id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
50429568
https://www.bbc.com/amharic/50429568
ያለታካሚዎች ፈቃድ ቀዶ ህክምና ያደረገው የማህጸን ሀኪም ተከሰሰ
ታካሚዎቹ የማያስፈልጋቸውን ቀዶ ህክምና ያለ ፈቃዳቸው አድርጓል የተባለ የማህጸን ሀኪም ቨርጂንያ ውስጥ ተከሰሰ።
ሀኪሙ ታካሚዎቹ የማያስፈልጋቸውን ቀዶ ህክምና ያለ ፈቃዳቸው አድርጓል ተብሏል ዶ/ር ጃቪድ ፐርዌዝ የተባለው ሀኪም፤ ህመም የሌለባቸው ሴቶችን 'ታማችኋል' በማለት ከፍተኛ ጉዳት እንዳደረሰ የአሜሪካው የምርመራ ተቋም ኤፍቢአይ አሳውቋል። ሀኪሙ ባለፈው ጥቅምት በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ ከ126 በላይ ሴቶች ጉዳት አድርሶብናል ብለዋል። የ69 ዓመቱ ሀኪም ሀሰተኛ መረጃ በመስጠትና በማጭበርበር ክስ ተመስርቶበታል። • 'ሀሰተኛ' የተባለችው ሀኪም ታሰረች • የአትሌቲክስ ቡድን ሀኪም 177 አትሌቶች ላይ ወሲባዊ ጥቃት አድርሷል ተባለ • የጡት ካንሰር የያዛት የጡት ካንሰር ሀኪም ኤፍቢአይ እንዳለው፤ ቨርጂንያ ውስጥ ሁለት ቢሮ ያለውና በሌሎች ሁለት ሆስፒታሎች የሚሠራው ሀኪሙ፤ ከታካሚዎች እውቅናና ፈቃድ ውጪ ቀዶ ህክምና ያደርግ ነበር። እንደ ጎርጎሮሳውያ አቆጣጠር ከ2014 እስከ 2018 ድረስ፤ በመንግሥት ድጋፍ ህክምና ካደረጉ ሴቶች በ40 በመቶ ያህሉ ያለ ፈቃዳቸው ቀዶ ጥገና አድርጓል። ከ510 ታካሚዎቹ፣ 42 በመቶው ቢያንስ ሁለት ጊዜ ቀዶ ህክምና ተደርጎባቸዋል። ኤፍቢአይ ስለ ሀኪሙ መረጃ ያገኘው 2018 ላይ ነበር። ከሀኪሙ ጋር በአንድ ሆስፒታል የሚሠራ ግለሰብ ጉዳዩን ከታካሚዎች ከሰማ በኋላ ለኤፍቢአይ ጠቁሟል። አንዲት ሴት ሀኪሙ በማህጸኗ ባደረገው ቀዶ ህክምና ሳቢያ መጸነስ እንደማትችል መግለጿን ኤፍቢአይ አስታውቋል። የኤፍቢአይ መርማሪ ዴዝሬ ማክስዌል እንዳሉት፤ ሀኪሙ ታካሚዎች ካንሰር እንደያዛቸው በማሳመን ቀዶ ህክምና ያደርግም ነበር። የሀኪሙ ጠበቃ ሊውረንስ ዉድዋርድ ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ አልሰጡም። ዶ/ር ጃቪድ ፐርዌዝ ፓኪስታን ውስጥ ህክምና አጥንቶ በአሜሪካ፣ ቨርጂንያ የሥራ ፈቃድ አግኝቷል። ከዚህ ቀደምም አላስፈላጊ ቀዶ ህክምናዎች በማድረግ ቨርጂንያ ውስጥ ምርመራ ሲደረግበት ነበር። 1996 ላይ ግብር በማጭበርበር ለሁለት ዓመት ከሥራ ታግዶም ነበር።
news-54520003
https://www.bbc.com/amharic/news-54520003
አፍሪካ፡ በናይጄሪያ የፖሊስ ጭካኔን ለመቃወም በተጠራው ሰልፍ ላይ ሁለት ሰዎች ተገደሉ
የፖሊስን የጭካኔ በትር መቋቋም አልቻልንም ያሉ ናይጄሪያውያን ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ስድስተኛ ቀናቸውን ይዘዋል።
በናይጄሪያ ትልቋ ከተማ ሌጎስ በነበረው የተቃውሞ ሰልፍ ላይም አንድ ፖሊስና ሰላማዊ ዜጋ ተገድለዋል። ፖሊስ ቀጥታ በሰልፈኞቹም ላይ ጥይት ተኩሷል የሚሉ ሪፖርቶችም እየወጡ ነው። እነዚህ ተቃውሞዎች በተለይም ዘረፋን ለማስቆም የተቋቋመውን ልዩ የፌደራል ፖሊስ ክፍል ወይም ሳርስ ተብሎ የሚታወቀው ላይ ያነጣጠሩ ናቸው። ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ሰዎችን ማሰር፣ ማሰቃየትና ግድያም ይፈፅማል በሚልም ከፍተኛ ውግዘትም የቀረበበት ሳርስ እንዲበተን ተደርጓል። ሆኖም የሳርስ አባላት በሌሎች የፖሊስ ክፍሎች እየተሰማሩና እየተመደቡ ነው የሚሉ ጉዳዮች መሰማታቸውን ተከትሎም እንደገና ተቃውሞቹ የቀጠሉት። ሰልፈኞቹ እነዚህ የሳርስ አባላት ለፈፀሙት ወንጀል ህግ ፊት መቅረብ አለባቸውም እያሉ ነው። ይህንንም ተከትሎ በተጋጋለው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ በርካታ ተቃዋሚዎችና ፖሊስ እንደተጋጩም የቢቢሲ ዘጋቢ አይዛክ ካሊድ ከመዲናዋ አቡጃ ዘግቧል። በትልቋ ከተማም ሌጎስ ሱሩሌ በሚባለው አካባቢ ፖሊስ በትናንትናው እለት ጥይት እንደተኮሰም ገልጿል። አንዳንድ ሰልፈኞች በፖሊስ ላይ ድንጋይ መወርወራቸውንም ተከትሎ ፖሊስ " የታጠቁ ሰልፈኞች" ናቸው በማለት ፈርጇቸዋል። አንድ ፖሊስ መሞቱንና ሌላኛው ደግሞ ክፉኛ መጎዳቱንም ፖሊስ አስታውቋል። ከዚህም በተጨማሪ በተቃውሞ ሰልፉ ላይ የሞተው የ55 አመቱ ሰላማዊ ግለሰብ ሞት ላይ ኃላፊነቱ የማን ነው በሚል የሌጎስ ፖሊስና ሰልፈኞች እየተወዛገቡ ይገኛሉ። የፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ረዳት በበኩላቸው በሰልፈኞቹ ላይ ጥይት መተኮሱን አውግዘዋል። የሌጎስ አየር መንገድን መንገድ የዘጉ ሰልፈኞችንም ለመበተን የታጠቁ ወታደሮችና መኪኖች እንደሚሰማሩም ሪፖርቶች እየወጡ ነው። ከሰሞኑ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት "ስር ነቀል" የፖሊስ ማሻሻያ እንደሚደረግና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈፅመዋል የተባሉትም የሳርስ አባላት ወደ ፍርድ ይቀርባሉ ብለው ነበር። ሆኖም በትናንንትናው ዕለት ፖሊስ በሰልፈኞች ላይ ጥይት መተኮሱ የነበረውን ተቃውሞ የበለጠ ሊያቀጣጥለው እንደሚችልም የቢቢሲ ዘጋቢ ይናገራል። ፕሬዚዳንቱ ሰኞ እለት ባስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክት ሳርስን መበተን የመጀመሪያ ሂደት ሲሆን ሌሎች ማሻሻያዎች ይኖራሉ ብለዋል። ሆኖም የፖሊስ አባላቱ ጠንካራ ሰራተኛ እንደሆኑ ገልፀው በጥቂት መጥፎ ፖሊሶች ምክንያት አጠቃላይ የፀጥታ ኃይሉ ስም ሊጠለሽ አይገባም ብለዋል። የናይጄሪያ ፖሊስ ኃላፊ መሃመድ አዳሙ በበኩላቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ያደረሱ ፖሊሶች የሲቪል ማህበረሰቡን ጨምሮ ከሌሎች አካላት በተዋቀረ ኮሚቴ ማጣራት ይደረጋል ብለዋል።
news-45339785
https://www.bbc.com/amharic/news-45339785
ትራምፕ ከፌስቡክ፣ ትዊተርና ጉግል ጋር ጦርነት ገጥመዋል
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከማሕበራዊ ድር አምባዎቹ ከፌስቡክና ትዊተር እንዲሁም ጉግል ጋር ጦርነት ገጥመዋል። ስለኔ ሚዛናዊ የሆነ ዘገባ እያቀረቡ አይደለም በማለትም እየከሰሷቸው ይገኛሉ።
ትራምፕን በተመለከተ ዜና ብለው ለሚፈልጉ ሰዎች የተዛባ መረጃ እያቀረበ ነው ያሉትን ጉግል «ቢጠነቀቅ ይሻላል» ሲሉ ዛቻ ሰንዝረዋል። «አስተዳደሬ መሰል የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ላይ ቁጥጥር ከማድረግ ወደኋላ አይልም» ሲሉም ተደምጠዋል። የጉግል ሰዎች በበኩላቸው የመፈለጊያ ዘዴዎቻችን ከማንኛውም የፖለቲካ አጀንዳ የፀዱ እና ሚዛናዊ ናቸው ሲሉ የአፀፋ ምላሽ ሰጥተዋል። ለመገናኛ ብዙሃን ቃላቸውን የሰጡት ትራምፕ «ጉግል ሰዎችን መጠቀሚያ እያደረገ ነው፤ ይህን ጉዳይ አቅልለን የምናየውም አይደል» ብለዋል። አክለውም ትዊተር እና ፌስቡክ የተባሉት የማሕበራዊ ድር አምባዎችም «ቢጠነነቁ ነው የሚሻላቸው» የሚል ማስፈራሪያ ጣል አድርገዋል። «በርካታ ሺህ ቅሬታዎች እየዘነቡ ነው፤ በሰዎች ላይ ይህን ማድረግም ተገቢ አይደለም» የትራምፕ ሃሳብ ነው። ሰውየው ምን ዓይነት እርምጃ ሊወስዱ እንደሚችሉ ግን ፍንጭ አልሰጡም። የፕሬዝደንቱ ምጣኔ ሃብት አማካሪ የሆኑ ግለሰብ ግን «ጉግል ላይ ምርመራ እያካሄድን ነው፤ አስፈላጊውን እርምጃም እንወስዳለን» የሚል አስተያየት ሰንዝረዋል። በዘርፉ ጥርስ የነቀሉ ተንታኞች ግን የትራምፕ ክስ ውሃ አያነሳም ይላሉ፤ ማስረጃ ለማቅረብ እንደሚከብዳቸውም ያስረዳሉ።
news-55328492
https://www.bbc.com/amharic/news-55328492
ፑቲን ለጆ ባይደን የዘገየ የእንኳን ደስ አለዎት መልእክት አስተላለፉ
ቭላድሚር ፑቲን ለጆ ባይደን የዘገየ የእንኳን ደስ አለዎት መልእክት አስተላለፉ
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከዓለም መሪዎች በጣም ዘግይተው ለተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የእንኳን ደስ አለዎት መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ በሩሲያ የፕሬዝዳንቱ ጽሕፈት ቤት፣ ክሬምሊን፣ የኅዳሩ ምርጫ አሸናፊው በውል እስኪለይ ድረስ ዝምታን እንደሚመርጥ አስቀድሞ ገልጾ ነበር፡፡ አሁን ፑቲን እንኳን ደስ አለዎ የሚለውን መልእክት ያስተላለፉት የግዛት ድምጽ ተወካዮች (ኤሌክቶራል ኮሌጅ አባላት) ተሰብስበው የጆ ባይደንን አሸናፊነት ትናንት ማወጃቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ባይደን ከ50 ግዛቶች 306 የወኪል ድምጽ ሲያገኙ ትራምፕ ግን 232 ላይ መቆማቸው ይታወሳል፡፡ በአሜሪካ የምርጫ አሰራር 270 እና ከዚያ በላይ የወኪል ድምጽ ያገኘ እጩ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ተብሎ ይጠራል፡፡ ያም ሆኖ ዶናልድ ትራምፕ እስከዛሬም ተሸናፊነታቸውን በይፋ አልተቀበሉም፡፡ ከወዳጆቻቸው ጭምር መሸነፋቸውን ጨክነው እንዲቀበሉ ውትወታው ቢበረታባቸውም ሽንፈት ሞት ሆኖባቸዋል፡፡ በአሜሪካ ሴኔት አብላጫ ወንበር መሪ ተወካይ ሪፐብሊካኑ ሚች ማኮኔል ለመጀመርያ ጊዜ ባይደንን እንኳን ደስ አለዎት ማለታቸው ዛሬ ተዘግቧል፡፡ እኚህ የትራምፕ ወዳጅ ዝምታውን መስበራቸው ትራምፕ ባይደንን የማቆም ዕድላቸው ስለመሟጠጡ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል፡፡ ዶናልድ ትራምፕ ምርጫው ተጭበርብሯል በሚል በዋና ዋና ግዛቶች ላይ እሳት የላሱ ጠበቆቻቸውን በማዝመት የክስ ዶሴ ማስከፈታቸው አይረሳም፡፡ ትራምፕ የሽንፈትን ጽዋ ለመቅመስ አሻፈረኝ ይበሉ እንጂ የአሜሪካ ምርጫ በተደረገ በሳምንት ውስጥ አብዛዎቹ የዓለም መሪዎች ለጆ ባይደን የመልካም ምኞች መግለጫ ልከዋል፡፡ ቭላድሚር ፑቲን ግን ይህ እንዲዘገይ አድርገዋል፡፡ ባይደንና ፑቲን ኦባማ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ከነበሩበት ዘመን ጀምሮ ግንኙነታቸው የሻከረ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ተመራጩን ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንን ዘግይተው ‹ሹመት ያዳብር› ለማለት ከፑቲን ሌላ የሜክሲኮው ፕሬዝዳንት ሎፔዝ ኦብራዶር ይጠቀሳሉ፡፡ ውዝግብ የማያጣቸው የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ዣዪር ቦልሶናሮን እንዲሁ ለጆሴፍ ባይደን መልካም ምኞት ለመግለጽ የዘገዩ መሪ ሆነዋል፡፡ እነዚህ ሦስቱ መሪዎች ከዶናልድ ትራምፕ ጋር በአገር ደረጃ ብቻም ሳይሆን በግልም ጠበቅ ያለ ግንኙነት የነበራቸው በመሆናቸው ምናልባት ቀደም ብለው ለጆ ባይደን መልካም ምኞች ቢያስተላልፉ ትራምፕን ማስቀየም ይሆንብናል ብለው ሰግተው የቆዩ እንደሆኑ ተገምቷል፡፡ ክሬምሊን ባወጣው የመልካም ምኞች መግለጫ ፑቲን ከአዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጋር በትብብር ለመሥራት ዝግጁ ስለመሆናቸው ገልጾ ለባይደን መልካም የሥራ ዘመንን ይመኛል፡፡ ‹‹በተለይ ሩሲያና አሜሪካ የዓለምን ደኅንነትና ሰላምን ለመጠበቅ ልዩ ኃላፊነት ያለባቸው አገራት እንደመሆናቸው ልዩነታቸው እንዳለ ሆኖ ብዙ ችግሮችን በመቀራረብ መፍታት እንደሚችሉ እናምናለን›› ይላል የመልካም ምኞቹ ሙሉ ቃል፣ አንድ አንቀጽ፡፡ ጆ ባይደን ትራምፕ አቅብጠዋቸዋል በሚባሉት ፑቲን ላይ ጠበቅ ያለ የዲፕሎማሲና የንግድ እቀባ እርምጃዎችን ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ እስከ አሁን ለጆ ባይደን እንኳን ደስ አለዎ የሚል መልእክት ያላስተላለፉት መሪ የሰሜን ኮሪያው ኪም ጆንግ ኡን ናቸው፡፡
54144151
https://www.bbc.com/amharic/54144151
ኢኮኖሚ፡ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የ200 ብር ኖት ይፋ አደረገች
ኢትዮጵያ በገበያ ላይ ባሉት የወረቀት ገንዘቦቿ ላይ ለውጥ ስታደርግ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በወረቀት ገንዘቧ ውስጥ ባለ 200 ብር ኖቶችን መጠቀም ጀመረች።
ይህ ይፋ የሆነው ዛሬ [ሰኞ መስከረም 04/2013] ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በትዊተር ገጻቸው በኩል ባስተላለፉት መልዕክትና የብር ኖቶቹ ምሰል ነው። በዚህም መሠረተው ከዛሬ ጀምሮ አገሪቱ የ10፣ 50 እና 100 ብር ኖቶቿን ስትቀይር ከዚህ በፊት ያልነበረው የ200 ብር ኖትን ደግሞ መጠቀም ጀምራለች። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት አዲሶቹን የገንዘብ ኖቶች ይፋ መድረግ ያስፈለገው ለሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎች የሚደረግን ድጋፍ፣ ሙስናንና የኮንትሮባንድ ሥራዎችን ለመቆጣጠር ያግዛሉ።በተጨማሪም አዲሶቹ የገንዘብ ኖቶች እንዲኖራቸው የተደረጉት የደኅንነት ገጽታዎች አመሳስሎ ሐሰተኛ የገንዘብ ኖቶችን ለማተም የሚደረጉ ሕገ ወጥ ጥረቶችንም ለማስቀረት እንደሚግዙ ተጠቁሟል። በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ የሚገኙት የብር ኖቶች ወደ ዝውውር እንዲገቡ የተደረጉት ከ23 ዓመት በፊት በ1990 ዓ.ም ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትን ተከትሎ እንደነበረ ይታወሳል። ከአጼ ኃይለ ሥላሴ አስተዳደር ዘመን ጀምሮ በኢትዮጵያ ሥራ ላይ በነበሩ የገንዘብ የወረቀት ገንዘቦች ላይ በተለያዩ ጊዜያት ለውጥ የተደረገ ሲሆን፤ ወደ አምሳ ዓመታት በሚጠጋው የንጉሡ የሥልጣን ዘመን አራት ጊዜ የብር ኖቶች ለውጥ ተደርጓል። ወታደራዊው መንግሥት ዘውዳዊውን ሥርዓት አስወግዶ አገሪቱን መምራት ከጀመረ ከጥቂት ዓመታት በኋላ በ1969 ዓ.ም የንጉሡ ምስልን የያዙትን የመገበያያ ገንዘቦች ለውጦት ቆይቷል። በተመሳሳይም ኢህአዴግ ደርግን አስወግዶ አገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላም ለሰባት ዓመታት ያህል ቀድሞ የነበረውን ገንዘብ ሲጠቀም ቆይቶ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የድንበር ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ የብር ኖቶቹ እንዲቀየሩ አድርጓል። በኢትዮጵያ ከንጉሡ ዘመን ጀምሮ አገልግሎት ላይ የነበሩት የገንዘብ ኖቶች 1፣ 5፣ 10፣ 50 እና 100 ብር የነበሩ ሲሆን፤ ለረጀም ጊዜ ከፍተኛ ዋጋ ያለው የገንዘብ ኖት 100 ብር ሆኖ ቆይቷል። ቢሆንም ግን በአጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ አገልግሎት ላይ ከዋሉት የብር ኖቶች መካከል የ2 ብር እና የ500 ብር ኖቶች ነበሩበት። ስለዚህም በአገሪቱ የወረቀት ገንዘብ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ዋጋ የነበረው የብር ኖት ባለ 500 ብር ኖት የነበረ ሲሆን በኋላ ላይ ግን ከግብይት እንዲወጣ መደረጉን የብሔራዊ ባንክ መረጃ ያመለክታል። ስለዚህም አሁን ከወረቀት የብር ኖቶች መካከል እንዲገባ የተደረገው የባለ 200 ብር ኖት በታሪክ ሁለተኛው ከፍተኛ ዋጋ ያለው ሲሆን ወደገበያ ሲገባም ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ የብር ኖት ለውጥ እንደሚደረግ በተለያዩ መንገዶች ሲነገር የቆየ ሲሆን፤ ከብር ዋጋ መቀነስ ጋር ተያይዞ 500 ዋጋ ያለው የብር ኖት ወደ ገበያ እንደሚገባ አንዳንድ ሰዎች ሲገልጹ ቆይተው ነበር። በአገሪቱ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች መደረግ ከጀመሩባቸው ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር እንደሚካሄድ በጉምሩክና በፖሊስ በኩል በተደጋጋሚ የሚወጡ ሪፖርቶች የሚያመለክቱ ሲሆን፤ ይህም ለውጥ ያስፈለገው ይህንኑ ለመከላከል መሆኑ ተነግሯል።
news-49931773
https://www.bbc.com/amharic/news-49931773
አሜሪካ የአባይ ወንዝ አጠቃቀምን በተመለከተ መግለጫ አወጣች
በኢትዮጵያ፣ በግብጽና በሱዳን መካከል የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሃ የመሙላት ሂደትንና አጠቃቀም ላይ ትብብር፣ ዘላቂነትና የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥን በተመለከተ እየተደረገ ያለውን ድርድር እንደምትደግፈው አሜሪካ አስታወቀች።
ይህ የተገለጸው ከኋይት የፕሬስ ጽህፈት ቤት ሐውስ በወጣና ዝርዝር ጉዳዮችን በማይጠቅሰው አጭር መግለጫ ላይ ሲሆን፤ መግለጫው የወጣበት ምክንያትም አልተገለጸም። በዚህ አጭር መግለጫ ላይ "ሁሉም የአባይ ተፋሰስ አገራት በምጣኔ ሃብት የመልማትና የመበልጸግ መብት አላቸው" ይልና ሲቀጥል "አስተዳደሩ [የአሜሪካ] ሁሉም አገራት እነዚህን መብቶች ሊያስከብር የሚችልና የእያንዳንዳቸውን የውሃ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን የሚያስከብር በጎ ፈቃደኝነትን የተላበሰ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ጥሪ ያቀርባል" ይላል። • በአባይ ግድብ ላይ ለዓመታት የተካሄድው ውይይት ውጤት አላመጣም፡ ግብጽ • ''የሚፈርስ የግድቡ አካል የለም'' የግድቡ ዋና ሥራ አስኪያጅ የፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት የፕሬስ ክፍል ይህንን መግለጫ ከምን ተነስቶ እንዳወጣ የገለጸው ነገር የሌለ ሲሆን ተጨማሪ የሰጠው ማብራሪያም የለም። ይህ መግለጫ ምናልባትም ዛሬና ነገ ካርቱም ውስጥ የሦስቱ አገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ያደርጉታል ተብሎ ከሚጠበቀው ቀጣይ የሦስትዮሽ ውይይት ጋር የተያያዘ እንደሚሆን ይገመታል። ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ኒውዮርክ ላይ በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባች ያለችውን ግድብን በተመለከተ የሚደረገው ድርድር ውጤት ላይ አለመድረሱ በአካባቢው ላይ አለመረጋጋትን ሊያስከትል እንደሚችል መናገራቸው ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያዋ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በዚያው መድረክ ላይ ለግብጹ ፕሬዝዳንት ንግግር ምላሽ በሚመስል ሁኔታ "የአባይ ወንዝ ለተፋሰሱ ሀገራት የጋራ ሃብት እንጂ የጥርጣሬና የውድድር ምንጭ ሊሆን አይገባም" በማለት ሃገራቱ የወንዙን ውሃ በጋራ መጠቀም እንዳለባቸው አመልክተዋል። ፕሬዝዳንቷ አክለውም የተፋሰሱ ሃገራት "የአባይን ወንዝ የጋራ ተጠቃሚነትን ባረጋገጠ መልኩ ለመጠቀምም በትብብርና በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ" በንግግራቸው ላይ አንስተዋል። ባለፈው መስከረም 3 እና 4/2012 ዓ.ም የኢትዮጵያ፣ የግብጽና የሱዳን ባለስልጣናት ካይሮ ላይ የግድቡን ውሃ አሞላል በተመለከተ በተከታታይ እያደረጉት ያለው የሦስትዮሽ ውይይት መካከል አንዱ የሆነው ካይሮ ላይ የተካሄደ ቢሆንም ያለስምምነት መጠናቀቁ ተነግሯል። የኢትዮጵያ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከካይሮው ድርድር በኋላ አዲስ አበባ ላይ በሰጡት መግለጫ ግብጽ በግድቡ ውሃ አሞላል ላይ አዲስ ሃሳብ እንዳቀረበችና ኢትዮጵያ ሃሳቡን ውድቅ እንዳደረገች ተናግረዋል። እንደ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ግብጽ ያቀረበችው ሃሰብ፤ የግድቡ የውሃ የሚሞላው በሰባት ዓመት እንዲሆን፣ ኢትዮጵያ በዓመት 40 ቢሊየን ሜትር ኪዮብ ውሃ እንድትለቅና የአስዋን ግድብ የውሃ መጠኑ ከምድር ወለል በላይ 165 ሜትር ላይ ሲደርስ ግድቡ በዋናነት ውሃ እንዲለቅ የሚጠይቅ ነው። ኢትዮጵያም ይህ የግብጽ ሃሳብ ቀደም ሲል በሦስቱ ዋነኛ የተፋሰሱ አገራት መካከል የተፈረመውን የአባይ ወንዝ ውሃን አጠቃቀም የተመለከተውን "የመርህ ስምምነት የጣሰና ጎጂ ግዴታን የሚያስቀምጥ ነው" በማለት እንደማትቀበለው አሳውቃለች። • ለህዳሴ ግድብ ግንባታ መዘግየት ምን አይነት መፍትሔዎች እየተሰጡ ነው? ሚኒስትሩ በተጨማሪም ይህ የቀረበው ሃሳብ "ግብጽ የወንዙ ዓመታዊ የውሃ ፍሰት 40 ቢልየን ሜትር ኪዩብ እንዲሆን ያቀረበችው ጥያቄ፤ በተዘዋዋሪ ኢትዮጵያ የአባይ ውሃን እንዳትጠቀም የሚከለክል በመሆኑ አልተቀበለችውም" ብለዋል። በግድቡ የውሃ አሞላልና የመልቀቅ ሂደት ዙሪያ ያሉትን ሁኔታዎች እንዲያጠና የተቋቋመው የኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ የሦስትዮሽ ብሔራዊ ገለልተኛ የሳይንሳዊ ጥናት ቡድን 5ኛ ስብስባውን ካርቱም ሱዳን ውስጥ ሰኞ እለት አካሂዶ የነበረ ሲሆን፤ ቡድኑ ዛሬ መስከረም 23 እና 24/2012 ዓ.ም እዚያው ካርቱም በሚካሄደው የሦስቱ አገራት የውሃ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ሪፖርት እንደሚያቀርብ ይጠበቃል።
news-42022225
https://www.bbc.com/amharic/news-42022225
ለኢትዮጵያውያን ዲፕሎማቶች ቪዛ ስለማትጠይቀው ኳታር 5 ነገሮች
ወደ ኳታር መጓዝ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ዲፕሎማቶች ካሁን በኋላ ቪዛ አያስፈልጋቸውም፤ ምክንያቱም ጠቅላይሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከሃገሪቱ ኤሚር ጋር ሥምምነት ተፈራርመዋል።
እስኪ ለወደፊቶቹ ጎብኚዎች 5 ጠቃሚ ነጥቦችን እናካፍላችሁ። 1. የዓለማችን ሃብታም ሀገር ናት ምንም እንኳ የነዳጅ ዋጋ እየቀነሰ ቢመጣም ኳታር ግን በሚያስገርም ሁኔታ እያደገች ነው። በሀገር ውስጥ ምርት በሚገኝ የነፍሰ ወከፍ ገቢ ዓለምን እየመራች ነው። ዓለማቀፉ የገንዘብ ተቋም ያወጣው አሃዝ እንደሚያሳየው እያንዳንዱ ዜጋ በነፍስ ወከፍ በዓመት 129,726 ዶላር ገቢ ያገኛል። ይህ ደግሞ በሁለተኝነት ከምትከተላት ሉክዘምበርግ እንኳን በ30, 000 ዶላር ይልቃል። ከአሜሪካ ደግሞ ከእጥፍ በላይ ይበልጣል። 2. የበርካታ ስደተኞች መኖሪያ ናት በኳታር 2.6 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ ይኖርባታል። ከእነዚህ መካከል 300,000 የሚሆኑት ብቻ ናቸው ዜጎቿ። ይሄ ማለት ከአጠቃላይ ነዋሪዎቿ የሀገሪቱ ዜጋ ከ7 ሰዎች አንዱ ብቻ ነው ማለት ነው። ከእነዚህ ደግሞ ብዙዎቹ ከደቡብ እሲያ ፣ ከህንድ ፣ከኔፓልና ከባንግላዴሽ የመጡ ናቸው። በዚህ የአውሮፓውያን ዓመት መጀመሪያ ለ80 ሃገራት ያለቪዛ የመግባት ፈቃድ በመስጠቷ ወደሃገሪቱ የመሄዱን ሂደት አቅለዋለች። 3. የወንዶች ቁጥር ከሴቶች በእጅጉ ይበልጣል በእርግጥ ኳታር ሚስት ለማግኘት ተመራጭ ሀገር አይደለችም ምክንያቱም ከህዝብ ብዛቷ ሴቶች 25 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው ። ከስደተኞቹ ብዙዎች ወንዶች መሆናቸው ለዚህ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። 4. ነጻ ሃሳብን ትደግፋለች(ገደብ ቢኖረውም) በርካታ የአረብ ሀገራት በመንግሥታቸው ላይ ትችቶችን ስለሚዘግብ በአልጀዚራ ደስተኞች አይደሉም። ይህም በአንዳንድ የአረብ ሀገራትና በኳታር መካከል ዲፕሎማሲያዊ ውጥረትን ፈጥሯል። ሆኖም የኳታሩ ኤሚር ራሳቸውን በተመለከተ ምንም አይነት ትችት አይቀበሉም፤ ይህን ተላልፎ እርሳቸውንም ሆነ ቤተሰባቸውን የሚያሳጣ ነገር ያሳተመ ከፍተኛ ቅጣትና የእስር ጊዜ ይጠብቀዋል። የስታዲያሞቿን ገጽታ ስዕላዊ ንድፎች ወደተግባር እየለወጠች ነው 5. የዓለም ዋንጫን ልታስተናግድ ነው በአምስት ዓመታት ውስጥ የዓለማችን ታልቁ የስፖርት ክስተት በኳታር አስተናጋጅነት ይካሄዳል። በእርግጥ እስካሁን የዓለም ዋንጫን ለማዘገጃት የሚያስችላትን ውድድር ለማሸነፍ ጉቦ ሰጥታለች በሚል በመወንጀሏ መቶ በመቶ አልተረጋገጠም። ይህ እውነት መሆኑ ከተረጋገጠ ዕድሉ ለሌላ ሀገር ሊሰጥ ይችላል።ካስተናገደች ደግሞ የኳታርን ከፍተኛ ሙቀት ለመከላከል በክረምት የሚካሄድ የሚጀመሪያው ዓለም ዋንጫ ይሆናል። ምንም እንኳ የዓለማችን ሃታም ሀገር ብትሆንም ጫወታው የሚካሄድባቸውን ስታዲየሞች በሚገነቡት ስደተኞች ላይ ያለፈቃዳቸው በጉልበት የማሰራትና የሰብአዓዊ መብት ጥሰት ትፈጽማለች በሚል በሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ተወንጅላለች።
49771013
https://www.bbc.com/amharic/49771013
የ87 ዓመቷ አዛውንት በተቆጡ ላሞች ተወግተው ሞቱ
የ87 ዓመቷ ሒላሪ አዳየር በሚኖርበት ምዕራብ ሰሴክስ አካባቢ በተቆጡ ላሞች ተወግተው መሞታቸው ተሰማ።
ሒላሪ አዳር ሒላሪ ላይ ጥቃት ያደረሱት ወገበ ነጭ የሆኑ የከብት ዝርያዎች ናቸው ተብሏል። ላሞቹ አዛውንቷን ወግተው ከጣሏቸው በኋላ ለመነሳት ሲሞክሩ በተደጋጋሚ እንደወጓቸው ተነግሯል። ጥቃቱ ከደረሰባቸው ስፍራ በአውሮፕላን ወደ ህክምና መስጫ የተወሰዱት ሒላሪ፣ ለሳምንት ያህን ሳይሰሙ ሳይለሙ ቆይተው ሕይወታቸው አልፏል። ላሞቹ እኚህን የእድሜ ባለፀጋ ከማጥቃታቸው አንድ ቀን ቀደም ብሎ ውሻቸውን እያንሸራሸሩ የነበሩ ጥንዶችም ላይ ተመሳሳይ ጥቃት አድርሰዋል። • አሜሪካ ጦሯን ወደ ሳዑዲ ልትልክ ነው ላሞቹን በባለቤትነት የሚያስተዳድሩት 'ሊንቺሜር ሶሳይቲና ሊንቺሜር ኮሚውኒቲ ግሬዚንግ ሲአይሲ' በዚህ ጉዳይ ችሎት ፊት የቀረቡ ሲሆን፤ ላሞቹ እያደረሱ ያለውን ጥቃት ከቁብ ጽፈው እየተከታተሉት እንዳልነበር ለማወቅ ተችሏል። እንደውም ከእለታት በአንዱ ቀን የተከሰተ ድንገተኛ አደጋ አድርገው ነው የወሰዱት። ብራይዮኒ ዲላሞር አዟውንቷ ጥቃት ሲደርስባቸው የተመለከተ ሲሆን፤ አዛውንቷ ራሳቸውን ለማዳን በተንቀሳቀሱ ቁጥር ላሞቹ የበለጠ ቁጡ በመሆን ይወጓቸው እንደነበር መስክሯል። ራቼል ቶምፕሰን በበኩሏ የደረሰባትን ለችሎቱ ስታስረዳ እርሷና ባለቤቷ አዛውንቷ ከመወጋታቸው አንድ ቀን ቀደም ብሎ በእነዚሁ ላሞች ጥቃት እንደደረሰባቸው መስክራለች። ሒላሪ አዳየር ላይ ጥቃት ያደረሱት ወገበ ነጭ የሆኑ የከብት ዝርያዎች ናቸው ተብሏል ባለቤቷም በጉዳቱ መድማት እንደደረሰበት ተናግሮ ላሞቹ "ተቆጥተዋል" ሲል ተናግሯል። ጥንዶቹ አደጋ እንደደረሰባቸው ላሞቹ ወዲያውኑ ወደ ሌላ መኖሪያ ስፍራ የተወሰዱ ሲሆን፣ ያለውን ሁኔታ በቀጣዩ ማለዳ ለመፈተሽ ታቅዶ ነበር ተብሏል። ነገር ግን በነጋታው ጠዋት አዛውንቷ ሒላሪ አዳየርና ውሻቸው ጥቃት ደረሰባቸው። • በመላው ዓለም ከ4 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ያሳተፈው ሰላማዊ ሰልፍ • ግብፃውያን ፕሬዝዳንት አል-ሲሲን በመቃወም ሰልፍ ወጡ ላሞቹን በባለቤትነት የሚያስተዳድሩት በጋራ ባወጡት መግለጫ "በድርጅታችን ውስጥ በጉዳዩ ላይ ኮስተር ያለ ውይይት እያደረግን ነው፤ ከቤተሰቦቹም ጋር ውይይቶች እያካሄድን ነው፤ ከማኅበረሰቡም ጋር ቢሆን የጋራ የግጦሽ ስፍራውን በሚመለከት ወደፊት በሚኖረን ግንኙነት ላይ ምንም አይነት ውሳኔ ከመወሰናችን በፊት እንነጋገራለን" ብለዋል። የአካባቢው ፖሊስ ከፍተኛ ኃላፊ "በአዛውንቷም ላይ ሆነ በጥንዶቹ ላይ ላሞቹ ጥቃት ለመፈፀም ምን እንዳነሳሳቸው ምንም የታወቀ ነገር የለም" ብለዋል። ይህ የሒላሪ አዳየር ሞት፤ ከብቶች በአንዳች ሁኔታ ሲቆጡ ምን ያህል አደገኛ መሆናቸውን ግንዛቤ የፈጠረ ክስተት ነው ሲሉም አክለዋል።
news-53127360
https://www.bbc.com/amharic/news-53127360
የናይጄሪያ ፖሊስ በሩዝ ፋብሪካ ተቆልፎባቸው እንዲሰሩ የተገደዱ 300 ሰራተኞችን ነፃ ማውጣቱን ገለፀ
የናይጄሪያ ፖሊስ በሩዝ ፋብሪካ ውስጥ ተቆልፎባቸው የነበሩ 300 ሰራተኞችን ነፃ ማውጣቱን ገልጿል። ሰራተኞቹ ከመጋቢት አጋማሽ ጀምሮ ከፋብሪካው እንዳይወጡ እግድ ተጥሎባቸውና ተቆልፎባቸው ይሰሩ ነበር ተብሏል።
በወለሉ ላይ የተኙ የፋብሪካው ሰራተኞች በሰሜናዊ ናይጄሪያ ግዛት በምትገኘው ካኖ በሚገኝ ፋብሪካ ውስጥ የሚሰሩት ሰራተኞች የኮሮናቫይረስ አስገዳጅ የቤት መቀመጥ አዋጅን ተከትሎ ወደቤታቸው እንዳይሄዱና በየወሩም ከሚያገኙት 2 ሺህ 600 ብር ደመወዝ በተጨማሪ 500 ብር እንደሚጨመርላቸው የፋብሪካው አስተዳዳሪዎች ቃል ገብተውላቸው ነበር። ወደቤታችን እንሄዳለን የሚሉት ደግሞ ከስራ እንደሚባረሩ ማስፈራራሪያም ደርሷቸዋል። በፋብሪካው ለመስራት የተስማሙ ሰራተኞች ከፋብሪካው ወጥተው መሄድ እንደማይችሉም ተነግራቸዋል። ይህንንም ተከትሎ አምስት አስተዳደር ላይ ያሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል። የህንዶች የሆነው ፖፑላር ፋርምስ የተሰኘው ፋብሪካ ከቢቢሲ በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጥ ቢጠየቅም ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቧል። የፖሊስ ቃለ አቀባይ አብዱላሂ ሃሩና ለቢቢሲ እንደተናገሩት ፋብሪካው እንደተዘጋና ባለቤቶቹም ሰራተኞቹን ያለፍቃዳቸው በመቆለፋቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቀዋል። አንዳንድ ሰራተኞች ለቢቢሲ እንደተናገሩት የነበሩበት ሁኔታ ከእስር ያልተናነሰ እንደሆነና ትንሽ ምግብም ብቻ ይሰጣቸው እንደነበር ገልፀዋል። "በጣም ለአጭር ጊዜ ብቻ እንድናርፍ ነበር የሚፈቀደልን። ፀሎት ማድረግ እንዲሁም ቤተሰብ እንዲጠይቀን አይፈቀድልንም ነበር" በማለት የ28 አመቱ ሃምዛ ኢብራሂም ለቢቢሲ ተናግሯል። ፖሊስ ጉዳዩን የተረዳው አንደኛው ሰራተኛ ለሰብዓዊ መብት ድርጅት እንዲያድኗቸው በመማፀን ከላከው ደብዳቤ ነበር። "ያየሁት ሁኔታ በጣም ልብ የሚሰብር ነው። ሰራተኞቹ ለእንስሳ እንኳን በማይመጥን ሁኔታ ነው እንዲቆዩ የተደረጉት" በማለት የግሎባል ሂውማን ራይትስ ኔትወርክ ሰራተኛ ካሪቡ ያሃያ ካባራ ለቢቢሲ ገልፀዋል። አክለውም "የሚሰጣቸው ምግብ በጣም አነስተኛ ነበር። ታመው ለነበሩትም ሕክምና ተከልክለዋል፤ የመድኃኒት አቅርቦት አልነበራቸውም" ያሉት ካሪቡ ለሰራተኞቹ ፍትህንም እንደሚሹ ጠይቀዋል። የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት እንዲቻል ናይጄሪያ ሁሉም ፋብሪካዎችም ሆነ የንግድ ቦታዎች እንዲዘጉ ያዘዘችው መጋቢት አጋማሽ ላይ ነበር። በናይጄሪያ እስካሁን 20 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን መዲናዋ ሌጎስም የስርጭቱ ማዕከል ሆናለች። ከሌጎስ በመቀጠልም የናይጄሪያ ሁለተኛ ትልቋ ከተማ ካኖም በቫይረሱ በተያዙ ሰዎች ቁጥር ትከተላለች። ወረርሽኙን ለመግታት የተላለፉ መመሪያዎች በሌሎች ቦታዎች ቢላሉም በካኖ ግን የቤት መቀመጥ አዋጁ እንዳለ ነው። ዜጎች ሰኞ፣ ረቡዕና አርብ መንግሥት በወሰነው ሰዓት ብቻ ምግብና አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ለመሸመት ይወጣሉ።
news-46601555
https://www.bbc.com/amharic/news-46601555
ከእንጀሯ አባቷ ያረገዘችውን ፅንስ ልታቋርጥ ሞክራለች የተባለችው ሴት ነፃ ሆና ተገኘች
ኤል ሳልቫዶራዊቷ ሴት የሃገሪቱን ጥብቅ የፀረ-ውርጃ ሕግ ጥሳለች በሚል ምክንያት ተፈርዶባት የነበረው እሥር እንዲነሳላት የሃገሪቱ ፍርድ ቤት ወሰነ።
ኢሜልዳ ኮርቴዝ የተሰኘችው የ20 ዓመት ወጣት ሴት ብዙ ወሲባዊ በደል በሚያደርስባት እንጀራ አባቷ ተደፍራ ነው ያረገዘችው። መፀዳጃ ቤት ውስጥ ሴት ልጅ ከመገላገሏ በፊት ውርጃ ለማካሄድ ሞክራለች ሲሉ ነው ዶክተሮች ኢሜልዳን የከሰሷት። ሴት ልጇ በመልካም ደህንነት ብትገኝም ኢሜልዳ በፖሊስ ተይዛ ፍርዷን እየተከታተለች ለ18 ወራት ያክል እሥር ቤት ከረመች። • "በምንም ዓይነት መልኩ ሕዝቡን የሚጎዳ ከሆነ ተቀባይነት የለውም" አቃቤ ሕግ ሴቲቱ ስለእርግዝናዋ ለማንም አለመናገሯ፤ ሕክምና አለመከታተሏ እና ውርጃ ለመፈፀም መሞከሯ እስከ 20 ዓመት እሥር የሚያደርስ ጥፋት ነው ሲል ተከራክሯል። ሰኞ ዕለት ችሎት የዋለው የሃገሪቱ ፍርድ ቤት ግን ኢሜልዳ በእንጀሯ አባቷ በተደጋጋሚ በመደፈሯ ምክንያት ነፍሰ-ጡር መሆኗን ሳታውቅ ነው የወለደችው በሚል ነፃ እንድትሆን በይኗል። ጠበቃዎቿ ቀለል ያለ ቅጣት መቀጣት ካለባትም ልጇን ችላ በማለቷ ለአንድ ዓመት ልትቀጣ ይገባል እንጂ 20 ዓመት አይገባትም በማለት ተከራክረው ነበር። ፍርድ ቤቱ ግን ምንም ዓይነት ወንጀል ባለመፈፀሟ ነፃ ናት ሲል ለሃገሪቱ ህዝብ ጆሮ አዲስ እና አስደሳች የሆነ ብይን አሰምቷል። • የቀይ ሽብር ተከሳሹ ሄግ ፍርድ ቤት ቀረበ ኢሜልዳ ነፃ መሆኗን የሰሙ ወዳጅ ዘመዶቿ እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ሰዎች መፈክር በመያዝ ፍርድ ቤቱን አጥለቅልቀውት ታይተዋል። አቃቤ ሕግ የ70 ዓመቱ አባቷ በቁጥጥር ሥር ውሎ ፍርዱን እየተከታተለ እንደሆነ አሳውቋል። ኤል-ሳልቫዶር ዓለማችን ላይ ጠንካራ ፀረ-ውርጃ ሕግ ካላቸው ጥቂት ሃገራት አንዷ ነች፤ ምንም ዓይነት የውርጃ ድርጊት ለእሥር ይዳርጋል። ውርጃ ለመፈፀም የሞከሩ ሴቶች ብቻ ሳይሆኑ ድርጊቱን እያወቁ የደበቁ የሕክምና ባለሙያዎችም ከበድ ያለ እሥር ሊጠብቃቸው ይችላል። • የፓኪስታን ፍርድ ቤት ሞት የተፈረደባትን ክርስቲያን ነፃ ለቀቀ
news-45255551
https://www.bbc.com/amharic/news-45255551
ለህዳሴ ግድብ ግንባታ መዘግየት ምን አይነት መፍትሔዎች እየተሰጡ ነው?
በአገርና በህዝብ ሃብት የሚካሄድ ትልቅ ብሄራዊ ፕሮጀክት በመሆኑ ታላቁ የህዳሴ ግድብ የሁሌም የኢትዮጵያዊያን አጀንዳ ነው።
ነገር ግን ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በሁለት አጋጣሚዎች የህዳሴው ግድብ ከመቼውም የበለጠ መነጋገሪያ ሆኗል። በመጀመሪያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እስካሁን እየሄደ ባለበት ፍጥነት ግድቡ በመጭው አስር ዓመትም አይጠናቀቅም ብለዋል የሚል መረጃ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በብዛት መንሸራሸሩን ተከትሎ ግድቡ የሁሉም መነጋገሪያ ሆነ። ከዚያ ደግሞ የግድቡ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑትና የግድቡ ምልክት ተደርገው የሚወሰዱት ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ግድያ የግድቡ ጉዳይ ብዙዎችን አነጋገረ፣ አሳሰበም ጭምር። •ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሕይወታቸው ያለፈው በጥይት ተመተው ነው፡ ፌደራል ፖሊስ •ስለኢንጂነር ስመኘው አሟሟት እስካሁን ምን እናውቃለን? •የኢንጂነር ስመኘው ቤተሰቦች የምርመራው ውጤት በምንፈልገው ፍጥነት እየሄደ አይደለም አሉ በኢንጅነር ስመኘው ህልፈት ማግስት መግለጫ የሰጡት የውሃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሃይል ሚኒስቴሩ የህዳሴው ግድብ የሲቪል ኢንጅነሪንግ ክፍሉ ግንባታ በጥሩ ደረጃ ላይ የሚገኝ ቢሆንም የኤሌክትሮ ሜካኒካል ግንባታ ክፍሉ ማለትም የጀነሬተርና ተርባይን ተከላ ስራ መዘግየቱን ገልፀው ነበር። ሌላው የኤሌክትሮ ሜካኒካል ግንባታ ክፍል ውስጥ ያለው የማመንጫ ጣቢያ ነው። በግድቡ ግንባታ ሂደት ላይ ችግር የሆነ ነገሮችን መፍታት የሚያስችሉ እርምጃዎችን እየተመለከቱ መሆኑንም አመልክተው ነበር። ከጥቂት ቀናት በፊት ደግሞ ግድቡ በተያዘለት የግንባታ ሂደት እየተከናወነ መሆኑን የገለፁትን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር አዜብ አስናቀን የግድቡ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ክፍል ከመዘግየቱ አንፃር አሁን የግድቡ ግንባታ ምን ላይ ነው ስንል ጠይቀናቸው ነበር። "ግንባታው በአንድ ሰው ላይ ሳይሆን አሰራር(ሲስተም)ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ሌላ ሰው ሃላፊነት ይረከባል ስራውም ይቀጥላል እየቀጠለም ነው"በማለት የግንባታው የዘገዩ ስራዎች መኖራቸውን ነገር ግን ይህ የተለየ ሳይሆን በዓምስት ተብሎ በአስር ዓመት እንደሚጠናቀቁ የመንገድም ይሁን የሃይል ፕሮጀክቶች እንደሆነ በመግለፅ መልስ ሰጥተዋል። ፕሮጀክቶች ለምን ይዘገያሉ ለሚለው ክፍያን ጨምሮ የተለያየ ምክንያት ይቀመጣል።በህዳሴው ግድብም ተመሳሳይ ነገር መከሰቱን ተናግረዋል። የህዳሴው ግድብ የሲቪልና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ግንባታ ሂደቶች ተቀባብተው(ኢንተርፌስ አድርገው) ነው መሰራት ያለባቸው። ብረታ ብረቱ ሲሰራ ኮንክሪቱ ይቀጥላል።ኮንክሪቱ ሲሰራ ብረታ ብረቱ ይቀጥላል።እንደዚ እንደዚ እያለ ነው የሚሄደው። የግድቡን ግንባታ ችግር ለመፍታት መፍትሄ የተባለው ስፔሻላይዝ ያደረጉ ሰብ ኮንትራክተሮችን ማስገባት ሲሆን የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራውን የሚያግዝ ተቋራጭ በማስገባትም የግድቡን የኤሌክትሮ ሜካኒካል ክፍል ግንባታ ችግር ለመፍታት እየተሞከረ እንደሆነ ኢንጅነር አዜብ ያስረዳሉ። እንደ አውሮፓውያን በቀጣዩ ወር ሁለት ተርባይኖች ሃይል ማመንጨት እንዲጀምሩ እቅድ እንደነበር ከዚህ ቀደም መዘገቡን በማስመልከት ጥያቄ ያነሳንላቸው ኢንጅነር አዜብ እንደዚህ ያሉ ነገሮች ላይ እርግጠኛ ሆኖ መናገር ከፕሮጀክቱ ውስብስብ ተፈጥሮ አንፃር ከባድ እንደሆነ ያስረዳሉ። "ፕሮጀክቱ በጣም ውስብስብ ነውና ይህ በዚህ ጊዜ ለማለት ይቸግራል።ከዚህ አንፃር መስከረም ላይ ይሄ ይሆናል አይሆንም ማለት አይቻልም።ነገር ግን የመጀመሪያዎቹ ሁለት ዩኒቶች ስራ ጀምረው ሃይል እንዲያመነጩ የተለያዩ የማፋጠን እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው"ይላሉ። ሳሊኒ በግንባታ መዘግየት ለደረሰበት ኪሳራ ካሳ የመጠየቁ ነገር እየተሰማ ሲሆን የዚህ አይነቱ የተቋራጮች የካሳ ጥያቄ የሚጠበቅ ነው ይላሉ ኢንጅነሯ። ጊቤ ሶስት እንዲሁም ገናሌ ደዋሌን በምሳሌነት በመጥቀስም የኮንትራክተሮች ካሳ ጥያቄ የተለመደ እንደሆነ ያመለክታሉ። ክፍያ ሲዘገይ ተቋራጩ ሰውና ማሽን ያለ ስራ ያስቀመጠበትን ጉዳት ደርሶብኛል ደርሶብኛል ብሎ የካሳ ጥያቄ ያቀርባል። በሌላ በኩል ወደ ስራ የሚገባው ያለቀለት ሳይሆን መሰረታዊ ዲዛይን ተሰርቶ በመሆኑና በመሰረታዊ ዲዛይኑም በተወሰነ መልኩ እንጂ መሬት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ምን እንዳለ ማወቅ ባለመቻሉም ኋላ ላይ የሚነሳ የካሳ ጥያቄ እንደሚኖር ያስረዳሉ። ስለዚህም መሬት ላይ ወደ ስራ ሲገባ ያልተጠበቀ ነገር ሊያጋጥም ይችላል።በተመሳሳይ ህዳሴው ግድብ ላይም ያልተጠበቀ ጂኦሎጂካል ሁኔታ አጋጥሞ እንደነበር ይጠቅሳሉ። "አንድ ቢሊየን ሜትር ኪዩብ እቆፍራለው ተብሎ ውል ቢገባ በእጥፍ ሊያስኬድ ይችላል። በዚህ ዓይነቱ አጋጣሚ ተቋራጩ ካሳ ይጠይቃል።አሁንም ከህዳሴው ግድብ ተቋራጭ ሳሊኒ መሰል ጥያቄ አለ" ቀደም ሲል የመጀመሪያ ኮንትራት ሲፈረም ሁለት ጀነሬተሮች እንደ አውሮፓውያኑ በ2014 ስራ እንዲጀምሩ በዚሁ መሰረትም በአሁኑ ወቅት (2018)ደግሞ ሁሉም ጀነሬተሮች ይጀምራሉ ተብሎ ታስቦ እንደነበር ለፕሮጀክቱ ቅርበት ያለቸው የቢቢሲ ምንጮች ይናገራሉ። ነገር ግን ከ2014 እስከ አሁንም የግድቡ ግንባታ በሂደት እያለ ስራ ይጀምራሉ የተባሉት ጀነሬተሮች አሁንም ስራ አለመጀመራቸው የግንባታውን በጣም መዘግየት እንደሚያሳይ ምንጮቹ ያስረዳሉ። በዚህ አካሄድ በቀጣዩ ዓመትም ሁለቱ ጀነሬተሮችን ወደ ስራ ማስገባት ፈታኝ እንደሚሆን ስጋታቸውን ይገልፃሉ። ምንጮቹ እንደሚሉት በአሁኑ ወቅት በሲቪል ስራው በኩል ችግር የለብንም እንደሚፈለገው ሊሄድ ይችላል የጎተተው ኤሌክትሮ ሜካኒካሉ ነው ሊባል ይችላል።ነገር ግን ሲቪል ስራውም በጊዜው ሄዷል ማለት አይቻልም። ስለዚህም በከፍተኛ ጉልበትና አቅም ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል።
news-54693280
https://www.bbc.com/amharic/news-54693280
የትራምፕ አማካሪ አሜሪካ የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝን መቆጣጠር አትችልም አሉ
የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፍተኛ አማካሪ አገሪቱ የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝን መቆጣጠር እንደማትችል ተናገሩ።
አማካሪው ማርክ ሚዶውስ እንዳሉት ኮቪድ-19ኝ መቆጣጠር የሚቻለው እንደ ክትባት እና መድሃኒት ሲገኝ ነው ብለዋል። አማካሪው ይህን ያሉት አሜሪካ ምርጫ ለማካሄድ 9 ቀናት በቀሩበትና በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች እየጨመረ ባለበት ወቅት ነው። ዴሞክራቱ ተፎካካሪው ጆ ባይደን ደግሞ ዋይት ሃውስ የሽንፈት ባንዲራን እያውለበለበ ነው ብለዋል። አክለውም ''የፕሬዝዳንቱ አማካሪ አስተያየት የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የአሜሪካ ዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ የመጀመሪያ ኃላፊነቱን በአግባቡ እየተወጣ እንዳልሆነ ማሳያ ነው'' ሲሉ ተደምጠዋል። ማርክ ሚዶውስ ከሲኤኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር መሞከር አዋጪ እንዳልሆነና ምክንያቱ ደግሞ ቫይረሱ ልክ እንደ ማንኛውም ጉንፋን አይነት ባህሪ ስላለው ነው ብለዋል። በአሜሪካ እስካሁን 225 ሺ ሰዎች በዚሁ ቫይረስ ምክንያት ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን ይህ ቁጥር ደግሞ አገሪቱን ከዓለም የመጀመሪያውን ደረጃ እንድትይዝ አድርጓታል። ባሳለፍነው ቅዳሜ ብቻ አሜሪካ 83 ሺ 718 አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ያገኘች ሲሆን አርብ ዕለት ደግሞ 83 ሺ 757 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን መዝግባ ነበር። በአሜሪካ የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝና ቫይረሱን ለመቆጣጠር መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች ጉዳይ ከፍተኛ የምርጫ ክርከር ጉዳይ ሆኗል። እስካሁን 59 ሚሊየን የሚሆኑ አሜሪካውያን ድምጻቸውን በፖስታ አማካይነት የሰጡ ሲሆን በአገሪቱ ታሪክ ከፍተኛው ቁጥር እንደሆነም ተነግሯል። በአሜሪካ የተላላፊ በሽታዎች ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ዶክተር አንቶኒ ፋውቺ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ለኮሮረናቫይረስ የሚሆን ክትባት ከዓመቱ መጨረሻ በፊት ዝግጁ ሊሆን እንደሚችልና የመጀመሪያዎቹ ብልቃጦች ግን ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ሰዎች እንደሚታደሉ ገልጸዋል። አክለውም ክትባቱ ለመላው ሕዝብ ለማዳረስ በርካታ ወራትን ሊፈጅ እንደሚችልም ጠቁመዋል።
news-46423380
https://www.bbc.com/amharic/news-46423380
የአየር ንብረት ለውጥ፤ የት ደረስን?
ወደ 200 የሚጠጉ የሃገራት ተወካዮች በአውሮፓዊቷ ሃገር ፖላንድ ተሰባስበው ስለ የአየር ንብረት ለውጥ ይመክራሉ፤ ይህም የፓሪሱን ስምምነት ትግበራ ያጠናክራል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።
የተባበሩት መንግሥታት 2015 ላይ በፓሪስ የተደረሰውን ስምምነት እንደ አሜሪካ እና አውሮፓ ያሉ ግዙፍ ኢኮኖሚዎች በገቡት ቃል መሰረት ስምምነቱን እየተገበሩት ስላልሆነ የዓለም ሙቀት መጨመር አሳስቦኛል ብሏል። የዓለምን ሙቀት መጨመረ የሚከታተሉት ተመራማሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ምንም እንኳ የፓሪሱ ስምምነት የዓለምን ሙቀት ከ2 ዲግሪ ሴሊሺየስ በላይ እንዳይጨምር ለማደረግ ቃል የተገባ ቢሆንም፤ መሆን የነበረበት ግን ከ1.5 ዲግሪ ሴሊሺየስ በታች ነበር። • ምድር በአስፈሪ ሁኔታ እየሞቀች ነው • ዓለምን ሊመግብ የሚችለው የስንዴ ዘር የዓለም ሙቀት ምን ያክል እየጨመረ ነው? ምንስ ማድረግ ይቻለናል? ዓለማችን ከመቼውም በላይ እየሞቀች ነው። እንደ የዓለም ሜትሮሎጂ ድርጅት ከሆነ፤ በዓለም ዙሪያ ኢንዱስትሪው ከመስፋፋቱ በፊት ከነበረው የአየር ጠባይ ጋር ሲነጻጸር በአሁኑ ሰዓት የዓለማችን ሙቀት በአንድ ዲግሪ ጨምሯል። በዚህ አካሄድ 2100 ላይ የዓለም ሙቀት ከ3-5 ዲግሪ ሰሊሺየስ የሚጨምር ይሆናል። የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሉት አንድ ዲግሪ ሴሊሺየስ ሲባል ከፍተኛ ለውጥ ላይመስል ይችላል። ይሁን እንጂ የዓለም መንግሥታት የዓለም ሙቀትን ለመቀነስ አስቸኳይ እርምጃ ካልወሰዱ፤ የባህር ወለል ይጨምራል፣ የባህር ሙቀት እና አሲዳማነት የከፋ ይሆናል እንዲሁም ሩዝ፣ በቆሎ እና ስንዴ የማብቀል አቅማችን አደጋ ላይ ይወድቃል። ይህ ዓመት በመላው ዓለም ከተለመደው በላይ ረዥም የሙቀት ወቅት እና ከፍተኛ ሙቀት የተመዘገበበት ዓመት ነው። ሰሜናዊ ንፍቀ-ክበብ ማለትም አውሮፓ፣ እስያ፣ ሰሜን አሜሪካ እና ሰሜን አፍሪካ ከፍተኛ ሙቀት ተስተውሎባቸዋል። • ክፍል 1 ፡በፅኑ የታመመው የዓባይ ወንዝ የአየር ንብረት ለውጥን ለመግታት የታለመው ዕቅድ የሚሳካ አይመስልም በተገባው ቃል መሰረት የፓሪሱ ስምምነት ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ቢደረግ እንኳ በዚህ ክፍለ ዘመን መጨረሻ ላይ ምድራችን ከ3 ዲግሪ ሴሊሸየስ በላይ ሙቀት ትጨምራለች። የዘርፉ ባለሙያዎች ለበርካታ ዓመታት የዓለም ሙቀት ከ2 ዲግሪ ሴሊሺየስ በታች ሆኖ መቆየት አለበት በማለት ሲወተውቱ ቆይተዋል። አሁን ላይ ግን የዓለም ሙቀት ከ1.5 ዲግሪ ሴሊሺየስ በታች መሆን አለበት ይላሉ። ቻይና እና አሜሪካ ከፍተኛ አመንጪዎች ናቸው በዓለማችን በካይ አየር በመልቀቅ ቻይና እና አሜሪካ ላይ የሚደርስባቸው የለም። በጠቅላላው ከሚለቀቀው በካይ አየር 40 በመቶው የሚሆነው ከቻይና እና አሜሪካ የሚወጣ ነው። ህንድ፣ ሩሲያ፣ ጃፓን፣ ብራዚል፣ ኢንዶኔዢያ፣ ኢራን፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ በካይ አየር ከሚለቁ የመጀመሪያዎቹ 10 በካይ ሃገራት ዝርዝር ውስጥ ይገኙበታል። ፕሬዚዳንት ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ከፓሪሱ ስምምነት እራሳቸውን እንደሚያገሉ ዝተው ነበር። በወቅቱ ትራምፕ የአሜሪካንን ንግድ እና ሰራተኞች የማይጎዳ ''የተሻለ'' ስምምነት እንዲኖር እሰራለሁ ብለው ነበር። ከተሞች በተለየ መልኩ አደጋ ውስጥ ናቸው ቬሪስክ ማፕልክሮፍት የተባለ ድርጅት ጥናት ይፋ እንዳደረገው፤ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ከፍተኛ አደጋ የተጋረጠባቸው 95 በመቶ የሚሆኑት ከተሞች በአፍሪካ ወይም በእስያ የሚገኙ ናቸው። የ20 ሚሊዮን ህዝብ መኖሪያዋ የናይጄሪያዋ ሌጎስ እና የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ መዲና ኪንሻሳ የመሳሰሉ በፍጥነት እያደጉ የሚገኙ ከተሞች ይገኙበታል። የአርክቲክ የበረዶ ግግር አደጋ ላይ ነው በቅርብ ዓመታት የአርክቲክ የበረዶ ግግር መጠን በፍጥነት እየቀነሰ ነው። 2012 ላይ ዝቀተኛው ደረጃ አስመዝግቦ ነበር። የሚለቀቀው በካይ አየር ካልቀነሰ የአርክቲክ ውቅያኖስ 2050 ላይ በረዶ አልባ ሊሆን ይችላል። እኛ ምን ማድረግ እንችላለን? ትልቁ ኃላፊነት እና ለውጥ ማስመዝገብ የሚችሉት መንግሥታት ቢሆኑም፤ ግለሰቦችም የራሳቸውን ኃላፊነት መወጣት ይችላሉ። ተመራማሪዎች እንደሚሉት አንድ ግለሰብ የአኗኗር ዘዬውን በመቀየር እየደረሰ ያለውን ጉዳት መቀነስ ይቻላል፤ ለዚህም የሚከተለውን ያስቀምጣሉ። ስጋ፣ ወተት፣ አይብ እና ቅቤ በትንሹ እንጠቀም። በአካባቢያችን የሚመረቱ ወቅታዊ የሆኑት አትክልት እና ፍራፍሬዎችን አዝወትረን እንመገብ። በተቻለ መጠን የምግብ ብክነትን እንቀንስ። በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰሩ መኪኖችን እናሽከርክር አጭር እርቀቶችን ደግሞ በእግራችን እንጓዝ አሊያም ሳይክል እንጋልብ። ከአወሮፕላን ይልቅ የባቡር እና አውቶብስ አማራጮችን እንጠቀም። ለስብሰባ ረዥም ጉዞዎችን ከማድረግ ይልቅ በቪዲዮ ኮንፍረንስ እንገናኝ። አነስተኛ የካርበን ልቀት ያላቸውን የቤት ውስጥ መገልገያዎችን እንምረጥ። ሳይቲስቶቹ ጨምረው እንደሚሉት ከሆነ ሰዎች አነስተኛ ስጋ እና የስጋ ውጤቶችን ቢመገቡ በከፍተኛ ደረጃ የአየር ብክለትን መቀነስ ይቻላል። አስተኛ ስጋ እና የስጋ ውጤቶችን በመጠቀም የስጋ ማቀነባበሪያ ኢንደስቱሪዎች የሚለቁትን የካርበን ልቀት መጠንን መቀነስ ይቻላል። • የሰው ልጅ ዝግመተ ለውጥ በአየር ፀባይ ይመራ ነበር
news-53954321
https://www.bbc.com/amharic/news-53954321
አሜሪካ ፡ የፖሊሶችን ዘረኝነትና መድልዎን ማስቆም ይቻላታል?
ጆርጅ ፍሎይድ በፖሊስ መገደሉን እንዲሁም በቅርቡ ፖሊስ ጄኮብ ብሌክ የተባለ ጥቁር አሜሪካዊን በበርካታ ጥይቶች ተኩሶ ማቁሰሉን ተከትሎ ተቃውሞዎች ሲካሄዱ ቆይተዋል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ዘረኝነትንና መድልዎን በመቃወም ድምጻቸውን አሰምተዋል። አንዳንዶች ዘረኝነት ከጭፍን ጥላቻ የሚመነጭ ይመስላቸዋል። ነገር ግን ሌሎች ሰዎችን የምናስተናግድበት መንገድ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ በርካታ ነገሮች አሉ። አንዳንዴ ለራሳችን ሳይታወቀን መድልዎ እንፈጽማለን። ይህም ከእምነታችን እና ከባህሪያችንን ሊጻረር ይችላል። እነዚህ ድርጊቶች ከግል ተሞክሮ፣ ከአስተዳደግ፣ ከባህል፣ ከምናነበው መጻሕፍት እና ከምንሰማው ዜና ይመነጫል። አሜሪካ ውስጥ ያሉ የፖሊስ ክፍሎች ለራስ የማይታወቅ መድልዎን ለመቅረፍ የሚረዱ መርሐ ግብሮች አሏቸው። ይህም ፖሊሶች ላይ የሚስተዋለውን ዘረኝነት ለመቅረፍ ሁነኛ መንገድ ነው። ፖሊሶች ሲያጠፉ የተለያዩ ማኅበራትና ሕግ አስከባሪዎችም ከተጠያቂነት እንዲያመልጡ ያደርጓቸዋል። ከዚህ ቀደም ከሥራ የተባረሩ ፖሊሶች ጥፋታቸውን በማያውቁ ክፍሎች ዳግመኛ ተቀጥረውም ታይቷል። ይህን ችግር ለመቅረፍ መዋቅራዊ ለውጥ እንደሚሻ፤ በተጨማሪም ሰዎች መድልዎ እንደሚያደርጉ መገንዘብ እንዲንዲችሉ ማድረግ አስፈላጊነት አጽንኦት እተሰጠው ነው። ለራስ የማይታወቅ መድልዎን በተመለከተ ቢቢሲን ጨምሮ በርካታ ተቋሞች ለሠራተኞቻቸው ስልጠና ይሰጣሉ። አንድ ሰው መተንፈስ እስኪያቆም ድረስ አንገቱ ላይ መቆም እጅግ የከፋ ድርጊት ቢሆንም፤ ለራስ የማይታወቅ መድልዎ እንዲህ አይነቱና ሌላም የተለያየ ቅርጽ አለው። ብዙ ጊዜ እኛና ሌሎችም መድልዎውን ልብ ላንለው እንችላለን። ለመሆኑ ለራስ የማይታወቅ መድልዎን በስልጠና ማስወገድ ይቻላል? እንዳለብን እንኳን የማናውቀውን መድልዎ መቀነስ ይቻላል? ሙሉ በሙሉ መድልዎን ማስወገድስ? የመጀመሪያው እርምጃ አድልዎ እንዳለብን ማመን ነው። ካሊፎርኒያ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በዚህ ጉዳይ ላይ ያተከረ ተቋም አለ። በተቋሙ በሚዘጋጅ ፈተና ቃላት ወይም ምስል በስክሪን ላይ ቀርበው በአንዳች መንገድ እንዲያዋቀሩ ይጠየቃሉ። ቃላቱ በጎ ወይም መጥፎም ሊሆኑ ይችላሉ። የሚታዩት ምስሎች የጥቁሮችና የነጮች ናቸው። ብዙ ነጮች በጎ ነገርን ከነጭ ጋር፣ መጥፎ ነገርን ከጥቁር ጋር ያዛምዳሉ። ይህን ፈተና ለብዙዎች አይን ገላጭ ነው። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ከ2007 እስከ 2015 በተሠራ ጥናት መሠረት 73 በመቶ ነጮች፣ 34 በመቶ ጥቁሮች እና 64 በመቶ የሌላ ዝርያ ያላቸው ሰዎች ነጭን የሚደግፍና ጥቁር ላይ መደልዎ የሚያሳድር አመለካከት አላቸው። የአራት ዓመት ሕጻናት ሳይቀር እንዲህ አይነቱ መድልዎ ተስተውሎባቸዋል። በዝግመተ ለውጥ ለሰው ወይም ስለእንስሳት ያለን አመለካከት ራሳችንን እንድንከላከል ይረዳ ይሆናል። አሁን ግን ወደ መድልዎ ይወስደናል። የካሊፎርንያ ዩኒቨርስቲው ጄፍሪ ሸርማን "ከአንድ ቀን በላይ የባህሪ ለውጥ ማምጣት ከባድ መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ" ይላሉ። ነገር ግን አንዳንድ ውጤታማ የለውጥ መንገዶች አሉ። 2012 ላይ የተሠራ ጥናት እንደሚያሳየው፤ ከላይ የተጠቀሰውን ፈተና ወስደው ምን ያህል መድልዎ እንደተጫናቸው የተረዱ ሰዎች አሉ። ሰዎቹ ለሁለት ወር ስልጠና ከተሰጣቸው በኋላ መድልዎን በመቀነስ ረገድ አንጻራዊ ለውጥ አሳይተዋል። አንደኛው የስልጠና መንገድ ስለሆነ ሰው አስቀድሞ የሚቀመጥ ግምትን ማስወገድ ላይ ያተከረ ነው። የሥነ ልቦና ተመራማሪዋ ፓትሪሽያ ዴቪን፤ ረዥም ጥቁር ሰው ሲታይ “ቅርጫት ኳስ ይጫወታል” ተብሎ ይገመታል። ይህ ግን ማስረጃ ያለው ሳይሆን ጭፍን መድልዎ ነው። ይህን ጭፍን መድልዎ መለወጥ ቀላል አይደለም። ሁሉም ረዥም ጥቁር ሰው ቅርጫት ኳስ እንደማይጫወት ለመረዳት ቢያንስ ሦስት ጥቁር ረዥም ቅርጫት ኳስ የማይጫወቱ ሰዎች ማወቅ እንደሚጠይቅ በማስረጃነት ያቀርባሉ ተመራማሪዋ። መድልዎን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት ስለመቻሉ እርግጠኛ ባይሆኑም በመጠኑ ባህሪን መቀነስ እንደሚቻል ያምናሉ። "ስር የሰደዱ አስተሳሰቦችን መለወጥ እንችላለን ብዬ ባላስብም አመለካከታችንን በተወሰነ መንገድ አቅጣጫ ማስቀየር እንችላለን። መድልዎ እንዴት ወደተዛባ ወይም ወደማይፈለግ ድምዳሜ እንደሚያደርሰን እንገነዘባለን። ትክክለኛ አመለካከታችንን ለማንጸባረቅ መሞከርም እንጀምራለን" በማለትም ያብራራሉ። ጾታን መሠረት ያደረገ መደልዎ በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በምህንድስና፣ በሒሳብ ሴቶች እንዳይቀጠሩ ምክንያት ነው። በዊስኮንሰን ጾታን መሠረት ስላደረገ መድልዎ ስልጠና ከመሰጠቱ በፊት ሴቶች የሚቀጠሩት 32 በመቶ ነበር። ከስልጠናው በኋላ ግን ወደ 47 በመቶ ከፍ ብሏል። በስታንፎርድ 61 ፖሊሶች ላይ የተሠራ ጥናት እንደሚያሳየው፤ ወንጀል፣ ምርመራ፣ እስር የሚሉትን ቃላት ከጥቁሮች ጋር ያያይዟቸዋል። በዩኒቨርስቲው የሚሠሩ ጥቁሮችና ነጮችን ፎቶ አሳይተው፤ የትኞቹ ወንጀለኛ ይመስላሉ ተብለው ሲጠየቁ የቆዳ ቀለማቸው ጥቁር ሰዎችን መርጠዋል። ሌላ የሥነ ልቦና ተመራማሪም ጥቁሮች ወንጀለኛ ብሎ መበየን፣ የሞት ፍርድ ማስተላለፍም እንደሚደጋገም ያስረግጣሉ። ፖሊሶች በየቀኑ በሚያሰማሩት ኃይል ላይ ለራስ የማይታወቅ መድልዎ ምን ሚና እንዳለው ገና እየተጠና ነው። ጥናቶች እንደሚየሳዩት ግን፤ መሣሪያ ያልያዙ ጥቁሮች ላይ የመተኮስ እድላቸው ሰፊ ነው። "ይህን ሰው የማስቆመው ለምንድን ነው?" የወንጀል ጥናት ባለሙያዋ ሎሪ ፍሪደል እንደሚሉት፤ ለፖሊሶች የሚሰጡት ስልጠና፤ አንድን ሰው የማስቆመው ለምንድን ነው? ብለው እንዲጠይቁ ያነሳሳል። "ይህን ሰው የማስቆመው ለምንድን ነው? ብለን ባዶ ቦታ እንተዋለን። ከዚያ የሚቀርቡት ምርጫዎች ሰውየውን የማስቆመው ዘሩን መሰረት በማድረግ ነው? ወይስ ቤት አልባ? እያልን አማራጮች እንሰጣለን።" ፖሊሶች ከመድልዎ ይልቅ መረጃ ላይ እንዲያተኩሩ እንደሚያበረታቱም ያስረዳሉ። "አንድ ማኅበረሰብ ውስጥ መድልዎ ባላቸው ሰዎች ምክንያት ለፖሊስ ቢደወልም ፖሊስ መድልዎውን ማስቀጠል የለበትም” ይላሉ። የፖሊስ ክፍሎች በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እያወጡ ይህን ስልጠና ቢሰጡም፤ ሁሉም ሰው ግን ውጤታማ ይሆናል ተብሎ አይታሰብም። ሰዎች መድልዎን መቆጣጠር እንደሚችሉ በሚገልጽ ሁኔታ ስልጠና መሰጠት እንዳለበት የሚናገሩ ባለሙያዎችም አሉ። በመድልዎ ላይ ጥናት የሠሩት ልዊስ ጄምስ ከስልጠና ጎን ለጎን ሌሎችም እርምጃዎች መወሰድ እንዳለባቸው ይጠቁማሉ። ለምሳሌ የፖሊሶችን እንቅስቃሴ የሚከታተልና ቪድዮ የሚቀርጽ መሳሪያ መለያ ልብሳቸው ላይ ማድረግ አንድ አማራጭ ነው። ባለሙያዎች እንደሚሉት መድልዎን ለማስወገድ፤ ራስን ለተለያዩ ተሞክሮዎች እንዲሁም አካባቢዎች ማጋለጥ አጋዥ ነው። ለሰባት ዓመታት ከጎዳና ተዳዳሪዎች ጋር የሠሩት ፍሪደል፤ ተሞክሯቸው አመለካከታቸውን እንደቀየረው ያስረዳሉ። የጎዳና ተዳዳሪዎችን በተመለከተ ለራሳቸው ያልታወቀ መድልዎ እንደነበራቸው፤ በማስታወስ በጊዜ ሂደት ግን ይህን መቅረፍ መቻላቸውን ያክላሉ። ‘ኮፊ ዊዝ ኤ ካፕ’ ወይም ከፖሊስ ጋር ቡና እንጠጣ የተሰኘ ፕሮጀክት ሌላው ምሳሌ ነው። የአንድ ማኅበረሰብ አባላት ከፖሊሶች ጋር እንዲተዋወቁ ይረዳል። ማኅበረሰብ ተኮር ፕሮጀክቶች ረዘም ላለ ጊዜ ሲቆዩ የበለጠ ውጤታማ እንደሚሆኑ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
news-45330180
https://www.bbc.com/amharic/news-45330180
ያለመከሰስ መብት ለማን? እስከምን ድረስ?
«ያለመከሰስ መብት»ን በተመለከተ በበርካታ የህግ መዝገበ ቃላት ላይ የሚደጋገመው ትርጓሜ «አንድ ግለሰብ ወይንም አካል የህግ ጥሰት የፈፀመ መሆኑ እየታወቀ ለወንጀሉ ተጠያቂ እንዳይሆን የሚደረግለት ህጋዊ ከለላ» ከሚለው ጋር የሚስተካከል ነው።
የፍትህ ወርቃማ ሚዛን የዚህ «ልዩ ከለላ» ተጠቃሚዎች ከሆኑት መካከል የህዝብ እንደራሴዎች፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት እና የዳኝነት አካላት ይገኙበታል። የመብቱ የጀርባ አመክንዮ ግለሰቦቹን እና አካላቱን በመክሰስ ወይንም ለፍርድ በማቅረብ ከሚገኘው ጠቀሜታ ይልቅ ካለ ክስ እና ተጠያቂነት በማለፍ የሚሳካው ማህበረሰባዊ ግብ የላቀ ነው ከሚል ዕምነት ጋር ይያዛል። ሆኖም ይሄ የከለላ መብት ተነስቶ ግለሰቡ ወይንም አካሉ ላይ ክስ የሚከፈትባቸው አግባቦች ፈፅሞ የሉም ማለት አይደለም። • አብዲ ሞሃመድ ያለመከሰስ መብታቸው ተገፈፈ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲዊ ሪፐብሊክ ህገ- መንግስት እና የክልል ህገ-መንግስታት ይሄንን መብት ከሰጣቸው ወገኖች መካከል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እና የክልል ምክር ቤት አባላት ተጠቃሽ ናቸው። ለአብነት የህዝብ ተወካዮችን በሚመለከተው የአፌዲሪ ህገመንግስት አንቀፅ 55 (6) ላይ የአለመከሰስ መብትን እና መብቱ የሚነሳበትን አግባብ እንደሚከተለው ደንግጓል። «ማንኛውም የምክር ቤቱ አባል ከባድ ወንጀል ሲፈፅም እጅ ከፍንጅ ካልተያዘ በስተቀር ያለ ምክር ቤቱ ፈቃድ አይያዝም፣ በወንጀልም አይከሰስም።» ይሄን መሰረት አድርጎ ያለመከሰስ መብታቸውን ከተነጠቁት የቀድሞ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት መካከል የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔ እና የቀድሞው የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ ዓለማየሁ ጉጆ ይጠቀሳሉ። • «ወይዘሮ ጎሜዝ፤ እርስዎ አያገባዎትም! አርፈው ይቀመጡ በልልኝ» ከሰሞኑ ደግሞ የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚደንት አብዲ ሙሃመድ ኡመር እና ስድስት የክልሉ ምክር ቤት አባላት በሶማሌ ክልል ምክር ቤት ውሳኔ ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰምቷል። እንደ ኢፌዴሪ ህገ-መንግስት ሁሉ በሶማሌ ክልላዊ መንግስት ህገ -መንግስት አንቀፅ 48 (6) ላይ የክልሉ ምክር ቤት አባላት ያለመከሰስ መብት የሚነጠቅበት አግባብ መቀመጡን ልብ ይሏል። • የፖለቲካ አለመረጋጋት ለኢንስትመንት ደንቃራ ሆኖ ነበር
news-55285173
https://www.bbc.com/amharic/news-55285173
ቱሪስቶችን ወደ ሕዋ ለሽርሽር የሚወስደው መንኮራኩር ሊሞከር ነው
ወደ ሕዋ የሚመጥቁ መንኮራኩሮች የሚያመርተው ቨርጅን ጋላክቲክ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ቱሪስት ይዞ የሚጓዝ በሮኬት የሚወነጨፍ አውሮፕላን ሊሞክር ነው።
በእንግሊዛዊው የንግድ ሰው ሰር ሪቻርድ ብራንሰን የተቋቋመው ቨርጅን ጋላክቲክ በቀጣዩ ዓመት (እአአ 2021) ላይ ወደ ሕዋ ቱሪስቶችን መውሰድ እንደሚጀምርም ተገልጿል። እስካሁን ከተመዘገቡት 600 ተጓዦች መካከል ጀስቲን ቢበር እና ሊዎናርዶ ዲካፕሪዮ ይጠቀሳሉ። ለዚህም ወደ ሕዋ ቱሪስቶችን ማመላለስ ከመጀመሩ በፊት የሙከራ በረራው ይካሄዳል። ሁለት ተጨማሪ የሙከራ በረራዎች የሚደረጉም ሲሆን፤ በሦስተኛውና የመጨረሻው የሙከራ ደረጃ ሰር ሪቻርድ ብራንሰንም ይሳፈራሉ። ላለፉት 16 ዓመታት ብዙ ሲባልለት የነበረው የሕዋ የቱሪስቶች ጉዞ ከመጀመሩ በፊት ቨርጅን ጋላክቲክ ዝግጅቱን ለማጠናቀቅ እየሞከረ ነው። የመጀመሪያው ሙከራ የሚካሄደው በሁለት አብራሪዎች ብቻ ነው። አብራሪዎቹ የቀድሞው የናሳ ጠፈርተኛ ሲጄ ስታርኮው እና የቨርጅን ጋላክቲክ ዋነኛ የሙከራ ፓይለት ዴቭ ማኬይ ናቸው። በረራው የሚነሳው ከአሜሪካዋ ኒው ሜክሲኮ ነው። የአውሮፕላኑን ዝግጁነት አብራሪዎቹ የሚፈትሹም ይሆናል። የድርጅቱ መሀንዲሶች ቴክኖሎጂውን አሁን ከሚገኝበት ለማድረስ ብዙ ርቀት ተጉዘዋል። ሂደቱ በኮቪድ-19 ምክንያት ቢስተጓጎልም፤ ሠራተኞች ኒው ሜክሲኮ እና ካሊፎርንያ ውስጥ ሲሠሩ ነበር። የዩናይትድ ኪንግደም የሕዋ ቡድን ፕሬዘዳንት ዊል ዋይትሆርን በረራው "ትልቅ እርምጃ ነው። አስተማማኝና ርካሽ ይሆናል። ሂደቱ ቀላል አልነበረም" ብለዋል። እአአ በ2014 ላይ ከባድ አደጋ ተከስቶ የሕዋ ጉዞ ሂደቱ እንዲመረመር ተወስኖ ነበር። ፕሬዘዳንቱ "የሕዋ ጉዞ እሽቅድድም አይደለም። ቅድሚያ የሚሰጠው ለደኅንት ነው" ብለዋል። አውሮፕላኑ ጠፈርተኞችን ለማሰልጠንም ይውላል። ዋናን ጨምሮ በተለየ ከባቢ አየር ውስጥ መንቀሰቀስና ሌላም ስልጠና ይሰጣል። "የሕዋ ቱሪዝም እና የሕዋ ሳይንስት ውስጥ ስልጠናው ጉልህ ቦታ አለው" ሲሉ ተናግረዋል። ቨርጅን ጋላክቲክ በቅርቡ ቱሪስቶችን ወደ ሕዋ የሚወስድበትን ዲዛይን ይፋ አድርጓል። ይህም ከምድር ወደ ሕዋ ተወንጭፈው ወደ ምድር የሚመለሱበትን መቀመጫ ያካትታል። ከእያንዳንዱ ተጓዥ ፊት ለፊት በሚገኝ ስክሪን ላይ በረራው በቀጥታ ይታያል። ዲዛይኑ ላይ 12 መስኮቶች አሉ። ይህም እስካሁን ከተሠሩ የሕዋ መንኮራኩሮች የበለጠ ነው። መስኮቶቹ ተጓዦች ሕዋን በደንብ እንዲመለከቱ ለማስቻል ነው የተሠሩት። በጉዞ ወቅት የመቀመጫቸውን ቀበቶ ፈትተው መንሳፈፍም ይችላሉ። ስበት ስለማይኖር ተጓዦች ሲንሳፈፉ ራሳቸውን እንዲያዩ በሚል ትልቅ መስታወትም ተገጥሟል።
news-55472572
https://www.bbc.com/amharic/news-55472572
ኮሮናቫይረስ ፡ ስፔን ክትባት አንወስድም የሚሉ ዜጎችን ልትመዘግብ ነው
የኮሮናቫይረስ ክትባት አንወስድም የሚሉ ዜጎችን እንደምትመዘግብ ስፔን አስታወቀች። ዝርዝሩን ለሌሎች የአውሮፓ አገሮች እንደምትሰጥም ተገልጿል።
የጤና ሚንስትሩ ሳልቫዶር ኢላ እንዳሉት፤ ይህ ዝርዝር ለሕዝቡና ለቀጣሪዎች ይፋ አይደረግም። “ቫይረሱን ማሸነፍ የሚቻከው ሁላችንም ስንከተብ ነው” ብለዋል ሚንስትሩ። ከአውሮፓ አገሮች መካከል በቫይረሱ ክፉኛ ከተጎዱት አንዷ ስፔን ናት። ባለፈው ሳምንት በአውሮፓ ሕብረት አባል አገራት ፍቃድ ያገኘውን የፋይዘር/ባዮንቴክ ክትባት መስጠትም ጀምራለች። የጤና ሚንስትሩ ክትባቱን መውሰድ ግዴታ አይደለም ካሉ በኋላ “አንወስድም የሚሉ ሰዎችን ግን እንመዘግባለን። ዝርዝሩን ለአውሮፓውያን አጋሮቻችን እንሰጣለን” ሲሉ ተደምጠዋል። የዜጎችን የግል መረጃ ለመጠበቅ ሲባል ዝርዝሩ ለሕዝብ ይፋ እንደማይደረግ አያይዘው ተናግረዋል። በቅርቡ በተሠራ ዳሰሳ መሠረት ክትባት አንወስድም ያሉ ስፔናውያን ቁጥር ጥቅምት ላይ ከነበረው 47% ወደ 28% ወርዷል። ክትባቱን ለመውሰድ ተራቸው የደረሰ ዜጎች በየግዛታቸው በኩል መረጃ እንደሚደርሳቸው ሚንስትሩ አስረድተዋል። “ክትባት አንወስድም የሚሉ ሰዎች ትክክል እንዳልሆኑ ብናምንም አልወስድም ማለት መብታቸው ነው። የሰዎችን ጥርጣሬ ለማስወገድ እንሞክራለን። መከተብ ሕይወትን ይታደጋል። ከወረርሽኙ ልንላቀቅ የምንችለው በክትባት አማካይነት ነው” ብለዋል። በስፔን በቫይረሱ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ከ50,000 በላይ ሆነዋል። 1.8 ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ በወረርሽኙ ተይዘዋል። በስፔን ከምሽት 5፡00 እስከ ንጋት 12፡00 ድረስ ብሔራዊ የሰዓት እላፊ ገደብ ጥላለች። ዜጎች ከቤት መውጣት የሚፈቀድላቸው ወደሥራ ለመሄድ፣ መድኃኒት ለመግዛት እንዲሁም አረጋውያንና ሕፃናትን ለመንከባከብ ብቻ ነው።
news-46608415
https://www.bbc.com/amharic/news-46608415
ከወንበርና ከሲጋራ የቱ ይገድላል?
መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስለ ወንበር ብዙም የለም። የሆሜር ስንኞችም ላይ አልተጻፈም። በሼክስፒር ሐምሌትም ላይ አልተገኘም።
ልክ 19ኛው ክፍለ ዘመን ሲጋመስ ወንበሮች ብቅ ብቅ ማለት ጀመሩ። ለምሳሌ በቻርለስ ዲከንስ ሥራዎች። ስለ ገጸ ባሕሪ አይደለም የምናወራው፤ መቀመጫ፣ የወገብ ማሳረፊያ ስለሆነው ወንበር ነው የምናወራው። • ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን? ሰው ተቀምጦ በሽታ መሸመት ጀምሯል እየተባለ ነው። የትም ሳይሄድ። ወንበሩ ላይ ሳለ። ጥናቶች መቀመጥ እንደማጨስ ያለ ነው ይላሉ። ልዩነታቸው አንዱ ሳንባን፣ ሌላው ነርቭን ከጥቅም ውጭ ያደርጋሉ። የወንበር አጭር የሕይወት ታሪክ እኛው ፈጥረናቸው እኛኑ የሚፈጁን መሣሪያዎች ብዙ ናቸው። አንዱ ኒክሊየር ነው። አንዱ ደግሞ ወንበር ነው። በጥንታዊ ታሪክ ወንበር ብዙም አልነበረም። ምናልባት ነገሥታት አካባቢ...። ዛሬ ዛሬ ግን ወንበር የሌለበት ቦታ የለም። ጥቂቱን ከዚህ እንደሚከተለው እንዘረዝራለን። ሻይ ቤት፣ ምግብ ቤት፣ ቡና ቤት፣ መኪና ውስጥ፣ ቢሮ ውስጥ፣ ሲኒማ ቤት፣ ሆስፒታል፣ ጸሎት ቤት፣ ትምህርት ቤት፣ መሰብሰቢያ አዳራሽ፣ የገዛ መኝታ ቤታችን ሳይቀር ወንበሮች አሉ። ወንበር ጨረሰን እኮ ጎበዝ! • አትክልት ብቻ ስለሚመገቡ ሰዎች ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮች ሰው ሥልጣን ይወዳል ለማለት "ሰው ወንበር ይወዳል" እንላለን። ያለ ምክንያት አይደለም። እንደው በዓለማችን ላይ ስንት ወንበሮች ይኖራሉ? ብለን ብናስብ በግምት "አንድ ሰው ስንት ወንበር አለው?" ብሎ ማሰብ ነው። ከላይ በተዘረዘሩት ቦታዎች ሁሉ ወንበር ካለ እያንዳንዱ ዜጋ በነፍስ ወከፍ 10 ወንበር አይኖርም? ይኖረዋል እንጂ! የዓለም ሕዝብ 6 ቢሊዮን ነው ብንል ከ60 ቢሊዮን በላይ ወንበሮች ምድርን አጨናንቀዋታል ማለት ነው። ልማድ ሆኖ ለዘመናት የተለየ ስም እንሰጣለን። ለምሳሌ የበረዶ ዘመን። ይህን ዘመን ምን ብለን እንጥራው? "የወንበር ዘመን?" ዓለማችን ድንገት እንዲህ ወንበር በወንበር የሆነችበት ምስጢር ግን ምንድነው? ሕዝቦች ሆይ! ወንበር አትውደዱ! ከ16ኛው እስከ 18ኛው ክፍለ ዘመን ብቅ ብቅ ማለት የጀመሩት ወንበሮች ቁጥራቸው በድንገት ማሻቀብ የጀመረው በኢንዱስትሪ አብዮት ዘመን እንደሆነ ይታመናል። ከዚያ በፊት ወንበር አልነበረም ባንልም አብዛኛው ሕዝብ ወንበር ነበረው ለማለት የታሪክ ሰነዶች አልተገኙም። ወንበር ድሮም የነገሥታትና የመኳንንት ንብረት ነበር። እንኳን ያኔ ይቅርና ዛሬም እኮ በቆንጆ ጣውላ የተላገ ምቹ ወንበር ያለው ሕዝብ ስንቱ ነው? ውድ ነዋ! ነገር ግን በ18ኛው ክፍለ ዘመን በፈረንሳይ ፍርድ ቤት ዘና ለጠጥ ብሎ መቀመጥ ለተራ ዜጎች በመፈቀዱ ወንበሮች ዝነኛ እየሆኑ መጡ። • ሀና እና ጓደኞቿ የሰሩት የእናቶች ምጥ መቆጣጠሪያ ከዚያ በፊት ግን ለዘመናት ወንበሮች ከሥልጣን ፣ ከብልጽግናና ከኑሮ ደረጃ ጋር ብቻ ነበር የሚዛመቱት። ድሮ ንጉሥ በወንበር ላይ ይቀመጥና አሽከሮቹ ከነወንበሩ ነበር ከቦታ ቦታ የሚያንቀሳቅሱት። ዛሬ ዛሬ እንኳ ያ የለም። ነገሥታትም አንድ ጊዜ ወንበሩ ላይ ከተቀመጡ በኋላ ማንም እንዲያንቀሳቅሳቸው አይፈቅዱም። ወንበርና ሥልጣን ወንበር "ሥልጣን" ለሚለው ቃል አቻ ነው። በእንግሊዝኛ ሥራ አስኪያጅ የሚለው ቃል «ቼይር ፐርሰን» የሆነውም ለዚሁ ነው። ድሮ የአገሪቱ ቆንጆውና ግዙፉ ወንበር የንጉሡ ነበር። በዚህ ዘመን ደግሞ ተሽከርካሪውና ባለቆዳው ወንበር የሥራ አስኪያጁ ነው። ድሮ ወንበር እምብዛምም ነበር ብለናል። በቪክቶሪያ ዘመን አብዛኛው ሥራ ፋብሪካ ውስጥ ስለነበር ወንበር አይታሰብም ነበር። • በሳተላይቶች ዙሪያ ሰባት አስደናቂ እውነታዎች ከፈረንሳይ አብዮት በኋላ ግን የሥራ ሁኔታ እየተቀየረ መጣ። በተለይ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ጀምሮ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ብቅ ብቅ ማለት ሲጀምሩ እነ መተየቢያ፣ እነ ስልክ፣ እነ ኤሌክትሪክ ሲመጡ ሥራ የሚሠራበትም መንገድም በዚያው መጠን እየተቀየረ ሄደ። ጋዜጣ፣ ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥን፣ መጻሕፍት፣ ቪዲዮ መጫወቻ፣ ኢንተርኔት ወዘተ ወደ ሕይወታችን ብቅ ብቅ ማለት ሲጀምሩ ነገሩ ሁሉ መልኩን ቀየረ። ከወንበራችን ተጣብቀን መዋል ጀመርን። ወንበር እና ሲጃራ በአሁን ዘመን ያለ ወንበር ሥራ መሥራት ይቻላል? ወንበሮች እጅግ አስፈላጊ እየሆኑ መጥተዋላ። የብሪታኒያ የልብ ጤና ፋውንዴሽን ባስጠናው ጥናት በቀን ውስጥ በአማካይ 9.5 ሰዓት እንቀመጣለን፤ በሥራም ይሁን በሌላ። ይህ ማለት ሲሶውን የሕይወታችንን ዘመን በሥልጣን ባይሆንም በወንበራችን ላይ እናሳልፈዋለን። ይህ በፍጹም መልካም ዜና አይደለም። ለምን? አጥንታችንና ጡንቻችን ስንቀመጥና ስንንቀሳቀስ ባሕሪያቸው ይለያያል። ስንንቀሳቀስ ወጠርጠር፣ ጠንከርና ፈርጠም ይላሉ። ቁጭ ካልን ደግሞ ይልፈሰፈሳሉ። • የአለማየሁ ተፈራ ፖለቲካዊ ካርቱኖች ዘለግ ላለ ሰዓት በወንበር ለጠጥ ብሎ መቀመጥ ወገባችንን የሚያደቅ ተግባር ነው። ለዚህም ይመስላል በዓለም ላይ ለጀርባ ሕመም አንደኛው አጋላጭ ምክንያት አብዝቶ መቀመጥ የሆነው። በቀደመው ዘመን ወረርሽኝ ገዳይ ነበር። በዚህ ዘመን ደግሞ ቁጭ ማለት በሚያመጣው ጣጣ ሕዝብ እያለቀ ነው። ስኳር፣ የልብ ሕመም፣ ካንሰር ወዘተ አንድ ቦታ በመወዘፍ የሚመጡ ናቸው። መቀመጥ አደጋ አለው! ከስድስት ዓመት በፊት አንድ ጥናት ተደረገ። 8ሺህ የሚሆኑ ሴቶች ላይ ነበር ጥናቱ ያተኮረው። ውጤቱ አስገራሚ ነበር። ዘለግ ላለ ሰዓት ወንበር ላይ ቁጭ ያሉት ሴቶች ሕዋሶቻቸው በፍጥነት ገረጀፉ። የማርጀት ምልክቶች ጎልተው ታዩባቸው። በደንብ ከሚንቀሳቀሱና ብዙም የማይቀመጡት ሴቶች ጋር ሲነጻጸሩ በ8 ዓመት ገርጅፈው ነው የተገኙት። • ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ስለተዘረፉ ቅርሶች ምን እናውቃለን? ረዥም ሰዓት ቁጭ የሚል ሰው ጉዱ ፈላ ይላሉ ተመራማሪዎች። አንዳንድ ጥናቶች እንደውም ረዥም ሰዓት በመቀመጥ የሚመጣው ፍዳ ኃይለኛ የሰውነት እንቅስቃሴ ቢደረግም የሚፈታ አይደለም ይላሉ። እና ምን ተሻለ? በየሩብ ሰዓቱ ከወንበራችን እየተነሳን በሰበብም ያለሰበምም መንቀሳቀስ ነው የሚበጀን። እግረኞች ተስፋ አላቸው። ባለመኪኖች ግን በጊዜ መላ ፈልጉ ተብላችኋል።
48159598
https://www.bbc.com/amharic/48159598
በቻይና ዢንጃን ግዛት ፖሊስ የስልክ መተግበሪያን በመጠቀም ክትትል ያደርጋል ተባለ
የቻይና ፖሊስ የሞባይል መተግበሪያዎችን በመጠቀም በዢንጃን ግዛት የሚኖሩ የዊጎር ጎሳ አባላትን መረጃ ይሰበስባል ሲል ሂይውመን ራይትስ ወች አስታወቀ።
ሐሙስ ይፋ በሆነ ሪፖርት ላይ እንደተገለፀው፤ የሞባይል መተግበሪያው ጥቅም ላይ የዋለው የጎሳው አባላት ጠባይን ለመከታተል፣ ከሰዎች ጋር ያላቸውን ማኅበራዊ ሕይወት ለመሰለል፣ የኤሌክትሪክ ፍጆታቸውን እንዲሁም ከባህር ማዶ ሰዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለመከታተል እንደሆነ ተገልጿል። የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የዊጎር ሙስሊሞች በቻይና ከፍተኛ በደል እንደሚደርስባቸው ይገልጻሉ። • ተቃዋሚዎቿ ፊት ፎቶ የተነሳችው ሙስሊም ሴት • የቻይና ሙስሊሞች ምድራዊ 'ጀሐነም' ሲጋለጥ የተባበሩት መንግሥታት በበኩሉ በሚሊየን የሚቆጠሩ የዊጎር ሙስሊሞች በዢንጃን ማረሚያ ቤቶች መታሰራቸው መረጃ እንዳለው ገልጿል። የቻይና መንግሥት ግን "የተሀድሶ ትምህርት ማዕከላት" ናቸው ሲል ያስተባብላል። የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እንደሚሉት፤ የቻይና መንግሥት የስልክ መተግበሪያውን የዜጎችን መረጃ ለመመዝገብና ለመሰነድ አገልግሎት ላይ ያውለዋል። በተጨባጭ 36 አይነት ግለሰቦች ላይ ትኩረት ያደርጋል። ይህም የቤታቸውን የፊት ለፊት መውጪያ በር አልፎ አልፎ የሚጠቀሙ፣ ከፍተኛ የሆነ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ያላቸው እንዲሁም ያለ አካባቢው ባለስልጣናት እውቅና ለሐጂ ጉዞ የሚሄዱ ግለሰቦችን ያካትታል። ከመተግበሪያው የተገኘው መረጃ ቻይና ዜጎቿን ወደምትከታተልበት የማዕከላዊ መንግሥቱ የመረጃ ቋት ውስጥ ይገባል። • ተመድ ቻይና ''ሙስሊሞችን በጅምላ መያዟ » አሳስቦኛል አለ • ሁሉንም በደህንነት ካሜራ የምትመለከተው ቻይና እንደ ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ከሆነ ይህ የማዕከላዊ መንግሥቱ ግለሰቦችን መከታተያ መንገድ "በዓለም ላይ ትልቁ ሰዎችን የመከታተያ ቋት" ነው። ይህ የመረጃ ቋት ከመንገድ ላይ የደህንነት ካሜራዎች፣ ከነዳጅ ማደያ ስፍራዎች፣ ከትምህርት ቤቶች የሚገኙ መረጃዎችን በመሰብሰብ፤ 'አጠራጣሪ' ባህሪ የሚያሳዩ ግለሰቦች ላይ ባለስልጣናት ክትትል እንዲያደርጉ መረጃ ይሰጣል ተብሏል። በመላው ቻይና ከ170 ሚሊየን በላይ የመንገድ ላይ ካሜራዎች የሚገኙ ሲሆን፤ በ2020 ደግሞ 400 ሚሊየን አዳዲስ ካሜራዎች ተተክለው ሥራ ላይ ይውላሉ ተብሏል። ይህ ቻይና በዓለም ላይ ትልቁ በካሜራ ክትትል ማድረግ የሚያስችል መረብ ለመዘርጋት ያላትኘዕ እቅድ አካል ነው።
51788581
https://www.bbc.com/amharic/51788581
"በኮሮናቫይረስ ተያዙ ስለተባሉት ኢትዮጵያዊያን ለጊዜው የምናውቀው ነገር የለም" በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ
ከትናንት በስቲያ በተባበሩት አረብ ኢምሬትስት በኮሮናቫይረስ ተያዙ ከተባሉ የተለያዩ አገር ዜጎች መሀል ሁለቱ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን የዚያው አገር የጤና ሚኒስቴር መግለጹ ይታወሳል።
ይህንኑ በተመለከተ ዝርዝር ማብራሪያ እንዲሰጡ ከቢቢሲ የተደወለላቸው በአቡዳቢ የአምባሳደሩ ተወካይ ወ/ሮ ኑሪያ መሐመድ "እኛም እንደናንተው በሚዲያ ከመስማት ውጭ ምንም መረጃው የለንም" ያሉ ሲሆን ዛሬ (እሑድ) ግን ለተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ ዝርዝር ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ኦፊሳሊያዊ ጥያቄ ማቅረባቸውን ተናግረዋል። ለምንድነው ጥያቄውን ለማቅረብ የዘገያችሁት ተብለው የተጠየቁት በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ተጠባባቂ ሚሲዮን መሪ (charge' d' affaires) የአምባሳደሩ ተወካይ ኑሪያ መሐመድ "ዛሬ ገና ነው ቢሮ የተከፈተው፤ ቅዳሜ ዝግ ነው እዚህ..." ሲሉ መልሰዋል። የአምባሳደሩ ተወካይ ሁለቱ ኢትዮጵያዊያን አሁን የት ሆስፒታል እንደሚገኙና የጤንነታቸውን ሁኔታ እንዲገልጹ በቢቢሲ ተጠይቀው "ሁለቱ ኢትዯጵያዊየን ከየት እንደመጡና አሁን የት እንዳሉ ምንም መረጃ እንደሌላቸው ተናግረው እኛም ጉዳዩን እንደናንተው በሚዲያ ነው የሰማነው" ብለዋል። "የሚመለከተውን መሥሪያ ቤት ጠይቀናል፤ አዲስ መረጃ ካለ እንነግራችኋለን፤ ለጊዜው መረጃ አልሰጡንም" ብለዋል። የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር 13 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ኮቪድ-19 ተጠቂዎች መሆናቸውን ደርሼበታለሁ ብሎ ነበር። ከነዚህ ውስጥ ሦስቱ የራሱ ዜጎች ናቸው። የተቀሩት ከሞሮኮ፣ ቻይና፣ ሕንድ፣ ታይላንድ፣ ሳኡዲና ኢትዯጵያ መሆናቸው ተዘግቦ ነበር። ከ13ቱ ሁለቱ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የጤናና የበሽታዎች መከላከል ሚኒስትር ከትናንት በስቲያ አርብ ዕለት ነበር ያሳወቀው። የኢትዮጵያ ኤምባሲ ግን 'ለጊዜው ዜጎቹ ስላሉበት ሁኔታ ምንም መረጃ የለኝም' ነው የሚለው። በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ከአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሌላ የዱባይ ቆንጽላ መረጃ ካለው በሚል ቢቢሲ ወደዚያው የደወለ ሲሆን "ጉዳዩ አቡዳቢ ስለሆነ እኛ ምንም የምናውቀው ነገር የለም፤ 'እዚያው ጠይቁ' የሚል ምላሽ አግኝቷል። ሁለቱ ኢትዯጵያዊያን ስላሉበት ሁኔታ በተመለከተ የአቡዳቢም ሆነ የዱባይ ኤምባሲ ቢሮዎች ለጊዜው መረጃ የለንም ቢሉም የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሁኔታውን እየተከታለ መሆኑን ገልጾ ሁለቱ ኢትዮጵያዊያን ለዓመታት እዚያው ይኖሩ የነበሩና በቅርቡ ወደየትኛውም አገር ጉዞ እንዳላደረጉ አረጋግጫለሁ ብሏል። የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሚኒስትር ዲኤታ ሊያ ታደሰ ዛሬ (እሑድ) ማለዳ በትዊተር ሰሌዳቸው ተያዙ ከተባሉት 13 ሰዎች 2ቱ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን አረጋግጠው ኢትዮጵያውያኑ ለረዥም ዓመታት የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የኖሩና በቅርቡ ወደየትኛውም ሃገር ያልተጓዙ ናቸው ብለዋል። ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ደግሞ ከሁለቱ መካከል አንደኛው ግለሰብ ድጋሚ ተመርምረው ቫይረሱ እንደሌለባቸው ተረጋግጧል ሲሉ በትዊተር ገፃቸው አሳውቀዋል። የተበባበሩት አረብ ኢምሬትስ እስካሁን በአገሬ 45 ሰዎች በኮሮና መያዛቸውን ደርሼበታለሁ ብላለች። ከ45ቱ በተጨማሪ 18 አዳዲስ ተጠቂዎች እንደተገኙ የዓለም ጤና ድርጅት ድረ ገጽ ያትታል። በአሁኑ ሰዓት የኮሮና ተጠቂዎቹ ተለይተው ሕክምና እየተደረገላቸው እንደሆነም ተዘግቧል። ይህን ተከትሎ ከዛሬ ጀምሮ ትምህርት ቤቶች ለአራት ሳምንታት እንዲዘጉ ትዕዛዝ ተላልፏል። አልፎም ዜጎቿ ወደ ሌሎች ሃገራትን የሚያደርጉትን ጉዞ ገታ እንዲያደርጉ አሳስባለች።
54920166
https://www.bbc.com/amharic/54920166
ኮሮናቫይረስ፡ ኮቪድ-19 ገና አልሰለቸንም- የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ
ዓለም የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባትን ወደማግኘት እየተቃረበ ቢሆንም የኮሮናቫይረስ መከላከያዎችን ማላላት የለበትም ሲሉ የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊው አሳሰቡ።
ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የኮሮናቫይረስ አሁንም የዛሬ ስምንት ወር እንደነበረው አስጊ ወረርሽኝ መሆኑን እንደቀጠለ ነው ብለዋል። በመላው ዓለም በኮቪድ-19 ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1.2 ሚሊዮን ደርሷል። በፓሪስ እየተካሄደ ባለው የሰላም ጉባዔ ላይ "በኮቪድ-19 ታክቶን ይሆናል ነገር ግን እርሱ ገና አልሰለቸንም" ብለዋል ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም። "የአውሮፓ አገራት እየታገሉ ነው ነገር ግን ስርጭቱን ለማቆም የተወሰዱት እርምጃዎች እንዲሁም ቫይረሱ ምንም ለውጥ አላሳየም" ሲሉም አክለዋል። ከቅርብ ቀናት ወዲህ በኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት ላይ የተሻሉ ግኝቶች እየታዩ መጥተዋል። ሰኞ ዕለት ፋይዘር እና ባዮንቴክ እየሰሩት ያለው ክትባት በተደረገለት የመጀመሪያ ደረጃ ፍተሻ 90 በመቶ የመከላከል አቅም እንዳለው አረጋግጠናል ብለዋል። ረቡዕ ዕለት ደግሞ የሩስያ ተመራማሪዎች የሰሩት የመከላከያ ክትባት 92 በመቶ ውጤታማ መሆኑን አስታውቀዋል። ነገር ግን ሁለቱም ክትባቶች የሚደረግላቸውን የቁጥጥር ፍተሻ ማለፍ አለባቸው ተብሏል። ዶ/ር ቴድሮስ ገና ደህንነቱ እና ውጤታማነቱ መፈተሽ ባለበት ክትባት ላይ መተማመን አደገኛ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል። "ክትባት በፍጥነት ያስፈልጋል፣ ነገር ግን እጃችንን አጣጥፈን ቁጭ አንልም" ብለዋል።
54690654
https://www.bbc.com/amharic/54690654
በዚህ ዓመት በጣና ላይ የሚታየውን አረም ለማጥፋት እየተሰራ ነው
በ2013 ዓ.ም በጣና ሐይቅ ላይ በዓይን የሚታየውን አረም ለማጥፋት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ።
ትኩረቱን እምቦጭ እና ሌሎች መጤ አረሞች ላይ ያደረገው የጣና ሃይቅና ሌሎች ውሃ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ አያሌው ወንዴ (ዶ/ር) እንዳስታወቁት በዘንድሮው ዓመት በዓይን ሊታይ የሚችለውን አረም ለማስወገድ ይሰራል ብለዋል። በዚህም በዕቅዱ መሠረት ሙሉ በሙሉ በዓይን የሚታይ አረም እንዳይኖር የሚደረግ ቢሆንም በቀጣዩ ዓመት የእምቦጩ ዘር በተለያየ ምክንያት ሐይቁ ላይ በመቅረት 10 በመቶ አረም በድጋሚ ሊኖር ይችላል ብለዋል። በጣና ሐይቅ ላይ የተከሰተውን የእምቦጭ አረም በአንድ ወር ዘመቻ ለማጥፋት ከጥቅምት 09 እስከ ህዳር 09/2013 ዓ.ም የሚቆይ የአንድ ወር ዘመቻ መጀመሩ ይታወቃል። የዘመቻው ዋና ዓላማ 90 በመቶ እምቦጭን ከጣና ሐይቅ ለማረም እና ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮችን በማቀናጀት በጋራ ችግሩን በመፍታት ተምሳሌት ለማድረግ መሆኑን ጠቁመዋል። የዘመቻው አፈጻጸም ከፌደራል እስከ ቀበሌ ድረስ ክትትል እና ግምገማ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው ከሰው ሃይል በተጨማሪ በማሽን እና ትራክተር የተደገፈ ዘመቻ መሆኑን አስረድተዋል። በቀን ወደ 12ሺህ ሰው ወደ ሥራ ለማሰማራት ታቅዶ እስካሁን በቀን ከ11 ሺህ በላይ ሰዎችን ማሰማራት ተችሏል። 43 የማስወገጃ ጣቢያ ባሉት በዚህ ዘመቻ ላይ ከአንድ ወረዳ በስተቀር በሌሎች ወረዳዎች ዕቅዱን እንደሚሳካ ግምት አለ ብለዋል። እምቦጭን ከጣና ሃይቅ ለማስወገድ የተጀመረው ዘመቻ በሁሉም ቀበሌዎች መጀመሩን ያስረዱት ዶክተር አያሌው እስካሁን ምን ያህል የሐይቁ ክፍል ከእምቦጭ እንደጸዳ ግን አልገለጹም። ከተለያዩ አካባቢዎች ለዘመቻው የሚመጡ ሰዎች የሚቆዩ ለተወሰነ ጊዜ መሆኑ እና ከኮሮናቫይረስ ስጋት ጋር ተያይዞ ሰዎች በገንዘብ እና በቁሳቁስ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። በተፋሰሶች ልማት ባለስልጣን ባልደረባ እና የብሔራዊ ደረጃ የቴክኒክ ኮሚቴ ተወካይ የሆኑት አቶ ዮሃንስ ዘሪሁን በበኩላቸው እምቦጭን ለማስወገድ ባለሃብቶች፣ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም የልማት ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። ወንዞች እና የጣና ሐይቅ ከሚገናኙባቸው 15 ቦታዎች 5 የሚደርሱትን አረሙን በማስወገድ በምትኩ ደንገል እና የእንስሳት መኖ በመትከል ሐይቁ ራሱ እንዲያገግም ጭምር መታቀዱን አስታውቀዋል። እምቦች አረም በሦስት ዞኖች፣ 9 ወረዳዎች እና አንድ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ በ30 ቀበሌዎች ላይ ተንስፋፍቶ 4 ሺህ 300 ሄክታር የሚሆነው የሐይቁን ክፍልም ወሯል፡፡
55056387
https://www.bbc.com/amharic/55056387
ኤለን መስክ የማይክሮሶፍቱን ቢል ጌትስን በልጦ የዓለማችን 2ኛው ቢሊየነር ሆነ
የቴክኖሎጂ ፈጣሪው ኤለን መስክ በአጭር ጊዜ ውስጥ የዓለማችን 2ኛው ቢሊየነር ሆነ።
ኤለን መስክ መስክ የማይክሮሶፍቱን ቢል ጌትስን በልጦ ነው እዚህ ደረጃ ላይ የተቀመጠው። የኤለን መስክ ሀብት በአጭር ጊዜ የተምዘገዘገው ቴስላ የተባለው የኤሌክትሪክ መኪና አምራች ኩባንያው በስቶክ ገበያ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱን ተከትሎ ነው። ይህ ድንገተኛ የሀብት ጭማሪ የኤለን መስክን የሀብት መጠን ከ7 ቢሊዮን ወደ 128 ቢሊዮን አድርሶታል። የቢሊየነሮችን ዝርዝር የሚያስቀምጠው ብሉምበርግ እንደሚለው ከሆነ በዚህ ሰዓት ኤለን መስክን የሚበልጠው የዓለማችን ቁንጮ ሀብታም የአማዞኑ ጄፍ ቤዞስ ብቻ ነው። ቴስላ የአሌክትሪክ አምራች በአሜሪካ የስቶክ ገበያ ትልልቆቹን 500 ኩባንያዎች ደረጃ በሚያስቀምጠው ኤስ ኤንድ ፒ (S&P 500) ዝርዝር እንደሚገባ ባስታወቀ በአጭር ጊዜ ውስጥ ነው የሀብት ግስጋሴው በአስደንጋጭ መልኩ ሽቅብ የወጣው። የዚህን ዜና መውጣት ተከትሎ በርካታ ሰዎች የቴስላ መኪናን ድርሻ ለመግዛት ሽሚያ እንዲፈጠር አድርጓል። የቴስላ ኩባንያ ጠቅላላ ግምትም ግማሽ ትሪሊዮን ዶላር አድርሶታል። ይህን ተከትሎ ምንም እንኳ የኤለን መስክ ድርሻ በቴስላ ኩባንያ ውስጥ አነስተኛ ቢሆንም የሰውየው ሀብት ጣሪያ እንዲነካ ምክንያት ሆኗል። ቴስላ መኪና ቴስላ ኩባንያው በዓለም ላይ ከፍተኛ ዋጋ ከሚሰጠው መኪና አምራች ኩባንያ ዋንኛው ነው። ሆኖም ከቶዮታ፣ ቮልስ ዋገን እና ጄኔራል ሞተርስ ጋር ሲነጻጸር የሚያመርታቸው መኪናዎች ብዛት እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። ማክሰኞ ዕለት መስክ ጀርመን በነበረ ጊዜ የአውሮጳ የመኪና ገበያ ውስጥ መኪና በገፍ የማምረት ሥራ ውስጥ መግባት እንዴት አዋጭ እንደሆነ ሲያስረዳ ነበር። አሜሪካ ብዙ ሰዎች ትልልቅ መኪና መንዳት ነው ምርጫቸው፤ እዚህ አውሮጳ ግን ትንንሽ ናቸው መኪናዎች፥ ቴስላ በርከት ያለ መኪና በማምረት የዋጋ ተፎካካሪ መሆን የሚችል ይመስለኛል ብሏል መስክ። ቴስላ የኤሌክትሪክ መኪና አምራች ለተከታታይ ዓመታት ኪሳራን ሲያስመዘግብ ቆይቶ ከዚያ በኃላ ግን ላለፉት ለ5 ተከታታይ ሩብ ዓመታት ትርፋማ እየሆነ ቆይቷል። የትርፍ እድገቱንየኮቪድ ወረርሽኝም አልበገረውም። መቀመጫውን ካሊፎርኒያ ያደረገው ቴስላ በኤስ ኤንደ ኤስ የስቶክ ማርኬት ግማሽ ትሪሊዮን የሀብት ግምት ዋጋ ይዞ በመግባት የመጀመርያው ነው። ቢልጌትስ በዓለም የቢሊየኖች ተርታ ለዘመናት ይዞት የቆየውን መሪነት የተነጠቀው በፈረንጆች 2017 ሲሆን አዲሱ ቢሊየነር ደግሞ የአማዞኑ ቤዞስ ነበር። የቢል ጌትስ ሀብት 127.7 ቢሊየን ዶላር ነው፤ ሆኖም ገንዘቡን በብዛት ለበጎ አድራጎት ስለሚሰጥ እንጂ ከዚህ በላይ የሀብት ግምት ይኖረው ነበር ይላል ብሉምበርግ። የጄፍ ቤዞስ ሀብት አሁን ላይ 182 ቢሊየን ደርሶለታል። ቤዞስም እንደ መስክ ሁሉ በዚህ ዓመት ገቢው በከፍተኛ ደረጃ ጨምሮለታል። ይህም ወረርሽኙ የበይነ መረብ ግዢ እንዲፋፋም እድል በመፍጠሩ ነው። ኤለን መስክ ባለፈው ሳምንት የኮቪድ ተህዋሲ ሳይዘኝ አልቀረም ብሎ በትዊተር ሰሌዳው ጽፎ ነበር። መጠነኛ ምልክቶችን ሲያሳይ ነበር። ኤሎን መስክ በፈጠራት የጠፈር ታክሲ "ስፔስ ኤክስ" 4 የስነ ፈለክ ተመራማሪዎች ወደ ዓለም አቀፉ የጠፈር ጣቢያ የተሳፈሩት በቅርብ ሳምንት ነበር። ኤሎን መስስ ተወልዶ ያደገው በፕሪቶሪያ ደቡብ አፍሪካ ሲሆን በ17 ዓመቱ ወደ ካናዳ ካቀና በኃላ ለትምህርት በልውውጥ የስኮላርሺፕ ፕሮግራም ወደ አሜሪካ ፔኒሲልቬኒያ ዩኒቨርስቲ ገባ። በዚያው አጋጣሚ ነው አሜሪካ የቀረው። አሁን ነዋሪነቱ በአሜሪካ ሎሳአንጀለስ ካሊፎርኒያ ውስጥ ነው። 49 ዓመቱ ሲሆን የ7 ልጆች አባትም ነው።
news-57196959
https://www.bbc.com/amharic/news-57196959
የሶሪያ ስደተኛ ነኝ ብሎ 'ያጭበረበረው' ጀርመናዊ ወታደር ለፍርድ ቀረበ
ከሰሞኑ አንድ ጀርመን ወታደር በሽብር ወንጀል ተከሶ ፍርድ ቤት ቀርቧል።
ወታደሩ ራሱን የሶሪያ ስደተኛ ነኝ በሚል ሃሰተኛ ሽፋን ተጠቅሞ በፖለቲከኞች ላይ ጥቃት ሊፈፅም ሲያቅድ ነበር ተብሏል። ፍራንኮ ኤ የተባለው ወታደር ነዋሪነቱን ፈረንሳይ ያደረገ ሲሆን ሁለት ህይወት ይመራም ነበር ተብሏል። በሌላ መልኩ ዴቪድ ቤንጃሚን በሚል ስደተኛ ስምም ተመዝግቦ ተገኝቷል። የግለሰቡ ሁለት ህይወት መምራት የተጋለጠው የእጅ ጣት አሻራ በመጠቀም ነው። በስራትስቦርግ ተቀማጭነቱን ያደረገው ይህ ወታደር ክርስቲያን የሶሪያ ስደተኛ ነኝ በሚልም መመዝገቡን ተከትሎ የጣት አሻራቸው ተመሳሳይ መሆኑም ታውቋል። አቃቤ ህግ ባቀረበው ክስ መሰረት የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሄይኮ ማስ፣ የፓርላማው ምክትል አፈ ጉባኤና አንድ የአይሁድ የመብት ታጋይ ግለሰቡ ኢላማ ካደረጋቸው ፖለቲከኞች ዝርዝር መካከል ተጠቅሰዋል። ይህንን ለማስፈፀም በሚል ግለሰቡ ሃሰተኛ የሩሲያ ስደተኛ ማንነትን በመላበስና ጥቃት ሊያቀነባብር ነበር በማለት ወንጅሎታል። ወታደሩ የሩሲያ ስደተኛ ማንነትን የተላበሰው በጥቃቱ ስደተኞች ጥፋተኛ ተብለው እንዲወነጀሉና ፀረ-እስልምና ሁኔታዎች ተጠናክረው እንዲወጡ ነው በማለት አቃቤ ህግ ክሱን አቅርቧል። በግለሰቡ ቤተሰቦች የዕቃ ማስቀመጫ ክፍል ውስጥ ተቀጣጣይ ፈንጆች እንዲሁም የቦምብ መስሪያ ቁሳቁሶች ተገኝቷል። እንዲሁም በተደረገው ፍተሻ ሂትለርን የሚያወድሱ ፅሁፎችና የድምፅ ቅጅዎች መገኛታቸውም ይፋ ተደርጓል። ይህ ጉዳይ የጀርመን ጦር አባላት ከጀርመን ቀኝ ክንፍ ፅንፈኞች ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ካሳዩት በርካታ ሁኔታዎች መካከል አንዱ ነው ተብሏል። ወታደሩ የተያዘው በአውሮፓውያኑ 2017 ሲሆን በቪየና አየር ማረፊያ ላይ በመፀዳኛ ቤት የተገኘ ሽጉጥን ለማውጣት ሲሞክር ነበር ተብሏል። ግለሰቡ ከተያዘም በኋላ በጀርመን የተከለከለው የናዚ አርማ በቤቱም ሳሎን ቤት እንደተገኘም ተገልጿል። ወታደሩ የቀኝ ክንፍ ፅንፈኛ ነው ቢባልም እሱ በበኩሉ ግን ፅንፈኛ እንዳልሆነና ምንም አይነት ጥቃት አልፈፀምኩም በማለቱ ፀንቷል። በጀርመን የግል መረጃን መጠበቅ መረጃ ጋር በተያያዘ በወንጀል ተጠርጥረው የቀረቡ ሰዎች የአባታቸው ወይም (የቤተሰባቸው ስም) ለህዝብ ይፋ አይሆንም።
news-51569235
https://www.bbc.com/amharic/news-51569235
በናይሮቢ በፖሊስ የተገደለው ሞተረኛ ጉዳይ ከባድ ተቃውሞ አስነሳ
በመቶዎች የሚቆጠሩ በኬንያ መዲና ናይሮቢ የሚገኙ ሞተረኞች ሆስፒታል ውስጥ አንድ ሞተረኛ መገደሉን ተከትሎ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል። ሞተረኛው አንድ ህጻንን ለመርዳት ድንገተኛ ክፍል ሲገባ በፖሊስ እንደተገደለ እየተዘገበ ነው።
የ 24 ዓመቱ ዳንኤል ምቡሩ ውሀ ውስጥ ሰምጦ በህይወትና ሞት መካከል የነበረን አንድ ህጻን ሕይወት ለማዳን ነበር ሞተሩን እየነዳ ወደ ድንገተኛ ክፍል ዘው ብሎ የገባው። ነገር ግን የሆስፒታሉ ጠባቂዎች እንዴት ከነሞተርህ ድንገተኛ ክፍል ውስጥ ትገባለህ በማለት ሊያስቆሙት ሲሞክሩ ግርግር ይፈጠራል። እሰጥ አገባው ለትንሽ ደቂቃዎች ከቆየ በኋላ የሆስፒታሉ ሰራተኞች ፖሊስ ይጠራሉ። በዚሁ ግርግር በሀል ሞተረኛው በፖሊስ ተተኩሶበት እንደሞተ ሌሎች ሞተረኞች ገልጸዋል። ምንም እንኳን ፖሊስ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከመስጠት ቢቆጠብም የኬንያ ተሟጋቾች ግን ፈጣን ምርመራ እንዲደረግ ጠይቀዋል። • ሮበርት ሙጋቤ እና አራፕ ሞይ: አንጋፋዎቹ የአፍሪካ መሪዎች ሲታወሱ • በደም እጥረት እየተፈተነች ያለቸው ኬንያ በኬንያ በተለይም በመዲናዋ ናይሮቢ 'ቦዳቦዳ' በመባል የሚታወቁት ሞተረኞች በከፍተኛ ሁኔታ የትራንስፖርት ፍሰቱን የሚያግዙ ናቸው። ''ወጣቱ ሞተረኛ ህፃኑን ለማዳን የቻለውን ሁሉ ነው ያደረገው። ሊመሰገን የሚገባው ዜጋ ነው። እሱ ያሰበው ወደ ድንገተኛ ክፍል ሄዶ ህጻኑን ስለማዳን ብቻ ነበር'' ብለዋል የብሄራዊ 'ቦዳቦዳ' ደህንነት ማህበር ዋና ጸሀፊው ኬቨን ሙባዲ። አክለውም የማህበሩ አባላትና ማንኛውም ሞተረኞች እንዲረጋጉና ፖሊስ ገለልተኛ በሆነ መልኩ አፋጣኝ ምርመራ እንዲጀመር አሳስበዋል። በአምነስቲ ኢንተርናሽናል የኬንያ ቅርንጫፍም በበኩሉ ምርምራ እንዲካሄድ የጠየቀ ሲሆን ሞተረኛው ድብደባ ከተፈጸመበት በኋላ ወደ ሆስፒታሉ የጥበቃ ቢሮ ከተወሰደ በኋላ በፖሊስ ተተኩሶበት ሕይወቱ አልፋለች ብሏል። • ''ባልሽን በጥንቆላ አሳብደሸል አሉኝ፤ እኔ ግን እስካሁን ከጎኑ አልተለየሁም'' በርካታ ኬንያውያን በማህበራዊ ሚዲያዎች በኩል ዳንኤል ምቡሩን ተኩሶ የገደለው የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ውሎ ለፍርድ እንዲቀርብ ቢጠይቁም ፖሊስ እስካሁን በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል። ሞተረኛው ተሸክሞት ወደሆስፒታል የመጣው ህጻን ህክምናውን እየተከታተለ እንደሆነና በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን ''ዳንኤል ምቡሩ ጀግናችን ነው፤ ሞት አይገባውም ነበር'' ብለዋል ኬንያውያን።
news-48768338
https://www.bbc.com/amharic/news-48768338
የራሱን ዘር ተጠቅሞ ታካሚዎቹን ያስረገዘው ዶክተር የሕክምና ፈቃድ ተከለከለ
ካናዳዊው የርቢ [ፈርቲሊቲ] ዶክተር የራሱን ወንዴ ዘር ተጠቅሟል በመበሏ የሕክምና መስጫ ፈቃዱን ተነጥቋል።
ካናዳውያውያን ፈቃድ ሰጭዎች 'እጅግ ኃላፊነት የጎደለው' ሲሉ የራሱን የወንዴ ዘር ለሕክምና የተጠቀመውን ዶክተር ወቅሰውታል። ዶክተሩ ከ1970ዎቹ ጀምሮ ሕክምና ሲሰጥ የነበረ [በግሪጎሪ አቆጣጠር] የ80 ዓመት፤ ዕድሜ ጠገብ እና ታዋቂ ሰው ነበር ተብሏል። • የሙያውን ፈተና ለመጋፈጥ ከከተማ ርቆ የሄደው ሐኪም የፈቃድ ሰጭ እና ነሺው አካል ሠራተኛ የሆኑት ዶክተር ስቲቨን ቦድሊ የቅጣታችን ልኩ ፈቃድ መንጠቅና ቀላል የገንዘብ ቅጣት ብቻ መሆኑ እጅግ ያሳዝናል ሲሉ ቁጭታቸውን ገልፀዋል። በግሪጎሪ አቆጣጠር ከ2014 ጀምሮ የሕክምና አገልግሎት ሰጥተቅ የማየውቁት የርቢ ዶክተሩ ባርዊን ቅጣታቸውን ለመቀበል ጠበቃቸውን ይላኩ እንጅ ብቅ አላሉም። በክሱ መሠረት ዶክተር ባርዊን ቢያንስ 13 ታካሚዎቻቸውን የራሳቸውን ወይንም ባለቤትነቱ ያልታወቀ የወንዴ ዘር ተጠቅመው አስረግዘዋል ተብሏል። ከ50-100 ያሉ ሕፃናት ዶክተሩ ለእናቶቻቸው በሰጡት የወንዴ ዘር አማካይነት ተወልደዋል ቢያንስ 11 ሕፃናት ደግሞ የዶክተሩ ልጆቸ መሆናቸው ታውቋል። ዶክተሩ እስካሁን ድረስ ክሳቸው እየታየ ያለው በሕክምና ፈቃድ ሰጭ እና ነሽ አካል እንጂ በፍርድ ቤት አይደለም። • 17 ታካሚዎችን የመረዘው ዶክተር
news-53204122
https://www.bbc.com/amharic/news-53204122
68 ቀናት ፅኑ ሕሙማን ክፍል የከረመው የኮቪድ-19 ታማሚ አስደናቂ ታሪክ
«ሌላ አገር ቢሆን ኖሮ ይሄኔ ሟች ነበርኩ» ይላል ስኮትላንዳዊው ስቴፈን ካሜሮን የሆስፒታል አልጋው ላይ እንዳለ።
የ43 ዓመቱ አውሮፕላን አብራሪ 68 ቀናት በፅኑ ሕሙማን ክፍል ውስጥ በመተንፈሻ መሣሪያ [ቬንቲሌተር] በመታገዝ ከርሟል። እነዚህን ሁሉ ቀናት የነብስ ግቢ፤ ነብስ ውጪ ትግል ሲያደርግ የነበረው ታድያ ተወልዶ ባደገባት ከተማ ሳይሆን ብዙ ሺህ ኪሎ ሜትሮች ርቃ ባለችው ሆ ቺ ሚን ነው። የቪዬትናም ዋና ከተማ ሆ ቺ ሚን ግርግር ይበዛታል። ወጪ ገቢው ብዙ ነው፤ ከባለ አንድ እግር ተሽከርካሪ፣ ባለሁት፣ ሦስትና አራት እግር ተሽከርካሪዎች እየተጋፉ፤ ፉጨታቸውን እያሰሙ የሚተራመሱባት። ቪዬትናም 95 ሚሊየን ሕዝብ አላት። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዓለምን ሲንጥ፤ ያልተናጠች እየተባለች ትንቆለጳጰሳለች። ከዚህ ሁሉ ሚሊዮን ሕዝብ በወረርሽኙ የተያዙባት ጥቂት መቶ ሰዎች ናቸው። የሞተስ? ካሉ መልስ ምንም ነው። ስቴፈን ቪዬትናም ውስጥ በኮቪድ-19 ምክንያት ወደ ፅኑ ሕሙማን ክፍል የገባ የመጨረሻው ሰው ነው። በአገሬው መገናኛ ብዙሃን አንድ ስም ተሰጥቶታል 'ታካሚ 91' የሚል። መጋቢት ላይ ህመም አጋጥሞት ሆስፒታል ሲገባ በጤና ባለሙያዎች የተሰጠው ሕጋዊ መለያው ነው። የስቴፈን የመትረፍ ዕድል 10 በመቶ ነበር። አብዛኛውን ጊዜ ራሱን ስቶ ነበር። ሐኪሞች 'Ecmo' የተባለ በጣም በፅኑ ለታመሙ ህሙማን የሚገጠም ማሽን ገጥመው ሲከታተሉት ነው የከረመው። ማሽኑ ከታካሚው ሰውነት ደም ይወስድና ኦክስጅን ሞልቶ ደሙን መልሶ ወደ ሰውነቱ ይለቀዋል። ሐኪሞች ስቴፈን ከትንፋሽ ማጠር ብቻ ሳይሆን ከሌሎችም እክሎች ማዳን ነበረባቸው። የደም መርጋት አንዱ ነበር። ኩላሊቱ መሥራት በማቆሙ ምክንያት ዳያሊስስ ማድረግ ነበረባቸው። የሳንባው የመተንፈስ አቅም ወደ 10 በመቶ ወርዶ ነበር። ስቴፈን ወርሃ ታህሳስ ላይ ነበር ወደ ቬዬትናም ያቀናው። እንደ አብዛኛዎቹ ምዕራባውያን አብራሪዎች ወደ ምሥራቅ ያቀናው የተሻለ ክፍያ ፍለጋ ነው። ለቪዬትናም አየር መንገድ የመጀመሪያ በረራውን ለማካሄድ ሁለት ቀናት ሲቀሩት ሆ ቺ ሚን ውስጥ የውጭ አገር ዜጎች የሚዝናኑባት አንዲት መጠጥ ቤት ጓደኛውን ለማግኘት አቀና። በወቅቱ ቪዬትናም በበሽታው የተያዙባት ሰዎች ቁጥር 50 ነበር። ነገር ግን በነጋታው ትኩሳት ይሰማው ጀመር። እሱ የነበረበት መጠጥ ቤት የነበሩ 12 ሰዎች ውጤታቸው ሲመጣ ኮቪድ-19 እንዳለባቸው ተነገራቸው። ስቴፈንም እንደዚያው። ከዚህ በኋላ ነው የአገሪቱ ባለሥልጣናት መጠጥ ቤቱን ዘግተው ሁኔታውን መመርመር የጀመሩት። ከመጠጥ ቤቱና እሱ ከሚኖርበት አፓርትማ ጋር ግንኙነት ያላቸው 4 ሺህ ሰዎች ተለይተው እንዲቆዩ ተደረገ። የስቴፈን ጤና እየተቃወሰ ሲመጣ 'ቬንቲሌተር' ተገጠመለት። ሌሎችም የፅኑ ሕሙማን ክፍል መግባት የነበረባቸው ሰዎች ገቡ። ነገር ግን ሌሎቹ ታካሚዎች አንድ በአንድ እየዳኑ ሲወጡ ስቴፈን ይብስበት ጀመር። ስቴፈን ለመትረፉ አንደኛው ምክንያት ሌሎች ሰዎች ተሽሏቸው ወደ ቤት ሲመለሱ እሱ ብቻ በመቅረቱ ሐኪሞች ትኩረታቸውን እሱ ላይ በማድረጋቸው ነው በሚለው ብዙዎች ይስማማሉ። ስቴፈን ከበርካታ ቀናት ራስን መሳት በኋላ ሰኔ 5 ነቃ። ስቴፈን አጋዥ መተንፈሻ ተገጥሞለት ፅኑ ህሙማን ክፍል ሲገባ በዓለማችን የኮሮናቫይረስ ተያዦች ቁጥር 1 ሚሊዮን ነበር። ስቴፈን ሲነቃ ቁጥሩ 7 ሚሊዮን ደርሷል። «በጣም ዕድለኛ ነኝ። እግሮቼ ብቻ ሰውነቴን መሸከም አቅቷቸዋል። ለእሱ ደግሞ በቀን ሁለት ጊዜ 'ፊዚዮቴራፒ' እየሰራሁ ነው» ይላል ስቴፈን። «ከክፍል ክፍል በተሽከርካሪ ወንበር ስወሰድ እንዲሁም ማሽን ሲገጠምልኝ ትዝ ይለኛል፤ የተቀረው ነገር ግን ደብዛዛ ነው አላስታውሰውም።» ስቴፈን ካሜሮን 20 ኪሎግራም ቀንሷል። አልፎም ከፍተኛ የሆነ ድካም አለበት። ካለፈበት ሁኔታ አንፃር ጭንቀት ሊገጥመውም ይችላል። «አሁን የምፈልገው አገሬ መግባት ነው። ፀጥ ረጭ ያለ ቦታ ናፍቆኛል። እዚህ ሙቀቱ በጣም ከባድ ነው። ቀዝቀዝ ያለ አየር በጣም ናፍቆኛል።»
48565572
https://www.bbc.com/amharic/48565572
ሩሲያ ውስጥ 23 ሜትር ርዝመት ያለው የብረት ድልድይ ተሰረቀ
በሩሲያዋ መርማንስክ ተብላ በምትታወቀው የአርክቲክ ግዛት ውስጥ አንድ የባቡር ሃዲድ ተዘርግቶበት የነበረ የብረት ድልድይ በመሰረቁ ምርመራ ሊጀመር ነው።
የግዛቲቱ አቃቤ ሕግ እንዳለው 23 ሜትር ርዝመትና 56 ቶን ክብደት ያለው የብረት ድልድይ ባልታወቁ ሰዎች ነው የተሰረቀው። ይህ ብዙም አግልግሎት አይሰጥም ነበር የተባለው ድልድይ ከግዛቲቱ ዋና ከተማ በ170 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ በሚገኝ በደን የተሸፈነ ስፍራ ላይ የሚገኝ እንደነበር የአካባቢው ጋዜጣ ዘግቧል። ተነቅሎ የተወሰደው ድልድይ በአካባቢው ይወጣ የነበረን ለየት ያለ ማዕድን የሚያመላልሱ ባቡሮች ይተላለፉበት የነበረ ሲሆን የማዕድን ማምረቻው ከአሥር ዓመታት በፊት ከስሮ በመዘጋቱ ብዙም እንቅስቃሴ አይደረግበትም ነበረ። የአካባቢው ነዋሪዎች ድልድዩ ከነበረበት ቦታ እንደሌለ ያወቁት ባለፈው ግንቦት ወር ላይ ነው። • በዱባይ በደረሰ የመኪና አደጋ 17 ሰዎች ሞቱ • የሞተር ብስክሌቶች እና ሕገወጥነት በአዲስ አበባ በማሕበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች ላይ የሚዘዋወሩት ምስሎች እንደሚያሳዩት የድልድዩ ዋነኛ ክፍል ከቦታው የለም። የተወሰነው አካሉ ግን በወንዙ መሃል ላይ ይታያል። ይህም ዘራፊዎቹ መጀመሪያ ድልድዩን አፍርሰው ወንዙ ውስጥ እንዲወድቅ ካደረጉ በኋላ ብረቱን እየለያዩ አንድ በአንድ ሳይወስዱት እንዳልቀረ ተገምቷል። ምንም እንኳን በድልድዩ ላይ የተፈፀመው ዝርፊያ ለየት ያለና ግዙፍ ቢሆንም ያስከተለው ጉዳት በገንዘብ ሲሰላ ከዘጠኝ ሺህ የአሜሪካ ዶላር እንደማይበልጥ በመጥቀስ በጣም ዝቅተኛ እንደሆነ አንድ ድረ-ገጽ ዘግቧል። በማቅለጥ መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል ሲባል ሩሲያ ውስጥ ከብረት የተሠሩ ነገሮች ላይ የሚፈፀም ዝርፊያ ከረዥም ጊዜ አንስቶ ችግር ሆኖ የቆየ ጉዳይ ነው። ከሁለት ዓመት በፊት 10 ሜትር ርዝመት ያለው የሶቪየት ዘመን ፀረ-አውሮፕላን ሚሳዔል ከወዳደቁ ብረቶች ጋር ተሽጦ ማቅለጫ ውስጥ መፈንዳቱ ይታወሳል። • "ደላላው ወደ ቤቱ ወሰደኝ፤ በዚያው ቀን አስገድዶ ደፈረኝ"
news-48224719
https://www.bbc.com/amharic/news-48224719
ሪፖርት፡ ብሔር ተኮር ግጭት ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር መጨመር ምክንያት ነው
በዓለማችን በአንድ ዓመት ውስጥ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 41 ሚሊየን መድረሱን አንድ ሪፖርት አመለከተ።
የጌድዮ ተፈናቃዮች 'ግሎባል ሪፖርት ኦን ኢንተርናል ዲስፕለስመንት' የተሰኘው ሪፖርት እንደጠቆመው፤ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተነሱ ግጭቶች የተፈናቃይ ሰዎች ቁጥር እንዲጨምር አድርገዋል። • በችግር ላይ የሚገኙት ተፈናቃዮች የሀገር ውስጥ መፈናቀል ላይ ያተኮረው ይህ መረጃ እንደሚያሳየው፤ ከዚህ ቀደም ዓለም ላይ ይህን ያህል ቁጥር ያላቸው ሰዎች ተፈናቅለው አያውቁም። በሪፖርቱ መሰረት፤ ባለፈው ዓመት ብቻ 28 ሚሊየን ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸውን ወደሌላ የሀገራቸው ክፍል ተሰደዋል። የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር እአአ ከ2017 መጨረሻ በአንድ ሚሊዮን ሲጨምር፤ ከአጠቃላይ የዓለማችን ስደተኞች ቁጥር ደግሞ በሦስት ሁለተኛ ብልጫ አሳይቷል። • የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ተፈናቃዮች ለችግር ተዳረግን አሉ ከፍተኛ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ካሉባቸው ሀገራት መካከል ለዓመታት ግጭት የነበረባቸው ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሶሪያ ቀዳሚዎቹ ሀገራት ናቸው። ኢትዮጵያም በቅርቡ በተከሰቱ ብሔር ተኮር ግጭቶች ሳቢያ ከፍተኛ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ካሉባቸው ሀገራት ዝርዝር የገባች ሲሆን፤ ባለፈው ዓመት ወደ ሶስት ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። • የሞያሌ ተፈናቃዮች ያሉበት አሳሳቢ ሁኔታ ጎርፍ፣ ሰደድ እሳትና ድርቅን የመሳሰሉት ተፈጥሯዊ ክስተቶች በቻይና፣ በሕንድ፣ በፊሊፒንስና በአሜሪካ ለሚሊየን ሰዎች መፈናቀል ምክንያት ሆነዋል። በጠቅላይ ሚንስትሩ ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ሰክሬታሪያት የሆኑት ቢልለኔ ስዩም ትናንት መግለጫ በሰጡበት ወቅት፤ ከግለሰቦች መፈናቀል ጀርባ ካሉ ተጠርጣሪዎች 1300 በቁጥጥር ሥር ውለዋል ብለው ነበር። ፕሬስ ሴክረተሪዋ በመግለጫቸው፤ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ወደቀያቸው እየተመለሱ እንደሆነና፤ እስካሁን 875ሺህ ሰዎች ይኖሩበት ወደነበሩበት አካባቢ እንደተመለሱ አሳውቀዋል። • የተጠበቀውን ያህል የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች አልተመለሱም ተፈናቃዮች ፍትሕዊ በሆነ መንገድ እርዳታ እንዲያገኙ፣ በግጭት የወደሙ ንብረቶችን ለመተካትም እየተሠራ መሆኑም ተገልጿል። ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች መካከል የተፈናቃዮችን ሰብዓዊ መብት ማስጠበቅ፣ ወደተፈናቀሉበት አካባቢ ከተመለሱ በኋላ መኖሪያ፣ ትምህርትና ህክምና እንዲያገኙ ማስቻል ተጠቅሷል። ከተፈናቃዮች ጉዳይ ጋር በተያያዘ ተግዳሮት ከሆነው አንዱ ስለተፈናቃዮች የሚሰራጭ ሀሰተኛ መረጃ ነው ያሉት ቢልለኔ፤ "ለሰዎች መፈናቀል ምክንያት የሆኑ ግለሰቦች በሕግ ይጠየቃሉ" ብለዋል። • መፈናቀል፡ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የአንድ ዓመት ፈተናዎች አንዱ እስካሁን በተለያዩ ክልሎች ግጭት በማስነሳት ከተጠረጠሩ 2517 ግለሰቦች መካከል 1300 ያህሉ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ገልጸዋል። እነዚህ ተጠርጣሪዎች በቅርቡ በቤንሻንጉል የተነሳውን ግጭት ጨምሮ በቡራዩ፣ በድሬዳዋና ሌሎችም አካባቢዎች ከተቀሰቀሱ ግጭቶች ጀርባ አሉ የተባሉ ተጠርጣሪዎች መሆናቸውን ፕሬስ ሴክረተሪዋ ተናግረዋል።
50668124
https://www.bbc.com/amharic/50668124
ኢንስታግራም ለአዳዲስ ተመዝጋቢዎች እድሜን ሊጠይቅ ነው
ኢንስታግራም በአባልነት የሚቀላቀሉትን አዳዲስ ግለሰቦች የትውልድ ቀናቸውን እንዲያስገቡ ሊጠይቅ መሆኑ ተሰማ። ለዚህም ምከንያቱ ነው የተባለው እድሜን ያገናዘቡ ምስሎችን ለማጋራት እንዲያስችለው መሆኑ ተገልጿል።
ምስል የሚጋሩበት ይህ የማህበራዊ ሚዲያ አባላቱ የራሳቸው አካውንት እንዲኖራቸው ቢያንስ እድሜያቸው 13 እንዲሆን ይጠይቅ ነበር። የትልውልድ ቀንን መጠየቅ ኩባንያው እድሜን መሰረት ያላደረጉ ማስታወቂያዎች ለልጆች እንዳይደርሱ ማድረግ ያስችለዋል ሲል ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። • የማህበራዊ ድረ-ገፅ ዘመቻዎች • የማሳይ ማህበረሰብን ሽርጥ ብቻ የሚለብሰው ስዊድናዊ ታዳጊ ኢንስታግራም ግን ማስታወቂያ ከለውጡ ጀርባ ያለ ምክንያት አይደለም ሲል አስታውቋል። ኩባንያው "ዕድሜ መጠየቃችን በእድሜ ትንንሽ ልጆች ይህንን ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይቀላቀሉ ለመከላከል፣ ታዳጊዎች ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን፣ እንዲሁም እድሜያቸውን ያገናዘበ አጠቃቀም እንዲኖር ለማድረግ ይረዳል" ሲል በጡመራ ገፁ ላይ አስታውቋል። " ለእኛ የምታጋሩንን የልደት ቀናችሁን ተጠቅመን፣ በእድሜያችሁ ልክ የተመጠነ አጠቃቀም እንዲኖራችሁ እንሰራለን፤ ለምሳሌ ለታዳጊዎች እንዴት የግል መረጃቸውንና ገፃቸውን መጠበቅና መከላከል አንደሚችሉ ትምህርት መስጠት" ሲልም ያክላል። መረጃው ኢንስታግራምን ለአዋቂዎች የሚለቃቸውን የቁመራ፣ አልኮሆል መጠጦች፣ እና የወሊድ መቆጣጠሪያን የተመለከቱ መልዕክቶች ለልጆች እንዳይደርሱ ለማድረግ ይረዳዋል። ኩባንያው በሚቀጥሉት ሳምንታት ወጣቶች የግል መረጃቸውን ደህንነት የሚጠብቁበትን ክፍል እንዲከፍቱት ያበረታታል። " በእድሜ ከፍ ያሉ ተጠቃሚዎች ለስራችን አስፈላጊ በመሆናቸው እድሜን ያማከለ ልምድ እንዲኖር ማድረግ ብቻ ሳይሆን ለረዥም ጊዜ አብሮን የኖረውን መመሪያ በማክበር አንዳንድ መልዕክቶች ለታዳጊዎች እንዳይደርሱ መከላከል ያስችለናል" ሲሉ የኢንስታግራም ምርቶች የበላይ ኃላፊ ቪሻል ሻህ ለሮይተርስ ተናግረዋል። እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከሆነ ኢንስታግራም እስካሁን ድረስ አዳዲስ አባላቱ አካውንት ሲከፍቱ እድሜ አይጠይቅም፤ እንዲሁም ፌስቡክ በባለቤትነት የሚያስተዳድረው ይህ የማህበራዊ ሚዲያ ገፅ፤ አባላት ያስገቡት የልደት ቀን እውነት መሆኑን አያረጋግጥም ነበር። • "ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ብወስድም አረገዝኩ" • ኢትዮጵያ ከኤርትራ የሚያደርጉት ጨዋታ ለምን አይካሄድም? በልጆች ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች የኢንስታግራምን ውሳኔን ሲተቹ "ተጣርቶ ለማይገኝ፣ ተጠቃሚዎች የልደት ቀን መጠየቃቸው ልጆችን እድሜ ተኮር የሆነ ልምድ እና አጠቃቀም እንዲኖራቸው እንዲሁም ለመከላከል ነው የሚሉት ምክንያቶች ውሃ አያነሱም" ብለዋል። ወደፊት የሚወጡ አዳዲስ የአጠቃቀም መመሪያዎች ሕጻናትና ታዳጊዎች በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ላይ ተጨማሪ ከለላ እንዲያገኙ ያስችላል ተብሏል። ነገር ግን የማህበራዊ ሚዲያዎች መጀመሪያውኑ ሕጻናት ሊጠቀሟቸው የሚችሏቸው መሆናቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋልም ብለዋል። ፌስቡክ በበኩሉ "ሁሉም ሰው እድሜውን በትክክል እንደማይሞላ እንረዳለን። በኦንላየን ተጠቃሚዎችን እድሜ እንዴት መሰብሰብና የተሻለ ማጣራት እንደሚቻል በዘርፉ ላይ የተሰማሩ በሙሉ እየሰሩበት ያለ ነው። እኛም መንግስትም የተሻለ ነው የምንለውን መንገድ ለመፈለግ እየሰራን ነው" ሲል ገልጿል። የየትኛውም ኢንስታግራም ተጠቃሚ እድሜው በገፁ ላይ ለተጠቃሚዎች ፊት ለፊት እንዲታይ አይደረግም።
news-54569299
https://www.bbc.com/amharic/news-54569299
ትራምፕ ዳግም ምርጫውን ሊያሸንፉ የሚችሉባቸው ምክንያቶች
ከምርጫ በፊት የሚከናወኑ አስተያየት መሰብሰቢያዎች የትራምፕ ተቀናቃኝ ጆ ባይደን ምርጫውን ሊያሸንፉ እንደሚችሉ የሚጠቁሙ ናቸው።
ትራምፕ ለደጋፊዎቻቸው ንግግር ሲያደርጉ ከምርጫ በፊት የምርጫ ውጤቶችን የሚተነብዩ ተቋማት ዲሞክራቱ ጆ ባይደን ምርጫን የማሸነፍ እድል ከ83.5 % እስከ 87% ያደርሱታል። ጥቅምት 24 በሚካሄደው ምርጫ ባይደን የማሸነፋቸው ነገር የማይቀር ነው የሚሉ በርካቶች ናቸው። የቢቢሲ የሰሜን አሜሪካ ፖለቲካ ተንታኙ አንቶኒ ዙራከር ግን ታሪክ እራሱን ከደገመ እውነታው ሌላ ሊሆን ይችላል ይላል። ትራምፕ ሳይጠበቁ ምርጫውን ሊያሸንፉ ይችላሉ። የዛሬ አራት ዓመት የሆነውም ይህ ነው ይላል አንቶኒ። . በመጀመሪያው የዶናልድ ትራምፕ እና የጆ ባይደን ክርክር ማን የበላይ ሆነ? . አንድ ወር ያህል በቀረው የአሜሪካ ምርጫ ማን ያሸንፋል? ባይደን ወይስ ትራምፕ? . ዶናልድ ትራምፕ ቻይና በጆ ባይደን ላይ ምርምራ ትጀመር ሲሉ ጠየቁ ልክ የዛሬ 4 ዓመት ምርጫው ሊካሄድ ጥቂት ሳምንታት ብቻ በቀሩበት ወቅት የወቅቱ የትራምፕ ተቀናቃኝ ሂላሪ ክሊንተን ትራምፕን እንደሚረቱ ቅድመ ግምቶች ነበሩ። የኋላ ኋላ ነገሮች ተቀያይረው ትራምፕ ምርጫውን አሸንፈዋል። ትራምፕ ቃለ መሃላ ፈጽመው አሜሪካንን ለተጨማሪ 4 ዓመታት እንዲመሩ ህዝቡ ከፈቀደ ለዚህ ምክንያቶቹ የሚከተሉት ናቸው። በምርጫ ዋዜማ ያልተጠበቀው ሲከሰት የዛሬ አራት ዓመት ለምርጫው 11 ቀናት ብቻ ሲቀሩ ሂላሪ ክሊንተን የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሳሉ የግል ኢሜል ሰርቨርን በመጠም የሥራ ኢሜይል ልውውጥ ስለማድረጋቸው ዳግም ምርመራ በኤፍቢአይ ይጀምራል ተባለ። የኤፍቢአይ ዳይሬክተር ጄምስ ኮሚይ በሂላሪ ላይ ምርመራ መከፈቱ ለትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ኃይል ሆኖ ነበር። የዘንድሮ ምርጫ ከመከናወኑ በፊትም ተመሳሳይ የፖለቲካ ውጥንቅጥ ለትራምፕ የድል በር ሊከፍት ይችላል። እስካሁን ግን የተከሰቱት ነገሮች ትራምፕን ነጥብ የሚያስጥሉ እንጂ ወደ ዋይት ሃውስ የሚያስገቡ ሆነው አልተገኙም። ለምሳሌ ኒው ዮርክ ታይምስ ትራምፕ የከፈሉትን የገቢ ግብር መጠን ይፋ ማድረጉ እና በኮቪድ 19 የተሳለቁት ፕሬዝደንት በኮቪድ 19 ምክንያት ሆስፒታል መግባታቸው ለምርጫ ቅስቀሳቸው ውድቀት ነው። ሃንተር ባይደን እና ጆ ባይደን እአአ 2014-2019 የጆባይደን ልጅ ሃንተር ባይደን በዩክሬን የሚገኝ አንድ ነዳጅ አውጪ ኩባንያ ቦርድ አባል ሆኖ ሰርቷል። በወቅቱ ባይደን ደግሞ በፕሬዝደንት ኦባማ አስተዳደር ውስጥ ምክትል ፕሬዝደንት ነበሩ። አባት እና ልጅ አንድ ወቀሳ ይቀርብባቸዋል። ሃንተር በቦርድ አባልነት የሚያገለግልበት ኩባንያ በዩክሬን መንግሥት የጸረ-ሙስና ምርመራ እንዳይደረግበት ባይደን ስልጣናቸውን ተገን በማድረግ ጫና አሳድረዋል የሚል። ባይደን ምክትል ፕሬዝደንት ሳሉ ይህን ስለመፈጸማቸው ቢረጋገጥ ታሪክ ቀያሪ ክስተት ሊሆን እንደሚችል ይታመናል። የቅድመ ምርጫ ግምቶች ስህተት ሪፐብሊካን ፓርቲን ወክለው ከዴሞክራቱ ጆ ባይደን ጋር አንገት ለአንገት የተናነቁት ፕሬዝደንት ትራምፕ ቁርጣቸውን የሚያውቁት ጥቅምት 24/2013 ነው። ይሁን እንጂ የአሜሪካ የምርጫ ትንቅንቅ የምርጫ ዕለት ብቻ የሚታይ አይደለም። የቅድመ ምርጫ ምርጫም አለው። ድምፅ ሰብሳቢ ድርጅቶች የትኛውን ዕጩ ነው የምትመርጡት እያሉ ከአሜሪካውያን የሚሰበስቡትን ድምፅ ይፋ የሚያደርጉበት ነው ቅድመ ምርጫ ማለት። መግቢያችን ላይ እንደጠቀስነው በዚህ ቅድመ ምርጫ ጆ ባይደን የማሸነፍ ሰፈ እድል ተሰጥቷቸዋል። 2016 የነበሩት ቅድመ ምርጫ ውጤቶች ግን የምርጫ ውጤት ተገላቢጦሽ ሆነው ነበር የተገኙት። የቅድመ ምርጫ ውጤቶች ሂላሪ እንደሚያሸንፉ ቢያመላክቱም የመጨረሻው ውጤት ግን ድሉን ለትራምፕ አሳልፎ ሰጥቷል። ቅድመ ምርጫ ውጤቶች ረብ የለሽ እና አሳሳች ሊሆኑ ይችላሉ ይላል የፖለቲካ ተንታኙ አንቶኒ ዙራከር። በ2016 የሆነውም ይሄው ነው። ምርጫውን ማን ሊያሸንፍ ይችላል ሲባል 'ማን ወጥቶ ድምጹን ሊሰጥ ይችላል?' የሚለውን መገመት ማለት ነው። ይህ ደግሞ ሁሌም ፈታኝ ነው ይላል። በኮሮናቫይረስ ስጋት ዘንድሮ መራጮች ድምጽ የሚሰጡት በፖስታ ቤት አማካኝነት ነው። ድምጽ ሰጪዎች የምርጫ ቅጾችን እና የፖስታ አድራሻ በትክክል መሙላት ካልቻሉ ድምጻቸው አይቆጠርም። ማርሽ ቀያሪ ፕሬዝደንታዊ የፊት ለፊት ክርክሮች ትራምፕ እና ባይደን ከሳምንታት በፊት ፊት ለፊት በተገናኙ ጊዜ ነጥብ የጣሉት ፕሬዝደንት ትራምፕ ነበሩ። ቁጡነታቸው፣ ባይደንን እና ጋዜጠኛውን በተደጋጋሚ ማቋረጣቸው በበካታ ድምጽ ሰጪዎች ዘንድ አልተወደደላቸውም። ትራምፕ ይህን ለመቀየር አንድ እድል አላቸው። በቀጣይ በሚኖራቸው ክርክር ላይ እርግት ብለው የተሻለ ነጥብ የሚያስመዘግቡ ከሆነ የምርጫውን ውጤቱን አቅጣጫ የማስቀየር እድል ይኖራቸዋል ይላል አንቶኒ። ወሳኝ ግዛቶች ላይ ድምጽ ማግኘት በዚህ ምርጫ ላይ የበላይነትን በመያዝ ለማሸነፍ ቁልፍ በሚባሉት ግዛቶች ላይ በልጦ መግኘት ያስፈልጋል። ትራምፕ እንደ ሚቺጋ እና ዊስኮንሲን ያሉ ቁልፍ ግዛቶች ላይ ማሸነፍ የሚችሉ አይምሰሉም። ይሁን እንጂ እንደ ፔንስያለቫኒያ እና ፍሎሪዳ ያሉ ግዛቶች ላይ የሚያሸንፉ ከሆነ ቀጣይ አራት ዓመታትን በዋይት ሃውስ መሰንበታቸውን ሊያረጋግጡ ይችላሉ።
44335789
https://www.bbc.com/amharic/44335789
ለአንድ ወር ከአልኮል መታቀብ በጤናችን ላይ የሚኖረው አስደናቂ ውጤት
በመጀመሪያው ሳምንት በጣም ከባድ ነው፤ በአስራ አምስተኛው ቀን እየቀለለ ይሄዳል፤ በሃያ ዘጠነኛው እና በሰላሳኛው ቀን የተለየ ስሜት ይሰማናል ከዚያም ሰውነታችን ምስጋና ያቀርባል።
ለአንድ ወር ያህል ከአልኮል መጠጥ መታቀብ በጤና ላይ እጅግ ጠቃሚ ውጤት እንደሚያስገኝ የሚሳይ ጥናት ይፋ ተደርጓል። ጥናቱ የመጀመሪያ እንደሆነም ተነግሮለታል። በለንደን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የተካሄደው የዚህ ጥናት ዓላማ የምግብ መዋሃድ ሂደትን (Metabolism) በተለይ ደግሞ ለካንሰር በሽታ ምክንያት የሚሆን የአመጋገብ ሥርዓትን፤ ለተወሰነ ጊዜ የአልኮል መጠጥን ከመተው ጋር በማገናኘት መዳሰስ ነው። በጥናቱ ከአልኮል የታቀቡት ሰዎች የኮሌስትሮል መጠናቸው ፣ የሰውነት ክብደታቸው እንዲሁም የደም ዝውውራቸው ላይ አወንታዊ ውጤት ታይቷል። ሌላኛው በቅርቡ የይፋ የሆነው የጥናቱ ግኝት እንደሚያስረዳው አልኮል መጠጣት ካንሰርን የሚያስከትሉ ሴሎችን እድገት ያፋጥናል። በዚህም አይነት ሁለት የስኳር በሽታና የጉበት በሸታን ያስከትላል። በተመራማሪዎቹ ጉአታም መህታ፣ ስቴዋርት ማክዶናልድ እና አሌክሳንድራ ክሮንበርግ የተመራው ይህ ጥናት አልኮል ለአካል ጉዳት ብሎም ለሞት በማይዳርጉ በሽታዎች ምክንያት ሞትን በማስከተል ዋነኛ ሰበብ ይሆናል። "ጥናቱ የአልኮል መጠጥ አልፎ አልፎ እንዲሁም በከፍተኛ ደረጃ የሚወስዱ 141 ሰዎች የተሳተፉበት ሲሆን፤ ሁሉም ሰዎች በአማካይ ከሚፈቀድላቸው እጥፍ በላይ የአልኮል መጠጥን ይጠቀማሉ" ሲል አንዲይ ኮግላን የተባለው ተመራማሪ ገልጿል። በጥናቱ ከተካተቱት ሰዎች 94ቱ ሙሉ በሙሉ አልኮል እንዲያቆሙ ሲደረጉ ቀሪዎቹ የነበራቸውን ልምድ እንዲቀጥሉ ተደረገ። የመጀመሪያው ቡድን ተሳታፊዎች እድሜያቸው ወደ አርባ ስድስት የሚጠጋ 43 ወንዶችና 51 ሴቶች ናቸው። ሁለተኛው ቡድን ደግሞ 47 ተሳታፊዎች ሲኖሩት 22 ወንዶችና 25 ሴቶች የነበሩበት ሲሆን እድሜያቸው በአማካይ ወደ አርባ ዘጠኝ የሚጠጋ ነው። ከሁሉም ተሳታፊዎች አልኮል ከማቆማቸው በፊትና ከአልኮል ከታቀቡ ከአንድ ወር በኋላ የደም ናሙና ተወሰደ። የአልኮል መጠጥን ለወራት ያሀል ከመውሰድ የታቀቡት ተሳታፊዎች በሰውነታቸው ላይ የኢንሱሊን አመራረት ላይ አወንታዊ የሆነ ለውጥ ለመታየት ችሏል። ይህም በሰውነታቸው ያለውን የስኳር መጠን ጤናማ እንዲሆን አድርጎታል። "ያገኘነው መረጃ እንደሚያስረዳው ከተፈለገው በላይ አልኮል መጠጣት ለአይነት ሁለት የስኳር በሸታ የመጋለጥ እድልን ያሰፋዋል" ሲሉ ከአጥኝዎቹ አንዷ የሆኑት መህታ ተናግረዋል። ምንም እንኳን የአልኮል መጠጥ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ጋር መያያዙ አዲስ ነገር ባይሆንም ከአልኮል መታቀባቸው ተሳታፊዎቹ ክብደታቸውን ለመቆጣጠር ረድቷቸዋል። አልኮል አዘውትሮ የመጠጣት ችግር ያለባቸው ሰዎችም የጤና ባለሙያ እንዲያማክሩና የአልኮል መጠጥ ፍጆታቸውን እንዲቀንሱ ጥናቱ መክሯል።
news-55112955
https://www.bbc.com/amharic/news-55112955
ትግራይ ፡ የኢትዮጵያ ሠራዊት መቀለን መቆጣጠሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አስታወቁ
የኢትዮጵያ ሠራዊት ትግራይ ክልል ዋና ከተማ የሆነችውን የመቀለ ከተማን መቆጣጠሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ዛሬ [ቅዳሜ] አመሻሽ ላይ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ እንዳሉት መቀለን ለመቆጣጠር በተደረገው ዘመቻ "ንጹሐን ዜጎች ዒላማ ሳይሆኑ፣ ከተሞቻችንና ቅርሶቻችን ሳይጎዱ" ሠራዊቱ ከተማዋን መያዙን አመልክተዋል። የአገሪቱ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሀኑ ጁላም ሠራዊቱ የመቀለ ከተማን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠሩን ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪም በዘመቻው ወቅት "በሸሸበት ላይ የነበረው ኃይል ያፈረሳቸውን መሠረተ ልማቶች በፍጥነት በመገንባት የትግራይ ሕዝብ ወደ ሰላማዊ ኑሮው እንዲመለስ ማድረግ የቻልነውን ሁሉ እንደምናደርግ ቃል እገባለሁ" ሲሉ መነግሥታቸው ለክልሉ መልሶ መቋቋም ያለውን ቁርጠንነት ገልጸዋል። ብሔራዊው ቴሌቪዥን ኢቲቪም የመቀለ ከተማ በሠራዊቱ መያዟን ጠቅላይ ሚኒስትሩንና የሠራዊቱን ኤታማዦር ሹሙን ጠቅሶ ዘግቧል። ቅዳሜ ረፋድ የኢትዮጵያ ሠራዊት የትግራይ ክልል ዋና ከተማ የሆነችውን መቀለ ከተማን ለመቆጣጠር ወታደራዊ ዘመቻ መጀመሩን የእርዳታ ሠራተኞችና የክልሉ አመራሮች ገለጹ። የክልሉ ገዢ ፓርቲ ህወሓት እንዳለው የመቀለ ማዕከላዊ ክፍል "በከባድ መሳሪያና በመድፍ" ጥቃት እንደተፈጸመበት አመልክቷል። ዛሬ ቅዳሜ ከረፋድ አራት ሰዓት ጀምሮ በከተማዋ ዙሪያ የከባድ መሳሪያ ድምጽና ፍንዳታዎች መሰማት እንደጀመሩ ቢቢሲ ያገኘው መረጃ አመልክቷል። የእርዳታ ሠራተኞችና ዲፕሎማቶች በከተማዋ ውስጥ ከባድ ፍንዳታዎች መሰማታቸውን ከነዋሪዎች እንደሰሙ ተናግረዋል። የአገሪቱ መከላከያ ሠራዊት ባለፉት ሦስት ሳምንታት በትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙ በርካታ ከተሞችን ተቆጣጥሮ ወደ መቀለ ከተማ መቃረቡን ተከትሎ፤ መንግሥት ሦስተኛና የመጨረሻው ምዕራፍ "ሕግ የማስከበር" ያለውን ዘመቻ መቀለ ውስጥ ይገኛሉ ባላቸው የህወሓት መሪዎችና ኃይሎች ላይ እንደሚያካሂድ አሳውቆ ነበር። ትናንት በአገሪቱ መከላከያ ሠራዊት በተሰጠው መግለጫ ጦሩ ወደ መቀለ ከተማ ለሚያደርገው ዘመቻ ቁልፍ የሆኑ ከተሞችንና ቦታዎችን መያዙን አመልክቶ በከተማዋ ዙሪያ አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተገልጾ ነበር። ሮይተርስ የዜና ወኪል የህወሓት መሪን ጠቅሶ የኢትዮጵያ መንግሥት ኃይሎች የክልሉን ዋና ከተማ መቀለን ለመያዝ ቅዳሜ ጥቃት ማካሄድ መጀመራቸውን ዘግቧል። ሮይተርስ ጨምሮም የህወሓት ሊቀመንበር የሆኑት ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) በአጭር የጽሁፍ መልዕክት መቀለ ላይ "የከባድ መሳሪያ ድብደባ" እየተካሄደ መሆኑን ነገሩኝ በማለት ዘግቧል። ነገር ግን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ፕሬስ ሴክሬታሪ ቢለኔ ስዩም ለሮይተርስ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ሠራዊት ሠላማዊ ሰዎች የሚገኙባቸውን አካባቢዎች ላይ የከባድ መሳሪያ ጥቃት አይፈጽምም ብለዋል። ጨምረውም "በመቀለ ከተማም ሆነ በትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ደኅንነት የፌደራል መንግሥቱ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ሆኖ ይቀጥላል" በማለት ሠራዊቱ ለሰላማዊ ሰዎች ጥንቃቄ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። ፌደራሉ ሠራዊት በመቀለ ላይ ወታደራዊ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ተከትሎ ከትግራይ አመራሮች በኩል በክልሉ ቴሌቪዥን ላይ የቀረበው መግለጫ ጥቃቱ ከትናት መጀመሩን ገልጾ የክልሉ ኃይል "የአጸፋ እርምጃ" እንደሚወስድ አስጠንቅቋል። ቅዳሜ ረፋድ ላይ በመቀሌ ከተማ ውስጥ መሰማት የጀመረውን የከባድ መሳሪያ ድምጽ ተከትሎ በነዋሪዎች ዘንድ ድንጋጤ የተፈጠረ መሆኑ ምንጮች ተናግረዋል። ከተቀሰቀሰ ከሦሰት ሳምንታት በላይ የሆነው ቀውስን ተከትሎ በትግራይ ክልል ያለው የስልክና የኢንትርኔት ግንኙነት በመቋረጡ ዝርዝርና አስተማማኝ መረጃ ለማግኘት አስቸጋሪ ሆኗል። መቀለ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች አሏት የምትባለው መቀለ የትግራይ ክልል አስተዳደር መቀመጫ ስትሆን የክልሉ ትልቋ ከተማ ናት። የህወሓት ከፍተኛ አመራሮችና ቀደም ሲል በፌደራል መንግሥቱ ከፍተኛ ኃላፊነት ላይ ይገኙ የነበሩ ባለስልጣናት መቀመጫቸው መቀለ እንደሆነ ሲነገር ቆይቷል። በፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልልን በሚያስተዳድረው ህወሓት መካከል ለረጅም ጊዜ የቆየው አለመግባባት ባለፈው ዓመት ሊካሄድ የነበረው አገራዊ ምርጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽን ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ መሸጋገሩን ተከትሎ በከፍተኛ ሁኔታ መካረሩ ይታወሳል። ተከትሎም የፌደራል መንግሥቱን ውሳኔ ባለመቀበል ባለፈው ዓመት ማብቂያ ላይ በትግራይ ክልል የተካሄደው የተናጠል ምርጫ የፌደራል መንግሥቱን ተቀባይነት ካለማግኘቱ በተጨማሪ በአገሪቱ ምክር ቤቶች ሕገ ወጥ ተብሎ ውድቅ ተደርጓል። የፌዴሬሽን ምክር ቤትም የክልሉን አስተዳዳሪዎች ሕገ መንግሥቱን በመጣስና ከሕግ ውጪ ተንቀሳቅሰዋል በማለት የፌደራል መንግሥቱ ከትግራይ ክልል ክልል አስተዳደር ጋር የነበረውን የቀጥታ ግንኙነት አቋርጦ የበጀት ዕቀባ ጥሎ ነበር። አለመግባባቱና መካሰሱ ያለማቋረጥ በቀጠለበት ሁኔታ ጥቅም 23/2013 ዓ.ም ምሽት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በትግራይ ክልል በነበረው የፌደራሉ ሠራዊት የሠሜን ዕዝ ላይ በህወሓት ኃይሎች ጥቃት መፈጸሙን ይፋ ካደረጉ በኋላ የፌደራሉ ሠራዊት በትግራይ ክልል ኃይሎች ላይ እርምጃ መውሰድ ጀመሩ ይታወሳል።
news-54425823
https://www.bbc.com/amharic/news-54425823
ኮሮናቫይረስ ፡ "መተቃቀፍ ናፍቆናል" ኮቪድ-19 ያደናቀፈው የእናትና ልጅ ትስስር
ለመጨረሻ ጊዜ ከሚወዱት ሰው ጋር የተቃቀፉት መቼ ነበር? ሰዎችን ማቀፍ በጣም ከናፈቀዎት ስሜቱ የእርስዎ ብቻ አይደለም።
ክላውዲያ ሃመንድ እና ባሏ ቲም መተቃቀፍ እና ሌሎችም ሰዋዊ ንክኪዎች የጤናማ ሥነ ልቦና መገለጫ እንደሆኑ ጥናቶች ያሳያሉ። ኮቪድ-19 ግን ከምንወዳቸው ሰዎች በአካል እንድንርቅ ምክንያት ሆኗል። "ፊልም ወይም ሙዚቃ ከፍቼለት ፊቱን እዳብሰው ነበር" "መተቃቀፍ ናፍቆናል" ከሚሉት አንዷ ሻረን ናት። ሻረን፤ ሮብ የሚባል ልጅ አላት። በ25 ዓመቱ የሞተር ብስክሌት አደጋ ገጥሞት አእምሮው ስለተጎዳ በእንክብካቤ መስጫ ውስጥ ይገኛል። ከአደጋው በኋላ ሮብ የሰው ልጅ ንክኪ እንደሚያስፈልገው ሻረን ተነግሯታል። ወረርሽኙ ከተከሰተ ወዲህ ግን ልጇን መደባበስ አልቻለችም። "ፊልም ወይም ሙዚቃ ከፍቼለት ፊቱን አዳብሰው ነበር። አቅፈው፣ እስመውም ነበር።" ባለፉት ስድስት ወራት ልጇን መንካት የቻለችው ሦስት ጊዜ ብቻ ነበር። ከላይ እስከ ታች በጭምብል ተሸፍና ጥፍሩንና ፀጉሩን ቆርጣለታለች፤ አቅፋዋለች። የወረርሽኙ ስርጭት ሲሰፋ ግን ልጇን መጎብኘት እንኳን አልቻለችም። "ልጄን ማቀፍና መሳም አለመቻሌ የሞት ያህል ነው። ማግኘት የምችለው በስልክ ብቻ ነው። አልያም ፎቶውን አያለሁ። በጣም ያሳዝናል።” አካላዊ ርቀት በተለይም በእንክብካቤ መስጫ ላሉ ሰዎች ከባድ ነው። ከወረርሽኙ በፊት መተቃቀፍን እንደ ቀላል ነገር ይወስዱ የነበሩ ሰዎች ሳይቀሩ አሁን ላይ ከሰው ጋር መነካካት ናፍቋቸዋል። ሙኒክ የምትገኘው ፕሮፌሰር መርሊ ፌርሀርስት መተቃቀፍ ላይ ምርምር እያደረገች ነው። ሰዎች ለመጨረሻ ጊዜ የተቃቀፉበትን ጊዜ እንዲያስታውሱ ትጠይቅና ከዚያም ራሳቸውን ለሁለት ደቂቃ እንዲያቅፉ ትመክራለች። ለንደን የሚኖሩ ደባሎች ቤተሰቦቻቸውን ማቀፍ ስለናፈቃቸው በየቀኑ 12 ሰዓት ላይ ለ25 ሰከንድ ብቻ ለመተቃቀፍ ተስማምተዋል። ሌላው አማራጭ መጻፍ ነው። አንድ ሰው ሲያቅፉ ማስተላለፍ የሚፈልጉትን መልዕክት በቃላት ለመግለጽ መሞከር ማለት ነው። ክላውዲያ ሃመንድ "ጓደኛዬን የአባቷ ቀብር ላይ ሳላቅፋት ቀረሁ" ክላውዲያ ሀመንድ የጓደኛዋ አባት ቀብር ላይ ተገኝታ ነበር። የጓደኛዋ አባት አስክሬን አፈር ሲለብስ ጓደኛዋን ማቀፍ ብትፈልግም አልቻለችም። ጓደኛዋን “አባትሽ እንደ ጓደኛችን ነበር። ደግ ነበር። አባትሽን ስላጣሽ አዝኛለሁ። አይዞሽ፤ ሁላችንም ከጎንሽ ነን” ብትላትም ከቃላት በላይ ትርጉም የሚኖረው ብታቅፋት እንደሆነ ታምናለች። ኦፊሊያ ዲዮሪ ፈላስፋ ናት። "አካላዊ ንክኪ ፍቅርን፣ ጓደኝነትን ይገልጻል። ፍላጎቱን መግታት አንችልም" ስትል ትገልጻለች። ፕሮፌሰር ማይክል ባንሲ በተባሉ የሥነ ልቦና ተመራማሪ መሪነት የተሠራ የበይነ መረብ የዳሰሳ ጥናት እንደሚያሳየው፤ በርካቶች ለመተቃቀፍ ቀና አመለካከት እንዳላቸው ይጠቁማል። ከ112 አገሮች 40,000 ሰዎችን ያሳተፈው ጥናት እንደሚያሳየው መተቃቀፍ መፈለግ የጤናማነት ምልክት ነው። ብቸኝነት የማያጠቃቸው ሰዎች መተቃቀፍ ይወዳሉ። ከጥናቱ ተሳታፊዎች 54 በመቶው የሰው ንክኪ ጎሎናል ሲሉ 3 በመቶ ደግሞ አካላዊ ንክኪ በዝቶብናል ብለዋል። የ80 ዓመቱ ጆን ማርዮት ያደጉት በአያቶቻቸው እጅ ነው። "አያቶቼ ቢወዱኝም አንድም ቀን አቅፈውኝ አያውቁም። ሁለቱም የተወለዱት በቪክቶሪያ ዘመን ስለነበር ልጆችን አይቅፉም" ይላሉ። አዛውንቱ ልጅ ሳሉ የእድሜ እኩያቻቸውን ወላጆቻቸው ሲያቅፏቸው ሲያዩ ግራ ይጋቡ ነበር። ባለቤታቸውን ከተዋወቁ በኋላ ግን ነገሮች ተቀየሩ። የመተቃቀፍ ዋጋም ገባቸው። ሁለቱ ሴት ልጆቻቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ ያቀፉበትን ወቅት የማይዘነጉት ጆን፤ ልጆቻቸውን፣ ስድስት የልጅ ልጆቻቸውን እንዲሁም የልጅ ልጅ ልጃቸውን እንደማቀፍ የሚያስደስታቸው ነገር የለም። "መተቃቀፍ የማይወዱ ሰዎችም አሉ" በበይነ መረብ የተሠራው ጥናት 27 በመቶ ሰዎች መተቃቀፍ እንደማይወዱ ያሳያል። መተቃቀፍ ሁሉንም ሰው ጤናማ እንደማያደርግም አጥኚዎች ይናገራሉ። መተቃቀፍ የሚወዱ ሰዎች ግልጽ ሲሆኑ፤ ሰው ማቀፍ የሚጠሉ ደግሞ ሰዎችን ማመን እንደሚቸገሩ ጥናቱ ያሳያል። ዶክተር ኤሚ ካቫንጋህ የመብት ተሟጋች ናት። ሰዎች ያለፍቃዳቸው የሚነኩበት አጋጣሚ እንዳለ ትናገራለች። አይነ ስውሯ ኤሚ በአንድ ቀን ውስጥ ቢያንስ አራት ሰው ያለፍቃዷ ይነካታል። "ደረጃ ስወርድ ሰዎች ይመሩኛል፤ ወንበር ላይ እንድቀመጥ ይመሩኛል፤ ክንዴን ወይም ትከሻዬን የሚይዙኝ አሉ። ሌሎች በትሬን ይዘው ይመሩኛል። ሰውነቴ ላይ ምልክት ወይም ጭረት የሚቀርበት ጊዜም አለ።” ሰዎች ሊረዷት ፈልገው እንደሆነ ብትረዳም ንክኪው መብቷን የሚጋፋ ሆኖም ይሰማታል። "አካል ጉዳተኛ ስለሆንኩ ሰዎች እኔን መንካት የሚችሉ ይመስላቸዋል" ስትል ስሜቷን ትገልጻለች። አንዳንድ ሰዎች እርዳታ ሲያደርጉላት፤ ሌሎች በእርዳታ ሰበብ ወሲባዊ ትንኮሳ ያደርሱባታል። በበይነ መረብ በተሠራው ጥናት መሠረት 63 በመቶ ሰዎች በማያውቁት ግለሰብ መነካት ደስ አይላቸውም። ከአዛውንቶች ይልቅ ወጣቶች በእንግዳ ሰው መነካት አይሹም። ብዙዎች የማያውቁት ሰው ከእጃቸው ውጪ ሌላ የሰውነት አካላቸውን እንዲነካ አይፈቅዱም። እንደ 'ሚቱ' አይነት ንቅናቄዎች አግባብ ስላልሆኑ ንክኪዎች ግንዛቤ አስፍተዋል። ሰዎችን ከመንካት በፊት ፍቃድ መጠየቅ አስፈላጊ መሆኑም እሙን ነው። ኮሮናቫይረስ ልጇን እንዳታቅፍና እንዳትደባብሰው እንቅፋት የሆነባት ሻረን ልጇ ሮብን የምታቅፍበትን ቀን በጉጉት እየጠበቀች ነው። “ይሄ ቫይረስ ሲወገድ ልጄን እንዴት እንደማቅፈው፣ ስንቴ እንደምስመው እኔ ነኝ የማውቀው” ትላለች።
news-44776427
https://www.bbc.com/amharic/news-44776427
ታንዛኒያ ቦይንግ "787-8 ድሪምላይነር" ገዛች
የታንዛኒያ አየር መንገድ በታሪኩ የመጀመርያ የሆነውን "787-8 ድሪምላይነር" ዘመናዊ አውሮፕላን ገዛች።
በዳሬሰላም የርክክርብ ሥነ ሥርዓት ላይ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ እንደተናገሩት ታንዛኒያ በአቪየሽን ኢንዱስትሪው ትልቅ ቦታ እንዲኖራት ትፈልጋለች። "በአሁኑ ጊዜ ትልቅ የአቪየሽን አገልግሎት የማይፈልግ አገር የለም" ያሉት ማጉፉሊ ታንዛኒያዊያን የንግድ ትስስር ከተቀረው ዓለም ጋር ለመፍጠር አቪየሽኑን ማሳደግ እንደሚያስፈግ አውስተዋል። 262 መቀመጫዎች ያሉትን ይህን ድሪምላይነር አውሮፕላን "ኪሊማንጃሮ" ስትል በአገሪቱና በአህጉሪቱ ትልቁን የተራራ ስም ሰጥታዋለች። በመጪው መስከረም ወደ ሙምባይ፣ ጓንዡ እና ባንኮክ በመብረር ሥራ እንደሚጀምር ታውቋል። ይህ አውሮፕላን የታንዛኒያ መንግሥት በኪሳራ ቋፍ ላይ የሚገኘውን የአቪየሽን ኢንደስትሪ ለመታደግ የሚያደርገው 4ኛው የአውሮፕላን ግዢ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ድሪምላይነርን 787-8 ለመረከብ በአፍሪካ የመጀመርያ ሲሆን አውሮፕላኑንም የተረከበው ከአምስት ዓመታት በፊት በነሐሴ 2005 ነበር።
43565706
https://www.bbc.com/amharic/43565706
ፈረንሳይ ህፃናት በሦስት ዓመታቸው ትምህርት እንዲጀምሩ ወሰነች
ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮ ባስተዋወቁት አዲስ ለውጥ መሰረት በፈረንሳይ ውስጥ የሚገኙ ህፃናት ትምህርት መጀመር የሚገባቸው ስደስት ዓመት መሆኑ ቀርቶ በሦስት ዓመታቸው እንዲሆን ተደረገ።
ይህ ለውጥ በአውሮፓ ውስጥ በዝቅተኛ እድሜ ትምህርት በማስጀመር ፈረንሳይን ቀዳሚ ሀገር ያደርጋታል። ነገር ግን አብዛኞቹ ፈረንሳያዊያን ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት የሚያስገቡት በሦስት ዓመታቸው ስለሆነ ይህ ውሳኔ ውስን ቁጥር ያለቸውን ወላጆች ብቻ ነው የሚመለከተው። የፈረንሳይ መንግሥት መረጃ እንደሚያመለክተው 2.4 በመቶ የሚሆኑ ልጆች ብቻ ናቸው ከሦስት ዓመታቸው በኋላ ወደ ትምህት ቤት የሚገቡት። ፕሬዝዳንት ማክሮ እንዳሉት ለውጡ ያስፈለገው በፈረንሳይ ውስጥና ፈረንሳይ በሌሎች አካባቢዎች ባሏት ግዛቶች ውስጥ ያሉ ድሃ ዜጎች ልጆቻቸውን በለጋ ዕድሜያቸው ወደ ትምህርት ቤት የሚያስገቡበት ዕድል ዝቅተኛ ስለሆነ፤ በሃገሪቱ ውስጥ ያለውን የትምህርት ዘርፍ ልዩነት ለማጥበብ ነው። በአውሮፓ ሃገራት ህፃናት ትምህርት የሚጀምሩበት ዕድሜ አራት ዓመት፡ ሰሜን አየርላንድ አምስት ዓመት፡ እንግሊዝ ፣ ስኮትላንድ፣ ዊልስ፣ ቆጵሮስ፣ ማልታ ስድስት ዓመት፡ ኦስትሪያ፣ ቤልጂየም፣ ክሮሺያ፣ ቼክ ሪፐብሊክ፣ ዴንማርክ፣ ጀርመን፣ ግሪክ፣ ሃንጋሪ፣ አይስላንድ፣ የአየርላንድ ሪፐብሊክ፣ ጣሊያን፣ ሌሽቴንስታይን፣ ሉክሰምበርግ፣ ኔዘርላንድስ፣ ኖርዌይ፣ ፖርቱጋል፣ ሮማኒያ፣ ስሎቫኪያ፣ ስፔን፣ ስዊትዘርላንድ፣ ቱርክ ሰባት ዓመት፡ ቡልጋሪያ፣ ኢስቶኒያ፣ ፊንላንድ፣ ላቲቪያ፣ ሉቱዋንያ፣ ፖላንድ፣ ስርቢያ፣ ስዊዲን
news-54885505
https://www.bbc.com/amharic/news-54885505
ብራዚል ተስፋ ያደረገችበት ቻይና ሰራሹ የኮቪድ ክትባት “በአስቸኳይ ይቁም” አለች
ብራዚል ትልቅ ተስፋ አሳድራበት የነበረው ቻይና ሰራሽ የኮቪድ ክትባት እንዲቆም አዘዘች። ምክንያቱ ደግሞ “ጠጠር ያለ የጎንዮሽ ጉዳት” በማስከተሉ ነው።
የብራዚል የጤና ቁጥጥር አንቪሳ እንዳለው በተሞከረባቸው ሰዎች ላይ ከበድ ያለ ጉዳት ያስከተለው በኦክቶበር 29 ነው። የቁጥጥር መሥሪያ ቤቱ ደረሰ ያለው የጤና ጉዳት ምን እንደሆነ ግን ከመናገር ተቆጥቧል። የቻይናው ሲኖቫክ ያመረተው ኮሮናቫክ ክትባት በዓለም ላይ የመጨረሻ ምዕራፍ ሙከራዎች እያደረጉ ከነበሩና ተስፋ ከተጠላባቸው ክትባቶች አንዱ ነበር። ብራዚል ይህ የቻይና ክትባት ይቅርብኝ ትበል እንጂ ቻይና ግን ክትባቱን አገልግሎት ላይ አውለዋለች። በሺ የሚቆጠሩ ዜጎችን በአስቸኳይ መከላከል እንዲረዳቸው ሰጥቻቸው በመልካም ጤንነት ላይ ናቸው ብላለች። ቻይና ይህን ክትባት የሚፈልግ ማንኛውም ዜጋዋ እንዲከተብ ታበረታታለች። ባለፈው ወር ዩዉ ከተማ ቢቢሲ በቀረጸው አንድ ቪዲዮ ይህንን ከትባት ለመውሰድ የተሰለፉ ሰዎችን ያሳያል። ሲኖቫክ መድኃኒት አምራች ሁሉም ሰራተኞቹ ይህንን ክትባት በቻይና ውስጥ መውሰዳቸውን ይናገራል። ቢቢሲ አሁን ብራዚል ላይ በዚሁ ክትባት ዙርያ ደረሰ በተባለው ጉዳት ከሲኖቫክ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም።ብራዚል በዓለም ላይ ኮሮና መጠነ ሰፊ ጉዳት ካደረሰባቸው አገራት ተርታ ትመደባለች። 5 ሚሊዮን 6መቶ ሺህ ዜጎቿ በተህዋሲው ተጠቅተውባታል። 163ሺ ሰዎች ደግሞ ሞተውባታል።ይህ አሐዝ ብራዚልን ከአሜሪካ እና ከሕንድ ቀጥሎ ሦስተኛዋ ተጎጂ አገር ያደርጋታል።ሙከራው ለምን እንዲቆም ተደረገ?ሰኞ ዕለት የቁጥጥር መሥሪያ ቤቱ ኮሮናቫክ የሙከራ ክትባት እንዲቆም ወሰነ። ይህም የተስተዋሉ የጎንዮሽ ጉዳቶች ስላሉ ነው በሚል ተገለጸ።ነገር ግን ምን እንደተከሰተም ሆነ የት እንደተከሰተ አልገለጠም። ይህ የሲኖቫክ ክትባት የመጨረሻ ሙከራ ከብራዚል ሌላ በኢንዶኒዚያ እና ቱርክም በሙከራ ላይ ይገኛል። ነገር ግን ሁለቱ አገሮች እንደ ብራዚል ያለ ተመሳሳይ ቅሬታን አላቀረቡም።ዲማስ ኮቫስ ቡታንታን የተባለው የሕክምና ጥናት ኢንስትዩት ኃላፊ ነው። እሱ እንደሚለው የቻይና ሰራሹ ክትባት እንዲቆም የሆነው ከሞት ጋር በተያያዘ ነው። ሆኖም ግን የተከሰተው ሞት ከክትባቱ ጋር ላይያያዝ ይችላል ብሏል።ሙከራ ላይ ያለ ክትባት በዚህ መንገድ እንዲቆም ማድረግ አዲስ ነገር አይደለም። ባለፈው ጥር ለምሳሌ የታላቋ ብሪታኒያ ተስፋ የተጣለበት ክትባት የጎንዮሽ ጉዳቶችን አስከትሏል በሚል እንዲቆም ማድረጓ ይታወሳል።ይህ ክትባት ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ከአስትራዜኒካ ጋር በጥምረት እየፈበረከው የሚገኝ ነበር። ሙከራው እንዲቆም ከተደረገ በኋላ ግን በአጭር ቀናት ውስጥ እንዲቀጥል ተደርጓል።የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ጃይል ቦልሴናሮ አገራቸው የቻይና ሰራሽ ክትባት እንደማትጠቀምና ምርጫቸው የኦክስፎርድ ክትባት እንደሆነ በይፋ ተናግረው ያውቃሉ። በአሁን ሰዓት የቻይናውን ሲኖቫክን ጨምሮ በመላው ዓለም በርከት ያሉ የክትባት ሙከራዎች የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ናቸው። ትናንት በወጣ ሰበር ዜና የአሜሪካው መድኃኒት አምራች ፊዘር እጅግ ውጤታማ የተሰኘ ክትባት ማግኘቱን ይፋ አድርጓል። ይህ ክትባት ፈዋሽነቱ 90 ከመቶ መሆኑ ለዓለም ብስራት ሆኗል።
news-54046346
https://www.bbc.com/amharic/news-54046346
ፌስቡክ ሞቴን ቀጥታ ካላስተላልፍኩ ያለውን ሰው አገደ
ግዙፉ ማሕበራዊ ድርአምባ ፌስቡክ በማይድን በሽታ የተያዘው ፈረንሳዊው ግለሰብ ሞቴን ቀጥታ ላስልተላልፍ ማለቱን ተከትሎ በፍፁም አይሆንም ብሏል።
አሌይን ኮክ የተሰኘው የ57 ዓመት ግለሰብ በዚች ምድር ላይ ያለውን የመጨረሻ ቀን በፌስቡክ ለማስተላለፍ አቅዷል። ሰውዬው ይህን ማድረግ ያሰበው ቅዳሜ ዕለት ነበር። ኮክ፤ ምግብ፣ መጠጥና መድኃኒት አልወስድም በማለት ነበር ፍፃሜውን ለማቅረብ ያሰበው። ፕሬዝደንት ኢማኑዔል ማክሮን ሰውዬው ከዚህ በፊት ‘የሞት መድኃኒት ይሰጠኝ’ ብሎ የጠየቀውን ጥያቄ ውድቅ አድርገው ነበር። ኮክ፤ ፈረንሳይ ውስጥ በማይድን በሽታ የሚታመሙ ሰዎች በፈቃዳቸው መሞት እንዲችሉ ይፈቅዳላቸው ሲል ይከራከራል። የካቶሊክ ቤተክርስትያንን ጨምሮ ሌሎች ደግሞ የፈቃድ ሞት [ዩታኔዚያ] መፈቀድ የለበትም፤ የሞራል ስብዕና ዝቅጠት ነው ሲሉ ይከራከራሉ። “ነፃ የመውጫ ጊዜዬ ደርሷል፤ እመኑኝ ደስተኛ ነኝ” ሲል ኮክ በፌስቡክ ገፁ ላይ አስፍሯል። ግለሰቡ የመጨረሻዬ ያለውን ምግብ ቅዳሜ ጥዋት በልቷል። “ቀጣይ ቀናት ከባድ እንደሚሆኑ አውቃለሁ ነገር ግን ውሳኔዬ ይህ ነው፤ ደግሞም እርጋታ ላይ ነኝ” ብሏል ከሆስፒታል አልጋው ላይ ሆኖ በላከው መልዕክቱ። ፈረንሳዊው ግለሰብ የደም ቧምቧውን [አርተሪስ] ግድግዳዎች አንድ ላይ በሚያጣብቅ በሽታ ክፉኛ እየተሰቃየ ይገኛል። ፌስቡክ ግን ሰውዬው ሞቴን ቀጥታ ላስተላልፍ ማለቱን አልተቀበለውም። ድርጅቱ ይህ ራስን የማጥፋት ተግባር ነው፤ ይህን አናስተላልፍም ብሏል። ፌስቡክ “ግለሰቡ ሓሰቡን በድርጊት ለመግለፅ ያደረገውን ሙከራ ብናደንቅም ባለሙያ ካማከርን በኋላ ጥያቄውን ውድቅ አድርገናል “ብሏል። “ሕጋችን ራስን የማጥፋት ሙከራዎችን እንዳናሳይ ያግደናል።” ኮክ፤ ፌስቡክ ጥያቄዬን ውድቅ ያደረገው እስከ ጳጉሜ 3/2012 ባለው ጊዜ ነው ብሏል። ስለዚህም ደጋፊዎቹ ድርጅቱ ላይ ጫና እንዲያሳድሩና ውሳኔውን እንዲያስቀይሩ ጥሪ አቅርቧል። ሰውዬው ባለፈው ሐምሌ ለፕሬዝደንት ማክሮን “በክብር እንድሞት ይፍቀዱልኝ” ሲል ደብዳቤ ፅፎ ነበር። ፕሬዝደንቱ በበኩላቸው በደብዳቤው የተሰማቸውን ሐዘን ገልፀው ነገር ግን ውሳኔው ከአቅማቸው በላይ ስለሆነ ተፈፃሚ ሊያደርጉለት እንደማይችሉ ተናግረዋል። ዩታኔዚያ [በበሽተኞች ፈቃድ የሚፈፀም ሞት] ፈረንሳይ ውስጥ አከራካሪ ርዕስ ነው። በርካቶች ሰዎች በፈቃዳቸው በክብር ሊሞቱ ይገባል ይላሉ። በተለይ የሐይማኖት ተቋማትን ጨምሮ ሌሎች ደግሞ ድርጊቱ ወንጀል መሆን አለበት ሲሉ ይሞግታሉ።
50619662
https://www.bbc.com/amharic/50619662
ብራዚል ተዋናይ ሌዎናርዶ ዲካፓሪዮ አማዞን ጫካ እንዲቃጠል አድርጓል ስትል ከሳለች
የብራዚሉ ፕሬዝደንት ጃይር ቦልሶናሮ ተዋናይ ሌዎናርዶ ዲካፕሪዮ የአማዞን ጫካ እሣት እንዲለብስ የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል ሲሉ ወቀሱ።
ፕሬዝደንቱ ተዋናይ ይህንን ስለማድረጉ ምንም ዓይነት ማስረጃ ባይሰጡም አማዞን ጫካ ላይ የሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ሲወቅሱ የመጀመሪያቸው አይደለም። ሰደድ እሣቱን ያስነሱት የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት የፈለጉ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ናቸው ያለው የብራዚል መንግሥት የጠረጠራቸውን በርካታ ሰዎች አሥሯል። ለአማዞን ጫካ መልሶ መቋቋም 5 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል የገባው ሌዎናርዶ የፕሬዝደንቱን ወቀሳ አስተባብሏል። አራት በጎ ፈቃደኛ የሰደድ እሣት ተከላካዮች በብራዚል መንግሥት መታሠራቸውን ተከትሎ በርካታ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የቦልሶናሮ መንግሥትን እየወረፉ ይገኛሉ። ኢ-መንግሥታዊ ድርጅቶች እና የመብት ተሟጋቾች የብራዚል መንግሥት ድርጊት ፖለቲካዊና ተፈጥሮ ላይ የሚሠሩ ድርጅቶችን ለመፈታተን ያሰበ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ያሰማሉ። ባለፈው ነሐሴ የሰደድ እሣት ሰለባ የሆነው የብራዚሉ አማዞን ጫካ ጉዳይ ብዙዎችን ያስጨነቀ ሆኗል። ፕሬዝደንቱ ባለፈው አርብ በመኖሪያ ቤታቸው ሳሉ ነው ወቀሳቸውን የሰነዘሩት። «ሌዎናርዶ ዲካፕሪዮ የሚሉት ሰውዬ ጥሩ ይመስላል አይደል? ገንዘብ ሰጥቶ አማዞንን የሚያነድ።» «እነዚህ ኤንጂኦ ተብየዎች ምንድነው የሚሠሩት? ጫካውን ያቃጥላሉ ከዚያ ፎቶ ያነሳሉ፤ ቪድዮ ይቀርፃሉ። ዎርልድ ዋይልድላይፍ ፈንድ [WWF] ለምሳሌ ከዲካፕሪዮ ጋር ነው የሚሠራው፤ እሱም 500 ሸህ ዶላር እርዳታ አድርጓል። በተፈጥሮ ጥበቃ ለተሰማሩ ድርጅቶች ድጋፍ በማድረግ የሚታወቀው ዲካፕሪዮ፤ ምንም እንኳ አማዞን ጫካ ውስጥ የሚሠሩ ድርጅቶች እርዳታ ቢሹም እኔ እርዳታ አላደረግኩም ሲል ወቀሳውን አስተባብሏል።
news-56425428
https://www.bbc.com/amharic/news-56425428
ደቡብ አፍሪካ፡ ተማሪውን መጸዳጃ ቤት ጉድጓድ ውስጥ የገባ ስልኩን እንዲያወጣ ያደረገው መምህር ተቀጣ
የ11 ዓመትን ልጅ የሞላ መፀዳጃ ቤት ውስጥ ገብቶ የጠፋ ስልክ እንዲፈልግ አስገድዷል በሚል ክስ የቀረበበት አንድ የደቡብ አፍሪካ ርዕሰ መምህር ከሥራው ታገደ፡፡
ግለሰቡ ልጁን ለመጸዳጃ ቤት በሚያገለግለው ጉድጓድ ውስጥ በገመድ አስሮ እንዲገባ ያደረገው ሲሆን፣ ለዚህ ተግባሩም 200 ራንድ (14 ዶላር ) እንደሚሰጠው ቃል ገብቶለት ነበር ተብሏል፡፡ በዚህ ምክንያት ተማሪዎች ያፌዙበት ስለነበር ልጁ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ መፍራቱን አያቱ ገልጸዋል፡፡ ጉዳዩን ሲሰማ "በሃፍረት" እንደተሰማው የአካባቢው የትምህርት ቢሮ ለታይምስ ላይቭ ገልጿል፡፡ በደቡብ አፍሪካ የጉድጓድ መጸዳጃ ቤቶች በጥቅም ላይ ይውላሉ። ባለፈው ዓመት በአገሪቱ ካሉ ትምህርት ቤቶች አንድ ስድስተኛ የሚሆኑት መጸዳጃ ቤቶቻቸው የአደጋ ስጋት እንዳለባቸው የተገለፀ ቢሆንም አሁንም ግን እንደሚጠቀሙባቸው ይገመታል፡፡ ፉንዲሌ ጋዴ የተባሉ የምስራቃዊ ኬፕ የትምህርት ቢሮ ባለሥልጣን ድርጊቱን "ከነውርም በላይ ነው" ያሉ ሲሆን፣ ራሳቸው ይቅርታ ለመጠየቅ የተማሪውን ቤት እንደሚጎበኙ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡ በሉቱቱ መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር የሆኑት ግለሰብ ላይ ተጨማሪ እርምጃ ለመውሰድ ምርመራ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በመጋቢት ወር መጀመሪያ በድንገት ወደ ሠራተኞቹ መጸዳጃ ቤት ጉድጓድ የገባውን ስልክ ለማውጣት እንዲረዱ ሌሎች ልጆችንም ማበረታታቸው ተነግሯል፡፡ የአካባቢው መገናኛ ብዙሃን እንደሚሉት ጉዳዩ ይፋ ተደረገው ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ የሚሠራ አንድ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት መረጃውን በማግኘቱ ነው፡፡ ለኩላ ማህበረሰብ ልማት ፕሮጀክት የሚሠሩት ፒተር ማጆላ ስልኩን ለመፈለግ ለአንድ ሰዓት መቀጠሉን ተናግረዋል፡፡ ይህን በሚመለከት የለቀቁት ቪዲዮውም በብዙዎች ተጋርቷል። እንደ ማጁላ ከሆነ ተማሪዎች የተወሰነውን ቆሻሻ ለማስወገድ ባልዲዎችን ተጠቅመዋል። በኋላም ልጁ "አይነ ምድር ውስጥ እስከ ጉልበቱ ድረስ እንዲገባ" ተደርጓል ብለዋል፡፡ "ስልኩን ለመፈለግ እጆቹን የተጠቀመ ሲሆን አይነ ምድሩን ከእጆቹ በላይ እስከ ክርኑ ድረስ ነክቶታል" ብለዋል፡፡ ኒውስ 24 እንደዘገበው ስልኩ ባይገኝም ርዕሰ መምህሩ ተማሪው ላደረገው ጥረት 50 ራንድ ሰጥቶታል፡፡ ስማቸው ያልተጠቀሰው የልጁ አያት ለመገናኛ ብዙሃን እንደገለፁት የልጅ ልጃቸው ከደረሰበት ችግር በኋላ ሃፍረት ተሰምቶታል፡፡ በጎርጎሮሳዊያኑ 2018 የአምስት ዓመት ተማሪ በአንድ መጸዳጃ ቤት ጉድጓድ ውስጥ መግባቱን ተከትሎ በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ያሉትን ሁሉንም የጉድጓድ መፀዳጃዎች ለማስወገድ መንግስት ቃል ገብቷል፡፡
news-56431851
https://www.bbc.com/amharic/news-56431851
በአትላንታ ስድስት እስያውያን ሴቶች የሞቱበትን ጥቃት የፈፀመው ግለሰብ በግድያ ወንጀል ተከሰሰ
በአትላንታ፣ ጆርጂያ ግዛት በሚገኙ ስፓዎች ተኩስ ከፍቶ ስምንት ሰዎችን የገደለው ግለሰብ በግድያ ወንጀል መከሰሱ ተሰምቷል
ፖሊስ የተጠቂዎችን ማንነትም እያጣራ ቢሆንም ስድስቱ እስያውያን ናቸው ተብሏል። በዚህ ግድያ ስድስት እስያውያን ሴቶች ቢሞቱም ፖሊስ ዘር ላይ ያነጣጠረ ስለመሆኑ ገና አላረጋገጥኩም ብሏል። አራቱ ሰለባዎች በትናንትናው ዕለት ስማቸው ይፋ ተደርጓል። ተጠርጣሪው በበርካታ የግድያ ወንጀሎችም ክስ እስር ሊጠብቀው ይችላል ተብሏል። ግድያውን የፈፀመው ሮበርት አሮን ሎንግ የሚባል የ21 ዓመት ግለሰብ ነው። የቼሪሮኬ ካውንቲ ሸሪፍ ፍራንክ ሬይኖልድስ እንዳሳወቁት ግለሰቡ የ"ወሲብ ሱሰኛ ነኝ" ማለቱን ነው። ከዚህ ቀደም እስያውያን ላይ የጥላቻ ወንጀሎች ቢኖሩም በቅርቡ ደግሞ የሚደርሱ ጥቃቶች በከፍተኛ ሁኔታ አሻቅበዋል ተብሏል። አራቱ ሰለባዎች አሽሊ ያውን 33፣ ፓውል አንድሬ ሚሸልስ54፣ ኪሳዎጄ ታን 49ና ዳዩ ፌንግ 44 ናቸው። ኤሊካስ አር ሄርናንዴዝ ኦርቲዝ በጥቃቱ ጉዳት ከደረሰባት መካከል ናት ተብሏል። ንዴትና ፍራቻ በእስያውያን ማህበረሰብ ልባችን ተሰብሯል፣ ፈርተናል እንዲሁም ተሰላችተናል የሚሉ ቃላቶችን ነበር በአሜሪካ የሚኖሩ እስያውያን ከግድያው በኋላ የተናገሩት። በርካቶች ከተኩሱ በኋላ በዋሽንግተን ዲሲ ሻማ በማብራት በሞት የተለዩዋቸውን ዘክረዋል። ቻይናታውን ተብሎ በሚጠራው ሰፈርም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በአትላንታ ግድያ ለተነጠቁት ስምንት ሰዎች ሃዘናቸውን ሻማ በማብራት ገልፀዋል። ባለስልጣናቱ ግድያዎቹን ከፀረ-እስያውያን የጥላቻ ወንጀል ጋር ባያገናኙትም በርካቶች ግን በእስያውያን ላይ ያነጣጠረ ወንጀል እንደሆነ እየተናገሩ ነው። "በአሁኑ ሰዓት በአሜሪካ እስያዊ ዝርያ ያላት ሴት መሆን አስፈሪ ነው" ነው በማለት አንዲት እስያዊ አሜሪካዊ ሴት ለቢቢሲ ተናግራለች። ስታድግ ከፍተኛ የሆነ ዘረኝነት ተጠቂ ብትሆንም ቤተሰቦቿ ዝምታን እንድትመርጥ በማድረጋቸው ለአመታት በዝምታ ተሸብባ እንደነበርም አስረድታለች። ስለ ተኩስሱምን እናውቃለን? የመጀመሪያው የተኩስ ልውውጥ የተከናወነው በቼሮኪ አውራጃ በአክዎርዝ በሚገኘው በያንግ ኤሲያን ማሳጅ ፓርለር ነበር፡፡ የፖሊስ ቃል አቀባዩ ካፕቴይን ጄይ ቤከር ሁለት ሰዎች በቦታው መሞታቸውንና ሶስት ሰዎች ደግሞ ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ገልፀዋል። ሆስፒታል ውስጥ ሌሎች ሁለት ሰዎች እንደሞቱ ተናግረዋል፡፡ ከተጎጂዎቹ ሁለቱ የእስያ ዝርያ ያለባቸው ወንድ እና ሴት መሆናቸውን ያረጋገጡ ሲሆን ሌላ የሂስፓኒክ ዝርያ ያለበት ግለሰብ መቁሰሉን ተናግረዋል። ከአንድ ሰዓት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ በሰሜን ምስራቅ አትላንታ በሚገኘው ጎልድ ስፓ "ዝርፊያ እየተካሄደ ነው" በሚል ፖሊስ መጠራቱን ገልጿል። ፖሊስ በሪፖርቱ እንደገለጸው "ፖሊሶች በቦታው በደረሱበት ወቅት የሞቱ ሶስት ሴቶች ተገኝተዋል፡፡ ከመንገዱ ባሸገር በሚገኘው የአሮማቴራፒ ስፓ የተጠሩት ፖሊሶች የተገደለች ሌላ ሴት አግኝተዋል፡፡ የአትላንታ ጆርናል-ኮንስቲትዩሽን፣ ፖሊስን ጠቅሶ እንዳስታወቀው ስድስቱ የአትላንታ ተጠቂዎች የእስያ ዝርያ ያላቸው ሴቶች ናቸው፡፡ መርማሪዎች በአንዱ ስፓ አቅራቢያ የተቀረጸን የተጠርጣሪ ምስል ለቅቀዋል፡፡ በጆርጂያ ጆርጅ ዉድስቶክ ነዋሪ የሆነው ሮበርት አሮን ሎንግ ከአትላንታ በስተደቡብ 240 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው ክሪስፕ ካውንቲ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
48619165
https://www.bbc.com/amharic/48619165
አርቲስት እቴነሽ ግርማ፡ “እዚህ ደረጃ የደረስኩት በእርሷ ብርታት ነው”
ከአርቲስት እቴነሽ ግርማ ጋር ላለፉት 31 አመታት ትዳር መስርቶ ይኖሩ እንደነበር ለቢቢሲ የተናገረው ድምጻዊ ደመረ ለገሰ ባለቤቱ እቴነሽ ግርማ ላለፉት አምስት አመታት በጡት ካንሰር ስትታመም መቆይቷን ገልጿል።
ድምጻዊት እቴነሽ የጡት ካንሰሯ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ ሕክምና እየተከታተለች እንደነበር ይናገራል። ነገር ግን ካንሰሩ በሰውነቷ ተሰራጭቶ ሳንባዋን ማጥቃቱንና ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷን ባለቤቷ ደመረ ለቢቢሲ ተናግሯል። አርቲስት እቴነሽ ላለፉት አምስት አመታት ብትታመምም አልጋ ላይ የዋለችው ግን ላለፉት ሶስት ወራት ብቻ ነው። "ከዚያ በፊት እየሰራችም እየታከመችም ነበር" ብሏል ባለቤቷ አርቲስት ደመረ። • በዲሞክራቲክ ኮንጎ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ስርጭት "እጅግ አስበርጋጊ" ነው ተባለ • በተበከለ ደም አራት ወንድሞቹ የሞቱበት እንግሊዛዊ • የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት ሕገ-ወጥ ስደትን ለመቀነስ አውሮፕላናቸውን ሊሸጡ ነው ህመሟ ካንሰር መሆኑ እንደተረጋገጠ ጡቷ እንዲቆረጥ ብትጠየቅም 'ሰውነቴን ቢላዋ አይነካውም' በማለት እምቢ እንዳለች ይናገራል። በበዓላት ወቅት በሚዘፈኑ ዘፈኖች የምትታወቀው ድምጻዊት እቴነሽ ድምጿ ይበልጥ ለአጃቢነት ይፈለግ እንደነበር አርቲስት ደመረ ይናገራል። አርቲስት እቴነሽ በአማርኛና በኦሮምኛ የተሰሩ ሁለት አልበሞች ያሏት ሲሆን ከሌሎች የሙያ አጋሮቿ ጋር ደግሞ አራት የስብስብ (ኮሌክሽን) ስራዎችን ለገበያ አቅርባለች። በግሏም ሶስት ነጠላ ዜማዎችን ሰርታለች። በአሁኑ ወቅትም አዲስ የኦሮምኛ አልበም እየሰራች እንደነበረ የተናገረው አርቲስት ደመረ በየመሃሉ ስትታመም ስለነበረ በተፈለገው ፍጥነት መጨረስ እንዳልቻለች ተናግሯል። "ወደፊት ከሙዚቃው አቀናባሪ ኢብራሂም ጋር ተመካክረን እንደሚሆን እናደርገዋለን" ብሏል። የተዋወቅነው በልጅነታችን በማረሚያ ቤት ባንድ ውስጥ ነበር የሚለው ድምፃዊ ደመረ ከዚያ በኋላ ትዳር መስርተን ልጆችም አፍርተን አብረን በዚህ ሙያ ውስጥ ላለፉት ሰላሳ አንድ አመታት በደስታ ኖረናል ብሏል። "እቴነሽ ባለቤቴ ብቻ ሳትሆን እናቴ ነች፤ ለዚህ ደረጃ የደረስኩት በእርሷ ብርታት ነው። ጠንካራ ሴት ነች" ብሏል። እቴነሽ ግርማ ጥሩ የጥበብ ሙያ ያላት ነበረች፣ እርሷን በማጣታችን ብዙ ነገር ጎድሎብናል ያለው ደግሞ አርቲስት ታደለ ገመቹ ነው። "እቴነሽ ግርማ በአማርኛና በኦሮምኛ ስራዎችን ከመስራቷ ውጭ ጥሩ የሙያ ስነ ምግባር ያላት አርቲስት ነበረች" በማለት ምስክርነቱን ሰጥቷል። ባለፈው ማክስኞ ከዚህ አለም በሞት የተለየችው አርቲስት እቴነሽ ግርማ የቀብር ስነ ሥርዓቷም ረቡዕ እለት በአዲስ አበባ ከተማ ለቡ አካባቢ በሚገኘው ገብርኤል ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል። በቀብር ሥነ ስርአቷ ላይም በርካታ የኪነጥበብ ባለሙያዎችና ቤተሰቦቿ ተገኝተዋል።
news-55313813
https://www.bbc.com/amharic/news-55313813
የአሜሪካ ምርጫ፡ ጆ ባይደን በመራጭ ወኪሎች የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው በይፋ ተሰየሙ
ጆ ባይደን የምርጫ ድላቸው በመራጭ ወኪሎች ስብስብ (ኤሌክቶራል ኮሌጅ) ተረጋግጦላቸው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው በይፋ ተሰይመዋል፡፡
ይህንን የድምጽ አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት ተከትሎ ባይደን ባደረጉት ንግግር "በመጨረሻም የሕዝቡ ፍላጎት አሸነፈ" ብለዋል። በአሜሪካ የምርጫ አሰራር መሰረት ሕዝብ ድምጽ የሚሰጠው በቀጥታ ለእጩ ፕሬዝዳንቶች ሳይሆን የግዛት ወኪሎችን ለመምረጥ ነው፡፡ በዚህ መንገድ 270 እና ከዚያ በላይ ድምጽ ውክልና ያገኘ አሸናፊ ይሆናል፡፡ በመጨረሻ እነዚህ የድምጽ ሰጪ የግዛት ወኪሎች ተሰባስበው በሕዝብ የተቀበሉትን ውክልና በድምጻቸው በማረጋገጥ ፕሬዝዳንቱን በይፋ ይመርጣሉ፡፡ ባይደን በአሜሪካ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ማሸነፋቸው በዚህ መንገድ በይፋዊ መረጋገጡን ተከትሎ ባደረጉት ንግግር፤ የአሜሪካ ዴሞክራሲ "ተገፍቶ፣ ተፈትኖ እና ስጋት ላይ ወድቆ ነበር" ካሉ በኋላ፤ የአሜሪካ ዴሞክራሲ፤ "እውነተኛ እና ጠንካራ መሆኑን አፈር ልሶ በመነሳት አረጋግጧል" ብለዋል። ባይደን ፕሬዝደንት ትራምፕ የምርጫውን ውጤት ለማስቀየር ያደረጉትን ጥረት ፍሬ ባለማፍራቱ አሁን ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ የምንሸጋገርበት ጊዜ ነው ብለዋል። ይህ በኤሌክቶራል ኮሌጁ የሚሰጠው ማረጋገጫ ባይደን ወደ ዋይት ሃውስ እንዲገቡ ማግኘት የሚገባቸው የመጨረሻው ማረጋገጫ የድምጽ አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት ነው። በአሜሪካ ምርጫ ስርዓት ውስጥ መራጮች ድምጻቸውን ለኤክቶራል ኮሌጅ መራጮች በየግዛቶቻቸው ከሰጡ በኋላ አሸናፊዎቹ "ኤሌክተርስ" በዚህ መንገድ ተሰባስበው ለፕሬዝደንታዊ እጩዎች ድምጻቸውን ይሰጣሉ። በአሜሪካ የምርጫ ውጤት መሠረት ዲሞክራቱ ጆ ባይደን ከወር በፊት በተካሄደው ምርጫ 306 ኤሌክቶራል ኮሌጅ ድምጽ ሲያገኙ ፕሬዝደንት ትራምፕ ደግሞ 232 ላይ መቆማቸው ይታወሳል፡፡ እስካሁን የምርጫውን ውጤት አልቀበልም የሚሉት ፕሬዝደንት ትራምፕ፤ ባይደን ምርጫውን ማሸነፋቸው በአሌክቶራል ኮሌጅ ከተረጋገጠ በኋላ ያሉት ነገር የለም። ትራምፕ ምርጫው ተጭበርብሯል ሱሉ ቢቆዩም ለዚህ ክሳቸው ግን እስካሁንም ማረጋገጫ ማቅረብ አልቻሉም። ስለመጭበርበሩ ለማስረዳት ጉዳያቸውን ወደ ተለያዩ ፍርድ ቤቶች ይዘው ቢሄዱም ክሳቸው ውድቅ ተደርጎባቸዋል። ምንም እንኳ ትራምፕ የምርጫውን ውጤት አልቀበልም በሚል አቋማቸው ቢጸኑም አንዳንድ የሪፓብሊካን ሴናተሮች ግን ትራምፕ የምርጫውን ውጤት በጸጋ እንዲቀበሉ ጥሪ እያቀረቡላቸው ይገኛሉ። የምርጫው ውጤት መረጋገጡን ተከትሎ ሪፓብሊካኑ ሴናተር ላማር አሌክሳንደር፤ "ፕሬዝደንታዊ ምርጫው ተጠናቋል። ግዛቶችን የምርጫውን ውጤት አረጋግጠዋል። ፍርድ ቤቶች ለክርክሮች ብይን ሰጥተዋል። የመራጭ ወኪሎች ‹ኤሌክተርስ› ድምጽ ሰጥተዋል። ፕሬዝደንት ትራምፕ ለአገራቸው ቅድሚያ ሰጥተው፤ለተመራጩ ፕሬዝደንት ባይደን መልካም ጅማሮ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተስፋ አድርጋለሁ" ብለዋል። "ኤልክቶረስ" በተለያዩ ግዛቶች ድምጻቸውን በሰጡበት ወቅት ከፍተኛ የደህንነት ጥበቃ ተደርጓል። በተለይ በሚሺጋን ግዛት የደህንነት ስጋት ሊኖር እንደሚችል ጥቆማ በመሰጠቱ አንዳንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ዝግ እንዲሆኑ ተደርገው ነበር።
news-55802358
https://www.bbc.com/amharic/news-55802358
ኮሮናቫይረስ፡ የዓለም ጤና ድርጅት ተመራማሪዎች በቻይና ዉኃን ግዛት ከለይቶ ማቆያ ወጡ
የኮሮና ተህዋሲ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ተገኘባት የቻይናዋ ዉሃን ከተማ ለምርመራ ያቀናው የዓለም ጤና ድርጅት የመርማሪዎች ቡድን ከለይቶ ማቆያ መውጣቱ ተገለፀ።
እአአ በ2019 ኮቪድ-19 ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው በቻይናዋ ዉሃን ከተማ ነበር ተመራማሪዎቹ የምርምር ተቋማት ሰራተኞችን፣ ሆስፒታሎችን እና ተህዋሲው ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘበት የባህር ምግቦች መሸጫ ስፍራ የሚነግዱ ሰዎችን ቃለ መጠይቅ ያደርጋሉ ተብሏል። ይኹን እንጂ የእነዚህ ባለሙያዎች የምርመር ስራ የሚወሰነው የቻይና ባለሥልጣናት በሚሰጡት መረጃ ላይ ነው ተብሏል። ይህ የሆነው በቻይናና እና በዓለም ጤና ድርጅት መካከል ወራትን የፈጀ ድርድር ከተካሄደ በኋላ ነው። በኮቪድ-19 ምከንያት ዘመዶቻቸውን ያጡ የተወሰኑ ግለሰቦች የመርማሪ ቡድን አባላቱን ለማግኘት ተስፋ አድርገዋል። 13 የባለሙያዎችን የያዘው ይህ ቡድን ዉሃን የደረሰው ከ14 ቀናት በፊት ነበር። አባላቱ ላለፉት ሁለት ሳምንታት በለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲቆዩ ተደርገው ሀሙስ እለት ወጥተዋል። በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩት ባለሙያዎች ከቻይና ተመራማሪዎች እና እርስ በእርሳቸው በቪድዮ ሲወያዩ ነበር። ሐሙስ ከሰዓት ራሳቸውን ለይተው ካቆዩበት ሆቴል በመውጣት ጋዜጠኞችን ሳያነጋግሩ አውቶቡስ ተሳፍረዋል። ቀደም ብሎ የቡድኑ አባላት ከሆኑት መካከል የተወሰኑት በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበራቸው ጊዜ መጠናቀቅን አስመልክተው፣ ከመንግሥት የተሰጣቸውን የምስክር ወረቀት ጨምሮ በትዊተር ገጻቸው ላይ ለጥፈው ነበር። የዓለም ጤና ድርጅት ባለሙያዎቹን ወደ ቻይና ከላከ በኋላ አንድ የቡድኑ አባል እንዳይገባ በመደረጉ እንዲሁም ሌሎቹ በአውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ በመስተጓጎላቸው ወደ ቻይና እንዳይገቡ ተከለከሉ ሲል ገልጾ ነበር። በኋላ ግን የቻይና መንግሥት ስህተቱ የተፈጠረው ይኹነኝ ተብሎ አለመሆኑን ገልጿል። ኮቪድ-19 በ2019 ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው በዉሃን ግዛት ሲሆን፣ ቻይና ግን ለበርካታ ወራት ተህዋሲው የተነሳበት ስፍራ ይህ አይደለም ስትል ቆይታ ነበር። የቻይና መገናኛ ብዙኀን በቅርቡ ወረርሽኙ ከቻይና ውጪ በስፔን፣ ጣልያን ወይንም በአሜሪካ መነሳቱንና ወደ ቻይናም በቅዝቃዜና በታሸጉ ምግቦች ወደ ቻይና ሳይገባ አልቀርም የሚል ዘገባ ሰርተዋል።
50093600
https://www.bbc.com/amharic/50093600
ተማሪዎች በተመደቡበት ዩኒቨርስቲ ብቻ ነው መማር የሚችሉት- የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
በትናንትናው ዕለት የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ አዳዲስ ተማሪዎችን ወደ አማራ ክልል አልክም ማለቱን ተከትሎ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ይህንን ለማለት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሥልጣን የለውም ሲል ለቢቢሲ ተናገረ።
ተማሪዎችን የመደበው የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት ነው ያሉት በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ደቻሳ ጉርሙ፣ ከመግለጫው በፊት በነበሩ መድረኮች ላይ በተደጋጋሚ ክልሉ ጥያቄውን ማቅረቡን ይናገራሉ። • የቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄ ከየት ወደ የት? የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ገ/መስቀል ካሕሳይ ትናንት እንደተናገሩት "ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ወደ ሚሰነዘሩባቸው ዩኒቨርሲቲዎች እና ኃላፊነት ወደማይወስድ ክልል አዲስ ተማሪዎችን ላለመላክ የክልሉ አቋም ነው" ሲሉ ተናግረዋል። በዚህም መሰረት የክልሉ አቋም ነው ያሉትን አማራ ክልል የተመደቡ 600 የሚደርሱ ተማሪዎችን ወደዚያ እንደማይልኩ ለሚመለከተው የፌደራል መንግሥቱ አካል ማሳወቃቸውን ገልጸዋል። አቶ ደቻሳ ለቢቢሲ እንዳስረዱት ከትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ጋር በተደጋጋሚ በዚህ ጉዳይ ላይ ንግግር ማድረጋቸውን ገልፀው፤ አሁን በክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ያለው ሰላም አስተማማኝ በመሆኑ ተማሪዎች ወደዚያው ሄደው እንዲማሩ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል። "ሁሉም ተማሪዎች ወደየተመደቡበት ዩኒቨርስቲ ሄደው ይማራሉ የሚል እምነት ነው ያለን" ያሉት ኃላፊው፤ በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ተጠሪነታቸው ለፌደራል መንግሥቱ በመሆኑ በየክልሉ የሚገኙ ትምህርት ቢሮዎች ማዘዝ አይችሉም ብለዋል። • "በማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር የተከሰተው ለመላው ሃገሪቱ የጸጥታ ስጋት ነው" የአማራ ክልል ደኀንነትና ጸጥታ ካውንስል የትግራይ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ጨምረው እንዳሉት ዘንድሮ በአማራ ክልል ወደሚገኙ የትምህርት ተቋማት ተመድበው የነበሩ ተማሪዎች ከ2ሺህ በላይ እንደነበሩና ከሚመለከተው አካላት ጋር በተደረገው ንግግር ቁጥሩ ወደ 600 ዝቅ እንዲል መደረጉን ገልጸዋል። ከትግራይ ክልል የቀረበውን ተከትሎም የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎችን በተለያዩ ክልሎች ውስጥ ወደሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ተመድበዋል፤ እነሱም ወደ ተመደቡበት ተቋም ሄደው መማር ያለባቸው ሲል አመልክተወል። አቶ ደቻሳ ጉርሙ እንዳሉት "የስፖርትና የትምህርት ጉዳይ ሲነሳ በሁለቱ ክልሎች መካከል እንዲህ አይነት ክፍተት አለ" በማለት ከትግራይ በኩል የቀረበውን ሃሳብም "አንተገብረውም፤ ሊሆንም አይችልም" ብለዋል። በትግራይ ክልል ያሉም ሆኑ ሌሎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፤ እነዚህን ልጆች ተቀብለው አያስተናግዱም ያሉት ኃላፊው "የለባቸውምም" ሲሉ አስረግጠው ይናገራል። • "አሁን ያለው ሁኔታ ከቀጠለ ነገ ወደ እርስ በርስ ጦርነት እንደሚገባ ግልጽ ነው" አቦይ ስብሃት ምክንያቱም ይላሉ ኃላፊው "ትግራይ ክልል ያሉትም ሆነ ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች መቀበል በሚችሉት ልክ ተማሪ መድበናል" በማለት "ዩኒቨርስቲዎቹ ምንም ዓይነት ተጨማሪ ተማሪ መቀበል አይችሉም፤ በጀትም የላቸውም" ብለዋል። በዩኒቨርስቲዎች ዘላቂ ሰላም እንዲኖር፣ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ተቀራርበን እየሰራን ነው ያሉት አቶ ደቻሳ፤ እስካሁን ድረስ ያለው ሁኔታ ጥሩ መሆኑን ተናግረዋል። የተሻለ አቀባበል ለተማሪዎች እየተደረገ ነው ያሉት የኮሙኑኬሽን ዳይሬክተሩ ከሃይማኖት ተቋማት፣ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከአካባቢዎቹ ማህበረሰብን አባላት የካተተበት ኮሚቴ በማቋቋም በቤተሰብ መንፈስ ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎቻቸውን እየተቀበሉ መሆኑን ገልፀዋል።
news-51556021
https://www.bbc.com/amharic/news-51556021
ጋና፡ ውጤት ለማሻሻል ወሲብን ተተቅመዋል የተባሉት የዩኒቨርሲቲ መምህራን ታገዱ
ወሲባዊ ትንኮሳ ሲፈፅሙ በቢቢሲ ጋዜጠኞች በድብቅ የተቀረፁት ሁለት ጋናውያን መምህራን የለምንም ደሞዝ ከሥራቸው እንዲታገዱ እንደተወሰነባቸው ተገለጸ።
በጋና ዩኒቨርሲቲ መምህራን የሆኑት ፕሮፌሰር ራንስፎርድ እና ዶክተር ፖል ክዋሜ ቡታኮር 'ሴክስ ፎር ግሬድ' የተሰኘው የምርመራ ዘገባ ላይ እንደተማሪ ሆነው በቀረቡት ሪፖርተሮች ላይ ወሲባዊ ትንኮሳ ሲፈፅሙ ተቀርፀዋል። ራንስፎርድ ግያምፖ ለስድስት ወራት ከስራ የታገዱ ሲሆን ፖል ቡታኮር ደግሞ ለአራት ወራት ከስራቸው ተገልለው እንዲቆዩ ዩኒቨርሲቲው ወስኗል። • በጋና በቢቢሲ ዘጋቢ ፊልም ላይ ወሲባዊ ትንኮሳ ሲፈፅሙ የታዩ መምህራን ከሥራቸው ታገዱ • የናይጄሪያ ዩኒቨርስቲ በቢቢሲ ዘገባ ላይ ወሲባዊ ትንኮሳ ሲፈፅም የታየውን መምህሩን አገደ አጣሪ ኮሚቴው ማስረጃዎቹን ከማጋለጡ በፊት ድርጊታቸውን እንዲያምኑ ለፕሮፌሰር ግያምቦ እና ዶክተር ቡታኮር የጋና ዩኒቨርሲቲ ጥሪ አቅርቦ ነበር። ይሁን እንጂ ሁለቱም የዩኒቨርሲቲው መምህራን "ድርጊቱን አልፈፀምንም" ሲሉ ውንጀላውን በመቃወም ክደውታል። በተመሳሳይ በዚሁ የቢቢሲ የምርመራ ዘገባ ላይ በድብቅ የተቀረፁት በናይጄሪያ የሚሰሩ መምህራንም ከሥራቸው መታገዳቸው ይታወቃል። በናይጄሪያ ሌጎስ ዩኒቨርሲቲ ፣ ዶክተር ቦኒ ፌስ ኢግቤኔጉ እና ዶክተር ሳሙዔል ኦላዲፖ የተባሉት ሁለት መምህራንን ከሥራቸው ያገደ ሲሆን ይህንኑ የሚመረምር ኮሚቴ አቋቁሟል። በምዕራብ አፍሪካ በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የተሰራው የቢቢሲ የምርመራ ዘገባ መምህራኖች የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ወሲብን እንደመደራደሪያነት እንደሚያቀርቡ ያሳያል። ማሳሰቢያ : ይህ ታሪክ ግልጽ ወሲባዊ ቃላት አሉበት በዘጋቢ ፊልሙ ውስጥ ዶክተር ፖል ቡታኮር ተማሪ መስላ የመጣችውን ሴት ሪፖርተር በድብቅ ጾታዊ ግንኙነት እንዲመሰርቱ ጥያቄ ሲያቀርብ ይታያል። ቀጥሎም ይህንን ካደረገች የትምህርት ሕይወቷ የተሳካ እንደሚሆን ይገልጻል። ፕሮፌሰር ራንስፎርድ ግያምፖ ደግሞ ለሪፖርተሯ የአግቢኝ ጥያቄ ሲያቀርቡ ይታያል። አስከትለው ደግሞ ከየትኛው ትምህርት ቤት እንደመጣች ጠይቀዋት ስትመልስላቸው ከዛ ትምህርት ቤት የሚመጡ ሴት ተማሪዎች 'የወንድ ብልት' እንደሚያስደስታቸው መስማታቸውን ይገልጻሉ። በምዕራብ አፍሪካ አገራት ያሉ የዩንቨርስቲ መምህራን በተማሪዎቻቸው ላይ የሚፈጽሙት ወሲባዊ ትንኮሳ በቢቢሲ ምርመራ ተጋለጠ። ዘጋቢ ፊልሙ ከተላለፈ በኋላ በጋና እና ናይጄሪያ ከፍተኛ ቁጣና ተቃውሞ ተቀስቅሶ የነበረ ሲሆን የጋና ዩኒቨርሲቲ መምህራኑ ምርመራው እስኪጠናቀቅ ያለምንም ክፍያ ከስራቸው ታግደው እንዲቆዩ ተደርገው ነበር። ባሳለፍነው ጥቅምት ወር ለእይታ የበቃውን የቢቢሲ የምርመራ ዘገባ ተከትሎ የጋና ዩኒቨርሲቲ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ምርመራውን ከጀመረ ወራት የተቆጠሩ ሲሆን ከትናንት በስቲያ (ሰኞ) ባስተላለፈው ውሳኔ ሁለቱም መምህራን የዩኒቨርሲቲውን ህግና ደንቦች ጥሰዋል ብሏል። ቅጣታቸውን ከጨረሱ በኋላም ስለዩኒቨርሲቲው የጾታዊ ትንኮሳ ሕጎች ስልጠና እንዲወስዱ የሚደረግ ሲሆን ጸባያቸው ታይቶ ደግሞ ወደ ማስተማር ስራቸው ሊመለሱ እንደሚችሉ ኮሚቴው ገልጿል። ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታትም ቁጥጥር ይደረግባቸዋል ብሏል ኮሚቴው። • ወሲባዊ ትንኮሳ ያደረሰባት አለቃዋን በማጋለጧ የታሠረችው ሴት • ወሲባዊ ትንኮሳን ሪፖርት በማድረጓ ተቃጥላ የተገደለችው በዩኒቨርሲቲ መምህራኑ ላይ የተላለፈው ውሳኔ በዋና ከተማዋ አክራ የተቀላቀለ ስሜትን እንደፈጠረ በቦታው የሚገኘው የቢቢሲ ሪፖርተር ቶማስ ናዲ ገልጿል። አንዳንዶች ውሳኔው እጅግ የሚያሳዝንና እንደውም ሌሎችንም የሚያበረታታ እንደሆነ ገልጸዋል። '' እስከዛሬ ሲደረግ የነበረውን ምርመራ ቀልድ የሚያስመስለው ውሳኔ ነው የተላለፈው። ስድስትና አራት ወራት ብቻ ያለደመወዝ ከስራ ማገድ ማለት እኮ ዓመታዊ እረፍት ወሰደው እንዲዝናኑ እንደማድረግ ነው። ይሄ ችግር አሁንም መፍትሄ አላገኘም'' ብላለች አንዲት ቢቢሲ ያነጋገራት የከተማዋ ነዋሪ። አንዳንዶች ደግሞ ተገቢው ውሳኔ በመተላለፉ ደስተኞች እንደሆኑ ገልጸዋል። '' ለእኔ ዩኒቨርሲቲው ያደረገው ነገር ለተማሪዎች ብርታት የሚሆንና ለአስተማሪዎች ደግሞ ማስጠንቀቂያ ነው'' ብሏል አንድ የዩቪርሲቲው ተማሪ። የቢቢሲን የምርመራ ዘገባ ተከትሎ የናይጄሪያ ምክር ቤት በዩኒቨርሲቲዎች የሚፈጸሙ ጾታዊ ትንኮሳዎች ላይ ሕግ ለማውጣት ሰኞ ዕለት ውይይቱን የጀመረ ሲሆን በቀረበው ረቂቅ መሰረት ጥፋተኛ ሆነው የተገኙ ግለሰቦች እስከ አምስት አመት በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ ሀሰብ ቀርቧል።
news-52695861
https://www.bbc.com/amharic/news-52695861
በቪዲዮ ምክንያት ሁለት ታዳጊ ፓኪስታናውያን በቤተሰብ አባል ተገደሉ
በሰሜናዊ ፓኪስታን የሚኖሩ ሁለት ታዳጊዎች ኢንተርኔት ላይ በተሰራጨ አንድ ቪዲዮ ምክንያት "የክብር ግድያ" በሚባለው ሁኔታ ተገድለዋል።
በፓኪስታን ውስጥ በማህበረሰቡ ዘንድ "አስነዋሪና ክብርን የሚያዋርድ" ስራ ሰርተዋል የሚባሉ ሴቶች "የክብር ግድያ" በሚባለው መንገድ ይሞታሉ። በአብዛኛው በቤተሰብ አባላት የሚገደሉ ሲሆን እነዚህም ታዳጊዎች በአንድ ቤተሰብ አባል በጥይት ተገድለዋል ተብሏል። •ታይዋን የአለም አቀፉ ጤና ድርጅት ወሳኝ ጉባኤ ላይ እንዳትሳተፍ ለምን ተደረገች? •"ለሃያ ዓመታት ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስዘጋጅ ነበር" የንፅህና ሱሰኛው ግድያው የተፈፀመው የተፈፀመው ሁለቱ ሴቶች ከአንድ ወንድ ጋር የሚያሳይ ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያዎች መውጣታቸውን ተከትሎ እንደሆነ ፖሊስ አስታውቋል። ፖሊስ ሁኔታውን ለመርመር ራቅ ብላ ወደምትገኘው ቦታ በርካታ የፖሊስ ኃይልን አሰማርቷል። ግድያው የተፈፀመው በዚህ ሳምንት ሐሙስ ሲሆን የድንበር ከተማ በምትባለው ሻም ፕሌይን ጋርዮም መሆኑንንም የፓኪስታን ሚዲያ የፖሊስን ሪፖርት ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። በሚዲያው ዘገባ መሰረት ለግድያው ተብሎ የተሰጠው ምክንያት የ16ና የ18 አመት ታዳጊዎቹ እንዲሁም አንዲት እድሜዋ ያልተጠቀሰና ከግድያው የተረፈች ታዳጊ ጋር ሰው በሌለበት ቦታ አንድ ወንድ አብሯቸው ሆኖ ቪዲዮ ሲቀርፅ የሚያሳይ ነው። ቪዲዮው ወሲባዊ ይዘት አለው የተባለ ሲሆን 52 ሶኮንዶችን ብቻ ነው የሚያሳየው። ቪዲዮው የተቀረፀው ባለፈው አመት ሲሆን በቅርብ ሳምንታትም ነው ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ወጥቶ ብዙዎች እንደተጋሩት ከፍተኛ የፖሊስ ኃላፊ ለጋዜጣው ተናግረዋል። "በአሁኑ ሰአት ዋነኛ ስራችን ሶስተኛዋን ታዳጊ እንዲሁም ግለሰቡ ላይ ወንጀል ከመፈፀሙ በፊት በህይወት ማቆየት ነው" ብለዋል። የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዋች በፓኪስታን በታዳጊና በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ግድያዎች አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ብሏል። የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች "የክብር ግድያ" በሚባለው መንገድ በፓኪስታን አንድ ሺህ ሴቶች እንደተገደሉ ይናገራሉ።
news-55581632
https://www.bbc.com/amharic/news-55581632
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ትዊተርን እንዳይጠቀሙ አስከመጨረሻው ታገዱ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ "ተጨማሪ የኃይል ድርጊቶችን ሊቀሰቅሱ ይችላሉ" በሚል ስጋት በዘላቂነት ትዊተር ገጽ ላይ ድርሽ እንዳይሉ ኩባንያው እግድ ጣለባቸው።
ትዊተር ጉዳዩን አስመልክቶ እንዳለው በትራምፕ ላይ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ፕሬዝዳንቱ በአካውንታቸው ላይ "በቅርቡ ያሰፈሯቸውን መልዕክቶች በደንብ ከመረመረ" በኋላ መሆኑን ገልጿል። አንዳንድ የአሜሪካ ሕግ አውጪዎችና ታዋቂ ሰዎች ትራምፕ ከትዊተር አስከወዲያኛ እንዲታገዱ ለዓመታት ሲወተውቱ ቆይተዋል። የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ሚሼል ኦባማ ሐሙስ ዕለት በትዊተር ገጻቸው ላይ የማኅበራዊ ሚዲያ ተቋማት ዶናልድ ትራምፕን ከመድረኮቻቸው በማስወገድ "በአደገኛ ባሕሪያቸው" እንዲገፉበት ከማድረግ እንዲቆጠቡ ጠይቀው ነበር። ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ረቡዕ ዋሽንግተን ውስጥ የሚገኘውን ካፒቶል ሒልን የወረሩትን ደጋፊዎቻቸውን "አርበኞች" በማለት ካሞገሱ በኋላ ለ12 ሰዓታት ትዊተርን እንዳይጠቀሙ ታግደው ነበር። የአሜሪካ ምክር ቤት አባላት የጆ ባይደንን የምርጫ ውጤት ለማረጋገጥ ተሰብስበው ባሉበት በመቶዎች የሚቆጠሩት የፕሬዝዳንቱ ደጋፊዎች ወደ ምክር ቤቱ ግዙፍ ሕንጻ ጥሰው በመግባት በተፈጠረ ግርግር አንድ ፖሊስን ጨምሮ የአምስት ሰዎች ህይወት አልፏል። ይህንንም ተከትሎ ትዊተር ፕሬዝዳንት ትራምፕ በድጋሚ የማኅበራዊ መድረኩን ደንቦች የሚጥሱ ከሆነ "እስከወዲያኛው" እንዳይጠቀሙ እገዳ እብደሚጥልባቸው አስጠንቅቆ ነበር። ነገር ግን ከሰዓታት በኋላ የፕሬዝዳንት ትራምፕ አካውንት መልሶ ቢከፈትም በድጋሚ አርብ ዕለት በሰሌዳቸው ላይ በለጠፏቸው ሁለት መልዕክቶች ሳቢያ አስከመጨረሻው ታገደዋል። ትዊተር እዚህ ውሳኔ ላይ እንዲደርስ ያስገደዱት የመጨረሻዎቹ መልዕክቶች ፕሬዝዳንቱ የድርጅቱን ፖሊሲ በመቃረናቸው መሆኑን አመልክቷል። ፕሬዝዳንት ትራም በአንደኛው መልዕክታቸው ላይ "እኔን የመረጡ 75 ሚሊዮን አሜሪካውያን ወደፊት ታላቅ ድምጽ ይኖራቸዋል። በየትኛውም መንገድም ሆነ አይነት ተገቢ ባልሆነ ሁኔታ ሊስተናገዱና አክብሮትን ሊነፈጉ አይገባም!!" በማለት አስፍረው ነበር። ይህንንም ተከትሎ ትዊተር እንዳለው "ይህ መልዕክታቸው ፕሬዝዳንቱ የሥልጣን ሽግግርን በአግባቡ ለማካሄድ ፍላጎት እንደሌላቸው በሚያሳይ ሁኔታ ተተርጉሟል" በማለት ለውሳኔው ምክንያት አቅርቧል። ፕሬዝዳንቱ በሁለተኛው መልዕክታቸው ደግሞ "ለጠየቃችሁኝ ሁሉ፤ [በጆ ባይደን] ሲመተ በዓል ላይ አልገኝም" ሲሉ ከሁለት ሳምንት ባለሰ ጊዜ ውስጥ በሚከናወነው የሥልጣን ርክክብ ላይ እንደማይሳተፉ ገልጸዋል። ትዊተር ይህንን መልዕክታቸውን በተመለከተም "ይህ በበርካታ ደጋፊዎቻቸው ዘንድ ምርጫው ሕጋዊ እንዳልሆነ እንደተጨማሪ ማረጋገጫ ተደርጎ ተወስዷል" ብሏል። በዚህም መሠረት ትዊተር እነዚህ የፕሬዝዳንቱ የትዊተር መልዕክቶች የድርጅቱን "የኃይል ድርጊትን የማበረታታት ፖሊሲን የሚጻረሩ ናቸው" በማለት ትራምፕን አስከመጨረሻው ከሚወዱት የትዊተር መድረክ ላይ አሰናብቷቸዋል።
news-53064060
https://www.bbc.com/amharic/news-53064060
በአቃቂ ቃሊቲ በለይቶ ማቆያ ያሉ የጤና ባለሙያዎች መሠረታዊ ፍላጎታችን እየተሟላ አይደለም አሉ
ከሳምንታት በፊት በኮቪድ-19 የተያዙ የህክምና ባለሙያዎች ቁጥር መጨመሩን የኢትዮጵያ ጤና ሚንስር ዶ/ር ሊያ ታደሰ መናገራቸው ይታወሳል። በተጨማሪም ቢቢሲ ያነጋገራቸው በተለያዩ የሕክምና ተቋማት የሚሰሩ ባለሙያዎችም የሕክምና መከላከያ ቁሳቁሶች (ፒፒኢ) እጥረት እንዳለባቸው ገልፀዋል።
ከእነዚህም መካከል ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በለይቶ ማቆያ የሚገኙት በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ተብሎ በሚጠራው ጤና ጣቢያ ውስጥ ያሉት ይገኙበታል። ወረዳ 10 ጤና ጣቢያ ተብሎ በሚጠራው ለይቶ ማቆያ ውስጥ እንደሚገኙ ለቢቢሲ የተናገሩ ሁለት የጤና ባለሙያዎች፤ በሚገኙበት ለይቶ ማቆያ መሠረታዊ የሚባሉ ግልጋሎቶችን በአፋጣኝ ማግኘት አልቻሉም። ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ዕለት ስናነጋግራቸው በጣቢያው ውሃ እና መብራት እንዳልነበረ ገልጸውልናል። ሰኞ፣ ሰኔ 9 ቀን 2012 በድጋሚ ስናናግራቸው ግን ለሳምንት ያክል ያልነበረው የመብራት እና ውሃ እገልግሎት እንደመጣ ተናግረው ሌሎች ጥያቄዎቻቸው አሁንም ምላሽ እንዳላገኙ ግን ጨምረው አስረድተዋል። • በቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ከታደሙ ሰዎች 4ቱ ቫይረሱ ተገኘባቸው • በኢትዮጵያ በአስክሬን ምርመራ ኮቪድ-19 መገኘቱ ምን ያመላክታል? ስማቸው እንዲጠቀስ የማይፈልጉ አንድ የጤና ባለሙያ እንደሚሉት፤ በሽታው በማኅበረሰቡ ውስጥ እየተሰራጨ ሲመጣ፣ ወደ ህክምና መስጫ ማዕከላት የሚሄዱ ሰዎች ቁጥር ሲጨምር፤ የጤና ባለሙያዎችም ለበሽታው የበለጠ ተጋላጭ ይሆናሉ። “ቀድሞውም ለጤና ባለሙያዎች በቂ የመከላከያ ቁሳቁስ [ፒፒኢ] መቅረብ ነበረበት። ይህ ግን አልሆነም። ማስክ በየጊዜው አይገኝም ነበር። ለሁለትና ለሦስት ቀን አንድ ማስክ [ይሰጣል] ጋዋን አይገኝም። የአገሪቱ የአቅርቦት ችግር ሊሆን ይችላል ብዬ አስባለሁ ግን [ሊታሰብልን ይገባል]” ይላሉ ባለሙያዋ። በሽታውን በግንባር ቀደምነት ለሚዋጉ የጤና ባለሙያዎች በቂ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባም ይናገራሉ። የጤና ባለሙያዎች በበሽታው ሲያዙ ደግሞ በለይቶ ማቆያ ውስጥ መሠረታዊ ፍላጎት መሟላት እንዳለበትም ያክላሉ። ወደ 15 የሚሆኑ ወንድ እና ሴት የጤና ባለሙያዎች በአንድ መጸዳጃ እየተጠቀሙ እንደነበረ የጤና ባለሙያዋ ተናግረዋል። አሁን በጣቢያው ውሃ ቢያገኙም ወደ ለይቶ ማቆያ ከአስር ቀን በፊት ሲገቡ ንጹህ መጸዳጃ እንዳልነበረ ይገልጻሉ። “በአንድ ወለል ላይ ከነበሩ ሁለት መጸዳጃ ቤቶች አንዱ ሙሉ በሙሉ ውሃ አልነበረውም። አንዱ ግን ውሃ ስለነበረው በአንድ ወለል ላይ ያሉ 15 ወንዶችና ሴቶችም አንድ መጸዳጃ ቤት ይጠቀማሉ። ይሄ ለሴቶች አስቸጋሪ ነው። የወር አበባቸው ሲመጣ ሸንት ቤት በደንብ መጠቀም አለባቸው. . .” ባለሙያዋ እንደሚሉት፤ ያለው ችግር እንዲቀረፍ ለማህበራቸውና ለጤና ሚንስትር በስልክ አሳውቀዋል። “ 'እየሄድንበት ነው' የሚል መልስ ነው የተሰጠን፤ የት እንደደረሰ አናውቅም” ሲሉም ያገኙትን ምላሽ ገልጸዋል። የጤና ባለሙያዋ አያይዘውም “ሕዝብ እያገለገልን ሳለን መንግሥት ለኛ ዋጋ አለመስጠቱ አሳዝኖኛል። ይህ ነው ብድራችን?” በማለት መሠረታዊ ፍላጎቶች እንዲሟሉላቸው ጠይቀዋል። በሌላ በኩል በሌሎች ለይቶ ማቆያዎች ውስጥ ያሉ የጤና ባለሙያዎች መሠረታዊ ፍላጎታቸው ተሟልቶ እንደቆዩ መስማታቸውን የጤና ባለሙያዋ ተናግረዋል። “በጥሩ ሁኔታ ቆይተው እንደወጡ ሰምቻለሁ። ምንም ቅሬታ የለም። እነሱ የነበሩበት ድሮም አገልግሎት ይሰጥ የነበረ ተቋም ወስጥ ነው። የኛ ግን አዲስ ጤና ጣቢያ ነው። መሠረተ ልማቱ መሟላቱ ሳይታይ ነው ለይቶ ማቆያ የሆነው። ናሙና ሰጥተን ውጤት የሚመጣውም ዘግይቶ ነው። ሌሎቹ ጋር እንዲህ አይደለም” ይላሉ። • በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ለምን ተስፋፋ? • የኮሮናቫይረስ ውጤት መዘግየት ስጋት እየፈጠረ ነው ሌላው ባለፈው ሳምንት (ሰኔ 4 ቀን 2012 ዓ. ም.) ያነጋገርናቸው የጤና ባለሙያ በለይቶ ማቆያ ከገቡ አስረኛ ቀናቸው እንደሆነ ገልጸውልናል። ነርሶችና ዶክተሮች በለይቶ ማቆያው እንደሚገኙ የሚናገሩት ባለሙያው፤ “ምርመራ እንዲደረግልን ስንጠይቅ ፍቃደኛ አይደሉም” ብለዋል። “በቫይረሱ ተይዞ ወደ ለይቶ ማቆያ የሚገባ ሰው በሰባተኛው ቀን በድጋሚ መመርመር አለበት የሚል መርህ አለ። ይህ መርህ እየተሟላ አይደለም። እስከ 14 ቀን የቆዩ አሉ” ይላሉ። ለክፍለ ከተማ እንዲሁም ለከተማው ጤና ቢሮ አሳውቀው “ጠብቁን” የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ገልጸው፤ “በሽታው የሚያስጠብቅ አይደለም። አገግሞ ለመሄድ የሚመች ሁኔታ አይደለም” ብለዋል። “የአገሪቱ ኢኮኖሚ ይታወቃል ቢሆንም ግን የጤና ባለሙያዎች እየተጋለጡ ያሉት በቂ ፒፒኢ ስለሌለ ነው። አንዳንዴ ሳኒታይዘር [እጅ ማጽጃ] በራስህ ወጪ ትገዛለህ. . . የታማሚን ስቃይ ለመቀነስ ስትሯሯጥ አንዳንዴ ራስህን የማታስታውስበት ደረጃ ላይ ትደርሳለህ” ሲሉ ከመጀመሪያውም በቂ ለቅድመ ጥንቃቄ የሚሆን የህክምና ቁሳ ቁስ አለመሟላቱን ያስረዳሉ። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እንኳን እንደ ኢትዮጵያ ደካማ የጤና መዋቅር ያላቸውን ይቅርና በምጣኔ ሀብት የተሻለ ደረጃ ደርሰዋል የሚባሉትን እንደ አሜሪካ፣ ስፔን እና ጣልያን ያሉ አገራትንም ፈትኗል። የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል፣ ጓንት እና ገዋንን የመሰሉ የሀኪሞች የግል መገልገያዎች (ፒፒኢ) እጥረት ጉዳይም የመላው ዓለም ራስ ምታት ነው። ሆኖም ግን ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ አገሮች ያሉ የጤና ባለሙያዎች በሽታውን በግንባር ቀደምነት እንደመከላከላቸው፤ በበሽታው እንዳይያዙ አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲደረግላቸው ይጠይቃሉ። በከፍተኛ ሁኔታ ለቫይረሱ ተጋላጭ እንደመሆናቸውም በበሽታው ሲያዙ መሠረታዊ ፍላጎቶች እንዲሟሉላቸውም ያሳስባሉ። • በኮሮናቫይረስ ወቅት ጀርመኖችን በሙያዋ የምታግዘው ኢትዮጵያዊት • ከቀብር በኋላ በደረሰ የምርመራ ውጤት ሰበብ 53 ሰዎች በሰሜን ሸዋ ወደ ለይቶ ማቆያ ገቡ ያነጋገርናቸው የጤና ባለጤና ባለሙያ፤ ከበሽታው አገግመው ወደ ሥራ ሲመለሱ፤ በለይቶ ማቆያ የነበሩበት ሁኔታ በሥራቸው ላይ ጫና ያሳድራል ብለው እንደሚሰጉ ገልጸውልናል። “ከዚህ የበለጠ ጊዜ ስለሌለ በትክክለኛ መንገድ ቁሳ ቁሶች [ፒፒኢ] መቅረብ አለባቸው። ሥራችን ስለሆነ የትም አንሄድም። የተማርኩት በሙያዬ ኅብረተሰቡን ለማገልገል ነው። መንግሥትም መሟላት ያለበትን ማሟላት አለበት።” በጉዳዩ ላይ ከጤና ሚንስትር ምላሽ ለማግኘት ሞክረን ወደ አዲስ አበባ ጤና ቢሮ መርተውናል። ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ እንዲሁም ከሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትም አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
news-53900469
https://www.bbc.com/amharic/news-53900469
ኮሮናቫይረስ፡ ዶ/ር ፋውቺ ለክትባት መጣደፉ ቢቀርብን ይሻላል አሉ
የአሜሪካ ዕውቅ የማኅበረሰብ ጤናና የተላላፊ በሽታዎች ጉዳይ ኃላፊ ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ ‹‹እኔ ተናግሪያለሁ! ይሄ ለክትባት የምንጣደፈው ነገር አላማረኝም›› እያሉ ነው፡፡
ይህን የተናገሩት ዶናልድ ትራምፕ የመጪው ምርጫ በለስ እንዲቀናቸው በሙከራ ላይ ያለን ክትባት ያለጊዜው ወደ ሕዝብ በማውጣት ‹ክትባት ደርሷልና ተከተቡ› እንዳይሉ ስጋት መፈጠሩን ተከትሎ ነው፡፡ ዶ/ር ፋውቺ በአሜሪካ ህዝብ ከትራምፕ የበለጠ ተሰሚነትና የመታመን ፀጋን ያገኙ ጎምቱ የጤና ባለሞያ ናቸው፡፡ ከሮይተርስ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት አንድን ክትባት የሕክምና ደንብና መርሆችን ሳይከተሉ ወደ ሕዝብ ማውጣት የሌሎች ክትባቶችን ተስፋ ያጨልማል፡፡ ትራምፕ አንድን ክትባት ሙሉ ሒደቱን ሳይጨርስና በብዙ ሰዎች ላይ ሙከራ ሳይደረግበት ይፋ ለማድረግ እየተዘጋጁ ነው የሚሉ መረጃዎች እየወጡ የሚገኙት ካለፈው ሳምንት ወዲህ ነው፡፡ ፕሬዝዳንቱ ይህን ለማድረግ የተበረታቱት በሕዝብ ዘንድ ያላቸውን ቅቡልነት በኅዳር ከሚደረገው ምርጫ በፊት ለመጨመር በመሻት ነው፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ትራምፕ ከጆ ባይደን ያነሰ ቅቡልና እንዳላቸው የሕዝብ ፖለቲካዊ ሙቀት መመተሪያ ዳሰሳ ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡ ዲሞክራቶች ‹‹እኚህ ትራምፕ የሚባሉ ሰውዬ ለዝናቸው ሲሉ የአሜሪካውያንን ሕይወት ለፖለቲካ ቁማር እያዋሉት ይገኛሉ›› ብለው ከሰዋቸዋል፡፡ ባለፈው ቅዳሜ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በትዊተር ሰሌዳቸው እንደጻፉት ከሆነ የአሜሪካ የምግብና የመድኃኒት አስተዳደር ለመድኃኒት አምራቾች ሥራቸውን እያደናቀፈባቸው ነው፡፡ ፕሬዝዳንቱ ይህን የሚሉት የመድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ‹ክትባት አምራቾች ትክክለኛውን የመድኃኒት አመራረት ሒደት ተከትለው እንዲሄዱ› በተደጋጋሚ በማሳሰቡ ነው፡፡ ፋይናንሻል ታይምስ ጋዜጣ ዶናልድ ትራምፕ በኦክስፎድና በአስትራዜኔካ አማካኝነት እየተሞከረ ያለው ክትባት ለአስቸኳይ የሕክምና አገልግሎት በአቋራጭ ለሕዝብ እንዲቀርብ የሚቻልበትን መንገድ እየፈለጉ እንደሆነ ዘግቦ ነበር፡፡ እነ ኦክስፎርድ እየሞከሩት ባለው ክትባት ለመሳተፍ 10 ሺ አሜሪካዊያን ፈቃደኝነታቸውን አሳይተዋል፡፡ ነገር ግን የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን 30ሺህ ፈቃደኞች ካልተሟሉ ይሁንታን አልሰጥም እያለ ነው፡፡ የኦክስፎርድ ክትባት አሁን ዓለም ላይ እየተሞከሩ ካሉ በዐሥራዎቹ ከሚገኙ ምርምሮች እጅግ ተስፋ የተጣለበት ነው፡፡ ባለፉት ሳምንታት ታዋቂ መድኃኒት ፋብሪካዎች መድኃኒቶቻቸውን በመሞከር ላይ ተጠምደው ቆይተዋል፡፡ ከዚህ ቀደም የኤሜሪካ የምግብና መድኃኒት አስተዳደር የወባ መድኃኒት የሆነው ሀይድሮክሲክሎሮኪዩን ለኮሮና ታማሚዎች ቢሰጥ እንደማይቃወም ተናግሮ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ግን መድኃኒቱ ከጥቅሙ ጉዳት ማመዘኑ በምርመራ በመረጋገጡ እውቅና ነፍጎታል፡፡ ዶናልድ ትራምፕ ይህን መድኃኒት ለሳምንታት መውሰዳቸውንና ፍቱን እንደሆነ እንደደረሱበት በተደጋጋሚ ይናገራሉ፡፡ ዶ/ር ፋውቺ እንደሚሉት ክትባቶች ትክክለኛውን አካሄድ ካልተከተሉ አደጋ ማስከተላቸው ብቻም ሳይሆን ሰዎች በቀጣይ በሚወጡ መድኃኒቶች እምነት ያጣሉ፣ እንዲመከርባቸው የሚፈቅዱ በጎ ፈቃደኞችንም ማሸሽ ይሆናል፡፡ ዶ/ር ፋውቺ ፖለቲካ ሕክምና ውስጥ ገብቶ መፈትፈት የለበትም፡፡ ሕክምና የራሱን መንገድ እንዲከተል ሊተው ይገባል የሚል አቋም አላቸው፡፡
news-48166994
https://www.bbc.com/amharic/news-48166994
አይ ኤስ በጀነራል ካሊፍ ጦር ላይ ጥቃት ሰነዘርኩ አለ
እስላማዊው ታጣቂ ቡድን (አይ ኤስ) ቅዳሜ ዕለት በካሊፍ ሃፍታር በሚመራው የጦር ቡድን መለማመጃ ካምፕ ላይ ጥቃት የሰነዘርኩት እኔ ነኝ አለ።
በጀነራል ካሊፍ የሚመራው ጦር ወደ መዲናዋ ትሪፖሊ የሚያደርገውን ዘመቻ አጠናክሮ ቀጥሏል። የሆስፒታል ምንጮች እንዳረጋገጡት አይ ኤስ በደቡባዊ ሊቢያ በምትገኘው ሳባህ ከተማ ላይ ፈጸምኩት ባለው ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች ተገድለዋል። በጦር አዛዡ ጀነራል ካሊፍ ሃፍታር የሚመራው ጦር ከወራት በፊት በወሰደው እርምጃ በነዳጅ ሃብታቸው የበለጸጉ ደቡባዊ የሀገሪቱን ሥፍራዎች ተቆጣጥሯል። የጀነራል ካሊፍ ጦር የሊቢያን መዲና ትሪፖሊን በቁጥጥር ሥር ለማድረግ እየተፋለሙ ይገኛሉ። • በትሪፖሊ አቅራቢያ በተደረገ ውጊያ የ21 ሰዎች ሕይወት ጠፋ • ሊቢያ ውስጥ 27 ሰዎች በቦምብ ጥቃት ተገደሉ አይ ኤስ በበይነ መረብ በለቀቀው መግለጫ ትናንት አደርስኩት ባለው ጥቃት 16 ሰዎች መግደሉን ወይም ማቁሰሉን ጠቅሶ በሥፍራው በእስር ላይ የነበሩ ሰዎችንም ነጻ ማውጣቱን ጠቁሟል። አንድ የጦር አዛዥ ለሮይተርስ ዜና ወኪል ሲናገሩ ጥቃት በደረሰበት ካምፕ ውስጥ የነበረ እስር ቤት ላይ ጉዳት መድረሱን አምነው ተጨማሪ መረጃ ሳይሰጡ ቀርተዋል። ሃመድ አል-ካህሊይ የተባሉ የአካባቢው ከንቲባ፤ አንድ ወታደር እንደተቀላ እና ወደ ሰባት የሚጠጉ ሌሎች ወታደሮች ደግሞ በጥይት ወይም ግፍ በተሞላበት መልኩ መገደላቸውን ለዜና ወኪሉ ተናግረዋል። በአካባቢው የሚገኝ የህክምና ማዕከል የሟቾች ቁጥር ዘጠኝ መሆኑን አስታውቋል። ጀነራል ካሊፍ የሊቢያ መንግሥት ከሚቀናቀኑ ሁለት ቡድኖች መካከል ከአንደኛው ጋር ጥምረት በመመስረት የትጥቅ ትግል ላይ ይገኛሉ። ጀነራል ካሊፍ የሊቢያ ብሄራዊ ጦር በሚሰኘው ጦራቸው አማካኝነት ከአራት ወራት በፊት ''አሸባሪዎች እና ወንጀለኛ ቡድኖች'' ባሏቸው አካላት ላይ ጥቃት መሰንዘር ጀምረዋል። ከአንድ ወር በፊት ጀነራል ካሊፍ ሃፍታር ጦራቸው ወደ ዋና ከተማዋ ትሪፖሊ እንዲዘምት ትዕዛዝ ሰጥተው ነበር። ይሁን እንጂ ዘመቻውን ተከትሎ ዓለም አቀፋዊ እውቅና ካለው እና በተባበሩት መንግሥታት ድጋፍ ከሚደረግለት የሃገሪቱ ጦር ጋር ፊት ለፊት ተጋፍጠዋል። የሊቢያ ጠቅላይ ሚንስትር ፋይዝ አል-ሴርዣ ትሪፖሊን አሳልፈው እንደማይሰጡ እና ጀነራል ካሊፍ ሃፍታር መፈንቅለ መንግሥት አውጀዋል ሲሉ ወቅሰዋል። ሊቢያ ከ8 ዓመታት በፊት በቀድሞ መሪዋ ሙአመር ጋዳፊ ላይ ተቃውሞ ከተነሳ ወዲህ ሰላም እና መረጋጋት እርቋት ቆይቷል።
50298752
https://www.bbc.com/amharic/50298752
ቱርክ የአል ባግዳዲን እህት ያዝኩ አለች
የቀድሞው የአይ ኤስ መሪ አቡ ባካር አል ባግዳዲ እህት በሰሜናዊ ሶርያ ውስጥ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው የቱርክ ባለሥልጣኖች አሳወቁ።
የ65 ዓመቷ አዛውንት ራስሚያ አዋድ የተያዙት ሰኞ ዕለት አዛዝ በተባለ ከተማ በተካሄደ አሰሳ እንደነበርም ተገልጿል። የቱርክ ባለሥልጣኞች ከአል ባግዳዲ እህት ስለ አይ ኤስ ጠቃሚ መረጃ ለማግኘት ተስፋ ማድረጋቸውን የተለያዩ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል። ባለሥልጣናቱ ራስሚያን በመጠቀም ስለ አይ ኤስ ውስጣዊ አሠራር ለማወቅ እንዳለሙ ለሮይተርስ ገልጸዋል። • የአይ ኤስ መሪ አቡ ባካር አል ባግዳዲ ማነው? አል ባግዳዲ በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ በሚገኘው መኖሪያው በአሜሪካ ልዩ ኃይሎች መከበቡን ተከትሎ ራሱን ማጥፋቱ ይታወሳል። የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአልባግዳዲ ሞት ቢኩራሩም፤ አይ ኤስ በሶሪያና በሌሎችም አገሮች አሁንም የጸጥታ ስጋት መሆኑ መዘንጋት እንደሌለበት የትራምፕ ተቺዎች በአጽንኦት ተናግረዋል። ስለ አል ባግዳዲ እህት እምብዛም መረጃ የለም። ቢቢሲ የታሠሩትን ሴት ማንነት ለማጣራት ያደረገው ጥረትም አልተሳካም። በኒው ዮርክ ታይምስ ዘገባ መሰረት አልባግዳዲ አምስት ወንድሞችን ብዙ እህቶች አሉት። ከእነዚህ ምን ያህሉ በሕይወት እንዳሉ ግልጽ መረጃ የለም። ራስሚያ አዋድ የተያዙት ከባለቤታቸው፣ ከአምስት ልጆቻቸውና ከልጃቸው ባለቤት ጋር በሚኖሩበት አካባቢ እንደሆነ አሶሽየትድ ፕሬስ ዘግቧል። ከጽንፈኛ ቡድን ጋር አብረው እንደሚሰሩ ስለሚጠረጠር ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነም አክሏል። • የአይ ኤስ መሪ ባግዳዲ ድምፁ ተሰማ ተንታኞች ከራስሚያ ምን ያህል ጠቃሚ መረጃ እንደሚገኝ እንዲሁም ከአል ባግዳዲ ጋር ምን ያህል ጊዜ እንዳሳለፉም ግልጽ መረጃ አለመኖሩን ገልጸዋል። በሀድሰን ኢንስቲትዮት የሚገኙ የሽብርተኝነት ተመራማሪ ማይክ ፕሬገንት፤ "በቅርብ ጊዜ ሊወሰዱ የታሰቡ ጥቃቶች የምታውቅ አይመስለኝም። ሆኖም አል ባግዳዲ ይተማመንባቸው የነበሩ ሕገ ወጥ ዝውውር የሚካሄድባቸውን መስመሮችን እና ታማኙ የነበሩ ሰዎችን ታውቅ ይሆናል" ሲሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ራስሚያና ቤተሰቦቻቸው ከቦታ ቦታ በሚስጥር ስለሚያዘዋውሩ የአል ባግዳዲ ተባባሪዎች መረጃ ሊገኝ እንደሚችልም ተመራማሪው ተናግረዋል። መጃው ለአሜሪካ የስለላ ሠራተኞች እና አጋሮቻቸው የአይ ኤስን የውስጥ መስመር በግልጽ የሚያሳይ ይሆናል። • አይኤስ አል ባግዳዲን የሚተካውን አዲስ መሪ ይፋ አደረገ
news-53987814
https://www.bbc.com/amharic/news-53987814
የአእምሮ ምጥቀት (IQ) ምንድን ነው?
ሰሞኑን በማህበራዊ መገናኛ ብዙኀን ላይ የኢትዮጵያውያንን የአእምሮ ምጥቀት መለኪያ (Intelligence Quotient) የሚያሳይ መረጃ ወጥቷል በሚል በርካቶች ሲቀባበሉት ነበር።
በርካቶች በወቅቱ ሲወያዩበት የነበረው ኢትዮጵያውያን በአስተሳሰብ ችሎታ ማነስ ከበርካታ የዓለማችን አገሮች ሁሉ ዝቅ ብለው መገኘታቸውን ነበር። ይህ መረጃ የኢትዮጵያውያን የአእምሮ ምጥቀት ተመዝኖ 63 መሆኑን ያሳያል። የኢትዮጵያውያን የማሰብ እና ነገሮችን የመረዳት የአዕምሮ አቅም (አይ ኪው) 163ኛ ደረጃ ላይ ያደረገው ይሄ መረጃ በርካታ አመታትን እንዳስቆጠረም ሀሰተኛ ዜናዎችን በሚከታተሉና ይፋ በሚያደርጉ ገጾች ቢገለፅም አነጋጋሪነቱና አወዛጋቢነቱ ቀጥሏል። ለመሆኑ በርግጥ የአእምሮ ምጥቀት ምንድን ነው? የአእምሮ ምጥቀትዎ ምን ያህል ነው? 120? 91? ደግሞስ ምን ማለት ነው? የአንድን ሰው የአእምሮ ምጥቀት መፈተሽ እና መናገር ይቻላል? ፈተናውንስ የሚያስቀምጠው ማን ነው? ውጤቱስ የሚያመጣው ለውጥ ምንድን ነው? በዚህ ጽሑፍ የአእምሮ ምጥቀት የምንለው IQ የሚለውን በአቻነት ወክሎ ቆሞ ነው። አንድ ማህበረሰብ ወይም እንደ አገር በአምዕምሮ ምጡቅ ነው ሲባል ምን ማለት ነው? የምጥቀት መለኪያም መስፈርቶችም ዘመናትን ቢሻገሩም አወዛጋቢነታቸው እንደቀጠለ ነው። የእነዚህን መስፈርቶችም ሆነ የማህበረሰቡን ሳይንስ ጥናቶች የሚያካሂዱት ምዕራባውያን ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ የአፍሪካ፣ የእስያ ባህልና ማንነት ያላገናዘበ ነው በሚልም ይተቻል። ምዕራባውያንን ያማከለ ከመሆኑ አንፃር በአንዳንድ አገራት ምጡቅ የሚባሉ እሳቤዎችንም አላካተተም ይባላል። ለመጀመሪያ ጊዜ ስለዚህ ጉዳይ የተሰማው ከአልፍሬድ ቢኔት ነው። ፈረንሳዊው አልፍሬድ በመንግሥት ፈተና እንዲያዘጋጅ ታዝዞ ነበር። ትእዛዙ ተማሪዎች በትምህርታቸው ላይ ድጋፍ ይፈልጉ እንደሆን ለማወቅ ያለመ ነው። በኋላ ላይ አይ ኪው (Intelligence Quotient) ተብሎ ተጠራ። መጀመሪያ ላይ የሆነ ችሎታን ለመመዘን የተዘጋጁ ፈተናዎች ነበሩ። ስለዚህ ቢኔት የመጀመሪያው የአእምሮ ምጥቀት (IQ) ምዘና መስራች ሲሆን ዛሬ ወዳለን የአይኪው ግንዛቤም አምርቷል። በዚህ ዘመን የአእምሮ ምጥቀት ስንል አንድ ግለሰብ ያለው አጠቃላይ የአእምሮ ምጥቀት ተመዝኖ ከ 1 እስከ 100 ድረስ ተሰፍሮ ሲለካ ማለታችን ነው። ከፈረንሳዊው ቢኔት በመቀጠል ደግሞ አትላንቲክን አቋርጦ በአሜሪካዊው የሥነልቦና ምሁር ሃሳቡ ጎልብቶ አይ ኪው ማለት ተፈጥሯዊ ነው፤ አብሮን ይወለዳል እንጂ የምንለውጠው ነገር የለም ወደሚል እሳቤ አደገ። ይኸው ምሁር የተለያዩ ኅብረተሰብ ቡድኖች፥ ብሔሮች ብሔረሰቦች የተለያየ የአእምሮ ምጥቀት አላቸው ሲል አስረዳ። እኤአ በ1995 ወደ አሜሪካ ለመምጣት ሙከራ የሚያደርጉ ስደተኞች የአእምሮ ምጥቀት ፈተና ይሰጣቸው ነበር። በሮም ግዛት ዙሪያ ተሰባስበው የነበሩት እነዚህ አይሁዳውያን በአእምሮ ምጥቀት ፈተናው ዝቅተኛ ውጤት ያስመዘግቡ ስለነበር የአሜሪካን መሬት እንዳይረግጡ ተደርገው ቆይተዋል። ከስዊድን፣ ኖርዌይ፣ ዴንማርክ፣ፊንላንድ እና አይስላንድ የሚመጡ ዜጎች ደግሞ ይህንን ፈተና ከፍተኛ ውጤት ስለሚያስመዘግቡ ወደ አሜሪካ እንዲገቡ ይደረግ ነበር። ይህ ቀድሞ በአሜሪካ ይደረግ የነበረው የአእምሮ ምጥቀት ፈተና ውድቅ ተደርጓል። አመክንዮአዊ ክርክር ከማይታጣበት ማኅበረሰብ የመጣ ግለሰብ፣ እንዲያነብ ከሚበረታታ፣ ውይይትን ከሚያበረታታ ማኅበረሰብ የተገኘ ግለሰብ በአመዛኙ ከፍተኛ የአእምሮ ምጥቀት ይኖረዋል በሮም ግዛት ዙሪያ የተሰባሰቡት አይሁዶች በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት አካባቢ የአእምሮ ምጥቀታቸው አማካኝ ነጥብ ዝቅተኛ ነበር። ነገር ግን በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ወቅት ከአማካኝ ነጥብ ከፍተኛ ሆኖ ተገኝቷል። ለዚህ ደግሞ ምክንያት የተሻለ መማር፣ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውም በተሻለ ፊደል ቆጥረው መገኘታቸው ነው። ይህ ማለት የአእምሮ ምጥቀትን ሊለውጡ የሚችሉ ምክንያቶች አሉ ማለት ነው። የተለያዩ ቡድኖች የተለያየ የአእምሮ ምጥቀት ውጤት አላቸው ማለት ምዘናው የሚለካው የማይጨበጥ የማይዳሰስ ምጡቅነትን ማለትም ነው። ምን ማለት ነው? የአንድ ሰው የማይጨበጥ አመክኗዊነትን በአግባቡ መረዳትና ተግባራዊ ማድረግ መቻል ማለት ነው። ይህንን ደግሞ በልጅነት እድሜ ውስጥ የሚገጥሙ ነገሮች ይወስኑታል። አመክኗዊ ክርክር ከማይታጣበት ማህበረሰብ የመጣ ግለሰብ፣ እንዲያነብ ከሚበረታታ፣ ውይይትን ከሚያበረታታ ማህበረሰብ የተገኘ ግለሰብ በአመዛኙ ከፍተኛ የአእምሮ ምጥቀት ይኖረዋል። ለበርካታ ዓመታት የአእምሮ ምጥቀት ምዘና የሚውለው ለፖለቲካ አላማ ነበር። ፖለቲከኞች፣ ጾተኛም ሆኑ ዘረኛ ሃሳባቸውን ደግፎ እንዲያቆምላቸው ይጠቀሙበታል። ደግሞ የምጥቀት ምዘናው 'ሳይንሳዊ" መሆን በበርካታ መንግሥታት ያለአግባብ ጥቅም ላይ እንዲውል በሩን ሰፋ አድርጎ ከፍቶታል። በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ደግሞ ከሌሎች በተለየ የሴቶች አእምሮ ምጥቀት ምዘና ዝቅ ብሎ ታይቷል። የአእምሮ ምጥቀት ምዘናዎች፣ እንቆቅልሾችን መጨረስ፣ ተግባራትን ማከናወን ናቸው። አንድ ሰው እነዚህን እንቆቅልሾችም ሆኑ ተግባራት ለማከናወን የሚፈጅበት ጊዜ አልያም አለመቻሉ ተመዝኖ ነጥቡ ይሰጣል። ከዚህ በፊት እንዲህ አይነት ተግባራትን ለማከናወን ተጋልጦ ካልነበራቸው፣ ከዚህ በፊት ተግባሩን ካከናወነ ጋር እኩል ሊወዳደሩ አይችሉም። የአእምሮ ምጥቀት ፈተና አንደኛው የተሳሳተ ግንዛቤ ሰዎች ከብልህነት ጋር በአቻነት መውሰዳቸው ነው። ነገር ግን የአእምሮ ምጥቀት ምዘናው የማይዳሰስ አመክንዮን የሚመዝን ሲሆን የተለያዩ ዓይነት ብልህነቶችም አሉ። ለምሳሌ የማስታወስ ችሎታ፣ ሊለካ የማይችለው ጥበብም የሚገኙት በብልህነት ስር ነው። ለምሳሌ እነዚህ ነገሮች ባይለኩም እንኳ የሒሳብ፣ ሳይንስ፣ ኮምፒውተር ሳይንስ እውቀት ላይ ያገለግላሉ። እነዚህ ደግሞ የአእምሮ ምጥቀት ለመለካትም ያገለግላሉ። የአእምሮ ምጥቀትን ከብልህነት ጋር በአቻነት አድርጎ መውሰድ በበርካቶች ዘንድ ይታያል። የአእምሮ ምጥቀት ፈተናውን ቀድሞ መለማመድ ከተቻለ በተለያየ ምክንያት ሊለያይ ይችላል። ስለዚህ የአእምሮ ምጥቀትን መለማመድ ከተቻለ በየጊዜው ሊሻሻል እና ከፍ ሊል የሚችል ጉዳይ ነው ማለት ነው። ብልህነት መልከ ብዙ ነው። መልከ ብዙ የሆነ ነገር ደግሞ በአንድ ቁጥር ብቻ የሚሰፈር አይደለም። ብልህነትን ለመለካት ዝርያን የሚጠቅሱ አካላት በሺዎች የሚቆጠሩ ጂኖች መኖራቸውን ማስተዋል ይገባቸዋል። ስለዚህ ብልህነት በነጠላ ቁጥር ከሚመዘነው የአእምሮ ምጥቀት ምዘና በእጅጉ የተለየና የተወሳሰበ ነገር መሆኑን ማስታወስ ያስፈልጋል።
49288811
https://www.bbc.com/amharic/49288811
ኮንጎ፡ ሦስት ዶክተሮች የሕክምና ቡድን አባላትን በመግደል ተጠርጥረው ተያዙ
ሦስት የኮንጎ ዜግነት ያላቸው ዶክተሮች የዓለም ጤና ድርጅት የሕክምና ቡድን አባላትን በመግደል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የአገሪቷ አቃቤ ሕግ አስታወቀ።
ካሜሮናዊው ዶክተር ሪቻርድ ሞኡዞኮ በሆስፒታል ውስጥ የኢቦላ ሕመምተኛ እያከመ እያለ በተተኮሰበት ጥይት የሞተው ባለፈው ሚያዚያ ወር ላይ ነበር። በወቅቱ የዓለም ጤና ድርጅት "ሥራ ወዳዱ የሕክምና ባለሙያ ምን ጊዜም የእርሱን እርዳታ የሚፈልጉ ሰዎች ወዳሉበት ለመሄድ ዝግጁ ነበር" በማለት አሞካሽቶት ነበር። • የጥሩ አባትነት ሚስጥሮች ምንድናቸው? • በምዕራብ ሀረርጌ ዞን በተሰነዘረ ጥቃት ሰባት ሰዎች መሞታቸው ተገለፀ ጥቃቱ ስለተፈፀመበት ሰበብ የታወቀ ነገር የለም። ዶ/ር ሞኡዞኮ በዓለም ጤና ድርጅት በኮንጎ ያለውን የኢቦላ ወረርሽኝ ለመግታት ከተመደቡ የሕክምና ባለሙያዎች አንዱ ነበር። አብረውት የሰሩ የማዳጋስካር፣ ካሜሮንና የኮንጎ ዜግነት ያላቸው የሕክምና ባለሙያዎች በሥራው ታታሪ እንደነበረና በመቶዎች የሚቆጠሩ የጤና ባለሙያዎችንና ዶክተሮችን ማሰልጠኑን ተናግረዋል። ባለፈው ዓመት ብቻ 1ሺህ 800 ሰዎች በኢቦላ ተይዘው የሞቱ ሲሆን የበሽታውን ሥርጭት ለመግታት የሚደረገውን ጥረት የታጠቁ አማፂያንና የውጪ የሕክምና ድጋፍ ላይ ያለው ጥርጣሬ እያደናቀፈው ይገኛል። ከፍተኛ የመከላከያ ኃይሉ አቃቤ ሕግ የሆኑት ሌተናል ኮሎኔል ዤን ባፕቲስቴ ኩምቡ፣ ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል እንደተናገሩት የታጠቁ አማፂያን የቡቴምቦ ሆስፒታልን ጨምሮ የሕክምና ተቋማትን በማጥቃቱ ውስጥ የተሳተፉት ላይ እየተደረገ ባለው ምርመራ አራት ዶክተሮች ከጥቃቱ ጀርባ መሆናቸው ተደርሶበታል ብለዋል። ሦስቱ ኮንጓዊ ዶክተሮች በ"ሽብር" እና "ወንጀልን በማቀነባበር" ይከሰሳሉ መባሉን የፈረንሳዩ የዜና ወኪል ዘግቧል። አራተኛው ዶክተር ግን ገና በቁጥጥር ሥር አለመዋሉንና በፍለጋ ላይ መሆናቸው ተገልጧል። • ለዓመታት የተጠፋፉት የወላይታ ሶዶዋ እናትና የኖርዝ ኬሮላይናዋ ልጃቸው በአሁን ሰዓት በምስራቃዊ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ የጀመረው ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ላይ ሲሆን በሽታው ለመጀመሪያ ጊዜ በሃገሪቱ ውስጥ ከተገኘበት ከአውሮፓዊያኑ 1976 ወዲህ ይህ በስፋቱ 10ኛ ደረጃን ይዟል። ከዚህ በፊት በምዕራብ አፍሪካ ከአውሮፓዊያኑ 2014-16 ድረስ ተከስቶ በነበረው የኢቦላ ወረርሽኝ 28ሺህ 616 ሰዎች የተያዙ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 11ሺህ 310 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። አብዛኞቹ የኢቦላ ወረርሽን ተጠቂዎች የጊኒ፣ ላይቤሪያ፣ ሴራሊዮን ሃገራት ዜጎች ነበሩ።
news-48458080
https://www.bbc.com/amharic/news-48458080
ፊቼ ጨምበላላ፦ የሲዳማ ሕዝብ አዲስ ዓመት
ገንዘብ ያበደረ እንዲመለስለት የማይጠይቅበት፣ ከብት የማይታረድበት፣ ዛፍ የማይቆረጥበት፣ ያጠፉ ይቅር የሚባሉበት ዕለት ነው- ጨምበላላ።
የፌቼ ጨምበላላ በዓል የሲዳማ ሕዝብ የጨረቃና ከዋክብትን አቀማመጥ በማጥናት አዲስ ዓመት ያከብራል። በዓሉም ፊቼ ጨምበላላ ይባላል። ይህ በዓል መከበር ከጀመረ ከ1800 ዓመታት በላይ ማስቆጠሩን የአገር ሽማግሌዎች ይናገራሉ። • ሜድ ኢን ቻይና- የሀገር ባህል አልባሳቶቻችን የባህል አጥኚው አቶ ብርሃኑ ሃንካራ ደግሞ ''የፊቼ ጨምበላላ በዓል የሲዳማ ሕዝብ ማንነቱን ከተረዳበት ጊዜ አንስቶ ሲከበር የቆየ ነው'' ይላሉ። የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ተቋም (ዩኔስኮ) በቅርስነት የመዘገበው ይህ በዓል ዛሬ መከበር ጀምሯል። ፊቼ ጨምበላላ በዓል የሚከበርበት ቋሚ ቀን የለውም። በአያንቱዎች ጥቆማ መሰረት በዓሉ የሚከበርበት ቀን ይቆረጣል። ከዚያም ለበዓሉ ሰፊ ዝግጅት ማድረግ ይጀመራል። ከዋዜማው አንስቶ በዓሉ መከበር ይጀምራል። ጎረቤት ተሰብስቦም ከእንሰት የሚዘጋጀውን ቦርሻሜ ተብሎ የሚጠራውን ምግብ በወተት ይመገባሉ። ያገቡ ሴቶች ልዩ የሆነ የጸጉር አሰራር አላቸው ለበዓሉ ከሚበሉ ባህላዊ ምግቦችና ከሚከናወኑ ጭፈራዎች በተጨማሪ የተለያዩ ባህላዊ ሁነቶችም ይካሄዳሉ። ቄጠላ፣ ኛፋሮና የመሳሰሉ ሙዚቃዎችም በበዓሉ ይከወናሉ። • ጤፏን ለማስመለስ እየተውተረተረች ያለችው ኢትዮጵያ ቄጠላ በተባለው ባህላዊ ሙዚቃ፤ አገር፣ ዘመን፣ የአገር ሽማግሌዎችና ታዋቂ ግለሰቦች እየተወደሱ ይጨፈራል። ቄጠላ የተሰኘው ባህላዊ ጭፈራ በቡድን ሲያዜሙ ''የፊቼ ጨምበላላ ዋነኛ ትርጉም ሰላም ነው'' የሚሉት አቶ ብርሃኑ ሃንካራ፤ አንድነትና ፍቅር የበዓሉ መለያ መሆናቸውን ይናገራሉ። የተጣሉ ሰዎች በፊቼ ጨምበላላ በዓል ላይ ይታረቃሉ። ሃዘን ላይ የነበሩ ሰዎችም የሃዘን ልብሳቸውን ይቀይራሉ። • ወንዶች አዞ ለመምሰል ቆዳቸውን የሚበሱባት ሃገር ፊቼ ጨምበላላ ዘንድሮ ያገባች ሴት ሙሽርነቷን ጨርሳ ከሌሎች ሴቶች ጋር የምትቀላቀልበት በዓል ነው። በተለያዩ ምክንያቶች ከቀዬው ርቆ የነበረ ሰው ለፊቼ ጨምበላላ ወደቀዬው ይመለሳል። በበዓሉ ወቅት ለአካባቢ እና ለእንስሳት ትልቅ ትኩረት ይሰጣል ለዚህ በዓል ተብሎ እርድ አይፈጸምም፤ ስጋም አይበላም። ክብቶችን መምታትም ክልክል ነው። ላሞች ሳር የበዛበት መስክ ላይ ይሰማራሉ። በሲዳማ ሕዝብ ዘንድ በፊቼ ጨምበላላ በዓል ወቅት ማረስ ነውር ነው። ለዚህም ምክንያቱ ደግሞ የፊቼ ጨምበላላ በዓል የሲዳማ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮም ነው ተብሎ ስለሚታመን ነው።ፊቼ የአዲስ ዓመት በዓል ዋዜማ ሲሆን፤ ጨምበላላ ደግሞ የአዲስ ዓመት መጀመሪያው ቀን ነው። የእድሜ ባለጸጎች ሁሉቃ ሲሠሩ ሲዳማ ከአንድ ዓመት ወደሌላው የሚሸጋገርበት ሂደት ሁሉቃ ይባላል። ሁሉቃ ማለት ከሸምበቆና ከአርጥብ ቅጠል ተሠርቶ የሚቆም ነገር ነው። • የኦነግ ጦር መሪ በትግላችን እንቀጥላለን አለ ሁሉቃ በቤተሰብና በማኅበረሰብ ደረጃ የሚሠራ ሲሆን፤ አዲስ ዓመት ሲገባ ሰዎችና ከብቶች ይተላለፉበታል። የሲዳማ ሕዝብ አዲስ ዓመትን ሲቀበሉ፤ ዓመቱ የብልጽግና እንዲሆንላቸው 'ፊቼ ጄጂ' ይላሉ።
news-55581635
https://www.bbc.com/amharic/news-55581635
የቻይናው ሚኒስትር ጭምብል ባለማድረጋቸው በታንዛኒያው ፕሬዝዳንት ተመሰገኑ
የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ ለጉብኝት ወደ አገራቸው የመጡት የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ባለማድረጋቸው ምሰጋና አቀረቡ።
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፕሬዝዳንቱ ይህ አጋጣሚም በአገራቸው የኮሮናቫይረስ አለመኖሩን የሚያረጋግጥ ማሳያ እንደሆነም ተናግረዋል። "ሚኒስተር ዋንግ ታንዛኒያ ውስጥ ኮሮናቫይረስ እንደሌለ አውቀው ጭምብል ባለማድረጋቸው ላመሰግናቸው እወዳለሁ። በጣም አመሰግናለሁ" ብለዋል ፕሬዝዳንቱ። ማጉፉሊ ካቀረቡት ምስጋና በተጨማሪም "ይህንንም ለማረጋገጥ አንድ ላይ ምግብ ለመመገብ በምንሄድበት ጊዜ በመጨባበጥ ይህንን አረጋግጣለሁ" ሲሉም ተናግረዋል። በእርግጥም የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ አብረዋቸው ወደ ታንዛኒያ ከተጓዙት የቡድናቸው አባላት በተለየ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ባለማድረግ ለየት ብለው ታይተዋል። የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሉ በዓለም የጤና ድርጅት የኮሮናቫይረስ መስፋፋትን ለመግታት ያግዛሉ ብሎ ተግባራዊ እንዲሆኑ ካዘዛቸው መመሪያዎች መካከል አካላዊ ርቀትን መጠበቅን የመሳሰሉ እርምጃዎችን በማጣጣልና በአገሪቱ ያለውን የወረርሽኝ ሁኔታን በተመለከተ በሰጡት ዝቅ ያለ ትኩረት ሳቢያ ጠንካራ ትችት ሲሰነዘርባቸው ቆይቷል። ታንዛኒያ ከሌሎቹ የአፍሪካ አገራት በተለየ በአገሯ ስላለው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዙሪያ መረጃ ማውጣት ካቆመች ረጅም ጊዜ ሆኗታል። በዚህም በታንዛኒያ በበሽታው የሞቱና የተያዙ ሰዎች አሃዝ በትክክል አይታወቅም። የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታንዛኒያን ጨምሮ በናይጄሪያ፣ በዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ በቦትስዋናና በሲሸልስ የአምስት ቀናት ጉብኝት ለመድረግ ነው ወደ አፍሪካ የመጡት። በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት መጀመሪያ ላይ ከአፍሪካ አገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯን የላከችው ቻይና "የሕክምና ባለሙያዎችን እንደምትልክ" ከውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቷ የወጣው መረጃ አመልክቷል። በተጨማሪም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሰበብ የተጓተቱ የግንባታ ሥራዎችን በማፋጠን ለማጠናቀቅ ጥረት እንደሚደረግ ተገልጿል። የሚኒስትሩ ጉብኝት የአፍሪካ ጉብኝት በቻይናና በአህጉሪቱ ሕዝቦች መካከል መቀራረብን በመፍጠር የጋራ የወደፊት ግብን መፍጠር መሆኑም ተገልጿል።
news-54970744
https://www.bbc.com/amharic/news-54970744
ትግራይ፡ ኬንያ የኢትዮጵያ መንግሥት ለተፈጠረው ችግር ሰላማዊ መፍትሄን እንዲሻ ጠየቀች
በምሥራቅ አፍሪካ አገራት ጉብኝት እያደረጉ ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የኬንያ ዋና መዲና ናይሮቢ የገቡት ትናንት ነበር።
የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከአቶ ደመቀ ጋር በነበራቸው ውይይት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረው ችግር በሰላም የሚፈታበት መላ እንዲበጅ ሐሳብ ማንሳታቸውን የፕሬዝዳንቱ ጽሕፈት ቤት ገልጧል። ኡሁሩ ህወሓት ሁኔታዎችን እንዲያረግብም ጥሪ ማቅረባቸውም ተነግሯል፡፡ "ይህ ጦርነት ኢትዮጵያ በአካባቢው የነበራት የኢኮኖሚ እምርታ የሚሸረሽር ነው" ብለዋል ፕሬዝዳንቱ። አቶ ደመቀ መኮንን ሰኞ ኬንያ ከመግባታቸው ቀደም ብሎ ከዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ጋር በተለያዩ አገራዊና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ስለመወያየታቸውን ዘገባዎች መውጣታቸው ይታወሳል። የ Twitter ይዘት መጨረሻ, 1 ፕሬዝደንት ሙሴቬኒ በህወሓትና በመንግሥት መካከል ድርድር ለማድረግ እየሞከሩ ነው የሚሉ ዜናዎች መውጣታቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት ይህ ዘገባ ሐሰት ነው ሲል ማስተባበሉ አይዘነጋም። ሙሴቬኒ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ያደረጉት ውይይት "ኢትዮጵያ ውስጥ እየተስተዋለ ካለው የሰላምና የፀጥታ ጉዳይ" ጋር የተገናኘ እንደሆነ በገጻቸው አስፍረው ነበር። ሙሴቬኒ አክለውም "እኔ ብሔር ላይ የተመሠረተ ፌዴራሊዝምን አልደግፍም። ትኩረት መስጠት ያለብን ለአንድነትና ለተመሳሳይ ፍላጎት ነው። ይህ ብቸኛው የምንበለጽግበት መንገድ ነው" ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ማስታወሻ አስፍረዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የናይጄሪያው የቀድሞ ፕሬዝዳንት ኦባሳንጆ በመንግሥትና በህወሓት መካከል ድርድር ለማስጀመር ወደ አዲስ አበባ እያቀኑ ነው ሲል ኤኤፍፒ የዜና ወኪል የዘገበው ትናንት ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥት በኦባሳንጆ ወደ አዲስ አበባ ማቅናት ጉዳይ ላይ የሰጠው አስተያየት የለም። ሆኖም የኢትዮጵያ መንግሥት ለችግሩ ሠላማዊ መፍትሄ እንዲሻ ዓለም አቀፍ ጥያቄዎች እየበረከቱ መምጣታቸውን ከቅርብ ቀናት ወዲህ የሚወጡ ዘገባዎች ያሳያሉ። በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የነበረውን ችግር በመቀረፍ ሠላም እንዲወርድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ላደረጉት ጥረት ባለፈው ዓመት ሽልማልት ያበረከተላቸው የኖቤል ኮሚቴ በትግራይ ውስጥ የተከሰተው ግጭት እንዳሳሰበውና ሠላም እንዲወርድ ጠየቁን ሮይተርስ ዘግቧል። የኢትዮጵያ መንግሥት እስካሁን የሚቀርቡለትን የድርድር ጥያቄዎች ውድቅ እያደረገ ያለው "ሕግ የማስከበር ውስጣዊ የመንግሥት ተግባር ላይ ነኝ" በሚል ነው። ይህ በእንዲህ እያለ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የተላከ መልዕክት ለጅቡቲው ፕሬዝዳንት ኡመር ጊሌ ማድረሳቸውን የአገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘግበዋል። መንግሥት ሕግን የማስከበር ዘመቻ ባለው በዚህ መጠነ ሰፊ ወታደራዊ እርምጃ ሂደት ዙርያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሕወሓት ኃይሎች እጃቸውን እንዲሰጡ መንግሥት ያስቀመጠው የሦስት ቀናት የጊዜ ገደብ መጠናቀቁን ዛሬ ማለዳ በፌስቡክ ገጻቸው አስፍረዋል። ፌደራል መንግሥቱ ትግራይ ውሰጥ ባለው ሠራዊቱ ላይ በክልሉ ኃይሎች ጥቃት መሰንዘሩን ገልጾ ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄድ ከጀመረ እነሆ ሁለት ሳምንት ሊሞላው ነው።
news-47607898
https://www.bbc.com/amharic/news-47607898
ስለምንጓዝበት የአውሮፕላን አይነት እንዴት ማወቅ እንችላለን?
ባለፈው ዕሁድ ጉዞውን በጀመረ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ተከስክሶ ከ150 በላይ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብርት የሆነው አውሮፕላን አደጋ መንስዔው እየተጣራ ቢሆንም በበርካታ ሃገራት ከአገልግሎት ውጪ እንዲሆን ተደርጓል።
በጥቅምት ወር የቦይንግ ሥሪት የሆነ አንድ አይነት ስያሜ ያለው ሌላ አውሮፕላን በተመሳሳይ ሁኔታ ተከስክሶ በርካቶችን ለህልፈት መዳረጉ ሲታወስ የአውሮፕላኑን አስተማማኝነት ጥያቄ ውስጥ ጥሎታል። • ስለ አደጋው እስካሁን የምናውቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት የሚባለው ዘመናዊ አውሮፕላን ካላቸው የዘርፉ ቀዳሚ ተቋማት መካከል አንዱ ሲሆን ከአደጋው በኋላ ይህ አውሮፕላን ከአገልግሎት ውጪ ሆኖ እንዲቆይ ከወሰኑት መካከልም ቀዳሚው ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድን ውሳኔ በመከተልም የቦይንግ አውሮፕላኖች አምራች የሆነችው አሜሪካንን ጨምሮ ከ50 በላይ ሃገራት ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት አውሮፕላን ከበረራ ውጪ እንዲሆን ወስነዋል። ይህም ከአውሮፕላኑ አደጋ ጋር በተያያዘ የሚደረገው ምርመራ እስኪጠናቀቅና ለሁለቱ አደጋዎች ምክንያት ናቸው የተባሉ ነገሮች ተለይተው በአስተማማኝ ሁኔታ መፍትሄ እስኪሰጣቸው ድረስ እንደሆነ የአየር ትራንስፖርት ባለሙያዎች ይናገራሉ። • ኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬም ስኬታማ ነው የተለያዩ ሃገራትና የበረራ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች ግን አሁንም ይህንን ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት አውሮፕላንን እየተጠቀሙበት ይገኛሉ። በዚህ ወቅትም የቦይንግ 737 ማክስ ኤይት የበረራ ደህንነት ሁኔታ አስተማማኝ ስላልሆነ በርካታ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚዎች በዚህ አውሮፕላን ከመጓዝ ተቆጥበዋል። እኛስ ቦይንግ 737 ማክስ ኤይትን ብቻ ሳይሆን በምን አይነት አውሮፕላኖች እንደምንጓዝ ለማወቅ ብንፈልግ ከመሳፈራችን በፊት እንዴት መለየት እንችላለን? ማድረግ ያለብን የምንጓዝበት የአውሮፕላን አይነትን ትኬት ስንቆርጥ ወይም ወንበር ስንመርጥ በቀላሉ ማወቅ እንችላለን። ካልሆነም የበረራ ቁጥሩን ኢንተርኔት ላይ በማስገባትም መለየት ይቻላል። በተጨማሪም የአውሮፕላኑን አይነት ለማወቅ የሚረዱ (FlightStats.com, SeatGuru.com, Expertflyer.com, FlightAware, Flightview.com) የመሳሰሉ የተለያዩ ድረ-ገፆችን በመጠቀም መለየት ይቻላል። እነዚህን መንገዶች ተጠቅመን ስለምንጓዝበት አውሮፕላን የምንፈልገውን መረጃ ማግኘት ካልቻልን፤ ወደ አገልግሎት ሰጪው አየር መንገድ በመደወል የምንፈልገውን መረጃ መጠየቅ እንችላለን። • ለ60 ዓመታት የዘለቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድና የቦይንግ ግንኙነት ነገር ግን በመጀመሪያ ላይ ስለምንጓዝበት አውሮፕላን የምናገኘው መረጃ በመጨረሻ ደቂቃ ላይ በቴክኒክ ምክንያት ሊቀየር እንደሚችልም መዘንጋት የለብንም። ምናልባት የሚጓዙበት አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት አውሮፕላንን በአሁኑ ወቅት እየተጠቀመ ከሆነና በዚሁ አውሮፕላን የመጓዝ ተራው የእርስዎ ቢሆን ምን ያደርጋሉ? የጉዞ ዕቅድዎን ይሰርዛሉ ወይስ ትኬትዎን ይቀይራሉ? የአየር ጉዞ አማካሪ የሆነው ሄንሪክ ዚልመር እንደሚለው "ተጓዦች ጉዟቸውን መሰረዝ ይችላሉ፤ ነገር ግን ውሳኔው ከእራሳቸው በኩል የሚመጣ በመሆኑ ገንዘባቸው እንዲመለስ መጠየቅ አይችሉም" ይላል። • "የሞተው የኔ ያሬድ ነው ብዬ አላሰብኩም" የካፕቴን ያሬድ የ11 አመት ጓደኛ ስለዚህ በአሁኑ ወቅት ያለው ዋነኛው አማራጭ ለደህንነት አስጊ የሆኑ አውሮፕላኖችን ከአገልግሎት ውጪ ያደረጉትን አየር መንገዶችን መጠቀም እንደሆነ የአየር ትራንስፖርት ባለሙያዎች ይመክራሉ።
news-50818733
https://www.bbc.com/amharic/news-50818733
እነ አፕል ጉግልና ማይክሮሶፍት በ14 የኮንጎ ቤተሰቦች ክስ ተመሰረተባቸው
አፕል፣ ጎግል፣ ቴስላ፣ ማይክሮሶፍት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሕጻናት የማዕድን አውጪዎች መሞታቸውን ተከትሎ በተከፈተው ክስ ላይ ስማቸው ተጠቅሷል።
ክሱ የተከፈተው 14 ኮንጓዊ ቤተሰቦችን በመወከል በዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋቾች በኩል ነው። ክሱ እንደሚያሳየው ድርጅቶቹ ለምርታቸው የሚጠቀሙበት ኮባልት ከህጻናት ጉልበት ብዝበዛ ጋር እንደሚያያዝ ያውቃሉ ሲል ያትታል። ዲሞክራቲክ ኮንጎ ዓለማችን ከሚያስፈልጋት የኮባልት ምርት 60 በመቶውን ታመርታለች። • ከኮርኔል በኮምፒውተር ሳይንስ ፒኤችዲ በማግኘት የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት የሆነችው ረድኤት አበበ ማዕድኑ የኤሌትሪክ መኪናዎችን፣ ላፕቶፖችንና ስማርት ስልኮችን ለማንቀሳቀስ የሚያገለግለውን ሊቲየም አየን ባትሪ ለማምረት ይውላል። ይኹን እንጂ ምርቱ ከሕገ ወጥ የማዕድን ማውጣት ጋር እንዲሁም ከሰብዓዊ መብት ጥሰትና ከሙስና ጋር ስሙ ተደጋግሞ ይነሳል። በአሜሪካ የተከፈተው ክስ እንደሚያስረዳው እነዚህ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎቹ የሚጠቀሙት የኮባልት ማዕድን ከሕጻናት ጉልበት ብዝበዛ ጋር ተያያዞ የተገኘ እንደሆነ "ተገቢ እውቀት" አላቸው ሲል ያትታል። አክሎም የምርት አቅርቦት ሰንሰለቱን በመቆጣጠር ረገድ ቸልተኝነት ታይቶባቸዋል፤ ይልቁንም ከዚህ የጉልበት ብዝበዛ ትርፍን አጋብሰዋል ሲል አስፍሯል። በክሱ ላይ ከተጠቀሱት ድርጅቶች መካከል የኮምፒውተር አምራቹ ዴልና 14ቱ ቤተሰቦች ልጆቻችን ሰርተውበታል ያሉትን የማዕድን ማውጫ በበላይነት የሚያስተዳድሩት የማዕድን አምራች ድርጅቶቹ ዚህጃንግ ሁአዮና ግሌንኮር ይገኙበታል። • "ማርታ፣ ለምን ለምን ሞተች?" ግሌንኮር በዩናይትድ ኪንግደም ለሚታተመው ቴሌግራፍ ጋዜጣ በሰጠው ምላሽ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን ተግባር እንዳልፈፀመ ገልጿል። ዲሞክራቲክ ኮንጎ ዓለማችን ከሚያስፈልጋት የኮባልት ምርት 60 በመቶውን ታመርታለች ቢቢሲ ከዚህጃንግ ሁአዮ ምላሽ ለማግኘት ጠይቋል። በዩኬ የሚታተመው ጋርዲያን ጋዜጣ ባስነበበው የክስ ዘገባው ላይ፣ ሕጻናት ማዕድን ቆፋሪዎች የሚሰሩበት ጉድጓድ ተደርምሶ ከነሕይወታቸው ተቀብረዋል፣ በመደርመሱ በደረሰባቸው ጉዳትም ዘላቂ የጤና ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጿል። • ከብራና ወደ ኮምፒውተር . . . 14ቱ ቤተሰቦች ኩባንያዎቹ ላደረሱባቸው የስነልቦናና የአካል ጉዳት ካሳ እንዲከፈሏቸው ይፈልጋሉ። ማይክሮሶፍት ለቴሌግራፍ በሰጠው ምላሽ ከማዕድን ማውጣት ጋር ተያይዞ የተፈጠረ ሕገወጥነትን እንደሚያጣራ አስታውቋል። ቢቢሲ ከጎግል፣ አፕል፣ ዴልና ቴስላ ምላሽ ለማግኘት ጠይቋል።
news-51527972
https://www.bbc.com/amharic/news-51527972
ኮሮናቫይረስ፡ ካሜሮናዊው ተማሪ በቻይና
የ 21 ዓመቱ ካሜሮናዊ ኬም ሴኑ ፓቬል በቻይናዋ ጂንግዙ ግዛት ተማሪ ሲሆን በኮሮናቫይረስ መያዙን ካወቀ በኋላ "ተሽሎሃል ወደ አገርህ ተመለስ እንኳን ቢሉኝ አልመለስም" ብሏል። ምክንያቱ ደግሞ ቫይረሱን ወደ አፍሪካ ይዞ ላለመግባት ነው።
'' ምንም ነገር ቢፈጠር ይህን በሽታ ወደ አፍሪካ ይዤ መመለስ አልፈልግም'' ያለው በዩኒቨርሲቲ ዶርምተሪ ውስጥ የ 14 ቀናት ክትትል በሚደረግለት ወቅት ነው። በመጀመሪያ ከባድ ትኩሳትና ደረቅ ሳል አጣድፎት ነበር፤ በመቀጠል ግን ፈሳሽ ከአፍንጫው መውጣት ጀመረ። ምልክቶቹን ካስተዋለ በኋላ በልጅነት ታሰቃየው የነበረችው ወባው እንደተነሳችበት አስቦም ነበር። ነገር ግን ያላሰበውና ዓለምን እያስጨነቀ የሚገኘው ኮሮናቫይረስ ሆኖ ተገኘ። • የኮሮናቫይረስ ስጋት ባጠላበት በርካቶች በአንዴ ተሞሽረሩ • የኮሮናቫይረስ ተጽዕኖ በቻይናና በዓለም ምጣኔ ሃብት ላይ '' ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሆስፒታል ስሄድ የምሞትበት ሰአት እንደተቃረበ አስብ ነበር። በቃ መሞቴ ነው እያልኩ ለራሴ ነግሬው ነበር'' ብሏል። ኬም ሴኑ ፓቬል አሁን በለይቶ ማቆያ ውስጥ 13ኛ ቀኑን ይዟል፤ በአንድ የቻይና ሆስፒታል ውስጥ። ህክምናው በተለይም የኤችአይቪ ታማሚዎችን ለማከም ጥቅም ላይ የሚውሉ መድሃኒቶችን በብዛት ይጠቀማል። ከሁለት ሳምንታት ተከታታይ ህክምና በኋላ እየተሻለው መጥቷል። በሲቲ ስካን በተደረገለት ምርመራም ቫይረሱ ከሰውነቱ እንደጠፋ ምልክቶች ታይተዋል። ፓቬል በገዳዩ ኮሮናቫይረስ የተያዘ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሲሆን ሙሉ የህክምናው ሙሉ ወጪ በቻይናዋ ግዛት ተሸፍኗል። '' ትምህርቴን ሳልጨርስ ወደ አገር ቤት መመለስ አልፈልግም። ወደ ካሜሩን የምምለስበት ምንም ምክንያት የለኝም፤ ሙሉ የሆስፒታል ወጪዬ በቻይና መንግስት ተሸፍኖልኛል''ብሏል። በሺዎች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ተማሪዎች፣ ሰራተኞችና ቤተሰቦች እስካሁንም ድረስ በቻይናዋ ሁቤ ግዛት እንቅስቃሴያቸው ተገድቦ የሚገኙ ሲሆን አብዛኛዎቹ ከቻይና አስወጡን የሚል ጩኸት እያሰሙ ነው። ዛምቢያዊቷ ሲልያኒ ሳሊማም ከነዚህ መካካል አንዷ ናት። እሷ እንደምትለው የአገሯ መንግሥት ምንም እያደረገ አይደለም። '' እኛ አፍሪካውያን ተለይተን ቀርተናል፤ እኛ ዜጎች አይደለንም እንዴ?'' ብላለች። ሲልያኒ ቫይረሱ እንዳይዛመት በመስጋት ለወራት እራሷን ከሰዎች ለይታ ቆይታለች። ቀኑን ሙሉ በመተኛትና ስለቫይረሱ አዲስ ነገር ካለ በማለት ዜና ስትከታተል ታሳልፋለች። የምግብና አንዳንድ አስፈላጊ ነገሮችም እጥረት እንዳያጋጥማት ከፍተኛ ስጋት አለባት። 80 ሺ የሚሆኑ አፍሪካውያን ተማሪዎች በተለያዩ የትምህርት ዕድሎች አማካይነት ቻይና ውስጥ ይገኛሉ። እርምጃ ለመውሰድ ከተንቀሳቀሱ የአፍሪካ መንግሥታት መካከል የአይቮሪ ኮስት መንግሥት አንዱ ሲሆን ከሳምንታት ውይይት በኋላ በዉሃን ለሚገኙ 77 ተማሪዎች 490 ዶላር ለመስጠት ተስማምቷል። በገንዘቡም የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች ገዝተው እንቅስቃሴያቸውን እንዲገድቡ አስጠንቅቋል። የጋና መንግሥት ለተማሪዎቹ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል። • በዉሃን ከሚገኙ ኢትዮጵያውን ተማሪዎች 95 በመቶ መመለስ ይፈልጋሉ • አፍሪካ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል አቅሙ አላት? በዉሃን ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎችም 95 በመቶ የሚሆኑት ወደ አገራቸው መመለስ እንደሚፈልጉ በበተነው መጠይቅ ማረጋገጡን በዉሃን የኢትዮጵያ ተማሪዎች ህብረት ለቢቢሲ ገልጾ ነበር። የህብረቱ ፕሬዝደንት ዘሃራ አብዱልሃዲ እንደገለፀችው በመጠይቁ ከተሳተፉ ተማሪዎች መካከል 41 በመቶ የሚሆኑት መንግሥት ወጪያችንን ሸፍኖ ወደ አገራችን ይመልሰን ያሉ ሲሆን፤ 54 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ በራሳችንም ወጪ እንመለሳለን መንግሥት ግን ጉዟችንን ያመቻችልን ሲሉ ፍላጎታቸውን አስታውቀዋል። ቀደም ሲል የተማሪዎቹን 'ወደ ኢትዮጵያ መልሱን' ጥያቄን ህብረቱ በቻይና ለኢትዮጵያ ኤምባሲ እንዳቀረበ የምታስታውሰው ዘሃራ፤ አሁንም የተማሪው ጥያቄ እጅግ እየገፋ በመምጣቱ መጠይቅ በትነው የተማሪውን ወደ አገራችን መልሱን ጥያቄ በጥናት ማረጋገጣቸውን ታስረዳለች። ዘሃራ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች፤ እንዲሁም የሟቾችም ቁጥር እየጨመረ መሆኑን በመጥቀስ "ተማሪው ከባድ የስነልቦና ጫና ውስጥ ነው ያለው" ብላለች። በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጥያቄ በቀረበለት ወቅት 'የተማሪዎቹን ጥያቄ ለመመለስ ሁኔታዎችን እያጤንን ነው' የሚል ምላሽ ለቢቢሲ ሰጥቶም ነበር። በሁኔታዎች መባባስ ምክንያት ስጋት የገባቸው በርካታ ተማሪዎች ወደ ሀገራችን መልሱን እያሉ ቢሆንም ኬም ሴኑ ፓቬል ግን ወደ ሀገሬ የቫይረሱን ስጋት ይዤ መግባት አልፈልግም ይላል።
news-45329901
https://www.bbc.com/amharic/news-45329901
የደሞዙን 100 እጥፍ በስህተት የተከፈለው ሰው ''ይቅርብኝ'' አለ
በአውስትራሊያ የሚገኙ አንድ የመንግስት ተቀጣሪ ሰው የገንዘብ ክፍል ሰራተኞች በሰሩት ስህተት የደሞዛቸውን 100 እጥፍ በአንድ ጊዜ አግኝተዋል።
ስህተቱ የተፈጠረው በቁጥሮቹ መካከል ነጥብ በሚገባበት ጊዜ እንደሆነም ታውቋል። ሰራተኛው ሊከፈለው ይገባ የነበረው 4921 ዶላር ከ76 ሳንቲም ሲሆን፤ በቁጥሮቹ መካከል ያለቦታዋ የገባችው ነጥብ ግን ደሞዙን ወደ 492 ሺህ 176 ዶላር ከፍ እንዲል አድርጋለች። ስህተቱ እንደተፈጠረ የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች ጉዳዩን ለአካባቢው የኦዲተር ቢሮ አሳውቀዋል። • የ15 ዓመቷ ታዳጊ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን ቀልብ እየገዛች ነው • ቶዮታ ያለአሽከርካሪ የሚንቀሳቀሱ መኪናዎችን ሊያሰማራ ነው በስራ ምክንያት ወደ ሰሜናዊ የሃገሪቱ ክፍል ራቅ ብሎ ተጉዞ የነበረው ሰው ያላሰበውና ያልገመተው ዓይነት ገንዘብ ወደ ባንክ ደብተሩ ሲገባ ትንሽ ቢደናገጥም፤ ምንም ሳያንገራግር ለመንግስት ለመመለስ ወስኗል። ይህኛው አጋጣሚ የመጀመሪያው እንዳልሆነና፤ በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ ተመሳሳይ 743 ስህተቶት እንደተሰሩ የኦዲተር ቢሮ ሃላፊው ገልጸዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘም በተመሳሳይ ክስተቶች እስካሁን 767 ሺ ዶላር ሳይመለስ እንደቀረ ጨምረዋል።
50245139
https://www.bbc.com/amharic/50245139
ባለቤቷ በቆዳ ቀለሟ የተሳለቀባት ህንዳዊት ራሷን አጠፋች
ባለቤቷ በቆዳ ቀለሟ ምክንያት አዘውትሮ ያንጓጥጣት የነበረ የ21 ዓመቷ ህንዳዊት ራሷን ማጥፋቷን ፖሊስ ገለጸ።
ራጃስታን የተባለው ግዛት ፖሊሶች እንዳሉት፤ የወጣቷ አባት ለልጃቸው ሞት ባለቤቷን ተጠያቂ አድርገዋል። ባለቤቱን በጥቁር የቆዳ ቀለሟ ምክንያት ያንጓጠጠው ግለሰብ ላይ ክስም ተመስርቷል። አባትየው ለፖሊስ እንደተናገሩት፤ ግለሰቡ በተደጋጋሚ በልጃቸው ጥቁር የቆዳ ቀለም እየተሳለቀ ያሸማቅቃት ነበር። • በወር አበባ ምክንያት መምህሯ ያንጓጠጣት ተማሪ ራሷን አጠፋች • የራሷን ፊት እንኳን ማስታወስ የማትችለው ሴት • ክፍያ ባልከፈለ ተማሪ እጅ ላይ ማህተም የመታው ትምህርት ቤት ተወገዘ ፖሊስ ለቢቢሲ ሂንዲ እንደተናገረው፤ ግለሰቡ እስካሁን በቁጥጥር ሥር አልዋለም። በርካታ ህንዳውያን ቀላ ያለ የቆዳ ቀለም ከጥቁር "የተሻለ እና የሚበልጥ" እንደሆነ ያምናሉ። ከዚህ ቀደምም ሌሎች ህንዳውያን በቆዳ ቀለማቸው ምክንያት በሚደርስባቸው መገለል ራሳቸውን አጥፍተዋል። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ2014 አንዲት የ29 ዓመት ሴት ባለቤቷ በቆዳ ቀለሟ መሳለቁን ተከትሎ ራሷን አጥፍታለች። በ2018ም የ14 ዓመት ታዳጊ በክፍል ጓደኞቿ "ጥቁር ስለሆንሽ አስቀያሚ ነሽ" በመባሏ ራሷን አጥፍታለች። ታዳጊ ሴቶች በቆዳ ቀለማቸው ምክንያት ትምህርት ቤት ውስጥ መገለል ይደርስባቸዋል። የእድሜ እኩዮቻቸው መሳለቂያም ያደርጓቸዋል። ቤተሰቦቻቸው ሳይቀር ቀላ ላሉ ልጆቻቸው ያዳላሉ። በመገናኛ ብዙሀን ሽፋን የሚሰጣቸው ታዋቂ ተዋናዮችና ሞዴሎች ነጣ ያለ የቆዳ ቀለም ያላቸው ናቸው። ጥቁር ሰዎችን አስቀያሚ አድርገው የሚስሉ ማስታወቂያዎች በሕግ የተከለከሉ ቢሆንም፤ ለቀይ ሰዎች የሚያደላው አመለካከትና ሥርዓት ሙሉ በሙሉ አልተለወጠም።
news-45279802
https://www.bbc.com/amharic/news-45279802
ደቡብ አፍሪካዊው ዘረኝነትን አስመልክቶ ባሰራጨው ተንቀሳቃሽ ምስል ከስራው ተባረረ
ደቡብ አፍሪካዊው ግለሰብ ዘረኝነትን የሚያነፀባርቅ ንግግሮችን የያዘ ተንቀሳቃሽ ምስል በስፋት መሰራጨቱን ተከትሎ ይሰራበት ከነበረው የቤተሰቦቹ የንግድ ስራ ተሰናብቷል።
የደቡብ አፍሪካ የባህል ሚንስተር ግለሰቡ የተጠቀመው ቋንቋ በህብረተሰቡ ቦታ የለውም ብለዋል ይህ አዳም ካተዛቭሎስ የተባለ ግለሰብ በውሃ ዳርቻ አካባቢ ሆኖ የቀረፀው ተንቀሳቃሽ ፊልም "ጥቁር ህዝቦች ባይኖሩ ኖሮ ገነት ምድር ላይ ነበረች" የሚል ዘረኛ መልዕክትንም አስተላልፏል። • በኢትዮጵያ የተፈናቃዮች ቁጥር ማሻቀብ የደቀነው ፈተና • ደቡብ አፍሪካ፡መውጫ አጥተው የነበሩ 955 የማእድን ቁፋሮ ሰራተኞች ወጡ እንደዚህ ያለ ደቡብ አፍሪካውያንን የሚያሳንስ የንቀት ንግግር በአፓርታይድ አገዛዝ ወቅት ነጮች ይጠቀሙበት የነበረ ቢሆንም በአውሮፓውያኑ 1994 የነጮች የበላይነት ካበቃለት በኋላ የዘረኝነት ንግግሮች በአገሪቱ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ሆኗል። በዚህም ምክንያት በቅርቡ በደቡብ አፍሪካ ዘረኛ ንግግር ያደረገች ሴት ለእስር ተዳርጋለች። • ጤፍ ሃገሩ የት ነው? ደቡብ አፍሪካ? አውስትራሊያ? . . . አዳም ካተዛቬሎስም ያሰራጨው ተንቀሳቃሽ ምስል ከባለፈው ማክሰኞ ጀምሮ በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት በመዘዋወሩ በተጠቃሚዎች ዘንድ መነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል። ከመነጋገሪያነቱም አልፎ የትዊተር ተጠቃሚዎች ቅመማ ቅመሞችንና ምግብ በማምረት የሚታወቀውን የቤተሰቡን ድርጅት "ማንም ሰው እንዳይጠቀም" የሚል ዘመቻ ጀምረዋል። ድርጊቱ ደቡብ አፍሪካውያንን አሳዝኗል፤አስቆጥቷል። አንዳንዶቹ ግን ከቁብም አልቆጠሩት፤ ምክንያቱ ደግሞ የነጮች የበላይነት እንደቀጠለ ነው ብለው በማመናቸው ነው። ይህ ደግሞ እንደ ተራና የተለመደ ነገር እንዲቆጠር እያደረገው ነው ተብሏል። መንግስት እንዲህ ዓይነት ዘረኛ ንግግሮችን ለመግታት የሚያስችል እቅድ እያወጣ ይሁን እንጂ መልዕክቱ በሚገባ ሁሉም ጋር የደረሰ አይመስልም ። "በዚህ ግለሰብ ላይ የሚጥለውን ቅጣት ማየት እንፈልጋለን። በአገሪቱ ያሉ ጥቁር ህዝቦች ትዕግስታቸውና ይቅር ባይነታቸው ከልክ እያለፈ ነው" ሲሉ የተደመጡም ነበሩ። የግለሰቡ ወንድም ኒክ ካተዛቬሎስ በበኩሉ "በሰማነው ነገር ቤተሰቡ ሁሉ ተሸማቋል፤ በማንኛውም መንገድ ዘረኛ አስተሳሰብን ማስወገድ ያስፈልጋል" ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። በዚህም ምክንያት ወዲያውኑ ከቤተሰቦቹ የንግድ ስራ እንዲባረር ሆኗል፤ ያለው ድርሻም በቅርቡ ይነጠቃል ብለዋል። የድርጅቱን ሰራተኞች ደህንነት ለመጠበቅም ሲባልም ለጊዜው ድርጅቱ መዘጋቱን አስታውቋል። የአገሪቱ የባህል ሚንስትር ናቲ ምቴትዋ እንዳሉት እንደዚህ ዓይነት የጥላቻ ንግግሮች የሚወገዙ ናቸው። "ሁላችንም ይህንን ለመታግል አብረን ልንሰራ ይገባል፤ ድርጊቱን የሚፈፅሙትን ሰዎችም ወደ ህግ ማቅረብ አለብን ብለዋል። የግለሰቡን ጉዳይ ወደ ህግ ያመራልም ተብሏል።
news-55156383
https://www.bbc.com/amharic/news-55156383
ትግራይ ፡ በውጊያ ምክንያት እርዳታ ማቅረብ እንዳልቻለ የተባበሩት መንግሥታት ገለጸ
በትግራይ ክልል በተለያዩ ቦታዎች በቀጠለው ውጊያ ምክንያት እርዳታ ለማቅረብ የሚያደርገው ጥረት እንደተስተጓጎለበት የተባበሩት መንግሥታት አስታወቀ።
ከ45 ሺህ በላይ ሰዎች ግጭቱን ሸሽተው ወደ ሱዳን ተሰደዋል በክልሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚያስፈልጋቸው የምግብና የመድኃኒት ክምችት እተሟጠጠ መሆኑ ተነግሯል። የተባበሩት መንግሥታት ባለስልጣናት ለፈረንሳይ ዜና ወኪል እንደተናገሩት፤ ምንም እንኳን ያልተቋረጠ የሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብ ከመንግሥት ጋር ስምምነት ላይ ቢደረስም ወደ አካባቢዎቹ መድረስ እንዳልቻሉ ገልጸዋል። የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት የመቀለ ከተማን ባለፈው ቅዳሜ ከተቆጣጠረና እየተካሄደ የነበረው ወታደራዊ ዘመቻ መጠናቀቁ ከተገለጸ በኋላ ቢቢሲ ለመጀመሪያ ጊዜ በትግራይ ዋና ከተማ መቀለ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ለማናገር ችሏል። በሳተላይት ኢንተርኔት ያናገራቸው ምንጮች እንደሚሉት "ከመቀሌ አቅራቢያ በሚገኙ ስፍራዎች ላይ ውጊያ እየተካሄደ ነው" ብለዋል። ቢቢሲ ያናገራቸውና ለደኅንነታቸው ሲሉ ማንነታቸው እንዲገለጽ ያልፈሉ ሁለቱ ግለሰቦች፤ በዚህ ሳምንት ረቡዕና ሐሙስ ራቅ ካለ አካባቢ የከባድ መሳሪያ ድምጽ መስማታቸውን ተናግረዋል። ምንጮቹ ጨምረውም ከመቀለ ከተማ ምዕራብና ደቡብ አቅጣጫ የተኩስ ድምፅ መስማት እንደቻሉ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት የዴሞክራሲ ግንባታ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ዛዲግ አብረሃ ግን "ጦርነት እየተካሄደ አይደለም" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሚኒስትሩ ጨምረውም "ህወሓት ጦርነት ማድረግ የሚያስችል ወታደራዊ ቁመና የለውም" ሲሉ ገልጸዋል። የህወሓት ኃይሎች ቃል አቀባይ ገብረ ገብረጻድቃን ረቡዕ እለት በትግራይ ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው ከመቀለ ከተማ አቅራቢያ ባሉ ቦታዎች ላይ ውጊያ እያካሄዱ መሆኑን ተናግረው፤ "ጦርነቱ በቀላሉ የሚያበቃ አይደለም" ብለው ነበር። 'መቀለ ውስጥ መንግሥት የለም' በክልሉ ዋና ከተማ መቀለ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች ግጭቱ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በመሠረታዊ አገልግሎቶች እጥረት እየተቸገሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። የፌደራሉ መንግሥት ሠራዊት ከተማዋን ከተቆጣጠረ በኋላ እንኳን ነዋሪዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን አመልክተዋል። አንድ ነዋሪ ለቢቢሲ እንደተናገረው "አሁን ድረስ በከተማዋ ውስጥ የውሃ፣ የመብራትና የባንክ አገልግሎት የለም።" ነዋሪው ጨምሮም የከተማዋ ፖሊስና የጸጥታ ኃይል በሌለበት ሁኔታ ዘረፋ በተደጋጋሚ እያጋጠመ ነው ብሏል። "በከተማዋ ውስጥ መንግሥት የለም" በማለት የመንግሥት ወታደሮች ግን በተወሰኑ የተከማዋ ክፍል ውስጥ እንደሚታዩ ተናግሯል ። በሌላ በኩል ግን ለኢትዮጵያ መንግሥት ቅርብ የሆኑ መገናኛ ብዙሃን ከተማዋ "ወደ መደበኛ ሕይወት እየተመለሰች ነው" ሲሉ ዘግበዋል። የአንድ ቤተሰብ አባላት ሞተውበታል የተባለው ቤት 'የሰላማዊ ሰዎች ሞት' ባለፈው ቅዳሜ የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ግማሽ ሚሊዮን የሚቆጠር ነዋሪ ያላትን የመቀለ ከተማን ከመቆጣጠሩ በፊት የከባድ መሳሪያ ድብደባ እንደነበር ተነግሯል። በዚህም ሳቢያ አንዳንድ ነዋሪዎች ከጥቃቱ ለማምለጥ ወደ ከተማዋ ዳርቻ ሸሽተው ነበር። ሰኞ ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በአገሪቱ ምክር ቤት ቀርበው እንደተናገሩት በዘመቻው "አንድም ሰላማዊ ሰው አልተገደለም" ብለዋል። ነገር ግን ቢቢሲ ያናገራቸው የመቀለ ነዋሪዎች እንዳሉት፤ ቅዳሜ ዕለት ከተፈጸመው የከባድ መሳሪያ ድብደባ በኋላ የቆሰሉና የሞቱ ሰላማዊ ሰዎችን ሆስፒታል ውስጥ መመልከታቸውን ገልጸዋል። ከምንጮቹ መካከል አንደኛው የከባድ መሳሪያ ጥይት አይደር እዳጋ በጊ በተባለ የመኖሪያ አካባቢ ወድቆ የአንድ ቤተሰብ አባላትን መግደሉን ለቢቢሲ ገልጾ፤ በተጨማሪም ነዋሪው በጥቃቱ የወደመ ቤትና የቆሰሉ ሰዎችን የሚያሳይ ምስል አቅርቧል። ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ባለፈው ሳምንት እንዳለው በመቀለ ከተማ የሚገኙ ሆስፒታሎችና የጤና ተቋማት ከባለፈው ቅዳሜ ውጊያ በኋላ በርካታ የሞቱና የቆሰሉ ሰዎችን መቀበላቸውን ገልጿል። የዲሞክራሲ ግንባታ ሚኒስትሩ ዛዲግ አብረሃ በዚህ ጉዳይ ላይ በሰጡት ምላሽ "በእኛ በኩል ሙሉ በሙሉ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ አድርገናል" ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ማብራሪያ አጠናክረዋል። 'ጦርነቱ ይቀጥላል' የትግራይ ኃይሎች በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ውጊያው እየተካሄደ መሆኑን ይናገራሉ። በክልሉ የነበሩ ሁለት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ህወሓትን የሚደግፉ ዝግጅቶችን ከዚህ ቀደም ከሚያሰራጩበት ቦታ ውጪ ሆነው እያስተላለፉ ይገኛሉ። የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ሐሙስ ምሽት በትግራይ ቴሌቪዥን ቀርበው "ጦርነቱ አልቆመም፤ ህልውናችንና ራስን የማስተደደር መብታችን እስካልተከበረ ድረስ ጦርነቱ አይቆምም" ብለዋል። ነገር ግን ሚኒስትር ዛዲግ አብረሃ ጦርነቱ ማብቃቱን ለቢቢሲ ገልጸው "የቀረው ነገር የህወሓት መሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል ነው" ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት የመቀለ ከተማን ከተቆጣጠረ በኋላ በትግራይ ውስጥ የተካሄደው "ወታደራዊ ዘመቻ" እንዳበቃና አሁን አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ሌሎች የህወሓት ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራሮችን ለመያዝ እያደነ መሆኑን ገልጿል። የትግራይ ኃይሎች በበኩላቸው ክልላቸውን "ወራሪዎች" ካሏቸው እየተከላከሉ መሆናቸውን አመልክተው ከ45 ሺህ በላይ ሰዎች እንዲፈናቀሉና ወደ ሱዳን እንዲሰደዱ ያደረገው ለአንድ ወር በቆየው ውጊያ እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
news-55068402
https://www.bbc.com/amharic/news-55068402
ትራምፕ ኤርትራን ጨምሮ በአፍሪካውያን ተጓዦች ላይ አዲስ ገደብ ጣሉ
የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የ15 አፍሪካ አገራት ዜጎች ወደ አሜሪካ ከመጓዛቸው በፊት ተመላሽ የሚሆን እስከ 15ሺህ ዶላር በቦንድ መልክ ማስያዝ አለባቸው የሚል አዲስ ጊዜያዊ ሕግ አውጥቷል።
ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ይህ ሕግ ተፈጻሚ መሆን የሚጀምረው ከአንድ ወር በኋላ ሲሆን ለስድስት ተከታታይ ወራት ከዘለቀ በኋላ ውጤታማ ሆኖ የሚገኝ ከሆነ ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል። ይህ ሕግ ተፈጻሚ የሚሆንባቸው አገራት፤ አንጎላ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ቻድ፣ ዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኦፍ ኮንጎ፣ ጂቡቲ፣ ኤርትራ፣ጋምቢያ፣ ጊኒ-ቢሳው፣ ላይቤሪያ፣ ሊቢያ፣ ሞሪታኒያ፣ ሱዳን፣ ሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፔ፣ ኬፕ ቨርዴ እና ቡሩንዲ ናቸው። አገራቱ የተለዩት ወደ አሜሪካ ካቀኑ ዜጎቻቸው 10 በመቶ እና ከዛ በላይ የሚሆኑት ዜጎቻቸው በተሰጣቸው ቪዛ መሠረት ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ በአሜሪካ በመቆየታቸው ነው ተብሏል። የእነዚህ አገራት ዜጎች እንደየ ሁኔታው ለጉብኝትም ይሁን በሥራ ጉዳይ ወደ አሜሪካ ከመጓዛቸው በፊት 5ሺህ፣ 10ሺህ ወይም 15ሺህ ዶላር ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ተሰናባቹ ፕሬዝደንት ትራምፕ በዋይት ሃውስ በነበራቸው የአራት ዓመት ቆይታ የኢሚግሬሽን ጉዳዮችን አስተዳደራቸው በትኩረት ሲያስፈጽመው የቆየ ጉዳይ ነው። ተመራጩ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የሪፓብሊካኑን ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በርካታ የኢሚግሬሽን ፖሊሲዎች እንደሚቀይሩ ቃል ገብተዋል።
news-56616314
https://www.bbc.com/amharic/news-56616314
ማኅበራዊ ሚዲያ፡ ፖሊስ ታዳጊዎች ራስን ስለማጥፋት የሚወያዩበት የኢንስታግራም ቡድንን አገኘ
የእንግሊዝ ፖሊስ ታዳጊ ሴት ልጆች ራስን ወደ ማጥፋት እንዲያመሩና በራሳቸው ላይ ከባድ ጉዳት እንዲያደርሱ የሚያበረታታ የማኅበራዊ ሚዲያ ቡድንን እንዳገኘ አስታወቀ።
ይህ ነዋሪነታቸው በደቡባዊ እንግሊዝ ውስጥ የሆኑ እድሜያቸው ከ12 አስከ 16 የሚደርሱ አስራ ሁለት ታዳጊ ሴቶች አባል የሆኑበት ስያሜው እራስን ከማጥፋት ጋር የተያያዘ የኢንስታግራም የውይይት ቡድን ነው ተብሏል። ቡድኑ የተደረሰበት ከአባላቱ መካከል ሦስቱ ጠፍተው ለንደን ውስጥ ጤናቸው ክፉኛ ተቃውሶ ከተገኙ በኋላ ነው። በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሰጠው ኢንስታግራም የቡድኑ አባላት ይለዋወጧቸው የነበሩ መልዕክቶች የማኅበራዊ ሚዲያውን ደንብ የሚጥሱ አልነበሩም ብሏል። ቢቢሲ ያገኘው ጉዳዩን በሚመለከት ፖሊስ ያደረገው የምርመራ ሰነድ እንደሚያመለክተው "የአቻ ተጽእኖ እራስን በማጥፋትና እራስ ላይ ከባድ ጉዳትን እንዲያደርሱ ታዳጊዎችን የሚያበረታታ ነው" ብሏል። ይህ ቡድን መኖሩ የታወቀው አባላቱ በባቡር ለንደን ውስጥ ለመገናኘት ከተቀጣጠሩ በኋላ ሦስቱ ታዳጊ ሴቶች መጥፋታቸው ለፖሊስ ሪፖርት ከተደረገ በኋላ ነበር። ጠፍተው የነበሩትን ታዳጊ ሴቶች ለማግኘት ፍለጋ ከተደረገ በኋላ ጤናቸው በአሳሳቢ ሁኔታ ተቃውሶ ጎዳና ላይ በፖሊስ የተገኙ ሲሆን ለአስቸኳይ ህክምና በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል ተወስደው ነበር። አንደኛዋ ታዳጊ ለፖሊስ እንደተናገረችው የቡድኑ አባላት መጀመሪያ የተዋወቁት በኢንተርኔት አማካኝነት መሆኑንና ራስን ስለማጥፋት መነጋገራቸውን ገልጻለች። ይህንንም ተከትሎ ፖሊሶች ቡድኑን ለመለየትና አባላቱን ለማወቅ በታዳጊዎቹ የማኅበራዊ ሚዲያ መጠቀሚያ ቁሶች ላይ ምርመራ አድርጓል። ፖሊስ ቡድኑ ላይ ከመድረሱ በፊት ከአስራ ሁለቱ አባላት መካከል ሰባቱ በራሳቸው ላይ ጉዳት አድርሰዋል። በተለያዩ ሰባት አካባቢያዊ መስተዳደሮች ስር የሚገኙ ለህጻናት የማኅበራዊ የጥበቃ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ክፍሎች የቡድኑ አባላት የሆኑ ታዳጊ ሴቶችን በመደገፍና በመንከባከብ በኩል ተሳትፎ አድርገዋል። ቢቢሲ ባደረገው ማጣራት ታዳጊ ሴቶቹ የተዋወቁት በሌላ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረክ ላይ ሲሆን፤ በኢንስታግራም ላይ ዝግ የሆነ ቡድን መስርተው በቀጥታ መልዕክት ይለዋወጡ ነበር። የቡድኑ መለያ ስም ላይም ግልጽ በሆነ ሁኔታ "ራስን ማጥፋት" እና "መጥፋትን" የሚያመለክቱ ቃላትን ይጠቀሙ ነበር። ባለፈው ኅዳር ወር ኢንስታግራም በገጹ ላይ የሚወጡ ራስ ላይ ጉዳት ማድረስንና ራስን ማጥፋትን የሚመለከቱ ይዘት ያላቸውን መረጃዎች የሚለይ አዲስ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ማድረጉን አስታውቆ ነበር። የኢንስታግራም ባለቤት የሆነው ፌስቡክ የታዳጊ ሴቶቹ የኢንስታግራም ቡድን ስያሜ "ራስን ማጥፋትን" የሚያመለክት መሆኑን አረጋግጦ፤ ነገር ግን የቡድኑ አባላት የሚለዋወጧቸው መልዕክቶች የመድረኩን ደንቦች የጣሱ ስላልነበሩ እገዳ እንዳልጣለባቸው ገልጿል። የድርጅቱ ቃል አቀባይ ጉዳዩን አስመለክቶ ባወጣው መግለጫ ከፖሊስ ጋር ተባብሮ እየሰራ መሆኑን አመልክቷል። "የቀረቡልንን ሪፖርቶች መርምረን ራስን በማጥፋትና በመጉዳት ዙሪያ ያለውን የማኅበራዊ መድረኩን ደንብ የሚጥስ ጉዳይ አላገኘንም። አሰቃቂ ምስሎችን ወይም ራስ ላይ ጉዳት ማድረስን የሚያበረታቱ ይዘቶችን አንፈቅድም ከተገኙም እንዲነሱ ይደረጋሉ" ብለዋል። ከክስተቱ ጋር በተያያዘም ለፖሊስ የሚያደርጉትን ድጋፍ እንደሚቀጥሉና ማንኛውንም መረጃ ለማግኘት ለሚቀርቡላቸው ሕጋዊ ጥያቄዎችም ምላሽ እንደሚሰጡም ቃል ገብተዋል።
news-50745914
https://www.bbc.com/amharic/news-50745914
ምያንማር ሮሂንጂያ፡ ሳን ሱ ቺ የቀረበባቸውን የዘር ማጥፋት ክስ ተቃወሙ
በተባበሩት መንግሥታት ፍርድ ቤት [አይ ሲ ጀ] የቀረቡት የምያንማር መሪ አን ሳን ሱ ቺ ፤ አገራቸው የቀረበባትን የዘር ማጥፋት ወንጀል ክስ ተቃውመዋል።
የዓለም የኖቤል ሰላም ሎሬት የሆኑት ሳን ሱ ቺ ክሱን የተቃወሙት የቀድሞዋ በርማ የአሁኗ ምያንማር በሮሂንጂ ሙስሊሞች ላይ ጭካኔ የተሞላበት የዘር ጭፍጨፋ ፈፅማለች በሚል በስፋት የተሰራጨውን ክስ በተመለከተ ነው። • ሙገሳ እና ወቀሳ የተፈራረቀባቸው ሳን ሱ ኪ • ተመድ ለሮሂንጂያ ሙስሊሞች አልደረሰላቸውም ተባለ በመክፈቻ ንግግራቸው በምያንማር ላይ የቀረበው ክስ "ያልተሟላና ትክክል ያልሆነ" ብለውታል። አክለውም ከክፍለ ዘመናት በፊት በርካታ ሮሂንጃዎች ይኖሩበት በነበረው ረካይን ግዛት ችግሮች እንደነበሩ አውስተዋል። የቡዲሂስት እምነት ተከታዮች የሚበዙባት ምያንማር በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር 2017 ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ ወስዳ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሮሂንጃ ሙስሊሞች ሲገደሉ ከ700 ሺህ በላይ የሚሆኑት ወደ ጎረቤት አገር ባንግላዴሽ ተሰደዋል። ምያንማር ሁል ጊዜም ቢሆን በረካይን ግዛት የፅንፈኞችን ጥቃት ለመከላከል ጥረት ታደርጋለች። በመሆኑም ሳን ሱ ቺ ይህንን አቋም በመያዝ፤ ጥቃቱን "ውስጣዊ የወታደሮች ግጭት" ነበር፤ ይህም የሮሂንጃን ታጣቂዎች በመንግሥት የፀጥታ አካላት ላይ ጥቃት በመፈፀማቸው የተቀሰቀሰ ነው ብለውታል። ሳን ሱ ቺ "በዚህ ጊዜ የምያንማር ወታደሮች ያልተመጣጠነና ያልተገባ ኃይል ተጠቅመው ይሆናል፤ በመሆኑም ወታደሮች የጦር ወንጀሎችን ፈፅመው ከሆነ እነርሱ ሊከሰሱ ይገባል" ብለዋል። በምያንማር ህዝብ ዘንድ ተደማጭነት እንዳላቸው የሚነገርላቸው ሳን ሱ ቺ፤ ያላቸው ሥልጣን ውሱን መሆኑ ቢነገርም የተባበሩት መንግሥታት መርማሪዎች አገኘነው ባሉት 'ውስብስብ መረጃ' ምክንያት ግን ክስ ተመስርቶባቸዋል። • አውሮፕላን ያለ ፊት ጎማው ያሳረፈው አብራሪ ይህም ለአራት ዓመታት በቁም እስር ላይ ላዋላቸው ጦር እንዲቆሙ የተመረጡት ሳን ሱ ቺ ትልቅ ውድቀት ነው ተብሏል። ሳን ሱ ቺ ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዱት አገራቸው ከራካይን የተሰደዱት ሰዎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ቁርጠኛ መሆኗን በመግለፅ፤ ፍርድ ቤቱ ግጭቱን እንዲያገረሽ ሊያደርግ የሚችል ድርጊት መፈፀሙን እንዲያቆም አሳስበዋል። ይህንን ንግግራቸውን በቴሌቪዥን የተከታተሉ እና በባንግላዴሽ በኩቱፓሎንግ የስደተኖች ካምፕ የሚገኙ ስደተኞች "ውሸታም ፣ ውሸታም፣ አሳፋሪ" እያሉ በመጮህ ተቃውሟቸውን ሲገልፁ ነበር። ከስደተኞቹ አንዱ የሆነው የ52 ዓመቱ አብዱ ራሂም "ውሸታም ናቸው፣ ትልቅ ውሸታም" ሲል ገልጿቸዋል። ከሄግ ፍርድ ቤት ውጭ የሮሂንጃ ሙስሊሞች ደጋፊ የሆኑ የተወሰኑ ሰዎች በቡድን በመሆን " ሳን ሱ ቺ፤ በአንቺ አፍረናል!" ሲሉ ተደምጠዋል። በሌላ በኩል የእርሳቸው ደጋፊ የሆኑ ወደ 250 የሚጠጉ ተቃዋሚዎች የእርሳቸውን ምስል በመያዝ " ከጎንዎ ነን!" ሲሉ ድጋፋቸውን አሳይተዋል። የምያንማር ዜጋ የሆነችውና አሁን ኑሮዋን በአውሮፓ ያደረገችው ፖ ፕዩ የሰልፉ አንዷ አስተባባሪ ስትሆን "ዓለም በአን ሳን ሱ ቺ ይበልጥ ትዕግስተኛ መሆን ይጠበቅበታል" ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች። "እስካሁን በእርሷ እምነት አለን፤ እንደግፋታለን። በአገራችን ሰላምና ብልፅግና ያመጡ እና ይህንን ውስብስብ ችግር የፈቱ ብቸኛ ሰው ናቸው" በማለትም አክላለች። ሳን ሱ ቺ ከዓመታት በፊት በሰብዓዊ እና ፖለቲካዊ መብት ተሟጋችነታቸው ሰበብ በተደጋጋሚ ለእስር እና እንግልት ተዳርገዋል። ለዚህ በጎ ተግባራቸውም እ.ኤ.አ. በ1991 የኖቤል ሰላም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። የተሰጣቸው የኖቤል ሽልማት እንዲነጠቅ የሚጠይቁ ወገኖችም ቢበራከቱም ኮሚቴው ግን ሽልማቱን መንጠቅ እንደማይችል ማስታወቁ ይታወሳል።
news-50025346
https://www.bbc.com/amharic/news-50025346
ከባህር ዳር - አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ ዛሬም አልተከፈተም
ትናንት ከረፋድ ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል ጎሃ ፂዮን አካባቢ መንገድ በመዘጋቱ ተሽከርካሪዎች ማለፍ እንዳልቻሉና ወደ ደጀን ከተማ ተመልሰው ለማደር መገደዳቸው ተሰምቷል።
ይሄው መንገድ ትናንት ይከፈታል ተብሎ የነበረ ቢሆንም ዛሬም አለመከፈቱን ተሳፋሪዎችና የደጀን ወረዳ አስተዳዳርና ፀጥታ ኃላፊ አቶ ካሳሁን አስፋው ለቢቢሲ ገልፀዋል። ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ ከጎንደር የተሳፈረችው ትዕግስት ደሴ ትናንት ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት አካባቢው ላይ ሲደርሱ በርካታ ቁጥር ያላቸው ተሽከርካሪዎች ተደርድረው እንደተመለከተችና መንገድ መዘጋቱን እንደሰማች ትገልጻለች። ተሳፋሪዎቹ አብዛኛዎቹ ተማሪዎች እንደሆኑ የምትናገረው ትዕግስት፤ ወደ ደጀን ከተማ ተመልሰው ለማደር እንደተገደዱ ትናገራለች። ደጀን ከተማ ተመላሽ ተሳፋሪዎችን በሙሉ የሚያስተናግዱ ሆቴሎች ባለመኖራቸው አብዛኛው ሰው በቤተክርስቲያንና ሌሎች ቦታዎች ደጅ ላይ ተጠልለው በከተማው ሕዝብ ምግብና አንዳንድ እርዳታዎች ተደርጎላቸው እንዳደሩ ተመልክታለች። ዛሬ ጠዋት መንገዱ ይከፈት ይሆናል በሚል ተስፋ ደጀን ያደሩት ተሳፋሪዎቹ፤ መንገዱ ዛሬም ባለመከፈቱ ሕፃናት፣ ሴቶች እና አረጋዊያን ለእንግልት እየተዳረጉ ነው ብላለች። • ነገ በአዲስ አበባ የሚደረግ ሠልፍም ሆነ ስብሰባ የለም-የአዲስ አበባ ፖሊስ • "ምን ተይዞ ምርጫ?" እና "ምንም ይሁን ምን ምርጫው ይካሄድ" ተቃዋሚዎች ዛሬ እንደውም ይባስ ብሎ ከአዲስ አበባ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎችም መንገዱ በመዘጋቱ ወደ መጡበት ለመመለስም የትራንስፖርት አገልግሎት አለመኖሩን አክላለች። ትናንት ከአዲስ አበባ የሚመጡ ተሽከርካሪዎች ማለፍ የሚችሉ ቢሆንም ይከፈታል በሚል ተስፋ ግን ከመመለስ ይልቅ መጠባበቁን እንደመረጡ በመናገር። "የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምዝገባ በጥቅምት አንድና ሁለት ነው፤ እኔ የተሳፈርኩበት አውቶብስ ውስጥ አብዛኞቹ ተሳፋሪዎች ለምዝገባ ለመድረስ የተሳፈሩ ተማሪዎች ናቸው" ትላለች። ትናንት በነበረው ሁኔታ የሕዝብ ማመላለሻዎች ብቻ ሳይሆኑ ማንኛውም ዓይነት መኪና ማለፍ እንዳማይችልም እንደታዘበችም ነግራናለች። የደጀን ወረዳ አስተዳደርና ፀጥታ ኃላፊ የሆኑት አቶ ካሳ አስፋውም በአሁኑ ሰዓት ኦሮሚያ ክልል ያለው መንገድ ስላልተከፈተ ደጀን ከተማ ላይ በርካታ መኪኖችና መንገደኞች በከተማዋ እንዳሉ ለቢቢሲ ገልፀዋል። መንገዱ የተዘጋው ኦሮሚያ ክልል የአባይ በረሃ አፋፍን ወጣ እንዳሉ ወረ ጃርሶ ወረዳ ላይ መሆኑን መስማታቸውን የሚናገሩት አቶ ካሳ ስለምክንያቱ የምናውቀው የለም ብለዋል። ከትናንት ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ በደጀን ከተማ ያለፉ የሕዝብ ማመላለሻ መኪኖች መመለሳቸውን የሚናገሩት ኃላፊው ትናንት ቀኑን ሙሉ ከኦሮሚያ ፖሊስ ባልደረቦች ጋር ሲደዋወሉ እንደነበር እና እናጣራለን እንዳሏቸውም ያስታውሳሉ። ትናንት ከቀኑ አስር ሰዓት ላይ መንገዱ ተከፈተ ተብሎ እንደነበር በመግለፅም መኪኖች መንቀሳቀስ ቢጀምሩም ምሽት አንድ ሰዓት ላይ ማለፍ ባለመቻላቸው በድጋሚ መመለሳቸውን ይገልፃሉ። መኪኖቹን የፀጥታ ኃይሎች ፈትሸው ቢያሳልፉም ወጣቶች እንደመለሷቸው ከመንገደኞቹ መስማታቸውን ይናገራሉ። በአንድ ቀን ሰባ፣ ሰማኒያ መኪና፣ በምሽት ደግሞ ከእጥፍ በላይ ከደጀን ወደ አዲስ አበባ መስመር የሚንቀሳቀሱ መኪኖች መኖራቸውን በመናገር ከተማዋ ላይ አሁን ከፍተኛ የመኪና ቁጥር መኖሩን ገልፀውልናል። በትናንትናው ዕለት በከተማዋ ከ200 በላይ መኪኖች ማደራቸውን ተናግረው፤ ተማሪዎች፣ አርሶ አደሮች፣ አዛውንቶች፣ ነፍሰጡሮች እንዳሉ፤ ተማሪዎቹም የመመዝገቢያ ቀን እንዳያልፍባቸው ስጋት እንደገባቸው ያስረዳሉ። ከትናንት ጀምሮ የሕዝብ ማመላለሻ መኪኖች ማለፍ እንደማይችሉ ሌሎች ግን ማለፍ እንዳልተከለከሉ አክለዋል- አቶ ካሳ። ዛሬ ማለዳ ግን ከኦሮሚያ ፖሊስ ምላሽ እንዳላገኙ ተናግረዋል። በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን የጸጥታ ኃላፊ አቶ ለማ ሆርዶፋ በበኩላቸው ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ የተዘጋበትን ምክንያት ለማጣራት አመራሮችን ወደ ሥፍራው እንደላኩ ገልፀው፤ ዛሬ ጠዋትም በጉዳዩ ላይ ተነጋግረውበት አንድም መኪና መቆም እንደማይችል አቅጣጫ አስቀምጠው መኪና በሰላማዊ መልኩ እያለፈ እንደሆነ መረጃ እንዳላቸው ነግረውናል። ለእርሳቸው ከመደወላችን በፊት ያነጋገርናቸው ተሳፋሪዎች አሁንም መንገዱ እንደተዘጋ እንደነገሩን ያነሳንላቸው ኃላፊው፤ "በአሁኑ ሰዓት ራሱ መኪና እያለፈ ነው፤ መንገድ ላይ ምንም ችግር እንደሌለ ተጨባጭ መረጃ አለኝ " ብለዋል። በየትኛውም አቅጣጫ ወደ አዲስ አበባ የሚገባ መኪና በሠላም እየተንቀሳቀሰ እንዳለም አስረግጠዋል። • ያለፈቃድ መንገድ ያጸዳው ናይጄሪያዊ ስደተኛ ቅጣቱ ተነሳለት • "ምርጫው እንዲራዘም እንፈልጋለን" አቶ አንዷለም አራጌ ትናንት ጠዋት ላይ መንገድ መዘጋቱን ያስታወሱት ኃላፊው "ከምስራቅ ጎጃም ዞን የፀጥታ ኃላፊዎች ጋር ተነጋግረን፤ ወዲያውኑ አቅጣጫ አስቀምጠን ችግሩ ተፈቷል" ብለዋል። ኃላፊው የሚያጣሩ ሁለት አመራሮችን ወደ ጎሃ ፅዮን መላካቸውን ከመግለፅ ባለፈ እስካሁን ምክንያቱ ተጣርቶ፤ በማንና ለምን እንደተዘጋ ግልፅ መረጃ እንደሌላቸው ነግረውናል። መንገዱ ስለመዘጋቱ የፀጥታ ኃይሉ እጅ ሳይኖርበት አይቀርም መባሉንም ያነሳንላቸው ኃላፊ "ይህንን ኃላፊነት ወስጄ አጣራለሁ፤ ችግር የለውም" ሲሉ ምላሽ ሰጥተውናል። ከአማራ ክልል የፀጥታ ኃላፊዎች ጋር አጎራባች አካባቢዎችን በተመለከተ አዳማ ስብሰባ ላይ እንደሚገኙ የገለፁልን ኃላፊው አክለውም፤ በደብረ ብርሃን በኩልም ወደ አዲስ አበባ የሚያስገባው መንገድ ተዘግቷል መባሉንም "ውሸት ነው" በማለት ሰላም መሆኑን እንደሚያውቁ ገልፀውልናል።
news-56411232
https://www.bbc.com/amharic/news-56411232
ኮሮናቫይረስ፡ የአስትራዜንካን ክትባት ተጠቀሙ- የዓለም ጤና ድርጅት
በርካታ የአውሮፓ ሃገራት የኮሮናቫይረስ መከላከያ የሆነውን አስትራዜንካ ክትባት ማገዳቸውን ተከትሎ የዓለም ጤና ድርጅት ክትባቱን እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርቧል።
ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣልያንና ስፔይንን ጨምሮ ሌሎች አገራት የኦክስፎርዱ አስትራዜንካ ክትባት ደም መርጋት በተያያዘ ችግር አለበት በሚል ክትባቱ እንዳይሰጥ አግደውታል። የዓለም ጤና ድርጅት በበኩሉ ደም መርጋት ስለማስከተሉ ምንም አይነት ማስረጃ የለም ይላል። የድርጅቱ የክትባት ደህንነት ልሂቃንም በዛሬው ዕለት ተሰብስበው ስለ ክትባቱ ይመክራሉ ተብሏል። የአውሮፓ መድኃኒት ኤጀንሲም እንዲሁ ስለ ክትባቱ በዛሬው ዕለት የሚወያዩ ሲሆን በያዝነው ሃሙስም የደረሱበትን ማጠቃለያ ለህዝብ ያሳውቃሉ ተብሏል። ሆኖም ኤጀንሲው ክትባቱን ተጠቀሙ ብሏል። በአውሮፓ ክትባቱን ከተከተቡ በኋላ የደም መርጋት ችግር ያጋጠማቸው ሰዎች አሉ ብሏል። ነገር ግን ባለሙያዎቹ እንደሚሉት በአጠቃላይ ከህዝብ ብዛቱ ጋር ሲነፃፀር የደም መርጋት ያጋጠማቸው ሰዎች ድንገተኛ መጨመር አላሳየም ይላሉ ። በአውሮፓ ህብረት አባላት አገራትና ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ 17 ሚሊዮን ሰዎች የአስትራዜንካ ክትባትን መከተባቸውና ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ 40ዎቹ የደም መርጋት ችግር እንዳጋጠማቸው አስትራዜንካ አስታውቋል። እየተወሰዱ ያሉ ጥንቃቄዎች ይህንንም ተከትሎ የጀርመን ጤና ሚኒስቴር በያዝነው ሳምንት ሰኞ ዕለት አስትራዜንካ ክትባት መስጠት በአስቸኳይ እንዲቆም ትዕዛዝ አስተላልፏል። ክትባቱ የአዕምሮ ደም መርጋት ወይም ሴሬብራል ቬይን ቶርምቦሲስ ችግር ጋር መገናኘቱን አይተናል ብለዋል። የጤና ሚኒስትሩ ጄንስ ስፋን እንዳሉት ውሳኔ "ፖለቲካዊ" እንዳልሆነ ነው። "ሁላችንም ቢሆን ይህ ውሳኔ ሊያስከትለው የሚችለውን ጉዳት እንረዳለን። በቀላሉም የደረስንበት አይደለም" ብለዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እንዲሁ የአውሮፓ መድኃኒት ኤጀንሲ ውሳኔውን እስኪያሳውቅ ድረስ አገራቸው ክትባቱን ታግዳለች ብለዋል። "ቀለል ያለ መመሪያ ነው ያለን፤ ሳይንስንና በዘርፉ ላይ ዕውቀት ያላቸውን የጤና ባለስልጣናት ምክር ነው የምንከተለው፤ ይህም የአውሮፓ ስትራቴጂ ምን መምሰል አለበት የሚለውን የሚጠቁም ይሆናል" ብለዋል። የጣልያን መድኃኒት ኤጀንሲም እንዲሁ የአውሮፓ መድኃኒት ኤጀንሲ የሚደርስበትን ማጠቃለያ እጠብቃለሁ በማለት አግዳዋለች። የስፔን ጤና ሚኒስትር ካሮሊና ዳሪያስ በበኩላቸው ክትባቱ ለመጪው ሁለት ሳምንት ይታገዳል ብለዋል። አየርላንድ፣ ፖርቹጋል፣ዴንማርክ፣ ኖርዌይ፣ ቡልጋሪያ፣ አይስላንድ፣ ስሎቬኒያ ክትባቱን በጊዜያዊነት ያገዱ ሲሆን ዲሞክራቲክ ኮንጎና ኢንዶኔዥያ የክትባት መስጪያ ጊዜያቸውን አራዝመውታል። ኦስትሪያን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ አገራት ለጥንቃቄ ሲሊ ቢያግዱትም ቤልጂየም፣ ፖላንድና ቼክ ሪፐብሊክ ክትባቱን እየሰጡ ነው። የቤልጂየም ጤና ሚኒስትር ፍራንክ ቫንደንብራውኬ እንዳስታወቁት ቤልጂየም ካላት ከፍተኛ የኮሮናቫይረስ ህሙማን ቁጥርን በማየት ክትባቱን አለመስጠት አትችልም ብለዋል። የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ በበኩላቸው አስትራዜንካን ጨምሮ በአገሪቱ እየተሰጡ ያሉ ክትባቶች ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን የጤና ባለስልጣናቱ ነግረውኛል ብለዋል።
news-54046811
https://www.bbc.com/amharic/news-54046811
የ53 ዓመቱ ፕሮፌሽናል እግር ኳሰኛው ካዙ
እርግጥ ነው የጃፓን ሊግ ካፕ ጨዋታዎች ይህን ያህል የዓለም አቀፍ ዘገባዎች ርዕስ አይሆኑም። በሃገሪቱ ዋናው ሊግ የሚጫወተው ዮካሃማ የስፖርት ክለብ ባለፈው ወር ያሰለፈው ተጫዋች ግን የብዙዎችን ዓይን ስቧል።
የ53 ዓመቱ ፕሮፌሽናል እግር ኳሰኛው ካዙ የዮካሃማ አምበል ካዙዮሺ ሚውራ 53 ዓመቱ ነው። ካዙዮሺ ከክለቡ ጋር የነበረውን ውል ሲያራዝም ቢቢሲና ሴኤንኤንን ጨምሮ በርካቶች አስደናቂ ዜና ሲሉት አውርተዋል። ሰውዬው በዕድሜ ትልቁ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ የጊነስ አስደናቂ ድርጊቶች መዝገብ ላይ መሥፈር ችሏል። ወዳጆቹ ‘ንጉስ ካዙ’ እያሉ የሚጠሩት ካዙዮሺ ማነው? እንዴትስ ይህን ሁሉ ዓመት እግር ኳስ ሊጫወት ቻለ? ካዙ ታሪኩ የሚጀምረው 1970 [በአውሮፓውያኑ] ነው ይላል። ምክንያቱ ደግሞ ፔሌ እና የአባቱ 8 ሚሊሜትር ካሜራ። የካዙ ቤተሰቦች እግር ኳሰኞች ናቸው። ታላቅ ወንድሙ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋች ነበር። አባቱ ደግሞ በእግር ኳስ ፍቅር የወደቁ ሰው ነበሩ። “አባቴ 1970 ሜክሲኮ የተካሄደውን የዓለም ዋንጫ ለማየት ሄዶ ነበር። ጨዋታዎቹን በ8 ሚሊሜትር ካሜራው ይቀርፃቸው ነበር።” ወቅቱ ብራዚላዊ ፔሌ የገነነበት ነበር። የካዙ አባት ፔሌ ኳሷን ሲያንቀረቅብ የቀረፁትን ይዘው መጥተው ለካዙ ያሳዩታል። ካዙም በእግር ኳስ ፍቀር ተነደፈ። ካዙ በወቅቱ ገና የ3 ዓመቱ ልጅ ነበር። ነገር ግን አባቱ የቀዱትን የፔሌ ቪድዮ አይቶ አይጠግብም ነበር። እያደገ ሲመጣ ከብራዚል እግር ኳስ በቀር ሌላ ነገር አታሳዩኝ ይል ጀመር። “ገና ከልጅነቴ ጀምሮ እግር ኳስ በጣም እወድ ነበር። ወደፊት ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋች እሆናለሁ እያልኩ እመኝ ነበር።“ የካዙ አባት ብራዚል ውስጥ ሥራ አገኙ። ቤተሰቡም ጓዙን ጠቅልሎ ወደ ሳዎ ፓውሎ አመራ። ካዙ በልጅነቱ ሳዎ ፓውሎ ውስጥ ለሚገኝ አንድ ጁቬንቱስ ለተሰኘ ክለብ መጫወት ጀመረ። ነገር ግን ሕይወት ቀላል አልነበረችም። አብረውት የሚኖሩት ዕድሜያቸው ከ15-20 የሚሆኑ ብራዚላዊያን ናቸው። ካዙ ደግሞ ፖርቼጊዝ [የብራዚል መግባቢያ ቋንቋ] ገና አልለመደም። “ቋንቋው ሊገባኝ አልቻለም። ባሕሉም ለኔ እንግዳ ነበር። በጣም ብቸኝነት ይሰማኝ ነበር። በተለይ የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት እጅግ ከባድ ነበሩ።” ቢሆንም ካዙ ተስፋ አልቆረጠም። በየቀኑ ልምምድ ያደርግ ጀመረ። ቋንቋ ማጥናቱንም ተያያዘው። እንደው በእግር ኳስ ባይሳካልህ ኖሮ በምን ሙያ ትሰማራ ነበር? ከቢቢሲ ለካዙ የቀረበ ጥያቄ። ካዙ ትንሽ ከቆዘመ በኋላ “እውነት ለመናገር ምንም አላውቅም። ሁሌም ምኞቴ እግር ኳሰኛ መሆን ነበር። ይህ በጣም ከባድ ጥያቁ ነው።” ከሶስት ዓመታት በኋላ ለሳንቶስ ፈረመ። በአባቱ ካሜራ ያየው የነበረው ፔሌ ልጅነቱን ያሳለፈበት ሳንቶስ። ካዙ ብራዚል ውስጥ ለተለያዩ ክለቦች ተጫውቷል። ወደ ጃፓን የተመለሰው 1990 [በአውሮፓውያኑ] ነበር። 1993 ላይ ጄ-ሊግ [የጃፓን ፕሪሚዬር ሊግ] ተመሠረተ። በወቅቱ ካዙ እጅግ ውድ ተጫዋች ነበር። በሚቀጥለው ዓመት ወደ ጣልያን አምርቶ ለጄኔዋ በመጫወት ታሪክ ሠራ - በሴሪአው የተጫወተ የመጀመሪያው ጃፓናዊ በመሆን። በመጀመሪያ ጨዋታው ከወቅቱ የጣልያን ኮከብ ፍራንኮ ባሬሲ ጋር ተጋጭቶ ተጎዳ። ከጄኖዋ ጋር የነበረው ጊዜም ይህን ያህል ውጤታማ አልነበረም። ወደ ሃገር ቤት ሲመለስ ግን ብዙዎች በአድናቆት ተቀበሉት። የጃፓን የስፖርት ጋዜጠኞች ካዙ ማለት ለጃፓን እግር ኳስ መዘመን ትልቅ ሚና የተጫወተ ሰው ነው ይላሉ። አርጀንቲና ማራዶና እንዳላት ሁሉ ጃፓንም ካዙ አላት ይላል የስፖርት ጋዜጠኛው ሾን ካሮል። ካዙ አሁን ለሚጫወትለት ዮካሃማ ክለብ የፈረመው 2005 ላይ ነው። በ38 ዓመቱ። ክለቡ በሱ መሪነት ከታችኛው ሊግ ወደ ዋናው ጄ-ሊግ በአንድ ዓመት አደገ። ነገር ግን ክለቡ ተመልሶ በሚቀጥለው ዓመት ወደ ታችኛው ሊግ ወረደ። ካዙ ግን ከክለቡ ጋር መቆራረጥ አልመረጠም። ካዙዮሺ በሚሠራቸው ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እጅጉን ይታወቃል። “እርግጥ ነው እንደ ወጣት ተጫዋቾች ለኔ ሁሉም ነገር ቀላል አይደለም። ነገር ግን እግር ኳስን በጣም ስለምወድ አደርገዋለሁ።“ ካዙ ይህን ሁሉ ዓመት በእግር ኳስ መቆየት የቻለው የሰውነት ብቃቱን በመጠበቁ ብቻ አይደለም። ባሕሪውም አስተዋፅዖ አድርጎለታል። ብዙዎች ከሱ ጋር የተጫወቱም ሆኑ እሱ ሲጫወት የተመለከቱ ፀባዩ እጅግ መልካም እንደሆነ ተናግረው አይጠግቡም። ለዚህም ነው ጃፓናውያን እጅግ የሚወዱት ይላሉ። በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነት ለሌለው ዮካሃማ የእግር ኳስ ቡድን እየተጫወተ እንኳ እሱ ይሰለፋል ሲባል ተጨማሪ 3 ሺህ 4 ሺህ ሰዎች ወደ ስታድየም ይመጣሉ። ካዙ አሁን ለሚጫወትበት ክለብ ብዙ ጊዜ ሲሰለፍ ባይስተዋልም ክለቡ ግን ልምዱን በጣም ይፈልገዋል። ለዚህም ነው ውሉን ያራዘሙለት ይላሉ የጃፓን ስፖርት ጋዜጦች። “መልበሻ ክፍል ውስጥ የሱ መኖር ትልቅ ለውጥ ይፈጥራል። ጃፓን ደግሞ በዕድሜ ገፋ ያሉ ሰዎች የሚከበሩባት ሃገር ናት” ይላል ጋዜጠኛው ሾን። በዚህ ዕድሜህ እግር ኳስ ለመጫወትህ ሚስጥሩ ምንድነው የሚለው ጥያቄ ለካዙ ብርቅ አይደለም። እሱ ግን እንዲህ ይላል፤ “ምንም ሚስጢር የለውም - ጠንክሮ መሥራትና መሰጠት እንጂ።”
news-41386172
https://www.bbc.com/amharic/news-41386172
አደገኛ ነው የተባለለት የወባ በሽታ በደቡብ ምሥራቅ እስያ ተስፋፍቷል
አደገኛ እንደሆነ የተነገረለት የወባ ዓይነት በደቡብ ምሥራቅ እስያ በፍጥነት መዛመቱ ለአፍሪካ አስጊ መሆኑን ተመራማሪዎች አስታወቁ።
የወባ በሽታን የምታስተላልፈው ትንኝ ይህን መሰሉ የወባ ዓይነት በመደበኛው የወባ መከላከያ መድኃኒት በቁጥጠር ሥር አይውልም ተብሏል። ይህ የወባ ዓይነት መጀመሪያ በካምቦዲያ የታየ ቢሆንም ወደ ደቡብ እስያ ሃገራት ተስፋፍቷል። በባንኮክ የሚገኘው ኦክስፎርድ ትሮፒካል ሜድሲን የምርምር ተቋም ባልደረቦች እንደሚሉት ይህን የወባ ዓይነት ለመዳን አስቸጋሪ ይሆናል። የምርምር ቡድኑ የበላይ የሆኑት ፕሮፌሰር አሪየን ዶንድሮፕ በሽታው በፍጥነት ከመዛመቱም በላይ አፍሪካ ሊደረስ ይችላል የሚል ስጋት አለን ብለዋል። የኢትዮጵያ ተሞክሮ በጤና ጥበቃ ሚንስቴር የወባ ፕሮግራም ባለሙያ ሆኑት አቶ ደረጀ ድሉ እንደሚሉት መስሪያ ቤቱ ስለስጋቱ መረጃው አለው። ወባ በሽታን በመከላከል አበረታች ውጤት እየተገኘ መሆኑን የገለጹት ባለሙያው እ.አ.አ በ2013 ላይ 3.31 ሚልዮን የነበረው የህሙማን ቁጥር በ2016 ወደ 1.8 ሚሊዮን መቀነሱን ጠቁመዋል። እስካሁን ባለው አሰራር ፕላስሞዲየም ፋልሲፓረም እና ፕላስሞዲየም ቫይቫክስ ለተየባሉት የወባ ዓይነቶች መድኃኒቶች ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው ብለዋል። እንደባለሙያው ከሆነ የመድኃኒቶቹን ውጤታማነት ለመከታተልም የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስትትዩት በየሁለት ዓመቱ ጥናት ያካሂዳል። የጨነገፉ መድኃኒቶች በወባ ትንኝ በሚዛመተው በዚህ በሽታ 212 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በየዓመቱ የሚያዙ ሲሆን ህጻናትን በመግደል ቀዳሚ ከሆኑት መካከልም ተጠቃሽ ነው። በሽታውን ለመቆጣጠር አርትሚሲኒንን ከፒፐራኩይን ጋር በማሃዋድ መጠቀም ተቀዳሚ ምርጫ ነው። አርትሚሲኒን ያለው ውጤታማነት እየቀነሰ ሲሆን በሽታው ደግሞ ፒፐራኩይንን እየተላመደ ይገኛል። በውህድ መድሃኒቶቹ በሽታውን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት በአንዳንድ ቦታዎች እስከ 60 በመቶ ድረስ መቀነሱን ፕሮፌሰር ዶንድሮፕ አስታውቀዋል። መድኃኒቱን የተላመደ ወባ መስፋፋቱ እስከ 92 በመቶ የሚሆነው የወባ በሽታ በሚከሰትበት የአፍሪካ አህጉር የከፋ ችግር ሊያስከትል ይችላል። በአፋጣኝ የሚቀርብ መፍትሔ "በሽታው መዳን ከማይቻልበት ደረጃ ደርሶ የሰዎችን ህይወት ከመቅጠፉ በፊት በፍጥነት መስራት ይኖርብናል" ብለዋል። "እውነቱን ለመናገር በጣም ሰግቻለሁ" ሲሉ ፕሮፌሰሩ የክስተቱን አሳሳቢነት ይናገራሉ። የዌልካም ትረስት ሜዲካል ሪሰርች ባልደረባ ሆኑት ማይክል ቼው እንደሚሉት፤ መድኃኒት የተላመደ የወባ በሽታ መስፋፋቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማህበረሰብ ጤና አስጊ ነው ብለዋል። እስካሁን በዓመት የ700 ሺህ ሰዎችን ህይወት ሲቀጥፍ የነበረው መድኃኒት የተላመደ የወባ በሽታ፤ ምንም ካልተሰራበት የሟቾች ቁጥር እ.አ.አ በ2050 በሚሊዮኖች ከፍ ሊል ይችላል ብለዋል። በኢትዮጵያ የአዲሱ የወባ በሽታ ዓይነት አለመከሰቱን አቶ ደረጀ ጠቅሰው፤ መድኃኒት የተላመደ ወባን ለመከላከል እና የመድኃኒቶችን ውጤታማነት ለማረጋገጥ ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስትትዩት ጋር የሚደረገው ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
news-48620235
https://www.bbc.com/amharic/news-48620235
በ10ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና 28 ተማሪዎች መውለዳቸው ተገለፀ
ትናንት በተጠናቀቀው የዘንድሮው 10ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ የአገር አቀፍ ፈተና 28 ሴቶች በፈተና ላይ ሳሉ መውለዳቸውን የትምህርት ሚኒስቴር ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሃረጓ ማሞ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
ዳይሬክተሯ እንዳሉት ተማሪዎቹ በምን ሁኔታ ጋብቻ ፈፀሙ? ያለ ዕድሜ ጋብቻ ነበር ወይ? የሚለው በጥናት የሚታወቅ ቢሆንም አሁን ባላቸው መረጃ ሁሉም በትዳር ላይ የነበሩ ሴቶች ናቸው። • የ29 ዓመቷ የህክምና ዶክተርና ኢንጅነር ዕልልታ ጉዞ ከእነዚህም መካከል 27ቱ የመደበኛ ትምህርት ተማሪዎች ሲሆኑ እንዷ የግል ተፈታኝ መሆኗም ታውቋል። በአገሪቷ የተለያዩ ቦታዎች በሚገኙ የመፈተኛ ጣቢያዎች ማለትም በደቡብ 11፣ በትግራይ 4፣ በአማራ 2፣ በኦሮሚያ 6፣ በቤኒሻንጉል 1፣ በአዲስ አበባ 1 እና በጋምቤላ 3 ሴት ተማሪዎች በፈተና ወቅት መውለዳቸው ሪፖርት እንደደረሳቸው ዳይሬክተሯ አስረድተዋል። "በዓለማችን ካሉ ህመሞች የከፋ ሕመም ምጥ ነው" የሚሉት ወ/ሮ ሃረጓ ተማሪዎቹ በአስቸጋሪና ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ፈተናውን ማጠናቀቃቸውን አድንቀዋል። "በወለደች በ30 ደቂቃ ገብታ የተፈተነችው ተማሪ ዜና በጣም አስገራሚ ሆኖ ነው ያገኘነው፤ ሌላም እንዲሁ ፈተናው ከጀመረበት ሰኞ ቀን አንስቶ እስከተጠናቀቀበት ረቡዕ ድረስ በምጥ ላይ እያለች ፈተናውን ሳታቋርጥ የተፈተነችው ተማሪ ለብዙዎች ግርምትን የፈጠረ ነበር" ሲሉ ምሳሌ ያነሳሉ። ሴቶች በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ሆነው ትምህርት ምን ያህል አስፈላጊና በመማር ራስን ለመለወጥ የተዘጋጀ ምዘና ግድ እንደሆነ ግንዛቤ መኖሩን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በበጎ መልኩ ተመልክቶታል ብለዋል። • ታሪክ እየቀየሩ ያሉት ሴቶች ትምህርትን ማጠናቀቅ ብቻ ሳይሆን ውጤቱም ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው፤ ታዲያ እነዚህ ተማሪዎች በእንዲህ ዓይነት ጊዜ የማይሰጥ ህመም ውስጥ ሆነው ምን ያህል ውጤታማ ይሆናሉ? ስንል ለዳይሬክተሯ ጥያቄ ሰንዝረን ነበር። እርሳቸውም "እነዚህ ሴቶች በእርግዝና ወቅት ተምረዋል፣ አጥንተዋል፣ በመሆኑም በፈተና ወቅት ባጋጠማቸው ምጥና ወሊድ ምክንያት አንድ ዓመት ወደኋላ እንቀርም ብለው ለፈተና መቅረባቸው ጥንካሬያቸውን ያሳያል" ሲሉ ምላሽ ሰጥተውናል። አክለውም በወሊድ ምክንያት በሚፈጠረው ህመም ምክንያት በትክክል ፈተናውን ለመውሰድ የማይችሉ ከሆነ በሚቀጥለው ጊዜ እንዲፈተኑ ሃሳብ ቀርቦላቸውም ነበር ብለዋል። • ትምህርት ዕድሜን እንደሚያስረዝም በጥናት ተረጋገጠ "ተማሪዎቹ አጥንተናል፣ ተዘጋጅተናል፣ መፈተን እንፈልጋለን እያሉ መከልከልም መብትን መጋፋት ነው" ሲሉ በተማሪዎቹ ፍላጎት ላይ ተመስርተው ባሉበት እንዲፈተኑ መደረጉን ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም ትዳር ላይ በመሆናቸው ከትምህርት የሚቀሩ ተማሪዎች በርካታ እንደነበሩ የሚጠቅሱት ወ/ሮ ሃረጓ ከእርግዝና ባሻገር በወሊድ ላይ ሆነው የመጡበትን አላማ ከግብ ለማድረስ ጥረት በማድረጋቸው እነዚህ ሴቶች አርአያ ናቸው ብለዋል። ዳይሬክተሯ እንደሚሉት ባለፈው ዓመትም ሆነ ከዚያ በፊት እንዲህ ዓይነት አጋጣሚዎች የነበሩ ሲሆን የዘንድሮው ግን ቁጥሩ ጨምሯል። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በፈተና ወቅት ሊከሰቱ ይችላሉ በማለት ቅድመ ዝግጅት ከሚያደርግባቸው አጋጣሚዎች አንዱ ወሊድ (ምጥ) ነው። በመሆኑም ምጥና ድንገተኛ ህመሞች ሲያጋጥሙ አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ከቀይ መስቀል ጋር በመሆን ቅድመ ዝግጅት አድርገው እንደነበርም ተናግረዋል። በዘንድሮው የ10ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 1.2 ሚሊየን የሚደርሱ ተማሪዎች ለፈተና የተቀመጡ ሲሆን ግምሽ ያህሉ ሴቶች መሆናቸውንም ገልፀውልናል።
news-46100893
https://www.bbc.com/amharic/news-46100893
"ምንም ከህዝብ የሚደበቅ ነገር አይኖርም" አዲሱ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሽመልስ አብዲሳ
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ ፍጹም አረጋ ከነገ ጀምሮ በኢንቨስትመንት ኮሚሽነርነት እንደሚቀጥሉ ገልጸው ምትካቸውን አቶ ሽመልስ አብዲሳን አስተዋውቀዋል።
በስራቸው በአዲስ መልክ የተቋቋመው ፕሬስ ሴክሬታሪያትም የመረጃ ፍሰቱን ቀጣይነት ባለውና በተደራጀ መልኩ ለማከናወን እንደሚያስችልም ተናግረዋል አዲሱ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሽመልስም ፕሬስ ስክሬቴሪዋን ቢልለኔ ስዩምን ባስተዋወቁበት አጭር የመግቢያ ንግግራቸው ለህበረሰተሰቡ ተገቢውን መረጃ በወቅቱና በተተቀናጀ መልኩ ለማዳረስ ሴክሬቴሪያቱ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው አንስተዋል። •የሴቶች መብት ታጋይዋ ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ማን ናቸው? •"ሌሎች ሴቶች ላይ የአሲድ ጥቃት ሳይ ይረብሸኛል፤ ህመሜን ያስታውሰኛል" ካሚላት መህዲ •ለቀናት የተዘጋው የአላማጣ- ቆቦ መንገድ ተከፈተ " ምንም ከህዝብ የሚደበቅ ነገር አይኖርም ፤ ካሁን በኋላ ከሚዲያ ተቋማት ጋር እንደአንድ ቤተሰብ ተባብረን አንሰራለን ብለዋል አቶ ሽመልስ ። የፕሬስ ሴክሬታሪዋ ቢልለኔ ስዩም ለመጀመሪያ ጊዜ በሰጡት መግለጫቸው ሴክሬቴሪያቱ በመንግስት ውሳኔዎችና አቋሞች ዙሪያ ወቅታዊ፤ ግልጽና ትክክለኛ መረጃ የመሰብሰብና የማሰራጨት ኃላፊነት አንደተሰጠው ተናግረዋል። በመንግሥት አሰራር ላይ የሚነሱ የህዝብ ምላሾች፤ አስተያየትና ግብረመልሶቸን የማቀናጀት፣ የመተንተንና የማሳደግ ስራም ይጠብቀዋል። ለተሻለ ግልጽነት ያለው ዘገባ በጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮና በመገናኛ ብዙሃን መካከል ያለውን ግንኙነት የማጠናከር ተግባርም ለሴክሬቴሪያቱ የተሰጠ ኃላፊነት እንደሚሆን ነው የገለጹት። በቅርቡም የሴክሬቴሪያቱን ዝርዝር አወቃቀር፤ ኃላፊነትና የመረጃ ፍሰት በተመለከተ መግለጫ እንደሚሰጡ አረጋግጠዋል። ፕሬስ ሴክሬቴሪዋ በቀላሉ ለመረዳት በሚያስችል መልኩ ለህዝብ ቅጂ በማቅረብ ገንቢ ግብዓቶችን በመውሰድ ትግበራዎችን የማስተካከል ዓላማ ስላለው የመንግሥት ባለአንድ ገጽ የዕቅድ ሰሌዳም አብራርተዋል። ባለአንዱ ገጽ የዕቅድ ሰሌዳ የመንግስት መሥሪያ ቤቶችን የሥራ አፈጻጸምና የሚመለከታቸውን የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ተጠያቂነት ለማረጋገጥ የተዘጋጀ ነው ብለዋል። "ተገቢውን መረጃ በወቅቱ ለህዝብ እናደርሳለን" አዲሷ ፕሬስ ስክሬቴሪ ቢልለኔ ስዩም
news-57271009
https://www.bbc.com/amharic/news-57271009
ባይደን የኮሮናቫይረስ መነሻ በአግባቡ እንዲመረመር አዘዙ
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የደኅንነት ባለሥልጣናት የኮሮናቫይረስ መነሻን ለማወቅ የሚያደርጉትን ጥረት "እጅግ እንዲያጠነክሩ" አዘዙ።
የሚካሄደው ምርመራ ቫይረሱ ከቤተ ሙከራ ነው ያፈተለከው የሚለውን መላ ምት ማጣራትም ያካትታል። ባይደን እንዳሉት የደኅንነት አባላቱ ቫይረሱ ከቤተ ሙከራ ያፈተለከ ነው በሚለው እና ከእንስሳት ወደ ሰው የተላለፈ ነው በሚሉት ሁለት መላ ምቶች ተከፋፍለዋል። ፕሬዝደንቱ የደኅንነት ቡድኑ በ90 ቀናት ውስጥ የደረሰበትን እንዲያሳውቃቸው ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። ቻይና፤ ቫይረሱ ከቤተ ሙከራ ነው የወጣው የሚለውን መላ ምት አትቀበልም። በአሜሪካ የቻይና ኤምባሲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ "ስም የማጥፋት ዘመቻውና ተጠያቂነትን ከራስ ማሸሹ በድጋሚ ተጀምሯል። ቫይረሱ ከቤተ ሙከራ የወጣ ነው የሚለው የሴራ ትንተናም እንዲሁ" ብሏል። ቫይረሱ በቻይናዋ ዉሃን ከተማ መጀመሪያ ላይ ከተከሰተ ወዲህ በዓለም ዙሪያ ከ168 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተይዘዋል። 3.5 ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ በተህዋሱ ምክንያት ሞተዋል። ቫይረሱ ዉሃን በሚገኝ የአሣ መሸጫ ገበያ ውስጥ እንደተነሳ በማጣቀስ ሳይንቲስቶች ቫይረሱ ከእንስሳት ወደ ሰዎች መተላለፉን ገምተዋል። ሆኖም ግን በቅርቡ በአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን የወጡ መረጃዎች ቫይረሱ ከቻይና ቤተ ሙከራ በድንገት እንዳመለጠ እየጠቆሙ ነው። ዶናልድ ትራምፕ ሥልጣን ላይ ሳሉ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ማይክ ፖምፔዮ እና ሌሎችም የአስተዳደሩ አባላት ቫይረሱ ከቤተ ሙከራ ስለማምለጡ በስፋት ይናገሩ ነበር። መላ ምቱ ይህ ነው የሚባል ተጨባጭ ማስረጃ ባይኖረውም፤ ቫይረሱ በቻይና ቤተ ሙከራ የተመረተው እንደ መሣሪያ ጥቅም ላይ ሊውል ነው ሲባልም ነበር። ቻይና የቫይረሱን መነሻ ለማወቅ የሚደረገውን ምርመራ ካልደገፈች ቫይረሱ እንዴት እንደመጣ ለማወቅ ያስቸግራል። ባይደን ሙሉና ግልጽ ምርመራ እንዲደረግ እያሳሰቡ ነው። ቫይረሱ ከቤተ ሙከራ ያመለጠ ከሆነ በቻይና እና አሜሪካ መካከል ያለው ግንኙነት መሻከሩ አይቀርም። ባይደን "ቫይረሱ ከቤተ ሙከራ ያመለጠም ይሁን ከእንስሳት ወደ ሰው የተሸጋገረ ምርመራ ሊደረግ ይገባል" ሲሉ መግለጫ ሰጥተዋል። ከሁለቱ መላ ምቶች አንዱ ላይ የበለጠ ትኩረት ለማድረግ በቂ መረጃ እንደሌለም ተናግረዋል። ስለዚህም የደኅንነት ባለሥልጣናቱ ማስረጃ ሰብስበው ተገቢውን ምርመራ እንዲያደርጉ አዘዋል።
news-46719277
https://www.bbc.com/amharic/news-46719277
የትራምፕ አማካሪ፡ የሜክሲኮ ግንብ ውጥን ውድቅ ከተደረገ ሰነባብቷል
በአሜሪካ እና ሜክሲኮ ድንበር ላይ ይገነባል ተብሎ የነበረው የኮንክሪት ግንብ ሃሳብ ውድቅ የተደረገው በትራምፕ የመጀመሪያዎቹ የፕሬዚዳንትነት ወራቶች ነው ሲሉ በቅርቡ ከሥራቸው የሚሰናበቱት የፕሬዚዳንቱ አማካሪ ተናገሩ።
ዶናልድ ትራምፕ ከምርጫ ቅስቃሳቸው ጀምሮ በሁለቱ ሃገራት አዋሳኝ ድንበር ላይ የኮንክሪት ግንብ ማቆም ስደተኞችን ለመግታት ሁነኛ አማራጭ ነው ይሉ ነበር። የትራምፕ አማካሪ ጆን ኬሊይ አስተያየት ግን ከፕሬዚዳንት ትራምፕ ጋር ይቃረናል። ትራምፕ በዚህ ወር ብቻ በትዊተር ገጻቸው ላይ ''ግንብ'' የሚለውን ቃለ ከ59 ጊዜያት በላይ ተጠቅመውታል። • ድምፅ ፈታዮቹ መረዋዎች • "በአንድ ሀገር ውስጥ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ ክልሎች ሊኖሩ አይገባም" ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋ ተሰናባቹ የትራምፕ አማካሪ ጆን ኬሊይ ምን አሉ? ፕሬዚዳንት ትራምፕን ለ17 ወራት ሲያማክሩ የቆዩት ተሰናባቹ አማካሪ ለኤልኤ ታይምስ በሰጡት ቃል፤ ከሜክሲኮ ወደ አሜሪካ የሚሻገሩ ስደተኞችን ለመቆጣጠር የትራምፕ አስተዳደር ከሚመለከታቸው ባለሙያዎች ምክርን ተቀብሎ ነበር። ''ባለሙያዎቹ ያሉት፤ 'አዎን በአንዳንድ ቦታዎች የሰዎችን እንቅስቃሴ የሚገድቡ አጥሮች ያስፈልጉናል። ቴክኖሎጂ እና በርከት ያለ የሰው ኃይል ነው የሚያስፈልገው ነው።'' ብለዋል ተሰናባቹ የፕሬዚዳንቱ አማካሪ። ''ፕሬዚዳንቱ አሁንም ስለ ''ኮንክሪት ግንብ'' ነው የሚያወሩት። ወዲፈት ግን ''የብረት አጥር'' የሚለውን ሃረግ መጠቀም ይጀምራሉ። አስተዳደሩ የኮንክሪት ግንብ ሃሳብን ውድቅ ካደረገው ወራት ተቆጥረዋል'' በማለት አስረግጠዋል። ትራምፕ ምን ብለው ነበር? ''ግዙፍ ግንብ እገነባለሁ፤ ማንም ሰው ከእኔ የተሻለ ግንብ መገንባት አይችልም። እመኑኝ። ከሜክሲኮ በሚያዋስነው ደቡባዊው ድንበር ላይ እጅግ ግዙፍ የሆነ ግንብ፤ በጣም አነስተኛ በሆነ ወጪ እገነባለሁ። የግንቡን ግንባታ ወጪ ሜክሲኮ እንድትሸፍን አደርጋለሁ።'' ይህን ያሉት ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከሶስት ዓመት ገደማ በፊት የምርጫ ቅስቀሳቸውን ባስጀመሩበት ጊዜ ነበር። በጊዜ ሂደት ግን ትራምፕ በግንቡ ግንባታ ላይ ያላቸውን አቋም እያለሰለሱ መጥተዋል። መስከረም ላይ ይገነባል ተብሎ የነበረው ግንብ ሙሉ ለሙሉ የኮንክሪት ሳይሆን የብረት ወይም የሽቦ አጥርን እንደሚጨምር ተናግረዋል። ፕሬዚዳንት ትራምፕ የኮንክሪት ግንቡንም ይሁን የብረት አጥሩን ለማስጀመር የሚያስችላቸውን በጀት ማግኘት አልቻሉም። ኮንግረሱ የግንቡን ግንባታ የካተተ የፍይናንስ ፍቃድ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆነም። • ትራምፕ ለ1.8 ሚሊዮን ስደተኞች ዜግነት ሊሰጡ ነው • አዲስ ዕቅድ ስደተኞችን ለማባረር ይህን ተከትሎም የትራምፕ አስተዳደር ለግንቡ ወይም ለአጥሩ ግንባታ በጀት እንዲያስገኝላቸው በማሰብ በሰሞኑ የበዓላት ወቅት አንዳንድ የአሜሪካ መስሪያ ቤቶች አገልግሎት መስጠት እንዲያቆሙ አስደርገዋል። ይህም ብቻ አይደልም፤ ትራምፕ የጠየቁት በጀት የማይጸድቅ ከሆነ ከሜክሲኮ ጋር የሚያዋስነውን ድንበር እንደሚዘጉ አስጠንቅቀዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱን መቀመጫ አብላጫ ቁጥር የያዙት ዲሞክራቶች እንደመሆናቸው መጠን ትራምፕ የጠየቁትን በጀት የማግኘታቸው ነገር አጠያያቂ ነው ተብሏል።
news-46738655
https://www.bbc.com/amharic/news-46738655
የቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ጌታቸው አሰፋ የእስር ትዕዛዝ እንደወጣባቸው ተገለፀ
ዋናው አቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ በትናንትናው ዕለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት የአምስት ወራት ሪፖርት የቀድሞው የደህንነት መስሪያ ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋን ለመያዝ ከትግራይ ክልል መንግሥት ትብብር ያለማግኘታቸውን ገልፀው ነበር።
ይህንን ተከትሎ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የሥራ ኃላፊዎች ዛሬ ከቀትር በኋላ በጽህፈት ቤታቸው በዚህና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተው ለቀረቡላቸው ጥኣቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል። የቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ጌታቸው አሰፋ የፍትህ ተሳዳጅ ናቸው ወይ? በሚል ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ በወንጀል የተጠረጠሩ እና የእስር ማዘዣ የወጣባቸው መሆኑን የጠቅላይ አቃቤ ጽህፈት ቤት ቃል አቀባይ አቶ ዝናቡ ቱኑ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተናግረዋል። •የሪፐብሊኩ ጠባቂ ሃይል መቋቋም ምን ያመለክታል? ከዚህም በተጨማሪ በቡራዩ፣ በቤንሻንጉል፣ በሐዋሳና በሶማሌ ክልል በነበሩት ብጥብጥ እና ሁከቶች የመንግሥት ኃላፊዎችና የፀጥታው መዋቅር ተሳትፈዋል ሲል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጽህፈት ቤት ተናግሯል። የጽህፈት ቤቱ ቃል አቀባይ አቶ ዝናቡ ቱኑ ለጋዜጠኞች እንዳሳወቁት የብሔር ግጭትን እና መፈናቀል እንዲከሰት አንዳንድ የመንግሥት እና የፀጥታ ኃላፊዎች በማቀድ እና በገንዘብ በማገዝ ጭምር ድጋፍ አድርገዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎችን የመለየት እና የመያዝ ሥራ እየተሰራ ነው። የድንበር ተሻጋሪ እና አገራዊ ጉዳት የሚያደርሱ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ፍቃዱ ፀጋ ሐዋሳ ላይ የነበረውን ግጭት በሦስት መዝገብ ምርመራ ሲደረግነት ቆይቶ በሁለቱ መዝገቦች ላይ ክስ ተመስርቷል ብለዋል። • በምዕራብ ኦሮሚያ የኦነግ ጦር አዛዥ ስለወቅታዊው ሁኔታ ምን ይላል? ተጠርጣሪዎቹ በከተማዋ በወላይታ እና በሲዳማ ብሔሮች መካከል ግጭት እንዲከሰት ያደረጉ እንዲሁም በማረሚያ ቤት የተፈፀመን ወንጀል ያከናወኑ ሲሆኑ ክስ ከተመሰረተባቸው መካከልም የቀድሞው የከተማዋ ከንቲባ ይገኙበታል። 75 ተጠርጣሪዎች ያሉበት መዝገብ ምርመራው አልተጠናቀቀም። የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን ለመቀበል ከነበረው ሥነ ሥርዓት ጋር በተያያዘ በቡራዩ እና አካባቢው ተከስቶ በነበረው ግጭት 37 ሰው የሞተ ሲሆን፤ በተተጨማሪ 26 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሞተዋል። ከሞት በተጨማሪ 315 ግለሰቦች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከ17 ሚሊዮን ብር በላይ ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል። ከዚህም ጋር በተያያዘ 649 ተጠርጣሪዎች ተይዘው የነበረ ሲሆን 320ዎቹ በወንጀሉ ለመሳተፋቸው ማስረጃ ባለመኖሩ እንዲለቀቁ ተደርጓል። 109 ተጠርጣሪዎች በግድያ በመሳተፍ እና በማነሳሳት ክስ ተመስርቷባቸዋል፤ እንዲሁም አስራ ሦስት በዋስ ተፈትተዋል። በአዲስ አበባ ደግሞ 'ቄሮ አይገባም' በሚል ግጭት ያነሳሱና የተሳተፉ 68 ሰዎች ክስ ተመስርቶባቸዋል። በቡራዩ በነበረው ግጭት አስቀድሞ የታቀደ ስለመሆኑ ምንም ዓይነት ማስረጃ አላገኝንም ያሉት ፍቃዱ፤ ኦነግን ለመቀበል ወደ አዲስ አበባ ይመጡ የነበሩ ወጣቶች አትገቡም እንገባለን በሚል ሙግት ግጭቱ ተለክሷል ብለዋል። ሐሰተኛ ወሬዎች መሰራጨታቸው ለግጭቱ መፋፋም ምክንያት ሆኗል ያሉት አቶ ፈቃዱ፤ የስድስት ዓመት ልጅ ተገድላ በኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሰንደቅ ዓላማ ተጠቅልላ መሞቷ መወራቱ ወንጀሉ ላይ እንዲሳተፉ የገፋፋቸው ሰዎች እንደነበሩ የገልፀው፤ የተባለው ድርጊት ስለመፈፀሙ ማስረጃ አላገኘንም ብለዋል። በሀሰት የስድስት ዓመት ልጅ በቡድን ስትደፈር አይቻለሁ ያለች ግለሰብ እንዲሁም የእህቴ ጡት ተቆርጧል ያለ ግለሰብም በሐሰት ወሬ ሰውን በማነሳሳት ክስ ተመስርቷል። በተጨማሪም መጪውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ በፌዴራል እና በክልል ማረሚያ ቤቶች ይገኙ ለነበሩ 530 የፌዴራል ታራሚዎች ይቅርታ ተደርጓል። •አቶ ጌታቸው አሰፋ የት ናቸው? የእስር ትዕዛዝ ወጥቶባቸዋል? በይቅርታው ተጠቃሚ ከሆኑ ታራሚዎች መካከል ከህፃናት ጋር አብረው የታሰሩ ታራሚዎች፤ ዕድሜያቸው ከስድሳ ዓመት በላይ የሆናቸው ታራሚዎች፣ ታማሚ ታራሚዎች የሚገኙበት መሆኑን የፌዴራል የይቅርታ እና ምህረት ቦርድ ኃላፊ አቶ ዘለቀ ተናግረዋል። የህገ ወጥ የገንዘብ እና የጦር መሳሪያ ዝውውር በተለያዩ ምክንያቶች እንዲበራከቱ ሆነዋል ያሉት የፅህፈት ቤቱ ቃል አቀባይ አቶ ዝናቡ ናቸው። የህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር በአንድ በኩል የህግ ማዕቀፉ የላላ መሆኑ በሌላ በኩል ደግሞ በየቦታው ያለው ግጭት ገበያውን ስላደረው ይሄንን የሚከላከል ኮስተር ያለ ህግ መረቀቁን ቃል አቀባዩ አክለው ገልፀዋል።
news-57237425
https://www.bbc.com/amharic/news-57237425
ዕፅ አዘዋዋሪው በለጠፈው የአይብ ፎቶ ምክንያት በፖሊስ ተያዘ
በእንግሊዝ አንድ ዕፅ አዘዋዋሪ በለጠፈው የአይብ ፎቶ ምክንያት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።
ግለሰቡ ስቲልቶን የተባለውን አይብ በእጁ ይዞ የተነሳውን ፎቶ ከለጠፈ በኋላ ፖሊስ ተከታትሎ በቁጥጥር ስር ሊያውለው ችሏል። ካርል ስቲዋርት የተባለው የ39 አመት ግለሰብ ተፈላጊው የዕፅ አዘዋዋሪ መሆኑ የታወቀው በጣት አሻራው ነው። ግለሰቡ በበይነ መረብ የመልዕክት መላላኪያ የለጠፈውን ፎቶ የእጅ አሻራ ከመረመረ በኋላ ነው ግለሰቡን ለማደን አሰሳውን የጀመረው። ይህ ግለሰብ ሂሮይን፣ ኮኬይን፣ ኬታሚንና ኤምዲኤምኤ የተባሉ አደንዛዥ ዕፆችን በማዘዋወርና ለተለያዩ አቅራቢዎች በማቅረብ ወንጀል 13 አመት ከስድስት ወር ተፈርዶበታል። ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈው የሊቨርፑል ክራውን ፍርድ ቤት ነው። ካርል ከዚህም በተጨማሪ የወንጀለኞችን ንብረቶች በማዘዋወር ክስም ተፈርዶበታል። ካርል ኢንክሮ ቻት በተባለው የመልዕክት መላላኪያ መንገድ ነበር ፎቶውን የለጠፈው ነገር ግን ፖሊስ መረጃውን በመበርበር በቁጥጥር ስር አውሎታል። ሊ ዊልኪንሰን የተባሉት የሜርሴሳይድ ፖሊስ መርማሪ እንዳሉት ቶፊ ፎርስ በተባለ የቅፅል ስም ይጠራ እንደነበርና ከፍተኛ የሚባል የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውርም ተሳታፊ ነበር። መርማሪው እንደሚሉት "ለስቲልቶን አይብ" የነበረው ፍቅር ለመውደቂያው ምክንያት ሆኗል። በእጁ ይዞት የነበረው የአይብ ፎቶን የጣት አሻራን በመመርመር የካርል አሻራ መሆኑን ፖሊስ ማረጋገጥ መቻሉን መርማሪው ገልፀዋል።
46806126
https://www.bbc.com/amharic/46806126
''መከላከያ በሌሎች ስፍራዎች ያሳየውን ትዕግስት በምዕራብ ጎንደርም መድገም ነበረበት''
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን በትናንትናው ዕለት ከመከላከያ ሠራዊት ጋር ተከሰተ በተባለ ግጭት የሰዎች ህይወት መጥፋቱን ተከትሎ የገንዳ ውሃ ከተማ በትናንትናው ዕለት የተቃውሞ ሰልፍ አስተናግዳለች።
ጎንደር የክልሉ ቃል አቀባይ አቶ አሰማኸኝ አስረስ ለቢቢሲ እንደገለጹት በግጭቱ ላይ የተሳተፉ አካላት እነማን እንደሆኑ ለማጣራት ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ወደቦታው ተንቀሳቅሷል። አቶ አሰማኸኝ ጨምረውም ''ሁኔታው በጣም አሳዛኝ ነው። ያለውን ሁኔታ በአግባቡ ተወያይቶ መተማመን ላይ እስከሚደረስ ድረስ ተጠብቆ ነው እንቅስቃሴ መጀመር የነበረበት። ነገር ግን መተማመን ሳይፈጠር ነው መከላከያ እንቅስቃሴ ሊያደርግ የሞከረው። ኅብረተሰቡ ደግሞ የራሱ ጥርጣሬ አለው፤ ምን እንደጫነ አያውቅም፤ ስለዚህ ልፈትሽህ አለ፤ ግጭት ተፈጠረ። በግጭቱም የንፁሃን ህይወት እጦት እና ቁስለት ተከስቷል።'' ብለዋል። ''ከሰሞኑ እንደምንሰማው በተለያዩ ቦታዎች ላይ ከልክ ያለፈ ትዕግስት ጭምር እያሳየ [መከላከያ] መተማ ላይ ግን ለተወሰነ ደቂቃ ወይንም ለውይይት መንገድ ባልሰጠ መልኩ፤ መተማመን ባለተደረሰበት ሁኔታ እንደዚህ ያለ እርምጃ መወሰዱ የሚያሳዝን ነው።'' ብለዋል የክልሉ የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ። በትናንትናው ሰልፍ የተሳተፉ የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ እንደገለፁት ግጭቱ አካባቢውን አቋርጠው ወደ ትግራይ ክልል ያመሩ ከነበሩ ንብረትነታቸው የሱር ኮንስትራክሽን ነው ከተባሉ የጭነት እና የግንባታ መኪናዎች ጋር የተገናኘ ነው። •የቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት ትውስታዎች በኢትዮጵያውያን ዓይን በመኪኖቹ እንቅስቃሴ ላይ ጥርጣሬ እንደገባቸው በመግለፅ ለማስቆም የፈለጉ የአካባቢው ነዋሪዎች መኪኖቹን ያጅቡ ከነበሩ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ጋር መፋጠጣቸውን ይህም ወደተኩስ እና ሞት ማምራቱን ለቢቢሲ የተናገሩት የከተማዋ ነዋሪ አቶ አገናኝ ካሱ ናቸው። "ትናንትን ቀን ላይ ጀምሮ መኪኖቹ ሲመጡ [ወጣቱ] ድንጋይ መወርወር ጀመረ። መከላከያ ሠራዊት ድንጋይ የሚወረውረው ወጣት ላይ ተኩስ ከፈተ። መጨረሻ ላይ አንዳንድ ሚሊሻዎችም መከላከያ ሠራዊት ላይ ተኩስ ከፈቱ" ሲሉ የግጭቱን ሒደት የሚያስረዱት አቶ አገናኝ፤ ከሠራዊቱ በኩል ሞትም ሆነ የመቁሰል አደጋ ይኑር አይኑር መረጃው ባይኖራቸውም ዕቃ ለመግዛት የወጡ ህፃናት እና በህዝብ መጓጓዣ በመሳፈር ላይ የነበሩ ሰላማዊ ዜጎች መሞታቸውን ይገልፃሉ። •"የመከላከያ ሰራዊትን እንቅስቃሴ የሚያግድ ስራ አንቀበልም" ዶ/ር ደብረፅዮን ሰልፈኞቹ ዛሬ "የህፃናት ግድያ ይቁም፥ መከላከያ ሰራዊት እየወሰደ ያለው እርምጃ ትክክል አይደለም፥ ሲያስጨፈጭፉን የነበሩ መኪኖች ከክልላችን ሊወጡ አይገባም" የሚሉ መፈክሮችን ማሰማታቸውንም አቶ አገናኝ ጨምረው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ህፃናት በጥይት ተመትተው ሆስፒታል ውስጥ ገብተው ማየታቸውን ሌላ የከተማው ኗሪ እና የሰልፉ ተሳታፊም ገልፀዋል። •የተነጠቀ ልጅነት የምዕራብ ጎንደር ዞን የፀጥታ እና አስተዳደር ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ግጭቱ የበርካቶችን ሞት እና ቁስለት ማስከተሉን ለቢቢሲ አረጋግጠው የሰለባዎቹ ቁጥር በትክክል ምን ያህል እንደሆነ ከመግለፅ ተቆጥበዋል። የፀጥታ ኃላፊው እንዳሉት የግጭቱ መንስዔ ናቸው የተባሉት ከአርባ በላይ ተሽከርካሪዎች ከገንዳ ውሃ ከተማ ወጣ ብለው አሁንም ቆመው የሚገኙ ሲሆን ቀጣይ ዕጣ ፈንታቸውን በሚመለከት የሚተላለፍ ውሳኔ ከህዝብ ጋር በሚደረጉ ውይይቶች ላይ የሚመሠረቱ ይሆናል። ቀዳሚ የትኩረታቸው አቅጣጫ "ለግጭት መንስዔ የሆነው ጉዳይ እንዴት መልክ ይያዝ" የሚለው መሆኑን የገለፁት አቶ ደሳለኝ ዓላማቸው "ሰው የማይሞትበትን አማራጭ መጠቀም ነው" ብለዋል። "መኪናዎች ለአንድ ቀንም ሆነ ለሁለት ቀን ይቁሙ፤ ኅብረተሰቡ ይወያይ። ለምን ዓላማ እንደሚገቡ፤ ምን እንደሚሰሩ እናስረዳው፤ ከዚያ በኋላ ወደሚፈልጉበት አቅጣጫ ይሄዳሉ።" ብለዋል።
news-49457672
https://www.bbc.com/amharic/news-49457672
ከመስመጥ አደጋ የተረፉት ሁለት ኤርትራዊያን ስደተኞች
ኤርትራዊያኑ ስደተኞቹ በኩረፅዮን ፀጋዘዓብና በክሪ መሐመድ አገራቸውን ጥለው የተሰደዱት "ሕይወታችን ይለወጣል" ብለው ነበር።
በኩረፅዮን ፀጋዘዓብ (በቀኝ) ብክሪ መሐመድ (ከግራ ሦስተኛው) እና ሌሎች ከጀልባዋ የተረፉ ኤርትራዊያን ስደተኞች ሊቢያ ከገቡ በኋላ ላለፉት ሁለት ዓመታት ከመዲናዋ ትሪፖሊ 120 ኪሎ ሜትር በምትርቀው ክሆምስ የስደተኛ ማቆያ አሳልፈዋል። እዚያም ከፀሐይ ብርሃን በሚያገኟት ትንሽ ጭላንጭል ውስጥ ተቆልፈው ነበር የቆዩት። • ለአፍሪካውያን ስደተኛ ልጆች አደገኛ የሆነው መጠለያ • አፍጋናዊቷ ስደተኛ በኢትዮጵያ ሕልማቸው የሜዲትራኒያን ባህርን አቋርጠው ወደ አውሮፓ መሻገር ነበር። በስደተኛ ማቆያው ውስጥ ያሳለፉትን አሰቃቂ ሕይወት ለማምለጥ ጀልባ ላይ ለመሳፈር እንደተገደዱ በኩረፅዮን ይናገራል። ባህሩን እንዲያሻግሯቸውም ለደላሎች ገንዘብ ከፍለዋል። ግን ምን ያህል እንደሆነ አልገለፁልንም። ሕገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪ ደላሎቹ ጀልባዋ በምሽት እንደምትነሳ ነገሯቸው። በርካታ ስደተኞች ያለቁበትን የሜዲትራኒያን ባህር ለማቋረጥ ምሽት ምቹ ሰዓት እንደሆነ አስረዷቸው። ሌላ አማራጭ ስላልነበራቸው ተስማሙ። ስለ ጀልባዋ ሁኔታ ምንም የሚያውቁት ነገር አልነበረም- እነሱ የሚያስቡት መዳረሻቸውን ነው። በእንጨት የተሠራ ጀልባ ውስጥ መሳፈራቸውን የነገራቸው አልነበረም፤ እነሱም አላወቁም። ይሁን እንጂ ለሦስት ሰዓታት ያህል እንደተጓዙ የባህሩ ውሃ ወደ ጀልባዋ መግባት ጀመረ። "አጠገባችን ባገኘነው እቃ ሁሉ ጀልባ ውስጥ የገባውን ውሃ እየጨለፍን ለማስወጣት ታገልን፤ ቢሆንም ውሃው በፍጥነት ጀልባዋን ሞላት" ይላል ስለነበረው ሁኔታ የሚያስታውሰው በኩረፅዮን። በዚያ ሰዓት አንድ የንግድ መርከብ እያለፈ ስለነበር ጀልባ ውስጥ ያሉት ሁሉ ለእርዳታ ጮኹ፤ ግን ጆሮ የሰጣቸው አልነበረም። ከዚያም ጀልባቸው ተሰብራ መስመጥ ጀመረች። ሁሉም እየዘለለ ወደ ባህሩ ገባ። ማንኛቸውም የመንሳፈፊያ ጃኬት እንኳን አለበሱም፤ የሚይዙት የሚጨብጡት ነገር አልነበረም። • በአገር ውስጥ ያለው መፈናቀል ሕገ ወጥ ስደትን አባብሷል? በኩረፅዮን እንደሚለው፤ ከመስመጥ ለመዳን መጀመሪያ ላይ የተሰበረ አንድ ጀሪካን በእጁ ጨምድዶ ያዘ። በዚያ ትንሽ ተንሳፎ እንደቆየ ለመንሳፈፍ የሚረዳው ሌላ እንጨት አገኘ። ይህም ሙሉ ሌሊቱን ለማለፍ ረዳው። ከአደጋው የታደጋቸው አንድ በአጠገባቸው ሲያልፍ የነበረ አሳ አጥማጅ ነው፤ አሳ አጥማጁ ወደ ትሪፖሊ ፖሊስ ጣቢያ አደረሳቸው። በአፍና በአፍንጫቸው ሲገባ ባደረው ውሃ ምክንያት ሁሉም ትውከት እያጣዳፋቸው ስለነበር አስቸኳይ የሕክምና እርዳታ ተደረገላቸው። በኩረፅዮን እና በክሪ እስካሁን በሊቢያ ትሪፖሊ ሆስፒታል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ከጉዳታቸው እያገገሙ ነው። "የተረፍኩት በፈጣሪ ኃይል ነው፤ እሱ እንድተርፍ ስለፈቀደ ብቻ! ምክንያቱም ዋና እንኳን አልችልም ነበር" ይላል። በክሪ በበኩሉ የሚረዳቸው ሰው ከማግኘታቸው አስቀድሞ ያነበሩትን ሰባት አሰቃቂና አስጨናቂ ሰዓታት ብዙም ማስታወስ እንደማይችል ይናገራል። የጀልባ መስመጥ አደጋው ካጋጠማቸው ሁለት ወራት ተቆጥረዋል፤ ነገር ግን ከአደጋው በተዓምር የተረፉት ሁለቱ ጓደኛሞች እስካሁን በጭንቀት ውስጥ ይገኛሉ። የወደፊት እጣ ፋንታቸው ምን እንደሆነ አያውቁም። "ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ጥሩ እንቅልፍ ተኝቼ አላውቅም። የጓደኞቼ፣ ጀልባው ላይ ተሳፍረው የነበሩት ሰዎች ፊት በሕልሜ ይመጣብኛል" ይላል በኩረፅዮን። "ስለ ሕይወቴም አብዝቼ እጨነቃለሁ። ምን እንደሚገጥመኝ አላውቅም። ምን ማድረግ እንዳለብንም አናውቅም " ሲል ጭንቀቱን ያስረዳል። ባሳለፍነው ሃምሌ ወር ላይ 300 የሚሆኑ ስደተኞችን ጭና ስትጓዝ የነበረችው ይህች ጀልባ ሰጥማ በትንሹ 115 የሚሆኑት ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።
42487666
https://www.bbc.com/amharic/42487666
ሁሉንም የምትመለከተው ቻይና፡ የዓለማችን መጠነ ሠፊው የደህንነት ካሜራ አውታረ መረብ
በቻይና በሚገኝ አንድ ከተማ እተጓዙ ነው። በትንሽ እርምጃ ርቀት አንድ፣ ሁለት ወይም ሦስት የደህንነት ካሜራዎች የሚያጋጥሞት ሲሆን በዚህ ወቅት ፖሊስ ስለ እርሶ ሙሉ መረጃ ለማግኘት ይችላል።
ቻይና "የዓለማችንን እጅግ ውስብስብ የደህንነት ካሜራ" እየሰራች ነው። 1.3 ቢሊዮን ህዝቧን ለመከታተልም በአሁኑ ወቅት 170 ሚሊዮን ካሜራዎች በመላ ሃገሪቱ በሥራ ላይ ውለዋል። በቀጣይ ሦስት ዓመታት ደግሞ 400 ሚሊዮን የደህንነት ካሜራዎች ይገጠማሉ ተብሎ ይጠበቃል። አብዛኛዎቹ እነዚህ ካሜራዎች እጅግ በረቀቁ ቴክኖሎጂዎች የታገዙ ናቸው። አንዳንዶቹ የሠው ፊት መለየት የሚያስችሉ ናቸው። ሌሎቹ ደግሞ የአንድን ሠው ዕድሜ፣ ዘር እና ጾታ መለየት ይችላሉ። ይህ ደግሞ ባለስልጣናት የመንገደኛን ምስል በመውሰድ ካላቸው መረጃ ጋር በማመሳከር ሙሉ መረጃ ከማግኘት በተጨማሪ እንቅስቃሴንም ለመቆጣጠር ይችላሉ። ዘዴው ተጠርጣሪ ተብሎ የተሰየምን ፊት ሲያገኝ ወደ መቆጣጠሪያ ክፍል የማንቂያ መልዕክት ያስተላልፋል። በዚያውም ለፖሊስ መልዕክቱን ያደርሳል። ለሙከራ ተብሎ የቢቢሲው ባልደረባ ጆን ሱድዎርዝ በቻይናዋ ጉይያንግ ከተማ ከሚገኙ ካሜራዎች በአንዱ ተለይቶ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ለመዋል የፈጀበት ሰባት ደቂቃ ብቻ ነበር። "ፊትን ከመኪናው ባለቤት፣ ዘመዶች እና ከሚገናኛቸው ሰዎች ጋር እናያይዛለን" ሲሉ አንድ ሚሊዮን ካሜራዎችን የሸጠው የዳሁአ ቴክኖሎጂ የጥናትና ምርምር ምክትል ፕሬዝዳንት ዪን ጁን ለቢቢሲ አስረድተዋል። "ብዙ ካሜራዎችን በመጠቀም በብዛት ማንን እንደሚያገኙም ማወቅ እንችላለን" ሲሉ ይገልጻሉ። ምንም መደበቅ ምንም መፍራት አያስፈልግም? እንደባለስልጣናቱ ከሆነ ይህ አስደናቂ የደህንነት ካሜራ ወንጀልን መከላከል ብቻ ሳይሆን ለመገመትም የሚረዳ ነው። "የግለሰቦችን መረጃ የምንመለከተው እነሱ የእኛን ድጋፍ ሲፈልጉ ብቻ ነው" ሲሉ በጉዪያንግ የፖሊስ ባልደረባ የሆኑት ዡ ያን ይገልጻሉ። "እነሱ ካልፈለጉት ባለን ትልቅ የመረጃ ቋት ውስጥ የሚቀመጥ ሲሆን አስፈላጊ ሲሆን ብቻ አውጥተን የምንጠቀመው ይሆናል" ብለዋል። ምንም መደበቅ የሌለባቸወ ዜጎች "ስለምንም መፍራት የለባቸውም" ሲሉም ጨምረው ያስረዳሉ። ይህ ሃሳብ ግን ሁሉንም አያስማማም። ጂ ፌንግ መንግሥትን በሚተቹት ግጥሞቹ ይታወቃል። ቤጂንግ ውስጥ በአርቲስቶች መኖሪያነት በምትታወቀው አካባቢ ይኖራል። እንደእርሱ ዕምነት ከሆነ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደጥቃት አድራሽ ተቆጥረዋል። "ሁሌም የሚከታተል እንዳለ ይሰማሃል" ሲል ለቢቢሲ ይገልጻል። "ምንም ነገር ሥራ ሁሌም የማይታዩ ዓይኖች እየተከታተሉህ ነው።" እነዚህ በቴክኖሎጂ የረቀቁ የደህንነት ካሜራዎች የፖሊስን ሥራ ቀላል አድርገዋል። "ይህ ነዋሪዎችን የመሰለል ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል" ይላል ገጣሚው። እንደሂዩማን ራይትስ ዎች ያሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እንደሚሉት የቻይና መጠነ ሠፊ መረጃ አሰባሰብ "ግላዊ መብትን" የሚጥስ እና "የነዋሪዎችን እንቅስቃሴ መከታተል እና መገመትን" ትኩረቱ ያደረገ ነው። በጥያቄዎች መካከል የሚደረግ ማስፋፋት የእነዚህ ካሜራዎች መመረት ብዙ ጥያቄዎችን አስነስቷል። "ምቾት የማይሰጥ ነገር አለው" ይላሉ የዳሁአ ቴክኖሎጂ ዳይሬክተር የሆኑት ዳንኤል ቻኡ ለቢቢሲ። "ቴክኖሎጂው በራሱ ሠዎች እንዲጠቀሙበት የተሰራ ቢሆንም በሽብርተኞች እጅ ከገባም የሚጎዳም ነገር አለው።" አሁን በትክክል እየሆነ ያለው ነገር በቻይና የደህንነት ካሜራዎች ቁጥር እያደገ መሆኑ ነው። እንደሮይተርስ ዘገባ ከሆነ ብዙ የቻይና እና የውጭ ኢንቨስተሮች የሠውን ፊት መለየት በሚችል የቴክኖሎጂ ዘርፍ ላይ በስፋት እየተሰማሩ ነው። አይኤችኤስ እንደተባለው ተቋም ከሆነ እ.አ.አ በ2016 ከደህንነት ካሜራ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ በቻይና 6 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ተደርጓል።
news-56081458
https://www.bbc.com/amharic/news-56081458
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሕዝቡ የህወሓት ኃይሎችን እንዳያስጠጋ አሳሰበ
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ክልሉ እንዳይረጋጋ ለማድረግ የሚሞክሩ "የተበተኑ የህወሓት ኃይሎችን" መጠጊያ እንዳይሰጥ አሳሰበ።
ጊዜያዊው አስተዳደር ማክሰኞ ምሽት ባወጣው መግለጫ ላይ "የተበተኑ" የህወሓት ኃይሎች በሕዝቡ ውስጥ ተሸሽገዋል በማለት አመልክቷል። በመግለጫው "የጥፋት ኃይሎች በመንደሮችና በከተሞች ውስጥ ተሰማርተው የሕዝቡን ሠላም በማናጋት ወደ ሌላ የከፋ ቀውስ እንዲገባ እየሰሩ ነው" ብሏል። በትናንትናው ዕለት፣ ማክሰኞ ፣ በትግራይ ክልል ቴሌቪዥን ላይ በቀረበው እና ከጊዜያዊው አስተዳደር የወጣው ይህ መግለጫ እንዳስጠነቀቀው፣ ሊወሰድ በሚችለው እርምጃ ሕዝቡ እንዳይጎዳ "የጥፋት ኃይሎቹን አሳልፎ እንዲሰጥ ወይም ለደኅንነቱ ሲል ራሱን ከእነዚህ ኃይሎች እንዲያርቅ" አሳስቧል። በተጨማሪም የክልሉ ነዋሪ ከምሽት 12 ሰዓት አስከ ንጋት 12 ሰዓት የተደነገገውን ሰዓት እላፊ ጨምሮ ሌሎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውሳኔዎችን እንዲያከብሩም አሳስቧል። መግለጫው ህወሓትን የተካው ጊዜያዊ አስተዳደር በክልሉ ጸጥታ ለማስፈን፣ የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባትና የህዝቡን መብቶች ለማስከበር እየሰራ መሆኑን ገልጾ ሕዝቡ እንዲደግፈው ጥሪ አቅርቧል። የትግራይ ክልልን ለ30 ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ በብቸኝነት ያስተዳደረው ህወሓት ባለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ በተናጠል ምርጫ ማካሄዱን ተከትሎ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር አለመግባባት ውስጥ ከገባ በኋላ በሰሜን ዕዝ ላይ በህወሓት ኃይሎች ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ወታደራዊ ግጭት መከሰቱ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ መንግሥት ሕግ ማስከበር ባለው ወታደራዊ ዘመቻ በሦስት ሳምንት ውስጥ የክልሉን ዋና ከተማ መቀለን በመቆጣጠር የህወሓት አመራሮችን ከስልጣን አስወግዷል። የፌደራል ሠራዊት በህወሓት ኃይሎች ላይ ወታደራዊ ዘመቻ በከፈተበት ጊዜ የፌደሬሽን ምክር ቤት የትግራይ ክልል ምክር ቤትና አስተዳደር እንዲበተን በማዘዝ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ተደርጓል። ከዚህ በኋላም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህወሓት ኃይልን መሠረት ያደረገ የአመጻ ተግባር ላይ መሳተፉን ማረጋገጡን በመግለጽ ሰርዞታል። በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች አሁንም አልፎ አልፎ ግጭቶች እንደሚያጋጥሙ የተነገረ ሲሆን ባለፈው ሳምንት በተለያዩ ከተሞች ተቃውሞ ተቀስቅሶ ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል። ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በርካታ የክልሉ ነዋሪዎች ለተለያዩ ሰብዓዊ ቀውሶች መጋለጣቸው ይታወቃል። ከ60 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለው ወደ ሱዳን ሲሰደዱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ደግሞ የለጋሽ ድርጅቶችን ድጋፍ ጠባቂ መሆናቸውን የተለያዩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በመግለጫዎቻቸው አመልክተዋል።
news-57340386
https://www.bbc.com/amharic/news-57340386
በታንዛንያ 'ጠበቅ ባለ ሱሪ' ምክንያት ከፓርላማ የተባረሩት የምክር ቤት አባል ጉዳይ ቁጣን ቀሰቀሰ
በታንዛንያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ሴት ፖለቲከኛ በሱሪያቸው ምክንያት ከፓርላማው መባረራቸው ቁጣን ቀስቅሷል።
የታንዛንያ ሴት ምክር ቤት አባላት ይፋዊ የሆነ ይቅርታም ያስፈልጋል እያሉ ነው። አንድ የፓርላማው አባል በያዝነው ሳምንት ማክሰኞ ሴቶች በአለባበሳቸው ምክንያት ፓርላማውን እየዘለፉት ነው ሲሉ ወቅሰው ነበር። በዚህም አላበቁም "አፈ ጉባኤ ለምሳሌ ያህል ቢጫ ሸሚዝ ያደረገችውን እህቴን ሱሪዋን ይመልከቱት" በማለት ሁሴን አማር የተባሉት የምክር ቤት አባል በቁጣ ተናገሩ። ይህንንም ተከትሎ የፓርላማው አፈ ጉባኤ ኮንደስተር ሲችዋሌ የተባሉትን የፓርላማ አባል እንዲወጡ ነገሯቸው። "ቤትሽ ሂጂና በስርዓት ለብሰሽ መጥተሽ ትሰበሰቢያለሽ" በማለት አፈጉባኤ ጆብ ንዱጋይ ተናገሩ። አፈጉባኤው አክለውም በሴቶች የፓርላማ አባላት አለባበስ ላይ ወቀሳ ሲቀበሉ ይህ የመጀመሪያቸው እንዳልሆነና "ያልተገባ ልብስ የለበሱ" የፓርላማ አባላት መግባት እንዲከለከሉም ለምክር ቤቱ ህግ አስከባሪ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። ሴት የፓርላማ አባሏን "አለባበሷ ያልተገባ ነው" ያሉት ሁሴን ምን እንደሆነ ዝርዝር ባይናገሩም የምክር ቤቱን የአለባበስ መመሪያ ጠቅሰዋል። በመመሪያው መሰረት ሴቶች ሱሪ እንዲለብሱ ቢፈቅድም ጠበቅ ያለ መሆን የለበትም በማለት ሁሴን ተከራክረዋል። ቢቢሲ አስተያየታቸውንም ፈልጎ ቢጠይቅም ግለሰቡ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም። ጃኩሊን ንጎንያኒና ስቴላ ማንያንያ በሚባሉ የሴት የምክር ቤት አባላት የሚመራ ቡድንም የተቋቋመ ሲሆን የፓርላማው ውሳኔ ትክክልም አይደለም ሲሉ ተቃውመውታል። የኮንደስተር ሲችዋሌ አለባበስ ምንም ስህተት የለውም ሲሉም ፓርላማው ይቅርታ እንዲጠይቅ እየሞገቱ ነው። ይህ ሁኔታ በአለም ላይ ባሉ ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ከፍተኛ ውግዘትን እያስተናገደ ይገኛል። በርካታ ወንዶች የሴቶችን አለባበስ ለመቆጣጣር እንደሚፈልጉ ፍንትው ያለ ማሳያ ነው ብለዋል።
news-41897059
https://www.bbc.com/amharic/news-41897059
ወባን በትንፋሽ መለየት የሚያስችለው ቴክኖሎጂ ተስፋ እንዳለው ተገለፀ
ትንፋሽን ለመሣሪያው በመስጠት ብቻ ወባ መኖር አለመኖሩን መለየት የሚያስችለው ቴክኖሎጂ በአፍሪካ ሙከራ እንደተደረገበት ታውቋል።
ሙከራው ወባ በሚታይባቸው አካባቢዎች በሚኖሩ ሕፃናት ላይ ተሞክሮ ተስፋ ሰጭ ሆኖ ቢገኝም መሻሻል ያለባቸው ነገሮች እንዳሉ ተገልጿል። መሣሪያው የወባ አሰራጭ የሆነችው ትንኝ የሚስባትን ተፈጥሯዊ ሽታ ተክትሎ ነው በሽታውን የሚያጣራው። ሳይንቲስቶቹ እንደሚናገሩት የወባ ትንኝን የሚስበው የተፈጥሮ ሽታ የወባ በሽታ ባለባቸው ሰዎች ላይ የሚታይ ነው። ምንም እንኳ መሣሪያው መሻሻል ቢኖርበትም በጣም ርካሽ የሆነ የወባ መመርመሪያ መሣሪያ እንደሚሆን ግን እየተነገረ ይገኛል። ልዩ ሽታ ሙከራ ላይ ያለው መሣሪያ በዋናነት ስድስት ለየት ያሉ ሽታዎችን የሚለይ ሲሆን ይህም በበሽታው ተጠቂ የሆነን ሰው እንዲለይ ያስችላል። ተመራማሪዎች ይህንን በመጠቀም ከማላዊ በሽታው ያለባቸውን እና ነፃ የሆኑ 35 ሕፃናትን በመመልመል ሙከራ አድርገዋል። ከተመረመሩት ሕፃናት መከካል ሃያ ዘጠኙ በትክክል ውጤታቸው ታውቋል። ይህም ማለት መሣሪያው 83 በመቶ ሙከራውን በድል ማጠናቀቅ ችሏል። መሣሪያውን አሻሽለው በቅርቡ ሙሉ በሙሉ ውደ ሥራ እንደሚያስገቡ በማሰብ፤ውጤቱ አኩሪ ባይሆንም እጅግ ተስፋ ሰጭ ነው ይላሉ ተመራማሪዎቹ ፈጣንና ቀላል የወባ መመርመሪያ መሣሪያዎች ገበያው ላይ ቢኖሩም አሁንም ውስንነት አላቸው ሲሉ ተመራማሪዎቹ ይከራከራሉ ። ደም ምርመራ ሕክምና ባልተስፋፋባቸው አካባቢዎች ውድ እና አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። ይህኛው መሣሪያ ግን ደም መውሰድ ሳይጠይቅ በቀላሉ ውጤት ማሳወቅ ይችላል።
51651424
https://www.bbc.com/amharic/51651424
ጀርመን 'በገዛ ፈቃድ ራስን የማጥፋት' ሕጓን አላላች
ጀርመን ዛሬ ራስን በሐኪም ድጋፍና በገዛ ፈቃድ ማጥፋት የሚከለክለውን ሕጓን ሽራለች።
ሕጉ ላለፉት አምስት ዓመታት ሲሠራበት ቆይቷል። የጀርመን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰዎች ፈቃዳቸውን መከልከል ሕገ መንግሥታዊ አይደለም ሲል ውሳኔ አስተላልፏል። •የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ማስጠንቀቂያ ምን ያህል ተጨባጭ ነው? •ሆስኒ ሙባረክና የአዲስ አበባው የግድያ ሙከራ በጀርመን በርካታ ሰዎች ተደራጅተው "በገዛ ፈቃድና በሐኪም እርዳታ ራስን ማጥፋት የሚከለክለው ሕግ ሊቀለበስ ይገባል ሲሉ ነበር። ፍርድ ቤትም ቅሬታቸውን ሰምቷል። ጀርመን ይህን ከልካይ ሕግ ከአምስት ዓመት ከማውጣቷ በፊት በሐኪም የሚደገፍ ሕይወትን የማቋረጥ ውሳኔን ትፈቅድ ነበር። የንግድ መልክ ያለውና ራስን በሐኪም እርዳታ የማጥፋቱን ነገር ቆየት ብላ ነው ሕገ ወጥ ያደረገችው። ይህን ተከትሎ በርካታ ጀርመናዊያን ከዚች ዓለም 'በሰላምና በጤና' ለመሰናበት ሲቆርጡ ወደ ጎረቤት ስዊዘርላንድና ኔዘርላንድ ለመጓዝ ይገደዱ ነበር። በጀርመን ሕይወትን በማጥፋት ጉዳይ አማካሪ የነበሩ ማዕከሎች እስር በመፍራት ተዘግተው ቆይተዋል። ቀደም ያለው ሕግ በቀጥታ ራስን በሐኪም እርዳታ ማጥፋትን ባይከለክልም በይበልጥ የሕይወት ጉዳይ የንግድ መልክ እንዳይዝ በሚል ራስን ከማጥፋት ጋር የሚያግዙ ተቋማትን የሚቀጣ አንቀጽ እንደነበር ተዘግቧል። "ራስን በሰላም ከዚች ምድር ለማሰናበት ሲፈልጉ እናግዝዎታለን" የሚል ንግዶችና የሕክምና ማዕከላትን በቀጥታ የሚከለክለው ሕግ በተዘዋዋሪ ራስን በሐኪም እርዳታም ቢሆን ማጥፋትን ወንጀል አድርጎት ቆይቷል። በዚህ አሁን በተሻረው የወንጀለኛ ሕግ አንቀጽ ላይ "ማንኛውንም እገዛ ገንዘብ ለማግኘት ሲባል ማድረግ..." የሚል ስለተካተተበት ባለፉት አምስት ዓመታት ሐኪሞች ደንበኞቻቸውን ራሳቸውን እንዲያጠፉ ለማገዝ ሳያስችላቸው ቆይቷል። •ኮሮናቫይረስ ከአውሮፓ አገራት አልፎ አፍሪካዊት አገር አልጄሪያ ደረሰ •የቴዲ አፍሮ ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር ጉዞ... በ80ዎቹ ተመሳሳይ ሕይወትን በሰላም የማሰናበት እርዳታ ሲሰጡ የቆዩት የሕክምና ሥነምግባር ጉዳዮች ተንታኝ ጊታ ኒውማን ለቢቢሲ እንደተናገሩት በሐኪም እርዳታ የገዛ ነፍስን ማጥፋት ተባባሪዎችን በ5 ዓመት ያስቀጣ ነበር። በሕክምና ስሙ 'ዩቴኒዚያ' የሚል ስም ያለው ይህ በሐኪም እርዳታና በገዛ ፈቃድ ንፍስን የማሰናበት ሂደት በብዙ የዓለም አገራት ወንጀል ነው። ሆኖም በአውሮፓ እነ ኔዜርላንድስ፣ ቤልጂየም፣ ሉክዘምበርግና ስዊዘርላንድ ሕጋዊ አድርገውታል። ኔዘርላንድስ ቤልጂየምና ሉክዘምበርግ ድርጊቱን የፈቀዱ ቢሆንም ጥብቅ ክትትል ያደርጉበታል። ስዊዘርላንድ በበኩሏ ራሱን የሚያጠፋው ሰው ያን እንዲፈጽም የሚያደርገው ሐኪም ከራስ ወዳድነት ባልመነጨ ሁኔታ እስካገዘው ድረስ የሟችን መብት ታከብራለች። ፖርቹጋል በቅርቡ ራስን በሐኪም እርዳታ የማሰናበትን ሁኔታ ትፈቅዳለች ተብሎ ይጠበቃል። ጀርመን ራስን በሐኪም እርዳታ የማጥፋት ጉዳይ አነጋጋሪ የሆነው ከናዚ ታሪክ ጋር በመተሳሰሩ ነው። ናዚ የአካልና የአእምሮ ጉድለት የነበረባቸውን ሦስት መቶ ሺ ሰዎችን በተመሳሳይ መንገድ አሰናብቷል።
news-53381702
https://www.bbc.com/amharic/news-53381702
በእንግሊዝ ተወልደው ያደጉ ጥቁር መንታዎች ወደማያውቋቸው አገራት እንዲባረሩ ተወሰነ
በለንደን ተወልደው በመንግሥት ይዞታ ስር ባለ ማደጎ ቤት ያደጉ መንታ ጥቁር ወንድማማቾች ወደተለያያዩ የማያውቋቸው የካሪቢያን አገራት እንዲባረሩ ተወስኗል።
የሃያ አራት አመት ወንድማማቾቹ ዳሬልና ዳሬን ሮበርትስ በፈፀሙት ወንጀል እስር ተፈርዶባቸው የነበረ ሲሆን አንደኛው ወንድሙ ከእስር ሲለቀቅም ውሳኔው ተፈፃሚ ይሆናል ተብሏል። የዳሬል ጠበቃ በበኩላቸው ደንበኛቸው የተፈረደበትን እስር እንዳጠናቀቀና እንግሊዛዊ ዜግነትም እንዳለው በመግለፅ ተከራክረዋል። ይሄንን ጉዳይ የሚመለከተው የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከአገር እንዲወጡ ውሳኔ አለማስተላለፉን ቃለ አቀባዩ ተናግረዋል። ሁለቱም ወንድማማቾች ከሃገር ለማስወጣት ትዕዛዝ እንዳልተላለፈ ቃለ አቀባዩ ቢናገሩም ቢቢሲ ለአንደኛው ልጅ ከዚሁ መስሪያ ቤት ከአገር እንዲወጣ የተላለፈለትን የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ አግኝቷል። መንታዎቹ የተወለዱት በምዕራብ ለንደን ሲሆን ወላጆቻውም ስደተኞች ሲሆኑ የመጡትም ከካሪቢያን ደሴቶች ከሆኑት ዶሚኒካና ግሬኔዳ ነው። ወላጆቻቸው እንግሊዛዊ ዜግነት የላቸውም ተብሏል። እናታቸው በ13 አመታቸው መሞቷን እንዲሁም አባትየውም ወደ ዶሚኒካ መመለሱን ተከትሎ በመንግሥት ይዞታ ስር ባለ የእንክብካቤ ማእከል ተወስደው በዚያው ነው ያደጉት። ዳሬል በአንድ ግለሰብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረሱ በ17 አመቱ የስድስት አመት እስር ተፈርዶበት ነበር። ከእስር ሲለቀቅም ወደ ዶሚኒካን ሪፐብሊክ እንዲሄድ ትዕዛዝ እንደደረሰውም ተገልጿል። ባለስልጣናቱ አባቱ አለበት ወደተባለበት ዶሚኒካ ደሴት ለመላክ በሚል ተሳስተው ወደ ዶሚኒካን ሪፐብሊክም እንዲሄድ ማድረጋቸውንም ተናግሯል። አባቱም ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለውም አስታውቋል።ወንድሙ ዳሬን በበኩሉ በተለየ ወንጀል እስር ቤት ይገኛል። ከእስር ሲወጣም የእናቱ ትውልድ ቦታ ወደሚባለው ግሬናዳ እንዲሄድ ትእዛዝ ደርሶታል። ከመንትዮቹ በተጨማሪም የእንግሊዝ ዜግነት ከሌላቸው ቤተሰቦች የተወለዱና ከአመት በላይ እስር የተፈረደባቸው ልጆች ከአገር እንዲባረሩ ተወስኗል። የሌላ አገር ዜጎች ልጆች ሆነው በእንግሊዝ መወለዳቸው ዜግነት እንዲያግኙ ቢያግዛቸውም በመወለዳቸው ብቻ ወዲያው ዜግነት የሚያገኙበት ሁኔታ የለም። የመንታዎቹ እህት ፍሬያ ቫሊ ሮበርትስ ይህ ሁኔታ በጣም ያበሳጫት ሲሆን "አገር አልባ አድርጓቸዋል" ብላለች። "ይሄ ስድብ ነው። ለምን ሁለት ወንድሞቼን ብቻ፤ አስራ አንድ ነን ሁላችንንም ከአገር ያባርሩን" ብላለች። ፍሬያ አይተውት የማያዉቁት አገር መላካቸውና መመለስም አለመቻላቸውም እንዳስጨነቃትም አልደበቀችም። የዳሬል ጠበቃ አንድሪው ስፔርሊንግ ይህንን ሁኔታም በጎርጎሳውያኑ 18ኛውና 19ኛው ክፍለ ዘመን ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦች ወደ አውስትራሊያ ግዞት የሚፈፀምበትን ሁኔታ ያስታውሰኛል ብለዋል። ደንበኛው እንግሊዛዊ መሆኑንም በመግለፅ እስሩን እንዳጠናቀቀና በተሃድሶ የሚያምን ማህበረሰብ እንደመሆኑ መጠን ድጋፍ ሊሰጠው ይገባልም በማለት ከአገር እንዲባረሩ መወሰኑ ኢ-ፍትሃዊ ነው ብለዋል። ሌሎች የቤተሰብ አካላትም መንትዮቹ እንግሊዝ እንዲቆዩና ውሳኔው እንዲቀለበስ ለማድረግ ፊርማ እያሰባሰቡ ነው።
41979679
https://www.bbc.com/amharic/41979679
የዚምባብዌ ጦር ገዢው ፓርቲ ላይ በሚደረገው ጣልቃ ገብነት ላይ ማስጠንቀቂያ ሰጠ
የዚምባብዌ የጦር ኃላፊ የሃገሪቱ ገዢ ፓርቲን ለማጥፋት የሚንቀሳቀሱ ድርጊታቸውን እንዲያቆሙ ካልሆነ ደግሞ ጦሩ ጣልቃ እንደሚገባ አስጠነቀቁ።
የዚምባብዌ ጦር ኃላፊ ጄነራል ኮንስታንቲኖ ቺዌንጋ ብዙም ያልተለመደው የጣልቃ ገብነት ጉዳይ የተከሰተው ሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ምክትላቸው ኤመርሰን ምናንጋግዋን ከስራ ካሰናበቱ በኋላ ነው። ከ90 ስራ ባልደረቦቻቸው ጋር ለጋዜጣዊ መግለጫ የቀረቡት ጄነራል ኮንስታንቲኖ ቺዌንጋ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የማንንም ስም አልጠቀሱም። የሙጋቤን ቦታ ሊተኩ ይችላሉ ሲባል የነበሩት ምናንጋግዋ ሸሽተው ሃገሪቱን ጥለው ወጥተዋል። አሁን የፕሬዝዳንት ሙጋቤ ባለቤት ግሬስ ሙጋቤ ባለቤታቸውን ለመተካት ቅድሚያውን አግኝተዋል። ምናንጋግዋንም "ጭንቅላቱ ሊደበደብ የሚገባ እባብ" ሲሉ ገልጸዋቸዋል። ባላቸው ብልህ አስተሳሳብ "አዞው" በሚል ስም የሚታወቁት ምናንጋግዋ "ዛኑ ፒ ኤፍ ፓርቲ ያንተና የሚስትህ እንደፈለጋችሁ የምታደርጉት የግል ንብረታችሁ አይደለም" ሲሉ ሙጋቤን ተችተዋል። በጦሩ ዋና መስሪያ ቤት መግለጫ የሰጡት ጄነራል ቺዌንጋ፤ በነጻነት ትግሉ ውስጥ የነበሩ እና እንደምናንጋግዋን ያሉ ሰዎችን ማባረር በትዕግስት የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም ብለዋል። ግሬስ ሙጋቤና ምክትል ፕሬዝዳንት ኤመርሰን መናንጋግዋ ቀጣይ ፕሬዝዳንት ሊሆኑ ይችላሉ ሲባል ነበር "በነጻነት ትግሉ ውስጥ ያለፉና እና የፓርቲው አባላት የሆኑት ሰዎች ላይ ያነጣጠረው የማባረር ስራ መቆም አለበት" ብለዋል። "ከአሁኑ ስራ ጀርባ ያሉ ሰዎች ሊገነዘቡት የሚገባው ጉዳይ አብዮታችንን በተመለከተ ጦሩ ጣልቃ ከመግባት ወደኋላ አይልም" ብለዋል። ምናንጋግዋ ቀደም ሲል የመከላከያ እና የብሄራዊ ደህንነት ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል። ሙጋቤ በበኩላቸው "ጀነሬሽን 40" (የአርባዎቹ ትውልድ) የሚባለው የዚምባብዌ ወጣት ፖለቲከኞች ድጋፍ አላቸው። በፖለቲከኞች መካከል ያለው እሰጣ አገባ "ሃገሪቱ ላላፉት አምስት ዓመታት የተጨበጠ ዕድገት እንዳታስመዘግብ አድርጓታል" ሲሉ ጄነራል ቺዌንጋ ተናግረዋል። በችግሩ ምክንያት ዚምባብዌ "በገንዘብ እጥረት፣ ግሽበትና በሸቀጦች ዋጋ መጨመር" እንድትሰቃይ አድርጓታል።
news-49267565
https://www.bbc.com/amharic/news-49267565
የውሃ እጥረት ዋነኛው የዓለማችን ስጋት
የዓለም ሕዝብ ቁጥር መጨመር፣ የሥጋ ተመጋቢዎች አሃዝ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍ እያለ መሄድ እንዲሁም እያደገ የመጣው ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የዓለማችን የውሃ ሃብት ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ነው።
ተለይተው በታወቁ 400 የዓለማችን ክልሎች ውስጥ ሰዎች ከፍተኛ በሚባል የውሃ እጥረት ውስጥ የሚኖሩ ሲሆን፤ ሁኔታው ይሻሻላል ተብሎ እንደማይጠበቅ መቀመጫውን ዋሽንግተን ዲሲ ያደረገው የዓለም ተፈጥሯዊ ሃብቶች ኢንስቲቲዩት የጥናት ውጤት ያሳያል። • በዓመት አንዴ ብቅ የምትለው ከውሃ በታች ያለችው መንደር • የንፁህ ውሃ ችግር ካለባቸው ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ናት በጥናቱ መሰረት የውሃ እጥረት ከግጭቶችና ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ጋር ሲደመር በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች ከመኖሪያ መንደራቸው እንዲፈናቀሉ ምክንያት ይሆናል። ከሜክሲኮ እስከ ቺሊ፣ ከአፍሪካ በከፍተኛ የቱሪስት ፍሰታቸው እስከሚታወቁት ደቡባዊ አውሮፓና ሜዲትራኒያን ክልሎች ድረስ በተደረገው ጥናት ምን ያክል ውሃ ከከርሰ ምድር እንደሚወሰድና ምን ያክሉ ደግሞ በአግባቡ ጥቅም ላይ እንደሚውል ተመልክቷል። ግኝቱም የዓለማችን የውሃ አቅርቦት አሳሳቢ በሚባል ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ያሳያል። ዓለም አቀፋዊ ስጋት አንድ ሦስተኛ የሚሆነው 2.6 ቢሊዮን የዓለማችን ህዝብ ከፍተኛ የውሃ እጥረት የሚያጋጥመው ሲሆን ከዚህ ውስጥ 1.7 ቢሊዮን የሚሆኑትና በ17 ሃገራት ውስጥ የሚገኙት ደግሞ እጅግ የከፋ የውሃ እጥረት ይጋረጥባቸዋል ተብሎ ተሰግቷል። በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ ሞቃታማ ሃገራት ለውሃ እጥረት የተጋለጡ የተባሉ ሲሆን ህንድ በምትከተለው የተዛባ የውሃ አጠቃቀም ምክንያት የከፋ የውሃ እጥረት እያጋጠማት እንደሆነ ተገልጿል። ፓኪስታን፣ ኤርትራ፣ ቱርክሜንስታን እና ቦትስዋና ደግሞ እጅግ የከፋ የውሃ እጥረት ውስጥ እንደሆኑ ጥናቱ ጠቁሟል። ይህ መረጃ የመጣው የዓለማቀፉ ተፈጥሯዊ ሃብቶች ኢንስቲቲዩት ሃገራት ካላቸው የውሃ ሀብት አንጻር ምን ያክሉን እንደሚጠቀሙ ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው። ሃገራት የሚጠቀሙት የውሃ መጠን ከ80 በመቶ ከፍ ካለ እጅግ የከፋ ውሃ ችግር እንደሚያጋጥማቸው የሚያሳይ ሲሆን ብዙ ሃገራት የሚገኙበትና አሳሳቢ የተባለው ከ40 እስከ 80 በመቶ ያለው ነው። • በክረምት ሲዘንብ የመሬት ሽታ ለምን ያስደስተናል? የጥናቱ ዋነኛ ተሳታፊ የሆኑት ሩትገር ሆፍስት ለቢቢሲ እንደተናገሩት በህንድ ያለው ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ የሚባል ነው። በመረጃው መሰረትም ህንድ በውሃ እትረት ከዓለም 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ምንም እንኳን በአሁኑ ጊዜ አሳሳቢ የሚባል ችግር ባይኖርም ሜክሲኮ የውሃ አጠቃቀሟን ካላስተካከለች ከህንድ የባሰ የውሃ እጥረት እንደሚያጋጥማት ጥናቱ ጠቁሟል። ከዚህ በተጨማሪም ምንም እንኳን ቻይና እና ሩሲያ እንደ ሃገር ከውሃ እጥረት ነጻ ናቸው ቢባሉም ዋና ከተሞቻቸው ቤዢንግ እና ሞስኮ እጅግ ከፍተኛ የውሃ እጥረት እንዳለባቸው ተገልጿል። ጣልያን እና ስፔንን ጨምሮ ደቡባዊ የአውሮፓ ሃገራት በሚያስተናግዱት ከፍተኛ የጎብኚ ቁጥር ምክንያት የውሃ ሃብታቸው ላይ ጫና እያሳደሩ ነው። በተለይ ደግሞ ደረቅ የሚባለው የዓመቱ ወቅት ሲመጣ ችግሩ በእጅጉ እንደሚባባስም ተጠቁሟል። ምዕራባዊ የደቡብ አፍሪካ ክፍሎች፣ 10 የቦትስዋና ክልሎች፣ አንዳንድ የናሚቢያ አካባቢዎችና አንጎላ ከፍተኛ የውሃ እጥረት እንደሚያጋጥማቸውም መረጃው ያሳያል። ከአውሮፓውያኑ 1961 እስከ 2014 ድረስ በዓለማችን ያለው የከርሰ ምድር ውሃ እና የገጸ ምድር ውሃ የመጠቀም ዝንባሌ በ2.5 እጥፍ ጨምሯል። ተክሎችን ለማብቀል የምንጠቀመው ውሃ መጠንም ባለፉት 50 ዓመታት ከእጥፍ በላይ ጨምሯል። • የ21ኛው ክፍለ ዘመን ነዳጅ. . . ውሃ! በመስኖ የሚለሙ ተክሎችና የተለያዩ ምርቶች ደግሞ በየዓመቱ 67 በመቶ የሚሆነውን የውሃ ፍጆታ ድርሻ ይወስዳሉ። በ2014 የተለያዩ ትልልቅ ኢንዱስትሪዎች የተጠቀሙት የውሃ መጠን በ1961 ከነበረው ጋር ሲነጻጸር በሦስት እጥፍ ጨምሯል። በሌላ በኩል የዓለማችን ህዝብ በቤት ውስጥ የሚጠቀመው ውሃ መጠን ባለፉት አርባ ዓመታት በስድስት እጥፍ ጨምሯል። ነገር ግን ተክሎችን ለማብቀል ጥቅም ላይ የሚውለው ውሃ ሁሌም ቢሆን ለሰው ልጆች ብቻ በቀጥታ እንደማይውል ሩትገር ሆፍስት ያስረዳሉ። እንደ ማሳያም ከብቶችን ለመመገብ የሚውለውን 12 በመቶ ውሃ ፍጆታ ያነሳሉ። ''ስለዚህ የዓለም ህዝብ የሥጋ ፍጆታውን መቀነስ ወይም መቆጣጠር ከቻለ በተዘዋዋሪ የውሃ ፍጆታውን ቀነሰ ማለት ነው'' ይላሉ። በረሃማነትን የሚዋጋው ተባበሩት መንግሥታት ድርጀት አካል እንደሚለው አሁን ያሉትን ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት በበረሃማና በከፊል በረሃማ አካባቢዎች የሚኖሩ እስከ 200 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በፈረንጆቹ 2030 ይፈናቀላሉ። ነገር ግን ይላሉ ሩትገር ሆፍስት እንደ ሲንጋፖርና እስራኤል ያሉ ሃገራት የውሃ እጥረትን ለመከላከል ብዙ ሥራዎችን እየሰሩ ነው። መላው ዓለምም የእነሱን ፈለግ መከተል አለበት ሲሉ አሳስበዋል።
49016911
https://www.bbc.com/amharic/49016911
አርባ ምንጭ፡ የዶርዜ የሽመና ጥበብ መናኸሪያ
የሃገር ባህል ሽመና ድንቅ ጥበብ ሲነሳ የዶርዜ ማራኪ የአልባሳት ውጤቶች በቀዳሚነት ከሚነሱት መካከል ነው። 'ሽመና የዶርዜዎች እጅ ትሩፋት ነው' ብለን አፋችንን ሞልተን ብናወራ ማጋነን እንደማይሆንብን ሃገር ይመሰክራል።
የጋሞ ጎፋ ዞን ዋና ከተማ የሆነችው ወቢቷ አርባ ምንጭ ደግሞ ለዚህ ምስክር ናት። እንደው አርባ ምንጭ ውስጥ ምርጡ ሸማኔ ማነው ብለን ስንጠይቅ ሁሉም መላሾች "ወደ ቶታል ሰፈር መሄድ ነው እንጂ ይሄማ ምን ጥያቄ አለው" ይሉናል። ከታችኛው ሰፈር ወይም ሲቀላ እና ከላይኛው ሴቻ መካከል ላይ ሰፍሮ የሚገኘው በተለምዶ 'ቶታል' ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ከሰዓት ገደማ ደርስን . . . ዘሪሁን ዘነበን ፍለጋ. . . በእግሩ እና በእጁ ጣቶች ጥበብን የጥጥ ፈትል ላይ የሚቀምም ሸማኔ። • ሜድ ኢን ቻይና- የሀገር ባህል አልባሳቶቻችን ዘሪሁን ከምሳ መልስ የሽመና ሥራውን ሊያጧጡፍ ሲዘጋጅ አገኘነው። «በጣም አሪፍ ምርጥ ሰዓት መጣችሁ. . .» ዘሪሁን በፈገግታ ተቀበለን። ከሽመና ሥራ አድካሚውና ጊዜ የሚወስደው ክሮቹን በሸማ መሥሪያው ላይ ክሩን አስማምቱ ማስቀመጡ እንደሆነ የነገረን ዘሪሁን፤ ከምሳ በፊት እሱን ሲያሰናዳ ማርፈዱን ነገረን። አሁን የተቀለሙትን ክሮች ከነጩ ጋር እያዋሃዱ ጥበብን ማፍለቅ ይሆናል ማለት ነው። «ሙያውን 1999 ላይ ነበር ሥራዬ ብዬ የያዝኩት። ያው ከአባቶቼ እያየሁ የሠራሁት ነው እንጂ በትምህርት ያገኘሁት ነገር የለም። ከዚያ 2002 አካባቢ ነው ከዶርዜ ወደ አርባ ምንጭ ወርደን መሥራት የጀመርነው። ምክንያቱም ዶርዜ እያለን ከሠራነው በኋላ የሚቀበለን የለም። አርባ ምንጭ ግን ወዲያው ነበር ገበያ ያገኘነው።» ዘሪሁንና ሌሎች አራት ወንዶሞቹ በጋራ በመሆን በማሕበር በመደራጀት 'ቶታል' አካባቢ የብረት ሱቅ ያገኛሉ። እዚህችው የብረት ሱቅ [ላሜራ] ውስጥ ነው ታድያ ዘሪሁን ሽመናውንም ንግዱንም የሚያጧጡፈው። • በእርጥብ ሳርና ቅጠል ጥቃትን ያስቆሙ አባቶች «ጥጥ የምናገኘው ሲሌ ከሚባል ከአርባ ምንጭ ወጣ ብሎ ከሚገኝ ቦታ ነው። ከዚያ እዚህ መጥቶ ሴቶች ይፈትሉታል፤ ከእነርሱ ነው እኛ የምንገዛው። ባለቀለሞቹ የሚመጡት ግን ከአዲስ አበባ ነው። እዚያ ይነከሩና ይመጣሉ፤ ገበያ ወርደን እንገዛቸዋለን። እርግጥ ዶርዜ ላይም በባሕላዊ መንገድ ተነክሮ የሚመጡ አሉ።» በዘሪሁን የላሜራ ሱቅ ውስጥ በቀለማት ያጌጡ በርካታ ባሕላዊ አልበሳት ይታያሉ፤ በርከት ያሉት ግን አንገት ላይ ጣል የሚደረጉ 'ስካርቮች' ናቸው። ዘሪሁን አርባምንጭና አካባቢዋ ያሉ ብሔሮችን የሚወክሉ አምስት ዓይነት አልባሳትን ጨምሮ የኢትዮጵያ ባንዲራ ጣል ያለበት 'ስካርቭ' እና የሚያሳሳ ቀለማት ያላቸው የአንገት ልብሶችን እንደጉድ ያመርታል። «የጊዲቾ የምንለው ወይን ጠጅና ቀይ ቀለማትን በነጭ መደብ ላይ ስናዋህድ ነው፤ ጋሞ ደግሞ ቢጫ፣ ጥቁርና ቀይ ቀለማትን የያዘ ነው፤ ኦይዳ የምንለውን በአምስት ዓይነት መልኩ እንሠራዋለን። አልፎም የዘይሴ የምንለው አለ።» • በኦሮምኛና በትግርኛ አፋቸውን የፈቱ የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ባለውለታዎች ዘሪሁን እንደሚለው፤ እያንዳንዱ ቀለም እና አሠራር የሚወክለው ብሔር አለ። ያው ለውጭ ሰው ብዙም ትርጉም ላይሰጥ ወይም ልዩነት ላይኖረው ይችል ይሆናል፤ እኛ ግን ሁሉን ጠንቅቀን እናውቀዋለን ይላል። የአልጋ ልብሶች [በተለይ ሆቴሎች ይወዷቸዋል ይላል ዘሪሁን]፣ ለሙሉ ልብስ የሚሆኑ ጥበቦች፣ ሰደርያ ላይ የሚውሉ ጥለቶች . . . ከዘሪሁን የሽመና ትሩፋቶች ጥቂቶቹ ናቸው። «ቱሪስቶች ሥራዬን ይወዱታል» አርባ ምንጭ እንግዳ ብዙ ናት። ከተለያዩ ዓለማት የሚመጡ ጎብኝዎችን ደፋ ቀና እያለች ስታስተናግድ ነው የምትውለው። 'ከትንሽ ብረት እና ከብዙ ጨርቅ የተሠራች ተሽከርካሪ' እንዲል ፀሐፊው፤ ከወዲያ ወዲህ ውር ውር የሚሉት ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎች [ባጃጅ] እግርዎ ውስጥ እየገቡ ቢጠልፍዎ ብዙ አይደናገሩ። አርባ ምንጭ፤ የውጭና የሃገር ውስጥ ቱሪስቶች ብቻ ሳይሆኑ ለስብሰባ ብለው የሚጎበኟት በርካቶች ናቸው። ይህ ደግሞ ለዘሪሁን ሠርግና ምላሽ ነው። «ብዙ ጊዜ በብዛት የምሠራው ስብሰባ ሲኖር ነው። ለሰስብሰባው ተካፋዮች የሚታደል ነው ተብዬ እንድሥራ ትዕዛዝ ይሰጠኛል፤ በዚያ መሠረት ሥሠራ እውላለሁ» ይላል። «በርካታ ዓይነት የአንገት ልብስ ስለምሠራ ፈረንጆች ይመጡና አማርጠው ይገዛሉ። ቀለም በዛ ያለበት የሚወዱት እነሱ ናቸው። ለቱሪስቶች እና ለሃገር ውስጥ ገዥ የምንጠራው ዋጋም ትንሽ ልዩነት አለው። ፈረንጆቹ ግን ደስ ብሏቸው ነው የሚገዙኝ። ታድያ ከዓመት ወይም ከሁለት ዓመት በኋላ ሲመጡ ፈልገው ያገኙኝና በብዛት ነው የምንፈልገው ብለው ይገዙኛል።» • ኢትዮጵያዊቷ ኮከብ ‘የ2017 የምስራቅ አፍሪካ ምርጥ ዲዛይነር’ ሆነች አንድ ስካርቭ ቀሙቱ 1.70 ሜትር፤ ስፋት 30 ሴንቲ ሜትር ነው፤ በዘሪሁን ልኬት ማለት ነው። ከ70 ብር ጀምሮ እስከ 400 ብር ድረስ ለገበያ ይውላሉ። ያው ዋጋው እንደ ስፋቱና ወርዱ ይለያያል። የሁለት ልጆች አባት ነው ሸማኔው ዘሪሁን። ቤተሰቤን በደንብ የማስተዳድርበት ጥበብ ነው ይላል፤ ሽመናን። «ዶርዜ ደሬ [ዶርዜ ሃገር] ቅርንጫፍ አለኝ፤ ወንድሞቼ እዚያ ይሠራሉ። እኔም አንዳንዴ እየሄድኩ አግዛቸዋለሁ። ታድያ ገበያ እንዴት ነው? «ኧረ ቆንጆ፤ በጣም አሪፍ ነው። ያው ዋናው ሥራ ነው እንጂ ቁጭ ካልክ ምንም የለም [ሳቅ. . .]» ዶርዜ ...ሸማኔ....ቀጭን ፈታይ...የቤት ፈትል...ጥንግ ድርብ... እያሉ የሽመናንና የእጅ ጥበብ ማደናነቅና አማርጦ ለመልበስ እንግዲህ ወደ አርባ ምንጭ ብቅ ማለት ነው።
54514018
https://www.bbc.com/amharic/54514018
ካናዳ፡ ዓሥር ዓመታት የፈጀው የኤርትራውያኑ የወርቅ ኩባንያ ክስ በስምምነት ተቋጨ
በኤርትራ የወርቅ ማዕድን ፍለጋ ላይ ተሰማርቶ የነበረው የካናዳ ኩባንያ ላይ የተመሰረተው ክስ በስምምነት ተቋጨ።
በኤርትራ ወርቅ በመፈለግ ላይ ተሰማርቶ የነበረው የካናዳው ኩባንያ ኔቭሰን ሪሶርስስ ላይ ከዓሥር ዓመታት በፊት ተመስርቶ የነበረው ክስ ነው በስምምነት መቋጨቱ ተሰምቷል። ካናዳዊው ኩባንያ ኔቭሰን ሪሶርስስ፤ በኤርትራ በወርቅ ማዕድን ፍለጋ ላይ በተሰማራባቸው አምስት ዓመታት ባደረሰው የጉልበት ብዝበዛ እና ኢሰብዓዊ አያያዝ ክሱ መመስረቱ ተገልጿል። ለመጀመሪያ ጊዜ ክሱን ሕግ ፊት ያቀረቡት ሦስት ኤርትራውያኖች መሆናቸውን ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ከዚህ ቀደም ዘግበውት ነበር። ጉዳዩን ለዓሥር ዓመታት ስትከታተል የነበረችው ኤርትራዊቷ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቿ ወ/ሮ ኤልሳ ጭሩም ለቢበሲ እንደገለፀችው፤ በወቅቱ ኩባንያው ያሰራቸው የነበሩ የብሔራዊ አገልግሎት ላይ የነበሩ ወጣቶች ምንም አይነት ክፍያ አልተከፈላቸውም። ኔቭሰን ሪሶርስስ ኩባንያ ለብሔራዊ አገልግሎት አባላቱ ምንም ዓይነት ክፍያ እንደማይከፈላቸው እያወቀ ከኤርትራ መንግሥት ጋር በመመሳጠር "ጉልበታቸው መበዝበዙን" በመጥቀስ በካናዳ ክስ ተመስርቶበታል። ክሱን የመሰረቱት አካላት እኤአ ከ2008 እስከ 2012 ኔቭሰን ሪሶርስስ በኤርትራ ቢሻ በሚባል አካባቢ የወርቅ፣ ዚንክና መዳብ ማዕድኖች ፍለጋ ሲያካሂድ፤ ከ1000 በላይ በሚሆኑ የብሔራዊ አግልግሎት አባላት ላይ ከኤርትራ መንግሥት ጋር በማበር የጉልበት ብዝበዛ እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽሟል ሲሉ መክሰሳቸው በወቅቱ ተዘግቦ ነበር። በካናዳ ፍርድ ቤት ሲታይ የቆየው ይህ ክስ በሽምግልና መጠናቀቁን የገለፁት ወ/ሮ ኤልሳ፤ በስምምነቱም ደስተኞች መሆናቸውን ለቢቢሲ ትግርኛ ክፍል ተናግረዋል። ኩባንያው ጉዳዩ በኤርትራ ላይ አልያም በሌሎች የአፍሪካ አገራት እንዲታይ በተደጋጋሚ ጥያቄ ሲያቀርብ ነበር ተብሏል። ሆኖም የካናዳ ፍርድ ቤት ጉዳዩ የዓለም አቀፍ ሕግ መጣሱን የሚመለከት በመሆኑ በካናዳ መታየቱ እንዲቀጥል ወስኖ ጉዳዩ ሲታይ ቆይቷል። የብሔራዊ አገልግሎት አባላቱ እአአ ከ2008 እስከ 2012 በማዕድን ቁፋሮ በሚሠሩበት ጊዜ የሰብዓዊ መብታቸው እንደተጣሰና፣ አያያዛቸውም መጥፎ እንደነበር በመጥቀስ ተከራክረዋል። ኔቭሰን ሪሶርስስ በበኩሉ ክሱን በመቃወም ለሠራተኞቹ ኃላፊነት እንዳልነበረው ሲከራከር ቆይቷል። ኩባንያው እና ክሱን የመሰረቱት አካላት የደረሱበት ዝርዝር ስምምነት ምን እንደሆነ አልተጠቀሰም።
41993762
https://www.bbc.com/amharic/41993762
የዚምባብዌ ጦር ዒላማዬ "ወንጀለኞች" እንጂ ሙጋቤ አይደሉም ብሏል
የዚምባብዌ ጦር ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ የሆነውን ዜድ ቢ ሲን ከተቆጣጠረ በኋላ ባወጣው መግለጫ "በወንጀለኞች ላይ ያነጣጠረ" እርምጃ በመውሰድ ላይ መሆኑን አስታውቋል።
የዚምባብዌ ጦር አባል መግለጫ ሲያነቡ ጦሩ "የመንግሥትን ስልጣን ለመቆጣጠር አልተንቀሳቀሰም" ሲል በመግለጫው ጠቅሶ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ደህንነታቸው እንደተጠበቀ አስታውቋል። ረቡዕ ጠዋት ላይ በዋና ከተማዋ ሃራሬ ሰሜን ክፍል ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ተኩስ ተሰምቷል። በደቡብ አፍሪካ የዚምባብዌ ልዑክ የሆኑት አይዛክ ሞዮ መፈንቅለ መንግሥት አለመኖሩን ጠቁመው መንግሥት በተለመደ መልኩ ሥራውን እያከናወነ ነው ብለዋል። የዚምባብዌ ጦር አባላት በሃራሬ ጎዳና ላይ የጦሩ መግለጫ የተነበበው በወታደሮች ሲሆን የዜድ ቢ ሲን ዋና መስሪያ ቤት ከተቆጣጠሩ ከሰዓታት በኋላ ነው። "ለህዝቡ የምናረጋግጠው ፕሬዝዳንቱ እና ቤተሰቦቻቸው በመልካም ሁኔታ ላይ ናቸው። ደህንነታቸውም ይጠበቃል" ሲል የጦሩ ባልደረባ ይፋ አድርጓል። "ዒላማ ያደረግነው በፕሬዝዳንቱ አቅራቢያ ሆነው ወንጀል በመፈጸም ሃገሪቱን ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ያጋለጡ ወንጀለኞችን ነው። ተልኳችንን እንዳጠናቀቅን ነገሮች እንደቀድሞው ይሆናሉ" ብሏል መግለጫው። መግለጫው ዒላማ የተደረጉ ሰዎችን ባይጠቅስም ሮይተርስ አንድ የመንግሥት ኃላፊን ጠቅሶ እንደዘገበው የገንዘብ ሚንስትሩ ኢግናቲስ ቾምቦ በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል ይገኙበታል። የጦሩን እንቅስቃሴ ማን እየመራው እንደሆነ የታወቀ ነገር የለም። የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ለዜጎቹ "ሁኔታዎች እስኪረጋጉ ድረስ በቤቶቻቹሁ ቆዩ" በማለት ምክር ሰጥቷል። ጄነራል ኮነስታንቲኖ ቺዌንጋ ጦሩ ጣልቃ እንደሚገባ አስጠንቅቀው ነበር በሃራሬ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ "ባለው አለመረጋጋት ምክንያት" ረቡዕ ዕለት ዝግ እንደሚሆን አስታውቋል። ሌላ መግለጫ እስኪወጣ ድረስ በዚምባብዌ የሚገኙ አሜሪካዊያን "ባሉበት እንዲቆዩ" በማለት መልዕክቱን አስተላልፏል። የአሁኑ ሁኔታ የሃገሪቱ ጦር አዛዥ በፓርቲ ክፍፍል ምክንያት ጦሩ ጣልቃ ይገባል ማለታቸውን ተከትሎ አዛዡ "የሃገር ክህደት ድርጊት" እየፈጸሙ ነው በሚል በዚምባብዌ ገዢ ፓርቲ ቅሬታ ከቀረበባቸው በኋላ የተፈጠረ ክስተት ነው። የ93 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ምክትል ፕሬዝዳንታቸውን ካባረሩ በኋላ ጉዳዩ በጄነራል ኮነስታንቲኖ ቺዌጋ ጥያቄ ቀርቦበታል። በሙጋቤ ዛኑ ፒ ኤፍ ፓርቲ ውስጥ አባላትን ያለአግባብ የማባረር ስራን ለማስቆም ጦሩ ጣልቃ ይገባል ብለዋል ጄነራሉ። ዓላማቸው ባይታወቅም ማክሰኞ ዕለት የጦሩ የታጠቁ መኪናዎች በሃራሬ ጎዳናዎች ላይ መታየታቸው ያለውን ውጥረት ከፍ አድርገውታል። ጦሩ ዜድ ቢ ሲን ሲቆጣጠር አንዳንድ የጣቢያውን ሠራተኞች ማንገላታቱን ምንጮች ለሮይተርስ ተናግረዋል። ግሬስ ሙጋቤ እና ሮበርት ሙጋቤን አካባቢውን ለመጠበቅ እንደመጡ እና "ምንም እንዳይፈሩ" ለሠራተኞች እንደተነገራቸው ምንጮቹ ጨምረው ጠቁመዋል። ፕሬዝዳንቱን ጨምሮ ብዙ የመንግሥት ኃላፊዎች መኖሪያ በሆነው ሰሜናዊ ሃራሬ ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ መሰማቱን የቢቢሲዋ ሺንጋይ ንዮካ ዘግባለች። አንድ የዓይን እማኝ ለኤ ኤፍ ፒ እንደገለጸው የተኩስ ድምጽ የተሰማው በፕሬዝዳንት ሙጋቤ መኖሪያ አካባቢ ነው። ማን ይተካቸዋል በሚለው ውዝግብ ምክንያት ሙጋቤ ምክትላቸው የነበሩትን ኤመርሰን ምናንጋግዋን አሰናብተዋል። በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት ዛኑ ፒ ኤፍ ፓርቲንም ለሁለት ከፍሎታል ተብሏል።
45873595
https://www.bbc.com/amharic/45873595
ጦላይ የሚገኙ የአዲስ አበባ ወጣቶች በሳምንቱ መጨረሻ እንደሚለቀቁ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ
ከአዲስ አበባ ተወስደው ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ የሚገኙ የአዲስ አበባ ወጣቶች በሳምንቱ መጨረሻ እንደሚለቀቁ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ብርጋዲየር ጄኔራል ደግፌ በዲ ለቢቢሲ ገለፁ።
ወጣቶቹ የተያዙት "በጎዳና ላይ ንብረት ሲያወድሙና ሁከት ሲፈጥሩ ነው" ያሉት ኮሚሽነሩ መጀመሪያ ከተያዙት ተጣርቶ አሁን በማሰልጠኛ ያሉት 1174 እንደሆኑ ገልፀዋል። . "ለወታደራዊ ደኅንነቱ የማንቂያ ደወል ነው" እሳቸው እንደሚሉት የፈፀሙት ተግባር በህግ የሚያስጠይቃቸው ቢሆንም መታነፅ እንዳለባቸው በማመን ለዚህም ከቤተሰብና ከማህበረሰብ ቀጥሎ ሃላፊነት ያለበት መንግሥት በመሆኑ ይህን ተግባሩን እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል። "ማነፅ ብቻ ሳይሆን የወጣቶቹን ማንነት በመገንዘብ ሥራ የሌለው ሥራ እንዲሰራ፣ ተማሪውም ትምህርቱን እንዲቀጥል ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ነው። እነዚህ ልጆች ላይ ሥራ እየሰራን ያለነው" ብለዋል ኮሚሽነሩ። ይህን ለማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ የሚመለከታቸው ትብብር ላይ መሆናቸውንም ገልፀዋል። በተጨማሪም የአዲስ አበባ ፖሊሶች ወጣቶችን በቡድን ሲደበድቡ የሚያሳይ ቪዲዮ ስለመለቀቁ የተጠየቁት ኮሚሽነሩ፤ ምንም እንኳ እሳቸው ተንቀሳቃሽ ምስሉን ባይመለከቱትም ቦታው ተገልፆ ትክክለኛ መረጃ ከደረሳቸው ማጣራት ተደርጎ ድርጊቱን በፈፀሙት አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ገልፀዋል። . የሰኔ 16ቱ ጥቃት ተጠርጣሪ ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተሰጠ በጅምላ ተይዘው ወደ ጦላይ ከተወሰዱ ወጣቶች መካከል መሳለሚያ ሞቢል አካባቢ ለግንቦት ሰባት መሪዎች አቀባበል ሲደረግ ሰንደቅ አላማ በመስቀልና ባነሮችን በመለጠፍ ተሳትፎ የነበረ ወጣት አንዱ ነው። ያሳደጉትና የክርስትና ልጃቸው በአመፅ ሳይሆን የግንቦት ሰባት መሪዎች አቀባበል ላይ ባደረገው ተሳትፎ ከዚያም የቡራዮውን ግድያ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣቱ መታሰሩን አቶ ዘመነ ሞላ ለቢቢሲ ይገልፃሉ። ከዚህ ውጭ ልጃቸው ሰላማዊ እንደሆነም ያስረዳሉ። . የዓለምፀሐይ፣ የፍስሃ እና የካሳሁን አዲስ ተስፋ ያሳደጉት ልጃቸው ወጣት ፍስሃ ደምስ የ25 ዓመት ወጣት ሲሆን እናቱ እንደሌለችና የሚኖረው ከአቅመ ደካማ አያቱ ጋር እንደነበር አቶ ዘመነ ይናገራሉ። እሳቸው እንደገለፁት የታሰረው ወደ ቤቱ የሚወስድ መንገድ ላይ አመሻሽ ላይ ነው። መጀመሪያ ወደ ተወሰደበት ፖሊስ ጣቢያ ሄደው ሲጠይቁ ጦላይ መወሰዱን መስማታቸውንና ከዚያ በኋላ ያለ ምንም መረጃ ቤተሰብ ስቃይ ላይ እንዳለ ይገልፃሉ። የአዲስ አበባ ወጣቶች ጅምላ እስር የመገናኛ ብዙሃንና የማህበራዊ ሚዲያ ርእሰ ጉዳይ ሆኖ ሰንብቷል። በማህበራዊ ሚዲያው የአዲስ አበባ ወጣቶች ይፈቱ የሚል ዘመቻም በመካሄድ ላይ ነው። አምነስቲ ኢንተርናሽናል የአዲስ አበባ ወጣቶችን በጅምላ አስሮ ስልጠና ማስገባት የህግ አግባብነት እንደሌለው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የህግ ባለሙያና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ፕሮጀክት አስተባባሪ የሆነችው ሶሊያና ሽመልስ መንግሥት እነዚህን ወታደሮች አስሮ ወደ ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ በመላኩ የጣሳቸው ህጎች አሉ ትላለች። "ተግባሩ በትንሹ አራት የሕገ መንግሥቱን አንቀፆች ይጥሳል። የታሰሩ ሰዎች መብት፣ የተከሰሱ ሰዎች መብት ፣ የተጠረጠሩ ሰዎች መብትና ከዚያም ጋር ተያይዞ መደረግ የሚገባቸው ነገሮች በትንሹ አንድ አራት የሕገ መንግሥቱ አንቀፆች ተጥሰዋል። የወንጀል ሥነ ሥርዓት ህጉንም ብንመለከት እዚያ ላይም የተጣሱ ነገሮች አሉ" ትላለች። እሷ እንደምትለው በመሰረተ ሃሳብ ደረጃ መንግሥት ሰዎችን ሰብስቦ ካሰረ ያሰረበትን ምክንያት ፍርድ ቤት አቅርቦ ፍቃድ መጠየቅ ይኖርበታል። በወሰደው እርምጃ የቀማው የግለሰቦችን ነፃነት በመሆኑ ይህን ደግሞ ያለ ፍርድ ቤት ፍቃድ ማድረግ አይቻልም። ስለዚህም ግለሰቦቹን ፍርድ ቤት አለማቅረብ፣ የተከሰሱበትን ምክንያት አለማወቃቸውን እንዲሁም የዋስትና መብታቸውን መነፈጋቸው በሃይማኖት አባቶችና በዘመድ መጎብኘት አለመቻላቸውን የመሰሉ ነገሮች ሲታዩ በእርምጃው ብዙ የመብት ጥሰቶች እንዳሉ ታስረዳለች።
54280346
https://www.bbc.com/amharic/54280346
ኮሮናቫይረስ፡ በኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች በሦስት ዙር እንዲከፈቱ እንደሚደረግ ተጠቆመ
የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በዓለም የጤና ድርጅትና በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን በሦስት ሳምንታት ውስጥ ያሟሉ ትምህርት ቤቶች ትምህርት እንዲጀምሩ መወሰኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
በዚህም መሠረት ትምህርት ቤቶች ከመከፈታቸው በፊት በጸረ ተህዋስ መድኃኒት እንዲጸዱ ማድረግና የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል፣ የእጅ ማጽጃ ማሟላት እንዲሁም አካላዊ ርቀትን ማስጠበቅ የሚያስችላቸውን ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። በተጨማሪም እንደየ ትምህርት ቤቶቹ ነባራዊ ሁኔታ ትምህርት በፈረቃ እና አንድ ቀን በመዝለል በተራ የማስተማር ሥራቸውን ማከናወን ይችላሉም ተብሏል። የተማሪዎችን ቁጥር በተመለከተም ሚኒስቴሩ ባስቀመጠው መስፈርት መሰረት በአንድ ክፍል ውስጥ ከ20 እስከ 25 ተማሪዎችን ማስተማር እንደሚቻል ፈቅዷል። በተጨማሪም በአገሪቱ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በሦስት ዙር ትምህርት እንዲጀምሩ ሊደረግ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት ቤቶችን ዳግም መክፈት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት እየተደረገ ባለው ውይይት ላይ ይህ ምክረ ሃሳብ መቅረቡን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጠቁሟል። ውይይቱ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀን ጨምሮ፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችና ሌሎች ሚኒስትሮችም የተገኙ ሲሆን፤ የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁንም በሦስት ዙር የሚከናወነውን ትምህርት የማስጀመር ሂደትን በተመለከተ ምክረ ሐሳባቸውን አቅርበዋል። በዚህም መስረት በገጠር ወረዳና ቀበሌ ከተሞች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች መጀመሪያ በተባለው ዙር ጥቅምት 9/2013 ዓ.ም፣ በሁሉም ዞንና የክልል ከተሞች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በ2ኛው ዙር ጥቅምት 16/2013 እንዲጀምሩ ሃሳብ ቀርቧል። ከዚህም በተጨማሪ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል ልዩ ዞን የሚገኙት ደግሞ ትምህርት ሚኒስቴር በሦስተኛ ዙር ብሎ ባስቀመጠው ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም ይጀምሩ የሚል ምክረ ሐሳብ ማቅረቡ ተገልጿል። የብሔራዊ ፈተና የሚወስዱት የ8ኛና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሁሉም ለፈተና እንዲቀመጡና የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናም ህዳር 22 እና 23/2013 ዓ.ም እንዲወስዱ ታቅዷል። ፈተና ላይ መቀመጥ የሚችሉት ተማሪዎች የ7ኛ ክፍልን ተምረው ያጠናቀቁና የ8ኛ ክፍል አንደኛ መንፈቀ ዓመት ትምህርትንም የተከታተሉ ሊሆኑ እንደሚገባም ሚኒስቴሩ ጠቁሟል። በተመሳሳይ መልኩ ለ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መቀመጥ የሚችሉትም የ11ኛ ክፍልን አጠናቀው ያለፉና የ12ኛ ክፍል የመጀመሪያ መንፈቀ ዓመት ትምህርት የተከታተሉ ሊሆኑ ይገባል ብሏል። የ12ኛ ክፍልም መልቀቂያ ፈተና ወቅትም ከህዳር 28 አስከ ታህሳስ 1/2013 ዓ.ም እንደሚሆንም በምክረ ሐሳቡ መጠቀሱን ሚኒስቴሩ አመልክተወል። የትምህርት አሰጣጡን ሂደት በተመለከተ ለመንግሥት ትምህርት ቤቶች የሚወጣው መመዘኛ በግል ትምህርት ቤቶች ተፈፃሚ እንደሚሆን ያሰፈረ ሲሆን በምክረ ሐሳቡ ላይ የሚደረገው ውይይት እንደቀጠለ መሆኑም ተገልጿል። ባለፈው ዓመት የኮሮናቫይረስ በኢትዮጵያ መገኘቱ ከተረጋገጠ በኋላ ትምህርት በቶች በመጀመሪያ ለሁለት ሳምንታት እንዲዘጉ ተደርጎ የነበረ ሲሆን፤ በተከታይነት የበሽታውን መስፋፋት ለመግታት በወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሰረት አስካሁን ተዘግተው መቆየታቸው ይታወሳል።
news-42310421
https://www.bbc.com/amharic/news-42310421
በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች ድንበር ግጭት የገዳ ስርዓት መፍትሔ ለምን አላመጣም?
የገዳ ስርዓት የኦሮሞ ሕዝብ ማንኛውንም ማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን ሲፈታበት የኖረ ሥርዓት እንደሆነ የታሪክ መዛግብት ይጠቅሳሉ።
ነገር ግን በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች ተከስቶ መጠነ-ሰፊ ቀውሶችን እያስከተለ ያለውን ግጭት በገዳ ስርዓት መፍታት ያልተቻለው በቁጥር ብዛት ያላቸው የታጠቁ ሃይሎችና ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች ስላሉበት አስቸጋሪ እንዳደረገው አባገዳዎች ይናገራሉ። በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች መካከል በተከሰተው ግጭት የብዙ ዜጎች ሕይወት ማለፉንና ከ 600 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች መፈናቀላቸው የሚታወስ ነው። ግጭቱ ከሐረርጌ ጀምሮ እስከ ቦረና የዘለቀና ድንበር አካባቢ ያሉ ሰዎችንም ለከፋ ችግር የዳረገ ነው። በቦረናና በሞያሌ የድንበር ግጭት እየከፋና በፀጥታ ኃይሎች በንፁሃን ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ችግር እያሳሰባቸውም እንደሆነ የቦረናው አባ ገዳ ኩራ ጃርሶ ገልፀዋል። ባለፈው ሐሙስ በቦረና ኦሮሞና በገሪ ሶማሌ መካከል በተፈጠረው ግጭት የሰው ሕይወት እንዳለፈና አሁንም ችግሩ አሳሳቢ እንደሆነ አባ ገዳ ኩራ ጃርሶ ጨምረው ይናገራሉ። "የገዳ ስርዓትን ተጠቅመን ህዝቡን እንዳናስታርቅ ያለው የፀጥታ ኃይል እክል ፈጥሮብናል። የገዳ ስርዓት በኦሮሞ ባለው በእርስ በርስ ግጭት ብቻ ሳይወሰን ከሌሎች ክልሎችም ጋር የሚከሰቱ ግጭቶችን መፍታት ይችላል። እሱን ግን ተግባራዊ ማድረግ አልቻልንም"ብለዋል። የገዳ ስርዓት በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ለምን መፍትሔ ማምጣት አልቻለም? አባ ገዳው ስለድንበር ችግሩ ሲናገሩ ከፍተኛ ግጭቶች ለውይይት እንዳይቀመጡ እንዳደረጋቸውና የችግሩ መጠን ከአቅማቸው በላይ መለጠጡን ነው። ''ለብዙ ዘመናት ሕዝቦችን በገዳ ስርዓት እያስታረቅን እንደቤተሰብ እንዲኖሩ በማድረግ ዛሬ ደርሰናል። በግጭቱ ያለው የፀጥታ ኃይል በዘመናዊ መሳሪያ የተደገፈ ስለሆነ ከአቅማችን በላይ ሆኗል" በማለት ይናገራሉ። የገዳ ስርዓት ዘመንን ተሻግሮ ለዓለም ባበረከተው ሥርዓት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣የሳይንስ እና የባህል ተቋም በማይዳሰሱ ቅርስነት ተመዝግቧል። የኦሮሞ ሕዝብ ለገዳ ስርዓት ትልቅ ክብር እንዳለው የሚናገሩት አባ ገዳ ኦሮሞዎችም የገዳ ውሳኔዎችንም እንደሚያከብሩ ይናገራሉ። ይህም ቢሆን ግን ከኦሮሚያ ክልል አልፎ የገዳ ውሳኔ በሀገሪቷ የፖለቲካ ውሳኔ ምን አይነት ተፅፅኖ ሊያሳርፍ ይችላል ወይም ተቀባይነቱ ምን ድረስ ነው የሚለው ጥያቄ አሳሳቢም እንደሆነ አባ ገዳው ያስረዳሉ። በሚፈለገው ደረጃ ባይሆንም በኦሮሚያ ውስጥ ለሚፈጠሩት ችግሮች ግን ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጠር ለማድረግ እየሰሩ እንዳሉ አባ ኩራ ጃርሶ ይናገራሉ። "በገዳ ስርዓት የሚተዳደረውን የኦሮሞን ሕዝብና በሀገሪቷ ያለውን የፖለቲካ ሁኔታ እንዴት ማስታረቅ እንደምንችል፤ ይህ ስርዓት ግንባር ቀደም ሚና እንዲጫወት ለማድረግ ስራችን ይቀጥላል" ብለዋል። የኦሮሞን ታሪክና የገዳ ስርዓት ታሪክ ተማራማሪ የሆኑት ዶር ቦኩ የኦሮሞ ሕዝብ ግጭቶችን የሚፈታበት ሁለት መንገዶች ሲኖሩ እነዚህም መከላከል (ፕሪ ኤምፕቲቭ ሜዠር ) እና ማቋቋም (ሚቲጌሺን ሜዠር) እንደሚባሉ ይገልፃሉ። በዚህም መሰረት ቂም በመያዝ አብሮ አይኖርም በሚልም እሳቤ በማስታረቅ ለግጭቶች ዘለቄታዊ መፍትሄ ማግኘት ይቻላል ብሎ የሚያምን ስርአት እንዳለው ዶ/ር ቦኩ ይናገራሉ። ገዳ በብቃት የማስተዳደር አቅሙን ማግኘት አለበት ብለው የሚያምኑት ዶ/ር ቦኩ ከተለያዩ የመንግስትም ሆነ ከፖለቲካ ጫና የገዳ ስርዓት ነፃ ሊሆን እንደሚገባ ይናገራሉ። "ሕዝብን ማወያየትም የገዳ ሚና ነው። ሰላምን ለማምጣት ሕዝቡ ገዳን መስማት አለበት''ብለዋል።
news-55212239
https://www.bbc.com/amharic/news-55212239
የኬንያና የሶማሊያ እሰጥ አገባ የጫት ንግድን እየጎዳው ነው ተባለ
ኬንያ እና ሶማሊያ የገቡበት ዲፕሊማሲያዊ እስጥ አገባ በጫት ንግድ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ማሳደሩ ተነገረ።
የሶማሊያ መንግሥት ከኬንያ በሚገባ የጫት ምርት ላይ እግድ መጣሉን ተከትሎ ጫት አምራች ኬንያውያን ገበሬዎች ከፍተኛ ኪሰራ እየገጠማቸው መሆኑ ተግልጿል። ሶማሊያ ከወራት በፊት ከኬንያ በሚገባው የጫት ምርት ላይ እግድ የጣለችው የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ምክንያት በማድረግ ነበር። ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን የኬንያ የጫት ምርት ወደ ሶማሊያ ከመግባቱ በፊት ኬንያ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ይኖርባታል ትላለች ሶማሊያ። ሶማሊያ የኬንያን የጫት ምርት ወደ አገሬ ከማስገባቴ በፊት ኬንያ በውስጣዊ ጉዳዬ ጣልቃ ከመግባት መቆጠብ ይኖርባታል፣ የሶማሊያን አየር ክልል ማክበር ይኖርባታል፤ እንዲሁም እንደ ስኳር፣ ወተት እና ማር ያሉ የሶማሊያ ምርቶችን እንድትቀበል ጠይቃለች። ኬንያ በበኩሏ በሶማሊያ ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ አለመግባቷን እና ፍትሃዊ ከሆነ የንግድ ስምምነት ለመድረስ ዝግጁ መሆኑኗን ትገልጻለች። ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ሶማሊያ ከኢትዮጵያ የጫት ምርት ማስገባቷን ቀጥላለች። ሶማሊያ በአብዛኛው የጫት ምርትን የምታገኘው ከኢትዮጵያና ከኬንያ ነው። በምስሥቃዊ ኬንያ የምትገኘው ሜሩ ጫት በማብቀል ትታወቃለች። ወደ ሶማሊያ ይላክ የነበረው የጫት ምርት ላይ እግድ መጣሉን ተከትሎ ጫት አምራች ገበሬዎች ለችግር ተጋልጠናል እያሉ ነው። የዘጠኝ ልጆች እናት የሆነችው ሜሪ ናቶንጃ “አረንጓዴው ወርቅ” የምትለውን ጫት ለበርካታ ዓመታት ስታመርት ቆይታለች። የጫት ምርት ወደ ዩናይትድ ኪንግደም እና ሶማሊያ በሚላክበት ወቅት ጥሩ ገቢ ታገኝ እንደነበረም ሜሪ ታስታውሳለች። ከስድስት ዓመታት በፊት ዩናይትድ ኪንግደም ጫት ወደ አገሬ አይገባም ስትል ወሰነች። ባሳለፍነው ዓመት ሕዳር ወር ላይም ሶማሊያ ከኬንያ በሚገባ የጫት ምርት ላይ ገደብ ጣለች። ይህን ጊዜ ሜሪ እሷ እና መሰል በሺዎች የሚቆጠሩ ጫት አምራች ገበሬዎች ሕይወታቸው መፈተኑን ትናገራለች። “ሕይወት ፈተና ሆኖብናል። ገንዘብ በእጃችን የለም። መልበስ እና መብላት ከባድ ሆኖብናል። ልጆቻችን ጾማቸውን እያደሩ ነው። በየሦስት ወሩ ምርት እየሰበሰብን ከአንድ እስከ አምስት ሺህ ዶላር እናገኝ ነበር። አሁን ግን አንድ ዶላር እንኳን ማግኘት አንችልም።” የኬንያ የጫት ነጋዴዎች ማኅበር እንደሚለው ከሆነ የኬንያ ጫት አምራች ገበሬዎች ከዚህ ቀደም እስከ 50 ቶን የሚመዝን ጫት ወደ ሶማሊያ በመላክ እስከ 140 ሺህ ዶላር ድረስ ገቢ ያስገኙ ነበር። አሁን ላይ ገበሬዎች ከምርታቸው እጅግ አነስተኛ የሚሆነውን ለኬንያ ገበያ ካቀረቡ በኋላ ሌላው ፈላጊ ስለሌለው ምርቱ እየተጣለ ነው ይላል ማኅበሩ። ባሳለፍነው ወር በሶማሊያ እና በኬንያ መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ አለመግባባት ተካሮ ሶማሊያ የኬንያን አምባሳደር አባራ በናይሮቢ የሚገኘውን አምባሳደሯን መጥራቷ ይታወሳል።
news-53900406
https://www.bbc.com/amharic/news-53900406
ሩሲያ ፡ የጀርመን ሐኪሞች አሌክሴ ላይሞት ይችላል አሉ
ፑቲን እንዳስመረዙት የሚጠረጠረው ተቀናቃኛቸው አሌክሴ ናቫልኒ ወደ ጀርመኑ ዝነኛ ሻርሌት ሆስፒታል ከተዛወረ በኋላ ላይሞት ይችላል የሚሉ መረጃዎች እየወጡ ነው።
ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አሌክሴ ከሰርቢያ ጀርመን፣ በርሊን በአውሮፕላን አንቡላንስ ከደረሰ በኋላ ፈጣን ምርመራ ተደርጎለታል። ሻርለት ሆስፒታል ከምርመራው በኋላ ባወጣው መግለጫ "የላቦራቶሪ ምርመራዎች አሌክሴ ሰውነቱ ውስጥ መርዝነት ያለው ንጥረ ነገር እንዳለ ያረጋግጣሉ" ሲሉ ይፋ አድርጓል። የመርዙ ዓይነትም "ኮሊነስትራሴ ኢንሂቢተር" ከሚባለው የወል ስም ከሚሰጠው ኬሚካል የሚመደብ ነው ብሏል ሆስፒታሉ። ሩሲያ አሌክሴን የመረመሩት ሐኪሞች ግን ሰውየው ላይ ምንም ዓይነት መርዛማነት ያለው ነገር አላገኘንም ብለው ነበር። አሌክሴ ናቫልኒ በጣሙኑ የሚፈሩትንና የማይደፈሩትን ፕሬዝዳንት ፑቲንን በይፋ በመቃወም፣ ሙስናዎችን በማጋለጥ፣ ተቃውሞዎችን በማስተባበር የሚታወቅ ሩሲያዊ ነበር። አሌክሴ ናቫልኒ ባፈለው ሳምንት ሐሙስ በሩሲያ የአገር ውስጥ በረራ ላይ ሳለ ነበር አውሮፕላን ውስጥ ከፍተኛ የስቃይ ድምጽ ካሰማ በኋላ ተዝለፍልፎ የወደቀው። ከሳይቤሪያ ቶምስክ ወደ ዋና ከተማ ይበርዋ በነበረው አውሮፕላን ተሳፍሮ የነበረው አሌክሴ ከፍተኛ የስቃይ ጣር ሲያሰማ እንደነበር በግለሰቦች የተቀረጸ ቪዲዮ አረጋግጧል። ይህንንም ተከትሎ አውሮፕላኑ በድንገት ሳይቤሪያ እንዲያርፍ ከተደረገ በኋላ ወደ ሕክምና ተወስዷል። አሌክሴ ምናልባት ቶምስክ አየር መንገድ ውስጥ ቁጭ ብሎ ሻይ ሲጠጣ ስለነበር በዚያች አጋጣሚ የሩሲያ ሰላዮች ያዘዘውን ሻይ መርዘውታል የሚል ከፍተኛ ጥርጣሬ አለ። የተቃዋሚው አሌክሴ መመረዝ ከተሰማ በኋላ የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ መርከልና የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አገሮቻቸው ለአሌክሴ ሕክምና ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸው በይፋ ገልጸው ነበር። ሆኖም የሩሲያ መንግሥት በሆስፒታሉ በኩል ሰውየው ወደ አምቡላንስ ለመግባት አቅም የለውም በሚል ሕክምናውን ሲከላከሉ ነበር። የአሌክሴ ሚስት በበኩሏ የሳይቤሪያው ሆስፒታል ታማሚው ባሏ ወደ ጀርመን እንዳይወሰድ እያዘገየ ያለው ወደሞት አፋፍ ከተጠጋ በኋላ እንደማይተርፈ ሲያውቁ ለመስጠት ነው በሚል ከፍተኛ ተቃውሞ ስታሰማ ነበር። በመጨረሻ አሌክሴ ወደ በርሊን ሻርለት ሆስፒታል የተወሰደው ቅዳሜ ዕለት ነበር። ሐኪሞቹ አሁን ተስፋ እንደሰጡት ከሆነ አሌክሴ ሕይወቱ ሊተርፍ የሚችልበት ዕድል ሰፊ ነው። የጀርመን ሐኪሞች እንደሚገምቱት ከሆነ ለአሌክሴ የተሰጠው እጅግ አደገኛ መርዝ ነው። አሁን መርዙን ለማርከስ እየሞከሩ ያሉት አትሮፒን በመስጠት ነው። አትሮፒን እውቅ የመርዝ ማርከሻ ሲሆን በዩናይትድ ኪንግደም ከዚህ ቀደም የተመረዘው የቀድሞው የኬጂቢ ሰላይ ሰርጌይ ስክሪፓልን ማዳን የተቻለው በዚህ መንገድ ነበር። አሌክሴ የተመረዘው በምንድነው? ኮሊኔስትራሴ ኢንሂቢተርስ የኬሚካል አይነት ሲሆን የዚህ ቀንጣት አልዛሚር የተባለውን የመርሳት በሽታን ለማከም ይውላል። በማዳበሪያና በነርቭ ጋዞች ውስጥ አገልግሎት ላይ ሲውል ግን ለሰው ልጅ እጅግ አደገኛ ነው። ይህ መርዝ ጥቃት የሚያደርሰው ከነርቭ ወደ ጡንቻ የሚሄዱ ወሳኝ ኢንዛይሞችን በመድፈን ነው። ስለዚህ ይህን መርዝ የወሰደ ሰው ጡንቻዎች አገልግሎት መስጠት፣ መለጠጥም ሆነ መኮማተር ያቆማሉ። ከዚህም ባሻገር መርዙ የአተነፋፈስ ሥርዓትን ስለሚያዛባ ሰዎች በዚህ መርዝ ሲጠቁ ራሳቸውን ይስታሉ። አሌክሴ የገጠመውም ይኸው ነው ይላሉ ሐኪሞች።
47222380
https://www.bbc.com/amharic/47222380
ኢትዮጵያ፡ ዲዛይን ዊክ አዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
ፓሪስ ዲዛይን ዊክ፣ ኒው ዮርክ ዲዛይን ዊክ፣ ኢስታንቡል ዲዛይን ዊክ፣ ዱባይ ዲዛይን ዊክ. . . በዓለም እውቅናን ካተረፉ የዲዛይን መሰናዶዎች መካካል ይጠቀሳሉ።
በዲዛይን ዊክ አዲስ አበባ የፈጠራ ሥራዎች ይተዋወቃሉ ቢያንስ ለአንድ ሳምንት በሚካሄዱት የዲዛይን መሰናዶዎች ሥነ ህንጻ፣ ሥነ ጥበብ፣ ቴክኖሎጂና ፋሽንን ጨምሮ በርካታ ዘርፎች ይዳሰሳሉ። የፈጠራ ባለሙያዎች ሥራዎቻቸውን ያሳያሉ፤ ግብይት፣ ውይይትና የልምድ ልውውጥም ይደረጋል። እነዚህ ዓለም አቀፍ የዲዛይን መድረኮች ከሚሰናዱባቸው ሀገሮች ባለፈ ከሌሎች ሀገራትም ታዳሚዎችን ይስባሉ። • የሀብ ኦፍ አፍሪካ ፋሽን ሳምንት ፎቶዎች • የ2010 የጥበብ ክራሞት አዲስ አበባ የዲዛይን ሳምንት የማስተናገድ ሀሳብን ከወረሰች አምስት ዓመታት ተቆጥረዋል። ዲዛይን ዊክ አዲስ አበባ የሚል መጠሪያም ተሰጥቶታል። የአራተኛው ዲዛይን ዊክ አዲስ አበባ ታዳሚዎች የዲዛይን ሳምንቱ በፈጠራ ዘርፍ ያለውን እንቅስቃሴ ለማስተዋወቅና ለማጠናከር እንደተወጠነ የዲዛይን ዊክ አዲስ አበባ መስራችና ዳይሬክተር መታሰቢያ ዮሴፍ ትናገራለች። በዲዛይን ዊክ አዲስ አበባ ከተካተቱ ዘርፎች ውስጥ የሥነ ህንጻና የከተማ ዲዛይን፣ ፋሽንና ጨርቃ ጨርቅ፣ ቴክኖሎጂ፣ ግራፊክ ዲዛይን፣ የምግብ አዘገጃጀት ይገኙበታል። ለፈጠራ ሥራዎች መድረክ መስጠት በተለያየ ዘርፍ ያሉ የፈጠራ ሥራዎች ተመልካች ጋር የሚደርሱበት በቂ መድረክ አለ? የሚለው አጠያያቂ ነው። አብዛኞቹ ፈጠራዎች ከሙያ ዘርፉ ውጪ ላሉ ሰዎች የሚደርሱበት መድረክ ሲያገኙ አይስተዋልም። መታሰቢያ ዮሴፍ በዲዛይን ሳምንት ውስጥ የተካተቱት የፈጠራ ዘርፎች በቂ መድረክ ማግኘት ያልቻሉ መሆናቸውን መታሰቢያ ታስረዳለች። ዲዛይን ዊክ አዲስ አበባ ክፍተቱን በመጠኑም ቢሆን ለመድፈን እንደሚሞክር መስራቿ ታክላለች። "ሁሉም ሥራቸውን በተወሰነ መንገድ ሲያቀርቡ ነበር። በዲዛይን ዊክ አዲስ አበባ ግን ሰፊ መድረከ ተሰጥቷቸዋል።" • ረሃብ የቀሰቀሰው ፈጠራ • የአገልግል ምግብ አምሮዎታል? ለምሳሌ አንድ ምግብ አብሳይ ቅመማ ቅመም አዋህዶ፣ ልዩ ጣዕም በመፍጠር አዲስ ምግብ ይሠራል። የምግብ አቀራረቡም ፈጠራ ይታከልበታል። ይህን ጥበብ እንደ ዲዛይን ዊክ አዲስ አበባ ባሉ መሰናዶዎች ማሳየት ይችላል። የቴክኖሎጂ ውጤቶች፣ የሥነ ህንጻና የከተማ ዲዛይን እንዲሁም የሥነ ጥበብ ሥራዎችም ለእያታ ይበቃሉ። ዲዛይን ዊክ አዲስ አበባ የተለያዩ ሀገሮች ተሞክሮን የተመረኮዘ ነው ከ18 ዓመት እስከ 60 ዓመት ዲዛይን ዊክ አዲስ አበባ ባለፉት አራት ዓመታት የተለያየ ሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ደረጃ ያላቸውን ሰዎች ማሰባሰብ መቻሉን መታሰቢያ ትገልጻለች። "ከ18 እስከ 60 ዓመት ሰው እናገኛለን። የተመልካቾች አይነት እየሰፋ፤ ቁጥሩም እየጨመረም ነው።" የተለያየ ዘርፍ የፈጠራ ውጤቶች አንድ ላይ መገኘታቸው ተመልካቾችን እንደሳበ ታምናለች። እንደ ፋሽንና ግራፊክስ ዲዛይን ያሉት ዘርፎች የተሻለ ተደራሽነት አላቸው። የቤት ውስጥ መገልገያዎች ሥራ እንዲሁም የቤት ውስጥ ዲዛይን ደግሞ ብዙም እውቅና ያልተቸራቸው ናቸው። የዲዛይን ሳምንት በሁለቱ መካከል ድልድይ ዘርግቷል። አራተኛው ዲዛይን ዊክ አዲስ አበባ የተጀመረው ሰኞ የካቲት 4/ 2011 ዓ. ም ሀያት ሪጀንሲ ውስጥ ነበር። 'ያኔ ኮሌክሽን' የተባለ ተቋም የኢትዮጵያና የኤርትራን ባህል የተመረኮዙ የጌጣ ጌጥ ምርቶች አስተዋውቋል። አንድ ፈረንሳዊ ዲዛይነር ላሊበላ ላይ የሠራውን ፕሮጀክት አቅርቧል። 'ሼፒንግ አዲስ ስሩ ኢኖቬሽን' በሚል ርዕስ የከተማ እቅድ ላይ ያተኮረ ወርክሾፕም ተካሂዷል። እስከ የካቲት 10/ 2011 ዓ. ም ድረስ ዐውደ ርዕይ፣ የሙዚቃና የምግብ መሰናዶ፣ ባዛርና ወርክሾፖች ይካሄዳሉ። የሥነ ህንጻና የከተማ ዲዛይን ከፈጠራዎቹ መካከል ይገኙበታል "ቀላል ባይሆንም አስፈላጊ ስለሆነ እናደርገዋለን" መሰል መሰናዶዎች ብዙም ባልተለመዱበት ሀገር የዲዛይን ሳምንትን በገንዘብ የሚደግፉ ሰዎች ወይም ድርጅቶች ማግኘት ከባድ መሆኑን መታሰቢያ ትናገራለች። ከተለያዩ ሀገሮች የዲዛይን ሳምንት የተወረሰው የአዲስ አበባው የዲዛይን ሳምንት፤ ፈጠራን በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት መስራቿ ገልጻ፤ "ቀላል ባይሆንም አስፈላጊ ስለሆነ እናደርገዋለን" ትላለች። ብዙዎች ሀሳቡን ባለመገንዘብ ለመደገፍ ቢያቅማሙም፤ ግንዛቤው ሲያድግ ሂደቱ ቀላል እንደሚሆን ተስፋ ታደርጋለች። ኢትዮጵያ ውስጥ የተመረቱና ኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠሩ ሥራዎችን በማስተዋወቅ እንደምትገፋ መታሰቢያ ትገልጻለች። በዲዛይን ዊክ አዲስ አበባ ላይ ሥራቸውን ማሳየት የሚፈልጉ ሰዎች፤ ሥራዎቻቸውን ከስድስት ወር በፊት ካስረከቡ በኋላ በኮሚቴ ተገምግሞ ለእይታ የሚበቁት ይመረጣሉ።
news-50285603
https://www.bbc.com/amharic/news-50285603
በኦሮሚያና በሐረሪ ክልሎች እንዲሁም በድሬዳዋ ከተማ ተከስቶ በነበረው አለመረጋጋት የሟቾች ቁጥር 86 መድረሱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዐብይ አስታወቁ
ከሳምንት በፊት በኦሮሚያና በሐረሪ ክልሎች እንዲሁም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ተከስቶ ከነበረው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 86 መድረሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዕሁድ አመሻሽ ላይ በሰጡት መግለጫ ከሞቱት ሰዎች መካከል 76ቱ በእርስ በርስ ግጭት እንዲሁም 10 ሰዎች ደግሞ በጸጥታ ኃይሎች በተወሰደ እርምጃ ህይወታቸው ማለፉን አመልክተዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ መግለጫ ላይ ሟቾቹ ከቁጥር ባሻገር በብሔር፣ በጾታና በሐይማኖት ተዘርዝረው የተጠቀሱ ሲሆን ከ86ቱ ውስጥ 4ቱ ሴቶች ናቸው። • "በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት ተቀባይነት ማሳጣት የሚሹ ግጭቱን አባብሰውታል" ቢልለኔ ስዩም • ኦሮሚያ ክልል ተፈጥሮ በነበረው ሁከት 359 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ "ይህ ክፉ ክስተት በኢትዮጵያ የግጭት እሳት ሲነሳ አንዱን ክፍል አቃጥሎ ሌላውን አሙቆ የሚያልፍ እንዳልሆነ ያሳየ ነው" በማለት እንዲህ አይነት ሁኔታ ሲከሰት ጉዳት የሚደርሰው በተወሰነው በአንድ ብሔር ወይም የሐይማኖት ተከታይ ላይ ብቻ ሳይሆን ሁሉንም የሚነካ መሆኑን ተናግረዋል። ከ80 በላይ የሚሆኑ ዜጎችን ህይወት የቀጠፈው አለመረጋጋትን ተከትሎም መንግሥታቸው "ያለፉ ስህተቶች ለማረም እየሰራን በሌላ በኩል ደግሞ ሰላምና ደህንነትን ለማረጋገጥ ህጋዊና ተመጣጣኝ እርምጃ እንወስዳለን" በማለት በድርጊቱ ውስጥ እጃቸው ያለ ሰዎች ሁሉም በጥፋታቸው መጠን ተጠያቂ እንደሚሆኑ ገልጸዋል። ይህንን ለማድረግም መንግሥታቸው በህግ በተቀመጠውና በተፈቀደው መሰረት አስፈላጊውን ለማድረግ አቅም፣ ዝግጁነትና ብቃት እንዳለው አመልክተዋል። መንግሥት አንዳንዶች እንዲማሩበት ብሎ የሰጠውን "ሰፊ ልብና ትከሻ ሳይጠቀሙበት ቀርተው የዜጎች ህይወት ለአደጋ የሚጋለጥበት ምክንያት ፈጥሯል" በማለት ወቅሰው ከዚህ በኋላ "መንግሥት የዜጎችንና የተቋማትን ደህንነት ለመጠበቅ የአገሪቱ ህግ ባስቀመጠው መሰረት" አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያደርግ አመልክተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪም መንግሥታቸው አገሪቱ ያለው የፖለቲካና የዴሞክራሲ መድረክ እንዲሰፋ በማሰብ ሆደ ሰፊነቱን አብዝቶ ነገሮችን ሲያስታምም መቆየቱንና "ከኃይል ይልቅ መመካከርን በመምረጥ መታገሱን" ጠቅሰው "ትዕግሰትን ፍርሃት፤ ማስታመሙ ድካም የመሰላቸው ካሉ ግን ተሳስተዋል" ብለዋል። • "በመንግሥት መዋቅር ሥር ሆነውም ግጭቶችን የሚያባብሱ እንዳሉ እናውቃለን" ኢዜማ • "ለውጡ ሐዲዱን ስቷል ብዬ ነው የማምነው" አርቲስት ታማኝ በየነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ መንግሥታቸው ከጀመረው የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ሥራው ወደኋላ እንደማይል በመግለጫቸው ላይ የተናገሩ ሲሆን "በአንድ በኩል የፖለቲካውንና የዴሞክራሲውን ምህዳር ለማስፋት፤ በሌላ በኩል ደግሞ ፍትህንና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ" እንደሚሰራ ገልጸዋል። የአገሪቱ የፀጥታ አካላትም በሁሉም ቦታ "ሰላም፣ ደህንነት፣ የህዝቦችን አብሮ መኖርና አንድነት፣ የተቋማትንና የኢንዱስትሪዎችን ደህንነት በህግ አግባብ የመጠበቅ ግዴታቸውን" በተገቢው ሁኔታ እንዲያከናውኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው ወቅት አሳስበዋል። "የፍትህ አካላትም በእንዲህ አይነቱ ድርጊት ውስጥ የተሳተፉ አጥፊዎች ትምህርት፤ ለተጎጂዎች ደግሞ ካሳ የሚሆን የተፋጠነ ፍትህ በማስፈን ፍትህን እንዲያረጋግጡ" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጥሪ አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዋልታ ረገጥ ብለው በጠሩት የተካረረ "የብሔርና የእምነት ጫፍ ላይ ቆመው ችግሮችን የሚያባብሱ ወገኖች ባላቸው አመለካከትና በሚያስተላልፉት መልዕክት ተጨማሪ እልቂትና ጥፋት እንዳይከሰት" እራሳቸውን እንዲቆጥቡ አሳስበዋል።
news-48595212
https://www.bbc.com/amharic/news-48595212
በኢትዮጵያ ብዙ ቦታዎች ተቋርጦ የነበረው የኢንተርኔት አገልግሎት ተመለሰ
ዛሬ ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ተኩል ጀምሮ በበርካታ የኢትዮጵያ ክፍሎች የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ኢትዮ ቴሌኮም ለቢቢሲ ያረጋገጠ ሲሆን፤ አገልግሎቱ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ተመልሷል።
የኔትብሎክስ መረጃ በአገሪቱ ብቸኛ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢ የሆነው የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ት ጨረር ኢንተርኔት ተቋርጦ እንደነበር ለቢቢሲአረጋግጠዋል። ወ/ት ጨረር ለኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡ ምክንያት ምን እንደሆነ አልተናገሩም። • ‹‹እነ ቴሌን ለግል ባለሀብት?›› ታሪካዊ ስህተት ወይንስ መልካም አጋጣሚ ? • ኢትዮጵያ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን በመበደል ከዓለም ቀዳሚ ሃገራት አንዷ ነች ተባለ የመረጃ መረብ ደኅንነትንና በዓለም ዙሪያ የኢንተርኔት ስርጭትን የሚከታተለው ኔትብሎክስ የተሰኘው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት በአገሪቱ ሙሉ በሙሉ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን በትዊተር ገፁ ላይ አስፍሮ ነበር። ለዚህም እንደ ምክንያትም የጠቀሰው በትናንትናው ዕለት በመላው አገሪቱ የተጀመረው አገር አቀፍ ፈተና ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ማጭበርበሮችን ለመከላከል እንደሆነ ነው። የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገፅ የኢንተርኔት ትራፊክ መቆጣጠሪያ ከዛሬ ጥዋት ጀምሮ እንዳመለከተው፤ ከኢትዮጵያ ድረ ገፁን የሚጎበኙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል። ከሁለት ዓመታት በፊት የብሔራዊ ፈተና ስርቆትን ለመከላከል በሚል በፈተናው ወቅት የኢንትርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ ተደርጎ እንደነበር ይታወሳል። እስካሁን የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን በተመለከተ ከመንግሥትም ሆነ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ማብራሪያ የለም።
news-57060398
https://www.bbc.com/amharic/news-57060398
ምርጫ 2013፡ ቦርዱ ምርጫው ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን አያሟላም ላሉት ሴናተሮች ምላሽ ሰጠ
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኢትዮጵያ ከሳምንታት በኋላ የምታካሂደው ምርጫ 'አሁን ባለበት ሁኔታ ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን አያሟላም' ላሉት የአሜሪካ ሴናተሮች ምላሽ ሰጠ።
የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ለሴናተሮቹ በጻፉት ደብዳቤ ዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲ እንዲያብብና የሰብዓዊ መብት እንዲጎለብት ከምታደርገው ጥረት አንፃር በቅርቡ አምስቱ ሴናተሮች በሰጡት አስተያየት 'ተገርሜአለሁ' ብለዋል። ከቀናት በፊት አምስት የአሜሪካ ሴናተሮች በቀጣይ የሚካሄደው አገራዊ ምርጫ አሁን ባለበት ሁኔታ ነጻ፣ ሚዛናዊ እና ግልጽ ሆኖ ዓለም አቀፍ መመዘኛዎች አያሟላም ብለው ነበር። ሴናተሮቹ ይህን ያሉት የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጆፍሪ ፌልትማን ወደ ቀጠናው ጉዞ ከማድረጋቸው በፊት በጻፉላቸው ደብዳቤ ነበር። ሰብሳቢዋ በበኩላቸው ዛሬ ይፋ በተደረገው ደብዳቤስድስት ዋና ዋና ነጥቦች አስፍረው ምርጫው ዓለም አቀፍ መስፈርት አያሟላም ላሉት ሴናተሮች ምላሽ ሰጥተዋል። በተመሳሳይ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ ቀጣዩን ምርጫ የሚያስፈጽመው ቦርድ ገለልተኛ መሆኑን በመጥቀስ ለሴናተሮቹ አስተያየት ምላሽ መስጠታቸው አይዘነጋም። ብርቱካን በደብዳቤያቸው ምን አሉ? የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ገለልተኛ ተቋም እንደመሆኑ፤ ቀጣዩ ምርጫ ዓለም አቀፍ ሕግጋት የተከተለ እንዲሆን እየጣረ ነው ያሉት ሰብሳቢዋ የሕዝብ ብዛትን፣ ያላደገ የዲሞክራሲ ባሕል፣ በየጊዜው እየተስፋፋ የመጣውን የደህንነት ስጋት ከግምት ውስጥ በማስገባት ቀጣዩ ምርጫ እንከኖች እንደሚኖሩት ይጠበቃል ብለዋል። ነገር ግን እነዚህ ጉዳዮች መራጩ ድምፁን ሲሰጥ እንቅፋት እንዳይሆኑ ለማድረግ የአጭር ጊዜ መፍትሄዎች ተቀምጠዋል። ቢሆንም በምርጫው የሚሳተፉ ሁሉ ስለሂደቱ ሲያስቡ እኚህን ነገሮች ከግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው ብለዋል። ሰብሳቢዋ አክለው የምርጫው ተሳታፊዎች በቅድመ ምርጫ ሂደቱ በነቂስ ተሳትፈዋል ብለዋል። በአሁኑ ወቅት በቦርዱ ከተመዘገቡ 49 የፖለቲካ ፓርቲዎች 46ቱ ዕጩዎቻቸውን አሳውቀዋል። 9 ሺህ ዕጩዎች በፌዴራልና በክልል ደረጃ ይሳተፋሉ። ይህ ቁጥር በኢትዮጵያ ምርጫ ታሪክ እስከዛሬ ከተመዘገበው ትልቁ ነው ይላል የሰብሳቢዋ ደብዳቤ። መግለጫው ጨምሮ ከ190 በላይ ሃገር በቀል የሲቪክ ሶሳይቲ ማሕበራት የምርጫ ትምህርት እንዲሰጡ ፈቃድ እንደተሰጣቸውና 34 ሃገር በቀል ድርጅቶች ደግሞ ምርጫውን እንዲታዘቡ ፈቃድ ማግኘታቸውን ጠቅሷል። እነዚህ ምርጫ ታዛቢ ድርጅቶች ድምፅ አሰጣጡንና ሌሎች ሂደቶችን እንዲታዘቡ ከ100 ሺህ በላይ ባለሙያዎችን ያሰማራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የሰብሳቢዋ መግለጫ ያትታል። ቀጣዩ የኢትዮጵያ ምርጫ አሁን ባለበት ሁኔታ ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን አያሟላም ያሉት ሴናተሮች የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን፤ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ዕጩዎች በምርጫ ሂደቱ ላይ በሃገሪቱ የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ እንደሆነ ጠቅሰዋል። የተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ዕጩዎች በሃገሪቱ እየተዘዋወሩ ቅስቀሳ እያደረጉ ነው፤ እነዚህ ፓርቲዎች ፈተና እንደሚገጥማቸው የታመነ ቢሆንም ምርጫ ቦርዱ የሚቀርቡት ቅሬታዎች ለመፍታት እየጣረ ነው ብለዋል ሰብሳቢዋ። ቅሬታዎች በተቋሙ አቅም የሚፈቱ ሲሆኑ ቦርዱ የታሰሩ ዕጩዎችንና የፓርቲ መሪዎችን እስከማስፈታት ድረስ ጥረት ያደርጋል ብለዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሰጣቸው የሚድያ ጊዜም በሁሉም ፓርቲዎች ዘንድ በፍትሃዊነት እንዲከፋፈል መደረጉን አሳውቀዋል። ሰብሳቢዋ በቦርዱ ማሕበራዊ ድር አምባ ገፆች ባሰራጩት መግለጫ ምርጫው ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን እንዲያሟላ ብዙ ጥረት መድረጉን አንስተዋል። ከእነዚህ ጥረቶች መካከል የምርጫው ተሳታፊዎችን ሐሳብና አስተያየት በምርጫው መመሪዎች ውስጥ ማስገባት አንዱ ነው ብለዋል። "በዚህም መሠረት እንደ የምርጫ ሳጥን፣ ስክሪኖች፣ ማሸጊያዎች እና የማይጠፋ ቀለም ያላቸው 'ማርከሮች' ግዢ፣ የምርጫ ወረቀት ዲዛይንና ሕትመት እንዲሳካ ተደርጓል። እነዚህ እርምጃዎችና ሌሎችም የዘንድሮውን ምርጫ ካለፉት ምርጫዎች በላቀ ተዓማኒ እንዲያደርገው ያግዛል" ብለዋል። ሰብሳቢ የ6ኛው አጠቃላይ ምርጫ አስተዳዳሪ በኢትዮጵያ ታሪክ ግልፁ ነው ብለዋል። "ከፈረንጆቹ 2019 መገባደጃ ጀምሮ በምርጫው ከሚሳተፉ አካላት ጋር 50 የውይይት መድረኮች ተደርገዋል። ይህ የሆነው ቦርዱ ከፌስቡክ፣ ትዊተር፣ ቴሌግራምና ዩትዩብ ገፆቹ ከሚያደርገው መደበኛ ግንኙነት በተጨማሪ ነው።" ጥልቅ ውይይቶች ያስፈለጉት ተሳታፊዎች ከምርጫው ሂደት ጋር ተያይዞ ያሉትን ፈተናዎች እንዲረዱትና መፍትሄ እንዲያዋጡ ለማድረግ መሆኑን ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሃገር በቀልና ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ክፍት ነው ያሉት ሰብሳቢዋ በኢንተርናሽናል ሪፐብሊካን ኢኒስቲትዩትና በናሽናል ዴሞክራቲክ ኢኒስቲትዩት ትብብር ለተቋቋመው ዓለም አቀፉ ምርጫ ታዛቢ ሚሽን ጥሪ አቅርበዋል። "መሰል ልዑካን የምርጫውን ግለፅነት ከፍ ያደርጉታል" ብለዋል ሰብሳቢዋ። ሰብሳቢዋ በምርጫ ወቅት የሚደረጉ ለውጦች ቴክኒካዊ፣ ፋይናንሳዊ፣ ፖለቲካዊና የደህንነት መዋቅር ስጋት ሊያመጡ ይችላሉ ብለዋል በመግለጫቸው። "ለውጥ ሲካሄድ ወቅቱን መጠበቁን፣ ዋጋን፣ ጥልፍልፍነቱን እንዲሁም ግልፅነቱን ከግምት ያስገባ መሆን አለበት። ስለዚህ በዚህ ወቅት የሚደረጉ ወሳኝ ለውጦች አይበረታቱም። በምትኩ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫው ተሳታፊዎች ተግባራዊ ለሚሆኑ መመሪዎች ተገዢ እንዲሆኑና ቅሬታቸውን በተገቢው መንገድ እንዲያቀርቡ ያበረታታል" ይላል መግለጫው። ሰብሳቢዋ መግለጫቸውን ሲያጠቃልሉ አሜሪካ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የዲሞክራሲ ለውጥ ሂደት በቅርበት መከታተሏንና መደገፏን እንደምትቀጥል ተስፋ አደርጋለሁ፤ አዲስ አበባ ከሚገኙት የአሜሪካው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር እንደምንገናኝ አስባለሁ ብለዋል።
news-55270755
https://www.bbc.com/amharic/news-55270755
በረራ እንዳያደርጉ ተከልክለው የነበሩ ሙስሊሞች ኤፍቢአይን እንዲከሱ ተፈቀደላቸው
በፌደራል ወንጀል ምርመራ መስሪያ ቤት (ኤፍቢአይ) በረራ እንዳያደርጉ ስማቸውን በጥቁር መዝገብ ላይ ተመዝግቦ የቆዩት ሦስት ሙስሊም ወንዶች ኤፍቢአይን እንዲከሱ የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በየነላቸው።
ፍርድ ቤቱ እንዳለው በአሜሪካ ነዋሪ የሆኑት ሦስቱ ግለሰቦች በአገሪቱ ሕግ መሠረት ካሳ መጠየቅም ይችላሉ። ለፍርድ ቤቱ አቤቱታቸውን ያቀረቀቡት ግለሶች በኤፍቢአይ አደገኛ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸው ሥራቸውን እንዳሳጣቸው እና ከሐይማኖታቸው በሚጻረር መልኩ ሌሎች ሙስሊሞች ላይ እንዲሰልሉ ጫና እንደተደረገባቸው ገልጸዋል። ጠበቆቻቸው እንደሚሉት ማናቸውም ከዚህ በፊት በወንጀል ተጠርጥረው የማያውቁ ሰዎች ናቸው። ከሦስቱ ሙስሊሞች መካከል አንደኛው በኤፍቢአይ ምክንያት በጠና የታመሙ እናቱን እንኳን ማስታመም እንዳልቻለ የገለጸ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ባለቤቱን ለረጅም ጊዜ ሳያጋኝ መቆየቱን ገልጿል። ኤፍቢአይ ፍርድ ቤት ቀርቦ ይህንን ተግባር ፈጽመዋል የተባሉት ኤጀንቶቹ ምንም አይነት ክስ እንዳይቀርብባቸው ማድረግ ይችላል። 'ኳሊፋይድ ኢምዩኒቲ' በሚሰኘው የአሜሪካ ሕግ መሠረት የፌደራል ደህንነት ሰራተኞች ሕገ መንግስቱን ቢጥሱ እንኳን ክስ እንዳይቀርብባቸው የሚመከላከል ሲሆን የዴሞክራት ኮንግረስ አባላት ይህ ሕግ እንዲገደብ በተደጋጋሚ ሲጠይቁ ነበር። ነገር ግን ሕጉ በሪፐብሊካኖች ድጋፍ አለው። ''በአሁኑ ሰዓት ጣም ደስ ብሎኛል። ሁሉም ምስጋና ለአላህ ይሁን'' ብሏል በኤፍቢአይ ኢላማ ተደርገው ከነበሩት መካከል አንዱ የሆነው ናቪድ ሺንዋሪ። ''ይህ ድምጻቸው ለማይሰማ ሙስሊሞች ትልቅ ድል ነው'' ሲል ለኤንፒአር ተናግሯል። አክሎም ''ይህ ውሳኔ ለኤፍቢአይና ሌሎች ተቋማት እንደፈቀዱ የሰዎችን ሕይወት ማክበድ እንደማይችሉ ትልቅ መልዕክት ይመስለኛል'' ማለቱ ተገልጿል። በአሜሪካ በአውሮፕላን መብረር የማይፈቀድላቸው 80 ሺ ሰዎች የሚገኙ ሲሆን ሁሉም የአሜሪካ ዜጎች ባለመሆናቸው ምክንያት ኤፍቢአይን መክሰስ እንደማይችሉ የሶስቱ ሙስሊሞች ጠበቆች ተናግረዋል።