input
stringlengths
1
130k
በኤኮኖሚው ረገድ በፋርስ ባህረ ሰላጤ በጋራ የሚያካሂዷቸው የነዳጅ ዘይት ሥራዎች እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን አይወዱትም።
ቀጠር ከሙስሊም ወንድማማቾች ማህበር ጋር ረዥም ጊዜ የዘለቀ ቅርብ ግንኙነት አላት።
ቡድኑ በጎርጎሮሳዊው ቱ የግብጽ ምርጫ ብዙ ድምጽ ሲያገኝ ቀጠር ከካይሮ ጋር ፖለቲካዊ ግንኙነትዋን ለማጠናከር ሞክራ ነበር።
የሳውዲ መንግሥት የሙስሊም ወንድማማቾች ማህበር ለአረብ ባህረ ሰላጤ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ስርዓት አደጋ አድርጎ ነው የሚያየው።
በዚህ የተነሳም ቀጠር አሁን የተጠየቀችውን ሁሉ ማሟላት አስቸጋሪ ነው የሚሆንባት ይላሉ ዞንስ።
ወይም ደግሞ ከአረብ ወንድሞቿ ጋር ጋር እንደ እስካሁኑ ጥሩውን ግንኙነት አጠናክራ ልትቀጥልም ትፈልግ ይሆናል።
ከጥቂት ቀናት በፊት የቀጠር አምባሳደር በርሊን ውስጥ ቀጠሮች እና ሳውዲዎች በመሠረቱ አንድ ቤተሰብ ናቸው ብለው ነበር።
በዚህ ውዝግብ ውስጥ የሚካፈሉት ወገኖች ገጽታቸውን ሳያበላሹ ከዚህ ውዝግብ የሚላቀቁበትን መንገድ ነው የሚፈልጉት።
በዛም ሆነ በዚህ ግን ቀጠር የተጠየቀችውን ታሟላላቸው ብዮ አላስብም።
ውይይቱ ወደ ሚካሄድበት ስፍራ ሄደው ለመግባት የጠየቁ ወጣቶችም እርሱ እንደሚለ በልዩ ፖሊስ ተደብድበው ጉዳት ደርሶባቸዋል የታሰሩም አሉ ።
በውይይቱ ላይ ከህብረተሰቡ ለተነሱ ልዩ ልዩ ጥያቄዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልስ ሰጥተዋል።
የትኛውንም ወረዳ እንደማይወክሉ የተናገሩት እኚሁ ነዋሪ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለህብረተሰቡ ጥያቄዎች የሰጡት መልስ ከሞላ ጎደል ጥሩ ነው ብለዋል።
ሆኖም ጥያቄ የማቅረብ እድል አለማግኘታቸውን ተናግረው በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ አጥጋቢ መልሶች እንዳላገኙ መነሳት ነበረባቸው ያሏቸው ጥያቄዎችም እንዳልተነሱ ተናግረዋል።
ወደ ውይይቱ አዳራሽ መግባት ተከለከልኩ የሚል ሌላው ወጣት ደግሞ የአፋር ወጣቶች ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ውይይት ላይ ለመካፈል ቢፈልጉም አለመጋበዛቸውን ይገልጻል።
ውይይቱ ወደ ሚካሄድበት ስፍራ ሄደው ለመግባት የጠየቁ ወጣቶችም እርሱ እንደሚለው በልዩ ፖሊስ ተደብድበው ጉዳት ደርሶባቸዋል የታሰሩም አሉ።
ከተጎዱት መካከል ሴቶች እና በእድሜ የገፉም እንደሚገኙበት ወጣቱ ተናግሯል።
በርሱ አባባል ወጣቶቹ ስብሰባው እንዳይገቡ የተከለከሉት በክልሉ ያለውን ችግር ያጋልጣሉ በሚል ስጋት ሳይሆን አይቀርም።
ዶቼቬለ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን የክልሉን ባለሥልጣናት ለማነጋገር ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።
አቶ ብሩክ መኮንን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ልዑክ ቃል አቀባይ ናቸው።
ባለፉት ሁለት አመታት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኩል የተጠኑ ጥናቶች አሉ።
የእነዚህ ጥናቶች አፈጻጸምን በሚመለከት ነው የዚህ ስብሰባ ዋና ትኩረት።
በአፈጻጸም ሒደቱስ መታየት ያለባቸው ጉዳዮች ምንድናቸው የሚለው ላይ ነው ይኸ ስብሰባ በዋናነት የሚያጠነጥነው።
ከትልልቆቹ ጥቆማዎች አንዱ ትኩረቱ ከሰላም ማስከበር ወደ ሰላም የማስፈን ተልዕኮ መሻገር አለበት የሚለው ነው።
የሰላም ማስፈን ተልዕኮ ስራ ግጭት የመከላከል እንቅስቃሴዎች የሰላም ግንባታ የድኅረ ግጭት መልሶ ማቋቋም እና የልማት ሥራን ያካትታል።
አንዱ ፈታኝ ነገር ሰላሙን ዘላቂ ለማድረግ ምንም ሥራ ሳይሰራ ወታደሮቹ እንዲወጡ መደረጉ ነው።
በቀውስ በተመቱ አገሮች በመንግሥታዊ አስተዳደር ውስጥ የሕግ የበላይነትን እና ሌሎች አገልግሎቶችን መልሶ ማስፈን ሌላው ችላ የተባለ ነገር ነው።
ግጭት የነበረባቸውን አካባቢዎች ስንመለከት መላ የጸጥታ ጥበቃ እና የፍትኅ ሥርዓቶቹ ፈርሰዋል።
ሪያና ፓኔራስ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ግጭት ባቀወሳቸው አካባቢዎች በወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ብቻ ተወስኖ ቆይቷል ሲሉ ይተቻሉ።
በ ገፆች የተቀነበበው ግምገማ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ የፖለቲካ ሒደትን የመደገፍ ሰፊ ሚና አንድ አካል ሊሆን ይገባል የሚል ጥቆማ ሰጥቷል።
የተባበሩት መንግሥታት በሰላም ማስከበር ተልዕኮዎቹ መስክ ተኮር እና ሰዎችን ማዕከል ሊያደርግ ይገባል ሲልም አትቷል።
አቶ ብሩክ መኮንን የተሰሩት ጥናቶች የተባበሩት መንግሥታት ተልዕኮዎች ከሰላም ማስከበር የዘለለ ሚና እንዲኖራቸው የታቀዱ ናቸው ሲሉ ይናገራሉ።
ሽብር እና ድንበር ተሻጋሪ የተደራጀ ወንጀል በሰላም ማስፈን ተልዕኮ ላይ መሰረታዊ ለውጥ አምጥተዋል።
የባለሙያዎቹ ጥቆማ እነዚህን ለመቀልበስ ሰላም ማስከበር በቀጥታ ጥቅም ላይ ሊውል አይገባም የሚል ኃሳብ አቅርቧል።
ነገር ግን ተፅዕኖ እስካለው ድረስ አንድ ተልዕኮ ቸል ሊለው ይገባል ብዬ አላምንም።
በዚያ የአፍሪቃ ኅብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪ አለ።
የተደራጀ ወንጀል ተቃዋሚዎችን እና አል ሸባብን ወደ ወደ ፊት እየገፋቸው ነው።
መንግሥት ይኸን ለመፍታት ደካማ በመሆኑ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ መፍትሔ ካልፈለገለት ማን ሊፈታው ነው
ከዚህ በተጨማሪ ግጭት ከተከሰተ በኋላ ከመታገል ይልቅ ከመከሰቱ በፊት እንዴት መከላከል ይቻላል የሚለው ኹነኛ መፍትሔ ይሻል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰላም ማስከበር ተልዕኮን ለማሻሻል ጠንካራ ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ ሪያና ፓኔራስ ተናግረዋል።
አምባሳደሯ የወጪ ቅነሳውን እንደ ታላቅ ስኬት ቢቆጥሩትም ተንታኞች ግን የሰላም ማስከበር ተልዕኮ መፃኢ ፈተና ጠቋሚ ምልክት አድርገውታል።
ይሁንና ሐላፊዋ አክለዉ እንዳሉት ወባ አሁንም ከዓለም በርካታ ሕዝብ ከሚገድሉ አምስት በሽታዎች አንዱ ነዉ።
በዚሕም ሰበብ የዘንድሮዉ የፀረ ወባ ቀን አብይ መርሕ በጣሙን የአፍሪቃ ሕፃናትን የሚፈጀዉን በሽታ ለመከላከል የሚደረገዉ ጥረት እንዲጠናከር የሚጠይቅ ነዉ።
በኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚንስቴር የወባ መከላከያ ዘርፍ አስተባባሪ ወይዘሪት ሕይወት ሰለሞን እንዳስታወቁት የፀረ ወባ ዕለት ኢትዮጵያ ዉስጥም ተከብሮ ነዉ የዋለዉ።
ከከሟቾቹ ከአምስት መቶ ሥልሳ ሺሕ የሚበልጡት ጨቅላ ሕፃናት ነበሩ።
የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቬዥንና የኦሮሞ ሚድያ ኔትዎርክ ለነዚህ ተከሳሾች እንደ ልሳን አገልግለዋል ሲል የክስ ዝርዝሩ ይጠቅሳል።
ዶክተር መረራ ከኅዳር ቀን ዓ ም ጀምሮ እስር ላይ ይገኛሉ።
ሦስቱም ተጠርጣሪዎች ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ስረዓቱን በኃይል እንናስወግዳለን በማለት እንደተንቀሳቀሱ የወንጀል ዝርዝሩ ያመለክታል።
ዶክተር መረራ በማዕከላዊ እስር ላይ እንደሚገኙ የሚናገሩት ጠበቃቸዉ አቶ ወንድሙ ኢብሳ ደንበኛቸዉ በወንጀል መቅጫ መከሰሳቸዉ ይናገራሉ።
እሳቸዉ በሚመሩት ድርጅት ላይ የቀረበዉን ዉንጀላም መሰረተ ቢስ ክስ መሆኑን ይናገራሉ።
ስርዓቱ የኔን ስም ተጠቅሞ ዶክተር መረራን ለመጉዳት ያሰበበት ክስ ነዉ የሚሉት ደግሞ ሦስተኛ ተከሳሽ አቶ ጀዋር መሃመድ ናቸዉ።
አቶ ጀዋር በአምስተኛ ደረጃ ላይ ክስ የተመሰረተበት የኦሮሞ ሚድያ ኔትዎርክ ሥራ አስኪያጅም ናቸዉ።
የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ ግዜያት ሲወነጅለን ነበር የሚሉት አቶ ጃዋር የሚመሩትን ተቋም ከክሱ ነፃ መሆኑን ይናገራሉ።
ዶክተር መረራ እስከ ትላንትና ድረስ ክስ ሳይመሰረትባቸዉ ለ ቀናት በእስር እንደቆዩ ጠበቃቸዉ አቶ ወንድሙ ኢብሳ ገልጸዋል።
ትላንትና የዋስትና መብት እንዲጠበቅላቸዉ ስምንት ሰዓት ላይ ቀጠሮ ነበራቸዉ።
የኢትዮጵያ የግድግዳ ጡፍ መግቢያ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
ኢትዮጵያ የቤተሰብ የበዓል አከባበር ሦስት ኢድ አልፈጥሮችን በሦስት የተለያዩ እስር ቤቶች አሳልፏል።
ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ጋዜጠኛ ኻሊድ ቤት ጎራ ብሎ የበዓል አከባበሩን ተመልክቷል።
የዜናነህ መኮንን የጤና መቃወስ ዜናነህ መኮንን ከ ዓ ም ጀምሮ ከጋዜጠኝነት በተለይም የኤሌክትሮኒክስ መገናኛ ዘዴዎችን ተለይቶ አያውቅም።
መጀመሪያ በኢትዮጵያ ራዲዮ ቀጥሎ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና በራዲዮ በዝግጅቶች እና በዜና አቅራቢነት ለረጅም ጊዜ ያገለገለ አንጋፋ ጋዜጠኛ ነው።
ወደ እስራኤል ከተሰደደ በኋላም በተለያዩ የራዲዮ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች እና በኢንተርኔት የተለያዩ ዝግጅቶችን በማቅረብ ይታወቃል።
በኢየሩሳሌም የዶይቸ ቬለ ተባባሪ ዘጋቢ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ የመካከለኛው ምሥራቅን የፖለቲካ ዲፕሎማሲን ውጥንቅጥን በመዘገብ እና በመተንተን ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል።
ዜናነህ ከጋዜጠኝነቱ በተጨማሪ የሁለት መጽሐፍት እና የግጥሞች ደራሲ ነዉ።
ነጻነት የተሰኘው የበኩር ስራው በጣሊያን የአምስት ዓመት የወረራ ወቅት የነበረውን ጦርነት የሚያሳይ ታሪካዊ ልቦለድ ነው።
በሁለተኛ መጽሐፉ ከጣራው ስር ደግሞ የአዲስ አበባን ድብቅ የማህበራዊ ህይወት በልቦለድ ከሽኖ አቅርቧል።
ጋዜጠኛው ከጎርጎሮሳዊው ጀምሮ የዶይቸ ቬለ የአማርኛው ክፍል የጣቢያ መክፈቻ እና በዝግጅቶች መግቢያነት የሚጠቀምባቸው ማስተዋወቂያዎች አንባቢም ነዉ።
እውቁ ጋዜጠኛ ከጥቂት ወራት በፊት የገጠመው የኩላሊት ሕመም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መጥቷል።
ዜናነህ ሁለቱም ኩላሊቶቹ አገልግሎት መስጠት ማቆማቸውን ሐኪሞቹ የነገሩት ከጥቂት ወራት በፊት ነበር።
ከኩላሊቶቹ ቢያንስ አንዱ በንቅለ ተከላ ካልተቀየረ የጤንነት ሁኔታው አሁን ካለበትም ሊከፋ እንደሚችልም አስጠንቅቀውታል።
ስለ ጋዜጠኝነት ህይወቱ ስለ መጽሐፍቶቹ የህዝቡን እርዳታ ስለጠየቀበት የኩላሊት ህመሙ አውግቶናል።
የኢትዮጵያውያን ውይይት በፓሪሱ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በፈረንሳይ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር በተካሄደ ውይይት ጥሪውን ያስተላለፈው ኤምባሲው ዜጎችን ለማገልገል ዝግጁ መሆኑንን አስታውቋል።
ፈረንሳይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ዘርፎች ሀገራቸውን ሊያግዙ እንደሚገባ ተጠየቀ።
ቡድኑ ወደኢትዮጵያ የገባው በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋባዥነት ሲሆን በዚህ አጋጣሚም ህክምና አከናውኗል።
ቡና ፈላጊዉ ዓለም በተለይ በተፈጥሮ መንገድ ለሚያድገዉ የጫካ ቡና የሰጠዉ ትኩረት የኢትዮጵያን ደን ከዉድመት ይታደገዉ ይሆን
በዓለማችን የጫካ ወይም ወፍ ዘራሽ ቡናን የሚያመርቱ ሃገራት ሶስት ብቻ ናቸዉ።
ከእነዚህ ሃገራት አንዷ ደግሞ በሀገር በቀል የተፈጥሮ ደን ዉስጥ ይህን ቡናዋን በማብቀል ትታወቃለች።
ይህችዉም ቡናን በዉድ ዋጋ ለጠጪዎች ማቅረቡን የሚያዉቅበት ዓለም በኩራት ጠቀም ባለ ገንዘብ የሚቸበችበዉ አረቢካ የተሰኘዉ ቡና መገኛ ምድር ኢትዮጵያ ናት።
በመቶ የሚሆነዉ የተፈጥሮ ደን በእርሻ ሥራ ማስፋፊያ በሰዎች መኖሪያና በሰፈራ እንቅስቃሴዎች እንዳልነበር ሆኗል።
በአሁኑ ወቅት ካለዉ የደን ሀብት በመቶዉ የሚገኘዉ በኦሮሚያ መስተዳድና አካባቢዉ ነዉ።
ጄፍሪ ያነጋገራቸዉ የጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ተቋም አማካሪ እንደሚሉት አማራጭ አጥቶ እንጂ ሕብረተሰቡ የደን ሀብቱን በመንከባከብ ሊያገኝ የሚችለዉን ጥቅም አልዘነጋዉም።
ቡናዉ በዓለም ገበያ እዉቅና አግኝቶለት ኑሮዉን የሚያሻሽልበት አማራጭ ሲቀርብለት መተባበሩም ይህንኑ አመላካች ነዉ።
ይህም ገበሬዎቹ ለዓለም ገበያ ለሚያቀርቡት ቡና ጥራት ትልቅ ዋስትና ነዉ።
እንደዘገባዉ ጃፓኖች በፈጣን ባቡሮቻቸዉ ለሚጓዙ መንገደኞች ይህንን ከጅማ ዞን የተፈጥሮ ደን ዉስጥ የበቀለ ቡና ማቅረብ ከጀመሩ አራት ወራት ተቆጥረዋል።
በዓለም ገበያ እጅግ ተፈላጊ የሆነዉ ወፍ ዘራሹ የጫካ ቡና ህልዉና እንዲቀጥልም የተፈጥሮ ደኑን መጠበቁ አማራጭ እንደሌለዉ ነዉ ግልፅ የሆነዉ።
ሆኖም ከሽያጩ ያገኙት ከበፊቱ የተሻለ ገቢ ትርጉም ሳይኖረዉ የቀረ አይመስም።
ምንም እንኳን አንዳንዶቹ አሁንም ያገኙት ገቢ የእነሱን ወገብ በጣሽ ልፋትና የፈሰሰ ላብ እንደማያካክስ በግልፅ ቢናገሩም።
በዚህ መልኩ እንቅስቃሴዉ ተጠናክሮ የኢትዮጵያ የጫካ ቡና ልዩ ሆኖ በዓለም ገበያ ሲቀርብም ደንን ከመራቆት መታደግ መቻሉም ትልቅ ግምት ይሰጠዋል።
ማብራሪያ በመስጠት የተባበሩንን የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አራርሳ ረጋሳን ከልብ እናመሰግናለን።
የደመራ በዓል አከባበር በጀርመን እንደ ብዙዎች ግምት በዚህ ክብረ በዓል ከ በላይ ሰዉ ነበር የተገኘዉ።
በዚህ ዝግጅታችን በፍራንክፈርት እጅግ በርካታ ኢትዮጵያዉያን የተገኙበትን የደመራ በዓል ቃኝተን በአሁኑ ወቅት በአዉሮጳ ብሎም በጀርመን ስላለዉ የስደተኝነት ቀዉስ እናያለን።
በየዓመቱም የከተማዉ ከንቲባ አልያም ሌሎች ከፍተኛ የጀርመን ባለስልጣናት በክብር እንግድነት ይጋበዙበታል።
ዘንድሮ የፍራንክፈርቱ ደመራ በዓል ላይ በክብር እንግድነት የተጋበዙት አዲስ ተሾመዉ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጀነራል ምህረትዓብ ሙሉጌታም ነበሩ።
ከቀኑ አስር ተኩል ሲሆን ምዕመናኑ ትልቁን ደመራ ከበዉ ዘማሪዎች ልብሳቸዉን ለብሰዉ ደመራዉ በተደመረበት ሰፊ ሜዳ ላይ ተሰበሰቡ።
ክብረ በዓሉም በፍራንክፈርት ደብረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስትያን አስተዳዳሪ በአባ ኃይለመለኮት ተስፋ ማርያም በይፋ ተጀመረ።
በፍራንክፈርት ደግሞ በየዓመቱ እንደዚሁ ከ ዓመት ጀምሮ በታላቅ ነዉ የሚከበረዉ።
በመጀመርያዎቹ ዓመታት የጀርመን ከፍተኛ ባለስልጣናት የፍራንክፈርት ከተማ ምክት ከንቲባ እየመጣ አብሮን አክብሮአል።
የደመራዉም አከባበር ልክ እንደ ሀገራችን ነዉ ደስ ይላል ሕዝቡም ደስተኛ ነዉ።
በአባ ኃይለ መለኮት በጀርመን ብሎም በአዉሮጳ የወቅቱ ያለዉን የስደት ቀዉስ በተመለከተ ቤተ ክርስትያኒቱ ምዕመኑ ሁሉ ስለ ችግሩ እንደሚያስብ እንደሚፀልይ ተናግረዋል።
ሁላችንም አይተናል ሰምተናል በተለይ በመካከለኛዉ ምሥራቅ ያለዉ ችግር በሶርያ በአፍጋኒስታን በኤርትራ እንደዚሁ ከባድ የስደት መከራ ነዉ ያለዉ።
ጀርመኖችም ሁኔታዉ የሁለተኛዉን ዓለም ጦርነት ያስታዉሳል ነዉ የሚሉት በቤተ ክርስትያናችን እንፀልያለን።
በአሁኑ ጊዜም ከአዉሮጳ ሀገራት በበለጠ ስደተኞችን የምትቀበለዉ ጀርመን ናት።