input
stringlengths
1
130k
ፕሬዝደንቷ ከእንግዲሕ የሚከራከሩትም ከሥልጣን እንዲታገዱ በወሰነባቸዉ ምክር ቤት ላይ ነዉ።
በዚሕም ምክንያት እስከ መጨረሻዉ የሚያደርጉት ሙግት ለድል መብቃቱ አጠራጣሪ ነዉ።
የያኔዉ የብራዚል ፕሬዝደንት ሉላ ደ ሲልቫ ግን ለአሜሪካኖች ላደሩት ለነ ቴሜር ግፊት ሴራና ዘመቻ የሚበገሩ አልሆኑም።
የዚያኑ ያክል እነ ቴሜርም ሮዉሴፍን የመሠሉ ደካማ መሪን ሾኬ መትተዉ የሠራተኛዉን ፓርቲ ከሥልጣን እስኪያስወግዱ ድረስ አድበዉ አልተቀመጡም ነበር።
ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ለመወዳደር የሪፐብሊካን ፓርቲን ዉክልና ያገኛሉ የሚባሉት ዶናልድ ትራምፕ ግን የቴሜር ትግል ለድል በመብቃቱ የሚደሰቱበት አመክንዮ የለም።
የሚመጡት ከመላዉ የደቡብ እና የላቲክ አሜሪካ ምናልባትም ከመካከለኛዉ ምሥራቅ ጭምር ነዉ።
ወደ ሰሜናዊ ሊባኖሳዊቱ ከተማ ቤታአቦዉራ በሚወስደዉ ጎዳና ላይ የተፃፈዉ የመንግድ ሥም እስካለፈዉ ሐሙስ ድረስ ምክትል ፕሬዝደንት ቴሜር የሚል ነበር።
የደስታ ኩራት ምክንያታቸዉ ፖለቲካዊ ምጣኔ ሐብታዊ ዲፕሎማሲያዊ ሐይማኖታዊም አይደለም።
ቴሜር በ እና በ የወላጆቻቸዉን የትዉልድ መንደር ጎብኝተዉ ዘመዶቻቸዉን አነጋረዉ ነበር።
ያኔ ያስተናገዷቸዉ የቅርብ ዘመዳቸዉ ኒዛር ቴሜር አሁን እደገና ሊባኖስን ቢጎበኝ ማን ያስተናግደዋል አሉ በቀደም።
ሊባኖሶች እንደ ቴሜር ተጠባባቂ እንደ ትራምፕ እጩም እንደ ኦባማ ፕሬዝደንትም የላቸዉም።
ያም ሆኖ ቴሜር ሥለ ሊባኖስ ለማሰብ አሁን ጊዜ የላቸዉም።
የመጀመሪያ ሥራቸዉ ተጠባባቂ የሚለዉን ቅፅል አዉልቀዉ ለመጣል የብራዚል ፖለቲከኞችን በዙሪያቸዉ መኮልኮል ነዉ።
እስካሁን ድረስ ከወግ አጥባቂዎቹ በተጨማሪ አቺዮ ኔቬስን የመሳሰሉ የሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ ሴናተሮች ቴሜርን ባይደግፉ እንኳን ሮዉሴፍን ስለሚጠሉ ከቴሜር የሚርቁ አይመስሉም።
ሰዉዬዉ በ በተደረገዉ የመለያ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ በፕሬዝደንት ሮዉሴፍ የተሸነፉ ናቸዉ።
ብቻ ዲልማቫና ሮዉሴፍ በቅርቡ በልዩ ክብር ተቀብለዉ ካነጋገሩት መሪ አንዱ የቡልጋሪያዉፕሬዝደንት ሮሰን አሴቭፕሌቭኔሊቭን ናቸዉ።
ሮዉሴፍ ለደሆችና ለዝቅተኛዉ መደብ የቆመዉን ግራ ዘመሙን የሠራተኛ ፓርቲ ይመራሉ።
ቴሜር ባንፃሩ ወደ መሐል ቀኝ የሚያዳላዉ ፓርቲ መሪ ናቸዉ።
ሁለቱ ፖለቲከኞች እንደ ስደተኛ ልጆችም እንደ ብራዚላዊም ፕሬዝደንትና ምክትል ሆነዉ ትልቂቱን ሐገር መምራት አልተሳናቸዉም ነበር።
በሮዉሴፍ ካቢኔ ዉስጥ አንዲት ጥቁርን ጨምሮ ስድስት ሴቶች ነበሩ።
ከሮሴፍ ጋር ብራዚልን ለ ዓመት የመራዉ የሠራተኞች ፓርቲ ከሥልጣን ተወግዷል።
እዚሕ እኛ ሐገር የተረጋጉና ጠንካራ ተቋማት አሉ እያሉ የሚናገሩ የሚሉ ሰዎች አሉ።
እኔ ለሁሉም የምናገረዉ ግን እዚሕ ሐገር የተቋማት ሥርዓተ አልበኝነት ነዉ የሰፈነዉ ብዬ ነዉ።
የጥቁር ኬንያዊዉ ተማሪ ልጅ ሥልጣን በያዙ በሰባተኛዉ ዓመት የጀርመኑ ስደተኛ ልጅ ዶናልድ ትራምፕ ሙስሊም እና ስደተኛ ባይኔ እንዳላይ ይሉ ገቡ።
የቡልጋሪያ ስደተኛዋ ልጅ ከሥልጣን ሲታገዱ የሊባኖሱ ስደተኛ ልጅ ሥልጣን ያዙ።
ሮይተርስ ዜና አገልግሎት የባንኩን ምክትል ገዢ ጠቅሶ እንደዘገበዉ የምንዛሪዉ ዋጋ የቀነሰዉ የወጪ ንግድን ለማበረታት ነዉ።
የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ሙላቱ ተሾመ ትናንት ለሐገሪቱ ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር የዉጪ ንግድን ለማበረታት የብር የምንዛሪ ዋጋ እንደሚቀንስ አስታዉቀዉ ነበር።
በአዲሱ ተመን መሠረት አንድ የአሜሪካን ዶላር ወደ የኢትዮጵያ ብር ገደማ ይመነዘራል።
ብሔራዊ ባንክ እስካሁን አምስት በመቶ የነበረዉን የወለድ መጠንም ወደ ሰባት ከመቶ ከፍ አድርጎታል።
ኢትዮጵያ ከሰባት ዓመት በፊት የብር የምንዛሪ አቅምን በ ከመቶ ቀንሳ ነበር።
አፍሪቃ የግብፅ የቀድሞዉ ፕሬዚዳት ሆስኒ ሙባረክ አረፉ የቀድሞዉ የግብጽ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
ዛሬ ማክሰኞ የካቲት ዓ ም ቀትር ላይ ሆስኒ ሙባረክ መሞታቸዉን የዘገበዉ የግብጽ መንግሥት ቴሌቬዥን ጣብያ ነዉ።
የቀድሞዉ የግብጽ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
ዛሬ ቀትር ላይ ሆስኒ ሙባረክ መሞታቸዉን የዘገበዉ የግብጽ መንግሥት ቴሌቬዥን ነዉ።
በካይሮ ሕክምና ላይ የነበሩት ሆስኒ ሙባረክ ከሳምንታት በፊት ቀዶ ጥገናን ለማካሄድ በፊርማቸዉ ማረጋገጣቸዉም ተያይዞ ተዘግቦአል።
የቀድሞዉ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ከረጅም ጊዜ ከባድ ሕመም በኋላ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
የቀድሞዉ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ በሆስፒታል አሳሳቢ የጤና ክትትል ክፍል ሕክምና ሲደረግላቸዉ ቆይተዉ በደረስባቸዉ ሕመም ሕይወታቸዉ ማለፉን ወንድ ልጃቸዉ ገልፆአል።
የግብፅ የመንግሥት ቴሌቭዥን የሆስኒ ሙባረክን ሞት ይግለፅ እንጂ በርግጥ መቼ እንደሞቱ በግልጽ ያስቀመጠዉ ነገር የለም።
ግብፅን ወደ ዓመት በፕሬዚዳንትነት የመሩት ሆስኒ ሙባረክ በጎርጎረሳዉያኑ ዓመት በሃገሪቱ በተነሳዉ አመፅ ከስልጣን መወገዳቸዉ ይታወሳል።
ህዝበ ውሳኔው ስርዓቱን የተከተለ ነው የሲዳማ ፓርቲዎች መግቢያ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
የጉብኝቱ አላማ ስለድርቁ ለለጋሽ አካላት ለማስገንዘብ ነው አውዲዮውን ያዳምጡ።
ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ኢትዮጵዊ ለዶቸ ቨለ እንደገለጹት ደግሞ ምርመራው ተጠናቆ የፍርድ ሂደቱ እስኪጀመር ከአራት እስከ ስድስት ወራት ይፈጃል፡፡
የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በሙስና ጠርጥሮ ካሰራቸዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ በርካታ ኩባንያ ያላቸዉ ሼሕ መሐመድ አል አሙዲ አንዱ ናቸዉ።
ወደፊት የህዝቡ ቁጥር እጅግ የሚንረው ደግሞ እጅግ በደኸዩት አገሮች ነው።
ይህ በፊናው ከዕድገት ጋር ባለመመጣጠን ብርቱ ሳንክ ነው የሚፈጥረው።
የህዝብ ቁጥር አለቅጥ ከፍ የሚለው ከሰሃራ በስተደቡብ በሚገኙ የአፍሪቃ ሃገራት ነው።
የተባበሩት መንግሥታት የህዝብ መመጠኛ ልዩ ድጎማ በመጀመሪያ እንደተነበየው ሳይሆን በአንዳንድ አገሮች ልጅ የመውለዱ ፍላጎት ከፍ አለ እንጂ አልቀነሰም።
መጥፎ ሁኔታ ሊያጋጥም የቻለው የቤተሰብ መምሪያ አገልግሎት ለማግኘት ስለ ከላዔ ፅንስም ማብራሪያ የሚሰጥበት ሁኔታ ተስፋ የተጣለበትን ያህል አለመስፋፋቱ ነው።
በያመቱ የተባበሩት መንግሥታት እንደሚለው በአዳጊ አገሮች ሚሊዮን ያህል ሴቶች ሳይፈልጉ ነው የሚያረግዙት።
በዓለም ዙሪያ ጥሬ ሀብቶች ውሃ የኃይል ምንጭ እንዲሁም የምግብ ዓይነቶች ይመናመናሉ ዋጋቸውም እጅጉን ውድ ይሆናል።
በሚመጡት ዓመታት የድህነትን መልክዓ ምድር በተወሰኑ ቦታዎች ጎልቶ እናየዋለን።
ይህም ውዝግብ የተስፋፋ የትጥቅ ፍልሚያ እንዲሁም ከፍተኛ የጥፋት አደጋ በሚያንዣብበትና መንሠራራት በሚያዳግትበት ደካማ አስተዳደርና የሚንገዳገድ መንግሥት ባለበት አገር ነው።
የሠለጠነ የሰው ጉልበት የማፍራቱ ተግባር በቀጣይነት መከናወን የሚገባው ጉዳይ ነው።
ብዙ ህዝብ ያላት ድሃይቱ ሀገር ኢትዮጵያ እንኳ እ ጎ አ እስከ ዜጎቿ መካከለኛ ገቢ ያላቸው እንዲሆኑ የማደረግ ዓላማ አላት።
ይሁን እንጂ በሚመጡት ዐሠርተ ዓመታት ሴቶችና ልጃገረዶች በትምህርትና ማሠልጠኛ እንዲገፉ በዛ ያለ ውች መመደብ ይኖርበታል ሲሉ ነው ሔለን ክላርክ የሚያስገዝቡት።
ሴቶችንና ልጃገረዶችን ያላሳተፈ ሀገር በአቅም ግንባታ ቢዳከም የሚያስገርም አይሆንም።
የዓለም ሥነ ህዝብ የጀርመን ድርጅት ባልደረባ ዑተ ሽታል ማይስተርም ዋናው የዕድገት ቁልፍ ትምህርት መሆኑን ነው የገለጡት።
አፍሪቃውያን የሚበጅ መርኅ ተከትለው በዚህ ረገድ ጠንክረው ከሠሩ እመርታቸው የነብር ሳይሆን የአንበሳ ሊሆን ይችላል ተብሎ ይታሰባል።
ኢሬቻ ተቃዉሞ እና ግድያ ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
የመልካሳ የምርምር ማዕከል የ ዓመት ጉዞ መግቢያ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
አፍሪቃ ዩራኒየም የገንዘብ ምንጭ የጤና ጠንቅ ዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ በተፈጥሮ ማዕድኖች የበለጸገች ናት።
በምስጢር የተያዘዉና በህገወጥ መንገድ የሚመረተዉ የዩራኒየም ማዕድን በስዉር ለተለያዩ ሃገሮች እንደሚሸጥ ነዉ የሚገለፀዉ።
ሆኖም ለኢራንና ለሰሜን ኮርያን ጭምር ሳይሸጥ እንዳልቀረ የሚጠቁም መረጃም የተመድ ይፋ አድርጓል።
ኮንጎ ዉስጥ በርካቶች በዚህ ማዕድን መጎዳታቸዉን ይገምታሉ በየጊዜዉም የተለያዩ የአካል ጉዳቶች ያሏቸዉ ህጻናት ይወለዳሉ።
ኪሚሎሎ የተሰኘዉ በካፉቡ ወንዝ ዳርቻ የሚገኘዉ አነስተኛ የሰፈራ መንደር በደቡባዊ ዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ ከሉቡምባሺ ከተማ ወጣ ብሎ ይገኛል።
የኩሬዉ ዓሶች በየጊዜዉ ይሞታሉ የአካባቢዉ ኗሪዎች ደግሞ በበሽታ ይሰቃያሉ።
ምክንያቱን ማወቅ የሚሹት የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ጃን ክላዉደ ባካ ለአስር ዓመታት ያህል የዉሃዉን ናሙና ሲወስዱ ቆይተዋል።
ስለዚህ ህገወጥ የዩራኒየም ማዕድን ስፍራ የበለጠ ለማወቅ የሚፈልግ በጣም ጥንቁቅ መሆን ይኖርበታል።
ምክንያቱም በፖለቲካዉም ሆነ በኤኮኖሚዉ ዋና የሚባሉት ሰዎች ከዚህ ህገወጥ ማዕድን ንግድ ገንዘብ ያገኛሉ።
ከሁለት ዓመት በፊት አንድ የጭነት መኪና ከተዘጋዉ የሽንኮሎብዌ የማዕድን ጉድጓድየወጣ ዩራኒየም እንደጫነ ተይዟል።
አሟሟቱ የተፈጥሮ ይሁን ይህን ታሪክ በመዘገቡ ግድያ ተፈጽሞበት ይሁን የተገኛ መረጃ የለም ፈጣሪ ብቻ ነዉ ያንን የሚያዉቀዉ።
ቁጥር የተሰኘዉ ክሊኒክ ሉቡምባሺ ዉስጥ የሚገኝ ነፍሰጡር ሴቶችን የሚያስተናግድ የህክምና ጣቢያ ነዉ።
እዚህ የምንገኝ ሃኪሞች የምንመዘግባቸዉ የከፋ የአካል ጉድለቶች እየጨመሩ ሄደዋል በተለይም የሸቀጦች ዋጋ በናረባቸዉ በ እና ዓ ም።
ፕሮፌሰር ጋብርየል ካፓያ ሽንኮሎብዌ ከሉቡምባሺ አንድ መቶ ኪሎ ሜትር የሚርቅ በዓለም ረዥም እድሜ ያስቆጠረ የዩራኒየም ማዕድን ማዉጫ ስፍራ ነዉ።
በጎርጎሪዮሳዊዉ ዓ ም ዩናይትድ ስቴትስ የጃፓን ከተሞች ሄሮሽማና ናካሳኪ ላይ የጣለችዉ አቶም ቦምብ ከዚህ ስፍራ በተገኘዉ ዩራኒየም የተሠራ ነዉ።
የዛሬ ዘጠኝ ዓመት የማዕድን ማዉጫ ስፍራዉ በይፋ ተዘግቷል አደገኛ ጨረር የሚያስከትለዉ ማዕድንም እንዳይሸጥ በህግ ተከልክሏል።
ሆኖም የአፍሪቃ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ኃላፊ ጎልደን ሚሳቢኮ በህገወጥ መንገድ ግን ድርጊቱ እንደሚፈፀም መረጃ ይፋ አድርገዋል።
አሁን የእሳቸዉን ስፍራ የያዙት ጃን ክላዉድ ባካ በዉሃና በአፈር ዉስጥ የሚገኘዉን የአደገኛ ጨረሩን መጠን መለካት ቀጥለዋል።
ኪንሻሳ ላይ በጎሮጎሪዮሳዊዉ የዘመን ቀመር ዓ ም የተገነባ በአፍሪቃ የመጀመሪያዉ የኒኩሊየር ማብላያ ይገኛል።
ያኔ ደግሞ የኮንጎ መንግስት መልሶ ዩራኒየም ማዕድን ማዉጣትን ዳግም ህጋዊ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
የሶማሊያ አቋም እነሳዉዲን አስደንግጧል ዓለም ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
አፍሪቃ የማሊ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ አሸናፊ ቡባከር ኬይታ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ኢብራሂም ቡባከር ኬይታ የማሊ ፪ኛ ዙር ፕሬዚደንታዊ ምርጫ አሸናፊ ሆኑ።
ቀደም ሲል የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን እንዳስታወቁት በከፊል በወጣው ውጤት ላይ ኬይታ ሲሴን በጉልህ የድምፅ ብልጫ በመምራት ላይ ናቸው።
ፕሬዚደንታዊወ ምርጫ በሀገሪቱ ሥርዓተ ዴሞክራሲን እና መረጋጋትን መልሶ ያስገኛል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።
እንደሚታወቀው፡ ይኸው አካባቢ በመጀመሪያየአዛዋድ ነፃ አውጪ ንቅናቄ በሚባለው ኤምኤን ኤልኤ በኋላም በተለያዬ እሥላማዊ ቡድኖች ተይዞ ነበር የቆየው።
የምርጫ ኮሚሽን በይፋ ባወጣው የመጀመሪያ ዙር ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ውጤት መሰረት፡ ኢብራሂም ቡባከር ኬይታ ሲሴ ሱማይላ ደግሞ የመራጭ ድምፅ አግኝተዋል።
ይህ በሁለተኛውም ዙር ምርጫ ብዙ መራጮችን ድምፅ አስገኝቶላቸው ለድል አብቅቶዋቸዋል።
የአዉሮጳ ሃገራት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተኅዋሲዉን አደገኝነት ተከትሎ ስርጭቱን ለማለዘብ ሲሉ የተለያዩ ዉሳኔዎችን እያሳለፉ ነዉ።
የአዉሮጳ ኅብረት መቀመጫ ብሩስል እደቀደመዉ ጊዜ በስብሰባ መጣበብ ቀርቶአል ቤልጂየም ሱቆች ሁሉ ተዘግተዋል።
ለ ቀናት የሚፀናዉ ሕግ በየሃገራቱም የተለያዩ ሱቆችን እያዘጋ ነዉ።
ፍርድ ቤቱ የዛሬ አሥር ዓመት ከተቋቋመ ወዲህ ብይን ሲያሳልፍ ይህ የመጀመሪያው ነበር።
ሉባንጋ ወደ ዴን ኻግ የተዛወሩት በ ዓም ሲሆን ችሎታቸው የተጀመረው በ ዓም ነበር።
የዴን ኻጉ ፍርድ ቤት ብይኑን በራድዮ ወይም በቴሌቪዥን በቀጥታ ያስተላልፋል የሚል ግምት ነበራቸው።
ግን ለሳተላይቱ አገልግሎት ባለመከፈሉ ዜናውን ሊያደምጡ የቻሉት በኮንጎ ከተሰማራው የተመድ ሰላም አስከባሪ ጓድ ራድዮ ነበር።
በፍርድ ቤቱ የቀረቡት አፍሪቃውያን ብቻ ናቸው አንድም አውሮጳዊ ወይም አሜሪካዊ የለም።
በኢቱሪ ተፈፀመ የሚባለውን ወንጀል ያካባቢ ፍርድ ቤት ቢመረምረው የተሻለ ይሆናል።
መንግሥታዊ ያልሆኑት ድርጅቶች ነበሩ ሕፃናቱን አግኝተው የመለመሉዋቸው፡ ያሰለጠኑዋቸው እና በመጨረሻም ሉባንጋ የመለመሉዋቸው ወታደሮች መሆናቸውን እንዲናገሩ የገፋፉዋችው።
ይህ፡ ማለትም ምስክሮች የዓቃቤ ሕጉ ቡድን ክሱን የሚደግፍለት ቃል እንዲሰጡ ተፅዕኖ አሳርፎባቸዋል የሚለው ዓይነቱ የመከራከሪያ ሀሳብ በኢቱሪ ክፍለሀገር አዘውትሮ ተሰምቶዋል።
የኮንጎ ያርበኞች ህብረት ፓርቲ በውትድርና ሲወስደኝ አሥራ ሁለት ዓመቴ ነበር ስወጣ ደግሞ አሥራ ስምንት ዓመቴ ነበር።
የተመድና መንግሥታዊ ያልሆኑት ድርጅቶች ብይኑ በጎሳዎች መካከል ግጭቱን እንደገና ይቀስቅስ ይሆናል በሚል ሰግተው ነበር።