲ ገልጸዋል። "ስለዚህ በነጻነት መኖር ስላለቻልን ወደ ጋምቤላ ተሰድደናል" ሲሉም ያክላሉ። • «የሕዳሴው ግድብ ለግብፅና ሱዳንም ይጠቅማል» ጥቁር አሜሪካውያን ፖለቲከኞች • የቀድሞው የጉግል ሠራተኛ የአሊባባው ጃክ ማን በሀብት በለጠው • ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ በአሜሪካ ኮሮና በአስደንጋጭ ሁኔታ ሊያንሰራራ እንደሚችል አስጠነቀቁ በእግራችን ሰባት ሰዓት ተጉዘን ነው ጋምቤላ የገባነው የሚሉት እኚህ ግለሰብ ለሊቱን ተጉዞ በነጋታው ጋምቤላ 03 የሚባለው አካባቢ የደረሰ መኖሩንም ያስረዳሉ። ጋምቤላ ያሉ ነዋሪዎችና የክልሉ መንግሥት ተቀብለዋቸው 03 የሚባል አካባቢ በማስፈር እንደረዷቸውም ተናግረዋል። በአካባቢው የሚገኙ ወጣቶች ምግብ እያቀረቡላቸው እንደነበር የተናገሩት እኚህ ግለሰብ ከቀይ መስቀል እርዳታ እንዲያገኙም እንዳስተባበሩላቸው ለቢቢሲ ገልፀዋል። ግለሰቡ እንደሚገልጹት በ03 አካባቢ ለስድስት ቀናት ከቆዩ በኋላ ከዞኑና ወረዳው የመጡ የመንግሥት ኃላፊዎች እንዳወያይዋቸው ይገልፃሉ። "ችግራችንን ካስረዳን በኋላ እነርሱ ግን መመለስ አለባችሁ በማለት በስድስት መኪና 120 የሚሆን ሰው በመጫን ወደ ስፍራው መልሰውናል።" ተመልሰውም ቢሆን ተመሳሳይ ችግር ውስጥ መውደቃቸውን በመግለጽ፣ አንመለስም ያሉ እና ጋምቤላ ክልል ውስጥ የቀሩ መኖራቸውን አክለው ተናግረዋል። ከ200 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ሸሽተው ጋምቤላ ውስጥ ተጠልለው መቅረታቸውን የተናገሩት ደግሞ ሌላው ግለሰብ፤ እነዚህ ሰዎች ከመኖሪያ አካባቢያቸው የሚመጡ ባለስልጣናት እንዳያገኟቸው በመስጋት በሰዎች ቤት ሸሽተው እንዳሉ ይናገራሉ። በጋምቤላ ለመቅረት የወሰኑት ለሕይወታቸው በመፍረታቸው መሆኑን የሚገልጹት ግለሰቡ አሁንም አዛውንቶች፣ ሴቶች፣ እናቶችና ሕጻናት በችግር ውስጥ መሆናቸውን ተናግረዋል። ወደ ጋምቤላ የተሰደዱትን ሲረዱ ከነበሩት ሰዎች መካከል አንዱ የሆነው የክልሉ የግብርና ሠራተኛ ተፈናቃዮቹ አሁን ያሉበት ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ይናገራል። ተፈናቅለው የመጡ ሰዎችን የአካባቢው ባለስልጣናት መጥተው እንደሚወስዷቸው የሚያናገሩት እኚህ ግለሰብ 03 አካባቢ እንዲቆዩ አድርገን ገንዘብ፣ ምግብ፣ መጠለያ እንዲረዱ ማድረጋቸውን ይገልጻሉ። የመንግሥት አካላት ከወረዳና ከዞን ከጸጥታ አካላት ጋር በመሆን በስፍራው በመገኘት እንዳወያይዋቸው የሚገልጹት እኚሁ የጋምቤላ ነዋሪ እንያዛለን በሚል ፍራቻ ያልተሳተፉ መኖራቸውን በመግለጽ የተሳተፉት ግን መመለሳቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። አሁን ጋምቤላ የቀሩት በየስፍራው ተበታትነው መሆኑን በመግለጽ ይህም ለመርዳት አስቸጋሪ እንዳደረገባቸው ገልፀዋል። ግለሰቦቹ ተበታትነው የሚገኙት የመንግሥት ኃላፊዎች መጥተው ይወስዱናል በሚል ፍራቻ መሆኑንም ጨምረው ያስራሉ። የአንፊሎ ወረዳ ጸጥታ እና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታሁን ሻምቢ በቀበሌው ችግር ተከስቶ እንደነበር አረጋግጠው፣ ወደ ጋምቤላ ተፈናቅለው የነበሩ በሙሉ ወደ መኖሪያ ስፍራቸው መመለሳቸውንና ሕይወታቸውን መቀጠላቸውን ይናገራሉ። እንደ እርሳቸው ገለጻ አንድም በጋምቤላ የቀረ ተፈናቃይ የለም። "ተጠልሎ ወደ ነበሩበት 03 አካባቢ ሄደን አነጋግረናቸው ወደ ቀያቸው መልሰናቸዋል" የሚሉት አቶ ጌታሁን ያፈናቀላቸው የሸኔ ወታደር መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል። ኃላፊው የተወሰደው እርምጃ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እንጂ ሕዝቡን ለመጉዳት አይደለም በማለት "ተኩስ ነበር በተኩስ መካከል ሰዎች ይጎዳሉ ነገር ግን የሞቱ ሰዎች መኖራቸውንም ሆነ ምን ያህ ሰው እንደሞተ የምናውቀው ነገር የለም" ብለዋል። ለኃላፊው ሕዝቡ ያለበትን የጸጥታ ችግር ለማረጋጋት እንደወሰደ እርምጃ አንዳለ ተጠይቀው የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል።
news-53627157
https://www.bbc.com/amharic/news-53627157
ኮሮናቫይረስ፡ሪፐብሊካኖች በሚያደርጉት እጩ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሚዲያዎች እንዳይሳተፉ ተወሰነ
የአሜሪካ የሪፐብሊካን ፓርቲ በዚህ ወር እጩ ፕሬዚዳንቱን በይፋ ለመምረጥ እቅድ ይዟል። ይህ ምርጫም ሚዲያዎች እንዳይሳተፉበትና በዝግም እንደሚካሄድ ተገልጿል።
የሪፐብሊካን ቃለ አቀባይ እንደተናገሩት ሚዲያ እንዳይሳተፍ የተወሰነው ከኮሮናቫይረስ መመሪያዎች ጋር በተያያዘ መሆኑንም አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል። በሰሜን ካሮላይና የሪፐብሊካን ልዑካን ተሰባስበውም እጩ ፕሬዚዳንቱን ዶናልድ ትራምፕን በይፋ እንደገና ይመርጣሉ። 336 የሚሆኑ ልዑካን በሰሜን ካሮላይና ግዛት፣ ቻርሎቴ ከተማ በዚህ ወር ይሰባሰባሉ። እነዚህ ልዑካን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ቁጥሩ በመገደቡ መገኘት ያልቻሉትን በሺዎች የሚቆጠሩ አባላትን ወክለው ይገኛሉ። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፓርቲያቸው ብቸኛ እጩ ተወዳዳሪ ሲሆኑ፤ እንደገና በይፋ መመረጣቸውም የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻቸውንም እንዲሁ በይፋ መጀመሩን የሚያበስር ነው ተብሏል። "ፓርቲያችን በፌደራል እንዲሁም በተለያዩ ግዛቶች የወጡ የኮሮናቫይረስ መመሪያዎችን በመከተልም ነው ስብሰባውን የሚሳተፉ ሰዎች ቁጥርን የወሰንነው" በማለት ቃለ አቀባይዋ ተናግረዋል። ይህ ውሳኔ ከዚህ በፊት ይደረጉ የነበሩ ስብሰባዎቸን አካሄድ የቀየረ ነው ተብሏል። ከዚህ ቀደም እንዲህ አይነቱ ስብሰባ የበርካታ ሚዲያዎችን ቀልብ የሚስብና ለህዝቡም መልዕክቶች ይፋ የሚሆኑበት ነበር። የሰሜን ካሮላይና አስተዳዳሪ በሚገኙት ሰዎች ብዛትና አካላዊ ርቀት ጋር ተያይዞ ስብሰባውን ወደ ሌላ ቦታ እንዲያደርጉት መጠየቀቻውን ተከትሎ ግንቦት ወር ላይ ወደ ጃክሰን፣ ፎሎሪዳ እንደሚደረግ ትራምፕ ተናግረው ነበር። ነገር ግን ወደ በኋላ ፍሎሪዳ ሊደረግ የነበረውን ስብሰባ በመሰረዝ ወደቀደመው እቅድ በመመለስ ሰሜን ካሮላይና እንዲካሄድ ተወስኗል።ግዛቲቷ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ያለምክንያት እያቀጣጠሉ ነው በማለት ወንጅለዋል።
news-49969123
https://www.bbc.com/amharic/news-49969123
ጂም ኢስቲል፡ 300 የሶሪያ ስደተኞችን የታደገው ካናዳዊ ባለሃብት
ካናዳዊው ባለሃብትና በጎ አድራጊ ከ300 በላይ የሶሪያ ስደተኞችን ሕይወት መለወጥ ችለዋል።
ጂም ኢስቲል ከ300 በላይ ሶሪያዊያን ስደተኞች በካናዳ አዲስ ሕይወት እንዲጀምሩ ረድተዋቸዋል። በሥራቸው ውጤታማ የሆኑት ካናዳዊው የንግድ ሰው በሶሪያ የሚካሄደውን የእርስ በርስ ጦርነት በቴሌቪዥን ሲመለከቱ እነርሱን ለመርዳት አንድ ነገር ማድረግ እንዳለባቸው መወሰናቸውን ይናገራሉ። በመሆኑም የሶሪያ ስደተኞች በካናዳ ውስጥ እንዲቋቋሙና ሕይወታቸውን በተስተካከለ መልኩ እንዲመሩ አስችለዋል። "ትክክለኛውን ነገር ነው ያደረኩት" ይላሉ ጂም። ይህንን ያደረጉት በጎርጎሮሳዊያኑ 2015 ሲሆን፣ በወቅቱ ምንም እንኳን የካናዳ መንግሥት ጦርነትን ሸሽተው የተሰደዱ ሶሪያውያንን ለመቀበል የሚያስችለውን ይፋዊ አሰራር እያስተካከለ የነበረ ቢሆንም ጂም የነበረው የሂደቶች መንቀራፈፍ እጅግ ያሰጋቸው ነበር። "በሶሪያ እየሆነ ያለውን ቀውስ አያለሁ፤ የምዕራባዊያን አገራት መንግሥታት አፋጣኝ ምላሽ ይሰጣሉ የሚል እምነት አልነበረኝም" ሲሉ የ62 ዓመቱ ባለሃብት ያስታውሳሉ። በመሆኑም ችግሩን በትንሹም ቢሆን ለመፍታት የሚችላቸውን ሁሉ ለማድረግ ወሰኑ። 1.1 ሚሊየን ዶላር ከራሳቸው ኪስ በማውጣት ከመካከለኛው ምስራቅ የሶሪያ ስደተኞችን ወደ ሚኖሩበት ካናዳ፣ ኦንታሪዎ መውሰድ ችለዋል። ጂም ይህንን ለማድረግ 'ፕራይቬት ስፖንሰርሽፕ' [የግል ድጋፍ አድራጊ] የስደተኞች ፕሮግራም በመፈቀዱ የካናዳን መንግሥት ያመሰግናሉ። በካናዳ ይህ አሠራር የተዋወቀው ከ41 ዓመታት በፊት ሲሆን በቪየትናም ጦርነት ጊዜ የካናዳ ዜጎች፣ ስደተኞችን ለመቀበልና በአገሪቷ እንዲቋቋሙ ለመደገፍ ትፈቅድላቸው ነበር። ድጋፍ አድራጊው ግለሰብ ለሚወስደው ስደተኛ የሚያስፈልገውን ወጭ ሁሉ ለአንድ ዓመት እንዲሸፍን ሕጉ ያስገድዳል። ጂም ይህንን እድል በመጠቀም ለ50 ሶሪያዊያን ስደተኞች የሚጠበቀውን አሟልተው 135 ሺህ የሕዝብ ብዛት ወደ የሚኖርባት ጎልፍ ወስደዋቸዋል። የተወሰኑትን በራሳቸው መኖሪያ ቤት ያስቀመጧቸው ሲሆን በከተማዋ ካለ የቤተ ክርስቲያን ቡድን 800 በጎ ፈቃደኞችን በማደራጀት እና በአካባቢው ካሉ የሙስሊም ማህበረሰብ ጋር በቅርበት በመሥራት ለመርዳትም ይሞክሩም ነበር። • በጦርነት የተጎሳቆሉ ስደተኞች መዳረሻቸው የት ነው? • የበጎ ሰው ኢትዮጵያዊ ዳያስፖራዎችን ሊሸልም ነው የአገሪቷ ነዋሪዎችም የማረፊያ ክፍሎችን በመስጠት፣ ክፍት የሆኑ የመኖሪያ ቤቶችን በማፈላለግ፣ አልባሳትን በመሰብሰብና ድጋፍ በማድረግ በወቅቱ የነበረውን ቅዝቃዜ በብርድ ሳይገረፉ እንዲያሳልፉ ረድተዋቸዋል። ልጆቻቸው እንዲማሩ እና ወላጆቻቸው ሥራ እንዲሰሩ በሚል ለእያንዳንዱ ሶሪያዊያን ቤተሰቦች እንግሊዝኛና አረብኛ ቋንቋ አስተማሪ ቀጥረውላቸዋል። ጂም ይህ ብቻ ሳይሆን 28 ለሚሆኑት ሶሪያውያን ስደተኞች ራሳቸው በሚመሩት የግል ድርጅታቸው የሙሉ ሰዓት ሥራ ሰጥተዋቸዋል። ለሌሎቹ ሶሪያዊያን ደግሞ በከተማዋ በግላቸው የንግድ ሥራ ላይ እንዲሰማሩ፤ ሱቅ እንዲከፍቱ የሚያስችላቸውን የገንዘብ ድጋፍ አድርገውላቸዋል። በአሁኑ ሰዓት ጂም በአጠቃላይ ቁጥራቸው ከሦስት መቶ የሚበልጡ 89 ሶሪያውያን ቤተሰቦችን ይደግፋሉ። "ይህንን የማደርገው እነዚህን መልካም ሰዎች እንዲቋቋሙ ለመርዳትና በክፉ ጊዜ ከጎናቸው ለመቆም ነው" ብለዋል። በካናዳ ገልፍ ከሚኖሩት ስደተኞች አንዱ የሆኑት አሕመድ አቤድ በጎርጎሮሳዊያኑ 2016 በተፈፀመ የቦምብ ጥቃት ጉዳት ከደረሰባቸው በኋላ አገራቸውን ጥለው እንደተሰደዱ ይናገራሉ። "ባለሃብቱንና የአገሪቷን 'የስፖንሰርሽፕ ፕሮግራም' አመሰግናለሁ፤ ጎልፍ አሁን አዲሱ አገሬ ሆኗል" ይላሉ ባለቤታቸው ከተማ ውስጥ ሱቅ በመክፍት መሥራት እንደጀመረች በመናገር። ጂም ሶሪያዊያኑ ሥራ እንዲያገኙ ጥረት ያደረጉ ሲሆን 28ቱን በራሳቸው ድርጅት ውስጥ ቀጥረዋቸዋል በጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠር 1980 ከካናዳ ዋተርሉ ኦንታሪዮ ዩኒቨርሲቲ በምህንድስና የመጀመሪ ዲግሪያቸውን ያገኙት ጂም፤ ሥራ የጀመሩት በኮምፒዩተር ኢንዱስትሪ ነበር። ይሁን እንጅ ተቀጥሮ ከመስራት ይልቅ በመኪና እየተዘዋወሩ ኮምፒዩተሮችን በመሸጥ ወደ ንግዱ ዓለም ተቀላቀሉ። የቢዝነስ ድርጅቱ ኢ ኤም ጀ ዳታ ሲስተም በጎርጎሮሳዊያኑ 2004 በአሜሪካዊያኑ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ቡድን 'ሰይኔክስ' በ56 ሚሊየን ዶላር ከመገዛቱ በፊት በነበሩት በ24 ዓመታት ውስጥ ቀስ በቀስ እያደገ መጥቶ ነበር። ከብላክቤሪ ሞባይል ጀርባ ላለው የካናዳ ድርጅት 'ሪሰርች ኢን ሞሽን' መሥራች የቦርድ አባል ሆነው እንዲሁም በሌሎች የቢዝነስ ዘርፎች ላይ አገልግለዋል። በ2015 በዳንቢይ ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆኑ። ድርጅቱ የልብስ ማጠቢያ ማሽኖችን፣ ማቀዝቀዣዎችን፣ የመመገቢያ እቃዎች ማጠቢያ ማሽን እና የአየር ሁኔታ ምቹ ማድረጊያ እቃዎችን ያመርታል። "እንደ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሳደርግ የነበረው፤ አሰራር መዘርጋት ነበር፤ ለስደተኞችም ያደረኩት ይኼው ነው፤ እቃዎቹን አላመርትም ወይም ራሴ ተዟዙሬ አልሸጥም። የማደርገው እያንዳንዱ ነገር እንዴት በተገቢው መንገድ እንደሚከናወን ማመቻቸት ነው። ሌሎችም ሥራ እንዲያገኙ ለመርዳት የምችለውን ነው ያደረኩት" ይላሉ። ጂም ባደረጉት በጎ ተግባር በዚህ ዓመት ሚያዚያ ወር ላይ የካናዳ መንግሥት በአገሪቷ በሁለተኛ ደረጃ ክብር የሚሰጠውን ሽልማት አበርክቶላቸዋል። ንግሥት ኤልሳቤጥ ሁለተኛን የወከሉት የካናዳ አስተዳዳሪ ጀኔራል ጁሌ ፓይቴ "የሚገርም ስኬት፣ ለማህበረሰቡ ያለውን ኃላፊነት እና ለአገሪቱ የሰጠውን አገልግሎት አሳይቶናል" ብለዋል። የገልፍ ከንቲባ ካም ጉትሬም ለቢቢሲ "እውነተኛ፣ ትሁት፣ ደግ እና ጨዋ መሪ ናቸው" ሲሉ ለጂም ያላቸውን ክብር ገልፀዋል። • ለ20 ዓመታት ዴንማርካዊት እህቱን የፈለገው ኢትዮጵያዊ ሀኪም "ለቀጠሯቸው ሠራተኞቻቸው እና ለሚኖሩበት ማህበረሰብ ይጨነቃሉ፤ ከካናዳ ውጭ የሚኖሩ ሌሎች ሰዎችን ወደ ገልፍ አምጥተዋል፤ ከምቾት ቀጠናቸው ወጥተው ከከተማቸው በዘለለ በዓለም ምን እየተከናወነ እንደሆነ ለማየት ዐይናቸውን ከፍተዋል" ሲሉ አክለዋል። ጂም እንደሚሉት ከሶሪያ ስደተኞች የሰሙት ታሪክ አሁንም ድረስ ከውስጣቸው አይጠፋም። ወደ ፈራረሰው ቤታቸው የተመለሱት ሰዎች ታሪክ፣ ከሞት አፋፍ ካሉ ወንድሞቻቸው ጋር በስልክ የሚያደርጉት ልውውጥ ከህሊናቸው አይወጣም። "እነዚህ ቤተሰቦች እንደማንኛውም ሰው ደስተኛ መሆን ይፈልጋሉ፤ ከጥቃትና ከስጋት ነፃ የሆነን ወደፊት ይመኛሉ። 99.9 በመቶ የሚሆኑት ካናዳዊያን ከሌላ አገር የመጡ ስደተኞች ቢሆኑም እንኳን አሁንም መቀበል አለብን" ብለዋል።
news-56066789
https://www.bbc.com/amharic/news-56066789
በጊኒ ኢቦላ ተቀስቅሶ ሦስት ሰዎች ሞቱ
በጊኒ ኢቦላ ተቀስቅሶ 3 ሰዎች ሞቱ። ሌሎች አራት ሰዎች ደግሞ ተቅማጥ፣ ማስመለስና የመድማት ምልክቶችን እያሳዩ እንደሆነ ተነግሯል።
አራቱ ሰዎች እነዚህን ምልክቶች ማሳየት የጀመሩት የአንድ በኢቦላ የሞተችን ነርስ ቀብር ከታደሙ በኋላ ነበር። ባለሥልጣናት አዲስ የተሰራ ክትባት በዓለም ጤና ድርጅት በኩል እንደሚገኝ እየተናገሩ ነው። በፈረንጆቹ ከ2013 እስከ 2016 ብቻ በምዕራፍ አፍሪካ ኢቦላ ወረርሽኝ የ11ሺ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል። ወረርሽኙ ጊኒን ጨምሮ ጎረቤቶቿን ላይቤሪያንና ሴራሊዮንን በከፍተኛ ሁኔታ አጥቅቶ ነበር። ይህን ተከትሎም በርካታ ክትባቶች ተሞክረዋል። ክትባቶቹ ወረርሽኞቹን ለማቆም በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ አገልግሎት ላይ ሲውሉ ነበር። የዓለም ጤና ድርጅት የጊኒ ተወካይ አልፍሬድ ጆርጅ ኪ ዜርቦ "አስፈላጊውን ክትባት ለማቅረብ የዓለም ጤና ድርጅት ከመድኃኒት አምራቾች ጋር እየተነጋገረ ነው ብለዋል። የኢቦላ ክትባት ለመጀመርያ ጊዜ በ2015 በጊኒ ሙከራ ተደርጎ ውጤት ማስገኘቱ ይታወሳል። ከክትባቱ ሌላ ታማሚው የመዳን እድሉን የሚጨምሩ መድኃኒቶች መፈብረካቸውም ይታወቃል። አሁን በጊኒ የተቀሰቀሰው ኢቦላ በአንድ ጤና ጣቢያ ትሰራ የነበረች ነርስ ታማ ከሞተች በኋላ በቀብሯ ላይ የተገኙ ሰዎች በተህዋሲው መጠቃታቸው ነው የተነገረው። ነርሷ ከሞተች ከ4 ቀናት በኋላ ነበር የተቀበረችው። ምናልባት አስክሬን በማጠብ ላይ የነበሩ ሰዎች ተህዋሲውን እንዳዛመቱ ይገመታል። ብዙውን ጊዜ በኢቦላ የሞቱ ሰዎች አስክሬን አደገኛና መርዛማ የኢቦላ ተህዋሲን የመሸከም አቅም አለው። የተህዋሲው እድሜም ከ2 ቀን እስከ 3 ሳምንት ይቆያል። ኢቦላ ቺምፓዚን ከመሰሉ እንሰሳት ወደ ሰው የሚተላለፍ ተህዋሲ ነው። ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈውም በደም፣ በሰውነት ፈሳሽ ወይም ተህዋሲው ከነካው አካባቢ ሊሆን ይችላል። አሁን ሁሉም በተህዋሲው የተለከፉት እድሜያቸው ከ25 ዓመት በላይ የሆኑና የነርሷን ቀብር የታደሙት ናቸው። የወረርሽኙን መቀስቀስ ተከትሎ ሴራሊዯንና ላይቤሪያ በተጠንቀቅ ላይ ይገኛሉ። የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃ ለጤና ሚኒስትሮቻቸው ጉዳዩን በንቃት እንዲከታተሉ አዘዋል። የቢቢሲ ዘጋቢ ከሴራሊዯን እንደጻፈችው በአገሪቱ ከኮቪድ ተህዋሲ በላይ ሕዝቡ ስጋት ያለበት ለኢቦላ ወረርሽኝ ነው። ኢቦላ ተህዋሲ ድንገቴ ትኩሳት በመፍጠር በአጭር ሰዓት ታማሚውን በማዳከም የጡንቻ ከባድ ሕመም ፈጥሮ ጉሮሮን አቁሱሎ የሚገድል በሽታ ነው። ከዚህም ባሻገር ማስመለስ፣ ማስቀመጥ እና የውስጥና የውጭ መድማትን ያስከትላል። ታማሚዎች የሚሞቱት ብዙውን ጊዜ ፈሳሽ ከሰውነታቸው ተሟጦ ስለሚያልቅ ነው። ይህም የአንዳች ሰውነት አካል ሥራ ማቆምን ያስከትልና ለሞት ይዳርጋል።
48159690
https://www.bbc.com/amharic/48159690
"ዳቪንቺ ሞናሊዛን ያልጨረሰው ስለታመመ ነው" ሀኪሞች
ከእውቅ ሠዓሊያን አንዱ የሆነው ሊዩናርዶ ዳቪንቺ ሊሞት አካባቢ የነርቭ ህመም ገጥሞት እንደነበረ የጣልያን ሀኪሞች ተናግረዋል።
ሊዮናርዶ ዳቪንቺ ሠዓሊው ህይወቱ ሊያልፍ አካባቢ የገጠመው የነርቭ ህመም ሥዕል እንዳይስል አግዶት ነበር ተብሏል። ዳቪንቺ ሠዓሊ ብቻ ሳይሆን የሥነ ህንጻ ባለሙያና ቀራጺም ነበር። • ሙንጭርጭር ሥዕሎች ሀኪሞች እንዳሉት፤ 'አንለር ፓልሲ' የተባለው የነርቭ ችግር የእጁን እንቅስቃሴ ገድቦት ብሩሽ እንዳይዝ አግዶት ነበር። ህመሙ በስትሮክ ምክንያት እንደተከሰተበት መላ ምቶች አሉ። በርካታ የሥነ ጥበብ ታሪክ አጥኚዎች ዳቪንቺ ይስል የነበረው በቀኙ ነው ወይስ በግራ እጁ በሚል ለዓመታት ተከራክረዋል። ሀኪሞቹ ከድምዳሜ የደረሱት ሁለት የዳቪንቺ ሥዕሎችን ካጠኑ በኋላ ነበር። ሥዕሎቹ ከዚህ ዓለም በሞት ሊለይ አካባቢ የሠራቸው ሲሆኑ፤ አንደኛው የራሱ ግለ ምስል (ፖርትሬት) ነው። • የለማ ጉያ ድንቅ የቆዳ ላይ ሥዕሎች በምስሉ ላይ ቀኝ ክንዱ ተሸፍኖ እጁም ተኮማትሮ ይታያል። ሮም ውስጥ ያሉ የፕላስቲክ ቀዶ ጥገና ሀኪምና የምርምሩ መሪ ዶ/ር ዴቪዴ ላዘሪ እንደሚሉት፤ በምስሉ ላይ ያለው የዳቪንቺ እጅ 'ክላው ሀንድ' በሚል መጠሪያ የሚታወቀው የነርቭ በሽታን ያሳያል። ዶ/ር ዴቪድ እንደሚሉት የዳቪንቺ የነርቭ ችግር ከስትሮክ ጋር የተገናኘ ላይሆን ይችላል። ምክንያቱም የአካሉ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ መገደቡን የሚያሳይ መረጃ የለም። "በሠዓሊነት ሙያ በቆየባቸው የመጨረሻው አምስት ዓመታት፤ ሞና ሊዛን ጨምሮ በርካታ ሥዕሎችን ሳያጠናቅቅ የቀረው በህመሙ ምክንያት ሊሆን ይችላል" ብለዋል። • ከ'ሶፍትዌር' ቀማሪነት ወደ ሥነ-ጥበብ ባለሟልነት • ካናዳን በጥበብ ሥራው ያስዋበው ኢትዮጵያዊ ሀኪሞቹ ለምርምር ከተጠቀሙባቸው ሥዕሎች በአንዱ የሙዚቃ መሣሪያ የሚጫወት ግለሰብ ይታያል። ግለሰቡ ዳቪንቺ እንደሆነ በቅርቡ ተደርሶበታል። አንቶኒዮ ደ ቢያቲስ እንደጻፈው፤ ዳቪንቺ በስተመጨረሻ ዘመኑ ቀኝ እጁ አልታዘዝ ብሎት ስለነበረ ጥሩ ሥዕል መሥራት አልቻለም ነበር።
news-56924980
https://www.bbc.com/amharic/news-56924980
የሳምሰንግ ኩባንያ ቤተሰብ በዓለም ትልቁን የውርስ ግብር ሊከፍል ነው
የሳምሰንግ ኤሌክትሮኒክስ ኩባንያ ትልቁ ባለድርሻ የሆኑት ግለሰብ ቤተሰብ ምናልባትም በዓለም ከፍተኛ የተባለውን የውርስ ግብር ለመንግሥት ሊከፍሉ ነው።
ሊ ኩን ሂ ሳምሰንግ የደቡብ ኮሪያ ግዙፍ ኩባንያ እንዲሆን አስችለውታል ቤተሰቡ ከሟቹ ሊቀመንበር ሊ ኩ ሂ ንብረቶች የውርስ ግብር የሚከፍሉት ጠቅላላ ገንዘብ ወደ 10.78 ቢሊዮን ዶላር ይጠጋል። ደቡብ ኮሪያ በዓለም ከፍተኛ የውርስ ግብር ከሚጥሉ አገራት አንዷ ናት። ሚስተር ሊ ሳምሰንግን ከአገር ውስጥ ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ በማምጣት ኩባንያው ትልቅ ስኬት እንዲቀዳጅ ያደረጉ ሰው ነበሩ። የሞቱት ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር ላይ እንደነበር ይታወሳል። ከሰሞኑ በርካታ ባለሀብቶች ይህንን የውርስ ግብር ጉዳይ በቅርብ ሲከታተሉት ነበር። ምክንያቱም በውሳኔው ላይ ቤተሰቡ በሳምሰመንግ ኩባንያ የሚኖረውን ድርሻ የሚወስን በመኾኑ ነው። በሳምሰንግ ኩባንያ ድርሻ ያላቸውና የሌላቸው ባለሀብቶች አሁንም ቢኾን ዝርዝር አፈጻጸሙንና ግብሩ ቤተሰቡ ላይ የሚፈጥረውን የድርሻ ክፍፍል በአንክሮ እየተከታተሉ ይገኛሉ። ይህ የግብር ክፍያ አሁን የሳምሰንግ ሊቀመንበር በሆኑትና በሚስተር ሊ ወንድ ልጅ ጄ ዋይ ሊ የሽርክና ድርሻ ላይ የሚያወጣው ለውጥ ካለ በሚል በብዙ ባለሀብቶች ዘንድ ጉዳዩ ትኩረት አግኝቷል። የሚስተር ሊ ወንድ ልጅ ጄ ዋይ ሊ ከአውሮፓውያኑ 2014 ወዲህ የሳምሰንግ ኤሌክትሮኒክስ ኩባንያ ባለቤት ተደርጎ ይታሰባል። ይሁን እንጂ ጄ ዋይ ሊ በአሁን ጊዜ ሰዓት በእስር ቤት ነው የሚገኘው። ምክንያቱ ደግሞ የቀድሞዋ የአገሪቱን ፕሬዝዳንት ፓርክን ጭምር ከፍተኛ ባለሥልጣናትንና ባለሀብቶችን ባነካካ የሙስና ቅሌት ሁለት ዓመት ተኩል ዘብጥያ እንዲወርድ ስለተፈረደበት ነው። ሳምሰንግ ኩባንያ ራሱ ባተመው የኩባንያው የጽሑፍ መግለጫ እንዳለው ከሆነ ይህ የውርስ ግብር በኮሪያም ሆነ በዓለም ምናልባትም ትልቁ ሳይሆን አይቀርም። የሚስተር ሊ ቤተሰብ ለመንግሥት የሚከፍለው የውርስ ግብር 12 ትሪሊዮን ዎን [የደቡብ ኮሪያ ገንዘብ] ወይም 10 ቢሊዮን ዶላር ሲሰላ ሟቹ ቢሊየነርና የሳምሰን ሊቀመንበር ከነበሩት ሚስተር ሊ በጊዜው ከነበራቸው ሀብት ግማሹን የሚሸፍን ነው። ሚስተር ሊ ከኤሌክትሮኒክስ ኩባንያው ሌላ በብዙ ዘርፎች በርካታ ሀብቶችን ነበሯቸው። የሚስተር ሊ ስብስብ ቅርሶችና ሥዕሎችን ለብሔራዊ የኮሪያ ሙዚየም እና ለሌሎች ባሕላዊ ተቋማት በስጦታ ይበረከታል። የሟቹ ሚስተር ሊ የጥበብ ስብስቦች በስመጥር አርቲስቶች የተሠሩ ብርቅዬ ሥራዎች ናቸው። የማርክ ቻጋል፣ የባብሎ ፒካሶ፣ የፖል ጋውጊን፣ የክላውድ ሞኔት፣ ጆን ሚሮ እና የሳልቫዶር ዳሊ ሥራዎች በሚስተር ሊ የጥበብ ስብስብ ውስጥ ተካተዋል። የደቡብ ኮሪያ መገናኛ ብዙሃን እንዳሉት እነዚህን ስጦታዎች ለሙዚየሞች በገጸበረከትነት ማበርከት የቤተሰቡን የውርስ ግብር በትንሹ ሊቀንሰው ይችላል። የደቡብ ኮሪያ የውርስ ግብር ከጠቅላላው ሀብት 50 ከመቶ እኩሌታ የሚሆን ሲሆን ይህም ከጃፓን ቀጥሎ በዓለም ትልቁ የውርስ ግብር ምጣኔ ነው። ሟቹ በኩባንያው ውስጥ ቁጥጥሩ ከፍ ያለ ከነበረ በዚህ የ50 ከመቶ ምጣኔ ላይ የፕሪምየም (ቀጥተኛ ያልሆኑ አበሎች) ክፍያዎችም ስለሚጨመሩበት ግብሩ ተቆልሎ የጠቅላላ ሀብቱን ከፍተኛ ድርሻ ይይዛል። በዩናይትድ ኪንግደምም ሆነ በአሜሪካ የውርስ ግብር ምጣኔ የሚሰላው 40 በመቶና ከዚያ በታች ሆኖ ነው።
news-55570802
https://www.bbc.com/amharic/news-55570802
አሜሪካ፡ የፕሬዝዳንት ትራምፕ ካቢኔ አባላት በፈቃዳቸው ስልጣናቸው እየለቀቁ ነው
ከመላው ዓለም ውግዘት እየደረሰባቸው ያሉተረ ፕሬዝዳንት ካቢኔ አባሎች ረቡዕ ዋሽንግተን ውስጥ በተከሰተው ግርግር ምክንያት በፈቃደሰቸው ሥልጣን እየለቀቁ ነው።
ነውጠኛ ደጋፊዎቻቸው የመንግሥት መቀመጫና የሁለቱ ምክር ቤቶች አዳራሾች የሚገኙበትን ካፒቶል ሒልን ጥሰው መግባታቸውን ተከትሎ በርካታ የዓለም መንግሥታት ዶናልድ ትራምፕን አውግዘዋል። የቅርብ ወዳጃቸው ናቸው የሚባሉት የታላቋ ብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ጭምር ጠንካራ ቃላትን ተጠቅመው የትራምፕን ንዝላልነት ተችተዋል። በእንዲህ ዓይነት ኩነቶች ዝምታን የሚመርጡት የጀርመኗ መራሂተ መንግሥት አንጌላ መርክልም ትራምፕን ወቅሰዋል። የዴንማርክ የኖርዌይ የፈረንሳይ መሪዎች በካፒቶል ሒል የታየውን ነውጥ ተችተዋል። ከዓለም መንግሥታት ትችት በተጨማሪ ትናንት ሐሙስ ምሽት ሁለት የትራምፕ የካቢኔ አባላት ሥልጣናቸው በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸው ተሰምቷል። የትምህርት ሚኒስትር ቤትሲ ዴቫስ ከሰዓታት በፊት መልቀቂያ አስገብተዋል። ለረዥም ጊዜ ያገለገሉት ሚስስ ቤትሲ ዴቫስ በመልቀቂያቸው ዶናልድ ትራምፕ የወንበዴዎችን አመጽ በማቀጣጠልና ይሁንታን በመስጠት ወንጅለዋቸዋል። ከሳቸው ቀደም ብሎ የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ኤሌይን ቻዎ ሥልጣን ለቅቀዋል። በሆነው ነገር ስለተረበሽኩ ከትራምፕ ጋር ለመሥራት እቸገራለሁ ብለዋል በመልቀቂያቸው። ወ/ሮ ቻው በሴኔት የሪፐብሊካኑ ተጠሪ ሚች መከኔል ባለቤት ናቸው። ከካቢኔ አባላት በተጨማሪ የትራምፕ ልዩ ረዳቶቻቸውም መልቀቂያ እያስገቡ ነው። በዲፕሎማሲ መስክ ልዩ መልእክተኛ ማይክ ማልቨኒ እንዲሁም የብሔራዊ ደኅንነት መኮንኖችና የቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ ረዳቶችም በብዛት ለቅቀዋል። የስቴት ዲፓርትመንቱ አማካሪ ደግሞ ትራምፕ ለአሜሪካ አይመጥኑም ማለታቸውን ተከትሎ ከሥራ ተሰናብተዋል። ይህንን ውግዘት ተከትሎ ዶናልድ ትራምፕ ለመጀመርያ ጊዜ ሰላማዊ የሥልጣን ርክክብ አደርጋለሁ ብለዋል። ይህን ያሉት ደጋፊዎቻቸው ካፒቶል ሒልን ጥሰው መግባታቸውን ተከትሎ በደረሰባቸው ዓለም አቀፍ ውግዘት ነው። ከጥብቅ ማስጠንቀቂያ ጋር የትዊተር ሰሌዳቸው የተመለሰላቸው ዶናልድ ትራምፕ ከዓለም መሪዎችና ተጽእኖ ፈጣሪዎች ከፍተኛ ውግዘት ከደረሰባቸው በኋላ መሸነፋቸውን በግልጽ ቋንቋ ባያምኑም የሥልጣን ርክክቡ ግን ሰላማዊ ይሆናል ብለዋል። ዲሞክራቶች በበኩላቸው ፕሬዝዳንቱ ሥልጣን ለማስረከብ 13 ቀናት ቢቀሯቸውም አሁኑኑ ከቤተ መንግሥት እንዲባረሩ ጥያቄ እያቀረቡ ነው። ሽግግሩ ሰላማዊ ይሆናል ብለው የተናገሩት ትራምፕ ይህ ንግግራቸው ለመጀመርያ ጊዜ ሽንፈታቸውን ዋጥ ያደረጉበት ነው ተብሏል። ዶናልድ ትራምፕ በባይደን የተሸነፍኩበት ምርጫው ተጭበርብሮ ነው ብለው ያምናሉ። ሆኖም ለዚህ ክሳቸው አንድም ማስረጃ ማቅረብ አልቻሉም። ተጭበርብሯል ያሉባቸው የግዛት ምርጫ ጣቢያዎች ሁሉ ትራምፕ ያቀረቧቸው ማስረጃዎች በፍርድ ቤት ጭምር ውድቅ ተደርገውባቸዋል። ሆኖም ዶናልድ ትራምፕ አሁንም ቢሆን የምርጫውን ውጤት በጸጋ መቀበል ተስኗቸዋል። የትራምፕ ወደ ትዊተር መመለስ ትራምፕ ወደ ትዊተር የተመለሱት ትናንት ሐሙስ ማታ ሲሆን ለ12 ሰዓታት የትዊተር ገጻቸው ተዘግቶ ነበር። ምክንያቱ ደግሞ የትዊተር ሕግና ደንቦችን ጥሰዋል በሚል ነው። ፌስቡክና ኢኒስታግራም ግን ላልተወሰነ ጊዜ ተዘግቶባቸዋል። ትራምፕ በትዊተር ሰሌዳ በቪዲዯ ባስተላለፉት መልእክት የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ባይደን 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ ስላጸደቀ በጃንዋሪ 20 ሥልጣን አስረክባለሁ ብለዋል። በዚህ ንግግራቸው ትራምፕ ነውጠኛ ደጋፊዎቻቸውን ያደነቁ ሲሆን ምስጋና ካቀረቡላቸው በኋላ 'ትግላችን ጀመረ እንጂ መቼ አበቃና' ብለዋል። የትራምፕ ደጋፊዎች የመንግሥት መቀመጫ የሆነውን ካፒቶል ሂልን ጥሰው መግባታቸው በስብሰባ ላይ የነበሩት የሕዝብ እንደራሴዎች ለጊዜው ልዩ ጥበቃ እንዲደረግላቸውና ወደ መደበቂያ እንዲወሰዱ አስገድዶ ነበር። ትራምፕ ያሰማሯቸው ነውጠኛ ደጋፊዎች ካፒቶል ሒልን ጥሰው ሲገቡ ታህታይና ላእላይ ምክር ቤት አባላት የባይደንን መመረጥ ከግዛት ተወካዮች የማረጋገጥ ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው ይህንኑ በመካሄድ ላይ ነበሩ። አፈ ጉባኤ ናንሲ ፒሎሲና ምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፔንስም በሸንጎ ላይ ተገኝተው ነበር። ሁለት የተለያዩ ነውጠኞች ካፒቶል ሂልን ሰብረው ከገቡ በኋላ በናንሲ ፒሎሲ ወንበር እንዲሁም ማይክ ፔንስ በሚቀመጡበት የሰብሳቢ ወንበር ላይ እግራቸውን ሰቅለው ተቀምጠው ታይተዋል። ይህንን ለአሜሪካ እንግዳ የሆነ ድርጊት ተከትሎ የሕግ መምሪያ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፒሎሲ 25ኛውን የሕገ መንግሥት አሜንድመንት በመጥቀስ ትራምፕ አሜሪካንን ለመምራት ብቁ ስላልሆኑ ከዋይት ሐውስ እንዲባረሩ ጥያቄ አቅርበዋል። ይህን ጥያቄ በርካታ ዲሞክራቶችና ጥቂት ሪፐብሊካኖች ጭምር ድጋፍ ሰጥተውታል። የሴኔት ዲሞክራት ተጠሪ ቸክ ሹመር ትራምፕ አመጽ በማቀጣጠላቸው ከሥራ ሊባረሩ ይገባል ብለዋል። 25ኛው አሜንድመንት አንድ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የአእምሮ ጤና ከራቀው በአስቸኳይ ተወግዶ ምክትል ፕሬዝዳንቱ አገሪቱን እንዲመሩ ያዛል። ሆኖም ይህ እንዲተገበር ናንሲ ፒሎሲን ጨምሮ በትንሹ 8 የካቢኔ አባላት በጉዳዩ መስማማት አለባቸው። ይህ የመሆን እድሉ ለጊዜው ጠባብ ነው ተብሏል። ዶናልድ ትራምፕ ከዋይት ሐውስ እንዲወገዱ እንቅስቃሴ የተጀመረ ሲሆን ለድርጊታቸው ክስ እንዲመሰረትባቸውም ናንሲ ፒሎሲ ጥሪ አድርገዋል። ክሱ ተፈጻሚ እንዲሆን ግን ዲሞክራቶች የሪፐብሊካኖችን ድጋፍ ማግኘት አለባቸው። ምክንያቱም ክሱ እንዲፈጸም የምክር ቤቱ ሁለት ሦስተኛው ድምጽ ስለሚያስፈልግ ነው። ይህ የመሳካት እድሉም አነስተኛ ነው። በአሜሪካ ታሪክ እምብዛምም ባልተለመደ ሁኔታ የትራምፕ ደጋፊዎች ነውጥ እንዴት ሊከሰት ቻለ የሚለው እያነጋገረ ነው፤ በተለይም የካፒቶል ሒል ጥበቃ መላላት ነገሩ የጸጥታ ኃይሎች ድጋፍ እንደነበረው ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል። ከትናንት በስቲያ በነበረው ነውጥ እስካሁን 4 ሰዎች መሞታቸው ተረጋግጧል። ከሳንዲያጎ ካሊፎርኒያ የመጣቸው የ35 ዓመቷ የአሜሪካ አየር ኃይል የቀድሞ ባልደረባ አሽሊ ባቢት በፖሊስ ተተኩሶባት መሞቷ ተረጋግጧል። ሌሎቹ ሟቾች ማንነትም የተለየ ሲሆን ቤንጃሚን ፊሊፕስ ከፔኒሲልቬኒያ ኬቭን ግሪንሰን ከአለባማ ሮዘን ቦይላንድ ከጆርጂያ መሆናቸው ፖሊስ ይፋ አድርጓል። ከነዚህ ሟቾች በተጨማሪ 14 ፖሊሶች ላይ የመቁሰል አደጋ ተመዝግቧል።
news-57251122
https://www.bbc.com/amharic/news-57251122
ህወሓት በርካታ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አባላትን መግደሉና ማፈኑ ተገለጸ
በትግራይ ክልል ውስጥ በርካታ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አባላት በህወሓት በተፈጸመባቸው ጥቃት መገደላቸውን፣ መቁሰላቸውን እና ታፍነው መወሰዳቸውን መንግሥት ገለጸ።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ የአስቸኳይ ጊዜ መረጃ ማጣሪያ ማዕከል ያወጣው መግለጫ፤ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከተቋቋመ በኋላ በተለያዩ አካባቢዎች በአስተዳደሩ አባላት ላይ በህወሓት በተፈጸሙ ጥቃቶች 22 ሰዎች መገደላቸውን አመልክቷል። በተጨማሪም በአራት የጊዜያዊው አስተዳደር አባላት ላይ በተፈጸመባቸው ጥቃት ጉዳት ደርሶባቸው በህክምና ላይ እንደሚገኙ ማዕከሉ ያወጣው መግለጫ ጠቅሷል። በዚህም ሳቢያ በአጠቃላይ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 46 የጊዜያዊው አስተዳደር ሲቪል አባላት በህወሓት ኃይሎች ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ተገልጿል። መግለጫው ጨምሮም በክልሉ መረጋጋት በማምጣት ሕዝቡ ወደ መደበኛው ሕይወት እንዲመለስ ለማድረግ ጥረት በማድረግ ላይ ባሉት የጊዜያዊ አስተዳደሩ አባላት ላይ ቡድኑ ከሚፈጽመው ጥቃት ባሻገር በንብረት ላይም ውድመት መድረሱን ጠቅሷል። መግለጫው በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ውስጥ በህወሓት ኃይሎች ጥቃት ተፈጸመባቸው ያላቸውን የጊዜያዊውን አስተዳደር አባላት ቁጥር በዝርዝር ያወጣ ሲሆን፤ ከፍተኛው ግድያ የተፈጸመው በሰሜን ምሥራቅ ክፍል ውስጥ ዘጠኝ ሰዎች የተገደሉበት መሆኑን አመልክቷል። ከዚህ ባሻገርም በማዕከላዊ ዞን 6፣ በደቡብ 3 እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ አንድ አንድ የጊዜያዊው አስተዳደር አባላት ተገድለዋል ይላል መንግሥት ያወጣው መግለጫ። በተጨማሪ ደግሞ በደቡብ ዞን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የጊዜያዊው አስተዳደር አባላት የታፈኑ ሲሆን ቁጥራቸውም ዘጠኝ ነው። በሌሎች ቦታዎች ደግሞ በደቡብ ምሥራቅ 5፣ በማዕከላዊ 4 እና በምሥራቅ 2 የአስተዳደሩ አባላት ታፍነዋል ተብሏል። ከጊዜያዊ አስተዳደሩ አባላት መካከልም በህወሓት ተፈጸመባቸው በተባለው ጥቃት አራት ሰዎች በተለያዩ ዞኖች ውስጥ የመቁሰል ጉዳት እንደደረሰባቸው መግለጫው አመልክቷል። ለሦስት አስርት ዓመታት ያህል በኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግሥት ሥልጣን ላይ ከፍተኛ ሚና የነበረው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ከሦስት ዓመታት በፊት በአገሪቱ የመጣውን የአመራር ለውጥ ተከትሎ ዋነኛ ማዕከሉን ትግራይ ውስጥ አድርጎ ቆይቶ ነበር። ህወሓት ከማዕከላዊው መንግሥት ጋር የነበረው አለመግባባት የአገራዊውን ምርጫ መራዘም ተከትሎ በትግራይ ክልል ውስጥ በተናጠል ባካሄደው ምርጫ ሳቢያ የፌደራል መንግሥቱ በወሰደው እርምጃ የበለጠ ተባብሶ መቆየቱ ይታወሳል። ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የህወሓት ኃይሎች ትግራይ ውስጥ በነበረው የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ላይ የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ካዘዙ ከሳምንታት በኋላ ህወሓት ከ30 ዓመታት በላይ ከተቆጣጠረው የክልሉ የሥልጣን መንበር ተወግዷል። በዚህም በርካታ ከፍተኛ አመራሮቹ በውጊያዎች ውስጥ መገደላቸውና በፌደራል መንግሥቱ መያዛቸው አይዘነጋም። ቢሆንም ግን ቡድኑ አሁንም ድረስ በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ ጥቃት እየፈጸመ እንደሆነ ከዚህ በፊት የሚወጡ መረጃዎች ያመከቱ ሲሆን፤ አሁን ከመንግሥት በኩል የወጣው ቡድኑ የፈጸማቸው ግድያዎችና ጥቃቶችን የሚያመለክተው መረጃ ይህንኑ ያረጋግጣል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይን (ህወሓት) የሽብር ቡድን ብሎ መሰየሙ ይታወሳል።
news-46374832
https://www.bbc.com/amharic/news-46374832
አውስትራሊያ፡- የማይሸጥ፤ የማይታረደው ግዙፉ በሬ
በምዕራብ አውስትራሊያ የሚገኘው 'ኒከርስ' የተባለው በሬ ከከብት መንጋዎች ሁሉ የተለየ ነው።
አብዛኛውን ጊዜ 'ኒከርስ' በሌሎች የቀንድ ከብቶች ተከቦ ይውላል፤ ይከተሉታልም ይህ የሰባት ዓመት ዕድሜ ያለው በሬ፤ 1400 ኪሎ ግራም የሚመዝን ሲሆን 1ሜትር ከ94 ሴንቲ ሜትር ይረዝማል፤ በአገሪቱ ካሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የቀንድ ከብቶችም በጣም ግዙፉ ነው። ባለቤትነቱም የምዕራብ አውስትራሊያዊው ጆን ፒርሰን ነው። • "ፓስፖርት መስጠት አልተከለከለም" የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች ተቋም • ታንዛኒያ "ከምዕራቡ ይልቅ የቻይናን እርዳታ ትመርጣለች" • እውን እንጀራ ሱስ ያስይዛል? ፒርሰን የቁም ከብቶችን ለውጭ ገበያ የሚያቀርብ ድርጅት አለው፤ ይሁን እንጂ ይህንን ግዙፍ በሬውን ወደ ውጭ መላክም ሆነ ለምግብነት መሸጥ እንዳልቻለ ይናገራል። ይህም የ'ኒከርስን' በሕይወት የመቆየት ዕድል ጨምሮለታል። በከብቶቹ መካከል ሲንጎማለል ላየው በእርግጥም የሰማይ ስባሪ ያክላል፤ ማንም እርሱን ደፍሮ ወደ ቄራ የሚወስደው አልተገኘም። የቄራ ሰራተኞች በበኩላቸው በሬውን ማረድም ሆነ ለመበለት የማይቻል ነው ብለዋል። በዚህም ምክንያት 'ዕድሜህ ይርዘም' የተባለው በሬ በደቡባዊ ግዛቷ ፐርዝ 136 ኪ.ሜ በምትርቀው ፕሪስቶን ሃይቅ አቅራቢያ እንደ ልቡ እየተንጎማለለ ይገኛል። የክኒከርስ ባለቤት ፒርሰን ለአገሪቱ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መረጃ በሬውን የ12 ወር ጥጃ እያለ የገዙት ሲሆን እንዲህ ይገዝፋል ብለው አላሰቡም ነበር፤ ዓመት ዓመትን እየተካ ሲሄድ ግን ከዝርያዎቹ ሁሉ በቁመቱም በክብደቱም የተለየ ሆነ ብለዋል። "ከሌሎቹ በጣም ንቁና ግዙፉ ነው" የሚሉት ፒርሰን የእርሱ ጓደኞች ግን ገና በለጋ ዕድሜያቸው የሰው እራት ሆነዋል ይላሉ። እርሱ ግን ድርብርብ ስጋው ያልከበደው ንቁና ቀልጣፋ በመሆኑ፤ እንዲሁም ማንንም አይጎዳም በሚል ለመሬቱ ግርማ ሞገስ ለዘመዶቹም ጋሻ መከታ ሆኖ እንዲቆይ እንደተውት ያስረዳሉ። ፒርሰን እንደሚሉት በሬው አሁንም ዕድገቱን አላቆመም። 20 ሺህ የሚሆኑ ቀንድ ከብቶች ባለቤት የሆኑት ፒርሰን አብዛኞቹ እንስሳት 'ዳልቻ' እና ጥቁር ቡናማ ቀለም ያላቸው ሲሆን እርሱ ግን ጥቁርና ነጭ ቀለም አለው። በመካከላቸው ሲቆምም ግርማ ሞገስ እንዳላበሳቸው ይናገራሉ። እስካሁን በቁመቱ በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ የሰፈረው የጣሊያኑ 'ቢሊኖ' ሲሆን 2.027 ቁመት አለው፤ ስሙ መዝገብ ላይ የሰፈረው ከ8 ዓመታት በፊት ነበር። ግዙፉ በሬ ''ኒከርስ'' የሚለውን ስያሜ ከየት አገኘው? ''ልጅ ሆኖ ስንገዛው 'በራህማን' የተሰኘ ሌላ የበሬ አይነት ዘር ነበረን። ይህን በሬ በአጭሩ 'ብራ' ብለን እንጠራው ነበር [ብራ ማለት ጡት ማስያዣ ማለት ነው] ከዚያም ይህን ወይፈን 'ኒከርስ' ብለን ሰየምነው [ኒከርስ ማለት ከወገብ እስከ ጉልበት ድረስ የሚሸፍን የሴት ልጅ የውስጥ ልብስ ማለት ነው] ከዛ በቃ ብራ እና ኒከርስ ኖረን።'' ፒረሰን ያስረዳሉ።
42091557
https://www.bbc.com/amharic/42091557
ህንዳዊቷ ተማሪ ራሷን በማጥፋቷ ተማሪዎች ዩኒቨርስቲውን አቃጠሉ
ፈተና ስታጭበረብር የተገኘት ተማሪ ራሷን በመግደሏ በህንድ ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ ተቃውሞ ተነስቷል።
ቼናይ በሚገኘው የሳትሀይብሃማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የመማሪያ ወንበሮችን ትናንት ምሽት ላይ እንዳቃጠሉ የሃገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ተቃውሟቸውን እየገለፁ ያሉ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲው መምህራንንና አስተዳደሩን ተማሪዋን በማሸማቀቅ ወንጅለዋል። የ18 ዓመት ዕድሜ የነበራት ይህቺ ተማሪ ፈተና ስታጭበረብር ተገኝታለች በሚል ከፈተና አዳራሽ የተባረረች ሲሆን ወዲያውም ክፍሏ ውስጥ ገብታ ራሷን አንቃ ገድላለች። ዘ ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ የተባለው የሀገሪቱ ሚዲያ የዩኒቨርስቲ ኃላፊዎችን አናግረው እንደዘገቡት ሬሳዋም በመንታ እህቷ ተገኝቷል። የሞቷም ዜና ሲሰማም ተማሪዎቹ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፋቸውን የጀመሩት። ምንጣፎችና ወንበሮችም በእሳት እንደተቀጣጠሉም በትዊተር ድረ-ገፅ ላይ የወጡ ቪዲዮዎችና ፎቶዎች ያሳያሉ። "የአንደኛ አመት ወንድ ተማሪዎች የሚያድሩበት ዶርሚተሪ ውስጥ ዕቃዎች አቃጥለዋል። ዛፎችንም አቃጠሉ። ህንፃዎቹ በቃጠሎው የተጎዱ አይመስለኝም። ወደ አምስት ሰዓትም አካባቢ በኮሌጁ በር አካባቢ ከፍተኛ የሆነ ህዝብም ተሰብስቦ ነበር" በማለት አንድ ተማሪ ለህንዱ ሚዲያ ዘ ኒውስ ሚነት ተናግሯል። ፖሊስ ሀሙስ ጥዋት ከተጠራ በኋላ ተቃውሞውም ተረጋግቷል።
news-51764736
https://www.bbc.com/amharic/news-51764736
ሮናሊዲኒሆ ሃሰተኛ ፓስፖርት በመያዝ ተጠርጥሮ በፓራጓይ በቁጥጥር ስር ዋለ
እውቁ የቀድሞ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ሮናልዲንሆ ወደ ፓራጓይ ለመግባት ሃሰተኛ ፓስፖርት ተጠቅሟል በሚል ጥርጣሬ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል።
በዚህም ምክንያት የፓራጓይ ፖሊስ ሮናልዲንሆ እና ወንድሙ በፓራጓይ መዲና ያረፉበትን ሆቴል በርብሯል። የፓራጓይ አገር ውስጥ ሚኒስትር ሮናልዲንሆና ወንድሙ እንዳልታሰሩ ነገር ግን ፖሊስ ምርመራ እያደረገባቸው እንዳለ ተናግረዋል። ሚኒስትሩ እንዳሉት ወንድማማቾቹ የተጠረጠሩበትን ወንጀል ክደዋል፤ በሚደረገው ምርመራ ላይ ግን አስፈላጊውን ትብብር እያደረጉ ነው። ሮናልዲንሆ ባለፈው የአውሮፓውያኑ ዓመት በታክስ ጉዳይ እንዲሁም በሕገወጥ ግንባታ የተጣለበትን ቅጣት ባለመክፈል የብራዚልና የስፔን ፓስፖርቱን ተነጥቆ ነበር። የፓራጓይ የአገር ውስጥ ሚኒስትሩ "በእግር ኳስ ችሎታው አደንቀዋለሁ ነገር ግን ማንም ሁን ማን ሕግ ደግሞ መከበር አለበት" ሲሉ ለአዣንስ ፈራንስ ፕሬስ ተናግረዋል። የ39 ዓመቱ ሮናልዲንሆ ወደ ፓራጓይ ያቀናው አንድ መፅሃፍን ለማስተዋወቅና ስለ ችግረኛ ህፃናት ዘመቻ ለማካሄድ እንደሆነ ተገልጿል። ሮናልዲንሆ እአአ በ2004 እና በ2005 የዓለም ምርጥ የዓመቱ እግር ኳስ ተጫዋች ሆኖ ተመርጦ ነበር። የሮናልዲንሆ አጠቃላይ ሃብት ከ80 እስከ 100 ሚሊዮን ፓውንድ ይገመታል።
news-46683802
https://www.bbc.com/amharic/news-46683802
የዛላምበሳ ድንበር ከፌደራል መንግሥት ፍቃድ ላልያዙ ተጓዦች ተከለከለ
ባለፈው የመስከረም ወር የተከፈተው የዛላምበሳ ድንበር ባልታወቀ ምክንያት ከፌደራል መንግሥት ፍቃድ ለሌላቸው ተጓዦች መከልከሉን የጉሎመኸዳ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ገብረህይወት ገብረየሱስ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በዛላምበሳ መስከረም ወር ላይ የነበረው አዲስ አመት አከባበር በኢትዮጵያ ድንበር በኩል "ከፌደራል መንግሥት ፈቃድ መያዝ አለባችሁ" የሚል ምላሽ እንተደተሰጣቸውና ከኤርትራ በኩል ደግሞ የይለፍ ወረቀት እየተዘጋጀ መሆኑን" ቢቢሲ ያናገራቸው ነዋሪዎች ገልፀዋል። •የትናንትናዋ እለት- በኢትዮ ኤርትራ ግጭት ቤተሰባቸው ለተለያየ? •መስመር ያልያዘው የኢትዮ-ኤርትራ የንግድ ግንኙነት ወዴት ያመራል? •የኦነግ እና የመንግሥት እሰጣገባ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚናገሩት ይህ መመሪያ ከመውጣቱ በፊት ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ የሚመላለሱ መንገደኞች ያለችግር ገብተው መውጣት ይፈቀድላቸው ነበር። በአሁኑ ወቅት ግን ያለ ይለፍ ወረቀት ከሁለቱም በኩል መንቀሳቀስ አይችልም። በተጨማሪም በኤርትራ በኩልም ድንበር ጥበቃውን እንዲያጠናክሩ በድንበር ጥበቃ ላይ ለተሰማሩ ከላይ መመሪያ እንደተሰጣቸውም ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚህ ጉዳይ ከኤርትራ መንግሥት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም። ዛሬ ደግሞ በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር ከራማ ወደ መረብ የሚወስደው የራማ-ክሳድ ዒቃ መተላለፊያ መዘጋቱን የመረብ ለኸ ወረዳ አስተዳደር አቶ ፅጌ ተስፋይ ለቢቢሲ ገልፀዋል። ማለፍ የሚችሉት ከፌደራል መንግስት የይለፍ ወረቀት ያላቸው ሰዎች ብቻ እንደሆኑ ተገልጿል።
48305965
https://www.bbc.com/amharic/48305965
ቦይንግ የ737 ማክስ ሶፍትዌርን አሻሽያለሁ አለ
ቦይንግ 737 ማክስ ሶፍትዌር ላይ እያደረገ የነበረውን ማሻሻያ መጨረሱን ይፋ አድርጓል። ባለፉት አምስት ወራት ብቻ ኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰከሰውን አውሮፕላን ጨምሮ በ737 ማክስ ሁለት የከፉ አደጋዎች መድረሳቸው ይታወሳል።
ቦይንግ የሶፍትዌር ማሻሻያ ባደረገባቸው 737 ማክስ አውሮፕላኖች 207 በረራ ማድረጉን አሳውቋል። • "አደጋውን ስሰማ በረራው ጠዋት እንዳልሆነ ራሴን አሳመንኩኝ" የረዳት አብራሪው ጓደኛ አብራሪዎች አውሮፕላኑን ስለሚቆጣጠሩበት መንገድ ለፌደራል አቪዬሽን አድሚንስትሬሽን (ኤፍኤኤ) መረጃ እንደሚሰጥም ተገልጿል። የኤፍኤኤ ባለሙያዎች ቦይንግ ማሻሻያው እንዲጸድቅለት መረጃውን በሚቀጥለው ሳምንት ለኤፍኤኤ እንዲያስረክብ ይጠብቃሉ። መጋቢት ላይ ኢቲ 302 ቦይንግ 737 ማክስ ሲከሰከስ አውሮፕላኑን ተሳፍረው የነበሩ 157 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል። ከኢቲ በፊት የኢንዶኔዥያው ላየን ኤር ተከስክሶ 189 ሰዎች መሞታቸውም አይዘነጋም። • አደጋው የደረሰበት ቦይንግ 737 የገጠመው ምን ነበር ? ሁለቱም አደጋዎች በቦይንግ 737 ማክስ ችግር ምክንያት መከሰታቸው ተገልጿል። የተሻሻለው ሶፍትዌር የቦይንግ 737 ማክስ ላይ የነበረውን ክፍተት የሚሞላ ነው ተብሏል። ቦይግን እንዳለው፤ አውሮፕላን አብራሪዎች እንዴት በተሻሻለው ሶፍትዌር እንደሚገለገሉ የሚጠቁም መረጃ ለኤፍኤኤ ከሰጠ በኋላ፤ የሙከራ በረራ ያደርጋል። ከዛም ማረጋገጫ ሰርተፍኬት እንደሚያገኝም ቦይንግ ገልጿል። • "አደጋውን ስሰማ ክው ነበር ያልኩት..." አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ለተሻሻለው ሶፍትዌር ማስተማሪያ አዘጋጅቶ ለኤፍኤኤ አስረክቦ እየተገመገመ መሆኑንም ቦይንግ አሳውቋል።
news-54954053
https://www.bbc.com/amharic/news-54954053
ኮሮናቫይረስ ፡ በአራት ቀናት ውስጥ 10 ኬንያዉያን ዶክተሮች በኮቪድ-19 ሞቱ
ባለፉት አራት ቀናት 10 ኬንያዊያን ዶክተሮች በኮሮናቫይረስ ምክንያት ህይወታቸውን ማጣታቸውን ተከትሎ የአገሪቱ ሐኪሞች ማኅበር የሥራ ማቆም አድማ እንደሚጠራ አሳወቀ።
በቀናት ውስጥ በርካታ አባላቱን በወረርሽኙ ያጣው ማኅበሩ የሥራ ማቆም አድማውን ከማድረጉ ከ21 ቀናት በፊት መስጠት የሚገባውን ማስጠንቀቂያ ይፋ አድርጓል። ዶክተሮቹ የኬንያን መንግሥት ለኮቪድ-19 እንድንጋለጥ አድርጎናል በሚል ከሰዋል። በኮሮናቫይረስ ከተያዙ ህሙማን ጋር ንክኪ ይኑራቸው አይኑራቸው ግልጽ ባይሆንም ባለፈው አርብ ብቻ አራት ዶክተሮች ሞተዋል። የሐኪሞቹ ማኅበር ተጠባባቂ ዋና ጸሐፊ የሆኑት ምዋቾንዳ ቺባንዚ እንዳሉት፤ ያቀረቧቸው ጥያቄዎች በሙሉ ምላሽ ካላገኙ የጠሩትን የሥራ ማቆም አድማ እንደማይሰርዙት ገልጸዋል። ማኅበሩ መንግሥት በግል ሆስፒታሎች ውስጥ የሚሰሩትን ጨምሮ በሁሉም የጤና ተቋማት ውስጥ ለሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች ደረጃቸውን የጠበቁና በቂ የመከላከያ አልባሳት እንዲያቀርብ ጠይቋል። በተጨማሪም ለሁሉም የጤና ባለሙያዎች መንግሥት አጠቃላይ የህክምና ዋስትና ሽፋን እንዲሰጥ ጥያቄ አቅርበዋል። ከአድማው በፊት ባሉት ሦሰት ሳምንታት ውስጥ ማኅበሩ ከመንግሥት ጋር ለመወያየት ዝግጁ መሆኑን ገልጾ "ይህ ካልሆነ ግን አባሎቻችንን አስተባብረን አገር አቀፍ የሥራ ማቆም አድማ እናካሂዳለን" ብለዋል ምዋቾንዳ። የአገሪቱ ጤና ሚኒስትር ሙታሂ ካግዌ በአገሪቱ ውስጥ ባሉ የጤና ባለሙያዎች መካከል እየተስፋፋ ስላለው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን በተመለከተ ስብሰባ እንደሚካሄድ አሳውቀዋል። እስካሁን ድረስ ኬንያ በግዛቷ ውስጥ ከ70 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተይዘው መገኘታቸውን ያረጋገጠች ሲሆን፤ በወረርሽኙ ምክንያትም 1ሺህ 269 ዜጎቿ ሞተውባታል።
news-47819868
https://www.bbc.com/amharic/news-47819868
በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር በተፈጠረ ግጭት ሰዎች ሞቱ
በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ደዌ ሃረዋ ወረዳ በታጠቁ ሃይሎችና የአከባቢው ነዋሪ መካካል ግጭት ተቀስቅሶ የሰው ህይወት መጥፋቱ ተገለፀ።
የወረዳው ነዋሪ የሆኑት አቶ ሞሃመድ ሰይድ ለቢቢሲ እንደገለጹት የጸጥታ ሃይል ነን ብለው የሚንቀሳቀሱና የመለያ ልብስ የሌላቸው የታጠቁ ሰዎች በአካባቢው ሰፍረው ነበር። "አለባበሳቸው ልክ እንደማንኛውም ሰው ነበር። የመለያ ልብስ ስላልነበራቸው የጸጥታ ሃይል አይመስሉም ። የያዙት ባንዲራም መሃሉ ላይ ኮከብ የሌለው ነው። በዚሁ ሁኔታ ለአንድ ሳምንት ከቆዩ በኋላ የመከላከያ የደንብ ልብስ የሚመስል ነገር እዛው በአካባቢ አሰፍተው ለበሱ።" ይላሉ። • ''አብራሪዎቹ ትክክለኛው መመሪያ ተከትለዋል'' በኋላም በአካባቢው መሳሪያ አንግበው በመንቀሳቀስ ነዋሪዎችን ትጥቅ ማስፈታት ሲጀምሩ ከተደራጁ የአካባቢው ወጣቶች ጋር ተኩስ ልውውጥ መደረጉን የሚናገሩት አቶ ሞሃመድ " የተኩስ ልውውጡ ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን ይዟል።''ይላሉ። • አውሮፕላኑ 'ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ነበር' የዞኑ የጸጥታ መምሪያ ሃላፊ የሆኑት አቶ አብዱ ሞሃመድ ግን በአካባቢው የሰፈሩትና ትጥቅ ይዘው የሚንቀሳቀሱት በክልሉ የተሰማሩ ጸጥታ አስከባሪዎች መሆናቸውን ያረጋግጣሉ። ግጭቱ መፈጠሩንም በማረጋገጥ ነገሮችን ለማረጋጋትም መከላከያ ቦታው ላይ መግባቱን ይናገራሉ ። ገና ተጨማሪ ማጣራቶችን እያደረጉ ቢሆንም የአምስት ሰዎች ህይወት መጥፋቱም ገልፀዋል ሃላፊው። • ኬንያውያን የኢትዮጵያ አየር መንገድንና ቦይንግን ሊከሱ ነው አቶ ሞሃመድም በግጭቱ ታጣቂዎችና የበአካባቢው ወጣቶች ስለመገደላቸው ይናገራሉ። "ከትናንት ማታ 12 ሰአት ጀምሮ የአካባቢው ሽማግሌዎችና የመከላከያ ሰራዊት በመሃል ገብተው ተኩስ አቁም ተደርጓል። እስካሁን ባለኝ መረጃ 10 ታጣቂዎች ሲገደሉ ሁለት ወጣቶች ህይወታቸው አልፏል።''
news-51816166
https://www.bbc.com/amharic/news-51816166
በመንዝ ጌራ መሐል ሜዳ ትናንት ምሽት በተፈጸመ ጥቃት አራት ሰዎች ተገደሉ
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ጌራ ወረዳ በመሐል ሜዳ ከተማ አንድ ግለሰብ በፈጸመው ጥቃት የአራት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ አስራ ስድስት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የአካባቢው ባለስልጣናት ለቢቢሲ ገለጸ።
ሰኞ ምሽት አንድ ሠዓት ከሩብ ላይ ኤፍ ዋን በተባለ የእጅ ቦንብ፣ በሽጉጥና በጩቤ በተፈጸመው በዚህ ጥቃት ሦስት ሰዎች ሲገደሉ በአስራ ስድስት ሰዎች ላይ ደግሞ የመቁሰል ጉዳት መድረሱን የመንዝ ጌራ ወረዳ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ት ቤት ኃላፊ አቶ ጌትነት አጎናፍር ተናግረዋል። ጥቃቱ የተፈጸመው መሐል ሜዳ ከተማ ቀበሌ ሦስት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ባለ አንድ መጠጥ ቤት ውስጥ በነበሩ ሰዎች ላይ ሲሆን፤ ይህንን ጥቃት የፈጸመው ግለሰብ የመጠጥ ቤቱ ባለቤት ልጅ ባል የሆነ ግለሰብ እንደሆነና ሚስቱን ለመግደል የፈጸመው ድርጊት እንደነበረ የመሃል ሜዳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ጥላሁን ደበበ አብራርተዋል። ግለሰቡ የኋላ የወንጀል ታሪክ እንዳለውም የተናገሩት ፖሊስ አዛዡ ከአሁን በፊትም ከ15 ዓመት በላይ አብራው የኖረችው ሚስቱን በሽጉጥ ተኩሶ ሲስታት፤ ወንድሟን አቁስሎ ታስሮ የነበረ ሲሆን፤ በ30 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር ተፈትቶ ጉዳዩ በፍርድ ቤት ሂደት ላይ ነው ብለዋል። ትናንት ምሽት የፈጸመው ጥቃትም ባለቤቱን ለመግደል መሆኑንና ጥቃት የተፈጸመበት ቤትም የሚስቱ እናት ቤት መሆኑን ኢንስፔክተር ጥላሁን ገልጸዋል። ጥቃቱ ሲፈጸም ሚስቱ በቦታው የነበረች ቢሆንም ጉዳት እንዳልደረሰባትም አመልክተዋል። ከሞቱት ሰዎች ሁለቱ በሽጉጥ በተተኮሰባቸው ጥይት ሲሆን አንደኛው ደግሞ ግለሰቡ ባፈነዳው ቦንብ እንደሆነ ተነግሯል። ግለሰቡ በመጠጥ ቤቱ ውስጥ በነበሩ ሰዎች ላይ ጥቃቱን ከፈጸመ በኋላም መንገድ ላይ ያገኘውን የ16 ዓመት ታዳጊ በጩቤ በፈጸመበት ጥቃት ክንዱ ላይ ጉዳት በማድረስ እንዳቆሰለውም አቶ ጌትነት ለቢቢሲ ተናግረዋል። በሽጉጥና በቦምብ ጥቃቱ ጉዳት ከደረሰባቸው ሰዎች መካከል ሦስቱ ወዲያውኑ ህይወታቸው እንዳለፈ ከአካባቢው ነዋሪዎች ቢቢሲ ያረጋገጠ ሲሆን፤ የመቁሰል ጉዳት ከደረሰባቸው 16 ሰዎች መካከል ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ስድስቱ እዚያው ከተማ ሃኪም ቤት ተኝተው ህክምና እያገኙ ሲሆን ሦስቱ ግን ለተጨማሪ ህክምና ወደ ደብረ ብርሃን መላካቸውን የፖሊስ ኃላፊው አረጋግጠዋል። የተቀሩት ደግሞ የደረሰባቸው ቀላል ጉዳት በመሆኑ የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ አግኝተው ወደ ቤታቸው መመለሳቸው ተነግሯል። የኮምዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊው አቶ ጌትነት አጎናፍር አክለውም ክስተቱ ከዚሁ ጋር እንደሚያያዝ ለጊዜው ያልተረጋገጠ ቢሆንም በተመሳሳይ ሰዓት እዚያው መሐል ሜዳ ከተማ ውስጥ አንድ ግለሰብ ጭንቅላቱ ላይ በመጥረቢያ ተመትቶ ሞቶ መገኘቱን ለቢቢሲ ገልጸዋል። በሟቹ ግለሰብ ኪሱ ውስጥ ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያም ሆነ መረጃ ባለመገኘቱ እስካሁን ማንነቱን ለመለየት እንዳልተቻለ ተናግረዋል። ግለሰቡ ተገድሎ የተገኘበት ቦታ በቦምብና በጥይት ጥቃት ከተፈጸመበት አካባቢ ቢያንስ በአንድ ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ የሚገኝ እንደሆነም ታውቋል። ሦስት ሰዎች የሞቱበትና በርካቶች የቆሰሉበት ጥቃት የተፈጸመበት መጠጥ ቤት በከተማዋ ለረጅም ጊዜ የቆየና ባለቤቷም ወይዘሮ ትርንጎ የመግደል ሙከራው የተደረገባት ሚስት እናት ሲሆኑ በጥቃቱ በሽጉጥ ከተመቱት አንዷ መሆናቸውን አቶ ጌትነት ተናግረዋል። በጥቃቱ በአጠቃላይ 16 ሰዎች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከመጠጥ ቤቱ ባለቤት ወይዘሮ ትርንጎ ውጪ ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ፤ በከተማዋ በሌላ ቦታ ላይ ተገድሎ የተገኘውን ሰው ጨምሮ የአራት ሰዎች ሕይወት አልፏል። ጥቃቱ በተፈጸመበት ቤት ውስጥ በርካታ ሰዎች የነበሩ ሲሆን ከሞቱትና ከቆሰሉት ውጪ ብዙዎቹ ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው እንደተረፉ አቶ ጌትነት ተናገረዋል። ጥቃቱን የፈጸመው ግለሰብ ሸሽቶ ያመለጠ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ፖሊስና የአካባቢው የጸጥታ አካላት መንገዶችን ዘግተው ፍተሻ በማድረግ ተጠርጣሪውን ለመያዝ ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ኢንስፔክትር ጥላሁን ደበበ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
news-49724522
https://www.bbc.com/amharic/news-49724522
ከምድር በታች ተደብቆ የሚገኘው የአሜሪካ መጠባበቂያ ነዳጅ
በሳዑዲ አረቢያ የነዳጅ ማቀነባበሪያ ተቋማት ላይ ጥቃት ከተሰነዘረ በኋላ የአሜሪካ ባለስልጣናት በተለያዩ ቦታዎች ለመጠባበቂያ በሚል የተደበቀው ነዳጅ ጥቅም ላይ ስለሚውልበት ሁኔታ ማውራት ጀምረዋል።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልእክት ''የነዳጅ ገበያውን ፍላጎት ለማሟላት መጠባበቂያውን ልንጠቀም እንችላለን'' ብለዋል። ትራምፕ የሚያወሩለት መጠባበቂያ ነዳጅ ከ640 ሚሊየን በርሜል በላይ የሚሆን ነዳጅ ሲሆን በቴክሳስና ሉዊዚያና ግዛቶች ከጨው በተሰራ ዋሻ ውስጥ ከምድር በታች ተደብቆ የሚገኝ ነው። ይህ ነዳጅን ደብቆ የማከማቸው ልምድ እ.አ.አ. ከ1970ዎቹ ጀምሮ ተግባራዊ ሲደረግ ቆይቷል። • ኬንያ የነዳጅ ድፍድፍ ወደ ውጭ መላክ ጀመረች • "ልዩ ነዳጅ መኖሩን አልደረስንበትም" የማዕድን፣ የፔትሮሊየምና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር ሁሉም የዓለማቀፉ ኤነርጂ ኤጀንሲ አባል ሃገራት ለሶስት ወራት የሚሆን መጠባበቂያ ነዳጅ ማስቀመት እንዳለባቸው የተስማሙ ሲሆን አሜሪካ ደግሞ ከሁሉም በላይ ብዙ መጠባበቂያ እንዳስቀመጠች ይነገራል። በአሜሪካ ብዙ የነዳጅ ጥርቅም ማስቀመጥ የተጀመረው እ.አ.አ. በ1973 በተካሄደው የአረብ እስራኤል ጦርነት ወቅት አሜሪካ ለእስራኤል ስትወግን ነዳጅ አምራች አረብ ሃገራት ማለትም ኢራን፣ ኩዌት፣ኳታርና ሳዑዲ አረቢያ ወደ አሜሪካ ነዳጅ አንልክም ማለታቸውን ተከትሎ ነበር። ምንም እንኳን ጦርነቱ ለሶስት ሳምንታት ብቻ ቢቆይም ነዳጅ አምራች ሃገራቱ እገዳውን እስከ 1974 ድረስ በማስቀጠላቸው የነዳጅ ዋጋ በመላው ዓለም በአራት አጥፍ ጨምሮ በወቅቱ 3 ዶላር ይሸጥ የነበረው አንድ በርሜል ነዳጅ ወደ 12 ዶላር ከፍ ብሎ ነበር። በአሜሪካ በአሁኑ ሰአት አራት የነዳጅ ማጠራቀሚያ ማዕከላት ሲኖሩ የሚገኙትም በቴክሳስ ፍሪፖርት፣ ዊኒ እና ቻርልስ ሃይቅ ወጣ ብሎ እንዲሁም በሉዊዚያና ባቶን ራፍ በሚባል አካባቢ ነው። እያንዳንዱ መጠባበቂያ እስከ አንድ ኪሎሜትር ጥልቀት ያለው የጨው ዋሻ ሲሆን ነዳጁን በታንከሮች ከማስቀመጥ በዋጋም ሆነ ከደህንነት አንጻር የተሻለ እንደሆነ ይነገርለታል። በጣም ትልቁ የሚባለውና ፍሪፖርት አካባቢ የሚገኘው ማጠራቀሚያ እስከ 254 ሚሊየን በርሜል ነዳጅ መያዝ እንደሚችል ይነገርለታል። የመጠባበቂያ ማዕከላቱን የሚከታተለው ተቋም እንዳስታወቀው በአሁኑ ሰአት አሜሪካ በአራቱ መጠባበቂያዎች ውስጥ 644.8 ሚሊየን በርሜል ነዳጅ አላት። የአሜሪካው የኃይል መረጃ አስተዳደር ባወጣው መረጃ መሰረት እ.አ.አ. በ2018 አሜሪካውያን በቀን 20.5 ሚሊየን በርሜል ነዳጅ ይጠቀማሉ። በዚሁ አጠቃቀማቸው የሚቀጥሉ ከሆነ መጠባበቂያው አሜሪካውያንን ለ31 ቀናት ብቻ ማቆየት ይችላል። በ1975 በወጣው ህግ መሰረት ከባድ የሆነ የነዳጅ እጥረት በአሜሪካ ካጋጠመ መጠባበቂያው ጥቅም ላይ እንዲውል ማዘዝ የሚችሉት ፕሬዝዳንቱ ብቻ ናቸው። • ናይጀሪያ በሙስናዊ ስምምነት 6 ቢሊዮን ዶላር ከነዳጅ አጣች • የምዕራብ ኦሮሚያ ነዋሪዎች ስጋትና ሰቆቃ ነዳጁ ከሚቀመጥበት ቦታ አስቸጋሪነት የተነሳ ነዳጁን በፕሬዝዳንቱ ትእዛዝ አጓጎዞ ለገበያ ለማቅረብ በትንሹ ሁለት ሳምንት ይፈጃል። ከዚህ በተጨማሪ ነዳጁ ያልተጣራ ስለሆነ በማቀነባበሪያዎች ገብቶ ለመኪና፣ ለአውሮፕላን እና ለመርከብ እንዲሆን ተደርጎ እስኪሰራ ድረስ ብዙ ቀናት መፍጀቱ አይቀርም። ይህ መጠባበቂያ ነዳጅ ለገበያ የቀረበባቸው አጋጣሚዎችም ነበሩ። ፕሬዝደንት ጆርጅ ቡሽ አንደኛ በ1991ዱ የገልፍ ጦርነት ወቅት ጥቂት የማይባል ነዳጅ ከመጠባበቂያው ሸጠዋል። ልጃቸው ጆርጅ ቡሽ ሁለተኛ ደግሞ ካትሪና የተባለው አውሎ ነፋስ አሜሪካን ባጠቃ ጊዜ 11 ሚሊየን በርሜል ነዳጅ ለገበያ አቅርበው ነበር። ፕሬዝደንት ክሊንተን ደግሞ በ1997 አጋጥሞ የነበረውን የገንዘብ እጥረት ለመቅረፍ በማሰበ 28 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ሸጠዋል።
news-41347987
https://www.bbc.com/amharic/news-41347987
የኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች ግጭት፡ በጭናክሰን ባለፉት ሦስት ቀናት የ22 ሰዎች ህይወት አልፏል
ባሳለፍነው እሁድ የኦሮሚያና የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንቶች ሰላም እንዲሰፍን እንሰራለን ካሉ በኋላ በምሥራቅ ሐረርጌ ጭናክሰን ወረዳ በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች ቀሰሉ።
ባደረግነው ማጣራት በጭናክሰን ወረዳ ባለፉት ሶስት ቀናት ውስጥ 22 ሰዎች መገደላችውን፣ 35 ሰዎች መቁሰላቸውንና 86 የአርብቶ አደር ቤቶች በእሳት መጋየታቸውን ታውቋል። የጭናክሰን ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ጀማል ሙሳ ጥቃቱ የተፈጸመው ከሶማሌ ክልል ተሻግረው በመጡ ታጣቂዎች ነው ሲሉ ለቢቢሲ የተናግረዋል። የኦሮሚያ ክልል ቴሌቪዥን የኦሮሚያ ብሮድካስት ኔትዎርክ ያናገራቸው የወረዳው የፀጥታ ሃላፊ ጥቃቱ የተፈፀው በልዩ ሃይል እንደሆነ ገልፀዋል። አቶ ጀማል ሙሳ ጨምረው እንደተናገሩት ጥቃቱ ከመቆም ይልቅ እየጨመረ የመጣ ሲሆን የጥቃት ፈጻሚዎቹም ቁጥር ከፍ እያለ መሆኑን ነው። የሁለቱ ክልል ፕሬዝዳንቶች ሰላም እንዲሰፍን ጥረት እናደርጋለን በማለት ቃል ገብተው የነበረ ቢሆንም ያለው ግጭት እንደቀጠለ ነው። የኦሮሚያ ብሮድካስት ኔትዎርክ ጋዜጠኛ ከጭናክሰን ወረዳ በጥቃቱ እየተቃጠለ የነበረ ቤት የተመለከተ ሲሆን በጥይት ተመተው የቆሰሉ ሰዎችንም አነጋግሯል። ከ86 በላይ ቤቶች መቃጠላቸው ተዘግቧል ጋዜጠኛው ያነገራቸው አንድ አዛውንት እንዳሉት ''እየደረሰብን ያለውን ጉዳት የኦሮሚያ ክልል ሊያስቆምልን ካልቻለ ለተቀረው ዓለም አቤቱታችንን ማሰማት እንፈልጋለን'' ሲሉ ተናግረዋል። ጋዜጠኛው ጥቃቱ በተፈፀመበት አካባቢ በነበረበት ወቅት የተኩስ ድምዕ መስማቱን ለቢቢሲ ተናግሯል። ከዚህ በተጨማሪ የጤና ባለሙያዎች ግጭቱን በመፍራት ከአካባቢ ስለሸሹ ሶስት ጤና ጣቢያዎች ሙሉ በሙሉ ሥራ እንዳቆሙ ማጣራት ችለናል። ከሶማሌ ክልል በኩል ያለውን ምላሽ ለማወቅ የደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት ሊሳካ አልቻለም። በሁለቱ ክልሎች መካከል በተከሰተው ግጭት ከአካባቢያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ55 ሺ በላይ ደርሷል።
news-53690163
https://www.bbc.com/amharic/news-53690163
የሳዑዲው ልዑል ካናዳ ውስጥ ሰው ለመግደል በማሴር ተወነጀሉ
የሳዑዲው ልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማን ቅጥረኞቻቸውን ወደ ካናዳ በመላክ የቀድሞ የሳዑዲ የደህንነት ቢሮ ባለሥልጣናንን ለመግደል አሲረዋል ተብለው ተወነጀሉ።
የከሸፈው ዕቅድ ዓላማ ሳድ አል-ጃብሪን መግደል ነበር ተብሏል። የልዑል ቅጥረኛ ገዳዮች ይህን ለመፈፀም ወደ ካናዳ ያመሩት ከጃማል ኻሾግጂ ግድያ በኋላ መሆኑን አንድ የአሜሪካ ፍርድ ቤት ተናግሯል። የሳዑዲ ደህንነት መሥሪያ ቤት ባለሥልጣን የነበሩት ጃብሪ ሃገራቸውን ጥለው ወደ ካናዳ የኮበለሉት ከሶስት ዓመታት በፊት ነበር። ሰውዬው ቶሮንቶ ውስጥ ጥብቅ ጥበቃ በሚደርግለት መኖሪያ ቤት ውስጥ ነው የሚኖሩት። ፍርድ ቤቱ እንደሚለው ግድያው ላይሳካ የቻለው የካናዳ ድንበር ጠባቂዎች ቅጥረኛ ገዳዮቹ የቶሮንቶ ፒርሰን ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያን አልፈ ሊሄዱ ሲሉ በጥርጣሬ ስለመለሷቸው ነው። የ61 ዓመቱ ጃብሪ ለዓመታት በብሪታኒያው ኤምአይ6 እንዲሁም ሌሎች ምዕራባውያን የስለላ ድርጅቶችና በሳዑዲ መካከል ያለውን ግንኙነት ሲመራ የነበረ ሰው ነው ተብሏል። 106 ገፅ ያሉት ዋሽንግተን ዲሲ ላለ ፍርድ ቤት የቀረበው ያልተረጋገጠ ክስ ልዑሉ፤ የጃብሪን ድምፅ ለማፈን ሲሉ ሊገድሉት አሲረዋል ሲል ይወነጅላል። ጃብሪ፤ ይህ ከሽፏል የተባለው ግድያ የታቀደለት 'ከባድ ምስጢር' በመያዙ እንደሆነ ይናገራል። ክሱ እንደሚያመለክተው ጃብሪ ከያዛቸው ምስጢሮች መካከል የባለሥልጣናት ሙስና ቅሌትና 'ታይገር ስኳድ' በመባል የሚታወቀው የቅጥረኛ ገዳዮች ቡድን መረጃ ነው። 'የታይገር ስኳድ' አባላት በፈረንጆቹ 2018 ቱርክ በሚገኘው የሳዑዲ ቆንስላ የተገደለው ጋዜጠኛ ጃማል ኻሾግጂን ግድያ በማቀነባበር ይወነጀላሉ። ክሱ እንደሚለው ልዑሉ፤ ሳድ አል-ጃብሪን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት የፈለጉት ሰውዬው በጣም በርካታ የሳዑዲ ባለሥልጣናትን ምስጢር ስለሚያውቁ ነው። ሳድ አል-ጃብሪ ልዑል አልጋ ወራሹ 2017 ላይ ካቀዱር ሹም ሽር በፊት ነው በቱርክ በኩል አድርገው ወደ ካናዳ የሸሹት። አል-ጃብሪ፤ "ልዑል አልጋ ወራሹ በተደጋጋሚ ወደ ሳዑዲ እንድመለስ ሙከራ አድርገዋል፤ ሌላው ቀርቶ 'ልናገኝህ ይገባል' የሚል የፅሑፍ መልዕክት ልከውልኛል" ይላል። ለፍርድ ቤቱ የቀረበው ክስ እንደሚያመለክተው የጃማል ኻሾግጂን ሰውነት በመገነጣጠል የተጠረጠረው ግለሰብ ለሬሳ ምርመራ የሚሆኑ መሣሪያዎች በሁለት ቦርሳዎች ይዞ ነበር ወደ ካናዳ ለመግባት የሞከረው። ነገር ግን የካናዳ ድንበር ጥበቃ ሰዎች የቡድኑ አባላት ላይ ጥርጣሬ በማሳደራቸው እንዳይገቡ ከለከሏቸው ይላል ክሱ። የሳዑዲ መንግሥት ስለ ክሱ እስካሁን ምንም ያለው ነገር ይለም። ሳድ አል-ጀብሪ (የተከበበው) እና የሳዑዲ መንግሥት ባለስልጣናት እአአ 2015 ላይ ለንደን በደረሱ ጊዜ በቀድሞ የዩኬ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትር ቴሬዛ ሜይ አቀባበል ሲደረግላቸው የካናዳ ሕዝብ ደህንነት ኃላፊ ቢል ብሌይርም በጉዳዩ ላይ አስተያየት መስጠት አልችልም ነገር ግን መንግሥት አንዳንድ የውጭ ኃይሎች ካናዳ ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ ሰዎች ላይ ጫና ለማሳደር እየሞከሩ እንደሆነ ያውቃል ብለዋል። ሳድ አል-ጃብሪ ለዓመታት የልዑል ሞሐመድ ቢን ናይፍ ቀኝ እጅ ነበር። አል-ቃኢዳ ወደ ሳዑዲ ዘልቆ እንዳይገባ በመመከትም ይሞገሳል። ሳዑዲ ከዩናይትስ ስቴትስ፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያ፣ ካናዳ፣ ዩናይትድ ኪንግደምና ኒው ዚላንድ ጋር ያላትን ግንኙነት በመምራትም ይታወቃል። ከኤደንብራ ዩኒቨርሲቲ በሰው ሰራሽ ልህቀት የዶክትሬት ድግሪ ያለው ሳድ አል-ጃብሪ ድምፁ ብዙም የማይሰማ የደህንነት ሰው ነው ይባልለታል። ሰውዬው በሃገር ውስጥ ሚኒስቴር የሜጀር ጄኔራል ማዕረግ መድረስ ችሏል። ነገር ግን በፈረንጆቹ 2015 ንጉስ አብዱላህ ሞተው ወንድማቸው ሳልማን ወደ መንበሩ በመምጣት ወጣቱ ልጃቸው ቢን ሳልማንን መከላከያ ሚኒስቴር አድርገው ሲሾሙ ሁሉም ነገር ተቀያየረ። በእንግሊዝኛው ምሕፃረ ቃል ኤምቢኤስ በመባል የሚታወቁት ቢን ሳልማን ደም አልባ መፈንቅለ መንግሥት አድርገው ቤተ መንግሥቱን ሲቆጣጠሩ ነው ጃብሪ ከሃገር ሸሽቶ ወደ ካናዳ የገባው።
news-50859219
https://www.bbc.com/amharic/news-50859219
የቻይና ልዑካን 'በፌደራል መንግሥት' ወደ ትግራይ እንዳይሄዱ ተከለከሉ
የትግራይ ክልል በተደጋጋሚ እያጋጠመኝ ነው ባለው ችግር ሳቢያ ከፌደራል መንግሥት ጋር ያለው ግንኙነት "በጣም አሳሳቢ" አሳሳቢ ወደ ሆነ ደረጃ እደረሰ መምጣቱን የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት ዶ/ር አብረሃም ተከስተ ለቢቢሲ ተናገሩ።
ዶ/ር አብረሃምይህንን ያሉት ከትናንት በስቲያ ለሥራ ጉብኝት ወደ ትግራይ ክልል ጉዞ ሊያደርጉ የነበሩ የቻይና የሻንሺ ግዛት ልዑካን 'በፌደራል መንግሥት ትዕዛዝ' ወደ ትግራይ ክልል እንዳይጓዙ ተደርጓል ሲል የትግራይ ክልል መንግሥት ቅሬታውን ካሰማ በኋላ ነው። በምክትል ፕሬዝደንት ማዕረግ የትግራይ ክልል የንግድ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር አብረሃም ተከስተ ለቢቢሲ ሲናገሩ፤ በቁጥር ስድስት የሆኑት አባላቱ ከቻይን ወደ ኢትዮጵያ ከመጡባቸው ምክንያቶች አንዱ ከትግራይ ክልል ጋር በልማት እና አቅም ግንባታ ዙሪያ ለመተባባር የሚያስችል ስምምነት ለመፈራረም እና ጉብኝት ለማድረግ ነበረ። ልዑካኑ ከትናንት በስቲያ ከፌደራል መንግሥት ጋር የነበራቸውን የሥራ ቆይታ አጠናቀው አመሻሹን ወደ መቀለ ለመብረር አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ከደረሱ በኋላ ወደ ትግራይ መጓዝ እንደማይችሉ ከተነገራቸው በኋላ ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ ስለመደረጉ መስማታቸውን ዶ/ር አብረሃም ይናገራሉ። • ህወሓት፡ ሃገራዊ ምርጫ የሚራዘም ከሆነ ትግራይ የራሷን ምርጫ ታካሂዳለች • የብዙ ኢትዮጵያዊያንን ህይወት እየቀየረ ያለው የተፈጥሮ ጥበቃ ሥራ "የምቀበላቸው እኔ ነበርኩ። አውሮፕላኑ በሰዓቱ ቢያርፍም እንግዶቹን ይዞ አልመጣም" ይህንንም ተከትሎ ባደረጉት ማጣራት ''የሚያስፈልገውን ጨርሰው አውሮፕላን ውስጥ ከገቡ በኋላ መሄድ እንደማይችሉ እንደተነገራቸው ነው የሰማነው" ብለዋል ዶ/ር አብረሃም። እንግዶቹ ወደ ትግራይ ክልል እንዳይጓዙ የሚከለክል ምንም ምክንያት የለም ያሉት ዶ/ር አብረሃም፤ የግዛቷ አስተዳዳሪዎች ወደ ትግራይ እንዳይሄዱ መደረጋቸውን ''ተቀባይነት የሌለው ነው" ብለዋል። ዶ/ር አብረሃም ከዚህ ቀደምም በፌደራል መንግሥት ባለሃብቶች እና የተቋማት ኃላፊዎች ወደ ትግራይ እንዳይጓዙ ጫና እንደሚደረግ ይናገራሉ። "ወደ ትግራይ ሄዳችሁ ተብለው ማስፈራሪያ የሚደርስባቸው ምሁራን፣ ተቋማት፣ ባለሃብቶች እና የውጪ ሃገር ዜጎች አሉ። ይህንንም የዚያ አካል አድርጌ ነው የማየው" ብለዋል። አክለውም "በትግራይ ህዝብ ላይ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች ይደረጋሉ። በትግራይ ህዝብ ላይም ውሸትም ጭምር በመጠቀም ሥነ-ልቦናዊ ጫና ለማሳደር ያልተደረገ ነገር የለም" ብለዋል። ወደ ትግራይ ጉዞ ሊያደርጉ የነበረው የሻንሺ ግዛት ልዑክ በግዛቷ ምክትል አስተዳዳሪ የሚመራ መሆኑን አስታውሰው፤ ልዑካኑ ወደ መቀለ መሄድ ባለመቻላቸው እሳቸው አዲስ አበባ መጥተው በግብርና፣ በኢንቨስትመንት፣ በማዕድን እና ቱሪዝም መስኮች የመግባቢያ ሰነድ አዲስ አበባ ላይ መፈራረማቸውን ዶ/ር አብረሃም ገልፀዋል። ዶ/ር አብረሃም በትግራይ ክልል እና በፌደራል መንግሥት መካከል ያለው ግንኙነት "በጣም አሳሳቢ" ሲሉ ይገለጹት ሲሆን፤ ግነኙነቱን ለማሻሻል የትግራይ ክልል ለመወያየት ሁልግዜም ቢሆን ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል። • "አሁን ያለው ሁኔታ ከቀጠለ ነገ ወደ እርስ በርስ ጦርነት እንደሚገባ ግልጽ ነው" አቦይ ስብሃት "ሁኔታዎች በጣም እየተወሳሰቡ እየሄዱ ነው። የፌደራል መንግሥቱ ይህን ቆም ብሎ ማጤን አለበት። . . . እንደ ሃገር እንድንቆም ያስቻለን ሥርዓት አለ። ይህ ሥርዓት መከበር አለበት። ያጎደልነው ነገር ካለ መጠየቅ አለብን። ሌላውም እንደዛው" ብለዋል። በትግራይ እና በፌደራሉ መንግሥት መካከል የተፈጠረውን ልዩነት በወዳጅነት እና በመቀራረብ ለመፍታት ለምን እንደተሳነ ተጠይቀው "ከአንዳንዶቹ ጋር ጓደኝነታችን እንዳለ ነው። ስንገናኝ የልብ የልባችንን እናወጋለን ይሁን እንጂ መሰረታዊ የሆነ የፖለቲካ ልዩነት ተፈጥሯል" ብለዋል። በምክትል ፕሬዝደንት ማዕረግ የክልሉ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊው ዶ/ር አብረሃም ተከስተ፤ ይህ የትግራይ ክልል እና የቻይናዋ ሻንሺ ግዛት ግንኙነት በኢትዮጵያ መንግሥት የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር አነሳሽነት የተጀመረ መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል። በጉዳዩ ላይ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴርን ምላሽ ለማግኘት በተደጋጋሚ በስልክ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። በተመሳሳይም ስለልዑካኑ ለማወቅ በኢትዮጵያ የቻይን ኤምባሲኒም ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ውጤት ሳያስገኝ ቀርቷል።
50212283
https://www.bbc.com/amharic/50212283
በግጭት ለተፈናቀሉት የተሰበሰበው አስቸኳይ እርዳታ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ
ሰሞኑን በተለያዩ አካባቢዎች በደረሱ ግጭቶች ለተፈናቀሉት የአስቸኳይ እርዳታ ማሰባሰብ በዛሬው እለት በሐገር ፍቅር ቴአትር ተጀምሯል።
ይህንን እርዳታ በማስተባበርም ላይ ያለው ከተለያዪ ቡድኖችና ግለሰቦች የተውጣጣውና ሃያ አምስት አባላትን የያዘው የሰብአዊ ድጋፍ ጥምረት የተባለ ኮሚቴ ነው። በርካታ ቦታዎች ላይ የድረሱልን ጥሪዎችን ተከትሎ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ዘመቻ የተጀመረ ሲሆን በዛሬው ዕለት ከጥዋት ሁለት ሰዓት ጀምሮ ለአስቸኳይ እርዳታ የሚውሉ ቁሳቁሶች ተሰብስበዋል። •መከፋፈል ያጠላበት ጉዞ አድዋ •"ሌቱም አይነጋልኝ" የተባለላት የውቤ በረሃ ትዝታዎች ከአስተባባሪዎቹ አንዱ የሆነው ያሬድ ሹመቴ ለቢቢሲ እንደገለፀው የማይበላሹ፣ ማደር መዋል የሚችሉ፣ የምርት ጊዜያቸው ያላለፈባቸው፣ እዛው ሊዘጋጁ የሚችሉ የእህል አይነቶች ስንዴ፣ ፓስታ፣ ፍርኖ ዱቄት፣ ማኮሮኒ፣ ሩዝ የመሳሰሉ የምግብ ጥሬ እቃዎችና የዘይት እርዳታ ተለግሷል። በተጨማሪ ደግሞ ተፈናቃዮቹ ለመኝታ የሚሆን ምንም ነገር ስለሌላቸው ብርድ ልብሶችና አልባሳትም ወደ ሐገር ፍቅር በተመሙ ነዋሪዎች ተሰጥቷል። ለህፃናት አልሚ ምግቦች፣ የንፅህና መገልገያ ቁሳቁሶች በእርዳታው ከተካተቱ ቁሶች መካከል ናቸው። በዛሬው እለትም የተሰበሰሰው ሶስት ጭነት መኪና የሚያክል ንብረት እንደሆነ ያሬድ ይናገራል። "በጣም በአስገራሚ ፍጥነት ነው ህዝቡ አለኝታ መሆኑን እያሳየ ያለው፤ በጣም የሚያኮራ ነው። አንዱ እንግዲህ ገፅታችን ይኸኛው ነው ማለት ነው። ማፈናቀሉንም እኛው ነን አፈናቃዮች፤ በደል የምንፈፅመውም እኛው ነን። በተጨማሪም ደግሞ እንዲህ እርዳታ ላይ የምንሳተፈው እኛው ነን የሚለውንም የሚያሳይ ስለሆነ ትንሽ ተስፋ የሚሰጥ ነው።" በማለት ያሬድ ያስረዳል። ኮሚቴው ተወያይቶ አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ያላቸው ስድስት ቦታዎች መርጧል። እነዚህም ምሥራቅ ሐረርጌ ጎሮ ጉቱ ወረዳ በሮዳና ካራሚሌ፣ በባሌ ሮቤ፣ በምዕራብ አርሲ ዶዶላ እና ኮፈሌ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዙሪያ ሰበታ ናቸው። በተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉና አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ያሏቸው ግለሰቦች ቁጥር የሚቀያየርና መረጃው ክፍተት ሊኖረው ቢችልም ሲሆን እስካሁን ባለው መረጃ ከአስራ አምስት ሺ የማያንስ ተፈናቃይ እንዳለ ያሬድ ያስረዳል። •የሆሊውዱ ሃኪም ገብረወልድን ያውቁታል? •በዶዶላ ቤተክርስቲያናት ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ ምዕመናን ስጋት ላይ ነን አሉ ምስራቅ ሐረርጌ ላይ መጀመሪያ የደረሳቸው ቁጥር 3ሺ ሰባት መቶ የነበረ ሲሆን በዛሬው እለት ደግሞ ወደ አምስት ሺ እንዳደገ መስማታቸውን ይናገራል። በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አማካኝነት ለሁለት ወይም ለሶስት ቀን የሚሆን አስቸኳይ እርዳታ እንደተላከ ያሬድ ጠቅሶ ከነሱ በኩል የተሰበሰበው ደግሞ ከነገ ማምሻውን ጀምሮ የሚሰራጭ ይሆናል። አስቸኳይ እርዳታውን ለማሰራጨት የመንገዱ ደህንነትና ፀጥታ ምን ያህል አስተማማኝ ነው በሚል ከቢቢሲ ለቀረበለት ጥያቄ ያሬድ ሲመልስ የትራንስፖርት አቅርቦት እንዲሁም የደህንነት ከለላ ከብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን እንደሚያገኙና በነሱም አማካኝነት እርዳታው ይላካል ይላል። እስካሁን ባለው መከላከያ አጀባ በመስጠት በመተባበር ላይ እንደሆነም ያሬድ ይናገራል። "በዚህ በኩል ብዙ ስጋት ይገጥመናል ብለን አናስብም። እነዚህን ስጋቶቻችንን ለመቅረፍ በሚል ሊያግዙንና ሊረዱን የሚችሉ አካላትን የኮሚቴያችን አባላት አድርገን ነው እየተንቀሳቀስን ያለነው" ብሏል ኮሚቴው እስከ ረቡዕ ባለው ድረስ እርዳታውን ለመቀጠል ያቀደ ሲሆን፤ በርካታ ሰው ጥያቄ እያቀረበ በመሆኑም እስከ አርብ ድረስ ሊቀጥል እንደሚችል ገልጿል።
news-52954511
https://www.bbc.com/amharic/news-52954511
የጀርመን ቡንደስሊጋ ቡድኖች ለ'ብላክ ላይቭስ ማተር' ያላቸውን ድጋፍ አሳዩ
የጀርመን ቡንደስሊጋ የእግር ኳስ ቡድኖች ለ'ብላክ ላይቭስ ማተር' እንቅስቃሴ ያላቸውን ድጋፍ በትናንትናው ዕለት በተለያዩ ተቃውሞዎች አሳይተዋል።
የብሩሲያ ዶርትሞንድና ሄርታ በርሊን ተጫዋቾች ውድድሩ ከመጀመሩ በፊት በጉልበታቸው ተንበርክከው ያላቸውን ድጋፍ አሳይተዋል። የብሮሲያ ዶርትሙንድና ሄርታ በርሊን ተጫዋቾች በሲግናል ኢዱና ፓርክ በመገኘት ሜዳውን በመክበብም በጉልበታቸው ተንበርክከው ነበር። የዶርትሙንድ ተጫዋቾች ከውድድሩ በፊት ሲያሟሙቁ "ፍትህ ከሌለ ሰላም የለም" እንዲሁም "ተባብረን እንቁም" የሚሉ መልእክቶች በተፃፈባቸው ማሊያዎች (ካናቴራዎች) ነው። የባየር ሙኒክ ተወዳዳሪዎች "ለዘረኝነት ቀይ ካርድ" የሚል ማሊያ (ካናቴራ) ለብሰው የነበረ ሲሆን፤ በዛኑ ዕለት ባየር ሌቨርኩሰንን 4 ለ2 በሆነ ውጤት ረትተዋል። የቡንደስሊጋ ቡድኑ አመራሮችም እንዲሁም የቡድኑ አባላት በጨዋታዎች ላይ 'ብላክ ላይቭስ ማተር' የሚል ፅሁፍ ያለበት እጃቸው ላይ አጥልቀው ነበር ተብሏል። የሜይንዝ ቡድን አጥቂ ካሜሮናዊው ፒየር ኩንዴ ከኤይንትራችት ፍራንክፈርት ጋር ባደረጉት ጨዋታም ላይ ጎል ካስቆጠረ በኋላ በጉልበቱ ተንበርክኳል። በግጥሚያው ቡድኑ 2 ለ0 ረትቷል። በዚህ ሳምንትም ታዋቂዎቹ የስፖርት ሰዎች ሴረና ዊልያምስ፣ ፓውል ፖግባና ሊውስ ሃሚልተን በአሜሪካ በጥቁሮች ላይ የሚፈፀመውን የፖሊስ ጭካኔ አስመልክቶ ድምፃቸውን አሰምተዋል። ባለፈው ሳምንት በሚኒያፖሊስ ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ እጁ ከኋላ እንደተጠፈረ ከመሬት ላይ ተጣብቆ ነጭ ፖሊስ አንገቱን በጉልበቱ ለዘጠኝ ደቂቃ ተጭኖት ህይወቱ ማለፉን ተከትሎ በበርካታ ግዛቶች ተቃውሞች ተቀጣጥለዋል። እንግሊዛዊው ተጫዋች ጃዶን ሳንቾኢ 'በብላክ ላይቨስ ማተር' እንቅስቃሴ ላይ በርካታ ጊዜ በሚያደርጋቸው ድጋፎች ይታወቃል የዶርሙንዱ ጎል ጠባቂ ሮማን ቡርኪ መልዕክት የባየርን ቡድን 'ለዘረኝነት የቀይ ካርድ እናሳይ" የመል መልእክት ያለው ማሊያ ለብሰው ነበር የባርን ሙኒክ ተጫዋቾች 'ብላክ ላይቭስ ማተር' የሚልም እጃቸው ላይ አጥልቀው ነበር ካሜሮናዊው ተጫዋች ፒየር ኩንዴ ጎል ካስቆጠረ በኀላ በጉልበቱ ተንበርክኮ ነበር
48960448
https://www.bbc.com/amharic/48960448
የእናቷን አስክሬን ለሦስት ዓመት ቤት ውስጥ ያቆየችው ታሠረች
አሜሪካ፣ ቴክሳስ ውስጥ አንዲት ሴት የእናቷን አስክሬን ለሦስት ዓመታት ቤቷ ውስጥ አስቀምጣ በመገኘቷ በቁጥጥር ሥር ውላለች።
ፓሊስ እንዳለው እናቷ የሞቱት ከሦስት ዓመት በፊት በ71 ዓመታቸው ነው። ከመሞታቸው በፊት ወድቀው የነበረ ቢሆንም፤ ጉዳታቸው ለሞት የሚያደርስ አልነበረም። ሆኖም ልጃቸው አስፈላጊውን እንክብካቤ ስላላደረግችላቸው ሕይወታቸው አልፏል። • ሬሳ ማቀዝቀዣ ክፍል ውስጥ እየተነፈሰች የተገኘችው ሴት በፖሊስ የተያዘችው ሴት ከልጇ ጋር በምትኖርበት ቤት ውስጥ ሁለት መኝታ ክፍል ነበራት። የእናትየዋ አስክሬን የተገኘው በአንዱ መኝታ ክፍል ወለል ላይ ሲሆን፤ ሌላኛው መኝታ ክፍል እሷና ልጇ የሚተኙበት ነበር። ከሬሳ ጋር ለሦስት ዓመት ለመኖር የተገደደችው የሴትየዋ ልጅ የ15 ዓመት ታዳጊ ስለሆነች፤ እናትየው ህጻንን አደጋ ላይ በመጣል ተከሳለች። • ከሁለት ወር በፊት ሬሳ ሳጥን ፈንቅለው የወጡት ሰው 'ዳግም' ሞቱ አሁን ልጅቷ ዘመድ ቤት ተጠግታ ትገኛለች። እናቷ የ20 ዓመት እሥርና የ10 ሺህ ዶላር ቅጣት ሊጣልባት ይችላል። ሟቿ በአካባቢያቸው ተወዳጅ ሰው ነበሩ። ለሚኖሩበት አካባቢ ጥበቃ ከማድረጋቸው ባሻገር ለ35 ዓመታት አስተምረዋል። ጡረታ ሲወጡ ደግሞ የስፖርት መርሀ ግብሮች መግቢያ ካርኒ ቆራጭ ነበሩ።
news-55285688
https://www.bbc.com/amharic/news-55285688
ትግራይ ፡ ተዘግቶ የቆው የሠሜን ኢትዮጵያ የአየር ክልል ለበረራዎች ክፍት ተደረገ
ከአንድ ወር በፊት በትግራይ ክልል የተቀሰቀሰውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ ተዘግቶ የነበረው የሠሜን ኢትዮጵያ የአየር ክልል ለዓለም አቀፍና ለአገር ውስጥ በረራዎች ክፍት መደረጉን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ለቢቢሲ አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ዋና ዳይሬክተር ወሰንየለህ ሁነኛው (ኮሎኔል) ለቢቢሲ እንደተናገሩት ከአንድ ወር በላይ ተዘግቶ የነበረው "በትግራይ ክልል በኩል የአየር ክልል ከሰኞ ታህሣሥ 5/2013 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ" ክፍት እንደተደረገ ገልጸዋል። በዚህም በሠሜን የኢትዮጵያ የአየር ክልል ውስጥ የሚያቋርጡ የዓለም አቀፍና የአገር ውስጥ የበረራ መስመሮች ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን አመልክቶ፤ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ አውሮፕላን ማረፊያዎች በረራዎችን ለማስተናገድ የተፈቀደላቸው መሆኑን ተናግረዋል። ዋና ዳይሬክተሩ ወሰንየለህ ሁነኛው (ኮሎኔል) ለቢቢሲ እንደገለጹት የአየር መስመሩ ዝግ ሆኖ በቆየባቸው ሳምንታት ውስጥ በረራዎች የተከለከለውን የአየር ክልል በመተው ሌሎች መስመሮችን ሲጠቀሙ መቆየታቸውን አመልክተዋል። የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን በሠሜን ኢትዮጵያ ለሚያቋርጡ ማናቸውም የዓለም አቀፍና የአገር ውስጥ የበረራ መስመሮች የአየር ክልሉ ለበረራ አገልግሎት ዝግ መሆኑን ለዓለም አገራት ያስታወቀው ጥቅም 25/2013 ዓ.ም ነበር። ይህም የሆነው በሠሜናዊ የኢትዮጵያ ክፍል በትግራይ ክልል ውስጥ የአገሪቱ ፌደራል መንግሥት በትግራይ ክልል ኃይሎች ላይ ወታደራዊ እርምጃ መውሰድ በጀመረ በተከታዩ ቀን ነበር። በወቅቱ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ከደኅንነት ጋር በተያያዘ የበረራ መስመሩ ለማንኛውም በረራ መዘጋቱን ባሳወቀበት ጊዜ "ማሳሰቢያ ተላልፎ በረራ የሚፈጽም ማንኛውም አውሮፕላን እንዳይኖር" በማለት በጥብቅ ማሳሰቡ ይታወሳል። ድርጅቱ በሠሜን ኢትዮጵያ ያለው የበረራ መስመር መዘጋቱን ካሳወቀ ከሁለት ቀናት በኋላ ጥቅምት 27/2013 ዓ.ም ደግሞ በትግራይ ክልል የሚገኙት የመቀለ፣ የሽሬ፣ የአክሱምና የሁመራ አውሮፕላን ማረፊያዎች ለማንኛውም የበረራ አገልግሎት ዝግ መሆናቸውን ማሳወቁ ይታወሳል። ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ምሽት በአገሪቱ ሠራዊት የሠሜን ዕዝ ላይ በህወሓት በሚመሩት ኃይሎች ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ውስጥ ወታደራዊ ግጭቶች ከመካሄዳቸው በተጨማሪ የፌደራሉ መንግሥት በወታደራዊ ኢላማዎች ላይ የአየር ድብደባ መፈጸሙን መግለጹ ይታወሳል። በተጨማሪም ሮኬቶችን ጨምሮ የከባድ መሳሪያዎች በወታደራዊ ግጭቱ ወቅት ጥቅም ላይ መዋላቸው ተነገረ ሲሆን፤ የህወሓት ኃይሎችም ከትግራይ ክልል ውጪ በባሕር ዳርና በጎንደር ከተሞች የሚገኙ የአውሮፕላን ማረፊያዎችን ኢላማ በማድረግ የሮኬት ጥቃት መሰንዘራቸውን ገልጸው ነበር። የትግራይ ክልልን ያስተዳድር የነበረው ከህወሓት ኃይሎች ጋር ለሦስት ሳምንታት በዘለቀው ተከታታይ ወታደራዊ ዘመቻ የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት በርካታ ከተሞችን ከተቆጣጠረ በኋላ የክልሉን መዲና መቀለን ኅዳር 19/2013 ሲይዝ ወታደራዊው ዘመቻ ማብቃቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ መግለጻቸው ይታወሳል። ነገር ግን የተባበሩት መንግሥታት ባለፈው ሳምንት በክልሉ ውስጥ አለ ባለው ወታደራዊ ግጭት ምክንያት የሰብአዊ እርዳታ ለተረጂዎች ለማቅረብ እንደተቸገረ ገልጾ ነበር።
news-54997629
https://www.bbc.com/amharic/news-54997629
ኮሮናቫይረስ፡በአሜሪካ በኮቪድ የሞቱ ዜጎች ቁጥር ሩብ ሚሊዮን አለፈ
የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ አሐዝ እንደሚያሳየው አሜሪካ በኮቪድ ያጣቻቸው ዜጎቿ ብዛት 250ሺ ደርሷል።
በኮቪድ የተያዙ ዜጎች ቁጥር ደግሞ 11 ሚሊዮን ተኩል አልፏል። በዓለም ላይ በዚህ ቁጥር ተህዋሲው ጉዳት ያደረሰበት ከአሜሪካ ሌላ አንድም አገር የለም። ባለፉት ሳምንታት ተህዋሲው በአዲስ መልክ አገርሽቶ መላው የአሜሪካ ግዛቶችን እያመሰ ይገኛል። በቀን የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በማሻቀቡ ባለፉት ቀናት ከ180ሺ ሰው በላይ በቀን በተህዋሲው የተያዘበት ዕለት ተመዝግቧል። ባለፈው ረቡዕ ለቢቢሲ ቃላቸውን የሰጡት የተዛማጅ በሽታዎች ሊቅ ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ "አገሪቱ በአስቸጋሪ ወቅት በተሳሳተ መንገድ እየሄደች ነው" ሲሉ አሜሪካ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ገልጸው ነበር። ይህ ወረርሽኝ የጀመረ ሰሞን የተህዋሲው ዋና መናኸሪያ የነበረችው ኒውዯርክ የተሳካ ሥራ በመስራት የተህዋሲውን ግስጋሴ መግታት ችላ ነበር። አሁን ችግሩ በማገርሸቱ ከሐሙስ ጀምሮ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ውሳኔ ላይ ደርሳለች። ዶ/ር ፋውቺ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ሰዎች ቀላል የሚመስሉ ነገር ግን የተህዋሲውን መዛመት የሚገቱ እርምጃዎችን ለመውሰድ ያመነታሉ፤ ይህ ደግሞ የተህዋሲውን መዛመት እጥፍ አድርጎታል። ጭምብል ማጥለቅ፣ እጅን ደጋግሞ መታጠብ፣ ሰዎች በበዙባቸው ቦታዎች አለመገኘት፣ ርቀትን መጠበቅ የተህዋሲውን የወረርሽኝ ግስጋሴ ይገታዋል ይላሉ ፋውቺ። ሆኖም ዜጎች ይህን ለማድረግ ተሰላቹ፣ ተህዋሲው ግን ለመዛመት አልሰለቸውም። ከወራት በፊት በመጋቢት ወር አሜሪካ 2ሺ200 ሰዎች በተህዋሲው ሞቱባት ጊዜ ከፍ ያለ ድንጋጤ ተፈጥሮ ነበር። ዶናልድ ትራምፕም ነገሩን ቢያጣጥሉትም አጣብቂኝ ውስጥ ገብተው ነበር። በዚያ ወቅት ዶ/ር ፋውቺ በዚህ ተህዋሲ በአሜሪካ 200ሺ ሰዎች ሊሞቱ ይችላሉ በሚል በመተንበያቸው ቀኝ አክራሪዎችና የትራምፕ ደጋፊዎች ሰውየውን ክፉኛ ሲተቿቸው ነበር። ይህ ሊሆን አይችሉም ያሉ በርካታዎች ነበሩ። አሁን ቁጥሩ እሳቸው ከገመቱት በ50ሺ ልቋል። ክትባት ለመፍጠር የሚጣጣሩት ፊዘር እና ባይንቴክ ትናንት ረቡዕ በሰጡት መግለጫ የፈጠሩት አዲስ ክትባት ዕድሜያቸው ከ65 እና ከዚያ በላይ በሆኑ ሰዎች የፈውስ ምጣኔው 94 ከመቶ መሆኑን ለዓለም አብስረዋል። ይህን ተከትሎም ሌላ የብስራት ዜና ከዚያ ከአሜሪካ ተሰምቷል። ሞደርና መድኃኒት አምራች የፈውስ ስኬት ምጣኔው 95 ከመቶ የሆነ ክትባት አግኝቻለሁ ብሏል። የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ከመግባቱ በፊት እነዚህ ክትባቶች ፍቃድ አግኝተው የአሜሪካንንም ሆነ የዓለምን ሕዝብ ይታደጉት ይሆን?የሚለውን የብዙዎች ተስፋ ነው።
news-44767977
https://www.bbc.com/amharic/news-44767977
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ከኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ጋር ተወያዩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በኤርትራ ጉብኝታቸው ወቅት ከኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውዲ ኢብሳ ጋር ተገናኘተው ተወያይተዋል።
የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳዉድ ኢብሳ የግንባሩ ቃል-አቀባይ አቶ ቶሌራ አደባ ለቢቢሲ እንደገለፁት ''ሁለቱ አካላት ፊት ለፈት ተገናኘተው በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከተወያዩ በኋላ በመርህ ደረጃ ተግባብተዋል'' ብለዋል። አቶ ቶሌራ ጨምረው እንደተናገሩት ሁለቱ አካላት ካገር ውጭ ውይይታቸውን ለመቀጠል ተስማምተዋል። ውይይቱ የት እና መቼ ይካሄዳል ተብሎ ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄም ውይይቱ በቅርብ ቀን እንደሚካሄድ አቶ ቶሌራ ገልፀወው ተጨማሪ መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል። የኦነግ እና መንግሥት ተወካዮች በሚገናኙበት ወቅት በበርካታ ርዕሰ ጉዳዮችም ላይ እንደሚወያያዩ አቶ ቶሌራ ተናግረዋል። ከቀናት በፊት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7 ከሽብርተኝነት ዝርዝር ማንሳቱ ይታወሳል። ምክር ቤቱ ከዓመታት በፊት እነዚህን የፖለቲካ ድርጅቶችን ጨምሮ አልቃይዳንና አልሻባብን በአሸባሪነት መፈረጁ የሚታወስ ነው። ፓርላማው የኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7 የሽብርተኝነት ፍረጃ መነሳትን አፀደቀ ከሳምንታት በፊትም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደግብፅ አምርተው ከፕሬዝዳንት አልሲሲ ጋር ከተወያዩ በኋላ የኦነግ ከፍተኛ አመራር የነበሩትን ኮሎኔል አበበ ገረሱን እና የአህዴድ መስራቸ የነበሩትን አቶ ዮናታን ዲቢሳን ወደ አገር ቤት ይዘው ገብተዋል። በግብጽ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ
news-50450487
https://www.bbc.com/amharic/news-50450487
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከህወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ሊወያዩ ነው
የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ግንባሩን በማዋሃድ ወጥ ፓርቲ ለመመስረት በቀረበለት የውህደት ዝርዝር ጥናት ላይ ተወያይቶ በስድስት ተቃውሞ በአብላጫ ድምፅ ከስምምነት ላይ መድረሱን አሳውቋል።
በስብሰባው ላይ ከተሳተፉት የግንባሩ አባል ድርጅቶች መካከል የቀረበውን ሃሳብ ተቃውመው ድምጽ የሰጡት የህወሓት አባላት ሲሆኑ ከቀድሞው የደህንነት ተቋም ኃላፊ ከአቶ ጌታቸው አሰፋ በስተቀር የህወሓት አባላት መሳተፋቸውን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አባል አቶ አስመላሽ ወልደሥላሴ ለቢቢሲ ተናግረዋል። • ኢሕአዴግ እዋሀዳለሁ ማለቱን የፖለቲካ ተንታኞች እንዴት ያዩታል? • ኢህአዴግን ያጣበቀው ሙጫ እየለቀቀ ይሆን? ውሳኔው በተሰጠበት ጊዜ ስድስት ብቻ መቃወማቸው ድምጽ በሚሰጥበት ወቅት ከተሳታፊዎች መካከል "መውጣትና መግባት" ስለነበረ በአጋጣሚ የተፈጠረ መሆኑን አቶ አስመላሽ ገልጸው በውይይቱ ሁሉም እንደተሳተፉና "በፓርቲያቸው አቋም ጸንተው መውጣታቸውን" ገልጸዋል። በዚህ ወሳኝ ድምጽ በሚሰጥበት ጊዜ ሁለቱ አባላት ያለመገኘታቸው አጠያያቂ ቢሆንም አቶ ስመላሽ በጉዳየ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል። የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የድርጅቱ ውህደትን በሚመለከቱ ቀጣይ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት ዛሬም ስብሰባውን የቀጠለ ሲሆን ውህደትን በተመለከተ የቀረበውን ሃሳብ የተቃወሙት የህወሓት አባላት ግን በዛሬው ስብሰባ ላይ እንደማይሳተፉ አቶ አስመላሽ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። • አቶ ጌታቸው አሰፋ የት ናቸው? የእስር ትዕዛዝ ወጥቶባቸዋል? • የ31 ዓመቱ ኢሕአዴግ ማን ነው? ይሁን እንጂ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ከህወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ጋር መገናኘት እንደሚፈልጉ በመግለጻቸው ከእርሳቸው ጋር እንደሚነጋገሩ አቶ አስመላሽ ጠቁመዋል። ጨምረውም ህወሓት የኢህአዴግ ውህደትን በተመለከተ ከዚህ ቀደምም አቋሙን እንዳሳወቀ አስታውሰው ነገር ግን ሂደቱ ገና ያልተጠናቀቀ በመሆኑ እስከ ድርጅቱ ጉባኤ ድረስ እንደሚቀጥል አመልክተዋል። የህወሓትን ቀጣይ ውሳኔ በተመለከተም "ከአሁን በኋላ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ በፓርቲው አቋምና አላማ ላይ ብቻ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል" ያሉት አቶ አስመላሽ በህወሓት መጻኢ ዕድል ላይ "ከፓርቲው ውጪ ሌላ ኃይል መወሰን አይችልም" ብለዋል። የውህደት እርምጃ ጅማሬ ለወራት ሲያነጋግር በቆየው የገዢው ግንባር የኢህአዴግን አባልና አጋር ፓርቲዎችን በማዋሃድ አንድ ወጥ አገራዊ ፓርቲ የመመስረት ሂደትን በተመለከተ የግንባሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ኅዳር 06/2012 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ውሳኔ ላይ መድረሱን አሳውቋል። አገሪቱን 30 ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ ሲመራ የቆየው ግንባሩ የአራት ክልላዊ ፓርቲዎች ኅብረት ሲሆን ለዓመታት ሲነሳና ሲተው የቆየውን አንድ ወጥ ውህድ ፓርቲ የመሆን ሂደትን ዕውን ለማድረግ ለወራት ሲሰራ መቆየቱን የተለያዩ የግንባሩ ባለስልጣናት ሲናገሩ ቆይተዋል። በዚህ መሰረትም 36 አባላት ያሉት የግንባሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ "የኢትዮጵያ ብልጽግና ፓርቲ" ተብሎ ይመሰረታል የተባለውን ድርጅት ዕውን ለማድረግ ያስችላል ተብሎ የቀረበለትን የውህደት ዝርዝር ጥናት ላይ ተወያይቶ በአብላጫ ድምፅ ስምምነት ላይ መድረሱን ይፋ አድርጓል። • ኢህአዴግ እዋሃዳለሁ ሲል የምሩን ነው? • "ኢህአዴግ ተዳክሟል ብላችሁ እንዳትሳሳቱ" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ይህንን ተከትሎም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ የኢህአዴግ ውህደትን በተመለከተ የተደረገው ወሳኝ ስብሰሰባ አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን ጠቅሰው "ውህደቱ የኢትዮጵያን የፌዴራል ሥርዓት ይበልጥ የሚያጠናክር፣ ተሰሚነት ላልነበራቸው አጋር ድርጅቶች እኩል ድምጽ የሚሰጥ ነው" ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጨምረውም ይህ እርምጃ "ኅብረ ብሔራዊነትን የሚያጸና፣ አካታችነትንና ፍትሃዊ ውክልናን የሚያረጋግጥ ሁነኛ አቅጣጫ ነው። የፓርቲው ውሕደት አገራዊ አንድነትን ከኅብረ ብሔራዊነት ጋር አስተሳስሮ ለመጓዝ ዕድል" እንደሚሰጥ ጠቁመዋል። የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ስብሰባውን ባደረገበት ጊዜ ከአራቱ የግንባሩ አባላት በተጨማሪ አጋር የተባሉት የሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የአፋር ብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄና የሐረሪ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ካለድምጽ ተሳትፈዋል። • ህወሓት: "እሳትና ጭድ የሆኑ ፓርቲዎች ሊዋሃዱ አይችሉም" • "ኢህአዴግ ነፃ ገበያም፣ ነፃ ፖለቲካም አላካሄደም" ፀደቀ ይሁኔ (ኢንጂነር ) የግንባሩን ውህደት በተመለከተ የተለያዩ ጉዳዮች ተነስተው ውይይት መደረጉ የተገለጸ ሲሆን በማስከተልም በስብሰባው ላይ የተገኙ የአራቱ የግንባሩ አባላት በቀረበው ሃሳብ ላይ ድምጽ ሰጥተው በስድስት ተቃውሞ በድምጽ ብልጫ ከውሳኔ ላይ መድረሳቸው ተገልጿል። በሥራ አስፈጻሚው ስብሰባ ላይ በሰባት አባላቱ የተወከለውና ቀደም ሲል ጀምሮ በውህደቱ ሂደት ላይ ጥያቄዎችን ሲያቀርብ የነበረው የግንባሩ አንጋፋ መስራች የህወሓት ስድስት አባላት ውሳኔውን እንደተቃወሙት ተነግሯል። ሰባተኛው ተሳታፊ በውሳኔው ላይ የያዙት አቋም እስካሁን ምን እንደሆነ አልታወቀም። ውህዱ ፓርቲ ምን ይዞ ይመጣል? የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ አባል የሆኑት አቶ ፍቃዱ ተሰማ ከውሳኔው በኋላ ለብሔራዊው ቴሌቪዥን በሰጡት ማብራሪያ በስብሰባው ላይ አሁን ስላለው ፌደራላዊ አስተዳደር፣ ቋንቋ፣ የብሔርና አገራዊ ማንነት፣ ፍትሃዊ ውክልናንና በሌሎች ጉዳዮች ላይ በዝርዝር መወያየቱን ገልፀዋል። በዚህም መሰረት የአዲሱ ውህድ ፓርቲ ዋነኛ ምሰሶ የሚሆኑትን በአምስት ነጥቦች አስቀምጠውታል። 1. ሕብረ ብሔራዊ ፌዴራላዊና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ይህም በፓርቲው ሕገ ደንብና ፕሮግራም ውስጥ እንደሚካተት። 2. የክልሎች እራስን በራስ የማስተዳደርና የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ሕገ መንግሥታዊ መብት እንደሚከበር። 3. አጋር ድርጅቶችን ጨምሮ ሁሉንም ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ያካተተና ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖራቸው እንደሚደረግ። 4. የብሔር ማንነትና አገራዊ አንድነት ተጠናክሮ ለማስቀጠል ብሔራዊ ማንነትና አገራዊ አንድነትን አስማምቶ የአገሪቱ ፖለቲካ መምራት። 5. የቋንቋ ብዝሐነትን በመቀበል ተጨማሪ የሥራ ቋንቋን በፓርቲ ደረጃ ቀጣዩ ውሳኔ ከማን ይጠበቃል? የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የግንባሩን ውህደት በተመለከተ ጉዳዩ እዚሁ ላይ የሚጠናቀቅ ሳይሆን በዓመት ሁለት ጊዜ ለሚካሄደው የድርጅቱ ምክር ቤት ይቀርባል። ምክር ቤቱ ከአራቱ ድርጅቶች የተወጣጡ 180 አባላት ያሉት ሲሆን ቁልፍ የሚባለው ውሳኔን የመስጠት ስልጣን አለው። ይህ ሂደት በመጨረሻም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የአራቱም ድርጅቶች ተወካዮች ለሚመክሩበት የኢህአዴግ ጠቅላላ ጉባኤ ይቀርብና የውህደቱ ጉዳይ የመጨረሻውን መቋጫ ሲያገኝ አገር አቀፉ ውህድ ፓርቲ አውን ይሆናል።
news-54193885
https://www.bbc.com/amharic/news-54193885
ሀሪኬን ሳሊ፡ በአሜሪካ ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ንፋስ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎችን ያለ መብራት አስቀረ
በተለያዩ አገራት የተፈጥሮ አደጋዎች በርካቶችን ለችግር እየዳረገ ነው። እዚህ እኛ አገርም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በጎርፍ ሳቢያ ተፈናቅለዋል፤ ንብረቶችም ወድመዋል።
በአሜሪካም ሳሊ በተባለ ንፋስ በቀላቀለ ዝናብ ሳቢያ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ አሜሪካዊያን ያለ መብራት ቀርተዋል። ለሕይወታቸውም ሰግተዋል። ሳሊ ባስከተለው በዚህ ከባድ ዝናብና ማዕበል የአሜሪካ ባህር ዳርቻዎች ክፉኛ ተመትተዋል። ቀስ እያለ የሚጓዘው ንፋስ የቀላቀለው ዝናብ ፍሎሪዳና አላባማ ግዛቶችን መምታቱን ቀጥሏል። በአደጋውም የአንድ ሰው ሕይወት ያለፈ ሲሆን በመቶዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በጎርፍ ከተጥለቀለቁ አካባቢዎች እንዲወጡ ተደርገዋል። በፍሎሪዳ የምትገኘው ፔንሳኮላም ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባት ሲሆን፤ በጎርፉ የተወሰደ መርከብ በባህሩ ላይ የተገነባውን የቤይ ድልድይን የተወሰነ ክፍል እንዲደረመስ አድርጎታል። የብሔራዊ ሄሪኬን ማዕከል "ድንገተኛ አደጋ የሚያስከትልና ለሕይወት አስጊ የሆነው ጎርፍ፤ በፍሎሪዳዋ ፓንሃንድል እና ደቡባዊ አላባማ አሁንም እንደቀጠለ ነው" ብሏል። የፔንሳኮላ የድንገተኛ አደጋ ኃላፊ ጊኒ ክራኖር በበኩላቸው፤ አውሎ ንፋስ የቀላቀለው ይህን ክስተት "በከተማዋ ላይ የ4 ወራትን ዝናብ በአራት ሰዓታት ያወረደ ነው" ሲሉ ለሲ.ኤን.ኤን. ተናግረዋል። በአላባማ ኦሬንጅ የባህር ዳርቻም በአደጋው አንድ ሰው የሞተ ሲሆን ሌላኛው የደረሰበት አለመታወቁን የከተማዋ ከንቲባ ገልፀዋል። ከንቲባው የሰጡት ተጨማሪ ማብራሪያ ግን የለም። ሳሊ በሰዓት 169 ኪሎሜትር እየተምዘገዘገ በአላባማ ግዛት ባህር ዳርቻዎች የደረሰው ረቡዕ ዕለት ነበር። እንደ ኤን.ኤ.ኤስ. ከሆነ ሁለተኛው ምድብ ሄሪኬን ያለማቋረጥ ንፋስ ይዞ የሚጓዘው በሰዓት ከ96 እስከ 110 ሜትር ነው። በዚህ ምድብ የሚገኘው ሄሪኬን፤ በጣም አደገኛ የሆነ ንፋስ ሲሆን በአብዛኛውም በቤቶች እና ጥልቅ ሥር በሌላቸው ዛፎች ላይ ጉዳት ያስከትላል ብሏል ማዕከሉ። ሳሊ በአትላንቲክ ውቅያኖስ አካባቢ ከሚከሰቱ ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ አንዱ ነው።
news-50731122
https://www.bbc.com/amharic/news-50731122
"ኢትዮጵያ ኢንተርኔት ማቋረጧን ማቆም አለባት" የተመድ ከፍተኛ ባለሙያ
አንድ የተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ የንግግር ነጻነት ባለሙያ ኢትዮጵያ ያለ ሕጋዊ መሠረት ኢንተርኔት ማቋረጧን ማቆም ይኖርባታል ሲሉ ተናገሩ። አክለውም ረቂቅ የጥላቻ ንግግር ሕጉ የመናገር ነፃነትን እንዳይገድብ ዳግመኛ ልታጤናው ይገባል ብለዋል።
ዴቪድ ኬይ በተባበሩት መንግሥታት የንግግር ነጻነት ከፍተኛ ባለሙያ ሲሆኑ ከሮይተርስ ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ ወቅት በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ አድንቀው፣ ለውጡን ያደናቅፋል ያሏቸውን ዘርዝረዋል። እርሳቸው እንደሚሉት ምንም እንኳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ሀሳብን በነጻነት መግለጽ የሚያበረታታ እርምጃ ቢወስዱም ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት ብቻ ኢንተርኔትን በተደጋጋሚ አቋርጣለች ብለዋል። • ኢትዮቴሌኮም ኢንተርኔት ለምን እንደተቋረጠ መግለፅ እንደማይችል አስታወቀ • የአማራ ሕዝብ የወሰንና ማንነት ጥያቄዎች የክልሉ መንግሥትም ጥያቄዎች መሆናቸው ተገለፀ "መንግሥት አሁንም ኢንተርኔትን መዝጋት እንደመሳሪያ እየተጠቀመ ይገኛል። እኔ ግን መንግሥት ይህንን እንዳያደርግ አጥብቄ እመክራለሁ" ማለታቸውን ሮይተርስ አስነብቧል። ሚስተር ኬይ በአስር ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያን የጎበኙ የመጀመሪያው የተባበሩት መንግሥታት የንግግር ነጻነት ባለሙያ መሆናቸውም ተገልጿል። እኚህ ባለሙያ ኢትዮጵያ የመናገርን ነጻነት በማክበር ረገድ ረዥም ርቀት ሄዳለች ሲሉ ተናግረው "ቢሆንም ግን ይህ በርካታ የሕግና የፖሊሲ ድጋፎችን የሚፈልግ ረዥም ዓመት የሚፈጅ ሂደት ነው" በማለት ቀጣይነት ያለው የሕዝቦች ተሳትፎና የሰብዓዊ መብት ምልከታ እንደሚያስፈልገው ተናግረዋል። ኬይ አክለውም እየተረቀቀ ያለው የጥላቻ ንግግር ሕግ የለውጡን ሂደት እንዳያደናቅፈው ያላቸውን ስጋት አስቀምጠዋል። ኬይ የጥላቻ ንግግርንና ሐሰተኛ ዜናዎችን ለመገደብ የሚደረገውን ጥረት አድንቀው፣ የጥላቻ ሕግ ረቂቁ ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን እንዳይገድብ ስጋት አለኝ ብለዋል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት የጥላቻ ሕጉን ረቂቅ አጽድቆ ወደ ተወካዮች ምክር ቤት የመራው በዚህ ወር ነበር። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም ወደ የሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራቱ ይታወሳል። ኬይ ከዚህ ቀደም የተነሳውን የጸረ ሽብር ሕጉን በእንዲህ ዓይነት አፋኝ ሕግ ለመተካት መሞከር " በቀጣይ ሂደቶች ላይ የሕዝብ አመኔታን የሚሸረሽር" ነው ሲሉ ገልጸውታል። ዴቪድ ኬይ ሃሳብን በነፃ መግለፅ መብትን በተመለከተ በአዲስ አበባ መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል።
news-52703736
https://www.bbc.com/amharic/news-52703736
የዓለም ጤና ድርጅት ጉባዔ፡ ኮሮናቫይረስን በተመለከተ ምርመራ እንዲደረግ አገራት ጥያቄ ያቀርባሉ ተባለ
የምድራችን የጤና ባለሥልጣናት ዓለም ኮሮናቫይረስን በተመለከተ እስካሁን የተወሰደው እርምጃ ላይ ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የዓለም ጤና ድርጅት 194 አባል አገራት ተወካዮች ዛሬና ነገ [ሰኞና ማክሰኞ] የኮሮናቫይረስ ወረርሸኝን ዋነኛ አጀንዳቸው አድርገው በኢንተርኔት አማካይነት 73ኛ ጉባኤያቸውን ያካሂዳሉ። በዚህም ጉባኤ ላይ በመላው ዓለም ከ300 ሺህ በላይ ሰዎችን በቀጠፈው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዙሪያ የዓለም ጤና ድርጅትና አባል አገራቱ የወሰዱት እርምጃ ላይ ጥያቄዎች ይነሳሉ ተብሏል። በየዓመቱ አባል አገራት በዓለም የጤና ድርጅት ጉባኤ ላይ እየተገኙ የድርጅቱን ሥራዎች በመገምገም በቀጣይ ዓመት የቅድሚያ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮችን ይወስናሉ። የአውሮፓ ሕብረት ከዩናይትድ ኪንግደም፣ ከአውስትራሊያና ኒው ዚላንድ ጋር በመሆን ዓለም አቀፉ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመቆጣጠር ስለተወሰዱ እርምጃዎች ምርመራ እንዲደረግና ከዚህ በሽታ ምን ትምህርት እንደሚወሰድ የሚነሳውን ጥያቄ በመሪነት ያቀርባል ተብሏል። የአውሮፓ ሕብረት ቃል አቀባይም በሚደረገው ግምገማ ላይ መመለስ ያለባቸው በርካታ ጥያቄዎች እንዳሉ ተናግረዋል። ጨምረውም "አንዱ አንዱን ለመወንጀል ጊዜው አይደለም" ሲሉም ተናግረዋል። ነገር ግን በዚህ ጉባኤ ላይ የዓለም ጤና ድርጅት ወረርሽኙን በተመለከተ በወሰዳቸው እርምጃዎች ሳቢያ በርካታ ጥያቄዎች እንደሚነሱበት ይጠበቃል። ይህንን በተመለከተ የዓለም ጤና ድርጅት ቃል አቀባይ ዶክተር ማርጋሬት ሃሪስ እንዳሉት "ይህ ጉባኤ ሁልጊዜም በርካታ ጥያቄዎች ለድርጅቱ የሚቀርብበት ነው" ሲሉ የዘንድሮው አዲስ ነገር ሊሆን እንደማይችል አመልክተዋል። የዓለም ጤና ድርጅት የሁሉንም አባል አገራት ጥቅምን በእኩል ደረጃ ይወክላል ተብሎ የሚታሰብ ቢሆንም፤ በአሁኑ ጊዜ ግን በቻይናና በአሜሪካ መካከል ባለው ፖቲካዊ ፍጥጫ ምክንያት አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል። በዚህም ፕሬዝዳንት ትራምፕ ድርጅቱን በሽታውን በአግባቡ ባለመያዝና ቻይና ውስጥ የተከሰተውን ወረርሽኝ በመሸፋፈን ከከሰሱ በኋላ ባለፈው ወር ለዓለም የጤና ድርጅት ከፍተኛውን ገንዘብ የምታበረክተው አሜሪካ ድጋፏን እንድታቋርጥ ምክንያት ሆኗል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አካል የሆነው የዓለም የጤና ድርጅት፤ አባል አገራቱ በጤና ጉዳዮች ላይ ያላቸውን መረጃ እንዲያጋሩ የሚያስገድድ ሥልጣን የሌለው ቢሆንም አሜሪካ ከቻይና አንጻር ድርጅቱን እየከሰሰች ነው። በአሁኑ ጉባኤ ላይ ግን ድርጅቱ ወረርሽኞች ወደሚከሰትባቸው በመግባት ገለልተኛ ምርመራ እንዲያደርግ የሚያስችለው ተጨማሪ ሥልጣን እንዲሰጠው ጥያቄ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል። በዓለም አቀፍ የጤና ደንብ መሰረት አገራት በግዛታቸው ውስጥ የሚከሰቱ በሽታዎችን ለድርጅቱ ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል። ዓለምን አስጨንቆ ያለው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ባለፈው ታህሳስ ወር ላይ ቻይና ውስጥ ከተቀሰቀሰ በኋላ ከ4.5 ሚሊዮን ሰዎች በላይ በበሽታው ተይዘዋል። ይህ ጉባኤም የሚካሄደው በሽታውን በተመለከተ ኃያላኑ አሜሪካና ቻይና እየተወዛገቡ ባሉበት ጊዜ ነው።