id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
news-54490412
https://www.bbc.com/amharic/news-54490412
አርሜኒያና አዘርባጃን የጦር ማቆም ስምምነት አደረጉ
አርሜኒያና አዘርባጃን ከባድ ጦርነት ላይ ነበሩ ባለፉት ሳምንታት፡፡
በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል ሩሲያ ሁለቱን አገሮች በማደራደር ተሳክቶላታል፡፡ ቢያንስ ጊዜያዊ የጦር አውርድ ስምምነት ለማድረግ መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡ የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ናቸው ይህን መልካም ዜና ይፋ ያደረጉት፡፡ የአዘርባጃንና የአርሜኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሞስኮ 10 ሰዓታት የፈጀ ንግግር ካደረጉ በኋላ ነው ይህ ውጤት የተገኘው፡፡ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ሁለቱ አገራት ባደረጉት ጦርነት በትንሹ 300 ዜጎቻቸውን አጥተዋል፡፡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፡፡ አሁን ጊዜያዊ የተኩስ ማቆም ስምምነቱ ዛሬ ቅዳሜ ሌሊት ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል፡፡ በዚህ ጊዜም የጦር ምርኮኞቻቸውን ይለዋወጣሉ፡፡ የሟች ወታደሮችን ሬሳ በወጉ የመለየትና ግብአተ መሬቱን የመፈጸም ሂደትም ይኖራል ተብሏል፡፡ ሁለቱን ጎረቤት አገራት ለጦርነት የዳረጋቸው ናጎርኖ ካራባህን የምትባል ግዛት የይገባናል ጥያቄ ነው፡፡ ናጎርኖ ካራባህን በአዘርባጃን ግዛት ውስጥ ያለች ቦታ ብትሆንም የሚኖሩባት የአርመን ዝርያ ያላቸው ዜጎች ናቸው፡፡ የምትተዳደረውም በአርሜኒያ ብሔር ተወላጆች ነው፡፡ በአርሜኒያ ድጋፍ ራሳቸውን እንደ ነጻ ግዛት ነው የሚቆጥሩት፡፡ ሆኖም ናጎርኖ ካራባህን የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ሆነ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአዘርባጃን ግዛት እንደሆነ ነው የሚያውቀው፡፡ ግዛቱ የሚገኘውም በአዘርባጃን አገር ውስጥ ነው፡፡ አርሜኒያና አዘርባጃን የቀድሞው የሶቭየት ሪፐብሊክ አካል የነበሩ ናቸው፡፡ ሩሲያ በአርሜኒያ የጦር ቀጠና ያላት ሲሆን ከአዘርባጃንም ጋር ጥሩ ወዳጅ ናት፡፡ ቱርክ በበኩሏ ጭልጥ ያለ ድጋፏን ለአዘርባጃን ሰጥታለች፡፡ የአዘርባጃንና የአርሜኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሞስኮ 10 ሰዓታት የፈጀ ንግግር ካደረጉ በኋላ ነው ይህ ውጤት የተገኘው አዘርባጃንና ቱርክ የዝርያና የሃይማኖት ቅርርብ እንዳላቸው ይነገራል፡፡ ይህን ተከትሎ ጦርነቱ ከሁለቱ አገራት አልፎ ሩሲያን፣ ኢራንን እንዲሁም ቱርክን ሊያካትት ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሮ ነበር፡፡ ይህ የጥቂት ሳምንታት ጦርነት ናጎርኖ ካራባህ ነዋሪ የሆነውን ግማሽ ሕዝብ ያፈናቀለ ሆኗል፡፡ ከ150ሺህ የግዛቲቱ ነዋሪዎች 70ሺህ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፡፡ አርሜኒያና አዘርባጃን ይህን ጦርነት ሲያደርጉ የመጀመርያቸው አይደለም፡፡ እንደ አውሮጳዊያኑ በ1988 ጀምሮ ለስድስት ዓመታት የዘለቀ ጦርነት አድርገው ያውቃሉ፡፡ ያን ጦርነትም እንዲሁ በተኩስ አቁም ስምምነት ነበር የደመደሙት እንጂ ወደ ጦርነት ላስገባቸው ግዛት ባለቤትነት ቁርጥ ስምምነት አላደረጉም ነበር፡፡ አሁን ከዓመታት በኋላ ወደ ጦርነት የተመለሱትም ለዚሁ ነው፡፡ አዘርባጃን 10 ሚሊዮን ሕዝብ ያላት የነዳጅ ዘይት እያበለጸጋት ያለች አገር ናት፡፡ የባሕር በር የሌላት አርሜኒያ የሕዝብ ቁጥሯ 3 ሚሊዮን አካባቢ ብቻ ነው፡፡
45593103
https://www.bbc.com/amharic/45593103
በቡራዩ ጥቃት የተጠረጠሩ ፍርድ ቤት ቀረቡ
በቡራዩ ከተማና አካባቢዋ በተፈፀመው ጥቃት እጃቸው አለበት የተባሉ ተጠርጣሪዎች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ።
ተጠርጣሪዎቹ በቡራዩ የወረዳ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት ነው የቀረቡት። ቁጥራቸው በርካታ የሆኑት ተጠርጣሪዎቹ ቃላቸውን ሰጥተዋል። መርማሪ ፖሊስ እንዳስታወቀው ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት ተጠርጣሪዎች በሰዎች ሕይወት ማለፍ፣ በከባድና ቀላል የአካል ጉዳት በማድረስ፣ በንብረት ውድመት እና ዘረፋ የተጠረጠሩ ናቸው። • በቡራዩ ጥቃት ፈጻሚዎቹ የባንክ ሂሳብ ውስጥ 8 ሚሊዮን ብር ተገኘ፡ ዶ/ር ነገሪ • ሞትና መፈናቀል በአዲስ አበባ ዙሪያ • ስለተፈፀመው ጥቃት እስካሁን የምናውቀው ችሎት ፊት በቀረቡት ተጠርጣሪዎች ላይም መርማሪ ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራዎችን ለማድረግ የ14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ የጠየቀ ሲሆን፤ ፍርድ ቤቱም የተጨማሪ ጊዜውን ፈቅዷል። ከቀናት በፊት በቡራዩ እና አካባቢዋ ጥቃት ፈጽመዋል ተብለው ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር በዋሉ ግለሰቦች የባንክ አካውንት ውስጥ 8 ሚሊዮን ብር መገኘቱን የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ማስታወቃቸው ይታወሳል። ዶ/ር ነገሪ የፖለቲካ ዓላማ ለማሳካት ገንዘብ በመመደብ የሕብረተሰቡን ሰላም ለማወክ ከአዲስ አበባ ጀምሮ የተንቀሳቀሰ ቡድን አለ ብለው ነበር።
55547007
https://www.bbc.com/amharic/55547007
የሮይተርሱ የካሜራ ባለሙያ ኩመራ ገመቹ ከእስር ተለቀቀ
የሮይተርስ የካሜራ ባለሙያ ኩመራ ገመቹ ከአስራ ሁለት ቀናት የእስር ቆይታ በኋላ መለቀቁን የሚሰራበት የዜና ተቋም አስታወቀ።
ፖሊስ የኩመራ ጠበቃ ለሆኑት መልካሙ ኦጎ፣ በጋዜጠኛው ላይ ሐሰተኛ መረጃ በማሰራጨት፣ ከመንግሥት ጋር ከሚዋጉ ኃይሎች ጋር ግንኙነት በማድረግ፣ እንዲሁም የሕብረተሰብን ሠላምና ደኅንነት በመረበሽ ጠርጥሮት በቁጥጥር ስር ማዋሉንና ምርመራ መጀመሩን ገልጾ ነበር። ሮይተርስ በዘገባው ላይ ሁለት ሳምንት ለሚጠጋ ጊዜ በአስር ላይ የቆው የካሜራ ባለሙያው ኩመራ ገመቹ በምን ሁኔታ እንደተለቀቀ ያለው ነገር የለም። "ኩመራ ተፈትቶ ከቤተሰቦቹ ጋር በመቀላቀሉ ደስተኞች ነን። ዛሬ መፈታቱ የሚያሳየን ምንም ዓይነት ጥፋት አለመፈፀሙን ነው" ብሏል የዜና ወኪሉ ከፍተኛ አርታኢ ስቴፈን ጄ አድለር። በተጨማሪም "ኩመራ ሁሌም ሙያውን የሚያከብርና ተዓማኒነት ላለው መረጃ ራሱን የሰጠ፣ እንደ ሮይተርስ የዜና ወኪል ባልደረባነቱም ከኢትዮጵያ ነጻ፣ ገለልተኛና ከአድልኦ የፀዳ መረጃን ለማድረስ የሚተጋ ነው። እንደ ኩመራ ያለ ጋዜጠኛ ያለምንም ፍርሃትና መሸማቀቅ በየትኛውም ስፍራ ሕዝብ የሚፈልገውን መረጃ እንዲያደርስ መፈቀድ አለበት" ብሏል። የኢትዮጵያ ፖሊስና አቃቤ ሕግ ቢሮዎች ኩመራ ለምን በቁጥጥር ሥር እንደዋለ ሮይተርስ ጥያቄ ቢያቀርብም ምላሽ ሊያገኝ አልቻለም ነበር። የ38 ዓመቱ ኩመራ ገመቹ ለሮይተርስ ከአስር ዓመት በላይ የሰራ የካሜራ ባለሙያ ሲሆን፤ ሐሙስ ዕለት ከሚከበረው የገና በዓል ቀደም ብሎ በመለቀቁ ቤተሰቡ ደስተኛ መሆኑን ተገልጿል። ቤተሰቡ "ኩመራ በመፈታቱ ትልቅ እረፍት ነው የተሰማን፤ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከጎናችን የነበሩትን ሁሉ እናመሰግናለን" ማለታቸውም ተገልጿል። አክለውም "ኩመራ ምንም ጥፋት ያልሰራ ሙያውን አክባሪ እና ትጉህ ጋዜጠኛ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ በነጻነት መዘገብ ብቻ ነው የሚፈልገው። በታሰረበት ወቅት ቤተሰቦቹ በጣም ናፍቀውት ነበር፤ ለገና በዓል ከቤተሰቡ ጋር በመቀላቀሉ እጅጉን ደስተኛ ነን።" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በእስር ላይ የሚገኙ በርካታ ጋዜጠኞችን የለቀቁ ሲሆን፤ በአገር ውስጥ እንዳይነበቡ እና እንዳይታዩ ታግደው የነበሩ ከ250 በላይ የመገናኛ ብዙሃን እንዲከፈቱ እና በነጻነት እንዲሰሩ ፈቅደዋል። ነገር ግን የመብት ተሟጋች ድርጅቶች እንደሚሉት ከሆነ የፌደራል መንግሥቱ ከህወሓት ኃይሎች ጋር ግጭት ውስጥ ከገባበት ጊዜ ወዲህ ጋዜጠኞች ላይ ወከባና እስር እየታየ መጥቷል። የትግራይ ግጭት ከተቀሰቀሰ ወዲህ ሰባት ጋዜጠኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የጋዜጠኛ መብት ተሟጋቾች ሪፖርት አድርገዋል። የኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ ጋዜጠኛ ኡዲ ሙሳ፣ የዓል-ዓለም ጋዜጣ ሪፖርተር አብርሃ ሃጎስ፣ የኢትዮጵያን ሄራልድ ጋዜጠኞቹ ሃፍቱ ገብረእግዚአብሔርና ፀጋዬ ሃዱሽ በአሁኑ ወቅት በእሥር ላይ ያሉ ጋዜጠኞች ሆነው ተመዝግበዋል። ሌላኛው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ቡድን ሲፒጄ ኅዳር 22/2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ ሰባት ጋዜጠኞች በሰሯቸው ዘገባዎች ምክንያት እስር ቤት መግባታቸውን ገልጾ ነበር። ከእነዚህ መካከል አምስቱ የታሰሩት ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በፌደራል መንግሥቱና በህወሓት ኃይሎች መካከል ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ ነው። ድርጅቱ ኢትዮጵያ ከፈረንጆቹ 2019 ጋር ሲነፃፀር ለጋዜጠኞች የተሻለ ነፃነት ሰጥታለች ይላል። አምና ከነበረችበት 119ኛ ደረጃም ወደ 99 ከፍ ማለት ችላለች። ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ የታየው የተስፋ ጭላንጭል እንዳይጨልም መንግሥት የጋዜጠኞችን ነፃነት ሊያስከብር ይገባል ይላል ማኅበሩ።
news-44734884
https://www.bbc.com/amharic/news-44734884
በደቡብ አፍሪቃ አውራሪስ አዳኞቹ በአንበሳ ተበሉ
ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ በሚገኝ አንድ የእንስሳት ማቆያ ውስጥ ዘልቀው በመግባት አውራሪስ በማደን ላይ የነበሩ ግለሰቦች በአንበሶች ተበልተዋል።
አንበሶቹ ቢያንስ ሁለት አዳኞችን 'ውጠው አላየሁም' ማለታቸው እየተዘገበ ሲሆን የማቆያው ሰዎች ግን አዳኞቹ ሶስት ሳይሆኑ አልቀሩም ሲሉ ይገምታሉ። የሁለቱ ሰዎች ቅሪት የተገኘ ሲሆን ለአደን ይረዳቸው ዘንድ ይዘውት የነበረ መሣሪያና መጥረቢያም ተገኝቷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አፍሪቃ ውስጥ የአውራሪስ አደን እየበረታ የመጣ ሲሆን ለዚህ ደሞ እንደምክንያት እየተጠቀሰ ያለው በውድ ዋጋ ለገበያ የሚቀርበው የአውራሪስ ቀንድ ነው። አውራሪስ በብዛት ከሚገኝባቸው የአፍሪቃ ሃገራት አልፎ ቻይና እና ቪየትናምን የመሳሰሉ ሃገራት በኢህ ጉዳይ ማጣፊያው አጥሯቸዋል። የእንስሳት ማቆያ ሥፍራው ባለቤት የሆኑ ግለሰብ በፌስቡክ ገፃቸው አዳኞቹ ወደ ቅጥር ግቢው የገቡት ድቅድቅ ጨለማን ተገን አድርገው እንደሆነ አሰውቀዋል። ግለሰቡ ጨምረው ሲገልፁ «አዳኞቹን አንክት አድርገው የበሏቸው አንበሶቹ በቁጥር ምን ያህል እንደሆኑ ባናውቅም በርከት እንደሚሉ ግን እንገምታለን» ብለዋል። የሰዎቹ ቅሪት ከተገኘ በኋላ ሁኔታውን ማጣራት ይረዳ ዘንድ አንበሶቹ ራሳቸውን እንዲስቱ ተደርጓል። ፖሊስ ሌላ በአንበሳ የተበላ አዳኝ ይኖር እንደሆን ለማጣራት አካባቢውን ቢያስስም ፍንጭ ሊገኝ አልቻለም። በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት ብቻ አዳኞች በዚህ ማቆያ ሥፋራ የሚገኙ ዘጠኝ አውራሪሶችን መግደላቸው ተመዝግቧል። ባለፉት አስርት ዓመታት ብቻ ደግሞ 7 ሺህ ያህል አውራሪሶች የአዳኞች ሲሳይ ሆነዋል።
53733350
https://www.bbc.com/amharic/53733350
ቤላሩስ ፡ ስለ ቤላሩስ ብዙ ሰው የማያውቃቸው አራት አስገራሚ ነገሮች
ቤላሩስን ብዙ ሰው አያውቃትም፡፡ እንደኛው ወደብ አልባ አገር ናት፡፡ በምሥራቅ አውሮፓ ነው የምትገኘው፡፡ ሩስያ፣ ዩክሬን፣ ፖላንድና ላቲቪያ ያዋስኗታል፡፡
ካለፈው እሑድ ጀምሮ የዓለም ሚዲያ ትኩረት ስባለች፡፡ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ለ6ኛ ጊዜ ምርጫ አሸነፍኩ ብለዋል፡፡ ለመሆኑ ስለ ቤላሩስ ምን ለየት ያለ ነገር አለ? አራት አስገራሚ ነገሮችን እንንገራችሁ፡፡ 1ኛ፡- በ2ኛው የዓለም ጦርነት 25 ከመቶ ሕዝቧን አጥታለች ብዙ ሰዎች ቤላሩስ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ውስጥ ነበረችበት እንዴ ሊሉ ይችላሉ፡፡ አዎ ነበረችበት፡፡ እንዲያውም በጦርነቱ ዋነኛ ተጎጂ አገር እንደ ቤላሩስ የለም፡፡ ምን ያህል ሕዝብ የሞተባት ይመስላችኋል? 1.6 ሚሊዮን ንፁሕ ዜጎችና 600,000 ወታደሮቿ አልቀዋል፡፡ ቤላሩስ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ የአይሁድ ዝርያ ያላቸው ቤላሩሳዊያን ሁሉም ማለት ይቻላል አልቀዋል፤ በ2ኛው የዓለም ጦርነት፡፡ ዋና ከተማዋ ሚንስክ ትባላለች፡፡ ይቺ ከተማ 85 ከመቶ ወድማ ነበር በሁለተኛው የዓለም ጦርነት፡፡ አንድ ሰው ከጦርነቱ በፊት ይቺን ከተማ ለቆ ከነበረና ከጦርነቱ በኋላ ቢመለስ ከተማዋን በመልክ ሊያውቃት ፈጽሞ በማይቻልበት ደረጃ ነበር የወደመችው፡፡ መልሳ የተገነባችው በ1950ዎቹና 60ዎቹ ነው፡፡ 2ኛ፡- የአውሮፓ የመጨረሻው አምባገነን ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ በአውሮፓ ባልተለመደ ሁኔታ ሥልጣናቸውን ርስት አድርገውት ቁጭ ብለዋል፡፡ ይኸው ስንት ዘመን ከቤተ መንግሥት አልወጣ ካሉ፡፡ 26 ዓመታት! በአውሮጳ እንዲህ ሥልጣኑን የሙጥኝ ያለ ሰው እንዳለ ብዙ ሰው አያውቅም፡፡ ሉካሼንኮ የይስሙላ ምርጫ ያደርጋሉ ተብለው ይታማሉ፡፡ ሁልጊዜም በከፍተኛ ድምጽ ያሸንፋሉ፡፡ ለምሳሌ በእሑዱ ምርጫ 80 ከመቶ ሕዝቤ መርጦኛል ብለው ይኸው ተቃውሞ ተነስቶባቸዋል፡፡ የአሁኑ ተቃውሞ ትንሽ ጠንከር፣ ጠጠር ያለ ይመስላል፡፡ ሰውየው ወደ ሥልጣን የመጡት ድሮ ነው፡፡ እንደነርሱ አቆጣጠር በ1994 ዓ.ም፡፡ ለዚያም ነው ‹‹የመጨረሻው የአውሮፓ አምባገነን›› በሚል ቅጽል ስም የሚጠሩት፡፡ ሉካሼንኮ አንድ ወቅት ላይ ምናሉ መሰላችሁ፡፡ «ከኔ ፓርቲ ሌላ ተቃዋሚ ፓርቲ የሚገባ ሰው አሸባሪ ነው፡፡ ስለዚህ አንገቱን እንደ ዶሮ ይዤ እቀነጥሰዋለሁ፡፡» 3ኛ፡- ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲን የገደለው ሰው ሊ ሃርቬይ ኦስዉልድ ቀድሞ የአሜሪካ የባሕር ኃይል አባል ነበር፡፡ ወደ ቀድሞዋ ሶቭየት ኅብረት ሲደርስ ገና 20 ዓመቱ ነበር፡፡ ማርክሲስት ሆኛለሁ ይል ነበር ያኔ፡፡ ከዚያ የሶቭየት ኅብረት የስለላ ድርጅት ኬጂቢ ለመግባት አመለከተ፡፡ ማመልከቻው ውድቅ ተደረገበት፡፡ ያን ቀን የቱሪስት ቪዛው ይቃጠልበት ነበር፡፡ ኦስዋልድ ተናደደና አንዱን እጁን ሰበረው፡፡ የገዛ እጁን፡፡ ነገሩ ልዩ ትኩረት እንዳይስብ ስለተፈራ ሶቭየቶች እንዲቆይ ፈቀዱለት፡፡ ከዚያ ወደ ሚንስክ ከተማ ተላከና የሬዲዮና ቴሌቪዥን ማምረቻ ፋብሪካ ውስጥ ሥራ ጀመረ፡፡ በቤላሩስ ዋና ከተማ ሚኒስክ አንድ ከፍል ቤት ተሰጥቶት መኖር ጀመረ፡፡ ኦስዋልድ ያን ጊዜ በዚያች ከተማ ብቸኛው አሜሪካዊ ነበር፡፡ በመጋቢት 1961 ማሪና ፕሩሳኮቫን አገባ፡፡ በዓመቱ ሴት ልጅ ወለዱ፡፡ ከዚያ በዓመቱ ደግሞ ወደ አሜሪካ አቀኑ፡፡ ከዚያ በዓመቱ ኅዳር ወር ላይ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የነበሩትን ጆን ኤፍ ኬኔዲን በዳላስ ቴክሳስ ተኩሶ ገደላቸው፡፡እና ይህ ነፍሰ ገዳይ ሲታሰብ እሱ የኖረባት ቤላሩስ አብራ ትነሳለች፡፡ 4ኛ፡- በዓለም እጅግ አደገኛው የኒክሌር ጨረር ብናኝ 70 ከመቶ የሚገኘው በቤላሩስ ነው በሚያዝያ 1986 በዩክሬን፣ ቼርኖቢል ከሚገኙት ከአራቱ የኒክሌር ማብሊያዎች ውስጥ አንዱ ፈነዳ፡፡ እስከዛሬ በዓለም ላይ በኒክሌየር ምርት መጥፎ አጋጣሚ ተደርጎ የሚታሰበው ይህ ክስተት ነው፡፡ እጅግ አደገኛና መርዛማ የሆነው ይህ የጨረር ኬሚካል ብናኝ ታዲያ ከዩክሬን ይልቅ የጎዳው ቤላሩስን ነው፡፡ የራዲዮአክቲቭ ጨረር ያረፈው በቤላሩስ መሬት ላይ ነበር፡፡ በዚህም አንድ አምስተኛው የአገሪቱ የእርሻ መሬት በመርዛማው ብናኝና ዝቃጭ በክሎታል፡፡ በዚህ የተነሳ 2ሺ ከተሞችና መንደሮች ፈርሰዋል፡፡ ግማሽ ሚሊዮን ሰዎች ሌላ ቦታ እንዲሰፍሩ ሆነዋል፡፡ ሁለት ሚሊዮን ቤላሩሳዊያን አሁንም በአደገኛ ቀጠና ውስጥ ነው የሚኖሩት፡፡ ቤላሩስ በዚህ የኒክሌር ብናኝና ዝቃጭ ጣጣ 300 ቢሊዮን ዶላር አጥታለች፡፡ መከራዋ እስከዘላለሙ ሊቀጥል ይችላል፡፡
news-42692210
https://www.bbc.com/amharic/news-42692210
ኢትዮጵያውያን ዛሬም ከአለት አብያተ-ክርስትያናትን ያንፃሉ
በሰሜን ኢትዮጵያ የምትገኘው ላሊበላ ከአለት ተፈልፍለው የተሰሩት ድንቅ አብያተ-ክርስቲያናት የሚገኙባት ከተማ ናት። ለየት ያሉት እነዚህ አብያተ-ክርስቲያናት አሁን በዩኔስኮ ከተመዘገቡት የዓለማችን ድንቅ ታሪካዊ ስፍራዎች መካከል ይገኛሉ።
ከአንድ ወጥ አለት በርና መስኮት እንዲኖራቸው ተደርገው የተሰሩት እነዚህ አብያተ-ክርስቲያናት አንዳንዶቹ እስከ 50 ሜትር የሚደርስ ጥልቀት አላቸው። የተገነቡትም በ12ኛው እና በ13ኛው ክፍለ ዘመን ነበር። በርካታ ምሁራንና የታሪክ አጥኚዎች እንደሚሉት ይህ ከአለት አብያተ-ክርስቲያናትን በመፈልፍል የመገንባት ጥበብ ከ500 ዓመታት ቀደም ብሎ የቀረ እንደሆነ ያምናሉ። ነገር ግን አሁን ባለንበት ዘመንም ከአንድ ወጥ አለት አብያተ-ክርስቲያናትን የመቅረፁ ሥራ በሰሜናዊ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተከናወነ መሆኑ ታውቋል። የቢቢሲው ዘጋቢ ኢማኑኤል ኢጉንዛ ወደ ስፍራው ተጉዞ ነበር። "እነዚህን አብያተ-ክርስቲያናትን የመስራቱ ጥሪና አጠቃላይ ቅርፁ ከእግዚአብሄር ዘንድ ተገልፆልኝ ነው'' ይላሉ የአርባ ዓመቱ ጎልማሳ አባ ገብረመስቀል ተሰማ ከአለት ፈልፍለው የሰሩትን አዲሱን ቤተክርስቲያ ተዘዋውረው እያሳዩ። በስፍራው በአጠቃላዩ አራት አብያተ-ክርስቲያናት ሲኖሩ እያንዳንዳቸው እርስበርሳቸው በሚያገናኝ ዋሻዎች ተያይዘዋል። የውስጥ ግድግዳቸውም በጥንቃቄ በተሰሩ ውብ ስዕሎች ተውበዋል። አባ ገብረመስቀል ተሰማ የኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ቄስ ሲሆኑ፤ ከሌሎች ሦስት ሰራተኞች ጋር በመሆን በዙሪያቸው ያሉ ምዕመናን የአምልኮት ሥነ-ሥርዓት ለማከናወን ሊጠቀሙበት የሚችሉባቸውን አብያተ-ክርስቲያናት ከአለት ለመፈልፈል ሙሉ ጊዜያቸውን ሰውተዋል። "አዲሱ ላሊበላ ብዬ ብሰይመው ደስ የሚለኝን ይህን የውቅር የአብያተ-ክርስቲያናት ስብስብን ሰርቶ ለማጠናቀቅ አራት ዓመታትን ፈጅቶብናል'' ይላሉ። በእሳተ-ገሞራ የተፈጠረውን አለት ለመፈልፈልና ቅርፅ ለማበጀት በቅርብ የሚገኙትን መሮ፣ መጥረቢያና አካፋን ተጠቅመዋል። በዚህ ሂደት ከባዱ ሥራ የሚጀምረው ከግዙፍ አለት ጫፍ ላይ በመሆን እየጠረቡ ወደታች በመውረድ ነው። ይህም መስኮቶችን፣ በሮችንና መተላለፊያዎችን መጥረብን ይጨምራል። አብያተ ክርስቲያናቱ ከተቀረፁበት ቦታ ለመድረስ ቀላል አይደለም። አንደኛው ቤተክርስቲያን እየተቀረፀ ያለበት ስፍራ ለመድረስ ድንጋያማ የሆነ መንገድን ተከትሎ ለአንድ ሰዓት ያህል መጓዝን ይጠይቃል። አንዳንዶቹም በጣም የራቀ ቦታ ላይ ከመገኘታቸው የተነሳ የአካባቢው ባለስልጣናት ሳይቀሩ አብያተ-ክርስቲያናት መሰራታቸውን ሲሰሙ ተደንቀዋል። አዳዲሶቹ አብያተ-ክርስቲያናት የሚገኙት አስደናቂ ኮረብታዎች ባሉበትና ታዋቂዎቹ ከአለት የተፈለፈሉ የላሊበላ አብኣተክርስቲያናትን ለማየት በሚኣስችለው የሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል ወሎ አካባቢ ነው። አስራአንዱ ከወጥ አለት የተፈለፈሉት የላሊበላ ውቅር አብያተ-ክርስቲያናት ለኢትዮጵያ ክርስትና ዋነኛ ሥፍራ በሆነው ቦታ ላይ በ12ኛው ክፍለዘመን ነበር የተሰሩት። ተፈልፍለው የተሰሩትም ወደ ኢየሩሳሌም ለመጓዝ ለሚቸገሩ ኢትዮጵያዊያን ምዕመናን ሲል አዲሲቱን ኢየሩሳሌም በቅርብ ለመገንባት በተነሳው በንጉሥ ላሊበላ ዘመን ነው። ረጅም ዘመንን ካስቆጠሩት የላሊበላ አብያተ-ክርስቲያናት መካከል ጣሪያው በመስቀል ቅርፅ የተሰራው ታዋቂው የቅዱስ ጊዮርጊስ ወይም ቤተ-ጊዮርጊስ እንዲሁም ከአንድ ወጥ አለት በመቀረፅ በዓለም ትልቁ የሆነው የቤተ-ማሪያም አብያተ-ክርስቲያናትን ጨምሮ አንዳንዶቹ ከመሬት በታች እስከ 40 ሜትር ይጠልቃሉ። አንዳንድ አፈ-ታሪኮች እንደሚሉት አብያተ-ክርስቲያናቱ በሚፈለፈሉበት ጊዜ በንጉሥ ላሊበላ ከውጪ እንዲመጡ የተደረጉ ሰራተኞች ቀን ቀን ሲሰሩ ይውሉና ሌሊት ደግሞ መላዕክት ሥራውን ያከናውኑ እንደነበር ይተርካሉ። ነገር ግን አባ ገብረመስቀል ይህንን አይቀበሉትም፤ አዲሶቹን ውቅር አብያተ-ክርስቲያናት ለመስራት የተነሳሱትም የላሊበላን አብያተ-ክርስቲያናት በእግዚአብሄር የተመሩ ኢትዮጰያዊያን የሰሩት መሆኑን ለማስመስከር እንደሆነ ይናገራሉ። "ኢትዮጵያዊያን ይህን መሰለ ተግባርን ለማከናወን የሚያበቃ እውቀትና ክህሎት አልነበራቸውም ብለው የሚያምኑ አንዳንዶች አሉ። ቢሆንም ግን አሁን እኔ በምሰራበት ጊዜ ማንም አንዳች ነገር አላሳየኝም፤ ይህን ድንቅ ሥራ እውን ያደረኩት በመንፈስ-ቅዱስ አማካይነት ነው'' ይላሉ። "በሰሜናዊው ኢትዮጵያ እየተገኙ ላሉት አዳዲስ አብያተ-ክርስቲያናት መንፈሳዊነት ዋነኛው መሰረት ነው'' ሲሉ የሚያብራሩት የቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ማይክል ገርቨርስ ናቸው። ፕሮፌሰር ማይክል ከሥነ-ህንፃ እና ከፊልም ባለሙያዎች ጋር በመሆን ይህንን እየጠፋ ያለውን የግንባታ ጥበብ መዝግቦ ለማስቀመጥ አንድ ሥራ ጀምረዋል። በዩናይትድ ኪንግደሙ አርኬዲያ ፈንድ ቢደገፈው እቅዳቸውም ዘመናዊ የመረጃ ቋት በማዘጋጀት ለሕዝብ ክፍት ማድረግ ነው። "ከድንጋይ የሚፈለፈሉ አብያተ-ክርስቲያናትን መስራቱ የሚቀጥል ከሆነ ዘመናዊነት እየተስፋፋ በሚመጣበት ጊዜ መፈልፈያ መሳሪያዎችን መጠቀም ስለሚጀመር፤ በእጅ የመስራቱ ጥበብ ሙሉ ለሙሉ ይጠፋል'' ይላሉ። "ስለሆነም ከአንድ የግንባታ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ እየሄድን የግንባታውን ጥበብ የሚያውቁትን ባለሙያዎችን በማነጋገር ሥራቸውን እንዴት እንደሚያከናውኑ ያላቸውን የግል ዕውቀት እንመዘግባለን። አላማችንም ያገኘውን መረጃ ለሕዝብ ክፍት ማድረግ ነው። ቡድኑ እስካሁን 20 አዳዲስ አብያተ-ክርስቲያናትን በተራራማዎቹ በሰሜናዊ የአማራና የትግራይ ክፍሎች ውስጥ አግኝቷል። "የበለጠ በፈለግን ቁጥር ተጨማሪ እናገኛለን። በርካታ አብያተ-ክርስቲያናት እንዳሉ ስለማምን ሌሎች በርካቶቸን አግኝተን እንደምንመዘግባቸው ተስፋ አደርጋለሁ። ከአለት የተፈለፈሉ አብያተ-ክርስቲያናት አንድ ጊዜ አገልግሎት መስጠት ከጀመሩ በኋላ ብዙም ጥገና የሚፈልጉ አይደሉም። ለሺህ ዓመታት አገልግኦት ሊሰጡ ይችላሉ'' ሲሉ ፕሮፌሰር ገርቨርስ ይጨምራሉ። ለአባ ገብረመስቀል ሥራቸው አብያተ-ክርስቲያናቱን የገነቡበት ጥበብ መኖሩን ከማረጋገጥ በእጅጉ የበለጠ ነው። "አብያተ-ክርስቲያናቱበይፋ ተከፍተው በአካባቢዬ ያለው ሕብረተሰብ የሐይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶችን ሲያከናውን ለማየት ጓጉቻለሁ። በቅርቡ... በጣም በቅርቡ እነዚህ የእግዚአብሄር ቤቶች በደስተኛ ሰዎች ይሞላሉ'' ብለዋል ገፃቸው በፈገግታ በርቶ።
51971612
https://www.bbc.com/amharic/51971612
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መቼ ይቆማል?
በየአገራቱ ለወትሮ የሰው ግርግር የሚያደምቃቸው ከተሞችና ቦታዎች የኮሮናቫይረስ መምጣትን ተከትሎ ሁሉም ነገር ፀጥ ረጭ ብሏል።
ትምህርት፣ ስራና ሌሎችም እንቅስቃሴዎች ሲቆሙ የጉዞ እገዳዎችም ተጥለዋል። ስብሰባም ሆነ ሌሎች ማህበራዊ መስተጋብሮች እንዳይደረጉ ታግደዋል። መንገዶች፣ ካፍቴሪያዎች እንዲሁም የገበያ ስፍራዎች ፀጥ ብለዋል፤ ከተሞች ኦና ሆነዋል በጥቅሉ ዓለም ተዘግታለች ማለት ይቻላል። • የአሜሪካ እስር ቤቶች በኮሮናቫይረስ ምክንያት እስረኛ መልቀቅ ጀመሩ • የኢትዮጵያ አበባ ላኪዎችን ገቢ ክፉኛ የጎዳው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ • የዓለም ጤና ድርጅት ወጣቶች ኮሮና ሊቋቋሙት አይችሉም አለ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ቆሞ ህይወት ወደነበረበት የሚመለሰው መቼ ነው? ብዙዎች በአእምሯቸው የሚያውጠነጥኑት ነገር ነው። የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን እንግሊዝ በሶስት ወራት ውስጥ የቫይረሱን ስርጭት ትገታለች ብለዋል። በዚህ ጊዜ ውስጥ የቫይረሱን ስርጭት መቆጣጠር ቢቻልም ግን የቫይረሱ ማብቂያ ገና እንደሆነ ተናግረዋል። ወረርሽኙን ማስቆም ረዥም ጊዜ ምናልባትም ዓመታት ሊወስድ ይችላል ሲሉም ፍርሃታቸውን ገልፀዋል። የማህበረሰቡን እንቅስቃሴዎች መግታትና እገዳዎችን መጣል ጊዜያዊ እንጂ ዘላቂ መፍትሄ ሊሆን አይችለም። እገዳዎቹን ዘላቂ ለማድረግ መሞከር ደግሞ ከባድ፣ የረዥም ጊዜ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስን ይፈጥራል። አገራት የሚያስፈልጋቸው የጣሉትን እገዳ ማንሳት የሚያስችላቸውን ስትራቴጂ መንደፍና የሰዎች ኑሮን ወደ ነበረበት እንዲመለስ ማድረግ እንደሆነ እየተገለፀ ነው። ምክንያቱም ኮሮናቫይረስ በዚህ ጊዜ ይጠፋል የሚባል አይደለም። ግን ደግሞ ምን ዓይነት ስትራቴጂ እገዳዎችን ማስነሳት ይችላል? የሚለው አሁንም የአገራት ራስ ምታት ነው። እገዳውን ማስቀጠልም ማንሳትም የሚያስከትሉት ቀውስ ፈርጀ ብዙ ነው። በኤደንብራ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ማርክ ውልሃውስ "በምን ዓይነት ስትራቴጂ ከዚህ እንወጣለን? እንዴት? የሚለው ትልቁ ችግራችን ነው" ይላሉ። አክለውም "እንግሊዝ ብቻም ሳትሆን ማንም አገር ከዚህ ቀውስ መውጫ ስትራቴጂ የለውም" ብለዋል። ይህ በእጅጉ የገዘፈ ማህበራዊና ሳይንሳዊ ፈተና ነው ይላሉ። ከኮሮናቫይረስ ቀውስ መውጫ ሶስት መንገዶች ክትባት፣ በቂ የሚባሉ ሰዎች ቫይረሱን መቋቋም የመቻል ተፈጥሯዊ መከላከያ ማዳበርና በዘላቂነት የግለሰቦችና የማህበረሰብ ባህሪ መቀየር እንደ አማራጭ የተቀመጡ ነገሮች ናቸው። ዓለም የኮሮናቫይረስ ክትባት ላይ ለመድረስ ቢያንስ ከአመት እስከ ዓመት ተኩል የሚሆን ጊዜ ይቀረዋል። ክትባቱ ቢያንስ 60 በመቶ ለሚሆኑ ሰዎች ተሰጥቶ እነዚህ ሰዎች ቫይረሱን የመከላከል አቅም አዳብረው ለቫይረሱ ተጋልጠው እንኳ የማይታመሙ መሆናቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። የዚህ ክትባት ሙከራ በአሜሪካ ሰው ላይ ባለፈው ሳምንት ተሞክሯል። • የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ምን እያደረጉ ነው? ከጊዜ ጋር እየተደረገ ባለው ሩጫ ምክንያት ክትባቱ በመጀመሪያ እንስሳት ላይ መሞከር የሚባውን መደበኛ አሰራር ሳይጠብቅ በቀጥታ የሰው ልጅ ላይ እንዲሞከር ተደርጓል። የኤደንብራው ፕሮፌሰር ውልሃውስ ክትባቱን መጠበቅን አገራት እንደ ስትራቴጂ ሊመለከቱት አይገባም ብለዋል። ተፈጥሯዊ በሽታውን የመቋቋም አቅምን ማዳበርም ቢያንስ ሁለት ዓመት የሚወስድ ጊዜ ነው እየተባለ ነው። የእንግሊዝ መንግሥት የአጭር ጊዜ ስትራቴጂ ያለው ነገር ቢኖር ሆስፒታሎች እንዳይጨናነቁ ማድረግ ሲሆን ይህ ደግሞ የኮሮናቫይረስ ሞት በከፍተኛ ሁኔታ እንዳይጨምር ይረዳል ተብሏል። በሌላ በኩል የእንግሊዙ ቁጥር አንድ ሳይንቲስት ሰር ፓትሪክ ቫላንስ ጊዜው በአሁኑ ወቅት ይህን አሁን ብናደርግ በዚህ ጊዜ ያንን እናሳካለን የሚባልበት ወቅት እንዳልሆነ ገልፀዋል። የዚህ ዓይነቱ ክትባት ውጤትም ቢገኝም ያልተጠበቁ ሌሎች ኮሮናቫይረሶችን የማስከተል እድልም እንዳለው ሳይንቲስቶች እየገለፁ ነው። ለምሳሌ እንደ መደበኛ ጉንፋን ምልክት ያላቸውን ኮሮናቫይረሶች ሊያስከትል፣ በዚህም ሰዎች በተደጋጋሚ ሊያዙ ይችላሉ። ይህ ደግሞ በሽታ የመከላከል አቅማቸው ደካማ ለሆኑ ሰዎች አደጋ ይሆናል። • ሁለት ኢትዮጵያዊያን ጣሊያን ውስጥ በኮሮናቫይረስ መሞታቸው ተረጋገጠ የመጨረሻው አማራጭ የሰው ዘር በዘላቂነት ባህሪውን መቀየርና የቫይረሱን ስርጭት መግታት እንደሆነ ሳይንቲስቶቹ ይናገራሉ። ይሀ እስካሁን እየተሰጡ ያሉ ምክር ሃሳቦችን በሙሉ መተግበርን እና በተደጋጋሚ የቫይረሱን ምርመራ ይጨምራል። ሰዎችን ዘወትር በለይቶ ማቆያ ማስቀመጥንም እንዲሁ። ኮቪድ-19 በውጤታማነት የሚያክሙ መድሃኒቶችን መስራትም ሌሎች ስትራቴጂዎችን ሊያግዝ የሚችል ይሆናል። የእንግሊዝ መንግሥት ዋና የጤና አማካሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ክሪስ ዊቲ መፍትሄ የሚሉት ስትራቴጂ ምን እንደሆነ በቢቢሲ ተጠይቀው ሲመልሱ " በረዥም ጊዜ ክትባት ከዚህ ጉዳይ መውጫ ነው፤ ይህም በሚቻለው ፍጥነት ይሆናል" ሲሉ መልሰዋል።
news-52996557
https://www.bbc.com/amharic/news-52996557
ታሪካዊው የፍቅር ፊልም በዘረኝነት ምክንያት ታገደ
በጎርጎሳውያኑ 1939 የተሰራው ታሪካዊው የፍቅር ፊልም 'ጎን ዊዝ ዘ ዊንድ' በበርካቶች ዘንድ ዘረኝነት ይንፀባረቅበታል በሚል በአሜሪካ ፊልም ከሚያሳዩ ድረገፆች እንዲወገድ የተነሳውን ጥሪ ተከትሎ ፊልሙ እንዲወርድ ተደርጓል።
ከሰሞኑ ውሳኔውን ያሳወቀው ፊልም በድረገፅ የሚያሳየው ኤችቢኦ ማክስ ፊልሙ ከስምንት አስርት አመታት በፊት የተሰራ ከመሆኑ አንፃር ጊዜውን ቢያሳይም"ዘረኝነት የሚንፀባረቅበት ነው። በወቅቱም ስህተት ነበር አሁንም ስህተት ነው ብሏል። ድርጅቱ አክሎ እንዳስታወቀው ፊልሙ እንዲሁ ከድረገፁ ላይ ማስወገድ ብቻ ሳይሆን ያለውን ታሪካዊ ዳራ የሚያሳይ ውይይት ተጨምሮበት እንደሚመለስ የገለፀ ሲሆን፤ ጊዜው መቼ እንደሆነ አልተጠቀሰም። መቼቱን የአሜሪካን የእርስ በርስ ጦርነት ያደረገው ይህ ፊልም ባርነትን የቀረፀበት መልኩ ከፍተኛ ትችቶችንና ውግዘቶችን ሲያስተናግድም ነበር። በማርጋሬት ሚቸል መፅሃፍ መነሻውን ያደረገው ይህ ፊልም ባርነት ከተወገደ በኋላ ጥቁር አሜሪካውያን በባርነት ዘመናቸው ህይወታቸው ሙሉ እንደነበርና ለቀድሞ ባለቤቶቻቸውም ታማኝ በመሆን በባርነት መቀጠል የሚፈልጉ ጥቁር አሜሪካውያን ህይወት ተንፀባርቆበታል። ፊልሙ ከፍተኛ ዝናን ከማትረፍ በተጨማሪም በፊልም ሽልማቶች ታላቅ የሚባለውን አስር የኦስካር ሽልማቶችን ማሸነፍ ችሏል። በፊልሙ ላይ የቤት ሰራተኛነትን ገፀ ባህርይ ተላብሳ የተጫወተችው ጥቁር አሜሪካዊቷ ሃቲ ማክ ዳንኤል በረዳት ተዋናይነት ያሸነፈች ሲሆን፤ የኦስካር ሽልማትን ለመቀበልም የመጀመሪያዋ ጥቁር ናት። ከሰሞኑም ታዋቂው ፀሃፊ ጆን ራይድሊ ፊልሙን አስመልክቶ ሎስ አንጀለስ ታይምስ በፃፈው ፅሁፍ " የባርነት ጊዜን ከፍ በማድረግ፤ ጥቁሮች ሲጨቆኑበትና ሲሰቃዩበት የነበረውንም ጊዜ ሌላ መልክ ለመስጠት ይሞክራል" የ'ትዌልቭ ይርስ ኦፍ ኤ ስሌቭ' ፀሃፊ አክሎም " በሆሊውድ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ችሎታ ያላቸው ተዋናዮች የተሰባሰቡበት ፊልም ቢሆንም ባርነት ጥሩ እንደነበርና ለጥቁሮችም ጥሩ ወቅት እንደነበር ለመስበክ ይሞክራል። ይህ ግን ትክክል አይደለም" ብሏል። ኤችቢኦ ማክስ ባወጣው መግለጫ "ፊልሙ ዘረኝነትን በሚያንፀባርቅ መልኩ እንዲሁ እንዲታይና ያለ መግለጫና ውግዘት መተው ሃላፊነት የጎደለው ነው" ብሏል። ድርጅቱ አክሎም ፊልሙ ሲመለስ ብዙ እንደማይቀየር አመላክቷል። ከኤችቢኦ ማክስ በተጨማሪ ዲዝኒ በበኩሉ በጎርጎሳውያኑ 1941 የተሰራው የአኒሜሽን ፊልም ደምቦን ጨምሮ የቀድሞ ፊልሞቹ "ባህልን ዝቅ የሚያደርጉ ይዘቶች" ሊኖራቸው እንደሚችሉ አስጠንቅቋል። ከሰሞኑ ከፀረ ዘረኝነትና የፖሊስ ጭካኔ ጋር የተያያዙ ተቃውሞዎችን ተከትሎ ፊልሙን ለማስወገድ የደረሰው ኤች ቢኦ ማክስ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም ድረገፆች ፊልሞቻቸውን እየገመገሙ ነው። 'ሊትል ብሪቴይን' የተሰኘው ፊልም ከኔት ፍሊክስ፣ ብሪት ቦክስና ቢቢሲ አይ ፕሌየር እንዲወገድ ተደርጓል። ፊልሙ ዘረኝነት የሚንፀባረቅበትና አንዲት ነጭ ሴት ጥቁር ቀለም ተቀብታ በጥቁር ባህልና ማንነት ላይ ስትዘባበት ያሳያል ተብሏል።
news-46644190
https://www.bbc.com/amharic/news-46644190
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር መልቀቂያ አስገቡ
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ጂም ማቲስ ከሃላፊነታቸው ለመልቀቅ ደብዳቤ አስገቡ።
መልቀቂያቸውን ያስገቡት ጂም ማቲስ ከሁለት ወራት በኋላ ስራ ያቆማሉ መከላከያ ሚኒስትሩ መልቀቂያ ያስገቡት ትራምፕ አሜሪካ ሙሉ በሙሉ ጦሯን ከሶሪያ እንደምታስወጣ ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው። ይህን የትራምፕ ውሳኔን ብዙዎች ያልተቀበሉት ሲሆን ጀነራል ማቲስም ምንም እንኳ በግልፅ ለሥራ መልቀቅ ምክንያታቸው ይህ መሆኑን ባይጠቅሱም በትራምፕና በእሳቸው መካከል የቋም ልዩነት መፈጠሩን ተናግረዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጀነራል ማቲስ ሌሎች አገራትን አጋር በማድረግና ወታደራዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ በማድረግ ትልቅ ሚና መጫወታቸውንም ገልፀዋል። ትራምፕ ጀነራል ማቲስን የሚተካ ሰው በአጭር ጊዜ እንደሚሾም ቢናገሩም ማንነቱን ከመግለፅ ግን ተቆጥበዋል። • «ሰው ሲበሳጭ ማስታወሻ እይዝ ነበር» አዲስ ዓለማየሁ ጀነራሉ በሥራ መልቀቂያ ደብዳቤያቸው ላይ ከትራምፕ ጋር አጋር አገራትን በአክብሮት ስለመያዝና የአሜሪካ የጦር ኃይል አጠቃቀም ላይ ልዩናት እንደተፈጠረ በመጥቀስ ፕሬዝዳንቱ ከእርሳቸው ጋር የሚቀራረብ አመለካከት ያለውን የመከላከያ ሚንስትር መምረጥ ተገቢ እንደሆነ አስፍረዋል። የመከላከያ ሚኒስትሩን መልቀቅ በተመለከተ የሪፐብሊካኑ ሴናተር ሊንዲሲ ግራሃም "ጀነራል ማቲስ ለትራምፕ አስተዳደርና ለአገራችን በሰጡት አገልግሎት ሊኮሩ ይገባል" ብለዋል። ለአስርታት አክራሪ እስልምናን በመዋጋትና ወሳኝ ወታደራዊ ምክር በመስጠት ትልቅ ሚና መጫወታቸውንም ገልፀዋል። በተቃራኒው የዲሞክራቲኩ ሴናተር ማርክ ዋርነር የጀነራሉ ስልጣን የመልቀቅ ዜናን "አስደንጋጭ" ብለውታል። ይህን ያሉት ውጥንቅተጡ በወጣው የትራምፕ አስተዳደር ውስጥ ጀነራሉ የመረጋጋት ማዕከል የነበሩ በመሆኑ ነው። በተያያዘ ዜና ከሶሪያ በተጨማሪ አሜሪካ ሰባት ሺህ የሚሆኑ ወታደሮቿን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከአፍጋኒስታንም ልታስወጣ መሆኗም ተሰምቷል። ይህ መረጃ የወጣው አሜሪካ ጦሯን ሙሉ በሙሉ ከሶሪያ እንደምታስወጣ ትራምፕ ከገለፁ ከአንድ ቀን በኋላ ነው። • "በኢትዮጵያ ፖለቲካ የኦነግ ስም ቅመም ነው" የኦነግ የፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ የአሜሪካን ጦር ከአፍጋኒስታን ስለማስወጣት አስፈላጊነት ትራምፕ ከመመረጣቸው በፊት በግልፅ ሲናገሩ የቆዩ ቢሆንም አገሪቱ ዳግም የታሊባን እጅ ውስጥ እንዳትወድቅ የተወሰነ ሰራዊታቸው በአፍጋኒስታን መቆየትን አስፈላጊነት ላይ አስምረው ነበር። ምንም እንኳ በአገሪቱ የመከላከያ ባለስልጣናት ባይፀድቅም የጦር ሃይሉን ቁጥር የመቀነስ ፍላጎት እንዳለም ተገልጿል። እአአ 2001 ከተፈፀመው የመስከረም 11 የአሜሪካ የሽብር ጥቃት በኋላ አሜሪካ ጦሯን በአፍጋኒስታን አሰማርታለች። የአሜሪካ ጦር ኃይል በአፍጋኒስታን ያደረገው ቆይታ ረዥሙ የአገሪቱ የጦርነት ታሪክ ነው። በጊዜው አፍጋኒስታንን ተቆጣጥሮ የነበረው ታሊባን ለመስከረም 11 የአሜሪካ ጥቃት ሃላፊነት የወሰደውን የአልቃይዳ መሪ ኦሳማ ቢላደንን አሳልፌ አልሰጥም በማለቱ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ደብሊው ቡሽ በአፍጋኒስታን ጦርነት መክፈታቸው የሚታወስ ነው። ከዚያ በኋላ የታሊባን ሃይል ቢዳከምም አገሪቱን ወደ መረጋጋት ለመመለስ የአሜሪካ ጦር በአፍጋኒስታን እንዲቆይ ሆኗል። • ተፈላጊነታቸው እየቀነሰ የሚመጡ የሙያ ዘርፎች የትኞቹ ናቸው?
news-50032123
https://www.bbc.com/amharic/news-50032123
የመደፈሬን ታሪክ ከስልሳ ሰባት ዓመታት በኋላ የተናገርኩበት ምክንያት
ታዋቂዋ ጋናዊት ጋዜጠኛና፣ የቀድሞ ሚኒስትር እንዲሁም በተለያየ ጊዜ ለቢቢሲ ትፅፍ የነበረችው ኤልዛቤት ኦሄኔ በቅርቡ ከስልሳ ሰባት ዓመታት በፊት የደረሰባትን የተገዶ መደፈር ጥቃት ይፋ አድርጋለች።
ኤልዛቤት ጥቃቱ ሲፈጸምባት የሰባት ዓመት ልጅ የነበረች ሲሆን፤ ከስድስት አስርት ዓመታት በኋላም ጥቃቱን ለህዝብ ለማሳወቅ የወሰነችበትን ጉዳይ በአንደበቷ እንደሚከተለው ትናገራለች። የደረሰብኝን የመደፈር ጥቃት ይፋ ባደርግ ምን ያስከትል እንደነበር ብዙም አላሰብኩበትም። •የተነጠቀ ልጅነት •"በወንድሜ ለአምስት ዓመታት ተደፍሬአለሁ" ባለፈው ረቡዕ ነው በጋና ውስጥ ከፍተኛ ስርጭት ላለውና እኔም በየሳምንቱ በምፅፍበት ደይሊ ግራፊክ ታሪኬን አጋራሁኝ። የሰባ አራት አመት የዕድሜ ባለፀጋ ነኝ፤ ወደ ኋላ ስልሳ ሰባት ዓመታትን በትዝታ ተጉዤ ነው የሆነውን የምናገረው፤ አንድ የቅርብ ወንድ ጓደኛዬ ለምን በታሪኬ ሸክምን እንደፈጠርኩባቸው ጠየቀኝ። ታሪኩ እንደተነገረኝ ከሆነ ለማንበብ ከባድ ነው። ለስልሳ ሰባት አመታትም ለራሴ ደብቄው ኖሬያለሁ፤ ለምን አሁን መናገር መረጥኩ? ሚስጥሬን ለምን አብሬው አልተቀበርኩም? መጀመሪያ ምናልባት ታሪኬን ልናገርና ለምን እንዳጋራሁ እገልፃለሁ። ጊዜው በጎርጎሳውያኑ 1952 ነው፤ ገና የሰባት ዓመት ታዳጊ፤ ደስተኛ ልጅ ነበርኩ። ከአያቴም ጋር በመንደራችን እንኖር ነበር። አንድ ቀን ቤተሰባችን ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለውና ጎረቤታችን የሆነ ግለሰብ ጎትቶ ቤቱ አስገባኝና ጥቃት አደረሰብኝ። ምን እንደደረሰብኝ ለመናገር ቃላት ያጥሩኛል። በወቅቱ ሰውየው ምን እንዳደረገኝ አላወቅኩም፤ ይህ ነው ብባልም ስሙንም መጥራት አልችልም ነበር። ጥቃት የደረሰበትንም አካሌንም በትክክል ስም አላውቅም ነበር። የማውቀው ነገር ቢኖር እጁ ሸካራና ጥፍሩን አስታውሳለሁ፤ ብልቴም ውስጥ ጣቱን ሲያስገባ ጥፍሩ መሰበሩን ትዝ ይለኛል። ምን እንዳለ አላስታውስም፤ ከባድ ሰውነቱ ሲጫነኝ፤ የሰውነቱ ሽታ ሲሰነፍጠኝ፤ ሸካራ ጣቶቹና የተሰበሩ ጥፍሮቹ ለስልሳ ሰባት አመታት ያህል ትናንት የተፈጠረ ይመስል አእምሮየን በሚጠዘጥዝ መልኩ አስታውሰዋለሁ። •ፆታዊ ትንኮሳን ደርሶብኛል በማለቷ ተቃጥላ እንድትሞት የተደረገችው ወጣት ዛሬ ምን እንደተፈፀመብኝ አውቃለሁ። አንድ የሚመረኝ ቢኖር ያለው የማህበረሰቡ እሴት የደረሰብኝን ነገር በዝርዝር እንዳወራ አይፈቅድልኝም፤ ተደፈርኩ ወይም ጥቃት ደረሰብኝ በሚል በደፈናው እንድናገር ነው የሚፈለገው። አያቴ በምትችለው መጠን ተንከባክባኛለች፤ አካላዊ እንክብካቤ። ምን እንደተፈጠረ አልነገርኳትም። በተደፈርኩ በነገታው ገላየን እያጠበችኝ እያለ ከብልቴ ፈሳሽ ሲወጣ አየች፤ ኢንፌክሽንም ፈጥሮ ነበር። ምን እንደተፈጠረ አልጠየቀችኝም፤ ዝም ብላ ተንከባከበችኝ። የምትወዳት የልጅ ልጇ ላይ እንዲህ አይነት ነገር ይፈጠራል ብላም አላሰበችም። ልጅነቴን ሌላ የቀማኝ ነገር የተፈጠረው በአስራ አንድ አመቴ ነው፤ ያው ሰው ደፈረኝ። በዚህም ወቅት ምን እንደተፈጠረ በትክክል ባይገባኝም፤ በህይወቴ የማይሽር ጠባሳን ትቶ አልፏል። በህይወት መቆየት ደግ ነው፤ መደፈሬ ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ አድርጎኛል ማለትም አልችልም። በማህበረሰቡ የተሳካለት አይነት ህይወት ኖሮኛል። ጋዜጠኛ፣ ፀሐፊ እንዲሁም የመንግሥት ባለስልጣን ለመሆን በቅቼያለሁ። አሁን በዚህ እድሜየ ብሞትም እንግዲህ በጋና ባለው የማህበረሰቡ አስተያየት መቃብሬ ላይ ከፍተኛ ስራ እንዳበረከትኩ ነው የሚፃፍልኝ። በሌላ ቋንቋ ኑሮየን በደንብ አጣጥሜ የኖርኩ ሰው ነኝ። እናም ለዛ ነው ብዙዎች አሁን ለምን እንዲህ አይነት አሰቃቂና ቆሻሻ ርዕስ ይዘሽ መጣሽ ያሉኝ፤ በእርግጠኝነት የምናገረው ነገር ቢሆን የሴት ህፃናት መደፈር በማህበረሰቡ ዘንድ በተወሰነ መልኩ ተቀባይነት እንዳለው ልምዴ አሳይቶኛል። በተለይ ትንንሽ ሴት ህፃናት በትልልቅ ወንዶች አደጋ ላይ ናቸው። እንደ ማህበረሰብም በጉዳዩ ላይም ለመነጋገር ፍቃደኛ አይደለንም። ምንም እንኳን በአሁኑ ሰዓት ትንሽ መሻሻሎች ቢኖሩም አንዲት ህፃን ተደፍራ ሪፖርት ያደረገ ሰው በማህበረሰቡ ከፍተኛ ጫና ይደርስበታል፤ ከፖሊስም ክሱን እንዲተውና በቤት ውስጥ ስምምነቶች እንዲደረስ በተደጋጋሚ ጫናዎች ይደረጋሉ። ደፋሪውን ወደ ፍርድ የሚወስዱ ከቤተሰብ ጋር ለመቆራረጥ የወሰኑ ናቸው፤ ለዛም ነው ችሎት የሚመጡ የመደፈር ጉዳዮች በጣም ጥቂት የሆኑት። ፍራቻየም ሰባት አመት ኧረ እንዲያውም ሶስት አመት የሆናቸው ህፃናት ሴቶች እኔ ከዘመናት በፊት ባለፍኩበት ስቃይ ውስጥ የሆኑ አሉ። ቁጣ በደፋሪዎች ሳይሆን በተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን በጥቃት ላይ መነጋገር ካልቻልን ሁኔታዎች አይቀየሩም። እንደ ማህበረሰብ ስለ ወሲባዊ ግንኙነት ለማውራትም ፍቃደኛ አይደለንም፤ በተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎች ጋር በተያያዘ ሁኔታ ብቻ ቁጣችንን ለማሰማት ካልሆነ በሌላ መንገድ ወሲብን አንጠቅሰውም። በጋና ውስጥ የተመሳሳይ ፆታ በከፍተኛ ሁኔታ ተቀባይነት የሌለው ሲሆን አንድ ጥናትም የሚያሳየው 97% የሚሆነው የማህበረሰቡ አካል የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን በጋና ውስጥ አሉ ብሎ አያምንም። ለዛም ነው በጋና ውስጥ ባሉ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የወሲብ ትምህርት ይሰጥ ሲባል ከባህል የራቀ፣ ፀረ ሃይማኖት፣ ፀረ ጋናና የተመሳሳይ ፆታን በማህበረሰቡ ውስጥ ለማስረፅ የሚደረግ አሻጥር ነው ብለው ብዙዎች የሚያምኑት። •"ለእናንንተ ደህንነት ነው በሚል እንዳሰሩን ተገልፆልናል" የባላደራ ምክር ቤት አስተባባሪ በቅርቡም ጋና ውስጥ በትምህርት ስርአቱ ውስጥ የወሲብ ትምህርት ይካተት ተብሎ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል። ሁኔታውንም ለማቀዝቀዝ ፕሬዚዳንቱም መግለጫ መስጠት ነበረባቸው። ብዙዎችም የሴቶች መደፈርንም እንደተለመደ ነገር ማየታቸውም ችግሩን ለመቅረፍ አልተቻለም። •በሠርግ ዕለት ማታ በጉጉት የሚጠበቀው 'የደም ሸማ' አንድም ሰው መርዳት ከቻልኩ ደስተኛ ነኝ ታሪኬን ከሰሙ ብዙዎች ያገኘሁት ምላሽ ከጠበቅኩት በላይ ነው። ምቾት የሚነሳ ታሪክ ነው፤ ምቾት እንዲነሳም ተደርጎ ነው የተነገረው። ስለዚህ ምቾት ቢነሳቸውም ብዙ አይደንቀኝም። ብዙዎችም እንደ ጀግና አይተውኛል። ለኔ ግን ይህንን ታሪክ ለመንገር የፈጀብኝ 67 አመታት መሆኑን ነው የማውቀው እናም ስለ ጀግንነቴ አላውቅም። አንዳንዶች እንዲህ አይነት ታሪክ በይፋ መናገሬ ከቆሻሻነትና ከማዋረድ ጋር ያያዙት አሉ- ለነሱ ምንም አይነት አስተያየት የለኝም። ብዙ ሴቶች አመስግነውኝ እንዴት ድፍረት እንደሰጣቸውና ከራሳቸውም ታሪክ ጋር ያያዙት አሉ፤ በሱ ተሰምቶኛል። ታሪኬ ስለ ወሲብ በግልፅ እንድናወራ ካደረገንና ጥቃት የደረሰባቸውንም ህፃናት አቅም የሚፈጥርላቸው ከሆነ በደስታ ወደ መቃብሬ እወርዳለሁ።
news-45192681
https://www.bbc.com/amharic/news-45192681
በሆሄ የስነ ጽሁፍ ሽልማት በእውቀቱ ስዩም፣ አለማየሁ ገላጋይና ዳንኤል ወርቁ ተሸለሙ
ለንባብ ከበቁ መፃሕፍት መካከል በአንባቢዎች እንዲሁም በሥነ-ጽሁፍ ሀያሲያን ዓይን የተደነቁ ሥራዎች የሚሞገሱበት ሆሄ የሥነ-ጽሁፍ ሽልማት በይፋ ከተጀመረ ዓመት ሞላው።
ዓመታዊው ሆሄ የስነ ጽሁፍ ሽልማት በሆሄ፤ በተለያዩ የሥነ-ጽሁፍ ዘርፎች የላቀ ሥራ ያበረከቱ ጸሃፍት ይሸለማሉ። የሥነ-ጽሁፉ ባለውለታዎችም ይሞገሳሉ። የዘንድሮው የሆሄ ሽልማት ሲካሄድ በረዥም ልቦለድ ዘርፍ አለማየሁ ገላጋይ "በፍቅር ስም" በተሰኘ መጽሀፉ፣ በልጆች መፃሕፍት ዘርፍ ዳንኤል ወርቁ "ቴዎድሮስ" በተባለ ሥራውና በእውቀቱ ስዩም "የማለዳ ድባብ" በሚለው የግጥም መድበሉ ለሽልማት በቅተዋል። • ዕድሜ ጠገቧ የጥድ መፃሕፍት ቤት መደብር ትውስታ • "ፍቅር እስከ መቃብር"ን በአይፎን 7? ለዓመታት መፃሕፍትና አንባቢዎችን በማገናኘት የሚታወቁት መፅሐፍ ሻጩ ተስፋዬ አዳል፣ እንዲሁም እውቆቹ ጸሃፍት ነጋድራስ ገብረህይወት ባይከዳኝ፣ አማረ ማሞ እንዲሁም የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኛ ሴቶች ማህበር ስለ አበርክቷቸው ተመስግነዋል። ከተሸማሚዎቹ አንዱ ዳንኤል ወርቁ "ደራስያን ያላቸው ሀብት እውቅና ማግኘት ነው" የሚለው ዳንኤል ወርቁ፤ ከላይ የተጠቀሱት አንጋፋ ጸሀፍት በተመሰገኑበት መድረክ በመሸለሙ ክብር እንደሚሰማው ይናጋራል። ሥነ-ጽሁፍ ደጋግሞ እየወደቀ በሚነሳበት ሀገር መሰል ሽልማቶች ቢበራከቱ ደራስያንን እንደሚያበረታቱም ያምናል። የሥነ-ጽሁፍ ሽልማቶች ለደራስያን እውቅና ከመስጠት ባሻገር ለማህበረሰቡ "እስኪ ይህን መፅሐፍ አንብቡ" የሚል መልዕክት በማስተጋባት ዘርፉን ማበረታታቸው እሙን ነው። • ከ'ሶፍትዌር' ቀማሪነት ወደ ሥነ-ጥበብ ባለሟልነት • ስለ ጠልሰም ወይም በተለምዶ የአስማት ጥበብ ተብሎ ስለሚጠራው ምን ያህል ያውቃሉ? ሆሄ በየዓመቱ ከሚታተሙ መፃሕፍት መካከል በሥነ-ጽሁፍ መስፈርቶች የተሻሉ የሚባሉትን በሙያተኞች ያስገመግማል። አንባቢያንም ድምጽ በመስጠት የወደዱትን መጽሐፍ እንዲጠቁሙ እድል ይሰጣቸዋል። "የንባብ ባህሉ አልዳበረም" እየተባለ በሚተች ማህበረሰብ ውስጥ መጽሐፍ አሳትሞ አመርቂ ውጤት ማግኘት ፈታኝ መሆኑን የሚናገረው ዳንኤል፤ የሥነ-ጽሁፍ ሽልማቶች መፃሕፍትና ደራሲያንን አስከብረው ዘርፉንም እንደሚያሳድጉ ተስፋ ያደርጋል። አለማየሁ ገላጋይ "በፍቅር ስም" በተሰኘ መጽሀፉ ተሸልሟል ዳንኤል እየተዳከመ የመጣው የረዥም ልቦለድ መጻሕፍት ህትመት እንዲሁም ብዙም ትኩረት ያልተቸረው የልጆች መጻሕፍት ዘርፍ በሽልማቱ መካታቸውን እንደ ምሳሌ ይጠቅሳል። በሀገር አቀፍ ደረጃ በሥነ-ጽሁፍ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ዘርፎችም ሽልማት መስጠት አዲሰ አይደለም። የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የሽልማት ድርጅትና የ1990ዎቹ የኪነ-ጥበባትና መገናኛ ብዙኃን ድርጅትም አይዘነጉም። ሁለቱም ግን መዝለቅ አልቻሉም። ከሁለቱ ሽልማቶች በተጨማሪ በግለሰቦች ተነሳሽነት የተጀመሩ ሽልማቶችም ይጠቀሳሉ። ሆኖም ብዙዎቹ ከጥቂት ዓመታት ሲሻገሩ አይስተዋልም። ሆሄ የተወጠነው ለዘርፉ አስተዋጽኦ በማበርከት እንዲዘልቅ ቢሆንም የአቅም ውስንነት እንደሚፈታተናቸው የሽልማቱ አስተባባሪ ዘላለም ምሕረቱ ይናገራል። ከዚህ ቀደም ተጀምረው የተቋረጡ ሽልማቶች ተመሳሳይ ተግዳሮት አንደነበረባቸው ደራሲው ዳንኤልም ይገምታል። ዘላለምና ዳንኤል መሰል የሽልማት መሰናዶዎች ድጋፍ ካልተደረገላቸው ቀጣይነታቸው እንደማያስተማምን ይስማሙበታል። መጽሀፍ ሻጩ ተስፋዬ አዳል ለአበርክቷቸው ተመስግነዋል የሽልማት መሰናዶዎች ድጋፍ ካገኙ ዘላቂነታቸውን ከማረጋገጥ ባሻገር አድማሳቸውንም ማስፋት ይችላሉ። ሥነ-ጽሁፍ ዘርፈ ብዙ እንደመሆኑ ከልቦለድና ሥነ-ግጥም በተጨማሪ ወግ፣ አጫጭር ልቦለዶች፣ የተውኔት ጽሁፍ፣ ኢ ልቦለድ የጽሁፍ ሥራዎችም በውድድሩ ማካተት ይቻላል። በዘላላም ገለጻ "ብዙዎች መርሀ ግብሩን ይወዱታል። በገንዘብ መደገፍ ላይ ግን ሁሉም ወደ ኋላ ይላል። ገንዘባቸውን 'ትርፋማ ' በሚሏቸው ዘርፎች ማፍሰስ ይመርጣሉ።" የሽልማት ዝግጅቶች ብዙ ርቀት የማይራመዱት አንድም በበጀት ውስንነት ሲሆን፤ ከሽልማት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የሚነሱ የፍትሀዊነት ጥያቄዎች እንቅፋት የሆኑባቸውም ይገኙበታል። የኢትዮጵያ ደራስያን ማህበር የሬድዯ መርሀ ግብር ዋና አዘጋጅ ጌታቸው አለሙ አንጋፋና አማተር ደራስያንም ሥራቸው እንደተወደደላቸው የሚመሰከርባቸው የሥነ-ጽሁፍ መድረኮች መበራከት አለባቸው ይላል። መፃሕፍትን የማስተዋወቅ፣ ደራስያንን በአንድ መድረክ የማገናኘት ሚና እንዳላቸውም ያክላል። "መሰል ሽልማት በትልቅ ተቋም መሰጠት ቢኖርበትም ሆሄ በወጣቶች ተነሳሽነት የተጀመረ ተስፋ ሰጪ ዝግጅት ነው" ሲል ሽልማቱን ይገልጻል። የሽልማት መሰናዶዎች ደራስያንን ያሸለሙ ሥራዎች ጎልተው እንዲወጡ፣ በማህበረሰቡ ዘንድ እንዲነበቡ፣ የውይይት መነሻ እንዲሆኑም ያበረታታሉ።
news-48470899
https://www.bbc.com/amharic/news-48470899
በአማራ ክልል በአተት ሳቢያ የአምስት ሰዎች ሕይወት አለፈ
በአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት ሳቢያ የአምስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአማራ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
በሽታው ከሚያዝያ 18/ 2011 ዓ. ም ጀምሮ በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ እንደተከሰተ የኢንስቲትዩቱ የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና የኅብርተሰብ ጤና ስጋት ቅብብል ባለሙያ አቶ አሞኘ በላይ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "እስካሁን በሦስት ወረዳዎች እነሱም በሰሜን ጎንደር ጠለምት እና በይዳ ወረዳዎች እንዲሁም በዋግህምራ ዞን ደግሞ አበርገሌ በሚባል ወረዳ በሽታው ስለመከሰቱ ሪፖርት ተደርጓል" ብለዋል። • አተት እና ኮሌራ ምን እና ምን ናቸው? በጤና ተቋምና ባለሙያዎች ቤት ለቤት እየሄዱ ባደረጉት ሪፖርት መሠረት፤ እስከትናንት ድረስ 190 ገደማ ሰዎች በአተት መያዛቸውን ባለሙያው ገልጸዋል። "በአተት ምክንያት በተቋም ደረጃ መሞታቸው የተረጋገጠው 5 ሰዎች ናቸው" ብለዋል። አቶ አሞኘ እንደሚሉት፤ በሽታው የመቀነስ እዝማሚያ እያሳየ ቢሆንም በቁጥጥር ሥር ማዋል ግን አልተቻለም። "አሁን ባለው ሁኔታ ሰሜን ጎንደር ላይ ተቆጣጥረነዋል ማለት ይቻላል። እስከ ሁለት ሳምንት ድረስ ምንም አይነት ህመምተኛ ሪፖርት አልተደረገም" ይላሉ። ሆኖም አበርገሌ ላይ አልፎ አልፎ ሪፖርት እንደሚደረግ ያስረዳሉ። "ትናንት ሪፖርት አልነበረም። ቆሟል ማለት አይቻልም። አሁን ሥራዎች እየተሠሩ ነው። ነገር ግን ቆሟል ከእንግዲህም አይነሳም የምንልበት ሁኔታ የለም። ምክንያቱም ሰፊ ሥራ ይጠይቃል" ሲሉ አቶ አሞኘ ይገልጻሉ። የተከሰተው አተት ነው ወይስ ኮሌራ? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፤ "አተት በተለያዩ ነገሮች ሊከሰት ይችላል። በባክቴሪያ፣ በቫይረስ፣ በፕሮቶዞዋ ወይም በምግብና ውሃ መመረዝ ሊከሰት ይችላል። አተት ከሚያመጡት ውስጥ አንዱ ባክቴሪያ ሲሆን፤ ከባክቴሪያዎቹ ውስጥ ደግሞ አንዱ ኮሌራ ነው፤ ልዩነታቸው ይሄ ነው። አተት ሰፊ ነው። በብዙ ነገሮች ሊከሰት የሚችል ማንኛውም አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት ማለት ሲሆን፤ ኮሌራ ማለት ግን አተትን ከሚያስከትሉ ባክቴሪያዎች አንዱና በወረርሽኝ መልክ ሲከሰት ነው" ብለዋል። • ጤና የራቀው የፈለገ ህይወት ሆስፒታልአተት በብዙ ነገሮች ሊከሰት ስለሚችል እያንዳንዱ ኮሌራ እየተባለ ሪፖርት በቢደረግ ስህተት ሊፈጠር እንደሚችልም ተናግረዋል። አክለውም "ናሙና እየወሰዱ ከማረጋገጥ ጎን ለጎን፤ ማንኛውንም ምልክት የሚያሳይ ሰው አተት በሚል መረጃውን እየተቀባበልን የመከላከልና መቆጣጠር ሥራ እንሠራለን" ብለዋል። ማንኛውም አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት ያለበት ሰው በፍጥነት በአቅራቢያው ወደሚገኝ የጤና ተቋም መሄድ እንዳለበት አቶ አሞኘ አሳስበዋል። አሁን የተከሰተውን ችግር ለመከላከል ባለሙያዎችና የህክምና ቁሳቁሶችን ወደቦታው በመላክ ከአጋር ተቋማት ጋር እየሠሩ መሆኑንም ባለሙያው ገልጸዋል።
news-50731120
https://www.bbc.com/amharic/news-50731120
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኖቤል የሰላም ሽልማታቸውን ተቀበሉ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኖርዌይ ኦስሎ ተገኝተው የኖቤል ሽልማታቸውን ተቀበሉ።
የኖቤል የሰላም ኮሚቴ ሊቀመንበር ቤሪት ሬይሳ አንደርሰን በሥነ ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ባስመዘገቧቸው ሦስት ዋና ዋና ውጤቶች የ2019 የኖቤል ሰላም ተሸላሚ እንዲሆኑ መመረጣቸውን አስታውቀዋል። እነዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በተለይ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ለዓመታት የዘለቀውን ውዝግብ በሰላም ለመፍታት ባሳዩት ተነሳሽነት፣ በኢትዮጵያ በዲሞክራሲ ግንባታ ለተጫወቱት ሚና እንዲሁም በኢትዮጵያ፣ በምስራቅና በሰሜን ምስራቅ አፍሪካ ሰላምና እርቅ እንዲመጣ ላደረጉት አስተዋፅኦ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ሊቀመንበሯ በንግግራቸው፤ "እንደ ኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርነትዎ በአገር ውስጥ በርካታ ተግዳሮቶችን እየተጋፈጡ ነው፤ የክልል እና የብሔር ክፍፍል ወደ 3 ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎች እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆኗል። እነዚህ ሰዎች በራሳቸው ሃገር ቤት አልባ ሆነዋል። እነዚህ ሰዎች ወደ ቀያቸው መመለስ አለባቸው። የኢኮኖሚ ቀውስ ፣ ሥራ አጥነት ፣ ትምህርት እና ጤና ላይም መሰራት አለባቸው" ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሽልማታቸውን ከተቀበሉ በኋላ እንደተናገሩት፣ የኖሮዌይ ኖቤል ኮሚቴ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ሰላም ለማስፈን የወሰዱትን እርምጃ ከግምት በማስገባት ሽልማቱን ስላበረከተላቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል። ሽልማታቸውን በኢትዮጵያ ሕዝብና በፕሬዝዳንት ኢሳያስ ስም በተለይ ደግሞ ሰላምን ለማምጣት የማይተካ ዋጋ በከፈሉ ግለሰቦች ስም እንደሚቀበሉ ገልጸዋል። • ዐብይ አሕመድ ለኖቤል ሽልማት ታጭተዋል? • የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የኖቤል ሽልማትን በመቃወም ኤርትራውያን በኦስሎ ሰልፍ ወጡ ዛሬ ከፊት ለፊታችሁ ቆሜ ስለ ሰላም ለማውራት የቻልኩት በእድል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በኢትዮጵያ ኤርትራ ጦር ከፊት ተሰልፈው የጦርነትን አስከፊነት ማየታቸውን ገልጸዋል። ባድመ የሬዲዮ ኦፕሬተር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩበት ጦር፣ ለጥቂት ዞር ብለው ሲመለሱ በደረሰበት ጥቃት አባላቱ ሙሉ በሙሉ መሞታቸውን ጠቅሰዋል። ጦርነት ለክፉዎች፣ ለልበ ደንዳኖችና ለጨካኞች ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በዛን ዕለት በጦርነት አውደ ግንባር ያጧቸውን ጓደኞቻቸውም ዛሬም ድረስ እንደሚያስታውሷቸው ገልጸዋል። 100 ሺህ ወታደሮችና ንጹኀን ሕይወታቸውን በዚህ ጦርነት አጥተዋል በማለትም በኢትዮጵያም በኤርትራም ወገን ያደረሰውን ቀውስ ገልጸዋል። ኢትዮጵያና ኤርትራ ለሁለት አስርታት ያለ ሰላምም ያለጦርነትም በቆዮበት ዓመታት ቤተሰቦች ተቆራርጠው መቅረታቸውን ገልጸዋል። ከ18 ወር በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር በሆኑበት ወቅት በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ሰላም ለማምጣት እንደሚችል ጠንካራ እምነት እንደነበራቸው ገልጸው ፕሬዝዳንት ኢሳያስም ይህ እምነት እንደነበራቸው ገልጸዋል። • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የ2019 የኖቤል የሠላም ሽልማት አሸናፊ ሆኑ ዛሬ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተለያዩ ቤተሰቦች ተገናኝተዋል፣ የአየርና የስልክ ግንኙነት እንዲሁም ዲፕሎማቲክ ግንኙነት ተጀምሯል በማለት ለሰላም ያላቸው ቁርጠኝነት ብርቱ እንደሆነ ገልፀዋል። የሰላም ያላቸው ግንዛቤ በመደመር እሳቤ ላይ የተመሠረተ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል። የዓለም ኃያላን ሀገራት በቀጠናው ወታደራዊ ኃይላቸውን ለማስፈር አሸባሪዎችና ጽንፈኛ ኃይሎች ደግሞ በቀጠናው ጠንካራ መሰረት ለመጣል እየጣሩ ነው ሲሉም ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ቀጠናው የኃያላን ሀገራት ጦርነት ሜዳ እንዲሆን የሽብር ነጋዴዎችና ደላሎችም መደበቂያ እንዲሆን እንደማይፈልጉ ቁርጠኝነታቸውን ገልፀዋል። በተጨማሪም እንደ አለም ዜጋ አባልነታችን ሰላም ላይ ሀብታችንን ማፍሰስ አለብን ብለዋል።
news-53537240
https://www.bbc.com/amharic/news-53537240
ከተከሰተው ሁከት ጋር ተያይዞ ታስረው የነበሩ ሁለት የአሜሪካ ዜጎች በዋስ እንዲፈቱ ተወሰነ
ከሳምንታት በፊት ተከስቶ ከነበረው ሁከት ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ሰዎች መካከል ሁለት የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ታሳሪዎች የዋስ መብት ተፈቀደላቸው።
ሬድዋን አማን እኣነ ዩሱፍ በሽር የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ተከስቶ ከነበረው ሁከት ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሰዎች ቁጥር ከ7 ሺህ በላይ መሆኑ ባለስልጣናት ማስታወቃቸው ይታወሳል። ከእነዚህም መካከል ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የሆኑ ሦስት የአሜሪካ ዜጎች ይገኙበታል። የአሜሪካ ዜግነት ካለቸው መካከል ትናንት ፍርድ ቤት የቀረቡት ሬድዋን አማን እና ዩሱፍ በሽር የዋስ መብታቸው እንዲከበርላቸው ፍርድ ቤት መወሰኑን ጠበቃቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሬድዋን አማን እና ዩሱፍ በሽር ነዋሪነታቸው በአሜሪካ አገር የነበረ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ነበር ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት። ጠበቃቸው አቶ ከድር ቡሎ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ሁለቱ ግለሰቦች አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው በ6 ሺህ ብር የዋስትና መብት ከእስር እንዲወጡ ተወስኗል ብለዋል። ጠበቃው ትናንት ለቢቢሲ ሲናገሩ ደንበኞቻቸው ዓርብ ወይም ቅዳሜ ከእስር ቤት ይወጣሉ ብለውን እንደሚጠበቁ ተናግረዋል። ሦስተኛው የአሜሪካ ዜግነት ያለው እና በእስር ላይ የሚገኘው ግለሰብ ሚሻ ጪሪ የሚባል ሲሆን፤ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኦ.ኤም.ኤን) ቴክኒሺያን ሆኖ ሲያገለግል ነበር። ሚሻ ከዚህ ቀደም ፍርድ ቤት ቀርቦ በነበረበት ወቅት በጉዳዩ ላይ የአሜሪካን ኤምባሲን ለማግኘት ያደረገው ተደጋጋሚ ጥረት እንዳልተሳካለት ለፍርድ ቤት ተናግሮ ነበር። ትናንት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ ላይ ሦስቱም የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች እንቁላል ፋብሪካ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው ጊዜያዊ እስር ቤት እንደሚገኙ ጠቅሷል። በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በበኩሉ ትናንት በትዊተር ገጹ ላይ “በኢትዮጵያ የሚገኙ የአሜሪካዊያን ደህንነት ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው” ካለ በኋላ፤ አሜሪካዊያን በኢትዮጵያ ታስረው ከሆነ በተቻለ ፍጥነት እንደሚጎበኙ እና አስፈላጊው ድጋፍ እና አገልግሎቶች እንደሚያቀርብ ኤምባሲው አስታወቋል።
50093606
https://www.bbc.com/amharic/50093606
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ "መደመር" መጽሐፍ ተመረቀ
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ 'መደመር' የተሰኘው የመጽሐፍ ምረቃ ሥነ ሥርዓት አዲስ አበባ ውስጥ በሚሌኒየም አዳራሽ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ተካሂዷል።
በሥነ ሥርዓቱ ላይ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር)፣ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር)፣ ሚኒስትሮች፣ የክልል ባለሰልጣናትና የኪነጥበብ ባለሙያዎች ተገኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ ባለቤታቸው ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ፣ እንዲሁም የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ መደመር የሚል ጽሑፍ የሰፈረበትን ኬክ በመቁረስ መጽሐፉ ተመርቋል። በምረቃው ሥነ ሥርዓት ላይ ከእንግዶቹ ጀርባ ተማሪዎች የተገኙ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተማሪዎቹ መጽሐፉን በስጦታ መልክ አበርክተውላቸዋል። ዛሬ ከተመረቅው መጽሐፍ ባሻገር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሥነ ሥርዓቱ ላይ አራት የታተሙ ሁለት ያልታተሙ መጽሐፎች እንዳሏቸውና የታተሙትም 'ዲርአዝ' በተሰኘ የብዕር ስም እንደቀረቡ ገልፀዋል። ከመጽሐፎቻቸው መካከል 'እርካብና መንበር'ና 'ሰተቴ' የተሰኙ የሚገኙ ሲሆን ይህ መጽሐፍ በስማቸው የታተመ የመጀመሪያው ስራቸው ነው። • ሐሰተኛ ዜና ወይስ የተቀለበሰ ውሳኔ? ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ባደረጉት ንግግር መደመር ነገን ያያል በማለት "የእኔና የእናንተ፣ የሁላችንም መጽሐፍ ነው" ብለዋል። መጽሐፉን የሚያነቡ ሰዎች መተቸት ብቻ ሳሆን የተሻለ አማራጭ ሃሳብ በማምጣት ሀሳቡን እንዲያዳብሩ ጠይቀዋል። መደመር መነሻውም መድረሻውም ሰውና ተፈጥሮ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመደመር አስተሳሰብ አገርኛ ነው ሲሉ ተናግረዋል። የሚሌኒም አዳራሽ ዝግጅትን ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ከመፅሐፉ መግቢያ ላይ በአማርኛና በኦሮምኛ በማንበብ አስጀምረዋል። መጽሐፉ በዛሬው ዕለት ከ20 በላይ በሀገሪቱ ከተሞች እየተመረቀ መሆኑንም በወቅቱ ተገልጿል። • የስፖርት ውርርድ አዲሱ የወጣቶች ሱስ ይሆን? ደራሲና ጋዜጠኛ አዜብ ወርቁ ከ'መደመር' መጽሐፍ ቀንጭበው ያነበቡ ሲሆን አቶ ሌንጮ ባቲ ደግሞ ዳሰሳ አቅርበዋል። አቶ ሌንጮ ዋና ዋና ነገሮች የኢትዮጵያን መሰረታዊ የህብረተሰባዊ ግንኙነት ስብራት፣ የፖለቲካ፣ የምጣኔ ሃብት ችግሮች የውጪ ግንኙነት ፖሊሲ ችግሮች ይፈታል ወይ? በማለት በመጠየቅ ጽሁፋቸውን አቅርበዋል። እንደ አቶ ሌንጮ ሃሳብ በጠቅላይ ሚኒስትሩ መጽሐፍ ውስጥ በስፋት ተዳሰሰው የመደመር ፍልስፍና "ትልቁ የመደመር እሳቤ የማደራጀት አቅም አለው፤ የለውም የሚለው ነው" በማለት ዳሰሳቸውን በዝርዝር አቅርበዋል። ተጨባጭ የሆኑ ጉዳዮችን መጽሐፉ ይዟል ያሉት አቶ ሌንጮ መጽሀፉ አራት ዋና ዋና ምዕራፎች እንዳሉት ተናግረዋል። አቶ ሌንጮ ቀዳሚው ምዕራፍ የሰው ልጅ መሠረታዊ ፍላጎቶች ምንድን ናቸው፣ ፖለቲካዊ ዕይታን ሦስተኛው መምጣኔ ኃብት፣ አራተኛው የውጪ ግንኙነትን ይዟል ሲሉ ተናግረዋል። መጽሀፉ እንደ ህዝብና እንደ ሀገር እንዴት ነው የምንቀጥለው የሚለውን ለመፍታት ይሞክራል ያሉት አቶ ሌንጮ፤ ደራሲው የኢትዮጵያ መሰረታዊ ችግር ብቸኝነት ነው ሲል እንደሚያቀርብ ይጠቅሳሉ። ይህ ብቸኝነት በአንድ ላይ ተሰባበስበን ችግራችንን ለመፍታት አቅም አሳጥቶናል ሲሉ የመደመርን አስፈላጊነት ይናገራሉ። • "የተርባይኖች መቀነስ በሚመነጨው ኃይል ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም" የህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የ2019 የኖቤል የሠላም ሽልማት አሸናፊ ሆኑ ፉክክርና ትብብር ሚዛን አለመጠበቃቸውን በመጽሐፉ ላይ ተጠቅሷል ያሉት አቶ ሌንጮ፤ በአጠቃላይ ፍላጎትን፣ አቅምን፣ ሀብትን በማሰባሰብ እና በማከማቸት አቅም ፈጥረን ወደ ማካበትና ወደ ውጤት መምራት አለብን የሚል እይታ አለው ብለዋል። የተሰሩ መልካም ሥራዎችን ጠብቆ ማቆየት ያስፈልጋል የሚል ሀሳብ በመጽሐፉ ውስጥ መነሳቱን የጠቀሱት አቶ ሌንጮ የመደመር እሳቤ ከዜሮ አይነሳም በማለት እስካሁን ለተሰሩት ትልልቅ ሥራዎች እውቅና ይሰጣል በማለት መሰረተ ልማት ላይ፣ ጤና ላይ፣ ትምህርት ላይ ለተሰሩት ሥራዎች እውቅና ይሰጣል ብለዋል። የመደመር ግብ የዜጎችን ክብር ማረጋገጥ ነው ያሉት አቶ ሌንጮ ይህ ደግሞ ሀገራዊ አንድነት ሲኖር ነው ሲሉ፤ የብሔራዊ አንድነት ሊኖር እንደሚገባ ከዚያም ሁሉን አቀፍ የሆነና ዙሪያ መለስ ብልጽግና እንደሚመጣ ይገልጻሉ። የመደመር እንቅፋቶች ተብለው በመጽሐፉ ውስጥ ከተጠቀሱት ነጥቦችም መካከል በማንሳት ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ፖለቲካ፤ ያለ ችግርን ሁሉ ትናንትናና ዛሬ ላይ ማላከክ እንዲሁም በአስተሳሰብም በተግባርም የሚፈጸም ሌብነት ነው ሲሉ አቶ ሌንጮ ባቲ ተናግረዋል። አክለውም ለእድገትና አብሮ ለመሆን ታታሪነት ወሳኝ ነው፤ ጉልበት እንኳ ባይኖር መልካም ፈቃድ መኖር አለበት ሲሉም ገልጸዋል። ዶ/ር ምሕረት ደበበ በበኩላቸው ይህ የመደመርን የሀሳብ ዘር የተሸከመ "የመደመር ፍሬ" ነው ሲሉ ገልጸዋል። መጽሐፉ ሁለት ዕይታዎችን እንድናይ ያደርገናል በማለትም እነዚያም ሀሳብና ሰው መሆናቸውን ገልፀዋል። ሀሳብ በሰዎች ውስጥ አድረጎ በሰው ውስት ትልቅ ለውጥ ያመጣል የሚል እምነት አለው ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።
news-50703911
https://www.bbc.com/amharic/news-50703911
አምስቱ ተስፋ የተጣለባቸው አፍሪካውያን ሙዚቀኞች
ዴቪዶ፣ ዊዝኪድ፣ በርና ቦይ ከአፍሪካ ማህፀን የተገኙ ሙዚቀኞች ሲሆኑ፤ ድንበር፣ ቋንቋ ፣ ባህል ሳይገድባቸው በአለም አቀፉ የሙዚቃ መድረክም ስመ ጥር ሊሆኑ ችለዋል።
ናይጀሪያዊው ዊዝ ኪድ ለዚያም ነው ምዕራባውያኖቹ መዚቀኞችም ሆነ ፕሮዲውሰሮች አይናቸውን ወደ አፍሪካ ሙዚቀኞች እያማተሩ ያሉት። በዚህ አመት በወጣው 'ላየን ኪንግ' የካርቱን ፊልም ተነሳስታ ቢዮንሴ አልበሟን ስትሰራም ታዋቂ አፍሪካዊ ሙዚቀኞችን አካታለች። •ባህልን በኤሌክትሮኒክ ሙዚቃ የቀመመው ሮፍናን •''አዝማሪዎቻችን የሙዚቃ ሳይንቲስቶች ናቸው" ሚስተር ኢዚና በርና ቦይም በሙዚቃው ዓለም ከፍተኛ ስፍራ በተቸረው በአመታዊው የኮቼላ ሙዚቃ ፌስቲቫል ተሳትፈዋል። ሊጠናቀቅ አንድ ወር በቀረው የአውሮፓውያኑ ዓመት የአድማጮችን ቀልብ መያዝ ከቻሉት ጥቂት አፍሪካውያን ሙዚቀኞች አምስቱ እነሆ፡ ሺባህ ካሩንጊ (ኡጋንዳ) ሺባህ በእናት ሃገሯ ኡጋንዳ በሙዚቃው ዘርፍ ተደማጭነት ያገኘችው ሺባህ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ሃገሯን አልፎ ሙዚቃዋ ወደሌሎች ሃገራት ደርሷል። በሚስረቀረቅ ድምጿ የብዙዎችን ቀልብ መሳብ የቻለችው ሺባህ ከተለያዩ አርቲስቶችም ጋር በመጣመር ትስራለች። ሙዚቃውን ከዳንስና ከፋሽን ጋር በማጣመር ለራሷም ሆነ ለሃገሯ ስም ማትረፍ ችላለች። • በፈረንጅ "ናይት ክለብ" ጉራግኛ ሲደለቅ በመድረክም ላይ ባላት ድንቅ ችሎታ እንዲሁ ታዳሚውን ወደ ሙዚቃዋ ጠልቃ የምታስገባበበት መንገድ ብዙዎችን እንዲደመሙ አድርጓቸዋል። ጆቦይ (ናይጀሪያ) ጆቦይ ናይጀሪያዊው ጆቦይ 'ቤቢ' በሚለው የፍቅር ዘፈኑ የብዙ አድማጮችን ጆሮ ማግኘት የቻለ ሲሆን፤ ይህ ሙዚቃውም በዩቲዩብ ላይ አስራ አምስት ሚሊዮን ተመልካቾችን ማግኘት ችሏል። በስሜት በተሞላ አዘፋፈኑና በሚንቆረቆረው ድምፁ የተለያዩ የሙዚቃ ስልቶችን ማጣመር የቻለ አርቲስት ነው። አፍሮ ቢትንና ፖፕን በማጣመር የሰራው ሌላኛው ዘፈኑ 'ቢጊኒንግ' ከፍተኛ ተቀባይነትን ማትረፍ ችሏል። • የኢትዮጵያ ሙዚቃ- ከመስከረም እስከ መስከረም በነዚህ ነጠላ ዘፈኖቹ እውቅናን ማትረፍ የቻለው ጆቦይ በተለያዩ ሃገራትም በሚገኙ ፌስቲቫሎች ላይ ከሚጋበዙ ሙዚቀኞች አንዱ መሆን ችሏል። ብሪያን ናድራ (ኬንያ) ከሁለት ዓመታት በፊት ባወጣው ነጠላ ዘፈን 'ሊዮ' የሙዚቃው ዓለም ላይ ስሙን የጣለው ብሪያን ሙዚቃውን "ከሚሊኒየሙ ባህል የተገኘ፤ የተንቀሳቃሽ ስልክ ዘመንን ያማከለ፤ የከተማ ድምፅ" በማለት ይገልፀዋል። ኬንያዊው ሙዚቀኛ፣ ገጣሚና የሙዚቃ ፀሐፊ የምስራቅ አፍሪካ የፖፕ ሙዚቃ ስልት አምባሳደር እየተባለ እየተጠራ ሲሆን፤ በዓለም አቀፉ ደረጃ ኬንያ የሙዚቃውን ገበያ ሰብሮ መግባት የቻለ ሙዚቀኛ የሌላት ሲሆን ብሪያን ይህንንም ሊቀይር ይችላል እየተባለ ነው። ለየት ያለ የአዘፋፈን ዘዬ ያለው ብሪያን ለስለስ ካሉ ዘፈኖቹ በተጨማሪ ራፕ ማድረግን እንዲሁም የተለያዩ የሙዚቃ ስልቶችን እንደ ሬጌና ሌሎችም ሙዚቃ ስልቶችን ማጣመር ችሏል። ኢኖስ ቢ (ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ) መነሻውን የኮንጎ ባህላዊ ሙዚቃ ያደረገው የ22 አመቱ ኢኖስ ሌሎች የሙዚቃ ስልቶችን በመጨመር ሙዚቃውን አንድ ደረጃ ወደፊት ሊያራምድ ይችላል እየተባለ ነው። ከታንዛንያው ሙዚቀኛ ዳይመንድ ጋር የተጣመረበት 'ዮፔ' የተባለው ነጠላ ዘፈኑም ብዙዎችን አስደስቷል። የሙዚቃ ቪዲዮው በወጣበት በሶስት ወራትም አስራ አራት ሚሊዮን ተመልካቾች አይተውታል። ኢኖስ ቢ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መለያ የሆነውን ሩምባ የሙዚቃ ስልትንም ከሪትም ኤንድ ብሉዝና አፍሮ ቢትስ ጋር ማቀላቀል ችሏል። ሾ ማድጆዚ (ደቡብ አፍሪካ) ሾ ማድጆዚ በአለም የሙዚቃ መድረክ ዝናዋ እየናኘ ያለው ደቡብ አፍሪካዊቷ የሂፕ ሆፕ አርቲስት ሾ በዚህ ዓመት የቢኢቲ (ብላክ ኢንተርቴይንመንት) አዲስ ዓለም አቀፍ አርቲስት በሚል ዘርፍ ሽልማትን ማግኘት ችላለች። በታላቅ ስሜት የምትዘፍነው አርቲስቷ መድረክ ላይ ሲሆን ያ ስሜቷ በሰው ላይ ይሰርፃል ይሏታል። የደቡብ አፍሪካ ግኮም የሙዚቃ ስልት በመሳሪያ ብቻ የተቀነባበረ ቢሆንም ሾ ግን ራፕ ታደርግበታለች፤ በአንድ ሳይሆን በተለያዩ ቋንቋዎች። ምንም እንኳን ብዙዎቹ የደቡብ አፍሪካ አርቲስቶች የሙዚቃ ገበያ ትኩረት ሃገራቸው ላይ ቢሆንም ሾ ግን የአለም አቀፉን ገበያ እያማተረች ነው።
news-45167164
https://www.bbc.com/amharic/news-45167164
በምሥራቅ ወለጋ በተፈፀመ ጥቃት ሁለት ሰዎች ተገደሉ
በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ ወለጋ ወሊጋልቴ ገጠር ቀበሌ ውስጥ ሁለት ግለሰቦች በወጣቶች በተፈፀመባቸው ጥቃት መገደላቸውን የዓይን እማኞች ገለጹ።
ቅዳሜ አመሻሽ ላይ የተደራጁ ወጣቶች መኪና በማስቆም ሁለቱን ግለሰቦች በኃይል ከመኪና ላይ በማውረድ በድንጋይ ደብድበው መግደላቸውን የዓይን እማኞች የገለጹ ሲሆን፤ የሲቡሴ ወረዳ የፖሊስ አዛዥ የሆኑት ምክትል ኮማንድር ጫላ ኦቦሶ ደግሞ ሁለቱ ሰዎች በድንጋይ መገደላቸውን አረጋግጠው የግድያው ምክንያት በግለሰቦች መካከል በነበረ ግጭት ነው ብለዋል። ምክትል ኮማንደር ጫላ ኦቦሶ ሟቾቹ ፍፁም መሃሪና ሃፍቱ ሃገዞም ይባላሉ ብለዋል። • በደብረማርቆስ 'ባለስልጣኑ አርፈውበታል' የተባለው ሆቴል ጥቃት ደረሰበት • በኮምቦልቻ ከተማ በተከሰተ ግጭት ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ • በደምቢ ዶሎ በተፈፀመ ጥቃት አንዲት ነፍሰጡር ስትሞት 4 ሰዎች ቆሰሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ሁለቱ ግለሰቦች 1977 ዓ.ም በህጻንነት ዕድሜያቸው በሰፈራ ከትግራይ ወደዚህ ወደ አካባቢው መምጣታቸውን ይናገራሉ። አቶ ፍጹም የተባለው ሟች መቀሌ ከተማ ቤት ሰርቶ ወደዚያው ለመመለስ እቃ ጭነው በመሄድ ላይ ሳሉ እንደተገደሉ የዓይን እማኞች የገለጹ ሲሆን የፖሊስ አዛዡ ግን ይህ መረጃ የለኝም ብለዋል። የሟች ቤተሰቦች እንደሚሉት ከሆነ አስክሬን ከፖሊስ ተቀብለው ለመውሰድ ሙከራ ቢያደርጉም እዚሁ ቅበሯቸው የሚል ማስፈራሪያ ደርሶናል ብለዋል። ምክትል ኮማንድር ጫላ ኦቦሶ የሟቾች አስክሬን ለምረመራ ወደ ሆስፒታል ተልኮ ከተመለሰ በኋላ እዛው ወሊገልቴ በተባለው ቀበሌ ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት ዛሬ ስርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል ብለዋል። ምክትል ኮማንደር ጫላ የቤተሰብ አባላቱ አስክሬን ይዘው እንዳይሄዱ ስለመከልከላቸው እንደማያውቁ ተናግረው፤ ሟቾቹ በምሥራቅ ወለጋ ከ30 ዓመታት በላይ መኖራቸውን እና ሌሎች የቤተሰብ አባላሎቻቸውም በቀበሌዋ እንደሚኖሩ ጨምረው ተናግረዋል። • ሰመጉ በኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች የፀጥታ አካላት የመብት ጥሰቶችን መፈፀማቸውን በሪፖርቱ ገለፀ • ሰመጉ በወልዲያ እና አካባቢው የመብት ጥሰት ተፈጽሟል አለ ከተፈጸመው ወንጀል ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር የዋለ ሰው ስለመኖሩ የተጠየቁት የፖሊስ አዛዥ ''በምረመራ ላይ ያለ ጉዳይ ስለመሆኑ በጉዳዩ ላይ መረጃ መስጠት አልችልም'' ብለዋል።
news-45868239
https://www.bbc.com/amharic/news-45868239
የአለም የምግብ ቀን: አስገራሚ የአለማችን ምግቦች
የምንበላው ምግብ የባህላችንና የማንነታችን መገለጫ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ። በባህሎች መካከል ያለ ልዩነት ደግሞ ስለምግቦች ያለንን መጥፎም ይሁን ጥሩ አመለካከት ይወስነዋል።
ምንም እንኳን አንድ ምግብ ስናይ እንዳንወደው የሚያደረገን ሰውነታችን እራሱን ከበሽታ ለመከላከል በሚያደርገው ጥረት ቢሆንም፤ ሁሉም ሰው በስምምነት የሚጠላው ምግብ አለመኖሩ ደግሞ የባህልን ተጽዕኖ ያሳያል። •ስለ አንጀታችን የማያውቋቸው ስድስት አስገራሚ እውነታዎች •የአስር ደቂቃ እንቅስቃሴ የማስታወስ ችሎታን እንዴት ይጨምራል? ዛሬ ጥቅምት 6 2011 የዓለም የምግብ ቀን ነው። ከዚህ ጋር አያይዘን በአለም ላይ ስላሉ የተለያዩ አስገራሚ ምግቦች ያገኘነውን መረጃ ልናካፍላችሁ ወደድን። እስቲ የትኞቹን ምግቦች ይወዷቸው ይሆን? በትል የተሞላ የገበታ አይብ (ጣልያን) በትልቅ ሰሃን ላይ አይብ ይደረግና ዝንቦች መጥተው እንቁላላቸውን እንዲጥሉበት መሃሉ ክፍት ይደረጋል። የዝንቦቹ እንቁላሎች ተፈጥሯዊ ሂደታቸውን ተከትለው አይቡ ውስጥ መፈልፈል ይጀምራሉ። በዚህ ሰአት አይቡ መሰባበርና መቅለጥ ይጀምራል። ይህ ደግሞ ለአይቡ የተለየ ጣእም ይሰጠዋል። የዚህ ምግብ ተመጋቢዎች ገበታ ላይ ሲቀርቡ የሚፈነጣጠሩት ትሎች ወደ አይኖቻቸው እንዳይገቡ መጠበቅ ያለባቸው ሲሆን፤ በህይወት ያሉትን ትሎች እንዳይበሉም ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። ለጤና ከሚኖረው ጠንቅ በመነሳት አውሮፓ ውስጥ ምግቡ እንዳይሸጥ ተከልክሏል። የበሬ መራቢያ አካል (ቻይና) የበሬ መራቢያ አካል የሚበላው ለጤና ካለው ከፍተኛ ጥቅም ሲሆን፤ አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ለስንፈተ ወሲብ ፍቱን መድሃኒት ነው ይላሉ። ባለሙያዎቹ እንደሚሉት ሴቶች ነጭ የሆነውን አካል መብላት ያለባቸው ሲሆን፤ ወንዶች ደግሞ ጠቆር ያለውን የበሬ መራቢያ አካል መብላት ይጠበቅባቸዋል። የተጠበሰ አንበጣ (ዩጋንዳ) በየምግብ ቤት ከምናገኘው የተጠበሰ ድንች በተቃራኒው ዩጋንዳና አንዳንድ የአፍሪካ ሃገራት ውስጥ አንድ ሁለት ቢራ ከጠጡ በኋላ የተጠበሱ አንበጣዎችን ቃም ቃም ማድረግ የተለመደ ነው። በዚህ ሀገር ሴቶች ይህንን ምግብ የማይበሉ ሲሆን፤ ተሳስተው ከበሉት ደግሞ ልክ እንደ አንበጣዎች አይነት ጭንቅላት ያለው ልጅ ይወልዳሉ ተብሎ ይታመናል። የጉንዳን እንቁላል (ሜክሲኮ) እንደ አንዳንድ የታሪክ ተመራማሪዎች የአሁኗ ሜክሲኮ ተብላ በምትጠራው ሀገር አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ከዛፍ ላእ የሚያገኟቸውን የጉንዳን እንቁላሉች እንደ ቆሎ ይበሏቸው እንደነበር ይገልጻሉ። በአካባቢው ሰዎች ' ኢስካሞልስ' ተብሎ የሚጠራው ምግብ የተለያዩ ቅመማ ቅመሞችን ከጉንዳኖች እንቁላል ጋር በመጥበስ ይበላል። የእባብ ልብ (ቪየትናም) አሁንም ይህ ምግብ በቪየትናም ለስንፈተ ወሲብ ፍቱን መድሃኒት እንደሆነ ይታሰባል። በመጀመሪያ እባቡ ይገደልና በውሃ ይቀቀላል። በመቀጠል የሰውነት ክፍሎቹ በባለሙያዎች ይበለትና ልቡ ለብቻው ይወጣል። ልቡን ለማወራረድ ደግሞ በአንዳንድ አካባቢዎች አብሮት እባበ ደም ይቀርባል። የእባቡ ሌሎች የሰውነት ክፍሎችም ቢሆን ለምግብነት ይውላሉ። የበግ አይንና አንጎል (ኢራን፣ አፍጋኒስታን እና ኢራቅ) እንደ አጋጣሚ በእነዚህ ሀገራት የመሄድ አጋጣሚ አግኝተው ቢሰክሩና ጠዋት ላይ ህምም (ሃንጎቨር) ቢሰማዎት በአቅራቢያዎት ያሉ ሰዎች መጀመሪያ የሚያቀርቡልዎት ምግብ 'ካሌ ፓሽ' ይባላል። የሚሰራውም ከበግ አይን፣ አንጎል፣ እግርና አንጀት ነው። ፍቱን መድሃኒት እንደሆነ ደግሞ የቀመሱት መስክረውለታል። የተቀቀለ የአሳማ ደም (እንግሊዝ ) 'ብላክ ፐዲንግ' ተብሎ የሚጠራው የእግሊዞች ባህላዊ ቁርስ ተቀቅሎ የተጠበሰ የአሳማ ደም ከጎን ይጨመርበታል። ለሰውነታችን ጠቃሚ የሆኑትን አይረን፣ ዚንክ እና ፕሮቲን በውስጡ እንደሚገኙም ይነገርለታል። የእንቁራሪት ጁስ (ፔሩ) 'ቲቲካካ' ተብለው የሚጠሩት በመጥፋት ላይ የሚገኙት የእንቁራሪት ዝርያዎች ፔሩ ውስጥ ከእንቁላል፣ ማር እና ቅመማቅመሞች ጋር ተፈጭተው እንደ ጁስ ይጠጣሉ። እንቁራሪቶች የተቀላቀሉበት ጁስም ሃይል ሰጪ ከመሆኑ በተጨማሪ እዚህም ጋር ለስንፈተ ወሲብ ጠቃሚ እንደሆነ ይታሰባል። የአይጥ ወይን (ቻይና) ይህንን ተወዳጅ ወይን ለማዘጋጀት አንድ ዓመት ይፈጃል። በመጀመሪያ ሩዝ ከሞቱ የአይጥ ልጆች ጋር ይቀላቀላል። አይጦቹ ጸጉር እንዳእኖራቸው ስለሚፈለግ ገና በቀናት እድሜ ያስቆጠሩ አይጦች ለዚህ ወይን ይመረጣሉ። በቻይናውያን ዘንድ የአይጦች ወይን ለመድሃኒትነት ሲያገለግል፤ የወገብ ህመምን፣ አስም እና የጉበት በሽታዎችን እንደሚፈውስ ይታመናል። የአሳ መራቢያ ፈሳሽ (ሩሲያ) 'ሞሎካ' የምግቡ ስም ሲሆን፤ ዋና ግብአቱ አሳዎች ለመራቢያ የሚጠቀሙት ፈሳሽ ነው። ሩሲያ ውስጥ በየዕለቱ የሚበላና ተቀዳጅ ምግብ ነው።
news-53469917
https://www.bbc.com/amharic/news-53469917
'ፈር ቀዳጅ' ነው የተባለ አዲስ የኮቪድ-19 ህክምና ግኝት ይፋ ተደረገ
የዩናይትድ ኪንግደም ኩባንያ ያከናወነው ክሊኒካል ሙከራ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎችን ለማከመው 'ፈረ ቀዳጅ' ነው ተባለ።
ኩባንያው ባደረገውም ክሊኒካል ሙከራ መሠረት፤ በኮቪድ-19 ተይዘው በሆስፒታል የሚገኙና የኩባንያው የምርምር ውጤት የሆነውን ህክምና የሚያገኙ ታማሚዎች ወደ ጽኑ ሕሙማን ክፍል የመግባት እድላቸውን በከፍተኛ መጠን ይቀንሳል ተብሏል። መቀመጫውን ሳውዝሃምፕተን ያደረገው የባዮቴክ ኩባንያው ሰይንኤርጄን፤ ባካሄዳው በዚህ ሙከራ ላይ ሰውነታችን ኢንፌክሽን ሲያጋጥመው የሚያመርተውን ኢንተርፌርኖ የተሰኘ ፕሮቲን ተጠቀሟል። ፕሮቲኑ የሰዎችን የበሽታ መከላከል አቅምን ከፍ ያደርጋል በሚል በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ፕሮቲኑን ወደ ውስጥ እንዲተነፍሱት በማድረግ ፕሮቲኑ ወደ ሳምባቸው እንዲገባ ተደርጓል። ከክሊኒካል ሙከራው በኋላ የተገኘው ውጤት እንደሚያሳያው፤ በኮቪድ-19 ተይዘው ወደ ሆስፒታል እንዲገቡ ከተደረጉ ሰዎች 79 በመቶው ቬንቲሌተር [የመተንፈሻ መርጃ መሣሪያ] እንዳያስፈልጋቸው አደርጓል ተብሏል። ኩባንያው እንደሚለው ከሆነ አብዛኞቹ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ይህ ህክምና ቢደረግላቸው በህመማቸው ምክያት የዕለት ተዕለት ሥራቸውን ማከናወን ሳያቋርጡ ከበሽታው ሊያገግሙ ይችላሉ። ህክምናውን ያገኙ ሰዎች ላይ "እጅግ ከፍተኛ" በሆነ መልኩ የትንፋሽ ማጠር ምልክት ቀንሶ ታይቷል። ኩባንያው ጨምሮ እንዳለው ህክምናውን ያገኙ ታማሚዎች በሆስፒታል የሚኖራቸው ቆይታም ይቀንሳል። በሆስፒታል ውስጥ በአማካይ 9 ቀናት ይቆዩ የነበሩ ታማሚዎች ህክምና ይህ ህክምና ከተደረገላቸው በኋላ የሚቆዩበት ቀናት ወደ 6 ቀናት ቀንሷል። ክሊኒካል ሙከራው የተካሄደው በዘጠኝ የዩናይትድ ኪንግደም ሆስፒታሎች ውስጥ በሚገኙ 101 በጎ ፍቃደኞች ላይ መሆኑ ተነግሯል። ኩባንያው አገኘሁት ያለው 'ፈር ቀዳጅ' ውጤት በጤና መጽሔቶች ላይ አልታተመም። ቢቢሲ የጥናቱን ሙሉ ውጤት የሚያመላክት መረጃ አልተመለከተም። ኩባንያው ግን ኮሮናቫይረስ የሚስከትለውን ኮቪድ-19 በሽታን ለማከም የምርምር ሥራው አመርቂ ውጤት አስገኝቷል እያለ ነው። በቀጣይ ምን እንጠብቅ? የሲይንኤርጂን ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ሪቻርድ ማርስዲን ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ኩባንያቸው በቀጣይ ቀናት የምርምር ውጤታቸውን ለሚመለከታቸው የአገሪቱ የጤና ኃላፊዎችና ለዓለም አቀፍ የጤና ተቋማት ያጋራል። ከዚያም በክሊኒካል ሙከራው የተገኘው ውጤት ለሰው ልጆች ማከሚያነት እንዲውል እንጠይቃለን ብለዋል። ይህ ህክምና ከጤና ተቋማትና ከመንግሥታት እውቅና የሚያገኝ ከሆነ ህክናው ለታማሚዎች በስፍት መሰጠት ይጀምራል።
news-45248579
https://www.bbc.com/amharic/news-45248579
የውጪ ሀገር ጥሪዎች ለምን በኢትዮጵያ ቁጥር ይወጣሉ?
ለዓመታት ከተለያዩ ሀገሮች ወደ ኢትዮጵያ የሚደወሉ የስልክ ጥሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ ቁጥር እንዲቀየሩ ያደረጉ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች የመታሰራቸው ዜና ይሰማል።
ኢትዮ-ቴሌኮም ማግኘት የሚገባውን ጥቅም ከሚያሳጡ ወንጀሎች መካከል የውጪ ጥሪዎችን በሀገር ውስጥ የስልክ ቁጥር ማስተላለፍ ይገኝበታል። ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች በተንቀሳቃሽ ስልካቸው የሚያዩት የኢትዮጵያ ስልክ ቁጥር ከሆነ ጥሪው የሀገር ውስጥ እንደሆነ ያስባሉ። ሆኖም ጥሪው ከጣልያን ወይም ከከሳዑዲ ሊሆን ይችላል። ቢሆንም ግን በጣልያን ወይም በሳዑዲ ሀገር የኮድ ቁጥር (ኤርያ ኮድ) ሳይሆን በኢትዮጵያ ቁጥር ይታያል። ለመሆኑ የውጪ ሀገር ጥሪዎችን የሀገር ውስጥ ማስመሰል ለምንና በማን ይሰራል? • ኢትዮ-ቴሌኮም፡ አንድ ወደፊት ሁለት ወደኋላ? • ኢትዮ ቴሌኮም... ወዴት? ወዴት? • የስልክዎን ባትሪን ለረዥም ጊዜ ለመጠቀም ቢቢሲ ያናገረው አቶ ተክሊት ኃይላይ ከሶስት ዓመታት በፊት በኢትዮ-ቴሌኮም የክራውድ ማኔጅመንት የአይቲ ባለሙያ ነበረ። አሁን በግሉ የማማከር ስራ የሚሰራው አቶ ተክሊት፤ ቴሌ ሳለ ትራንጉላይዜሽን በሚባል መንገድ የውጪ ሀገር ጥሪን ወደ ሀገር ውስጥ ቁጥር የሚቀይሩ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች ያሉበትን ቦታ ይለይ ነበር። እንዴት የውጪ ሀገር የስልክ ጥሪዎች በኢትዮጵያ ቁጥር እንዲወጡ ይደረጋል? ሲም ቦክስ ክራውድ ይባላል። ከተለያዩ ሀገሮች ወደ ኢትዮጵያ የሚደወሉ የስልክ ጥሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ ቁጥር እንዲቀየሩ ለማድረግ የሚፈልጉ ግለሰቦች ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነው የኢትዮጵያ ሲም ካርድና የኢንተርኔት መስመር ይገዛሉ። በሌላ ወገን "ኢንተርኮኔክት" የተባለ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋሞች ከኢትዮጵያ ውጪ ይገኛሉ። ከያሉበት ሀገር ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉ ጥሪዎች በኢትዮጵያ ቁጥር እንዲታዩ ማድረግ ይችላሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ግለሰቦች ከተቋሞቹ ጋር ስምምነት ላይ ይደርሳሉ። ከዛም ተቋሞቹ የውጪ ሀገር የስልክ ጥሪዎች (ራውቲንግ) ወደ ቴሌ ሳይሆን ግለሰቦቹ ወዳዘጋጁት ሲም ካርድ (አይፒ አድራሻ) አንዲላክ ያደርጋሉ። "እነዚህ ጥሪዎች በቴሌ በኩል መተላላፍ ሲኖርባቸው ግለሰቦቹ ወደገዟቸው ሲም ካርዶች (የስልክ ቁጥሮች) ይሄዳሉ" ሲል ተክሊት ይገልጸዋል። ስልክ የሚደወልላቸው የኢትዮጵያ ነዋሪዎች ምን እየተከናወነ እንደሆነ አያውቁም። በእርግጥ ከኢትዮጵያ ውጪ ያሉ ደዋዮችም ሆነ ሀገር ውስጥ የሚገኙ የጥሪው ተቀባዮች ስለ ሂደቱ አያውቁም። የሚያገኙት ጥቅምም የለም። የስልክ ቁጥሩን መቀየር ለምን አስፈለገ? አንድ ጥሪ ከውጪ ሀገር ወደ ኢትዮጵያ ሲደረግ በደቂቃ ወደ 11 ብር ገደማ ያስከፍላል። በአንጻሩ የሀገር ውስጥ ለሀገር ውስጥ የስልከ ጥሪ በደቂቃ ወደ 75 ሳንቲም ገደማ ያስከፍላል። ግለሰቦቹ በሚጠቀሙበት መንገድ ለውጪ ሀገር ጥሪ 75 ሳንቲም ብቻ በማስከፈል፤ ከ 11 ብር ላይ የቀረውን ገንዘብ ኢንተርኮኔክት ከሚሰሩ ተቋሞች ጋር ይቀራመቱታል። ግለሰቦቹ ጥሪውን ለማስተላለፍ የሚያወጡት የኢንተርኔት ወጪ ብቻ ነው። • በኤሌክትሪክ ኃይል ታሪፍ ላይ ጭማሪ ሊደረግ ነው • አዲስ የሞባይል ቀፎ በኢትዮ ቴሌኮም ኔትዎርክ ላይ ለማሰመዝገብ ማወቅ ያለብዎት በኢትዮጵያ ህግ መሰረት የግለሰቦቹ ተግባር ህገ ወጥ ቢሆንም፤ ሂደቱን ህጋዊ አድርገው የሚገለገሉበት ሀገሮች ብዙ ናቸው። አቶ ተክሊት እንደምሳሌ የሚጠቅሰው የሳዑዲ ቴሌኮምን ነው። የሳዑዲ ቴሌኮም የአለም አቀፍ ጥሪ ወጪ ለመቀነስ ሲም ቦክስ ክራውድን በይፋ ይጠቀማል ይላል። በብዙ ሀገሮች ሲም ቦክስ ክራውድ መጠቀም ህጋዊ ስለሆነ ጥሪው የሚደረግባቸው ሀገሮች መንግሥታትን በህግ መጠየቅ አይቻልም። ግለሰቦቹ ከውጪ ተቋማት ጋር የሚቀራመቱትን ገንዘብ ማግኘት የነበረበትን ቴሌ እንደሆነ የሚያስረግጠው ባለሙያው "ሂደቱ ህጋዊ ቢሆን ኖሮ ቴሌ ይጠቀም ነበር" ይላል። መፍትሔው ምንድን ነው? አቶ ተክሊት እንደሚለው ከተለያዩ ሀገሮች ወደ ኢትዮጵያ የሚደወሉ የስልክ ጥሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ ቁጥር እንዲቀየሩ የሚያደጉት ግለሰቦች ወይም ቡድኖች በብዛት የሚሰሩት አዲስ አበባ፣ መተማና ሞያሌ ነው። የስልክ ጥሪዎቹ በዋነኛነት የሚነሱባቸው ሀገሮች ደግሞ ቻይና፣ ጣልያንና ሳዑዲ ናቸው። ከተለያዩ ሀገሮች ወደ ኢትዮጵያ የሚደወሉ የስልክ ጥሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ ቁጥር እንዲቀየሩ የማድረጉ ሰዎች በተደጋጋሚ ቢታሰሩም ብዙም ሳይቆይ ሌላ ቡድን ስራውን ይጀምራል። "ቴሌ በምሰራበት ወቅት ተቋሙ በየወሩ ወደ ሶስት ሚሊየን ዶላር ያጣ ነበር" ይላል። ባለሙያው እንደሚለው አሰራሩ ሀጋዊ ቢሆን የውጪ ተቋማት ከግለሰቦች ጋር ሳይሆን በቀጥታ ከቴሌ ጋር መደራደር ይችላሉ። ግለሰቦቹ በህገ ወጥ መንገድ የሚያገኙት ጥቅምም የተቋሙ ይሆናል።
48523528
https://www.bbc.com/amharic/48523528
የሱዳን ተቃውሞ፡ የሟቾች ቁጥር 100 መድረሱን ተቃዋሚዎች እያስታወቁ ነው
በሱዳን የተቃውሞ ሰልፉን የሚመሩ አክቲቪስቶች በዋና ከተማዋ ካርቱም በወታደሮች የተገደሉ ሰልፈኞች አስክሬን ከናይል ወንዝ ውስጥ እየወጣ መሆኑን ተናግረዋል።
የሱዳን ደኀንነት ኃይሎች በዋና ከተማዋ ካርቱምና በጦር ኃይሉ ዋና መሥሪያ ቤት ተሰማርተዋል ዛሬ ማለዳ የተቃዋሚ ዶክተሮች ስብስብ የሆነ አንድ ማሕበር በሱዳን ተቃውሞ የሞቱ ሰዎቸ ቁጥር 60 መድረሱን አስታውቆ ነበር። ከሰኞ እለት ጀምሮ በወታደሮች የተገደሉ ተቃዋሚ ሰልፈኞች አንድ መቶ መድረሱ የተዘገበው ዛሬ ከሰአት በኋላ ነው። የሚሊሻ አባላቱ ንፁሐንን በመግደል ተጠርጥረዋል። ከሰኞ ጀምሮ ተቃውሞ እንደ አዲስ የበረታባት ካርቱም የሰላም እንቅልፍ ሳታሸልብ ሁለት ቀን ኦልፏታል። ጊዜያዊው ወታደራዊ መንግሥት ሥልጣን ለሲቪል ያስረክብ ያሉ ተቃዋሚዎች ጋር ግጭት ውስጥ የገባው ነውጠኛው የሚሊሻ ቡድን የሰው ሕይወት አጥፍቷል ሲሉ ተቃዋሚዎች ይወነጅላሉ። የወታደራዊ ኃይል ቡድኑ ዓለም አቀፍ ጫና የበረታበት ይመስላል። እንግሊዝ እና ጀርመን የተባበሩት መንግሥታት ወታደራዊው ጊዜያዊ መንግሥት መፍትሄ ያበጅ ዘንድ ተማፅነዋል፤ ቻይና እና ሩስያ በሱዳን ጉዳይ እያሤሩ ነው ሲሉም ወቅሰዋል። • የሰሀራ በረሐን በክራች ያቋረጡት ስደተኞች • በደቡብ ሱዳን የምሽት ክለቦች ታገዱ የሱዳን መከላከያ ኃይል ዋና መሥሪያ ቤት ደጃፍ ሲደረግ የነበረው የመቀመጥ አድማ ለወራት የዘለቀ ቢሆንም ዕለተ ሰኞ የሆነው ግን ተቃዋሚዎች ያልጠበቁት ነበር። የሱዳን ልዩ ኃይል በአስለቃሽ ጋዝ በመታገዝ ሰልፈኞችን ይበታትን ያዘ። ሱዳናውያን በአል-ባሽር ዘመን ጃንጃዊድ በሚል ስያሜ የሚታወቀው ልዩ ኃይሉ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የተጠና እርምጃ ወስዷል ሲሉ ይከሳሉ። ጊዜያዊው ወታደራዊ አገዛዝ በዘጠኝ ወራት ጊዜ ውስጥ ምርጫ ይካሄዳል የሚል መግለጫ ቢያወጣም ሱዳናውያን የአል-በሽር ሽታ ያልለቀቃቸውን ሰዎች ለማፅዳት ረዘም ያለ ጊዜ ያሻል ሲሉ ይሞግታሉ። ወታደራዊው መንግሥት እና የነፃነትና የለውጥ ኃይል የተሰኘው ተቃዋሚ ቡድን ደርሰውት የነበረውን ስምምነት ጊዜያዊው አስተዳደር አፍርሶታል ይላል የቢቢሲ አፍሪቃው ተንታኝ ፈርጋል ኪን። •አሜሪካ፡ የመድኃኒት ዋጋ ሰማይ የደረሰባት ሃገር አክሎም ወታደራዊው መንግሥት ከዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ብርቱ ጫና እየደረሰበት አይደለም ባይ ነው ተንታኙ። በዚህ የክፍፍል ዘመን ጫና ሁሉም ተባብረው ጫና ያደርሳሉ ማለት ዘበት ነው ይላል ኪን። ወጣም ወረደ ሱዳናውያን የረመዳን ፆምን ከሚቃጠል ጎማ በሚወጣ ጭሥ ታጅበው፤ ሠላም እንደራቃቸው አሳልፈዋል፤ ፆሙንም የፈቱት አደባባይ ላይ ሆነው ነው። ማሕበራዊ ድር አምባዎች ላይ የሚለቀቁ ምስሎች የሱዳን ወታደሮች መንገዶችን እንደተቆጣጠሩት የሚያሳዩ ናቸው። ጥርስ አልባ እንበሳ እየተባለ የሚታማው የተመባበሩት መንግሥታት ወታደራዊው መንግሥት መፍትሄ እንዲያበጅ ከመማፀን ወደኋላ አላለም። • በተቃውሞ እየተናጠች ባለችው ሱዳን ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ ቀረበ
news-41857302
https://www.bbc.com/amharic/news-41857302
የትራምፕ ትዊተር ገጽ በኩባንያው ሠራተኛ ተዘጋ
የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የትዊተር ገጽ ዕለተ ሃሙስ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ከተዘጋ በኋላ እንዲከፈት መደረጉን ትዊተር አስታውቋል።
የትራምፕን የትዊተር ገጽ ተዘግቶ በቆየባቸው ደቂቃዎች ተጠቃሚዎች ማየት የቻሉት "Sorry, that page doesn't exist!" (ይቅርታ ገጹ አልተገኘም) የሚለውን መልዕክት ብቻ ነበር። ትዊተር ማንነቱን ያልገለፀው ሠራተኛ የዶናልድ ትራምፕን የትዊተር ገጽ @realdonaldtrump እንዲዘጋ ወይም ከጥቅም ውጭ እንዲሆን በማድረጉ ሠራተኛውም በኩባንያው የመጨረሻው ቀን ነው ብለዋል። የትራምፕ ትዊተር ገጽ ለ11 ደቂቃዎች ያህል ነው ተዘግቶ የቆየው። ከ41 ሚሊየን በላይ ተከታዮች ያላቸው ትራምፕ በአውሮፓውያኑ 2009 ጀምሮ ከ36,000 በላይ ሃሳቦችን ገፃቸው ላይ አስፍረዋል። 'የሠራተኛው የመጨረሻ ቀን' ትዊተር "ጉዳዩን እያጣራሁ ነው። ይህ ዓይነት ክስተት በድጋሚ እንዳይከሰት የተለያዩ እርምጃዎችን እንወስዳለን" ሲል አስታውቋል። ''ባደረግነው ማጣራት የትራምፕ ገጽ የተዘጋው በደንበኞች ድጋፍ አገልግሎት ሰጪ ሠራተኛችን መሆኑን ደርሰንበታል። ይህም ለሠራተኛው የመጨረሻው ቀን ነው'' ብሏል ትዊተር። ዶናልድ ትራምፕ የትዊተር ገጻቸው እንደገና እንዲሠራ ከተደረገ በኋላ የመጀመሪያው ትዊታቸው ስለ ሪፓፕሊካኖች የግብር ቅነሳ በተመለከተ ነበር። ትራምፕ ፕሬዝዳንት ከመሆናቸው በፊት እና የፕሬዝዳንትነት ሥልጣንን ከተረከቡ በኋላ ትዊተርን አብዝቶ በመጠቀም ፖሊሲዎቻችውን ከማስተዋወቅ አልፎ ለፖለቲካ ተፎካካሪዎቻቸው ምላሽም ይሰጡበታል።
49969270
https://www.bbc.com/amharic/49969270
የጨለቆት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የተዘረፈው ዘውድ ይመለስልኝ እያለች ነው
ከሰሞኑ ለ21 ዓመታት ተደብቆ የኖረ ዘውድ በኔዘርላንድስ መገኘቱ አነጋጋሪ ጉዳይ ሆኖ ነበር።
ለ41 ዓመታት በኔዘርላንድ የኖሩት አቶ ሲራክ አስፋው ዘውዱ ቤታቸው የገባው በአጋጣሚ እንደሆነ ይናገራሉ ለ41 ዓመታት በኔዘርላንድ የኖሩት አቶ ሲራክ አስፋው ዘውዱ ቤታቸው የገባው በአጋጣሚ እንደሆነ ይናገራሉ። የጥገኝነት ጥያቄና ሌላም ጉዳያቸው ተጠናቆ ወደ ሌላ ቦታ እስኪሄዱ ድረስ የግል ሰነዶቻቸውን ጨምሮ ሌሎችም እቃዎች አቶ ሲራክ ቤት በአደራ የሚያስቀምጡ ሰዎች ነበሩ። ከአራት መቶ ዓመታት በላይ እድሜ ያለውን የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርስ አቶ ሲራክ ቤት ይመላለሱ ከነበሩ ሰዎች አንዱ ትተውት እንደሄዱም ይናገራሉ። ሥላሴ ጨለቆት ቤተ ክርስቲያን ዘውዱ የማን ነው? መቼ የነበረ ዘውድ ነው? የሚሉ ጥያቄዎች ተፈጥረዋል። አንዳንዶች በላሊበላ እንዲሁም በፋሲለደስ ወቅት የነበረ ነው ቢሉም፤ ኒው ዮርክ ታይምስ ያናገረው በኢትዮጵያ ቅርሶች ላይ ከፍተኛ ጥናት ያደረገው ጃኮፖ ጊንስቺ፤ ዘውዱ ከሥላሴ ጨለቆት ቤተ ክርስቲያን በ1990ዎቹ የተሰረቀ ሊሆን እንደሚችል ተናግሯል። • ለ21 ዓመታት የኢትዮጵያን ቅርስ ደብቀው ያቆዩት ኢትዮጵያዊ • አደጋ የተጋረጠበት የአፄ ፋሲለደስ ቤተ መንግሥት በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪ የሆነው ጃኮፓ እንደሚለው፤ ዘውዱ ከመጥፋቱ በፊት በ1980ዎቹ መጨረሻ ላይ አንድ የቤተ ክርስቲያን ቄስ ዘውዱን ራሳቸው ላይ ጭነው ፎቶ ተነስተዋል። ዘውዱ በአይነቱ የተለየ እንደሆነ የሚናገረው ተመራማሪው፤ ዋጋውንም 55 ሺህ ዶላር አድርሶታል። ከመቐለ 16 ኪሎ ሜትር በደቡብ ምሥራቅ አቅጣጫ የሚገኘውና ረዥም ዕድሜ ያስቆጠረው የሥላሴ ጨለቆት ቤተ ክርስትያን ውስጥ በርካታ ንዋየ ቅድሳት እንዳሉ ይነገራል። በተለይም ራስ ወልደሥላሴ ለቤተ ክርስትያኑ እልፍ ንዋየ ቅዱሳን ማበርከታቸውን ቤተ ክርስትያኑ ግቢ ውስጥ ለዓመታት የኖሩ አባቶች ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ። ለአሥራ ስድስት ዓመታት መንነው በቤተ ክርስቲያኗ የሚኖሩት የ82 ዓመቱ የዕድሜ ባለፀጋ አባ ገብረሥላሴ ለአሥራ ስድስት ዓመታት መንነው በቤተ ክርስቲያኗ የሚኖሩት የ82 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ አባ ገብረሥላሴ፤ ሦስት ዘውዶችን ራስ ወልደሥላሴ ለቤተ ክርስቲያኗ መስጠታቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል። በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር ከ1745-1865 በወቅቱ የእንደርታ ዙሪያ የሚባለውን ሰፊ ግዛት ያስተዳደሩት ራስ ወልደሥላሴ በአራት ቦታዎች ማለትም በጨለቆት፣ በአንጣሎ፣ በፈለግዳሮና በመቐለ ቤተ መንግሥቶችን ገንብተው ነበር። በአንድ ወቅትም ጨለቆትን ዋና ከተማቸው አድርገዋታል። • ከላሊባላ ጥገና ጀርባ ያለው ማን ነው ? • "የዘረፉትን ቅርስ በውሰት እንመልስ ማለታቸው ተገቢ አይደለም" ሚኒስትር ሂሩት ካሳው ራስ ወልደሥላሴ ካበረከቷቸው ዘውዶች መካከል አሁን በኔዘርላንድ የተገኘው ዘውድ አንዱ ሲሆን፤ ከ24 ዓመታት በፊት መሰረቁንና ከዚያም መሰወሩን ተናግረዋል። ዘውዱን በመስረቅ የተጠረጠረው የቤተ ክርስቲያኑ አቃቤ ነዋይ (ጠባቂ)፤ ከአምስት ዓመታት እስር በኋላ ቅርሱ ሳይገኝ መለቀቁን ገልፀው "መንግሥት ኃላፊነቱን አልተወጣም" በማለት የትግራይ አስተዳደር ላይ ቅሬታቸውን ያሰማሉ። ከሰሞኑ የዘውዱን መገኘት ዜና የሰሙት አባ ገብረሥላሴ፤ ምንም እንኳን ጥልቅ ደስታቸውን ቢገልፁም "እንዴት ተወሰዶ፣ እንዴትስ ነው እየተመለሰ ያለው የሚል ጥያቄ በውል መመለስ ይኖትበታል" ሲሉ አበክረው ይጠይቃሉ። ከኢትዮጵያ ተሰርቆ የተወሰደ አንድ ዘውድ ኔዘርላንድ ውስጥ መገኘቱንና በቅርቡ ወደ አገሩ እንደሚመለስ የሰማው የአከባቢው ማኅበረሰብ ዘውዱ የሥላሴ ጨለቆት ስለመሆኑ ቅንጣት ታህል አይጠራጠርም። ለ41 ዓመታት በኔዘርላንድ የኖሩት አቶ ሲራክ አስፋው ቄስ ንጉሠኃጎስ ላለፉት ሦስት ዓመታት የቤተ ክርስትያኑ ዓቃቤ ነዋይ በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ። "ሥላሴ ጨለቆት ውስጥ ሦስት ዘውድ ነበር። የተሰረቀው አንድ ነው። ሦስቱም የወርቅ ቅብ ሳይሆኑ ከተጣራ ወርቅ የተሠሩ ናቸው። የጠፋው ዘውድ ከወርቅ መሠራቱን ለማወቅ ያሉትን አይቶ ማረጋገጥ ይቻላል" ሲሉ ስለ ነዋየ ቅድሳኑ ጥራት ይመሰክራሉ። ሌላው የመቐለ ከተማ ኗሪ አቶ ብስራት መስፍን፤ በ1987 ዓ. ም. (ከ24 ዓመታት በፊት) የቀይ መስቀል ሠራተኛ በመሆን ወደ ትግራይ ከመጣው እንግሊዛዊ ዴቪድ ስቴብልስ ጋር ይተዋወቃል። አቶ ብስራት መስፍን እና አሁን በሕይወት የሌለው አቶ ክንዴ ተፈራ ዴቪድ ብስራትን ይዞ አካባቢውን ለማስጎብኘት ወደ ሥላሴ ጨለቆት ይሄዳል። ብስራት ቤተ ክርስትያኑን መጎብኘቱንና እዛው ከነበሩት ዘውድና የወርቅ ፅዋ ጋር ፎቶ መነሳቱን ያስታውሳል። ፎቶውን ያነሳው ዴቪድ ነው። "ዘውዱ መሰረቁን ሰምቼ ስለነበረ ሰሞኑን ዳግም መገኙቱን ስሰማ ያንን ፎቶ ስፈልግ ነበር ያደርኩት። መጨረሻ ላይ ተሳክቶልኛል" ሲል በፎቶ የተደገፈ ማስረጃ ይዞ ቀርቧል። ፎቶው ላይ ያኔ የዴቪድ ሹፌር የነበረና አሁን በሕይወት የሌለው አቶ ክንዴ ተፈራ ጋር የተነሱት ምስል ይታያል። አቶ ብስራት መስፍን በአሁኑ ሰዓት ራሱ ያቋቋመውን 'ትምህርታዊ ድጋፍ ለኢትዮጵያውያን ወጣቶች' የተሰኘውን ምግባረ ሰናይ ድርጅት ይመራል። የዘውዱ መገኘት ከተሰማ በኃላ ከዴቪድ ጋር በኢንተርኔት መፃፃፉንም ይጠቅሳል። • የሠላም ተጓዧ ሉሲ (ድንቅነሽ) ምን ደረሰች? • ሲዳማዎች 2011ን ቀድመው ጀመሩ "ወደ ሥላሴ ጨለቆት በሄድንበት ወቅት ከዘውድ በተጨማሪ ወርቃማ ዋንጫ እንዲሁም ስድስት በወርቅ የተዋበ መጽሐፍ ቅዱስ አይተናል። የሚያሳዝነው ግን በጣም ጥቂቶች ብቻ የሚያውቁት በጣም ብዙ ታሪክ ነው ያላችሁ" ይላል። አቶ ብስራት መስፍን እና አሁን በሕይወት የሌለው አቶ ክንዴ ተፈራ በሌላ በኩል የዘውዱን መገኘት በሚመለከት የትግራይ የባህልና ቱሪዝም ቢሮም መግለጫ ሰጥቷል። የቢሮው ኃላፊት ወ/ሮ ብርኽቲ ገብረመድህን ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ጉዳዩን በቅርብ ርቀት እየተከታተሉት እንደሚገኙ ተናግረዋል። "ምን ዓይነት ቅርስ ነበር የጠፋው? ምን ያህል ሕጋዊ ማስረጃስ ይኖራል? አሁን ተገኝቷል የተባለው ቅርስስ ምን ይመስላል? የሚለውን በሚገባ አጥንተን ሕጋዊነት ባለው መንገድ ለመሄድ እየሠራን ነው" ሲሉ አስረድተዋል። ቢሮው ከሚመለከተው የፌደራል መንግሥታዊ አካል ጋርም በስልክ ተገናኝቶ ስለ ጉዳዩ በዝርዝር መወያየቱን አሳውቋል። "የሚመለከተው አካል ስለ ጉዳዩ መረጃ ማግኘቱንና እየተከታተለው እንደሚገኝ ገልጾልናል" ብለዋል ወ/ሮ ብርኽቲ። ዘውዱ ወደ አገር ቤት ከገባ በኃላ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደሚረከበውና እንዴትና የት ይቀመጣል የሚል ራሱን የቻለ ሕጋዊ አሠራር እንዳለው ለመረዳት ተችሏል።
news-52230764
https://www.bbc.com/amharic/news-52230764
ኮሮና ቫይረስ፡ የዓለም ባንክ ከሰሃራ በታች የሚገኙ አገራት ኢኮኖሚያዊ ድቀት እንደሚያጋጥማቸው ተነበየ
የዓለም ባንክ ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገራት ከግማሽ ምዕተዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮቪድ-19 ምክንያት የኢኮኖሚ ድቀት ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ተነበየ።
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም የአህጉሪቱ ምጣኔ ሃብት በዚህ ዓመት ብቻ በ2.1 በመቶ የሚጎዳ ሲሆን ይህ ጉዳት እስከ 5.1 ድረስ ሊደርስ ይችላል ብሏል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በ52 የአፍሪካ አገሮች የተከሰተ ሲሆን እስካሁን ድረስ በመላ አህጉሪቱ 10,250 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎችም ቁጥርም 492 ደርሷል። የዓለም ባንክና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ፈንድ አበዳሪ አገራት ለአፍሪካ እዳቸውን ለተወሰነ ጊዜ እንዲያራዝሙ እና አገራት ያላቸው ገንዘብ ወደ ሕይወት ማዳንና ኑሮን ማሻሻል ላይ ማዋል እንዲችሉ ጥሪ አቅርበዋል። አፍሪካ በኮቪድ-19 ከተጠቁ አህጉራት የመጨረሻዋ ስትሆን፣ አገራት ድንበራቸውን መዝጋት፣ ዜጎቻቸው ከቤት ውጪ እንዳይንቀሳቀሱ ማድረግ፣ መንገደኞችን በለይቶ ማቆያ ማስቀመጥ ርምጃዎችን የወሰዱት በፍጥነት ነበር። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የመጀመሪያው ጉዳት ንግድን ማስተጓጎል ነበር። የዓለም ባንክ እንደሚለው ከሆነ የግብርና ምርቶች አቅርቦት መቀነስ፣ የአቅርቦት መስተጓጎል፣ እና የሕይወት መጥፋት ወደ ምግብ እጥረት ሊመራ ይችላል። በአፍሪካ በምጣኔ ሃብታቸው ግዙፍ የሆኑት ናይጄሪያና አንጎላ በወረርሽኙ ምክንያት የነዳጅ ዋጋ መውረድ ምጣኔ ሃብታቸው ክፉኛ ከተጎዳ አገራት መካከል ይገኙበታል። ደቡብ አፍሪካም ብትሆን የማዕድን ገቢዋ አሽቆልቁሏል። • በኮሮናቫይረስ ከተያዙት ኢትዮጵያዊያን ሦስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው ከኢትዮጵያና ኬንያ የሚላኩ የግብርና ምርቶች ሁሉም ተዘግተዋል። ከባህርማዶ ወደ አገር ውስጥ ይደረግ የነበረው የጎብኚዎች ፍሰት፣ የሚላክ የውጪ ምንዛሪ፣ እንዲሁም የቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ቆሟል። በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የበረሃ አንበጣ ወረርሽኝ፣ የእርስ በእርስ ግጭት፣ እንዲሁም በደቡባዊ አፍሪካ ያለው ድርቅ በአፍሪካ ያለውን ችግር ተደራራቢ አድርጎታል። የዓለም ባንክ ብድር መክፈል ለተወሰነ ጊዜ እንዲቆም የሚል ምክረ ሃሳብ ያቀረበ ሲሆን፣ ይህም በዓመት ለብድር ክፍያ የሚውለውን ወደ 35 ቢሊየን ዶላር እንዲሁም ለወለድ ክፍያ የሚውለውን 44 ቢሊየን ዶላር ነፃ ያደርጋል ተብሏል። ድርጅቱ አክሎም የአፍሪካ አገራት ለድሃ ዜጎቻቸው ምግብ እንዲያከፋፍሉ፣ መሰረታዊ ግልጋሎቶች ላይ የተጣሉ ክፍያዎችን እንዲያነሱ መክሯል።
news-53536340
https://www.bbc.com/amharic/news-53536340
በቺካጎ ሁለት የክርስቶፈር ኮለምበስ ሃውልቶች ተነሱ
በአሜሪካዋ ቺካጎ ከተማ ቆመው የነበሩት ሁለት የክርስቶፈር ኮሎምበስ ሃውልቶች በጊዜያዊነት እንዲነሱ ተደረጉ።
ለሳምንታት ዘልቆ በነበረው የተቃውሞ ስለፍ ላይ ሰልፈኞች የጣሊያናዊውን አሳሽ ሃውልት ለማፍረስ ሙከራ ሲያደርጉ ነበር። ሃውልቶቹ ቆመው ከሚገኙበት ስፍራ የሚነሱት በጊዜያዊነት ነው ቢባልም፤ በሰዎች ቆዳ ቀለም ምክንያት አድልዎ ፈጽመዋል ተብለው ሃውልቶቻቸው እንዲነሱ ከተደረጉት መካከል የክርስቶፈር ኮለምበስ ሃውልት ተካቷል። የጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ ግድያ በአሜሪካ እና በመላው ዓለም በፖሊስ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ለማስቆም እና በጥቁር እና ነጭ ሰዎች መካከል እኩልነት እንዲሰፍን የተቃውሞ ስለፎች ተቀጣጥለው ነበር። በኢሊኖይስ ግዛት የምትገኘው የቺካጎ ከተማ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ በግራንት እና አሪጎ ፓርክ ውስጥ የሚገኙት የክርስቶፈር ኮሎምበስ ሃውልቶች “በጊዜያዊነት . . . ላልተወሰነ ጊዜ ተነስተዋል” ብሏል። ባሳለፍነው ሳምንት ለተቃውሞ የወጡ ሰዎች በግራት ፓርክ የሚገኘውን ሃውልት ለማፍረስ ጥረት ሲያደርጉ ከፖሊስ ጋር ተጋጭተው ነበር። የቺካጎ ነዋሪዋ ብሬንዳ አረሜንታ የኮሎምበስ ሃውልት እየተነሳ ባለበት ወቅት “ሃውልቱ ሲወርድ መመልከት ሃሴት ይሰጣል” ስትል ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል ተናግራለች። ሃውልቱ እንዲነሳ የሚፈልጉ ተቃዋሚዎች እንዳሉ ሁሉ ሃውልቶቹ የታሪካችን አካል ናቸው በማለት፤ በሃውልቶቹ ላይ የሚደርሰውን ጉዳት አጥብቀው የሚያጥላሉ አሜሪካውያን አልጠፉም። የኮሎምበስ ሃውልቶች ከመፍረሳቸው በፊት በደጋፊ እና ተቃዋሚዎች መካከል የጋል አለመግባባት ተፈጥሮ ነበር። በቦስተን የነበረው የኮሎምበስ ሃውልት አንገቱ ተቆርጦ ተጥሏል። ባሳለፍነው ወር 3 ሜትር ርዝመት የነበረው እና በሴንት ፖል ሚኒሶታ ግዛት ቆሞ የነበረው የኮለምበስ ሃውልት በተቃዋሚዎች እንዲወድቅ ተደርጎ ነበር። በቦስተን የነበረው የኮሎምበስ ሃውልት ደግሞ አንገቱ ተቆርጦ ተጥሏል። አሳሹ ክርሰቶፈር ኮለምበስ በ15ኛው ክፍለ ዘመን “አዲሲቷን ዓለም” ያገኘ አሳሽ ሲባል በትምህርት መጻሕፍት ጭምር ይወዳሳል። በሌላ በኩል የኮለምበስ ተቺዎች እና ቀደምት የአሜሪካ ነዋሪዎች፤ የኮለምበስ ወደ አሜሪካ መምጣት ቅኝ ግዛትን ያስፋፋ እና የዘር ፍጭት ያስከተለ ነው በማለት ይኮንኑታል።
news-56228216
https://www.bbc.com/amharic/news-56228216
ኮሮናቫይረስ ፡ አንድ ጊዜ ብቻ የሚሰጠው የኮቪድ-19 ክትባት አሜሪካ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዲውል ተፈቀደ
የዩናይትድ ስቴትስ መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣናት አንድ ጊዜ ብቻ የሚሰጠውን ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የተሰኘው የኮቪድ-19 ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቃድ ሰጡ።
ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የተሰኘው የኮቪድ-19 ክትባት ክትባቱ ፋይዘርና ሞደርና ከተሰኙት ሌሎች ክትባቶች ጋር ሲነፃፀር ዋጋው አነስተኛ ነው ተብሏል። አልፎም እንደ ሌሎቹ ክትባቶች ፍሪጅ ውስጥ እንጂ ፍሪዘር [በረዶ የሚሰራ ከፍተኛ ቅዝቃዜ ያለበት] ውስጥ ማስቀመጥ አያስፈልገውም ተብሏል። ሙከራዎች እንደሚያመለክቱት ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት ሰዎች በጣም እንዳይታመሙ ይረዳል፤ ነገር ግን አነስተኛ ሕመም ባላቸው ላይ ያለው ውጤታማነት 66 በመቶ ነው። ክትባቱ በቤልጂየሙ ኩባንያ ያንሰን የተመረተ ነው። ኩባንያ በሚቀጥለው ሰኔ ወር መጨረሻ 100 ሚሊዮን ብልቃጦች አምርቶ ለአሜሪካ ለመስጠት ቃል ገብቷል። ቢሆንም ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ክትባቱ አሜሪካ ውስጥ መታደል እንደሚጀምር ታውቋል። ዩናይትድ ኪንግደም፣ አውሮፓ ሕብረት እንዲሁም ካናዳ ከክትባቱ እንዲደርሳቸው ያዘዙ ሲሆን 500 ሚሊዮን ብልቃጦች ደግሞ ኮቫክስ በተሰኘው ፕሮግራም መሠረት የመግዛት አቅም ለሌላቸው ሃገራት ይከፋፈላሉ። ፕሬዝደንት ጆ ባይደን "ይህ ለአሜሪካዊያን አስደሳች ዜና ነው፤ ዕድገትም የታየበት ነው" ብለዋል። "ምንም እንኳ የዛሬውን ዜና በደስታ ብንቀበለውም ሁሉም አሜሪካዊያን እጃቸውን እንዲታጠቡ፣ ርቀታቸውን እንዲጠብቁና የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ እንዲቀጥሉ ማሳሳብ እወዳለሁ" ብለዋል በመግለጫቸው። ገለልተኛ የሆኑ ሙያተኞች ክትባቱን ካፀደቁት በኋላ ነው የአሜሪካ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ለክትባቱ ፈቃድ የሰጠው። ዩናይትድ ስቴትስ፣ ደቡብ አፍሪካና ብራዚል ውስጥ የተሠሩ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ክትባቱ ጠንከር ያለ ሕመምን በመከላከል ረገድ 85 በመቶ ውጤታማ ነው። መካከለኛ ደረጃ የሚባለውን ሕመም በመከላከል ደግሞ 66 በመቶ ውጤታማነትን አሳይቷል። ጥናቱ ላይ የተሳተፉ ሰዎች ለ28 ቀናት ክትትል የተረገባቸው ሲሆን አንድም ሰው አልሞተም በጎንዮሽ ጉዳት ምክንያት ወደ ሆስፒታል አልተወሰደም። ነገር ግን አዳዲስ የኮቪድ-19 ዝርያዎች የታዩባቸው ብራዚልና ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የክትባቱ መከላከል አቅም ዝቅ ያለ ቢሆንም ከባድ ሕመምን በመከላከል ግን እመርታ አሳይቷል። ደቡብ አፍሪካ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ፈቃድ ከማግኘቱ በፊት በጥናት መልክ የጤና ሙያተኞች እንዲወስዱት ማድረግ ጀምራ ነበር። ኦክስፎርድ-አስትራዜኔካ የተሰኘው ክትባት በአዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ላይ ያለው ውጤታማነት ዝቅተኛ ነው መባሉን ተከትሎ ነው ደቡብ አፍሪካ ወደ አዲሱ ክትባት ያመራችው። ክትባቱ አንድ ጊዜ ብቻ የሚሰጥ ስለሆነ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲሁም በአነስተኛ የጤና ሙያተኞች መስጠት ይቻላል። ዩናይትድ ኪንግደም 30 ሚሊዮን ክትባት እንዲደርሳት ትዕዛዝ ሰጥታለች፤ የአውሮፓ ሕብረት ደግሞ 200 ሚሊዮን። ካናዳ ከጆንሰን ኤንድ ጆንሰን 38 ሚሊዮን ክትባት እንደሚደርሳት ተሰምቷል፤ ኮቫክስ የተሰኘው ፕሮግራም ደግሞ ግማሽ ቢሊዮን ብልቃጥ ክትባት ይደርሰዋል። አሜሪካ ውስጥ እስካሁን ድረስ ከ78 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ክትባት አግኝተዋል። ይህ በቀን ሲሰላ አንድ 1.3 ሚሊዮን ማለት ነው። ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በመጀመሪያዎቹ 100 ቀናት 100 ሚሊዮን ሰዎች ለማስከተብ ቃል ገብተዋል። አሜሪካ በኮቪድ-19 ምክንያት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎች አጥታለች። ነገር ግን አዳዲስ የሚያዙ ሰዎች፣ ወደ ሆስፒታል የሚገቡ ሰዎች ቁጥርና ሞት እየቀነሰ ነው። የጤና ባለሙያዎች ግን ጥንቃቄ ከሌለ ቫይረሱ እንደ አዲስ ሊያገረሽ ይችላል ይላሉ።
news-48013883
https://www.bbc.com/amharic/news-48013883
ኢትዮጵያ፡ ሲራክ ስዩም የዓለማችን ትልቁን ተራራ መውጣት ጀመረ
ነዋሪነቱን በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ያደረገውና የኤሌክትሪካል ምህንድስና ባለሙያው ሲራክ ስዩም ከበርካታ ልምምድ በኋላ የዓለማችን ትልቁን ተራራ፤ ኤቨረስትን ዛሬ ሚያዚያ 15/2011 ዓ.ም መውጣት እንደጀመረ ለቢቢሲ ገለፀ።
• በረዷማ ተራራ ላይ ለ7 ቀናት ጠፍቶ የነበረው በህይወት ተገኘ ሲራክ እንደሚለው ተራራውን በመውጣት ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ነው። "የኔፓል የቱሪዝም ኮሚሽን ማን ተራራ እንደወጣ፣ ማን እንደሞከረ፣ ማን ድጋሜ እንደወጣ የሚመዘግቡበት መዝገብ አላቸው፤ መዝገቡ ከአውሮፓውያኑ አቆጣጠር 1937 ጀምሮ የወጡ ሰዎች ስም ዝርዝር ሰፍሮበታል፤ በመሆኑም እስካሁን ብቸኛው ኢትዮጵያዊ እንደሆንኩ ነው የማውቀው" ሲል የመጀመሪያው ስለመሆኑ ያስረዳል። በርካቶች ሲያዩትም የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ በመሆኑ ፎቶ ለመነሳት ይሽቀዳደማሉ ብሎናል። ተራራ መውጣት የረዥም ጊዜ ህልሙ የነበረ ሲሆን፤ ከዛሬ 10 ዓመት በፊት ይህንኑ ተራራ ለመውጣት እቅድ እንደያዘ አሳውቆ ነበር። አንድም በቂ ልምምድ ማድረግ እንዳለበት ልምድ ካላቸው ሰዎች ስለተነገረው፤ ሁለትም ያለው የገንዘብ አቅም ወጭውን የሚሸፍን ሆኖ ስላላገኘው፤ በሌላም በኩል በአባቱ ሕልፈት ምክንያት ከባድ ሃዘን ውስጥ ስለነበር ህልሙን ሳያሳካው ቆይቷል። "በጣም ደስ የሚል መጽሐፍ አንብበን ስንጨርስ፤ ሌላ ማንበብ እንደሚያሰኘን ሁሉ፤ ተራራ መውጣትም እንደዚያው ነው" የሚለው ሲራክ፤ በኢኳዶር የሚገኘውን ቺምፖራዞን ተራራ ከወጣ በኋላ ተራራ የመውጣት ፍቅር እንዳደረበት ይናገራል። • ባሕልና ተፈጥሮን ያጣመረው ዞማ ቤተ መዘክር እዚህ ላይ የእውቋን ፈረንሳዊት ተራራ ወጪ ኤልሳቤት ሮቨርን ተሞክሮ ያነሳል። እሱ እንደሚለው ፈረንሳዊቷ ከዚህ ቀደም ከጓደኛዋ ጋር ሆና ይህንኑ ተራራ ሲወጡ የጓደኛዋ ሕይወት አልፏል። እሷ ደግሞ በበረዶው ምክንያት የአይን ጉዳት አጋጥሟታል። ይሁን እንጂ አሁንም ተመልሳ ለመውጣት ከእነሱ ጋር ተገኝታለች- ልክ እንዲህ ነው ሱስ የሚያሲዘው። በአሁኑ ጉዞ የተለያየ ዜግነት ያላቸው ዘጠኝ ሰዎች ተሳትፈዋል። ታዲያ አብዛኞቹ ተራራውን ከአንድም ሁለት ሶስቴ የወጡ ናቸው። ሲራክም ልምድ ያላቸው ሰዎች ባሉበት ቡድን ውስጥ መሆኑ ተጨማሪ ልምድ የማግኘት ዕድልን ፈጥሮለታል። ምን ስንቅ ቋጠረ? ሲራክ ከተራራው ጫፍ ደርሶ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ የማውለብለብ ተስፋ ሰንቋል። ተስፋ ብቻም ሳይሆን በቂ ልምምድ አድርጓል። ከዚያ ባሻገር ግን ከቤት የወጣው ሁለት ትላልቅ ሻንጣዎች ይዞ ነው። ምን ያዝክ? አልነው። መጀመሪያ የጠራልን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የታሰረበት ከአልሙኒየም የተሰራ የበረዶ መቆፈሪያን ነው። ጫማው ላይ በረዶውን ቆንጥጦ የሚይዝ አስር ሹል ነገሮች ያሉት ብረት መያዝም ግድ ነው። ከፍተኛ የሆነ ሙቀት የሚሰጡ አልባሳት፣ ጓንት እንዲሁም የታሸጉ ሙቀት የሚሰጡ ኬሚካሎች እና ሌሎች መጠባባቂያ እቃዎችን አሰናድቷል። የሆድ ነገር ሆድ ይቆርጣል ነውና ምግብን በተመለከተ ከተፈራረመው አንድ የእንግሊዝ ኩባንያ የሚቀርብለት ሲሆን አሁን ባሉበት ደረጃ በጣም ኃይል የሚሰጡና ገንቢ የሆኑ ምግቦችን ያዘወትራሉ። ተራራው አራት ካምፖች ያሉት ሲሆን ይህ አገልግሎት ከካምፕ አራት በኋላ ይቋረጣል። ከዚህ በኋላ ተራራው ጫፍ ለመድረስ የየራሳቸውን ምግብ ይዘው መጓዝ ግድ ይላቸዋል። "እኔ ምግብ እምቢ ብሎኝ ባያውቅም፤ የተራራው ከፍታ በጨመረ ቁጥር ምግብ እንደማይበላ ነግረውኛል" ይላል። እሱ እንደሚለው ተራራው ከፍ እያለ ሲሄድ የኦክስጅን እጥረት ስለሚኖር እሳት ለማያያዝ ስለሚያስቸግር አብስሎ ለመብላት ያስቸግራል። ካምፕ አራት አብስሎ ለመብላት የሚቸገሩበትም ብቻ ሳይሆን ኦክስጅን የሚጠቀሙበት ከፍታ ነው፤ ብዙ የማይተኛበትም ቦታ ሲሆን ከተኙም ኦክስጅን መጠቀም ግድ ይላቸዋል። ካምፕ አራት ከደረሱ በኋላ የአየር ሁኔታው ታይቶ ከምሽቱ 5 ሰዓት ገደማ ተነስተው ረፋድ ሶስት ሰዓት ላይ በተራራው አናት ላይ መድረስ እንደሚጠበቅባቸው ይናገራል። ቅድመ ዝግጅት ይህን ተራራ ለመውጣት ሲሞክሩ በኦክስጅን እጥረት፣ ተንሸራተው በመውደቅና በሌሎች ምክንያቶች በርካቶች ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ የአካል ጉዳትም አጋጥሟቸዋል። "ብዙዎቹ ለዚህ የሚዳረጉት ራሳቸውን በመኮፈስ በቂ የሥነ ልቦና ዝግጅትና ልምምድ ሳያደርጉ ስለሚጀምሩ ነው" ይላል ሲራክ። በዚህ በበረዶ ግግር በተሞላና ከኔጋቲቭ 25 ዲግሪ ሴልሺየስ የአየር ጠባይ ተራራ ለመውጣት እርሱስ ምን ዝግጅት አደረገ? በተራራው ግርጌ ካለው ካምፕ ሆነው ልምምድ ያደርጋሉ፤ አየሩን ይለማማዳሉ። ሌሎች ተራራሮችን ይወጣሉ፤ ይወርዳሉ። ሲራክም ከባህር ጠለል በላይ 6090 ሜትር ከፍታ ያለውን ሎቦቼ ተራራን ወጥቷል። ይህም ከመጀመሪያው ካምፕ ወደ አንደኛው ለመሄድ የሚያስችላቸውን አቅም የሚፈታተኑበት ነው። ወደ ዋናው ጉዟቸው ከመነሳታቸው ሁለት ቀን ቀድሞ በኔፓሎች ባህል 'ፑጃ' የተባለው ዝግጅት ይከናወናል። ይህ ዝግጅት የቡደሃ እምነት በሚከተሉት ኔፓሎች የፀሎትና የምርቃት ሥነ ሥርዓት ይደረግላቸዋል። በእነሱ ባህል መሠረት አንድ ሰው ይህን ዝግጅት ሳይካፈል ከወጣ ለተራራውም ሆነ ለወጭው መጥፎ ዕድል ነው ብለው ያምናሉ። ተመራርቀው በጸሎት ነው የሚሸኛኙት። በመሆኑም እሁድ ሚያዚያ 13/2011 ዓ.ም ሥነ ሥርዓቱን ተካፍሏል። ሲራክ እንደነገረን በአንድ ጊዜ ተራራውን መውጣት አዳጋች ነው፤ በመሆኑም ከመነሻ ካምፕ ወደ አንደኛው ከሄዱ በኋላ ወደ መነሻው ካምፕ ይመለሳሉ። እንደገና ሁኔታቸው ታይቶ ከመነሻ ካምፕ ወደ ሁለተኛው ካምፕ ይጓዛሉ። እንደገና ተመልሰው ወደ መነሻ ካምፕ ይወርዳሉ። ከዚያ በኋላ ነው እንግዲህ በቀጥታ ተራራውን መውጣት የሚጀምሩት። ተራራውን በመውጣቱ ምን ያተርፋል? ሲራክ ተራራውን ለመውጣት የተነሳው በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ያገለግል የነበረውንና መሃሉ ላይ የአንበሳ ምልክት ያለውን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ይዞ ነው። አንበሳ የኢትዮጵያ ምልክት ነው የሚለው ሲራክ፤ "ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ለአፍሪካ አንድነት ባደረጉት አስተዋጽኦ ምክንያት የአፍሪካ አንድነት ምልክት ሆኖ ይሰማኛል፤ ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት እጅ አለመውደቋን ያስገነዝበናል፤ በመሆኑም ሁል ጊዜ በልቤ ተጽፎ ይኖራል" ይላል። የኢትዮጵያን ስም ማስጠራትና ሰንደቅ ዓላማዋን ተራራው ጫፍ ላይ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ በማድረግ አገሪቱ ያላትን የርሃብና የኋላቀርነት ታሪክ መለወጥ ዓላማው እንደሆነ ይናገራል። በአሁኑ ጉዞው የምዝገባ ክፍያውን ጨምሮ ለአልባሳትና አንዳንድ ለሚያስፈልጉት ወጪዎች በትንሹ እስከ ስልሳ ሺህ የአሜሪካ ዶላር (1 ሚሊየን 740 ሺህ ብር ገደማ) አውጥቷል። ሲራክ በዚህ ብቻ አያቆምም ፓኪስታን ውስጥ እንደሚገኘው ኬቱ 8,611 ሜትር (28,251 ጫማ) ከፍታ ያላቸው ፈታኝ ተራራዎችን የመውጣትም እቅድ አለው። አግራሞት ሲራክን ካለበት ስናነጋግረው በተራራው ግርጌ ባለው ካምፕ ውስጥ ሆኖ ነበር። በእርግጥ በሥፍራው በቀጥታ የስልክ መስመር ማግኘት ባይቻልም ኢንተርኔት ግን ይሰራል። ይህ ለሁላችንም አግራሞትን የፈጠረ ነበር። • ማንዴላን ውትድርና ያሰለጠኑት ኢትዮጵያዊ ሁለት ኔፓላውያን 'ኤቨረስት ሊንክ' የሚባል የኢንተርኔት ኮኔክሽን እንዳዘጋጁላቸው ይናገራል። 'ኤቨረስት ሊንክም' ኔፓላውያን ተራራውን ለሚወጡት ደንበኞቻቸው የፈጠሩት የኔትወርክ ስም ነው። ለሁለት ጊጋ ባይት የኢንተርኔት ጥቅል አገልግሎት 75 የአሜሪካ ዶላር በውድ እየገዙ እንደሚጠቀሙ ሰምተናል።
news-47068404
https://www.bbc.com/amharic/news-47068404
እየከበዱ የመጡት የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ችግሮች
በአዲስ አበባ ያለውን የሕዝብ ትራስፖርት ችግር ለመቅረፍ በሁለት ዋነኛ መስመሮች ከአራት ዓመት በፊት አገልግሎት መስጠት የጀመረው ቀላል ባቡር ከጊዜ ወደ ጊዜ በተለያዩ ምክንያቶች እየተዳከመ መሆኑን ተገልጋዮችና የድርጅቱ ሰራተኞች ይናገራሉ።
• ወንበር የሚለቅላት አጥታ ልጇን ቆማ ያጠባችው እናት አብዱልማሊክ አሊ በአብዛኛው የባቡር አገልግሎት ይጠቀማል። "ባቡሩ እንደታሰበው ቶሎ ቶሎ አይመጣም፤ አንዳንዴም ብልሽት አጋጥሞት መንገድ ላይ ይቆማል" ይላል። ይሄው ችግር አጋጥሞት በእግሩ የተጓዘበትን አጋጣሚ ያስታውሳል። ተገልጋዮች በዝናብና በፀሐይ ሳይንገላቱና ሳይጉላሉ አገልግሎቱን መጠቀም ቢችሉ ምኞቱ ነው። ብዙ ጊዜ ከአውቶብስ ተራ - ሳሪስና ከአውቶብስ ተራ - ስታዲም ለመሄድ እገለገልበታለሁ ያሉን ሌላኛው የባቡር አገልግሎት ተጠቃሚ አቶ ዘለቀ ናቸው፤ ልክ አንደ አብዱልማሊክ ሁሉ እርሳቸውም የባቡሩ መዘግየት ያማርራቸዋል። ባነጋገርናቸው ጊዜም ባቡሩን ሲጠብቁ 45 ደቂቃ ገደማ እንዳሳለፉ ነግረውናል። ከዚህ ቀደምም በኃይል መቋረጥ ምክንያት ጉዟቸው ተስተጓጉሎ እንደነበር አይዘነጉትም፤ የባቡሮቹ ቁጥርና የተሳፋሪዎች ብዛት አለመመጣጠኑም ችግር እንደሆነባቸው ለቢቢሲ ገልፀዋል። • ሞሮኮ በአፍሪካ ፈጣኑን ባቡር በይፋ አስመረቀች ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገው የባቡር አገልግሎቱ ሲጀምር አንስቶ በባቡር አሽከርካሪነት (ትሬይን ማስተር) ሲሰራ የቆው የድርጅቱ ባልደረባ እንደሚለው በተለያዩ ችግሮች ምክንያት በአገልግሎት ላይ የሚገኙት ባቡሮች፤ ድርጅቱ ካሉት መካከል ግማሽ ያህሎቹ ብቻ ናቸው። በተለይ ለባቡሮቹ የሚያስፈልገው መለዋወጫ በቀላሉ ስለማይገኝ ትናንሽ እክሎች ሳይቀሩ ባቡሮቹን ለመቆም ያስገድዷቸዋል። የድርጅቱ የጥገና ሰራተኞች እንደሚናገሩት መለዋወጫዎች ከቻይና ስለሚመጡ ሂደቱ አዝጋሚና ጊዜን የሚፈጅ በመሆኑ ባቡሮቹ ለወራት ከአገልግሎት ውጪ ይሆናሉ። የቀላል ባቡሮቹን የሚጠቀመው ሕዝብ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ቢመጣም የአገልግሎታቸው አቅም ግን እየቀነሰ መሆኑን የሚናገሩት ሰራተኞቹ ባቡሮቹ በሚገጥሟቸው ችግሮች የተነሳ በጥንድ ፉርጎዎች የሚሰጠው አገልግሎት ቁጥር በተለያዩ ጊዜያት እየቀነሰ በአንድ ፉርጎ ብቻ ውስን ሰዎችን ሲያጓጉዙ በተደጋጋሚ ይታያል። በተጨማሪም ድርጅቱ ለሰራተኞቹ ከሚሰጠው ክፍያና ጥቅማጥቅም አንጻር ባለፈው ዓመት ሰራተኞቹ ባካሄዱት የሥራ ማቆም አድማ ምክንያት አገልግሎቱ ተስተጓጉሎ ነበር። ያናገርናቸው የባቡር አሽከርካሪዎች እንደሚሉት ባነሷቸው የተወሰኑ ጥያቄዎች ላይ ማሻሻያ መኖሩን ቢናገሩም ባለው ሁኔታ ግን ደስተኛ አይደሉም። "የምንለብሰው የደንብ ልብስ እንኳን ባቡሩ ሥራ ሲጀምር የተሰጡን ናቸው፤ አንዳንዶቻችን የደንብ ልብሳችን በማለቁ በእራሳችን ልብስ ነው ሥራችንን የምናከናውነው" ሲል የሚናገረው ሌላኛው የባቡር አሽከርካሪ፤ "ድርጅቱ ከበድ ያሉ ችግሮቹን በአጭር ጊዜ ይፈታል ብሎ ለማሰብ እቸገራለሁ" ይላል። ባቡሮቹ በአገልግሎት ሂደት እያረጁ ስለሚሄዱ ተገቢው ጥገናና ለውጥ ቢያስፈልጋቸውም ያንን የማድረጉ ነገር ቀላል እንዳልሆነ አሽከርካሪዎችና የጥገና ባለሙያዎች ይናገራሉ። • "ሰልፊ" ፎቶ እና የሞራል መላሸቅ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገው አሽከርካሪ እንደሚለው አንዳንድ ወሳኝ የባቡሩ ክፍሎች በየጊዜው ካልተለወጡ ችግር ስሚያስከትሉ ስጋት አለብን ይላል። "የአንዳንድ ባቡሮች ፍሬን በጊዜ ሂደት እየተዳከሙ በመሄዱ በጉዞ ላይ እያሉ በድንገት ሰው ወይም መኪና በመንገዳቸው ገብቶ ለማቆም ቢገደዱ ያንን ማድረግ ስለሚቸገሩ አደጋ ሊከሰት ይችላል" ይላል። በተደጋጋሚ የሚያጋጥመው የኤሌክትሪክ መቋረጥ በርካታ ተሳፋሪዎችን እያማረረ ያለ ሆኗል። በድንገት የሚከሰተው የኤሌክትሪክ መቋረጥ ተሳፋሪዎችን ግማሽ መንገድ ላይ እንዲወርዱ አሊያም ለሰዓታት በባቡሩ ውስጥ እንዲቀመጡ ያስገድዳል። "ተሳፋሪው እኛ ያለንበትን ሁኔታ ስለማይረዳ ቁጣውንና ንዴቱን እኛ ላይ ያሳርፋል፤ ይህ ደግሞ ለእኛ ሁለት ቅጣት ነው" ሲል ምሬቱን ይናገራል። በአፍሪካ ውስጥ ካሉ ጥቂት የከተማ ውስጥ ቀላል የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎቶች ውስጥ የሚጠቀሰው የአዲስ አበባው ባቡር በአራት ዓመት ውስጥ ባሳላፈው ጉዞ ፈተናዎች ገጥመውታል። ጉዳዩን አስመልክተን ያነጋገርናቸው የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ተፈራ በበኩላቸው የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ካለበት መሰረታዊ ችግሮች በስተቀር ባቡሮቹ አሁንም አገልግሎት እየሰጡ ነው ብለዋል። እርሳቸው እንደሚሉት የኃይል መቆራረጥና የመለዋወጫ ዕቃዎች እጥረት ፈተና ቢሆንም ካሉት 41 ባቡሮች 34 የሚሆኑት አሁንም ለአገልግሎት ዝግጁ ሲሆኑ ከእነዚህ መካከል 2 ባቡሮች እንደመጠባበቂያ ይቀመጣሉ። በመሆኑም ከ20-28 ባቡሮች በየቀኑ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ ናቸው። ባሉት ችግሮች ሳቢያ ሁሉንም ባቡሮች በሙሉ አቅም ማሰራት እንዳልተቻለ ግን አልሸሸጉም። ይህም ችግር ባቡሮቹ ቀድሞ በተያዘላቸው እቅድ በየ6 ደቂቃው በእያንዳንዱ የባቡር ጣቢያ ይደርሳሉ መባሉን አፍርሶታል፤ በ40 ደቂቃ ግፋ ሲልም ለአንድ ሰዓት መዘግየታቸውን የተለመደ አድርጎት ነበር። አሁን ግን ተሻሽሎ ለ15 ደቂቃ ዝቅ ማለቱን ዳይሬክተሩ ያስረዳሉ። እርሳቸው እንደሚሉት ከቻይና መንግስት ጋር ያላቸው ውል መለዋወጫን ስለማያካትት ለመንግስት ተጨማሪ የመለዋወጫ በጀት ለማቅረብ መገደዳቸውን ይናገራሉ። • "ቻይና በአፍሪካ ውስጥ የታይታ ፕሮጀክት የላትም" ፕሬዚዳንት ሺ ዢፒንግ ለዚህም ባቡሩ አገልግሎት እየሰጠ መለዋወጫዎቹን ማቅረብ ይቻላል በሚል እሳቤ በስምምነቱ ሳይካተት መቅረቱን ያስታውሳሉ፤ አገሪቷ እየገጠማት ባለው የውጭ ምንዛሬ እጥረትም ይህንን ሙሉ በሙሉ ማሟላት አልተቻለም ይላሉ። ጥገናውን አስመልክቶም ለሁለት የቻይና ኩባንያዎች የ3 ዓመት ኮንትራት የተሰጠ ሲሆን የጥገና ስራ፣ የሰው ኃይል የማሰልጠንና ባቡሩን የማስተዳደር ሥራ ይሰራሉ። ነገርግን ቀስበቀስ ኃላፊነቱን ኢትዮጵያውያን እየተረከቡ እንደሚገኙ ዳይሬክተሩ ገልፀዋል። "ስምምነቱ ለአንድ ዓመት ባይራዘም ኖሮ፤ እስካሁን ኢትዮጵያውያን ሥራውን ሙሉ ለሙሉ ይረከቡ ነበር" ብለዋል። አሁን ላይ ያለውን ችግር ለማቃለልም ቢያንስ 15 ኪሎ ሜትር የሚሆን የኤሌክትሪክ ገመዶችን የተቀየረ ሲሆን የባቡሮቹን ሙሉ አቅም ለመጠቀም እየተሰራ ነው። መለዋወጫዎቹ ተገዝተው ጥገና ሲደረግላቸው አገልግሎቱ እንደሚሻሻል ተስፋ ሰጥተዋል። እስከ አሁን የትኛውም አካባቢ ላይ በእቅድ ደረጃ የተያዘ ሌላ የባቡር ማስፋፊያና አዲስ ፕሮጀክት አለመኖሩንና የባቡሮቹን ቁጥር የማሳደጉም ጉዳይ አገሪቷ ባላት የገንዘብ አቅም እንደሚወሰን አክለዋል።
news-49444561
https://www.bbc.com/amharic/news-49444561
አከራካሪው የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ ካርታ
ለሁለት ዓመታት ጥናት ሲደረግበት የቆየው የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ ካርታ ነሐሴ 14፣ 2010 ዓ.ም በጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት ይፋ ተደርጓል። የቀረበውን ጥናት መሠረት በማድረግም ውይይት ሲካሄድበት መቆየቱ ይታወሳል።
ይሁን እንጂ ባለፉት ቀናት የአገሪቱን የትምህርት ሥርዓት በሚመለከት እየተላለፉ ያሉ ምክረ ሃሳቦች በርካቶችን እያነጋገሩ ይገኛሉ። የዛሬ ዓመት የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ ካርታ ረቂቅ ይፋ በሆነበት ወቅት በተለይ እንደ ቋንቋ ያሉ ጉዳዮች አሁንም ድረስ እያከራከሩ ነው። • ፍኖተ ካርታው ወደ ቀድሞ የትምህርት ፖሊሲ ሊመልሰን ይሆን ? • ብሔራዊ ፈተናዎች ምን ያህል ከስርቆትና ከስህተት የተጠበቁ ናቸው? የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ትናንት ባወጣው መግለጫ በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ የአማርኛ ቋንቋ ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እንዲሰጥ መደረጉና የ8ኛ ክፍል ፈተና ሃገራዊ መሆኑን እንደማይቀበለው ማስታወቁን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። የ8ኛ ክፍል ፈተናን ሃገራዊ ማድረግም የክልሉን ሥልጣን የሚጋፋ ነው ሲል ተችቶታል። መግለጫው አክሎም "ፍኖተ ካርታው በምሁራን የተጠና ነው በሚል ለተነሱ ጥያቄዎች በቂ ምላሽ ሳይሰጥ ወደ ተግባር እየተለወጠ ነው" ሲል ይኮንናል። ፍኖተ ካርታው የተለያዩ የትምህርት ፖሊሲውን የሚነካ ሆኖ ሳለ የሃገሪቱ ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮችና የፖሊሲ ለውጥ ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎች ውሳኔ ሳያሳልፉና አስተያየት ሳይሰጡበት ወደተግባር መግባታቸው ተቀባይነት እንደሌለው በመግለጫው ተመልክቷል። ከዚህ ባሻገርም ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ደረጃውን 6-2-4 ብሎ መግለጫ ከማውጣቱ በፊት በቂ ማብራሪያ መሰጠት ነበረበት ይላል። "ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ትምህርት የሚሰጠው በአፍ መፍቻ ቋንቋ ሆኖ ሳለ የ8ኛ ክፍልን ፈተና ሃገራዊ ማድረግ ምን አመጣው?" ሲልም ይጠይቃል። "የትግርኛ ቋንቋ ከአማርኛ ቋንቋ ጋር ይወራረሳል" የሚለው መግለጫው፤ የሰባት ዓመት ሕፃን እነዚህን ቋንቋዎች በአንድ ላይ መስጠት ማደናገር ነው ብሏል። በመሆኑም የአማርኛ ቋንቋን ከአንደኛ ክፍል መጀመርና የ8ኛ ክፍልን ፈተና ሃገራዊ ማድረግን የክልሉ ትምህርት ቢሮ እንደማይቀበለው አስታውቋል። • ትምህርት ዕድሜን እንደሚያስረዝም በጥናት ተረጋገጠ የፍኖተ ካርታው አካል የሆኑት ውሳኔዎች ላይ አስተያየታቸውን የጠየቅናቸው የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቶላ በርሶም በበኩላቸው ሕፃናት ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸውንና እንግሊዝኛ እንደሚማሩ ገልጸው፤ ፍኖተ ካርታው በተማሪዎች ቋንቋ ላይ ተፅዕኖ ማድረግ የለበትም" ሲሉ ይቃወማሉ። "የማስተማሪያ ቋንቋን በተመለከተ የተለወጠ ነገር የለም። ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ያሉትን የትምህርት ዓይነቶች የሚማሩት በአፋን ኦሮሞ ነው" ይላሉ። አማርኛን በተመለከተ፤ ሕፃናት ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ ሦስት ቋንቋዎችን መማር ስለማይችሉ አማርኛን መማር ያለባቸው ከፍ እያሉ ሲሄዱ መሆኑንም ይገልጻሉ። ከስድስተኛ ክፍል የክልል ፈተና በተጨማሪ ክልሎች የስምንተኛ ክፍል ፈተናን እንደሚሰጡም ያክላሉ። ባለፈው ዓመት የፍኖተ ካርታው ረቂቅ ቀርቦለት የነበረው የምሁራን ቡድን አባል የነበሩት የሥርዓተ ትምህርት ባለሙያው ዶ/ር ፍርዲሳ ጀቤሳ "መዋቅር አትንኩ፣ የነበረው ሥርዓተ ትምህርት ችግር አይደለም፤ የትምህርት ጥራቱን እንዲወድቅ ያደረገው የግብዓት፣ የትግበራ፣ የብቃትና የአመራር ችግር ነው" የሚል ሃሳብ ተነስቶ እንደነበር ያስታውሳሉ። ዶ/ር ፍርዲሳ እንደሚሉት በወቅቱም ሌሎች አከራካሪ ጉዳዮች ተነስተው ነበር፤ በመሆኑም መግባባት ላይ ሳይደርሱ ውይይቱን እንዳጠናቀቁ ይናገራሉ። ይሄው ሐሳብ ዛሬም እንደ አዲስ መምጣቱን ያስረዳሉ። "የአማርኛ ቋንቋ ከሦስተኛ ክፍል ጀምሮ እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት እንዲሰጥ ሚንስትሩ መግለጫ ሲሰጡ ሰምቻለሁ፤ በጽሑፍ ላይ የተቀመጠው ደግሞ ከአንደኛ ክፍል ይጀምራል ይላል" ሲሉ በጽሑፍ ላይ ያለውና በመግለጫ የተሰጠው ሐሳብ ተጣርሷል ይላሉ- ዶ/ር ፍርዲሳ። የተለያዩ ሳይንሳዊ የትምህርት ጥናቶችን የሚያጣቅሱት ዶ/ር ፍርዲሳ፤ በተጠቀሰው የክፍል ደረጃ የሚገኙ ተማሪዎች ከሁለት ቋንቋ በላይ አዕምሯቸው መሸከም ስለማይችል ግርታ ሊፈጠርባቸው ይችላል በማለት ይሞግታሉ። በዚህም ላይ መግባባት እንዳልነበር ያስታውሳሉ። ከዚህም በተጨማሪ ለ10ኛ ክፍል የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተና እንዲቀር መደረጉም የራሱ ችግር እንዳለው ዶ/ር ፍርዲሳ ሳይጠቅሱ አላለፉም። ምክንያታቸውን ሲያስቀምጡም "የክልል ቋንቋዎች ያለማጠቃለያ ፈተና ሊቆሙ አይችሉም፤ በመሆኑም የክልል ቋንቋዎች እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል ይቀጥሉ ይባላል፤ ይህም አልተወሰነም፤ ግልፅም አይደለም" ይላሉ። በክልል ደረጃ ሲሰጥ የነበረው የስምንተኛ ክፍል ፈተናን ብሔራዊ ፈተና ማድረግም ሕጋዊ አይደለም ሲሉ ተችተውታል። • በዋግ ኸምራ አስተዳደር 7 የዳስ ት/ቤቶች አሉ • የስኮላስቲክ አፕቲቲዩድ ፈተና ውጤትን የሚያጣራ ኮሚቴ ተዋቀረ "ሕገ መንግሥቱ 'ክልል አንደኛ ደረጃን ይመራል' ይላል፤ ይሁን እንጂ የተነሳው ሐሳብ የክልሉን ሥልጣን እስከ ስድስተኛ ያወርደዋል፤ የክልል ቋንቋ እስከ ስምንተኛ ክፍል ድረስ ይቀጥላል ይላል፤ በሌላ በኩል ደግሞ እኛ የምንሰጣችሁን ፈተናው ተርጉማችሁ ነው የምትፈትኑት ይላል" ሲሉ እርስ በርሱ የሚጋጭ እና ወጥነት የሌለው ሐሳብ እንደሆነ በምሳሌ ያስረዳሉ። ዶ/ር ፍርዲሳ እንደሚሉት ክልሎች የአንደኛ ደረጃ ያለውን ትምህርት ያቅዳሉ፣ ይዘት ይመርጣሉ፣ ያደራጃሉ፣ ይተገብራሉ፣ ይፈትናሉ፣ ሪፖርት ያደርጋል እንጂ፤ እዚያ ውስጥ መግባት አልነበረባቸውም። የተነሱትን ሐሳቦች አንስተን ያነጋገርናቸው የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ ዶ/ር ገረመው ሁሉቃ፤ ከቋንቋ ጋር በተያያዘ የክልልና የፌደራል መንግሥት ሥልጣንን በሚመለከት አሁንም መጣራት ያለባቸው ጉዳዮች እንዳሉ በማንሳት ፍኖተ ካርታው ገና እየተሠራበት ያለ ሰነድ እንደሆነ ተናግረዋል። "የፌደራል መንግሥት የሥራ ቋንቋ ከሦስተኛ ክፍል ጀምሮ ይሰጣል ይላል፤ በሌላም በኩል የ8ኛ ክፍል ፈተና ብሔራዊ ፈተና ሆኖ ተተርጉሞ ለክልሎች ይሰጣሉ ይላል፤ በመሆኑም እነዚህ ጉዳዮች የክልል መንግሥታትን ሥልጣን ይነካሉ" በማለት ሕገ መንግሥቱ ከ1- 8ኛ ክፍል ያለውን ትምህርት መስጫ ቋንቋ የሚወስነው የክልሉ መንግሥት መሆኑን ገልጸዋል። ይህም መታየት ያለበት ጉዳይ ስለሆነ ትምህርት ሚኒስቴር እየሠራበት ይገኛል ብለዋል። ታዲያ ውሳኔ ያላገኘ ጉዳይ ላይ መግለጫ መስጠት ለምን አስፈለገ? ሚንስትር ዲኤታው የትናንት በስቲያ መግለጫ በ2012 ዓ.ም ፍኖተ ካርታው ተግባራዊ እንደሚሆን ለማስተዋወቅ እንጂ አከራካሪ ተብለው የተያዙና ውሳኔ ያልተሰጠባቸው ጉዳዮች መኖራቸውን ያነሳሉ። "ፍኖተ ካርታው ገና እየተጠና ያለ ጉዳይ ነው፤ የመጨረሻው ውሳኔ አይደለም" ብለዋል። በሚቀጥለው ሳምንት በጅግጅጋ በሚደረገው የትምህርት ኮንፈረንስ ፍኖተ ካርታው ውይይት ይደረግበታል፤ በውይይቱ ላይ ክልሎችም ስለሚሳተፉ እነዚህ ጉዳዮች መፍትሔ ያገኛሉ ሲሉ ሚንስትር ዲኤታው ዶ/ር ገረመው ለቢቢሲ ገልጸዋል። ትምህርት ሚኒስቴርም በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ በትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ ካርታ ጥናት ምክረ ሃሳብ መሠረት ውሳኔ የሚሹ 36 ጉዳዮች መለየታቸውን አስታውቋል።
news-49340988
https://www.bbc.com/amharic/news-49340988
ብሩክ ዘውዱ፡ በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት አስመዝጋቢ
በዘንድሮው ዓመት የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ሃገር አቀፍ ፈተና የተመዘገበው ከፍተኛው ውጤት 645 ሲሆን፤ ይህ ውጤትም በአማራ ክልል መመዝገቡን የትምህርት ሚኒስቴር የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ሃረጓ ማሞ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
ውጤቱን ያስመዘገበውም ብሩክ ዘውዱ የተባለ በባህርዳር የአየለች ደገፉ መታሰቢያ (ኃይሌ) ትምህርት ቤት ተማሪ መሆኑን ሰምተናል። ስላስመዘገበው ውጤት ለማነጋገር ወደ ብሩክ ስልክ መታን። ምን ተሰማህ አልነው። ብሩክ ውጤቱን እንደሚያመጣ ይጠብቅ ስለነበር ብዙም አልደነቀውም። "ደስ ብሎኛል" አለን በአገር አቀፍ ደረጃ ግን ከፍተኛ ውጤት አስመዘግባለሁ ብሎ እንዳላሰበ በመግለፅ። •"እናቴ ካልመጣች አልመረቅም" ኢዛና ሐዲስ ከማንችስተር ዩኒቨርስቲ እርሱ እንደሚለው በትምህርት ቤቱ ውስጥ የሚያስተምሩ መምህራን ብቃት ፣ በትርፍ ጊዜው [ቅዳሜና እሁድ] መምህራን የሚሰጡትን ማጠናከሪያ ትምህርት መከታተሉ እና የራሱ የንባብ ልምድ ላስመዘገበው ከፍተኛ ውጤት አስተዋፅኦ አድርጎለታል። "ሁሉም ሰው የራሱ ሆነ የጥናት ስልት አለው፤ የእኔ የንባብ ስልት ለሌላው ላይፈይድ ይችላል" የሚለው ብሩክ በፕሮግራም፣ ብዙም ሳይጨናነቅ እና ደስ እያለው እንደሚያነብ ከዚያም ፈተናን ተረጋግቶ የመፈተን ልምድ እንዳለው ገልፆልናል። •በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት ብሩክ ወላጅ አባቱን በሞት ያጣው የ10 ዓመት ታዳጊ እያለ ነበር። ከዚያም በኋላ እናታቸው የእናትንም የአባትንም ቦታ ተክተው እነርሱን ማሳደግ ያዙ። ታዲያ እርሱም ሆነ እህትና ወንድሙ በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ እናታቸው የሚያደርጉላቸው ድጋፍና ክትትል ከፍተኛ እንደነበር ሳይጠቅስ አላለፈም። "እናቴ ብዙም አንብቡ ብላ አትጎተጉተንም ፤ እኛ በፈለግንበት ሰዓት አምነንበት ነው እንድናነብ የምታደርገው" ይላል። ተማሪ ብሩክ ገና ትምህርት ቤት ሳይገባ በእህቱ የወላጆች በዓል ሥነ ሥርዓት ላይ ከአትሌት ኃይሌ ጋር ካልተነሳሁ ብሎ የተነሳው(እናቱ እንደነገሩን) ብሩክ እንደሚለው ታላቅ እህቱም የዛሬ ሦስት ዓመት እርሱ በተማረበት አየለች መታሰቢያ (ኃይሌ) ትምህርት ቤት፤ በትምህርት ቤቱ ከፍተኛ ውጤት እንዳስመዘገበች ያስታውሳል። የእርሱ ታናሽ ወንድምም ቢሆን የዋዛ አይደለም፤ ጥሩ የትምህርት አቀባበል አለው። ብሩክ ለጊዜው የትኛውን የትምህርት ዘርፍ ሊያጠና እንደሚችል ውሳኔ አላሳለፈም። በጤና ዘርፍ፣ በኮምፒዩተር ሶፍት ዌር ኢንጅነሪንግ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች የመማር ፍላጎት ቢኖረውም ወደ ሕክምናው ዘርፍ ሳያደላ እንደማይቀር ግን ይናገራል። ብሩክ ወደፊት አንድ ግብ ብቻ አስቀምጦ መጓዙ አያዋጣም ከሚሉት ወገኖች ነው። ወደፊት የተሻለ ነገር ፍለጋ በተለያዩ ዘርፎች እንደሚታትር ነግሮናል። "ደስታ ያሰክራል፤ ደስታ እንባ እንባ ይላል" ሲሉ በልጃቸው ውጤት እንደተደሰቱ የገለፁልን ደግሞ እናቱ ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ጥላሁን ናቸው። የልጃቸውን መልካም ውጤት ዜና የሰሙትም ከራሱ ከልጃቸው ነበር። "ደውሎ፤ እንዳትደነግጭ፤ ስድስት መቶ ምናምን አምጥቻለሁ ብሎ ስልኩን ዘጋው" ይላሉ የስልክ ልውውጣቸውን ሲያስታውሱ። ከዚያ በኋላ ግን ጓደኛው ደውሎ ብሩክ ከኢትዮጵያ ተፈታኞች አንደኛ እንደወጣ ሲነግራቸው ደስታቸውን መቆጣጠር እንዳልቻሉ ይናገራሉ። •በአገር ውስጥ ያለው መፈናቀል ሕገ ወጥ ስደትን አባብሷል? በወቅቱ ጓደኛቸው ቤት ነበሩና " እሷን አቅፌ ጮህኩ፤ እሷን አቅፌ አለቀስኩ፣ ተንበረከኩ...ፈጣሪን አመሰገንኩ" ይላሉ። ወ/ሮ ኤልሳቤት ከ12ኛ ክፍል በላይ በትምህርታቸው አልገፉም- አንድም ውጤት ስላላስመዘገቡ፤ በግልም ለመማር አቅም ስላልነበራቸው፤ በሌላም በኩል በትዳር ኃላፊነት ውስጥ ስለገቡ። የዛሬ ዘጠኝ ዓመት ባለቤታቸው በሞት ከተለዩዋቸው በኋላ 'ልጆቼ ናቸው ሥራዎቼ' ብለው የሚችሉትን ሁሉ እያደረጉ እንደሆነ ያስረዳሉ። "እናንተ የምታስመዘግቡት ውጤት ለእኔ ደመወዜ ነው እያልኩ ስለማሳድጋቸው ተግተው ነው የሚሰሩት " ይላሉ- ወ/ሮ ኤልሳቤት። መልካም ውጤት ሲያመጡም ደመወዝ እንደከፈሉኝ ነው የሚሰማቸው ሲሉ ከልጆቻቸው ጋር ያላቸውን ተግባቦት ይገልፃሉ፤ እንዲያጠኑ ብዙም ጫና አያሳድሩባቸውም። "በትምህርት ብቻ ሳይሆን ጥሩ ዜጋ እንዲሆኑ ፤ ገንዘብ በምንም መንገድ ይገኛል፤ መማር ስብዕናን ያንጻል፤ ስብዕናን ያሟላ ሰው እንድትሆኑ እፈልጋለሁ እያልኩ ነው ያሳደግኳቸው" ይላሉ። ለእርሳቸው ብቻ ሳይሆን ለአገር የሚጠቅሙ ዜጎች እንዲሆኑ እንደሚለፉ ይናገራሉ። •የቀድሞው የአንጎላ መሪ ልጅ የ15 ሚሊዮን ዶላር ቤቷን ልታፈርስ ነው "የምንኖረው ሁለት ክፍል ቤቶችን እያከራየን ነው፤ ለልጆቼ የማወርሳቸው ምንም ሀብት የለኝም" የሚሉት ወ/ሮ ኤልሳቤት እነርሱ ላይ ፍሬያቸውን ማየት ይፈልጋሉ። ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ስለ ብሩክ ሲናገሩም "ብሩክ በተሰማራበት ሁሉ ውጤታማ መሆን የሚችል ልጅ ነው፤ የሞከረው ሁሉ ይሳካል"ሲሉ ብዙ ጊዜ ናሳ የመሄድ ምኞት እንዳለው ገልፀውልናል። በአገር አቀፍ ደረጃ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ለመውሰድ ከተመዘገቡት 322 ሺህ 717 ተማሪዎች መካከል 319,264 የሚሆኑት ፈተናውን መውሰዳቸውን የትምህርት ሚኒስቴር በይፋዊ ገፁ አስታውቋል። ፈተና ላይ ከተቀመጡት ውስጥም 59 ተማሪዎች ከ600 በላይ ውጤት ሲያመጡ 48.59 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ከ350 በላይ ውጤት አምጥተዋል። በዘንድሮው ዓመት በፈተናው ወቅት በተፈጸመ የደንብ ጥሰት የ68 ተማሪዎች ውጤት መሰረዙም ተገልጿል። በመጨረሻም... አፕቲቲዩድ የትምህርት ዘርፍ የበርካታ ተማሪዎች ውጤት ዝቅ ማለቱ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው። ለብሩክ ይህንኑ ጥያቄ ሰንዝረንለት ነበር። በእርግጥ እርሱ"86 አካባቢ አስመዝግቤያለሁ"ይላል። ቢሆንም ግን ምክንያቱን ሳንጠይቀው አላለፍንም። እርሱም የትምህርቱ ዘርፍ የተማሪዎችን ጠቅላላ እውቀት ለመመዘን እንደሚሰጥ ጠቅሶ "ትምህርቱ እንደ አንድ የትምህርት ዘርፍ አይሰጥም፤ መምህራን ናቸው በበጎ ፈቃደኝነት እገዛ የሚያደርጉት፤ በዚያ ምክንያት ይሆናል" ሲል የግል አስተያየቱን አካፍሎናል።
news-42389948
https://www.bbc.com/amharic/news-42389948
ቀጣዩን የኤኤንሲ መሪ ለመምረጥ ሩጫ
የደቡብ አፍሪካ ገዢ ፓርቲ የሆነው የአፍሪካዊያን ብሔራዊ ኮንግረስ (ኤኤንሲ) ፕሬዝዳንት የሆኑትን ጃኮብ ዙማን በፓርቲው መሪነት የሚተኩ ሁለት ተወዳዳሪዎች ታውቀዋል።
ሁለቱ ተወዳዳሪዎች ንኮሳዛና ድላሚኒ ዙማና ሲሪል ራማፎዛ እነሱም ምክትል ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛና የቀድሞው ካቢኔ ሚኒስትር ንኮሳዛና ድላሚኒ ዙማ ማለትም የፕሬዝዳንት ዙማ የቀድሞው ባለቤት ናቸው። ለሌሎች አምስት የፓረቲ የሥልጣን ቦታዎች የተሰየሙ ተወዳዳሪዎችም አሉ። በምርጫው ዙሪያ የነበሯቸውን ቅሬታዎች ስሜታዊ በሆነ መንገድ ጩኸት በተሞላበት መልኩ ያንፀባረቁ ልዑካን ነበሩ። ለመሪነት ቦታው የሚደረገው ፉክክር የተጋጋለ ፖለቲካዊ ፍትጊያን በማስከተሉ በመጪው ዓመት ከሚከናወነው ምርጫ በፊት ፓረቲው ለሁለት እንዳይከፈል የሚል ፍራቻን አሳድሯል። ፕሬዝዳንት ዙማም ቢሆኑ ፓረቲው አደጋ ላይ እንደሆነ ''መስቀለኛ መንገድ ነው'' በማለት አስጠንቅቀዋል። በኔልሰን ማንዴላ ሥር ሃገሪቷ ዲሞክራሲን ስትቀበል ጀምሮ ኤኤንሲ ሥልጣን ላይ ቆይቷል። በጆሃንዝበርግ በተካሄደው የአራት ቀናት የፓርቲው የምርጫ ኮንፈረንስ ላይ ከ5ሺህ በላይ ልዑካን ተሳታፊ ሆነዋል። ለቢቢሲ ጋዜጠኛዋ ሌቦ ዲስኮ በዚህ ኮንፈረንስ ላይ የተገኙ እንደነገሯት ውጤቱ ይፋ ሲደረግ በማሸነፍና በመሸነፍ መካከል የሚኖረው ልዩነት ትንሽ እንደሚሆን ነው። የአመራሩ ምርጫ በምስጢር ዝግ በሆነ መልኩ ስለተካሄደ ሕጋዊ ጥያቄዎች ሊያስከትል እንደሚችል ይታሰባል። ውጤቱ እሁድ ዕለት ይታወቃል ተብሎ ቀድሞ ተነግሮ ነበር። ልዑካኑ የተጣሉበት የምርጫው ሂደት ክፍፍል ይንጸባረቅበት ነበር የምርጫው ሂደት ተገቢ ውክልና የሌላቸው ልዑካን እውቅና ሲያገኙ እውነተኛ ልዑካን ደግሞ ተከልክለው የሚለው ውዝግብ መፍትሄ እስኪያገኝ ድረስ ዘግይቶ ነበር። እ.አ.አ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በሥልጣን ላይ የነበሩት ፕሬዚዳንት ዙማ ብሔራዊ ምርጫ እስከሚካሄድበት እ.አ.አ እስከ 2019 ድረስም በሥልጣን ላይ እንደሚሆኑ ይጠበቃል። ደቡብ አፍሪካ ለፕሬዝዳንት ሥልጣን ሁለት የአምስት ዓመት ገደብ አስቀምጣለች። የ75 ዓመቱ ፕሬዚዳንት ዙማ በኤኤንሲ ፓርቲ ዙሪያ ባሉት በርካታ ውዝግቦች ዋና ርዕስ ናቸው። ከዚህ ቀደም በሥልጣን እያሉ በፓርላማ መተማመኛ ድምጽ ተሰጥቶባቸው ሥልጣን ነበር። በአሁን ሰዓት ደግሞ እሳቸው የሚያስተባብሏቸው በርካታ ብዙ የሙስና ክስ ይቀርብባቸዋል። ፕሬዝዳንቱ የቀድሞ ባለቤታቸው ለሆኑት ድላሚኒ ዙማ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል። የ68 ዓመቷ ድላሚኒ ዙማ የረጅም ዘመን ፖለቲከኛ ሲሆኑ በሃገሪቱ ያሉ በነጮች የተያዙ ንግዶችን ሲቃወሙ ቆይተዋል። አራት ልጆችን ቢወልዱም ከተፋቱ 20 ዓመት ገደማ ሊሆናቸው ነው። የኤኤንሲ የሴቶች ክንፍ ቀድሞ መሪ የነበሩት ድላሚኒ ዙማ ለደቡብ አፍሪካ መንግሥት የውጪ ጉዳይ፣ የቤትና የጤና ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል። የድላሚኒ ዙማ ኢኮኖሚያዊ አጀንዳ ከዋና ተቃዋሚያቸው ባለሃብቱ የቀድሞ የሠራተኞች መሪ ከነበሩት የአሁኑ ምክትል ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ የተለየ ነው። የ65 ዓመቱ ራማፎዛ በሙስና ላይ ያላቸውን ጥብቅ አቋም ያሳወቁ ሲሆን የንግድ ማህበረሰቡም ድጋፍ አላቸው። የምርጫው ውጤት ሌላ ቢሆንም ፕሬዚዳንት ጄኮብ ዙማ እ.አ.አ 2019 ድረስ በሥልጣን ይቀጥላሉ ባላፈው ቅዳሜ እንደ ፓርቲ መሪ የመጨረሻ የሆነውን የኮንፈረንሱ መክፈቻ ንግግራቸው ላይ ፕሬዚዳንት ዙማ የተፈጠረውን የአመራር ሽኩቻ አስመልክቶ 'አሳፋሪ ጭቅጭቅ' በማለት ቁጣቸውን ገልፀዋል። ባለፈው ዓመት በተደረጉት የአካባቢ ምርጫ ላይ ኤኤንሲ ባስመዘገበው ውጤት ዙሪያ ''ይህ ውጤት ኤኤንሲን በተመለከተ ሕዝባችን ደስተኛ እንዳልሆነ የሚያሳይ ነው'' በማለት ፕሬዚዳንቱ ተናግረው ነበር። በዚህ ንግግር ላይ 'ሌብነትና ሙስና' በመንግሥትም ዘርፎች እንዳለ ሁሉ በግሉም ዘርፍ እንዳለ በእርግጠኝነት ሲገልፁ፤ በተጨማሪም ''ጥቁር ሆኖ ስኬታማ የሆነ ሰው በሙስና እንደሆነ ይታሰባል'' በማለት ተናግረዋል። የሃገሪቱን ሚዲያ 'ኢፍትሐዊና የሚያዳላ' ነው በማለት ቁጣቸውንም ገልጸዋል። የሃገሪቱን የፍትሕ ሥርዓትም ዒላማ በማድረግ በፓርቲው ውስጣዊ ጉዳዮች ጣልቃ መግባት እንደሌለበት አሳስበዋል። በዲሞክራሲያዊ ሥርዓት በነጮች ትመራ የነበረቸው ሃገር በምርጫ ከተረከበበት ጊዜ አንስቶ ፓርቲው በሚገርም ሁኔታ ሁሉንም ምርጫ እያሸነፈ መጥቷል። ባለፈው ዓመት በተደረገው ምርጫ ግን ኤኤንሲ ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ አስመዝግቦ የማያውቀውን ዝቅተኛ የተባለውን የ54% ውጤት አግኝቷል። የቢቢሲው አንድሩው ሐርዲንግ እንዳለው ጥያቄው ኤኤንሲ በከፋ ውድቀት ውስጥ ከሆነ ይህ የደቡብ አፍሪካን መረጋጋትና የወደፊት ዕጣ ፈንታን ጥያቄ ውስጥ ያስገባል ብሏል።
57322192
https://www.bbc.com/amharic/57322192
"ድምጹን ያቀነባበሩት ሕዝብና መንግሥት በጥርጣሬ እንዲተያዩ የሚፈልጉ ናቸው" ብልጽግና
ብልጽግና ፓርቲ ሐሰተኛውን ድምጽ አቀነባብረው ይፋ ያደረጉት ሕዝብ እና መንግሥት በጥርጣሬ እንዲተያዩ የሚፈልጉ የአገር ውስጥ እና የውጪ ኃይሎች ናቸው አለ።
የብልጽግና ፓርቲ ሕዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ለቢቢሲ ሲናገሩ፤ "ዜጎች የራሳቸውን መንግሥት መርጠው ተቀባይነት ያለው መንግሥት ተመስርቶ ስኬታማ ሥራ እንዳይሰራ የሚሰሩ የውስጥ እና የውጪ ኃይሎች አሉ" ብለዋል። ቢቂላ (ዶ/ር) ዛሬ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ሐሰተኛው የጠቅላይ ሚንስትሩ ድምጽ ከየት ተቆርጦ እንደተቀጠለ የሚያሳይ ማስረጃ ለሕዝብ ይቀርባል። ትናንት ምሽት ኬሎ የተባለ መቀመጫውን ከአገር ውጪ ያደረገ መገናኛ ብዙሃን ከአንድ ሳምንት በፊት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ በብልጽግና ስብሰባ ላይ የተናገሩት ንግግር ነው በሚል አንድ ቅጂ አስደምጧል። በቅጂው ላይ ጠቅላይ ሚንስትሩ ፓርቲያቸው ምርጫው እንዲራዘም ፍላጎት እንዳለው፣ ለበርካታ ዓመታት በሥልጣን የመቆየት ፍላጎት እንዳላቸው እና ምርጫውን ከወዲሁ እናሸንፋለን ብለው ስለመናገራቸው ኬሎ ሚዲያ ዘግቧል። የዚህ ድምጽ መሰማትን ተከትሎ የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት የተለቀቀው የድምፅ ፋይል በውሸት የተቀነባበረና እና ጠቅላይ ሚንስትሩ በተለያዩ ጊዜያት የተናገሩትን በመቁረጥና በመቀጠል የተፈጠረ የሐሰት መረጃ መሆኑን አረጋግጣለሁ ብሎ ነበር። ብልጽግና ፓርቲም በተመሳሳይ "ከስብሰባው የተወሰደ አንድም ቃል የሌለው፣ የፓርቲያችን ፕሬዝደንት በተለያዩ ጊዜያት ካደረጓቸው ንግግሮች የተወሰዱ ቃላትን በመገጣጠም የተቀነባበረ ሐሰተኛ ድምጽ ነው" ብሏል። ቢቂላ (ዶ/ር) ይህን ድምጽ ተቆርጦ የተቀጠለው ሙያውን ጠንቅቆ በማያውቅ ሰው በመሆኑ፤ "ሁሉም ድምጹን እንደሰማ መረዳት የሚችለው ነው" ብለዋል። "ከአንድ ቦታ የተወሰደ ድምጽ አይደለም። በተለያዩ አጋጣሚዎች ክቡር ጠቅላይ ሚንስትሩ የተናገሯቸውን እና በሚዲያዎች የተላለፉ ድምጾችን ቆርጦ በመቀጠል ነው ዓረፍተ ነገር ለማስመሰል የሞከሩት" ያሉት ቢቂላ (ዶ/ር)፤ ድምጾቹ ከየትኛው የጠቅላይ ሚንስትሩ ንግግር ተቆርጠው እንደተቀጠሉ እየተለዩ እየተሰራ ነው ብለዋል።
news-56330390
https://www.bbc.com/amharic/news-56330390
ለሜጋንና ሃሪ መጠለያና ጥበቃ የሰጠው ጥቁሩ ቢሊየነር ማነው?
የሰሴክስ ዱክና ደችስ በመባል የሚታወቁት ሜጋንና ሃሪ ከሰሞኑ በሰጡት ቃለ ምልልስ አነጋጋሪ ሆነዋል።
ጥንዶቹ ከአሜሪካዊቷ ጉምቱ የቴሌቪዥን ሴት ኦፕራ ዊንፍሬይ ጋር በነበራቸው ቆይታ ከዩናይትድ ኪንግደም ንጉሣዊ ቤተሰብ ለምን ራሳቸውን ማግለል እንዳስፈለጋቸውና ሌሎችንም ምስጢሮች አውጥተዋል። ባልና ሚስት በቃለ-ምልልሳቸው ንጉሣዊው ቤተሰብ የገንዘብ ድጎማ ሲያቋርጥባቸው አሜሪካዊው ባለሃብትና የሲኒማ ሰው ታይለር ፔሪ ቤትና ጥበቃ እንደመደበላቸው ተናግረዋል። ለመሆኑ ታይለር ፔሪ ማነው? እንዴትስ ስኬታማ ሊሆን ቻለ? የ51 ዓመቱ ጥቁር አሜሪካዊ ፊልም ሠሪ፣ ኮመዲያን፣ ተዋናይ፣ አዘጋጅ እንዲሁም ፀሐፊ ነው። ፔሪ የሠራቸው ፊልሞችና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች በተለይ በጥቁር አሜሪካዊያን ዘንድ እውቅናና ክብር አትርፈውለታል። በተለይ ደግሞ ማደያ የተሰኘውን ፊልም በመፃፍ፣ በማዘጋጀት እንዲሁም በመተወን ይታወቃል። ታይለር ፔሪ በዚህ ፊልም ላይ አንዲት ጥቁር አያትን ሆኖ ይተውናል። በፈረንጆቹ 2015 134 ሄክታር ስፋት ያለው የፊልም ስቱዲዮ በጆርጂያ ግዛት አትላንታ ከተማ በመገንባት ከተማዋን የፊልም መናገሻ ለማድረግ ችሏል። ከዚህ ስቱዲዮ ግንባታ አንድ ዓመት በኋላ ፔሪ ቢሊየነር መሆኑን ፎርብስ መፅሔት አስታወቀ። ታይለር ፔሪ ከጥቂት ወራት በፊት ከረዥም ጊዜ ፍቅረኛውና ከአንድ ልጁ እናት ገሊላ በቀለ ጋር መለያየቱን አሳውቆ ነበር። ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊቷ ገሊላ በቀለና ታይለር ፔሪ ልጃቸውን አማን ታይለር ፔሪ ብለው መሰየማቸው አይዘነጋም። ታይለር ከፍቅረኛው ጋር ከተለያየ በኋላ "አሁን 51 ዓመቴ ነው። የፍቅር ጓደኛም የለኝም። በቀጣይ ምን እንደማደርግ ባለውቅም እግዚአብሔር ከጎኔ እንደሆነ አልጠራጠርም። መልካም አባት መሆኔን እቀጥላለሁ። ቀና ብዬ ማድረግ የምችለውን ሁሉ አደርጋለሁ" ብሎ ነበር። ታይለር በኢንስታግራም ገፁ ባጋራው መልዕክት ላይ አክሎ "በዚህ ሃዘን በሞላው ዓለም እባካችሁ መልካም መሆን ሻቱ" ብሎ ፅፎ ነበር። ፔሪ፤ ሃሪና ሜጋንን እንዴት ረዳቸው? ሜጋንና ሃሪ ዩናይትድ ኪንግደምን ለቀው ሲወጡ ወደ ካናዳ ነበር ያመሩት። ነገር ግን በ2020 ወደ አሜሪካዋ ካሊፎርኒያ ሄዱ። በዚህ ወቅት ነው ታይለር ፔሪ ሆሊውድ ውስጥ ካሉት 'ፈረስ የሚያስጋልቡ' ቤቶቹ መካከል አንዱን ከነጥበቃው [በነፃ እንደሆነ የተዘገበ] ለጥንዶቹ የሰጠው። ጥንዶቹ ሁለት ሰዓት በፈጀው ቃለ-ምልልሳቸው ነው ይህን ይፋ ያደረጉት። ሃሪና ሜጋን ከካናዳዋ ቫንኩቨር አይላንድ ለቀው የወጡት የሚኖሩበት ቤት አድራሻ በመታወቁ እንደሆነ ተናግረዋል። "ለቀን ስንወጣ ምንም ዕቅድ አልነበረንም" ብላለች ሜጋን በቃለ-ምልልሱ። "ቤት ያስፈልገን ነበር እሱ [ታይለር ፔሪ] ቤት ሰጠን፤ ጥበቃም እንዲሁ። ቀጣይ ምን እናድርግ የሚለውን እስክናሰላስል ድረስ እፎይታን ሰጥቶን ነበር።" "ካናዳ የሰው ቤት እያለን ትልቁ ጭንቀታችን የነበረው ድንገት ሳናስበው ከዚህ በኋላ ጥበቃ የላችሁም መባላችን ነበር" በሏል ሃሪ። ሃሪና ሜጋን ከቆይታ በኋላ ካሊፎርኒያ ውስጥ ሞንቴሲቶ የሚባል ሥፍራ ቤት ገዝተው ለመኖር መወሰናቸውን ይፋ አድርገዋል።
news-56841523
https://www.bbc.com/amharic/news-56841523
መንግሥት የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትን በተመለከተ ቀጣይ እርምጃውን እንዲያሳውቅ ተጠየቀ
በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የሚፈፀሙ ግድያዎችን፣ መፈናቀሎችና የንብረት መውደምን በተመለከተ መንግሥት የሚወስደውን ቀጣይ እርምጃ እንዲያብራራ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ጠየቀ።
ኢሰመጉ "የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትን በማስቆም አገርን እንታደግ" በሚል ሚያዝያ 13/2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፤ መንግሥት ዘርፈ ብዙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን መከላከልና ማስቆም ያልቻለበትን ምክንያት እንዲሁም ቀጣይ እርምጃዎችን በተመለከተ ይፋዊ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠይቋል። ኢሰመጉ በአገሪቱ ላይ በተለያዩ ወቅቶች የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ይፋ በማውጣት መንግሥት ከመባባሳቸው በፊት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ካልሆነ ግን ተጠያቂነት የማይቀር መሆኑን እንዲሁ በቅርቡ ማሳሰቡን በመግለጫው አስፍሯል። ኢሰመጉ በቅርቡ በአጣዬ ከተማና አካባቢው ስለተፈፀመው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መግለጫዎችን አውጥቶ ለመንግሥት ምክረ ሐሳብ ማቅረቡን አስታውሶ "ነገር ግን አስፈላጊው ጥንቃቄ አልተደረገም" ብሏል። "የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ሰለባዎች ከጉዳታቸው ሳያገግሙ እንዲሁም የአካባቢው የፀጥታ ስጋተ እንዳለበት ታውቆ" አስፈላጊው ጥንቃቄ መወሰድ ሲገባው ባለመሆኑ ከሚያዝያ 6/2013 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት በከባድ መሳሪያ በታገዘ ነዋሪዎች ላይ በተፈፀመ ጥቃት ሰዎች ሞተዋል፣ ንብረት ወድሟል እንዲሁም ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል ብሏል። ከዚህ ቀን ቀደም ባሉት ተከታታይ ቀናትም እንዲሁ በአጣዬ ዙሪያ ባሉት በማጀቴ፣ ቆሪና ሌሎችም አካባቢዎች በተደራጁና በከባድ ጦር መሳሪያ በታገዙ ታጣቂዎች በማጀቴ በርካታ ነዋሪዎች መገደላቸውን፣ በካራ ቆሬ የጸጥታ ኃይሎች መቁሰላቸውንና በርካታ ነዋሪዎች አካባቢውን ጥለው መሰደዳቸውን ኢሰመጉ መረጃ ደርሶኛል ብሏል። ከዚህም በተጨማሪ አጣዬ፣ ቆሪሜዳ፣ ዙጢ፣ ካራቆሬ የተባሉ ከተሞች በከፍተኛ ሁኔታ እንደወደሙ ድርጀቱ መረጃዎችን ዋቢ አድርጎ በመግለጫው አስፍሯል። በኦሮሚያ ክልል እንዲሁ "በምሥራቅ ወለጋ ጊዳ አያና ወረዳ በተለያዩ አካባቢዎች የሚፈፀሙ ግድያዎች፣ የአርሶ አደሮች ቤቶችና የእህል ጎተራ እንደሚቃጠል እና በርካቶችም ቀያቸውን ለቀው እንደሸሹ" በዚህ መግለጫ ዳስሷል። ጥቅምት 24/2013 ግጭት በተነሳባት ትግራይ ክልለ ነዋሪዎች ለችግር መጋለጣቸውንና አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያስፈልግ ኢሰመጉ አሳስቦ የፀጥታ ሁኔታው አሁንም ያልተሻሸለና ለመንቀሳቀስም ምቹ አለመሆኑን መረጃዎች ደርሰውኛል ብሏል። ከዚህም በተጨማሪ በቤንሻንጉል ጉሙዝ በተለያዩ አካባቢዎች በርካታ ነዋሪዎች በታጣቂዎች እንደሚገደሉ፣ በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በኮንሶ ዞን በጉማይዴና አማሮ ልዩ ወረዳ የነዋሪዎች ግድያ መበራከቱንና የሕገ ወጥ እስር መጨመሩን ኢሰመጉ የደረሱትን አቤቱታዎች ዋቢ አድርጎ አስፍሯል። በአፋር ክልል በዜጎች ላይ የሚፈፀመው ግድያና የንብረት መውደም አስከፊ መሆኑን በዚህ መግለጫው አካቷል። ኢሰመጉ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ውስጥ ያለው "የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ወደ ከፋ ደረጃ ላይ መድረሱን" ጠቁሞ "የአገሪቱ ቀጣይ እጣ ፋንታ አሳሳቢ" እንደሆነም አመላክቷል። "በአገራችን ያለው የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ከመሻሻል ይልቅ እየተባባሰና እጅግ አስከፊ ደረጃ ላይ ደርሶ ሰብአዊ መብቶች ምንም ዋስትና የላቸውም ማለት የሚቻልበት ጊዜ ላይ ደርሰናል" ብሏል። ኢሰመጉ በዚህ መግለጫው ላይ እንደ መፍትሔ ብሎ ያቀረባቸው በሰብዓዊ መብቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥሰቶች ተስፋፍተው ሰዎችን ለእልቂት ከመዳረጉ በፊት የሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት፣ የሐይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች በአገሪቱ ሰላም የሚወርድበትን ሁኔታ እንዲወያዩና የሰብዓዊ መብቶች ዋስትና ስለሚያገኙበት ሁኔታ እንዲመክሩ ብሏል። በተጨማሪም የጸጥታ ስጋት ያለባቸውን እንዲሁም መሰል ጥቃቶች ሲፈጸሙባቸው የነበሩ አካባቢዎችን በመለየት የተለየ ጥበቃ የሚደረግበትን ስልት በአፋጣኝ መዘርጋት የሚሉት እንደ መፍትሔ ኢሰመጉ ከጠቆማቸው መካከል ናቸው።
news-54822258
https://www.bbc.com/amharic/news-54822258
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በትግራይ ክልል ላይ የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፀደቀ
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት መሰብሰቢያ አደራሽ አካሂዶ፤ ትናንት የሚኒስትሮች ምክር በትግራይ ክልል ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አጽድቋል።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት፤ ጥቅምት 25፣ 2013 ዓ. ም. ባደረገው አስቸኳይ ልዩ ስብሰባ መንግሥት በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 93/1/ሀ መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደንገጉን አስታውቋል። . የሚኒስትሮች ምክር ቤት በትግራይ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ . ስለ ፌደራል መንግሥትና የትግራይ ክልል ግጭት ማን ምን አለ? . የትግራይ እና የፌደራል መንግሥት ከየት ወዴት? የሚኒስትሮች ምክር ቤት መግለጫ አክሎም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለስድስት ወራት ተፈጻሚ እንደሚሆን አስታውቆ፤ ይህንን አዋጅ የሚያስፈፅም በኢፌድሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሰብሳቢነት የሚመራና አግባብነት ካላቸው አካላት የተወጣጡ አባላት ያሉት ግብረ ኃይል መቋቋሙን ገልጿል። ግብረ ኃይሉ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲሆን ‘‘የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ግብረ ሀይል’’ ተብሎ እንደሚጠራም ተነግሯል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መደንገግ ያስፈለገበትን ምክንያት ሲያስረዳም፤ የሀገርን ሰላምና ሕልውና፣ የሕዝብንና የዜጎችን ደህንነት የማረጋገጥ እና ሀገሪቷን ወደ ሁከትና ብጥብጥ የሚወስዱ ማናቸውንም ድርጊቶችን የመከላከል ሕገ መንግሥታዊ ኃላፊነት እንዳለበት ገልጿል። ይህን ሁኔታ በመደበኛው የሕግ ማስከበር ሥርዓት ለመከላከልና ለመቆጣጠር የማይቻልበት ደረጃ ላይ መደረሱን የጠቆመው መግለጫው፤ በሕገ መንግሥቱ በተደነገገው መሠረት ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለመጠበቅ ልዩ እርምጃዎችን መውሰድ የሚያስችል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመደንገግ እና ተግባራዊ በማድረግ ሁኔታውን መቆጣጠር በማስፈለጉ አዋጁ መታወጁን ገልጿል። አዋጁ በመላው የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መስተዳድር ለስድስት ወራት ተፈፃሚ የሚደረግ ሲሆን፤ እንደያስፈላጊነቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተፈፃሚ ወይም ቀሪ የሚሆንባቸውን ተጨማሪ አካባቢዎችነ ግብረ ኃይሉ በሚያወጣው በመመሪያ ይወስናል ተብሏል።
news-47479370
https://www.bbc.com/amharic/news-47479370
አሜሪካዊቷ ሴናተር ማርታ ማክሳሊ በአየር ኃይል ባለስልጣን እንደተደፈሩ ተናገሩ
አሜሪካዊቷ ሴናተር ለስራ ባልደረቦቿ እንደተናገሩት አየር ኃይል በነበሩበት ወቅት በከፍተኛ ጦር መኮንን እንደተደፈሩ ተናግረዋል።
ሴናተር ማርታ ማክ ሳሊ በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያዋ ሴት የጦር አውሮፕላን አብራሪ ሲሆኑ በሰራዊቱ ውስጥ ስላለው ወሲባዊ ጥቃትን በተመለከተ በነበረ ስብሰባ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የሪፐብሊካን አባል የሆኑት ሴናተሯ በተደፈሩበት ወቅት መሸማቀቅ፣ ግራ መጋባትና በአጠቃላይ የመረበሽ ስሜት ስለደረሰባቸው ለማንም ሳይናገሩ ዋጥ አድርገው እንደቆዩ ተናግረዋል። •የአሜሪካዋ ሴናተር በስልጣን ላይ ሆነው ልጅ በመውለድ የመጀመሪያዋ ሆኑ በአሜሪካ ጦር ውስጥ የሚፈፀሙ ፆታዊ ቃቶች የህዝብ ጆሮ የማያገኙ ሲሆን፤ ከሁለት አመት በፊት ያለውም መረጃ እንደሚያሳየው 10% ብቻ ናቸው ይፋ የወጡት። ሴናተሯ ምክር ቤቱ ላቋቋመው ኮሚቴ ረቡዕ ዕለት እንደተናገሩት "ለረዥም አመታት ዝም ብየ ቆይቻለሁ" ብለዋል። "ነገር ግን ጦሩ በተለያዩ ቅሌቶች ከመዘፈቁ ጋር ተያይዞና ለሚመጡት ጥቃቶችም የሚሰጡት ምላሽ እርባና የሌለው በመሆኑ እኔም በዚህ ጥቃት አልፌ የተረፍኩ መሆኔን መንገር ፈለግኩ" ብለዋል። •የተነጠቀ ልጅነት በአሜሪካ የአየር ኃይል አባልነት ለ26 አመታት ያገለገሉት ሴናተሯ ብዙ ጥቃት እንደደረሰባቸው ግለሰቦች በሀዘን ከቦታው እንደለቀቁ ይናገራሉ። " ብናገር ሊደርስ የሚችለውን ሰቆቃ ሳስበው ፤ ስርአቱ በተደጋጋሚ እንደደፈረኝ ይሰማኛል" ብለዋል። •"በወንድሜ ለአምስት ዓመታት ተደፍሬአለሁ" ጡረታ ከመውጣታቸው በፊት ኮሎኔል ማዕረግነት የደረሱት በአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሁለት ጊዜ ተመርጠዋል። በባለፈው አመትም የምክር ቤቱን ምርጫ አሸንፈዋል። ሴናተሯ 17 አመታቸውም ላይ ፆታዊ ጥቃት እንደደረሰባቸው ለዋል ስትሪት ጆርናል ተናግረው ነበር። በጥር ወር ላይም ጆኒ ኧርነስት የተባሉ በሰራዊቱ ውስጥ ለብዙ ዘመናት ያገለገሉ ሴናተር እንደተደፈሩ ተናግረው፤ በወቅቱ ለፖሊስም እንዳልተናገሩ ገልጸዋል።
news-56228408
https://www.bbc.com/amharic/news-56228408
ሕንዳዊው ለጥል ባዘጋጀው የገዛ አውራ ዶሮው ተገደለ
በሕንድ ለአውራ ዶሮዎች ጥል በዝግጅት ላይ የነበረው ዶሮ ባለቤቱን ገደለ።
[ፋይል ፎቶ] የአውራ ዶሮዎች ጥል በሕንድ የተከለከለ ቢሆንም በተለይም በገጠራማ የሕንድ ግዛቶች በርካቶች ድርጊቱን እንደየመዝናኛ ትርዒት ይጠቀሙበታል። ሕንዳዊው በገዛ አውራዶሮው የተገደለው የአውራ ዶሮው እግር ላይ ታስሮ በነበረው ስለት ከተቆረጠ በኋላ መሆኑን የሕንድ ፖሊስ አስታውቋል። የአውራ ዶሮዎች ጥል በሕንድ የተከለከለ ቢሆንም በተለይም በገጠራማ የሕንድ ግዛቶች በርካቶች ድርጊቱን እንደየመዝናኛ ትርዒት ይጠቀሙበታል። በአውራ ዶሮዎች ጥል ውርርድ ማድረግም በስፋት የተለመደ ነው። ፖሊስ እንዳለው ሟቹ ግለሰብ እግሩ ላይ ስለት የታሰረ አውራ ዶሮውን ለጥል እያዘጋጀ ሳለ፤ አውራ ዶሮ ከባለቤቱ እጅ ለማምለጥ ሲሞክር ግለሰቡ ታፋው ላይ በስለቱ ከተቆረጠ በኋላ ብዙ ደም ፈሶት ሕይወቱ አልፏል። ፖሊስ በስም ያልጠቀሰው ግለሰብ ዶሮው እግር ላይ ታስሮ በነበረው 7 ሴ.ሜ ርዝማኔ ባለው ቢላዋ ጉዳቱ ካጋጠመው በኋላ ወደ ሆስፒታል ቢወሰድም ብዙ የደም መፍሰስ ስላጋጠመው ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ብሏል። በሳምንቱ መጨረሻ ላይ አውራዶሮዎችን በማደባደብ ሕገ-ወጥ ተግባር ተሳትፈዋል ያላቸውን 15 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ለማዋል እየሰራ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል። በስነ-ስርዓቱ የተሳተፉ ሰዎች በሰው ሕይወት ማጥፋት፣ በሕገ-ወጥ ውርርድ እና የአውራዶሮ ጥል ክስ ይመሰረትባቸዋል ሲል ኤኤፍፒ ዘግቧል። በሕንድ በተመሳሳይ ሁኔታ በአውራ ዶሮ ምክንያት የሰው ሕይወት ሲጠፋ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። ከአንድ ዓመት በፊት አንድህራ ፕራዴሽ የተባለ ግለሰብ እግሩ ላይ ስለት በተገጠመልት የገዛ አውራዶሮ አንገቱንተቆርጦ ሕይወቱ አልፏል። ይህ አድጋም ያጋጠመው በሕገ-ወጥ የአውራ ዶሮች ጥል ትርዒት ላይ ነበር።
news-45797143
https://www.bbc.com/amharic/news-45797143
በዴምህት ወታደሮች ላይ በደረሰው የመኪና አደጋ የሰዎች ህይወት አለፈ
የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ዴምህት) ወታደሮች ዛሬ ጠዋት ከኤርትራ ወደ ዛላምበሳ በሚመጡበት ወቅት ነበር ሰገነይቲ በሚባለው የኤርትራ ድንበር ላይ የመኪና አደጋ ያጋጠማቸው።
ከተጓዦቹ መካከል ከፊሎቹ ዛላምበሳ ደርሰዋል በአደጋው አራት ወታደሮች ሕይወታቸው ሲያልፍ ከ 20 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸው በኤርትራ በደቀምሃሬ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው እንደሆነ በስፍራው የሚገኘው ሪፖርተራችን ዘግቧል። ተሳፍረውበት የነበረው መኪናም የጭነት መኪና እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። በአደጋው ብዙ የዴምህት ወታደሮች እንደተጎዱ ከአካባቢው ወደ ዛላምበሳ የመጣ የድርጅቱ አመራር አባል ለቢቢሲ ተናግሮ ነበር። በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውን የወታደሮች ቁጥር በውል ባይገልጽም፤ ሰራዊቶቹን የያዘች መኪና እንደተገለበጠች ግን ቀደም ሲል ለቢቢሲ ገልፆ ነበር። • ኢትዮጵያና ኤርትራ የመጨረሻውን የሠላም ስምምነት ፈረሙ • ኢትዮጵያና ኤርትራ የት ድረስ አብረው ይራመዳሉ? • ኤርትራ ውስጥ በአጋጠመ የመኪና አደጋ 33 ሰዎች ሞቱ መንግሥት ባቀረበው የሰላም ጥሪ መሰረት ከ2000 በላይ የደምህት ወታደሮች ዛሬ ማለዳ ዛላምበሳ ይደርሳሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር። ከተጓዦቹ መካከል ከፊሎቹ ዛላምበሳ መድረሳቸውን ለማወቅ ተችሏል። ከአደጋው መከሰት ጋር ተያይዞ ቀሪዎቹ የደምህት ወታደሮች ጉዟቸውን ወደ ዛላምበሳ ይቀጥሉ አልያም ወደ ኤርትራ ይመለሱ የሚታወቅ ነገር የለም። የሠራዊቱን አባላት የሚቀበሉ የህዝብ አውቶብሶች በዛላምበሳ ከተማ ተዘጋጅተው እየተጠባበቁ ይገኛሉ።
news-50668127
https://www.bbc.com/amharic/news-50668127
የኮሌስትሮል መጠናችን ማወቅ ያለብን መቼ ነው?
ማንኛውም ሰው የኮሌስትሮል መጠኑን በሃያዎቹ አጋማሽ እድሜ ላይ ማወቅ እንዳለበት ተመራማሪዎች ገለጹ።
ተመራማሪዎቹ እንደገለጹት የኮሌስትሮል መጠንን ቀድሞ ማወቅ በህይወታችን ሊያጋጥሙን የሚችሉ የልብ በሽታ እና ስትሮክ የመከሰት ዕድላቸው ምን ያክል እንደሆነ ለማስላት ቸእድልን ያሰፋል። በዘርፉ ብዙ ጥናቶች የሰሩት ባለሙያዎች ሰዎች ቀድመው የኮሌስትሮል መጠናቸውን ማወቃቸውና ህክምና መጀመራቸው በምድር ላይ የሚኖራቸውን ቆይታ የመወሰን አቅም ሊኖርው ይችላል ብለዋል። • ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን? • እውን እንጀራ ሱስ ያስይዛል? ኮሌስትሮል በጮማ የተሞላ ንጥረ ነገር ሲሆን በአንዳንድ ምግቦች ውስጥ የሚገኝና በጉበታችን ውስጥም የሚመረት ነው። ኮሌስትሮል በትክክለኛው መጠን ሲሆን እንደ 'ኦስትሮጂን' እና 'ቴስተስትሮን' ያሉ ሆርሞኖችን ለማምረት እንዲሁም ቫይታሚን ዲ እና ሌሎች ውህዶችን ለመቆጣጠር ይረዳል። ሁለት የኮሌስትሮል አይነቶች አሉ፡ በ 19 ሀገራት በሚገኙ 400 ሺ ሰዎችን አካትቶ የተሰራው ጥናት መጥፎ በሚባለው የኮሌስትሮል መጠን እና የተለያዩ የልብ በሽታዎች መካከል ያለውን ግንኙነትና እድሜያችን ከ 40 ሲያልፍ ሊከሰቱ ስለሚችሉ ተያያዥ ችግሮች መረጃ ሰብስቧል። ተመራማሪዎቹ እድሜያቸው 35 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች በመውሰድ፤ በጾታቸው፣ መጥፎ የኮሌስትሮል መጠን ክምችት፣ እድሜ፣ ሲጃራ እና መጠጥ ያሉ መጥፎ ልማዶች፣ ስኳር፣ ቁመት፣ ክብደት እና በደም ግፊታቸው መሰረት ለልብ በሽታ የመጋለጥ ዕድላቸውን ለመተንበይ ሞክረዋል። ከሀምቡርግ የልብ ማዕከል የመጡትና በጥናቱ ተሳታፊ የሆኑት ፕሮፌሰር ስቴፋን ብላንክንበርግ እንደሚሉት የኮሌስትሮል መቆጣጠሪያ መድሃኒቶችን የሚወስዱ ሰዎች በእድሜያቸው ቀጣዮቹ 10 ዓመታት ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ የልብ በሽታዎችን በደንብ መከላከል ይችላሉ'' ብለዋል። • አትክልት ብቻ ስለሚመገቡ ሰዎች ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮች • ጫትን መቆጣጠር ወይስ ማገድ? በእንግሊዝ የሚገኙ እስከ 8 ሚሊየን የሚደርሱ ሰዎች 'ስታቲንስ' የተባለውን በደም ውስጥ መጥፎ የኮሌስትሮል መጠን መቀነሻ መድሃኒት ይወስዳሉ። ምንም እንኳን ውጤታማነቱ ላይ ብዙ ጥያቄዎች ቢነሱም መድሀኒቱን ለተከታታይ አምስት ዓመቱ ከወሰዱ 50 ሰዎች መካከል አንዱ ለልብ ድካም ወይም ስትሮክ የመጋለጥ ዕድሉን በእጅጉ ይቀንሳል። በአካላዊ እንቅስቃሴ የተሞላና ጤናማ አመጋጋብ ደግሞ የኮሌስትሮል መጠንን ለመቆጣጠር ሁነኛ መንገዶች ናቸው። ፕሮፌሰር ስቴፋን ብላንክንበርግ በበኩላቸው በተለይ እድሜያቸው ያልገፉ ሰዎች በጊዜ የኮሌስትሮል መጠናቸውን አውቀው የራሳቸውን ውሳኔ ቢያደርጉ ተመራጭ ነው ብለዋል። ''መድሃኒቱን መውሰድ አንድ አማራጭ ሲሆን አካላዊ እንቅስቃሴና ጤናማ አመጋጋብ ግን ሁሉም ሰው ከግምት ውስጥ ሊያስገባቸው የሚገቡ ናቸው።''
news-56318086
https://www.bbc.com/amharic/news-56318086
ትግራይ፡ በእስር ላይ የሚገኙት የህወሓት አመራር አባላት 'ክሳችን ፖለቲካዊ ነው' ማለታቸው ተነገረ
አዲስ አበባ ውስጥ በእስር ላይ የሚገኙት የቀደወሞው ህወሓት ከፍተኛ አመራሮች የቀረበባቸው ክስ ፖለቲካዊ ነው ብለው እንደሚያምኑ ተናገሩ።
እስረኞቹ ይህንን የተናገሩት ስለእስር አያያዛቸው ሁኔታ ለመመልከት ለጎበኟቸው ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ለዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) እና ለኮሚሽኑ ከፍተኛ ባለሙያዎች ነው። ኮሚሽኑ ባለፈው ቅዳሜ የካቲት 27/2013 ዓ.ም የጎበኟቸው አብረሀም ተከስተ (ዶ/ር)፣ አምባሳደር አባይ ወልዱ፣ አቶ ስብሃት ነጋ፣ አምባሳደር አባዲ ዘሙ፣ አቶ ቴዎድሮስ ሐጎስ፣ ሰለሞን ኪዳኔ (ዶ/ር)፣ አዲስ ዓለም ባሌማ (ዶ/ር)፣ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር፣ ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋን ጨምሮ 21 እስረኞችን ነው። ከታሰሩት ግለሰቦችና ከፖሊስ ኃላፊዎች ጋር ውይይት መደረጉን የገለጸው ኢሰመኮ ባወጣው መግለጫ ላይ "አብዛኞቹ ታሳሪዎች የቀረበባቸው ክስ ፖለቲካዊ ነው ብለው እንደሚያምኑ፣ የተጠረጠሩበት ጉዳይ በተናጠል አለመቅረቡና የምርመራ ሂደቱ በአፋጣኝ አለመታየቱን ገልጸው አቤቱታ አቅርበዋል" ብሏል። ኮሚሽኑ እንዳለው ታሳሪዎቹ በጥሩ አካላዊ ደኅንነት የሚገኙ ሲሆን የተያዙበት አጠቃላይ ሁኔታ ተቀባይነት ያለው መሆኑን ተመልክቶ፤ የተጠቀሱት ታሳሪዎች ወደ ፌዴራል ፖሊስ እስር ቤት ከመጡ ወዲህ "ተገቢ ያልሆነ የእስር አያያዝ አለመኖሩንና ፖሊሶች በተገቢው የሙያ ሥነ ምግባር የሚሰሩ መሆኑን" ገልጸዋል ብሏል። በተጨማሪም የህክምና አገልግሎት ባለው አቅም እያገኙ እንደሆነ፣ ከቤተሰባቸው ጋር ተገናኝተው አቅርቦት እንደሚቀበሉና ከጠበቆቻቸው ጋር መገናኘት መቻላቸውን እንደተናገሩ ኮሚሽኑ በመግለጫው ላይ አመልክቷል። ታሳሪዎቹ ከአስተዳደራዊ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ ከጠበቆች ጋር የሚገናኙበት ጊዜ ማጠሩን እንዳነሱና የተወሰኑ ታሳሪዎች የራሳቸውና የቤተሰቦቻቸው የባንክ ሒሳብ በመታገዱ ቤተሰቦቻቸው መቸገራቸውን እንደተናገሩ ገልጸዋል ብሏል። አስረኞቹ አሁን ካሉበት ሁኔታ ባሻገር ገጠሙን በሚሏቸው ጉዳዮች ላይ ቅሬታቸውንም ለኮሚሽኑ አባለት መግለጻቸውን አመልክቷል። ከዚህም ውስጥ "ከተያዙ በኋላ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ለረጅም ጊዜ መቆየታቸውን፣ በትግራይ ክልል ከመቀለ ከተማ ሸሽተው ሲሄዱ በተያዙበት ጊዜ ስድብ፣ ድብደባ፣ ማስፈራራትና ተኩስ እንደነበረ እንዲሁም የአካል መቁሰል እንደደረሰባቸው" ገልጸዋል ብሏል። በተጨማሪም ተይዘው ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ "ነፃ ሆኖ የመገመት መብታቸውን በሚጋፋ መልኩ በሚዲያ አሰልፎ የማቅረብና የማንኳሰስ ሁኔታ እንደነበረ" በማንሳት ቅሬታቸውን ያቀረቡ እስረኞች እንደነበሩ ኢሰመኮ ገልጿል። ኮሚሽኑ ታሳሪዎቹ አሁን በእስር የተያዙበት ሁኔታ በተገቢው ደረጃ መሆኑን ማረጋገጡንና በታሳሪዎች የተነሱ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ከእስር ቤቱ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ማድረጉን አመልክቷል። የቀድሞ የህወሓት አመራሮች አዲስ አበባ ውስጥ በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ በሚገኘው እስር ቤት ያሉበትን ሁኔታ ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ከተመለከቱ በኋላ በተጠርጣሪዎቹ ላይ የሚደረገውን "ምርመራ በተቻለ ፍጥነት በማጠናቀቅ፤ የሕግ አግባብ በሚፈቅደው መልኩ በዋስትና ሊለቀቁ የሚገባቸውን ታሳሪዎች መለየት አስፈላጊ ነው" በማለት ማሳሰባቸው ተገልጿል። ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ምሽት የህወሓት ኃይሎች በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ተከትሎ በትግራይ ክልል ወታደራዊ ግጭት ተቀስቅሶ ክልሉን ይመራ የነበረው ህወሓት ከሥልጣን መወገዱ ይታወሳል። በትግራይ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር በተያያዘ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና የፌደራል ፖሊስ በበርካታ የህወሓት ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራሮች ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣታቸው ይፋ አድርገው ነበር። ለእስር ማዘዣውም ዋነኛ ምክንያቶቹ ህወሓትን በበላይነት በመምራት፣ በትግራይ ክልል በሚገኘው በአገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈፀም፣ የአገር ክህደት ወንጀል ፈጽመዋል፣ የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አባላት እንዲታገቱ አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው መሆኑ መገለጹ ይታወሳል።
53509808
https://www.bbc.com/amharic/53509808
ቴሌቪዥን የምንመለከትበትን ሰዓት መመጠን የከፉ የጤና ችግሮችን ይቀንሳል
በአንድ ቀን ከሁለት ሰዓታት በታች ቴሌቪዥን መመልከት ከአሳሳቢ የጤና ችግር እንደሚጠብቅ አንድ ጥናት ጠቁሟል።
የቴሌቪዥንና መሰል ስክሪኖችን አብዝቶ ከመመልከት ጋር ግንኙነት ያላቸው ካንሰር እና የልብ ሕመሞች በየቀኑ ከሁለት ሰዓታት ያልበለጠ ስክሪን በመመልከት ሊቀንሱ እንደሚችሉ ነው ጥናቱ የጠቆመው። የግላስጎው ዩኒቨርሲቲ የሠራው ይህ ጥናት ዕድሜያቸው ከ37 እስከ 73 ያሉ 500 ሺህ ሰዎች የተሳተፉበት ሲሆን በአውሮፓውያኑ ከ2006 እስከ 2018 ድረስ ቆይቷል። የጥናቱ ውጤት እንደሚጠቁመው አዋቂዎች [ጎልማሳዎች] ከስክሪን ጋር ያላችውን ቁርኝት ሊቀንሱ ይገባል። በጥናቱ ላይ የተሳተፉ ሁሉም ሰዎች በቀን ለሁለት ሰዓታት ብቻ ስክሪን ተመልክተው ቢሆን ኖሮ የመሞት እድላቸውን በ5.62 በመቶ ሊቀንሱ ይችሉ ነበር። ከልብ በሽታ ጋር የተገናኙ ሞቶች ደግሞ በ7.97 ሊቀንሱ ይችሉ ነበር ይላል ጥናቱ። ጥናቱ ያካተተው ቴሌቪዥን መመልከት ብቻ ሳይሆን በተንቀሳቃሽ ስልኮች ላይ ቪድዮዎችን መመልከትንም ይጨምራል። የግላስጎው ዩኒቨርሲቲ የጤና ተቋም ባለሙያው ዶክተር ሃሚሽ ፎስተር ናቸው ጥናቱን የመሩት። እሳቸው እንደሚሉት አብዝቶ ቴሌቪዥን መመልከትም ሆነ ከስክሪን ጋር ተጣብቆ መዋል ለጤና መቃወስ ያጋልጣል። "ጥናታችን እንደሚጠቁመው ቴሌቪዥን አዘውትሮ አለመመልከት ለከፋ የጤና ችግር የመጋለጥ ዕድላችንን ከመቀነሱም በላይ ሊያዘገየው ይችላል።" ዶክተሩ፤ በዘርፉ ላይ ተጨማሪ ጥናት እንደሚያደርጉ ይጠቁማሉ። አልፎም አብዝቶ ቴሌቪዥን መመልከት ማለት ቁጭ ብሎ የተለያዩ ምግቦችን ማጋበስ ስለሆነ ሌላ የጤና ቀውስ ነው ይላሉ ባለሙያዎች። ባለሙያዎቹ ቁጭ ብሎ ቴሌቪዥን ከመመልከት ይልቅ እንደ እርምጃ ያሉ ሌሎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ማዳበር ለጤናማ ሕይወት ጠቃሚ ነው ሲሉ ይመክራሉ።
news-53620346
https://www.bbc.com/amharic/news-53620346
ዶናልድ ትራምፕ 'ቲክቶክ' አሜሪካ ውስጥ እንዳይሰራ ሊያግዱ ነው
ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከወደ ቻይና መጥቶ ዓለምን ጉድ እያሰኘ የሚገኘው 'ቲክቶክ' የተባለው ማኅበራዊ ሚዲያ አሜሪካ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዳይውል እንደሚያግዱት አስታውቀዋል።
ፕሬዝዳንቱ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ ''እስከ ቅዳሜ ድረስ ባለው ጊዜ ውሳኔውን ማስተላለፍ እችላለሁ'' ብለዋል። 'ባይትዳንስ' በመባል በሚታወቀው የቻይና ድርጅት የሚተዳደረው ቲክቶክ የአሜሪካውያንን ግላዊ መረጃ ለመበርበር ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚችል የአሜሪካ የደኅንንት ኃላፊዎች ስጋታቸውን ገልጸው ነበር። ቲክቶከ በበኩሉ ከቻይና መንግሥት ጋር መረጃ ይለዋወጣል መባሉን አስተባብሏል። በዓለም ላይ በፍጥነት ተወዳጅነቱ እየጨመረ የመጣው ቲክቶክ በአሜሪካ ብቻ እስከ 80 ሚሊየን የሚደርሱ ተጠቃሚዎች ያሉት ሲሆን እገዳው ለድርጅቱ ትልቅ ኪሳራ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። ''ቲክቶክን በተመለከተ፤ አሜሪካ ውስጥ ሙሉ በሙሉ እናግዳቸዋለን'' ብለዋል ፕሬዝዳንቱ ኤር ፎርስ ዋን ወደ ሚባለው አውሮፕላናቸው ውስጥ እየገቡ። የቲክቶክ ቃል አቀባይ ሂላሪ ማክኩዌድ ከዋሽንግተን ፖስት ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ በውሳኔው ላይ አስተያየት ከመስጠት የተቆጠቡ ሲሆን፤ ድርጅቱ ግን አሁንም ቢሆን የረዥም ጊዜ የስኬት እቅዱ እንደማይጎዳ ገልጸዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ቲክቶክን ለመዝጋት ምን አይነት ስልጣን እንደሚጠቀሙ፣ እገዳው እንዴት ተግባራዊ እንደሚሆን እና ምን አይነት የሕግ መሰናክሎች እንደሚጠብቃቸው እስካሁን የታወቀ ነገር የለም። ማይክሮሶፍት ደግሞ በቅርቡ ቲክ ቶክን ለመግዛት ፍላጎት እንዳለው ለባለቤቱ ባይትዳንስ ያሳወቀ ቢሆንም የፕሬዝዳንቱ ንግግር ምን አይነት ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችልም እስካሁን አልታወቀም። ቲክቶክን በተመለከተ ፕሬዝዳንቱ ያሰተላላፉት መልእክት በዋሽንግተን እና በቤይጂን መካካል እየተካረረ የመጣው አለመግባባት ማሳያ ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎች ገምተዋል። አሜሪካ እና ቻይና በንግዱ ዘርፍ ከነበራቸው አለመግባባት ባለፈ ከኮሮናቫይረስ በኋላ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር በተወሰዱ እርምጃዎች ዙሪያም ሲወነጃጀሉ ቆይተዋል። የአሜሪካ ባለስልጣናትና ፖለቲከኞች ባይትዳንስ በቲክቶክ በኩል የሚሰበስበውን መረጃ ለቻይና መንግሥት አሳልፎ ሊሰጥ ይችላል በማለት ሲወነጅሉ ቆይተዋል። ቲክቶክ ሁሉም የአሜሪካ ተጠቃሚዎቹን መረጃ እዚያው አሜሪካ ውስጥ እንደሚያስቀምጥና መጠባበቂያው ደግሞ ሲንጋፖር ውስጥ እንደሚገኝ በተደጋጋሚ አስታውቋል። በዚህ ሳምንት ደግሞ ለተጠቃሚዎቹ እና ለተቆጣጣሪዎች ባስተላለፈው መልዕክት የመተግበሪያውን አሰራር መመልከት የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋትን ጨምሮ ከፍተኛ ግልጽነት ያለው ሂደት እንደሚከተል ገልጿል። ''ዓላማችን ፖለቲካዊ አይደለም፣ ማንኛውም አይነት ፖለቲካዊ ማስታወቂያም ሆነ አጀንዳ ይዘን አናቀርብም፤ የእኛ ዋነኛ አላማችን ፈጠራን በማበረታታት ተጠቃሚዎቻችን እንዲዝናኑ ማድረግ ብቻ ነው'' ብለዋል የቲክቶክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኬቨን ሜየር። አክለውም ''ቲክቶክ አዲሱ የአሜሪካ ኢላማ ሆኗል፤ ነገር ግን እኛ ጠላት አይደለንም'' ብለዋል።
news-56021547
https://www.bbc.com/amharic/news-56021547
የሳዑዲዋ የሴቶች መብት ተሟጋች ከእስር ተለቀቀች
ታዋቂዋ የሳኡዲ አረቢያ የሴቶች መብት ተሟጋች ሉጃይን አል ሃትሎል ከእስር መፈታቷን ቤተሰቦቿ አስታውቀዋል።
የ31 ዓመቷ ሉጃይን አል ሃትሎል በሳኡዲ ሴቶች መኪና ማሽከርከር እንዲፈቀድላቸው ከፍተኛ አስተዋጽ አድርጋለች። በአውሮፓውያኑ 2018 ላይ ክልከላው ከመነሳቱ ከሳምንታት በፊት ነበር በቁጥጥር ስር የዋለችው። ታህሳስ ወር ላይ ደግሞ የአገሪቱ ፍርድ ቤት ፖለቲካዊ ስርአቱን ለመቀየርና የአገር መረጋጋትን በማወክ ጥፋተኛ ሆና አግኝቻታለሁ ብሎ ነበር። ይህን ውሳኔ ተከትሎም ከፍተኛ ጥበቃ በሚደረግበት ማረሚያ ቤት ውስጥ ስድስት ዓመት እንድታሳለፍ ተፈርዶባት የነበረ ቢሆንም ሁለት ዓመትና 10 ወራት ግን ተቀንሰውላታል። ምንም እንኳን ሉጃይን አል ሃትሎል ከእስር ብትለቀቅም ሙሉ በሙሉ ነጻ አለመሆኗን ቤተሰቦቿ ገልጸዋል። አክለውም በርካታ ክልከላዎች እንዳሉባትና ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ከአገር መውጣት እንደማትችል አስታውቀዋል። ''ሉጃይን ወደቤት ተመልሳለች'' ስትል እህቷ ሊና ረቡዕ ዕለት በትዊተር ገጿ ላይ በማስፈር የሴቶች መብት ተሟጋቿ ከ1001 ቀናት የእስር ቤት ቆይታ በኋላ መለቀቋን አብስራለች። ሌላኛዋ እህቷ ደግሞ ''በሕይወቴ ምርጥ የምለው ቀን ይህ ነው'' ስትል ደስታዋን ገልጻለች። ሉጃይን 2018 ላይ እሷ እና በርካታ የሴቶች መብት ተሟጋቾች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ ነበር በአገሪቱ የሴቶች መብት ተምሳሌት ተደርጋ መወሰድ የጀመረችው። በወቅቱ የሴቶች መብት ተሟጋቾቹ የአገሬው ሴቶች መኪና ማሽከርከር እንዲፈቀድላቸው መንግስት ላይ ከፍተኛ ጫና አሳድረው ነበር። ቤተሰቦቿ እንደሚሉት በቁጥጥር ስር ከዋለች በኋላ ለሶስት ወራት ምንም አይነት ግንኙነት ማድረግ አልቻሉም ነበር። በተጨማሪም በኤሌክትሪክ ሾክ ስቃይ ይደርስባት እንደነበር፣ ግርፊያ ይፈጸምባት እንደነበርና ጾታዊ ጥቃት እንደደረሰባት ገልጸዋል። ምንም አይነት ስቃይ አልደረሰብኝም ብላ ቃሏን የምትሰጥ ከሆነ ደግሞ በነጻ እንደምትሰናበት ተነግሯት ነበርም ብለዋል ቤተሰቦቿ። የሳዑዲ አረቢያ መንግስት የሚቀርቡበትን የማሰቃየት ክሶች ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርጓል። የመንግሥት ባለስልጣናት ሉጃን በቁጥጥር ስር የዋለችው ለሴቶች መብት ባደረገችው እንቅስቃሴ ሳይሆን ከውጭ አገር ዲፕሎማቶች፣ ከመገናኛ ብዙሀን እና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በነበራት ግንኙነት ምክንያት ነው ብለዋል። አሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ብሄራዊ የደህንነት አማካሪ ጄክ ሱሊቫን የሉጃይን ከእስር መለቀቅ ዜና አስደሳች መሆኑን ገልጸው ''ጥሩ ነገር ነው'' በማለት ገልጸውታል። ምንም እንኳን በሳዑዲ በርካታ የሴቶች መብት ተሟጋቾች በእስር ላይ የሚገኙ ቢሆንም የሉጃን ጉዳይ ግን ዓለማቀፍ ትኩረትን መሳብ ችሏል። ለማንም እጅ እንደማይሰጡ የሚነገርላቸው ቤተሰቦቿ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ተከታታይ የትፈታልን ዘመቻ ጉዳዩን ዓለም አቀፍ እንዲሆን አግዞታል። የመታሰሯ ጉዳይ ልዑል አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢል ሰልማንን ከሚያስተቹ ሁነቶች አንዱ ነው። ሴቶች መኪና እንዳይነዱ የሚከለክለውን ሕግ በማንሳትና ወግ አጥባቂዋን ሳኡዲ ለኢንቨስትመንት ክፍት በማድረግ ተራማጅ መሪ ቢባሉም፤ የመብት ተሟጋቾች መታሰር ግን በእጅጉ አስኮንኗቸዋል።
49386116
https://www.bbc.com/amharic/49386116
የምንኖርበትን ዘመን በ60ዎቹ በፃፋቸው መፃሕፍት የተነበየው ደራሲ
1968 ላይ የተፃፈው 'ስታንድ ኦን ዛንዚባር' የተሰኘው ልብወለድ፤ ከብዙ በጥቂቱ ስለ ቫያግራ [ወሲብ አበረታች ክኒን]፣ ስለ ቪድዮ ስልክ ጥሪ፣ ስለተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ ያወራል።
ይህ ልብ ወለድ መፅሐፍ የጆን በርነር ነበር፤ የሳይንሳዊ ልብ-ወለድ ደራሲው በርነር። እርሱ ይኖርበት በነበረበት ዘመን ገመድ አልባ የነበረው ነገር ያኔ አጀብ የተባለለት ራድዮ ነበር። ጆን በርነር በግሪጎሪጎሪሳውያን አቆጣጠር 1934 ዓ.ም. ኦክስፎርድ በተሰኘችው የእንግሊዝ ከተማ ጆን ሂውስተን በርነር የተባለ ጨቅላ ከነቃጭሉ ዱብ ይላል። ቤተሰቦቹ 'ነብይ ልጅ ተወለደልን' ብለው የሚደሰቱበት ወቅት አልነበረም። ዓለም በጦርነት የታመሰችበት ዘመን ነበርና። የበርነር አያት አንዲት መፅሐፍ ነበረቻቸው። መፅሐፏን ጎናቸው ሻጥ አድርገው ካልዞሩ ሰላም አይሰማቸውም። 'ዋር ኦፍ ዘ ዎርልድስ' ትሰኛለች። ታድያ ይህች መፅሐፍ በርነር ገና የ6 ዓመት እንቦቃቅላ ሳለ ከእጁ ትገባለች። በርነር፤ ከአያቱ መፅሐፍ ጋር ከተዋወቀ ወዲህ ነበር በሳይንሳዊ ልብ-ወለድ መፃሐፍት ፍቅር ቅልጥ ያለው። ዕድሜው 9 ሲረግጥ ከማንበብ አልፎ መሞነጫጨር ይጀምራል። በ13 ዓመቱ አጠር ያለች አንድ ሳይንሳዊ ልብ-ወለድ ይዘት ያላት ፅሑፍ ለአንድ ጋዜጣ ይልካል። 'አንት ታዳጊ ገና አልበሰልክምና አርፈህ ቁጭ በል' የሚል ምላሽ ይደርሰዋል። ምላሹ ለበርነር የሚዋጥ አልነበረም። በ17 ዓመቱ አሜሪካ ውስጥ ላለ አንድ ጋዜጣ 'ዘ ዋቸርስ' ሲል ርዕስ የሰጣትን ፅሑፍ ይልካል፤ ፅሑፏም ትታመለታለች። በርነር ይሄኔ የግል ትምህርት ቤት ተማሪ ነበር፤ ጉዞው ደግሞ ወደ ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ። 'ትምህርት ለምኔ' ያለው በርነር አስኳላውን ትቶ ቁጭ ብሎ መሞነጫጨር ይይዛል። ቢሆንም አንዳች ውስጣዊ ፍራቻ ሰቅዞ ይይዘዋል። ምናልባት ባይካልኝስ? ኦክስፎርድ ዪኒቨርሲቲ መማር እችል የነበርኩ ሰው እንዲሁ በዋዛ ስባትት ልኖር? የሚሉ ሃሳቦች ይመላለሱበታል። ይሄን ብድግ ይልና በኤሌክትሪክ የምትሠራ 'ታይፕራይተሩን' ከፊቱ አመቻችቶ ይቀመጣል። ዘውጋቸው ሳይንሳዊ ልብ-ወለድ የሆኑ ፅሑፎችን ማምረትም ይጀምራል። ፅሑፎቹ ለተለያዩ ጋዜጣዎች የሚከፋፈሉ ናቸው። በርነር በወጉ 25 ዓመት ሳይሞላው 80 ያክል ልብ-ወለድ ፅሑፎችን በስሙ አሳትሞ ነበር። በ14 ዓመት የምትበልጠው የፍቅር ጓደኛው ማርጆሪን ያገኛትም ጋዜጣ ላይ 'ትዳር ፈላጊ' የተሰኘው ዓምድ ላይ አይቷት ነው። በተገናኙ አራት ወራት ውስጥ የተጋቡት ጥንዶቹ በፍቅር ክንፍ ይላሉ። ማርጆሪ እስከ ዕለተ ሞቷ ድረስ የበርነር አማካሪ፣ ወኪል እና የልብ ወዳጅ ሆና እንደቆየች ይነገርላታል። 'ነብዩ በርነር' ሰው ሰራሽ ልህቀት [አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ]፣ ዘረኝነት፣ ዕፅ፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ የሕዋ ጉዞ እና ቴክኖሎጂ የበርነር ሥራዎች ውስጥ ትልቅ ሥፍራ ያላቸው ሃሳቦች ናቸው። ሥራዎቹ ገደብ የለሽ ምስጠት የሚስተዋልባቸው ሲሆኑ አንዳንድ ልብ-ወለድ ትልሞቹ እንደው የማይሆን ነገር ተብለው ቢታለፉም በርካታ ታሪኮቹ አሁን የምንኖርበትን ዓለም ቁልጭ አድርገው የሚያሳዩ ናቸው። 1972 ላይ የፃፈው 'ዘ ሺፕ ሉክ አፕ' የተሰኘው ልብ-ወለድ የሰው ልጆች ቁጥር በዝቶ ምድር በሕዝብ ብዛት ስትጨናነቅ እና አካባቢ ብክለት ዓለምን ወደ መጥፊያዋ ሲያቀርባት ያሳያል። በርነር በጭስ የታፈነች ዓለም ብሎ የፃፈው 1975 ላይ ነበር፤ ይህ ፎቶ ሕንድ ውስጥ የተነሰው ደግሞ 2017 ላይ ነው 1975 ላይ የሳለው አንድ ገፀ-ባሕርይ ደግሞ ዓለም ያጨበጨበለት የኮምፒውተር ሞጭላፊ [ሃከር] ነው። በበርነር ዘመን 'ሃከር' ምናልባት የኪስ ቦርሳ ሞጭልፎ የሚሮጥ እንጅ ከኮምፒውተር ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር አልበረም። ኮምፒውተሩንስ ማን በውል አውቆት። ነገር ግን በርነር ከአታሚዎቹ ጋር ሰላማዊ ግንኙት አልነበረውም። ለፅሑፉ አርትዖት ከሚሰጡ ሰዎች ጋር ይጋጭ የነበረው ደራሲው የኋላ ኋላ አታሚ እያጣ ይመጣል። የሚስቱ በሞት መለየት ደግሞ ነገሮችን 'በእንቅልፍ ላይ ጆሮ ደግፍ' ያደርጉበታል። ይሄኔ ነው ሎንዶን ውስጥ የነበረውን መኖሩያ ቤት ሸጦ ወደ አንዲት የገጠር መንደር መሰደድን የመረጠው። 'ስታንድ ኦን ዛንዚባር' በርነር ከሚታወቅባቸው ሥራዎች ጉምቱ ያሰኘው 'ስታንድ ኦን ዛንዚባር' የተሰኘው ልብ-ወለድ ነው። እዚህ መፅሐፍ ላይ በ2010 የዓለም ሕዝብ 7 ቢሊዮን እንደሚደርስ በርነር ፅፏል፤ ተንብይዋል ማለቱ ሳይቀል አይቀርም። የዓለም ሕዝብ 7 ቢሊዮን መድረሱ ይፋ የሆነው 2011 ላይ ነበር። ልብ-ወለዱ ሁለት ኒው ዮርክ ከተማ ውስጥ አፓርታማ ተጋርተው የሚኖሩ ሰዎችን ምናባዊ ታሪክ የሚከተል ነው። አንደኛው ነጭ ሰላይ፣ ሌላኛው ደግሞ አፍሪቃ አሜሪካዊ የንግድ ሰው። አክሎም መፃሐፉ የዓለም ኃያላን መንግሥታት ከሰው ልጆች የላቀ ዘረ-መል ለመፍጠር ሲያሴሩ ያስነብባል። እንደ አውሮፓ ሕብረት ያለ አንድ ድርጅት እና ቻይና የአሜሪካ ተቀናቃኝ ሃገር ሆና መገኘት በበርነር ሥራዎች ውስጥ በ1960ዎቹ የተዳሰሱ ናቸው። በርነር ሳይንሳዊ ልብ-ወለድ ሥራዎቹ የምንኖርበትን ዓለም ዓይነት ቅርፅ ይኖራቸው ዘንድ እንዲያግዘው በማሰብ የተለያዩ ክፍለ ዓለማትን ዞሮ ጎብኝቶ ነበር። እስካዛሬ ያላየናቸው ነገር ግን በርነር የተነበያቸው በርካታ ጉዳዮች አሉ። ወደፊትም አይፈጠሩም ብሎ መገመት ግን ከባድ ነው። * ከላይ የተጠቀሱት ጊዜዎች ሁሉም በግሪጎሪሳውያን አቆጣጠር የተፃፉ ናቸው።
44478997
https://www.bbc.com/amharic/44478997
የግሪንፊል ማማ እሳትና የሐበሾች ምስክርነት
ለንደን በሚገኘው ግሬንፌል ታወር ሕንፃ ሰባተኛ ፎቅ ላይ ባለ ቤት ውስጥ የተነሳ እሳት ለአደጋ ሰራተኞችና ለነዋሪዎች እድል ሳይሰጥ ሙሉውን ህንጻ እሳት ወረሰው።
በአደጋው የደነገጡ ጨርቄን ማቄን ሳይሉ የወጡ ሰዎች ሁኔታዉን በተረበሸ መንፈስ ይመለከቱት ጀመር። የእሳት አደጋ ሰራተኞች የአቅማቸውን ያህል ቢጥሩም እሳቱ ግን ህንፃውን ሙሉ በሙሉ ከመበላት አልታደጉትም። ማዳን የቻሉትም 65 ሰዎችን ብቻ ነው። ህንፃው ጠቁሮ የከሰል ክምር መሰለ። ይሄንን ክስተት በመገናኛ ብዙሃን የተከታተሉት ከአደጋዉ የተረፉ፣ ጎረቤቶችና የለንደን ከተማ ነዋሪዎች የዚህ ክስተት ልዩ ትዝታ አላቸው። አብረዉ ሲጫወቱ አምሽተዉ በነጋታው እንዲገናኙ በቀጠሮ የተለያዩት ጓደኛሞች፣ የረመዳንን ጾም አንድ ላይ አፍጥረዉ "ደህና እደሩ" ተባብለዉ የተለያዩ ቤተሰቦች በተኙበት እስከወዲያኛው አንቀላፉ። "እንደዚህ አይነት አደጋ አይቼ አላውቅ፤ ያንን ሳይ ደግሞ ህንጻው ላይ የሚኖሩ ሰዎችን ስለማውቅ ደንግጬ ቀረሁኝ" ሲል የገጠመውን ድንጋጤ ይገልጻል አሚር ዮሃንስ ። ሞገስ ብርሃነ በህንጻዉ አቅራቢያ ከጓደኛዉ ጋር ለአንድ ዓመት ያህል ኖሯል"ወደ ሰማይ ይንቀለቀል የነበረውን እሳት ቴሌቪዥን ላይ ሳይ ይህ ቃጠሎ የአሜሪካ መንትያ ህንጻዎች ላይ ያጋጠመው ነው በማለት ነበር ያሰብኩት" ይላል ሁኔታውን ወደ ኋላ ተመልሶ ሲያስታውስ። በአንድ በእሳት በሚነድ ህንጻ ስር ሆነህ በቅርብ የምታውቃቸውን ሰዎች፣ ጓደኞችና ዘመድ ሞት ከማየት የከፋ ነገር የለም የምትለዋ ደግሞ ፌሩዝ አህመድ ናት። በተጨማሪም "ህንጻዉ ላይ በቅርብ የምናውቃቸዉ ሰዎች ስለሞቱ እስካሁን ከህሊናችን አልወጣም" ትላለች። ፌሩዝ ልጇና እናቷ የሆነውን ሁሉ በአቅራቢያው ከሚገኝ ህንፃ በመሆን ተመልክተዋል። የግሪንፌል አደጋ ሁሌም በአእምሯችን ውስጥ ተሰንቅሮ አለ ስትል የምትናገረው ፌሩዝ ልጇና እናቷ ግን በአንድ ቃል "ይሄንን አጋጣሚ ማውራት አንፈልግም" በማለት ያንን ጥቁር ቀን ዳግም ማንሳት እንደማይፈልጉ ይናገራሉ። በኃይሉ ከበደ በአደጋው በጣም የተረበሸ ሲሆን አሁን ህይወቱን ዳግም ለመገንባት እየጣረ ነው የእውነት አፋላጊው ሸንጎ በግሪንፊል ማማ ላይ ይኖሩ የነበረውና እሳቱ ከእርሱ ቤት እንደተነሳ ይጠረጠር የነበረው ትውልደ ኢትዮጵያዊው በጠበቃው በኩል እንደተገለጸው "ምንም የፈጸሙት ስህተት የለም" የእውነት አፋላጊው ሸንጎ በአቶ በኃይሉ ከበደ ዙርያ ያሉ እውነታዎችን ከጠበቃው አዳምጧል። ጠበቃ ራጂቭ ሜኑን እንዳሉት ደንበኛቸው በኃይሉ ከበደ አደጋው በደረሰ ጊዜ ስልክ መደወሉን፣ ጎረቤቶቹን ስለሁኔታው እንዲያውቁ ማድረጉን ተናግረዋል። ይህን ሁሉ ያደረገው ጭሱን በተመለከተበት ቅጽበት ነበር። ስልኩን ብቻ ይዞ በባዶ እግሩ አፓርትመንቱን መልቀቁን፤ ከዚያ በኋላም እሳቱ ወደ ጎረቤት ሲዛመት ተስፋ በመቁረጥ ስሜት በድንጋጤ ይመለከት እንደነበር አብራርተዋል። ጠበቃ ሜነን ጨምረው እንዳሉት "እሳቱ ድንገተኛ ነው። ደንበኛዬም ኃላፊነቱን የሚወስደብት ምንም አግባብ የለም።" "አቶ በኃይሉ ከበደ በእርግጥ መልካም ሰው ነው። ምንም ያጠፋው ነገር የለም" ብለዋል ጠበቃው። ያም ሆኖ እሳቱ በተነሳ ማግስት አቶ በኃይሉ ከበደ ጥፋቱን በሌላ ማላከኩና እሳቱ የተነሳው ግን የእርሱ ፍሪጅ ከፈነዳ በኋላ እንደነበር አንዳንድ ጋዜጦች ሳያረጋግጡ ጽፈዋል። ከዚያም በሻገር አቶ ኃይሉ ባለሞያ ከመጥራት ይልቅ አንዳንድ የቤት ውስጥ ኤሌክትሪክ ሥራዎችን በራሳቸው ለመስራት ሞክረዋል በሚል ሲተቹ ነበር። ሆኖም ይህንን አቶ በኃይሉ አስተባብለዋል። ፖሊስ ስለ አቶ በኃይሉ ደህንነት በመስጋቱም ለፍርድ ቤት መስካሪዎች የሚደረገው ጥበቃ በሚደረግበት መርሀግብር እንዲታቀፉም ሐሳብ ተሰጥቷል። የጥፋተኝነት ስሜት 25 ዓመታትን በማማው የኖሩት ትውልደ ኢትዮጵያዊው አቶ በኃይሉ እሳቱ ወደ ሌሎች ሲዛመት ጎረቤቶቹን ለመርዳት ፍላጎት እንደነበረው አጣሪ ኮሚሽኑ አዳምጧል። "ነገር ግን ምን ማድረግ ይችል ነበር?" ይላሉ ጠበቃው። ያን ምሽት አቶ በኃይሉ በተደረገላቸው ጥሪ መሠረት ቀጥታ ወደ ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ ቃላቸውን መስጠታቸው ታውቋል። ጠበቃው ደጋግመው እንደሚሉት አቶ በኃይሉ ለፖሊስ መረጃ በመስጠት የተባበሩ ሰው እንጂ የወንጀል ተጠርጣሪ ተደርገው መታሰብ የለባቸውም። የደህንነት ጉዳይ በዚህ የእሳት አደጋ ምክንያት በግሪንፌል ታወር ላይ እስከ አሁን ያልተመለሰው"የደህንነት" ጥያቄ አለ። በ1974 (እአአ) የተገነባውና በ 2016 በ8.6 ሚልዮን ፓውንድ እድሳት ተደርጎለታል የተባለዉ ህንጻ ለምን የደህንነት መጠበቂያዎቹ በአግባቡ በቦታቸው እንዳልነበሩና ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎች በመገናኛ ብዙሃን ላይ የመነጋገሪያ አጀንዳዎች ሆኖው ነበር። የአካባቢው አስተዳዳሪ ህንጻው በታደሰበት ወቅት አውቶማቲክ ተቆጣጣሪ እንዳልተገጠመለት ተናግረው ነበር። "ባለ 17 ፎቅ ተመሳሳይ ህንጻ ውስጥ ስለምኖር ከግሪንፌል ታወር አደጋ በኋላ ሰስጋት ውስጥ ነው የምኖሮው" የሚለዉ ሞገስ በዚህ በሰለጠነ አገር እንዲህ አይነት ቸልተኝነት ማየቱ እንደማይዋጥለት ይናገራል። "ለሁሉም ሰው የምንኖርባቸዉ ህንጻዎች ጥንካሬ ስለሌላቸዉ እንጠንቀቅ እላለሁ።" የግሪንፌል ታወር ፍጻሜ በእንግሊዝ አገር ፖለቲካ አነጋጋሪ ጉዳይ ሆኗል። ለዚህ አደጋ ቀድሞ መደረግ የነበረበት ጥንቃቄ አለመደረጉን የሚያጠና ኮሚቴ ተቋቁሞ ሥራዉን እየሰራ ነዉ። ይሁን እንጂ ከዚህ ህንጻ የተፈናቀሉ ቤተሰቦች ቋሚ መጠለያ ስላላገኙ አስተዳደሩ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው ጥያቄ ላይ ናቸው።
56179064
https://www.bbc.com/amharic/56179064
በሌጎስ ብቻ በኮቪድ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከመላው አፍሪካ በላይ ይሆናል ተባለ
በናይጄሪያ ትልቋ የንግድ ከተማ ሌጎስ የተካሄደ ጥናት 4 ሚሊዮን የከተማዋ ነዋሪዎች በኮሮናቫይረስ ሳይያዙ እንዳልቀረ ጠቆመ።
ይህ አሃዝ በመላው አፍሪካ በቫይረሱ እንደተያዙ በይፋ ከተነገረው ሰዎች ቁጥር በላይ ነው። ናይጄሪያ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር 153 ሺህ ነው ያለች ሲሆን፤ ከበሽታው ጋር በተያያዘ ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥርን ደግሞ አንድሺህ 862 ነው ብላለች። በአራት የናጄሪያ ግዛቶች ላይ የተካሄደው የዳሰሳ ጥናት ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ባላት አፍሪካዊቷ አገር የቫይረሱ ስርጭት ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ ለማወቅ ያለመ ነበር። መስከረም እና ጥቅምት ወራት ላይ የተካሄደው ጥናት ያስመለከተው ውጤት በርካቶችን ያስገረመ ሆኗል። በጥናቱ ውጤት መሠረት ከአራቱ ናሙና ከተሰበሰበባቸው ግዛቶች በሦስቱ ግዛቶች ከአምስት ሰዎች አንዱ በቫይረሱ ተይዞ እንደነበረ 'የአንቲቦዲ' ምርመራ ውጤቶች አስመልክተዋል። በአራተኛዋ ጎምቤ ግዛት ደግሞ ከ10 ሰዎች አንዱ በቫይረሱ ተይዞ ነበር ተብሏል። ጥናቱ እንዳሳያው በቫይረሱ የተያዙት አብዛኛዎቹ ወንዶች ሲሆኑ የከተማ ነዋሪዎች ደግሞ የበለጠ ተጋለጭ እንደሆኑ ጥናቱ አስመልክቷል። የናጄሪያ የበሽታ ቁጥጥር ማዕከል እና የሕክምና ምርምር ተቋም ያካሄዱት የዳሰሳ ጥናት 186 ሚሊዮን የናይጄሪያ ዜጎች ለቫይረሱ ተጋላጭ መሆናቸውን አሳይቷል። የናይጄሪያ ጠቅላላ የሕዝብ ብዛት 206 ሚሊዮን እንደሆነ ይገመታል። "በአራቱ ግዛቶች ከሚኖረው ጠቅላላ ሕዝብ 81 በመቶ የሚሆነው አሁንም ለቫይረሱ ተጋላጭ ነው። ይህም ክትባት መሰጠትን እጅግ ወሳኝ ያደርገዋል" ሲሉ የናይጄሪያ የበሽታ ቁጥጥር ማዕከል ዳይሬክተር ዶ/ር ቺኬዋ ኢሄንከዌዙ ተናግረዋል። ናይጄሪያ በቅርቡ ኦክስፎርድ-አስትራዜኔካ ያመረቱትን ክትባት ለዜጎቿ ለመስጠት ወስናለች። ባለሙያዎች በቫይረሱ ማን የት እና መቼ እንደተያዘ መለየት እንዲሁም በቫይረሱ ህይወታቸውን ያለፈ እና ያገገሙ ሰዎችን በትክክል መለየት ግብዓቶችን በትክክል ለመመደብ ያስችላል ይላሉ። በአፍሪካ በኮሮናቫይረስ የተያዙ እና የሞቱ ሰዎችን አሃዝ በተመለከተ መንግሥታት የሰጧቸው ቁጥሮች አነስተኛ ሊሆኑ እንደሚችሉ ባለሙያዎች ይጠቁማሉ። ለዚህ ደግሞ ምክንያታቸው በአህጉሪቱ የሚከናወኑት የኮሮናቫይረስ ምርመራዎች ቁጥር አነስተኛ መሆኑ ነው።
news-56228377
https://www.bbc.com/amharic/news-56228377
ቲክቶክ ከተጠቃሚዎች መረጃ ሰብስቧል በመባሉ ካሳ ለመክፈል ተስማማ
ቲክቶክ ሰው ሰራሽ ልህቀት [አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ] ተጠቅሞ ከተጠቃሚዎች መረጃ ሰብስቧል መባሉን ተከትሎ 92 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ለመክፈል ተስማማ።
አንድ ቡድን፤ ቲክቶክ ከተጠቃሚዎች መልክ ላይ ዕድሜ፣ ፆታና የዘር ሐረግ የሚለይ ቴክኖሎጂ በመጠቀሙ ሕግን ጥሷል ሲል ከሶ ነበር። ቡድኑ እንደሚለው የተጠቃሚዎች መረጃ ወደ ቻይና ጭምር ተልኳል። ቲክቶክ የቱንም ድርጊትን አላደረግኩም ሲል ቢያስተባብልም ካሳ የከፈለው ወደ ፍርድ ቤት ከመሄድ ብሎ እንደሆነ አሳውቋል። ክሱን ያቀረበው ቡድን እንደሚለው 'ፌሺያል ሪኮግኒሽን' [የተጠቃሚዎች የፊት ገፅታ መለየት] የተባለውን ቴክኖሎጂ ቲክቶክ ተጠቅሞ መረጃ ሰብስቧል። ይህ ያደረገበት አንደኛው ምክንያት ደግሞ የትኛውን ማስታወቂያ ለየትኞቹ ተጠቃሚዎች እንልቀቅ የሚለውን ለመለየት እንዲያመቸው ነው። በዚህ ክስ ዙሪያ መግለጫ የሰጠው ቲክቶክ "የቀረቡብን ክሶች ብናስተባብልም ረዥም ወደሆነ የፍርድ ቤት ውሎ ከመሄድ ለቲክቶክ ማሕበረሰብ ደህንነቱ የተጠበቀና አስደሳች መድረክ መፍጠር ላይ ትኩረታችንን ማድረግ እንፈልጋለን" ብሏል። ጉዳዩ አሜሪካ ውስጥ ባለ የፌዴራል ፍርድ ቤት ታይቶ ቢሆን ኖሮ ገንዘቡን አሜሪካዊያን የቲክቶክ ተጠቃሚዎች ይከፋፈሉት ነበር። ቲክቶክ ላይ የቀረበው ክስ የተሰማው በአሜሪካዋ ኢሊኖይ ግዛት ነው። ግዛቲቱ ከበይነ መረብ የሚሰበሰብ መረጃን በተመለከተ ጥብቅ ሕግ አላት። ቲክቶክ 'ፕራይቬሲ ፖሊሲው' [ከተጠቃሚዎች ጋር በሚገባ ስምምነት] ላይ የሰዎችን መረጃም ሆነ አድራሻ እንደሚሰበስብ አሊያም እንደማያሰበስብ፤ አልፎም መረጃ ከአሜሪካ ውጭ እንደሚያስቀምጥ አሊያም እንደማያስቀምጥ በግልፅ ለማስፈር ተስማምቷል። ፕሮፕራይቬሲ የተሰኘው የግል ድርጅት ባለሙያ የሆኑት ሬይ ዋልሽ "ቲክቶክ ይህን ያክል ገንዘብ ለመክፈል የተስማማው ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ቢሄድ እንደማያሸንፍ ስለገባው ነው" ይላሉ። "እርግጥ ነው ቲክቶክ ወደ ፍርድ ቤት ሄዶ ለመፋለም የሚያስችል ገንዘብ አለው። ነገር ግን በጣም ብዙ በመክፈል ክሱን መሸፋፈን መርጧል። የኩባንያው ቻይናዊ ባለቤት ባይትዳንስ ገንዘብ ከስሮም ቢሆን ይህንን ጉዳይ ከመገናኛ ብዙሃን አፍ ማውጣትን የተሻለ አማራጭ አድርጎታል።" ባይትዳንስ የተሰኘው የቲክቶክ እናት ኩባንያ መሰል ክስ ሲቀርብበት ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በፈረንጆቹ 2019 ከታዳጊ ተጠቃሚዎች ላይ መረጃ ሰብስቧል የሚል ክስ ቀርቦበት ነበር። ነገር ግን ኩባንያው ምንም ዓይነት መረጃ ከአሜሪካ ወደ ቻይና አላኩም ሲል በተደጋጋሚ ያስተባብላል። የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ቲክቶክ መረጃ ወደ ውጭ ሃገር በመላክ የሃገራችንን ደህንነት አደጋ ላይ ጥሏል በሚል ነበር መተግበሪያውን [አፕሊኬሽን] ከማውረጃ ገፆች ያገዱት።
news-56876897
https://www.bbc.com/amharic/news-56876897
ጆ ባይደን የአርመን ጅምላ ግድያ የዘር ጭፍጨፋ ነበር አሉ
ጆ ባይደን በአርመኖች ላይ በአውሮፓውያኑ 1915 የተፈፀመው የጅምላ ግድያ የዘር ጭፍጨፋ መሆኑን ተናገሩ።
ይህንን በይፋ በማለትም የመጀመሪያው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነዋል። የጅምላ ግድያው የተከሰተው በቀድሞዋ ኦቶማን ኢምፓየር ወይም የአሁኗ ቱርክ እየተዳከመች በነበረችበት ወቅት ነው። ሁኔታው ለአመታት አወዛጋቢ ሆኖ የቆየ ሲሆን ቱርክ የጅምላ ግድያዎች ተፈፅመዋል ብላ ብታምንም "የዘር ጭፍጨፋ" የሚለውን ግን አልተቀበለችውም ነበር። የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ በያዝነው ሳምንት ቅዳሜ እንዳሉት አገራቸው የአሜሪካን ውሳኔ "ፍፁም አትቀበለውም" ብለዋል። "ከማንም ቢሆን ስለ ታሪካችን መማር አንፈልግም" በማለት በትዊተር ገፃቸው ሃሳባቸውን አስፍረዋል። የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዲሁ በአገሩ የሚገኙትን የአሜሪካ አምባሳደር ጠንካራ መልዕክት እንዲያስተላልፉ ጠርቷቸው ነበር። ከዚህ ቀደም የነበሩ የአሜሪካ መሪዎች የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን አገሮች ድርጅት (ኔቶ) አጋር የሆነችው ቱርክ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ያበላሸል በሚል ስጋት "የዘር ጭፍጨፋ" የሚለውን ቃል በይፋ ከመጠቀም ተቆጥበው ነበር። በአውሮፓውያኑ 1915 ምን ተከሰተ? ኦቶማን ቱርኮች በሩሲያ ኃይል መሸነፋቸውን ተከትሎ ለዚህ ደግሞ ክርስቲያን አርመኖችን በመወንጀል ወደ ሶሪያ በረኃና ሌሎች ቦታዎችም በአስገዳጅ በግዞት ይልኳቸው ጀመር። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አርመኖችም ተጨፍጭፈዋል፣ በረሃብ ሞተዋል ወይም በምግብ እጦት እንዲሞቱ ተደርገዋል። በወቅቱ የነበረውን አሰቃቂ ጭፍጨፋ የአይን እማኞች፣ ጋዜጠኞች፣ ዲፕሎማቶችና የሃይማኖት ልዑካን መዝግበውታል። የሞቱ ሰዎች ቁጥርም ምን ያህል እንደሆነ አጨቃጫቂ ሆኗል፤ አርመኖች 1.5 ሚሊዮን ሰዎች ሞተዋል ይላሉ። ቱርክ በኩሏ የሟቾች ቁጥር 300 ሺህ ነው ትላለች። አለም አቀፉ የዘር ጭፍጨፋ ላይ ያተኮሩ ምሁራን ማህበር በበኩሉ የተገደሉ አርመናውያን ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን በላይ እንደሆነ አስታውቋል። ምንም እንኳን የቱርክ ባለስልጣናት የጅምላ ግድያዎች ተፈፅመዋል ቢሉም ክርስቲያን አርመናውያን ከምድረገፅ ለማጥፋት ሙከራም ሆነ የተዘረጋ ስርዓት አልነበረም ይላሉ። በዚህ አንደኛው አለም አቀፍ ጦርነት ወቅት በርካታ ቱርክ ሙስሊሞችም ሞተዋል የሚሉ መከራከሪያዎችን ቱርክ ታቀርባለች። ባይደን ምን አሉ? አርመኖች የዘር ጭፍጨፋ መታሰቢያን በሚያከብሩበት በመጀመሪያዋ ቀን ባይደን ባወጡት መግለጫ "በኦቶማን አገዛዝ ወቅት በዘር ጭፍጨፋ የሞቱ አርመናውያንን ህይወት እናስባለን። እንዲህ አይነት ጭፍጨፋም እንዳይደገም ጠንክረን እንሰራለን" ያሉት ፕሬዚዳንቱ አክለውም "በየትኛውም አይነት የሚመጡ ጥላቻዎችንና ሊያደርሱት የሚችለውንም ጫና ጠንቀቅ ብለን እናያለን" ብለዋል። ጆ ባይደን ይህንን መግለጫ ሲሰጡ ለመወንጀል ወይም ጣት ለመጠቆም ሳይሆን "መቼም ቢሆን እንዳይደገም ለማድረግ ነው" ብለዋል። ይህንንም ተከትሎ የአርመን ጠቅላይ ሚኒስትር ኒኮል ፓሽንያን እንዳሉት የጆ ባይደን ቃል " ለሞቱት ክብር ሰጥቷል" በማለት በትዊተር ገፃቸው ያሰፈሩ ሲሆን አክለውም "አሜሪካ ለሰብዓዊ መብት ጥበቃና አለም አቀፋዊ እሴቶች ያላትን ቁርጠኝነት ያሳየ ነው" ብለዋል። ቱርክ በበኩሏ መግለጫውን አውግዛ ይህ የሆነው "ፅንፈኛ በሆኑ የአርመን ቡድኖችና ፀረ-ቱርክ በሆኑ አካላት ጫና ነው"ስትል ተናግራለች። ይህም ሁኔታ የሃገራቱን ግንኙነትና ወዳጅነት እንደሚያጠለሸውም አስጠንቅቃለች።
56855661
https://www.bbc.com/amharic/56855661
የአፍሪካ አገራት ግዜው ያለፈበት የኮቪድ ክትባትን እንዳያስወግዱ ተጠየቁ
የዓለም ጤና ድርጅት የመጠቀሚያ ግዜያቸው ያለፈ የኮሮናቫይረስ ክትባት በእጃቸው የሚገኝ የአፍሪካ አገራት ክትባቱን ከማስወገድ እንዲቆጠቡ አሳሰበ።
አገራቱ ቀጣይ መመሪያዎች እስኪሰጡ ድረስ የመጠቀሚያ ግዜያቸው ያለፈባቸውን ክትባቶችን ይዘው እንዲያቆዩ ተጠይቀዋል። ማላዊ እና ደቡብ ሱዳን በሚያዚያ ወር አጋመሽ ላይ 70 ሺህ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ክትባቶችን ለማስወገድ ማሰባቸውን ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው የዓለም የጤና ድርጅት ይህን ማሳሰቢያ የሰጠው። ማላዊ 16 ሺህ የአስትራ ዜኔካ ብልቃጦችን፤ ደቡብ ሱዳን ደግሞ 59 ሺህ ተመሳሳይ ብልቃጦችን ለማስወገድ አስበዋል። የአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ (ሲዲሲ) ግን ምንም እንኳን ክትባቶቹን ለመጠቀም የተቀመጠው ግዜ ቢያልፍም ክትባቶቹ ጥቅም ላይ መዋል እንደሚችሉ ገልጾ ነበር። በዓለማችን ያሉ ሌሎች ክትባቶች ከተመረቱ ጀምሮ እስከ 36 ወር ድረስ ጥቅም ላይ የሚውሉ ሲሆን የኮቪድ ክትባት ግን አዲስ መሆኑን ተከትሎ ነው ለምን ያህል ግዜ ውጤታማ ሆኖ መቆየት እንደሚችል ገና ያልተለየው። እነዚህ ግዜያቸው ያለፈባቸውን ክትባቶች ጥቅም ላይ የማዋል ውሳኔ የሚሰጠው በብሔራዊ የመድሃኒት ተቆጣጣሪዎች እንደሆነ የቢቢሲ የጤና ጉዳዮች ዘጋቢ ርሆዳ ኦዲያምቦ ታብራራለች። የአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ዋና ዳይሬክተር ማክሰኞ ዕለት በሰጡት መግለጫቸው ላይ፤ "ለአባል አገራት የማቀርበው ጥሪ ቢኖር፤ እኛ ክትባቱን አስተባብረን ለማቅረብ የራሳችንን ድርሻ እየተወጣን ነው፤ እናንተም ክትባቶቹን በመጠቀም የድርሻችሁን ተወጡ" ሲሉ ተማጽነዋል። የኮሮናቫይረስ ክትባትን በአፍሪካ በሚፈለገው ፍጥነት እስካሁን ማድረስ ያልተቻለ ሲሆን፤ ለዚህም የአቅርቦት እጥረት እንዲሁም ስለ ክትባቱ ጥርጣሬዎች መኖራቸው እንደ ምክንያት ይነሳሉ።
news-56121979
https://www.bbc.com/amharic/news-56121979
’ኮሮናቫይረስ፡ ካልተከተቡ አይቀጠሩም’ የሚል ህግ ለአዳዲስ ሠራተኞች ተግባራዊ ሊሆን ይችላል
ኩባንያዎች አዳዲስ ሠራተኞቻቸው፣ ከመቀጠራቸው በፊት እንዲከተቡ ቢጠይቁ ህጋዊ ሊሆን ይችላል ሲሉ የእንግሊዝ የፍትህ ሚንስትር አስታወቁ።
እንደሮበርት ባክላንድ ከሆነ ነባር ሠራተኞች ባላቸው ውል መሠረት ክትባቶችን እንዲወስዱ የመጠየቅ ነገር ላይኖር ይችላል። የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ቢሮ ሰዎች በሥራቸው እንዲቀጥሉ ክትባት እንዲወስዱ ማዘዙ "አድሎአዊ" ነው ብሏል። ነገር ግን አንዳንድ ድርጅቶች ክትባቱን ለመውሰድ ፈቃደኛ ያልሆኑ አዳዲስ ሠራተኞችን እንደማይቀጥሩ ይናገራሉ፡፡ ባክላንድ ረቡዕ ዕለት ከአይቲቪ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ አዳዲስ በሥራ ውል ላይ በጽሑፍ እስከቀረበ ድረስ ሠራተኞችን እንዲከተቡ ማስገደድ ይቻል ይሆናል ብለዋል፡፡ ሆኖም አሠሪዎች ምናልባት ነባር ሠራተኞች እንዲህ ዓይነቱን ትዕዛዝ እምቢ ካሉ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ ሊያስፈልጋቸው ይችላል ተብሏል። አክለውም "ያለ ክትባት ሥራ የለም" የሚሉት መስፈርት ሕጋዊነት "በቅጥርና በልዩ ውል ላይ የተንጠለጠለ ነው" ብለዋል፡፡ "በአጠቃላይ አካሄዱን ሕጋዊ ያደረጉት አሁን ያሉት የሥራ ኮንትራቶች ቢኖሩ እደነቃለሁ፡፡ እውነቱን ለመናገር ጉዳዩ መፈተሽ ያለበት ይመስለኛል" ብለዋል፡፡ መቀመጫውን ለንደን ያደረገው የፒምሊኮ ፕለምበርስ ከህክምና ጋር በተያያዘ ካልሆነ በስተቀር ክትባቱን አልፈልግም የሚሉ አዳዲስ ሠራተኞችን አልቀጥርም ካሉት ኩባንያዎች አንዱ ነው፡፡ ከቅጥር ጋር በተያያዘ የሚሠሩ የህግ ባለሙያዎች በመጀመሪያ እርምጃው ላይ ጥያቄ ቢያነሱም መስራቹ ቻርሊ ሙሊንስ ህጋዊ እንደሆነ ምክር እንደተሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ "እኛ በግልጽ ከጠበቆች ጋር የተነጋገርን ሲሆን ክትባቱ ሙሉ በሙሉ ከወጣ በኋላ ከእኛ ጋር ለሚጀምሩ ማናቸውም አዳዲስ ሠራተኞች የክትባቱ ጉዳይ በውሉ ውስጥ በመካተቱ ባለሙያዎቹ በጣም ደስተኞች ናቸው" ብለዋል ለቢቢሲ፡፡ "አዲሶቹን ኮንትራቶች ከሁለት እስከ ሶስት ወራቶች ውስጥ እንጠቀማቸዋለን፡፡ ሰዎች ከእኛ ጋር ሥራ ለመሥራት ሲመጡ ያንን በመፈረም ደስተኛ ካልሆኑ የእነሱ ምርጫ ነው። በእርግጠኝነትም ሥራው ከፒምሊኮ ፕላምበርስ አይሰጣቸውም" ሲሉ ገልጸዋል፡፡ የቤት እንክብካቤ ላይ የተሠማራው ባርቸስተር ሄልዝኬርም ሁሉም አዲስ ቅጥር ሠራተኞችየመከተብ ግዴታ አለባቸው ብሏል፡፡ "ከሠራተኞቻችን ጋር በተያያዘ ፍላጎት ያላቸውን ክትባቱን እንዲያገኙ ለማበረታታት የተቻለንን ሁሉ እያደረግን ነው። በተጨማሪም ሁሉም አዲስ ሠራተኞች ክትባቱን መውሰዳቸውን ሥራ ከመጀመራቸው በፊት ማረጋገጥ አለብን" ያለው ድርጅቱ ደንበኞቹን እና ሠራተኞቹን ጤንነት መጠበቅን ደግሞ በምክንያትነት አስቀምጧል። 'የህግ ክፍተት' ሌዊስ ሲልኪን በሚባለው የሕግ ኩባንያ የሕግ ዳይሬክተር የሆኑት ዴቪድ ሳሙኤል እንዳሉት ድርጅቶች በአዳዲስ ቅጥር ሠራተኞቻቸው ኮንትራቶች ውስጥ "ያለ ክትባት ሥራ የለም" የሚል አንቀጽን ከማስገባት የሚያግዳቸው ሕጋዊ ማዕቀፍ የለም፡፡ አሠሪዎች እያንዳንዱን የሥራ ሚና መተንተን እና እንዲህ ዓይነቱን ሐረግ ከማስተዋወቅ በፊት የጤና እና የደህንነትን አደጋዎችን መገምገም አለባቸው ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ ይህ ባለማድረጉና አንድ ሠራተኛ ያልተከተበት ምክንያት ቢኖረው ውሉ ኢ-ፍትሃዊ ወይም አድሎአዊ ነው ብሎ ለመከራከር ያስችለዋል፡፡ ሌሎች ስጋቶችም አሉ። ለምሳሌ ፣ "ካልተከተቡ ሥራ የለም" የሚለው ፖሊሲ ክትባቱን ለመውሰድ የመጨረሻ መስመር ላይ ባሉ ወጣቶች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ የሚል ስጋት አለ፡፡ "ይህን ለማጽደቅ ከባድ ይሆናል። በተለይም በዚያ ሂደት ውስጥ ካልገቡ እና ካልሰነዱት በሕጋዊ ጥያቄ የመፈታተናቸው ዕድላቸው ሰፊ ነው" ሲሉ ሳሙኤል ለቢቢሲ ገልጸዋል፡፡ የአንዳንድ ሠራተኞች የሥራ ሁኔታ በቢሮ ወይም በፋብሪካ እንዲሠሩ የሚያስገድድ ከሆነ ድርጅታቸው እንደዚህ ዓይነት አንቀፅ ሊቀመጥ ይችላል ወይ የሚል ጥያቄ እንደደረሳቸው አክለው ገልጸዋል፡፡ "ክትባት መውሰድ ግዴታ አይደለም፤ እናም አንድ ሰው እንዲወስድ ማስገደድ አድልአዊ ነው" ብለዋል የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ፡
news-54361553
https://www.bbc.com/amharic/news-54361553
ከኤችአይ ቪ የተፈወሰው የመጀመሪያ ግለሰብ ህይወቱ አለፈ
ከኤች አይ ቪ ለመፈወስ የመጀመሪያ የሆነው ግለሰብ በካንሰር ህይወቱ አለፈ።
በቅፅል ስሙ "የበርሊኑ ህመምተኛ" ተብሎ የሚታወቀው ቲሞቲ ሬይ ብራውን መቅኒ (ቦን ማሮው) የለገሰው ግለሰብ ኤችአይቪ በተፈጥሮ ከማይዛቸው ጥቂት ሰዎች ውስጥ አንዱ ከመሆኑም ጋር ተያይዞ ነበር ያልተጠበቀ ፈውስ የመጣለት። ንቅለ ተከላውም የተካደበት ወቅትም በጎሮጎሳውያኑ 2007 ነበር። ቲሞቲ የፀረ ኤች አይ ቪ መድኃኒት መውሰድ ያቆመ ሲሆን ከቫይረሱ ነፃ መሆኑንም የህክምና ባለሙያዎች አረጋግጠዋል። የቲሞቲ ከቫይረሱ በዚህ መልኩ መፈወስም በሽታው ለወደፊቱ እንደሚድን ተስፋን የፈነጠቀ ነው በማለትም አለም አቀፉ የኤድስ ማህበረሰብ አስታውቆ ነበር። የአምሳ አራት አመቱ ቲሞቲ ትውልዱ አሜሪካዊ ሲሆን በኤች አይ ቪ መያዙንም ያወቀው በበርሊን ይኖር በነበረበት በጎሮጎሳውያኑ 1995 ነው። በ2007ም አኪዪት ማይሎይድ ሉኬሚያ በተባለ የደም ካንሰር አይነት መታመሙም ታወቀ። እናም የደም ካንሰሩንም ለመፈወስ በካንሰር የተበከለውን መቅኒ (ቦን ማሮው) ማጥፋትና በሌላ መቅኒም (ቦን ማሮው) መተካት (ንቅለ ተከላ) ማድረግ ነበር። የለጋሹ ግለሰብ ዘረመል ባልተለመደ መልኩ ኤች አይ ቪ በተፈጥሮ የማይዛቸውና የመከላከል አቅም ያለው ሲሲአር5 ተብሎ የሚጠራው መኖሩ ለቲሞቱም መፈወስ ምክንያት ሆኗል። ይሄም ዘረ መል ቲሞቲ ቫይረሱ ከደሙ ውስጥ እንዳይኖር ረድቶታል። ነገር ግን ለመፈወስ ምክንያት የሆነው የሉኬሚያ ካንሰር ከአመታት በኋላ በዘንድሮው አመት አገርሽቶ ጭንቅላቱን እንዲሁም አከርካሪ አጥንቱን ክፉኛ ጎድቶትም ለሞት አድርሶታል። "በከፍተኛ ኃዘንና ድንጋጤም ሆኜ ነው ቲሞቲ ህይወቱ እንዳለፈ የምናገረው። ከአምስት ወራት ካንሰር ትግል በኋላ እኔም፣ጓደኞቹና የቅርብ ሰዎቹ አጠገቡ ባለንበት ይህቺን አለም ጥሏት ሄዷል" በማለትም የህይወት አጋሩ ቲም ሆፍጀን በፌስቡክ ገፁ አጋርቷል። አክሎም "ቲም ከኤች አይቪ እንዴት እንደተፈወሰ በተደጋጋሚም ያወራ ነበር። ለብዙዎችም የተስፋ አምባሳደር ሆኗል" ብሏል።
news-47621605
https://www.bbc.com/amharic/news-47621605
ኢትዮጵያዊያን፣ ጃፓናዊትና ህንዳዊ በታጣቂዎች ተገደሉ
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ወረዳ ሁምነ ዋቀዮ በተባለ ቀበሌ ውስጥ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የአምስት ሰዎች መገደላቸውን የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ።
ታጠቂዎቹ ጥቃቱን የፈጸሙት ዛሬ (ማክሰኞ) ጠዋት አንድ ሰዓት ተኩል ገደማ ሲሆን፤ በጥቃቱም ሁለት የውጪ ሀገራት ዜጎች እና ሦስት ኢትዮጵያዊያን በአጠቃላይ አምስት ሰዎች መገደላቸውን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ገልጿል። • በምዕራብ ኦሮሚያ በታጠቁ ኃይሎች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 41 መድረሱ ተገለፀ • በምዕራብ ኦሮሚያ ምን ተከሰተ? በአካባቢው የተሰማራው ኮማንድ ፖስት አባል የሆኑት አቶ አደም ኢስማኤል ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት የውጪ ሃገር ዜጋ የተባሉት ሟቾች አንዲት ጃፓናዊትና አንድ ህንዳዊ ናቸው። በታጣቂዎቹ የተገደሉት ሰዎች ሰንራይዝ የሚባል ኩባንያ ሰራተኞች እንደነበሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ጥቃቱ የተፈጸመባቸው ሰዎች በአንድ መኪና ሲጓዙ በተጠቀሰው አካባቢ በተከፈተባቸው ተኩስ መገደላቸውን የጠቀሱት አቶ አደም፤ አጥቂዎቹ ኋላም መኪናውን በእሳት እንዳቃጠሉትም ተናግረዋል። • ኦነግ እና መንግሥትን ለማግባባት የሃገር ሽማግሌዎች እየጣሩ ነው • የኦነግ እና የመንግሥት እሰጣገባ በእሳት የተያያዘውን መኪና ማጥፋት በአካባቢው ከነበሩት ሰዎች አቅም በላይ ሆኖ በመቆየቱ የተገደሉት ሰዎች አስከሬን ለቃጠሎ መዳረጉንና ለመለየት አስቸጋሪ እንደነበር ተገልጿል። ከጥቃቱ በኋላ የጸጥታ አካላት ባደረጉት አሰሳ በግድያው የሚጠረጠሩ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ተገልጿል። ግድያውን የፈጸሙት ታጠቂዎች ማንነታቸው ያልታወቀ ሲሆን እንደሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ለጸጥታ ኃይሎች ጥቆማ ሰጥተዋል።
news-54778255
https://www.bbc.com/amharic/news-54778255
ምዕራብ ወለጋ፡ ግድያው የተፈጸመው ስብሰባ ተብለው በተጠሩ ሰዎች ላይ ነው ተባለ
የኦሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ባልቻ በምዕራብ ወላጋ ትናንት የተገደሉት ሰዎች ለስብሰባ በተጠሩበት ስፍራ ነው አሉ።
የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ በምዕራብ ወለጋ ዞን፣ ጉሊሶ ወረዳ፣ ጋዋ ቃንቃ ቀበሌ በሰላማዊ ዜጎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት የሰዎች ሕይወት ማለፉን አስታውቆ ነበር። አቶ ጌታቸው ለቢቢሲ እንደተናገሩት በሐሰተኛ መልኩ ነዋሪዎች ለስብሰባ ከሰበሰቡ በኋላ በተወረወረባቸው ቦምብ ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል። "በኦነግ ሸኔ ስም የሚንቀሳቀስው ቡድን ትናንት በስበሰባ ስም ሰዎችን ከሰበሰቡ በኋላ ቦምብ ወርውረውባቸው ጉዳት መድረሱን የሚጠቁም መረጃ ነው ያለን" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ሕዝብ በአንድ ቦታ ሰብስቦ በቦምብ ማቃጠል ለምን እንዳስፈለገ ግልጽ አይደለም። ጥቃቱ እጅግ ጭካኔ የተሞላበት ነው" ብለዋል። ጥቃቱ የተፈጸመው ከምሽቱ 12 ሰዓት አከባቢ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ጌታቸው፤ "ቦምቡን የወረወሩት ሐሰተኛ ስበሰባ የጠሩት ናቸው" በለዋል። አቶ ጌታቸው በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው መረጃ አጣርቶ የሚልክ ቡድን ወደ ሥፍራው ተልኳል በማለት በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎች አሃዝ ከመጥቀስ ተቆጥበዋል። "የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ እየተጠቀሰ ነው። ነገር ግን ትክክለኛውን ቁጥር ለማወቅ በአካባቢው ያለው አካል አጣርቶ እስኪልክልን እየተጠባበቅን ነው" ብለዋል አቶ ጌታቸው። የኦሮሚያ ክልል መግለጫ የኦሮሚያ ክልል ዛሬ ጠዋት ላይ ባወጣው መግለጫ፤ “ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ሕይወታቸው እንዲያልፍ ባደረገው የኦነግ ሸኔ ቡድን ላይ እርምጃ ይወሰዳል” ሲል አስታውቆ ነበር። “ትናንት በምዕራብ ወለጋ ዞን፣ ጉሊሶ ወረዳ፣ ጋዋ ቃንቃ ቀበሌ ጨለማን ተገን በማድረግ በተፈጸመው የሽብር ጥቃት ሰላማዊ ዜጎች ጭካኔ በተሞላበት መንገድ በአንድ ስፍራ ሕይወታቸው እንዲያልፍ ተደርጓል” ይላል የክልሉ መግለጫ። ለግድያው ተጠያቂ ነው ያለው ቡድን በሕዝቡ ላይ አሰቃቂ ጉዳት እያደረሰ እንደሆነ የክልሉ መግለጫ ይጠቁማል። ክልሉ በመግለጫው ምን ያክል ሰዎች በምን አይነት ሁኔታ እንደተገደሉ ያለው ነገር የለም። “የጥፋት ኃይሎቹ መንግሥት የፖለቲካ እና የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት እየሠራ ባለበት ወቅት በተቃራኒው በመቆም ጭቃኔ የተሞላበት ተግባር በሕዝቡ ላይ እየፈጸሙ ነው” ብሏል። ክልሉ በመግለጫው፤ "የኦነግ ሸኔ ሽፍታ ህወሓት ጋር በመሻረክ በኦሮሚያ ክልል እና በአገሪቱ ሰላም እና መረጋጋት እንዳይኖር ሲሰሩ ቆይተዋል" ብሏል። ቡድኑ በተለያዩ ወቅቶች ግጭት እንዲቀሰቀስ እንዳደረገ እና በሕገ ወጥ መንገድ የገቡ የጦር መሣሪያዎችን በመጠቀም በጸጥታ ኃይሎች፣ በመንግሥት ሠራተኞች እና በማኅበረሰቡ ላይ ግድያ መፈጸሙን የኦሮሚያ ክልል ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ድርጊቱ ሕብረተሰቡ ላይ የሥነ ልቦና ጫና እንደፈጠረ እንዲሁም የማኅበረሰቡ የእለት ከእለት ሕይወት በስጋት እንደተሞላም ተገልጿል። በተለይም በምዕራብ ኦሮሚያ ሕፃናት፣ ሴቶች፣ አረጋውያን እና ወጣቶች መገደላቸውን እና የአካል ጉዳትም እንደደረሰባቸው በመግለጫው ተጠቅሷል። ቡድኑ፤ ሰዎችን ጠልፎ በመውሰድ ጉዳት ሲያደርስ መቆየቱን የጠቀሰው መግለጫው፤ “በተለያዩ ጊዜያት የጸጥታ እና የአስተዳደር አካላት በተመሳሳይ መንገድ ጫካ ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ ሕይወታቸው እንዲያልፍ ሲያደርግ ቆይቷል” ብሏል። የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የሕዝቡን ሰላም ለማረጋገጥ፤ ሕዝቡን ባሳተፈ ሁኔታ የሕግ የበላይነትን የማስከበር ሥራ እያከናወነ መሆኑም ተገልጿል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ እርምጃ ይወሰዳል ስለማለታቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ማንነትን መሠረት ባደረጉ ጥቃቶች ማዘናቸው በፌስቡክ ገፃቸው ገልፀዋል። "የኢትዮጵያ ጠላቶች፤ "ወይ እኛ እንገዛለን፤ ወይ ሀገር አትኖርም" ብለው ተነሥተዋል። ለዚህም የጥፋት ዐቅማቸውን ሁሉ እየተጠቀሙ ነው። አንደኛው ዒላማቸውም የሕዝባችንን ቅስም መስበር ነው" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። "ግራ ቀኝ የሚያውቁ ሰዎችን እየሰበሰቡ በማሠልጠንና በማስታጠቅ በየአካባቢው ማንነትን መሠረት ያደረገ አረመኔያዊ ጥቃት ማድረስ" ጠላቶች ያሏቸው ሰዎች አላማ ነው ሲሉ በመግለጫቸው አትተዋል። "መንግሥት በተለያዩ ቦታዎች ሊፈጠሩ ይችላሉ ያላቸውን ጥፋቶች በቅድሚያ መረጃ ሰብስቦ ርምጃ በመውሰድ ሲያከሽፍ ቆይቷል። ነገር ግን ያለፈው ሥርዓት ያወረሰንን ቀዳዳዎች ሁሉ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ደፍኖ መጨረስ አልተቻለም" ይላል የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ኦፊሴላዊ ገፅ ላይ የሰፈረው መልዕክት። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጥፋት ኃይሎች ያሏቸው ከውጭና በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ከሚገኙ ሰዎች ትብብር እየተደረገላቸው ነው ሲሉም ወቅሰዋል። አክለውም "የጸጥታ አካላት ጥቃቱ ወደተፈጸመበት አካባቢ ተሠማርተዋል። ርምጃም እየወሰዱ ነው። በቀጣይም የሕዝባችንን ደኅንነት ለማስጠበቅ መንግሥት የመንግሥትነቱን ሥራ በቁርጥና በጽናት ይሠራል" ብለዋል። የክልሉ ፕሬዝደንት መልዕክት የክልሉ ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳም በዜጎች ላይ ለደረሰው ጥቃት "ጥልቅ ሃዘኔን እገልጽለሁ" ያሉ ሲሆን "በኦነግ ሸኔ አሸባሪ ቡድን ላይ እየተወሰደ ያለው ውጤታማ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ላረጋግጥ እወዳለሁ" ብለዋል። ፕሬዝደንት ሽመልስ "እንደዚህ አይነት የፈተና ወቅት የሕዝቦችን ወንድማማችነትና በጽናት አብሮ በመቆም ፈተናን የማለፍ ልምድን ያጠናክራል እንጂ ጠላት እንደተመኘው ሕዝቦችን የሚያባላ ፈጽሞ አይሆንም" ብለዋል። የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ መግለጫ የአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ባወጣው መግለጫ፤ ትላንት ምሽት የተፈጸመው ጥቃት መጠን እና ዝርዝር ሁኔታዎችን ከፌደራልና ከክልሉ መንግሥት ጋር በመተባበር እየተጠራ ነው ብሏል። "በዚህ ጭካኔ በተሞላበት ድርጊት የአማራ ሕዝብና ድርጅታችን የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ክፉኛ አዝኗል፤ ተቆጥቷል። ይህን ድርጊት የሚያወገዝ ከመሆኑም በላይ አጥፊዎቹ እንደየሥራቸው በሕግ አግባብ ሊዳኙ ይገባል ብለን እናምናለን" ሲልም መግለጫው አክሏል።
news-45267604
https://www.bbc.com/amharic/news-45267604
ፍኖተ ካርታው ወደ ቀድሞ የትምህርት ፖሊሲ ሊመልሰን ይሆን ?
ይፋ የሆነው ፍኖተ ካርታ ሰፊ መዋቅሮችን ያካተተ በመሆኑ ትምህርት ሚኒስቴርን በሶስት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የሚያደራጅ መሆኑ ተነግሯል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶቹም የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ሚኒስቴር፣ አጠቃላይ የትምህርት ስልጠና ሚኒስቴርና የክህሎትና ፈጠራ ሚኒስቴር መሆናቸው ተነግሯል። ለሁለት ዓመታት ጥናት ሲደረግበት የቆየው የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ነሐሴ 14፣ 2010 ዓ.ም በጠቅላይ ሚንስትር ፅ/ቤት ይፋ ተደርጓል። የቀረበውን ጥናት መሰረት በማድረግም ውይይት እየተደረገበት ይገኛል። ከውይይቱ ተሳታፊዎች አንዷ የሆኑት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር በርሄ "የፍኖተ ካርታው እየተተገበረ ያለውን የትምህርት ፖሊሲ ውጤቶችንና ተግዳሮቶቹን በመለየት የቀረበ ነው'' ይላሉ። • ዩኒቨርሲቲ ብሎ ለመጥራት የሚያስቸግሩ "ዩኒቨርሲቲዎች" • የብቃት ማረጋገጫ ምዘና የትምህርት ጥራትን ያሻሽል ይሆን? • 'ዕውቀት ሳያገኙ ትምህርት ቤት መመላለስ' ውይይቱ በቡድን ተከፋፍሎ የተካሄደና በእያንዳንዱ ቡድን ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ የትምህርት ባለሙያዎችና መምህራን የተሰባጠረ ነው። ከተነሱት ተግዳሮቶች መካከል የጎልማሶች ትምህርት ውጤታማ አለመሆኑና አሁንም በርካታ ያልተማሩ ወገኖች መኖራቸው ተነግሯል። ህፃናት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በ6 ዓመት ዕድሜያቸው እንዲጀምሩ እና ከዚህ ቀደም የአንደኛ ደረጃ ትምህርት እስከ ስምንተኛ ክፍል የነበረው እስከ ስድስት ቢሆንና ለከፍተኛ ትምህርት የሚዘጋጁበት አራት ዓመት እንዲሆን ጥናቱ ጥቁሟል ሲሉ ወ/ሮ አስቴር ተናግረዋል። ወ/ሮ አስቴር፤ የመምህራንና ባለሙያዎች ጥቅማ ጥቅም፣ የከፍተኛ ትምህርት ጥራት ችግር፣ የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ሶስት ዓመት የነበረው ወደ አራት ዓመት ከፍ እንዲል፣ የአማርኛ ቋንቋና እንግሊዝኛ ቋንቋ ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት እንዲሰጥ የተነሳበት ነው ሲሉ ከብዙ በጥቂቱ ይገልፃሉ። • ሙስጠፋ ኡመር የሶማሌ ክልል ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ • ጎዳና ተዳዳሪዎችን በህክምና መታደግ • ደቡብ አፍሪካዊው ዘረኝነትን በተላበሰ ንግግሩ ከስራ ተባረረ ወ/ሮ አስቴር "የአተገባበር ችግር ስላለ ነው እንጂ ቀድሞ የነበረው ፖሊሲ የአማርኛ ቋንቋ እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት እንዲሰጥ ያዛል" ይላሉ አሁን በትግበራ ላይ ያለው ፖሊሲ ቀረፃ ላይ እንደተሳተፉ በማስታወስ። ሌሎች ትምህርት ጋር የተገኛኙ ጉዳዮችም ላይ ውይይት ማድረጋቸውን ገልፀውልናል። አጥኝዎቹ ምን ይላሉ? "ከማህበረሰቡ በርካታ ትምህርት ነክ ጉዳዮች ሲነሱ ቆይተዋል" ይላሉ ከአጥኝዎች አንዱ የሆኑትን ዶ/ር ፈቀደ ቱሊ። እነዚህንም ጥያቄዎች ለመፍታት በትምህርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት የጥናት ቡድን ተዋቅሮ እስካሁን በትምህርት ስርዓቱ የተመዘገቡ ውጤቶችና ስርዓቱ ውስጥ ያሉ ክፍተቶች፣ ወደፊት እንዴት ይሻሻላል በሚል ጥናቱ ለሁለት ዓመታት ሲካሄድ ቆይቷል። የፍኖተ ካርታውም ቅድመ መደበኛ ትምህርትና አንደኛ ደረጃ ትምህርት፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት፣ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት፣ የትምህርት አስተዳደር ጉዳይ በሚል ተከፋፍሎ በ36 አጥኝዎች መካሄዱን ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ጥናቱ ጥልቅና ሰፊ በመሆኑ የተገኙ ውጤቶችን አንድ ሁለት ብሎ መዘርዝር ያዳግታል ሲሉ በደምሳሳው አልፈውታል። በፍኖተ ካርታው የተነሱ ነጥቦች ወደ ድሮው የትምህርት ስርዓት ሊመልሰን ይችላል ወይ ያልናቸው ባለሙያው፤ "የተሻለ ሆኖ ከተገኘ ሃሳብ መውሰዱ ጉዳት ባይኖረውም፤ ይህ ግን ወደ ድሮው የትምህርት ስርዓት የሚመልስ አይደለም። ምን አልባት በአንዳንድ ነጥቦች ላይ የመመሳሰል ነገር ሊኖረው ይችላል። ለመመለስ ዘመኑም አይፈቅድም" ሲሉ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል። በተለይ በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የፍኖተ ካርታ ጥናቱን እንደ ትምህርት ፖሊሲ ተደርገው እየተወሰዱ መሆናቸውን ያነሳንላቸው ዶክተር ፈቀደ፤ "ከየት አምጥተው እንደሆነ አይገባኝም፤ ፍኖተ ካርታው ረቂቅ በመሆኑ መረጃ የማሰባሰብ ሂደቱ እንደ ቀጠለ ነው፤ ህዝቡ ሳይወያይበትና ጥናቱ ዳብሮ ለሚመለከተው አካል ሳይቀርብ ወደ ፖሊሲ የሚለወጥበት ምንም ምክንያት የለም" ሲሉ መልሰዋል። ተሳታፊዎቹ እነማን ናቸው? በረቂቅ ፍኖተ ካርታው ጥናት ውይይት ላይ ከ1300 በላይ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል። ተሳታፊዎቹም ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ የትምህርት ባለሙያዎች፣ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች፣ የትምህርትና ስልጠና ቋሚ ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ ሎሎች ባለ ድርሻ አካላትም ተገኝተዋል። የትምህርት ሚኒስቴር ቀጣይ ርምጃ ጥናቱ ከተጠናቀቀ በኋላ መምህራን፣ ተማሪዎችና፣ ህብረተሰቡና በትምህርት ጉዳይ የሚመለከታቸው አካላት ከመጭው መስከረም ጀምሮ ውይይት እንደሚደረግበት በትምህርት ሚኒስቴር የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳሬክተር ወ/ሮ ሀረጓ ማሞ ገልፀዋል። ይህ ውይይት ከተጠናቀቀ በኋላም ወደ 15 ዓመቱ ዕቅድ ይካተታል የሚባሉት ሃሳቦች ተካተው ፍኖተ ካርታው ይዘጋጃል። ምንም እንኳን ረቂቅ ፍኖተ ካርታው ያልተጠናቀቀ በመሆኑ አሁን ላይ የቀረበው ፍኖተ ካርታ የፖሊሲ ለውጥ ሊያስከትል ይችላል አይችልም ብሎ መናገር ባይቻልም፤ የህብረተሰቡን ውይይት መነሻ በማድረግ ሃሳቡን አፅድቆ ወደ ቀጣይ ተግባር መሸጋገሩ ግን አይቀርም ብለዋል።
news-53393151
https://www.bbc.com/amharic/news-53393151
በትግራይ ክልል የምርጫ ኮሚሽን አባላትን ለመምረጥ የሕዝብ ጥቆማ እየተሰበሰበ ነው
በትግራይ ክልል የምርጫ ኮሚሽን አባላት ለመምረጥ የሕዝብ ጥቆማ ከቅዳሜ ጀምሮ እየተሰበሰበ መሆኑን የክልሉ ምርጫ ኮሚሽን ጊዜያዊ አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አሰፋ ገብረሥላሴ ለቢቢሲ ገለጹ።
በትግራይ ክልል ስድስተኛ ዙር ክልላዊና አካባቢዊ ምርጫ ለማካሄድ አስፈፀሚ ኮሚሽን ለማቋቋም የክልሉ ምክር ቤት በወሰነው መሰረት ሕዝቡ የኮሚሽኑ አባላትን እንዲጠቁም ጥሪ ቀርቧል። ከሕዝቡ ጥቆማ መሰብሰብ የተጀመረው ቅዳሜ ሲሆን የሚያበቃው ደግሞ ማክሰኞ ሐምሌ 7 2012 ዓ.ም መሆኑ ሰብሳቢው ተናግረዋል። በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት አገራዊ ምርጫ ከተራዘመ ወዲህ የትግራይ ክልል ክልላዊ ምርጫውን ለማካሄድ መወሰኑ ይታወሳል። የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከክልሉ ጥያቄ ቢቀርብለትም በወቅቱ ጥያቄውን ተቀብሎ ለማስተናገድ እንደማይችል ገልጾ ነበር። ከዚህ በኋላ ክልሉ የራሱን ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችለውን የምርጫ ሥነ ምግባር ሕግ እንዲሁም የኮሚሽኑን ማቋቋሚያ አዋጆች አጽድቋል። የትግራይ ክልል ምርጫ ኮሚሽን ጊዜያዊ አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አሰፋ ገብረሥላሴ ለቢቢሲ እንዳሉት እስካሁን ድረስ ከአገር ውጪና ውስጥ ከ300 በላይ ሰዎች ተጠቁመዋል። የኮሚቴ ሰብሳቢው አቶ አሰፋ አክለውም ጥቆማ መስጠቱ እንደተጠናቀቀ በነጋታው ረቡዕ የተጠቆሙ ሰዎች ለክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ስማቸው ቀርቦ ከፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ውይይት ይደረግበታል። ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት ከተደረገ በኋላ አስር ሰዎች ተመርጠው ለክልሉ ምክር ቤት በማቅረብ የኮሚሽኑ ኮሚሽነርና ምክትልን ጨምሮ አምስት አባላት እንዲፀድቁ ይደረጋል ብለዋል። ህወሓት ከዚህ በፊት ከተቃዋሚ ድርጅት አመራሮች፣ ሳልሳይ ወያነ፣ ባይቶና፣ እንዲሁም የትግራይ ነጻነት ጋር በምርጫ ህጉ ላይ ተወያይተው ነበር። እስካሁን ድረስ በትግራይ ክልል ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አረና ትግራይና፣ የትግራይ ዲሚክራሲያዊ ንቅናቄ ድርጅቶች በውይይቱ ላይ አልተሳተፉም። ለትግራይ ክልል ምርጫ ኮሚሽን አባልነት ለመመረጥ መስፈርቶች የተቀመጡ ሲሆን፣ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው፣ የክልሉ ቋንቋ የሚችል፣ የየትኛውም ፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆነ፣ ለክልሉም ሆነ ለአገሪቱ ሕገ መንግሥት ተገዥ የሆነ፣ ሥነምግባር ያለው፣ ከምርጫ ጋር በተያያዘ ትምህርት፣ ልምድና አቅም ያለው ግለሰብ መሆን እንዳለበት ተዘርዝሯል።
news-46589370
https://www.bbc.com/amharic/news-46589370
ሀና ጥላሁንና ጓደኞቿ የእናቶችን ምጥ በሚቆጣጠረው የፈጠራ ሥራቸው አሸነፉ
ሀና ጥላሁንና ጓደኞቿ በጂማ ዩኒቨርሲቲ የባዮ ሜዲካል ኢንጂነሪንግ ትምህርታቸውን ተከታትለው በ2010 ዓ.ም ተመርቀዋል።
ይሁን እንጂ የእናቶችና ሕጻናት ጤንነት ጉዳይ ወጣቶቹን ያሳሰባቸው ገና ትምህርታቸውን ሳያጠናቅቁ ነበር። "ሴት በመሆናችን ነገ እኛንም የሚገጥመን ጉዳይ ነው" ይላሉ ወጣቶቹ። ታዲያ ሃሳብ ብቻ ሆኖ እንዳይቀር በመመረቂያ ጽሁፋቸው ለዚሁ ጭንቀታቸው መላ የሚሆን ሃሳብ ጸነሱ። የጥናታቸው ይዘት በወሊድ ወቅት የእናቶችን ምጥ የሚቆጣጠር መሣሪያ ለመሥራት የሚያስችል ነበር። በቡድን በሠሩት በዚህ የመመረቂያ ጽሁፋቸውም በይበልጥ ይህንኑ ሃሳብ አጎለበቱት። የፈጠራ ሥራቸው ሀ ሁ ም በዚህ መልኩ ተጀመረ። በጋራ ሆነው የእናቶች ምጥ መቆጣጠሪያ መሳሪያ (Agumentation and Induction Monitoring Device) እውን አደረጉት። • ''የሚፈርስ የግድቡ አካል የለም'' የግድቡ ዋና ሥራ አስኪያጅ ይህንን የፈጠራ ሥራ ከሠሩት ወጣቶች መካከል አንዷ የሆነችውና ቡድኑን ወክላ ያነጋገርናት የ23 ዓመቷ ሀና ጥላሁን ሁሉም ለጥናትና ምርምር የተለየ ፍቅር እንዳላቸው ትናገራለች። በመሆኑም የእናቶችን አወላለድ የህክምና ሂደት ለማየት የጂማ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ የካቲት፣ የጦር ኃይሎችና የሌሎች ሆስፒታሎች ማዋላጃ ክፍሎችን ጎብኝተዋል፤ የዘርፉ ሐኪሞችንም አማክረዋል። ይህም ብቻ ሳይሆን እናቶች ለመውለድ ዝግጁ መሆን አለመሆናቸውን እንደ ሐኪሞቹ እነርሱም በወላድ እናቶች የማህጸን በር ጣታቸውን በማስገባት ስሜቱን ለመረዳት ሞክረዋል። ከዚህ በኋላ ነበር እነሱ የሠሩት የአንዲትን ሴት የምጥ ሁኔታ የሚቆጣጠረው መሳሪያ ያለምንም ንክኪ ለእናትየዋም ሆነ ለሐኪሞች የሚኖረውን ጠቀሜታ በይበልጥ መረዳት የቻሉት። የፈጠራ ሥራቸው በቀበቶ መልክ የተዘጋጀ ሲሆን ሆድ ላይ በማስቀመጥ አንዲት ሴት ምጥ መጀመሯን አለመጀመሯን የሚያመላክት ነው፤ ምን ያህል መጠን መድሃኒት እንደሚያስፈልጋትም የሚጠቁም መሣሪያ እንደተገጠመለትም ሀና ታስረዳለች። • ሳዑዲ የአሜሪካ 'ጣልቃ ገብነትን' አወገዘች ሀና እንደምትለው መሣሪያው ምንም ዓይነት የኤሌክትሪክ ጨረር የሌለው ሲሆን በእናትየዋም ሆነ በፅንሱ ላይ የሚያሳድረው አንዳችም ተፅዕኖ የለም። "ልክ እንደ አልትራ ሳውንድ መሣሪያ ሲሆን ልዩነቱ አልትራ ሳውንድ በምስል መልክ ሲያሳይ የእኛ ግን በቁጥር ይገልጻል" ትላለች። መሣሪያው በቀላሉ በተገኙና በርካሽ ከውጭ አገር በተገዙ ቁሳቁሶች መሠራቱ ልዩ እንደሚያደርገው የምትናገረው ሀና በአጠቃላይ 2500 ብር ብቻ እንዳስወጣቸው ትናገራለች። ከቦታ ቦታ ለማንቀሳቀስም አይከብድም፤ የሚመዝነው 1.5 ኪሎግራም ብቻ ነው። እርሷ እንደምትለው ውስብስብ ባለመሆኑም በ30 ደቂቃ ሥልጠና ማንኛውም ሰው ተገንዝቦ ሊሠራበት ይችላል። በተለይ በአገራችን የሚታየው የመብራት መቆራረጥ ችግርን ከግምት በማስገባት የፈጠራ ሥራውን በባትሪ እንዲሠራ ለማድረግ እቅድ እንዳላቸው ትናገራለች። "ያደጉት አገራት እንዲህ ዓይነት መሣሪያ የሚጠቀሙ ሲሆን፤ ዋጋው የማይቀመስ በመሆኑ በአገር ውስጥ የጎበኘናቸው ሆስፒታሎች መሣሪያው የላቸውም" የምትለው ሀና የሠሩት ፈጠራ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሊያበረክት እንደሚችል እምነት አላት። በውድድሩ አሸናፊ ከመሆን ባሻገር መሣሪያው በደንብ ተፈትሾ ተግባር ላይ ሲውል ማየት የሀናና የጓደኞቿ ህልም ነው። የእናቶች ምጥ መቆጣጠሪያ አዋላጅ ሐኪምና በአዋላጅ ሐኪሞች ማህበር የቀድሞ ፕሬዚደንት የነበሩት አቶ ያለው ላይቀር አንዲት እናት ምጥ ላይ ሆና መግፋት ቢያቅታትና ብትደክም ምጡን ለማፋጠን የሚጠቀሙት መድሃኒት (Augmentation)፤ በሌላ በኩል ደግሞ የመውለጃዋ ቀን ደርሶ ምጥ ባይጀምራትና የማህፀን በሯ ዝግ ከሆነ ምጥ ለማስጀመር የሚጠቀሙት (Induction) እንደሚባል ያብራራሉ። ምንም እንኳን እነዚህን ሁኔታዎች ለማረጋገጥ እናትየዋ በምታሳየው ምልክቶች መረዳት ቢቻልም በማህፀን በር ገብቶ በእጅ ማየት ግን ግድ ነው ይላሉ። የማህፀን በሯ ዝግ ከሆነ የአንድን ጣት ጫፍ እንኳን ማስገባት አይችልም፤ በዚህም መሠረት ልኬቱ እናትየዋ ልትወስዳቸው የሚገቡ መድሃኒቶችን ለመስጠትና ለመመጠን እንደሚያስችላቸው ይናገራሉ ባለሙያው። እርሳቸው ባላቸው ልምድ ይህንን የሚያሳይ መሣሪያ ጎራ ባሉባቸው እንግሊዝና አሜሪካ ቢያዩም ኢትዮጵያ ውስጥ ግን እስካሁን እንዳልገጠማቸው ይናገራሉ። • ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን? ይህ በውጭው ዓለም ያዩት መሣሪያ በአንድ ጊዜ አስር የሚሆኑ እናቶችን ምጥና የአወላለድ ሁኔታ መከታተል ያስችላል ይላሉ። "እንደዚህ ዓይነት መሳሪያዎች ደግሞ ሥራን በማቀላጠፍና በትንሽ የሰው ኃይል መስራት በማስቻል ጠቀሜታቸው ከፍተኛ ነው" የሚሉት አቶ ያለው የወጣቶቹን ፈጠራም ሳያደንቁት አላለፉም። በተለይ አንዲት ሴት ስትወልድ ማንም ሊያያት አይገባም የሚል ልማድ ባለበት አገር፤ ወላዶች የተዋልዶ አካላቸውን ነጻ ሆነው ሌላ ሰው እንዲነካቸው እንደማይፈልጉ ያስረዳሉ። በዚህም ምክንያት "እናቶቹ ስለሚሸማቀቁና ደስተኛ ስለማይሆኑ የባሰ ሰውነታቸው እንዳይፍታታ ቆጥበው ይይዙታል" ይላሉ አቶ ያለው። እንዲህ ዓይነት የባህል ችግሮችን ለመፍታትም ሆነ ጉዳዩን ከማቅለል አንፃር የመሳሪያው ጠቀሜታ ከፍተኛ እንደሚሆንም እምነት አላቸው። ይሁን እንጂ እያንዳንዱ ቴክኖሎጂ የራሱ የሆነ ተጽዕኖም ሊኖረው ስለሚችል ሳይንሱን ማሳደግና መፈተሽ እንደሚያስፈልግ ይመክራሉ። ውድድሩ በማን ተዘጋጀ አፍሪካውያን ወጣቶች የፈጠራ ሥራቸውን ያቀረቡበት ይህ ውድድር በኢትዮጵያ ወጣቶች ሳይንስ አካዳሚ፣ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ፣ ተቀማጭነቱን ፈረንሳይ አገር ባደረገው Association for Promotion Science in Africa (APSA) እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ትብብር ነበር የተዘጋጀው። በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የሚዲያ ኮሚዩኒኬሽን ባለሙያው አሰግደው ሽመልስ እንደተናገሩት ውድድሩ በፈጠራ ሥራ ላይ የተሠማሩ ወጣቶች ሥራዎችን በአፍሪካ ደረጃ አወዳድሮ ማቅረብ፣ ድጋፍ ማድረግና አስፈላጊውን ሥልጠና እንዲያገኙ ማስቻል ዋና ዓላማው ነበር። በመሆኑም ለመላው አፍሪካ ወጣቶች በቀረበው የውድድር ጥሪ 129 የፈጠራ ሃሳቦች የቀረቡ ሲሆን ከ7 የአፍሪካ አገራት፤ የካሜሩን፣ ቤኒን፣ ግብፅ፣ ኢትዮጵያ፣ ናይጀሪያ፣ ቶጎና ኡጋንዳ ወጣቶች ለመጨረሻ ዙር መሻገር ችለዋል። የእነዚህ ወጣቶች ሥራ የሆኑት የግብርና ሥራን የሚያቀላጥፉ ፣ የቤት ውስጥ ሥራን የሚያቃልሉ፣ ከወሊድ ጋር በተያያዘ የእናቶችና ህጻናትን ሞት ለመቀነስ የሚረዳ መሣሪያ፣ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሠራ ምርታማ የሽመና መሣሪያ፣ አዝዕርትን የሚያጠቁ ነፍሳትን በኤሌክትሪክ ዘዴ ለአርሶ አደሮች መረጃ ማቅረብ የሚችል ቴክኖሎጂዎች ቀርበው ለአራት ቀናት ተጎብኝተዋል። • የሃምዛ ሃሚድ ገመድ አልባ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ በዚህም በኢትዮጵውያን ወጣቶች የተሠራው የምጥ መቆጣጠሪያ መሣሪያ የአንደኝነት ደረጃ በመያዝ አሸናፊ መሆን ችሏል። በዕርቅ እስከመቼና በጓደኛው የተሠራው በኤሌክትሪክ የሚሠራ የሽመና መሣሪያ ሁለተኛ ደረጃን ሲይዝ የካሳቫ ተክልን ከቆሻሻና ከሰው ንክኪ በጸዳ መልኩ የተለያዩ ምርቶችን እንዲሰጥ የሚያስችለው የካሜሩናዊው የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ፈጠራ በሦስተኝነት ተመርጧል። "እንዲህ ዓይነት ውድድሮች በፈጠራ ሥራ ላይ የተሠማሩ ወጣቶችን ለማበረታታት ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው" የሚሉት አቶ አሰግደው ተመሳሳይ ውድድሮችን በየዓመቱ ለማካሄድ እቅድ እንደተያዘም ለቢቢሲ ገልጸዋል።
news-55359920
https://www.bbc.com/amharic/news-55359920
ትግራይ፡ የተባበሩት መንግስታት ለተጎጂዎች የ36 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ
የተባበሩት መንግሥታት በሰሜናዊ ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ባለው ግጭት ምክንያት ለተጎዱ ሰዎች የሚሆን 36 ሚሊየን ዶላር የድንገተኛ ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል።
የተባበሩት መንግስታት እንዳለው 25 ሚሊየን ዶላር የሚሆነው የድጋፍ ገንዘብ የታመሙትንና ጉዳት የደረሰባቸውን ለማከም የሚረዱ መድሀኒቶችን ለመግዛት እንዲሁም ምግብና ንጹህ የመጠጥ ውሃ ለማቅረብ የሚውል ነው። ቀሪው 10.6 ሚሊየን ዶላር ደግሞ በጎረቤት አገር ሱዳን ለሚገኙ በሺዎች ለሚቆጠሩ ስደተኞች መጠለያዎችን ለመገንባት፣ የጤና አገልግሎት ለመስጠት እና ንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ለማረጋገጥ ይውላል ተብሏል። '' እንዲህ አይነት ግጭቶች አንድ ጊዜ ከቁጥጥር ውጭ ከሆኑ በኋላ ለማስቆም ከባድ ናቸው። የሞቱትን መመለስ አይቻልም፤ ሰዎች ላይ የሚደርሰውም ሀዘን ለዘላለም የሚኖር ነው። በአሁኑ ሰአት ህጻናት እርዳታ ማግኘት አልቻሉም። ምንም ገደብ በሌላው መልኩ እንድንንቀሳቀስ ሊፈቀድልን ይገባል'' ብለዋል በተባበሩት መንግስታት የድንገተኛ እርዳታ አስተባባሪው ማርክ ሎውኩክ። በሌላ በኩል በትግራይ ክልል ባለው ግጭት ምክንያት 2.3 ሚሊዮን የሚሆኑ ህፃናት ከሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ውጪ መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት ከትናንት በስቲያ ማስታወቁ የሚታወስ ነው። "ከእነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ ስደተኛና የተፈናቀሉ ናቸው። በአጠቃላይ ህፃናቱን መጠበቅ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ሥራ ነው" በማለት የተባበሩት መንግሥታት የዓለም አቀፉ የህፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) ኃላፊ አስታውቀዋል። ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የሰብዓዊ እርዳታዎችን ለማድረስ ስምምነት ላይ ቢደረስም ድርጅቶቹ በክልሉ የእርዳታ አቅርቦት ለማድረስ አልተቻለም እያሉ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ከትግራይ ኃይሎች ጋር የገባበት ግጭት የተቀሰቀሰው ጥቅምት 24/ 2013 ዓ.ም እንደነበር የሚታወስ ሲሆን በዚህ ግጭት በርካታ ሰዎች ሲገደሉ ከ60 ሺህ በላይ የሚሆኑ ደግሞ ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን መሰደዳቸው ይነገራል። "ለህፃናቱ የሚሰጠው እርዳታ አቅርቦት በዘገየ ቁጥር፣ ምግብ፣ በችግር ለተጋለጡት ህፃናትን ለማድረስ የሚያስፈልጉ ሌሎች አልሚ ምግቦች፣ ህክምና፣ ውሃ፣ ነዳጅና እና ሌሎችም አስፈላጊ ነገሮች እያጠሩ ወደ ከፋ ሁኔታ ያመራሉ" ብሏል ዩኒሴፍ ባወጣው መግለጫ። አክሎም "አፋጣኝ፣ ዘላቂ፣ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ማንንም ባላገለለ መልኩ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ለየትኛውም ቤተሰብ በያሉበት እንዲመቻች እንጠይቃለን" ብሏል ድርጅቱ። ባሳለፍነው ሳምንት ደግሞ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ተቋም በትግራይ ወታደራዊ ግጭት ከተከሰተ በኋላ በክልሉ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ሁኔታ አሳስቦኛል ማለቱ የሚታወስ ነው። ድርጅቱ ኤርትራውያን ስደተኞች መገደላቸውን እንዲሁም በግድ ታፍነው ወደ ኤርትራ እየተወሰዱ እንደሆነ የሚያሳዩ ሪፖርቶች እጅግ እንዳሳሰበው አስታውቋል። የተመድ የስደተኞች ክንፍ ኃላፊ ፊሊፖ ግራንዲ ስደተኞቹን እንዳጋጠሙ የተጠቀሱት ድርጊቶች ተፈጽመው ከሆነ ከፍተኛ የዓለም አቀፍ ሕግ ጥሰት ነው ብለዋል። ባሳለፍነው ሳምንት አርብ ዕለት ኤርትራውያን ስደተኞችን በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግሥት፤ የተካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ ምንም አይነት ስጋትን የሚደቅን እንዳልሆነ አመልክቶ፤ ነገር ግን በተሳሳተ መረጃ ሳቢያ ከካምፖቻቸው ወጥተው ወደ አዲስ አበባ የሄዱ ስደተኞች እንዳሉ ገልጿል። ጨምሮም በትግራይ ክልል ከሚገኙ የስደተኞች መጠለያዎች ወደ አዲስ አበባ የሄዱ ስደተኞችን እየመለሰ እንደሆነም አስታውቋል። ትግራይ በሚገኙ የስደተኛ ማቆያዎች ካምፖች ውስጥ በአገራቸው ፖለቲካዊ እስርና አስገዳጅ ወታደራዊ አገልግሎትን የሸሹ ወደ 100 ሺህ የሚጠጉ ኤርትራውያን ስደተኞች እንደሚገኙ ይነገራል።
44138789
https://www.bbc.com/amharic/44138789
“አንቺሆዬ”፡ የኢትዮጵያዊያት ታሪክን መናገር
ባለፈው ሳምንት ማብቂያ በአገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውና "አንቺሆዬ" የተሰኘው ፌሚኒስት ፊልም ፌስቲቫል ተካሄዷል።
ፌስቲቫሉ ምሳሌ የሆኑ ኢትዮጵያዊያት ታሪክን የመናገር መንፈስን የተላበሰም ነበር። ዝግጅቱ ብዙ ጊዜ እንዲሁ በፊልም ስለምትሳለው ሳይሆን የዛሬዋን እናም ብዙዎች ራሳቸውን ሊያዩ ስለሚችሉባት ሴት ለምን አይወራም አይነገርም? የሚል ጥያቄንም ያነገበ ነበር። የአርበኛዋና የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ስንዱ ገብሩን ህይወት የሚያስቃኘው ፊልም በፌስቲቫሉ ለእይታ ከበቁት ፊልሞች አንዱ ነበር። ሴቶች ከወንዶች እኩል እንዲቆሙ በማይጠበቅበትና ሴት ልጅ እንደዚህ ወይም እንደዚያ መሆን አለባት የሚለው የማህበረሰቡ ጫና ያይል በነበረበት፤ በእርሷ ዘመን እንደ ፍላጎቷና እንደ እምነቷ በኖረችው አስናቀች ወርቁ ህይወት ዙሪያ የሚያጠነጥን ፊልምም ታይቷል። ሴታዊትና የሎው ሙቭመንት "አንቺሆዬን" ያዘጋጁት ሚዲያ ማህበረሰብንና ባህልን በመቅረፅ ረገድ ያለውን ተፅኖ በማጤን ነው። የየሎው ሙቭመንቷ ረድኤት ከፍአለ "ያሳየነው የፌሚኒስት (የሴቶች እኩልነት) ሃሳቦችን ለማንፀባረቅና ከሥርዓተ-ፆታ ጋር በተያያዘ በማህበረሰቡ ዘንድ ሊቀየሩ ይገባል፣ ለውጥ ያስፈልጋል የምንልባቸውን ጉዳዩች የሚያመላክቱ ፊልሞችን ነው" ትላለች። በፌስቲቫሉ የውይይት መድረኮችን ተዘጋጅተው ነበር። በመገናኛ ብዙሃን የሴቶች ውክልና ምን ይመስላል? በፊልሞች ላይ ሴቶች የሚሳሉት እንዴት ነው? የሚሉና መሰል ርዕሰ ጉዳዩች ተነስተው የነበረ ሲሆን፤ በፊልሙ ኢንዱስትሪ ተጠቃሽ የሆኑት አዜብ ወርቁና መአዛ ወርቁም ጽሁፍ አቅራቢዎች ነበሩ። "ሥራ የላትም" የተሰኘውን ፊልም ያዘጋጀው ሃኒባል አበራም ፅሁፍ አቅርቧል። "አብዛኛውን ጊዜ ፊልም ላይ የሚሳሉት ሴቶች እኛን ልናይ የማንችልባቸው ናቸው" ትላለች የሴታዊቷ ካምላክነሽ ያሲን። በውይይቱ ተሳታፊ የነበሩ የፊልም ፕሮዲውሰሮችና ዳይሬክተሮች ከተለመደው ሴቶች ከሚሳሉበት መንገድ መውጣት ከባድ እንደሚሆንባቸው መግለፃቸውን ትናገራለች። በአጠቃላይ ፌስቲቫሉ የፌሚኒስት ሃሳቦችን ማስረፅን ጨምሮ ሴቶች በሚዲያ የሚሳሉበት መንገድ እንዲስተካከል አስተዋፆ እንደሚያደርግ ታምናለች። ፌስቲቫሉ የተካሄደው በቫንዳስ ሲኒማ ባለፈው ሳምንት ከአርብ እስከ እሁድ ነበር። የመጀመሪያው ፌሚኒስት ፊልም ፌስቲቫል ከመሆኑ አንፃር የታዳሚው ቁጥር ጥሩ የሚባል እንደሆነ አዘጋጆቹ ገልፀዋል። የሴቶች ሚና በቴክኖሎጂ ዘርፍም በፌስቲቫሉ አንድ መወያያ ርእሰ ጉዳይ ነበር።
news-41320265
https://www.bbc.com/amharic/news-41320265
አፍሪካ ውስጥ ጥሬ ገንዘብ ሊቀር የሚችልበት ሀገር የት ይመስልዎታል? ሶማሊላንድ?
ከሶማሊያ እአአ በ 1991 ተለይታ የራሷን ነፃ ሀገር የመሰረተች ቢሆንም በኣለም አቀፉ ማህበረሰብ ችላ ተብላ ቆይታለች። ምንም እንኳን በዓለም አቀፍ መድረክ የምትታወቅበት ነገር ባይኖራትም በጥሬ ገንዘብን መገበያየትን ለመቀየር በዝግጅት ላይ ነች።
በሶማሌላንድ ሀርጌሳ የተንቀሳቃሽ ስልካቸውን በመጠቀም ግብይት ሲያደርጉ በዋና ከተማዋ ሀርጌሳ በሰፈር ሱቆችም ውስጥ፣ በመንገድ ዳር ወይም በትልልቅ መደብሮች በተንቀሳቃሽ ስልክ የሚደረጉ ክፍያዎች የአገሪቷ መደበኛ መገበያያ መንገድ ከሆነ ሰንበትበት ብሏል። በሶማሊላንድ ውስጥ ያሉ የሱቅ በደረቴዎችና ሸማቾች ኢንተርኔት በማያስፈልገው ቀላል ፕሮግራም ይገበያያሉ። "በአሁኑ ወቅት ብዙዎቹ የሚከፍሉት የተንቀሳቃሽ ስልካቸውን በመጠቀም ነው።" በማለት የሚናገረው ኡመር በአንደኛው እጁ ክፍያ ለመፈፀም እየሞከረ "በጣም ቀላል ሂደት ነው።" በማለትም በተጨማሪ ይናገራል። በቴክኖሎጂ ያደጉ ሀገራትም ሆነ ያላደጉ ሀገራትን ግብይትን ጥሬ ገንዘብን በማያካትት መንገድ ለማድረግ በሂደት ላይ ቢሆኑም፤ የሶማሊላንድ ከፍተኛ ለውጥ ለየት ተብሎ የሚታይ ክስተት ነው። ሶማሊላንድ ጥሬ ገንዘብ ከሌለበት ግብይት ግር የተዋወቀችው፤ የመገበያያዋ ሽልንግ በከፍተኛ ሁኔታ እያሽቆለቆለ ስለመጣ ነው። አሁን ባለው ምንዛሬም 1 የአሜሪካን ዶላር በ 9 ሺህ የሶማሊያ ሽልንግ ይመነዘራል። ከጥቂት አመታት በፊት ይህ የምንዛሬ በግማሽ ያነሰ ነበር። የመገበያያ ሽልንግዋን እአአ በ1994 ያስተዋወቀችው ሶማሊላንድ፤ በዚያን ጊዜ ከተለያዩ ቡድኖች ጋር በነበረው ጦርነት የጦር መሳሪያን ለመግዛት አገልግሎት ላይ ውሏል። ከጊዜም በኋላ ሀገሪቱ ውስጥ ካሉ ፖለቲከኞችም በመጣ ከፍተኛ ፍላጎት ሽልንግ የሀገሪቷ መገበያያ ሆኗል። በዓመታት ውስጥ ሽልንግ በማሽቆልቆል ላይ ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰ እቃ ለመግዛት በሻንጣ ብር ይዞ መሄድ የሚጠይቅ ሆኗል። በተለይም በመንገድ ላይ ዶላርና ዩሮን በመቀየር የሚተዳደሩት ነጋዴዎች ብዙ ብር ለማንቀሳቀስ ቀለል ያለ ጋሪን መጠቀም ይኖርባቸዋል። ከዚህ ሸክምና ውጣ ውረድ ለመውጣት ብዙዎች በዲጂታል መንገድ መክፈልን ይመርጣሉ። በሀርጌሳ ሽልንግ በማሽቆልቆሉ ሁኔታ ብዙዎች ግብይታቸውን በዲጂታል መንገድ እያደረጉ ነው። ሶማሊላንድ ዓለም አቀፍ ባንክ ባይኖራትም ሁለት የግል ባንኮች አሉዋት። ስምንት ዓመታትን ያስቆጠረው ዛድ እንዲሁም በቅርብ የተጀመረው ኢዳሀብ የተንቀሳቃሽ ስልክ ባንክ አገልግሎትን በማጠናከር ገንዘብን በቀላሉ ወደ ተንቀሳቃሽ ስልክ የሚዘዋወርበትን የመገበያያ ሁኔታን ፈጥሯል። በጌጣጌጥ መሸጫ ውስጥ በአስተባባሪነት ተቀጥሮ የሚሰራው የ18ቱ ዓመቱ ኢብራሂም አብዱልራህማን በሽልንግ ወርቅ ለመግዛት የመጣን ሰው እየጠቆመ "ይሄንን ወርቅ ለመግዛት በትንሹ አንድ ወይም ሁለት ሚሊዮን ያስፈልገዋል። ያንን ያህል ገንዘብ ደግሞ ተሸክሞ መምጣት ለአንድ ሰው ከባድ ነው"ይላል። ብዙ ገንዘብ ለመያዝ ከባድ በሆነበት ሁኔታ ያለ ጥሬ ገንዘብ መገበያየት ህይወትን ቀለል እንዳደረገው ሳይታለም የተፈታ ነው። ክፍያን ለመፈፀም ቁጥሮችን የሚያስገቡ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ከሻጩ ለየት ያለ ኮድ ያገኛሉ። ለዚህ ግብይት ኢንተርኔት ካለማስፈለጉም በላይ ቀለል ባሉ ስልኮችም ካርድ የመሙላትን ያህል ቀለል ብሎ ይከናወናል። ይህ የክፍያ ሁኔታ የብዙዎችን የግብይት የቀየረ ሲሆን ከነዚህም አንዷ የ50 አመት እድሜ ያላት ኤማን አኒስ ናት። በሁለት አመታት ብቻ ከ5% ወደ 40% ሽያጭ ያደገላት ሲሆን የቀን ሽያጯም ወደ 50 ሺ ብር ደርሷል። ገንቧንም እየቆጠረች "የዛሬ ብቻ ነው"ትላለች። "ተንቀሳቃሽ ስልክ መጠቀም የግብይት ሂደቶችን ቀለል አድርጓቸዋል። ገንዘብ ወደ ዶላር ወይም ዩሮ ከመቀየር ይልቅ በሞባይል በኩል በቀላሉ ክፍያዎችን መፈፀም ይቻላል።" በማለት የምትናገረው አኒስ "በአሁኑ ወቅት የሚለምኑ ሰዎችም የሞባይል ግብይት አካውንት አላቸው።" ብላለች። ከዚህ ማየት እንደሚቻለው ለተገበያዮች ብቻ ሳይሆን በድህነት ውስጥ ላሉት አዲስ እድል እንደፈጠረ ነው። በተለይም ሶማሌላንድ ባለፈው ዓመት በከፍተኛ ድርቅ በተመታችበት ወቅት ከተማ ያሉት በገጠር ላሉ ዘመዶቻቸው በቀላሉ ገንዘብ ለመላክ አስችሏቸዋል። "በድርቁ ምክንያት የምንሸጠው አልነበረንም፤ ይሄም ሁኔታ የገቢ ምንጫችንን አድርቆት ነበር። ነገር ግን ዘመዶቻችን ገንዘብ በመላክ ረድተውናል።" በማለት የሚናገረው የግመል እረኛው ማህሙድ አበዱሰላም በድርቁም ምክንያት ከአካባቢው ተፈናቅሏል። "በገጠርም የተንቀሳቃሽ ስልክ የባንክ አገልግሎት እንጠቀማለን" በማለትም ይናገራል። ሻጮች በአንድ ዓመት ውስጥ የተንቀሳቃሽ ስልክ ክፍያ ከ 10-20% ወደ 50% እንዳደገ መናገራቸው ምን ያህልም ተፈላጊነቱ እየጨመረ ያሳያል። ሻጮች ብቻ ሳይሆኑ ቀጣሪዎችም በተንቀሳቃሽ ስልክ የደሞዝ ክፍያን እያከናወኑ ነው። ባለፈው ዓመት የተካሄደ ጥናት እንደሚያሳየው 88በመቶው የሚደርሱ እድሜያቸው ከ16 ዓመት የሆኑ ሰዎች ከ 1 ሲምካርድ በላይ እንዳላቸው አመልክቷል። ጥናቱም ጨምሮ እንደሚያሳየው 81% ከተሜዎች እንዲሁም 62% የገጠር ነዋሪዎች የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚ ናቸው። በዚህ ከፍተኛ ለውጥ ሁሉም ደስተኛ አይደሉም። ከሙስናም ጋር ተያይዞ የተለያዩ ማጉረምረሞች ይሰማሉ። በተለይም ሁለቱ የግል ባንኮች ያለምንም ተቆጣጣሪ በበላይነት እየመሩት በመሆናቸው መረጋጋት በሌለው ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጫና እያደረሰ እንደሆነ ይነገራል። በተለያዩ ሀገራት የተንቀሳቃሽ ስልክ የባንክ አገልግሎት በሀገሪቷ የመገበያያ ገንዘብ ሲሆን በሶማሊላንድ ያሉት ሁለት ባንኮች የሚገበያዩት በዶላር ነው። ገንዘብ በማሽቆልቆሉ ምክንያት እቃ ለመግዛትከተፈለገ በሻንጣ ብር ይዞ መሄድ ግድ እየሆነ ነው በብዙ ክምር ሽልንግ የተከበቡት እንደነ ሙስጠፋ ሀሰን ያሉ የመንገድ ላይ ነጋዴዎች "በሙስና በተዘፈቀው" የተንቀሳቃሽ ስልክ ግብይት ምክንያት፤ ከፍተኛ የሆነ ግሽበትን እየፈጠረ በአጠቃላይ ደግሞ ህገወጥ ኢኮኖሚን እያንሰራፋ ነው በማለት ይወነጅላሉ። "መንግሥት በተቻለ መጠን ይህንን የግብይትና የገንዘብ ልውውጥ እንዲቆጣጠረው ወይም እንዲያቆመው ጠብቀን ነበር። ከተንቀሳቃሽ ስልክ ግብይት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ችግሮች አሉ። በሁለት ባንኮች ቁጥጥር ሥር መሆኑ ገንዘብ እያመረቱ ይመስላል። " በማለት ሀሰን ሲናገር በአካባቢው የተገኙትም ነጋዴዎች በንግግሩ ራሳቸውን በመነቅነቅ መስማማታቸውን ያሳዩ ነበር። "ትንሽም ሆነ ትልቅ ነገር ለመግዛት ብዙዎች የተንቀሳቀሽ ስልኮቻቸውን ስለሚጠቀሙ ለገንዘብ ለግሽበት ዋነኛ ምክንያት እየሆነ ነው። ይሄም የሚከናወነው በሀገሪቱ የመገበያያ ገንዘብ ላይ ሳይሆን በዶላር ነው። " ይላል። ምንም እንኳን ሀሰን በከፍተኛ ሁኔታ ቢያማርርም እርሱም ከሸማቾች በዶላር ገንዘብ ለመቀበል የተንቀሳቃሽ ስልክን ይጠቀማል። "በእውነቱ ከሆነ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ግብይትን ቀለል አድርገውታል። ሰዎች በቀላሉ ገንዘብ እንዲልኩልኝም አስችሎኛል። "በማለት እውነቱን የሚናገረው ሀሰን "ይህ ሁኔታ ግን እንደእኔ ላሉ ገንዘብ በመቀየር ለሚተዳደሩ ሰዎች ምን ማለት ነው? አላውቅም"።
news-49991087
https://www.bbc.com/amharic/news-49991087
"መንገደኞች የሚጓዙት በመከላከያ ታጅበው ነው" የማዕከላዊ ጎንደር ኮሙኒኬሽን
ባለፈው ሳምንት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በተለይ ጭልጋ አካባቢ በቅማንት የማንነት ጥያቄ አስመላሽ ኮሚቴና በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች መካከል ተፈጠረ በተባለው ግጭት በዞኑ ማህበራዊ አገልግሎቶችና መንገዶች እስከመዘጋት መድረሳቸው ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ካርታ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሃብታሙ ጌታሁን ለቢቢሲ እንደተናገሩት ግጭቱ ከተነሳባቸው አካባቢዎች መካከል ቢያንስ በሶስት ወረዳዎች እስከ አሁን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ቆመዋል። •በተሻሻለው የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህግ ረቂቅ ጥፋተኛና አቃቤ ህግ ይደራደራሉ •"ምን ተይዞ ምርጫ?" እና "ምንም ይሁን ምን ምርጫው ይካሄድ" ተቃዋሚዎች አቶ ሃብታሙ እንደሚሉት "በዞኑ ከሶስት ወረዳዎች ውጭ ሁሉም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እየተከናወነ ይገኛል"። እንቅስቃሴው የተገደበባቸው ሶስቱ ወረዳዎችም ጭልጋ ነባሩ፤ ጭልጋ አዲሱ (በቅማንት የራስ አስተዳደር የተካለለው) እና አይከል ከተማ መሆናቸውን ተናግረዋል። ችግሩን ለመቀነስ በፍጥነት መሰራቱን የገለጹት አቶ ሃብታሙ የትራንስፖርት አገልግሎትን በተመለከተ ከጎንደር መተማ በደርሶ መልስ በቀን ሁለት ጊዜ ጉዞ መኖሩን ገልፀዋል። "ተሽከርካሪዎቹ በመከላከያ ታጅበው የሚመላለሱ ሲሆን ጥዋት ከጎንደር-መተማ ይሄዱና ማታ ከመተማ ወደ ጎንደር ይመለሳሉ" ብለዋል። በሶስቱ ወረዳዎች የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ የቆመ ሲሆን፤ እንደገና ያልተጀመረበት ምክንያት "አንደኛ ችግሩ በዘላቂነት ባለመፈታቱና በሌላ በኩል ደግሞ ባለሃብቶቹ 'ንብረቴ ይወድምብኛል' ከሚል ስጋት ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ነው" ብለዋል አቶ ሃብታሙ። ማዕከላዊ ጎንደር የሚገኙት ማለትም ከትክል ድንጋይ ወደ ታች አርማጭሆና ጠገዴ የሚወስዱት ሌሎች የዞኑ መንገዶች ግን ያለምንም የመከላከያ እጀባ አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን ገልጸዋል። •ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ላይ የሦስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነትን እንደማትቀበል አሳወቀች ከሰሞኑ በተያያዘ ሁኔታ ከጭልጋ ወደ ጎንደር የሚጓዙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመታገታቸው ዜና በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት ተሰራጭቶ እንደነበረ ይታወሳል። አቶ ሃብታሙ ግን ይህ መረጃ ከእውነት የራቀ እንደሆነ ያስረዳሉ። "ተማሪዎች ታግተዋል የሚባለው መረጃ እውነትነት የለውም። እንዲያውም ተማሪዎች ወደተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ መጉላላት ሳይደርስባቸው እንዲሄዱ ጥረትና ድጋፍ እየተደረገ ነው" ብለዋል። በሶስቱ ወረዳዎች አሁንም በነዋሪው ዘንድ ውጥረትና ስጋት እንዳለ የሚናገሩት ኃላፊው "እንደ አጠቃላይ ግን በዞኑ ሁሉም አካባቢዎች ምንም አይነት ትንኮሳና ግጭት የለም" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። በተነሳው ግጭት የሰዎች ህይዎት ማለፉ ቢነገርም የሟቾችን ቁጥርና የወደመውን የንብረት መጠን ለመግለጽ እንደሚቸገሩ የተናገሩት አቶ ሃብታሙ፤ በቀጣይ በጉዳዩ ላይ ምርመራ የጀመረው የጸጥታ መዋቅር እንደሚያሳውቅ ተናግረዋል። መረጃውን ለማረጋገጥ የዞኑን ፖሊስ በስልክ ለማግኘት ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም።
news-55000106
https://www.bbc.com/amharic/news-55000106
ትግራይ ፡ ዶ/ር ቴድሮስ አድሐኖም ህወሓትን ደግፈዋል ተብለው የቀረበባቸውን ክስ አስተባበሉ
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሐኖም በኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናት በኩል ከመንግሥት ሠራዊት ጋር ግጭት ውስጥ የገባውን ህወሓትን ለመደገፍ ጥረት አድርገዋል በሚል የቀረበባቸውን ክስ ውድቅ አደረጉ።
ዶ/ር ቴድሮስ ለቀረበባቸው ክስ በትዊተር ገጻቸው ላይ በሰጡት ምላሽ ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ እየሆነ ያለው ነገር ልባቸውን እንደተሰበረ ገልጸው "በዚህ ውስጥ አንድ ወገንን እንደደገፍኩ የሚገልጹ ዘገባዎች ሲወጡ ቆይተዋል። ነገር ግን ይህ እውነት አይደለም" ብለዋል። ጨምረውም "እኔ የምደግፈው አንድ ወገን ቢኖር ሠላም የሚመጣበትን መንገድ ብቻ ነው" ሲሉ ለሠላም ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል። ዶክተር ቴድሮስ ምላሽ የሰጡት ከማዕከላዊው መንግሥት ጋር ወታደራዊ ፍጥጫ ውስጥ የገባው የትግራይ መስተዳደርን የጦር መሳሪያ እንዲያገኝና በሌሎች መንገዶች ለመርዳት ሞክረዋል በሚል የወጡ ዘገባዎችና ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናት ክስ መቅረቡን ተከትሎ ነው። ዶ/ር ቴድሮስ በአገሪቱ ውስጥ በተከሰተው ነገር ማዘናቸውን ገልጸው "ሁሉም ወገኖች ለሠላም እንዲሰሩና የሰላማዊ ሰዎች ደኅንነት ተጠብቆ የጤናና የሰብአዊ ድጋፍ የሚያገኙበት መንገድ እንዲመቻች" በመልዕክታቸው ላይ ጠይቀዋል። በዶ/ር ቴድሮስ ላይ የቀረበው ቅሬታ ምን ነበር? የኢትዮጵያ መንግሥት የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተሩ ቴድሮስ አድሐኖምን በተመለከተ ቅሬታ እንዳለውና ደስተኛ አለመሆኑን አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለጹ። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታው አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት ዶክተር ቴድሮስ በአገሪቱ ውስጥ ምን እንደተከሰተ ከመንግሥት በኩል ለመረዳት አለመሞከራቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም ዶ/ር ቴድሮስ "አንዳንድ በሮችን ማንኳኳታቸውን" መንግሥት እንደሚያውቅ አመልክተው ይህንንመ በተመለከተ መንግሥት በቀጣይ ምን ማድረግ እንዳለበት ይወስናል ሲሉ ተናግረዋል። በተያያዘም የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክትር የሆኑት ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ግጭት ውስጥ የሚገኘው ህወሓትን የሚደግፍ የማግባባት ሥራ አከናውነዋል ሲሉ የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ ከሰሱ። ሦስተኛ ሳምንቱን በያዘው በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊትና በትግራይ ክልል ኃይሎች መካከል እየተካሄደ ባለው ግጭት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸውና በሺዎች የሚቆጠሩ መሰደዳቸው እየተነገረ ነው። ዶ/ር ቴድሮስ የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ከመሆናቸው በፊት በህወሓት በሚመራው መንግሥት ወቅት የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ማገልገላቸው ይታወቃል። ቢቢሲ ዋና ዳይሬክተሩ ላይ የቀረበውን ክስ አስመልክቶ ምላሽ እንዲሰጡ ጥያቄ ቢያቀርብም እስካሁን ምላሽ አልሰጡም። የአገሪቱ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ጀነራል ብርሃኑ ጁላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳሉት ህወሓትን ለመደገፍና የጦር መሳሪያ እንዲያገኝ ለማድረግ ዶ/ር ቴድሮስ "ያልፈነቀሉት ድናጋይ የለም"። "ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን ቆመው እነዚህን ሰዎች ያወግዛሉ ብለን አንጠብቅም። እነሱን ለመደገፍ ሁሉንም ነገር ሲያደርጉ ነበር፤ ጎረቤት አገራት ጦርነቱን እንዲያወግዙ ሲቀሰቅሱ ነበር" ብለዋል ጀነራል ብርሃኑ። "የጦር መሳሪያ እንዲያገኙ ሲሰራላቸው ነበር" ብለዋል። ከሦስት ዓመት በፊት የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ኃላፊ ሆነው የተመረጡት ዶ/ር ቴድሮስ፤ የኮሮናቫይረስን ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ በዓለም ዙሪያ ዕውቅናን አግኝተዋል። በፌደራል መንግሥቱና የትግራይ ክልልን በሚመራው ህወሓት መካከል ለወራት የቆየው አለመግባባትና መካሰስ ባለፈው ዓመት ማብቂያ ላይ በትግራይ ክልል በተናጠል የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ መባባሱ ይታወሳል። በጥቅምት ወር ማብቂያ ላይ በትግራይ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ ላይ በክልሉ ኃይሎች ጥቃት መፈጸሙን በመግለጽ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ማዘዛቸውን ተከትሎ ፍጥጫው ወደ ግጭት አምርቶ ሁለት ሳምንት አልፎታል።
news-46669970
https://www.bbc.com/amharic/news-46669970
የሱዳን ፖሊስ ተቃዋሚዎች ላይ አስለቃሽ ጭስ ተኩሷል
የሱዳንን መንግሥት በመቃወም ወደ አደባባይ የወጡ ሰዎችን ለመበተን ፖሊስ አስለቃሽ ጭስ ተጠቅሟል።
የሱዳን ተቃውሞ እየተጋጋለ አምስተኛ ቀኑን ይዟል በመቶዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች ከፖሊሶች ጋር ከመጋጨታቸው በፊት በሱዳን መዲና ካርቱም ውስጥ የሚገኝ መንገድ ዘግተው ነበር። የአይን እማኞች እንዳሉት፤ ተቃዋሚዎች "ፈጽሞ አንራብም" በማለት ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ፖሊሶች አስለቃሽ ጭስ ተኩሰውባቸዋል። • አል-በሽር ካቢኔያቸውን በተኑ • በሱዳን እስር ላይ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ተለቀቁ ተቃዋሚዎች ካለፈው ሳምንት ረቡዕ ጀምሮ 22 ሰዎች ተገድለዋል ቢሉም፤ የመንግሥት ባለስልጣኖች የሟቾች ቁጥር ተጋኗል ብለዋል። 'ሴንትራል ሱዳኒዝ ኮሚቴ ኦፍ ዶክተርስ' የተባለ ተቋም አባላት እንዳሉት ከሆነ፤ ብዙ ሟቾች፣ በጥይት ተመተው የቆሰሉና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ተቃዋሚዎች በህክምና መስጫዎች ታይተዋል። የሱዳን ተቃውሞ የተቀሰቀሰው የዳቦና የነዳጅ ዋጋ ይፋ መደረጉን ተከትሎ ነበር። ባለፈው ዓመት የተለያዩ ሸቀጦች ዋጋ በእጥፍ ጨምሯል። የዋጋ ንረት70 በመቶ ሲያሻቅብ፤ የሱዳን መገበያያ ዋጋ በጣም አሽቆልቁሏል። የሱዳኑ ፕሬዘዳንት ኦማር አል-በሽር ላይ ጫና ለማሳረፍ ሀኪሞች በዚህ ሳምንት አድማ እንደሚመቱ ተናግረዋል። ተቃውሞውን ተከትሎ 'ናሽናል ኮንሰንሰንስ ፎርስስ' የተባለው የተቃዋሚዎች ጥምረት 14 አመራሮች ያሳለፍነው ቅዳሜ ታስረዋል። የጥምረቱ ቃል አቀባይ፤ መንግሥት ተቃውሞውን ለማዳፈን አመራሮቹን ማሰሩን ተናግረው "በአፋጣኝ ይፈቱ" ብለዋል። • ሱዳን ውስጥ የዳቦና የነዳጅ ዋጋ ንሮብናል ያሉ ዜጎች ከፖሊስ ጋር ተጋጩ • የደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር አልተሳካም • ጠ/ሚ ዐብይ አልበሽርን የድንበር ግጭቱን አብረን እንፍታ አሉ 'ኡማ' የተባለው ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ሳዲቅ አል-ማዲ፤ ሕዝቡ ወታደራዊ ጭቆና እንዳስመረረው ተናግረዋል። የአል-በሽር አስተዳዳር በሰላማዊ መንገድ ስልጣኑን መልቀቅ አለበትም ብለዋል። አል-ማዲ ሁለት ጊዜ የሱዳን ጠቅላይ ሚንስትር የነበሩ ሲሆን፤ ከአንድ ዓመት ስደት በኋላ በቅርቡ ወደ ሱዳን ተመልሰዋል። አል-በሽር መፈንቅለ መንግሥት እስካደረጉባቸው ጊዜ ድረስ፤ የሳቸው አመራር በሱዳን ለመጨረሻ ጊዜ የተመረጠው ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ነበር። ለሱዳን ኢኮኖሚ መላሸቅ እንደ ምክንያት ከሚጠቀሱት መካለከል፤ እንደ አውሮፓውያኑ በ1990ዎቹ አሜሪካ "የአል-በሽር መንግሥት ሽብርተኞችን ይደግፋል" በሚል እስከ 2017 ድረስ ጥላው የነበረው የንግድ ማዕቀብ ይጠቀሳል። ደቡብ ሱዳን በ2011 ስትገነጠል የሀገሪቱን አብላጫ የነዳጅ ሀብት ይዛ መሄዷም ይገኝበታል።
43638046
https://www.bbc.com/amharic/43638046
ኩዌት ኢትዮጵያውያን የቤት ሰራተኞችን እንደምትፈልግ አሳወቀች
ፊሊፒንስ ዜጎቿ ወደ ገልፍ ባህረ-ሰላጤ እንዳይሄዱ ያዘዘችውን እገዳ ተከትሎ የተከሰተውን እጥረት ለመመሙላት የኩዌት ባለስልጣናት የቤት ሰራተኞችን ከኢትዮጵያ እንደሚወስዱ አስታውቀዋል።
የነዋሪዎች ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት ጄኔራል ታላል አል ማሪፊ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደተናገሩት ሀገሪቷ በሯን ለኢትዮጵያውያን የቤት ሰራተኞች ክፍት እንዳደረገችና ይህም በቤት ሰራተኞች እጥረት ያለውን ክፍተት እንደሚሞላና ዋጋውም እንደሚቀንስ ነው። ፊሊፒንስ ዜጎቿ ለስራ እንዳይሄዱ እገዳ የጣለችው የ29ዓመቷ ጆዋና ዴማፌሊስ ግድያን ተከትሎ ነው። በአውሮፓውያኑ 2016 ከጠፋች በኋላ ሬሳዋ በማቀዝቀዣ ውስጥ ተገኝቷል። በሰውነቷም የመሰቃየት ምልክቶች ነበሩ። ቀጣሪዎቿ ሌባኖሳውያው ወንድና ሶሪያዊ ሴትም በዚህ ሳምንት የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸዋል። ኢትዮጵያ በበኩሏ በውጭ አገር የሥራ ስምሪት ላይ ለዓመታት ጥላው የነበረውን እገዳ ከጥቂት ወራት በፊት አንስታለች። በቤት ሰራተኝነት ወደ ተለያዩ አረብ አገራት የሚሄዱ ኢትዮጵያዊያን ላይ በአሰሪዎች መደብደብ፣ መደፈር፣የጉልበት ብዝበዛ ፣ክፍያ መከልከልና ሌሎችም አስከፊ ስቃዮች ወደ አረብ አገራት የሄዱ በርካታ ኢትዮጵያዊያን እጣ ነበር። በባለፈውም ዓመት የኩዌት ፖሊስ አንዲት የቤት ሰራተኛ ከሰባተኛ ፎቅ ላይ ልትዘል ስትል የሚያሳይ ቪዲዮን በመቅረጿ በቁጥጥር ስር ውላ ነበር። የተለያዩ የመብት ተሟጋቾች ኩዌትን ጨምሮ በተለያዩ አረብ አገራት ላይ ያለውን "ከፋላ" ተብሎ የሚታወቀውን የስደተኞችን የሰራተኛ ህግ በከፍተኛው ይተቹታል። ከፋላ ወይም በስፖንሰር አድራጊዎች የሚደገፈው ይህ ስርዓት ሰራተኞቹ ከአሰሪዎቻቸው ፍቃድ ሳያገኙ ከአገር እንዳይወጡና ስራም እንዳይቀይሩ ያስገድዳቸዋል። ማሪፊ ጨምረውም በአሁኑ ወቅት በኩዌት 15ሺ ያህል ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች እንዳሉ ተናግረዋል።
news-56870720
https://www.bbc.com/amharic/news-56870720
ኦስካር፡ የእዚህ ዓመቱ የኦስካር ሽልማት ሆሊዉድን ይቀይረው ይሆን?
ከአምስት ዓመታት በፊት 2015 (እአአ) ለ'አካዳሚ አዋርድ' ሽልማት የቀረቡት 20 ዕጩዎች በሙሉ ነጮች መሆናቸውን ተከትሎ፤ የኦስካር ዕዕጩዎቹ እና ተሸላሚዎች ነጮች ብቻ ናቸው በሚል ትችት ገጥሞት ነበር።
የሽልማት ድርጅቱ በማኅበራዊ ሚዲያ የደረሰበትን ጠንካራ ትችት ተከትሎ ማስተካከያዎችን አድርጓል። የዘንድሮው የኦስካር ዕጩዎችም ከመቼውም ጊዜ በላይ ብዝሃነት የተንጸባረቀበት ነው ተብሏል። በዘንድሮው የኦስካር ሽልማት ላይ ታሪክ ሊጽፉ ይችላሉ የተባለላቸው የሚከተሉት ዕጩዎች ናቸው። ምርጥ ዳይሬክተር ክሎዊ ቻው ክሎዊ ቻው ምርጥ ዳይሬክተር ሆና የምትመረጥ ከሆነ በዚህ ዘርፍ ሽልማት የተቀዳጀች የመጀመሪያዋ ነጭ ያልሆነች ሴት ትሆናለች። ይህም ብቻ ሳይሆን ክሎዊ አሸናፊ የምትሆን ከሆነ በ92 ዓመት የወድድሩ ታሪክ ሁለተኛዋ አሸናፊ ሴት እንደምትሆን ይጠበቃል። ከዚህ ቀደም ካትሪን ቢግሎ ኢራቅ ውስት በተካሄደው ጦርነት ላይ በሚያጠነጥነው 'ዘ ሀርት ሎከር' በተሰኘው ፊልሟ የምርጥ ዳይሬክተርነት ሽልማትን አሸንፋ ነበር። ቻይናዊቷ ፊልም ሰሪ ክሎዊ ቻው፤ 'ኖማድላንድ' በተሰኘው ፊልሟ 2008 (እአአ) የፋይናንስ ቀውስ በኋላ ሥራዋን ያጣች ሴት በመላው አሜሪካ ጉዞ ስለምታደርግ ሴት ታሪክን ያስቃኛል። በኖማድላንድ ፊልም ቀረጻ ወቅት ክሎዊ ቻው ለዘንድሮ የኦስካር ሽልማት ዕጩ ሆና የቀረበችው በምርጥ ዳይሬክርነት ብቻ አይደለም። ቻው 'በምርጥ ፊልም'፣ 'በምርጥ የፊልም ጽሁፍ' እና 'በምርጥ ኤዲቲንግ' ዕጩ ሆና ቀርባለች። ክሎዊ ቻው ዕጩ ሆና በቀረበችባቸው አራት ዘርፎች አሸናፊ ከሆነች በሽልማቱ ታሪክ ሁለተኛ ሰው ትሆናለች። በተጨማሪም ቀዳሚዋ እንስት በመሆን ታሪክ ታስመዘግባልች። በሽልማቱ ታሪክ ውስጥ በበርካታ ዘርፎች አሸናፊ በመሆን የዲዝኒ ኢንተርቴይመንት መስራች ዋልት ዲዝኒ ላይ የሚደርስ የለም። ዋልት ዲዝኒ 22 የኦስካር ሽልማቶችን በመውደስ ቀዳሚ ባለሙያ ነው። 1954 (እአአ) ላይ በምርጥ ዘጋቢ ፊልም፣ በምርጥ አጭር ዘጋቢ ፊልም የተባሉትን ጨምሮ በአራት ዘርፎች አሸናፊ ሆኖ ነበር። የዲዝኒ ኢንተርቴይመንት መስራች ዋልት ዲዝኒ ምርጥ ፊልም ትልቅ ሥፍራ በሚሰጣቸው የኦስካር ዘርፎች ዕጩ ሆና የቀረበች ሴት ክሎዊ ቻው ብቻ አይደለችም። እንግሊዛዊቷ ተዋናይት እና ጸሐፊ ኤሜራልድ ፌነል 'ፕሮሚሲንግ ያንግ ውመን' በሚለው ፊልሟ በምርጥ ፊልም፣ በምርጥ ዳይሬክተር እና በምርጥ የፊልም ጽሑፍ ዘረፎች ዕጩ ሆና ቀርባለች። በሦስቱም ዘርፎች ድል ከቀናት፤ ትልቅ ትኩረትን በሚያገኙት ዘረፎች አሸናፊ የምትሆን የመጀመሪያዋ ሴት ትሆናለች። ተዋናይት እና ጸሐፊ ኤሜራልድ ፌነል የኦስካር ሽልማት በማግኘት ታሪክ ሊሰሩ የሚችሉ ደግሞ ፕሮዲዩሰር ሻክ ኪንግ፣ ቻርልስ ዲ ኪንግ እና ራይን ኮግለር ናቸው። ሦስቱ ባለሙያዎች 'ጁዳስ ኤንድ ብላክ ሜሲህ' ከተባሉት ፊልሞች ጀርባ ያሉ ናቸው። ለሽልማቱ መመረጥ ከቻሉም የመጀመሪያዎቹ ጥቁር የፊልም ባለሙያዎች ስብስብ ይሆናሉ። ምርጥ ተዋናይ በዚህ ዓመቱ የኦስካር ሽልማት ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙስሊም ተዋናይ በምርጥ ትወና በዕጩነት ቀርቧል። በዚህም ሙስሊሙ ሪዝ አህመድ የመስማት ችግር ያጋጠመው የአንድ ባንድ የከበሮ ሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋች ገጸባህሪን ወክሎ 'ሳውንድ ኦፍ ሜታል' በተሰኘ ፊልም ላይ በመተወን በዕጩነት ቀርቧል። ሪዝ አሕመድ ሙስሊም ተዋናይ በኦስካር መድረክ ላይ ታሪክ ሲሰራ የመጀመሪያው አይደለም። ከሦስት ዓመት በፊት ማሄርሻላ አሊ የተባለው ሙስሊም ተዋናይ 'ሙንላይት' በተሰኘው ፊልም ላይ በነበረው ተሳትፎ ምርጥ ረዳታ ተዋናይ ተብሎ ተሸልሞ ነበር። ከዚያም ከሁለት ዓመት በኋላ በተመሳሳይ አንድ በ1960ዎቹ ኮንሰርት ላይ በፒያኖ ተጫዋችንት በግሪክ መጽሐፍ ላይ የቀረበን ገጸ ባህሪን ወክሎ በተጫወተበት ፊልም በድጋሚ ሽልማት አግኝቶ ነበር። ነገር ግን ከዚያ በኋላ ሌላ ሙስሊም ተዋናይ ለኦስካር ሽልማት ዕጩ ሆኖ እስኪቀርብ እሳካለንብት ዓመት ድረስ ሁለት ዓመታት መጠበቅ ግድ ሆኖ ነበር። በዚህ ዓመት ሪዝ አህመድ በሽልማቱ አሸንፎ ክብረ ወስን ለማስመዝገብ ከተዘጋጀ ከሌላ ብሪታኒያዊ ተዋናይ ፉክክር ገጥሞታል። እንደ አብዛኞቹ የምርጥ ተዋናይነት ሽልማት አሸናፊዎች ሁሉ ሰር አንተኒ ሆፕኪንስ ነጭ ተዋናይ ናቸው። የ83 ዓመቱ ተዋናይ በዚህ ዓመት ሽልማት ላይ ከተመረጡ "ዘ ፋዘር' በተሰኘው ፊልም ላይ በነበራቸው ሚና በዕድሜ የገፉ ቀዳሚው ተሸላሚ ሆነው ታሪክ ያስመዘግባሉ። ሰር አንተኒ ሆፕኪንስ በ'ዘ ፋዘር' ፊልም ላይ ሰባት ጊዜ ለሽልማት ታጭታ ያልተሳካላት ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካዊቷ የረዥም ዘመን ተዋናይት ለስምንተኛ ጊዜ በዘንድሮ ኦስካር ሽልማት ላይ ዕጩ ሆኖ ቀርባለች። ከዚህ ቀደም ሰባት ጊዜ ዕጩ ሆና አንዴም ለማሸነፍ አልቻለችም ነበር። ተዋናይት ግሌን ክሎስ ለ8ኛ ጊዜ ዕጩ ሆና ማሸነፍ ካልቻለች አዲስ ታሪክ ታሪክ ታስመዘግባለች። ተዋናይት ግሌን ክሎስ
news-52741453
https://www.bbc.com/amharic/news-52741453
ብሩንዲ ምርጫውን ተከትሎ ማህበራዊ ሚዲያዎችን ዘጋች
ብሩንዲያዊያን ረዥም ጊዜ አገሪቷን ያስተዳደሯትን ፕሬዚደንት ንክሩንዚዛን ለመተካት ዛሬ ምርጫ እያካሄዱ ነው፡፡ ይህንን ተከትሎም የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ የሆኑትን ዋትስአፕ፣ ፌስቡክ እና ትዊተርን ዘግታለች፡፡
ፕሬዚደንት ፒየሬ ንክሩንዚዛ (በቀኝ) እና የገዥው ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ ኢቫርስቴ ዳይሽሚየ ማህበራዊ ሚዲያዎቹ መዘጋታቸውን ቢቢሲም ሊያረጋግጥ ችሏል፡፡ እነዚህን አገልግሎቶች ማግኘት የሚችሉትም የግለሰቦችን ማንነት የማያሳየውን ቪፒኤን የተሰኘ ኔትወርክ የሚጠቀሙ ብቻ ናቸው፡፡ • በኮሮናቫይረስ ምክንያት ኢትዮጵያውያን እየተፈተኑባት ያለችው ኢስሊ በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ የተጠየቁ ባለሥልጣናት ምላሻቸውን ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም። በአገሪቷ የምርጫ ጣቢያዎች የተከፈቱት ዛሬ ማለዳ ጀምሮ ሲሆን አንድ የአገሪቷ ጋዜጠኛ በአንድ የምርጫ ጣቢያ ለመምርጥ የተሰባሰቡ ሰዎችን ፎቶ አጋርቷል፡፡ ፕሬዚደንቱን ለመተካት 7 እጩዎች የቀረቡ ሲሆን ምርጫው ነጻና ፍትሃዊ ላይሆን ይችላል የሚል ስጋት አለ፡፡ የምርጫ ቦርድ ኮሚሽን አፍሪካ ህብረትን ጨምሮ ከ53 የውጭ ኤምባሲዎች የተመረጡ ተወካዮች ምርጫውን እንዲታዘቡ ፈቅዷል፡፡ ፕሬዚደንት ንክሩንዚዛ ከሥልጣን የሚወርዱት ከ15 ዓመታት በኋላ ሲሆን፤ አዲስ ወደ ተመቻቸላቸው ኃላፊነት ይሸጋገራሉ ተብሏል፡፡ ይሁን አንጅ ምርጫው በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት መካሄዱ እየተተቸ ነው፡፡ • ትራምፕ አሜሪካ በቫይረሱ በተያዙ ሰዎች ቁጥር ቀዳሚ መሆኗ 'ክብር' ነው አሉ ብሩንዲ እስካሁን ከ40 በላይ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎችን የመዘገበች ሲሆን በቫይረሱ የአንድ ሰው ሕይወትም አልፏል፡፡ ምርጫውን ተከትሎ ሕዝባዊ ሰልፎች መካሄዳቸውም ወቀሳን አስከትሏል፡፡ ከሁለት ወራት በፊት የመንግሥት ቃል አቀባዩ በቫይረሱ ሰው ባልተመዘገበበት ወቅት አገሪቷን ፈጣሪ እንደጠበቃት ተናግረው ነበር፡፡ ባለሥልጣናትም ዜጎች ንጽህናቸውን እንዲጠብቁ እንዲሁም በሚችሉት መጠን ሰዎች ከሚሰበሰቡባቸው ቦታዎች እንዲታቀቡ ከመምከር ውጭ ጥብቅ የሆኑ ገደቦችን ለመጣል አልፈለጉም፡፡ በእርግጥ በምርጫው ዘመቻ ወቅት ይህም ሲተገበር አልታየም፡፡
news-53563611
https://www.bbc.com/amharic/news-53563611
እስራኤል በሂዝቦላህ "የተቃጣብኝን ጥቃት መከትኩ" አለች
ከሰሞኑ በአገሬው ተቃውሞ የበረታባቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ናታንያሁ 'ጽንፈኛው' ሂዝቦላህ በድንበር በኩል ጥቃት ቢከፍትም አከርካሪውን ብለን መልሰነዋል' ብለዋል፡፡
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ አራት የሚሆኑ ሚሊሺያዎች በሰሜን እስራኤል፣ የጎላን ኮረብቶች አቅጣጫ፣ በዶቭ ተራራ በኩል ወደ እስራኤል ክልል ድንበር ጥሰው ሲገቡ አግኝተን መክተናቸዋል ብሏል፡፡ ሂዝቦላህ በበኩሉ ባወጣው መግለጫ ወደዚያ ድንበር ዝርም አላልንም፤ የእስራኤል መከላከያ ተደናግጦ ነው "የሚዘባርቀው" ሲል ምላሽ ሰጥቷል፡፡ ከሰሞኑ አንድ የሂዝቦላህ ከፍተኛ መሪ በእስራኤል የአየር ጥቃት ከተገደለ ወዲህ ይህ ሰሜናዊ እስራኤል ድንበር ከፍተኛ ውጥረት ነግሶበት ቆይቷል፡፡ እስራኤል ባለፈው ሰኞ ነበር ይህን ከፍተኛ የሂዝቦላህ ወታደራዊ መሪ በአየር ጥቃት የገደለችው፡፡ ኾኖም እስራኤል ስለ ጥቃቱ ማረጋገጥም ሆነ ማስተባበል አልፈለገችም፡፡ ነገር ግን ሂዝቦላህ የበቀል እርምጃ ለመውሰድ እጁን እንዳያነሳ ስታስጠነቅቅ ቆይታለች፡፡ የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እንዳለው ትናንት የሂዝቦላህ ጦር ወደ እስራኤል ድንበር ለመሻገር ከሞከረ በኋላ ጠንካራ መከላከል ስለገጠመው እግሬ አውጭኝ ብሎ ፈርጥጧል፡፡ ናታንያሁ በቴሌቪዥን ቀርበው ለሕዝባቸው ባደረጉት ንግግር የሒዝቦላህን የድንበር ጥቃት ሙከራ በዋዛ እንደማይመለከቱት አረጋግጠዋል፡፡ ናታንያሁ በዚህ ንግግር ጨምረው እንዳሉት በድንበር አካባቢ ለሚመጣው ጦስ ተጠያቂዎቹ ሂዝቦላህና የሊባኖስ መንግሥት ይሆናሉ፡፡ ሂዝቦላህ 'ከእሳት ጋር እየተጫወተ እንደሆነ ሊያውቀው ይገባል'፡፡ የእስራኤል ሚዲያ የመከላከያ ሰራዊት ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ አንዲት የሂዝቦላህ ጋንታ በድንበር አካባቢ በሚገኝ አንድ የእስራኤል ወታደሮች ካምፕ ላይ ጥቃት ለመፈጸም ተንቀሳቅሶ ነበር፡፡ እስራኤል ግን ገና ብሉናይል ተብሎ የሚጠራውን ድንበር ከማለፋቸው በፊት ጥቃት ሰንዝራ አስቁማዋለች፡፡ ብሉናይል ድንበር የተባበሩት መንግሥታት የእሰራኤልና የሊባኖስ ድንበር ብሎ የሚያውቀው መስመር ነው፡፡ ሂዝቦላህ በሊባኖስ ፖለቲካ ውስጥ ሁነኛ ሚናን የሚጫወትና በኢራን የሚደገፍ እስከ አፍንጫው የታጠቀ ኃይል ሲሆን በእስራኤል እንደ አሸባሪ ቡድን ይታያል፡፡ ብዙውን ጊዜ የሚንቀሳቀሰው በደቡብ ሊባኖስ ድንበር አካባቢ ነው፤ ሂዝቦላህ ከሊባኖስ ጦር ጋር እጅና ጓንት ሆኖ ይሰራል፡፡ ሂዝቦላህ ስለትናንቱ ክስተት ባወጣው መግለጫ ወታደሮቹ ምንም ዓይነት ጥቃት አለማድረሳቸውን፣ በድንበር አካባቢ እስራኤል ተከሰተ የምትለው ነገር ሁሉ ከፍርሃት የመነጨ ፈጠራ መሆኑን ተንትኗል፡፡ ሆኖም በመግለጫው በእስራኤል የአየር ጥቃት ባለፈው ሰኞ የተገደለበትን መሪውን ለመበቀል መዘጋጀቱንና በቀሉም በቅርቡ እንደሚፈጸም ዝቷል፡፡ እስራኤልና ሂዝቦላህ በነፍስ የሚፈላለጉ ባላንጣዎች ሲሆኑ በጎርጎሳውያኑ 2006 ዓ.ም አንድ ወር የፈጀ መራር ጦርነት አድርገው ሂዝቦላህ 8 የእስራኤል ወታደሮችን ገድሎ ሁለቱን ጠልፎ መውሰዱና ያልተጠበቀ ድል ማስመዝገቡ አይዘነጋም፡፡ እስከዛሬም እየቀጠለ ባለው የሂዝቦላህና የእስራኤል ግጭት ከ1ሺህ 191 ሊባኖሳዊያን በላይ የተገደሉ ሲሆን ብዙዎቹ ሰላማዊ ሰዎች ናቸው፡፡ በእስራኤል በኩል ደግሞ ግጭቱ አንድ መቶ ሃያ አንድ ወታደሮችና 44 ሰላማዊ ዜጎች ሕይወት ተቀጥፏል፡፡
news-56081519
https://www.bbc.com/amharic/news-56081519
ቻይና ሃሰተኛ የኮቪድ-19 ክትባት ሲቸበችብ የነበረውን ግለሰብ አሠረች
ቻይና አንድ ንጥረ ነገር ከውሃ ጋር ደባልቆ የኮሮናቫይረስ ክትባት ነው በማለት ሲቸበችብ የነበረውን ቡድን መሪ በቁጥጥር ሥር አዋለች።
ቡድኑ በርካታ ሚሊዮን ዶላሮች ፈሰስ አድርጎ ሃሰተኛ የኮቪድ-19 ክትባት አሽጎ ሲያጓጉዝ ነበር ተብሏል። ኮንግ በሚል ስያሜው የሚታወቀው ግለሰብ ትክክለኛ የክትባት ብልቃጦችን አስመስሎ በመሥራት ከ58 ሺህ በላይ ክትባቶችን አምርቷል። ክትባቶቹ ወደ ውጭ ሃገር ታሽገው እንደተላኩ ቢደረስበትም ወደ የትኛው ሃገር እንደተላኩ መረጃው የለም። ኮንግ በተመሳሳይ ወንጀል በቁጥጥር ሥር ከዋሉ 70 ግለሰቦች መካከል አንዱ ነው። ቤይጂንግ ሃሰተኛ የኮሮናቫይረስ ክትባቶች ገበያ ላይ እንደዋሉ ከደረሰችበት በኋላ ወንጀለኞቹን ለቅሞ ለማሰር ቃል ገብታ ነበር። ምንም እንኳ ጉዳዩ አደባባይ መውጣት የጀመረው ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ቢሆንም ከሰሞኑ ግን አዳዲስ መረጃዎች ብቅ ማለት ጀምረዋል። በማጭበርበር የተጠረጠሩትን ግለሰቦች ጉዳይ ያየው ፍርድ ቤት ኮንግና አጋሮቹ 18 ሚሊዮን ዩዋን አትርፈዋል ብሏል። ገንዘቡ ወደ ዶላር ሲመነዘር 2.7 ሚሊዮን ገደማ ይሆናል። ግለሰቦች ከባለፈው ነሐሴ ጀምሮ ሳሊን ሶሉሽን የተሰኘ ንጥረ ነገር እንዲሁም ውሃ በሲሪንጅ ወደ ብልቃጡ በመሙላት ነው ሲያመርቱ የነበረው። 600 ብልቃጦች ወደ ውጭ ከመላካቸው በፊት ወደ ሆንግ ኮንግ ተጓጉዘው እንደነበርም ተደርሶበታል። ብልቃጦች ለገበያ እየቀረቡ የነበረው ከትክክለኛ ክትባት አምራቾች 'በውስጥ መስመር' የተገኙ ናቸው በሚል መንገድ ነበር። በሌላ መዝገብ ደግሞ ሃሰተኛ ክትባቶች በርካሽ ዋጋ ሆስፒታሎች ውስጥ ሲሸጡ እንደነበር ፍርድ ቤቱ ተመልክቷል። የቻይና ከፍተኛው ችሎት ክልላዊ ወኪሎች ከፖሊስ ጋር ተባብረው ወንጀሎቹን ለሕግ እንዲያቀርቡ አሳስቧል። የቻይና ባለሥልጣናት ከባለፈው ሳምንት በፊት 100 ሚሊዮን ሰዎች እንከትባለን ብለው አስበው የነበረ ቢሆንም እስካሁን 40 ሚሊዮን ሰዎች ብቻ ናቸው የተከተቡት። ነገር ግን ቻይና የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን በቁጥጥር ሥር በማዋል ረገድ ከዓለም ሃገራት ቀድማ የምትጠቀስ ናት።
news-55383949
https://www.bbc.com/amharic/news-55383949
በየመን ተጣብቀው የተወለዱትን መንትዮች ለማዳን ጥሪ ቀረበ
በየመኗ መዲና ሰንዓ ተጣብቀው የተወለዱ መንትዮችን ህይወት ለማዳን ዶክተሮች እየተማፀኑ ነው።
በዚህ ሳምንት ረቡዕ በአል-ሳቢያን ሆስፒታል ተጣብቀው የተወለዱት መንትዮች ህይወታቸው በአስጊ ሁኔታ ላይ እንዳለና ቀዶጥገናውም ውጭ አገር ብቻ መካሄድ እንደሚችልም የህክምና ባለሙያዎች ተናግረዋል። በየመን ባለው የርስበርስ ጦርነት ምክንያት ሰንዓ አየር ማረፊያ ተዘግቷል። የአገሪቷ የጤና ስርአትም ባለው ጦርነትም ዳሽቋል። ሳዑዲ አረቢያ የሚገኝ የእርዳታ ማዕከል የእርዳታ እጁን ለመለገስ ሁኔታዎችን እየገመገምኩ ነው በማለት አስታውቋል። "የህክምና መረጃዎች እንደሚያሳዩት መንትዮቹ የየራሳቸው ልብ አላቸው። ሆኖም የአንደኛው ልብ አቀማመጥ ትክክል እንዳልሆነ ያሳያል" በማለት የአል ሳቢን ሆስፒታል ዳይሬክተር ማጅዳ አል ካቲብ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪል ተናግረዋል። ዳይሬክተሯ እንደሚሉት የመንትዮቹ የትኞቹ አካላት ተጣብቀው እንዳሉ ለማወቅ የሚያስፈልጉት የህክምና መሳሪያዎች በሆስፒታሉ የሉም። ለዶክተሮቹም ጥሪ የንጉስ ሳልማን ሰብዓዊ እርዳታ ማዕከልም በበኩሉ የመንትዮቹን ሁኔታ በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዶክተሮች ለመገምገምና መንትዮቹን ለመነጣጠል ዝግጁ ነን በማለት በትዊተር ገፁ አስታውቋል። ሰንዓ በአሁኑ ወቅት በሁቲ አማፅያን ስር ቁጥጥር ናት። በሳዑዲ ከሚመራ ወታደራዊ ጥምር ኃይል የሚመራውንም ቡድን እየታገለ ይገኛል። ባለፈው አመት በየመን ተጣብቀው የተወለዱ መንትዮች በተወለዱ በሁለት ሳምንታቸው ህይወታቸው አልፏል። ተጣብቀው የተወለዱ መንትዮች፦
news-50892107
https://www.bbc.com/amharic/news-50892107
አቶ ለማ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጋር መስማማታቸው ተነገረ
ከጥቂት ሳምንታት በፊት በገዢው ፓርቲ ውህደትና እየተከተለ ባለው አካሄድ ላይ እንደማይስማሙ በመግለጽ ልዩነታቸውን አሳውቀው የነበሩት አቶ ለማ መገርሳ ከአዲሱ ፓርቲ ጋር አብረው ለውጡን እንደሚያስቀጥሉ ተነገረ።
"ልዩነቱ የግል ሀሳብን በነፃነት ማራመድን የሚያመላክት ዴሞክራሲያዊ መብት የተንፀባረቀበት እንጂ የተካረረ የግለሰቦች ፀብ አልነበረም" የኢህአዴግ ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ ላይ የሰፈረው መልዕክት፣ በመከላከያ ሚኒስትሩ በአቶ ለማና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ መካከል ጉልህ ልዩነት እንደተፈጠረ ተደርጎ የተነገረው ትክክል አለመሆኑን ጠቅሷል። • “ኦዲፒ ዋጋ የተከፈለባቸውን ጥያቄዎች ወደ ጎን መተው አይገባውም” ፕ/ር መረራ ጉዲና • "የጠቅላይ ሚኒስትሩና የመከላከያ ሚኒስትሩ መቃቃር ውሎ አድሯል" የቱለማ አባ ገዳ አክሎም "ልዩነቱ የግል ሀሳብን በነፃነት ማራመድን የሚያመላክት ዴሞክራሲያዊ መብት የተንፀባረቀበት እንጂ የተካረረ የግለሰቦች ፀብ አልነበረም" በማለት የተከሰተው ለውጡ ዘላቂነት እንዲኖረው ለማድረግ በሚመራበት መንገድ ላይ የተወሰነ "የአካሄድ ልዩነት" እንጂ ሲነገር እንደነበረው የጎላ አልነበረም ብሏል። ይህንን በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ የሆኑት ኢንጂነር ታከለ ኡማ በትዊተር ገጻቸው ላይ አጭር መልዕክት አስፍረው የነበረ ሲሆን ትናንት አመሻሽ ላይም የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (ኦቢኤን) ዝርዝር የሌለው አጭር ዜና አውጥቶ ነበረ። ሁለቱ ከፍተኛ የመንግሥትና ፓርቲው አመራሮች በተፈጠረው ልዩነት ላይ ቁጭ ብለው መወያየታቸውንና ተፈጥሮ የነበረውን የሐሳብ ልዩነት ላይ መግባባት እንደቻሉና አብረው ለመስራት መስማማታቸው ተገልጿል። በዚህም ሁለቱ መሪዎች የተጀመረውን አገራዊ ለውጥ በጋራ በመስራት እውን ለማድረግ ከመግባባት ላይ መድረሳቸውን ፓርቲው በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ አስፍሯል። የመደመር እሳቤን መሰረት አድርጎ ከህወሓት በስተቀር ቀሪዎቹን የኢህአዴግ አባል ድርጅቶችንና አጋር የተባሉትን ፓርቲዎች በማቀፍ የተመሰረተውን የብልጽግና ፓርቲ ይፋ መሆን ተከትሎ አቶ ለማ መገርሳ ልዩነት እንዳላቸው በተናገሩበት ጊዜ ግራ መጋባት ተፈጥሮ ነበር። • ከኢትዮጵያ ሀብት ከሸሸባቸው ሃገራት ጋር ግንኙነት ተጀምሯል-ጠቅላይ አቃቤ ሕግ • ዐቃቤ ሕግ ኢትዮጵያ ውስጥ የጠፋው ኤርትራዊ ምርመራ እንዲጠናቀቅ አዘዘ አቶ ለማ በፓርቲዎቹ ውህደት ላይ ያላቸውን ጥያቄና የተሄደበት መንገድን በማንሳት የተለየ አቋም ከማንጸባረቃቸው ባሻገር ተሰሚነት እንዳልነበራቸው ጠቅሰው ነበር። ይህንን ተከትሎም ከተለያዩ ወገኖች በፓርቲው ውስጥ ስለሚኖራቸው ቀጣይ ዕጣ ፈንታና ይህ ልዩነትም የሚያስከትለውን ውጤት በተመለከተ መላምቶች ሲሰነዘሩ ቆይተዋል። አሁን ከፓርቲው በኩል የሚወጣ መረጃ እንደሚያመለክተው አቶ ለማ በልዩነታቸው ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተወያይተው መግባባት ላይ እንደደረሱና የተጀመረውን ለውጥ በጋራ ለማስቀጠል እንደተስማሙ ተገልጿል።
news-48263581
https://www.bbc.com/amharic/news-48263581
በሱዳን በተቀሰቀሰ ግጭት ቢያንስ ሰባት ሰዎች ሞቱ
በሱዳን፣ ካርቱም በተፈጠረ ግጭት የፀጥታ ኃይልን ጨምሮ በትንሹ ስድስት ሱዳናውያን ተቃዋሚዎች መሞታቸው ተሰምቷል።
ሰልፈኞቹ በወታደራዊ ዋና መሥሪያ ቤት አካባቢ ተሰባስበው የሲቪል መንግሥት እንዲመሰረት በሚጠይቁበት ወቅት በተተኮሰ ጥይት ተገድለዋል ተብሏል። ተቃዋሚዎች ተኩሱን የከፈቱት ወታደሮች ናቸው ቢሉም፤ ወታደሮቹ ግን ተኳሾቹ ማንነታቸው ያልታወቀ አካላት እንደሆኑ ተናግረዋል። • የሱዳን የቀድሞ ፕሬዚዳንት አል በሽር ተከሰሱ ባለፈው ወር ፕሬዚደንት ኦማር አል በሽር ከሥልጣን መውረዳቸውን ተከትሎ፤ ሱዳን በሽግግር ወታደራዊ ምክር ቤት እየተዳደረች ትገኛለች። ፕሬዚደንቱ ከሥልጣን ከመውረዳቸው ከስድስት ቀናት አስቀድሞም ተቃዋሚዎች በዋናው ወታደራዊ መሥሪያ ቤት አቅራቢያ ያለውን አደባባይ ተቆጣጥረውት እንደነበር ይታወሳል። የወታደራዊ መንግሥቱና የተቃዋሚዎች ስምምነት ሰኞ ዕለት የተቃዋሚዎች ጥምረትና ሀገሪቷን እየመራ ያለው ወታደራዊ መንግሥት በሽግግሩ ወቅት ስለሚኖረው የሥልጣን ተዋረድ ስምምነት ላይ ደርሰዋል። የተቃውሞ እንቅስቃሴው ቃል አቀባይ ታሃ ኦስማን "በዛሬው ስብሰባችን የሥልጣን ተዋረዱና ክፍፍሉ ላይ ስምምነት ላይ ደርሰናል" ሲሉ ለኤ ኤፍ ፒ የዜና ወኪል ገልፀዋል። • የሱዳን ተቃዋሚ ሰልፈኞች ወታደሩ ያስቀመጠውን ሰዓት እላፊ ጣሱ ቃል አቀባዩ የስልጣን ተዋረዱ የከፍተኛው ምክር ቤት፣ የካቢኔት ምክር ቤት እና የሕግ አውጭው አካል እንደሆነ ዘርዝረዋል። ወታደራዊ ምክር ቤቱ በበኩሉ በሽግግር መንግሥቱ የሥልጣን ተዋረድ ላይ ሥምምነት ላይ መድረሱን አስታውቋል። ሁለቱ አካላት ዛሬ በሚኖራቸው ስብሰባ የሽግግር መንግሥቱ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይና በሥልጣን መዋቅሩ የሚካተቱ አካላት ኃላፊነት ላይ ስምምነት እንደሚደርሱ ይጠበቃል። • አልበሽር በማህበራዊ ሚዲያ የተቀሰቀሰባቸውን ተቃውሞ ተቹ ጄኔራሎቹ የሽግግሩ ወቅት ሁለት ዓመት መሆን አለበት ቢሉም ተቃዋሚዎች አራት ዓመታት እንዲሆን ይፈልጋሉ።
news-55785136
https://www.bbc.com/amharic/news-55785136
ኮሮናቫይረስ፡ የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያ መጠጥን ያበረታቱት የሲሪሊንካ ሚኒስትር በቫይረሱ ተያዙ
ከዕፅዋት የተሰራ የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያ መጠጥን አገራቸው እድትጠቀም ያበረታቱት የሲሪላንካ የጤና ሚኒስትር በቫይረሱ ተያዙ።
የጤና ሚኒስትሯ ፓቪትራ ዋኒያራቺቺ በዚህ ሳምንት በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን የመስሪያ ቤታቸው ሚዲያ ዘርፍ ፀሐፊ ለቢቢሲ አስታውቀዋል። የአገሪቱ የባህል ህክምና አዋቂ ለህይወት ዘመን የሚሆን የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያ መጠጥ ማምረታቸውን ተከትሎ ሚኒስትሯም አገራቸው እንድትጠቀም ሲያበረታቱ ነበር። ፓቪትራ ዋኒያራቺቺ የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያ መጠጡን በይፋ ሲጠጡም ታይተዋል። ወረርሽኙ ከተከሰተ ጀምሮ በሲሪሊንካ 56 ሺህ 76 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 276 ዜጎቿንም አጥታለች። በቅርብ ወራትም በከፍተኛ ሁኔታ እያገረሸ ነው ተብሏል። የጤና ሚኒስትሯ በኮሮቫይረስ የተያዙ አራተኛ ሚኒስትር ሆነዋል። የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያ መጠጡ ማርና ገውዝን ጨምሮ ከሌሎች ንጥረ ነገሮች የተቀመመ ሲሆን ውህዱም በህልም እንደተሰጣቸው የባህል ሃኪሙ ተናግረዋል። የአገሪቱ የጤና ባለሙያዎች የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያው ፍቱንነት አልተረጋገጠም ቢሉም በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የባህል ሃኪሙ ወደሚገኝበት መንደር ይጎርፉ ነበር ተብሏል። የጤና ሚኒስትሯ ሁለት የኮቪድ-19 ምርመራ ቢያደርጉም ሁለቱም በቫይረሱ መያዛቸውን እንደሚያሳይ የሚዲያ ፀሃፊው ቪራጅ አብይሲንጌ ተናግሯል። ሚኒስትሯ ራሳቸውን አግልለው እንዲቆዩና የቅርብ ቤተሰባቸውም እንዲሁ ራሳቸውን እንዲያገሉ ተጠይቀዋል። ሲሪላንካ ለድንገተኛ ጊዜ የሚሆነውን የኦክስፎርዱን አስትራዜኔካ ክትባት ዜጎቿ እንዲከተቡ ፈቃድ ሰጥታለች። የመጀመሪያ ዙር ክትባት በሚቀጥለው ወር ይደርሳል ተብሏል። ፍቱንነቱ ያልተረጋገጠ የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያ መጠጥ የአንድ አገር ባለስልጣን ሲያበራታቱ እሳቸው የመጀመሪያ አይደሉም። ባለፈው አመት የማዳጋስካሩ ፕሬዚዳንት አንድሪ ራጆሊና ከዕፅዋት የተቀመመ የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያ ተገኝቷል ማለታቸው ከፍተኛ ትችትን እንዲያስተናግዱ አድርገዋቸዋል። በመዲናዋ መጠጡን ሲያከፋፍሉ ታይተዋል። ወረርሽኙ ከተከሰተ በኋላ የአለም መሪዎች፣ ሚኒስትሮችና ባለስልጣናት በቫይረሱ ተይዘዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፣ የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንና ዶናልድ ትራምፕ በቫይረሱ ተይዘው ማገገማቸው ይታወሳል።
news-48325665
https://www.bbc.com/amharic/news-48325665
ገበታ ለሸገር፡ "እራት ለመመገብ አይደለም የምንሄደው" በላይነህ ክንዴ
የአዲስ አበባ ወንዞችና ዳርቻዎቻቸውን የማልማት ሥራን ለመተግበር በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ታቅዶ አስተዋጽኦ ለማድረግ የሚፈልጉ ግለሰቦችና ተቋማት በነፍስ ወከፍ አምስት ሚሊዮን ብር በማበርከት የሚታደሙበት የእራት ድግስ ዛሬ ይካሄዳል።
የዐፄ ምኒሊክ የግብር አዳራሽ 'ገበታ ለሸገር' በሚል ስያሜ የተዘጋጀው የገንዘብ ማሰባሰቢያ የእራት ዝግጅት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድና ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት የሚታደሙበት ሲሆን በዝግጅቱ ላይ ለመገኘት አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተሳታፊዎች የተለያየ መታሰቢያ መዘጋጀቱ ተነግሯል። • የ5 ሚሊዮን ብር እራት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጋር ዛሬ የሚከናወነው 'ገበታ ለሸገር' የእራት ዝግጅት ከሰዓት በኋላ ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች የሚጀመር ሲሆን ከዋናው የእራት ግብዣ ቀደም ብሎ የተለያዩ ግንባታዎችና ጥገና እየተካሄደበት የሚገኘው የጠቅላይ ሚኒስትሩ መንበር የሚገኝበት ታሪካዊው ቤተ መንግሥት ውስጥ የሚደረግ ጉብኝት እንደሚኖር ታውቋል። በጠቅላይ ሚኒስትሩ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የ'ገበታ ለሸገር' የ5 ሚሊዮን ብር እራት ላይ ለመገኘት ከተመዘገቡ እንግዶች መካከል በተለያዩ ዘርፎች ላይ የተሰማራው የቢኬ ግሩፕ (በላይነህ ክንዴ ግሩፕ) ባለቤት አቶ በላይነህ ክንዴ እንዱ ናቸው። "ገበታ ለሸገር የልማት ሥራ ነው፤ እንደ አንድ ባለሃብት የአፍሪካ መዲና፣ የዓለም መሰብሰቢያ የሆነችው ሸገር እንድትዋብ እንዲትለወጥ ፍላጎታችን ነው" የሚሉት አቶ በላይነህ ዓላማውን በመደገፍ ያለምንም ማመንታት ገንዘቡን እንደከፈሉ ይናገራሉ። እራቱ ላይም ይህንን ዓላማ ለማስተዋወቅ እንደሚገኙ ገልፀው "በአጋጣሚውም እራታችንን እንጋበዛለን" ብለዋል። • የማትተነፍሰው ከተማ: አዲስ አበባ "ምግብ ለመመገብ አይደለም የምንሄደው" የሚሉት አቶ በላይነህ "ሃብት ያለው ሰው በሕብረት ሌሎች ከተሞችንም ካለማ አገር ያድጋል" የሚል ሃሳብ አላቸው። የዚህ እራት ዓላማውም የልማት ነው ሲሉ አክለዋል። የፕሮግራሙ ዝርዝር ባይደርሳቸውም ዛሬ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት እንዲገኙ የግብዣ ወረቀት ደርሷቸዋል። በፕሮግራሙም ላይ ተገኝተው በሚኖረው መርሃግብር ላይ እንደሚሳተፉ ነግረውናል። የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ የሚኖረው ገጽታ ሌሎች የአፍሪካ ከተሞችን እንዳዩና በጽዳት የተሻሉ እንደሆኑ በቁጭት የሚናገሩት አቶ በላይነህ "አገር በግለሰብ ለማልማት ሊሞከር ይችላል፤ እንደዚህ በጋራ ሆኖ ማልማት ጠቃሚ ነው" በማለት ይህንን ዓላማ እንደደገፉ ገልጸዋል። የእራት መስተንግዶውም በቤተ መንግሥቱ ውስጥ በሚገኘው በታሪካዊው የአፄ ምኒልክ የግብር አዳራሽ ውስጥ እንደሚካሄድ የተነገረ ሲሆን እስካሁን ከሁለት መቶ በላይ ግለሰቦችና ተቋማት በእራት ድግሱ ላይ በመታደም አስተዋጽኦ ለማበርከት መመዝገባቸው ተነግሯል። • ''አዲስ አበባ የሁላችንም ከተማ ናት'' ከንቲባ ታከለ ኡማ ሸገርን የማስዋብ ዕቅድ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አነሳሽነት የተጀመረ የሦስት ዓመታት ፕሮጀክት ሲሆን በዚህም ከእንጦጦ እስከ አቃቂ የሚዘልቅ የ56 ኪሎ ሜትር ርዝመትን የሚሸፍን በወንዝ ዳርቻዎች አካባቢ የሚገኙ ስፍራዎችን ለማልማት የታቀደ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል። የታቀደው የአዲስ አበባ የወንዞችና የወንዞች ዳርቻን የማልማት ዕቅድ ተግባራዊ ሲሆን በተለያዩ የፕሮጀክቱ ሥፍራዎች ላይ በእራት ዝግጅቱ የታደሙ ሰዎች ስም በተናጠል ተጽፎ የሚቀመጥ ሲሆን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጋርም የአንድ ለአንድ ፎቶ የመነሳት እድልን ያገኛሉ ተብሏል። ይህም ፎቶግራፍ የአዲስ አበባን ገጽታ የቀየሩ ግለሰቦች በሚል ተሰባስቦ በአንድ ጥራዝ ላይ እንዲቀርብ ይደረጋል ተብሏል። በጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ 'ገበታ ለሸገር' ላይ ከሚሳተፉት ሰዎች አንዱ የሆኑት አቶ በላይነህ ክንዴ "እንደ ግለሰብ፤ 5 ሚሊዮን ብር ስለከፈልኩ በእኔ ስም ቦታ ይሰየምልኝ ብዬ አላስብምም፤ መሆንም የለበትም፤ ስሜን ለማስተዋወቅ አይደለም የከፈልኩት" ይላሉ። • አዲስ አበባ፡ የፈጠራ ማዕከል ለመሆን እየጣረች ያለች ከተማ የእርሳቸው ፍላጎት በከፈሉት 5 ሚሊዮን ብር ልማቱ እውን ሆኖ ከተማው ሲለወጥና እድገት ሲመጣ ማየት ነው። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ዛሬ ባቀረበው የግብዣ ጥሪም የንግድ ተቋማት ባለቤቶችና አመራሮች እንዲሁም የዓለም አቀፍና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት በዚሁ የእራት ዝግጅት ላይ እንዲታደሙ ጋብዟል። በቫርኔሮ ኩባንያ የሚከናወነው የአዲስ አበባን ገጽታ በከፍተኛ ደረጃ ይለውጣል ተብሎ የታሰበው ፕሮጀክት በ29 ቢሊየን ብር ወጪ የሚከናወን ሲሆን በሦስት ዓመታት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተነግሮለታል። ሥራው የአዲስ አበባ ከተማን ለሁለት ከፍለው የሚያልፉ ወንዞችን መሰረት ያደረገ ሲሆን ከእንጦጦ ተራራ እስከ አቃቂ ወንዝ ያለውን 56 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍን ነው። የአዲስ አበባ ወንዞችና ዳርቻዎች ልማት ሥራ ሲጠናቀቅ 4 ሺህ ሄክታር መሬት እንደሚለማ የተነገረ ሲሆን፤ በውስጡም አስፈላጊው ነገር የተሟላላቸው የመዝናኛ፣ የመጓጓዣ፣ የንግድ ማዕከላትና አረንጓዴ ሥፍራዎች ይኖሩታል ተብሏል።
news-56277294
https://www.bbc.com/amharic/news-56277294
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ከስድስተኛው አገራዊ ምርጫ "ተገፍቶ መውጣቱን" ገለፀ
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከሦስት ወራት በኋላ ይካሄዳል ከተባለው ምርጫ ከፍላጎቱ ውጪ በደረሱበት ጫናዎች ለመውጣት መገደዱን አስታወቀ።
የፓርቲው ፀሐፊ የሆኑት አቶ ጥሩነህ ገምታ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የኦሮሞ ፌደራሊስ ኮንግረስ ከስድስተኛው አገራዊ ምርጫ "ተገፍቶ ለመውጣት ተገድዷል" ብለዋል። ኦፌኮ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ሲያወጣቸው በነበሩ መግለጫዎች የታሰሩ አመራሮቹ እንዲፈቱ፣ በኦሮሚያ የተለያዩ ስፍራዎች የተዘጉ ቢሮዎቻቸው እንዲከፈቱ፣ እንዲሁም ታማኝነት ያለው ምርጫ ለማድረግ የሚያስችል አገራዊ ምክክር እንዲደረግ ጥሪ ሲያቀርብ ነበር። ኦፌኮ ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ በተካሄዱ አገራዊ ምርጫዎች ላይ ተሳታፊ የነበረ ሲሆን ከምርጫ ውድድር እራሱን ሲያገል ይህ የመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል። አቶ ጥሩነህ ገምታ ባለፈው ሳምንት ከምርጫ ቦርድ ኃላፊዎች ጋር ፖለቲካ ፓርቲዎች የዕጩ ምዝገባን በተመለከተ በተደረገ ውይይት ላይ መሳተፋቸውን አስታውሰው፤ ኦፌኮ ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች ካልተሟሉ ዕጩ እያስመዘገበ እንዳልሆነ እና ማስመዝገብም እንደማይችል፣ ስለዚህም ምርጫው ላይ መሳተፍ እንደማይችል ለምርጫ ቦርድ አስታውቋል ብለዋል። በተጨማሪም የፖለቲካ ምኅዳር መጥበብ እና ምርጫው ላይ አገራዊ መግባባት አለመኖር ምርጫው ፍትሃዊ እና ተዓማኒነት እንዲኖረው እንደማያደርግ በስበሰባው ላይ መናገራቸው አስታወሰዋል። ሆኖም ግን ፓርቲያቸው ላነሳው ሃሳብም ሆነ ላቀረባቸው ጥያቄዎች ምንም ምላሽ አለማግኘታቸውን አቶ ጥሩነህ ተናግረዋል። በመሆኑም እነዚህ ጥያቄዎች ባልተሟሉበት ሁኔታ ፓርቲው በምርጫው ላይ ለመሳተፍ እንደማይችል አቶ ጥሩነህ ገምታ ለቢቢሲ ተናግረዋል። እስካሁን ድረስ ቢሮዎቻቸው በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች ተዘግተው እንዳሉ የሚናገሩት አቶ ጥሩነህ፣ ከዋናው የፓርቲው ጽህፈት ቤት ምርጫውን እንዲያስፈጽሙ ከተመደቡ አምስት ሰዎች አራቱ እስር ቤት መሆናቸውን ተናግረዋል። ስለዚህም "አፌን ሞልቼ መናገር የምችለው ከዚህ ምርጫ የወጣነው ተገፍተን እንደሆነ ሕዝባችንም ሆነ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ሊያውቅልን እንደሚገባ ነው።" እስር ቤት ካሉ የኢፌኮ አመራሮች መካከል የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ፣ የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ እንዲሁም ባለፈው ዓመት ፓርቲውን የተቀላቀሉት አቶ ጃዋር መሐመድን እና ሐምዛ አዳነ (ቦረና) ይገኙበታል። "አንድ ፓርቲ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ቢያንስ ነጻ ሆኖ መንቀሳቀስ መቻል አለበት። እኛ ግን አሁንም አባላቶቻችን፣ በወረዳና በዞን ደረጃ ያሉ አመራሮች፣ እጩ ተወዳዳሪ እና ታዛቢ ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎች እስር ቤት ነው ያሉት። ስለዚህ እንሳተፍ እንኳ ብንል መሳተፍ አንችልም፤ ከምርጫው የመውጣት ውሳኔ ላይ የደረሰነው ተገደን ነው" ብለዋል። እነዚህ የምናነሳቸው ጥያቄዎች በተደጋጋሚ ስንጠይቅ የቆየን ቢሆንም ባለፈው ሳምንት ግን የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች ካልተመለሱ ምርጫው ላይ ላለመሳተፍ ወስኗል ብለዋል። ከኦፌኮ በተጨማሪ በኦሮሚያ ካሉ የተፎካካሪ ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆነው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የአመራሮቹ መታሰር እና የቢሮዎች መዘጋትን በማንሳት ምርጫው ላይ ለመሳተፍ እንደሚቸገር ከዚህ በፊት ለቢቢሲ መናገሩ ይታወሳል። በምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የዕጩዎች ምዝገባ ዛሬ የሚጠናቀቅ ሲሆን፤ ኦፌኮ እስከ ትናነትናው ዕለት ድረስ ምንም ዓይነት ዕጩ እንዳላስመዘገበ ለቢቢሲ አረጋግጧል። አቶ ጥሩነህም የዕጩዎች ምዝገባ የሚጠናቀቅ መሆኑን ጠቅሰው ያነሷቸው ጥያቄዎች፤ የፓርቲ አመራሮቻቸው መፈታትን ጨምሮ ምላሸ የሚያገኙ ከሆነ እና የዕጩ ምዝገባ ጊዜ የሚራዘም ከሆነ ድርጅቱ አሁንም በምርጫው ውስጥ ለመቆየት ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል። አቶ ጥሩነህ ከዚህ ቀደም የኦነግም ሆነ የኦፌኮ አመራሮች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጋር ተገናኝተው በጉዳዩ ላይ እንደተወያዩ ተናግረው ከዚህ ውይይት በኋላ ግን ምንም ዓይነት ለውጥ አለማየታቸውን ገልጸዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ከምርጫ ቦርድም ሆነ ከመንግሥት በኩል አስካሁን የተባለ ነገር የለም። በኦሮሚያ ክልል ከሚንቀሳቀሱና ዋነኛ ከሚባሉት የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል አንዱ ዮነው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ፤ በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ይመራ በነበረው የኦሮሞ ፌደራሊስት ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኦፌዴን) እና በፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በሚመራው የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኦሕኮ) መካከል በሐምሌ 2004 ዓ.ም በተደረገ ውህደት የተመሰረተ ድርጅት ነው።
news-46205934
https://www.bbc.com/amharic/news-46205934
የህግ የበላይነት ሳይሸራረፍ እንዲተገበር የሚጠይቀው የትግራይ ክልል መንግሥት መግለጫ
ማናቸውም ብሔር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እንዳይፈፀም የትግራይ ህዝብ በከፍተኛ ኃላፊነት እንዲታገለው የትግራይ ክልል መንግስት ጥሪ አቀረበ።
የክልሉ መንግስት ትናንት አመሻሽ ላይ ባወጣው መግለጫ የትግራይ ህዝብ ለፍትህ ሲል ከፍተኛ መስዋእትነት መክፈሉን አስታውሶ አሁንም በሚሰሩ ሴራዎችና ችግሮች ሳይንበረከክ በአንድነት ትግሉን እንዲቀጥልበት ያሳስባል። "አሁን እየተወሰደ ያለው እርምጃም በማናቸውም ብሔር ላይ የተለየ ጥቃት የሚፈፀምበት እንዳይሆን፣ መስመር እንዲይዝና ህግን የተከተለ እንዲሆን የትግራይ ህዝብ በከፍተኛ ኃላፊነትና ጥንቃቄ እንዲታገለው" በማለት ጥሪ አድርጓል። ከሌሎች የአገሪቱ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ጋር በአንድነት እንዲሰራም ይጠይቃል። "የትግራይ ህዝብ ማንኛውም ዓይነት ጭቆናና ባርነት እንደማይቀበል ሁሉ ይህ ሌላው ላይም እንዲሆን አይፈልግም፤ ይሁን እንጂ ሊያጠቃን ለሚመጣ ማናቸውም ኃይል እንደማንምበረከክ የትናንት፣ የዛሬና የነገ ቃልኪዳናችን ነው" ይላል መግለጫው። • "ሃገሬን ሳላስብ የዋልኩበት፤ ያደርኩበት ቀን የለም" ብርቱካን ሚደቅሳ • ሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር መበራከት ምንን ያመለክታል? • እምቦጭ የጣና ቂርቆስ መነኮሳትን ከገዳሙ እያስለቀቀ ነው በሰብዓዊ መብት ጥሰትና በሙስና የተጠረጠሩ በርከት ያሉት የመከላከያ ብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ሜቴክና የደህንነት አገልግሎት የቀድሞ ኃላፊዎች በቁጥጥር ስር ላይ እየዋሉ እንደሆነ የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ አስታውቋል። ትናንትም የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘው በቁጥጥር ውለዋል። ቀደም ሲል በተካሄዱት የኢህአዴግ መድረኮች ላይ እንዲህ ዓይነት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና የሙስና ተግባራት ማስተማሪያ ይሆኑ ዘንድ ህግንና ስርዓትን በተከተለ ፤ ብሄርን መሰረት ሳያደርግ እርምጃ እንዲወሰድ መግባባት ላይ መደረሱንም መግለጫው አክሎ ያትታል። እንዲሁም እርምጃው እርቅንና ይቅርታን መሰረት ተደርጎ የተጀመረውን ጥረት ወደኋላ የሚመልስ እንዳይሆን ፤ የህግ የበላይነትን ሳይሸራረፍ እንዲፈፀም መግለጫው ያሳስባል። ህዝቡንም አካባቢውን ነቅቶ እንዲጠብቅና ሊመጣ የሚችለውን ማናቸውንም ጥቃት ከመንግስት ጋር በመሆን ለመመከት እንዲዘጋጅ ይጠይቃል። እየተወሰደ ባለው እርምጃ የማጣራት ሂደቱ በግልፅነትና ከማንኛውም ኃይል ተፅእኖና ጣልቃ ገብነት ውጪ እንዲሆንም የክልሉ መንግስት ይታገላል ብሏል። በሌላ በኩል የኦሮሚያ ክልል መንግስት የህግ የበላይነት እንዲከበር እየወሰደ ያለውን እርምጃ እንደሚያደንቅና ለዚህም አስፈላጊውን ትብብር እንደሚያደርግ ትናንት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
news-56359823
https://www.bbc.com/amharic/news-56359823
ምርጫ 2013፡ ብልጽግና፣ ኢዜማ እና እናት ፓርቲዎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዕጩዎች አቀረቡ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከሦስት ወራት በኋላ በሚካሄደው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ላይ ከሚሳተፉ ፓርቲዎች መካከል ብልጽግና፣ ኢዜማ እና እናት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ዕጩዎች ማቅረባቸው ተገለጸ።
በምርጫው ከሚሳተፉት 47 የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል በርካታ ቁጥር ያላቸውን ዕጩዎች በማቅረብ በኩል ገዢው ፓርቲ ብልጽግና 2432 ዕጩዎችን በማስመዝገብ ቀዳሚው መሆኑ በመግለጫው ላይ ተመልክቷል። ከዚህ አንጻር ከብልጽግና በመከተል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ዕጩዎች በማስመዝገብ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) 1385 ዕጩዎችን እንዲሁም እናት ፓርቲ ደግሞ 573 ዕጩዎችን አስመዝግበዋል። ሦስቱን ፓርቲዎች ጨምሮ በምርጫው ለመወዳደር በፓርቲና በግል ለመወዳደር ከስምንት ሺህ ሁለት መቶ በላይ ዕጩዎች መመዝገባቸውን ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። ቦርዱ ይህንን ይፋ ያደረገው ለሳምንታት ሲያካሂድ የነበረው የዕጩዎች ምዝገባ መጠናቀቁን በተመለከተና አስካሁን ካለው ሂደት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በተመለከተ ዛሬ [ሐሙስ] መግለጫ በሰጠበት ወቅት ነው። የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በሰጡት ማብራሪያ ላይ እንደተናገሩት በምርጫው ላይ ለመሳተፍ 47 ፓርቲዎች የተመዘገቡ ሲሆን ከዕጩዎች አንጻርም 8209 ዕጩዎች ለተመራጭነት መመዝገባቸውን አመልክተዋል። ነገር ግን የተጠቀሰው የዕጩዎች ቁጥር ያለቀለትና የመጨረሻው ሳይሆን፣ ሊጨምር እንደሚችል የገለጹት ሰብሳቢዋ፤ በምርጫው ለመሳተፍ የተመዘገቡት ፓርቲዎች ቁጥር ግን ከዚህ በኋላ ከተጠቀሰው እንደማይቀየር ተናግረዋል። በተጨማሪም ለ22 ቀናት በተካሄደው የእጩዎች ምዝገባ በምርጫው 125 ግለሰቦች በግል ለመወዳደር በዕጩነት መመዝገባቸውን ገልፀዋል። የዕጩዎች ምዝገባ ከትግራይ ክልል ውጪ በሁሉም ክልሎች እንዲሁም በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች በአጠቃላይ በ673 የምርጫ ክልሎች ላይ ተካሂዷል። የኦነግ እና ኦፌኮ ጉዳይ ባሳለፍነው ሳምንት ኦፌኮ እና ኦነግ ከስድስተኛው አገራዊ ምርጫ "ተገፍተናል" በሚል እንደማይሳተፉ ማስታወቃቸው ይታወቃል። ሐሙስ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዕጩዎች የተመዘገቡበትን መዝገብ ይፋ ባደረገበት ጊዜ፣ የእነዚህ ፓርቲዎችን የሚወክሉ ዕጩዎች ዝርዝር በሰነዱ ላይ አልተካተተም። እነዚህ ፓርቲዎች ከምርጫ ራሳቸውን ስለማግለላቸው የተጠየቁት ሰብሳቢዋ፣ ብርቱካን ሚደቅሳ፣ "ወደ ዕጩዎች ምዝገባ ከመሄዳችን በፊት ፓርቲዎች ስለገጠማቸው ችግር በቡድን እና በግለሰብ አግኝተን ለችግራቸው መፍትሄ ለመስጠት ሞክረናል" ብለዋል። ኦፌኮ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጦ፣ ካልተሟሉ በስተቀር ምርጫ ውስጥ አልገባም በማለት መውጣቱን ጠቅሰው፤ ምርጫ ቦርድ እንደምርጫ አስፈጻሚ ተቋም ከቀረቡት ጉዳዮች አንጻር እንደማይሰራ አንዳንዶቹም የሚመለከቱት አይደሉም ብለዋል። "እውነት ለመናገር አንዳንዶቹ ደግሞ እንዴት መልስ እንደሚያገኙ አናውቅም፤ በቀጥታ ከምርጫ ቦርድ ጋር የሚገናኙ አይደሉም። ስለቢሮዎቻቸው መዘጋት፣ ፓርቲዎቹ የት አካባቢ እንደተዘጋባቸው ቢጠየቁም የት አካባቢ እንደተዘጋባቸው አላቀረቡም" ብለዋል። ሁሉም ፓርቲዎች በምርጫ ሂደት ውስጥ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ማድረግ የቦርዱ ግዴታና ኃላፊነት ነው ያሉት የቦርዱ ሰብሳቢዋ፣ ሁለቱ ፓርቲዎች በቦርዱ ከምርጫ አልተገፉም ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። በተጨማሪም ሁለቱ ፓርቲዎች በምርጫ አለመሳተፋቸው የሚያሳዝን መሆኑን የገለፁት ወ/ት ብርቱካን፣ ነገር ግን በዚህ ምክንያት ችግር ይፈጠራል ብለው የተዘጋጁበት ነገር እንደሌለም ተናግረዋል። በዕጩዎች ምዝገባ ወቅት የገጠመው ችግር ቦርዱ በዕጩዎች የምዝገባ ሂደት ጊዜ አጋጠሙኝ ያላቸውን ዋና ዋና ችግሮች በመግለጫው አንስቷል። ከእነዚህም መካከል የቁሳቁስ ማጓጓዣ የትራንስፖርት ትብብር ማነስ፣ የቁሳቁስ ማዘጋጃ ቦታና ቢሮ ባለመሟላት የተፈጠሩ መዘግየቶችና በሠላምና በፀጥታ በኩል ችግሮች እንደነበሩ ተጠቅሰዋል። ችግሩንም ለመፍታት ተከታታይ ውይይቶችን የኦፕሬሽን ዘርፍ በማቋቋም ለመፍታት ጥረት መደረጉንም ሰብሳቢዋ አስረድተዋል። ቤንሻንጉል ጉሙዝና እና በአራቱ የወለጋ ዞኖች በፀጥታ ስጋት ምክንያት ከተቀሩት የኦሮሚያ አካባቢዎች የዕጩዎች ምዝገባ ዘግይቶ የተካሄደ ሲሆን በእነዚህ አካባቢዎች አሁንም የፀጥታ ችግር ስጋት መኖሩን ሰብሳቢዋ ተናግረዋል። በዚህም ሳቢያ በአራቱ የወለጋ ዞኖች እና በቤንሻንጉል መተከል ዞን "ግጭት በነበሩባቸው አካባቢዎች የተለየ ዝግጅት እና እቃዎችን ማጓጓዝ ስላስፈለገ የዕጩዎች ምዝገባው ጊዜ ወስዷል።" ነገር ግን በአራቱም የወለጋ ዞኖች የዕጩዎች ምዝገባ ዘግይቶ ቢጀመርም በአሁኑ ጊዜ ምዝገባው ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን ተናግረዋል። ከዚህ ባሻገር ደግሞ በዕጩዎች ምዝገባ ሂደት ወቅት ዕጩዎች የታሰሩባቸው አካባቢዎች እንዳሉ ሰብሳቢዋ ገልጸው፤ ለምሳሌ በቤንሻንጉል ጉሙዝ አሶሳ ከተማ እና ሐረሪ ክልል ሁለት የአብን ዕጩዎችና ሦስት አባላቱ ታስረው እንደተፈቱ ጠቅሰዋል። እንዲሁም በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል፣ በመስቃን አካባቢ ሁለት የግል ዕጩዎች ታስረው እንደሚገኙና ይህንን ጉዳይ ለክልሉ መንግሥት አሳውቀው እንዲፈቱ እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል። ምርጫ 2013 ባለፈው ዓመት ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ወደዚህ ዓመት ከተሸጋገረ በኋላ፤ በመጪው ግንቦት ማብቂያና በሠኔ ወር መጀመሪያ ላይ ለማካሄድ የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶለት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስፈላጊውን ዝግጅት እያካሄደ መሆኑ ይታወቃል። ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ከትግራይ ክልል በስተቀር በሌሎቹ የአገሪቱ ክፍሎች ይካሄዳል በተባለው በዚህ ምርጫ 50 ሚሊዮን መራጮች ማለትም ከአገሪቱ ሕዝብ ወደ ግማሽ የሚጠጋው ድምጽ በመስጠት ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ምርጫ ቦርድ ገልጿል። በዚህ ምርጫ በመላው አገሪቱ ድምጽ የሚሰጡባቸው ከ50 ሺህ በላይ የምርጫ ጣቢያዎች፣ ከ152 ሺህ በላይ የመራጮች ምዝገባን የሚያከናውኑ ባለሙያዎችና ከ254 ሺህ በላይ ምርጫ አስፈጻሚዎ እንደሚሰማሩ ተገልጿል።
news-53943220
https://www.bbc.com/amharic/news-53943220
ቭላድሚር ፑቲን፡ "አስፈላጊ ከሆነ ወደ ቤላሩስ ፖሊስ እልካለሁ"
የሩሲያው ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን አስፈላጊ ከሆነ ወደ ቤላሩስ ለመላክ ተጠባባቂ የፖሊስ ኃይል ማዘጋጀታቸውን አስታወቁ።
ፑቲን "የቤላሩስ ፕሬዚደንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ የተወሰነ ተጠባባቂ የፖሊስ ኃይል እንዳዘጋጅላቸው ጠይቀውኛል። እኔም ባሉኝ መሰረት አድርጌያለሁ" ሲሉ ነበር ለሩሲያ የመንግሥት ቴሌቪዥን የተናገሩት። ነገር ግን በቤላሩስ ያለው ሁኔታ ከቁጥጥር ውጭ ካልሆነ በስተቀር ግን የፖሊስ ኃይሉን ላለመጠቀም መስማማታቸውን ፑቲን ለሮሲያ 1ቲቪ ገልፀዋል። በምሥራቅ አውሮፓ የምትገኘው ቤላሩስ ሩስያ፣ ዩክሬን፣ ፖላንድና ላቲቪያ ያዋስኗታል። ታዲያ በነሃሴ ወር መጀመሪያ ለ26 ዓመታት ያህል አገሪቷን እያስተዳደሩ ያሉት ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ለ6ኛ ጊዜ ምርጫ አሸነፍኩ ማለታቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ተቃውሞ ተቀስቅሶባት ነበር። በወቅቱም የቢቢሲን ጨምሮ ቢያንስ 13 ጋዜጠኞች በዋና መዲናዋ ሚንስክ የተቃውሞ ሰልፎ ከመካሄዱ ቀደም ብሎ ታስረው ነበር። የአገሪቷ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጋዜጠኞቹ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው የነበረው ማንነታቸውን ለማረጋገጥና ለመፈተሽ ነው ብለዋል። ይሁን እንጂ የቢቢሲው ስቲቭ ሮሰንበርግ "ድርጊቱ ዘገባቸውን ለማስተጓጎል የተደረገ ግልፅ ሙከራ ነበር" ብሏል። ፕሬዚደንት ፑቲን ሩሲያ ከቤላሩስ ጋር ባላት የባህል፣ የቋንቋና የብሔር ትስስርን ጨምሮ የጠበቀ ወዳጅነት ስላላት በፀጥታው ዘርፍ የመደገፍ ግዴታ አለባት ብለዋል። ይሁን እንጂ አዲስ ያዘጋጁት ተጠባባቂ የፖሊስ ኃይል፤ ገደብ ለመጣስ፣ በታጠቁ ኃይሎች ዝርፊያ ለማካሄድ፣ መኪኖችን፣ ቤቶችን፣ ባንኮችን ለማቃጠል፣ የመንግሥት ሕንፃዎችን ለመያዝ እና የመሳሰሉ ነገሮችን ለመፈፀም የፖለቲካ መፈክሮችን እንደ ሽፋን በመጠቀም ዋልታ ረገጥ የሆነ ተግባር ከሌለ በስተቀር ተጠባባቂ ኃይሉ ወደ ቤላሩስ እንደማይላክ አስታውቀዋል። በአጠቃላይ በቤላሩስ ያለው ሁኔታ አሁን እየተረጋጋ መሆኑንም ፑቲን አክለዋል። የፖላንዱ ጠቅላይ ሚኒስተር ማቴውስዝ ሞራዌኪ በበኩላቸው ፑቲን በቤላሩስ የተከሰተውን ዓለማቀፋዊ ሕግ ጥሰት ለመሸፋፈን በቤላሩስ ያለውን ፀጥታ እንደገና ለመመለስ የሚለውን ሃሳብ እንደ መሳሪያ እየተጠቀሙበት ነው ሲሉ ይከሳሉ። በመሆኑም "ፑቲን የፖሊስ ኃይል ወደ አገሪቷ ልልክ እችላለሁ የሚለውን እቅዳቸውን አሁኑኑ ሊሰርዙ ይገባል" ብለዋል። ሩሲያና ቤላሩስ የቀድሞ የሶቪየት ሕብረት አገራት [ሩሲያ፣ አርሜኒያ፣ ካዛኪስታን፣ ክይርጊስታን፣ ታጂኪስታን እና ኡዝቤኪስታን] በፈረንጆቹ 1992 የመሰረቱት የጦር ትብብር ድርጅት አባል ናቸው። ሁለቱ አገራት ያላቸውን ትስስር የሚያጠናክር፣ ዜጎች የመስራት መብታቸው እንዲረጋገጥ እና ዜጎች በሁለቱም አገራት በነፃነት እንዲኖሩ የሚያስችል ሕብረት የመሰረቱትም በፈረንጆቹ 1996 ነበር።
news-53047756
https://www.bbc.com/amharic/news-53047756
"ሙሶሎኒ በኢትዮጵያ የመርዝ ጋዝ አልተጠቀመም" ያለው ጋዜጠኛ ሐውልት እንዲፈርስ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ
ኤርትራዊቷን በባርነት ገዝቶ የኖረው እና "ሙሶሎኒ በኢትዮጵያ የመርዝ ጋዝ አልተጠቀመም" ያለው ጋዜጠኛ ሐውልት እንዲፈርስ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ።
ኢንድሮ ሞንታኔሊ ጣሊያናዊ ጋዜጠኛ ነበር። የዚህ ሰው ችግር ቅኝ ግዛት እጅግ አስፈላጊም ተገቢም ነበር ብሎ ማመኑ ነው። ሰሞኑን በዚህ ሰውዬ ላይ ቂም የያዙ ሰዎች ለእርሱ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የቆመን ሐውልት በቀለም ፊቱን አበለሻሽተውታል። "አንተ ሴት ደፋሪ፣ አንተ ዘረኛ" ብለውም በሚላን ከተማ የቆመውን ሐውልቱን በቀለም ቸክችከውበታል። የጣሊያን ፖሊስ ይህን ደርጊት ማን ነው የፈጸመው ብሎ ሲጠይቅ ጸረ ዘረኝነትን ያነገቡ ሰልፈኞች "እኛ ነን ሐውልቱን ያበላሸነው" ብለዋል። ይህ ሐውልት ቆሞ የሚገኘው በጣሊያን ሚላን ፓርክ ውስጥ ነው። ተቃዋሚዎች ይህ ሐውልት በአስቸኳይ መፍረስ አለበት ብለው ተነስተዋል። ሞንታኔሊ የሞተው እንደ አውሮፓዊያኑ በ2001 ነበር። እአአ በ1930ዎቹ በውትድርና አገልግሎት ላይ ሳለ አንዲት የ12 ዓመት ኤርትራዊትን በገንዘብ ገዝቶ እና በኋላም አግብቷት ይኖር እንደነበር አምኗል። በአሜሪካና በአውሮፓ ጸረ ባርነትና ጸረ ዘረኝነት ተቃውሞዎች መስፋፋታቸውን ተከትሎ በጣሊያንም ተቃዋሚዎች የዚህን ሰው ሐውልት በአስቸኳይ አፍርሱልን እያሉ ነው። ይህ ዓለም አቀፍ መልክ እየያዘ የመጣው የጸረ ዘረኝነትና የጸረ ባርነት ተቃውሞ እየተስፋፋ የመጣው ባለፈው ወር በሜኔሶታ ግዛት ሚኒያፖሊስ ከተማ አንድ ነጭ ፖሊስ ጆርጅ ፍሎይድ የተባለ ጥቁር አሜሪካዊያን መተንፈስ እስኪሳነው ድረስ በጉልበቱ ማጃራቱን አንቆ በግፍ ከገደለው በኋላ ነበር። በጣሊያን አገር ሬተስቱደንቲሚሊኖ የሚባሉ የመብት ተቆርቋሪ ቡድኖች ይህንን ሞንታኔሊ የተባለ ሰው "እጅግ ነውረኛና ዘረኛ የነበረ፣ የቅኝ ግዛት ደጋፊና የባርነት አቃፊ›› ሲሉ ይነቅፉታል። "ለዚህ ነውረኛ ሰው ሐውልት ማቆም ነውር ነው" ሲሉ ቅዋሚያቸውን አስተጋብተዋል። የሚላን ከንቲባ በበኩላቸው "ሞንታኔሊ ሐውልቱ የቆመለት በነበረው የጋዜጠኝነት ጀብዱ ነው" ሲሉ ተከላክለውታል። "እንዴት ያለ ጋዜጠኛ ነበር መሰላችሁ፤ ለነጻ ፕሬስና የመናገር ነጻነት ሲታገል ነው የኖረው። እያንዳንዳችን ስለ ሕይወታችን መለስ ብለን ብናይ ከሐጥያት ነጻ ነን ወይ? የአንድ ዜጋ ሕይወት መለካት ያለበት ከጥላሸቱ ጭምር ነው" ሲሉ ሰውየውን ተከላክለውለታል፤ ከንቲባው። ትናንትና እሑድ የሚላን ማዘጋጃ ቤት የጽዳት ሠራተኞች ተቃዋሚዎች ያጎደፉትን የሰውየውን ሐውልት ሲያጸዱ ነው የዋሉት። ኢንድሮ ሞንታኔሊ ማን ነበር? እንደነርሱ አቆጣጠር ከ1909 እስከ 2001 ድረስ የኖረው ይህ ጣሊያናዊ ጋዜጠኛ በፋሺስቱ ቤኒቶ ሙሶሎኒ ዘመን ነበር ወደ ፕሬስ ዓለም የተቀላቀለው። ለፋሺስቶች ልሳን በነበረው 'ሰልቫጂዮ' ለሚባል ጋዜጣ ይሰራ ነበር። ይህ በ1930ዎቹ ቤኔቶ ሙሶሎኒ ከሂትለር ጋር እጅና ጓንት ኾኖ አውሮፓን በሚያምስበት ዘመን መሆኑ ነው። በ1935 እንደ አውሮፓዊያኑ ፋሺስቱ ሙሶሎኒ ወደ ኢትዮጵያ በርካታ ወራሪ ሠራዊት ሲልክ ይህ ጋዜጠኛ እኔም መዝመት እፈልጋለሁ ብሎ ተነሳ። ለዚህ በዋናነት ወደ ሶማሊያና ከኤርትራ ለመጓዝ ከተሰባሰበው የጣሊየን ወራሪ ጦር፣ ለዚያ ለቅኝ ገዢዎች ሠራዊት ወዶና ፈቅዶ በወዶ ገብነት ተመዘገበ። ሞንታኔሊ በኋላም በስፔን የእርስበርስ ጦርነት ጊዜም በፋሺስቶቹ ወገን ሆኖ ዜና ያቀርብ የነበረ ሰው ነበር። በ2ኛው የዓለም ጦርነትም ይህን ተግባሩን ቀጥሎበታል። ከሥራው በጡረታ ከተገለለ በኋላ ይህ ሰው በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና እየተሰጠው መጣ። በ2012 የዓለም የፕሬስ ኢንስቲትዩት ከዓለማችን የፕሬስ ጀግኖች አንዱ ሲል ሰየመው። ዓለም አቀፍ ዕውቅናና መልካም ስሙ ታዲያ ሰውየው ለፋሺስት አስተዳደርና እና ለቅኝ ግዛት በነበረው መልካም አተያይ ሲጎድፍበት ቆይቷል። ይህ ሰው ለረዥም ዘመን የፋሺስት ጦር በኢትዮጵያ አርበኞች ላይ የጋዝ መርዝ አልተጠቀመችም ሲል ክዶ የኖረ የዘረኝነት ጠበቃ ነበር። "ጣሊያን ኢትዮጵያ ላይ የጋዝ መርዝ ተጠቅማለች የሚሉት በአምባ አራዳ ውጊያ ነው። እኔ እዚያው ነበርኩ። ያ ሲሆን አላየሁም። በሠራዊቱ ውስጥ የእኔ ሽርክ የነበረ ወዳጄ ሽንኩርት እንደሸተተው ነግሮኛል። የመርዝ ጋዝ ሽታ አልነበረም። ለዚያ ጦርነትስ የመርዝ ጋዝ አስፈላጊ ነበር ብላችሁ ነው? በዚያ አካባቢ ጠላትም አልነበረም እኮ…" ሲል ፋሺስት ጣሊያንን የተከላከለ ሰው ነው ይህ ሞንታኔሊ የሚባል ሰው። በኋላ ላይ በ1996 አካባቢ አንጄሎ ዴል ቦካ የተባለ የታሪክ አዋቂ በማስረጃ ሲያፋጥጠው ግን በእርግጥም ጣሊያን ያን መጠቀሟን (መስታርድ ጋዝ) አምኗል። ይህ ሰው ለረዥም ዓመታት ለዕለታዊው ኮሪየር ዴላ ሴራ ጋዜጣ ሲሰራ ቆይቶ በኋላ ላይ የቀኝ አክራሪዎች ልሳን የሆነውን ጂዮርናሌ የተባለ ጋዜጣን መሠረተ። ይህ በ1973 መሆኑ ነው። ኋላ ላይ ቢሊየነሩ ሲልቪዮ በርልስኮኒ ይህን ጋዜጣ ሲገዛው ሞንታኔሊ ሥራ ለቀቀ። በ1977 አንድ የቀኝ አክራሪ ሬድ ቢርጌድ አባል ሞንታኔሊን እግሩን በሽጉጥ ተኩሶት መትቶት ነበር፤ እዚያው ራሱ በመሰረተው ጋዜጣ በር ላይ ነው ክስተቱ የተፈጠረው። ሆኖም ሞንታኔሊ ቆሰለ እንጂ አልሞተም። ሕይወቱ ያለፈችው በ2001 እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ነበር።
news-52378019
https://www.bbc.com/amharic/news-52378019
ኮሮናቫይረስ፡ አሜሪካ ለቀጣዮቹ 60 ቀናት ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ መስጠት ልታቆም ነው
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኮሮናቫይረስ ምክንያት በአሜሪካ ለቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት የሚያመለክቱ የውጭ ዜጎች መቀበል ማቆማቸውን ተናገሩ።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ይህ እርምጃቸው የአሜሪካውያንን የሥራ እድል ይታደጋል ብለዋል ፕሬዝዳንቱ አሻሚ የሆነ ትዊታቸውን ከጻፉና እርምጃቸውን ካሳወቁ በኋላ ውሳኔው የአሜሪካውያንን ሥራ ይታደጋል ብለዋል። አብዛኛዎቹ የቪዛ ጥያቄዎች በወረርሽኙ ምክንያት ቀድመው የተቋረጡ በመሆኑ አሁን ይህ እንዴት ተግባራዊ እንደሚሆን የታወቀ ነገር የለም። የፕሬዝዳንቱ ተቺዎች ግን ዶናልድ ትራምፕ የቫይረሱን ወረርሽኝ ምላሽ የሰጡበት መንገድ ስላስተቻቸው ትኩረት ለመስረቅ ያደረጉት ነው ብለዋል። በአሜሪካ 45 ሺህ ሰዎች ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ሞተዋል። • የነዳጅ ዋጋ መውደቅ ምርቱን በነጻ እንድናገኝ ያስችለናል? • ሳኡዲ አረቢያ ባለፈው ዓመት 184 ሰዎችን በሞት ቀጥታለች- አምነስቲ • ለሕክምና ከሄዱበት ሕንድ መመለስ ያልቻሉ ኢትዮጵያዊያን ችግር ላይ ነን አሉ ዲሞክራቶች በበኩላቸው የትራምፕ አስተዳደር የቫይረሱን ወረርሽኝን ስደተኞችን ለማጥቃት እየተጠቀመበት ነው ሲሉ ተደምጠዋል። ይህ የፕሬዝዳንቱ እርምጃ የምርጫ ዘመቻቸው አካል የነበረ ቢሆንም የኮሮና ወረርሽኝ መከሰት እንዲቀዛቀዝ አድርጎት ነበር። ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ይህንን ውሳኔያቸውን ረቡዕ እለት ፊርማቸውን እንደሚያኖሩበት ተናግረዋል። ይህ እገዳ የአሜሪካ ምጣኔ ሃብት መሻሻል እስኪያሳይ ድረስ እንደሚቆይ ፕሬዝዳንቱ ጨምረው ገልፀዋል። ሰኞ እለት የትኛውንም ወደ አሜሪካ የሚደረግ ጉዞ ለማገድ ቃል ከገቡ በኋላ ከአንዳንድ የቢዝነስ ሰዎች ተቃውሞ በመሰማቱ የመጀመሪያ እቅዳቸውን ሰርዘውታል። የፕሬዝዳንቱ የቀደመ ውሳኔ በግብርና ላይ በጉልበት ሥራዎች ላይ ለመሳተፍ እንዲሁም ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ባለሙያ ሆነው ለሚቀጠሩ ጊዜያዊ ቪዛ ለመስጠት አያስችልም ሲሉ ነበር ቅሬታቸውን ያቀረቡት። በአሜሪካ ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ከ20 ሚሊዮን በላይ አሜሪካውያን ሥራቸውን አጥተዋል፤ ፕሬዝዳንት ትራምፕም እነዚህ አሜሪካውያን ተመልሰው ሥራ እንዲይዙ የማድረግ "ኃላፊነት አለብን" ብለዋል። አክለውም " በቫይረሱ ምክንያት ሥራቸውን ያጡ አሜሪካውያንንን በሌሎች ስደተኞች ሥራቸውን እንዲነጠቁ ማድረግ ስህተትም ነው ፍትሃዊም አይደለም" ብለዋል። በተጨማሪም "ለአሜሪካውያን ሰራተኞች መከላከል ነው የምንፈልገው፤ ወደፊት ደግሞ የበለጠ እንከላከላለን" በማለት ለዚህ እርምጃ አንዳንድ የሚዘለሉ ነገሮች እንደሚኖሩ ፍንጭ ሰጥተው ነበር። • በሴቶች የሚመሩ አገራት ወረርሽኙን በተሳካ ሁኔታ እንዴት ተቆጣጠሩት? ይህ የፕሬዝዳንቱ ውሳኔ ግን የሕግ ተግዳሮት ይገጥመዋል የሚሉ አልጠፉም። እንደጆንስ ሆፕኪንስ አሁናዊ መረጃ ከሆነ አሜሪካ በኮሮናቫይረስ ክፉኛ ከተጎዱ አገራት መካከል ስትሆን እስካሁን ድረስ 820 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተመዝግቧል። የአሜሪካ ግሪን ካርድ ሕጋዊ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ሲሆን ለአሜሪካ ዜግነት ለማመልከት እድል ይሰጣል። አሜሪካ በየዓመቱ አንድ ሚሊየን ግሪን ካርድ ትሰጣለች።
news-53669799
https://www.bbc.com/amharic/news-53669799
ኮሮናቫይረስ፡ “ስለበሽታው ሲናገሩት እና ታመው ሲያዩት በጣም የተለያዩ ናቸው” ድምጻዊ ኢቲቃ ተፈሪ
በኦሮምኛ የፖለቲካ ዘፈኖቹ የሚታወቀው ድምጻዊ ኢቲቃ ተፈሪ በኮሮናቫይረስ መያዙን ካወቀ ሳምንታት መቆጠሩን ለቢቢሲ ተናግሯል።
ስለበሽታው ሲናገሩት እና ታመው ሲያዩት በጣም የተለያዩ ናቸው፤ ስለዚህ ለራስ ጥንቃቄ ማድረግ በጣም አስፈላጊ ነው ድምጻዊው "በሽታው እንዲህ አይነት ቦታ ያዘኝ ብዬ መናገር አልችልም" ካለ በኋላ የሚጠረጥረው ስፍራ እንዳለ ግን ገልጿል። ድምጻዊው ሃጫሉ ሁንዴሳ፣ በተገደለበት እለት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርግ ከጓደኞቹ ጋር በሆስፒታል ውስጥ ከወዲያ ወዲህ ሲሯሯጡ እንደነበር ያስታውሳል። አምቦ በነበረው የቀብር ስነስርዓት ላይም አብዛኛው ሰው በሐዘን ስሜት ውስጥ ሆኖ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አልተጠቀመም ነበር። ትልቁ ጥርጣሬዬ ይህ እንደሆነ የሚናገረው ድምጻዊ ሂቲቃ፣ ከአምቦ ከተመለሰ በኋላ የሕመም ስሜት ተሰምቶት ወደ ግል ጤና ጣብያ ቢሄድም ሌላ በሽታ ነው ተብሎ መርፌና ኪኒን ታዘዘለት። ይሁን እንጂ በራሱ ላይ የተመለከታቸው የሕመም ስሜቶች የኮሮናቫይረስ ነበሩ ይላል ድምጻዊ ሂቲቃ። " ሰውነቴ በጣም ይደክማል፤ ደረቅ ሳል ሳያቋርጥ ለሶስት ሰዓት ያስለኝ ነበር" በማለት ከዚያ በኋላ ለጤና ቢሮ በመደወል ምርመራ እንደተደረገለት እና በኮሮናቫይረስ መያዙ ሲረጋገጥም ወደ ሚሌኒየም አዳራሽ ተወስዶ ሕክምና እና እንክብካቤ ሲደረግለት መቆየቱን ይናገራል። "የምኖረው ከእህቴ ጋር ነው፣ እርሷም ተይዛ ነበር፤ እርሷ ህመም እንደኔ ስላልጠናባት ቤት ውስጥ በተደረገላት እንክብካቤ ነው የተሻላት፤ እኔ ግን ለሁለት ሳምንታት ሚሌኒየም አዳራሽ ውስጥ ሕክምና ድጋፍ ተደርጎልኛል።" ይላል በሚሊኒየም አዳራሽ ያሳለፋቸው ሁለት ሳምንታት ፈታኝ እንደነበረ የሚናገረው ኢቲቃ ሆኖም በጤና ባለሙያዎቹ ለታማሚዎች የሚደረገው ህክምናና እንክብካቤ ሊደነቅ የሚገባው መሆኑን ይጠቅሳል። በከባድ ህመም ያሳለፈባቸው ሳምንታት በመጥቀስ ማህበረሰቡ በሽታውን አቅልሎ ማየት እንደሌለበትም ይመክራል። " ሳሉ በጣም ከባድ ነበር፤ ሁለት ለሊት ጭንቅላቴን ይዤ ነበር ሳስል ያሳለፍኩት፤ ከሚነገረው በላይ በጣም በጣም ከባድ ጊዜ ነበር፤ ስለበሽታው ሲናገሩት እና ታመው ሲያዩት በጣም የተለያዩ ናቸው፤ ስለዚህ ለራስ ጥንቃቄ ማድረግ በጣም አስፈላጊ ነው።" በማለት መልእክቱን አስተላልፏል። ድምጻዊ ሂቲቃ፣ በአሁኑ ሰዓት ሙሉ በሙሉ የዳነ ባይሆንም ከአምስት ቀናት በፊት ከሚሌኒየም የማቆያና ህክምና ማእከል በመውጣት ወደ ቤቱ ተመልሷል። "ቤት እየተመላለስን እንከታተልሃለን ተብዬ ነው የወጣሁት" በማለት የጤና ባለሙያዎቹ ቃል በገቡት መሰረት ከማቆያው ከተመለሰ በኋላ ቤቱ ድረስ እየመጡ ክትትል እንዳደረጉለት ገልጿል። በአሁኑ ሰዓት ሞልቶ ባይሻለውም ከነበረበት ሁኔታ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ተናግሯል። "በህመሜ ሰዓት በሁሉም መንገድ ይጠይቁኝና ሲያበራቱኝ የነበሩ አድናቂዎቼና ማህበረሰቡን ላመሰግን እወዳለሁ፤ አሁን በጥሩ ጤንነት ላይ እገኛለሁ፤ ከሚያሰጋኝ ነገር ውስጥ ወጥቻለሁ ማለት እችላለሁ።"
news-50980159
https://www.bbc.com/amharic/news-50980159
ህወሃት በታሪኩ የመጀመሪያ የሆነውን አስቸኳይ ጉባዔ እያካሄደ ነው
ህውሃት ከዛሬ ታህሳስ 25/2012 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት የሚቆይ አስቸኳይ ድርጅታዊ ጉባኤ በመቀሌ ከተማ ሰማዕታት ሐውልት አዳራሽ እያካሄደ ነው።
እስካሁን 13 ድርጅታዊ ጉባዔዎችን ያካሄደው ህወሃት አስቸኳይ ጉባዔ ሲጠራ ይህ የመጀመሪያው ነው። በጉባዔው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የህወሃት ሊቀመንበር ደብረፂዎን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር)፤ ጉባዔውን "ቀጣይ የህወሃትን ህልውና የሚወስን ልዩና ታሪካዊ ጉባዔ ነው" ብለውታል። ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም፤ ጉባኤው በህወሃት ፍላጎት የተጠራ ሳይሆን፤ በአገሪቷ ያለው ሁኔታ አስገድዶ የተጠራ አስቸኳይ ጉባዔ መሆኑንም ተናግረዋል። የፓርቲው ጽ/ቤት ኃላፊና ከጉባዔው አስተባባሪ ኮሚቴዎች አንዱ የሆኑት አቶ አለም ገ/ዋህድ የጉባዔውን ሦስት አጀንዳዎች አስተዋውቀዋል። ከኢህአዴ መፍረስና እና ከአዲሱ ብልፅግና ፓርቲ መመስረት ጋር በተያያዘ የማዕከላዊ ኮሚቴውን በጥልቀት መገምገም፣ በምርጫ አዋጅ መሠረት የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና ሥነ ምግባር ጋር እንዲሁም ከኢህአዴግ ጋር ስላላቸው ግንኙነት የሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ በፓርቲው የመተዳደሪያ ደንብ ላይ ለውጥ ለማድረግ እና የፓርቲው ፕሮግራም ከኢህአዴግ ጋር ከነበረው ግንኙነት እና ከወቅቱ ጋር የሚሄዱ ጉዳዮችን ለማሻሻል እንደሆነ አስረድተዋል። • አቶ ጌታቸው አሰፋ በሚያውቋቸው አንደበት በጉባዔው ላይ ከፓርቲው አባላት ውጭ እስከ 150 የሚሆኑ ምሁራን፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ የተለያዩ ብሔረሰብ ተወካዮች እና ሌሎች እንግዶች በመክፈቻውና እና በመዝጊያው ላይ ብቻ እንዲሳተፉ መፈቀዱም ታውቋል። ዛሬ ጠዋት የተጀመረው ጉባኤ በአጀንዳዎቹ ላይ ውሳኔ በማሳለፍ ነገ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። በተመሳሳይ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የመጀመሪያውን ስብሰባ ትናንት ማካሄዱ ይታወሳል። ፓርቲው ከግንባር ወደ ውህደት ከተሸጋገረ በኋላ የመጀመሪያውን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ነበር ያካሄደው። በስብሰባው ላይ ውይይት ከተደረገባቸው አጀንዳዎች መካከል ምርጫ 2012 አንዱ መሆኑ ተነግሯል።
news-46549177
https://www.bbc.com/amharic/news-46549177
ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን?
ጤናማና የተስተካከለ ሰውነት ያላቸው ሰዎች ቁርሳቸውን አይዘሉም ይባላል። ነገር ግን ቁርስ መብላት ሙሉ በሙሉ ጤናማ ወይም ቀጭን ያደርገናል ማለት አይደለም።
ነገር ግን ምን ያህሎቻችን ቁርስ በትክክለኛው ሰአት እንመገባለን? ቁርስ ሳይዘሉ መመገብ ትክክለኛ መሆኑን ለማሳየት የሚቀርበው ምክንያት ሌሊቱን ሙሉ ሲጾም ያደረ ሰውነታችንን በምግብ መጠገን አለብን የሚለው ነው። ከዚህ በተጨማሪ ሰውነታችን የሚያድገው እና ጉዳት የደረሰባቸው የሰውነት ክፍሎች የሚጠገኑት በምንተኛበት ወቅት መሆኑ፤ ብዙ ጉልበት እንድንጨርስ ያደርገናል። • ስለ አንጀታችን የማያውቋቸው ስድስት አስገራሚ እውነታዎች ስለዚህ በቁርስ ሰአት ምግብ መብላት ብቻ ሳይሆን የተመጣጠነ ምግብ መመገብ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን የስነ ምግብ ባለሙያዋ ሳራ ኤልደር ትናገራለች። ነገር ግን አሁንም ድረስ ቁርስ የዕለቱ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነው ወይ? በሚለው ሃሳብ ዙሪያ ስምምነት ላይ መድረስ አልተቻለም። ቁርስ አስፈላጊ ነው ወይስ አይደለም? በተለያዩ ጥናቶች መሰረት ቁርስ መብላትም ሆነ ቁርስ መዝለል ተያይዘው የሚነሱት ካላስፈላጊ ውፍረት ጋር ነው። ምንም እንኳን በዚህ ጉዳይ ዙሪያ የተለያዩ ሃሳቦች ቢኖሩም፤ ግንኙነቱ ግን ምንድነው? ሰባት ዓመታት በፈጀና 50 ሺ ሰዎች በተሳተፉበት አንድ ጥናት መሰረት የተመጣጠነ ቁርስ በሰአቱ የሚመገቡ ሰዎች ምሳ ወይም እራት ሰአት ላይ ከበድ ያለ ምግብ ከሚመገቡ ሰዎች አንጻር፤ የክብደት መጠናቸው ጥሩ በሚባል ደረጃ ላይ እንደተገኘ ያሳያል። • አትክልት ብቻ ስለሚመገቡ ሰዎች ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮች አጥኚዎቹ እንደሚሉት እነዚህ ቁርሳቸውን በትክከል የተመገቡ ሰዎች ቀኑን ሙሉ የሚሰማቸው የረሃብ ስሜት የቀነሰ እንደሚሆንና የሚመገቧቸው ምግቦች መጠን እንደሚቀንስ ያስረዳሉ። የተመጣጠነ ቁርስ በተገቢው ሰአት መመገብ ያልቻሉት ሰዎች ደግሞ ሰውነታቸው ሌሊቱን ሙሉ ያቃጠለውን ሃይል መተካት ስላለበት፤ ቀኑን ሙሉ ምግብ ቢመገቡም የመርካት ስሜት ስለማይኖራቸው ከመጠን ያለፈ ምግብ እንዲመገቡ ይገደዳሉ። ሆኖም አጥኚዎቹ ቁርስ ያልተመገቡ ሰዎች በቀጥታ ላላስፈላጊ ውፍረት የተጋለጡ ናቸው የሚለውን ሃሳብ ማረጋገጥ አልቻሉም። ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመስጠት ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያጋጠማቸው 52 ሴቶችን ያካተተ የ12 ሳምንት ጥናት ተደርጓል። ሁሉም ተመሳሳይ ይዘት ያለው ምግብ ሲሆን የሚሰጣቸው፤ ግማሾቹ ቁርስ እንዲበሉና ግማሾቹ ደግሞ ቁርስ እንዳይበሉ ተደርገዋል። በተገኘው ውጤት መሰረትም ተሳታፊዎቹን ክብደት እንዲቀንሱ ያደረጋቸው ቁርስ ሳይሆን፤ በተደጋጋሚ የሚያደርጉት ነገር በመቅረቱ ነው። በጥናቱ ለመሳተፍ ከምጣታቸው በፊት ቁርስ ይመገቡ የነበሩት ግማሾቹ ሴቶች ቁርስ ሳይመገቡ ለ12 ሳምንታት ከቆዩ በኋላ 8.9 ኪሎ የቀነሱ ሲሆን፤ ከጥናቱ በፊት ቁርስ የማይመገቡ የነበሩት ግማሾቹ ደግሞ ለ12 ሳምንታት ቁርስ እንዲመገቡ ከተደረጉ በኋላ 7.7 ኪሎ ቀንሰዋል። • ልጆችዎ ጤናማ ምግብ እንዲመገቡ ማድረጊያ መላዎች ቁርስ መብላት ወይም አለመብላት ውፍረት ለመቀነስ ማረጋገጫ መሆን ካልቻለ፤ በሁለቱ መካከል ያለው ግንኙነት ታዲያ ምንድነው? በአቤርደን ዩኒቨርሲቲ የምግብ ፍላጎት ፕሮፌሰር የሆነችው አሌክሳንድራ ጆንስቶን እንደምትለው አብዛኛዎቹ ቁርስ የሚመገቡ ሰዎች የጠዋት እንቅስቃሴ የማድረግና ከሱሶች የመራቅ ባህሪ አላቸው። ስለዚህ በቁርስና በውፍረት መካከል ያለውን ግንኙነት እስኪረጋገጥና በደንብ የዳበረ ጥናት እስኪሰራበት ድረስ ይሄ ነው ብሎ ለመደምደም ከባድ ነው ትላለች አሌክሳንድራ። • ከሰዎች ጋር ያለንን ግንኙነት ለማስተካከል የሚረዱ ዘጠኝ ሚስጥሮች በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት በተሰራ ሌላ የዳሰሳ ጥናት መሰረት የቁርስ ሰአትን ማሳለፍ በደማችን ውስጥ የሚገኘውን የስኳር መጠንና የደም ግፊትን ለመቀነስ እንደሚረዳ ያሳያል። ምንም እንኳ ሙሉ ውጤቱ ገና ይፋ ባይደረግም፤ ከሰሬይና አቤርደን ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ የጥናት ባለሙያዎች የደረሱበት መረጃ እንደሚያሳየው ከበድ ያለ ቁርስ መመገብ ክብደትን ለመቆጣጠር ይረዳል። አሁን አሁን እየወጡ ባሉ መረጃዎች መሰረት ግን ቁርስ የሚያያዘው ከብደት ጋር ብቻ አይደለም። ቁርሳቸውን የማይበሉ ሰዎች በልብ በሽታ የመጠቃት እድላቸው 27 በመቶ የጨመረ ሲሆን፤ ታይፕ 2 በሚባለው የስኳር በሽታ የመያዝ እድላቸው ደግሞ 21 በመቶ የጨመረ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ቁርስ መመገብ የአእምሮ መነቃቃት ለመፍጠርም ይረዳል ተብሏል። ይህ ማለት ለነገሮች ትኩረት ሰጥተን እንድንሰራና ህጻናት ደግሞ በቀላሉ ቋንቋዎችን እንዲማሩ ይረዳቸዋል። • ጫትን መቆጣጠር ወይስ ማገድ? ቁርስ መብላት በራሱ ወሳኝ እንዳልሆነና ጉልህ ልዩነት የሚፈጥረው በቁርስ ሰአት የምንመገበው የምግብ አይነት ነው ብለው የሚከራከሩም አልጠፉም። የተመጣጠነ ቁርስ መመገብ ለብዙ ነገር ቢጠቅምም፤ ማንኛውንም የምግብ ሰአት አክብሮ መመገብና ለሰውነት ጠቃሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ለማግኘት መሞከር ተገቢ እንደሆነ የስነ ምግብ ባለሙያዋ ሳራ ኤልደር ትመክራለች።
53610860
https://www.bbc.com/amharic/53610860
ቬትናም የመጀመሪያውን የኮቪድ-19 ሞት መዘገበች
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር በምታደርገው ጥረት የምትመሰገነው እስያዊቷ አገር ቬትናም የመጀመሪያውን የኮቪድ -19 ሞት መዘገበች። ይህም እስካሁን በቫይረሱ ሳቢያ ሞት ላልመዘገበችው ቬትናም አሳዛኝ ክስተት ሆኗል።
በበሽታው የሞቱት የ70 ዓመቱ ግለሰብ ከሆይ አን ከምትባል ግዛት መሆናቸውንም የአገሪቷ ሚዲያ ዘግቧል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በዳ ናንግ ሪዞርት አቅራቢያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ከመመዝገባቸው በፊት ከሦስት ወራት ለሚበልጥ ጊዜ በአገሪቷ አዲስ በቫይረሱ የተያዘ ሰው አልነበረም። 95 ሚሊየን ሕዝብ ያላት ቬትናም፤ ወረርሽኙ ከጀመረ አንስቶ እስካሁን 509 በቫይረሱ ተይዘውባታል። ይህም ከሌሎች አገራት ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛ ቁጥር ነው። በእርግጥ አገሪቷ ከሌሎች አገራት በተለየ ቫይረሱን ለመከላከል እርምጃ መውሰድ የጀመረችው አንድም በቫይረሱ የተያዘ ሰው ሳይኖር ነበር። ድንበሮቿንም ወደ አገራቸው ከሚገቡ ዜጎቿ በስተቀር ለተጓዦች ዝግ ያደረገችው ቀድማ ነበር። ከዚህም ባሻገር ወደ አገሪቷ የሚገባ ማንኛውም ግለሰብ መንግሥት ባዘጋጀው ለይቶ ማቆያ ለ14 ቀናት መቆየትና መመርመር ግድ ነው። እነዚህ የጥንቃቄ እርምጃዎችም ውጤት አሳይተው ከሚያዚያ ወር አጋማሽ ጀምሮ በአገሪቷ አዲስ በቫይረሱ የተያዘ ሰው አልነበረም። በዚህ በወቅት በሽታውን ለመቆጣጠር ባደረገችው ጥረት እንዲሁም በቫይረሱ ተይዞ ሁለት ወራትን በሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ላሳለፈው ስኮትላንዳዊ አብራሪ ላደረገችው እንክብካቤም አድናቆት ተችሯታል። ይሁን እንጂ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በታዋቂው ዳ ናንግ ሪዞርት አዳዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የመገኘታቸው አሳዛኝ ዜና ተሰምቷል። በዚህ ወቅትም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የአገሪቷ ጎብኝዎች በከተማዋ ውስጥ ነበሩ ተብሏል። መንግሥት ረቡዕ ዕለት በከተማዋ ሙሉ ለሙሉ የእንቅስቃሴ ገደብ ከመጣሉ በፊትም ከተማዋን ለጎብኝዎች ዝግ አድርጎ ነበር። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በዳ ናንግ የተከሰተውን ወረርሽኝ ተከትሎም ጠቅላይ ሚኒስተር ጉየን ዡዋን ፑክ "ወረርሽኙን ለመቆጣጠር በፍጥነትና በትጋት እርምጃ መውሰድ አለብን" በማለት በአገሪቷ ያሉ ግዛቶችና ከተሞችን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማስጠንቀቃቸውን የመንግሥት ሚዲያ ዘግቧል።
news-55212004
https://www.bbc.com/amharic/news-55212004
ትግራይ፡ የጠ/ሚ ጽሕፈት ቤት ህወሓት የትጥቅ ትግል የማድረግ አቅም የለውም አለ
የህወሓት ኃይል በከፍተኛ ደረጃ መሸነፉንና ተበታትኖ ባለበት ሁኔታ የተራዘመ የሽምቅ ውጊያ ማድረግ በሚችልበት አቋም ላይ እንዳልሆነ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤት ጽህፈት ቤት ገለጸ።
ጽህፈት ቤቱ በትግራይ ክልል እተካሄደ ያለው ሕግን የማስከበር ዘመቻ አሁን ያለበትን ደረጃ በተመለተ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው መቀለ ከሳምንት በፊት "ሰላማዊ ሰዎች ሳይጎዱና ንብርት ሳይወድም" በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ቁጥጥር ስር ከገባች በኋላ ወታደራዊ ዘመቻው ተጠናቋል ብሏል። ነገር ግን ከዋና ከተማዋ መቀለ የወጡት የትግራይ ኃይሎች አመራሮች ለተለያዩ የዜና ማሰራጫዎች እንደተናገሩት ውጊያው እንዳላበቃና ተጠናክሮ መቀጠሉን አመልክተው ነበር። ይህንንም በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግሥት የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሚንስትር የሆኑት ዛዲግ አብረሃ በበኩላቸው፤ በክልሉ ጦርነት እየተካሄደ አለመሆኑንና ህወሓት ጦርነት የማካሄድ ቁመና እንደሌላው ጠቅሰው በወንጀል የሚፈለጉ የቡድኑ አመራሮችን ለመያዝ የሚደረግ ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ባለፈው አርብ ተባበሩት መንግሥታት ባለስልጣናት ለፈረንሳይ ዜና ወኪል እንደተናገሩት በተለያዩ የትግራይ ክልል አካባቢዎች በቀጠለው ውጊያ ምክንያት እርዳታ ለማቅረብ የሚያደርጉትን ጥረት እንደተስተጓጎለባቸው ተናግረው ነበረ። የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽህፈት ቤት ሰኞ ረፋድ ላይ ባወጣው መግለጫ ላእ እንዳመለከተው የፌደራል መንግሥት በአሁኑ ተልዕኮ በሕግ የሚፈለጉ የህወሓት አመራሮችን ይዞ ለሕግ ማቅረብ፣ ሕግና ሥርዓትን ማረጋገጥ እንደሆነ አመልክቷል። በተጨማሪም በግጭት ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታ እንዲያገኙ ማድረግ፣ ግጭቱን በመሸሽ ወደ ጎረቤት አገራት የተሰደዱትን ወደ ቀያቸው መመለስ፣ የትራንስፖርት እና የግነኙነት መስመሮችን ጠግኖ ሥራ ማስጀመር እንደሆነ ገልጸወል። "ህወሓት በሐሰት ኃይሎቹ በጦርነት የተፈተኑና የታጠቁ መሆናቸውን በመጥቀስ በትግራይ ተራራማ ቦታዎች ላይ የተራዘመ የትጥቅ ትግል ማካሄድ ይችላሉ ሲል ነበር" ያለው መግለጫው "እውነታው ግን ህወሓት ሙሉ በሙሉ ተሸንፏል፤ ለረዥም ጊዜ የሚዘልቅ የትጥቅ ትግል የመከፍት አቅምም እየለውም" ብሏል። የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽህፈት ቤት ጨምሮም ህወሓት በትግራይ ክልል የተከሰተውን ቀውስ ዓለም አቀፍ መልክ እንዲኖረው መሞከሩን አመልክቶ፤ "ሐሰተኛ ክሶችን እንደ መጨረሻ አማራጭ በመደርደር ዓለም አቀፍ ድርድር እንዲኖር ጫና በማሳደር ከተጠያቂነትና ከፍትሕ ለማምለጥ ጥረት አድርጓል" ይላል የጠቅላይ ሚንስትሩ መግለጫ። በአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት እና በማይካድር ከተማ ንሑሃን ዜጎች ላይ የተሰነዘረውን ጥቃት እንዲሁም በባሕር ዳር እና ጎንደር ከተሞች ላይ የተፈጸሙ የሮኬት ጥቃቶችን በመስታወስ፤ የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት "ቡድኑ ሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርስ ጉዳት ያሳስበኛል ለማለት የሚያስችል ሞራል ሊኖረው አይችልም" ብሏል። የዜጎችን ደኅንነት መጠበቅ የፌደራል መንግሥቱ ቀዳሚ ትኩረት እንደሚሆን በመጥቀስም ከተባበሩት መንግሥታት ተቋማት ጋር በመሆን በግጭቱ ምክንያት ለችግር የተጋለጡትን በትግራይ ውስጥ ባሉ የስደተኞች መጠለያ ውስጥ የሚገኙትን የሌላ አገር ዜጎችን ጭምር ለመርዳት እየሰራ መሆኑን ገልጿል። በፌደራል መንግሥቱና የትግራይ ክልልን ሲያስተዳድር በነበረው ህወሓት መካከል ለወራት የቆየው ውዝግብ ባለፈው ዓመት ሊካሄድ የነበረው አገራዊ ምርጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽን ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ መሸጋገሩን ተከትሎ በከፍተኛ ሁኔታ ተካሮ ቆእቶ ነበር። አለመግባባቱና መካሰሱ ያለማቋረጥ በቀጠለበት ሁኔታ ጥቅም 24/2013 ዓ.ም ምሽት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በትግራይ ክልል በነበሩት የሠሜን ዕዝ አባላት ላይ በህወሓት ኃይሎች ጥቃት መፈጸሙን ይፋ ካደረጉ በኋላ የፌደራሉ ሠራዊት በህወሓት ኃይሎች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩ ይታወሳል። ለሦሰት ሳምንታት ያህል በዘለቀው ወታደራዊ ዘመቻ የትግራይ መዲና መቀለ ጨምሮ በርካታ የክልሉ አካባቢዎች በፌደራል መንግሥት ሠራዊት ቁጥጥር ሰር ከዋሉ በኋላ ወታደራዊ ዘመቻው መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከአንድ ሳምንት በፊት ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።
48523385
https://www.bbc.com/amharic/48523385
ኢንተርኔትን የሚሾፍረው የወሲብ ፊልም ይሆን?
ቁጥሮች እንደሚያሳዩት ከሰባት ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች አንዱ የወሲብ ፊልምን ለማየት ሲል ድረ-ገጾችን ያስሳል። በእርግጥ ጉዳዩን ማንኳሰስ ባይሆንም ስድስቱ ተጠቃሚዎች ሌላ መረጃ ፈላጊዎች ናቸው።
በጣም ዝነኛው የወሲብ በይነ መረብ - Pornhub - ከእነ ኔትፍሊክስና ሊንክደን ጋር እኩል ተመልካች አለው። የወሲብ ፊልም ዝነኛነቱ በዓለም ላይ 28ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ውድና ተዓማኒነት የሚጎድላቸው ናቸው። ቴክኖሎጂውን በቀላሉ መረዳት የሚችሉ ደንበኞችን ለመያዝ ለገበያው የሚመጥን ስራ ያቀርባሉ። አንድ ጊዜ ዋጋው ከወረደና ተዓማኒነት ካገኘ ግን ተጠቃሚና ትልቅ ገበያ ያገኛል። የወሲብ መረጃዎች ለኢንተርኔት እድገት አዎንታዊ ሚና መጫዎታቸውን የሚገልጽ ጽንስ ሃሳብ አለ። ለሌሎች ቴክኖሎጂዎችም እንዲሁ። • እንግሊዛውያን የወሲብ ሕይወታቸው ''ደካማ ነው'' ተባለ ዘመናዊ ምጣኔ ሃብትን የሚያመጡ ሌሎች ጉዳዮች ጥበብ ሲወለድ ጀምሮ ወሲብ ቀዳሚ ጉዳይ ነው። የቀደምት ስልጣኔ የዋሻ ላይ ስዕሎች እንደሚያሳዩት መቀመጫ (ቂጥ)፣ ጡት፣ የሴት ብልትን አካባቢ የሚያሳዩና ትልቅ የወንድ ብልት ዋነኛ የጥበብ መገለጫዎች ናቸው። ከ11 ሺህ አመታት በፊት የአይሁድ እረኞች በዋሻ ላይ ወሲብ ሲፈጽሙ የሚያሳይ ስዕል ቀርጸዋል። ከ4 ሺህ ዓመት በፊት በሜሶፖታሚያ ስልጣኔ ሁለት ጥንዶች በሸክላ ግድግዳ ላይ ወሲብ ሲፈጽሙና ሴትዮዋ ቢራ ስትጎነጭ ያሳያል። በሰሜን ፔሩም ከብዙ አመታት በፊት በሴራሚክስ ላይ የተሰራ ወሲብ የሚፈጽሙ ጥንዶችን አስቀምጧል። ነገር ግን የጥበብ ውጤቶች እነዚህን ወሲባዊ ይዘት ያላቸው ጉዳዮች ይዘው ቢወጡም ዋነኛ ጥበቡን ለመስራት ያነሳሳቸው ቀዳሚ ምክንያት ወሲብ ነው ማለት ግን አይቻልም። እንደዚህ ለማሰብ የሚያስችል በቂ ምክንያት የለም። የጉተንበርግን የህትመት ማሽን ማሰብ ይቻላል። በዋናነት ወሲብ ቀስቃሽ መጽሃፍት የሚታተሙበት ቢሆንም መነሻው ግን የሃይማኖት መጽሃፍት እንዲታተሙበት ነበር። በሚገርም ሁኔታ ደግሞ የ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ፋሽን ፎቶ የነበረው ከንፈርን ማዕከል ያደረገ ፎቶ ነበር። በፈረንሳይ ፓሪስ የፎቶ ስቱዲዮን መገንባት መቻል ትልቅ የንግድ ስኬት ተደርጎ ይወሰድ ነበር። መንግስትም ክልከላ ስለሚያደርግበት ጭምር። በወቀቱ ደንበኞች ለዚህ አይነቱ ፎቶ የተጠየቁትን ይከፍሉ ነበር። በጊዜው ዋጋ ወሲብ አነሳሽ ፎቶን ለመግዛት የሚያወጡት ዋጋ በወሲብ ስራ የተሰማራችን ሴት ለማግኘት ከሚያስፈልገው ገንዘብ በላይ ነበር። • ለወሲብ ትክክለኛው ዕድሜ የቱ ነው? • 100 ሺህ ብር፤ ብልትን ለማወፈር ተንቀሳቃሽ ምስል ሲጀመር ደግሞ ውድ በመሆኑ ፊልም የሚያሳዩ ሰዎች ገንዘባቸውን ለማካካስ ሲሉ ብዙ ተመልካች ይፈልጉ ስለነበር በዚህ ምክንያት ወሲብ ነክ ፊልሞችን በአደባባይ አያሳዩም ነበር። እየቆየ ሲመጣ ግን አንዳንዶች በቤታቸው ሲመለከቱት በአደባባይ ከህዝብ ጋር የሚያዩ ወጣቶችም ነበሩ። በ1960ዎቹ ደግሞ ሳንቲም ተጨምሮበት ማንም ሊያይ በማይችልበት ሁኔታ ለብቻ የወሲብ ፊልሞችን ማየት የሚያስችሉ አነስተኛ ቤቶች ተፈጠሩ። አንዷ ቤትም በሳምንት ብዙ ሸህ ዶላር ትሰበስብ ነበር። በግል ሳይሳቀቁ ማየት የሚቻልበት እድል ሙሉ በሙሉ የተፈጠረው ግን የቪዲዮ መቅረጫ መሳሪያ (VCR) ሲመጣ ነው። ሰው በጣም በግሉ ማየትን ይሻ ስለነበርም መመረት እንደተጀመረም ጠጥሩ ገበያ አግኝቷል። ቤት ተቀምጠው ፊልሙን ማየት የሚሹ ወጣቶች ደግሞ ይህን መሳሪያ በመግዛት ቀዳሚ ናቸው። በ1970ዎቹ አብዛኛዎቹ የቪዲዮ ቴፖች የሚሸጡት የወሲብ ፊልሞችን ነበር። በጥቂት አመታት ውስጥ ደግሞ የቤተሰብ ፊልም የሚመለከቱ ሰዎች በመበራከታቸው በአንጻሩ የወሲብ ፊልሙ መቀዛቀዝ ታይቶበታል። በቴሌቪዥንና በኢንተርኔት ላይም እየሆነ ያለው ተመሳሳይ ታሪክ ነው። በ1990ዎቹ በተጠቃሚዎች ላይ በተደረገ ጥናት ኢንተርኔት ላይ ከሚጋሩ ስድስት መረጃዎች አንዱ ከወሲብ ጋር የተያያዘ ነው። በቅርቡ በኢንተርኔት ላይ የተደረጉ ወሬዎች (chats) ውጤት የሚያሳየውም ተመሳሳይ ነው። በአሁኑ ወቅትም ከዚሁ ጋር በተያያዘ አጥኝዎች የሚሰጡት ሃሳብ ስህተት ሊሆን የሚችልበት እድል የለውም። የወሲብ መረጃዎች ፍላጎት በመኖሩ ፈጣንና አቅም ያለው ኢንተርኔት እንዲኖርም ምክንያት ሆኗል። • የወሲብ ቪዲዮ ህይወቷን ያሳጣት ወጣት • በወሲብ ፊልሞች ሱሰኛ የሆኑ ወጣት ሴቶች በሌሎች ዘርፎችም ግኝቶችን አስገኝቷል። በድረ-ገፆች የሚቀርቡ የወሲብ ፊልሞችን ለማቅረብ የበይነ መረብ ቴክኖሎጂን ወደፊት ለማራመድ የመጀመሪያዎቹ ነበሩ። ለምሳሌ የቪድዮ ፋይሎችን ለእይታ እንዲቀርቡ ማሳነስ፣ ለተጠቃሚው ቀለል ያሉ በበይነ መረብ የመክፈያ ዘዴዎችን በመፈየድ እና የማርኬቲንግ ፕሮግራሞችና ሌሎችም ንግዶች ማስተዋወቂያ በገፃቸው እንዲያሳዩ በማድረግ ረገድ ማለት ነው። እነዚህ ሁሉ ሰፊ ተደራሽነትን ለማግኘት የሚደረጉ ጥረቶች ናቸው። ኢንተርኔት በመስፋፋቱም በሌሌች ጉዳዮች ላይ እንዲያተኩሩና ወሲብ ላይ ያላቸው ተሳትፎ እንዲቀንስ ያደርጋል። በአሁኑ ወቅት የወሲብ ፊልምን ሞያዬ ብለው ለሚሰሩት ሰዎች ፈተና ሆኗል። ጋዜጦችንና ሙዚቃዎችን የሚያቀርቡ ሰዎች ገበያው በኢንተርኔት ተወስዶባቸው ገዥ እንዳጡት ሁሉ የወሲብ ሰራተኞችም ቪዲዮውን እነ ፖርን ሃብ (Pornhub) በበየነ መረብ በበቂ ሁኔታ ቀድመው በማቅረባቸው እነርሱ ገዥ የላቸውም። ጆን ሮንሰን The Butterfly Effect በሚለው ተከታታይ ገለጻው እነዚህን የተዘረፉ የወሲብ ፊልሞች መመለስና ገበያውን ነጻ ለማድረግ ሙከራ ቢኖርም ከባድ መሆኑን ገልጸዋል። በጣም እያደገ የመጣው ዘርፍ 'ካስተም' ማለትም እያንዳንዱ በፍላጎቱ የሚስተናገድበት ዘርፍ ነው። ለምሳሌ ብዙዎች እንደሚያደርጉትና አንድ ግለሰብ ኬሲ ካልቨርት የተሰኘችውን ወሲብ ፊልም ተዋናይ የቴምብር ስብስቦቹን በፊልም እንድታወድም እንደከፈላት ማለት ነው። • የሥራ ቦታ ወሲባዊ ትንኮሳ የቱ ነው? • ግብጽ 'የፒራሚድ የእርቃን ምሰል' ላይ ምርመራ ጀመረች በርግጥ ይዘቱን ለሚፈጥሩት ሰዎች መጥፎ ቢሆንም እንደ አጠቃላይ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን በማሳደግ ረገድ ግን አዎንታዊ ተጽዕኖ አለው። ምክንያቱም ከብዙ ተጠቃሚዎች ገንዘብ በመሰብሰብና ማስታወቂያ በመስራት ዳጎስ ያለ ገንዘብ ለመሰብሰብ አስችሏል። በወሲብ ፊልም በአሁኑ ወቅት የፖርን ሃብንና ሌሎች ሰባት የወሲብ በይነ መረቦችን በባለቤትነት የሚመራው ማይንድጊክ ከአስሩ ቀዳሚዎች አንዱ ነው። በኪው ጎዳና (Avenue Q) የሚታየው ኀሳይ መሲሁ ድርጅት ቀኑን ሙሉ ምንም አይሰራም። የወሲብ ፊልም ብቻ። በመጨረሻ ግን ሌሎች ገጸ ባህሪያት እርሱ ሚሊኒየር ሲሆን ይገረማቸዋል። በመሆኑም ኀሳይ መሲሁ እውነት ባይሆንም ለእውነት የቀረበ ነው። በርግጠኝነት መናገር የሚቻለው ግን ወሲብ ላይ ገንዘብ አለው። ይህን ለማድረግ የተሻለው ነገር ግን ይህን መተካት የሚችል ቴክኖሎጂ መስራት ነው። ምናልባትም ሮቦቶችን ለወሲብ ፊልም መጠቀም ሊሆን ይችላል። በየጊዜው በሚፈጥነው የቴክኖሎጂ ግኝት ግን የወሲብ ጉዳይ መቋጫ ሊያገኝ አልቻለም።
news-49317091
https://www.bbc.com/amharic/news-49317091
ዓለም አቀፏ የህዋ ጣቢያ ዛሬ ማታ በአዲስ አበባ ሰማይ ላይ ትታያለች
በህዋ ላይ እየተንቀሳቀሰች መረጃዎችን የምትሰበስበው ዓለም አቀፍ የህዋ ጣቢያ ዛሬ ምሽት አንድ ሰዓት ከ52 ደቂቃ ሲሆን በአዲስ አበባ ሰማይ ላይ እንደምታቋርጥ ተነገረ።
ዛሬ ነሐሴ 06/2011 ዓ.ም ምሽት 1 ሰዓት 52 ላይ ሲሆን በአዲስ አበባ ሰማይ ላይ የምትታይ ሲሆን የአየሩ ሁኔታ ደመናማ ሆኖ ካልጋረዳት በስተቀር፤ አመቺ ቦታ ላይ ከተሆነ ያለምንም መሳሪያ እገዛ በዓይን ልትታይ እንደምትችል ተገልጿል። ዓለም አቀፏ የህዋ ጣቢያ በአዲስ አበባ ሰማይ ላይ ስታቋርጥ ልትታይ የምትችለው ለስድስት ደቂቃዎች ያህል እንደሆነም ተገልጿል። • ኢትዮጵያ ሳተላይት ማምጠቅ ለምን አስፈለጋት? የህዋ ጣቢያዋ ምን ታደርጋለች? የህዋ ጣቢያዋ ከመሬት ስበት ውጪ ሆና በምድር ዙሪያ የምትሽከረከር ናት። አንድ የእግር ኳስ ሜዳን የምታክለው ጣቢያዋ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምሮችና ሙከራዎች ያለማቋረጥ በውስጧ ባሉ ባለሙያዎችና በእራሷ አማካይነት ታደርጋለች። በምድር ዙሪያ በምትንሳፈፈው በዚች የህዋ የሙከራ ጣቢያ ምድር ላይ ላለው የሰው ልጅ ጠቀሜታ ያላቸው ምርምሮችን ከማድረግ በተጨማሪ ለወደፊቱ የህዋ አሰሳ የሚጠቅሙ መረጃዎችን ትሰበስባለች። መቼ ነው የምትታየው? ይህች የህዋ ጣቢያ ደመና ካላጋረዳት በስተቀር እንደ ጨረቃ የፀሐይን ብርሐን ስለምታንጸባርቅ ያለምንም መሳሪያ መመልከት ይቻላል። ነገር ግን ይህችን የህዋ ጣቢያ የቀን ብርሃን ባለበት ጊዜ ለመመልከት አስቸጋሪ ነው። በተለይ የፀሐይ ብርሐን በሌለበት ጊዜ ከመንጋቱ በፊትና ምሽት ላይ በደንብ ማየት እንደሚቻል ባለሙያዎች ይናገራሉ። • ለ20 ዓመታት ዴንማርካዊት እህቱን የፈለገው ኢትዮጵያዊ ሀኪም የህዋ ጣቢያዋ ምን ትመስላለች? የህዋ ጣቢያዋ ግዙፍ አውሮፕላን ወይም እጅግ ደማቅ በሰማይ ላይ የምትንሳፈፍ ኮከብ የምትመስል ስትሆን ብልጭ የሚል ብርሃን የላትም። እንዲሁም የጉዞ መስመሯን ሳትቀይር በአንድ አቅጣጫ የምትጓዝ ናት። የመንቀሳቀስ ሁኔታዋም አንድ አውሮፕላን ከሚጓዝበት ፍጥነት እጅግ በበለጠ ሁኔታ በሰማይ ላይ ትጓዛለች። የህዋ ጣቢያዋ በምን ያህል ፍጥነት ትጓዛለች? ዓለም አቀፏ የህዋ ጣቢያ 28 ሺህ ኪሎ ሜትሮችን በሰዓት በመጓዝ በየዘጠና ደቂቃው ዓለምን ትዞራለች። በዚህም በጣቢያዋ ውስጥ ያሉ ጠፈርተኞች በየዕለቱ ፀሐይ 16 ጊዜ ስትጠልቅና ስትወጣ የማየት ዕድል አላቸው። • የውሃ እጥረት ዋነኛው የዓለማችን ስጋት የህዋ ጣቢያዋ በጨለማ እንዴት ልትታይ ትችላለች? ደመናማ የአየር ሁኔታ ካልጋረዳት በስተቀር የህዋ ጣቢያዋ ልክ እንደ ጨረቃ ከፀሐይ የምታገኘውን ብርሐን ስለምታንጸባርቅ በደንብ ትታያለች። በምሽት ጨረቃ ባትታይ እንኳን የህዋ ጣቢያዋን ለመመልከት ምንም አዳጋች ሁኔታ አይፈጠርም።
news-56755327
https://www.bbc.com/amharic/news-56755327
በምሥራቅ ኢትዮጵያ ሐሙስ ምሽት የመሬት መንቀጥቀጥ አጋጠመ
በኢትዮጵያ ምሥራቃዊ ክፍል ውስጥ በሚገኙ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ትናንት ሐሙስ ምሽት ርዕደ መሬት መከሰቱን ባለሙያና ነዋሪዎች ገለጹ።
የሐረር ከተማ የመሬት መንቀጥቀጡ ያጋጠመው በሃረማያ፣ በድሬዳዋና ሐረር ከተሞች እንዲሁም በአቅራቢያቸው በሚገኙ አካባቢዎች እንደሆነ ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል። ይህ የመሬት መንቀጥቀጥ አነስተኛ መጠን እንዳለውና በርዕደ መሬት መለኪያ ሦስት እንደተመዘገበ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጂኦሎጂ፣ አስትሮኖሚና የህዋ ምርምር ዳይሬክተር እንዲሁም የርዕደ መሬት ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር አታላይ አየለ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ርዕደ መሬቱ ባጋጠመባቸው አካባቢዎች የነበሩ ሰዎች ለቢቢሲ እንደተናገሩት ለጥቂት ሰከንዶች የቆየው ይህ የመሬት መንቀጥቀጥ ሐሙስ ከምሽቱ 2 ሰዓት ከ38 ደቂቃ ላይ እንደተከሰተ ገልጸዋል። የመሬት መንቀጥቀጡ ባጋጠመበት ጊዜ በሃረማያ ዩኒቨርስቲ ውስጥ የነበረ አንድ ተማሪ ርዕደ መሬቱ በተከሰተበት ጊዜ ተማሪዎች ከነበሩባቸው ህንጻዎች ተሯሩጠው መውጣታቸውን ለቢቢሲ ተናግሯል። ጨምሮም በመሬት መንቀጥቀጡም ሆነ ተማሪዎች ከህንጻዎች ለመውጣት በሚሯሯጡበት ጊዜ "ከድንጋጤ በስተቀር የደረሰ አደጋ ወይም ጉዳት የለም" ብሏል። "እንቅጥቃጤው በተከሰተባቸው ጥቂት ሰከንዶች ውስጥ ህጻው ወደ ግራና ቀኝ የሚወዛወዝ ወይም የሚነቃነቅ ይመስል ነበር። እንዲሁም ከባድ ድምፅ ይሰማ ነበር" ሲል ተናግሯል። ርዕደ መሬቱ ከተከሰተባቸው ከተሞች አንዷ በሆነችው ሐረር ነዋሪ የሆነው አብዱራህማን በበኩሉ "ይህ የመሬት መንቀጥቀጥ ሲፈጠር ቤታችን ላይ አንዳች ነገር የወረደ ያህል ነበር የተሰማኝ፤ ነገር ግን ወደ ውጪ በመውጣት ስመለከት ግን ምንም ነገር አልነበረም" ብሏል። የርዕደ መሬት ተመራማሪው ፕሮፌሰር አታላይ አየለ እንደሚሉት "ይህ የመሬት መንቀጥቀጥ በዋናነት የተከሰተው ኤጀርሳ ጎሮ በምትባለው ቦታ ሲሆን ስፍራው ለሃረማያና ለድሬዳዋ የሚቀርብ ነው።" ሐሙስ ምሽት ያጋጠመው ቀላል የመሬት መንቀጥቀጥ የፈጠረው ንዝረት እስከ ሐረር ከተማ እንደተሰማ ማረጋገጣቸውን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲው ፕሮፌሰር አታላይ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጨምረውም ርዕደ መሬቱ በሬክተር ስኬል 3 ደረጃ ላይ የተመዘገበ ሲሆን መጠኑም አነስተኛ ከሚባሉት የሚመደብ በመሆኑ ሊያደርስ የሚችለው ጉዳት እንደሌለ አመልክተዋል። ኢትዮጵያን ለሁለት በሚከፍለው የስምጥ ሸለቆ ውስጥ በሚገኙ በርካታ ቦታዎች ላይና ከፍታማ ስፍራዎች ላይ እንዲህ አይነቱ ርዕደ መሬት መከሰቱ የሚጠበቅ እንደሆነ ፕሮፌሰር አታላይ ተናግረዋል። ርዕደ መሬቱ የተከሰተበት "ይህ ቦታ በስምጥ ሸለቆ ጫፍ ላይ የሚገኝ ስለሆነ የሚጠበቅ ነው። ከዚህ በፊትም በአካባቢው ተመሳሳይ ነገር ተከስቶ ያውቃል" ብለዋል። እንዲህ አይነቱ የመሬት መንቀጥቀጥ በተደጋጋሚ የሚያጋጥመው ግን አፋር ውስጥ በሚገኘው ሰመራ አካባቢ 'አይሻ ብሎክ' በሚባለው ቦታ መሆኑን ጠቁመዋል። የመሬት መንቀጥቀጦች መጠንና የሚከሰቱባቸው ጊዜያት በትክክል ቀድሞ ስለማይታወቅ በተለይ በስምጥ ሸለቆ ውስጥ ባሉ ቦታዎች የሚገነቡ ህንጻዎች አደጋውን በሚቋቋሙበት ሁኔታ በጥንቃቄ መሠራት እንዳለባቸው ፕሮፌሰር አታላይ ይመከራሉ።
news-46137254
https://www.bbc.com/amharic/news-46137254
"ለኢትዮጵያ ሳተላይት ማምጠቅ ቅንጦት አይደለም" የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር
የመሬት ምልከታ ሳተላይት (Earth Observation Satellite) የሰው ልጅ በህዋ ሳይንስ ካስመዘገባው ውጤቶች አንዱ ነው።
የመሬት ምልከታ ሳተላይት መሬትን እየቃኘ መረጃዎችን በፎቶ ይመዘግባል ሳተላይቱ ከምድር ወደ ህዋ ከተመነጠቀ በኋላ መሬትን እየቃኘ መረጃዎችን በፎቶ ይመዘግባል። እንደያስፈላጊነቱም መረጃውን ወደ ምድር ይልካል። አፍሪካ ውስጥ እስካሁን ሳተላይቱን ያመጠቁ በጣት የሚቆጠሩ ሀገሮች ናቸው። ኢትዮጵያም የአምጣቂዎቹን ቡድን ለመቀላቀል መሰናዶ የጀመረችው ከሁለት ዓመት በፊት ነበር። ሳተላይቱን ሀገር ውስጥ ለመስራት እንዲሁም ከኢትዮጵያ ለማምጠቅ የሚያስፈልገው ቴክኖሎጂና የሰው ሀይል ባለመኖሩ ወደ ሩቅ ምሥራቅ ስታማትር፤ ቻይና የገንዘብና የሙያም እገዛ ለመስጠት ተስማማች። • ኦነግ እና መንግሥትን ለማግባባት የሃገር ሽማግሌዎች እየጣሩ ነው • ትራምፕ ጠቅላይ አቃቢ ሕጉን አባረሩ ከቻይና 6 ሚሊየን ዶላር ተለግሶ ስራው ተጀመረ። ቻይናውያን ኢንጂነሮች ኢዮጵያውያንን እያሰለጠኑ ሳተላይቱ ቻይና ውስጥ እንዲሁም በከፊል ኢትዮጵያ ውስጥ ተገነባ። 70 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ሳተላይት በ2012 ዓ. ም. መባቻ ላይ ከቻይና ይመጥቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሰለሞን በላይ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሳተላይቱ በቻይና እገዛ ከምድረ ቻይና ይምጠቅ እንጂ፤ "ተቆጣጣሪዋም፣ አዛዧም ኢትዮጵያ ናት" የሚለውን አስምረውበታል። ሳተላይት ማምጠቅ ለምን አስፈለገ? የህዋ ጥናት በዓለም ላይ በፍጥነት እየዘመኑ ካሉ ዘርፎች መካከል ይጠቀሳል። የሰው ልጅ ምድር ጠባው አልያም ከምንኖርበት ዓለም ውጪ ያለውን ለማወቅ ጓጉቶ ዘወትር እየቆፈረ ነው። ከህዋ ፍተሻ በተጨማሪ ህዋን ተጠቅሞ መሬትን ማሰስ የመሬት ምልከታ ሳተላይት ተግባር ነው። ሳተላይቱ መረጃ ሲሰበስብ ይህ ቀረህ አይባለውም። ከግዙፍ ክንውኖች እስከ ጥቃቅን እንቅስቃሴዎች ይመዘግባል። እንደ ባለሙያዎች አባባል ሳተላይቱ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው። የአየር ንብረት ለውጥን ለመቆጣጠር፣ የተፈጥሮ አደጋዎች ከመድረሳቸው አስቀድሞ ለመተንበይ፣ ደህንነትን ለመጠበቅ ወዘተርፈ ይውላል። በእርግጥ ብዙዎች በታዳጊ ሀገር የህዋ ጥናት አስፈላጊነቱ ላይ ጥያቄ ቢያነሱም፤ ዶ/ር ሰለሞን "ህዋ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገሮች የመኖርና ያለመኖር ጥያቄ ነው፤ ቅንጦት አይደለም" ይላሉ። የአየር ንብረት ለውጥ የመላው ዓለም ስጋት በሆነበት ዘመን፤ አንዳች ተፈጥሯዊ አደጋ ከመድረሱ በፊት አስቀድሞ መረጃ ማግኘት ብልህነት ነው። የዛፍ ቁጥር፣ የአየር ንብረት ለውጥና ሌሎችም መረጃዎች ከተሰበቡ በኋላ እንደ ጎርፍ ያሉ አደጋዎች ከመከሰታቸው በፊት መተንበይ ይቻላል። • ግጭትን ለማባባስ ፌስቡክ ጥቅም ላይ ውሏል ተባለ • በቤታችን ውስጥ ያለ አየር የጤናችን ጠንቅ እንዳይሆን ማድረግ ያለብን ነገሮች ግብርና ቀዳሚ መተዳደሪያ በሆነባት ሀገር የቱ አካባቢ ምርታማ ነው? የአየር ንብረት ለውጥ ይኖር ይሆን? የሚሉ ጥያቄዎች በቀላሉ እንዲመለሱ የሳተላይቱ መረጃ አስፈላጊ ይሆናል። ዶ/ር ሰለሞን እንደሚሉት፤ አንድ የግብርና አካባቢን የሚያሳይ ፎቶግራፍ ስለ እርሻ መሬቱ፣ ስለ ውሀው፣ ስለ አፈሩ ዝርዘር መረጃ ይሰጣል። መረጃዎቹን በመጠቀም ምርታማ የሆኑ አካባቢዎችን መለየት፣ የምርት መጠንን በትክክል ማወቅም ይቻላል። ኢንዱስትሪዎች እየተስፋፉ በመጡባት ኢትዮጵያ፤ ፋብሪካዎች የት መገንባት አለባቸው? ለሚለው ጥያቄ የሳተላይቱ መረጃ መልስ ሊሰጥ ይችላል። ሕዝብ መቁጠር ሲያስፈልግ ከዘልማዳዊው መንገድ ሳተላይቱን መጠቀም ይመረጣል። ትክክለኛ መረጃ ከማግኘት፣ ገንዘብና የሰው ሀይል ከማዳን አንጻርም የተሻለው አማራጭ ነው። ሳተላይቱን ደህንነትን ከመጠበቅ ጋር የሚያስተሳስሩት ባለሙያዎች አሉ። ዶ/ር ሰለሞን በበኩላቸው "በመርህ ደረጃ ህዋ የሚውለው ለሰላማዊ እንቅስቃሴ ነው" ብለው፤ ለጦርነት፣ ለጦር መሳሪያ ማሳለጫነት እንደማይውል ያስረዳሉ። የ 'ኢንተርናሽናል የአውተር ስፔስ' ተቋም አባል መሆን፤ ኢትዮጵያን ከመሰል ድርጊቶች እንደሚያግዳትም አክለዋል። ኢትዮጵያ እስካሁን መረጃውን እንዴት ታገኝ ነበር? ኢትዮጵያ እነዚህን መረጃዎች ሳተላይት አምጥቀው ፎቶ ከሚያስነሱ ሀገሮች ትሸምት ነበር። ዶ/ር ሰለሞን የሚያጣቅሱት ከአራት ዓመት በፊት በተሰራ ጥናት መሰረት ኢትዮጵያ በዓመት 250 ሚሊየን ብር ታወጣለች። ጥናቱ ለደህንነት የሚወጣውንና ዩኒቨርስቲዎች የሚከፍሉትን አያካትትም። ወጪው ከዓመት ወደ ዓመት እንደሚጨምርም ያስረዳሉ። የከተሞች መስፋፋት፣ ኢንቨስትመንቶች እየጨመሩ ሲሄዱም በዛው መጠን የመረጃው አስፈላጊነት ይንራል። የሚወጣው ገንዘብም እንዲሁ። ሳተላይት ማምጠቅ እነዚህን ወጪዎች እንደሚቀንስ ይጠበቃል። አፍሪካ ውስጥ መሰል ሳተላይት ለሌላቸው ሀገሮች መረጃ መሸጥም ይቻላል። የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተሩ "ትልቅ ቢዝነስ ነው" የሚሉትም ለዚሁ ነው። "ሲያስፈልግ መረጃ እንሸጣለን። ከኛ የላቀ ቴክኖሎጂ ካላች ሀገሮች ጋር መረጃ መለዋወጥም ይቻላል፤" ኢትዮጵያ በህዋ ጥናት የት ደረሰች? ዓለም በህዋ ጥናት ቴክኖሎጂ እየመጠቀ ሄዷል። ኢትዮጵያ ከተቀረው ዓለም አንጻር ጀማሪ ናት። አፍሪካ ውስጥ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ አልጄሪያና ግብጽ ጥሩ ስም አላቸው። ኢትዮጵያ "ህዋ ለልማት" የሚል የምሥራቅ አፍሪካ ሀገሮች ትብብር ቢሮ አቋቁማ አበረታች እንቅስቃሴ ማድረጓ ተጠቃሽ ስኬት ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በ2030 ይደረስባቸዋል ብሎ ካስቀመጣው ግቦች አብዛኞቹ የህዋ ቴክኖሎጂን ያማከሉ መሆናቸው፤ ዘርፉን ችላ ማለት እንደማያዋጣ ያመላክታል። ዶ/ር ሰለሞን የመሬት ምልከታ ሳተላይት ማምጠቅ ኢትዮጵያ በህዋ ሳይንስ ዘርፍ እንቅስቃሴ እያደረገች ስለመሆኑ ለዓለም መልእክት ማስተላለፊያ መንገድ እንደሚሆን ያምናሉ። "ቴክኖሎጂው እጅግ አስፈላጊ ነው፤ ሳተላይቱን ማምጠቅ ኢትዮጵያን በህዋ ዘርፍ ጠንካራ ተወዳዳሪና እኩል ተጽእኖ ፈጣሪ ማድረግ የሚያስችል ነው" ሳተላይቱ አንዴ ከመጠቀ በኋላ ከሶስት እስከ አራት ዓመት ያገለግላል። ከዛ በላይ ሊቆይም ይችላል። በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት፤ የመሬት ምልከታ ሳተላይቶች ህዋ ላይ እንዲቆዩ የሚፈቀደው ለስምንት አመት ነው። ኢትዮጵያ ከምታመጥቀው ሳተላይት፤ በየአራት ቀኑ የመላው ኢትዮጵያ መረጃ የዓለም ደግሞ በ55 ቀን ይገኛል። በህዋ ምርምር ዘርፍ ቅርብ ጊዜ እውን ይሆናሉ ተብለው ከሚጠበቁ ፕሮጀክቶች ውስጥ ላሊበላ ላይ ይገነባል የተባለው ዓለም አቀፍ ኦፕቲክ ቴሌስኮፕ አንዱ ነው።
news-44831310
https://www.bbc.com/amharic/news-44831310
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ የኢትዯጵያና የኤርትራ ሕዝቦች አንድ ናቸው አሉ
የኢትዮጵያና የኤርትራን ሕዝብ ከዚህ በኋላ ሁለት ሕዝቦች ናቸው የሚል ካለ እውነቱን ያለተረዳ ነው ሲሉ በኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን ዛሬ የጀመሩት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ተናገሩ።
በብሔራዊ ቤተ-መንግሥት በተደረገ የምሳ ሥነ-ሥርዓት ላይ በትግርኛ አጭር ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ እንደተናገሩት የኤርትራ ሕዝብ ለሠላም ያለውን ፍቅርና ፍላጎት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ሲመጣ ደስታውን ለዓለም ለማሳየት ስሜቱን ከገለፀበት በበለጠ ሁኔታ ዛሬ መግለፅ አልችልም ብለዋል። በሁለቱ ሃገራት በኩል እየተደረገ ያለውን የሠላም ሂደት "ታሪክ" ነው ሲሉ፤ ይህም እንዲሳካ እንደሚሰሩና እንደሚጥሩ ተናግረዋል። • የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አዲስ አበባ ገቡ • ስለ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ምን ያህል ያውቃሉ? "ከዚህ በኋላም የኢትዮጵያና የኤርትራ ሕዝቦች ሁለት ሕዝቦች ናቸው ብሎ የሚያስብ እውነታውን ያልተረዳ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከሃያ ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ገብተው ጉብኝታቸውን ጀምረዋል። • የኤርትራ ኤምባሲ የማደስ ሥራ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ ተገለፀ • የኢትዮጵያና ኤርትራን የአብሮነት እርምጃ ምን ይፈትነዋል?
news-51924424
https://www.bbc.com/amharic/news-51924424
የአውስትራሊያ ተመራማሪዎች ሰውነታችን የኮሮናቫይረስን ሊከላከል የሚችልበትን መንገድ መለየት ቻሉ
የአውስትራሊያ ሳይንቲስቶች የሰውነታችን በሽታን የመከላከል ሥርዓት እንዴት አድርጎ ኮቪድ-19 [ኮሮናቫይረስን] ሊዋጋው እንደሚችል ለመለየት ችለዋል።
በሽታን ተከላካይ ህዋሳት መታየት ከጀመሩ በኋላ የበሽተኛው ሳንባ ሲያገግም የሚያሳይ ራጅ 'ኔቸር' በተሰኘው የህክምና መጽሔት ላይ ዛሬ በወጣው የምርምር ግኝት መሰረት፤ ሰዎች ከኮሮናቫይረስ እየዳኑ ያለው ከጉንፋን በሚድኑበት ሁኔታ ጋር የሚመሳሰል መሆኑን አረጋግጠዋል። ባለሙያዎቹ እንዳሉት በዚህ ወቅት የትኞቹ የሰውነት በሽታን መከላከያ ህዋሳት እንደሚታዩ መለየት በቀጣይ ክትባት ለመስራት ያግዛል። • አሜሪካ የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ ጀመረች • ሞሮኮ እንደ ፍልውሃ ያሉ የጋራ መታጠቢያ አገልግሎቶችን አገደች • መዓዛ መላኩ፤ መስማት ለተሳናቸው ዜጎች ስለኮሮናቫይረስ መረጃ የምታቀብለዋ በጎ ፍቃደኛ በዓለም ዙሪያ እስካሁን ከ160 ሺህ በላይ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች ሲኖሩ ከ6500 በላይ ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን በወረርሽኙ አጥተዋል። "በምርምር ለማወቅ የተቻለው ጠቃሚ ነገር ነው፤ ምክንያቱም ይህ የሰውነት የመከላከያ ሥርዓታትን በምን መልኩ የኮሮናቫይረስን እንደሚዋጋ በመረዳት በኩል የመጀመሪያው በመሆኑ ነው" ሲሉ የምርምሩ አካል የሆኑት ካትሪን ኬደዜርስካ ተናግረዋል። ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ አንጻር ተመራማሪዎች የደረሱበት ይህ ግኝት "ፈር ቀዳጅ" እንደሆነ ተነግሮለታል። የሜልበርን ፒተር ዶሬቲ የበሽታዎችና በሽታን የመከላከል ተቋም ውስጥ የሚገኙት ጥናቱን ያደረጉት ባለሙያዎች ባገኙት ውጤት አድናቆትን አግኝተዋል። አስካሁን በርካታ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች የዳኑ ሲሆን፤ ይህም የሰው ልጅ በሽታን የመከላከል ሥርዓት በተሳካ ሁኔታ ቫይረሱን ተቋቁሞ ማሸነፍ ይችላል ማለት ነውም ተብሏል። በዚህ የምርምር ግኝትም ለመጀመሪያ ጊዜ ኮቪድ-19ን ሊከላከሉ የሚችሉ አራት አይነት የተፈጥሮ በሽታን መከላከል የሚችሉ ህዋሳትን ለይተው አግኝተዋል። ህዋሳቱ ቀደም ያለ ሌላ የጤና ችግር የሌለባቸውና ከቀላል እስከ መካከለኛ ሁኔታ ውስጥ ያሉ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን በመከታተል መለየት እንደተቻለም ታውቋል። ከቻይናዋ ዉሃን ከተማ በበሽታው ተይዘው አውስትራሊያ ወደሚገኝ ሆስፒታል የመጡ የ47 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሴት በ14 ቀናት ውስጥ ከቫይረሱ መዳናቸው ተገልጿል። የጥናት ቡድኑም የእኚህን ሴት "አጠቃላይ በሽታን የመከላከል አቅም" መፈተሹን ፕሮፌሰር ካትሪን ኬደዜርስካ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ታማሚዋ በጤናቸው ላይ መሻሻል ከመታየቱ ሦስት ቀናት ቀደም ብሎ በደማቸው ውስጥ የተለየ ህዋስ እንደታየ ባለሙያዎቹ ገልጸዋል። ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ ህዋስ በኢንፍሉዌንዛ በተያዙ ሰዎች ላይ ከበሽታው ከመዳናቸው ቀደም ብሎ መታየቱን ፕሮፌሰሯ ጠቅሰዋል። የአውስትራሊያ ጤና ሚኒስትር ግሬግ ሃንት ስለአዲሱ ግኝት እንደተናገሩት፤ ወረርሽኙን ለመከላከልና በበሽታው የተያዙ ሰዎችን ለማከም የሚያስችል መፍትሔን በቶሎ ለማግኘት ይረዳል ሲሉ ተስፋቸውን ገልጸዋል።
news-44977468
https://www.bbc.com/amharic/news-44977468
የኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሞትን ተከትሎ በጎንደር ረብሻ ተከሰተ
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ የኢንጂነር ስመኘው በቀለን ህልፈት ተከትሎ ዛሬ በጎንደር ከተማ ረብሻ እንደነበር የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ተቀባ ተባበል ለቢቢሲ ገለጹ።
አለመረጋገቱ "ለኢንጂነሩ ሞት ተጠያቂ የሆኑ ሰዎች ለፍርድ ይቅረቡ" በሚል የተቀሰቀሰ ሲሆን ትላንት አንድ የሠላም ባስ አውቶብስ መቃጠሉን ከንቲባው ገልጸዋል። ዛሬ ረፋድ ላይ የተጀመረው ተቃውሞና ግርግር ለሰዓታት ዘልቋል። ሰልፉን ባካሄዱ ሰዎች ላይም ፖሊስ አስለቃሽ ጭስ መተኮሱም ተነግሯል። ቢሆንም ግን በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ባይኖርም ሰልፉ በተካሄደበት አካባቢ አንድ ሱቅ ላይ በድንጋይ ጉዳት ደርሷል። •ስለኢንጂነር ስመኘው አሟሟት እስካሁን ምን እናውቃለን? •"የእሱ አባት ኩራዝ የላቸውም፤ እሱ ግን ኢትዮጵያን ሊያበራ ነው የሞተው" •ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሕይወታቸው ያለፈው በጥይት ተመተው ነው፡ ፌደራል ፖሊስ የአሜሪካ ኤምባሲም ዜጎቹ ወደ ጎንደር እንዳይሄዱ የጉዞ እገዳ ማስጠንቀቂያ አስተላልፏል። ከንቲባው በበኩላቸው "ያልተፈቀደና ባለቤት የሌለው" ካሉት የዛሬው ሰልፍ ጀርባ ያሉት ሰዎች እንዳልታወቁ ገልጸውልናል። "ትላንት የነበረው ሁኔታ ኢንጂነር ስመኘው እዚሁ አካባቢ ተወልዶ ከማደጉ ኣንጻር በመሞቱ ሀዘን ለመግለጽ እንጂ ሌላ አጀንዳ አልነበረውም። ሆኖም አጋጣሚውን በመጠቀም ጎንደርን ለመበጥበጥ የሚፈልጉ ሊጠቀሙበት ሞክረዋል" ሲሉ ከንቲባው ተናግረዋል። ማህበራዊ ሚዲያ ላይ አለመረጋጋቱን ተከትሎ ሰዎች እንደተጎዱ፣ ንብረትም እንደወደመ እንዲሁም የእለት ከእለት እንቅስቃሴ መስተጓጎሉን ብዙዎች እየገለጹ ይገኛሉ። የተጎዳ ሰው ስለመኖሩና የንብረት ውድመት ስለመድረሱ ከንቲባውን ስንጠይቃቸው የተጎዳ ሰው እንደሌለና ከተሰበረው ሱቅ ውጪ ሌላ ንብረት ላይ ጉዳት እንዳልደረሰ ገልጸውልናል። ከንቲባው ከሰዓት በኋላ ነገሮች መረጋጋታቸውን ገልፀው ረብሻው የከተማዋ ኢኮኖሚ ላይ ተጽእኖ እንደማያሳድርም አክለዋል። ትላንት ከሰዓት የኢንጅነሩን አባት፣ እህት፣ የአክስት ልጆችና ሌሎችም ቤተሰቦች በመቀላቀል ሀዘናቸውን የገለጹ የከተማዋ ነዋሪዎች ነበሩ። ከከተማዋ ነዋሪዎች መካከልም ወደ አዲስ አበባ የሚያቀኑ የኢንጂነሩን ቤተሰቦቹን በማጀብ ሀዘናቸውን ያስተጋቡም ነበሩ። ትላንት አመሻሽ ላይ በዛሬው እለት በጎንደር ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ጥሪ የሚያቀርብ በራሪ ወረቀት የተበተነሲሆን፤ ከንቲባው እንደሚሉት በራሪ ወረቀቱን ያሰራጩ ሰዎች ማንነት እስካሁን አልታወቀም። ከንቲባው ሰልፉን የጠሩትንና ያካሄዱትን ሰዎች "ጎንደርን ወደቀደመው አለመረጋጋት ለመክተት ሞክረዋል" ቢሉም ለኢንጂነር ስመኘው ህልፈት ተጠያቂ የሆኑ ሰዎች ለፍርድ ይቅረቡ የሚል መልዕክትን የያዘ እንደሆነ ተገልጿል። የአሜሪካ ኤምባሲን ማስጠንቀቂያ በተመለከተ ዛሬ ጠዋት የኤምባሲው መግለጫ ቢደርሳቸውም የከተማዋን መረጋጋት በማየት እገዳው እንደሚነሳ ተስፋ እንደሚያደርጉ አቶ ተቀባ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም በተፈጠረው አለመረጋጋት የከተማዋ የቱሪስተ ፍሰት ማሽቆልቆሉ ይታወሳል።
48406923
https://www.bbc.com/amharic/48406923
ሀርቪ ዋንስታይን 44 ሚሊየን ዶላር ካሳ ሊከፍል ነው
ሀርቪ ዋንስታይን በወሲባዊ ጥቃት ለከሰሱት ሴቶች 44 ሚሊየን ዶላር ካሳ ለመክፈል መስማማቱን የአሜሪካ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል። ፊልም ፕሮዲውሰሩ ሀርቪ በርካታ የፊልም ባለሙያ ሴቶች ላይ ወሲባዊ ጥቃት አድርሷል በሚል መከሰሱ ይታወሳል።
ገንዘቡን ክስ ያቀረቡት ሴቶች እንደሚካፈሉት የተገለጸ ሲሆን፤ የሴቶቹ ማንነት እስካሁን ይፋ አልተደረገም። ዋልስትሪት ጆርናል እንደዘገበው፤ ካሳው ሀርቪ በአሜሪካ፣ እንግሊዝና ካናዳ ለቀረበበት ክስ ነው። ሀርቪ የፊታችን ሰኔ ኒው ዮርክ የሚገኝ ፍርድ ቤት የሚቀርብ ሲሆን፤ ከቀረቡበት ክሶች መካከል አስገድዶ መድፈር ይገኝበታል። የፊልም ፕሮዲውሰሩ 75 ሴቶች ላይ ወሲባዊ ጥቃት በማድረስ ቢከሰስም መካዱ ይታወሳል። ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ የእድሜ ልክ እስራት ይጠብቀዋል። በሀርቪ ወሲባዊ ጥቃት እንደደረሰባቸው በይፋ ከተናገሩ ተዋንያን አንዷ አሽሊ ጁድ በበኩሏ ሀርቪን በግሏ ፍርድ ቤት እንደምታቆመው በትዊተር ገጿ አሳውቃለች። 'ሼክስፒር ኢን ላቭ'፣ 'ዘ ኪንግስ ስፒች'፣ 'ዘ አርቲስት' እና ሌሎችም ስኬታማ ፊልሞች ፕሮዲውስ ያደረገው የ67 ዓመቱ ሀርቪ፤ በሠራቸው ፊልሞች በአጠቃላይ 81 የኦስር ሽልማት አግኝቷል። • ቢል ኮዝቢና ፖላንስኪ ከኦስካር አካዳሚ ተባረሩ እንደ ጎርጎራሳውያኑ አቆጣጠር በ1970 'ሚራማክስ ኢንተርቴይመንትን' አቋቁሞ ነበር። 2005 ላይ ከወንድሙ ቦብ ዋንስታይን ጋር 'ዋንስታይን ሶኦ' መስርቷል። 2017 ላይ ኳርትዝ ባቀረበው ዘገባ ሀርቪ በሆሊውድ ስሙ ከመግነኑ የተነሳ፤ የኦስካር ሽልማት ሲይገኙ ፈጣሪን ከሚያመሰግኑ የፊልም ባለሙያዎች ይልቅ ሀርቪን የሚያመሰግኑት ባለሙያዎች ቁጥር ይበልጥ ነበር። ሆኖም በርካታ የሆሊውድ የፊልም ባለሙያ ሴቶች ሀርቪ ወሲባዊ ጥቃት እንዳደረሰባቸው ሲናገሩ ክብርና ዝናው ተገፏል። ኒው ዮርክ ታይምስ 2017 ላይ ሀርቪ ወሲባዊ ጥቃት ስላደረሰባቸው ሴቶች ዘገባ አቅርቦ ነበር። አሽሊ ጁድና ሮዝ መግዋን ሀርቪ ያደረሰባቸውን ጥቃት በይፋ ከተናገሩ ግንባር ቀደም ሴቶች መካከል ይጠቀሳሉ። ከቀረቡበት ክሶች መካከል ሴቶች እርቃኑን እንዲያዩትና ማሳጅ እንዲያደርጉት ማስገደድ ይገኝበታል። ለሦስት አስርት ዓመታት ሴቶች ላይ ጥቃት ማድረሱን የካደው ሀርቪ፤ "ያሳዘንኳቸውን ሰዎች ይቅርታ እጠይቃለሁ" ማለቱ ይታወሳል። ሀርቪ ላይ የቀረበው ክስ 'ሚቱ' ንቅናቄ ለመነሳቱ ምክንያት ሲሆን፤ በርካታ ሴቶች በተለያየ ሙያ ላይ የተሰማሩና ወሲባዊ ጥቃት ያደረሱባችን ወንዶች በይፋ ለመክሰስ ድፍረት ያገኙበት እንቅስቃሴ ነው።
news-46875230
https://www.bbc.com/amharic/news-46875230
ለናይሮቢው የሽብር ጥቃት አልሸባብ ኃላፊነቱን ወሰደ
በኬንያዋ መዲና ናይሮቢ ከሚገኙት ቅንጡ ሆቴሎች አንዱ በሆነው ዱሲት2ናይሮቢ የሽብር ጥቃት እየተፈጸመ ነው።
ለሽብር ጥቃቱም አልሸባብ ኃላፊነቱን ወስዷል። የአልሸባብ ቃል አቀባይ በናይሮቢ ለደረሰው ጥቃት አልሸባብ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ ለቢቢሲ ሶማልኛ በስልክ ተናግሯል። የአልሸባብ ቃል አቃባይ ጨምሮም ''በናይሮቢ ኦፕሬሽን እያካሄድን ነው'' ብሏል። ከሁለት ከፍተኛ ፍንዳታ በኋላ ለተወሰኑ ደቂቃዎች የተኩስ ድምጽ ሳይቋረጥ ተሰምቶ ነበር። የአይን እማኞች እንደሚሉት አራት የታጠቁ ወንዶች ወደ ሆቴሉ ቅጥር ጊቢ ሲገቡ አይተዋል። ከፍንዳታው በኋላ የተኩስ ድምፅም የተሰማ ሲሆን አንድ ግለሰብም በጥይት ቆስሎ ሰዎች ተሸክመውት ሲወጡ ታይቷል። በጥይት ተመተው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በህንጻው አቅራቢያ ህክማና እየተደረገላቸው ነው። በስፍራው የነበረው ሮበርት ሉታ የተባለ የፌስቡክ ተጠቃሚ የነበረውን ሁነት እንደሚከተለው በፌስቡክ አማካኝነት በቀጥታ አሰራጭቶት ነበር። በዚህ በቀጥታ በተሰራጨው ምስል ላይ ሰዎች ህይወታቸውን ለመታደግ ሲሯሯጡ፣ ከፎቅ ላይ ሲዘሉ እና በጥይት የተመቱ ሰዎችን ምስል ያሳያል። • በምዕራብ ኦሮሚያ ምን ተከሰተ? • ከቤተሰቦቿ አምልጣ ካናዳ የገባችው የሳዑዲዋ ወጣት፡ 'ምንም የሚጎልብኝ የለም' ''ጥቃት እየተፈጸመብን ነው'' በማለት በዱሲት2ናይሮቢ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኝ አንድ ሰው ለሬውተርስ የዜና አገልግሎት ተናግሯል። ሌላው የትዊተር ተጠቃሚ ሮን ንጌኖ የተሰኘው ፍንዳታው በተሰማበት አካባቢ በነበረው ሆቴል ውስጥ በመታጠቢያ ቤት መደበቁንና ጥቃት እየተፈፀመባቸው እንደሆነ ገልጿል። ከባድ ፍንዳታ ከመስማቱም በተጨማሪ ተኩስ መሰማቱንም አክሎ ከተናገረ በኋላ "ዛሬ ከሞትኩኝ ፈጣሪዬን እንደምወድና ለቤተሰቤ እንደምወዳቸው ንገሩልኝ" ብሎ ስማቸውን ዘርዝሯል። ዱሲት2ናይሮቢ የሆቴል አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ ቢሮዎች አሉት። የኬንያ የፖሊስ አገልግሎት ቢሮ ሆቴሉ በሚገኘበት ስፍራ ጥቃት መኖሩን ገልጾ ስፍራው መከለሉን እና አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንግዶችን እንዲጠቀሙ በመግለጽ ዝርዝር መረጃዎችን ይዞ እንደሚቀርብ በትዊተር ገጹ አስታውቋል። ጥቃቱ የተፈጸመው ዌስትላንድስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው
54869298
https://www.bbc.com/amharic/54869298
ትራምፕ ምርጫው ተጭበርብሯል የሚሉት ምኑን ነው?
ዲሞክራቱ ጆ ባይደን የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫን ማሸነፋቸው እሙን ነው።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግን በአንዳንድ ቁልፍ ግዛቶች ላይ በምርጫ ውጤት ላይ ሕጋዊ ጥያቄዎችን አነሳለሁ እያሉ ነው። የትራምፕ ጠበቃ ሩዲ ጁሊያኒ ለፎክስ ኒውስ ሲናገሩ ትራምፕ ሽንፈቱን ቢቀበሉ ስህተት ነው ብለዋል። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ፤ "ይህ ምርጫ ቢያንስ ሦስት ወይም አራት እንደውም 10 በሚሆኑ ግዛቶች ስለመሰረቁ ማስረጃ አለ። " ጠበቃው ጨምረውም የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን ምርጫው ስለመጭበርበሩ የሚያረጋግጡ "ጠንካራ ማስረጃዎችን" ይዞ ይቀርባል። የትራምፕ ጠበቆች በቁልፍ ግዛቶች የሚያነሷቸው ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው። ፔንሲልቬኒያ ጠበቃው ሩዲ ጁሊያኒ በፔንሲልቬኒያ የምርጫ ታዛቢዎች ወደ ምርጫ ጣቢያዎች መሄድ አለመቻላቸውን በማስመልከት ክስ ይመሰረታል ብለዋል። የምርጫ ታዛቢዎች ከምርጫ ቀን ጀምሮ ፍቃድ እስካገኙ ድረስ የምርጫ ቆጠራውን የመታዘብ መብት አላቸው። በዘንድሮ ምርጫ ከምርጫ ቀን በፊት የተጣሉ ገደቦች ነበሩ። ለዚህም ከምክንያቶቹ መካከል አንዱ ኮሮናቫይረስ ነው። በፊላዴልፊያ በሚገኝ የምርጫ ጣቢያ ላይ እስከ 6 ሜትር ርቀት እንዲኖር ተወስኖ ነበር። የትራምፕ ጠበቃ ምንም እንኳ ፍርድ ቤት የሪፓብሊካን ታዛቢዎች ቆጠራውን ተጠግተው እንዲታዘቡ ቢፈቅድም ይህ ሳይሆን ቀርቷል ይላሉ። የግዛቲቱ ምርጫ አስፈጻሚዎች ግን ስራችንን ያከናወነው ሕግን ተከትለን ነው ይላሉ። የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን የሚያነሳው ሌላ ጉዳይ ዘግይተው በፖስታ የተላኩ ድምጾች ለምን ተቆጠሩ የሚለው ይገኝበታል። በምርጫው ቀን ተልከው ምርጫው ከተከናወን ከሶስት ቀናት በኋላ በቆጠራ ጣቢያ የደረሱ ድምጾች መቆጠር የለባቸውም ይላሉ የትራምፕ ጠበቆች። ሚሺጋን ከአራት ዓመት በፊት በነበረው ምርጫ ትራምፕ በሚሺጋን ግዛት ማሸነፍ ችለው ነበር። ባይደን በዚህ ግዛት እንደሚያሸንፉ ተገምቷል። የትራምፕ የቅስቀሳ ቡድን በምርጫው ዕለት የሪፓብሊካን ምርጫ ታዛቢዎች ወደ ድምጽ መቁጠሪያ ጣቢያዎችን ገብተው መታዘብ አልቻሉም በሚል ምክንያት በሚሺጋን የድምጽ ቆጠራው እንዲቆም ያቀረቡት ጥያቄ በፍርድ ቤት ውድቅ ተደርጎባቸዋል። የፍርድ ቤቱ ዳኛ የትራምፕ ጠበቃቆች ጥያቄን ውድቅ ያደረጉት በቂ ማስረጃ መቅረብ አልቻለም በሚል ነው። ዊስኮንሰን የትራምፕ የቅስቀሳ ቡድን በዊስኮንሰን ግዛት ዳግም ቆጠራ እንዲካሄድ እጠይቃለሁ ብሏል። በዊስኮንሰን ግዛት ድምጽ ተቆጥሮ አልተጠናቀቀም በዚህም የጠበቆቹ ጥያቄ መቼ ምላሽ ሊያገኝ እንደሚችል ግልጽ አይደለም። በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር የሆኑት ሪቻርድ ብሪፎልት እአአ 2016 ተካሂዶ በነበረው ምርጫ በዊስኮንሰን ግዛት ምርጫው ዳግም ተካሂዶ "በመቶዎች የሚቆጠር የድምጽ ለውጥ ታይቷል" ይላሉ። ነቫዳ የነቫዳ ሪፓብሊካን ፓርቲ "ከዚህ ቀደም የኔቫዳ ነዋሪ የነበሩ እና አሁን በሌላ ስፍራ የሚኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የምርጫ ሕጉን ተላለፈው ድምጽ እንዲሰጡ ተደርጓል" ብሏል። የፕሬዝደንት ትራምፕ ጠበቆች ነዋሪነታቸው ኔቫዳ ግዛት ሳይሆን በነቫዳ ድምጽ የሰጡ የሰዎች ስም ዝርዝርን ይፋ አድርገዋል። ምርጫ አስፈጻሚዎች ግን የተጣሰ የምርጫ ሕግ የለም እያሉ ነው። ጆርጂያ በጆርጂያዋ ቻታም ካውንቲ የድምጽ ቆጠራው እንዲቆም ፍርድ ቤት እንዲያዝ የትራምፕ ጠበቆች ጠይቀው ነበር። ሪፓብሊካኖች ታዛቢዎቻችን ድምጽ ሳይቆጠር ገሸሽ እንዲደረግ ሲያደርጉ ተመልከተዋል ይላሉ። ፍርድ ቤት ግን ለዚህ ማስረጃ አልቀረበም በሚል ቆጠራው እንዲቀጥል ወስኗል። አሪዞና የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን አባላት ቅዳሜ ዕለት በሕጋዊ መንግድ ድምጽ ለመስጠት የተመዘገቡ ድምጽ ሰጪዎች ድምጻቸው እንዳይቆጠር ተደርጓል በማለት በአሪዞና ይግባኝ ብለዋል። ይህ ይግባኝ ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየተመረመረ ይገኛል። ጉዳዩ ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያመራ ይሆን? ፕሬዝደንት ትራምፕ በምርጫ ዕለት ምንም አይነት ማስረጃ ሳያቀርቡ ምርጫው ተጭበርብሯል ካሉ በኋላ ጉዳዩን ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንደሚወስዱት ተናግረው ነበር። ትራምፕ ጉዳዩን ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከመውሰዳቸው በፊት ይግባኝ ያሉባቸው ጉዳዮች በየግዛቱ በሚገኙ ፍርድ ቤቶች መታየት ይኖርባቸዋል። የግዛት ፍርድ ቤቶች ምርጫው ዳግም እንዲቆጠር የሚያዙ ከሆነ ብቻ ነው ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ጣልቃ እንዲገባ ሊጠየቅ የሚችለው። የሕግ መምህሩ ብሪፎልት ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የምርጫውን ጉዳይ የመመልከቱ ዕድል በጣም አነስተኛ ነው ይላሉ።
43081912
https://www.bbc.com/amharic/43081912
ሲሪል ራማፎሳ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሆኑ
በኤኤንሲ የበላይነት በሚመራው ፓርላመንትም ብቸኛ እጩ አድርጎ ያቀረባቸው ሲሆን ዜናው ሲሰማም የፓርላመንት አባላቶቹ በዘፈን ደስታቸውን ገልፀዋል።
የ65 ዓመት ዕድሜ ባለፀጋው ራማፎሳም በመጀመሪያው ቀን የተናገሩት በዙማ አስተዳደር ወቅት የተንሰራፋውን ሙስና እንደሚያጠፉ ነው። ፓርቲያቸው ኤኤንሲ ዙማን ከሥልጣን እንዲወርዱ ካለበለዚያ እንደሚያወርዷቸው ማስጠንቀቃቸው የሚታወስ ነው። በብዙ የሙስና ውንጀላዎች ተዘፍቀዋል ቢባሉም ዙማ ምንም ስህተት እንዳልሰሩ ይናገራሉ። አንደኛው የቀረበባቸውም ክስ ከባለፀጋዎቹ የጉፕታ ቤተሰብ ጋር አሻጥር በመስራት በሀገሪቱ ፖሊሲ ተፅእኖ እንዲፈጥሩ ፈቅደውላቸዋል የሚል ነው። ከሶስቱ የጉፕታ ወንድማማቾች በአንደኛው አጄይ ጉፕታ ላይ የእስር እዝም ትናንት እንደወጣም ባለስልጣናት ተናግረዋል። ሮብ ዕለትም ቤታቸው በፖሊስ ተከቦ እንደነበር ተዘግቧል። ቤተሰቡ ከምንም አይነት የሙስና ጉዳዮች ነፃ ነን በማለት ክደዋል። የመጀመሪያ ቀን ንግግራቸው በሙስና ላይ ያተኮረው ራማፎሳ አርብ እለት ለህዝቡ ንግግር ያደርጋሉ ተብለው ይጠበቃሉ። ይህ የዘገየበት ምክንያትም ዙማ ከስልጣን አልወርድም እምቢተኝነታቸው ስለፀኑ ነው። አንደኛው ተቃዋሚ ፓርቲ ለኢኮኖሚ ነፃነት ታጋዮች (ኢኮኖሚክ ፍሪደም ፋይተር) ፓርላማ የነበረውን ክርክር ረግጠው ወጥተዋል። ኤኤንሲ አዲስ ፕሬዚዳንት ከመምረጥ አዲስ ምርጫ ያስፈልጋልም ብለዋል። በመጨረሻም ህልማቸው ተሳካ ከአፓርታይድ መገርሰስና ስልጣኑን ኤኤንሲ ከተቆጣጠረበት ጀምሮ ራማፎሳ ፕሬዚዳንት ለመሆን ይፈልጉ ነበር። ኔልሰን ማንዴላ የሳቸው ስልጣንን ተተኪ አድርገውም ስላልመረጧቸው የፖለቲካውን አለም ትትው ወደ ቢዝነሱ ተቀላቀሉ። በመጨረሻም ራማፎሳ ህልማቸውን አሳኩ። ቅድሚያ የሚሰጡትም የተሟሟተውን የደቡብ አፍሪካን ኢኮኖሚ ማነቃቃት ነው። ቀላል እንደመይሆንም እየተነገረ ሲሆን ምክንያቱም የስራ አጥነት ቂጥር 30% ሲሆን ለወጣቱም 40% ነው። ራማፎሳ ስልጣን ከያዙ በኋላ በደቡብ አፍሪካ አዲስ ተስፋ እያቆጠቆጠ ይመስላል። ገበያውም በዙማ መልቀቅ የተደሰተ ይመስላል። የደቡብ አፍሪካ የገንዘብ ኖታ በሶስት አመት ውስጥ ከነበረው ጠንካራ ቦታም ተመልሷል። አንዳንዶች ግን አሁን ቢሆን ይናፍቋቸዋል ምክንያቱም ይላል የቢቢሲው ሚልተን ኢንኮሲ ለከፍተኛ ትምህርት ክፍያን ማስወገዳቸው አንዱ ውጤታቸው ስለሆነ ነው። በዘረኛው የነጩ አፓርታይድ አገዛዝ ወቅት በኤኤንሲ የወታደራዊ ክንፍ የነበሩት ዙማ በተለያዩ የስልጣን እርከኖችም በማለፍ ፕሬዚዳንት ሆነዋል።
50528148
https://www.bbc.com/amharic/50528148
ዴሞክራቲክ ኮንጎ የተዘረፉ ቅርሶቿ እንደሚመለሱ ተስፋ ሰንቃለች
የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዘዳንት፤ በኪንሻሳ አዲስ ብሔራዊ ሙዝየም ይመርቃሉ።
በብሔራዊ ሙዝየሙ የሚገኝ ከእንጨት የተሠራ ጭንብል በደቡብ ኮርያ ዓለም አቀፍ ድጋፍ ተቋም እርዳታ የተገነባውን ሙዝየም ለማጠናቀቅ ሦስት ዓመት ወስዷል። ባህልና የእለት ከእለት ሕይወትን የሚያሳዩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቅርሶችም በሙዝየሙ ይገኛሉ። • ለአደጋ የተጋለጡ ሦስት የትግራይ ቅርሶች • ከኢትዯጵያ የተዘረፉ ቅርሶች በውሰት ሊመለሱ ነው • የተዘረፉ ቅርሶች በውሰት መመለሳቸውን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ምላሽ ምንድን ነው? የመንግሥት ኃላፊዎች እንዳሉት፤ በቅኝ ግዛት ዘመን ከአገሪቱ የተዘረፉ ቅርሶች ተመልሰው የሙዝየሙ ስብስብ ይሰፋል የሚል ተስፋ አላቸው። በተለይም አምና በድጋሚ በተከፈተው የቤልጂየሙ 'ሮያል ሙዝየም ፎር ሴንትራል አፍሪካ' ውስጥ የሚገኙ ቅርሶች በዋነኛነት ተጠቅሰዋል። የቀድሞው የዴሞክራቲክ ኮንጎ መሪ ጆሴፍ ካቢላ፤ በቤልጂየሙ ተቋም ያሉ ቅርሶች እንዲመለሱ እንደሚጠይቁ መናገራቸው ይታወሳል። ሆኖም ይፋዊ ጥያቄ አልቀረበም። አገሪቱ ነጻነቷን የተቀዳጀችው እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ1960 ነበር። ከበርካታ የአፍሪካ አገሮች በቅኝ ገዢዎች የተዘረፉ ቅርሶች ይመለሱ የሚለው ጉዳይ መነጋገሪያ አጀንዳ ከሆነ ሰነባብቷል። 2018 ላይ ፈረንሳይ በሺዎች የሚቆጠሩ ቅርሶች ወደ አህጉሪቱ እንዲመለሱ ወስናም ነበር። በሙዝየሙ የተለያዩ ቅርሶች ይገኛሉ ምዕራባውያን፤ አፍሪካ ውስጥ "የቅርሶች ደህንነት ተጠብቆ የሚቀመጥበት ቦታ እና ፖለቲካዊ መረጋጋት የለም" በሚል ቅርሶችን ለመመለስ ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። በዴሞክራቲክ ኮንጎ የተሠራው አዲስ ብሔራዊ ሙዝየም ቀድሞ የነበሩትን ይተካል። የቀድሞዎቹ ሙዝየሞች ለቅርሶች ምቹ አይደለም ይባል ነበር። በአዲሱ ሙዝየም በሁለት ፎቅ፤ የተለያዩ ቁሳ ቁሶች ተቀምጠዋል። በአገሪቱ በሚገኙት ከመቶ በላይ ብሔሮች የተሠሩ አነስተኛ ቅርጾችና ጭንብሎችን መጥቀስ ይቻላል። አይሜ ምፔኔ የተባሉ የሥነ ጥበብ መምህር ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ የሙዝየሙ ስብስብ ለአገሪቱ ዘመነኛ ሥነ ጥበበኞችን እንደሚያነሳሳ ተስፋ ያደርጋሉ።
45962289
https://www.bbc.com/amharic/45962289
በፈረንሳይ ልማደኛው ሌባ የአንበሳ ደቦል ሰርቆ ተያዘ
የ30 ዓመቱ ፈረንሳዊ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ የአንበሳ ደቦል ደብቆ በመገኘቱ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ባለሥልጣናቱ የዱር እንሰሳትን እንደለማዳ እንሰሳ ቤት ውስጥ ማቆየት ወንጀል ስለመሆኑ ሲናገሩ ነበር እንደ ፈረንሳይ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ ከሆነ ፖሊስ መረጃው የደረሰው ግለሰቡ የስድስት ሳምንት ዕድሜ ያላትን ደቦል በ 10 ሺህ ዮሮ ለመሸጥ ሲያስማማ ነው። ማክሰኞ ዕለት ጎረቤቶቹ ቤት ቁምሳጥን ውስጥ የደበቃት ሲሆን ደቦሏ ግን የሕፃን አልጋ ላይ ተገኝታለች። • በአሜሪካ አንበሳዋ የልጆቿን አባት ገደለች • ከአዕዋፍ እስከ አንበሳ ያሉ እንስሳት በግለሰቦች እጅ ለስቃይና ለጉዳት እየተዳረጉ ነው። • ለህገወጥ አዳኞች ፈተና የሆኑት ውሾች ደቦሏ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደምትገኝ የተነገረ ሲሆን ለዱር አራዊት ባለሥልጣናትም ተላልፋ ተሰጥታለች። እንደ የፈረንሳይ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ ወንጀለኛው ልማደኛ ሌባ ነበር ተብሏል። ፖሊስ በሕገወጥ መልኩ በሰዎች መኖሪያ ውስጥ የዱር እንስሳትን ሲያገኝ የመጀመሪያ ጊዜው አይደለም። በ2017 አንድ ግለሰብ በምግብ እጥረት የተጎዳ የአንበሳ ደቦል ሰው በማይኖርበት ሕንፃ ውስጥ ደብቆ መገኘቱ ይታወቃል። ወንጀለኛው የተደረሰበትም ከደቦሏ ጋር ምሥለ-ራስ ፎቶ (ሰልፊ) ተነስቶ ፎቶውን ከተሠራጨ በኋላ ነው። የኋላ ኋላ ደቦሉ ወደ ደቡብ አፍሪካ የእንስሳት ማቆያ ተወስዷል። በዚህ ወርም ኔዘርላንዳዊ መንገደኛ አንድ ደቦል በመንገድ ላይ ተጥሎ አግኝቷል።
news-46218036
https://www.bbc.com/amharic/news-46218036
ማላዊቷ ነርስ በማዋለጃ ክፍል 'ሰልፊ' በመነሳቷ ከስራ ታገደች
የማላዊ ዜግነት ያላት ነርስ በማዋለጃ ክፍል ውስጥ 'ሰልፊ' ተነስታ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በመለጠፏ ከስራ ታግዳለች።
ቀጣይ ምርመራም እንደሚደረግ ተገልጿል። ይህ ብዙዎች ያጋሩትና ለመውለድ የተዘጋጀች ሴት እርቃኗን ተንጋላ የሚያሳየው ፎቶ ቁጣን አስነስቷል። የማላዊ የጤና ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት ጆሹዋ ማላንጎ ለ ቢቢሲ ፎከስ አፍሪካ ራዲዮ ፕሮግራም እንደተናገሩት ፎቶውን "አስደንጋጭ" ብለውታል። •"ቀጣዩን ምርጫ ከዳር ሆኜ ባልታዘብም ተወዳዳሪ ግን አልሆንም" ብርቱካን ሚደቅሳ •"ሌሎች ሴቶች ላይ የአሲድ ጥቃት ሳይ ይረብሸኛል፤ ህመሜን ያስታውሰኛል" ካሚላት መህዲ •የ "ጥርስ አልባው" ማዕቀብ መነሳት ፖለቲካ? በተጨማሪም ጉዳዩ ወደ ነርሶች ማህበር የተመራ ሲሆን ፎቶውን ማን እንዳነሳውና እንዳሰራጨው ምርመራ እየተደረገ እንደሆነ ገልፀዋል።
news-54886520
https://www.bbc.com/amharic/news-54886520
ትግራይ፡ ጦርነቱን ተከትሎ ከ6ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሱዳን ሸሽተዋል
በፌደራል መንግሥቱ እና በትግራይ ኃይሎች መካከል የሚደረገውን ጦርነት ተከትሎ ከ6ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሱዳን መሸሻቸውን የሱዳን ባለስልጣናትን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።
የሱዳን ባለስልጣናት በቀጣይ ቀናት እስከ 200 ሺህ ኢትዮጵያውን ድንበር ተሻግረው ወደ ሱዳን ሊገቡ እንደሚችሉ ጠቁመዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የትግራይ ልዩ ኃይል በአገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ሰንዝሯል ካሉ በኋላ የአገር መከላከያ ሠራዊት እርምጃ እንዲወስድ ማዘዛቸው ይታወሳል። ሮይተርስ የዜና ወኪል በዘገባው ወደ ሱዳን ድንበር የተሻገሩት ስደተኞች ሲቪል ወይም ወታደራዊ ይሁኑ ያለው ነገር የለም። የስደተኞቹ ቁጥር ትናንት ማክሰኞ 6ሺህ መድረሱን የሱዳን የስደተኞች ኮሚሽን ገልጾ ቁጥሩ ከዚህም ሊለቅ እንደሚችል ስጋቱን አስቀምጧል። ሮይተርስ የአገሬውን የዜና አገልግሎት ጠቅሶ እንደዘገበው 6ሺህ የሚሆኑ ስደተኞች ወደ ሱዳን የዘለቁት ሉቅዲ፣ ቁዳይማህ እና ሐምዳይት በተባሉ የሱዳን ድንበር አካባቢዎች በኩል ነው። ሌሎች በርካታ ስደተኞችም በአትባራ ወንዝ ዳርቻ ወደ ሱዳን ለመሻገር በመጠባበቅ ላይ ናቸው። ሮይተርስ የሱዳን ዜና አገልግሎትን ጠቅሶ ከቀናት በፊት እንደዘገበው ደግሞ የጦርነቱን ማገርሸት ተከትሎ የሱዳን መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስነውን ድንበር በከፊል እንደዘጋ ጽፎ ነበር። የሱዳን ዜና አገልግሎት እንደሚለው በምሥራቅ ሱዳን አል ቃዳሪፍ ክልል የሚገኘው አስተዳደር ከአማራና ትግራይ የሚያገናኙትን አዋሳኝ ድንበሮችን ላልተወሰነ ጊዜ ዘግቷል። የዜና አገልግሎቱ ዘገባ እንዳተተው በሱዳን በኩል ሁለቱን የኢትዮጵያ ክልሎች በሚያዋስኑ ግዛቶች አሁን ምርት የመሰብሰቢያ ወቅት ስለሆነ የጦርነቱ ዳፋ የስደተኛ ጎርፍ አስከትሎ ገበሬዎችና ማሳቸው ላይ ችግር ሊፈጥር ይችላል። በጎረቤት አገር የሚደረገው ጦርነት ያሳሰበው የሱዳን መንግሥት የደኅንነትና ጸጥታ ጉዳዮች ምክር ቤት ባለፈው ማክሰኞ ልዩ ስብሰባ መቀመጡንና በጉዳዩ ዙርያ መምከሩም ተዘግቧል። የሱዳን የመከላከያ ሚኒስትር ያሲን ኢብራሂም ይህን ስብሰባ ተከትሎ እንዳሉት በጎረቤት አገር ኢትዮያ ያለውን ሁኔታ በአንክሮ እየተከታተሉት እንደሆነና ሁለቱም ተዋጊ ወገኖች ወደ ሰላምና መረጋጋት እንዲመለሱ ማሳሰባቸውን ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል። የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስተር ቢሮ እንደገለጠው አብደላ ሐምዱክ ለኢትዮጵያ አቻቸው ዐቢይ አሕመድ አራት ጊዜ ያህል እንደደወሉላቸውና ከህወሓት ጋር ለድርድር ዝግጁ እንዲሆኑ እንደወተወቷቸው ይኸው ጋዜጣ ዘግቧል። አቶ ገዱ በሱዳን ይህ በአንዲህ እንዳለ የኢፊዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩትና በቅርቡ የጠቅላይ ሚኒስትር የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር ተደርገው የተመደቡት አቶ ገዱ አንዳጋቸው ሱዳን ገብተዋል ሲሉ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። አቶ ገዱ ወደ ካርቱም ያቀኑት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተላከ መልዕክት ለሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ለሌትናልት ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን እና ለሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ ሀምዶክ ለማድረስ ነው። አቶ ገዱ ከሌትናልት ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን እና ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ ሀምዶክ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ዙርያ መነጋገራቸውም ተዘግቧል።
48850621
https://www.bbc.com/amharic/48850621
የዱባይ ልዕልት ከባለቤቷ ሸሽታ ለንደን ተደብቃለች
ልዕልት ሀያ ቢንት አል-ሁሴን የዱባይ መሪ ከሆነው ባለቤቷ ሞሀመድ አል ማክቱም ሸሽታ እንግሊዝ፣ ለንደን ውስጥ ተደብቃለች። ባለቤቷን ጥላ መኮብለሏን ተከትሎ ሕይወቷ አደጋ ውስጥ መሆኑንም ተናግራለች።
የ69 ዓመቱ ቢልየነር ሼህ ሞሀመድ አል ማክቱም ኢንስታግራም ላይ በቁጣ የተሞላ ግጥም አስፍሯል። ግጥሙን ለማን እንደጻፈ ባይናገርም አንዲት ሴትን "ከዳተኛ" ሲል በግጥሙ ይገልጻታል። ልዕልቷ በያዝነው ዓመት መባቻ ላይ ወደ ጀርመን ሸሽታ በመሄድ ጥገኝነት ጠይቃ ነበር። አሁን በማዕከላዊ ለንደን ውስጥ በሚገኝ 85 ሚሊየን የሚያወጣ መኖሪያ ውስጥ እንደምትገኝ ተነግሯል። ጉዳዩን ወደ ፍርድ አደባባይ ለመውሰድም ዝግጁ ናት ተብሏል። • በሊቢያ በስደተኞች መጠለያ በደረሰ የአየር ጥቃት በርካቶች ሞቱ ዮርዳኖስ ተወልዳ ትምህርቷን እንግሊዝ ውስጥ የተከታተለችው ልዕልት ሀያ 45 ዓመቷ ሲሆን፤ ከሼህ ሞሀመድ ጋር ትዳር የመሰረተችው እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር 2004 ላይ ነበር። ሼህ ሞሀመድን ስታገባ፤ "ንዑስ ሚስቶቹ " ተብለው ከሚጠሩት ስድስተኛዋ ሆና ነበር። ሼህ ሞሀመድ ከተለያዩ ሚስቶች 23 ልጆች እንደወለደ ይነገራል። ልዕልቷ ለምን ኮበለለች? ልዕልቷ በዱባይ የነበራትን "ቅንጡ" የሚባል ሕይወት ጥላ ለምን ኮበለለች? ለምንስ ሕይወቷ አደጋ ውስጥ ወደቀ? ለልዕቷ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንሚሉት፤ ልዕልቷ ለመኮብለል የወሰነችው ከሼህ ሞሀመድ ልጆች ስለ አንዷ አስደንጋጭ መረጃ በማግኘቷ ነው። ከሼህ ሞሀመድ ልጆች አንዷ ሸይካ ላቲፋ ባለፈው ዓመት ከዱባይ ኮብልላ ነበር። • አምስት ሰዎች ደቡብ ወሎ ውስጥ በደቦ ጥቃት ተገደሉ ልጅቷ በፈረንሳውያን ድጋፍ ባህር ተሻግራ ከዱባይ ከሸሸች በኋላ በሕንድ ጠረፍ አካባቢ በወታደሮች ተይዛ ወደ ዱባይ እንድትመለስ ተደርጓል። የዱባይ መንግሥትም ሸይካ ከዱባይ ስትጠፋ "ለጥቃት ተጋልጣ" እንደነበርና "ደህንነቷ ወደሚጠበቅበት" ዱባይ እንደመለሷት ተናግሮ ነበር። በወቅቱ ልዕልት ሀያና የቀድሞው የአየርላንድ ፕሬዘዳንት ሜሪ ሮቢንሰን ዱባይ ትክክለኛ እርምጃ እንደወሰደች ገልጸው መንግሥትን ተከላክለው ነበር። ሆኖም የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ልጅቷ ያለፍቃዷ ታፍን መወሰዷን ይናገራሉ። ልዕልት ሀያ ስለ ልጅቷ መኮብለልና ወደ ዱባይ መመለስ አዳዲስ መረጃ ማግኘቷን ተከትሎ ከባለቤቷ ቤተሰቦች ጫና እንደበረታባት ተነግሯል። ከምትገኝበት እንግሊዝ ታግታ ወደ ዱባይ ልትወሰድ እንደምትችል በማሰብ ስጋት ውስጥ እንደምትገኝም ለልዕልቷ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ይገልጻሉ። • "መደናገጥ ባለበት ወቅት ስህተቶች ሊያጋጥሙ ይችላሉ" አቶ ንጉሱ ጥላሁን ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲን ጨምሮ በእንግሊዝ በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋሞች የተማረችው ልዕልት እስከወዲያኛው እንግሊዝ መቆየት ትፈልጋለች። ትታው የሄደችው ባለቤቷ እንድትመለስ ጫና ለማሳደር ከሞከረ ከእንግሊዝ ጋር ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። ልዕልቷ የዮርዳኖስ ንጉሥ አብዱላህ እህት እንደመሆኗ በሼህ ሞሀመድና በሷ መካከል የሚፈጠር ነገር በሁለቱ አገራት ግንኙነት ላይ ማጥላቱ አይቀርም።
news-51347078
https://www.bbc.com/amharic/news-51347078
ግብፃዊቷ ታዳጊ በግርዛት መሞቷን ተከትሎ ቤተሰቦቿ ታሰሩ
ግብፃዊቷ የ14 አመት ታዳጊ ግርዛት እየተፈፀመባት ባለበት ወቅት ህይወቷ በማለፉ ፖሊስ ወላጆቿን እንዲሁም አክስቷን በቁጥጥር ስር አውሏል።
ግርዛቱ የተፈፀመው 'አስዩት' በተባለች ግዛት ሲሆን ግርዛቱን አከናውኗል የተባለውም ዶክተር በእስር ላይ ነው። ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት የታዳጊዋ አጎት ለባለስልጣናት በማሳወቁ ነው። • የሴት ልጅ ግርዛት በከፍተኛ ደረጃ ቀነሰ • የሴት ልጅ ግርዛት ምንድነው? የት እና ለምን ይፈጸማል? ግርዛት በግብፅ እንደ ጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር በ2008 ቢታገድም ሃገሪቷ የሴት ልጅ ግርዛት በከፍተኛ ሁኔታ ከሚፈፀምባቸው ሃገራት ትመደባለች። የዩኒሴፍ መረጃ እንደሚያሳየው ዕድሜያቸው ከ15-49 አመት ከሆኑ ሴቶች መካከል 87 በመቶዎቹ የተገረዙ ሲሆን፤ ከህዝቡም ግማሹ የሴት ልጅ ግርዛትን በሃይማኖት ከተቀመጡ መስፈርቶች ውስጥ አንዱ መሟላት ያለበት ግዴታ እንደሆነ የያስባል። ናዳ አብዱል ማክሱድ የተባለችዋ ታዳጊ በአንድ የግል ክሊኒክ ውስጥ ግርዛቱ በሚከናወንበት ወቅት በተፈጠረ መወሳሰብ ህይወቷ ሊያልፍ ችሏል። የታዳጊዋን ሞት ተከትሎ በግብፅ መብት ተሟጋቾች ዘንድ ከፍተኛ ቁጣ ተቀስቅሷል። ልጅነትና እናትነት ላይ የሚሰራው ብሄራዊ ጉባኤን ጨምሮ ሌሎች ድርጅቶችም ለድርጊቱ ተጠያቂ የሆኑ ግለሰቦች ወደ ፍርድ ሊቀርቡ ይገባል ማለታቸውን የግብፁ ሚዲያ 'አክህባር ኤል ዮም' አስነብቧል። ግብፅ የሴት ልጅ ግርዛትን በወንጀልነት የደነገገችው እንደ ጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር በ2008 ሲሆን ከሶስት አመታት በፊትም አንዲት ታዳጊ በግርዛት መሞቷን ተከትሎ ቅጣቱ ጠበቅ እንዲደረግ ውሳኔ ተላልፏል። • "እናቴ ካልመጣች አልመረቅም" ኢዛና ሐዲስ ከማንችስተር ዩኒቨርስቲ ግርዛት እንዴት ይከናወናል? ምንጭ፦ የአለም ጤና ድርጅት