input
stringlengths 1
130k
⌀ |
---|
ይሄ እንግዲህ በሀገራችን በመላዉ ኢትዮጵያ በድምቀት የሚከበር አንዱ በዓል ነዉ። |
ይሄ የሁሉም የክርስትና ኃይማኖት ተከታዮች በዓል ስለሆነ በጣም ደስ የሚል ነዉ። |
በዚህ በተለይ በዉጭ በጀርመን ሃገር ሁሉ ተሰብስቦ እንዲህ ሲያከብር ሳይ በጣም ነዉ ደስታ የተሰማኝ። |
ለኔ ደግሞ በተለይ በጀርመን ሳከብር የመጀመርያዬም ስለሆነ በጣም ተደስቻለሁ። |
በዓለም ላይ ሀገራት የሚሰደዱ ሰዎችን ተቀብሎ ማስተናገድ ዓለማቀፍ ሕግ ነዉ። |
ደብረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስትያን ዘማሪ አስካለ ማርያም ደመራን በፍራንክፈርት ስታከንር ይህ ለሦስተኛ ጊዜ ነዉ። |
በድምቀት አክብረናል የተለያዩ ኃይማኖታዊ ክንዉኖችን በማድረግ አሳለፍን የከርሞ ሰዉ ይበለን። |
በስደት ሀገር ላይ ሆነን እንደዚህ በዝማሪ በተለያዩ ባህላዊ ክንዉኖች ታጅበዉ ህዝቡም የሀገር ባህል ልብሱን ለብሶ ተዉቦ ነዉ የተገኘዉ። |
እዚህ የተወለዱትንም ልጆቻችንን ባህላቸዉንና ወጋቸዉን እንዲያዉቁ የባህል ልብስን አድርገዉ ነዉ የመጡት በጣም ደስ ይል ነበር። |
ባቡር ዉስጥ ሆነዉ ፎቶ ሲያነሱም አይቻለሁ ጀርመናዊዉ ዮሴፍ ዩስት መስቀል በዓልን በፍራንክፈርት ሲያከብሩ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነዉ። |
በዚህ በባዕድ ሀገር ይህን ያህል ሰዉ ይገኛል ብዬ አልገምትም። |
ምዕመናኑ ስላሉ ነዉ አባቶች ወደዚህ የመጡት ምዕመናኑ ስላሉ ነዉ ቤተ ክርስትያንዋ ወደዚህ የመጣችዉ። |
ይህ በዓል ብዙ እሴት ያለዉ ነዉ ለዚህ ሀገርም ቢሆን ጀርመን የክርስትያኖች ሀገር ነች እና ነዋሪዉ ይህን ሲያይ ይደሰታል። |
መላከ ስብሃት ተክሌ ሲራክ ጀርመን በርካታ የዉጭ ዜጋ መኖሩን ሀገሪትዋ ለስደተኞች በርዋን መክፈትዋ በተመለከተ የጀርመን ታላቅነት ያሳያል ሲሉ ነዉ የገለፁት። |
ይህ ጉዳይ የነሱ ጉዳይ ሆኖ የሚያስፈልገዉን ነገር አሟልተዉ ተቀብለዉ አስተናግደዉ ማስቀመጣቸዉ በጣም የሚደነቁ ህዝቦች ናቸዉ። |
ወ ሮ መብራት በፍራንክፈርት ደብረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስትያን ስትመሰረት ጀምሮ ወደዚች ቤተ ክርስትያን እንደሚሄዱ ነዉ የነገሩን። |
ይህች ቤተ ክርስትያን ስትመሰረት ጀምሮ ወደዚህ ቤተ ክርስትያን እመጣለሁ። |
የብሪታንያ መንግሥት በበኩሉ የየመን መንግሥት አቶ አዳርጋቸዉን ለኢትዮጵያ አሳልፎ መስጠቱን የጄኔቫ ሥምምነትን የጣሰ ብሎታል። |
በአቶ አንዳርጋቸዉ ላይ ግርፋት ወይም ሌላ በደል እንዳይፈፀምባቸዉ ከኤምባሲና ከሕግ ባለሙያዎች ጋር የመነጋገር መብታቸዉ እንዲጠበቅ ጠይቋል። |
አዉሮጳ እና ሰሜን አሜሪካ የሚኖረዉ ኢትዮጵያዊ በየከተማዉ ባደረገዉ የተቃዉሞ ሠልፍ የአቶ አንዳርጋቸዉን መያዝና መጋዝ አዉግዟል። |
የኢትዮጵያ መንግሥትን ባለሥልጣናትን ሥለ ጉዳዩ ለማነጋገር ቢቻል በዚሕ ዉይይት እንዲሳተፉ ለመጋበዝ ለተከታታይ ቀናት ሞክረን ነበር ያገኘናቸዉ እስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አይደሉም። |
የእርምጃዉ ሕጋዊ ሠብኣዊና ፖለቲካዊ እድምታ የዛሬ ዉይይታችን ትኩረት ነዉ። |
ከ ዓመት ገደማ በፊት ሚሊዮን ሰዎች ናቸው በልብ ድካም ወይም በስኳር በሻታ ሳቢያ ሕይወታቸውን ያጡት። |
ከእነዚህም መካከል ከሞላ ጎደል ገሚሱ ለምሳሌ ያህል ሚሊዮን ገደማ የሚሆኑት ዓመት ሳይደፍኑ ነው ለሕልፈተ ሕይወት የተዳረጉት። |
የሞቱትም በካንሠር በልብ ድካም በሰውነት ውስጥ የደም የዝውውር ሳንክ እና በስኳር በሽታ ነው። |
ድርጅቱ እንደሚያስገነዝበው ከሆነ ከመደበኛ በሽታዎች ይልቅ ቀደም ሲል እንደተጠቀሰው በቀላሉ ሊገቱ የሚችሉት ናቸው የጤና ጠንቆች የሆኑት። |
ትምባሆ የአልኮል መጠጥና አለመንቀሳቀስ ለተጠቀሰው የሥልጣኔ በሽታ ሰፊ ድርሻ አላቸው። |
በምግብ ላይ ጨው ማብዛትና የደም ጋፊት ማየልም ዕድሜን እንደሚያሳጥሩ የሚያጠራጥር አልሆነም። |
እ ጎ አ እስከ በዚሁ የሥልጣኔ በሽታና ፍጻሜው ሳቢያ በሚያድጉ አገሮች የ ቢሊዮን ዶላር ያህል ኪሣራ ማስከተሉ የማይቀር ነው። |
ታዲያ ተደጋጋሞ የሚሰጠው ምክርም ሆነ ማስጠንቀቂያ ችላ ስለሚባል ሊሆን ይችላል የሥነ ቴክኒኩ ዓለም ተጨባጭ ያለውን ማስገንዘቢያ ይዞ ለመቅረብ የተገደደው። |
በዚያ የኤሌክትሮኒክስ ዐውደ ርእይ ላይ ከ ያላነሱ በዋናነት የሚጠቀሱ የረቂቅ ኤልክትሮኒክስ ውጤቶች መቅረባቸውም ነው የተገለጠው። |
በግዙፉ ማለትም ካሬሜትር ስፋት ባለው የዐውደ ርእይ ቦታ እጅግ ዘመናዊ የተሰኙ አውቶሞቢሎችም ቀርበዋል። |
የጀርመኑ ሜርሰደስ ቤንዝ በላስ ቬጋስ ጎዳና ያለ ዘዋሪ የሚሽከረከር አውቶሞቢል አቅርቦ ነበር። |
ሙሉ አውቶማቲክ ተሽከርካሪ ያለአሽከርካሪ ተንቀሳቅሶ በአውቶሞቢሎች ማቆሚያ ሥፍራ ቦታ ፈልጎ ያላንዳች ሳንክ መቆም እንደሚችል አሳይቷል። |
በተመሳሳይ ሁኔታ አውዲ አውቶሞቢልም ይህን ማድረግ እንደሚችል በዐውደ ርእዩ ላይ ለመታዘብ ተችሏል። |
እንዲሁም የደቡብ ኮሪያው ሂዩንዴይ የተለያዩ የአውቶሞቢል ክፍሎች በልዩ የእጅ ሰዓት ትእዛዝ የሚንቀሳቀሱበትን ሁኔታ አሳይቷል። |
ከብስክሌተኞች ቆብ ብርሃን ይንጸባረቅና ፊት ለፊት የሚመጣ ቮልቮ ተሽከርካሪ ካለ ስልኩ የመንቀጥቀጥም ሆነ የንዝረት ምልክት ይሰጣል። |
ሆኖም ገበያ ላይ ከመዋሉ በፊት ቆቡ አሁንም ተጨማሪ ፍተሻ እንደሚያሻው ቮልቮ አስታውቋል። |
በዚያው የተጠቃሚዎች የኤልክትሮኒክስ ዐውደ ርእይ የስፌት መኪናም በካሜራ ርዳታ ቅድን ጥለትን እንደ መራጩ ፍላጎት አሳምሮ ራሱ መስፋትም መጥለፍም እንደሚችል ታይቷል። |
የዓይን መንጽር ተንቀሳቃሽ ምስልና የመሳሰለው የሚታይበት ኢምንት የቴሌቭዥን ሣጥን ሆኖም ያገለግላል። |
በባርሴሎና እስፓኝ ከዚያም በሃኖፈር ጀርመን ዘንድሮ ምን ተጨማሪ አዳዲስ የኤልክትሮኒክስ ውጤቶች ይቀርቡ ይሆን ጊዜው ሲደርስ የምንመለከተው ይሆናል። |
የስፖርት ዘገባ መጋቢት ቀን ዓ ም በስፔን ላሊጋ ክሪያስቲያኖ ሮናልዶ በ ደቂቃ ሐትሪክ በመሥራት ለቡድኑ ግቦችን አስቆጥሯል። |
የውጭ ጉዳይ ሚንሥትር መግለጫ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንሥትር ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። |
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንሥትር ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። |
ከድምፅ ሰጭዎቹ አብዛኛዎቹ እቅዱን ቢቃወሙም ድምጹን ለመስጠት የወጣው ህዝብ ቁጥር ከ በመቶ በማነሱ ህዝበ ውሳኔው ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። |
በስተሰሜን ስሎቫክያ በስተሰሜን ምዕራብ ኦስትሪያ በስተምዕራብ ስሎቬንያ በስተደቡብ ምዕራብ ክሮኤሽያ እና በስተደቡብ ሰርቢያ በስተምሥራቅ ሩሜንያ በስተሰሜን ምሥራቅ ደግሞ ዩክሬን። |
ሀንጋሪ የአሁኑን ድንበርዋን የያዘችው ከግዛትዋ በመቶውን ከህዝብዋ ደግሞ በመቶውን ካሳጣት ከአንደኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ነው። |
ከጦርነቱ በኋላ በኮሚንስቶች ጎራ ስር የወደቀችው ሀንጋሪ የምሥራቁ ጎራ ሲፈረካከስ በጥቅምት ዴሞክራሲያዊ ምክርቤታዊ ሪፐብሊክ ሆነች። |
በጎርጎሮሳዊው ዓ ም የአዉሮጳ ኅብረት የሆነችው ሀንጋሪ ወደ ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ አላት ። |
ድምፅ ለመስጠት ከወጡት ሀንጋርያውያን በመቶው ወይም ሚሊዮኑ እቅዱን ተቃውመዋል ። |
ይሁንና ድምጽ የሰጠው ህዝብ ቁጥር በመቶ ብቻ በመሆኑ ህዝበ ውሳኔው ውድቅ ተደርጓል ። |
ያም ሆኖ ኦርባን ለፓርቲያቸው ለፊዴስዝ ደጋፊዎች ባሰሙት ንግግር ውጤቱን እጹብ ድንቅ ብለውታል ። |
በንግግራቸው የህዝበ ውሳኔውን ተቀባይነት አለማግኘት ግን ፈጽሞ አላነሱም ። |
ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ የተባለ ስደተኛ በገባበት ባለፈው ዓመት ድንበሯን በመዝጋት የመጀመሪያዋ የምሥራቅ አውሮጳ ሀገር ናት ። |
እርምጃው በአውሮጳ ኅብረት ቢወገዝም የሀንጋሪ መንግሥት ከዚህ አቋሙ አሁንም ፍንክች አላለም ። |
ከእሁዱ ህዝበ ውሳኔ በኋላም ኦርባን ግባቸውን ለማሳካት በመጪዎቹ ቀናት ህገ መንግሥታዊ ማሻሻያዎችን ለማድረግ የሚያስችሉ ህጎችን እንደሚያወጡ እና እንደሚሰሩም አስታውቀዋል ። |
ኦርባን መንግሥታቸው አሁንም የህብረቱን እቅድ መቃወሙን እንደሚቀጥል አስታውቀዋል ። |
ጥያቄው ብራሰልስ አሁን የብዙሃኑን ውሳኔ ይቀበላል አይቀበልም ነው ። |
የኦርባንን ማስፈራሪያ እና አዝማሚያቸውን የብራሰልስ ባለሥልጣናት እንደ ዋዛ አላለፉትም ። |
እጅግ ዝቅተኛው የምርጫ ተሳትፎ የሌሎችን መብት የሚጋፉ ህዝበ ውሳኔዎች የአውሮጳ ፖለቲካ የሚካሄድበት መንገድ አለመሆኑን በድጋሚ ያሳያል ። |
እዚህ ጥያቄው ህዝበ ውሳኔ ሳይሆን አንድ አምባገነን መሪ ለፀረ የውጭ ዜጋ መርሁ ምኞት እና ፍላጎት ማረጋጋጫ ማግኘት ነበር ። |
ህብረቱ እስከ መጪው የጎርጎሮሳውያኑ ዓም መጨረሻ ደግሞ ሺህ ያህሉን ለአባላቱ ለማከፋፈል አቅዷል ። |
የህብረቱ አባል ሀገራት የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባሳለፉት ውሳኔ መሠረት ሀንጋሪ ስደተኞችን መቀበል አለባት ። |
ሀንጋሪ ግን ይህን በመቃወም አቤቱታዋን ለአዉሮጳ የበላይ ፍርድ ቤት አቅርባ ነበር ። |
ከዚያ በኋላ ደግሞ በእቅዱ ላይ ህዝበ ውሳኔ ጠራች ። |
ሀንጋሪያዊው የፖለቲካ ሳይንቲስ ጋቦር ቶሮክ አሁን ሊተኮርበት የሚገባው ዋናው ጉዳይ ውጤቱ ነው ይላሉ ። |
ውድቅ ከሆነው ህዝበ ውሳኔ በኋላ ተቃዋሚዎቹ የግራ እና የቀኝ ፓርቲዎች ኦርባን ከሥልጣን ይውረዱ እያሉ ነው ። |
ሀገሪቱ አንድ ላይ ናት ዋናው ነገር ብዙሀኑ ኮታውን እምቢ ሲል ድምጹን መስጠቱ ነው ። |
በመቶ የሚሆነው ህዝብ ለህዝበ ውሳኔው ደንታ አልነበረውም ወይም በጥያቄው አልተስማማም ። |
እኚህ አስተያየት ሰጭ ደግሞ ኦርባን እስካሁን ከተናገሩት በላይ የህዝበ ውሳኔው ውጤት ሊያመጣ የሚችለውን ነገር ያብራሩልን ሲሉ ጠይቀዋል ። |
ቪክቶር ኦርባን ውጤቱ በብራሰልስ ምን እንደሚያስከትል አንድ የተጨበጠ ነገር መናገር ከቻሉ የበለጠ እናውቃለን ። |
ማንም ምንም እስካልተናገረ ድረስ እኛ የምናውቀው ህዝበ ውሳኔው ተቀባይነት እንደሌለው ነው ። |
ተቃዋሚዎች እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም የመብት ተሟጋቾች ህዝቡ ድምጹን ለመስጠት እንዳይወጣ ሲቀሰቅሱ ነበር ። |
ከተሰጠው ድምፅም ከ ሺህ በላይ የሚሆነው ተቀባይነት አላገኘም ። |
ከህዝበ ውሳኔው በፊት መንግሥት ለቅስቀሳ የተጠቀመባቸው የቴሌቪዥን ማስታወቂያዎች ስደተኞችን ከአሸባሪነት እና ከወንጀል ጋር የሚያያዙ ነበሩ ። |
ሀንጋርያውያን አብዛኛው ህዝብ ስለ መጻኤ እድሉ አለመጨነቁ አሳስቧቸዋል ። |
ከአውሮጳ ኅብረት ጋር በጀመሩት እሰጣ ገባ የቀጠሉት ኦርባን ግባቸውን ለማሳካት እወስዳለሁ ያሏቸው እርምጃዎች በርካታ ትችቶች እየተሰነዘሩባቸው ነው ። |
የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት ጠቅላይ ሚንሥትር አቢይ አህመድ የአምቦ ጉብኝት እና የኅብረተሰቡ የለውጥ ተማጽኖን ይዳስሳል። |
ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እንዲያነሱ የለውጥ አቅጣጫቸውንም እንዲያመላክቱ የሚወተውቱ ጥያቄዎች በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች እየተነሱ ነው። |
ከተለያዩ የማኅበረሰቡ አባላት ጋር ከጀመሩት ንግግር ባሻገር ሌሎች ጉዳዮችን ለመመልከት ጊዜ ያስፈልጋቸዋል ሲሉ የሚሞግቱም አሉ። |
ረቂቁ በኢትዮጵያ ገዢው መንግሥት ሰብአዊ መብቶችን እንዲያከከብር ብሎም ለመልካም አስተዳደር ትኩርት እንዲሰጥ ይጠይቃል። |
በሳምንቱ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች መነጋገሪያ ከኾኑ ጉዳዮች መካከል የጠቅላይ ሚንሥትር አቢይ አህመድ በአንቦ ከተማ ያደረጉት ንግግር ይገኝበታል። |
በሺህዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች የጠቅላይ ሚንሥትሩ ንግግርን በሥፍራው ተገኝተው ያደመጡ ሲኾን ይኽን መልእክት የያዘው የቪዲዮ ምስልም በትዊተር እና ፌስቡክ ተንሸራሽሯል። |
በጠቅላይ ሚንሥትሩ ንግግር በመደመም አድናቆት የሰጡም ትችት እና ተቃውሞ የሰነዘሩም ነበሩ። |
በትዊተር እና በፌስቡክ ብሎም በዋትስአፕ ከተሰጡት የድጋፍ እና የትችት አስተያየቶች የትዊተሮቹን እናስቀድም። |
የቀድሞ የአዲስ ነገር ጋዜጣ አዘጋጅ አቢይ ተክለማርያም በትዊተር ገጹ ቀጣዩን መልእክት በእንግሊዝኛ አስፍሯል። |
አቢይ ሰዎችን ማነጋገር ይወዳል በማለት ይንደረደራል አቢይ ጠቅላይ ሚንሥትር አቢይን ሲገልጣቸው። |
ስትል ጽሑፏን የጀመረችው ሐና ጫላ፦ የቀድሞው ሰርዐት ስትሉ ከዶክተር አብይ በፊት የነበረውን ኢህአዴግ ነው የምናስገባው ወይስ ደርግን ነው |
እናመሰግናለን ክቡር ጠቅላይ ምኒስትር አሁን ከሁሉም ነገር በላይ የሆነው አንድነትና ሰላም እየሸተተን ነው በሞገስ ሀረጎት የተሰጠ አስተያት ነው። |
አብይ የበፊቱን በሚያወግዝ መልኩ ከአሁን በኃላ በሚሉ ቃላቶች የታጨቀ ንግግር ነው የሚናገረው። |
በከዚህ በፊቱም አመራር ላይ እኮ እሱም ነበረ አሁን መቼስ አዲስ ጭንቅላት አላስገጠመ ብሏል። |
ኤች አር የተባለው የውሳኔ ሐሳብ በዩናይትድ ስቴትስ ሕግ መምሪያ ምክር ቤት መጽደቁ በሣምንቱ ዋና የመነጋገሪያ የነበር ርእሰ ጉዳይ ነበር። |
ውሳኔ ሐሳቡ በኢትዮጵያ የተፈጸሙ ግድያዎች እንዲጣሩ የታሰሩ እንዲፈቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ እና አፋኝ የተባሉ ሕግጋት እንዲሻሩ ይጠይቃል፡፡ |
የውሳኔ ሐሳቡ ከመጽደቁ ቀደም ባሉት ጊዜያት በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የምክር ቤት አባላቱን ለማሳመን ከፍተኛ ዘመቻ ተከናውኗል። |
የዘመቻው ተሳታፊዎች በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙ የኮንግሬስ አባላትን የትዊተር አድራሻ በማያያዝ ድጋፍ እንዲሰጡ በተደጋጋሚ ወትውተዋል። |
የውሳኔ ሐሳቡ መጽደቁ የዘመቻው ተሳታፊዎችን እና ሌሎች የውሳኔው ደጋፊዎችን እጅግ አስደስቷል። |
ማይክ ኮፍማን፦ በኮሎራዶ ግዛት የስድስት የምርጫ ወረዳዎች ተወካይ ሲኾኑ ክሪስ ስሚዝ የኒው ጄርሲ አራተኛውን የምርጫ ወረዳ ይወክላሉ። |
እነዚህ ሁለት የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መምሪያ ምክር ቤት አባላትን ኢትዮጵያውያን ውለታችሁን መቼም አንረሳም ሲሉ አወድሰዋል። |
ፕራውድ ኢትዮጵያ በሚል የትዊተር አድራሻ ለማይክ ኮፍማን የቀረበ መልእክት እንዲህ ይነበባል። |
በትጋት ላደረጉት በተጨቆነው የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ስም እጅግ በጣም አመሠግናለሁ ማለት እፈልጋለሁ። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.