input
stringlengths
1
130k
እንደ ጥናቱ ከሆነ በ ሀገራት ለበሽታው የመጋለጥ አደጋ የተደቀነበት ህዝብ ቢሊዮን ይሆናል።
ከዓለም ህዝብ ግማሽ ያህሉን ሊያጠቃ ይችላል የሚባልለት ይህ በሽታ ዴንጊ ፌቨር ይባላል።
በጎንደር ዩኒቨርስቲ በሜዲካል ማይክሮ ባዮሎጂ ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት አቶ ጌታቸው ፈረደ ስለበሽታው ምንነት ያስረዳሉ።
ትኩሳት በዋናነት ሆኖ ማንቀጥቀጥ የመገጣጠሚያ ቦታዎች ህመም ማቅለሽለሽ ይኖራል ።
እነዚህ ደግሞ በወባም በሌሎችም በሽታዎች የሚታዩትን ነው እርሱም የሚያሳየው እና ብዙም በምልክት መለየት ከባድ ነው አይቻልም።
ከሦስት ዓመት በፊት በተደረገ ጥናት ይህ ቁጥር በሦስት እጥፍ ጨምሮ ተገኝቷል።
የዓለም ጤና ድርጅትን የመሳሰሉ ተቋማትን እያሳሳባቸው ያለው የቁጥሩ እንዲህ በፍጥነት መመደንግ ብቻ ሳይሆን ከዚህ ቀደም በሽታው ወዳልታየባቸው ሀገራት መስፋፋቱ ነው።
ከዓመታት በፊት በሽታው አይደለም በኢትዮጵያ በአፍሪካ ደረጃም ይሄን ያህል የሚወራለት አልነበረም።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በሽታው በአህጉሪቱ እዚህም እዚያም ይታይ ይዟል።
የዛሬ ሁለት ዓመት በቡርኪናፋሶ በተቀሰቀሰ የዴንጊ ወረርሽኝ ከአንድ ሺህ የሚልቁ ሰዎች በበሽታው ተጠቅተዋል ተብሏል።
በኢትዮጵያም በተመሳሳይ ወቅት በድሬዳዋ እና ሶማሌ ክልል ወረርሽኞች መከሰታቸውን የናሙና ምርመራ ውጤቶች አመላክተዋል።
እኔ እንዳየሁት ወረርሽኝ ተነስቶ በጣም ከፍተኛ ትኩሳት ያለባቸው በሽተኞችን ሪፖርት ተደረጉ።
ሪፖርት ሲደረግ እዚያ ከድሬዳዋ ላይ ምክንያታቸው ያልታወቁ ግን ብዙ በሽተኞች ታመዋል።
ወባን ጨምሮ ታይፎይድ የሎው ፊቨር አይነት ብዙ በሽታዎችን መርምረዋል።
ያ ነው እንግዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ሪፖርት የተደረገው ሲሉ የጥናቱን ውጤት ያስታውሳሉ።
የጎንደር ዩኒቨርስቲው መምህር በሌሎች በሽታዎችን ላይ ከባልደረቦቻቸው ጋር ጥናቶች ባደረጉባቸው የመተማ እና ሁመራ አካባቢዎችም ተመሳሳዩን አስተውለዋል።
ወባም ከሌለ ከዚህ በፊት ካደረግነው ጥናት እዚያ አካባቢ በብዛት የሚገኙት እንደ ካላዛርም ከሌላቸው ከዚህ ተነስተን ምን ሊሆን ይችላል
የእነ አቶ ጌታቸው ጥናት ውጤት እንደሚያመለክተው በመተማ ከተመረመሩት ናሙናዎች መካከል አርባ በመቶው የዴንጊ ፊቨር ተገኝቶባቸዋል።
ዘጠኝ አጥኚዎች የተሳተፉበት ይህ ጥናት በግንቦት ዓ ም በሳይንስ መጽሔቶች ጆርናሎች ላይ ታትሟል።
አጥኚዎቹ ጥናቱን በሚያካሂዱበት ወቅት ካስተዋሉት ነገር አንዱ ዴንጊ ፊቨር በበሽታነት እንኳ ያለመታወቁ እውነታ ነው።
አካባቢው ላይ ቃለ መጠየቅ ስናደርግ ዴንጊ ምናምን ስንል ሙያተኞቹ ጭምር ምንድነው ይሄ በሽታ ሲሉ ነበር።
እና ሙሉ ለሙሉ እንደዚህ አይነት የለም ተብሎ ነበር የሚታወቀው ሲሉ በአካባቢው የተመለከቱትን ያጋራሉ።
የእስያ እና የደቡብ አሜሪካ በሽታ ይባል የነበረው ዴንጊ ፊቨር በአፍሪካ ሊያውም በኢትዮጵያ እንዴት ሊገኝ ቻለ
በሚል የተጠየቁት አቶ ጌታቸው ምክንያቱን በትክክል ለማወቅ ተጨማሪ ዝርዝር ጥናቶች ያስፈልጋል የሚል ምላሽ ይሰጣሉ።
በሽታው በጎረቤት ሀገራት ጭምር እንደታየ የሚናገሩት ጥናት አድራጊው ምክንያቶች ሊሆኑ ይችላሉ ያሏቸውን ያስቀምጣሉ።
በአሁኑ ጊዜ ከአየር ንብረት ለውጥ እና ከከተሞች መስፋፋት ጋር ተያይዞ እንደ ወባ ትንኝ አይነት የበሽታ አምጪ ተዋህሲያን በቀላሉ እንዲራቡ ያደርጋል።
ለምሳሌ በአሁኑ ጊዜ ያው በኢትዮጵያ ውስጥ ከተሞቹ እየተስፋፉ ነው።
ከእነኚህ መስፋፋት ጋር ተያያዞ በቀላሉ እርጥበት ውሃ የመሳሰሉ ለወባ ትንኞች መራቢያ ምቹ ነገሮች ይፈጥራል።
እነኚህ ዴንጊ ፊቨር የሚባለው በሽታ አምጪ ተዋህሲያን በቀላሉ እንዲራቡ የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል።
እና በዚያ በተባሉት ቦታዎች ላይም የአየር ንብረቱም ቆላማ ነው።
ለወደፊቱ ደግሞ ምንድነው ምክንያቱ የሚለውን ደግሞ ቀጥለን የምናጠናው ይሆናል ይላሉ።
በዴንጊ ፊቨር ላይ የሚደረገው ቀጣዩ ጥናት አሁን በመካሄድ ላይ እንደሆነ አቶ ጌታቸው ይናገራሉ።
በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ጥናት ከዚህ ቀደም ከተደረገው ዘርዘር እና ሰፋ ያለ እንደሚሆን ይገልጻሉ።
ጥናቱ ከአራቱ የበሽታው አይነቶች የትኞቹ በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ለማወቅ እንደሚረዳ እና በሽታውን ለመከላከል ወደፊት ለሚደረገው ጥረት አንድ መነሻ ሊሆን እንደሚችል ያስረዳሉ።
እስከ ሞት ሊያደርስ ለሚችለው ዴንጊ ፊቨር ፍቱን መድኃኒት እስካሁን ባይገኝም ተመራማሪዎች ግን የመከላከያ ክትባት መስራታቸውን አስታውቀዋል።
ክትባቱን ያመረተው ዓለም አቀፍ ኩባንያ መድኃኒቱ ተጠቃሚዎች ዘንድ እንዲደርስ ለገበያ ያወጣው የዛሬ ሁለት ዓመት ግድም ነው።
የዓለም ጤና ድርጅትም በሽታው አዘውትሮ በሚከስትባቸው ሀገራት መድኃኒቱ ጥቅም ላይ መዋል እንደሚችል አዎንታዊ አስተያየቱን ሰጥቷል።
በ ሀገራት እውቅና እና ፍቃድ የተሰጠው ይህ ክትባት ከዘጠኝ እስከ ዓመት ላሉ ሰዎች የሚሰጥ እንደሆነ ተገልጿል።
ለመሆኑ ዴንጊ ፊቨር እስከ ሞት ሊያደርስ የሚችለው ምን ሲፈጠር ነው
የተቃጠሉ መስጊዶች መልሶ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት ግዛሉ ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
ራድዮ የሮሒንግያዎች ሥቃይ ዓለም አቀፉ ድርጅት ያነጋገራቸዉ ስደተኞች እንደሚሉት የምያንማር ወታደሮች የሮሒንግያ ሙስሊሞችን በጥይት ይገድላሉ ይደበድባሉ መኖሪያ ቤታቸዉን ያቃጥላሉም።
እንደሚለዉ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ሌሎች ስደተኞች የምያንማርን ድንበር አልፈዉ ባንግላዴሽ ለመግባት እየሞከሩ ነዉ።
ዓለም አቀፉ ድርጅት ያነጋገራቸዉ ስደተኞች እንደሚሉት የምያንማር ወታደሮች የሮሒንግያ ሙስሊሞችን በጥይት እየመቱ ይገድላሉ ሌሎቹን ይደበድባሉ መኖሪያ ቤታቸዉን ያቃጥላሉም።
ሊሸከሙት የማይችሉትን ግፍ ሥቃይ እና መከራን የሸሹ ሺሕ ሰዎች እስካሁን ባንግላዴሽ ዉስጥ ከለላ አግኝተዋል።
የምያንማር መንግሥት አማፂያንን እዋጋለሁ በሚል ሽፋን በሮሒንግያ ሙስሊሞች ላይ የሚፈፅመዉን ግፍ እንዲያቆም የተለያዩ መንግሥታት ቢጠይቁም እስካሁን ድረስ ተቀባይነት አላገኙም።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሌሎች ማሕበራትም ሆኑ መንግሥታትም በምያንማር መንግስት ላይ እርምጃ ለመዉሰድ አልቃጡም።
ተቃውሞ በባሕርዳር ዛሬ በባህር ዳር የክልሉን ገዥ ፓር የሚነቅፍ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በባህር ዳር ተካሂዷል፡፡
የአማራዴሞክራሲዊ ፓርተ ስለጉዳዩ አስተያየት እንዲሰጥ ሙከራ ቢደረግም ስብሰባ ላይ ናቸው ስለተባለ አልተሳካም።
ባሕር ዳር በአንድ ሳምንት ውስጥ የተለያዩ ዓላማዎችን ያነገቡ ሶስት ሰላማዊ ሰልፎችን አስተናግዳለች፡፡
ተመሳሳይ ይዘት ላቸው ሰልፎች በደብረታቦር በጎንደርና በምስራቅ ጎጃም የተለያዩ የወረዳ ከተሞች መካሄዳቸውን የየዞን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች አረጋግጠውልናል።
በጉዳዩ ዙሪያ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲን አመራሮች የመስተዳድሩን ኃላፊዎች ሀሳብ ለማካትት ያደረግሁት ጥረት ጎንደር ላይ ስብሰባ ናቸው በሚል አልተሳካልኝም።
ይህ መጥፎ ውጤት የ ን የበላይ መራኂተ መንግሥት አንጌላ መርክልንም አላስደነገጠም አይባልም።
የ ምርጫ ውጤት ለፌደራሉ መንግሥት ምን ዓይነት መልእክት ይሆን የሚያስተላልፈው
አፍሪቃ ናሚቢያዊው ሽምቅ ተዋጊ ሔንድሪክ ዊትቦይ አብዛናዎቹ የናሚቢያ ገንዘቦች የተዘረጋ ባርኔጣ ራሳቸው ላይ የደፉ የሔንድሪክ ዊትቦይ ፎቶግራፎች አሏቸው።
ሔንድሪክ ዊትቦይ የጀርመን ቅኝ ገዢዎችን ተፋልመዋል ናሚቢያ በአፍሪቃ ከቅኝ አገዛዝ ነጻ በመውጣት የመጨረሻዋ ሃገር ናት።
ውይይት የኢትዮጵያ መንግሥት ዉሳኔውን የተቀበለው ከ ዓመት በፊት ነዉ።
የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ባለፈዉ ረቡዕ ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ መንግሥት የሁለቱን አገሮች ውዝግብ ለማስወገድ ያሳለፈዉን ዉሳኔ እንደሚደግፍ ፍንጭ ሰጥተዋል።
ጉዳዩን የሚያጠና የልዑካን ቡድንም ወደ አዲስ አበባ ለመላክ አቅደዋል።
የሁለቱ ሃገራት መንግሥታት ሰሞኑን ያሳዩት መቀራረብ ዓመታት ያስቆጠረዉን ጦርነትና ውዝግብ ለማስወገድ ይጠቅማል የሚል ተስፋን አሳድሮአል።
ሌሎች ደግሞ የኢህአዴግ መሪዎች የጋራ አቋም መያዝ እንደተሳናቸው ያመላክታል ይላሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የአልጀርስን ስምምነት በተመለከተ ስለተነሳዉ ተቃዉሞ በያዝነዉ ነው ሳምንት ለም ቤቱ ሰፊ ማብራርያ ሰጥተዋል።
በማብራርያቸውም የኢትዮጵያ መንግሥት ስምምነቱንና የድንበር ኮሚሽኑን ዉሳኔ የተቀበለው ከ ዓመት በፊት መሆኑን አመልክተዋል።
ስለዚህ የተቃውሞው ምንጭ የአልጀርሱ ስምምነት ሳይሆን ሌሎች ፖለቲካዊና ምጣኔ ሃብታዊ ጉዳዮች ሊሆኑ ይችላሉ የሚለዉን ግምት ይበልጥ እያጎላዉ መጥቶአል።
የኢትዮ ኤርትራ አዲስ ግንኙነት የኢህአዴግ ዉሳኔና የህወሓት ተቃዉሞ መወያያ ርዕሳችን ነዉ።
የሐረር ገበያ ዳግም እሳት ሐረር ከተማ ዉስጥ በሳምንት ልዩነት ባለፈዉ ቅዳሜ ማታም የእሳት አደጋ መድረሱን ኗሪዎቿ ይናገራሉ።
ኢትዮጵያ ድርቅና የእርዳታ ጥሪ በበርካታ የሀገሪቱ ክፍሎች ዉስጥ የተከሰተዉን ድርቅ በሚመለከት ተደጋጋሚ ዓለም አቀፍ የርዳታ ጥሪዎች ተደርገዋል።
እስካሁን ለችግር የተጋለጠዉ ሕዝብ ከ ሚሊየን በላይ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የእርዳታ ድርጅቶች ቁጥሩ ሊጨምር እንደሚችልም ያሳስባሉ።
ኢትዮጵያ ዉስጥ ከ ዓመታት ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ በተባለዉ ድርቅ የተጎዱትን ወገኖች ለመርዳት ከአንድ ቢሊየን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።
የዓለም አቀፍ ለጋሾች እርዳ መዘግየቱን ያመለከተዉ የኢትዮጵያ መንግሥትም ለጋሾች አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጡ አሳስቧል።
በርከት ያለ የእህል ምርት ለማፈስ ከጥንት ጀምሮ አርሶ አደሮች የዘር እኽል እየመረጡ በመዝራት አያሌ ዘመናት ጠብቀው ለማቆየት መቻላቸው የሚታበል አይደለም።
አንድ ርምጃ ሲወሰድ የሚያስከትለው ጉዳት ምን ሊሆን እንደሚችል ታሳቢ አድርጎ መንቀሳቀስ እንደሚገባ ራሳቸው ከታዘቡት አንድ ታሪክ በመነሣት እንዲህ ይላሉ።
ለዚህ ዝግጅት መነሻ የሆነን ባለፈው ሳምንት እንደጠቀስነው በሜክሲኮ ያህል ከአነዚህም ገሚሱ አነስተኛ የመሬት ይዞታ ያላቸው ባቄላ አምራቾች ያነሱት ጥያቄ ነው።
በፖላንድ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ብቻ በመጠቀም የሚያመርቱ አርሶ አደሮች ቁጥር ባፋጣኝ በመጨመር ላይ መሆኑ ይነገራል።
አዉሮጳና ሕገ ወጥ የሰዉ አሻጋሪዎች ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
ጀርመን ስደተኞች እና የመራሒተ መንግሥቷ አቋም ቢያንስ የሰው አመለካከት ለሁለት ተከፍሎአል፡፡
አሁንም ቢሆን አንዳዶቹ ከፊታችን የተደቀነውን ችግር እንፈታዋለን እንወጠዋለን ብለው የሚያምኑ ናቸው፡፡
ከዚያም አልፈው እንዲያውም እነሱ መራሂተ መንግሥትዋን ይህን እሳቸው ያለፈው ዓመት እንወጣዋልን ያሉትን ቃል ፊት ለፊት አሁን ይቃወማሉ ይተቻሉም፡፡
በጀርመን አገር ውስጥ ነገሮች እየተቀያየሩን እየተለዋወጡ እንደመጡ እዚያ እና እዚህ የሚታዩ ፍንጮች በቂ ምስክሮች ናቸው፡፡
ጊዜው ተቀይሮ ግን አሁን ለድርጅቱ አመቺ የሆነ ሰዓት የመጣ ይመስላል፡፡
እንዲያውም አንዳንዶቹ እዚህ እንደሚሉት የመጠጥና የራት ግብዣ አርዕስትም ሁኖ ብዙ ሰው ሳይፈራ ፊት ለፊት የሚነጋገርበት ጉዳይ ሁኖአል፡፡
በሌላ አካባቢ በታላቁዋ ብርታኒያ ለየት ያለ ሥዕል እዚያ እናያለን፡፡
እርግጥ ኑዋሪው ሕዝብ በመራሂተ መንግስትዋ ላይ ያለው አመለካከት እንደ አለፉት ጊዜያት ሳይሆን አሁን ተቀይሮአል፡፡
እንደ አለፉት አመታት ዘነድሮ መራሂተ መንግሥትዋ ወይዘሮ አንጌላ ሜርክል በሕዝቡ ዘንድ ተወዳጅ አይደሉም፡፡
አብዛኛው የጀርመን ሕዝብ ስደተኞቹን አስታኮ የመጣውን ችግር እንፈተዋለን የሚለውን ነገር ሙሉ በሙሉ አምኖ በልቡ አልተቀበለውም፡፡
በውጭ ጉዳይ ፖለቲካ ፖሊሲአቸውም ሆነ በሚያቀርቡት አመለካከታቸው መራሂተ መንግስትዋ እንደ አለፉት ዘመናት ዘንድሮም በአዉሮጳ መሪዎች ዘንድ ትልቅ ድምጽና ተቀባይነት አላቸው፡፡
ግን ያም ሁኖ ጀርመኖችም በስደተኞች ላይ ያላቸውና የነበራቸው አመለካከት ደግሞ እንዳለ ተቀይሮአል፡፡
በመጀመሪያ ቀናት ይታይ የነበረው የእንግዳ ተቀባይነትና የማስተናገድ መንፈስ ቀስ እያለ እየቀዘቀዘና እየበረደ አሁን ሌላ መልክ ይዞአል፡፡
ድንበሩ ቢዘጋ ደግሞ በሺህና በአሥር ሺህ በመቶና በሁለት መቶ ሺህ የሚቆጠሩ ነፍሳቸውን ለማዳን የሚሸሹትን ስደተኞች መርዳት በአልተቻለ ነበር፡፡
ትናንሽ ልጆችን የጀርመንኛ ቋንቋ በማስተማር አንዴ የጀመሩትን ሥራ አሁንም ቀጥለውበት ያስተምሩአቸዋል፡፡
ብቻቸውን እዚህ የደረሱትን ገና ለአቅመ አዳም ያልደረሱትን ወጣት ልጆች ወስደው እየተንከባከቡአቸው አሁንም ያሳድጉአቸዋል፡፡
መሥራት ለሚፈልጉት ሥራ የሙያ ትምህርት ቤት ገብተው ለመማር ለሚፈልጉት ለእነሱም ትምህርት ቤት አብረው ፈልገው እዚያ ይልኩአቸዋል፡፡
በሚሊዮን ከሚቆጠሩት አንዱም ስድተኛ መንገድ ላይ ሳያድር ሁሉንም ማስተናገድ በቀላሉ ታይቶ የሚታለፍ ሥራም አይደለም፡፡
የሆነው ሆኖ አሁንም ቢሆን ትልቁ ገና ያልተፈታው ችግርም ከፊታችን ተደቅኖ እንደ ቆመም መረሣት የለብንም፡፡
እሱም ሕብረተሰቡ የተገን ጠያቂን ስደተኛ ልጆችን ትምህርት ቤት አስገብቶ እነሱን ማስተማር አለበት፡፡
ነፍስ ያወቁትን ጎልማሦዎችን እንደዚሁ እነሱን አስተምሮና አሠልጥኖ የሥራ ዓለም ውስጥ ማሰማራትም ይኖርበታል፡፡
ይህ ሁሉ ደግሞ ሲሆን ጊዜና ጉልበት ከዚያም በላይ ብዙ ወጪ ገንዘብም የሚጠይቅ ሥራና ኃላፊነት ነው፡፡
እዚህ ቀርተው ለመኖር ለሚፈልጉ ስደተኞች የጀርመንን ቋንቋ መማር አላባቸው፡፡
ይህ አዲስ ሁኔታ ደግሞ አዲስ ነገር ይዞልን ሊመጣም ይችላል፡፡
ቁም ነገሩ ያለው ስደተኞቹን አቅፎና ተቀብሎ እነሱን ከሕብረተሰቡ ጋር በቀላሉ እንዲዋሃዱ መርዳቱ ላይ ነው፡፡
ያኔ ነው አብረው እነሱም ጀርመንን በአላቸው ችሎታ ለመገንባት አስተዋጽኦቸውን የሚያበረክቱት፡፡