input
stringlengths 1
130k
⌀ |
---|
ሩሲያም ከአዉሮጳ ሕብረት ጋር የመጋጨቱ ፍላጎት ሊኖራት አይገባም ብዬ አምናለሁ። |
ይሕ ቢቀር የአዳዲሶቹ የኪየቭ መሪዎች ርምጃ ሩሲያን አዉሮጳ ዉስጥ የነበራትን ተሠሚነትና የምታሳርፈዉን ተፅዕኖ ከፍፃሜዉ የሚያደርስ ነዉ ከሚል ሥጋት ባልዶላት ነበር። |
ተገንጣዮቹ በሩሲያ የሠለጠኑ በሩሲያ የታጠቁ በሩሲያ ገንዘብ የሚደገፉ ናቸዉ። |
ሩሲያ ሆን ብላ እና በተደጋጋሚ የዩክሬንን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ጥሳለች። |
የሩሲያ ወታደሮች ዩክሬን ዉስጥ መግባታቸዉን የሚያሳየዉ አዲሱ ምሥል ደግሞ ዓለም ሁሉንም በግልፅ እንዲያዉቀዉ ያደርጋል። |
ዓለም አዉቆ የሚያደርገዉ ወይም ለማድረግ የሚችለዉ ካለ የሚያዉቀዉ ሁሉንም ነዉ። |
ተሰናባቹ የአዉሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ሆሴ ማኑኤል ባሮሶ እንዳሉት ምዕራባዉያንም ሩሲያም ቀጥታ ግጭት ጦርነቱን አይፈልጉት ይሆናል። |
ባለፉት አስምስት ወራት ብቻ ከሁለት ሺሕ በላይ ሰዉ ሞቷል። |
የአሽተን ዲፕሎማሲ የባሮሶ የድርድር ሐሳብ ከዘገየ የፑቲንም የድርድር መልዕክት በርግጥ አርፍዷል። |
ለሠላም ካሰቡ ግን የዉይይት ድርድሩ መፍትሔ ዘገየ እንጂ ጨርሶ አልቀረም። |
ኮምፒውተር ሳይንስ ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። |
ቃዛፊ ከተገደሉ በኋላ ሊቢያ የጦር አበጋዞች የየጎጥ ሚሊሺያ መፈንጪያ የአሸባሪዎች መደራጂያ የስደተኞች መገደያ መሸጪያ መደፈሪያ መታገቻ ሆናለች። |
የሊቢያ መዘዝ ለሳሕሎች ተርፎ ከማሊ እስከ ለኒዠር ከቡርኪና ፋሶ እስከ ቻድ ሺዎች ተገድለዋል። |
ሞስኮ ላይ ድርድር በርሊን ላይ ጉባኤ ብራስልስ ላይ ዉይይት እያለ ይራወጥ ያዘ። |
በሊቢያ እና በሶሪያ ጦርነት ተቃራኒ ኃይላትን የሚረዱት የቱርክ የፈረንሳይ የሩሲያ እና የግብፅ መሪዎች እንደ እንደ ፖለቲካ ዲፕሎማሲዉ ወግ ተነጋግረዋል። |
የአንዲት ሊቢያ የአንድ ዘመን ትዉልዶች ግን የተፋላሚ ኃይላት መሪዎች ስለገዛ ሐገራቸዉ መነጋገር ዓይደለም አንድ አዳራሽ ዉስጥ አብሮ መቀመጥም አልፈለጉም። |
ምክንያቱም ልዩነታቸዉ ስር የሰደደ ስለሆነ ይላሉ የጉባኤዉ አስተናጋጅ የጀርመኗ መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል። |
በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለዉ ልዩነት በጣም ሰፊ በመሆኑ አይነጋገሩም። |
ይሁንና እዚሁ በቅርብ ነበሩ አንድ ክፍል ዉስጥ ግን አልነበሩም። |
የዓለም ኃያላን በርሊን ላይ ሥለ ሊቢያ ዉድመት ሲነጋገሩ የሐፍጣር ጦር የነዳጅ ማምረቻና ማከማቻ ተቋማት ነዳጅ ዘይት እንዳሸጡ አግዷል። |
ሐፍጣር እንደ ጦር አበጋዝ ወታደራዊ እርምጃ ሲወስዱ አል ፈራጅ እንደ ሲቢል መሪ የተረፋቸዉን አማራጭ ቀሰቀሱ። |
ምክንያቱም ተኩስ አቁሙን ወንጀለኛዉ ሐፍጣር ትሪፖሊን ለመቆጣጠር እና ተጨማሪ ደም ለማፍሰስ ጦር መሳሪያ ለማከማችትና ወታደሮቹን ለማደራጀት ይጠቀምበታልና። |
ተቃዉሟችን ለምዕራባዉያን ለፀጥታዉ ምክር ቤትና ለአዉሮጳ ሕብረት መልዕክት ለማስተላለፍ ነዉ። |
ቱርክ የኔቶ አባል ብትሆንም የቱርኩ ፕሬዝደንት አጋጣሚዉን በመጠቀም ጦራቸዉን ወደሊቢያ ለማዝመት ይፈልጋሉ። |
በ የሁለተኛ ደረጃ ትምሕርቱን ለመከታተል ከሰሜን ምስራቃዊቱ የትዉልድ መንደሩ አጅዳቢያ ሻል ወዳለችዉ ከተማ ደርና ገባ። |
በዚያዉ ዓመት ከጥንቷ ጣራቦሊስ ቅኝ ገዢ ከቱርክ ደም የሚወርሱት የንጉስ ኢድሪስ ሐብታም ሚንስትር መሐመድ አል ሳራጅ የወንድልጅ አባት ሆኑ። |
ፋይዝ እንደ ሐብታም ሚንስትር ከቱጃሮቹ ትምሕርት ቤት ፊደል ሲቆጥር ወጣቱ ኸሊፋ ጦር ትምሕርት ቤት ገባ። |
በ ሻለቃ ሙዓመር ቃጣፊ በመሩት መፈንቅለ መንግሥት የንጉስ ኢድሪስን ዘዉዳዊ አገዛዝ ሲያስወግዱ ወጣቱ የጦር መኮንን ከቃዛፊ ቀኝ እጆች አንዱ ነበር። |
ኸሊፋ እንደ ወታደር ምሽግ ገብቶ እንደ ፖለቲከኛ ቤተንግስትን የሚያማትረዉን የናስር አስተምሕሮን ሲያቀነቅኑ ፋይዝ ትምሕርት ቤት እያማረጡ ዩኒቨርስቲ ለመግባት ይዘጋጁ ነበር። |
በዉልደት ክልስ ባመለካከት ቅይጥ የሆኑት የመስመር መኮንን ሶቭዬት ሕብረት ሔደዉ የአብዮታዊ የጦር መኮንንነትን ተምረዉ ተመለሱ። |
በ አረቦች እና እስራኤል ሲዋጉ ሲና በረሐ የነበረዉን የእስራኤል ጦር ምሽግ ሰብሮ የገባዉ የአረብ ጦር አባል በመሆናቸዉ ተሸልመዉ ተሾሙ። |
በ ቻድን የሚወጋዉን ጦር እንዲያዙ ሲሾሙ ፈይዝ አልሰራጅ በሥነ ሕንፃ አርክቴቸር ትምሕርት ከዩኒቨርስቲ ተመረቁ። |
የአሜሪካዉ ማዕከላዊ የስለላ ድርጅት መረጃ አቀባይ ሰላይ መሆናቸዉ በሰፊዉ መነገር የጀመረዉም ያኔ ነዉ። |
የሥነ ሕንፃዉ ባለሙያ ፋይዝ አልሰራጅ ግን በዚህ ሁሉ መሐል የሊቢያ የቤቶች ጉዳይ ሚንስቴር ባልደረባ ሆነዉ ይሰሩ ነበር። |
ከ ጀምሮ አልሰራጅ የፖለቲካ ኃይልና ተጣማሪ እየቀያየሩ የትሪፖሊን ፖለቲካ ሲዘዉሩ ሐፍጣር ከቤንጋዚ ተቀናቃኞቻቸዉን ተራ በተራ እያጠፉ ኃይላቸዉን ያጠናከሩ ነበር። |
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሊቢያ ተዋጊዎች ላይ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ማዕቀብ ጥሏል። |
በ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤትን ዉሳኔን በመጣስ ሊቢያ በቦምብ እድትደበደብ ሲወሰን ኢጣሊያ የትነበረች። |
የያኔዎቹን ጀብደኞቹን መሪዎች ማንነት ሁሉም ስለሚያወቀዉ እኔ መጥቀስ ያለብኝ አይመሰለኝም። |
ላቭሮቭ ጀብደኛ ያሏቸዉ የ ዶቹ ወራሪዎች ሳርኮዚ ካሜሩን እና ኦባማ ነበሩ። |
የአንካራና የሞስኮ መሪዎች የሊቢያ ተፋላሚ ኃይላትን ተኩስ እንዲያቆሙ ማስገደዳቸዉ ንቅናቄዉ ለሰላም ወዳዶች ሳይደግስ አይጣላም ዓይነት ሆኖ ነበር። |
ይሁንና ባለፈዉ ሳምንት ተኩስ አቁሙን በፊርማ ለማፀደቅ ሞስኮ ላይ የተጠራዉን ድርድር የጦር አበጋዝ ኸሊፋ ሐፍጣር ማቋረጣቸዉ ተስፋ በተስፋ ያስቀረዉ መስሏል። |
ትናት በርሊን የተደረገዉ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ደግሞ የሞስኮዉን ጅምር የሚያጠናክር የተኩስ አቁሙን የሚያፀና መሆኑ በሰፊዉ ተነግሯል። |
የጀርመኑ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ሐይኮ ማስ ከሚነገረዉም አለፍ ብለዉ ለሊቢያ ሰላም የሚወርድበት ቁልፍ አግኝተናል ይላሉ። |
የገንባንበት ጉባኤን ዓላማ ዛሬ ከግቡ ካደረስን በኋላ የሊቢያን ጦርነት የምንፈታበትን ቁልፉ አግኝተናል ማለት እችላለሁ። |
እስካሁን በሊቢያዉ ቀዉስ በቀጥታ እጃቸዉን ካላስገቡ ትላልቅ የአዉሮጳ ሐገራት አንዷ ጀርመን ናት። |
ጀርመን የጨበጠችዉ በማስ አገላለጥ የመትሔ ቁልፍ የአዉሮጳ ሕብረት እንዲሆን የሕብረቱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች እየመከሩ ነዉ። |
የቱርክ የረጅም ጊዜ ጠላት ግሪክ ግን የሕብረቱን የጋራ አቋም ለመሻር ትፎክራለች። |
ግብር ከፋዮች በሐረሪ ክልል ቅሬታ እያሰሙ ነው ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። |
የሰማያዊ ፓርቲ ውዝግብ በነኢንጅንየር ይልቃል ጌትነት የሚመራው የሰማያዊ ፓርቲ ክንፍ ፓርቲውን ወደ ቀድሞው ህጋዊ የአመራር ጥንካሬው ለመመለስ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስታወቀ። |
ይኸው የፓርቲው ክንፍ ትናንት በአዲስ አበባ ባካሄደው ስብሰባ ይህን የፓርቲውን እቅድ የሚያስፈጽም አንድ የስራ አስኪያጅ ኮሚቴም ማቋቋሙንም ገልጿል። |
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተኅዋሲዉን ስርጭት ለመቀነስ ይህን ያህል ሚና ይጫወታል ብለን መዘርዘር ባንችልም አደጋዉን ለመቀነስ ሚና እንዳለዉ እሙን ነዉ። |
በኤች አይቪ ላይ የሰራነዉ ስህተት የኮሮና ላይ ልንደግም አይገባም። |
ሁሉም በጥምረት በጋራ የሚሰራበት ጊዜ ነዉ ተወያዮች ያነስዋቸዉ ነጥቦች ናቸዉ። |
ያም ሆኖ ለተኅዋሲዉ ማርከሻ የሚሆን መድሐኒትም ይሁን መከላከያ ክትባት አልተገኘም። |
የኮሮና ተኅዋሲ ስርጭትን ለመግታት የዓለም ሃገራት መንግሥታት በየሃገሮቻቸዉ የተለያዩ የጥንቃቄ ድንጋጌዎችን እያሳለፉ ነዉ። |
የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሮና ሥርጭትን ለመግታት ለአምስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደንገጉን አስታዉቋል። |
በኢትዮጵያ ኅብረተሰቡ በተኅዋሲዉ እንዳይያዝ ነባሩን ማኅበራዊ ትስስር እንዲገታ ለማድረግ የሚደረገዉ ሙከራም ከባድ ሲሆን ታይቶአል። |
የኮሮና ስርጭትን ለመግታት ኢትዮጵያ ከሌሎች ሃገሮች ምን ልምድን ትዉሰድ |
በሃገሪቱ ዉኃ በወረፋ የሚታደልበት አሰራር በመኖሩ የንጽሕና መጠበቅያ ዉኃ እጥረት ቢኖር እንኳ ንክኪን መቀነስ አካላዊ ቅርቀትን መጠበቅ ያስፈልጋል። |
የኮሮና ተኅዋሲ አደገኝነነት ለጥቁር አልያም ለአፍሪቃ አደጋ የለዉም በሚል በተሳሳተ መረጃ ችላ ተብሎ ነበር። |
ነገር ግን ሃገሪቱ ላይ የመጀመርያዉ የኮሮና ተኅዋሲ ታማሚ ከተገኘ በኋላ ጉዳዩ አጽኖት ተሰጥቶት ጥንቃቄ ለማድረግ እየተሞከተረ ነዉ። |
የኮሮና ተኅዋሲ በመጀመርያ በኢትዮጵያ ሳይሆን በሌሎች ሃገሮች ተዛምቶ መረጃዉ እኛ ጋር ቢደርስም በቅድምያ ጥንቃቄ ለማድረግ እድሉን አልተጠቀምንም። |
ለዚህ ምክንያቱ የኅብረተሰቡ አንድ ላይ የመኖር ባህላዊ ሁኔታ ሊሆን ይችላል። |
ወይም ኅብረተሰቡ ላይ ያለዉን የባህሪ ለዉጥ ለማምጣት አስቸጋሪ ይሆናል። |
ኮሮና ከሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ወዲህ የተከሰተ ከባድ ቀዉስ ነዉ። |
እንዲህ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕዝብን የሚያፈናቀል እንዲህ ፍርሃት ዉስጥ የሚከት ሁኔታ ታይቶ አይታወቅም። |
ማኅበራዊ ትስስር በጎላበት በኢትዮጵያ ኮሮናን ለመከላከል የሚደረገዉ ጥረት ከባድ አድርጎታል። |
ለምሳሌ ከአዲስ አበባ ም ከንቲባ ጀምሮ የተለያዩ ሚኒስትሮች ኅብረተሰቡን ስለኮሮና ጥንቃቄ ንቃትና ትምህርት ለማድረግ ሲጥሩ ይታያል። |
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተኅዋሲዉን ስርጭት ለመቀነስ ይህን ያህል ሚና ይጫወታል ብለን መዘርዘር ባንችልም አደጋዉን ለመቀነስ ግን ሚና እንዳለዉ እሙን ነዉ። |
በአፍሪቃ የኮሮና ተኅዋሲ መዛመት ታሪክ ሲታይ አብዛኛዉን የሚታየዉ በከተሞች ላይ ነዉ። |
ይህ የሆነዉ በአፍሪቃ ዋና ከተሞች ከአዉሮጳ አልያም ከሌላ ክፍለዓለማት ከተኅዋሲዉ ጋር ንኪኪ ያላቸዉ ተጓዦች ስለሚገቡ ነዉ። |
ኢትዮጵያ ላይ ያለዉን ሁኔታ ስንወስድ አዲስ አበባ ላይ ይህ ይታያል። |
በሌላ በኩል ከተማ ዉስጥ የሚኖረዉ ሕዝብ ቁጥር በጣም ከፍተኛ እና ተጠጋግቶ የሚኖር በመሆኑ ነዉ። |
የተኅዋሲዉን መዛመት ስናጤን አዲስ አበባ ከሌሎች ከተሞች ጋር ያ ለዉን መስተጋብርም ማጤን ይኖርብናል። |
ግን አሁንም ይህ ጉዳይ ሊጤን ይገባል ወደ አዲስ አበባ እንደልብ መዉጣት መግባት ይቻላል። |
ስንት ሰዉ ተመርምሮ ስንት ሰዉ ተገኘበት ብሎን ልንጠይቅ ይገባል። |
በሃገሪቱ ዉስጥ ኮሮናን ለመርመር ያለዉ አቅም እጅግ ጥቂት ነዉ። |
ስለዚህም መረጃ ስንሰጥ ከዚህ ሰዉ መካከል ይህን ያህል ተመርምሮ ይህን ያህል በተህዋሲዉ ተይዞ ተገኘ ብለን ግልፅ ልናደርግ ይገባል። |
በመረጃዉ ላይ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል ተብሎ በአጽሕኖት ሊነገር ይገባል። |
በዚህ ወቅት ምንም አይነት የፖለቲካ ልዩነት የሚታይበት መድረክ ሊኖር አይገባም። |
የኮረና ተኅዋሲ ወረርሺኝ የዓለምን የጤና ፖሊስ የጤና መርህ ያጋለጠበትም አጋጣሚ ነዉ። |
የሃገራት ፖለቲከኞችም ሆኑ የጤና ባለሞያዎች በጤና ፖሊስያችን እንዴት እናስተካክል በተለይ የወረርሽኝ ሕክምናን እንዴት እናቃል ብለዉ ዳግም መርሃቸዉን የሚፈትሹበት ይሆናል። |
በሌላ በኩል በተለይ በአፍሪቃ የኮሮና መፈወሻ መድሃኒት ናቸዉ ተብሎ እየተራገፉ ናቸዉና ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል። |
ተኅዋሲዉን ማርከሻም ሆነ መከላከያ መድሃኒትም ሆነ ክትባት እስካሁን አልተገኘም። |
በዉይይቱ የተሰታፉትን በማመስገን ሙሉ ዉይይቱን የድምፅ ማድመቻ ማይቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን |
ከመቶ ዓመታት በላይ ዘልቋል ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። |
የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ውጤቶች በየጣቢያዎች ይፋ ተደርገዋል መግቢያ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። |
የመንግሥት ባለስልጣናት መታሠር በዛሬዉ ዕለትም የኦሮሚያ ፍትህ ቢሮ የኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ታዬ ደንደኣ መታሰራቸዉ ተሰምቷል። |
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኤርትራ ላይ የጣለዉ ማዕቀብ እንዲነሳ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ከዚሕ ቀደም ያቀረቡት ጥያቄ ድጋፍም ተቃዉሞ ገጥሞታል። |
ይህ ዕልቂት በሰዉ ልጆች ላይ የተፈፀመ ወንጀል ነዉ ሲልም ድርጅቱ ገልጿል። |
የድርጅቱ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሀላፊ ሚሸል ባችሌት እንደገለፁት ግጭቱ ከተቀሰቀሰባቸዉ አራት ቦታዎች ዉስጥ በሶስቱ ድርጅቱ ማጣራት አድርጓል። |
በዩንምቢ ከተማ ዉስጥ ቦንጌንዴ እና እንኮሎ መንደሮች ቢያንስ ወንዶች ሴቶችና ህፃናት መገደላቸውን እና ሌሎች ሰዎች ደግሞ መጎዳታቸውን ማረጋገጥ ችለናል። |
የተወሰኑ አስከሬኖች ወደ ኮንጎ ወንዝ በመወርወራቸው የሟቾች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊጨምር ይችላል ተብሎ ይታመናል። |
የድርጅቱ የምርመራ ቡድን ናባናዚ በተባለዉ ቦታ ማጣራት ያላደረገ በመሆኑ የሟቾችና የጠፉ ሰዎች ቁጥር ሊያሻቅብ ይችላል የሚል ግምት መኖሩንም ሃላፊዋ አመልክተዋል። |
እንደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዘገባ ማጣራቱ በተደረገባቸዉ ቦታዎች የጅምላ መቃብሮች ተገኝተዋል። |
ግድያዉ ለማምለጥ ጊዜ በማይሰጥ ሁኔታ በፍጥነት የተካሄደና ዘግንኝ እንደነበርም በሪፖርቱ በዝርዝር መቀመጡን ሃላፊዋ ገልፀዋል። |
በአንዳንድ ኹኔታዎች የዐይን እማኞች የኮንጎን ወንዝ ለማቋረጥ ሲሞክሩ በርካቶች መገደላቸውን ሌሎች ከነ ሕይወታቸው መቃጠላቸውን ገልጸዋል። |
ከቃጠሎዉ በህይወት የተረፉትም ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል በጎሳዎቹ መካከል ዕርቅ ለማዉረድ በድርጊቱ የሚጠየቅ አካል መኖር አለበት ብለዋል። |
ግጭቱ በተቀሰቀሰበት አካባቢ የሚገኙ የመንግስት ባለስልጣናትም ህዝቡን ከአደጋ መከላከል ባለመቻላቸዉ ተወቃሾች መሆናቸውን ተናግረዋል። |
በወቅቱ ውጥረቶች እየጨመሩ መሔዳቸውን የሚጠቁሙ ምልክቶች ቢኖሩም እና የኹከት ሥጋት ቢያይልም ከጥቃቶቹ በፊት የጸጥታ ኹኔታውን ለማጠናከር እርምጃ አልተወሰደም። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.