input
stringlengths
1
130k
ዛሬ በድጋሚ በተዋቀረው ካቢኔ ውስጥ በተለያየ ዘርፍ የዶክተርነት ማዕረግ ያላቸው ሚኒስትሮች እንደተካተቱ የተገለጸ ሲሆን ሁለት ፕሮፌሰሮችም ቦታ አግኝተዋል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲው አቶ ይልቃል የቀደመው ካቢኔ ሲጸድቅ ማስተርስ ያላቸው እና የተማሩ እየተባለ የትምህርት እና የትምህርት ልምዳቸው ሲነገር እንደነበር ያስታውሳሉ፡፡
የኢህአዴግ አብዮታዊ ዲሞክራሲ እና ጥፍንግ ያለ የማዕከላዊነት አመለካከት እስካልተለወጠ ድረስ የግለሰብ መቀየር ምንም ዓይነት ለውጥ አያመጣም ይላሉ፡፡
ሁለቱም የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ኢትዮጵያ ያለችበት ወቅታዊ ችግር የሚፈታው በሚኒስትሮች መለዋወጥ ሳይሆን ኢህአዴግ መሰረታዊ እና የፖሊሲ ለውጥ ሲያደርግ ነው ይላሉ፡፡
ሳይንስ እና ኅብረተሰብ የህዋ ሳይንስ በኢትዮጵያ የሕዋ ሳይንስ እየረቀቀና እየመጠቀ እንደሄደ ብዙዎች ያምናሉ።
ኢትዮጵያ በጠፈር ሳይንስ ከአፍሪካ ስድስተኛ ሀገር ሆናለች ወደ ህዋ የምትመጥቀዉ ሳተላይት የምንኖርበትን አካባቢ የምድር ገፅታን የሚያመለክቱ መረጃዎችን ወደ ምድር ትልካለች።
የከፋ ዞን ጥብቅ የተፈጥሮ ደን በተፈጥሯዊ መስህብነት በዩኔስኮ ተመዝግቧል ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
ኢትዮጵያ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የአምቦ ጉብኝት አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ ር አብይ አህመድ አምቦን ዛሬ ጎበኙ።
የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የአምቦ ጉብኝት አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዛሬ የረፋድ ውሏቸውን በአምቦ ከተማ አድርገዋል፡፡
ከአዲስ አበባ በስተ ምዕራብ ኪሎ ሜትር የምትርቀው የአምቦ ከተማ ነዋሪዎች የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር ለማድመጥ ማልደው ወደ አምቦ ዩኒቨርስቲ ስቴድየም ተምመዋል፡፡
በሀገር ባህል ልብሶች ያጌጡ እና የዶ ር አብይ ምስሎች የታተሙባቸው ካኔቴራዎችን ለብሰው ወደ ዝግጅቱ ቦታ ሲሄዱ የታዩም ነበሩ፡፡
ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቀባበል ለማድረግ በተሸሞነሞኑ ፈረሶቻቸው ሆነው ወደ አደባባይ የወጡ በርካታ ፈረሰኞች እንደነበሩ የከተማይቱ ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡
ከፈረሰኞቹ ውስጥ በአምቦ ዙሪያ ካሉ አካባቢዎች ጭምር የመጡ እንደሚገኙበት ገልጸዋል፡፡
ለዶይቼ ቬለ አስተያየታቸውን የሰጡ አንድ የከተማይቱ ነዋሪ ህዝቡ በብዛት የወጣው ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ተጨማሪ የቤት ስራ ለመስጠት ነው ብለዋል፡፡
አምቦ እና አካባቢዋ ከሶስት አመታት በላይ ጠንካራ ተቃውሞ ከታዩባቸው የኦሮሚያ ከተሞች ቀዳሚዎቹ ናቸው፡፡
ለዚህም ይመስላል ከተሾሙ ገና ሁለተኛ ሳምንታቸውን እንኳ ያልደፈኑት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከቀዳሚ የስራ ጉብኝታቸው ስፍራዎች አምቦን ያካተቱት፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ወደ ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ሲጓዙ እንዳደረጉት ሁሉ በአምቦ ጉዟቸውም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን አካትተዋል፡፡
በስነ ስርዓቱ ላይ የታደሙት የአምቦ ዩኒቨርስቲ መምህር ኩማ ዴቢሳ ንግግሮቹን በጥሞና ከተከታተሉት አንዱ ናቸው፡፡
አቶ ለማ ዛሬ የመጣነው እንደከዚህ ቀደሙ እሳት ለማጥፋት ሳይሆን ተስፋን ለመናገር ነው ማለታቸውን ይጠቅሳሉ፡፡
የአቶ ደመቀ ንግግር ቀድሞ ሲያሰሙት ከነበረው የተለየ እንደነበር የሚናገሩት የዩኒቨርስቲው መምህር ከታዳሚው ጥሩ ድጋፍ ማግኘታቸውን ገልጸዋል፡፡
በስተመጨረሻ ንግግር ለማድረግ መድረኩን የተረከቡት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለታዳሚው ሰላምታ ሲያቀርቡ ህዝቡ በሆታ እና በፉጨት አጅቧቸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሌሎቹ ተናጋሪዎች ሁሉ ቄሮ በሚል ስያሜ የሚጠሩትን የኦሮሞ ወጣቶችንም አንስተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በንግግራቸው የክልሉን ፕሬዝዳንት እና የምክትላቸውን መልዕክት አስተጋብተዋል፡፡
አምቦ ከዚህ በኋላ የቱሪዝም የባህል እና የፖለቲካ ማዕከል ትሆናለች፡፡
ለሦስት ቀናት በግብፅ ተካሄደ ዓለም ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
በስደት ሊኖሩበት ከተመኙ እስኪደርሱ የብራስልስ መናፈሻ ቤታቸው ሆኗል እግሮቹ በቤልጂግ መዲና ብራስል ጎዳናዎች ላይ ሲመላለሱ አይታክታቸውም አንዳች ግብ አላቸውና።
ልቡ ግን በብዙ ሺህ ኪሎ ሜትሮች ርቀት ኢትዮጵያ ከእናታቸው ጋር የሚገኙት ሁለት ሕጻናት ልጆቹ ጋር ቀርቷል።
የተመድ ኛ ዓመት በዓለም ዓቀፉ ማኅበረሰብ ትንታኔ የዓለም መንግስታትን በአንድነት እንደሚያስተሳስር የሚነገርለት የተመድ ዘንድሮ ኛ ዓመቱን ትናንት አከበረ።
ከ ዱ አባል አገራት አንዷ በሆነችዉ ኢትዮጵያ መዲናም ዛሬ የድርጅቱ ምስረታ ኛ በዓል ታስቦ ዉሏል።
በዓለም የስደተኞች ቁጥር ማሻቀብ እና በፈረንሳይ የስደተኞች የምግብ ዝግጅት ፌስቲቫልን የተመለከቱ ዘገቦችም አሉን።
ይድረስ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መቼም ለጤናዎት እንደምን አሉ ብዬ አልጀምር ነገር የአካል ደህንነትዎን እያየሁት ነው፡፡
የመንፈስዎን ደግሞ መገመት ይቻላል ኢትዮጵያን የሚያህል ሀገር ከመቶ ሚሊዮን ህዝብ ጋር መምራት ከባድ እንደሆነ ለመረዳት አይቸግርም፡፡
ክቡር ሆይ እርስዎ ወደዚህ መንበር ከመጡ በኋላ ሀገራችን ብዙ ተስፋ የጫሩ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡
በዚህም በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና አግኝተውበት የ የሰላም ኖቤል ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
እኔ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ሽልማቱ መቶ በመቶ ይገባዎታል ብዬ የማምን ዜጋ ነኝ፡፡
በእኔ ምልከታ በብዙ ፈተና ውስጥ እያለፉም ቢሆን ብዙ ውጤቶችን በማስመዝገብዎት ትልቅ እውቅና እሰጣለሁ፡፡
በሀገራችን የህግ የበላይነት ባለመከበሩ ከዕለት ወደ ዕለት የዜጋው ሰላም ውሎ መግባት ጥያቄ ውስጥ ሲወድቅ ማየት በእጅጉ የሚረብሽ ጉዳይ ነው፡፡
በእርግጥ ብዙዎቻችን ነገሮችን የምንመለከተው በተናጠል በመሆኑ መፍትሔው ቀልሎ ቢታየንም ሀገር መምራት የብዙ ዘርፎች ድምር ውጤት ነውና ሊከብድ እንደሚችል መገመት ይቻላል፡፡
ለመሆኑ ሰሞኑን የተከሰተው ግጭትና የሰዎች ህልፈት መነሻው ከወዴት ይሆን
በሚዲያ ዘራፍ ያዙኝ ልቀቁኝ ባይነታቸው በሁሉም የኢትዮጵያ ክልል ውስጥ እንደገባ ወረርሽኝ ከዳር ዳር እየተስተጋባ ይገኛል፡፡
ይህ ሁሉ ሲሆን ተው የሚል አካል ባለመኖሩ ይኸው እሳቱ እየፈጀን ይገኛል፡፡
ስለዚህ መንግስት የህግ የበላይነትን ማስከበር ባለመቻሉ ሃገር እየታመሰች እንደሆነ አውቆ ለነገ በማሰብ መንቀሳቀስ ዋና ሥራው እንደሆነ ሊታሰብበት ይገባል፡፡
የዚህ ችግር መፍትሔ በመራቁ አሁንም መንግስትንና ህዝብን ንቀው የሚንቀሳቀሱ አካላት በአራቱም ማዕዘናት ማየት የተለመደ ነው፡፡
በሌሎቹም ዘርፎችም እንዲሁ አዎንታዊነቱንና አሉታዊነቱን እያነሱ ብዙ ማለት ይቻላል፡፡
ጉዳዩ የእርስዎን ያላሰለሰ የሰላም ጥረትና ከጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት በኋላ የሚደረግ ውሳኔ ይጠብቃል፡፡
እነዚህም ቡድኖች የሞቱለትን ዓላማ ዘንግተው በተቃራኒው ጎራ በመቆም ሰውን የሚያህል ክቡር ፍጥረት በድንጋይ ወግረው እስከ መግደል እየደረሱ ነው፡፡
ግን አሁን የእርስዎ ዘመን ነውና በሚዲያ ወጥቶ የእንባ አድርቅ ቃላት የሚወረውር አንድ የፌደራል ባለሥልጣን መጥፋቱ ለምን ይሆን አስብሎናል፡፡
ሀሳብዎት ገዢ በመሆኑ አለመደገፍ ባንችልም ሃሳብዎትን ለማስፈፀም የሚችሉበትን ሜዳ እያጠበቡት መመልከታችን ያሳስበናል ከዚያም አልፎ ሀገራችን ነችና ያገባናል፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን አዕዋፋት ተሰብስበው እያደኑ ስለሚይዟቸው ጠላቶቻቸው ይወያያሉ አሉ፡፡
በዚህም መሠረት የተለያዩ አዕዋፋት ለምርጫ ቀረቡና በከፍተኛ ድምጽ የተመረጠችው ቆቅ ሆነች፡፡
እናንተን እወክል ዘንድ ስለመረጣችሁኝና ዕምነታችሁን ስለጣላችሁብኝ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡
ሆኖም ካለመሳተፍ መሳተፍ የበለጠ ጥቅም ይኖረዋልና እናንተን መስዬ እናንተን አክዬ እና እናንተን ሆኜ ለመቅረብ ዝግጁ ነኝ፡፡
ኛው እነሱን አለመናቅና ሊበልጡኝ የሚችሉበት አንዳንድ ጉዳይ እንደሚኖር ማመን ነው፡፡
ይኸውም ቆቅ ቆቅ የሚለውን ስሟን ይዛ የትም አትደርስም የሚል ዕምነት ነው ያለኝ፡፡
ማን እንበላት ካላችሁም እኔ ዋ ኔ የሚል ስም ቢሰጣት መልካም ነው እላለሁ አለች፡፡
እርግብም ቀጥላ አሁን የሚያዋጣን ዛሬ ከባላንጦቻችን መወዳጀት ነው አለች፡፡
እያንዳንዱ ድል አንድ አንድ ጠላት እንደሚወልድ አትርሳ ይላሉ ፀሐፍት፡፡
ስለዚህም አሸነፍኩ ብሎ ዘራፍ ማለት ከመሸነፍ አንድ የሚሆንበት ጊዜ አለ፡፡
ድልን በማጭበርበር የምንቀዳጅ ከሆነም ዕድሜ ልካችንን እንቅልፍ እንዳይወስደን ያደርገናል፡፡
ደራሲና ፀሐፌ ተውኔት ፀጋዬ ገ መድህን በአንደኛው ቴያትሩ እንዳለው አብዮትኮ ኳስ ጨዋታ ነው፡፡
አቀበለ ተቀበለ ይዞ ሄደ መታ ፎሪ ወጣ አብዮቱ ከሸፈ ይባላል ወይም ቀጥሎ ደግሞ ይዞ ሄደ
መቼ እንደምናቀብል መቼ ወደፊት እንደምንሄድ መቼ አብዶ ምሣ እንደምንሠራ ካላወቅን ፖለቲከኛ መሆን አንችልም፡፡
የጐጃም ትውልድ በሙሉ ከአባይ እስከ አባይ በሚለው መጽሐፉ ደራሲ ግርማ ጌታኹን እንዲህ ይላል ወለተ አልፋ አመተ አልፍን ወለደች፡፡
እርሱ ግን የውርጭ ድደን ጥርሱን ገጥሞት መናገር ቸግሮት ነበርና ከዛፉ አውርደው ፀሐይ ቢአሞቁት ዘመድ ላይ ከጃራ ሹም የመጣሁ ነበርሁ፡፡
የዚህ ጊዜ እናትና ልጆች የኔ ባል ይሁን የኔ ባል ይሁን ተባባሉበት፡፡
ተያይዘው ከዲማ መነኮሳት ከነአባ ተጠምቀ መድኅንና ከነአባ ዮሐኒ ዘንድ ለፍርድ ሄዱ፡፡
እኒያም ሲፈርዱ አንች ባል አግብተሺ ቤት ሠርተሺ እርስዋን ወልደሻል፡፡
አንች ብታገኝ አግቢ ብታቂ መንኩሺና ተቀመጪ ብለው ፈረዱ ይባላል፡፡
ድፍረትን ከሀፍረት ሳንነጥል የምናይበት ዐይን ይስጠን በተለይ በምርጫ ወቅት፡፡
ዘራፍ ማለት አለሁ አለሁ ማለት ያለ እኔ ማን አለ ማለት ካለፈው አለመማር ከመርገምት ሁሉ የከፋ መርገምት ነው፡፡
ምንጊዜም ቢሆን የሚባለው ነብር ከጓዳ ሳይወጣ የሚበላው ፍየል ተክለፍልፎ መጣ የሚለውን አገርኛ ግጥም አንርሣ
ኢትዮጵያ የአስቸኳይ ግዜ አዋጁና የኦሮሚያው ተቃዉሞ ለ ወር የዘለቀው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናቶች ይቀሩታል።
የአዋጁን አፈፃፀም በበላይነት የሚከታተለዉ ብሔራዊ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙም ይታወቃል።
አቶ ሲራጅ ለላፉት ወራቶች ሲተገበር የነበረዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአገሪቱ ሠላም እና ፀጥታ መማምጣት ችለዋልም ብለዋል።
በባቱ ከተማ ብዙ ሱቁች መዘጋታቸዉንና የማህበረሰቡ ብሶት ከግብር ዉጭ እንደሆነም ጠቅሰዋል።
በዚህ ክልል ዉስጥ ያለዉ ማህበረሰብ ከመንግስት ምንም ነገር እየጠበቀ አይደለም።
የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ጥሩ ዉጤት አስገኝተዋል የሚሉት ለራሳቸዉ እንጅ ለሕዝቡ አደገኛ አዋጅ ነዉ።
በኦሮሚያ ያለዉ ሠላምና ፀጥታ በተሻሻለ ሁኔታ ላይ እንደምገኝ አቶ አዲሱ አረጋ ተናግረዋል።
በተወሰኑ ቦታዎች የተከሰተዉን መጠነኛ ክስተት ወስዶ አዋጁ ይራዘማል አይራዘምም የሚል ድምዳሜ መዉሰድ ግን ያሳስታል ብለዋል።
ወደ መቐለ ይደረጉ የነበሩ በረራዎች በኮሮና ሳቢያ ቀነሱ በኢትዮጵያ በኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለበዓልና ዕረፍት ይደረጉ የነበሩ በረራዎች እየተስተጓጎሉ ይገኛሉ፡፡
ኃላፊው ሙሉ በሙሉ ትምህርት ቤቶች የፈረሱባቸው አካባቢዎች አሉ ብለዋል ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
ኢትዮጵያ የተቃዉሞ ሰልፎችና አስተያየት በኢትዮጵያ ከተሞች የተቃዉሞ ሰልፎች መካሄድ ከጀመረ ሰነባበተ።
በኦሮምያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ከወራት በፊት የተቀሰቀሰዉ ተቃዉሞ እየበረደ ዳግምም እያገረሸ ቀጥሏል።
ተቃዉሞ ጎንደር ባለፈዉ እሁድ በታላቅ ሕዝባዊ ሰልፍ ብትጥለቀለቅም አጀማመሩም አፈፃጸሙም ሰላማዊ እንደነበር ተነግሮላታል።
የፊታችን እሁድ ባህር ዳር ከተማ ላይ ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ መዘጋጀቱን ያረጋገጡት አቶ አዲሱ በበኩላቸዉ የሰልፉን አላማ ዘርዝረዋል።
ትራምፕ ስደተኞችን በግንብ ሙስሊሞችን በመግቢያ ፍቃድ ለማገድ ሲዝቱ የፓኪስታኑ ሙስሊም ስደተኛ ልጅ ሳዲቅ ካሕን የለንደን ከንቲባ ሆኑ።
ለዶናልድ ትራፕ ግን ዉሳኔዉ በዘር ቀለም ሐይማኖት ጥላቻ ከተሞላ መርሐቸዉ ጋር መጣጣሙ አጠራጣሪ ነዉ።
የመካከለኛዉ ምሥራቅና የምሥራቅ አዉሮጳ ትናንሽ ሐገራት በደቡባዊ አሜሪካዊቱ ትልቅ ሐገር ትልቅ ፖለቲካዊ ቀዉስ ለመደሰት ማዘናቸዉ ፖለቲካዊ ምክንያት የላቸዉም።
የብራዚል ፖለቲካዊ ቀዉስ መነሻ ዉስጣዊና ዉጪያዊ ምክንያቱማጣቀሻ እድምታዉ መድረሻችን ነዉ።
ከ ዎቹ ማብቂያ እስከ ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር ነዉ ድረስ በምጣኔ ሐብት በፍጥነት በማደግ ከዓለም ቻይናን አስቀድማ ትከተል ነበር።
የተፈጥሮ ሐብቷን ብዛት አይነት ዉበት ሥብጥሩን መዘርዘር ሲበዛ አታካች ነዉ።
የሐገሬዉ አንጡራ ተወላጅ ጉልበት ለአዉሮጳዉያኑ ሠፋሪዎች ባለመብቃቱ ወይም ባለማርካቱ የሠፋሪዎቹን ፍላጎት ለማሟላት ጥቁር አፍሪቃዉያን በባርነት በገፍ በግፍ የተጋዙትም ያኔ ነበር።
ይሁንና ፌርናንዶ ኮሎር ከሁለት ዓመት በላይ ሥልጣን ላይ አልቆዩም።
በሙስና ተጠርጥረዉ የሐገሪቱ ሕግ መምሪያ ምክር ቤት ኮንግረስ እንዲከሰሱ ወሰነባቸዉ።
ዉሳኔዉን ሕግ መወሰኛዉ ምክር ቤት ሴኔቱ እንደሚያጸድቀዉ ሲያዉቁ ሥልጣናቸዉን በፈቃዳቸዉ ለቀቁ።
በ ኛ ዓመቱ ዘንድሮ ተራዉ በሉላ ደ ሲልቫ ጠንካራ ድጋፍ ሥልጣን የያዙት የግራ ፖለቲከኛዋ የዲልማ ቫናሮዉሴፍሆነ።
ፕሬዝደንቷ በሕግ መወሰኛዉ ምክር ቤት ክስ ይመሥረትባቸዉ የሚለዉን ሐሳብ ከምክር ቤቱ አባላት ቱ ደግፈዉታል።
ሮዉሴፍ የምክር ቤቱን ዉሳኔ ዘመናይ መፈንቅለ መንግሥት በማለት አዉግዘዉታል።
የተያዘባቸዉን ሥልጣንን አለ አግባብ የመጠቀም ክስ ዉድቅ ለማድረግም እስከ መጨረሻዉ ድረስ እንደሚከራከሩም አስታዉቀዋል።
ይሁንና ምክር ቤቱ የወሰነዉን እንዳይወስን የሐገሪቱ ሕገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤት እንዲያግደዉ የፕሬዝደንቷ ጠበቆች ያቀረቡትን ማመልከቻ ፍርድ ቤቱ ዉድቅ አድርጎታል።