input
stringlengths
1
130k
በሃገሪቱ በያዝነዉ ዓመት ብቻ ከ ሰዎች በላይ የግድያ ቅጣት ተፈጽሞባቸዋል።
በዓለማችን የሚገኙ ቀጭኔዎች ቁጥር በከፍተኛ መጠን በመቀነሱ የመጥፋት ስጋት እንደተጋረጠባቸዉ የዓለም የተፈጥሮ ጥበቃ ማኅበር ገለፀ።
በመረጃዉ መሰረት በዓለም ዙርያ ያሉት ቀጭኔዎች ቁጥር ሺህ አይበልጥም።
የአሸባብ ታጣቂዎች ኤል አዴ የሚገኘዉን የጦር ሰፈር አጥቅተዉ አንድ መቶ የሚሆኑ ወታደሮችን ገድለናል ይላሉ።
የኬንያ ወታደሮች ስንብት የኬንያ መንግሥት የሟቾቹን ቁጥር ባይጠቅስም በፅንፈኛዉ ቡድን ጥቃት ላለፉ ወታደሮቹ ትናንትበብሄራዊ ደረጃ የመጨረሻዉን ስንብት አድርጓል።
የኬንያ ባለስልጣናት እስካሁን ፅንፈኛዉ ቡድን ድንገት በወታደሮቹ ላይ በሰነዘረዉ ጥቃት የሞቱትም ሆነ የተማረኩትን ቁጥር ይፋ አላደጉም።
የሀዘን እና ስንብት ሥርዓቱ የተደረገዉ በተጠቀሰዉ ስፍራ ህይወታቸዉን ካጡት አብዛኞቹ ወታደሮች በመጡባት ከናይሮቢ በስተምዕራብ በምትገኘዉ ኤልዶርት ከተማ ነዉ።
በሥነሥርዓቱ ላይ ፕሬዝደንት ዑሁሩ ኬንያታ ባደረጉት ንግግር አሸባብን ከፍተኛ ዋጋ ለማስከፈል ዝተዋል።
የወደቁት ሰዎች የእኛን ደህንነት ለመጠበቅ ከቤታቸዉ ብዙ ርቀዉ እጅግ በአስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ ሲያገለግሉ ነበር።
እነሱን የገደሉ እነዚያ ፈሪዎች እያንዳንዳቸዉ ከያሉበት ታድነዉ ለፍርድ ይቀርባሉ።
ስነሥርዓቱ ከመጀመሩ በፊትም በሀዘን ለተጎዱት የሟቾቹ ቤተሰቦች የማፅናኛ እና የምክር አገልግሎት ተካሂዷል።
ኬንያ በጎርጎሪዮሳዊዉ ዓ ም ነዉ እስላማዊ ፅንፈኛ ታጣቂዎች ድንበሯን እየተሻገሩ በሀገር ጎብኚዎች ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት ለመከላከል በሚል ወታደሮቿን ወደሶማሊያ ያዘመተችዉ።
አሸባብ በወቅቱ ርምጃዋን በመቃወም በኬንያ ግዛቶች ዉስጥ ተጨማሪ ጥቃቶችን ለማድረስ ዝቶ ነበር።
ጥቃቱን ለመከላከል ኬንያ ድንበሯ ላይ ግዙፍ ግንብ ለማቆም አቅዳ ነበር።
ምንም እንኳን አሸባብ ከዋና ዋናዎቹ የሶማሊያ ከተሞችና መንደሮች ተገፍቶ ቢወጣም ቡድኑ አሁንም በደፈጣ ዉጊያ እና ጥቃቱን በመላ ሀገሪቱ ማድረሱን አላቋረጠም።
አሸባብ በተደጋጋሚ የሚያደርሰዉ ጥቃትም የአፍሪቃ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ወታደሮች የሶማሊያ መንግስት ባለስልጣናት እና የዉጭ ዜጎች ላይ ያነጣጠረ ነዉ።
የሶማሊያ ፕሬዝደንት ኬንያ ትናንት በአሸባብ ጥይት ለወደቁ ወታደሮቿ ባካሄደችዉ የመታሰቢያ ሥርዓት ላይ የናይጀሪያ እና ሶማሊያ ፕሩዝደንቶች ተገኝተዋል።
እዚህ ኬንያ ዉስጥም ሆነ እዚያ በሶማሊያ ለምታደርጉት ለዚህ በጎነት ሶማሊያ ሁሌም ባለዕዳ እንደሆነች ትኖራለች።
በጋራ የምንዋጋዉ ይህን እኩይ ኃይል የሰብዓዊነት ጠላት ነዉ ድል እናደርጋቸዋለን።
ቀድሞ ድል አድርገናቸዉ ነበር በየቀኑም እያሸነፍናቸዉ ነዉ እናም በመጨረሻም በዚህኛዉ የዓለም ክፍል ድል እናደርጋቸዋለን።
ሽብርተኝነት ድንበር የለዉም ጎሳ የለዉም እንዲሁም ፍፁም ሃይማኖት የለዉም።
ፕሬዝደንት ቡሀሪ ፅንፈኞችን ድል ለማድረግ ሀገራቸዉ ከኬንያም ሆነ ከሌሎች የአፍሪቃ ሃገራት ጎን እንዲሁም ከዓለም ኅብረተሰብ ጋር በትብብር እንደምትቆም አመልክተዋል።
ሁላችንም ወደሽብር በሚያመሩት ባለመቻቻል ባህል ጥላቻ እና ፅንፈኝነት ላይ በጋራ መነሳት ይኖርብናል።
ፅንፈኝነት ላይም ጠንካራ አቋም ሊኖረን ይገባል ማንም ቢሆኑ እና የትም ቢገኙ አሸባሪዎችን መዋጋት አለብን።
በጥቃቱ ሁለት የቼክ ሪፓብሊክ ዜጎችን ጨምሮ አራት አገር ጎብኝዎችም መጎዳታቸዉን ታዉቋል።
የጋምቢያ ፕሬዚደንት አዳማ ባሮ መንግሥታቸዉ የቀድሞዉን ፕሬዚደነት ያህያህ ጃሜን ኃብት ለማጣራት አራት ግለሰቦችን ያካተተ አንድ አጣሪ ኮሚሽን ማዋቀሩን ገለፁ።
የወቅቱ የአፍሪቃ ኅብረት ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ አዉሮጳ የምታራምደዉ ፖለቲካ ገደብ እንዳያመጣ ሲሉ አስጠነቀቁ።
ድንበር በመዝጋቱ የሚያስከተለዉ የሰዎች ሕይወት መቅጠፍ ብቻ ነዉ ሲሉም አዉሮጳን አሳስበዋል።
የቻይና መንግሥት ቻይና ላይ ትችት የሰነዘሩት ሃገራት የቻይናን የሕግ ሉዓላዊነት እንዲያከብሩ ጠይቀዋል።
የጀርመን ፌዴራል መንግሥት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ጃፓን አሻሽላ ያቀረበችዉን የሞት ቅጣት ብይን ክፉኛ ተቹ።
በኢንዱስትሪ ከበለፀጉት ሃገራት መካከል ጃፓን እንደ ዩናይትድ ስቴትስ የሞት ቅጣት መፈጸሟን የቀጠለች ሀገር ናት።
የኢጣልያ የፖለቲካ ቀውስ በኢጣልያ ባለፈው ሳምንት የተጀመረው ጥምር መንግሥት ምሥረታ ከተቋረጠ በኋላ ሀገሪቱ ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር ተሰይሞላታል።
በሀገሪቱ ምርጫ እስከሚካሄድ ይቆያል የተባለው ጊዜያዊ መንግሥት የኢጣልያ ምክር ቤትን ድጋፍ ካላገኘ መፍረሱ አይቀርም።
የስድሳ አንድ ዓመቱ ቴይለር እአአ ከሰኔ ዓ ም ወዲህ በእስራት ዘ ሄግ ይገኛሉ።
ብዙዎች ቴይለርን ተወዳዳሪ እንደሌላቸው ጭራቅ ይቆጥሩዋቸዋል አንዳንዶች የአፍሪቃ ሚሎሴቪች ይሉዋቸዋል።
ሌሎች ደግሞ በአፍሪቃ ከሚካሄዱት ብዙዎቹ ጦርነቶች ትርፍ ካካበቱት መካከል እንደ አንዱ ይመለከቱዋቸዋል።
አስራ አራት ልጆችና የልጅ ልጆች እንዳሉዋቸው የገለጹት ቴይለር ለስብዕና ፍቅር ያላቸውና ዕድሜአቸውን ሙሉ ለፍትህና ለትክክለኛ አሰራር የታገሉ መሆናቸውን ነው ያመለከቱት።
ሰዎች ሳይወግኑ በቴይለር አንጻር የተሰነዘረውን ክስ በትክክለኛ መንገድ እንዲመለከቱትም ግሪፊትስ አክለው ተማጽነዋል።
ብዙዎች በአንጻራቸው አስቀድመው ስለፈረዱዋቸው ሚስተር ቴይለር ጉዳያቸውን በሚያቀርቡበት ወቅት ብዙ ችግር እንደሚገጥማቸው ተረድተነዋል።
ይሁንና፡ ከህዝብ የምንጠይቀው የሚቀርቡ መረጃዎችን ባልወገነ መንገድ እንዲመለከቱና ቴይለር የሚሉትን እንዲያደምቱ ነው የምንጠይቀው።
ህጻናትን በውትድርና ተግባር የሚሰማሩበት ተግባር የቻርልስ ቴይለር ፈጠራ አይደለም።
ዘጠና አንድ በብዛት ከሲየራ ልዮንና ከላይቤርያ የመጡ ምስክሮችን አቅርበናልል።
ከነዚህም ሰላሳ ሰባቱ በቻርልስ ቴይለር እና በትዕዛዝ በሲየራ ልዮን በትዕዛዝ በተፈጸሙት አስከፊ የጭካኔ ተግባራት መካከል ግንኙነት መኖሩን መስክረዋል።
እና የተከሳሽ ጠበቆች ለዚሁ ለቀረበው ማስረጃ አንጻራዊ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
የቴይለር ጠበቃ ግን ደምበኛቸው ራሳቸውን ከቀረበባቸው ክስ ነጻ እንደሚያወጡ በርግጠኝነት ተናግረዋል።
ምንም እንኳን ምስክሮቻችን አደጋ ላይ ሊወድቁ ቢችሉምና ለወደፊቱ ስጋት ቢኖራቸውም ቃላቸውን ለመስጠት ፈቃደኟ በመሆናቸው በጣም ተደስተናል።
በሲየራ ልዮን ለተካሄደው የጭካኔ ተግባር ቻርልስ ቴይለር ብቸኛው ተጠያቂ አለመሆናቸው ይታወቃል።
በዚህ አካባቢ ለብዙ ጊዜ ትልቅ ስልጣን ያላቸው ግለሰቦች ቅጣት ይደርስብናል ብለው አይሰጉም ነበር።
አሁን በልዩው ፍርድ ቤት አማካይነት አሁን ይህንን አሰራር ቀይረናል።
በዚህ ሀገር ወንጀልን በመታገሉ ረገድ ትልቅ መሻሻል እያደረግን እንገኛለን።
የቻርልስ ቴይለር ጠበቃ ምስክሮቹን የሚያቀርብበት ጊዜ ከስድስት እስከ ዘጠኝ ወር ሊወስድ እንደሚችል ተገምቶዋል።
የቀድሞው የላይቤርያ ፕሬዚደንት ቻርልስ ቴይለርም ጠበቆቻቸው ከቀረበባቸው ክስ ነጻ እንደሚያደርጉዋቸው እርግጠኛ መሆናቸው ተገልጾዋል።
ይህ ተስፋቸው ገሀድ መሆን መቻሉ ግን እስኪታወቅ ድረስ ገና ብዙ ወራት ማለፋቸው እንደማይቀር ነው ከፍርድ ቤቱ አካባቢ የተገኙ ምንጮች የሚያመለክቱት።
የፈረንሣይ ፖሊስ የካሌ ስደተኞች ላይ ጥቃት እና በደል በመፈጸም ስደተኞች ላይ የሚረጭ አቃጣይ ንጥረ ነገርም ይጠቀማል የሚል ነው ክሱ።
የፈረንሣይ መንግሥት በሀገር ውስጥ ሚንሥትርሩ በኩል በሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የቀረበበትን ክስ እና ውንጀላዎች በጽሑፍ መግለጫ አስተባብሏል።
ተጨባጭ መረጃ እንኳን ባይገኝም የኃይል አጠቃቀም እና ሕግን መተላለፍ እንዲሁም የሥነ ምግባር ጥሰት የመኖሩን ትክክለኛነት ማረጋገጡን ግን በዘገባው ላይ አመልክቷል።
የአንድነት ፓርክ ጉብኝት መግቢያ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
አቶ መለስ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ወደ ገደማ ሚሲዮኖች አሏት።
አሁን ጥሪ የተደረገላቸው ሰራተኞች ከአንድ የተወሰነ ቦታ የተጠሩ እንዳልሆኑ አቶ መለስ ጨምረው ተናግረዋል።
ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዲፕሎማቶች ስልጠና ተሰጥቷቸው በተለያዩ ኤምባሲዎች ለሥራ መመደባቸውን አስታውቋል።
የተቋሙ አጠናሁት ያለው መዋቅር በጠቅላይ ምኒስትሩ ጸድቆ በቅርቡ የዲፕሎማቶች ዳግም ምደባ እንደሚደረግም አክሏል።
ኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኛ ህጻናትና የጤና ሥርዓቱ በኢትዮጵያ የጤና አገልግሎቱ ለኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ሕጻናት ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ተገለጠ።
ከሕጻናት ማሳደጊያ እስከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ ለአካል ጒዳተኞች የጤና ሥርዓት በአዲስ መልክ እየተዘረጋ መሆኑም ተገልጧል።
የጤና ሥርዓትና አካል ጉዳተኞች ህጻናት በኢትዮጵያ የጤና አገልግሎቱ ለኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ሕጻናት ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ተገለጠ።
ቢሊዮን ኪዩቢክ ውኃ በየዓመቱ ይልቀቅ የሚለው ሃሳባቸው የሚሆን ነገር አይደለም አውዲዮውን ያዳምጡ።
የአዉሮጳ ኅብረት አባል ሃገራት መሪዎች ከትናንት ከቀትር በኋላ አንስቶ እስከዛሬ ያካሄዱትን የሁለት ቀናት ጉባኤ አጠናቀቁ።
የ ዓም የኢትዮጵያ እቅዶችና ተግዳሮቶቻቸው ኢትዮጵያ ን ሸኝታ አዲሱን ን ከተቀበለች ሁለተኛ ሳምንቷን አገባደደች።
የፀረ ሽብር ሕግ አጠቃቀም ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
ኢትዮጵያ የኑሮና የገቢ ልዩነት በኢትዮጵያ በኢትዮጵያ በሀብታምና በድሃ መካከል ያለዉ የኑሮ ልዩነት እየሰፋ መጥቷል ተባለ።
ኢትዮጵያ የእሳት አደጋ በመርካቶ በዛሬዉ ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ መርካቶ የገበያ ስፍራ የእሳት አደጋ መድረሱ ተሰማ።
የእሳት አደጋ በመርካቶ እሳቱን ለማጥፋት የእሳት አደጋ ሠራተኞችና ተሽከርካሪዎች በርከት ብለዉ ቢሰማሩም መንገዱ ጠባብ በመሆኑ ሁሉንም ማስተናገድ እንዳልቻለም ዘጋቢያችን ገልጾልናል።
የብሔራዊ ፈተና ዝግጅት ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
በኦሮሚያ የተጠራው አድማ መወያያ ሆኗል ኦሮሚያ ያለፈውን ዓመት እዚህም እዚያም በሚገነፍሉ ተቃውሞዎች ስትናጥ ነበር ያሳለፈችው፡፡
ሆኖም አሠሪዎች በክፍት የሥራ ቦታቸው የፈረንሳይ ዜጋ መቅጠር ያልቻሉበትን ምክንያት ማስረዳት ይኖርባቸዋል።
የፈረንሳይ የስደተኞች ረቂቅ ሕግ ፈረንሳይ የውጭ ዜጎችን ለሥራ በኮታ ወደ ሃገርዋ የማስገባት እቅድ እንዳወጣች መንግሥት በቅርቡ አስታውቋል።
ይኽው የኮታ አሠራር በመጪው ዓመት በሃገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ሥራ ላይ ይውሏል ተብሏል።
የሠለጠነ የውጭ ባለሞያን ወደ ፈረንሳይ የማስገባቱ እቅድ ከቀኝ ጽንፈኞች እና የውጭ ዜጎች ፈረንሳይ መግባታቸውን ከሚቃወሙ ወገኖች ተቃውሞ እየቀረበበት ነው።
ዝርዝሩን የፓሪስዋ ዘጋቢያችን ሃያማኖት ጥሩነህ በዛሬው አውሮጳ እና ጀርመን ዝግጅታችን ታቀርብልናለች።
የተመድና የዓለም ሠላም መግቢያ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
ዩክሬን የምሥራቅ ምዕራቦች መሻኮቻ ሀገር ባለፉት አስምስት ወራት ብቻ ከሁለት ሺሕ በላይ ሰዉ ሞቷል።
በስንዴ ምርቱ ከዓለም የታወቀዉ ግዛት በነፋሻ አየሩ የሚወደደዉ ያ ግዛት እየጠፋ ነዉ።
የሩሲያና የዩክሬን መሪዎች እንደ ወዳጅ እየተጨባበጡ ለመደራደር ለማደራደር ቃል እየገቡ እንደ ጦረኛ ወታደሮቻቸዉን ያዋጋሉ።
የዋሽግተን ብራስልስ ተሻራኪዎች ሩሲያ ጦር ማዝመቷን እያወገዙ እሩሲያ ድንበር ጥግ ጦር ያሰፍራሉ።
እንደ ጦርኛ ጦር እያሰፈሩ እንደ ሠላም ወዳድ ዩክሬንን የሚያብጠዉ ዉጊያ በድርድር መፈታት አለበት ይላሉ።
የናትሴ ጀርመን ጦር ፖላንድን መዉረሩን ለመበቀል ብሪታንያና ፈረንሳይ በጀርመን ላይ ጦርነት ካወጁ እነሆ ዛሬ ሰባ አምስተኛ ዓመቱን ደፈነ።
የዓለምና ሁለተኛዉ የተባለዉን ያን ዘግናኝ ጦርነት በድል አድራጊነት ካተጠናቀቁት እዉቅ የዓለም መሪዎች አንዱ የሶቬት ሕብረቱ ጆሴፍ ስታሊን አንድ አባባል ነበራቸዉ።
የኪየቭና ኪየቭን የሚደግፉት የምዕራብ ፖለቲከኞች ባንፃሩ የፑቲንዋ ሩሲያ ሥለ ዩክሬን የምትከተለዉን ምርሕ ከስታሊኗ ሶቬት ሕብረት መርሕ እርምጃ ጋር ያመሳስሉታል።
የሩሲያ ወታደሮችን እንቅስቃሴ የሚያሳይ የሳተላይት ፎቶ ግራፍ አለ የሚል ዘገባ ነበር።
በተጨባጭ ግን በኮፒዉተር የተሠራ ጨዋታዎች መሆናቸዉንና ያ ምሥል ከዚያ የተወሰደ መሆኑ ተረጋግጧል።
የሠላም ሂደት እንዲጀመር በሚጥሩት በዩክሬንና በሩሲያ ጦር ሐይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሞች መካከል የምክክር መርሐ ግብር ለማዘጋጀት ተስማምተናል።
ወደ ጋራ የተኩስ አቁም ሥምምነት የሚደረገዉን ሽግግር ለማፋጠን በሰወስትዮሹ አገኛኝ ቡድን አማካይነት ምክክር እናደርጋለን።
አነሱ የቡድኑ አባላት የጋራ የሆነዉ የተኩስ አቁም የመቆጣጣሪና የማጣሪያ መርሐ ግብራቸዉን እንደሚያቀርቡ ተስፋ አለን።
ሚንስክ ላይ ሥለሠላም ድርድር ለመናገር በስታሊን ሥልት ዉጪ ጉዳይ ሚንስራቸዉን ያልጠበቁት ፖሮሼኮ ብራስልስ ላይ ተቃራኒዉን ለማለትም መከላከያ ሚንስትራቸዉን አልጠበቁም።
ለሠላም የተጠናከረ ዓለም አቀፍ ጥረት ቢደረግም እና ከፍተኛ ጉጉት ቢኖረንም ዩክሩን ባሁኑ ሰዓት የዉጪ ወረራና የሽብር ሠለባ ሆናለች።
ከነሐሴ ሃያ ሰባት ጀምሮ ደግሞ በሺ የሚቆጠሩ የዉጪ ወታደሮችና በመቶ የሚቆጠሩ ታንኮች ዩክሬን ግዛት ዉስጥ ሰፍረዋል።
ይሕ ለዩክሬን ብቻ ሳይሆን ለመላዉ አዉሮጳ ሠላምና መረጋጋት ሲበዛ አደገኛ ነዉ።
ግን ለሐያላኑ ግልፁ ሐቅ ሕቅታ ለሠላም መሆን የነበረበት አለመሆኑ ወይም አለማድረጋቸዉ መኩሪያ የሆነ ነዉ የመሠለባቸዉ።
ባለፈዉ ማክሰኞ በሚንስኩ ጉባኤ የተካፈሉት የአዉሮጳ ሕብረት የዉጪ ግንኙነት ሐላፊ ወይዘሮ ካትሪን አሽተን ጉባኤዉ ጦርነቱ የሚቆምበትን ብልሐት መቀየሱን አስታዉቀዉ ነበር።
ዉጊያዉ የሚቆምበትን መንግድ ለመፈለግ በጣም ወሳኝ በሆነዉ በሠላምና በፀጥታ ጉዳይና የአዋሳኝ ድንበር አካባቢዎችን ደሕንነት በማረጋገጡ ላይ ።
እኛ አዉሮጳ ሕብረት ዉስጥ ያለነዉ ከሩሲያ ጋር መጋጨቱን አንፈልገዉም።