input
stringlengths
1
130k
ላለፉት ሶስት ዓመታትም በአንድ መንግስታዊ ባልሆነ ድርጅት ዉስጥ በማህበራዊ አገልግሎት ሰራተኝነትና በሥነ ልቡና አማካሪነት ተቀጥራ እየሰራች ትገኛለች።
ቤዛዊት የክበቡን ዓላማ በመደገፍ አባል የሆነችዉ ከ ወር በፊት ሲሆን አባላቱን የተዋወቀቻቸዉም በፌስ ቡክ ነዉ።
ወጣቶቹ ለበጎ አድራጎት ስራዎቻቸዉ ጫማ በመጥረግ የሥነ ፅሁፍ ምሽቶችን በማዘጋጀት እና ከበጎ አድራጊ ግለሰቦች የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፎችን በመቀበል ይሰራሉ።
እዛ ላይ ያሉ ቃላቶች ናቸው ችግር እየፈተጠሩ ያሉት ።
እና አብዛኛው ሰው ትንታኔ ይሰጣል ለነገሩ ክብደት ሰጥቶ አይደለም ።
ከዚያ ነው ወደ መሬት ወርዶ ብዙ ዩኒቨርሲቲዎች ብዙ ቦታዎች እና ከተማዎች እየተበጠበጡ ያሉት።
ካለች በኋላ ወጣቱን ይህንን ለመለወጥና ለማስተካከል እንችላለን የሚል እምነት አለኝ።
በእነዚህ ዉይይቶች ፌስ ቡክ ላይ ያለዉ ገፅታ ከነባራዊዉ ሁኔታ የተለዬ መሆኑን ተገንዝበናል ይላል ወጣት ናኦል።
የክበቡ አባላት በአዳራሽ ከሚያዘጋጁት ዉይይት በተጨማሪ ዘረኝነትን የሚቃወም ፍቅርና ሰላምን የሚሰብኩ ቃላትን በመጠቀምና በተናጠል ሰዎችን በማነጋጋርም የጎዳና ላይ ቅስቀሳዎችንም ያደርጋሉ።
የዚህ አይነቱ ቅስቀሳ በኢትዮጵያ ብዙ የተለመደ ባይሆንም ከማህበረሰቡ ያገኙት ምላሽ ግን በጣም ጥሩ እንደነበር ወጣት ገላዉዲዎስ ያብራራል።
እንደ ወጣት ገላዉዲዮስ እምነት እስካሁን ለወጣቶች መፍትሄ የሚፈልጉት ትልልቆቹ በመሆናቸዉ ወጣቱ የመፍትሄ አካል አልነበረም።
በመሆኑም ወጣቶች በሚያመቻቸዉ መንገድ በመሰባሰብና በመወያየት የሀገሪቱን ችግር በመፍታት ሂደት ሊሳተፉ ይገባልም ይላል።
ወጣቶች በያሉበት በጣም ብዙ ችግር ያለበት አገር ስለሆንን ትንሽ ነገር ማድረግ እንኳ በጣም የ ሶሉሽን አካል እንደ መሆን ነዉ።
ከክፉ ስራ ጋር አላለመተባበር ራሱ ትልቅ የ ሶሉሽን አካል መሆን ነዉ።
ወጣቶቹ በግል በመሰረቱት ክበብ በትርፍ ጊዜያቸዉ የሚንቀሳቀሱ በመሆኑ የሚሰጡት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በአቅምም በጊዜም የተወሰነ በመሆኑ የፈለጉትን ያህል አለመስራታቸዉን ይገልፃሉ።
በመሆኑም በቀጣይ በተሻሻለዉ የሲቪክ ማህበራት እና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች አዋጅ መሰረት ክበቡን ህጋዊ ሰዉነት ለማሰጠት አቅደዋል።
ይህም በቦታና በጊዜ እንዲሁም በአቅም ሳይወሰኑ ሀገራቸዉን በበጎ ፈቃድ ለማገልገል እንደዚሁም ሰፊ ስራ ለመስራት እንደሚያስችላቸው ይናገራሉ።
ኢትዮጵያ በ ኛዉ የተመድ ጉባኤ የኢትዮጵያ ተሳትፎና የሕዳሴዉ ግድብ ኢትዮጵያ በ ኛው የተመድ ጉባዔ በከፍተኛ ባለሥልጣናት ደረጃ እንደምትሳተፍ ተገለጸ።
ኢትዮጵያ በተመድ ኛ ጉባዔ በከፍተኛ ደረጃ ትሳተፋለች ኢትዮጵያ በ ኛው የተመድ ጉባዔ በከፍተኛ ባለሥልጣናት ደረጃ እንደምትሳተፍ ተገለጸ።
አገሪቱን የሚያስተዳድረው ወታደራዊ ምክር ቤት ሥልጣኑን ለሲቪል መንግሥት እንዲያስረክብ የሚሹት የአገሪቱ ተቃዋሚዎች መከፋፈል ቀውሱ እንዲህ በቀላል መፍትሔ ለምግኘቱ አጠራጣሪ አድርጎታል።
የሱዳን የቀድሞ ፕሬዝዳን ኦማር ሐሰን አል በሽር ከስልጣን ገለል ቢሉም ይመሩት የነበረው ሥርዓት አሁንም እንዳለ ነው።
የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች የአፍሪካ ኅብረት እና ኢትዮጵያን ጨምሮ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በየራሳቸው መንገድ ለሱዳን ፖለቲካዊ ቀውስ መፍትሔ እያፈላለጉ ነው።
በሱዳን የሚኖር የኃይል አሰላለፍ ለውጥ በኢትዮጵያ እና የምስራቅ አፍሪካ አገራት ላይ ምን አይነት ተፅዕኖ ያሳድራል
በዛሬው የማኅደረ ዜና መሰናዶ ገበያው ንጉሴ የሚመለከተው ጉዳይ ነው።
ኮሮና በአውሮጳ ያሳደረው ተጽእኖ በአሜሪካ እና በአውሮጳ ተህዋሲው በአስደንጋጭ ፍጥነት እየተሰራጨ ነው።
ዶ ር እንዳወቀ የጠፈር ሳይንስ በአዳጊ አገራት በማስፋፋት ይታወቃሉ ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
ተግባር ላይ የዋለው የማስተማሪያ ዘዴ የአንደኛ ክፍል ተማሪዎች በፊት አባጫዳ በሚል ሲማሩ የነበሩበትን የአፋን ኦሮሞን ፊደል አሁን ላአጋማ በሚል ተክቷል።
ን በመዋዕለ ሕፃናት ተምረው ወደ አንደኛ ክፍል የገቡት ተማሪዎች በአዲሱ የማስተማሪያ ዘዴ እንደተደናገሩና ይህም ለአስተማሪዎችም ይህም ትልቅ ችግር መሆኑ ተገልጿል።
ይህ ጉዳይ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ከተሰራጨ በኋላ በሁለተ ጎራዎች የተከፈለ ከፍተኛ ክርክር ቀስቅሷል።
የመጀመሪያው ቡድን በትዊተር ላይ የተሰኘና የሚል ሃሽታግ በመጠቀም የፊደሉ ቅደም ተከተል እንዳይቀየር ዘመቻ አካሂደዋል።
የተባባሩት መንግስት እቅድ በሆነው የምዕተ አመቱ የልማት ግቦች ዉስጥ ድህነት ቅነሳ አንዱ ነዉ።
አገሮች በ ዘዴ በመጠቀም በ ቋንቋዎች ላይ የተማሪዎች የማንበብና የመጻፍ ችሎታ መፈተሻቸውን ዶክተር ቶላ ባርሶ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል።
በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ተወስደው ሺህ ተማሪዎች ላይ ጥናቱ ተደርጓል።
በኦሮሚያም በ ዞን ዉስጥ በ ትምህርት ቤቶች ላይ ጥናቱ ተካሂዷል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአፋን ኦሮሞ ክፍለ ትምህርት የስነ ቋንቋ መምህር የሆኑት ዶክተር ቶላማርያም ፉፋ በዝህ ጥናት ላይ መሳተፋቸዉን ይናገራሉ።
እንደ ዶክተር ቶላማርያም ገለጻ በቋንቋዎች ዉስጥ የትኛዉ ፊደል ተደጋግሞ እንደሚመጣ ወይም የሚለካ ፕርምያር ፕሮ የተሰኘዉን ሶፍትዌር ተጠቅመዋል።
በዝህም መሰረት የተገኘዉ ዉጤት ለምሳሌ በአፋን ኦሮሞ ፍደል ዉስጥ ከ በላይ ተደጋግሞ መጥቷል።
ተደጋግመው በመጡት ፊደላት ላይ በመመርኮዝ ለአንደኛ ክፍል አዲስ መፅሃፍ መዘጋጀቱንም ይናገራሉ።
በመጻፉም ላይ ተማሪዎች በፊት በሚመሩበት ፈንታ በ እንዲማሩ መደረጋቸዉን ዶክተር ቶላማርያም አክለውበታል።
ይልቁንስ በፊደል ተርታ ላይ በ ኛ ደረጃ ላይ እንደተቀመጠጠቅሰዋል።
የዚህ ፕሮጄክት አባል የሆኑት የስነ ቋንቋ ባለሙያ አቶ አማኑኤል ራጋ ይህ ዘዴ አለው ያሉትን ተጽዕኖ ለዶይቼ ቬሌ እንዲህ ገልጸዋል፥
ሁለተኛዉ የዚህ የአዲሱ የቁቤ አፋን ኦሮሞ ታኣማኒነት ጥያቄ ዉስጥ ነዉ ያለዉ።
እዉነት ይህ የቁቤ ችግር ነዉ ወይ የሚል ጥያቄ ማንሳት አለብን።
ከዛ በተረፈ የቁቤ አፋን ኦሮሞ ከኦሮሞ ቀንቋ ታሪክና ከሕዝቡ ጋር የተገናኘ ነዉ።
የአሮሞ ማንነት በዚህ ሰዓት የሚገለጸዉ ወይም ኦሮሞነትን ለመግለጽ የቀረዉ ነገር ካለ ቀንቋዉ ነዉ።
ስለዚህ ይህን ከማንነት ጋር የተቆራኘ ነገር መነካካት አስፈላጊ አይደለም።
ተማሪዎችን መጀመርያ የሚለዉን እስከ መጨረሻ ድረስ ካስተማርክ በኋላ የማንበብና መጻፍ ማስተማርያ ዘዴ ነዉ የተባለዉን ብታስከትል ኖሮ ችግር አልነበረም።
ከ የሚጀምረዉን ፍደል ሰዉ በመጽሀፉ ሲመልከት የቁቤ አፋን ኦሮሞ ቅደም ተከተል ተቀየረ የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሱና መከራከሩ ትክክል ነበረ።
ባለሙያዎችን ለምን ቀየራችሁት ተብለው ሲጠየቁም በመዋለ ሕፃናት የተለመደዉን ፊደል ተምረው ስለሚመጡ የሚል መልስ ተሰጥቶ ነበር።
ከከተማ ዉጭ በገጠር ያለዉ አብዛኛዉ ተማሪ መዋዕለ ሕፃናት ስለሌለ የተለመደዉን ፊደል የት ተምረው ይመጣሉ ብዬ ጠይቃቸዉ ነበር።
ጽህፈት ቤቱ ህብረተሰቡንና አብዣኞቹን ባለሙያዎች ስለማስተማሩ ዘዴ አለማሳወቁን ዶክተር ቶላ እንደ ችግር ይቀበላሉ።
በጥናቱ እና መጽሀፉን በማሳተም አስተዋፅዖ የነበራቸዉ ዶክተር ቶላማርያም ዶክተር ቶላ ያቀረቡትን ሃሳብ ይጋራሉ።
ባላፈዉ እሁድ የክልሉ ትምህርት ጽህፈት ቤት ብሮ ባለሙያዎችን በመሰብሰብ በአንድ ወር ዉስጥ መጻሃፉ እንዲገመገም የጎደለዉ እንዲሟላ ማመወያየቱን ለመረዳት ተችለዋል።
የስነ ቋንቋ ባለሙያዉ አቶ አማኑኤል ራጋ ትምህርት ጽህፈት ቤቱ ሊያደርግ ያቀደዉን ለዉጥ ተቀብለው ዉጤቱን ግን ቆይቶ የሚታይ ይሆናል ብለዋል።
እንደ ጎርጎሮሳዊው የተመሠረተው የሃገራቱ ቡድን ቦርኪናፋሶ ማሊ ሞሪታንያ ኒጀር እና ቻድን ያቅፋል፡፡
የአውሮጳ ኅብረት መቀመጫ በሆነችው ብራስልስ የሚገኘው ዘጋቢያችን ኅብረቱ ለመርሃ ግብሩ ማስፈጸሚያ ስለለገሰው እርዳታ ዘገባ ልኮልናል፡፡
ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ንግድ ባንክ ሀብታሙን እንጅ ድሃውን አማራ አልፈልገውም በማለቱ በርካቶች አማራጭ ባንክ እየፈለጉ ነው።
ገንዘቡን ከንግድ ባንክ በማውጣት ደግሞ ይበልጥ አጋርነቱን ማሳየት አለበት ሲል በንግድ ባንክ ላይ የተነሳውን ተቃውሞ አበረታቷል።
ጌታቸው በተቃውሞ የተቀዳደዱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መገልገያ ደብተሮች የሚያሳይ ምስል በፌስቡክ ገጹ አሰራጭቷል።
ኪዳነማርያም ደግሞ ንግድ ባንክ ላይ የተከፈተው ዘመቻ አግባብነት የለውም።
ንግድ ባንክ መስጠት ካልፈለገ ትዝብቱን ለህዝብ እንተወው የሚል ሐሳባቸውን አጋርተዋል።
ንግድ ባንክ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀጥሎ የሐገሪቱ እና የኢትዮጵያውያን ሐብት ነው በማለት ዘመቻውን ነቅፈዋል።
በማኅበራዊ ድረ ገፆች የተደረገው ዘመቻ ፍሬ አፍርቶ ባንኩ ሚሊዮን ብር ለመስጠት ቃል መግባቱን የሚጠቁም ደብዳቤ ተሰራጭቶ ነበር።
ወሬው ከተሰማ በኋላ ደጀን ምንይሉ ንግድ ባንክ ሚሊዮን ብር እያለቃቀሰ ሰጠ ነዉ ምትሉኝ
በገዛ ገንዘባችንም አንደለልም ከዚህ በኋላ ለሁሉም ጉዳይ የራሳችን ምርጫዎች ይኖሩናል ሲሉ ሐሳባቸውን አጋርተዋል።
ባንኩ ለአምቦ ስታዲየምም ሆነ ለአማራ ክልል ተፈናቃዮች የሰጠው የገንዘብ ድጋፍ የለም።
ስለሆነም እያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ የሚያገለግለውና የሚደግፈው ፍትሃዊና ምክንያታዊ በሆነ አግባብ በራሱ ተነሳሽነት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል የሚል ሐሳብ ይዟል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለተፈናቃዮች ድጋፍ አልሰጠም የሚለው ዘመቻ የቀሰቀሰው ፍጭት ከፍ ብሎ የተቋሙን አመራሮች የብሔር ስብጥር ወደማጠያየቅ ተሻግሯል።
የማኅበራዊ ድረ ገፆች ተጠቃሚዎች አራማጆች እና ፖለቲከኞች ይኸንንው የብሔር ስብጥር ያሳያል ያሉትን ቁጥር እያጋሩ ነው።
ቆጠራው የኢትዮጵያ መንግሥት በመጪው መጋቢት ቀን ይጀመራል ተብሎ ይጠበቅ የነበረውን የሕዝብ እና የቤት ቆጠራ ለማራዘም ሐሳብ አቅርቧል።
ዮሐንስ የተባሉ የትዊተር ተጠቃሚ የኢትዮጵያ የሕዝብ ቆጠራ ውጤትን ሳስበው ሳስበው በጣም ያስቀኛል።
ኦሮሞ እና አማራ እያንዳንዳቸው ሚሊየን ነን ማለታቸው አይቀርም ሲሉ በቀልድ ሥራው የገጠመውን ፈተና አስቀድመው ለመጠቆም ሞክረው ነበር።
የማራዘም ሐሳቡ በይፋ መቅረቡ ከመሰማቱ በፊት ማሒ የተባሉ ትዊተር ተጠቃሚ የሕዝብ እና የቤት ቆጠራውን እናራዝመው።
በሚሊዮን የሚቆጠሩ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ቆጠራውን ለማካሔድ ትክክለኛው ጊዜ አይደለም።
ኖሌ ጃላል የተባሉ የትዊተር ተጠቃሚ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ከቆጠራው አውጪኝ።
ኖሌ ለመሆኑ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን በቆጠራው እንዴት ሊያካትቷቸው አቅደዋል
በተለያዩ ግጭቶች የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ መኖሪያ ቀያቸው አለመመለሳቸው ቆጠራውን ለማራዘም ካስገደዱ ምክንያቶች መካከል እንደሚገኝበት የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት አስታውቋል።
ዐቢይ ኢትዮጵያውያን አቅማቸውን በማኅበራዊ ሚዲያ ዐውደ ውጊያ ሀገር ለማተራመስ ከመጠቀም እንዲቆጠቡ መክረዋል።
አለሙ ማንአለብህ አንዳንድ ጊዜ ጠቅላይ ምኒስትሩ እንደ አራማጅ ይሆናሉ።
ትክክል የሚሰሩ እውቅና ሊሰጣቸው የተሳሳተ ሥራ የሚሰሩ ደግሞ በሕግ ሊጠየቁ ይገባል የሚል አስተያየታቸውን በጠቅላይ ምኒስትሩ ደብዳቤ ግርጌ አስፍረዋል።
ጴጥሮስ ታደሰ በበኩላቸው ያለውን እውነት ማወቅ አለበኝ ብዬ ሙሉ ፅሁፍን አነበብኩት።
እውነት አለህ በፍቅር ታምናለህ እውነቱን ለህዝብ አስረዳ ውስጣችሁ ምንድን ነው የገባው
ቆፍጠን መረር ጨከን ማለት ካልቻሉ ሀገራችን እንዳይሆን እየሆነች ነው።
ከሙሉ አክብሮት ጋር ቦታዎን ለሚመጥነን ጉልቤ መሪ ይልቀቁና የመኖርም የመሥራትም ዋሥትናችን ይረጋገጥ የሚል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ጃራ ፈጠነ በበኩላቸው የተከበሩ ጠቅላይ ምኒስትር የማኅበራዊ ድረ ገፆች አጠቃቀምን የሚገዛ መመሪያ ይዘጋጅ ዘንድ ያስቡበት።
ፅንፈኞች ኹከት ከመፍጠራቸው በፊት ጊዜ ያለ አይመስለኝም ሲሉ ሥጋታቸውን ገልጸዋል።
ጌታቸው ሳሙኤል ፈለቀ በወገናቸው እነዚህ የሀሰት ዜና የሚፈበርኩትን ለይቶ እርምጃ የማይወሰደው ለምንድ ነው
ያም ከሆነ ሶሻል ሚዲያውን ድርግም አርጎ ሰው ልቡን እስኪገዛ መዝጋት ነው ሲሉ ከጃራ ፈጠነ ጋር ተመሳሳይ ሐሳብ አንጸባርቀዋል።
ኢትዮጵያ ድሬደዋ አዲስ ከንቲባ ተሾመላት የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት በዛሬው ዕለት አዲስ ምክትል ከንቲባ ሾመ።
በፊደራል መንግሥት እና በአስሰተዳደሩ የተከናወነው የፖለቲካ ሪፎርም አካል ተደርጎ የሚወሰድ ነው የዛሬው የአመራር ለውጥና ሽግሽግ።
በዚህ ሂደት በዛሬው ዕለት በምክትል ከንቲባነት አስተዳደሩን እንዲመሩ የተሾሙት አቶ መሀዲ ጌሬ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት እንደሚሰሩ ተናግረዋል ፡፡
ምክትል ከንቲባው የወጣቶችን ችግሮችን ለመፍታት ከወጣቱ ጋር በሰለጠነ አግባብ እንሰራለን ብለዋል ፡፡
በዕለቱ የም ቤቱ ስብሰባ በሀላፊነት የተሾሙ አካለት ሀላፊነታቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን በቃለ መሀላ አረጋግጠዋል ፡፡
በአስተዳደሩ የተካሄደው የፖለቲካ ሪፎርም በሚፈለገው መልኩ ውጤት ስለማምጣቱ ቀጣዩ ጊዜ ምላሽ ይሰጣል።
ወባ መሰሉ ዴንጊ በሽታ በኢትዮጵያም መስፋፋት ጀምሯል በመላው ዓለም በበርካታ ሀገራት በስፋት የሚታየው የዴንጊ ትኩሳት በኢትዮጵያ እምብዛም ስሙ ሲነሳ አይሰማም።
በቅርቡ የተደረገ ጥናት ግን በሽታው በሰሜን ኢትዮጵያ ባሉት በመተማ እና ሁመራ መታየቱን አመልክቷል።
በአካባቢው በሽታውን እንደ ወባ የመውሰድ ችግር እንዳለ ጥናቱን በዋነኛነት ያካሄዱት የጎንደር ዩኒቨርስቲ ምሁር ይናገራሉ።
በርካቶችን ለአልጋ በሚዳርግባቸው በእስያ ደቡብ አሜሪካ እና ምዕራብ ፓስፊክ ባሉ ሀገራት በከፍተኛ የጤና ችግርነት ተመዝግቧል።
በመላው ዓለም ደግሞ በዓመት እስከ ሚሊዮን ሰዎች በበሽታው እንደሚለከፉ በጉዳዩ ላይ የተደረገ አንድ ጥናት ጠቁሟል።
በበሽታው ተጋላጭነት ላይ የተደረገ ሌላ ጥናት ቁጥሩን ከሚሊዮን ወደ ቢሊዮን ያሻግረዋል።