input
stringlengths
1
130k
በአንፃሩ ሁሉ ሰላም እንደነበር የሌንዱ ጎሳ ቃል አቀባይ ፍራንስዋ ዳዳ ገልጾዋል።
ጊዜ ራሱ በጎሳዎቹ መካከል ያለው ልዩነት እንዲቆም ድርሻ አበርክቶዋል።
ጦርነት እስከሌለ ድረስ ሕዝቡ ባለፉት ዓመታት የደረሰበትን በደል ረስቶዋል።
ይህንን ብንልም ግን በደስታ እንፈነድቃለን ማለት አይደለም ምክንያቱም ከሳሾች እኛ አልነበርንምና።
ምንም እንኳን የትኛውም ከባድ ቅጣት የግዳጁ ምልመላ ሰለባ የሆኑት ሕፃናት የደረሰባቸውን የዕድሜ ልክ ሥቃይ ባይቀንስም።
ጥያቄው የብዙ ሕፃናትን ሕይወት ላበላሸ ግለሰብ ትክክለኛው ቅጣት የቱ ነው የሚለው ነው።
በመግቢያው መግለጫችን እንዳስታወቅነው፡ ከፍተኛው የእሥራት ቅጣት እንዲበየንባቸው ነው የምንጥረው።
የኢሬቻ በዓል አከባበር በአዲስ አበባ ኢሬቻ በዓል ዛሬ በአዲስ አበባ ለግምት የሚያስቸግር በርካታ ህዝብ በተገኘበት ተከብሯል።
የኢሬቻ በዓል ዛሬ በአዲስ አበባ ለግምት የሚያስቸግር በርካታ ህዝብ በተገኘበት ተከብሯል።
የመስከረም ቀን ዓ ም የዜና መጽሔት ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
የሰመርጃም ሬጌ የሙዚቃ ትርኢት ኛ ዓመት መግቢያ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ከ በላይ እንዲሁም በቀጠሮ ታራሚዎች መኖራቸውን ከፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።
በዚህ ሳምንት በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች መነጋገሪያ ከኾኑ ነጥቦች መካከል አራት ጉዳዮች ጎልተው ወጥተዋል።
የአትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገ ሥላሴ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኾኖ መመረጥ አንደኛው ርእስ ነው።
የአትሌት ምሩጽ ይፍጠር የጤንነት ኹኔታን በተመለከተ የቀረቡ ዘገባዎችም አነጋጋሪ ኾነዋል።
የዶናልድ ትራምፕ ባልተጠበቀ መልኩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ኾነው መመረጥ በስፋት አነጋጋግሯል።
አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት በመኾን መመረጡ በማኅበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች መነጋገሪያ ኾነው ከቆዩ ጉዳዮች አንዱ ነበር።
ዘካርያስ ዘላለም በትዊተር ማኅበራዊ መገናኛ ገጹ ባሰፈረው ጽሑፉ፦ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በርካት ጉዳዮች ተቆልለው ይጠብቁታል።
ከእነዚያም መካከል በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተንሰራፋው ሙስና እና አትሌቶችን ስልታዊ በኾነ መልኩ መበደል ይገኝበታል።
ሰማኸኝ ጋሹ አበበ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ምርጫን በፌስቡክ ገጹ እንደሚከተለው ተችቷል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴን የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንትነት አድርጎ መርጦታል።
ግለሰቡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሕዝባዊ ትግሉ ላይ የሚሰጣቸዉ አስተያየቶች እንደሚጠቁሙት ከስርአቱ ጋር የጠበቀ ቁርኝት አንዳለዉ ነዉ።
እንዲመረጥ ያስደረገዉም ይህ ለስርአቱ ያለዉ ድጋፍ ነዉ ሲል ጽፏል።
ሰማኸኝ በመቀጠል ጽሑፉን ሲያብራራ፦ ስርአቱ ከደረሰበት የፖለቲካ ኪሳራ ለመዉጣት እንዲህ አይነት ቁማር መጫወቱ የሚጠበቅ ነዉ።
ገብረ እግዚአብሔር ገብረ ማርያም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አዲሱ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ነው።
ፌዴሬሽኑ በቀድሞ ታላቅ አትሌቶች በመመራት የባየር ሙይንሽንን ሞዴል እየተከተለ ነው ብሏል።
ናታሊ አሚዮት በትዊተር ቀጣዩን ባስነበበችው መልእክቷ፦ ንጉሡ እርቃኑን ነው።
ዶ ር ቴድሮስ በግልጽ የሕወሃት ተጨማሪ ማጭበርበር እና ሐፍረት ነው ብላለች።
እንዳልካቸው ኃይለሚካኤል ግሎባል ቮይስ በተባለ ድረ ገጽ ላይ ያሰፈረውን ዘለግ ያለ ጽሑፍ ትዊተር ገጹ ላይ አካፍሏል።
የሚለውን የዶ ር ቴድሮስ አድሃኖም ጥያቄ እና አወያዩ ጥያቄውን በድጋሚ ለማብራራት መሞከራቸው የሚያሳፍር መኾኑን አካቷል።
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ድረ ገጽ አድራሻ የያዘ ዜና ረቡዕ ጥቅምት ቀን ዓም ኢንተርኔት ላይ ሰፍሮ ይገኛል።
ዜናው በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተጻፈ ሲኾን፦ ዕውቁ የኢትዮጵያ አትሌት ምሩጽ ይፍጠር አርፏል ይላል።
በቅድሚያም ዜና ረፍት ሲል የሚንደረደረው የስፖርት ዜና ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ድረ ገጽ እንደተሰረዘ የሚያመለክተው የተፈለገው መረጃ አልተገኘም የሚል መልእክትም ይነበባል።
አጥናፍ ብርሐኔ በትዊተር ገጹ የመንግሥት መገናኛ አውታሮች በረዥም ርቀት ታዋቂው አትሌት ምሩጽ ይፍጠር አርፏል በማለት ሰዉን አሳስተዋል ሲል ጽፏል።
የአብይ አጠር ያለው ስላቃዊ ጽሑፉ፦ የፖለቲካ ትንታኔ ነፍስሽን በሠላም ያሳርፈው የሚል ነው።
ዘላለም ክብረት በትዊተር ገጹ የሪፐብሊካኖች ፓርቲ መለያ የኾነውን ቀይ ቀለም ከኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በማነጻጸር አጠር ያለ መልእክት አስተላልፏል።
የምርጫ መዘርዝር ውጤቱን ለማሳየት የቀረበው የዩናይትድ ስቴትስ ካርታን በስፋት አልብሶ የሚታየው ቀይ ቀለም ሪፐብሊካኖች በፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በስፋት ማሸነፋቸውን ያመለክታል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቀይ ዞን ከሚል ጽሑፍ ጋር በቀይ ቀለም የተዋጠ የኢትዮጵያ ካርታም ከጎኑ ሰፍሯል።
ዘላለም፦ ከዩናይትድ ስቴትስ እና ከኢትዮጵያ ካርታ ጋር ያያዘው አጭር ጽሑፍ ቀይ በቀይ የሆነ ጊዜ ይላል።
የብዥታው ምንጭ የመንግሥት መገናኛ አውታሮች ዘገባ እንደኾነ ብዙዎች ጽፈዋል።
በሳምንቱ ውስጥ የተከናወነ ወይም የሚከናወን አንድ ዓቢይ ፖለቲካዊ ጉዳይን ያስተነትናል።
ከኤኮኖሚው ዓለም ለዓለም በተለይ ለኢትዮጵያ ኤኮኖሚያዊ ሂደቶች ትኩረት የሚሰጥ ዝግጅት ነው።
የባህል መድረክ በተለይ የኢትዮጵያውያን የኪነ ጥበብ ስራዎችን እንዲሁም በጀርመን አውሮጳ እና በሌሎች ባህሎች መካከል የሚደረገውን ግንኙነት የሚያስቃኝ ሳምንታዊ ዝግጅት ነው።
የወጣቶች ዓለም ወጣት ኢትዮጵያውያንን የሚመለከቱ እና የሚያዝናኑ አርዕስትን እያነሳ ከሚመለከታቸው ጋር በሚደረግ ውይይት የሚጠናቀር ሳምንታዊ ዝግጅት ነው።
ኢንክሪፕሽን በመረጃ እና ግንኙነት ዘርፍ ማንኛውም መልእክት ከላኪው ወደ ተቀባዩ ከመድረሱ አስቀድሞ የሚያልፍበት መንገድ አለው።
መልእክቱ ካልተቆለፈ በስተቀር ከላኪ እና ከተቀባይ ውጪ መሀል መንገድ ላይ በሦስተኛ ወገን ሊበረበር ይችላል።
በእርግጥ አንድ መልእክት ከላኪ እና ከተቀባዩ ውጪ በሦስተኛ ወገን ተለይቶ እንዳይታወቅ ማድረጊያ የመቆለፊያ ሒደት አለ በእንግሊዝኛው ይሰኛል።
ኢንክሪፕሽን ከመደበኛው የመስመር ስልክ ውጪ የኢንተርኔት የመገናኛ መግባቢያን በመጠቀም የኢንተርኔት መረብ ውስጥ የስልክ ጥሪ የማከናወን እና ሰነዶችን የመላክ ስልትን ይጠቀማል።
አቶ ሰለሞን ሙሉጌታ ካሳ የስነ ቴክኒክ ከፍተኛ አማካሪ እና የሶፍትዌር አበልጻጊ ናቸው።
ቴክ ቶክ የተሰኘውን የኢቢ ኤስ ቴሌቪዥን ፕሮግራም በማዘጋጀትም ያቀርባሉ።
ኢንክሪፕሽን በጥቅሉ ምንነቱ ሳይታወቅ በሆነ መንገድ ተቆልፎ የተላከ መልእክት ተቀባዩ ጋር ብቻ ሲደርስ ግልጽ ሆኖ እንዲፈታ የማድረግ ሒደት ነው።
የዲጂታሉ ዘመን የጀመረበት የመጀመሪያ ዓመታት አካባቢ ተቆልፈው ይላኩ የነበሩ መልእክቶች በቀላሉ ሊፈቱ የሚችሉ ነበሩ።
የኮምፒውተሮች መስፋፋት እና መርቀቅ ግን የተቆለፈው መልእክት እጅግ ውስብስብ እንዲሆን እና በቀላሉ እንዳይፈታ ለማድረግ አግዘዋል።
በተለይ የኢንተርኔት የመገናኛ መግባቢያን በመጠቀም የኢንተርኔት ጥሪ አገልግሎት መጀመሩ መልእክቶች የበለጠ እንዲቆለፉ አስችሏል።
በዓለማችን መልእክቶችን ቆልፎ የመላክ ጥበብ የዲጂታሉ ዘመን ብቻ ያመጣው አዲስ ነገር አይደለም።
መልእክት ቊለፋ በሮማን ኢምፓየር ዘምን ጭምር ጥቅም ላይ የነበረ ጥበብ ስለመሆኑ የታሪክ ድርሳናት ይጠቅሳሉ።
ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ትልቁ እና አንደኛው ነገር ምሥጢራዊነትን መጠበቅ መሆኑን አቶ ሰለሞን ተናግረዋል።
የጥረቱ ምንጭ በእርግጥ ዘርፈ ብዙ እና ሰፊ ነው ከማጭበርበር አንስቶ የፖለቲካ ተልዕኮ እስከ ማስፈጸም ሊደርስ ይችላል።
ለመሆኑ የመልእክት ቊለፋ እንደ ቫይበር ዋትስአፕ ስካይፕ መሴንጀር እና በመሳሰሉት የመልእክት መቀበያ ወይም መላኪያ ማስተናበሪያዎች የሚሠራው እንዴት ነው
ያን የሚያደርገውም መልእክት ላኪው እና ተቀባዩ ጋር የሚገኘው አፕሊኬሽን ነው።
የጋራ ቊልፍ ኖሮ ቊልፉን የሚያውቁ አካላት ብቻ ሊፈቱት የሚችሉት የቊለፋ አይነት ወይንም አንደኛው ነው።
በዚህ ዘዴ የተቆለፈውን መልእክት ለመፍታት ላኪው እና ተቀባዩ ተመሳሳይ መቆለፊያ እና መፍቻ ዘዴን ነው የሚጠቀሙት።
ሆኖም ቊልፉ ከላኪ እና ተቀባይ ከወጣ የመልእክቱ ምሥጢር በሦስተኛ ወገን በቀላሉ ሊፈታ ይችላል።
ሌላኛው ዘመናዊ የቊለፋ አይነት በመልእክት ላኪው እና ተቀባዩ መካከል ብቻ የሚመሰጠር ነው።
መልእክቱን የሚቀበለው ሰው ላኪውም የራሳቸው የግል ቊልፍ ይኖራቸዋል መፍቻ ቊልፍ መቀባበል አያስፈልግም።
ይህ ዘዴ ይፋ የሆነው እንደ ጎርጎሪዮሳስ አቆጣጠር በ ነው።
በኢንተርኔቱ ዓለም ሙሉ ዲጂታል መረጃ አገልግሎት የሚሰጡ ማስተናበሪያዎች በርካታ ናቸው።
የቊለፋ ስልት በመጠቀም የኢንተርኔት ጥሪን የሚያስተናግዱ ማስተናበሪያዎች ግን አይነታቸው በሁለት ይከፈላል።
አንደኛው ከላኪው እና ተቀባዩ ውጪ አገልግሎት ሰጪው እንኳን መልእክቱን ማየት የማይችልበት ነው።
የዚህ ተጠቃሚዎች ለአብነት ያኽል ዋትስአፕ እና የአፕል አይ ሜሴጅ ይጠቀሳሉ።
ሌሎቹ እንደነ ትዊተር ሀንግ አውት የፌስቡክ መሴንጀር ስካይፕ የመሳሰሉት ሲሆኑ እነሱም እንደነዋትስአፕ የቁለፋ ስልትን ይጠቀማሉ።
ሆኖም ለየት የሚያደርጋቸው የአፕሊኬሽኖቹ ባለቤቶች ያልተቆለፈው መልእክት የሰነድ ማከማቻ ቋታቸ ውስጥ መገኘቱ ነው።
ደም መታየቱ በራሱ በሽታ ሳይሆን ምልክት ነዉ ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
አፍሪቃ በግድያ የተጠረጠረዉ ኤርትራዊ ኤርትራዊዉ ፍራንክፈርት ባቡር ጣቢያ የነበሩ እናት ልጅን በፍጥነት በሚጓዝ ባቡር ፊት ገፍትሮ ጥሏቸዋል።
እናትየዋ ከባቡሩ ሐዲድ ተንከባላ ስታመልጥ የስምት ዓመቱ ሕፃን ግን እዚያዉ ሞቷል።
የጀርመን የፌደራል ፖሊስ አዛዥ ዲተር ሮማን ዛሬ እንዳስታወቁት ሰዉዬዉ ሲዊዘርላንድ ዉስጥ አንዲት ጎረቤቱን በጩቤ ለመዉጋት በማስፈራራት ወንጀል ሲታደን ነበር።
አቃቤ ሕግ የግድያና ድርብ የግድያ ሙከራ ክስ ለመመስረት እየተዘጋጀ ነዉ።
ከ ጀምሮ ሲዊትዘርላንድ ዉስጥ እንደኖረ ባለትዳርና የ ልጆች አባት እንደሆነም ተነግሯል።
ኤርትራዊዉ ፍራንክፈርት ባቡር ጣቢያ የነበሩ እናት ልጅን በፍጥነት በሚጓዝ ባቡር ፊት ገፍትሮ ጥሏቸዋል።
ፖሊስ እንዳስታወቀዉ ኤርትራዊዉ ሌላ ሴትዮ ወደ ሐዲዱ ለመገፍተር ሞክሮ አልተሳከለትም።
አደጋዉን ካደረሰ በኋላ ለማምለጥ ሲሮጥ ባካባቢዉ በነበረዉ ሕዝብና እርፍት ላይ በነበረ ፖሊስ ርብርብ ተይዟል።
ኦነግ በሰጠው መግለጫመንግስት እየወሰደ ነው ባለው መብቶችን የሚጥሱ እርምጃዎች ሃገሪቱን ወዳልተፈለገ ችግር ሊያመራት ይችላል ሲል አስጠንቅቋል።
መንግሥት የዜጎችን የመደራጀት የመሰብሰብ እና በነጻነት የመንቀሳቀስ መብት ሊያከብር ይገባል ሲል የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ አሳሰበ።
መንግሥት የዜጎችን መሰረታዊ የዴሞክራሲ መብቶች መጣሱን የሚቀጥል ከሆነ ግን ነገሮች ወደማይፈልጉት አስቸጋሪ ሁኔታ ሊያስገባ ይችላል ብለዋል።
መንግስት የሰብዓዊ መብትን ጨምሮ የመደራጀት በነጻነት የመንቀሳቀስ እና የመስበሰብ መብቶችን ነጻ እንዲያደርግ እና እነዚህኑ ከሚያደናቅፉ ተግባራት እንዲቆጠብ እንጠይቃለን።
ይህ ካልሆነ ግን ሀገሪቷ ወደማይፈለግ የጥፋት መንገድ እየሄደች መሆኗን ለማስታወስ እና መንግስት አካሄዱንም ሆነ መዋቅሩን እንዲያስተካክል እናሳስባለን።
አቶ ዳውድ አያይዘውም የመንግስት መዋቅርም ሆነ ባለስልጣናቱ የሕግ የበላይነትን አክብረው መንቀሳቀስ ይኖርባቸዋል ብለዋል።
አንዳንድ የገዢው ፓርቲ አባላት የቀደመውን መንግስት ለመመለስ እያደረጉ ካለው እንቅስቃሴያቸው ይቆጠቡ ሲሉም ጠይቀዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀሰቀሰውን የኮረና ወረርሽን ለመግታት ሁሉም ርብርብ እንዲያደርግም አቶ ዳውድ በዚሁ ወቅት ጠይቀዋል።
በጉራጌ ዞን በተቀሰቀሰ ግጭት ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ አውዲዮውን ያዳምጡ።
ሪቻርድ ፎን ቫይሴከር ተኛው የጀርመን ፕሬዝዳንት መግቢያ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
ኢትዮጵያ ካለፉት ጥቂት ሳምንታት ወዲህ በፍጥነት የሚለዋወጡ ክስተቶችን እያስተናገደች ነው።
በነዚህ ጊዜያት የኢትዮጵያ መንግሥት የሚወስዳቸው እርምጃዎችም የዜጎችን ልብ እያንጠለጠሉ እና ብዙ ጥያቄዎችን እያስነሱ ነው።
ማን ይተካቸዋል የሚለውም ከመላ ምት በስተቀር እስካሁን ቁርጥ ያለ መልስ አላገኘም።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዳይ አነጋግሮ ሳያበቃ በማግሥቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደንገጉ ሌላው ካለፈው ሳምንት አንስቶ የሚያጠያይቅ ዐብይ ክስተት ሆኖ ዘልቋል።
አዋጁ ከተደነገገ በኋላም ህብረተሰቡ ሌሎች ጥያቄዎቹ እንዲመለሱ በመጠየቅ አድማ ማካሄዱን ቀጥሎ ነበር የሰነበተው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥልጣን እለቃለሁ ካሉ በኋላ የሰው ሳይሆን የስርዓት ለውጥ ነው የምንፈልገው የሚሉ የሽግግር መንግሥት ጥያቄዎች እየቀረቡ ነው።
የአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋቾቹ ከባቢ አየርን ጠብቁ የድንጋይ ከሰል ቊፋሮን አቊሙ ሲሉም መፈክር አስተጋብተዋል።
በሺህዎች የሚቆጠሩ የአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋቾች መንግሥታት የዓለም ሙቀት መጨመርን ለመግታት ርምጃዎችን መውሰድ እንዲጀምሩ በጀርመን ቦን ከተማ ባካሄዱት ሰልፍ ጠየቁ፡፡
ሰልፈኞቹ መንግስታት በድንጋይ ከሰል የሚሠሩ የኃይል ማመንጫዎችን በፍጥነት ከአገልግሎት ውጭ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡