input
stringlengths
1
130k
የመጀመሪያዉ ሥለ ኑክሌር መርሐ ግብራችን ግልፅ ጎዳናን መከተል ነዉ።
ይሁንና የኢራን የኑክሌር መርሐ ግብር የዓለም ሕግን የጠበቀ መሆኑን ለዓለም ይበልጥ በግልፅ ለማሳየት ዝግጁ ነን።
በኢራንና በሌሎች ሐገራት መካካል ያለዉ መተማመን አደጋ በገጠመዉ ሥፍራ ሁሉ መተማመንኑን ለማዳበር እንጥራለን።
በኔ እምነት በኢራን ላይ የተጣለዉን ማዕቀብ ማስወገድ የሚቻለዉ በዓለም ሕግ መሠረት ግልፅንነትንና መተማመን በማዳበር ነዉ።
የአዮቶላሕ ሆሚንዋ ታላቅ ሰይጣን እና የጆር ቡሽዋ የሰይጣን ዛቢያ መሪዎች ለየጥቅማቸዉ መከበር የጎበዝ መዉጪያ ዉን እኩል አዉቀዉታል።
ካላሰለሰ ድርድር በኋላ በጋራ የድርጊት መርሐ ግብር ላይ ዛሬ ከስምምነት ደረስን።
ቴሕራንና ዋሽግተኖች በሰላሳ አራት አመታት ለመጀመሪያ ጊዜ አግባቢ ሥምምነት ተፈራረሙ።
ስምምነቱን ከፈረሙት አንዱ የዩናይትድ ስቴትሱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ጆን ኬሪ ስምምነቱ ከማንም በላይ የእስራኤልን የደሕንነት ሥጋት እንደሚያስወግድ እርግጠኛ ነበሩ።
ይሕ የመጀመሪያዉ እርምጃ የኢራን መርሐ ግብርን አሁን ካለበት ወደ ኋላ እንደሚመልሰዉ በአፅንኦት መናገር እፈልጋለሁ።
ይሕ ስምምነት ባይደረግ ኖሮ የማይኖረዉን የማብላላት ማቋረጫ ጊዜ ያሰፋዋል።
ጠቅላይ ሚንስትሯ ቤንያሚን ኔታንያሁ ታላቁን ስምምነት ታላቅ ስሕተት አሉት።
ከዓለም እጅግ አደገኛዉን የጦር መሳሪያ ለመታጠቅ ታላቅ እርምጃ አድርጓልና።
የዓለም ሐያላን እራሳቸዉ ያስፀደቁትን የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤትን ዉሳኔ ተቃርነዉ ኢራን ዩራኒየም ማንጠሯን እንድትቀጥል ለመጀመሪያ ጊዜ ተስማሙ።
የትልቂቱ ሐገር ልዩ ወዳጅ ተቃዉሞ ለፕሬዳት ኦባማ በግል ለመስተዳድራቸዉ በጥቅል ታላቅ ቅሬታን ነበር የፈጠረዉ።
ይሁንና ኦባማ ለልዩ ወዳጅነቱ ክብር ብለዉ የሰላም ዉል መብጠልጠሉን አልፈቀዱም።
ጠንካራ ቃላትና ፉከራ ፖለቲካን ለማራመድ ቀላሉ ነገር ይሆን ይሆናል።
የቃለ መሐላዉ ሥርዓት መጠን ሰብሰብ ቀዝ ቀዝ ያለ ነበር።
እስከ ሰሜን ኮሪያ እንደታየዉ ጦረኝነታቸዉን በሰላም አራማጅነታቸዉ ለማካካስ አንድ ሁለት ያሉበት ዘመን ነበር።
በሳልስቱ እስራኤል ዉስጥ በተደረገዉ አጠቃላይ ምርጫ አክራሪዉ የጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔትንያሁ ፓርቲ ሊኩድ አሸነፈ።
ደቡብ ኮሪያዎች ሁለት ሺሕ አስራ ሰወስትን የተቀበሉት አለምን ባስደደመዉ በድምፃዊ ፓርክ ጄ ሳንግ አዲስ ሙዚቃ ዳንኪራ እየረገጡ ነበር።
የዓለም ወጣት በገፍ ሊያጅባቸዉ ሲታደም ግን ሶሎች ከፒዮንግዮንግን የሚንቆረቆርላቸዉን የጦርነት ቀረርቶ ለማዳመት ተገደዱ።
ጥርያ ሃያ ሰወስት ሰሜን ኮሪያ ሰወስተኛ የኑክሌር ቦምብ እንደምትሞክር አስጠነቀቀች።
ለፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ አዲስ ዘመነ ሥልጣን አዲስ ቀዉስ ለአዲሱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትራቸዉ ለጆን ኬሪ የመጀመሪያዉ ፈተና ነበር።
ከቶኪዮ ከኒዮርክ ብራስልስ ዉግዘት ማስጠንቀቂያዉ ቢጎርፍም የሰላሳ ዓመቱ ወጣት መሪ ኪም ጆንግ ኡን ከቁብ አልቆጠሩትም።
ኪም ጆንግ ኡን ግን ደም ሳያፈሱ ሁለት ሺሕ አስራ ሰወስትን መሰናበት አልፈቀዱም።
ወጣቱ ኪም ምክትላቸዉንና አማቻቸዉን ዦዉግ ሶንግ ቴን ለኮሪያ ልሳነ ምድር ቆሌ ጭዳ አደረጉ።
ደቡባዊ ብራዚል ዉስጥ አንድ የዳንካሪ ቤትን ያጋየ እሳት ሁለት መቶ ሰላሳ ሰዎችን ገደለ።
እስራኤል ካንዴም ሁለቴ ሶሪያን መደብደቧ አማፂያን ደማስቆን አሌፖን ዳራዕ፥
ሐማ ሆምስን ወዘተ ማሸበራቸዉ የተማረኩ ወታደሮችን ማረድ መተልተላቸዉ ለዋሽግተን ብራስልስ ለሪያድ ዶሐ አንካራ ገዢዎች የሚወገዝ ወንጀል አልነበረም።
የብሪታንያ ምክር ቤት የጠቅላይ ሚንስትር ዴቪድ የካሜሩንን የዉጊያ ዕቅድ ዉድቅ ሲያደርገዉ፥
ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማም ከኢራን በፊት ሶሪያ ላይ የጎበዝ መዉጪያ ያፈላልጉ ያዙ።
በሌላ በኩል የደማስቆ ገዢዎች ኬሚካዊ ጦር መሳሪያቸዉን እንዲያስረክቡ በመገፋፋታቸዉ አስፈሪዉ ጦርነት ሳይቀጣጠል ከሰመ።
ኦባማም የሶሪያ ኬሚካዊ ጦር መሳሪያ የሚወድምበት ጊዜ እንዲገደብ ከመጠየቅ ጋር ከጦርነት ተገላገሉ።
ቻይና እና ሩሲያ ለተጫወቱት ገንቢ ሚና ምስጋና ይግባዉና ሶሪያን ለመዉጋት የሚቀርብ ምክንያት አይኖርም።
ግብፅ የሠላሳ ዘመን አምባገነን ገዢዋ በሕዝባዊ አመፅ የተወገዱበትን ሁለተኛ ዓመት ባከበረች ማግስት ሐገር ጎብኚዎች ሞቱባት።
የካቲት ሃያ ስድስት በተንሳፋፊ የላስቲክ ፊኛ ይጓዙ የነበሩ ሐገር ጎብኚዎች ፊኛቸዉ አየር ላይ ነዶ ሞቱ።
አደጋዉ ፕሬዝዳት መሐመድ ሙርሲን የሚቃወሙ ግብፆችን ከሠልፍ ተቃዉሟቸዉ አላናጠባቸዉም ነበር።
ሞቅ ቀዝቀዝ የሚለዉን ተቃዉሞ አድፍጠዉ ሲጠባበቁ የነበሩት ጄኔራል አብዱል ፈታሕ አል ሲሲ የልባቸዉን አደረሱ።
መፈንቅለ መንግሥቱን የተቃወመዉን ሰልፈኛ የጄኔራል አል ሲሲ ጦር ከሰማይ በሔሊኮብተር፥
የሰላሳ ዘመኑ ወታደራዊ መሪ ሆስኒ ሙባራክ ወደ በቁም እረኝነት እንዲጠበቁ ከወሕኒ ቤት ተፈቱ።
የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት አስራ ስድስተኛ ሥልጣን ለቀቁ።
ቤኔዲክት አስራ ስድስተኛ ሥልጣን ሲለቁ በቤተ ክርስቲያኒቱ የስድስት መቶ ዓመት ታሪክ የመጀሪያዉ ናቸዉ።
መጋቢት ላይ የመጀመሪያዉ ደቡብ አሜሪካዊ ቄስ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳስነቱን ሥልጣን ያዙ።
በተለይ ፕሬዝዳት ጆርጅ ደቡሊዉ ቡሽ እንደ ሰይጣን በመቁጠር የቆሙበትን ሥፍራ ድኝ ድኝ ይሸታል በሚል ተረባቸዉ እዉቅናን አትርፈዉ ነበር።
በወሩ የቀድሞዋ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ባሮነስ ማርጋሬት ታቸር ተከተሉ።
ወግ አጥባቂዋ ፖለቲከኛ የመጀመሪያዋ የብሪታኒያ ሴት ጠቅላይ ሚንስትር ግን አወዛጋቢ ፖለቲከኛ ነበሩ።
ባንግላዴሽ ዉስጥ አንድ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ሕንፃ ተንዶ አንድ ሺሕ አንድ መቶ ሃያ ሰባት ሠራተኞችን ፈጀ።
የሃያ ዘጠኝ ዓመቱ የዩናይትድ ስቴትስ ሰላይ ሐገሩን ከድቶ ሆንግ ኮንግ መግባቱ ተነገረ።
በሆንግ ኮንግ አድርጎ ሞስኮ የገባዉ ስኖደን የትልቂቱ ሐገር የስለላ ቅሌትን ይዘረግፈዉ ገባ።
ዩናይትድ ስቴትስ የቅርብ ወዳጅዋን የጀርመን መራሒተ መንግሥት የአንጌላ ሜርክልን የስልክ ንግግር ሳይቀር የመጠለፏ ቅሌት የዓለም መሪዋን ሐገር፥
በዓለም ሕዝብ ዘንድ እንዳቀለላት ዓለም ሌላ ጉድ ግን አሳዛኝ ጉድ ከወደ ላምፔዱዛ ኢጣሊያ ሰማ።
በአብዛኛዉ የኤርትራ ስደተኞችን ያሳፈረች አንዲት ጀልባ ሰጥማ ከሰወስት መቶ በላይ ስደተኞች አለቁ።
በነዳጅ ዘይት የበለፀገችዉ ሳዑዲ አረቢያ ሕገ ወጥ የዉጪ ስደተኞችን ወደየሐገራቸዉ ማጋዝ ጀመረች።
እና እስራኤል ፍልስጤሞሽ ለሰባ ዘመናት ያሕል እንደኖሩበት ድርድር እያሉ እንደተጋደሉ፥
ብራዚል ኳስ እንዳለች ሁለት ሺሕ አስራ ሰወስት አዲዮስ አሚጎስ።
የኢራን እና ስዑዲ ዓረቢያ ውዝግብ በሞት መቅጣቷ የፈጠረው ቁጣ ነገሩን እንዳጦዘው ተገልጧል።
የሼሕ ኒምር አል ኒምር በስዑዲ ዓረቢያ በሞት መቀጣት የኢራንን ሕዝብ አስቆጥቶ አደባባይ እንዳስወጣው ይታወሳል።
ያም ብቻ አይደለም ሕዝቡ በመዲናዪቱ ቴሕራን የሚገኘው የስዑዲ አረቢያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢን በእሳት መለኮሱ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱ እንዲቋረጥ ሰበብ ተደርጎ ይወሰዳል።
በእርግጥ በስዑዲ ዓረቢያ እና ኢራን መካከል በአካባቢው ተሰሚነትን ለማግኘት የሚደረግ ፉክክር ቢኖርም ማለት ነው።
የኢራን እና ስዑዲ ዓረቢያ ውጥረትን በተመለከተ የጂዳ ተባባሪ ዘጋቢያችን ነቢዩ ሲራክን በሥልክ አነጋግሬዋለሁ።
የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት መቋረጥን ተከትሎ የሌሎች ሃገራት ውሳኔ ምን እንደሚመስል በመተንተን ይጀምራል።
በመቶ እናቶች በጤና ተቋማት ይገላገላሉ ኢትዮጵያ ውስጥ የጤናማ እናትነት ወር በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲታሰብ ዓመታት እንዳስቆጠረ ተገልጿል።
አባል ሀገራቱ በዚሁ ጥያቄ ላይ አንድ አቋም መያዝ ሳይችሉ ነው የቀሩት።
የራሱ የኪምበርሊ ሂደት አባል መንግስታት የጠበብት ኮሚሽን፡ የዚምባብዌ አባልነት ለስድስት ወራት እንዲቋረጥ ሀሳብ አቅርቦ ነበር።
ይሁንና፡ ይኸው ሀሳቡ ግን በስብሰባው ተካፋዮች ዘንድ ተቀባይነትን ሳያገኝ የቀረበት ድርጊት ታዛቢዎችን እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን አብዝቶ አስቆጥቶዋል።
ዚምባብዌ ከሂደቱ አባልነት ለጊዜው ብትገለል ኖሮ በዓለም ገበያም ላይ የአልማዝ ምርትዋን መሸጥ ባልቻለች ነበር።
ከዚምባብዌ የማዕድን አካባቢዎች በዚህ በተያዘው ዓመት እጅግ አሳሳቢ የሆኑ ዘገባዎች ተገኝተዋል።
በብዙ መቶ የሚገመቱ ሰዎች በፕሬዚደንት ሙጋቤ ጸጥታ አስከባሪዎች ሳይገደሉ አልቀሩም ነው የሚባለው።
ይህ ለኛ ዚምባብዌን ከአባልነት ለማግለል የሚያስችል ሁነኛ ምክንያት ነው።
ይሁንና፡ ብዙዎቹ የኪምበርሊ ሂደት ተወካዮች ከዚህ የተለየ አቋም ነው የያዙት።
የአስተናጋጅዋ ሀገር ናሚቢያ ኬኔዲ ሀሙሴንያ የኪምበርሊ ሂደት ለዚምባብዌ ፖለቲካዊ ችግር ተጠያቂ እንዳልሆነ አስረድተዋል።
የኪምበርሊ ሂደት የሰብዓዊ መብትን የማስከበር ዓላማ ይዞ የተነሳ መድረክ አይደለም።
ለዚህ የቆሙ ለምሳሌ፡ የተመድ ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤትን የመሳሰሉ ሌሎች ድርጅቶች አሉ።
ያማጽያን ቡድኖች አንድን በህጋዊ መንገድ የተመረጠ መንግስትን ከስልጣን ለማውረድ የሚጠቀሙበት አልማዝ ማለት ነው።
ብዙዎች አሁን የሚሉት አልማዝ ግን ለንዲህ ዓይነቱ ውዝግብ አገልግሎት የሚሰጥ አይደለም።
ቮልፍ ክርስትያን ፔይስ ይህን የ መከራከሪያ ሀሳብ አርኪ ሆኖ አላገኙትም።
በርስበርስ ጦርነት እና በሌሎች ውዝግቦች መካከል ልዩነት ለማድረግ የሚሞከርበት ሁኔታ ትርጉም አልባ ነው።
እርግጥ ነው የደም አልማዝ የሚለው ቃል ትርጉም ግልጽ አይደለም።
ይህም ቢሆን ግን፡ አሁን በዚምባብዌ ይፈጸማል የሚባለው የኃይል ተግባር ደረጃ ሲታይ አንድ ርምጃ መውሰዱ ተገቢ ይሆናል።
ችግሩ ከቦትስዋና በስተቀር ሁሉም የዚምባብዌ ጎረቤት ሀገሮች ሀራሬ በሚገኘው መንግስት አንጻር ጠንካራ ርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ አለመሆናቸው ነው።
የኪምበርሊ ሂደት ተወካዮች በናሚቢያው ስብሰባቸው ከዚምባብዌ ጎን መመልከት የነበረባቸው ሌሎች ተጨማሪ ችግሮችም ነበሩ።
የኪምበርሊ ሂደት አባላት የአልማዙ ሽያጭ ገቢ ለርስበርሱ ጦርነት ማካሄጃ ሳይውል እንዳልቀረ አስረድተዋል።
ከዚያን ጊዜ ወዲህ የኮት ዲቯር የአልማዝ ምርት አልቀነሰም አልማዙ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ከሀገር እንዲወጡ ይደረጋል።
ለውዝግቦች የመፍትሄ ሀሳቦችን የሚያቀርበው ድርጅት ባልደረባ ፔይስ በኪምበርሊ ሂደት ዙርያ ሁለትዮሽ የሆነ አመልካከት ነው ያተረፉት።
በዓለም ገበያ ላይ የሚሸጠው በህገ ወጥ መንገድ የሚወጣው አልማዝ መጠን ንዑስ ነው።
መጠኑ እአአ በዘጠነኛዎቹ ዓመታት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር በርግጥ ቀንሶዋል።
በርካታ ውዝግቦች ጥሩ ፍጻሜ አግኝተዋል ግን በኪምበርሊ ሂደት የተነሳ አይደለም ምክንያቱም፡ ይህ የተቋቋመው እአአ በ ዓም ነውና።
ይህ አንዳንዴ ከፖለቲካ ጋር፡ አንዳንዴም ከኤኮኖሚያዊ ጥቅም ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል።
ይህም የመሻሻል ሂደት ሊያስገኝ ይችል ይሆናል የሚባል ውሳኔ ተቀባይነት እንዳያገኝ ሊያግድ ይችላል ማለት ነው።
ከዚህ በተጨማሪም የተላለፉ ውሳኔዎችን በትክክል መቆጣጠር የሚቻልበት አውታር መተከል ይኖርበታል።
የዘንድሮው የኪምበርሊ አባል ሀገሮች ተወካዮች ስብሰባ ሂደቱ በትክክል የሚሰራ የመቆጣጠሪያ አካል ለመሆን ገና ብዙ እንደሚቀረው የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ያምናናሉ።
በመሆኑም፡ የኪምበርሊን ሂደት ለማሻሻል በወቅቱ የተደረገው ጥረት የተጠበቀውን ውጤት ሳያስገኝ ነው የቀረው።
የበረሃ አንበጣን የመከላከል ጥረት ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መግለጫ ፓርቲው ከዚህ ቀደም ከሚያወጣቸው መግለጫዎች የተለየ ነገር ይዞ አልመጣም የሚሉ አሉ፡፡
አሳሳቢው የማዕድን ዘርፍ አካሄድ የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ልማት ታሪክ እዚህ ግባ የሚባል እንዳልሆነ ይነገርለታል።
የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች እንደሚሉት አጭር ጊዜ ያለው ከመሆኑም ባሻገር በትክክልም ሀገሪቱ ካላት ገጸ በረከት ይልቅ ተጠቃሚ መሆን እንዳልቻለች ነው የሚወሱት።
ወርቅን በተመለከተ በ አካባቢ ወደ ከወጪ ንግድ አኳያ ከቡና ንግድ ቀጥሎ ሚሊዮን ዶላር ይገኝ ነበር።
ባለፈው ዓመት ይሄ ወርዶ ወርዶ ወደ ሚሊዮን ዶላር ነው የሆነው።
በዚሁ ከቀጠለ ከወርቅ የምናገኘው የውጭ ምንዛሬ ከጊዜ በኋላ ይኖራል ብሎ መገመት ያስቸግራል ሲሉ ዶ ር ይናገር የሁኔታውን አሳሳቢነት ጠቁመው ነበር።
የብሔራዊ ባንክ ገዢው ማዕድናትን ወደ ውጭ ሀገር ይልኩ የነበሩ ኩባንያዎች ችግር እንደገጠማቸውም በሪፖርታቸው አንስተዋል።