input
stringlengths
1
130k
እንደ አጀማመሩ ከዘለቀም በሻምፒዮንስ ሊግ ፍልሚያ ከሪያል ማድሪድ ጋር በሚያደርገው ጨዋታም አይበገሬ ሊሆን ይችላል ተብሏል።
በሳምንቱ መጨረሻ በተደረጉ የእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ የእግር ኳስ ግጥሚያዎች እንደ ማንቸስተር ሲቲ ኃያል በትር የሰነዘረ ቡድን የለም።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከአሜሪካ የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግ ተጨዋቾች ጋር እሰጥ አገባ ገብተዋል።
ፕሬዚዳንቱ ደግሞ ተጨዋቾቹ ይሰናበቱልኝ ጥሪ በተለመደው የትዊተር ገጻቸው አስተጋተዋል።
ኬኒያዊው ውድድሩን በአንደኛነት ያጠናቀቀው ሰአት ከ ደቂቃ ከ ሰከንድ በመግባት ነው።
ጉዬ አዶላ ለጥቂት በ ሰከንዶች ብቻ ተቀድሞ ሁለተኛ ደረጃ ማግኘት ችሏል።
የሦስተኛ ደረጃን በ በመሮጥ የተቆናጠጠው ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሞስነት ገረመው ነው።
በሴቶች የበርሊን ማራቶን የሩጫ ፉክክር ኢትዮጵያዊቷ ሩቲ አጋ በ ሰከንዶች ብቻ ተቀድማ ሁለተኛ ደረጃን አግኝታለች።
የሀገሯ ልጅ ቫለሪ አያባይ ብርቱ ፉክክር በማድረግ በሩቲ አጋ ለጥቂት በ ሰከንድ ተበልጣ ሦስተኛ ኾናለች።
እግር ኳስ በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ የሳምንቱ መጨረሻ ግጥሚያዎች እንደ ማንቸስተር ሲቲ ኃያል ብትሩን ያሳረፈ ቡድን የለም።
ማንቸስተር ሲቲ ክሪስታል ፓላስን አይቀጡ ቅጣት የቀጣው ለ በሆነ ሰፊ ልዩነት በማሸነፍ ነው።
ቸልሲም የግብ ክልሉን ሳያስነካ ስቶክ ሲቲን ለ ኩም አድርጎ ሸኝቷል።
ሊቨርፑል ላይስተር ሲቲን ለ ሲረታ ማንቸስተር ዩናይትድ ሳውዝሐምፕተንን ያሸነፈው ለ ነው።
ሊቨርፑል የቅዳሜ ድሉ ለአራት ጊዜያት ድል አልባ የነበረው ጉዞውን ቀይሮለታል።
ከ ዓመታት ወዲህ ደግሞ ከሜዳ ውጪ በተደረጉ ተከታታይ ጨዋታዎች ግብ ሲቆጠርበት የመጀመሪያው ኾኗል።
በቅዳሜው ሌላ የፕሬሚየር ሊግ ጨዋታ ዋትፎርድ ስዋንሲ ሲቲን ለ አሸንፏል።
ትናንት በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ብሪንግቶን ኒውካስልን ለ በማሸነፍ በአንድ ደረጃ መሻሻል አሳይቷል።
ቡንደስ ሊጋ በጀርመን ቡንደስሊጋ ስድስት ጨዋታዎች ቦሩስያ ዶርትሙንድ መሪነቱን አስጠብቋል።
በተለይ ቅዳሜ ዕለት ቦሩስያ ሞይንሽን ግላድባኅን ለ በኾነ ሰፊ ልዩነት ማሸነፍ ችሏል።
በዚህ አያያዙ ቦሩስያ ዶርትሙንድ በነገው የሻምፒዮንስ ሊግ ግጥሚያ ለስፔኑ ኃያል ሪያል ማድሪድ ብርቱ ተገዳዳሪ መኾኑ አይቀርም።
ይህን ብቃት ታዲያ አሁን መተግበር የሚጠበቅባቸው በሻምፒዮን ሊጉ የሚገጥሙት የስፔኑ ኃያል ሪያል ማድሪድ ላይ ነው።
በሲግናል ኢንዱንዳ ስታዲየም የሚገናኙት ሁለቱ ኃያላን ቡድኖች ከባድ ፉክክር ያሳያሉ ተብሎ ተጠብቋል።
ሁለቱ ቡድኖች በስድስት የውድድር ዘመኖች ለአምስት ጊዜያት ተገናኝተው ያውቃሉ።
በአጠቃላይ ውድድሩ ሪያል ማድሪድ በጠበበ መልኩ ቦሩስያ ዶርትሙንድን ይበልጣል።
ከሪያል ማድሪድ ጋር በሜዳው ባደረጋቸው ግጥሚያዎች እስካሁን ድረስ አንድም ጊዜ ተሸንፎ አያውቅም።
ዶርትሙንድ በሜዳው ሪያል ማድሪድን ለሦስት ጊዜያት ያሸነፈ ሲሆን ሦስት ጊዜ ደግሞ አቻ መውጣት ችሏል።
የሳምንቱ ማሳረጊያ ቦሩስያ ሞይንሽን ግላድባኅን ለ ያንኮታኮተው ቦሩድያ ዶርትሙንድ እስካሁን በድል ጎዳና ላይ እየተረማመደ ነው።
ከስድስት የቡንደስ ሊጋውእ ግጥሚያ አምስቱን ድል በማድረግ አንዱን አቻ ወጥቷል።
በደርጃ ሠንጠረዡ ነጥብ የሰበሰው ቦሩስያ ዶርትሙንድ ግቦችን የግብ እዳ አስተናግዷል።
በዋናነት ተቃውሞውን ያሰሙት ስፖርተኞች የአሜሪካ የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግ ተጨዋቾች ናቸው።
ፕሬዚዳንቱ በበርካታ ስፖርተኞች የተዛመተው እና ከጨዋታ በፊት የብሔራዊ መዝሙሩ ሲሰማ የሚታየው ተቃውሞ ከዘር ጋር አንዳችም ግንኙነት የለውም ብለዋል።
ትናንት በተከናወኑ ጨዋታዎች ብቻ ተጨዋቾች አንድም በአንድ እግራቸው ሸብረክ ብለው በመንበርከክ አለያም እጅ ለእጅ በመያያዝ ተቃውሟቸውን ፕሬዚዳንቱ ላይ አንፀባርቀዋል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው ታላቅ የኔነት ስሜት ለብሔራዊ መዝሙራችን እና ለሀገራችን።
እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር ከ ወዲህ ስፖርተኞች በስፋት እና በጋራ ያሳዩት ተቃውሞ ተብሎለታል።
ሁሉም የሻምፒዮንስ ሊግ ግጥሚያዎች በተመሳሳይ ሰአት ከምሽቱ ሰአት ከ ደቂቃ ነው የሚከናወኑት።
ገዜልሻፍት ፊውር በድሮተ ፈልከር የተባለው ድርጅት እንዳመለከተው ስደተኞቹ ይመለሱ በሚባልባት ኤርትራ ውስጥ አሁንም ግዙፍ የሰብዓዊ መብት ረገጣ ይታያል።
የአውሮጳ ህብረት ሁኔታውን በመመርመር ፈንታ ለምንድን ነው አንዳንድ ጥሪ በማቅረቡ ላይ ብቻ ራሱን የሚገድበው
በኤርትራ እና በኢትዮጵያ መካከል ባለው ውዝግብ ላይ አዘውትረው የኢትዮጵያ መንግሥትን አቋም ነው የሚወስዱት።
እና የኤርትራ መንግሥት አመራር ራሱን ያገለለበትን ርምጃ እየደገፉ ነው።
ለዚህ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ለቀጠለው መጥፎ ውዝግብ ከኤርትራ አመራር ጋር የይስሙላ ያልሆነ ግንኙነት እንዲፈጥሩ ከማሳሰብ አልቦዘንም።
በመሆኑም በውዝግቡ መንሥዔ ላይ በማትኮር መፍትሔ መሻቱ ትርጉም ይኖረዋል።
አዎ ምክንያቱም በእጃችን ያሉትን መረጃዎች ስንመለከት የዴንማርክ የስደተኞች ጉዳይ መስሪያ ቤት ተሻሽሎዋል በሚል ያወጣው ዘገባ መሠረተ ቢስ ነው።
ውሳኔው ስደተኞችን ወደሀገራቸው መመለስ የሚያስችል ሁኔታ አለመኖሩን የሚያሳይ ነው።
ስደተኞች የመቀበል አለመቀበል ጉዳይ ለአውሮጳ በጠቅላላ ችግር በመሆኑ በዜርትራ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ለሚሻሻልበት ጉዳይ ትኩረት ሊሰጥ ይገባዋል።
በትናንቱ ምርጫ በመቶ ድምጽ በማግኘት ያሸነፈው ፓርቲያቸው ሲሪዛ ነፃይቱ ግሪክ በአህፅሮቱ ከተባለው ፓርቲ ጋር ተጣምሮ መንግሥት እንደሚመሰርት ተገልጿል ።
በእሁዱ ምርጫ ወግ አጥባቂው አዲስ ዲሞክራሲ በመቶ ድምፅ በማግኘት ሁለተኛውን ደረጃ ይዟል ።
የናዚ አስተሳሰብ የሚያራምደው ጎልድን ዶውን የተባለው ፓርቲ በመቶ ድምፅ በማሸነፍ ተኛ ደረጃ አግኝቷል ።
በእሁዱ ምርጫ ከ ግሪካውያን ከ በላይ የሚሆኑት ድምጻቸውን እንዳልሰጡ ተዘግቧል ።
ስለ ግሪክ ምርጫና አንድምታው የብራሰልሱ ወኪላችን ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል ።
የሶማሌ ክልላዊ መንግሥት ሶስት የገጠር ቀበሌዎች ወደ አፋር ክልል እንዲተላለፉ ከአመታት በፊት የተላለፈውን ውሳኔ ውድቅ ያደረገው በትናንትናው ዕለት ነበር።
ውሳኔው የአካባቢውን የጸጥታ ሁኔታ ላይ ስለሚያሳድረው ተጽዕኖ የተጠየቁት አቶ አብዱላሂ መጀመሪያም በሕገ መንግሥቱ አግባብ አይደለም የተካሔደው።
በአካባቢው የሚኖሩት አፋር እና ሶማሌ የግጦሽ መሬት ለመቆጣጠር በሚያደርጉት ፉክክር ግንኙነታቸው ለዓመታት ሻክሮ ቆይቷል።
የሶማሌ ክልል ካሳለፈው ውሳኔ በኋላ የፌድራል መንግሥቱም ይሁን የአፋር ክልል በይፋ እስካሁን ያሉት ነገር የለም።
የትግራይ ክልል ምክር ቤት ውሳኔ በምሁራን እይታ ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ቀዉስ መንስኤና መፍትሔዉ የኢትዮጵያ መሪዎች አዲስ አበባ ዉስጥ ይሰበሰባሉ ይነጋገራሉ ይናገራሉም።
በሐገሪቱ ሠላም እንደሚያስከብሩ ጦር ሠራዊታቸዉን ይወዳል ያሉትን ሕዝብ ደሕንነት እንደሚያስጠብቁ ልማትን እንደሚያፋጥኑ ይደሰኩራሉ።
የሰላም ደሕንነቱ ቃል ተስፋ ጭናቅሰን አይደለም ጫንጮ ሳይደርስ የወለፊንድ የመባረቁ ሐቅ እንጂ ሕቅታዉ።
ከአምቦ እስከ ጭሮ ከጂጂጋ እስከ ቦሎ ዴዴሳ ሰዎች እየተገደሉ እየታሰሩ እየታገዙ መቶ ሺዎች እየተሰደዱ ነዉ።
ሐብት ንብረት ወድሟል ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ የሸቀጦች ዝዉዉር ተገድቧል መተማመን ጠፍቷል።
የቀድሞዉ የኢትዮጵያ መንግሥት ደርግ የተቃዋሚዎቹን ጩኸት ጥያቄ ለማጣጣል በጫጫታ የፈረሰች ሐገር ብትኖር እያሪኮ ብቻ ናት በሚል መግለጫ ያኪያኪስ ነበር።
የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ መስራች እና የቀድሞ መሪ ዶክተር አረጋዊ በርሔ ቀዉሱን አስጊ ይሉታል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፌደራሊዝም ጉዳይ መምሕር ናሁሰናይ በላይ እንደ ሂሳብ ያሰሉታል።
ዶክተር አረጋዊ የረጅም ጊዜ ተደራራቢ ችግር ዉጤት ነዉ ባይ ናቸዉ።
ካቢኔ ሽሮ አዲስ ሾሟል ጥልቅ ያለዉን ተሐድሶ ማድረጉን አስታዉቋል ወራት የቆየ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንግጓል ሁነኛ መፍትሔ ግን እስካሁን የለም።
አቶ ናሆሰናይ በዴሞክራሲ እጦት ተፈጠረ ያሉት ችግር ከተፈጠረ በኋላም ዴሞክራሲያዊ መፍትሔ አልተሰጠም ይላሉ።
አቶ ናሁሰናይ ተጠያቂነት የሚሰማዉ ባለሥልጣን አለመኖሩ ነዉ ባይ ናቸዉ።
በኢሕአዲግ መሪዎች መካከል ሽኩቻ አለ የሚለዉን ግምትም የሚጋሩ ይመስላሉ።
ፈረንሳሲዉ ጋዜጠኛ እና የፖለቲካ ተንታኝ ሬኔ ለፎ በቅርቡ እንደ ፃፈዉ ደግሞ በኢሕአዴግ ነባር እና አዳዲስ መሪዎች መካከል መግባባት ያለ አይመስልም።
በጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የሚመራዉ ካቢኔ ሐገሪን ሙሉ በሙሉ ማስተዳደሩን ይጠራጠራል።
ዶክተር አረጋዊ በርሔ ግን ጉዳዩን ሰፋ አድርገን ማየት አለብን ባይ ናቸዉ።
የሐገሪቱን ፖለቲካዊ ሥርዓት በመዘወሩ ሒደት የኃያላን እጅም አለበት እንደ አንጋፋዉ ፖለቲከኛ።
አቶ መለስ ለሁለተኛ ጊዜ ኪጋሊን ሲጎበኙ ትንሽቱ ሐገር የትልቅ ጥፋትዋን ማቅ እንዳጠለቀች በዓለም አደባባይ ብቅ ያለችበት ጊዜ ነበር።
አቶ መለስ በያኔዉ የሩዋንዳ ምክትል ባሁኑ ፕሬዝደንት ፖል ካጋሚ ጋባዥነት አዲስ ለተከፈተዉ ለኪጋሊ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ንግግር አደረጉ።
አሰቃቂዉን ግፍ አንስተዉ እንዳትረሱት ግን ይቅር በሉ አሉ ኢትዮጵያዊዉ መሪ አዳራሹን ላጨናነቀዉ ተማሪ ።
ጠንካራ መሪዋን ከሸችበት ጊዜ ጀምሮ ግን እሳቸዉ ብሔራዊ ካሉት ዓይነት ትልቅ ቀዉስ ዉስጥ ናት።
አሸባሪ ፀረ ሠላም የጎረቤት መንግሥታት ተላላኪ እየተባለ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችዋን ጋዜጠኞችዋን የመብት ተሟጋቾችዋን የኃይማኖት መሪዎችዋን ወሕኒ መወርወሩም የተከረዉ የለም።
አውሮጳ ጀርመን የጋናዉ ፕሬዝደንት የጀርመን ቆይታ የጋና ፕሬዝደንት ናና አኩፎ አዶ ጀርመንን በመጎብኘት ላይ ናቸው።
የጀርመን እና የጋና መሪዎች በዋናነት የኤኮኖሚ ትብብር ላይ ያተኮረ ዉይይት ቢያካሂዱም ሕገ ወጥ ስደትንም በመዋጋቱ ላይ በጋራ ለመሥራት ተስማምተዋል።
ሆኖም ሊደረግ የነበረዉን ወታደራዊ አቀባበል ግን በዚሁ ምክንያት ቀርቷል።
ጋና በምዕራብ አፍሪቃ የአርአያነት ገፅታ የገነባች ሀገር መሆኗን የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ገልጸዋል።
ሁለቱም ፖለቲከኞች በሀገራቱ መካከል የኤኮኖሚ ትብብሩን ማስፋት እንደሚፈልጉ አመልክተዋል።
ከጀርመንም ሆነ ከሌሎች የበለፁ ሃገራት ጋር የሚኖረን ትስስር ከእርዳታ ይልቅ በንግድ እና በመዋዕለ ንዋይ ፍሰት ላይ እንዲሆን እንፈልጋለን።
እርዳታ የመቀበሉ ዘመን ለአገሮቻችን ልማት ጠቃሚ አልነበረም ብለን እናስባለን።
ይህም ድጋፍ የመፈለግ አስተሳሰብን ፈጥሯል ይህ ደግሞ እኛን አልጠቀመንም።
ሁለቱም ሃገራት የዉጭ የግል ባለወረቶች ትኩረት ወደ አፍሪቃ ቢሳብ ይሻሉ።
ጀርመን የቡድን ፕሬዝደንት በነበረችበት ወቅት የመሠረተችዉ ኮምፓክት አፍሪቃ የተባለዉ የትብብር መድረክ ይህንኑ እንዲያመቻች የተቀየሰ ነው።
ከፕሬዝደንት አኩፎ አዶ ጋር ከተነጋገሩ በኋላም ሜርክል የጀርመን የግል ባለወረቶች ወደጋና እንዲሄዱ ለማድረግ እያበረታቱ እንደሆነ ገልጸዋል።
የጋና የፋይናስ ሚኒስትር ኮምፓክት ስኬታማ እንዲሆን አብሮ በመሥራት ላይ ይገኛል በተለይም ጋና ዉስጥ አስፈላጊ ማሻሻያዎችን በማድረግ ረገድ ማለት ነው።
በእኛ በኩልም የጀርመን የግል ባለሃብቶች ወደጋና በመሄድ ፕሮጀክቶቻቸዉን ተግባራዊ እንዲያደርጉ በመገፋፋት ላይ ነን።
ሜርክል አክለውም በመጪዉ የመፀው ወራትም የኮምፓክት አፍሪቃ አባል ሃገራት በዚሁ ጉዳይ ይመክሩ ዘንድ በርሊን ላይ ስብሰባ እንደሚጠሩም ከወዲሁ አስታዉቀዋል።
እስካሁን ግን በዚህ ረገድ ስብስቡ ያከናወነው ተጨባጭ ነገር የለም።
የጀርመን የአፍሪቃ ፖሊሲ በዚህ ስብስብ ላይ ነፍስ እንዲዘራበት በአፍሪቃ የጀርመን የንግድ ማኅበረሰብ ማኅበር ሊቀመንበር ሽቴፈን ሊቢንግ አሳስበዋል።
የጀርመን የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት አፍሪቃ ዉስጥ ለሚንቀሳቀሱ ኩባንያዎች ከመንግሥት የተሰጠ ተጨማሪ ዋስትና የለም ሲል ይወቅሳል።
ፌደራል ጀርመን መንግሥት በዚህ ላይ ቃል ቢገባም ከምርጫ ጋር በተያያዘዉ ረዥም ጊዜ በወሰዱ የዉስጥ ፖለቲካዉ ምክንያት እንስካሁን ተግባራዊ አልሆነም።
በጋናም በኩል ቢሆን መንግሥት ሊሠራቸዉ የሚገባ በርካታ ነገሮች አሉ።
ከምንም በላይ የኃይል መቆራረጥ ሙስና እና የሠራተኞች ዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ የዉጭ ባለሃብቶች ላይ ፍርሃት ፈጥሯል።
ከኤኮኖሚ ጉዳዮች በተጨማሪም ሁለቱ መሪዎች ስደትን ለመከላከል በጋራ ለመሥራትም ተስማምተዋል።
የጋናዉ መሪ ወጣቶች በስደት እና ሜዲትራኒያን ባህርን በማቋረጥ አቅማቸዉን ከሚያባክኑ የበለፀገች ሀገር በመገንባቱ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
ጀርመን የጥገኝነት ጥያቄያቸዉ ተቀባይነት ያላገኘ የጋና ዜጎች ወደሀገራቸዉ የሚመለሱበትን ሁኔታ እያፋጠነች ነው።
ሜርክል ይህን አስመልክተዉ ባለፈዉ ታኅሳ ወር እንዲህ ነበር ያሉት በግዳጅ ከመመለሱ አስቀድሞ በፈቃደኝነት የሚመለሱትን እናበረታታለች።