id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
news-56555595
https://www.bbc.com/amharic/news-56555595
ቦርዱ የኦነግን ጠቅላላ ጉባኤና በምርጫ የመሳተፍ ጥያቄን ውድቅ አደረገ
በቅርቡ አዲስ የአመራር አባላትን መርጫለሁ ያለው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ክንፍ ያካሄደው ጠቅላላ ጉባኤና በምርጫ ለመሳተፍ ያቀረበው ጥያቄ በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ውድቅ ተደረገበት።
አቶ አራርሶ ቢቂላ በኦነግ ከፍተኛ የአመራር አባላት መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ሳቢያ ግንባሩ በሁለት ወገኖች መካከል ተከፍሎ በቀጣዩ ምርጫ ለመሳተፍ የዕጩዎች ምዝገባ ሳያከናውን የጊዜ ገደቡ ጊዜ እንዳለፈው ይታወሳል። ቦርዱ ውሳኔውን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ላይ እንደጠቀሰው በግንባሩ አመራሮች መካከል የተፈጠረውን ክፍፍልና ውዝግብን ተከትሎ ከሁለቱም ወገን አቤቱታዎችና የማሳወቂያ ደብዳቤዎችን ሲቀበል መቆየቱ በመግለጽ ችግሩ መፍትሄ እንዲያገኝ የበኩሉን ጥረት ማድረጉን ገልጿል። ግንባሩ በቀደምት ሊቀመንበሩ በአቶ ዳውድ ኢብሳና ምክትላቸው በነበሩት በአቶ አራርሶ ቢቂላ መካከል ለሁለት ተከፍሎ የተለያየ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ውሳኔዎችን እየሰጠ ነው። በአቶ ዳውድ የሚመራው ቡድን በግንባሩ ላይ የተለያዩ ጫናዎች እየደረሱ ነው በሚል በምርጫው ላይ እንደማይሳተፍ ቢገልጽም የአቶ አራርሶ ቡድን ግን ተገቢውን ማስተካከያ እንዳደረገ በመግለጽ በምርጫው የመሳተፍ ፍላጎቱን ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አቅርቦ ነበር። በግንባሩ ውስጥ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታትም ሁለቱ ወገኖችን በተናጠል እንዲሁም የፓርቲውን የሥነ ሥርዓት እና የቁጥጥር ኮሚቴን በማነጋገር ያሉ አስተዳደራዊና ሕጋዊ መንገዶች ሁሉ በመጠቀም መፍትሔ ለመስጠት ጥረት ማድረጉን ቦርዱ ገልጿል። በመጨረሻም የግንባሩን ጠቅላላ ጉባኤ መጥራት ፓርቲው ለገጠመው ችግር ብቸኛ መፍትሔ መሆኑን በማስረዳት በውዝግብ ውስጥ ያሉ አመራሮችም ይህንኑ ሃሳብ በመቀበል የተፈጠረውን ችግር በጠቅላላ ጉባኤ እንዲፈታ መወሰኑ የምርጫ ቦርድ መግለጫ አስታውሷል። በዚህም የግንባሩ አንደኛ ወገን ጠቅላላ ጉባኤ በማካሄድ አዲስ የአመራር አባላት መምረጡን በመግለጽ፣ "በውስጥ ችግሩ ምክንያት የጠቅላላ ጉባኤ ሳያካሂድ በመቆየቱ የነበረበትን ችግር ግምት ውስጥ በማስገባት የምልክት መረጣና የዕጩ ተወዳዳሪዎች ምዝገባ እንዲያደርግ እንዲፈቅድለት ጠቅላላ ጉባኤውንም እንዲጸድቅለት" መጠየቁን ምርጫ ቦርድ አመልክቷል። ቦርዱም የቀረቡለትን ሰነዶች መርምሮ በጠቅላላ ጉባኤው አካሄድና ተሳታፊዎች በኩል የግንባሩን ሕገ ደንብ ባከበረ መንገድ አለመካሄዱን የሚያመለክቱ አምስት ነጥቦችን በማስቀመት የቀረበለትን የጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔና በምርጫ የመሳተፍ ጥያቄን እንዳልተቀበለው ገልጿል። ስለዚህም በመጪው ግንቦት ወር ማብቂያ ላይ በሚካሄደው አጠቃላይ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎቱን ገልጾ የነበረው በአቶ አራርሶ ቢቂላ የሚመራው የኦነግ አንድ ክፍል ያካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። ባለፈው ሳምንት በአገሪቱ ምክር ቤት ቀርበው ለተነሱ ጥያቄዎች መልስና ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በምርጫው ለመሳተፍ ፍላጎት ያለው ፓርቲን አሁንም ቦርዱ ቢቀበለው እንደሚደግፉ ገልጸው ነበር። በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆነው ኦነግ በምርጫው የመሳተፉ ሁኔታ ጥያቄ ውስጥ የቆየ ቢሆንም አሁን በገጠመው ችግር ምክንያት ከምርጫው ውድድር ውጪ ሆኗል። ከዚህ ቀደምም የኦሮሞ ፌደራሊስte ኮንግረስ በአባላቱ መታሰርና በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ጽህፈት ቤቶቹ መዘጋትን እንደምክንያት በማቅረብ በምርጫው ላይ ለመሳተፍ እንደሚቸገር መግለጹ ይታወሳል። የብልጽግና ፓርቲ ሕዝብ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ፓርቲዎቹ መንግሥት ጫና ያደርስብናል፣ አባላቶቻችንን ያስራል፣ ጽህፈት ቤታችንን ዘግቷል ሲሉ የሚያቀርቡትን ውንጀላ "መሰረት የሌለው" ሲሉ ከዚህ በፊት ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። በመጪው ግንቦት ወር መጨረሻና በሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ ከትግራይ ክልል በስተቀር በቀሪው የአገሪቱ አካባቢዎች በሚካሄደው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ላይ የሚወዳደሩ 47 የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም 125 የግል ዕጩዎች ለመወዳደር ተመዝግበዋል። ባለፈው ሳምንት ደግሞ ሁለት ወር ያህል በቀረው ምርጫ ላይ ድምጽ የሚሰጡ የመራጮች ዝገባ መጀመሩን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳውቋል።
news-54480081
https://www.bbc.com/amharic/news-54480081
ኬንያ፡ ፍርድ ቤት በነፃ ያሰናበተው ኬንያዊ ሽብር ተጠርጣሪ በታጣቂዎች ታገተ
በኬንያዋ መዲና ናይሮቢ የሚገኘው ዌስት ጌት የገበያ ማዕከል ላይ ጥቃት ፈፅመዋል በሚል በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ከነበሩት መካከል አንደኛው ፍርድ ቤት በነፃ ቢያሰናብተውም ባልታወቁ ታጣቂዎች መታገቱ ተሰምቷል።
የሽብር ጥቃቱ በጎሮጎሳውያኑ 2013 የደረሰ ሲሆን በዚህም ጥቃት 71 ሰዎች ሞተዋል ተብሏል። ሊባን አብዱላሂ ኦማር የተባለው ግለሰብ ነው በዚህ ሽብር ጥቃት እጁ የለበትም ብሎ ፍርድ ቤቱ በዚህ ሳምንት ረቡዕ በነፃ ያሰናበተው። ወንድሙ የሽብር ጥቃቱን ካደረሱት መካከል አንዱ ነው የተባለ ሲሆን በወቅቱም በፖሊስ ተገድሏል። ሃሙስ እለትም ሊባን ተሳፍሮበት የነበረውን ታክሲ መሳሪያ የታጠቁ ግለሰቦች አስቁመውም እንዳገቱትም የአይን እማኞች ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። የሶማሌ ስደተኛ የሆነው ሊባን የታገተውም የፖሊስ ፀረ-ሽብር ቢሮ ሲወጣ መሆኑንም የእስልምና እምነት ተከታዮች የሰብዓዊ መብት ላይ የሚሰራ መንግሥታዊ ድርጅት ዳይሬክተር ኬሌፍ ካሊፋ ለቢቢሲ አሳውቀዋል፥ ታስሮበት ከነበረው ካማቲ እስር ቤትም ከተለቀቀ በኋላም ፀረ-ሽብር ቢሮው የሄደው መጨረስ ያለበትን ጉዳዮችም ለማጠናቀቅ ነው ተብሏል። ባለ ጥቁር ኮፍያ ያለው ሹራብ የለበሱ ታጣቂዎች ታክሲውን ካስቆሙ በኋላም የደህንነት ኃይል መሆናቸውን መናገራቸውንም ጠበቃው ምቡጋ ሙሬቲ ለኬንያው የቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግረዋል። ፖሊስ ምንም አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል። ያገቱት ግለሰቦችን ማንነት በተመለከተ ማንም አስተያየት ከመስጠት ቢቆጠብም በጠራራ ፀሃይና በቀን እንዲህ ታጥቀው ሊባንን ሊያግቱት የሚችሉት ከፖሊስ ፀረ-ሽብር ቢሮ ጋር ግንኙነት ያላቸው እንደሆኑ በርካቶች እየተናገሩ ነው። በሽብር ተጠርጥረው ፍርድ ቤት በነፃ ያሰናበታቸው ግለሰቦች አብዛኛውን ጊዜ ደብዛቸው ይጠፋል ወይም ተገድለው ይገኛሉ። በግድያቸውም ሆነ በመጥፋታቸው ተጠያቂ የሚሆን አካልም የለም። የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ግን በዘፈቀደና በጭካኔ ለሚገደሉትም ሆነ ለሚጠፉት የፀጥታ ኃይሎችንና ፖሊስን ጥፋተኛ ያደርጋሉ። አምነስቲ በተደጋጋሚ በሚያወጣቸው ሪፖርቶች ፖሊስ ዳኛም ሆነ የሞት ፍርድ መፍረድ አይችልም ቢልም ፖሊስ በበኩሉ በነዚህ እገታዎችም ሆነ ግድያዎች እጄ የለበትም ይላል። በጎሮጎሳውያኑ 2013 በዌስት ጌት የመገበያያ ማእከል በደረሰው ጥቃት ታጣቂዎች በሸማቾች ላይ ተኩስ የከፈቱ ሲሆን፤ ለአራት ቀናት ያህልም ቆይቷል። በዚህም ቢያንስ 62 ንፁሃን ዜጎች፣አምስት ፖሊሶችና አራት ታጣቂዎች ተገድለዋል።
news-53404778
https://www.bbc.com/amharic/news-53404778
ኢራን ለሲአይኤ መረጃ አቀብሏል ያለችውን ግለሰብ በሞት ቀጣች
ኢራን የቀድሞ የመከላከያ ሚንስቴር ሠራተኛዋን ለአሜሪካ ምረጃ አቀብሏል በሚል ክስ በሞት መቅጣቷን አስታወቀች።
ኢራን በመካከለኛው ምሥራቅ ካሉ አገራት ግዙፍ የሚሳኤል ክምችት ያለባት አገር ናት። ሬዛ አስጋሪ የተባለው ግለሰብ የሞት ብይኑ የተፈጸመበት ባሳለፍነው ሳምንት መሆኑን የፍርድ ቤት ቃል አቀባይ ጎላምሁሴን ኢሰማኢሊ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ቃል አቀባዩ እንዳሉ የሞት ብይኑ የተፈጸመበት ሬዛ አስጋሪ የኢራንን የሚሳኤል ፕሮግራም ዝርዝር መረጃ ለአሜሪካ የስላል ተቋም (ሲአይኤ) እአአ 2016 ላይ አሳልፎ ሰጥቷል ተብሎ ነው። አስጋሪ መረጃውን ሰጠ የተባለው ከኢራን መከላከያ ሚንስቴር ሠራተኝነት በጡረታ ከተገለለ በኋላ ነው። ቃል አባዩ አስጋሪ መቼ በቁጥጥር ሥር እንደዋለ፣ የፍርድ ሂደቱ መቼ እንደተከናወነና ብይኑ ተግባራዊ የሆነው መቼ እንደሆነ ዝርዝሩን ከመናገር ተቆጥበዋል። ቃል አቀባዩ ጎላምሁሴን ኢሰማኢሊ የሞት ቅጣቱ ስለተፈጸመበት ግለሰብ የተናገሩት ስለ ሌላ ለውጪ ኃይሎች ሰልሏል ተብሎ ስለተከሰሰ ተጠርጣሪ በገለጹበት ወቅት ነበር። ቃል አቀባዩ እንደተናገሩት መሐሙድ ሙሳቪ-ማጃድ የተባለ ሌላኛው ግለሰብ ለሲአይኤ እና ለእስራኤል መንግሥት የስለላ ድርጅት ሞሳድ መረጃ አሳልፎ ሰጥቷል ተብሎ የሞት ፍርድ እንደተላለፈበት ተናግረዋል። መሐሙድ ሙሳቪ-ማጃድ ለሲአይኤ እና ሞሳድ አሳልፎ የሰጠው መረጃ በሶሪያ የኢራን ጦር እንቅስቃሴን በተመለከተ ነው ተብሏል። የአሜሪካ ባለስልጣን አስጋሪ በኢራን መንግሥት የሞት ፍርድ ተፈጻሚ እንዲሆንበት መደረጉን ተከትሎ ያሉት ምንም ነገር የለም። ከአንድ ዓመት በፊት የኢራን የደኅንነት ሚንስቴር የአገሪቱን የኒውክሌር እና ሌሎች ወታደራዊ ተቋማት ዝርዝር መረጃ ለሲአይኤ አሳልፈው ሰጥተዋል ያላቸውን 17 ሰዎች በቁጥጥር ሥር አውሎ እንደነበረ ማሳወቁ ይታወሳል። በወቅቱ ሚንሰቴር መስሪያ ቤቱ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል በስም ያልጠቀሳቸው የሞት ፍርድ የተላለፈባቸው እንዳሉ አሳውቆ ነበር። በተመሳሳይ ከአንድ ወር በፊት የቀድሞ የኢራን መከላከያ ሚንስቴር መስሪያ ቤት ሠራተኛ የነበረው ጃላል ሃጂዛቫር ለሲአይኤ ሰልሏ ተብሎ በሞት ተቀጥቷል። በወቅቱ ሃጂዛቫር በክፍያ ለሲአይኤ ሲሰልል መቆየቱን አምኗል ተብሎ ነበር።
44897335
https://www.bbc.com/amharic/44897335
ቆይታ ከኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረ-መስቀል ጋር
የቢቢሲ ጋዜጠኛ ቃልኪዳን ይበልጣል የኢትዮጵያና የኤርትራ ወቅታዊ ሁኔታ፤ እንዲሁም ወደፊት ኤርትራ ውስጥ ሊኖር ስለሚችለው ለውጥ ከኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል ጋር አሥመራ ውስጥ ቃለ-ምልልስ አድርጓል።
ቢቢሲ፦ ጠቅላይ ሚኒስተር ዐብይ አሕመድ ወደ አሥመራ በመጡበት ወቅት ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ደግሞ ወደ አዲስ አበባ በሄዱበት ወቅት ህዝቡ ደስታውን ሲገልፅ ነበር። አሁንም ቢሆን ደስታው እንደቀጠለ ነው። ይህ ለእናንተ የሚሰጠው ትምህርት ምንድን ነው? አቶ የማነ ፦ ከ1960 ጀምረን ካሰብን ያለፉት 53 ዓመታት የጦርነት ወይም የመሳሳብ ዓመታት ነበሩ። በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል አንፃራዊ ሰላም የተገኘው ለሰባት ዓመታት ብቻ ነበር። ይህን ምዕራፍ ወደ ጎን በመተው እንደ ሁለት ሃገራት፣ የታሪክ የባህልና ሌሎች ዝምድናዎችም እንዳሏቸው ህዝቦች አብረን ለልማት እንድንሰራ ህዝብ ይፈልጋል። • ኤርትራ የሐይማኖት እሥረኞችን ፈታች • አሥመራ፡ የአዛውንቶች ከተማ ጠቅላይ ሚኒስተር ዐብይ አሕመድ ወደ አሥመራ እንደመጣ፤ የህዝቡ ስሜት ምን ይመስል እንደነበር ሁሉም አይቶታል። ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ወደ አዲስ አበባ በሄደበት ወቅትም የኢትዮጵያ ህዝብ ስሜት ታይቷል። ባጭሩ ስገልፀው፤ ይህ ሁኔታ ሊከሰት የቻለው ሁለቱም መሪዎች ጥሩ ራዕይ ስላላቸው፣ አስፈላጊና ደፋር ውሳኔ ስለወሰኑ፣ ሁለቱ ህዝቦችም ቢሆኑ የጦርነትን አስከፊነት ስለሚያውቁ የእነዚህ ሁሉ ድምር ውጤት ነው። መጪው ግዜ ደግሞ ጥሩ ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው። ቢቢሲ፦ ባለፉት ሦስት ወራት ኢትዮጵያ ውስጥ ፈጣን ለውጦች እየተደረጉ በመሆናቸው ከኤርትራ ጋርም እንደገና ግንኙነት ተጀምሯል። ይህ ግንኙነት ኤርትራ ውስጥ ተመሳሳይ ለውጦችን ሊያመጣ ይችላል? ከኤርትራ ወገን ምን ዓይነት ለውጦች ሊኖሩ ይችላሉ? አቶ የማነ፦ የኤርትራ ህዝብ ሲታገል ለመብቱ ነው የታገለው። መብት ደግሞ ብዙ ነው። የመልማት፣ ዜግነት የማግኘት እና እንደህዝብ የመኖር መብቶችን ያጠቃልላል። ምናልባት ጦርነት ካለ ከጦርነቱ ጋር የሚዛመዱ ችግሮች ሊኖሩ ይችላሉ። በሰላሙ ጊዜ ግን ለሀገሪቷ ብልፅግና፣ ለሰብአዊ መብቶችና ለዜጎች ደህንነት መደረግ ያለበት ነገር ሁሉ ይደረጋል ማለት ነው። • ''የኤርትራ ኢኮኖሚያዊ ዕቅድ የተነደፈው በኢትዮጵያ ሃብት ላይ ነበር'' አምባሳደር አውዓሎም ወልዱ • የአሥመራን ጎዳናዎች በፎቶ ቢቢሲ፦ የሃይማኖት እስረኞች ተፈትተዋል የሚል ዜና ሰምተናልና. . . . . አቶ የማነ፦ ይህን በተመለከተ አላውቅም። ነገር ግን ኤርትራ ላይ የተሳሳተ አመለካከት ስላለ ነውን'ጂ፤ ኤርትራ የእምነት ነፃነት የምታከብር ሃገር ነች። ኢትዮጵያ ውስጥም ተመሳሳይ ይመስለኛል። ክርስትና ወደ ኤርትራ የገባው በ320ኛው ዘመን ከክርስቶስ ልደት በኋላ ነው። ክርስትና፣ እስልምናና ካቶሊክ እንዲሁም ወንጌላውያን ተፋቅረው ነው የኖሩት። መንግሥት ደግሞ ሃይማኖት ውስጥ እጁን አያስገባም። ማንኛውም ሰው የእምነት ነፃነት አለው። ምናልባት በቅርብ ጊዚያት ያየነው ግን፤ በውጭ ኃይሎች የሚደገፍና ህብረተሰቡን የሚረብሽ ነገር ስለመጣ በሃገሪቱ ደህንነት ላይ ተፅዕኖ የሚኖረው ነገር ሲኖር መንግሥት እጁን ያስገባል፤ ሰው ሲፈልግ አማኝ ሲፈልግ ኢ-አማኝ መሆን ይችላል። ስለዚህ፤ ይህ አንዳንድ ስለኤርትራ የሚፃፈው ነገር ሌላ ፍላጎት ያላቸው የሚያራግቡት ካልሆነ በስተቀር፤ አሥመራ ውስጥ ተንቀሳቅሰህ አይተህ ይሆናል፤ የተለያዩ ቤተ-ክርስትያናትና መስጊዶች ጎን ለ ጎን ነው ያሉት። አሁን አሁን ብዙ የሉም እንጂ፤ አይሁዳውያንም ስለነበሩ፤ ቤተ-መቅደሳቸውም ሳይቀር አለ። ስለዚህ የሃይማኖቶች መዋደድ እና መቻቻል አለ። መንግሥትም እጁን አያስገባም። እኔ ብፈልግ አምናለሁ ባልፈልግ አላምንም። መንግሥት ይሄን እመን ይሄን አትመን ሊለኝ አይችልም። እንዳልኩህ፤ አክራሪነት በዚህም በዚያም ስለሚመጣ፤ በህብረተሰቡም ላይ ችግር ስለሚያመጣ አንዳች ሥርዓት ያስፈልገዋል። ይህ ሲባልም፤ ይከልከል ማለት ሳይሆን ሥርዓት ግን ያስፈልገዋል። እንዴት ነው የሚመዘገበው? እምነት ላይ የተመረኮዘ ነው ወይስ ሌላም ዓላማ አለው? የሚለውን የሚመለከቱ ህጎች አሉ። ከዚህ ጋር በተያያዘ አንዳንድ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ።
49916629
https://www.bbc.com/amharic/49916629
ኬንያ ገንዘብ ከመቀየሯ ጋር ተያይዞ ከሰባት ቢሊዮን ሺልንግ በላይ ጥቅም አልባ ሆነ
የኬንያ ማዕከላዊ ባንክ እንዳሳወቀው ኬንያ የመገበያያ ገንዘብ ከመቀየሯ ጋር ተያይዞ ከ95% በላይ የሚሆነው የአንድ ሺ ሺልንግ ተመልሶ በአዲሱ ተተክቷል።
በዚህ መካከል ግን መሃል ላይ ተንሳፎ የቀረ ገንዘብ እንዳለም ተገልጿል። "ይህ ማለት 7.3 ቢሊዮን ሺልንግ ጥቅም አልባ ሆኗል፤ እንደ ወረቀት ነው የሚቆጠረው" በማለት የባንኩ አስተዳዳሪ ፓትሪክ እንጆሮጌ ለጋዜጠኞች አስረድተዋል። •የኢትዮጵያ ሙዚቃ- ከመስከረም እስከ መስከረም •ከአንደኛ ክፍል ዲግሪ እስኪጭኑ ከልጃቸው ጋር የተማሩት አባት ባንኩ እንዳሳወቀው አዲስ የመገበያያ ገንዘብ የታወጀው ሰኔ አንድ ቀን ሲሆን ከዚያ ዕለትም ጀምሮ ሲዘዋወር የነበረ 217 ሚሊዮን ሽልንግም ተገኝቷል። ከመስከረም ሃያ ጀምሮ አሮጌው የመገበያያ ገንዘብ ከጥቅም ውጭ ሆኗል። በዚህ ወቅትም ከሶስት ሺ የሚበልጡ አጠራጣሪ ልውውጦች ሪፖርት የተደረጉ ሲሆን በሚመለከተው የመንግሥት አካልም ምርምራ እንደሚደረግም ኢንጆሮጌ አክለው ገልፀዋል። የገንዘብ ቅየራው በሃገሪቷ ውስጥ የተንሰራፋውን ሙስና ለማስቀረትና ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርንም ለመቆጣጠር እንዲያስችል ነው። •ኬንያ ሳንቲሞቿ ላይ የነበሩ መሪዎችን በእንስሳት ቀየረች አፍሪካ ታክስ ጀስቲስ ኔትወርክ የተባለ ድርጅት እንዳሳወቀው በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ምክንያት ኬንያ በየአመቱ 400 ሚሊዮን ዶላር እንደምታጣ አስታውቋል። ባንኩ እንዳስታወቀውም የገንዘብ ቅይይሩ መሳካቱንና ከዚህ በኋላ ስርአት ባለው መንገድ የገንዘብ ዝውውር እንደሚከናወን ነው።
news-53075611
https://www.bbc.com/amharic/news-53075611
ከባሪያ ንግድ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሁለት የእንግሊዝ ግዙፍ ኩባንያዎች ጥቁሮችን ይቅርታ ጠየቁ
ከዘመናት በፊት ከባሪያ ንግድ ጋር የተቆራኘ ታሪክ አላቸው የተባሉ እድሜ ጠገብ ድርጅቶች በባርያ ፍንገላ ስርዓት ውስጥ በነበራቸው ተሳትፎ ምክንያት ይቅርታ ጠየቁ።
ግሪን ኪንግ የቢራ ሙዚየምና ለንደን የሚገኘው የሎይድስ ህንጻ አካባቢ ሁለቱ የዩናይትድ ኪንግደም ድርጅቶች "በታሪካችን አፍረናል፤ ይቅርታ አድርጉልን" ያሉት የጆርጅ ፍሎይድን ሞት ተከትሎ እየተቀጣጠለ የመጣውን ተቃውሞ ተከትሎ ነው። አንዱ ድርጅት ግሪን ኪንግ ይባላል። በመላው ዓለም በርካታ የአልኮል መጠጦችን የሚያቀርቡ "ቡና ቤቶች" ያሉት በዕድሜ ግዙፍ ኩባንያ ነው። የተመሰረተው በጎርጎሳውያኑ 1799 ሲሆን በዩናይትድ ኪንግደም እንደርሱ ቢራ የጠመቀ የለም ይባልለታል። ላለፉት 200 ዓመታትም በሥራ ላይ ቆይቷል። ግሪን ኪንግ በኢንግላንድ፣ በዌልስና በስኮትላንድ ብቻ 2 ሺህ 700 ቅርንጫፎች አሉት። የዚህ ግዙፍ ድርጅት መሥራቾች ከነበሩት አንዱ ቤንጃሚን ግሪን በካሪቢያን ሰፋፊ እርሻዎችን በባሪያዎች ጉልበት ያሳርስ፣ ያሳጭድ፣ ያስወቃና ያሰበስብ ነበር። በዚህም የተነሳ ነው የግሪን ኪንግ ኩባንያ "ላለፈው ታሪካችን ይቅር በሉን" ያለው። የዚህ ቢራ ጠማቂ ኩባንያ መሥራች የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት 1833 የባሪያ ንግድን በሕግ ሲከለክል ያሳድራቸው የነበሩ ባሪያዎቹ ነጻ ስለሚሆኑበት ለሚደርስበት የንግድ ኪሳራ ከመንግሥት ከፍተኛ መጠን ያለው ካሳ ተከፍሎታል። ለመርከብ ድርጅቶች መድኅን በመስጠት የሚታወቀው ሎይድስ ሌላኛው ይቅርታ የጠየቀ የዩናይትድ ኪንግደም ግዙፍ የኢንሹራንስ ኩባንያ ነው። ይህ ኩባንያ ድሮ ባሪያዎችን በአትላንቲክ ውቅያኖስ ያጓጉዙ ለነበሩ መርከቦች የመድን ዋስትና አገልግሎት ይሰጥ የነበረ ነው። ሁለቱም ድርጅቶች ይቅርታ ከመጠየቃቸውም በላይ ለጸረ ዘረኝነት እንቅስቃሴ ገንዘብ እንደሚደጉሙ ቃል ገብተዋል። ሎይድስ የተመሰረተው እንደ አውሮፓዊያኑ በ1688 ሲሆን ከአፍሪካና ከካሪቢያን የተፈነገሉ ባሪያዎችን ለሚያመላልሱ የመርከብ ድርጅቶች መድን ዋስትና በመስጠት በይበልጥ ይታወቃል። በዓለም ካሉ እውቅ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች አንዱ የሆነው ሎይድስ በተለይም በኃይልና በባሕር ትራንስፖርት መድን በመስጠት ዝነኛ ነው። ይህ ኩባንያ የሰሞኑን ተቃውሞ በማስመልከት ባወጣው መግለጫ "በታሪካችን ውስጥ የምናፍርበት የታሪክ ሰበዝ አለ። በ18ኛውና በ19ኛው ክፍለ ዘመን በባሪያ ንግድ ላይ በነበረን ሚና እናፍራለን፤ ይህ ለዩናይትድ ኪንግደምም ይሁን ለእኛ አሳፋሪው ጊዜ ነው፡፡ ይቅር እንድትሉን እንፈልጋለን" ብሏል። የግሪን ኪንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኒክ ማኬንዚ በበኩላቸው የሚከተለውን ብለዋል። "ይቅር የማይባል ተግባር ነበር። የእኛ ኩባንያ መሥራች ከባሪያ ንግድ ሀብት ሲያጋብስ የኖረ ሰው መሆኑ የሚያኮራን አይደለም። በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ደግሞ የባሪያ ንግድ መቅረት የለበትም ሲል ሽንጡን ገትሮ ተከራክሯል። ይህ ሁሉ የታሪካችን አካል እንደሆነ ባንክድም እኛ የአሁኑን እና ወደፊትን የተሻለ በማድረግ ላይ እናተኩራለን።" የጆርጅ ፍሎይድን በሚኔሶታ ግዛት፣ ሜኒያፖሊስ ከተማ በነጭ ፖሊስ በግፍ መገደል ተከትሎ በተነሳው ዓለም አቀፍ ተቃውሞ በርካታ ታሪካቸው ከባሪያ ንግድ ጋር የተነካካ ኩባንያዎች ተመሳሳይ እርምጃ ለመውሰድ እየተዘጋጁ ነው።
news-54245652
https://www.bbc.com/amharic/news-54245652
ምርጫ 2013፡ የተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ እንዲካሄድና ትምህርት ቤቶች እንዲከፈቱ ወሰነ
በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተራዝሞ የነበረው ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ እንዲካሄድ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ስብሰባው ወሰነ።
ከአምስት ዓመት በፊት በተካሄደው ምርጫ ድምጽ የሰጡ ሴት ምክር ቤቱ በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ አስቸኳይ ስብሰባው ለስድስተኛ ጊዜ የሚካሄደው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ የዓለም ጤና ድርጅትና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባስቀመጡት ምክረ ሃሳብ መሰረትም ቫይረሱን ለመካላከል የሚያስችሉ እርምጃዎችን በመውሰድ እንዲከናወን ወስኗል። ይህም የውሳኔ ሐሳቡ በአንድ ተቃውሞና በስምንት ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ እንደፀደቀም ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ጠቁሟል። በተጨማሪም ምክር ቤቱ ከኮሮናቫይረስ መከሰት በኋላ የበሽታውን መስፋፋት ለመቆጣጠር በሚል ተከልክለው የነበሩ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች እንዲጀመሩ እንዲሁም ተዘግተው የከረሙ ትምህርት ቤቶችም እንዲከፈቱ ወስኗል። የውሳኔ ሐሳቡና ሪፖርቱን ያቀረቡትም የሴቶች፣ ወጣቶችና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ አበባ ዮሴፍ ናቸው። ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምላሽ አሰጣጥና ቀጣይ እርምጃዎችን በተመለከተ ምክር ቤቱ መስከረም 8/ 2013 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ምርጫው ከጥንቃቄ ጋር መደረግ ይችላል የሚል ምክረ ሐሳብ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በኩል ቀርቦለት ነበር። ይህንንም ሪፖርትና ምክረ ኃሳብ ለሴቶች፣ ወጣቶችና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በተባባሪነት ለሕግ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር እይታ መመራቱ ይታወሳል። ምርጫው እንዲካሄድ ምክር ቤቱ ዝግጅት እንዲጀመረው ከመወሰኑ ውጪ መቼ እንደሚሆን የተሰጠ መረጃ የለም። ምክር ቤቱ በተጨማሪ በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ያቀረቧቸውን የአራት ሚኒስትሮች ሹመትና የዳኞችን ሹመት አፅድቋል። በዚህም መሰረት ዶ/ር ቀነዓ ያዴታ የሃገር መከላከያ ሚኒስትር፣ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ፣ዶ/ር ሳሙኤል ሁርቃቶ - የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትርና ፣ ኢንጅነር ታከለ ኡማ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትርነት ሹመት አፅድቋል። የቀረበውንም ሹመት በአምስት ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ ማፅደቁንም ምከር ቤቱ በፌስቡክ ገፁ አስፍሯል። ከዚህም በተጨማሪ 40 የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመትና የ50 የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ሹመቶችንም በአብላጫ ድምፅ ማፅደቁን አስፍሯል። ተሿሚዎችም ቃለ መሃላቸውን መፈፀማቸውንም ሰፍሯል።
51789012
https://www.bbc.com/amharic/51789012
የአል-ሻባብ ቁልፍ ሰው ሶማሊያ ውስጥ በአየር ድብደባ ተገደለ
የአል-ሻባብ ከፍተኛ አመራር ባሽር ቆርጋብ፤ ሶማሊያ ውስጥ በደረሰበት የአየር ድብደባ መገደሉን የሶማሊያ ብሔራዊ ራድዮ ጣብያ ዘግቧል።
በግሪጎሪ አቆጣጠር 2008 ላይ አሜሪካ ባሽር ሞሐመድ ቆርጋብ ያለበትን ለጠቆመ 5 ሚሊዮን ዶላር እሸልማለሁ ብላ መግለጫ ማውጣቷ አይዘነጋም። ዩናይትድ ስቴትስ ሶማሊያ ውስጥ የአል-ሻባብ አባላትን ዒላማ ያደረገ ጥቃት በየጊዜው ትሰነዝራለች። ምንም እንኳ አሜሪካ በሰውየው ግድያ ዙሪያ አስተያየት ባትሰጥም የግለሰቡ ቤተሰቦች ሞቱን አረጋግጠዋል። በወታደራዊ ካምፖች ላይ ጥቃት በማድረስ የሚፈለገው ባሽር ኬንያ ውስጥ አል-ሻባብ ባደረሳቸው ጥቃቶችም ላይ እጁ እንዳለበት ይነገራል። የሶማሊያ ብሔራዊ ራድዮ ጣብያ እንደዘገበው ባሽር የካቲት 14/2012 አሜሪካና ኬንያ በጋር ባደረሱት የአየር ድብደባ ነው የተገደለው። ራድዮ ጣብያው ዜናው ዘግይቶ ለምን እንደወጣ ያለው ነገር የለም። ባለፈው ወር የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን ባሽር ቆርጋብ ከአል-ሻባብ መሪዎች ጋር ባለመስማማቱ ሳይገነጠል አይቀርም ሲሉ ዘግበው ነበር። ከአል-ቃይዳ ጋር ትሥሥር እንዳለው የሚነገርለት አል-ሻባብ በደቡብ እና መአከላዊ ሶማሊያ ጥቃቶችን በማድረስ ይታወቃል። አልፎም የሶማሊያ ጎረቤት በሆነችው ኬንያ ውስጥ በርካታ ጥቃቶች ያደርሳል። ባለፈው ወር የአል-ሻባብ ታጣቂዎች ኬንያ ውስጥ የኬንያና አሜሪካ ወታደሮች የሚገለገሉበትን ካምፕ አጥቅተው ሶስት አሜሪካውያንን መግደላቸው አይዘነጋም። ሶማሊያ፡ በደም የተሸፈነችው ምድር
news-57088297
https://www.bbc.com/amharic/news-57088297
በኢትዮጵያ የጨቅላ ህፃናትን ሞት መቀነስ እንዳልተቻለ ተጠቆመ
በኢትዮጵያ የጨቅላ ህፃናት ሞት መጠን ከ 1 ሺህ በህይወት ከሚወለዱት መካከል 33ቱ እንደሚሞቱ የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ተቋም አስታውቋል።
ይህም አሃዝ ከአምስት አመት በፊት ከአንድ ሺህ ህፃናት 29 ሞት ከነበረው ጭማሬ ማሳየቱም ተገልጿል። ለህፃናቱ ሞት ምክንያቶች ተብለው የተገለፁትም በዋነኝነት የጨቅላ ህፃናት መታፈን (Asphyxia)፣ ኢንፌክሸን እና ያለ ጊዜያቸው የሚወለዱ ህፃናት ናቸው ተብሏል። ከዚህም በተጨማሪ የቅድመ ወሊድ ክትትል አለማድረግ ፣ በጤና ማዕከላት አለመውለድ ቢወለዱም በቂ እና ጥራት ያለው አገልግሎት አለማግኘት፣ ሌሎች ምክንያቶች እንደሆኑም ተገልጿል። በባለፉት 10 አመታት የእናቶች ሞትን መቀነስ ቢቻልም የጨቅላ ህፃናት ሞት ግን መቀነስ ባለመቻሉ ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሻም ተገልጿል። ተቋሙ ይህንን ያስታወቀው በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ባወጣው መግለጫ ሲሆን የጨቅላ ህፃናትን ሞት ለመቀነስ ይቻል ዘንድ ከሚያዝያ 28-29 2013 ዓ.ም በቀረበ ፖሊሲ ላይ በቢሾፍቱ ከተማ ውይይት ተካሂዷል። በዚህ መድረክ ላይም የፓርላማ አባላት፣ ጤና ሚኒስቴርን ጨምሮ ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት ተገኝተዋል። በውይይት መድረኩ ላይም የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ተቋም የምርመራ ትግበራ ዳይሬክቶሬት ተቀዳሚ ዳይሬክተር ወይዘሪት ፊርማዬ እንደገለፁት ውይይቱ በዋነኝነት የጨቅላ ህፃናትን ሞት ለመቀነስ የሚደረውን ሃገር አቀፍ እንቅስቃሴ በመረጃ መደገደፍና ብሔራዊ የጨቅላ ህፃናትና ልጆች ስትራቴጂ ግብአት እንዲሆን ማድረግ ነው ብለዋል። የጨቅላ ህፃናትን ሞት ለመቀነስ መፍትሄ ተብለው ከቀረቡ ኃሳቦችም መካከል የጤና አገልግሎትን ማጠናከር፣ ከቅድመ እርግዝና ጀምሮ የእናቶችና የጨቅላ ህፃናትን የጤና አገልግሎትን ማሻሻልና በየደረጃው ለሚሰጠው አገልግሎት የጥራት ደረጃ ማስቀመጥ መሆናቸውም ተገልጿል። ከዚህም በተጨማሪ ከህክምና ቁሳቁስ አቅርቦት እና መሰረተ ልማት ጋር የተገናኙ ችግሮችም ሊፈቱ ይገባል ተብሏል።
news-49527349
https://www.bbc.com/amharic/news-49527349
ቅዱስ ሲኖዶስ የኦሮሚያ ቤተክህነት አደራጅ ኮሚቴ የጠራውን መግለጫ መንግሥት እንዲያስቆም ጠየቀ
የኦሮሚያ ቤተክህነት አደራጅ ኮሚቴ የጠራውን መግለጫ መንግሥት እንዲያስቆም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሲኖዶስ ጠየቀ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቤተ ክህነት በኦሮሚያ ቤተክህነት አደራጅ ኮሚቴ የተጠራውን መግለጫ እንደማያውቀውና እውቅናም እንዳልሰጠው የጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ስራ አስኪያጅ ርዕሰ ደብር መሀሪ ኃይሉ በዛሬው የቅዱስ መግለጫ ላይ ተናግረዋል። በተጨማሪም የኦሮሚያ ቤተክህነት አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ቀሲስ በላይ መኮንን ምንም እንኳ በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ትልቅ ሃላፊነት የነበራቸው ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን የኦሮሚያ ክልል እንባ ጠባቂ ቢሮ ሃላፊ መሆናቸውን የቤተክህነት የስብከተ ወንጌል እና ሃዋሪያዊ ተልእኮ መምሪያ ሃላፊ የሆኑት አቶ ሶሎሞን ቶልቻ ገልፀዋል። ቅዱስ ሲኖዶስ የኦሮሚያ ቤተክህነትን የማቋቋም ጥያቄ መምጣት ያለበት ምእመናኑ ተወያይቶበት እንጂ በተወሰኑ ሰዎች ፍላጎት መሆን የለበትም ብሏል። ከቀናት በፊት ቢቢሲ ያናገራቸው የአደራጅ ኮሚቴው ሰብሳቢ ቀሲስ በላይ የኦሮሚያ ቤተክህነትን የማቋቋም ጥያቄ ከማንነት እና ከቋንቋ ጋር የሚገናኝ እንደሆነ ገልፀው ነበር። ኮሚቴው ጥያቄውን ለቅዱስ ሲኖዶስ አቅርቦ ምላሽ እየጠበቀ እንደነበርም ገልፀው ነበር። • የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን መነኮሳት ጳጳስ በመግደል ተከሰሱ
news-43806424
https://www.bbc.com/amharic/news-43806424
ዳይመንድ ድረገጹ ላይ በለቀቀውን ቪዲዮ ለእስር ተዳረገ
ከአፍሪካ እውቅ ድምጻውያን መካከል አንዱ የሆነው ዳይመንድ ፕላትነምዝ በኢንስታግራም ገጹ ላይ ከአንዲት ሴት ጋር ሲሳሳም የሚያሳይ ምስል ከለቀቀ በኋላ በታንዛኒያ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።
ፖሊስ የእውቁ ድምጻዊ ተግባር አሳፋሪ እና የማህብረሰቡን እሴት የጣሰ ነው ብሏል። ዳይመንድ ከሳምንታት በፊት የተለያዩ ሽልማቶችን ያገኘበት ''ቦንጎ ፍላቭ'' የተሰኘው የሙዚቃ ቪዶዮ በታንዛንያ መንግሥት ወሲብ ቀስቃሽ ምስሎች እና ግጥሞች አሉበት በሚል በአገሪቱ እንዳይታይ ካገደ በኋላ የትውልድ ሃገሩን ጥሎ እንደሚወጣ ዝቶ ነበር። የኢንፎርሜሽን ሚንስትሩ ሃሪሰን ማክዌምቤ ለምክር ቤት አባላት እንደተናገሩት ሙዚቀኛው ከጥቂት ሳምንታት በፊት የተላለፈውን የኤሌክትሮኒክ እና ፖስታል ህግጋትን ተላልፏል። ዳይመንድ በኢንስታግራም ገጹ ላይ የለጠፈውን ተንቀሳቃሽ ምስል የሰረዘ ቢሆንም የታንዛኒያ ባለስልጣናት ግን በሙዚቀኛው ላይ ክስ ለመመስረት ተዘጋጅተዋል። አምስት ነጥቦች ስለ ዳይመንድ ፕላትነምዝ ዳይመንድ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ የ5 ሚሊየን የታንዛኒያ ሽልንግ ቀጣት ወይም የ12 ወራት እስር ይጠብቀዋል። እራሱን መከላከል ካልቻለ ደግሞ የእስር እና የገንዘብ ቅጣቱ ይጠብቀዋል ተብሏል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የዳይምንድ አድናቂዎች መንግሥት አዲስ ህግ በማርቀቅ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን እየተላለፈ ነው በማለት ይተቻሉ። የታንዛንያ መንግሥት በበኩሉ የአገሪቱን ''ባህል እና ወግ'' እየጠበቅን ነው ይላል።
news-56439795
https://www.bbc.com/amharic/news-56439795
ትግራይ፡ መንግሥት ከህወሓት ጋር የተባበሩ በሠላም እንዲመለሱ ተፈላጊዎች ደግሞ እጅ እንዲሰጡ የጊዜ ገደብ አስቀመጠ
የኢትዮጵያ መንግሥት ከህወሓት ጋር በተያያዘ በወንጀል ድርጊት ተጠርጥረው የመያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸው እጃቸውን እንዲሰጡ ሌሎች ደግሞ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ወደ ሠላማዊ ህይወት እንዲመለሱ ጥሪ አቀረበ።
ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት "ከሕገ ወጡ የህወሓት ቡድን ጋር ለተባበሩ አካላት የተሰጠ የመጨረሻ ማሳሰቢያ" በሚል በወጣው መግለጫ መንግሥት በህወሓት ላይ በወሰደው ሕግን የማስከበር እርምጃ የቡድኑ ወታደራዊ አቅምና ዝግጁነት በከፍተኛ ደረጃ መደምሰሱን ገልጿል። በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ ትግራይ ውስጥ በሚገኘው የአገር መከላከያ ሠራዊት የሠሜን ዕዝ ላይ የህወሓት ኃይሎች ጥቃት ከፈጸሙ በኋላ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ማዘዛቸው ይታወሳል። ለሦስት ሳምንታት በተካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ ክልሉን የመንግሥት ኃይሎች የክልሉን ዋና ከተማ መቀለን ሲቆጣጠሩ የትግራይ ክልልን ለሦስት አስርት ዓመት ሲያስተዳድር የነበረው ህወሓት ከስልጣኑ ተወግዷል። ይህንን ተከትሎም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የህወሓትን ሕጋዊ ሰውነት መሰረዙን አስታወቋል። በወቅቱ ምርጫ ቦርድ በሰጠው መግለጫ ፓርቲው ሃይልን መሠረት ያደረገ የአመፃ ተግባር ላይ መሳተፉን ማረጋገጡን ገልጾ ነበር። የተካሄደውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ በክልሉ ውስጥ ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳት መድረሱን የሚያመለክቱ ሪፖርቶች እየወጡ ነው። መንግሥት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ከደረሰው ጉዳት በኋላ የክልሉን አስተዳደርና ልማትን ለማሻሻል የክልሉ ተወላጆች ሚና ወሳኝ መሆኑን ጠቅሶ፤ ነገር ግን "አንዳንዶች በህወሓት ፕሮፓጋንዳና አሰገዳጅነት ነፍጥ አንስተው በውጊያ ሜዳ ላይ አስከመሰለፍ ደርሰዋል" ሲል አመልክቷል። ጨምሮም መንግሥት እነዚህ ዜጎች ዋነኛ ፈጻሚዎች አይደሉም በማለት "ከዝርፊያና ከምዝበራው ተሳታፊ ያልነበሩና. . . በቡድኑ ቅስቀሳ መሳሪያ ታጥቀው የተሰለፉ በመሆናቸው መንግሥት ጉዳያቸው በሆደ ሰፊነት መታየት እንዳለበት ያምናል" በማለት ወደ ቀደመ ህይወታቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቧል። በመሆኑም በተፈጸሙ ጥቃቶችና ከዚሁ ጋር በተያያዙ የወንጀል ተግባራት ጉልህ ተሳትፎ አላቸው ተብለው ከተጠረጠሩና የፍርድ ቤት መያዣ ትዕዛዝ ከወጣባቸው የህወሓት ወታደራዊና የፖለቲካ አመራሮች በስተቀር ሌሎቹ ያለምንም የሕግ ተጠያቂነት በሰላም ወደ ኑሯቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቧል። ለዚህመም መንግሥት የአንድ ሳምነት የጊዜ ገደብ ያስቀመጠ ሲሆን ለዚህም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ በክልሉ ላሉ የጸጥታ፣ የአስተዳደርና የሕግ አካላት መመሪያ መሰጠቱን ገልጿል። በተጨማሪም ፈጽመውታል በተባሉ የወንጀል ድርጊቶች የተጠረጠሩና ከፍተኛ ተሳትፎ አላቸው ተብለው እየተፈለጉ የሚገኙ የህወሓት ወታደራዊና የፖለቲካ አመራሮችም እጃቸውን በሠላም እንዲሰጡ ጥሪ አቅርቧል። ከዚህ ውጪ በተሰጠው የጊዜ ገደብ በቀረበው ጥሪ መሠረት ወደ ሠላማዊ ኑሯቸው ያልተመለሱና ተፈላጊዎችም ለሕግ አስከባሪ አካላት እጃቸውን ካልሰጡ "ሕግ ለማስከበር ሲባል አስፈላጊው ሁሉ የሚፈጸም ይሆናል" ሲል አስጠንቅቋል። በትግራይ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር በተያያዘ በርካታ የህወሓት የፖለቲካና ወታደራዊ አመራሮች ላይ ቡድኑን በበላይነት በመምራት፣ በትግራይ ክልል በሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት የሠሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈፀም፣ የአገር ክህደት ወንጀል በመፈጸምና በሌሎችም ወንጀሎች ተጠርጥረው የመያዣ ትዕዛዝ እንደወጣባቸው ይታወሳል። በተጨማሪም የቀድሞው የአገሪቱ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም የነበሩት ሜጀር ጄኔራል ጻድቃን ገብረተንሳይን ጨምሮ፣ ከፍተኛ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ኃይል፣ የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አመራሮችም በአገር ክህደትና በሠራዊት አባላት ላይ በተፈጸመ ወንጀል ተጠርጥረው የእስር ትዕዛዝ ወጥቶባቸዋል። ይህንንም ተከትሎ ባለፉት ወራት ውስጥ የቀድሞ የህወሓት አመራሮችን ጨምሮ በአገሪቱና በክልሉ የሲቪልና ወታደራዊ ከፍተኛ ኃላፊነቶች ላይ የነበሩ በርካታ የቡድኑ አባላት በቁጥጥር ስር ሲውሉ ሌሎች ደግሞ መገደላቸው ተገልጿል።
49080466
https://www.bbc.com/amharic/49080466
አሜሪካ ስደተኞችን ፍርድ ቤት ሳታቀርብ ወደመጡበት አገር መመለስ ልትጀምር ነው
የአሜሪካ መንግሥት የስደተኞች ፍርድ ቤትን አልፎ ስደተኞችን በፍጥነት ወደ መጡበት አገር ለመመለስ የሚያስችል መመሪያ አወጣች።
በአዲሱ ደንብ መሰረት ማንኛውም ማስረጃ የሌለው ስደተኛና በተከታታይ ለሁለት ዓመት አሜሪካ ውስጥ እንደነበር ማረጋገጥ ያልቻለ ግለሰብ ወደ መጣበት አገር እንዲመለስ ይደረጋል። ፖሊሲው ዛሬ ይፋ ተደርጎ በሁሉም የአሜሪካ ግዛቶች በአፋጣኝ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል ተብሏል። አሜሪካን ሲቪል ሊበርቲስ ዩኒየን የተባለ የመብት ተሟጋች ቡድን ፖሊሲውን በመቃወም ፍርድ ቤት ወስዶ ለመሟገት ማሰቡን ተናግሯል። የአሜሪካ የስደተኞች ፖሊሲ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጥብቅ እየሆነ እየመጣ መሆኑን የሚያስረዱ አካላት፤ አገሪቱ በደቡብ በኩል ከሜክሲኮ ጋር በሚያዋስናት አካባቢ የምታደርገውን በመጥቀስ የጉዳዩን አሳሳቢነት ያብራራሉ። • የሱዳን አማጺ መሪ ከአዲስ አበባው ድርድር ሊባረሩ እንደነበር ተነገረ • ከአዞዎች ጋር ለ30 ዓመታት የኖሩት ኢትዮጵያዊ የአገር ውስጥ ደህነንነት መሥሪያ ቤቱ ተጠባባቂ ዋና ጸሀፊ ኬቨን ማክአሌናን፤ "ይህ ለውጥ በድንበር አካባቢ ያለብንን ጫናና የአቅም ጉዳይ ያነሳልናል" ሲሉ አሞካሽተውታል። አክለውም "ቀጣይነት ላለው የስደተኞች ቀውስ ምላሽ የሚሰጥ" ብለውታል። የአሜሪካ የስደተኞች ጉዳይ ላይ ትንታኔ የሚሰጡ ባለሙያዎች በበኩላቸው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለ2020 ምርጫ ስደተኞችን መቆጣጠርን ቁልፍ ጉዳይ ለማድረግ መወሰናቸውን ያሳያል ይላሉ። ምንድን ነው የተለወጠው? ከዚህ ቀደም ሰዎች ወደ መጡበት አገር ወዲያውኑ እንዲመለሱ የሚደረገው ከአሜሪካ ድንበር በ160 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ውስጥ ሲገኙና አሜሪካ ከገቡ ከሁለት ሳምንት በታች የሆናቸው ከሆኑ ብቻ ነበር። በአገሪቱ የትኛውም አካባቢ የሚገኙ ስደተኞች ወይንም ከሁለት ሳምንት በላይ የሆናቸው ግለሰቦች ጉዳያቸው ወደ ፍርድ ቤት ተመርቶ ሕጋዊ ውክልና የማግኘት መብታቸው ተጠብቆ እንዲቆዩ ይደረግ ነበር። አዲሱ ሕግ ግን ማንኛውም ስደተኛ በየትኛውም የአገሪቱ ስፍራ ቢገኝ በቁጥጥር ስር ከዋለ ያለ ጠበቃ ውክልና ወደመጣበት እንዲመለስ ይደረጋል። ጥገኝነት ለመጠየቅ የሚያበቃ ምክንያት ያላቸው፤ የጥገኝነት ጉዳዮችን የሚከታተለውን ባለሙያ የማናገር መብት አላቸው ይላል። ምላሹ ምን ነበር? ሰኞ ዕለት ፖሊሲው በተዋወቀ በሰአታት ውስጥ የመብት ተሟጋች ድርጅቱ አሜሪካን ሲቪል ሊብረቲስ ዩኒየን ጉዳዩን ፍርድ ቤት በመውሰድ ለመሞገት ማሰቡን አስታውቋል። "ይህንን የትራምፕ እቅድ ለማስቆም በፍጥነት ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስደን ክስ እንመሰርታለን" ሲሉ በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል። • አዲሱ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ማን ናቸው? "በአሜሪካ ለረዥም ጊዜ የቆዩ ስደተኞች በትራፊክ ደህንነት ጥሰት ፍርድ ቤት ከሚቀርቡ ሰዎች ያነሰ በፍርድ ቤት የመከራከር እድል አላቸው" ሲሉም ምሬታቸውን ገልፀዋል። በሲቪልና ሰብዓዊ መብቶችን ጉባኤ ፕሬዝዳንት የሆኑት ቫኒታ ጉፕታ፤ የፕሬዝዳንት ትራምፕን እቅድ የስደተኞች ጉዳይ የሚያየውን ተቋም "ወረቀታችሁን አሳዩን ወደሚል ፈርጣማ ኃይል" እየቀየሩት ነው ብለዋል። የሕግ ባለሙያ የሆኑት ጃኪ ስቲቨንስ በበኩላቸው ወደመጣችሁበት አገር ተብለው ከሚመለሱ ሰዎች መካከል የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው እንደሚገኙበት ገልፀዋል።
43958910
https://www.bbc.com/amharic/43958910
እንግሊዝ፦ 'ከኢራን ጎን ነኝ'
እስራኤል እና አሜሪካ ኢራን የአቶሚክ መሳሪያዎችን እያመረተች ነው ብለው ቢከሱም፤ እንግሊዝ ከኢራን ጋረ የተደረሰውን በጣም ወሳኙን የኒውክሌር ስምምነት ደግፋለች።
እስራኤል ኢራን የአቶሚክ መሳሪያዎችን በድብቅ እያመረተች እንደሆነ የሚያሳይ መረጃ አለኝ ብትልም ኢራን ግን ጉዳዩን አልተቀበለችውም። አሜሪካ በበኩሏ 'የእስራኤል የመረጃ ምንጭ ታማኝና ቀጥተኛ ነው' ስትል ደግፋታለች። በ2015 ነበር ኢራን የኒውክሌር ማምረት ተግባሯን ለማቆምና ስድስት ሃገራት ደግሞ ተጥሎባት የነበረውን ማእቀብ ለማንሳት የተፈራረሙት። የእንግሊዝ መንግስት ቃል አቀባይ የሆኑ ግለሰብ "በስምምነቱ መሠረት የተመደቡት መርማሪዎች ያለ ማንም ተጽዕኖ ኢራን ስምምነቱን እንዳላፈረሰች እና በጣም ወሳኝ የሆኑ ሌሎች መረጃዎችን እያቀረቡ እንደሆነ አስረድተውናል" ሲሉ ይናገራሉ። ሰኞ ዕለት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የኢራን ሚስጥራዊ የኒውክሌር ማምረት ሂደት የሚያሳይ ያሉትን መረጃ ይፋ አድርገው ነበር። "በእስራኤል የተገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰነዶች እንደሚያሳዩት ኢራን የኒውክሌር ማምረቻ የለኝም በማለት ዓለምን እንደሸወደች ነው" ሲሉ ያክላሉ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር። ኢራን በበኩሏ፤ የእስራኤልን ውንጀላ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በግንቦት አጋማሽ ሃገራቸው በስምነቱ ትቀጥል ወይስ አትቀጥል የሚለውን ውሳኔያቸውን ላይ ጫና ለማደረግ የተቀነባበረ የህጻን ጨዋታ ነው ስትል ኣጣጥላዋለች። ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው ስምምነቱን የፈረሙት የአውሮፓ ሃገራት ችግሩን በአፋጣኝ እንዲፈቱት ካለሆነ ግን አሜሪካ ከኢራን ላይ ተነስቶ የነበረውን ማእቀብ ለማራዘም እንደምትቸገር ገልጸዋል። ዋይት ሃውስ በለቀቀው መግለጫ እንዳለው ስለ ኢራን ኒውክሌር ማምረት በእስራኤል የቀረበው መረጃ አዲስ እና ኣሳማኝ ነው። መግለጫው ሲያክልም ሰነዶቹ አሜሪካ ከሰነደችው መረጃ ጋር የሚመሳሰል እና ቀጥተኛ ሲሆን ኢራን ከዜጎቿ እና ከመላው ዓለም ልትደብቀው እየሞከረች ያለውን ሚስጥር ያጋለጠ ነው ብሏል።
56179065
https://www.bbc.com/amharic/56179065
ብርቱካን የኦነግ አመራሮችን እስር በተመለከተ 'ከሚመለከተው አካል ጋር' እየተነጋገርን ነው አሉ
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅዳ የኦነግ አመራሮችን እስር በተመለከተ 'ከሚመለከተው አካል ጋር' እየተነጋገርን ነው አሉ።
ሰብሳቢዋ ይህን ያሉት ቦርዱ ትናንት ከፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር በእጩዎች ምዝገባ እና ተያያዥ ጉዳያዎች ላይ ውይይት ባደረገበት ወቅት ነው። በውይይቱ ላይ ብርቱካን ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየተየ ያሉ እስረኞች በመጪው ምርጫ ለመወዳደር በእጩነት መመዝገብ አይችሉም ብለዋል። በዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ በቴ ኡርጌሳ፤ በፍርድ ቤት ጉዳያቸው የተዘጋ እነዲሁም ዐቃቤ ሕግ የማቀርበው ክስ የለም ያላቸው ነገር ግን በእስር ላይ የሚገኙ የኦነግ አባላት መኖራቸውን ገልጸዋል። አቶ በቴ "በሕግ መብታቸው ያልተገፈፈ" ግን በእስር ላይ የሚገኙ አባላትን በዕጩነት ማቅረብ ይቻላል ወይ? ሲሉ ጥያቄያ ሰንዝረዋል። የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ "በፍርድ ቤት ጉዳይ የሌላቸው" ነገር ግን በእስር ላይ የሚገኙ በተለይ የኦነግ አመራሮችን በተመለከተ "ከሚመለከተው አካል ጋር እየተነጋገርን ነው" ብለዋል። "[የፍርድ ቤት] ቀጠሮ እስከሌላቸው ድረስ በእስር የሚቆዩበት ምክንያት የለም" የሉት ሰብሳቢዋ፤ በጉዳዩ ላይ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ጋር እየተነጋገርን ነው ብለዋል። ነገር ግን በእስር ላይ ያሉና ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ያሉ እስረኞች በዕጩነት መቅረብ እንደማይችሉ ብርቱካን ተናግረዋል። ሰብሳቢዋ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ያሉ ሰዎችን በእጩነት ለመመዝገብ የምርጫ ሕጉ እንደማይፈቅድም አስረድተዋል። ከዚህ በተጨማሪ የኦጋዴነ ነጻነት ግንባር ተወካይ አቶ አህመድ መሐመድ መንግሥት በፓርቲያቸው ላይ የተለያዩ ጫናዎችን እያደረሰ እንደሆነ በመድረኩ ላይ ተናግረዋል። አቶ አህመድ ጽህፈት ቤቶቻቸው መዘጋታቸውን እና ለዕጩዎች ዝግጅት ወደ ወረዳዎች የተጓዙ የፓርቲው አባላት ወደ ጅግጅጋ እንዲመለሱ ተደርገዋል ብለዋል። ገዢውን ፓርቲ ወክለው በመድረኩ የተገኙት ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)፤ "ያለ አግባብ ሰው መታሰር የለበትም። ምርጫ እናዳምቃለን፤ እናሳምራለን ተብሎ ደግሞ የሕግ የበላይነት መጣስ የለበትም" ብለዋል። ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)፤ "የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች ላይ የሚደርስ ጫና ካለ ችግሩ አጋጠመ የተባለበት ቦታ በትክክል ይጠቀስ እኛ ከማዕከል ሰው እንመድባለን፤ ቦታ ድረስ ሄዶ አስፈላጊው የእርምት እርምጃ ይወሰዳል። . . . ይህ በሌላ ቦታ እንዳይደገም የእርምት እርምጃ ለመውሰድ ዝግጉ ነን" ብለዋል። "ከክልሎች በቂ ድጋፍ እያገኘን አይደለም" ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስፈላጊ የምርጫ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ከክልሎች በቂ ድጋፍ እያገኘ እንዳልሆነ አስታውቋል። ብርቱካን እያንዳንዱ ክልል ለምርጫ ቦርድ ሠራተኞች ተሽከርካሪ እንዲያቀርቡ ከአራት ጊዜ በላይ በደብዳቤ መጠየቃቸውን ተናግረው፤ እስካሁን አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረጉ ያሉት የአማራ እና የሶማሌ ክልሎች ብቻ ናቸው ብለዋል። ሠራተኞች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው ሥራቸውን መስራት ካልቻሉ ምርጫውን በታቀደው ጊዜ ማከናወን እንደማይቻል ያስጠነቀቁት ሰብሳቢዋ፤ ሆነ ተብሎም ይሁን በግዴለሽነት አስተዳደራዊ ትብብር አለማግኘት ለፓርቲዎች እና ለምርጫ ቦርድ ፈተና ሆኗል ብለዋል። የዕጩዎች በበቂ ቁጥር አለመመዝገብ በማክሰኞ ዕለት በተደረገው ውይይት ክፍት በተደረጉ የምርጫ ጣቢያዎች ዕጩዎች በበቂ ቁጥር እየተመዘገቡ እንዳለሆነ ብርቱካን ተናግረዋል። ሰብሳቢዋ ክፍት በሆኑ ጣቢያዎች ፓርቲዎች ዕጪዎቻቸውን እንዲያስመዘግቡ ጥሪ አስተላልፈዋል። ይሁን እንጂ በዕጩዎች ምዝገባ ወቅት ወጥነት የሌለው አሰራር በዕጩዎች ምዝገባ ወቅት ችግር እንደሆነ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ ተወካይ ተናግረዋል። የኢዜማ ተወካይ አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ዕጩዎችን ለማስመዝገብ ቦርዱ በይፋ ከጠቀሳቸው መሠፈርቶች በተጨማሪ ዕጩዎች ሌሎች ማስረጃዎችን እንዲያቀርቡ እየተጠየቁ መሆኑን ገልጸዋል። የመንግሥት ሠራተኞች በዕጩነት ለመመዝገብ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በሚያመሩበት ወቅት ከሚሰሩበት የመንግሥት መስሪያ ቤት የመልቀቂያ ደብዳቤ እንዲያመጡ ይጠየቃሉ ብለዋል። የቦርዱ ሰብሳቢ በበኩላቸው በዕጩነት ለመወዳደር መልቀቂያ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ዳኞች፣ ዐቃቤ ሕጋን እና የጸጥታ መዋቅር ሠራተኞች መሆናቸውን አስታውሰው፤ በዚህ ላይ ማስተካከያ እንደሚደረግ ተናግረዋል። በውይይቱ ላይ የኦነግ፣ የኢዜማ፣ የብልጽግና፣ የኦፌኮ እና የኦብነግን ጨምሮ የሌሎች ፓርቲ ተወካዮች ተገኝተዋል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የዕጩዎች ምዝገባ ከየካተቲት 8 ጀምሮ እስከ የካቲት 21 ድረስ ይካሄዳል ተብሏል። ይሁን እንጂ የቁሳቁስ አቅርቦት በተለያዩ ክልሎች በሁሉም ጣቢያዎች ማድረስ ባለመቻሉ፤ ይህን ተከትሎ ሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች ባለመከፈታቸው ሁለተኛ ዙር የዕጩዎች ምዝገባ እስከ መጋቢት 6 ድረስ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
news-47520898
https://www.bbc.com/amharic/news-47520898
ቻይና በቦይንግ 737 ማክስ 8 የሚደረጉ በረራዎችን አገደች
ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 737 አውሮፕላን ትላንት መከስከሱን ተከትሎ የቻይና አየር መንገዶች በቦይንግ 737 ማክስ 8 የሚደረጉ በረራዎችን እንዲያቆሙ የሃገሪቱ ኤቪዬሽን ተቆጣጣሪ መስሪያ ቤት አስታወቀ።
ማንኛውም የንግድ በረራ የሚያካሂዱ የቻይና አየር መንገዶች ከዛሬ ጠዋት 12 ሰአት ጀምሮ አውሮፕላኑን መጠቀም አይችሉም ተብሏል። አውሮፕላኑ ከቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የተነሳው ጠዋት 2፡38 ሲሆን ከ6 ደቂቃ በኋላ ከአብራሪዎቹ ጋር ይደረግ የነበረው ግንኙነት ተቋርጦ ከደቂቃዎች በኋላ መከስከሱ ተረጋግጧል። ቦይንግ 737 ማክስ 8 ከተባለው አውሮፕላን ጋር በተያያዘ አደጋ ሲከሰት ባለፉት ስድስት ወራት ይህ ሁለተኛው ነው። የዘርፉ ባለሙያዎች አደጋው በምን ምክንያት እንደተከሰት ለማወቅ ጊዜው በጣም ገና ነው ያሉ ሲሆን ባለፈው ጥቅምት ''የላየን'' አየር መንገድ ንብረት የሆነ ተመሳሳይ አውሮፕላን ተከስክሶ 189 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል። • ዶ/ር አምባቸው ማን ናቸው? የቻይናው ሲቪል ኤቪየሽን ባለስልጣን በሰጠው መግለጫ በአጭር ጊዜ ውስጥ አንድ የአውሮፕላን ሞዴል አደጋ ሲደርስበት በቸልታ ማለፍ ይከብደኛል ብሏል። ቻይና ውስጥ ከ90 በላይ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላኖች አገልግሎት የሚሰጡ ሲሆን ይህኛው ሞዴል ቦይንግ በቅርቡ በፈንጆቹ 2017 ዓ.ም. ነበር ለገበያ ያቀረበው። የአውሮፕላኑ አምራች ኩባንያ ቦይንግ በበኩሉ በተፈጠረው አደጋ እጅግ ማዘኑን በመግለጽ የቴክኒክ ድጋፍ የሚሰጥና የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት በሚደረገው ስራ ላይ እርዳታ የሚሰጥ ቡድን እንደሚልክ አስታውቋል። የምርመራ ሂደቱም የሚመለከታቸው የኢትዮጵያ መስሪያ ቤቶች ከቦይንግ ባለሙያዎችና ከአሜሪካ የትራንስፖርት ደህንነት መስሪያ ቤት ጋር በመተባበር የሚካሄድ እንደሆነ ተገልጿል። • በኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም የተቀሰቀሰው ውዝግብ የቻይና አየር መንገዶች የቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላንን መጠቀም የሚችሉት የኤቪዬሽን መስሪያ ቤቱ ወደፊት በሚሰጠው መግለጫ መሰረት እንደሆነ አስታውቋል። በትናንትናው ዕለት በቦይንግ 737 በረራ ቁጥር ET302 የ157 ሰዎችን ህይወት በቀጠፈው አሰቃቂ አደጋ ከሟቾቹ መካከል 8ቱ ቻይናዊያን መሆናቸው ታውቋል።
news-56197939
https://www.bbc.com/amharic/news-56197939
ከሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ተጠርጣሪዎች መካከል ላምሮት ከማል እንድትለቀቅ ሌሎቹ ደግሞ እንዲከላከሉ ተወሰነ
በድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ተጠርጥረው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከነበሩት መካከል አንዷ የሆነችው ላምሮት ከማል በነጻ እንድትለቀቅ ፍርድ ቤት ወሰነ።
በግድያው ተጠርጥረው መዝገብ ከተከፈተባቸው አራት ግለሰቦች ውስጥ ላምሮት ከማል ግድያውን በማመቻቸት ተጠረጥራ የነበረ ሲሆን ፍርድ ቤቱ በወንጀል ድርጊቱ ውስጥ ተሳትፎዋን የሚያረጋግጥ የሰውም ሆነ የሰነድ ማስረጃ ዐቃቤ ሕግ አለመቅረቡን በመግለጽ ነው እንድትለቀቅ የወሰነው። ዛሬ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ የፀረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ወንጀል ሁለተኛ ምድብ ችሎት የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን የሰው ማስረጃና የሰነድ ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ነው ብይን የሰጠው። ፍርድ ቤቱ አንደኛ ተከሳሽ ጥላሁን ያሚ የድምጻዊ ሃጫሉን ግድያ መፈፀሙን ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ መርምሮ ማረጋገጡን ገልጿል። አንደኛ ተከሳሽን በተመለከተ የፖለቲካ ተልዕኮን ከግብ ለማድረስ ሰዎችን በመግደል በመንግሥት ላይ ጫና ለመፍጠርና ሕዝብን ለማሸበር የሸኔ አባል ከሆነው ገመቹና ሌላ ለጊዜው ካልተያዘ ግለሰብ ተልዕኮ በመቀበል ሃጫሉን መግደሉን ዐቃቤ ሕግ ያቀረበው የሰውና የሰነድ ማስረጃ አረጋግጧል ብሏል። ከዚህ ውጪም ይህ ተከሳሽ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር እያለ እንዴት ወንጀሉን እንደፈፀመ ለፖሊስ በሚያሳይበት ወቅት ይህን ድርጊቱን እነዴት እንደፈፀመ በቪዲዮና በድምጽ ተቀርጾ ማሳየቱን ገልጿል። ከዚህም ውጪ ግለሰቡ ድምጻዊ ሃጫሉን የገደለበት ሽጉጥ ከአንደኛ ተከሳሽ ቤት መገኘቱ እንዲሁም ወንጀሉ የተፈፀመበት ቦታ የተገኙት ቀለህና እርሳስ ከሽጉጡ ውስጥ የተተኮሱ መሆናቸውን በተካሄደው የፎረንሲክ ምርምራ መረጋገጡን ፍርድ ቤቱ ተናግሯል። በዚሁ መረት የአንደኛ ተከሳሽ ጥላሁን ያሚ ጉዳይ ሽብርን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ቁጥር 1176/2012 በመተላለፉ እንዲታይና እንዲከላከል ተወስኗል። ሁለተኛ ተከሳሽ ከበደ ገመቹ የፖለቲካ አመለካከትን ከግብ ለማድረስ ሰዎችን በመግደል መንግሥት ላይ ጫና በመፍጠርና ሕዝብን ለማሸበር ድርጊቱን መፈፀሙን ዐቃቤ ሕግ ያቀረበው የሰውና የሰነድ ማስረጃ እንዳልተረጋገጠ ተናግሯል። ይሁን እንጂ ሁለተኛ ተከሳሽ ከበደ ገመቹ አንደኛ ተከሳሽ የሆነው ጥላሁን ያሚ በሚፈጽመው የዝርፊያ ድርጊት እንዲተባበረው አስማምቶ በግድያው ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆን እንዳደረገው መረጋገጡ ተገልጿል። ስለዚህ የግድያ ድርጊቱን ለመፈፀም አውቆና ተዘጋጅቶ ባለመሳተፉ ጉዳዩ በወንጀል ሕግ 1996 በወጣው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 540 ስር እንዲታይና እንዲከላከል ተወስኗል። በሌላ በኩል ሦስተኛ ተከሳሽ አብዲ አለማየሁ ድርጊቱን መፈፀሙ ያልተረጋገጠ ሲሆን፣ ነገር ግን ድርጊቱ በሚፈፀምበት ወቅት አይቶ ለሕግ አካል ባለማሳወቁ ጉዳዩ በ1996 በወጣው የወንጀል እግ አንቀጽ 443/1ሀ ስር እንዲታይና እንዲከላከል ተወስኗል። በመጨረሻም ፍርድ ቤቱ ከአንድ እስከ ሦስት ያሉትን ተከሳሾች ጥላሁን ያሚ፣ ከበደ ገመቹ እና አብዲ አለማየሁ የመከላከያ ማስረጃን ለመስማት ለመጋቢት 20 እና 21/2013 ቀጠሮ ይዟል። ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ አዲስ አበባ ውስጥ የተፈጸመውን የታዋቂውን ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ተከትሎ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በተከሰተ አለመረጋጋት ከ150 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን በመቶ ሚሊዮኖች የሚገመት ንበረት መውደሙ ይታወሳል። ከተከሰተው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ በርካታ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችና አመራሮችን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው እንደነበር በወቅቱ ተገልጿል።
news-56622890
https://www.bbc.com/amharic/news-56622890
ራፐር ዲኤምኤክስ ባጋጠመው የልብ ህመም ምክንያት ሆስፒታል ገባ
አሜሪካዊው የራፕ ሙዚቃ አቀንቃኝ እና ተዋናይ ዲኤምኤክስ የልብ ህመም አጋጥሞት ሆስፒታል መግባቱን ጠበቃው ሙሪ ሪችማን ተናገሩ።
ሪችማን ለአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን እንደገለጸው ድምጻዊውን ያጋጠመው የልብ ህመም ከፍተኛ መጠን ያለው መድኃኒት ከመውሰድ ጋር የተያያዘ ይሆን አይሆን እንደማያውቅ መናገሩን ቲኤምዚ ዘግቧል። ዲኤምኤክስ ለዓመታት ከአደንዛዥ ዕፅ ሱሰኝነት ጋር ሲታገል የነበረ ሲሆን በተደጋጋሚ ወደ ማገገሚያ ገብቶ ነበር። በአድናቂዎቹ የሂፕ ሆፕ ታላቅ ሰው ተደርጎ የሚታየው ራፐሩ፣ ፊልሞች ላይ ከመሳተፍ በተጨማሪ ከጄይ ዚ፣ ጃ ሩል፣ ኢቭ እና ኤልኤል ኩል ጄ ጋር በጋራ የተለያዩ ሙዚቃዎችን ተጫውቷል። ዲኤምኤክስ በሙያው ከ20 ዓመት በላይ የቆየ ሲሆን ክሬድል 2 እና ሮሚዮ መስት ዳይ ፊልሞች ላይ ከጄት ሊ ጋር ተውኗል። የ50 ዓመቱ ራፐር የመታወቂያ ስሙ አርል ሲመንስ ሲሆን ሆስፒታል የገባው አርብ ማታ መሆኑን ጠበቃው አክሎ ተናግሯል። በዙሪያው ቤተሰቦቹ መኖራቸውንም ገልፀዋል። "በመተንፈሻ መሳሪያ ታግዞ ነበር የሚተነፍሰው፤ አሁን ግን እርሱ ተነቅሎ በራሱ እየተነፈሰ ነው" ብሏል ጠበቃው። የ15 ልጆች አባት የሆነው ራፐሩ ከዚህ ቀደም የጦር መሳሪያ እና አደንዛዥ ዕፅ በመያዝ፣ በግዴለሽነት በማሽከርከርና በእንስሳት ላይ ያልተገባ ነገር በመፈጸም እስር ቤት ገብቶ ያውቃል። እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2018 በታክስ ማጭበርበር ተከስሶ ችሎት ፊት በቀረበበት ወቅት ከሙዚቃ ሥራዎቹ መካከል አንዱን ለዳኛው በመጫወት የመገናኛ ብዙሃን ደጋግመው ስሙን ያነሱት ነበር። በወቅቱ ዳኛው ሙዚቃውን ካዳመጡ በኋላ ዲኤምኤክስ "መልካም ሰው ነው" በማለት የአንድ ዓመት እስር ብቻ ፈርደውበታል። በ2016 ደግሞ በኒው ዮርክ ከተማ በሚገኝ አንድ ሆቴል የመኪና ማቆሚያ ስፍራ ላይ ሳለ ለመተንፈስ ተቸግሮ የህክምና እርዳታ ለማግኘት ወደ ሆስፒታል ተወስዶ ነበር። ጠበቃው "አርል በጣም መልካመ ሰው ነው፤ ታሪክ መናገር የሚችል እጅግ መልካም ሰው" በማለት በደረሰበት የጤና መታወክ የተሰማውን ሐዘን ገልጿል።
news-48628094
https://www.bbc.com/amharic/news-48628094
ባቡር ላይ የተወለደችው ህጻን ለ25 ዓመታት ነጻ የባቡር ትኬት ተሰጣት
በአየር ላንድ ባቡር ውስጥ የተወለደችው ጨቅላ ለ25 ዓመታት በባቡር በነጻ ለመጓዝ የሚያችል ስጦታ ተበርክቶላታል።
ከጋልዌይ ወደ አየር ላንድ መዲና ደብሊን ይጓዝ በነበረው ባቡር ላይ ተሳፍራ የነበረችው ነብሰ ጡር እናት ድንገት ምጥ ይዟት ባቡሩ ላይ ሴት ልጅ በሰላም ተገላግላለች። በባቡሩ ላይ ተሳፍረው የነበሩ አንድ ዶክተር እና ሁለት ነርሶች እናቲቷን አዋልደዋታል። • ያለ እናት የመጀመሪያው የእናቶች ቀን • ከወለደች ከ30 ደቂቃዎች በኋላ ለፈተና የተቀመጠችው እናት በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ የተነገረላቸው እናቲቱ እና አዲስ የተወለደችው ህጻን፤ ደብሊን ከደረሱ በኋላ ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። የአየር ላንድ ምድር ባቡር ተወካይ ህጻኗ ከልጅነት እሰከ 25 ዓመት እስኪሞላት ድረስ ምድር ባቡሩ የነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጣታል ብለዋል። በባቡሩ ላይ የምግብ አገልግሎት አቅራቢ ከሆኑት መካከል አንዷ ለመገናኛ ብዙሃን ስትናገር፤ ከመጸዳጃ ቤት ውስጥ አንዲት ሴት ስታቃስት ስሰማ አንድ ችግር እንዳለ ተረዳሁ ትላለች። የመጸዳጃ ቤቱን በር ስትከፍት በምጥ የተያዘች ሴት ማየቷን እና እርዳታ እንደታገኝ ለባቡሩ ሹፌር እና ከተሳፋሪዎች መካከል ሃኪሞች ካሉ በሚል ጥሪ ማድረጓን ታስረዳለች። ባቡሩ ከጋልዌይ ወደ አየር ላንድ መዲና ደብሊን እየተጓዘ ነበር። በባቡሩ ከተሳፈሩት መካከል የህክምና ዶክተሩ አለን ዲቫይን ይገኙበታል። • ወንበር የሚለቅላት አጥታ ልጇን ቆማ ያጠባችው እናት • ሰማይ ላይ ወልዳ አሥመራ የምትታረሰው ኢትዮጵያዊት ዶክተር አለን አርቲኢ ለተሰኘ መገናኛ ብዙሃን ሲናገሩ ''ዘግይቼ ነበር የደረሰኩት፤ በቦታው ስደርስ ሁለት ነርሶች ለወላዷ ጥሩ ድጋፍ እያደረጉላት ነበር'' ብለዋል። ከ20 ደቂቃ ምጥ በኋላ እንደተገላገለች የሚናገሩት ዶክተሩ፤ በባቡሩ ላይ ተሳፋሪ የነበሩት ነርሶች ሙያዊ ስነ-ምግባርን በጠበቀ መልኩ አስደናቂ ሥራ ሰርተዋል ሲሉ አሞካሽተዋቸዋል። የባቡር ጣቢያው ተወካይም ሰራተኞቻችን እና ደንበኞቻችን እናቲቱ በሰላም እንድትገላገል ባደረጉት ትብብር እጅጉን ተደስተናል ብለዋል።
news-49194526
https://www.bbc.com/amharic/news-49194526
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት የአሜሪካ ዜግነታቸውን በይፋ መለሱ
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆ በይፋ የአሜሪካ ዜግነታቸውን መተዋቸውን ከፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት የወጣ መግለጫ አመለከተ።
ምንም እንኳን የሶማሊያ ሕገ መንግሥት ጥምር ዜግንትን የሚፈቅድ ቢሆንም ፕሬዝዳንቱ ከሁለት ዓመት በፊት የሶማሊያን የመሪነት መንበር ሲረከቡ የአሜሪካ ፓስፖርታቸውን ለመመለስ መወሰናቸው ተገልጿል። • ብዙ ባሎችን አግብታለች የተባለች ሴት በአልሻባብ ተገደለች • የጋዜጠኛዋ መገደል ለምን የዓለም መነጋገሪያ ሆነ? ከ28 ዓመታት በፊት ሶማሊያ ውስጥ የአርስ በርስ ጦርነት በተጀመረበት ጊዜ ሞሃመድ ፋርማጆ ትምህርታቸውን ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ እየተከታተሉ ነበር። ግጭቱ ለዓመታት በመቀጠሉ ጥገኝነት ጠይቀው እዚያው በመኖራቸው ዜግነትን ለማግኘት ችለው ነበር። ሞሃመድ ፋርማጆ አሜሪካ ውስጥ በምትገኘው የቡፋሎ ከተማ የትራንስፖርት መስሪያ ቤት ውስጥ በመስራት ላይ ሳሉ ነው የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ ጥሪ የቀረበላቸው። ከአስር ዓመት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትርነቱ ቦታ ላይ ለስምንት ወራት ብቻ አገልግለው ወደ አሜሪካ ተመልሰው ነበር። • የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ከኢትዮጵያና ኤርትራ ጋር ባላቸው ግንኙነት ጥያቄ ቀረበባቸው • የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይቅርታ ጠየቀ ሞሃመድ ፋርማጆ ከሦስት ዓመታት በፊት ቤተሰቦቻቸውን ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ትተው እንደገና ወደ ሶማሊያ በመመለስ ለፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር እጩነታቸውን አሳወቁ። ሶማሊያ ለሦስት አስርት ዓመታት በጦርነትና በግጭት ስትታመስ በመቆየቷ የተነሳ የወቅቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ጨምሮ በርካታ ፖለቲከኞች ጥምር ዜግነት አላቸው። ፕሬዝዳንቱ የአሜሪካ ዜግነታቸውን የተዉት የተለያዩ ጥቅሞችን በሚያስገኘው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የአሜሪካን ዜግነት ይዘው መሳተፍ ባለመቻላቸው ይሁን ወይም በሌላ ግልጽ አልሆነም። ሞሃመድ ፋርማጆ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሆነው ከተመረጡ ጊዜ አንስቶ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኒው ዮርክ ውስጥ በየዓመቱ በሚያካሂደው ጉባኤ ላይ ተሳትፈው አያውቁም።
news-47689737
https://www.bbc.com/amharic/news-47689737
የሩስያ የጦር አውሮፕላኖች ቬኔዝዌላ ገቡ፤ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ተሰግቷል
ቅዳሜ ሁለት የሩስያ የጦር አውሮፕላኖች ቬኔዝዌላ ዋናው አየር መንገድ ገብተዋል። አውሮፕላኖቹ በርካታ መሣሪያዎችንና ተዋጊዎችን ጭነው ነው ካራካስ የደረሱት።
አውሮፕላኖቹ 'ለአንዳንድ ቴክኒካዊ ድጋፍ' ነው የገቡት ብሏል አንድ የሩስያ ዜና ወኪል። ማዮርካ የተባለ የቬኔዝዌላ ጋዜጠኛ በትዊተር ሰሌዳው እንደፃፈው ከሆነ ቢያንስ መቶ የሚሆኑ ወታደሮችን በርከት ካሉ የጦር መሣሪያዎች ጋር መመልከቱን ተናግሯል። ይህ የሆነው ሁለቱ ሃገራት የጋራ ወታደራዊ ንግግር ካደረጉ ከሦስት ወር በኋላ መሆኑ ነው። • ቬንዙዌላ በተቃዋሚ መሪው ላይ የጉዞ እገዳ ጣለች ሩስያ የቬኔዝዌላ አጋር ከሆነች ሰንበትበት ብሏል። በተይም ለነዳጅ ሃብቷ ማበልፀጊያና ለጦር ሠራዊቷ ማዘመኛ የሚሆኑ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ብድሮችን ለማዱሮ መንግሥት ሰጥታለች። ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮን የሚቃወሙ የምዕራብ መንግሥታትን በመገሰፅም ትልቅ ሚናን ስትጫወት ቆይታለች፣ ሩስያ። በፀጥታው ምክር ቤት ቬኔዝዌላ ለመቅጣት የሚወጡ ውሳኔዎችን በመቀልበስም አጋርነቷን አስመስክራለች። ቬኔዝዌላዊው ጋዜጠኛ ማዮርካ እንደሚለው ከሆነ አንቶኖቭ አየር ኃይል-124 ካርጎ ትንንሽ ጀቶችንና የጦር መሣሪያዎችን ይዞ ነው ካራካስ የደረው። ቡድኑን ይዘው የመጡትም የሩስያ ጄኔራል ቫሲሊ ቶንኮሽኩሮቭ ናቸው። ሩስያ ምዕራባዊያን በቬኔዝዌላ ጉዳይ እጃቸውን እንዳያስገቡ እያስጠነቀቀች ቆይታለች። አሜሪካ በበኩሏ ኒኮላስ ማዱሮን ሥልጣናቸውን እንዲለቁ ግፊት ከማድረግም አልፋ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችንም አቋርጣ ቆይታለች። ለማዱሮ ተቃዋሚ ጓይዶ ሙሉ ድጋፍ በመስጠት ሁሉን አቀፍ ዲፕሎማሲያዊ እርዳታ ስታደርም ነበር። እጅግ ተወዳጅ እንደነበሩ የሚነገርላቸው ፕሬዝዳንት ሁጎ ቻቬዝ በ2013 ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ እንዲተኳቸው ያዘጋጇቸው ሰው ኒኮላስ ማዱሮን ነበር። • ዋና የደስታ አስፈፃሚ ሥራ ምንድን ነው? ማዱሮ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ ግን የቬኔዝዌላ ምጣኔ ሀብት ተንኮታኩቶ ቆይቷል። ሃገሪቷም በዋጋ ግሽበት ቁም ስቅሏን ስታይ ነበር። እጅግ ሰፊ የነዳጅ ሃብት ያላት ቬኔዝዌላ ሕዝቦቿ በችግር ተተብትበው አንዳንዴም የሚላስ የሚቀመስ ያጡበት ሁኔታ ተፈጥሮ ያውቃል። ባለፉት ሳምንታት እንኳ አብዛኛው የሃገሪቱ ክፍል መብራት በፈረቃ ለማድረግ ተገዶ ነበር። በርካታ ቬኔዝዌላዊያን ችግሩ ሲጠናባቸው ወደ ጎረቤት ሃገራት መሸሽ ጀምረዋል። እስከዛሬ ከ3 ሚሊዮን የማያንሱት ዜጎች ከሃገር መውጣታቸው ተዘግቧል። አሁን ሩስያ የጦር አውሮፕላኖችን ወደ ካራካስ መላኳ ምናልባት ኃያላኑ ቬንዝዌላን የጦር አውድማ እንዳያደርጓት ተሰግቷል። ሩስያ ለመውደቅ ጫፍ ደርሶ የነበረውን የሦሪያ መንግሥትን በመደገፍና በምዕራባዊያን ከሚደገፉ ኃይሎች ጥቃት በመከላከል የአሳድን አስተዳደር ከመንኮታኮት በመታደግ የተሳካ ተግባርን ማከማወኗ አይዘነጋም።
news-53680864
https://www.bbc.com/amharic/news-53680864
ትግራይ፡ በትግራይ በምርጫ ሥርዓትና በምክር ቤት መቀመጫ ብዛቱ ላይ ለውጥ ተደረገ
የትግራይ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባው በክልሉ ሕገ መንግሥት ላይ ማሻሻያ በማድረግ የምርጫ ሥርዓት ለውጥና በምክር ቤቱ ውስጥ ባለው የመቀመጫ ብዛት ላይ ጭማሪ አደረገ።
ምክር ቤቱ በስብሰባው የክልሉን ሕገ መንግሥት አንቀጽ 48ን በማሻሻል ነው የምክር ቤቱ የመቀመጫ ቁጥር እንዲጨምርና እስካሁን የነበረውን የምርጫ ሥርዓት ያሻሻለው። በምክር ቤቱ ውሳኔ መሰረት በክልሉ ከዚህ በፊት የነበረውን የአብላጫ ድምጽ የምርጫ ሥርዓት በመቀየር በ"ቅይጥ ትይዩ የምርጫ ሥርዓት" እንዲተካ በማድረግ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል። በተጨማሪም በምክር ቤቱ ውስጥ ካሉ መቀመጫዎች ውስጥ 80 በመቶዎቹ የአብላጫ ድምጽ ባገኘው የፖለቲካ ድርጅት የሚያዙ ሲሆን፣ 20 በመቶው ደግሞ በተመጣጣኝ ውክልና ለተወዳዳሪ ድርጅቶች እንደሚከፋፈል ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል። ከዚህ ጋር ተያይዞም አስካሁን ድረስ በክልሉ ምክር ቤት የነበረው የመቀመጫ ብዛት 152 ሲሆን፤ በማሻሻያው መሰረት አሁን 38 መቀመጫዎች ተጨምረው ወደ 190 ከፍ እንዲል ተደርጓል። ዛሬ በጸደቀው የመቀመጫ ድልድል መሰረት የተጨመሩት 38 መቀመጫዎች ወይም ከአጠቃላዩ የምክር ቤት መቀመጫ 20 በመቶው በምርጫ የተወዳደሩ ድርጅቶች ከተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች የሚያገኙት ድምጽ ተሰብስቦ ባገኙት የድምጽ ብዛት አንጻር የሚከፋፈሉት ይሆናል ተብሏል። ምክር ቤቱ እንዳለው እነዚህ ድርጅቶች የተመደቡትን መቀመጫዎች ለመከፋፈል የሚችሉት ቀድመው የተወካዮቻቸውን ስም ለምርጫ ኮሚሽኑ ማገስባት ሲችሉ መሆኑም ተገልጿል። እነዚህ መቀመጫዎች ለተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ብቻ የተተዉ በመሆናቸው የግል ተወዳዳሪዎች ከ38ቱ መቀመጫዎች ምንም ድርሻ እንደማይኖራቸው ተነግሯል። በአገሪቱ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው ምርጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ ቢደረግም የትግራይ ክልል ከሌሎቹ የአገሪቱ አካባቢዎች በተለየ ምርጫውን በተናጠል ለማካሄድ ወስኖ እየተዘጋጀ እንደሆነ ይታወቃል።
news-46093851
https://www.bbc.com/amharic/news-46093851
የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ጥቃት፡ የግብፅ ፖሊስ 19 እስላማዊ ታጣቂዎችን ገደለ
በግብፅ የኮፕቲክ ክርስቲያኖች ላይ ጥቃት የፈፀሙ 19 እስላማዊ ታጣቂዎች በፖሊስ እንደተገደሉ የግብፅ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በክርስቲያኖቹ ላይ የደረሰው ጥቃት በርካቶችን አስቆጥቷል ሚንስትሩ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት ታጣቂዎቹ በምዕራብ ሚነያ ግዛት በሚገኝ በረሃ ለማምለጥ ሲሞክሩ በፖሊስ በተተኮሰባቸው ጥይት ሊገደሉ ችለዋል። • ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር የፈጠረው ስጋት • ተፈጥሮን በብሩሽ የሚመዘግበው መዝገቡ በወቅቱ እጃቸውን እንዲሰጡ ቢያግቧቧቸውም ስላልቻሉ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ እንደተገደሉ ሚንስትሩ ጨምረው ተናግረዋል። ሚንስትሩ ይህንኑ ለማረጋገጥ የሟቾቹን አስክሬን ፣ ታጣቂ ቡድኖቹ መሽገውበታል የተባለውን ድንኳንና ፣ የጦር መሳሪያዎች እንዲሁም የቡድኑን የፕሮፖጋንዳ መልዕክት ፎቶ በድረ ገፃቸው ላይ ለጥፈዋል። ባለፈው አርብ በቅዱስ ሳሙዔል ገዳም አቅራቢያ በሁለት አውቶብሶች ላይ በተሰነዘረ ጥቃት ሰባት የኮፕቲክ ክርስቲያኖች ሲሞቱ ሌሎች ሰባት ሰዎች ተጎድተዋል፤ ከተጎጂዎቹ መካከልም ህፃናት ይገኙበታል። እስላማዊ ታጣቂ ቡድኑ (አይ ኤስ) ለጥቃቱ ኃላፊነቱን ወስዷል። • "ሌሎች ሴቶች ላይ የአሲድ ጥቃት ሳይ ይረብሸኛል፤ ህመሜን ያስታውሰኛል" ካሚላት መህዲ በእነዚህ በቁጥር ትንሽ በሆኑት አክራሪ ክርስቲያኖች ላይ ከተሰነዘሩት ጥቃቶች ይሄ የቅርብ ጊዜው መሆኑ ነው። የሟቾች የቀብር ሥነ ስርዓት የተፈፀመ ሲሆን በርካታ ሰዎች ቁጣቸውን እየገለፁ ይገኛሉ። በጥቃቱ ጎረቤቱን ያጣው የ23 ዓመቱ ሚካዔል " አሸባሪዎች ከእኛ ምንድን ነው የሚፈልጉት? ሙስሊሞችን ላይ ጥላቻ እንዲኖረን ነው የሚፈልጉት?" ሲል በምሬት ይጠይቃል። ከሶስት ዓመት በፊት በተፈፀመ ተመሳሳይ ጥቃትም 28 ክርስቲያኖች መገደላቸው የሚታወስ ነው። የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በግብፅ የሚገኝ ዋነኛ ቤተክርስቲያን ሲሆን፤ በርካታ መነኮሳትም እዚያው ይኖራሉ። ቤተክርስቲያኑ በውጭ አገር አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ አባላት አሉት።
news-56330257
https://www.bbc.com/amharic/news-56330257
ኮሮናቫይረስ፡ አሜሪካ የተከተቡ ዜጎቿ ጭምብል ሳያደርጉ መሰባሰብ ይችላሉ አለች
የአሜሪካ የበሽታዎች መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከል (ሲዲሲ) የኮሮናቫይረስ ክትባት የተከተቡ ሰዎች ወደቀደመ ህይወታቸው መመለስ ይችላሉ የሚል መመሪያ አውጥቷል።
በዚህም መሰረት ክትባቱን የተከተቡ ሰዎች ጭምብል (ማስክ) ሳያደርጉ በቤት ውስጥ መሰብሰብ ይችላሉ ተብሏል። ሲዲሲ እንዳስታወቀው የመጨረሻውን ክትባት ከተከተቡ ከሁለት ሳምንት በኋላ ከኮሮናቫይረስ ስጋት ነፃ ናቸው ብሏል። እስካሁን ድረስ አሜሪካ ከ30 ሚሊዮን በላይ ዜጎቿን ከትባለች። የአገሪቱ የጤና ባለስልጣናት አዲሱን የደህንነት መመሪያ ይፋ ያደረጉት በትናንንትናው እለት ዋይት ሃውስ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ግብረ- ኃይል መግለጫ ላይ ነው። መመሪያው የኮሮናቫይረስ ክትባትን የወሰዱ ሰዎች ማድረግ ይችላሉ ብሎ ካስቀመጣቸው መካከል፦ "ከኮቪድ-19 በኋላ ሊኖር የሚችለውን አለም ማየት ጀምረናል። የበለጠ ዜጎቻችን በተከተቡ ቁጥር ማከናወን የምንችላቸውን ተግባራትም ይጨምራሉ" በማለት የዋይት ሃውስ ከፍተኛ አማካሪ አንዲ ስላቪት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ነገር ግን አሁንም ቢሆን ክትባቱን የተከተቡ ሰዎች ህዝባዊ በሆነ ቦታ ላይ ጭምብል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፤ እንዲሁም አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣ ህዝባዊ ስብሰባዎችን ማስወገድና የተጣሉ የጉዞ ገደቦችን መከተል ይኖርባቸዋል ተብሏል። ከዚህም በተጨማሪ መመሪያው ያልተከተቡና ለኮሮናቫይረስ በበለጠ ተጋላጭ ከሆኑ ማህበረሰቦችም በተለይ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ እንደሚያስፈልግ አስቀምጧል። አሜሪካ በቅርቡ የምትከትባቸውን ዜጎቿን ቁጥር በከፍተኛ እየጨመረ መሆኑን ያስታወቀች ሲሆን እስካሁን ድረስ 90 ሚሊዮን ሰዎች ተከትበዋል። በተለይም የጆንሰን ጆንሰን የአንድ ጊዜ ክትባት እውቅና ማግኘቱ አቅርቦቱን ጨምሮታል ተብሏል። ነገር ግን በኮሮናቫይረስ ክፉኛ በተመታችው አሜሪካ ኮቪድ-19 የማህበረሰቡ የጤና ጠንቅ መሆኑ ቀጥሏል። አገሪቱ እስካሁን ድረስ 29 ሚሊዮን ዜጎቿ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ያስታወቀች ሲሆን 525 ሺህ ዜጎቿንም አጥታለች።
news-51499406
https://www.bbc.com/amharic/news-51499406
በማህበራዊ ሚዲያ ውሃ አጣጭን ለማግኘት የሚረዱ ሰባት ነጥቦች
ዛሬ፣ በፍቅረኞች ቀን፣ ሁሉም ጥንድ ጥንድ ሆኖ ሲሄድ እያዩ እርስዎ ግን ብቻዎን በመሆንዎ ቆዝመዋል? የፍቅር አጋርዎን ማግኘት ይፈልጋሉ?
አጣማሪዎን እናገናኛለን የሚሉ መተግበሪያዎች ላይ ውሃ አጣጭ መፈለግ ነውር አይደለም። ነገር ግን ፍለጋውን እርስዎ ሊወዱት ይገባል እንደ ስታስቲስታ ግምት ከሆነ 240 ሚሊዮን የሰዎች ጎርፍ ወደ የፍቅር አጋር አገናኝ ድረ ገጾች ይተማሉ። ነገር ግን ሁሉም 'ያሰብኩት ተሳካ ያለምኩት ደረሰ፤ ሐሳቤም ተሟላ መንፈሴ ታደሰ' ብሎ አይመለስም። • ከራሱ ሠርግ በጠራቸው እንግዶች የተባረረው ሙሽራ ለዚያም ነው የፍቅርና የትዳር ግንኙነቶች አማካሪና የበርካታ መጽሐፍት ደራሲ የሆነችው ሱዚ ሄይማንን ምክር ልናካፍላችሁ የወድነው። 1. የፍቅር አጋር ለማግኘት ብለው ብቻ ቀጠሮ አይቀበሉ ደንብ አንድ፡ ካልፈለጉ አያድርጉት "መሞከር" አድካሚ ነው፤ ያሰለቸናል፣ ስሜታችንን ያደፈርሰዋል፤ ስለራሳችን ያለንንም ግምት ዝቅ ያደርግብናል። ስለዚህ ካልፈለጉ፤ ልብዎን ደስ ካላለው አያድርጉት። በማህበራዊ ሚዲያ የተዋወቁትን ሰው ልብዎን ካላሞቀው፣ ቀልብዎን ካልሳበው አያግኙ። 2. ደመ ነፍስዎን ይመኑ ደስ ካላለዎት ወይንም ሊያገኙ የቀጠሩትን ሰው ካላመኑት ወዲያውኑ ይወስኑ በማንኛውም ሰዓት አደጋ የሚመስል ነገር ከሸተትዎት ወዲያውኑ እርምጃ ይውሰዱ። አንዳንዴ አእምሮ ውስጥ 'እንዲሁ ተጠራጣሪ ሆኜ' ነው የሚል ቀጭን ሐሳብ ሰበዝ መጥቶ ወይንም ሌላ ሰበብ ሰጥተው ወደ ቀጠሮዎ ሊሄዱ ይችላሉ። • በሠርግ ዕለት ማታ በጉጉት የሚጠበቀው 'የደም ሸማ' ይህ ግን በማህበራዊ ሚዲያ ለተዋወቁት ሰው አይመከርም። ከተጠራጠሩ ደመ ነፍስዎን ይመኑ። 3. በማህበራዊ ሚዲያ መልዕክት ሲቀባበሉ ቁጥብ መሆን ብልህነት ነው በማህበራዊ ሚዲያ የመልዕክት ናዳ ከማዝነብ ይልቅ ቁጥብና ወደ ነጥቡ የሚያተኩር መልዕክት መለዋወጥ ይመከራል በማህበራዊ ሚዲያ ለተዋወቁት ሰው የመልዕክት ዶፍ ከማዝነብ ይልቅ፤ ልብዎን የሚያሞቅ ገንቢ የሆነ ጥቂት መልዕክት በቂ ነው (ከብዛት ይልቅ ጥራት)። በፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ቲውተር፣ ቴሌግራም... ለተዋወቁት ሁሉ መልዕክት መጻፍ፣ ለተጻፈልዎት መመለስ የእርስዎንም ልብ ማፍሰሱ፣ ስሜትዎንም ማጎሹ አይቀርም። ስለዚህ ለተመረጠ ብቻ የተቀነበበ መልዕክት መላክ ብልህነት ነው። በተለይ ሲያወሯቸው ደስ የሚልዎትን ሰው ብቻ ቢያዋሩ ጠቃሚ ነው። ያ ማለት የወደፊት አጋር የመሆን እድል ካላቸው ሰዎች ጋር መልዕክት መለዋወጥ ጥሩ ነው። 4. የፍቅር አጋርን በማህበራዊ ሚዲያ ለማግኘት ከወሰኑ በርካታ ተጠቃሚ ያላቸውን መተግበሪያዎችን ይጠቀሙ በርካታ ተጠቃሚ ያላቸው ማህበራዊ ሚዲያዎችን የሚጠቀሙ ከሆነ በርካታ ምርጫ ይኖርዎታል። ብዙም ሰው የማያውቃቸው ማህበራዊ ሚዲያዎችን ያርቁ ልፋት ብቻ የሚያደርግዎ ተጣማሪ አገናኞችን አልያም ማህበራዊ ሚዲያዎችን ያስወግዱ። በርካታ ሰዎች ወደሚጠቀሟቸው ድረገፆች ወይም መተግበሪያዎች ጎራ ይበሉ። በማህበራዊ ሚዲያ የፍቅር አጋር የማግኘት ጉዳይ የምርጫ ጉዳይ ነው። ምርጫ ደግሞ ካለ በርከት ያለ የሚመረጥ አጋር መኖር አለበት። ስለዚህ ከበርካታ ራሳቸውን ቀባብተው ብቅ ከሚሉ አማላይ የፍቅር አጋር ፈላጊዎች መካከል የእርስዎን እንቁ (የሚኮሩበትን) ለማግኘት ይትጉ። 5. በቅድሚያ ጓደኝነት ከሁሉም በላይ ጓደኝነት ይቀድማል በትዳር ረዥም ዓመት በስኬትና በደስታ የቆዩ ሰዎች፣ የትዳር አጋር ብቻ ሳይሆን ጓደኛቸውን እንዳገኙም ሲናገሩ ይደመጣል። እርስዎም የልብዎን ፍላጎት፣ በክፉ ቀን ምርኩዝ የሚሆን፣ በደስታ በሐዘን የማይለይዎትን የትዳር አጋር ለማግኘት ሲጀምሩ ከጓደኝነት ቢሆን መልካም ነው። ግንኙነት ለትዳር ተብሎ እንደማይጀመር በፍለጋዎ የመጀመሪያው ምዕራፍ የመጀመሪያ ገጽ ላይ ማወቅ ጠቃሚ ይሆናል። ደግሞ የወደፊት ውሃ አጣጭዎን በጥሩ ጓደኛዎ በኩልም ሊተዋወቁ እንደሚችሉ ማስታወስ ተገቢ ነው። 6. ምርጫዎትን አይገድቡ ከሰው የሚወዱትን ነገር በቀላሉ እንደሚለዩና ምን እንደሚፈልጉ የሚያውቁ ሊመስልዎት ይችላል። ነገር ግን ይህ ሰው ምኑም እኔ የምፈልገውን አይመስልም ካሉት ጋር ተጣምረው የሕይወት ዘመንዎን በደስታና በተድላ ሊኖሩ ይችላሉ። ስለዚህ የሚፈልጉትን ለማግኘት መስፈርትዎን አያጥብቡት። ምርጫን ሳይገድቡ ግራ ቀኝ ማየት ጥሩ ነው። በማህበራዊ ሚዲያ ሕይወቴ ሕይወት የሚሉትን ሰው ሊያገኙ ይችላሉ፤ ያ ማለት ግን መጠናናት፣ የመምረጫ መስፈርትዎን ሁሉ አሽቀንጥረው ይጥላሉ ማለት አይደለም 7. ጥንቁቅ ይሁኑ በኢንተርኔትና በማህበራዊ ሚዲያ የፍቅር አጋርን መተዋወቅ ግንባር ቀደም ድክመቱ የጋራ የሚሉት ሰው፣ ወዳጅ አለማወቅዎ ነው። ስለሚያገኙት ሰው ተሟላ መረጃ የሚሰጥ ማንም የለም። • የኢትዮጵያዊያንን ትዳር አከርካሪ እየሰበረ ያለው ምን ይሆን? ከሚያገኙት ሰው አጠራጠጣሪ ነገር በገጠመዎ ወቅት ቸል አይበሉ። በተዋወቁ ሰሞን ገንዘብ የሚጠይቁ፣ በተደጋጋሚ ሚይዙትን ቀጠሮ የሚሰርዙ፣ ስለራሳቸው በሚገባ ማይገልጽ እና ሌሎች አጠራጣሪ ነገሮች ሲፈጠሩ ይጠንቀቁ። በስሜት አበላ አይዘፈቁ። ጥንቃቄ...ጥንቃቄ...ጥንቃቄ...
news-45109054
https://www.bbc.com/amharic/news-45109054
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ለኖቤል ታጭተዋል?
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን በመጡ በጥቂት ወራቶች ውስጥ ከፍተኛ የሕዝብ ድጋፍ ማግኘት ብቻም ሳይሆን የኖቤል ሽልማት እንዲያገኙም ጭምር ዘመቻ እየተደረገላቸው ነው።
የኢትዮጵያ ዜጎችን ጨምሮ ከዚያም ባሻገር ዐብይ አሕመድ በአገር ውስጥና በአጎራባች አገሮች እያመጡ ያሉትን ጉልህ ለውጥ ተከትሎ ሽልማቱ ይገባቸዋል የሚሉ ድምጾች በርክተዋል። በተለይም ከኤርትራ ጋር የጀመሩት የሰላም ጉዞ በደጋፊዎቻቸው የሽልማት "ይገባዎታልን" ዘመቻ ከፍ ብሎ ተሰምቷል። • "አካል ጉዳተኛ መሆኔ ጥሩ ደረጃ እንድደርስ አድርጎኛል" • 'ገዳይ ጨረር' እንዴት ራዳርን ለመፈብረክ ረዳ? እንደ ጎርጎሪዮሳዊያኑ አቆጣጠር በሐምሌ 23 የቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ አማካሪ የነበሩት ኸርማን ኮኸን በትዊተር ገጻቸው ላይ የሚከተለውን ጻፉ- "በሞያ ዘመኔ ለመጀመርያ ጊዜ አንድ ሰው ለኖቤል እጩ ማድረጌ ነው፤ ያ ሰው ዐብይ አሕመድ ነው፤ ለአገሩ አሳታፊ ዲሞክራሲን ካመጣ መላው የአፍሪካ ቀንድ ወደተሻለ ቀጠና ይሸጋገራል።" ይህ የኸርማን ጄ ኮኸን ሐሳብ ብዙዎች በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን ላይ ተጋርተውታል፣ አጋርተውታል። ኖቤል በዘመቻ ይገኛል? በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን እንደሚታየው ከሆነ ዶክተር ዐብይ ለእጩነት፣ አንዳንዴም ለአሸናፊነት ጫፍ ደርሰዋል። የሚያስፈልጋቸው የሕዝብ ድምጽ ነው የሚሉ መረጃዎች በስፋት ሲዘዋወሩ ሰንብተዋል። ለመሆኑ የኖቤል የሽልማት ሥርዓት እንዲህ አይነቱን አሠራር ይከተላል? እነማን መጠቆም ይችላሉ? ከኖቤል ሽልማት ይፋዊ ድረ-ገጽ እንደተገኘው መረጃ ከሆነ የኖቤል እጩዎች ጥቆማ የሚሰጠው በበቁ ሰዎች ብቻ ነው። እነዚህ የበቁ ጠቋሚዎች የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው። • የአንድ ሉአላዊት አገር የካቢኔ አባላት ወይም የአገር መሪዎች • የሄግ የግልግል ፍርድ ቤት ወይም የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት አባላት አልያም በውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ወይም በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሚገኙ ፕሮፌሰሮችና ተባባሪ ፕሮፌሰሮች • ቀደም ብለው ኖቤል ያሸነፉ ሰዎች ወይም ያሸነፉ ድርጅቶች የቦርድ ሰብሳቢዎች • የኖርዌይ የኖቤል ኮሚቴ የቀድሞም ሆኑ የአሁን አባላት • የኖርዌይ ኖቤል ኮሚቴ አማካሪዎች ናቸው። ከላይ በተዘረዘሩት አባላት እጩው ሲቀርብ ነው ሕጉን ተከተለ የሚባለው። አንድ ሰው ራሱን እጩን አድርጎ ማቅረብ አይችልም። የኖቤል ኮሚቴ አምስት አባላት ያሉት ሲሆን የኮሚቴው አባላት የሚሰየሙት በኖርዌይ ፓርላማ ነው። የኖቤል የሰላም ሽልማትን ካገኙ ሰዎች መካከል ማንዴላ አንዱ ናቸው ዐብይ አሕመድ ስለመጠቆማቸው ማን ሊነግረን ይችላል? ኮሚቴው የእጩዎችንም ሆነ የጠቋሚዎችን ማንነት ለሚዲያም ሆነ ለእጩዎቹ በምንም መልኩ አይገልጽም። ማን ማንን ጠቁመ፣ እነማን እንዴት ተመረጡ ወይም ተጠቆሙ የሚሉ መረጃዎች የሚወጡት ሽልማቱ ከተካሄደ ከ50 ዓመታት በኋላ ብቻ ነው። ይህ ማለት ዐብይ አሕመድ የ2018 የኖቤል እጩ ስለመሆናቸው እርግጡን የምናውቀው በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2060 ይሆናል። የኖቤል ኮሚቴው የጊዜ ሰሌዳ መስከረም፡- በፈረንጆች መስከረም (ሴፕቴምበር) የኖርዌይ ኖቤል ኮሚቴ እጩዎችን ለመቀበል ይሰናዳል። እጩ የመቀበሉ ሥራ ለቀጣይ ስድስት ወራት ይጸናል። እጮዎቹን መጠቆም የሚችሉት ከላይ የተዘረዘሩት ብቁ ጠቋሚ የተባሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ብቻ ናቸው። የካቲት፡- በየካቲት የእጩዎች መቀበያ ጊዜ ያበቃል። ከየካቲት 1 በፊት ያልተጠቆመ በዚያ ዓመት እጩ መሆን አይችልም። መጋቢት፡-ኮሚቴው የእጮዎችን ዝርዝር ያቀርባል። ከእጮዎቹ ውስጥ ከ20 እስከ 30 የሚሆኑትን ብቻ ለተጨማሪ ማጣሪያ ይቀርባሉ። ጥቅምት፦ በጥቅምት መጀመርያ ኮሚቴው አሸናፊውን በድምጽ ብልጫ ይመርጣል። ይግባኝ የማይባልበት ምርጫ ነው ታዲያ። በታኀሳስ፦ 10 (በፈረንጆቹ) በኦስሎ ኖርዌይ የሽልማት ሥነ ሥርዓቱ ይካሄዳል። የጊዜ ሰሌዳውና ዐብይ አሕመድ የኖቤል ሽልማት ከአንድ ዓመት ዘለግ ያለ ጊዜን የሚወስድ ሂደት ነው። ኾኖም ጥቆማ የመቀበያ ጊዜ ከፈረንጆች መስከረም ጀምሮ ለ6 ወራት የሚዘልቅ ነው። ይህ እንግዲህ መጪውን የመስከረም ወር ሳይሆን የ2017ቱን ወር አንድ ብሎ የሚጀምር ነው። የእጩ መስኮቱ ከተዘጋ ከሁለት ወራት በኋላ ወደ ሥልጣን የመጡት ዐብይ አሕመድ ቢያንስ የ2018 የኖቤል ሽልማት እጩ የመሆናቸው ነገርን አጠያያቂ ያደርገዋል። ምናልባት የኖቤል ኮሚቴው በመጨረሻዎቹ ጊዜያት እጩ የመጨመር ሥልጣን ስላለው ያ ተግባራዊ ከሆነ ጠባብ እጩ የመሆን እድል ሊኖራቸው ይችላል። አልያ ግን ከወር በኋላ ጀምሮ ለ6 ወራት በሚጸናው የ2019 የኖቤል ሽልማት ለመካተት ካልሆነ በስተቀር፤ ዐብይ አሕመድ ከዚህ ውጭ በማንኛው አካል የሚደረገው ዘመቻ በኮሚቴው ምርጫ ሂደት ላይ ምንም አይነት ተጽእኖ እንደማያደርግ ይታወቃል። ለዓለማችን የላቀ አስተዋፅኦን ላበረከቱ ሰዎች የሚሰጠው የኖቤል ሽልማት አጀማመር። ተጨማሪ መረጃዎች ይህ በእንዲህ እያለ በታሪክ ከፍተኛው የእጩ ቁጥር የቀረበው በ2016 ነበር። በዚያ ጊዜ የተመዝጋቢ እጩዎች ቁጥር 376 ሲሆን የዘንድሮውም ቀላል የሚባል አይደለም። 330 እጩዎች ቀርበዋል። ከእነዚህ ውስጥ ዐብይ አሕመድ ይገኙበታል ወይ ነው ጥያቄው። ዘንድሮ ከቀረቡት ከነዚህ እጩዎች ውስጥ 216 የሚሆኑት ግለሰቦች፣ 114ቱ ደግሞ ድርጅቶች ናቸው። ይህ ሽልማት በ1901 ጀምሮ ለ96ኛ ጊዜ ተሰጥቷል። ይህንንም ሽልማት 16 ሴቶች እና 23 ድርጅቶች አሽንፈዋል።
54528183
https://www.bbc.com/amharic/54528183
ቴክኖሎጂ፡ ቻይና አደንዛዥ እጽ አዘዋዋሪዎችን ድሮን ተጠቅማ ያዘች
የቻይና ፖሊስ ሰው አልባ አነስተኛ አውሮፕላን (ድሮን) በመጠቀም አደገኛ እጽ አዘዋዋሪዎች የንግድ ልውውጥ ለማድረግ ሲደራደሩ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል አግኝቷል። አዘዋዋሪዎቹን በቁጥጥር ስርም አውሏል።
በብሔራዊው የቴሌቭዥን ጣቢያ ተንቀሳቃሽ ምስሉ ተሰራጭቷል። አንዳንዶች ድሮን ሌሎች ወንጀሎችንም ለማጋለጥ መዋል አለበት ሲሉ፤ "ሚሥጥራዊነት ቀረ" ብለው ቅሬታ ያሰሙም ነበሩ። የግላዊነት መብት ተሟጋቾች ዩናይትድ ኪንግደምና ሌሎችም የአውሮፓ አገራት የሚጠቀሟቸው የስለላ ቴክኖሎጂዎች ያሰጓቸዋል። የቻይና ሚዲያ እንደዘገበው፤ ድሮኑ ፖሊሶችን በደቡባዊ ግዛት ወደሚገኝ የጡብ ፋብሪካ መርቷቸዋል። ግለሰቦቹ አደንዛዥ እጽ ሲለዋወጡ ነበርም ተብሏል። ሂደቱን በቀጥታ ሲከታተሉ የነበሩ ሰዎች እጽ አዘዋዋሪዎቹን በቁጥጥር ስር አውለዋል። 'ቢግ ብራዘር ዋች' የተባለው ተቋም ኃላፊ ሲልኬ ካርሎ "የስለላ ቴክኖሎጂ አስጊነቱ እየጨመረ ነው። በተለይም ዩኬ እና ቻይና ዜጎቻቸውን እየተከታተሉ መሆኑ ያሳስባል" ብለዋል። ኮቪድ-19 ከመጣ ወዲህ ኢንግላንድ ውስጥ በውበት ሳሎኖች ላይ በድሮን ስለላ ሲካሄድ እንደነበረ የጠቀሱት ኃላፊው "ምክር ቤት ፖሊሶች እንዴት ድሮንን መጠቀም እንዳለባቸው የሚደነግግ ሕግ ማውጣት አለበት" ብለዋል። የእጽ አዘዋዋሪዎቹ ተንቀሳቃሽ ምስል ከተሰራጨ በኋላ፤ የቻይና ማኅበራዊ ሚዲያ ዌይቦ ተጠቃሚዎች አስተያየት እየተለዋወጡ ነው። አንዳንዶች "እጽ አዘዋዋሪዎች በድሮን መገደል አለባቸው" ብለዋል። በሌላ በኩል "የቻይና መንግሥት በሰማይ ላይም አይን አለው" በማለት ስለላው መባባሱን የተቹም አሉ። አምና መስከረም ላይ ለ17 ዓመታት በሕግ ይፈለግ የነበረ ሰው በድሮን መያዙ ተገልጾ ነበር። ግለሰቡ ዋሻ ውስጥ ተደብቆ ነበር። ኮቪድ-19ን ተከትሎ ድሮን በብዛት ጥቅም ላይ እየዋለ ነው። የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ አደባባይ ላይ የተገኙ ሰዎችን በመቆጣት ለማሸማቀቅ ድሮን ጥቅም ላይ ውሏል። ስፔንም እንቅስቃሴ ላይ የጣለችውን ገደብ ለማስተግበር ድሮን ተጠቅማለች።
news-56648760
https://www.bbc.com/amharic/news-56648760
ኪም ካርዳሺያን የናጠጡ ቢሊየነሮች ክበብን ተቀላቀለች
የአሜሪካ የቴሌቪዥን ትዕይንት ኮከብ ኪም ካርዳሺያን ዌስት የናጠጡ ሀብታሞች ተርታ መግባቷን ፎርብስ መጽሔት አወጀላት።
ኪም ካርዳሺያን ዌስት የኪም ካርዳሺያን የተጣራ ሀብቷ 1 ቢሊዮን ዶላር ደርሶላታል። በዋናነት የመዋቢያ እቃዎች ምርትና የማስታወቂያ ጉርሻ ለገቢዋ እዚህ መድረስ ሁነኛ ቦታ አላቸው። አሁን ኪም ካርዳሺያን ዌስት ከዓለም ቢሊየነሮች ተርታ የባለጸጎች መዝገብ ላይ 2 ሺህ 755ኛ ሆና ተቀምጣለች። በዚህ ዓመት ቢሊየነሮች ክበብን ከተቀላቀሉት መሀል የ'በብል' የፍቅር ጓደኛ አጣማሪ መተግበሪያ ፈጣሪ ዊትኒ ዎለፍ ህርድ በ1.3 ቢሊዮን ዶላር፣ የፊልም ጥበበኛ ታይለር ፔሪ በአንድ ቢሊዮን ዶላር፣ የካሲኖ አቋማሪ ድርጅት ባለቤት የነበሩት የሼልደን አደልሰን ሚስት ሚሪየም አደልሰን በ38 ቢሊዮን ዶላር አዱኛ ዝርዝር ውስጥ ይገኙበታል። ይህንን የናጠጡ ቢሊየነሮች ክበብን የአማዞኑ ጄፍ ቤዞስ በበላይነት በ177 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ገቢ ይመራዋል። ከኪም ካርዳሺያን ጋር አብሮ መኖር ያቆመው አቀንቃኙ ካኒዬ ዌስት ከኪም ቀደም ብሎ በ1.8 ቢሊዮን ዶላር ይህን የቢሊየነሮች ክበብ ተቀላቅሏል። ፎርብስ ዘንድሮ የኪምን ግማሽ እህት ኬሊ ጄነርን ከዚህ ክበብ ሰርዟታል። ምክንያቱ ደግሞ ገቢዋ ማሽቆልቆሉ ነው። ፎርብስ 40 ዓመት የደፈነችውን ኪም ካርዳሺያንን ሀብት ከ780 ሚሊዮን ዶላር እንዴት ወደ 1 ቢሊዮን ዶላር እንደደረሰ የገለጸ ሲሆን፤ ኬኬደብሊው የመዋቢያ እቃዎች ቢዝነሷና ስኪምስ የውስጥ ቅንጡ ልብስ ኩባንያዋ እንዲሁም ከማስታወቂያ ገቢ የተገኘ ረብጣ ዶላር ነው ምክንያቱ ብሏል። ኪም ባለፈው ዓመት የኬኬደብሊው ኮስሞቲክን 20 ከመቶ ድርሻ 'ኮቲ' ለተሰኘው ስመ ጥር ኩባንያ በ200 ሚሊዮን ዶላር ሽጣው ነበር። መዘነጫ የውስጥ ልብሶችንና ሸንቃጣ የሚያደርጉ አልባሳትን በመሸጥ የሚታወቀው ስኪምስ በዚህ ዓመት ስኬታማ ሆኖላታል። ኪም የምርቶቹን ገበያ መቆጣጠር ያስቻላት ከ200 ሚሊዮን በላይ በኢኒስታግራም ተከታዮች ስላሏት ነው። በትዊተር ደግሞ 70 ሚሊዮን የሚጠጉ ተከታዮችን አፍርታለች። ኪም ባለፈው የካቲት ከሙዚቀኛው ካንዬ ዌስት ጋር ፍቺ መጠየቋ ተዘግቦ ነበር። ኪምና ካንዬ 7 ዓመታት በዘለቀ ጋብቻ 4 ልጆችን አፍርተዋል።
news-53253345
https://www.bbc.com/amharic/news-53253345
የኦሮሞ ፌራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) የፓርቲዬ ከፍተኛ አመራሮች መታሰራቸው አሳስቦኛል አለ
ከድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ የቀበር አፈጻጸም ሁኔታና ከአንድ የጸጥታ አባል መገደል ጋር በተያያዘ ፖሊስ ከሌሎች ሰዎች ጋር አስሯቸዋል የተባሉት የኦሮሞ ፌደራሊስ ኮንግረስ (ኦፌኮ) አባላት ማዕከላዊ ውስጥ እንደሚገኝ ፓርቲያቸው ገለጸ።
"የፓርቲያችን አባላት የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ጃዋር መሐመድ እና አቶ ሐምዛ ቦረና በተዘጋው ማዕከላዊ ታስረው ይገኛሉ” ሲሉ ለቢቢሲ የተናገሩት የኦፌኮ ጽህፈት ቤት ኃላፊ እና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ጥሩነህ ገምታ ናቸው። ፖሊስ ትናንት ሰላሳ አምስት ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የገለጸ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል የአቶ በቀለ ገርባ ሴት ልጅ የሆነችው እና ሹፌራቸው ከታሰሩት መካከል እንደሚገኙ አቶ ጥሩነህ ለቢቢሲ ገልጸዋል። የፓርቲው ኃላፊ የሆኑት አቶ ጥሩነህ ጨምረውም በአሁኑ ጊዜ "በአጠቃላይ የታሰሩ ሰዎች ቁጥር 40 ነው” ብለዋል። አቶ ጥሩነህ እንደተናገሩት በቁጥጥር ስር ከዋሉት ሰዎች በተጨማሪ ትናንት ተከስቶ በነበረው ግጭት በመላው ኦሮሚያ የሞቱት ሰዎች ቁጥር የክልሉ መንግሥት ከሚለው በላይ መሆኑን የሚጠቁም መረጃ እንዳላቸው አመልክተዋል። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ትናንት በክልሉ በተከሰቱ ግጭቶች ከ50 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ይፋ ማድረጉ ይኣወሳል። የክልሉ ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት ከሃጫሉ ሞት ጋር በተያያዘ በኦሮሚያ ተቀስቅሶ በነበረው ተቃውሞ ከሃምሳ በላይ ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች ቆስለዋል ብለዋል። አቶ ጥሩነህ ገምታ በእስር ላይ የሚገኙ አባሎቻቸውን ሁኔታ ለማወቅ ጠበቃ ተቀጥሮ ወዳሉበት ቦታ በመሄድ ለማነጋገር ቢሞከርም በከተማው ውስጥ ያለው ሁኔታ አመቺ ባለመሆኑ አለመሳካቱን ተናግረዋል። በእስር ላይ ስሚገኙት አባሎቻቸው በተመለከተም “የከፍተኛ አመራሮቻችን መታሰር በፓርቲው እና በሕዝባችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል” ብለዋል። ትናንት ምሽት የፌደራል እና ኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽኖች በሰጡት መግለጫ ላይ እንደተነገረው 35ቱ ሰዎች በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ የተደረጉት የሃጫሉ ሁንዴሳ አስክሬን ወደ ትውልድ ከተማው አምቦ እንዳይሄድ እክል በመፍጠራቸው እና በአዲስ አበባ ከአንድ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባል ግድያ ጋር በተያያዘ መሆኑ ተነግሯል። መግለጫው አክሎም በቁጥጥር ስር ከዋሉት ሰዎች መካከል የጃዋር ጠባቂዎች ይዘውት ነበር የተባሉ የጦር መሳሪያዎች እና መገናኛ ሬዲዮችም መያዛቸውን አመልክተዋል።
news-44288533
https://www.bbc.com/amharic/news-44288533
ቀዶ ህክምና በአፍሪካ ስጋት መሆኑ ከፍ ብሏል
በአፍሪካ ቀዶ ህክምና የሚያካሂዱ ህሙማን ከተቀረው ዓለም ጋር ሲነጻጸር የመሞት ዕድላቸው በሁለት እጥፍ የጨመረ እንደሆነ ተመራማሪዎች ገለጹ።
ነገሮችን ይበልጥ አስከፊ የሚያደረገው ደግሞ ይላሉ ተመራማሪዎቹ፤ ቀድመው ቀጠሮ ተይዞላቸው የሚደረጉ ቀዶ ህክናዎች ቁጥር ትንሽ መሆኑ ነው። የሚካሄዱ ቀዶ ህክምናዎች ቁጥር ካለው የህክምና ፍላጎት ጋር ሲነፃፀር በሃያ እጅ ያነሰ ነው። ለዚህም ነው ድምጽ አልባው ገዳይ የሚሉት። ከኬፕታውን ዩኒቨርሲቲ የመጡት እና የጥናቱ ተባባሪ ፕሮፌሰር ብሩስ ቢካርድ እንደሚሉት የችግሩ ዋና መንስኤ የጤና ባለሙያ እጥረት እና ችግሩን ቀድሞ ያለመለየት እንደሆነ ይናገራሉ። በዓለም አቀፍ ደረጃ ቀዶ ህክምና ከሚያካሂዱ ህሙማን 1በመቶ የሚሆኑት የሚሞቱ ሲሆን፤ በአፍሪካ ግን ቁጥሩ ወደ 2.1 በመቶ ከፍ ይላል። ምንም እንኳን ህመምተኞቹ በእድሜ ወጣት እና ከባድ የሚባል የጤና ችግር ያለባቸው ባይሆኑም፤ ከቀዶ ህክምና በኋላ የመሞታቸው እድል ከፍ ያለ ነው። በአፍሪካ በብዛት የተለመደውና 33 በመቶ የሚሆነውን የሚይዘው 'ሲ ሴክሽን' የሚባለው ልጅን በቀዶ ህክምና መውለድ ነው። ይህ ቀዶ ጥገና ብዙ ጊዜ ለኢንፌክሽን የተጋለጠና እናቶቹን ለሞት የሚዳርግ ነው። በአይነቱ ትልቅ የተባለው ጥናት ኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ እና ግብፅን ጨምሮ ሃያ አምስት የአፍሪካ ሃገራትን የሸፈነ ሲሆን ከ11 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ነበሩት። ቀላል የሚባል ቀዶ ህክምና እንኳን ያካሄዱ አፍሪካውያን ከላይ በተጠቀሱት ምክነያቶች ብቻ ይሞታሉ። ከሰሃራ በታች ባሉ ሃገራት ከ10 ሰዎች አንዱ ብቻ የቀዶ ህክምና ህክምና ያገኛል። አገልግሎቱን ማግኘት ከባድ ቢሆንም፤ ከቀዶ ህክምናው ጋር የተያያዙ ችግሮች ግን ብዙ ናቸው። ይሄ ሁሉ ታዲያ የሚያያዘው ከደካማ የጤና ሥርዓት፣ የባለሙያዎች ቁጥር ማነስ እና ታካሚዎቹ በጊዜ መሰረታዊ የጤና አገልግሎት አለማግኘታቸው ነው ይላሉ ተመራማሪዎቹ። የቀዶ ህክምና ደግሞ ሁሌም ቢሆን ከህክምናው በኋላ ያለው እንክብካቤ ወሳኝነት አለው፤ ምክነያቱም በቀላሉ ወደ ሌላ ህመም ሊቀየር ስለሚችል። ታካሚዎቹ ከህክምናው በኋላ ጥብቅ ክትትል የሚያስፈልጋቸው ቢሆንም፤ አብዛኛዎቹ አገልግሎቱ ከሚሰጥበት የጤና ማዕከል በብዙ ርቀት ላይ ስለሚኖሩ ቀጠሯቸውን አክብሮ ባለሙያ ጋር መምጣት ከባድ ነው። ይህ እና ሌሎች ምክነያቶች ተደማምረው የታካሚዎቹን ከቀዶ ህክምና በኋላ የመሞት ዕድልን ይጨምረዋል እላል የአጥኚዎቹ ድምዳሜ።
49310397
https://www.bbc.com/amharic/49310397
እውን ኢትዮጵያ በአንድ ቀን 350 ሚሊዮን ችግኞች ተክላለች?
የዛሬ ሁለት ሳምንት ገደማ ነበር ኢትዮጵያ '350 ሚሊዮን ያህል ዛፎች ተክያለሁ፤ የዓለም ሪከርድም ሰብሪያለሁ' ስትል ያሳወቀችው። ግን ይህ መረጃ ምን ያህል እውነት ነው? የቢቢሲ 'ሪያሊቲ ቼክ' ቁጥሮችን አገላብጦ ያገኘው መረጃ እነሆ።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የደን መመናመንን ለመከላከል አርባ ቢሊዮን ብር የሚያወጣ ችግኝ የመትከል ዕቅድ ይዘው የተነሱት በቅርቡ ነው። የተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ የደን ሽፋን ከሚሊኒዬም በፊት ከነበረው 35 በመቶ ወደ 4 በመቶ ዝቅ ብሏል ይላል። ሐምሌ 22/2011 ዓ.ም. ኢትዮጵያ በ12 ሰዓታት ውስጥ 200 ሚሊዮን ዛፎችን ለመትከል ቆርጣ ተነሳች። በቀኑ መገባደጃ ላይ የፈጠራ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌታሁን መኩሪያ ሃገሪቱ 350 ሚሊዮን ዛፎች መትከሏን አሳወቁ። • ለአራት ቢሊዮን ችግኞች አርባ ቢሊዮን ብር ወጥቷል መንግሥት እንደሚለው ለበጎ ፈቃደኞች የሚተከሉት ዛፎች መታደል የጀመሩት ከሶስት ቀናት በፊት ጀምሮ ነበር። በርካታ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ዕለተ ሰኞ ሐምሌ 22/2011 ዓ.ም መደበኛ ሥራቸውን በመተው ዛፍ በመትከል እንዲውሉ ተደረገ። የተባበሩት መንግሥታት ሠራተኞች ጨምሮ የአፍሪቃ ሕብረት እና ሌሎች መንግሥታዊ ያለሆኑ ድርጅቶችም በዛፍ መትከሉ ላይ በፈቃደኝነት ተሳተፉ። በርካቶቹ ችግኞች ሃገር በቀል መሆናቸውም ተነግሯል፤ እንደ አቮካዶ የመሳሰሉ የፍራፍሬ ዛፎችም መትከላቸው ታውቋል። በጎ ፈቃደኞቹ የሚተክሉትን ዛፎች ይቆጥሩ ዘንድ በየቦታው ሰዎች መመደባቸውም በዛፍ ተከላው ቀን ተዘገበ። አሁን ጥያቄው ይህን ያህል ዛፎች በአንድ ቀን መትከል ይቻላል ወይ የሚለው ነው። የዘርፉ ባለሙያዎች 'መቻሉን ይቻላል፤ ነገር ግን በጣም ትልቅ ዝግጅት ይጠይቃል' ይላሉ። «እርግጥ ነው ይቻላል። ቢሆንም በጣም ዘለግ ያለ ዝግጅት ይሻል» ይላሉ በተባበሩት መንሥታት ውስጥ የአየር ንብረት ለውጥ ባለሙያ የሆኑት ቲም ክሪስቶፈርሰን። ኤኤፍፒ ለተሰኘው ዜና ወኪል ሃሳባቸውን የሰጡት ቲም አንድ በጎ ፈቃደኛ በቀን 100 ዛፎች መትከል ይችላል ይላሉ። ከ23 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን በዛፍ ተከላው ላይ እንደተሳተፉ የብሔራዊ ደን ልማት ፕሮግራም አስተባባሪ ዶ/ር ተፈራ መንግሥቱ ይናገራሉ። ስለዚህ 23 ሚሊዮን ሰዎች በቀን 100 ያህል ዛፎች ከተከሉ ቁጥሩ ከ350 ሚሊዮን በላይ ሊሆን እንደሚችል አያጠያይቅም። ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው ምን ያህል ዛፍ እንደተከለ በውል የሚታወቅ ቁጥር እንደሌለ ተገልጿል። • ችግኝን በዘመቻ መትከል መቼ ተጀመረ? 350 ሚሊዮን ዛፎችን ለመትከል ቢያንስ 346 ሺህ 648 ሄክታር መሬት ይጠይቃል። ነገር ግን ምን ያህል ሄክታር መሬት ዛፎችን ለመትከል ጥቅም ላይ እንደዋለም መረጃ የለም። አንድ የመንግሥት መሠሪያ ቤት ሠራተኛ መሥሪያ ቤታቸው 10 ሺህ ዛፎችን እንዲተክልና ወጭውንም እንዲሸፍን እንደታዘዘ ለቢቢሲ ይናገራሉ። የበጀት እጥረት ስላጋጠማቸው አምስት ሺህ ዛፎችን ብቻ ነው የተከሉት። 5 ሺህ ዛፎችን ተክለው ነገር ግን 10 ሺህ የሚል ቁጥር ገቢ ማድረጋቸውን ነው ለቢቢሲ አስረድተዋል። አልፎም አንዳንድ ቦታዎች ላይ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ተተከሉ ያሏቸው ዛፎች ቁጥር የጠቅላይ ሚኒስትሩ ድረ-ገፅ ላይ ከሰፈረው ጋር ልዩነት እንደታየበት ቢቢሲ ታዝቧል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጠን የጠየቅነው ጥያቄ እስካሁን ምላሽ አላገኘም። የተባበሩት መንግሥታት ኢትዮጵያ ለዛፍ ተከላው አመስግኖ ጎረቤት ሃገራትም ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ አሳስቧል። ቢሆንም የዛፎቹ ቁጥር ጉዳይ ከበርካታ ወገኖች ትችት አላጣም። «እኔ በበኩሌ ይህን ያህል ዛፍ ተክለናል ብዬ አላምንም» ይላሉ የኢዜማ ፓርቲ ቃል-አቀባዩ ዘላለም ወርቅአገኘሁ። ተቺዎች ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መንግሥታቸው የገጠመው ብሔር ተኮር እክልን የዛፍ ተከላው ቅስቀሳውን ሽፋን በማድረግ እያደባበሱት ነው ሲሉ ይወቅሳሉ። እውን ሪከርድ ተሰብሯል? የዓለም ድንቃድንቅ ድርጊቶች መዝጋቢው ጊነስ ዎርልድ ሪከርድስ በበኩሉ የዛፍ ተከላ ሬከርድ የመስበር ሙከራውን እንዲያረጋጥ የሚያስችለው የግብዣ ማመልከቻ ከኢትዮጵያ መንግሥት መቀበል አለመቀበሉን የሚያረጋግጥ ምላሽ አልሰጠም። ኢትዮጵያ እውን ሪከርዱን ሰብራ ከሆነ ምን ያህል ሰዎች እንደተሳተፉ፣ የት እና መቼ እንደተከናወነ የሚገልፅ ውል ያለው መረጃ መስጠት ይኖርባታል። አልፎም ሁለት ገለልተኛ ምስክሮች ሪከርዱ መሰበሩን በሥፍራው ተገኝተው ማረጋገጥ ይጠብቅባቸዋል። በአሁኑ ወቅት ዛፍ በመትከል የዓለም ሪከርድ ይዛ ያለችው ህንድ ናት። በግለሰብ ደረጃ ደግሞ ካናዳዊው ኬን ቻፕሊን በአንድ ቀን 15 ሺህ 170 ዛፎችን በመትከል የዓለም ሪከርድ ይዞ ይገኛል። • የጠቅላይ ሚኒስትሩ 200 ሚሊዮን ችግኞች
44778468
https://www.bbc.com/amharic/44778468
የሰልፍ "ሱሰኛው" ስለሺ
ስለሺ ሐጎስ ለሰልፍ ባይታወር አይደለም። በተለይም ለተቃውሞ ሰልፍ። እንዲያውም ሱሰኛ ሳይሆን አይቀርም። ባለፉት ዐሥርታት በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ በተደረጉ መንግሥትን የሚነቅፉና ፖለቲካዊ ጥያቄዎችን የሚያፋፍሙ ሰልፎች ላይ ሁሉ ተሳትፌያለሁ ይላል።
በሳቅ በተኳለ ንግግሩ እንደሚተርከው የቸርቸል ጎዳናን ታክኮ በሚገኘው የኢትዮ-ኩባ አደባባይ ቆሞ የቅዋሜ ድምፁን አስተጋብቷል፤ ከስድስት ኪሎ ተነስቶ አራት ኪሎ እስከሚገኘው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ድረስ እጁን እያወናጨፈ ተጉዟል፤ ፍርሃት በደም ሥሩ ሲላወስ አስተውሎ ራሱን ታዝቧል፤ በዱላ ተቀጥቅጦ ሩሁን ስቷል፤ የሆስፒታል አልጋን ተለማምዷል፤ እስካሁን የዘለቀ ሕመምን ተቀብሏል። አሁን በሰላሳዎቹ የዕድሜ አፅቅ ውስጥ የሚገኘው ስለሺ፥ በጉርምስናው ወራት በትውልድ ቀዬው መቂ ከተማ ከ1997 ዓ.ም ምርጫ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ የተከናወኑትን ሰልፎች ያስታውሳል። በተለይም በወርሃ ሚያዝያ በቅንጅት ለአንድነት እና ዲሞክራሲ ፓርቲ ደጋፊዎች የተከናወነው መስቀል አደባባይን እና ዙርያ ገባውን የሞላ ሰልፍ እጅጉን አስደምሞት ነበር። "ሚያዝያ ሠላሳ የነበረውን የቅንጅት ሰልፍ በቴሌቭዥን መታደም እጅግ የሚያስቀና ነገር ነበረው" ይላል ለቢቢሲ። • "ጠቅላይ ሚኒስትሩን አምባገነን እንዳያደርጉት እሰጋለሁ" ጃዋር መሀመድ ሰልፉ፣ የድጋፍ ወይስ የተቃውሞ? ለስለሺ ከምርጫ 97 በኋላ ያሉት ተከታታይ ዓመታት የገዥው ፓርቲ ድምፅ ብቻ የተስተጋባባቸው፥ የገዥ ፓርቲ ድምፅ ብቻ የተፈቀደባቸው ሆነው ለመዝለቃቸው አንዱ ማሳያ ከአዲስ አበባ ትልልቅ አደባባዮች አንዱ የሆነው መስቀል አደባባይ ነው። በእነዚህ ዓመታት መስቀል አደባባይ ከሃይማኖታዊ በዓላት በዘለለ፤ ኢህአዴግ "ደግፉኝ እያለ ከየቀበሌው በሚቀስቅሳቸው ሰዎች አጥለቅልቆ" ራሱን የሚያሞካሽበት መድረክ ሆኖ ነበር ይላል። በመሆኑም ስለሺ በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን፥ በቀይ ሽብር ሰማዕታት ቤተ መዘክር፥ በዋናው አውደ ርዕይ ማዕከል እና የኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜያት የምጣኔ ሃብት እርምጃ ምልክት ተደርጎ በሚቆጠረው ቀላል የከተማ ባቡር መንገድ እቅፍ ውስጥ ወደተዘረጋው መስቀል አደባባይ ከረዥም ጊዜ በኋላ ጎራ ያለው በቅርቡ ነበር። በሰኔ 16ቱ ሰልፍ። ሰልፉን በርካቶች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እና ለለውጥ እርምጃዎቻቸው ድጋፍን ለማሳየት እንደተከናወነ ሲገልፁ ማዳመጥ እንግዳ ባይሆንም፥ ለስለሺ ግን ይህ አገላለፅ የሰልፉን መንፈስ ሙሉ በሙሉ አይወክልለትም። ለስለሺ ሰልፉ የድጋፍነቱን ያህል የተቃውሞም ጭምር ነው። ለእርሱ መስቀል አደባባይ ላይ የተካሄደው ሰልፍም ይሁን አሁን በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች የሚከናወኑ ሰልፎች አስኳላቸው ተቃውሞ ነው። "ሕዝቡ ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት በነበረው የኢህአዴግ አስተዳደር ላይ ያለውን ቅሬታን፥ ብሶት እና ተቃውሞ ለመግለፅ የሚከናወኑ ሰልፎች ናቸው" ይላል። "ይሄንን ለመለወጥ የተነሳውን አንድ ሰው እና አጋሮቹ ለማበረታታት በዚህም ተቃውሞውን ለማጠናከር የሚደረጉ ሰልፎች ናቸው። ዐብይን መደገፍ ኢህአዴግን መደገፍ ነው ብለው የሚያስቡ ሰዎች ተሳስተዋል።" ብዙ ከተባለለት ደማቅ ትዕይንት እና ከዚያም በኋላ አንኳሩ ዜና የነበረው የቦንብ ፍንዳታ የሚያስተምሩን አንኳር ነጥቦች አሉ ይላል ስለሺ። "የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዘመናት ብዙ ጥያቄ አላቀረበም። መንግሥትን እጅህን ዘርጋልኝ አላለም፤ እጅህን ሰብስብልኝ ነው ሲል የነበረው። አንደኛ ይህንን ማስተዋል ችያለሁ" የሚለው ስለሺ፥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥልጣን ላይ ከወጡ በኋላ የወሰዷቸው እርምጃዎች በአብዛኛው ይሄንን ያለቅጥ ተዘርግቶ የነበረ የመንግሥት እጅ መሰብሰብ ነበር" ይላል። "[ኮከብ ከሌለው] አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ እስከ ኦነግ ባንዲራ" ድረስ የተለያዩ የአስተሳሰብ ጽንፎችን የሚወክሉ ትዕምርቶች በሰልፉ ላይ ቢስተዋሉም፥ እነዚህን የአስተሳሰብ መስመሮች ባንፀባረቁ ተሰላፊዎች መካከል ምንም ዓይነት ግጭትም ሆነ ውጥረት ያለመከሰቱ የሚነግረን ነገር አለ ይላል ስለሺ። "ተቃራኒ አስተሳሰቦቹን የሚያራምዱ ፖለቲከኞች ቁጭ ብለው መነጋገር የማይቻላቸው ቢመስልም፥ ደጋፊዎቻቸው ግን ተቃቅፈው ሁሉ መዘመር እንደተቻላቸው" ከጠቀሰ በኋላ "ይህም ብዙ አስተምሮኛል" ይላል። በስለሺ ዕይታ ይህ ወደ ዲሞክራሲ ለሚደረግ ጉዞ የተመቸ ሕዝብ እንዳለ የሚጠቁም ነው። ቅድመ ዐብይ ሰልፎች ስለሺ በትምህርት ምክንያት ወደ መዲናዋ ከዘለቀ እና እርሱንም ተከትሎ ኑሮውን በቋሚነት ከመሠረተ በኋላ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሳተፍ የነበረውን ድባብ ሲያስታውስ ፈገግታ ያመልጠዋል። በሁለት ሺዎቹ የመጀመሪያ ዓመታት ነው። ጉምቱዋ የተቃውሞ ፖለቲካ መሪ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ለሁለተኛ ጊዜ ለእስር ተዳርገዋል፤ ይህ ያስቆጣቸው የአንድነት ፓርቲ አባላት ስሜታቸውን በአደባባይ ለመገልፅ ቆርጠዋል። በምርጫ 97 በኋላ ከተደረጉት ቀዳሚ የተቃውሞ ሰልፎች አንዱን ለማከናወንም ፈቃድ አግኝተዋል። ሦስት መቶ የማይሞሉ የፖርቲው አባላት ከፓርቲው ጽሕፈት ቤት ተነስተው እስከ አራት ኪሎ ቤተ መንግሥት ድረስ የተቃውሞ ድምፃቸውን እያሰሙ ሲጓዙ ስለሺ ከመካከላቸው ነበር። "በ97 ዓ.ም የነበረው ግድያ እና ደም አእምሯችን ውስጥ ስለነበር ስጋት ሰንጎን ነበር" ይላል። "በማንኛውም ሰዐት ጥይት ሊተኮስ እንደሚችል እያሰብን ነበር የምንሄደው።" ሰልፈኞቹ ወደ ቤተ መንግሥት እየተቃረቡ ሲመጡ በርከትከት ብለው የቆሙ ወታደሮች ስሜታቸውን የበለጠ እንደረበሹት የሚናገረው ስለሺ፥ ይሄኔ ከሰልፈኞቹ አንደኛው ሰልፉን በጠንካራ መፈክሮች ከሚመራውን ሰው የድምፅ ማጉያ ነጥቆ "እኛ ሰላማዊ ነን" የሚል መፈክር እንዲያሰማ እንዳስገደዱት ያስታውሳል። ከዚያም በኋላ ተቃዋሚዎቹ ሰማያዊ እና አንድነት ፓርቲዎች ባዘጋጇቸው ሰልፎች ላይ የተሳተፈው ስለሺ፥ የአንድነት ለፍትህ እና ዲሞክራሲ ፓርቲ ልሳን የነበረች "የሚሊዮኖች ድምፅ" የተሰኘች ጋዜጣን ማዘጋጅትም ጀምሮ ነበር። ፓርቲው የጠራውን ሰልፍ ለመዘገብ ከነ ፎቶ መቅረጫ በወጣበት አንድ ወቅት ለፖሊስ ዱላ መዳረጉን ይገልፃል። "ካሜራየን ደብቄ ዞር ስል፥ አንድ ዱላ መትቶ ጣለኝ" ከዚያም "በርካታ ፖሊሶች ቀጥቅጠው ግራ እጄ እንዲሰብር አደረጉ፤ በብረት ነው ያለው። ብረቱ አሁንም ድረስ አለ" ሲል ይናገራል ስለሺ። በድብደባው ምክንያት ስምንት ወር ይተኛ እንጂ እስካሁም በጣም የሚገርመው ግን በወቅቱ ከሠላሳ ለማይበልጡ ሰልፈኞች በመቶዎች የሚቆጠሩ ፖሊሶች መምጣታቸው መሆኑን ያስታውሳል። የዐብይ መቶ ቀናት በስለሺ ስለሺ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይን ወደ መሪነት መምጣት እና እርሳቸውም በጠቅላይ ሚኒስትርነት ከተሰየሙ በኋላ የወሰዷቸውን እርምጃዎች "የአብዮት ትርፉቶች" ናቸው ሲል ይገልፃቸዋል። እናም "የኢትዮጵያ አብዮት ገና መጠናት አለበት።" ይሁንና ስለሺ የቅርብ ጊዜ የቅርብ አገራትን ተሞክሮ ማጤን ለንፅፅር ይጠቅማል ባይ ነው። "የሊቢያ አብዮት ጋዳፊን በመግደል ነው የተጠናቀቀው፤ የግብፅ አብዮት ሙባረክን በማሰር ነው የተጠናቀቀው።" ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ከነባር የኢህአዴግ አመራሮች መካከል ማንም ሳይሞት፥ ማንም ሳይታሰር "ኃሳባቸው ነው የሞተው" ይላል። ለስለሺ እንደሚለው አይበለውና ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን በመቶኛ ቀናቸው ድንገት ሥልጣን ቢለቁ እንኳ የእስካሁኑ እርምጃዎቻቸው በቂ ስኬትን ይዟል። "ዐብይ ከዚህ በኋላ የሚመጣው ጠቅላይ ሚኒስትር ምን ዓይነት መሆን እንዳለበት ልኬታ አስቀምጧል።"
news-44762560
https://www.bbc.com/amharic/news-44762560
በጃፓን ጎርፍ የመቶ ሰዎችን ሕይወት ቀጠፈ
በጃፓን ቢያንስ አንድ መቶ ሰዎች በጎርፍ መወሰዳቸው ተሰምቷል። ይህ የሆነው ባለፉት ቀናት በተከታታይ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ ነው።
ከሞቱት ሰዎቸ ሌላ ሐምሳ ሰዎች የገቡበት አልታወቀም። ካለፈው ሐሙስ ጀምሮ ምዕራብ ጃፓን ሌላ ጊዜ ከነበረው የሐምሌ የዝናብ መጠን በሦስት እጥፍ ጥሏል። ይህንንም ተከትሎ ሁለት ሚሊዮን ዜጎች ቀያቸውን ለቀው እንዲወጡ ታዘዋል። ምክንያቱ ደግሞ ወንዞች ግድቦቻቸውን ጥሰው እየፈሰሱ ስለሆነ ነው። 'እንዲህ ዓይነት ዝናብ ዘንቦ አያውቅም' ሲሉ የጃፓን የአየር ትንበያ ባለሞያ ለቢቢሲ ተናግሯል። አብዛኛዎቹ የሞት አደጋዎች የተመዘገቡት በሂሮሺማ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ለመገናኛ ብዙኃን እንደተናገሩት የነፍስ አድን ሠራተኞች ቀንተሌለት እየሠሩ ነው። በሺኮኩ ደሴት ሞቶያማ በምትባለው ከተማ 583 ሚሊ ሚትር ዝናብ መጠን መመዝገቡ ተሰምቷል። በቀጣይ ቀናትም ከዚህ የባሰ የዝናብ መጠን ሊኖር እንደሚችል ስጋት አለ።
42971436
https://www.bbc.com/amharic/42971436
የጣና ዕጣ ፈንታ ለገዳማቱ መነኮሳት አሳሳቢ ሆኗል
በጣና ሐይቅ ላይ ያንዣዘብበውን አደጋ ለክፍላተ ዘመናት ያህል ኃይማኖታዊ፣ ታሪካዊ እንዲሁም ባህላዊ ቅርሶችን ጠብቀው ባቆዩት ገደማት እና አብያተ ክርስትያናት የሚያገለግሉ መነኮሳት እና መናንያን እንዳሳሰባቸው ለቢቢሲ ገልፀዋል።።
በሐይቁ ባሉ ደሴቶች ከአስራ አምስት ሺ ሕዝብ በላይ ይኖራሉ። ደሴቶቹ የበርካታ ገዳማትና አብያተ ክርስትያናት መቀመጫም ናቸው። አባ ወልደሰንበት ያለፉትን ወደሃያ የሚጠጉ ዓመታት ያሳለፉት በጣና ሐይቅ ተከብባ የምትገኘውን የእንጦስ እየሱስ ገዳም በማገልገል ነው። ከብዙሃን ተነጥለው ዕድሜያቸውም ለፀሎት ይስጡ እንጅ አካባቢውን ለሚያሳሳቡ ጉዳዮች ባይታወር ናቸው ማለት አይደለም። ከሰሞኑ ጣናን ስለወረረው አረም የሚሰሙት ነገር ያሳሰባቸውም ለዚህ ነው። "እምቦጭ አረሙ መጥቷል ማሽን እየተፈለገ ነው። አረሙ አስቸጋሪ እንደሆነም ሰማሁ። እኛማ ሃገር ከተቸገረ እኛም አብረን መቸገራችን ነው። ምን እናደርጋለን። እርሻ ላይ እንደገና ይበቅልበታል፤ እህልም ያበላሻል። ይህ ደግሞ ምን ዓይነት ፈተና ብዬ አዘንኩ። " በማለትም ይናገራሉ። በጣና ሀይቅ ላይ ከሚገኙ የ37 የደሴት ገዳማት መካከል አንዱ የሆነው የክብራን እንጦንስ ኢየሱስ ገዳም መነኮሳትም ሀይቁ ላይ የተጋረጡት አደጋዎች አሳሳቢ ናቸው ይላሉ። በቅርብ ርቀት ላይ ባለው የገዳሙ የሴቶች መኖሪያ ያገኘናቸው እማሆይ ወለተማርያም ስጋቱን ይጋራሉ። ችግሩን ለመመከትም ፀሎት መጀመራቸውንም ይናገራሉ። "እምቦጭ አረም እዚህ አካባቢአይደለም ያለው። ጣና ቂርቆስ አካባቢ ነው። እኛ ሲነገር ነው የምንሰማው ቢሆንም በጣም ያሳቅቀናል" የሚሉት እማሆይ ወለተማርያም "ጣና የእኛም ሆነ ሃገራችን ሃብት ነው። እኛ መሃል ላይ ስለሆንን ሊደርስብንም ላይደርስብንም ይችላል። ውሃውን እያመናመነ ሊያደርቀው ይችላልም ብለን እየተሳቀቅን ነው። ስለዚህም እንጸልያለን። ጸሎት መናንያን የሚፀልዩት ለእነርሱ ብቻ ሳይሆን ዓለም ሁሉ ነው። እኔ ሳልሆን አባቶችና እናቶች ዘወትር የሚፀልዩት ለዓለም ነው። ዓለምን አድንልን ብለው ነው" ይላሉ። ሆኖም የሐይቁን ደህንነት መጠበቅ የሰዎች ኃላፊነት መሆኑን መነኮሳቱ የሚያስረዱት አፅንኦት ሰጥተው ነው። ለምሳሌ በአካባቢው ፋብሪካዎች እና ሆቴሎች የሚደርሰው ብክለት ለአባ ወልደሰንበት ሊታረም የሚገባው ጥፋት ነው። "ኃጥያት ነው እንጅ ፤ በጣም እንጅ በሚገባ" ይላሉ።
news-47634987
https://www.bbc.com/amharic/news-47634987
ደስታን ለመፍጠር የሚረዱ አምስት መንገዶች
ዛሬ መጋቢት 11 ዓለም አቀፍ የደስታ ቀን ነው። በዕለት ከለት ህይወታችን ውስጥ የተለያዩ ገጠመኞች ደስታን ይሰጡናል። ነገር ግን በአጋጣሚዎች ብቻ ሳይሆን አስበንበት ደስታን መፍጠር እንደምንችል ባለሙያዎች እናገራሉ።
ደስታ እንዲሁ የሚመጣ ሳይሆን ልምምድን ይጠይቃል ይላሉ ባለሙያዎች ይህም ልክ እንደ እስፖርተኞችና ሙዚቀኞች ሁልጊዜም ደስታም ልምምድና የትግበራ ቅደም ተከተል ያስፈልገዋል። በሂደትም የሚፈልጉትን አይነት ደስተኛ ሰው ይሆናሉ። "ደስተኝነት ዝም ብሎ የሚመጣ ነገር አይደለም፤ ይልቁንም ራሳችንን ለደስታ በማዘጋጀትና በማለማመድ የምናመጣው ነው" ይላሉ በአሜሪካ ያሌ ዩኒቨርሲቲ የሥነ አዕምሮ ፕሮፌሰሯ ላውሪ ሳንቶስ። • ደስታን አጥብቀን ስለፈለግን ለምን አናገኘውም? በርግጥ ቀላል ላይሆን ይችላል ነገር ግን ደጋግሞ በመለማመድ ውጤታማ መሆን ይቻላል ባይ ናቸው ፕሮፌሰሯ። ለዚህም ያግዝ ዘንድ የሚከተሉትን አምስት መንገዶች በመጠቀም በተማሪዎቼ ላይ ውጤት አምጥቼባቸዋለሁና እነዚህን መከተል ተገቢ ነው ብለዋል። 1. የረኩባቸውን ተግባራት በዝርዝር መያዝ በሥራም ይሁን በማንኛዉም አጋጣሚ ያገኟቸውን ስኬቶች በእያንዳንዱ ቀንና ሳምንት በመዘረዝር ከእነዚህ ስኬቶች የሚያገኟቸውን እርካታዎች ማጣጣም ያስፈልጋል። • «ስጦታ ከመቀበል፤ መስጠት ያዋጣል» 2. በደንብ እና በተሻለ ሁኔታ መተኛት ማንኛውም ደስተኛ መሆን የሚፈልግ ስው በቀን ቢያንስ 8 ስዓት መተኛት ይኖርበታል። በርግጥ ከሁሉም የደስታ መለማመጃ መንገዶች መካከል ተማሪዎች ይህን ለመተግበር እንደሚቸገሩ ፕሮፌሰሯ ይገልጻሉ። ዝምብሎ ሲታይ ቀላል ሊመስል ይችላል ነገር ግን በቂ እንቅልፍ ማግኘት ድብርትን በመቀነስና የደስተኝነትን ስሜት በመጨመር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው። ለራስዎ የፅሞና ጊዜ ይስጡ 3. ለተወሰነ ደቂቃ የፅሞና ጊዜ መውሰድ በቀን ቢያንስ የ10 ደቂቃ ፅሞና ማድረግ ይኖርብናል። ፅሞና ማድረግ ሙሉ ትኩረትን በመሰብበስብ ለአፍታ ከራስ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ቀጣይ በምን ነገሮች ላይ ደስታን ማምጣት እንደሚቻል መንገዱን ክፍት አድርጎ ያሳያል። 4. ከቤተሰብና ጓደኛ ጋር ብዙ ጊዜ ማሳለፍ በህይዎታችን ቅድሚያ የምንሰጣቸውንና ጤናማ ግንኙነት ካለን ሰዎች ጋር ጊዜ ሰጥተን ማውራትና መጫወት ተጨማሪ ደስታ ያመነጫል። ነገር ግን ጊዜው መብዛት እንደሌለበት ፕርፌሰር ሳንቶስ ይመክራሉ። ምክንያቱም ጊዜው በበዛ ቁጥር ከነዚህ ሰዎች ጋር ጥገኛ የመሆን እድላችን ሊሰፋ ይችላልና ነው። በተለያዩ እንቅስቃሴ ላይ ይሳተፉ 5. የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን መቀነስና ብዙ የሥራ ግንኙነት መመስረት ማህበራዊ ሚዲያ የሃሰት ደስታ ሊሰጠን ይችላል፤ በመሆኑም በዚህ ድርጊት ላለመደበር አጠቃቀማችንን መቀነስ ያስፈልጋል። በቅርብ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሰዎች በብዛት በተለይ ኢንስታግራም የሚጠቀሙት ትንሽ የመደሰት እድል ሲኖራቸው የማይጠቀሙት ደግሞ የተሻለ ደስታ እንዳላቸው ተረጋግጧል። • እራስን መፈለግ፣ እራስን መሆን ፣ እራስን ማሸነፍ በአጠቃላይ በህይወትዎ ደስተኛ መሆን ከፈለጉ በምስጋና ይጀምሩ፣ ጥሩ የእንቅልፍ ሌሊት ይኑረዎ፣ የፅሞና ጊዜ ይኑርዎ፣ ከሚወዷቸው ሰዎች ጋር ጊዜ የያሳልፉ እንዲሁም የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምዎን ያስተካክሉ። ፕሮፌሰር ሳንቶስ እነዚህን መንገዶች በተማሪዎቻቸው ላይ ተግብረውት ውጤት እንዳመጡ ይናገራሉ። ለእርሰዎም ደስታ ሊያስገኝልዎ ስለሚችል ይሞክሯቸው።
53604861
https://www.bbc.com/amharic/53604861
ሪፐብሊካን ለትራምፕ፡ ምርጫውን ማዘግየት አይችሉም
ጎምቱ የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት ፕሬዝዳንት ትራምፕ በመጪው ህዳር የሚካሄደው የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዲራዘም ያቀረቡትን ሃሳብ ተቃወሙ።
ፕሬዝዳንቱ ምርጫው እንዲራዘም ፈልገው የነበረው በፖስታ የሚሰጥ ድምጽ ማጭበርበር አያጣውም ከሚል ስጋት ነው። በሪፐብሊካን የበላይነት የሚመራው ሴኔት አባል የሆኑት ሚች ማክኮኔል እና በህግ መምሪያ ምክር ቤት ውስጥ አነስተኛ ቁጥር ያላቸውን ሪፐብሊካን የሚወክሉት ኬቨን ማክ ካርቲ ናቸው የትራምፕን ሃሳብ የተቃወሙት። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ምርጫውን የማራዘም ሥልጣኑ የላቸውም፤ የትኛውም የምርጫ ማራዘም እቅድ መጽደቅ ያለበት በኮንግረሱ ነው ተብሏል። ቀደም ብሎ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በህዳር ወር የሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በፖስታ የሚሰጥ ድምጽ ወደ ማጭበርበርና የተሳሳተ ውጤት ያመራል በሚል ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ ሃሳብ አቅርበው ነበር። ምርጫው የሚዘገየው እስከመቼ ድረስ እንደሆነ ሲናገሩም ሰዎች "በአግባቡ፣ ደህንነታቸውና ምስጢራቸው ተጠብቆ" መምረጥ ሲችሉ ብለው ነበር። • ዶናልድ ትራምፕ መጪው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዲዘገይ ጠየቁ • ጭምብል የማይለብሱ የአሜሪካ የሕግ መምሪያው ምክር ቤት አባላት ይባረራሉ ተባለ • አውሮፓ ሁለተኛ ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ያሰጋታል? የፕሬዝዳንቱን ስጋት የሚያረጋግጥ መረጃ ያለው በጣም አነስተኛ ቢሆንም እርሳቸው ግን በተደጋጋሚ በፖስታ የሚሰጥ ድምጽን በመቃወም ሲናገሩ ይደመጣሉ። የአሜሪካ ግዛቶች በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በፖስታ የሚሰጥ ድምጽን ቀለል ማድረግ ይፈልጋሉ። ሴናተር ማ ኮኔል አሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ከዚህ በፊት አንዴም ዘግይቶ እንደማያውቅ ተናግረዋል። " በአገሪቱ ታሪክ ታይቶ አይታወቅም። በጦርነት፣ በኢኮኖሚ ድቀት ውስጥ እያለን አንኳ በፌደራል ደረጃ የተያዘ ምርጫ በወቅቱ ተካሂዶ ነው የሚያውቀው። በዚህ ዓመት ህዳር ወር ላይም ያንን ነው የምናደርገው' ብለዋል። ማክ ካርቲም የእርሳቸውን ሃሳብ በመደገፍ " በፌደራል በሚደረግ የምርጫ ታሪክ ይህ ተከስቶ አይታወቅም፤ ስለዚህ ምርጫችንን በታቀደለት ጊዜ እናከናውናለን" ብለዋል። የትራምፕ ደጋፊ የሆኑት ሴናተር ሊንድሲ በበኩላቸው ምርጫውን ማራዘም "መልካም ሃሳብ አይደለም" ብለዋል። ነገር ግን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማይክ ፖምፒዮ በፕሬዝዳንቱ ሃሳብ ላለመጠለፍ ሲታገሉ ተስተውሏል። ጋዜጠኞች፣ ፕሬዝዳንቱ ምርጫውን ያራዝሙት እንደሆነ ሲጠይቋቸው " በእንዲህ ያለ የህግ ትርጓሜ ውስጥ " መግባት እንደማይፈልጉ ተናግረዋል። የትራምፕ ዳግም ምርጫ ቃል አቀባይ ሆጋን ጊድሊ ፕሬዝዳንት ትራምፕ "ጥያቄ ነው ያነሱት" ሲሉ ተከላክለዋል። በአሜሪካ ህግ መሰረት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ምርጫውን የማራዘም መብት የላቸውም። የምርጫውን ቀን መቀየር የሚያስፈልግ ከሆነ መጽደቅ ያለበት በኮንግረሱ እና በህግ መወሰኛ ምክር ቤት ይሆናል። የህግ መወሰኛ ምክር ቤትን ደግሞ የሚቆጣጠሩት ዲሞክራቶች ሲሆኑ ከአሁኑ አስቀድመው አንዳንድ ምክር ቤት አባላት የምርጫው መራዘምን ሃሳብ ተቃውመውታል። የአሜሪካን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ወደ 2021 ለመግፋት የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ ህገ መንግሥት ማሻሻያ ማድረግን እንደሚጠይቅ የሕገ መንግሥት ባለሙያ የሆኑ ግለሰቦችን ጠቅሰው አሜሪካ መገናኛ ብዙኀን ዘግበዋል። በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ስድስት የአሜሪካ ግዛቶች በህዳር ወር የሚካሄደውን ምርጫ በአጠቃላይ "በፖስታ በሚሰጥ ድምጽ" ለማድረግ አቅደው ነበር። እነዚህ ግዛቶች ዋሺንግተን፣ ኦሪገን፣ ኮሎራዶ፣ ሃዋይ፣ ዩታህ እና ካሊፎርኒያ ናቸው። እነዚህ ስድስት ግዛቶች ለተመዘገቡ መራጮች ወዲያውኑ በፖስታ ድምጽ መስጫ የሚልኩ ሲሆን፤ ፖስታዎቹም በምርጫ ቀን ተመልሰው የሚላኩ አልያም በምርጫ ጣቢያ የሚመለሱ ይሆናል። ይህ የፕሬዝዳንቱ ሃሳብ የተሰማው የአሜሪካ ምጣኔ ሃብት በ1930 ከገባበት ድቀት በባሰ መጎዳቱን የሚያሳይ መረጃ ከወጣ በኋላ ነው።
news-46143929
https://www.bbc.com/amharic/news-46143929
ዝቅተኛ የሴት እንደራሴዎች ቁጥር ያላቸው አገሮች እነማን ናቸው?
የዓለምን ዐይንና ጆሮ ይዞ የቆየው የአሜሪካ ምርጫ በርከት ያሉ ሴቶችን ወደ ፖለቲካ ተሳትፎ ማምጣቱ በአያሌው ተወስቷል። በአሜሪካ የሰሞኑ የ'ሚድተርም' ምርጫ ክብረ ወሰን በተባለ ቁጥር ሴቶች የሴኔት ወንበር ማሸነፋቸውን ሰምተናል።
የሩዋንዳ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባላት የምርጫው ውጤት መቶ በመቶ ባልተጠናቀቀበት ሁኔታ እንኳ 98 ሴቶች የታችኛው ምክር ቤት በእንደራሴነት መግባታቸው ተዘግቧል። በተለይ በአሜሪካ ሚዲያ እንዲህ በስፋት ከበሮ የሚደለቅለት ይህ የሴቶች ተሳትፎ የእኩልነት ተምሳሌት ተደርጋ ለምትታየው አሜሪካ እንዴት አስደናቂ ሆነ? ለመሆኑ በሁለቱ የአሜሪካ ምክር ቤቶች ውስጥ የሚገኘው የሴቶች ቁጥር የዓለም ምሳሌ ሊሆን ይችላል? •ኢንጅነር አይሻ መሃመድ የሃገር መከላከያ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ •ሃምሳ በመቶ የሚኒስትሮች ሹመት ለሴቶች •"የመከላከያ ሚኒስቴርን በተሻለ መልኩ መምራት ይቻላል" ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ጥናቶች ተቃራኒው ይመሰክራሉ። በዓለም ላይ አሜሪካንን የሚያስንቁ በርካታ ታዳጊ አገሮች የተሻለ ቁጥር ያላቸው ሴት እንደራሴዎች አሏቸው። ለምሳሌ በአሜሪካ በታችኛው ምክር ቤት የሴቶች ቁጥር ከጠቅላላው እንደራሴ 23 እጅ አካባቢ ነው። ይህ ለብዙ አገራት አስቂኝ ቁጥር ነው። የኢንተር ፓርላመንታሪ ክበብ በጥቅምት 2011 ባወጣው አንድ ጥናት አሜሪካ ሴቶችን በፓርላማ እንደራሴነት በማስመረጥ ከዓለም 'ውራ ናት' ይላል። ከ193 አገራት መካከል ስትወዳደር ያላት ደረጃም 104ኛ ነው። የ'ሚድተርም ምርጫን ተከትሎ ከፍተኛ እድገት አሳየ የተባለውን ጨምረን እንኳ ብናሰላው አሜሪካ ከዓለም 70ኛ ደረጃን ነው የሚያሰጣት። እንዲያውም በዚህ ረገድ እነ ዩጋንዳ፣ ዚምባብዌና ኢራቅ የተሻሉ ናቸው። አሰቃቂ የእርስ በርስ ፍጅት ታሪክ ያላት ሩዋንዳ በከፍተኛ የሴት እንደራሴዎች ቁጥር ዓለምን ትመራለች። • የካቢኔ አባላት በፌስቡክ ማስታወቂያ ተመረጡ የታችኛው ምክር ቤት 61.3፣ በሴኔት ደግሞ 38.5 በመቶ ሴት ተመራጮች ናቸው የያዙት። ኢትዮጵያ የሴት ውክልና ልቆ ከሚታዩባት ሀገሮች መካከል አንዷ ስትሆን 32 % የሴት እንደራሴዎች አሏት። የአሜሪካ የረዥም ጊዜ የርእዮተ ዓለም ባላንጣ ኩባ ደግሞ 53.2 በመቶ የምክር ቤቷ እንደራሴዎች ሴቶች ናቸው። ቦሊቪያ፣ ሜክሲኮ፣ ግሬናዳ፣ ናሚቢያና ስዊድን ከ3-7 ያለውን የደረጃ ሰንጠረዥ ይዘውታል። ከአፍሪካ ዝቅተኛ የሴት እንደራሴ ቁጥር ያላት አገር ናይጄሪያ ስትሆን ከጠቅላላ ተመራጮች 5.6 በመቶ ብቻ ምክር ቤት መግባት ችለዋል። ከአለም በመጨረሻ ደረጃ የተቀመጠችው የመን ስትሆን 1.8% እንደራሴዎቿ ሴቶች እንደሆኑ ጥናቱ ያሳያል።
news-57278704
https://www.bbc.com/amharic/news-57278704
ባራክ ኦባማ የእንግሊዙ እና የማንቸስተር ዩናይትዱን አጥቂ ማርከስ ራሽፎርድን አወደሱ
የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንና የማንቸስተር ዩናይትዱ አጥቂ ማርከስ ራሽፎርድ በጸረ ድህነት ዘመቻው ከባራክ ኦባማ አድናቆት ተቸረው።
በዙም አማካይነት በኢንተርኔት በተካሄደው ውይይት ላይ ራሽፎርድን "እኔ በእሱ ዕድሜ ከነበርኩበት ቀድሞ የሄደ" ሲሉ የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት አወድሰውታል። ማንቸስተር ከሚገኘው መኖሪያው ማዕድ ቤት ሆኖ በውይይቱ የተካፈለው የ23 ዓመቱ እግር ኳስ ተጫዋች ከኦባማ ጋር መነጋገሩን "የማይታመን" ነው ብሏል። ኦባማ እንደ ራሽፎርድ ያሉና "በማኅበረሰባቸው አዎንታዊ ተጽዕኖ ፈጣሪ" የሆኑ ወጣቶችን ደግፈዋል። ፔንግዊን በተባለው አሳታሚ በተዘጋጀው ውይይት ላይ በቀድሞው ፕሬዝዳንት 'ማስታወሻ' ላይ በመወያየት፤ በእናት እጅ ብቻ ስለማደግ እና በማኅበረሰብ ፕሮጀክቶች ውስጥ ስለመሳተፍ ያሉት ልምዶች ተነስተዋል። 'መከራ እና እንቅፋቶች' "በአነስተኛ ደረጃ አዎንታዊ ነገር ብታደርጉ እንኳ ለውጥ እያመጣ ነው። ከጊዜ በኋላም አዎንታዊ ነገሮችን የሚያደርጉ ሰዎች መጨመር ካለፈው ትውልድ ትንሽ እንድንሻል ያደርገናል" ብለዋል ኦባማ። በተጨማሪም ወጣት በነበሩበት ጊዜ ፕሬዝዳንት የመሆን ተስፋ እንዳልነበራቸው ተናግረዋል። "የበለጠ ችሎታ ቢኖረኝ ኖሮ እንደ ማርከስ ስፖርተኛ መሆን እመርጥ ነበር" ብለዋል ኦባማ። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ለማርከስ ራሽፎርድ "ማኅበራዊ እንቅስቃሴዎች ብዙውን ጊዜ የሚጀምሩት በወጣቶች ነው" ሲሉ ነግረውታል። የእግር ኳስ ተጫዋቹ ግን ብዙውን ጊዜ "ድምጻቸው ምን ያህል ኃይል እንዳለው አይረዱም" ብሏል። የህጻናትን ረሃብ ለመከላከል ከፍተኛ ዘመቻ የሚያካሂደው የማንችስተር ዩናይትዱ አጥቂ "ፕሬዝዳንት ኦባማ ሲናገሩ ማድረግ የምትፈልገው ማዳመጥ ብቻ ነው" ሲል ተናግሯል። "ማለቴ ማንቸስተር ውስጥ በሚገኘው ማዕድ ቤቴ ተቀምጬ ከፕሬዚዳንት ኦባማ ጋር እየተነጋገርኩ ነው። ግን ወዲያውኑ እንድረጋጋ አደረገኝ። በጣም የማይታመን ነው አይደል?" ብሏል። "ለአሁኑ ማንነታችን መፈጠር ልጆች እያለን ያጋጠሙንን ልምዶች ምን ያህል እንደሚመሳሰሉ የተረዳሁት ብዙም ሳይቆይ ነበር" ሲል ገልጿል። የምግብ ድህነት በዚህ ሳምንት ቡድኑ ማንቸስተር ዩናይትድ በዩሮፓ ሊግ ፍጻሜ መሸነፉን ተከትሎ ራሽፎርድ "የዘረኝነት ጥቃቶች" በማኅበራዊ የትስስር ገጾች እንደገጠሙት ሲገልጽ ቡድኑ ደግሞ "አሳፋሪ የዘረኝነት ጥቃት" ብሎታል። ሁለቱ ተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎች በመጽሐፍትን እና በንባብ አስፈላጊነት ዙሪያ ተወያይተዋል። እናታቸው "የንባብ ፍቅር እንደዘሩባቸው" የተናገሩት ባራክ ኦባማ ሲሆኑ ራሽፎርድ በበኩሉ መጻሕፍት የራሱን ሃሳብ የመከተል ነፃነት እንደሰጠው ተናግሯል። "ሰው ይህን አድርግ ያንን አድርግ ከሚለኝ ይልቅ መጽሐፍት በራሴ መንገድ እንድፈጽም ረድቶኛል" ብሏል ራሽፎርድ። ችግረኛ ወጣቶችን የንባብ ችሎታን ለማሻሻል የእግር ኳስ ተጫዋቹ ባለፈው ዓመት የራሱን የልጆች መጽሐፍ ክበብ አቋቁሟል። ራሽፎርድ ከቴሌቪዥን የምግብ አብሳዩ ቶም ኬሪጅዝ ጋር በመሆን የምግብ ድህነትን የዘመቻው አካል በማድረግ የተመጣጠነ እና በቀላሉ የሚገኝ ጤናማ ምግቦች አዘገጃጀት ዙሪያ ምክሮችንም ይሰጣል። ራሽፎርድ በልጅነቱ ስለመራብ እና በልጅነት በነጻ የትምህርት ቤት ምገባ ላይ ጥገኛ ስለመሆን ተናግሯል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት ትምህርት ቤቶች በነጻ ምግባቸው እንዲቀጥሉ ሃሳብ በማቅረብ ከመንግሥት ጋር የተሳካ ጥረት አድርጓል። የቀድሞው የጠቅላይ ሚንስትሩ አማካሪ ዶሚኒክ ኩሚንግስ ለተመረጡት የፓርላማ አባላት እንደገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ከራሽፎርድ ጋር ጠብ አትምረጡ" የሚል ምክር እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።
news-48166897
https://www.bbc.com/amharic/news-48166897
ጋዛ በእስራኤል ላይ በሰነዘረችው ጥቃት የተነሳ ውጥረት ነገሰ
በእስራኤልና በጋዛ ያለው ግጭት በድጋሜ ከተቀሰቀሰ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል። የጋዛ ወታደሮች 250 የሚሆኑ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል መተኮሳቸውን የአገሪቱ ወታደሮች አስታውቀዋል።
አስራኤል በጋዛ የሚገኘው የወታደራዊ ካምፕ ኢላማዋ እንደነበር አስታውቃለች • እስራኤል ረጅሙን የጋዛ ዋሻ አፈረሰች ባለስልጣናቱ እንዳስታወቁት በተወረወረ ቦምብ አንድ እስራኤላዊ ሲገደል ከእስራኤል በተሰነዘረ ጥቃት ደግሞ እናትና ልጅን ጨምሮ አራት ፍሊስጤማውያን መገደላቸውን ገልጸዋል። ይሁን እንጂ እናትና ልጅ የተገደሉት በፍሊስጤም በተተኮሰና ዒላማውን በሳተ ሮኬት ነው ስትል እስራኤል አስተባብላለች። ባለፈው ወር ከተደረገው የድንበር ስምምነት በኋላ የሁለቱ አገራት ቁርሾ በድጋሜ ያገረሸ ሲሆን ሁለት የእስራኤል ወታደሮች ከተገደሉ በኋላ ሁለት የሃማስ ታጣቂዎችን ጨምሮ አራት ፍሊስጤማውያን በሳለፍነው አርብ ተገድለዋል። በግብፅና በተባበሩት መንግስታት ጣልቃ ገብነት የተደረገው የተኩስ አቁም ስምምነት ወደ ጎን በመተው አሁን በቅርቡ በደረሰው ጥቃት ውጥረት መንገሱን በእየሩሳሌም የሚገኘው የቢቢሲ ጋዜጠኛ ቶም ባቲማን ዘግቧል። • አይ ኤስ በጀነራል ካሊፍ ጦር ላይ ጥቃት ሰነዘርኩ አለ ጥቃቱ የተጀመረው አካባቢው መከለሉን ተከትሎ በጋዛ በተነሳ ተቃውሞ ምክንያት ሲሆን እስራኤል አካባቢውን የከለልኩት በጋዛ የሚደርሱ የጦር መሳሪያዎችን ለመቆጣጠር ነው ብላለች። ሁለት የሃማስ ወታደሮች መገደላቸውን ተከትሎም እስራኤል በሰነዘረችው ጥቃት ሌላ ሁለት ፍሊስጤማውያን በድንበር አካባቢ መገደላቸው ታውቋል። የፍሌስጤም ታጣቂ ሁለት የእስራኤል ወታደሮችን በድንበር አካባቢ የገደለ ሲሆን አይ ዲ ኤፍ ጥቃቱን በእስላማዊ ጂሃድ አሳቧል። እስላማዊ ጂሃድ በበኩሉ አርብ ዕለት በተፈፀመው የአፀፋ ጥቃት የሮኬት ጥቃት መፈፀሙን አምኗል። • ቻይና ሙስሊም ዜጎቿን እየሰለለች ነው ተባለ በመግለጫውም እስራኤል ባለፈው ወር በግብፅ አሸማጋይነት የተደረገውን የተኩስ አቁም ስምምነት መጣሷንም ጨምሮ ተናግሯል። የሃማሱ ቃል አቀባይ አብደል ላቲፍ አል ቃኑዋ " የአፀፋ ምላሹ የተሰጠው ህዝባችንን ከጥቃት ለመከላከል ነው፤ የህዝባችን ደም ፈሶ አይቀርም፤ ትግላችንም የሚቀጥል ይሆናል" ሲሉ ቅዳሜ ዕለት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። በጋዛ እስራኤል ድንበሯን መዝጋቷንና የውጭ እርዳታ መቋረጡን ተከትሎ በኢኮኖሚ ችግር የሚንገላቱ 2 ሚሊዮን ፍሊስጤማውያን ይኖራሉ።
news-41024187
https://www.bbc.com/amharic/news-41024187
ሰዓትን በትክክል የመቁጠር ጠቀሜታ
ከጥንት ጀምሮስለጊዜ ያለን ግንዛቤ በፕላኔቶች እንቅስቃሴ ላይ የተመረኮዘ ነው። ምድር ፀሐይን እንደምትዞር ከማወቃችን በፊትም ስለቀናትና ዓመታት እናወራ ነበር።
የጨረቃ ድምቀት መጨመርና መቀነስን እየተመለከትንም የወራትን እሳቤ ለየን። ምንም እንኳን የፀሐይን እንቅስቃሴ ለመረዳት ባለንበት ቦታ የሚወሰን ቢሆንም፤ ፀሐይ ሰማይን አቋርጣ ስትጓዝ እኩለ ቀንንና አመሻሽን መገንዘብ ግን እንችላለን። በተለምዶ ሰዎች በብዛት ሰዓታቸውን የሚያስተካክሉት በሚኖሩበት አካባቢ ሰማይ ላይ በሚታዩ ምልክቶች ላይ በመመርኮዝ ነው። ይህንንም በአካባቢያቸው ካሉ ሰዎች ጋር ተመሳሳይ እንዲሆን ለማድረግ ከቻሉ ብዙም ችግር አይፈጥርም ነበር። ነገር ግን ሁለት ሰዎች በተለያዩ ሥፍራዎች ላይ ሆነው ሰዓት ቢመለከቱ የተለያየ ስለሚሆን ትክክለኛው ሰዓት ይህ ነው ለማለት ያስቸግራል። ይህንን የሰዓት መለያየት ለማስቀረት የአንዳንድ ከተሞች ባለሥልጣናት በሃገር ደረጃ የሚያገለግል ተመሳሳይ የሰዓት አቆጣጠር ቢኖር ጥቅሙ የጎላ እንደሚሆን ተገነዘቡ። ሌሎች ግን በሃሳቡ ደስተኛ አልነበሩም። በእርግጥም 'ትክክለኛ' የሚባል የሰዓት አቆጣጠር የለም። ለዚህም ነው ልክ ለገንዘብ እንደሚሰጠው ተመን ጥቅሙ በብዙሃኑ ዘንድ ባለው ተቀባይነት ላይ የተመሠረተ የሚሆነው። ያጋጠመ ችግር ቀደም ባለው ዘመን ሰዓትን በተመለከተ ትክክል የሚባል የአቆጣጠር ዘዴ ግን ነበረ። ይህም የሰዓት አቆጣጠር ከ1656 (እ.አ.አ) ጀምሮ የነበረ ሲሆን የዳች ዜጋ በሆነው በክርስቲያን ሃይገንዝ ነው የተተዋወቀው። ከጥንት ግብፃውያን ጊዜ አንስቶ እስከ መካከለኛው የፋርሶች ዘመን ድረስ ውሃን በመጠቀም ሰዓት ይቆጠር ነበረ። ሌሎች ደግሞ ሻማ ላይ በሚፈጠሩት ምልክቶች አማካይነት ጊዜን ይለያሉ። ሆኖም ግን እጅግ የላቀ የተባለለት የሰዓት አቆጣጠርም ቢሆን እኳን በቀን የ15 ደቂቃዎች ልዩነት ሊያሳይ ቢችልም፤ የፀሎት ሰዓትን ለማወቅ ለፈልጉ መነኮሳት ግን ይህ ብዙም ለውጥ አያመጣም። ነገር ግን ሰዓትን በትክክል ለመቁጠር አለመቻል እጅግ ጠቃሚ በሆነው የባህር ጉዞ ላይ ግዙፍ የሆነ ኢኮኖሚያዊ አድምታ አለው። መርከበኞች የፀሐይን መዓዘን በመመልከት ከሰሜን ወደ ደቡብ የትኛው ስፍራ ላይ እንደሚገኙ ያሉበትን አቅጣጫ ያሰሉ ነበር። ነገር ግን ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ ያሉበትን ሥፍራ ለመለየት ከግምት ውጪ አማራጭ አልነበራቸውም። ይህ ደግሞ ብዙ ጊዜ ለስህተት ክፍት የነበረ ሲሆን፤ መርከበኞቹ ሳያውቁ መድረስ ከነበረባቸው ቦታ በሺህ በሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች ርቀው በመጓዝ ከመሬት አካል ጋር እስከመጋጨት ድረስ ችግር ይገጥማቸው ነበር። ታድያ ሰዓትን በትክክል መቁጠሩ እንዴት ይረዳ ይሆን? ከግሪንዊች የሰዓት መከታተያ ወይንም ከማንኛዉም ሌላ ቦታ ላይ እኩለ ቀን መሆኑ ከታወቀ፤ የፀሐይን አቀማመጥን ተመልክቶ የጊዜ ልዩነትን በማስላት ርቀትን ለማወቅ ይቻላል። የሃይግንዝ የፔንዱለም ሰዓት ቀድመው በጊዜው ከነበሩት የሰዓት መቁጠሪያዎች አንፃር ከ60 ጊዜ ያህል በላቀ ሁኔታ ትክክለኛ የነበረ ሲሆን፤ በየዕለቱ የሚገጥመው የ15 ሰከንዶች ልዩነት ግን ሲደማመር ትልቅ ልዩነት ያስከትላል። ፔንዱለሞች ደግሞ በማዕበል በሚናጡ መርከቦች ላይ በአግባቡ መወዛወዝ አይችሉም ነበር። የባህር ግዛቶችን የሚያስተዳድሩ መንግሥታትም በሰዓት አቆጣጠር በኩል ያለውን ጉድለት ተረድተውት ነበረ። ለዚህም የስፔን ንጉስ ሃይግንዝ ሥራውን ከማቅረቡ አንድ ክፍለ ዘመን ቀደም ብሎ ይህንን ችግር ለመፍታት የሚያስችል መፍትሄ ለሚያቀርብ ሰው ሽልማት ለመስጠት ቃል ገብቶ ነበር። ከዚህም በኋላ የብሪታኒያ መንግሥት ያቀረበውን ሽልማት ተከትሎ በ 1700 (እአአ) በእንግሊዛዊው ጆን ሃሪሰን የተሰራውና በቀን የጥቂት ሰከንዶችን ልዩነት ያለው መቁጠሪያ ዕውን ሆነ። ይህ የዓለማችንን የሰዓት ቀጠናዎችን የሚያስታርቀው ትክክለኛው የሰዓት አቆጣጠር መላውን ዓለም አስማማ። ይህም ሁሉን አቀፍ የሰዓት አቆጣጠር ዩቲሲ (UTC) በመባል ይታወቅ ጀመር። በአብዛኛው የተለያዩ የሰዓት አቆጣጠር አይነቶች እኩለ ቀን የሚሆነው ፀሐይ አናት ላይ ስትሆን ነው በሚል ሐሳብ ይስማማሉ። ነገር ግን ሁልጊዜ እንደዛ ላይሆን የሚችልበት አጋጣሚ ይኖራል። ለምሳሌ ሊቀመንበር ማኦ ቻይናን በአምስት የሰዓት ቀጠናዎች የሚከፍለውን የጊዜ አቆጣጠር አስቀርተው የቤይጂንግ ሰዓት በመላ ሃገሪቱ እንዲሰራ ሲወስኑ በምዕራባዊ የቻይና ግዛት ፀሐይ ስትወጣ ሰዓቱ ግን እኩለ ቀን ስድስት ሰዓት ላይ ያመለክታል። የሰከንድ ሽርፍራፊዎች ለምን ይጠቅሙ ይሆን? የሃይግንዝና ሃሪስን ሥራ ተከትሎ ሰዓቶች ይበልጥ ትክክለኛ ጊዜን እያመለከቱ መጥተዋል። ሁሉን አቀፍ የሰዓት አቆጣጠር (ዩቲሲ) የአቶሚክ ሰዓቶችን ተጠቅሞ ኤሌክትሮኖች ውስጥ ያለውን የኃይል መጠን ስለሚመዘግብ በመቶ ሺህ ዓመታት ውስጥ ሰዓቱ በሰከንድ ሽርፍራፊዎች ውስጥ ሳይቀር መዘባት አይገጥመውም። እንዲህ አይነቱ ትክክለኛ የሰዓት አቆጣጠር አስፈላጊ ነውን? የዕለት ተለት ሥራዎቻችንን የሰከንድ ሽርፍራፊዎቸን ግምት ውስጥ በማስገባት አናቅድም፤ እንዲያውም ብዙውን ሰዎች የእጅ ሰዓቶችን የሚያደርጉት ከሚሰጡት ጊዜን የመቁጠር አገልግሎት ይልቅ ከክብር ጋር ለተያያዘ ትርጉም ነው። ይህ ዕውነት ቢሆንም እንኳን የሰከንድ ሽርፍራፊዎቸ ትልቅ ለውጥ የሚያመጡባቸው አጋጣሚዎች ደግሞ የሉም ማለት አይቻልም። ምክንያቱም የሩጫ ውድድሮች ላይ አሸናፊ ሊኖር የሚችለው አንድ ብቻ ሲሆን እሱም ደግሞ በአንድ በሽራፊ ሰከንድ ልዩነት ምክንያት ሊሆን እንደሚችል መዘንጋት አያስፈልግም። ትክክለኛና ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው የሰዓት አቆጣጠር ለኮምፕዩተርና ለሌሎች የግንኙነት መገልገያዎች መዘርጋት እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው። የአቶሚክ ሰዓት አቆጣጠር እንደቀደመው ዘመን ሁሉ ለባህር ላይና ለባቡር ጉዞዎች የበለጠ አስተዋጽዎ አበርክቷል። ባለንበት ዘመን የፀሐይን ማዕዘን እየተመለከቱ መጓዝ ቀርቷል፤ ምክንያቱም ጂፒኤስ (አቅጣጫ ጠቋሚ) ቴክኖሎጂ በመስፋፋቱ። እንዲያውም ዘመናዊ የሞባይል ስልኮች ሳይቀሩ ባላቸው የኔትወርክ ትስስር ሳተላይቶችን ተጠቅመው በምድር ላይ የት ቦታ ላይ እንዳለን በቀላሉ እንድናውቅ ያግዙናል። ይህ ቴክኖሎጂ ከአየር እስከ ባህር ጉዞና በተራራማ ስፍራዎች ጭምር አገልግሎት በመስጠት ትልቅ ለውጥ አምጥቷል። ነገር ግን ይህ የሚሠራው ሳተላይቶቹ በሚጠቀሙት ሰዓት ላይ የሚስማሙ ከሆነ ብቻ ነው። አሁንም ድረስ የሰዓት አቆጣጠር እድገትና መሻሻልን ከማስተናገድ አልተገታም። በቅርቡም ሳይንቲስቶች ይተርቢየም የተሰኘ ንጥረ ነገር በመጠቀም አዲስ የሰዓት መቁጠሪያ ሰርተዋል። ይህ ሰዓት በትክክለኝነቱ ወደር የለሽ የሚባል ነው። ምክነያቱም በአምስት ቢሊዮን ዓመታት ውስጥ የሰከንድ አንድ መቶኛ የማይሞላ መዘግየት ብቻ ስለሚገጥመው ነው። ይህ እጅግ በጣም አስተማማኝ የሰዓት አቆጣጠር በቀደመውና በአሁኑ ዘመን መካከል ምን አይነት ኢኮኖሚያዊ ሽግግርን ያመጣ ይሆን? ሰዓቱ ሲደርስ የምናየው ይሆናል።
news-56211981
https://www.bbc.com/amharic/news-56211981
ሻሚማ ቤገም፡ አይኤስን የተቀላቀለችው ተማሪ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም እንዳትመለስ ብይን ተሰጠ
የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ፍርድ ቤት እስላማዊ ታጣቂ ቡድን [አይኤስ]ን የተቀላቀለችው ተማሪ ስለዜግነቷ ለመከራከር ወደ አገሪቷ መመለስ እንደማትችል ብይን ሰጠ።
ሻሚማ አይ ኤስን ለመቀላቀል ወደ ሶሪያ ያቀናቸው ታዳጊ ሳለች ነበር። ፍርድ ቤቱ በአንድ ድምፅ ባሳለፈው ውሳኔ፤ ለመመለስ ፈቃድ ባለማግኘቷ መብቷ አልተጣሰም ብሏል። የ21 ዓመቷ ሻሚማ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር የእንግሊዝ ዜግነቷ እንዲነሳ ያሳለፉትን ውሳኔ ለመከራከር ወደ ዩኬ መመለስ ትፈልጋለች። ሻሚማ አሁን የምትገኘው በሰሜን ሶሪያ በታጣቂዎች በሚጠበቅ ካምፕ ውስጥ ነው። ሻሚማ እርሷ እና ሁለት የኢስት ለንደን ተማሪዎች እአአ በ2015 እስላማዊ ታጣቂ ቡድኑን ለመቀላቀል ዩኬን ለቀው ወደ ሶሪያ ሲጓዙ የ15 ዓመት ታዳጊ ነበረች። እአአ በ2019 የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሳጂድ ጃቪድ፤ የብሔራዊ ደህንነት ሕግን መሰረት በማድረግ የሻሚማን ዜግነት ሰርዘዋል። ባለፈው ሐምሌ ወር የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ፍትሐዊ የሆነው ብቸኛው አማራጭ ሻሚማ ወደ ዩኬ እንድትገባ መፍቀድ እንደሆነ ውሳኔ አሳልፎ ነበር። ፍርድ ቤቱ ለዚህ ያስቀመጠው ምክንያት ካለችበት በሰሜናዊ ሶሪያ ከሚገኝ ካምፕ ሆና በተላለፈባት ውሳኔ ላይ ይግባኝ ማለት አልቻለችም የሚል ነበር። የአገር ውስጥ መስሪያ ቤቱ ግን እርሷን ወደ ዩኬ እንድትመለስ መፍቀድ በብሔራዊ ደህንነት ላይ አደጋ ሊኖረው ይችላል በሚል በተደጋጋሚ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ፤ የይግባኝ ሰሚ ፍርድቤቱ ያሳለፈውን ብይን በድጋሜ እንዲመረምር ጠይቋል። አርብ ዕለት የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዚደንት ሮበርት ጆን ሪድ፤ መንግሥት ሻሚማ ወደ ዩኬ እንዳትመለስ የማድረግ መብት አለው ብለዋል። ፕሬዚደንቱ የፍርድ ቤቱን ውሳኔው ሲያሳውቁም "ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የአገር ውስጥ ሚኒስትሩ ያቀረቡትን ይግባኝ ተቀብሎ ፤ የሻሚማን አቤቱታ ውድቅ አድርጓል" ሲሉ ተናግረዋል። አክለውም የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ የአንድ ግለሰብ መብት በፍትሐዊ መልኩ እንዲሰማ ሲደረግ ከብሔራዊ ደህንነት መርሆች ጋር በሚጋጭበት ጊዜ፤ የመሰማት መብቷ የበላይ መሆን አለበት የሚል የተሳሳተ እምነት ነበረው ሲሉም ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ብይን ውድቅ አድርገዋል። ፍትሐዊ የመሰማት መብት እንደ የሕዝብ ደህንነት ባሉ ጉዳዮች አልተደፈረም ሲሉም አክለዋል። የሻሚማን ጉዳይ የሚከታተለው ሊበርቲ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድን አሁን የተሰጠውን ፍርድ "እጅግ አደገኛ ምሳሌ " ብሎታል። ሻሚማ ቤገም ማን ናት? ሻሚማ ከባንግላዴሽ ቤተሰቦቿ የተወለደችው በዩናይትድ ኪንግደም ነው። ከሁለት የትምህርት ቤት ጓደኞቿ ጋር በመሆን አይኤስን ለመቀላቀል ወደ ሶሪያ ያመራችው የ15 ዓመት ታዳጊ ሳለች ነበር። ሻሚማ ራቃ ወደሚገኘው የአይ ኤስ ዋና መስሪያ ቤት ያቀናችው በቱርክ አድረጋ ነበር። እዚያም ሆላንዳዊ መልማይ አገባች። በአይኤስ ቁጥጥር ሥርም ከሦስት ዓመታት በላይ ኖራለች። ከዚያም እአአ በ2019 በሶሪያ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ የዘጠኝ ወር ነፍሰጡር ሆና ተገኝታለች። ህጻኑ በኋላ ላይ በሳምባ ምች በሽታ ሕይወቱ አልፏል። ሻሚማ እንደምትለው ከዚህ በፊት ሁለት ልጆቿን አጥታለች።
news-51695003
https://www.bbc.com/amharic/news-51695003
ጆ ባይደን በመጪው ምርጫ የትራምፕ ተቀናቀኝ ሆነው ሊቀርቡ ይችላሉ
በቀጣዩ የአሜሪካ ምርጫ ላይ የቀድሞ ምክትል ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ዲሞክራቶችን በመወከል የትራምፕ ተቀናቃኝ ሆነው ሊቀርቡ ይችላሉ ተባለ።
መራጮች ዲሞክራቶችን ወክሎ ሪፓብሊካኑን ዶናልድ ትራምፕን የሚገዳደር እጩ እየመረጡ ይገኛሉ። በደቡብ ካሮላይና በተደረገው ምርጫ ጆ ባይደን ማሸነፍ ችለዋል። ይህም በቀጣይ ምርጫ ዲሞክራቶችን ወክለው እንዲወዳደሩ ሊያስችላቸው ይችላል ተብሏል። ግራ ዘመሙ በርኒ ሳንደርስ፤ በደቡብ ካሮላይና በተደረገው ምርጫ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። የፊታችን ማክሰኞ ዲሞክራቶችን ወክሎ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ላይ የሚሳተፈው እጩ ይለያል። ለሶስተኛ ጊዜ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ላይ የሚሳተፉት ጆ ባይደን፤ በአፍሪካ አሜሪካውያን ዘንድ ድጋፍ እንዳላቸው ይታመናል። በደቡብ ካሮላይና እንዲያሸነፉ ያስቻላቸው ከጥቁሩ የኮንግረስ አባል ጄምስ ክላይበርን ይሁንታ በማግኘታቸው ነው የሚሉም በርካቶች ናቸው። በቀጣይ ምን ይፈጠራል? 'ሱፐር ቲዩስደይ' የሚል ስያሜ የተሰጠው የፊታችን ማክሰኞ የዲሞክራቶች እጩ ማን ሊሆን እንደሚችል የሚቀበት ቀን ነው። በ14 ግዛቶች የሚገኙ ዲሞክራቶች ድምጽ ይሰጣሉ። ከእነዚህም መካከል በርካታ የህዝብ ቁጥር ያላቸው ካሊፎርኒያ እና ቴክሳስ ይገኙበታል። በርኒ ሳንደርስም ሆኑ የኒው ዮርኩ ቢሊየነር ማይክል ብሎምበርግ ዲሞራቶችን በመወከል የትራምፕ ተቀናቃኝ ሆነው ሊቀርቡ የሚችሉበት እድል አለ። የ78 ዓመቱ አዛውንት በርኒ ሳንደርስ ድጋፋቸው በዋናነት የሚመነጨው ከወጣቶች ነው። ባለፈው ምርጫ በሂላሪ ክሊንተን ተሸንፈው ከዲሞክራት እጩነት መውጣታቸው ይታወሳል። በዘንድሮ ምርጫም ከጆ ባይደን በተጨማሪ ዲሞክራቶችን ወክሎ የትራምፕ ተቀናቃኝ የመሆን ስፊ እድል ያላቸው ሴናተር ናቸው።
news-53176031
https://www.bbc.com/amharic/news-53176031
እውቁ ካሜራ ኦሊምፐስ ከ84 ዓመት በኋላ መመረት ቆመ
የፎቶግራፍ ምስሎችን በማንሳት ከሚታወቁ ምርጥ ካሜራዎች መካከል አንዱ የነበረው ኦሊምፐስ ካሜራ መመረት እንዳቆመ ኩባንያው አስታወቀ።
ኦሊምፐስ ልክ እንደ ኒከን፣ ሶኒና ካነን ሁሉ በመላው ዓለም እውቅ ካሜራ ሆኖ ዘመናትን ተሻግሯል። በዓለም ግዙፍ ከሚባሉ ካሜራ አምራቾችም አንዱ ነበር። ከ84 ዓመታት በኋላ የካሜራ ምርቱን የሚመለከተውን ክፍል ለጃፓኑ ኢንዱስትሪያል ፓርትነርስ መሸጡ ተሰምቷል። ኩባንያው እንዳለው በዚህ ዘመን የካሜራ ቢዝነስ ምንም ሊያዋጣ አልቻለም። ምክንያቱ ደግሞ ዘመናዊ ካሜራ የተገጠመላቸው ዘመናዊ ስልኮች ገበያውን ማጥለቅለቃቸው ነው። ባለፉት ሦስት ዓመታት ምርት ላለማቆም በኪሳራ ሲንገታገት እንደነበረም ከኩባንያው ተገልጸዋል። ይህ የጃፓን ኩባንያ የመጀመሪያውን ኦሊመፐስ ካሜራ ምርቱን ለገበያ ያቀረበው በ1936 እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ነበር። ኩባንያው ከዚያ በኋላ ምርቱን እያሻሻለ አንድ ክፍለ ዘመን ሊያስቆጥር ጥቂት ዓመታት ሲቀሩት ነው በቃኝ ብሎ የካሜራ ምርቱን ለሌላ ድርጅት ያስተላለፈው። "ለኦሊምፐስ ካሜራ በመላው ዓለም ልዩ ፍቅር አለ" ይላል የአማተር ፎቶግራፊ መጽሔት አርታኢ ኒጀል አተርተን። በተለይ በ1970ዎቹ ኦሊመፐስ ካሜራ እነ ዴቪድ ቤይሌይ እና ሎርድ ሊችፊልድን በመሰሉ ዝነኛ ሰዎች ማስታወቂያ ይሰራለት ስለነበር በዓለም ደረጃ እውቅ ካሜራ ለመሆን አስችሎታል። "በጊዜው በጣም ትንሽ፣ በጣም የሚያማምሩ፣ በጣም ብርሃን ያላቸውና አጓጊ ነበሩ" ይላል የፎቶግራፍ መጽሔት አርታኢው ኒጀል አተርተን። የእጅ ካሜራዎች ገበያ ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ በ84 ከመቶ ወድቋል። ድርጅቱ የኦሊምፐስ ካሜራ ምርት ክፍሉን ለሌላ የጃፓን ኩባንያ ይሽጠው እንጂ ኦሊምፐስ እንደ ኮርፖሬሽን አልፈረሰም። ኦሊምፐስ ካሜራን የገዛው የጃፓን ኢንዱስትሪያል ፓርትነርስም ምርቱን መቼ እንደሚቀጥል ፍንጭ አልሰጠም። ሆኖም ኦሊምፐስ ኮርፖሬሽን የዚህን ካሜራ ምርት ከ84 ዓመታት በኋላ ማምረት ቢያቆምም ሌሎች ሌንሶችን፣ ማይክሮስኮፖችንና ለሕክምና የሚያገለግሉ ኢንዶስኮፖችን ማምረቱን ይቀጥላል። በኦሊምፐስ ካሜራ ምርት መቆምና ወደ ሌላ ኩባንያ መዛወር በርካታ የፎቶ ጥበብ ባለሞያዎች ሐዘናቸውን እየገለጹ ነው።
48605324
https://www.bbc.com/amharic/48605324
አሜሪካዊቷ እናት አምስት ልጆቿን የገደለው ሰው የሞት ፍርድ አይገባውም ትላለች
አሜሪካዊቷ እናት አምስት ልጆቿን ያለርህራሄ የገደለው ግለሰብ የሞት ፍርድ አይገባውም ስትል ምስክርነቷን ሰጥታለች።
አምበር ኪዘር የአምስት ልጆች እናት ነበረች፤ ነገር ግን ጨካኝነቱ ጥግ ባጣ አባታቸው ተገድለዋል። እናታቸውን ግን ግለሰቡ ሞት አይገባውም ባይ ነች። ለምስክርነት የተጠራችው እናት «አባታቸው ለልጆቼ ቅንጣት ታክል ርህራሄ ባያሳይም፤ ልጆቼ ግን ከልባቸው ይወዱት ነበር» ስትል ሳግ እየተናነቃት ተናግራለች። • ደቡብ ኮሪያዊው ፓስተር በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ታሰሩ ግለሰቡ ዕድሜያቸው ከአንድ እስከ ስምንት የሆኑትን ሕፃናት የገደለው 2014 ወርሃ ነሃሴ ላይ ነበር። ግለሰቡን ወንጀለኛ ሆኖ ያገኘው ፍርድ ቤት የሞት ፍርድ ወይስ እሥር የሚለው ላይ እየመከረ ነው። ጥንዶቹ ለዘጠኝ ዓመታት ያክል በትዳር ከቆዩ በኋላ ነበር የተፋቱት፤ ምክንያቱ ደግሞ ሰውዬው ወ/ሮ አምበርን መበደል በመጀመሩ ነው። ግለሰቡ ከወ/ሮ አምበር የተሻለ ገቢ ስለነበረው የአሳዳጊነት ድርሻውን ወስዶ አምስቱን ልጆች ያሳድጋቸው ያዘ። እናት ደግሞ ዘወትር እሁድ እንድትጎበኛቸው ሆነ። • የቀድሞው ፕሬዝደንት ልጅ በጉልበት ብዝበዛ ወንጀል ተፈረደባቸው «ልጆቼ በምንም ዓይነት ስቃይ እንዳለፉ ሰምቻለሁ። እንደ አንድ እናት የፊቱን ቆዳ ብገፈው አልጠላም። ውስጤ የሚመኘው ያንን ነው።» እናት፤ እኔ ድሮም ቢሆን ማንም ሰው የሞት ፍርድ አይገባውም የሚል እምነት አለኝ ስትል ለፍርድ ቤቱ አስረድታለች። የስድስት ዓመት ልጃቸው በኤሌክትሪክ ገመድ ሲጫወት ያገኘው አባት መጀመሪያው የስድስት ዓመቱን ልጅ ለጥቆም የተቀሩትን ሕፃናት አንቆ ገድሏል ሲል ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጥቷል። ግለሰቡ የአእምሮ ጤና በሽተኛ ነኝና ወንጀለኛ ልባል አይገባም ሲል ተከራክሯል። ጠበቃዎቹም 'ስኪትዞፍሬኒያ' የተሰኘው የአእምሮ በሽታ ተጋላጭ በመሆኑ ነፃ ሊሆን ይገባል እያሉ ነው። • ነብሰ ጡር ጓደኛቸውን ያስገደሉት ባለሥልጣን
news-54948971
https://www.bbc.com/amharic/news-54948971
ኮሮናቫይረስ፡ በሮማንያ ሆስፒታል የደረሰው የእሳት አደጋ የኮሮና ህመምተኞችን ቀጠፈ
በሮማንያ በሚገኝ የኮሮናቫይረስ ህክምና ማዕከል በተነሳ የእሳት አደጋ ቢያንስ አስር የኮሮናቫይረስ ህመምተኞችን መግደሉን ባለስልጣናቱ አስታውቀዋል። ከዚህም በተጨማሪ በርካቶችም ክፉኛ ተጎድተዋል ተብሏል።
በሰሜን ምስራቅ ከተማ ፒያትራ ኒያምት ከተማ በሚገኝ የህዝብ ሆስፒታል ውስጥ የኮሮና ፅኑ ህመምተኞች ማቆያ ውስጥም ነው እሳቱ የተነሳው። ህመምተኞቹን ለማዳን የሞከረው ዶክተር ሰውነቱ በእሳት በመቃጠሉ በሞትና በህይወት መካከል ነው ተብሏል። የሮማንያ የጤና ሚኒስትር ኔሉ ታታሩ ለአገር ውስጥ ሚዲያ እንደተናገሩት እሳቱ የተነሳው በኤሌክትሪክ የቴክኒክ ችግር ምክንያት ነው ብለዋል። በሆስፒታሉ ውስጥ ያሉ ሌሎች የኮሮና ህመምተኞች ኢያሲ ወደምትባል ከተማ ተዛውረው ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የጤና ሚኒስትሩ አክለው ገልፀዋል። ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል የተባለው ዶክተር በርካታ የሰውነት ክፍሉ በእሳት የተቃጠለ ሲሆን በወታደራዊ አውሮፕላንም ወደ መዲናዋ ቡካሬስት ለበለጠ ህክምና መወሰዱን የአገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል። "ከዶክተሩ በተጨማሪ ሌሎች የህክምና ባለሙያዎችም በእሳት ቃጠሎው አደጋ ደርሶባቸዋል" ብለዋል የጤና ሚኒስትሩ ኔሉ በትናንትናው ዕለት ህዳር 5/2013 ዓ.ም የተነሳውን እሳት አደጋ ያስከተለውንም ጉዳትና ሌሎች ሁኔታዎች ለመቆጣጠር የጤና ሚኒስትሩ ወደ ፒያትራ እንደሚያመሩ ተናግረዋል። ስምንቱ ህመምተኞች የሞቱት እሳቱ በተነሳበት ሁለተኛ ፎቅ ሲሆን ሁለቱ ደግሞ በሚቀጥለው ክፍል ውስጥ የነበሩ ናቸው። ሁሉም የኮሮናቫይረስ ህመምተኞች ሲሆኑ በርካቶች ደግሞ የኦክስጅን መተንፈሻ (ቬንቲሌተር) የተገጠመላቸው ናቸው። እሳቱ በሆስፒታሉ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ መዛመት እንደቻለ የገለፁት የጤና ሚኒስትሩ ለዚህም ለህመምተኞች የሚገጠመው ኦክስጅን በከፍተኛ ሁኔታ አስተዋፅኦ አድርገዋል ብለዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተነሳበት እለት ጀምሮ በሮማኒያ 350 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን 8 ሺህ 813 ሞቶች ተከስተዋል። ከሰሞኑ አርብ ዕለት አገሪቷ 9 ሺህ 489 አዲስ ህመምተኞችን የመዘገበች ሲሆን፣ 174 ሞቶችና 1 ሺህ 149 ህመምተኞችም በፅኑ ማዕከል ውስጥ በአንድ ቀን ተከስቷል ተብሏል።
news-56884287
https://www.bbc.com/amharic/news-56884287
ጅማ ዞን ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ '20 ሰዎች መገደላቸው' ተነገረ
በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ውስጥ በሚገኙ ሁለት ቀበሌዎች ታጣቂዎች ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ በፈጸሙት ጥቃት በርካታ ሰዎችን መግደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ።
ከምሰል ማኅደር የተገኘ ፎቶ ጥቃቱ አርብ ሚያዝያ 15/2013 ዓ.ም ሊሙ ኮሳ ወረዳ፣ ቀጮ ክርክራ እና ጋሌ በተባሉ ቀበሌዎች ውስጥ የተፈጸመ ሲሆን ቢያንስ 20 ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን ኢሰመኮ ለቢቢሲ ገልጿል። ኮሚሽኑ አክሎም ይህንን ቁጥር በገለልተኛ ወገን አለማጣራቱን ጠቅሶ አካባቢው አስተዳደር መረጃውን ማግኘቱን አመልክቷል። በተመሳሳይ እንዲሁ ሐሙስ ሚያዝያ 14/2013 ዓ.ም በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ፣ ዳኖ ቀበሌ ውስጥ በታጠቁ ኃይሎች በተፈጸመ ጥቃት አንድ ሰው መገደሉን ኮሚሽኑ ጨምሮ አመልክቷል። የኮሚሽኑ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት አቶ ኢማድ ቱኔ እንደተናገሩት በጅማ ዞን ሊሙ ኮሳ ወረዳ ውስጥ የፀጥታ ኃይሎች የደረሱት ታጣቂዎቹ ጥቃት ፈጽመው በስፍራው በርካታ ንፁሃን ሰዎች ከተገደሉ በኋላ ነው። ቢሆንም ግን ከዚያ ክስተት በኋላ በነዋሪዎች ላይ ተጨማሪ ጥቃት እንዳይደርስ ለመከላከል መቻላቸውን ጠቅሰው ባለፉት ቀናት የፀጥታ ኃይሎች በተለይም በጅማ ዞን ተሰማርተው ጥቃቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን አመልክተዋል። ኮሚሽኑ ጥቃቶቹን ተከትሎ ወደ አካባቢዎቹ ባለሞያዎችን ለማሰማራትና የደረሰውን ጉዳት በትክክል ማጣራት አለመቻሉን አቶ ኢማድ ቱኔ ተናግረዋል። ኮሚሽኑ ከአካባቢው ባሰባሰበው መረጃ በጅማ ዞን የተፈጸመው ጥቃት የአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ መሆኑን የሚያመለክት መረጃ እንዳገኘ አቶ ኢማድ ገልጸዋል። ቢቢሲ ጥቃት ከተፈጸመበት አካባቢ ነዋሪዎች፣ ከዞኑ እንዲሁም ከወረዳው አስተዳዳሪዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም። በተመሳሳይ ኮሚሽኑ ጥቃት እንደተፈጸመበት የተገለጸው የአማሮ ልዩ ወረዳ የሰላም እና ደኅንነት ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት ኤሊያስ ይልማ ጉዳትና ዝርፊያ መፈጸሙን አረጋግጠዋል። እንደ ኃላፊው ገለጻ በጥቃቱ ከብት ጥበቃ ላይ የነበረ አንድ ግለሰብ መገደሉን እንዲሁም ከ70 በላይ ከብቶች በታጣቂዎቹ ተነድተው መወሰዳቸውን ለቢቢሲ አስረድተዋል። ይህን ጥቃት የፈፀሙትም ከአጎራባች ቀበሌ የተነሱ ሽፍቶች መሆናቸውን ገልፀዋል። ጨምረውም ባለፉት አራት ዓመታት በአማሮ ልዩ ወረዳ እና በአጎራባች የቡሌ ሆራ ዞን ሲያጋጥም የነበረው ጥቃት ከታጠቁ ኃይሎች ወደ ኅብረተሰቡ አድጓል ሲሉም አብራርተዋል። አቶ ኤልያስ አንደሚሉት የአማሮ ወረዳ 17 ቀበሌዎች በእነዚህ በተደጋጋሚ በሚፈጸሙ ጥቃቶች መጎዳታቸውን አመልክተው፤ "ከሁለት ቀበሌዎች ደግሞ የመንግሥት መዋቅርን ጨምሮ ነዋሪዎች ጥለው መውጣታቸውን" በመጥቀስ በአጠቃላይ በአካባቢው ስላለው የጸጥታ ሁኔታ አብራርተዋል። በአካባቢው ያለው የጸጥታ ችግር አራት ዓመት እንዳስቆጠረ የሚናገሩት ኃላፊው፤ ከዚህ ቀደም የሁለቱም የወረዳ አመራሮች ችግሩን ለመፍታት ተወያይተው እርቀ ሰላም መፈጸማቸውን አስታውሰዋል። ባለፉት አራት ዓመታት በአማሮ ወረዳ ከ150 በላይ ንፁሃን ዜጎች መገደላቸውን እንዲሁም 158 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን አክለው ተናግረዋል። በየካቲት ወር በዚሁ የአማሮ ልዩ ወረዳ ውስጥ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የወረዳው የብልጽግና ጽህፈት ቤት ኃላፊና አንድ የፖሊስ ባልደረባን ጨምሮ ስድስት ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል። ሰዎቹ የተገደሉት ልዩ ወረዳውን ከኦሮሚያ ምዕራብ ጉጂ ዞን በሚዋስነውና ዳኖ በተባለ የገጠር ቀበሌ ውስጥ ነበር። ጥቃቱ የፈጸመው የአማሮ እና የጉጂ ተጎራባች ነዋሪዎች በእርቅ ጉዳይ ላይ ለመምከር ከአገር ሽማግሌዎች እና ከሁለቱ አካባቢዎች የተወጣጡ አመራሮች በተሰበሰቡበት ወቅት ነው። በጅማ ዞን ሊሙ ኮሳ ወረዳ የተፈጸመውን ጥቃት በዝርዝር ለማወቅ እየጣረ ያለው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከፍተኛ አማካሪ ጥቃት ፈጻሚው ኃይል በውል አለመለየቱን ገልጸዋል። ጥቃቶቹ በታጠቁ ኃይሎች የተፈጸሙ መሆናቸውን አመልክተው መንግሥት ተጣያቂው ኦነግ-ሸኔ ነው እንደሚል ነገር ግን ኢሰመኮ ግን በገለልተኛ ወገን የተጣራ መረጃ እንደሌለው አቶ ኢማድ ተናግረዋል። ጥቃቱን የፈጸመው "ማንም ይሁን ማን አንድም ንጽህ ሰው መገደል የለበትም" ብለዋል። ከዚህ በፊት በሊሙ ኮሳ ወረዳ ተመሳሳይ ጥቃት ስለመኖሩ መረጃው እንደሌላቸው የተናገሩት ኃላፊው፤ ነገር ግን በጅማ ዞን ውስጥ በሚገኙ ሌሎች ወረዳዎች ታጣቂ ኃይሎች መንቀሳቀስ መጀመራቸውን እና ጥቃቶች እንደነበሩ ከሦስት ሳምንት በፊት መረጃ እንደነበራቸው ገልጸዋል። የኢትዯጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በቅርብ ጊዜ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተፈጸሙ በተመሳሳይ ጥቃቶች የተከሰቱ ሞቶችን፣ የአካል ጉዳት እንዲሁም የንብረት መውደምን ደጋግሞ ይፋ አድርጓል። ነገር ግን ባለፉት ዓመታት እነዚሀ ጥቃቶች እየተባባሱ ሲሄዱ እንጂ መሻሻል አለመታየቱን አቶ ኢማድ ጠቅሰው፤ "መፍትሄው መንግሥት ችግሮችን ከዚህ ቀደም ለመፍታት ከሞከረበት መንገድ የተለየ መንገድ መሞከር ይኖርበታል" ሲሉ መክረዋል። ባለፉት ዓመታት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ውስጥ የብሔር ማንነትን የለዩ በታጣቂዎች የሚፈፀሙ ጥቃቶች በተደጋጋሚ ሲደርሱ የተስተዋሉ ሲሆን በተለይ በዚህ ዓመት ባለፉት ጥቂት ወራት እየከፉ መምጣታቸውን ሲወጡ የነበሩ ሪፖርቶች ያመለክታሉ። በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ ቤኒሻልጉልና በደቡብ ክልሎች ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ አካባቢዎች ውስጥ ባለፉት ወራት ውስጥ በተፈጸሙ ጥቃቶች በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ተፈናቅለዋል። በቅርቡ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋና የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን ውስጥ በመጋቢትና በሚያዝያ ወራት ውስጥ በተፈጸሙ ጥቃቶች 500 የሚደርሱ ሰዎች ህይወት ማለፉንና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸውን ኤኤፍፒ እና ሮይተርስ የዜና ወኪሎች በተለያዩ ጊዜያት ያወጥዋቸው ሪፖርቶች ያመለክታሉ። በተጨማሪም መጠኑ በትክክል እስካሁን ያልታወቀ በመኖሪያ ቤቶች፣ በንግድ ተቋማት፣ በተሽከርካሪዎችና በሌሎች ንበረቶች ላይ ከባድ የሚባል ውድመት መድረሱን የአካባቢዎቹ ኃላፊዎች ይናገራሉ። እነዚህ ጥቃቶች አገሪቱ ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ ጥቂት ወራት በቀሯት ጊዜ ከሌላው ወቅት በተለየ በተደጋጋሚ እየተከሰቱ ይገኛል።
news-50850160
https://www.bbc.com/amharic/news-50850160
ለማግባት ሲሉ ለመገረዝ የተገደዱ ሱዳናውያን ሴቶች
አንዳንድ ሱዳናዊያን ሴቶች ሰርጋቸው አንድ ወር ገደማ ሲቀረው ይገረዛሉ። ከዛ ቀደም የተገረዙ ቢሆንም እንኳን በድጋሚ ይገረዛሉ። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ሴቶቹ ድንግል እንደሆኑ ማስመሰል ስላለባቸው ነው።
ሱዳን ውስጥ ከአራት እስከ አስር ዓመት ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሴቶች ይገረዛሉ። በተለይም በሙስሊሙ ማኅበረሰብ ዘንድ ሴቶች ሲገረዙ የብልታቸው ከንፈር ይቆረጣል፤ ብልታቸው እንዲጠብ ይሰፋል። ይህ ስፌት የሚለቀው የግብረ ሥጋ ግንኙነት ሲፈጽሙ ነው። 87 በመቶ የሚደርሱ ከ14 እስከ 49 ዓመት የሚሆናቸው ሱዳናዊያን ሴቶች እንደተገረዙ የተባበሩት መንግሥታት ሰነድ ያሳያል። አንዲት ልታገባ ያለች ሴት ከሰርጓ በፊት ልትገረዝ ከሆነ ብልቷ በድጋሚ እንዲሰፋ ይደረጋል። የግርዛት አይነቶች "ለቀናት መራመድ አልቻልኩም ነበር" ማሀ (ለዚህ ታሪክ ሲባል ስሟ ተቀይሯል) የተገረዘችው ከሠርጓ ከሁለት ወር በፊት ነበር። ያገባችው ከእሷ በእድሜ በመጠኑ የሚበልጥ ሰው ነበር። "በጣም ያም ነበር። እናቴ መገረዜን እንድታውቅ ስላልፈለግኩ እስካገግም ድረስ ለቀናት ከጓደኛዬ ጋር መቆየት ነበረብኝ፤ በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ቀናት ለመራመድ ተቸግሬ ነበር፤ መሽናትም ከብዶኝ ነበር።" • ያለእድሜ ጋብቻን በእግር ኳስ የምትታገለው ታዳጊ ማሀ እንደምትለው፤ ባለቤቷ ከጋብቻ በፊት ወሲብ እንደፈጸመች ቢያውቅ በእሷ ላይ እምነት አይጥልም። "ከመጋባታችን በፊት ወሲብ እንደፈጸምኩ ካወቀ በእኔ ላይ እምነት ማሳደር ያቆማል፤ ከቤት እንዳልወጣ ሊያግደኝ፣ ስልኩን እንዳልጠቀም ሊከለክለኝም ይችላል።" የዩኒቨርስቲ ምሩቋና በ20ዎቹ እድሜ ክልል የምትገኘው ማሀ ያደገችው ግርዛት በተከለከለበት ሰሜናዊ ሱዳን ሲሆን፤ የምትሠራውም ግርዛት ሕጋዊ በሆነባት በመዲናዋ ካርቱም ነው። ማሀ ከሠርጓ በፊት በድብቅ በአዋላጅ ለመገረዝ ወደ ትውልድ ቀዬዋ ተመልሳ ነበር። ማሀና አዋላጇ ይተዋወቃሉ። አዋላጇ ማሀን በ5 ሺህ የሱዳን ፓውንድ (3,190 ብር ገደማ) ለመግረዝ ተስማሙ። "የምገርዘው ብር ለማግኘት ነው" በበርካታ ማኅበረሰቦች ባህል ሴቶች እስኪያገቡ ድንግል እንዲሆኑ ይጠበቃል። ሴቶች ሊያገቡ ሲሉ በቀዶ ህክምና ድንግል እንደሆኑ ለማስመሰል የሚገደዱትም ለዚሁ ነው። ሀይመኖፕላስቲ "hymenoplasty" በመባል የሚታወቀው ቀዶ ህክምና ሱዳን ውስጥ አይሰጥም። አንድ ክሊኒክ ደግሞ ለባለትዳር ሴቶች ብቻ ቀዶ ህክምናውን ይሰጣል። • የሴት ልጅ ግርዛት ምንድነው? የት እና ለምን ይፈጸማል? ሱዳናዊያን ሴቶች ብልታቸው ተሰፍቶ እንዲጠብ ከማድረግ ውጪ አማራጭ የላቸውም። አዋላጆቹ የሴቶችን የብልት ከንፈር ይቆርጣሉ፤ ሰፍተውም እንዲጠብ ያደርጋሉ። ግርዛትን ለማስቆም የሚንቀሳቀሱት የማህጸን ሀኪም ዶ/ር ሳዋን ሰኢድ፤ "የሴት ልጅን የመራቢያ አካል መስፋትም ሆነ መብሳት ግርዛት ነው" ይላሉ። የሱዳን የህክምና ባለሙያዎች ማኅበር ግርዛትን ስለከለከለ በካርቱም የሚገኙትን ጨምሮ በሌሎች ሆስፒታሎች ውስጥም ግርዛት አይካሄድም። ሲገርዙ የሚገኙ አዋላጆች ከሥራቸው ይባረራሉ፤ የህክምና መሣሪያቸውም ይወሰዳል። ይህንን ጽሑፍ ያጠናቀረችው ጋዜጠኛ በጎበኘቻቸው ሦስት ሆስፒታሎች ውስጥ ያገኘቻቸው አዋላጆች ግን ሴቶችን ለመግረዝ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸውላታል። ከአዋላጆቹ አንዷ ለጸሐፊዋ እንደነገረቻት፤ አንዳንዴ ሴቶችን የምትገርዘው ገንዘብ ለማግኘት ስትል ነው። "በቅርቡ የ18 ዓመት ልጅ ገርዣለሁ (የኢንፊቢዩሊሽን ግርዛት)፤ ታዳጊዋ በአጎቷ ልጅ ተደፍራ ነበር። እናቷ እያለቀሱ ስለነበር ልርዳቸው ብዬ ገረዝኳት። በ'ሳሊም ኢኒሺየቲቭ' ሴቶችን ላለመግረዝ ቃል ብገባም፤ የልጅ ልጆቼን ለማሳደግ፣ የትምህርት ቤት ወጪያቸውን ለመሸፈን ገንዘብ ስለምፈልግ ገርዣታለሁ።" 'ሳሊም ኢኒሺየቲቭ'፤ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ2008 ግርዛትን ለመግታት በተባበሩት መንግሥታት የተጀመረ ፕሮጀከት ነው። • የሴት ልጅ ግርዛት በከፍተኛ ደረጃ ቀነሰ ሱዳን ውስጥ በተለይም በወግ አጥባቂዎች ዘንድ ያለውን አመለካከት ለመቀየር ጊዜ ይወስዳል። አንድ ካርቱም ውስጥ የሚኖር ግለሰብ "ለወደፊት የማገባት ሴት ድንግል እንድትሆን እፈልጋለሁ፤ ካልሆነች ግን ከእኔ ውጪ ከሌላ ሰው ጋር ወሲብ ትፈጽማለች ብዬ እጠረጥራታለሁ" ይላል። ሱዳን ውስጥ ብዙ ወንዶች ከዚህ ግለሰቡ ጋር ተመሳሳይ አመለካከት አላቸው። በርካታ ወንዶች ሴቶች "እንዲሰፉ" ይሻሉ። ግርዛትን ለማስቆም ንቅናቄ እያደረጉ ያሉ የመብት ተሟጋቾች ለውጥ እንደሚመጣ ተስፋ ያደርጋሉ። ሴቶች ሱሪ እንዳይለብሱ ከመከልከል ባሻገር፤ በአደባባይ እንዴት መልበስና መንቀሳቀስ እንዳለባቸው፣ ከማን ጋር መነጋገር እንደሚችሉ እና ምን ሥራ መያዝ እንደሚፈቀድላቸው የሚደነግገው ሕግ ባለፈው ወር መሻሩ ደግሞ ተስፋቸውን የበለጠ አለምልሞታል። ሕጉ 30 ዓመት በዘለቀው የኦማር አል-በሽር የአገዛዝ ዘመን የወጣ ነበር። ጥፋተኛ የተባሉ ሴቶች በግርፋት እና በድንጋይ ተወግረው ይቀጣሉ። ሊገደሉም ይችላሉ። 'አን ላን' የተባለው ግርዛትን ለማስቆም የሚሠራ ተቋም መስራች ናሂድ ቶዩባ እንደምትለው፤ ካለፉት ዘመናት በተሻለ አሁን ላይ ያሉ ሴቶች ግንዛቤ ጨምሯል። "አሁን መንታ መንገድ ላይ ናቸው። በአንድ በኩል ግብረ ሥጋ ግንኙነት የማድረግ መብት እንደላቸው ያምናሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ብልታቸው ዳግመኛ እንዲሰፋ በማድረግና ሂጃብ በመልበስ ውሳኔያቸውን ይቀለብሳሉ።" [ይህ ጽሑፍ በአፍሪካ ጋዜጠኞች የተጻፉ ደብዳቤዎች በሚስተናገዱበት "letters from African journalists" ለተባለው አምድ ከጋዜጠኛ ዘይነብ መሐመድ ሳላህ የተላከ ነው።]
news-52240991
https://www.bbc.com/amharic/news-52240991
ኮሮናቫይረስ፡ ሰዎች ለምን ስለኮሮናቫይረስ የሚነገሩ ሐሰተኛ ወሬዎችን ያምናሉ?
ከተማሪዎች እስከ ፖለቲከኞች ያሉ ብዙ ብልህ ሰዎች ስለኮሮናቫይረስ በተሰራጩ አደገኛ ውሸቶች ተታለዋል። ለምን? እንዴት እራስዎን ከተሳሳተ መረጃ መጠበቅ ይችላሉ?
ማንኛውም የጤና ቀውስ የራሱ የሆነ የተሳሳተ የመረጃን መቅሰሱ የሚያሳዝን እውነት ነው። በተለያዩ ወቅቶች ስለኤድስ የሐሰት ወሬዎች ተሰራጭተው አይተናል። የኤችአይቪ ቫይረስ በመንግሥት በቤተ ሙከራ ውስጥ እንደተፈጠረ፤ የኤችአይቪ ምርመራዎች እምነት የማይጣልባቸው ናቸው የሚሉ ወረሬዎችን ሰምተናል። አልፎ ተርፎም ሊታመን በማይችል መልኩ በሽታው በፍየል ወተት ሊታከም እንደሚችል በስፋት ሲነገር ነበር። ነገር ግን እነዚህ ሐሰተኛ መረጃዎች የሰዎችን ተጋላጭነት ከማስፋት ባሻገር ቀውሱን ያባብሳሉ። • ለቭላድሚር ፑቲን ገንዘብ ያበደረው ቢሊየነር ታሪክ • "መደብር ሄጄ የውጪ አገር ሰው አንቀበልም አሉኝ" ኢትዮጵያዊቷ በቻይና አሁን ደግሞ ተራው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ነው። ከፌስቡክ እስከ ዋትስአፕ ድረስ ከወረርሽኙ አመጣጥ ጀምሮ እስከ መከላከያው ድረስ ብዙ የተጋሩ የተሳሳቱ መረጃዎችን እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል። ከፀሐይ ብርሃን አስከ ሞቃት የአየር ሁኔታ እንዲሁም ትኩስ ውሃ መጠጣት የኮሮናቫይረስ መስፋፋት ላይ እንዴት ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩበት የተነገሩ በርካታ ሐሰተኛ መረጃዎችን ቢቢሲ አጋልጧል። ከዚህ አንጻር በጣም መጥፎው ነገር የሚሰራጩት የሐሰት ወሬዎች ራሳቸው ጎጂ መሆናቸው ነው። ከወደ ኢራን የተገኘ አንድ ሪፖርት እንዳመለከተው ከኮቪድ-19 ያድናል በሚል ብዙዎች ጠንካራ አልኮል በመጠጣታቸው ምክንያት ሞተዋል። የፈጠራ የሚመስሉ ሃሳቦች እንኳን ወደ ተሳሳተ የደኅንነት ስሜት ውስጥ ከማስገባት ባለፈ ሰዎች የመንግሥት መመሪያዎችን እንዳይከተሉ እና በጤና ባለስልጣኖችና በድርጅቶች ላይ ያለን አመኔታ ያሳጣሉ። ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ ይቻላል። ዩጎቭ እና ዘ ኢኮኖሚስት ባለፈው ወር ባደረጉት አንድ ጥናት እንዳመለከቱት 13 በመቶ የሚሆኑ አሜሪካዊያን የኮቪድ-19 ቀውስ ውሸት ነው ብለው ያምናሉ። 49 በመቶዎቹ ደግሞ ሰው ሰራሽ ሊሆን ይችላል ብለዋል። እናም የማገናዘብ ብቃት ወይም ትምህርት እውነቱን ለመለየት ሊረዳን ይችላል የሚል ተስፋ ቢኖርም በእነዚህ የሐሰት መረጃዎች የተታለሉ ብዙ የተማሩ ሰዎችን ማግኘት ቀላል ነው። ታዋቂዋ የኮቪድ-19 ሴራ ተንታኟ ጸሐፊ ኬሊ ብሮጋንን ብቻ አስቡ። ከማሳቹሴትስ የቴክኖሎጂ ተቋም ዲግሪ ያላት ሲሆን በኮርኔል ዩኒቨርስቲ ደግሞ ሥነልቦናን አጥንታለች። ሆኖም እንደ ቻይና እና ጣሊያን ባሉ ሀገሮች ውስጥ ቫይረሱ ያደረሰውን አደጋ አትቀበለውም። • በአንድ ቀን ከ5 ሺህ በላይ ሞት ያስመዘገበችው አገር • ፌስቡክ ከኮሮናቫይረስ ጋር የተያያዙ ሐሰተኛ መረጃዎችን ሊጠቁም ነው ይህንን ክስተት በዝርዝር ለመረዳት የሥነ ልቦና ባለሙያዎች ጥናት እያደረጉ ነው። በመጨረሻም የሚደርሱበት ግኝት ምናልባት ራሳችንን ከውሸት የምንጠብቅበት አዲስ መንገድ ሊጠቁሙና የተሳሳተ መረጃን መስፋፋት ለማስቆም ሊረዳ ይችላል። መጠነ ብዙ የመረጃ የተወሰነው የችግሩ ክፍል መነሾ በመልዕክቶቹ ተፈጥሮ ላይ ነው። በየቀኑ ብዙ መረጃ ይደርሰናል። ስለሆነም ብዙውን ጊዜ አንድ ነገር ትክክል መሆኑን ለመወሰን በፍላጎታችን እንመራለን። ከዚህ በፊት ቢቢሲ እንደገለፀው የሐሰት ዜና አዘጋጆች በቀላሉ ሠርተን እውነታውን እንዳናውቅ መልእክቶቻቸው "እውነት" እንዲመስሉ ያደርጋሉ። ለምሳሌ ምስልን ከመግለጫ ጋር ማቅረብ በእውነታው ላይ ያለንን እምነት ይጨምረዋል። የአውስትራሊያ ብሔራዊ ዩኒቨርስቲ ባልደረባ ኢሪ ኒውማን ያስረዳሉ። ከቫይረሱ ምስል ጋር የቀረበ ጽሑፍ ማረጋገጫ ባይኖረውም ጥቅል ጉዳይን እንድናስብ ያደርገናል፤ እንደእውነታም እንወስደዋለን። በዚህ ምክንያት የተሳሳተ መረጃ ገላጭ ቋንቋን ወይም ግልጽ የግል ታሪኮችን ያጠቃልላል። እንዲሁም እንደ ታዋቂ ህክምና ተቋም ያሉ የምናውቃቸውን እውነታዎችና ቁጥሮችን በመጨመር ከእውቀታችን ጋር በማዛመድ አሳማኝ ይመስላሉ። ድግግሞሽ እንኳን መላመድን ፈጥሮ "እውነታነትን" ሊፈጥር ይችላል። መጀመሪያ ብንጠራጠርም ተደጋግሞ የመጣን ነገርን እውነት ነው ብለን እናስባለን። ከማሰብ በፊት መጋራት የቅርብ ጊዜ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ብዙ ሰዎች አንድን ይዘት ስለትክክለኛነቱ እንኳን ሳይያስቡ እንደሚጋሩ ነው። ካናዳ በሚገኘው ሬጂና ዩኒቨርሲቲ ሐሰተኛ መረጃን የሚያጠኑት የሥነ ልቦና ተመራማሪው ጎርደን ፔኒኩክ ለጥናታቸው ተሳታፊዎች ስለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የእውነተኛ እና የሐሰተኛ አርዕስቶች ድብልቅ እንዲመለከቱ ጠየቁ። ስለእያንዳንዱ አርዕስት እውነተኛነት ሲጠየቁ 25 በመቶ ያህል ጊዜ ሐሰተኛ ዜናዎቹ እውነተኛ ናቸው ብለዋል። ስለማጋራት ሲጠየቁ 35 በመቶዎቹ ሐሰተኛ ዜናውን እንደሚያጋሩ ተናግረዋል። ምናልባትም አንጎላቸው ትክክለኛነቱን ከማጤን ይልቅ ምን ያህል 'ላይክ' እና 'ሪትዊት' እንደሚያገኝ በማሰብ ላይ አተኩሯል። "ማኅበራዊ ሚዲያ እውነትን አያበረታታም። እውነታው ያለው ሼር እና ላይክ ላይ ነው" ይላሉ ፔኒኩክ። • ከሚስታቸውና ከልጃቸው ጋር ከኮሮናቫይረስ ያገገሙት የአዳማ ነዋሪ ወደ ቤታቸው ተመለሱ • "ያስጨነቀኝ ከእኔ ጋር ንክኪ የነበራቸው ሰዎች ጤንነት ነበር" የኮሮናቫይረስ ታማሚዋ ከባህር ዳር ምናልባትም ኃላፊነትን ወደ ሌሎች እነዳሳለፉ ተሰምቷቸው ይሆናል። ብዙ ሰዎች ከላይ "ይህ እውነት ስለመሆኑ አላውቅም፤ ግን…" የሚል ነገር በመጻፍ መረጃ እያጋሩ ነው። መረጃው እውነትነት ካለው ለጓደኞችና ተከታዮች ሊጠቅም ይችላል፤ እውነት ካልሆነ ግን አይጎዳም በሚል ነው። ስለዚህ ማበረታቻው ማጋራት ነው። ግን ማጋራትም ጉዳት ያስከትላል ብሎ አለማገናዘብ ነው። የደመ ነፍስ ምላሽን መቆጠጠር ሥነ-ልቦናዊ ምርምር እንደሚያሳየው አንዳንድ ሰዎች ተፈጥሮአዊ የሆኑ የደመ ነፍስ ምላሾቻቸውን በመቆጣጠር በኩል ከሌሎች ይልቅ የተሻሉ ናቸው። ይህ ግኝት አንዳንድ ሰዎች ከሌሎች ይልቅ ለሐሰት ዜናዎች የበለጠ የሚጋለጡበትን ምክንያት እንድንገነዘብ ይረዳናል። ብልህ እና የተማሩትም ጨምሮ ብዙዎች በሐሰተኛ መረጃ ላይ የተመሠረተ የተሳሳተ አመለካከት እንዳላቸው ማወቃችን የተሳሳተ መረጃ መስፋፋትን ለማስቆም ይረዳናል። ሐሰተኛ መረጃዎችን ለመከላከልም ድርጅቶች የተወሳሰበ አገላለጽን ከመጠቀም መቆጠብ ያስልጋቸዋል። ይልቁን እውነታውን በቀላል ዘዴ ማቅረብ አለባቸው። ሀሳቦችን በቀላሉ ለመሳል ምስሎችን እና ግራፎችን በመሳሰሉ ዘዴዎች በመጠቀም ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከቻሉ ሃሰተኛ መረጃዎችን ከመድገም መቆጠብ አለባቸው። መደጋገም ሀሳቡን የበለጠ የታወቀ አድርጎ እንደእውነት የመቀበል ዕድሉን ይጨምረዋል። ነገር ግን ይህ ሁልጊዜ ሊሆን አይችልም። ዘመቻዎች ግን ከሐሰተኛ መረጃዎቹ ይልቅ እውነታዎች የበለጠ ጎልተው እንዲታዩ እና የማይረሱ በማድረግ በሰዎች አዕምሮ ውስጥ ተቀርጸው የመቆየት ዕድላቸውን ማሳደግ ይችላሉ። እኛም በይዘቱ ካለው ስሜት ለመራቅ ልንሞክር እና ከማጋራታችን በፊት ስለ እውነታው ትንሽ ለማሰብ እንሞክራለን።ስለዚህም ስለምናጋራቸው መረጃዎች የሚከተሉትን ጥያቄ መመለስ ያስፈልገናል። በሰማ በለው ነው ወይስ በጠንካራ ሳይንሳዊ ማስረጃ ላይ የተመሠረተ ነው? ወደ መጀመሪያው ምንጭ ብንመለስ መረጃውን ማግኘት እንችላለን? አሁን ካለው መረጃ ጋር እንዴትስ ይነፃፀራል? ለሌሎች ይጠቅማል ወይም 'ላይክ' ያመጣል ከማለት በፊት ልንጠይቃቸው የሚገቡ ጥያቄዎች ናቸው። እናም ሁላችንም ይህንን ዓይነት አስተሳሰብ በተግባር በመለማመድ የተሻልን መሆን እንደምንችል ማስረጃዎች ያሳያሉ።
news-47891186
https://www.bbc.com/amharic/news-47891186
ትውስታ- የዛሬ 20 ዓመት ኢትዮጵያ ሞባይል ስልክን ስትተዋወቅ
ኢትዮ ቴሌኮም የተንቀሳቃሽ ስልክ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ሃያ ዓመታት ተቆጥረዋል። በወቅቱ አገልግሎቱን ማግኘት የሚችሉት የመንግሥት ባለሥልጣናትና በንግዱ ዘርፍ የተሰማሩ ጥቂት ባለሃብቶች ነበሩ።
በአሁኑ ሰዓት ኢትዮ-ቴሌኮም የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚዎች 39.5 ሚሊየን የደረሱ ሲሆን የመጀመሪያዎቹ ደንበኞች አገልግሎቱን ለማግኘት የቤት ካርታ፣ ምሥክሮችና የማስያዣ ገንዘብ ማቅረብ ነበረባቸው። • ማህበራዊ ሚዲያዎችን መጠቀም የሌለብዎት ሰአት መቼ ነው? • ኢትዮ ቴሌኮም የታሪፍ ቅናሽ አደረገ ዛሬ ላይ ግን ከተማሪ እስከ ሠራተኛው፤ ከደሃ እስከ ሃብታሙ ሁሉም የተንቀሳቃሽ ስልኮች ተጠቃሚ ሆኗል። ነገር ግን የዛሬ 20 ዓመት አካባቢ የመጀመሪያዎቹን ሲም ካርዶች የወሰዱ ደንበኞች አሁን አሁን እንደዚህ ሁሉም ነገር በቀላሉ መገኘቱ እንደሚያስገርማቸው ይናገራሉ። አቶ ፀጋዬ አስፋው የዛሬ 20 ዓመት አካባቢ ኢትዮ-ቴሌኮም ደንበኞች ተመዝግበው ሲም ካርድና ተንቀሳቃሽ ስልክ እንዲወስዱ ማስታወቂያ ሲያስነግር ያስታውሳሉ። በወቅቱ ለእርሳቸው ቅርብ የነበረው ቦሌ ለንደን ካፌ አካባቢ የሚገኘው ቅርንጫፍ ሄደው እንደተመዘገቡም ነግረውናል። ''በመጀመሪያ ለመመዝገብ በጣም ብዙ ወረፋ ነበር። ከዚህ በተጨማሪም ማንነትን የሚገልፅ መታወቂያ፣ የቤት ካርታና ምሥክሮችን ይዞ መገኘት ግዴታ ነበር። ዛሬ ላይ ሆኜ ሳስታውሰው በጣም የሚያስቅ ሁኔታ ነበር ግን ሌላ ምንም አማራጭ ስላልነበረ አድርጌዋለሁ'' ይላሉ። እንደ አጋጣሚ ሆኖ በመሥሪያ ቤታቸው በኩል የተመዘገቡት አቶ ፀጋዬ እንደ ሌላው ሰው በጣም ብዙ ወረፋ አልጠበቁም ነበር። ''ምናልባትም ከአንድ ሰዓት በላይ አልቆየሁም "ይላሉ። በወቅቱ አገልግሎት ሰጪው ኢትዮ-ቴሌኮም ከሚያቀርበው ተንቀሳቃሽ ስልክ ውጪ መጠቀም አይቻልም ነበር። አንድ ግለሰብ የእራሱን ስልክ ይዞ መንቀሳቀስ የማይፈቀድ ሲሆን ቴሌ ከሲም ካርድ ጋር አብሮ የሚሰጠውን ተንቀሳቃሽ ስልክ መጠቀም ግዴታ ነበር። ''በሚያስገርም ሁኔታ ሁላችንም ተጠቃሚዎች በመላው ሃገሪቱ ተመሳሳይ ተንቀሳቃሽ ስልክ ነበር የምንጠቀመው'' ይላሉ። ሌላኛዋ ተጠቃሚ ምስራቅ አሰግድ ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ ተንቀሳቃሽ ስልክ የያዘችው የመጀመሪያዎቹ ማለትም 091120... ብለው የሚጀምሩት ስልኮች አልቀው ሁለተኛው ዙር 091121... ላይ እንደሆነ ትናገራለች። ''የማልረሳው ነገር ቢኖር የመጀመሪያውን ዙር ተመዝግበው ስልክ ያወጡ ሰዎች በጣም ሃብታምና የኑሮ ደረጃቸው ከፍ ያሉ ሰዎች እንደሆኑ ይታሰብ ነበር'' በማለት ታስታውሳለች። በወቅቱ ተንቀሳቃሽ ስልኩ ምን ያደርጋል፤ አላስፈላጊና ትርፍ ነገር ነው ብለው ከሚከራረኩት መካከል እንደነበረች የምትናገረው ምስራቅ "አሁን ላይ ሆኜ ስመለከተው ግን ከእስትንፋስ ባልተናነሰ መልኩ ከኑሯችን ጋር መቆራኘቱ ያስገርመኛል" ትላለች። ከኢትዮ-ቴሌኮም ሲም ካርድ አብሮ የተሰጣት ስልክ 'ኖኪያ' ሲሆን በጣም ትልቅ እንደነበርና "እንደውም ካውያ ነበር የሚያክለው። ሌላ ስልክ መግዛትና መጠቀም አይቻልም ነበር'' በማለት ስለነበረው ሁኔታ ታስረዳለች። • አዲስ የሞባይል ቀፎ በኢትዮ ቴሌኮም ኔትዎርክ ላይ ለማሰመዝገብ ማወቅ ያለብዎት በኢትዮ-ቴሌኮም ይሰጡ የነበሩት ስልኮች ልክ የቤት ስልክ እጀታን የሚያክሉና ይዞ ለመንቀሳቀስ እጅግ አስቸጋሪ እንደነበሩ አቶ ፀጋዬም ያስታውሳሉ። ''ኪስ ውስጥ ይዞ መንቀሳቀስ ከባድ ስለነበረ ምናልባት መኪና ያላቸው ሰዎች መኪናቸው ውስጥ ያስቀምጡት ነበር። ተንቀሳቃሽ ስልክ ብሎ ለመጥራት ይከብድ ነበር፤ ምክንያቱም ይዞ መንቀሳቀስ የማይታሰብ ነው'' ይላሉ። የወቅቱ አገልግሎት የዛሬ 20 ዓመት የነበሩ ደንበኞች ስልኩን ይጠቀሙት የነበረው ለድምፅ መልዕክት ብቻ ሲሆን በወቅቱ የጽሑፍ መልዕክት አገልግሎት የተጀመረው ትንሽ ቆይቶ ነው ። ''መንገድ ላይም ተንቀሳቃሽ ስልኩን ይዤ ከሰዎች ጋር እያወራሁ ስራመድ በአካባቢዬ ያሉ ሰዎች ትኩር ብሎ የመመልከትና ከማን ጋር ነው የምታወራው እያሉ ይጠቋቆሙ ነበር'' የምትለው ምስራቅ ስልክ ከመደውል ውጪ ሌላ አገልግሎት የማይታሰብ እንደነበር ትናገራለች።። ''ሌላው ቀርቶ የድምፅ አገልግሎቱን እራሱ ብዙ አልጠቀምም ነበር። ያኔ ትንሽ ፍርሃት ነበር፤ እንደ አሁኑ እንደልብ እዚም እዚያም መደወል ያስቸግር ነበር። ወጪውም አይቻልም'' ትላለች። ''አሁን ግን ሁሉም ሰው ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዞ ከመጠቀሙ በተጨማሪ እንደልቡ ሲደውልና ሌሎች ነገሮች ሲጠቀም ስመለከት ይሄ ነገር በነፃ ነው እንዴ እላለው'' ትላለች ምስራቅ። አቶ ፀጋዬም በምስራቅ ሃሳብ ይስማማሉ። "በአካባቢዬ የነበሩ ሰዎች በቃ ወይ ጉድ፤ እንዲህም ይቻላል? እያሉ በጣም ይገረሙ ነበር። በወቅቱም የመሻሻልና የሥልጣኔ ምልክት ተደርጎም ይወሰድ ነበር'' ሲሉ በሰዓቱ የነበረውን ሁኔታ ያስታውሳል። • አዲስ አበባ፡ የፈጠራ ማዕከል ለመሆን እየጣረች ያለች ከተማ • ተፈላጊነታቸው እየቀነሰ የሚመጡ የሙያ ዘርፎች የትኞቹ ናቸው? በጊዜው ስልክ ይዞ እየተነጋገሩ መንቀሳቀስ የተለመደ አልነበረም። አቶ ፀጋዬ በግላቸው ያጋጠማቸው ነገር ባይኖርም ሰዎች ሲያወሩ ከሰሙት ግን ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው መንገድ ላይ እያወሩ ይሄዱ የነበሩ ሰዎች እንደ ብርቅ ይታዩ እንደነበርና እንደውም አንዳንዶቹ አብደዋል መባላቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ''አሁን ያለው የስልክ አግልግሎትና የድሮውን ሳወዳድረው ልክ የቀንና የጨለማ ዓይነት ስሜት ነው የሚሰማኝ። አሁን ላይ ሆኜ ሳስበው እንዴት አድርጌ ሥራ እሠራና እንቀሳቀስ እንደነበረ አይገባኝም። አሁን ያለው አገልግሎት በጣም ፈጣንና የማያስቸግር ነው፤ የዝያኔ ግን እንዴት እንጠቀመው እንደነበር አይገባኝም'' ይላሉ።
news-55672699
https://www.bbc.com/amharic/news-55672699
የአሜሪካ 50 ግዛቶች ነውጥ ይነሳል በሚል በተጠንቀቅ ላይ መሆናቸውን አሳወቁ
በመጪው ረቡዕ በዓለ ሲመታቸው የሚፈፀመው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንን ሹመትን ለማስተጓጎል በትጥቅ የታገዘ አመፅ ይኖራል በሚል አምሳዎቹ ግዛቶች በተጠንቀቅ ላይ ናቸው ተባለ።
በተለይም ከበዓሉ በፊት ባለፈው ሳምንት ካፒቶል ሂል እንደነበረው ሁከት ይፈጠራል በሚልም የአገሪቱ ብሔራዊ ዘብም ዋሽንግተን ዲሲ ላይ ሰፍሯል። ከቀናት በፊት በ50ዎቹ ግዛቶች በሙሉ የተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ደጋፊዎች በጦር መሳሪያ የታገዘ ሁከትና አመፅ ሊያስነሱ ይችላሉ የሚል ማስጠንቀቂያ የፌደራሉ የምርመራ ቢሮ ኤፍቢአይ አስተላልፎ ነበር። መጪው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንም ሹመታቸውን ከሚረከቡበት ቀንም ቀድመው ሊከሰቱ እንደሚችሉ ቢሮው መረጃ ደርሶኛል ብሏል። በጦር መሳሪያ የታገዙ ሁከቶች ዋሽንግተን ዲሲን ጨምሮ በአምሳ የተለያዩ ግዛቶች መታቀዳቸውን ሪፖርቶች ቢሮው አግኝቷል። ከረቡዕ በፊትም በርካታ የዋሽንግተን ዲሲ አካባቢዎች ይዘጋሉ፤እንቅስቃሴም አይኖርም። በሺዎች የሚቆጠሩ የብሔራዊ ዘብ በጥብቅ የሚቆጣጠሩ ይሆናል። ባለፈው ሳምንት ነውጥ የተነሳበት ካፒቶልን የሚያዋስኑ እንዲሁም በአቅራቢያው ያሉ ጎዳናዎች በሙሉ በብረት ታጥረዋል። ከዚህ ቀደም በርካቶች የፕሬዚዳንቶችን ሹመት የሚከታተሉበት ናሽናል ሞል የተባለው እንዲዘጋ የፕሬዚዳንቱን ደህንነት በበላይነት የሚቆጣጠረው ብሄራዊ ደህንነት ቢሮ ትእዛዝ አስተላልፏል። የባይደን ቡድን ኮቪድ-19 ወረርሽኝ መዛመት እንዳይኖር በሚል አሜሪካውያን ለበዓለ ሲመቱ ሲሉ ወደ መዲናዋ እንዳይመጡ ጠይቋል። የተለያዩ ግዛቶች ባለስልጣናትም ቢሆኑ ዝግጅቶቹን በርቀት ሊከታተሉ እንደሚገባም በተጨማሪም ተነግሯል። በዛሬው ዕለትም የትራምፕ ደጋፊዎችና ፅንፈኞች በትጥቅ የታገዘ የአመፅ ጥሪ እንደሚኖር ማሳወቃቸውን ተከትሎም ከፍተኛ ጥበቃ ይኖራል ተብሏል። አንዳንድ የፅንፈኞች ቡድን ደጋፊዎቻቸውን የዛሬውን የአመፅ ጥሪ ከፍተኛ የደህንነትና ጥበቃ ስለሚኖር ከዚህም በተጨማሪ ፖሊስ እንደ ወጥመድ ያዘጋጀው ነው በማለትም እንዳይሳተፉ ጠይቀዋል። በትናንትናው ዕለትም መሳሪያ የታጠቀ አንድ ግለሰብ መሳሪያና 509 ተቀጣጣይ ነገሮች ይዞ በፍተሻ እንደተያዘ የካፒቶል ፖሊስ አረጋግጧል። ነገር ግን ይህ ዌስሊ አለን ቢለር የተባለው ግለሰብ ወዲያው እንደተፈታም ለማወቅ ተችሏል። ግለሰቡ በግል የደህንነት ኩባንያ ተቀጥሮ እንደሚሰራና ወደ ዋሽንግተንም ሲመጣ የጦር መሳሪያ ይዞ ለመምጣት አስቦ እንዳልነበር ለዋሽንግተን ፖስት ተናግሯል። ባይደን በዓለ ሲመታቸው ከተጠናቀቀ እንዲሁም በይፋም ስልጣናቸውን ካወጁ በኋላ በቀድሞው አስተዳደር የተሰሩ አንዳንድ ውሳኔዎችን እንደሚቀለብሱ የአሜሪካ ሚዲያዎች የደረሳቸው መረጃ ጠቁሟል። ዋይት ሃውስ በገቡ በሰዓታት ውስጥ ይወስዷቸዋል ከተባሉ እርምጃዎች መካከል፦ ልክ እንደ ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ባይደንም ቢሆኑ በርካታ ጉዳዮች ምክር ቤቱን በማለፍ በበላይ ውሳኔ ማስፈፀም ይችላሉ። ነገር ግን ባለፈው ሳምንት ያወጁት የ1.9 ትሪሊዮን ዶላር የምጣኔ ኃብት ማዕቀፍ፣ እንዲሁም በስደተኞች ጉዳይ ያቀረቡት ረቂቅ በምክር ቤቱ መፅደቅ ይኖርበታል። የአሜሪካ ህግ መምሪያ ምክር ቤት እንደራሴዎች ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ሳምንት የተከሰተውን የካፒቶሉን ነውጥ አነሳስተዋል በሚል እንዲከሰሱ ውሳኔ ማስተላፋቸው የሚታወስ ነው። ከስልጣን ሊለቁ ቀናት የቀራቸው ፕሬዚዳንት ትራምፕ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲገፈፍና በአመፅና ሁከት እንዲከሰሱም ለማስቻል እንደራሴዎቹ በአብላጫ ድምፅ ነው የወሰኑት። በዚህም መሰረት በስልጣን ላይ እያሉ ሁለት ጊዜ እንዲከሰሱ የተወሰነባቸው ወይም ኮንግረሱ በወንጀሎች የጠየቃቸው የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት አድርጓቸዋል።
news-55040027
https://www.bbc.com/amharic/news-55040027
ትግራይ፡ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በ167 ሰዎች ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣቱን አስታወቀ
በትግራይ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር በተያያዘ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በ167 ሰዎች ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣቱን ይፋ አደረገ።
ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) ይህ የተባለው የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ትናንት በጋራ በሰጡት መግለጫ ነው። ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ በመግለጫው ላይ በህውሓት ኃይሎች የተፈጸሙት ተግባራት በአገሪቱ የወንጀል ሕግ አንጻር በከፍተኛ ወንጀል የሚያስጠይቁ ናቸው ብለዋል። በአገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የተፈጸመው ጥቃት 'የመንግሥትን አገሪቱን የመከላከል ኃይል ለማዳከም' በተፈጸመ ወንጀል በሚል የሚያስጠይቅ መሆኑን ጠቁመዋል። በባሕር ዳር እና ጎንደር ከተሞች ላይ የተፈጸሙትን የሮኬት ጥቃቶች በተመለከተም፤ ድርጊቱ በሽብር ወንጀል እንደሚያስጠይቅ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን መናድ፣ ታጥቆ አመጽ መቀስቀስ እና በአገር ክህደት ወንጀሎች የሚያስጠይቁ ወንጀሎች መፈጸማቸውን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ተናግረዋል። ይህንንም ተከትሎ በበርካታ ተጠርጣሪዎች ላይ የእስር ማዘዣ መውጣቱን አስታውሰዋል። እስካሁን ድረስ በፌደራል ፖሊስ እና በፌደራል ዐቃቤ ሕግ የተለዩ 167 ተጠርጣሪዎች ላይ የእስር ማዘዣ መውጣቱን ተናግረዋል። ከእነዚህም መካከል በቁጥጥር ሥር የዋሉ ተጠርጣሪዎች መኖራቸውን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ጨምረው አመልክተዋል። ከዚህ በተጨማሪም ከአገር ውጪ ያሉ ተጠርጣሪዎች ከሚገኙበት አገር ተላልፈው እንዲሰጡ መንግሥት መጠየቁን ጠቅሰው፤ ይህ አይነት አሰራር በባህሪው ረዥም ጊዜ የሚወስድ ነው ሲሉም ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ገልጸዋል። ከግለሰቦቹ በተጨማሪም ከህውሓት ጋር ግነኙነት አላቸው የተባሉ 38 ኩባንያዎች ንብረት እንዳይቀሳቀስ እግድ እንደተጣለባቸው አስታውሰዋል። እነዚህ ኩባንያዎች በርካታ ሰዎችን ቀጥረው ያሚያስተዳድሩት መሆናቸው ከግንዛቤ በማስገባት የኩባንያዎቹን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ለማስቀጠል የፌደራል ፍርድ ቤት እነዚህን ኩባንያዎች የሚያስተዳደር ባለአደራ አስተዳደር ይሰይማል ብለዋል። የተጣለው እግድ ኩባንያዎቹ ንብረት እና ገንዘብ እንዳይስተላልፉ ወይም ለህወሓት ድጋፍ እንዳደርጉ የሚያደርግ መሆኑንም አመልክተዋል። በአዲስ አበባ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ተጠርጣሪዎች ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ህወሓት በአዲስ አበባ እና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች የሽብር ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል ከነዋሪዎች ጥቆማ ደርሶናል ያሉ ሲሆን፤ ይህንን ተከትሎ በተደረጉ ምርመራዎች በአዲስ አበባ 343 ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን እና ከእነዚህም መካከል 160 የሚሆኑት በዋስ መለቀቃቸውን ተናግረዋል። ፖሊስ የሚደርሱትን ጥቆማዎች ተከትሎ በሚያደረገው ፍታሻ ላይ ቅሬታዎች እየደረሷቸው እንደሆነ የጠቀሱት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ፤ "የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በከፍተኛ ጥንቃቄ ነው የምንመለከተው፤ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የፌደራል ፖሊስ ቅሬታ መቀበያ መንገዶችን እየዘረጉ ነው" ብለዋል። አስተያየት መቀበያ የስልክ መስመሮች እና ዴስኮች ተዘጋጅተዋል። እነዚህም በተቋማቱ ይፋ እንደሚደረጉ ገልጸዋል። ይደረጋሉ" ብለዋል። የመብት ጥሰቶች ምርመራ ይደረጋል እንደ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ያሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች እና ሌሎች አካላት በሰሜን ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን ሪፖርት ማድረጋቸውን ተከትሎ፤ መንግሥት መርማሪዎችን እና ዐቃቤ ሕጎች ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ማስማራቱን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ጨምረው ተናግረዋል። ይህ ምርመራ በከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚከናወን አረጋግጠው፤ ምርመራው ሲጠናቀቅ ውጤቱም ለሕዝብ ይፋ እንደሚሆን ተናግረዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን መቀለ ከ50-60 ኪ.ሜ ርቀት ተከባለች በትናንቱ መግለጫ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በበኩላቸው ትላልቅ ከተሞችን ጨምሮ አብዛኛው የትግራይ ክልል መሬት በአገር መከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ሥር እንደሚገኝ ተናግረዋል። አክሱም፣ አደዋ እና አዲግራት ከተሞች ደግሞ በቅርቡ ከህወሓት ነጻ የወጡ ከተሞች ናቸው ያሉት አምባሳደር ሬድዋን፤ የክልሉ መዲና የሆነችውን መቀለን ለመቆጣጠር መከላከያ ሠራዊት ከ50 እስከ 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ ተከባ እንደምትገኝ ተናግረዋል። አምባሳደሩ ጨምረው እንደተናገሩት፤ የህወሓት ኃይሎች ለቀው ለመውጣት ሲገደዱ በመሠረተ ልማቶች ላይ ጉዳት እያደረሱ እየሸሹ ነው ብለዋል። እንደምሳሌም የአክሱም አየር ማረፊያ ላይ ጉዳት እንዲደርስ መደረጉን እንዲሁም ከስድስት ያላነሱ ድልድዮች እንዲፈርሱ መደረጋቸውን እና መንገዶች መቆፈራቸውን ተናግረዋል። አምባሳደር ሬድዋን "የመቀለ ከተማ ነዋሪ እውነታውን ተረድተው፤ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የህወሓት መሪዎችን አሳልፎ መስጠት ይኖርበታል" ብለዋል። የአፍሪካ ኅብረት የወቅቱ ሊቀመንበር የሆኑት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎሳ ልዑክ እንደሚልኩ አስታውሰው፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህን ልዑክ ተቀብለው የሚያነጋግሩት ለአፍሪካ ኅብረት እና ለአፍሪካ መሪዎች ካለ አክብሮት የመነጨ መሆኑን አስታውሰው፤ "ከህወሓት ኃይሎች ጋር ግን እንደ ሕጋዊ አካል ቆጥሮ የሚደረግ ውይይት አይኖርም" ብለዋል። በፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልልን በሚመራው ህወሓት መካከል ለወራት የቆየው አለመግባባትና መካሰስ ባለፈው ዓመት ማብቂያ ላይ በትግራይ ክልል በተናጠል የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ መባባሱ ይታወሳል። በጥቅምት ወር ማብቂያ ላይ በትግራይ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ ላይ በክልሉ ኃይሎች ጥቃት መፈጸሙን በመግለጽ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ማዘዛቸውን ተከትሎ ፍጥጫው ወደ ግጭት አምርቶ ሦስተኛ ሳምንቱን ሊደፍን ተቃርቧል። ባለፉት ሳምንታት በተካሄዱት ወታደራዊ ዘመቻዎች የመንግሥት ኃይሎች የተለያዩ ከተሞችን መያዛቸው የተነገረ ሲሆን በክልሉ ዋና ከተማ መቀለ አቅራቢያ መድረሳቸውም ተገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ መቀለ የአገሪቱ ሠራዊት ከመንቀሳቀሱ በፊት ሊደርስ ይችላል የተባለ ጉዳትን ለማስቀረት የትግራይ ክልል ኃይሎችን የህወሓት አመራሮች እጃቸውን እንዲሰጡ ነገ ረቡዕ የሚያበቃ የ72 ሰዓታት የጊዜ ገደብ አስቀምጠዋል።
48197245
https://www.bbc.com/amharic/48197245
ሩስያ፡ ከንቲባው የዱር እንስሳትን የሚያሳትፍ ሰርከስ ከለከሉ
በደቡባዊ ሩስያ የምትገኘው ሜጋስ ከተማ ከንቲባ የሆኑት ባስላን ሴቾይቭ የዱር እንስሳትን የሚያሳትፍ ሰርከስ ማገዳቸውን አስታውቀዋል።
እንስሳትን የሚያሳትፍ ሰርከስ በሩስያዋ ከተማ ተከልክሏል ከንቲባው "የዱር እንስሳት ትርኢት ያለበት ሰርከስ እጅግ የከፋ የእንስሳት መብት ጥሰት ነው። እንስሳቱ እንዲኖሩ የሚደረጉት ባልተመቸ ቦታ ነው። ሜጋስ ውስጥ የዱር እንስሳ የሚጠቀም ማንም የሰርስ ባለሙያ ትርኢት እንዲያሳይ አይፈቀድለትም" ብለዋል። • ዳንስን በሁለተኛ ዲግሪ ሩስያ ዘመናት ያስቆጠረ የሰርከስ ባህል ያላት ሀገር እንደመሆኗ የከንቲባው ውሳኔ የመገናኛ ብዙሀንን ትኩረት ለመሳብ ግዜ አልወሰደበትም። ውሳኔያቸውን ተከትሎም በቅርቡ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረ የሰርከስ ትርዒት ተሰርዟል። በተያያዥም የከተማው ካውንስል፤ ታዳጊዎች በምን መንገድ እንስሳትን መያዝ እንዳለባቸው የሚማሩበት ንቅናቄ እንደሚጀምርም ይፋ አድርጓል። ከንቲባው፤ የዱር እንስሳትን በሰው ሰራሽ ማቆያ ውስጥ እያኖሩ ለሰረከስ ትርኢት መጠቀም "እንስሳቱን እንደ እስረኛ ማድረግ ነው" ብለዋል። • ከአዕዋፍ እስከ አንበሳ ያሉ እንስሳት በግለሰቦች እጅ ለስቃይና ለጉዳት እየተዳረጉ ነው። የ38 ዓመቱ ከንቲባ፤ ከተማዋን ለአራት ዓመታት ያስተዳደሩ ሲሆን፤ የእንስሳትን መብት ለማስጠበቅ በሚያደርጉት ጥረት ይታወቃሉ። አዘውትረውም አቋማቸውን በኢንስታግራም ገጻቸው ለሕዝብ ያጋራሉ። ከዚህ ቀደም ሰው ሰራሽ የዶልፊኖች ማቆያ ይሠራ ሲባል አሻፈረኝ ብለው ነበር። "እነዚህ ተወዳጅ እንስሳት መኖር ያለባቸው በነጻነት በተፈጥሯዊ አካባቢያቸው ነው" ብለዋል። መኖሪያ ለሌላቸው እንስሳት ማቆያ እንዲሠራ አድርገዋል። ድመቶችና ውሾች ሲበርዳቸው ቤታቸውን በማሞቅ፤ ሲሞቃቸው ደግሞ ሰውነታቸውን የሚያቀዘቅዙበት መዋኛ ገንዳ አሠርተዋል። • በ500 መዥገሮች የተወረረው እባብ የደም ህዋስ ማነስ አጋጠመው የዱር እንስሳትን የሚያሳትፍ ሰርከስ በበርካታ የአውሮፓ ሀገሮች ታግዷል። ከንቲባውም ከዓለም አቀፍ የእንስሳት መብት ተሟጋቾች ጋር የሚጣጣም ውሳኔ በማስተላለፍ ሩስያ ውስጥ የሚደርስባቸው የለም።
news-57333180
https://www.bbc.com/amharic/news-57333180
በኢትዮጵያ 37 ሺህ ኮምፒውተሮች ላይ የሳይበር ጥቃት ለመፈፀም ሙከራዎች አሉ ተባለ
በኢትየጵያ 37 ሺህ በሚሆኑ ኮምፒውተሮች ላይ የሳይበር ጥቃት ለመፈፀም ሙከራዎች እየተደረጉ ነው ሲል የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ አስታውቋል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ በማኅበራዊ የትስስር ገፁ ባወጣው መግለጫ ይህንን ለመፈፀም እየሞከረ ያለው 'ሳይበር ሆረስ ግሩፕ' የተባለ የመረጃ ሰርሳሪ ቡድን ነው ብሏል። ቡድኑ አዲስ የኮምፒውተር ቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ ኮምፒውተሮች ላይ ለመልቀቅ ዝግጅት እንዳደረገ እንደተደረሰበት መግለጫው አክሏል። ኤጀንሲው እንደገለፀው ቫይረሱ "ብላክ ፒራሚድ ዋር" የሚል ስያሜ እንደተሰጠውና 37 ሺህ በሚደርሱ የአገሪቱ ኮምፒውተሮች ላይ የሳይበር ጥቃት ለማድረስ እየሞከረ መሆኑን ገልጿል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ቡድኑ ያነጣጠረባቸው እነዚህ 37 ሺህ ኮምፒውተሮች የት እንደሚገኙ፣ የማን እንደሆኑ ወይም ዝርዝር ጉዳዮችነም አላስቀመጠም። ቡድኑ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ውሃ ሙሌት ጋር ተያይዞ በአገሪቱ ላይ ያሉ ድረ-ገፆችን የመበርበር ሙከራ ሲያደርግም መቆየቱንም ቢቢሲ ከኤጀንሲው ካገኘው መረጃ መረዳት ተችሏል። ተቋሙ ቡድኑ የትኞቹን ድረ-ገፆች ላይ የመበርበር መከራ እንዳከናወነ ዝርዝር መረጃ አልሰጠም። የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ሆኖም "ሁሉም የሳይበር ምህዳር ተጠቃሚዎች ተገቢውን የሳይበር ደኅንነት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ" በማሳሰብ ምክሩን አስተላልፏል። ኤጀንሲው ከዚህ በፊት መሰረታቸውን ከግብጽ ያደረጉ የመረጃ መረብ ሰርሳሪዎች ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ ተቋማት የመረጃ መረብ መዋቅር ላይ ጥቃት ለማድረግ ሞክረው እንደነበር መግለጹ ይታወሳል። የኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በወቅቱ እንዳስታወቀው በሦስት የተለያዩ ቡድኖች አማካይነት የተሞከረው የመረጃ መረብ ጥቃት በአገሪቱ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጫናን ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ አመልክቶ ነገር ግን በኤጀንሲው አማካይነት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጾ ነበር።
news-53041151
https://www.bbc.com/amharic/news-53041151
"እየተካሄደ ያለው ድርድር የተጓተተው ግብፅ የቅኝ ግዛት ስምምነቱን ሙጥኝ በማለቷ ነው"
በኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ መካከል በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ሲካሄድ የነበረው ድርድር ቀጥሎ ለአራተኛ ቀንም በትናንትናው ዕለት ተካሂዷል።
በትናንትናው ዕለትም የግብፅ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ ያወጣው ጋዜጣዊ መግለጫን አስመልክቶ የኢትዮጵያ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ምላሸ ሰጥቷል። ቃለ አቀባዩ የሦስቱ አገራት ድርድር እንደተፈለገ መካሄድ ያልቻለው በኢትዮጵያ ችግር ነው ማለታቸው ውንጀላ መሆኑን የገለፀው ሚኒስቴሩ፤ በተቃራኒው ስምምነቶቹ ውጤታማ መሆን ያልቻሉት ግብፅ የቅኝ ግዛትን የውሃ ስምምነት ሙጥኝ ብላ በመያዟ እንደሆነ ገልጿል። ይህ ስምምነት ኢትዮጵያንም ሆነ የላይኛው ተፋሰስ አገራትን የተፈጥሮና ተገቢ የውሃ መብታቸውን የሚከለክል ነው ብሏል። ሚኒስቴሩ አክሎም የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብንም ግራ ለማጋባትም ሆነ ኢትዮጵያ የቅኝ ግዛት ስምምነትን እንድትቀበል የሚደረግ ጫና፣ ግፊም ሆነ ዘመቻ ተቀባይነት የለውም ብሏል። ኢትዮጵያ በሌለችበት የተፈረመ ስምምነት እንዲሁም ሕጋዊ ከሆነው የአባይን ወንዝ መጠቀም መብት ለመካለከል ግብፅ የምትሄድበት መንገድንም እንደሚቃወም አስታውቋል። ሚኒስቴሩ ከሰሞኑ የተደረጉ ድርድሮችን በተመለከተም በሱዳን ሊቀ መንበርነት አገራቱ የውሃ ሙሌቱን በተመለከተና የግድቡን አጠቃላይ አሰራርን በተመለከተ ቴክኒካዊ ውይይቶች ማካሄዳቸውን ጠቅሶ፣ ድርድሩ ከናይል ወይም አባይ ውሃ ክፍፍል ጋር የተያያዘ እንዳልሆነ አስታውቋል። በመግለጫውም የግድቡን የመጀመሪያ ደረጃ ሙሌት እንዲሁም አጠቃላይ የህዳሴ ግድብ አሰራርን በተመለከተ ኢትዮጵያ ከታችኛው ሁለት የተፋሰስ አገራት ጋር በመርሆች ስምመነት መመሪያዎችና ሕጎች እንደምትመራ አስታውቋል። አገራቱ የሚያደርጓቸው ድርድሮች ቀናና ግልፅ በሆነ መንገድ ማካሄድ ከተቻለ ሁሉም አሸናፊ የሚሆኑበት ስምምነት ላይ መድረስ እንደሚችሉም ተስፋ እንደሰነቀም መግለጫው ጠቁሟል። አገራቱ የግድቡን ደኅንነት ሕጎች፣ አካባቢያዊና ማኅበራዊ ግምገማ ጥናት እንዲሁም መመሪያዎችና ሕጎች አጠቃቀም ላይም የጋራ መግባባት ላይ እንደደረሱ ገልፆ፤ ድርድሩ በነገው ዕለትም [ሰኞ] የሚቀጥል ሲሆን በግብፅ የሊቀመንበርነት የሚካሄድ ይሆናል።
news-51924425
https://www.bbc.com/amharic/news-51924425
በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት በርካታ ቻይናዊያን በኢትዮጵያ ለመቆየት እየጠየቁ ነው
በኮሮናቫይረስ ስጋት ምክንያት በርካታ ቁጥር ያላቸው ቻይናዊያን ወደ አገራቸው ላለመመለስ በኢትዮጵያ ለመቆየት የሚያስችላቸውን ቪዛ እያራዘሙ መሆኑ ተገለጸ።
ቻይናዊያኑ ለተለያዩ ሥራዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ቆይተው በአሁኑ ወቅት የተሰጣቸው የመቆያ ቪዛ ሲያበቃ ነው ወረርሽኙን በመፍራት ኢትዮጵያ ውስጥ ለመቆየት የሚያስችላቸውን ፈቃድ እየጠየቁ ያሉት ተብሏል። በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ውስጥ የኢሚግሬሽን ኃላፊ የሆኑት አቶ አይክፋው ጎሳዬ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ጥቂት የማይባሉ ቻይናዊያን በኢትዮጵያ ለመቆየት የሚያስችላቸውን የቪዛ ጥያቄ አቅርበው ምላሽ እያገኙ ነው። "ቻይናዊያኑ በአገራቸው ያጋጠመውን ወረርሽኝ በመስጋት ነው በኢትዮጵያ ለመቆየት ጥያቄ እያቀረቡ ያሉት" ብለዋል አቶ አይክፋው። ይህንን ከግንዛቤ በማስገባትም መንግሥት ጥያቄ እያቀረቡ ላሉ ቻይናዊያንም ሆነ የሌሎች አገራት ዜጎች የመቆያ ጊዜያቸው እንዲራዘም እያደረገ ነው ብለዋል። ሕገ ወጥነትን ለመከላከል ቀደም ሲል ቻይናዊያን የመቆያ ጊዜያቸውን ሲያጠናቅቁ እንዲራዘምላቸው በሚጠይቁ ጊዜ ለ10 ቀናት የሚቆይ ማራዘሚያ ይፈቀድላቸው እንደነበር የጠቀሱት አቶ አይክፋው፤ አሁን ግን በአገራቸው የተከሰተውን ሁኔታ ከግምት በማስገባት ለአንድ ወር የሚቆይ ቪዛ ይሰጣቸዋል ብለዋል። ከዚህ ባሻገርም በአንዳንድ ማኅበራዊ ድረ ገጾች ላይ በርካታ ጣሊያናዊያን ቱሪስቶች በኢትዮጵያ መቆየት የሚያስችላቸው ቪዛ ቢያበቃም በአገራቸው ያለውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መስፋፋትን በመፍራት ኢትዮጵያ ውስጥ ለመቆየት ጠይቀዋል ለሚለው ወሬ ማረጋጫ አልተገኘም። ቢቢሲ ይህንኑ ለማጣርት አዲስ አበባ የሚገኘውን የጣሊያን ኤምባሲን የጠየቀ ሲሆን በተሰጠው ምላሽ መሰረት እንዲህ አይነት ጥያቄ አለመቅረቡንና የተባለው ነገር "ሐሰተኛ ወሬ" መሆኑን ተነግሮታል። አቶ አይክፋው ጎሳዬም ይህንን መረጃ ሰምተው ለማጣራት መሞከራቸውንና እንደተባለው ከተጠቀሱት ጣሊያናዊያን ቱሪስቶች በኩል ቪዛ የማራዘም ምንም አይነት ጥያቄ ለመስሪያ ቤታቸው አለመቅረቡን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
news-54672467
https://www.bbc.com/amharic/news-54672467
ትምህርት፡ በሰላም መደፍረስ ምክንያት ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎች እጣ ፈንታ ምን ይሆናል?
በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ትምህርት አቋርጠው የነበሩ ዩኒቨርስቲዎች በጥቅምት ወር መጨረሻ ሳምንት አንስቶ ተመራቂ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን የሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስቴር ለቢቢሲ ተናገረ።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ከጥቅምት 23 እስከ 30/2013 ዓ. ም የመጀመሪያ ዙር የተማሪዎች ቅበላ እንደሚያርጉ ተገልጿል። የሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነት ደቻሳ ጉርሙ ለቢቢሲ እንዳስረዱት ከጥቅምት ወር አንስቶ የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች ጥሪ ይከናወናል። ተማሪዎቹ ቀርተዋቸው የነበሩ ኮርሶች በቀጣይዎቹ ሁለት ወራት ውስጥ እንዲያጠናቅቁ መወሰኑን የተናገሩት አቶ ደቻሳ፤ ከዚያ በኋላ ደግሞ የኮሮናቫይረስ ሁኔታን በማየት ለተቀሩት ተማሪዎች ጥሪ ይተላለፋል ብለዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ኮቪድ-19ን እየተከላከሉ ትምህርትና ስልጠናን ለማስቀጠል ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ከጥቅምት 23-30/2013 ዓ. ም አስፈላጊውን ዝግጅት በማጠናቀቅ የመጀመሪያ ዙር የተማሪዎች ቅበላ እንዲያደርጉ ማሳሰቡ ተዘግቦ ነበር። በቅርቡ ዩኒቨርስቲዎች በሃዋሳ ከተማ ለሶስት ቀናት ባካሄዱት ስብሰባ ትምህርት ለማስጀመር መወሰናቸውን አቶ ደቻሳ ጨምረው ተናግረዋል። በአገሪቱ የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ ላለፉት ሰባት ወራት ትምህርት ለማቋረጥ መገደዳቸው ይታወሳል። በጉዳዩ ላይ ቢቢሲ ካነጋገራቸው ዩኒቨርስቲዎች መካከል አንዱ የሆነው የወለጋ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሐሰን የሱፍ ከጥቅምት 23 እስከ 30 2013 ዓ. ም ባሉት ቀናት ውስጥ የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎችን እንቀበላለን ብለዋል። "በቀጣይ ደግሞ የሁለተኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ ያሉትን ተማሪዎች ጥሪ እናደርጋለን" ሲሉ የሌሎች ተማሪዎችን እጣ ፈንታ ያስረዳሉ። ከሁለተኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች የአንደኛ መንፈቀ ዓመት ትምህርታቸውን አጠናቅቀው ለሁለተኛ መንፈቀ ዓመት ዝግጅት ላይ በነበሩበት ወቅት በኮሮናቫይረስ ምክንያት ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ ቤተሰባቸው መመለሳቸውን ዶ/ር ሐሰን ያስታውሳሉ። የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ግን የአንደኛ መንፈቀ ዓመት ፈተናቸውን ጀምረው ሳያጠናቅቁ መሄዳቸውን ተናግረው፤ መማር የሚገባቸውን ቁልፍ የሆኑ ትምህርቶች በመለየት በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ አስተምሮ ለማስጨረስ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን አብራርተዋል። ቢቢሲ በጉዳዩ ላይ ያነጋገራቸው የሀሮማያ እና መደወላቡ ዩኒቨርስቲዎችም የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን ተናግረው፤ በተመሳሳይ የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን ገልፀዋል። በሰላም መደፍረስ ምክንያት ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎችስ? ባለፈው ዓመት የትምህርት ዘመን ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በፊት በአንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች ተከስቶ የነበረውን የሰላም መደፍረስ ተከትሎ አንዳንድ ተማሪዎች ትምህርታቸው አቋርጠው ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለሳቸው ይታወሳል። ለምሳሌ ከኦሮሚያ ክልል የሄዱና በአማራ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ፣ በተመሳሳይም ከአማራ ክልል የሄዱና በኦሮሚያ ክልል ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች ባጋጠመው የሰላም መደፍረስ ምክንያት ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ ቤተሰቦቻቸው ተመልሰዋል። ይሁን እንጂ አንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች ባደረጉት ውይይት ተማሪዎች ተመልሰው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ተደርጎ እንደነበር ይናገራሉ። ከእነዚህም መካከል የወለጋ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሐሰን የሱፍ እንዳሉት፤ በዩኒቨርስቲው አልፎ አልፎ ተከስቶ በነበረው የሰላም መደፍረስ ትምህርታቸውን በማቋረጥ ወደ ቤተሰቦቻቸው ተመልሰው የነበሩ ተማሪዎች ተመልሰው ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ መተላለፉን ያስታውሳሉ። በዚሁ መሰረት ገሚሶቹ ተመልሰው የነበረ ቢሆንም ገሚሶቹ ደግሞ በነበረው ሁኔታ ስጋት ገብቷቸው ሳይመለሱ መቅረታቸውን ተናግረዋል። "እነዚህ ተማሪዎች ተመልሰው እኛ ጋር እንዲማሩ እንፈልጋለን፤ ይሁን እንጂ የአንደኛ ሴሚስተር ትምህርት ስላመለጣቸው፣ ፈተናም ስላልተፈተኑ ከመጀመሪያው መጀመር የግድ ይላቸዋል" ከዚህም በተጨማሪንእነዚህ ተማሪዎች ትምህርት ሲያቋርጡ መሙላት የሚገባቸውን ቅጽ (ዊዝድሮዋል) ሳይሞሉ ግቢውን ለቅቀው መውጣታቸውን የሚናገሩት ዶ/ር ሐሰን፤ አሁን ምን ዓይነት ውሳኔ ነው የሚተላለፈው በሚለው ላይ ትምህርት ሚኒስቴር እስካሁን ድረስ ያለው ነገር እንደሌለ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በኦሮሚያ ክልል በሰላም መደፍረስ ትምህርት ተቋርጦቸባቸው ከነበሩት ዩኒቨርስቲዎች መካከል አንዱ የሆነው የመደወላቡ ዩኒቨርስቲ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ፈለቀ ረጋሳ በበኩላቸው፤ በዘንድሮው ዓመት የሚመረቁ 2016 ለሚሆኑ ተማሪዎች ጥሪ መተላለፉን ገልፀው ትምህርታቸውን እንደሚከታተሉ ይናገራሉ። በሌላ በኩል አምና ገጥሞ በነበረው የሰላም መደፍረስ ምክንያት ትምህርታቸውን አቋርጠው የሄዱ ተማሪዎች መኖራቸውን ያስታወሱት ዶ/ር ፈለቀ፤ " ይሁን እንጂ በኋላ ላይ ባደረግነው ጥሪ 75 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ተመልሰው ትምህርታቸውን መከታተል ችለዋል" ብለዋል። በወቅቱ አምልጧቸው የነበረውን ትምህርት ለማካካስም አስተማሪዎች በተጨማሪ ሰዓት ሲያስተምሯቸው እንደነበር ይናገራሉ። "ጥሪ ቢተላለፍም 25 በመቶ የሚሆኑት ሳይመለሱ ቀርተዋል። የሚተላለፈው ውሳኔም ለእነርሱ ብቻ ሳይሆን ለመላው ዩኒቨርስቲው ተማሪዎች በሚሆን ሁኔታ በዩኒቨርስቲው ሴኔት የሚወሰን ይሆናል፤ ለእነርሱ ብቻ የሚሰራ ሕግ አይኖርም።" ዶ/ር ፈለቀ እንደሚሉት በሕጉ መሰረት የሚታገዱ ከሆነ ይታገዳሉ የሚመለሱ ከሆነም ተመልሰው ትምህርታቸውን ይከታተላሉ። በተመሳሳይም የሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጀማል የሱፍ ባለፈው ዓመት በነበረው የሰላም መደፍረስ ትምህርታቸውን አቋርጠው የሄዱ ተማሪዎችን በሚመለከት እስካሁን የተላላፈ አዲስ ውሳኔ እንደሌለ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በሰላም መደፍረስ ምክንያት ወደቤተሰቦቻቸው የተመለሱ ተማሪዎችን በሚመለከት እንደ አገር በትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ መተላለፍ እንዳለበት ዶ/ር ጀማል ይናገራሉ። ይህንኑ ጉዳይ በሚመለከት ቢቢሲ ጥያቄ ያቀረበላቸው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሕዝብ ግንኙነት አቶ ደቻሳ ጉርሙ፤ እስካሁን በዚህ ጉዳይ ላይ የተላለፈ ምንም ዓይነት ውሳኔ አለመኖሩን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። የተማሪዎቹ ቁጥር ምን ያህል እንደሆነ ከዩኒቨርስቲዎቹ ከተጣራ በኋላ እንዴት ይህን ችግር እንፍታ በሚለው ላይ እየተሰራ እንደሆነ በመግለጽ "ውሳኔ ላይ ስንደርስ የምናስታውቅ ይሆናል" ብለዋል። "ያለን አንድ አገር ስለለሆነ ከአንዱ ክልል ወደ ሌላ ክልል አልሄድም የሚል አስተሳሰብ ካለ አናስተናግድም" ሲሉም ሃሳባቸውን ይቋጫሉ።
55147187
https://www.bbc.com/amharic/55147187
"ከ50 በላይ የመጀመሪያ ሕክምና እርዳታ ሰጪ አሰማርተናል" የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር
በትግራይ ክልል ወታደራዊ ግጭት ከተቀሰቀሰ ወዲህ በአካባቢው ሰብአዊ እርዳታ እየሰጠ ያለው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በስፍራው ከ50 በላይ የመጀመሪያ እርዳታ ሰጪ ቡድን ማሰማራቱን ለቢቢሲ ገልጿል።
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ምክትል ዋና ጸሐፊ አቶ እንግዳ ማንደፍሮ እንደተናገሩት፤ በአካባቢው ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ ድጋፍ እያደረጉ ሲሆን፤ ከ35 በላይ አምቡላንሶችን አሰማርተዋል። "የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የትግራይ ቅርንጫፍ እና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የአማራ ቅርንጫፍ አንድ ላይ የአምቡላንስ አገልግሎት፣ የመጀመሪያ ሕክምና እርዳታ አገልግሎትና ሌላም ድጋፍ እያደረጉ ነው" ብለዋል። የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በአካባቢው ለሚገኙ ሆስፒታሎች ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን እየደጎመም መሆኑ ተገልጿል። "ለተጎዱ ሰዎች የአምቡላንስ አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ፤ በምዕራብ ትግራይ አካባቢ ለተፈናቀሉ ሰዎች ምግብ ነክ ያልሆኑ እንደ ብርድ ልብስ እና ፍራሽ ያሉ አስፈላጊ ቁሳቁሶችንም አከፋፍለዋል" ብለዋል አቶ እንግዳ። የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ከዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማኅበር ጋር በመሆን ለሆስፒታሎች የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ ቁሳቁስ ከአምቡላንስ ጋር እንደሚደርስና ድጋፉ በሽረ፣ መቀለ፣ ወልድያ፣ ዳንሻ፣ ጎንደር እንደተዳረሰ አስረድተዋል። በግጭቱ ሳቢያ ጉዳት ስለደረሰባቸው ሰዎች ላቀረብንላቸው ጥያቄ፤ "እስካሁን እያጓጓዝን ያለነው የተጎዱ ወታደሮችን ነው። ማይካድራ አካባቢ ጉዳት የደረሰባቸው ሰላማዊ ሰዎችን አጓጉዘናል። በሌላ አካባቢ ግን ሰላማዊ ሰዎች አላየንም" ብለው መልስ ሰጥተዋል። ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማኅበር በመቀለ አይደር ሆስፒታል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ቁሳቁሶች እንዲሁም የአስክሬን ማቆያ የፕላስቲክ ከረጢት እያለቀ መሆኑን ማስታወቁ ይታወሳል። ሆስፒታሉን የጎበኙ የድርጅቱ ባልደረቦች "80 በመቶው ታካሚዎች በግጭቱ ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው። ሌሎች ሕክምናዎች ቆመው ለድንገተኛ አደጋ ብቻ አገልግሎት እየተሰጠ ነው" ብለዋል። የማኅበሩ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ኃላፊ ማሪያ ሶልዳድ "ቁስል ለመስፋት የሚውል መገልገያ፣ ጸረ ተህዋሲ መድኃኒት፣ የህመም ማስታገሻ እና ሌሎችም መድኃኒቶች በአሳሳቢ ሁኔታ እያለቁ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። በግጭቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ሕክምና በመስጠት ላይ ያሉ በአካባቢው የሚገኙ ሆስፒታሎች ውስጥ መጨናነቅ እንደሚፈጠር የገለጹት አቶ እንግዳ፤ ለሆስፒታሎቹ ድጋፍ እንዲደረግ አሳስበዋል። ይህ መጨናነቅ ቀደም ያለ ህመም ያለባቸው ሰዎች፣ ነፍሰ ጡር ሴቶች እና ሌሎችም ተገቢውን አገልግሎት እንዳያገኙ እንቅፋት መሆኑን አይቀርም። "ሆስፒታሎቹ ከመደበኛው ውጪ ሥራ ሲኖራቸው ለሌሎች ህመምተኞች እገዛ ለማድረግ ይቸገሩ ይሆናል። ተጨማሪ ፍራሽ እና መድኃኒት የሚጠይቁትም ከመደበኛው ከፍ ያለ ሰው ስለገጠማቸው ነው። እኛም በደረስንባቸው አካባቢዎችም ይህን አስተውለናል። ሆስፒታሎቹ እና ጤና ተቋሞቹ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል" ብለዋል። የተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ እርዳታ ሰጪዎች ለአካባቢው ማኅረበረሰብ ድጋፍ ለማድረግ መንገዶች ክፍት መደረግ አለባቸው ብለዋል። ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰብአዊ እርዳታ ሰጪዎች መንገድ እንደሚያመቻች መግለጹ አይዘነጋም። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ድጋፍ ለማድረግ እንቅፋት ገጥሟቸው እንደሆነ የጠየቅናቸው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ምክትል ዋና ጸሐፊ አቶ እንግዳ "ሠራተኞቻችን ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ቦታው ገብተው እየሠሩ ነው። አሁንም መስራት ቀጥለዋል። የደኅንነት ችግር አይኖርም አይባልም። እንደ ማንኛውም ድርጅት አንዳንድ ቦታዎች የደኅንነት ስጋቶች አሉን" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ከሦሰት ሳምንታት በላይ በትግራይ ክልል ውስጥ በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊትና በህወሓት ኃይሎች መካከል የተካሄደው ወታደራዊ ግጭት ባለፈው ቅዳሜ የመቀለ ከተማ መያዝን ተከትሎ ዘመቻው ማብቃቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ማስታወቃቸው ይታወሳል። ግጭቱ ከተከሰተበት ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ጀምሮ በአካባቢው ያሉት የግንኙነት መስመሮች አስካሁን በመቋረጣቸው በጦርነቱ የሞቱ ሰዎችና የደረሰውን ጉዳት ለማወቅ አስተማማኝ መረጃ ማግኘት አዳጋች ሆኗል። ነገር ግን የተለያዩ የዕርዳታ ተቋማት በሦሰት ሳምንቱ ወታደራዊ ግጭት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት ሳያልፍ እንዳልቀረ ይገምታሉ፤ ቀውሱን በመሸሽም ከ40 ሺህ በላይ ሰዎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው መሸሻቸው ተነግሯል። የፌደራል መንግሥቱ መቀለን ከተቆጣጠሩ በኋላ በክልሉ ውስጥ መረጋጋትን በመፍጠር ጉዳት የደረሰባቸውን ለመርዳት እየሰራ መሆኑን ከመግለጹ በተጨማሪ ተፈናቅለው ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን የገቡ ዜጎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደቀያቸው ተመልሰው እንዲቋቋሙ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
news-52645165
https://www.bbc.com/amharic/news-52645165
መጨባበጥ ቀረ? ከመጨባበጥ ውጪ ስላሉ ሰላምታዎችስ ያውቃሉ?
ኮቪድ-19 ማኅበራዊ መስተጋብርን እየቀየረ ነው። ለምሳሌ ከሰዎች ጋር ሰላምታ የምንለዋወጥበት መንገድ ተለውጧል።
አሁን ላይ መጨባበጥ፣ መተቃቀፍ አይታሰብምና በርካቶች ወደ ሌላ አማራጭ ፊታቸውን አዙረዋል። ሰላምታ የምንለዋወጥበት መንገድ ከሰው ሰው ይለያያል። ሰላም ከምንለው ሰው ጋር እንዳለን ቅርርብም ይወሰናል። ስለ ሰብዕናችንም የሚጠቁመው ነገር አለ። የባህል አጥኚው አሌሳንድሮ ዱራንቲ፤ ሰላምታ መለዋወጥ ትርጉም አዘል መስተጋብር ነው ይላሉ። ለመሆኑ በተለያዩ አገሮች የተለመዱ ሰላምታ አሰጣጦች ምን ይመስላሉ? ስንል ሰባት አገሮችን ቃኝተናል። ከቻይና እንጀምር. . . ቻይና ኮሮናቫይረስ መጀመሪያ የተገኘባት የቻይናዋ ውሃን ግዛት ውስጥ ‘ውሃን ሼክ’ የተሰኘ ሰላምታ ተፈጥሯል። ሰዎች አንድ እግራቸውን ከሌላ ሰው እግር ጋር በማነካካት ሰላምታ የሚለዋወጡበት መንገድ ነው። የታንዛንያው ፕሬዘዳንት ጆን ማጉፉሊን ጨምሮ የተለያዩ አገራት ባለሥልጣኖች ‘ውሃን ሼክ’ን ወርሰው፣ በአደባባይ በዚህ መንገድ ሰላም ሲባባሉ ታይቷል። የባህል አጥኚው ቹዋን ካንግ ሺህ “ሰዎች ውሃን ሼክን በመጠቀም በዚህ አስከፊ ወቅት አብሮነት እንዳልተሸረሸረ ያሳያሉ። ቀለል ያለ፣ አዝናኝም ሰላምታ ነው” ይላሉ። ‘ውሃን ሼክ’ ምናልባትም ለዘመናት የሚቆይ ዓለም አቀፍ ሰላምታ ይሆን? በእርግጥ ቻይና ውስጥ 3,000 ዓመታት ያስቆጠረ ሰላምታ አለ። መዳፍን አገናኝቶ፣ ወደ ደረት አስጠግቶ፣ ከወገብ ጎንበስ በማለት ይከናወናል። በተለይም በቻይናውያን አዲስ ዓመትና ሠርግ ላይ ይዘወተራል። ኒው ዚላንድ የኒው ዚላንድ ቀደምት ማኅበረሰብ ‘ሆንጊ’ የተባለ ሰላምታ አላቸው። አንድ ሰው አፍንጫውንና ግንባሩን ከሌላ ሰው አፍንጫና ግንባር ጋር አነካክቶ ሰላም ይላል። የዓለም ጤና ድርጅት ኮቪድ-19 ወረርሽኝ መሆኑን ከማወጁ ከሳምንታት በፊት ማኅበረሰቡ ይህንን ሰላምታ ያቁም ተብሎ ነበር። ጠቅላይ ሚንስትር ጀሲንዳ አርደንም ‘ሆንጊ’ ይቁም፤ መጨባበጥና መተቃቀፍም ይቅር ብለው ነበር። ዜጎች አሁን በአይን ወይም አገጭ ከፍ በማድረግ ሰላምታ ይሰጣጣሉ የሚሉት ፕሮፌሰር ራንጊ ማታሙና ናቸው። ‘ሆንጊ’ ከማኅበረሰቡ ጋር የተቆራኘ ባህል ነው። የደን አምላክ ታኔ በመጀመሪያዋ ሴት ሕይወትን ከዘራበት መንገድ ጋር የተሳሰረ ነው እብለው ያምናሉ። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ1918 ‘ኢንፍሉዌንዛ’ ወረርሽኝ ሲሰራጭ ሰላምታው እንዲቆም ተደርጎ ነበር። ፕሮፌሰሩ “የጥንት ልማዶቻችን ለአሁኑ ማኅበረሰብ ካልሠሩ እንለውጣቸዋለን” የሚሉትም ለዚህ ነው። ፈረንሳይ ፈረንሳውያን ጉንጭ ለጉንጭ ይሳሳማሉ። ‘ቢስስ’ ይባላል። ልክ እንደ ኒው ዚላንዱ ‘ሆንጊ’ ሰላምታ የፈረንሳይ ሰላምታም በ ‘ኢንፍሉዌንዛ’ ወረርሽኝ ጊዜ ታግዶ ነበር። ፈረንሳይ እንቅስቃሴ ከማቆሟ በፊት 60 በመቶ ዜጎቿ ጉንጭ ለጉንጭ ይሳሳሙ ነበር። ከዛ ግን ወደ ስድስት በመቶ ወርዷል። የፈረንሳይ መንግሥት ‘ቢስስ’ ቢቆምም፤ ጉንጭ ለጉንጭ ስትሳሳሙ የምታወጡትን ድምፅ በመጠቀም በሩቁ ሰላም ተባባሉ ብሏል። የባህል አጥኚዋ ክላውዲ ጋውተው፤ ‘ቢስስ’ በቶሎ ማቆም አልተቻለም ነበር ይላሉ። በተለይ በሴቶች ዘንድ የሚዘወተረውን ሰላምታ መተው ከባድ ነበር። እስከ 1960ዎቹ ድረስ በጣም በሚቀራረቡ የቤተሰብ አባላት መካከል የሚሰጥ ሰላምታ እንደነበርም ያስታውሳሉ። “ሰላምታው የባህሉ አካል ነው” የሚሉት አጥኚዋ፤ አካላዊ ርቀት መጠበቅ ከመታወጁ በፊት ይህን ሰላምታ እምቢ ማለት ከደንብ መውጣት እንደነበር ያስረዳሉ። ጉንጭ ለጉንጭ የመሳሳም ድምፅን ተጠቅሞ ሰላምታ መለዋወጥ ይቀጥል ይሆን? አጥኚዋ እንደሚሉት ከሆነ፤ ማኅበረሰቡ ዘንድ ስለ ጤና የሚኖረው አመለካከት ይህ ሰላምታ እንዲቀጥል ወይም እንዲቆም ያደርጋል። ታንዛንያ የታንዛንያ ባህል አንድ ሰው በማኅበረሰቡ ውስጥ ያለውን ቦታ መሠረት ያደረገ ነው ሲሉ ባህል አጥኚው አሌክሳንደር ሙጃጌ ይናገራሉ። ታዳጊዎች ከወገባቸው ጎንበስ ብለው ለአዛውንቶች ሰላምታ ይሰጣሉ። በምላሹ አዛውንቶች የታዳጊዎችን ጭንቅላት ይዳብሳሉ። በሌላ በኩል አንድ ሰው በማኅበሰቡ ባለው ሥፍራ መሠረት፣ ዘለግ ላለ ጊዜ በመጨበጥ፣ በማቀፍ ወይም ጉንጭ በመሳም ሰላም ሊል ይችላል። አሁን ላይ ሰላምታ የሚሰጠው በእግር ሆኗል። የቻይናው ‘ውሃን ሼክ’ ታንዛንያ ደርሷል። በሩቁ ከወገብ ጎንበስ ብሎ ሰላም መባባልም እየተለመደ መጥቷል። “ኮቪድ-19 እንድንራራቅ አድርጓል። እግር የተፈጠረው ለመራመድ ነው። በእገር ሰላም መባባል ፍቅርን፣ መተሳሰብን፣ መከባበርን ያሳያል?” ሲሉ አጥኚው ሐሳባቸውን ገልጸዋል። የአፍና የፊት መሸፈኛ ጭንብል፤ ሰዎች በፊት እንቅስቃሴ እንዳይግባቡም አድርጓል። ለምሳሌ ቀድሞ ከንፈር በማጠማዘዝ ‘በሐሳቡ ተስማምቻለሁ’ ማለት ይቻል ነበር። ቱርክ የቱርክ ሰላምታ ከእስልምና ጋር የተቆራኘ ነው። ታዳጊዎች የጎልማሳ ዘመዳቸውን አይበሉባ ስመው ግንባራቸው ላይ ያሳርፉታል። በበዓል ወቅት፤ ጓደኛሞች፣ የሥራ አጋሮችም ጉንጭ ለጉንጭ ሁለት ጊዜ ይሳሳማሉ። ጋዜጠኛው ኬናን ሻርፕ “ጉንጭ ሁለት ጊዜ የሚሳምበት ምክንያት አለው፤ ሰው ሲሳም ጎዶሎ ቁጥር መሆን የለበትም” ይላል። ለቱርኮች ሰላምታ መስጠት እንግዳ ተቀባይነት፣ ሰው ያለውን ዋጋ መሳያም ነው። የኮሮናቫይረስ ሥርጭትን ተከትሎ ለበሽታው የማያጋልጥ ሰላምታ ለማግኘት የእስልምና ታሪክን ፈትሸዋል። ‘ኢቫላህ’ ዘመናት ያስቆጠረ ሰላምታ ነው። አንድ ሰው ክንዱን ደረቱ ላይ አድርጎ ለሌላው ሰላምታ ይሰጣል። እርስ በእርስ መከባበርን የሚያንጸባርቅም ነው። ቃሉ አረብኛ ሲሆን፤ በፈጣሪ እናምናለን ማለት ነው። በመላው ዓለም የእስልምና ተከታዮች ዘንድም ይዘወተራል። ዩናይትድ አረብ ኤሚሬትስ የጤና ሚንስትር መሰባሰብን ማገዱን ተከትሎ፤ መተቃቀፍ ቀርቷል። ባህላዊው አፍንጫ መሳምም እንዲሁ ቀርቶ ክንድን ደረት ላይ አሳርፎ በሩቁ ሰላም በመባባል ተተክቷል። ሰላምታው ድሮም በተቃራኒ ጾታ መካከል የተለመደ ነበር። በሌላ በኩል ሴቶች ጉንጭ ለጉንጭ ይሳሳሙ የነበረ ሲሆን፤ ኮሮናቫይረስ ይህ አይነቱን ሰላምታ አሰጣጥ አስቀርቷል። ጸሐፊ ናታሻ አማር እንደምትለው፤ ኮቪድ-19 የአንድ ማኅበረሰብ አባል መሆንና ከሰው ጋር መቀራረብ ዋጋ እንዳለው እንድንረዳ አድርጓል። አፍጋኒስታን በአፍጋኒስታን ያሉ የተለያዩ ማኅበረሰቦች ሰላም ሲባባሉ አክብሮትን እንዲሁም ፈጣሪና አገር መውደድን ያሳያሉ። መጨባበጥ፣ መተቃቀፍና መሳሳም ይዘወተራሉ። በአንዳንድ ማኅበረሰቦች እስከ ስምንት ጊዜ መሳሳም የተለመደ ነው። ሰዎች ሲያወሩም በጣም ተጠጋግተው ነው። ፕሮፌሰር ኮስሚን ኢቫንሲዩ እና ቪያና ፖፒካ እንደሚሉት፤ ጥሩ ጠረን ያለው ሰው ጥሩ ቀልብ እንዳለው ይታመናል። በአፍጋኒስታን መተቃቀፍ፣ መሳሳም የፍቅር መግለጫ ነው። በርከት ያሉ ሰዎች ተሰባስበውም አክብሮታቸውን ያሳያሉ። ወታደራዊ ሰላምታ መስጠትም የአክብሮት ማሳያ ነው። ሆኖም ግን ኮሮናቫይረስ ነገሮችን ለውጧል። ሩቅ ለሩቅ እጅ ማውለብለብ አዲሱ ሰላምታ ከሆነም ሰነባብቷል።
news-53792337
https://www.bbc.com/amharic/news-53792337
ኮሮናቫይረስ ፡ ኮቪድ-19 በየትኞቹ የዓለም አገራት ላይ በርትቷል?
ኮሮናቫይረስ በቻይናዋ ዉሃን መነሳቱ ከተሰማ ወዲህ ከግማሽ ዓመት በላይ ሆኖታል። እስካሁንም ከ21 ሚሊየን በላይ ሰዎች በአጠቃላይ መያዛቸው ሲረጋገጥ ቫይረሱ 188 የዓለም አገራትን አዳርሷል።
ከ765 ሺ በላይ ሰዎች ደግሞ ከዚሁ ቫይረስ ጋር በተያያዘ ሕይወታቸው አልፏል። በበርካታ አገራት በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር አሁንም በአሳሳቢ ሁኔታ እየጨመረ ሲሆን አንዳንዶች ደግሞ የወረርሽኙን ስርጭት ስኬታማ ሊባል በሚችል መልኩ እየተቆጣጠሩት ይገኛሉ። በዓለም ጤና ድርጅት መረጃ መሰረት ደግሞ የላቲን አሜሪካ አገራት የቫይረሱ ዋነኛ ማዕከል ሆነዋል። ብራዚል እስካሁን ከ100 ሺ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሞተውባት ከአሜሪካ በመቀጠል ከዓለም ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ሌላኛዋ አገር ሜክሲኮ ደግሞ በኮቪድ-19 ሳቢያ የሞቱባት ሰዎች ቁጥር ከ50 ሺ በላይ መሆኑን አስታውቃለች። በተጨማሪም እንደ ኮሎምቢያ፣ ፔሩ፣አርጀንቲና እና ቬንዙዌላ የመሳሰሉ አገራትም በቫይረሱ ክፉኛ ተጠቅተዋል። ከላቲን አሜሪካ ውጪ ደግሞ ኢራን የቫይረሱን ጉዳት መቋቋም ካልቻሉት መካከል ትጠቀሳለች። መንግሥታዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በአገሪቱ ስርጭቱ እንደ አዲስ እያገረሸ ሲሆን 20 ሺ የሚጠጉ ሰዎች ሞተዋል። ነገር ግን የቢቢሲ የምርመራ ዘገባ እንዳጋለጠው በአገሪቱ በቫይረሱ የሚያዙና ህይወታቸው የሚያልፍ ሰዎች ቁጥር መንግሥት ከሚናገረውም በላይ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል። ኮቪድ-19 የበረታባቸው በአፍሪካ ደቡብ አፍሪካና ግብጽ እስካሁን በአህጉሪቱ ከፍተኛውን ቁጥር አስመዝግበዋል።በዚህም ምክንያት ደቡብ አፍሪካ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ከ500 ሺ በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን በማስመዝገብ በዓለማችን ከተዘረዘሩት ሰባት አገራት ተርታ ተቀምጣለች። እንደ አጠቃላይ በአህጉሪቱ ግን እስካሁን ከአንድ ሚሊየን በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን እያደረሰ ያለው ጉዳትና ሊያስከትለው የሚችለው ጉዳት መጠን እስካሁን ግልጽ አይደለም። ሕንድ ደግሞ በዓለማችን ከፍተኛውን በአንድ ቀን የሚያዙ ሰዎች ቁጥር አስመዝግባለች። እስካሁንም 2.5 ሚሊዮን ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸውን ያረጋገጠች ሲሆን በየቀኑ ደግሞ ከ60 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ይያዙባታል። ይህ ቁጥር ደግሞ በዓለማችን እስካሁን ከፍተኛ ሆኖ ተመዝግቧል። ከቻይና በመቀጠል ከፍተኛውን የዓለም ህዝብ ቁጥር የያዘችው ሕንድ በአጠቃላይ በሟቾች ቁጥር አራተኛ ናት። ነገር ግን አሁንም ቢሆን አገሪቱ የእንቅስቃሴ ገደቡን ማላላቷን ቀጥላበታለች። የአውሮፓ አገራትም ቢሆኑ የቫይረሱን ስርጭት መቆጣጠር ተስኗቸዋል። ስፔን በወረርሽኙ የመጀመሪያ ወራት ክፉኛ ተጠቅታ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን በቅርብ ሳምንታት ደግሞ ቫይረሱ እንደ አዲስ እያገረሸ እንደሆነ እየተገለጸ ነው። ፈረንሳይም ብትሆን መጋቢት ወር ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችና የሟቾች ቁጥር አስመዝግባለች። ነገር ግን ከሚያዝያ በኋላ በወሰደቻቸው እርምጃዎች ከፍተኛ የነበረውን የስርጭት መጠን መቀነስ ችላለች። በአሜሪካ ደግሞ የቫይረሱ ስርጭት እንደ አዲስ ካገረሸ በኋላ አሁን ላይ ትንሽ መቀነስ እያሳየ ነው። እስካሁን በአጠቃላይ በቫይረሱ ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ወደ 170 ሺ የተጠጋ ሲሆን ይህም ከዓለም አንድ አምስተኛውን ቁጥር እንድትይዝ አድርጓታል። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕም ''ካልደፈረሰ አይጠራም'' በማለት ነገሮች ከዚህም በላይ ሊከፉ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል። የዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ እንደተነበየው ከሆነ የፊታችን ታህሳስ ወር ላይ በአሜሪካ በቫይረሱ ሳቢያ ብቻ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ295 ሺ በላይ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቋል። ዩኒቨርሲቲው አክሎም ከ90 በመቶ በላይ አሜሪካውያን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ የሚያደርጉ ከሆነ ግን ቁጥሩን ወደ 230 ሺ ዝቅ ማድረግ እንደሚቻል ጠቁሟል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በአሜሪካ ኢኮኖሚ ላይ ከባድ ተጽእኖ አሳድሯል። ከሚያዝያ ጀምሮ ባሉት ሶስት ወራት ብቻ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት 33 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል። በአጠቃላይ በአለም ላይ ያለው ቁጥር ምን ይመስላል? እስካሁን ድረስ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች ቁጥር 21 ሚሊዮን አካባቢ ሲሆን ከ765 ሺ በላይ ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም ሲናገሩ ''በቀላሉ ለመግለጽ ወረርሽኙ ከዚህ በፊት ከነበሩት የከፋና አስቸጋሪ ዓለማቀፍ የጤና እክል ነው ካሉ በኋላ ድርጅቱ እንዲህ አይነት ፈተና ገጥሞት አያውቅም ''ብለዋል። ዳይሬክተሩ አክለውም የቫይረሱ ስርጭት በ188 አገራት እንደደረሰም አስታውሰዋል። እናም በዓለማችን ላይ በበቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የሚገኙት በአሜሪካ፣ ብራዚል እና ሕንድ እንደሆነም ጠቁመዋል። በመላው ዓለም የሚገኙ አገራት መንግሥታት ስርጭቱን ለመቆጣጠር ይበጀናል ያሏቸውን እርምጃዎች በሙሉ በመውሰድ ላይ ናቸው። አንዳንዶች አሁነም የእንቅስቃሴ ገደቡን ማላለት ተገቢ አይደለም ሲሉ፤ ሌሎች ደግሞ ኢኮኖሚያችን ከሚደቅ ጠንቀቅ እያልን የንግድ ተቋማትን መክፈት አለብን እያሉ ነው። የተባበሩት መንግሥታት እንዳስታወቀው በያዝነው ዓመት መጨረሻ አካባቢ በዚሁ ቫይረስ ሳቢያ እስከ 265 ሚሊየን የሚደርሱ የዓለማችን ዜጎች የምግብ እጥረትና ረሀብ ሊያጋጥማቸው ይችላል።
44079205
https://www.bbc.com/amharic/44079205
የደፈራት ባሏን የገደለችው ሱዳናዊት ሞት ተፈረደባት
የደፈራትን ባሏን የገደለችው ሱዳናዊት ላይ ሀሙስ የዋለው ችሎት ሞት ፈርዶባታል።
በኦምዱርማን የሚገኙት ዳኛ በኑራ ሁሴን ላይ የሞት ቅጣቱን የጣሉባት የባሏ ቤተሰቦች የገንዘብ ካሳውን ውድቅ ካደረጉ በኋላ ነው። ይህንንም ተከትሎ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ፍርዱ እንዲቀለበስ ጠይቀዋል። በ16 ዓመቷ ተገዳ ለትዳር የበቃችው ኑራ ለሦስት ዓመታትም ለማምለጥ ሙከራ አድርጋለች። ትምህርቷን ጨርሳ መምህር የመሆን ህልም ነበራት። ጉዳይዋም በመላው ዓለም የሚገኙ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን ቀልብ የሳበ ሲሆን በትዊተር ድረ-ገፅም ፍትህ ለኑራ በሚልም ሰዎች ዜናውን እየተቀባበሉት ነው። ግድያው እንዴት ተፈጠረ? ኑራ አምልጣ አክስቷ ቤት ተጠግታ ትኖር የነበረ ሲሆን ከሦስት ዓመት በኋላም በቤተሰቦቿ ተታልላ ወደ ባሏ እንድትመለስ ተደርጋለች። ከተመለሰች ከስድስት ቀናት በኋላም የባሏ አጎት ልጆች ጠፍረው ይዘዋት ባልየው እንዲደፍራት ተባብረዋል። በተከታዩ ቀንም ይህንንኑ ተግባር ሊፈፅም ባለበት ወቅት ቢላ በማውጣት እስኪሞት ወግታዋለች። አምልጣም ወደ ቤተሰቦቿ ብትሮጥም እነሱ ግን ለፖሊስ አሳልፈው ሰጥተዋታል። የሸሪዓ ፍርድ ቤቱም ባለፈው ወር በመርፌ ተወግታ እንድትገደል ውሳኔ ቢሰጥም ሀሙስ ዕለት በዋለው ችሎት በስቅላት እንድትቀጣ መወሰኑን ሮይተርስ ዘግቧል። ጠበቃዎቿም ይግባኝ ለማለት 15 ቀናት ብቻ እንዳላቸው ተገልጿል። "በሸሪዓ ህግ መሰረት የባሏ ቤተሰቦች የገንዘብ ካሳን ወይም ደግሞ ሞት መጠየቅ ይችላሉ" በማለት የአፍሪካ ወጣቶች እንቅስቃሴ አባል የሆነው የመብት ተሟጋች ባድር ኤልዲን ሳላህ በፍርድ ቤቱ ለተገኘው ለሮይተርስ ዜና ወኪል ተናግሯል። በተጨማሪም "ሞትን ነው የመረጡት፤ የሞት ቅጣቱም ተሰጥቷቸዋል" ብሏል። የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ምን አሉ? የፍርድ ቤቱ ውሳኔ እንዲቀለበስ እየሰሩ ካሉት መካከል "ኢኳሊቲ ናው" (አሁን እኩልነት) ከተሰኘው ድርጅት የመጣችው ያስሚን ኃሰን ውሳኔው እንዳላስደነቃት ተናግራለች። "ሱዳን አባታዊ ሥርዓት እንዲሁም የወንድ የበላይነት የሰፈነበት ሀገር ነው። እንደዚህ ዓይነት ባህሎችም ማህበረሰቡ ውስጥ ጠልቀው የሰረፁ ናቸው" በማለት ተናግራለች። "የ10 ዓመት ህፃናት ሴት ልጆችን ለጋብቻ የሚያስገድድ ባህል ነው። ወንዶች ለሴቶች ጠባቂ የመሆን ሕጋዊ መብት አላቸው" ብላለች። "ኑራን በተመለከተ ደፋር ልጅ ናት። ትምህርቷን ከሁሉ በላይ በማስቀደም በዓለም ላይ ጥሩ ነገሮችን መስራት የምትፈልግ ልጅ ናት። የሚያሳዝነው በማይሆን ወጥመድ ውስጥ ተተብትባ የሥርዓቱ ሰለባ ሆናለች" ብላለች። በሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ የሚሰራው ዓለም አቀፉ ድርጅት አምነስቲ ባወጣው መግለጫ ራሷን ለመከላከል ደፋሪዋን ገደለች ብሎ በሞት መቅጣት ማለት ባለሥልጣናቱ የህፃናት ጋብቻን፣ ጠለፋን እንዲሁም በጋብቻ ላይ ያለ መደፈር ላይ ያላቸውን ጉድለት ማሳያ እነደሆነ ገልጿል። "ኑራ ሁሴን የሥርዓቱ ተጠቂ ናት፤ በእሷ ላይ የተወሰነውም ውሳኔ ከፍተኛ ጭካኔ ነው" በማለት የአምነስቲው ተወካይ ሴይፍ ማጋንጎ ገልፀዋል። "የሱዳን ባለስልጣናት ፍርደ-ገምድል የሆነውን ውሳኔ በማስተካከል ያለችበትን ሁኔታ ግምት ውስጥ የሚያስገባ ፍትሀዊ ውሳኔ ሊወስኑ ይገባል" ብለዋል።
news-54915498
https://www.bbc.com/amharic/news-54915498
ትግራይ ፡ በማይካድራ ስለተፈጸመው ግድያ ማስረጃዎችን እንዳገኘ አምነስቲ ገለጸ
አምነስቲ ኢንተርናሽናል በትግራይ ክልል ውስጥ ሰኞ ምሽት በርካታ ሰዎች የተገደሉበት ጥቃት መፈጸሙን የሚያመለክቱ ማስረጃዎች እንዳገኘ ገለጸ።
ጥቃቱ ተፈጸመ የተባለበት ማይካድራ ከሁመራ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ ትገኛለች የሰብአዊ መብቶች ተቆርቋሪው ድርጅት እንዳለው በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ በምትገኘው ማይካድራ ከተማ ውስጥ በተፈጸመው በዚህ ጥቃት ቁጥራቸው በመቶዎች ሊቆጠሩ የሚችሉ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ በስለት ተገድለዋል። ድርጅቱ ከማይካድራ ከተማ የወጡና በየቦታው ወድቀው የሚታዩ አስከሬኖችን የሚያሳዩ አሰቃቂ ፎቶግራፎችንና ቪዲዮዎችን በመመርመር ምስሎቹ የቅርብ ጊዜና ስፍራውም ማይካድራ መሆኑን ለማረጋገጥ መቻሉን ገልጿል። ጨምሮም በጥቃቱ የተገደሉት ሰዎች ተዋጊዎች ሳይሆኑ ሰላማዊ ሰዎች መሆናቸውን ጠቅሶ፤ ግድያውን ማን እንደፈጸመው ለማረጋገጥ አለመቻሉን አመልክቷል። ነገር ግን ያነጋገራቸው እማኞች ከፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ጋር የሚዋጉትን የህወሓት ታማኝ ኃይሎች ጥቃቱን እንደፈጸሙ ይከሳሉ። በአገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ተፈጸመ የተባለውን ጥቃት ተከትሎ ለወራት በውዝግብ ውስጥ የቆዩት የፌደራል መንግሥት እና የትግራይ ክልል አስተዳደር ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ወደ ግልጽ ጦርነት መግባታቸው ይታወሳል። በአሁኑ ሰዓት ወደ ጦርነት የተሸጋገረው በፌደራል መንግሥቱና በትግራይ ክልል መስተዳደር በኩል የነበረው ቅራኔ እየተባባሰ የመጣው ባለፈው ዓመት ሊካሄድ የታቀደው ምርጫ በኮሮናቫይረስ ስጋት ምክንያት እንደማይካሄድ ከታወቀ በኋላ በትግራይ የተናጠል ምርጫ በመደረጉ ሳቢያ ነው። በማይካድራ ከተማ የተፈጸመውን ግድያ በተመለከተ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያወጡትን መግለጫ ተከትሎ የትግራይ ክልል ባለስልጣናት በድርጊቱ የህወሓት ኃይሎች እጃቸው አለመኖሩን ገልፀው ነበር። "በርካታ ቁጥር ያላቸውና እየተካሄደ ካለው ወታደራዊ ጥቃት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌላቸው ሰላማዊ ሰዎች ላይ ግድያ መፈጸሙን አረጋግጠናል። በትግራይ ውስጥ ያለው የግንኙነት ዘዴ ዝግ በመሆኑ የዚህ አሰቃቂ ድርጊት ትክክለኛ መጠን በጊዜ ሂደት የሚታወቅ ይሆናል" ሲሉ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅና ደቡብ አፍሪካ ዳይሬክትር የሆኑት ዴፕሮስ ሙቼና ተናግረዋል። አምነስቲ ኢንትርናሽናል በማይካድራ ስለተፈጸመው ነገር ለማረጋገጥ ከጥቃቱ በኋላ ወደስፍራው የሄዱ እማኞችን ያነጋገረ ሲሆን በከተማዋ ውስጥ በየቦታው የወደቁ አስከሬኖችንና ከጥቃቱ ቆስለው የተረፉ ሰዎችን እንደተመለከቱ ተናግረዋል። አብዛኞቹ አስከሬኖችም የተገኙት በከተማዋ ማዕከላዊ ክፍል ውስጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሚገኝበት አካባቢና በአቅራቢያ ወደ ምትገኝ የሁመራ ከተማ የሚያመራውን መንገድ ተከትሎ መሆኑን የአይን እማኞችና የተገኙት ምስሎች አመልክተዋል። አምነስቲ ኢንትርናሽናል በመግለጫው ላይ ግድያውን ማን እንደፈጸመው ለማረጋገጥ ባይችልም፤ ያነጋገራቸው የአይን እማኞች ግን በፌደራሉ ሠራዊት ሽንፈት የገጠማቸው "ለህወሓት ታማኝ የሆኑ ኃይሎች ለግድያው ተጠያቂ እንደሆኑ ይናገራሉ" ብሏል። "የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ይህንን ግልጽ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በጥልቀት፣ በገለልተኝነትና በግልጽ መርምረው ተጠያቂዎቹን ለፍርድ ማቅረብ አለባቸው" ሲሉ የአምነስቲ ዳይሬክተር ዲፕሮስ ሙቼና ጠይቀዋል። ጨምረውም "የህወሓት ባለስልጣናትና አዛዦችም በስራቸው ላሉ ኃይሎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ሆን ተብሎ የሚፈጸም ጥቃት ተቀባይነት የሌለውና የጦር ወንጀል መሆኑን ግልጽ ማድረግ አለባቸው። በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም ወገኖች በሚያካሂዱት ዘመቻ ዓለም አቀፍ ሕግጋትን ማክበር ይጠበቅባቸዋል። የሰላማዊ ሰዎች ደኅንነትና ጥበቃ ቀዳሚ ጉዳይ መሆን አለበት" ብለዋል። ከሳምንት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በትግራይ ውስጥ በሚገኘው የአገሪቱ ሠራዊት ላይ ጥቃት መፈጸሙን በመግለጽ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ትዕዛዝ ከሰጡ በኋላ በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ውጊያ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል።
news-55112951
https://www.bbc.com/amharic/news-55112951
ትግራይ ፡ የኢትዮጵያ ሠራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ገለጸ
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በትግራይ ክልል የሚገኙ በርካታ ከተሞችን እየተቆጣጠረ ወደ መቀለ እየቀረበ መሆኑን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት ሠራዊቱ በትግራይ ክልል በሚገኙና በህወሓት በሚመሩት ኃይሎች ላይ ዘመቻ ከከፈተ ሳምንታት የተቆጠሩ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ኢላማውን መቀለ ላይ ማድረጉ ተነግሯል። የፌደራል ሠራዊቱ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት ሌተናል ጄኔራል ሀሰን ኢብራሂም እንደተናገሩት መንግሥት የመጨረሻ ምዕራፍ ያለው ዘመቻ ከተጀመረ በኋላ በመቀለ አቅራቢያ የሚገኙት ሃውዜን፣ አል ነጃሺ፣ አዲቀየህ፣ ማይመሳኖን፣ ውቅሮና ሌሎች አካባቢዎችን መቆጣጠር እንደቻሉ ገልጸዋል። እነዚህ አካባቢዎች በአገሪቱ ሠራዊት ቁጥጥር ስር እንደገቡ የተነገረው የህወሓት አመራሮችና የክልሉ ልዩ ኃይል አባላት እጃቸውን እንዲሰጡ የተቀመጠው የሦስት ቀናት ገደብ ማብቃቱን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ሐሙስ ዕለት ሠራዊቱ ዘመቻውን እንዲጀምር ካዘዙ በኋላ ነው። ሌተናል ጄኔራል ሀሰን ኢብራሂም ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን እንደገለጹት ሠራዊቱ በአድዋ፣ በአዲግራትና በራያ በኩል ባሉ የተለያዩ ግንባሮች ከሐመስ ጀምሮ ባካሄደው ዘመቻ በርካታ አካባቢዎችን መቆጣጠሩን አመልክተው፤ መቀለ አቅራቢያ ያለውን መሰቦ ተራራን በመያዝ ወደ ከተማዋ እንደሚያመሩ ገልጸዋል። ወታደራዊ ግጭቱ ከተቀሰቀሰ ሦስት ሳምንት ያለፈው ሲሆን የኢትዮጵያ ሠራዊት በትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎችን በመቆጣጠር በማዕከላዊ ምሥራቅ የክልሉ ክፍል ውስጥ የምትገኘውን ዋና ከተማዋ መቀለን ለመያዝ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ወታደራዊ ባለስልጣኑ አመልክተዋል። በትግራይ ክልል የሚገኙት የስልክ፣ የሞባይል እና የኢንተርኔት ግንኙነቶች በመቋረጣቸው ዝርዝር መረጃዎችን ለማግኘት ከባድ ቢሆንም፤ የተለያዩ ተቋማት እንደሚሉት ከሆነ በግጭቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሳይሞቱ እንዳልቀረ የተገመተ ሲሆን በአስር ሺዎች ደግሞ ተፈናቅለው ወደ ጎረቤት ሱዳን ገብተዋል። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አርብ ዕለት ከአፍሪካ የሰላም መልዕክተኞች ጋር ባደረጉት ውይይት በአካባቢው ያሉ ሰላማዊ ሰዎች እንደሚጠበቁ ተናግረዋል። እየተካሄደ ያለው ወታደራዊ ግጭት አብቅቶ በውይይት ወደ መቋጫ እንዲያገኝ ማድረግን በተመለከተ የተባለ ነገር የለም። የኢትዮጵያ መግግሥት ግን ከህወሓት አመራሮች ጋር ምንም አይነት ውይይት እንደማይኖር በተደጋጋሚ አስታውቋል። ወታደራዊ ዘመቻው ወደ መቀለ እተቃረበ ባለበት በአሁኑ ጊዜ በከተማዋ ነዋሪዎች እንዳይጎዱ የተለያዩ አካላት ማሳሰባቸውን ተከትሎ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ 500 ሺህ በላይ ሰዎች በሚኖሩባት መቀለ ነዋሪዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ሠራዊቱ አስፈላጊውን ሁሉ ጥንቃቄ እንደሚያደርግ ገልጸ እንደነበር ይታወሳል። መቀለን የሚቆጣጠረው የህወሓት ኃይል አመራሮች እጃቸውን እንደማይሰጡና ከመንግሥት በኩል የሚመጣውን ጥቃት እንደሚጋፈጡ ገልጸዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በበኩሉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በመቀለን የሚያጠቃ ከሆነ የጦር ወንጀሎች ሊያጋጥሙ ይችላሉ ሲል ስጋቱን አስቀምጧል። በተጨማሪም የሰብዓዊ እርዳታ ለሚፈልጉ በክልሉ ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች ለማድረስ ምቹ ሁኔታ አለመኖሩንም ድርጅቱን እንዳሳሰበው አመልክቷል። ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ሐሙስ ዕለት እንዳሉት በመንግሥት ቁጥጥር በሚገኙ አካባቢዎች "ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል መንገድ እንደሚከፈት እና ከተባበሩት መንግሥታት ተቋማት ጋር ለመስራት፣ ሰላማዊ ዜጎችንና ድጋፍ የሚፈልጉትን ለመጠበቅ" ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል። በፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልልን በሚያስተዳድረው ህወሓት መካከል ለረጅም ጊዜ የቆየው አለመግባባት ባለፈው ዓመት ሊካሄድ የነበረው አገራዊ ምርጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽን ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ መሸጋገሩን ተከትሎ የበለጠ መካረሩ ይታወሳል። በዚህም ባለፈው ዓመት ማብቂያ ላይ በትግራይ ክልል የተካሄደው የተናጠል ምርጫን የፌደራል መንግሥቱ ተቀባይነት የሌለውና ሕገ ወጥ በማለት ከክልሉ አስተዳደር ጋር የነበረውን የቀጥታ ግንኙነት አቋርጦ ነበር። ይህንንመ ተከትሎ ጥቅም 23/2013 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በትግራይ ክልል በነበረው የፌደራሉ ሠራዊት የሠሜን ዕዝ ላይ በህወሓት ኃይሎች ጥቃት መፈጸሙን ይፋ ካደረጉ በኋላ የፌደራሉ ሠራዊት በትግራይ ክልል ኃይሎች ላእ እርምጃ መውሰድ ጀመሩ። ይህ ወታደራዊ ግጭት ሦሰት ሳምንት ያለፈው ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊቱት ወደ መቀለ ለመግባት እየተዘጋጀ መሆኑ ተነግሯል።
56977451
https://www.bbc.com/amharic/56977451
የትግራዩ ግጭት 5ሺህ ሕጻናትን ከወላጆቻቸው ለይቷል ተባለ
የተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት አድን ድርጅት በትግራዩ ግጭት ምክንያት ወደ 5ሺህ የሚጠጉ ሕጻናት ከወላጆቻቸው ጋር ተለያይተዋል አለ።
ሕጻናት አድን ድርጅቱ እንዳለው ከወላጆቻቸው የተለዩ ሕጻናት በስደተኛ እና ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ይገኛሉ። ሴቭ ዘ ቺልድረን እንደሚለው ከወላጆቻቸው የተለዩት ሕጻናት ለረሃብ፣ ለአካላዊ እና ጾታዊ ጥቃቶች ተጋላጭ ናቸው። ድርጅቱ የሰብዓዊ እርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች ለበርካታ የክልሉ ስፍራዎች እርዳታ ማቅረብ ባለመቻላቸው፤ ሕጻናቱ ያለማንም ድጋፍ እራሳቸውን ለመርዳት ጥረት ያደርጋሉ ብሏል። ከስድስት ወራት በላይ በቆየው የትግራይ ጦርነት ከ1.7 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ቀያቸውን ጥለው ተሰደዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ግጭቱ በክልሉ የከፋ የሰብዓዊ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል ሲል ያስጠነቅቃል። ተመድ ሕጻናት፣ የሚያጠቡ እና ነብሰ ጡር እናቶች ከፍተኛ የሆነ የምግብ እጥረት እያጋጠማቸው ስለመሆኑ የሚያሳዩ መረጃዎች አሉ ይላል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የሆነው አምነስቲ ኢንተርናሽናል፤ የአፍሪካና የተቀረው ዓለም መሪዎች በትግራይ ስላለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ድምፃቸውን የበለጠ እንዲያሰሙ ጥሪ አቅርቧል። ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ለስድስት ወራት በዘለቀው የትግራይ ጦርነት በርካታ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተፈጽመዋል ብሏል። አምነስቲ፤ 'ኦፕን ሶርስ' የተሰኘ የምርመራ መንገድ እንዲሁም የሳተላይት ምስሎች ትንተና እና የቪድዮ ምስሎች ማስረጃዎችን በመጠቀም የተለያዩ ጥሰቶችን እንደመዘገበ በመግለጫው አሳውቋል።
44355106
https://www.bbc.com/amharic/44355106
ሃይ ባይ ያጣው ብሔር ተኮር መፈናቀል
በሰሜን ወሎ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙና ከምዕራብ ኦሮሚያ የተፈናቀሉ የአማራ ብሄር ተወላጆች ዘላቂ መፍትሄ እንሻለን ይላሉ።
በራያና ቆቦ፣ ጉባ ላፍቶ እንዲሁም ሀብሩ አካባቢዎች በከተሞች እና በገጠር ቀበሌዎች የተሰባሰቡት ተፈናቃዮች በመቶዎቹ የሚቆጠሩ እንደሆነ ሲዘገብ ቢቆይም፤ ከትናንት በስትያ የአማራ ክልል መገናኛ ብዙሃን ድርጅት አንድ ሺህ አራት መቶ እንደሚጠጉ አትቷል። ቁጥሩ ከዚህም እየጨመረ ሊሄድ እንደሚችል ቢቢሲ ያናገራቸው ተፈናቃዮች ይገልፃሉ። የ42 ዓመቱ አቶ ተበጀ ጉበና ገና የስድስት ወይንም የሰባት ዓመት ልጅ ሳሉ በወቅቱ በሰሜን ኢትዮጵያ ተከሰቶ የነበረውን ድርቅ እና ረሃብ ተከትሎ በወቅቱ መንግሥት የሰፈራ መርኃ ግብር አማካይነት ከደምቢ ዶሎ አስራ አምስት ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው ገላን መቲ የገጠር ቀበሌ መኖር እንደጀመሩ ይገልፃሉ። ከሃያ ሰባት ዓመት በፊት የመንግሥት ለውጥ በነበረበት ጊዜ ለተወሰነ ጊዜ ያህል ወደ ትውልድ ቀያቸው ራያ ቆቦ ከመመለሳቸው በስተቀር ህይወታቸውን በሙሉ በዚያው ሲመሩ እንደቆዩ፤ ባለፉት ሦስት ዓመታት ግን የ"ውጡልን" ድምፆችን መበርታትን ተከትሎ በስጋት ሲናጡ መክረማቸውንም ያስረዳሉ። ስጋቱን ተግ የሚያደርግ ነገር አላገኘሁም የሚሉት አቶ ተበጀ የግብርና ሥራቸውን ትተው ወደቆቦ ከተማ ያመሩት ከስድስት ወራት በፊት እንደሆነ ይናገራሉ። "ታላቅ እና ታናሽ ወንድሞቼ ግን በዚህ ሦስት ሳምንት ውስጥ ነው የመጡት። አባቴ እና የእህቴ ባል እዚያው ናቸው። ለመምጣት እየተዘጋጁ ናቸው" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "እህቴም በእርግጥ ልጆቿን ይዛ መጥታለች።" የራያ እና ቆቦ ወረዳ የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ምላሽ ባለሞያ የሆኑት አቶ ሞላ ደርቤ ካለፈው የካቲት ወር አንስቶ የተፈናቃዮቹ ቁጥር እየጨመረ መሄዱን እና ይሄም መስሪያ ቤታቸው በቂ እርዳታ እንዳይሰጥ እየተፈታተነው እንደሆነ ይገልፃሉ። "አሁን ለተፈናቃዮቹ እየተደረገ ያለው ድጋፍ ብዙም አይደለም" የሚሉት አቶ ሞላ በወረዳቸው ብቻ ያሉ ከምዕራብ ኦሮሚያ የመጡ ተፈናቃዮች ቁጥር ከ510 በላይ መድረሱን ይናገራሉ። ከጥቂት ወራት በፊት ተፈናቃዮቹ 270 ግድም ብቻ የነበሩ ሲሆን፤ ይህንንም ቁጥር ለዞን መስተዳድር በማሳወቅ በቤተሰብ 45 ኪሎ ግራም እህል እና አልባሳትን ሲለግሱ ነበር አቶ ሞላ እንደሚሉት። የተፈናቃዮቹ መበራከት እና የሚሰጠውም እርዳታ በቂ ያለመሆን እገዛ ለማድረግ እንድንንቀሳቀስ ገፊ ምክንያት ሆኖናል የሚሉት ደግሞ በወሎ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት አቶ ያሲን መሃመድ ናቸው። አቶ ያሲን ከሌሎች ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን ለተፈናቃዮቹ ገንዘብ የሚያሰባስብ ቡድን ያቋቋሙ ሲሆን ይሄውም ቡድን የባንክ ሂሳብ ከፍቶ የዜጎችን እና የተቋማትን ልግስና በመጠባበቅ ላይ ይገኛል። የተፈናቃዮቹን የዕድሜ እና የፆታ ስብጥር ፈትሸናል የሚሉት አቶ ያሲን እንደሚያስረዱት "ብቻውን ከሆነ እና ሌላ ምንም ቤተሰብ ከሌለው ሰው አንስቶ ስምንት አባላት ያሉትን ቤተሰብ እስካፈራ ሰው ድረስ ተፈናቅሏል፤ አዛውንቶችም አሉበት፣ ሴቶችም አሉበት፣ ትምህርታቸውን ያቋረጡ ህፃናት አሉ።" በወርሃ ጥቅምት ከመቻራ፤ ደምቢዶሎ ስፈናቀል የስምንት ወር ነብሰ ጡር ነበርኩ ስትል ለቢቢሲ የተናገረችው ደግሞ የሰላሳ ዓመቷ ወይዘሮ ፈንታነሽ ሁሴን ናት። "በሰዓቱ ችግር ነበረ፤ ውጡ ሂዱ፤ አገራችንን ልቀቁልን ነበር የሚሉት" የምትለው ፈንታነሽ ያለፉት በርካታ ወራት በየዘመድ ቤቱ በመጠለል እንዳሳለፈቻቸውና ቋሚ መፍትሄ የምታገኝበትን ቀን እንደምትናፍቅ ትገልፃለች። በአነስተኛ ንግድ እና ግብርና ሥራ ላይ ተሰማርታ ለበርካታ ዓመታት ወደኖረችበት ቦታ መመለስ የምትፈልግ አትመስልም፤ "መንግሥት ማረፊያ ቦታ እና መንቃሰቀሻ ገንዘብ" ቢሰጣት ህይወቷን በቆቦ ከተማ እንደ አዲስ ለመገንባት ትፈልጋለች። ሌላኛው ተፈናቃይ አቶ ተበጀም ወደቀደመ ህይወታቸው የመመለስ ጠንካራ ፍላጎት እንደሌላቸው ነው የሚናገሩት፤ የአማራ ክልል መንግሥት "ስለእኛ ብዙ ይቆረቆራል ብዬ ስለማላስብም፤ እርዳታ ለመቀበል እንኳ ሄጄ አልተመዘገብኩም" ይላሉ። ነገር ግን የቆቦ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ተሻለ ግደይ አስተዳደሩ ለተፈናቃዮቹ ዘላቂ መፍትሄ የሚሰጥበት አግባብ ላይ እየመከረ መሆኑን ይናገራሉ። "ሁለት አማራጮች ናቸው ያሉት፤ የመጀመሪያው ወደነበሩበት አካባቢ እንዲመለሱ በመንግሥት የተጀመረ እንቅስቃሴ አለ። የሚመለሱት ይመለሳሉ፤ የማይመለሱት ደግሞ እዚህ በዘላቂነት የሚቋቋሙበትን ሁኔታ እያመቻቸን ነው" ይላሉ አቶ ተሻለ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ። መመለስ ወይንም ያለመመለስ ግን የተፈናቃዮቹ ምርጫ መሆኑን አክለው ያስረዳሉ። "ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል፤ በአካባቢውም ሰላም እየሰፈነ ስለሆነ ብትመለሱ በነበራችሁበት አካባቢ መስራት ትችላላችሁ የሚል አማራጭ ይቀርብላቸዋል፤ ከዚህ በኋላ በሰዎቹ ፍላጎት ላይ ነው የሚወሰው። ፍላጎት ካላቸው ይሄዳሉ፤ ከሌላቸው ግን በዘላቂነት እዚሁ የሚቋቋሙበት ሁኔታ ላይ እንሰራለን።" የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ምላሽ ባለሞያ የሆኑት አቶ ሞላ መመለስ ለሚፈልጉ ተፈናቃዮች ሁኔታዎችን የሚመቻች ቡድን ወደደምቢዶሎ አካባቢ መንቀሳቀሱን ይናገራሉ። ስለጉዳዩ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ስለተፈናቃዮቹ የአካባቢው የወረዳ እና የዞን አስተዳደሮች መረጃ እንዳልደረሳቸው፤ ይሁንና ችግር ደረሰብን የሚሉ ዜጎችን ለማስተናግድ የክልሉ መንግሥት ቁርጠኛ መሆኑን ይገልፃሉ። "ችግሩ መፈጠሩን ሪፖርት አልተደረገም። ከ1977 ዓ.ም አንስቶ ሰዎች ተዋደው የሚኖርበት ቦታ ነው" የሚሉት ዶክተር ነገሪ አክለውም "ቢቻል ወረዳ ላይ ወይም ዞን ላይ መጨረስ ነበረባቸው። ካለሆነ ግን የእኛ ቢሮ እነርሱን ለማገልገል ክፍት ነው። አንድም ሰው ከክልላችን እንዲፈናቀል አንፈልግ" ሲሉ ለቢቢሲ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
news-47729876
https://www.bbc.com/amharic/news-47729876
የወንድ የእርግዝና መከላከያ፤ ለምን እስካሁን ዘገየ?
የወንዶች የእርግዝና መከላከያ የመጀመሪያ የሙከራ ሂደቱን ማለፉን ባለሙያዎች ተናገሩ። በየቀኑ የሚወሰደው የመከላከያ አይነት ወንዶች የዘር ፈሳሽ እንዳያመነጩ የሚያደርግ ነው።
ይህም አሁን ላይ ጥቅም ላይ እየዋሉ ካሉት ኮንዶምና ቫዝክቶሚ በተጨማሪ ሌላ አማራጭ ነው ተብሏል። ነገር ግን ሃኪሞች እንደሚሉት ምርቱን በተሟላ ሁኔታ አጠናቅቆ ለገበያ ለማቅረብ ምናልባትም አስርት ዓመታትን ሊጠይቅ ይችላል። ለምን እስካሁን አልነበረም? የሴቶች የእርግዝና መከላከያ የተጀመረው ከ50 ዓመታት በፊት በሀገረ እንግሊዝ ነበር። ምነው ታዲያ የወንዶችን የእርግዝና መከላከያ ለመስራት ለምን ይህን ያህል ጊዜ ወሰደ? የሚለው ዋናው ጥያቄ ነው። አንዳንዶቹ ይህ ያልሆነው ምናልባትም ወንዶች ስለማይፈልጉ ነው የሚሉ ቢኖሩም በሌላ በኩል ደግሞ ስለጉዳዩ የተጠየቁ ወንዶች ቢኖር ኖሮ መከላከያውን እንጠቀም ነበር ብለዋል። • ለወሲብ ትክክለኛው ዕድሜ የቱ ነው? • በርካቶች ከምጥ ይልቅ በቀዶ ህክምና መውለድን እየመረጡ ነው ሌላኛው ነገር ደግሞ ሴቶች ራሳቸው ወንድ የእርግዝና መከላከያ ወስጃለሁ ቢላቸው ያምኑ ይሆን? ወይ የሚለውም ነው። ሩስኪን ዪኒቨርሲቲ በ2011 እንግሊዝ ውስጥ ባደረገው ጥናት መሰረት ከ134 ሴቶች 70 የሚሆኑት ወንድ የፍቅር ጓደኞቻቸው የእርግዝና መከላከያ መውሰዳቸውን ይዘነጋሉ ብለው ይሰጋሉ። የወንዶችን የእርግዝና መከላከያ በወሲባዊ ግንኙነት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንዳይኖረው መጠንቀቅ ያስፈልግ ስለነበር ነው ጉዳዩ ጊዜ የወሰደው የሚል አስተያየት የሰነዘሩም አሉ። የወንድ የዘር ፈሳሽ ማመንጨትን በተመለከተ መካን ያልሆነ ወንድ በሆርሞኖች አማካኝነት እየታገዘ በተከታታይ የዘር ፈሳሽ ያመነጫል። የእርግዝና መከላከያ ይህን ሂደት ሊያዛባ ይችላል ውይ? የሚል ጥያቄ ተነስቶ ነበር። ተመራማሪዎች እንደሚሉት ግን አሁን በኤልኤ ባዮሜድ እና በዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲዎች የተደረገው ጥናት ውጤታማ ነው። በ40 ወንዶች ላይ የመጀመሪያ ሙከራ ተደርጎ ያለችግር ውጤታማ መሆኑን ኒውኦርሊንስ ውስጥ በተካሄደው ውይይት ላይ ተገልጿል። • «የወሊድ መቆጣጠሪያን ወዲያ በሉት»፦ ፕሬዚዳንት ማጉፉሊ ከሙከራው በኋላ የተወሰኑ የጎንዮሽ ጉዳቶች ተገኝተዋል። የእርግዝና መከላከያን ከወሰዱት ወንዶች መካከል አምስቱ የወሲብ አቅማቸው ቀንሷል፤ ሁለቱ ደግሞ የብልት መቆም ችግር አጋጥሟቸዋል። በአጠቃላይ ግን የወሲብ ተነሳሽነት ላይ ችግር አልተገኘም። የጥናቱ መሪ ክሪስቲና ዋንግና ጓደኞቿ "ሙከራችን የሚያሳየው ሁለቱን ሆርሞኖች አንድ ሥራ ላይ እንዲተባበሩ ማድረግን ነው። የዘር ፈሳሽን ማመንጨት ይቀንሳል፤ በአንጻሩ ለወሲብ ያለው ተነሳሽነት እንዳለ ይቀጥላል" ብለዋል። የስሜት መዘበራረቅን በተመለከተ ሌሎች ሳይንቲስቶች በየወሩ የሚወሰድ የእርግዝና መከላከያ በማዘጋጀት ላይ ነበሩ። ነገር ግን የመጀመሪያውን ዙር ካጠናቀቁ በኋላ ሁለተኛውን ሙከራ አቁመዋል። ምክንያታቸው ደግሞ የስሜት መዘበራረቅና ድብርትን ያመጣል የሚል ነው። በጥናታቸውም የዘር ፈሳሽን እንቅስቃሴ የሚገድብ ምናልባትም ከወንድ ብልት እንዳይወጣም ሊያደርግ ይችላል ብለዋል። እናም ቫዛልጀል (vasalgel) የተሰኘ በሁለቱ የወንድ የዘር ፍሬዎች የሚወጋና የዘር ፈሳሽን ከግራና ቀኝ ፍሬዎች ወደ ብልት የሚወስድ ህክምና ተጀምሯል። ነገር ግን እስካሁን ትግበራው በእንስሳት ላይ ብቻ የተገደበ ቢሆንም ውጤታማ በመሆኑ ተመራማሪዎች ሰው ላይ ለመጀመር ተዘጋጅተዋል። የገበያ ሁኔታን በተመለከተ ፕሮፌሰር ሪቻርድ አንደርሰን ይህን ምርምር በእንግሊዝ ከሚያደርጉት መካከል አንዱ ናቸው።እሳቸው እንደሚሉት ፋርማሲዎች ይህን የእርግዝና መከላከያ ዘዴ ለመሸጥ ፍላጎታቸው አነስተኛ ነው ምክንያታቸው ደግሞ ወንዶችና ሴት ጓደኞቻቸው በዚህ ጉዳይ ላይ እምነት የላቸውም ሚል ነው። "ያለውን የገበያ ሁኔታ በደንብ ለማሳመን የተደረገ ጥረት ያለ አይመስለኝም" ይላሉ ፕሮፌሰሩ። ፕሮፌሰሩ እንደሚሉት ተመራማሪዎቹ በእርዳታና በምርምር በጀት ላይ የተንጠለጠለ ሥራ ነው የሚሰሩት። ምክንያቱም በዘርፉ ያለው የኢንቨስትመንት ተሳትፎ አነስተኛ በመሆኑ ነው። • ሞባይል ለኢትዮጵያ እናቶችና ህፃናት ጤና በሼፊልድ ዩኒቨርሲቲ የአንድሮሎጂ ፕሮፌሰር የሆኑት አለን ፒሴይ "እስካሁን የወንዶች የእርግዝና መከላከያ በደንብ አልተሰራበትም ስለዚህ አዳዲስ ሥራዎችን መስራት ይኖርብናል" ብለዋል። ቁልፉ ጥያቄ ፋርማሲዎች በበቂ ሁኔታ ያከፋፍሉታል ወይ? የሚለው ነው ይላሉ ፕሮፌሰሩ። እሳቸው እንደሚሉት እስካሁን ፋርማሲዎች ለዚህ ጉዳይ ፍላጎት አያሳዩም ፤ ትኩረታቸውም ለቢዝነሳቸው ነው።
news-56697408
https://www.bbc.com/amharic/news-56697408
አሜሪካ በሰባት የቻይና የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ላይ እገዳ ጣለች
በብቃታቸው የላቁ ኮምፒውተሮችን ለቻይና ጦር ሠራዊት እየገነቡ ነው ያለቻቸውን ሰባት የቻይና የቴክኖሎጂ ተቋማትን ጥቁር መዝገቧ ውስጥ እንዳስገባቻቸው አሜሪካ አስታወቀች።
ይህ እርምጃ የጆ ባይደን አስተዳደር ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ ቻይና የአሜሪካንን የረቀቁ ቴክኖሎጂዎችን እንዳታገኝ የሚያደርግ የመጀመሪያው ውሳኔ ነው ተብሏል። በዚህም መሠረት ሦስት ኩባንያዎችና አራት የቻይና ብሔራዊ የላቁ የኮምፒዩተሮች ምርምር ማዕከል ቅርንጫፎች ናቸው ከዚህ በፊት ከነበራት ጥቁር መዝገብ ውስጥ ያካተተቻቸው። ይህ እርምጃም የአሜሪካ ኩባንያዎች የትኛውንም አይነት ቴክኖሎጂ ለእነዚህ የቻይና ተቋማት በሚያቀርቡበት ጊዜ ከአገሪቱ መንግሥት ተገቢውን ፈቃድ እንዲያገኙ ያስገድዳል። የአሜሪካ የንግድ መሥሪያ ቤት እንዳለው እነዚህ ተቋማት በቻይና ጦር ሠራዊት ሥር ላሉ ክፍሎች የመጠቁ ኮምፒውተሮችን (ሱፐር ኮምፒውተርስ) በመገንባት ሥራ ውስጥ የሚሳተፉና የጅምላ እልቂትን ሊያስከትሉ የሚችሉ ጦር መሳሪያዎችን ለመስራት በሚካሄዱ ፕሮግራሞች ውስጥም ያሉ ናቸው። በአሜሪካ ጥቁር መዝገብ ውስጥ እንዲገቡ የተደረጉት ድርጅቶች ቻይና እያካሄደችው ባለው የላቁ ኮምፒውተሮች ግንባታ ውስጥ ቀዳሚ ሚና ያላቸው ሲሆን በተጨማም አገሪቱ በኮምፒውተር "ቺፕ" ምርት እራሷን እንድትችል ጥረት የሚያደርጉ ናቸው ተብሏል። የአሜሪካ የንግድ ሚኒስትር ጊና ሬይሞንዶ እንዳሉት አዲሱ የባይደን አስተዳደር "ቻይና አለመረጋጋትን ሊያስከትል በሚችል ሁኔታ ወታደራዊ ተቋሞቿን የማዘመን ሥራዋን ለመከላከል የአሜሪካንን ቴክኖሎጂ እንዳትጠቀም ታደርጋለች" ብለዋል። የቀድሞው የትራም አስተዳደር የስልክ አምራቹን ሁዋዌን ጨምሮ የአሜሪካንን ቴክኖሎጂ ለወታደራዊ ግልጋሎት እያዋሉ ነው ብሎ የጠረጠራቸውን በደርዘኖች የሚቆጠሩ ተቋማትን ለይቶ ነበር። በአሁኑ የጆ ባይደን ውሳኔ ጥቁር መዝገብ ውስጥ እንዲገቡ የተደረጉት የቻይና ተቋማት በኮምፒውተር ቴክኖሎጂው ዘርፍ በጣም ተፈላጊ የሆኑ የቴክኖሎጂ ግብአቶችን ከአሜሪካ ለመግዛት ሲፈልጉ ፈቃድ ማግኘት ይጠበቅባቸዋል። ይህ እግድ በዋናነት መቀመጫቸውን አሜሪካ ያደረጉ ተቋማት ምርቶቻቸውንና አገልግሎታቸውን ጥቁሩ መዝገብ ውስጥ ለተካተቱት የቻይና ድርጅቶች እንዳይሸጡ የሚያግድ ሲሆን፤ ነገር ግን በሌላ አገር ያሉ የአሜሪካ ተቋማት ይህ ገደብ አይመለከታቸውም ተብሏል።
45257183
https://www.bbc.com/amharic/45257183
ካለሁበት 45፡አካል ጉዳተኝነቱ ከኮንተምፐረሪ ደንስ ባለሙያነት ያላገደው አንዱዓለም
ስሜ አንዱዓለም ከበደ ይባላል ብዙ ሰዎች በቅጽል ስሜ 'ሞንዶ' በሚለው ያውቁኛል። አሁን የምኖርባትን ከተማ ሉድቪግስሃፍን በምትባለው የጀርመን ከተማ ነው። አዲስ ለሆነ ሰው የምኖርባታ ከተማ ስም ለማስታውስም ሆነ ለመጥራት ተንሸ ከበድ ትላለች።
በግል ምክንያት ወደ ጀርመን ከመጣሁ በኋላ ጥገኝነት ጠይቄ ነው እዚሁ ነዋሪ ልሆን ችያለው። ወደዚህ ከመጣሁ ዓመት ሊሞላኝ ነው። ጀርመን ሃገር አንድ ሰው ጥገኝነት በሚጠይቅበት ወቅት ሁኔታዎች ከተመቻቹ በኋላ ጥገኝነት ጠያቂው በመረጠው ከተማ እንዲኖር ይደረጋል። እኔም በዚህ ከተማ እንድኖር ተደርጊያለሁ። • ካለሁበት 42 : ''የጠበቀ ቤተሰባዊ ፍቅራቸውና ትስስራቸው ከኢትዮጵያውያን ጋር ያመሳስላቸዋል'' • ካለሁበት 43፡" የናይሮቢ ነዋሪ በጣም የዋህ ህዝብ ነው" ለእኔ ጀርመንን ከኢትዮጵያ ማነፃፀር በጣም ይከብደኛል ምክንያቱም ሁለቱን ሃገራት የሚያመሳስሏቸውን ነገሮች ማግኘት ያቅተኛል። ጀርመን በጣም ፀጥ ያለች ሃገር ናት። በተለይ ከሌሎች ሃገራት ጋር ሲነፃፀር ሽብርቅርቅ ያለ ሃገር አይደለም፣ ዝም ያለ ነው። የአየር ሁኔታው ግን በጣም የተለየ ነው። ብርዱም ሆነ ሙቀቱ ሁልጊዜ ጽንፍ ነው። ወይ በጣም ይበርዳል ወይ በጣም ይሞቃል። ስለዚህ ለእኔ አዲስ አበባ ትሻለኛለች ከጽዳቷ በቀር። በተረፈ ግን የሕዝብ ማመላለሻ አማሮጮቹ በተለይ ለእኔ፣ አካል ጉዳተኛ በመሆኔ እዚህ በጣም አመቺ ነው። ከዚያ የበለጠ ግን ብዙ የሚመሳሰሉም ሆነ የሚላያዩ ነገሮችን አላይም። ከኢትዮጵያ ከወጣሁ ወዲህ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የሆነ ቢሾፍቱ የሚባል አውቶቡስ አለ ተብያለሁ። እንደውም በማህበራዊ ድረ-ገፆች ላይ አያቸዋለሁ፤ እንደ አጋጣሚ ሆኖ ደግሞ እሱን የሚመስል ባስ እዚህ ሉድቪግስሃፍን አለ። የዚህ ሃገር አውቶቡሶች ደግሞ ለየት ያሉ ናቸው። ሹፌሮቹ አካል ጉደተኛ ሰዎች፣ አዛውንቶችና ሕፃናት ወደ አውቶብሱ ሳይቸገሩ በቀላሉ እንዲገቡ የአውቶብሱን በር ዝቅ ያደርጉላቸዋል። አዲስ አበባ በጣም ትናፍቀኛለች። አንድ ሃገር ጠረን አለው። የሃገሬ ጠረን በጣም ይናፍቀኛል። ሰኳር ስላለብኝ ብዙ ጊዜ የምመገባቸውን ምግቦች በጣም እጠነቀቃለሁ፣ 'ጠየም' ያሉ ነገሮችን ነው እየመረጥኩ የምመገበው። ብዙውን ጊዜ ፓስታ፣ሩዝ እና ኩስኩስ መመገብ እመርጣለሁ። ወደ ከተማ ለተለያዩ ጉዳዮች በወጣሁ ቁጥር 'ኬባብ' ወይም 'ዶነር' የሚባለውን ምግብ በምላት ያስደስተኛል። ዶነር የበሰለ ስጋ ቂጣ በሚመስል ወፈር ያለ ዳቦ ውስጥ ሆኖ የሚቀርብ ምግብ ነው። እንደውም የፊታችን ቅዳሜ ወጣ ስለምል እናንተንም እጋብዛችኋለሁ። 'ኬባብ' ወይም 'ዶነር' እዚህ ከመጣሁ በጣም ያስደነቀኝ ነገር ሰዎች የዘመናዊ ሙዚቃ ተወዛዋዥ መኖኔን ሲያውቁ ሰዎች ያላቸው ሁናቴ ነው። እኛ ብዙ ጊዜ ለነጮች የምንሰጣቸው ግምት ትልቅ ነው ባይ ነኝ። ይህን የምለው ደግሞ ከእራሴ ሁኔታ ጋር በማነጻጸር ነው ''እንዴት ልትደንስ ትችላለህ'' ወይም '' አካል ጉዳተኛ ሆነህ እንዴት ልትደንስ ቻልክ?'' ይሉኛል እንደውም አንዳንዴ የመጠራጠር ምልክት በፊታቸው ላይ አነባለሁኝ። ያንኑ ያህል ደግሞ ግራ እስኪገባኝ ''ሥራ ለምንድነው የማትሠራው'' የሚመሳስሉ ጥያቄዎችም ይቀርቡልኛል ከእነአካቴው አካል ጉዳተኛ መሆኔን እየረሱ ይመስል። ይህ ደግሞ ጠንካራ ያደርጋል። • "አካል ጉዳተኛ መሆኔ ጥሩ ደረጃ እንድደርስ አድርጎኛል" • የኢትዩጵያውያን አካል ጉዳተኞች ፈተናዎች ምን ድረስ? ከቤቴ ሆኜ በመስኮቴ በኩል የሚታዩ በጣም የሚያስደስቱኝ ዛፎች አሉ። ዛፎቹ የሚያስገርም ግርማ ሞገስ አላችው። እነሱን ማየት በጣም ያስደስተኛል። ዛፎቹን በክረምት ወቅት በደንእበ አድርገው ይከረክሟቸዋል። በበጋ ደግሞ ከታች በምስሉ ላይ እንዳለው ውብ ያደርጓቸዋል። ከእነዚህ ዛፎች ውጪ ሌላ ብዙም የሚታይ ነገር የለኝም። እዚህ ከመጣሁ አንስቶ የተለያዩ ነገሮችን ታዝብያለሁ። እንደውም አንዳንዴ አቅም ቢኖረኝ ማድረግ የምሻው ነገር አለ። ይህም፤ በመንግሥት መስሪያ ቤት ውስጥ ተቀምጠው ያሉ ስደኞችን የማይወዱ እና የስደተኛ ጉዳይ ደንታቸው የልሆኑ ግለሰቦችን ካሉበት ማንሳት ብችል ደስ ይለኛል። በስደተኛው ላይ መልካም ያልሆነ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ፣ ሰቀቀን የሚፈጥሩ ሰዎች አሉ። በሌላ በኩል ደግሞ በግል ተደራጅተው ስደተኞችን መርዳት የሕይወት ዓላማቸው ያደረጉም አሉ። እስካሁን የሚገርመኝ ነገር አዚህ እንደመጣሁኝ ምን የት እንዳለሁ እና የት መሄድ እንዳለብኝ የማውቀው ነገር አልነበረም። አምጥተው ብቻ ነው ያስቀመጡኝ። ቋንቋውን አልችል፣ ቦታ አላውቅ ምን እንደማደርግ ግራ ገብቶኝ ነበር። የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት ቀጠሮ ሲሰጠኝ እንኳ አድራሻው በቁጥር ነበር የተነገረኝ። በጣም ከባድና ፈታኝ የምለው ጊዜ ያጊዜ ነበር። ሆኖም ግን አንድ ሰው ምንም አማራጭ ሳይኖረው ሲቀር መሄድና መሞከር ይጀመራል ማለት ነው። አሁን ኢትዮጵያ በቅስበት መመለስ ብችል እራሴን በቅድስተ ማሪያም ቤተ-ክርስቲያን ባገኘው እመኛለሁ።
news-44173313
https://www.bbc.com/amharic/news-44173313
ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች መፈፀም የሌለባቸው ስህተቶች
ዓለም ከኮምፒውተር ጋር ከተዋወቀ በርካታ ዓመታት ቢቆጠሩም የብዙዎች የኢንተርኔት አጠቃቀም መስመርን የሳተ ነው።
ከመረጃ ደህንነት ጋር የተያያዙ የትየለሌ እሮሮዎች በተደጋጋሚ የሚሰሙትም ከአጠቃቀም ስህተቶች ጋር በተያያዘ ነው። የኢንተርኔት አጠቃቀም ስህተት ለአካላዊ ወይም አእምሯዊ ጉዳት እንደሚያጋልጥ ተመራማሪዎች ይናገራሉ። በስፔን የሚገኘው የበይነ-መረብ ደህንነት ተቋም ኢንተርኔት ሰክዩሪቲ ኦፊስ (ኢኤስኦ) በተደጋጋሚ የሚሰሩ ስህተቶችን ይፋ አድርጓል። ከኮምፒውተር መረጃ መዝባሪዎች ራሳችሁን ለመታደግ ስህተቶቹን ከመፈጸም ተቆጠቡም ብሏል። የማይታወቁ ማስፈንጠሪያዎች የኮምፒውተር መረጃ መዝባሪዎች ሰዎችን ከሚያጠምዱባቸው መንገዶች አንዱ የተሳሳቱ ማስፈንጠሪያዎች መላክ ነው። ሰዎችን በቀላሉ ማማለል የሚችሉ 'የዋጋ ቅናሽ' ወይም 'በነጻ የሚታደሉ ምርቶች' ማስታወቂያ ይጠቀሳሉ። ማስፈንጠሪያዎቹ ቫይረስ ወደተሸከሙ ገጾች ስለሚወስዱ የተጠቃሚዎችን የመረጃ ደህንነት አደጋ ውስጥ ይጥላሉ። ኢኤስኦ "ማስፈንጠሪያዎች ከመከተልዎ በፊት ቆም ብለው ያስቡ" ይላል። ያረጁ ሶፍትዌሮች በስልክ ወይም በኮምፒውተር የሚጫኑ ሶፍትዌሮች በየግዜው መታደስ አለባቸው። ሳይታደሱ ከቆዩ የኮምፒውተር ወንጀለኞች በየግዜው ለሚሰሯቸው አደገኛ ቫይረሶች ያጋልጣሉ። አጠራጣሪ መተግበሪያዎች መተግበሪያዎችን (አፕ) ከተለያዩ ድረ ገጾች መጫን ለደህንነት አስጊ ነወ። ትክክለኛ የሚመስሉ ነገር ግን ለቫይረስ የሚያጋልጡ መተግበሪያዎች ብዙ ናቸው። ብዙዎችም ያለማወቅ ይጭኗቸዋል። ቀላል የይለፍ ቃል የኮምፒውተር መረጃ መዝባሪዎች የተጠቃሚዎችን የግል መረጃ ለመስረቅ የይለፍ ቃላቸውን ይሰብራሉ። ስለዚህም ኢኤስኦ "ጠንካራ የይለፍ ቃል ይኑራችሁ" ይላል። ምክንያቱም በቀላሉ የሚገመቱ የይለፍ ቃሎች በርካቶችን ለአደጋ አጋልጠዋል። የመረጃ ቅጂ አለማስቀመጥ በኮምፒውተር ወይም በስልክ ላይ ያሚገኙ መረጃዎችን ቅጂ አለማስቀመጥ ሌላው ችግር ነው። የኮምፒውተር መረጃ መዝባሪዎች የግል መረጃ ካገኙ ለባለቤቱ ለመመለስ ገንዘብ ይጠይቃሉ። ተጠቃሚዎች የመረጃቸው ቅጂ ካላቸው ግን ከመዝባሪዎች ጋር መደራደር አያስፈልጋቸውም።
news-52781480
https://www.bbc.com/amharic/news-52781480
የወባ መድኃኒት የኮቪድ-19 በሽተኞች ከማዳን ይልቅ ለሞት እየዳረገ ነው
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የኮሮናቫይረስ በሽተኞች ቢጠቀሙት ይበጃል ያሉት የወባ መድኃኒት በሽታውን ከመከላከል ይልቅ የሞትን ዕድልን እንደሚያሰፋ ተመራማሪዎች ተናገሩ።
የወባ መድኃኒት ላንሴት የተሰኘው የሕክምና መፅሔት ላይ የወጣው የሳይንቲስቶች ጥናት እንደሚያሳየው የኮቪድ-19 በሽተኞችን በሃይድሮክሲክሎሮኪን ማከም ጉዳት እንጂ ጥቅም የለውም። ፕሬዝደንት ትራምፕ በሽታው ባይኖርብኝም በሽታው ገሸሽ ለማድረግ የወባ መድኃኒት እየወሰድኩ ነው ማለታቸው አይዘነጋም። ነገር ግን የሕክምና ባለሙያዎች መድኃኒቱን መውሰድ ጥቅም አልባ ከሆኑም በላይ ከልብ ሕመም ሊዳርግ ይችላል ሲሉ ያስጠነቅቃሉ። የወባ መድኃኒቶች ዝናቸው የጎላው ትራምፕ ጠቃሚ ናቸው ካሉ በኋላ ነው። ሃይድሮክሲክሎሮኪን ለወባ እንዲሁም ሉፐስና አርቲሪትስ የተሰኙትን በሽታዎች ለማከም ይረዳል። ክኒናው የኮሮናቫይረስን ለማከም እንደሚረዳ እስካሁን በጥናት አልተረጋገጠም። አዲሱ ጥናት 96 ሺህ የኮቪድ-19 ታማሚዎችን ያሳተፈ ነው። 15 ሺህ ያክል ተሳታፊዎች ሃይድሮክሲክሎሮኪን ወይም ክሎሮኪን ተሰጥቷቸዋል። አንዳንዶች መድኃኒቱ ከባክቴሪያ መካለከያ ጋር ሲሰጣቸው ሌሎች ደግሞ ብቻውን እንዲወስዱ ተደረጉ። ሃይድሮክሲክሎሮኪን የወሰዱ ሰዎች የመሞት ዕድላቸው 18 በመቶ ሲጨምር ክሎሮኪን የወሰዱ ደግሞ 16 በመቶ ጨምሯል። የወባ መድላኒቶችን ከባክቴሪያ መከላከያዎች ጋር ቀላቅለው የወሰዱ ደግሞ የሞመት ዕድላቸው ይበልጥ ከፍ ያለ ነው ተብሏል። ጥናቱን ያካሄዱት ሰዎች የወባ መድኃኒቶች ለጥናት ካልሆነ በቀር እንዲሁ ማንም እንዳይወስዳቸው ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ትራምፕ ምንም እንኳ ኮቪድ-19 ባይዘኝም የወባ መድኃኒት የምወስደው አዎንታዊ ተፅዕኖ ስላለው ነው ይላሉ። የወባ መድኃኒት ለኮሮናቫይረስ ፍቱን እንደሆነ ለማየት ከ40 ሺህ በላይ የሕክምና ባለሙያዎች የሚሳተፉበት ጥናት እየተካሄደ ነው። ባለሙያዎቹ ከአፍሪካ፣ አውሮፓ፣ እስያና ደቡብ አሜሪካ የተውጣጡ ናቸው። አብዛኛዎቹ ሙያተኞች ከኮቪድ-19 በሽተኞች ጋር ንክኪ የነበራቸው ናቸው። የዋይት ሃውስ ኮሮናቫይረስ መከላከል አስተባባሪ የሆኑት ዶ/ር ዴብራህ ቢርክስ ስለ ጥናቱ ተጠይቀው የአሜሪካ ምግብና መድኃኒት አስተዳዳር የወባ መድላኒቶችን ለኮሮናቫይረስ ስለ መጠቀም በጣም ግልፅ የሆነ መልዕክት አስተላልፏል ብለዋል። የአሜሪካ ምግብና መድኃኒት አስተዳደር የወባ መድኃኒቶችን ያለ ሐኪም ምክር ጭራሽ አትውሰዱ ይላል። የዓለም ጤና ድርጅትም መድኃኒቶቹን ለኮሮናቫይረስ መውሰድ ሌላ የጤና እክል ሊያስከትል ይችላል ሲል ያስጠነቅቃል።
51043968
https://www.bbc.com/amharic/51043968
ኬኒያ፡ በላሙ ሶስት አሜሪካውያን ከተገደሉ በኋላ የሰዓት እላፊ ታወጀ
የኬኒያ መንግሥት በላሙ የኬኒያና አሜሪካ ጥምር ጦር ወታደራዊ ካምፕ ላይ አልሸባብ ጥቃት ፈጽሞ ሶስት አሜሪካውያን ከተገደሉ በኋላ ሰዓት እላፊ አወጀ።
አልሸባብ በላሙ በተደጋጋሚ ጥቃት የሰነዘረ ሲሆን የበርካታ ኬኒያውያን ሕይወት ማለፉም ይታወሳል። የሰዓት እላፊው ከምሽቱ ሶስት ሰዓት እስከ ንጋት አስር ሰዓት ድረስ ይቆያል ተብሏል። • በአልሸባብ ጥቃት ሶስት አሜሪካውያን ተገደሉ • "ወንድ ወይ ሴት መሆን ትልቅ ቦታ ለመድረስ አያግዝም ወይ አያስቀርም" • ሶማሊያውያን፤ አውስትራሊያን ግመሎቻችን መልሺልን እያሉ ነው በኬኒያ የሚታተመው ስታር ጋዜጣ እንደዘገበው ከሆነ፣ የሰዓት እላፊው የተጣለው የጸጥታ ባልደረቦች የሚያደርጎትን የሰላም ማስከበር እንቅስቃሴ ለማገዝ እንዲሁም የሚኖሩ አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎች ለመከታተል እንዲረዳቸው ነው ተብሏል። የኬኒያዋ ላሙ የባህር ዳርቻ ለሶማሊያ ድንበር ቅርብ ነች። በስታር ጋዜጣው ላይ የተጠቀሱት የለላሙ ፖሊስ ኃላፊ፣ ሙቻንጊ ኪኦኢ፣ በሰዓት እላፊው ወቅት መኪኖች እንዲንቀሳቀሱ አይፈቀድላቸውም። በቀንም ፖሊስ መኪኖችን ላይ ፍተሻ ያካሂዳል ማለታቸው ተዘግቧል። እሁድ እለት በጦር ካምፑ ላይ አልሸባብ ባደረሰው ጥቃት ከሰው ሕይወት በተጨማሪ አውሮፕላኖችና መኪኖችም ተቃጥለዋል። በጦር ካምፑ አቅራቢያ የሚኖሩ ሰዎች ተጨማሪ ጥቃት ሊኖር ይችላል በሚል አካባቢያቸውን ለቅቀው ወደ ሌላ ስፍራ ሄደው ነበር። ከዚህ ቀደም በዝችው የኬኒያዋ ላሙ ከተማ አልሸባብ አድርሶታል በተባለ የመኪና ላይ ጥቃት ሶስት ሰዎች ሲሞቱ ሁለቱ ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው የሚታወስ ነው። ወደ ሞምባሳ በመጓዝ ላይ የነበረውን የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ አንድ ግለሰብ ካስቆመ በኋላ በርካታ ጥይቶችን እንዳርከፈከፈበት የአይን እማኞች ገልጸው ነበር። ኬኒያ ወደ ሶማሊያ ጦሯን ያዘመተችው እ.አ.አ. በ2011 ሲሆን ለዚህም ምክንያቴ ነው ብላ የነበረው ከሶማሊያ ወደ ግዛቷ ድንበር እያቋረጡ የሚፈፀሙ ጥቃቶችና እገታዎች በመበራከታቸው ነበር። በአሁኑ ሰዓት የኬኒያ ጦር በአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ጦር ስር ሲሆን በምዕራባውያን የሚደገፈውን የሶማሊያ መንግሥት በመደገፍ የሠላም ማስከበር ሂደቱን ይሰራል። አልሸባብ በሶማሊያና በኬኒያ መቀመጫውን በሶማሊያ ያደረገው አልሸባብ በምስራቅ አፍሪካ አሁንም የደህንንት ስጋት እንደሆነ መቀጠሉ እየተገለፀ ነው። አልሸባብ በሶማሊያና በኬኒያ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን የፈፀመ ሲሆን እኤአ በ2013፣ 67 ሰዎችን የቀጠፈው የዌስት ጌት ሞል ጥቃት የሚታወስ ነው። በ2014 ደግሞ 148 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው የጋሪሳ ጥቃት የተፈፀመውም በአልሸባብ ነበር። በ2017፣ በሶማሊያ ከ500 በላይ ሰዎችን የገደለው በመኪና ላይ የተጠመደው ቦምብ ፍንዳታም የተቀነባበረው በአልሸባብ መሆኑ ይታወቃል። በ2019 ደግሞ በኬኒያ መዲና ናይሮቢ የሚገኘው ዱሲት ዲ2 ሕንፃ ላይ የደረሰውና ከ21 ሰዎችን የሞቱበት ጥቃትንም የፈፀመው አልሸባብ ነበር። የአልሸባብ አማፂያን በሶማሊያና በኬኒያ ላሙ የሚገኙ ወታደራዊ ካምፖች ላይ የደረሱ የተለያዩ ጥቃቶችን መፈፀሙን በተደጋጋሚ ጊዜ ተናግሯል። አሜሪካ የአልሸባብን እንቅስቃሴ ለመግታት ተደጋጋሚ የአየር ጥቃቶች ፈፅማለች።
52343049
https://www.bbc.com/amharic/52343049
ኮሮና ቫይረስ፡ ስቲቪ ወንደር፣ ጆን ሌጀንድ፣ ሌዲ ጋጋ፣ በርና ቦይ... የጤና ባለሙያዎችን ያወደሱበት የቤት ኮንሰርት
በዓለማችን ውስጥ በሙዚቃው ኢንዱስትሪ ዘርፍ ከፍተኛ ስፍራ ያላቸው አርቲስቶች ህይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው ኮሮናን እየተጋፈጡ ያሉትን የጤና ባለሙያዎች ለማሰብ ከቤታቸው ሆነው የሙዚቃ ኮንሰርት አካሂደዋል።
ከሙዚቀኞቹም መካከል ስቲቪ ወንደር፣ ሌዲ ጋጋ፣ ጆን ሌጀንድ፣ ጄኔፈር ሎፔዝ፣ በርና ቦይ፣ ፓውል ማካርቲና በአጠቃላይ 100 የሚሆኑ ሙዚቀኞች ከቤታቸው ሆነው ዘፍነዋል። የሮሊንግ ስቶን ባንድ አባላትም አራት የተለያዩ ቦታዎች ላይ ሆነው በአንድ ላይ መጫወት ችለዋል። • በዓለም ላይ ያሉ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ትንሳኤን እንዴት እያከበሩት ነው? • የኮሮናቫይረስ ለሮቦቶች የስራ ዕድል ይከፍት ይሆን? ለስምንት ሰአታት ያህል በቆየው በዚህ ኮንሰርት የኮሮናቫይረስ ህሙማንን በሚያክሙና ድጋፍ በሚሰጡ ሰራተኞች አንደበት እውነተኛ ታሪኮች ተሰምተዋል። ኮንሰርቱን በማዘጋጀት ትልቅ ስፍራ የነበራት ሌዲ ጋጋ " ይሄ ለዓለም የፍቅር ደብዳቤ ነው" ብላለች። አክላም የጤና ባለሙያዎችም ሆነ ድጋፍ ሰጪ አካላት ለዓለም ብዙ እያበረከቱ ነው "እናም ላሳያችሁን ደግነትን በትንሹም ለመመለስ ነው" ብላለች። ፖል ማካርቲንም ቢሆንም የጤና ባለሙያዎቹን እንዲሁም ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን " እውነተኛ ጀግኖች" በማለት ያሞካሻቸው ሲሆን፤ በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ወቅት ነርስ የነበረችውን እናቱንም በዚህ ወቅት አስታውሷታል። "ዋን ወርልድ ቱጌዘር አት ሆም" (One World: Together At Home) የሚል ርዕስ የተሰጠው ይህ ኮንሰርት የተዘጋጀው በግሎባል ሲትዝን ሙቭመንትና በዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት አማካኝነት ነው። ሃገራት የቤት መቀመጥ አዋጅ ባወጁበት ሰአት ቤተሰቦቻቸውን፣ ልጆቻቸውንና የሚወዷቸውን ሰዎች እንዲሁም ለህይወታቸው ሳይሳሱ ክፉኛ በቫይረሱ በተጎዱ እንደ ፈረንሳይ፣ ስፔን፣ አሜሪካና በመሳሰሉት አገራት ያሉ የጤና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪዎች ፎቶዎች ታይተዋል። • "መደብር ሄጄ የውጪ አገር ሰው አንቀበልም አሉኝ" ኢትዮጵያዊቷ በቻይና • ኢንሹራንስና ቤት ለኮሮናቫይረስ ጤና አገልግሎት ሰጪዎች "ፊት ለፊት እየተጋፈጣችሁ ያላችሁ የጤና ባለሙያዎችም ሆነ ድጋፍ ሰጪዎች አብረናችሁ ነን። ስለረዳችሁን፣ ከጎናችን ስለቆማችሁ እናመሰግናለን" የሚልም መልእክት ተላልፏል። ከሙዚቃ ዝግጅቱ የተገኘው ገንዘብ የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ኮቪድ 19ን ለመታገል ለሚያደርገው ድጋፍ ይውላል ቢባልም ሌዲ ጋጋ በበኩሏ ይህ የእርዳታ ማሰባሰቢያ አይደለም። ትኩረቱም ማዝናናትና የትብብር መልእክቶች የሚተላለፉበት ብቻ ነው ብላለች። ከነዚህም ሙዚቀኞች በተጨማሪ የዋን ዳይሬክሽኑ ኒያል ሆራን "ምንም እንኳን የጨለመ ቢሆንም መተባበርም የሰፈነበት ነው የሚል መልእክት አስተላልፏል። ጆን ሌጀንድም ከሳም ስሚዝ ጋር በመጣመር 'የቤን ኢ ኪንግ' ስራ የሆነውን 'ስታንድ ባይ ሚን' አቀንቅነዋል። የእንግሊዟ ዘፋኝ ሪታ ኦራ "አይ ዊል ኔቨር ሌት ዩ ዳውን' የሚለውን ዘፈን ከመዝፈኗ በፊት የዓለም አቀፍ ጤና ድርጅትን ምክር ህዝቡ እንዲሰማ መልእክቷን አስተላልፋለች። አኒ ሊኖክስ በበኩሏ ዶናልድ ትራምፕ ለዓለም አቀፉ ጤና ድርጅት የሚለግሱትን ገንዘብ አቆማለሁ ማለታቸውን በተመለከተ "ወቅቱ ዓለም ተባብሮ ይህንን ወረርሽኝ የሚያጠፋበት ወቅት እንጂ የምንበታተንበት ጊዜ አይደለም" ብላለች። ኮንሰርቱ ለሁለት የተከፈለ ሲሆን የመጀመሪያው ስድስት ሰአት በፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ትዊተር፣ ዩ ቲዩብ በቀጥታ የተላለፉ ሲሆን የሁለት ሰአቱ የሙዚቃ ዝግጅት ደግሞ በሶስቱ የአሜሪካ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ቀርቧል። ከዚህም በተጨማሪ በስቴፈን ኮልበርት፣ ጂሚ ኪሜልና ጂሚ ፋለን በሚያዘጋጇቸው ዝግጅቶች ላይ የተወሰነው ክፍል ኮንሰርት ቀርቧል። ጂሚ ፋለንም ከሂፕሆፕ ቡድን ዘ ሩትስና የተለያዩ የጤና ባለሙያዎችን በመጋበዝ በ80ዎቹ ታዋቂ የነበረውን ዳንስ አብረው ደንሰዋል። ስቲቪ ወንደር፣ ጄኔፈር ሎፔዝ፣ በርና ቦይ፣ ሉይስ ፎንዚ፣ ሆዚየር በጥምረት ሆነው በቅርቡ ህይወቱ ያጣውን የቢል ዊዘር ዘፈን 'ሊን ኦን ሚን' ተጫውተዋል። ቴይለር ስዊፍትም እናቷ በካንሰር ታመው እያለ ሆስፒታል ተቀምጦ መጠበቅ ያለውን ተስፋ አስቆራጭ ስሜት የገለፀችበትን "ዩ ዊል ጌት ቤተር' ኮሮና ቫይረስ የታመሙባቸው ቤተሰቦችን በመዘከር ተጫውታለች። የኮንሰርቱም ማጠናቀቂያ የነበረው ጆን ሌጀንድ፣ ሴሊንድዮን፣ አንድሪያ ቦሴሊ በመጣመር በፀሎትና በዜማ ያቀነቀኑት ዘፈን ነው። ይሄ ፀሎት የተወሰደው በጎርጎሳውያኑ 1998 ለተሰራው ካሜሎት ፊልም ላይ ሲሆን መልእክቱም ከጨለማ መውጣትን የሚማፀን ነው።
news-45986089
https://www.bbc.com/amharic/news-45986089
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፡ በሚያውቋቸው ሰዎች አንደበት
አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸውን ተከትሎ በተለያየ አጋጣሚ የሚያውቋቸው ብዙዎች ስለ እርሳቸው አስተያየታቸውን እየሰነዘሩ ነው። በተለይ በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን ብዙዎች ስለርሳቸው ብዙ ብለዋል፤ ብዙ እያሉም ነው።
አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴን ለረዥም ጊዜ በሥራ አጋጣሚ በቅርበት የሚያውቋቸው ስለ እርሳቸው ምን ይላሉ? "በሥራ ብቁና ፀባየ ሸጋ ናቸው" ዲና ሙፍቲ (በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር) በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አዲሲቷን ርእሰ ብሔር "ብቁና ጸባየ ሸጋ" ሲሉ ያሞካሿቸዋል። አምባሳደር ሳሕለወርቅ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በተለያዩ ኃላፊነቶች አገራቸውን ማገልገላቸውን ከጠቀሱ በኋላ ውጤታማ ሥራ ሠርተዋል ከሚባሉ የውጭ ጉዳይ ባልደረቦች አንደኛዋ እንደነበሩ ያወሳሉ። "እንደ ውጭ ጉዳይ ባልደረባ ረዥም ጊዜ ነው የማውቃቸው። እኔ አምባሳደር በነበርኩበት ወቅት እሳቸው በዋና ኃላፊነት፤ እኔ ዋናው መሥሪያ ቤት በነበርኩበት ወቅት ደግሞ በአምባሳደርነት በሴኔጋል፣ በጅቡቲም በፈረንሳይም ሲያገለግሉ በደንብ አውቃለሁ።" የሚሉት አምባሳደር ዲና፣ ሳሕለወርቅን "ውክልናቸውን በሚገባ ሙያዊ ብቃት የተወጡ መልካምና ፀባየ ሸጋ።" ሲሉ ስለርሳቸው የሚያውቁትን ይመሰክራሉ። አምባሳደር ዲና በሚመሩት በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲው ውስጥ በሚዘጋጁ ልዩ ልዩ መርሐ ግብሮች "አምባሳደር ሳሕለወርቅ ዝግጅቶቹን ከሚያደምቁልን ሰዎች መሀል ዋንኛውነበሩ" ሲሉም ያስታውሷቸዋል። "እዚህ በኬንያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ልዑክ ሆነው ውክልናቸውን በሚገባ ሙያዊ ብቃት የተወጡ በሥራቸውም የተዋጣለቸው ባለሙያም ነበሩ።" • የመጀመሪያዋ ሴት ርዕሰ ብሔር- አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ "አዲስና ጀማሪ ባለሙያዎችን በጣም ያግዛሉ" አቶ ዘሩባቤል ጌታቸው ከአምባሳደር ሳሕለወርቅ ጋር በናይሮቢ የተባበሩት መንግሥታት ቢሮ ውስጥ አብሯቸው የሠራው አቶ ዘሩባቤል ደግሞ ስለርሳቸው የሚከተለውን ይላል። በኬንያ ናይሮቢ ተመድቤ ስመጣ መጀመሪያ ያገኘኋቸው እሳቸውን ነበር። በጣም ትሁት ናቸው፤ ቢሯቸውም ሁል ጊዜ ክፍት ነው። እኔን ከተቋሙ ኃላፊዎች ጋር በማስተዋወቅና እሳቸው የሄዱበትን መንገድ በማሳየት ረድተውኛል፣ አግዘውኛልም። በተለይም ጀማሪና በመካከለኛ ደረጃ የሚገኙ ሠራተኞችን በጣም ይደግፉ ነበር። እዚህ ናይሮቢ ላይ የተለያዩ አገራት ልዑካን የኮሚቴ ስብሰባ ነበረን እና ፕሬዝዳንት ሆነው የመመረጣቸው ዜና ከተሰማ በኋላ ሁሉም ወደ እኛ መጥተው በስሜት ነበር ደስታቸውን የገለፁልን። ይህ ስለነበራቸው ቆይታ የሚናገር ነው። የሥራ ደረጃቸው ኑሯቸውም እንደዚያው በጣም ከፍተኛ ስለሆነ ስለ ማኅበራዊ መስተጋብራቸው ምን እንደሚመስል መናገር ባልችልም እኛን ዝቅ ብለው ስለ ኑሯችን ያኛው ይሄኛው እንዴት ሆነ ብለው ይጠይቁ ነበር። ስለዚህ በማኅበራዊ ሕይወታቸውም ሙሉና ቀና ሰው እንደሆኑ አምናለው። • አዲሷ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ማን ናቸው? በሥራ አጋጣሚ ከሚያውቋቸው ሰዎች በተጨማሪ ሌሎችንም የአምባሳደር ሳሕለወርቅ ርእሰ ብሔርነት ምን ስሜት ፈጠረባችሁ ስንል ጠይቀናቸው ነበር። "የሴቶችን አቅም ያሳያል" ረድኤት ከፍአለ (የ'የሎው ሙቭመንት' አባል ) የአምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ ፕሬዘዳንት ሆኖ መሾም ትልቅ ትርጉም አለው።በመጀመሪያ ደረጃ የሴቶችን አቅም፤ሴቶች በዚህ ዓይነቱ ኃላፊነት መምራት እንደሚችሉ ያሳያል። ከቀናት በፊት አስር ሴት ሚኒስትሮች መሾማቸውን ተከትሎ የአምባሳደር ሳህለወርቅ ሹመት ሲታይ በአጠቃላይ እንደማኅበረሰብ የሴቶችን መሪነት እንድንለምደው የሚያደርግ ነው። ይህ ልምድ ደግሞ ለወደፊቱ ሴቶችን ለዚህ ዓይነቱ ትልቅ ኃላፊነት መሾም እንዲቀለን ያደርጋል ብዬ አስባለሁ። በአጠቃላይ ሹመታቸው ከተምሳሌትነት አንፃር ያለው ጠቀሜታም ለኔ ጉልህ ነው። • የቻይና ሙስሊሞች ምድራዊ 'ጀሐነም' ሲጋለጥ "የተመረጠቸው እናት ናት" ወ/ሮ አበባ ገብረሥላሴ (የመቀሌ ነዋሪ) በኢትዮጵያ ሴት ለመጀመሪያ ጊዜ ፕሬዝዳንት ሆና መመረጧ በጣም ደስ ይለኛል። የተለየ ነገር እንኳ ባይመጣ አሁን ኢትዮጵያ ላይ በጣም ችግር የሆነው የሰላም መደፍረስና ሙስና በመሆኑ የተመረጠችው ደግሞ እናት በመሆኗ ነገሮች ይቀየራሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ምክንያቱም እናት ለሰላም ብዙ ጥረት ታደርጋለች።እናት ለሰላም ትፀልያለች፤ ብዙ ትሞክራለች፤ ፍትህ ታመጣለች። ሁከት ሲፈጠር ልጄ፣ባሌን እና ወንድሜን ነው የሚጎዳው ብላ ሰላምን ፍለጋ ብዙ ትጥራለች። ከዚህ አንጻር "የተመረጠችው እናት ናት" እላለሁ።
news-51260441
https://www.bbc.com/amharic/news-51260441
በኮሮናቫይረስ እስካሁን ስንት ሰዎች ሞቱ? ወደ የትኞቹ አገሮች ተዛመተ?.
ይህ ዘገባ እስኪታተም ድረስ 80 ሰዎች ሞተዋል። 3 ሺህ ሰዎች ታመዋል፤ 300ዎቹ በጽኑ ሁኔታ ታመው አልጋ ይዘዋል።
ውሃን ውስጥ ሆስፒታሎች በታማሚዎች ተጨናንቀዋል ሆኖም ይህ ኮሮና ቫይረስ በትክክል ምንጩ ምን እንደሆነ የሚያውቅ የለም። በዉሃን ከተማ የዓሳ ገበያ ውስጥ እንደተነሳ ግን ይጠረጠራል። ቻይና አዲስ ዓመቷን በስጋት ተሸብባ እያከበረች ነው። በዓሉ ለሦስት ቀናት የተራዘመ ሲሆን ይህም የሆነው ቫይረሱን ለመቆጣጠር እንዲያመች በሚል ነው። የቫይረሱ መነሻ ናት የተባለችው ዉሃን ከተማ በሆበይ አውራጃ የምትገኝ ሲሆን በዓለም 42ኛ፣ በቻይና 7ኛዋ ትልቅ ከተማ ናት። አብዛኛዎቹ ከተሞች የጉዞ እገዳን ጥለውባታል። • ስለአዲሱ ኮሮና ቫይረስ ማወቅ የሚገባዎ ነጥቦች የዉሃን አየር ማረፊያ በትንሹ 20 ሚሊዮን መንገደኞችን በዓመት ያስተናግዳል። ለዚህም ይመስላል በሽታው ቶሎ የተዛመተው። በዚህች ከተማ ብቻ የሟቾቹ ቁጥር ከ56 ወደ 76 አድጓል። ከቻይና ውጭ ደግሞ በትንሹ 41 ሰዎች ታመዋል። ከነዚህ መሐል አሜሪካ ታይላንድና አውስትራሊያ ይገኙበታል። መልካሙ ዜና እስካሁን ከቻይና ውጭ በቫይረሱ የተያዙ እንጂ በቫይረሱ የሞቱ አለመኖራቸው ነው። በሽታው የመተንፈሻ አካልን የሚያውክ ሲሆን እስካሁን ክትባትም ሆነ መድኃኒት አልተገኘለትም። ብዙዎቹ ሟቾች በእድሜ የገፉና መጀመርያውኑም ከመተንፈሻ አካላቸው አንዳች እክል የነበረባቸው ናቸው እየተባለ ነው። በዉሃን አውራጃ ምን እየሆነ ነው? የቻይናዋ ዉሃን ከተማ ለንደንን ነው የምታክለው፤ 11 ሚሊዮን ሰዎች ይኖሩባታል። ጉዞ ክልከላ የተደረገባት ዉሃን፤ እጅግ አስፈላጊ የሆኑ ተሽከርካሪዎች ካልሆኑ በስተቀር አይገቡም፣ አይወጡም። የሚገቡትም ሆነ የሚወጡት ሰዎች የትኩሳት መጠናቸው እየተለካ ነው። • የአፍ ጭምብል ማጥለቅ ከቫይረስ ይታደገን ይሆን? ከግማሽ ሚሊዮን ያላነሱ የጤና ባለሞያዎች በግዛቷ ገብተው ተፍ ተፍ እያሉ ነው። ሁለት ግዙፍ ጊዜያዊ ሆስፒታሎች በፍጥነት ተገንብተዋል። ፋብሪካዎቿ የአፍ መሸፈኛ ማስክ በማምረት 24 ሰዓት ተጠምደዋል። የግዛቷ ከንቲባ ዡ ዢያዋንግ እንደተናገሩት በትንሹ 5 ሚሊዮን ዜጎች ከግዛቷ ወጥተዋል፤ ይህም የሆነው የጉዞ እቀባ ከመደረጉ አስቀድሞ ነው። በቻይና ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል? ለክፋቱ ይሄ ቫይረስ በቻይናዎቹ አዲስ ዓመት ነው የተከሰተው፤ የቻይና አዲስ ዓመት ደግሞ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ሕዝብ ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀስበት እጅግ ትልቅ አውዳመት ነው። እስካሁን ቤይጂንግ፣ ሻንጋይ፣ ዢኣን እና ቲያንጂን አገር አቋራጭ አውቶቡስ እንዳይገባ እንዳይወጣ እግድ ጥለዋል። • አገሯን 'በሙስና ያራቆተችው' የአፍሪካ ሃብታሟ ሴት ቤይጂንግ ታላቁን ግንብ በከፊል፣ ሌሎች ዝነኛ የቱሪስ መዳረሻዎቿን ደግሞ ሙሉ በሙሉ ዘግታለች። በጉዋንግዶንግ አውራጃ ደግሞ በርካታ ከተሞች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ማጥለቅ ግዴታ ነው ሲሉ አውጀዋል። በሆንግ ኮንግና ሻንጋይ ግዙፉ የዲስኒ ፓርክ መዝናኛ ለጊዜው አገልግሎት አልሰጥም ብሏል። የዚህ ቫይረስ ክፋቱ አንድ በሽተኛ ምንም አይነት ምልክት ሳያሳይ ለ14 ቀናት መቆየቱ ሲሆን የክፋቱ ክፋት ደግሞ በዚህ የበሽታው መራቢያ ወቅት ቫይረሱ ድምጽ አጥፍቶ ከሰው ወደ ሰው መተላለፍ መቻሉ ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ ቫይረሱ የት ደርሷል? ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የሚመሩት የዓለም ጤና ድርጅት ለቫይረሱ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ሲሆን ከቻይና ውጭ 41 ሰዎች በቫይረሱ ስለመያዛቸው አረጋግጧል። ከእነዚህ መካከል 8ቱ በታይላንድ፣ 5ቱ በአሜሪካ፥ 4ቱ በሲንጋፖር አውስራሊያ፣ ታይዋንና ማሌዢያ፣ ሦስቱ በፈረንሳይና ቬትናም፣ አንድ በኔፓል አንድ በካናዳ ይገኛሉ። ታዲያ ሁሉም ታማሚዎች በቅርብ ጊዜ ዉሃን ከተማ ነበሩ። ኮሮና ቫይረስ እንሰሳትን የሚያጠቃ በሽታ ነበር። በፈረንጆች 2003 ሳርስ የሚባል ሌላ ወረረሽኝ ተከስቶ በርካቶችን እንደገደለ የሚታወስ ነው።
news-54008819
https://www.bbc.com/amharic/news-54008819
ጆ ባይደን ጄኮብ ብሌክ ላይ የተኮሰው ፖሊስ እንዲከሰስ ጠየቁ
ከፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ለፕሬዘዳንትነት የሚወዳደሩት የዴሞክራት እጩው ጆ ባይደን፤ ሁለት ጥቁር አሜሪካውያን ላይ የተኮሱ ፖሊሶች እንዲከሱ ጠየቁ።
ባይደን እንዲከሰሱ የጠየቁት ጄኮብ ብሌክ ላይ የተኮሰው ፖሊስ እና ብሬዎና ቴይለርን ተኩሰው የገደሉ ፖሊሶች ናቸው። ዳልዌር ውስጥ ባደረጉት ንግግር፤ በክሱ ምን መካተት እንዳለበት ዝርዝር ነገር አልሰጡም። የዴሞክራት እጩው ከነሐሴ ወዲህ ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ድጋፍ አሰባስበዋል። ከምርጫው በፊት የተሠራ ዳሰሳ ከትራምፕ በተሻለ የመራጮች ድጋፍ እንዳላቸውም አሳይቷል። ካምላ ሀሪስ ከዚህ ቀደም ጄኮብ ብሌክ እና ብሬዎና ቴይለር ላይ የተኮሱ ፖሊሶች እንዲከሰሱ ጠይቀው ነበር። ይህንን ይደግፉ እንደሆነ የተጠየቁት ባይደን “የፍትሕ ሂደቱ በራሱ መንገድ መሥራት አለበት። ፖሊሶቹ መከሰስ እንዳለባቸው አምናለሁ” ብለዋል። ጄኮብ ሰባት ጊዜ ከጀርባው ፖሊስ ከተኮሰበት በኋላ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል። እስካሁን የተኮሰው የፖሊስ አባል ላይ ግን እርምጃ አልተወሰደም። የ26 ዓመቷ ብሬዎና ቤቷ ተኝታ ሳለች ፖሊሶች ተኩሰው እንደገደሏት ይታወሳል። አንድ ፖሊስ ከሥራ ሲሰናበት፤ ሁለት ሌሎች ፖሊሶች በጊዜያዊነት ታግደው ምርመራ እየተካሄደ ይገኛል። ፖርትላንድ ውስጥ የትራምፕ ደጋፊ ላይ የተኮሰና በሚዲያዎች ግራ ዘመም አቀንቃኝ የተባለውን ግለሰብ በተመለከተ ባይደን “ፍትሕ መገኘት አለበት” ብለዋል። ጆ ባይደን ከጄኮብ አባት ጋር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ትራምፕ ወደ ኪኖሻ ግዛት ሲሄዱ ከጄኮብ ቤተሰቦች ጋር አልተገናኙም። ትራምፕ “ሕግ አልባ” ላሏቸው የኒው ዮርክ፣ ሲያትል፣ ዋሽንግተን ዲሲ እና ፖርትላንድ ግዛቶች የፌደራል መንግሥት የሚያደርገውን ድጋፍ ለማቋረጥ ሐሳብ እንዳላቸው ተናግረዋል። ትራምፕ ይህን ባሉበት ቀን፤ ባይደን ነሐሴ ውስጥ 364 ሚሊዮን ዶላር ማሰባሰባቸውን ተናግረዋል። ይህም ፕራምፕ ካገኙት በላይ ነው። የዴሞክራት እጩው ወደ 45 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ማስታወቂያ ያሠራሉ። የባይደን ተቀናቃኞች፤ ባይደን አመጸኞች ላይ እርምጃ አይወስድም ማለታቸውን ተከትሎ፤ ባይደን አቋማቸውን የሚያሳዩት በዚህ ማስታወቂያ ነው ተብሏል።
news-47958652
https://www.bbc.com/amharic/news-47958652
ታዋቂው ኩባንያ ኢትዮጵያዊያን ሠራተኞችን ''ይበድላል'' ተባለ
በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የሚሠሩ ሠራተኞች በአሠሪዎቻቸው በደል ይደርስባቸዋል ተባለ።
የፋሽን ምርቶች አምራቹ ፒቪኤች (PVH) በስሩ የሚገኙና በኢትዮጵያ እየሠሩ ያሉ ተቋሞቹ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞችን ይዘልፋሉ፣ አድልዎ ይፈፀምባቸዋል እንዲሁም በሰዓት እስከ 12 የአሜሪካ ሳንቲም (3 ብር ከ50 ሳንቲም ገደማ) ብቻ የሚከፈላቸው ሠራተኞች አሉ መባሉን ተከትሎ ፒቪኤች (PVH) ምርመራ እንደሚያደርግ ሮይተርስ ያነጋገራቸው የኩባንያው የሥራ ኃላፊ አስታወቁ። ፒቪኤች (PVH) ኩባንያ ቶሚ ሂልፊገር እና ካልቪን ክሌን የመሳሰሉ ታዋቂ ኩባንያዎች ባለቤት ነው። • የኢንዱስትሪ ፓርኮች ፈተና እና ተስፋ በኢትዮጵያ ለፒቪኤች (PVH) ኩባንያ ግብዓት የሚሆኑ ምርቶችን ለሚያመርቱ ድርጅቶች እየሠሩ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች በሥራ ገበታቸው ላይ በደል እንደሚፈፀምባቸው መቀመጫውን አሜሪካን ሃገር ያደረገ ዎርከር ራይትስ ኮንሶርቲየም (Worker Rights Consortium) የተባለ ድርጅት ባደረገው ጥናት አጋልጧል። ዎርከር ራይትስ ኮንሶርቲየም ገለልተኛ የሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በፋብሪካዎች ውስጥ የሚሠሩ የሠራተኞችን መብት የሚቃኝ እና የሥራ ቦታ ሁኔታን የሚመረምር ድርጅት ነው። ድርጅቱ እንደሚለው ለፒቪኤች (PVH) ኩባንያ ግብዓት የሚሆኑ ምርቶችን ለሚያመርቱ ኩባንያዎች እየሠሩ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች ያለ ክፍያ ትርፍ ስዓት እንዲሠሩ ይገደዳሉ እንዲሁም በሥራ ቦታቸው ላይ ውሃ በመጠጣታቸው ብቻ ከደሞዛቸው ተቆራጭ ይደረጋል ይላል። የዎርከር ራይትስ ኮንሰርቲየም ምረመራ ውጤት እንዳመላከተው ሥራ ቀጣሪ ኃላፊዎች በሥራ ቅጥር ወቅት ሴት ሠራተኞችን ሲቀጥሩ ነብሰጡር መሆን አለመሆናቸውን እጃቸውን ሆዳቸው ላይ በማድረግ ለማረጋጋጥ ይጥራሉ። • የፖለቲካ አለመረጋጋት ለኢንስትመንት ደንቃራ ሆኖ ነበር በኢንዱስትሪ ፓርኩ በሠራተኞች ላይ ተፈጽሟል የተባለውን የመብት ጥሰት ለማረጋጋጥ ቢቢሲ ሁለት በፓርኩ የሚሠሩ ሠራተኞችን አነጋግሯል። ስሟ እንዲጠቀስ ያለፈለገች ወጣት ሠራተኛ፤ በፓርኩ ውስጥ ለሚገኘው አንድ የጨርቃ ጨርቅ ኩባንያ እንደምትሠራ ትናገራለች። ተማሪ ሳለች በዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ድረስ በመምጣት የሥራ ቃለ መጠይቅ አድርጋ ከምርቃት በኋላ ሥራ እንደ ጀመረች ታስረዳለች። ''እርጉዝ ብቻ ሳይሆን እናቶችንም አይፈለጉም። ለፈተና ሲቀርቡ ልጅ እያላቸው ልጅ የለኝም ብለው የሚቀጠሩ አሉ'' በማለት ነብሰጡር እና የልጆች እናት የሆኑ ሴቶች በሥራው ላይ አድልዖ እንደሚፈፀምባቸው ታስረዳለች። የቅርብ ኃላፊዎቿም ''የሥራው ባህሪ ለእርጉዞች እና ለእናቶች አይመችም'' የሚል ምክንያት እንደሚያቀርቡ ይህችው ወጣት ትናገራለች። ያነጋገርነው ሌላው በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ የሚሠራ ወጣት፤ የሚከፈላቸው ክፍያ በሐዋሳ ከተማ ላይ ቤት ተከራይተው እና ወጪያቸውን ሸፍኖ ስለማያኖራቸው በቡድን ሆነው ቤት ተከራይተው ለመኖር መገደዳቸውን ይናገራል። በሥራ ቦታው ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ፤ በ8 ሰዓት ልዩነት ሦስት ፈረቃ መኖሩን ተራ በደረሰ ቁጥር የምሽት ፈረቃን በ10 ብር ጭማሪ ብቻ እንዲሠሩ እንደሚገደዱ ይናገራል። • ትውስታ- የዛሬ 20 ዓመት ኢትዮጵያ ሞባይል ስልክን ስትተዋወቅ የዎርከር ራይትስ ኮንሰርቲየም ምርመራ ውጤት ይፋ መሆኑን ተከትሎ የፒቪኤች (PVH) ኩባንያ ቃል አቀባይ ለሮይተርስ ''ማናቸውም ዓይነት የመብት ጥሰቶች ተደርገው ስለመሆኑ ለማረጋገጥ አስቸኳይ እና ዝርዝር ምረመራ እናደርጋለን። የመብት ጥሰቶች ከደረሱም አስፈላጊውን እርምጃ እንወስዳለን'' ሲሉ ተናግረዋል። የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ሌሊሴ ነሜ ስለ ጉዳዩ ጠይቀናቸው፤ ኮርፖሬሽኑ የኢንዱስትሪ ፓርክ እና መሠረተ ልማቶች ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ በመጥቀስ ጉዳዩ የእርሳቸውን መሥሪያ ቤት እንደማይመለከት ለቢቢሲ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሸን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መኮንን ኃይሌ በበኩላቸው በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ በሚሠሩ ሠራተኞች ላይ በደል ይፈፀማል የተባለው ከእውነተ የራቀ ነው ይላሉ። አቶ መኮንን የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ መከፈት ለአከባቢው ነዋሪዎች በተለይም ለወጣቶች ዕድል መክፈቱን በመናገር፤ በፓርኩ ውስጥ ብዙዎቹ ተቀጣሪዎች ሴቶችና ናቸው። ነብሰጡር እና እናቶች ላይ ይፈፀማል የተባለው ከእውነት የራቀ ነው ይላሉ። ሠራተኞች ከደምወዛቸው በተጨማሪ የትራንስፖርት እና የምግብ አገልግሎት ስለሚቀርብላቸው የተሻለ ተጠቃሚዎች ናቸው በማለት የዎርከር ራይትስ ኮንሶርቲየም የጥናት ውጤት እውነታውን እንደማያሳይ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የፌደራል እና የደቡብ ክልል የሠራተኛ እና ማህብራዊ መሥሪያ ቤቶች በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ ያደረግነው ጥረት ሊገኙ ባለመቻላቸው ሳይሳካ ቀርቷል። የሠራተኞች ፌዴሬሽንም ስለ ሠራተኞቹ ቅሬታ የሚያውቀው ካለ ለመጠየቅ ብንጥርም እነርሱም ሊገኙ አልቻሉም። ሮይተርስ በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት አስተያየት ለማካታት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ቢሮ እና የሠራተኛ እና ማህበረዊ ሚኒስቴርን ለማነጋገር ያደረገው ጥረት እንዳልተሳካ አመላክቷል። • የኢቲ 302 የመጨረሻዎቹ ስድስት ደቂቃዎች በእሲያ የጉልበት፣ የጥሬ ግብዓት እና የግብር ወጪ መጨመርን ተከትሎ ግዙፍ ኩባንያዎች ፊታቸውን ወደ አፍሪካ አዙረዋል። ኢትዮጵያም የተመቻቸ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማቅረብ የግዙፍ ኩባንያዎችን ትኩረት ለመግኘት ትጥራለች። ኢትዮጵያ የተተመነ ዝቅተኛ ክፍያ መጠን ባይኖራትም፤ ማንኛውንም ዓይነት ጥሰቶችን መፈፀም የሚከለክል የአሠራር ሥርዓት አላት። ፒቪኤች (PVH) በዓለማችን ከሚገኙ ግዙፍ የአልባሳት አምራች ድርጅቶች መካከል አንዱ ሲሆን አንድ ሚሊዮን ከሚጠጉ ሠራተኞቹ ባሳለፈነው የፈረንጆቹ ዓመት ብቻ 9.7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መሰብሰብ ችሏል።
news-57056786
https://www.bbc.com/amharic/news-57056786
ምዕራብ ኦሮሚያ፡ በደምቢ ዶሎ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች የተገደለው ወጣት ማን ነው?
ትናንት ማክሰኞ፣ በምዕራብ ኦሮሚያ ቄለም ወለጋ ዞን ደምቢ ዶሎ ከተማ አማኑኤል ወንድሙ የተባለ ወጣት በአደባባይ በመንግሥት ኃይል መገደሉን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ።
የአካባቢ የመንግሥት ባለስልጣናትም የወጣቱን መገደል አረጋግጠው፤ ወጣቱ ለሕዝብ እንዲታይ ተደረገ እንጂ በአደባባይ አልተገደለም ሲሉ አስተባብለዋል። የአካባቢው የመንግሥት ባለሥልጣናት ወጣት አማኑዔል 'የአባ ቶርቤ' ቡድን አባል በመሆኑ 'እርምጃ ተወስዶበታል' በማለት ማብራሪያ ሰጥተዋል። የደምቢ ዶሎ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት በበኩሉ ሰዎችን ሲገድል በነበረው እና 'የአባ ቶርቤ' ቡድን አባል በሆነው ግለሰብ ላይ እርምጃ ተወሰደ ሲል በፌስቡክ ገጹ ላይ ጽፏል። የከተማው ጽ/ቤት በፌስቡክ ገጹ ላይም ወጣቱ ከመገደሉ በፊት የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል አትሟል። በአካባቢው በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው የ"ሸኔ" ቡድን እንደሚንቀሳቀስ ይነገራል። በምዕራብ ኦሮሚያ በተለያዩ አካባቢዎች ቡድኑ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት በማድረስ በተደጋጋሚ ይወነጀላል። በዚህ ቪዲዮ ላይ ምን ይታያል? በዚህ የፌስቡክ ገጽ ላይ ወጣቱ ከመገደሉ በፊት ለቀረቡለት ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጥ ይታያል። ቪዲዮን እየቀረጸ የሚገኘው ሰው የወጣቱን ስም እና የትውልድ ስፍራውን ይጠይቀዋል። እጁ ወደ ኋላ የታሰረው ወጣት አንገቱ ላይ ሽጉጥ ተንጠልጥሎ ይታያል። በወጣቱ እግር ላይ እና በዙሪያው ደም የሚታይ ሲሆን ልብሱም በጭቃ ተለውሷል። አደባባይ ፊትለፊት የቆመው ወጣት ስሙ አማኑኤል ወንድሙ ከበደ እንደሚባል እና ትውልዱ ደምቢ ዶሎ ከተማ 07 ተብሎ በሚጠራ ስፍራ እንደሆነ ይናገራል። በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ የደንብ ልብስ በለበሱ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎ ተከቦ ይታያል። ወጣቱ ለምን ተገደለ? የከተማው ኮሚውኒኬሽን ጽ/ቤት እንደሚለው ከሆነ ይህ ወጣት የመንግሥት ባለስልጣናት በመግደል የሚታወቀው "አባ ቶርቤ' የተሰኘው ህቡዕ ቡድን አባል ነበር። ወጣቱ ትናንት በቁጥጥር ሥር ከመዋሉ በፊትም ንጋት ላይ ገመቹ መንገሻ የተባለ ግለሰብ በጥይት መትቶ ለማምለጥ ሲሞክር "በጸጥታ ኃይሎች ጠንካራ ትስስር እግሩን ተመትቶ ተይዟል" ብሏል። ከዚህ በተጨማሪም ከቀናት በፊት በደምቢዶሎ ከተማ የኦሮሚያ ብሮድካስቲን ኔትዎርክ ጋዜጠኛ የነበረውን ሲሳይ ፊዳ የገደለው የአባ ቶርቤ ቡድን ነው ሲል አክሏል። የዓይን እማኝ ምን ይላሉ? የደምቢዶሎ ከተማ ነዋሪ የሆኑት እና ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸውን እንዳይጠቀስ የጠየቁ ግለሰብ ወጣቱ በአደባባይ ሲገደል ማየታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። "አማኑኤል ሕዝብ የሚወደው ልጅ ነበር" ካሉ በኋላ፤ በጥይት ተመትቶ ከተያዘ በኋላ "ሲገደል በዓይናችን አይተናል" ብለዋል። እኚህ ነዋሪ እንደሚሉት ከሆነ የመንግሥት ጸጥታ አስከባሪ አካላት ወጣቱ ለመያዝ ሲንቀሳቀሱ ወጣቱ ከአንድ ሱቅ እቃ እየገዛ ነበር ይላሉ። ይህ ነዋሪ በአደባባይ ከተገደለው ወጣት በተጨማሪ በተመሳሳይ ቀን ሌሎች ሁለት ወጣቶች በጥይት ተመትተው ለተጨማሪ ሕክምና ወደ ሌላ ስፍራ ስለመወሰዳቸው አውቃለሁ ብለዋል። የቄለም ወለጋ ዞን የደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተሰማ ዋሪዮ በበኩላቸው ወጣቱ ቆስሎ ከተያዘ በኋላ ለሕዝብ እንዲታይ ተደረገ እንጂ በአደባባይ አልተገደለም ይላሉ። "ተጠርጣሪ አይደለም" የሚሉት አቶ ተሰማ፤ ይህ ወጣት ሁለት ሰዎች በጥይት መትቶ እያመለጠ ሳለ በፀጥታ ኃይሎች በጥይት ተመትቶ መያዙን ይናገራሉ። ወጣቱ ለፍርድ ሳይቀርብ ለምን መሰል እርምጃ ተወሰደበት ለሚለው ጥያቄ ወጣቱ 'ተጠርጣሪ አይደለም' ከማለት ውጪ አቶ ተሰማ ተጨማሪ ማብራሪያ አልሰጡም። ለዚህ ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት የሚመለከታቸውን የክልሉን ባለስልጣናት ለማናገር ያደረግነው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል። አቶ ተሰማ በደምቢዶሎ አካባቢ ከሰሞኑ በኦነግ ሸኔ እና በመንግሥት ኃይሎች መካከል የተኩስ ልውውጥ እንደነበረ ተናግረው፤ ወጣቱ አንገት ላይ የተንጠለጠለው ሽጉጥ ንጹሃን ዜጎችን እና የመንግሥት ኃይሎችን ሲገድልበት የነበረ ነው ብለዋል። ቢቢሲ የዞኑ ፖሊስ ባልደረቦችን አነጋግሮ ያገኘው ምላሽ አቶ ተሰማ ከሰጡት አስተያየት ጋር ተመሳሳይ ነው። ማክሰኞ ዕለት 'አባ ቶርቤ' ተብሎ በሚጠራው ቡድን ተመቱ ከተባሉት የከተማዋ ነዋሪዎች መካከል አንዱ አቶ ገመቹ መንገሻ በመባል የሚጠሩ ባለሃብት መሆናቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በበኩሉ በቄለም ወለጋ ዞን ደምቢ ዶሎ በወንጀል የተጠረጠረውን አማኑኤል ወንድሙ ከፍርድ ውጭ የተፈፀመበት ግድያ እንዳሳሰበው ገለጿል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ በኦሮሚያ ክልል ያለው የእስረኞች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ ያሳስበኛል ማለቱ ይታወሳል። ኮሚሽኑ በጎበኛቸው የፖሊስ ጣቢያዎች በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢና በአፋጣኝ ሊሻሻል የሚገባው ነው። ተጠርጣሪዎችን በሕግ ከመዳኘት ይልቅ የፖለቲካ (የአስተዳደራዊ) ውሳኔዎች ሰለባ እንዲሆኑ ተድርጓል ብሎ ነበር። አባ ቶርቤ ማነው? "አባ ቶርቤ" የኦሮምኛ ቃል ሲሆን ትርጉሙም "ባለ ሳምንት" ማለት ነው። ይህ ቡድን በኦሮሚያ የተለያዩ ስፍራዎች ታጥቆ ከሚንቀሳቀሰው እና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ ከሚጠራው አካል ጋር ግንኙነት እንዳለው የክልሉ ባለስልጣናት ይናገራሉ። ከዚህ ቀደም የኦሮሚያ ክልል አስተዳደርና ፀጥታ ኃላፊ አቶ ጅብሪል መሐመድ "አባ ቶርቤ ማለት የአሸባሪው ሸኔ የከተማው ክንፍ ነው" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። በከተማ ደግሞ 'አባ ቶርቤ' እና 'ሶንሳ' ተብሎ የሚጠራ ቡድን አለው። እነዚህ ቡድኖች በተቻላቸው መጠን ግድያ በመፈጸም ሽብር ለመፍጠር የሚሞክሩ ናቸው ሲሉ ተናግረው ነበር። አቶ ጅብሪል መሐመድ እንደሚሉት የዚህ ቡድን አባላት ምንም አይነት የተለየ ስልጠናም ሆነ መሳሪያ የላቸውም። የሚጠቀሙት ስልት፤ ማህበረሰቡን በመምሰል፤ ለማምለጥ በሚያመቻቸው ቦታ በድንጋት አደጋ አድርሰው ይሰወራሉ" ብለው ነበር አቶ ጅብሪል። የኦሮሚያ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ አባ ቶርቤ የሚባለው ቡድን በክልሉ በተለያየ ጊዜ በመንግሥት ባለስልጣናት፣ የጸጥታ ኃይል አባላት እና ንሑሃን ዜጎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት ሲያደርስ መቆየቱን ይገልጻሉ።
50258990
https://www.bbc.com/amharic/50258990
ከፕሬዘዳንቱ ጋር 'ፊት በመለዋወጥ' ተይዞ የነበረው ቀልደኛ ተለቀቀ
ፎቶውን ከታንዛንያው ፕሬዘዳንት ጆን ማጉፉሊ ጋር በመለዋወጡ ተይዞ የነበረው ቀልደኛ (ኮሜድያን) ኢድሪስ ሱልጣን በዋስ ተለቀቀ።
ቀልደኛው ኢድሪስ ሱልጣን እና ፕሬዘዳንት ጆን ማጉፉሊ ፊታቸው ተቀያይሮ የሚያሳየው ምስል ታንዛንያዊው ኮማኪ ዘና ብሎ ከተነሳው ፎቶ ላይ የፊት ገጽታውን ቆርጦ በመውሰድ፤ ፕሬዘዳንቱ ኮስተር ብለው የሚያሳይ ፎቶግራፍ ላይ አስቀምጦታል። የፕሬዘዳንቱን ፊት ቆርጦም በሱ ፎቶ ላይ በሚታየው ፊቱ ተክቶታል። • ትሬቨር ኖዋ የዓለማችን አራተኛው ቱጃር ቀልደኛ ሆነ • ፈረንሳያዊው ደራሲ የአምሳ አመት ሴቶችን ለፍቅር ዕድሜያቸው "የገፋ' ነው ማለቱ ቁጣን ቀስቅሷል • ቢል ኮዝቢ ወደ ዘብጥያ ወረዱ ኮሜድያኑ፤ እሱና ፕሬዘዳንቱ ፊት ተለዋውጠው የሚያሳየውን ፎቶ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ማጋራቱን ተከትሎ ለምርመራ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስዶ ነበር። የኢድሪስ ጠበቃ ኢሊያ ሪዮባ፤ በአገሪቱ የመረጃ ደህንነት ሕግ መሰረት እንደተያዘ ገልጸዋል። በሕጉ ሰዎችን ማስመሰል የተከለከለ ነው። ቀኝ ዘመም የመብት ተሟጋቾች ሕጉ የመናገር ነጻነትን ይገድባል ሲሉ ተችተዋል። ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ከአምስት ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያሉት ኢድሪስ ፎቶውን ሲለቅ "ፕሬዘዳንቱ ልደታቸውን በሰላም እንዲያከብሩ ከእኔ ጋር ሚና ተለዋውጠዋል" ሲል በስዋሂሊ ጽፏል። ፎቶውን ከለጠፈ በኋላ የዳሬ ሰላም ፖሊስ ኮሚሽነር ፖል ማኮንዳ "ሥራው ምን ድረስ የተገደበ እንደሆነ አያውቅም" ብለዋል። ፕሬዘዳንቱ 60ኛ ዓመት ልደታቸውን ያከበሩት ባለፈው ማክሰኞ ሲሆን፤ ቀልደኛው ለምርመራ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስዶ የነበረው እሮብ ነበር።
news-52965328
https://www.bbc.com/amharic/news-52965328
ደቡብ ኮሪያ ‹‹ሰሜን ኮሪያ ስልኬን አታነሳም›› ስትል ከሰሰች
ሰሜን ኮሪያ ቅር ተሰኝታለች። ከጎረቤት ደቡብ ኮሪያ ጋር የተጀመሩ ግንኙነቶችን በሙሉ አቆማለሁ ብላ ስትዝት ነበር፤ ይህንንም አድርገዋለች።
ሰሜን ኮሪያዊያን ተማሪዎች ወደ ደቡብ የከዱ ዜጎቻቸውን ያወገዙበት ትናንት የተካሄደ ሰልፍ ደቡብ ኮሪያ እውነትም ደንበኛ ጠላት አገር ናት ብላታለች። ሰሜን ኮሪያን ያስኮረፋት ከደቡብ ኮሪያ የሚነሱ "ጠብ አጫሪ" ያለቻቸው ፊኛዎች ናቸው። ፊኛዎቹ የሚላኩት ደግሞ ሰሜን ኮሪያን ከከዱ ከዐዕራሷ ዜጎች መሆኑ አበሳጭቷል። ከሰኞ ጀምሮ በሰሜን ኮሪያ ድንበር ከተማ ካውሶንግ በኩል ሲደረግ የነበረው ዕለታዊ የስልክ ግንኙነትም አብቅቷል ብለዋል የሰሜን ኮሪያ ባለሥልጣናት። ሁለቱ አገራት በመሀላቸው ያለውን ጠላትነት ለመቀነስ በዚህች የድንበር ከተማ ቢሮ ከፍተው ከ2018 ጀምሮ ግንኙነት ለማድረግ ሲጥሩ እንደነበር ይታወሳል። ሰሜንና ደቡብ ኮሪያ ዛሬም ድረስ በጦርነት ላይ እንዳሉ ነው የሚገመተው፤ ምክንያቱ ደግሞ በፈረንጆቹ 1953 ጦርነት ሲያቆሙ አንዳችም የረባ መደበኛ የሰላም ስምምነት ስላልተፈራረሙ ነው። የኮሪያ ማዕከላዊ ዜና አገልግሎት (ኬሲኤንኤ) እንዳስተላለፈው መግለጫ ከሆነ ታላቋ ሰሜን ኮሪያ ከጠላት አገር ደቡብ ኮሪያ ጋር ለመቀራረብ ከፍታው የነበረችው ጊዜያዊ ቆንስላ ከማክሰኞ ሰኔ፣ 2020 ማለዳ ጀምሮ ዘግታዋለች። ወታደራዊ የግንኙነት መስመሮችም ከእንግዲህ አንድ በአንድ ይዘጋሉ። ይህ ሁለቱን አገራት አገናኝ ቢሮ ባለፈው መስከረም በወረርሽኙ ምክንያት ቢዘጋም ሁለቱ አገራት እርስ በእርስ የሚያደርጉትን የስልክ ግንኙነት ሲያሳልጥ ቆይቶ ነበር። ሁለቱ ኮሪያዎች በቀን ቢያንስ ሁለት ጊዜ ስልክ ይደዋወሉ ነበር። አንዱ ጠዋት 3 ሰዓት ላይ ሌላኛው አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ። ሰኞ ዕለት ግን በ21 ወራት ለመጀመርያ ጊዜ "ስልክ ደውዬላት ሰሜን ኮሪያ ስልኬን አላነሳችውም" ስትል ደቡብ ኮሪያ አስታውቃለች። ሰሜን ኮሪያ ለዚህ በሰጠችው ምላሽ "ስልክሽን ያላነሳሁት ከዚህ ወዲህ ፊት ለፊት መገናኘትም ሆነ በስልክ ማውራቱ ዋጋ ቢስ በመሆኑና ድርጊትሽ ሁሉ ለብስጭት እየዳረገኝ ስለሆነ ነው" ብላታለች። የሰሜን ኮሪያው ተፈሪ መሪ የኪም እህት የሆነችው ኪም ዮ ጆንግ ባለፈው ሳምንት በአገሪቱ ቴሌቪዥን ባስተላለፈችው መልዕክት "ከአገሬ የከዱ ባንዳዎች ከደቡብ ኮሪያ ሆነው በራሪ ወረቀቶችን የያዙ ፊኛዎችን እየላኩ አበሳጭተውኛል፤ ስለዚህ እርምጃ እወስዳለሁ" ስትል አስፈራታ ነበር። በዚህ መግለጫዋ ይህ ጠብ አጫሪ መልእክቶችን የያዙ ፊኛዎችን ወደ ሰሜን ኮሪያ መላክ ሁለቱ ጎረቤት አገራት የደረሱበትን የሰላም ስምምነት የሚጥስና እኛንም የሚያበሳጭ ነው ብላለች። ድርጊቱ በፍጥነት ካልቆመ ግንኙነት ልታቋርጥ እንደምትችልም ስትዝት ነበር። ሁለቱ አገራት በ2018 ፓንሙጆም ላይ ባደረጉት ጉባኤ ሙን እና ኪም ሰላም ለመፍጠር መስማማታቸው ይታወሳል። ከሰሜን ኮሪያ የከዱ ዜጎች ደቡብ ኮሪያ ከገቡ በኋላ ፖስት ካርዶችና በራሪ ወረቀቶችን የያዙ ፊኛዎችን ወደ ሰማይ በማጎን ወደ ሰሜን ኮሪያ እንዲገቡ የማድረግ ነገር ለዓመታት የተለመደ ተግባራቸው ሆኖ ቆይቷል። ፊኛዎቹ አንዳንድ ጊዜ ቼኮሌትና የፍቅር ደብዳቤዎችም ይታጨቁባቸዋል። የፖለቲካ መልእክቶችንም ይይዛሉ። ይህ ነገር ደግሞ ሰሜን ኮሪያን እጅጉኑ ያበሳጫታል። ደቡብ ኮሪያ ግን ነገሩ ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ ጉዳይ አድርጋ ነበር የምትመለከተው። በደቡብ ኮሪያ የሚኖሩ ከሰሜን ኮሪያ የከዱ የሰሜን ኮሪያ አርበኞች ማኅበር አባላት ይህንን በፊኛ መልዕክት በንፋስ ወደ ሰሜን የመላኩን ተግባር በፍጹም እንደማያቆሙት ሲዝቱ ነበር። ይህ ሐሳብን የመግለጽ መብታችን ካልተከበረማ ምኑን ደቡብ ኮሪያ ኖርነው ሲሉ አስተያየት ይሰጡ ነበር። ድርጊታቸውን እንዲያቆሙ ደቡብ ኮሪያም ፍላጎት እንዳላት ገልጻ ነበር፤ ምክንያቱም ሰሜን ኮሪያ በዚህ ድርጊት ክፉኛ አየተበሳጨችና ደሟ እየፈላ በመምጣቷ ነበር። ሰሜን ኮሪያዊያን በአብዛኛው ኢንተርኔት የላቸውም፤ ቢኖራቸውም መረጃን እንደልብ ማሰስ አይችሉም። ብቸኛ የመረጃ ምንጫቸውም የአገሪቱ ቴሌቪዥን ጣቢያ ነው። በሁለቱ ኮሪያዎች መካከል የነበረው ጠላትነት ረገብ ያለው እንደ ፈረንጆቹ በ2018 የሁለቱ አገራት መሪዎች ሦስት ጊዜ ከተገናኙ በኋላ ነበር። እንዲህ በከፍተኛ ባለሥልጣናት ደረጃ ሁለቱ አገራት ከዚያ በፊት ተገናኝተው አያውቁም። ፒዮንግያንግ ከሴኡል ጋር ያላትን ግንኙነት እየቆረጠች የመጣችው ዛሬ ሳይሆን ኪም ከዶናልድ ትራምፕ ጋር በቬትናም ሃኖይ ሊያደርጉት የነበረው ግንኙነት ከተሰረዘ በኋላ ነው። ሁለቱ ኮሪያዎች ከ1950-53 ያደረጉት ጦርነት ያበቃው በሰላም ስምምነት ሳይሆን በተኩስ አቁም ብቻ ስለነበረ አሁንም ድረስ ሁለቱም አገራት ጦርነት ላይ እንደሆኑ ነው የሚያስቡት።
news-51717024
https://www.bbc.com/amharic/news-51717024
ኮሮናቫይረስ፡ ትዊተር በቫይረሱ ምክንያት ሠራተኞቹ ከቤታቸው እንዲሠሩ ፈቀደ
ትዊተር የተሰኘው ግዙፍ የማሕበራዊ ሚድያ ኩባንያ ሠራተኞቹ ኮሮናቫይረስ እንዳይዛቸው በመስጋት ከመኖሪያ ቤታቸው ሆነው እንዲሠሩ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ድርጅቱ በድረ-ገፅ እንዳሳወቀው ሆንግ ኮንግ፣ ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ የሚገኙ ሠራተኞቹ በጠቅላላ ከቤታቸው ሆነው እንዲሠሩ ተፈቅዶላቸዋል። ከእነዚህ ሃገራት አልፎ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ 5 ሺህ ሠራተኞች ከመኖሪያቸው ሆነው እንዲሠሩ እያበረታታ መሆኑ ተሰምቷል። ድርጅቱ ከጥቂት ቀናት በፊት በጣም አስፈላጊ ካልሆነ ሠራተኞቹ በፍፁም ጉዞ እንዳያደርጉ እንዲሁም አላስፈላጊ ዝግጅቶች እንዲቀሩ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ትዊተር፤ ሂዩስተን ቴክሳስ ውስጥ ሊካሄድ የታሰበ የሚድያ ኮንፈረንስ ላይ እንደማይሳተፍ ማሳወቁ አይዘነጋም። የድርጅቱ ሰው ኃይል አስተዳዳሪ ጄኒፈር ክሪስቲ "ዓላማችን ኮሮናቫይረስ በሠራተኞቻችን መካከል የሚሠራጭበት ፍጥነትን መግታት ነው። አልፎም የሠራተኞቻችንን ቤተሰቦች መታደግ ነው" ሲሉ ውሳኔያቸውን አስረግጠዋል። የትዊተር አለቃ ጃክ ዶርሲ ከኮሮናቫይረስ መከሰት በፊት ጀምሮ ከቤት መሥራት አዋጭ ነው ብሎ እንደሚያምን ይነገርለታል። ባለፈው ጥቅምት ለስድስት ወራት ያክል አፍሪካ ውስጥ መኖር እፈልጋለሁ ሲልም አስታውቆ ነበር። እስያ ውስጥ ያሉ በርካታ ኩባንያዎች ተመሳሳይ መርህ እየተከተሉ ነው። የቫይረሱ ሥርጭት ያሰጋቸው የትየለሌ ድርጅቶች ሠራተኞቻቸው ከቤት ሆነው እንዲሠሩ ትዕዛዝ ሰጥተዋል። አልፎም ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በዚህ ዓመት የሚካሄዱ ስብሰባዎች ላይ እንደማይሳተፉ እያሳወቁ ነው። ሠራተኞቻቸው ከሃገር ሃገር የሚያደርጉትን ጉዞ ገታ እንዲያደርጉም አሳስበዋል። በዚህ ፌስቡክና እና ጉግል ተጠቃሽ ናቸው። በኮሮናቫይረስ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከሶስት ሺህ በላይ መድረሱ ተሰምቷል።
news-52796480
https://www.bbc.com/amharic/news-52796480
የስክሪን ሱሰኛ ነዎት? እንግዲያውስ እነዚህን ይሞክሩ
ድንገት ሳያስቡት ስልክዎን ከኪስዎ መዘው ያወጣሉ? ከኢንተርኔት መላቀቅ አይችሉም? ማኅበራዊ ድረ ገጹ ሱስ ሆኖቦታል? በቲቪ መስኮት ላይ እንዳፈጠጡ መሽቶ ይነጋል? ነግቶስ ይመሻል?
ይህ የእርስዎ ብቻ ችግር አድርገው አይውሰዱት። በዓለም ላይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከተንቀሳቃሽ ስልኮቻቸው ጋር ተጣብቀው አሉ። ይሰቃያሉ፣ እንቅልፍ ያጣሉ፣ ስልኮቻቸውን አለመነካካት አይችሉም። ባል ከሚስት፣ እናት ከልጅ፣ አባት ከቤተሰቡ ጋር አፍ ለአፍ ገጥሞ ማውራት ተስኖታል። በሽታ ነው። ክፉ በሽታ። የስክሪን በሽታ። በዚህ በኮሮናቫይረስ ዘመን ደግሞ ብሶበታል። አይፎን ከያዙ በቀን ስንት ሰዓት በስክሪንዎ ላይ እንዳፈጠጡ ይነግርዎታል። በእውነቱ ይደነግጣሉ። በኮሮናቫይረስ ምክንያት የሰዎች የስክሪን ላይ የመደቀን አባዜ በ30 ከመቶ መጨመሩን አንድ ጥናት አሳይቷል። እውነት ለመናገር ስልክዎ ላይ የሚያጠፉት አብዛኛው ሰዓት የሚያስቆጭ ነው። መጻሕፍት ቢያነቡ የተሻለ እንደሚጠቀሙ እሙን ነው። ከልጆችዎ ጋር ቢጫወቱ የተሻለ እንደሚደሰቱ አሌ አይባልም። ወጣ ብለው ዱብ ዱብ ቢሉ የተሻለ ጤና እንደሚያገኙ አያጠራጥርም። ታዲያ ከስልክዎ ጋር ለምን አይፋቱም? የስክሪን ሱስ በጊዜ ሃይ ካልተባለ እያሳሳቀ የሚወስድ ደዌ ነው። ኾኖም ከሱሱ መፈወስ እንዲህ የዋዛ አይደለም። የስክሪን ሱስን መስበር ቁርጠኝነት ይጠይቃል። አሁን የጤና ባለሞያዎችን እያሳሰበ ያለው ሰዎች ከስልኮቻቸው ጋር መለያየት ባለመቻላቸው ለአእምሮ ጤና ችግር የመጋለጥ ዕድላቸው እየመጨመረ መምጣቱ ነው። ይሄ ነገር ይመለከተኛል ካሉ ዘላቂ መፍትሄ እስኪያገኙለት ድረስ እነዚህን አምስት መንገዶች ይከተሉ። 1. እረፍት ይውሰዱ ዶ/ር ቼትና ካንግ በናይንቲንጌል የአእምሮ ሆስፒታል የቴክኖሎጂ ውጤቶች ሱስ ማገገሚያ ክፍል ሐኪም ናቸው። እርሳቸው እንደሚሉት ምን ያህል ሰዓት በስክሪን ላይ አፍጥቶ መዋል ነው ጤናማ ለሚለው ቁርጥ ያለ መልስ የለም። ሆኖም ለሰዓታት ከቆዩ በሽታ ነው። እስኪ በትንሽ በትንሹ እነዚህን ለማድረግ ይሞክሩት። ለምሳሌ አንድ ሰዓት ስልክዎ ላይ የሚያፈጡ ከሆነ ቢያንስ 15 ደቂቃ እረፍት ይውሰዱ። 30 ደቂቃ ከሆነ ቢያንስ 7 ደቂቃ ፋታ ያድርጉ። ይህ የሚመከረው እንዲሁ አይደለም። ለተከታታይ ሰዓት ስክሪን ማየት መጀመሪያ ዓይንን ስለሚጎዳ፣ ቀጥሎ ራስ ምታትንን ስለሚያስከትል፤ ቀጥሎ ደግሞ ድብርትን ስለሚቀሰቅስ ነው። ዶ/ር ቼትና ካንግ እንደሚሉት ዘለግ ላለ ሰዓት ያለ እረፍት ስክሪን ማየት ቀስ በቀስ ራስን ወደ መጥላት፣ በራስ ላይ ቁጥጥርን ወደ ማጣትና በመጨረሻም የአእምሮ መላላትን ያመጣል። ስለዚህ እባክዎ ቢያንስ የ15 ደቂቃ እረፍት መውሰድን ይለማመዱ። 2. ሱስዎን ምን እንደሚቀሰቅሰው ይለዩ አንዳንድ ጊዜ እንዴት እጅዎ ተንደርድሮ ኪስዎ ውስጥ እንደገባ ለራስዎ እንኳን ሳይገርምዎ ይቀራል? ሴቶች ሳያስቡት ቦርሳቸው ውስጥ ሰተት ብለው ይገባሉ። ስልካቸውን ለምን እንደፈለጉት እንኳ አያውቁም። ወንዶችም እንዲሁ። ለምን ይመስልዎታል? ነገሩ ሱስ ነው! አንዳንዴ ከሱሱ ይልቅ ወደ ሱሱ የሚመሩንን ነገሮች መፈተሸም ተገቢ ነው። ለምሳሌ ድብርት፣ ሥራ መፍታት፣ የስሜት መታወክ ሊሆን ይችላል። በተለይ ደግሞ ብቸኝነት ከተሰማን አጫዋች እንፈልጋለን። በዚህ ጊዜ እጃችን ተንደርድሮ ስልክ መዞ ያመጣል። ስለዚህ ሱሱን ከማከምዎ በፊት ስሜትዎ ላይ ይስሩ። ለምሳሌ የሚሰማዎትን ስሜት ለጓደኛዎ ያጋሩት። ስክሪን ላይ ከሚያፈጡ በድምጽ ያውሩት። ወይም ወረቀት ላይ ይጻፉት፣ ወይም መጻሕፍት ገልጠው ያንብቡ። ያ መጥፎ ስሜት ሲጠፋ የስልክ ሱስዎ ረገብ ማለት ይጀምራል። 3. የስልክ መመልከቻ ሰዓት ይወስኑ ሁላችንም ጠዋት ተነስተን የመጀመሪያ ተግባራችን ስልክ ላይ ማፍጠጥ ከሆነ አደጋ አለው። መጀመርያ እጅዎን ወደ ስልክዎ እንዲዘረጉ የሚያደርጉ ምክንያቶችን ይለዩ፤ ከዚያ እነርሱ ላይ ቁጥጥር ያድርጉ። ለምሳሌ ከእንቅልፍ የሚቀሰቅስዎትን ደወል ስልክዎ ላይ ከመጫን በሌላ ደውል ይተኩት፤ ስልክዎ ከቀሰቀሰዎ ስልክ ላይ የማፍጠጥዎ ዕድል ከፍተኛ ስለሚሆን። ወደ መኝታ ሲገቡ ስልክዎን ይዘው ባይገቡ ይመረጣል። ለምን መሰልዎ? አንደኛ ከስክሪን የሚወጣው ጨረር ለዓይን ጤና ጸር ነው። ለእንቅልፍ እጦትም ይዳርግዎታል። የእንቅልፍዎን ጥራትም ይቀንሰዋል። 4. ከስልክዎ ይልቅ ሰው ይምረጡ ከሰዎች ጋር ለመገናኘት ስልካችን ሁነኛው መንገድ ነው። ዙም፣ ፌስታይም፣ ስካይፕ፣ ሃውስፓርቲ የተሰኙት የማኅበራዊ መገናኛ የስክሪን ቡና ቤቶች አሁን የሰው ለሰው ግንኙነትን እየተኩ ነው። ዶ/ር ቼትና ካንግ እንደሚሉት በዚህ መንገድ ሰዎችን ማግኘት ብቸኛው ወይም ዋንኛው ዘዴ መሆን አይኖርበትም። ሰዎችን በአካል ማግኘት እጅግ የማይተካ ስሜትን ይሰጣል። ያን ይሞክሩ። ይሄ ታዲያ በኮሮናቫይረስ ጊዜ ማለት እንዳልሆነ መቼስ ለእርስዎ አይነገርም። 5. እስኪ ስልክዎን እርግፍ አድርገው ወደ ደጅ ይውጡ አንዳንድ ጊዜ ከስልክ በፊት ሕይወት እንዴት ነበር የተኖረው ብለው አልጠየቁም? እርግጥ ነው ከተንቀሳቃሽ ስልክ መፈጠር በፊት የሰው ልጅ ምድር ላይ ኖሯል። ያን ለማወቅ ለምን ስልክዎን ቤት አስቀምጠው ትንሽ ንፋስ ተቀብለው፣ በሰፈር ወዲያ ወዲህ ብለው፣ ጓደኛዎን አግኝተው፣ ሻይ ቡና ብለው፤ ጋዜጣ አንብበው አይመጡም? ሁሌም ባይሆን አንዳንዴ። አሁን እኮ ነገሩ እየከበደ ነው። ከስልካችን ቴሌቪዥን ይቀበለናል፤ ቴሌቪዥን እያየንም እጃችን ስልካችንን መነካካቱን አይተውም፤ ከዚያ ደግሞ ላፕቶፕ አለ፤ ከዚያ ኔትፍሊክስ ወደ አልጋችን አንከብክቦ ይወስደናል። ከስክሪን ወደ ስክሪን ሆነ ነገሩ ሁሉ። ዶ/ር ቼትና ካንግ እንደሚሉት ይሄ ነገር ለጤና ጥሩ አይደለም። መጀመርያ አይናችንን ቀስ በቀስ ደግሞ አእምሯችንን ይነካል። በሳምንት አንድ ቀን ጨርሶዉኑ ስክሪን ላይ የማያፈጡበት ቀን ለምን አይመድቡም? ያን ማድረግ ከቻሉ ጥሩ ጅማሮ ነው። ከመጻሕፍት ጋር አንድ ጊዜ በፍቅር ከወደቁ ደግሞ ስክሪን ትዝም ላይልዎ ይችላል።
news-52212410
https://www.bbc.com/amharic/news-52212410
ኮሮናቫይረስ ፡የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ ባንክ እያዘጋጀሁ ነው አለ
የኮሮናቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ከተሰማበት ዕለት አንስቶ መንግሥት ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ይረዳኛል ያላቸውን በርካታ እርምጃዎች ሲወስድ ቆይቷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም በከተማዋ ያለውን ሥርጭት ለመግታት ከውጭ ለሚመጡ ተጓዦች የለይቶ ማቆያ ቦታ ማዘጋጀትን ጨምሮ ሌሎች ሥራዎችንም ሲሰራ ነበር። ከእነዚህ ሥራዎች ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባ ፅ/ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪ ወ/ሪት ፌቨን ተሾመ የከተማዋ ባለሃብቶች፣ ግለሰቦችና ወጣቶች የከንቲባውን ጥሪ ተከትሎ በርካታ ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀዋል። ድጋፉ የገንዘብ፣ የቁሳቁስ እንዲሁም የበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎት ነበር ያሉት የፕሬስ ሴክረተሪዋ እስካሁን ከ200 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የገንዘብና የአይነት ድጋፍ መሰብሰቡን ተናግረዋል። የተሰባሰቡት የንጽህና መጠበቂያዎች አቅም ለሌላቸው የከተማዋ ነዋሪዎችን በየክፍለ ከተማው በመለየት የመስጠት እንቅስቃሴ በዚህ ሳምንት ይጀመራል ያሉት ወ/ት ፌቨን፣ በየክፍለ ከተማው ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተብሎ ከ450 ሺህ በላይ ዜጎች መለየታቸውንም ጨምረው አስረድተዋል። • የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የኢትዮጵያ ዝግጁነት ምን ይመስላል? በሌላ ዓለም እንደታየው የቫይረሱ ሥርጭት ከፍ ካለ እና ዜጎች ተንቀሳቅሰው መስራት የማይችሉበት ነገር ከተፈጠረ በማለት የከተማ አስተዳደሩ የምግብ ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀቱንም ፕሬስ ሴክሬታሪዋ ጠቁመዋል። በዚህም መሰረት በየወረዳው ከ1 ሺህ 20 በላይ የምግብ ማከማቻና ማሰራጫ ማዕከላት እየተደራጁ ነው በማለት ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ወገኖች የመለየት ሥራም ተከናውኗል። ፕሬስ ሴክሬታሪዋ እንዳሉት በእነዚህ በተዘጋጁት ማዕከሎች በኩል ግዢ የተፈፀመባቸው እህሎችንና ሌሎች ቁሳቁሶች የማስገባት ሥራ ተጀምሯል። በከተማዋ የሚገኙ በርካታ ግለሰቦች የመኖሪያ ቤታቸውን፣ የእምነት ተቋማት የአምልኮ ሥፍራቸውን እንዲሁም ሆቴሎች ቦታቸውን ለለይቶ ማቆያነት ለመስጠት ቃል መግባታቸውን አስታውሰው፤ የከተማ አስተዳደሩ እነዚህን ሥፍራዎች ለለይቶ ማቆያነት እንዲሆኑ ለማድረግ በቁሳቁስ የማሟላት ሥራ እየተከናወነ ነው። እነዚህን ሥፍራዎች ውስጥ አልጋ፣ ፍራሽ፣ አልባሳት እንዲሁም የሕክምና አገልግሎት እንዲሟላላቸው የማድረግ ሥራ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
news-55191619
https://www.bbc.com/amharic/news-55191619
አርጀንቲና በወረርሽኙ የተጠቁትን ለመደጎም የናጠጡ ኃብታሞቿ ላይ ግብር ጣለች
አርጀንቲና አገሯ በሚገኙ የናጠጡ ኃብታሞች ላይ ለየት ያለ ግብር ጥላለች።
ግብሩ ለኮሮናቫይረስ የሚያስፈልጉ የህክምና ቁሳቁሶች ግብዓትና በወረርሽኙ ምክንያት ክፉኛ ለተጠቁት ኑሯቸውን መደጎሚያ እንዲሆን ነው። የምክር ቤቱ አባላት "የሚሊዮነሮች ግብር" ብለው የጠሩት በአንዴ የሚከፈል ገንዘብ ሲሆን በዚህ ሳምንት አርብም 42 ለ 26 በሆነ የድምፅ ብልጫም ፀድቋል። በዚህም መሰረት ከ200 ሚሊዮን ፔሶ (2.5 ሚሊዮን ዶላር) ኃብት ያከማቹ ግለሰቦች መክፈል አለባቸው። በአገሪቱ ይህ የገንዘብ መጠን ያላቸውም ወደ 12 ሺህ ግለሰቦች ናቸው ተብሏል። አርጀንቲና በወረርሽኙ ክፉኛ ከተጠቁ አገራት አንዷ ስትሆን እስካሁን ባለውም መረጃ 1.5 ሚሊዮን በቫይረሱ ሲያዙ 40 ሺህ ደግሞ ህይወታቸው አልፏል። የህዝብ ቁጥሯ 45 ሚሊዮን ብቻ የሆነው አርጀንቲና በወረርሽኙ በሚሊዮኖች በተያዙ ተርታ አምስተኛ ደረጃን ይዛለች። ከህዝብ ቁጥሯ ጋር ሲነፃፀር ደግሞ ከሚሊዮን በላይ ካስመዘገቡ ትንሿ አገር አድርጓታል። ወረርሽኙን ለመግታት ያስቀመጠቻቸው መመሪያዎች ከፍተኛ ተፅእኖን አሳርፈዋል። በስራ አጥነት፣ በርካታዎች በድህነት ወለል በሚኖሩባትና አገሪቷ ራሷ በብድር በተዘፈቀበችበት ሁኔታ መመሪያዎቹ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆነዋል። አርጀንቲና ከ2018 ጀምሮም በምጣኔ ኃብት ድቀት ላይ ናት። የሚሊዮነሮችን ግብር ካረቀቁት መካከል አንዱ ህጉ 0.8 በመቶ የሚሆነውን ግብር ከፋይ ብቻ ነው የሚመለከተው ብለዋል። በአርጀንቲና ውስጥ ያሉት ሃብታሞች፣ ከአንጡራ ሃብታቸው 3.5 በመቶ እንዲሁም ከአገር ውጭ ያሉ አርጀንቲናውያን ደግሞ 5.25 በመቶ እንዲከፍሉ ውሳኔ ተላልፏል። ከግብሩ የተሰበሰበው ገንዘብም መካከል 20 በመቶ ለህክምና ቁሳቁሶች፣ 20 በመቶ ለጥቃቅንና አነስተኛ ነጋዴዎች፣ 20 በመቶ ለተማሪዎች የትምህርት ቤት ክፍያ፣ 15 በመቶ ለማህበራዊ ልማትና ቀሪው 25 በመቶ ደግሞ ለተፈጥሮ ነዳጅ ስራዎች እንደሚውል ኤኤፍፒ በዘገባው አስነብቧል። ግራ ዘመሙ ፕሬዚዳንት አልበርቶ ፈርናንዴዝ መንግሥት 300 ቢሊዮን ፔሶም ለማሰባሰብ እቅድ ይዘዋል። ሆኖም የተቃዋሚዎች ፓርቲ ቡድኖች በበኩላቸው ይህ የአንድ ጊዜ ግብር ሊሆን ስለማይችል የውጭ አገራት ኢንቨስትሮችን ፍራቻ ላይ ይጥላል በማለት ተችተዋል። የቀኝ ክንፍ ፓርቲ ጁንቶስ ፖር ኤል ካምቢዮ በበኩሉ የማይገባ ሲል የፈረጀው ሲሆን "ነጠቃም" ነው ብሎታል።
news-50864747
https://www.bbc.com/amharic/news-50864747
ኢትዮጵያ 4 ቢሊዮን ችግኞችን ተክላለች?
ኢትዮጵያ በሦስት ወራት ውስጥ አራት ቢልዮን ዛፎች ለመትከል ማቀዷን ይፋ ያደረገችው አምና ነበር።
ባለፈው ዓመት ሐምሌ ላይ በመላው አገሪቱ በአንድ ቀን 350 ሚሊዮን ችግኞች መተከላቸው መነገሩ ይታወሳል ባለፈው ዓመት ሐምሌ ላይ በመላው አገሪቱ በአንድ ቀን 350 ሚሊዮን ችግኞች ለመትከል ተወጥኖ በርካቶች መሰማራታቸው ይታወሳል። ነሀሴ መጨረሻ ላይ መንግሥት ግቡን እንደመታም ይፋ አድጓል። ለመሆኑ በነበረው አጭር ጊዜ የተባለውን ያህል ችግኝ መትከል ይቻላል? የተያዘው እቅድ ግቡን ለመምታቱስ ምን ማስረጃ አለ? የሚለውን የቢቢሲው 'ሪያልቲ ቼክ' ፈትሿል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የተቀናበረው የግሪን ሌጋሲ የችግኝ ተከላ ሳምንት አልፎታል። 'አረንጓዴ አሻራ' የተባለው የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ዘመቻ፤ በመላው ዓለም ያሉ ፖለቲከኞች ኢትዮጵያን በችግኝ ዘመቻ ተምሳሌት አድርገው እንዲያነሷት ምክንያት ሆኗል። የተፈጥሮ ኃብት ላይ ጉዳት የሚያደርስ ግብርና እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለመቀልበስም እንደ ምሳሌ ተጠቅሳለች። በቅርቡ በእንግሊዝ ምርጫ ሲካሄድ፤ አውራዎቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዛፎችን እንደሚተክሉ ቃል ሲገቡ፤ ማጣቀሻ ያደረጉት የኢትዮጵያን ተነሳሽነት ነበር። 'ሌበር ፓርቲ' እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ2040 ሁለት ቢሊዮን ዛፎች እንደሚተክል፣ ወግ አጥባቂዎች ደግሞ በየዓመቱ ቢያንስ 30 ሚሊዮን ዛፎች ለመትከል መወጠናቸውን ገልጸዋል። 'ግሪን ፓርቲ' በበኩሉ በ2030 700 ሚሊዮን ዛፎች እንደሚያደርስ ቃል ገብቷል። ካናዳ በቀጣይ አሥር ዓመታት ሁለት ቢሊዮን ዛፎች የማብቀል እቅድ ነድፋለች። ክብረ ወሰን የመስበር ውጥን ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓ. ም. ኢትዮጵያ አንድ ቀን የወሰደ የችግኝ ተከላ ዘመቻ አከናውናለች። የታቀደው በመላው አገሪቱ 200 ሚሊዮን ችግኞች ለመትከል ነበር። የኋላ ኋላ ግን መንግሥት ከታቀደው በላይ በ12 ሰዓት ውስጥ 353,633,660 ችግኝ መተከሉን ይፋ አደረገ። • የጠቅላይ ሚኒስትሩ 200 ሚሊዮን ችግኞች የችግኝ ተከላ ዘመቻው ሲተዋወቅ፤ የዓለም ክብረ ወሰንን መስበር እንደ አንድ ግብ ተይዞ ነበር። ሆኖም ቢቢሲ ለ'ጊነስ ወርልድ ሬከርድ' ጥያቄ ሲያቀርብ፤ ገና ማስረጃ እንዳልቀረባቸው ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በሦስት ወራት ውስጥ አራት ቢልዮን ዛፍ ለመትከል መወጠኗን ይፋ ያደረገችው አምና ነበር የተቋሙ ቃል አቀባይ ጀሲካ ስፒሌን "የመረጃ አጣሪ ክፍላችን እንዲያረጋግጥ፤ አዘጋጆቹ ያላቸውን ማስረጃ እንዲያሳውቁን እንጠይቃለን" ብለዋል። የጠቅላይ ሚንስትር ቢሮ፤ ተተከለ ስለተባለው የችግኝ ብዛት እንዲሆም መረጃው እየተጣራ ስለመሆኑ እንዲያብራራልን ብንጠይቅም፤ በችግኝ ተከላው ዙርያ ላሉ ብዙ ጥያቄዎች ኢትዮጵያ ምላሽ እንደሰጠች በመግለጽ፤ አስተያየት ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆነም። አራት ቢሊዮን ዛፎች መትከል ይቻላል? በሦስት ወራት ውስጥ አራት ቢልዮን ዛፎች ለመትከል ሲወጠን፤ በቀን ቢያንስ 45 ሚሊዮን ዛፎች ይተከላሉ ማለት ነው። በአንድ ቀን (ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓ. ም.) 350 ሚሊዮን ችግኞች መተከላቸውን ከግምት ብናስገባ፤ የዘመቻውን ግብ ለመምታት በተቀመጠው የጊዜ ክልል ውስጥ በቀን 40 ሚሊዮን ችግኝ መትከል ያስፈልጋል። የመንግሥት እቅድ ዛፎቹን በገጠሪቱ ኢትዮጵያ፣ በ6.5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ መትከል ነው። በትግራይ ክልል የተተከሉት አዳዲስ ችግኞች አካባቢው ደረቅ በመሆኑ ሳቢያ ለማደግ እየታገሉ ነው የአንድ ዛፍ መጠነ ስፋት በአማካይ በሄክታር 1,500 ነው ብንል፤ አራት ቢልዮን ዛፎችን መትከል የሚያስችል በቂ መሬት አለ ማለት ነው። ሆኖም ይህ ስለተተከሉት ችግኞች የሚነግረን ነገር የለም። • የተተከሉት ችግኞች እንዴት ተቆጠሩ? ያለን መረጃ የተገኘው ከመንግሥት ሲሆን፤ መረጃው በሦስት ወራት ውስጥ ከ3.5 ቢሊዮን በላይ ችግኞች እንደተተከሉ ይጠቁማል። በተጨማሪም ያልተተከሉ 1.3 ቢልዮን ችግኞች ፈልተዋል። ይህ ሁሉ ዛፍ የሚቆጠረው እንዴት ነው? ሁሉንም ዛፎች መቁጠር ባንችልም፤ በቅርቡ የተተከሉ ችግኞች ከሚገኙባቸው አካባቢዎች በአንዱ ተገኝቶ ፎቶ እንዲያነሳ ዘጋቢያችንን ልከን ነበር። በትግራይ ክልል የተተከሉት አዳዲስ ችግኞች አካባቢው ደረቅ በመሆኑ ሳቢያ ለማደግ እየታገሉ ነው። የሳተላይት ፎቶ የሚያጠና ድርጅትም አነጋግረን ነበር። ድርጅቱ አዲስ የተተከሉትና በመጠን አነስተኛ የሆኑትን ችግኞች ከእርሻ መሬት ለመለየት አዳጋች እንደሆነ ገልጾልናል። በተባበሩት መንግሥታት የደን ባለሙያ የሆኑት ቲም ክሪስቶፈርሰን፤ የዛፍ ተከላው ተግዳሮቶች ላይ ምንም ባይሉም፤ ኢትዮጵያ የደን ሽፋኗን ለማስፋት የምታደርገው ጥረት እንደሚያበረታታቸው ይናገራሉ። "ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በችግኝ ተከላው በተለይም ደግሞ ዛፎቹን በመንከባከብ ረገድ ድጋፍ እንዲሰጣት ጠይቃለች" የሚሉት ባለሙያው፤ አገሪቱ በ2030፤ 15 ሚሊዮን ሄክታር የሚደርስ የተመነጠረ ደን እንዲያገግም ቃል መግባቷን ይናገራሉ። እንቅስቃሴው የደን ምንጣሮን ለመከላከል የተጀመረ ዓለም አቀፍ ንቅናቄ አካል ነው። ዛፍ ተካላ ከግብርና መሬት ፍላጎት ጋር መመጣጠን አለበት ኢትዮጵያ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ዛፎች ለመትከል ማቀዷ፤ በአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች ቢመሰገንም፤ በተያዘው ጊዜ ውስጥ ምን ያህል ችግኝ እንደተተከለ ለመለካት ይሄ ነው የሚባል ሥራ አልተሠራም። • ችግኝን በዘመቻ መትከል መቼ ተጀመረ? ኢትዮጵያን አረንጓዴያማ ለማድረግ፤ ሐምሌ ላይ የአውሮፓ ኅብርት እና ኢትዮጵያ የ40 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ተፈራርመው ነበር። በመላው አገሪቱ የሚገኙ አገር በቀል ድርጅቶች፤ ችግኞች እንዲተክሉ የገንዘብ ድጋፍ ተሰጥቷቸዋል። ድርጅቶቹ ከተተከለው ችግኝ የበለጠ ቁጥር ለክልል ኃላፊዎች ነግረው፤ ኃላፊዎቹም በአገር አቀፍ ደረጃ ለሚሰበሰበው መረጃ ቁጥሩን መስጠታቸውን ማወቅም ብዙ አያስገርምም። ለወደፊት ሊያጋጥሙ የሚችሉ የአካባቢ ጥበቃ ችግሮች የተተከለው ችግኝ ብዛት ምንም ይሁን ምንም፤ ኢትዮጵያ የደን ምንጣሮን ለማሸነፍ ከፍተኛ ጥረት እያደረገች እንደምትገኝ አይካድም። ከግማሽ ምዕተ ዓመት በፊት የኢትዮጵያ የደን ሽፋን 40 በመቶ ነበር። አሁን ግን ወደ 15 በመቶ አሽቆልቁሏል። የችግኝ ተከላ ዘመቻው ይህንን ችግር እንዲቀርፍ ከተፈለገ፤ ችግኞቹን በየጊዜው ውሀ ማጠጣት ያስፈልጋል። በእርግጥ የውሀ እጥረት ባለበት አገር ውስጥ ይህንን እውን ማድረግ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። በውሀ ጥበቃ ዙርያ የተሻለ አካባቢ ሊፈጥርም ይችላል።
news-46055136
https://www.bbc.com/amharic/news-46055136
አትክልት ብቻ ስለሚመገቡ ሰዎች ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮች
በዓለም ላይ ምንም አይነት የእንስሳት ተዋጽኦ የማይመገቡ (ቪጋን) በርካታ ሰዎች አሉ። ምንም እንኳን የእንስሳት ተዋጽኦን አለመመገብ በዓለማችን እየተለመደ የመጣ ቢሆንም፤ የሥጋ ተጠቃሚዎች ቁጥር ደግሞ ከእጥፍ በላይ ነው።
በእንግሊዝኛው ቪጋን ተብለው የሚጠሩት ሰዎች ምንም አይነት ሥጋ፣ እንቁላል፣ አሳ ወይም ማር በአጠቃላይ የእንስሳት ሥጋና ከእንስሳት የሚገኙ ምግቦችን አይመገቡም። ምንም አይነት የእንስሳት ተዋጽኦን አለመጠቀም የሚለው እሳቤ ለምግብነት ስለሚጠቀሟቸው ነገሮች ብቻ አይደለም፤ በማንኛውም መልኩ በእንስሳት ላይ የሚፈጸምን ብዝበዛ መቃወምም ያካትታል። ይህ ማለት ደግሞ ከእንስሳት ቆዳ የሚሰሩ አልባሳትን እስካለመጠቀም ድረስ ማለት ነው። ይህንን የህይወት መንገድ ለመከተል ጠበቅ ያለ ውሳኔ ማሳለፍ ይፈልጋል። በአለማችን ከሌላው ጊዜ እጅግ በጨመረ መልኩ ሰዎች ከእንስሳት ተዋጽኦ ነጻ የሆኑ ምግቦችን ለመጠቀም ብዙ ገንዘብ እየከፈሉ ነው። • ጓደኛ ለማፍራት ማወቅ ያለብን ጠቃሚ ነጥቦች • ስለድምጻችን ልናውቃቸው የሚገቡ ሰባት ነገሮች ከተክሎች ጋር የተያያዙ ምግቦችም በበይነ መረብ በመላው ዓለም እየተቸበቸቡ ነው። ማንናውም አይነት የእንስሳት ተዋጽኦ ስለማይመገቡ ሰዎች ሊያውቋቸው የሚገቡ አምስት ነገሮች እነሆ። 1. ታሪካዊ አመጣጥ ምንም አይነት የእንስሳት ተዋጽኦ የማይመገቡ ሰዎች ማህበር የተቋቋመው እ.አ.አ. በ1944 እንግሊዝ ውስጥ ነው። ዋትሰን የተባለ ስጋ የማይመገብ ሰው በስጋ ማቀነባበሪያዎች ውስጥ በእንስሳት ላይ የሚፈጸመውን ግፍ ከተመከለተ በኋላ ነው ይህንን አስተሳሰብ ማራመድ የጀመረው። ምንም አይነት ስጋ ነክ ምግቦችን ያለመመገብ አስተሳሰብ ከመጀመሩ ከ2500 ዓመታት በፊት ግን በጥንታዊ ህንድና ምስራቅ ሜዲትራኒያኒያን አካባቢዎች የተለመደ እንደነበር የታሪክ ተመራማሪዎች ይናገራሉ። ህንድ ውስጥ ከፍተኛ የተከታዯች ቁጥር ያለው ሂንዱይዝም ሃይማኖት እንስሳት በተለይ ላሞች ስጋቸው መበላት እንደሌለበት የሚገልጽ ሲሆን፤ የዚህ ዘመነኛ አስተሳሰብ መነሻ ተደርጎም ይወሰዳል። ቡድሂዝም፣ ሂንዱይዝምና ጃኒዝም የተባሉ ሃይማኖት ተከታዮች ሰዎች ማንኛውም አይነት እንስሳ ላይ ህመም ማድረስ የለባቸውም ብለው ያምናሉ። በ500ኛው ክፍለ ዘመን የኖረው ታዋቂው ግሪካዊ ፈላስፋና የሂሳብ ባለሙያ ፓይታጎረስ በእንስሳት ላይ የሚፈጸሙ ግፎችን በእጅጉ ይቃወም ነበር። ወደ ስጋችን ሌላ ስጋ ማስገባት ርኩስነት ነው ብሎ ያምን ነበር። የአንድን ሰው ህይወት ለማስቀጠል የሌላውን ፍጥረት ነፍስ ማጥፋት የወንጀሎች ሁሉ ወንጀል በማለት ሲከራከር ኖሯል። 2. የጤና ጥቅሞቹ በቅርቡ እንግሊዝ ውስጥ በተሰራ ጥናት መሰረት ማንኛውም አይነት የእንስሳት ተዋጽኦ ከማይመገቡ ሰዎች 49 በመቶ የሚሆኑት ለጤና ካለው ጥቅም የተነሳ የአመጋገብ ስርአቱን እንደመረጡ ተናግረዋል። ቀይ ስጋ እና ሌሎች በፋብሪካ የተቀነባበሩ የስጋ ምርቶችን የሚመገቡ ሰዎች ለአንጀት ካንሰር ያላቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ መሆኑን ጥናቶች ጠቁመዋል። በአውሮፓውያኑ 2015 የዓለም ጤና ድርጅት በፋብሪካ የተቀነባበሩ የስጋ ውጤቶችን ካንሰር ከሚያመጡ ንጥረ ነገሮች መካከል የመደባቸው ሲሆን፤ በፋይበርና ሌሎች ቫይታሚኖች የበለጸጉ አትክልትና ፍራፍሬዎችን መመገብ ደግሞ በካንሰር የመያዝ እድልን በከፍተና ሁኔታ እንደሚቀንሱ ገልጿል። • የ29 ዓመቷ የህክምና ዶክተርና ኢንጅነር ዕልልታ ጉዞ • የመንገድ አቅጣጫ እየጠፋብዎ ተቸግረዋል? ጠቃሚ ነጥቦች እነሆ ምንም አይነት የእንስሳት ተዋጽኦ የማይመገቡ ሰዎች ከሚመገቡ ሰዎች ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ጤናማ ህይወት እንዳላቸው የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ነገር ግን እነዚህ ሰዎች ለአጥንት እድገት፣ ለተስተካከል የደም ስርአት፣ ለነርቭ ስርአትና ለአንጎል እድገት የሚጠቅሙ እንደ ቫይታሚን ዲ፣ ቫይታሚን ቢ12 እና አዮዲን የተባሉ ንጥረ ነገሮችን ማግኘት አይችሉም። ይህንን ለማካካስ ደግሞ ወደ ሰው ሰራሽ እንክብሎች ፊታቸውን ማዞር አለባቸው። እሱም ቢሆን የራሱ የሆነ አሉታዊ ውጤት ይኖረዋል። 3. አካባቢ ላይ ያለው ተጽእኖ አሁን አሁን ይህ የአመጋገብ ስርአት ብዙ ተከታዮችን እያፈራ ቢሆንም በአለማችን ያለው የስጋ ተተቃሚ ቁጥር ግን ከግምት በላይ ነው። እንደ ቻይናና ህንድ ባሉ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ባሉባቸው ሃገራት ዜጎች የምግብ ፍላጎታቸውን ለማርካት ፊታቸውን ወደ ስጋ እያዞሩ ነው። በቅርቡ የተሰሩ የተባበሩት መንግስታት ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት እየጨመረ የመጣው የአለም ህዝብ ቁጥር በምድራችን የተፈጥሮ ሃብቶች ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳረፈ ነው። እንደ ሪፖርቶቹ ትንበያ የሰው ልጅ የምግብ ፍላጎቱን ለማርካት እየሄደበት ባለው ሁኔታ አሁን ከሚያመርተው 70 በመቶ ተጨማሪ ምግብ ማምረት ካልቻለ፤ እ.አ.አ. በ2050 ዓለማችን ምግብ አልባ ትሆናለች። በ2013 የተባበሩት መንግስታት የምግብና ግብርና ድርጅት ባወጣው ጥናት መሰረት አካባቢን ከሚበክሉ ግሪንሃውስ ጋሶች 14.5 በመቶ የሚሆኑት የሚመነጩት የቀንድ ከብቶች ከሚለቁት ሚቴን ከተባለ ጋስ ነው። ይህ ደግሞ እያንዳንዱ መኪና፣ ባቡር፣ አውሮፕላንና መርከቦች ወደ ምድር ከሚለቁት ጋስ ጋር እኩል ነው። ከዚህ በተጨማሪ የስጋ ምርት ብዙ የተፈጥሮ ሃብት ያባክናል። ለምሳሌ 450 ግራም የሚመዝን ቆስጣ ለማደግ 104 ሊትር ውሃ የሚጠቀም ሲሆን፤ ተመሳሳይ ክብደት ያለው ስጋ ግን 23 ሺ ሊትር ውሃ ይፈጃል። የተባበሩት መንግስታ የዓለም ህዝብ ቁጥር 7 ቢሊየን እንደሆነ የሚገምት ሲሆን፤ በ2050 ደግሞ 9.2 ቢሊየን እንደሚደርስ ግምቱን አስቀምጧል። ምንም እንኳን የተረጋገጠ ቁጥር ማግኘት ባይቻልም የአለም አቀፉ የእንስሳት ተዋጽኦ የማይጠቀሙ ሰዎች ማህበር እንደሚለው ቁጥራቸው ከ550 እስከ 950 ሚሊየን ሊደርስ ይችላል። 4. አዋጪ የስራ ዘርፍ ቪጋኒዝም ወይም የእንስሳት ተዋጽኦ ያለመጠቀም ባህል አሜሪካ ውስጥ ብቻ 600 በመቶ ያደገ ሲሆን፤ እንግሊዝ ውስጥ ደግሞ 400 በመቶ እድገት አሳይቷል። ይህ ዓለም በአዲስ መልክ እየተከተለችው ያለው የአመጋገብ ስርአት ብዙዎችን እየሳበ ነው። ከስጋ ነጻ የሆኑ ምግቦችን የሚያዘወትሩ ሰዎች ቁጥር በ2017 ብቻ በ1000 ፐርሰንት ያደገ ሲሆን፤ በ2018 ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጨምር ይጠበቃል። በተለይ ደግሞ ታዋቂ ሰዎችና ስፖርተኞች የሚከተሉትን ጤናማ የአመጋገብ ስርአት በተመለከተ ኢንስታግራም በተባለው የማህበራዊ ሚዲያ የሚያሰፍሯቸው መልእክቶች በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን እየሳቡ ነው። • ሞባይል ለኢትዮጵያ እናቶችና ህፃናት ጤና • ስለ አንጀታችን የማያውቋቸው ስድስት አስገራሚ እውነታዎች እንደ 'ኔስሌ' ያሉ የዓለማችን ትልልቅ የምግብ አምራች ኩባንያዎችም ፊታቸውን ወደ እነዚህ ሰዎች እያዞሩ ነው። 'ጀስት ኢት' የተባለው የተለያዩ ምግቦችን ሰዎች ባሉበት ድረስ የሚያቀርብ ድርጅት በአንደኛ ደረጃ በደንበኞች የሚታዘዙት ምግቦች ከእንስሳት ተዋጽኦ ነጻ የሆኑት እንደሆኑ ገልጿል። ራዕይ አላቸው ተብለው የሚታሰቡ የስራ ፈጠራ ባለሙያዎችም እውቀታቸውንና ገንዘባቸውን በዚህ ዘርፍ ላይ እያዋሉ ነው። በመጪዎቹ ሁለት ዓመታትም ዘርፉ እስከ 4 ቢሊየን ዶላር ድረስ ሊያንቀሳቅስ እንደሚችል ተገምቷል። 5. ልክ ያለፈ አክራሪነት 'የቪገኒዝም' እንቅስቃሴ ገና ከጅምሩ እንስሳት ፍቅርና ክብር ይገባቸዋል በሚል የተጠነሰሰ ቢሆንም፤ አሁን አሁን የሚታዩ ተግባራት ግን ወደ ማክረሩ የተጠጉና ሌሎችን እስከመከልከል ይደርሳሉ። ብዙ የቀንድ ከብት የሚያረቡ ገበሬዎች በአክራሪዎች ፍርድ ቤት ተከሰዋል፣ ስጋ መሸጫዎች ጥቃት ደርሶባቸዋል፤ እንዲሁም ሰዎች ለምን ስጋ ትመገባላችሁ ተብለው እስከ መገለል ደርሰዋል። ''ገዳይ ወይም ነፍስ አጥፊ ተብለህ ስትጠራ በጣም ያሳዝናል፤ ያስደነግጣል'' ትላለች እንግሊዝ ውስጥ በግብርና ስራ የምትተዳደረው አሊሰን ዋግ።
50889278
https://www.bbc.com/amharic/50889278
በሞጣ በደረሰው ጥቃት 27 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ
በምሥራቅ ጎጃም ሞጣ ከተማ ቤተ እምነቶች ላይ ጥቃት አድርሰዋል የተባሉ 27 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።
የምሥራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ዋና ኢንስፔክተር አያልነህ ተስፋዬ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በጥቃቱ የተጠረጠሩ እስካሁን ድረስ 27 ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ማህበረሰቡ ጥፋተኞችን እየጠቆመ በመሆኑ ቁጥሩ ሊጨምር እንደሚችል ተናግረዋል። በፖሊስ የተያዙት ተጠርጣሪዎችም እንደተያዙበት ቅደም ተከተል ወደ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ መደረጉንም ዋና ኢንስፔክትር አያልነህ ጨምረው ገልፀዋል። የተጠርጣሪዎቹ ቁጥርም ሊጨምር ስለሚችል አዳዲስ ሰዎች በቁጥጥር ስር የሚውሉ ከሆነም ምርመራ በማድረግና ሕጉ በሚያዘው መሰረት ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ይደረጋል ብለዋል። • ከኢትዮጵያ ሀብት ከሸሸባቸው ሃገራት ጋር ግንኙነት ተጀምሯል-ጠቅላይ አቃቤ ሕግ • ኢትዮጵያ 4 ቢሊዮን ችግኞችን ተክላለች? • ዐቃቤ ሕግ ኢትዮጵያ ውስጥ የጠፋው ኤርትራዊ ምርመራ እንዲጠናቀቅ አዘዘ በሞጣ ከተማ ሁኔታዎች መረጋጋታቸውን የተናገሩት ዋና ኢንስፔክተር አያልነህ፤ በከተማዋም ያለው ጥበቃም መጠናከሩን ተናግረዋል። የክልሉ ፖሊስ ከልዩ ኃይል ጋር በመሆንም የሞጣ ከተማን ወደነበረችበት መረጋጋት ለመመለስ እየተሰራ ነው ያሉት ኢንስፔክተር፤ በተፈጸመው ወንጀል ዙሪያ የምርመራ ሥራውም፣ የማረጋጋት ሥራውም ሆነ ሕዝብ ለሕዝብ የማገናኘት ሥራውን ጎን ለጎን እየተካሄዱ መሆናቸውንም አስረድተዋል። ትምህርት ቤቶች፣ የመንግሥት ቢሮዎች ተከፍተዋል በማለት ምናልባት የተቃጠሉ ሱቆች አካባቢ ያሉት ካልሆነ በስተቀር ሁሉም ወደ መደበኛው ሕይወቱ ተመልሷል ሲሉ አረጋግጠዋል። ከክስተቱ ቀደም ብሎ አንዳንድ ግለሰቦች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በከተማዋ ግጭት ሊቀሰቀስ እንደሚችል ለከተማው ፖሊስ ጥቆማ ቢያቀርቡም ፖሊስ ጥቆማውን ቸል በማለቱ ጥፋት መድረሱን በተመለከተ ለቀረበው ወቀሳም ምላሽ ሰጥተዋል። ዋና ኢንስፔክተር አያልነህ እንዳሉት "ይህንን በማኅበራዊ ሚዲያ የሚመላለሱ መረጃዎችን እኛም አይተናቸዋል፤ ነገር ግን ምንም በጽሁፍም ሆነ በቃል ተደራጅቶ የቀረበ ጥቆማና መረጃ አልነበረም" ብለዋል። አርብ ማምሻውን በአማራ ክልል፣ በምሥራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ የሚገኘው ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን፣ ጀሚዑል ኸይራት ታላቁ መስጊድ እና አየር ማረፊያ መስጊድ ላይ ቃጠሎ መድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች በወቅቱ ለቢቢሲ ተናገረዋል። • እንደወጡ የቀሩት ተመራማሪዎች ከዚህ በተጨማሪም በከተማዋ ውስጥ በሚገኙ ሆቴሎች እንዲሆም ሌሎች የንግድ ተቋሞች ላይም ጉዳት መድረሱንም በስልክ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎቹ ገልጸውልናል። የአማራ መገናኛ ብዙኃን፤ የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሰኢድ አሕመድን ጠቅሶ እንደዘገበው ደግሞ አራት መስጊዶች የተቃጠሉ ሲሆን፤ ሱቆችና ሌሎች ድርጅቶችም ተዘርፈዋል። የኢትዮጵያ ሐይማኖት ጉባኤ አባላትና የአማራ ክልል ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባላት ሞጣ ከተማ ላይ የደረሰውን አውግዘው ወደ ስፍራው በማቅናት ከነዋሪዎች ጋር እንደሚወያዩና የተለያዩ ድጋፎችን እንደሚያደርጉም አስታውቀው ነበር።
news-54046818
https://www.bbc.com/amharic/news-54046818
ናይጄሪያዊያን ከቢግ ብራዘር ለተባረረችው ሴት 100ሺህ ዶላር እያሰባሰቡ ነው
በዝነኛው የናይጄሪያ ቢግ ብራዘር የቲቪ ትዕይንት በጊዜ ለተሰናበተች አንዲት ተወዳዳሪ 100ሺ ዶላር (3.7 ሚሊዮን ብር) እየተሰበሰበላት ነው፡፡
ኤሪካ ብለው ለሚያቆላምጧት ለዚህች ተባራሪ እጩ ገንዘብ የሚዋጣላት አሸናፊ መሆን የነበረባት እሷ ናት በሚል ነው፡፡ አድናቂዎቿ ከውድድሩ መባረሯን አምነው መቀበል ከብዷቸዋል፡፡ እስከአሁን ወደ አስራ አራት ሺህ ዶላር በጎፈንድሚ በኩል ተዋጥቶላታል፡፡ መዋጮው በፍጥነት እየሄደ ነው፡ ኤሪካ ከትናንት በስቲያ እሁድ ነበር ከውድድሩ ውጭ የተደረገችው፡፡ በትእይንቱ ላይ ያልተገባ ባህሪ ታሳያለች ተብሏል፡፡ አብረው ክፍል ለሚጋሯት ተወዳዳሪዎች ክብር የላትም "ምላሰኛ" ናት ብለዋል ድምጽ ሰጪዎች‹‹ ሁለት ተከታታይ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣትም ልታሻሽል ባለመቻሏ ነው ቀይ ካርድ የተሰጣት፡፡ ይህ ግን ወዳጆቿን አሳዝኗል፡፡ መባረሯን ተከትሎ ታማኝ ወዳጆቿ ወዲያውኑ ባሰባሰቡት ገንዘብ 100ሺህ ዶላር ለመስጠት አልመው ተነስተዋል፡፡ የውድድሩ አሸናፊ የሚያገኘው/የምታገኘው ገንዘብ 223ሺ ዶላር ቢሆንም ለሷ ግምሹን ለመስጠት ነው ደጋፊዎቿ ቆርጠው የተነሱት፡፡ ከዚህ ገንዘብ በተጨማሪ አንድ የናይጄሪያ የመኪና አምራች እኔ መኪናና 5ሺ ዶላር እሰጣታለሁ ብሏል፡፡
news-56013324
https://www.bbc.com/amharic/news-56013324
አሜሪካ በሚየንማር መፈንቅለ መንግሥት መሪዎች ላይ ማዕቀብ ጣለች
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በሚየንማር መፈንቅለ መንግሥት አመራሮች ላይ ማዕቀብ መጣል የሚያስችላቸውን ትእዛዝ አስተላልፈዋል።
ጆ ባይደን ያሳለፉት እቀባ የጦሩ አመራሮች፣ ቤተሰቦቻቸውና ከነሱ ጋር የንግድ ሽርኪያ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉት ሁሉ ላይ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በአሜሪካ ተቀማጭ የሆነ የሚየንማር 1 ቢሊዮን ዶላር ገንዘብ ጦሩ እንዳያገኘው ለማድረግ እግድ ለመጣል በሂደት ላይ ነው ተብሏል። መፈንቅለ መንግሥቱን ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ አንዲት ግለሰብ ጭንቅላቷ ላይ በጥይት ተመትታ በመዲናዋ ናይ ፓይ ታው በሚገኝ ሆስፒታል ህይወቷ አልፏል። በዚህ ሳምንት ማክሰኞ ፖሊስ ተቃዋሚዎችን ለመበተን ውሃ፣ አስለቃሽ ጋዝና ጥይት በመተኮስ በሚሞክርበት ወቅት ነው ሴትዮዋ የቆሰለችው። ግለሰቧ በጥይት እንደተመታች ማስረጃ መኖሩን የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ይናገራሉ። በባለፈው ሳምንት በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡትን የአንግ ሳን ሱቺ መንግሥት በኃይል መገርሰሱን ተከትሎ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአደባባይ ተቃውሞ አንስተዋል። ተቃዋሚዎቹ በቀድሞዋ በርማ በአሁኗ ሚየንማር የተላለፈውን የስብሰባ እግድ በመጣስ ነው ተቃውሟቸውን እየገለፁ ያሉት። ስልጣን በኃይል የተቆጣጠረው ጦር ያንጎንና ማንዳላይ በመሳሰሉ ከተሞች ከአምስት ሰዎች በላይ መሰብሰብ አይቻልም የሚል ትዕዛዝ ከማስተላለፍ በተጨማሪ የሰዓት እላፊ አዋጅ ጥሏል። ሆኖም ተቃዋሚዎቹ ሳምነት ባስቆጠረው የጎዳና ላይ ሰልፍ በኃይል የተገረሰሱትን አን ሳን ሱቺን ከስልጣን መወገድ እየተቃወሙ ነው። ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር መመለስ አለበት በማለት ጥሪያቸውን እያሰሙ ነው። ፖሊስ ተቃዋሚዎቹን ለመበተን የሚጠቀመውን ኃይል በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ ከፍተኛ የአካል ጉዳቶች ሪፖርት ቢደረጉም ሞቶች አልተከሰቱም ተብሏል። ባይደን ሚየንማር ምን እንድታደርግ ነው የሚጠይቁት? ጆ ባይደን መፈንቅለ መንግሥቱ እንዲቀለበስና መሪዋን አንግ ሳን ሱቺን ጨምሮ በእስር ላይ ያሉት የሲቪል አመራሮች እንዲፈቱ ጠይዋል። "የሚየንማር ዜጎች የተቃውሞ ድምፃቸውን እያሰሙ ነው፤ አለምም እየተመለከተ ነው" በማለት የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ አስፈላጊም ከሆነ ሌሎች እርምጃዎች እንደሚወስዱ ቃል ገብተዋል። "ተቃውሞዎች በተቀጣጠሉበት በአሁኑ ወቅት ዲሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን የሚጠይቁ ዜጎች ላይ ኃይል መጠቀም ተቀባይነት የለውም። ይህንንም ሁኔታ በዝምታ አናየውም" ብለዋል። አስተዳደራቸው ማዕቀቡ የሚጣልባቸውን የመጀመሪያ ዙር የጦር አመራሮች ዝርዝር በዚህም ሳምንት ያወጣል ተብሏል። ነገር ግን አንዳንዶቹ የጦር አመራሮች ከሮሂንጃ ሙስሊሞች ጭፍጨፋ ጋር ተያያዞ በጥቁር መዝገብ ውስጥ ያሉ ናቸው። "በሚየንማር ወጪ ንግድ ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እንጥላለን። የሚየንማርን መንግሥት የሚረዳ ማንኛውንም የአሜሪካ ንብረት ላይ እግድ እናሳልፋለን። ለአገሪቷ የጤና ስርአት፣ ሲቪል ሶሳይቲ ቡድኖችና የሚየንማርን ህዝብ በቀጥታ የሚጠቅሙ ድጋፎችን ከማድረግ ወደኋላ አንልም" ብለዋል። በባለፈው ወር ስልጣን የተረከቡት አዲሱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ይህ የመጀመሪያ ማዕቀባቸው ነው።
news-56186304
https://www.bbc.com/amharic/news-56186304
ሌዲ ጋጋ የተሰረቁ ውሾቿን ለሚመልስ ግማሽ ሚሊዮን ዶላር እሰጣለሁ አለች
እውቅ የሙዚቃ ሰው ሌዲ ጋጋ ሎስ አንጀለስ ከተማ ውስጥ የተሰረቁ ውሾቿን ለመለሰ ሰው ግማሽ ሚሊዮን ዶላር እሰጣለሁ አለች።
ሌዲ ጋጋ ውሾቿን በመንከባከብ የምትታወቅ ሲሆን በአሜሪካ የሙዚቃ ሽልማት መድረኮች እና በሱፐር ቦውል ትርኢት ላይ ውሾቿን ይዛ ተገኝታ ነበር። አንድ ታጣቂ ረቡዕ ምሽት የሌዲ ጋጋ ሶስት ውሾችን ሲያናፍ የነበረ ተንከባካቢን በጥይት መትቶ ካቆሰለ በኋላ ሁለት ውሾች ይዞ ተሰውሯል። በአሜሪካ የመገናኛ ብዙሃን ዘገባዎች ውሾቹን ሲያናፍስ የነበረው ሪያን ፊሸር በሚል ስሙ የተገለጸው ሲሆን፤ በጥይት መመታቱን ተከትሎ ወደ ሆስፒታል ቢወሰድም ፖሊስ የደረሰበት የጉዳት መጠን አልገለጸም። ሌዲ ጋጋ ኮጂ እና ጉስታቭ የሚባሉትን የፈረንሳይ ዝርያ ያላቸውን ሁለት ውሾቿን የት እንዳሉ ለሚጠቁም ወረታ እንደምትከፈል ገልጻለች። ሚስ ኤሲያ የተባለችው ሦስተኛው ውሻ ሮጣ ከስፍራው ካመለጠች በኋላ ፖሊስ አግኝቶ መልሷታል። በእውነተኛ ስሟ ስቲፋኒ ጀርማኖታ ተብላ የምትታወቀው ሌዲ ጋጋ በወቅቱ ሮም ውስጥ በፊልም በመሥራት ላይ ነበረች። ውሾቹን ለሚመለስ ለማንኛውም ሰው 500,000 ዶላር ወረታ ለመስጠትም ቃል ገብታለች። የፕሬስ ወኪሏ ውሾቹ ስላሉበት ቦታ መረጃ ያለው ማንኛውም ሰው መረጃ እንዲሰጣቸው በውሾቹ ስም የተከፈተ የኢሜይል አድራሻ አስተዋውቀዋል። የውሾቹ ዝርያ ውድ ከሚባሉት መካከል ሲሆኑ የአንድ ቡችላ ዋጋ ከ2 ሺህ እስከ 10 ሺህ ዶላር ሊጠየቅባቸው ይችላል። የሎስ አንጀለስ ፖሊስ መምሪያ ረቡዕ ምሽት "ከማይታወቅበት ቦታ ተኩሶ ተጎጂውን ያቆሰለውን" ሰው እየፈለገ መሆኑን አረጋግጧል።"ተጠርጣሪ ሊሆን ይችላል" የተባለው ግለሰብ ወንጀሉን ፈጽሞ በነጭ ተሽከርካሪ ሸሽቷል ሲልም ፖሊስ አክሏል። የሌዲ ጋጋ ውሾች በጥቃቱ ዒላማ የተደረጉ ስለመሆናቸው ግልጽ አይደለም። ጋጋ ውሾቿን በመንከባከብ የምትታወቅ ሲሆን በአሜሪካ የሙዚቃ ሽልማት መድረኮች እና በሱፐር ቦውል ትርኢት ላይ ውሾቿን ይዛ ተገኝታ ነበር። ከጥቃት አድራሹ ያመለጠችው ሚስ እስያ የተባለችው ውሻ ይፋዊ የኢንስታግራም ገጽ ያላት ሲሆን በገጿ ከ224ሺህ በላይ ተከታዮች አሏት።
news-44810663
https://www.bbc.com/amharic/news-44810663
"የጌዲዮና ጉጂ ተፈናቃዮች ቸል ተብለዋል" የዓለም ቀይ መስቀል ማኀበር
ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ከሰሞኑ በደቡብ ኢትዮጵያ የደረሰውን ቀውስ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎታል ሲል የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማኀበር ወቀሰ።
የማኀበሩ የቡድን መሪ ሸሪን ሐናፊ እንደተናገሩት ስምንት መቶ ሺህ ዜጎችን ላፈናቀለው ለዚህ ሰብአዊ ቀውስ የተፋጠነ ምላሽ አለመስጠት የኋላ ኋላ መዘዝ ማስከተሉ አይቀርም። በተለይ መጪው የክረምት ጊዜ በመሆኑ በአካባቢው የተለያዩ በሽታዎች ሊቀሰቀሱ ይችላሉ የሚል ስጋት ተፈጥሯል። ማኀበሩ ዛሬ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ጋር በመሆን በአካባቢው ጉብኝት ማድረጉን ጠቅሶ የደረሰውን ሰብአዊ ቀውስ አሳሳቢ መሆኑን መረዳቱን አብራርቷል። • በጉጂ እና ጌዲዮ ግጭት ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቀሉ • የተጠበቀውን ያህል የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች አልተመለሱም ያም ሆኖ በደረሰው ግጭት የተከሰተው ሰብአዊ ቀወስ በዓለም አቀፉ ማኀበረሰብ ዘንድ ተገቢው ትኩረት እንዳልተሰጠው ማኅበሩ ገልጿል። ተፈናቃዮቹ ያሉበት ሁኔታ ሰዋዊ ክብራቸውን ለማስጠበቅ እንኳ የሚመች እንዳልሆነ የተናገሩት የማኀበሩ የቡድን መሪ በትምህርት ቤቶች፣ በቢሮዎች፣ በአብያተ-ክርስቲያናት ወለሎች ላይ የሚተኙበትና የሚለብሱት ነገር እንኳን ሳይኖራቸው እያደሩ ነው ብለዋል። መግለጫው ተፈናቃዮቹ ምግብና ንጹሕ ውሃ እንኳ ማግኘት እንዳልቻሉ ይጠቅሳል። ድርጅቱ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ጋር በመሆን በጌዲዮ ዞን ኮቸሬ ወረዳ ለሚገኙና መቶ ሺ ለሚሆኑ ተጎጂዎች በቅርቡ ድጋፍ ማድረግ እንደሚጀምር አስታውቋል።
news-49520570
https://www.bbc.com/amharic/news-49520570
ዶናልድ ትራምፕ በስሎቬኒያ የባለቤታቸው መኖሪያ ቤት ሐውልት ቆመላቸው
አነጋጋሪው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስሎቬኒያ በሚገኘው የባለቤታቸው መኖሪያ ቤት ከእንጨት የተሰራ ሐውልት ቆመላቸው።
የዶናልድ ትራምፕ ከእንጨት የተሰራ ሐውልት ከባለቤታቸው ሜላኒያ ሐውልት በስተግራ 8 ሜትር የሚረዝመው ሐውልት የቆመው በግለሰብ ይዞታ ላይ ሲሆን ጭንቅላታቸውና አገጫቸው አራት መዓዘን ቅርፅ ይዞ የተሰራ ነው። ዶናልድ እጃቸውን በድል ምልክት ወደላይ ዘርግተው ይታያል። ሰማያዊ ሙሉ ልብስ በቀይ ክራቫት ለብሰውም የኒዮርኩን የነፃነት ሐውልት ያስታውሳሉ። • አሜሪካ ሩሲያዊቷን በሰላይነት ከሰሰች • አሜሪካ፡ የመድኃኒት ዋጋ ሰማይ የደረሰባት ሃገር ታዲያ በርካቶች በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከመስጠት አልተቆጠቡም። የሐውልቱ ቀራፂ ለኤ ኤፍ ፒ የዜና ወኪል እንዳለው የሕዝቡን ስሜት ለማንፀባረቅ መስራት እንደፈለገ ተናግሯል። ሐውልቱ የተሰራውም የባለቤታቸው ሜላኒያ ትራምፕ ሐውልት በትውልድ ቦታዋ ስቭኒካ ከቆመ በኋላ ነው። ሐውልቷ ከእንጨት ተፈልፍሎ የተሰራ ሲሆን ሰማያዊው ኮት ለብሳ እጇን ወደ ላይ ዘርግታ ይታያል። አንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎችም "ክብረ ቢስ! የቀዳማዊት እመቤት ሳይሆን የአሻንጉሊት ቅርፅ ይመስላል" ሲሉ ተሳልቀውበታል። አዲሱ የትራምፕ ሐውልትም ከሰሜን ምስራቅ ጁቢልጃና 32 ኪሎሜትር በሚርቅ ሥፍራ ነው የቆመው። ቀራጺውም ቶማስ ስችሌግል ሐውልቱ ለአክራሪ ፖለቲከኝነታቸው ግብረ መልስ እንደሆነ ተናግሯል። ሐውልቱ የተቀረፀው በስሎቬኒያዊው ቀራፂ ቶማዝ ስችሌግል ነው "ተመልከት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ እየሆነ ያለውን፤ አክራሪ ፖለቲከኞች እንደ አሸን እየፈሉ ነው። የእንግሊዙን ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰንን፣ ትራምፕን፣ የአገራቸንን ፕሬዚዳንት እንዲሁም የሀንጋሪን ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶርን ተመልከታቸው! ይህ ዓለም ወዴት እያመራ ነው እንድትል ያደርጉኻል። ሰዎች ዲሞክራሲ ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንዲያውቁ እና ዐይናቸውን እንዲከፍቱ እንፈልጋለን" ብሏል። • የአይኤስ አባል የነበረችው አሜሪካ እንዳትገባ ተከለከለች ቀራጺው እንደሚለው በእንጨቱ ውስጥ የተቀመጠው ጥበባዊ ቅርፅ፤ የሀውልቱ ስሜት ተለዋዋጭ እንዲሆን ያግዛል። "በሳምንቱ የአዘቦት ቀናት በጣም ተግባቢ፥ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ደግሞ አስፈሪ ሆኖ እንዲለዋወጥ የሚረዳ ነው። ተምሳሌትነቱም የአክራሪ ፖለቲከኞች ግብዝነት ማሳየት ነው።" ብሏል። ባለፈው ቅዳሜ በነበረው የሐውልቱ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ አንድ የአካባቢው ነዋሪ በቁጣ ትራክተሩን እያሽከረከረ መጥቶ ሊደመስሰው ነበር። አንዳንድ የኦንላይን ተጠቃሚዎች ደግሞ 'የእንጨት ብክነት' ሲሉ ሀውልቱን ተቃውመዋል። የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ለስሎቬኒያ ምልክት እየሆኑ መጥተዋል፤ በአውሮፓዊኑ 2016 ሥልጣን ላይ ከወጡ አንስቶም የባለቤታቸው ትውልድ አገር የቱሪስት መዳራሻ ሆናለች። ጎብኝዎች ሲሄዱም የሜላኒያ ምስል ያለበት ነጠላ ጫማ፣ ኬክና በርገር ይቀርብላቸዋል። ምንም እንኳን ባለፈው ወር የተሰራው የሜላኒያ ሐውልት ትችት ቢሰነዝረበትም አንድ የአካባቢው ነዋሪ 'ጥሩ ሃሳብ ነው' ሲሉ ለኤ ኤፍ ፒ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። "ሜላኒያ የስሎቬንያ ጀግና ናት፤ በአሜሪካ ትልቁን የፖለቲካ ማማ ወጥተዋለች" ሲሉ የ66 ዓመቷ ካትሪና አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
41578249
https://www.bbc.com/amharic/41578249
የብር የመግዛት አቅም መቀነስ አንድምታዎች
የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ የገንዘቧን የመግዛት አቅም ዝቅ እንድታደርግ ግፊት ሲያደርግ ቢቆይም የብርን የመግዛት አቅም እንዲቀንስ ማድረግ ከሚያስገኘው ጥቅም ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል በማለት መንግሥት ሳይቀበለው ለረጅም ጊዜ ቆይቷል።
አሁን ግን የተቀዛቀዘው የወጪ ንግድን እንዲያንሰራራ ለማድረግ የብር የውጭ ምንዛሬ ዋጋ በ15 በመቶ እንዲቀንስ ተደርጓል። ይህ እርምጃ በህብረተሰቡና በገንዘብና በምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ዘንድ ትልቅ ስጋትን ፈጥሯል። በተለይ ይህ ከፍተኛ የመግዛት አቅም ማሽቆልቆል ወትሮም በፍጆታ እቃዎች እጥረት እየተቸገረ ለሚገኘው ሸማቹ ህብረተሰብ አስደንጋጭ ክስተት ነው። በየወሩ የሚደረገውን የነዳጅ ዋጋ ክለሳን ተከትሎ በፍጆታ ምርቶች ላይ የሚታየው የዋጋ ጭማሪ ያስመረራቸው የአዲስ አበባ ነዋሪው አቶ ደቻሳ ''በዚህ እርምጃ ምክንያት እየተጋፈጥነው ያለው ችግር ከቁጥጥር ውጪ ይሆናል'' ብለው እንደሚሰጉ ይናገራሉ። የመዋዕለ ነዋይ ባለሙያው አብዱልመናን መሃመድም ይህንን ስጋት ይጋሩታል። ''ከውጪ በሚመጡ የፍጆታ ምርቶች፣ የጥሬ ዕቃና የማምረቻ መሳሪያዎች ግዢ ምክንያት የንግድ ጉድለት እየሰፋ በሚመጣበት ሃገር ውስጥ፤ በዚህ መጠን የብርን የመግዛት አቅም እንዲቀንስ ማድረግ በአጭር ጊዜ ውስጥ የዋጋ መጋሸብን ያስከትላል'' በማለት ሊያስከትል የሚችለውን ጫና አስቀምጠዋል። የብር የመግዛት አቅም እንደሚቀንስ ከተነገረ በኋላ በምርቶችና በአገልግሎት ዋጋ ላይ ከፍ ያለ ለውጥ እንደሚኖር በእርግጠኝነት የሚናገሩት አቶ ደቻሳ ''በዕለታዊ ሥራና እንደኔ ተቀጥሮ ለሚተዳደረው ብዙ ህዝብ ይህ ለውጥ ከባድ ችግርን የሚያስከትል ይመስለኛል'' ይላሉ። አክለውም "የታሰበው ለውጥ መምጣቱን እርግጠኛ ለመሆን በማይቻልበት የውጪ ንግድ ሲባል ድሃው መስዋዕት መሆን አለበት ወይ?" በማለት ይጠይቃሉ። ግብይት የኢንቨስትመንት አማካሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው ተክለማርያም እንደሚሉት ''የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በአብዛኛው መሠረቱን ከውጭ በሚመጡ ምርቶች ላይ ያደረገ በመሆኑ፤ በመጋዘን ምርት ያለው ነጋዴ እንኳን ወደፊት የሚጠብቀውን የኢትዮጵያ ብር መጠንን በወጪነት እያሰላ የዋጋ ጭማሪ ማድረጉ አይቀርም'' ይላሉ። ይህም ምግብ፣ አልባሳትና መድኃኒትን ጨምሮ ለየዕለት ፍጆታም ሆነ ለዘላቂ ኑሮ የምንጠቀምባቸውን አብዛኞቹ ህብረተሰቡ የሚፈልጋቸው ምርቶች ላይ የምንዛሪ ለውጡን መሠረት ያደረገ ጭማሪ መከሰቱ አይቀሬ መሆኑን አቶ ጌታቸው ያክላሉ። መርካቶና ካዛንችዝ አካባቢ በፍጆታና ቋሚ ምርቶች ንግድ ላይ የሚገኙ ነጋዴዎችን ጠይቀን እንደተረዳነው፤ የብር የመግዛት አቅም እንዲቀንስ በመደረጉ ምክንያት በአቅርቦታቸው ላይ የዋጋ ጭማሪ እንደሚኖር እርግጠኛ ቢሆኑም በምን ያህል መጠን የሚለው ላይ ለመወሰን የገበያው ሁኔታና የነጋዴውን ስምምነት እየጠበቁ መሆናቸውን ገልፀውልናል። አቶ ጌታቸው እንደሚሉት ''የብር የመግዛት አቅም አንሷል የምንለው በጥቁር ገበያ እና በባንኮች የብር ምንዛሬ መካከል የሰፋ ልዩነት ሲታይ ነው። ይህ የሚያሳየው በገበያ ውስጥ ያለው የውጭ ምንዛሪ ፍላጎትና አቅርቦት ከፍተኛ አለመመጣጠን ስለሚታይበት ነው'' በማለት ያስረዳሉ። ከዚህ አንፃር ''አሁን የተወሰደው የብርን የመግዛት አቅም የመቀነስ እርምጃ ይህንን ክፍተት ከማጥበብ አንጻር አወንታዊ ሚና ሊኖረው ይችላል'' ተብሎ እነደሚታሰብ አቶ ጌታቸው ይናገራሉ። ስጋት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ ደሴ ከተማ ውስጥ በንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ግለሰብ እነደነገሩን "ለገበያ የሚቀርቡ ሸቀጦች በዶላር እጥረት ምክንያት ከገበያ እየጠፉ ባሉበት ሁኔታ የብር የመግዛት አቅም በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱ በህብረተሰቡም ሆነ በነጋዴው ላይ ከባድ ጫናን መፍጠሩ አይቀርም'' ይላሉ። ይህ የመንግሥት እርምጃ ወትሮውንም የተቀዛቀዘውን የንግድ ሥራቸውን የበለጠ ሊጎዳው እንደሚችልም ይሰጋሉ። ሁለቱም የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ይህን ያህል የብር የመግዛት አቅም ቅነሳ መንግሥት ያሰበውን ያህል ወጤት ቢያመጣለት እንኳን ዘለቄታው ላይ ጥርጣሬ አላቸው። አቶ አብዱልመናን እንደሚሉት ''ከሰባት ዓመት በፊት የብር የመግዛት አቅም እንዲቀንስ ሲደረግ በወጪ ንግድ ላይ የታየውን አይነት ውስን ለውጥ ያመጣል። ነገር ግን ለውጪ ንግድ ምርት የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ዋጋ ስለሚጨምር ይህ አውንታዊ ለውጥ ዘላቂነት አይኖረውም'' ሲሉ፤ አቶ ጌታቸውም ''በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ የሚታዩ ብዙ ችግሮች አሉ፤ ስለዚህ ይህ እርምጃ የሚታየውን የማክሮ ኢኮኖሚ ያለመመጣጠን ችግርን ይቀርፈዋል ማለት አይደለም'' ይላሉ። በመንግሥት በኩል ለዚህ እርምጃ የሚቀርበው ምክንያት የውጪ ንግድን ለማበረታታት እንደሆነ ቢነገርም አቶ ደቻሳም ሆኑ የደሴዋ ነጋዴ ህዝቡ ላይ የሚፈጠረውን ጫናና የኑሮ ውድነትን በምን እንዲቋቋመው ታስቦ እነደሆነ ይጠይቃሉ። ''የብር የመግዛት አቅም እንዲቀንስ ሲደረግ የውጭ ምንዛሪ መጠን አብሮ ይለወጣል። ይህ ደግሞ በምርቶች አቅርቦት ላይ ስለሚንፀባረቅ ችግሮች ይከሰታሉ። የሚያጋጥመው የዋጋ ጭማሪም ከተቀነሰው የብር የመግዛት አቅም በላይ ሊሆን ይችላል'' የሚሉት አቶ አብዱልመናን የህብረተሰቡ ስጋት ተገቢ መሆኑን ያሰምሩበታል። ሌላ ዕዳ ''የብርን የመግዛት አቅም በመቀነስ የወጪ ንግድን ማበረታት ይቻላል የሚለው የፖሊሲ አውጪዎች ዕይታ የራሱ የሆኑ ፈተናዎች አሉት'' የሚሉት አቶ ጌታቸው፤ ''እንዴት የብርን የመግዛት አቅም በመቀነስ ብቻ ነው የወጪ ንግድን ማበረታታ ይቻላል? ላኪዎች በዓለምአቀፍ ገበያ ውስጥ ያላቸው ተወዳዳሪነትስ የተገደበው በብር የመግዛት አቅም ምክንያት ነው?'' በማለት ይጠይቃሉ። ይህ እርምጃ በሃገሪቱ ላይም ከበድ ያለ ጫናን እነደሚፈጥር የሚያምኑት አቶ አብዱልመናን ''የብር የመግዛት አቅም መቀንስ በመንግሥት የልማት ድርጅቶችና በመንግሥት የውጪ ብድር ላይ ከፍ ያለ ተፅዕኖ ይኖረዋል። እስከ ሰኔ 2009 ድረስ ሃገሪቱ ከ23.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጪ ብድር ዕዳ አለባት። የብር የመግዛት አቅም በ15 በመቶ እንዲቀንስ ሲደረግ የሃገሪቱ ዕዳ በአስር ቢሊዮን ብሮች ያሻቅባል ማለት ነው'' በማለት ይገልፃሉ። ይህም ሃገሪቱ ያለባትን የብድር ጫና ከማክበዱ በተጨማሪ ሌሎች ችግሮችን ያስከትላል። ከሁሉ አሳሳቢው ደግሞ የዋጋ ግሽበት እንዲጨምርና ሌሎች ምጣኔ ሃብታዊ ቀውሶች እንዲከሰቱ ሊያደርግ ይችላል። የብርን የመግዛት አቅም ዝቅ በማድረግ ሊከሰቱ የሚችሉ አሳሳቢ ሁኔታዎች አቶ አብዱልማናንና አቶ ጌታቸው እንዲህ ያስቀምጧቸዋል። ከውሳኔው በፊት የነበረው የቅርብ ጊዜ የዋጋ ግሽበት 10.8 በመቶ እንደሆነ የሚናገሩት አቶ ጌታቸው ''ገና ከጅምሩ ይህ ግሽበት በጣም ከፍ ሊል ይችላል'' ሲሉ፤ አቶ አብዱልመናን ድግሞ ''ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ከውጪ ንግድ የሚገኘው ገቢ ቀድሞ በነበረበት ይቀጥላል። ይህ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እርምጃ ወደማያቋርጥ የብር የመግዛት አቅም ቅነሳና የዋጋ ግሽበት አዙሪት ውስጥ ያስገባናል'' በማለት ያጠቃልላሉ።
news-54826543
https://www.bbc.com/amharic/news-54826543
እስራኤል የበርካታ ፍልስጥኤማውያንን ቤቶች ማፍረሷን ተመድ ኮነነ
እስራኤል ለአስርት አመታት በወረራ የያዘችው ዌስት ባንክ ላይ የፍልስጥኤማውያንን ቤቶች ማፍረሷን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኮንኗል።
በዮርዳኖስ ሸለቆ የሰፈሩ 73 ቤተሰቦች ቤት አልባ ሆነዋል፤ ከነዚህም ውስጥ 41 ህፃናት መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል። የእስራኤል ወታደራዊ ኃይል በበኩሉ ቤቶቹ በህገወጥ መንገድ የተሰሩ ናቸው ብሏል። ይህንን የእስራኤል ድርጊት በፅኑ የኮነነው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአለምአቀፍ ህጎችንም የጣሰ ነው ብሎታል። የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ አስተባባሪ ቢሮ እንደገለፀው 76 መኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ፣ የእንስሳት መጠለያዎችና ሌሎች ንብረቶችም በእስራኤል ቡልዶዘሮች ማክሰኞ፣ ጥቅምት 24/ 2013 ዓ.ም መፈራረሳቸውን አስታውቋል። የእስራኤል ባለስልጣናት በበኩላቸው በዚህ ቁጥር የማይስማሙ ሲሆን ሰባት ድንኳኖችና ስምንት የእንስሳት መጠለያዎች ብቻ ናቸው የፈረሱት ይላሉ። ተቀማጭነቱን በእስራኤል ያደረገው የሰብዓዊ መብት ድርጅት ቢቲ ሴሌም ቤቶቹ ሲፈራርሱ የሚያሳይ ቪዲዮም አውጥቷል። "ይህ ከፍተኛ ኢ-ፍትሃዊነት ነው" በማለትም ሃርብ አቡ አል ካባሽ ለእስራኤሉ ጋዜጣ ሃሬትዝ ተናግሯል። "እንደሚመጡ ስላማናውቅ ቀድመን ለመዘጋጀት እድሉን አላገኘነም። በአሁኑ ሰዓት ቤት አልባ ሆነናል እየዘነበብን ነው" ብሏል። የሰላማዊ ዜጎችን ጉዳይ የሚመለከተው የእስራኤል ወታደራዊ ኃይል ክፍል ባወጣው መግለጫ የፈረሱት ቤቶች ወታደራዊ ማሰልጠኛ አካባቢ "በህገወጥ መንገድ" የተሰሩ ስለሆኑ ነው የሚል ምክንያት ሰጥቷል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በዚህ አይስማማም የእስራኤል ድርጊት አራተኛውን የጄኔቫ ድንጋጌ የጣሰ ነው ይላል። በአለም አቀፉ ህግ መሰረት አገራት በወረሩዋቸው (በተቆጣጠሩዋቸው) ግዛቶች ውስጥ የሚኖሩ ሰላማዊ ዜጎችን ደህንነት የማስጠበቅ ግዴታ አለባቸው። በጎሮጎሳውያኑ 1967 የተደረገውን የመካከለኛ ምስራቅ ጦርነት ተከትሎ ነው እስራኤል ዌስት ባንክ ግዛትን በመውረር በቁጥጥሯ ስር ያዋለችው። በተለያየ ጊዜ የተፈፀሙ ስምምነቶችን ተከትሎ ፍልስጥኤማውያን የተወሰነውን የዌስት ባንክ ግዛት በተወሰነ መልኩ በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ ቢያስችላቸውም መላውን ግዛት የምትቆጣጠረው እስራኤል ናት። ቤቶቹ የፈራረሱባቸው ክርበት ሁምሳ ከፍልስጥኤማውያን ቁጥጥር ውጭ ነው። በእስራኤል አገዛዝ ስር ያሉ የፍልስጥኤም ነዋሪዎች ቤቶችም ሆነ ህንፃ ለመገንባት ፍቃድ አይሰጠንም በማለት ይወቅሳሉ።
news-51179301
https://www.bbc.com/amharic/news-51179301
በየመኑ ጥቃት የሟቾች ቁጠር 111 ደረሰ
በየመን አንድ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ላይ ቅዳሜ ዕለት በተፈጸመው የሚሳኤል ጥቃት የሟቾች ቁጥር በትንሹ 111 መድረሱን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ።
ሚሳኤሉ የተተኮሰው በወታደራዊ ማሰልጠኛው ውስጥ በሚገኝ መስጂድ ውስጥ ወታደሮች የምሽት ጸሎታቸውን በማድረስ ላይ እያሉ ነበር ተብሏል። መንግስት ጥቃቱን የፈጸሙት የሁቲ አማጺያን ናቸው ቢልም ቡድኑ ግን ለጥቃቱ ወዲያው ሀላፊነት ከመውሰድ ተቆጥቧል። በየመን የዛሬ አምስት ዓመት የእርስ በርስ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ይሄኛው ጥቃት እጅግ ዘግናኝ ከሚባሉት መካከል እንደሆነም ተገልጿል። • ቦንብ የሚዘንብባትን የሶሪያ ከተማ አልለቅም ያለው የነፍስ አድን ሰራተኛ • በርካቶች መርሳት ያልቻሉት ጦርነት ሲታወስ በሳኡዲ የሚደገፈው መንግስት ታማኝ ወታደሮች እና የሁቲ አማጺያን መካከል የሚደረገው ጦርነት ሀገሪቱን ከማፈራረስ አልፎ እስካሁን ለ 100 ሺ የሚደርሱ ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆኗል። በየመን ከ 11 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች የዕለት ጉርሳቸውን ለማግኘት የሚቸገሩ ሲሆን 240 ሺ የሚሆኑት ደግሞ ለከባድ ረሀብ የቀረበ በሚባል ደረጃ ህይወታቸውን ይመራሉ ብሏል የዓለም የምግብ ፕሮግራም። በአማጺያን ቁጥጥር ስር ከምትገኘው ሳናአ በምስራቅ በኩል 170 ኪሎሜትሮች ርቀት ላይ የሚገኘው አል ኤስቲቅባል የተባለው ወታደራዊ ካምፕ ላይ በደረሰው ይህ ጥቃት 80 ወታደሮች ወዲያውኑ መሞታቸው ታውቋል። ነገር ግን በሚሳኤል የተደረገው ጥቃት ከፍተኛ ስለነበረ ጉዳት አጋጥሟቸው የነበሩ ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል። በዚህም የሟቾች ቁጥር ቢያንስ 111 እንደደረሰ ተገልጿል። 'ኤኤፍፒ' የተባለው የዜና ወኪል ደግሞ ከወታደሮችና የህክምና ባለሙያዎች አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት የሟቾች ቁጥር ከ 116 በላይ ይደርሳል። • በብሩንዲ ከአራት ሺህ በላይ የጅምላ መቃብሮች ተገኙ • እውን ሶስተኛው የዓለም ጦርነት ተቀስቅሶ እናየው ይሆን? እነሆ ምላሹ የየመኑ ፕሬዝዳንት አብደራቡህ ማንሱር ሃዲ ከጥቃቱ በኋላ '' የከሀዲዎችና የሽብረተኞች ተግባር ነው'' ብለዋል ጥቃቱን። አክለውም ''የሁቲ አማጺያን ለሰላም ምንም አይነት ፍላጎት እንደሌላቸው ማሳያ ነው'' ብለዋል። የሳኡዲ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በበኩሉ ጥቃቱን ''አማጺዎቹ ሁቲዎች ክብር ላለው የእምነት ቦታ እና ለየመን ዜጎች ህይወት ምንም ክብር እንደማይሰጡ ማሳያ ነው'' ብሎ ገልጾታል።
51641656
https://www.bbc.com/amharic/51641656
ኢትዮጵያ በዋሽንግተኑ የህዳሴ ግድብ ድርድር ላይ እንደማትሳተፍ አሳወቀች
ኢትዮጵያ በዋሽንግተን የመጨረሻ ቀጠሮ ተይዞለት በነበረው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ቀጣይ ድርድር ላይ እንደማትሳተፍ ለአሜሪካ አሳወቀች።
በአሜሪካ ዋሽንግትን ዲሲ ነገ እና ከነገ በስቲያ ሊካሄድ ታስቦ በነበረው ቀጣዩ የታላቁ ህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ላይ በሚደረገው ድርድር ላይ ኢትዮጵያ እንደማትካፈል የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቋል። ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው የአሜሪካ መንግሥትና የአለም ባንክ በታዛቢነት በሚገኙበት የካቲት 17 እና 20/2012 ዓ.ም ከሱዳን እና ግብጽ ጋር ሊካሂድ በታቀደው ቀጣይ የሦስትዮሽ ድርድር ላይ ኢትዮጵያ እንደማትገኝ አስታውቋል። ጨምሮም በዋሺንግተን ከተማ ለሁለት ቀናት ሊካሂድ ታስቦ በነበረው የሦስትዮሽ የድርድር መድረክ ላይ ኢትዮጵያ የማትሳተፈው፤ ተደራዳሪ ቡድኑ በአገር ውስጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚያደርገውን ውይይት ባለማጠናቀቁ በተጠቀሰው ጊዜ በአሜሪካ በመገኘት ውይይቱን ማድረግ እንዳልተቻለ ጥሪውን ላደረገው የአሜሪካ የትሬዠሪ ቢሮ ማስታወቁን ገልጿል። ለድርድሩ ቅርብ የሆኑ ባለሙያዎች ለቢቢሲ እንደተናገሩት ግብጽ የውይይቱን አቅጣጫ ከውሃ አሞላልና አለቃቅ ርዕሰ ጉዳይ በማውጣት በተለያዩ ወቅቶች ማግኘት በሚገባት የውሃ ድርሻ ላይ በማተኮሯ ሂደቱ በተፈለገው ፍጥነት ለመሄድ አልቻለም። ግብጽ የሱዳንን ድጋፍ በመያዝ በደረቅና ድርቅ በሚያጋጥምባቸው ጊዜያት ከአባይ ወንዝ ላገኘው ይገባል ብላ ባስቀመጠችው የውሃ መጠን ላይ የኢትዮጵያ ተደራዳሪዎችን ተቀባይነት አላገኘችም። ባለሙያዎቹ ጨምረውም በዚህ ድርድር ሱዳንና ታዛቢ የተባሉት ወገኖች ከግብጽ ፍላጎት ጎን የመቆም አዝማሚያ አሳይተዋል። በዋሽንግተን ከተማ የተካሄደውን የመጨረሻውን ውይይት ተከትሎ ነገና ከነገ ወዲያ ይደረጋል በተባለው ድርድር ላይ ከስምምነት ተደርሶ በፊርማ መቋጫ እንደሚያገኝ ተነግሮ የነበረ ቢሆንም ኢትዮጵያ በውይይቱ ላይ እንደማትግኝ በማሳወቋ ለሌላ ጊዜ መተላለፉ አይቀርም። ቀደም ሲል ተደረገውን ድርድር ተከትሎ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ስልክ ደውለው ሂደቱ በዚህኛው ድርድር መቋጫ እንደሚያገኝ ተስፋ እንዳለቸው ተናግረው ነበር። በቅርቡም የውጪ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ማይክ ፖምፒዮ አዲስ አበባ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተገናኝተው ነበር። ምንም እንኳ የመጨረሻውን ድርድር ለማድረግና ስምምነት ላይ ለመድረስ ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ቢሆንም የውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር በግድቡ ጉዳይ የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት አወያይቶ ስላልጨረሰ በመድረኩ ሊሳተፍ እንደማይችል አሳውቋል። በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅን በተመለከተ የተካሄዱት ውይይቶች ያለስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ ከ9 ቀናት በፊት በጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት ስላሉት የድርድር አካሄድ እና አቅጣጫ ላይ ውይይት መደረጉ ይታወሳል። በዚያ ውይይት ላይ ሚኒስትሮች፣ የተደራዳሪ ኮሚቴ አባላት፣ ምሁራን፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና ሌሎችም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ግለሰቦችን በውይይቱ ተሳትፈው ነበር። ለመገናኛ ብዙሃን ዝግ በነበረው ውይይት ላይ ኢትዮጵያ በቀጣዩ የዋሽንግትን ስብሰባ እንደማትሳተፍ ስለመወሰኑ የታወቀ ነገር የለም። በአሜሪካ መንግሥትና የዓለም ባንክ አደራዳሪነት በአዲስ አበባ፣ ካይሮ፣ ካርቱም እና ዋሽንግተን ዲሲ ሲደረጉ የነበሩት ውይይቶች ያለውጤት እንዲበተኑ የሆነው የግብጽ መከራከሪያ ነጥቦች መለዋወጥ መሆኑ ተጠቁሟል። ቢቢሲ ለውይይቱ ቅርበት ካላቸው ባለሙያዎች እንደተረዳው ምንም እንኳን የሚካሄደው ውይይት በግድቡ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ዙሪያ እንዲሆን ኢትዮጵያ ጥረት እያደረገች ቢሆንም በግብጽ በኩል ድርድሩ የውሃ ድርሻ ላይ እንዲያተኩር ግፊት እያደረገች ነው።
news-56742661
https://www.bbc.com/amharic/news-56742661
አሜሪካ በአፍጋኒስታን ያሉ ወታደሮቿ በመጪው መስከረም ይወጣሉ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ወታደሮቻቸው በመጪው መስከረም ወር መጀመሪያ ላይ አፍጋኒስታንን ለቅቀው እንደሚወጡ ለማስታወቅ መዘጋጀታቸውን የአሜሪካ ባለስልጣናት ለመገናኛ ብዙሀን ገለጹ።
ባሳለፍነው ዓመት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከታሊባን መሪዎች ጋር ግንቦት ወር ላይ ወታደሮቻቸውን ለማስወጣት ተስማምተው የነበረ ቢሆንም አዲሱ ፕሬዝዳንት ግን ወደ መስከረም ገፍተውታል። በአዲሱ ቀነ ገደብ መሰረት ወታደሮቹ አፍጋኒስታኒንን ለቅቀው የሚወጡ ከሆን ከዛሬ 20 ዓመት በፊት በዓለም የንግድ ማዕከል ላይ ከደረሰው የሽብር ጥቃት 20ኛ ዓመት ጋር ሊገጣጠም እንደሚችል ተገምቷል። ከዚህ ቀደም ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ግንቦት ወር ላይ ወታደሮቹን ከአፍጋኒስታን ማስወጣት ከባድ ሊሆን እንደሚችል ተናግረው ነበር። የአሜሪካ እና የኔቶ ኃላፊዎች እንዳሉት ታሊባን በተስማሙት መሰረት በአካባቢው የሚፈጸሙ ጥቃቶችን መቀነስ አልቻለም። ታሊባን አሜሪካ ወታደሮቿን በምታስወጣበት ጊዜ ላይ ጥቃት የሚፈጽም ከሆነ ከባድ የሀነ አጸፋዊ ምላሽ እንደሚጠብቀው ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሲሰጡ የነበሩት ከፍተኛ ኀላፊ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ተቻኩሎ ወታደሮቹን ለማስወጣት መሞከር ወታደሮቹን አደጋ ላይ ሊጥላቸው እንደሚችል በማሰብ ይህንን እንደወሰኑ ኃላፊው ጨምረው ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱም ዛሬ ስለወታደሮች መመለስ በይፋ እንደሚናገሩ ይጠበቃል። ጥቂት የአፍጋኒስታን ኃላፊዎች የአዲሱ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር አዲስ የሆነ የሰላም መስመር እንደሚከተል ተስፋ እንደሚያደርጉ የገለጹ ሲሆን ወታደሮቹን የማስወጣት ሂደቱን ወደ መስከረም መግፋታቸው ግን አንዳንዶችን አሳስቧል። በአፍጋኒስታን መንግስትና በታሊባን መካከል የመንግሥት ሰልጣንን እንዴት መካፈል ይቻል በሚለው ላይ ሲደረግ የነበረው ድርድር በጣም አዝጋሚ መሆኑን ተከትሎ የአሜሪካ ወታደሮች ከመውጣታቸው በፊት ስምምነት ላይ ላይደርሱ እንደሚችሉ ተገምቷል። ምናልባት ከስምምነት ላይ የሚደርሱ ከሆነ ታሊባን ለዓመታት ሲናፍቀው የቆየው ዓለማቀፍ ተቀባይነት ሊረጋገጥ ይችላል። ነገር ግን በርካቶች ደግሞ የአሜሪካ ወታደሮች መውጣታቸውን ተከትሎ ታሊባን በኃይል ነገሮችን ለመቆጣጠር ሊሞክር እንደሚችል እየተናገሩ ነው። ምክንያቱም የአፍጋኒስታን መንግሥት አሁንም ቢሆነ የአሜሪካ ወታደሮች የሚያደርጉለት ድጋፍ ከፍተኛ ነው። ታሊባን በበኩሉ ማክሰኞ ዕለት ባወጣው መግለጫ በሚቀጥለው ወር ቱርክ ውስጥ የአፍጋኒስታን መጻኢ ተስፋ ላይ በሚደረገው ውይይት ላይ እንደማይሳተፍ ያስተወቀ ሲሆን ''ምክንያቴ ደግሞ የውጭ አገር ወታደሮች እስካሁን ከአፍጋኒስታን ስላልወጡ ነው'' ብሏል። ''ሁሉም የውጭ አገራት ኃይሎች ሙሉ በሙሉ አገራችንን ለቅቀው እስካልወጡ ድረስ በቱርክ በሚካሄደው ስብሰባ ላይ አንሳተፍም'' ብለዋል መቀመጫውን ኳታር ያደረጉት የታሊባን ቃል አቀባዩ ሞሀመድ ናኢም። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊው አንቶኒ ብሊንከን እና የአሜሪካ መከላከያ ኃላፊ ሎይድ ኦስቲን ዛሬ የኔቶ አጋሮቻቸውን ከአፍጋኒስታን ወታደሮችን ማስወጣት በተመለከተ ማብራሪያ እንደሚሰጧቸው ይጠበቃል። አሜሪካ ባለፉት 20 ዓመታት በአፍጋኒስታን ብቻ በርካታ ሚሊየን ዶላሮችን ፈሰስ ያደረገች ሲሆን በአጠቃላይ ደግሞ ከ2 ሺ በላይ ወታደሮቿ ተገድለውባታል።
news-44984860
https://www.bbc.com/amharic/news-44984860
"ደም የመሠለች ጨረቃ" ዛሬ ምሽት በኢትዮጵያ ሠማይ ላይ ትታያለች
ለአንድ ሰዓት ከ 43 ደቂቃ የሚዘልቀው ግርዶሽ ዛሬ ሐምሌ 20፣ 2010 ዓ. ም ይታያል። በ21ኛ ክፍለ ዘመን ለዚህን ያህል ጊዜ የቆየ ግርዶሽ አልታየም፣ አይታይምም። የጨረቃ ግርዶሽ ምንድነው ?
የጨረቃ ግርዶሽ የሚከሰተው መሬት፣ ጨረቃና ፀሐይ በሚያደርጉት መስተጋብር ነው። ፀሐይ፣ ምድርና ጨረቃና በሰልፍ ሲሰደሩ ግርዶሽ ይከሰታል። ይህም ማለት መሬት በፀሐይና በጨረቃ መሐል ድንገት ስትደነቀር ነው። በዚህን ጊዜ ወደ ጨረቃ የሚሄደው የፀሐይ ብርሃን በምድር ይጋረዳል። ምድር በፀሐይና ጨረቃ መሐል መደንቀር ደግሞ አንዳች ጥላ ይፈጥራል። በዚህን ጊዜ ጨረቃ በተፈጠረው ጥላ መሐል ሰተት ብላ ስትዘልቅ የጨረቃ ግርዶሽ ተፈጠረ እንላለን። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ሁለት ፓትሪያርክ ይኖራታል "የእሱ አባት ኩራዝ የላቸውም፤ እሱ ግን ኢትዮጵያን ሊያበራ ነው የሞተው" ግርዶሹ የት ይታያል? ግርዶሹን በጉልህ ማየት የሚቻለው በከፊል አውሮፓ፣ እሲያ፣ አፍሪካ፣ አውስትራሊያ እና ኒውዝላንድ አካባቢ ነው። ከሰሜን አሜሪካ በስተቀር በአመዛኙ በተቀሩት አሕጉራት መታየት ይችላል። ቀይዋን ጨረቃ ለማየት ቴሌስኮፕ አያስፈልግም። ቀለል ያለ አቅርቦ ማሳያ (ባይናኩላር) በቂ ነው። በኢትዯጵያና አካባቢው ከምሽቱ 4 ሰዓት ከ20 አካባቢ ማየት ይቻላል። የሚፈጠረው ግርጃ ጨረቃ ቀላ ያለ መልክ እንድትይዝ ያደርጋታል የዛሬ ምሽቷ ጨረቃ ለምን ትቀላለች? የጨረቃ ምህዋር ዘመም ያለ በመሆኑ ጨረቃ በየወሩ በምድር ጥላ በኩል ልታልፍ አትችልም። ለምን? ከፀሐይ ብርሃን የሚመጣው የቀለማት ሽብልቅ በምድር ከባቢ አየር አማካይነት ይበተናል። ኾኖም ባለቀይ ቀለሙ ረዥም የጨረር ሞገድ ከባቢውን አልፎ በመግባት ወደ ጨረቃ ነጥሮ ይመለሳል። ይህ ኩነት ለጨረሩ የተለየ ደማቅ ቀይ ቀለም ይሰጠዋል። ክስተቱ "የደም ጨረቃ" ወይም ቀይዋ ጨረቃ ተብሎ የሚጠራውም ለዚሁ ነው። ደቡብ ሱዳን ለመኪና መግዣ 16 ሚሊየን ዶላር አወጣች በጉልህ የሚታየው ከየት አካባቢ ነው? ይህን ታሪካዊ ኩነት ለመታደም ሁነኛው ሥፍራ ምሥራቅ አፍሪካና መካከለኛው ኢሲያ ነው። ኾኖም በመካከለኛውና በሰሜን አሜሪካ ግርዶሹን ለመመልከት አይቻልም። ከምሥራቅ አፍሪካ ሌላ በደቡብ አሜሪካ በምሥራቁ ክፍል በተለይም በቦነስ አይረስ፣ ሳኦፖሎና ሪዯ ዲጂኔሩ የተሻለ ትታያለች።
news-53758757
https://www.bbc.com/amharic/news-53758757
እስክንድር ነጋ ፡ አቶ እስክንድር ጉዳያቸው በግልጽ ችሎት የማይታይ ከሆነ ችሎት መቅረብ እንደማይፈልጉ ገለጹ
የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዚደንት አቶ እስክንድር ነጋ ጉዳያቸው በግልጽ ችሎት የማይታይ ከሆነ በዚህ ሂደት ውስጥ መሳተፍ እንደማይፈልጉና ጠበቃቸውንም ማሰናበታቸውን ለፍርድ ቤት ገለጹ።
አቶ እስክንድር ነጋ ለፍርድ ቤት ይህን ያሉት እራሳቸውና አብረዋቸው የተከሰሱ ሰዎች ጉዳይ ዐቃቤ ሕግ በጠየቀው መሰራት ለምስክሮች ደኅንነት ሲባል ከመጋረጃ ጀርባ በዝግ ችሎት ምስክርነታቸውን እንዲሰጡ ውሳኔ መሰጠቱን ተከትሎ ነው። ረቡዕ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ጉዳያቸው የታየው የአቶ አስክንድር ነጋ፣ አቶ ስንታየሁ ቸኮልና ቀለብ ስዩም መሆኑን ለቢቢሲ የገለጹት ጠበቃቸው አቶ ሄኖክ አክሊሉ ችሎቱ ዐቃቤ ህ ቀደም ቀደም ሲል ያቀረባቸውን ጥያቄዎች ተመልክቷል። ጠበቃው እንዳሉት ዐቃቤ ሕግ ያቀረባቸውን የምስክሮች ዝርዝር ለተጠርጣሪዎቹ መድረስ የለበትም እንዲሁም ደግሞ ምስክርነት መስጠትን በተመለከተ ከቀረቡት ሰባት ምስክሮች ውስጥ ሦስቱ ማንነታቸው ሳይገለጽና ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው እንዲመሰክሩ የተቀሩት አራት ምስክሮች ደግሞ ችሎቱ ዝግ ሆኖ ምስክርነታቸው እንዲሰማ ጥያቄ አቅርቦ ነበር። ይህንን ጉዳይ ከደንበኞቻቸው ጋር ተማክረው የጽሁፍ መልስ ይዘው እንደቀረቡ የሚናገሩት ጠበቃ ሄኖክ፤ በዚህም መሰረት ይህ ሂደት የተከሳሾችን መብት በእጅጉ እንደሚነካና የተከሳሾችን የመከላከል መብት እንደሚጎዳ እንዲሁም ቀሪ ምስክሮችም ቢሆኑ በዝግ ሳይሆን በግልጽ ችሎት ምስክርነታቸውን ሊሰጡ ይገባል ማለታቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። "ስለዚህ በተጀመረው ሂደት መቀጠል አለበት፤ በቀረቡት ማስረጃዎች ላይ በአደባባይ እንሟገት፣ እንከራከር የሚል ነበር በአጭሩ የሰጠነው መልስ" ብለዋል ጠበቃው። ለዚህም ዐቃቤ ሕግ በሰጠው ምላሽ የምስክሮች ጥበቃ አዋጅን ጠቅሶ ከሚደረጉ ጥበቃዎች ውስጥ ለምስክሮች ደኅንንት ሲባል ማንነታቸው ሳይገለጽና ሳይታዩ እንዲሁም በዝግ ችሎት እንዲመሰከሩ እንደሚደረግ ገልጿል። ጨምሮም የምስክሮችን ደኅንነት ለማስጠበቅ በአዋጁ መሰረት የሚደረገው በዝግ ችሎትና ማንነታቸው ሳይገለጽ ምስክርነት መስጠታቸው ተጠርጣሪዎች ላይ ጉዳት የሌለው መሆኑን አመልክቶ የተጠርጣሪዎች አቤቱታ ውድቅ እንዲደረግ ጠይቋል። ፍርድ ቤቱም ይህንን ከሰማ በኋላ በተከሳሾችና በጠበቆች የቀረበውን ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርጎ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን ሀሳብ ሙሉ በሙሉ በመቀበል ምስክሮቹን የመስማት ሂደቱ እንዲቀጥል ብይን መስጠቱን አቶ ሄኖክ ተናግረዋል። በዚህ ጊዜም አቶ እስክንድ ነጋ ለፍርድ ቤቱ የሚገልጹት ሀሳብ እንዳላቸው በመጠየቅ፤ የተጠረጠሩበት ጉዳይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ባህሪ ያለው መሆኑን በመጥቀስ፤ እንዲህ አይነት መሰል ጉዳዮች ደግሞ በዝግ ችሎት መካሄድ የለባቸውም፤ ዓለም አቀፍ ተሞክሮውም በግልጽ እንደሚካሄድ ነው የሚያሳየው ብለዋል። "ስለዚህ አቃቤ ሕግ ሂደቱ በዝግ እንዲካሄድና ምስክሮች ከመጋረጃ ጀርባ እንዲመሰክሩ መደረጉ እኛ ፍትህ እንዳናገኝ ያደርገናል፣ የፍርድ ሂደቱን ይጎዳብናል፣ በእንደዚህ አይነት ፍትህ በማናገኝበት ሁኔታ የክርክሩ ሂደት አካል መሆን ስለማንፈልግ እራሳችንን ከጉዳዩ አግልለናል" ማለታቸውን ጠበቃው ተናግረዋል። ጨምረውም ከዚህ በኋላም በዚህ ሂደት እንደማይሳተፉና ፍርድ ቤት መምጣት እንደማይፈልጉ ጠቅሰው፤ ፍርድ ቤት ወክለዋቸው ሲቀርቡ የነበሩ ጠበቃዎችንም ማሰናበታቸውን ለችሎቱ ተናግረዋል። ሌሎቹም ተከሳሾች ተመሳሳይ ሃሳብ እንዳላቸው መግለጻቸውን ጠበቃ ሄኖክ ለቢቢሲ አስረድተዋል። በጉዳዩ ላይ ዐቃቤ ሕግ ያለውን አስተያየት በፍርድ ቤቱ ተጠይቆ፤ ፖሊስ ተከሳሾችን በቀጠሮ አስገድዶ እንዲያቀርብላቸው ለችሎቱ አመልክቷል። ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ሕግን አቤቱታ ከሰማ በኋላ ፖሊስ በቀጣይ ቀጠሮ ምስክሮቹን እንዲያቀርብና እንዲሁም ተጠርጣሪዎቹን አስገድዶ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቶ፤ ለእነአቶ እስክንድርም መንግሥት ጠበቃ እንዲያቆምላቸው ሲል ውሳኔ ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱ ይህንን ካደረገ በኋላ አቶ እስክንድር ነጋ ይሄ ትክክል አይደለም በሚል ''እኛ ማንም ጠበቃ እንዲያቆምልን አንፈልግም፤ መከራከር አንፈልግም፤ መንግሥት ጠበቆች እንዲያቆምልን ፈቃደኞች አይደለንም። እኛ የእንደዚህ አይነት የፍርድ ሂደት አካል መሆን አንፈልግም፤ ከዚህ በኋላ ወደ ችሎቱ መምጣትም አንፈልግም''' በማለት መናገራቸውን ጠበቃው ገልጸዋል። ፍርድ ቤቱ በሰጠው ውሳኔ መሰረት የምስክሮችን ቃል ለመስማት ለነሐሴ 8/2012 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል።
50348472
https://www.bbc.com/amharic/50348472
በቃፍታ ሸራሮ ፓርክ ኤፍኤምዲ የተባለ በሽታ የዱር እንስሳትን እየገደለ ነው
በቃፍታ ሸራሮ ፓርክ ኤፍኤምዲ (ፉት ኤንድ ማውዝ) የሚል መጠሪያ ያለው በሽታ የዱር እንስሳትን በተለይ ደግሞ አጋዘን እየገደለ እንደሆነ ታውቋል።
በበሽታው ምን ያህል ቁጥር ያላቸው አጋዘኖች እንደሞቱ ለማወቅ ባይቻልም በአካባቢው የሚገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ እንዳረጋገጠው በርካቶች ሞተዋል፤ በርከት ያሉትም ታመዋል። የፓርኩ ባለሞያ ሃፍቶም ሐጎስ ለቢቢሲ እንደገለፁት በሽታው የዱር እንስሳትን እንዲሁም ቤት እንስሳትን ያጠቃል። •'የዓለም ሳምባ' የሚባለው አማዞን ጫካ በአስፈሪ ሁኔታ እየነደደ ነው •በቤተ መንግሥት ግቢ የተገነባው አንድነት ፓርክ በውስጡ ምን ይዟል? በቀላሉም የሚተላለፍ ሲሆን እስካሁን ባለው የዱር እንስሳት ብቻ እንደተጠቁ ባለሞያው ተናግረዋል። በበሽታው የተጠቃ እንስሳ ጆሮውና መቀመጫው ላይ የመቁሰል ምልክት ይታይበታል ተብሏል። በምዕራብ ትግራይ የሚገኘው ቃፍታ ሸራሮ ፓርክ ከ200 ሺሕ ሄክታር በላይ ስፋት ያለው መሬት የሚሸፍን ሲሆን፤ በርካታ ዓይነት የዱር እንስሳትና ዕፅዋትም ይገኙበታል። በተለይም ዝሆንና አጋዘን በብዛት የሚኖሩበት ነው። •ኢትዮጵያ ውስጥ የጠፉት ጀርመናዊ ፕሮፌሰር ዱካ አልተገኘም ከሰሞኑ በአካባቢው የእሳት ቃጠሎ ተንስቶ ከ1500 በላይ ሄክታር መሬት ላይ ውድመት አስከትሏል። የፓርኩ ባለሞያ ሃፍቶም ሐጎስ ባለፈው ሰኞ አመሻሽ ላይ በፓርኩ የተነሳው የእሳት ቃጠሎ ከትናንት ወድያ ጥቅምት 26፣2012 ዓ.ም በቁጥጥር ማዋል ቢቻልም፤ በተመሳሳይ ቀን ዓዲ ጎሹ በተባለ ሌላ ኣቅጣጫ እንደ አዲስ የተነሳው ቃጠሎ ጉዳት እንዳደረሰ በአከባቢው የሚገኘው ሪፖርተራችን ታዝቧል። ፓርኩ በፌደራል መንግሥት ስር የሚተዳደር ቢሆንም አጥር እንደሌለውና በበጎ ፈቃደኝነት ተሰማርተው የሚሰሩ ሰዎች ቁጥርም በቂ እንዳልሆነም ተገልጿል። •የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ከቃጠሎው በኋላ በተለያዩ ጊዜያቶች በተደጋጋሚ የእሳት ቃጠሎ እንደሚነሳና የአካባቢው ታጣቂዎች (ሚሊሻ) ገብተው እርዳታ እንደሚያደርጉ ለማወቅ ተችሏል። በአካባቢው የሚነሳው ቃጠሎ በአብዛኛው በፓርኩ ውስጥ ወርቅን በማውጣትና ማርን በመቁረጥ የተሰማሩ እረኞች የሚያስነሱት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
news-53496857
https://www.bbc.com/amharic/news-53496857
ወላጆቿን የገደሉትን የታሊባን ታጣቂዎች የገደለችው ታዳጊ ‘ጀግና’ ተባለች
ባሳለፍነው ሰምንት ወላጆቿን የገደሉትን ሁለት የታሊባን ታጣቂዎችን በጥይት መታ የገደለችው ታዳጊ በማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ‘ጀግና’ ተብላ እየተወደሰች ነው።
ታዳጊዋ ኤኬ-47 የጦር መሣሪያ ይዛ የሚያሳየውን ምስል በርካቶች በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተጋሩ ነው። ከ14 እስከ 16 እድሜ መካከል ሳትሆን እንደማትቀር የተገመተችው ታዳጊ፤ በምትኖርበት መንደር የታሊባን ታጣቂዎች ወላጆቿን የገደሉባት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። በዚህ የተበሳጨችው ታዳጊ የወላጆቿን ኤኬ-47 ክላሺንኮቨ መሣሪያ ይዛ በመውጣት ሁለት የታሊባን ሚሊሻ አባላትን ስትገድል በርካቶችን ማቁሰሏን የጋሆር ግዛት ባለስልጣናት ተናግረዋል። ታጣቂ ሚሊሻዎቹ ታዳጊዋ የምትኖርበት መንደር ድረስ በመምጣት እናት እና አባቷን የገደሉት ወላጅ አባቷ የመንግሥት ደጋፊ ነው በማለት እንደሆነ ባለስልጣናቱ ጨምረው ተናግረዋል። ታዳጊዋ ኤኬ-47 የጦር መሣሪያ ይዛ የሚያሳየውን ምስል በርካቶች በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተጋሩ ነው። “ለጀግንነቷ ክብር ይገባታል” ሲል አንድ የፌስቡክ ተጠቃሚ ተናግሯል። “ወላጆችሽን መልሰሽ እንደማታገኚ እናውቃለን፤ የወሰድሽው የበቀል እርምጃ ግን የህሊና እረፍት ሊሰጥሽ ይችላል” ሲል ሞሐመድ ሳሌህ የተባለ የፌስቡክ ተጠቃሚ ጽፏል። የአፍጋኒስታን መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ከሆነ፤ በምዕራብ አፍጋኒስታን የምትገኘው ግሆር ግዛት፤ መሠረተ ልማት ካልተስፋፋባቸው የአፍጋን ግዛቶች አንዷ ስትሆን በአካባቢው በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች መጠንም ከሌሎች ግዛቶች ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል። ታሊባን እና የአሜሪካ መንግሥት ከወራት በፊት የሰላም ስምምነት ላይ ደርሰው የነበረ ቢሆንም፤ በርካታ የታሊባን አባላት የአፍጋኒስታን መንግሥት ከስልጣን እንዲወርድ ጫና እያሳደሩ ይገኛሉ።
news-53496413
https://www.bbc.com/amharic/news-53496413
የዩክሬኑ እገታ በፕሬዝደንቱ ያልተለመደ ቪዲዮ ተቋጨ
በዩክሬን አንድ አጋች ከ10 በላይ የሚሆኑ ሰዎቸን በአውቶብስ ላይ አግቶ መቆየቱ ይታወሳል።
በከፍተኛ ደረጃ የታጠቀው ሩሲያዊው አጋች ወደ ፖሊስ ሁለት ጊዜ ከመተኮሱም ባለፈ የእጅ ቦምብ ወደ ፖሊስ ወርውሮ ነበር። ይሁን እንጂ የዩክሬን ፕሬዝደንት በጉዳዩ ጣልቃ ገብተው በአጋቹ ጥያቄ ሠረት ያልተለመደ ይዘት ያለው ተንቀሳቃሽ ምስል የፌስቡክ ገጻቸው ላይ ከለጠፉ በኋላ ፖሊስ 10 ታጋቾችን ነጻ አውጥቶ አጋቹን በቁጥጥር ሥር አውሏል። የዩክሬን መገናኛ ብዙሃን ከእገታው በኋላ አጋቹ እጁ ወደኋላ ተጠርንፎ እና መሬት ላይ በደረቱ ተንጋሎ አሳይተዋል። አጋቹ ከመያዙ በፊት ፕሬዝደንት ቮሎደይመር ዜሌኔስኪ በአጋቹ ጥያቄ መሠረት፤ “ሁሉም ሰው 2005 ላይ የተሠራውን 'ኤርዝሊንግ' የተሰኘውን ፊልም መመልከት አለበት” የሚል ቪዲዮ ለጥፈው ነበር። አጋቹ በቁጥጥር ሥር እንደዋለ ፕሬዝደንት ዜሌኒስኪ ተንቀሳቃሽ ምስሉን ከገጻቸው ላይ አጥፍተውታል። በሆሊውድ የተሠራው ይህ ፊልም የእንስሳት መብት ላይ የሚያጠነጥን ዘጋቢ ፊልም ነው። በዘጋቢ ፊልሙ ግዙፍ የዓለማችን ኢንደስትሪዎች የንግድ እንቅስቃሴያቸውን ለማስቀጠል ምን ያህል እንስሳት ላይ እንደሚመረኮዙ ያሳያል። አጋቹ የሩሲያ ዜጋ የ44 ዓመት ጎልማሳ ማከሰይም ክራይቮሽ እንደሆነ የዩክሬን ፖሊስ ይፋ አድርጓል። አጋቹ የሩሲያ ዜጋ የ44 ዓመት ጎልማሳ ማከሰይም ክራይቮሽ እንደሚባል እና ከዚህ ቀደም በወንጀል ድርጊቶች የተፈረደበትበን አጠናቆ ከእስር የወጣ ስለመሆኑ፤ እንዲሁም የአእምሮ ጤና ችግር አጋጥሞት የህክምና ድጋፍ ሲደረግለት እንደነበረ ተነግሯል። በምሥራቅ ዩክሬን በምትገኘው ሉተስክ ከተማ 20 ሰዎችን አግቶ ይዞ የነበረው ሩሲያዊ፤ ተቀጣጣይ ነገሮችን ታጥቆ እንደሚገኝ በማሳወቅ እውቅ ፖለቲከኞች እራሳቸውን "ሽብርተኛ ነን" ብለው እንዲጠሩ ጠይቆ እንደነበረ ቀደም ሲል ፖሊስ አስታውቋል። በጠቅላላው ታግተው የነበሩት 13 ሰዎችን ከበርካታ ሰዓታት በኋላ ምንም አይነት አካላዊ ጉዳት ሳይደርስባቸው ከእገታው ነጻ ወጥተዋል።