input
stringlengths
1
130k
የዚህ ህግ ዓላማ ሰርቢያ ቦስኒያና ሌሎች ሃገራትን የተረጋጉና አስተማማኝ ከሚባሉ ሃገራት ዝርዝር ውስጥ ማስገባት ነው ።
ይህ ከተደረገም ከነዚህ ሃገራት የሚመጡ የተገን ጥያቄ ማመልከቻዎችን ወዲያውኑ ውድቅ ለማድረግ ይቻላል ።
ለስደተኞች መብት ተቆርቃሪው ድርጅት ምክትል ሃላፊ ቤርንት ሜሶቪክ ይህ ትርጉም የለሽ አሰራር ነው ይላሉ ።
ጀርመን ተገን እንዲሰጣቸው ከሚጠይቁት መካከል የተሻለ እድል ያላቸው ሶሪያውያን ናቸው ።
በጥብቅ መስፈርት ተመርጠው እስካሁን ጀርመን የገቡት ግን ብቻ ናቸው ።
ከዚህ በተጨማሪም በሌሎች መንገዶች ጀርመን የገቡ የሶሪያ ስደተኞች ጥገኝነት እንዲሰጣቸው አመልክተዋል ።
የሶሪያ ስደተኞች ጀርመን ከሚገኙት ተገን ጠያቂዎች ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛሉ ።
የተገን ጠያቂዎቹ ብዛትና ጀርመን ልትቀበል ቃል የገባችው የሶሪያ ስደተኞች ቁጥር የሚመጣጠን አይደለም ።
ሁሌም ወደነርሱ የምንጠቁማባቸው ሌሎቹ ቁጥሩ ሊታመን የማይችል ስደተኛ ጫንቃቸው ላይ ተጭኗል ።
ከኛ በኤኮኖሚ እጅግ ደካማ በሆኑ ጎረቤት ሃገራ ከሁለት ሚሊዮን የሚበልጡ ስደተኞች አሉ ።
እኛ ደግሞ ምን ማድረግ እንችላለን ብለን ራሳችንን መጠየቅ አለብን ።
አንዳንድ ጀርመናውያን አስተያየት ሰጭዎች ጀርመን ስደተኞች በብዛት ከተቀበለች ጫናው ይከብዳታል ሲሉ ስጋታቸውን ይገልፃሉ ።
ሪኮቭስኪ ግን ለዚህ መልስ የሚሰጡት እጎአ ከ እስከ በተካሄደው የቦስኒያ ጦርነት ወቅት ጀርመን የተቀበለቻቸውን ስደተኞች ብዛት በማስታወስ ነው ።
በወቅቱ ጀርመን ግጭት ከተከሰተበት ከዚህ አካባቢ ከ ሺህ በላይ ስደተኞችን ተቀብላለች ።
ይህ አሃዝ ሪኮቭስኪ እንዳሉት በ ጀርመን ተገን እንድትሰጣቸው ከጠየቁት ስደተኞች በሶስት እጥፍ ይበልጣል ።
በሌላ በኩል ጀርመን ህጋዊ ሰነድ የሌላቸው ሺህ የሚደርሱ የውጭ ዜጎች የሚገኙባትም ሃገር ናት ።
ከዛሬ ነገ ወደ ሃገራችን እንባረራለን ከሚል ስጋት ጋር የሚኖሩት እነዚህ ሰዎች በሃገሪቱ ምንም መበት የላቸውም ።
ማርያ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ስትንቀሳቀስ ጥንቃቄ ተለይቷት አያውቅም ።
ባቡር ከተሳፈረች ትክክለኛውን ቲኬት ይዛ ነው መንገድ ስታቋርጥ እንኳን መኪና የለም ብላ ቀይ መብራት ጥሳ አታልፍም ።
በቀን ሰዓት ወለልና መፀዳጃ ቤቶችን በምታጸዳበት የስራ ቦታዋ እረፍት አታውቅም ።
በቂ ደሞዝ ባታገኝም ሁሌም በሰዓቱ በሥራ ገቦታዋ ላይ የምትገኝ አንድም ቀን አመመኝ ብላ የማታውቅ ታታሪ ሴት ነበረች ።
ዋናው ባቡር ጣቢያ ስትደርስ እንደ አጋጣሚ ፖሊሶች የሰዎችን ህጋዊነት ለማረጋገጥ መታወቂያ ሲጠይቁ ትደርሳለች ።
ማርያ ባለፉት ዓመታት ያለ ህጋዊ ሰነድ ነበርና የምትኖረው ተፈላጊውን ማስረጃ ማቅረብ አልቻለችም ።
በዚህ አጋጣሚ የተያዘችው የአንዲት ልጅ እናት ማርያ ከልጅዋ ጋር ወደ ሃገርዋ ተጠርዛ ተልካለች ።
ልጅዋንና ርስዋን በህክምና ይረዱ ቦን የሚገኝ የግብረ ሰናይ ድርጅት ባልደረቦች ጀርመንን ለቃ ከመሄዷ በፊትም ተሰናብታቸዋለች ።
የድርጅቱ ምክትል ሃላፊ ኡልሪሽ ኮርትማን በጀርመን የማርያን መሰል ህይወት የሚገፉ ስደተኞች ህይወት አስቸጋሪ መሆኑን ያስረዳሉ።
ግን በድብቅ መኖር ግዴታዋ ነበር ያልተከፈለበት የመጓጓዣ ቲኬት በባቡር ውስጥ ይዞ መገኘት ከሃገር እስከመባበረር የሚያደርስ ትልቅ አደጋ አለው ።
እናም ዘወትር እያዛለሁ ወይም ተቆጣጣሪዎች ይደርሱብናል በሚል ስጋት ይኖራሉ ።
ለህክምና አገልግሎት የሚሆን ገንዘብ የላቸውም ጀርመን ውስጥ ያለ ገንዘብ ምንም ማድረግ አይቻልም ።
ወይዘሮዋ እና ሌሎች ባልደረቦቻቸው ስደተኞቹን ሊረዷቸው ከሚፈልጉ ሃኪሞች ጋር ያገናኟቸዋል ።
የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውም ሰዎች የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ እንፈልጋለን ።
የዛሬ ዓመታት ሲመሰረት ይህን ያህል እድሜ ይኖረዋል የሚል ግምትም አልነበረም ።
በግብረ ሰናዩ ድርጅት ስር በልዩ ልዩ የህክምና ዘርፎች አገልግሎት የሚሰጡ ዶክተሮች ታቅፈዋል ።
እነዚህ ሃኪሞች የጤና ኢንሹራንስ የሌላቸውን ሰነድ አልባ ስደተኞች ያክማሉ ።
የድርጅቱ ምክትል ሃላፊ ኡልሪሽ ኮርትማን እንደሚሉት አንዳንዴ የስደተኞቹ የጤና ችግር ከባድ ከሆነ መንግስት አስተያየት ሊያደርግላቸው ይችላል ።
በተግባር እስካሁን እንደታየው ከባድ ህመም ያለባቸው ሰዎች ከሃገር እንዲወጡ አይገደዱም ።
እነዚህ ስደተኞች በአንድ አጋጣሚ በተቆጣጣሪዎች እጅ ከወደቁ የማርያ እጣ ሊገጥማቸው ይችል ይሆናል ።
የ መልዕክቶቻችሁን በ ፃፉልን ኤሚላችን ነው በስልክ መልዕክት መተው የምትፈልጉ ደግሞ ቁጥራችን ነው ።
ዓለም ኢትዮጵያውያን ሐጃጆች በሳዑዲ አረቢያ የኢድ አል አደሐ አረፋ በዓል በነገው ዕለት ይከበራል።
ጠቅላይ ምኒስትር አብይ አሕመድ ለመላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ኢትዮጵያውያን ሐጃጆች በሳዑዲ አረቢያ የኢድ አል አደሐ አረፋ በዓል በነገው ዕለት ይከበራል።
ሳዑዲ አረቢያ የሚገኘው ነብዩ ሲራክ ደግሞ የዕምነት ግዴታቸውን ሊወጡ መንገድ የገቡ ሐጃጆችን አነጋግሯል።
የሁለት ሀገራት ምርጫ ታሕሳስ ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎርጎሪያዉያን አቆጣጠር ነዉ ጋምቢያዎች የወደፊት ፕሬዝደንታቸዉን መረጡ።
የምርጫዉ ሒደት ዉጤት አንድነት ተቃርኖዉ ያፍታ ዝግታችን ትኩረት ነዉ።
መልከዓ ምድራዊ ካርታዋን ትኩር ብሎ ያየ የብሪታንያ እና የፈረንሳይ ቅኝ ገዢዎች ሽኩቻ ዉጤት መሆንዋን ለማወቅ ሌላ ምርምር አይጠይቀዉም።
ካርታዉን ከባሕሩ ወደ ምድሩ ሲመለከቱ በቀድሞዋ የፈረንሳይ ቅኝ ተገዢ ሴኔጋል ላይ ያረፈ የአንድ እግር ፈለግ ትመስላለች።
ወይም አካሉን ባሕር ዉስጥ ደብቆ መላሱን ሴኔጋል ላይ የጎለገለ ሰዉ ወይም እንስሳ።
ሴኔጋል ራስዋን ደረቷ ላይ አስደግፋ እግሯን ባሕሩ ዉስጥ ነክራ የተቀረ አካሏን በሁለት ክንዶችዋ ታቅፋ የምታጥባት ሕፃን ትመስላለች።
ጋና በቆዳ ስፋትም በሐብትም በሕዝብ ብዛትም ጋምቢያን ከአስር ጊዜ በላይ ታጥፋታለች።
የቀድሞዋ የወርቅ ጠረፍ ጎልድ ኮስት የ ሚሊዮኖች ሐገር ናት።
ጋና ቀደም ጋምቢያ ከተል ብለዉ ሁለቱም በ ዎቹ ከቅኝ ገዢያቸዉ ነፃ ወጡ።
ሥለ ነፃነት ገድል ድል ታሪካቸዉ ሲያወሩ ጋናዎች ክዋሚ ንኩሩማን ይዘክራሉ።
ጋናዎች በመፈንቅለ መንግሥት በአመፅ ሁከት ሲተራመሱ ጋሚቢያዎች በየአምስት ዓመቱ እንዴ መሪ እና እንደራሴዎቻቸዉን እየመረጡ ቀዝቃዛዉን ጦርነት ዘመን ተሻገሩ።
በሁሉም ምርጫ የሚያሸንፈዉ ግን ዳዋድ ጃዋራ የሕዝብ ዕድገት ያሉት ፓርቲያቸዉ ነበር።
የጋምቢያ ሕዝብ በጣሙን ጦር ሐይሉ ብዙ ዘግይቶ ከጋና እና ከብዙዎቹ የአፍሪቃ ሐገራት የተማረዉን ገቢር አደረገ።
የመጀመሪያዉን መፈንቅለ መንግስት የመሩት መቶ አለቃ ያሕያ አብዱል አዚዝ ጄሙስ ጁንኩንግ ጃሜሕ የትሺቱ ሐገር ሁለተኛ መሪ ሆኑ።
ምክንያቱም ይሕ ከመላዉ ዓለም በጣም ግልፅና የማይጭበረበር ምርጫ ነዉ።
ምርጫ እንዲደረግ የወሰነዉም የሚመራችሁን ሰዉ ማንነት የምትወስኑት እናንት የጋምቢያ ሕዝብ በመሆናችሁ ነዉ።
ተቃዋሚዬ በአንድ ድምፅ እንኳን ቢበልጠኝ ምርጫዉ ነግልፅ እስከሆነ ድረስ ዉጤቱን እቀበላለሁ።
የምርጡኝ ዘመቻዉ የተፎካካሪዎች አሰላለፍ የድምፅ አሰጣጡ ሒደትም ታዛቢዎች እንደመሰከሩት የጋምቢያም የጋናም ተመሳሳይ ነበር።
እንደ ምርጫዉ ጊዜ ሁሉ ዉጤቱ ቀደሞ የታወጀዉ ግን ከባንጁል ነበር።
ከተሰጠዉ ድምፅ ዉን ድምፅ በማግኘት አዳማ ቦሮዉ የጋምቢያ ሪፐብሊክን በፕሬዝደትነት እንዲያገለግሉ መመረጣቸዉን አስታዉቃለሁ።
ጃሜሕ ቤተ መንግሥት የገቡበትን ስምንተኛ ዓመት ሲያከብሩ ፖለቲካ የማያዉቁት የዕድሜ አቻቸዉ ያሁን ተቀናቃኛቸዉ ወደ ብሪታንያ ተሰደዱ።
የድሮ የሐገራቸዉ ቅኝ ገዢዎች ያሉ ያደረጓቸዉ ወይም ያደረጉላቸዉ አይታወቅም።
ድላቸዉ ሲታወጅ ደግሞ ከትራምፕ በላይ አስደናቂ ዉጤት እያሉ አደነቋቸዉ።
የፖለቲካ ተንታኞች ባሮዉን የ ዓመቱን አምባ ገነን ገዢ ያንበረከኩ የማይደፈረዉን የደፈሩ እያሉ አወደሷቸዉ።
ትንሺቱ ዓመት በአምባገነን የብረት ጡንቻ ስትገዛ የኖረችዉ ጋምቢያ ያስተናገደችዉ ምርጫ በቅርቡ ዩናይትድ ስቴትስ ከተደረገዉ ምርጫም የበለጥ ሽግግር ነዉ የሚመስለዉ።
የምዕራባዉያንን መርሕ ባደባባይ በማጋለጥ በመዝለፍ መሳደብ የሚበልጥ እና በቅርቡ ዘመን የሚቀድማቸዉ ከነበረ።
የምዕራባዉያን ጃሜሕን የሚጠሉ ዜጎቻቸዉ ለዉጥ የፈለጉ ምናልባትም የአዳማ ባሮዉን ትኩረት መሳብ የሚሹ ሁሉ እንጂ።
በፌስታ ፈንጠዝያዉ መሐል ጋምቢያዊዉ አንጋፋ ድምፃዊ ጃሊብ ኩያቴሕ ባንድ ወቅት ሐገሬን ስጠራ አፍሬ ነበር አለ።
ባንጁል የ ዓመት ገዢዎችዋን አንገት አስደፍታ አሸናፊዎችን ሥታስቦርቅ አክራ የምርጫ ዉጤትዋን አወጀች።
አሁን በሥልጣን ላይ ያሉትን ፕሬዝደንት ጆን ድራማኒ ማሐማን በከፍተኛ የድምፅ ልዩነት አሸነፉ።
የአኩፎ አዶ ደጋፊ አድናቂዎች በተገኘዉ ዉጤት መፈንደቅ መቦረቃቸዉ አልቀረም።
ፍንደቃ ቡረቃዉ ግን እንደ ጋምቢያዎች ተሸናፊዉን በማዉገዝ መዝለፍ መወረፍ ላይ ያተኮረ አልነበረም።
ስለዚሕ አዲሱ መሪ በጋራ ሆነን እንድንታገል የሚያስተባብረን መሆን አለበት።
ያም ሆኖ ሁሉም ተመሳሳይ መልዕክት ወይም አቋም አለዉ ማለት አይደለም።
ጋና ጋምቢያ ናጄሪያ ሆነ ኢትዮጵያ ለመጥፎ ይሁን ለጥሩ የአብዛኛዉን ሕዝብ አስተሳሰብ የሚቀርፁ የሚቀይሱ አቅጣጫ የሚያመለክቱትም አንድም መሪዎቹ ሁለትም አዋቂዎቹ ናቸዉ።
አሸናፊነታቸዉ በታወጀ በሳልስቱ የ ዓመቱን ገዢ ያስጠነቅቁ ያሳሰቡ ለማዘዝም ይንጠራሩ ገቡ።
በሥልጣን ላይ ያለዉ መንግሥት የፖለቲካ እስረኞቹን መፍታት አለበት አሉ።
ይሕን ካደረጋችሁ ሥልጣን ስትለቁ ጥሩ የንግድ ምልክት ትታችሁ ትሔዳላችሁ።
በስልጣን ላይ ያለዉን መንግስት ባለሥልጣናት ፍርድ ቤት እንደሚያቀርቡ ዛቱ።
ጋምቢያ በጃሜሕ ዘመን የገባባቻቸዉን ዓለም አቀፍ ዉሎች ዳግም እንደሚያጤኑት አስታወቁ።
ጃሜሕ አሁንም ሥልጣን ላይ መሆናቸዉን ዘነጉት መሰለኝ አሉ የባንጁል ነዋሪ።
ጋናዎች ከተሸናፊዎች ጋር ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ለማድረግ እንደሚመክሩ ሲያስታዉቁ የጋምቢያ ምርጫ ዉጤት የወለፊንድ ባረቀ።
የ ዓመቱ ገዢ ተቀናቃኛቸዉ በአንዲት ድምፅ ቢበልጣቸዉ እንኳን ዉጤቱን ለመቀበል ቃል የገቡት ጃሜሕ የምርጫዉን ዉጤት ዉድቅ አደረጉት።
በተመድ የየመን የሰላም መልክተኛ ኢስማኢል ኦልድ ቼክ ረቡዕ ዕለት በሰጡት መግለጫ በየመን ተቀናቃኞች መካከል ያለዉ ልዩነት የሰፋ ነዉ።
አሳሳቢዉ የየመን ሁኔታ ዳግም ለሰላም ለድርድሩ ለመቀመጥ ተስፋ አይታይም በየመን በአየርና በምድር የሚደረገዉ ጦርነት ተባብሶ ቀጥሎአል።
በሌላ በኩል የየመኑን ጦርነት አልፈዉ ወደ ስዑድ አረብያ የሚገቡት ኢትዮጵያዉያን ቁጥር ጥቂት እዳልሆነ በጅዳ የሚገኘዉ ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ገልፆልናል።
በተመድ የየመን የሰላም መልክተኛ ኡልድ ቼክ አህመድ በየመን በአየርም ሆነ በመሪት ለመሪት ዉግያዉ ተጠናክሮ መቀጠሉን ትናንት በሰጡት መግለጫ አዉግዘዋል።
እንደ ኡልድ ቼክ አህመድ ከሁለቱም የየመን ተቀናቃኝ ኃይሎች በኩል የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ምንም ዓይነት ጥረትም ሆነ ፍንጭ አይታይም።
ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ እንደገለፀዉም የየመን ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መጥቶአል።
በየመን የየርስ በርሱን ጦርነት አልፈዉ ወደ ርያድ የሚገቡ የኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ቁጥርም ከፍተኛ መሆኑን ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ገልጾልናል።
የየመንን ቀዉስ እየተባባሰ ነው ሲሉ የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ተጠሪ ስቴፈን ብሪይን በሳምንቱ መጀመርያ ላይ አስጠንቅቀዋል።
በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ደግሞ በዞኑ የተደራጀና የታጠቀ ኃይል ፈፅሞ የለም ባይ ነው።
ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በሰሜን ሸዋ ዞን አጣየ አካባቢ በተፈጠረው ግጭት ሰዎች መገደላቸውና መቁሰላቸው ተነግሯል፡፡
የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር አጣየን ለማጥቃት የተዘጋጀ እና የተደራጀ ኃይል በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ውስጥ አለ ይላል።
ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በሰሜን ሸዋ ዞን አጣየ አካባቢ በተፈጠረው ግጭት ሰዎች መሞታቸውና መቁሰላቸውን አመራሮቹ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡
አፍሪቃ አሸባብ ላይ ያነጣጠረው የኬንያ በቀል የኬንያ መንግስት የዳዳብ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያን ሊዘጋ መሆኑን የጀርመን የዜና ወኪል ዘገበ።
በጣቢያው የሚገኙ ከ ሺ በላይ የሶማሊያ ስደተኞች የአሸባብ ታጣቂ ቡድን ወደ ማይገኝባቸው የሶማሊያ ግዛቶች እንዲመለሱ ይደረጋል ተብሏል።
የኬንያ መንግስት ከዚህ ውሳኔ የደረሰው በጋሪሳ ከተፈጸመው ጥቃት በኃላ መሆኑን የዜና ወኪሉ አክሎ ዘግቧል።