id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
51445329
https://www.bbc.com/amharic/51445329
'ሃሎ ሪማይንደር'፡ የረሳነውን ነገር የሚያስታውስ መሣሪያን የፈጠሩ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች
ያስቀመጡትን ዕቃ እየረሱ ተቸግረዋል? ቁልፍ፣ ስልክ፣ ቦርሳ፣ . . . እንደዋዛ እንዳስቀመጡት ረስተው የወጡበትንና የተቸገሩበትን ጊዜ ያስታውሱታል? የረሱትን ዕቃ ለማምጣት ወደ ቤትዎ አሊያም ወደ ሥራ ቦታዎ ምን ያህል ጊዜ ተመላልሰዋል?
ሕፃን ልጆችዎ ለጨዋታ በወጡበት ከዐይንዎ ተሰውረው ሲባዝኑ አልደነገጡም? "ሁለተኛ እነዚህን ልጆች ወደ ሕዝብ መዝናኛ ይዤ አልወጣም" ብለው አልዛቱም? ለአዕምሮ እድገት ውስንነት የተጋለጡ ልጆችዎ አሊያም ቤተሰብዎ ከዕይታዎ እየተሰወሩ ተቸግረዋል? አዎ ምን አልባትም ለቁጥር የሚታክት ጊዜ ሊሆን ይችላል። ታዲያ ወጣት ፍቅርተ ሙሉዬ እና በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሆነው ጓደኛዋ ናትናኤል ውበት ይህ ችግር የማኅበረሰብ ችግር ነው በማለት መላ ዘይደዋል። ፍቅርተ ሙሉዬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኢንጅነሪንግ ትምህርት ክፍል የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ ናት። የምትማረውን የትምህርት ዘርፍ ገና ያልመረጠች ቢሆንም የኮምፒዩተር ሳይንስ አጥንታ እንደ ሰው የሚያስብ ሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ [አርተፊሻል ኒዩራል ኔትወርክ] ላይ መስራት የወደፊት ህልሟ ነው። ፍቅርተ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን በባህር ዳር ከተማ ነው የተከታተለችው። በትምህርቷ የደረጃ ተማሪ እንደነበረች የምትናገረው ወጣቷ፤ እዚያው ባህር ዳር በሚገኘው ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግና ሒሳብ ማበልፀጊያ ማዕከል (STEM CENTER) ነፃ የትምህርት ዕድል አገኘች። ማዕከሉ የ8ኛ ክፍል ውጤት ላይ ተመስርቶ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን የሚመርጥ ሲሆን ዕድሉን የሚሰጠው የመግቢያ ፈተናውን ለሚያልፉ ተማሪዎች ነው። ፍቅርተም ይህንን አጋጣሚ ያገኘችው ተቋሙ ያወጣውን ማስታወቂያ በመከታተል ነው። በማስታወቂያው መሠረት የተጠየቀውን መሥፈርት አሟልታ፤ ይህንን መልካም ዕድል የራሳቸው ካደረጉ ተማሪዎች መካከል አንዷ ሆነች። እርሷ እንደምትለው በወቅቱ ማዕከሉን የተቀላቀሉት 100 የሚሆኑ ተማሪዎች ነበሩ። እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ መደበኛ ትምህርታቸውን የሚከታተሉትም እዚያው ነው። ለመደበኛ ትምህርታቸውንም ቤተ ሙከራዎችን በተለይ የተግባር ሥራዎችን የሚጠይቁ ትምህርቶችን ይማሩበታል። ትምህርቱም በዩኒቨርሲቲ መምህራን ይሰጣል። ማዕከሉ ውስጥ ከመደበኛው ትምህርት በተጨማሪ የተግባር ልምምዶችንም ይወስዳሉ። ታዲያ ለፈጠራ ሥራና ለቴክኖሎጂ ፍላጎት የነበራት ፍቅርተ፤ በማዕከሉ ውስጥ በነበራት ቆይታ የተለያዩ ውድድሮች ላይ ተሳትፋለች። በተለይ በየዓመቱ ለወላጆች በዓል በሚዘጋጁ ውድድሮች ላይ የፈጠራ ሥራዎቿን ታቀርብ ነበር። ፍቅርተ [ከግራ ወደ ቀኝ ሁለተኛ] በቅርቡ ቻይናዊው የቢዝነስ ሰው ጃክ ማ ኢትዮጵያ በመጡበት ወቅት በአይኮግላብስ ጀማሪ የፈጠራ ባለሙያዎች ወክላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በተገኙበት በተካሄደ ውይይት ላይ ተሳትፋለች። ትኩረቷ ወደ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሳያዘነብል በፊት በኬሚስትሪ እና ሌሎች የሳይንስ ትምህርቶች ላይ ፍላጎት ነበራት። ከዚህ ቀደም ምንም የሳይንስና ቴክኖሎጅ ክህሎቷን የምታዳብርበት አጋጣሚው እንዳልነበራት የምትናገረው ፍቅርተ፤ ይህንን ዕድል ካገኘች በኋላ ግን በሚሰጣቸው ትምህርትና እገዛ ፍላጎቱ እያደረባት መጣ። ውድድሮች በትምህርት ቤታቸው በተሳተፈችበት የመጀመሪያ ውድድሯ ላይ ሽቶ በመሥራት አሸናፊ ሆና ሽልማት ተበርክቶላታል። በግቢ ውስጥ የነበሩ የብርቱካን፣ የናና እንዲሁም የጤና አዳም ቅጠሎችን በመጠቀም ነበር ሽቶ የሠራችው። ያኔ የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ ነበረች። ፈጠራዋንም በወላጆች በዓል ዝግጅት ላይ አቀረበች። ፍቅርተ ሽቶዎቹን እያርከፈከፈች፤ እርሷም እየተቀባች በመዓዛው እንግዶችን አስደምማለች። በጊዜው የሞባይል ስልክ ሽልማትም ተበርክቶላታል። የ10ኛ ክፍል ተማሪ እያለችም እንዲሁ ከጓደኞቿ ጋር ሆና አንድ ፕሮጀክት ሠሩ። ፕሮጀክቱ የአልኮል መጠጦችን አልኮል አልባ ማድረግና በተቃራኒው አልኮል አልባ መጠጦችን ደግሞ ወደ አልኮል መጠጥነት መቀየር ነበር። ኮካን ወደ ወይን፤ ወይንን ወደ ኮካ እንደማለት። ፍቅርተ የፈጠራ ሥራው ባዮሎጂ መምህራቸው የተደሰተበት እንደነበርም ታስታውሳለች። የፈጠራ ሙከራዎቿ በዚህ መልኩ እየተቃኘ ቆይቶ 11ኛ ክፍል ላይ እያለች የአይኮግላብስ ወድድር ወደ ማዕከሉ መጣ። የሶልቭ አይቲ' ማስታወቂያ ፖስተሮችም ተለጠፈ። ውድድሩ ከ18 ዓመት በላይ ያሉ ወጣቶችን የሚያሳትፍ ቢሆንም ያኔ እርሷ 18 ዓመት አልሞላትም ነበር። ውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት ቢኖራትም እድሜ ገደባት። መስፈርቱን የሚያሟሉ ጓደኞቿ ግን ተመዝግበው ገቡ። እርሷ ግን በሥልጠናው ወቅት ከአዳራሹ ደጅ ላይ ተቀመጠች። ይሁን እንጅ ገለፃውን ከሚሰጡት መካከል ቤተልሔም ደሴ ከዚህ በፊት 'ፕሮግራሚንግ' ስላሰለጠነቻት እና ፍላጎቷን ታውቅ ስለነበር፤ ምናልባትም በቀጣዩ ዓመት እንድትሳተፍ ተስፋ ለመስጠት ብላ ገብታ ዝግጅቱን እንድትከታተል አደረገቻት። ታዲያ በኦሬንቴሽኑ ላይ የፈጠራ ሃሳብ እንዲሰነዝሩ ተጠየቁ፤ ሃሳብ መጣላቸው። በደንብ አሰቡበት። ሃሳቡም በጣም ተወደደ- አስተዋሽ መሣሪያ- 'ሃሎ ሪንማይንደር'። 'ሃሎ ሪንማይንደር' እነፍቅርተ ቀደም ብለው ፕሮጀክቱን ከመጠንሰሳቸው በፊት መጠይቅ አዘጋጅተው ነበር። በባህርዳር ከተማ በመጠይቁ ከተካተቱት 200 ሰዎች ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት ዕቃቸውን ይረሳሉ። እነዚህ ሰዎች ደግሞ ከመርሳታቸውም በላይ ለችግራቸው ምንም ዓይነት መፍትሄ ያላገኙ ሰዎች ናቸው። የ'ሃሎ ሪማይንደር' [አስታዋሽ መሣሪያ] የተወሰኑ ሞዴሎች ከመጠየቁ እንደተረዱትም የመርሳት ህመም ከዕድሜ ጋር ተያያዥነት ቢኖረውም፤ በሁሉም የዕድሜ ክልል የሚገኙት ሰዎች መጠኑ ቢለያይም ችግሩ ያጋጥማቸዋል። 'ሃሎ ሪንማይንደር'፤ ለምሳሌ አንድ ሰው ቁልፍ ረስቶ ቢሄድ ወደ ስልክ መልዕክት የሚልክ መሣሪያ ነው። መሣሪያው በብሉቱዝ የተገናኘ ስለሆነ ምናልባት ከቤትዎ ግቢ ሳይወጡ መልዕክቱ ሊደርስዎት ይችላል። የሰው ልጅ የሚረሳቸው በጣም ብዙ ነገሮች አሉ። ስልክ፣ ቦርሳ፣ ፍላሽ ዲስክ፣ ቁልፍ፣ እንዲሁም የመርሳት በሽታ [አልዛይመር] የጤና ችግር ያለባቸው ሰዎችም ልጃቸውን እስከ መርሳት ይደርሳሉ። ይህ ሁኔታ የሚያጋጥመው የጤና ችግር ያለባቸው ሰዎች ላይ ብቻ ሳይሆን፤ ልጆች ራሳቸው በጨዋታ ቦታ፣ በሕዝብ ቦታዎች ድንገት ሊሰወሩ ይችላሉ። በመሆኑም ይህንን ችግር ለመፍታት የፍቅርተና የጓደኛዋ ናትናኤል ቢተው ፕሮጀክት መፍትሔ ሆኖ ነበር የቀረበው። መሳሪያው ቁልፍ፣ የፀጉር ጌጥ፣ ቦርሳ፣ ጫማ፣ ቀበቶ ላይ የሚለጠፍ ወይም የሚንጠለጠል ነው። ከዚያም ስልክ ላይ በሚጫን መተግበሪያ አማካኝነት በብሉቱዝ እንዲናበቡ በማድረግ "ረስተዋል" የሚል መልዕክት እንዲላክልዎት ያስችላል። በዚህ ፕሮጀክትም ከሁለት ዓመታት በፊት የመጀመሪያው የሶልቪት ውድድር አሸናፊ ሆነዋል። እነፍቅርተ በአገር አቀፍ በተካሄደው ውድድር ላይ የተሳተፉት በክልል ደረጃ 4ኛ ወጥተው ሲሆን በውድድሩ ሦስተኛ በመውጣት የ25 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ ተበርክቶላቸዋል። ስልክ ብንረሳስ? በቀጣይ በሚሰሩት ፈጠራቸው ላይ ይህንን ጥያቄ ለመመለስ እየተጉ ነው። መልዕክቱን ወደ መሳሪያው ጭምር እንዲልክ የሚያስችል ፈጠራ ለማከል ያስባሉ። የፈጠራ ሥራውን በብሉቱዝ መገናኛ እንዲሰራ ያደረግነው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የኢንተርኔት ችግርና እጦት ታሳቢ በማድረግ ነው የምትለው ፍቅርተ፤ የኢንተርኔት አቅርቦቱ እንደልብ የሚገኝና ፈጣን ሲሆን በአቅጣጫ አመላካች (ጂፒኤስ) ይህንኑ የፈጠራ ሥራ እቃው ወይም ግለሰቡ ያለበትን ቦታ የሚያመላክት አድርጎ መስራት እንደሚቻል ትናገራለች። ወደፊትም ይህንን አገልግሎት በማካተት ለመሥራት ሃሳቡ አላቸው። "አሁን ላይ ሊያሰራን የሚችል ትልቅ ሃሳብ ይዘን ነው የተጠቀምነው" የምትለው ፍቅርተ፤ የፈጠራ ሥራውን ለማሳደግ የገንዘብ ድጋፍ እያፈላለጉ እንደሚገኙ ገልፃልናለች። ፍቅርተ እስከ 11ኛ ክፍል ድረስ የአንጎል ቀዶ ህክምና ዶክተር መሆን ትፈልግ ነበር። ስለ አእምሮ በጥልቀት የማወቅ ፍላጎቷ ከፍተኛ ነበር። ለዚህም 'ዘ ዶክተርስ' የተሰኘውን ተከታታይ የቴሌቪዥን ፕሮግራምም አብዝታ ትመለከት ነበር። አንደ አጋጣሚ ወደ ቴክኖሎጂው እየተሳበች ስትመጣ በ'አርቲፊሻል ኒዩራል ኔትወርክ' ሃሳቡ በጣም እንደተማረከች ትናገራለች። • የታኘከ ማስቲካ ዳግም ነብስ ሲዘራ አሁን ላይ የሕይወት ግቧ የአርተፊሻል ኢንተሌጀንስ ዴቨሎፐር መሆን ነው የምትፈልገው። በመሆኑም የሚያስፈልገውን ትምህርት በመማር አርተፊሻል ኒዩራል ኔትወርክ ላይ መሥራት ትፈልጋለች። ስቴም ሶሳይቲ ምንድን ነው? ስቴም ማዕከል በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጅነሪንግ እና ሒሳብ ትምህርቶች ትኩረት በማድረግ ሥልጠና እና ትምህርት የሚሰጥ ተቋም ነው። ተቋሙ እንደሚለው እነዚህ የትምህርት ዘርፎች ለአንድ ተማሪ ውጤታማ መሆን አስፈላጊ ናቸው ተብሎ ሳይሆን አሁን ካለው እውናዊ ዓለም ጋር ቅርበት ስላላቸው ነው። ዓላማውም በእነዚህ የትምህርት ዘርፎች ያለውን እውቀት ማሳደግ እና በዩኒቨርሲቲ ለሚኖራቸው ትምህርት በጎ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ማስቻል ነው። ማዕከሉ በዘርፉ ላይ ፈጣሪ የሆኑ አሊያም ልዩ ተሰጥኦ ላላቸው ተማሪዎች ብቻ ሳይሆን ትኩረቱ በትምህርት ቤቶች፣ በማኅበረሰቡ፣ ሥራ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ትርጉም ያለው ግንኙነት መፍጠር ነው። ትምህርቱን ከአንደኛ ደረጃ፣ በሁለተኛ ደረጃ፣ እና በመሰናዶ ትምህርት ላይ ለሚገኙ ተማሪዎችም ይሰጣል።
news-55601345
https://www.bbc.com/amharic/news-55601345
ሠላማዊ ነዋሪዎች ሰለባ እየሆኑበት ያለው የኦሮሚያ ክልል ግጭት
የኢትዮጵያ ፌደራል ሠራዊት በሁለት ሳምንት ውስጥ እንደሚደመስሰው የተናገረው በኦሮሚያ ክልል ያለው የአማጺ ቡድን እንቅስቃሴ በትግራይ ውስጥ ቀውስ በተከሰተበት ባለፉት ወራት ውስጥ ተባብሷል።
ኪቲላ ጉደታ መረጋጋት በራቃቸው የኦሮሚያ ምዕራባዊና ደቡባዊ ክፍሎች ውስጥ መንግሥት ኦነግ-ሸኔ ብሎ ከሚጠራቸው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ኃይሎች ጋር ፍልሚያ ላይ ነው። ይህ አማጺ ቡድን በቀደመው የኢትዮጵያ መንግሥት ሽብርተኛ ድርጅት ተብሎ በሕገ ወጥነት በስደት ላይ የነበረው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ወታደራዊ ክንፍ ነበር። ቡድኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ወደ አገር ቤት ከተመለሱ በርካታ የታጠቁና ያልታጠቁ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አንዱ ነው። ኦነግ ወደ አገር ቤት ከተመለሰ በጥቂት ወራት ውስጥ ታጣቂ ኃይሉን ትጥቅ በማስፈታት ከአገሪቱ ሠራዊት ጋር በሚዋሃድበት መንገድ ላይ አጠቃላይ ስምምነት ለመድረስ ሳይችል ቀረ። ኋላ ላይም የቡድኑ ወታደራዊ ክንፍ ከፓርቲው በመለየት የትጥቅ ትግሉን እንደሚቀጥል አስታወቋል። ከዚህም በኋላ ከመንግሥት ወታደሮች ጋር ምዕራብና ደቡብ ኦሮሚያ ሲዋጉ ግጭቶች ሲካሄዱ ቆይተዋል። በትግራይ ክልል ውስጥ ወታደራዊ ግጭት ከተከሰተ በኋላ አማጺ ቡድኑን የመቆጣጠሩን ኃላፊነት የተረከበረው የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል ለአንድ ወር ባካሄደው ዘመቻ ከ350 በላይ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎችን መግደሉንና ከ170 በላይ የሚሆኑትን ደግሞ መያዙን ታኅሣስ 10/2013 ዓ.ም ላይ አስታውቋል። በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ በትግራይ ክልል ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ በምዕራብ ኦሮሚያ ውስጥ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎቶች ተቋርጠዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች የክልሉን ልዩ ኃይል ከሕግ ውጪ ሠላማዊ ሰዎችን በመግደል ይከሳሉ። የ32 ዓመቱ የሁለተኛ ደረጃ መምህር ኪቲላ ጉደታ በምዕራብ ኦሮሚያ ሆሮ ጉድሩ ዞን ውስጥ በልዩ ኃይል ፖሊሶች ተገድለዋል ከሚባሉት ሰዎች መካከል አንዱ ነው። ለደኅንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የሟች ቤተሰብ አባል ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ኪቲላ ኅዳር ሐሙስ 10/2013 ዓ.ም ከ10 በላይ በሚሆኑ የኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ አባላት ምሽት 3፡30 ላይ ሰከላ ከተማ ውስጥ ከሚገኘው ቤቱ ነበር የተወሰደው። "የሁለት ልጆቹ እናት የሆነችው ባለቤቱ ከእሱ ይልቅ እሷን እንዲወስዷት ለምናቸው ነበር፤ ነገር ግን ከተወሰኑ ጥያቄዎች በኋላ ተመልሶ እንደሚመጣ ነገሯት" ብሏል። ቤተሰብ ኪቲላን በሚቀጥለው ቀን ቢፈልገውም የትም ሊገኝ አልቻለም። ስልኩም እንደተዘጋ ነበር። "አርብ ዕለት ምሽት 1 ሰዓት አካባቢ እንደተገደለ አንዳንድ ሰዎች ነገሩን፤ ነገር ግን አስከሬኑን ልናገኝ አልቻልንም" ብሏል። "ቅዳሜ ጠዋት ሃሮ አጋ ተብሎ በሚታወቀውና ከከተማዋ ወጣ ብሎ ከሚገኝ ቦታ ላይ አስከሬኑ እንደታየ ሰማን፤ እኔ ነበርኩ ቦታው ላይ ቀድሜ የደረስኩት።" "በወንዝ አቅራቢያ ባለ አለት ላይ ነው ተገድሎ ያገኘነው። እጁ ወደኋላ ታስሮ ከኋላው ተተኩሶበት ነበር የተገደለው። የተኩስ መለማመጃ ያደረጉት ነበር የሚመስለው" ሲሉ ዘመዱ ተናግሯል። ቤተሰቦቹ እንዳሉት ከኪቲላ ጋር የሌሎች ሁለት ሰዎች አስከሬንም ተገኝቷል። በኋላ ላይ የሁለቱ ማንነት የተለየ ሲሆን አንደኛው በመንግሥት መሥሪያ ቤት ጥበቃ የነበረው ጋዲሳ አለማየሁ የተባለ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የጉልበት ሠራተኛው ብርሃኑ ገበየሁ ነው። ሁለቱም የከተማዋ ነዋሪዎች ናቸው። የኪቲላ ጉደታ ቤተሰቦች እንደሚሉት አስካሁን እንዴትና ለምን እንደተገደለ የተነገራቸው ነገር የለም። ኪቲላ ቀደም ሲል የኦነግ ደጋፊ ነህ ተብሎ በተደጋጋሚ ታስሮ ተፈትቶ ነበር። ስለቀረቡት የግድያ ክሶች ከኦሮሚያ ልዩ የፖሊስ ኃይል ምልሽ ለማግኘት ያደርግናቸው ጥረቶች አልተሳኩም። ነገር ግን የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ጌታቸው ባልቻ፤ ከአማጺው ቡድን እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ የሠላማዊ ሰዎችን ሞት ለመከላከል መንግሥት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። "እርምጃ የተወሰደባቸው ወንጀላቸው በታወቀና በሕዝቡ በተጋለጡት ላይ ብቻ ነው" ብለዋል። "በሠላማዊ ሰዎች ላይ ስለተፈጸመ ግድያ የማውቀው ነገር የለም። ነገር ግን የፖሊስ አባላትም ሆኑ የመንግሥት ባለሥልጣናት ወንጀል ፈጽመው ከተገኙ ተጠያቂ ይሆናሉ" ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል። ኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ ኃይል አባላት 'ለምን እንደገደሉት አናውቅም' አንዳንዶቹ ግድያዎች የተፈጸሙት የአማጺ ቡድኑ እንቅስቃሴ በሌለባቸው ቦታዎች ጭምር ነው። አርብ ኅዳር 10/2013 ዓ.ም ኪቲላ ከቤቱ ከተወሰደ በኋላ ባለው ቀጣይ ምሽት ተመሳሳይ ነገር በአርባዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ በሚገኘው ገላና ኢማና ላይ እንደተፈጸመ ቤተሰቦቹ ይናገራሉ። የሁለት ልጆች አባት የሆነው ገላና ነዋሪነቱ ከአዲስ አበባ 100 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው በአምቦ ከተማ ነበር። ምሽት አራት ሰዓት አካባቢ 20 በሚደርሱ የታጠቁ የኦሮሚያ ልዩ ፖሊሶች ከቤቱ ተይዞ ተወሰደ። ከአዲስ አበባ ወጣ ብላ የምትኖረው ታናሽ እህቱ ጫልቱ ኢማና ወንድሟ መያዙን ስትሰማ ቅዳሜ ዕለት ወደ አምቦ መሄዷን ለቢቢሲ ተናግራለች። ለሁለት ቀናትም በከተማዋ ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ እስር ቤቶችና ፖሊስ ጣቢያዎች ወንድሟን ብትፈለግም ልተገኘው አልቻለችም ነበር። "ዕሁድ የኦሮሚያ ልዩ ፖሊሶች ወደሚገኙበት ካምፕ ሄጄ በር ላይ ያገኘሁትን ሰው ወንድሜ የት እንዳለ እንዲነግረኝ ለመንኩት። ስሙንም ስነግረው ያለበትን ቦታ በመፈለግ እንዳልደክም መከረኝ። "እንደማላገኘውም ነገረኝ። ወንድሜ ከከተማዋ ውጪ ወደሚገኝ የተሃድሶ ስልጠና መስጫ እንደተላከና ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ለቤተሰቡ የት እንዳለ ይነገራል" አለኝ። ሰኞ ምሽት ኅዳር 14/2013 ከከተማዋ ወጣ ብሎ በሚገኝና ዳቢስ ተብሎ በሚጠራ ወንዝ አካባቢ ፖሊስ የሞተ ሰው አግኝቶ መቅበሩን የሚገልጽ ወሬ ቤተሰቡ መስማት ጀመረ። ጫልቱም በሚቀጥለው ቀን ማክሰኞ ፖሊስ አግኝቶ ስለቀበረው ግለሰብ ማንነት ለማወቅ ወደ አካባቢው ፖሊስ ጣቢያ ሄደች። "ከብዙ ንግግር በኋላ ፎቶውን እንድናመጣና በተያዘበት ጊዜ ለብሶት የነበረውን የልብስ አይነት እንድንነግራቸው ጠየቁን። በኋላም ከሰጠናቸው መረጃ ተነስተው የቀበሩት ግለሰብ ከወንድሜ ጋር ተመሳሳይ እንደሆነ አረጋገጡ" ትላለች። "ከዚያም አስከሬኑ ሳይኖር ወደ ቤታችን ሄደን ሐዘን እንድንቀመት ነገሩን። ምንም ምርጫ አልነበረንም።" በተጨማሪም ወንድሟ በጥይት ተመቶ መገደሉን ፖሊሶቹ እንደነገሯትና ከመቀበሩ በፊት ለቤተሰቡ ያላሳወቁት አድራሻቸውን ስላላወቁ መሆኑን ተናግረዋል። "መያዙን ብቻ ነው የምናውቀው። ምን ወንጀል እንደፈጸመና ፍርድ ቤት ከማቅረብ ይልቅ ለምን መግደል እንደመረጡ የምናውቀው ነገር የለም" ትላለች ጫልቱ። ወንድሟ ቀደም ሲል የኦነግ መሪዎች ወደ አገር ቤት ሲመለሱ በአቀባበል ኮሚቴ ውስጥ በመግባት ማገልገሉን እህቱ ታስታውሳለች። 'ሠላማዊ ሰዎች ዋጋ እየከፈሉ ነው' የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በኅዳር ወር ብቻ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ቦታዎች በጸጥታ ኃይሎች ተገደሉ የተባሉ 12 ሰላማዊ ሰዎችን እንደመዘገበ ይናገራል። ኮሚሽኑ እንደሚለው ጥቅምት 13/2013 ዓ.ም ምሥራቅ ወለጋ ነቀምቴ ውስጥ በአንድ ቤት ውስጥ የተገደሉ የአምስት ወጣቶችን ጉዳይ ጨምሮ በተወሰኑት ግድያዎች ላይ ምርመራ እያደረገ ነው። "እንደ ኮሚሽን የተገነዘብነው ነገር ቢኖር በኦሮሚያ ውስጥ ፖለቲካዊ አለመግባባት ሠላማዊ ሰዎችን ውድ ዋጋ እያስከፈላቸው ነው" ሲሉ የኮሚሽኑ አማካሪ ኢማድ አብዱልፈታህ ለቢቢሲ ተናግረዋል። እሳቸው እንዳሉት ግድያው የሚፈጸምበት መጠን "በጣም አሳሳቢ" እንደሆነ ገልጸው ሠላማዊ ሰዎች ኢላማ የሚደረጉት በመንግሥት ኃይሎች ብቻ ሳይሆን በአማጺያኑም ጭምር መሆኑን ተናግረዋል። በምዕራብ ኦሮሚያ ሆሮ ጉድሩ ውስጥ አባይ ጮመን በተባለው ወረዳ ነዋሪ የሆኑ ሁለት የዓይን እማኞች በኅዳር 29/2013 ዓ.ም ላይ ሰባት ሠላማዊ ሰዎች መገደላቸውን እንደተመለከቱ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ማክሰኞ ምሽት በድምጽ ማጉያ ለአስቸኳይ ስብሰባ የሚደረግ ጥሪ ሰማን" ይላሉ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉት የአካባቢው ነዋሪ። "ስምንት ጸጉራቸው ረዥምና ፊታቸውን የሸፈኑ ታጣቂዎች፤ ከተሰበሰበው ሰው መካከል አማራዎች የሆኑ እራሳቸውን እንዲያሳውቁ ከጠየቁ በኋላ ቀሪዎቻችንን ወደ ቤታችን እንድንሄድ ነገሩን። ከዚያም 10 የሚሆኑትን ይዘዋቸው ሄዱ።" "ተለቀው ይመጣሉ ብለን ሌሊቱን በሙሉ ብንጠብቅም ሳይመጡ ቀሩ። በሚቀጥለው ቀንም የሰባቱን አስከሬን አገኘን" ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል። በሌላ በኩል ደግሞ እነዚህ ታጣቂዎች በሆሮ ጉድሩ ውስጥ አሙሩ በሚባለው ወረዳ ውስጥ 14 አማራዎችን እንደገደሉ አቶ ጌታቸው ባልቻ ለቢቢሲ ተናግረዋል። 'ባንኮች ተዘርፈዋል፣ አምቡላንስ ተቃጥሏል' ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በወለጋ ሆሮ ጉድሩ ውስጥ በታጣቂዎች የሚፈጸመው ጥቃት ካለፈው ጊዜ ጋር ሲነጻጸር ምናልባትም በብዛቱ የማይወዳደርና ያልተነገረ ነው። በታኅሣስ ወር መጀመሪያ ላይ ታጣቂዎች ፊንጫ ስኳር ፋብሪካ አካባቢ በምትገኘው ሐጋማሳ በምትባል መንደር ውስጥ የሚገኙ ሁለት ባንኮችን እንደዘረፉ ነዋሪዎችና የባንክ ባለሙያዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ምን ያህል ገንዘብ እንደተዘረፈ ግን የታወቀ ነገር የለም። በዚህ ክስተትም የዞኑ ዋና ከተማ በሆነችው ሻምቡ ውስጥ የሚገኙ ባንኮች ተመሳሳይ ጥቃት ሊፈጸም ይችላል በሚል ስጋት ከአንድ ቀን በላይ ተዘግተው አገልግሎት ሳይሰጡ ቆይተዋል። በተጨማሪም ከሻምቡ ከተማ አቅራቢያ በምጥ የተያዘችን እናት ሐኪም ቤት አድርሶ የሚመለስ አምቡላንስና የግል ትራንስፖርት ተሽከርካሪ በታጣቂዎቹ በእሳት ተቃጥሏል። "ታጣቂዎቹ ሚኒባሱን በእሳት ከመለኮሳቸው በፊት ከተሳፋሪዎቹ ላይ የሞባይል ስልኮችንና ገንዘብ ወስደዋል" ሲል አንድ የሻምቡ ከተማ ነዋሪ ለቢቢሲ ተናግሯል። ወደ አዲስ አበባ ይጓዝ በነበረ አውቶብስ ላይ በታጣቂዎቹ ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ ለጥቂት ቀናት ወደ አገሪቱ ዋና ከተማዋ የሚደረግ የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጦ ነበር። ከፊንጫ ስኳር ፋብሪካ አቅራቢያ አዲስ በተከፈተ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግሉ አንድ ቄስም ታኅሣስ 08/2013 ዓ.ም በታጣቂዎቹ መገደላቸውን ፋብሪካው ውስጥ የሚሰራ ግለሰብ ለቢቢሲ ተናግሯል። የአካባቢዎቹ ባለሥልጣናት ጭምር የታጣቂዎቹ ጥቃት ኢላማ የሆኑባቸው ግድያዎች ምክንያት ግልጽ አይደለም። ባለስልጣናቱም ምላሽ እንዲሰጡን ያደረግነው ጥረት ሊሳካ አልቻለም። ነዋሪዎች እንደሚሉት ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ከስኳር ፋብሪካው አቅራቢያ ተኩስ ይሰማ እንደነበር ገልጸው፤ ይህም በታጣቂዎቹና በመንግሥት ኃይሎች መካከል የሚደርግ የተኩስ ልውውጥ ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል። በባንኮች ላይ ለደረሱ ዘረፋዎች፣ በመንግሥት ባለሥልጣናትና በሠላማዊ ዜጎች ለተፈጸሙ ግድያ ኦነግ-ሸኔ ብሎ የሚጠራውን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን መንግሥት በተደጋጋሚ ይከሳል። መንግሥት ጨምሮም ታጣቂው ቡድን በህወሓት እየተደገፈ አገሪቱ እንዳትረጋጋ ለማድረግ እየሞከረ ነው ይላል። የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ግን ይህንን ክስ ያስተባብላል። ባህላዊው መሪ አባ ገዳ ኩራ ጃርሶ 'የሕዝብ ጠላት' መንግሥት ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት በትግራይ ውስጥ ወታደራዊ ግጭት ከመቀስቀሱ ከሦስት ቀናት ቀደም ብሎ 34 ሠላማዊ ሠዎች በጉሊሶ ወረዳ አንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ለስብሰባ ተብለው ከተጠሩ በኋላ በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ተገድለዋል። ከጥቃቱ የተረፉ ሰዎች እንደተናገሩት በታጣቂዎች በተከፈተባቸው ተኩስ እዚያው ቦታው ላይ ቢያንስ 34 የአማራ ብሔር ተወላጆች ተገድለዋል። ለሁለት ዓመታት ያህል በዘለቀው በዚህ የአማጺያን እንቅስቃሴ ወቅት ምን ያህል ሰዎች እንደሞቱ የሚያመለክት ግልጽ አሃዝ የለም። ነዋሪዎች እንደሚሉት አማጺያኑን በመዋጋት በአካባቢው ሰፍሮ የነበረው የመከላከያ ሠራዊት በድንገት ለቆ መውጣቱ በታጣቂዎቹ ለሚፈጸመው ጥቃት እንዳጋለጣቸው ገልጸዋል። የተፈጸሙትን ግድያዎች ተከትሎ የኦሮሚያ ፖሊስ በወሰደው የአጸፋ እርምጃ 142 ታጣቂዎችን መግደሉን ኅዳር 09/2013 ዓ.ም አስታውቋል። ምንም እንኳን መንግሥት በተለያዩ ጊዜያት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ታጣቂዎችን መግደሉን ቢያስታውቅም ውጊያው የተጠናቀቀ አይመስልም። የአሁኑ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ ምክትል በነበሩበት ጊዜ ባለፈው ዓመት የካቲት ወር ላይ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ ሠራዊቱ አብዛኛውን ምዕራብና ደቡብ ኦሮሚያን ከአማጺያኑ ነጻ ማውጣቱንና "የቀሩት ተወሰኑ ታጣቂዎች" መሆናቸውን መግለጻቸው ይታወሳል። ነገር ግን የአማጺያኑ እንቅስቃሴ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እየሰፋ መምጣቱን የክልሉ ፖሊስ በቅርቡ በማዕከላዊና በምሥራቃዊ የኦሮሚያ አካባቢዎች ውስጥ ታጣቂዎችን እንደገደለ መግለጹ አመላካች ሊሆን ይችላል። በደቡባዊ ኢትዮጵያ የቦረና አካባቢ የአማጺው ታጣቂዎች ከአንድ ወር በፊት አንድ ህጻን በመግደላቸው ቡድኑ የአካባቢው ባህላዊ መሪ በሆኑት በአባ ገዳ ኩራ ጃርሶ "የሕዝብ ጠላት" ተብሎ ተወግዟል። ታጣቂዎቹ ለረጅም ጊዜ ሲንቀሳቀሱበት በነበረው ኢትዮጵያና ኬንያ በሚዋሰኑበት የቦረና አካባቢ ሠላማዊ ሰዎችን ሲገድሉ፣ ሴቶችን ሲደፍሩና ከብቶችን ሲዘርፉ ቆይተዋል ሲሉ አባ ገዳ ኩራጃርሶ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከፕሬዝደናት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ኅዳር 30/2013 ዓ.ም የኢትዮጵያና የኬንያን የድንበር መተላለፊያ መርቀው በከፈቱበት ጊዜ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን ከአል-ሻባብ ጋር አብረው ጠቅሰውታል። ጨምረውም የሕዝቡን ህይወት ለመቀየር ሁለቱ አገራት ኦነግ-ሸኔን እና አል-ሻባብን ከአካባቢው ለማጥፋት በጋራ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።
42484518
https://www.bbc.com/amharic/42484518
ግብፅ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ አዲስ ሃሳብ አቀረበች
የግብፁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሹክሪ ከኢትዮጵያው አቻቸው ከዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር ባደረጉት ውይይት የሁለትዮሽ ግንኙነትን በማጠናከር ላይ የተነጋገሩ ሲሆን፤ ሹክሪ ቀላልና ተግባራዊ መሆን የሚችል ያሉትን ምክረ-ሃሳብ ኢትዮጵያ እንደምትመለከተው ዶክተር ወርቅነህ ገልፀዋል።
የግብፅ እና የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሁለቱ ሃገራት መሪዎች ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እየሰሩ መሆናቸውን ያስታወሱት ሳሚ ሹክሪ፤ "ሉአላዊነትን፣ የጋራ መተማመንን መሰረት ያደረጉና ዓለም አቀፍ ሕግን የተከተሉ ሥራዎች ተከናውነዋል" ብለዋል። ሆኖም ግን ላለፉት አስር ወራት ሲካሄዱ የቆዩት ውይይቶች በቂ ውጤት ማስገኘት አለመቻላቸውንም ገልፀዋል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳዮች ሚንስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በበኩላቸው፤ የህዳሴው ግድብ ግንባታ የሚፈጥረው ስጋት እንደማይኖር በመግለፅ "አለመግባባቶች ሲኖሩም ሕጋዊ አሰራሮችን በመከተል መፍታት ይቻላል። በሁለቱም ሃገራት የሚቆጣ ህዝብ አይኖርም። ኢትዮጵያም ግብፅን ለመጉዳት የምትሰራው ሥራም አይኖርም" ብለዋል። 96 በመቶ ህዝባቸው በረሃማ በሆነ አካባቢ እንደሚኖርና ህይወቱም በአባይ ወንዝ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ያስታወሱት የግብፁ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር "የግብፅ ህዝብ ተቆጥቷል ባልልም ስጋት ላይ መውደቁን ግን መናገር እችላለሁ" ሲሉ ተናግረዋል። ቢሆንም ግን የኢትዮጵያን የመልማት እንቅስቃሴ እንደሚቀበሉ አስታውቀዋል። ጉዳዩ የሁለቱ ሃገራት ብቻ ሳይሆን ሱዳንንም እንደሚመለከት የገለፁት ሁለቱም ሚንስትሮች፤ በውይይትና በጋራ በመስራት መፍትሄ ለማምጣት እንደሚጥሩ ገልፀዋል። ፖለቲካዊ ሳይሆን ሳይንሳዊ ጥናቶችን መሰረት ያደረገ መፍትሄ እንደሚበጅና ተቀባይነት እንደሚኖረውም ሳሚ ሹክሪ ተናግረዋል። አዲሱ ምክረ-ሃሳብ የእስካሁኑን መጓተት ለማካካስና ቶሎ ወደ መፍትሄ ለመግባት የሚረዳ ቀላል፣ ከፖለቲካዊ እሳቤ የራቀና ተግባራዊ ሊሆን የሚችል መሆኑን ሹክሪ አስረድተዋል። ጉዳዩን ለፖለቲካና ለመሪዎች ብቻ የሚተው አለመሆኑን በማስረዳት "ጥናቱን እንዲያካሂድ የሦስታችንንም ሃገራት ፍቃድና ተቀባይነትን ያገኘው ዓለም አቀፉ ተቋም፤ የሚደርስበትን ማንኛውንም ውጤት ግብፅ ትቀበላለች" ሲሉም አረጋግጠዋል። ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በበኩላቸው "በህዳሴው ግድብ ዙርያ ግልፅ ለመሆን እየጣርን ነው። አሁን የቀረበውን ምክረ-ሃሳብንም እናየዋለን። የሦስት ሃገራት ጉዳይ ስለሆነ በጥንቃቄ መያዝና መታየት አለበት" ብለዋል። ሃገራቱ በሌሎች የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ በተጠናከረ መንገድ የመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ሚንስትሮቹ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አሳውቀዋል።
news-56648228
https://www.bbc.com/amharic/news-56648228
የበረራ አስተናጋጇን ወደ ኢትዮጵያ እንዲመልሷት ከፍተኛ ጥረት አድርገን ነበር- በቱርክ የኢትዮጵያ ቆንስላ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ አስተናጋጅ የሆነችው ሰላማዊት እጅጉ "በአደራ ወደ ቱርክ የወሰደቻቸው ሁለት ስዕሎች ላይ ኮኬይን ተገኝቶባቸዋል" በሚል በእስር ላይ እንደምትገኝ ቢቢሲ ከቤተሰቦቿ መረዳት ችሏል።
ታናሽ እህቷ ቤተልሄም እጅጉ ለቢቢሲ እንደተናገረችው ሰላማዊት በአሁኑ ወቅት በቱርኳ ከተማ ኢስታንቡል 1.6 ኪሎግራም የሚመዘዝን ኮኬይን የተባለውን አደንዛዥ ዕፅ ይዛ ስትገባ ተገኝታለች በሚል ከታሰረች 13 ቀናትን አስቆጥራለች። በኢስታንቡል አየር ማረፊያ ስትደርስ በቁጥጥር ስር የዋለችው ሰላማዊት እጅጉን ወደ አገሯ ለመመለስ በአየር ማረፊያው ከሚገኙ የፀጥታ ኃይሎችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ለመደራደር በቱርክ የሚገኙት የኢትዮጵያ ኤምባሲና ቆንስላ ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም ሊሳካ እንዳልቻለ አቶ ወንድሙ ገዛኸኝ የኢስታንቡል ቆንስላ ጄኔራል ለቢቢሲ ገልፀዋል። ስለ ክስተቱ ከቤተሰቦቿ የተሰማው.... እለቱ ረቡዕ መጋቢት 15፣ 2013 ዓ.ም ነበር። በኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ አስተናጋጅ የሆነችው ሰላማዊት እጅጉ ወደ አመሻሹ አራት ሰዓት ላይ ነው ወደ ቱርክ የበረረችው። ከዚያ ቀደም ብሎ ግን አንዲት ሴት ሁለት በቆዳ የተሰሩ ባህላዊ ስዕሎችን በአደራ እንድታደርስላት በስልክ ጠየቀቻት። ቤተልሔም እንደምትናገረው እህቷ በወቅቱ "አልወስድም" በማለት አንገራግራ የነበረ ቢሆንም ሁልጊዜም የምትልካቸው ስዕሎች እንደሆኑ ግለሰቧ ነግራ አግባባቻት። በዕለቱም ስዕሎቹን ውሰጂልኝ ያለቻት ግለሰብ "ጠብቂን አሁን እንልካለን" እያለች እንዳስረፈደቻትና የአየር መንገድ ሰርቪስ መኪናም እንዳመለጣት ታወሳለች። በመጨረሻም ግለሰቧ እንደምታደርሳትና መኪናም እንደምትልክ ነገረቻት። መኪናውን ይዞ የመጣው የደወለችላት ግለሰብ ሳትሆን፣ ሌላ አሽከርካሪ ነበር። ሁለት በቆዳ የተወጠሩና፣ ዳር ዳራቸው ፀጉር ያላቸው ባህላዊ ስዕሎችን ግለሰቡ ሰጣት። አርፍዳም ስለነበር እቃውን ለማየትም ሆነ ለመፈተሽ ጊዜው እንዳልነበራት የምትናገረው ቤተልሔም፣ ሻንጣዋ ላይ አስገብታ ወደ በረራዋ አቀናች ትላለች። አዲስ አበባ አየር ማረፊያ ምንም ያላጋጠማት ሰላማዊት፣ ኢስታንቡል ስትደርስ በቁጥጥር ስር ዋለች። ስለ ጉዳዩ ምንም እንደማታውቅና "ስዕሎቹን በአደራ አድርሺልኝ" እንደተባለች ተናግራ ይቀበሏታል የተባሉ ሰዎችን ብታስይዝም ግለሰቦቹ ሊያምኑ እንዳልቻሉም ቤተልሄም ታስረዳለች። ኢስታንቡል በቁጥጥር ስር ከዋለች በኋላ ፖሊሶች፣ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሲወስዷት ለምና ለባለቤቷ መደወሏንና "ያመጣሁት እቃ ውስጡ አደንዛዥ ዕፅ ነው ብለውኛል" በማለት እያለቀሰች መናገሯን ቢቢሲ ከእህቷ ሰምቷል። በወቅቱ ምን አይነት አደንዛዥ ዕፅ እንደነበር እንደማታውቅና ምርመራ ከተደረገም በኋላ ነው ኮኬይን መሆኑን አሳወቋት። ለሁለተኛ ጊዜም ፖሊስ ለቃለ መጠይቅ ይዘዋት በወጡበት ወቅት ፖሊሶቹን ለምና ለባለቤቷ ደውላለታለች። እስካሁን ድረስ ቤተሰቦቿ ሁለት ጊዜ ብቻ ነው ማናገር የቻሉት። ስእሎቹን "በአደራ አድርሺልን" ብላ የደወለችላት ግለሰብ ጋር እውቅና አላቸው ወይ ተብሎ ከቢቢሲ ለቀረበላት ጥያቄ ቤተልሔም ስትመልስ፣ እንደማታውቃትና በስልክ አንዲት ሴት እንደደወለችላት ትናገራለች። ከዚህ ቀደምም ቢሆን የበረራ አስተናጋጆች ወደተለያዩ ውጭ አገራት በሚጓዙበት ወቅት የአደራ እቃ አድርሱልኝ ማለት የተለመደ በመሆኑ "ትንሽ ብር ተከፍሏቸው" ማድረስ የነበረ አሰራር ነው ትላለች። በተለይም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሽሮ፣ በርበሬና ሌሎችንም እቃዎች ይዘው መሄድ የተለመደ ቢሆንም ነገር ግን ስዕሎች ከዚህ በፊት ወስዳ እንደማታውቅ ትናገራለች ። "ከግለሰቧ ጋር በስልክ በምታወራበት ጊዜ አምናታለች ። እንዲህ አይነት ነገር ደግሞ በፍፁም አልመጣላትም፤ ያሰበችው አይመስለኝም" በማለት ታስረዳለች። ከዚህ ቀደም የነበራትን ልምድ በማስታወስ "ፈሪ ናት" ትላለች። ጓደኞቿንም ሆነ የሥራ ባልደረቦቿን ዕቃ እንዳይወስዱም እንደምትከለክል ጠቁማለች። "ልብስ ወይ አንዳንድ ነገር ካልሆነ ከሌላ አገር ይዛ አትመጣም ከዚህም ይዛ አትሄድም" ስትል ታስረዳለች። ቤተሰቦቿ ኢትዮጵያ ውስጥ ደወለችላት የተባለችውን ሴት ድምፅ ከኢትዮ ቴሌኮም ለማስወጣት እንዲሁም የፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮም በመሄድ ስለ ግለሰቧ ዘርዘር ያለ መረጃ ለማግኘት ያደረጉት ሙከራ አልተሳካም። የፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮው ብዙ ተስፋ የለውም እንዳሏቸው የምትገልፀው ቤተልሔም "ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን ግለሰቦች መክሰስ ፈልገን ነበር። እዚህ ያሉት ሰዎች እስር ብዙ ጥቅም እንደሌለውና እዛ ያለውን ማጠናከር እንደሚገባም ነግረውናል" ትላለች። ሆኖም አሁንም የግለሰቦቹን ማንነት ለማወቅ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ መሆናቸውንም አስታውቃለች። በወቅቱ የአንድ አመት ከሰባት ወር ልጃቸውን እያባበለ የነበረው ባለቤቷ ከዚህ ቀደም በራይድ ስትሄድ ለጥንቃቄ ሲባል የታርጋ ቁጥሮችን ይመዘግብ የነበረ ቢሆንም በዚህኛው ወቅት ግን ልጃቸው እያለቀሰ ስለነበር የታርጋ ቁጥር ሙሉ ማየት እንዳልቻለም ቤተልሔም ታስረዳለች። በአሁኑ ወቅት ጠበቃ ቀጥረው ጉዳዩን እየተከታተሉ ሲሆን ጡት የሚጠባ ህፃን ልጅ ስላላት የፍርድ ሂደቱ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲሆንና ህፃኑን የምታይበትን ሁኔታ እንዲመቻችም እየጠየቁ ነው። ጠበቃቸው 7 ሺህ ዶላር እንዲከፍሉም ተነግሯቸው እሱንም በአንድ ቤተሰብ አቅም የሚቻል ባለመሆኑ ገንዘብ የማሰባሰብ ስራ እየሰሩ ነው። "በሂደት ሁሉም እውነት መውጣቱ አይቀርም ነገር ግን ዋናው ነገር ኢትዮጵያ ውስጥ መጥታ የፍርድ ሂደቷ ቢታይና ልጇን ማየት ብትችል ጥሩ ነበር" ትላለች። የእስሯ ሁኔታ "አጠቃላይ ቤተሰቡን አመሰቃቅሎታል" የምትለው ቤተልሔም እናቷ በልጃቸው እስር ምክንያት ደማቸው ከፍ እንዳለና ልጇም በለቅሶ፣ አጠቃላይ ቤተሰቡም በኃዘን ላይ ይገኛል ትላለች። ሰላም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ በኤሌክትሪካል ምህንድስና አራት አመት ተምራ መጨረሻ አመት ላይ በተለያዩ ምክንያቶች አቋርጣ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ተቀላቀለች። በበረራ አስተናጋጅነትም ለሰባት አመታት ያህል ሰርታለች። የኢትዮጵያ ቆንስላና ኤምባሲ ጥረት ሰላማዊት በኢስታንቡል አየር ማረፊያ በቁጥጥር ስር መዋሏ ሲሰማ በኢስታንቡል የሚገኘው ቆንስላ ወደ ሃገሯ እንዲመልሷት (ዲፖርት እንዲያደርጓት) የአየር ማረፊያ ፀጥታ ኃይሎችን መጠየቁን እንዲሁም ድርድር ለማድረግም በርካታ ጥረት ማድረጉን አቶ ወንድሙ ያስረዳሉ። ቆንስላውም በራሱ የኮኬይኑን መነሻ ለማግኘት በሚል፣ ግለሰቧ ተመልሳ የሰጧትን ሰዎች እንድትጠቁም ለማድረግ እንድትመለስ ቢደራደሩም ነገር ግን የአየር ማረፊያው የፀጥታ ኃይሎች "ወንጀሉ የተፈፀመው በክልላችን ስለሆነ ወደ ኋላ የምንመልስበት ምንም ምክንያት የለም" የሚል መልስ ሰጥተዋቸዋል። አንካራ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ወደ ሃገሯ እንድትመለስ የጠየቁ ቢሆንም በተመሳሳይ መልኩ የተሰጣቸው ምላሽ "ወንጀሉ በተገኘበት ነው የምትዳኘው ወደ ኋላ የምትመለስበት ምንም ምክንያት የለም" የሚል ነው። "በአገሪቷ ህግ ነው መተዳደር ያለብን እንጂ በተለየ ህግ መተዳደር የምንችለው ነገር የለም። ይኼንን ከመቀበል ውጭ ምንም ሌላ አቅም የለንም" ይላሉ አቶ ወንድሙ። ከዚህ በተጨማሪ "ቱርክ ከኮኬይን ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ችግር ስላለ እንዲህ በቀላሉ የሚታይ ወንጀል አይደለም። በጣም ጠንካራ ቁጥጥር ነው የሚያደርጉት። ሰላምን ወደ ሃገሯ ትመለስ ብለው በመጠየቃቸው ብዙም ደስተኛ አልነበሩም" በማለት ያስረዳሉ። በአሁኑ ሰዓት የሰላምን ደህንነት በጥብቅ እየተከታተሉ እንደሚገኙና እርሷንም በአካል ለመጎብኘት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ጥያቄ ማቅረባቸውን ተናግረዋል። በአለም አቀፉ አሰራር መሰረት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ፈቃድ ሲገኝ እስረኛ መጎብኘት እንደሚቻል ይናገራሉ። በኮቪድ-19 ጥብቅ መመሪያ መሰረት እስረኞችን መጎብኘት ስለማይቻል፣ በቁጥጥር ስር ከዋለችበት ዕለት ጀምሮ በአካል አይተዋት አያውቁም። አቶ ወንድሙ ሲፈቅድላቸው የእስር ሁኔታ ዝርዝሩን እንደሚረዱ ገልፀዋል። በአሁኑ ወቅት በኢንስታንቡል ከተማ እስር ቤት የምትገኝ ሲሆን አቃቤ ህግ ክስ እስኪመስርት እየተጠበቀ ይገኛል። ቆንስላው የሚያውቀው ቱርካዊ የህግ ባለሙያ ምን መደረግ አለበት የሚለውን እንዲያማክራት መጠየቃቸውንና በዚያም በኩል እየተከታተሉ እንደሚገኙ አቶ ወንድሙ ያስረዳሉ። ከዚህ በኋላ ሰላማዊትን ለማግኘት እንዲሁም ቤተሰቦቿን በስልክ የምታገኝበትን ሁኔታ ፈቃድ እንዲኖር እየጠየቁ እንደሆነ ገልፀው፣ ጉዳዩም ወደ ፍርድ ቶሎ እንዲቀርብ ለማድረግ ግፊት የማድረግ ስራ ብቻ እንደሚሰሩ አክለው አስረድተዋል። ከዚህ ቀደም እንዲህ አይነት ሁኔታ አጋጥሞ ያውቃል በማለት ቢቢሲ አቶ ወንድሙን የጠየቃቸው ሲሆን እሳቸውም ኮኬይን የመጀመሪያ ቢሆንም በጫት ምክንያት ሶስት ሰዎች መያዛቸውን ተናግረዋል። በተለያዩ ጊዜዎች ማህበራዊ ሚዲያዎችን ጨምሮ በተለያዩ ስብሰባዎች ላይ በቱርክም ሆነ በውጭ አገራት የማይፈቀዱ ነገሮችን ይዘው እንዳይገቡ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ እንደተሰራ ያስረዳሉ። በተለይም በመካከለኛው ምስራቅ አገራት በርካታ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ለእስር ተዳርገዋል ይላሉ። አቶ ወንድሙ በቻይናም ኮኬይን ይዛ በመገኘቷ የቻይና መንግሥት ያሰራት ናዝራዊት አበራ ጉዳይን በመጥቀስ "ሰዎች የማያውቁትን እቃ እንዴት ይወስዳሉ?" በማለት ይጠይቃሉ። "የስዕል ፍሬም ውስጥ ነው ኮኬይን አድርገው የሰጧት። ለአንዱ የሚነገረው ነገር ለሌሎቻችንም ትምህርት መሆን አለበት። የተለያዩ ሚዲያዎች ላይ የመደጋገፍ ባህላችን እያሉ የሚፅፉ አሉ። እሱኮ ባህል ድሮ ቀረ"በማለት በርካቶች ጥንቃቁ እንዲያደርጉ መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ። ቤተሰቦቿ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ስለ ሰላም እስር ሁኔታ ዝርዝር መረጃ የጠየቁ ሲሆን ሁኔታው"ኮንፊደንሻል ነው" ከማለት ውጭ ለመናገር ፈቃደኛ እንዳልሆኑም ቤተልሄም ታስረዳለች። ቢቢሲም የኢትዮጵያ አየር መንገድን ስለ ጉዳዩ የጠየቀ ሲሆን፣ ምላሽ እንዳገኘን ዝርዝሩን እናቀርባለን።
news-50798734
https://www.bbc.com/amharic/news-50798734
"ማርታ፣ ለምን ለምን ሞተች?"
ያች እለት! ከአርባ ሰባት አመታት በፊት 94 መንገደኞችን የያዘች ቦይንግ 720 በአስመራ በኩል ወደ ፓሪስ ለማቅናት ከአዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት ተነሳች።
የበረራ ቁጥር 708፣ ንብረትነቷም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነበረች። እንደተለመደው ተጓዥ በሙሉ በየእምነቱ ጸሎት አድርሶ፣ አገር ሰላም ብሎ የፍቅር ከተማ ብለው ወደሚጠሯት ፓሪስ ለመድረስ ተስፋ ሰንቋል። ከመንገደኞቹ መካከልም ማርታ መብራህቱ፣ ዋልልኝ መኮነን፣ አማኑኤል ዮሃንስ፣ ጌታቸው ሃብቴ፣ ታደለች ኪዳነማርያም፣ ዮሃንስ ፍቃዱ እንዲሁም ተስፋየ ቢረጋ ነበሩበት። • "ማንም መብታችንን ሊሰጠን ስለማይችል፤ ሴቶች ማንንም ሳይጠብቁ በራሳቸው መታገል አለባቸው" • የተነጠቀ ልጅነት የተማሪዎች እንቅስቃሴን ታሪክ ለሚያውቅ እነዚህ ወጣቶች ምን ያህል የእንቅስቃሴው ቁንጮ እንደሆኑ መረዳት ቀላል ነው። ስር ነቀል ለውጥን በማቀንቀንና መሬትን ለአራሹ በሚል እንቅስቃሴያቸው የአብዮቱ ጠባቂ (ዘ ጋርዲያን ኦፍ ዘ ሪቮሉሽን) ተብሎ በሚጠራው በተማሪዎች እንቅስቃሴ ውስጥ የነማርታ መብራህቱ ስም የገነነ ነበር። በ1953 ዓ.ም የተካሄደውና በጄኔራል መንግሥቱ ንዋይ የተጠነሰሰው መፈንቅለ መንግሥት ምንም እንኳን ባይሳካም ለውጥን ያበሰረ እንዲሁም ስርዓቱን መገርሰስ እንደሚቻል ያመላከተ ነበር። ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በተለያዩ ሃገራት ያሉ እንቅስቃሴዎች የተጋጋሉበት ወቅት ነበር። በወቅቱ ይፃፉ ነበሩ የትግል ጥሪዎችን ለምሳሌ ብንወስድ፤ የአውሮፓ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማህበር ልሳን ከነበረው ታጠቅ የሚከተለው ፅሁፍ ሰፍሮ ነበር። "በፊውዳሊዝም እና በኢምፔሪያሊዝም መቃብር ላይ የሁላችን የሆነች ህዝባዊት ኢትዮጵያን ለመመስረት ኢትዮጵያውያን የሆንን ሁሉ እፍኝ ከማይሞሉት ጨቋኝና ደጋፊዎቻቸው በቀር በአንድ የትግል ግንባር ውስጥ ተሰብስበንና ተደራጅተን በአንድነት መራመድ አለብን" ምንም እንኳን መሳፍንቱም በአልበገር ባይነት ሙጭጭ ቢሉም የተንሰራፋው ስራ አጥነት፣ ረሃብ እንዲሁም ኢፍትሃዊነት መስፈን ትግሉን አቀጣጠለው። ትግሉ ተጋጋለ፣ "መሬት፣ መሬት፣ መሬት ላራሹ፣ ተዋጉለት አትሽሹ" የሚሉ መፈክሮች፣ ሰላማዊ ሰልፎችና የስራ አድማዎች መጠናከር ስርዓቱን ያንገዳግዱት ጀመር። ተቃውሞን ለመገለጽ ተግባር ላይ ይውሉ ከነበሩት የትግል መንገዶች መካከል አንዱ የአውሮፕላን ጠለፋን ማካሄድ ዋነኛው ነበር። ለአውሮፕላን ጠለፋ ተልዕኮም ነበር እነ ማርታ መብራህቱ በበረራ ቁጥር 708 የተሳፈሩት፤ ማርታ ከትግል ጓዶችዋ ጋር አውሮፕላን ለመጥለፍ ከመጓዟ ቀደም ብላ በዘውዳዊው ስርዓት ላይ የነበራትን ጠንካራ አቋምና የነገ ህልሟ የሚገልጽ ጽሑፍ "ማኒፌስቶ" ትታ ነበር የተሳፈረችው። ይሄው መልእክት እንዲህ ይነበባል። • "የመከላከያ ሚኒስቴርን በተሻለ መልኩ መምራት ይቻላል" ኢንጂነር አይሻ መሀመድ "እኛ የኢትዮጵያና የኤርትራ ሴቶች ትግላችንን ለመጀመር ዝግጁ መሆናችንን ለማሳየት ለዓለም ህዝብ የምናሳውቅበት ወቅት ላይ ደርሰናል። ትግላችን ትልቅ መስዋእትነት የሚጠይቅና ጉልተኞችና አጼዎችን የሚመክት ይሆናል። በዚሁ የትግል ማዕበል ጭቁን ህዝባችንን ለማዳን ቆራጦችና የማንወላወል መሆን አለብን። ጠላቶቻችን እንዲህ ዓይነት ቋንቋ ብቻ ነው የሚገባቸው። ነጻነትም ይሁን እኩልነት መና ሆኖ ከሰማይ አይወርድም። በተለይ እኛ ሴቶች ደግሞ የበለጠ የተጨቆንን ስለሆን፤ በርትተን፤ ታጥቀን መታገል አለብን። ጥረታችንም ሆነ ለውጥ ፈላጊነታችን ከሁሉም በላይ ሊሆን ይገባል።" ማርታ መብራህቱ ማን ናት? ማርታ ውልደቷ በ1943 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ሲሆን፤ ትምህርቷን በደብረ ዘይት እንዲሁም አባቷ በስራ ምክንያት ወደ ናይጀሪያ ሲሄዱ በዛው አጠናቃለች። በወቅቱም አሜሪካን የመጎብኘት እድል ያገኘችው ማርታ ዓለም አቀፉን የጭቆና ትግሎችን በተለይም በአሜሪካ ውስጥ የሚደረገውን የሲቪል መብቶች ትግል መረዳት አስችሏታል። የኢትዮጵያ ትግል ለብቻው እንዳልሆነና በተለይም ከዓለም አቀፉ ፀረ- ኢምፔሪያሊዝም፣ ቅኝ ግዛት እንዲሁም ዘረኝነት ትግሎችም ጋር አብሮ እንደሚቆም በማኒፌስቶዋ ገልፃለች። አሜሪካ በቬትናም ላይ ያደረገችውን ወረራ በመቃወም፣ የፍልስጥኤምን ጥያቄ እንዲሁም በላቲን አሜሪካ ለነፃነት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በመደገፍ ቆማለች። "ድል ለታጋዩ ህዝብ፤ ወንድሞቼና እህቶቼ በትግላችን እንቀጥል" በማለትም ለትግሉ ያላትን ፅኑ አቋም አንፀባርቃለች። ምንም እንኳን በወቅቱ አባቷ ምህንድስና እንድትማር ከፍተኛ ፍላጎት ቢኖራቸውም እሷ ግን በዛሬው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በቀድሞው ኃይለስላሴ ዩኒቨርስቲ ገና በአስራ አምስት አመቷ ህዝቡን ለመርዳት ካላት ፍላጎት ጋር ተያይዞ የህክምና ትምህርቷን ለመከታተል ተቀላቀለች። በወቅቱም የአርሶ አደሩ ሁኔታ፣ የሰፈነው ድህነትን ትታገል ነበር ፤ ትግሉ ዓለም አቀፋዊ ይዘት እንዲኖረው ብዙ የታገለች ሲሆን ጓደኞቿም በጥቁር አሜሪካ የትግል ታሪክ ዘንድ ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጣት አንጄላ ዴቪስ ጋር ያመሳስሏት ነበር ማርታ "ኢትዮጵያዊቷ አንጄላ ዴቪስ"። ማርታ አይበገሬ፣ አንደበተ ርቱዕ፣ አንባቢ፣ የህዝብ በደል የሚያንገበብግባት ነበረች፤ በተማሪዎች እንቅስቃሴም የጎላ አስተዋፅኦ ነበራት። በትምህርቷ በጣም ጎበዝ የነበረች ሲሆን የህክምና ተማሪዎች ማህበርም ፕሬዚዳንት ነበረች። አባቷ ራሳቸው እንዴት እንዲህ አይነት ጨቋኝ ስርአት አካል ትሆናለህ በማለትም በከፍተኛ ሁኔታ ትተቻቸው እንደነበር ተናግረዋል። በአንድ ወቅትም መሬት መግዛታቸውን ስትሰማ "እኛ መሬቱን ለአራሹ ለባለቤቱ ለማስመለስ እንጥራለን፤ አንተ መሬት ትገዛለህ" ማለቷን ነብዩ ሃይለሚካኤል 'Life in Twentieth century Ethiopia Autobiographical Narrative of Brigadier General Mebrahtu Assefa' በሚለው የመመረቂያ ፅሁፉ አካቶታል። ማርታ ትምህርቷን ጨርሻ ዶከተር ለመሆን አንድ ሴሚስተር ሲቀራት ነበር ከትግል ጓደኞችዋ ጋር በጠለፏት አውሮፕላን ሰማይ ላይ የቀረችው። የእርሷና የትግል ጓዶቿ የአውሮፕላን ጠለፋ ወሬ በሰላዮች ጆሮ መግባቱ ጋር ተያይዞ መጨረሻቸውን የሚያሳዝን አድርጎታል። የአውሮፕላኑ ጠለፋ ሕዳር 29፣ 1965 ዓ.ም ከዋለልኝ መኮንን፣ ከአማኑኤል ዮሃንስ፣ ከጌታቸው ሐብቴ፣ ከዮሃንስ በፍቃዱ፣ ከተስፋዬ ቢርጋናና ከታደለች ኪዳነ ማርያም ጋር አውሮፕላኑን ለመጥለፍ አልመው ገቡ። ዋለልኝ ሰባራ ሽጉጥ ይዟል፣ ማርታ በበኩሏ የእጅ ቦምብ ይዛ እንድትገባ በተሰጣት ትዕዛዝ መሰረት በውስጥ ሱሪዋ (በፓንትዋ ይዛው ገባች)። ጥበቃውን አልፈው ቦታውን ያዙ፤ አውሮፕላኑም በተያዘለት ፕሮግራም መሰረት ሊበር ማንኮብኮብ ጀምሯል። አውሮፕላኑ ከተነሳ ከአስራ ሶስት ደቂቃ በኋላ አንድ ሽጉጥ የያዘና ቦምብ የያዘ ግለሰብ " አውሮፕላኑ ተጠልፏል፤ አርፋችሁ ተቀመጡ" አለ። የፀጥታ ኃይሉ ተኮሰበት፤ የያዘውን የእጅ ቦምብም ማፈንዳት አልቻለም። ማርታ እሱን ለመከለል በትግል ጓደኛዋ ላይ ወደቀች፤ አልተረፈችም! ተተኮሰባት። ከጠላፊዎቹ መካከል አማኑኤል ዮሃንስ ቦምብ ይዞ ነበር፤ አማኑኤል በአውሮፕላን ጠለፋ ላይ ሲሳተፍ ለሁለተኛ ግዜው ነው።አውሮፕላኑ በጠላፊዎች እጅ ስለገባ ባለበት እንዲቆይ ቀጭን ትዕዛዝ ተላለፈ፤ ሰማይና ምድር የተገለባበጡ ይመስል ሁኔታዎች ተቀያሩ። በነዛ ወጣቶች ላይ የተኩስ እሩምታ ተከፈተባቸው፤ በተዓምር ከተረፈችው ከታደለች ኪዳነ ማርያም በስተቀር ፤ ሰባቱም ተገደሉ። አውሮፕላኗ በደም አበላ ተሞላች። ገና በ22 አመቷ የተቀጨችው ማርታ፤ ባለ ትልቅ ስሟ ማርታ መሞቷ የእግር እሳት የሆነባቸው አባቷ " ይህንን ስርአት አገልግያለሁ እና ጨክኖ ይገድላታል ብዬ አላሰብኩም ነበር" ማለታቸውን ነብዩ ሃይለሚካኤል በፅሁፉ አካቶታል። የነሱ ሞት ትግሉን አቀጣጠለው፤ ወላጆች አነቡ፤ እናቶች ልባቸው ተሰበረ፤ ተማሪዎች ዘመሩላቸው " ጥላሁን፣ ለምን ለምን ሞተ?፣ ማርታ ለምን ለምን ሞተች? ገርማሜ ለምን ለምን ሞተ? ታከለ ለምን ለምን ሞተ? በኃይል በትግል ነው፤ ነፃነት የሚገኘው" "ማርታ ለሀገርሽ ራስሽን ሰጥተሻል፤ ስምሽ የማይሞት ነው ዘላለም ይኖራል፤ ለቀሩት እህቶሽ ምሳሌ ሆነሻል ተባለላት፤ • የሴቶች መብት ታጋይዋ ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ማን ናቸው? የአውሮፕላን ጠለፋ እንደ ትግል ዘዴ በስልሳዎቹ የአውሮፕላኖች ጠለፋ ለዘውዳዊት መንግሥት ትልቅ ስጋት ፈጥሮበት እንደነበር የታሪክ ተንታኞች ይናገራሉ። በተጋድሎ ሐርነት ኤርትራ (ተሓኤ) የተመለመሉ ወጣቶች በውጭ አገር በተደጋጋሚ የኢትዮጵያን አየር መንገድ አውሮፕላኖች ይጠልፉ የነበረ ሲሆን፤ ቀስ በቀስም ከኢትዮጵያውያን ጓዶቻቸው አብረው የጠለፋውን ስራ ተያያዙት። በጎርጎሳውያኑ 1969 ዓሊ ስዒድ ዓብደላ የተባለ የህዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ ታጋይ ከሁለት ጓዶቹ ተባብሮ በካራቺ ፓኪስታን የኢትዮጵያን አየር መንገድ በመጥለፍ ከባድ ጉዳት አደረሱ። ዓሊ ስዒድ በስልሳዎቹ ወደ ትጥቅ ትግል የተሰማራና ከመስራቾቹ አንዱ ነው። በትጥቁ ትግል ጊዜም የአብዮት ዘብ የሚባለውን የድርጅቱ ክፍል በሃላፊነት መርቷል። የታሪክ ተማራማሪው ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ በኢንሳይክሎፒድያ ኢትዮፒካ ስለ ብርሃነ መስቀል ረዳ እንደሚከተለው ጽፈዋል። በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር ነሐሴ 1969 ብርሃነ መስቀል ከእነ አማኑኤል ገብረየሱስ፣ እያሱ አለማየሁ፣ ገዛኸኝ እንዳለና ሌሎች ጓዶቹ አብሮ አውሮፕላን ጠልፈው በአልጀርያ ጥገኝነት እንደጠየቀና በመቀጠልም የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) መመስረቱን ፅፈዋል። ባህሩ ዘውዴ " The Quest for Socialist Utopia" በሚለው መጽፋሃቸውም በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር በ1971 በወቅቱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የነበሩት ሙሴ ተስፋሚካኤል፣ ዮሃንስ ስብሃቱ፣አማኑኤል ዮሃንስ፣ ደበሳይ ገብረስላሴ ከባህርዳር ወደ ጎንደር ትበር የነበረች የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ጠልፈው ወደ ሊብያ እንደሄዱም ፅፈዋል። አውሮፕላኑን ከጠለፉት መካከል ሁለቱ ሙሴና ዮሃንስ በጎርጎሳውያኑ 1973 በህዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ ድርጅት በዴሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ ጥያቄ በማንሳታቸው አክራሪ ግራዘመም ናችሁ ተብለው እንደተገደሉ ኤርትራዊው ፕሮፌሰር ጋይም አስፍሯል። አማኑኤል ዮሃንስ ደግሞ በድጋሚ አውሮፕላን ሊጠልፍ ሲል በጸጥታ ኃይሎች ተመትቶ ህይወቱ አልፏል። የማርታ ቤተሰብ ቅድመ ታሪክ ማርታ የብርጋዴር ጄነራል መብራህቱ ፍስሃና ወ/ሮ አርያም ገብረየሱስ የበኸር ልጅ ስትሆን፤ አራት ወንድምና እህቶችም አሏት። አባቷ ጄነራል መብራህቱ የተወለዱት አስመራ ሲሆን አያቷም አቶ ፍስሃ አስመራ ውስጥ ገዛ ከኒሻ እየተባለ የሚጠራ ሰፈር ነበር ተወልደው ያደጉት። አያቷ አቶ ፍስሃ በጎርጎሳውያኑ 1923ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውን ተከትሎ አባቷ ጄነራል መብራህቱ ያደጉት አዲስ አበባ እንዲሁም አሰበ ተፈሪ ነው። ትምህርታቸውንም በአዲስ አበባ ዳግማዊ ሚኒልክ ነው ያጠናቀቁት። በጣልያን ወረራ ጊዜ አያቷ በራስ እምሩ ሃይለስላሴ ስር ሆነው ጣልያንን ተዋግተዋል። የሞቱትም ገራ በተባለ ቦታ ላይ በተካሄደው ውጊያ ነው። በዚህም ምክንያት የጄነራል መብራህቱ ቤተሰብ ወደ አስመራ ተመልሰው ለመኖር የተገደዱ ሲሆን በአስመራ ከሚስዮናውያን ጋር ትምህርታቸውን ቀጥለዋል። በጎርጎሳውያኑ 1936 ዓ.ም እንግሊዝ ኤርትራን ለመቆጣጠር በከረን በኩል ሲገባ አባቷ ጄነራል መብራህቱ መንገድ ላይ ቆመው ነበር የተቀበሉዋቸው። ከእንግሊዞች ጋር ሆነው ለመስራት ፍቃደኛ እንደሆኑና የአባታቸውም ሞት ያንገበግባቸው ስለነበር ለመበቀል እንደሚፈልጉም ገለጹላቸው። እንግሊዞችም ተርጓሚ ያስፈልጋቸው ስለነበር ጄነራል መብራህቱን ተርጓሚ አድርገው ቀጠሩዋቸው። በወቅቱ ገና የ17 ዓመት ልጅ ነበሩ፤ የጣልያንኛና እንግሊዝኛ ቋንቋ ጥሩ ችሎታ ነበራቸው። ማርታ ከእንደዚህ ዓይነት ቤተሰብ ነበር የተወለደችው። በትንሽ እድሜ ትልቅ ስራ የሰራች፤ ትውልድን ያነቃቃችው ማርታ መካነ መቃብር 'ጴጥሮስ ወጳውሎስ' ሲሆን መቃብሯም ላይ "እጆቼ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን አንስቼ፤ ወደ አንተ ስለምን፤ ጸሎቴን ስማው" መዘዝ8፡3] የሚል የመጽሃፍ ቅዱስ ጥቅስ አርፎበት ይገኛል።
41497363
https://www.bbc.com/amharic/41497363
የጦር መሣሪያ እና አሜሪካ በቁጥሮች
ስቴፈን ፓዶክ የተባለ አሜሪካዊ 59 ሰዎችን በጥይት በመግደል 500 የሚሆኑትን ባቆሰለ ማግስት አሜሪካ ውስጥ መሰል ድርጊቶች ምን ያህል የሰው ነፍስ እያጠፉ እንሆነ የሚያሳይ መረጃ መውጣቱን ቀጥሏል።
በፈረንጆቹ 2015 ብቻ በአሜሪካ 372 ጅምላ የጦር መሣሪያ ጥቃቶች የደረሱ ሲሆን፤ 475 ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ 1800 የሚደርሱት ቆስለዋል። ጅምላ የጦር መሣሪያ ጥቃት ማለት ጥቃት ፈጻሚውን ጨምሮ ቢያንስ የአራት እና ከዚያ በላይ ሰዎችን ሕይወትን የሚያጠፋ ጥቃት ነው ሲሉ ባለሙያዎች ይተነትኑታል። በአንድ ወቅት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ የጦር መሣሪያን አስመልክቶ እንባ እየተናነቃቸው ሲናገሩ የሚያሳይ ምስል ወጥቶ መነጋገሪያ እንደነበረ የሚታወስ ነው። ፕሬዝደንቱ የጦር መሣሪያን በተመለከተ ለማሻሻል ያሰቡት ሕግ ሳይሳካላቸው እንደቀረ ይታወቃል። እርግጥ የሆነው ቁጥር ይፋ ባይሆንም አሜሪካ ውስጥ 300 ሚሊዮን የጦር መሣሪያዎች ቢያንስ 75 ከመቶ በሚሆኑ አሜሪካውያን እጅ ስር እንዳሉ ይነገራል።
news-48754362
https://www.bbc.com/amharic/news-48754362
“የኢህአፓና መኢሶን ነገር አማራ ክልል ላይ ሊከሰት ይችላል ብዬ ነበር” አቶ ቹቹ አለባቸው
አቶ ቹቹ አለባቸው ከጥቂት አመታት በፊት ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት እስከተለያዩበት ጊዜ ድረስ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራር ነበሩ። የሟች ዶ/ር አምባቸው መኮንንም የቅርብ ጓደኛ ነበሩ። ቢቢሲ በአዴፓ ውስት አሉ ስለሚባሉ ልዩነቶች አነጋግሯቸዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(አዴፓ) ውስጥ ልዩነቶች እየጎሉ መጥተዋል፤ መካረሮችም ነበሩ ይባል ነበር?
አቶ ቹቹ፡ ቆይቷል፤ ከአንድ ዓመት በላይ ይሆነዋል። የድርጅቱ ባህሪ እየተቀየረ አንድ ቡድን የበላይነቱን ይዞ ለመውጣት የሚያደርገው ትግል (እኔ የዚያ አካል ስለነበርኩ ነው የምነግርሽ)። ቀድሞ መካረርም ቢኖር ድርጅቱ ወደዚህ ደረጃ የሚያመራ ባህል አልነበረውም። በተለይም ባለፉት አንድ ሁለት አመታት እንደዚህ ያለው የስልጣን ሽኩቻና ፍትጊያ እንዲሁም በጎጥና በአካባቢ መሿሿም ከባድ ችግር ነበር። ልዩነቱና መካረሩ ምን ሀሳብ በሚያራምዱና ምን በሚፈልጉ መካከል የተፈጠረ ነው? አቶ ቹቹ፡ ዋነኛው ጉዳይ ከህወሓት ጋር ያለ የግንኙነት ችግርን የመፍታትና ያለመፍታት ጉዳይ ነው። አንዱ ቡድን በተለይ እነ አምባቸው ፤ የለውጥ ኃይል የሚባለው ችግር መኖሩን አምኖ፣ ችግሩን የምንፈታው ግን በውይይትና በድርድር፣ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ነው የሚል አለ። ቀደም ሲል የነበሩት፣ የተወገደው የነበረከት ቡድን የሚባለው ደግሞ የአማራን ሕዝብ ጥቅም አሳልፎ የሰጠ የሚል ከፍተኛ ክስ ነበረበት። አሁን ነገሩ የተባባሰው ግን ለውጡን ተከትሎ ምህረት ተደርጎላቸው ከስር የተፈቱት ወደ ድርጅቱ እንደገና እንዲቀላቀሉ ሲደረግ ነው። እኒህ ኃይሎች ነገሮችን በሚዛኑ ካለው አመራር ጋር ተጣጥሞ መሄድ አልቻሉም። ብሶቱ፣ ቁጭቱ አለ። የአማራን ሕዝብ በደልን በስፋት ያነሳሉ። ወጣቱ በስሜት ይከተላል። ማስተዋል፣ መምከር ላይ በጣም ከፍተኛ ችግር አለ። በእነዚህ ጉዳዮች ትንሽ ልምድ ያለው ነባሩ አመራር ጉዳዩን በተረጋጋ መልኩ መፍታት ይፈልጋል። ይሄኛው ኃይል ደግሞ አሁንም ብአዴንን [የአሁኑ አዴፓ] የህወሃት ተላላኪ ነው፣ የአማራን ሕዝብ ጥየቄ አይመልስም የሚል ጫፍ የወጣ ነገር እየያዘ ሄደ። ሁለቱም ላይ መካረሮች ተከስተዋል። • በሃየሎም ይምሉ የነበሩት ጄነራል ሰዓረ መኮንን ማን ናቸው? • መፈንቅለ መንግሥቱና የግድያ ሙከራዎች መካረሮቹ ምን ደርሰው ነበር? አቶ ቹቹ፡ እዚህ ላይ እንደሚደረስ ለድርጅቱ አመራሮች በፅሁፍ፣ በግል፣ በአካል አግኝቼ ተናግሬአለሁ።ነገር ግን አብሮ ማደግ ችግር ነው፤ ያጣጥሉታል። አካሄዱ እንዳለ እዚህ ደረጃ ላይ ሊደረስ እንደሚችል የሚያሳይ ነበር። ከውስጥ የምናገኘው መረጃም ስለነበር አንድ ሁለት ሶስት ብለን ነግረናቸዋል። የኢህአፓና መኢሶን ነገር አማራ ክልል ላይ ሊከሰት ይችላል ብዬ ተናግሬ ነበር። ከጥቂት ቀናት በፊት የድርጅቱ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ዮሃንስ ቧያለውን አግኝቼ ነግሬዋለሁ። "ይሄ የሚባል ሰው ይሄን ክልል ያፈርሰዋል ብዬ ተናግሬአለሁ" "ይሄ ሰው" የሚሉት ማንን ነበር? አቶ ቹቹ፡ ከጀነራሉ ጋር አይደል መካረር የደረሰው፤ ግን ከእሱ ጋር ብቻም ሳይሆን ሌሎችም አሉ። የመድረክ ንግግሮችን ተከታትለሽ ከሆነ መካረሮች ይታዩ ነበር እና ከዚህ ሰው ጋር ያለው ልዩነት ካልተፈታ ነገሩ ክልሉን ወደ ማፍረስ ይሄዳል ብለን ነበር። ለፕሬዘዳንቱም ነግሬው ነበር። የቅርብ ጓደኛዬ ነበር፤ በአንድ ወቅት ምክትሉም ነበርኩ። ከፌደራል ወደ ክልል እንዳይሄድ ተነጋግረን ተማምነን ቃል ገብቶልኝም ነበር። • ስለ'መፈንቅለ መንግሥት' ሙከራው እስካሁን የማናውቃቸው ነገሮች ለምን ነበር የክልል ሹመት ተቀብለው እንዳይሄዱ የነገሯቸው? አቶ ቹቹ፡ የማውቃቸው የማይመቹ ብዙ የተበላሹ ነገሮች ነበሩ። እዚህ ሚዲያ ላይ ላወጣቸው አልችልም። አልሄድም ብሎ ቃል ገብቶልኝ ከዚያ በኋላ ሳይነግረኝ መሾሙን ሰማሁ። በዚህ ተኮራርፈን ቆይተን በመጨረሻ ለአንድ ጉዳይ ከመሞቱ ሳምንት በፊት ተደዋወልን። ልንገናኝ ነበር ሳይመቻች፣ ሳንገናኝ በዚያው እንደተለያየን ቀረን። ያደዋወላቹህና ሊያገናኛችሁ የነበረው ጉዳይስ ምን ነበር? አቶ ቹቹ፡ በኢትዮጵያና የሱዳን ድንበር ጉዳይ አንዲት ስብሰባ ነበራቸውና ስለዚያ እንድንመካከር ፈልገው ነበር። አሁን የተፈጠረው ነገር በፓርቲው ቀጣይ እርምጃ ላይ ምን ዓይነት ተፅእኖ ሊያሳድር ይችላል ብለው ይገምታሉ? አቶ ቹቹ፡ ይህ ነገር መከራ ብቻም ሳይሆን ተስፋም ይዟል ብዬ አምናለሁ። ትንሽ ዋጋ ሊያስከፍለን ቢችልም ድርጅቱ ቆሞ ራሱን የሚገመግምበትና ራሱን የሚያስተካክልበት እድል ስለሚኖር። ብቁ መሪ ከተገኘ የበለጠ ጉልበት አግኝቶ ወደ ፊት ለመስፈንጠር አንድ እንድል አድርጎ መጠቀም የሚቻል ይመስለኛል።
news-43631218
https://www.bbc.com/amharic/news-43631218
ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ስደተኞችን የማስጠለሉን ሃሳብ እንደተዉት አስታወቁ
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በተደረገ ስምምነት መሠረት ስደተኞችን ከሃገሯ የማስወጣቱን መርሃ ግብር እንዳቋረጠች አስታውቃ የነበረችው ሃገራቸው ሃሳቧን እንደቀየረች አስታወቁ።
አብዛኛዎቹ ስደተኞች እንደሚኖሩባት የሚነግርላት የቴል-አቪቭ ከተማ ነዋሪዎችን ካናገርኩ ወዲህ ነው ሃሳቤን የቀየርኩት ሲሉ ቤኒያሚን ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ሰርጎ ገቦችን ከሃገር ለማስወጣት ሁሉንም አማራጭ እንጠቀማለን" ሲሉም ተደምጠዋል። 30 ሺህ እንደሚደርሱ ከሚገመቱት ስደተኞቹ አብዛኛዎቹ ኤርትራውያንና ሱዳናውያን እንደሆኑም ዘገባው አትቷል። ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በተደረሰው ስምምነት መሠረት 16 ሺሕ ያህል ስደተኞች በአንዳንድ የምዕራቡ ዓለም ሃገራት እንደሚጠለሉ እንዲሁም 18 ሺህ ያህል ደግሞ በእስራኤል ቋሚ የነዋሪነት መታወቂያ እንደሚሰጣቸው ተነግሮ ነበር። ከጥቂት ወራት በፊት ነበር የእስራኤል መንግሥት አፍሪካውያን ስደተኞች 5 ሺህ ዶላር ተሰጥቷቸው ወደ ሶስተኛ የአፍሪካ ሃገር እንዲሸጋገሩ የሚያስገድድ ህግ አውጥቶ የነበረው። ፍቃደኛ ያልሆኑ ስደተኞች ወደ እስር ቤት እንደሚወረወሩ የሚያስገድደውን ህግ የእስራኤል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለተወሰነ ጊዜ ያህል ሥራ ላይ እንዳይውል እንዳገደው ይታወሳል። ትላንት የተደረሰው ስምምነት ተግባራዊ ቢሆን 18 ሺሃ ያህል ስደተኞች በ5 ዓመት ጊዜ ውስጥ ወደ ጀርመን፣ ካናዳና ጣልያን ይሸጋገሩ ነበር።
news-41896924
https://www.bbc.com/amharic/news-41896924
የፓራዳይዝ ሰነዶች በአፍሪካ ተፈጥሯዊ ሃብቶች ላይ እየተደረገ ያለውን ዝርፍያ እያጋለጡ ነው
በዓለማችን ከሚገኙ ታላላቅ ኩባንያዎች አንዱ የሆነው ግሌንኮር በ45 ሚሊዮን ዶላር ሙስና ለሚጠረጠር ነጋዴ ገንዘብ ካበደረ በኋላ ድሃ በሆኑ በመካከለኛው አፍሪካ በሚገኙ ሃገራት ውስጥ የማዕድን ፍለጋ ሥራ ላይ ለመሰማራት ፍቃድ እንዲደራደር መጠየቁን የፓራዳይዝ ሰነዶች (የፓራዳይዝ ፔፐርስ) አጋልጧል። የፓራዳይዝ ስነዶች ምድን ናቸው?
ካታንጋ የማዕድን ማውጫ ስፍራ-ዲሞክራቲክ ሪፓፐሊክ ኦፍ ኮንጎ የፓራዳይዝ ሰነዶች አምልጠው የወጡ የፋይናንስ (የገንዘብ) ሰነዶች ናቸው። ሰነዶቹ የዓለማችን ፖለቲከኞች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች እና ብዙ ትርፍ የሚያስገቡ ግለሰቦች ገንዘባቸውን ከከፍተኛ ግብር ለማሸሽ ሲጠቀሙበት የነበረውን የረቀቀ ዘዴ ያጋለጡ ናቸው። ባለፈው ዓመት የፓናማ ሰንዶች በጀርመኑ ጋዜጣ ዙተቹ ሳይተን እጅ ከገቡ በኋላ ቢቢሲ ፓኖራማ እና ዘ ጋርድያንን ጨምሮ ከሌሎች 100 የህዙሐን መገናኛ ተቋማት ጋር በመሆን በሰነዶቹ ላይ ምርመራ እየተካሄደ ነው። የአንግሎ-ስዊዝ ኩባንያው ግሌንኮር የብድር አቅርቦቱን የሰጠው እአአ በ2009 ለእስራኤላዊው ቢሊየነር ዳን ገርትለር ሲሆን ግለሰቡ በዲሞክራቲክ ሪፓፐሊክ ኦፍ ኮንጎ ውስጥ ከፍተኛ ባለስልጣናት መሃል የደለላ ስራ ይሰራ ነበር ተብሏል። ቢሊየነሩ ገርትለር እንዲያስማማ ተጠይቆ የነበረው ለማዕድን አውጪ ኩባንያ አዲስ የማዕድን ውጣት ፍቃድን ማስገኘት ነበር። በዚህ የማዕድን አውጪ ኩባንያ ውስጥ ግሌንኮር ትልቅ ድርሻ የነበረው ሲሆን ተሟጋቾች ይህ ስምምነት ድሃዋን የአፍሪካ ሃገር ዲሞክራቲክ ሪፐሊክ ኦፍ ኮንጎን በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር አሳጥቷታል ይላሉ። ቢሊየነሩ ገርትለር እና ግሌንኮር ምንም አላጠፋንም ይላሉ። ግሌንኮር ለዳን ገትለር በያዝነው ዓመት የካቲት ወር ላይ ከዲሞክራቲክ ሪፐሊክ ኦፍ ኮንጎ ማዕድን ቁፋሮ ወለድ የሚገኝ 534 ሚሊዮን ዶላር ለመክፍል ተስማምቶ ነበር። የመካከለኛዋ አፍሪካ ሃገር በግጭት ስትታመስ እና ለአስርት ዓመታት በሙስና ተዘፍቃ ከመኖሯ በላይ ከግማሽ በላይ የሚሆኑ ዜጎቿ ከድህነት ወለል በታች ህይወታቸውን ይገፋሉ። ይህ ይሁን እንጂ የሃገሪቷ ሰፊው የማዕድን ሃብት የተጠቀሙበት በየዓመቱ በመቶ ሚሊዮኞች የሚቆጠር ገንዘብ ያስገባሉ። ይህም ግዙፉን ግሌንኮር፥ የአንግሎ-ስዊዝ የማዕድን እና ሸቀጥ ንግድ ኩባንያን ይጨምራል። በገቢ ልኬት ግሌንኮር በፕላኔታችን 16ኛው ግዙፉ ኩባንያ ነው። ግሌንኮር በዲሞክራቲክ ሪፐሊክ ኦፍ ኮንጎ ውስጥ በማዕድን ሥራ በተለይ መዳብ በማምረት ለበርካታ ዓመታት ተሰማርቶ ቆይቷል። ኩባንያው እንደሚለው በሃገሪቱ ውስጥ 50 ቢሊያን ዶላር በስራ ላይ አውሏል። ከአስር ዓመት በፊት ግሌንኮር በሃገሪቱ ደቡባዊ ክፍል መዳብ የማውጣት ፍቃድ ከነበረው ካታንጋ ኩባንያ ውስጥ የ8.52 በመቶ ድርሻ ነበርው። ሰኔ 2008 የግሌንኮር ከፍተኛ ባለስልጣናትን የያዘው የካታንጋ ቦርድ መልካም ያልሆነ ዜና ሰማ። በፕሬዝዳንት ጆሴፍ ካቢላ የሚመራው የዲሞክራቲክ ሪፐሊክ ኦፍ ኮንጎ መንግሥት በማዕድን ማውጣት ፈቃድ አስጣጥ ላይ በድጋሚ መደራደር እንደሚፈልግ አስታወቀ። በወቅቱ ግሌንኮር በካታንጋ ኩባንያ ውስጥ 150 ሚሊዮን ዶላር ፈሰስ አድርጎ ነበር። ኩባንያው በማዕድን ማውጣት ስራ ላይ ካልተሳተፈ ይህን ያህል መጠን ያለው ገንዘብ መባከኑ ነው። በሃገሪቱ መንግሥት ስም ተመዝግቦ የነበረው ጌካማይንስ መዳብ እና ኮባልት ለማውጣት 585 ሚሊዮን ዶላር ጠየቀ። ቀድሞ የነበረው ስምምነት ግን 135 ሚሊዮን ዶላር ነበር። በፓራዳይዝ ሰነዶች ውስጥ የተገኙ መረጃዎች እንደሚያሳዩት የካታንጋ ቦርድ የዲሞክራቲክ ሪፐሊክ ኦፍ ኮንጎ መንግሥት ጥያቄ ተቀባይነት የሌለው ከልክ ያለፈ እንደሆነ ተሰምቷቸው ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜም የኩባንያው ዳይሬክተሮች እራኤላዊውን ዳን ገትለርን ለእርዳታ ጠርተውት ሊሆን ይችላል። የሰነዱ ምንጭ፡ የካታንግ ቦርድ ቃለጉባኤ- ሰኔ 2008(እአአ) በካታንጋ ቦርድ ቃለጉባዔ ''ቦርዱ በኩባንያው ከፍተኛ ተዘዋዋሪ ጥቅም የሚያገኘው ዳን ገትለር ከኮንጎ ባለስልጣናት ጋር የመደራደር ስልጣን ሊሰጠው ይገባል'' የሚል ጽሁፍ ሰፍሯል። ''ቦርዱ... ገርትለር በዚህ መልኩ ለመንቀሳቃስ ዝግጁ መሆኑን ቀርቦ ማረጋገጥ አለበት'' ይላል። ገርትለርም ካታንጋን ወክሎ ስምምነት ላይ ለመድረስ እንዲደራደር ጥያቄ ቀረበለት። በዚሁ ተመሳሳይ ወቅት ግሌንኮር በካሪቢያን የብሪታንያ ደሴቶች ለሚገኘው ሎራ ኢንተርፕራይዝ የ45 ሚሊዮን ዶላር ብድር ለመስጠት ተስማማ። ሎራ ኢንተርፕራይዝ በገርትለር ቤተሰቦች የሚመራ ድርጅት ነበር። ግሌንኮር ለካታንጋም 265 ሚሊዮን ዶላር አበደረ። በኋላ ደግሞ የብድሩ ገንዘብ ወደ አክሲዮን ድርሻ ተቀየረና ግሌንኮር ከፍተኛው ባለድርሻ ሆነ። ዳን ገርትለርም ቢሆን ከሎራ ኢተርፕራይዝ ብድር ምንም ጥቅም እንዳላገኘ ቢናገርም በማዕድኑ ጉዳይ እጁን እንዲያስገባ መንገድ ከፍቶለት ነበር። የሰነዱ ምንጭ ካታንጋ በአውሮፓውያኑ 2009 በቶሮንቶ የአክሲዮን ዝውውር ጊዜ የብድሩን ወደ ድርሻ መቀየር ይፋ ቢያደርግም ዝርዝር መረጃው ግን እስካሁን ግልጽ አልነበረም። በገርትለር የበድር ስምምነት ላይ በ3 ወራት ውስጥ አዲስ የመብት ስምምነት ማቅረብ ካልቻለ ግሌንኮር ብድሩን በፍጥነት የማስመለስ መብት እንደሚያገኝ ተጠቅሶ ነበር። የፓራዳይዝ ሰነዶች ገርትለር ይህ በፍጥነት ተሳክቶለት እንደነበረ ይጠቅሳሉ። ጌካማይንስም የመጀመሪያውን የ585 ሚሊዮን ዶላር የመነሻ ክፍያ ጥያቄ ወደ 140 ሚሊዮን ዝቅ አድርጎታል። ይህ ደግሞ ካታንጋ በመጀመሪያው ስምምነት ያቀረበው መነሻ ገንዘብ ጋር እኩል መጠን ስላለው 445 ሚሊዮን ዶላር አትርፎለታል። የሰነዱ ምንጭ ፒት ጆንስ ግሎባል ዊትነስ ፀረ-ሙስና ዘመቻ እንደተናገሩት እንደ ግሌንኮር ያሉ ስምምነቶች እንደ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ላሉ ሀገራት ከፍተኛ መዘዞችን ሊያስከትሉ ይችላሉ። "በሀገሪቷ ተፈጥሮአዊ ሀብት ጥገኛ ለሆኑ እንደ ዴሞክራቲክ ሪፓፐሊክ ኦፍ ኮንጎ ላሉ ሃገራት ከኢኮኖሚው ገንዘቡን ሙጥጥ አድርገው የሚወስዱ ስምምነቶች ውጤታቸው አሉታዊ ነው። ገትለር በበኩላቸው ለዲሞክራቲክ ሪፐፓሊክ ኦፍ ኮንጎ ጥሩ ያልሆነ ስምምነት ነው በሚለው ሀሳብ አጥብቀው ይከራከራሉ "ጌካሚንስ ከአዲሱ ጄቪኤ እንዲሁም ካታንጋ ከነበረው የመዳብ እንዲሁም የኮባልት ማዕደኖች ክምችት በ82.5 ሚሊዮን ዶላር መውሰዱ ጠቅሞታል" ብለዋል። ግሌንኮር ለቢቢሲ እንደተናገሩት ለሎራ ኢንተርፕራይዝ 45 ሚሊዮን ብድር " በንግድና እንዲሁም ስምምነቱ የተፈፀመውም ነፃ ሆነው ነው" ከሰባት አመታትም በፊት ሙሉ በሙሉ ተከፍሏል። የገትለር ጠበቆች በበኩላቸው የንግድ ሽርክና ሲፈርስ አበዳሪው አካል ይከፈለኝ ማለቱ ያልተለመደ ጉዳይ አይደለም ብለዋል። በተጨማሪም "ሎራ ኢንተርፕራይዝ፣ ገትለርም ይሁን የትኛውም ኩባንያ የብድሩን ፈንድ በቀጥታ አልተቀበሉም" ብለዋል። ገርትለር በዲሞክራቲክ ሪፓፕሊክ ኦፍ ኮንጎ ያላቸው መጥፎ ስም ሁለት አስርት ዓመታትን አስቆጥሯል። እአአ 2001 የተባበሩት መንግሥታት የአልማዝ ማዕድን ቁፋሮ መብትን በዋናነት ለመቆጣጠር በጦር መሳሪያና የውትድርና ስልጠና ስምምነት እንዳደረጉ የሚወነጅል ሪፖርት ወጥቷል። በቀድሞው የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ ኮፊ አናን የሚመራው የአፍሪካ ፕሮግረስ ፓናል ከአራት ዓመት በፊት ባወጣው ሪፖርት የገርትለር ኩባንያ በዲሞክሪቲክ ሪፐሊክ ኦፍ ኮንጎ የአልማዝ ማዕድን የማውጣት ስራን የፈፀሙት ካለው ትክክለኛ ዋጋ በዝቅተኛ እንደሆነ ይጠቁማል። የእስራኤላዊው ባለሀብት ጠበቆች በበኩላቸው በ2001ም ሆነ በ2013 የወጡትን ሪፖርቶች ፍፁም ውንጀላ ነው በማለት ይክዳሉ። በባለፈው ዓመት ሄጅ ፈንድ ኦች ዚፍ በአሜሪካ ባለስልጣናት በተለያዩ አፍሪካ ሀገራት ጉቦ ከፍለዋል የሚለውን ክስ 412 ሚሊዮን ዶላር በመክፈል ስምምነት ላይ ለመድረስ ሞክሯል። አቃቤ ህጎቹ እስራኤላዊው ባለሀብትን በስም ባይገልፁትም በኮንጎ የማዕድን ቦታን ከሌሎች ኩባንያዎች ጋር በመሆን 100 ሚሊዮን ዶላር ጉቦ ከፍለዋል በሚልም ወንጅለውታል። ዳን ገርትለር በበኩላቸው ይህንን ውንጀላ ክደዋል። በዋናነትም ገርትለር በ2012 የሞቱት የፕሬዘዳንት ካቢላ ቁልፍ አማካሪ የነበሩት ካቱምባ ምዋንኬ ቅርብ ጓደኛ መሆናቸውም ጥርጣሬ ላይ ጥሏቸዋል። ግሎባል ዊትነስ ለተባለው መንግስታዊ ላልሆነ ድርጅት የሚሰሩት ዳንኤል ብሊንት ኩርቲ በዋነኝነት በዳን ገርትለርና በግሌንኮር መካከል ያለውን የዓመታት ግንኙነት ሲመረምሩ የነበረ ሲሆን ኩባንያው ከባለሃብቱ ጋር የነበረውን ሽርክና ማጤን ነበረበት ይላሉ። " የኮንጎው ፕሬዚዳንት ቅርብ የነበረ ሰው ቀጥረው ገንዘብ በማንበሽበሽና ለሚደረጉ ስምምነቶች ሙሉ ስልጣን መስጠታቸው ራሳቸውን አደጋ ውስጥ ከተዋልም" ይላሉ። የዳን ገትለር ጠበቆች ለቢቢሲ እንደተናገሩት "እርሳቸው ብዙ ሀብታቸውን ለተቸገሩ ሰዎች የሚለግሱ የተከበሩ ሰው ናቸው" ብለዋል።
news-49922350
https://www.bbc.com/amharic/news-49922350
እየበረታ በመሄድ ላይ ያለው የዋጋ ንረት አዙሪት
ባለፉት ጥቂት ወራት የሸቀጦች የዋጋ ንረት እና አጠቃላይ የኑሮ ዋጋ መወደድ በልዩ ልዩ የኢትዮጵያ የብዙሃን መገናኛዎች ተደጋግመው የሚወሱ ጉዳዮች ሆነዋል።
የብር የመግዛት አቅም እየቀነሰ ነው የመንግሥት ኃላፊዎች እና የሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶችም የችግሩን አሳሳቢነት ከመቀበል በዘለለ እየተወሰዱ ናቸው የሚሏቸውን እርምጃዎች ሲናገሩ ተስተውለዋል። በወርሃ ግንቦት 2011 ዓ.ም መገባደጃ ላይ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ኢንጂነር እንዳወቅ አብጤ በመዲናዋ በግንባታ ዕቃዎች፣ በእህል፣ በጥራጥሬ እና በአትክልት ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪዎች መከሰታቸውን ጠቅሰዋል። እንደመፍትሄም ችግሩን አባብሰዋል ያሏቸው ህገ ወጥ ነጋዴዎችን ወደ ህጋዊ መስመር ማምጣት፣ ፈቃደኛ ያልሆኑት ላይ ደግሞ ይህንን የሚከታተል ግብረ ኃይል በማቋቋም እርምጃ መውሰድ፣ እንዲሁም ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ የአቀርቦት ሥርዓቱን ማሰተካከል የከተማዋ አስተዳደር የሚያከናውናቸው ተግባራት መሆናቸውን ገልፀው ነበር። • "ኢህአዴግ ነፃ ገበያም፣ ነፃ ፖለቲካም አላካሄደም" ፀደቀ ይሁኔ (ኢንጂነር ) • "መንግሥት የዋጋ ንረቱን ለመቆጣጠር መሰረታዊ የምግብ ሸቀጦችን ያስገባል"ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ይሁንና ክረምቱ ሲገባ የዋጋ ንረቱ ከመርገብ ይልቅ ከፍ ብሎ ታይቶ የዋጋ ግሽበቱ ባለሁለት አሀዝ ሆኗል። በወርሃ ነሐሴ እንዲያውም ባለፉት ስድስት ዓመታት ከታየው የዋጋ ግሽበት መጠን ከፍተኛው ተመዝግቧል። የሸቀጦች የዋጋ ንረት ህይወታቸው ላይ ቀጥተኛ ጫና ካሳረፈባቸው የአዲስ አበባ ኗሪዎች መካከል ደግሞ የአርባ ዓመቱ ጎልማሳ ጋሹ መርከቡ አንዱ ነው። በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚኖረው ጋሹ ላለፉት ከአስራ ለሚልቁ ዓመታት በሚኒባስ ታክሲ ሾፌርነት ቤተሰቡን ሲያስተዳድር ኖሯል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን "የኑሮ መወደድ ከአቅሜ በላይ ሆኖ እያንገዳደገደኝ ነው" ይላል። "በዋጋ ላይ ያለውን ለውጥ ከቀን ወደ ቀን እያየሁት የመጣሁት ጉዳይ ነው፤ በእኔ [ህይወት] እንኳ ታክሲ ሠርቼ ብሩን ይዤ ብገባም ምንም የሚገዛው ነገር የለም" ይላል ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ። "የልጆች ትምህርት ቤት፣ የእህሉ ውድነት፣ እንዲያውም ተስፋ ወደማስቆረጥ ደረጃ እየደረሰ ያለ ይመስለኛል" ይላል። መጪውን ፍራቻ ጋሹ የአራት ልጆች አባት ሲሆን ትልቋ የአስራ ሁለት ዓመት ልጁ የስድስተኛ ክፍል ተማሪ ናት። ሌሎቹ ሦስት ልጆቹም በመዋዕለ ሕፃናት እና በአንደኛ ደረጃ ትምርት ቤቶች ውስጥ ይማራሉ። ባለፉት ዓመታት ሁሉንም ልጆቹን በግል ትምህርት ቤቶች ያስተምር የነበረ ሲሆን አሁን ግን በኑሮ ውድነት ላይ በየጊዜው የሚጨምረውን የትምህርት ቤት ክፍያን መቋቋም ባለመቻሉ አንደኛውን ልጁን የመንግሥት ትምህርት ቤት፣ ሁለቱን ደግሞ በለጋሽ ድርጅቶች በሚደጎም እና በዚህም ምክንያት በአንፃራዊነት አነስተኛ ከፍያ ወደሚጠይቅ ትምህርት ቤት አስገብቷል። ለእያንዳንዳቸው በየወሩ ሦስት መቶ ብር በመደበኛነት ይከፍላል። • ኢትዮጵያዊያን ለምን ሥጋ አይመገቡም? • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የኖቤል የሰላም ሽልማትን ሊያሸንፉ እንደሚችሉ ግምቶች አሉ አንደኛዋን ልጁን ብቻ በግል ትምህርት ቤት መማሯን እንድትቀጥል አድርጓል። ለብቸኛዋ የግል ትምህርት ቤት ተማሪ ልጁ መደበኛ ክፍያ ብቻ በዓመት ከአስር ሺህ ብር በላይ ያወጣል። ይህም የትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ፣ የአልባሳት፣ የምግብ ወጪዎች ሲደመሩበት "ናላን የሚያዞር" ሆኗል ይላል ጋሹ። በዚህ ላይ የቤት ኪራይ ወጪ ይታከልበታል። "ህይወታችንን ለማቆየት እየሰራን ነው እንጅ እየኖርን ነው ብዬ አላወራውም።" አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ መጪውን ጊዜ ይበልጥ እንዲፈራው እንዳደረገው ይናገራል ጋሹ፤ "ወደፊት እንዴት እንደማስተምራቸው ራሱ ግራ ግብት እያለኝ ነው" በማለት። ተስፋው ከዕለት ወደ ዕለት እንዲሟጠጥ አንድ ምክንያት የሆነው እርሱን ለመሰሉ ከኑሮ ጋር እልህ አስጨራሽ ግብግብ ለገጠሙ ሰዎች በፖለቲካ ልሂቃን ዘንድ ብዙም ትኩረት እየተሰጠ አይደለም ብሎ ማመኑ ነው። • ‹‹እነ ቴሌን ለግል ባለሀብት?›› ታሪካዊ ስህተት ወይንስ መልካም አጋጣሚ ? የፖለቲካ ልሂቃኑ "በብሔርም ጉዳይ፣ በምንም ጉዳይ የራሳቸውን ለማመቻቸት እንጂ የድሃውን [ጉዳይ] አንስቶ ልብህን [የሚነካ] ነገር ሲናገሩ እኔ እስካሁን ሰምቼም አላውቅም። የራሳቸውን ጉዳይ ከማስፈፀም በስተቀር ውስጥህን የሚነካ ነገር፣ ስለኑሮህ፣ ስለሽንኩርት የሚያወራ የለም" ይላል። ከጋሹ አስተያየት ጋር በሚስማማ መልኩ አጠቃላይ ምርጫ በሚከናወንበት ዓመት በፖለቲካዊ መድረኮች ላይ የዋጋ ንረት የሚገባውን ያህል ስፍራ ይዞ ያለመታየቱ እንደሚገርማቸው የሚያስረዱት የምጣኔ ሃብት የፖሊሲ ተንታኝ የሆኑት አሚን አብደላ ናቸው። "ምርጫ ኖረም አልኖረም፤ የማንኛውም አገር መንግሥት ፈተና የሚሆኑ ሁለት የማክሮኤኮኖሚ አመላካቾች አሉ፤ የሥራ አጥነት እና የዋጋ ንረት።" በፖለቲካው መልክዐ ምድር ገኖ ያለው መንግሥታዊው ሥርዓት "የፌዴራል ይሁን አይሁን የሚል ዓይነት እንጅ የሥራ አጥነት እና የዋጋ ንረት ላይ ብዙም የፖለቲካ ልሂቃን ሲጨቃጨቁ አይቼ አላውቅም" ባይ ናቸው ተንታኙ። ለአንድ አገር መረጋጋት እና የምጣኔ ሃብት ዕድገት ወሳኝ ናቸው የሚሏቸው እነዚህ ጉዳዮች ብዙም ያለመነሳታቸው "ዋናው ነገር የተዘነጋ ይመስለኛል" አስብሏቸዋል። በምግብ ምርቶች ላይ ከፍተኛ የዋጋ መጨመር የምርት-አቅርቦት ሰንሰለት ችግር የምጣኔ ሃብት ፖሊሲ ተንታኙ አሚን አብደላ እንደሚሉት አጠቃላይ የዋጋ ንረት ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ እንዳለ መረጃዎች ያሳያሉ ይላሉ። በተሰናበተው 2011 ዓ.ም የሐምሌ ወር የዋጋ ግሽበቱ ከ15 በመቶ በላይ ደርሶ እንደነበረ የሚያስታውሱት አሚን በወርሃ ነሐሴ ደግሞ ይህ ቁጥር ወደ 18 በመቶ ከፍ ብሎ እንደነበርም ይጠቅሳሉ። ይህም ቁጥር በስድስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ የታየው ትልቁ አሃዝ ነው። ለቁጥሩ ከፍ ማለት የምግብ ዋጋ፣ በተለይም የእህል ሰብል ዋጋ ንረት ምክንያት መሆኑን የስታትስቲክስ መረጃዎች ያመላክታሉ። • «አማካሪ አያስፈልገኝም ብሎ የሚያስብ መሪ አልገባውም ማለት ነው» ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ • በተሻሻለው የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህግ ረቂቅ ጥፋተኛና አቃቤ ህግ ይደራደራሉ በዚህ ረገድ በአንዳንድ ትርፍ አምራች በሆኑ አካባቢዎች የነበረው የፀጥታ ሁኔታ፣ የመጓጓዣ አገልግሎት እንደልብ ያለመገኘት እና ከዚህም ጋር በተያያዘ ምርትን በተፈለገው ደረጃ ማቅረብ ያለመቻል ለችግሩ ምክንያት ሳይሆኑ እንዳልቀሩ ተንታኙ አሚን ያነሳሉ። እየናረ ያለውን የዋጋ ንረት ለማቃለል ሁለት የመፍትሄ እርምጃዎች ሊወሰዱ ይችላሉ የሚሉት ባለሙያው፤ "አንደኛው በአቅርቦት በኩል ሌላኛው ደግሞ በፍላጎት በኩል ያሉ ናቸው" እንደአሚን ገለፃ። "ከፍላጎት አንፃር የመንግሥት ወጪ የቀነሰበት ሁኔታ አለ። ያለፉትን ዓመታት ዓይነት እድገት ስለሌለ፤ ምጣኔ ሃብቱ ውስጥ የሚለቀቀው የገንዘብ መጠን ቀነስ ያለ ይመስላል። ይሁንና በአቅርቦት በኩል እምብዛም ለውጥ ያለ አይመስልም" ሲሉ ለቢቢሲ አስረድተዋል አቶ አሚን። የምርቶች በተገቢው መጠን አለመገኘት ለዋጋ መወደድ በአንዳንድ ሰዎች እንደምክንያት ተደጋግሞ የሚነሳ ሲሆን፤ ባለሙያውም በምርት እና በአቅርቦት መካከል ያለው ሰንሰለት ችግር እንደሚስተዋልበት ይናገራሉ። "ገበሬው አምርቶ ለምርቱ የሚያገኘው ዋጋ እና ከተማ ላይ መጥቶ የሚሸጥበት ዋጋ በጣም ከፍተኛ ልዩነት አለው። ገበሬው ከአንድ ኪሎ ሙዝ እያገኘ ያለው ገቢ እና አንድ ኪሎ ሙዝ ከተማ ውስጥ እየተሽጠበት ያለው ዋጋ ልዩነት አለው። "በዚህ መካከል ያለው የአገልግሎት፣ የደላላ፣ የመጓጓዣ፣ የቦታ ኪራይ እና የመሳሰሉት ወጪዎች ከፍተኛውን ድርሻ የሚወሰዱ ናቸው። ይህ የገበያ ሰንሰለት ሥርዓት እሰካልያዘ ድረስ፤ የምርቶች ዋጋ ከፍ እንዲል ማድረጉ አይቀሬ ነው" ለአሚን። • ሸማቹ በውጭ ምንዛሪ ለውጡ ማግስት • ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ጋር ማዕድ የቀረቡት ምን ይላሉ? ከውጭ የሚመጣ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር የንግድ ውድድርን ማሳለጥ እንዲሁም የሸማቾችን ጥበቃ ማጠናከር ይገባል የሚሉት ባለሞያው፤ ከውጭ የሚመጡ ምርቶችን የሚያስመጡ ተቋማት እና ግለሰቦች በየተሰማሩበት ዘርፍ ጥቂት መሆናቸው ዋጋው ላይ ከሚገባው በላይ ጫና እንዲፈጠር መንገዱን ይጠርጋል ባይ ናቸው አቶ አሚን። ከውጭ የሚመጣ የዋጋ ንረት በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምከንያትም ሊከሰት ቢችልም በእኛ አገር እየተስተዋለ ያለው እውነታ ግን በውጭ ምንዛሬው እጥረት መጠን ያህል መኖር ከሚገባው በላይ ጭማሪ ነው፤ ሲሉ የዋጋው ጭማሪ አሳሳቢ መሆኑን ይጠቅሳሉ። ባለሞያው አቶ አሚን አብደላ ለፖለቲካዊ ጉዳዮች እየተሰጠ ካለው ጋር የሚመጣጠን አትኩሮት የዋጋ ንረትን ለመሳሰሉ ምጣኔ ሃብታዊ ተግዳሮቶች መቸር አለበት ባይ ናቸው። በዚህ አስተያየታቸው ጋሹም የሚስማማ ይመስላል፤ "ይሄ ሁሉ እየታየ ቸል የሚባለው እስከመቼ እንደሆነ አይገባኝም።"
news-55440758
https://www.bbc.com/amharic/news-55440758
ኮሮናቫይረስ ፡ ኢትዮጵያዊያን የሕክምና ባለሙያዎች ስለኮቪድ-19 ክትባት ይናገራሉ
በአሜሪካው የመድኃኒት አምራች ኩባንያ ፋይዘር እና በጀርመኑ የሕክምና ቴክኖሎጂ ኩባንያ ባዮንቴክ በጋራ የተሰራው የኮቪድ -19 ክትባት በአሜሪካ መሰጠት ከጀመረ ሁለት ሳምንታት አልፎታል።
ክትባቱም ለበሽታው ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑ እንደ የጤና ባለሙያዎችና በዕድሜ የገፉ ሰዎች በቅድሚያ እየተሰጠ ነው። በዚያው የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የጤና ባለሙያዎችም ክትባቱን እየወሰዱ ነው። ዶክተር ፍፁም ኃይለማሪያም በአሜሪካ ፊላደልፊያ ቶማስ ጃፈርሰን ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ውስጥ የውስጥ ደዌና የኩላሊት ሕክምና ስፔሻሊስት ነው። በቅርቡ ፋይዘር /ባዮንቴክ ያበለፀጉት የኮቪድ-19 ክትባትን ከተከተቡ ባለሙያዎች አንዱ ነው። ዶክተር ፍፁም በበሽታው የታመሙትንም፣ የሞቱትንም፣ ወረርሽኙ ያስከትለውንም ዘርፈ ብዙ ችግር በቅርበት ስለተመለከተው ክትባቱ እስከሚመጣ እየተጠባበቀ ነበር። በዚህም ምክንያት ክትባቱን ለመከተብ ለመወሰን አልተቸገረም። "ክትባቱ ያለፈበትን የምርምር ሂደት በቅርብ ለመከታታል ችያለሁ። በምን ደረጃ እንዳለፈ፣ ውጤታማና ደህንነቱ የተጠበቀ እንደሆነ መረጃው ስላለኝ ለመከተብ አላመነታሁም" ይላል። ሌላኛው ክትባቱን የወሰዱት የሕክምና ባለሙያ ደራራ ዳዲ ይባላሉ። በካሊፎርኒያ ሳን ሆዜ ከተማ ፓልምትሪ የእንክብካቤ ማዕከል ነርስ ናቸው። እርሳቸውም ከዶ/ር ፍፁም የተለየ ሃሳብ የላቸውም። "በእውነቱ ይሄ ክትባት በመገኘቱ ሁላችንም ደስተኞች ነን። በተለይ ደግሞ ከህሙማን ጋር ንክኪ ያለን ሰዎች ከዛሬ ነገ ይይዘኛል የሚል ስጋት ነበረብን። . . . አሁን ማንኛውም የጤና ባለሙያ በክትባቱ ደስተኛ ነው" በማለት በክትባቱ መገኘት የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል። በኮሮናቫይረስ ተይዘው ያገገሙ ክትባቱን ይወስዳሉ? አንዳንድ በበሽታው ተይዘው ያገገሙ ሰዎች በራሳቸው የበሽታ መከላከል አቅም እንዳጎለበቱና ዳግም እንደማይዛቸው በማሰብ ሲዘናጉ ይስተዋላል። ክትባቱንም መከተብ እንደማያስፈልጋቸው የሚያስቡም አሉ። ዶክተር ፍፁም ወረርሽኙ ከተከሰተ አንስቶ ሦስት ጊዜ ያህል የኮሮናቫይረስ ምርምራ አድርጓል። ሦስቱንም ጊዜ ግን ነጻ ነበር። "ምን አልባት ባልተመረመርኩባቸው ጊዜያት ይዞኝ ሊሆን ይችላል" ይላል። ዶ/ር ፍፁም እንደሚለው ምን አልባት በቅርብ ጊዜ የታመሙ ሰዎችና በሕክምና ላይ ያሉ ሰዎች ክትባቱን ላይወስዱ ቢችሉም፤ በበሽታው ተይዘው የዳኑ ሰዎች ግን ክትባቱን ወስደዋል፤ መውሰድም ይገባቸዋል ሲል ያስረዳል። "አንዳንድ ጥናቶች በበሽታው ተይዘው የዳኑ ሰዎች በሽታ የመከላከል አቅማቸው ከተወሰነ ወራት በኋላ ሲቀንስ አሳይተዋል። በእርግጠኝነት በአንድ ጊዜ መታመም በሽታውን ይከላከላል ወይ? የሚለውን ማወቅ አይቻልም። በሽታው ከያዛቸው በኋላ በበሽታው ድጋሜ የተያዙ ሰዎች አሉ፤ በመሆኑም ክትባቱን መውሰዱ ጥሩ ነው" ሲልም ይመክራል። ክትባቱ የሚሰጥበት ሂደት ምን ይመስላል? በሕክምና ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች ክትባቱን እንዲወስዱ የተደረገው እንደ ተጋላጭነታቸው ሁኔታ ነው። በተለይ ደግሞ ፅኑ ሕሙማንና ድንገተኛ አደጋ ክፍል የሚሰሩ ባለሙያዎች ቅድሚያ እንደተሰጣቸው ዶ/ር ፍፁም ይናገራል። ዶ/ር ፍፁም እንደሚለው ማንኛውም ሰው ክትባቱን ከመውሰዱ በፊት ወደ 10 የሚደርሱ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ይኖርበታል። ለምሳሌ አለርጅ [የሰውነት መቆጣት] ያለባቸው ፣ ነፍሰጡር ሴቶች፣ የማንኛውም ህመም ምልክት ያለባቸው እንዲሁም በማንኛውም በሽታ ለህመም ተዳርገው ሆስፒታል ያሉ ሰዎች ክትባቱን አይወስዱም። እነዚህንና ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎችን ያሟሉ ግን ክትባቱን ይወስዳሉ። ክትባቱ ከተወሰደ በኋላም ለ15 ደቂቃ እዚያው እንዲቆዩ ይደረጋል። ይህ የሚደረገው ምን አልባት የተለየ የሰውነት ግብረ መልስ ካለ በሚል ነው። ዶ/ር ፍፁም ክትባቱን ከወሰደ በኋላ ምንም ዓይነት ችግር ስላልገጠመው በቀጥታ ወደ ሥራው እንዳመራ ይናገራል። የኮቪድ-19 ክትባት ከሌሎቹ ክትባት የሚለየው ነገር የለም የሚለው ዶ/ር ፍፁም፤ "በክንድ ላይ በመርፌ የሚሰጠው ክትባቱ የሚወሰደው ሁለት ጊዜ ነው። የመጀመሪያው ክትባት በተወሰደ በሁለተኛ ሳምንቱ ሁለተኛው ክትባት ይሰጣል። ውጤታማ የሚሆነውም ከዚያ በኋላ ነው" ይላል። እርሱ እንደሚለው ክትባቱ በተወጋበት ቦታ ላይ መርፌ ሲወጋ የሚሰማ ስሜት፣ መጓጎል ዓይነት ምልክቶች ካልሆነ በስተቀር ሌላ የተለየ ስሜት አልተሰማውም። ነርስ ደራራም በበኩላቸው ክትባቱ ምንም የተለየ ስሜት እንዳልፈጠረባቸው ተናግረዋል። "ከተከተብኩ ከ30 ደቂቃ በኋላ ነው ወደ ሥራ የሄድኩት። የተወጋሁበት ቦታ ትንሽ ህመም ነበረው፤ ከዚያ ውጭ ምንም ነገር የለኝም" ብለዋል። አንዳንድ ሰዎች ክትባቱን ከወሰዱ ጥንቃቄ ማድረግ እንደማያስፈልግ ሲናገሩ ይሰማል። ዶ/ር ፍፁም ግን ከተከተብኩ በኋላ ኃላፊነት ተሰምቶኝ ነው የወጣሁት ይላል። " ክትባቱ ለበሽታው የመጋለጥና የመታመም ዕድሌን 95 በመቶ ይቀንሰዋል እንጂ፤ ኢንፌክሽን ሊኖርና በሽታውን ለሌላ ሰው ላስተላልፍ እችላለሁ። ስለዚህ እስከ 60/70 በመቶው የማሕበረሰብ ክፍል እስኪከተብ ድረስ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግና ሌሎች ጥንቃቄዎችን አልተውም፤ ግዴታም ነው" በማለትም የሚወሰዱ የጥንቃቄ እርምጃዎች መቀጠል እንዳለባቸው ይመክራል። በክትባቱ ላይ ያላቸው አመኔታ ስለ ክትባቱ በርካታ የተሳሳቱ መረጃዎች ይሰማሉ። በተለይ ደግሞ ዓመታትን ይወስዳል የተባለው ክትባት በአጭር ጊዜ መገኘቱ አንዳንድ ሰዎች በክትባቱ ላይ እምነት እንዳያሳድሩ ካደረጓቸው ምክንያቶች አንዱ ነው። ይህንን እና ሌሎች የተሳሳቱ አመለካከቶችን ለመለወጥ የአገር መሪዎች በቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት ሲከተቡ ታይተዋል። ከእነዚህ መካከል ተመራጩ ፕሬዚደንት ጆ ባይደንና ምክትል ፕሬዚደንት ማይክ ፔንስ ይጠቀሳሉ። "እዚህ እኛ በምንኖርበት አሜሪካ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ስለ ወረርሽኙ ብዙ የተሳሳቱ ነገሮችን ይናገሩ ስለነበር፤ ዓለም ላይም የተሳሳቱ አስተሳሰቦችን ፈጥሯል" የሚለው ዶ/ር ፍፁም፤ እርሱ ግን የሕክምና ባለሙያ በመሆኑ በጥናቱ ምን ያህል ሰዎች እንደተሳተፉ፣ ምን ያህል ክትባት እንዳገኙ፣ ከዚያ ውስጥ ምን ያህሉ ደህና ሆነው እንደቆዩ እና ክትባቱን ያልወሰዱ በበሽታው እንደተያዙ መረጃው ስላለው ጥርጣሬ አልፈጠረበት። ክትባቱ እንዴት በቶሎ ደረሰ? ለሚለውም ወረርሽኙ መላው ዓለምን አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደከተተው በመጥቀስ፤ በዚህም የተነሳ የዓለም ጤና ድርጅትና የዓለም አገሮች ክትባቱን ስለደገፉት እንዲሁም ሳይንሱም ስላደገ ቶሎ ሊደርስ መቻሉን ይናገራል። ምንም እንኳን አብዛኞቹ ክትባቱን እየወሰዱ ቢሆንም፤ አንዳንድ በእድሜ ገፋ ያሉና ሌሎች ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸው ሰዎች 'የክትባት አለርጂ አለብኝ' በማለት ክትባቱን ሲሸሹም ነርስ ደራራ ታዝበዋል። ዶ/ር ፍፁም እንደሚለው በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ስለክትባቱ የሚጻፉ መረጃዎች በርካቶችን እያሳሳተ ነው። እርሱም ከቤተሰቦቹ ተቃውሞ አይግጠመው እንጂ ጥርጣሬ እንዳላቸው ሲገልፁለት እንደነበር ይናገራል። ይህም ጥርጣሬያቸው የመነጨው ከማኅበራዊ ሚዲያ ከሚያገኙት የተሳሳተ መረጃ የተነሳ ነው ይላል። "ሐኪሞች ከሚሰጡት መረጃ ይልቅ፤ የተሳሳቱ መረጃ የሚሰጡ ማህበራዊ ሚዲያዎች ብዙ ናቸው። ብዙ ሰውም ይመለከታቸዋል። ይህ ደግሞ ብዙውን ሰው ያሳስታል። በመሆኑም እዚህ ላይ ከፍተኛ ሥራ መሰራት አለበት። የተሳሳተ መረጃ ከእውነተኛ መረጃው ፈጥኖ እየተሰራጨ በመሆኑ 'አልከተብም' የሚለው ሰው እንዳይበዛ እፈራለሁ" ሲል ስጋቱን ገልጿል። ክትባቱ 'ማይክሮቺፕ' አለው፤ እኛን ለመከታተልና ለመሰለል የተደረገ ነው፣ የአፍሪካን ሕዝብ በ500 ሚሊየን ለመቀነስ የተደረገ ሴራ ነው" የሚሉ የተሳሳቱ መረጃዎችን እንደተመለከተም አስታውሷል። በመሆኑም የሚዲያ ባለሙያዎችና የጤና ባለሙያዎች በዚህ ላይ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስቧል። ክትባቱ የሰጠው ተስፋ ነርስ ደራራ በተለይ የጤና ባለሙያዎች ክትባቱን መውሰዳቸው ለጤና ዘርፉ ትልቅ ድጋፍ ያደርጋል ይላሉ። ከዚህ ቀደም በእድሜያቸው ገፋ ያሉ ነርሶች በሽታውን ፈርተው ጡረታ የወጡና ቤታቸው የተቀመጡ እንዳሉ ያስታወሱት ነርስ ደራራ፤ በዚህ ምክንያት የጤና ባለሙያዎች እጥረት በማጋጠሙ በሌሎች ሰራተኞች ላይ ጫና እንደነበር ይናገራሉ። ክትባቱን ከተከተቡ እነዚህ ባለሙያዎች ወደ ሥራ ይመለሳሉ የሚል ተስፋን ፈንጥቋል። "ይህ መሆኑም ሥራውን ያቀላጥፋል፣ በራስ መተማመንን ይጨምራል፤ የጤና ሰራተኞች የመታመም ዕድልን ይቀንሳል" ብለዋል። ዶ/ር ፍፁም በበኩሉ ክትባቱ በግለሰብም፣ በተቋማትም ሆነ በአገር ደረጃ የሰጠው ተስፋ ቢኖርም፤ በዚህ ተስፋ መዘናጋት እንዳይኖር ጥንቃቄዎች ላይ ትኩረት መደረግ ይኖርበታል ይላል። "ክትባቱም ቢመጣም አብዛኛው ሰው እስኪከተብ ድረስ አሁን የምናደርጋቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች የሚቋረጡ አይደሉም። ሰው በሙሉ ከመከተቡ የተነሳ ሌላውን ከማስያዝ የምንከላከልበት ደረጃ [ኸርድ ኢሚዩኒቲ] ስናዳብር ወደ ቀደመው ሕይወት ልንመለስ እንችላለን። አሁን ግን ሁሉም ሰው ጥንቃቄ ማድረግ አለበት። ክትባቱ ተስፋ ነው፤ ተጀምሯል፤ ነገር ግን አሁኑኑ ወደ ቀድሞው ሕይወት እንመለሳለን ማለት አይደለም" ሲል መዘናጋት እንዳይኖር መክሯል። በዓለማችን እስካሁን ከ78 ሚሊየን 837 ሺህ ሰዎች በላይ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሲሆን፤ ከ1 ሚሊየን 733 ሺህ ሰዎች በላይ ደግሞ በቫይረሱ ሳቢያ ሕይወታቸው አልፏል። ከዚህ ውስጥ ከ18 ሚሊየን 466 ሺህ ሰዎች በላይ በቫይረሱ የተያዙ፤ ከ326 ሺህ ሰዎች በላይ በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች የተመዘገቡት በአሜሪካ ነው። ዩናይትድ ኪንግደም እና አሜሪካ በፋይዘርና በባዮንቴክ የበለፀገውን የኮሮናቫይረስ ክትባት ለዜጎቻቸው እየሰጡ ነው። 95 በመቶ ኮሮናቫይረስን ይከላከላል የተባለለት ይህንን ክትባት ለዜጎች በመስጠት ዩናይትድ ኪንግደም ቀዳሚዋ አገር ናት። ሩሲያና ሕንድን ጨምሮ ሌሎች አገራትም ክትባቱን መስጠት መጀመራቸው ተዘግቧል። ኢትዮጵያን ጨምሮም ሌሎች የአፍሪካ አገራትም ክትባቱን ለማቅረብ እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በዩናይትድ ኪንግደም ተገኘ የተባለው አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ሌላ ስጋት ፈጥሯል። አንዳንድ አገራትም ወደ ዩኬ የሚያደርጉትን በረራ አቋርጠዋል። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽንም በዚሁ ሳምንት በጉዳዩ ላይ መክሯል። አገራትም በዩኬ ላይ የጣሉትን የበረራ እገዳ እንዲያነሱ አሳስበዋል። አዲሱ የኮሮናቫይረስ የመዛመት እድሉ ከነባሩ 70 በመቶ የበለጠ ቢሆንም ገዳይነቱ ግን እንደ ቀድሞው አይደለም እየተባለም ነው።
news-51750604
https://www.bbc.com/amharic/news-51750604
አሰቃቂ መከራን አልፋ ለህይወት ስኬት የበቃቸው ሄለን
ወይዘሮ ሄለን ወረደ፤ ሦስት ልጆችዋን ብቻዋ ያሳደገች ነገር ግን በድንገት ከእቅፍዋ የተነጠቀችው እናት ናት።
እስከ ዛሬዋ እለት ድረስ 'መላዕክቶቼ' ብላ የምትጠራቸውና በአሰቃቂ ሁኔታ ላጣቻቸው ለሦስት ልጆችዋ፣ ለእህቷና ለእህቷ ልጅ ያላት ፍቅር ዘላለማዊ እንሆነ ትናገራለች። "ለብቻ ልጆች ማሳደግ ቀላል አይደለም፤ ቢከብድም ግን የልጆቼን ትምህርት በአግባቡ እከታተልና ሥራዬን እሰራ ነበር። ሦስቱም ልጆቼ የተለያየ ትምህርት ቤት ይማሩ ስለነበር እነሱን ማመላለስና መልሶ ወደ ሥራ መሄድ አስቸጋሪ ነበር" ትላለች። ነገር ግን ግን ሁል ጊዜ በፍቅር የምትወጣው ኃላፊነት ስለነበረ እንደለመደችው እና "ስሰራበት የነበረው የሥራ መስሪያ ቤቴ ሁኔታዬን በመረዳት ያግዘኝ ስለነበር ከብዶኝ አያውቅም።" የ13 ዓመቱ ዮሴፍ፣ የ5 ዓመቱ ያሴን ሻማምና የ6 ዓመቷ ኒስረን ሻማም፤ ሄለን በተለያዩ ጊዜያት የወለደቻቸው የህይወቷ ጌጦች ነበሩ። ከዕለታት በአንዱ ቀን ግን፤ የዚህ ቤተሰብ ህይወት ባልተጠበቀ ሁኔታ የሚቀይር ክፉ አጋጣሚ ተከሰተ። ከዛሬ አስር ዓመት በፊት በአውሮፓዊያኑ ሐምሌ 2010 ዕለተ ቅዳሜ ረፋድ ላይ፤ ሰማይና ምድር የሚያናውጥ ኡኡታ የወይዘሮ ሄለን ቤት ካለበት አካባቢ ተሰማ። ሃዘናቸውን የሚገልጹ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ሲያትል ውስጥ ተሰብስበዋል። የልጆቹ እናትም "ልጆቼን ነው የምፈልገው" እያለች ደረትዋን እየደቃች ወደ መሃል መንገድ ትሮጥ ስለነበር፤ "ሊያቅፏትና ሊያጽናኗት የሚከተሉዋት ሴቶችም ነበሩ" ሲል ሲያትል ታይምስ የወቅቱን ክስትት ጽፎ ነበር። ሄለን በዚያች መጥፎ ዕለት በተመሳሳይ ሰዓትና በተመሳሳይ አደጋ ሦስቱንም ልጆችዋን፣ የ22 ዓመት እህቷንና የእህቷን ልጅ በድንገት አጣቻቸው። በእያንዳንዷ ቀን ገደብ አልባ ፍቅርና እንክብካቤ በመስጠት ሳቅና ደስታ እየፈጠረች በስስት ለብቻዋን ስታሳድጋቸው የነበሩትን ልጆችዋን በእሳት አደጋ የማጣት መዓት ወደቀባት። በወቅቱ የእሳት አደጋው በሲያትል በአስርት ዓመታት ውስጥ ያጋጠመ ከባዱ የእሳት አደጋ እንደነበርም ተነግሯል። ሄለን ከቤተሰቦቿ ጋር በመጨረሻ ያሳለፈችውን ዕለት ፈጽማ አትረሳውም። አርብ ማታ ነበር፤ ሄለንና ሦስት ልጆችዋ፣ እህቷና የእህቷ ልጅ አንድ ላይ ፊልም በፍቅርና በደስታ ቅዳሜ መልሰው እንደሚገናኙ በማሰብ ወደ መኝታቸው አመሩ። በእሳቱ አደጋ የሞቱት የሄለን ልጆች ነገር ግን ቅዳሜ ይህ ቤተሰብ እንደወትሮው አንድ ላይ የሚያሳልፋት ቀን አልሆነችም፤ እልቁንም ሄለንን ብቻዋን ያስቀረች ዕለት ሆነች። ከቤቱ ውስጥ የተነሳው ድንገተኛ የእሳት ቃጠሎ እጅግ ከባድ ነበር፤ አደጋውን ለመቆጣጠር ይጥሩ ለነበሩት የእሳት አደጋ ሠራተኞችም አዳጋች ሆነ። ከባድ ጭስና የእሳት ነበልባል ሌሊቱን በፍቅር አቅፋቸው ካደረችው ቤት መውጣቱን ቀጠለ። እሳቱን ሊቆጣጠር የመጣው የእሳት አደጋ መኪና የውሃ ሞተር ውሃ መግፋት አልቻለም። ሌላ እርዳታ የሚሰጥ መኪና እስኪ መጣ ደግሞ ደቂቃዎች አለፉ፤ በዚህም በእሳት በሚጋየው ቤት ውስጥ ያሉትን የአምስት ሰዎችን ነፍስ ማዳን ሳይቻል ቀርቶ በእሳቱ ተበሉ። በዚህ ክስተትም ሲያትል ላይ ከባድ ሃዘን ሆነ፤ ክስተቱን የሰሙ ሁሉ በእሳቱ ከተቀጠፉት ልጆች በተጨማሪ ከባዱ ሃዘን ለወደቀባት ሄለንም አነቡ፤ የበርካቶች ልብም በሃዘን ተሰበረ። "ለእኔ ሁሉም ነገር ከቁጥጥሬ ውጪ ነበር፤ የውዶቼን ህይወት ማዳን የምችልበት አቅም አልነበረኝም። ስለዚህ ጉዳይ በጭራሽ ማውራት ይከብደኛል። እንዴት ብዬ ልንገርሽ? እህህህ . . . በቃ ከባድ ነው" ትላለች ሄለን ያለፈውን አስታውሶ ለማውራት አቅም እንደሌላት በመግለጽ። ወይዘሮ ሄለን የአሜሪካ ህልም በመቋደስ የእራሳቸውንና የቤተሰባቸውን ህይወት ለመቀየር ላይና ታች ከሚሉ በርካታ ኢትዮጵያዊያን መካከል አንዷ ነች። "በዚች አገር ብዙ እድሎች አሉ፤ ጭንቅላታችንን ከፍተን ከፈለግን የምናጣው ነገር የለም። ዋናው ነገር ለመማርም ሆነ ለመስራት ዝግጁ መሆን ነው" ትላለች። ሄለን ወረደ፤ እትብቷ ከተቀበረበት ቀዬ ወጥታ ወደሌላ አገር ስትሄድ ገና የሁለት ዓመት ህጻን ነበረች። ቤተሰቦችዋ ወደ ሱዳን አቅንተው እዚያ ስምንት ዓመት ሱዳን ላይ ኖረዋል። ሄለን የ10 ዓመት ልጅ ስትሆን ደግሞ ወደ አሜሪካዋ ሲያትል ተጉዘው ኖሯቸውን እዚያው አደላደሉ። ሄለን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ካጠናቀቀች በኋላ ልጆች ወልዳ ልጆችዋን የማሳደግ ኃላፊነትን ለብቻዋን በመወጣት ላይ ሳለች ነበር የወጣትነት እድሜዋን ደስ እያለት መስዋዕት ያደረገችላቸው ልጆቿን በድንገት ያጣችው። በህይወት ሁለተኛ እድል ሄለን በዚህ ሁሉ መከራ ውስጥ አልፋ እናቷን፣ የሲያትል ማኅበረሰብንና ጓደኞችዋን አንስታም ሆነ አመስግና አትረካም። ዘወትር ከልቧና ከንግግሯ የማይጠፉትን በዚያ ዘግናኝ አደጋ ያጣቻቸው ልጆችዋና እህቷ ደግሞ 'ፋይቭ ኤንጅልስ' [አምስቱ መላዕክ] ስትል ትጠራቸዋለች። ሄለን የገጠማትን መከራ የዘወትር የሃዘኗ ምንጭ ከማድረግ ይልቅ በህይወቷ ውስጥ የሚከሰቱ መልካም ነገሮች አድርጋ ነው የምታስበው። በሌላው አዲስ የህይወቷ ምእራፍ ያገኘቻቸውን ነገሮች በሙሉ ደግሞ፤ አምስቱ መላዕክት መርቀው ሰጥተውኛል" በማለት ፈጣሪዋን ተመሰግናለች። "ሁሉም ነገር የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። እግዚአብሔር ለእኔ ያሰበው ነገር ስለነበር ያጋጠመውን ነገር ሰጠኝ። ቤተሰቦቼ፣ ጓደኞቼና የሲያትል ማኅበረሰብ በሰጠኝ ብርታት ሁሉንም ነገር አለፍኩት። ከዚያ በኋላም መንታ ወንድ ልጆች ተሰጠኝ። አሁን አምስት ዓመት ሆኗቸዋል። ስለዚህ ሁሉም የሆነው በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው" ትላለች። ሄለን ከእንደዚህ አይነት እጅግ አሰቃቂ አደጋና ሞት በኋላ ለመኖር ተስፋ የምታደርግበት ሌላ ህይወት አለ ብላ ታስብ ነበር። "የነበረህን ለማጣት ምክንያት አለው። የሚያበረታህ፣ ተስፋ የሚሰጥህ ሰው አጠገብህ ሲኖር ደግሞ ሁሉንም አሸንፎ እንደገና መሳቅ፣ በህይወት መኖርና ህይወትን እንደ አዲስ መጀመር ይቻላል" ትላለች። ከገጠማት ከባድ መከራ አንጻር "ቤት አልባ፣ የተጎሳቆለች፣ በሽተኛ ነበር የምሆነው። ግን ደግሞ እግዚአብሔር ያንን እንዳልፈው ጥንካሬ ሰጠኝ፣ ትክክለኛውን ነገር እንዳደርግ ደግሞ መራኝ። እኔም ሁሉንም ነገር ለፈጣሪዬ፣ ለእናቴና ለሁሉም ከጎኔ ለነበሩ ሰዎች አሳልፌ ሰጠኋቸው" ትላለች። በአደጋው ያጣቻቸው እህቷ፣ የእህቷ ልጅና የእሷ ልጆች በዚህ ምክንያትም ካጋጠማት ዘግናኝ አደጋ ባሻገር ሌላ ህይወት እንዳለ ማየቷን ሄለን ትጠቅሳለች "ፈጣሪ ሌላ ህይወት ሰጠኝ፤ 'ፋይቭ ኤንጅልስ' ህይወት ሰጡኝ። እኔ ህይወትንና ያጋጠመኝ ነገር በዚህ መንገድ ነው የማያቸው" ትላለች። ይሁን እንጂ፤ በዚህ በህይወቷ ሁለተኛ ስጦታዬ ነው በምትለው ህይወቷ ውስጥ ሁሉን ነገር "ማስረሻ" ሆነውኛል የምትላቸው "የፈጣሪ ስጦታ" ብላ የምትገልጻቸው መንትያ ልጆችዋ፤ እውነትም የእኔ ልጆች ናቸው ብላ ለመቀበል ትልቅ የሥነ ልቦና ፈተና ገጥሟት እንደበረ ትናገራለች። "በጣም ፈታኝ የነበረው ነገር መንትያ ልጆቼን የወለድኩ ጊዜ ነው። አሁን ለእነዚህ ልጆች ሊኖረኝ የሚገባው ስሜት ምን አይነት ነው መሆን ያለበት? የሚለውን አላውቅም ነበር። ፈጣሪ ስለሰጠኝ ብቻ መውደድ ነው ያለብኝ? እውነት የእኔ ልጆች ናቸው? በሚሉ ጥያቄዎች ተወጥሬ ነበር።" የእናት ሆድ ስለሚባባ ያለፈውን ቶሎ ለመርሳት ተቸግራ ነበር፤ ስለሆነም እቅፏ ውስጥ ያደሩትን ሦስት ልጆችዋን የነጠቃት አጋጣሚን አሁንም አሁንም ማስታወሷ አልቀረም። በዚህ ምክንያት፤ "የወለድኳቸው ልጆች ተመልሰው ይወሰዱብኝ ይሆን? ጤነኞች ይሆናሉ? ልክ ለመጀመሪያ ልጆቼ የነበረኝ ፍቅር ለእነዚህም መስጠት አለብኝ? የሚሉ ብዙ ሞጋች ጥያቄዎች ይፈትኑኝ ነበር" ትላለች። ነገር ግን ሄለን እንደገና ይሄንንም የህይወት ፈተና በጥንካሬ አለፈችው። ፈጣሪ የሰጣትን መንታ ስጦታ በሙሉ ልበቧ ተቀብላ እንደቀድሞዋ ዳግም ልጆችዋን በስስት የምታሳድግ እናት ሆነች። "እነዚህ ልጆች ለእኔ ስለሚገቡኝ የእኔ ሆነዋል፤ ፈጣሪ የእኔ የሆነውን መልሶ ሰጥቶኛል፤ ብዙ ነገርም እየሰጠኝ ነው" በማለት የሁለተኛው ህይወቷን ሀሴት ትገልጻለች። "ልጆቼን የአሸንዳ በአል እንዲያዩ ወደ ትግራይ ወስጃቼዋለው። እዛ ጥሩ ጊዜ አሳልፈን ተመልሰናል፤ ይህ ለእኔ ትልቅ ነገር ነው። አሁን በየዓመቱ ልወስዳቸው ዕቅድ አለኝ። እኔ ልጅ ሆኜ ከአገር ስለወጣሁኝ እድሉን አላገኘሁም፤ እነሱ ግን በዚህ መንገድ የአገራቸውን ባህልና ሀረጋቸው ማወቅና መማር ይችላሉ።" መልስ ወደ ትውልድ አገሯ ሄለን ወረደ፤ እሷም ልክ ከአገሩ ወጥቶ እንዳደገ ህጻን የአፍ መፍቻ ቋንቋዋን ለመናገር በተወሰነ መልኩ ትቸገራለች። "ሲያትል ውስጥ ትልቅ የትግራይ ተወላጆች ማህበር አለ፤ እናቴም እኔ በእንግሊዘኛ ብመልስላትም በትግርኛ ታወራኛለች። ሁል ጊዜም አገር ቤት ስላለው ወገኔ እጠይቃለው፣ ከየት እንደመጣሁ ላለመርሳት እጥር ስለነበር፣ ሰዎችም በትግርኛ እንዲያናግሩኝ እያደረግኩኝ ተምሬዋለው" ትላለች። ሄለን ትግራይ ውስጥ ሽረ እንዳሥላሴ ከተማ ነው የተወለደችው። በሁለት ዓመቷ የተለየችውን የትውልድ አካባቢዋን ከሦስት አስርት ዓመት በኋላ ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ መጥታ ያየችው። ከዚያ በኋላም አራት ጊዜ ተመላልሳ ሃገርዋን ሁኔታ ማወቅ እንደቻለች ትናገራለች። በዚህ ዓመት ደግሞ በድንገት ባጣቻቸውና ለእነሱ ያላት ፍቅር በማይደበዝዘው በልጆቿና በእህቷ የጋራ መጠሪያ 'ፋይቭ ኤንጅልስ' ብላ የሰየመችው እና 12 ሚሊየን ብር ወጪ ያደረገችበት የሴቶችና የህጻናት የጤና ማዕከል በአገሯ ውስጥ ገንብታ አስመርቃለች። ለምን የህጻናትና እናቶች ክሊኒክ? ሄለን ለእናቷና ለልጆቿ ባላት ገደብ የለሽ ፍቅር የተነሳ ዋነኛ ትኩረቷ በእነሱ ላይ አድርጋለች። "የእኔ ፍላጎትም የሴቶችና የህጻናት ጤንነት ማሻሻል ነው" ትላለች። "ልጆችን እናት ሆኖ ለብቻ ማሳደግ ምን እንደሚመስል ያየሁ ሴት ነኝ። አገር ቤት ያሉ እናቶች ህክምና የማያገኙበት አጋጣሚ እንዳለ አውቃለሁ። በዚህ ምክንያትም ለሞት ሊዳረጉ ስለሚችሉ እዚህ ላይ ትኩረት ማድረግ ነው መረጥኩት" ትላለች። በተለይ ትግራይ ውስጥ ያለውን የጤና አገልግሎት መሰረተ ልማትን ከአደግኩበት አገር ጋር ሳስተያየው እጅግ ዝቅተኛ ነው፤ "ብዙ እናቶች ይታመማሉ፣ የህክምና ድጋፍ ባለማግኘትም በወሊድ ጊዜ ልጆች ይሞታሉ። የእኔ ፍላጎትም ይሄንን ችግር መፍታት ነው።" ወደ ኢትዮጵያ በምመጣበት ጊዜ "ብዙ አሳዛኝ ነገሮችን ስለማይ በየቀኑ አለቅስ ነበር። ልጆች የያዙ እናቶች መንገድ ላይ ማየት ደግሞ ሌላው ከባድ ነገር ነበር፤ አገር ቤት ጥሩ ነገር ሳላይ ወደ ሲያትል ተመለስኩ። እናም ለምን አንድ ነገር አላደርግም ብዬ አሰብኩ" በማለት የዕዷን መነሻ ታስታውሳለች። ሄለን በሽረ እንዳሥላሴ ከተማ ያስገነባቸው የመጀመሪያው የጤና ማዕከል ግንባታው ተጠናቆ ባለሙያዎችና የህክምና መሳሪያዎች ተሟልተውለት አገልግሎት ለመስጠት ተዘጋጅቷል። ይህ የዕቅዷ የመጀመሪያ እንደሆነና ሌሎችማ ተመሳሳይ ማዕከላት በተለያዩ ቦታዎች ላይ እንዲገነቡ እንደምታደርግ ትናገራለች። በከባድ መከራ ውስጥ ያለፈችው ሄለን የገጠማትን ከባድ ፈተና በጥንካሬ ማለፍ ከመቻሏ በተጨማሪ ለወገኖቿ ለውጥና እድገት የበለጠ አስተዋጽኦ ማድረግ ትመኛለች።
news-53879109
https://www.bbc.com/amharic/news-53879109
እንግሊዝ፡ የተሳሳተ አስከሬን የተሰጣቸው ቤተሰቦች ሌላ ግለሰብ ቀበሩ
ክስተቱ ያጋጠመው በእንግሊዟ ካርሊስል በምትባል ከተማ ነው።
ከሆስፒታል የተሰጣቸውን የቤተሰባቸውን አስከሬን በቀብር አስፈፃሚው ድርጅት መሰረት ይቀብራሉ። የቀብሩ ስነ ስርዓት የተፈፀመውም ካርሊስል በሚባል መካነ መቃብር ዘመድ፣ ወዳጅ፣ ቤተሰብ በተሰባሰበበት በባለፈው ወር ነው። በኋላም ነው ቤተሰቡ የተሰጣቸው አስከሬን የተሳሳተ መሆኑንና ለሌላ ግለሰብ የቀብር ስነ ስርዓት አካሂደው መቅበራቸውን የተረዱት። የተሳሳተ አስከሬን መቀበሩን በመጀመሪያ ይፋ ያደረገው ኒውስ ኤንድ ስታር የተባለ ጋዜጣ ሲሆን ፤ ቤተሰቡም ቆፍረው ለማውጣት ተገደዋል። ስህተቱ ተፈፅሞበታል ተብሎ የሚታመነው ኩምበርላንድ የተባለው ሆስፒታል ስራ አስፈፃሚዎችም ምርመራ መጀመራቸውን አስታውቀዋል። የቀብር ስራ አስፈፃሚው ጆርጅ ሃድሰንና ልጆቹ ለጋዜጣው እንደተናገሩት "የሚያሳዝንና ከፍተኛ ስህተት ነው የተፈፀመው" ብለዋል። ፈታኝ ወቅት የቀብር አስፈፃሚው ቃለ አቀባይ እንደተናገሩት "የሌላ ሰው ግለሰብ አስከሬን እንደቀበርን አላወቅንም ነበር። ለቤተሰቦቻቸው ከልብ አዝነናል" ብለዋል። ጆርጅ ሃድሰንና ልጆቹ ከ150 አመታት በላይ ቀብር በማስፈፀምም ስራ ተሰማርተው እንዳገለገሉና እንዲህ አይነት ስህተትም አጋጥሟቸው እንደማያውቅ አስረድተዋል። ቢቢሲም ከቀብር አስፈፃሚዎቹ ተጨማሪ መሪጃ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም። በሰሜን ኩምብሪያ የሚገኘው የእንግሊዝ ጤና አገልግሎት ቢሮ ቃለ አቀባይ በበኩላቸው የቀብር አስፈፃሚዎቹ እንዲህ አይነት ስህተት እንዴት እንደተፈፀመ የሚያደርጉት ምርመራን እንደሚደግፉና "ቤተሰባቸውን ላጡትና በፈታኝ ሁኔታም እያሉ እንዲህ አይነት አሰቃቂ ነገር ለደረሰባቸውም ኃዘናችን ጥልቅ ነው" ብለዋል። መስሪያ ቤቱም የራሱን የውስጥ ምርመራ እንደጀመረና ሲጠናቀቅም ስለተፈጠረው ሁኔታ ለቤተሰቦቻቸው በጥልቀት እንደሚያስረዱ ተገልጿል።
news-52267353
https://www.bbc.com/amharic/news-52267353
ኮሮናቫይረስ፡ አገራትን ጭምብል እስከመሰራረቅ ያደረሳቸው የኮሮናቫይረስ ዲፕሎማሲ
የአንዳንደ አገራትን እውነተኛ ባህሪ አውጥቶታል ኮቪድ-19። ጭምብል እስከመሰራረቅ የደረሰ።
የኮሮናቫይረስ በአሜሪካና በቻይና መካከል ያለውን ውዝግብ አብሶታል ወረርሽኙን ተከትሎ በአገራት መካከል ቬንትሌተር ለማግኘት የሚደረገው ሽሚያ ለጉድ ነው። ሁሉም ቅድሚያ ለዜጋዬ ስለሚል ማለት ነው። ክትባቱን ቀድሞ ለማግኘትም ፉክክሩ ጦፏል። ሁሉም አገር በሳይንስ የበላይነቱን ለማስጠበቅ። የአውሮፓ ኅብረት ከኮቪድ-19 በኋላ ዕድሜ ይኖረዋል? ሲሉ መጠየቅ የጀመሩም አልጠፉም። ምክንያታቸው ደግሞ በሰሜንና በደቡብ የአውሮፓ አገራት መካከል የታየው መቃቃር ነው። ጣሊያንና ስፔን እንዴት በችግራችን አትደርሱልንም ሲሉ በእነ ጀርመን ላይ ጥርስ ነክሰዋል። ተንታኞች 'የኮቪድ ዲፕሎማሲ' ሲሉ ስም አውጥተውለታል ይህን ምስቅልቅል። አንዳንዶቹን ቀጥለን እንመለከታለን። ቱርክና ስፔን ስፔን እጅግ በወረርሽኙ ከተጎዱ አገራት ተርታ ትመደባለች። 166 ሺህ የሚጠጋ ሕዝብ በበሽታው ተይዞባታል፤ ከ17 ሺህ በላይ ደግሞ ሞቶባታል። ባለፉት ሦስት ወራት የመድኃኒት እጥረት ቁምስቅሏን እንድታይ አድርጓታል። ሐኪሞቿ የመከላከያ ያለህ ይላሉ፤ ታማሚዎቿ ቬንትሌተር ይሻሉ።፡ ብዙዎቹ የህክምና ተቋማቶቿ እጅግ አስፈላጊ የሕክምና መርጃ ቁሳቁሶችን በበቂ አልቀረቡም፤ ለሐኪምም ለታማሚም። ከሰሞኑ ደግሞ ከቱርክ ጋር መቃቃር ውስጥ ገብታለች፤ ስፔን። ምክንያቱ ደግሞ በስፔን ሦስት ግዛቶች የሚገኙ የጤና ኤጀንሲዎች የገዟቸው ከመተንፈሻ አካላት ጋር የተያያዙ የሕክምና ቁሳቁሶችን የጫነ መርከብ በቱርክ መታገቱ ነው። የስፔን መገናኛ ብዙኀን ነገሩን "አይን ያወጣ ሌብነት" ሲል ነው የዘገበው። የማድሪድ ባለሥልጣናት አንካራ የህክምና መሣሪያዎቻችንን ወስዳ የራሷን በሽተኞች እያከመች ነው እስከማለት ደርሰው ነበር። በቱርክ የተያዘባቸውን የህክምና መሣሪያዎችን የስፔን ሆስፒታሎች ይጠብቁ ነበር የስፔን ጋዜጣ 'ኤል ሙንዶ' በበኩሉ የሕክምና መሣሪዎቹ በስፔን ትዕዛዝ ቻይና እንድታመርታቸው የተከፈለባቸው ናቸው። ሆኖም ቁሳቁሶቹ የሚመጡት ከቻይና በመሆኑና አምራቹ በቱርክ ውስጥ የሚገኝ የስፔን ኩባንያ መሆኑ ነው ነገሩን ያወሳሰበው ብሏል። በዚህ መካከል አንካራ አገሯ የተመረቱ ቬንትሌተሮች ከአገር እንዳይወጡ ከውሳኔ ላይ ደርሳ ነበር። ሳምንት ከፈጀ እልህ አስጨራሽ የዲፕሎማሲ ጥረት በኋላ የስፔን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የህክምና መሣሪያ የጫነችውን መርከብ ከቱርክ ለማስለቀቅ ችሏል። ይህ ክስተት ኮሮናቫይረስ በአገራት መካከል የፈጠረውንና እየፈጠረ የለውን ውጥረት የሚያሳይ ነው። ቻይናና አሜሪካ፣ ዶ/ር ቴድሮስና ትራምፕ በአሜሪካና በቻይና መሀል የተፈጠረው ዲፕለማሲያዊ ውጥረት ከቃላት ይጀምራል። አንድ የቻይና ባለሥልጣን ቫይረሱ ዉሃን ከተማን በጥቅምት ወር ጎብኝተው በተመለሱ የአሜሪካ ወታደሮች ሳይቀመም እንዳልቀረ እንደሚጠረጥር ተናገረ። የባለስልጣኑን ክስ ተከትሎ ዶናልድ ትራምፕ የሚፈልጉት ያገኙ መሰሉ። ቫይረሱንም "ቻይና ቫይረስ" አሉት። ይህ ደግሞ የቻይና ባለሥልጣናትን ጨጓራ የላጠ ጉዳይ ነበር። የኋላ ኋላ ቻይና ነገሩን ባናከረው፣ ሰዎችን በማዳን ላይ ብንጠመድ ይሻላል በማለቷ፤ ትራምፕም ቫይረሱን "የቻይና ቫይረስ" ብለው መጥራቱን እርግፍ አድርገው ተዉት። ትራምፕን በዚህ ረገድ እስከወዲያኛው ማመን ቢከብድምድ። መጪውን ምርጫ ለማሸነፍ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም የሚባሉት ትራምፕ፤ ባለፉት ዓመታት ያመጡትን የምጣኔ ሀብት ስኬት ኮቪድ-19 ጠራርጎ በልቶታል። ይህ ደግሞ አስቆጥቷቸዋል። የተቆጡት በቫይረሱ አይደለም። በአገራቸው በተቋማት ነው። ከዚህ በኋላ እርሳቸው ዋይት ሐውስ ከገቡ በኋላ ስንት ሚሊዮን ሥራ እንደፈጠሩ መናገር ብዙም ስሜት የሚሰጥ አይሆንም። በወረርሽኙ ምክንያት ሥራ ያጣው 7 ሚሊዮን ተጠግቷልና። 'ተራ ጉንፋን ነው በቅርቡ ይጠፋል' ያሉት ቫይረስ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሕዝባቸውን አዳርሶ፣ 20 ሺህ ዜጎችን ቀጥፎ አገራዊ ቀውስ ፈጥሯል። ይህም አናዷቸዋል። ትራምፕ ይህን ችግር በተቻለ መጠን ከራሳቸው ማራቅ ነበረባቸው። መጀመርያ ዲሞክራቶች ከቫይረሱ ጀርባ ተደብቀው የፈጠሩት ሴራ አለ ብለው ቫይረሱን ወደ ዲሞክራቶች አጠጋጉት። ቀጥለው ወደ ቻይና ወሰዱት። በመጨረሻም ዶ/ር ቴድሮስ ወደሚመሩት የዓለም ጤና ድርጅት ገፉት። የዓለም ጤና ድርጅት ሥራው ሁሉ 'ቻይናን ማዕከል ያደረገ ነው' ሲሉ ተችተዋል፤ ትራመፕ። በየዓመቱ ለድርጅቱ የሚሰጡትን የአራት መቶ ሚሊዮን ዶላር ድጎማም በድጋሚ ሊያጤኑት እንደወሰኑ አስታውቀዋል። ይህ ክስተት ቻይና እንደግዛቷ በምትመለከታት ታይዋን፣ የዓለም ጤና ድርጅትን በሚመሩት ዶ/ር ቴድሮስና የታይዋን የምንጊዜም አጋር በሆነችው አሜሪካ መሀል ፍጥጫን ፈጥሯል። አሜሪካ ቻይናን "ትክክለኛውን የቫይረሱን ተጠቂዎች ቁጥር ደብቃለች" ስትል መክሰስ የጀመረችው ቀደም ብላ ነው። የቻይና፣ የዶ/ር ቴድሮስና የታይዋን የዲፕሎማሲ ምስቅልቅ የኮሮናቫይረስ ዘመን የዲፕሎማሲ ችግር ሌላ ማሳያ ሆኖ ተወስዷል። "በጽንሰ ሐሳብ ደረጃ በዓለም እንዲህ ዓይነት የጋራ ጠላት ሲከሰት አገራት ይበልጥ ተቀራርበው፤ ሊሰሩ ነበር የሚገባው" ትላለች በለንደን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተመራማሪ ሶፊያ ጋስተን ለቢቢሲ። ህንድን ከአሜሪካ ጋር ያወዛገበው መድኃኒት "ይህ ወረርሽኝ ግን በተቃራኒው አገራት ወደራሳቸው ብቻ እንዲመለከቱና እርስበርስ እንዲፎካከሩ ነው እንጂ እንዲተባበሩ አላደረጋቸውም።" ለዚህ የሶፊያ ነጥብ ሁነኛ ማሳያው የአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት ናቸው። መጀመሪያ ጣሊያን ወረርሽኙን መቆጣጠር ሲያቅታት አባል አገራት እንዲያግዟት ጠይቃ ነበር። ሆኖም ጀመርንና ፈረንሳይ ጣሊያን የጠየቀቻቸው የህክምና መሣሪያዎች ወደ ውጭ እንዳይወጡ እግድ ጥለዋል። "ይህ ለአውሮፓ ኅብረት ትብብርና ወንድማማችነት መልካም ምልክት አይደለም ሲሉ ጽፈዋል" በብራስልስ የጣሊያን አምባሳደር ማሪዚዮ ማሳሪ። ጣሊያኖች በበኩላቸው ጀርመን እነሱን ለመርዳት ዳተኛ መሆኗ አስቀይሟቸዋል። በርሊን በወረርሽኙ ምጣኔ ሀብታቸው እጅግ የተጎዱ አገራትን በመደገፉ ሐሳብ ብዙም ያመነችበት አይመስልም። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ላደቀቀው ኢኮኖሚ የሚሆን የብድር ቦንድ መኖር የለበትም፤ የተጎዱ አገራትንም ጭምር ወደ ችግር ይከታል ትላለች ጀርመን። የተጎጂ አገራትን ምጣኔ ሐብት በምን ሁኔታ እንደግፍ በሚለው ዙርያ ግልጽ ልዩነት አለ። ኔዘርላንድስ፣ ኦስትሪያ እና ፊንላንድም እንደ ጀርመን ሁሉ የኮሮናቫይረስ ትብብር ቦንድን በጋራ ማተሙን አይደግፉትም። ስፔን፣ ፈረንሳይ፣ ቤልጂየም፣ ግሪክ፣ አየርላንድ፣ ፖርቹጋል፣ ስሎቬኒያና ሉክዘምበርግ ግን ለነጣሊያን በኅብረቱ ደረጃ ድጋፍ ሊሰጥ ይገባ ነበር ይላሉ። ይህም የሚያሳየው በአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት ዘንድ የዋዛ የማይባል ክፍፍል መኖሩን ነው። እጅግ እልህ አስጨራሽ ከሆነ ድርድር በኋላ 27 አባል አገራቱ የጋራ የብድር ማዕቀፍ አሰናድተው 500 ቢሊዮን ዶላር አጽድቀዋል። ይህ ቁርሾና የአባል አገራት ክፍፍል ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኋላ እንደ ወረርሽኙ ብን ብሎ ይጠፋል ተብሎ አይጠበቅም። አክራሪ ነጭ ብሔርተኞች ኅብረቱ ከንቱ እንደሆነና ከኅብረቱ ለመውጣትም ሕዝቡን ለማነሳሳት ይጠቀሙበታል ተብሎ ይጠበቃል። ቻይናና አዲሱ ዓለም አቀፋዊ ሚናዋ ቻይና ወረርሽኙን በአስተማማኝ ሁኔታ መቆጣጠሯን ካረጋገጠች ወዲህ ሌሎች አገራትን ወደ መርዳቱ ተሸጋግራለች። መጀመሪያ እጇን የዘረጋቸውም ለጣሊያን ነው። ሮም ከቻይና የመድኃኒትና የህክምና መሣሪያዎችን እርዳታ ብቻ ሳይሆን የቻይና ሐኪሞችን ጭምር በእርዳታ አግኝታለች። በዚህም ቻይና በጣሊያዊያኑ ዘንድ ክብርና ሞገስን አግኝታለች። #grazieCina (እናመሰግናለን ቻይና) የሚሉ የማኅበራዊ ሚዲያ የምስጋና ዘመቻዎችም ተከፍተው ነበር። መቀመጫውን ለንደን ባደረገ አማካሪ ድርጅት የሚሰሩት የዲፕሎማሲ አዋቂ ሚስተር አንቶኒ እንደሚሉት፤ የቻይና ተግባር አሜሪካ ቸል ብላ የቆየችውንና በቅድመ ትራመፕ ዘመን የነበራትን ዓለም አቀፋዊ የተጽእኖ ፈጣሪነት ሚና የሚሞላ ነው ይላሉ። ትራምፕ ሁሉ ነገር በቅድሚያ ለአሜሪካዊያን የሚለው ፖሊሲያቸው ብዙ አገራት የሚወዱላቸው አይደለም። ከ2016 ወዲህ አሜሪካ ሁሉን ለእኔ ብቻ የሚለውን አተያይ በተለያየ መንገድ አንጸባርቃለች። ይህ ከተገለጸበት መንገድ አንዱ ትራምፕ በክትባት ምርምራ ላይ የነበሩ የጀመርን ሳይንቲስቶችን በገንዘብ ሊያባብሉ የሞከሩበት መንገድ ነው። በቅርቡ ደግሞ የህንዱ ወዳጃቸውን ፕሬዝዳንት ሞዲን ጭምር ሀይድሮክሲክሎሮኪን የወባ መድኃኒትን ለአሜሪካ ካልሰጡ እበቀልዎታለው ብለው ማስፈራራታቸው ሌላው ነው። ህንድ የአሜሪካንን ቅጣት ፈርታ በሚመስል ሁኔታ የወባ መድኃኒቱ ወደየትም አገር እንዳይላክ የጣለችውን ዕቅድ ወዲያዉኑ አንስታዋለች። የዲፕሎማሲ አዋቂው አንቶኒ እንደሚሉት አሜሪካ በዓለም የዲፕሎማሲ መድረክ ትጫወተው የነበረው ሚና በትራምፕ ዘመን አክትሟል፤ በምትኩ ቻይና ወደ መድረኩ ብቅ እያለች ነው። የቻይናና ብራዚል መቋሰል አሜሪካ ቻይናን የቫይረሱን ጉዳት መጠን ቀንሰሽ ታቀርቢያለሽ ስትል ትወቅሳለች። በወቀሳው ብራዚላዊያንም ተደምረዋል። ነገሮች እየተካረሩ ሄደው የቻይናና የብራዚል ሹሞች በማኅበራዊ ሚዲያ አንድ ሁለት መባባል ጀምረው ነበር። በቅርቡ የቦልሶኒሮ የትምህርት ሚኒስትር አብረሃም ዌንትሮብ "ቻይና ይሄን ቫይረስ የፈጠረችው ዓለምን ለመቆጣጠር ካላት ፍላጎት ነው" ብለዋል። ይህን የጻፉበት መንገድ ደግሞ ቻይናዎችን በሚያስቆጣ መልኩ ነው። ይህን ተከትሎ ቻይና ጨርቋን እስክትጥል ነው የተቆጣችው። ማብራሪያም ጠይቃለች። ከጤናማ አነጋገር የራቁት የትምህርት ሚኒስትሩ እንደ ብራዚሉ ቦልሶኒሮ መዘባረቅ የሚያበዙ ናቸው። የእሲያ ሰዎች የሰውየውን ንግግር ዘረኛ ሲሉ ኮንነውታል። "እንዲህ አይነቱ አነጋገር አስቀያሚና የዘረኛ መርዝ የተሸከመ ነው" ብለውታል በብራዚል የቻይና ኤምባሲ ተወካይ። የትምህርት ሚኒስትሩ ይቅርታ እንዲጠይቁ ቢጠየቁም በጄ አላሉም። "ቻይና አንድ ሺህ ቬንትሌተር ከሰጠችን ግን ኤምባሲዋ ድረስ በእምብርክኬ ሄጄ ይቅርታ እጠይቃለሁ" ሲሉ አፊዘዋል። የሚገርመው የብራዚል ትልቋ የንግድ አጋር ቻይና ናት። 80 ከመቶ የሶያ አተር ብራዚል የምትሸጠው ለቻይና ነው። የብራዚል የጤና ጥበቃ ባለሥልጣናት ከቻይና ቬንትሌተርና ሌሎች የህክምና ቁሳቁሶችን ለማግኘት በዝግጀት ላይ ነበሩ፤ ይህ የዲፕሎማሲ ቁርሾ እስኪፈጠር ድረስ። ማዱሮ ለኮሎምቢያ ካበረከቱት ማሽን ጋር ቬንዝዌላና ኮሎምቢያ በዚህ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዘመን ዲፕሎማሲ ከመድኃኒት ባልተናነሰ አስፈላጊ ነው የሚሉ አልጠፉም። ይህ ቫይረስ ቀድሞ የነበሩ የዲፕሎማሲ ቁርሾዎች ደግመው እንዲያንሰራሩም አድርጓል። ለምሳሌ ኮሎምቢያና ቬኒዝዌላን ማየት ይቻላል። የኮሎምቢያ ባለሥልጣናት ለፕሬዳንት ኒኮላስ ማዱሮ እውቅና አይሰጡም። ሁለቱ ተጎራባች አገራት በዚህ የተነሳ እንደተቋሰሉ ነበሩ፡፡ በሚሊዮኖን የሚቆጠሩ የቬንዝዌላ ነዋሪዎችም በስደት ወደ ኮሎምቢያ አቅንተዋል። ለዚህ የሁለቱ ጎረቤት አገራት ጸብ ኮሮናቫይረስ አዲስ መልክ ሰጥቶታል። በዚህ ወር መጀመርያ ኒኮላስ ማዱሮ ለኮሎምቢያው አቻቸው ኢቫን ዱኮ 2 የኮቪድ-19 መመርመሪያ ማሽኖችን በስጦታ ያቀርባሉ። ከዚያ ቀደም ብሎ የአካባቢው ሚዲያዎች "ኮሎምቢያ ቫይረሱን መመርመሪያ አንድ ማሽን ብቻ ነበራት፤ እሱም ተሰበረባት" ሲሉ ጽፈው ነበር። ይህን ተከትሎ ነበር ማዱሮ ስጦታ ያቀረቡት። የስጦታው ጥያቄ ከኮሎምቢያ በኩል እሺም እምቢም አልተባለም። እንዲያውም እንደ ነገር ፍለጋ ሳይታይ አልቀረም። የኮሎምቢያ ዝምታ ያናደዳቸው የቬንዝዌላ ባለሥልጣናት ነገሩን አባባሱት። የቬኒዝዌላው ምክትል ፕሬዝዳንት ደልሲ ሮድሪጎዝ የሚከተለውን በትዊተር ሰሌዳቸው ጻፉ። "የኮሎምቢያ ባለሥልጣናት ስጦታችንን ለመቀበል አልፈቀዱም። ለኮሎምቢያ ሕዝብ ግድ እንደሌላቸው ያሳያል።" ይህ ደግሞ በምላሹ ኮሎምቢያን አስቆጣ። አንድ የኮሎምቢያ ባለሥልጣን በራዲዮ በሰጡት ምላሽ "የቬንዝዌላ ስጦታ እጀ ሳባራ ነው፤ አሰራሩ ከእኛ ጋር አይገጥምም" ብለዋል። ኳታር በባሕረ ሰላጤው ከሚገኙ አገራት በርካታ የወረርሽኙ ታማሚዎች አሏት ግብጽና ኳታር የኮሮናቫይረስ ዲፕሎማሲ በመካከለኛው ምሥራቅም ጥላውን አጥልቶ ቆይቷል። ምክንያቱ ደግሞ ግብጻዊያን ዜጎች በኳታር መውጣት ሳይችሉ መቆየታቸው ነበር። ኳታር ለአልጀዚራ እንዳለችው ግብጻዊየኑ በቻርተርድ አውሮፕላን ከጉልበት ሰራተኞች ጋር ሆነው ከአገር ለመውጣት አለመፍቀዳቸው ነው ችግሩ። ግብጽ ወትሮም ከኳታር በተቃራኒው ከቆመው የአረብ አገራት ጥምረት ጋር ነው የምትወግነው። የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች፣ ሳኡዲና ሌሎች ሆነው በትንሽዋ ኳታር ላይ ካደሙ ሦስት ዓመታት አልፏል። ኳታር መንግሥታችንን ለመገልበጥ አክራሪ ታጣቂዎችን ትደግፋለች ሲሉ ይከሳሉ፥። ኮሮና ይህንኑ የቆየ የዲፕሎማሲ ቁርሾን አባብሶታል። አውሮፓና ሩሲያ ከነዚህ ለየት የሚለው የዲፕሎማሲ ቁርሾ በአውሮፓ አገራትና በሩሲያ መካከል የተከሰተው ነው። ለሩሲያ የሚቀርብ ሚዲያ በኮቪድ19 ጉዳይ ሆን ብሎ ሐሰተኛ ዜና ለአውሮፓዊያን ይነዛል ሲሉ አውሮፓዊያኑ ይከሳሉ። የሩሲያ መንግሥት ቃል አቀባይ ይህንን ክስ "መሰረተ ቢስ" ብለውታል። የዲፕሎማሲ ተንታኟ ሶፊያ እንደምትለው ከዚህ በኋላ በመላው ዓለም ቀኝ አክራሪዎች ኅብረት እንደማይሰራ ማስረጃ አግኝተዋል። "ኮሮናቫይረስ ለአውሮፓዊያንና ከዚያ ባለፈም ላሉ አገራት መልካም የትብብር መመስረቻ ሊሆን በተገባ ነበር። የሆነው ግን በተቃራኒው ነው።" አንድ የጋራ ጠላት ካላስማማ ምን ሊያስማማ ይችላል?
news-49218295
https://www.bbc.com/amharic/news-49218295
ሊዮኔል ሜሲ ከዓለም አቀፍ ጨዋታዎች ታገደ
ታዋቂው የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አምበል ሊዮኔል ሜሲ ለሦስት ወራት በዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ እንዳይሳተፍ እገዳ ተጣለበት። ሜሲ ላይ እገዳው የተጣለው የአህጉረ አሜሪካ ሃገራት የሚሳተፉበት የኮፓ አሜሪካ እግር ኳስ ውድድር "በሙስና የተበላሸ ነው" በማለት አስተያየት መስጠቱን ተከትሎ ነው።
የባርሴሎናው የፊት መስመር ተጫዋች ሜሲ ሲካሄድ በሰነበተው የኮፓ አሜሪካ ውድድር ላይ አርጀንቲና ሦስተኛ ደረጃን ለመያዝ ቺሊን 2 ለ 1 ባሸነፈችበት ጨዋታ ላይ በቀይ ካርድ ከሜዳ ከወጣ በኋላ የሰጠው አስተያየት ለቅጣት ዳርጎታል። የ32 ዓመቱ ሜሲ ውድድሩ ብራዚል አሸናፊ እንድትሆን ታቅዶ የተካሄደ ነው ማለቱ የደቡብ አሜሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽንን አስቆጥቶ ከጨዋታ እንዲታገድና የ50 ሺህ ዶላር ቅጣት ተጥሎበታል። • "ሥራዬን ለቅቄ ልጆቼን ያጠባሁት እድለኛ ሆኘ ነው" ሮዝ መስቲካ • በጀርመን ከፍተኛ መጠን ያለው ኮኬይን በቁጥጥር ሥር ዋለ ሜሲ ለሦስት ወራት ከዓለም አቀፍ ጨዋታዎች የተጣለበት እገዳና የገንዘብ ቅጣቱን በተመለከተ ይግባኝ የመጠየቂያ ሰባት ቀናት አሉት። የጨዋታ እገዳው የሚጸና ከሆነ ሜሲ ሃገሩ አርጀንቲና በመጪዎቹ መስከረምና ጥቅምት ከቺሊ፣ ከሜክሲኮና ከጀርመን ጋር በምታደርጋቸው የወዳጅነት ግጥሚያዎች ላይ አይሳተፍም። አርጀንቲና በኮፓ አሜሪካ ውድድር የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ በብራዚል 2 ለ 0 ስትሸነፍ የሃገሪቱ እግር ኳስ ማህበር በጨዋታው ላይ "በርካታና ወሳኝ የዳኝነት ስህተቶች ነበሩ" ሲል ቅሬታውን አቅርቦ ነበረ፤ የውድድሩ አዘጋጆች ግን ክሱን ውድቅ አድርገውታል። በግጥሚያው 37ኛ ደቂቃ ላይ በቀይ ካርድ የተባረረው ሜሲ እንዳለው "የዚህ በሙስና የተበላሸ አሰራር ውስጥ መሳተፍ የለብንም" በማለት በውድድሩ ወቅት አክብሮት የጎደለው ሁኔታ እንደገጠማቸው ተናግሯል። "የሚያሳዝነው ደግሞ ሙስናውና ዳኞቹ ተመልካች በጨዋታው እንዳይደሰት በማድረግ እግር ኳሱን አበላሽተውታል" ሲል ሜሲ ወቅሷል።
news-53135330
https://www.bbc.com/amharic/news-53135330
ሚሼል ኦባማ፡ ቀጣይዋ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት?
ጆ ባይደን እኔ የዲሞክታሪክ ፓርቲ እጩ ውድድርን ካሸነፍኩ የፕሬዝዳንታዊ የውድድር ሸሪኬ ሴት ትሆናለች ብለው በመጋቢት ወር ቃል ገብተው ነበር።
አሁን ቃላቸውን መፈጸም የግድ ነው። ማን ትሆን ለዚህ ትልቅ ኃላፊነት የምትታጨው? የአሜሪካ ፖለቲካ አዋቂዎች የሚከተሉት ሴቶቹ ሰፊ ዕድል አላቸው ይላሉ። ካማላ ሀሪስ ሀሪስ የባይደን የውድድር ሸሪክ ለመሆን ሰፊ ዕድላ አላት። የካሊፎርኒያ አቃቤ ሕግ ነበረች። በአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ካሊፎርኒያን በመወከል አባል ናት። በሳንፍራንሲስኮም የአንድ ቀጠና አቃቢ ሕግ ሆና ሠርታለች። እናቷ ከሕንድ ናቸው፣ አባቷ ከጃማይካ። ባለፈው ዓመት ለፕሬዝዳንትነት መፎካከርም ጀምራ ነበር። ሃሪስ ለባይደን በቅርቡ 2 ሚሊዮን ዶላር በበይነ መረብ ገንዘብ ማሰባሰብ ችላ ነበር፤ በግዛቷ ካሊፎርኒያ። ባይደን ሸሪኩ ጥቁር ሴት እንድትሆን ፍላጎት አላቸው። በተለይ በጥቁር አሜሪካዊያን ዘንድ። ይህንንም ፍላጎት በደንብ ታሟላለች። ከጆርጅ ፍሎይድ ጋር በተያያዘ ደግሞ ሰሞኑን በነበሩ ትላልቅ ሰልፎች የሕዝብ ትኩረት ያገኙ ንግግሮችን አድርጋ ነበር። ግሪቸን ዊትመር ዊትመር የሚቺጋን ገዥ ከሆነች ገና ሁለት ዓመቷ ነው። እምብዛምም አትታወቅም ነበር። ኮሮናቫይረስ ነው ይበልጥ ያሳወቃት ይባላል። ቫይረሱን በሚቺጋን ለመቆጣጠር በወሰደችው እርምጃ ዶናልድ ትራምፕ አፍ ውስጥ ገባች። በአሜሪካዊያን ዘንድ ይበልጥ ያስተዋወቃትም በትራምፕ አፍ ውስጥ መግባቷ ሳይሆን አይቀርም። ከዓመታት በፊት በ2016 ሂላሪ ክሊንተን በሚቺጋን በዶናልድ ትራምፕ የተበለጡት ለጥቂት ጊዜ ነበር። ያን ጊዜ በሚቺጋን ሂላሪ አሸንፈው ቢሆን ኖሮ ትራምፕ ፕሬዝዳንት ላይሆኑ ይችሉ ነበር። ተመሳሳይ እጣ ፈንታ ባይደን እንዳይገጥማቸው ዊትመርን የውድድር ሸሪካቸው ሊያደርጓት ይገባል የሚሉ ተንታኞች አሉ። ታሚ ደክዎርዝ ታሚ ደክዎርዝ የኢሊኖይ ሴናተር ናት። በኢራቅ እርሷ ታበረው የነበረው ሄሊኮፕተር በጠላት ተመትቶ በመውደቁ ነው ሁለት እግሮቿን ያጣችው። ከዚያ በኋላም ከወታደር ቤት አልወጣችም። ጡረታ የወጣችው የሌተናል ኮሎኔልነት ማዕረግ ይዛ ነው። ከዚያ በኋላ በዶናልድ ትራምፕ ዘመን የጡረታ ጉዳዮች ረዳት ዋና ጸሐፊ ሆና አገልግላለች። ደክዎርዝ በታችኛው ምክርት ቤት እንደራሴ ሆና ካገለገለች በኋላ በ2016 የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ወንበርን አሸንፋለች። የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ለመግባት የመጀመርያዋ የታይላንድ ዝርያ ያላት ሴት ናት። በአሜሪካ ታሪክ ሁለት እግሯን በአደጋ አጥታ የኮንግረስ አባል የሆነች የመጀመርያዋ ሴት ናት። በ2018 የሴኔት አባል ሆና እያገለገለች ልጅ የተገላገለች የመጀመርያዋ ሴት ናት፣ ደክዎርዝ። እርግጥ ነው ኢሊኖይ ግዛት የዲሞክራቶች ናት። ሆኖም በብዙ መልኩ ባይደን ታሚ ደክዎርዝን ሸሪካቸው አድርገው ሊመርጧት የሚችሉበት ዕድል አለ። ኤልዛቤት ዋረን ኤልዛቤት ዋረን በቅድመ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ብዙ ርቀት ትሄዳለች፣ ዲሞክራቶችን ትወክላለች ተብላ ስትጠበቅ በአጭር ቀረች። በ2019 አጋማሽ ጥሩ ተጉዛ በሕዝብ ድምጽ መለኪያ ሁሉ መምራት ጀምራ ነበር። ከዚያ ድንገት ደጋፊዎቿ እንደ ጉም ተነኑ። ግማሾቹ ወደ በርኒ ሳንደርስ ሄዱ። ብዙዎች እርሷ ውድድሩን ጥላ ስትወጣ ሳንደርስን ይቅናዎ ብላ ትባርካቸዋለች፤ ደጋፊዎቿንም ወደ ሳንደርስ ትሸኛቸዋለች ብለው ጠብቀው ነበር። ይህን ባለማድረጓ ባይደን ውስጥ ውስጡን ሳያደንቋት አልቀሩም። ባይደን ኤልዛቤት ዋረንን በዚህም ሆነ ባላት እምቅ አቅምና ድጋፍ የምርጫ ሸሪካቸው ሊያደርጓት ሰፊ ዕድል አለ ይላሉ ተንታኞች። ታሚ ባልድዊን ከአራት ዓመት በፊት ሂላሪ ክሊንተርን በዊስኮሲን ቅስቀሳ አለማድረጋቸው ቅሬታን ፈጥሮ ነበር፡፡ ግዛቷን ንቀዋት ይሆን? ዋጋ አስከፈለቻቸው። ዲሞክራቶች ይህንን ስህተት ይደግማሉ ተብሎ አይጠበቅም። ባይደን ዊስኮንሲንን መዘንጋት ካልፈለጉ ታሚ ባልደዊንን ሸሪካቸው አድርገው ሊመርጧት ይችላሉ። ታሚ በሴኔት ውስጥ 2ኛ ዓመቷ ነው። በሕግ መምሪያ ታችኛው ምክር ቤት ለ14 ዓመታት አገልግላለች። እሷ ብትመረጥ አንድ አዲስ ታሪክም ይመዘገባል። በግልጽ የተመሳሳይ ጾታ ወዳጅ የሆነች ሴት ለእጩ ፕሬዝዳንትነት ውድድር ምክትል ሆኖ መወዳደር አዲስ ታሪክ ነው። ለሕግ መወሰኛ ምክር ቤትም ቢሆን በአሜሪካ ታሪክ ግልጽ የተመሳሳይ ጾታ ወዳጅ የሆነች ሴት አባል ሆና አታውቅም። ክሪስተን ሲኒማ በ2018 ከሪስተን ሲኒማ አሪዞናን ለማሸነፍ በ30 ዓመት የመጀመርያዋ ሴት ናት። ሲኒማ ወጣት ናት፣ ቆንጆ ናት። የቴሌቪዥን ተመልካቾችን የመማረክ አቅም አላት። በፖለቲካ አቋሟም አማካይ አመለካከት ትይዛለች ይሏታል። ድንገቴ ባህሪ አላት፣ አትፈራም፣. ያልተጠበቁ ነገሮች በማድረግ ትታወቃለች። የሚዲያ ትኩረትን በቀላሉ መሳብ ትችላለች። በቅርቡ ሐምራዊ አርቴፊሻል ጸጉር አድርጋ በሴኔት መታየቷ ሲያነጋግር ነበር። ያደረገችው ዊግ ርካሽ የ12 ዶላር ተራ ዊግ ነበር። ጸጉር ቤት አትሂዱ በኮሮናቫይረስ ዘመን ዝም ብላችሁ ዊጋችሁን አጥልቁ የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ነበር የሞከረችው ተብሏል። ዶናልድ ትራምፕ ባይደንን በሹፈት "እንቅልፋሙ ባይደን" እያሉ ነው የሚጠሩት። ጆ ባይደን እንቅልፋም ባይባሉም ትንሽ ፍዝ ባህሪ ነው ያላቸው። ክሪስተን ሲኒማ ንቅት፣ ፍክት ያለችና ጉዳይ መቀስቀስ የምትችል ስለሆነች የባይደንን ፍዝነት ታካክስላቸው ይሆናል። ቫል ደሚንግስ ባለፈው ዓመት ቫል ደሚንግስ እምብዛምም የማትታወቅ የኮንግረስ አባል ነበረች። ከዚያ ድንገት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፒሎሲ የትራምፕ ክስ የሚያየው ኮሚቴ ሊቀ መንበር አደረገቻት። ከዚያ ሁሉም አወቃት። ቫል ደሚንግስ ገና ጆርጅ ባይደን በግፍ በነጭ ፖሊስ ከመገደሉ በፊት ጉዳዩን የአሜሪካዊያን ጉዳይ ለማድረግ ጥራለች። የቀድመው የኦርላንዶ፣ ፍሎሪዳ የፖሊስ አዛዥ ቫል በባይደን ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው ጥቁር ሴት ሸሪኮች አንዷ ናት። አንጻራዊ በሆነ መልኩ ከሌሎች አነስ ያለ የፖለቲካ ጥበብ ያላት ቫል ባይደን የጥቁሮችን ጉዳይ መሪ ጉዳዬ ላድርገው ካሉ ይቺ ሴት ወሳኝ ልትሆነን ትችላለች። ሚሼል ግሪሻም በቀዳሚው የምርጫ ፍክክር ወቅት የስፓኒሽ ዝርያ ያላቸው አሜሪካዊያን ለባይደን ድምጻቸውን ለመስጠት አቅማምተዋል። በካሊፎርኒያ፣ በቴክሳስና በኔቫዳ በርኒ ሳንደርስ ባይደንን በልጠዋቸው ነበር። አንዱ ምክያትም ይኸው ሊሆን ይችላል። ባይደን የድጋፍ መሰረታቸው የስፓኒሽ ዝርያ ባላቸው አሜሪካዊያን ዘንድ ከፍ እንዲል ከፈለጉ የኒው ሜክሲኮ ገዥ ሚሼል ግሪሻም ወሳኝ እጩ ሆነው ይታያሉ። ስታንሲ አብራምስ ስታንሲ የተለመደ ጮሌ ፖለቲከኛ የሚፈለግበት ዓይነት የሥራ ታሪክና ተሞክሮ የላትም። ጆርጂያን ወክላ በሕግ መምሪያ ምክር ቤት ውስጥ ለ10 ዓመት ቆይታለች። በ2018 የጆርጂያ ገዢ ለመሆን ተወዳድራ ለጥቂት ተሸንፋለች። ከሌሎች እጩዎች በተለየ አብራምስ የባይደን ምክትል ለመሆን ብዙ ርቀት ሄዳለች። 'ሸሪክህ ልሁን' ብላ በግልጽ ጠይቃለች። ብዙዉን ጊዜ እጩ አድርገኝ ብሎ በግልጽ መቀስቀስ የተለመደ አይደለም። በዲሞክራቲክ ፓርቲ ውስጥ አብራምስ አዲስ ድምጽ ሆናለች ይላሉ ተንታኞች። ኬይሻ ቦተምስ ጆርጅ ፍሎይድ በነጭ ፖሊስ መገደሉን ተከትሎ የተነሳው አመጽ ለትልልቅ ከተሞች ከንቲባዎች የመታያ መድረክ ከፍቶላቸዋል። የአትላንታ ከንቲባ ኬይሻ በዚህ ረገድ ትጠቀሳለች። ፖሊስ ተመጣጣኝ እርምጃ ብቻ እንዲወስድ በማግባባትም፣ ሰልፈኞቹና ጥያቄዎቻቸው የእርሳቸውም ጥያቄ እንደሆነ በማንሳትም ድምጿን ከፍ አድርጋ ጉዳያችሁ ጉዳዬ ነው ብላለች። እርሷ ራሱ ጥቁር መሆኗና የርሷም አራት ልጆች እጣ ፈንታ እንደሚያሳስባት ተናግራ ነበር። ኬይሻ "የ12 ዓመት ልጄን እባክህን በአሻንጉሊት ሽጉጥ አትጫወት እለዋለሁ፤ ምክንያቱም ፖሊስ የምር ሽጉጥ የያዝክ መስሎት እንዳይተኩስብህ" ስል እመክረዋለሁ ብላ መናገሯ የብዙዎችን ስሜት የነካ ጉዳይ ነው። በከንቲባነት ገና የጀመሪያ ዘመኗን እያገባደደች ቢሆንም ኬይሻ የባይደን ተቀዳሚ ምርጫ ልትሆን እንደምትችል ይገመታል። ሱሳን ራይስ የሱዛን ራይስ በዚህ ዝርዝር ውስጥ መካተት ለብዙዎች አዲስ ዜና ነው። ምክንያቱም ምንም የመመረጥም ሆነ የቅስቀሳ ልምድ የላትም። ብዙ አሜሪካዊያንም ያውቋታል ማለት ይከብዳል። ይቺ ዲፕሎማት ግን ባይደን ጠንቅቀው ያውቋታል። ምክንያቱም በኦባማ ጊዜ በዋይት ሐውስ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሆና ሰርታለች። በኋላም በተባበሩት መንግሥታት የአሜሪካ አምባሳደርም ሆና አገልግላለች። ራይስ የባይደን ምርጫ ከሆነች በውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ላይ የነቃ ሚና ይኖራታል ተብሎ ይገመታል። ራይስን ሪፐብሊካኖች አይወዷትም። በ2012 በሊቢያ ቤንጋዚ የአሜሪካ አምባሳዳር መገደልን ተከትሎ የአሜሪካንን ሕዝብ ዋሽታለች ይሏታል። ሚሼል ኦባማ የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ለዚህ ቦታ ከበቂ በላይ መሆኗ ነው ችግሩ። እጅግ ተወዳጅ ሴት ናት ሚሼል፤ በአሜሪካዊያን ዘንድ። ፈተናው የሚሆነው ይኸው ነው። አንደኛ እርሷ ፖለቲካ ውስጥ የመግባት ፍላጎት እንደሌላት "ቢካሚንግ" በሚለው የግለታሪክ መጽሐፏ ገልጻለች። ሁለተኛው ፈተና እርሷ የባይደን ሽርክ ብትሆን ባይደንን ዞር ብሎ የሚያይ አይኖር ይሆናል። ትኩረቱ ሁሉ እርሷ ላይ ይሆንና ሌላ ጉዳት ያመጣል። በተለምዶ ምክትል የሚሆነው ሰው እንደ ኮከብ እንጂ እንደ ጨረቃ እንዲደምቅ አይፈለግም። ሚሸል ኦባማ ግን ጨረቃ ናት።
news-53666383
https://www.bbc.com/amharic/news-53666383
ሂሮሺማ እና ናጋሳኪ፡ የአውቶሚክ ቦምብ ጥቃቱ 75ኛ ዓመት ሲታወስ
ሐምሌ 30 እና ነሐሴ 3 ዓለም በአሰቃቂነቱ የሚያወሳው የጃፓኖቹ ሂሮሺማና ናጋሳኪ ከተሞች ላይ የአሜሪካ የአውቶሚክ ቦምቦች የዘነቡበት፣ የሰው ልጅ እንደ ቅጠል የረገፈበት 75ኛ ዓመት ነው።
በሂሮሺማ የአቶሚክ ቦምብ ጥቃት ህይወታቸውን ያጡ ሲዘከሩ በእነዚህ የቦምብ ጥቃቶች ምን ያህል ሰዎች እንዳለቁ ትክክለኛ ቁጥር ባይኖርም ከሂሮሺማ 350 ሺህ ሕዝብ ውስጥ 140 ሺህዎቹ ሞተዋል። በናጋሳኪም እንዲሁ 74 ሺህዎች ተፈጅተዋል። በአውቶሚክ ቦምቡ ጥቃቱ ምክንያት ጃፓን በ1937 እጅ ሰጥታለች። እንዲሁም የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ክፍል የሆነውና በእስያ የነበረውን ጦርነት ማብቂያን ያበሰረ ነው ቢሉም አንዳንዶች በዚህ ሃሳብ አይስማሙም። ጃፓን እጅ ለመስጠት ዳር ዳር እያለች የነበረች ከመሆኑ አንፃር ሽንፈቷን ከአውቶሚክ ቦምብ ጥቃቱ ጋር ማያያዝ ትርጉም አልባ ነው ይላሉ። ማን ያውራ የነበረ? ማን ያርዳ የቀበረ እንዲሉ ከዚህ እልቂት የተረፉት ስለማይሽር ጠባሳቸውና ህመማቸው ይናገራሉ። የእልቂቱ ተራፊዎችም በጃፓናውያን ዘንድ ስም ተሰጥቷቸዋል፤ 'ሂባኩሻ' ይባላሉ። ተራፊዎቹም ከሞቱት በላይ ሆኑ እንጂ ያጋጠማቸው ችግርና ስቃይ እንዲሁ ዝም ብሎ በቃላት የሚነገር አይደለም። በጨረር በመመረዛቸው ለዘመናት የሚወልዷቸው ልጆች የአካል ጉዳት ያለባቸው እንዲሆኑ እንዲሁም ለሥነ ልቦና ጉዳት እንዲዳረጉ ምክንያት ሆኗል። የእንግሊዟ ፎቶ ጋዜጠኛ ሊ ካረን ስቶው የእልቂቱን የተረፈውን በፎቶ አስቀርታለች፤ እንዲሁም ትናንት የተፈጠረ በሚመስል ሁኔታ ከ75 ዓመታት በፊት የተፈጠረውንም ስቃይ ከሦስት ሴቶች አንደበት ሰምታለች። ቴሩኮ ኡኖ ነርስ ሆነው እያገለገሉ በነበረበት ወቅትና ከአራት አመት በፊት ቴሩኮ ኡኖ ዕለቱ ሐምሌ 30/1937 ዓ.ም ነበር፤ የአሜሪካ የጦር አውሮፕላኖች በሂሮሺማ ላይ የአውቶሚክ ቦምብ የጣሉት። በህይወት የተረፉት ቴሩኮ የ15 አመት ታዳጊ ነበሩ። በጥቃቱ ወቅት ቴሩኮ የሁለተኛ ዓመት የነርስ ተማሪ ነበሩ። ትምህርታቸውንም ይከታተሉ የነበረው ሂሮሺማ ሬድ ክሮስ በሚባል ሆስፒታል ውስጥ ነበር። በጥቃቱም የተማሪዎቹ ማደሪያ በእሳት ጋየ፤ ቴሪኮ እሳቱን ለማጥፋት ቢታገሉም የበርካታ ተማሪዎች ህይወት በእሳት አደጋው ተቀጠፈ። አንዳንድ ነገሮች እንደ ሩቅ ህልም ትዝ ቢሏቸውም፤ በዚያ ሳምንት በእሳት የተቃጠሉ ሰዎችንና አሰቃቂ አደጋዎችን በህይወት እያሉ አይረረሷቸውም። በሞትም ቢሆን የሚከተላቸው ይመስላቸዋል። እሳቸውን ጨምሮ በርካታ ነርሶች ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ህይወት ለማትረፍ ቀን ከሌት እየለፉ ነበር። ምግብም ውሃም ለሁሉም በቂም አልነበረም። ቴሩኮ ተመርቀውም በዚያው ሆስፒታል ሥራቸውን ቀጠሉ። በቃጠሎው ወቅት በሚደርስ አደጋ የሰውነት ቆዳቸው ለተለበለበ ግለሰቦች የሚደረገውን የቀዶ ህክምና ድጋፍም ማድረግ ጀመሩ። ቶሞኮ ከእናቷ ቴሩኮና ከአባቷ ታትሱዩኪ ጋር በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ቢሆን ህይወት ትቀጥላለችና ቴሩኮ ከአውቶሚክ ቦምም ፍንዳታ የተረፈውን ታትሱዩኪም ጋር በትዳር ተጣመሩ። የመጀመሪያ ልጃቸውንም ፀነሱ፤ አይናቸውን በአይናቸው ለማት ቢጓጉም ልጃቸው በጤና ትወለድ ይሆን? የሚለውም ሌላ ጭንቀት ነበር። በህይወትስ ትኖራለች? የሚለውም አሳሳቢ ሆነ። ልጃቸው ቶሞኮም ተወለደች፤ ለቴሩኮም ተስፋን ፈነጠቀችላቸው፤ ለቤተሰቡም የአዲስ ህይወት መመስረትን አበሰረች። "ሲዖልን ባላየውም በህይወታችን ያሳለፍነው ስቃይ ግን ሲዖል ተብሎ ሲነገር እንደሰማሁት ነው። መቼም ቢሆን ሊደገም የማይገባ ሰቆቃ ነው" ይላሉ ቴሩኮ። "የኒውክሊየር ጦር መሳሪያን ለማስወገድ አንዳንድ ሰዎች ጥረት ቢያደርጉም የመጀመሪያ ደረጃ ቁርጠኝነት የሚያስፈልገው ከመንግሥታት ነው። እነሱ ይህ ሊወገድ ይገባል ማለት አለባቸው" የሚሉት ቴሬኮ "የዓለም መንግሥታት ሁሉ በአንድነት የኒውክሊየር መሳሪያዎችን በመቃወም ትብብራቸውን ሊያሳዩ ይገባል" ይላሉ። ቴሩኮ ከልጃቸው ቶሞኮና ከልጅ ልጃቸው ኩኒኮ ጋር ከአራት አመታት በፊት "ለሰባ አምስት ዓመታት ያህልም ዛፍ፣ ሳርም አይበቅልም የተባለባት ሂሮሺማ በአሁኑ ጊዜ አረንጓዴ ሆናለች። የከተማዋ ወንዞች ከእጸዋቱ ጋር ውብ አድርገዋታል" ትላለች የቴሩኮ ልጅ ቶሞኮ። ምንም እንኳን ከተማዋ ተመልሳ ውበቷን ብትጎናፀፍም "ሂባኩሻ" [ከቦምቡ ጥቃት የተረፉት] በጨረሩ መርዛማነት እየተሰቃዩ ነው። ሰቆቃቸውም ለልጅ ልጅ ተርፏል። "የሂሮሺማና ናጋሳኪ ቦምብ ጥቃት ትዝታዎች ከአዕምሯችን ቢደበዝዝም አሁንም መስቀለኛ መንገድ ላይ ነን።" "የወደፊቱ ዕጣ ፈንታችን በእጃችን ነው። ሰላም እውን የሚሆነው እሳቤያችንን ሰፋ ስናደርገው ነው። ለሌሎች ማሰብ ስንጀምር፤ እሱንም እውን ለማድረግ የሚጠበቅብንን ስንተገብር ነው። ሰላምን ለመገንባት የማያሰልስ ጥረት ያስፈልጋል" በማለት የቴሩኮ የልጅ ልጅ ኩኒኮም ታስረዳለች። "የአውቶሚክ ቦምቡ ገፈት ቀማሽ አይደለሁም፤ ሂሮሺማን የማውቃት እንደገና ከተገነባች በኋላ ነው። ግን ምን አይነት ዘግናኝና አሰቃቂ እልቂት እንደነበር መገመት እችላለሁ" ትላለች። ከእልቂቱ የተረፉትን ታዳምጣለች። በዚያች ቀን ከተማዋ እንዴት እንደጋየች፣ ሰዎች፣ ወፎች፣ ዛፍ፣ ሳርና ቅጠሉ ሳይቀር እንደተቃጠለም ነግረዋታል። ሂሮሺማ ከአቶሚክ ቦምብ ጥቃቱ በኋላ የከተማዋ ነዋሪዎች ብቻ አይደሉም፤ ለእርዳታ የመጡ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ሞተዋል። ቤተሰቦቻቸውን፣ ዘመድ፣ ጓደኛ ፍለጋ ከሌላ ከተሞች የመጡ እንዲሁ አልቀዋል። የተረፉትም ለማይድን ህመም ተጋልጠዋል። ኩኒኮ ከሂሮሺማና ናጋሳኪ የተረፉትን ብቻ ሳይሆን በዩራኒየም ማዕድን ቁፋሮ የሚሰሩ፣ በማዕድን ማበልፀጊያ አካባቢ የሚኖሩ፣ የኒውክሊየር መሳሪያዎችን የሚሞክሩና፣ በዚህም ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰቃዩ ሰዎችም ዕጣ ፈንታ ተመሳሳይ ከመሆኑ አንፃር ከእነሱም ጋር ያላት ግንኙነት ጠበቅ ያለ ነው። ኤሚኮ ኦካዳ ኤሚኮ ኦካዳ በአለም ላይ ያሉ የኒውክሊየር ጦር መሳሪያዎችን ቁጥር የያዘ ግራፍ እያሳዩ በሂሮሺማ ላይ የአውቶሚክ ቦምብ ሲጣል ኤሚኮ የስምንት ዓመት ልጅ ነበሩ። በፍንዳታውም ታላቅ እህታቸው ሚየኮን ጨምሮ አራት የቤተሰባቸው አባላት ተገድለዋል። እህታቸው ኤሚኮንም ሆነ ሌሎች ቤተሰባቸውን ፎቶ ዘመድ ቤት ሲያዩ ያ ጨለማ ጊዜ ድቅን ይልባቸዋል። ኤሚኮ ከእናታቸው ፉኪ ናካሶና ከእህታቸው ሚዬኮ ጋር የዚያችን ዕለት እህታቸው በጠዋት ተነስታ "በኋላ እንገናኝ" ብላ እየፈነደቀች ወጣች። "ገና አስራ ሁለት ዓመቷ ነበር። ፈገግታ የማይለያት፤ ህይወትን በተስፋ የምታይ ልጅ ነበረች" ይላሉ ኤሚኮ። ነገር ግን ከወጣችበት አልተመለሰችም፤ የት እንደደረሰችም አልታወቀም። ቤተሰቦቿም ለዓመታትም ተስፋ ሳይቆርጡ እናገኛታልን ብለው ካሰቡበት ቦታ ሁሉ ፈለጓት። አስከሬኗንም አላገኙ። እናም በህይወት ትኖራለች በማለትም በተስፋ መኖር ጀመሩ። በወቅቱም የኤሚኮ እናት ነፍሰ ጡር ነበሩ፤ ነገር ግን ትንሽ ቆይቶ በሚያሳዝን ሁኔታ ፅንሱ ጨነገፈ። "በቤታችን የሚላስ የሚቀመስ አልነበረም። ስለ ጨረሩ የምናውቀው ነገርም ስላልነበረ ተመረዘ አልተመረዘ ያገኘነውን ዕቃም ሆነ ምግብ መሰብሰብ ጀመርን" ይላሉ። በእነዚያ ተስፋ አስቆራጭ ቀናትም ሰዎች የሚበሉት ሲያጡ ምግብም ይሰርቁ ነበር፤ "ውሃማ ብርቅ ነበር" ይላሉ። ያ አስቸጋሪ ጊዜ አሁን ተረስቷል። የኤሚኮ እህት ሚዬኮ የጃፓን ባህላዊ ዳንስ ቡዮን እየደነሰች ከትንሽ ጊዜያት በኋላ አስደንጋጭ ነገር መከሰት ጀመረ። የኤሚኮ ፀጉራቸው ይረግፍ ጀመ፣ ድዳቸው ያለማቋረጥ ይደማል እንዲሁም ያለ ምክንያትም መድከም አመጡ። "በወቅቱ በጨረር መመረዝ ምን እንደሆነ አናውቅም ነበር። ከአስራ ሁለት ዓመታት በኋላ ነው የደም ህዋሳቶቼ በትክክል ማመንጨት እንደማይችሉ የተነገረኝ" ይላሉ። በሂሮሺማ በየዓመቱ ጥቂት ቀናት ፀሐይዋ ስትጠልቅ ደማቅ ቀይ ቀለም ሰማይ ላይ ይታያል። ከመድመቋ የተነሳ የሰዎችም ፊት ወደቀይነት ይቀየራል። ይህም ሁኔታ አስደሳች ቢመስልም ለእሳቸው ግን ወደኋላ ይወስዳቸውና፤ ከተማዋ የተቃጠለችበት ሁኔታ ድቅን ይልባቸዋል። "ለሦስት ቀናት ያህል ከተማዋ ስትቃጠል ነበር፤ ለዚያም ነው ያንን የሚያስታውሰኝን ሁሉ የምጠላው። ፀሐይዋ ስትጠልቅ ማየት አልፈልግም፤ በከፍተኛ ሁኔታ ነው የምጠላው" ይላሉ። ከቦምቡ ጥቃት የተረፉት በርካቶች ታሪካቸውንም ሳይነግሩ፤ እንደተማረሩ ህይወታቸው አልፏል። "እነሱ መናገር ባይችሉም እኔ የነበረውን እናገራለሁ" ይላሉ። "በርካቶች ዓለም ሰላም እንድትሆን ምኞታቸውን ይናገራሉ። ለእኔ ግን የሚቀድመው ድርጊት ነው። የዓለም ሕዝቦች ማድረግ የምንችለውን መፈፀም አለብን።" "እኔም ብሆን ለልጆቼና ለልጅ ልጆቼ የተሻለ ህይወት እንዲመሩ፤ በደስታ እንዲኖሩ የምችለውን ማድረግ አለብኝ።" ሬይኮ በአምስት አመታቸውና ከአራት አመታት በፊት ሬይኮ ሃዳ የትውልድ ቀያቸው ናጋሳኪን አውቶሚክ ቦምቡ እንዳልነበረ ሲያፈራርሳት ሬይኮ የዘጠኝ ዓመት ታዳጊ ነበሩ። ዕለቱ ነሐሴ 3/1937 ከረፋዱ አምስት ሰዓት ገደማ ነበር። ያስታውሳሉ ዕለቱ ሐሙስ ነበር። በጠዋትም በአየር ጥቃት ዙሪያ አንዳንድ ማስጠንቀቂያዎች ይተላለፉ ስለነበር ሬይኮም ቤታቸው እድብ ብለው ተቀመጡ። ማስጠንቀቂያው ሲቆምም አካባቢያቸው ወደሚገኝ ምኩራብ አመሩ። የአየር ጥቃት ይደርሳል የሚሉ ማስጠንቀቂያ በተደጋጋሚ በመነገሩ ልጆች ትምህርት ቤት መሄድ አቁመው ነበር። ጊዜያቸውንም በምኩራብ ውስጥ በማጥናት ያሳልፉ ነበር። ሬይኮ ወደ ምኩራቡ ከደረሱ ከአርባ ደቂቃ በኋላ መምህራቸው አሰናበቷቸው፤ ሬይኮም ወደቤታቸው አቀኑ። ቤት ሊገቡ ሲሉ "ደረጃውን ወጥቻለሁ መሰለኝ። ድንገት የሆነ ድብልቅልቅ ያለ ነገር ተፈጠረ። በቃላት መግለፅ የማይቻል የብርሃኑ ድምቀት አይንን የሚያጥበረብር ቀለማት ማየት ጀመርን። ቢጫ፣ ብርቱካናማ፣ . . . ሁሉም ተደባልቆ እንደ ህልም አየን።" "ምን እንደሆነ እንኳን ለማሰብ ጊዜ ሳላገኝ ሁሉ ነገር ነጭ ሆነ።" "ከዚያም ብቻዬን የቀረሁ መሰለኝ። ከዚያም ከፍተኛ ድምፅ አምባረቀ፤ ሁሉ ነገር ፀጥ ረጭ አለ። እኔም አቅሌን ስቼ ወደቅኩ።" በአቶሚክ ቦምቡ የፈራረሰችው የናጋሳኪ ከተማ ከዚያም ድንገት ሲነቁ መምህራቸው ያላቸው ነገር ትዝ አላቸው። በአየር ጥቃት ወቅት ወደተዘጋጁት ድንገተኛ መሸሸያ ቦታዎች ማምራት። እናታቸውን ቤት ውስጥ አገኟቸውና ተያይዘውም በአቅራቢያቸውም ወዳለ መጠለያ አመሩ። "ምንም መቧጨር እንኳን አልደረሰብኝም። የኮንፒራ ተራራ አድኖኛል። በተራራው ሌላ ክፍል የሚኖሩት ግን እንደኛ እድለኛ አልነበሩም በከፍተኛ ሁኔታ ጉዳት ደርሶባቸዋል።" በርካቶችም ተሰደው ወደእነሱ አካባቢ መጡ። ሁኔታቸው የሚዘገንን ነበር። "አይናቸው የተጎለጎለ፣ ፀጉራቸው የተቃጠለ፤ እርቃናቸውንና ብዙዎቹም ሰውነታቸው ተቃጥሎ ቆዳቸው ተንጠልጥሎ ነበር" በማለት ያስታውሳሉ። እናታቸውን ጨምሮ የአካባቢው ማኅበረሰብ እናቶች ጥቃት የደረሰባቸውን ሰዎች አቅራቢያቸው ወደሚገኘው የንግድ ኮሌጅ አዳራሽ ወሰዷቸው። እዚያም አረፍ እንዲሉ አደረጓቸው። ሬይኮ ከአባታቸው ኬዚዮ ኡራና ታላቅ እህታቸው ሺዙዬ ኡራ "ውሃ ጠማን ይላሉ። ውሃም እንዳመጣም ታዘዝኩ። የተሰባበረ ባሊ አገኘሁና ቅርብ ወዳለ ወንዝ ሄጄ ቀድቼ መጣሁ።" "ውሃውን እንደጠጡትም ብዙዎቹ ሞቱ። . . . አንድ በአንድ ሞቱ።" "ወቅቱ ሞቃታማ ነበር ። አስከሬናቸው እተበላሸ ጠረን በማምጣቱ እንዲቃጠል ተደረገ። አስከሬናቸው በኮሌጁ መዋኛ ገንዳ ተከምሮ ነበር። እንጨትም ተሰብስቦ ነደደና ተቃጠ፤ አመድም ሆኑ።" "እነዚህ ሰዎች እነማን እንደሆኑ ማወቅ ይከብዳል። እንደ ሰው ልጆች በክብር አልሞቱም።" "የወደፊቱ ትውልድ መቼም ቢሆን እኛ ባለፍንበት መንገድ ማለፍ የለበትም። መቼም ቢሆን፤ በጭራሽ የኒውክሊየር ጦር መሳሪያዎች ጥቅም ላይ እንዲውሉ መፍቀድ የለብንም።" "ሰላምን የሚፈጥሩት ሰዎች ናቸው። ምንም እንኳን በተለያዩ አገራት ብንኖርም፣ የተለያዩ ቋንቋዎችን ብንናገርም ሰላም እንዲሰፍን ያለን ምኞት ተመሳሳይ ነው።" ሬይኮ ሃዳ
news-57306933
https://www.bbc.com/amharic/news-57306933
ግብጽ ከየትኞቹ የአባይ ተፋሰስ አገራት ጋር ወታደራዊ ስምምነት ተፈራረመች?
ኢትዮጵያ እየገነባችው ያለው ግዙፉ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ከአባይ ወንዝ የምታገኘውን የውሃ መጠን ይቀንስብኛል በማለት ስጋቷን ስትገልጽ የቆየችው ግብጽ ጥቅሟን ለማስጠብቅ የተለያዩ ጥረቶችን ስታደርግ ቆይታለች።
የኬንያ መከላከያ ሚኒስትር ሞኒካ ጁማ ከግብጽ ኤታማዦር ሹም ሌፍተናንት ጄነራል ሞሐመድ ፋሪድ ሃጋዚ ጋር የመከላከያ ስምምነት ባለፈው ሳምንት ሲፈራረሙ ለዓመታት ሲካሄድ የቆየውን የመጨረሻ ስምምነት ሳይደረስበት በእንጥልጥል የቆየው ግድቡን የሚመለከተው ድርድር ሳይቋጭ ኢትዮጵያ ሁለተኛውን ዙር የውሃ ሙሌት ለማካሄድ ተቃርባለች። በዚህ ጊዜ ሁሉ ግብጽ የአባይ ተፋሰስ አገራትን ከጎኗ ለማሰለፍ የተለያዩ ጥረቶችን ስታደርግ ቆይታለች። ከዚህ አንጻር ግብጽ በኢትዮጵያ ዙሪያ ከሚገኙ አገራትና ከአባይ ተፋሰስ አገራት ጋር በተለያዩ መስኮች ያላትን ትብብር ለማጠናከርና አዳዲስ ስምምነቶች ላይ ለመድረስ በከፍተኛ ባለሥልጣናቷ የሚመሩ ልዑካንን ስታሰማራ ቆይታለች። ግብጽ ከአገራቱ ጋር ካደረገቻቸው ስምምነቶች መካከል የወታደራዊ ትብብር ስምምነቶች ተጠቃሾች ናቸው። በዚህም በተለይ ከአባይ ተፋሰስ አገራት ጋር በተለያየ ደረጃ የሚገለጽ ወታደራዊ ስምምነቶችን አድርጋለች። ለመሆኑ ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ዙሪያ ውዝግቡት ውስጥ በሚገኙበት ወቅት ግብጽ ከየትኞቹ የተፋሰሱ አገራት ጋር ወታደራዊ ስምምነት ተፈራረመች? ሱዳን ባለፈው መጋቢት ወር የግብጽ ጦር ዋና አዛዥ ሌፍተናንት ጄኔራል ሞሐመድ ፋሪድ ወደ ካርቱም አቅንተው አገራቸውን በመወከል ከሱዳን ጋር ወታደራዊ ስምምነት ተፈራርመዋል። ግብጽ "ከሱዳን ጋር በሁሉም መስኮች በተለይም በወታደራዊ እና በደኅንነት መስኮች ግንኙነቷን ለማጠናከር እንደምትፈልግ" አመልክተው፤ ሱዳን እና ግብጽ የጋራ ፈተናዎች እንዲሁም የብሔራዊ ደኅንነት ስጋት እንደሚገጥማቸው ፋሪድ በወቅቱ አስታውቀዋል። በተጨማሪም ከሱዳን ጋር ከወታደራዊ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን በሙሉ ለማሟላት ካይሮ ዝግጁ መሆኗን በመግለጽ የወታደራዊ ትብብሩን ደረጃም "ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታውቅ" ብለውታል። የሱዳኑ አቻቸው ሌፍተናት ጄኔራል ሞሐመድ ኦትማን አል ሁሴን "የስምምነቱ ዓላማ የሁለቱ አገራት ብሔራዊ ደኅንነትን ማስከበር እና በልምድ እና በዕውቀት የደረጀ ኃይል ለመገንባት ነው" በማለት፤ ሁሴን በአስቸጋሪ ጊዜያት ግብጽ ከሱዳን ጎን በመቆየቷ አመስግነዋል። ግብጽ እና ሱዳን በቅርቡ "የአባይ ንስሮች 1" እና "የአባይ ንስሮች 2" የተባሉ የጋራ ወታደራዊ ልምምዶችን አካሂደዋል። ከሰሞኑም የስድስት ቀን የጋራ ወታደራዊ ልምምድ አካሂደው ማጠናቀቃቸውን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ኬንያ ኬንያ ከግብጽ ጋር በመከላከያ ትብብር ላይ የቴክኒክ ስምምነት ከቀናት በፊት ነበር የደረሰችው። የኬንያ መከላከያ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ የመከላከያ ሚኒስትሯ ሞኒካ ጁማ እና የግብጹ ዋና አዛዥ ሌፍተናንት ጄኔራል ሞሐመድ ፋሪድ ሄጋዚ ተገናኝተው ስምምነቱን መፈራረማቸውን አመልክቷል። ሚኒስትሩ "በሁለትዮሽ የመከላከያ ውይይት ወቅት አገራቱ በጋራ ተጠቃሚነት ጉዳዮች ላይ አጋርነታቸውን የበለጠ ለማሳደግ የሚያስችል የመከላከያ የቴክኒክ ስምምነት ተፈራረሙ" ብሏል። ስምምነቱ ምን ምን ጉዳዮችን እንደሚይዝ ግን ተጨማሪ መረጃ ይፋ አልተደረገም። ጂቡቲ ግብጽ እና ኬንያ ከስምምነት ከደረሱ ከቀናት በኋላ ጂቡቲ የደረሱት ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል-ሲሲ፤ ጂቡቲ ነጻነቷን ካወጀች በኋላ አገሪቱን የጎበኙ የመጀመሪያው የግብጽ ፕሬዝዳንት ሆነዋል። አል-ሲሲ እና የጂቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጉሌህ የሕዳሴው ግድብ አካባቢያዊ መረጋጋትን ለማስጠበቅ እና የሁሉንም ወገኖች ጥቅም ለማስከበር የሚያስችል ፍትሃዊ ስምምነት ላይ እንዲደረስ እንደሚፈልጉ መመካከራቸው ተገልጿል። አል-ሲሲ ከጉሌህ ጋር ያደረጉትን ውይይት "ገንቢና ፍሬያማ" ሲሉ ያወደሱ ሲሆን ሁለቱም መሪዎች የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ወታደራዊ ትብብርን ማሻሻል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን አብራርተዋል። ሁለቱም መሪዎች በአፍሪካ ቀንድ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ስላላቸው "ስትራቴጂያዊ አጋርነት" አፅንኦት ሰጥተዋል። ከቀናት በፊትም ሁለት የግብጽ ወታደራዊ አውሮፕላኖች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የህክምና እርዳታዎችን ጭነው ጂቡቲ ደርሰዋልም ተብሏል። ጂቡቲ የአባይ ተፋሰስ አገር ባትሆንም ከፍተኛ መጠን ያለው የኢትዮጵያ ወጪና ገቢ ንግድና ምርቶች የሚተላለፉባት ቁልፍ አገር መሆኗ ይታወቃል። የግብጽና የሱዳን ወታደራዊ ባለሥልጣናት ዲሞክራቲክ ኮንጎ ግብጽ ከተለያዩ የናይል ተፋሰስ አገራት ጋር ካደረገችው ወታደራዊ ስምምነት በተቃራኒ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር በኢንቨስትመንት ላይ ያተኮረ ስምምነት ደርሳለች። የኮንጎ ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ትሺከዲ የካቲት 2 ቀን የካይሮ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት የግብጽ እና የኮንጎ መንግሥታት የመሠረተ ልማት፣ የኃይል እና የመጠጥ ውሃን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ስምምነቶችን ተፈራርመዋል። የኮንጎ መንግሥትም በማዕከላዊ ኮንጎ ውስጥ በሳንቡሩ ጠቅላይ ግዛት በሉቢ ወንዝ ላይ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ማዕከል ለመገንባት ከግብጽ ኩባንያዎች ጋር ከስምምነት ደርሷል። ፌሊክስ ትሺከዲ የግብጽ ኩባንያዎች በኮንጎ በተለይም በግንባታ፣ በኢነርጂ እና በመሠረተ ልማት ዘርፎች የሚጫወቱትን ሚና አወድሰዋል። ፕሬዝዳንቱ ከግብጹ አቻቸው ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ጋር የካቲት 2 ቀን ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት በኮንጎ የግብጽ ኢንቨስትመንቶችን እና የንግድ ልውውጥን ለማሳደግ ስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል፡፡ ሩዋንዳ የግብጽ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ሌፍተናንት ጄኔራል ሞሐመድ ፋሪድ እአአ ከግንቦት 27 እስከ 29 ድረስ በሩዋንዳ ጉብኝት አድርገው ነበር። ጉብኝቱን ተከትሎም ግንቦት 29 በተሰጠው መግለጫ ሌፍተናል ጄኔራል ሞሐመድ ፋሪድ እና የልዑካን ቡድናቸው በሩዋንዳ መከላከያ ሠራዊት ዋና መሥሪያ ቤት ከመከላከያ አዛዡ ጄኔራል ጄን ቦኮ ካዙራ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸው ተነግሯል። በውይይቶቹ ቀደም ሲል የነበሩትን ወታደራዊ ትብብሮች በማጎልበት ላይ ያተኮሩ መሆናቸውን ተገልጾ ነበር። ሩዋንዳ እና ግብጽ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር እና በኢኮኖሚ እና በንግድ፣ እንዲሁም በመከላከያ እና በደኅንነት የጋራ ጥቅሞችን ለማጎልበት በሚያስችሉ መንገዶች ላይ ሲሠሩ ቆይተዋል ተብሏል። ሩዋንዳ ከዚህ ቀደም ተማሪዎቿን ለወታደራዊ ትምህርት ወደ ግብጽ ስትልክ ቆይታለች። ደቡብ ሱዳን ግብጽ ከደቡብ ሱዳን ጋር በወታደራዊ መስክ በቅርቡ ስለደረሰችው ስምምነት ምንም መረጃ ማግኘት አልተቻለም። ይልቁንም ደቡብ ሱዳን ከአንድ ዓመት በፊት በድንበሯ ውስጥ ግብጽ ወታደራዊ ካምፕ ለማቋቋም ያቀረበችውን ጥያቄ አጸደቀች መባሉን አስተባብላለች። የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴሩ ለአናዱሉ የዜና ወኪል በወቅቱ "እንደዚህ ዓይነት ነገር የለም" ብለው ነበር። "በደቡብ ሱዳን ግዛት ውስጥ ለግብጽ ወታደራዊ ሥፍራ ቅንጣት መሬት ለመመደብ ከስምምነት አልተደረሰም።" ግብጽ በፓጋክ ወታደራዊ ካምፕ ለመገንባት ያቀረበችውን ጥያቄ የደቡብ ሱዳን መንግሥት ስለመስማማቱ በማኅበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ በስፋት ተነግሮ የነበረ ቢሆንም ደቡብ ሱዳን ጉዳዩን አስተባብላለች። ፓጋክ በደቡብ ሱዳን የላይኛው ናይል ግዛት ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የሚገኝ ከተማ ነው። ቡሩንዲ የግብጽ እና የቡሩንዲ መከላከያ ኃላፊዎች ከወራት በፊት ካይሮ ተገናኝተው በስልጠና እና የጋራ ልምምድ መስኮች ትብብርን የሚያካትት ወታደራዊ ስምምነት ተፈራርመዋል። የትብብር ስምምነቱ ሁለቱ አገራት ባለሙያዎችን ለመለዋወጥ የሚያስችላቸው ነው ተብሏል። ይህም በሁለቱ አገራት ሠራዊት መካከል የጋራ መግባባት በሚፈጥሩ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን መተባበር የሚያንፀባርቅ መሆኑን የግብጽ ጦር ኃይል ቃል አቀባይ ማስታወቃቸውን ኢጅፕት ቱዴይ ዘግቦ ነበር። የቡሩንዲ ጦር ኃይሎች አዛዥ ፕራይም ኒዮንጋቦ በግብጽ ይፋዊ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን ስለሁለትዮሽ ትብብር ከግብጽ ጦር ዋና አዛዥ ሞሐመድ ፋሪድ ጋር ተገናኝተው መክረዋል። ፋሪድ እና ኒዮንጋቦ በሁለቱ አገራት መካከል በተለያዩ መስኮች ወታደራዊ ትብብርን ስለማሳደግ መወያየታቸው በወቅቱ ተነግሯል። ታንዛንያ ታንዛንያ እና ግብጽ በወታደራዊ መስክ ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ የሚያግዝ ውይይት ያደረጉት ከዓመት በፊት ነበር። የታንዛኒያ የመከላከያ እና ብሔራዊ አገልግሎት ሚኒስትር ሁሴን ምዊኒ አገራቸው ከግብጽ ጋር በተለያዩ መስኮች ግንኙነቷን ለማጠናከር ፍላጎት አንዳላት በወቅቱ ገልጸው ነበር። ሚንስትሩ ከግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አል-ሲሲ ጋር የአገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር ሞሐመድ ዛኪ እና በግብጽ የታንዛኒያ አምባሳደር በተገኙበት ውይይት ማድረጋቸው ተዘግቧል። ምዊኒ በሁለቱ አገራት የመከላከያ ሚኒስትሮች መካከል በተለይም ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ትብበራቸውን ለማሳደግ ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል። በተጨማሪም ታንዛኒያ የግብጽ የታደራዊ ማምረቻ ኩባንያዎችን የቴክኖሎጂ እና የሰው አቅም የመጠቀም ፍላጎት እንዳላት አመልክተዋል። ፕሬዚዳንት ሲሲ በበኩላቸው ከታንዛኒያ ጋር የተደረገውን ወታደራዊ ትብብርን በደስታ እንደተቀበሉ በወቅቱ ገልጸዋል። ኡጋንዳ ግብጽ እና ኡጋንዳ በወታደራዊ መረጃ ማጋራት ዙሪያ የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረሙት ከሁለት ወራት በፊት ነው። በኡጋንዳ ወታደራዊ የደኅንንት ኃላፊ አቤል ካንዲሆ እና በግብጹ ወታደራዊ ደኅንነት ጄኔራል ሳሜህ ሳበር ኤል-ደግዊ የተፈረመው ስምምነት ሁለቱ አገራት "ሽብርተኝነትን መዋጋትን" ጨምሮ መረጃዎችን መለዋወጥን ያካትታል ተብሏል። ሳሜህ ሳበር ኤል-ደግዊ በወቅቱ "ኡጋንዳ እና ግብጽ አባይን የሚጋሩ በመሆናቸው በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ትብብር የማይቀር ነው ምክንያቱም ኡጋንዳውያንን የሚነካው ነገር በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ግብጽን ይነካል" ብለው ነበር።
54597783
https://www.bbc.com/amharic/54597783
ዐብይ አሕመድ፡ ጠ/ሚር ዐብይ ከሕወሓት ጋር የተከሰተው አለመግባባት "በሕግ እና ሕግ ብቻ የሚመለስ ይሆናል" አሉ
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ ተካሂዷል። በዚሁ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።
ጠቅላይ ሚንሰትሩ ማብራሪያ ከሰጡባቸው ጉዳዮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል። ምጣኔ ሃብት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ባለፈው ዓመት በኢትዮጵያ የ6.1 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት መመዝገቡን ይፋ አድርገዋል። የኢንደስትሪ ዘረፉ ደግሞ ከፍተኛውን እድገት ካስመዘገቡ ዘርፎች መካከል ቀዳሚው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ2012 የበጀት ዓመት 3.37 ትሪሊየን ብር ጠቅላላ አገራዊ ምርት መመዝገብ መቻሉንም ተናግረዋል። የነፍስ ወከፍ ገቢም 1ሺህ ዶላር መድረሱን ተናግረው፤ ይህም መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ ኢትዮጵያን ማሰለፏን እንደሚያረጋግጥ ጠቅላይ ሚንስትሩ ይፋ አድርገዋል። በትግራይ እና በፌደራል መንግሥት መካከል ስላለው ግነኙነት በትግራይ እና በፌደራል መንግሥት መካከል ያለው ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተካረረ መጥቷል። ጠቅላይ ሚንስትር የትግራይ ሕዝብ በከፍተኛ ችግር እና ድህነት ውስጥ ያለ ሕዝብ ነው፤ "በሠላም እና ልማታዊ ሆኖ የመኖር መብት አለው። መለወጥ ይፈልጋል' ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ከክልሉ ጋር የተከሰተው አለመግባባት "በሕግ እና ሕግ ብቻ የሚመለሰው ይሆናል" ያሉ ሲሆን የፌዴሬሽን እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚሰጡት ውሳኔ ላይ ብቻ በመመሠረት ጉዳዩ በሕግ የሚመለስ መሆኑን ተናግረዋል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስለሚፈጸሙ ግድያዎች ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚከሰቱት ጥቃቶች ውስብስብ መሆናቸውን በሰጡት ምላሽ ወቅት አብራርተዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በክልሉ ያለው አለመረጋጋት ከሕዳሴ ግድብ ጋር እንደሚገናኝም ጠቁመዋል። "ከሕዳሴ ጋር ይገናኛል። የሕዳሴን መንገድ መቁረጥ ጋር ይያያዛል" ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ችግር በሚያጋጥምባቸው ስፍራዎች የመኪና መንገድ አለመኖሩንም ጨምረው ተናግረዋል። በዚም ምክንያት የመከላከያ ሠራዊት አባላት ጥቃት የተፈጸመበት ቦታ ለመድረስ እስከ 7 ሰዓት ድረስ በረዣዥም ሳር ውስጥ በእግራቸው እንደሚጓዙ አስረድተዋል። "ጥቃቱ የሚፈጸመው በቀስት ነው። ሳቫና ግራስ ላንድ ውስጥ። ብዙ መስዋእትነት ተከፍሏል" ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች መማረካቸውን እና ብዙዎቹ ጥቃት አድራሾች ደግሞ መሸሻቸውን ተናግረዋል። "ችግሩ አሁንም ከምንጩ ካልደረቀ ችግር [ዳግም] ይከሰታል" ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ መንግሥታቸው ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት እንደሚሰራ ተናግረዋል። የገንዘብ ኖት ለውጥ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ባለፉት ሶስት ወራት መንግሥታቸው ካከናወነው ስኬታማ ሥራዎች መካከል የብር ኖት ለውጡ አንዱ መሆኑን አስታውሰዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ የገንዝብ ለውጥ ውስጥ የነበረውን የሥራ ሂደት አስታውሰው በ31 ቻርተር አውሮፕላን አዲሱ የገንዘብ ኖት ወደ አገር ውስጥ መግባቱን ተናግረዋል። የሥራ ሂደቱም ከፍተኛ ጥንቃቄ እና በሚስጥር ተጠብቆ መቆየቱን አብራርተዋል። አዲሱ የገንዘብ ኖት በ6ሺህ 628 የባንክ ቅርንጫፎች ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ መሰራጨቱን ተናግረዋል። 1.3 ሚሊዮን ሰዎች አዲስ የባንክ አካውንቶች መከፈታቸውን እና በእነዚህ የባንክ አካውንቶች 37 ቢሊዮን ብር ተቆጥቧል ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህ ሥራ ሲሰራ የጎላ ችግር አንዳላገጠመ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ከፍተኛ የገንዘብ መጠን የመቀየሪያ ጊዜ ማብቃቱን አስታውሰው አነስተኛ መጠን ያለውን የብር ኖት መቀየር ሥራ ይቀጥላል ብለዋል። "እጅግ የተሳካ ሥራ ነው የተሰራው" ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፣ ለባንኮች እና የመንግሥት የጸጥታ አካላት እንዲሁም ብሔራዊ ባንክ እና የማክሮ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ቡድን ለሠሩት ስኬታማ ሥራ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ባንክ በተያያዘ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በኢትዮጵያ የባንኮች ቁጥር መጨመሩን ተናግረው፤ የባንኮች መጨመር ቁጠባን ከፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ምንም እንኳን የባንኮች ቁጥር ከፍ ይበል እንጂ ዲጂታል ባንኪንግ የሚፈለገውን ያክል ለውጥ አለማምጣቱን ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ የባንኮችን የካፒታል አቅም ከፍ እንዲል እና ግዙፍ ባንኮች እንዲፈጠሩ ይሰራል ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም አነስተኛ እና ጥቃቅን የፋይንስ ተቋማት ወደ ባንክ ደረጃ ከፍ እንዲሉ መንግሥታቸው ጥረት እንደሚያደርግ አስታውቀዋል። የዋጋ ግሽበት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ መግሥታቸው ተጨማሪ ሥራ የሚጠይቀው የዋጋ ግሽበት መጠኑን ዝቅ ማድረግ መሆኑን ተናግረዋል። "ሰፊ ሥራ የሚፈልገው የዋጋ ግሽበት ነው። ባለፉት ሶስት ወራት መቀነስ ያመላክታል። ግን ይህ በቂ አይደልም" ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሩ። እንደማሳያም፤ ምግብ ነክ ባልሆኑ ሸቆጦች ላይ ባለፈው ሐምሌ የነበረው የዋጋ ግሽበት መጠን 22 በመቶ፣ ነሐሴ ወር 20 በመቶ እንዲሁም መስከረም ወር 18.7 በመቶ መሆኑን አመልክተዋል። ባለፉት ሶስት ወራት ምግብ ነክ ባልሆኑ ሸቆጦች የተመዘገበው የግሽበት መጠን እየቀነስ ቢሆንም ይህ ግን በቂ አለመሆኑን አስምረውበታል። በምግብ ምርቶች ላይም በተመሳሳይ ባለፉት ሶስት ወራት የዋጋ ግሽበት መጠኑን እየቀነሰ ቢሆንም በቂ አለመሆኑን ተናግረዋል። ሐምሌ ወር 24.9 በመቶ፣ ነሐሴ ወር 22 በመቶ እንዲሁም መስከረም ላይ ደግሞ 21 በመቶ መሆኑን አመልክተዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የዋጋ ግሽበቱን መጠን ለመቀነስ በቅድሚያ ለዋጋ ግሽበቱ ገፊ ምክንያቶች ምንድናቸው የሚለውን መለየት ያስፈልጋል ብለዋል። የግብርና ምርት ውጤቶችን ማሳደግ ደግሞ ሌላው የዋጋ ግሽበቱ መጠን ለመቆጣጠር ሌላኛው መፍትሄ መሆኑን ተናግረዋል። ሉዓላዊ አገር ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ኢትዮጵያ የትኛውንም አይነት ጥቃት የመከላከል አቅም እንዳለት ተናግረዋል። ባለፉት ሁለት ዓመታት የተለያዩ የሪፎርም ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል። "መከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ የትኛውንም ጥቃት የመከላከል አቋም ላይ ይገኛሉ" ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሩ። ፍትሕ የፍትህ ስርዓቱ ነጻ እና ገለልተኛ መሆን አለበት ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ሰኔ 16፣ ሰኔ 15 እና ሰኔ 23 የተያዙ ጉዳዮች የደረሱበትን ደረጃ አብራርተዋል። በጠቅላይ ሚንስትሩ ድጋፍ በተጠራው ሰልፍ ላይ ለተደረው "የግድያ ሙከራ" ወንጀል ክስ በተመሰረተባቸው ግለሰቦች ላይ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን በሙሉ መስማታቸውን ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል። ተከሳሾችም መከላከያዎቻቸውን ማቅረባቸውን ተናግረው በቅርቡ ብይን ይሰጣል ተብሎ እንደሚተበቅ ተናግረዋል። ሰኔ 15 በአዲስ አበባ እና በአማራ ክልል በከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ላይ የተፈጸውን ግድያ ተከትሎ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሰዎች የክስ ሂደት የደረሰበትን ደረጃም ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል። በአዲስ አበባ በቁጥጥር ሥር በዋሉት ተከሳሾች ዙሪያ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ሙሉ ለሙሉ መሰማታቸውን ተከሳሾችም መከላከያዎቻቸውን እያሰሙ መሆኑን ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል። በአማራ ክልል ለተከሰተው ወንጀልንም በተመለከተ ሲናገሩ ዐቃቤ ሕግ ምስክሮቹን እያሰማ ይገኛል ብለዋል። ሰኔ 23 ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ተከትሎ ከተፈጠረው ሁከት ጋር በተያያዘ 114 የክስ መዝገቦች መከፈታቸውን ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ተናግረው፣ በመዝገቦቹ ላይ የወንጀል ክስ መመሠረት ስራ ከሞላ ጎደል ተከናውኗል ብለዋል። ይሁን እንጂ የዳኛ እጥረት እና የኮሮናቫይረስ ስርጭት በፍትሕ ስርዓቱ ላይ ፈተና ሆኖ እንደነበረ ተናግረዋል። የእዳ መጠን ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በአገሪቱ የሚገኙ ግዙፍ ኩባንያዎች ከ600 ቢሊዮን ብር በላይ እዳ ተከማችቶባቸው እንደነበረ ተናግተዋል። እነዚህ ኩባንያዎች ከአገሪቱ በጀት በላይ እዳ ውስጥ ተዘፍቀው እንደነበረ ተናግረው እነዚህን ኩባንያዎች መልሰው እንዲዋቀሩ በመደረጉ ተጋርጦባቸው ከነበረው አደጋ መንግሥት እንደታደጋቸው ተናግረዋል። መልሶ የዋቃሩ ስራ ባይሰራ ኖሮ "ስለመብረት እና ስኳር ማውራት አንችልም ነበር" ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ። ሲሚንቶ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በአገሪቱ የሲሚንቶ እጥረት ተከስቶ እንደነበረ አስታውሰው፤ በአሁኑ ሰዓት 10 የሲሚንቶ ፋብሪካዎች 14 ሚሊዮን ቶን በየዓመቱ የማምረት አቅም ቢኖራቸውን እየተመረተ ያለው ግን 8 ሚሊዮን ቶን ብቻ ነው ብለዋል። በዚህም ምክንያት የሲሚንቶ ዋጋው ከፍ ብሎ እንደነበረ አስታውሰው፤ የሲሚንቶ ምርትን ለመጨመር ከፋብሪካዎቹ ጋር ውይይቶች መከናወናቸውን ተናግረዋል። ሲሚንቶ አምራቾች የውጪ ሚንዛሬ እና የኃይል አቅርቦት ጥያቄዎቻቸው ምላሽ ለመስጠት ሞክሯል፤ በዚህም የምርት መጠን ላይ ለውጥ ታይቷል ብለዋል። "በአሁኑ ሰዓት በአንድ ኩንታል ሲሚንቶ ላይ የ60 ብር ቅናሽ ታይቷል" ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሩ። የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ለውጥ ለማምጣት በትኩረት ሊሰራባቸው ከሚገቡ ጉዳዮች መካከል አንዱ ኤሌክትሪክ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ፣ ባለፉት ሶስት ወራት 69 ከተሞች መብራት ማግኘታቸውን አስታውሰዋል። የሕዳሴ ግድብ ግንባታን በተመለከተም፤ "ጥሩ ሥራ ሰርተናል። የዘንድሮ ሥራ ግን ፈታኝ ይሆናል" ብለዋል። የሕዳሴ ግድብ የዘንድሮ የኤልክትሮ መካኒካል እና የሲቪል ሥራው ፈታኝ እንደሚሆን ጠቅላይ ሚንሰትሩ ጠቁመው፤ "ሥራው ከውስጥም ከውጪም እንዲደናቀፍ የሚፈልጉ አሉ" ካሉ በኋላ በተባበረ መንፈስ በሙሉ ልብ የሕዳሴ ግድብ ላይ ትኩርት መደረግ አለበት ብለዋል። መፈናቀል የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር በከፍተኛ መጠን የቀነሰ ቢሆንም አሁንም በሚከሰቱ ግጭቶች ሰዎች ከቀያቸው እየተፈናቀሉ መሆኑን ጠቅላይ ሚንስትሩ አስታውሰዋል። ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወደ 56ሺህ ያህል ሰዎች መፈናቀላቸውን ተናግረው፤ ከእነዚህ መካከል ወደ 50ሺህ የሚጠጉት ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን ተናግረዋል። አሁንም የአገር ውስጥ መፈናቀል እንዲከሰት በሚያደርጉ መንስኤዎች ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ ተናግረዋል። አንበጣ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የአንበጣ መንጋው ጥቃት ያደረሰው በ240 ወረዳዎች መሆኑን ገልጸዋል። በቅርቡም ከሌሎች አገራት መሪዎች ጋር በነበሯቸው ውይይቶች አንዱ አጀንዳ የአንበጣ መንጋ መሆኑን ጠቅሰዋል። ከውጪ ኬሚካል የሚረጩ አውሮፕላኖችን እና ድሮኖችን [ሰው አልባ አውሮፕላን] ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው ሂደቱ ግን አልጋ ባልጋ አለመሆኑን ጠቅላይ ሚንስትሩ አመልክተዋል።
44052564
https://www.bbc.com/amharic/44052564
ብዙ ባሎችን አግብታለች የተባለች ሴት በአልሻባብ ተገደለች
በርካታ ባሎችን በማግባት ክስ ተመስርቶባት በአክራሪው የሶማሊያ እስላማዊ ቡድን በሚመራ ፍርድ ቤት የቀረበች ሴት በድንጋይ ተወግራ እንደተገደለች ለታጣቂው ቡድን ቅርብ የሆነ የዜና ድረ-ገፅ ዘግበ።
ሹክሪ አብዱላሂ ዋርሳሜ የተባለችው ይህች ሴት ቀደም ካሉ ባሎቿ ጋር የፈፀመችውን ጋብቻ ሳታፈርስ አሰራ አንድ ጊዜ አግብታለች በሚል ነው የተከሰሰችው። ተከሳሿ እስከአንገቷ ድረስ መሬት ውስጥ እንድትቀበር ከተደረገች በኋላ በታችኛው የሸበሌ ክልል ሳብላሌ ከተማ ውስጥ በሚገኙ የአልሻባብ ታጣቂዎች በድንጋይ ተወግራ ነው የተገደለችው። ዜናውን የዘገበው ድረ-ገፅ እንዳለው ተከሳሿ በሙሉ ጤንነት ላይ የነበረች ሲሆን ለቀረበባት ክስ ጥፋተኝነቷን አምናለች ብሏል። ከአራት ዓመት በፊትም አል-ሻባብ በደቡባዊ ሶማሊያ የባሕር ዳርቻ አካባቢ ባለችው የባራዌ ግዛት በተመሳሳይ በምስጢር አራት ባሎችን አግብታለች ተብላ የተከሰሰችን ሴት በድንጋይ ተወግራ እንድትገደል አድርጓል።
44530513
https://www.bbc.com/amharic/44530513
ኢትዮጵያ፦አሲድን እንደ መሳሪያ
የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ደጃፍን የፍትህ ያለህ ብለው ከሚረግጡ ጉዳዮች መካከል 90 በመቶዎቹ የባልና የሚስት ናቸው።
ኢትዮጵያዊቷ ሞግዚት፣ ሽዌይጋ ሙላህ በሊቢያ ድብደባና ቃጠሎ ደርሶባት ነበር ከእነዚህ መካከል ደግሞ ላቅ ያለውን ድርሻ የሚይዙት የቤት ውስጥ ጥቃቶቸች መሆናቸውን የድርጅቱ ኃላፊ ወ/ሮ ሜሮን አራጋው ይናገራሉ። በርግጥ የቤት ውስጥ ጥቃት ሰፊ ነው የሚሉት ወ/ሮ ሜሮን የአካል፣ የስነልቦና፣ የኢኮኖሚ መብት ጥሰት፣ የወሲብ ጥቃቶችን ሁሉ እንደሚጨምር ያሰምሩበታል። ወደ ቢሯቸው የሚመጡትም ሴቶች እነዚህን ሁሉ ጥቃቶች አልፈው የሚመጡ መሆናቸውን ያስረዳሉ። አሁን ግን ይላሉ ወ/ሮ ሜሮን የተለመዱትን ጥቃቶች በህግ ፊት አቅርበን ፍትህ ሳናሰጥ አዳዲሰ የምንላቸው ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች እየበረከቱ መጥተዋል። ከእነዚህ ጥቃቶች መካከል የአሲድ ጥቃትና በቡድን ሆኖ ደፈራ ይጠቀሳሉ። ማስረጃ 1- ዳንግላ በ2007 ዓም ነው ነገሩ የሆነው። ለ5 ዓመታት በፍቅር ጓደኝነት አብረው ቆዩ። እርሱ በተለያዩ ሱሶች ስለተጠመደ አልተግባቡም፤ ተለያዩ። አንቺ የኔ ካልሆንሽ መኖር አትችይም በማለት በተደጋጋሚ ዛቻና ማስፈራሪያ ሲያደርስ እንደቆየ ወ/ሮ ሜሮን ይናገራሉ። አክለውም እርሷ የምትሰራውና የምታድረው ሆቴል ውስጥ በመሆኑ ጥቃቱን መፈፀም ባሰበ ጊዜ አብራው ከምትሰራው እና ለእርሱ ጓደኛ ከሆነ ግለሰብ ጋር በመተባበር፣ የምትገባበትን የምትወጣበትን ሰአት በመጠበቅ፣ አሲድ አዘጋጅቶ ልትተኛ በተዘጋጀችበት ወቅት በሯን አንኳኩቶ በመግባት አሲድ ፊቷ ላይ ደፍቶባታል ይላሉ። በወቅቱ በተደረገ ምርመራም መሬት ላይ "በወደቀችበትም ደጋግሞ እንዳርከፈከፈባትና ከቁምሳጥን ውስጥ ልብሷን በማውጣት እሰይ እንኳን እያለ በእርካታ ስሜት እንደደፋበት ለማወቅ ተችሏል" ሲሉ ያስረዳሉ። እየተንከባለለች ራሷን እስክትስት ድረስ ድርጊቱን በእርካታ ስሜት እንደፈፀማባት የሚናገሩት ወ/ሮ ሜሮን ይህ ግለሰብ በአሁን ሰአት 19 አመት ተፈርዶበታል። ልጅቷ በጉዳቱ አይኗን መጨፈን አትችልም፤ ጆሮዎቿ በሙሉ ተቆራርጠዋል፤ ከፊቷ እስከ ጡቷ ድረስ የደረሰውን ጉዳት በሀገር ውስጥ ለማከም ከ 20 ጊዜ በላይ ቀዶ ጥገና አድርጋለች። በአሁኑ ሰአት በውጭ ሀገር ህክምና ለማግኘት ወደዛው አቅንታለች በማለት የደረሰባትን አካላዊ ስቃይ ያስረዳሉ። እነዚህ ጥቃቶች ድርጅቱ በ23 አመት የስራ ዘመኑ በተደጋጋሚ ያልገጠመው ነገር ግን አሁን በሩን እያንኳኳ ያለ ጉዳይ ነው በማለት የሚያስረዱት ወ/ሮ ሜሮን በዚህ አመት ብቻ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሁለት ሶስት የአሲድ ጥቃቶች እንደመጡና እነዚህ ጥቃቶች ትኩረት ያሻቸዋል በማለት ሌላ አስረጅ ይጠቅሳሉ። ማስረጃ 2- አዲግራት በዚሁ በ2010 ዓ.ም የሆነ ነው። በአዲግራት ልጅ አብረው የወለዱና ባለመግባባት ምክንያት ትዳራቸውን በስምምነት ያፈረሱ ግለሰቦች ናቸው። ባል ከሐገር ውጭ ሲኖር እርሷ ደግሞ ኑሮዋን እዛው አዲግራት አድርጋለች። አንድ ቀን ድንገት በሯ ይንኳኳል፤ ስትከፍት የቀድሞ የትዳር አጋሯ ነው፤ በእጁ አሲድ ይዟል። እንደመጣ እንኳን አልሰማችም ድንገት በበሯ ተከስቶ አሲድ ፊቷ ላይ ደፍቶ ተሰወረ። ይህች ሴት ፊቷ ሙሉ በሙሉ ተቃጥሏል። ሁለት አይኖቿ ጠፍተዋል ጆሮዎቿ አፍንጫዋም እንደተቆራረጠ ወይዘሮ ሜሮን ይናገራሉ። አዲግራት ሆስፒታል ብትገባም ለ40 ቀናት ህክምና ሳታገኝ በበርካታ ሴቶች ማህበራት ጥረት በኋላም ወደ አዲስ አበባ ተልካ ህክምና እያገኘች ትገኛለች፤ እስካሁን ድረስ ተጠርጣሪው አልተያዘም በማለት ግለሰቧ ያለችበትን ሁኔታ ያስረዳሉ። ወ/ሮ ሜሮን አራጋው፣ የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ዳይሬክተር ማስረጃ 3- አዲስ አበባ- ቦሌ ቡልቡላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ አስተናጋጅ የሆነች የ24 ዓመት ወጣት ትዳር መስርታ አንድ ልጅ ወልዳለች። ከትዳር አጋሯ ጋር ባለመስማማቷም በፍቺ ተጠናቀቀ። ንብረት ክፍፍል ላይ ደርሰው ባለበትም ወቅት የልጃቸውን ሰነድ ልስጥሽ ብሎ ይጠራታል። ተገናኝተው በመኪናው አብረው እየተጓዙ እያለ ጫካ ያለበት ሰዋራ አካባቢ ሲደርሱ መኪናውን ተበላሸ በማለት ያቆመዋል። ከዛ ፊቷ ላይ አሲድ ይደፋባታል፤ ይህች ወጣት ግማሽ ፊቷ ነው የተቃጠለው። ግለሰቡ ተይዞ ህግ ፊት ሲቀርብ የተጠየቀው በአካል ጉዳት ስለሆነ የተፈረደበት 5 አመት ብቻ ነው በማለት ህጉ ላይ ስላለው ክፍተት ክፍተት ወ/ሮ ሜሮን ይናገራሉ። ድርብርብ ፈተናዎች የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ስለሚሰራ ሴቶቹ ጥቃት ደረሶባቸው የፍትህ ያለህ ሲሉ ስነልቦናቸው ተጎድቶ፣ አካላቸው ጎድሎ መታከሚያ ቤሳ ቤስቲን ሳይኖራቸው ስለሚመጡ ፈተና ውስጥ ይወድቃል። እነዚህን ሴቶች ወደ ቀድሞው ጥንካሬያቸው ለመመለስ፣ ጤናቸውን እንዲያገኙ ለማድረግ እጅ አጥሮት እንደተቸገረም ድርጅቱ ገልጿል። ቢያንስ እነዚህ ሴቶች አደጋ የደረሰባቸው ሴቶችን በማቆያ ቤት ውስጥ ለማድረግ የቀድሞ አቅሙ በበጎ አድራጎት ህጉ ምክንያት ስለተነጠቀ ፈተናውን እንዳከበደበት ይናገራሉ። ለዚህም ማስረጃ አድርገው የሚጠቅሱት በቅርቡ ከወደ ሐረር የቢሯቸው ደጃፍ የደረሰውን ጉዳይ በማንሳት ነው። በሰው ቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ ትሰራ የነበረች የ13 ዓመት ህፃን የአስገድዶ መድፈር እና ማስረጃ ለማጥፋት ከወገብ በታች ተቃጥላ ነበር ወደ ቢሯቸው የመጣችው። ቃጠሎዋ ከፍተኛ እንደሆነ የሚገልፁት ወ/ሮ ሜሮን እስከ አጥንቷ ድረስ የዘለቀ መሆኑን የየካተት 12 ሆስፒታል የሕክምና ባለሙያዎች መግለፃቸውን ይናገራሉ። ይህች ታዳጊ የካቲት 12 ሆስፒታል ተኝታ የፍትህም የህክምናም አገልግሎትም እየተከታተለች ቢሆንም የህክምና ወጪዋን ለመሸፈን አቅም እግር ተወርች አስሯቸው ደግ ልብ ያላቸው ኢትዮጵያውያንን ድጋፍ ለማሰባሰብ የባንክ ሒሳብ በእናቷ ስም እንደከፈቱ ተናግረዋል። ወ/ሮ ሜሮን አክለውም ይህ ማህበር ከ2001 ዓም ጀምሮ የበጎ አድራጎት ህግ በመታወጁ እና በዚህም መሰረት 90 በመቶ ገቢውን ከሀገር ውስጥ መሰብሰብ መቻል ስላለበት በርካታ የህዝብ ማስተማር ስራዎቹ ተቀዛቀቅዘዋል ይላሉ። እንደቀድሞው በተከታታይነት ማህበረሰቡን ስለ ፆታ እኩልነት ለማስተማር ስልጠና ለመስጠት ተግዳሮት እንደሆነባቸው ያስረዳሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በሴቶች ዙሪያ በጎ የሆነ እና በአዲስ አቅጣጫ ትኩረት የሚሰጥ አመላካች ንግግሮችን እንዲሁም መልእክቶችን ሲያስተላልፉ ቆይተዋል የሚሉት ወ/ሮ ሜሮን ይህንን ተከትለው የእርሳቸው ማህበር ከሌሎች አቻ ማህበራት ጋር እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ተናግረዋል። "ይህንን ተከትሎ የእርሳቸውንም ጥረት ለመደገፍ የሲቪክ ማህበረሰቡ ድርሻም ስላለው በተለይ ሴቶች ላይ የምንሰራ የሲቪክ ማህበራት ድርጅቶች ተሰባስበን ወዲያውኑ እርሳቸው ወደስልጣን እንደመጡ ውይይቶችን አድርገናል።" ይላሉ። በውይይታቸውም በፖሊሲ ደረጃ፣ በህግ አፈፃፀም እንዲሁም በመዋቅር ደረጃ የሴቶች መብት መከበር፣ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን ለመከላከል የመንግስት ትኩረት ምን መሆን አለበት የሚለውን ሰፊና ጥልቅ ውይይት በማድረግ የመፍትሄ ሃሳቦችን እንዳሰባሰቡ ይናገራሉ። ይህንንም የመፍትሄ ሃሳባቸውን ይዘው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ለመነጋገር ደብዳቤ አስገብተው ምላሽ እየተጠባበቁ እንደሆነ ተናግረዋል። ማህበሩ በተናጠል ደግሞ በቅርቡ ቀዳማይ እመቤት በሴቶችና በህፃናት ላይ ከሚሰሩ ድርጅቶች ጋር አብረው ለመስራት ደስተኛ እንደሆኑ መግለጫ ስለሰጡ እርሳቸውንም ለመነጋገር ቀጠሮ እንዲያዝላቸው ደብዳቤ ማስገባታቸውን ጠቅሰዋል። የማህበሩ ታሪክ የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር በሀገር አቀፍ ደረጃ እየሰራ ያለ መንግስታዊ ያልሆነ ኢትዮጵያዊ ተቋም ነው። ይህ ድርጅት ከተመሰረተ 23 ዓመታት የሞላው ሲሆን በእነዚህ አመታት በሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ሲሰራ ቆይቷል። አንደኛው ነፃ የህግ አገልግሎት ለሴቶች ብቻ መስጠት ሲሆን ሁለተኛው የህዝብ ማስተማርና የአቅም ማጎልበት ስልጠና መስጠት ነው። ሶስተኛው የጥናትና ምርምር ስራ ነው። የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር በዚህ ዘርፍ ህጎች እንዲለወጡ እና እንዲሻሻሉ የሚሉት ወ/ሮ ሜሮን በዚህም የቤተሰብ ህጉ እና የወንጀለኛ መቅጫ ህጉ ይጠቀሳል በማለት ያብራራሉ። ማህበሩ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ በነፃ የህግ አገልግሎቱ ከ 200 ሺህ ሴቶችን ተጠቃሚ ያደረገ ሲሆን፣ በህዝብ ማስተማርና በአቅም ማጎልበት ስራዎቹ ደግሞ 80 ሺህ ሰዎችን በቀጥታ በማግኘት ስለሴቶች መብቶች ቀጥተኛ ባልሆነ መልኩ በተለያዩ ህትመቶችና ሬዲዮን ፕሮግራሞች በሌሎች መንገዶች ደግሞ 10 ሚሊየን ሰዎችን በመድረስ ውጤታማ ስራ ሰርቷል በማለት ይናገራሉ። ማህበሩ በአሁን ሰአት 260 በጎ ፈቃደኞች ያሉት ሲሆን በአዲስ አበባ፣ በአዳማ ፣ድሬዳዋ፣ ጋምቤላ፣ ሃዋሳ፣ አሶሳ እና በ53 ገጠር ቀበሌዎች ነፃ የህግ ድጋፍ ይሰጣል።
news-44804246
https://www.bbc.com/amharic/news-44804246
በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ 100 ቀናት ውስጥ ዶላር በጥቁር ገበያ ለምን ቀነሰ?
ዶላርና ብር ለዘመናት እንደተኳረፉ አሉ። ከሰሞኑ ያሳዩት መቀራረብ ግን ማንም የጠበቀው አልነበረም። ከሳምንት በፊት አንድ ዶላር በ36 ብር ይመነዘር ነበር፤ በጥቁር ገበያ። በዚህ ሳምንት አንድ ዶላር ተመኑ ወደ 31 ብር ወርዷል። በሰባት ቀናት የአምስት ብር ቅናሽ እጅግም ያልተለደመ ነው። ይህ ለምን ሆነ?
የውጭ ምንዛሬ ወትሮም የአንድን አገር ኢኮኖሚያዊ ጤና የሚያሳብቅ የትኩሳት መለኪያ ብልቃጥ 'ቴርሞሜትር' ነው። በተለይም ጥቁር ገበያ ከመንግሥት ቁጥጥር ያፈነገጠ፣ በገበያ ፍላጎት የሚመራ በመሆኑ የተሻለውና የሚታመነው የትኩሳት መለኪያ ተደርጎ ይወሰዳል። ታዲያ የታመመው ምጣኔ ሐብታችን ትኩሳቱ እየበረደለት ይሆን? ቢቢሲ በዚህ ድንገተኛ የጥቁር ገበያ ዶላር ተመን ማሽቆልቆል ዙርያ የምጣኔ ሃብት ባለሞያዎችን አወያይቷል። • የብር የመግዛት አቅም መቀነስ አንድምታዎች • ዓለም አቀፍ የንግድ ተቋማትና ኢትዮጵያ - 'ፒዛ ሃት' "የድንበር ቁጥጥሩ ይመስለኛል..." ዶክተር ቆስጠንጢኖስ የዋጋ ከፍና ዝቅ መሬት ላይ ባለ ነገር ብቻ አይከሰትም። በተለይም የምንዛሬ ምጣኔ አንዳች ኮሽታ በተሰማ ቁጥር ሊናጥ የሚችል ድንጉጥ ገበያ ነው። ዶክተር ቆስጠንጢኖስ ከዚሁ ጋር የሚያያዝ ምሳሌን ያነሳሉ። "የአሜሪካ "ትሬዠሪው" በሚሰበሰብበት ጊዜ ማርኬቱ ገና ስብሰባው ሊካሄድ ነው ሲባል ነው መናወጥ የሚጀምረው" በተመሳሳይ ከሰሞኑ በድኀረ ዐብይ የተሰሙ፣ የታዩ፣ የተገመቱና የተከሰቱ ዐበይት ክንውኖች የጥቁር ገበያውን ዶላር አደብ ሳያስገዙት አልቀሩም። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የውጭ ምንዛሬ ጥሪ ለዳያስፖራው በይፋ ማቅረባቸው፣ በሶማሌ ክልል ነዳጅ የማውጣቱ ዜና፣ በአገሪቱ አንጻራዊ ሰላም እየሰፈነ መምጣቱ ከሚጠቀሱት ክስተቶች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው። • የኢትዮጵያ የዕዳ መጠን እየጨመረ ነው • ወሳኝ ምጣኔ ሃብታዊ እርምጃዎች በ100 ቀናት አፍሪካ በየዓመቱ ከምታገኘው ሁሉን አቀፍ እርዳታ 10 እጥፍ የሚበልጠው በኀቡእ የሚሸሽ ነው። ኢትዮጵያም የዚሁ አካል ናት። ቢሊየን ዶላሮች በሕገ ወጥ መንገድ በየዓመቱ ያፈተልካሉ። በተለይም ኢትዮጵያ ውስጥ በነበረው አለመረጋጋት ብዙ ዜጎች ገንዘባቸውን በዶላር ቀይረው ወደ ውጭ ያሸሹ እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ። በመንግሥት ሹሞች የሚፈጸም ሌብነትና ዝርፍያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ 'ሌቦች' የሚሏቸውን ጨምሮ ጥቁር ገበያውን ሲያንሩት እንደነበር ዶክተር ቆስጠንጢኖስ ይገምታሉ። እነዚህ ዘራፊዎች የአገሬውን ገንዘብ ወደ ባንክ ወስደው ለማስቀመጥ አይችሉም። ጥያቄ ስለሚፈጥርባቸው። ስለዚህ የዘረፉትን ወደ ዶላር በመቀየር ማሸሽን ይመርጣሉ። አገር በስፋት ስትዘረፍና ብራቸውን ወደ ዶላር መቀየር የሚፈልጉ ዘራፊዎች ቁጥር ሲጨምር የጥቁር ገበያ የምንዛሬ ዋጋ በዚያው መጠን ይመነደጋል። • የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት ኢኮኖሚያዊ ትርፍ? • የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ እርምጃዎች የት ድረስ? በብር የሚከፈላቸው የውጭ ተቋራጮች ዶክተር ቆስጠንጢኖስ ለጥቁር ገበያ ዋጋ መናር ሌላ ምክንያት ይመስለኛል የሚሉት አገር ውስጥ ትልልቅ ግንባታ ለማካሄድ የሚጫረቱ የቻይና ኩባንያዎችን ነው። እነዚህ ኩባንያዎች ጨረታ የሚገቡት በብር እንዲከፈላቸው በመዋዋል ነው። ነገር ግን በቢሊዮን ብር ከተከፈላቸው በኋላ ብሩን ወደ ዶላር ቀይረው ከአገር ያስወጡታል። ይህን ግብይት የሚያደርጉት ደግሞ በጥቁሩ የዶላር ጉሊት ነው። ዶክተር ቆስጠንጢኖስ እንደምሳሌ የሚያነሱት ሰሞኑን ድንበር አካባቢ አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ዶላር በትራክ ተጭኖ ሊወጣ ሲል መያዙን ነው። ይህ ዓይነቱ የድንበር ቁጥጥር የጥቁር ገበያ የዶላር ግዢ ፍላጎቱን የቀነሰ ይመስለኛል ይላሉ። ምክንያቱም ኩባንያዎቹ የሕግ ተጠያቂነት ስለሚያስፈራቸው። የቀድሞው የንግድ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ክቡር ገና ግን በዶክተር ቆስጠንጢኖስ ሃሳብ የሚስማሙት በግማሹ ነው። "የጠረፍ ቁጥጥር ሲኖር (የዶላር) ገበያውን ቀነስ አያደርገውም አልልም። ተጽእኖ ይኖረዋል። ሆኖም የጠረፍ መዘጋት በዚህ ዓይነት ዶላሩን በአንድ ጊዜ ዝቅ ያደርገዋል ብዬ አላስብም...።" ከዚያ ይልቅ ይላሉ አቶ ክቡር፣ የአገሪቱ እጣ ፈንታ አሳስቦት፣ ግሽበት አሳስቦት፣ ገንዘቤ ከሚሟሟ ብሎ ብሩን በዶላር የሚያስቀምጠው ሰው ቁጥር በሂደት እየቀነሰ መምጣቱ የዶላሩን የጥቁር ገበያ ተመን እንዲወርድ አንድ ምክንያት ሆኗል። "ፖለቲካ ላይ ተስፋ ሲታይ የብር ፈላጊ ይጨምራል።" ለአቶ ክቡር ከሁሉም በላይ ሰሞነኛው ፖለቲካ ለዶላሩ መውረድ ሚና ተጫውቷል። "...የፖለቲካ ችግር እንደሚቀንስ የሚያሳዩ ምልክቶችን አየ፤ የዶላሩ ግዢ ሩጫውን ቀነሰ" ካሉ በኋላ በእንደዚህ ሁኔታ ውስጥ ደግሞ ትርፍ ከፍሎ ዶላር የመግዛት ፍላጎት እየጠፋ እንደሚመጣ ያትታሉ። ዶክተር ቆስጠንጢኖስ በበኩላቸው የውጭ ኩባንያዎች አገር ውስጥ የሚያገኙትን ብር በጥቁር ገበያ ስለሚመነዝሩት የዶላር ፍላጎት በጥቁር ገበያ ንሮ እንዲቆይ እንዳደረገው አይጠራጠሩም። "...በቻይና ኩባንያዎች ለምሳሌ ትልልቅ ሕንጻዎች እየተሠሩ ነው። እነዚህ ኩባንያዎች በብር ነው ጨረታ የሚገቡት። በብር ጨረታ ሲገቡ በብር ነው የሚከፈላቸው፥ በዶላር አይደለም። ስለዚህ የሚከፈላቸውን ብር የማውጫ ዘዴ ይፈልጋሉ። ይህን ፍላጎታቸውን የሚያሟላላቸው ጥቁር ገበያው ነው። በጥቁር ገበያው ብራቸውን ወደ ዶላር ቀይረው በትራክ ወደ ጅቡቲ ወስደው ጅቡቲ ባንክ ተቀምጦ ሕጋዊ ገንዘብ ያደርጉታል።" የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ 100 የሥራ ቀናት በቁጥር ሲቀመጡ ምን ይመስላሉ? "ዶላሩን ይዤ ብቆይ ይሻላል በሚል ፍላጎት አድጎ ነበር" አቶ ክቡር ገና ወደ ጥቁር ገበያ የሚተመው ደንበኛ መልከ ብዙ ነው። ለስብሰባ፣ ለትምህርት፣ ለሽርሽርና ለሕክምና ወደ ውጭ የሚሄድ ሰዎች ባንኮቻቸው ዶላር ሊያቀርቡላቸው ስለማይችሉ ወደ ጥቁር ገበያ ያቀናሉ። በሕገ ወጥ መንገድ ገንዘብ ያገኙ ሹመኞችም ወደ ጥቁር ገበያ ይሄዳሉ። የግል ባንኮቻቸው እጅ አልፈታ ያላቸው አስመጪ ነጋዴዎች ወደ ጥቁር ገበያ ይሄዳሉ። ይሄ ሁሉ የጥቁር ገበያው ደንበኛ ነው። ሌሎች ዜጎች ደግሞ ብራቸውን በዶላር በማኖር የብር ግሽበትን ለመከላከል ይሞክራሉ። ይህ ሁኔታ ዶላር በጥቁር ገበያ ያለውን ዋጋ ከፍ ሳያደርገው አልቀረም። የጥቁር ገበያው ደንበኛ እንዲህ መብዛት ደግሞ በተዘዋዋሪ የዶላሩን ተፈላጊነት ያንረዋል። አቶ ክቡር እንደሚሉት ኢ-መደበኛው የዶላር ገበያ በፖሊሲ ሳይሆን በገበያ ፍላጎት የሚመራ ነው። ስለዚህ ፍላጎት ሲጨምር ዋጋው ይጨምራል። ታዲያ አሁን የዶላር ፍላጎት ቀንሶ ነው ጥቁር የዶላር ተመን የቀነሰው? ሊያውም ፋብሪካዎች በምንዛሬ እጦት በሚዘገቡት ወቅት? አቶ ክቡር ገናም ይሁኑ ዶክተር ቆስጠንጢኖስ ይህንን ጥያቄ በቀጥታ አይመልሱም። አቶ ክቡር መደበኛው የዶላር ትመና ምጣኔ ሃብቱን የሚመሩት ተቋማት (ብሔራዊ ባንክን ጨምሮ) በአንድም ሆነ በሌላ ዘዴ የገንዘብ ልውውጡን መጠን፣ ፍጥነትና ሁኔታ እንደሚወስኑ ካብራሩ በኋላ የኢ-መደበኛው የገበያ ባህርያት በአጭሩ ያወሱና አሁን ዶላር በጥቁር ገበያ ለምን ቀነሰ ለሚለው አንኳር ጥያቄ የሚመስላቸውን ያስቀምጣሉ። አንዱ ወደ ታክስ ሥርዓት ውስጥ ያልገቡ ኩባንያዎች ወደ ጥቁር ገበያ መሄድ ማቆማቸው ነው። "ወትሮም በመደበኛ ግብይት የቆዩ፣ የታክስ ሥርዓት ውስጥ የቆዩ ኩባንያዎች ወደ ኢ-መደበኛ የዶላር ገበያ አይሄዱም። ወደ ኢ-መደበኛው የሚሄዱት አዳዲሶች ናቸው። በተለያየ ምክንያት።" ካሉ በኋላ "መጪውን ጊዜ በማስላት ዶላር ገበያው ውስጥ ያልነበሩ ሰዎች ገበያ ውስጥ ገቡ። እነሱ የፈሩት ፖለቲካዊ ሁኔታ እየተቀየረ ሲመጣ ከገበያው ወጡ፤ ይህ የጥቁር ገበያውን አረጋጋው " ሲሉ ግምታቸውን ያስረዳሉ፣ አቶ ክቡር። ከጥቂት ዓመታት በፊት አገሪቱ አስፈሪ ሁኔታ ውስጥ እንደነበረች የሚያወሱት ሁለቱም የምጣኔ ሐብት ባለሞያዎች ይህንንም ተከትሎ ነገሮች እስኪጠሩ ድረስ ገንዘቡን በዶላር ማስቀመጥ፣ ወይም ማሸሽ፣ ወይም ዶላሩን ይዤ ብቆይ ይሻላል የሚል ፍላጎት አድጎ እንደነበር ያስታውሳሉ። ይህ ሁኔታ በአንጻራዊ መልክ እየተለወጠ መምጣቱ ደግሞ የጥቁር ገበያን የዶላር ፍላጎት አረጋግቶታል። የዐብይ አሕመድ ያለፉት ወራት እንቅስቃሴዎች በዶላር መቀነስ ያለውን ሚና የተጠየቁት አቶ ክቡር ገና በበኩላቸው፣ "በንግግርም ይሁን 'በጀስቸር' ዜጎች ያ የፖለቲካ ፍርሃት ሲቀንስላቸው፣ የፖለቲካው ውጥረት ተንፈስ ሲል የምንዛሬ ሩጫው ይገታል። ይህ ብዙውን ጊዜ ከተስፋ ጋር የሚሄድ ነገር ነው። አገር ሲረጋጋ የብር ፈላጊው እየጨመረ፣ በኢ-መደበኛ መንገድ የዶላር ፍላጎቱ እየረገበ ይሄዳል። ያንን ዶላር በብዙ ትርፍ ገዝቶ የማስቀመጥ ፍላጎቱ እየቀነሰ ሲመጣ ደግሞ የምንዛሬ መጠኑ ወደ መደበኛው ተመን እየተጠጋ ይመጣል።" ይላሉ። • ካለሁበት ልዩ መሰናዶ፡ ሎስ አንጀለስ ከዐብይ አህመድ በፊትና በኋላ ዶላር በቀጣይ ይቀንሳል ወይስ ይጨምራል? የውጭ ንግድ ሲፋፋም፣ የአገር ውስጥ ምጣኔ ሐብት ጤና ሲጠበቅ፣ ኢኮኖሚው ለገበያ ክፍት ሲሆን፣ አግባብ ያላቸው የ"ሞኒቴሪ"ና የ"ፊስካል" ፖሊሲ ሲተገበር፣ የፋይናንስ አስተዳደሩ ሲዘምን ጥቁር ገበያ እየቀጨጨ በመጨረሻም አስፈላጊ ወደ ማይሆንበት ደረጃ ይደርሳል። ይህ ዓለማቀፋዊ የምጣኔ ሐብት ሐተታ ነው። ይህ ሁኔታ ግን እንደየ አገሩ መልክና አስተዳደር ገጽታው ይለያያል። ዶክተር ቆስጠንጢኖስ ይህ ችግር የሚፈታው ገበያን በማፍታታት ነው ብለው በጽኑ ያምናሉ። "አሁን ያሉት የአገር ውስጥ ባንኮች ተጨማሪ የውጭ ምንዛሬ ለማምጣት የሚያስቸል አቅሙም ጉልበቱም የላቸውም።" ዶላር አሁንም ቢሆን ከእርዳታ፣ ከብድር፣ ከዳያስፖራና ከውጭ ንግድ ምንጮች ነው የሚገኘው። "የውጭ ባንኮች ቢገቡ ግን የራሳቸውን ካፒታል ይዘው ስለሚመጡ የምንዛሬ መንበሽበሽ ሊያመጡ ይቻላቸዋል" ይላሉ ዶክተር ቆስጠንጢኖስ። ከዚሁ ጋር አብሮ የፋይናንስ አስተዳደሩ እንዲታሰብበት ይፈልጋሉ። ዶክተር ቆስጠንጢኖስ አገሪቱ በሯን እንድትከፋፍት በሚያሳስቡበት መጠን ወጪዎቿን እንድትቀንስ ይወተውታሉ። ጥቁር ገበያ የሚደራው ከመንግሥት የተዘረፈ ገንዘብ ከአገር ለማሸሽ ሲሞከር ነው። አሁን መንግሥት የራሱን ወጪ እየቀነሰ ሲሄድና ኢኮኖሚውን ክፍት ሲያደርገው ሁኔታዎች እንደሚለወጡ ያስባሉ። "በፓርቲ የተያዙ ድርጅቶች አሉ፥ በመንግስት የተያዙ አሉ፥ እነዚህ ሁሉ ኢኮኖሚውን ሲያምሱት ምስቅልቅሉ የወጣ የፋይናንስ ሥርዓት ነው የተፈጠረው። መሠረታዊው መልስ የሚሆነው የፋይናንስ ሥርዓቱን ማስተካከል ነው።" ይላሉ ዶክተር ቆስጠንጢኖስ። እንደ ስኳር ፋብሪካና ማዳበሪያ ፋብሪካ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ያባከኑት ገንዘብ እንደማሳያ በማንሳት ጭምር። አቶ ክቡር ገና በበኩላቸው አሁን ያለው የጥቁር ገበያ ዋጋ አገሪቱ ውስጥ ተቃውሞ ከመነሳቱ በፊት ከነበረው የምንዛሬ ዋጋ መቀራረቡን ያወሱና በአገሪቱ የተሻለ መረጋጋት እየተፈጠረ ስለመምጣቱ አመላካች እንደሆነ ያትታሉ። መንግሥት በዳያስፖራ ሃዋላ ላይ ከፍ ያለ ተስፋን ማሳደሩ ግን ብዙም ምቾት አይሰጣቸውም። ከዚያ ይልቅ መንግሥት አገር ውስጥ ምጣኔ ሐብቱን የሚያነቃቃ እርምጃ እንዲወስድ ነው ፍላጎታቸው። "የጥቁር ገበያው ዶላር ከብር ጋር የሚያሳዩት የምንዛሬ ምጣኔ መጠጋጋቱ እስከየት ይዘልቃል?" ተብሎ የተጠየቁት አቶ ክቡር ፍላጎት እየጨመረ ስለሚሄድ በአጭር ጊዜ ውስጥ 28/29 ድረስ ይወርዳል ብለው እንደማያስቡ ያስረዳሉ። ከ30 እስከ 32 ድረስ እየዋለለ እንደሚቆይም ግን ይተነብያሉ። ለዚህ ትንበያ ያደረሳቸው ደግሞ በኢኮኖሚው ውስጥ ምንም አዲስ የተጨመረ ነገር አለመኖሩ ነው። "እኔ እንደሚገባኝ ከዛሬ ሁለት-ሦስት ዓመት በፊት የነበርነበት ቦታ እየተመለስን እንደሆነ ነው።"
news-41357416
https://www.bbc.com/amharic/news-41357416
ኪም ጆንግ ኡን ፡ 'እብዱ' ትራምፕ የኑክሊዬር መርሃ ግብርን አስፈላጊነት አሳይቶኛል
'እብዱ' የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለሰሜን ኮሪያ የኑክሊዬር ጦር መሳሪያ ማበልጸጌ ትክክል እንደሆነ አሳምነውኛል ሲሉ ኪም ጆንግ ኡን ተናግረዋል።
በመንግስት መገናኛ ብዙኃን ከዚህ በፊት ባልተለመደ ሁኔታ በሰጡት መግለጫ ትራምፕ በተባበሩት መንግስታት ላይ ያደረጉት ንግግር 'ትልቅ ዋጋ ያስከፍላቸዋል' ብለዋል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባለፈው ማክሰኞ ሃገራቸው ራሷን ለመከላከል በመገደዷ ሰሜን ኮሪያን 'ሙሉ በሙሉ ልታጠፋት ትችላለች' የሚል ንግግር አሰምተው ነበር። ፕሬዝዳንቱ ኪምን 'ራሱን የማጥፋት ተልእኮ ላይ ያለ ባለሮኬቱ ሰው'' ሲሉም ተሳልቀውባቸው ነበር። ሁለቱ ሃገራት ከቅርብ ወራት ወዲህ ጥላቻ የተሞላበትን የቃላት ጦርነት እያዘወተሩ መጥተዋል። የሰሜን ኮሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም የትራምፕን ንግግር 'ከሚጮህ ውሻ' ጋር አመሳስለውት ነበር።
news-57065442
https://www.bbc.com/amharic/news-57065442
የህወሓት እና ሸኔ ሽብርተኛ መባል የኢትዮጵያን የጸጥታ ሁኔታ ወዴት ይወስደው ይሆን?
ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ጀምሮ ባሉት ሶስት አመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ግዜ ሁለት ቡድኖች አሸባሪ ተብለው ሚያዚያ 28 2013 ዓ.ም ተፈርጀዋል።
ስራ አስፈፃሚው ሕዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ (ሕወሃት) እና ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ብሎ የሚጠራውን ቡድን ‹‹ሸኔ›› በማለት ላለፉት ሶስት አመታት የተለያዩ የሽብር ተግባራትን ፈፅመዋል ሲል ለተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ አስፍሯል። ይህ የውሳኔ ሃሳብ ከፀደቀበት ዕለት ጀምሮ ስራ ላይ እንደሚውል ምክትል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ፈቃዱ ፀጋ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የውሳኔ ሃቡን ተከትሎ የሚወጡ ዝርዝር ማብራሪያዎች ይኖራሉ ያሉት ፍቃዱ እነዚህ ማብራሪያዎች በተለይም አዋጁ ላይ ያሉ ድንጋጌዎች ላይ ያተኮሩ ናቸው ይላሉ። ይህንን ውሳኔ አስመልክቶ እስካሁን ያለው ዘርዘር ያለ መረጃ ይሄው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ነው። የውሳኔ ሃሳቡን ይዘት ዝርዝር እንመልከት በጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) ለምክር ቤቱ የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ በመግቢያው ላይ ለምን ሁለቱ ቡድኖች በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ ጥያቄው እንደቀረበ ያብራራል። ‹‹ሰላማዊ ዜጎች ከድርጅቱ ጋር አንዳይተባበሩ፣ ድጋፍ እንዳይሰጡ አባል እንዳይሆኑ ብሎም የድርጅቱን ንብረቶች በመውረስ የፋይናንስ አቅሙን ለማዳከም›› ያለመ መሆኑን ይገልፃል። ከሁለቱ ድርጅቶች በተለይም ስለ ሕወሃት ዘርዘር ያለ ማብራሪያ ያቀረበው ሰነዱ የትግራይ ማዕከላዊ ወታደራዊ ኮማንድ የተሰኘ ሃይል በክልሉ የፀጥታ ቢሮ ድጋፍ ማቋቋሙን ይገልፃል። ቀጥሎም የትግራይ መከላከያ ሃይል የተባለ ወታደራዊ ሃይል ለማደራጀት የሚያስችል ዶክትሪን በማዘጋጀት ለህወሓት ስራ አስፈፃሚ ቀርቦ ፀድቋልም ይላል። የዚህን አደረጃጀት መፅደቅ ተከትሎ ለጦርነት ሰፊ ዝግጅት ተደርጓል፤ በ 2012 ዓ.ም መጀመሪያ ላይም ‹‹በይፋ ዘመኑ የመከታ ነው›› በማለት ሕዝቡን ቀስቅሷል ሲልም ይወቅሳል። ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ያሰናዳው ይህ ባለ 12 ገፅ የውሳኔ ሃሳብ ህወሓት ‹‹የፌደራሉን መንግስት ለማዳከም በየክልሉ ችግር ለመፍጠር በማሰብ›› በተለያዩ ክልሎች ካሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር አብሮ ሰርቷል ሲል የተለያዩ ፓርቲዎችን ጠቅሷል። የተጠቀሱት ፓርቲዎች የትኞቹ ናቸው? በቅድሚያ የተጠቀሰው የአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር (አርዱፍ) ሲሆን የጦር መሳሪያ እና በጀት ከህወሃት ቀርቦለታል ሲል ይህ ሰነድ ያስነብባል። ‹‹በአማራ ክልል በቅማንት አካባቢ ለሚነሱ ግጭቶች ሕወሃት የጦር መሳሪያ እና ገንዘብ አቅርቧል፤ እንዲሁም በኦሮሞ ብሄረሰብ አካባቢ የሚኖር ሕዝብ ከአፋር ሕዝብ ጋር እንዲጋጭ ከ 100 በላይ የጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ የተደረገ ሙከራም ነበር›› ሲል አክሏል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ህወሃት ከሁለት ፓርቲዎች ጋር ሲሰራ ነበርም ይላል። የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ እና የቤንሻንጉል ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ ለሰላም እና ዴሞክራሲ የተባሉ ድርጅቶችን በገንዘብ ብሎም በመሳሪያ ደግፏል የሚለው ይህ የውሳኔ ሃሳብ እነዚህ ፓርቲዎች በክልሉ ውስጥ ላሉ ቀውሶች ተጠያቂ ናቸው ሲልም ይወቅሳል። እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ‹‹በተለምዶ ሸኔ ተብሎ ለሚጠራው ቡድን በገንዘብ እና በመሳሪያ ድጋፍ አድርጓል›› ይህም ‹‹ የሰው ህይወት እና ንብረት እንዲጠፋ ምክንያት ሆኗል›› ሲልም ይከስሳል። በተጨማሪም ‹‹የመከላከያ ሰራዊት ላይ ህወሓት ጥቃት ሲፈፅም የዚህን ቡድን ታጣቂዎች በአጋዥነት አብሮ አሰልፏል›› ይላል። በመጨረሻም ህወሓት በመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ሲያደርስ እና የፌደራል መንግስቱን ሲቆጣጠር አብረውት ስልጣን እንዲይዙ በማሰብ የፌደራሊስት ሃይሎች ህብረት የተባለ ጥምረት ፈጥሮ ተንቀሳቅሷል ሲልም አብራርቷል። ህወሓት ከቀረቡበት ክሶች መካከልም ወደ ባህርዳር፣ ጎንደር እና ኤርትራ ሮኬት በማስወንጨፍ በንጹሃን ላይ እና በመሰረተ ልማት ላይ ጉዳት አደርሷል የሚሉ ይገኙበታል። ‹‹ይሄው ሃይል መቀሌን እና የክልሉን ዋና ዋና አካባቢዎች ቢለቅም ማህበረሰብ መሃል እና በየበረሃው ተደብቆ ንፁሃን ላይ ጥቃት በማድረስ ላይ ይገኛል›› ብሏል። ‹‹ሸኔ›› በውጪ አገር በትጥቅ ትግል ውስጥ የቆየው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ወደ አገር ውስጥ ከገባ በኋላ ‹‹የተወሰነው የወታደራዊ ክንፉ አባላት በጫካ ውስጥ በመቅረት እንቅስቃሴውን ቀጥሏል›› ሲል ሰነዱ ያስነብባል። በኦሮሚያ ክልል ብሎም ከክልሉ ውጪ በመንቀሳስ ሰዎችን መግደል እና ከቤት ንብረት ማፈናቀል ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ብሎ የሚጠራው ሰራዊት ወይም በውሳኔ ሃሳቡ ላይ ‹‹ሸኔ›› የተባለው ቡድን ላይ የቀረበ ክስ ነው። በድርጅቱ ተግባር በ 2013 ብቻ 112 ፖሊስ፣ 57 ሚሊሻ፣ እና 18 በተለያየ ደረጃ ያሉ አመራሮችን ገድሏል የሚለው ሌላኛው ክስ ነው። ሸኔ በጥቅምት ወር በምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ 36 ንፁሃን ሰዎችን ገድሏል የሚል ክስም ሰፍሯል። ሌላው የሸኔ ተግባር ነው የተባለው አባ ቶርቤ የተሰኘ ገዳይ ቡድን አዋቅሮ ግድያዎችን መፈፀም ነው። የውሳኔ ሃሰቡን ያፀድቅልኛል ሲል የሚኒስትሮች ምክር ቤት የላከው ይህ ሰነድ ሁለት የክስ መዝገቦችን በሸኔ ላይ ማስረጃ ይሆኑኛል ሲል ይጠቅሳል። ከዚህ ቀደም ኮሎኔል ገመቹ አያን ጨምሮ 20 ሰዎች ተከስሰውበት የነበረው የእነ ኪሱ ቂጡማ መዝገብ አንዱ ነው። ኪሱ ቂጡማ በአምቦ ከተማ በሚያዚያ 08/2011 ዓ.ም የቦምብ ጥቃት በመፈፀም ክስ የቀረበባቸው ግለሰብ ነበሩ። በተጨማሪም በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ ከነበሩ ተማሪዎች እገታ ጋር ተያይዞ የተከፈተው የእነ ካሊፋ አብዱራህማን መዝገብ ሌላኛው ለምክር ቤቱ የቀረበ ሰነድ ነው። ይህ ፍረጃ ለዜጎች ምን ማለት ነው? የውሳኔ ሃሳቡ ከመፅደቁ በፊት በኦሮሚያ ክልል ያሉ የፀጥታ ሃይሎች ዜጎችን ከሸኔ ጋር በመስራት እና በመደገፍ በሚል ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ያስራሉ፣ ያሰቃያሉ የፍርድ ቤት ስልጣንም እንደማይከበር የሚያሳዩ ማስረጃዎችን ሰብስቤያለሁ ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባሳለፍነው ሳምንት ዘለግ ያለ ሪፖርት ይፋ አድርጓል። ሪፖርቱም በ 21 የተመረጡ የፖሊስ ጣቢያዎች ላይ በተካሄደ ክትትል ላይ የተመሰረተ ነው ተብሏል። ኮሚሽኑም የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ህልፈት ተከትሎ ‹‹በወቅታዊ ሁኔታ›› በሚል፣ በተለያዩ ግዜያት በተጠሩ ሰልፎች ተሳታፊ ናችሁ በሚል እንዲሁም የኦነግ ሸኔ አባል ወይም ደጋፊ ናችሁ በሚል የታሰሩ ሰዎችን ማግኘቱን አስታውቆ ነበር። ከእስረኞቹም በርካታ ኢ-ሰብአዊ አያያዞች መኖራቸውን መረዳቱን እና መደበኛ የፍርድ ሂደት የተጓደለባቸውን በርካታ ግለሰቦችን ማግኘቱን አስታውሶ ይህ እንዲሻሻልም ምክረ ሃሳብ ሰጥቶ ነበር። ታዲያ ይህ የሽብርተኝነት ፍረጃ ይህንን ችግር አያባብሰውም ወይ ይህንን ውሳኔ የዜጎችን መብት አደጋ ውስጥ ሳይከት መፈፀም የሚችል መወቅር አለ ወይ ስንል ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ህጉን ፈቃዱን ጠይቀናቸዋል። ከመደበኛው ስልጠና የላቀ ስልጠና የሚያስፈልገው የፀጥታ ሃይል እንደሚያስፈልግ የሚያምኑት ምክትል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ ፈቃዱ ፀጋ የኮሚሽኑን ሪፖርት ግን ገና የምንመለከተው ነው ይላሉ። ‹‹ይህ የውሳኔ ሃሳብ ብሎም ያሉትን ህጎች ያለመፈፀም የሚያስቀጣው ሕግ አስከባሪውንም ነው፣ በኮሚሽኑ የተጠቀሰው መግለጫም መግለጫ ሆኖ አይቀርም፤ ለኛ ይላካል እንመረምረዋለን›› ሲሉ ፈቃዱ ለቢቢሲ ተናግረዋል። መንግሥት በትግራይ ክልል የመንግስት መዋቅር መፍረሱን ተከትሎ መደበኛ ፖሊስ፣ ማረሚያ ቤቶች ብሎም ፍርድ ቤቶች ወድመውብኛል በማለት ሲገልፅ ቆየቷል። ታዲያ መደበኛ የሕግ እና የፀጥታ መዋቅር በሌለበት ይህንን ውሳኔ የንፁሃንን መብት እና ደህንነነት ሳይጋፋ መተግበር ይቻላል ወይ ስንል ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ሕጉን ጠይቀናቸዋል። ‹‹በትግራይ ክልል በአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ምክኒያት የተወሰኑ ከመደበኛ የሕግ ስርአት የወጡ ተግባራት ይኖራሉ እነሱን እየመረመርን ነው›› ያሉት ፈቃዱ የሕግ ተቋማትን መልሰን እያቋቋምን ነው ሲሉም ተናግረዋል። ‹‹አንዳንዴ ከማዕከላዊ መንግስት በጣም የራቁ ቦታዎች ላይ ችግሮች እንዳሉ እንረዳለን፣ ለሕግ አስፈጻሚዎችም ተከታታይ ስልጠና እንሰጣለን›› ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የውሳኔው እንድምታ እና ውጤት ምን ይዞ ይመጣ ይሆን ? ምን አልባትም ይህ ውሳኔ በኦሮሚያ ብሎም በትግራይ ክልል እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን ወደ ሕግ ማዕቀፍ ለማምጣት እንዲሁም የእርምጃዎቹን ስፋት የሚጨምር ይሆናል ሲሉ አደም (ዶ/ር) ይናገራሉ። ከፋይናንስ አንፃር ሕወሃት ከሸኔ በላይ ከፍተኛ የሆነ ንብረት አለው ይላሉ። በቅርቡ ኢሕአዴግ ሲፈርስ የተከፋፈሉት ሃብት ትልቅ ነበር የሚሉት አደም ከምርጫ ቦርድ ሲሰረዝም የፓርቲው ንብረት በወኪል ተቆጣጣሪ ሲተዳደር የነበረው። ከዚህ ውሳኔ በኋላ ግን ይህ ገንዘብ ወደ መንግሥት እንዲወረስ ማድረጉ ከፍተኛ የሆነ እና የሚታይ ተጽእኖ ይኖረዋልም ይላሉ። ህወሓት አባላት የነበሩት የተመዘገበ ፓርቲ ነበር። ይህ አባላቱ በሙሉ ከዚህ በኋላ በአባልነት እንዲሁም በድጋፍ እንዳይቀጥሉ ያደርጋል ሲሉም አደም (ዶ/ር) ይናገራሉ። ‹‹እስከዛሬ የትግራይ ተወላጆችን በጥርጣሬ ብቻ እርምጃ ሲወሰድ ነበር። ይህ ውሳኔ ያንን በሕግ ማዕቀፍ ውስጥ ለማስገባት ብሎም ለማጠናከር የታሰበም ይመስላል›› ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ‹‹ይህንን የውሳኔ ሃሳብ የሚተገብረው በተለያዩ አካባቢ ያለው ሰው ነው። ሸኔ ማነው? ህወሓት ማነው? የሚለውን በመሬት ላይ ያለው ፈጻሚ በሚገባው ልክ የሚተገብረው እንደመሆኑ ከፍተኛ የሆነ የመብት ጥሰት ሊያስከትል መቻሉ እሙን ነው›› ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አደም በተለይም አንድ ቡድን አሸባሪ ተብሎ የሚፈረጅበት ሂደት በፍርድ ቤት የሚወሰን መሆን ነበረበትም ይላሉ። ይህ በተለይም የሚኒስትሮች ምክር ቤትም ሆነ የተወካዮች ምክር ቤት ፖለቲካዊ ተቋማት እንደመሆናቸው ውሳኔውን ለፖለቲካ አላማ ሊያውሉት መቻላቸውን እንደምክንያት ያነሳሉ። ሂደቱ ለሕግ ተርጓሚው ተሰጥቶ ቢሆን ሆሮ ግን እነዚህ ቡድኖች ማናቸው? ቡድኖቹ መሬት ላይ ያሉ ቡድኖች ናቸው ወይ? እንዲሁም አሸባሪ ቡድን ብሎ ለመፈረጅ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች ተሟልተዋል ወይ? የሚለውን ይመረምሩ ነበር ሲሉም አደም ያብራራሉ። ለዚህም በምሳሌነት ጋናን ያነሳሉ። ‹‹በጋና መንግሥት ያለውን መረጃ አቅርቦ ተመዝኖ ነው ይህ የሚወሰነለት›› የሚሉት አደም ‹‹ምርጫ ሳምንታት ሲቀረው የተወሰነ ውሳኔ መሆኑ በራሱ ይህ ነገር ሙሉ በሙሉ ከፖለቲካ ተፅዕኖ ውጪ ነው ብሎ ለማመን ከባድ ያደርገዋል›› ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። መጪው ምርጫ ላይ ያለው ተፅዕኖ ቀጥተኛ ላይሆን ቢችልም በተለይም መንግስት በአማራ ክልል ሸኔ ላይ እርምጃ አልወሰደም በሚል ሲወቀስ ቆይቷል፤ ይህንን ለመከላከል ያቀደ ሊሆን ይችላልም ብለዋል። ‹‹እነዚህ ቡድኖች መንግስትን ማሸነፍ ባይችሉ እንኳን ከፍተኛ ጫና መፍጠር የሚችሉ እንደሆነ የሚያሳይ ውሳኔ ነው። ምንም እንኳን ከአለማቀፍ ህብረተሰቡ የሚመጣውን የተደራደሩ ግፊት ለመከላከል መንግሥት ሊጠቀመው ይችላል። ውኔው አለማቀፍ ገዢነት ያለው ውሳኔ ስላልሆነ ግፊቱን ያቆመዋል የሚል ግምት የለኝም›› ሲሉ አደም ለቢቢሲ ገልፀዋል። በኦሮሚያ ክልል ግን ይህ መንግሥት እየወሰደ ያለው እርምጃ ሊጠነክር እንደሚችል ያሳያል፤ እንደ አደም። ‹‹እንደዛ ከሆነ በኦሮሚያ ክልል ያለው የጸጥታ ሁኔታ ሊባባስ እንደሚችል ያሳል። ይሻሻል እንኳን ቢባል ከዛ በፊት ሊያበላሸው ይችላል›› ሲሉ አደም ገለጸዋል።
41021976
https://www.bbc.com/amharic/41021976
ዓለማችንን በግኝቱ ወደፊት ያራመደው አይንስታይን ወጣ ባሉ ባህሪያቱም ይታወቅ ነበር።
ዓለማችን ካፈራቻቸው ታላ ላ ቅ ጠቢባን መካከል አልበርት አይንስታይን አንዱ ነው። አይንስታይን ከምጡቅነቱ ባለፈ ወጣ ባሉ ባህርያቱ ይታወቃል። ከኤነርጂ አቶም ማምረት እንደሚቻል ያሳየን አይንስታይን ፤ ምን ይታወቃል ለየት ካሉ ባህርያቱ አንድ ወይም ሁለት ነገር ያስተምረን ይሆናል። እነሆ አምስቱ። 1. የአስር ሰዓታት መኝታ እና የአንድ ሴኮንድ እረፍት
እንቅልፍ ለጤናችን እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው። አይንስታይንም ይህንን ምክር ችላ አላለውም። አሁን ላይ የአንድ አሜሪካዊ አማካይ የእንቅልፍ ጊዜ 6.8 ሰዓት ነው። አይንስታይን ግን በቀን ቢያንስ ለአስር ሰዓታት ይተኛ ነበር። ግን በቀን ለአስር ሰዓታት እየተኛ እንዴት ባለምጡቅ አእምሮ መሆን ይቻላል? ዓለማችንን ከለወጡ ግኝቶች መካከል እንደ አርኬያዊ ሰንጠረዥ ወይም ፔሪየዲክ ቴብል፥ የዘር ቅንጣት ወይም የዲኤንኤ መዋቅር እንዲሁም የአይንስታይን የአንፃራዊነት ፅንሰ ሀሳብ ወይም ሪላቲቪቲ ቲየሪ ፈጣሪዎቹ በእንቅልፍ ውስጥ ሳሉ የመጡላቸው ኃሳቦች ናቸው። አይንስታይን የአንፃራዊነትን ፅንሰ ሀሳብ ወይም ሪላቲቪቲ ቲየሪን ሊያስበው የቻለው በህልሙ ላሞች በኤሌክትሪክ ሲያዙ በማየቱ ነበር። እውነት ግን ይህ ነገር ተዓማኒ ነው? እ.አ.አ. በ2004 ዓ.ም. በጀርመን የሉቤክ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ያደረጉት ጥናት ጥሩ እንቅልፍ የሚያገኙ ሰዎች ጥሩ እንቅልፍ ካላገኙ ሰዎች ሁለት እጥፍ በተሻለ ሁኔታ በፍጥነት የማሰብና የማስታወስ ችሎታ እንዳላቸው ያሳያል። እንቅልፍ ላይ ስንሆን ተመራማሪዎቹ ስፒንድል ኤቨንትስ እያሉ የሚጠሯቸው በአዕምሯችን ውስጥ ያሉ ፍንጣቂዎች እንደ ጆሮ ሆነው በማገልገል መረጃ ከውጭ ወደውስጥ ያስገባሉ። የኦቶዋ ዩኒቨርሲቲው ኒውሮሳይንቲስት ስቱዋርት ፉገል እንደሚያምኑት "የአይንስታይን ምጡቅነት ከልህቀት ወይም ነገሮችን ከማስታወስ ጋር ብዙ ተያያዥነት የለውም። ለዚህም ነው አይንስታይን መደበኛ ትምህርት እና ቀላል ነገሮችን ማስታወስ ላይ ጥላቻ የሚያሳየው።" ከዚህም በተጨማሪ አይንስታይን አጠር ያለ እረፍት ማድረግ ያዘወትር እንደነበር ይነገራል። ከልክ ያለፈ እረፍት እንዳይወስድ በማሰብም በተቀመጠበት ወይም ጋደም ባለበት ቦታ በእጁ ማንኪያ ይይዛል። ከማንኪያው ትይዩ ከስር የብረት ሳህን ያስቀምጣል። እንቅልፍ ሲወስደው ልክ ማንኪያው ከእጁ ወድቆ ብረት ላይ በማረፍ በሚያሰማው ድምፅ ይነቃል። በዚህ ሁኔታ ለአንድ ሴኮንድም ቢሆን እረፍት ያደርግ እንደነበር ይነገራል። 2. የእግር መንገድ አይንስታይን የእግር መንገድን እንደተቀደሰ ተግባር ነበር የሚያየው። በኒው ጀርሲ ፕሪንስተን ዩኒቨርሲቲ በሚያስተምርበት ወቅት በቀን እስከ 1.6 ኪሎ ሜትር ድረስ በእግሩ ይራመድ ነበር። ቻርልስ ዳርዊንም በቀን ሶስት ጊዜ ለ45 ደቂቃዎች ይራመድ እንደነበረ ልብ ይሏል። አይንስታይን ይህንን ያደርግ የነበረው የሰውነቱን ቅርፅ ለመጠበቅ አልነበረም፤ እርግጥም የእግር እርምጃ ማድረግ ለማስታወስ፥ ለፈጠራ ችሎታ እንዲሁም ችግር ፈቺነትን ለማዳበር ጠቃሚ እንደሆነ የሚያሳዩ በርካታ መረጃዎች አሉ። 3. ፓስታ መመገብ የምጡቅ አዕምሮ ባለቤቶች ምን ይሆን የሚመገቡት? የአይንስታይን አዕምሮ በምን ኃይል እንደተሞላ ባይታወቅም በይነመረብ ወይም ኢንተርኔት ላይ አይንስታይን ፓስታ መመገብ አብዝቶ እንደሚወድ ተፅፏል። እንደውም በአንድ ወቅት " ከጣልያኖች ምን እንደሚመቸኝ ታውቃላችሁ. . .ፓስታቸው እና ሌዊ ሲቪታ (ጣልያናዊው የሒሳብ ሊቅ) ነው" ሲል ቀልዷል። ከሰውነታችን ሁለት በመቶ ብቻ ክብደት የሚይዘው አዕምሯችን ከምንበላው ሃያ በመቶውን ይጠቀማል። የአይንስታይን አዕምሮ ክብደት ከተለመደው የሰው ልጅ አዕምሮ በክብደት ያነሰ ነበር። ኃይል ሰጪ ምግብ ለአዕምሯችን ጥቅም ቢኖረውም ፓስታን አብዝቶ መመገብ ግን ሁሌም ጠቃሚ ላይሆን ይችላል ይላሉ የሮይሀምፕተን ዩኒቨርሲቲ አስተማሪ የሆኑት ሌይ ጊብሰን። 4. ፒፓ ትምባሆ እና መሰል ነገሮችን የማጨስ ጉዳቶች አሁን ላይ በሰፊው የሚታወቁ ነገሮች ናቸው። ይህም የሚያስረግጥልን ከአይንስታይን መሰል ልምድ መውሰድ የብልህ ተግባር እንዳልሆነ ነው። አይንስታይን በህይወት ዘመኑ ፒፓ ያጨስ ነበር። ፒፓ ማጨስ ሰዎች ፍርድ እናዳያጓድሉና ሚዛናዊነት እንዳይጎድላቸው ያግዛል ብሎም ያምናል። የሲጋራ ቁሩ መንገድ ላይ ካገኘም ወስዶ ወደ ፒፓው ይጨምራት ነበር። አይንስታይን ትምባሆ ማጨስ ለሳንባ በሽታ እንደሚያጋልጥ ጥናቶች ከማረጋገጣቸው ሰባት ዓመታት በፊት እ.አ.አ. በ1955 ዓ.ም. ነበር ሕይወቱ ያለፈው። ነገር ግን ስለትምባሆ ሲነሳ አንድ አስገራሚ ጥናት ሁሌም አብሮ ይነሳል። በአሜሪካ በ20 ሺህ ወጣቶች ላይ ለ15 ዓመታት ተግባራዊ የተደረገው ይህ ጥናት እንደሚጠቁመው የላቀ አስታሳሰብ ያላቸው ሕፃናት ሲያድጉ ትምባሆ አጫሾች እንደሚሆኑ ነው። እርግጥ ሁሉም ቦታ ይህ ፅንሰ ኃሳብ ተግባራዊ አይደለም። ለምሳሌ በዩናይትድ ኪንግደም ትምባሆ የሚያጨሱ ስዎች ንቃተ-ህሊናቸው ዝቅ ያለ ነው የሚል ጥናት አለ። 5. ካልሲ ምን ያደርጋል? የአይንስታይን ለየት ያሉ ባህርያት አሁን ከምንነግራችሁውጭ ብዙም ወዝ አይኖራቸውም ነበር። አይንስታይን ካልሲ አይወድም። አዎ ካልሲ አይወድም። ኋላ ላይ ሚስቱ ለሆነችው የአጎቱ ልጅ ኤልሳ በፃፈው ደብዳቤ አይንስታይን ሲናገር "ሁሌም አውራ ጣቴ የካልሲዬን ጫፍ ይቀደዋል፤ ከዛ በኋላ ካልሲ ማድረግ ተውኩኝ።" አንዳንዴ ሰንደል ጫማዎቹን ማግኘት ካልቻለ የሚስቱ ኤልሳን ታኮ ጫማ አድርጎ ይወጣ ነበር። እርግጥ ካልሲ አለመጠቀም ጥቅም እንዳለው የሚያሳይ ጥናት የለም። ነገር ግን ሁሌም አዲስ ነገር ከመሞከር ወደኋላ የማይለው አይንስታይን ከካልሲ ጋር ዓይን እና ናጫ እንደሆነ እ.አ.አ. ሚያዝያ 18 ቀን 1955 ዓ.ም. አለፈ።
news-43467268
https://www.bbc.com/amharic/news-43467268
ለተማሪዎች የሚሰጠው የቤት ሥራ ምን ያህል ቢሆን ጥሩ ነው? ይህ ጥያቄ በወላጆችና በመምህራን ተደጋግሞ የሚጠየቅ ነው።
የቤት ሥራዎች ተማሪዎችን ለትምህርታቸው ያግዛሉ?
"አዎ" ይላል ላውረን "ምክንያቱም የቤት ሥራ ብለን የምንሠራውን ካወቅን፤ በሚቀጥለው ትምህርት ላይ ምን መሥራት እንዳለብን እንገነዘባለን።" ግን የቤት ሥራ ይበዛል? "አንዳንድ ጊዜ ይበዛል" ይላል ሪያን "የጥበብ ትምህርትን ለመሳሰሉ ትምህርቶች የሚሰጡት የቤት ሥራዎች ለወደፊቱ ብዙም የሚጠቅሙ አይመስሉኝም።" የዘርፉ ባለሙያዎችስ ምን ይላሉ? ምላሻቸው የተደበላለቀ ነው። ከአራት ዓመት በፊት ይፋ የሆነ አንድ ለትምህርት ሚኒስቴር የቀረበ ትልቅ ሪፖርት እንዳሰፈረው በሳምንቱ ቀናት በአማካይ ከሁለት እስከ ሦስት ሰዓታት የቤት ሥራ ለመሥራት የሚያጠፉ 9 ዓመት የሆናቸው ተማሪዎች የቤት ሥራ ከማይሠሩት ከአስር እጥፍ በላይ ጥሩ ውጤትን በፈተና ላይ ያስመዘግባሉ። ታዲያ የቱ ጋር ነው መጠኑ የሚወሰነው? መቼ ነው የቤት ሥራ በጣም አስጨናቂ የሚሆነውና አሉታዊ ውጤትን የሚያስከትለው? ይህም ሱተን በተባለው ትምህርት ቤት ያሉ ተማሪዎች አብዝተው የሚያስቡት ጉዳይ ነው። "የቤት ሥራው የሚበዛና በቶሎ ተሠርቶ መቅረብ ካለበት እንዲሁም ቤት ውስጥ የሚሠራ ሥራ ካለ በእርግጥም በጣም አስጨናቂ ነው'' ይላል ፖርሽ "አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፤ ግን ጠቃሚ ይሆናል።" "ሥራ ለማግኘት ሊረዳን ስለሚችል ሂሳብና የቋንቋ ትምህርትን በደንብ ማወቅ እንዳለብን በተደጋጋሚ ሲነገረን ቆይቷል" ትላለች ሳማንታ "አንዳንድ ጊዜ በጣም ቀላል ይሆናል፤ አዲስ ዓይነት የቤት ሥራ ከሆነ ግን ያስቸግራል።" እስከ አውሮፓውያኑ 2012 ድረስ በእንግሊዝ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ምን ያህል የቤት ሥራዎችን ለተማሪዎቻቸው መስጠት እንዳለባቸው ምክር ይሰጣቸው ነበር። ነገር ግን አሁን ለተማሪዎቻቸው በሚስማማ ሁኔታ እራሳቸው እንዲወስኑ ተደርጓል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የተደረጉ ንፅፅሮች እንደሚያረጋግጡት አንድ ዓይነት ዘዴ ለሁሉም የትምህርት ስኬቶች ተግባራዊ ማድረግ እንደማይቻል ነው። ባለሙያዎች እንደሚሉት በቻይና የሚገኙ ተማሪዎች መጠኑ እጅግ የበዛ የቤት ሥራ የሚሰጣቸው ሲሆን በትምህርታቸውም ከፍተኛ ነጥብ ከሚያስመዘግቡ ተማሪዎች መካከልም ይመደባሉ። ነገር ግን ጣሊያን ምንም እንኳን በአንፃራዊነት ከፍተኛ መጠን ያለው የቤት ሥራ ለተማሪዎቿ ብትሰጥም በውጤት ረገድ ግን የሚንፀባረቀው የሚጠበቀውን ያህል አይደለም። በተቃራኒው ፊንላንድ ውስጥ በእንግሊዝ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች አንፃር ለቤት ሥራና ለፈተናዎች የሚሰጠው ትኩረት ዝቅ ያለ ነው። ከብሔራዊ ትምህርት አንፃር ሌሎች ነገሮችም ከግምት ውስጥ መግባት አለባቸው። እያንዳንዳቸው ተማሪዎች የተለዩ በመሆኑ የሚሰጣቸውንም የሚሠሩት በተለያየ መንገድ ነው። ትምህርት ቤቶችም የተለያዩ ደረጃዎች አሏቸው። በተጨማሪም ተማሪዎች በየቤታቸው ያላቸው የተረጋጋ ሕይወት በአጠቃላይ የትምህርት ተሳትፏቸውና የቤት ሥራቸውን በሚያከናውኑበት ብቃት ላይም ጉልህ ሚና አለው። ለማጠቃለልም፤ የቤት ሥራ ጠቃሚ ነው በተማሪዎች ላይም ልዩነትን ያመጣል። ነገር ግን ቁጥሩ የበዛ የቤት ሥራ ለተማሪዎች መስጠት ጥሩ ውጤትን እንዲያመጡ አያደርጋቸውም። በሌላ አባባል በቤት ሥራውና በዕለት ተለት ሕይወት ውስጥ ያለውን ሚዛን መጠበቅ በርካታ ወላጆችን የሚያሳስባቸው ከመሆኑ በተጨማሪ በትምህርት ቤት ላሉ ተማሪዎችም ወሳኝ ነገር ነው።
news-45339565
https://www.bbc.com/amharic/news-45339565
አቶ ታደሰ ካሳ፡ "ሙሉ ሕይወቴን ለአማራ ሕዝብ ጥቅም ነው ስሠራ የኖርኩት"
የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ ታደሰ ካሳን እና አቶ በረከት ስምኦንን ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ማገዱ ይታወሳል።
አቶ ታደሰ ካሳ አቶ ታደሰ የብአዴንን ውሳኔ በተመለከተ፤ በጥረት ኮርፖሬሽን ውስጥ ስለነበራቸው ተሳትፎ እንዲሁም ቀጣይ የፖለቲካ ህይወታቸው ምን ሊመስል እንደሚችል ለቢቢሲ አካፍለዋል። ጥያቄ፦ ከብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ለምን የታገዱ ይመስልዎታል? አቶ ታደሰ፦ የጥረት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ነበርኩ። ለዘጠኝ ዓመት ያህል አገልግለናል። በዛ ቆይታ ጥረት ብዙ ለውጥ አምጥቷል። እኔ አመራር ላይ እያለሁ በጣም አስደናቂ ለውጥ እያመጣ የነበረ ደርጅት ነው። ሂደቱ የማይስማማቸው ሰዎች ይኖራሉ። አንዳንድ የሚነሱ ነገሮች ነበሩ። ችግር አለ ይባል ነበር። እኛም በየጊዜው እየተማርን ነው ሥራውን ስንመራ የነበረው። የቢዝነስ ሥራ ነው። በ20 ሚሊየን ብር ተጀምሮ እኔ በምወጣበት ጊዜ ወደ 11 ቢሊየን ብር ካፒታል ያላቸው 20 ኩባንያዎችን ነው የፈጠርነው። ጉድለት ነበር የሚለውን አስቀድመን ራሳችን ያየነውና እየገመገምን፣ መጨረሻም ሥር ነቀል የሆነ መፍትሄ ለማምጣት የሚችል ሥራ ስንሠራ ነው የነበረው። ከዛ የጤንነትም የዕድሜም ጉዳይ ስላለ ከዚህ በኋላ «ጥረት» ላይ በቃኝ በሚል ሚያዝያ ወር ላይ በራሴ ለቅቄ ወጣሁ። ጥያቄ፦ በራስዎ ፍቃድ እንጂ ተገድጄ አይደለም የወጣሁት እያሉ ነው? አቶ ታደሰ፡- ደብዳቤው እኮ በእጄ አለ። በግልጽ ነግሬያቸው ነው…። አሉ የምትሏቸውን ጉድለቶች ራሳችን የገመገምናቸው ናቸው። ከዚ ውጪ ያባከንነው ገንዘብ የለም። በግልም ደግሞ የሠራነው ጥፋት የለም። በዚህ ረገድ ማንም ደፍሮ ይሄን ሀብት ወስደሀል፤ ይሄን አድርገሀል የሚለኝ ካለ ይምጣ። የጀመርኳቸው አምስት ፕሮጀክቶች ስለነበሩኝ 'የኮርፖሬት ፋይናንሱን ወርልድ ክላስ ለማድረግ'…፣ ነው ትንሽ የቆየሁት እንጂ፤ ለመውጣት ካሰብኩኝ ቆይቷል። • አቶ በረከት ስምኦን ከብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት ታገዱ • የብአዴን መግለጫ፡- ከስያሜ መቀየር እስከ ኢትዮ ሱዳን ድንበር • ያለመከሰስ ለማን? እስከምን ድረስ? 'እኛ ስለማንፈልግ ውጣ የምትሉኝ ከሆነ እናንተ ልቀቅ ስላላችሁኝ ወይም እናንተ ስላገዳችሁኝ አልወጣም፤ እስከመጨረሻው ድረስ እታገላችኋለሁ። ቆይም ብትሉኝ አልቆይም። በራሴ ውሳኔ ለቅቄ ነው የምወጣው' የሚል ነገር ተነጋግረን፣ 'ባንተ ውሳኔ ነው' ተብሎ ደብዳቤውም በዛ ነው የተሰጠኝ። ሚያዝያ ላይ ከ3000 በላይ የክልሉ ካድሬ በተሰበሰበበት 'በራሱ ፍቃድ ጠይቆ ነው የወጣው' ብሎ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩም ተናግሯል። ሰለዚህ ከጥረት በራሴ ነው የወጣሁት። ጥያቄ፦ ከማእከላዊ ኮሚቴ እባረራለሁ ብለው ይጠብቁ ነበር? አቶ ታደሰ፦ አንደኛ ያለፈው ሰባተኛው ጉባኤ ላይ እኛ አንመረጥም እያልን አባላት መመረጥ አለባቸው ተብሎ አስገድደውን ነው የተመረጥነው። ከተመረጥን በኋላ ደግሞ በቃ ብትመርጡንም አንቀጥልም ብለን ስናንገራግር ነው የቆየነው። የዛሬ ሦስት ዓመት በነበረው ጉባኤ ላይ አንመረጥም ያልነው 'ለውጥ የለውም፣ ይሄ ድርጅት ሊለወጥ ፍቃደኛ አይደለም። ባለፈው ምርጫም ቢሆን ሕዝቡ ማስጠንቀቂያ ነው የሰጠን እንጂ ደግፎን አልመረጠንም። ስለዚህ አሁንም ካልታረምን በስተቀር በ2008 አመጽ አይቀርም በሚል በግልጽ ነበር ስናነሳ የነበረው። ጥያቄ፦ ግን እንደዚህ ዓይነት ሐሳቦችን የሚያነሱት ስለተባረሩ ነው ወይስ ከዛ በፊትም ለሕዝብ አሳውቀዋል? አቶ ታደሰ፦ አይደለም! አይደለም። የድርጅታችን ባህል አለ። በድርጅቱ አመራር ውስጥ ትታገላለህ። ከድርጅቱ እስካለቀቅክ ድረስ በአደባባይ አትናገርም። በድርጅታችን ጉባኤ ስንናገር ነበር። በጉባኤ ላይ ስንታገል ነበር። አንመረጥም ስንል ነው የነበረው። አባላት ያውቁታል ይሄን። በድርጅቱ ሰነዶች የተመዘገበ ነው። ጥያቄ፦ ለምን ይመስልዎታል ታዲያ እርስዎና አቶ በረከት ድጋፍ እያጣችሁ የመጣችሁት? አቶ ታደሰ፦ ዘረኛ የሆኑ አስተሳሰቦች በድርጅታችን ነበሩ፤ አንቀበልም አልን። 'የዚህ ብሔር የበላይነት አለ። ይሄኛው ብሔር አማራን ጎዳ፤ ይሄ ተጠቀመ ምናምን' የሚባል ነገር ስንታገል ቆይተናል። ከዚያ ውጭ ግን ዘረኝነቱ አለ። ከአቶ በረከት ጋር የሚነሳው እናትና አባቱ የኤርትራ ሰው ስለሆኑ የሚል ነው። እኔም ኮረም አካባቢ ስለሆነ የተወለድኩት ከዚህ ጋር ተያይዞ ዘረኝነት አለ። 'ሰው ለየትኛው ዓላማ ይታገላል?' የሚለው ሳይሆን እያንዳንዱ ሰው ባደገበት አገር፣ በገነባው ሥነ ልቦና ነው የሚታገለውና የሚኖረው። ቤተሰቡ ከየትም ቦታ ሊመጡ ይችላሉ። ግን ተወልዶ ያደገበት አካባቢ ላይ ደግሞ የሱ ሥነልቦና ይገነባል። በዚያ ሥነ ልቦና ተመርኩዞ በዚያ በዚያ ነው የማንኛውም ሰው እንቅስቃሴ የሚለካው ብለን እናምናለን። ሆኖም እነዚህ የቆዩ የዘረኝነት ቅሪቶች አሉ። አኔ የተወልዱት ኮረም በሚባል አካባቢ ነው። ኮረም አሁን ትግራይ ክልል ያለበት ቦታ ነው። ስለዚህ ቤተሰቦቼ አማራም፣ አገውም፣ ትግራይም የሦስቱም ቅልቅል ያለባቸው ናቸው። እና ንጹሕ አማራ አይደለም የሚባለው ነገር… አለ። እኔ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም የብአዴን አመራሮችም በተለያየ ጊዜ እንዲህ ዓይነት ነገር ይነሳባቸዋል። ጥያቄ፦ እርስዎ ራስዎን ከየትኛው ብሔር ነኝ ነው የሚሉት? አቶ ታደሰ፦እኔ ወሎ ወስጥ ነው ያደኩት፤ ወሎዬ ነኝ መታወቂያዬም አማራ የሚል ነው። ጥያቄ፦ ባለፉት ዓመታት የአንድ ፓርቲ የበላይነት ነበረ ብለው ያምናሉ? አቶ ታደሰ፡- አልነበረም። ኢህአዴግ የአራት አቻ ፓርቲዎች ድርጅት ነው። እያንዳንዱ ድርጀት በእኩል ይወከላል። እኩል ድምጽ አለው። አንዱ የበላይ ሆኖ ሊያዝበት የሚችል ድርጅታዊ አሠራር አልነበረም። ጥያቄ፦ ብአዴን በህወሓት ይዘወር ነበር የሚለውን ሐሳብ ይቀበሉታል? አቶ ታደሰ፦ ይሄንን አልቀበልም። ብአዴን ድርጅታዊ ነጻነቱን ጠብቆ የሚሄድ ድርጅት ነው። ህወሓትም እንደ ድርጅት እኔ ያልኳችሁን ብቻ ፈጽሙ የሚል ድርጅት አልነበረም፣ በባሕሪው። ብአዴን የሕወሓት ተጎታች ሆኖ አያውቅም። የኢትዮጵያ ችግርም የአንዱ የበላይ የመሆን ችግር ነበር ብለን አናስብም። ጥያቄ፦ ለአማራው ታግያለሁ ብለው ያስባሉ? አቶ ታደሰ፦ እኔ ዕድሜ ልኬን፣ ሙሉ ሕይወቴን ለአማራ ሕዝብ ጥቅም ነው ስሠራ የኖርኩት። ያንን ሕዝብ ወክዬ ስታገል ኖሪያለሁ። ጥቅሙን ለማስከበር ስታገል ኖሪያለሁ። አልታገልክም የሚለኝ ሰው ካለ ያላደረኩበትን መንገድ መናገር ያለበት እሱ ነው። ጥያቄ፦ በፓርቲ ደረጃም በሕዝቡም ለምን ተቃውሞ የበረታባችሁ ይመስልዎታል? አቶ ታደሰ፦ሕዘቡ ኢህአዴግ ላይ ያሳደረው ጥላቻ 'አንደርስታንደብል' ነው። ድክመቶች አልተፈጠሩም የሚል አስተሳሰብ የለንም። ሁለተኛ አመራር ላይ በነበርንበት ሁኔታ ላይ እኛ ነባር አመራር ስለሆነ ድክመቶቹን ኋላ የመጡ ሰዎች ናቸው የፈጠሯቸው ብለን አንልም። በጋራ የተሠሩ ስህተቶች አሉ። በጋራ ተጠያቂ ነን። በ17ቱ ቀን ውይይት ሁሉንም ጨርሰነዋል እኮ። ከዚህ በኋላ መሠረታዊ ለውጥ ካላመጣን አደጋው የአገር አደጋ ነው ብለን ተስማምተን ወጥተናል። ማንም ይመረጥ ማንም አብረነው እንጓዛለን ብለናል። ከዚያው ውጭ ግን አንዱ ተጠያቂ፣ አንዱ ነጻ የሚባል ነገር ብዙም የሚያስኬድ አይመስለኝም። ጥያቄ፦ አሁን ላይ የሚታየውን ለውጥ ዶክተር ዐብይ ያመጡት ነው ብለው ያምናሉ? አቶ ታደሰ፦ እርሳቸውም እኔ ያመጣሁት ለውጥ ነው ሲሉ ሰምቼ አላውቅም። ኢህአዴግ መለወጥ አለብኝ ብሎ፣ ሰፊ ግምገማ አድርጎ፣ ለሠራው ጥፋትም የኢትዮጵያ ሕዝብን ይቅርታ ጠይቆ የመጣ ለውጥ ነው። እርሳቸውንም የመረጣቸው ኢህአዴግ ነው። ስለዚህ ኢህአዴግ እያካሄደ ያለው ለውጥ አድርጎ ማየት ትክክል ነው የሚመስለኝ። የርሳቸውን አካሄድ በሚመለከት ኢህአዴግ ውሳኔ ይወስናል፤ የወሰነውን ውሳኔ ለመተግበር አመራሮችን ያደራጃል። ዶክተር ዐብይ ፈጣን የሆኑ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ረገድ ጥሩ እየሄዱ እንደሆነ እገነዘባለሁ። የኢህአዴግ ውሳኔዎች መሆናቸው አንዳለ ሆኖ ማለቴ ነው። ጥያቄ፦ ጥቃት ይደርስብኛል ብለው ይሰጋሉ? አቶ ታደሰ፦ እኔ በመጀመሪያ ደረጃ የኢትዮጵያ ሕዝብ አስተዋይ ሕዝብ እንደሆነ አምናለሁ። ሁለተኛ በግሌ ለጥቃት የሚያጋልጠኝ የሠራሁት ጥፋት አለ ብዬ አላምንም። ስለዚህ ጥቃት ይደርስብኛል ብዬ የምጨነቅባቸው ነገሮች የሉም። ይህ እንዳለ ሆኖ ጥቃት ቢመጣ ደግሞ ምንም የምፈራበት ምክንያት የለም። ለኔ አሁን ያለሁበት ሕይወት ትርፍ ሕይወት ነው። ብዙ መስዋእትነት አልፈን ነው እዚህ የደረስነው። የማምነበትን ነገር እናገራለሁ፤ እሠራለሁ። ከዚህ አንጻር በስጋት አገሬ ጥዬ የምሄድበት ሁኔታ የለም። በይፋ እየተንቀሳቀስኩ ነው ያለሁት። አንዳንድ ቦታዎች ላልሄድ እችላለሁ። ከሁሉ በፊት መቅደም ያለበት ግን የአገራችን ሰላም ነው። እኔ፣ የኔ መስዋእትነት ተከፍሎ አገር ሰላም የሚሆን ከሆነ ደስታውን አልችልም። ጥያቄ፦ ከ"ጥረት" ጋር በተያያዘ በምዝበራ የሚጠየቁ ይመስልዎታል? አቶ ታደሰ፡-ሁሉም በይፋ ያለ ነገር ነው። በኦዲት እየተረጋገጠ የሄደ ነገር ነው። ሁሉም ነገር መሬት ላይ ነው ያለው። ፋብሪካዎቹ አሉ፤ ሰነዶቹ አሉ። በዚያ ማረጋገጥ ይቻላል። አሁን እኔ በዚህ ጉዳይ ላይ 'ተጠያቂ እሆናለሁ፤ እርምጃ ይወሰድብኛል' የሚል ስጋቱም ፍርሃቱም የለኝም። የሚመጣ ነገር ካለም ለመብቴ እታገላለሁ። ጥያቄ፦ ከኢህአፓ-ኢህዴን፣ ከኢህዴን- ብአዴን…ቀጣይ ሕይወትዎ ወዴት ያመራል? አቶ ታደሰ፡-ከ40 ዓመት በላይ ፖለቲካ ሕይወት ውስጥ ኖረናል። አሁን መጽሐፍ የምንጽፍበት፤ በማኅበራዊ ጉዳዮች የምንሳተፍበት የማረፊያ ዕድሜ ላይ ነን። ወደ አክቲቭ ፖለቲካ ግን አልመለስም።
52450157
https://www.bbc.com/amharic/52450157
ኮሮናቫይረስ፡ ኤርትራውያን ስደተኞች ስጋት በኢትዮጵያ
"ስደተኞች መመዝገብ ተከልክሏል፤ ወደ አገራችሁ ተመለሱ።"
"አንመለስም።" "አንመለስም ካላችሁ ለ14 ቀናት ለይቶ ማቆያ ትገባላችሁ። ሙሉ ወጪያችሁንም እራሳችሁ ትሸፍናላችሁ።" "ገንዘብ የለንም።" "ኋላ ላይ ተቸገረን እንዳትሉ አስቀድመን እየነገርናችሁ ነው።" "ምርጫ የለንም፤ እኛም አሁን እንደማንመለስ እየነገርናችሁ ነው።" ይህ ምልልስ ኢትዮጵያና ኤርትራን በሚያዋስነው ራማ-ክሳድ ዒቃ ድንበር በኤርትራውያን ስደተኞችና በኢትዮጵያውያን ድንበር ጠባቂዎች መካከል የተደረገ ነው። ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጇ ይታወሳል፤ ማንኛውም ከሌላ አገር የሚመጣ ሰው ደግሞ ለ14 ቀናት መንግሥት ባዘጋጃቸው ለይቶ ማቆያ ማዕከላት ገብቶ መቀመጥ እንዳለበት ተደንግጓል። በማቆያ ማዕከሉም የራሱን ወጪ መሸፈን እንዳለበት ከዚህ ጋር ተያይዞ ተነግሯል። በእርግጥ በአዲስ አበባ አቅም ለሌላቸው ተመላሾች የከተማ አስተዳደሩ ያዘጋጀው መቆያ እንዳለ ተገልጿል። ይህ ግን በአዲስ አበባ እንጂ በትግራይ የለም። • ኤርትራውያን ስደተኞች በድንበር በኩል ምዝገባ ተከልክለናል አሉ በድንበር በኩል ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ ተሻግረው ለሚመጡ ሰዎች በአካባቢው እራሳቸውን ለይተው የሚያቆዩባቸው የተዘጋጁ ማዕከላት የሉም። በየዕለቱ በርካታ ኤርትራውያን ድንበር እያቋረጡ ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ። በቅርቡ ኢትዮጵያና ኤርትራን በሚያዋስነው ራማ-ክሳድ ዒቃ የገቡት ኤርትራውያን ስደተኞች፤ በአንድ ግንባታው ያላለቀ ህንጻ ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ቢቢሲ ያናገራቸው ስደተኞች ይገልጻሉ። እነዚህ ስደተኞች ስማቸው እንዳይገለፅ ቢቢሲን ጠይቀዋል። የከተማዋ ሕዝብ በተቻለው መጠን ድጋፍ እያደረገላቸው እንደሆነ ለቢቢሲ የገለፁት እነዚህ ስደተኞች፣ አቶ ተክኤ የተባሉ አንድ የከተማዋ ኗሪ በርካታ ገንዘብ አውጥተው እንደደገፏቸው ይገልጻሉ። ሆኖም ከእለት ወደ እለት ቁጥራቸው እየጨመረ ስለመጣ ሁሉንም በግል አቅማቸው ብቻ ለመርዳት እንደተቸገሩና የሚመለከተው አካል ኃላፊነት ወስዶ እንዲረዳቸው መጠየቃቸውን ያስረዳሉ። በስፍራው ለሁለት ሳምንታት የቆዩት ደግሞ፤ የትግራይ ክልል መንግሥት በደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሰረት ከከተማ ወደ ከተማ መንቀሳቀስ ስለማይችሉ፤ በሌላ ግንባታ ላይ ባለ ህንጻ ውስጥ መቀመጣቸውን ገልፀዋል። አንዳንዶቹም ቢሆኑ በከተማዋ ውስጥ በሚገኙ የሻይ ቤቶች ተጠግተው በርካታ ቀናቶች እንዳሳለፉ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በሌላም በኩል ደግሞ፤ በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ሸራሮ ከተማ፣ 300 የሚጠጉ ኤርትራውያን ስደተኞች በትምህርት ቤቶች ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ። በሸራሮ ከተማ እንኳን ለስደተኞች ለአካባቢው ኗሪም ለቀላል በሽታዎች እንኳ የሚውል የመድኃኒት አቅርቦት እጥረት መኖሩን ቢቢሲ ያነጋገራቸውና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉት የከተማዋ ነዋሪ ያስረዳል። "ለራስ ምታት ሆነ ለተቅማጥ የሚሆን መድኃኒት ባለመኖሩ፤ ስደተኞቹ ችግር ላይ ናቸው" በማለት ለቢቢሲ የተናገሩት እኚህ ግለሰብ፣ "ከሁሉም በላይ ግን ከባድ የውሃ እጥረት ችግር አለ" በማለትም አክለዋል። በዚህ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመግታት እጅን ደጋግሞ በውሃና ሳሙና መታጠብ አስፈላጊ በሆነበት ወቅት፤ በትግራይ ክልል ስደተኞቹ በሚገኙባቸው ስፍራዎች ሁሉ የውሃ እጥረት መኖሩን ቢቢሲ ካነጋገራቸው ሰዎች መረዳት ችሏል። ስደተኞቹ በሚጠለሉባቸው ጣቢያዎች፤ በአንድ ቤት ውስጥ በርከት ያሉ ሰዎች በጋራ ስለሚኖሩ በዚህ በሽታ የታመመ ሰው ቢኖር ለይቶ ለማቆየትም ሆነ ለመከላከል ያላቸው እድል ጠባብ መሆኑንም ጨምረው ያስረዳሉ። በመሆኑም ስደተኞቹ የመሰረታዊ ሸቀጦች መወደድና ለይቶ ማቆያና ማከሚያ ያለመኖር ከሚያሳስባቸው ይልቅ፤ የውሃ እጥረት ከልክ በላይ እንደሚያስጨንቃቸው ገልፀዋል። ኤርትራውያን ስደተኞች ከሚገኙባቸው የመጠለያ ጣቢያዎች አንዱ የሆነው ሕጻጽ ይዘጋል በሚልም ብዙዎች ጭንቅ ላይ እንደሆኑ ቢቢሲ ያነጋገራቸው ስደተኞች ገልፀዋል። የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት፤ በየዓመቱ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ስደተኞች የሚመድበው በጀት በሁለት ሚሊዮን ዶላር እንደቀነሰና፤ በትግራይ ለሚገኙ ስደተኞች የሚውል የዚህ ዓመት በጀት በ34 ሚሊዮን ብር በመቀነሱ፤ ስደተኞቹን ወደ ሌሎቹ ካምፖች ማሸጋሸግ አስፈላጊ እንደሆነ ስሙን እንዲገለጽ ያልፈቀደ የትግራይ ክልል የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት ሠራተኛ ይናገራል። የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንን የስደተኞች ማሸጋሸግ ሥራ ባለፈው ወር እንደሚያከናውን ለተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኤጀንሲ ቢያሳውቅም፤ በአገሪቱ ኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው ከተገኘ በኋላ እንደተራዘመና ማዟዟሩ በሚያዚያ ወር መጨረሻ እንደሚጀመር የድርጅቱ ምክትል ዳይሬክተር አቶ እዮብ አወቀ ለፈረንሳይ የዜና ወኪል ገልፀዋል። ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ ስደተኞች ድርጅት (ዩኤንኤችሲአር) ተወካይ የሆኑት አን ኤኖክተር፤ ተቋሙ ከዚህ ዓመት ጀምሮ ለኢትዮጵያ የሚሰጠው እርዳታ በ14 በመቶ መቀነሱን አረጋግጠው፤ ይህ ግን ካምፑን ለመዝጋት በቂ ምክንያት እንዳልሆነ ለኤኤፍፒ ተናግረዋል። በዚህ ወቅት ስደተኞቹን ወደ ሌላ መጠለያ ጣቢያ ማዟዟር ለኮሮናቫይረስ እንደሚያጋልጣቸው በመግለጽ፤ ሌሎቹ የስደተኞች መጠለያዎችም በውሃና የህክምና አገልግሎት ችግር ላይ እንዳሉ ጠቅሰዋል። ቢቢሲ ያነጋገረው የትግራይ ክልል ስደተኞች ጉዳይ ድርጅት ሠራተኛ ግን ስደተኞች የሚገኙባቸው የዓዲ ሓርሽና ማይ ዓይኒ መጠለያ ጣቢያዎች የኤሌክትሪክና የውሃ አገልግሎት በማግኘት ሕጻጽ ከተባለው ካምፕ የተሻሉ መሆናቸው ይገልጻል። በኢትዮጵያ የስደተኞች ጉዳይ የሚከታተለው አካል አዲስ የሚገቡ ስደተኞችን መመዝገብ ስላቆመ፤ ሳይመዘገቡ በተለያዩ አካባቢዎች ወድቀው የሚገኙት ስደተኞች ደግሞ፤ የክልሉ ሕዝብ እና አንዳንድ ኤርትራውያን በሚሰጧቸው ጊዜያዊ እርዳታዎች የዕለት ኑሯቸውን እንደሚገፉ ለቢቢሲ አስረድተዋል። እነዚህ ስደተኞች በቀይ መስቀልና የትግራይ ክልል መንግሥት እርዳታ እየተደረገላቸው ቢሆንም፤ ከባድ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ ውስጥ እንደሚገኙ፣ ኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚያስፈልጉ እቃዎች ለመለገስ ወደ ስፍራው የሄዱ በመቀለ የሚኖሩ ኤርትራውያን ለቢቢሲ ገልጸዋል። የሰሜናዊ ምዕራብ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ተክላይ ገብረመድኅን በበኩላቸው፤ የፌደራል መንግሥት አዲስ የሚገቡ ስደተኞች የማይቀበላቸው ከሆነ፤ የትግራይ መንግሥት የመኖሪያ ፍቃድ ሰጥቶ በፈለጉት አካባቢ ሄደው እንዲኖሩ ለመፍቀድ እንደሚገደድ ጠቁመዋል። በአሁኑ ወቅት በሽረ ከተማ ብቻ 2 ሺህ ኤርትራውያን ህጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ ተሰጥቷቸው በተለያዩ የንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ እንደሚገኙ አቶ ተክላይ ይናገራሉ። • በኢትዮጵያ ስላሉ ስደተኞች አንዳንድ ነጥቦች ሂዩውመን ራይትስ ዋች ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት አዲስ ስደተኞችን አልቀበልም ማለቱ "ኢሰብአዊና ዓለም አቀፋዊ ሕጎችን የሚጥስ" በመሆኑ፤ ተቀባይነት የለውም ብሏል። በትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኙት የስደተኞች መጠለያ ማዕከላት ውስጥ 80 ሺህ ኤርትራውያን ስደተኞች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚገመት አቶ ተክላይ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
news-50420557
https://www.bbc.com/amharic/news-50420557
“ከብሔርም ከሐይማኖትም በላይ ሰውነት ከሰሃራ በረሃ ስቃይ አውጥቶኛል"
ከሰሃራ በረሃ ሃሩር፣ ከደላሎች ዱላና እንግልት ተርፎ ጀርመን የሚኖረው ሃሩን አሕመድ፣ በበረሃው ውስጥ አቅም አጥቶ ሲወድቅ የደገፉትን፣ ሲታረዝ ያለበሱትን፣ በውሃ ጥም የከሰለ ከንፈሩን ያረሰረሱለትን ሲያስታውስ "የሰው ልጅ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ተቻችሎ መኖር እንዳለበት ብዙ ተምሬያለሁ" ይላል።
"በብሔርና በሃይማኖት ያቻቻለን የሰሃራ በረሃ ስቃይ" ሃሩን አሕመድ በባሌ ዞን አጋርፋ የተወለደው ሃሩን፣ እንደማንኛውም ወጣት በፖለቲካ ምክንያት ችግር ቢደርስበትም እርሱ ግን "ከሀገር የወጣሁት በግል ምክንያት ነው" ይላል። እኤአ በ2013 ከሻሸመኔ ተነስቶ ወደ ሱዳን አመራ። ከአንድ ዓመት የሱዳን ኑሮ በኋላ እዚያ ከሚገኙ ከአራት ጓደኞቹና ከሌሎች ስደተኞች ጋር በ2014 መጀመሪያ ወደ ሊቢያ ጉዞ ጀመሩ። • ህወሓት፡ ሃገራዊ ምርጫ የሚራዘም ከሆነ ትግራይ የራሷን ምርጫ ታካሂዳለች "ከካርቱም ትንሽ ወጣ ያለ ቦታ ላይ ከኤርትራዊያን፣ ሶማሊያዊያንና ሱዳናዊያንና ከኢትዮጵያ ከተለያዩ አካባቢዎች ከመጡ ስደተኞች ጋር ሰበሰቡን" ሲል በወቅቱ የነበረውን ያስታውሳል። ስቃያችን የጀመረው ገና ከካርቱም ስንነሳ ነው የሚለው ሃሩን፤ ሁሉንም በጋራ የሰበሰቡበት ስፍራ ከመድረሳቸው በፊት የያዙትን አራግፈው እንደወሰዱባቸው ሲናገር "ሴቶችን ልብስ አስወልቀው ጭምር ነበር የፈተሿቸው" በማለት ወርቅና ገንዘባቸውን እንደወሰዱባቸው ይገልጻል። ሁለት ቀን እዚያ በረሃ ውስጥ ካሳደሯቸው በኋላ ወደ ሰሃራ የሚወስደዳቸው ግለሰብ መጥቶ መንገድ ጀመሩ። በአንድ መኪና ላይ ከ90 በላይ ሰዎች ሲጫኑ ሁሉም እንደትውውቃቸው፣ እንደመጡበት ሀገርና አካባቢ ብሔራቸውን ጭምር መሰረት አድርገው መቧደናቸውን ያስታውሳል። • እሷ ማናት፡ ዘቢብ ካቩማ "ለዩኤን እሠራለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም" አራት ቀንና ሌሊት ከተጓዙ በኋላ መኪናዋ ላይ የተሳፈሩ ስደተኞች ጥል እየተካረረ መጣ። ሰዎች ከፍርሃትና ከተስፋ መቁረጥ የተነሳ የራሳቸውን ምግብና ውሃ እየደበቁ የሌላ ግለሰብ ስንቅ መስረቅ በመጀመራቸው አለመግባባቱ ወደ ድብድብ አደገ። መጎሻሸሙ፣ ቡጢውና ጉልበት መፈታተሹ እርስ በእርስ ብቻ ሳይሆን ወደ ሰሃራ ይዟቸው እየሄደ ከነበረው ግለሰብ ጋርም ሆነ። ጉዞ በጀመሩ በሰባተኛው ቀን ሱዳን፣ ግብጽንና ሊቢያን የሚያዋስነው ድንበር ላይ ስደተኞችን የሚለዋወጡበት ስፍራ ደረሱ። ስፍራው ላይ ሲደርሱ ግን እድል ከእነርሱ ጋር አልነበረችም። ከሊቢያ ሊቀበላቸው የመጣው ግለሰብ በታጣቂዎች ተይዞ ጠበቃቸው። ቀደም ብሎ እኔ ስለተያዝኩ አታምጣቸው ብሎ ይዞን እየሄደ ለነበረው ሰው መልዕክት ልኮለት ነበር የሚለው ሃሩን "እርሱ ግን ከእኛ ጋር ተጣልቶ ስለነበር የራሳቸው ጉዳይ በሚል ስሜት ነበር ይዞን ሄደ" ይላል። በሦስቱ ሃገራት ድንበር ላይ ሲደርሱ ወደ ስምንት የሚሆኑ መኪኖች ከብበዋቸው፣ መሳሪያ ከደቀኑባቸው በኋላ እነ ሃሩንንም ሆነ ከሱዳን ይዟቸው የሄደውንና ከሊቢያ ሊወስዳቸው የመጣውንም አንድ ላይ ወሰዷቸው። መሳሪያ መታጠቃቸውን እንጂ ምን እንደሆኑና ማን እንደሆኑ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ የሚገልፀው ሃሩን ከበርሃ ወጥተው እንደከበቧቸው ያስታውሳል። "እነዚህ ታጣቂዎች ያለምንም ምግብና ውሃ ሁለት ቀንና ሌሊት ይዘውን ከሄዱ በኋላ የማይታወቅ በረሃ ውስጥ አወረዱን። ለአንድ ሰው 5ሺህ ዶላር ካልከፈልን ከዚያ መንቀሳቀስ እንደማንችል ነገሩን። እኛ ብቻ ሳንሆን ከሊቢያ ሊወስደን የመጣው ሰውዬም ያለንበትን ስፍራ አያውቀውም ነበር።" • ኢትዮጵያ ወይስ ናይጄሪያ? የትዊተር አለቃ የፈጠረው ክርክር ከዚህ በኋላ 5ሺህ ዶላሩን መክፈል የምትችሉ መኪና ላይ እንዲወጡ የማይችሉ ግን እዚያው እንዲቆዩ ተነገራቸው። ኤርትራዊያንና ሱዳኖች እንከፍላለን ብለው መኪና ላይ መውጣታቸውን የሚናገረው ሃሩን፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊያኖች ግን ገንዘብ ለመክፈል እንደማይችሉ ተናግረው እዚያወቅ ለመቆየት መወሰናቸውን ያስታውሳል። በኋላም ኤርትራዊያኑንና ሱዳናዊያኑን ይዞ የሄደው መኪና መንገድ ከጀመረ በኋላ ተመልሶ በመምጣት በመሳሪያና በዱላ እያስፈራሩ መኪናው ላይ እንዳሳፈሯቸውና እንደወሰዷቸው ይናገራል። ሃሩን አህመድ የተጓዘበት መስመር ጉዞ ወደ ሊቢያ ሦስት ቀን ያለማቋረጥ ከተጓዙ በኋላ አንድ ቦታ መድረሳቸውንወ የሚናገረው ሃሩን፤ ስፍራው ሰዎች እንደ ባሪያ የሚሸጡበት መሆኑን ያስታውሳል። ስፍራው ላይ ከደረሱ አራት ወርና ከዚያ በላይ የሆናቸው፣ ልብሳቸው ላያቸው ላይ የነተበ፣ ሰው የማይመስሉ ከ200 በላይ ስደተኞች፣ አብዛኛዎቹ ሶማሊያዊያን መሆናቸው ማግኘታቸውን ያስታውሳል። "እዚያ እንቆያለን ብለን ስላላሰብን የቀረችንን ስንቅም ውሃም ሰጠናቸው።" እነሃሩን እንዳሰቡት ሳይሆን የስደተኛ አቀባባዮቹ እንደፈቀዱት ሆነ። • "ትልቅ ዋጋ ተከፍሎበት ዋጋ ያላገኘሁበት ቢኖር ትምህርት ነው" ይዘዋቸው የመጡ ታጣቂዎች አራት አራት ሺህ ዶላር ካልከፈሉ በስፍራው እንዳቆይዋቸው እና ከሰውነት ጎዳና የወጡ ስደተኞች እንደሚሆኑ በመንገር አስፈራሯቸው። ማስፈራራቱ ከስፍራው ባለመንቀሳቀስ ጸና። ቀና ቢሉ ጠራራ ጸሀይ፣ ዞር ቢሉ ጎስቋላ ስደተኛ፣ ድካም ያዛለው፣ ውሃ ጥም ያቃጠለው የሀገር ልጅ በሚያዩበት ምድረ በዳ መጋዘን ተገኝቶ እዚያ ውስጥ ታሰሩ። አሳሪዎቻቸው እጃቸው የተፈታ ቀን፣ በቀን አንዴ ሆዳቸው የጨከነ እለት ደግሞ፣ በሁለት ቀን አንዴ ምግብ ይሰጧቸዋል። "ሌሊት ሌሊት ደግሞ ይደበድቡናል" የሚለው ሃሩን በአጠቃላይ ለአራት ወራት በዚያ ስፍራ መታሰራቸውን ይናገራል። አራት ወር ሲሞላቸው ልብሳቸው አልቆ፣ አብረዋቸው ከተሰደዱት ጋር ተረሳስተው፣ የት ለመሄድ እንደሚፈልጉ ዘንግተው እስትንፋሳቸውን ማቆየት ብቻ የህይወት ግባቸው ሆኖ እንደነበር ይናገራል። "በዚህ ስፍራ በረሃውንና የደረሰባቸውን ድብደባና ስቃይ መቋቋም ያቃታቸው አንድ ኢትዮጵያዊ ጓደኛችንን ጨምሮ አስራ ሁለት ሶማሌያዊያንን ቀብረናል።" በዚህ ሁሉ ስቃይ ውስጥ ይላል ሃሩን የመጡበት ሃገርን፣ ብሔራቸውንና ዘራቸውን ዘንግተው ሰው መሆናቸውን ብቻ ያስታውሱ እንደነበር የሚናገረው ሃሩን በመካከላቸው መደጋገፉና መረዳዳቱ ጠንካራ እንደነበር ይናገራል። የመረዳዳታቸውን ጣሪያ ሲያስታውስ ከመካከላቸው አንድ ሰው በውሃ ጥም ሞቶ ለሌሎች ከንፈራቸውን የሚያረጥቡበት ውሃ እንዲያገኙ ለማድረግ እስከመፍቀድ እንደነበር ይገልጻል። የኩላሊት ገበያ "አንድ ቀን..." ይላል ሃሩን "ኩላሊት የሚገዙ ሰዎች ወደ ታሰርንበት መጋዘን መጡ" የሚገዛው ግለሰብ ግን የበረሃው ሃሩርና ውሃ ጥም ያከሰላቸውን ስደተኞች ተመልክቶ፣ እነዚህማ ለራሳቸውም ደክመዋል ምንስ ኩላሊት አላቸው በማለት ትቷቸው መሄዱን ይጠቅሳል። ስደተኞቹ ኩላሊታቸው ተሸጦ ዋጋ እንደማያወጡ፣ ቤተሰቦቻቸው ገንዘብ ልከውም እንደማይከፈላቸው የተረዱት ደላሎች ለሌላ ነጋዴ አሳልፈው ሸጧቸው። የገዛቸው ሰው ለእያንዳንዳቸው ሦስት ሺህ ዶላር እንዳወጣና ገንዘቡን እንዲከፈለው እንደሚፈልግ ቀጭን ማሳሰቢያ አዘል ማስፈራሪያ ተናገረ። በበረሃው የተዳከሙ፣ በተስፋ መቁረጥ የሚዋልሉ ስደተኞች 'ከዚህ ብቻ አውጣን እንጂ እንከፍልሃለን' በሚል ተስማምተው አብረውት ሄዱ። ከዚህ ሰውዬ ጋር ቀንና ሌሊት ለአራት ቀን ከተጓዙ በኋላ ሳባ የምትባል የሊቢያ ከተማ ላይ ደረሱ። • የሴቶች ዘብ የነበሩት ዶ/ር ቦጋለች ገብሬ ይዘዋቸው የሚሄዱት ሰዎች የደረሱበትን የሚያውቁት ካርታ ዘርግተው፣ የፀሐይን አቅጣጫ አይተው ወይንም ነዋሪውን ጠይቀው አይደለም። አሸዋውን ዘገን አድርገው ብቻ የት ሃገር እንደደረሱ ይናገራሉ። ዓይን ማየት የቻለበት ርቀት ሁሉ አሸዋ ለሆነበት ስደተኛ፣ የአንዱ ሀገር አሸዋ ከሌላኛው ሀገር የሚለይበት መልክ አይገለጥለትም። ለሀገሬው ግን አቅጣጫ ጠቋሚ፣ ሀገር አመላካች ነው። እነ ሃሩንን ሳባ የወሰዳቸው ግለሰብ በከተማዋ እንደ ሃገረ ገዢ እንደሚታይ ግን ማወቅ ችለዋል። የተጠየቀውን ገንዘብ የከፈለ ስደተኛ በሳባ ውስጥ እንዳሻው የመውጣት የመግባት ነጻነትን ይጎናጸፋል። "እኛ ግን ገንዘብ ስላልነበረን" ይላል ሃሩን "ትልቅ መጋዘን ውስጥ አስገባን።" ገንዘብ የሌላቸውና መጋዘን ውስጥ የታጎሩት እነሃሩን የተፈጠሩበትን ቀን እስኪረግሙ ድረስ ድብደባ ይደርስባቸው ጀመር። "ወገባችንን በብረት፣ እጆቻችንን ወደኋላ አስረው እየደበደቡ ውሃ የተሞላ በርሜል ውስጥ በጭንቅላታችን ዘቅዝቀው ይከቱንና ከዚያ አውጥተው ቤተሰቦቻችን ጋር ደውለን ገንዘብ እንድናስልክ ስልክ ይሰጡናል" ሲል ያስታውሰዋል። በዚህ ሁኔታ ቤተሰቦቻችን ጋር ደውለን ያላቸውንም ሸጠው ተበድረውም ሆነ ተለቅተው ገንዘብ ይልኩልን ነበር። ቀድሞ ገንዘብ ከቤተሰቡ የሚላክለት ሰው ቀደሞ ከዚያ አሰቃቂ እስር ቤት የሚወጣ ሲሆን ቀሪው ግን እስኪላክለት ድረስ እዚያው ይቆያል። ሃሩን በዚህ ስፍራ አንድ ወር ቆየ። ከእርሱ ቀድመው የወጡ የበረሃ ጓደኞቹ፣ እንዲሁም ቤተሰቡ ያላቸውን ሳንቲም በማዋጣት ሦስት ሺህ ዶላር መክፈሉን ይናገራል። እዚህም በገንዘብም ሆነ በሌሎች ጉዳዮች ሲተጋገዙ፣ ብቸኛው ግምት ውስጥ የሚያስገቡት አብረው የሚያሳልፉትን የሰቆቃ ጊዜያት፣ ሰው መሆናቸውን እንጂ መነሻቸው ላይ የነበረው የአንድ አገር ልጅነት እንዳልነበር ይናገራል። • ኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃን የተመለከተ አዋጅን ልታጸድቅ ነው "መጀመሪያ ላይ በቋንቋ በብሔር በሃይማኖትና በዘር ስንጣላ የነበርን ሰዎች ከዚያ ሁሉ ስቃይ ሁሉ በኋላ የቀረልን ሰው መሆናችን ብቻ ነበር።" ሰው መሆን ከሁሉ ነገር በፊት የሚቀድም መሆኑ የገባኝ ያኔ ነበር በማለትም ከእስር ቤቱ ቀድመው የወጡ እንዴት እንደረዷቸው ያስረዳል። ሳባ ከነበረው እስር ቤት ቀድማቸው የወጣች ጽጌ የምትባል ኤርትራዊት ለቤተሰቦቻቸው በመደወል ገንዘብ እንዲላክላቸውና የጎደላቸውን ከሌሎች በማሟላት እንዲወጡ እንዳገዘቻቸው ይመሰክራል። በዚህ መደጋገፍና መረዳዳት መካከል አዲስ አሸናፊ ከምትባል ልጅ ጋር ፍቅር ጀመረ። እርሱ የእስልምና ዕምነት ተከታይ ሲሆን እርሷ ደግሞ ክርስትያን ነበረች። ነገር ግን እዚያ በነበረው እንግልትና ስቃይ ሁለቱ ወጣቶች በፍቅር ተጋመዱ። "እስር ቤት ውስጥ በጭካኔና በኃይል የሚደበደቡት ወንዶች ስለነበሩ ለእርሷ የተላከላትን ገንዘብ ለእኔ ከፍላ እኔ እንድወጣ አደረገች" በማለት የሁለቱ የፍቅር ታሪክ በራሱ በተቃርኖ ውስጥ ሲጋጩ ለሚኖሩ ሌሎች ትምህርት እንደሚሆን ያነሳል። ትሪፖሊ ሃሮን ፍቅረኛውና ቤተሰቦቹ በማዋጣት በከፈሉት ገንዘብ ሳባ ከሚገኘው እስር ቤት ከወጣ በኋላ ወደ ትሪፖሊ ጎዞ ጀመረ። ነገር ግን በክፉ አጋጣሚ ትሪፖሊ ከመድረሱ በፊት በሌሎች ሰዎች እጅ ወድቆ እስር ቤት ተወረወረ። እነዚህ አሳሪዎቹ በቀን አንዴ ደረቅ ዳቦ እየሰጧቸው፣ ሌሊት ሌሊት ደግሞ ገንዘብ አምጡ እያሉ እደበድቧቸው እንደነበር ይናገራል። ፍቅረኛውን አዲስን ጨምሮ ሌሎች ከሱዳን አብረው የተነሱና ሳባ አብረው ታስረው የነበሩ ስደተኞችም በሂደት ተቀላቀሏቸው። ከ18 ቀናት እስር በኋላ እንደ ከዚህ ቀደሙ ተረዳድተው ስድስት ስድስት መቶ ዶላር በመክፈል ተለቀቁ። ከዚህ በመቀጠል ያመሩት በቀጥታ ትሪፖሊ ክሪሚያ የምትባል ስደተኞች በብዛት የሚያርፉባት መንደር ነበር። • "ሶስት ጊዜ ለተለያዩ ነጋዴዎች ተሽጫለሁ" ክሪሚያ ወደ አውሮፓ በባህር ለማቋረጥ ወረፋ የሚጠብቁና ከባህር ላይ ተይዘው የተመለሱ ስደተኞች በብዛት ያሉባት መንደር ናት። ሃሩንና አዲስ ያገኙትን እየሰሩ ለእለት ጉርስ ለነገ ደግሞ ስንቅ እያኖሩ ከሌሎች መንገድ ላይ ከተዋወቋቸው ሰዎች ጋር ቤት ተከራይተው ለሰባት ወራት በክሪሚያ ኖሩ። በሰባት ወር ቆይታቸው በመንደሯ በየዕለቱ የሚሰማው ወሬ የባህር ተሻጋሪ ስደተኞች ሞት አልያም በሰላም ወደ አውሮፓ መሻገር ነበር። ይህንን በየማለዳው የሚሰሙት ሃሩንና አዲስ በየሃይማኖታቸው በሰላም የሜዴትራኒያንን ባህር ተሻግረው የሚያልሙት አውሮፓ እንዲደርሱ ይጸልዩ ነበር። "በወቅቱ..." ይላል ሃሩን "አንዳችን የሌላኛችንን ሃይማኖት ለማስቀየር ወይም እንደ ክፍተት በመቁጠር ተነጋግረን አናውቅም።" ክሪሚያ የከተመ ስደተኛ ሰርቶ ያገኘውን አጠራቅሞ፣ ቤተሰብ የላከለትን ቋጥሮ ሲሞላለት፣ በጀልባ ተሳፍሮ ወደ አውሮፓ ጉዞ ይጀምራል። ያንን ሁሉ በረሃ አቋርጠው፣ ስቃይና እንግልቱን ችለው ክሪሚያ የደረሱ መጥፎ ዕጣ ከገጠማቸው ሜዴትራኒያን ባህር ውስጥ ሰጥመው ይሞታሉ። ሃሮንም በዚህ ሁኔታ ብዙ ሰው ነው ያለቀው በማለት "ባህር ውስጥ ሰጥመው የሞቱ በርካታ ጓደኞቻችን አሉ" ይላል። መጀመሪያ በባህር ወደ ጣሊያን ከዚያም ወደ ጀርመን ያቀናውና አሁን እዚያ የሚኖረው ሃሩን፤ በሃይማኖት በብሔር ወገን ለይቶ መጠላላትና መጋደል አስፈላጊ እንዳልሆነ በመግለጽ የእርሱ የስደትና የመከራ ሕይወት ይህንን እንዳስተማረው ይገልጻል። ሃሩንና አዲስ በስደት እያሉ አንድ ልጅ የወለዱ ሲሆን ጀርመን ከገቡ በኋላ ሁለቱም በየሃይማኖታቸው ለመቆየት በመወሰናቸው፣ ልጃቸውን በጋራ ለማሳደግ ተስማምተው ለየብቻቸው እየኖሩ ነው።
news-52870103
https://www.bbc.com/amharic/news-52870103
የደረሱበት ያልታወቀው ተማሪዎች ስድስት ወር ሆናቸው
በምዕራብ ኢትዮጵያ ከሚገኘው የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተነስተው ወደ መኖሪያ ቀያቸው በማምራት ላይ የነበሩ ተማሪዎች ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች መታገታቸው ከተነገረና ያሉበት ሳይታወቅ እነሆ ዛሬ ግንቦት 24 ስድስተኛ ወር ሆነ።
አቶ ሐብቴ እማኘው የተማሪዎቹ ወላጆች ልጆቻቸው ችግር እንደተጠማቸው የሰሙት ኅዳር 24/2012 ዓ.ም ነበረ። ወላጆች ክስተቱን ከእራሳቸው ከልጆቻቸው ተደውሎላቸው እንደሰሙ የተናገሩ ሲሆን ጉዳዩ ትኩረት ለማግኘት ሳምንታትን ወስዶ ነበር። ጉዳዩ አንዴ ሞቅ ሌላ ጊዜ ደግሞ ቀዝቀዝ እያለ እስካሁን ቀጥሏል። ቢቢሲ የደረሱበት ሳይታወቅ ስድሰት ወራት ስላስቆጠሩት ተማሪዎች ጉዳይ የተሰማ ነገር እንዳለ ለማጣራት የተወሰኑ የተማሪዎቹ ቤተሰቦችን አናግሯል። ወይዘሮ እመቤት መለሰ የተማሪ አሳቤ አያል እናት ተማሪ አሳቤ አያል የት እንዳሉ ካልታወቁት ተማሪዎች መካከል አንዷ ናት። ስለነበረው ጉዳይ እንዲያጫውቱን ለመጠየቅ እናቷን ወይዘሮ እመቤት መለሰን ለማግኘት በልጃቸው ስልክ ነበር ያገኘናቸው። ልጃቸው ሊተባበረን ፈቃደኛ ቢሆንም እናቱ በሐዘን መጎዳታቸውን ነግሮን "[ተማሪ አያል] በህይወት እንዳለች ነግራችሁ አናግሯት" ካልሆነ ከማልቀስ ውጪ ምንም እንደማያናግሩን ነግሮን ይህንንም እሱ ከነገራቸው በኋላ ነበር ተረጋግተው ማናገር የጀመሩት። "ለመጨረሻ ጊዜ ታህሳስ አንድ ቀን አወራን" ሲሉ የነበረውን ነገር ያጫውቱን የጀመሩት ወይዘሮ እመቤት "ለመጨረሻ ጊዜ ታህሳስ አንድ ቀን አወራን። 'እኛ ታግተናል ይዘወናል። እንግዲህ አንገናኝም ደህና ሁኚ' ነበር ያለችኝ" ሲሉ የነበረው ሁኔታ ያስታውሳሉ። ሐዘን ክፉኛ በተጫነው ድምጽ ለምንጠይቃቸው ጥያቄዎች አጭር አጭር መልስ የሰጡን ወይዘሮ እመቤት ከፌደራል መንግሥት ጀምሮ እስከ ክልል መስተዳደር ድረስ የተለያዩ ቦታዎች በመሄድ ጉዳዩን ለማሳወቅ መጣራቸውን ይናገራሉ። ከዚያም በኋላ ልጃቸውና ሌሎች የቤተሰቡ አባላት ለዚሁ ጉዳይየ ተለያዩ ቦታዎች መሄዳቸውን ጠቅሰው "እኔ አልሄድኩም እዚሁ ነው [ቤታቸው] የማለቅሰው" ብለውናል። ልጃቸው የደረሰችበትን ሳያውቁ ስላለፉት ስድስት ወራትም "ምን ኑሮ አለ። እሷን ነው የምናስብ እንጂ ምን ሃሳብ አለ። እኛ አንሰራ ምን አንል እንጉርጉሮ እና ለቅሶ ነው። በእሷ ሃሳብ ገብተን ምኑን አድርጌ ልስራው" ሲሉ ያሳለፉትን የሰቆቃ ጊዜያት ይናገራሉ። ምንም እንኳን ሐዘኑ ቢጎዳቸውም ደህና ነኝ የሚሉት የተማሪ አሳቤ እናት "ባለው ሁኔታ ደህና ነኝ እስከዛሬ። እኔ ነኝ ያሳደኳትም እኔ ነኝ ይዣት ያለሁ። ያው የሚያስፈራኝና የሚያሳስበኝ ወጥታ ከቀረች ነው" ሲሉ ይሰጋሉ። "አንደኛ ተማሪ ናት። እኔን ትደግፈኛለች ትመራኛለች ብዬ ነው የምቀመጠው። እንዲህ ሆና ቀረችብኝ። [እምባ በተናነቀው ድምጽ] 'አንደኛ ነኝ። እኔ ትምህርቴን ነው እንጂ የምቀጥል ለባል አልዳርም ነው ነበር የምትለኝ'" ሲሉ ልጃቸው ስለነበራት ሃሳብ እያነሱ ይናገራሉ ወይዘሮ እመቤት። ምንም እንኳን ወራት ቢቆጠሩም አሁንም የልጃቸው መምጣት እየተጠባበቁ ነው። "መንግሥት ልጄን እንዲያመጣልኝ ነው የምፈልገው። ልጄን በሠላም ማግኘት እንጂ ሌላ ምንም ሃሳብ የለኝም" ሲሉ ጉጉታቸውን ይገልጻሉ። አቶ ሐብቴ እማኘው የተማሪ ግርማ ሐብቴ አባት ከወራት በፊት ቢቢሲ የተማሪ ግርማ ሐብቴ አባት ከሆነት ከአቶ ሐብቴ እማኘው ጋር ቆይታ አድርጎ ነበር። ከዚያ ወዲህ ስላሉበት ሁኔታ ጠይቀናቸው "ምን አዕምሮ አለኝ። በአዕምሮዬ አይደለም የማነጋግራችሁ። የመንግሥትን ውጤት ነው የምጠብቀው። መንግስት ምን ያደርግልን ይሆን? እያልኩኝ ነው" ሲሉ አሁንም በጥበቃ ላይ መሆናቸውን ይጠቅሳሉ። አቶ ሐብቴ ልጃቸው መታገቱን ያወቁት ኅዳር 24 ነው። ከዚያ ቀን ጀምሮ እስከ ታህሳስ 5/2012 ድረስ ልጃቸው ስልክ እየደወለ ከቤተሰቡ ጋር ተነጋግሯል። "የሥራ ወቅት በመሆኑ አጨዳ ላይ ስለነበርኩ ከእናቱ ጋር ነው የተነጋገረው" የሚሉት አቶ ሐብቴ "'ተይዘናል። ከሰው ጋር ነን። ችግር የለም። አያንገላቱንም። የምንለቀቅበትን ቀን ጸሎት አድረጉልኝ' ነው ያለው። ምን አደርጋለሁ እስካሁን ድረስ እያለቀስኩ ነው" ሲሉ ለመጨረሻ ጊዜ ያወሩትን ያስታውሳሉ። "ከሰሞኑ ምንም የሰማነው ነገር የለም" የሚሉት አቶ ሐብቴ ከዚህ ቀደም የተለያዩ የመንግሥት ኃላፊዎችን ማናገራቸውን አስታውሰዋል። "እነአቶ ንጉሡ ጥላሁን አናግረውናል። ሥራ እየሠራን ነው ብለውናል። ከእናነተ ጋር ነን እያሉን ነው። መንግሥትን ነው የምንጠበቀው። የመንግሥትን ምላሽ ነው የምንጠብቀው። ሌላ ምን የምናደርገው ነገር አለን። ከቤታችን ቁጭ ብለን እያለቀስን እያነባን ነው። ሥራ አንሰራም ልጆቻቸን ተበትነው ነው ያሉት።" "ባለቤቴ ምንም ዋጋ የላትም በህክምና ላይ ነው ያለችው። ህክምና ላይ ነው ያለችው። በጸበል ላይ ነው ያለሁት። ምንም አዕምሮ የላትም። ከወለል ላይ ወደቀች። እግዚኦ እያለች እየተንፏቀቀች እህል አትበላ፤ ምን አትል ይኼው መከራችንን ነው የምናየው" ሲሉ የልጃቸው መጥፋት ቤተሰባቸውን እንደጎዳው ይናገራሉ። "[አሁን ወቅቱ] የእርሻ ወራት ነበር። እርሻ አላርስ ብዬ ቅጡ ጠፍቶኝ ዛሬ ቤተሰቦችን በመንከባከብ እና አይዟችሁ በማለት ላይ ነው ያለሁት። መንግሥት እየረዳን ነው" ሲሉ ተስፋቸውን በመንግሥት ላይ መጣላቸውን ይናገራሉ። ልጃቸውን ፍለጋ መሄጃው መንገድ የጠፋባቸው አቶ ሐብቴ ባለፉት ወራትን በጭንቅ እንዳሳለፉ ይናገራሉ "ከቤቴ ሆኜ ከማሰብ እና ከመጨነቅ በስተቀር። የማውቀው ነገር ለኝም።" የሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ተማሪ የሆነው ልጃቸው ግርማ ከደብተሩ ውጭ ምንም የሚያውቀው ነገር እንደሌለ አባቱ ይናገራሉ። "የሚበላውን እንጅራውን እንኳን አያውቀውም። ሞኝ ዝም ብሎ የዋህ ነው። እሱ ነው የሚያስለቅሰኝ። ትምህርቱና የዋህነቱ ነው የሚያስለቅሰኝ። ሞኝ ነው የሚያውቀው ነገር የለም በቃ [እያለቀሱ]።" የታገቱት ተማሪዎች፡ የቤተሰብ ሰቀቀን እና የመንግሥት ዝምታ አቶ ሐብቴ ከወራት በኋላም ተስፋ ሳይቆርጡ የልጃቸውን መምጣት እየተጠባበቁ ነው። "መንግሥት ሥራ እየሰራን ነው እያለን ነው። መንግሥት በእነሱ ሃሳብ ላይ ነው ያለነው ብሎ ነግሮናል። ዞሮ ዞሮ እምነቴ መንግሥት ላይ ነው ያለው። በገቡበበት ገብቶ ጉዳዩን መንግሥት ይፈታዋል ብዬ አምናለሁ" ብለዋል። አቶ ታረቀኝ ሙላቴ፤ የተማሪ ጤናዓለም ሙላቴ ታላቅ ወንድም የደረሱበት ካልታወቀው የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል አንዷ ጤናዓለም ሙላቴ አንዷ ናት። ከስድስት ወራት በፊት እንደታገተች የምትደዋወለው ከታላቅ ወንድሟ አቶ ታረቀኝ ሙላቴ ጋር ነበር። "በወቅቱ እንደታገተች እኔ ጋር ነበር የምትደውለው 'ታግቻለሁ' አለች። 'ታግቻለሁ ምንም ማድረግ አልችልም' አለች" ሲሉ ክስተቱን ያስታውሳሉ። "ከተያዘችበት ቀን አንስቶ እስከ በተለያዩ ቀናት በስልክ ታወራኝ ነበር። መጨረሻ ላይ 'በህይወት አለን እስካሁን ባለው እንሞታለን ብለን አናስብም። ምናልባትም ከዚህ በኋላ ስልክ ላይሠራ ይችላል። አትጨናነቁ በቃ'" እንዳለቻቸው ይናገራሉ። እሳቸውም ስለደኅንነታቸው ሲጠይቋት "የያዟቸው ሰዎች 'አይዧችሁ አንገድላችሁም እህቶቻችን ናችሁ። እናንተን ምንም አናደርጋችሁም እያሉን ነው፤ እናንተ ጸሎት አድርጉልን' ብላ ነግራኛለች" ብለዋል። ከዚህ በኋላም በስልክ ግንኙነታቸው ተቋረጠ። አቶ ታረቀኝ በተደጋጋሚ ስልክ ለመደወል ቢሞክሩም ጠፉ በተባለበት አካባቢ የስልክ አገልግሎት በመቋረጡ መገናኘት ስላልቻሉ እህታቸውን ተማሪ ጤናዓለምን ሳያገኙና ስለእሷ ሳይሰሙ እንሆ ወራት ተቆጠሩ። "ለመንግሥት አሳወቅን። እነሱም ያለወን ነገር መንግሥት በአጭር ቀን ይፋ ያደርጋል" መባላቸውንና ልጆቹ በህይወት መኖራቸው ቢነገራቸውም "ከዚያ ወደዚህ ምንም ብለውንም አያውቁም። ማንም ደውሎልን አያውቅም። እኛም ያየነው የለም። ለፈጣሪ እየጸለይን ነው" ብለዋል። የጤናዓለም ጉዳይ አለመታወቅ ባለፉት ወራት ቤተሰቡ ላይ ከባድ ሃዘንን ጭኗል ይላሉ አቶ ታረቀኝ "እናቴ ለቅሶዋ ወደር የለውም። መያዟን ከሰማችበት ቀን ጀምራ ሸራ አንጥፋ ውጪ ነው የምትተኛው። በየደብሩ እና በየጸበሉ ነው የምትንከራተተው።" ሲሉ እናታቸው ያሉበትን ሁኔታ ገልጸዋል። ስለእህታቸው ለመስማት ወራትን የጠበቁት አቶ ታረቀኝና ቤተሰባቸው "ምናለ ሞቷን ወይንም ህይወቷን ቢያሰማን በሚል ነው እየተጨናነቅን ያለነው። መንግሥት ባለበት አገር ለወራት የደረሰችበት አለመታወቁ መላ ቤተሰቡን እየጎዳው ነው። እኛ ፖለቲካ አናውቅም ፖለቲካ አልጠየቅንም፤ ብቻ መንግሥት የእህቶቻችንን ሞት ወይ ህይወታቸወን ያሳውቀን።" ተማሪዎቹ በህይወት አሉ ብለው የሚያምኑት አቶ ታረቀኝ ለማወቅ ግን ምንም መንገድ አለመኖሩ ቤተሰባቸውን አስጨንቆታል። "ካሉ አሉ ተብሎ ቢነግረን ካልሆነ ደግሞ ምን እናደርጋለን ማንም ሰው ላይሞት አልተፈጠረምና ከሞቱ ቤተሰብ እና አገር ይዘህ አልቅሰን እርማቸውን እናወጣ ነበር፤ አሁን ግን ያለንበት ጭንቀት አይወራል" በማለት መደበኛ ህይወታቸው እንደተስተጓጎለ ይናገራሉ። መንግሥት ምን እያደረገ ነው? ጉዳዩን የሚከታተል ግብረ ኃይል አቋቁሞ ለወራት የደረሱበት ስላልታወቁት የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አጠቃላይ ዝርዝር ሁኔታ የሚያሳይ መረጃ በቅረቡ ለሕዝቡ ይፋ እንደሚደረግ መንግሥት ከሰሞኑ አስታውቋል። በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራው ግብረ ኃይል ጉዳዩን በቅርበት በመከታተል እየሰራ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ለአሃዱ ቴሌቪዥን መናገራቸው ተዘግቧል። ስለጉዳዩ መረጃ ለመስጠት የተገባው ቃል ሁኔታው ውስብስብ በመሆኑ ጊዜ ሊወስድ እንደቻለ ነው ኃላፊው የተናገሩት። ጨምረውም ከውስብስበነቱ ባሻገርም በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ በርካታ ሰዎች በጉዳዩ ውስጥ መሳተፋቸው ጊዜ መጠየቁን እንዲሁም ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው 28 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አቶ ንጉሡ ገልጸዋል። "ታግቼ ነበር ተማሪ ነበርኩ "ብለው በተለያየ መልኩ የቀረቡ ወደ 4 ያህል ተማሪዎች እንደተያዙ ጠቁመዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ጉዳዩን ለማድበስበስ የሞከሩም ተይዘዋል ብለዋል። በፌዴራል ደረጃ እንዲሁም በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች የተቋቋመው ግብረ ኃይል ሥራውን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸው፤ ስለጉዳዩን በመደበኛ መልኩ መረጃ ለመስጠት እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች ሲጠናቀቅ ዝርዝሩ ለሕብረተሰቡ ይገለጻል ሲሉ አቶ ንጉሡ ተናግረዋል። "ጉዳዩ በርካታ አካባቢዎችንና አካላትን አነካክቷል" ያሉት አቶ ንጉሡ፤ "የአማራ እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥታት እንዲሁም በከፊል ከቤንሻንጉል ክልል የሚያገናኘው ነገርም ስላለ ከፌዴራል መንግሥት ጋር ሆነው በጋራ እየሰሩ ነው" ብለዋል። ታህሳስ 2012 ዓ.ም የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ታህሳስ መጨረሻ ላይ ለጋዜጠኞች፤ ስለተማሪዎቹ መረጃውን ለመከላከያ እና ፌደራል መንግሥት መስጠታቸውን ገልጸው፤ ከተለቀቁት ተማሪዎች ውጪ "አራት ተማሪዎች ታግተው እንደሚገኙ መረጃው አለኝ" ብለው ነበር። ጥር 2/2012 ዓ.ም ቢቢሲ ታግተው ከሚገኙት የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል በሦስተኛው ቀን አመለጥከሉ ካለችው ተማሪ አስምራ ሹሜን አናግሮ ነበር። እሷም 17ቱ የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል 13ቱ ሴት ተማሪዎች መሆናቸውን ተናግራ ነበር። ጥር 19/2012 ዓ.ም ሁለት ወር ለሚጠጋ ጊዜ የደረሱበት ያልታወቀው የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ደኅንነት ያሳሰባቸው በተለያዩ የአማራ ክልል ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች ድርጊቱን የሚቃወሙ ሰልፎች አካሄዱ። ጥር 21/2012 ዓ.ም ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች ከታገቱት የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወላጆች ጋር ተወያዩ። በውይይቱም ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚልና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች ተሳትፈዋል። ጥር 23/2012 ዓ.ም በተማሪዎቹ ላይ የተፈጸመው ድርጊት በአሁኑ ወቅት እንደ አገር ካገጠሙ ችግሮች ውስጥ አንዱ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ። ጨምረውም "በአጭር ጊዜ ውስጥ አንድ የተጨበጠ ውጤት ላይ ለማድረስ መንግሥት ሙሉ ኃይሉን አሰባስቦ እየተረባረበ" መሆኑንም አመልክተዋል። መጋቢት 2/2012 ዓ.ም የተማሪዎቹ ቤተሰቦች ከአማራ ክልል ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር ለመነጋገር ባህር ዳር ተገኝተው ነበር። በባህር ዳር ቆይታቸውም የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ቢሮ እና ፖሊስ ኮሚሽን በመሄድ ስለጉዳዩ ምላሽ ለማግኘት ቢሞክሩም በተለያየ ምክንያት ኃላፊዎችን ሳያገኙ መቅረታቸውን ገልጸዋል። መጋቢት 17/2012 ዓ.ም የኢትዮጵያ መንግሥት ከወራት በፊት ባልታወቁ ሰዎች ምዕራብ ኦሮሚያ ውስጥ ታግተው የደረሱበት ስላልታወቁት 17 የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ለማስለቀቅ የወሰደውን እርምጃ እንዲያስታውቅ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ። ማን ምን አለ? ለወራት የደረሱበት ስላልታወቀው ተማሪዎች የተለያዩ ወገኖች መግለጫና አስተያየት ሲሰጡ ቆይተዋል። ተማሪዎቹ ከታገቱ በኋላ መንግሥት ተማሪዎቹን ለማስለቀቅ የወሰደው እርምጃ የለም በማለት በርካቶች የተቃውሞ ድምጻቸውን እያሰሙ ነው። ከእነዚህ መካከል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ፓርቲ (አብን) ባወጣው መግለጫ የታገቱ ተማሪዎች እንዲለቀቁ እና ጥቃት አድራሾቹ ለሕግ እንዲቀርቡ መጠየቁ ይታወሳል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ባወጣው መግለጫም፤ የታገቱት ተማሪዎች ምንም ዓይነት ጉዳት ሳይደርስባቸው እንዲለቀቁ መንግሥት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በአስቸኳይ እንዲወጣ ጠይቋል። የአማራ ክልል ሴቶች ፌደሬሽን በተማሪዎቹ ላይ እየተፈፀመ ያለውና ኢ-ሰብዓዊ ተግባራት እንዲቆሙ፤ ጥፋተኞችም ለሕግ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል። የአማራ ሴቶች ፌደሬሽንና እና የአማራ ሴቶች ማኅበርም የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ ያለውን አቋም መንግሥት ግልፅ ማድረግ እንዳለበት ጠይቀዋል። የአማራ ዴሞክራሲ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) በተማሪዎቹ ላይ የተፈፀመውን ድርጊት አውግዞ፤ ይህ የመንግሥት ችግር እንደሆነ እንደሚያምን ገልጾ ነበር። 'የታገቱት ተማሪዎች ይለቀቁ' የሚል ዘመቻም በማኅበራዊ ሚዲያዎች ሲካሄዱ ቆይተዋል። መንግሥትም መፍትሄ እንዲሰጥ ሲጠየቅ ቆይቷል። ለስድስት ወራት የደረሱበት ያልታወቁት እነዚህ የደንቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን በሚመለከት እስከ ዛሬ ድረስ በማን እንደተያዙና ያሉበትን ቦታ በእርግጠኝነት የገለጸ ወገን የለም። ተማሪዎቹ ከጠፉበት ጊዜ አንስቶ የተለያዩ የክልልና የፌደራል የመንግሥት አካላት ያሉበትን ለማወቅ ጥረት እያደሩ እንደሆነ ቢገልጹም "እዚህ ናቸው" የሚል ግን አልተገኘም። ተማሪዎቹ የደረሱበት ሳይታወቅ በማን እጅና ለምን አላማ ለወራት እንደተያዙ አለመታወቁ የወላጆችንና የቤተሰቦችን ጭንቀት የከፋ አድርጎታል። ለዚህም ነው መኖር መሞታቸውን አውቀን ተረጋግተን እንቀመጥ ካልሆነም እርማችንን አቅጥተን ለስቃያችን ፍጻሜ እናብጅለት የሚሉት።
54821150
https://www.bbc.com/amharic/54821150
ስለ ፌደራል መንግሥትና የትግራይ ክልል ግጭት ማን ምን አለ?
ትላንት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ መከላከያ ሠራዊት ሕወሓት ላይ የኃይል እርምጃ እንዲወሰድ መታዘዙን መግለጻቸው ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚንስትሩ ትላንት ማምሻውን በሰጡት መግለጫ በሁመራ፣ በዳንሻ እና በቅርቃር አካባቢዎች የአገር መከላከያ ሠራዊት እና የአማራ ክልል ልዩ ኃይልና ሚሊሻ "ሕወሓት ያሻውን ሳያደርግ የሞከራቸው ሙከራዎች ከሽፈዋል" ብለዋል። የአገር መከላከያ ሠራዊትም "የተቃጣበትን ጥቃት በመመከት እንዲሁም በማክሸፍ የሕዝቦችን ደህንነት እና የአገሪቱን ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ኃላፊነቱን እየተወጣ" እንደሆነ ገልጿል። ከቅርቃር በቅርብ ርቀት የሚገኝ ቦታን በቁጥጥር ስር ማዋሉም ተገልጿል። የትግራይ ክልል መንግሥት ትላንት ባወጣው መግለጫ በክልሉ የሚገኙት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰሜን ዕዝ ሠራዊት አባላትና አዛዦች ከትግራይ ክልል መንግሥት ጎን ለመሰለፍ መወሰናቸውን ገልጿል። ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጽሕፈት ቤት በተገኘው መረጃ መሠረት፤ ከአገር መከላከያ ሠራዊት ተቀንሰው የነበሩ ሦስት መኮንኖች ወደ ሠራዊቱ እንዲመለሱ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸዋል። እነዚህም ሌ/ጀነራል ባጫ ደበሌ፣ ሌ/ጀነራል ዩሐንስ ገብረመስቀል እና ሌ/ጀነራል አበባው ታደሰ ናቸው። በተጨማሪም የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አደም ፋራህ እና የገንዘብ ሚንስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ወቅታዊ ጉዳዮችን በማስመልከት ለውይይት ጅግጅጋ መሄዳቸው ተዘግቧል። በትግራይ ክልል እና በፌደራል መንግሥት የነበረው ውጥረት ወደ ግጭትን ማምራቱን በማስመልከት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ፣ የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፔዮ እና ሌሎችም አካላት መግለጫ አውጥተዋል። የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ባወጣው መግለጫ፤ "በፌደራል መንግሥትና በትግራይ ክልል መንግሥት መካከል የተፈጠረው አለመግባባት፣ ውጥረትና መካረር ገደቡን አልፎ ግልጽ የሆነ ወታደራዊ ግጭት መጀመሩ አሳዝኖናል። ይህ እንዳይሆን በማሰብ ሁለቱን አካላት አቀራርበን ለማወያየት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው ሳይሳካ መቅረቱም በእጅጉ ያሳዝናል" ብሏል። የተፈጠረው ግጭት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መቆም እንዳለበትና የፌደራል መንግሥትም ሆነ የትግራይ ክልል መንግሥት ቅድሚያ መስጠት ያለባቸው ለአገሪቱ ሰላምና መረጋጋት መሆኑ በመግለጫው ተመልክቷል። "የብልጽግና ፓርቲ እና የሕወሓት መሪዎች በመካከላችሁ የተፈጠረው የፖለቲካ ልዩነት በመነጋገር የሚፈታ ስለሆነ አሁንም በጉዳዮቻችሁ ላይ በግልጽ በመነጋገር እንድትፈቱ ጥሪ እናስተላልፋለን" ሲል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤው መግለጫ ያትታል። በተጨማሪም የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ እናቶች፣ አባገዳዎች እና ሌሎችም ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ሁለቱን ወገኖች ወደ ሰላማዊ ድርድር እንዲያመጡ መግለጫው አሳስቧል። አሜሪካ እና የአውሮፓ ሕብረት የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፔዮ በትዊተር ገጻቸው፤ "ሕወሓት በትግራይ የመከላከያ ሠራዊት ካምፕ ላይ ጥቃት አድርሷል የሚለው ሪፖርት አሳስቦናል" ብለዋል። የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ አክለውም "ሰላም እንዲመለስ እና ውጥረቱን እንዲረግብ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ እናሳስባለን" ብለዋል። የአውሮፓ ሕብረት የውጪ ጉዳይ እና ደህንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ወኪል እና የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ፕሬዘዳንት የሆኑት ጆሴፍ ቦሬል ፎንቴልስ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ "ወታደራዊ ግጭት መከሰቱ ለአገሪቱና ለቀጠናው መረጋጋትም አስጊ ነው" ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ጽፈዋል። ዋነኛው ትኩረት መሆን ያለበት ውጥረቱን ማርገብና ችግሩን በሰላማዊ መንገድ መፍታት እንደሆነም ገልጸዋል። ትላንት የአሜሪካ እና የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥታት፤ የትግራይና የፌደራል መንግሥት የገቡበትን ውጥረት ሊያረግቡ እንደሚገባ በኤምባሲዎቻቸው በኩል መግለጻቸው ይታወሳል። አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ትላንት ባወጣው መግለጫ፤ ሁለቱም ወገኖች የገቡበትን ውጥረት እንዲያረግቡ ጥሪ አቅርቦ፤ ለሰላማዊ ሰዎች ደህንነት ቅድሚያ ሊሰጡ ይገባል ብሏል። የዩናይትድ ኪንግደም ኤምባሲም ውጥረቱ በአፋጣኝ እንዲረግብ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ስም የጠየቀ ሲሆን፤ ሁለቱም ወገኖች የሰላማዊ ዜጎቻቸውን ደህንነት እንዲያስጠብቁ ጠይቋል። የመብት ተሟጋቾች የአገር ውስጥ ተቋሞች የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በፍጥነት እየተባባሰ የመጣው የትግራይ ክልል የጸጥታ ሁኔታ እንደሚያሳስበው በመግለጽ ክስተቱን በቅርበት እንደሚከታተለው አስታውቋል። ዋና ኮሚሽነሩ ዶ/ር ዳንኤል በቀለ 'የፌደራልና የክልሉ የጸጥታ ኃይሎች የሲቪል ሰዎችን ደህንነት እና የሰብዓዊ መብቶችን በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ እንዲጠብቁና እንዲያከብሩ'' ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። ኮሚሽነሩ አክለውም፤ በተለይም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በትግራይ ክልል ተፈጻሚ እንዲሆን የቀረበውን የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ረቂቅ አቃጅ ለመምከር በሚሰበሰብበት የዛሬው ዕለት፤ ምግብና መድኃኒት የመሳሰሉ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቶችን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት እንዲሁም ትራንስፖርት ሙሉ በሙሉ እንዳይቋረጥ በማሳሰብ፤ ትግራይ ክልል በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ስደተኞች እንደሚያስጠልልም አስታውሰዋል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በበኩሉ፤ በትግራይ ክልልና አዋሳኝ ቦታዎች ያለው እንቅስቃሴ የሰላማዊ ሕዝብን ሕይወትና አካላዊ ደህንነት ብሎም የሲቪል ንብረቶችን አደጋ ላይ የማይጥል እንዲሆንና ሁሉም ወገኖች ከግጭት እንዲቆጠቡ ጥሪ አቅርቧል። ሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የሲቪል ማኅበራት፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪዎችና መላው ኢትዮጵያውያን ግጭቱ ተባብሶ የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት በመንቀሳቀስ ልዩነቶች በውይይት እንዲፈቱ በሁሉም ወገኖች ላይ ግፊት እና ጫና እንዲያደርጉ ኢሰመጉ ጠይቋል። መንግሥትም በየጊዜው የሚፈጠሩ ነገሮች ዙሪያ ተከታታይ መረጃዎችን ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ ኢሰመጉ አሳስቧል። ሁሉም የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችና መገናኛ ብዙኃን፤ ሕዝብን ለግጭት የሚያነሳሱ እና ለሰብዓዊ መብቶች ጥሰት የሚዳርጉ የሐሰት ዜናዎችን እና የተዛቡ መረጃዎችን ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ ኢሰመጉ ጥሪውን አቅርቧል። ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሂውማን ራይትስ ዋች የአፍሪካ ዳይሬክተር ማውሲ ሴጋን፤ የፌደራልና የክልል መንግሥታት ሰብዓዊ መብትን ሳይጥሱ ግጭት ማርገብ አለባቸው ብለዋል። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ድምጹን ማሰማት እንዳለበትም አክለዋል። "በትግራይ ክልል የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡ ክስተቱ በማኅበረሰቡ ላይ ስላሳደረው ጫና መረጃ እንዳይገኝ አድርጓል። ሕዝቡ ጤናውና ደህንነቱን በተመለከተ መረጃ እንዳያገኝም ያግዳል" ብለዋል። ዳይሬክተሯ አያይዘውም፤ የስልክም ይሁን ኢንተርኔት መቋረጥ "መንግሥት ከሚሰጠው መረጃ ባለፈ ሕዝቡ ሐሳቡን እንዳያንሸራሽር ይገታል" ብለው፤ የቴሌኮም አገልግሎቶች በአፋጣኝ እንዲመለሱ አሳስበዋል። ሌላው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አምንስቲ ኢንተርናሽናል፤ የምሥራቅና ደቡብ አፍሪካ ዳይሬክተር ዴፕሮሴ ሙቻናም መግለጫ አውጥተዋል። "መከላከያ መላኩ በትግራይ ክልል እና በፌደራል መንግሥት መካከል ያለውም ውጥረት ያባብሳል። የሰዎችን ሕይወት አደጋ ላይ ከመጣሉም ባሻገር ሰብዓዊ መብቶች እንዲጣሱ በር ይከፍታል" ብለዋል። በትግራይ ክልል ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ፤ ለፌደራል መንግሥትና ለትግራይ ክልል መንግሥትም አሳስበዋል። "ሞትና የአካል ጉዳት እንዳይከተል ከፍተኛ ኃይል መጠቀም መገታት አለበት" ሲሉም በመግለጫው ጠይቀዋል። ሰዎች እርስ በእርስ መረጃ እንዲለዋወጡ፣ የንግግር ነጻነት እንዲከበርና ሰብዓዊ መብት አለመጣሱን ለማረጋገጥ የሰልክና ኢንተርኔት አገልግሎቶች እንዲመለሱም ተጠይቋል።
news-56697411
https://www.bbc.com/amharic/news-56697411
የኤደንብራው መስፍን፣ ልዑል ፊሊፕ ለምን ንጉሥ አልተባሉም?
ልዑል ፊሊፕ የኤደንብራ መስፍን ነበሩ። ምናልባትም በዓለም ዝነኛው ባል ሊባሉ ይችሉ ይሆናል። ዘመናቸውን በሙሉ ቆፍጣና፣ ስፖርተኛና ሠርተው የማይደክማቸው ባተሌ ነበሩ።
የ780 ድርጅቶች ፕሬዝዳንት፣ አባልና የበላይ ጠባቂ ሆነው እድሜያቸውን አሳልፈዋል። በ143 አገራት ይፋዊ ጉብኝት አድርገዋል። ፈረንሳይኛና ጀርመንኛን አቀላጥፈው ይናገሩ ስለነበር የቋንቋ ችሎታቸው በብዙ መልኩ ረድቷቸዋል። በተወለዱ በ99 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ከግርማዊነታቸው ዳግማዊት ንግሥት ኤልዛቤት ጋር ላለፉት ሰባት አስርታት አብረው በትዳር ዘልቀዋል። 73 ዓመት በትዳር መዝለቅ ቀላል ጊዜ አይደለም። ፊሊፕ ለምን ንጉሥ አልተባሉም? ለመሆኑ ንግሥቲቱን ካገቡ በኋላ የኤደንብራው መስፍን፣ ልዑል ፊሊፕን ለምን 'ንጉሥ ፍሊፕ' ሳይባሉ ቀሩ? በቅድሚያ በንጉሣዊ ቤተሰብ ውስጥ እነማን እንዳሉ እንዘርዝርና ለዚህ ጥያቄ ምላሽ እናገኛለን። ዳግማዊት ንግሥት ኤልዛቤት እንደ አውሮፓውያኑ ከ1952 ጀምሮ የታላቋ ብሪታኒያ ርዕሰ ብሔር ናቸው። ይህም ማለት የንግሥቲቱ አባት ንጉሥ ጆርጅ 4ኛ ከሞቱ ዕለት ጀምሮ ማለት ነው። ዳግማዊት ንግሥት ኤልዛቤት ርዕሰ ብሔር የሆኑት ለታላቋ ብሪታኒያ ብቻ አይደለም። ለሌሎች 15 አገራት ጭምር እንጂ። በታላቋ ብሪታኒያ ታሪክ እንደ ንግሥት ዳግማዊት ኤልዛቤት ንግሥናውን ለረዥም ጊዜ አጽንቶ የቆየ የለም። ሌሎች የንጉሣዊያን ቤተሰቦችን ለመጥቀስ ያህል፡ 1. የዌልሱ ልዑል ቻርለስ፣ ዕድሜ 72፣ ባለቤታቸው የኮርንዌሏ ካሚላ፣ ልዑል ቻርለስ የንግሥቲቱ የበኩር ልጅ ናቸው፡፡ ንግሥቲቱ ሲሞቱ ንጉሥ የሚሆኑትም እሳቸው ናቸው። 2. የኬምብሪጁ መስፍን፣ ልዑል ዊሊያም። ልዑል ዊሊያም የኬምብሪጇን ካትሪንን ነው ያገባው። ልዑል ዊሊያም የዌልሷ ልዕልት ዳያና የበኩር ልጅ ነው። 3. የሰሴክሱ መስፍን፣ ልዑል ሐሪ፡፡ ሐሪ የዊሊያም ወንድም ነው። ሐሪ ያገባው የሰሴክሷን ሜጋንን ሲሆን ባለፈው ዓመት ከንጉሣዊ ቤተሰብ ወጥተው በራሳቸው ሕይወትን ለመምራት መወሰናቸውን ይፋ አድርገው ነበር። አሁን የሚኖሩትም አሜሪካ ሎስ አንጀለስ ውስጥ ነው። ልዕለት ኤልዛቤት ከልዑል ፊሊፕ ጋር ጋብቻቸውን በፈጸሙበት ጊዜ እንዴት ነው የንጉሣዊ ቤተሰብ የሚኮነው? አንድ ሰው የንጉሣዊ ቤተሰብ አባልን ሲያገባ/ስታገባ የንጉሣዊውን ቤተሰብ ይቀላቀላሉ። ትዳር ሲመሰርቱም የክብር ስም ይሰጣቸዋል። ለምሳሌ ሌዲ ዲያና ስፔንሰር የዌልስ ልዕልት የተባለችው ከልዑል ቻርለስ ጋር በትዳር ስትጣመር ነበር። ይህም እንደ አውሮፓውያኑ በ1981 ዓ.ም የሆነ ነው። ነገር ግን ንጉሥ ወይም ንግሥት ለመሆን ከንጉሣውያኑ ቤተሰብ ጋር በጋብቻ በመጣመር ብቻ የሚሆን አይደለም። የግድ ከንጉሣዊያን ቤተሰብ መወለድ ያስፈልጋል። ይህም በመሆኑ አሁን በአልጋ ወራሽነት ቅደም ተከተል ለንግሥናው ከልዑል ቻርለስ የቀረበ ሰው የለም። ከልዑል ቻርለስ ቀጥሎ ለዙፋኑ የቀረበው ሰው የልዑል ቻርለስ የመጀመሪያ ወንድ ልጅ ልዑል ዊሊያም ነው። ከልዑል ዊሊያም ቀጥሎ ደግሞ የልዑል ዊሊያም የበኩር ልጅ ልዑል ጆርጅ በ3ኛ ደረጃ ለዙፋኑ ይቀርባል። ሟቹ ልዑል ፊሊፕ ግን መቼም ለዙፋኑ ቀርበው አያውቁም። ቅርብ ቢሆኑም ሩቅ ነበሩ። ይህ ለምን ሆነ ብለን ስንጠይቅ በታላቋ ብሪታኒያ ንጉሥ ያገባች ሴት ንግሥት የሚለውን ስም ስትወስድ በተቃራኒው ግን ስለማይሰራ ነው። ይህም ማለት ወንድ ንግሥቲቱን ስላገባ የንጉሥነት ማዕረግን አያገኝም። ልዑል ፊሊፕ ንጉሥ ሳይባሉ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትም ለዚሁ ነው። ሆኖም ዳግማዊት ንግሥት ኤልዛቤት እና ልዑል ፊሊፕ አራት ልጆቻቸው ለዙፋኑ ቅርቦቹ ናቸው። አራት ልጆችንም አፍርተዋል። ልዑል ቻርለስ የበኩር ልጅ ሲሆን አሁን ዕድሜው 72 ደርሷል። ልዕልት አን 70፣ ልዑል አንድሩ 61 እና ልዑል ኤድዋርድ 57 ዓመታቸው ነው። የተነሳንበትን ጥያቄ መልሰናል። ስለዚህም ሟቹ የኤደንብራው መስፍን፣ ልዑል ፊሊፕ ንግሥቲቱን ስላገቡ ብቻ ንጉሥ ሊባሉ አልቻሉም። ኬትና ዊሊያም በጋብቻቸው ዕለት የንጉሣዊያኑ የሠርግ ሥነ ሥርዓት ምን ይመስላል? የንጉሣዊ ቤተሰብ ጋብቻ ብዙውን ጊዜ የዓለምን ትኩረት የሚይዝ ነው። እጅግ በርካታ ሰዎችም ሥነ ሥርዓቱን ይታደማሉ። ለምሳሌ ንግሥቲቱና ሟቹ መስፍን ፊሊፕ ትዳር የመሠረቱት በ1947 በዌስትምኒስትር አቤይ ነበር። ዌስትሚኒስትር አቤይ ቤተ ክርስቲያን ሲሆን ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ960 የተመሰረተ ነው። ከፓርላማው አቅራቢያ የሚገኝም ነው። በርካታ የንጉሣዊ የሠርግ ሥነ ሥርዓቶች የተደረጉበት ሥፍራም ነው። ባለፉት አንድ ሺህ ዓመታት ትልልቅ ጋብቻዎች የተደረጉበት እንዲሁም የትልልቅ ነገሥታት መቃብር የሚገኝበት ሥፍራም ነው። ከንግሥቲቱና ከሟቹ ልዑል ፊሊፕ ጋብቻ ስድስት አስርት ዓመታት በኋላ በ2011 የልዑል ዊሊያምና የልዕልት ካተሪን ሚድልተን ጋብቻ የተፈጸመውም እዚሁ ነበር። የኬምብሪጇ ሶፋኒት ልዕልት ተብለው የተሰየሙትም በዚሁ ሥፍራ ነበር። ሌሎች የንጉሣን ቤተሰቦች በዊንድሰር ጥንታዊ ቤተ መንግሥት ውስጥ በሚገኘው በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ መቅደስ ጋብቻቸውን ፈጽመዋል። ይህ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ 900 ዓመታትን ያስቆጠረ ነው። የቅርብ ጊዜ ትዝታ የሆነውና ሚሊዮኖች የተከታተሉት የልዑል ሐሪ እና የሜጋን ማርክል የጋብቻ ሥነ ሥርዓትም እዚህ ነበር የተፈጸመው። የንጉሣዊያን ቤተሰቦች የት ሆስፒታል ይወለዳሉ? በርካታ የንጉሣዊያን ቤተሰቦች ምርጫ የለንደኑ ሴይንት ሜሪ ሆስፒታል ነው። ልዕልት ዳያና ልዑል ዊሊያምንና ልዑል ሐሪን የተገላገለችው እዚህ ሆስፒታል ነበር። የኬምብሪጇ ልዕልት ሦስት ልጆች፣ ልዑል ጆርጅ 7 ልጆች፣ ልዕልት ሻርለት አምስት ልጆች እና ልዑል የልዊስ ሁለት ልጆች የተወለዱትም እዚሁ ሴይንት ሜሪ ሆስፒታል ውስጥ ነበር። ልዕልት ዳያና እና ልዑል ቻርለስ ልጃቸው ዊሊያም በተወለደበት ጊዜ የንጉሣዊ ቤተሰቦች ተግባርና ኃላፊነት ምንድነው? የብሪታኒያ መንግሥት የግርማዊነታቸው መንግሥት ተብሎ ነው የሚጠራው። ይህ ማለት ግን ንግሥቲቱ የጎላ የፖለቲካ ሥልጣን አላቸው ማለት አይደለም። ንግሥቲቱ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በሳምንት አንድ ቀን ይገናኛሉ። ይህም ንግሥቲቱ በመንግሥት ላይ ያላቸውን ቦታ እንደማሳያም እንደማስታወሻም የሚያገለግል ነው። ያም ሆኖ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፖሊሲ ጉዳዮች የንግሥቲቱን ይሁንታ ማግኘት አያስፈልገውም። ሌሎች አገሮች ጉብኝት ሲኖር ከንጉሣዊ ቤተሰቦች መካከል አንዳቸው ንግሥቲቱን ሊወክሉ ይችላሉ። ለምሳሌ ባለፈው መጋቢት የኬምብሪጅ ልዑልና ልዕልቲቱ በአየርላንድ ሪፐብሊክ ጉብኝት ሲያደርጉ ይፋ ንጉሣዊ ጉብኝት ሆኖ ነው የተወሰደው። ንጉሣዊ ቤተሰቦች ከቀጥታ ፖለቲካዊ ተሳትፎ ይልቅ በብዛት በበጎ አድራጎት ሥራዎችና በተቋሞች የበላይ ጠባቂነት መደቦች ላይ ነው የሚሰማሩት። አንዳንዶቹ የራሳቸው የበጎ አድራጎት ሥራ ድርጅትም አላቸው። ለምሳሌ ሟቹ ልዑል፣ የኤደንብራው መስፍን ፊሊፕ የወጣቶች የሽልማት ድርጅት መሥርተው ነበር። ከመከላከያ ኃይሉ ጋር ቅርበት አላቸው። ለምሳሌ ልዑል ዊሊያም በአየር ኃይል ውስጥ አገልግሏል። ልዑል ሃሪ ደግሞ በጦር ሠራዊት ውስጥ ተሳትፎ ነበረው። ንጉሣውያን ቤተሰቦች ምን ግዴታ አለባቸው? ግዴታ የለባቸውም። ለምሳሌ ባለፈው ዓመት ልዑል ሃሪ እና ሜጋን ከይፋዊ የንጉሣዊ ቤተሰብ ተሳትፎዎች ራሳቸውን ገሸሽ አድርገው በራሳቸው ገቢ እንደሚተዳደሩ ይፋ አድርገው ዓለም ጉድ ብሎ ነበር። የባኪንግሃም ቤተመንግሥት ጥያቄያቸውን ተቀብሎ የክብር ንጉሣዊ ማዕረጎቻችንና መጠርያዎቻቸውንም እንደሚመልሱ አረጋግጧል። ለጥንዶቹ ይውል የነበረው ገንዘብ እና ማዕረግም ለሌሎች ንጉሣዊያን ቤተሰቦች ይተላለፋል። ሃሪና ሜጋን የንጉሣዊ ቤተሰብን ገንዘብ፣ ስምና ጥቅማጥቅምን አንፈልግም ሲሉ የመጀመሪያዎቹ አይደሉም። የዮርክ መስፍን የነበረው ልዑል አንድሩ በ2019 በተመሳሳይ ከንጉሣዊ ቤተሰቡ ራሱን አግልሏል። ይህም የሆነው ከቢቢሲ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ከወሲብ ቅሌት ጥፋተኛው ጄፍሪ ኤፒስቲን ጋር ጓደኝነት እንዳለው ካመነ በኋላ ነበር። ሃሪና ሜጋን ንጉሣዊ ቤተሰቡ የገቢ ምንጭ ምንድነው? በየዓመቱ የብሪታኒያ መንግሥት ለንግሥቲቱ አንድ ከፍተኛ ክፍያን ይፈጽማል። ይህም የ'ሶቨሪን ግራንት' ይባላል። ለምሳሌ የዚህ ዓመት የሶቨሪን ግራንት መጠን 85.9 ሚሊዮን ፓውንድ ነበር። ይህ ገንዘብ ለንጉሣዊ ቤተሰቡ ወጪና ለቤተ መንግሥት እድሳቶች የሚውል ነው። ልዑል ቻርለስ ደግሞ ከዱቺ ኦፍ ኮርንዎል ጠቀም ያለ ገንዘብ ይቀበላል፡፡ ዶቺ ኦፍ ኮርንዎል ገንዘብ የሚያስገባ በ14ኛ ክፍለ ዘመን ጀምሮ የነበረ የይዞታና የፋይናንስ ኢንቨስትመንት ነው። ባለፈው ዓመት ብቻ 22.3 ሚሊዮን ፓውንድ ገቢ አምጥቷል። የንጉሣዊያን ቤተሰቦች የት ነው የሚኖሩት? የንግሥቲቱ ይፋዊ መቀመጫ የሚገኘው በመሀል ለንደን ባኪንግሃም ቤተ መንግሥት ውስጥ ነው። ብዙውን ጊዜ ንግሥቲቱ የሳምንቱን መጨረሻ ቀናትና የፋሲካ ማግስትን በዊንድሰር ካስል፣ በርክሻየር ነው የሚሳልፉት። ሆኖም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ ንግሥቲቱ በበርክሻየር ነው በቋሚነት እየኖሩ ያሉት። ባለቤታቸው ልዑል ፊሊፕም የሞቱት እዚያው ነው። ልዑል ቻርለስ የሚኖረው በለንደን ከባኪንግሃም ቤተመንግሥት በቅርብ ርቀት በሚገኘው ክላርንስ ሐውስ ውስጥ ነው። ልዑል ዊሊምና ካትሪን ደግሞ ብዙም ሳይርቁ ኬንሲግተን ቤተ መንግሥት ውስጥ ይኖራሉ።
44158896
https://www.bbc.com/amharic/44158896
"እንደምፈታ ያወቅኩት ባለፈው መስከረም ነበር" አንዷለም አራጌ
የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ መስራች እና ሊቀ-መንበር አንዷለም አራጌ ከስድስት ዓመታት ተኩል እስር በኋላ ባለፈው የካቲት ወር ከተፈታ ከወራት በኋላ በአውሮፓ ጉብኝት እያደረገ ይገኛል። ጉዞውን ከማድረጉ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረገው አንዷለም ወደ ተቃውሞ ፖለቲካ ለመግባት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን እና አዲስ ፓርቲ የመመሥረት እንቅስቃሴ መጀመሩንም ተናግሯል።
“ኢትዮጵያ የሚያስፈጋት ስር ነቀል ለውጥ ነው። 27 ዓመት ከበቂ በላይ ነው።” - አንዷለም አራጌ ረዥም ጊዜ ተለይቶ ለብቻው በመታሰሩ ለዓመታት የሰው ዐይን ሲራብ መቆየቱን የሚገልፀው አንዷለም፤ ዛሬ በወዳጅ በአድናቂዎች ተከብቦ በሰው ፍቅር እየተካሰ ይመስላል። "አጋጣሚ ኖሮኝ በዚህ ህዝብ መሃል መንከላወሱ፤ መመላለሱ በጣም ደስ የሚል ነገር ነው" ይላል አንዷለም። ቢሆንም ግን ከእስር እንደወጣ ወዲያው በተቃውሞ ፖለቲካ እንዲሁም በፅሁፍ ሥራዎች የመጠመድ ሃሳቡ እንዳልተሳከለት አይደብቅም። ለዚህ አንድም መፈታቱን ተከትሎ የነበረው የጠያቂና የጎብኝ ብዛት የሚያፈናፍን ስላልነበር፥ በሌላ በኩል ደግሞ ከእስር በኋላ ካለው ህይወት ጋር መለማመድ የራሱን ፈተናዎች ይዞ በመምጣቱ ምክንያት እንደሆነ ይገልፃል። በእስር ቤት ቆይታው ህይወቱን በተለያዩ እንቅስቃሴዎች መትሮ ይመራ እንደነበር ይናገራል አንዷለም። "ማንዴላ እንዳሉት የአሳሪው ዓላማ ታሳሪውን በአካልም በመንፈስም ሰብሮ ማውጣት ነው፤ የታሳሪው ዓላማ ደግሞ በአካልም በመንፈስም ጠንክሮ መውጣት ነው። ይህ ለረጅም ጊዜ የእኔ መርኅ ነበር። በአካል በመንፈስም ለመጠንከር የሚረዱኝ ነገሮች ነበሩኝ፤ የተከፋፈለ ህይወት ነበረኝ።" በማለት ህይወቱ በፀሎት፣ በአካላዊ እንቅስቃሴ እና በማንበብ እንዲሁም ዘወትራዊ ክንውኖችን በመፈፀም ያሳልፍ እንደነበር ይናገራል። በዚህ መልኩ ዓመታትን ካሳለፈ በኋላ ወደ ውጪው ዓለም መቀላቀል የራሱ ግርታዎች እንደነበሩት ለቢቢሲ ተናግሯል። "እንደምፈታ ያወቅኩት ባለፈው መስከረም ነበር" ከእስር ከመፈታቱ ስድስት ወራት ቀደም ብሎ ጉዳዩም ጎልቶ መስተዋል ከመጀመሩ በፊት እንደሚፈታ እርግጠኛ ሆኖ እንደነበርና ራሱን አዘጋጅቶ፣ ሻንጣውንም ሸክፎ እንደነበርም ይገልፃል። ከዚያ ቀደም በነበረው የእስር ቆይታ በመንግሥት ቀናኢነት ላይ የነበረው ጥርጣሬ እፈታለው የሚል ሃሳብ እንዳይኖረው አድርጎት ነበር። "የተፈረደብኝን የዕድሜ ልክ እስራት ለመጨረስ ተዘጋጅቼ ነበር። ምንም እንኳ የማይገባኝን ዋጋ ከነልጆቼ ለዓመታት ብከፍልም፤ የገዥው መንግሥት ልሂቃን ፈርጣ እጆች እስካልላሉ ድረስ ለሌሎች ማስፈራሪያ ለማድረግ ሲሉ እስር ቤት ሊያቆዩኝ እንደሚችሉ አምን ነበር። ነገር ግን ምንም እንኳ ከባድ ቢሆንም ይቅርታ በመጠየቅ ልጆቼን አንገት የሚያስደፋ፥ ማኅበራዊ ልዕልና የሚያሳጣ ነገር ላለማድረግ ወስኜ ነበር።" ታዲያ እነዴት እርግጠኛ ሊሆን ቻለ? ለዚህ ምክንያታዊ መልስ እንደሌለው ይናገራል፤ "እንዲሁ ቀልቤ፥ ደመነብሴ ነው የነገረኝ። የአምላክ መንገድ ብዙ ነውና በራሱ መንገድ እንደሚያወጣኝ አምን ነበር።" አንዷለም የእስር ቆይታው እየገፋ ሲሄድ የመዘንጋት ስጋት በርትቶብኝ ነበር ይላል። "ፓርቲዬ ፈርሷል፤ ሰውም ረስቶኛል ብየ አስብ ነበር፤ ጊዜው ስለረዘመ ሰዎች የረሱኝ ይመስለኝ ነበር።" በእስር ቤት ዋነኛ የመረጃ ምንጮቹ ብሄራዊውና ክልላዊው የመንግስት የቴሌቭዥንጣብያዎች ነበሩ።ከጣቢያዎቹ የሚያገኛቸው መረጃዎች ስለ አገሪቷ ነባራዊ የፖለቲካ ሁኔታ ሙሉ እውነታ ባይሰጡትም ከጠያቂ ዘመድ ወዳጆች ግርድፍ መረጃዎችን ያገኝ እንደነበር ይገልፃል። "እንዲያም ቢሆን ከእስር ስወጣ ያስተዋልኩት ነገር ከጠበቅኩት እጅግ የላቀ ነው" ይላል። "እኔ ስታሰር የነበረችው ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖረው በፍርሃት በጣም የተቀፈደደ ህዝብ ነበር" የሚለው አንዷለም የመታሰሩ ምክንያት ይሄንን ፍርሃት ለመስበር በመትጋቱ እንደሆነ ያምናል። ከእስር የባሰ መዘዝንም ሲጠብቅ እንደነበርም ይናገራል፤ "ሊገድሉን እንደሚችሉኝ ሁሉ አምን ነበር። ያለማገነን ሞትን በየቀኑ እለማመደው ነበር። ሞት የሚያስፈራ ቢሆንም፥ መታሰር የሚያስፈራ ቢሆንም ያንን ደረጃ ማለፍ ካለተቻለ ለውጥ እንደማይመጣ አምን ነበር።" ፍርሃትና ተስፋ ይሁንና በወቅቱ ሲያደርጋቸው የነበሩ እንቅስቃሴዎች በበርካታ ሰዎች ዘንድ ራስ ላይ አደጋን እንደመጋበዝ ወይንም በህይወት ውስጥ ስኬት ከማጣት የመነጨ እርምጃ ተደርገው ይቆጠሩ እንደነበር ይናገራል። ከእስር ሲወጣ ያስተዋለው ግን ከዚህ እጅግ የተለየ ሁኔታ እንደነበር ይገልፃል። "ህዝቡ በከተማም በገጠርም ተነቃቅቶ፥ እኛም እንደ ጀግና ተቆጥረን ሲታይ እውን የሆነ፥ የማይጨበጥ ይመስል የነበረ፥ ነገር ግን አሁን የተጨበጠ ህልም ነው ለእኔ። ህዝቡ ፍርሃትን አሸንፏል፤ የመጡት ለውጦችም ትልቅ ናቸው። በዲሞክራሲ ትግል ውስጥ ትልቁ ነገር ፍርሃትን ማሸነፍ ነው። ለፍርሃት የማይገብር ሕዝብ ካለ አገዛዝ በጫንቃው ላይ ሊሰፍር አይችልም።" ይህ እውነታ ከገዥው ቡድን እልፍኝም መግባቱን እንደታዘበ ይገልፃል አንዷለም። "በውጭ የተደረገው ትግል፥ ኢህአዴግ ውስጥም መነቃነቅ የፈጠረ ይመስለኛል።" የሚለው አንዷለም ኢህአዲግን በሊቀ መንበርነት፥ አገሪቱን በጠቅላይ ሚኒስትርነት እንዲመሩ የተሾሙት ሰው በብዙኃን ዘንድ ተስፋ መፈንጠቃቸውን ባይክድም፥ ጥያቄዎቹን መሰንዘሩ ግን አልቀረም፤ "የተባለውን ነገር በተግባር መተርጎም ይችላሉ ወይ? የተባለውስ በቂ ነው ወይ? ጥገናዊ ለውጥ ነው ወይ የሚያስፈልገው? አይመስለኝም። ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ስር ነቀል ለውጥ ነው። ሃያ ሰባት ዓመት ከበቂ በላይ ነው።"በማለት ጥያቄውን ይመልሳል። ከዚህ በኋላ ከኢህአዴግ በሚሰፈር ዳረጎ የሚኖርበት ጊዜ እንዳበቃ የሚያምነው አንዷለም በቀጣይ ሁሉንም አካላት ያሳተፈ ንግግር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያደርጋሉ ብሎ እንደሚጠብቅ ያስረዳል።
news-49672583
https://www.bbc.com/amharic/news-49672583
"ስተዳደር የቆየሁት በዋናነት ለመለስ በሚሰጠው የጡረታ ገቢ ብቻ ነው" ወ/ሮ አዜብ መስፍን
ወ/ሮ አዜብ መስፍን የሕወሓት ነባር ታጋይና የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ባለቤት ናቸው። ቀዳማዊ እመቤት በነበሩበት ወቅት የትግራይ መልሶ ማቋቋሚያ ማኅበር (ትዕምት ወይም ኤፈርት) መሪ ነበሩ። ወ/ሮ አዜብ፤ የባለቤታቸው መታሰቢያ የሆነው የመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን መስራችና የቦርድ ሰብሳቢም ናቸው።
ቀዳማዊ እመቤት በነበሩበት ወቅት፤ በአዕምሮ ህሙማን ዙሪያ የሠሩትን ሥራ በጣም እንደሚኮሩበት ይናገራሉ። በተለያየ ዘርፍ ከሌሎች አካላት ጋር በመሆን ያከናወኗቸው በርካታ ሥራዎች ስለመኖራቸውም ያስታውሳሉ። በኢትዮጵያ ሴቶች ፌደሬሽን የተቋቋመው "የጉልት ማዕከል" የተባለውን ሃሳብ ከማመንጨት ጀምሮ እስከመጨረሻው መሳተፋቸውን እንደ አብነት ያነሳሉ። ["የጉልት ማዕከል" በጎዳና የንግድ ሥራ የተሠማሩ ሴቶች የሚደገፉበት ፕሮጀክት ነው።] ታዲያ በዚህ ጊዜ ዋናውና መደበኛ ሥራቸው በፓርቲው የሚሰጣቸውን ሥራ መሥራት ነበር። "ራሴን የምወቅስበት ሥራ ሳልሠራ እና ጥሩ ሥራ ሰርቼ ከፓርቲው መውጣቴን እኮራበታለሁ፤ ሰው የፈለገውን ቢል" ይላሉ። • "ሕገ-መንግሥቱ ተተኪ ጠቅላይ ሚኒስትርን በሚመለከት ክፍተት አለበት" ውብሸት ሙላት • 'ደብረፅዮን'፣ 'ጌታቸው አሰፋ'...ከዘንድሮው አሸንዳ አልባሳት ስሞች መካከል ድህነትን በመታገል ረገድ በርካታ ሥራዎችን እንዳከናወኑም ይናገራሉ። "ለሕዝብ ይጠቅማሉ ብዬ የተንቀሳቀስኩባቸው ሥራዎች ጥሩ ናቸው ብዬ አምንባቸዋለሁ" ሲሉ ያክላሉ። ባለቤታቸው፤ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ሰባት ዓመት ሞልቷቸዋል። ለመሆኑ የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ባለፉት ዓመታት ምን ሲሠሩ ቆዩ? አሁንስ በምን ሥራ ላይ ነው ያሉት? አዲስ ዓመትን አስመልክተን ከብዙሃን መገናኛ የጠፉትን ስንፈልግ፣ ስናስፈልግ ካገኘናቸውና ለቃለ መጠይቅ ፈቃደኛ ከሆኑት ከወ/ሮ አዜብ ጋር ጥቂት ተጨዋውተናል. . . እንኳን አደረሰዎት ወ/ሮ አዜብ እንኳን አብሮ አደረሰን። አሁን የት ነው የሚኖሩት? ተቀማጭነትዎ የት ነው? ብዙ ሰዎች አዲስ አበባ የለችም ይላሉ። ግን አዲስ አበባ ነው ያለሁት- አንዳንዴ ገባ ወጣ ከማለቴ ውጭ። ባለቤትዎን፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር መለስን በሞት ካጡ በኋላ ቤተ መንግሥት የሄዱበት አጋጣሚ አለ? [ፋታ]. . . ብዙ ጊዜ አልሄድም። የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ በነበርኩበት ጊዜ አንድ ሁለት ቀን የጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ሄጃለሁ። ያው ስብሰባው እዚያው ግቢ ውስጥ ስለነበር። ከዛ ውጭ ግን አልሄድኩም፤ መሄድም አልፈልግም። በጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ አስተዳደር ጊዜ ማለት ነው? አዎ! በቅርቡ አንድ ጊዜ የሄድኩ ይመስለኛል። በስብሰባዎች ምክንያት ስሄድ ነበር፤ ነገር ግን ብዙም አልሄድኩበትም። ቤተ መንግሥቱ ከልጆችዎ፣ ከቤተሰብዎ ጋር ለረዥም ዓመታት የኖሩበት ነውና አይናፍቅዎትም? እ. . . [ዝምታ] በዚያ ሳልፍ እንኳን ምንም ስሜት አይሰማኝም። ምክንያቱም አወጣጤ ላይ. . . መለስን ቀብሬ ነው የወጣሁት። እና ደግሞ ቤተ መንግሥትን እንደ ታጋዮች ነው የኖርንበት። የሥራ ድርሻ ተሰጥቶን ነው የኖርንበት። ከቤተ መንግሥት ስንወጣ መለስን ቀብሬ እወጣለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር። ሁለታችን አብረን የምንወጣበትና እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነፃ ሆነን ተንቀሳቅሰን የምንኖርበትን ጊዜ እመኝ ነበር። እኔ ብንቀሳቀስም፤ መለስ ግን የመንቀሳቀስ እድል አላገኘም ነበር። እዚያው እንደታሰረ፣ እዚያው ቀብሬው መውጣቴ ይሰማኛል [ሳግ በተናነቀው ድምፅ]. . . ከቤተ መንግሥት ይልቅ ሥላሴ [ቤተ ክርስቲያን] ስገባ በጣም ይሰማኛል። እና. . . ቤተ መንግሥትን ሳይ፤ መለስን ቀብሬ የተመለስኩበትን ሰዓት ብቻ ነው የማስታውሰው። አስክሬኑን ይዤ የወጣሁበትን ደቂቃዎች ብቻ ነው የማስታውሰው። ሌላው በሙሉ ለምን እንደሆነ አይገባኝም. . . ትዝ አይለኝም። የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ሕልፈትን ተከትሎ፤ ወ/ሮ አዜብ መስፍን በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጩኸቱ. . . አስክሬኑ ሲወጣ፤ አስክሬን ይዤ ስገባ. . . ድንጋጤው። መጨረሻ ደግሞ ስንወጣም፤ አወጣጣችን ራሱ ትልቅ ችግር ነበረው። እ. . . እሱም የራሱ ድርሻ አለው መሰለኝ፤ ላለማስታወሴ። የማስታውሰው ግን ይኼኛው ነው። የቀብር ቀኑን፣ ከቀብሩ ስንመለስ፣ አስክሬኑን ይዘን ስንገባ. . . ባለቤትዎ በሞት ከተለዩ ሰባት ዓመታት ተቆጥረዋል። እስካሁን ምን ሲሠሩ ነው የቆዩት? እንደሚታወቀው በፓርቲ ሥራ ላይ አይደለም ያለሁት። ለእኔና ለልጆቼ የሚያስተዳድሩንን ሥራዎች ለማስተካከል ደፋ ቀና ስል ነው የቆሁት። በተጨማሪ ዋናው ሥራዬ የባለቤቴን ሥራዎች ለማስቀጠል፣ ፅሁፎቹን ለማሳተም የሚያስችለኝን አጠቃላይ ዶክመንቶቹን በማዘጋጀት ላይ ነበርኩ። እርሱም ተጠቃሏል። ታዲያ ለግልዎ መተዳደሪያ የሚሆን ምን ሥራ አገኙ? በንግድ ዘርፍ ለመግባት እያሰብኩ ነው። እንዴት እንደምሠራ፣ መነሻ ገንዘቡን እንዴት እንደማገኝ ወይ ከሰዎች ጋር ሆኖ. . . እስካሁን የተለያየ ድርጅትን ለማማከር. . . ፓርቲው የንግድ ሥራ ላይ አሰማርቶኝ ስለቆየሁ እኔን የሚመለከት ምንም አልነበረም። ለሕዝብ ነው የሠራሁት። ለሕዝብ አስረክቤ. . . ይረከባሉ ለተባሉ ሰዎች አስረክቤ፤ ባዶ እጄን ነው የወጣሁት። ስተዳደር የቆሁት በዋናነት ለመለስ በሚሰጠው የጡረታ ገቢ ነው። እና ከቤተሰብ፣ ከዛም ከዛም. . . ከአሁን በኋላ ግን የራሴን ሥራዎች መሥራት እፈልጋለሁ። አልፎ አልፎ ከተለያዩ ትልልቅ ድርጅቶች ጋር ለማማከርም ከእነርሱ ጋር ለመሥራትም የሞካከርኳቸው እዚያም እዚህም አሉ. . . ከተሳኩልኝ አንዳንድ ነገሮች ለመጀመር ፍላጎትና ዝግጁነት አለኝ። የባለቤትዎ የጡረታ ገንዘብ ምን ያህል ነው? በወር አስራ አራት ሺህ ብር ገደማ መሰለኝ። በትዳር ስንት ዓመት ነው የቆዩት ኦው. . . ሕወሓት ሠርግ ከፈቀደ ጀምሮ እስከ መስዋዕቱ ድረስ አብረን ነበርን። 25/26 ዓመታት። ሦስት ልጆች አሉን። አንዷ በረሃ ነው የተወለደችው። ሁለቱን አዲስ አበባ ነው የወለድኳቸው። አንዱ. . . ብዙ ጊዜ ሰው ይምታታበታል። እኔ አልወለድኩትም። እናት አለችው ግን የሟቹ ጓደኛችን ክንፈ ገብረ መድህን ልጅ፣ ያሳደኩት ልጅ አለን። ሁሉም ልጆችዎ ከእርስዎ ጋር ነው የሚኖሩት? አሁን ለአባታቸው ሙት ዓመት ገብተው ነበር። አንዱ ወደ ውጭ አገር ሄዷል። ሦስቱ ግን ከእኔ ጋር ነው ያሉት። እንግዲህ ራሳቸውንም እየቻሉ ነው፤ ተመርቀዋል። የጨረሱም ያልጨረሱም አሉ። እና እነሱም ጥግ ጥጋቸውን ይይዛሉ። የባለቤትዎመለስ ዜናዊን ዶክመንቶችና ጽሁፎች ሲያሰባስቡ እንደቆዩ ነግረውኛል። ምን ያህል ቢበረክቱ ነው ይህን ያህል ዓመታት የፈጀብዎት? ባለፈው ዓመት አሳውቀን ነበር። ወደ ስምንት መጻሕፍት. . . ራሱ የደረሳቸው፣ የራሱ መሆናቸው በራሱ የእጅ ፅሁፍ የተረጋገጡ፣ ባለፈው ደግሞ በመንግሥትና በፓርቲ ስም ሲወጡ የነበሩ፣ ፅድት ብለው ዝግጅታቸው የተጠናቀቁ ወደ ስምንት መጻሕፍት አሉ። በአጠቃላይ ግን ወደ 30 ምናምን ይደርሳሉ። እነርሱንም ባለፈው ከነበረው ሁኔታ ጋር ከማተሙ ይልቅ ይዞ መቆየቱ ይሻላል ብለን አንዳንዶቹን ይዘናቸው ነበር። የበጀት እጥረትም አጋጥሞን ነበር። የነበረንንና ያገኘነውን በሙሉ በቅድሚያ ለሕዝብ መናፈሻው 'ኢንቨስት' ስላደረግነው ነው። ስለ ዲሞክራሲ የፃፈው በቅርቡ ይታተማል። ስለ ግብርና የፃፈውና ሌሎችም ጠቅለል ተደረገው በቅርቡ ይታተማሉ። • ''ከ122 ዓመት በፊት የተጣለ መሰረት ዛሬ እየተናደ እንዳይሆን'' ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀ አሁን ላለው ትውልድም ሆነ ለመጭው ትውልድ ይጠቅማሉ ያልናቸውና መውጣት አለባቸው ብለን ያሰብናቸው ጠቅለል ጠቅለል ብለው ይወጣሉ። በተለይ የመደራደር አቅሙ ምን ይመስል እንደነበር እና ነገሮችን አስቀድሞ የሚያይባቸው፣ የሚመለከትባቸው፣ የሚተነትንባቸው፣ የሚገመግምበት መንገድ ምን ይመስል እንደነበር፤ ሁኔታዎችን አስቀድሞ ይበጃል፤ ለትውልዱ ይጠቅማል ያልናቸው የተዘጋጁ ነገሮች አሉ። እነሱም በዚህ ዓመት ይወጣሉ ብዬ አምናለሁ። ዝግጅታቸው የተጠናቀቁት ወደ ስምንት ወይም አስራ አንድ ይደርሳሉ። ስለዚህ ስምንቱ መጻሕፍት ተጠናቀው አልቀዋል ማለት ነው? ተጠቃሎ አልቋል። የመጨረሻ ዲዛይናቸው ይቀራል። ሁለቱ ግን ዲዛይናቸውም ምናምናቸውም ስላለቀ በቅርቡ ታትመው ይወጣሉ። የት ነው የሚታተሙት? በ 'ቮሉዩም' [በክፍል] ስለጀመርነው እና የ 'ሃርድ ከቨሩ' [ሽፋኑ] ነገር አስቸጋሪ ስለሆነ የተወሰነው ውጭ ይታተማል። በብዙው ደግሞ እዚህ ታትሞ ለአንባቢያን በቅርብ እንዲገኝ እናደርገዋልን። በአጠቃላይ ስንት መጽሐፍ አላቸው? በአጠቃላይ ከ30 በላይ ናቸው የጻፋቸው። ያዘጋጀናቸው ሰነዶቹ በጣም ብዙ ናቸው። አሁን በቅርቡ እንዲታተሙ ያልፈለግናቸው የራሱ የጥናት ፅሁፎችም አሉ። በእንግሊዝኛ ተዘጋጅተው የተቀመጡ፤ በጣም ግዙፍ። እነርሱን ሳያካትት ማለት ነው እንጅ፤ ብናካትታቸው በጣም ብዙ ናቸው። ከ30 በላይም ይሄዳሉ። ግን አሁን ዝግጁ ናቸው፣ ሊወጡ ይችላሉ ብለን ያመንባቸው ስምንቱ ናቸው። እነዚህን ነገሮች ለማስተካከል ማነው የሚረዳዎት? ትልቋ ልጄ ከእኔ ጋር ትሠራለች። ከአባቷ ፋውንዴሽን ጋር ትሠራለች። ሌሎች በፋውንዴሽኑ ስር የተሠሩ አሉ። አብዛኛውን ሰነዶቹን እኔ አውቀው ስለነበር ለዛ ነው ባለፉት ዓመታት ፀጥ ብዬ ሰነዶቹን መለየት ላይ፣ ማደራጀት ላይ [ያተኮርኩት]። አንዳንዶቹ 'ኦሪጅናል' [የራሱ የእጅ ጽሁፍ] እኔ ጋር ስለነበሩ፤ የማሰባሰቡ ጉዳይ፣ የማደራጀቱ ጉዳይ በቅርብ በእኔ ነበር የሚሠራው። ከዚያ በኋላ ግን ሌሎቹን ሥራዎች ልጄም አለች፤ ሌሎችም አሉ የሚሠሩ። አዘጋጅቶ ለልጆቹ ማስረከብ ነበር. . . እኔ የቤት ሥራዬን ጨርሻለሁ። መናፈሻው ላይም እየሠሩ እንደሆነ ገልፀውልኛል። ከምን ደርሷል? መናፈሻው በጉለሌ ተራራ ላይ የሰፈረ ነው። በጣም ትልቅ ነው። ስፋቱን አሁን በትክክል አላስታውሰውም። ለማንኛውም. . . ማዕከሉ ቤተ መጻሕፍት፣ የጥናት ማዕከል፣ ለጥናትና ምርምር ለሚመጡ እንግዶችና ተማሪዎች የእንግዳ ማረፊያ ክፍል አለው። መሰብሰቢያ አዳራሽ አለው። 'አውት ሉክ' [እንደ መናፈሻ] አለው። ከአንዱ ወደ አንዱ ሲኬድም የመሬት አቀማመጡና የመሬት ዲዛይኑ ለታሪኩ እንዲመች ተደርጎ ተዘጋጅቷል። በአብዛኛው የተሸፈነው በአገር በቀል ዛፎች ነው። መሄጃዎቹ፣ መውረጃዎቹ ያለፋቸው የሕይወት ታሪኩን የሚገልፁ ሆነው ተዘጋጅተዋል። በ7ኛ ሙት ዓመቱ ላይ ምስሎቹ አለፍ አለፍ ብለው ቀርበዋል። በጣም በታወቁ ባለሙያዎች፣ ትውልድ ተሻጋሪ ሆኖ እንዲቀር ታስቦ በጥንቃቄ የተዘጋጀ ዲዛይን ነው። እያንዳንዳቸው የራሳቸው መልዕክት አላቸው። ከመልዕክታቸው በተጨማሪ ውበትም አላቸው። እንደ ቤት. . . እንደ ግንባታ ብቻ ሳይሆን እንደ 'አርት ፒስ' [የጥበብ ሥራ] ሆነው እንዲቀሩ ተደርጎ ነው የተሠራው። ለአገልግሎት መቼ ነው የሚከፈተው? በቅርቡ ይሆናል። ጊዜው በውል አይታወቅም፤ ምክንያቱም አስመርቀን መክፈቱን አልፈለግነውም። ሲመረቅ ወዲያውኑ ሥራ ከመጀመሩ ጋር መያያዝ አለበት። የሰው ኃይሉም፣ መጻሕፍቱም. . . ሁሉም ዝግጅቶች ተጠቃለው እንደተመረቀ ወዲያውኑ ሥራ እንድንጀምር አድርገን ለመክፈት ስለፈለግን ነው። እነዚህን ሥራዎች ለማከናወን የገንዘብ ድጋፉ ከየት ነው የተገኘው? ባለፈው መለስ እንደተሰዋ፤ የመለስ ፋውንዴሽን ሲመሰረት፤ ጎረቤት አገራትም፣ የአገራችን ክልሎችም፣ የፌደራል መንግሥትም እና ከሌላ. . . ከሕዝብ የተውጣጣ የገንዘብ ድጋፍ ነበረ። ያንን እንዳለ ወደዛ ነው ያስገባነው። ወደ ቤተሰብ የመጣ ምንም ነገር የለም። እርሱ እንደ ቋሚ ቅርስ ሆኖ እንዲቀር ስለፈለግነው። እናም ግንባታው እየተጠቃለለ ያለው በዚያ ነው። የመጻሕፍቱ የሕትመት ወጪም? አዎ! በዚያው በተደረገው ድጋፍ ነው። የራሱ የፋውንዴሽኑ አካውንት አለው። ወደ ፋውንዴሽኑ አካውንት ነው ገቢ የተደረገው። ከፋውንዴሽኑ አካውንት ደግሞ እያንዳንዱ ክፍያ ይካሄዳል። እርሱ ደግሞ በየዓመቱ ኦዲት ይደረጋል። ፋውንዴሽኑ ላይ ያለዎት ሚና ምንድን ነው? እንዳልኩሽ. . . ባለፈው ዋና፣ ትልቁ የእኔ ሥራ የተበታተኑ የመለስ ጽሁፎችን ማዘጋጀት ነበር። ሕወሓት እኔን ማስወጣቱ ትልቅ እድል ነው የሰጠኝ። ጊዜ አላገኝም ነበር፤ ማሰባሰብም አልችልም ነበር። የተበታተኑትን በሙሉ የማስታውሳቸውን፣ እጄ ላይ የነበሩትንና ሌላ ጋር የነበሩትን ለማሰባሰብ ቅድሚያ የሰጠሁት እሱን ነበር። • የሕወሓት ግምገማና እርምጃ ወዴት ያመራ ይሆን? ይህን አዘጋጅቶ 'ዲጂታይዝ' ማድረግ፣ ለሚችሉት ለማስተላለፍ የጨረስኩትም በቅርቡ ነው። ዋናው ትኩረቴ የመለስን ሰነዶች የማዘጋጀት፣ ያው ሳዘጋጅ ደግሞ 'ካታጎራይዝ' ለማድረግ እየተነበበ ስለሆነ፤ ለማንበብም ትልቅ እድል ነው ያገኘሁት። እና ዋናው ሥራዬ እሱ ነው የነበረው። አልፎ አልፎም ሌሎች የምሠራቸው ነገሮች ነበሩ። ይህን ስላጠቃለልኩ ነው አሁን ወደ ሌላ ሥራ መግባት አለብኝ የምለው። የገፈርሳ የአዕምሮ ህሙማን ማዕከል ጉዳይስ? ያን ጊዜ ግንባታውን አጠቃለን ቁልፉን አስረከብን። ጤና ሚኒስቴር ተረክቦ ከአማኑኤል ሆስፒታል ጋር እንዲያያዝ ነበር ያደረግነው። ማዕከሉ ተከፍቶ እንዲሠራ 'ብራዘርስ' የተባሉ የካቶሊክ ሃይማኖት ተከታዮች፤ በ 'ሳይካትሪስት' [የሥነ ልቦና አማካሪነት] እንዲያገለገሉ ከውጪ አምጥተናል። አራት፣ አምስት ዓመታት አገልግለዋል። አሁን በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሥር ነው የሚሠራው። የእኔ ኃላፊነት የነበረው ግንባታውን አስጨርሶ፣ ማዕከሉን አደራጅቶ፣ አብቅቶ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንዲከታተለው ማድረግ ስለነበር፤ አሁን በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሥር ሆኖ አገልግሎት እየሰጠ ነው። የወደፊት ዕቅድዎ ምንድን ነው? ዋናው ሥራዬ ብዬ የማምነው በመለስ ስም የተሰየመውን የሕዝብ መናፈሻ ለሕዝብ ክፍት ማድረግ ነው- ወደ ማጠቃለል ደረጃ ስለደረሰ። እሱንና ልጆቼ ላይ አተኩሬ በዋናነት መስራት። የራሴን ሥራዎች፣ የግሌን ሕይወት የማስተዳድርበትን ለመጀመር እፈልጋለሁ። በየትኛው አቅጣጫ? እንዴት ብሎ? የሚለውን አጠቃልዬ ስጨርስ እገልፀዋለሁ። በትርፍ ጊዜዎ ምንድን ነው የሚያዝናናዎት? አትክልት እወዳለሁ። ጊዜዬን ከአበባ ጋር፣ ከችግኝ ጋር፣ ከአትክልቶች ጋር ባሳልፍ እመርጣለሁ። ቤቴን እወዳለሁ። ከቤት ውጭ ብዙ መውጣት አልፈልግም። ከሥራ ወደ ቤቴ ነው የምመጣው። ስፖርት. . . የእግር ጉዞ አደርጋለሁ። ረዥም መንገድ እጓዛለሁ። አልፎ አልፎ ተራራዎችን እወጣለሁ. . . ራሴን ለመፈተን ስፈልግ መውጣት እችላለሁ። አልችልም ግን እወጣለሁ። የት ተራራ ወጥተው ያውቃሉ? ያው. . . ከሽሮ ሜዳ ወደ እንጦጦ ማሪያም እወጣለሁ። ባለቤትዎ የድምጻዊት አስቴር አወቀ ሙዚቃ አድናቂ እንደነበሩ ሲናገሩ ሰምቻለሁ። የእርስዎ ምርጫስ? የመለስ ተፅዕኖ መሰለኝ አስቴርን በጣም እወዳታለሁ። 'አልበሟ' ከመኪናዬ ተለይቶኝ አያውቅም. . . አዳዲስ የወጡ ሙዚቃዎችንም አዳምጣለሁ። ሌሎች ብዙዎችን አዳምጣለሁ። ብዙ ጊዜ ግን የአስቴርን ሙዚቃ እወዳለሁ። በጣም ብዙ ጊዜ ከራሴ ሕይወት ጋር የሚገጥም ስለምትዘፍን ደጋግሜ የእርሷን እሰማለሁ። ሌሎችንም ትግርኛ ሙዚቃዎችን እሰማለሁ። የትኞቹ ሙዚቃዎች ናቸው ከራስዎ ሕይወት ጋር የሚገጥሙት?አንድ ሁለት ምሳሌ ቢሰጡኝ? በጣም ብዙ አጋጣሚዎች ሕይወቴ ጋር. . . ወደ ዝርዝር ልታስገቢኝ ነው እንጂ. . . [ሳቅ] ለምሳሌ አንድ ጊዜ የዘፈነችው ዘፈን አለ። ስለ ሰው፣ ስለ ሰው ቀድጄ ልልበሰው የምትለው። በዚያ ሰዓት ሕወሓት ውስጥ መከፋፈል የገጠመበት ወቅት ነበር። እርሱ እኔን ካጋጠሙኝ አጋጣሚዎች ጋር ገጥሞልኝ ነበር። [የአስቴር 'ወየው ጉድ!' የሚለው ሙዚቃዋ ከስንኙ ትንሽ እንበላችሁ] [. . . አትሸበር ልቤ ለሆነ ላልሆነው፣ ስለ ሰው፣ ስለ ሰው ቀድጀ ልልበሰው. . . ] እ. . . እነ አያ ጅቦ. . . ወይ ሥራን አይሠሩ፤ ወይ ሰው አያሠሩ ብላ የዘፈነችውንም እወደዋለሁ። እንደዛ አይነት አጋጣሚ ገጥሞኛል። [ይህ ዘፈን 'እማሙ' ይሰኛል። ከስንኞቹ ጥቂቶቹን እናካፍላችሁ] [ሰው ጥሩ ሰው ጥሩ እባካችሁ፣ እነ ቆርጦ ቀጥል እንዴት አደራችሁ? *** ለምን ይነኩኛል ይወሰውሱኛል፣ ቆራርጠው ቀጥለው ይወነጅሉኛል፤ *** ፀጉር አትሰንጥቁ አየር አትመትሩ፣ ፈጣሪን አክብሩ ሠርታችሁ እደሩ፤ ] ድሮ ልጅ ሆኜ፤ ሜዳ ሆኜ፤ የምወደው ዘፈኖቿም አሉ። 'አገር አገር አለች፤ ይች አገረ ብርቁ' ብላ የምትዘፍነውን ደጋግሜ [እሰማው] እወደው ነበር። እ. . . የማን ነበር? ድንገት ሳለስበው ብላ የምትዘፍነዋ [የድጻዊት ብዙነሽ በቀለን ነው] የሚለውንም እወደው ነበር። አስቴር አወቀ ከመለስ መሰዋዕት በፊት ያወጣችው ሲዲ ነበር። ከትራሳችን የማይለይ። 'ጨጨሆ' ያለበት። እዚያ አልበም ላይ አምስተኛው ወይም አራተኛው ቁጥር ላይ ያለው አለ። 'ካለ እሱ በስተቀር ሰው እንደሌለ' ምናምን ብላ የምትዘፍነው። እሱን እወደዋለሁ። [ዘፈኑ 'ፍቅር አያልቅበት' ይሰኛል፤ አንድ ስንኝ እነሆ] [. . . ትዝታህ በሙሉ ይደቀናል ከዐይኔ ሰው እንዳልተሠራ ካንተ በቀር ለእኔ] መለስ ከተሰዋ በኋላ ያወጣችው ሲዲም ገጥሞልኛል። ስለዚህ አስቴር ትስማማኛለች ለእኔ። አቶ መለስ የአስቴርን ሙዚቃ አብዝተው የሚወዱት ለምን ነበር? የተለየ ምክንያት ነበራቸው? መለስ ሙዚቃ ማዳመጥ ይወዳል። አዳማጭ ብቻ አይመስለኝም። የሙዚቃ መሣሪያዎቹ እንዴት እንደገቡና የሚሰጡትን ድምፅ ለይቶ ማውጣት ይችል ነበር። ግጥሞቹን፣ ትርጉማቸውን፣ ቅኔያቸውን ያውቃቸዋል። በጣም ትልቅ ዋጋ ይሰጣቸዋል። ከትግርኛ ዘፈኖች የታጋይ እያሱ በርሄን ሙዚቃዎች በጣም ያደንቅ ነበር። የእርሱ ትግርኛ ብዙዎቻችን ሳይገባን መለስ ይገባዋል- ቅኔው ውስጥ ላይ ያለው። ይዘቱን የመተንተን፣ ሙዚቃዎችን የማወቅ፣ የመረዳት ችሎታ ነበረው መለስ። እንግሊዝኛም ሲሰማ እንደዛው ነው። አቶ መለስ ያንጎራጉሩ ነበር? አዎ በጣም! ጠዋት ጠዋት ሲነሳ . . . አሊያም ማታ ሲገባ ያንጎራጉር ነበር። ያው ድምፅ የለውም ግን ግጥሞቹ ይወጣሉ። • አቶ ጌታቸው አሰፋ በሚያውቋቸው አንደበት
news-57193971
https://www.bbc.com/amharic/news-57193971
በኤርትራ ምርጫ ተካሂዶ የማያውቀው ለምንድን ነው?
የኤርትራ ሕዝብ፤ በ1983 ዓ.ም ነጻነቱን ካገኘ በኋላ በዴሞክራሲያዊና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት የሚመራ መንግሥት ለመትከል ለ30 ዓመታት ቢጥርም፤ እስከ ዛሬ ሕገ መንግሥቱ ሥራ ላይ ሳይውል፣ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ሳይካሄድ ቆይቷል። በቅርብ ዓመታት ውስጥ ይህ እንደሚሆን የሚታይ ፍንጭ የለም።
የአገሪቷ ፕሬዝደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ አገራዊ ምርጫ እንዲካሄድ ያልፈቀዱበት ምክንያት ምንድን ነው? የኤርትራ የነጻነት ትግል ሻዕቢያና የኤርትራ ነጻነት ትግል [ተሓኤ] "ቅኝ ግዛትን በማስወገድ ሕገ መንግሥታዊና ዴሞክራሲያዊ ነጻ ኤርትራ" መገንባት የሚል አላማ ይዘው መታገላቸውን ኤርትራን በቅርበት የሚከታተሉ ምሁራን ይናገራሉ። በሳሕል በተካሄደው ሁለተኛው ጉባኤ [እኤአ 1987] የወጣው አገራዊ ዴሞክራሲያዊ ፕሮግራም እንዲሁም በ1994 (እኤአ) በተካሄደው ሦስተኛው ጉባኤ የጸደቀው አገራዊ ቻርተር አላማው "ዴሞክራሲያዊና ሕገ መንግሥታዊ መንግሥት መፍጠር" እንደነበረ የሕግ ሙሁር ዳዊት ፍስሃየ ይናገራሉ። "ዴሞክራሲያዊ መንግሥት መመስረት" በሚል ርዕስ በ1987 የተዘጋጀው ፕሮግራም "የትግሉ አላማ የሕዝብ ጥቅም የሚያስጠብቅ መንግሥት መመስረት ሆኖ፣ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ ነጻ የሕዝብ ወኪል፣ ሕገ መንግሥት የሚያረቅ፣ አዲስ ውሎች የሚያጸድቅ፣ የዜጎች መብቶች የሚያስከብርና ሕዝብን የሚያገለግል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማቆም" እንደነበረ ያስረዳል። በ1994 የጸደቀው ቻርተር ደግሞ፣ አገራዊ የዴሞክራሲ ፕሮግራም ሃሳብን የሚያነሳ እንደሆነ የሚናገሩት አቶ መጎስ ብርሃነ በበኩላቸው፤ "ሕግና ሥርዓት የሚያከብር፣ አንድነትና ሰላም የሚያስጠብቅ፣ አገራዊ አንድነት የሚያረጋግጥ ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ሥርዓት ለመገንባት" ያለመ ነበር ይላሉ። በ1990 ፕሬዝደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ የድርጅታቸው ሊቀመንበር በነበሩበት ወቅት፤ ሁሉም እንደየአቅሙ አገር በመገንባትና በአገሪቷ ላይ በሚገነባው ሥርዓት ተሳታፊነት እንዲኖረው፣ ሁሉንም የሚወክል ሥርዓት እንዲመጣ፣ የመድብለ ፓርቲ ሥርሥት እንዲገነባ፤ አንድ ፓርቲ የሚመራው የፖለቲካ ሥርዓት ግን መረጋጋትና ዋስትና እንደማይፈጥር መግለጻቸውን ያስታውሳሉ። ታዲያ ሁኔታዎች በምን ምክንያት ተቀየሩ? የኤርትራ ሕዝብ በ1993 በተካሄደው ሪፈረንደም 99.8 በመቶ ነጻነት መምረጡ ይታወሳል። በግንቦት 19/1993 ደግሞ በአዋጅ 37/1993 ሕገመንግሥት እና የፕሬስ ሕግ የሚያረቅና የሚያጸድቅ እንዲሁም የፖለቲካ ድርጅቶች የሚመሩበት፣ አገራዊ ምርጫ የሚካሄድበት ሕግ የሚያዘጋጅ፣ አራት ዓመት የስልጣን እድሜ ያለው ጊዜያዊ መንግሥት እንደተቋቋመ የኤርትራውያን የሕግ ምሁራን ማኅበር አባል አቶ ኤልያስ ሃብተሥላሴ ይናገራሉ። ይህ አዲስ መንግሥት ጊዜያዊ የኤርትራ መንግሥት በመባል እንደሚታወቅና ሕግ አውጪ፣ ሕግ ፈጻሚና፣ ሕግ ተርጓሚ አካላትን እንደሚያጠቃልል አዋጁ ያስረዳል። ይህ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት የመገንባት ሂደት በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ግጭት እስኪስተጓጎል ድረስ ሕገ መንግሥት የሚያረቅ ኮሚሽን ደግሞ ግንቦት ወር 1997 ዓ.ም በኤርትራ ምክር ቤት ጸድቋል። በ1996 ደግሞ የፕሬስ ሕግ ረቂቅ ተዘጋጅቶ የግል ጋዜጦች ተበራክተው ነበር። "ሁሉም ኤርትራዊ በአገራዊ ጉዳዮች መሳተፍ አለበት" ሲሉ የነበሩት ፕሬዝደንት ኢሳይያስ ከነጻነት በኋላ በአገራዊ ጉዳዮች ለመሳተፍ ጥያቄ የሚያቀርቡ የተሓኤ አባላት "ከአሁን በኋላ የፖለቲካ ዥዋዥዌ አይፈቀድም" በማለት በግል እንጂ በፓርቲ ደረጃ መግባት እንደማይችሉ ከለከሉ። "የኢሳያስ ባህሪ በሚገባ የሚገነዘብ ሰው ሕብረ ብሔራዊ ሥርዓት የመገንባት ፍላጎት አካባቢው ላይ የነበሩ ሰዎች ፍላጎት እንጂ የእሱ አይመስለኝም" ይላሉ አቶ ኤልያስ። በርካታ የምክር ቤትና የመንግሥት አባላት በወጉ ማስቀረት ይቻል የነበረውን የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ግጭት መገምገም አለበት በማለት ከፕሬዝደንት ኢሳይያስ ጋር ከፍተኛ አለመግባባት ፈጥረው እንደነበረ ይታወሳል። በወቅቱ በርካታ ዝግ ስብሰባዎች ሲካሄዱ ቆይተው በታኅሣሥ 2001 አገራዊ ምርጫ እንዲካሄድ በመወሰን የምርጫ ሕግና የፖለቲካ ድርጅቶች የሚመለከት ሕግ የሚያረቁ ሁለት ቡድኖች ተመረጡ። ሆኖም በወቅቱ የተዘጋጀው ሃሳብ ወደ ሕዝብ ቀርቦ ክርክር ሳይደረግበት በፕሬዝደንቱ ከተቋረጠ በኋላ ልዩነት በመበርታቱ በርካታ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ለእስር ተዳረጉ። ከዚያ በኋላ የምርጫ ጉዳይ እንደ ሃሳብም ሳይነሳ እስከ ዛሬ ድረስ ተራዝሞ ይገኛል። "እንደ እኔ አረዳድ" ይላሉ አቶ ኤልያስ፤ "በትጥቅ ትግል ወቅት ቫንጋርድ [የሁሉ የበላይ] ፓርቲ ሲመራ የነበረው ኢሳያስ ለማስመሰል ሕብረ ብሔራዊ ፓርቲ እንመሰርታለን ሲል ነበር። በ1994 የተሰጣት ተልዕኮ ጨርሳ ፈርሳለች ያለን ድብቅ ፓርቲ አሁንም በሚስጥር የምትሰራ ይመስለኛል። ቫንጋርድ ፓርቲ ደግሞ ስልጣን ከሌሎች ጋር መጋራት ስለማይፈቅድ በዚህ ምክንያት ምርጫ ሳይካሄድ ቆይቷል እላለሁ።" አቶ ዳዊት ፍስሃዬ ግን በ2001 በኤርትራ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት የመመስረት ሂደት የሚቃወም መፈንቅለ መንግሥት እንደተካሄደ ይናገራሉ። "ፕሬዝደንት ኢሳያስ ምክር ቤት አፍርሶ ሕገ መንግሥታዊ መንግሥት እንዲገነባ የሚጠይቁ የቅርብ ሰዎችን ያለ ክስና ፍርድ አስሮና አጥፍቶ ፖሊሳዊ መንግሥት የመሰረተበት ምክንያት ምርጫ እንዳይካሄድ ነው።" "ምርጫ ተጠያቂነት እንዲኖር የሚያስችል ሂደት በመሆኑ ህግ ጥሶ በኃይል ሕገ ወጥ ተግባር የፈጸመ ሰው ተጠያቂ እንዲሆን አይፈልግም" በማለት አቶ ኢሳያስ እስከ መጨረሻው ምርጫ እንደማይፈቅዱ ይገልጻሉ። ፕሬዝደንቱ ሃሳባቸው ለምን ቀየሩ? የትጥቅ ትግል በተካሄደበት ወቅት "የኤርትራ ነጻነት ዘግይቶ የመጣው ስለሆነ የአፍሪካ መሪዎች የፈጸሙት አይነት ስህተት አትደግምም" የሚል አመለካከት እንደነበረ የሚናገሩት አቶ መጎስ ብርሃነ "ሕዝባችን ግን በሁሉም አይነት ጥፋት ስንከሳቸው ከነበሩት የአፍሪካ መሪዎች በታች መሆናችንን ተገንዝቦ ነበር" ይላል። የኢትዮ ኤርትራ የድንበር ግጭት እስከተከሰተበት ወቅትም ሁኔታዎች ከዛሬ ነገ ይስተካከላሉ በሚል ተስፋ ሲያደርግ ቆይቷል። ይሁን እንጂ ሁሉም እንደታሰበው አልሆንም። በ1988 አቶ ኢሳያስን የትጥቅ ትግሉ ማዕከል በነበረው ሳህል ውስጥ ለአራት ሰዓታት እንዳነጋገሯቸው የሚያስታውሱት አቶ ኤልያስ "ቻይና ውስጥ ምንድን ነው የተማራችሁት? ብዬ ጠይቄዋለሁ" ይላሉ። "ብዙ ነገር እንደተማሩ ነገር ግን ቻይናውያን የማኦን አምልኮተ ሰብ [ፐርሰናል ካልት] መታገል እንደነበረባቸው ነገረኝ። ይሁን እንጂ ራሱ ሰብአዊ አምልኮ ፈጥሮ አገርን በአምባገነንነት ይዞ ይገኛል" ሲሉ ይኮንናሉ። ፕሬዝደንት ኢሳይያስ አንድ በአሜሪካ የሚታተም ጋዜጣ "ስልጣንህ የመተው እቅድ አለህ ወይስ አፍሪካ አገራት መሪዎች እስክትሞት ትቆያለህ?" ብሎ ላቀረበላቸው ጥያቄ "እኔ የኤርትራ ሕዝብ ሲጠይቀኝ ሳልዘገይ ስልጣኔን ለመተው ዝግጁ ነኝ። ምርጫው ሙሉ በሙሉ የሕዝብ ነው" ማለታቸውን ዘግቦ ነበር። በተጨማሪም ፕሬዝደንት ኢሳይያስ 17ኛው የነጻነት በዓል በሚከበርበት ወቅት ከአልጀዚራ ጋር በነበራቸው ቆይታ በኤርትራ መቼ ምርጫ ይካሄዳል የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር። እርሳቸውም "አሜሪካ የምታካሂደው ምርጫ የሚመጣው ውጤትና እውነተኛ ምርጫ እስክናይ ለ30 ወይ ለ40 ዓመታት እንጠብቃለን . . ." ማለታቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት በምርጫ ላይ ያላቸው አመለካከት ማሳያ ነው። በተጨማሪም ፕሬዝደንት ኢሳያስ በ23ኛው የነጻነት በዓል ላይ ". . . ለሁኔታዎች የሚስማማ አዲስ ሕገ መንግሥት ማርቀቅ እንጀምራለን" በሚል ተናግረው ነበር። ይሁን እንጂ ይህ በኤርትራ ምርጫ የሚባል እንደማይታሰብ ማረጋገጫ ነው የሚሉት አቶ ኤልያስ፤ "አቶ ኢሳያስ ስልጣን ላይ እያለ ምርጫ የማይ አይመስለኝም" ይላሉ። ለሁለት አስርት ዓመታት ተፋጠው የነበሩት ኤርትራና ኢትዮጵያ ጉዟቸው ምን ይመስላል?
news-56249153
https://www.bbc.com/amharic/news-56249153
ትግራይ- የአክሱም 'ቄስ' የተባለው ግለሰብና የፈጠረው ውዝግብ
ባለፈው ሳምንት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባካሄደው ምርመራ በትግራይ ክልል የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ የኤርትራና ወታደሮች በአክሱም ከተማ ሰላማዊ ሰዎችን መግደላቸውን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎችን ይፋ ካደረገ በኋላ፣ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ነዋሪነቱን በአሜሪካ ያደረገ ግለሰብ "በሀሰት ራሱን የአክሱም ጽዮን ማርያም ካህን ነኝ" በማለት ስለ ክስተቱ መረጃ ሰጥቷል ሲሉ ተደምጠዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥትም የአምነስቲን የምርመራ ሪፖርት ተከትሎ ባወጣው መግለጫ ላይ "እንደ መረጃ ምንጭ ሆኖ የተጠቀሰው [በአምንስቲ ሪፖርት ላይ] አንድ ግለሰብ እንደሚለው የአክሱም ቄስ ሳይሆን ቦስተን የሚኖር ግለሰብ ሆኖ ተገኝቷል" ብሏል። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትም በዚያው ዕለት ቄሱን " አታላዩ" ሲል ዘግቧል። ይኸው የመገናኛ ብዙኀን መቀመጫቸውን ኒውዮርክ ያደረጉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አባ ጴጥሮስ የተባሉ ካህንን ጠቅሶ፣ በቪዲዮው ላይ የሚታየው ግለሰብ የቤተክርስትያኒቱ ተከታይ አለመሆኑን ዘግቧል። ይህ ዘገባ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር በሆኑት ፍፁም አረጋ ይፋዊ የትዊተር ሰሌዳ ላይ ተጋርቷል። አምነስቲ ኢንተርናሽናልም በበኩሉ ለቢቢሲ የዚህ ግለሰብ ቪዲዮ ላይ ምንም ዓይነት ተሳትፎ እንደሌለው አረጋግጧል። ታዲያ በትክክል የሆነው ምንድን ነው? ራሱን ቄስ ነኝ በማለት በሀሰት ያቀረበስ አለ? አክሱም ላይ የተሰራው ዘጋቢ ፊልም የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የአምነስቲ ሪፖርት በወጣበት አርብ ዕለት በዩቲዩብ ላይ ከተለቀቀው ዘጋቢ ፊልሙ ላይ የተወሰዱ ቅንጭብጭብ ቪዲዮዎችን ሲያጋሩ ነበር። የተወሰኑት ቪዲዮዎች ነዋሪነቱ አሜሪካ ቦስተን የሆነውን የሚካዔል በርሄን ምስል በመጨመር "በሀሰት ቄስ' ስለማለቱ ጽሁፍ ጨምረው አጋርተውታል። ይህንን ቪዲዮ ያዘጋጁት ሰዎች ግለሰቡ በአክሱም የደረሰውን ተጎጅ ታሪክ በድምፅ የተረከው ነው ሲሉ ይገልጻሉ። አክለውም ግለሰቡ "የተጎጂዎች ድምጽ" እንዲሆን መፈለጋቸውንና፣ ይህንንም በግልጽ ማስቀመጣቸውን ይናገራሉ። ሳይቆራረጥ በዩቲዮብ ላይ የተለቀቀው ቪዲዮ በመግቢያው ላይ "የተጎጂዎቹ ታሪክ በሌሎች ግለሰቦች ተተውኗል" (re-enactment) የሚል መግለጫ ተካትቶበታል። ይህም ማለት በቪዲዮው ላይ የሚታየው ምስል እና የሚሰማው ድምጽ በትክክል የተጎጂዎቹ አይደለም ማለት ነው። ይህንን ዘጋቢ ፊልም የሚያስተዋውቀው አንድ ፖስተር ላይም ይኸው ማሳሰቢያ በግልጽ ሰፍሮበት ይታያል። ይኹን እንጂ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከሁለት ቀናት በፊት ዘጋቢ ፊልሙን ለማስተዋወቅ የተሰራጨው አጭር ቪዲዮ ላይ ግን ይህ ማሳሰቢያ አልተካተተበትም። የተወሰኑ ምስሎች ከታዩ በኋላ በቀጥታ ወደዚህ የአንድ ካህንን ታሪክ ወደ ተወነው ግለሰብ ያልፋል። "ቄስ ወልደማርያም እባላለሁ፤ በሕዳር ወር በአክሱም ጽዮን ማርያም ፀሎት ላይ ነበርን " ሲል ይታያል ግለሰቡ። " ልናስቆማቸው ግን አልቻልንም፤ ሁላችንም ላይ መተኮስ ጀመሩ" ይላል ሌላ ስፍራ ደግሞ። ከዚህ ቪዲዮ ጀርባ ያለው ማን ነው? ቪዲዮው በዩቲዩብ ላይ የተለቀቀው በትግራይ ሚዲያ ሀውስ አማኻኝነት ነው። ትግራይ ሚዲያ ሀውስ በትግራይ ጉዳይ ላይ አተኩሮ የሚሰራ የኦንላየን ሚዲያ ሲሆን፣ ራሱን ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት በማለት ይገልጻል። ይህ ቪዲዮ ግን ፕሮዲውስ የተደረገው በ መርሃዊ ዌልስ ቦግ እና ስታንድ ዊዝ ትግራይ የተሰኘው ቡድን መስራች በሆኑት ሉዋም ግደይ እና ራህዋ ግደይ ጋር በጥምረት ነው። በዚህ ቪዲዮ ላይ መርሃዊ እና ልዋም ዳይሬክተሮች መሆናቸውም ተጠቅሷል። በዘጋቢ ፊልሙ ላይ እንደ ቄስ በመሆን የተወነው እና በማህበራዊ መገናኛ ብዙኀን መነጋገሪያ የሆነው ሚካኤል በርሄም በዘጋቢ ፊልሙ ላይ የተሳተፉ ሰዎች ስም ዝርዝር ውስጥ ታከትቶ ይታያል። መርሃዊ በኦንላየን ላይ በስፋት የሚንቀሳቀስ ግለሰብ ነው። ከተለያዩ እንግዶች ጋር በመሆንም በየሳምንቱ በቀጥታ በትግራይ ስላለው ግጭት ይወያያል። በታህሳስ ወርም በርሄ ቋሚ እንግዳ በመሆንም ይቀርብ ነበር። መርሃዊ በፌስ ቡክ ገፁ ላይ ዘጋቢ ፊልሙ የተዘጋጀው ቦስተን በሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች መሆኑን ጽፏል። ራሱንም ሲገልጽ የማህበረሰብ አደራጅ (community organizer)ብሎ ነው። " ይህንን ነገር ግልጽ ማድረግ ያስፈልጋል፤ ሚካዔል በርሄ ቄስ አይደለም፤ እንደ ቄስ በመሆን የተወነ ነው" ሲል ስለ ሁኔታው ለቢቢሲ አብራርቷል። "ሆሊውድ እንዲህ ዓይነት ነገሮችን ሁሌ ይሰራል። ሆሊውድ ስለ ኢየሱስ ክርስተስ ቪዲዮዎችን በመስራት መጠመዱን አታውቁምን? ኢየሱስ ክርስቶስን በመሆን ይተውናሉ ነገር ግን አይደሉም፣ ትወና ነው።" ልዋም እንዳለችው ይህንን ቪዲዮ ያዘጋጁት ታሪካቸውን ለመናገር መንገድ ለሌላቸው ተጎጂዎች ድምጽ ለመሆን በማሰብ ነው። ቢሆንም ግን በመንግሥት እና በተቺዎች ግብረ መልስ መገረሟን አልሸሸገችም። ከመንግሥት ወገን ይህንን አስተያየት የሚሰጡ ወገኖች የተመለከቱት ዘጋቢ ፊልሙን ለማስተዋወቅ የተሰራውን አጭር ቪዲዮ ብቻ እንደሚሆን እንደምታምን አክላ ገልጻለች። በተጨማሪም "ማስታወቂያውን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስናጋራ አርብ ለእይታ እንደሚበቃ ገልፀን ነበር፣ ስለዚህ በርካታ ሰዎች፣ የሚጠሉንን ሰዎች ጨምሮ፣ ምናልባት ሙሉ ቪዲዮው ያ ብቻ መስሏቸው ሊሆን ይችላል" ብላለች። " የማይክን (ሚካኤል በርሄን) ስክሪንሾት በማምጣት ልክ ቦስተን እንደሚኖር ፣ ቄስ አለመሆኑን እንደደረሱበት አስመስለው አቀረቡ። በጣም አስቂኝ አስተያየቶች አሉ ልክ በጥይት ተመትቶ በሕይወት እንደተረፈ እና እንደሚናገር ያለ።" ራህዋ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከተጠቃሚዎች፣ እነርሱን በማካተት በርካታ አስተያየቶች እንደደረሳቸው ትገልፃለች። "ካነበብኳቸውና ካሳቁኝ መካከል ቄሱ ቆዳውን ለመንከባከብ የሚቀባው ምን እንደሆነ ትነግሩናላችሁ፤ የሚለው ነው ይህ በጣም ነው ያሳቀኝ" ትላለች። ከአምንስቲኢንተርናሽናል ጋር ግንኙነት ነበረው? መርሃዊ የእነርሱ ዘጋቢ ፊልም የአምንስቲ ሪፖርት ከወጣበት ቀን ጋር መገጣጠሙ "ያጋጣሚ ጉዳይ ነው" ይላል። " ወቅቱ በመግጠሙ ሰምሯል። ስለአክሱም ጭፍጨፋ ሪፖርት እንደሚወጣ አናውቅም ነበር ፤ እና ቪዲዮውን ለቅቀን ግንዛቤ እንፍጠር የሚለው ሃሳብ ብቻ ነው የነበረን" ሲል አክሏል። የአምነስቲ ቃል አቀባይ ለቢቢሲ ከዘጋቢ ፊልሙ ጋር ምንም የሚያገናኛቸው ነገር አለመኖሩን አረጋግጠዋል። ኮኖር ፎርቹን ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ "አምንስቲ ኢንተርናሽናል እንደ ቄስ በመሆን ከተወነው ግለሰብ ጋር ወይንም ደግሞ ቪዲዮውን ከሰሩት ግለሰቦች ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለውም። በምንም ዓይነት ቪዲዮውን የተጠቀምንበት ወይንም ያጣቀስንበትም አጋጣሚ የለም" ሲሉ መልስ ሰጥተዋል። "የማህበራዊ ሚዲያ ሴራ ተንታኞች ከእኛ ጋር አገናኝተው እስኪናገሩ ድረስ እና በሚገርም ሁኔታ የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴርም ያንኑ ተቀብሎ እስኪያስተጋባ ድረስ ስለመኖሩም ምንም የምናውቀው ነገር አልነበረም" ራህዋ ግደይ እነርሱ በዘጋቢ ፊልሞቻቸው ውስጥ ታሪካቸውን የተጠቀሙት ሰዎች ለአምንስቲም ምስክርነታቸውን ሰጥተው ሊሆን እንደሚችል ታምናለች። ነገር ግን ይህ በስራቸው ውስጥ ጥልቅ ጥናት ማካሄዳቸውን እንደሚያሳይ ገልጻለች። "በእኛ ቪዲዮ ውስጥ ካለ ባለታሪክ ጋር ተመሳሳይ ታሪክ ያለው አይቻለሁ፤ ያ ማለት እኛ ጥናታችንን አካሂደናል። ቀድመን ነበር እንዲሁም በትግራይ ውስጥ ምን እየተካሄደ እንዳለ እያንዳንዱን ነገር እየተከታተልን ነው" ስትል ታክላለች። " አሜሪካ ስለምንኖር ምስክር መሆን አንችልም ነገር ግን ጥናት እንሰራለን፤ በስፍራው ካለ ሕዝባችን ጋር እጅና ጓንት ሆነን እንሰራለን" ትላለች ልዋም ግደይ የእነርሱን ቪዲዮ ላይ ዘመቻ የተከፈተበት ምክንያት ትኩረትን ለማስቀየር እንደሆነ እንደምታምን ገልጻ ነገር ግን የበለጠ ግፊት ሰጥቶናል ብላለች። "አሁን ወደፊት መገስገስ መቀጠል አለብን" ስትልም ሃሳቧን ትቋጫለች።
news-51602765
https://www.bbc.com/amharic/news-51602765
ኮሮናቫይረስ፡ ጣልያን ቫይረሱ የተገኘባቸው አካባቢዎች ዘጋች
ጣልያን ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ 'እጅግ ጥንቃቄ የተሞላበት' የተባለው እርምጃ መውሰድ መጀመሯ ተዘግቧል። በአውሮፓ ትልቁ በተባለው ወረርሽኝ ስጋት የገባት ጣልያን ኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው አካባቢዎችን ሙሉ በሙሉ መዝጋት ጀምራለች።
ጠቅላይ ሚኒስትር ጉሴፔ ኮንቴ ድንገተኛ ጊዜ እቅዳቸውን ቅዳሜ ዕለት ይፋ ባደረጉበት ወቅት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 79 ከፍ ብሎ ነበር ተብሏል። ጣልያን ይህንን ውሳኔ ለማስተላለፍ የተገደደችው ሁለት ዜጎቿ በቫይረሱ ተይዘው ሕይወታቸው ካለፈ በኋላ ነው። • በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በአንድ ቀን ውስጥ በእጥፍ ጨመረ • የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝና የአየር መንገዶች የገቢ ማሽቆለቆል ስጋት • በሽታውን ለመደበቅ ባለስልጣናት ዶክተሮችን ያስፈራሩ ነበር ከአስር በላይ የሚሆኑ በሰሜናዊ ሎምባርዲ እና ቬኔቶ ግዛቶች የሚገኙ ከተሞች በፍጥነት እንዲዘጉና ሰዎች በቀላሉ መውጣትና መግባት እንዲቆምም ተደርጓል። በሁለቱ ሰሜናዊ ግዛቶች የሚገኙ እስከ 50 ሺ ሚደርሱ ዜጎች ከማንኛውም አይነት እንቅስቃሴ እንዲቆጠቡና ከቤታቸው እንዳይወጡ ተጠይቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳስታወቁት የተለየ ፈቃድ ካላቸው ሰዎች ውጪ ከከተሞቹ መውጣትም ሆነ መግባት የከተለከለ ነው። በከተሞቹ የሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶችና የስፖርት ማዘውተሪያዎችም እንዲቋረጡ የተወሰነ ሲሆን ዛሬ ሊደረጉ የነበሩ የጣልያን ሴሪ አ ጨዋታዎችም በዚሁ ምክንያት እንደማይካሄዱ ታውቋል። ፖሊስ አስፈላጊ ከሆነ ደግሞ መከላከያ ኃይሉ የወጡትን ደንቦች የማስከበር ግዴታ አለባቸውም ተብሏል።
news-44876188
https://www.bbc.com/amharic/news-44876188
ቻይና በግዙፎቹ ማሽኖቿ ዓለምን እንድታገናኝ እያደረጉ ነው
ቻይና በታሪክ ግዙፍ የሆነው የመሠረተ ልማት ሥራ ላይ ከመሰማራት ባለፈ ባቡሮች የሚገነቡበትን መንገድም እየለወጠች ነው። በፍጥነት እያደገ የሚገኘውን ኢኮኖሚዋን ለማሳለጥ ቻይና በየብስ እና ባህር ከአፍሪካ እና አውሮፓ ጋር ለማገናኘት ተስፈኛ ዕቅድ ይዛለች።
እአአ 2013 የተጀመረው የፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ተስፈኛ ዕቅድ የዓለማችንን አንድ ሶስተኛ የሚሆኑ ሰባ አገራትን በየብስ በባህር ማገናኘትን ያለመ ነው። • ሁሉንም በደህንነት ካሜራ የምትመለከተው ቻይና • የቻይና የዕርዳታ ሚስጢር ሲገለጥ ከባንኮች፣ ከተሳታፊ አገራትና ከቻይና መንግሥት በሚሰበሰበው በትሪሊዮን ዶላሮች በሚገመት ወጪ የሚከናወነው ግንባታ ዘመን ተሻጋሪ ኢንቨስትመንት እንደሆነ እየተወራለት ነው። ይህ ዕቅድ የማይሳካ ቢመስልም የዚህ የግዙፍ ማሽኖች ግንባታ መዋዕለ ንዋዩ ፍሰት በቻይናና እና በሌሎችም አካባቢዎች እየታየ ነው። የድልድይ ግንባታ በስምጥ ሸለቆዎችና ጠመዝማዛ ቦታዎች ላይ እንዴት ፈጣን የባቡር መስመር ዝርጋታ ሊካሄድ ይችላል? ድልድይን ከድልድይ የሚያገናኘው ኤስ ኤል900/32 ማሽን ግዙፉ ብረት ገጣጣሚ። ኤስ ኤል ጄ ሁሉንም በአንድ ያጠቃለለ ማሽን ሲሆን አንድን ማዕዘን ከሌላኛው ማዕዘን ጋር የሚያያይዙ የድልድይ ክፍሎችን መሸከም፣ ማንሳትና ማስቀመጥ የሚችል ነው። SLJ900"፡ ''ብረት ገጣጣሚው'' ክብደት: 580 ቶን ርዝመት: 92 ሜትር ቁመት: 9 ሜትር ጭነት ሳይዝ የሚኖረው ፍጥነት: 8ኪ.ሜ/በሰዓት ጭኖ የሚኖረው ፍጥነት: 5ኪ.ሜ/በሰዓት 92 ሜትር የሚረዝመው እና 64 ጎማዎች ያሉት ማሽን አንዱን የድልድይ ክፍል ካስቀመጠ በኋላ፤ የሌላ ድልድይ ክፍል ለመውሰድ ይመለሳል። በዚህም ቀደም ሲል ያስቀመጠው ድልድይ ክፍል ላይ ይሄዳል። • የቻይናውያንን ኑሮ ለማወቅ አምስት ነጥቦች ማሽኑ ወደ ጎንም የመሄድ ብቃት ያለው ነው። ሙሉ ጭነት ተሸክሞም በሰዓት 5 ኪሎ ሜትር መጓዝ ይችላል። ይህም ሙሉ ሂደቱ ብዙ እቃ ማንሻ ክሬኖችን በመጠቀም ከመሬት ይሰራበት ከነበረው ባህላዊው አሠራር የፈጠነ ያደርገዋል። 580 ቶን ጭኖ ቀደም ሲል ባስቀመጠው ድልድይ ክፍል ላይ አለፈ ማለት ደግሞ ድልድዩ ከመደበኛው ባቡር መስመር የመሸከም ብቃት በላይ መሆኑን ያሳያል። ይህ ማሽን ከወዲሁ ብዛት ያላቸው ፈጣን የባቡር መስመር ዝርጋታዎች ላይ ጥቅም ላይ ውሏል። ከእነዚህ ውስጥ በ2020 ቻይና 30 ሺህ ኪሎ ሜትር የፈጣን ባቡር ባለቤት ለመሆን ያላእ ዕቅድ አካል የሆነው የቻይና ማዕከላዊ ሞንጎሊያ ባቡር መስመር አንዱ ነው። የዋሻዎች ቁፋሮ ከሆንግ ኮንግ ብዙም በማይርቀውና በስተደቡብ በሚገኘው ሱአይ ሃይዌይ በሚሰኘው የሻንቱ ፕሮጀክት በአንዴ ስድስት መኪና የሚያስተናግድ 5 ኪሎ ሜትር የዋሻ መንገድ ለመገንባት ተስፈኛ ዕቅድ ተቀምጧል። መንገዱ የመሬት መንቀጥቀጥ በሚያጠቃው አካባቢ የሚሠራ ነው። ዋሻው በ2019 ሲከፈት ሻንቱን ከወደብ ጋር በማገናኘት የትራንስፖርት ዘርፉን ያዘምነዋል ሲሉ ባለስልጣናት ያምናሉ። መንገዱ ቁልፍ ከሆኑ 15 የወደብ መስመሮች መካከል አንዱ ነው። አንድ የጀርመን አምራች የሰራው ዋሻ ቦርቧሪ ማሽን በዘርፉ ፈር ቀዳጅ ከሆኑት መካከል ይመራ ነበር። ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የቻይና ኩባንያዎች ክፍያ እየፈጸሙ ስመጥር ሆኑ ድርጅቶች የዋሻ ቦርቧሪ ቴክኖሎጂውን ለመጠቀም የሚያስችል ፈቃድ እያደረጉ ነው። በውጤቱም 15.3 ሜትር ስፋት ያለው ዋሻ ቦርቧሪ ማሽን በቻይና ሬይልዌይ ኢንጂነሪንግ ኢኪውፕመንት ግሩፕ ካምፓኒ ከተባባሪ የጀርመን መሃንዲሶች ጋር ስራ መጀመራቸውን በ2017 ይፋ አድርገዋል። 15.3 ሜትር ቲቢኤም ስለሪ የቻይና የባቡር መንገድ ምህንድስና አቅራቢዎች ኩባንያ የክበቡ አጋማሽ: 15.3 ሜትር ርዝመት: 100 ሜትር ክብደት: 4,000 ቶን የሱዓኢ የዋሻ ውስጥ መተላለፊያ ሲጠናቀቅ የሚኖረው ርዝመት፡ 5 ኪ.ሜ እንደጀርመን አጋሮቻቸው ማሽኖቹ ከፊት ለፊት የሚሽከረከሩ ጠፍጣፋ መቁረጫ ያላቸው ሲሆን ይህም መሬትን ሆነ አለቶችን ለመሰርሰር የሚያስችል ነው። 4 ሺህ ቶን ሚመዝን ሲሆን መቶ ሜትር ድረስ ማሽኖችን ማስከተል ይችላል። ይህ ደግሞ መሣሪያው እቦረቦረ በሚሄድበት ወቅት የዋሻውን ግድግዳ እግር በእግር እተከተሉ ለመስራት የሚያስችላቸው ነው። ከመቦርቦሪያው ማሽን የሚወጣ አፈርና ስብርባሪዎች ተሰብስበው ዝቃጩ በቱቦ አማካኝነት ይወገዳል። ማቀላቀያው ፍርስራሹን ከሸክላ ጋር በማዋሃድ ዝቃጩ እንዲፈጠር ያደርጋል። ሰፊው መቦርቦሪያ ማሽን አይደለም። በዚህ ዘርፍ ቀዳሚ ሸላሚው ቤርታ ነው። ቤርታ 17.4 ሜትር ስፋት ያለው ማሽን ለሲያትሉ አላስካን ዌይ ገንብቷል። ሆኖም 15.3 ሜትር መሠራቱ በራሱ ቻይና በዋሻ ግንብታ ውሰጥ ቁልፍ ሚና ለመጫወት ስለማቀዷ ማሳያ ነው። የሃዲድ ዝርጋታ የቤልት እና ሮድ ኢኒሽዬቲቭን መሠረት በመላው ቻይና የተጣለ ሲሆን በቻይና ድጋፍ የሚሰሠሩ ፕሮጀክቶች በሺህ ኪሎሜትሮች ርቀት ላይ ተግባራዊ መደረግ ጀምረዋል። የኬንያው የሞምባሳ-ናይሮቢ የባቡር መስመር ግንቦት 2017 ሲጠናቀቅ ዓለም አቀፍ ትኩረትን የሳበው መጠናቀቅ ከነበረበት በ18 ወራት ቀደም ብሎ ሥራ በመጀመሩ አይደለም። 480 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው ባቡር መስመር ሃገሪቱ ነጻነቷን ካገኘች በኋላ መጀመሪያዋ ነው። 90 በመቶ ሚሆነው የግንባታው ገንዘብ ከቻይናው ኤግዚም ባንክ የተገኘው ነው። መስመሩ ከቻይና ውጭ በሀገሪቱ የግንባታ መስፈርት እና በሃገሪቱ ማሽኖች የተሰራ የመጀመሪያው የባቡር መስመር ነው። መስመሩ እንዴት 700 ሜትር በቀን በሚፈጥን ጊዜ እንደተሰራ ለማወቅ ሃዲዱን የሚዘረጋውን ማሽን መመልከት አስፈላጊ ነው። ሃዲድ የሚደረድር ማሽን የቻይና የመንገድ እና ድልድይ ኮርፖሬሽን በቀን ሊዘረጋ የሚችለው ርቀት: 700 ሜትር ስህተት ሊኖር የሚችለው: 2 ሴ.ሜትር የአንዱ ማሽን ክፍል ክብደት: 15 ቶን የአንዱ ማሽን ክፍል ርዝመት: 25 ሜትር ሃዲድ የሚዘረጋው ማሽን የተመረተ የባቡር ሃዲድ ያስቀምጥና ባስቀመጠው ሃዲድ ላይ በመጓዝ አዲስ የባቡር ሃዲድ ያስቀምጣል። ይህ ከተከናወነ በኋላ አጭር ሆነው የተገጣጠሙት የባቡር ሃዲዶች በረዣዥሙ እንዲያያዙ በማድረግ የባቡሩ ጉዞ የተቃና እንዲሆን ያደርጉታል። እያንዳንዱን የባቡር ሃዲድ ክፍል ለመግጠም አራት ደቂቃ ብቻ በቂ ነው። ይህ አዲስ ሃሳብ ሳይሆን ለአስር ዓመታት በብዙ ሃገራት ተግባራዊ ሲደረግ የቆየ ነው። ሆኖም ቻይና በፍጥነት መሥራቱን ቻለችበት። ለዚህ ደግሞ የረዳት በፍጥነትና በርካሽ ዋጋ ማሽኖችን ከመስራት ባለፈ ከፍተኛ ክብደት ያለው የባቡር ሃዲድ ክፍል እንዲሸከሙ በማድረግ ነው። ማሽኖቹ እጅግ ዘመናዊ ቢሆኑም አሁንም ቢሆን ከፍተኛ ሰው ጉልብት የሚጠይቁ ናቸው። የአካባቢው ሠራተኞች በቻይና መሃንዲሶች በመታገዝ በባቡር መስመሩ አካባቢ ባሉት ጊዜያዊ ፋብሪካዎች ውስጥ የባቡር ሃዲዱን የተወሰነ ከፍል ይሠራሉ። ከዚህ በተጨማሪ የባቡር ሃዲዱ ክፍሎች በትክክለኛው መጠን መሠራታቸውን ይቆጣጠራሉ። ስህተት ሊፈጠር የሚችለው 2 ሴንቲ ሜትር ላይ ብቻ ነው። በደህንነታቸው ዙሪያ ስጋቶች አሉ። "በሥራ ቦታ ሚከሰቱ አደጋዎች የሚኖሩ ናቸው" ሲሉ በሞምባሳ-ናይሮቢ የባቡር መስመር ላይ የሚሠሩ አንድ ቻይናዊ ከፍተኛ መሃንዲስ ባለፈው ዓመት ለዢኑዋ አስታውቀዋል። "በሚከሰቱበት ወቅት ከፍተኛ ከመሆናቸውም በላይ አንዳንዴ እስከ ሞት የሚያደርሱ ናቸው።" ሆኖም እስካሁን ባለው ሁኔታ የቻይና ባቡር መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክቶች በአፍሪካ ሃገራት ያላቸው ተቀባይነት ከፍተኛ ነው። የናይሮቢ-ሞምባሳ ባቡር መስመር በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ጊዜ የተሰራውንና 10 ሰዓት የሚፈጀውን የመኪና መንገድ ጉዞ ወደ 4 ሰዓታት የቀነሰ ነው። እስከ የካቲት ድረስ ብቻ 870 ሺህ መንገደኞች ባቡሩን ተጠቅመዋል። ምስጋና ለኤግዚም ባንክ 1.5 ቢሊዮን ዶላር ብድር ይግባውና መስመሩን በምዕራብ የሃገሪቱ ክፍል የምትገኘው ኪሱሙ ድረስ ለማድረስ ስራዎች ከወዲሁ ተጀምረዋል። ይህም ዩጋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኢትዮጵያን የሚያገኛኝ ነው። እነዚህ ትልልቅ ማሽኖች እውን ያደረጉትን የግንባታ ፍጥነት ከግምት በማስገባት ሁሉም ነገር በእቅዱ መሠረት ከተሠራ ኬንያ በቻይና ድጋፍ የተሰራው የምስራቅ አፍሪካ የባቡር መሥመር ማዕከል ለመሆን ረዥም ጊዜ አይፈጅባትም።
news-50499120
https://www.bbc.com/amharic/news-50499120
ጉግል የፖለቲካ ማስታወቂያዎች ላይ እገዳ ሊጥል ነው
ጉግል በመላ ዓለም የፖለቲካ ማስታወቂያዎችን ሊያግድ እንደሆነ አስታወቀ።
ይህ እገዳ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ዩቲውብና ጉግል ሰርችን መራጭ ለማግኘት መጠቀም እንዳይቻል ያደርጋል ተብሏል። ቢሆንም ግን አሁንም የምርጫ ቅስቀሳ እንቅስቃሴዎች ጉግልን ተጠቅመው የመራጭ እድሜ፣ፆታና አድራሻን ለማወቅ ይችላሉ። ጉግል በመላ ዓለም ሊተገብረው ያቀደው ይህ እገዳ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ እንግሊዝ ውስጥ ይጀመራል ተብሏል። የፖለቲካ ማስታወቂያዎችን ማገድ ብቻም ሳይሆን አሳሳች መረጃ በሚይዙ ሌሎች ማስታወቂያዎች ላይም እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል ጉግል። ይህ እርምጃ ጉግልን ቀደም ሲል የፖለቲካ እጩዎች ወይም የምርጫ ቅስቀሳ ማስታወቂያዎች መረጃን እንደማያጣራ ካስታወቀው ፌስቡክ ጋር ግጭት ውስጥ ሊከትታቸው ይችላል ተብሎም ተሰግቷል። የጉግል ዘርፍ ማናገጀር የሆኑት ስኮት ስፔንሰር ሰፊ የፖለቲካ ውይይት የዴሞክራሲ ወሳኝ ክፍል ስለሆነ ማንም እንደፈለገ የፖለቲካ ሃሳቦችን፣ ተቃራኒ ሃሳቦችን ሊያደላድል፤ እንዲሁም ሊመራና ሊቆጣጠር አይገባም ብለዋል። "በቀጣይ እርምጃቸው የምንወስድባቸው የፖለቲካ ማስታወቂያዎች ምንም እንኳ ውስን ቢሆኑም እንቀጥልበታለን"ብለዋል • ስለጉግል የማያውቋቸው 10 እውነታዎች • «ፌስቡክና ትዊተር ብትጠነቀቁ ይሻላል» ትራምፕ • ሁዋዌ አንድሮይድን እንዳይጠቀም ገደብ ተጣለበት
news-54526622
https://www.bbc.com/amharic/news-54526622
የኢትዮ-ኤርትራ ስምምነትና የፕሬዝደንት ኢሳያስ ጉዞዎች
የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን መምጣትን ተከትሎ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ለሁለት አስርት ዓመታት ሰላምም ሆነ ጦርነተ የሌለበት ሁኔታ ተቀይሮ በአገራቱ መካከል ሰላም ሰፍኗል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ፣ ፕሬዝዳንት ፋርማጆና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ የሁለቱ አገራት መሪዎች ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ከአንዳቸው ወደ ሌላኛው አገር ለሥራ ጉብኝት ተደጋጋሚ ጉዞ አድርገዋል። የሦስት ቀናት የሥራ ጉብኝታቸውን ዛሬ ያተናቀቅቃሉ ተብሎ የሚጠበቀው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሁለቱ አገራት መካከል የሰላም ስምምነት ከተደረሰ በኋላ ቢያንስ ለስድስት ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ አምርተዋል። በእነዚህ ጉብኝቶች በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩሩ በደፈናው ከመጥቀስ በዘለለ የተደረጉ ውይይቶች የተደረጉ ቢሆንም አስካሁን በይፋ በዝርዝር የተነገረ ጉዳይ የለም። ለመሆኑ ፕሬዝደንት ኢሳያስ ወደ ኢትዮጵያ መቼ መጡ? ቅዳሜ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም [14/7/2018] ፕሬዝደንት ኢሳያስ ከሃያ ዓመታት በላይ ከሚሆን ጊዜ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም ነበር። ፕሬዝደንት ኢሳያስ ወደ ኢትዮጵያ ከምምጣታቸው በፊት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕምድ የሁለቱ አገራትን የሰላም ሂደት ለማስጀመር ሐምሌ 1 ቀን 2010 ላይ ወደ አሥመራ ማቅናታቸው ይታወሳል። ፕሬዝደንት ኢሳያስ ከ20 ዓመታት በኋላ በኢትዮጵያ ጉብኘት ለማድረግ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ሲደርሱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ፕሬዝደንቱ በዚህ ጉብኝታቸው ነበር ለሃያ ዓመታት ተዘግቶ የነበረውን የኤርትራ ኤምባሲ የከፈቱት። ይህም በሁለቱ አገራት መካከል ተቋርጦ የነበረው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መታደሱን በይፋ ያመላከተ ነበር። ዓርብ ጥቅም 30/2011 ዓ.ም [9/11/2018] ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለጉብኝት በታሪካዊቷ በጎንደር ተገኙ። ፐሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆ የአማራ ክልልን ለመጎብኘት በጎንደር ተገኝተው ነበር። መሪዎቹን ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በጎንደር ተገኝተው አቀባብል አድርገውላቸዋል። መሪዎቹ በቆይታቸው ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን የጎንደር ቆይታቸውን አጠናቀው ወደ በባሕር ዳር ከተማም አቅንተውም ነበር። ማክሰኞ መስከረም 1/2011 [11/09/2018] በዘመን መለወጫ ዕለት ፕሬዝደንት ኢሳያስ እና ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በሁለቱ አገራት አዋሳኝ ድንበር ላይ ተገናኝተው ኤርትራንና ኢትዮጵያ ከሚያገናኙት ሁለቱን የደንበር በሮች ማለትም ደባይሲማ-ቡሬ እና ሰርሐ-ዛላምበሳን ከ20 ዓመታት በኋላ ከፈቱ። የድንበሮቹን መከፈት ተከትሎ 'የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ሕዝቦች ዝምድና ሰላማዊ መልክ ለማስያዝ ባደረጉት አስተዋጽኦ' በሚል የሳዑዲ አራቢያ መንግሥት "የንጉሥ አብደልአዚዝ ኒሻን" ሽልማትን ለሁለቱ መሪዎች አበረከተላቸው። እሁድ ሚያዚያ 25/ 2012 [3/05/2020] በዕለተ እሁድ ሚያዚያ 25/2012 ዓ.ም ፕሬዝደንት ኢሳያስ ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ተገኝተው ነበር። የውጭ ጉዳይ ሚንስትራቸውንና አማካሪያቸውን አስከትለው አዲስ አበባ የገቡት ፕሬዝደንቱ፤ የጉብኝታቸው ዓላማ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን እንዲሁም የበረሃ አንበጣን ለመዋጋት ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር መምከር አንዱ መሆኑ በወቅቱ ተገልጾ ነበር። የኤርትራው የማስታወቂያ ሚንስትር የማነ ገብረመስቀል፤ ሁለቱ መሪዎች የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን የሚያጠናክሩበት ሁኔታ ላይ ይወያያሉ ሲሉ በወቅቱ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረው ነበር። ሰኞ ጥቅምት 2/2013 [12/10/2020] ፕሬዝደንት ኢሳያስ ለሶስት ቀናት ጉብኝት ከትናንት በስቲያ ጅማ መግባታቸው ይታወሳል። ፕሬዝደንት ኢሳያስ በዚህ ጉብኝታቸው የታላቁ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ በደቡብ ክልል ውስጥ እተገነባ ያለ የኃይል ማመንጫን ጎብኝተዋል። በሁለቱ አገራት መካከል የሰላም ስምምት ከተደረሰ በኋላ ፕሬዝደንት ኢያሳያስ አፈወርቂ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በቀጠናው ወደሚገኙ የተለያዩ አገራትም በመጓዝ የሚያደርጉት የሥራ ጉብኝት ጨምሯል። ባለፉት ሁለት ዓመታት ፕሬዝደንት ኢያሳያስ ወደ ሶማሊያ፣ ኬንያ፣ ግብጽ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ተጉዘዋል። ፕሬዝደንት ኦሳያስና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የህዳሴ ግድብን ሲጎበኙ (ማክሰኞ) ኤርትራ እና ሶማሊያ ኤርትራ ነጻነቷን ከተጎናጸፈች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ፕሬዝደንት ኢሳያስ ታህሳስ 4/2011ዓ.ም ወደ ሶማሊያ ተጉዘው ነበር። በወቅቱ የሶማሊያ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ፕሬዝደንት ኢሳያስ እና ፕሬዝደንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፈርማጆ የሁለትዮሽ ስምምነት ይፈርማሉ ሲል የዘግቦ ነበር። ፕሬዝንት ኢሳያስ ሶማሊያን ሲጎበኙ ይህ የመጀመሪያቸው ነበር። ፕሬዝደንት ኢሳያስ ወደ ሞቃዲሹ ከማምራታቸው በፊት ከሶማሊያው አቻቸው ጋር በአሥመራ እና አዲስ አበባ ተገናኝተው ነበር። መስከረም 5/2011 ዓ.ም. የኢትዮጵያ፣ የሶማሊያ እና የኤርትራ መሪዎች በአሥመራ ከተማ የትብብር ስምምነት ፈርመው እንደነበረ እና የዚህን የትብብር ስምምነት አፈጻጸምን ለመገምገም መስከረም 29 እና 30 በአዲስ አበባ ተገናኝተው እንደነበረ የኤርትራ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል። ከዚህ በተጨማሪም ኤርትራ ሶማሊያን እና ራስ-ገዝ አስተዳደር የሆነችውን ሶማሊላንድን ለማሸማገል ፍላጎት እንዳላት በስፋት ሲዘገብ ቆይቷል። ለሶማሊላንድ የሚወግነው 'ጋሮዌኦላይን' የተባለው የድረ ገጽ ዜና ምንጭ ኤርትራ ሁለቱን አካላት ለማሸማገል ለመሪዎቹ ጥያቄ ስለማቅረቧ ዝርዝር ዘገባ አስነብቦ ነበር። ከኤርትራ በተጨማሪ አሜሪካ እንዲሁም የአውሮፓ ሕብረትን ጨምሮ ሌሎች የቀጠናው አገራት የሶማሊያን ፌደራል መንግሥትን እና ፑንትላንድን ለማሸማገል ፍላጎት ስለማሳያታቸው የሶማሊያን ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ጠቅሶ ጋርዌኦላይን ዘግቧል። መስከረም 24/2013 የሶማሊያው ፕሬዝደንት በአሥመራ ተገኝተው ነበር። የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስትር የማነ ገ/መስቀል ፕሬዝደንት ኢሳያስ እና ፕሬዝደንት ሞሐመድ ፈርማጆ ሰፊ ውይይት ማካሄዳቸውን ጠቁመው፤ በአሥመራ የተደረሰውን ስምምነትን አጠናክር ለማስፈጸም መስማማታቸውን በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። ኤርትራ እና ኬንያ ፕሬዝደንት ኢሳያስ ታህሳስ 2011 ዓ.ም ላይ የሱማሊያ ጉብኝታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ያቀኑት ወደ ኬንያ ነበር። ሁለቱ የምስሥቅ አፍሪካ አገራት ያላቸው ፖለቲካዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ትስስር እዚህ ግባ የሚባል አልበረም። ኬንያ በአሥመራ ኤምባሲ የላትም። ጉዳዮቿንም የምታስፈጽመው ካይሮ በሚገኝው ኤምባሲዋ በኩል ነው። እአአ 2011 ላይ የኬንያው የውጭ ሚንስቴር ኤርትራ በሱማሊያ ለሚንቀሳቀሰው አል-ሸባብ የትጥቅ ድጋፍ ታደርጋላች ብሎ መክሰሱን ሮይተርስ ዘግቦ ነበር። የአሁኑ ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያት አሥመራን በቅርቡ ከመጎብኘታቸው በፊት ኤርትራን የጎበኙት የመጨረሻው የኬንያ ፕሬዝደንት ዳንኤል አራፕ ሞይ ነበሩ። እአአ 1996 ላይ የወቅቱ ኬንያ ፕሬዝደንት በአሥመራ የነበራቸው ቆይታ ከሰዓታት የዘለለ አልነበረም። ፕሬዝደንት ኢሳያስ ወደ ኬንያ ያመሩት ከፕሬደዝንት ኡሁሩ ኬንያት በቀረበላቸው ግብዣ ነበር። በኬንያ ብሔራዊ ደኅንነት ዳይሬክተር ጀነራል የተመራ ልዑክ ወደ አሥመራ ባቀናበት ወቅት ነበር ከፕሬዝደንት ኡሁሩ የተላከውን ግብዣ ያቀረበው። ታህሳስ 6/2011 ዓ.ም ፕሬዝደንት ኢሳያስ ናይሮቢ የገቡት ለሁለት ቀናት ጉብኝት ነበር። ፕሬዝደንቱ በቆይታቸው ከኬንያው አቻቸው ፕሬዝደንት ኡሁሩ ጋር "በሁለቱ አገራት መካከል የንግድ ግንኙነትን ማጠንከር" የሚለው ትልቁ አንጀንዳ እንደነበረ የኤርትራ ቴሌቪዥን ዘግቦ ነበር። ሚያዚያ 25/2011 ዓ.ም ላይ ደግሞ ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ ወደ አሥመራ ተጉዘው ነበር። ከፕሬዝደንት ኡሁሩ በተጨማሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድም በአሥመራ ተገኝተው መሪዎቹ የሦስትዮሽ ምክክር አድርገዋል። ኤርትራ እና ሱዳን ከዚህ ቀደም ኤርትራ እና ሱዳን በተለያዩ አጋጣሚዎች ይወቃቀሱ ነበር። እአአ 2005 ላይ ሱዳን ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት፤ ኤርትራ በምሥራቅ ሱዳን ለሚገኙ ታጣቂዎች የቁሳቁስ ድጋፍ ታደርጋለች ስትል ከሳ ነበር። ኤርትራ በበኩሏ ይህን የሱዳን መንግሥት ክስን አጣጥላለች። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ግነኙነት እየታደሰ ይገኛል። የሱዳኑ ፕሬዝደንት ኦማር አል-በሽር ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ ሚያዚያ 2012 ላይ ፕሬዝደንት ኢሳያስ ወደ ሱዳን ተጉዘው ነበር። በድጋሚ ሰኔ 13/2012 በሱዳን መዲና ካርቱም ተገኝተው ነበር። ፕሬዝደንቱ በጉብኝታቸው ወቅት ከሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሌተናል ጀነራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን ጋር ተገናኝተዋል። ሁለቱ መሪዎች በሁለትዮሽ ጉዳዮች እንዲሁም በቀጠናው ሰላም ዙሪያ ምክክር አድርገው ነበር። ጳጉሜ 2/2012 ዓ.ም ላይ ደግሞ ሌተናል ጀነራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን ለአንድ ቀን ይፋዊ ሥራ ጉብኝት አሥመራ ተገኝተው ነበር። የኤርትራ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር የማነ ገ/መስቀል ሌተናል ጀነራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን እና ፕሬዝደንት ኢሳያስ በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ በሁለቱ አገራት ፍላጎቶች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል ብለዋል። ሐምሌ 2012 ላይ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ በኢትዮጵያ፣ በሱዳን እና በግብጽ መካከል በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ያለውን አለመግባባት ለማጥረት ኤርትራ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን አያደረገች ነው ብለው ነበር። ኤርትራ እና ግብጽ መስከረም 13/2011 ላይ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ የግብጹን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሳሚ ሸኩሪን በቤተ-መንግሥታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸውን የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስቴር አስታውቆ ነበር። በቀጣናው ሰላም እና ትብብር ስለማስፈን እንዲሁም የሁለቱ አገራት የሁለትዮሽ ስምምነት ዙሪያ ውይይት ማካሄዳቸው ተጠቁሟል። ሰኔ 28/2012 ዓ.ም ደግሞ ፕሬዝደንት ኢሳያስ ወደ ግብጽ ካይሮ ለሦስት ቀናት አምርተው ነበር። ፕሬዝደንት ኢሳያስ በካይሮ ቆይታቸው ከፕሬዝደንት አብድል ፋታህ አል-ሲሲ እና ከሌሎች የግብጽ ባለስልጣናት ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ኤርትራ ቴሌቪዥን ዘግቦ ነበር። ኤርትራ እና ደቡብ ሱዳን ሚያዚያ 25/2011 ላይ ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ ጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አሕምድ እና ፕሬዝደንት ኢሳያስ በአሥመራ ከተገናኙ በኋላ በቀጣዩ ቀን ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ወደ ደቡብ ሱዳን አምርተዋል። ፕሬዝደንት ኢሳያስ እና ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ሚያዚያ 26/2011 ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት ጁባ ከደረሱ በኋላ ከፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር ጋር በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ የሦስትዮሽ ውይይት አድርገዋል። የኤርትራ ግንኙነት መሻሻል ኢትዮጵያና ኤርትራ ደም አፋሳሽ የድንበር ጦርነት ካካሄዱ በኋላ ኤርትራ በአካባቢዊ፣ በአህጉራዊና በዓለም አቀፋዊ መድረኮች ላይ የነበራት ተሳትፎ ከመቀዛቀዙ በተጨማሪ ማእቀቦችም ተጥለውባት ቆይተዋል። በእንዲህ ያለው ሁኔታ ከኢትዮጵያ ጋር በፍጥጫ ከሌሎች አገራት ጋር ደግሞ በጥርጣሬ ውስጥ ለ20 ዓመታት ያህል የቆችው ኤርትራ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ወደ ስልጣን መጥተው በሁለቱ አገራት መካከል የሰላም ስምምነት ከተደረሰ በኋላ ኤርትራ ከጂቡቲ በስተቀር ከአካባቢው አገራት ጋር ያላት ግንኙነት መጠናከርን ያሳየ ይመስላል። ከሰላም ስምምነቱ በኋላ ያታው ለውት ምናልባትም ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ለዓመታት የቆየችበት ፍጥጫ ከሌሎች አገራት ጋር በነበራት ግንኙነት ላይ ጥላውን አጥልቶበት ቆይቷል ለማለት ያስደፍራል።
48224211
https://www.bbc.com/amharic/48224211
ወመዘክር፡ ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመን እስከዛሬ
". . . በዚህ የሕዝብ መጻሕፍት ቤት የሚታተሙ መጻሕፍት፣ ያልታተሙ ጽሑፎችና ለታሪክ የሚጠቅሙ ነገሮች ሁሉ ተሰብስበው የሕዝባችን የአእምሮ ቅርስና የተስፋው ማነቃቂያ እንዲሆኑ ይጠበቃሉ፡፡ ዓላማችን በኢትዮጵያ የሚታተሙትን መሰብሰብ ብቻ አይደለም፡፡ በማናቸውም አገር የታተሙ ቢሆኑ የአገራችንን ጉዳይ የሚነኩትን መጻሕፍትና ጽሑፎች ሁሉ በተቻለ መጠን ለመሰብሰብ የምንደክምበት ነው. . .
ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ ወመዘክርን ንጉሡ ሲመሰርቱት . . . ማንበብ ወይም ምልክት ማድረግ ብቻ የበቃ አይደለም። የቅን ትምህርት ዋናው ምልክቱ የተነበበውን ከአእምሮ ጋራ ማዋሃድ ነው፡፡ ላይ ላዩን ከማንበብ የሚገኝ ዕውቀትና ከአንድ መጽሐፍ ውስጥ አንዳንድ ገጽ በመመልከት ብቻ ተገኝቶ የሚጠቀስ ቃል ሁሉ ለእውነተኛው የዕውቀት መሻሻል እጅግ የሚያሰጋና መሰናክል ይሆናል. . . " ሚያዝያ 27 ቀን 1936 ዓ. ም. ላይ የአሁኑ የኢትዮጵያ ቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲ ያኔ የሕዝብ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር በሚል መጠርያ ሲመሰረት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ካደረጉት ንግግር የተቀነጨበ ነው። • "ሌቱም አይነጋልኝ" የተባለላት የውቤ በረሃ ትዝታዎች ንጉሡ የግል ንብረታቸው የነበሩ መጻሕፍትን ለወመዘክር አበርክተው እንዳቋቋሙት የታሪክ መዛግብት ያወሳሉ። ከመዛግብት ክፍሎች አንዱ በቅድሚያ 138 ከዛም በተለያየ ጊዜ 600 መጻሕፍት ለግሰዋል። ወመዘክር መዛግብት ብቻ ሳይሆን ሌሎችም ቅርሶች እንዲያሰባስብ ጭምር ታቅዶ ስለነበር የተለያዩ ነገሥታት አልባሳት፣ ከእንጨትና ከወርቅ የተሰሩ መገልገያዎችም ተሰባስበው ነበር። እነዚህ ቅርሶች ዛሬ በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ውስጥ ይገኛሉ። ተቋሙ 1958 ዓ.ም. ላይ ብሔራዊ ቤተ መጻሕፍት የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ሥራውን ማከናወን የቀጠለ ሲሆን፤ ከዛ በኋላም በተደጋጋሚ የመዋቅር ለውጦች ተደርጎበታል። በ1968 ዓ. ም. የቀድሞው የባህልና ስፓርት ሚንስቴር ሥር እንደነበር ለአብነት መጥቀስ ይቻላል። ወመዘክር ኤጀንሲ የሆነው በ1998 ዓ. ም. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያፀደቀውን አዋጅ ተከትሎ ነው። • የሠላም ተጓዧ ሉሲ (ድንቅነሽ) ምን ደረሰች? በዚህ ዓመት 75ኛ የአልማዝ ኢዮቤልዮውን የሚያከብረው ወመዘክር፤ ባለፉት ሰባት አሰርታት ከጽሑፍ፣ ከድምፅና ከምስል ህትመቶች ሦስት ቅጂ ሰብስቧል። የመጽሐፍ፣ የመጽሔት፣ የጋዜጣ፣ የሙዚቃ፣ የሀይማኖታዊ ዝማሬ፣ የቴአትር፣ የድራማ ቅጂዎች በማዕከሉ ይገኛሉ። የቃል ትውፊቶች በድምፅ ተቀርጸው እንዲሁም በጽሑፍ ሰፍረውም ይገኛሉ። ኢትዮጵያ በዩኔስኮ ያስመዘገበቻቸው የሥነ ጽሑፍ ቅርሶች ዝርዝር ከሸክላ ሙዚቃ እስከ ሲዲ፤ ከብራና እስከ ጥራዝ መጻሕፍት ማግኘት ይቻላል። ለተመራማሪዎች አገልግሎት የሚሰጥ ክፍልና 24 ሰዓት የሚሠራ ቤተ መጻሕፍት የተቋሙ አካል ናቸው። ኢትዮጵያውያን ደራስያን ለመጽሐፋቸው የባለቤትነት እውቅና የሚያገኙበትና በዓለም አቀፍ የድረ ገጽ ገበያ ሥራቸውን ለመሸጥ የሚያስችላቸው የመጻሕፍትና የመጽሔት መለያ ቁጥር (ISBN) የሚሰጠውም ኤጀንሲው ነው። ወመዘክር እንደ ተክለፃዲቅ መኩሪያና ከበደ ሚካኤል ያሉ አንጋፎች የመሩት ተቋም ነው። • የመይሳው ካሳ የልጅ ልጆች • ከኢትዯጵያ የተዘረፉ ቅርሶች በውሰት ሊመለሱ ነው እንደ ሀገር ግዛት ሚንስትር፣ አዲስ ለስላሳ መጠጥ ፋብሪካ፣ ፌደራል ግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባዔ ካሉ ቀደምት ተቋሞች የተዛወሩ ስብስቦች ይገኙበታል። ከታዋቂ ግለሰቦች ወደተቋሙ ከተዛወሩ የመዛግብት ስብስቦች መካከል፤ ዶክተር አምባሳደር ዘውዴ ገበብረሥላሴ ያሰባሰቧቸው 285 ፋይሎችና አለቃ ታዬ ገብረማርያም ያሰባሰቡት 48 አቃፊ መዛግብት ይጠቀሳሉ። የወመዘክር ቤተ መጻሕፍት ለህጻናትና ለአይነ ስውራን ክፍል አለው። የኢትዮጵያ ጥናት ክፍል (17000 መጻሕፍት ያሉት)፣ የየእለቱ የጋዜጣና መጽሔት እትም ማንበብያ ክፍል እንዲሁም የማይክሮ ፊልም ክፍልም አለው። የመጻሕፍት ውይይት፣ የመጻሕፍት ሽያጭ ያካሂዳሉ። ደራሲያን፣ አሳታሚዎች፣ አታሚዎችና መጻሕፍት ሻጮች የሚሳተፉበት የመጻሕፍት ዓውደ ርዕይም ይከናወናል። • የፈረሰው የደጃዝማች ዐምዴ አበራ ቤት ጠባቂ ምን ይላል? የዘመናት ጉዞ አፍሪካ ውስጥ ብሔራዊ መጻሕፍት በማቋቋም ግንባር ቀደሟ ግብጽ እንደሆነች ይነገራል። ኢትዮጵያም ብሔራዊ ቤተ መጻሕፍት በመመስረት ስመ ጥር ከሆኑ ሀገሮች አንዷ ነች። ወመዘክር 75ኛ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ ባወጣው መጽሔት ላይ እንደተመለከተው፤ ብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደሥላሴ 1903 ዓ. ም. ላይ ለንደንን ጎብኝተው ወደኢትዮጵያ ሲመለሱ፤ ኢትዮጵያ ዘመናዊ ቤተ መዛግብት እንዲኖራት አሳስበው ነበር። ህልማቸው እውን የሆነው በ1936 ዓ. ም. ነበር። በወመዘክር ጥንታዊ መዛግብት ይገኛሉ ወመዘክር በመዋቅር ታቅፎ ጠንካራ እንቅስቃሴ እንዲያደርግ በ1968 ዓ. ም. ላይ የተላለፈ ውሳኔ ጉልህ ሚና መጫወቱን የታሪክ መጽሔቱ ያትታል። በወቅቱ አንዳንድ መሥሪያ ቤቶች ጥንታዊ መዝገቦቻቸውን ለወረቀት ፋብሪካ መሸጥ፤ ፍርድ ቤቶች ደግሞ ቦታ አጣበዋል ያሏቸውን አሮጌ መዛግብት ማቃጠል እንዲፈቀድላቸው ይጠይቃሉ። "የወታደራዊ መንግሥቱ የወቅቱ ሊቀመንበር የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል ተፈሪ በንቲ የብሔራዊ ቤተ መዛግብት ማቋቋሚያ ሕግ ወጥቶ በሥራ ላይ እስኪውል ማንኛውም መዛግብትና ሰነዶች በነበሩበት ሁኔታ ተጠብቀው እንዲቆዩ ሰርኩላር አስተላለፉ።" በማሳሰቢያው መሠረትም የባህል፣ ስፖርትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር የሀገር ቅርስ የሆኑ መዛግብት በነበሩበት ሁኔታ ተጠብቀው መቆየት መቻላቸው በመጽሔቱ ተገልጿል። ወመዘክር የታተሙ፣ በከፊል የታተሙና ያልታተሙ ጽሑፎች አሰባስቦ ከመጠበቅ ባሻገር ወደቀጣዩ ትውልድ የማሸጋገር ኃላፊነትም አለበት። ባለፊት ዓመታት ግቡን ምን ያህል አሳክቷል? ስንል የብሔራዊ ቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሽመልስ ታዩን ጠይቀናል። ኃላፊው እንደሚሉት፤ ኤጀንሲው መሰብሰብ የሚገባውን ያህል መዛግብት አልሰበሰበም። ለዚህ በምክንያትነት የሚያስቀምጡት የጥንታዊ ሥነ ጽሑፍ ባለቤት የሆኑ የሀይማኖት ተቋሞች መዛግብት ለተቋሙ ለመስጠት ፍቃደኛ አለመሆናቸውን ነው። "የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያንም ይሁን የእስልምና ጉዳየች፤ በመስጅድና በገዳም ያሉ መዛግብትን አይሰጡንም። ከጥንት ጀምሮ ሲጠቀሙበት ለነበረው የሥነ ጽሑፍ ሀብት በመቆርቆር 'ማን የኛን ያህል ሊጠብቃቸው ይችላል' ከሚል እምነት ማጣት የመነጨ ሊሆን ይችላል።" የነዚህን መዛግብት ዋና ማግኘት ባይቻልም፤ ተቋሙ ዲጂታል ቅጂ ይወስዳል። መዛግብቱ ሰው ሰራሽ ወይም ተፈጥሯዊ አደጋ ቢደርስባቸው ቅጂውን መጠቀም ይቻላል። ማንኛውም የጽሑፍ፣ የድምፅ ወይም የምስል ህትመት የሚያወጣ ግለሰብ አልያም ተቋም፤ ሦስት ቅጂ ለወመዘክር መስጠት ቢገባውም፤ ስንቶች ያደርጉታል? የሚለው አጠያያቂ ነው። "እነሱም ያልሰጡን እኛም ያልሰበሰብናቸው አሉ" ይላሉ አቶ ሽመልስ። ከግለሰቦች የአርባ ቀን መታሰቢያ ካርድ አንስቶ ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሀገሮች ጋር የተጻጻፈቻቸው ደብዳቤዎች በተቋሙ ይገኛሉ። ከተቋሙ ሠራተኞች ጥቂቱ በ15ኛው ክፍለ ዘመን የተጻፈው መጽሐፈ ሄኖክ እና ዳግማዊ አጼ ምኒልክ ለሞስኮው ንጉሥ ኒኮላስ ቄሳር የጻፉትን ደብዳቤ ጨምሮ ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ተቋም (ዩኔስኮ)ያስመዘገበቻቸው 12 የሥነ ጽሑፍ ቅርሶችም ለጎብኚዎች ክፍት ናቸው። በቀጣይ ክታብ አልፋራይድ፣ ክታብ አልሙሳጣፊ፣ መጽሐፈ ድጓ እና ባህረ ሃሳብ በዓለም አቀፍ መዝገብ እንዲሰፍሩ ጥያቄ ቀርቧል። በዓመታት መረጃ የማሰባሰብ ሂደት ክፈተት ከተፈጠረበት ወቅት አንዱ ዘመነ ደርግ እንደነበር አቶ ሽመልስ ይናገራሉ። በወቅቱ የህትመት ቅጂ የማሰባሰብ ሥራ ያከናውኑ የነበረ ቢሆንም፤ መንግሥት አልፈልገውም ያለውን መረጃ ማከማቸት አይቻልም ነበር። "የኔ መረጃ ከዛኛው ይበልጣል፤ የኔ ድርጅት ይበልጣል፤ ይባል ስለነበረ ሁሉንም አይነት ህትመት ማሰባሰብ አልተቻለም። መረጃ ማቃጠል፣ ማውደምና እንዳይገኙ ማድረግ የተበራከተው በዛ ዘመን ነው።" ወመዘክር ውስጥ ለዓመታት በቴክኒክና ስልጠና ክፍል የሠሩት አቶ ተስፋዬ ካሱ በበኩላቸው "ትውልዱ አንባቢና የሚጽፍም ነበር። ነገር ግን በፖለቲካ አቋም መሰብሰብ የማንችላቸው መረጃዎች መኖራቸው ስብስቡን ጎድቶታል" ይላሉ። በሌላ በኩል ወቅቱ ትምህርትን በማስፋፋት ረገድ ብዙ የተደከመበት መሆኑን በበጎ ያነሳሉ። ወደ 70 የሚጠጉ ቤተ መጻሕፍት የነበሩበት ዘመን ከመሆኑ ባሻገር አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በቤተ መጻሕፍት ሙያ ትምህረት ይሰጥ ነበር። ዛሬ ላይ ግን ይህ ነው የሚባል የስልጠና ተቋም ባለመኖሩ በወመዘክር ተነሳሽነት እንደ አቶ ተስፋዬ ያሉ ባለሙያዎች የአጭር ጊዜ ስልጠና ይሰጣሉ። አቶ ሽመልስ የቀድሞውን ወመዘክርን ከዛሬ ጋር ሲያነጻጽሩ፤ ንጉሡ የራሳቸውን መጻሕፍት ለወመዘክር እንደሰጡት ቤተ መጻሕፍትን የመደገፍ ተግባሩ በሌሎች መሪዎችም መቀጠል ነበረበት ይላሉ። "ስንቱ መሪ ነው ለዜጎች አስቦ ለቤተ መጻሕፍት መጽሐፍ የሚሰጠው? ትውልድን በእውቀት ለማነጽ የሚሞክር መሪስ ማነው?" ሲሉ ይጠይቃሉ። አቶ ተስፋዬ በተለያየ ዘመን የኢትዮጵያ የሥነ ጽሑፍ ሀብቶች በወራሪዎች መዘረፋቸው፣ በሕገ ወጥ መንገድ እየተሰረቁ መውጣታቸው ትልቁን ክፍተት እንደፈጠረ ያስረዳሉ። ከወመዘክር የመጻሕፍት ስብስቦች መካከል የኢትዮጵያ ጥንታዊ ጽሑፎች እንግሊዝ ጣልያንና በሌሎችም ሀገሮች ይገኛሉ። በውጪ ዘራፊዎች ብቻ ሳይሆን በእርስ በእርስ ጦርነትም ጉዳት ደርሶባቸዋል። "የፈረንሳይ ብሔራዊ ቤተ መጻሕፍት አንዱ የስብስብ ክፍሉ የኢትዮጵያ ማኑስክሪፕት ነው። ከቤተ መንግሥት፣ ከትምህርትና ሥነ ጥብበ ሚኒስቴርና የአጥቢያ ኮኮብ ማኅበር ቤተ መጻሕፍት መዛግብት በጣልያኖች ተዘርፈዋል" ይላሉ በቁጭት። አቶ ሽመልስ ባለፈው ዓመት ከሀገር ውስጥ በሕገ ወጥ መንገድ ሊወጡ የነበሩ 100 የብራና መጻሕፍት በጉምሩክ ተይዘው ለወመዘክር መሰጠታቸውን አስታውሰው፤ "ይህ በጣም ያሳዝናል። ትውልዱ ማንነቱን፣ ታሪኩን እየሸጠና አሳልፎ እየሰጠ ነው። ቀጥሎ ለሚመጣው ትውልድ ማሰብ ይገባ ነበር" ይላሉ። ባለሙያ ማጣትና ሌሎችም ተግዳሮቶች ዋነኛ ትኩረቱን በቤተ መጻሕፍትና በቤተ መዛግብት ሙያ ላይ አድርጎ ስልጠና የሚሰጥ ተቋም አለመኖሩ በዘርፉ ክፍተት እንደፈጠረ አቶ ሽመልስና አቶ ተስፋዬ ይናገራሉ። አቶ ሽመልስ "በመዛግብት አስተዳደርና በሪከርድ ሥራ ላይ ዋነኛ ትኩረቱን ያደረገ ስልጠናም ስለሌለ መዛግብቶች እየተጎዱ ነው፤ በባለሙያ መያዝ ሲገባቸው ልምዱና እውቀቱ በሌላቸው ሰዎች እጅ ይገኛሉ" ይላሉ። ኤጀንሲው ይህንን ክፍተት ለመሙላት ማስተማሪያ አዘጋጅቶ የቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት ስልጠና ይሰጣል። አቶ ተስፋዬ እንደሚሉት፤ ቤተ መጻሕፍት መስፋፋት እንዳለባቸው ሁሉ ባለሙያዎችም መበራከት አለባቸው። የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው የኤጀንሲው መዋቅር ሌላው ተግዳሮት እንደሆነ ያስረዳሉ። ተቋሙ ራሱን ችሎ በሚንስትር ደረጃ ቢዋቀር የተሻለ ነው ይላሉ። አሁን ከክልሎች ጋር በጋራ የመሥራት ስልጣን በአዋጅ ስለሌለው መገደቡን ይናገራሉ። አዋጁ እንዲሻሻል ጥያቄ ቢያቀርቡም እስካሁን አለመፅደቁን ያክላሉ። "ራሱን ችሎ የቆመና ተጠሪነቱ ቀጥታ ለጠቅላይ ሚኒስትር ቢሆን ጉዳዮቹን ቶሎ ያሰፈጽማል።" በሌላ በኩል ሀገር በቀል እውቀት ዘመን ተሻግሮ በዚህኛው ትውልድ እምብዛም ጥቅም ላይ እንዳልዋለ ብዙዎች ይስማሙበታል። "የንባብ ባህል እንዲዳብር እንፈልጋለን። በእውቀት የበለጸገና በምክንያት የሚያምን ማኅበረሰብ ያስፈልገናል። ትውልዱ ጥንታዊ የኢትዮጵያን ታሪክ፣ ፍልስፍናና ሀብቶቹን እንዲያውቅ እንሻለን" ሲሉ ኃላፊው ይናገራሉ። በወመዘክር ያሉትን የሥነ ሕዋ ምርምር፣ የመድሀኒት ቅመማና ሌሎችም ሀገር በቀል እውቀት የያዙ መዛግብትን ትውልዱ እንዲጠቀምባቸው አቶ ሽመልስ ያሳስባሉ። ጥንታዊ የብራና መጸሕፍትን ምስጢር መመርመር ይቻል ዘንድ የግዕዝና የአረብኛ ቋንቋ ትምህርት መስጠት እንደጀመሩም ያስረዳሉ። በዲጂታል ቅጂ ከዘመኑ ጋር መራመድ ዓለም ወደ ዲጂታል መረጃ ክምችት እየተሸጋገረ እንደመሆኑ፤ ሰዎች ከየትም ቦታ ሆነው በተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም በኮምፒውተር መረጃ የሚያገኙበትን መንገድ ይመርጣሉ። ተቋሙም ጥንታዊ መዛግብትን ዲጂታል ቅጂ በማዘጋጀት ይታወቃል። ቀደምት የሥነ ጽሑፍ ሀብቶች ከንክኪ መጠበቅ ስላለባቸው ግለሰቦች በቅጂዎቹ ይጠቀማሉ። አቶ ሽመልስ "ጥናትና ምርምር የሚያደርግ ሰው የግድ ጣና ገዳማት፣ ድሬ ሼህ ሁሴን መሄድ አያስፈልገውም። ብሔራዊ ቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት የተከማቸውን መጠቀም ይችላል" ይላሉ። • እምቦጭ የጣና ቂርቆስ መነኮሳትን ከገዳሙ እያስለቀቀ ነው ዲጂታል ስነዳ ከኢትዮጵያ አልፎ ከተቀረው ዓለም ጋር ለመተሳሳርም አንድ መንገድ ነው። ኤጀንሲው 200ሺህ የሚጠጉ የመረጃ ሀብቶች ያሉት ሲሆን፤ ከነዚህ ውስጥ ዲጂታይዝ የተደረጉት 2537 ይሆናሉ። ከነዚህ መካከል 1173 ማኑስክሪፕት፣ 256 መዛግብት ይገኙበታል። በማይክሮፊልም የተያዙ 11ሺህ መረጃዎችም ይገኛሉ።
news-45440254
https://www.bbc.com/amharic/news-45440254
''በሐረሯ ሕጻን ጫልቱ ሞት የተጠረጠው ግለሰብ እስካሁን ክስ አልተመሠረተበትም''
በ14 ዓመቷ ጫልቱ አብዲ ላይ አሰቃቂ ጥቃት አድርሷል የተባለው ግለሰብ እስከዛሬ ክስ እንዳልተመሠረተበት ጉዳዩን የሚከታተሉት ጠበቃ ለቢቢሲ ተናገሩ።
ጉዳዩን ሲከታተሉ የነበሩት በኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር ከፍተኛ የሕግ ባለሙያ የሆኑት ወይዘሮ ኤልሳቤጥ ከበደ ግልጽ ባልሆኑ ምክንያቶች ግለሰቡ ላይ ክስ ሳይመሠረት አራት ወራት መውሰዱንም ጠቁመዋል። ፖሊስ ማስረጃ ሰብስቦ ለአቃቢ ሕግ ሲያስተላልፍ መደበኛ ፍርድ ቤት ፋይል እንደሚከፈት የሚናገሩት ጠበቃዋ እስካሁን ግን በተጠርጣሪው ላይ መደበኛ ፍርድ ቤት ክስ አልተመሠረተም። ክሱ ለምን እንደዘገየ የተጠየቁት ጠበቃዋ ጉዳዩን የያዙት የክልሉ ፖሊስ መርማሪዎች የሐኪም ማስረጃ ሐረር ድረስ ወስደው ለማስተርጎም በሚል አላስፈላጊ ጊዜ እንደወሰዱ አስረድተዋል። ክስ ለመመሥረት በሚጠበቅበት ጊዜም ሐረር ድረስ ይዘውት የሄዱትን የሐኪም ማስረጃ «የትርጉም ስህተት አለው» በሚል በድጋሚ አዲስ አበባ ተመልሰው «ተጨማሪ ማስረጃ ፈልገን ነው የመጣነው» በሚል ክስ እንዳዘገዩም ነግረውናል። • የዓመቱ የቢቢሲ አማርኛ ተነባቢ ዘገባዎች • ቻይናዊው በዘረኛ ንግግሩ ምክንያት ከሃገር ሊባረር ነው የሆስፒታል ማስረጃ በእንግሊዝኛ እንደሚጻፍ፣ የፍርድ ቤት የሥራ ቋንቋ ደግሞ አማርኛ በመሆኑ ማስረጃው መተርጎሙ አስፈላጊ እንደሆነ ካብራሩ በኋላ፣ የሐኪም ማስረጃን ለማስተርጎም አዲስ አበባ በብዙ መልኩ ከክልል የተሻለ እንደሆነ የታወቀ ቢኾንም፤ ፖሊስ ማስረጃውን ክልል ድረስ ይዞ መሄድ ለምን እንዳስፈለገው ለጠበቃ ኤልሳቤጥ ግልጽ አልሆነላቸውም። የሐኪም ማስረጃን ከወሰዱ በኋላ አራት ሆነው በድጋሚ ተመልሰው መምጣታቸውንና ማስረጃውን ይዘው የካቲት 12 ሆስፒታል መሄዳቸውን ጠቅሰዋል። ለአራት ወራት ክስ ላለመሥረት ምክንያታቸውም ይኸው ነው ብለዋል። በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓቱ መሠረት አንድ ፖሊስ ከ21 ቀን በላይ ጊዜ ቀጠሮ ማቆየት አይችልም የሚሉት ጠበቃዋ፤ ፖሊስ ማስረጃ አልተሟላልኝም ካለ ሦስት ጊዜ ሰባት ሰባት ቀናት ማራዘም እንደሚችል ጠቅሰዋል። ነገር ግን እስከ አራት ወራት ክስ ሳይመሰረት ማለፉ እንዳስገረማቸው አብራርተዋል። ''ባለፉት ወራት ሟች ቃል ትሰጣለች፥ ፖሊስ ተመላልሶ ይመጣል። ለምን ክስ መመሥር እንዳልፈለጉ ግልጸ አይደለም።'' የሆስፒታሉ ማስረጃ ምን እንደሚያሳይ የተጠየቁት ጠበቃዋ የሞቷ መንስኤ ምን እንደሆነ ያስረዳል ብለዋል። "18 በመቶ ሰውነቷ በቃጠሎ ተጎድቷል። ይህም ከጡቷ ሥር እስከ ጉልበቷ ይደርሳል። ቃጠሎው ወደ ጀርበዋም ዘልቋል።" ይላሉ። ጠበቃ ኤልሳቤት ጨምረው እንደተናገሩት መጀመሪያ ተጠርጣሪና ተባባሪዎቹ ልጅቷን እንዳስፈራሯትና በኋላ ላይ ግን በፖሊስ ስትጠበቅበት ከነበረ ክፍል ውስጥ ላገኘቻቸው ሰዎች የደረሰባትን መናገሯን ጠቅሰው፤ ለኔም መደፈሯን ነግራኛለች ብለዋል። ሟችን በሆስፒታል ሳለች ብልቷ አካባቢ ከጥቅም ውጭ ሆና እንደነበረና በመደፈር ስንጥቅ ስለደረሰባት ምናልባትም ያንን ለመሸፈን ሲባል ቃጠሎ እንደደረሰባት የሚገምቱም አልጠፉም። ጠበቃዋም ተመሳሳይ ግምት አላቸው። ''ምንም ሳትሆን የተቃጠለች ቢሆን ኖሮ እንዳለ ሁሉም ነጭ ይሆን ነበር። ከማህጸኗ እስከ ፊንጢጣዋ ድረስ ስንጥቅ አለው። እዛጋ ደም አለው። ለነርሱ [ለሐኪሞች] ትንገራቸው አትንገራቸው፥ ወይም ደግሞ በምርመራ ሂደት ይድረሱበት አይድረሱበት አላውቅኩም። ግን ለኔ የሆነችውን ነግራኛለች።'' ብለዋል። ሟች ላይ ጥቃት ከደረሰ በኋላ ወላጆቿ አቅም ስላልነበራቸው የካቲት 12 ሆስፒታል የሚያሳክምላችው እንዳልነበረ ያወሱት ጠበቃዋ፤ በኋላ ላይ በፌስቡክ በተሰበሰበ እርዳታ 32ሺ ብር መገኘቱንና ልጅቱ በሱ መታከም መጀመሯን አስታውሰዋል። የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር ዳይሬክተር ወ/ሮ ሜሮን አራጋው ጫልቱ ጥቃቱ ከተፈፀመባት በኋላ ያለምንም እርዳታ በተደፈረችበት ቤት ውስጥ ለ15 ቀናት እንድትቆይ መደረጉን ለቢቢሲ ገልፀዋል። የታዳጊዋ ቃጠሎም ሦስተኛ ደረጃ ማለትም አጥንት ዘልቆ የሚገባ እንደነበርም አመልክተዋል። ቢቢሲ የሟችን እናትና አባት ለማግኘት ሙከራ ያደረገ ቢሆንም ስልክ ስለሌላቸው ማግኘት አዳጋች ሆኗል። "በክልሉ ልዩ ኃይል ጥበቃ ይደረግላት ነበር" የ14 ዓመት ታዳጊዋ ጫልቱ አብዲ በአሰሪዋ ተገዳ ከተደፈረች በኋላ ምንነቱ ያልታወቀ ፈሳሽ ተደፍቶባታል ተብሏል። በዚህም ታዳጊዋ ከጉልበትዋ እስከ እምብርቷ ድረስ ከፍተኛ የመቃጠል ጉዳት እንደደረሰባት ተገልጿል። ከምሥራቅ ሐረርጌ በደኖ ከሚባል ቦታ ወደ ሐረር የመጣችው ታዳጊ፤ በተጠርጣሪው ቤት ውስጥ በቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ ነበር የምትሰራው። ጉዳዩን ሲከታተሉ የነበሩት ከፍተኛ የሕግ ባለሙያ ኤልሳቤጥ እንደሚሉት ታዳጊዋ ከመደፈሯ በተጨማሪ በሰውነቷ ላይ የተደፋባት ፈሳሽ ያደረሰባት ጉዳት እያለ ምንም ዓይነት ሕክምና ሳታገኝ በቤት ውስጥ እንድትቆይ ተደርጋለች። ''ሕመሙ እየባሰባት ሲመጣና ሕይወቷ አስጊ ደረጃ ላይ ሲደርስ ወደ ሐረር ምሥራቅ አርበኞች ሆስፒታል በድብቅ ተወስዳለች።'' በሆስፒታሉ ውስጥም ማንም ሰው እንዳያያት ባዶ ክፍል ውስጥ እንድትተኛና ሌሎች ሰዎች ወደ ክፍሉ እንዳይገቡ በክልሉ ልዩ ኃይል ጥበቃ ይደረግባት እንደነበረ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ''የሚከታተላት ነርስም ቢሆን ከውጪ ነው የተቀጠረው'' በማለት የጉዳዩን ውስብስብነት ያመለክታሉ። • ከውጭ ሀገራት የሚላከው የገንዘብ መጠን አምስት ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተገለፀ • ወንበር የሚለቅላት አጥታ ልጇን ቆማ ያጠባችው እናት ሁኔታው ጥርጣሬ የጫረባቸው የሆስፒታሉ ሠራተኞችና ሌሎች አስታማሚዎች ወደ ክፍሉ ለመግባት ጥረት ሲያደርጉም በወታደሮቹ ይከለከሉና ይባረሩ እንደነበረ ነግረውናል ይላሉ ጠበቃ ኤልሳቤጥ። በመጨረሻ ተሳክቶላቸው መግባት የቻሉ ሰዎች አስር ታካሚዎችን በሚያስተናግድ ክፍል ውስጥ ለምን ብቻዋን እንደተኛች ሲጠይቋት፤ የደረሰባትን ነገር እንዳስረዳች ጠበቃዋ ያመለክታሉ። ጥቃቱን ያደረሰባት ግለሰብ ባለትዳር ሲሆን፤ የተጠርጣሪው ባለቤትም ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር ውላ ከአንድ ቀን በኋላ መፈታቷን ወይዘሮ ኤልሳቤጥ ነግረውናል። "ሐረር ካልተቀበረች ብለው መቃብር ቆፍረው ነበር" ለደኅንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉና የጫልቱን ጉዳይ በቅርብ የሚከታተሉ አንድ ግለሰብ ጉዳዩን ለመሸፋፈን የተጠርጣሪው ቤተ ዘመድና በሐረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስተዳደር ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጭምር እጃቸውን ያስገቡ እንደነበር ጠቁመዋል። በተጨማሪም ሕክምናውን አስመልክቶ በቴሌቨዥን እሷን የተመለከቱ መርሐግብሮች እንዳይተላለፉ ጫና መደረጉን፣ ከዚያም ባሻገር ቃሏን እንድትቀይር የሚያደርጉ ተጽእኖዎችም ነበሩ ተብሏል። ወይዘሮ ሜሮን አራጋው ከእናቷ አንደበት ሰማሁ ብለው ለቢቢሲ እንደተናገሩት ደግሞ ጫልቱን ሐረር ሕክምና ላይ ሳለች መሣሪያ የያዙ ፖሊሶች ናቸው ሲጠብቋት የነበረው። "ይህም ጉዳዩ ተድበስብሶ እንዲቀር ሙከራ ይደረግ እንደነበር ያሳያል" ብለዋል። እነዚህን ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት የፍርድ ሒደቱ ምን ያህል ነጻ ሊሆን ይችላል በሚል የተጠየቁት ወይዘሮ ሜሮን ፍርድ ሂደቱ ሐረር ክልል ላይ ቢታይ መጨረሻ ላይ የሚሰጠው ፍትህ ላይ ተጽእኖ እንደሚኖረው ለፌዴራል ጠቅላይ አቃቢ ሕግ አቤት ማለታቸውን ገልጸው "የፌዴራሉ ጠቅላይ አቃቢ ሕግም ምላሽ ሰጥቶናል።" ብለዋል። በገንዘብ የማባበል ሙከራን ጨምሮ የተጠርጣሪ ቤተሰቦች የተለያየ የማዋከብ ሥራ ሲሠሩ ነበር ያሉት እኚህ ግለሰብ፤ ቀብሯ በተወለደችበት ቀዬ እንዳይፈጸም ይልቁንም ሐረር ከተማ ካልተቀበረች ብለው መቃብር ቆፍረውም እንደነበርም ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉት ግለሰብ ገልፀዋል።
news-48198783
https://www.bbc.com/amharic/news-48198783
''እያሉ'' በሌሉበት የተከሰሱት አቶ ጌታቸው አሰፋ
አቶ ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ በ26 የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ላይ ክስ መመስረቱን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ማክሰኞ ዕለት ማስታወቁ አይዘነጋም።
በቁጥጥር ሥር ያልዋሉት በከፍተኛ የሙስና እና ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም በሚሉ ወንጀሎች ክስ የተመሰረተባቸው አቶ ጌታቸው፤ በትግራይ ክልል እንደሚገኙ ጠቅላይ ሚንስትሩ እና የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ቀደም ሲል በተለያየ ጊዜ ጠቁመዋል። ታዲያ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ጌታቸው አሰፋ በትግራይ ክልል እንዳሉ እየታወቀ ለምን ''በሌሉበት'' የሚል ክስ ተመሰረተባቸው የሚለው በርካቶችን አነጋግሯል። እኛም በዚሁ ጉዳይ ላይ አስተያየታቸውን እንዲሰጡን የሕግ ባለሙያው አቶ ዮሃንስ ወ/ገብርኤልን ጠይቀናል። አቶ ዮሃንስ የደርግ ከፍተኛ አመራሮችን ለመክሰስ ተቋቁሞ በነበረው ልዩ አቃቤ ሕግ ጽሕፈት ቤት እንዲሁም በሥነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በዋና ዓቃቤ ሕግ ከዚያም በቀድሞው የኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለሥልጣን የሕግ ክፍል ሃላፊ ነበሩ። • አቶ ጌታቸው አሰፋ ላይ ክስ ተመሰረተ ''በሌሉበት'' አቶ ዮሃንስ ''አንድ ተጠርጣሪ ሃገር ውስጥ ሳለ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ በሕግ አስከባሪ አካል እንዲያዝ እና እንዲቀርብ ታዞ ሳይቀርብ ቢቀር እንኳ ተጠርጣሪው በሌለበት ጉዳዩ በፍርድ ቤት መታየቱ አይቀርም'' በማለት ያስረዳሉ። አንድ ተከሳሽ በሌለበት በፍርድ ቤት ውሳኔ ከተላለፈበት፤ ፍርደኛው ለፍርድ ቤቱ በሌለሁበት ጉዳዩ መታየቱ አግባብ አይደለም ብሎ ሊያመለክት ይችላል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ ተከሳሹ ሆነ ብሎ አልያም መጥሪያው ሳይደርሰው ቀርቶም ከሆነ ፍርድ ቤት የሚያጣራው ጉዳይ ይሆናል። ተከሳሹ ሆነ ብሎ ፍርድ ቤት ሳይቀርብ ከቀረ የተላለፈበትን ውሳኔ የመከላከል እድሉን እንዳልተጠቀመ ተደርጎ ይወሰዳል። ይሁን እንጂ ተከሳሹ መከሰሱን ሳያውቅ ውሳኔ እንደተላለፈበት ፍርድ ቤቱ ካመነ፤ ተከሳሹ ማስረጃውን እና መከላከያውን ሊያቀርብ የሚችልበት ሁኔታ እንዳለ የሕግ ባለሙያው አቶ ዮሃንስ ያስረዳሉ። እሳቸው እንደሚሉት ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር ባይውልም የፍርድ ሂደቱ ይቀጥላል። ''ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ሕግን ምስክሮች መስማት ይጀምራል። በሌለበት ውሳኔ ይሰጣል። በተጨማሪም ተከሳሹ ፍርድ ቤት ሳይቀርብ በጠበቃ ሊወከል አይችልም። በኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ መሰረት በእንዲህ አይነት ወንጀል ክስ የተመሰረተበት በውክልና ሊከታተል አይችልም።" ይላሉ። አቶ ጌታቸው አሰፋን በተመለከተም፤ የወጣባቸው የእስር ትዕዛዝ እና ክስ በመገናኛ ብዙሃን በስፋት ተሰራጭቷል ተብሎ ስለሚታመን ተከሳሹ የፍርድ ቤቱ መጥሪያ ደርሷቸዋል ብሎ ፍርድ ቤቱ ሊደመድም እንደሚችል የሕግ ባለሙያው ይገልፃሉ። ''የትግራይ ክልል አሳልፎ አይሰጥም'' በሰብዓዊ መብት ጥሰት እና በከፍተኛ የሙስና ወንጀል የእስር ትዕዛዝ የወጣባቸውን ከዚያም ክስ የተመሰረተባቸውን የቀድሞ የስለላ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋን የትግራይ ክልላዊ መንግሥት አሳልፎ ለመስጠት ፍቃደኛ አለመሆኑን ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ከወራት በፊት አሳውቆ ነበር። ይህን ያሉት ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ብርሃኑ ጸጋዬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመስሪያ ቤታቸውን የአምስት ወራት የሥራ ሪፖርት ይፋ ባደረጉበት ወቅት ነበር። በወቅቱ የፌደራል መንግሥት ከትግራይ ክልል ፍቃድ እና እውቅና ውጪ ግለሰቡን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የሚያስችለው የሕግ አግባብ አለ? አቶ ጌታቸው አሰፋ በየትኛው የሕግ አግባብ ለፌደራል መንግሥት ተላልፈው ሊሰጡ ይችላሉ? የሚሉ ጥያቄዎችን ለሕግ ባለሙያዎች አቅርበን ነበር። የፌደራል ፍርድ ቤቶችን ሥልጣን ለመወሰን በወጣው የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1996 አንቀጽ 4.3 መሠረት የፌደራል ፍርድ ቤቶች በሰው ልጆች መብት ላይ በሚፈጸሙ ወንጀሎች የዳኝነት ሥልጣን እንዳላቸው ይደነግጋል። የሕግ ባለሙያው አቶ አዲ ደቀቦ፤ በወንጀል የተጠረጠረው ግለሰብ ማንም ይሁን ማን፤ ፈጽሟል ተብሎ የተጠረጠረበት ወንጀል በፌደራል መንግሥት ስልጣን ስር የሚወድቅ እስከሆነ ድረስ፤ የፌደራል መንግሥቱ የማንንም ፍቃድ ሳይጠይቅ ወደ የትኛውም ክልል ሄዶ በወንጀል የተጠረጠረውን ግለሰብ በቁጥጥር ሥር የማዋል ስልጣን አለው ይላሉ። የፌደራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ስልጣን ከሚኖረው የወንጀል እይነቶች መካከል፤ በሰው ልጆች መብት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ጨምሮ በውጪ ሃገራት መንግሥታት ላይ የሚፈጽሙ ወንጀሎች፣ የበረራ ደህንነትን የሚመለከቱ ወንጀሎች እና የመሳሰሉት በፌደራል ፍርድ ቤቶች የሚታዩ የወንጀል አይነቶች ናቸው። አቶ አዲ አንደሚሉት አንድ ግለሰብ የፌደራል መንግሥት ሰራተኛ ሳለ ፈጽሟል ተብሎ የተጠረጠረበት ወንጀል ካለ፤ የፌደራል መንግሥት የየትኛውንም ክልል ፍቃድም ይሁን ይሁንታ ሳያስፈልገው ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ሥር አውሎ የመመርመር ስልጣን አለው ይላሉ። • ሜጀር ጄኔራል ክንፈ: ‘‘ቤት የለኝም፣ መኪና የለኝም፣ ንብረት የለኝም፤ ያለኝ ሰውነቴ ብቻ ነው’’ በተመሳሳይ መልኩ ሌላው የሕግ ባለሙያ ሆኑት አቶ ኤፍሬም ታምራት አንድ የክልል መንግሥት በሰብዓዊ መብት ጥሰት የተጠረጠረን እና በፌደራል አቃቤ ሕግ ክስ የተመሰረተበትን ግለሰብ አሳልፌ አልሰጥም ቢል፤ ሕገ-ምንግሥቱን፣ የፌደራል የወንጀል ሕጉን፣ የፌደራል ፍርድ ቤቶችን ሥልጣን ለመወሰን የወጣውን የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅን፣ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕጉን እና የፌደራል ፖሊስ ማቋቋሚያ አዋጅን ይተላለፋል ይላሉ። አቶ ኤፍሬም ሃሳባቸውን ሲዘረዝሩ፤ በሕገ-መንግሥቱ ሦስተኛው ምዕራፍ ላይ በማንኛውም ደረጃ የሚገኙ የፌዴራል መንግሥትና የክልል ሕግ አውጪ፣ ሕግ አስፈጻሚ እና የዳኝነት አካሎች የመብቶችና የነፃነቶች ድንጋጌዎችን የማክበርና የማስከበር ኃላፊነትና ግዴታ እንዳለባቸው ተጠቅሷል። ''የማክበር ግዴታ ማለት እራሱ የመንግሥት አካል ወንጀል እንዳይፈጽም መከላከል ሲሆን የማስከበር ማለት ደግሞ ወንጀል የፈጸመውን ግለሰብ የመመርመር እና ሕግ ፊት የማቅረብ ኃላፊነት ማለት ነው'' ይላሉ። አቶ ኤፍሬም የክልሉ ውሳኔ የፌደራል ፖሊስ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 720/2004 እንዴት እንደሚጻረር ሲያስረዱ፤ አንቀጽ 6 ሥር የተቀመጠውን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንን ሥልጣን እና ተግባርን በመዘርዘር ያስረዳሉ። አቶ ኤፍሬም እንደሚሉት ከኮሚሽኑ ሥልጣን እና ተግባራት መካከል በፌደራል ፍርድ ቤቶች የሥልጣን ክልል ስር የሚወድቁ ወንጀሎችን ይከላከላል፤ ይመረምራል። የፌደራል ፍርድ ቤቶችን ሥልጣን ለመወሰን የወጣውን የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1996 የፌደራል ፍርድ ቤቶች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ የተፈጸሙ የወንጀል ተግባራትን ማየት የሚችለው የፌደራል ፍርድ ቤት መሆኑን በመጥቀስ ለፌደራል መንግሥት የተሰጠ ስልጣን ክልሎች እንደማይኖራቸው የሕግ ባለሙያው ያስረዳሉ። የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕጉም ማንኛውም ዜጋ በተግባሩ ጉዳት እስካልደረሰበት ድረስ፤ በወንጀል የተጠረጠረን ግለሰብ አሳልፎ የመስጠት ግዴታ እንዳለበት እንደሚያትት የሚናገሩት የሕግ ባለሙያው የክልል መንግሥታትም ቢሆኑ ይህን የሕግ ኃላፊነት ከመወጣት ወደኋላ ማለት አይችሉም ይላሉ። • አቶ ጌታቸው አሰፋ የእስር ትዕዛዝ እንደወጣባቸው ተገለፀ በወንጀል የሚፈለግን ግለሰብ አሳልፌ አልሰጥም ማለት በራሱ ፍትህን የማስተጓጎል ወንጀል ነው የሚሉት አቶ ኤፍሬም፤ ዛሬ ላይ በሰብዓዊ መብት ጥሰት የተጠረጠረን ግለሰብ አሳልፌ አልሰጥም የሚል የሕግ አስፈጻሚ አካል፤ ነገ ሰልጣንን ያለ አግባብ በመጠቀም በሚል በወንጀል ሊጠየቅ ይችላል ይላሉ። ይህን ተግባራዊ ሊያደርግ የሚችለው የየትኛው የፌደራል አካል ነው? የሕግ ባለሙያው አቶ አዲ ይህ ከወንጀል ምርመራ ጋር የተያያዘ ሰለሆነ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ሥር የማዋል ስልጣኑ የፌደራል ፖሊስ ነው ይላሉ። የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ከፌደራል ፖሊስ ጋር በመጣመር ሥራውን ሊያከናውን እንደሚችልም ይጠቁማሉ። የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ለአቶ ጌታቸው አሰፋ ከለላ ሰጥቷል ለሚለው ክስ እስካሁን ምንም አይነት ይፋዊ ምላሽ አልሰጠም። ነገር ግን ቀደም ብሎ ከሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው እስር ጋር በተያያዘ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕስ መስተዳደር የሆኑት ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ክስ እና እስሩን በመኮነን ጠንከር ያለ መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል። የቀረቡት ክሶች በአንድ ወገን ላይ ያነጣጠረ መሆኑን አንስተው ''የኛ ሰው ለምን ታሰረ? አንልም።. . . ሁሉም መጠየቅ አለበት" በማለት እርምጃው ፖለቲካዊ አላማን የያዘ መሆኑን ተናገረዋል። ጨምረውም ክሱ የተለየ ዘመቻ መሆኑንና ማንነታቸውውን በግልጽ ያላስቀመጧቸው ወገኖች እጅ እንዳለበት "ትግራይን ለማዳከም የውጪ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት እየታየ ነው፣ በትግራይ ህዝብ ላይ አዲስ ዘመቻ ተጀምሯል'' በማለት ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ክስ እና እስሩን ተቃውመውት ነበር።
news-49814329
https://www.bbc.com/amharic/news-49814329
ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጣ ስእል በአንዲት አዛውንት ማእድ ቤት ተገኘ
በፈረንሳይዋ ፓሪስ አቅራቢያ በአንዲት አዛውንት ኩሽና ተገኘ የተባለው የስእል ስራ በአስራ ሶስተኛው ክፍለ ዘመን እንደተሰራ የሚታመን ነው።
ለረዥም ጊዜያት የት እንደገባ ጠፍቶ የነበረው እሄ የስእል ስራ ባለቤት ጣልያናዊው ሲምባው ወይም ሲኒ ዲ ፒፖ እንደሆነም ኤክስፐርቶች አስታውቀዋል። እርግጥም ይህ የጥበብ ስራ የዚህ ጣልያናዊ መሆኑን ለማረጋገጥ በኢንፍራሪድ ምርመራም ተካሂዷል። ስእሉ እአአ በሚቀጥለው ወር ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን 6̂.5 ሚሊዮን ዶላር ድረስ ሊያወጣ እንደሚችል ተገልጿል። ዘመናትን የተሻገረውና ከፍተኛ ዋጋ ያለው ይህ ስእልን ያስቀመጡት አዛውንት ስእሉ ትልቅ የጥበብ ዋጋ ያለው ሃይማኖታዊ ስእል እንደሆነ ያምኑ እንደነበርም ተገልጿል። • የለማ ጉያ ድንቅ የቆዳ ላይ ሥዕሎች • ስለኢትዮጵያ የቤተ ክርስቲያን ስዕሎች ምን ያህል ያውቃሉ?
46733683
https://www.bbc.com/amharic/46733683
መከፋፈል ያጠላበት ጉዞ አድዋ
የአድዋ ድልን ከድንበር ሉዓላዊነት ጋር አያይዞ መተንተን የተለመደ ከመሆኑ አንጻር ድሉ አነሰ በዛ የሚለው ጭቅጭቅ ከዚህ መሰረት እንደሚፈልቅ በዕውቀቱ ስዩም ሐተታ አድዋ በሚለው ፅሁፉ ያትታል።
ነገር ግን ይላል በዕውቀቱ "በኔ ግምት የአድዋ ድል ትልቅ ጭብጥ "የሰውነት ክብር" ይሰኛል። ቀደምቶቻችን ወደ አድዋ የጋለቡት በግፍ የተነጠቁትን የሰውነት መታወቂያ ለማስመለስ ነው። እንዲያውም ሰው መሆናቸውን በማያዳግም መንገድ ያረጋገጡት አድዋ ላይ ነው ማለት ይቻላል" አክሎም ወገኖቼ ሰው መሆንን ማረጋገጥ ቀላል ነገር አይምሰላችሁ" ይላል። የቅኝ ግዛትን አሻፈረኝ ያሉ ቀደምቶችን በሚዘክረው በዚህ ፅሁፉ "በውርደት ከመኖር በክብር መሞት ይሻላል" የሚለውንም መርጠው ከሰው በታች ሊያደርጋቸው የመጣውን ቅኝ ግዛት እንዴት አድርገው ድል እንደነሱትም ዘክሯል። • ድምፅ ፈታዮቹ መረዋዎች • ስልክዎ እንደተጠለፈ የሚያሳዩ ሰባት ምልክቶች ለዘመናት ያህል "የጥቁር ነፃነት ተምሳሌት"፤ የዓለም ድሃ ሀገሮችን የናቀና ጦር መሳሪያውን የተማመነ ኃይል የተንበረከከበት በሚልም ሲዘከር ቢኖርም፤ የአድዋ ታሪካዊ አተረጓጎም አንዳንድ ሀሳባዊ ፍጭቶችንም ያስተናግዳል። በአሁኑም ሰዓት አፄ ሚኒልክ የነበራቸው ሚና፣ የሰንደቅ አላማ ጉዳይ በታሪክ ተርጓሚዎች ዘንድ መነታረኪያ ሆኗል። በዚህ አመት ደግሞ ሀገሪቱ ካለችበት የተለያዪ የብሔር ግጭትና ስጋት ጋር ተያይዞ ለአምስት አመታት ሲካሄድ የነበረው አድዋን የሚዘክረው ጉዞ አድዋ አወዛጋቢ ሁኔታን ፈጥሯል። ጉዞው ከመካሄዱ በፊት በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ዘመቻዎች የተከፈቱ ሲሆን፤ ይህም የሰንደቅ አላማው ልሙጥ መሆን፣ የሚሰሙ መፈክሮች፣ "ሁለቱን ትግርኛ ተናጋሪዎች ህዝቦች እንዲከፋፈሉ ያደረገውን ዕለት ማክበር" እንዲሁም ቀጥታ የጉዞውን አስተባባሪዎች "ፀረ-ትግራይ" ናቸው በሚል ወደ ትግራይ ክልል እንዳይመጡ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። የዚህንም አመት የጉዞ አድዋ ለየት የሚያደርገው በእንደዚህ አይነት በተከፋፈለ ስሜት መደረጉ መሆኑን የጉዞው አንደኛው አስተባባሪ ያሬድ ሹመቴ ይናገራል። "በጣልያን ወረራ ወቅት ትልቁ ዘመቻ ወራሪውን ጦር ከኢትዮጵያ ለማስወጣት ነበር። አሁን ደግሞ የተወረርነው በሌላ የውጭ ጦር ሳይሆን በራሳችን አመለካከት ውስጥ ባለው የአንድነት ስሜት መደብዘዝ፣ የኢትዮጵያዊነት ሀሳብ ጥርጣሬ ውስጥ በወደቀበት ወቅት መሆኑ ነው።" ይላል። ከወትሮው በተለየ መልኩ ከአዲስ አበባ ሳይሆን ከሐረር የተነሳው ጉዞ አድዋ ተሳታፊዎችን ከመላው ኢትዮጵያ ማሳተፉ ህዝቡን በአንድ ቦታ፣ ስሜትና ሀሳብ የሚያሰባስብ ኃይል እንደሆነም ያምናል። • መከላከያ በዛላምበሳ ድንበር እንዲቆይ ስምምነት ተደረሰ • ስልክዎ እንደተጠለፈ የሚያሳዩ ሰባት ምልክቶች እንዲህ አይነት ዘመቻ መከፈቱ አዲስ እንደሆነ የሚናገረው ያሬድ ጉዳዩ በሀገሪቱ ውስጥ ያለው የፖለቲካ ዕውነታ ነፀብራቅ ስለሆነ፤ ግራ ቀኙን መፈተሽ እንደሚያስፈልግ ይናገራል። ባለው የሃገሪቱ የፖለቲካ ሁኔታ ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም የሀሳብ መሪዎች የህዝቡን ስሜት የሚያስተጋቡ አክቲቭስቶች ትኩረት መስጠትና ሌሎች ችግሮችን አንስተው በይበልጥ ድምፃቸውን ለማሰማት እንደሞከሩ ያምናል። ይህንን በሁለት መልኩ የሚያየው ያሬድ በአሉታዊ ብቻ ሳይሆን በአዎንታዊ ጎኑ መታየት እንዳለበት ያምናል። በአንደኛው በኩል የሚያነሳው በአሁኑ ሰዓት ሀገሪቷ ላይ ያልተመለሱ ጥያቄዎችና ብዙዎችን እያስጨነቀ ያለው በአንድነት፣ በህብረትና በፍቅር የመኖር ጥያቄ አደጋ ውስጥ በወደቀበት ሰዓት፤ ሀሳቦች የተንፀባረቁበት መድረክ የአድዋ ጉዞ መሆኑ፣ እንዴት ትኩረት እንዳገኛና በበጎነት መታየት እንዳለበት ገልጿል። " መንግሥትም ራሱ በዋናነት በዚህ በፌደራሊዝም ስርአት ውስጥ ከትግራይ ክልልና ከትግራይ ነዋሪ ህዝብ ባለው ግንኙነትና መስተጋብር ውስጥ እንዲህ ደመቅ ብሎ የተለያዩ አሉታዊ ተፅእኖ መፍጠር የሚችሉ ቅስቀሳዎች መደረጉ የስሜቱ ነፀብራቅ በመሆኑ ምክንያት፤ ይህንን ቆም ብሎ ሁሉም አካል ማየት እንዲችል ለምንድን ነው አብዛኛው ሰው ላይ ጥርጣሬ ያደረው የሚለውን እንዲፈተሽ እድል የሚሰጥ ነው" ይላል። በተቻለ መጠን የመፍትሄው አካል ለመሆን እንደሚፈልጉ የሚናገረው ያሬድ በተቻለ መጠን መሰዳደብና እልህ ውስጥ ከመገባባት ይልቅ "የፍቅርን ኃያልነትና ታጋሽነት" ማሳየት እንደሚያስፈልግም ይገልጻል። • "ሌቱም አይነጋልኝ" የተባለላት የውቤ በረሃ ትዝታዎች "ዘመቻውን የከፈቱት ሰዎች የተናገሩበት ምክንያት ሊኖራቸው ይችላል። ማጥናት እና ለዚህ መልስ እንዲሰጥ በሁሉም በኩል ግፊት ማድረግ አለብን ብየ አስባለሁ። ስለዚህ የመግፋትም የመሳብም ሀሳብ ውስጥ በየትኛው በኩል ምን አይነት ሚና ነበር የሚለውን እያየን ካልሄድን ምንም ለውጥ አያመጣም። "ይላል የትግራይን ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደር ህዝብ ነው የሚለው ያሬድ በባለፉት አምስት አመታትም የነበረውንም መስተንግዶ እንደ ምሳሌ ያነሳል። "በፍቅር በተለየ ትህትና እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በጨዋነት ሲያስተናግደን እንደዚሁ አልጋውን እየለቀቀ ሲያሳድረን ያለውን መሶቡን ገልብጦ እያበላ ሲቀበለን የነበረ ህዝብ ነው። በኛ ላይ ችግር አለው ብለን በጭራሽ አናምንም።" ይላል። በአንዳንድ ዘመቻዎች ላይ ማስፈራሪያ ቢሰጣቸውም፤ እነ ያሬድ ግን በጭራሽ በህዝቡ ላይ ከፍተኛ እምነት እንዳላቸው ይናገራሉ። ጥበቃን ወይም የህግ ከለላን ማግኘት መፍትሔ አይደለም የሚለው ያሬድ፤ የግላቸውን ሳይሆን ሀገሪቷ ላይ ያጠላውን ስጋት በቀረፈ መልኩ ችግር እንደሌለ አሳይተው የበለጠ መተማመን በኢትዮጵያ ውስጥ መፍጠር ዋነኛ አላማቸው ነው። "እኛ አንድ ነገር ብንሆን በሀገር ላይ የሚያመጣው መጥፎ ጥላ ስላለ ይህንን አንመኘውም፤ ባዶ መስዋእትነት የሚከፈልበት ጉዳይ አይደለም" የሚለው ያሬድ ምንም አይነት ጥበቃ ሳይደረግላቸውና የሀገር ስሜት ሳይጠፋ ከአንድ አካባቢ ወደ ሌላ መንቀሳቀስ ችግር አለመሆኑን በሚያሳይ ሁኔታ ማከናወን ይፈልጋል። በዚህ ጉዞም ዋነኛ ማሳካት የሚፈልጉት በጎ የሆኑ ህዝባዊ ስሜቶች የሚተላለፉበት መድረክን ለመፍጠ ነው። በማህበራዊ ሚዲያ የሚነገሩ ነገሮች ተሰሚነታቸው ከፍተኛ ደረጃ ላይ እየደረሰ ከመሆኑ አንፃር በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ብቻ የቀረ ነው ብሎ እንደማያምንና ከእውነታው የራቀ ነው የሚል ሽፋን ተሰጥቶ ሊድበሰበስ አይገባም ይላል። ነገር ግን ከትግራይ ክልል ብዙ ነዋሪዎች የሚደውሉላቸው ሲሆን በባለፉት አምስት አመታት እንደደገፏቸው አሁንም እንደሚደግፏቸውና፤ አይዟችሁ አትስጉ ምንም አዲስ ነገር የለም የሚሉ ሲሆኑ ይህም ለያሬድ ተስፋ ሰጭ ነው። "ይህ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያለው መሬት ላይ ካለው የተለየ ነው። ይህም ጉልበት የሚሰጥና የሚያነሳሳ ነው።'' ብሏል። የሚደውሉላቸው ሰዎች ብቻ ሳይሆን ከፌዴራል መንግሥት በኩል ድጋፍ እንዲሁም ፍቃድ ተሰጥቷቸዋል። ለየክልሎቹም የድጋፍ ደብዳቤ ተጽፎላቸዋል። የተለያዩ የክልል መሪዎች የሚያስተዳድሩትን አካባቢ ደህንነት በማረጋገጥ በተለያዩ አካባቢዎች መንቀሳቀስ ስጋት የለውም በሚል አጋርነታቸውን ያሳያሉ እንዲሁም ኑልን ይላሉ ብሎ ቢያስብም፤ ባይጠሯቸው እንኳን መሄዳቸው እንደማይቀር ይናገራል። "መሄዳችን አይቀርም በግድና በእልህ ሳይሆን በፍቅር እያሸነፍን እስከ መጨረሻው ድረስ እንደርሳለን። ይህንን ካደረግን አድዋ ኢትዮጵያውያንን አንድ ለማድረግ በድጋሚ ምሰሶ ይሆናል" ይላል። የታሪክን አረዳድ በሚመለከት የተለያየ ትንታኔ የሚሰጥበት ከመሆኑ አንፃር፤ በታሪክ ላይ ያለው ግንዛቤ መለያየቱ የፖለቲካው ጫና ውጤት ነው ብሎ የሚያምነው ያሬድ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ መንግሥት ኃላፊነት ወስዶ ማስታረቅ፣ ማስተካከል እንደሚያስፈልገውና ይህም እስከ ትምህርት ስርአቱ ድረስ ሊዘልቅ እንደሚገባ በአፅንኦት ይናገራል። በአጠቃላይ 35 ሰዎች በሚሳተፉበት ይህ ጉዞ መነሻውን ሐረር ያደረገ ሲሆን፤ 1540 ኪሎ ሜትር ርቀትን ይሸፍናል። ሁለት ወር ከአንድ ቀን በሚፈጀውም ጉዞ የኢትዮጵያን ስምና ለሀገሪቷ አንድነት፣ ህብረት፣ ፍቅር የሰሩ ጀግኖች እንደሚዘከሩ ያሬድ ይናገራል።
news-56348597
https://www.bbc.com/amharic/news-56348597
በቡድን ተደፍራ የተገደለችውን ሴት ታሪክ ለመዘገብ በመሞከሩ የታሰረው ሕንዳዊ ጋዜጠኛ
በያዝነው ዓመት ጥቅምት ወር ሲገባ በሰሜን ሕንድ ወደምትገኘው ፕራዴሽ ግዛት አቀናሁ።
ሲዲሂኬ ካፓን ይለቀቅ የሚል ፖስተር ወደ ግዛቲቷ የሄድኩበት ዋነኛ ምክንያትም "ሃትራስ" የሚል መጠሪያ የተሰጠውን ተደፍራ የተገደለች ሴትን ጉዳይ በተመለከተ በጥልቀት ዘገባ ለመስራት ነው። ከቀናት በፊት የ19 ዓመት ሴት ከላይኛው መደብ በሆኑ አራት ወንዶች በደቦ ተደፍራ ተገድላ ነበር። መደፈሩም ሆነ ግድያው የተፈፀመው ቅንጦት በተሞላበት ሃትራስ በሚባል ሰፈር ነው። ወጣቷ ተደፍራ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደሏ እንዲሁም ያለ ቤተሰቦቿ ፈቃድ በሕንድ ባህል እንደሚደረገው አስከሬኗ ተቃጥሎ አመዷ እንዲበተን መደረጉ በዓለም ላይ ባሉ ሚዲያዎች መነጋገሪያ ሆኗል። አካባቢው ደርሼ በሐዘን የተሞሉ ቤተሰቦቿን አገኘሁ። ቤተሰቦቿ፣ ዘመዶቿም ሆነ ጎረቤቶቿ ስለእሷ የሚሉት ነገር ቢኖር ቆንጆ፣ ትንሽ አይናፋርና ረዥም ጥቁር ፀጉር ያላት መሆኑን ነው። በተደፈረችበት ወቅት አካሏ ላይ ስለደረሰባት ድብደባ ፖሊስ ከሞተች በኋላ እንዴት ያለምንም ማጣራት እንድትቀበር እንደፈለገና መንግሥት ጉዳዩን ለምን መሸፋፍን እንደፈለገ አስረዱኝ። እኔ አካባቢው በደረስኩበት በዚያኑ ጥዋት ሲዲሂኬ ካፓን የተባለ በማላያላም ቋንቋ የሚሰራ የ41 ዓመት ጋዜጠኛ ወደ አካባቢው እየመጣ ነበር። ለዘጠኝ ዓመታት ያህል መኖሪያውን በዋና መዲናዋ ዴልሂ ያደረገው ሲዲሂኬ ብሁልጋርሂ መንደር ለመምጣት ያሰበው እንደኔው ተደፍራ የተገደለችውን ሴት ታሪክ ለመዘገብ ነበር። ጉዞው ግን እንደኔው የተቃና አልነበረም። ሃትራስ የሚባለው ሰፈር አካባቢ ለመድረስ 42 ኪሎ ሜትር ሲቀረው እሱና ሦስት ሌሎች ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ። በወቅቱም ወደ ስፍራው ለማምራት በመኪናው ውስጥ ነበሩ። ባለፈው ሳምንትም በእስር ላይ 150ኛ ቀኑን አስቆጥሯል። በቡድን ተደፍራ የተገደለችው ግለሰብ ቤተሰቦች ሲዲሂኬ ካፓን በቁጥጥር በዋለበት በዚያው ምሽት በዱላ ተደብድቧል፣ ፖሊሶች በጥፊ በተደጋጋሚ አጩለውታል እንዲሁም ሙሉ ሌሊቱን በሙሉ ሳይተኛ ጥያቄ ሲጠየቅ እንደነበር ቤተሰቦቹና ጠበቆቹ ይናገራሉ። ጋዜጠኛው የስኳር ህመምተኛ ቢሆንም መድኃኒቱን እንዳይወስድ ተከልክሏል። ፖሊስ በበኩሉ ጋዜጠኛው ላይ የተባለው ነገር አልተፈፀመም ይላል። ፖሊስ እንደሚለው ጋዜጠኛው በቁጥጥር የዋለበት ዋና ምክንያት ወደ ሃትራስ በመሄድ በተለያዩ የማኅበረሰቡ መደቦች መካከል አመፅ ለማነሳሳት አሲሯል በማለት ሲሆን ፖሊስ ሁእርምጃውን ሕግ ማስከበር እንደሆነ አስታውቋል። መኪና ውስጥ አብረውት የነበሩ ሦስት ግለሰቦችም እንዲሁ በተመሳሳይ ተወንጅለዋል። ከሲዲሂኬ ጋር አብረው ሲጓዙ የነበሩት ሦስት ግለሰቦች በኬራላ ግዛት ተቀማጭነቱን ያደረገው ፖፑላር ፍሮንት ኦፍ ኢንዲያ (ፒኤፍአይ) ተብሎ ከሚታወቀው ፅንፈኛ የሙስሊም እንቅስቃሴ ጋር ግንኙነት አለው የሚባል ድርጅት አባል ናቸው ተብለዋል። የኡታር ፕራዴሽ ግዛት ድርጅቱ እንዲታገድ ጥሪ አቅርቧል። ፖሊስ ሲዲሂኬ የተዘጋ ጋዜጣ ላይ እሰራለሁ በማለት አጭበርብሯል በማለት የከሰሰው ሲሆን በዋነኝነት ግን የፒኤፍአይ አባል ነው ይላል። የኬራላ የጋዜጠኞች ማኅበር፣ የጋዜጠኛው ጠበቃ እንዲሁም ፒኤፍአይ በፖሊስ ውንጀላ አይስማሙም። ሲዲሂኬ በአመራር ላይ ያለበት የጋዜጠኞች ማኅበር በበኩሉ የኡታር ፕራዴሽ ፖሊስ "ፍፁም ሐሰተኛ መግለጫ" በማውጣት ከመወንጀሉም በተጨማሪ የጋዜጠኛውን እስር "ሕገ ወጥ ነው" ብሎታል። ማኅበሩ እንደሚለው ሲዲሂኬ ወደ ሃትራስ ያመራው ለዘገባ እንደሆነና ብቸኛ ሥራውም ጋዜጠኝነት እንደሆነ ተናግሯል። ከዚህም በተጨማሪ ከእስር እንዲለቀቅም ለጠቅላይ ፍርድ ቤት የተቃውሞ ፊርማ አስገብቷል። ሲዲሂኬ የሚሰራበት አዝኢምኡካም የተባለው ሚዲያም በበኩሉ ጋዜጠኛው ሠራተኛቸው እንደሆነና ወደ ሃትራስም ያቀናው ለዘገባ ተመድቦ እንደሆነ በመግለጫው አስታውቋል። የሲዲሂኬ ባለቤት ራይሃናት ከልጆቿ ጋር ጋዜጠኛ ሲዲሂኬን እንዲሁም የጋዜጠኞች ማኅበሩን የወከሉት ጠበቃ ዊልስ ማቲውስ ደንበኛቸው ቀለል ባለ ወንጀል መከሰሱንና ዋስትና የማያስከለክል መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። ነገር ግን ግን ጋዜጠኛው በቁጥጥር ስር ከዋለ ከሁለት ቀናት በኋላ ሲዲሂኬ 'አንሎውፉል አክቲቪቲስ ፕሪቨንሺን አክት' ተብሎ በሚጠራው የፀረ-ሽብር ወንጀል ተከሰሰ፤ በዚህም በዋስ መውጣት አይችልም። ጠበቃው በበኩላቸው ደንበኛቸው "መቶ በመቶ ገለልተኛና ነፃ ጋዜጠኛ ነው" ይላሉ። አክለውም "ከግለሰቦች ጋር በአንድ መኪና ውስጥ መሳፈር ጥፋተኛ ሊያስብልህ አይገባም" በማለትም ይከራከራሉ። "አንድ ጋዜጠኛ በተለያየ የህይወት አቅጣጫ ላይ ያሉ ሰዎችን ያገኛል። ይህም በወንጀል የተከሰሱ ግለሰቦችንም ሊያካት ይችላል። የተወነጀሉ ሰዎች ጋር አንድ ላይ መገኘት ሊያሳስር አይገባም" ይላሉ ጠበቃ ዊልስ ማቲውስ። ጋዜጠኛው ከታሰረ ከሳምንታት በኋላ ማንኛውንም ሰው እንዳያገኝ መከልከሉንም የፍርድ ቤት መረጃ ያሳያል። ቤተሰቦቹን ጋር መደወል የቻለው ከታሰረ ከ29 ቀናት በኋላ ነበር። ባለቤቱንም ከሰላሳ ስድስት ቀናት በኋላ ነው በስልክ ማናገር የተፈቀደለት። ጠበቃው ዊልስ ማቲውስ ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የተቃውሞ ፊርማ ካስገቡና ጋዜጠኛው ከታሰረ ከ47 ቀናት በኋላ ነው ማናገር የቻሉት። የሲዲሂኬ ባለቤት ራይሃናት ባለቤቷ በስልክ ደውሎ እስኪያዋራት ድረስ በህይወት መኖሩን እርግጠኛ እንዳልነበረች በስልክ ተናግራለች። በቅርቡ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋዜጠኛው በጠና የታመሙት የ90 አመት እናቱን እንዲጠይቅ በማለት ለአምስት ቀናት ያህል በዋስ እንዲወጣ ፈቅዶለታል። በነዚህ ቀናትም ከኡታር ፕራዴሽ የመጡ ስድስት ፖሊሶችና በበርካታ የፌደራል ፖሊሶች ጥበቃ ስር ነበር። የሲዲሂኬ እናት የጋዜጠኛው የእናቱ ጉብኝት በፍራቻ የተሞላ እንደነበር ባለቤቱ ራይሃናት ትናገራለች። "የእናቱ የጤና ማሽቆልቆልና የእኛም የገንዘብ ሁኔታና የሦስቱ ልጆቹ የወደፊቱ እጣ ፈንታ በጣም ያስጨንቀዋል" ብላለች። ባለቤቷ ምንም ስህተት እንዳልሰራና ኢላማ የሆነውም ሙስሊም በመሆኑ እንደሆነ ትናገራለች። እንደ ራይሃናት ከሆነ ፖሊሶች በተደጋጋሚ ባለቤቷን የበሬ ሥጋ በልቶ እንደሆነ ጠይቀውታል። በሂንዱ እምነት ተከታዮች ዘንድ ላምና በሬ እንደ ቅዱስ እንስሳ ተደርገው የሚታዩ ሲሆን በቅርብ ዓመታትም ሙስሊሞች የበሬ ሥጋ በመብላታቸው እንዲሁም በማጓጓዛቸው ኢላማ ሆነዋል። ከዚህ በተጨማሪም በአገሪቷ ውስጥ አወዛጋቢ የሚባሉት የእስልምና እምነት ሰባኪ የሆኑት ዶክተር ዛኪር ናይክ ጋር ምን ያህል ጊዜ ተገናኝቶ እንደሆነም በተደጋጋሚ በፖሊሶች መጠየቁን ባለቤቱ ትናገራለች። ሰባኪው ዶክተር ዛኪር ናይክ መኖሪያቸውን በግዞት በማሌዥያ ያደረጉ ሲሆን በጥላቻ ንግግርና ሕገ ወጥ ገንዘብ ዝውውር ተከሰዋል። ሰባኪው ግን ይህንን አይቀበሉትም። ጋዜጠኛው የእስልምና እምነት ተከታዮች ዳሊት ከሚባሉት ዝቅተኛ የደረጃ መደብ ላይ ከሚቀመጡት ማኅበረሰብ ጋር ለምን ጥብቅ ግንኙነት እንዳለቸው በተደጋጋሚ ፖሊሶች መጠየቃቸውንም ባለቤቱ ጠቅሳለች። ዳሊት የሚባሉት ማኅበረሰብ በቀድሞው የማይነኩ (አንተቼብልስ) ተብለው የሚጠሩ ናቸው። በጠቅላይ ፍርድ ቤት ውስጥ ከፍተኛ ጠበቃ የሆነው አብሂላሽ ኤምአር እንደነገረኝ ከሆነ "የሲዲሂኬ ካፓን እስር ከፀረ- እስልምና ጋር የተገናኘ ነው የሚሉትን እቀበለዋለሁ" ይላል። አብሂላሽ የጋዜጠኛውን እስር በቅርብ እየተከታተለው ሲሆን ሁኔታውንም ፖለቲካዊ ጥቃት ይለዋል። አክሎም "የጋዜጠኛው መሰረታዊ መብቶች ተጥሰዋል" በማለትም ይከራከራል። በርካታ ተችዎች የኡታር ፕራዴሽን አስተዳደርም እያወገዙ ይገኛሉ። በተለይም የእስልምና እምነት ተከታዮችን ኢላማ በማድረግና አወዛጋቢ በሆነው የሂንዱ መነኩሴ ዮጊ አዲትያናት አመራር ጋር በተያያዘ ግዛቲቷ ከፍተኛ ትችቶችን እያስተናገደች ትገኛለች። ዮጊ አዲትያናት በሕንድ ውስጥ በከፋፋይና ፀብ አጫሪ ፖለቲከኛነቱ የሚታወቅ ሲሆን በተለይም በምርጫ ቅስቀሳው ወቅት ፀረ-እስልምና ሁኔታዎችን በማነሳሳት ይወቀሳሉ። የእሳቸው አስተዳደርም ሆነ የአካባቢው የፖሊስ ኃይል በደቦ ተደፍራ የተገደለችው ግለሰብ ጋር በተገናኘ ዓለም አቀፍ ውግዘትን አስተናግደዋል። በተለይም ባለስልጣናቱ የቤተሰቧን ፍቃድ ሳያገኙና ሚዲያውን አርቀው በሌሊት ግለሰቧን መቅበራቸው በርካታ ጥያቄዎችን አጭሯል። የግለሰቧን ተደፍሮ መገደል ለመቃመወም የወጡ ሰዎችን ፖሊሶች ሲደበድቡ የግለሰቧን መሞት ተከትሎ በነበሩ ቀናት መላውን ሕንድ ያናወጡ በርካታ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል። በኡታር ፕራዴሽ ግዛት የፀጥታ ኃይሎች የጥቃት ሰለባ የሆነችውን ግለሰብ ቤተሰቦች ለማፅናናት የሚሄዱ ሰልፈኞችን መደብደባቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ውግዘትን አስተናግደዋል። በፖሊስ ከተጎሸሙት መካከልም የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ይገኙበታል ተብሏል። እኔና ጋዜጠኛ ሲዲሂኬ ወደ አካባቢው ከማምራታችን ከአንድ ቀን በፊት የግዛቲቷ አስተዳዳሪ ዮጊ አዲትያናት የግዛቲቷን ስም ለማጠልሸት ዓለም አቀፋዊ የሆነ ሴራ እየተካሄደ ነው ብለዋል። ይሄንንም ሁኔታ በግዛቲቷ ብልፅግና የተናደዱ ሰዎች እየተጠቀሙበት ነው ብለዋል። የጋዜጠኛው እስር በርካታ የነፃነት ታጋዮችን ስጋት ውስጥ ጥሏቸዋል። ሕንድ ለጋዜጠኞች የምታሰጋ አገር ሆናለችም እያሉ ነው። ባለፈው ዓመት የጋዜጠኞችን ሁኔታ በሚገመግመው የወርልድ ፕሬስ ፍሪደም ኢንዴክስ የሰንጠረዥ ደረጃ ከ180 አገራት መካከል 142 ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ይህንን ዓመታዊ ሪፖርት የሚያዘጋጀው ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን ካለፈው ዓመት ሁለት ደረጃ እንደወረደችም አስታውቋል። በያዝነው ዓመት የካቲት ወር ላይ በዴልሂ የተደረገውን የአርሶ አደሮች አመፅ የዘገቡ ስምንት ጋዜጠኞች ላይ የወንጀል ክስ ተመስርቷል። በተለይም ይህ ሁኔታ በሴት ጋዜጠኞችና በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ የሚፀና ሲሆን በማኅበራዊ ሚዲያዎችም ላይ ከፍተኛ ውርጅብኝን ያስተናግዳሉ። አብሂላሽ እንደሚለው ፖሊስ በጋዜጠኛ ሲዲሂኬ ላይ ምንም አይነት መረጃ ማቅረብ አለመቻሉን ነው። ነገር ግን የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ጠበቃ እንደሚለው የአካባቢው ባለስልጣናት የተሳካላቸው ነገር ቢኖር ወደ ሃትራስ ሄደው ዘገባ መስራት የሚፈልጉ ጋዜጠኞችን ማስጠንቀቂያ እንዲደርሳቸው ሆኗል፤ ወደ ቦታው ከመሄድም ከልክሏቸዋል። የሲዲሂኬ ጠበቃ በበኩላቸው "የጋዜጠኛ እስር ከሌላ ሰው እስር ጋር ይለያያል" ይላሉ "ምክንያቱም ሚዲያን ዝም ማሰኘት ማለት የዲሞክራሲ መጨረሻ ነው" ብለዋል።
news-56442845
https://www.bbc.com/amharic/news-56442845
ኮሮናቫይረስ፡ በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ጽኑ ህሙማንን የሚከታተሉ ሐኪሞች ስጋትና ጭንቀት
በኢትዮጵያ ውስጥ የኮሮናቫይረስ መገኘቱ ከታወቀ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ቀን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸውን የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ገለጸ።
ትናንት ሐሙስ በተደረገ ምርመራ በኢትዮጵያ በአንድ ቀን ከፍተኛው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች አሃዝ ተመዝግቧል። በዚህም ምርመራ ከተደረገላቸው 8,055 ሰዎች መካከል በሽታው በ2,057 ሰዎች ላይ መገኘቱን ኢኒስቲቲዩቱ ያወጣው መረጃ አመልክቷል። ይህ ማለት ከተመረመሩት 100 ግለሰቦች ውስጥ 26 ወይም 25.5 በመቶው የኮቪድ-19 ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል በማለት "በማኅበረሰብ አቀፍ የምርመራ ዘመቻ ወቅት እንኳን ይህን ያህል ከፍተኛ ቁጥር አልተመዘገበም" ብሏል። ከዚህ በተጨማሪም በኮቪድ-19 ክፉኛ ታመው በጽኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ክትትል የሚደረግላቸው ሰዎች ቁጥርም ከዚህ በፊት ከተመዘገበው በበለጠ ከፍተኛው ቁጥር ላይ ደርሷል። በዚህም ሐሙስ ዕለት 600 ሰዎች በጽኑ የታመሙ ሰዎች እንዳሉ ተገልጿል። ከሰሞኑ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ "በአስደንጋጭ ሁኔታ" እየጨመረ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር እና የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት የሰጧቸው መግለጫዎች ያመለክታሉ። ቢሆንም ግን ወረርሽኙ እየፈጠረ ያለውን ከባድ አደጋ ከግንዛቤ በማስገባት ተገቢውን የመከላከያ ጥንቃቄ "ከማድረግ ይልቅ መዘናጋት በሰፊው እንደሚታይ" ቢቢሲ ያናገራቸው የሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። በርካታ ቁጥር ያለው ሕዝብ የተሳተፈባቸው የተለያዩ ስብሰባዎችና ዝግጅቶችን የታዘቡት የጤና ባለሙያዎች ችግሩ ሕብረተሰቡ ጋር ብቻ ሳይሆን መንግሥት የጤና ሚኒስቴር የሚያስቀምጣቸውን የኮሮናቫይረስ መከላከያ መመሪያዎች "ለማስፈፀም ተነሳሽነት ይጎድለዋል" አስብሏቸዋል። ይህንንም ተከትሎ ከጊዜ ወደ ጊዜ የበሽታው መስፋፋት እጨመረ ባለፉት ሳምንታት ውስጥ በወረርሽኙ የሚያዙ፣ በጽኑ የሚታመሙና ለህልፈት የሚዳረጉ ሰዎች ቁጥር አሳሳቢ ደረጃ ላይ ከመድረሱ ባሻገር የጤና ተቋማት ህሙማንን ለማስተናገድ ፈተና እየገጠማቸው ነው። በዚህም ሳቢያ በመላው አገሪቱ በጽኑ ለታመሙ ሰዎች አጅጉን አስፈላጊ የሆኑት የኦክስጅንና የሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ (ቬንትሌተር) እጥረት በመከሰቱ በርካታ የኮቪድ-19 ታማሚዎች ህይታቸውን እንዲያጡ ሊያደርግ እንደሚችል ስጋት ፈጥሯል። "በአንድ ጊዜ በርካታ ኦክስጅን የሚፈልጉ ህሙማን ወደ ህክምና ተቋማት ይመጣሉ" የሚሉት ዶ/ር ብሩክ አለማየሁ ኦክስጂን ባለመኖሩ ብቻ ህሙማን ወደ ቤታቸው ለመመለስ የሚገደዱበት ጊዜ ላይ መደረሱን ይናገራል። "በርካታ ሰዎች በግላቸው የኦክስጂን ሲሊንደር እየገዙ ወደ ቤታቸው እየገቡ ነው" በማለት፣ ሆስፒታል አልጋ ይዘው የሚታከሙም ቢሆኑ የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ ለማግኘት ረዥም ወረፋ እንደሚጠብቁ ይገልጻሉ። በኮቪድ-19 ተይዘው በቤታቸው ውስጥ እራሳቸውን ለይተው እንዲቆዩ ከሚደረጉት ባሻገር ወደ ህክምና ተቋማት የሚመጡ ህሙማንን የመቀበል አቅማቸው እየተሟጠጠ መሆኑንም አልሸሸጉም። በኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል የኮቪድ-19 ህክምና ማዕከል የጽኑ ህክምና ክፍል ኃላፊ ዶክተር ህሩይ አርዓያ ለፋና እንደተናገሩት ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ወደ ማዕከሉ የሚመጡ የቫይረሱ ታማሚዎች ቁጥር እንዲሁም ወደ ጽኑ ህክምና ክፍል የሚገቡ ታካሚዎች ቁጥር እያሻቀበ ነው ብለዋል። የሚሊኒየም ኮቪድ-19 ህክምና ማዕከል ዳይሬክተር ዶክተር ውለታው ጫኔ ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት ወደ ማዕከላቸው ከሚመጡ ሕሙማን መካከል ከ75 በመቶ በላይ ኦክስጅን የሚፈልጉ መሆናቸውን ተናግረዋል። በማዕከሉ የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ ድጋፍ የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር መበርከቱን ገልፀው "በመካኒካል ቬንትሌተር እጥረት ምክንያት የማንቀበላቸው ህሙማን ይኖራሉ" ብለዋል። ዶ/ር ውለታው ጨምረውም የኦክስጅን እጥረት ስለገጠማቸው ድጋፉን ፈልገው የሚመጡ ሁሉንም ጽኑ ህሙማን ማስተናገድ አለመቻላቸውን ገልፀዋል። የጽኑ ህሙማን ቁጥር እየጨመረ ነው ዶ/ር ብሩክ ዓለማየሁ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ካለፉት ሁለት ወራት ወዲህ መጨመር እያሳየ መምጣቱን እነዳስተዋሉ የጠቆሙ ሲሆን፤ ዶ/ር ውለታው ጫኔም በበኩላቸው በተለይ ባለፉት ሁለትና ሦስት ሳምንታት በኮቪድ-19 በጠና ታምመው ወደ ማዕከላቸው የሚመጡ ሰዎች በመርከቱን ተናግረዋል። በየተቋማቱ ለህሙማን አልጋ በመጥፋቱ አስቸጋሪ ሁኔታ መፈጠሩን የሚናገሩት ዶ/ር ብሩክ፣ ይህም በህክምና ባለሙያዎች ላይ ጫና መፍጠሩን አስረድተዋል። እርሳቸው እንደሚሉት ኮቪድ-19 የተያዙ ሕሙማን እየበዙ በመምጣታቸው በሌላ የሕክምና ክፍል ያሉ አልጋዎችን እስከ መሻማት ተደርሷል። ዶ/ር ብሩክ በሚሰሩበት ህክምና ተቋም ከዚህ በፊት አንድ ታካሚ በኮቪድ-19 ተይዞ ኦክስጂን ባያስፈልገው እንኳን ተኝቶ ህክምና እንዲያገኝ ይደረግ እንደነበር አስታውሰው፣ በአሁኑ ወቅት ግን አስተኝቶ ለማከም ህሙማኑ ኦክስጅን የሚያስፈልጋቸው መሆን አለመሆኑ ይወስነዋል ይላሉ። "አሁን የምናስተኛቸው ታካሚዎች በሙሉ ኦክስጂን ፈላጊዎች ናቸው።" እንደ ዶ/ር ብሩክ ከሆነ ሁሉም ተኝተው የሚታከሙ ሰዎች ኦክስጂን የሚፈልጉ መሆናቸውን ገልጸው፤ በአሁኑ ጊዜም የኦክስጂን ድጋፍ የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል ብለዋል። ይህንን ሲያብራሩም በአሁኑ ጊዜ ተኝተው የሚታከሙ ህሙማን በሙሉ ኦክስጅን ፈላጊ ሲሆኑ የሚፈልጉት የኦክስጅን መጠን ከፍተኛ መሆኑን አመልክተዋል። "ከአምስት እና ከአስር ሊትር በላይ መጠን ያለው ኦክስጂን፣ የመተንፈሻ መሳሪያ ድጋፍ የሚፈልጉ ህሙማን ቁጥር ጨምሯል።" ይህ የግብአት እጥረት በተወሰኑ ተቋማት ላይ ብቻ የታየ ሳይሆን ዶ/ር ብሩክ እንደሚሉት የኮቪድ-19 ህሙማንን በተለይ በሚያክሙት በሚሌኒየም እና ኤካ ኮተቤ ሆስፒታሎች ጭምር እንደሚስተዋል ከባልደረቦቻቸው ተረድተዋል። በተጨማሪም በግል ሆስፒታሎች የረር፣ ቤተዛታ፣ ሃሌሉያ የሚሰሩ ባለሙያዎችም ተመሳሳይ ነገሮችን ማስተዋላቸውን እንደነገሯቸው ይጠቅሳሉ። ዶ/ር ብሩክ እርሳቸው የሚሰሩበት ተቋም ከፍተኛ የኦክስጂን ተጠቃሚ ህሙማንን መቀበል የማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱንም ይናገራሉ። ይህ የኦክስጂን እጥረት በአዲስ አበባ እና በክልል በሚገኙ ሆስፒታሎች እንደሚስተዋል የሚናገሩት ዶ/ር ብሩክ፣ ችግሩን ለመቅረፍ የጤና ሚኒስቴር የተለያዩ እርምጃዎችን ለመውሰድ እንቅስቀሴ እያደረገ መሆኑን እንደሚያውቁ አስረድተዋል። ዶ/ር ብሩክ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመቀነስ ከተቀመጡ መመሪያዎች ሁሉ ቢያንስ ቢያንስ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አጠቃቀምን መጨመር በወረርሽኙ ስርጭት ላይ ከፍተኛ ለውጥ እንደሚያመጣ ይመክራሉ። የበሽታው መስፋፋት ከዚህም በላይ እንዳይጨምር በግለሰብ ደረጃ የመከላከያ እርምጃዎችን ከመውሰድ ባሻገር በርካታ ሰዎች የሚሰበሰቡባቸውን ዝግጅቶችና ሥነ ሥርዓቶችን በተመለከተ የተቀመጡ መመሪያዎችን አጠናክሮ ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ነው ሲሉ አሳስበዋል። አዲስ የኮቪድ-19 ዝርያ ተከስቶ ይሆን? ዶ/ር ብሩክ በሚሰሩበት እና በሌሎች የኮቪድ-19 ህክምና በሚሰጥባቸው ተቋማት የሚሰሩ ባልደረቦቹ ለኮሮናቫይረስ ታማሚዎች መጨመር አንዱ ምክንያት የጥንቃቄ ጉድለትና መዘናጋት ነው ይላሉ። በዚህ ወቅት እንዲህ በሽታው እንዲንሰራፋ ያደረገው ሌላም ምክንያት ሊኖር እንደሚችል ጥርጣሬ አላቸው። "ደቡብ አፍሪካ እና ኬንያ ውስጥ እንደተደረገው በቫይረሱ ላይ ጥናት ቢደረግ አዲስ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ሊኖር ይችላል" ሲሉ ይሰጋሉ። ይህንንም ሲያስረዱ መጀመሪያ ላይ በኮቪድ-19 ተይዘው እና ታመው ወደ ህክምና ተቋማት ከሚመጣ ሰዎች መካከል ህመሙ የሚጠናባቸው በጣም አነስተኛ ቁጥር ያላቸው እንደነበሩ ይጠቅሳሉ። በተጨማሪም በአንድ ቤተሰብ ውስጥ አንድ ሰው ታሞ ሌሎች የቤተሰብ አባላት ሳይታመሙ ይገኙ እንደነበርም አስታውሰው፤ ምልክት የማያሳዩ ህሙማን ቁጥርም በርካታ እንደነበሩ ጠቅሰዋል። አሁን ግን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች መታመማቸው፣ በእድሜም ሲታይ በርካታ ወጣቶች በበሽታው መያዛቸውና ወደ ህክምና ተቋማት መጥተው አልጋ መያዛቸውን ማስተዋላቸውን ይናገራሉ። ከዚህ በፊት በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቢኖሩም በሚሰጣቸው ህክምና በፍጥነት የማገገም ይታይባቸው እንደነበር የገለጹት ዶ/ር ብሩክ፣ በዚያን ወቅት አልጋ ይዘው የሚቆዩ ሰዎች ቁጥር በጣም አነስተኛ ነበር ይላሉ። በአሁኑ ጊዜ የቫይረሱ የመተላለፍ አቅም እና የመግደል አቅሙ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው "በእርግጥ ጥናት ያስፈልገዋል፤ በእኔ እይታ አዲስ ዓይነት የቫይረስ ዝርያ ሳይሆን አይቀርም የሚል ግምት አለኝ" ብለዋል። ጨምረውም በዚህ ወቅት ከአንድ ቤተሰብ ሁለት ሦስት ሰው የሚታመምበት እና አልጋ የሚይዝበት አጋጣሚ ተደጋጋሚ መሆኑን ዶ/ር ብሩክ ዓለማየሁ ይናገራሉ። ለበሽታው እንዲህ በአሳሳቢ ሆኔታ መስፋፋት ሁሉም ሰው ማድረግ ያለበት የመከላከያ ጥንቃቄን አለመተግበር መሆኑን ዶ/ር ውለታው ጫኔ እና ዶ/ር ብሩክ ዓለማየሁ የሚስማሙበት ጉዳይ ነው። በአዲስ የወረርሽኙ ዝርያ ተከስቶ ሊሆን ይችላል የሚለው የዶ/ር ብሩክ ጥርጣሬ እነዳለ ሆኖ፤ ሁለቱም የህክምና ባለሙያዎች እዚህ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ ተገቢው ምርመራ መደረግ እንዳለበት ይናገራሉ።
news-48970216
https://www.bbc.com/amharic/news-48970216
"የመጀመሪያውን ድራማ አንተ፤ ሁለተኛውን እኔ እፅፈዋለሁ" ኤርሚያስ አመልጋ
በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ 'የማይሰበረው' የተሰኘና በአቶ ኤርሚያስ አመልጋ ሕይወት ዙሪያ የሚያጠነጥን መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል። በአቶ ኤርሚያስ ከአገር መሰደድና በተደጋጋሚ መታሰር በመቋረጡ የመጽሐፉ ዝግጅት ሰባት ዓመታትን ፈጅቷል። ስለ መጽሐፉ ዝግጅትና በመጨረሻ እንዴት ለህትመት እንደበቃ ጸሐፊውን አቶ አንተነህ ይግዛውን አነጋግረነዋል። መፅሃፉን የማዘጋጀት ሃሳብ ከማን ነው የመጣው መጀመሪያ?
አቶ አንተነህ፡ ሃሳቡ የመጣው ከአቶ ኤርሚያስ ነው። የቀድሞ የሥራ ባልደረባዬ በነበሩ ሰው የሕይወት ታሪካቸውን ማፃፍ እንደሚፈልጉ ነገሩኝ። ይህ የሆነው 2003 ዓ. ም መጨረሻ ወይም 2004 ዓ. ም መጀመሪያ ላይ ይመስለኛል። ከዚያ የመረጃ ስብሰባ፣ መረጃ ማደራጀት እና ቃለ መጠይቅ የሚደረግላቸው በርካታ ሰዎች ነበሩ፤ እንደገና ድምፁን ገልብጦ ወደ መጽሐፍ ስክሪፕት የመቀየር ሥራዎች ተሠሩ። 2005 ዓ. ም ወይም 2006 ዓ. ም አካባቢ ተጠናቀቀ። ግን ሥራው ወዲያው ተቋረጠ። • መጽሐፍ ቅዱስን መጀመሪያ ወደ ኦሮምኛ የተረጎሙት ኦኒስሞስ ነሲብ ማን ናቸው? ለምን ነበር የተቋረጠው? አቶ አንተነህ፡ የመጀመሪያውን ረቂቅ እያዘጋጀን እያለ አቶ ኤርሚያስ ከአክሰስ ሪል እስቴት ችግር ጋር በተያያዘ አገር ጥለው ወጡ። አቶ ኤርሚያስ የአክሰስ ሪል እስቴትን ችግር እፈታለሁ ብሎ ከመንግሥት ጋር በተደረገ ድርድር ከሁለት ዓመት የዱባይና አሜሪካ ቆይታ ሲመለስ መጽሐፉን ለምን አንቀጥለውም የሚል ሃሳብ አነሳልኝና እንደገና ቀጠልን። ምክንያቱም የአክሰስን ቀውስ ያላካተተ መጽሐፍ የኤርምያስ ታሪክ አይሆንምና፤ በቆይታህ ምን ስታደርግ ነበር? እንዴትስ መጣህ? እና ከመጣህስ ምን አደረግክ? የሚሉት ነገሮች ላይ እንደገና ቃለ መጠይቅ አድርጎ ወደ መጽሐፍ መቀየር ያስፈልግ ነበር። ያን ጨርሰን ወደ መጨረሻ የዲዛይን ሥራ ልንገባ ስንል ደግሞ ከዚሁ ከአክሰስ ችግር ጋር በተያያዘ አቶ ኤርሚያስ ማዕከላዊ ታሰረ። ለሁለተኛ ጊዜ መጽሐፉ ተቋረጠ። አልቆ ከነበረ አቶ ኤርሚያስ እስር ቤት ቢገባም መጽሐፉን ማውጣት አይቻልም ነበር? አቶ አንተነህ፡ እሱን ማግኘት አልችልም ነበር ምክንያቱም ከአባቱ፣ ባለቤቱና እህቱ ውጭ ማንንም ማግኘት አልተፈቀደለትም ነበር። በቃ ይህንን ታሪክ እንድንጀምር እንጂ እንድንቀጥል አልተፈቀደልንም አልኩና ተውኩት። ከዚያ እንዴት እንደገና ሥራው ተጀመረ? አቶ አንተነህ፡ እንደገና ሲፈታ አቶ ኤርሚያስ ደወለልኝ። ደውሎ ምን ነበር ያለህ? አቶ አንተነህ፡ [ይሄን መጽሐፍ እንደገና መቀጠል አለብን ታሪኩ እየጦፈ ወደ ክላይማክሱ እየሄደ ነው] አለኝ። እስር ቤት ከነማን ጋር እንደነበር፣ ምን ያደርግ እንደነበር? አፈታቱስ እንዴት ነበር? የሚለውን ደግሞ አዲስ ምዕራፍ ጨምረን ሥራ ጀመርን። አሁንም ሥራችንን እያጠናቀቅን እያለ ከኢምፔሪያል ሆቴል ሽያጭ ጋር በተያያዘ አቶ ኤርሚያስ እንደገና ታሰረ። ነገሩ ለኔ በጣም አስደንጋጭ ነበር። 2004 ዓ. ም ገደማ የተጀመረ መጽሐፍ ለሦስተኛ ጊዜ መቋረጡ በመሆኑ ተስፋ ቆረጥኩ። • "ኢህአዴግ ነፃ ገበያም፣ ነፃ ፖለቲካም አላካሄደም" ፀደቀ ይሁኔ (ኢንጂነር ) በመጨረሻ መጽሐፉ አሁን እንዴት ለህትመት በቃ? አቶ አንተነህ፡ አንድ ቀን ኤርሚያስ ከሚገኝበት ቂሊንጦ እስር ቤት አስጠራኝ። [እንግዲህ አንተ ይሄን መጽሐፍ እዚህ አድርሰኸዋል] አለኝ። እኔ የፃፍኩት ከማዕከላዊ እስከተፈታበት ምሽት ድረስ ያለውን ነበር። [ከዚህ በኋላ ቂሊንጦ ከገባሁ በኋላ ያለውን እኔ ራሴ እፅፈዋለሁ። አንተ የፃፍከው ይታተም] አለኝ። በዘህ ተስማምተን መጽሐፉ ወደ ህትመት ገባ። አሁን አቶ ኤርሚያስ የቂልንጦ ቆይታውን እየፃፈ ነው? አቶ አንተነህ፡ አሁን ቂሊንጦ ስለተገኘበት የሜቴክ/የኢምፔሪያል ሆቴል ሽያጭ ክስ ጉዳይ እዚያው ቂሊንጦ ሆኖ የሠራቸው ወደ አስር የሚሆኑ የጥናት ፅሁፎች 'ኢትዮጵያ አት ኤ ቲፒንግ ፖይንት' [Ethiopia at a Tipping Point] በሚል ርዕስ ታትመው አማዞን ላይ ወጥቷል። ከሁለት ከሦስት ሳምንት በኋላ ደግሞ ኢትዮጵያ ይገባል። ይኸው ፅሁፍ እንደገና በአማርኛ 'ኢትዮጵያ በመስቀለኛ መንገድ ላይ' በሚል ርዕስ ተተርጉሞ ለገበያ ይቀርባል። አሁን ቂሊንጦ የሚገኘው አቶ ኤርሚያስ ለንባብ የበቃው 'የማይሰበረው'ን ከመታተሙ በፊት አንብቦታል? አቶ አንተነህ፡ እስር ቤት እየገባ ኤዲት ተደርጓል፤ አምስት ጊዜ አይቶታል። ጠበቃውን ጨምሮ ኤርሚያስን እንዲያዩ ከተፈቀደላቸው ሰዎች መካከል አንዱ እኔ ስለሆንኩኝ እኔም እየገባሁ እያሳየሁት እያነበበው እየተስተካከለ ነው የሠራነው። መጽሐፉ ለምን አሁን ታተመ? አቶ ኤርሚያስ እስር ላይ ስለሆነ ተፅእኖ ለመፍጠር ነው? አቶ አንተነህ፡ መጽሐፉ ሦስት ጊዜ ተቋርጧል። በዚህ ሳይሆን በሌላ ርዕስ ዲዛይን ተደርጎም ነበር አንድ ጊዜ። ግን በተደጋጋሚ መታሰር መፈታቱና አጠቃላይ ርዕሱንም የታሪኩንም ትኩረት እንዳስተካክል የሚያስገድዱ ሁኔታዎች መጡብኝ። ከአራት ከአምስት ዓመታት በፊት ሊታተም የነበረ መጽሐፍ ነው። አሁን ምንም አይነት ተፅእኖ ለመፍጠር አይደለም። በነገራችን ላይ አሁንም ላሳትመው አልፈለግኩም ነበር። ታዲያ እንዴት ታተመ? አቶ አንተነህ፡ በኤርሚያስ ግፊት። [አሁን መታተም አለበት ከዚህ በኋላ የምጠብቀው ጊዜ የለኝም። የመጀመሪያውን ክፍል ድራማ አንተ ፃፈው ሁለተኛውን እኔ እፅፈዋለሁ] ስላለኝ። በመጽሐፉ ድህረ ታሪክ ገፅ ላይ እኔ ያሰፈርኩት ነገር የነበረውን ሁኔታ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የመጽሐፉ አሳታሚ ማን ነው? አቶ አንተነህ፡ ኤርሚያስ አመልጋ ስንት ኮፒ ታተመ? ምን ያህል ብርስ ፈጀ? አቶ አንተነህ፡ አስር ሺህ ኮፒ ነው የታተመው፤ ግን ስለ ወጪ እና ገቢ አሁን መናገር ይቸግረኛል። • ዕድሜ ጠገቧ የጥድ መፃሕፍት ቤት መደብር ትውስታ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ብዙዎች 'የማይሰበረው' እያሉ እየፃፉ መጽሐፉን ለማስተዋወቅ የተሞከረበት መንገድ ለየት ያለ ነበር። የማን ሃሳብ ነው? አቶ አንተነህ፡ የኔ ሀሳብ አይደለም። ከዚህ በፊት በአንዲት ደራሲ ጓደኛዬ ሃሳብ የአዳም ረታን 'መረቅ' በዚህ መልኩ ለማስተዋወቅ ተሞክሯል። ለአዳም ረታ ሥራዎች የተለየ ቦታ በምንሰጥ ሰዎችና አድናቂዎቹ። እና ከዚያ ልምድ በመነሳት የተደረገ ነው። ፌስቡክ ገፅህ ላይ እንዳሰፈርከው በአጠቃላይ መጽሐፉ ሰባት አመት ፈጅቶብሃል? አቶ አንተነህ፡ አዎ ሰባት አመት ገደማ፤ በተደጋጋሚ በመቋረጡ። ይህን መጽሐፍ በማዘጋጀት ሂደት እንደ ፀሃፊ ለኔ ትልቁ ፈተና ከኤርሚያስ የሕይወት ፍጥነት ጋር እኩል መራመድ ነበር። የሱ ሕይወት ሁሌም በአዳዲስ ስኬትና ውድቀት የተሞላ ስለሆነ፤ መሰደድ መታሰር ነው። ሠራሁት ብለሽ ስጨርሽ ሌላ ታሪክ ጨምሮ ይጠብቅሻል። ለዚህ እንጂ የመፃፍ ጉዳይ ጊዜ የሚወስድ ሆኖ አይደለም።
48306036
https://www.bbc.com/amharic/48306036
የቦይንግ 737 ማክስ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን?
በመጨረሻዋ ሰዓት አብራሪዎቹ ማድረግ የሚችሉት ምንም ነገር አልነበረም። በአብራሪዎቹ ክፍል ውስጥ የአደጋ ጊዜ ድምጽ ሲሰማ ዋና አብራሪውና ምክትሉ አውሮፕላኑን ለመቆጣጠር ታግለዋል።
ልክ ወደ ምድር በፍጥነት ማስቆልቆል ሲጀምሩ ካፕቴን ያሬድ ጌታቸው በአየር ላይ ለመንሳፈፍ ሙከራ አደረገ። ነገር ግን ካፕቴን ያሬድ ይህንን በሚያደርግበት ሰዓት ኤምካስ የተባለውና አውሮፕላኑን በከፍተኛ ሁኔታ ወደላይ እንዳይወጣ ወይም ወደታች እንዳያሽቆለቁል ለመቆጣጠር ተብሎ የተሰራው ሥርዓት ይህንን ከማድረግ ገታው። አውሮፕላኑም ወደታች ማሽቆልቆሉን ቀጠለ። • አደጋው የደረሰበት ቦይንግ 737 የገጠመው ምን ነበር ? በዚህ ሁሉ ጭንቀት ካፕቴን ያሬድና ረዳቱ አህመድኑር ሞሃመድ መፍትሄ ለማግኘት መታገላቸውን አላቆሙም ነበር። በዚህ ጊዜ አውሮፕላኑ ሙሉ በሙሉ እራሱን በራሱ እያበረረ ነበር። ካፕቴን ያሬድና ረዳቱ የበረራ ቁጥጥሩን በእነሱ እጅ ለማድረግ ከባድ አካላዊ ትግል ማድረግ ነበረባቸው። ሁለቱም የሚችሉትን ያህል ቢሞክሩም ሳይሳካላቸው ቀረ። ሁሉም ነገር ከቁጥጥር ውጪ ሲሆን ግን አውሮፕላኑ ለበረራ በተነሳ በስድስት ደቂቃዎች ውስጥ በሰዓት 500 ሜትር እየተምዘገዘገ ወደ ምድር ተወረወረ። 149 መንገደኞችንና 8 የበረራ ሰራተኞችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረው ET 302 ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ሲከሰከስ የ35 ሃገራት ዜግነት ያላቸው ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። ከእነዚህ መካከል 32 ኬንያዊያን፣ 18 ካናዳዊያን፣ 18 ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፕሮቶኮል ሻሀድ አብዲሻኩርን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሰራተኞች ይገኙበታል። • ሁለቱን የአውሮፕላን አደጋዎች የሚያመሳስላቸው ነገር አለ ከአደጋው አምስት ወራት በፊት በኢንዶኔዢያው አውሮፕላን ላይ የደረሰውን አደጋ ለማወቅ በተደረገው የምስለ በረራ ሙከራ ላይ እንደተደረሰበት አውሮፕላኑ ቁልቁል በአፍንጫው ባህር ላይ ሊከሰከስ መሆኑን ያወቁት ከ40 ሰከንዶች ያነሰ ጊዜ ሲቀራቸው መሆኑን ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል። የኢንዶኔዢያው አውሮፕላን እ.ኤ.አ ኦክቶበር 26 ድረስ ብቻ ስድስት ያህል ችግሮች ገጥመውት ነበር። እነዚህ የገጠሙት ችግሮች በአየር ላይ እያለ ያለውን ፍጥነትና የከፍታ መረጃውን ያካትታሉ። አውሮፕላኑ ከክንፎቹ እና በአየር ፍሰቱ መካከል ያለውን አቅጣጫ የሚለካውም ችግር ገጥሞት ነበር። አደጋው ከመድረሱ በፊት በነበረው በረራ አብራሪው አስቸጋሪ ሁኔታ ገጥሞት እንደነበር የሚያሳይ ምልክት ልኳል። የኢንዶኔዢያ አውሮፕላን የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት እንደሚያሳየው አውሮፕላኑ አፍንጫው የመደፈቅ ሁኔታ ሲገጥመው የማስጠንቀቂያ መልዕክት የሚያሳው መሳሪያ በበረራው ጊዜ በሙሉ በርቶ ነበር። በአደጋውም 198 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። የአውሮፕላኖቹን ወደ ላይ የመውጣትና የመውረድ ፍጥነት ንባብ እንደሚያመለክተው ሁለቱም አውሮፕላኖች ከፍና ዝቅ እያሉ እንደነበሩና አብራሪዎቹም ይህንን በመቆጣጠር አውሮፕላኖቹ ከፍ ብለው እንዲበሩ ጥረት ሲያደርጉ ነበር። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላኑ ዋና አብራሪ ያሬድ ጌታቸው ችሎታን በተመለከተ አብራሪው ከ8 ሺህ ሰዓታት በላይ የማብረር ልምድ እንዳለው በመጥቀስ "የሚያስመሰግን ብቃት" እንዳለው መስክሮለታል። አደጋው በደረሰበት ዕለትም አብራሪው ያሬድ ጌታቸው ችግር እንደገጠመውና ተመልሶ ለማረፍ ለበረራ ተቆጣጣሪዎች መልዕክት አስተላልፎ ነበር። ከኢትዮጵያ፣ ከአሜሪካ፣ ከፈረንሳይ እና ከአውሮፓ የአየር ትራንስፖርት ባለስልጣን አጣሪ ባለሙያዎች በተሳተፉበት ምርመራ የመጀመሪያ ዙር ውጤት አውሮፕላኑ ለበራ ሲነሳ በትክክለኛ መስመር ለመብረር በሚያስችለው ሁኔታ እንደነበር የገለጸ ሲሆን አብራሪዎቹም አውሮፕላኑን ለመቆጣጠር ያስችላል የተባለውን ቅደም ተከተል ተግባራዊ ማደረጋቸውን አረጋግጧል። በአውሮፓውያኑ 2015 ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖችን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያስመርቅ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞች ተገኝተው ደስታቸውን ገልጸቀው ነበር። በወቅቱም አውሮፕላኑ እጅግ የተራቀቀና ሁሉም አየር መንገዶች የሚፈልጉት ነበር። በዓለማችን ላይም ተወዳጁና ተፈላጊው አውሮፕላን ሆኖ ነበር። የኢቲ በረራ ቁጥር 302 አውሮፕላን ከተከሰከሰ በኋላ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት መውጣቱን ተከትሎ ቦይንግ በአደጋው ምክንያት ለጠፋው የሰው ህይወት ሃዘኑን በመግለጽ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት እንዳሳየው እንደ ከዚህ ቀደሙ ኤምካስ የተሰኘው ሶፍትዌር በተሳሳተ መረጃ 'አክቲቬትድ' (ሥራውን መጀሩን) ምክንያት መሆኑን ገልጿል። • 'መጥፎ ዕድል' አውሮፕላኑ የወደቀበት ስፍራ ስያሜ እንደሆነ ያውቃሉ? "አደጋን ሊያስከትል የሚችል ሁኔታን የመቅረፍ ሥራ የእኛ ነው። አውሮፕላኑ የእኛ ስሪት ነው። እንዴት እንደሚስተካከልም የምናውቀው እኛው ነን" በማለት ችግሩን እንደሚያስወግ ቃል ገብቶ ጥረት እያደረገ ነው። ለኤምካስ ሶፍትዌር ማስተካከያ ከተደረገለት በኋላ 737 ማክስ አውሮፕላን ወደ በረራ ሲመለስ በበረራ ደህንነታቸው አስተማማኝ ከሆኑ አውሮፕላኖች መካከል አንዱ ይሆናል በማለት የምርመራ ውጤቱን እንደሚቀበለውም አስታውቋል። ቦይንግ አሰቃቂው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተከሰከሰበት ቦታ ላይ አዳዲስ መረጃዎች በመገኘቱ 737-8 ማክስ አውሮፕላኖቹን በሙሉ ማገዱንም ገልጾ ነበር። ኩባንያው እንዳሳወቀው ያሉትን 371 አውሮፕላኖች እስካሁን ከበረራ ውጪ እንዲሆኑ ተደርጓል። የአሜሪካ ፌዴራል አቪዬሽን አስተዳደር እንደገለፀው አደጋው በደረሰበት ቦታ ላይ የተገኙ አዳዲስ መረጃዎችና የተጣሩ የሳተላይት ምስሎች አስተዳደሩ በጊዜያዊነት የእግድ ውሳኔውን እንዲያስተላልፍ አድርጎታል። የአሜሪካ ፌደራል ኤቪዬሽን አስተዳደር ከብሔራዊ የትራንስፖርት ጥበቃ ቦርድ ጋር በመተባበር አደጋውን የሚመረምር ቡድን የላኩ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራው ዱካ ከላየን አየር መንገድ ጋር ተመሳሳይ እንደሆነ ተነግሯል። በተጨማሪም የመከስከስ አደጋው በደረሰበት ቦታ ላይ የተገኙት መረጃዎች በላየን አየር መንገድ ከደረሰው ዕጣ ፈንታ ጋር ተመሳሳይነት እንዳላቸውም በተጨባጭ የሚያስረዱ መረጃዎች መኖራቸው የአውሮፕላኑ የመቆጣጠሪያ ሥርዓት ላይ ችግር እንዳለ ማሳያ ሆኗል። የኢንዶኔዢያ አውሮፕላን የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት እንደሚያሳየው አውሮፕላኑ አፍንጫው የመደፈቅ ሁኔታ ሲገጥመው የማስጠንቀቂያ መልዕክት የሚያሳው መሳሪያ በበረራው ውስጥ በሙሉ በርቶ ነበር። ይህንንም ተከትሎ ቦይንግ ኤምካስን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ለአብራሪዎች መመሪያ ቢያወጣም፤ ነገር ግን በአውሮፕላኑ ወስጥ ያለው ሥርዓትን የሚቆጣጠረው ሶፍትዌር ላይ ያስፈልግ የነበረው ማሻሻያ ዘግይቶ ነበር ይፋ የተደረገው። በተጨማሪም በበረራ ወቅት ችግር በሚያጋጥም ጊዜ አብራሪዎችን ሊያስጠነቅቅ ይችል የነበረው የማስጠንቀቂያ መብራትም አደጋው በደረሰባቸው ሁለቱ የኢትዮጵያ እና የኢንዶኔዢያ አውሮፕላኖች ላይ አልተገጠመም ነበር። ከሁለቱ አደጋው ከደረሰባቸው አውሮፕላኖች የተገኙ የበረራ መረጃዎችም ተመሳሳይነት እንዳላቸው መርማሪዎች አመልክተዋል። የአውሮፕላኖቹን ወደ ላይ የመውጣትና የመውረድ የፍጥነት ንባብ እንደሚያመለክተው ሁለቱም አውሮፕላኖች ከፍና ዝቅ እያሉ እንደነበሩና አብራሪዎቹም ይህንን በመቆጣጠር አውሮፕላኖቹ ከፍ ብለው እንዲበሩ ጥረት ሲያደርጉ ነበር። የአሜሪካ የአቪዬሽንት ተቆጣጣሪ መሥሪያ ቤት (ኤፍኤኤ) የቦይንግ ምርቶችን ደረጃና ጥራት በመቆጣጠርና በማጽደቅ ሂደት ላይ በሕግ የተሰጠውን ሥልጣንና ኃላፊነት ከመወጣት ይልቅ ለቦይንግ አሳልፎ መስጠቱ ዓለምን አስደንግጧል። ባለሥልጣኑ ባሳለፍነው ሳምንት ለሲያትል ታይምስ የምርመራ ዘገባ በሰጠው ቃል፤ ባጋጠመኝ የፋይናንስ አቅም መመናመን የአውሮፕላኑ አምራች እራሱ የአዳዲስ አውሮፕላኖችን ብቃት በከፊል እንዲያረጋግጥ አድርጊያለሁ ሲልም አምኗል። ለዚህም ነው ይህ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ያላቸው ሃገራት በአውሮፕላኑ ላይ ያለው ችግር ተጣርቶ መፍትሄን እስኪያገኝ ድረስ ከበረራ ውጪ እንዲሆኑ ለማድረግ የተገደዱት። የአውሮፕላኑ አምራች የሆነችው አሜሪካም ለአውሮፕላኑ አገልግሎት ላይ መዋል የተሰጠውን ፍቃድ በተመለከተ ምርመራ እንዲደረግ አዛለች። የተለያዩ ዓለም አቀፍ የመገኛኛ ብዙኃን የኢትዮጵያው አየር መንገድ አብራሪ ይህን አውሮፕላን ለማብረር የሚያስፈልግን ተጨማሪ ስልጠና እንዳልወሰደ በመጥቀስ ያቀረቡት ዘገባ ከተለያዩ ወገኖች ቁጣንና ተቃውሞን አስከትሏል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ አብራሪዎች አውሮፕላን አምራቹ ባወጠው እና በአሜሪካ የአየር ትራንስፖርት ባለሥልጣን ተቀባይነት ባለው መንገድ ተገቢውን ስልጠና መውሰዳቸውን አረጋግጧል። • ስለምንጓዝበት የአውሮፕላን አይነት እንዴት ማወቅ እንችላለን? ቦይንግ 737 ማክስ ሶፍትዌር ላይ እያደረገ የነበረውን ማሻሻያ መጨረሱንና ማሻሻያ ባደረገባቸው አውሮፕላኖች 207 በረራዎች ማድረጉን አሳውቋል። አብራሪዎች አውሮፕላኑን ስለሚቆጣጠሩበት መንገድ ለፌደራል አቪዬሽን አድሚንስትሬሽን (ኤፍኤኤ) መረጃ እንደሚሰጥም ተገልጿል። የኤፍኤኤ ባለሙያዎች ቦይንግ ማሻሻያው እንዲጸድቅለት መረጃውን በሚቀጥለው ሳምንት ለኤፍኤኤ እንደሚያስረክብም ይጠብቃሉ። ማሻሻያውም አብራሪዎች አውሮፕላኑን ከአደጋ ለመከላከል ይጠቀሙት የነበረውን አንድ መንገድ ወደ ሁለት አማራጭ አሳድጎታል። ቀደም ብሎም የአደጋ ጠቋሚ መልዕክት ይደርሳል ተብሏል። ለፌደራል አቪዬሽን አድሚንስትሬሽን (ኤፍኤኤ) ተወካይ ሃላፊ ዳንኤል ኤልዊል እንደገለጹት ቦይንግ በሚቀጥለው ሳምንት ማሻሻያውን እስከሚያቀርብ ድረስ ምንም አይነት ውሳኔ አይሰጥም። 737 ማክስ አውሮፕላኖችም በአሜሪካ አየር ክልል ውስጥ በድጋሚ መብረር የሚጀምሩት እጅግ ጠንካራና የተራቀቀ የሙከራ ፈተናዎችን ማለፍ ሲችሉ እንደሆነ ተገልጿል። አብዛኞቹ 737 ማክስ አውሮፕላን ያላቸው አየር መንገዶች የምስለ በረራ መለማመጃ የሌላቸው ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን ለስልጠናው የሚያገለግለው ይህ ዘመናዊ መሣሪያ ባለቤት ነው።
41071650
https://www.bbc.com/amharic/41071650
የሮቦት ነገር. . . ወዴት ወዴት?
የአንድ ፎቶ ኮፒ ማሽን ያህል ክብደት እና ቅርፅ ቢኖራት ነው። እ ን ደብዙዎቹ አዳዲስ ሮቦቶች የጃፓን ሥ ሪት ናት ። እንደ አዲስ መኪና ዓይነት ድምፅ እያወጣች በመጋዘኑ ወዲያ ወዲህ በመንጎራደድ የም ት ታዘውን ነገር በ ሥ ር ዓ ዓቱ ታከናውናለች። በግራ እጇ የወረቀት ሳጥኑን በመጎተት ከሳጥኑ ውስጥ በቀኝ አጇ ጠርሙስ መሳብ እ ን ዲችል ታመቻቻለች።
እርግጥ ከወረቀት ሳጥን ጠርሙስ ለመሳብ የመጀመሪያዋ ሮቦት ላትሆን ትችላለች ነገር ግን በሮቦት ቴክኖሎጂ ዘርፍ ነገሮችን እንዲህ በቀላሉ እና በፍጥነት ልክ እንደ ሰው ልጅ በመከወን አንድ እርምጃ የተራመደች ነች። አሁን ላይ የሰው ልጅ እና ማሽን በመተባበር ነገሮችን እያንቀሳቀሱ ይገኛሉ። ወደፊት ደግሞ ሮቦቶች ሰዎችን ተክተው በመጋዘን ውስጥ ወዲያ ወዲህ ማለት መጀመራቸው የማይቀር እንደሆነ ይነገራል። ሰዎች እና ሮቦቶች አብረው የሚሰሩባቸው ፋብሪካወችም ነበሩ። እ.አ.አ. በ1961 ጄኔራል ሞተርስ የተሰኘው ፋብሪካ ዩኒሜት የተባለ ባለአንድ እጅ ሮቦት በመግጠም በዋነኛነት የብየዳ ሥራውን እንዲያቀላጥፍለት አደረገ። ነገር ግን እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ሮቦቶች በሰው ልጅ ሥራ ውስጥ ሰርገው መግባት አልቻሉም። አንድም ለሰው ልጅ ህልውና ሲባል ሌላም ሮቦቶች በጣም ቁጥጥር የሚያሻቸው ስለሆኑ ያንን ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው። የረቀቁ ሮቦቶች በሚመረቱበት በአሁኑ ዘመን ግን ሮቦቶቹን ስለመቆጣጠር ብዙ መጨነቅ አስፈላጊ አይደለም። በዕድሳት ላይ ሪቲንክ ሮቦቲክስ በተባለው ፋብሪካ የተሰራው 'ባክስተር' የተሰኘው ሮቦት ሰዎች ላይ አይወድቅም ሰውም ቢወድቅበት እንኳ ፍንክች የአባ ቢላዋዱ ልጅ. . አይንቀሳቀስም። ከአያቶቹ በተለየ ሁኔታ 'ባክስተር' ከሥራ ባልደረቦቹ ልምድ ይቀስማል። የዓለም ሮቦቶች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ነው። በኢንዱስትሪ ውስጥ የሚሰሩ ሮቦቶች ሽያጭ ቁጥር በዓመት በ13 በመቶ እያደገ ነው። በሌላ አገላለፅ የሮቦቶች የውልደት መጠን በየአምስት ዓመቱ እጥፍ እያደገ ነው። የዚያኑ ያህል ተግባራቸውም እየረቀቀ መጥቷል። ሮቦቶች ከመጠጥ ቤት እስከ ሆስፒታል እንደየሁኔታው እያገለገሉ ነው። ነገር ግን አሁንም የምንፈልገውን ያክል እያገለገሉን እንዳልሆነ ይታመናል። ተሻሽለው ለመጡ የሮቦት ሀርድዌሮች ምስጋና ይግባቸውና ሚዛን መጠበቅ፣ የተሻለ እይታ እና ዳሳሽ እጆችን የተገጠመላቸው ሮቦቶችን ማየት እየተዘወተረ መጥቷል። ከዚህ ባሻገርም ሮቦቶች ሰው-መሰል ችሎታን ተላብሰው የተሻለ አእምሮ ይዘው መፈጠር ጀምረዋል። እጅግ በጣም የተሻለ ችሎታ ያላቸው ሮቦቶችን ለመፍጠር ሙከራው አሁንም ቀጥሏል። የሰው ልጅ ዕጣ ቴክኖሎጂ የሰው ልጆችን የሥራ ዕድሎች እያጠበበ በሌሎች መተካቱ አዲስ ነገር አይደለም። ነገር ግን ከሮቦቶች መበራከት በኋላ ለሰው ልጆች የሚተርፈው ሥራ እጅግ የከፋ እና የወረደ እንደሚሆን ይገመታል። ለዚህም ምክንያት የሚሆነው ቴክኖሎጂ ከሥራው የይልቅ ማሰቡ ላይ እየበረታ መመጣቱ ነው። የሮቦቶች አእምሮ ከሰውናታቸው በፈጠነ መልኩ እያደገ መጥቷል። ራይዝ ኦፍ ዘ ሮቦትስ በተሰኘው መፅሃፉ የሚታወቀው ማርቲን ፎርድ ''ሮቦቶች አውሮፕላን ማሳረፍ ይችሉ ይሆናል ዎል ስትሪትም ሄደው አክስዮን መገበያየታቸውም አይቀርም። ነገር ግን ሽንት ቤት ማፅዳት አይችሉም'' ሲል ይሞግታል። በተጨማሪም ሮቦቶች የቤት ሥራዎቻችንን እንዲሰሩልን ባንጠብቅ ጥሩ ነው ባይ ነው። ሮቦቶች የሰው ልጅን በማሰብ የሚበልጡት ከሆነ፤ ሰዎች ደግሞ ሮቦቶችን በፍጥነት የሚበልጧቸው ከሆነ እና ለምን የሰውን ልጅ በሮቦት ጭንቅላት መቆጣጠር አይቻልም? እርግጥ የማይዋጥ ሀሳብ ሊመስል ይችላል ግን ሊሆን የሚችል ነገር ነው።
44672023
https://www.bbc.com/amharic/44672023
"ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን አምባገነን እንዳያደርጉት እሰጋለሁ" ጃዋር መሀመድ
ጃዋር መሀመድ ባለፉት ሶስትና አራት አመታት በኦሮሚያ የተካሄዱ አመጾችን ከጀርባም ከፊትም ሆኖ በማስተባበር ይታወቃል። የሚወዱትም ሆነ የሚጠሉት ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ምስል ውስጥ ሊፍቁት አይቻላቸውም።
ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ለታየው ፖለቲካዊ ለውጥ የእርሱን የትግል ስልት በዋነኝነት የሚያነሱም በርካታ ናቸው። ናይሮቢ ለስራ በመጣበት ወቅት ሶስት ጉዳዮች ላይ ጥያቄ ሰንዝረንለታል። ቢቢሲ አማርኛ- በዚህ ወቅት ሀገር ቤት ለመግባት ምክንያትህ ምንድን ነው? ጃዋር፤- መጀመሪያም እኤአ በ2003 በ 17 አመቴ ከሀገር የወጣሁት ለትምህርት ነው። ከዛ በኋላም እየተመላለስኩ በየዓመቱ ጥናቴን የምሰራው እዛው ነበር። ነገሮች ከመንግስት ጋር እየተካረሩ ሲመጡ እንዲሁም ደግሞ ውጭ ቆይቼ ትግሉን መርዳት የምችልበት መንገድ ስለተገኘ ባለፉት ዓመታት ትግሉን በማህበራዊ ሚዲያም፣ በሚዲያም፣ በአካዳሚውም ትግሉን ስረዳ ነበረ። ያ ትግል ባይቋጭም በአብዛኛው ውጤት አምጥቷል። የነደፍነው ስልት ውጤት አምጥቶ በስርዓት ውስጥ ለውጥ አምጥቷል። የፖለቲካ ምህዳሩ እየሰፋ ነው ያለው። ወደ ዲሞክራሲ የምናደርገው ሽግግር በፍጥነት እየተካሄደ ነው ። ከዚህ አንፃር ውጭ ከመቆየት ሀገር ውስጥ ገብቶ መስራት ይረዳል። በተለይ ደግሞ እየተደረገ ላለው ሽግግር ምሁራዊ እርዳታ፣ በሚዲያውም ፣ ህዝብን በማስተባበር እርዳታ ማድረግ ያስፈልጋል። ገዢው ፓርቲ ላይም ጫና በመፍጠር ሽግግሩ በፍጥነት እንዲሄድና የተቃውሞ ኃይሉም በፍጥነት እየተዘጋጀ ለሽግግሩ አቅሙ እየጎለበተ እንዲሄድ ማድረግ አስፈላጊ ነው። ለዚህ ደግሞ በትምህርትም በልምድም ያለኝን ለማካፈል ሚዲያውንም ደግሞ ለመምራትና ለማጠናከር አስፈላጊ ነው ብዬ ስላመንኩ በዚህ ወቅት ለመሄድ ወስኛለሁ። ቢቢሲ አማርኛ፤- አንተ የምትታወቅበት የትግል ስልት አለ። ከዚህ በኋላ ያ የትግል ስልት ነው የሚቀጥለው ወይስ ሌላ የትግል መንገድ ይኖርሃል? ጃዋር- የምትለው የሰላማዊ ትግሉን መሰለኝ። ሰላማዊ ትግል በተለያየ መልኩ ልትጠቀመው ትችላለህ። አንደኛው አምባገነናዊ ስርአትን ለመጣል ልትጠቀመው ትችላለህ። ከጦር የተሻለ ውጤት አለው። በዚህ የዛሬ አስራ ምናምን ዓመት ስከራከር ሰዎች ይስቁ ነበር። አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ለመጣው ለውጥ ትልቅ መስዋዕትነት ተከፍሏል፤ ግን በጦር ቢሆን ኖሮ መስዋዕትነቱ እጥፍ ድርብ ነበር። የሚመጣውም ለውጥ ከፍተኛ ውድመትን ሊያስከትል ይችል የነበረ ሲሆን ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለማሸጋገርም ብዙ እድል አይኖርም ነበር። ስለዚህ ሰላማዊ ትግል በህዝባችን ውስጥ እንዲተዋወቅና ህዝባችን ከውጭ ያሉ ወይም ደግሞ በጫካ ያሉ አማፅያንን ከመጠበቅ ይልቅ በየቦታው በየሰፈሩ እንዲታገል ማድረጉ ጠቃሚ ነው። እና ሰላማዊ ትግል አምባገነን ስርዓትን ለመጣል ይረዳል። በሁለተኛነት ደግሞ አምባገነናዊ ስርዓትን ከገለበጥክ በኋላ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን ለመገንባት ይረዳል። አሁን እያየህ ያለኸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚደረገው ድጋፍ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ብቻ ሳይሆን ለውጥን ለማበረታታትና ወደ ዲሞክራሲ የሚደረገው ሽግግር እንዲፋጠን ሽግግሩን የሚያደናቅፉ ኃይሎችን ተስፋ ለማስቆረጥም ነው። ስለዚህ ሰላማዊ ትግል አምባገነናዊ ስርዓትን ለመገልበጥም ከዛ በኋላ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን ለመገንባትም ይረዳሃል ማለት ነው። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ኃይል ሁለት ነው። አንድ የመንግስት ኃይል ሁለተኛው የህዝብ ኃይል አለ። የመንግስት ኃይል አሁንም ባብዛኛው ለውጥ በማይፈልጉት እጅ ነው ያለው። እነሱ ናቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጠልፈው ሊጥሉ የነበሩት። ግን ህዝባችን በሰላማዊ ትግል በደንብ ስለታነፀ በቀላሉ ሊያከሽፍባቸው ቻለ። ወደ ዲሞክራሲ ከተሸጋገርን በኋላም ይህ ስልት ይረዳል። ፀረ ሙስና ላይ መስራት ትችላለህ። የሚዲያ ኃላፊነትን የማጠናከር ስራ ላይ ማተኮር ትችላለህ። በህዝቦች መካከል ግጭት እንዳይፈጠር የምትከላከልበት ብዙ ስልቶች አሉ። እነዚህን ነገሮች ማስተማር እፈልጋለሁ። ሀገር ቤት ስገባ አንዱ ማድረግ የምፈልገው ከሚዲያው አንፃር 'ቲንክ ታንክ' ማቋቋም እፈልጋለሁ ። ከዛው ጋር በተያያዘ ደግሞ ከጥቂት ዓመታት በኋላ የአመራር ስልጠና ተቋም በተለይም ከስር የሚወጣውን ወጣት ብቁ አመራር እንዲወጣው ለማድረግ። ሀገራችን ብዙ ስጦታ አላት፤ ብዙ ልጆች ይወለዳሉ፤ በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ የአመራር ክህሎትን በተፈጥሮ እንዲሁም በትምህርት ታገኘዋለህ። የተፈጥሮ ክህሎት ያላቸውን ልጆች በማሰልጠንና በማጠንከር እንዲተዋወቁ ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ ማድረግ ይቻላል፤ እዚህ ላይ እንግዲህ እኔም የተማርኩት አለ ከኔም ጋር የሚሰሩ ባልደረቦች አሉ፤ በዚህ ላይ መስራት እንፈልጋለን ወደፊት። ቢቢሲ አማርኛ፤- ብዙ ጊዜ ለነፃነትና ለለውጥ ሲታገሉ የሚቆዩ ሰዎች እድሉን ካገኙ በኋላ ጭልጥ ካለ ተቃዋሚነት ወደ ጭልጥ ያለ አመስጋኝነት የሚዘዋወሩበት አጋጣሚ ይኖራል። አንተን የምናውቅህ ስርአቱን በመንቀፍ ነው። አሁን በስልጣን ላይ ካሉት ሰዎች ጋር ያለህ መልካም ግንኙነት ወትሮ የምትታወቅበትን የትግል መልክ ምን ያህል ይለውጠዋል? እኔ እንደውም የምፈራው ቋሚ ተቃዋሚ እንዳልሆን ነው። ምክንያቱም እኔ አንደኛ የመንግስት ስልጣን የመያዝ ፍላጎት የለኝም። መንግስት ሲባል ደግሞ ሁሌም መግፋት አለብህ። የኛ ወጣቶች ማወቅ ያለባቸው መንግስት ሁሌም ካልገፋኸው አስቸጋሪ ነው።መደገፍ ጥሩ ነው። ግን ከደገፍከው ውስጥ ገብተህ ባለህ እውቀትና ባለህ ችሎታ መርዳት መቻል አለብህ። ከኦህዴድ ልጆች ጋር ስንከራከር የነበረውም ይህው ነው።ኦህዴድን የሚደግፉ ልጆች ቁጭ ብሎ ለኦህዴድ ማጨብጨብ ዋጋ የለውም። ለአብይ ሰልፍ መውጣት ማጨብጨብ የአንድ ቀን ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ በመለስ ዜናዊ እና በኢህአዴግ ጊዜ እውቀት ያለው ችሎታ ያለው ተገፍቶ ወጥቷል። አሁን ያን ችሎታና እውቀት ወደ ሀገር በመመለስ የሀገሪቷን ቢሮክራሲ ውስጥ ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎች አቅምን መጨመር ያስፈልጋል። መንግስትን የሚወዱ፣ አብይን የሚወዱ የተለወጠውን ኢህአዴግን እንወዳለን የሚሉ ሰዎች ማጨብጨብ አይደለም የሚያስፈልጋቸው። ገብተው በችሎታቸው መርዳት መቻል አለባቸው። ብዙዎች ደግሞ እየገቡ እየረዱ ነው።በፖለቲካ መንግስት ውስጥ መግባት የማንፈልግ ነገር ግን በሲቪክ ማህበረሰቡ ውስጥ መቆየት የምንፈልግ ሰዎች ወደድንም ጠላንም ተቃዋሚ ሆነን ነው የምንቀጥለው። ተቃዋሚ እንደተቃዋሚ ፓርቲ ሳይሆን የመንግስት ተቺዎች ሆነን ነው የምንቀጥለው። ምክንያቱም አክቲቪስት ከሆንክ ልትረካ አትችልም። ምንም ቢያደርግ መንግስት ሊያስድስትህ አይችልም። ምክንያቱም አንድ ነገር ከሟላልህ አሁንም ሌላ የሚጎድል ነገር አለ። አይደለም ኢትዮጵያ ከፍተኛ የፍትህ እጦት ፣ የኢኮኖሚ ችግርና ብዙ ነገሮች ያሉበትን ሀገር ተውና እኔ በምኖርበት አሜሪካ ወይንም ደግሞ ገነት በምትላት እንደ ስዊድንና ኖርዌይ ራሱ አክቲቪዝም መሰረታዊ ፍላጎት ነው። ሙስናን ለመታገል መንግስት ብቃቱ እንዲጨምር አቃቂር እያወጣህ መግፋት መቻል አለብህ። እናም ወደፊት በማደርገው ሂደት እርግጥ ነው ከዚህ በፊት እንደማደርገው ጭልጥ ያለ ተቃውሞ ውስጥ መቀጠል አልችልም። ይሄንን አፍርሱ ይሄንን ናዱ ማለት አልችልም። ምክንያቱም እኔና ሌሎች ያለብን አንዱ ችግር ባለፉት አራት ዓመታት ወጣቱ መንግስት እንዲያፈርስ (ወጣቱ መንግስት የማፍረስና የማሽመድመድ) አሰልጥንነዋል። በአሁኑ ወቅት እኮ ኢትዮጵያ ውስጥ በተግባር መንግስት አለ ማለት አይቻልም። ከታች ያለውን መዋቅር አሽመድምደነዋል።ይህን ወጣት እንደገና ዲሞክራሲን የመገንባት ፤ ሀገርን መልሶ የመገንባት ክህሎት ማስተማር መቻል አለብን። እና ያንን ከመንግስት ጋር እየተረዳዳን የምንሰራው ብዙ ነገር አለ። በተለይ ደግሞ አሁን ባለው ሽግግር ላይ መንግስትን ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እደግፋለሁ። ምክንያቱም ሀገሪቱ ወደ ገደል እየሄደች ሳለች ነው ትንሽ ያስቀየሳት እርሱ። ወደ ገደል ሊመሯት የሚፈልጉ ሰዎች አሉ። ስለዚህ ከእነርሱ ጋር መሆን አንችልም። አሁን ያለን እድል ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በመቆም የሚያጠፋቸውን ነገሮች እየተቸን ግን በተለይ ይህንን ለውጥ ሊያኮላሹና ሊያከሽፉ የሚፈልጉ ኃይሎች ባለን ተሰሚነትና ባለን እውቀት ባለን ስልት እያዳከምን ሀገሪቷን ወደፊት ማሻገር አለብን። ሀገሪቷ ወደ ብጥብጥ እንዳትሄድ እንደገና ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩንም አምባገነን ሊያደርጉት ይችላሉ። እየነካኩ ከሄዱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኃይል ወደ መጠቀም ወደ አምባገነንነት የሚሄድበት እድል ሊኖር ይችላል። ፈልገው ሳይሆን ሳያውቁ አምባገነን የሆኑ ብዙ አምባገነኖች አሉ። ሁኔታዎች ወደዛ ይገፏቸዋል። አለበለዚያ ደግሞ እርሱን ገልብጠው ወደ እርስ በርስ ጦርነት እንዳያስገቡን ለምሳሌ አሁን በድጋፍ ሰልፉ ላይ ቢገሉት ኖሮ ለውጥን የሚደግፈው የኛ ወገንም ተመሳሳይ እርምጃ ለመውሰድ የሚገደድበት ሁኔታ ነበረ። ያ ደግሞ ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ይከተናል። እና እዛ ውስጥ እንዳንገባ ከመንግስት ሰዎች ጋር እንወያያለን። በበለጠ ደግሞ የተቃውሞውን አቅም ማጠናከር እፈልጋለሁ። እኔ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል መሆን አልፈልግም ። ግን ክህሎቶች አሉኝ የተማርኳቸው ስልቶች አሉ ። እድሜ ልኬን ይሄንን ነው የሰራሁት። በዚህ የተቃውሞ ኃይል ወደ አንድ እንዲመጣ እንዲጠናከር የሚሰራውን ስራ በስትራቴጂ እየደገፈ እንዲሄድ እፈልጋለው። ጠንካራ ተቃዋሚ የሌለበት ሀገር ውስጥ ዲሞክራሲን መገንባት አትችልም፤ የአማራጭ ፖሊሲዎች ብፌም ሊኖረው ይገባል የኛ ህዝብ። ዝም ብሎ ዶሮ ወጥ ቢበላ የኛ ህዝብ ይደብረዋል ሽሮ መኖር አለበት። እና ይሄ የተወዳዳሪ እድል ምርጫ ሊኖረው ይገባል የኛ ህዝብ። እኛና ሌሎች ባለፉት ዓመታት ስርዓቱን የማዳከም ስራ ስርተናል። በጣም በተዋጣ መልኩ። በ2020 እዚህ እንደርሳለን እንል ነበር። ነገር ግን ፍጥነቱ በጣም ስለሄደ አሁን እዚህ ደርሰናል። እርሱ ራሱ ችግር አለው። አሁን ደግሞ በተቀሩት አመታት አትሊስት በ2020 ወደ ሙሉ ዲሞክራሲ እንድንሸጋገር ከዛ በኋላ ደግሞ የተሸጋገርንበት ዲሞክራሲ እየተጠናከረ እንዲሄድ የሚመጣው መንግስት በተለይ የኢኮኖሚ ሁኔታዎችን እየፈታ እንዲሄድ እናስባለን። አሁን እዚህ የመጣሁት (ናይሮቢ) አንዱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተናገሩት ያሉት ሁኔታ አለ። ለምስራቅ አፍሪካ የኢኮኖሚ ውህደት በጣም አስፈላጊ ነው። ኢትዮጵያ ትልቅ እምቅ ኃይል አላት ትልቅ የሆነ ሃብትም አላት። ይህንን ሃብት ከአካባቢው ህዝቦች ጋር የኢኮኖሚ ቁርኝት በማድረግ ማሳደግ መቻል አለባት። ከኤርትራ ጋር እየተደረገ ያለው ነገር በጣም አስፈላጊ ነው። ብዙ ሰዎች ከኤርትራ ጋር ያለውን ጉዳይ ከፖለቲካ አንፃር ብቻ ነው እያዩ ያሉት። ፖለቲካውን ለጊዜው ገሸሽ አድርገነው ኢኮኖሚው ላይ እያተኮርን መሄድ መቻል አለብን። ከሶማሊያ ጋር ያለን ግንኙነት እየተጠናከረ መሄድ መቻል አለበት። ከኬኒያ ጋር ያለን ግንኙነት እየተጠናከረ መሄድ መቻል አለበት። ይሄንን መንግስት በፖሊሲ ደረጃ ይሰራል። እኛ ደግሞ ያንን መንግስት የሚያመጣውን ፖሊሲ አስቀድመን ጥናት በማድረግ በተለያዩ ኮንፍረንሶች በተለያዩ የጥናት ወረቀቶች በተለያዩ ሚዲያዎች ህዝቡን ማዘጋጀት መቻል አለብን። እና እንግዲህ እንዲህ አይነት ነገሮች ላይ ነው መስራት የምፈልገው።
54851976
https://www.bbc.com/amharic/54851976
"የጦርነቱ መዘዝ ለቀጠናውም ይተርፋል" አወል አሎ (ዶ/ር)
ከጊዜ ወደ ጊዜ የሻከረው የትግራይ ክልልና የፌደራል መንግሥት ግንኙነት ወደማይታረቅ ደረጃ ደርሶ ወደ ጦርነት አምርቷል። ለመሆኑ የዚህ ጦርነት መዘዙ ምንድን ነው? የሚሉና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ በዩናይትድ ኪንግደም በኬል ዩኒቨርስቲ መምህርና የምስራቅ አፍሪካ የፖለቲካ የግጭቶች ተንታኝ አወል አሎ ቃሲም (ዶ/ር) ጋር ቢቢሲ ቆይታ አድርጓል። ቢቢሲ፡ -በትግራይ ክልልና በፌዴራል መንግስት የተከሰተው ጦርነት አራተኛ ቀኑን አስቆጥሯል። ሁኔታው ወደ ጦርነት ያመራል የሚል ግምት ነበረዎት? ሁለቱም ወገኖች ችግራቸውን በሰላምና በእርቅ ሊጨርሱት ያልቻሉበት ምክንያት ምንድን ነው?
አወል አሎ (ዶ/ር)፦ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የሚመራው የፌዴራል መንግሥትና ህወሃት የሚመራው የትግራይ ክልል መንግሥት ልዩነቶች የቆዩ ናቸው። እንደዚህ ዓይነት ልዩነት ደግሞ በሳል በሆነ ሁኔታ በወቅቱ የማይፈታ ከሆነ አደገኛ ወደ ሆነ ሁኔታ ሊያመራ እንደሚችል በጣም ግልጽ ነበር። በርካቶች ሊመጣ እንደሚችል ሲገምቱት የነበረ ጦርነት ነው። ያልተጠበቀ ነገር አይደለም። ምናልባት በዚህ ወቅት ይመጣል ብሎ የጠበቀ ላይኖር ይችላል። ነገር ግን የፌዴራል መንግሥቱ የስልጣን ወቅት ከሚያልቅበት እስከሚቀጥለው ምርጫ መሃከል ግጭት ሊከሰት እንደሚችል የተለያዩ ተንታኞች ሲያመለክቱ ነበር። ምክንያቱም ህወሃት እንደሚታወቀው ምርጫው መደረግ አለበት ብሎ የፌዴራል መንግሥቱን በመቃወም ምርጫውን ማካሄድ ግንኙነታቸውን እያካረረው መጣ። ከህወሃት እይታ አንፃር የዐብይ መንግሥት ላይ ትልቅ ጫና መፍጠር የሚቻለው የፌዴራል መንግሥት ስልጣን ማብቂያ ጊዜ ነው የሚል እምነት ያለ ይመስላል። ሁለቱም በአቋማቸው ለድርድር ፍቃደኛ እንዳልሆኑ የሚያሳዩ ብዙ ምልክቶች አሉ። በመጨረሻም በሁለቱም ጎን ወደ ኋላ የመመለስ ፍላጎት ስላልነበረ ሁለቱም መንግሥታት በጣም አሳፋሪ ወደሆነ ምናልባትም በቀላሉ ሊያባራ ወደማይችል ጦርነት እንደሚያመራ ግልጽ ነበር። ቢቢሲ፡ -ጦርነቱ እንዲህ በቀላሉ ሊያባራ አይችልም ከተባለ ምን ሊያስከትል ይችላል? አወል አሎ (ዶ/ር)፦ መመልከት ያለብን ነገር በሁለቱም መሃከል ያለው ፖለቲካዊ ልዩነት ምንድን ነው የሚለውን ነው። በመሰረቱ በዐብይ መንግሥትና በህወሃት መሃከል ያለው ልዩነት የርእዮተ ዓለም ልዩነት ነው። ከዚህ ርእዮተ ዓለም በሚነሳ ኢትዮጵያ ለወደፊት ምን ዓይነት አገር መሆን አለባት? የምትከተለው መርህ ምን መምሰል መቻል አለበት? ሃገረ መንግሥቱ ምን ዓይነት ቅርጽ ሊኖረው ይገባል? በሚሉ ሁኔታዎች ላይ መሰረታዊ የሆኑ ልዩነቶች አሉ። በተለይም ደግሞ ኢህአዴግን ከማፍረስና (ማዋሃድና) ብልጽግና ፓርቲን ከመፍጠር ጋር ተያይዞ የተሰሩት ነገሮች መሰረታዊ የርእዮተ አለም ልዩነቶች መኖራቸውን የሚያሳዩ ናቸው። በየቦታው የምናያቸው ችግሮች ፌዴራል መንግሥቱ ህወሓት የፈጠራቸው ናቸው ይበል እንጂ ህወሃት ይፍጠራቸው መንግሥት በሁለቱ መሃከል ያለውን ርእዮተ ዓለምና የሃይል ልዩነት ከመሸናነፍ አንጻር ሊታዩ የሚገባቸው ናቸው። አሁን በቅርቡ ጊዜ ወለጋ አካባቢ ተፈጸመ የተባለው የንጹሃን ዜጎች ግድያ ወዲያውኑ ታጣቂ በሆነው ኦነግ ሸኔ በሚባል ቡድን ነው የተፈፀመው፤ ህወሃትም ከጀርባው አለ ተባለ። በህወሃትና በኦነግ መካከል የነበረው መጥፎ ግንኙነት የሚታወቅ አይደለም? ይህንን ተከትሎ በተወሰኑ ቀናት ውስጥ ጦርነት ተጀመረ። ጥቃት ተፈፀመ የሚሉ ምክንያቶች ከመቅረብ ባለፈ በሁለቱ መንግሥታት መካከል ያለው ልዩነት የሚያሳዩ አይደሉም። እነዚህ ህዝብ ሊያያቸውና ሊፈራ የሚችልባቸው ልዩነቶች ናቸው። ስለዚህ ይሄ ጦርነት መሰረታዊ የሆነ የርእዮተ ዓለም ልዩነት ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ጦርነቱ በአጭር ግዜ ሊያባራ አይችልም። በቀላሉ አሸናፊ የሆነ አካል የሚኖርም አይመስለኝም። ጦርነቱ ከቀጠለ ደግሞ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ቀጠናው ላይ ሊያስከትል የሚችለው መዘዝ ቀላል አይደለም። የኤርትራ መንግሥት እንቅስቃሴ ከቅርብ ግዜ ወዲህ እየተጠናከረ መጥቷል። በርግጥ ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸው ግንኙነት የመንግሥት ለመንግሥት ግንኙነት አይመስልም፤ ግላዊ የሆነ ግንኙነት የሚመስል ሁኔታ ነው ያለው። የኤርትራ መንግሥት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ስርዓት በተመለከተ አቋሙን በግልጽ ሲያንጸባርቅ እንደነበረ እናውቃለን። ይሄ ደግሞ በዐብይ መንግሥትና በህወሃት መሃከል ያለው የርዕየተ ዓለም ልዩነት ጋር በቀጥታ የሚገናኝ ነው። ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ ብሄርን መሰረት ያደረገው ፌዴራሊዝም ኢትዮጵያ ውስጥ አያስፈልግም የሚል እምነት አላቸው። ሶማሊያ ላይ ያሉ የኢትዮጵያ ወታደሮች መውጣታቸው አይቀርም። የዚህም አንድምታ አልሻባብ እንደ ልቡ ይንቀሳቀሳል ማለት ነው። ሱዳንም ላይ እንደዚሁ ችግር እንዳለ ይታወቃል። ስለዚህ ችግሩ ሰፋ ያለ ቀጠናው ውስጥ ችግር ሊፈጥር እንደሚችል ምንም ጥያቄ የለውም። ቢቢሲ፡ ከኤርትራ መንግሥት ጋር በተያያዘ በተለይ ደግሞ ህወሃት በአገሪቱ ጣልቃ ገብነት ሲከስ ይሰተዋላል። በሁለቱ አገራትም ያለው ድንበር እንደተዘጋ ነው። በሁለቱ አገራት ላይ ከተፈጸመው እርቅ ጋር ተያያዞ እርቀ ሰላሙ ምን ደረጃ ላይ አለ ይላሉ? አወል አሎ (ዶ/ር)፦ መጀመርያ ላይ በሁለቱም አገሮች መሃከል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወሰዷቸው እርምጃዎች ሁላችንም ያደነቅነው ነው። የሚደገፍ ሂደት ነበር። የሁለቱም አገሮች ግንኙነት ወደሰላም ማምጣት የሚደገፍ ነበር። ነገር ግን ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው ችግር በተለይ በፌዴራል መንግሥትና በትግራይ መንግሥት መካካል የነበረው ችግር ያ የሰላም ስምምነት ወደፊት እንዳይሄድ አድርጓል። እንደሚታወቀው ችግሩ በዋናነት የነበረውና ዋናው መገለጫው የድንበር ችግር ነው ተብሏል። ድንበሩ ደግሞ ያለው በትግራይ ክልል ነው። የፕሬዚዳንት ኢሳይያስና የትግራይ ክልል ግንኙነት ጥሩ አልነበረም። የዐብይና የኢሳያስ ፍላጎት ህወሃትን ማስወገድና ኮርነር (አጣብቂኝ ውስጥ የመክተት) ነው። ከምንም ፖሊሲ ላይ የተመሰረተ ከመሆን በላይ ። የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ህወሓት የመራውና ኢሳይያስ የተሸነፉበት ጦርነት ስለሆነ ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ ህወሃትን መልሰው ማሸነፍ ይፈልጋሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይም የራሳቸው የሆነ ርእዮተ ዓለም ስላላቸው ይህንን ርእዮተ ዓለም ከጫፍ እንዳይደርስ ትልቁ እንቅፋት የሆነው ህወሃት ነው ብለው ስለሚያስቡ ሁለቱም ፕሬዚዳንት ኢሳይያስና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ህወሃትን እንደ ጋራ ጠላት አድርገው ያያሉ። እዚህ ጉዳይ ላይ ይከባበራሉ የሚልም የትንታኔ መሰረት አለው። ስለዚህ አስመራ ልክ እንደ አዲስ አበባና መቀሌ የዚህ ጦርነት አባል ናት ብንል ስህተት አይመስለኝም። ተሳትፏቸው ምንያህል ነው የሚለውን ነገር አሁን ባለንበት ሁኔታ መመዘን ባንችልም ኤርትራ በዚህ ጉዳይ ላይ ትልቅ ፍላጎት እንዳላት መገመት ይቻላል። ቢቢሲ፡ ስለዚህ ከኢትዮ-ኤርትራ የእርቀ ሰላሙ ጋር ተያይዞ እርስዎ የሰላም የኖቤል ሽልማት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ እንዲሰጥ ዕጩ አድርገው ከጻፉት መካከል አንዱ ነበሩና በዚህ ወቅት ዘወር ብለውሲያዩት 'ምናልባት ያልበሰለ ነገር ነበር? ቸኩያለሁ' የሚል ስሜት ፈጥሮብዎታል? አወል አሎ (ዶ/ር)፦ የኖቤል ሽልማት ዕጩነት ደብዳቤ ባስገባሁበት ጊዜ የመጻፍ ውሳኔ የተመሰረተው በወቅቱ በማየውና በነበረው ነባራዊ ሁኔታ ነው። በአብዛኛው አንዳንድ ጊዜ የምናከናውነው ነገር ወደኋላ ሂደን ተመልሰን ስናየው ስህተት መስሎ የሚታይበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል። እኔ አሁንም በዛን ግዜ በነበረው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በሰሩት ስራ የተሰጣቸው እውቅና መጥፎ ነው ብዬ አላስብም። ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው ችግርና የኢትዮ-ኤርትራ ግጭት ሙሉ ለሙሉ ይፈታል የሚልም አልነበረም ግምቴ። ቢያንስ ግን ለሰላም ባደረጉት ጥረት ይህንን እውቅና ቢሰጣቸው ወደፊት የተሻለ ስራ ይሰራሉ የሚል ግምት ነበረኝ። የነበረኝ ግምትና ትንታኔ ስህተት ነበር። ግን ደግሞ ለሽልማቱ በማጨቴ የሚቆጨኝ ነገር የለም። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ያንን ሽልማት አግኝተው አሁን በምናየው ሁኔታ ጦርነት ማወጃቸው በዚህ ደረጃ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ምን ነካቸው ተብሎ እንዲነገር ዕድል ይሰጣል። ስለዚህ ስማቸው በዛው ደረጃ እንደገነነ ሁሉ የሚፈፀሙ ድርጊቶች ከዚያ ከፍ ያለ እውቅና ጋር የሚመጣጠን እንደሆነ ነው። ሳይሆን ሲቀር ደግሞ እንደዛው ተጠያቂነት እንደሚመጣ ነው በዚህ መልኩ ነው የማየው። ቢቢሲ፡ -በአሁኑ ወቅት ጦርነቱ እንዲረግብና ዘላቂ መፍትሄ እንዲመጣ ምን ምን መደረግ አለበት ይላሉ? ከሁለቱም ወገንና ከዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ምን ይጠበቃል? አወል አሎ (ዶ/ር)፦ ጦርነት መጀመር ቀለል ያለ ነገር ሊሆን ይችላል ግን ከጦርነት መውጣት በጣም ከባድ ነው። ሁሉም በእልህ ጦርነቱ ውስጥ ከገቡ በኋላ ተሸናፊ መምሰል ስለማይፈልጉ የተለያዩ የዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ አካላት ጫና የመቀበል ሁነታ ያነሰ ነው የሚሆነው። አንዳንድ ሚድያዎች እንደዘገቡት የፌዴራል መንግሥቱ ድርድር እንደማይቀበልና ጉዳዩ በጦርነት ብቻ መፈታት እንዳለበት እንደሚያምን የሚያሳይ ነው። ህወሃትም ግጭቱ እንዲባባስ የራሱን ሚና ተጫውቷል። በሁለቱም በኩል ነገሩ በሰላም እንዲፈታ ፍላጎት ያለ አይመስለኝም። ግን ደግሞ እንደዚህ ዓይነት ጦርነቶች ቶሎ አይጠናቀቁም። የሚዳከም ቢኖርም ግልጽ በሆነ መልኩ ተሸንፎ እጅ የሚሰጥ፣ ተንበርክኬያለሁ የሚል አካል አይኖርም። ስለዚህ ከዚህ ጦርነት የሚጠቀም አንድም የለም። የሚጎዳ ግን ሁሉም ማለት ይቻላል። ስለዚህ ሁሉም ማድረግ ያለበት፤ ከውስጥም ከውጭም ሁለቱም ወገኖች ችግራቸው ለመፍታት ለውይይት ይቀመጡ ነው። ግን ሁለቱም አከባቢ ዝግጁነት ያለ አይመስለኝም። በጦርነት ሊፈታ የሚችልም ችግር ያለ አይመስለኝም። ችግሩ ፖለቲካዊ ነው፤ የርእዮተ ዓለም ችግር ነው፡ ስለዚህ ዲሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ ፖለቲካዊ መፍትሄ የመስጠት እና የኢትዮጵያ የወደፊት እጣ ፈንታ ምን መሆን አለበት የሚለው ነገር ለኢትዮጵያ ህዝብ መተው አስፈላጊ ነው። ቢቢሲ ጠቅላይ ሚኒስተር ዐብይ ወደ ስልጣን ከመጡ ጊዜ ጀምሮ፤ በአገሪቱ ግጭቶችና ግድያዎችተበራክተዋል የሚሉ ሪፖርቶች አሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ የኢትዮጵያ ቀጣይ እጣ ፈንታ የሚወስን ራእይ ተቀባይነት እንዳላገኘ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል? አወል አሎ (ዶ/ር)፦ ከርእዮተ ዓለሙ አንጻር እነዚህ ችግሮች እየተፈጠሩ ያሉት ስርዓቱ በራሱ የፈጠራቸው ናቸው የሚል ክርክር ይቀርባል። በሌላ መልኩ ደግሞ ብሄርን መሰረት ያደረገው ፌደራሊዝም የፈጠረው ችግር የለም የሚሉ ኣሉ።። አገሪቱ ውስጥ እየተፈጠረ ያለው መከፋፈል ስናይ ምናልባት ኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈጠሩ ያሉት እነዚህ ችግሮች ወደፊት ምን ዓይነት አገር መኖር አለበት የሚል ህልም ለማሳካት የራሳቸውን ርእዮተ ዓለም ለማጠናከር የሚፈልጉ ሃይሎች የሚያደርጉትን ሊሆን ይችላል። ነገር ግን መንግሥት እዚህ ነገር ውስጥ እጁ የለም የሚለው አመለካከት ለእኔ በጣም ከባድ ነው። ሻሻመኔ የተፈጠረውን ጥቃት በምናይበት ግዜ የሰው ልጅ በዚያ ደረጃ እየተገደለ የጸጥታ ሃይሉ ጣልቃ አልገባም። "ጣልቃ ለምን አትገቡም "ተብሎ ሲጠየቅ 'ትእዛዝ አልተሰጠንም' ብለው ሲከራከሩ ነበር። የሆነ ሆኖ ግን ለሚካሄደው የርእዮተ ዓለም ጦርነት እንደግብዓት ስራ ላይ እየዋለ ነው። እልቂቶቹን ግን በትክልል ማነው እየፈፀማቸው ያለው ለሚለው ለማወቅ ገለልተኛና እሙን የሆነ ማጣራት መደረግ አለበት። ከዚያ ውጪ እገሌ ነው እገሌ ነው ለማለት የምንችልበት መረጃ ማግኘት ከባድ ነው። ቢቢሲ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ራሳቸው ከ20 ዓመታት በላይ በፌዴራሊዝም ስርዓት የሚያምነው ኢህአዴግ ውስጥ የነበሩ ሰው ናቸው። በተለያየ ጊዜ ሲናገሩም የፌዴራሊዝም ስርዓት ደጋፊ እንደሆኑ የሚናገሩበት ሁኔታ አለ። በዚህ ደረጃ የርእዮተ ዓለም ጦርነት ብለን ልንገልጸው የምንችለው ክህወሓት ጋር ምን ልዩነት ቢኖራቸው ነው? አወል አሎ (ዶ/ር)፦ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብዙ ጊዜ በሚያወሩበት ወቅት በጣም ግልጽ የሆነ ርእዮተ ዓለማዊ አቋም የላቸውም። በየቦታው የተለያየ ለእሳቸው ፖለቲካ በሚመች መንገድ ይናገራሉ። አሀዳዊ የሆነ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች ሲያናግሩ በእነሱ ቋንቋ ያወራሉ። ሌሎችም ሲያናግሩ ሌላ ነገር ይናገራሉ። ከድርጊታቸውና ከሚወስዷቸው ተቋማዊ እርምጃዎች ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግልጽ የፌዴራል ፕሮጀክት ወይም ደግሞ ፌዴራሊዝም የሚቆምባቸው መሰረቶችና ሊያሳካ የሚፈልጋቸው የሚደግፉ ሰው ናቸው ብሎ ማሰብ አይቻልም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሃዳዊ ናቸው ማለት ይቻላል። ከተግባራቸው በትክልል መረዳት እንደሚቻለው ፌዴራላዊ የሆነ መዋቅር ሳይሆን፤ በተወሰነ ደረጃ የተማከለ የራሳቸውን ስልጣን የሚያጎላ ዓይነት የፖለቲካ መዋቅር እንደሚፈልጉ በጣም ግልጽ ነው። ባይናገሩትም። ከህወሃት ጋር እንደነበሩ ግልጽ ነው።ያለፈው ስርዓት በሚወቅሱበት ጊዜ በፖለቲካው ደረጃ ህወሃትን መተቸት በአብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ተቀባይነት ስላለው፤ ዋና ባላንጣቸው አሁን ህወሓት ስለሆነ፤ ያንን ድርጅት ከማጥላላት ከማንቋሸሽ አንጻር የሚሰራ የፖለቲካ ስራ ነው። ቢቢሲ፡- አሃዳዊነት ለሚሉት ዋና ማሳያዎቹ ምንድን ናቸው? አወል አሎ (ዶ/ር)፦ ዋናው ነገር ብልጽግና ፓርቲ የተዋቀረበት መንገድ ነው። ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ፕሮግራሙ ለማስፈጸም የቀረጸውና የፈቀደው የፖለቲካ ስራ ነው። ከዚህ ውጪ ማሳያ ማምጣት አያስፈልግም። በተለያዩ መድረኮች የተናገሩዋቸውን ማምጣት ይቻላል ግን ዋናው ማሳያ ፓርቲው ራሱ የተዋቀረበት መንገድ ነው። መሬት ላይ የሚታየው፤ ተቋማዊ መንግሥት የሚመራ ድርጅት አወቃቀሩም አመለካከቱም አሃዳዊ ነው። ግልጽ የሆነ ርዕዮተ አለም ባይኖረውም የሚታየው ነገር አሃዳዊ ነው።
news-53719604
https://www.bbc.com/amharic/news-53719604
አሞኒየም ናይትሬት ፡ ቤይሩት ውስጥ የፈነዳው አደገኛ ኬሚካል በየትኞቹ አገሮች ተደብቆ ይገኛል?
የሊባኖሷን ዋና ከተማ ቤይሩትን ያየ በኬሚካል አይጫወትም።
ኢንዶኔዢያ ውስጥ የተያዘው የአሞኒየም ናይትሬት ክምችት ይሄ አሞኒየም ናይትሬት ኬሚካል ከቤይሩት ፍንዳታ በኋላ ሚዲያው ሁሉ ስሙን እያነሳ ያወሳዋል። በስፋት ለግብርና ማዳበሪያነት ነው የሚውለው። ከዚያ ሌላ ማዕድን በማውጣት ሂደት ውስጥ ፍንዳታን ለመፍጠር አገልግሎት ላይ ይውላል። አልፎ አልፎ ደግሞ መሬት ላይ ለሚጠመድ ተቀጣጣይ ፈንጂዎች መስሪያነት ያገለግላል። አሁን ስለ አሞኒየም ናይትሬት ሁሉም አገር መጨነቅ ጀምሯል። ደብቆ ያስቀመጠም መጋዘኑን እየወለወለ ነው። ኋላ የሚሆነው አይታወቅም! ይህ ኬሚካል ምን ዓይነት ቦታ መቀመጥ ይኖርበታል፣ ለምን ያህል ጊዜ፣ ጥንቃቄውስ ምን መምሰል አለበት በሚለው ላይ ጥብቅ መመሪያዎች አሉ። ሐቁ ይህ ነው፤ ብዙ አገሮች ይህ አሞኒየም ናይትሬት ኬሚካል እንዳላቸው መናገር አይፈልጉም። ምክንያቱም ፈንጂ እያመረቱ እንደሆነ እንዳይጠረጠሩ ስለሚሰጉ ነው። የሚከተሉት አገራት ግን ከኬሚካሉ ጋር ስማቸው ይነሳል። ሕንድ በትንሹ 740 ቶን የሚሆን አሞኒየም ናይትሬት በ37 ኮንቴይነር ውስጥ ቺናይ ከሚባለው ከተማዋ በ20 ኪሎ ሜትር ርቆ፣ ተከማችቶ ይገኛል። መጋዘኑ የሚገኘው ከመኖሪያ መንደር በ700 ሜትር ብቻ ርቀት ላይ ነው። እዚያ ሰፈር ከተቀመጠ አሁን አምስት ዓመት ሊያልፈው ነው። ቤይሩት የፈነዳው ከስድስት ዓመታት ክምችት በኋላ መሆኑን ልብ ይሏል። አሁን የአካባቢው ባለሥልጣናት ኬሚካሉን ከደቡብ ኮሪያ ካስመጣው ኩባንያ ጋር ፍርድ ቤት እየተካሰሱ ነው። ጉዳዩ ፍርድ ቤት ደረሰበት ምክንያት ደግሞ ኩባንያው ኬሚካሉትን ያስመጣው ሕጋዊ ፍቃድ ሳይኖረው ነው። ኬሚካሉን ለማይታወቁ አካላት እንደሚቸበችውም ተደርሶበታል። ዩናይትድ ኪንግደም አንድ ምርመራ እንዳረጋገጠው ኬሚካሉ በዩናይትድ ኪንግደም፣ ሐምበር ክልል፣ በኢሚንግሀማ ሊንከንሻየር ወደብ ውስጥ ይገኛል። የብሪቲሽ ወደቦች ማኅበር እንዳስጠነቀቀው የአገሪቱ ወደቦች አስፈላጊውን ጥብቅ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል። በፍንዳታ የወደመው የቤይሩት ወደብ የመን በኤደን ወደብ መቶ ካርጎ አሞኒየም ናይትሬት ተከማችቷል የሚል ዘገባ መውጣቱን ተከትሎ የየመን ዐቃቢ ሕግ ምርመራ እንዲጀመር አዘዋል። ኬሚካሉ ወደ ኤደን ወደብ ከገባ ሦስት ዓመት አልፎታል ተብሏል። ወደ አገር ውስጥ ሲገባ የተያዘውም በሳኡዲ መራሹ ኃይል አማካኝነት ነው። የኤደን ገዥ ጣሪቅ ሳላም "ለዚህ ተጠያ የሚሆኑት ታጣቂ ኃይሎች ናቸው" ብለዋል። 130 የመርከብ መጋዘን ሙሉ የተከማቸው ይህ ኬሚካል 5ሺህ ቶን ገደማ ይመዝናል። የየመን የኤደን ባሕረ ሰላጤ ወደቦች ኮርፖሬሽን እንደሚለው ግን የተከማቸው ኬሚካል አገልግሎቱ ለማዳበሪያ ሲሆን ምንም የተቀጣጣይነትም ሆነ የጨረራማነት አደጋን አያስከትልም። "ማከማቸቱ አልተከለከለም፤ ችግርም የለውም፤ ተረጋጉ" ብለዋል። ኢራቅ የቤይሩቱን ጥፋት የተመለከቱት የኢራቅ ባለሥልጣናት በአስቸኳይ በሁሉም ወደቦች አካባቢ የሚገኙ ኬሚካሎች ላይ ፍተሻ እንዲደረግ አዘዋል። ከዚህ ቀደም በባግዳድ አየር መንገድ መጋዘን ውስጥ ይህ ኬሚካል ተከማችቶ ይገኝ ነበር። ከትናንት በስቲያ አንድ የወታደራዊ ዕዝ በትዊተር ሰሌዳው ላይ እንደገለጸው የኢራቅ መከላከያ ሚኒስቴር ይህንን አደገኛ ኬሚካል ከባግዳድ አየር መንገድ ወደ ሌላ ቦታ ወስዶታል። አውስትራሊያ ከሳምንት በፊት በቤይሩት የደረሰውን ፍንዳታ ገና ከመድረሱ ቀደም ብሎ በአውስትራሊያ ኒውካስል እና በኒው ሳውዝ ዌልስ የሚገኙ ሰዎች በ3 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚገኘው ይህ ኬሚካል ገለል እንዲደረግላቸው ሲጠይቁ ነበር። ነገር ግን ኦሪካ የተሰኘውና ለማዕድን ኩባንያዎች ይህንን ኬሚካል የሚያቀርበው ኩባንያ "ምንም አስጊ ነገር የለም። በልዩ ጥንቃቄ ነው የተቀመጠው፣ መጋዘኑንም እሳት በማያነደው ቁስ ነው የገነባነው" ብሏል። የደቡብ አውስትራሊያ የሥራ ቦታ ደኅንነት መሥሪያ ቤት እንዳለው ከሆነ በአሁኑ ሰዓት አሞኒየም ናይትሬት በአውስትራሊያ 170 መጋዘኖች ውስጥ በጥብቅ ጥንቃቄና ክትትል ተከማችቶ ይገኛል።
news-48242861
https://www.bbc.com/amharic/news-48242861
በጆርጅያ ግዛት ፅንስ ማቋረጥን የሚከለክለው ሕግ በሆሊውድ አድማ አስከተለ
ውርጃን አስመልክቶ የተደነገገው የጆርጅያ ሕግ ብዙ የሆሊውድ ተዋናዮችን አስቆጥቶ አድማ አስነስቷል። ይህንን ተከትሎም የ'ሚ ቱ' ተሟጋች የሆነችው አሊሳ ሚላኖ እና ሌሎችም የሆሊውድ ተዋንያን በጆርጅያ ውርጃን አስመልክቶ በተደነገገው ሕግ ምክንያት የወሲብ አድማ ጠርተዋል።
አሊሳ ሚላኖ በጆርጅያ ሕጉ ቢፀድቅ ሥራ ለማቋረጥ ቃል ከገቡት መካከል አንዷ ናት እስከ 6 ሳምንታት ያስቆጠረን ፅንስ ማቋረጥ የሚከለክለው ሕግ ቢፀድቅ ተዋናዮች ሥራ ለማቆም ዝግጁ እንደሆኑ በፊርማቸው አሳውቀው ነበር። ፅንስ ማቋረጥ የከለከሉትን የአሜሪካ ግዛቶች ጆርጅያ ተቀላቅላለች። 'ሚ ቱ' በተሰኘው እንቅስቃሴ የምትታወቅ ተዋናይ አሊሳ ሚላኖ ሴቶች በቅዳሜ ዕለት የወሲብ አድማውን እንዲቀላቀሏት ጠይቃለች። በትዊተር ገጿ ያሰፈረችውም የብዙዎችን ትኩረት ከመሳቡም ባሻገር የተከፋፈሉ ሃሳቦችንም አስተናግዷል። ሕጉ ምንድን ነው ? ጥያቄስ ለምን አስነሳ? በታህሳሥ 22 ቀን 2012 ዓ. ም ሥራ ላይ የሚውለው ሕግ በጆርጅያ ገዢ ብራየን ኬምፕ ባለፈው ማክሰኞ የፀደቀ ሲሆን ስሙም "ሃርትቢት" ወይም የልብ ትርታ ነው። ይህም ሆኖ ህጉ በፍርድ ቤት ብዙ ተቃውሞዎችን ያስነሳል ተብሎ ይጠበቃል። ኬንታኪ በተሰኘችው ግዛት ተመሳሳይ ሕግ በፌዴራል ዳኛ እንዲወጣ የተደረገ ሲሆን በሚሲሲፒ ደግሞ ከሁለት ወር በኋላ ሥራ ላይ ይውላል የተባለው ሕግ ብዙ ተቃውሞ ማስነሳቱ ይታወቃል። የማቅለሽለሽ ስሜት ብዙውን ጊዜ ከ9ኛው ሳምንት በመጀመሩ ብዙ ሴቶች በ6ኛ ሳምንታቸው ማርገዛቸውን ላያውቁ ይችላሉ። የፊልምና የቴሌቪዥን ዘርፉ ባለፈው ዓመት ብቻ ለጆርጅያ ግዛት 2.7 ቢልየን ዶላር አስገብቷል። ታዋቂ የሆኑት እንደ ብላክ ፓንተር፣ ሃንገር ጌምዝ፣ ዘ ዎኪንግ ዴድና ስትሬንጀር ቲንግስ የተሰኙት ፊልሞች በጆርጅያ ነው የተቀረፁት። አድማው ምንድን ነው? ሕግ ከመደንገጉ በፊት ወደ 50 የሚሆኑ ተዋንያን በጆርጅያ የሚሠሩ ፊልሞች ላይ እንደማይሳተፉ በደብዳቤ አሳወቁ። ከእነርሱም መካከል አሊሳ ሚላኖ፣ ኤሚ ሹመር፣ ክሪስቲና አፕልጌት፣ አሌክ ባልድዊንና ሾን ፔን ይገኙበታል። ደብዳቤውም "እኛ ጆርጅያ መሥራት እንፈልጋለን፤ ቢሆንም ግን ይህ ሕግ የሚፀድቅ ከሆነ ዝም ብለን ለመቀበል ዝግጁ አይደለንም፤ የሴቶች ደህንነት ወደ ተጠበቁባቸው ግዛቶች መሄዳችን አይቀርም። " ብለዋል። 'ኢንሳቲየብል' በተሰኘው የኔትፍሊክስ ፊልም ላይ የምትተውነው አሊሳ "ኢንሳቲየብልን መብታችንን ወደሚያከብር ቦታ ለማዘዋወር እንጋደላለን" ስትል ለባዝፊድ ተናግራለች። በስምምነቷ መሠረት የቀረፃ ተጨማሪ አንድ ወር ቢቀራትም ሦስተኛውን ክፍል ግን በጆርጅያ የመቅረፅ ሃሳብ እንደሌላት ትናገራለች። ብዙ ተዋናዮችም ድጋፋቸውን አሰምተዋል። ክሪስቲን ቫሾ ኪለር ፊልምስ የተሰኘው የፕሮዳክሽን ድርጅቷ ከአሊስ ጋር እንደሚቆም "ይህ ሕግ እስኪቀር ድረስ" ጆርጅያ ውስጥ ለመሥራት አላስብም ትላለች። ዘ ዋየር የተሰኘው ፊልም ደራሲ ዴቪድ ሳይመን እና ሌሎችም አድማውን ተቀላቅለዋል። የአሜሪካ ደራስያን ማህበር ሕጉን ከመተቸቱም ባሻገር "በፊልም ዘርፉ ለተሰማሩት አባሎቻችን ጆርጅያ ከባድ ቦታ ሊሆን ነው" ብሏል። ጄጄ አብረሃምና ጆርደን ፒል የተሰኙት የፊልም ዳይሬክተሮች 'ላቭ ክራፍት' የተሰኘውን ፊልም በጆርጅያ መሥራታቸውን ባያቆሙም ከአሁን ወዲህ ከሚሠሯቸው የፊልሙ ክፍሎች የሚያገኙትን ሙሉ ገቢ ሕጉን ለሚዋጉት ሰዎች እንደሚለግሱ ተናግረዋል። የጆርጅያ 'ፊታል ሃርትቢት' ወይም የፅንስ ልብ ትርታ ሕግ አግባብ እንዳልሆነና የሴቶችን መብት ከመጋፋቱም በላይ በራሳቸው ጤና ላይ ለመወሰን የሚያስችላቸውን አቅም የሚጋፋ ነው በማለት አስረድተዋል። "አትሳሳቱ ይህ ሆን ተብሎ ሴቶች ላይ ዒላማ ያደረገ ሕግ ነው" ብለዋል። ይህም ሆኖ የሕግ ድርድሩ ምን ላይ እንደሚደርስ ለማየት እየተጠባበቁ ያሉ አድማውን ያልተሳተፉ ብዙዎች አሉ። የሞሽን ፒክቸር አሶሲዬሽን ቃል አቀባይ የሆኑት ክሪስ ኦርትማን "የፊልምና የቴሌቪዥን ዘርፉ ወደ 92 ሺህ ሠራተኞችን የሚቀጥር በመሆኑ የማሕበረሰቡን ቤተሰብ እና ኢኮኖሚያቸውን የቻለ ነው" ሲል ያስረዳል። ጆርጅያ ላይ አድማ ከማድረግ ይልቅ ሕጉን በፍርድ ቤት መገዳደሩ የተሻለ ነው የሚል ሃሳብም ያንፀባርቃል። "በመላው ግዛት የሚሠሩትስ ሠራተኞች? ለእነርሱ አድማው እንዴት ሊጠቅማቸው ነው?" ስትል ተሟጋቿ ኦሪዬል ማሪ በትዊተር ገጿ ላይ አስፍራ ተዋናዮቹ ከዚህ ይልቅ ለሃገር በቀል ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ ቢያደርጉ ይሻላል ብላለች።
sport-44763711
https://www.bbc.com/amharic/sport-44763711
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማልያዎች ለምን ውድ ሆኑ?
እየጨመረ የመጣው የማልያዎች ዋጋ ከፍተኛ መሆን እና በተለይ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ትልልቅ ክለቦች ማልያቸውን መቀያየራቸው አነጋጋሪ ጉዳይ ሆኗል። የእንግሊዙ ሊድስ ዩናይትድ በ1973 የክለቡን መለያ በ7 ዶላር መሸጥ ከጀመረ ወዲህ የማሊያዎች ዋጋ እጅጉን የጨመረ ሲሆን፤ በአሁኑ ሰዓት ይህ ዋጋ ከ10 እጥፍ በላይ ጨምሯል።
ከ2011/2012 ውድድር ዘመን ጀምሮ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማልያዎች ዋጋ በ18.5 በመቶ ጨምሯል። በቅርቡ በተደረገ ጥናት መሰረት በዚህ ዓመት የአንድ ትልቅ ሰው ማልያ 68 ዶላር ያወጣል። • ቢጫና ቀይ ካርዶች እንዴት ወደ እግር ኳስ ሜዳ መጡ? • አፍሪካ የዓለም ዋንጫን ለማዘጋጀት አዲስ አሰራር እንዲኖር ትፈልጋለች • አወዛጋቢው የእግር ኳስ ዳኞች ማስመሪያ በጣም ውድ የሆኑት ማልያዎች የትኞቹ ናቸው? የማንቸስተር ሲቲ፤ ማንቸስተር ዩናይትድ እና ቶተንሃም ሆትስፐር መለያ ልብሶች ከ80 እስከ 88 ዶላር ይሸጣሉ። አሁን ባለው የእግር ኳስ ባህል ደግሞ የማልያዎች መሸጫ ዋጋ ብቻ አይደለም እየጨመረ ያለው፤ የማልያዎች ቁጥርም እንጂ። ለቡድኖች ሶስተኛ ተቀያሪ ማልያ ማዘጋጀት ልምድ እየሆነ መጥቷል። የ1968ቱን የውድድር ዘመን ለማስታወስ ተብሎ 145 ሚሊየን ዶላር ወጪ ተደርጎበት የተሰራው የማንቸስተር ዩናይትድ ሰማያዊ መለያ በደጋፊዎች ስላልተወደደ ለኪሳራ ተዳርጎ ነበር። ታድያ እነዚህ መለያዎች ውድ ናቸው ተብሎ ቢታሰብም፤ በሌሎች የአውሮፓ ሃገራት የሚገኙ ደጋፊዎች ግን ከዚህም በላይ ነው የሚከፍሉት። በጣልያን ደጋፊዎች በአማካይ እስከ 90 ዶላር ድረስ የሚከፍሉ ሲሆን፤ በፈረንሳይ እና ጀርመን ያሉ ደጋፊዎች ደግሞ ከ91 እስከ 95 ዶላር ድረስ ይከፍላሉ። ዋጋዎች ይህን ያህል ለምን ተጋነኑ? ብለን ስንጠይቅ፤ በዋነኛነት የሚጠቀሰው ምክንያት በማሊያዎች ምርት ወቅት ስፖንሰር የሚያደርጉት ድርጅቶች ወጪያቸውን ለመሸፈን ሲሉ በማሊያዎች ላይ የዋጋ ጭማሪ ያደርጋሉ። የእግር ኳስ ቡድኖች ሶስት ዋነኛ ገቢ ምንጮች አሏቸው። ከእያንዳንዱ ጨዋታ የሚገኝ ገቢ፤ ከመገናኛ ብዙሃን የሚገኝ ገቢ እና እንደ ማልያ ካሉ የተለያዩ ምርቶች ሽያጭ የሚገኝ ገቢ። በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሚጫወቱት 20 የእግር ኳስ ቡድኖች ከባለፈው ዓመት 73.65 ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ በማሳየት በ2017/2018 ስፖንሰር ከሚያደርጉ ድርጅቶች ጋር ለቲሸርት ብቻ የ377.36 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ፈጽመዋል። ይሄ ሁሉ ገንዘብ ግን የት ነው የሚሄደው? ምንም እንኳን ደጋፊዎች የማልያዎችን ዋጋ ቀንሱልን ብለው ክለቦቹን ቢጠይቁም፤ እውነታው ግን ከፍተኛ የሚባለው ትርፍ የሚገባው እንደ 'ናይክ'፤ 'አዲዳስ' እና 'ፑማ ላሉ ጥቂት አምራች ድርጅቶች ነው። 'ናይክ' ብቻውን በሶስት ወራት ያገኘው ገቢ ሁሉም የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች በቀጣዩ ዓመት ከሚያስገቡት ገቢ ይበልጣል። በአጠቃላይ 80.35 ዶላር ከሚያወጣ መለያ 5.8 በመቶ የሚሆነው ወጪ ለጨርቅ፤ ለስፌትና ለማጓጓዣ ነው የሚውለው። በዚህ መሰረት 11.5 በመቶ የሚሆነው ትርፍ ለአምራቹ ሲሆን፤ 3.6 በመቶው ለእግር ኳስ ክለቦቹ ነው። አከፋፋዮች ደግሞ ከሽያጭ ከሚገኘው ገቢ 22 በመቶውን ይወስዳሉ፤ ቀሪው ለግብር፤ ለማከፋፈያ ወጪዎችና ማስታወቂያ ላይ ይውላል።
news-56170890
https://www.bbc.com/amharic/news-56170890
በ22 ሳምንቷ የተወለደችው ህፃን ከሆስፒታል ወጣች
መወለድ ከሚገባት ጊዜ አራት ወራት ቀደም ብላ ይህችን ምድር የተቀላቀለችው ህፃን ከሆስፒታል ወጣች።
ሶፊያ 132 ቀናትን በሆስፒታል ካሳለፈች በኋላ ወደ ቤት እንድትሄድ ሲፈቀድላት የማስታወሻ ልብስ ለብሳ ነበር። በስኮትላንድ ኤርዲሪ ከተማ የተወለደችው ህፃን ሶፊያ፤ ከአንድ ወፈር ያለ ዳቦ የበለጠ አትመዝንም ነበር። ሶፊያ ስትወለድ 500 ግራም የምትመዝን ሲሆን በእናቷ ማህፀን የቆየችው 22 ሳምንታትና አራት ቀናት ብቻ ነው። እናቷ በነበራት የምጥ ወቅት ሶፊያ የመትረፍ እድሏ 10 በመቶ ብቻ እንደሆነ ተገምቶ ነበር። ሶፊያ ጥር 24፣ 2013 ነበር ትወለዳለች ተብላ የተጠበቀችው። እርሷ ግን ብዙም ባልተለመደ ሁኔታ ከጊዜዋ ቀድማ ከተፍ አለች። ከጊዜዋ አራት ወራትን ቀድማም መስከረም 22 ይህችን ምድር ተቀላቀለች። ስትወለድ በሕይወት ለመቆየቷ የተሰጠው ግምት አነስተኛ ነበር። ሶፊያ አራት ወራትን ስኮትላንድ ውስጥ በሚገኘው ዊሻው ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል አሳልፋለች። በዚያም የሕክምና ድጋፍ ተደርጎላት፤ በሕይወት ለመቆየት ችላ ከልዩ የሕክምና መስጫ ክፍል ወጥታለች። በወላጆቿ እቅፍም ወደ ቤት እንድትሄድ ተደርጋለች። ሶፊያ ይህ ዕድሜዋ በስኮትላንድ በሕይወት የሚገኝ ትንሽ ዕድሜ ያላት ሰው ሳያድርጋት እንዳልቀረ ይገመታል። እናቷ ኢጌጃና አባቷ ኢንራስ፤ ኢጌጃ "132 ረጅምና ፈታኝ ቀናት" ያለችውን ጊዜ ከሳለፉ በኋላ ልጃቸውን ይዘው ወደ ቤት ሄደዋል። የሶፊያ እናት የትውልድ አገሯ ላቲቪያ ቢሆንም በስኮትላንድ 12 ዓመታት ኖራለች። ስለተፈጠረው ስትናገረም "እስከ 20ኛ የእርግዝና ሳምንቴ ድረስ ሁሉም ነገር መልካም ነበር። ከሳምንት በኃላ ግን ህመም ሲሰማኝ ወደ ሆስፒታል ሄድኩ። ወደ ምጥ እየተቃረብኩ እንደሆነም ተነገረኝ።" ትላለች። ሆስፒታል አልጋ ከያዘች ከ10 ቀናት በኃላም ሶፊያ ተወለደች። ሶፊያ ወደዚህ ዓለም ስትመጣ በከፋ ጩኸትና በመረረ ለቅሶ እንደነበርም ታስታውሳለች። "ትተርፋለች ብለን አልጠበቅንም ነበር። ሆኖም የሕይወታችን ጉዞ ከዚህ ጀመረ።" ትላለች አጌጃ። "እጅ ነበር የምታክለው" ስትወለድ 500 ግራም ትመዝን የነበረችው ሶፊያ፤ ቁመቷ 26 ሴንቲ ሜትር ነበር። የአንድ አዋቂ ሰው እጅ ነበር የምታክለው። ሶፊያ የመጀመሪያዎቹን ሦስት ወራት በልዩ ሙቀት መስጫ ውስጥ ስታሳልፍ ወላጆቿ ጭንቀት ውስጥ ነበሩ። "ያለማጋነን የአዋቂ እጅ ነበር የምታክለው። በቀላሉ የምትጎዳም ዓይነት ነበረች። በቆዳዋ ውስጥም ሰውነቷ ይታይ ነበር። ልጄን ለማቀፍ አንድ ሳምንት ቆይቻለው።" ብላለች ኢጌጃ። የሶፊያ ወላጆች አራት ወራትን በሆስፒታል ካሳለፉ በኋላ ልጃቸውን አቅፈው ወደ ቤት ወደ ቤት ወስደዋል። ሶፊያ የልብ ችግር፣ የአንጎል ደም መፍሰስ፣ የዓይን ህመምና በርካታ ኢንፌክሽኖች የነበረባት ቢሆንም፤ አሁን ግን ጤናዋ ተመልሷል። ሳምባዋም ቢሆን በሚገባ ያልዳበረ በመሆኑ ለመተንፈስ ትቸገር ነበር። በዚህም ምክንያት በመተንፈሻ መሳሪያ ለመታገዝ ተገዳለች። አሁን ከሆስፒታል ወጥታ ወደ ቤት ብትሄድም ተጨማሪ ኦክስጅን እንድታገኝ አነስተኛ ተቦ ተደርጎላታል። የሶፊያ እናት ኢጌጃ "ሁሉንም ጊዜ ሆስፒታል ነበር ያሳለፍኩት። አንዳንድ ቀን እስከ 16 ሰዓታት የምቆይበት ጊዜ ነበር። ባለቤቴ ከሥራ በኃላ ይመጣ ነበር። በተለይ በእነዚያ አስቸጋሪ ወቅቶች ከእርሷ መለየት አልፈልግም ነበር" ስትል ያሳለፈችውን ገልጻለች። "ብዙ የሕክምና መሳሪያዎች ተገጥመውላት ነበር። መጀመሪያ ላይ በራሷ እንድትተነፍስ ተሞክሮ ነበር። 20 ደቂቃ ከቆየች በኃላ የልብ ምቷ መውረድ ጀመረ። ያጣኋት ነበር የመሰለኝ። ግን የሕክምና ባለሙያዎቹ አስደናቂ ነበሩ።" ስትልም ለልጇ የተደረገላትን የሕክምና እርዳታ አሞግሳለች። የሶፊያ ውብ ፈገግታ ሶፊያ ያለመተንፈሻ መሳሪያ እንድትተነፈስ በሳምንታት ውስጥ ስድስት ጊዜ ተሞክሯል። ሶፊያ እየጠነከረችና ክብደቷም እየተሻሻለ የመጣው ግን ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ነበር። በመጨረሻም ከሆስፒታል መውጫዋ ጊዜ ደረሰ። የሶፊያ እናት።"ወደ ቤት ከሄድን ጀምሮ ሶፊያ መልካም ሁኔታ ላይ ትገኛለች። ፊቷ ላይ በጣም ውብ ፈገግታ ይነበባል። አዲሱንም አካባቢ እየተላመደችው ነው። ከተወለደች አራት ወር ተቆጥሯል። እያየኋት አሁንም ማህፀኔ ውስጥ እንደሆነች አስባለው። ምክንያቱም ከተወለደችበት ክብደት በአራት እጥፍ ብትልቅም አሁንም በጣም ትንሽ ናት።" ስትል ሶፊያ አሁን ስላለችበት ሁኔታ ገልጻለች። ሶፊያ ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ቋሚ የሕክምና ክትትል ማድረግ ይኖርባታል። ለሦስት ወይም ለአራት ዓመታት ደግሞ በሳንባ ክሊኒክ መታየት ይኖርባታል። እድገቷ ግን በትክክለኛ መንገድ እየተጓዘ ነው ተብሏል። ኢጌጃ " በዚህ አይነት ሁኔታ የምታልፉና ምጥ ቀድሞ የሚመጣባችሁ እናቶች ተስፋ አለ። በፍፁም ተስፋ አትቁረጡ" በማለትም መክራለች። የሆስፒታሉ ዋና አዋላጅ ቼራል ክላርክ በበኩሏ "የህፃኗ ሳፊያ የሕክምና ሂደት መነሳሳትን የሚፈጥር ነው። አሁን ከቤተሰቦቿ ጋር ወደ ቤቷ በመሄዷ በጣም ደስተኛ ነኝ።" በማለት፤ በዚህ ሂደት ውስጥ በተሳተፉ የሕክምና ባለሙያዎች ስም ለሶፊያና ለወላጆቿ መልካም ምኞቷን ገልጻለች።
news-45405008
https://www.bbc.com/amharic/news-45405008
ቻይና በአፍሪካ የምታደርገው ኢንቨስትመንት ፖለቲካዊ አንድምታ እንደሌለው ፕሬዚዳንት ሺ ዢፒንግ ገለፁ
የቻይናው ፕሬዘዳንት ሺ ዢፒንግ ቻይና ለአፍሪካ ቀጣይ ልማት የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ገንዘብ እያፈሰሰች መሆኑን ተናገሩ።
ፕሬዘዳንት ዢ ዢፒንግ ለአፍሪካ ብልጽግና የሚውል ተጨማሪ 60 ቢሊየን ዶላር ለመመደብም ለማድረግ ቃል ገብተዋል ፕሬዚዳንቱ ይህን የተናገሩት ቻይና በአፍሪካ ውስጥ "የታይታ ፕሮጀክት" የላትም ማለታቸውን ተከትሎ ነው። ፕሬዚዳንቱ የቻይና-አፍሪካን ጉባኤን በቤጂንግ ሲከፍቱ፤ ለአፍሪካ ብልጽግና የሚውል ተጨማሪ 60 ቢሊየን ዶላር ለመመደብም ለማድረግ ቃል ገብተዋል። ገንዘቡ በእርዳታና በብድር መልክም ለአህጉሪቱ የሚሰጥ ይሆናል። • ዘጠኝ አየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ታሰሩ • ጥቁር ገበያውን ማሸግ መፍትሄ ይሆን? በጉባኤው ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አህመድን ጨምሮ፣ ከኢስዋቲኒ በስተቀር ሁሉም የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ተገኝተዋል። ቻይና ለአፍሪካ መሰረተ ልማት ግንባታ የገንዘብ ፈሰስ በማድረግ ቀዳሚዋ ሀገር ናት። ተቺዎች በበኩላቸው አፍሪካ ከቻይና የምታገኘው ብድር ወደማይወጡት አዘቅት እንዳይከታት ከማስጠንቀቅ ወደ ኃላ አላሉም። ሺ ዢፒንግ ትርፋማ የሆኑ ዘርፎችን ለይቶ፤ በቻይናና አፍሪካ መሀከል ያለውን ትብብር ዳግም መቃኘት እንደሚያስፈልግ በጉባኤው ላይ ተናግረዋል። "የቻይናና የአፍሪካ ጥምረት በዋነኛ የልማት ስራዎች ላይ ያነጣጠረ ነው" ሲሉም ተደምጠዋል። የቻይና ኢንቨስትመንት ለአፍሪካ ጠቀሜታ በሚሰጡ ፕሮጀክቶች ላይ ያተኮረ መሆኑንም ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል። አፍሪካ ውስጥ እየተስፋፋ የመጣውን የቻይና ኢንቨስትመንት ያወደሱት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዘዳንት ሲሪል ራማፎሳ፤ "አንዳንዶች አፍሪካ በአዲስ አይነት ቅኝ ግዛት ስር ወድቃለች ከሚሉት ጋር አልስማማም" ብለዋል። በፕሬዚዳንት ሺ ዢፒንግ ገለጻ አፍሪካ ውስጥ ያላቸው ኢንቨስትመንት "ከፖለቲካ ጋር የተነካካ አይደለም"። የተመደበው 60 ቢሊየን ዶላር ለመሰረተ ልማትና ለወጣቶች ነጻ የትምህርት እድል ለመስጠት ይውላል። • ሁሉንም በደህንነት ካሜራ የምትመለከተው ቻይና • ቻይና የዝሆን ጥርስ ንግድን አገደች ለአህጉሪቱ ሰላምና መረጋጋት፤ ቻይና ወታደራዊ ስልጠና መስጠቷን እንደምትቀጥል ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው አክለዋል። እንደ አውሮፓውያኑ ከ2000 እስከ 2016፤ ቻይና ለአፍሪካ 125 ቢልየን ዶላር ማበደሯን ጥናቶች ያሳያሉ። ገንዘቡ በቀዳሚነት በመንገድ፣ የባቡር ሀዲድ፣ የወደብ ዝርጋታ ላይ ውሏል። ከኬንያ መዲና ናይሮቢ እስከ ሞምባሳ የተዘረጋውና 3.2 ቢሊየን ዶላር የወጣበት ባቡር ሀዲድ በብድሩ ከተሰሩ መካከል ይጠቀሳል። ወደብ አልባዎቹ ሀገራት ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎና ብሩንዲን ከህንድ ውቅያኖስ ጋር ያስተሳስራል ተብሎ ይጠበቃል።
news-53714315
https://www.bbc.com/amharic/news-53714315
ቻዽ፡ 44 እስረኞች በአንድ ምሽት "በመርዝ ራሳቸውን አጥፍተዋል" መባሉ አወዛጋቢ ሆነ
በቻድ እስር ቤት በአንድ ክፍል ውስጥ ከነበሩ እስረኞች መካከል አርባ አራቱ መሞታቸውን ተከትሎ የአሟሟታቸው መንስኤ አወዛጋቢ ሆኗል።
አቃቤ ህግ በበኮ ሃራም አባልነት ተጠርጣሪ ናቸው ያሏቸው እነዚህ እስረኞች በመርዝ ራሳቸውን ገድለዋል ቢሉም ምርመራው ግን ከዚህ ተቃራኒ ነው የሚያሳየው። 46 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ በሆነ ከፍተኛ ሙቀት፣ ውስጥ በአንድ ክፍል ተጨናንቀው በመታሰራቸው እንደሞቱ የብሔራዊ ሰብዓዊ መብት ኮሚሸን የምርመራ ውጤት አሳይቷል። የኮሚሽኑ ሪፖርት የምርመራ ውጤት እንዳተተው ታሳሪዎቹ በከፍተኛ ሁኔታ የተጨናነቀ፣ የሚያቃጥል በሚባል ሙቀት ክፍል ውስጥ ነው ታስረው የነበረው፤ ምግብና ውሃ ተከልክለዋል ብሏል። በተጨማሪም ኮሚሽኑ ግለሰቦቹ ታጣቂዎች ሳይሆኑ ሰላማዊ ዜጎች ናቸው ብሏል። የቻድ የፍትህ ሚኒስትር ድጂመት አራቢ በበኩላቸው የኮሚሽኑን ሪፖርት እንዲሁም የአቃቤ ህግጋቱን መረጃም በመውሰድ የእስረኞቹን አሟሟት የሚያጠናና አዲስ ምርመራ እንዲከፈት ማዘዛቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል። ታሳሪዎቹ ሚያዝያ አጋማሽ ላይ ከመዲናዋ ራቅ ብሎ በሚገኝ እስር ቤት ውስጥ ሞተው ነው የተገኙት። የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች 98 ክርስቲያን ወታደሮችን መግደላቸውን ተከትሎ ነው ጦሩ አካባቢውን ከታጣቂዎች ነፃ ለማድረግ በሚል የስምንት ቀናት ተልዕኮ ያደረገው። በነዚህም ቀናትም አንድ ሺህ ያህል ታጣቂዎችን መግደላቸውን ያሳወቀ ሲሆን ፕሬዚዳንት ኢድሪስ ደቢ ቻድን ከቦኮ ሃራም ታጣቂዎች ነፃ አድርገናልም ብለዋል። 44ቱ እስረኞች አገሪቷ ባደረገችው የጦር ተልዕኮ 58 የቦኮ ሃራም ታጣቂ ተጠርጣሪዎች ተብለው ከተያዙት መካከል ናቸው፥ አርባዎቹ እስረኞች ወዲያው እንደተቀበሩና የአራቱ አስከሬን ደግሞ ለምርመራ ተልኮ መርዝ ተገኝቷል ተብሏል። በህብረት ራሳቸውን እንዳጠፉና ከአያያዝ ጋር የተገናኘ ነው የሚለውንም እንደማይቀበሉ አቃቤ ህጉ አስታውቀዋል። ነፃ የሆነው ኮሚሽን ግን አቃቤ ህግ ከሚለው በሙሉ ተቃራኒ ነው። ግለሰቦቹ አርሶ አደሮች እንደሆኑና የአካካቢውን ነዋሪዎችንም በዘፈቀደ እንዳሰሩ ገልጿል። አገሪቷ የጦር ተልዕኮ አድርጌያለሁ ከምትለውም ጋር ጊዜው እንደማይገጥምም አስፍሯል። ታሳሪዎቹ የተሰጣቸው ምግብም በቀን በቁጥር የሚቆጠር ተምር ሲሆን ለረሃብና ጥማትም ተጋልጠዋል ብሏል። በአንድ ክፍል ውስጥ ከነበሩት እስረኞች መካከል ተራፊ የሆኑትን 14ቱ ለኮሚሽኑ እንደተናገሩት የሙቀት ሁኔታው በጣም ከፍተኛ በመሆኑ በርካቶች ራሳቸውን ስተው መውደቃቸውንና ለእርዳታ ቢጣሩም ችላ እንደተባሉ ነው። "እስረኞቹ ሙሉ ምሽቱን በፀሎት እንዲሁም ለእርዳታ ቢጣሩም ጠባቂዎቹ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለዋቸዋል" በማለትም አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል። የእስረኞቹ ሞትም በአካባቢው ቁጣን ቀስቅሷል።
news-51993423
https://www.bbc.com/amharic/news-51993423
ኮሮናቫይረስ፡ ማኅበራዊ እርቀትን መጠበቅና እራስን ለይቶ መቆየት ምንድንናቸው?
እጅን በአግባቡ ከመታጠብና ከማጽዳት በተጨማሪ ከሰዎች ጋር ያለንን የቀረበ ንክኪ ማስወገድ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ወሳኝ እርምጃ መሆኑ በስፋት እየተነገረ ነው።
በኢትዮጵያ ውስጥና በሌሎችም አገራት ውስጥ ሁሉም ሰው እጅግ በጣም አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ከሰዎች ጋር እጅግ ተጠጋግቶና ንክኪን ማስወገድ እንዲሁም ከቦታ ቦታ የሚደረጉ ጉዞዎችን አለማድረግ በጥብቅ እየተመከረ ነው። ይህም ማኅበራዊ እርቀትን መጠበቅ በሚል በስፋት መልዕክቶች እየተላለፉ ነው። በእርግጥ ስንቶቻችን ይህንን በሽታውን ለመከላከል የሚያስችለውን ዋነኛ አማራጭ እየተገበርነው? በዙሪያችንስ ምን እየታዘብን ነው? ምንም እንኳን የጤና ባለሙያዎችና የመንግሥት ባለስልጣናት በተደጋጋሚ ቢመክሩም በማኅበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ የሚሰፍሩ ጽሁፎችና እየተሰራጩ ያሉ ምስሎች ኢትዮጵያ ውስጥ በርካቶች ማኅበራዊ እርቀትን በመጠበቅ በኩል ቸልተኝነት እንዳለ የሚያመልከቱ ናቸው። በተጨማሪም ከኮሮናቫይረስ በሽታ ምልክቶች ጋር የሚመሳሰሉ ከጉንፋን ጋር የሚያያዙ ምልክቶች ከታዩብን ደግሞ የህመሙ ምንነት እስኪለይ ስረስ ማኅበራዊ እርቀታችንን ከመጠበቅ ባሻገር ወደ ሌሎች በሽታውን ላለማጋባት እራሳችንን ለይተን ማቆየት ይጠበቅብናል። በተለይ ከጉንፋን ጋር የሚዛመዱ ምልክቶች ለምሳሌም ትኩሳት፣ ማስነጠስና ደረቅ ሳል ካለብን ለቤተሰቦቻችንና በዙሪያችን ላሉ ሰዎች ደኅንነት ስንል በቤታችን ውስጥ እራሳችንን ከሌሎች ለይተን ማቆየት ያስፈልገናል። እነዚህ የኮሮናቫይረስን መስፋፋት ለመግታት ወሳኝ የሆኑት ሁለቱ እርምጃዎች ማላትም ማኅበራዊ እርቀትን መጠበቅና እራስን ለይቶ ማቆየትን በተመለከተ ልናውቅ የሚገቡን ነገሮች ምንድን ናቸው? ማኅበራዊ እርቀትን መጠበቅ ሲባል ምን ማለት ነው? ማኅበራዊ እርቀትን መጠበቅ ማለት ከሌሎች ሰዎች ጋር የሚኖርን አላስፈላጊ ቅርርብና ንክኪን ማስወገድ ማለት ነው። ይህም ማለት በርካታ ሰዎች ሊገኙባቸው በሚችሉ የሕዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች ላይ የምናሳልፈውን ጊዜ መቀነስ ወይም ማስቀረት ነው። ሁሉም ሰው በተለይ ደግሞ ከ70 ዓመት በላይ የሆናቸው ሰዎች፣ ነፍሰጡር ሴቶችና ከጉንፋን ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች በዙሪያቸው ካሉ ሰዎች ጋር የሚኖራቸውን መቀራረብ በማስወገድ እርቀታቸውን እንዲጠብቁ ይመከራል። እንዴት አድርገን እርቀታችንን እንጠብቃለን? ከማኅበራዊ ግንኙነት በምንርቅበት ጊዜ ምን ማድግ እንችላለን? እራስን ለይቶ መቆየት ማለት ምን ማለት ነው? እራስን ለይቶ መቆየት ማለት ለአካል ብቃት እንቅስቃሴ ካልሆነ በስተቀር በቤት ውስጥ ሆኖ መቆየት ማለት ነው። ይህም ሲባል በየትኛውም ሰዓት ወደ ሥራ፣ ትምህት ቤትና በርካታ ሰው ወደ ሚሰበሰብባቸው ስፍራዎች አለመሄድ ማለት ነው። የሚቻል ከሆነም ምግብና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን ለመግዛት ከቤት አለመውጣትን ያካትታል። ካልሆነ ግን ከቤት በሚወጣበት ጊዜ ከሰዎች ጋር የሚኖረንን መቀራረብና ንክኪ ለመቀነስ የተቻለንን ያህል ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል። እራስን ለይቶ መቆየት ያለበት ማነው? የኮሮናቫይረስ በሽታ ምክልቶች የሆኑት ትኩሳት፣ የማይቆም ሳልና የመተንፈስ ችግር ያጋጠመው እንዲሁም ምልክቶቹ ከታዩበት ሰው ጋር በአንድ ቤት የሚኖር ማንኛውም ሰው እራሱን ለይቶ ማቆየት ይኖርበታል። ምልክቶቹ የታየበት ሰው በቤቱ ውስጥ ካሉት ሌሎች ሰዎች ተለይቶ መስኮት ባለውና አየር በደንብ በሚያገኝ ክፍል ውስጥ ተለይቶ መቆየት አለበት። ሌሎችስ እነማን ናቸው እራሳቸውን ለይተው መቆየት ያለባቸው? ቀደም ያለና ከባድ የጤና ችግር ያለባቸውን ሰዎች በቫይረሱ ከመያዝ ለመጠበቅ በልዩ ለይቶ የማቆያና የቅድም ጥንቃቄ እርምጃዎች ስር ለ12 ሳምንታት ተለይተው እንዲቆዩ ማድረግ ያስፈልጋል። እነዚህም ሰዎች የሚከተሉት ያካትታል፡ እራሳችንን ለይተን በምንቆይበት ጊዜ በቀላሉ ለጉዳት የተጋለጡ ሰዎች አብረውን የሚኖሩ ከሆነ ምን ማድረግ አለብን? በእድሜ የገፉ ሰዎች፣ ነፍሰጡር ሴቶችና ሌላ የጤና ችግር ያለባቸው ሰዎች አብረውን የሚኖሩ ከሆነ፤ እራሳችንን ለይተን በምንቆይበት ጊዜ ከእነዚህ ሰዎች ቢያንስ በሁለት ሜትር መራቅ አለብን። ማእድ ቤትንና ሌሎች በጋራ በምንቆይባቸው ክፍሎች ውስጥ አብረን የምናሳልፈው ጊዜ የተወሰነ እንዲሆን ማድረግና በክፍሎቹ ውስጥ አየር እንደ ልብ እንዲገባ ማድረግ ይኖርብናል። የሚቻል ከሆነም እነዚህ ለጉዳት ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች ተለይተው ምግባቸውን በክፍላቸው ውስጥ እንዲመገቡ ማድረግ። የምንጠቀምባቸው ፎጣዎችን መለየት ከተጠቀሙ በኋላ ለንክኪ የተጋለጡ የመታጠቢያ ቤት መገልገያዎችን ማጽዳትና ንጽህናቸውን በአግባቡ መጠበቅ። የሚቻል ከሆነም የተለየ መጸዳጃ ቤት እንዲጠቀሙ ማድረግ። እራሳቸውን ለይተው በመቆየት ላይ ካሉ ሰዎች ጋር የሚኖሩ ሰዎች በተለይ በየትኛውም አጋጣሚ ንክኪ ካላቸው ወይም እቃዎችን ከነኩ በኋላ አዘውትረው እጃቸውን ለ20 ሰከንዶች በሳሙናና በውሃ መታጠብ ይኖርባቸዋል። ለጽዳት የተጠቀምንባቸውን ሶፍትን የመሳሰሉ ቆሻሻዎችን በድርብ የፕላስቲክ መያዣ ውስጥ ለ72 ሰዓታት ለይቶ በጥንቃቄ በማስቀመጥ ከዚያም ከሌሎች ቆሻሻዎች ጋር እንዲወገድ ማድረግ ያስፈልጋል። ስለዚህም ከኮሮናቫይረስ እራሳችንንና ሌሎችን ለመጠበቅ የግድ ካልሆነ በስተቀር በቤታችን ውስጥ መቆየት ወሳኝ እርምጃ ነው። ከዚህ ባሻገር ግን በየትኛውም ቦታና አጋጣሚ መገኘት ካለብን ከሌሎች ሰዎች ጋር የሚኖረን እርቀት ከሁለት ሜትር ያነሰ እንዳይሆን ማድረግ አለብን። ይህም ማኅበራዊ እርቀትን መጠበቅ ማለት ይሆናል። በተጨማሪም የበሽታው ምልክቶች በእራሳችንም ሆነ ከእኛ ጋር የቅርብ ንክኪ ባላቸው ሰዎች ላይ ከታየ ከሰባት እስከ 14 ቀናት እራሳችን ከሌሎች ሰዎች ለይተን በቤት ውስጥ በማቆየት የበሽታው ሁኔታ እስኪለይ ድረስ መጠበቅ ያስፈልጋል። ይህም እራስን ለይቶ ማቆየት እርምጃ ነው። ከዚህ ባሻገር ስለበሽታውና ስላለንበት ለቅርብ ሰዎቻችን ማሳወቅ እንዲሁም ድጋፍ ለማድረግ በተዘጋጁ የነጻ የስልክ መስመሮች 8335 ወይም 952 ላይ በመደወል ምክርና ድጋፍ ማግኘት ይቻላል።
news-55255846
https://www.bbc.com/amharic/news-55255846
አቶ ልደቱ አያሌው ከወራት እስር በኋላ በ30 ሺህ ብር ዋስትና ተፈቱ
ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው ከአምስት ወራት አስር በኋላ በገንዘብ ዋስትና ከአስር መውጣታቸውን የኢትዮጵኣዊያን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አዳነ ታደሰ ለቢቢሲ ተናገሩ።
አቶ ልደቱ በ30 ሺህ ብር ዋስትና ተፈተው ለወራት ፍርድ ቤት ያመላለሳቸውን ጉዳያቸውን ከውጪ ሆነው እንዲከታተሉ የወሰነው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምሥራቅ ሸዋ ችሎት መሆኑን ጠበቃቸው አቶ አብዱል ጀባር ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ከአቶ ልደቱ ጠበቆች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ አብዱልጀባር ሁሴን እንደተናገሩት፤ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምሥራቅ ሸዋ ችሎት ዛሬ በዋለው ችሎት አቶ ልደቱ በ30 ሺህ ብር ዋስትና ጉዳያቸውን ከውጪ ሆነው እንዲከታተሉ ፈቅዷል። የአቶ ልደቱ ፓርቲ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፕሬዚዳንት አቶ አዳነ ታደሰ ለዋስትና የተጠየቀውን ገንዘብ በመክፈል አስፈላጊውን ሁኔታ አሟልተው ከሰዓት በኋላ ከአስር መውጣታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ፍርድ ቤቱ ከዚህ ቀደም አቶ ልደቱ ላይ "ሕገ-መንግሥቱን እና ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን መናድ" በሚል የቀረበባቸው ክስ እንዲሻሻል ባዘዘው መሠረት ዐቃቤ ሕግ የተሻሻለውን ክስ ለፍርድ ቤት አቅርበዋል ብለዋል። "የተሻሻለውን ክስ ዐቃቤ ሕግ አቅርቦ ነበር። እኛም በቀረበው ክስ ላይ መቃወሚያ አሰምተን፤ አቶ ልደቱ የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ፍርድ ቤቱን ጠየቅን" ብለዋል አቶ አብዱልጀባር። በዚህም መሠረት ፍርድ ቤቱ አቶ ልደቱ በ30 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር ተለቀው ጉዳያቸውን ከውጪ ሆነው እንዲከታተሉ መበየኑን ተናግረዋል። ዐቃቤ ሕግ በዋስትና መብቱ ላይ መቃወሚያ የለንም ማለታቸውን ጠበቃው አብዱልጀባር ሁሴን ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ልደቱ ከወራት በፊት በተመሳሳይ በ100 ሺህ ብር የዋስትና መስያዣ ከእስር እንዲወጡ በፍርድ ቤት እንዲወጡ ቢታዘዝም ጉዳዩ በእንጥልጥል ቆይቷል። የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በቢሾፍቱ ከተማ የተፈጠረውን ሁከት በማነሳሳት፣ በመምራትና በገንዘብ መደገፍ በሚል ወንጀል ተጠርጥረው ነበር አቶ ልደቱ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይታወሳል። የአቶ ልደቱ አያሌው ጉዳያቸውን ሲያይ የነበረው ፍርድ ቤት "ሁከት በማነሳሳት፣ መምራትና በገንዘብ መደገፍ" የሚለውን ክስ ከዘጋው በኋላ "ያልተፈቀደ የጦር መሳሪያ መያዝ" የሚል ሌላ ክስ ተመስርቶባቸው ነበር። ይህም ክስ ውድቅ ከተደረገ በኋላ፤ "ሕገ-መንግሥቱን እና ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን መናድ" የሚል አዲስ ክስ ተመስርቶባቸዋል። ። የአቶ ልደቱን ጉዳይ ከዚህ በፊት ሲያይ የነበረው በቢሾፍቱ ከተማ ይገኝ ከነበረው ፍርድ ቤት በመውጣት ጉዳያቸው አዳማ ከተማ በሚገኝ ፍርድ ቤት ሲታይ ቆይቷል። አቶ ልደቱ ኢዴፓን ከመሰሩቱ ፖለቲከኞች መካከል አንዱ ሲሆኑ በ1997 ዓ.ም ምርጫ ወቅት ከፍተኛ ተጽእኖን ፈጥሮ ከነበረው ቅንጅት ውስጥም ጉልህ ሚና ከነበራቸው ሰዎች መካከል አንዱ እንደሆኑ ይታወቃል።
news-53511871
https://www.bbc.com/amharic/news-53511871
ማይክ ታይሰን ወደ ቦክስ መድረክ ሊመለስ ነው
የቀድሞው የከባድ ሚዛን የቦክስ ሻምፒዮን ማይክ ታይሰን ወደ ቡጢው ዓለም ሊመለስ ነው።
ዝነኛው የቦክስ ተፋላሚ ማይክ ታይሰን ዕድሜው 54 ደርሷል። ወደ ቦክስ መፋለሚያ መድረክ የመመለሱ ዜና እያነጋገረ ነው። ማይክ ታይሰን ለአጭር ደቂቃ በሚቆየው ፍልሚያ የሚገጥመው የአራት ጊዜ የቀድሞው የዓለም ሻምፒዮን የነበረውን ሮይ ጆንስ ጁኒየርን ይሆናል። ሁለቱ ዝነኞች ለዚሁ ግጥሚያ የሚገናኙት መስከረም 12 ላይ በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ ውስጥ ነው። ማይክ ታይሰን ለመጨረሻ ጊዜ ደንበኛ የቦክስ ግጥሚያ አደረገ የሚባለው እንደ አውሮፓዊያኑ በ2005 ነበር። በዚያ ውድድር ላይ በአየርላንዳዊው ተወዳዳሪ ኬቪን ማክብራይድ ክፉኛ ተደብድቦ ነበር። ይህም ታይሰን ካደረጋቸው 58 የቡጢ ፍልሚያዎች 6ኛው ሽንፈቱ ነበር። በመጪው መስከረም ወር ታይሰንን የሚገጥመው ጆንስ ዕድሜው 51 ሲሆን በየካቲት 2018 ቡጢኛ ስኮት ሲግመንን ካሸነፈ ወዲህ ውድድር አድርጎ አያውቅም። የካሊፎርኒያ ግዛት የአትሌቲክስ ኮሚሽን ይህ የቡጢ ፍልሚያ ሰዎች በተገኙበት እንዳይካሄድ ያዘዘ ሲሆን፤ ውድድሩ በክፍያ ብቻ በቀጥታ ይተላለፋል ተብሏል። ፍልሚያው 8 ዙሮች ይኖሩታል። ማይክ ታይሰን የዓለም የከባድ ሚዛንን ሻምፒዮና የሆነው ገና በ20 ዓመቱ ነበር። ይህም የሆነው በፈረንጆቹ በ1986 ትሪቨር በርቢክን ማሸነፉን ተከትሎ ነው። በቅርቡ ታይሰን በማኅበራዊ ሚዲያ የቦክስ ልምምድ ሲያደርግ የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች መውጣታቸውን ተከትሎ ወደ ቦክስ ስፖርት ሊመለስ ነው የሚሉ ጉምጉምታዎች እዚያም እዚህም መሰማት ጀምረው ነበር። በ2006 ታይሰን ተመሳሳይ አራት ዙር የቦክስ ግጥሚያ ከኮሪ ሳንደርስ ጋር ማድረጉ ይታወሳል። ያም የሆነው ማይክ ታይሰን በ2003 የገንዘብ ኪሳራ ገጥሞት ስለነበረና ገንዘብ ስላስፈለገው ነበር። በቅርብ ጊዜ ደግሞ ማይክ ታይሰን ከኢቫንደር ሆሊፊልምድ ጋር ዳግም ሊገጥም ይችላል የሚሉ ወሬዎች መውጣት ጀምረው ነበር። የ57 ዓመቱ ሆሊፊልድ ከቡጢ ራሱን ያገለለው በ2016 ነበር። ከታይሰን ጋር በ1990ዎቹ ሁለት ጊዜ በቦክስ መድረከረ ላይ ተገናኝተው ሁለቱንም ጊዜ ሆሊፊልድ ድል ቀንቶት ነበር። ከዚህ ውስጥ በብዙዎች አእምሮ የቀረው በ1997 ታይሰን የሆሊፊልመድን ጆሮ መንከሱ ነበር። የታይሰን የአሁኑ ተጋጣሚ ጆንስ ጁኒየር ስለ ውድድሩ በለቀቀው የቪዲዮ ማስታወቂያ "የታይሰንና የእኔ ወድድር የዳዊትና የጎሊያድ ፍልሚያ ነው የሚሆነው" ሲል ቀልዷል።
42480106
https://www.bbc.com/amharic/42480106
ቻይና ባሕር ላይ የሚያርፍ ግዙፍ አውሮፕላን ሞከረች
ቻይና በዓለም ላይ ግዙፍ በመሬትና በውሃ ላይ ማረፍ የሚችል አውሮፕላን ሰርታ የተሳካ የአንድ ሰዓት የሙከራ በረራ አደረገ።
የደቡባዊ ቻይና ግዛት ከሆነችው የጓንግዶንግ ዡሃይ አየር ማረፊያ ተነስቶ የሙከራ በረራውን ያደረገው ይህ በውሃ ላይም ማረፍ የሚችል አውሮፕላን ቦይንግ 737ን የሚያክል ሲሆን ባለአራት ሞተር ነው። አውሮፕላኑ እስከ 50 የሚደርሱ ሰዎችን አሳፍሮ በአየር ላይ ለ12 ሰዓታት ሊቆይ ይችላል። ይህ አውሮፕላን በእሳት አደጋ ወቅትና በባህር ላይ በሚያጋጥሙ አደጋዎች ነፍስ የማዳን ተግባራት ላይ መሰማራት ከመቻሉም በላይ ለወታደራዊ አገልግሎት ሊውል ይችላል። በተለይ በአወዛጋቢው የደቡብ ቻይና ባሕር አካባቢ ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚችል ተነግሯል። ይህ ኤጂ600 በመለያ ስም ኩንሎንግ የተባለው አውሮፕላን ቻይና የእኔ ናቸው ወደምትላቸው ደቡባዊ የባሕር ግዛቶች ድረስ የመጓዝ አቅም አለው። የቻይና መንግሥት የዜና ወኪል የሆነው ዥንዋ አውሮፕላኑን ''የባሕር ጠረፍንና ደሴቶችን የሚጠብቅ መንፈስ'' ሲል ገልፆታል። አውሮፕላኑ ሲነሳ በሀገሪቱ የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን በቀጥታ ተላልፏል፤ ሲያርፍም በሰንደቅ ዓላማና በወታደራዊ ሙዚቃዎች በታጀቡ ዜጎች አቀባበልተደርጎለታል። የግንባታው ሂደት 8 ዓመታትን የፈጀው ይህ አውሮፕላን መሸከም የሚችለው ከፍተኛ ክብደት 53.5 ቶን ያህል ነው። ከአንዱ ክንፍ እስከሌላኛው ደግሞ 38.8 ሜትር ይረዝማል። በቻይና ብቻ እስካሁን 17 የግዢ ጥያቄዎች መቅረባቸውም ተዘግቧል። ከዚህ አውሮፕላን ቀደም ብሎ የተሰራው በራሪው ጀልባ በመጠን ከፍ ያለ ነበር። ስፕራውስ ጉዝ ወይንም ደግሞ በቴክኒክ ስያሜው ሁግስ ኤች-4 ሔርኩልስ 97.54 የሚረዝም ክንፍ ነበረው። ምንም እንኳ በ1947 ለ26 ሰከንድ ብቻ የቆየ በረራ አንዴ አድርጎ ቆሟል። በአሁኑ ወቅትም በኦሪገን ሙዚየም ተቀምጦ ይጎበኛል። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ለአሜሪካ ጦር መጓጓዣ እንዲሆን ተብሎ የተሰራ ሲሆን የክንፎቹ ርዝማኔ 61 ሜትሮች ያህል ነበር።
news-49880257
https://www.bbc.com/amharic/news-49880257
ጤፍ ከእንጀራ አልፎ አሜሪካ ውስጥ ቢራ ሆነ
ከጤፍ የተሠራው "አዲስ ጤፍ አምበር ኤል" የሚል ስያሜ የተሰጠው ቢራ ሰኞ ዕለት በአሜሪካ ለገበያ መቅረቡን የአምራች ኩባንያው ንጉሥ ቢራ የሥራ ተወካይ አቶ ሚካኤል አለሙ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
በዕለቱም በሦስት የአሜሪካ ግዛቶች ዋሽንግተን ዲሲ፣ ሜሪላንድና ቨርጂኒያ ውስጥ ለተደረገው ሥርጭት 20 ሺህ ጠርሙሶች ከጤፍ የተመረተ ቢራ ቀርቧል። በኢትዮጵያዊያንና በኤርትራዊያን ዘንድ ዋነኛ ምግብ የሆነውን የጤፍ እህልን ወደ ቢራነት መቀየሩ አዲስ ሃሳብ ከመሆኑ አንፃር 'አዲስ የሚል ስያሜ የተሰጠበትን ምክንያት አቶ ሚካኤል ያስረዳሉ። • ጤፍን ሰዳ የምታሳድደው ኢትዮጵያ ቢራው ከሠርገኛ ጤፍ የተሰራ ሲሆን የአልኮል መጠኑም 5.4 በመቶ ነው። ለጊዜው አንድ አይነት ቢራ ብቻ የቀረበ ሲሆን ከነጭ ጤፍ የተሰራውም በቅርቡ ለገበያ እንደሚውል እቅድ ተይዟል። የጤፍ እህል እጥረትም ሆነ ስጋት እንዳይፈጠር፤ የጤፍ ምርታቸውን ከአሜሪካ ከሚገኙ ገበሬዎች የሚያገኙ ሲሆን አሜሪካ ለሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን ተጠቃሚዎችን ፍላጎት በማይነካ መልኩ እየሠሩ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተው ይናገራሉ። • ጤፏን ለማስመለስ እየተውተረተረች ያለችው ኢትዮጵያ "ጤፍን ለቢራነት ስንጠቀም ሊወደድብን ይሆን የሚል ሁኔታን ሊፈጥር ይችላል" የሚሉት አቶ ሚካኤል እሱ እንደማይፈጠርም ያስረዳሉ። ለወደፊቱም ጤፍ ዘርተውና አብቅለው ቢራውን የማምረት እቅድንም ይዘዋል። ቢራ ከጤፍ ለምን? ኢትዮጵያ ቡናን ጨምሮ የተለያዩ አዝርዕቶችና መገኛ ብትሆንም የሕዝቡም ሆነ የአገሪቷ ተጠቃሚነት በጣም ዝቅተኛ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ሚካኤል፤ የጤፍ ምርትንም እንደ ምሳሌ ይጠቅሳሉ። የጤፍ ምርትን በባለቤትነት ለማስመዝገብ የሚደረገው እሽቅድድም የሚጠቀስ ሲሆን ከዚህ በፊትም ማሽላን ኢትዮጵያ ማስመዝገብ ባለመቻሏ በአንድ የካናዳ ኩባንያ መነጠቋ የሚታወስ ነው። ዓለም አቀፍ የኦንላይን መገበያያ በሆነው አማዞን ላይ የአሜሪካ ገበሬዎች ከጤፍ የተለያዩ ምርቶችን፤ ለምሳሌ የጤፍ ፓስታና ከግሉተን ነፃ የሆነ ዳቦ በማምረት ይሸጣሉ። ከዚህም በተጨማሪ በጤፍ ላይ የተደረጉ የምርምር ውጤቶች እንደሚያሳዩት በንጥረ ነገሩ የተሻለ ይዘት ያለውና 'ቀጣዩ ልዕለ ምግብ' (ዘ ኔክስት ሱፐር ፉድ) እንደሆነ የሚናገሩት አቶ ሚካኤል ይህም ምርት ከዚህም አንፃር ኢትዮጵያዊያን ተጠቃሚ ለማድረግ አልሞ ተነስቷል ይላሉ። • ፍርድ ቤት የቀረበው የጤፍ ባለቤትነት ጉዳይ "እኛም የሃገራችን ምርት ላይ ቀድመን አንድ ነገር አናደርግም፤ ምክንያቱም ብዙ ጊዜ የእኛ ነበር ማለት እንጂ፤ እኛ ምንም ነገር አድርገን አናልፍም የሚለው ነገር ነው ለዚህ ያነሳሳን" ይላሉ። ንጉሥ ቢራ ከጤፍ ቢራን ለማምረት ሃሳቡን ከጠነሰሰ ስምንት ዓመታትን ያህል ያስቆጠረ ሲሆን፤ ከሦስት ዓመት ወዲህ ፈቃዱን አውጥቶ ወደ ሥራ ገብቷል። ኩባንያው እስካሁን ድረስ የሚታወቅበት ፕሪምየም ክራፍት ላገር ሲሆን በዲሲ፣ ሜሪላንድና ቨርጂኒያ ግዛቶች (ዲኤምቪ) ግዛቶች በተጨማሪ በኒውዮርክ ፈቃዳቸውን የጨረሱ ሲሆን በቦስተን፣ ሚኒሶታና ጆርጂያም እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ናቸው። ለዘመናት ቢራ የሚመረተው ከገብስ ብቻ የነበረ ሲሆን ጊዜያት በኋላ የፍራፍሬ ጣዕም ያላቸው ቢራዎች በመምጣታቸውና የቤልጂየም ቢራዎች ወደ ገበያው ሰብረው መግባታቸው መነሻ እንደሆናቸውም ይጠቅሳሉ። በተለይም የቤልጂየም ምርት የሆነውና ስንዴን ጨምሮ፣ ከብርቱካን ልጣጭ እንዲሁም ከአጃ የሚሰራው የብሉ ሙን ቢራ መምጣት ገበያውን እንደቀየረው ይናገራሉ። ባደረጉት ጥናትም ብሉ ሙን በኢትዮጵያዊያን ዘንድ ተወዳጅ መሆኑ መነሻ ሆኗቸዋል። ከዚህም በመነሳት በጤፍ ላይ ምርምር ቢያደርጉ እንዲሁም ከጤፍ ቢራ ቢሰሩ ሃገሪቷንም ሆነ ጤፍን የማሳወቅ እድል እንደሚፈጥር ተስፋ በማድረግም እንዳመረቱት ያስረዳሉ። ነገር ግን ማምረቱ ቀላል እንዳልነበር የሚናገሩት አቶ ሚካኤል ጤፍ ባለው የተለየ ባህሪ ምክንያት ከከፍተኛ ምርምርና ሙከራ በኋላም ተሳክቷል። "ጤፍ በባህሪው ይተኛል፤ እንዲሁም ይዘቅጣል እሱ እንዳይሆን በቴክኖሎጂ በመታገዝ ንቁ በሆነ መንገድ እንዲብላላ (ፈርመንት) እንዲያደርግ ብዙ ሥራ ሰርተናል" ይላሉ። የጤፍ ቢራ ጣዕም ምን አይነት ይሆን? የተለያዩ ንጥረ ነገሮችን በመጠቀም እንደተፈለገው አይነት ጣዕም ማምጣት እንደሚቻል የሚናገሩት አቶ ሚካኤል ቢራ ወፈር (ጠንከር) ሲል ሰው ስለማይመርጠው አሁን ገበያ ላይ የዋለው ቢራ ቀላል እንደሆነ ገልፀዋል። ሠላሳ ሦስት ዶላርም ለመሸጥ የታቀደው ይህ ቢራ ጤፍ ያለውን የራሱን ይዘት እንዳያጣ አድርገው፤ ከቢራም ጣዕም ራቅ እንዳይል ተደርጎ እንደተቀመመም ጨምረው አስረድተዋል። በአሁኑ ወቅት ምርቶቹ የሚሸጡት አሜሪካ ሲሆን በያዙትም እቅድ መሰረት ከሦስት ዓመታት በኋላ ወደ ወደ ኢትዮጵያ የመላክ እንዲሁም በከፊል ኢትዮጵያ ውስጥ ገብተው የቢራ ፋብሪካ የመጀመርም እቅድ እንዳለም ጨምረው ገልፀዋል። ንጉሥ ቢራ ኩባንያ የተቋቋመው በሶስት በትውልደ ኢትዮጵያዊያን ቢሆንም ባለቤትነቱ አሜሪካ የሚገኙ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን የማድረግ እቅድና ሁሉም የሚሳተፍበት የማድረግ አላማ አላቸው። • "ልዩ ነዳጅ መኖሩን አልደረስንበትም" የማዕድን፣ የፔትሮሊየምና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን ዲያስፖራ የሚሳተፉበት ትልቅ ፋብሪካ የማቋቋም፣ ከጀርባው መዝናኛዎችና ብሪው ፐብ (መቅመሻዎችን) የማቋቋም እቅድ ያላቸው ሲሆን ለወደፊትም ጠጅና ጠላን በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪነቱን በጠበቀ መልኩ ለማምጣትም አስበዋል። "እዚህ አገር ላይ ያለን ኢትዮጵያዊኖችና ኤርትራዊያን ተባብረን መስራት ከቻልን አሁን እዚህ አገር ላይ እንዳሉት ሌይማርት፣ ኤችማርት እንዲሁም ሌሎች በቻይኖችና በኮርያዎች የተቋቋሙ አክስዮኖች አንድ ላይ በመስራታቸው ትልቅ ደረጃ ላይ መድረስ ይቻላል" ይላሉ።
news-53627275
https://www.bbc.com/amharic/news-53627275
ፌስቡክ የብራዚሉን ፕሬዚዳንት ደጋፊዎች አካውንት እንዲዘጋ ታዘዘ
የብራዚል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፤ ፌስቡክ የፕሬዚዳንት ጄር ቦልሶናሮ በርካታ ደጋፊዎች የፌስቡክ ገፅ እንዲዘጋ ትዕዛዝ አስተላለፈ።
የደጋፊዎች ቡድኑ የተከሰሰው በዳኞች ላይ ሃሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት ሲሆን የማህበራዊ ሚዲያ ተቋሙ ፌስቡክ ግን ውሳኔው ከመናገር ነፃነት ጋር የሚፃረር ነው ሲል በጉዳዩ ላይ ይግባኝ እንደሚጠይቅ አስታውቋል። ፌስቡክ ኮንግረሱንና ጠቅላይ ፍርድቤቱ እንዲዘጋ ለማድረግ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ለመጥራት አገልግሎት ላይ ውሏል ብሏል- ፍርድ ቤቱ። ግንቦት ወር ላይ ፌስቡክ 12 ገፆችን እንዲዘጋ የታዘዘ ሲሆን ትዊተርም 16 ገፆችን እንዲዘጋ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ አስተላልፎ ነበር። አርብ ዕለት የብራዚል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፌስቡክ እነዚህ የፌስቡክ ገፆች ከየትኛውም የዓለም ክፍል አገልግሎት እንዳይሰጡ አልዘጋም በማለቱ 368 ሺህ ዶላር የቀጣ ሲሆን፤ በወቅቱ ፌስቡክ ገፆቹ ከብራዚል ብቻ መጠቀም እንዳይቻል ለመዝጋት ነበር የተስማማው። ከዚህም በተጨማሪ የተላለፈውን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ አልተገብርም በማለቱ በቀን 19 ሺህ 184 ዶላር እንዲከፍል ወስኖበታል። ይሁን እንጂ ቅጣቱ በተመሳሳይ መልኩ በትዊተርም ላይ ስለመጣል አለመጣሉ የታወቀ ነገር የለም። ፌስቡክ በበኩሉ ባወጣው መግለጫ የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ከዓለም አቀፍ ሕግ እና ሥልጣን ጋር የሚጋጭ ነው ሲል ተቃውሞታል። ድርጅቱ አክሎም ለፍርድቤቱ ይግባኝ እንደሚል ጠቅሶ " በአገሪቷ ባሉ የድርጅቱ ሰራተኞች ላይ የወንጀል ተጠያቂነት ስጋት የፈጠረ በመሆኑ፤ የፌስቡክ ገፆቹ ከየትኛውም የዓለም ክፍል አገልግሎት እንዳይሰጡ የተላለፈውን ውሳኔ ከመተግበር ውጪ በዚህ ጊዜ ሌላ አማራጭ የለንም" ብሏል። በዚህም መሠረት ከተዘጉ ገፆች መካከል የፓርቲው መሪና የፕሬዚዳንቱ ታማኝ ሮበርቶ ጀፈርሰን እና ሉሲያኖ ሃንግ የተባሉ የብራዚል ታዋቂ የቢዝነስ ሰው ይገኙበታል። ፌስቡክ ሐምሌ ወር ላይም ጋዜጠኛና የዜና ገፆች በመምሰል የተከፈቱ በርካታ ሃሰተኛ የፌስቡክና የኢንስታግራም ገፆችን ዘግቷል። እነዚህ ገፆች በፕሬዚደንቱ ጽህፈት ቤቶች ሰራተኞች እንዲሁም ከልጆቻቸው ኤድዋርዶ እና ፈላቪዮ እና ሌሎች ጋር የተያያዙ እንደነበሩ ፌስቡክ ገልጿል። ፌስቡክና ትዊተር የጥላቻ ንግግሮችን እና ሐሰተኛ መረጃዎችን ለመዋጋት በሚያደርጉት ጥረት ውጥረት ውስጥ ናቸው።
news-56072930
https://www.bbc.com/amharic/news-56072930
ኮካ-ኮላ ከወረቀት በተሠራ ኮዳ ብቅ ሊል ነው
ኮካ-ኮላ ምርቶቹን በፕላስቲክ ከማሸግ ለመቆጠብ ባቀደው መሠረት በወረቀት ኮዳዎች ብቅ ሊል መሆኑን አስታውቋል።
ኮካ ኮላ የመጀመሪያውን ሙከራውን በሁለት ሺህ የወረቀት ቡትሌዎች ለመሞከር አቅዷል ፔፐር ቦትል በተባለው የዴንማርክ ኩባንያ የሚመረቱት የወረቀት ኮዳዎች ጠንከር ካለ ወረቀትና ከቀጭን ፕላስቲክ የሚሠሩ ናቸው። ነገር ግን በጊዜ ሂደት ኩባንያው ሙሉ በሙሉ ከወረቀት በተሠራ ኮዳ ኮካ-ኮላ ለማከፋፈል አቅዷል። አዲሱ ከወረቀት የሚሠራ ኮዳ ምንም ዓይነት ፋይበር ወደ ፈሳሹ እንዳይገባ ማድረግ አለበት። ይህን ማድረግ ካልቻለ ግን የኮካ-ኮላ ጣዕም ሊቀየር እንዲሁም ጤና ላይ አደጋ ሊያመጣ እንደሚችል ተነግሯል። ነገር ግን ታላላቅ ኩባንያዎች የኮካ-ኮላ ተግባር ይበል የሚያሰኝ ነው እያሉ ነው። ኮካ በፈረንጆቹ 2030 ምንም ዓይነት ተረፈ ምርት የሌለው ምርት ለማምረት ቆርጦ ተነስቷል። 'ብሬክ ፍሪ ፍሮም ፕላስቲክ' የተሰኘ አንድ ኩባንያ ኮካ-ኮላ በዓለማችን በካይ ፕላስቲክ አምራች ኩባንያ ነው ሲል ባለፈው ዓመት ፈርጆት ነበር። ፈተና የሚሆነው የወረቀት ኮዳው መሰል መጠጦች የሚፈጥሩትን ግፊት መቋቋም እንዲችል ማድረግ ነው። እንደ ኮላና ቢራ ያሉ መጠጦች ግፊት ተጨምሮባቸው ስለሚታሸጉ የወረቀት ኮዳው ይህንን መቋቋም አለበት። አልፎም የወረቀት ቡትሌው ኩባንያዎች በሚፈልጉት ልክና ቅርፅ ተጣጣፊ እንዲሆን ይጠበቅበታል። የኩባንያዎቹ ስም የሚፃፍበት ቀለምም ወደ ውስጥ እንዳይሰርግ ሆኖ ሊሠራ ይገባዋል። ኮዳ አምራቹ ኩባንያ ከሰባት ዓመታት ሙከራ በኋላ ይህን ወረቀት ማምረት ችያለሁ እያለ ነው። የወረቀት ኮዳዎቹ በሚቀጥለው ክረምት ሃንጋሪ ውስጥ አዴዝ የተሰኘው የኮካ-ኮላ የፍራፍሬ መጠጥ ታሽጎባቸው ለገበያ ይቀርባሉ ተብሏል። አብሱሉት የተሰኘው ቮድካ አምራች ኩባንያ 2 ሺህ የሚሆኑ በወረቀት ኮዳ የታሸጉ መጠጦችን አምርቶ ዩኬና ስዊድን ውስጥ ለገበያ ለማቅረብ ተሰናድቷል። ቢራ አምራኡ ካርልስበርግ ደግሞ ለቢራዎቹ የሚሆኑ የወረቀት ኮዳዎችን ለማምረት ደፋ ቀና እያለ ነው። ኮካ-ኮላ እንዲሁም አብሶሉት የተሰኙት ፋብሪካዎች በቅርቡ የሚያደርጓቸው ሙከራዎች በወረቀት የታሸጉ መጠጦች እንዴት ከቦታ ቦታ ሊጓጓዙ ይችላሉ የሚለውንም መለያ ናቸው። ኮካ-ኮላ የወረቀት ኮዳዎቹ ከፈሳሹ ጋር ግንኙነት እንዳይኖራቸው ለማድረግ ሲል የኮዳዎቹን ውስጠኛ አካል ከእፅዋት በተሠራ ቁስ ሊለብጠው አስቧል። ለጊዜው የወረቀት ኮዳዎቹ የፕላስቲክ ቆርኪ ቢኖራቸውም በጊዜ ሂደት ወደ ወረቀት ይቀየራሉ ተብሏል።
47944679
https://www.bbc.com/amharic/47944679
የአጤ ቴዎድሮስ የልጅ ልጆች
አጤ ቴዎድሮስ "መይሳው ካሳ" እያሉ ይፎክሩ ነበር አሉ። ጠላታቸውን ጥለው ሲሸልሉ "መይሳው ካሳ፣ አንድ ለናቱ ሺ ለጠላቱ" ብለው ይፎክሩ እንደነበር ይነገራል።
ዘመናዊ ኢትዮጵያን ለመፍጠር ጥረት ያደረጉት አጤ ቴዎድሮስ፣ ያለሙትን ለውጥ ለማምጣት ሳይሳካላቸው ከሀገር ውስጥና ውጪ በተቀሰቀሰባቸው ተቃውሞ ምክንያት የእንግሊዝ ጦርን ተፋልመው በሚያዚያ ወር 1860 መቅደላ አምባ ላይ እራሳቸውን ሰዉ። በመቅደላ ጦርነት ወቅት ለእንግሊዞች እጅ አልሰጥም ብለው ራሳቸውን ያጠፉት የአፄ ቴዎድሮስን ቁንዳላም ከ150 ዓመታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰው በቅርቡ ነው። አጤ ቴዎድሮስ በጀግንነት እና በሀገር አንድነት ያልተነሱበት የኢትዮጵያ ጫፍ ያለ አይመስልም። ቴዎድሮስ "አጤ" ከመባላቸው በፊት ስማቸው ካሣ ኃይሉ እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ፡፡ አጤ ቴዎድሮስ የተባሉት የሰሜኑን ገዥ ደጃዝማች ውቤን፤ ደረስጌ ላይ ድል አድርገው ዘውድ ከጫኑ በኋላ ነው። • የአፄ ቴዎድሮስ ቁንዳላ ሊመለስ ነው • ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ስለተዘረፉ ቅርሶች ምን እናውቃለን? አጤ ቴዎድሮስ በኢትዮጵያዊያን ልብ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በሥነ ጽሑፉ ዓለም ውስጥም ስማቸው ገናና ነው። በልቦለድ ሥራዎች ውስጥ እንፈልጋቸው ብንል የብርሃኑ ዘሪሁን የቴዎድሮስ እንባ፣ የአቤ ጉበኛ አንድ ለናቱን እናገኛለን፣ በተውኔት ደግሞ የሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን አጤ ቴዎድሮስና የጌትነት እንየው የቴዎድሮስ ራዕይን መጥቀስ እንችላለን። ስማቸው በዘፈን ያልተነሳበት፣ ያልተወሳበትም ዘመን የለም። ኢትዮጵያን ያነሳ፣ ጎንደርን የጠቀሰ ስለ አጤው ያዜማል። ጎንደር፣ ጎንደር፣ የቴዎድሮስ አገር፤ ለአንዲት ኢትዮጵያ ዋልታና ማገር የሚለው የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የቅርብ ጊዜ ዜማን ማስታወስ በቂ ነው። አጤ ቴዎድሮስ መቅደላ ላይ ከእንግሊዝ አገር ከመጡ 32 ሺህ ወታደሮች ጋር ተዋግተው ራሳቸውን ማጥፋታቸውን ተከትሎ በሀገሪቷ ላይ ከፍተኛ ዘረፋ እንደተፈፀመ የታሪክ መዛግብት ያወሳሉ። የእንግሊዝ ወታደሮች የዘረፉት መጻሕፍትን፣ የተለያዩ ከወርቅ የተሠሩ ቅርሶችን፣ መንፈሳዊ ሥዕሎችን፣ ታቦታትን፣ ታሪካዊና ባሕላዊ ቅርሶችን ብቻ ሳይሆን ልጃቸው አለማየሁ ቴዎድሮስንም ጭምር ነው። አለማየሁ በሰው ሀገር በብቸኝነት፣ በለጋ እድሜው መሞቱና እዚያው መቀበሩ ይታወቃል። ሌሎች የአጤው ዘመዶችስ? የት ናቸው? የአጤ ቴዎድሮስ የልጅ ልጆች የአጤ ቴዎድሮስ የልጅ ልጆች ለበርካታ ኢትዮጵያዊያን የአጤ ቴዎድሮስ ልጅ ተብሎ የሚታወቀው ልዑል አለማየሁ ብቻ ነው። በርግጥ አጤው ሌላ ልጅ የላቸውም? ስንል እንፍራንዝ ያገኘናቸውን ወ/ሮ አበበች ካሳን ጠየቅናቸው። በእርግጥ በጊዜው በአጠገባቸው የተገኘው ልጅ እርሱ ነበር። ለዚህም ይሆናል የእርሱ ስም ብቻ የሚነሳው ሲሉ ሌሎች ስድስት ልጆች እንዳሏቸው ነገሩን። እኛም እስቲ ስማቸውን ይዘርዝሯቸው ስንል ጠየቅን፦ "በጎጃም ኃይሉ ቴዎድሮስ፣ በወሎ ይማም ቴዎድሮስ፣ በትግራይ አልጣሽ ቴዎድሮስ፣ በጎንደር አለማየሁ ቴዎድሮስና መሸሻ ቴዎድሮስ" ሲሉ ዘረዘሯቸው። ታዲያ እርስዎ አጤ ቴዎድሮስን ይዛመዳሉ ማለት ነው? ቀጣይ ጥያቄያችን ነበር። "ዛዲያሳ" የእርሳቸው መልስ። የማን ልጅ ነዎት ተከታይ ጥያቄያችን አደረግን የደጃዝማች ካሳ መሸሻ ቴዎድሮስ፣ የአጤ ቴዎድሮስ የመጀመሪያ ልጅ፣ የልጅ ልጅ ነኝ፤ ብለውናል። ከእንፍራንዝ ወጥተን ጎንደር ስንሄድ ያገኘናቸው የአጤ ቴዎድሮስ አራተኛ ትውልድ ደግሞ ስለ ቤተሰቦቻቸው ሲያስረዱ፤ አጤ ቴዎድሮስ የመጀመሪያ ልጃቸውን ራስ መሸሻን ወለዱ፣ ራስ መሸሻ ቴዎድሮስ ደጃዝማች ካሳን፣ ደጃዝማች ካሳ ባንች አምላክ ካሳን ወለዱ ከዚያም እኔ ፋሲል ሚናስ ተወለድኩ ይላሉ። • እምቦጭ የጣና ቂርቆስ መነኮሳትን ከገዳሙ እያስለቀቀ ነው ሌላው እዚያው ጎንደር የሚኖሩት የአጤው ቤተሰብ አለማየሁ ቴዎድሮስ ናቸው። እርሳቸው እንደሚሉት አጤ ቴዎድሮስ መሸሻ ቴዎድሮስ፣ መሸሻ ቴዎድሮስ ደግሞ ደጃዝማች ካሳን፣ ደጃዝማች ካሳን ደግሞ እናታቸውን ሙሉ ካሳን መውለዳቸውን ይናገራሉ። እነዚህ የንጉሱ አራተኛ ትውልዶች የአጤውን ታሪክ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ ብቻ ሳይሆን እንደ ራሳቸው ቤተሰብ ታሪክ እየሰሙ ነው ያደጉት። ነዋሪነታቸው እንፍራንዝ የሆነው ወ/ሮ አበበች ስለ አጤ ቴዎድሮስ ደግነት፣ ሩህሩህነት፣ ጀግንነታቸውን እየሰሙ ነው ያደጉት። "ለወስላቶች አይቀጡ ቅጣት የሚቀጡ ለሀገራቸው ደግሞ ባለ ራዕይ የነበሩ መሆናቸውን እየሰማሁ ነው ያደግኩት።" እንደውም እቴጌ ተዋበች ከሞቱ በኋላ ሆድ እየባሳቸው ሄደ እንጂ ከዚያ በፊት ሐይማኖተኛና ጥሩ ሰው ነበሩ ይላሉ ወ/ሮ አበበች። የአጤው ቅርስ ይኖርዎት ይሆን ቀጣይ ጥያቄያችን ነበር? ንግሥት ቪክቶሪያ የሰጠቻቸው ደወል አለኝ። ሌላው ግን ይላሉ ወ/ሮዋ በደርግ ዘመን መትረየስ አለሽ እያሉ ሲያንገላቱኝ፣ ሲያስሩኝ ቀበርነው። ስፍራውን አሁን ሰዎች ቤት ሰርተውበታል። ቴዎድሮስ ንጉሠ ነገሥት ዘ ኢትዮጵያ ተብሎ የተፃፈበት ጎራዴ ሁሉ ነበር ይላሉ። ከጎራዴው ጋር ሌሎች ትናንሽ ቅርሳ ቅርሶችንም ቀብረናል ሲሉም ያስታውሳሉ። እነ ፋሲል እና አለማየሁ ጋር ግን የአጤ ቴዎድሮስ ማስታወሻ የሚሆን ምንም ነገር በቤታቸው የለም። በስማቸው ፎክረው ያውቁይሆን? አለማየሁ ቴዎድሮስና ፋሲል ሚናስ በስማቸው ብቻ በመኩራት በባዶ መኖር አትችልም ይላሉ። የአጤ ቴዎድሮስን ስም ለመጥራት እና የልጅ ልጅ ነኝ ለማለት የራስህን ሥራ ሥራ እየተባልን ነው ያደግነው ሲሉም ያስረዳሉ። አቶ ፋሲል አክለውም ለሀገር የከፈሉትን መስዋዕትነት እና ያደረጉትን ነገር በታሪክም በታላላቆቻቸውም ሲነገራቸው ማደጋቸውን ያስታውሳሉ። ወ/ሮ አበበች ከጎንደር ዩኒቨርስቲ እንዲሁም ከእንግሊዝ ድረስ እየመጡ ቴዎድሮስን ያሉ፣ ስለ እርሱ ለማወቅ የሚፈልጉ እንደሚጠይቋቸው ይናገራሉ። እንደው ፎክሪ ፎክሪ ካላቸውም 'የቴዎድሮስ ዘር' ሲሉ ይፎክራሉ። የአጤ ቴዎድሮስ ቁንዳላ ተመለሰ ሲሏቸው የተሰማቸውን ደስታም ሲገልጡም "የልዑል አለማየሁ አፅም ቢመጣ" ይላሉ። ከዚያ በኋላ የሄደው ቅርስ ሁሉ ቢመለስ ደስ ይለኛል ብለዋል። አለማየሁና ፋሲልም የአጤው ቁንዳላ መመለሱ የፈጠረባቸውን ሲናገሩ ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለመላው ኢትዮጵያ ትልቅ ነገር መሆኑን በመጥቀስ የተሰማቸውን ደስታ ነግረውናል። ቴዎድሮስ አለማየሁ አክሎም "ስሜን እንደ እርሳቸው የሚያስጠራ ታሪክ መሥራት እፈልጋለሁ" ይላል።
news-54179744
https://www.bbc.com/amharic/news-54179744
መዓዛ መንግሥቴ፡ 'ቡከር' በተባለው ዓለም አቀፍ ሽልማት የታጩት አፍሪካዊ ሴት ደራሲዎች
'ቡከር ፕራይዝ' በቀድሞ ስሙ 'ቡከር ሚክኮኔል ፕራይዝ' እና 'ዘ ማን ቡከር ፕራይዝ' በመባል ይታወቃል።
ዓለም አቀፍ የሽልማት ድርጅቱ በየዓመቱ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተፃፉ እና በዩናይትድ ኪንግደም ወይም በአየርላንድ የታተሙ ወጥ የልብ-ወለድ መፅሐፍትን አወዳድሮ ይሸልማል። የሽልማት ድርጅቱ የተቋቋመው በጎርጎሮሳዊያኑ 1969 ሲሆን የመጀመሪያውን ሽልማት የሰጠውም በዚያው ዓመት ነበር። ላለፉት ከ50 ዓመታት በላይም ይህንን ሲያደርግ ነው የቆየው። በዘንድሮው ዓመትም ሁለት ሴት አፍሪካዊያን ደራሲዎች ለሽልማቱ ታጭተዋል። በትውልድ ኢትዮጵያዊ- አሜሪካዊት መዓዛ መንግሥቴ አንዷ ናት። 'ዘ ሻዶው ኪንግ' [The Shadow king] በሚል ርዕስ የታተመው መፅሐፏ ነው ለሽልማቱ የታጨው። መጽሐፉ መቼቱን ያደረገው የሁለተኛው አለም ጦርነት ጅማሮ የሚባለውና ፋሽስት ጣልያን ኢትዯጵያን በወረረችበት ወቅት ነው። መፅሀፉ በጦርነቱ ውስጥ ሴት የነፃነት ታጋዮች ከፍተኛ ተጋድሎ ቢያደርጉም ምን ያህል ከታሪክ መዝገብ እንደተፋቁ የሚዘክርና የነበራቸውንም ግዙፍ ሚና ያወጣ ነው። ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ መዓዛ በጎርጎሮሳዊያኑ 2010 የወጣው 'ቢኒዝ ዘ ላየንስ ጌዝ' [Beneath the Lion's Gaze] በተሰኘው መጽሐፏ ጨምሮ በሌሎች ሥራዎቿ ትታወቃለች። በወቅቱም የጋርዲያን የአፍሪካ ምርጥ 10 መፅሐፍት ተርታ ተመድቧል። መዓዛ እጩ መሆኗን በሰማች ወቅት በትዊተር ገጿ ላይ "ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም። ኦ ፈጣሪየ!" ስትል ነበር ደስታዋን የገለፀችው። ለሽልማቱ ከታጩት 6 መጽሐፍት መካከል ለሽልማቱ የታጨው ሁለተኛው መጽሐፍ በዚምባብዌያዊቷ ደራሲ ጺጺ ዳንጋሬምባ ድርሰት ነው። መጽሐፏ ' ዚስ ሞርነብር ቦዲ' 'This Mournable Body' ይሰኛል። ከዚህ ቀደም ያወጣችውና ከፍተኛ እውቅናን ያተረፈላት 'ነርቨስ ኮንዲሽንስ' ተከታይ ነው። ዚምባብዌ ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ነፃ መውጣቷን ተከትሎ የመጣውን የድህረ-ቅኝ ግዛት ጭቆና፣ የእንግሊዝ ቅኝ ግዛት አገሪቱን ማሽመድመድና ካፒታሊዝም ጥምረት ምን ያህል መርዛማ እንደሆነም ያስቃኛል። መፅሀፉ 'ሾና' ቤተሰቦች ላይ የሚያጠነጥን ነው። የሾና ህዝብ በደቡባዊ የአፍሪካ አካባቢዎች ይኖራሉ። አሁን ላይ 10 ሚሊየን ገደማ ሾናዎች በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ተብሎ ይገመታል። አብዛኞቹ የሚኖሩት በዚምባብዌ ነው። ጺጺ ለሽልማቱ በመታጨቷ ደስታ እንደተሰማት በትዊተር ገጿ ላይ አጋርታለች። ደራሲ ፣ የተውኔት ፀሐፊ እና ፊልም ሰሪዋ ጺጺ፤ ይህን መጽሐፏን ከሁለት ዓመታት በፊት ቢቢሲ ዓለምን ከለወጡ 100 መጽሐፍት አንዱ አድርጎ መርጦት ነበር። ባለፈው ዓመት እንግሊዛዊ ናይጀሪያዊቷ ደራሲ ቤርናዲኔ ኢቫሪስቶል ሽልማቱን በማሸነፍ የመጀመሪያዋ ጥቁር አፍሪካዊት ነበረች። ከዚህ ቀደም ናዲን ጎርዲመር፣ ጀም ኮትዜ እና ቤን ኦኪሪን ጨምሮ ሌሎችም የሽልማቱ አሸናፊ ሆነዋል። ለዚህ ዓመቱ ሽልማት እጩ የሆኑት ሌሎቹ መፅሐፍት፦ •በዲያኔ ኩክ የተፃፈው 'ዘ ኒው ወይልደርነስ' [The New Wilderness] •በአቭኒ ዶሽ የተፃፈው 'በርንት ሹገር' [Burnt Sugar] •በብራንደን ቴይለር 'ሪል ላይፍ' [Real Life] •በዳግላስ ስቱዋርት የተፃፈው 'ሹጌ ቤን' [Shuggie Bain] አሸናፊዎቹ 64 ሺህ ዶላር ሽልማት ይበረከትላቸዋል ተብሏል። በእንግሊዝኛ የተፃፈ እና በዩናይትድ ኪንግደም የታተመ ማንኛውም መፅሐፍ በውድድሩ ላይ መሳተፍ ይችላል።
news-55232281
https://www.bbc.com/amharic/news-55232281
ታላቁ የኤቨረስት ተራራ በአንድ ሜትር አድጓል ተባለ
በአለማችን ትልቁ ተራራ፣ኤቨረስት አንድ ሜትር በሚጠጋ (0.86 ሜትር) የእርዝማኔ ብልጫ አሳይቷል ተባለ።
የኤቨረስት ተራራ የተራራው እርዝመት ከዚህ ቀደም ከተመዘገበበት በአንድ ሜትር በሚጠጋ ብልጫ ማደጉንም የኔፓልና የቻይና ባለስልጣናት አሳውቀዋል። አገራቱ በተራራው እርዝመትም ተስማምተው የማያውቁ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ግን ሁለቱም 8 ሺህ 848̇.86 ሜትር እርዝማኔ አለው ብለዋል። ቻይና ከዚህ ቀደም በልኬቴ መሰረት 8 ሺህ 8444.43 ሜትር ነው ስትል የነበረ ሲሆን ይህም ኔፓል ለካሁት ከምትለው በአራት ሜትር ያንስ ነበር። ኤቨረስት ተራራ በቻይናና በኔፓል መካከል የሚገኝ ሲሆን በሁለቱም አገራት በኩል ተራራውንም መውጣት ይቻላል። ከኔፓል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተውጣጡ ባለስልጣናት እንዲሁም ቦታዎችን በበላይነት የሚቃኘው ድርጅት እንዳሳወቁት ሁለቱም አገራት በመተባበር እንደተሳተፉበትና በአዲሱም ልኬት መስማማታቸውን ነው። ከዚህም በተጨማሪ የአለማችን ትልቁ ተራራ ማደግ ሁኔታንም በጥምረት ነው ያወጁት። የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ዢንፒንግ ወደ ኔፓል መዲና ካታማንዱም ባቀኑበትም ወቅት ነው በአንድ ላይ የገለፁት። ሆኖም የተራራው እርዝማኔ ለምን ልዩነት አመጣ የሚሉ ጥያቄዎች መነሳታቸው አልቀረም። የቻይና ባለስልጣናት የኤቨረስት ተራራ መለካት ያለበት ድንጋዩ መጨረሻ ድረስ ነው ሲሉ ኔፓል በበኩሏ ተራራውን የሸፈነው በረዶም ሊካተት ይገባል በማለትም ትከራከር ነበር። የቻይና የቅኝት ሰራተኞች አገሪቷ በጎሮጎሳውያኑ 2005 ተራራውን በለካችበት ፀንተው ቆይተው ነበር። የኔፓል የመንግሥት ባለስልጣናት በበኩላቸው ቻይና የራሷን ልኬት እንዲቀበሉ ከፍተኛ ጫና እያሳደረችባቸው እንደሆነ ለቢቢሲ በጎሮጎሳውያኑ 2012 ተናግረው ነበር። ይህንንም ተከትሎ ኔፓል የራሷን የተራራ ልኬት ማድረግ እንዳለባትም ውሳኔ ላይ ደርሳለች። ኔፓል የኤቨረስት ተራራ 8 ሺህ 848 ሜትር እርዝማኔ አለው ስትል የነበረው ህንድ በ1954 ካደረገችው ቅኝትና ልኬት ተነስታ ነው። በመጨረሻም አገሪቷ የተራራውን ልኬት ለመጀመሪያ ጊዜ አከናውናለች። አራት የኔፓል የመሬት ቅኝት ሰራተኞችም ለሁለት አመት ያህል ስልጠና ወስደዋል።
news-51986046
https://www.bbc.com/amharic/news-51986046
የኢትዮጵያ አበባ ላኪዎችን ገቢ ክፉኛ የጎዳው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ
በዓለም አቀፍ ደረጃ ወረርሽኝ በሆነው ኮሮናቫይረስ ምክንያት በጥቂት ቀናት ውስጥ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ማጣታቸውን የአበባ አምራቾች ገለጹ።
ኢትዮ አግሪሴፍት በሆለታ እና በባህርዳር ካሉት ሁለት የአበባ እርሻዎች በዓመት እስከ 40 ሚሊዮን አበባ ዘንግ ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ ያቀርብ እንደነበር ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ኢሳያስ ከበደ ለቢቢሲ ገልጸዋል። እንደ አቶ ኢሳያስ ገለጻ በቀጥታ እና በጨረታ ለዓለም ገበያ በሽያጭ ይቀርብ የነበረው አበባ ባለፉት ሶስት ሳምንታት ዋጋው በከፍተኛ ደረጃ ወርዷል። በየቀኑ እስከ 45ሺህ ዘንግ የሚጠጋ አበባ ለዓለም ገበያ ያቀርብ የነበረው አግሪ ሴፍት ከማርች 15 በኋላ በመቋረጡ በየቀኑ 21200 የአሜሪካ ዶላር ወይም 678400 ብር እያጣ መሆኑን ገልፀዋል። • በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ ሦስት ሰዎች ተገኙ • የአሜሪካ እስር ቤቶች በኮሮናቫይረስ ምክንያት እስረኛ መልቀቅ ጀመሩ ድርጅቱ ሠራተኞቹን እረፍት እንዲወጡ እያደረገ ከመሆኑም በላይ በየቀኑ ወደ አንድ መቶ ሺህ የሚጠጋ የአበባ ዘንግ ወደ ኮምፖስተነት ለመቀየር ተገዷል። ከባህርዳር ከተማ ወጣ ብሎ የሚገኘው ጣና ፍሎራም በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተመሳሳይ ችግር ገጥሞታል።ድርጅቱ ባለፉት ስምንት ቀናት ብቻ አንድ ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ዘንግ ገበያ በማጣት ምክንያት ለመጣል መገደዱን የጣና ፍሎራ ሽያጭ መምሪያ ሥራ አስኪያጅ አቶ አብነት በላይነህ ገልጸዋል። ባለፉት ስምንት ቀናት በገጠመው የገበያ ችግር ምክንያት ወደ 10 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ማጣቱን አስታውቀዋል። አክለውም ከ700 በላይ የሚሆኑ ሠራተኞቹም ያለሥራ መቀመጣቸውን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ አበባና አትክልት አምራች ላኪዎች ማህበር ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ዘውዴ በተለይ ለቢቢሲ እንደገለጹት ማህበሩ ከኮሮና ቫይረስ መከሰት ጀምሮ በሥራቸው ላይ ሊፈጥር የሚችለውን ተጽዕኖ እና በእርሻዎቹ እንዳይሰራጭ ለማድረግ እየተሠራ ቆይቷል። ከየካቲት እስከ ግንቦት ያሉት ወራት በአበባ ሥራ ትልቅ የንግድ እንቅስቃሴ ያለበት መሆኑን ጠቅሰው አሁን ያለው የአበባ ዋጋ ካለፈው አመት አማካይ ጋር ሲነጻጸር በ85 በመቶ መቀነሱን አስታውቀዋል። በቶሎ የሚበላሽ እና የማይከማች ምርት ከመሆኑም በላይ የወጪ ንግዱ 80 በመቶ ቅናሽ በማሳየቱ አምራቾችን በገንዘብ ረገድ እንዲፈተኑ እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። እንደ አቶ ኢሳያስ ገለጻ ከሆነ በአሁኑ ወቅት አበቦች እንዳይጎዱ በመንከባከብ እና ቀሪ ሠራተኞችን ደግሞ እረፍት እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ከስምንት መቶ በላይ ሠራተኞች ያሉት ድርጅቱ ችግሩ በዚሁ ከቀጠለ ደሞዝ ለመክፈል እንደሚቸገር ተናግረዋል። በዚህ ሃሳብ የሚስማሙት አቶ አብነት በበኩላቸው መንግስት በዘርፉ ለተሰማሩ አካላት ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል። • ሁለት ኢትዮጵያዊያን ጣሊያን ውስጥ በኮሮናቫይረስ መሞታቸው ተረጋገጠ ችግሩ ከመባባሱ በፊት መንግስት ድርጅቶች ብድር የሚከፈሉበትን ጊዜ በማስረዘም፤ ተጨማሪ ብድር የሚያገኙበትና የአበባ ፍላጎት ወዳሉባቸው አገራት ካርጎ እንዲጀመር የኢትዮጵያ አበባና አትክልት አምራች ላኪዎች ማህበር ጠይቋል። መንግስት ችግሩን መገንዘቡንና በሚቀጥለው ሳምንት መጀመሪያ ምላሽ ይሰጣል ብለው እንደሚጠብቁ አቶ ቴዎድሮስ ተናግረዋል። የኮሮና ወረርሽኝ በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተጨባጭ ጉዳት ፈጥኖ በመለየት የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ መንግሥት እንቅስቃሴ መጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መግለፃቸው ይታወሳል።
news-48905036
https://www.bbc.com/amharic/news-48905036
በቤኒሻንጉል፤ ማንዱራ በተፈፀመ ጥቃት ቢያንስ 8 ሰዎች ተገደሉ
በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል፤ መተከል ዞን፤ ማንዱራ ወረዳ ከዕሁድ ሌሊት ጀምሮ በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ የስምንት ሰዎች ሕይወት ማለፉንና በ13 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የመተከል ዞን አስተዳዳሪ አቶ ግርማ ታደሰ ለቢቢሲ ገለፁ።
ስለታም በሆኑ ቁሶችና በጦር መሳሪያ ጥቃቱ እንደተፈፀመ የሚናገሩት አቶ ግርማ ጉዳት ያጋጠማቸው ግለሰቦች በፓዊና ቻግኒ ሆስፒታሎች ሕክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኙ ገልጸዋል። • በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈፀመ ጥቃት 17 ሰዎች ሞቱ • በኦሮምኛና በትግርኛ አፋቸውን የፈቱ የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ባለውለታዎች አስተዳዳሪው እንዳሉት በቀበሌው ውስጥ አንድ ቤት ተቃጥሏል፤ ሁኔታውን በማረጋጋት ላይ የነበረ አንድ የመከላከያ ሠራዊትም ላይ ጉዳት ደርሷል። ጥቃቱ ሰኔ 29 ቀን 2011 ዓ.ም ሌሊት ላይ ያልታወቁ ሰዎች በወረዳው ገነተ ማሪያም ቀበሌ ሊቀመንበር ቤት ውስጥ በመግባት መሳሪያውን ቀምተው፤ በጩቤ ጉዳት አድርሰውበት ከሄዱ በኋላ ግጭቱ እንደተከሰተ አቶ ግርማ ያስረዳሉ። በዚህም ምክንያት የሊቀመንበሩ ቤተሰቦች ከተለያዩ ጎጦች ተውጣጥተው በመምጣት ቀበሌዋን ከበው ባገኗቸው በሰዎች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ይናገራሉ። "ከዚህ ቀደም በአካባቢው በተፈጠረው ችግር ማህበረሰቡ እርስ በርሱ እየተማመነ ስላልሆነ፤ ከዚያ ጋር የተያያዘ ይመስላል" ብለዋል- አቶ ግርማ። ከዚህ በፊት ጃዊ ላይ የተፈፀመውን ጥቃት የሚያስታውሱት አቶ ግርማ አሁን ላይ የበቀልና የአፀፋ ስሜት በተለያዩ አካባቢዎች በስፋት እየታየ እንደሆነ አስረድተዋል። ጥቃቱ ከተከሰተ በኋላ አካባቢውን ለማረጋጋት ጥረት እየተደረገ እንደሆ የመተከል ዞን አስተዳዳሪ ተናግረዋል። • "መግለጫ የምንሰጠው ሰዎችም ልንታሰር እንችላለን" የአማራ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የማንዱራ፤ ገነተማሪያም ቀበሌ ነዋሪም የግጭቱን መነሻ ምክንያት የገነተ ማሪያም የቀበሌ ጥበቃ ላይ ባልታወቁ ሰዎች ጥቃት መፈፀሙ እንደሆነ ይናገራሉ። ነዋሪው እንደሚሉት በግለሰቡ ላይ ጥቃት የፈፀሙት ሰዎች ያልታወቁ ቢሆንም፤ ይህ እንደምክንያት ተደርጎ 'ቱራ'[የድግስና የዘፈን መሳሪያ] እርሱን በመንፋት በሁሉም አቅጣጫ የሚኖሩ የጉምዝ ነዋሪዎች እንዲሰባሰቡ ተደረገ ይላሉ። ከዚያም በእርሻ ሥራ ላይ የነበሩ ሰዎች ላይ ጥቃት እንደሰነዘሩና ወደ ከተማ በመግባትም ቤት እንዳቃጠሉ ነዋሪው ነግረውናል። "እስካሁን ያልተሰበሰበ አስክሬን አለ፤ በርካታ ሰዎችም ሕይወታቸውን አጥተዋል" ሲሉም ያክላሉ። ትናንት መከላከያ ከገባ በኋላ በአንፃሩ የተረጋጋ ቢሆንም ዛሬም ተመሳሳይ ስጋትና ፍርሃት እንዳለ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
news-45749023
https://www.bbc.com/amharic/news-45749023
የኮምፒዩተር ትምህርት ለኬኒያ ሴት እስረኞች ሁለተኛ እድል ይሰጣቸው ይሆን?
የ44 ዓመቷ ዶርካስ ፈገግ እያለች ከማረሚያ ቤቱ ኮምፒተሮች የአንዱን ዋነኛ የማንቀሳቀሻ ክፍል (ሴንትራል ፕሮሰሲንግ ዩኒት) በማውጣት ለአዳዲሶቹ የክፍሎቿ ልጆች እያንዳንዱ የኤሌክትሪክ ክፍል ለምን ለምን እንደሚያገለግል ታብራራለች።
"አሁን ማንኛውንም ነገር መስራት እችላለሁ። ኮምፒውተር ሳይቀር ልሰራላችሁ እችላለሁ" በማለት ታክላለች። ዶርካስ በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ብቸኛው የሴቶች ማረሚያ ቤት በሆነው እና ከፍተኛ ጥበቃ በሚደረግለት ላንጋታ ማረሚያ ቤት ከሚገኙ 500 ታረሚያዎች አንዷ ናት። የተወሰኑት ታራሚዎች በድብደባ፤ ለውዝ እና ፍራፍሬ የመሳሰሉት ነገሮችን መንገድ ዳር በመሸጥ እስከ ሁለት ዓመት ድረስ የተፈረደባቸው ናቸው። ሌሎች ደግሞ ግድያ እና ከባድ ስርቆትን በመሳሰሉ ከባድ ወንጀሎች ምክንያት እድሜ ልክ የተፈረደባቸው ናቸው። ወንጀሉ ምንም ይሁን ምን በ2014 ከኬንያ ማረሚያ ቤቶች የወጣ አሃዝ እንደሚያመለክተው በሀገሪቱ ከሚገኙ ፍርደኞች ከ60 እስከ 80 በመቶው የሚሆኑት ተመልሰው ማረሚያ ቤት ይገባሉ። • በእራስ ውስጥ ሌሎችን ማየት • ሮናልዶ "ደፍሮኛል" ያለችው ሴት ከመብት ተሟጋቾች ድጋፍ አገኘች • የፍስሀ ተገኝ የቤተሰብ ፍለጋ ጉዞ የ31 ዓመቱ አገሬይ ሞካያ በማረሚያ ቤቱ ክፍል በር ላይ ቆሟል። ሰማያዊ እና ነጭ ቀለም መስመር ያለውን የደንብ ልብስ የለበሱ ታራሚዎች ደማቅ ብርቱካናማ ሹራቦች ደርበው በኮምፒዩተሮች ዙሪያ ተሰባስበው የተራቀቀውን ኮድ በጥቁር የኮምፒተር መተግበሪያ ገጾች ላይ ይተይባሉ። ቴክኖሎጂን ማዕከል ያደረገው መልሶ ማቋቋሚያ መርሃግብር ''ቼንጅ ሀብ'' መስራች እና በጆሞ ኬንያታ የእርሻ ዩንቨርሲቲ መምህር ነው። "ለሰዎች ሁለተኛ እድል የመስጠት ጉዳይ ነው" ይላል። "ከዚህ ቀደም ተሳታፊ ካልነበሩበት ኢኮኖሚ ተቋዳሽ እንዲሆኑ እድል የመስጠት ጉዳይ ነው።" ''ቼንጅ ሀብ'' ሴቶችን ከኮዲንግ እና ድረ ገጽ ዝግጅት እስከ ኮምፒውተር ጥገና ሁሉንም ነገር ያስተምራቸዋል። እንደ አግሬይ እምነት ከፍተኛ መጠን ያለውን የኬንያውያን ወደ ማረሚያ ቤት ተመልሶ የመግባት የሚቀንሰው የዚህ የቴክኖሎጂ ተደራሽነት ነው። "ከዚህ በፊት የተፈረደበትም ሆነ ምንም ወንጀል ፈጽሞ የማያውቅ ሰው በህግ ፊት ተመሳሳይ ናቸው" ይላል። "ስለዚህ በኢኮኖሚው በስራ ፈጠራ ወይም በእድሎች ፊትም ተመሳሳይ መሆን እንዳለበት አስባለሁ።" "የመለወጥ እድላቸውንና እና ለራሳቸው የሆነ ነገር ሊያደርጉ የሚችሉባቸውን አጋጣሚዎች ከነፈግናቸው በዋናነት ውድቀታቸውን እያመቻቸልናቸው ነው።" በሀሰተኛ ሰነድ ምክንያት ሶስት ዓመት የተፈረደባት ዶርካስ ግማሹን ከጨረሰች በኋላ በጥቅምት 2018 ከማረሚያ ቤቱ ተሰናብታለች። "አምስት ልጆች አሉኝ፤ ባለቤቴም በህይወት የለም። ስለዚህ ለእኔ እጅግ ጠቃሚው ነገር ወደ እነዚህ ልጆች መመለስ ነው" ትላለች። ከእስር ቤት ስትወጣ ልትጀምረው ላሰበችው አዲስ የልብስ ስራ ንግድ የሚሆናትን ድረ ገጽ አዘጋጅታ ጨርሳለች። "መኪና ስለሌለኝ ከቦታ ቦታ እየተዘዋወርኩ እግሮቼን ለአቧራ አልዳርግም። ህይወቴን ይቀይረዋል፤ ጊዜ እና ገንዘብም እቆጥባለሁ" በማለት ታብራራለች። በከፍተኛ ፍርድ ቤት ጠበቃ የሆኑት አቼይንግ ኦሬሮ እንደሚሉት የኬንያ የፍትህ ስርዓት መልሶ ከማቋቋም ይልቅ በቅጣት ላይ እጅጉን ያተኩራል። እናም ይህ ለውጥ ያስፈልገዋል። "እስረኞችን መልሶ ለማቋቋ የተቀናጀ እና የታሰበበት ጥረት እየተደረገ ነው ብዬ አላስብም" ይላሉ። "መልሶ ማቋቋምን ማካተት ወይም ቅጣትን ማዕከል ካደረገው አስተሳሰብ መውጣት በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ግለሰቦች በመጨረሻ ከእስርቤት ይወጣሉ፡፡ እናም በማህበረሰብ ውስጥ ይበልጥ ጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው ዋነኛው ስንቅ ትምህርቱ ነው።" በሌላኛው የናይሮቢ አቅጣጫ በትንሽ እና ሞቃታማ ኩሽና ውስጥ የ35 ዓመቷ ራሀብ ንያዊራ ጣፋጭና ነጫጭ ማሳመሪያዎች በትልቁ ባለሁለት ደረጃ ኬክ ላይ በጥንቃቄ ትቀባለች፡፡ በዚህ ዓመት ነበር በከባድ የዘረፋ ወንጀል የተፈረዳበትን የስድስት ዓመት ቅጣት ጨርሳ ከላንጋታ ማረሚያ ቤት የወጣችው፡፡ "ከማረሚያ ቤት ጋር ልታወዳድሩት የምትችሉት ምንም ነገር የለም" ትላለች፡፡ "ማረሚያ ቤት ከቦታዎች ሁሉ አስከፊው ነው። ለእኔ ግን የሕይወት መስመሬን መቀየሪያ ሆነልኝ።" ራሃብ አሁን የራሷን የዳቦና ኬክ ጋግሮ መሸጥ ስራ እያካሄደች ሲሆን፤ አንዲ ሴት እና ሁለት ወንድ ልጆቿን ወደዚህ ኩባንያ የማምጣት እቅድ አላት፡፡ "ለንግድ ስራዬ እድገት እጅግ የገዘፈውን ሚና የሚጫወተው ድህረ-ገጼ ነው ማለት እችላለሁ" በማለት በፈገግታ ታብራራለች፡፡ "በኬንያ ማንኛውም ቦታ አዳዲስ ደንበኞችን በቀጥታ እንዳገኝ ያግዘኛል፡፡" ድህረ-ገጹን ያበለጸገችው ማረሚያ ቤት እያለች ነበር፡፡ "በቼንጅ ሀብ አማካኝነት ብዙ ነገሮችን ተምሬአለሁ፡፡ ለድህረ-ገጽ የሚያግዙትን ኤችቲኤም ኤል፤ ሲኤስኤስ እና ጃቫ ስክሪብትን ምንነት አውቄያለሁ፡፡ ለድህረ-ገጼ ሁሉንም ነገር የቀመርኩት ደግሞ እራሴ ነኝ፡፡" ትላለች። "አሁን ሴት ልጄ ስታየኝ በጣም ኩራት ይሰማኛል፡፡" • ረሃብ የቀሰቀሰው ፈጠራ እንደ አገሬይ እምነት አንዴ ከማረሚያ ቤት ከወጡ በኋላ የሴት ታራሚዎች ህይወት ፍጹም ሊቀይረው የሚችለው ለዚህ ለቴክኖሎጂ ያላቸው ቅርበት ነው፡፡ ለምን ሴት እስረኞች ላይ እንዳተኮረ ሲያብራራ"ሁሌም ቢሆን ከቴክኖሎጂ ጋር የተገናኙ ነገሮች ላይ የጾታ አድሎ አለ"ይላል። "የአንዲት ሴት ህይወት ላይ ተጽዕኖ መፍጠር ቻልኩ ማለት ተፅዕኖው ተያያዥነት ይኖረዋል ማለት ነው፡፡ ለህጻናቱም ቢሆን ከኮምፒዩተር ፕሮግራሚንግ ጋር ገና በጊዜ ለመተዋወቅ እድል ይፈጥርላቸዋል፡፡" አግሬይ በኬንያ እንዳሉ የሚገመቱትን 8000 ሴት ታራሚዎች ለመድረስ ''ቼንጅ ሀብን'' ለማስፋፋት የገንዘብ ድጋፍ እያፈላለገ ነው። እስካሁንም በላንጋታ የሚገኙ 21 ታራሚዎች በእርሱ ፕሮግራም ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ታራሚዎች የኮምፒዩተር ኮድ አንዲሰሩ እና ስሪዲ ማተሚያዎችን ተጠቅመው የተለያዩ መገልገያዎችን እንዲያበለጽጉ ከሚከፍሉ ኩባንያዎች ጋር አብሮ በመስራት ፕሮጀክቱን ዘላቂ የማድረግ እቅዶች አሉት፡፡ ከዚህ በኋላ ህልሙ ''ቼንጅ ሀብን'' በሀገሪቱ ውስጥ ወዳሉ ሁሉም ማረሚያ ቤቶች መውሰድ ነው፡፡ በሚገርም ሁኔታ የቴክኖሎጂ ፕሮጀክት መስራት እንደምትፈልግ ስታወራ ሁሉም ሰው ለምን የወንዶች ወይም የወጣቶች ማረሚያ ቤት አትሄድም? ይሉሃል።" "የእኔ መልስ አዎ እሱም ጠቃሚ ነው፤ ነገር ግን ሁለተኛ ላይ የሚመጣ ነው እላቸዋለሁ፡፡ በሴቶች ማረሚያ ቤት ካሳካነው በኋላ ወደ ሌሎች እንሄዳለን።"
53719601
https://www.bbc.com/amharic/53719601
አፋር፡ የአዋሽ ወንዝ ባሰከተለው ጎርፍ ከ27 ሺህ በላይ ሰዎችን አፈናቀለ
በአፋር ክልል ባለፉት ሁለት ሳምንታት የአዋሽ ወንዝ በከፍተኛ ሁኔታ ሞልቶ ሰፊ አካባቢን በማጥለቅለቁ ከ27 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቦታቸው ተፈናቀሉ።
የክልሉ የአደጋ መከላከልና የምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መሐመድ ሁሴን ለቢቢሲ እንዳስታወቁት አደጋው የተከሰተው በአዋሽ ወንዝ መሙላትና በደራሽ ጎርፍ ምክንያት መሆኑን ጠቁመዋል። በዚህም በተለይ በ12 ወረዳዎች ውስጥ 67 ሺህ የሚሆን ሕዝብ በጎርፍ አደጋው ሰለባ መሆኑን ጠቁመዋል። በአደጋው ምክንያት የአንድም ሰው ህይወት አላለፈም ያሉት መሐመድ ከ10 ሺህ በበላይ እንስሳት ላይ ጉዳት መድረሱን አስታውቀዋል። ችግሩን ለመቅረፍ ክልሉ በራሱ አቅም የምግብ፣ የመጠለያ እና ህክምና ቁሳቁሶችን በማቅረብ ላይ ይገኛል። ከፌደራል መንግሥት በቀረበ ሔሊኮፕተር በአደጋው ቀጣና ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን የማውጣት ሥራ ከማከናወን ጎን ለጎን ምግብ የማቅረብ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል። ሰዎችን ከአደጋ ቀጣና ከማውጣት ጎን ለጎን ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው የክረምቱ ዝናብ እስከ መስከረም አጋማሽ እንደሚቀጥል ትንበያዎች ያሳያሉ ያሉት አቶ መሐመድ፤ ከዚያ በኋላ ደግሞ በዘላቂነት ለማቋቋም መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። ካለው የሃብት እና የሎጂስቲክስ እጥረት በተጨማሪ በመኪና በመንቀሳቀስ እርዳታ ለመስጠት ስለማይመች ተጨማሪ ሔሊኮፕተር እንዲቀርብ ጥያቄ ለፌደራል መንግሥት ቀርቧል ብለዋል። በፌደራል መንግሥት በኩል እርዳታ መቅረብ መጀመሩን ኃላፊው አስታውቀው ነገር ግን በተለይ ለሰብዓዊ እርዳታዎች ትኩረት በመስጠት በፍጥነት እንዲደርስ ሊሠራ ይገባል ብለዋል። በአገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንም ከክልሉ የአደጋ መከላከልና የምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። የአዋሽ ወንዝ በተደጋጋሚ ጊዜ የሚያደርሰው ጉዳት ተፈጥሮአዊ በመሆኑ መከላከል ባይቻልም ወንዙ ላይ የተለያዩ ግድቦችን በመሥራትና የቅድመ መከላከል ሥራ በማከናወን ችግሩን መቀነስ እንደሚገባ አሳስበዋል። በጎርፉ አደጋ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተፈናቃዮች በሚገኙበት አሳኢታ ተገኝተው ሁኔታውን የተመለከቱት የአፋር ክልል ቀይ መስቀል ቅርንጫፍ ጽፍፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሊ ሷሊህም፤ ማህበሩ የላከው 400 ኩንታል ምግብ እየተጓጓዘ መሆኑን ገልጸው አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልግ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ተፈናቃዮቹ በአሁኑ ውቅት በትምህርት ቤቶች ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ የገለፁት አቶ አሊ ያሉበት ሁኔታ ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ አጋላጭ በመሆኑ ይህንንም በተወሰነ መልኩ ለማቃለል ከምግብ እርዳታው ጋር የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ፣ የእጅ ማጽጃ እና ንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ማቅረብ እንደሚያስፈልግ አመልከተዋል። የአዋሽ ወንዝ በየዓመቱ በዝናብ ወቅት ሞልቶ በሚያስከትለው የጎርፍ መጥለቅለቅ ሳቢያ በአፋር ክልል ተደጋጋሚ ጉዳት በየጊዜው ያደርሳል።
sport-45118558
https://www.bbc.com/amharic/sport-45118558
ቀጣዩ የፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ማን ይሆን?
እ.አ.አ በ2009 ማንቸስተር ዩናይትድ በተከታታይ አሸናፊ ከሆነ በኋላ የትኛውም የእንግሊዝ ቡድን በተከታታይ ዓመታት የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ አንስቶ አያውቅም። ይሄ ዓመት የተለየ ነገር ያሳየን ይሆን?
በስፔን ላሊጋ እንዲሁም በጀርመን ቡንደስሊጋ ባርሴሎናንና ባየር ሙኒክን ይዞ ለተከታታይ ሶስት ዓመታት የሊጎቹ አሸናፊ መሆን የቻለው የማንቸስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ዋና አላማ ደግሞ ይህንን ታሪክ በእንግሊዝም መድገም ነው። በመጪው አርብ በሚጀመረው የ2018-19 የእንግሊዝ ፕሪምር ሊግ የትኞቹ ቡድኖች ለዋንጫው ይገመታሉ? በክረምቱ የዝውውር መስኮት ብዙ ገንዘብ ወጪ ያደረጉት ሊቨርፑሎች ወይስ በሞሪንሆ የሚመራው ማንቸስተር ዩናይትድ? ባለፉት ሁለት ዓመታት ድንቅ አቋም እያሳዩ ያሉት ቶተንሃሞች ወይስ አዲስ አሰልጣኝ የቀጠሩት አርሰናሎች? • ያለእድሜ ጋብቻን በእግር ኳስ የምትታገለው ታዳጊ • የአፍሪካ እግር ኳስ ቅሌት • ክለባቸውን ሊለቁ የሚችሉ ዘጠኝ የፕሪምየር ሊጉ ተጫዋቾች በቢቢሲ የቴሌቪዥንና ራድዮ የስፖርት ፕሮግራም የሚያዘጋጁ 24 የእግር ኳስ ተንታኞች የትኛው ቡድን ያሸንፋል ብለው እንደሚገምቱ ተጠይቀው ያሸንፋል የሚሉትን ቡድንና ምክንያታቸውን አስቀምጠዋል። ማንቸስተር ሲቲ ማን ያሸንፋል ተብለው ከተጠየቁት 24 እግር ኳስ ተንታኞች መካከል ሃያ አንዱ ማንቸስተር ሲቲ የ2018-19 የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ይሆናል ሲሉ የተቀሩት ሶስቱ ግን ሊቨርፑል ብለዋል። ማንቸስተር ሲቲዎች ያለ ምንም ጥርጥር ለሁለተኛ ጊዜ ሻምፒዮን ይሆናሉ የሚለው የቀድሞው የኒውካስል አጥቂ አለን ሺረር፤ ይህ ደግሞ የሚሳካው በአሰልጣኙ ፔፕ ጋርዲዮላ በሳል አመራር ብቻ ነው ሲል አስተያየቱን አስቀምጧል። ባለፈው ዓመት የተከተሉትን አጨዋወት የሚደግሙት ሲሆን፤ ሊቨርፑልና ማንቸስተር ዩናይትድ ግን ከባለፈው ወቅት በተለየ መልኩ በቅርብ ርቀት ይከተሏቸዋል ብሏል። ሌላኛው ማንቸስተር ሲቲ በቀጣዩም ዓመት አሸናፊ ይሆናል የሚለው ደግሞ ማቲው አፕሰን ነው። እሱ እንደሚለው ማንቸስተር ሲቲዎች በደንብ እንደ ለሰለሰ ማሽን ናቸው። ''በባለፈው የኮሚዩኒቲ ሺልድ የዋንጫ ጨዋታ ወሳኝ የሚባሉት ኬቨን ደብራይነ እና ዴቪድ ሲልቫን እንኳን ሳይዙ ማሸነፍ ችለዋል። ስለዚህ ይህ ቡድን እጅግ የተሟላና በቀጣይም አሸናፊ የሚሆን ቡድን ነው።'' ሊቨርፑል ባለፈው ውድድር ዘመን ሊቨርፑል ስንተኛ ሆኖ ይጨርሳል ተብለው ከተጠየቁ ሰዎች መካከል 13 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ነበሩ አራቱ ውስጥ ይገባል ብለው የገመቱት። በዚህ ዓመት ግን በአስገራሚ ሁኔታ 96 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች ምርጥ አራት ውስጥ ይጨርሳሉ ብለው ሲገምቱ፤ 14 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ዋንጫውን ያነሳል ብለዋል። ሊቨርፑሎች የዘንድሮውን ዋንጫ እንደሚያነሱ ከፍተኛ ተስፋ ደረገው የቀድሞ የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ኮከብ ኢየን ራይት ነው። እንደ እሱ ሃሳብ ከሆነ ሊቨርፑሎች የታመቀ ጉልበት ባላቸው ወጣቶች የተሞላ ቡድን ነው። ምናልባትም ለዋንጫው ብዙ ግምት እያገኙ ያሉት ማንቸስተር ሲቲዎችን ሊያስጨንቋቸው የሚችሉት ሊቨርፑሎች ብቻ ናቸው ይላል። ሊቨርፑሎች በፕሪምር ሊጉ ጥሩ ሲሆኑ አጠቃላይ የእንግሊዝ ፕሪምር ሊግ ይደምቃል ብሏል። የዚህኛው ዓመት ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ሊቨርፑሎች ይሆናሉ ብሎ የሚያምነው ሌላኛው ተንታኝ ሩድ ጉሌት የየርገን ክሎፕ የአጨዋወት ስልት ከማዝናናት ባለፈ ውጤታማ ያደርጋቸዋል ይላል። ባለፈው ዓመት ቢቢሲ ካነጋገራቸው የእግር ኳስ ተመልካቾች መካከል 33 በመቶ የሚሆኑት ዋንጫው የማንቸስተር ዩናይትድ እንደሚሆን ገምተው የነበረ ሲሆን፤ ማንቸስተር ዩናይትድ ግን ሁለተኛ ሆኖ ጨርሷል። በዚህ ዓመት ግን የትኛውም ሰው ማንቸስተር ዩናይትድ ዋንጫውን ያነሳል ብሎ አያስብም። ምንም እንኳን ማንቸስተር ዩናይትዶች ብዙ ኮከብ ተጫዋቾችን በቡድናቸው ውስጥ ቢይዙም ደጋፊዎቻቸውን የሚያስደስት ውጤትም ሆነ አጨዋወት ማሳየት ሳይችሉ ቀርተዋል። በሆዜ ሞሪንሆ ስር ግን በቡድኑ ውስጥ ብዙ ለውጦች እየታዩ ነው።
news-52508461
https://www.bbc.com/amharic/news-52508461
በርካቶች ኮሮናቫይረስን ለማከም በሚደረገው ሙከራ ለመሳተፍ ፈቃደኛ ሆኑ
ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ በሺህዎች የሚቆጠሩ ከኮሮናቫይረስ የዳኑ ሰዎች የደም ፕላዝማ ሆስፒታል የገቡ የኮሮናቫይረስ ታማሚዎችን ለማከም ያስችል እንደሆነ ለማወቅ በሚደረገው ሙከራ ላይ ፈቃደኛ ሆኑ።
ከ6,500 በላይ ሰዎች በሙከራው ላይ ለመሳተፍ የተመዘገቡ ሲሆን ሙከራውም መካሄድ ጀምሯል። በዚህም ከበሽታው ካገገሙ ሰዎች ደም ውስጥ በሚወሰደው የተፈጥሮ መከላከያ በበሽታው የተያዙ ሰዎችን ለማዳን ያስችላል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል። ባለፈው ሳምንት የብሪታኒያ ብሔራዊ ጤና አገልግሎት ከኮሮናቫይረስ ካገገሙ ሰዎች ደም ማሰባሰብ ጀምሯል። እንግሊዝ ውስጥ 148 ሰዎች እስካሁን ደማቸውን ለዚሁ አላማ መለገሳቸው ተገልጿል። ባለሙያዎች ተጨማሪ የደም ለጋሾችን ለማግኘት ቀደም ሲል ቫይረሱ ተገኝቶባቸው የነበሩ ሰዎችን ለማግኘት መረጃ በመፈተሽ ስልክ ደውለው ፈቃደኛ መሆናቸውን ይጠይቃሉ ተብሏል። አንድ ሰው በኮሮናቫይረስ ሲያዝ የተፈጥሮ በሽታን የመከላከያ ሥርዓቱ በሽታን አምጪ ተህዋስን የመከላከያ ዘዴን ያዘጋጃል፤ ይህም ቫይረሱን በማጥቃት ወደ በሽታ እንዳይሸጋገር ያደርጋል። ይህ ሂደትም በአንድ ወር ውስጥ የሚፈጠር ሲሆን ፕላዝማ በተባለውና በደም ውስጥ ባለው ፈሳሽ ክፍል ውስጥ የሚገኝ ነው። ይህንን ፕላዝማ በኮቪድ-19 በጠና ለታመሙ ሰዎች በመስጠት ከቫይረሱ ጋር ፍልሚያ የገጠመውን የእራሳቸውን ተፈጥሯዊ በሽታን የመከላከያ ሥርዓት በማጠናከር ከበሽታው እንዲያገግሙ ለማገዝ ያስችላል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል። በአራት የዩናይትድ ኪንግደም ግዛቶች ውስጥ በሚገኙ ሆስፒታሎች የሚካሄደውን ይህንን ሙከራ የሚመሩት ዶክተር ማኑ ሻንካር፤ የኮቪድ-19 ቫይረስ አዲስ በመሆኑ ምክንያት ብዙም የሚታወቅ ነገር እንደሌለ ተናግረዋል። ጨምረውም "ማናችንም በተፈጥሮ በሽታን የመከላከያ ሥርዓትችን ውስጥ ከዚህ ቫይረስ ሊከላከለን የሚችል ዘዴ የለንም" በማለት አሁን የሚደረገውን ሙከራ አስፈላጊነት አመልክተዋል።
news-56937339
https://www.bbc.com/amharic/news-56937339
የትንሳዔ ገበያ፡ በወሊሶ አካባቢ 115 ሺህ ብር የተገዛው በሬ
በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ለሚከበረው ለትንሳኤ በዓል በየአካባቢው ለአውደ ዓመት የሚቀርቡ የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶች ሞቅ ባሉ የግብይት ስፍራዎች ለሽያጭ ይቀርባሉ።
በዚህም ሁሉም እንደ አቅሙ እና ፍላጎቱ ይሸምታል። በዓልን በዓል ከሚያስመስሉ ነገሮች መካከል ደግሞ አንዱ የገበያው ድባብ ነው። ዶሮ፣ እንቁላል፣ ቄጤማ፣ ቅቤ፣ ፍየል፣ በግ፣ በሬው ገበያውን በስፋት ይቆጣጠሩታል። ሸማችና ሻጭ በዋጋ ክርክር ይወዛገባሉ። የከተሞች ዋና መንገዶች በእርድ እንስሳት፤ በሰው ትርምስ ይሞላሉ። በዚህ ሁሉ መካከል አንዱ ሸማች ሌላኛውን የገበያውን ውሎ ይጠይቃል። መቼም ቢሆን "ርካሽ ነው" የሚል ወሬ ከገበያተኛ አይሰማም። እኛም ከሰሞኑ አንድ በሬ በ115 ሺህ ብር ስለመሸጡ ሰምተናል። 115 ሺህ ብር አውጥተው ይሄን ግዙፍ ሰንጋ የገዙት ሰው ደግሞ አቶ አሸብር ናቸው። አቶ አሸብር ጎሳ ባልቻ የከብት ነጋዴ ናቸው። ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ወሊሶ አካባቢ በሚገኝ የከብት ገበያ ከቀናት በፊት በሬውን በ115ሺህ ብር መግዛታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ አሸብር 115 ሺህ ብር ስለወጣበት በሬ ምን አሉ? "በሬው ትልቅ ነው። ሁለት ዓመት አካባቢ ነው የተቀለበው። በሬውን የገዛሁት ከገበሬ ነው። ሻጩ ሦስት ዓመት ሲቀልበው እንደነበር ነግሮኛል" ሲሉ ለቢቢሲ አስረድተዋል። እሳቸው የተፍኪ ከተማ ነዋሪ ናቸው። በሬውን የገዙት ደግሞ ኢሉ ወረዳ ተጂ ውስጥ ነው። "እኔ የከብት ነጋዴ ነኝ። ለሥጋ ቤት ወይም በበዓሉ ሰሞን ዝግጅት ላላቸው ወይም ሆቴል ለሚያስመርቁ ሰዎች ለመሸጥ ነው ያሰብኩት። ያው እንደ ገበያው ሁኔታ ሆኖ እስከ 3ሺህም 2ሺህም አትርፌ እሸጣለሁ። እንደ ገበያው ነው።" ብለዋል። ለዚህ ከብት 115ሺህ ብር አውጥተው የገዙት በገበያው ሁኔታ እንደሆነ የሚናገሩት አቶ አሸብር፤ "ፋጉሎ እኮ እስከ 3ሺህ ብር እያወጡ ነው የሚገዛው። ይሄ በሬ ሁለት እና በሦስት ዓመት ሲቀለብ ስንት ኩንታል ጨርሷል የሚለውን ማሰብ ነው።" ሲሉ ዋጋው ያን ያህል እንዳልተጋነነ በስሌት አስረድተዋል። እንዲህ በውድ ዋጋ የተሸጠ በሬ ከዚህ በፊት ያውቁ ይሆን? እኔ እስከማውቀው በትልቅ ብር የተሸጠው በሬ ይሄ ነው። ትልቁ ይሄ ነው። ከዚህ በታች ያለው 85ሺህ፣ 75ሺህ፣ 65ሺህ የሚሸጥ አለ። በግ ራሱ 12ሺህ ብር ተሽጧል። ዳዎ ወረዳ ቡሳ ከተማ አንድ በግ 12 ሺህ ብር ተሽጧል። በሌሎች አካባቢስ ከፍተኛው የከብት ዋጋ ስንት ይሆን? መልካም በዓል!
52902907
https://www.bbc.com/amharic/52902907
በነቀምቴ አንድ የፖሊስ አባል በ'አባ ቶርቤ' በጥይት ሲገደል ሌላኛው ቆሰለ
በነቀምቴ ከተማ 'አባ ቶርቤ' በሚባለው ቡድን ሁለት የከተማው ፖሊስ አባላት ዛሬ ረቡዕ በጥይት ተመትተው የአንደኛው ህይወት አለፈ።
በፖሊሶቹ ላይ ጥቃቱ የተፈጸመው ከቀትር በፊት ከረፋዱ አምስት ሰዓት ገደማ ላይ ሲሆን በጥይት ከተመቱት የአንደኛው የከተማዋ ፖሊስ አባል ህይወቱ ሲያልፍ ሌላኛው ደግሞ ሆስፒታል ገብቶ በጽኑ ሕሙማን ክፍል ውስጥ እንደሚገኝ የነቀምቴ ከተማ ጸጥታ እና አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚስጋኑ ወቅጋሪ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ኃላፊው እንዳሉት "በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሰዎችን በማስፈራራት ከዚያም ጥቃት በሚፈጽመው በዚህ ቡድን የከተማው ሁለት የፖሊስ አባላት በሽጉጥ ተመትዋል። አንዱ ህይወቱ ሲያልፍ አንዱ ደግሞ ቆስሎ በነቀምቴ ሆስፒታል ህክምና ላይ ይገኛል።" ሳጅን ደበላ እና ሳጅን አዱኛ የተባሉት እነዚህ የከተማው የፖሊስ አባላት ነቀምቴ ከተማ ቀበሌ 05 በእግር እየተጓዙ ሳሉ ነበር በጥይት የተመቱት ሲሉ አቶ ሚስጋኑ ተናግረዋል። በጥቃቱም የሳጅን አዱኛ ህይወት ማለፉንም አረጋግጠዋል። ይህ በከተማው በሚገኙ የጸጥታ አባላት ላይ የተፈጸመው ጥቃት የመጀመሪያ አለመሆኑ የተገለጸ ሲሆን ከቀናት በፊትም ግንቦት 16/2012 ዓ.ም በተመሳሳይ መልኩ በነቀምቴ ከተማ በጠራራ ፀሐይ የኮሚኒቲ ፖሊስ አባል የሆነ ግለሰብ ጫማ እያስጠረገ ሳለ በጥይት ተመቶ መገደሉን አቶ ሚስጋኑ አስታውሰዋል። ኃላፊው እንደሚሉት ዛሬ በፖሊስ አባላቱ ላይ የተፈጸመው ግድያና ጥቃት ከቀናት በፊት በኮሚኒቲ ፖሊስ አባል ላይ ከተፈጸመው ግድያ ጋር ተመሳሳይ መሆኑን አመልክተዋል። "የታጠቀ እና በድብቅ የሚንቀሳቀስ ኃይል በከተማው ውስጥ አለ። ይህ ኃይል በመንግሥት አመራሮች እና የጸጥታ ኃይል አባላት ላይ ማስፈራሪያ እና ዛቻ ሲያደርስና ጥቃት ሲፈጽም ቆይቷል" ሲሉ ክስተቱ የቆየ እንደሆነና ኢላማ ያደረገውም የመንግሥት አካላት ላይ መሆኑን ጠቅሰዋል። 'አባ ቶርቤ' ወይም ባለሳምንት የተባለው ቡድን የተለያዩ የፌስቡክ ገጾችን በመጠቀም ጥቃት እፈጽምባቸዋለሁ የሚላቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር በገጹ ላይ እንደሚያሰፍር አቶ ሚስጋኑ ተናግረዋል። "የሳጀን ደበላ ስምም ከዚህ በፊት በቡድኑ የፌስቡክ ገጽ ላይ ሰፍሮ ነበር። በዚህም ምክንያት ጥንቃቄ እንዲያደርግ ተነግሮት አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሲደረግ ነበር። ግን መቼ ይፈጸማል የሚለው ማወቅ ስለማይቻል አስቸጋሪ ነበር" ሲሉ የቡድኑን ድርጊት ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ጥቃቱ የተፈጸመባቸው ግለሰቦች የፖሊስ አባላት እንደመሆናቸው የኅብረተሰቡን ሰላም እና ደህንነት ለማረጋገጥ በኅብረተሰቡ ውስጥ እየተጓዙ ሳሉ ነው ይህ ችግር ያጋጠመው" ብለዋል። ለአንድ የፖሊስ አባልና ለሌላው ከባድ ጉዳት ምክንያት ከሆነው ጥቃት ጋር በተያይዘ በቁጥጥር ስር የዋለ ሰው የለም የተባለ ሲሆን ፖሊስ ክትትል እያደረገ መሆኑ ተገልጿል። አባ ቶርቤ ማነው? የኦሮሚያ ክልል አስተዳደርና ፀጥታ ኃላፊ አቶ ጅብሪል መሐመድ "አባ ቶርቤ ማለት የአሸባሪው ሸኔ የከተማው ክንፍ ነው" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሸኔ በጫካ ታጥቆ የሚንቀሳቀስ ኃይል አለው። በከተማ ደግሞ 'አባ ቶርቤ' እና 'ሶንሳ' ተብሎ የሚጠራ ቡድን አለው። እነዚህ ቡድኖች በተቻላቸው መጠን ግድያ በመፈጸም ሽብር ለመፍጠር እየሞከሩ ናቸው ብለዋል። እነዚህ ቡድኖች ጥቃት የሚያደርሱት በጠራራ ፀሐይ ከተማ መሃል ነው። ይህን መንግሥት መቆጣጠር ለምን ተሳነው? ተብለው የተጠየቁት አቶ ጅብሪል "ከዚህ ቀደም በቁጥጥር ሥር የዋሉ አሉ። ለመግደለ ሲሄዱ የተገደሉም አሉ። ምንም አይነት የተለየ ስልጠናም ሆነ መሳሪያ የላቸውም። የሚጠቀሙት ሰልት የሚጠቀሙት ሰልት፤ ማህበረሰቡን በመምሰል፤ ድንገት ነው አደጋ የሚያደርሱት። ለማምለጥ በሚያመቻቸው ቦታ በድንጋት አደጋ አድርሰው ይሰወራሉ" ብለዋል አቶ ጅብሪል። ከዚህ ቀደምም ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኘው የቡራዩ ከተማ አስተዳደርና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ሰለሞን ታደሰ የአባ ቶርቤ አባላት ናቸው በተባሉ ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል።
news-47785828
https://www.bbc.com/amharic/news-47785828
መፈናቀል፡ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የአንድ ዓመት ፈተናዎች አንዱ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ቃለ መሃላ ፈጽመው ስልጣን ከተረከቡ ድፍን አንድ ዓመት ሆናቸው። በዚህ ቆይታቸውም በርካቶች በሃገሪቱ ታይተው የማይታወቁ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ የለውጥ እርምጃዎችን እንደወሰዱ በመጥቀስ አድናቆታቸውን ይገልጹላቸዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የአንድ ዓመት የአስተዳደር ቆይታ ወቅት የተለያዩ ፈታኝ ሁኔታዎች አጋጥመዋል። ከእነዚህም መካከል በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የተከሰቱት የብሔር ግጭቶችና እነሱንም ተከትሎ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች መፈናቀል መንግሥታቸው ከሚተችበት ምክንያት አንዱ ነው። • ጌዲዮ በዐቢይ ጉብኝት ማግስት በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ውስጥ በምትገኘው ቻግኒ ውስጥ ያለው ተፈናቃዮች የሰፈሩበት አካባቢ ከሁለት ወራት በፊት ምንም ነገር ያልነበረበት ክፍት መስክ ነበረ። ዛሬ ግን በብሔር ግጭት ምክንያት ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተፈናቀሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በነጭና አረንጓዴ ድንኳኖች ተጠልለውበታል፤ መስኩን ሸፍነውታል። በመጠለያው ውስጥ ከሚገኙት ሰዎች መካከል የሁለት ልጆች እናት የሆነችው የ32 ዓመቷ ፍቅሬ አሳዬ አንዷ ናት። ፍቅሬ ትኖርበት የነበረውን ቀዬዋን ጥላ የሸሸችው ከተቀናቃኝ ጎሳ የመጡ በከፍተኛ ሁኔታ የታጠቁ ቡድኖች ጥቃት አድርሰው በርካቶችን ከገደሉና ካቆሰሉ በኋላ ነበር። ባሏም የት እንደደረሰ አታውቅም። በመጠለያው ውስጥ ያለውን ሕይወት በተመለከተም ፍቅሬ ስትናገር "እዚህ ከልጆች ጋር መኖር በጣም አስቸጋሪ ነው። በቀያችን በነበርን ጊዜ ለልጆቻችን የሚያስፈልጋቸውን ነገር እናቀርብ ነበር። አሁን ግን ይህን ማድረግ አንችልም፤ በመጠለያው ውስጥ ያለው ሁኔታ በጣም አስከፊ ነው" ትላለች። • በተፈናቃዮች ብዛት ኢትዮጵያ ከዓለም ቀዳሚ ሆነች ወደ ቀያቸው የመመለሱም ሁኔታ የማይሆን ነገር እንደሆነ የምትናገረው ፍቅሬ "ወደቤታችን መመለስ አንችልም። ሰው እንዴት ብሎ ከወንድሙ ገዳይ ጋር ሊኖር ይችላል?" ስትል ትጠይቃለች። ነገር ግን በኢትዮጵያ በብሔር ግጭት የተፈናቀሉ ሰዎች የሚገኙት በሰሜን ምዕራቡ የሀገሪቱ ክፍል ብቻ አይደለም። ከቻግኒ በሺህ ኪሎሞትሮች ርቆ በሚገኘው የደቡባዊ ኢትዮጵያ ክፍልም በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተፈናቅለው በአስቸጋሪ ሁኔታ በጊዜያዊ መጠለያዎች ውስጥ ይገኛሉ። ያለው ሁኔታ እጅግ አስከፊ ሲሆን ባለፉት ስምንት ወራትም ያለበቂ ምግብ፣ መጠለያና የህክምና አገልግሎት በችግር ውስጥ ይገኛሉ። በኦሮሞዎችና በጌዲዮዎች መካከል ያገረሸውን ግጭት ተከትሎ ከወራት በፊት መኖሪያዋን ጥላ በመሸሽ ላይ እያለች ነበር እቴነሽ አበበ የወለደችው። እሷ እንደምትለው ጨቅላዋ በህይወት በመቆየቷ እድለኛ እንደሆነች ትናገራለች። ምንም እንኳን መንግሥት ደህንነቸውን ለመጠበቅ ቃል ቢገባም እንደሌሎቹ ተፈናቃዮች ወደቀዬዋ ለመመለስ ፈቃደኛ አይደለችም። • የብሔር ግጭት የሚንጣት ሀገር ወደመጠለያው ከመጣች በኋላ ልጇ ታማባት እንደነበር የምትናገረው እቴነሽ ያለፈችበትን ችግር ስታስታውስ "ስወልድ የነበርኩበት ሁኔታ በጣም አስቸጋሪ ነበር። ከመጀመሪያው እየተሳደድን ነበር። እኔም በጣም ደም እየፈሰሰኝ ነበር። ባሌ አብሮኝ ስለነበረ ሁለቱን ቀሚሶቼን በመጠቀም ደሙን ለማስቆም እየሞከርን ነበር።" በኢትዮጵያ ውስጥ ከብሔር ጋር በተያያዙ ግጭቶች ምክንያት ሁለት ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች ከሚኖሩበት አካባቢ ተፈናቅለዋል። ለግጭቶቹ እንደምክንያት የሚጠቀሱት ለዘመናት የዘለቁ የድንበር ጥያቄዎች፣ በግጦሽ ቦታ ይገባኛልና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደስልጣን ከመጡ በኋላ በተከሰቱ ውዝግቦች ነው። በዚህም ሳቢያ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አስተዳደር በሃገሪቱ የተከሰተውን የተፈናቃዮች ቀውስ የያዘበት ሁኔታ ለከባድ ትችት አጋልጦታል። ይህም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ያጋጠማቸው ትልቁ ፈተና ነው። የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መስራችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ኦባንግ ሜቶ በሃገሪቱ ውስጥ እየተከሰተ ስላለው አሳሳቢ ሁኔታ ሲናገር ባለፉት ዓመታት በሃገሪቱ የነበረውን ሁኔታ ይጠቅሳል። • የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ተፈናቃዮች ለችግር ተዳረግን አሉ "ሰዎች የሌሎችንን ሰውነት መመልከት እስኪተዉ ድረስ ባለፉት 27 ዓመታት ለሕዝቡ ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ ጎሳውን እንዲያስቀድም ነው ሲነገረው የቆየው። ይህ የኢትዮጵያን የአስተሳሰብ ውድቀት ሲሆን ይህንንም ለማስተካከል በጥልቀት ማሰብንና ወደሕዝቡ በመሄድ መነጋገርን ይፈልጋል። እኛን አንድ የሚያደርገን ጎሳችን ሳይሆን ሰው መሆናችን ነው።" መንግሥት የተፈናቀሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን እንደ አንድ ምክንያት ጠቅሶ በዚህ ወር ማብቂያ ላይ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው የሕዝብ ቆጠራ ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ አድርጓል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰነዘረባቸውን ትችት ተከትሎ ለመጀመሪያ ጊዜ በከባድ ችግር ውስጥ ካሉት የተፈናቃይ መጠለያዎች መካል በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኘውን በመጎብኘት ተፈናቃዮቹን ወደቀያቸው እንዲመለሱ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።
news-55362370
https://www.bbc.com/amharic/news-55362370
ሱዳን ፡ ለዓመታት ከመንደራቸው ርቀው የቆዩት የዳርፉር ነዋሪዎች ተስፋና ስጋት
ዓለም አቀፍ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች በጦርነት ከምትታመሰው የደቡብ ሱዳኗ ዳርፉር ግዛት መውጣት መጀመራቸውን ተከትሎ የንጹሃን ዜጎች ደኅንነት አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ሊወድቅ እንደሚችል እየገተገለጸ ነው።
ካዲጃ ባሏ ከተገደለ በኋላ ከዘመዶቿ ጋር ሐዘን ላይ ሆና የ14 ዓመቱ ታዳጊ አብዱላህ በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ሰዎች የሚኖሩበት መጠያ ካምፕ ውስጥ ነው ኑሮውን እየመራ የሚገኘው። የተወለደው ከዳርፉር በስተሰሜን በኩል በሚገኘው አቡ ሾክ በተባለው መጠለያ ካምፕ ውስጥ ሲሆን ሙሉ ሕይወቱን ያሳለፈው እዚያው ነው። ቤተሰቦቹ ቤታችን እያሉ የሚጠሩትን መንደር በስም እንጂ አይቶት አያውቅም። "ቤተሰቦቼ እና በርካታ ዘመድ አዝማዶቼ ተሰባስበው በደን በተከበበች አንዲት በጣም በምታምር መንደር ውስጥ ይኖሩ እንደነበር ሰምቻለሁ" ይላል። "ቤተሰቦቼ እንደነገሩኝ ከሆነ መንደሯ በጣም ሰላማዊና ለሕይወት ምቹ ነበረች። ሁሉም ነገር በመንደሪቱ ቀላል ነበር።" አብዱላህ በሕይወቱ ቴሌቪዥን አይቶ የሚያውቀው አንድ ጊዜ ብቻ ነው። እነሱ በሚኖሩበት ካምፕ ደግሞ ትልቅ ስጋት አለ። ታጣቂ ቡድኖች ሌሊት ሌሊት ወደ አካባቢው በመምጣት ጥቃት ይፈጽማሉ። "ሁሌም መደበቅ አለብን፤ ምንም ለማድረግ አንችልም። መልሰን ለማጥቃት ወይም ለመከላከል ከሞከርን ልንገደል እንችላለን" ይላል አብዱላህ። በደቡብ ሱዳን ይደረስበታል ተባለው የሰላም ስምምነት ለ17 ዓመታት የዜጎችን ሕይወት ሲያመሳቅል የቆው ጦርነት እንዲያበቃና የአብዱላህ ቤተሰቦቹን የመሳሰሉ በርካቶች ወደ ቀድሞ ቀያቸው እንዲመለሱ ሊያደርግ እንደሚችል ተስፋ ተጥሎበታል። እስካሁን ድረስ ባለፉት 17 ዓመታት 300 ሺህ ሰዎች በዚሁ ጦርነት ምክንያት ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን 2.5 ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ቤት ንብረታቸውን ጥለው ለመሰደድ ተገደዋል። አብዱላህ ይሄ ሁሉ ቀውስ የጀመረው በአውሮፓውያኑ 2003 ላይ በዚህ አካባቢ የሚኖሩ ዜጎች መንግሥት ዘንግቶናል በማለት አመጽ በማስነሳት የትጥቅ እንቅስቃሴ ማድረግ መጀመራቸውን ተከትሎ ነው። የተነሳውን ተቃውሞ ለመቆጣጠርም ካርቱም አርብቶ አደር አረቦችን በማስታጠቅ እርምጃ ወሰደች። እንዚህ የታጠቁ አርብቶ አደሮችም 'ጃንጃዊድ' በመባል የሚታወቁ ሲሆን የሱዳን መንግሥት ጠቀም ያለ ገንዘብ ይከፍላቸውም ነበር። በርካታ አማጺያን ከመንግሥት ጋር የስምምነት ፊርማቸውን ቢያኖሩም እንደ አብዱላህ እና ቤተሰቦቹ ያሉ ቢያንስ 1.5 ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎች እስከ 60 በሚደርሱ መጠለያ ጣቢያዎች ተበታትነው ይገኛሉ። የሱዳን ዳርፉር ግጭት ላለፉት 17 ዓመታት መኖሪያቸውን በአቡ ሾክ መጠለያ ውስጥ ካደረጉ ሰዎች መካከል አንዷ የሆነችው ዛራ ምንም ያህል ወደ ቀድሞ ቤቷ መመለስ ብትፈልግም ሁኔታዎች እስካሁን አልፈቀዱላትም። "ወደ መሬታችን ሄደን እንኳን እርሻ መስራት አንችልም፤ ምክንያቱም በሌሎች ሰዎች ተይዟል። እነሱ ናቸው የሚደግሉን፣ እነሱ ናቸው ከመኖሪያችን የሚያፈናቅሉን። እኛ ግን አሁንም እዚህ መጠለያ ውስጥ እስካሁን አለን" ትላለች። ከአቤ ሾክ መጠለያ ካምፕ በስድስት ሰዓት የመኪና ጉዞ ርቀት ላይ በምትገኘው ጂተሪ መንደር ያለው ሁኔታ ሰዎች አሁንም ድረስ ወደ ቀድሞ መኖሪያቸው ለምን እንደማይመለሱ ጥሩ ማሳያ መሆን ይችላል። አብዛኛዎቹ በዚህ መንደር የሚገኙ ገበሬዎች ወደ ቀድሞ መሬታቸው ሄደው እርሻ ለመጀመር በጣም ነው የሚፈሩት፤ ምክንያቱም ይህን አስበው ወደቦታው የሄዱ ሰዎች ይገደላሉ፤ ሴቶችም ይደፈራሉ። የተባበሩት መንግሥታት ሠላም አስከባሪዎች ሌላው ቀርቶ በዚህች መንደር ውስጥ የፍርሀት ኑሮ እየመሩ እንኳን ደኅንነታቸው የተረጋገጠ አይደለም። ጃንጃዊድ በመባል ሚታወቁት የታጠቁ ቡድኖች በዚች መንደር በቅርቡ መጥተው የካዲጃን ባለቤት እንዲሁም አንደኛውን ወንድ ልጃቸውን ተኩሰው ሲገድሉ እሷንም አቁስለዋታል። "ሁሌም ቀውስ ነው፤ ሁሌም ግድያ ነው" ትላለች። "መንግሥታችንን፣ ወታደሮችንም ሆነ ፖሊሶችን አናምናቸውም። ምንም አይነት እምነት የምንጥላባቸው አይደሉም። በፍጥነት መፍትሄ የማይፈለግ ከሆነ እዚህ ቦታ ላይ የዘር ማጥፋት ይፈጸማል።" እነ ካድጃ የመንግሥት ወታደሮችን ለማመን ከሚቸገሩባቸው ምክንያቶች መካከል አንደኛው በሠራዊቱ ውስጥ እነዚሁ የሚያውቃቸው የጃንጃዊድ አባላት መኖራቸው ነው። በሰላም ስምምነቱ መሰረትም የሁሉም አማጺያን ወታደሮች ወደ መንግሥት ኃይሎች ተጠቃለው እንዲገቡ ይደረጋል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ሌላ ነዋሪዎቹን ስጋት ላይ የጣለ አንድ ጉዳይ አለ። የሰላም ስምንቱን ተከትሎ ዓለም አቀፍ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ከ13 ዓመታት በኋላ ለቀው መውጣት ጀምረዋል። ምንም እንኳን ውጤታማነቱ እስከዚህም ነው ቢባልም ላለፉት ዓመታት በተባበሩት መንግሥታትና በአፍሪካ ሕብረት የሚመራው ሰላም አስከባሪ ኃይል ንጹሃን ዜጎችን ከመጠበቅና ሰላምን ከማረጋገጥ አንጻር ቀላል የማይባል ሥራ አከናውኗል። በሱዳን በቅርቡ የተቋቋመው ከፊል ወታደራዊ ጊዜያዊ መንግሥት ላይ ደግሞ በርካቶች ተስፋቸውን እንዲጥሉ አድርጓቸዋል። ጊዜያዊ መንግሥቱ ወደ ስልጣን የመጣው በአውሮፓውያኑ 2019 ላይ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ከስልጣናቸው ከተባረሩ በኋላ ነው። ከዚህ በኋላ ከዳርፉር ጋር በተያያዘ የጦር ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ክስ የሚቀርብባቸው በሙሉ ለፍርድ ይቀርባሉ። ማንም የሚቀር ሰው እንደማይኖርም እየተገለጸ ነው። ፋይሳል ሞሀመድ ሳሊህ የሱዳን የባህልና መረጃ ሚኒስትር ናቸው። የቀድሞው የሰብአዊ መብት ተሟጋች በቀድሞው ሥርዓት ለእስር ተዳርገው ነበር። በአሁኑ ጊዜ ደግሞ የሽግግር መንግሥቱ አካል ናቸው። ''በዳርፉር ማንኛውም አይነት ወንጀል የፈጸሙ ሰዎች ለፍርድ ይቀርባሉ። ማንም ሰው አያመልጥም'' ብለዋል። ነገር ግን በአቡ ሾክ መጠለያ ውስጥ የሚኙት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መሰል እርምጃዎች ከዚህ በፊት ተጀምረው ሲጠናቀቁ ባለመመልከታቸው አብምዛም ተስፋ የሚጥሉበት እንዳልሆነ እየገለጹ ነው። ምናልባት ከጦርነት፣ ረሃብና መፈናቀል ውጪ ምንም አይነት ነገር አይቶ ለማያውቀው የ14 ዓመቱ አብዱላህ ተስፋ ሰጪ ሊሆን እንደሚችል ቢገመትም አሁንም ቢሆን ግን ሕይወት በጣም ከባድነቱ አያጠራጥርም። "ሁሌም በህልሜ ምንም ስጋት የሌለበት ቦታ ላይ ሰዎች ሰብሰብ ብለው ማሳቸውን ሲንከባከቡ አያለሁ። ሰዎች በሰላም መኖር የሚችሉበትን ቦታ ሁሌም አስባለው፤ ነገር ግን ይህ ነገር ለማሰብ እንኳን የሚከብድ ነገር ነው'' ይላል አብዱላህ።
news-52982777
https://www.bbc.com/amharic/news-52982777
የቡሩንዲው ፕሬዝዳት ፒዬር ንኩሩንዚዛ በድንገት አረፉ
የቡሩንዲወ ፕሬዝደንት ፒዬር ንኩሩንዚዛ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
ከሳምንታት በፊት በተደረገ ምርጫ ፓርቲያቸው ማሸነፉ የተነገረላቸው የቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ፒየር ንኩሩንዚዛ በድንገት ነው ህይወታቸው ያለፈው። የቡሩንዲ መንግሥት እንዳስታወቀው የፕሬዝደንት ኑኩሩንዚዛ ህይወት ያለፈው "በልብ ድካም" ነው ሲል ከአገሪቱ መንግሥት ስለፕሬዝዳንቱ ሞት የወጣው መግለጫ አመልክጠወል። የ55 ዓመቱ ንኩሩንዚዛ ባሳለፍነው ቅዳሜ ጤንነት ስላልተሰማቸው ለህክምና ወደ ሆስፒታል እንዲገቡ ተደርገው ጤናቸው መሻሻል አሳእቶ ነበር። ነገር ግን ሰኞ ዕለት የልብ ችግር እንደገጠማቸውና ነፍሳቸውን ለማትረፍ ጥረት ተደርጎ ሳይሳካ በመቅረቱ ማረፋቸው ተገልጿል። ንኩሩንዚዛ ለ15 ዓመታት ቡሩንዲን በፕሬዝዳንትንት ሲመሩ የቆዩ ሲሆን ነሐሴ አጋማሽ ላይ መንበራቸውን በእሳቸው ይሁንታ ለፕሬዝዳናትነት ቀርበው ለተመረጡት አጋራቸው ያስረክባሉ ተብሎ ነበር። እአአ ከ2005 ጀምሮ ቡሩንዲን የመሩት ንኩሩንዚዛ በቅርቡ በተደረገው ምርጫ እንደማይሳተፉ አሳታውቀው የፓርቲያቸው አባል እና እርሳቸው የመረጡት እጩ ምርጫውን ካሸነፈ በኋላ፤ በቡሩንዲ ፖለቲካ ውስጥ ቁልፍ ሚና ይዘው ይቆያሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር። ከሳምንታት በፊት በተካሄደው ምርጫ ኢቫሪስቴ ዳየሺሚዬ 68 በመቶ ድምጽ በማግኘት ፕሬዝደንታዊ ምርጫውን ማሸነፋቸው ታውጇል። ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ፒዬር ንኩሩንዚዛ አዲስ ለተመረጡት ፕሬዝደንት ነሐሴ 14 ሰልጣን ያስረክባሉ ተብሎ ነበር። ንኩሩንዚዛ ለ15 ዓመታት በስልጣን ላይ ሲቆዩ በየአምስት ዓመቱ በሚካሄዱ ሦስት ምርጫዎች ላይ ተሳትፈዋ። ከአምስት ዓመታት በፊት በተካሄደው ምርጫ ላይ ንኩሩንዚዛ እንደሚሳተፉ ከሳወቁ በኋላ በቡሩንዲ ከፍተኛ ተቃውሞ ተቀስቅሶ ነበር። በዚህም ሳቢያ ተከስቶ በነበረው ግጭት ቢያንስ 1200 ሰዎች መሞታቸው እና ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉት ደግሞ ቀያቸውን ጥለው መሰደዳቸው ይነገራል።
news-54256224
https://www.bbc.com/amharic/news-54256224
ስልክዎ ውስጥ ያለው ወርቅ ለእጽ አዘዋዋሪዎች ገቢ ሊያስገኝ እንደሚችል ያውቃሉ?
አንድ ወርቅ የሚያጣራ ድርጅት ወንጀለኞች ሕገ ወጥ ገንዘብን ወደ ሕጋዊ መስመር እንዲያስገቡ መንገድ ያመቻቻል። ይህ ድርጅት ለተንቀሳቃሽ ስልኮች እና ለመኪና ሥራ የሚውል ወርቅ ለገበያ አቅርቧል።
ካሎቲ የተባለው ድርጅት መቀመጫው ዱባይ ነው። ወርቅ ከወንጀለኞች ይሸምታል። ከስድስት ዓመት በፊት ድርጅቱ ሕገ ወጥ ገንዘብን ወደ ሕጋዊ በማስገባት ቀንደኛ መሆኑን ለዓለም እንዲያስጠነቅቅ ለአሜሪካ ግምዣ ቤት ተገልጾ ነበር። ማስጠንቀቂያው ግን አልተሰጠም። ካሎቲ ለምርቶቻቸው ውድ ማዕድን ለሚጠቀሙት አፕል፣ አማዞን እና ጀነራል ሞተርስ ወርቅ ሸጧል። ይህ ማለት እነዚህ ተቋሞችና ሸማቾች በተዘዋዋሪ ለወንጀል እንቅስቃሴ ድጋፍ አድርገዋል ማለት ነው። የካሎቲ ወኪሎች ወንጀል ወይም ሕገ ወጥ ክንውንን ሆነ ብለን አልደገፍንም ብለዋል። ካሎቲ ያደረገው ምንድን ነው? ዓለም አቀፍ የምርመራ ጋዜጠኞች ቡድን እንዲሁም ቢቢሲም ያገኟቸው ሚስጥራዊ ሰነዶች እንደሚጠቁሙት፤ የአሜሪካ ግምዣ ቤት እአአ 2014 ላይ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጥ ተጠይቆ ነበር። መረጃውን ያቀበሉት ለሦስት ዓመታት ጉዳዩን ያጣሩ መርማሪዎች ነበሩ። ‘ሀኒ ባጀር’ የሚል ቅጽል ስም የተሰጠው ምርመራ የተካሄደው በአሜሪካው የጸረ አደንዛዥ እጽ ተቋም (ዲኢኤ) ነው። ካሎቲ ወርቅን ተጠቅሞ በርካታ ሕገ ወጥ ገንዘብ አዘዋውሯል፤ አስተላልፏልም። በየትኛውም አገር ያሉ ወንጀለኞች ከእጽ ዝውውር ወይም በሌላ መንገድ በተገኝ ገንዘብ ቅንጥብጣቢ ወርቅ ወይም ጌጣ ጌጥ ገዝተው ለካሎቲ እንደሚሰጡ ሰነዶች ይጠቁማሉ። ካሎቲ ደግሞ ለወርቁ ምላሽ በርካታ ገንዘብ ይሰጣቸዋል። ወይም ያስተላልፍላቸዋል። የአሜሪካ ግምዣ ቤት ማስጠንቀቂያ እንዲሰጥ ተነግሮት ምንም እርምጃ ያልወሰደው የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን ላለማስቀየም ነው። ካሎቲ በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጥ በመርማሪዎች ስላልተጠየቀ ያለው ነገር የለም። የአሜሪካ ግምዣ ቤትም ምንም አላለም። በመላው ዓለም ካሎቲ ገንዘብ ባስቀመጠባቸው ባንኮች አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎች እንደነበሩ ምርመራው ያሳያል። የአሜሪካ መንግሥት ይህን ምርመራ ለሕዝብ ይፋ አላደረገም። ደችስ ባንክ፣ ባርክሌስ እና ሌሎችም 34 ባንኮች ስለ ካሎቲ ለአሜሪካ ግምዣ ቤት ከገንዘብ ጋር የተገናኙ ወንጀሎች ክፍል ሪፖርት አስገብተዋል። በሪፖርቱ መሠረት፤ ከ2007 እስከ 2015 ድረስ 9.3 ቢሊዮን ዶላር ዝውውር ተደርጓል። 2017 ላይ ሕገ ወጥ ገንዘብን በሕጋዊ መስመር የሚያስገባ ቡድን ፈረንሳይ ውስጥ ተከሷል። በአውሮፓ አደንዛዥ እጽ ያሰራጭ ነበር። ይህ ቡድን የሚቆጣጠረው ረንዴ ኢንተርናሽናል ለካሎቲ 146 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ወርቅ መሸጡን ቢቢሲ ከወራት በፊት ደርሶበት ነበር። ካሎቲ ሕግ ወጥ ተግባር እንዳልፈጸመና በአሜሪካ ባለሥልጣናት እንዳልተከሰሰ ይናገራል። የድርጅቱ ጠበቆች እንደሚሉት፤ በየዓመቱ የሚካሄደው ኦዲት በሕጋዊ መንገድ ይከናወናል። ግዙፍ ተቋሞች እጅ የገባው የካሎቲ ወርቅ ዲኢኤ የመራው ምርመራ እንደሚጠቁመው፤ ካሎቲ ለመጀመሪያ ጊዜ ሕገ ወጥ ገንዘብ ወደ ሕጋዊ መስመር ያስገባው በነሐሴ 2014 ነው። በካሎቲ የተሸጠ ወርቅ በግዙፍ ተቋሞች እጅ ገብቷል። ስዊዘርላንድ የሚገኘው ግዙፍ የወርቅ አምራች ቫልካምቢ ከካሎቲ ወርቅ ከገዙት መካከል ይጠቀሳሉ። ቫልካምቢ ከ2018 እስከ 2019 ድረስ ወደ 20 ቶን ወርቅ ከካሎቲ ገዝቷል። 60 ቶን ወርቅ ደግሞ ከካሎቲ ጋር ግንኙነት ካለው አካል ሸምቷል። ከላሎቲ ወርቅ መግዛቱን ግን ማመንም መካድም እንደማይችል ተናግሯል። ተንቀሳቃሽ ስልኮች (በተለይም ስማርትፎን) ከሚሠሩባቸው ንጥረ ነገሮች አንዱ ወርቅ ነው። ስልክ አምራቹ አፕልም ከካሎቲ ወርቅ ገዝቷል። አፕል ባወጣው መግለጫ “ወርቅ አጣሪ ድርጅት ያስቀመጥነውን ደረጃ የማይመጥን ከሆነ ወይም ፍቃደኛ ሆኖ ካልተገኘ ምርቱን መግዛት እናቆማለን። ከ2015 ወዲህ ከ63 ተቋሞች ጋር ስምምነታችንን አፍርሰናል” ብሏል። አያይዞም “ከ2015 ጀምሮ ገለልተኛ አካል ያደረገው ምርመራ እንደሚያሳየው የካሎቲ ወርቅ በአፕል ምርቶች ጥቅም ላይ ስለመዋሉ ማስረጃ የለም” ሲል አቋሙን አስታውቋል። ካሎቲ ለጄነራል ሞተርስ እና ለአማዞንም ወርቅ ማቅረቡን የምርመራ ሰነዶች ያሳያሉ። መኪናዎች ሲገጣጠሙ ወርቅ የሚጠቀመው ጄነራል ሞተርስ ከካሎቲ ጋር ቀጥታ የንግድ ግንኙነት እንዳልነበረው እና ለምርት የሚያውለውን ቁሳቁስ የሚያቀርቡለትን ተቋሞች ኃላፊነት በተሞላው መንገድ እንደሚመርጥ ገልጿል። ምርት ከሚያቀርቡለት መካከል ስለ ካሎቲ ቅሬታ ያቀረበለት እንደሌለም አክሏል። አማዞን በበኩሉ “ምርት የሚያቀርቡልኝ ተቋሞች ሰብአዊ መብትና የአካባቢ ጥበቃ ሕግጋትን የሚያከብሩ መሆናቸውን አረጋግጣለሁ። የምንጠቀምባቸው ንጥረ ነገሮች ከየት እንደሚመጡ በማጣራት ረገድ ምርት አቅራቢዎቻችን እንዲተባበሩን እንጠብቃለን” ብሏል። ለዓመታት ስለ ካሎቲ ምርመራ ሲያደርጉ የነበሩና ሕገ ወጥ ገንዘብ ወደ ሕጋዊ ማስገባቱን ያጋለጡት አካላት የአሜሪካ ግምዣ ቤት ለጉዳዩ ትኩረት አለመስጠቱ አስቆጥቷቸዋል። አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ የማይሹ የዲኢኤ ሠራተኛ፤ “ለሦስት ዓመታት ለፍተናል። ሕይወታችን ምርመራው ሆኗል። ከበቂ በላይ ማስረጃ ነበረን ብለን ስለምናምን ሁላችንም ተበሳጭተናል” ሲሉ ምሬታቸውን ገልጸዋል።
news-53998600
https://www.bbc.com/amharic/news-53998600
በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በጎርፍ ምክንያት 43 ሺህ 670 ነዋሪዎች ተፈናቀሉ
በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ እስከ ዛሬ ድረስ 43 ሺህ 670 ሰዎች በጎርፍ ምክንያት መፈናቀላቸው ተገለፀ።
የደቡብ ክልል ኀብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር፣ እንዳሻው ሽብሩ ለቢቢሲ እንደገለፁት በወረዳው ላይ 62 ሺህ ነዋሪ እንዳለ ይገመታል። በደቡብ ኦሞ ዞን በዳሰነች ወረዳ ከሐምሌ 25፣ 2012 ዓ.ም ጀምሮ የተከሰተው የኦሞ ወንዝ ሙላት ያስከተለው ጎርፍ ተከትሎ በውሃ የተከበቡ 19 ደሴቶች ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ሰዎችን ለማውጣት በሞተር ጀልባ የታገዘ ጥረት በማድረግ 43 ሺህ 670 ቤተሰቦችን ማውጣትና በ8 ደረቃማ አካባቢዎች ማስፈር መቻሉን የወረዳው ኮሙኑኬሽን በፌስ ቡክ ገፁ ላይ አስታውቋል። በክልሉ በስልጤ ዞን እንዲሁም ደቡብ ኦሞ ዳሰነች ወረዳ ላይ ጎርፍ ተከስቶ ሰዎች መፈናቀላቸውን የተናገሩት ኃላፊው ወደፊት ዝናቡ እየጠነከረ ሲመጣ ስጋት ካለባቸው የደቡብ ኦሞ አካባቢዎች መካከል በናፀማይ፣ ኛንጋቶም ፣ እና ሀመር እንደሚገኙበት ተናግረዋል። በዳሰነች ወረዳ የተፈናቀሉት ሰዎች በመጠለያ ውስጥ እንደሚገኙ ተናግረው፣ ወደ ስድስት ሺህ ሰዎች ይኖሩበት ከነበረው ሃይቅ ደሴት ላይ እንዲወጡ መደረጉን ተናግረዋል። ለተፈናቀሉ ወገኖች የመጠለያ እንዲሁም የተለያዩ ድጋፎች እየተደረገ ነው ያሉት አቶ እንዳሻው፣ በጎርፍ አደጋው ወቅት ሊከሰቱ የሚችሉ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል የክልሉ እንዲሁም የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ተወካዮች በስፍራው እንደሚገኙ አስረድተዋል። በወረዳው የኮሌራ ወረርሽኝ ይከሰታል የሚል ስጋት የነበረ ቢሆንም እስካሁን ግን በጎርፍ ምክንያት በኮሌራ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ስድስት ብቻ መሆናቸውንም ገልፀዋል። ለተፈናቃዮቹ የመጠለያ ሲዘጋጅ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝመን ታሳቢ ማድረጉንም ጨምረው አስረድተዋል። መተሃራ የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ እንደ መተሃራ እና ወንጂ ያሉ የምስራቅ ሸዋ ከተሞች ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለጸ። መተሃራ ከተማ ካሏት ሁለት ቀበሌዎች መካከል አንደኛውን ሙሉ በሙሉ ማጥለቅለቁን ነዋሪዎች ተናግረዋል። የመተሃራ ከተማ ከንቲባ አቶ ታደለ ዲሪርሳ ለቢቢሲ፤ ይህ አይነት ጎርፍ በከተማዋ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ነው ብለዋል። በሰው ላይ የደረሰው ጉዳት እስካሁን አለመመዝገቡን ይሁን እንጂ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ከተንቲባው ጨምረው ተናግረዋል። በጎርፍ በተጥለቀለቀው የከተማዋ ቀበሌ ወደ 20ሺህ የሚገመቱ ነዋሪዎች መኖራቸውን የገለጹት አቶ ታደለ ተፈናቃዮችን ወደ ሌላኛው ቀበሌ እያሰፈሩ መሆኑን ተናግረዋል። የውሃ መጠኑን አሁንም እየጨመረ በመሆኑ ተጨማሪ አደጋ እንዳይከሰት ከፍተኛ ስጋት እንዳለባቸው ከንቲባው ተናግረዋል። አፋር በአፋር ክልል በሚገኙ 14 ወረዳዎች ውስጥ ከ120 ሺህ በላይ ሰዎች በጎርፉ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን የክልሉ የአደጋ መከላከል ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ እና ምላሽ ኃላፊ አቶ ማሂ አሊ በተለይ ለቢቢሲ ገልጸዋል። በአሳይታ፣ አፋምቦ፣ ዱብቲ እና ዞን 3 አካባቢዎች ለተፈናቀሉት ሰዎች ከፌደራል መንግሥት፣ ከክልሎች እና ከተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የተገኙ ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎች እየተደረጉ ነው ብለዋል። በጎርፍ አደጋው እስካሁን ሰው ህይወት አለመጥፋቱን የገለጹት አቶ ማሂ ሆኖም ሰዎች ከቤታቸው ሲፈናቀሉ ምግብና መገልገያ ቁሳቁሶችን ባለመያዛቸው ለችግር ተጋልጠዋል ብለዋል። ጎርፉ ቲማቲም፣ ሽንኩርት፣ ጥጥ፣ በቆሎን ጨምሮች ከ 21 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ የነበሩ የደረሱ ሰብሎችን ከጥቅም ውጭ ማድረጉ ታውቋል። ገለአሎ ወረዳ ላይ ደበል እና ገፍረሞ በሚባሉ ቀበሌዎች በውሃ የተከበቡ ሰዎች መኖራቸውን የገለጹት አቶ ማሂ ሰዎቹን ከአካባቢዎቹ ለማውጣት ጀልባ እና ከመከላከያ ሚንስትር ደግሞ ሄሊኮፕተር ተጠይቆ እየተጠበቀ ነው። በክልሉ አሁንም የጎርፍ ስጋት መኖሩን የጠቆሙት አቶ ማሂ አዋሽ ፈንታሌ፣ ገዋኔ፣ ገልአሎ፣ አሚበራ እና ዱለቻ በሚባሉ አካባቢዎች ከቆቃ እና ቀሰም ግድቦች በሚለቀቀው ውሃ፣ በአካባቢው እና በሌሎች አካባቢዎች እየጣለ ባለው ዝናብ ምክንያት ስጋት መኖሩን ጠቁመዋል። ስጋት ባለባቸውን አካባቢዎች ኮማንድ ፖስት በማቋቋም የስጋት ቦታዎችን ከመለየት፣ የጥንቃቄ ሥራዎችን ከማከናወን ባለፈ ጎርፍ ተከስቶ ህብረተሰቡን ከመጉዳቱ በፊት 24 ሰዓት መረጃ ለህብረተሰቡ የሚሰጥ ቡድን ወደ ሥራ ገብቷል ብለዋል። የተፈናቀሉ ሰዎች በ14 ጣቢያዎች ውስጥ መኖራቸውን ጠቁመው በጣቢያዎቹ ጥግግት ቢኖርም የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የህክምና ባለሙያዎች እና በጎ ፈቃደኞች ትምህርት በመስጠት ላይ ናቸው ብለዋል። ባለፉት ሳምንታት ከፌደራል መንግስት በቀረበ ሔሊኮፕተር በአፋር ክልል በአደጋ ቀጣና ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን የማውጣት ሥራ ከማከናወን ሲሠራ መቆየቱ ይታወሳል።
news-52491113
https://www.bbc.com/amharic/news-52491113
ኮሮናቫይረስ፡ በኒው ደልሂ አጣብቂኝ ውስጥ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ታካሚዎች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
የኮሮናቫይረስ ወረርሽን ተከትሎ ህንድ ባሳለፈችው የእንቅስቃሴ ገደብ ለሳምንታት በኒው ደልሂ ለመቆየት ተገደው የነበሩ 100 የሚሆኑ ኢትዮጵውያን ታካሚዎች ከሰሞኑ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።
ለህክምና ወደ ህንድ የሄዱ ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገራቸው መመለስ ሲኖርባቸው ባልጠበቁት ሁኔታ እንዲቆዩ መደረጋቸው ለኢኮኖሚያዊና ለተለያዩ ችግሮች መጋፈጣቸውን በባለፈው ሳምንት ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። ይህንንመ ተከትሎ በኒው ደልሂ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመተባበር ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ሚያዝያ 14/2012 ዓ.ም ወደ አገራቸው እንደመለሷቸው ታካሚዎቹ ለቢቢሲ ገልፀዋል። "ታፍነን ነበርን" ከኒው ደልሂ ወደ ኢትዮጵያ የመመለስ እድል ካገኙት መካከል አንዱ አቶ ሃብቶም በህክምና ምክንያት ከወንድሙ ጋር ለሁለት ወራት በህንድ ቆይቷል። "በአንደኛው ወር ህክምናዬን ብጨርስም የህንድ መንግሥት እንቅስቃሴ እንዳይኖር መመሪያ በማውጣቱ ለተጨማሪ አንድ ወር በከባድ ችግር ነው ያሳለፍነው። ቅዳሜ እለት ግን የኤምባሲ እና የአየር መንገዱ ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመልሱን ነገሩን። ብዙ መከራ ብናሳልፍም አሁን ግን ደስተኞች ነን" ይላል። የ68 ዓመት አዛውንቱ አቶ ገብረመስቀል ገብሩም ለኩላሊት ንቅለ-ተከላ ሦስት ሁነው ነበር ወደ ኒውደልሂ የሄዱት። ከባለቤታቸው እና ኩላሊት ከሚለግስላቸው ሰው ጋር የሄዱት እኚህ የእድሜ ባለፀጋ በህንዷ መዲና ለሦስት ወራት እንዲቆዩ ተገደው ነበር። "እዚህ ታፍነን ነበር፤ ከማንም ጋር መነጋገር አይቻልም። በችግር ውስጥ ነው የነበርነው" በማለት አሁን ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ በመደረጋቸው ደስተኛ መሆናቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሌላ ስጋት….. በህንድ ሁለቴ በታወጀው ረዥም የእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት ላልተፈለገ ወጪ ተጋልጠው የቆዩት እነዚህ ታካሚዎች አሁን ወደ ኢትዮጵያ ቢመለሱም በመዲናዋ ለሁለት ሳምንታት በለይቶ ማቆያ ያሳልፋሉ። "የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆቴሎች ዝርዝር ልኮልናል፤ ዝቅተኛው ዋጋ በቀን 30 ዶላር ነው። በህንድ የኢኮኖሚ ችግር ስለደረሰብን ይህ ለመክፈል አቅማችን አይፈቅድም። በውድ ሆቴሎች ገብተን ምንድን ነው የምንሆነው?" ሲል አቶ ሃብቶም ይናገራል። በአዲስ አበባ ለ14 ቀናት በለይቶ ማቆያ ሆቴሎች የነበሩና ጉዟቸውን ወደ ትግራይ የሚቀጥሉ ተጓዦችም የክልሉ መንግሥት በጣለው አስቸኳይ ግዜ አዋጅ ምክንያት ለሁለተኛ ግዜ በክልሉ ወደ ለይቶ ማቆያ ማዕከል አሊያም ሆቴሎች መግባታቸው ግድ ነው። አቶ ገብረመስቀል በውድ ሆቴሎች ለዚያውም ሁለት ግዜ ወደ ለይቶ ማቆያ መግባት የሚለውን ውሳኔ አይቀበሉትም። "ከሆስፒታል እንደወጣሁኝ ኩላሊት ለለገሰልኝ ሰው እና ለእኛ ሁለት ማረፍያ ነበር የያዝኩት። በጣም ውድ ነው፤ በዚያ ላይ ለሦስት ወር መቆየት በጣም ከባድ ነው። የገንዘብ ቀውስ ደርሶብናል" ይላሉ አቶ ገብረመስቀል። "በአዲስአበባ ለ14 ቀናት፤ በመቀለም ለ14 ቀናት ባጠቃላይ ለአንድ ወር በለይቶ ማቆያ መቆየት ጥሩ አይደለም። ወደ መቀለ የሚሄደውን እዚያ ተለይቶ መቆየት አለበት። በአዲስ አበባ አንዴ ተለይተን ከቆየን ይበቃል። ሰው በተጓዘበት ሁሉ መታሰር ግን ትክክል አይደለም" ብለው ያምናሉ። የሌሎቹ እጣፈንታስ? አሁን በኢትዮጵያ መንግሥት የተወሰደው እርምጃ በኒውደልሂ የነበሩ ታካሚዎች ብቻ ላይ ያተኮረ እንደሆነ ተገልጿል። ይሁን እንጂ አሁንም በተለያዩ የህንድ ግዛቶች በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ታካሚዎች አሉ። በሀገሪቱ በወረርሽኙ ምክንያት የትራንስፖርት አገልግሎት በመከልከሉ ከኒውደልሂ ውጪ ያሉ ታካሚዎች ወደ መዲናዋ መምጣት አልቻሉም። የኢትዮጵያ አየር መንገድም ከኒውደልሂ ውጪ ወደ ሌሎች አካባቢዎች አለመብረሩ ደግሞ ይህንን እድል ለማግኘት እንዳልቻሉ ነው ቢቢሲ ያነጋገራቸው ኢትዮጵያውያን የሚገልፁት። አሁን ወደ አገር ቤት የተመለሱት 100 እንደማይሞሉ እና ቁጥሩ በተለያዩ የህንድ ግዛቶች የሚገኙትን ታካሚዎች ከዚህ በርካታ መሆናቸውን ይናገራሉ። ከአዲስ አበባ እናቱን ለማሳከም ወደ ኖይዳ ከተማ የሄደው አቶ ዳናይ ግደይም በህንድ ካሰቡት በላይ እንዲቆዩ እና ለገንዘብ ችግር ከተጋለጡት ኢትዮጵያውያን መካከል አንዱ ነው። "እናቴ ዕጢ ስለነበራት እሱን ለማስወገድ በመጋቢት 13 ነው ወደ ጄፒ ሆስፒል የሄድኩት። አስፈላጊውን ቀዶ ህክምና ብንጨርስም ለማደሪያ በቀን 1800 ሩፒ በመክፈል ነው እየኖርን ያለነው። ይህንን የምግብና የመድኃኒት ክፍያን አይጨምርም" ይላል ዳናይ። በእጁ የነበረውን ብር እየጨረሰ መሆኑ እና ከቤተሰብ በዌስተርን ዩኒየን እንዳያስልክም የአገሪቱ ባንኮች ዝግ በመሆናቸው መንቀሳቀስ እንዳልቻለ ገልፆልናል። በህንድ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በየቀኑ መጨመር ለእናቱ ጤና ስጋት እንደሆነበት የሚናገረው አቶ ዳናይ ወደ ኢትዮጵያ ኤምባሲ ቢደውልም ኤምባሲው በአገሪቱ በተጣለው አዋጅ ዝግ መሆኑ እንደተነገረው ይገልፃል። "የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከአየር መንገዱ ጋር በመተባበር ኒውደልሂ የሚገኙትን እየወሰደ እንደሆነ ገና ዛሬ ነው የሰማነው። የምናውቀው ነገር አልበረም። እንደሰማን እኛም ወደ ሀገራችን መመለስ እንፈልጋለን እባካችሁ ድረሱልን ብለናቸዋል" ቢሆንም የቪዛ ቁጥራቸውን ከመመዝገብ ባሻገር መፍትሄ እንዳላገኙ ነው የሚናገረው። "አገራት ዜጎቻቸውን በቻርተር አውሮፕላን እያስወጡ ነው" ቢቢሲ በዚህ ጉዳይ ላይ ምላሽ ለማግኘት ኒውደልሂ ወደሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተደጋጋሚ ቢደውልም ከሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ለማግኘት አልቻለም። በሰሜናዊ ህንድ የሚኘውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥራ አስኪያጅ የሆኑትን አቶ ክሩቤል ሽታሁን ግን ይህን ጉዳይ እንደሚያውቁት፤ አየር መንገዱ መንገደኞች ለማጓጓዝ ፈቃድ እንዳልተሰጠው እና በረራዎች መንግሥታት እንደሚያስተባብሩት ባለፈው ሳምንት ለቢቢሲ ገልፀው ነበር። "ከኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ ከህንድ መንግሥት መንገደኞች ለማጓጓዝ ፈቃድ ስላልተሰጠን ምንም ማድረግ አልቻልንም። አንዳንድ አገራት ዜጎቻቸውን በቻርተር አውሮፕላን እያስወጡ እንደሆነ እናውቃለን" ማለታቸው ይታወሳል። በዚህ ጉዳይ ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መልስ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
44299018
https://www.bbc.com/amharic/44299018
ፌስ ቡክ በፓፓዋ ኒው ጊኒ ለአንድ ወር ሊታገድ ነው
ፓፓዋ ኒው ጊኒ ሐሰተኛ የፌስ ቡክ ገጾችን ለመለየት እና ድረገፁ በሀገሪቱ ላይ ያለውን ተፅእኖ ለመለየት በሚል ፌስ ቡክን ለአንድ ወር ልታግድ ነው።
የሀገሪቱ ኮሙኑኬሽን ሚኒስትር፣ ሳም ባዚል እንዳሉት ወሲብ ተንቀሳቃሽ ምስሎችንና ሀሰተኘኛ መረጃዎችን የሚያሰራጩ ይለያሉ። አክለውም ከፌስ ቡክ ጋር የሚስተካከል ማህበራዊ ድርአምባ ሊከፍቱ እንደሚችሉም ተናግረዋል። በፓፓዋ ኒው ጊኒ ከአጠቃላይ ሕዝቡ 10 እጅ የሚሆነው ብቻ የኢንተርኔት ተጠቃሚ ቢሆንም ሐገሪቱ ግን በድረገፅ የሚሰራጩ መረጃዎች ላይ የሚወጡ ህጎችን በማውጣት ቀዳሚ ነች። መንግስት በአንድ ወር የእቀባ ጊዜ ውስጥ ፌስ ቡክ እንዴት ጥቅም ላይ እየዋለ እንደሆነ የሚመረምር ሲሆን የ2016ቱን የሀገሪቱ የሳይበር ወንጀል ሕግ የተላለፉት ላይ ክስ ይመሰርታል። የኮሙኑኬሽን ሚኒስትሩ ባዚል በሀገር ውስጥ ለሚንቀሳቀስ አንድ መገናኛ ብዙሃን እንዳሉት "ጊዜውን ከሐሰተኛ አካውንቶች ጀርባ ማን እንዳለ መረጃ ለመሰብሰብ እንጠቀምበታለን፤ ወሲብ ነክ ምስሎችን የሚለጥፉ እና ሐሰተኛ መረጃዎችን የሚያሰራጩ ተጠቃሚዎችን እንለይበታለን"" በአለም አቀፍ ደረጃ ለሚንቀሳቀሱ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች "ሐሰተኛ ዜናዎች" ዋነኛ እንቅፋት ሆነውባቸዋል፤ ተጠቃሚዎቻችን መረጃው ስህተት ሲሆን አላስጠነቀቁም በሚልም ይተቻሉ። "ለሀገራችን ዜጎች በእውነተኛ ማንነታቸው የሚጠቀሙበት አዲስ ማህበራዊ ድር አምባ እንከፍታን" ብለዋል ባዚል። "አስፈላጊ ከሆነ በሀገር ውስጥ ያሉ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎችን ሰብስበን ለህዝባችን የበለጠ ተስማሚ የሆነ በሀገረ ውስጥ ሆነ በውጭ የሚሰራ እንዲፈጥሩ እናደርጋለን"ብለዋል። ፌስ ቡክ ከካምብሪጅ አናሊቲካ ጋር በተያያዘ ምርመራ የተደረገበት ሲሆን ሐሰተኛ ዜናዎችን እንዳይሰራጩ ለመከላከል ያደረገው ጥረት የለም በሚል ትችት እንደቀረበበት ይታወሳል።
news-48400974
https://www.bbc.com/amharic/news-48400974
የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለማሻሻያዎች ችኮላ እንደማይገባ ገለፁ
የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሀገሪቱ ላይ ሊደረጉ ለሚገቡ ዋና ዋና ማሻሻያዎች ችኮላ እንደማይገባ የኤርትራን 28ኛ አመት የነፃነት ክብረ በዓል አስመልክቶ በዛሬው ዕለት ባደረጉት ንግግር ገልፀዋል።
ሁለቱ ሃገራት ጦርነትና ሰላም በሌለበት ሁኔታ ከሁለት አስርት አመታት ፍጥጫ በኋላ በሰላም በመቋጨቱ ማግስት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ፖለቲካዊ ማሻሻያዎችን ሊያውጁ ይችላሉ በሚልም በተለያዩ አገራት በሚኖሩ ኤርትራውያን ዘንድ እየተጠበቁ ነበር። •የኤርትራ 28ኛ ዓመት ነፃነት ከየት ወደየት? •የ "ጥርስ አልባው" ማዕቀብ መነሳት ፖለቲካ? •ታዋቂዎቹ ኤርትራዊያን በሙዚቃቸው ምክንያት ይቅርታ ጠየቁ በኤርትራ መዲና አስመራ ባደረጉትም ንግግር "ሰላም የሰፈነበት የአዲሱ ዘመን ምኞትና ፍላጎት ፈተናዎቹን ሊጋርዱዋቸው አይገባም" ብለዋል። በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል ሰላም መፈጠሩን ተከትሎ በኤርትራውያን ዘንድ አዲስ የዲሞክራሲ ምዕራፍ ይፈነጥቃል የሚል ተስፋ ቢኖርም ፕሬዚዳንቱ ምንም አይነት ለውጥ አላመጣም በማለት በእምቢተኝነታቸው ቀጥለዋል በሚልም እየተተቹ ነው። •ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በአዲስ አበባና ሃዋሳ ጉብኝት ያደርጋሉ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ሃገሪቷን አሁንም ቢሆን ያለ ህገ መንግሥት እየመሩ ሲሆን ብሔራዊ ምክር ቤቱን (ፓርላማ) እንደበተኑት ነው። የተለያዩ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞችን፣ ጋዜጠኞችንና በዘፈቀደ በማሰር ይከሷቸዋል። የሁለቱን ሃገራት እርቀ ሰላም ተከትሎ ለአስርት ዓመታት ተዘግተው የነበሩት የሁለቱም አገራት ድንበሮች ቢከፈቱም፤ ከጥቂት ወራት በፊት ምንም አይነት መግለጫ ሳይሰጥ ከኤርትራ በኩል ተዘግተዋል።
45792452
https://www.bbc.com/amharic/45792452
የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ለውጡን ማስቀጠል ተቋማዊ መሰረት እንደሚያስፈልገው ገለፁ
ዛሬ የጋራ 5ኛ ዘመን 4ኛ ዓመት አንደኛ መደበኛ ጉባኤን በንግግር የከፈቱት የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) ስለ 2010 ዓመት አፈፃፀምና የመንግሥት ቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎችን በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል።
"መንግሥት ሰላምና የተረጋጋ ሀገር መፍጠርና በዚህ ሁኔታ ማስቀጠል የሚችለው የተሟላ የዲሞክራሲ ስርዓት ሲፈጠር ነው ብሎ ያምናል" ብለዋል። •ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ •«አዲስ አበባ የሁሉም ናት» አርበኞች ግንቦት 7 •«የምታገለው ለማንም ብሔር የበላይነት አይደለም» አቶ በቀለ ገርባ በሀገሪቱ ውስጥ እየተከሰቱ ያሉ ለውጦችን እንደ ጥሩ እመርታ በማየት ይህንን ለማስቀጠል የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ተቋማዊ መሰረት እንደሚያስፈልግም ገልፀዋል። የፍትህና የዴሞክራሲን ስርዓት ለማበልፀግም ሚና የሚኖራቸው ተቋማትን፣ ህግጋትንና አዋጆችን ማሻሻል እንደሚያስፈልግ የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ በዚህም መሰረት ልዩ ትኩረት የሚሰጥባቸውን ጉዳዮችን ጠቁመዋል። "የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ተቋማዊ መሰረት ከሌለው ረዥም መንገድ ሊጓዝ እንደማይችል ግልፅ ነው" ብለዋል። መንግሥት የዜጎች ሰብዓዊ መብት እንዲከበርና የፖለቲካ ምህዳሩ እንዲሰፋ በማለምም በርካቶችን ከእስር መፍታት፤ እንዲሁም ለዓመታት ነፍጥ አንስተው ሲታገሉ ከነበሩ ኃይሎች ጋር ድርድር መጀመራቸውን እንደ ትልቅ እርምጃ በማንሳት በቅርቡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያፀደቀው የምህረት አዋጅንም መንግሥት በዚህ ረገድ እየሄደ ያለበት አቅጣጫ አመላካች እንደሆነ ጠቅሰዋል። የዴሞክራሲ ስርዓቱ እንዲያብብና የተጀመሩ ማሻሻያዎችም በዘላቂነት ተቋማዊ መሰረት እንዲኖራቸው ለማድረግም አማካሪ ኮሚቴ መቋቋሙንም ገልፀዋል። አማካሪ ኮሚቴው በቴክኒክ ኮሚቴ የሚታገዝ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ገልፀው በዚህ ዓመትም የፀረ-ሽብር አዋጅ፣ የሲቪክ ማህበራትና በጎ አድራጎት ማህበር አዋጅ፣ የመገናኛ ብዙኃን እና የመረጃ ነፃነት አዋጅን ጨምሮ ሌሎች አዋጆችን የማሻሻል ስራ ይሰራል ብለዋል። በንግግራቸው ከለውጥና ከማሻሻያ ሂደት ጋርም በተገናኘ የፖለቲካ ምህዳርን ስለ ማስፋት፣ በዓመቱ ያጋጠመውን የምጣኔ ኃብት ነክ ችግር ለመቅረፍ የሚያስችሉ እርምጃዎችን ስለ መውሰድ፣ ዲፕሎማሲ፣ ቀጠናውንም ሆነ አህጉሪቷን እንዴት በንግድ ማስተሳሰር ይቻላል የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮችንም በንግግራቸው ዳሰዋል። ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከርም ከ2011 ጀምሮ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ የመዳረሻ ቪዛን ለመስጠትና እቅድ እንዳለ ገልፀው በተለይም ኢትዮጵያ የአፍሪካ መዲና ከመሆኗም ጋር ተያይዞ ትስስሩን እንደሚያጠናክርና ከቦታ ቦታ መዘዋወርንም ለማቅለል እንደሚረዳ ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል እንድትሆን በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
news-52031559
https://www.bbc.com/amharic/news-52031559
ከባድ በተባለ ጥቃት ቦኮ ሃራም 92 የቻድ ወታደሮችን መግደሉ ተነገረ
የቻድ ፕሬዝዳንት 92 የአገራቸው ወታደሮች በቦኮ ሃራም ታጣቂዎች በተጸመ ጥቃት መገደላቸውን አስታወቁ።
ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢ እንዳሉት ታጣቂው ቦኮ ሃራም ሰኞ እለት ጠዋት ላይ በፈጸመው ጥቃት ነው ወታደሮቹ የተገደሉት። ይህም በእስላማዊው ቡድን ባለፉት አምስት ዓመታት ከተፈጸሙ ጥቃቶች ሁሉ የአሁኑ እጅጉን የከፋ እንደሆነም አመልክተዋል። ፕሬዝዳንቱ በምዕራባዊ ቻድ አገራቸውን ከናይጄሪያና ከኒጀር ጋር የሚያዋስነውን አካባቢ ጎብኝተዋል። ከአምስት ዓመታት በፊት ከናይጄሪያ የተነሳው የቦኮ ሃራም ታጣቂ ቡድን እንቅስቃሴ በአካባቢው ወዳሉ አገራት ከተስፋፋ በኋላ በደርዘኖች የሚቆጠሩ የቻድ ወታደሮች የተገደሉ ሲሆን ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ በጦርነት ምክንያት ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተፈናቅለዋል። ማክሰኞ ዕለት ደግሞ የናይጄሪያ መንግሥት እንዳስታወቀው የቦኮ ሃራም ታጣቂ ቡድን በአገሪቱ ሰሜን ምሥራቅ በምትገኘው ማይዱጉሪ ከተማ ውስጥ በፈጸመው ጥቃት 47 ወታደሮች ተገድለዋል። የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች ይህንን ጥቃት የፈጸሙት ቦንብና ጥይቶችን ጭነው ከማይዱጉሪ ከተማ በመውጣት በአጀብ ሲጓዙ በነበሩ የናይጄሪያ ሠራዊት ተሽከርካሪዎች ላይ ነው። የናይጄሪያ መንግሥት በመግለጫው ከተገደሉት ወታደሮቹ ውጪ በተፈጸመው ጥቃት ሸማቂው ቡድን ከተሽከርካሪዎቹ ላይ የወሰደው ወታደራዊ መሳራያዎች ስለመኖሩ ያለው ነገር የለም። ቦኮ ሃራም የሚባለው እስላማዊ ታጣቂ ቡድን በሰሜንና ሰሜን ምሥራቅ ናይጄሪያ ውስጥ የመንግሥት ተቋማትንና ወታደሮችን ጨምሮ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃቶችን በመፈጸም ይታወቃል። ቡድኑ ከናይጄሪያ ባሻገርም በጎረቤት አገራት ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ጥቃት የሚፈጽም ሲሆን 92 ወታደሮቿ የተገደሉባት ቻድም ተደጋጋሚ ጥቃት ተፈጽሞባታል።
57155173
https://www.bbc.com/amharic/57155173
ባይደን እስራኤል እና ፍልስጤም የተኩስ አቁም እንዲያደርጉ ጠየቁ
የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን በእስራኤል እና በፍልስጤም ሚሊሻዎች መካከል ለስምንት ቀናት ያክል በጋዛ የቀጠለው ግጭት እንዲቆም ሁለቱ ኃይሎች የተኩስ አቁም እንዲያደርጉ ጠየቁ።
ባይደን ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ከግብጽ እና ሌሎች አገራት ጋር በመሆን የሁለቱን አገራት ጠብ ጋብ ለማድረግ እየሰሩ እንደሆነም ነግረዋቸዋል፡፡ አሜሪካ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በሁለቱ አገራት መካከል የተኩስ አቁም እንዲደረግ ሊያወጣው የነበረውን መግለጫ ባለመስማማቷ አስቁማለች። ለሁለት ሳምንታት የዘለቀው ግጭት እስካሁን ድረስ 61 ህፃናትን ጨምሮ የ212 ሰዎች ህይወትን በጋዛ ቀጥፏል። እስራኤል ደግሞ 10 ሰዎች ሲሞቱባት ሁለቱ ህፃናት ናቸው። እስራኤል በጋዛ ተዋጊዎችን ብቻ ነው የገደልኩት ማለቷን የቀጠለች ሲሆን የሲቪል ሰዎች ሞት ካለ እንኳን ሆን ብዬ አይደለም ብላለች። ሃማስ ግን ይህንን ይቃወማል። "ባይደን የሲቪል ሰዎችን ደህንነት ለመጠበቅ እስራኤልን አስፈላጊውን ሁሉ ጥረት እንድታደርግ አበረታተዋል" ሲል የነጩ ቤተ መንግሥት መግለጫ አስነብቧል። "ሁለቱ መሪዎች ሃማስ እና ሌሎች የአሸባሪ ድርጅቶች ላይ የእስራኤል ወታደራዊ ኦፕሬሽኖችን በተመለከተ ውይይት አድርገዋል" ስልም አክሏል። በግጭቱ ዓለማ አቀፉ ህብረተሰብ ስጋቱን እየገለፀ ሲሆን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችም የሲቪል ሰዎች ሞት እና የግንባታዎች ብሎም የመሰረተ ልማት መውደም እንዲቆም ግልፅ ጥሪዎች እያደረጉ ይገኛሉ። የፀጥታው ምክር ቤት እስራኤል የምታካሂደውን ወታደራዊ ዘመቻ እንድታቆም እና ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄዎችን እንድትከተል የሚጠይቀው የተኩስ አቁም ጥሪ መግለጫን አሜሪካ ስታስቆም ይህ ለሶስተኛ ግዜ ነው። "የኛ ስሌት ይህንን ውይይት ከጀርባ ማካሄድ ነው። እስካሁን ልንወስደው የምንችለው ያለን ገንቢ አማራጭ ነው›› ሲሉ የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ተናግረዋል።
news-52852570
https://www.bbc.com/amharic/news-52852570
ትዊተር የትራምፕ ጽሑፍ ‘ግጭትን ያሞግሳል’ ብሎ ከገጹ ደበቀ
ትዊተር ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጽሑፎች አንዱን ግጭት ያበረታታል በሚል መልዕክታቸው በገጻቸው ላይ እንዳይታይ አድርጓል።
ጽሑፉ ከገጻቸው ላይ እንዲጠፋ ባይደረግም፤ አንባቢዎች እውነተኛነቱን እንዲያጣሩ የሚጠቁም መልዕክት ተያይዞ ተለጥፏል። ትዊተር ጽሑፉን ሰዎች ለማንበብ ይፈልጋሉ በሚል ሳያጠፋው እንደቀረ አስታውቋል። ትዊተርና የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር አንድ ሁለት መባባል ጀምረዋል። በሚኒያፖሊስ ጆርጅ ፍሎይድ የተባለ አፍሪካ አሜሪካዊ በፖሊስ መገደሉን ተከትሎ ሕዝብ ተቃውሞውን እያሰማ ነው። ፕሬዘዳንቱ “የአገር መከላከያ ይላካል። ማውደም ከተጀመረ መተኮስ ይጀመራል” ሲሉ ትዊት አድርገዋል። ትዊተር “ማውደም ከተጀመረ መተኮስ ይጀመራል” የሚለውን ትዊት ነው በትራምፕ ገጽ እንዳይታይ ያደረገው። ትዊተር ታዋቂ ሰዎች የሚጽፉትን ከማጥፋት ይልቅ ከማስጠንቀቂያ ጋር ለማውጣት ውሳኔ ያስተላለፈው ባለፈው ዓመት ነበር። ሆኖም ግን የትራምፕ ትዊቶች ላይ ሕጉ እስካሁን አልተተገበረም ነበር። በዩናይትድ ኪንግደም የማኅበራዊ ሚዲያ ተንታኝ ካርል ሚለር “ትዊተርም ይሁን ሌላ ማኅበራዊ ሚዲያ እንዲህ ድፍረት የተሞላው ተግባር ሲፈጽሙ አላየሁም” ብለዋል። የትዊተር እርምጃ በድረ ገጽ ስለሚደርስ ጥቃት እንዲሁም ስለ ንግግር ነፃነት ያለውን ክርክር ያጦዘዋል ሲሉም ተንታኙ ተናግረዋል። ትራምፕ በፌስቡክ ላይ ያሰፈሩት ተመሳሳይ ጽሑፍ ያለምንም ማስጠንቀቂያ ተለጥፏል። ባለፉት ዓመታት፤ ትዊተር ዶናልድ ትራምፕን እንደ ሌሎች የትዊተር ተጠቃሚዎች እንዲመለከታቸውና የተቋሙ ሕጎች ተፈጻሚ እንዲሆኑባቸው ቢጠየቅም፤ ትዊተር አንዳችም እርምጃ አልወሰደም ነበር። ያሳለፍነው እሮብ ግን የትራምፕን ጽሑፍ “እውነታውን ያጣሩ” ከሚል መልዕክት ጋር አወጣ። ተቋሙ የትራምፕን ትዊቶች ባወጣቸው ሕጎች መሠረት መቃኘት ወይም ካለፈው እሮብ በኋላ የተከተለውን ውዝግብ የማሳለፍ አማራጮች ነበሩት። እናም ትዊተር ሕጎቹን መከተል የመረጠ ይመስላል። የፕሬዘዳንቱ ጽሑፍ ግጭትን የሚያበረታታ ማለቱም ውሳኔውን በግልጽ ያሳያል። ሌላ የትዊተር ተጠቃሚ መሰል ጽሑፍ ቢያሰፍር፤ ትዊተር ጽሑፉን ያጠፋው ነበር። የተጠቃሚው ገጽም ይሰረዝ ነበር። በትዊተር ሕግ መሠረት፤ የትዊተር ተጠቃሚዎች ለትራምፕ ጽሑፍ መልስ መስጠት፣ መልሰው ትዊት ማድረግ ወይም ጽሑፉን መውደዳቸውን ለመግለጽ ‘ላይክ’ ማድረግ አይችሉም። ጽሑፉን መልሰው ለሌሎች ማጋራት ከፈለጉ አብሮት አስተያየት ይኖራል። “ይህ ትዊት ግጭትን የሚያበረታተቱ ጽሑፎችን ለመግታት ያወጣነውን ፖሊሲ ይጻረራል። የጽሑፉን ታሪካዊ ዳራ ሲታይ ከግጨት ጋር የተያያዘና ግጭት ሊቀሰቅስ የሚችልም ነው” ሲል ትዊተር አቋሙን ገልጿል። ትዊተር የጽሑፉ ታሪካዎ ዳራ ያለው፤ የማያሚ የፖሊስ ኃላፊ ዋልተር ኸርድሊ እአአ በ1967 “ማውደም ከተጀመረ መተኮስ ይጀመራል” ሲሉ የተናገሩትን በማጣቀስ ነው። የፖሊስ ኃላፊው ይህን የተናገሩት ጥቁሮች በሚኖሩበት ሰፈር ፖሊሶች ከፍተኛ እርምጃ እንዲወስዱ የሚያደርገውን ፖሊሲያቸውን ደግፈው ነበር። የፖሊስ ኃላፊው የማያሚ ፖሊሶች በጥቁሮች ሰፈር መሣሪያና ውሾች ይዘው እንዲዘዋወሩ የሚያበረታታ ፖሊሲ ነበራቸው። ይህም በአካባቢው ከስምንት ወራት በኋላ ተቃውሞ እንዲቀሰቀስ ምክንያት ሆኗል። ትዊተር “ሰዎች ለግጭት እንዳይነሳሱ ስንል እርምጃውን ወስደናል። ትዊቱን ግን አላጠፋነውም። ምክንያቱም አሁን እየተከናወኑ ካሉ ነገሮች አንጻር ሕዝቡ ትዊቱን እንዲመለከት እንሻለን” ሲል መልዕክት አስተላልፏል። ትዊተር የትራምፕ ጽሑፍ ላይ ማስጠንቀቂያ ካስቀመጠ በኋላ ፕሬዘዳንቱ ትዊተር ሪፐብሊካኖች ላይ አነጣጥሯል ሲሉ ወንጅለዋል። “የቻይና እና የግራ ዘመሙ ዴሞክራቲክ ፓርቲን ውሸትና ፕሮፓጋንዳ በተመለከተ ትዊተር እርምጃ አልወሰደም” ብለዋል። ትዊተር ማስጠንቀቂያውን ከማውጣቱ ከአንድ ቀን በፊት ለማኅበራዊ ሚዲያዎች የተሰጠውን ከለላ የሚያነሳ ውሳኔ ማስተላለፋቸውንም ፕሬዘዳንቱ አስታውቀዋል። ትዊተር ለመጀመሪያ ጊዜ የትራምን ትዊት “እውነታውን ያጣሩ” ከሚል ማስጠንቀቂያ ጋር ማውጣቱን ተከትሎ፤ ፕሬዘዳንቱ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ነፃ ንግግርን እያገዱ ነው ብለው ተቋሞቹን ለመዝጋት ሲያስፈራሩ ነበር። በእርግጥ ትራምፕ ያስተላለፉት ውሳኔ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ አሁን ጫና አያሳርፍም። በጊዜ ሂደት ግን አንዳንድ ለውጦች ሊያስከትል ይችላል።
news-46395977
https://www.bbc.com/amharic/news-46395977
በአዲስ አበባ ዕድሜያቸው ከ15-24 የሚሆኑ አፍላ ወጣቶች በከፍተኛ መጠን በኤች አይቪ እየተያዙ ነው
በአዲስ አበባ የኤች አይቪ የስርጭት መጠን እየጨመረ እንደመጣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኤችአይቪ መከላከያና መቆጣጠያ ፅ/ቤት ኃላፊ ሲስተር ብርዛፍ ገብሩ ለቢቢሲ ገለፁ። ይህም የሆነው የመከላከል ስራው ላይ መዘናጋት በመታየቱ እንደሆነ አስረድተዋል።
በአዲስ አበባ የስርጭት መጠኑ 3.4 በመቶ መሆኑን የሚናገሩት ኃላፊዋ ዛሬም በከፍተኛ ሁኔታ በቫይረሱ ከተያዙ መካከል ሴቶች ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛሉ ብለዋል። በከተማዋ ኤች አይቪ በደማቸው የሚገኙ ግለሰቦች 109 ሺህ መሆናቸውን ያስታወሱት ሲስተር ብርዛፍ ከእነዚህ መካከል ዕድሜያቸው ከ15-24 የሚሆን ወጣቶች በከፍተኛ ቁጥር በቫይረሱ መያዛቸውን ጥናቶች እንደሚያሳዩ ተናግረዋል። • በኢትዮጵያ 76 በመቶ የሚሆኑት ወጣት ሴቶች ስለ ኤችአይቪ እውቀት የላቸውም ተባለ • ሳይንቲስቱ መንትዮች ኤች አይ ቪ እንዳይዛቸው ዘረ መላቸውን አስተካከለ • የማትተነፍሰው ከተማ: አዲስ አበባ በዘውዲቱ ሆስፒታል የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር አስቴር ሸዋአማረም በኃላፊዋ ሀሳብ ይስማማሉ። ለኤች አይቪ ምርመራ ወደ ዘውዲቱ ሆስፒታል ከሚሄዱ መካከል እድሜያቸው ከ15 እስከ 24 የሆነ አፍላ ወጣቶች መካከል የኤች አይቪ ቁጥሩ ከፍ ብሎ አንደሚታይ ይናገራሉ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኤችአይቪ መከላከያና መቆጣጠያ ፅ/ቤት ኃላፊ ሲስተር ብርዛፍ እንደሚሉት አዲስ አበባ ከጋምቤላ ቀጥሎ በከፍተኛ ሁኔታ የኤች አይቪ ስርጭት የሚታይባት ከተማ ናት። በጋምቤላ የኤች አይቪ የስርጭት መጠን 4.8 መሆኑን አስታውሰው አንዳንድ የሀገሪቱ ከተሞች ላይም የስርጭት መጠኑ ከፍ ማለቱን ጠቅሰዋል። ለዶ/ር አስቴር በከተማዋ በአፍላ ወጣቶች ያለው የኤች አይቪ የስርጭት መጠን ከፍ ማለት ምክንያት መዘናጋት ነው። ሲስተር ብርዛፍም ከዚህ የተለየ ሀሳብ የላቸውም፤ መንግስትና አጋር ድርጅቶች ኤች አይቪ ላይ የሚሰጡት የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶች መቀዛቀዛቸው በአዲሱ ትውልድ የስርጭት ምጣኔው ከፍ እንዲል ምክንያት መሆኑን አበክረው ገልፀዋል። ከዚህ ቀደም ወደ ህዝቡ ወጥተው ስለ ኤች አይቪ የሚያስተምሩ ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ ግለሰቦች ዛሬ አለመኖራቸውም በአሁኑ ወቅት ለተፈጠረው መዘናጋት አስተዋፆ እንዳለው ሲስተር ብርዛፍ ያምናሉ። • ስለኤች አይ ቪ /ኤድስ የሚነገሩ 8 የተሳሳቱ አመለካከቶች በአሁኑ ወቅትም ከእነዚህ ግለሰቦች ጋር ለመስራት እቅድ መኖሩን አስረድተው አሁን ከተፈጠረው መዘናጋት የተነሳ አድልኦና መገለል እንደ አዲስ እያገረሸ ስለሆነ የከተማው አስተዳደር መደገፍ በሚገባቸው በኩል ደግፎ እንዲያስተምሩ እንዲያደረግ እንደሚያመቻቹ ተናግረዋል። የኤችአይቪ መከላከያና መቆጣጠያ ፅ/ቤት ኃላፊዋ እንደሚሉት በከተማዋ ያለውን የኤች አይቪ የስርጭት መጠን አሳሳቢ የሚያደርገው በአፍላ ወጣቶች መካከል ያለው የስርጭት መጠን ከፍተኛ መሆኑ ነው። ለዚህም ኃላፊዋ እንደምክንያትነት የጠቀሱት ከስራ አጥነት ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን ነው። "ስራ አጥነት ለኤች አይቪ የሚያጋልጡ ስፍራዎች እንዲውሉ ገፊ ምክንያት ነው" የሚሉት ሲስተር ብርዛፍ በከተማዋ ያሉ የኢንዱስትሪና የሆቴሎች መስፋፋት ሌላው እንደምክንያት ያነሱት ነው። በከተማዋ የመጤ ባህሎች መስፋፋትም እንደሚታይ የገለፁት ሲስተር ብርዛፍ የራቁት ዳንስ ቤት፣ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት፣ ጫት፣ ሺሻና ቡና ቤቶች መበራከታቸው ለኤች አይቪ መስፋፋት አስተዋፅኦ ማድረጉን ገልፀዋል። በአዲስ አበባ ከተማ የሚታየው የኮንስትራክሽን ስራዎች ላይ ለመሰማራት ከተለያዩ ከተሞች የሚመጡ ወጣቶች ቁጥር ከፍ ማለትም የስርጭቱ መጠን ከፍ እንዲል እንዳደረገው አብራርተዋል። ፅህፈት ቤታቸው በከተማዋ ለኤች አይቪ ተጋላጭ ብሎ የለያቸውን የከተማዋ የህብረተሰብ ክፍሎችን ሲዘረዝሩ በትምህርት ቤትም ሆነ ውጭ ያሉ ወጣቶች፣ የቀን ሰራተኞች፣ የከባድ መኪና የረዥም ርቀት አሽከርካሪዎች፣ በወህኒ ቤት የሚገኙ ታራሚዎች፣ በወሲብ ንግድ የተሰማሩ ግለሰቦች፣ እና በቅርቡ በተደረጉ ጥናቶች እንደታየው ደግሞ ባሎቻቸውን በፈቱ ሴቶች የስርጭት ምጣኔው ከፍ ያለ ነው። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶቹ በብዛት በሚገኙባቸው አካባቢዎች የትምህርት ስራውን ሊያውኩና ወጣቶቹን ለኤች አይቪ ሊያጋልጡ የሚችሉ መዝናኛዎችን ከትምህርት ቤት መራቅ አለባቸው የሚል አቋም ይዞ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ለመስራት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ተናግረዋል። የአለም ጤና ድርጅት እኤአ በ2030 አዲስ በቫይረሱ የሚያዝ ግለሰብ መኖር የለበትም የሚል ራዕይ አስቀምጧል። በኢትዮጵያ የኤች አይቪ የስርጭት መጠኑ 0.9 በመቶ ነው።
news-49165029
https://www.bbc.com/amharic/news-49165029
ኬንያ ውስጥ ታየ የተባለው "ኢየሱስ" ማን ነው?
በተለምዶ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ የለበሰ የአንድ ግለሰብ ፎቶና ቪዲዮ በማህበራዊ መገናኛዎች ላይ በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል። እርስዎስ አጋጥሞዎታል?
ይህ ግለሰብ ማን ነው? ምንስ ሲያደርግ ነበር? ይህንን በተመለከተ ከተሰራጩት የማህበራዊ ሚዲያ በርካታ መልዕክቶች መካከል በአንዱ ላይ "ደቡብ አፍሪካዊው ፓስተር ወደሚሰብክበት ቤተ ክርስቲያን ኢየሱስ ክርስቶስን ከመንግሥተ ሰማያት ጋብዞ እንዲያስተምር አደረገ" የሚለው በታዋቂ ሰዎች ጭምር ሲጋራ ቆይቷል። የ Twitter ይዘት መጨረሻ, 1 ነገር ግን ይህ የሆነው ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ሳይሆን ኬንያ ውስጥ እንደሆነ እየተነገረ ነው። የወጡት ምስሎች ኪሴሪያን ተብላ በምትጠራው ከመዲናዋ ናይሮቢ በደቡብ ምዕራብ 25 ኪሎ ሜትሮች እርቃት በምትገኝ ስፍራ የተገኙ ናቸው። ይህ ምስሉ በስፋት እየተሰራጨና እያነጋገረ የሚገኘው ግለሰብ ማይክል ጆብ የተባለ አሜሪካዊ ሰባኪና የፊልም ተዋናይ ሲሆን፤ በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ ላይ ንግግር እንዲያደርግ ግብዣዎች ይቀርቡለታል። እራሱን "ህያው የመጽሐፍ ቅዱስ ሙዚየም" ብሎ የሚጠራው እና ነዋሪነቱን ኦርላንዶ ፍሎሪዳ ያደረገው ጆብ፤ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆኖ 'ዘ ሆሊላንድ ኤክስፒሪያንስ' በሚባል ፊልም ላይ ተውኗል። • ቀብር አስፈጻሚዎች ከሞት አስነሳሁ ያለውን ፓስተር ሊከሱ ነው • በደቡብ ኢትዮጵያ አጥማቂው በአዞ ተገደሉ ግለሰቡ የፌስቡክ ገጹ ላይ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ባወጣው ቪዲዮ ኬንያ ውስጥ ያሉ የግብርናና የቤት ውስጥ ቁሳቁሶች የሚሸጡባቸው ሱቆች የሚታዩ ሲሆን፤ ነገሩ የተከሰተው ደቡብ አፍሪካ ውስጥ እንደሆነ የሚገልጹት የማህበራዊ ሚዲያ መልዕክቶችም ላይ ተመሳሳይ ነገር ይታያል። ከዚህ ምስል ጋር በተያያዘ እየተዘዋወሩ የሚገኙት በርካቶቹ የማህበራዊ ሚዲያ መልዕክቶችም 'አፍሪካ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ሰባኪያን እንዴት እያደረጉ ተአምራትን እናደርጋለን እንደሚሉ ያሳያል' በማለት አስፍረዋል። ይህንን ምስል በመጠቀም የተሰራጨ አንድ ጽሁፍም "ኬንያዊው ፓስተር እየሱስ ክርስቶስን በኬንያ ጎዳናዎች ላይ አገኘሁት ይላል" ሲል አስፍሯል። በትዊተር ላይ እየተዘዋወረ ያለው ፎቶም ማይክል ጆብ ኪቴንጌላ በተባለች ከተማ ውስጥ በሚገኝ በአንድ ቤተ ክርስቲያን ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ አካባቢ ሲሰብክ የተነሳው ነው። • በምሥራቅ ወለጋ የአራት ቀን ሬሳ አስነሳለሁ ብሎ መቃብር ያስቆፈረው 'ነብይ' በቁጥጥር ሥር ዋለ በአንድ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት ላይ ኬንያ ውስጥ በተቀረጸው ቪዲዮ አሜሪካዊው ግለሰብ ተአምራትንና ፈውስን እንደሚፈጽም ሲናገር ይታያል። በዚህም በማህበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ ትችቶች ቀርበውበታል። ግለሰቡ አፍሪካ ውስጥ ጉብኝት ሲያደርግ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፤ ከወራት በፊት ወደ ቶጎ ሄዶ የነበረ ሲሆን እዚያ የተነሳቸው ፎቶግራፎች ግን ኮትና ሱሪ ለብሶ ስለነበረ የአሁኑን ያህል አነጋጋሪ አልነበረም።
news-56582176
https://www.bbc.com/amharic/news-56582176
የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ውሻ ዳግም የዋይት ሐውስ ሠራተኛ ነከሰ
ሜጀር የተሰኘው የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ውሻ ዳግም የዋይት ሐውስ ሠራተኛ መንከሱ ተሰማ።
ሜጀር ከዚህ ወር ቀደም ብሎ በዋይት ሐውስ ሰው በመንከሱ የተነሳ ለስልጠና ወደ ዴልዌር ተልኮ የነበረ ቢሆንም በተመለሰ ማግስት ሌላ ሠራተኛ መንከሱ ተነግሯል። የቀዳማይት እምቤት ጂል ባየደን ቃል አቀባይ "ተገቢውን ጥንቃቄ ለማድረግ ሲባል" የተነከሰው ግለሰብ ወደ ሥራ ከመመለሱ በፊት በዋይት ሐውስ የሕክምና ቡደን ክትትል እየተደረገለት እንደሆነ ገልጸዋል። ሜጀር ጆ ባይደን ካሏቸው ሁለት የጀርመን ዝርያ ካላቸው ውሾች መካከል በእድሜ ትንሹ ሲሆን ወደ ዋይት ሐውስ የገባ የመጀመሪያው በማደጎ የተወሰደ ውሻ ነው ተብሏል። ባይደን "በጣም ተወዳጅ ውሻ ነው" ሲሉ ያንቆለጳጵሱታል። የጂል ባይደን ቃል አቀባይ ሚሼል ላሮሳ ሰኞ እለት ክስተቱ የተፈጠረው ሜጀር ከአዲሱ አካባቢ ጋር ራሱን ለማላመድ እየጣረ ባለበት ወቅት በአጠገቡ የሚያልፍን ግለሰብ በመንከሱ ነው ብላለች። ሲኤንኤን ውሻው የብሔራዊ ፓርክ ሠራተኛ የሆነ ግለሰብ መንከሱንና በዚህም የተነሳ ግለሰቡ ሕክምና ለመከታተል ሥራ ማቆሙን ዘግቧል። የብሔራዊ ፓርክ አገልግሎት መስሪያ ቤቱ ለሲኤን ኤን ጥያቄ ምላሽ አልሰጠም። በመጋቢት ወር የጆ ባይደን ሁለቱ ውሾች ሜጀርና ቻምፕ ሠራተኞችን መንከሳቸውን ተከትሎ ዊልሚንግተን ዴልዌር ወደሚገኘው የባይደን ቤተሰቦች ቤት ተወስደው ነበር። ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ ግለሰብ ለሲኤንኤን እንደገለፀው ሜጀር የዋይት ሐውስ ሠራተኞችንና የደኅንነት ሰዎችን በሚያይበት ወቅት ይጮሃል ይዘላል። ፕሬዝዳንት ባይደን ሜጀር በርካታ ሰው በዙሪያው ከመኖሩ ጋር የተፈጠረበትን ስሜት እየተላመደ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ለኤቢሲ ጉድ ሞርኒንግ አሜሪካ ፕሮግራም ላይ በየአቅጣጫው በዞረ ቁጥር የማያውቃቸው ሰዎች ሲንቀሳቀሱ ሲያይ ለመከላከል ሲል እንደሚጮህ አስረድተዋል። "በዋይት ሐውስ ያሉ 85 በመቶ ሠራተኞች ይወዱታል። እርሱም ጭራውን እያወዛወዘ ይልሳቸዋል። ነገር ግን እንደተረዳሁት አንዳንድ ሰዎች በተፈጥሯቸው ውሾች ይፈራሉ" ብለዋል። ባይደን የሚያሳድጉት ሜጀር ሦስት ዓመቱ ሲሆን ቻምፕ ግን ፕሬዝዳንት ባይደን የኦባማ ምክትል ሳሉ አብሯቸው በቤተመመንግሥት ውስጥ ነበር ተብሏል።
news-53160667
https://www.bbc.com/amharic/news-53160667
ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ በአሜሪካ ኮሮና በአስደንጋጭ ሁኔታ ሊያንሰራራ እንደሚችል አስጠነቀቁ
የአሜሪካንን የኮቪድ ወረርሽኝ ትግል የሚመሩት እውቁ ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ ለሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ቀርበው ለእንደራሴዎች ማብራሪያ በመስጠት ላይ ነበሩ፡፡ እርሳቸው እንደሚሉት አሁን አገራቸው አሜሪካ በድጋሚ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ በወረርሽኙ ሊያዝባት ይችላል ብለዋል፡፡
‹‹የሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ወሳኝ ናቸው፡፡ ምናልባት ወረርሽኙ በአዲስ መልክ ሊያንሰራራም ይችላል፤ አስፈሪ ምልክቶችን እያየን ነው›› ብለዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአሜሪካ በኮቪድ 19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአንዳንድ ግዛቶች እየጨመረ መጥቷል፡፡ ከዶ/ር ፋውቺ ጋር ቃላቸውን እንዲሰጡ በምክር ቤቱ የተጠሩ ሌሎች አራት የጤና ባለሞያዎች በዶናልድ ትራምፕ ጉዳይ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል፡፡ • ከሰኔ 16ቱ ጥቃት ጋር በተያያዘ የተከሰሱ ሰዎች ጉዳይ ከምን ደረሰ? • ኢትዮጵያ መሰረታቸውን ግብጽ ባደረጉ ቡድኖች የመረጃ መረብ ጥቃት ተሞከረብኝ አለች • በአፍሪካ የመጀመሪያው የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ ሊደረግ ነው ‹‹ለመሆኑ ዶናልድ ትራምፕ ብዙ ምርመራ አታድርጉ ብሏችሁ ያውቃል ወይ›› ተብለው የተጠየቁት የጤና ባለሞያዎቹ ‹‹በፍጹም›› ብለዋል፡፡ ዶናልድ ትራምፕ በቅርቡ በኦክላሆማ ምርጫ ቅስቀሳ በሚያደርጉበት ወቅት የጤና ባለሞያዎችን ‹‹እባካችሁ ብዙ ሰው አትመርምሩ፤ ብዙ ሰው ከመረመራችሁ ብዙ ሰው በሽታው እንደያዘው ይታወቃል›› ብያቸዋለሁ ሲሉ ለደጋፊዎቻቸው ተናግረው ነበር፡፡ ኋላ ላይ ዋይት ሃውስ ፕሬዝዳንቱ እንዲያ ያሉት እኮ ለቀልድ ነው ሲል አስተባብሎላቸዋል፡፡ የጤና ባለሞያዎቹ ጥያቄው የቀረበላቸው ይህንን የትራምፕን የኦክላሆማ ምርጫ ቅስቀሳ ተከትሎ ነው፡፡ የጤና ባለሞያዎቹ ለሕግ መወሰኛው ምክር ቤት እንደመሰከሩት በሚቀጥሉት ወራት በወር ከ40 እስከ 50 ሚሊዮን ሰዎችን ለመመርመር እቅድ ተይዟል፡፡ በኦክላሆማው ንግግራቸው ዶናልድ ትራምፕ ‹‹ብዙ ሰው አትመርምሩ›› ስለማለታቸው ዋይትሃውስም ይሁን የጤና ባለሞያዎች ቢያስተባብሉላቸውም ማክሰኞ ለታ ትራምፕ ራሳቸው ‹‹እኔ እየቀለድኩ አልነበረም›› ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡ ዶ/ር ፋውቺ በቀጣይ ቀናት ወረርሽኙ በአስደንጋጭ ሁኔታ ሊያንሰራራባቸው ይችላል ካሏቸው አካባቢዎች መሀል ደቡባዊና ምዕራባዊ አሜሪካ ይገኙባቸዋል፡፡ ከቀናት በፊት በአንድ ቀን በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር 30ሺህ ደርሶ ነበር፡፡ ‹‹ይህ አስደንጋጭ ቁጥር ነው›› ብለዋል ፋውቺ፡፡ ‹‹ይህ የሚያሳየው ወረርሽኙ በማኅበረሰቡ ውስጥ ዘልቆ መግባቱን ነው፡፡›› ዶ/ር ፋውቺ ለኮቪድ-19 ፍቱን ክትባት በዚህ የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ እንደሚገኝለት ያላቸውን ተስፋ ለምክር ቤቱ አባላት ገልጸዋል፡፡ አሪዞና፣ ነቫዳ፣ ቴክሳስ በቀን የተያዦች ቁጥር እየገሰገሰባቸው ከሚገኙ ግዛቶች ይጠቀሳሉ፡፡ ካሊፎርኒያ፣ ሳውዝ ካሮላይና፣ ሚሲሲፒ እና ሊዊዚያናም እንዲሁ የተያዦች ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረባቸው ነው፡፡ አሁን 2.3 ሚሊዮን አሜሪካዊያን በኮሮና የተያዙ ሲሆን ከ120ሺህ በላይ ሞተዋል፡፡
52350418
https://www.bbc.com/amharic/52350418
ኮሮናቫይረስ: የአፍጋኒስታን ቤተመንግሥት ሠራተኞች በኮቪድ-19 ተይዘዋል ተባለ
በአፍጋኒስታን ፕሬዝዳንት ቤተ መንግሥት የሚሰሩ በርካታ ሠራተኞች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተነገረ።
እስካሁን ድረስ ፕሬዝዳንት አሽራፍ ስለመያዛቸው የተገኘ መረጃ የለም በቅድሚያ 20 ሠራተኞች በኮቪድ-19 መያዛቸው ቢነገርም እሁድ እለት ኒውዮርክ ታይምስ ባወጣው ዘገባ ግን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 40 ይደርሳል ተብሏል። የአፍጋኒስታን መንግሥት በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከመስጠት የተቆጠበ ሲሆን ፕሬዝዳንት አሽራፍ ጋሃኒ እስካሁን ስለመያዝ አለመያዛቸው የታወቀ ነገር የለም። የ70 ዓመቱ አዛውንት ጋሃኒ እአአ በ1990ዎቹ በካንሰር ምክንያት ቀዶ ጥገና ማድረጋቸው ይታወሳል። ቅዳሜ እለት አንድ የመንግሥት ባለስልጣን ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል "በፕሬዝዳንቱ ቤተ መንግሥት ውስጥ የሚሰሩ 20 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። ነገር ግን መደናገጥ እንዳይፈጠር በሚል ተሸፋፍኖ ቀርቷል" ብለዋል። ሐሙስ ዕለት በትዊተር ላይ የተለቀቀው ምስል ፕሬዝዳንት አሽራፍ ከካቢኔ ሚኒስትሮቻቸው ጋር በቪዲዮ ኮንፍረንስ ስብሰባቸውን ሲያካሄዱ ያሳያል። ነገር ግን በዚያው እለት ፕሬዝዳንቱ የኢራን ባለሰልጣናትን በአካል አግኝተው ሲያናግሩ በሰሌዳው ላይ ተለጥፏል። በአፍጋኒስታን እስካሁን ድረስ 933 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሲያዙ 33 ሰዎቹ መሞታቸው ተመዝግቧል። የአፍጋኒስታን የጤና ሥርዓት ለዓመታት በዘለቀው ግጭትና ጦርነት ምክንያት የተጎዳ ሲሆን አገሪቱ ካላት አነስተኛ የመመርመር አቅም አንጻር ቁጥሩ አነስተኛ ነው ተብሏል። በተጨማሪም 150 ሺህ አፍጋናውያን በቫይረሱ ክፉኛ ከተጠቃችው ኢራን ባለፈው ወር ወደ አገራቸው መምጣታቸውን በማንሳት እንዲሁም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ከፓኪስታን መመለሳቸውን ተከትሎ የቫይረሱ ስርጭት እንዳይስፋፋ ተሰግቷል።
news-55642920
https://www.bbc.com/amharic/news-55642920
ኮሮናቫይረስ፡ ብራዚል ቻይና ሰራሹ የኮሮቪድ-19 ክትባት ውጤታማነቱ 50.4 በመቶ ነው አለች
በቻይናው ሲኖቫክ የተመረተው የኮሮናቫይረስ ክትባት በብራዚል ቤተሙከራዎች ውስጥ ተፈትሾ 50.4 በመቶ ብቻ ውጤታማ መሆኑ ተገለፀ።
የብራዚል መንግሥት ለዜጎቹ ለመስጠት ካዘጋጃቸው ሁለት ክትባቶች መካከል የቻይናው አንዱ ነበር የዚህ ክትባት ውጤታማነት ከዚህ ቀደም ይፋ በተደረገው መረጃ መሰረት ከፍ ያለ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን የብራዚል ተመራማሪዎች 50 በመቶን ያለፈው ለጥቂት ነው ሲሉ ተናግረዋል። የብራዚል መንግሥት ለዜጎቹ ለመስጠት ካዘጋጃቸው ሁለት ክትባቶች መካከል የቻይናው አንዱ ነበር። ብራዚል በኮሮናቫይረስ ክፉኛ ከተጠቁ አገራት መካከል አንዷ ናት። ሲኖቫክ መቀመጫውን ቻይና ቤይጂንግ ያደረገ የመድኃኒት አምራች ኩባንያ ሲሆን፣ ኮሮናቫክ የተሰኘ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባትን ማምረቱ ተገልጿል። ክትባቱ የተሰራው ከሞቱ የተህዋሲው አካላት ሲሆን፣ ያለምንም ተጨማሪ ሕመም ሰውነትን ለቫይረሱ በማጋለጥ የመከላከል አቅምን ያዳብራል ተብሎ ነበር። ይህ ኩባንያ ያመረተውን ክትባት ኢንዶኔዢያ፣ ቱርክ እና ሲንጋፖር ማዘዛቸውም ተሰምቷል። ባለፈው ሳምንት የቡታንታን ምርምር ማዕከል ተመራማሪዎች፣ በብራዚል የክትባቱን ውጤታማነት የፈተሹ ሲሆን፤ በኮሮናቫይረስ ተይዘው ከመካከለኛ እስከ የከፋ ምልክት ያሳዩ ሰዎች ላይ 78 በመቶ ውጤታማ ነው ብለው ነበር። ነገር ግን ማክሰኞ ዕለት ተመራማሪዎቹ ከዚህ ቀደም ይፋ ያደረጉት ውጤት የሕክምና ተቋም እርዳታ ፈልገው ያልመጡ እና "በጣም መካከለኛ ሕመም" ያለባቸውን ሰዎች መረጃ አለማካተቱን ገልፀዋል። ይህ መረጃ ሲካተትም የክትባቱ ውጤት 50.4 በመቶ ነው ብለዋል ተመራማሪዎቹ። ነገር ግን የቡታንታን ተመራማሪዎች አጽንኦት ሰጥተው እንደተናገሩት ከሆነ፣ የሕክምና ክትትል የሚፈልጉ መካከለኛ ህመም ያለባቸው ሰዎች ላይ የመከላከል አቅሙ 78 በመቶ ሲሆን፣ ከመለስተኛ እስከ ጽኑ ህሙማን ላይ ደግሞ እስከ መቶ በመቶ የመከላከል አቅም አለው ብለዋል። የሲኖቫክ ክትባት በተለያዩ አገራት በተደረገለት ፍተሻ የተለያዩ ውጤቶችን አሳይቷል። ባፈው ወር የቱርክ ተመራማሪዎች የሲኖቫክ ክትባት 91.25 በመቶ ውጤታማ ነው ያሉ ሲሆን፤ ከዛሬ ጀምሮ በጅምላ ክትባቱን የምትሰጠው የኢንዶኔዢያ ተመራማሪዎች ደግሞ 65.3 በመቶ ውጤታማ ነው ብለዋል። ቻይና የሰራችው የኮሮናቫይረስ ክትባት ምዕራባውያኑ እንደፈበረኳቸው ክትባቶች ተገቢው ፍተሻ እና ክትትል አልተደረገበትም በሚል ወቀሳ ይቀርብበታል። ይሁን እንጂ ብራዚል በኦክስፎርድ የተመረተው የአስትራዜኔካን እና የሲኖቫክ ክትባቶችን ለአስቸኳይ ጊዜ ለመጠቀም የአገሪቱ የመድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣንን ፈቃድ እየጠበቀች ነው። ብራዚል በኮሮናቫይረስ በተያዙ ሰዎች ብዛት ከአሜሪካ እና ከሕንድ በመቀጠል ሦስተኛዋ አገር ናት። 8.1 ሚሊዮን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ያሉባት ብራዚል ክትባቱን መቼ መስጠት እንደምትጀምር የታወቀ ነገር የለም። የኮሮናቫይረስ ክትባት ዝግጁ የሚሆነው መቼ ነው?
news-56186308
https://www.bbc.com/amharic/news-56186308
በኦሮሚያ የፍርድ ቤቶች ትዕዛዝ አለመከበሩ እንዳሳሰበው ኢሰመኮ ገለጸ
በኦሮሚያ ክልል የፍርድ ቤቶች ትዕዛዝ አለመከበሩ እንደሚያሳስበው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ።
ኢሰመኮ ይህንን ያለው ሙሐመድ ዴክሲሶ የተባለ ተማሪን የጅማ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በዋስ እንዲለቀቅ ያሳለፈውን ውሳኔ ተግባራዊ አለመሆኑ እንዳሳሰበው ባመለከተበት መግለጫ ነው። የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) እንደተናገሩት "በኦሮሚያ ክልል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው የፍርድ ቤቶች ትዕዛዝ አለመከበር እጅግ አሳሳቢ በመሆኑ አፋጣኝ ትኩረትና እልባት ይሻል" ብለዋል። ኮሚሽኑ ጨምሮም "በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል እስር ቤቶች የዋስትና መስፈርቶችን ያሟሉ ነገር ግን በእስር ላይ የሚገኙ እስረኞች ከእስር እንዲለቀቁ" ጠይቋል። ግለሰቡ በፖሊሶች በጥፊ እንደመቱት፣ በዱላ ሁለቱን እግሮቹን መደብደቡንና ጎኑ አካባቢም እንደተመታ ገልጾ፤ ኢሰመኮም በእግሮቹ ላይ መጠነኛ እብጠት እንደሚታይና የሚያነክስ መሆኑን መመልከቱን ገልጿል። የጅማ ወረዳ ፍርድ ቤት የካቲት 16/2013 ዓ.ም ሙሐመድ ዴክሲሶ በሁለት ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና ከእስር እንዲለቀቅ የወሰነ ቢሆንም ተጠርጣሪው አስፈላጊውን የዋስትና መስፈርት ቢያሟላም እስከ የካቲት18 ቀን ድረስ በእስር ላይ እንደሚገኝ ኮሚሽኑ ማረጋገጡን ገልጿል። ቢቢሲ የአስረኛው ጠበቃ የሆኑትን ኦብስናን ግርማ ዛሬ ሐሙስ [የካቲት 18/2013 ዓ.ም] ጠዋት በማናገር እንዳረጋገጠው ሙሐመድ ዴክሲሶ አሁንም እስር ላይ ነው። "ግለሰቡ በፍርድ ቤት በዋስትና እንዲለቀቅ ከተወሰነና ለዋስትና አስፈላጊው ነገር ከተሟላ ወዲያወኑ ከእስር ሊለቀቅ ሲገባ፤ በእስር ላይ መቆየቱ የተደራረበ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ነው ያለው" ኮሚሽኑ፤ እስረኛው በአፋጣኝ ከእስር እንዲለቀቅ አሳስቧል። በተጨማሪም እስረኛው በፖሊሶች ተፈጽሞብኛል ያለውን ድብደባ በተመለከተም ተገቢው ማጣራት ተደርጎ የድረጊቱ ፈጻሚዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ ጠይቋል። ኮሚሽኑ ጨምሮም ሙሐመድ ዴክሲሶ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የፈጸመው ድርጊት "ከነገሩ ሁኔታ አንጻር ምናልባት ሊነቀፍ ወይም ሊያስወቅስ ከሚችል በስተቀር፣ ከመነሻውም ለወንጀል ክስና አስር ምክንያት ሊሆን አይገባም ነበር" ብሏል። የካቲት 6 ቀን 2013 ዓ.ም የፌደራልና የኦሮሚያ መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣንት በታደሙበት የጅማ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ከተመራቂዎቹ አንዱ የነበረው ሙሐመድ ዴክሲሶ የድምጽ ማጉያ ተቀብሎ በእስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እንዲፈቱና አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን በማስመልከት መፈክሮችን ማሰማቱን ተከትሎ ነበር ለእስር የተዳረገው።
news-51414510
https://www.bbc.com/amharic/news-51414510
የአይፎን ስልክ አምራቹ ኩባንያ ኮሮናቫይረስ መከላከያ ጭምብል ማምረት ሊጀምር ነው
ግዙፉ ኤሌክትሮኒክስ አምራቹ ፎክስኮን ኮሮናቫይረሰን ለመከላከል ወይም በቀዶ ህክምና ወቅት ሊደረግ የሚችል የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ወይም ጭምብል ሊያመርት መሆኑ ተነግሯል።
የአይፎን ስልክ አምራች ጭምር የሆነው ኩባንያው በኮሮናቫይረስ ምክንያት በቻይና ለመዝጋት የተገደደውን ማምረቻ ጣቢያዎቹን ለመክፍት ጥረት እያደረገ ይገኛል። የኮሮናቫይረስ መከሰት በመላው ዓለም የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ 'ማስክ' እጥረት እንዲያጋጥም አድርጓል። ፎክስኮን በዚህ ወር መጨረሻ ላይ በቀን ሁለት ሚሊዮን የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛዎችን ለማምረት ማቀዱን አስታውቋል። "ይህን ወረርሽኝ ስንዋጋ እያንዳንዷ ሰከንድ ትርጉም አላት" ሲል ኩባንያው 'ዊቻት' በተሰኘው ማህብራዊ ሚዲያ ላይ አስፍሯል። "የመከላከል እርምጃ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ያስችላል። የሰዎችን ህይወት መታደግ መቻል ማለት በፍጥነት ቫይረሱን ማሸነፍ ማለት ነው" ብሏል አይፎን አምራቹ ኩባንያ። ይህ ኩባንያ የዓለማችን ግዙፉ የኤሌክትሮኒክስ አምራች ሲሆን፤ ከአይፎን በተጨማሪ፣ አይፓድ፣ የአማዞን ኪንድል እና ፕለይስቴሽኖችን ያመርታል። ኩባንያው በቅድሚያ የሚያመርታቸው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ምርቶች ለሠራተኞቹ እንደሚያድል ከዚያ በኋላ ምርቶቹን ለገበያ እንደሚያቀርብ አስታውቋል።
news-49786245
https://www.bbc.com/amharic/news-49786245
በተያዘው ዓመት ለሁለት የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ፍቃድ ይሰጣል ተባለ
የኢትዮጵያ የኮሚኒኬሽን ባለስልጣን በያዝነው አዲሱ 2012 ዓመት ለሁለት የቴሌኮም ተቋማት ፍቃድ እንደሚሰጥ አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ባልቻ ሬባ። ይህን ያሉት በቅርቡ በጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አሕምድ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ተደርገው የተሾሙት አቶ ባልቻ ሬባ ናቸው። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባጸደቀው አዋጅ ቁጥር 1148/2011 መሰረት፤ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለስልጣን የቴሌኮም ዘርፉን በመቆጣጠር በዘርፉ ለሚሰማሩ የግል ተቋማት የውድድር ገብያውን ምቹ ለማድረግ የተቋቋመ ነው። • የኢትዮ ቴሌኮም 49 በመቶ ድርሻ ለሽያጭ ይቀርባል ተባለ • የውጪ ሀገር ጥሪዎች ለምን በኢትዮጵያ ቁጥር ይወጣሉ? አቶ ባልቻ ሬባም ተቋሙን ከያዝነው አዲስ ዓመት ጀምሮ በዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ ተሹመዋል። "ይህ ተቋም በዚህ ዓመት ለመፈጸም ካቀዳቸው ዋና ተልዕኮዎች መካከል፤ ለሁለት በቴሌ-ኮሚዩኒኬሽን ኦፐሬሽን ለሚሰሩ ተቋማት ፍቃድ መስጠት ነው" በማለት ለቢቢሲ ተናግረዋል። መንግሥት ከዚህ በፊት 51 በመቶ የሚሆነውን የኢትዮ ቴሌኮም ድርሻ በእራሱ ሥር አቆይቶ 49 በመቶውን ደግሞ ወደ ግል ለማዘዋወር ፍላጎት እንዳለው ማስታወቁ ይታወሳል። የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ መንግሥት የቴሌኮም ዘረፉ ለግል ድርጅቶች ክፍት እንደሚደረግ ይፋ ካደረገ በኋላ በርካታ ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ገብያ ላይ ፍላጎት ሲያሳድሩ ቆይተዋል። አየር መንገድንና ቴሌን ለሽያጭ ለማቅረብ ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው? "ከስድስት ወራት በኋላ ፍቃድ ወደመስጠቱ ሥራ እንገባለን" የሚሉት አቶ ባልቻ የአውሮፓውያኑ 2019 ከመጠናቀቁ በፊት የቴሌኮሚኒኬሽን ኦፕሬሽን ፍቃድ ይሰጣል ተብሎ ነበር ይላሉ። ዋና ዳይሬክተሩ እንደሚሉት ከሆነ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለስልጣን ፍላጎት ያላቸው ተቋማት የንግድ ሃሳባቸውን እንዲያስገቡ ጥሪ ሲያቀርብ በዘርፉ መሰማራት የሚፈልጉ ተቋማት ጥሪውን መሰረት አድርገው ገቢ ያደርጋሉ። እስከዛው ግን የንገድ ሃሳብ ገቢ ማድረግ እንደማይቻል ይናገራሉ። ''የቴሌኮሚዩኒኬሽን ኦፐሬሽን ፍቃድ የሚሰጣቸው ተቋማት የውጪ ሃገር፣ የሃገር ውስጥ ወይም በሽርክና የሚሰሩ ሊሆኑ ይችላሉ" ብለዋል። ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚንስትሩ የሆነው ይህ ባለስልጣን ያልተገቡ የገበያ ውድድሮችን ከመቆጣጠር እስከ የቴሌኮም አገልግሎት ፍቃድ እስከመሰጠት ስልጣን ተሰጥቶታል። "ለቴሌኮም ኦፕሬተሮች ፍቃድ ይሰጣል፣ የቴሌኮሚዩኒኬሽን እና ፖስታ አገልግሎት ላይ መሰማራት ለሚፈልጉም ፍቃድ ይሰጣል፤ እንዲሁም ኦፐሬተሮች ለህዝብ የሚሰጡት የአገልግሎት ደረጃን ይወስናል" ይላሉ። ፍቃድ የተሰጣቸው የቴሌኮም ኦፐሬተሮች አገልግሎት የሚሰጡበትን ታሪፍ ለባለስልጣኑ ካቀረቡ በኋላ ባለስልጣኑ የመጨረሻውን ውሳኔ እንደሚሰጥበትም ተናግረዋል። መንግሥት ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኝለትን ኢትዮ ቴሌኮምን የ49 በመቶ ድረሻ ለግል ለማዘዋወር ክፍት ማድረጉ ስህተት ነው የሚሉም አልታጡም። አቶ ባልቻ ግን መንግሥት በብቸኝነት ከኢትዮ ቴሌኮም ሲያገኝ ከነበረው በላይ ገቢ እንደሚያገኝ ይናገራሉ። ይህም የሚሆነው ከግብር እና ከፍሪኩዌንሲ ከሚገኝ ገቢ እንደሆነ ይናገራሉ። "ለሞባይል ኦፐሬተሮች ፍቃድ የምንሰጥበት ፍሪኩዌንሲ ከፍተኛ ገቢ የሚያመጣ ነው" ብለዋል። እስካሁን ኢትዮ ቴሌኮም ፍሪኩዌንሲ በነጻ እየተጠቀመ ነበር ማለት ይቻላል የሚሉት አቶ ባልቻ፤ ከአሁን በኋላ የሚመጡት ተቋማት ግን ብዙ ገንዘብ እንደሚከፍሉ ያስረዳሉ። በተጨማሪም፤ የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶች ወደ ሃገር ውስጥ መግባታቸው የቴሌኮም ኢንቨስትመንትን ያስፋፋል፣ የጥራት አገልግሎት ያሳድጋል፣ የቴሌኮም አገልግሎት ወጪን ይቀንሳል እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎትን ያሻሽላል በማለት ጠቀሜታውን ያስረዳሉ። አቶ ባልቻ ሬባ ማናቸው? አቶ ባልቻ በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል። በቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌኮሙዩኒኬሽን ኤጀንሲ ከ1990ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ እስከ ተጠባባቂ ዋና ዳይሬክተርነት ባሉ በሃላፊነቶች አገልግለዋል። ለ7 ዓመታት በመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር የስታንዳርድና ቁጥጥር ዳይሬክተር ሆነው አገልግለዋል። አቶ ባልቻ የኢትዮጵያ የኮሚኒኬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ከመሾማቸው በፊት በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የቴሌ-ኮም፣ ፖስታ እና ኮሚዩኒኬሽን የስታንዳርድና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በመሆንም አገልግለዋል።
news-48494283
https://www.bbc.com/amharic/news-48494283
ሩሲያዊው ኩባንያ ሴት ሰራተኞቹ ቀሚስ እንዲለብሱ በመክፈሉ እየተወቀሰ ነው
አንድ የሩሲያ ኩባንያ ሴት ሰራተኞቹ ቀሚስ እንዲለብሱ ተጨማሪ መክፈሉ ከፍተኛ ወቀሳ እየቀረበበት ነው።
ታት ፐሮፍ የተባለው የአሉሙኒየም አምራች ኩባንያ "የሴትነት ማራቶን" (ውድድር) በሚል ባዘጋጀው ዘመቻ ነው ይህንንም እያካሄደ ያለው ከጉልበታቸው በታች አምስት ሳንቲሜትር ቁመት የማይረዝም አጭር ቀሚስ የለበሱ ሴቶች ከደመወዛቸው በተጨማሪ መቶ ሩብል ወይም አርባ አምስት ብር ይከፈላቸዋል። ገንዘቡንም ለማግኘት ፎቷቸውን ለኩባንያው መላክ ይጠበቅባቸዋል። •"ማንም መብታችንን ሊሰጠን ስለማይችል፤ ሴቶች ማንንም ሳይጠብቁ በራሳቸው መታገል አለባቸው" •ታሪክ እየቀየሩ ያሉት ሴቶች •የተነጠቀ ልጅነት በብዙ ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ከፍተኛ ወቀሳን እያስተናገደ ያለው የኩባንያው አሰራር የሴቶችን አስከፊ አያያዝ ያሳየ ነው ተብሏል። ታዋቂዋ የፌሚኒስት ጦማሪና ጋዜጠኛዋ ዛሊና ማርሽንኩሎቫ ይህንን ጅማሮም "ያረጀ ያፈጀ" በማለት ወርፋዋለች። ኩባንያው በበኩሉ በፆተኝነት ሊወቀስ እንደማይገባና ስልሳ ሴቶችንም ያሳተፈ እንደሆነ ለኃገሪቱ ሚዲያ ገልጿል። "የስራ አካባቢያችንን ብሩህ ለማድረግ የተጠቀምንበት ዘዴ ነው" በማለት የኩባንያው ቃል አቀባይ ጎቮሪት ሞስክቫ ለተባለ የሬድዮ ጣቢያ ገልፀዋል። "ሰባ ፐርሰንት ሰራተኞቻችን ወንዶች ናቸው፤ እንዲህ አይነት ዘመቻዎች ህብረትን ለመፍጠር ይጠቅማሉ" ብለዋል። አክለውም " ሴት ሰራተኞቻችን አብዛኛውን ጊዜ ወደ ስራ ቦታ የሚመጡት ሱሪ ለብሰው ነው፤ ለዚህም ነው የሴት ሰራተኞቻችንን ግንዛቤ በመጨመር ሴትነታቸውንና ማራኪነታቸው እንዲሰማቸው ቀሚስ እንዲለብሱ የምናበረታታው" ሩሲያዊያን የትዊተር ተጠቃሚዎች ግን የኩባንያውን ዘመቻ በቀላል አላዩትም "ፆተኛ" የሚሉና እንዲሁም ሌሎችን ትችቶች አስተናግዷል። " ወንዶች በሚበዙበት መስሪያ ቤት ውስጥ አጭር ቀሚስ ለለበሰችና ሜካፕ ለተቀባች ሴት አርባ አምስት ብር ተጨማሪ መስጠት ምን ማለት ነው? ፌሚኒዝም ምን ያደርግልናል ሴቶች ገንዘብ ተከፍሏቸው ወንዶችን ማስደሰት እየቻሉ" በማለትም በምፀት የወቀሷቸውም አልታጡም።
50863097
https://www.bbc.com/amharic/50863097
ኢትዮጵያ ሳተላይት ማምጠቋ ለምን ይጠቅማታል?
ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያ የሆነችውን ሳተላይት ከቻይና የሳተላይት ማስወንጨፊያ ጣቢያ ወደ ህዋ ላከች።
ሳተላይቷ ከቻይና ስትመጥቅ ሳተላይቷ ለግብርና፣ ለማዕድን፣ ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለአየር ንብረት ጥበቃና ለመልከዓ ምድር ጥናት የመረጃ አገልግሎትን ትሰጣለች ተብሏል። Ethiopian Remote Sensing Satellite - 01 (ETRSS - 01) የተሰኘችው ሳተላይት በቻይና መንግስት የተገነባች ሲሆን በግንባታው ሂደትም በርካታ ኢትዮጵያውያን ባለሞያዎች ከቻይና አጋሮቻቸው ጎን ተሰልፈው ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡ ከቻይና 6 ሚሊየን ዶላር ተለግሶ የተሠራችው ይህቺ ሳተላይት በአጠቃላይ 210 ሚሊየን እንደፈጀች ተነግሯል። • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሊያድኑት የነበረው ለገሰ ወጊ ማን ነበሩ? የሳተላይቷ የመረጃ መቀበያ እንጦጦ ላይ የተሠራ ሲሆን ከማምጠቅ ሥራው ጀምሮ ቁጥጥሩ ሙሉ ለሙሉ እንጦጦ ላይ በኢትዮጵያውያን የህዋ ዘርፍ ባለሞያዎች ይከናወናል። ይህ ሳተላየት የማምጠቅ ሥራ ከተለያዩ አካላት 10 ሚሊየን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ማግኘቱ የተነገረ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግሥትም ተጨማሪ በጀት መመደቡ ተገልጿል። ቻይናውያን ኢንጂነሮች ኢትጵያውያንን እያሰለጠኑ ሳተላይቱ ቻይና ውስጥ እንዲሁም በከፊል ኢትዮጵያ ውስጥ ተገነብቷል። 70 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ሳተላይት ታኅሣሥ 10፣ 2012 ዓ. ም. ማለዳ ከቻይና መምጠቁ በቀጥታ በተላለፈ ፕሮግራም ታይቷል። ሳተላይቱ በቻይና እገዛ ከምድረ ቻይና ይምጠቅ እንጂ፤ "ተቆጣጣሪዋም፣ አዛዧም ኢትዮጵያ ናት" ይላሉ የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሰለሞን በላይ ለቢቢሲ። ሳተላይት ማምጠቅ ለምን አስፈለገ? የህዋ ጥናት በዓለም ላይ በፍጥነት እየዘመኑ ካሉ ዘርፎች መካከል ይጠቀሳል። የሰው ልጅ ምድር ጠባው አልያም ከምንኖርበት ዓለም ውጪ ያለውን ለማወቅ ጓጉቶ ዘወትር እየቆፈረ ነው። ከህዋ ፍተሻ በተጨማሪ ህዋን ተጠቅሞ መሬትን ማሰስ የመሬት ምልከታ ሳተላይት ተግባር ነው። ሳተላይቱ መረጃ ሲሰበስብ ይህ ቀረህ አይባለውም። ከግዙፍ ክንውኖች እስከ ጥቃቅን እንቅስቃሴዎች ይመዘግባል። እንደ ባለሙያዎች አባባል ሳተላይቱ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው። የአየር ንብረት ለውጥን ለመቆጣጠር፣ የተፈጥሮ አደጋዎች ከመድረሳቸው አስቀድሞ ለመተንበይ፣ ደህንነትን ለመጠበቅ ወዘተርፈ ይውላል። በእርግጥ ብዙዎች በታዳጊ ሀገር የህዋ ጥናት አስፈላጊነቱ ላይ ጥያቄ ቢያነሱም፤ ዶ/ር ሰለሞን "ህዋ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገሮች የመኖርና ያለመኖር ጥያቄ ነው፤ ቅንጦት አይደለም" ይላሉ። የአየር ንብረት ለውጥ የመላው ዓለም ስጋት በሆነበት ዘመን፤ አንዳች ተፈጥሯዊ አደጋ ከመድረሱ በፊት አስቀድሞ መረጃ ማግኘት ብልህነት ነው። የዛፍ ቁጥር፣ የአየር ንብረት ለውጥና ሌሎችም መረጃዎች ከተሰበቡ በኋላ እንደ ጎርፍ ያሉ አደጋዎች ከመከሰታቸው በፊት መተንበይ ይቻላል። • በቤታችን ውስጥ ያለ አየር የጤናችን ጠንቅ እንዳይሆን ማድረግ ያለብን ነገሮች ግብርና ቀዳሚ መተዳደሪያ በሆነባት ሀገር የቱ አካባቢ ምርታማ ነው? የአየር ንብረት ለውጥ ይኖር ይሆን? የሚሉ ጥያቄዎች በቀላሉ እንዲመለሱ የሳተላይቱ መረጃ አስፈላጊ ይሆናል። ዶ/ር ሰለሞን እንደሚሉት፤ አንድ የግብርና አካባቢን የሚያሳይ ፎቶግራፍ ስለ እርሻ መሬቱ፣ ስለ ውሀው፣ ስለ አፈሩ ዝርዘር መረጃ ይሰጣል። መረጃዎቹን በመጠቀም ምርታማ የሆኑ አካባቢዎችን መለየት፣ የምርት መጠንን በትክክል ማወቅም ይቻላል። ኢንዱስትሪዎች እየተስፋፉ በመጡባት ኢትዮጵያ፤ ፋብሪካዎች የት መገንባት አለባቸው? ለሚለው ጥያቄ የሳተላይቱ መረጃ መልስ ሊሰጥ ይችላል። ሕዝብ መቁጠር ሲያስፈልግ ከዘልማዳዊው መንገድ ሳተላይቱን መጠቀም ይመረጣል። ትክክለኛ መረጃ ከማግኘት፣ ገንዘብና የሰው ሀይል ከማዳን አንጻርም የተሻለው አማራጭ ነው። ሳተላይቱን ደህንነትን ከመጠበቅ ጋር የሚያስተሳስሩት ባለሙያዎች አሉ። ዶ/ር ሰለሞን በበኩላቸው "በመርህ ደረጃ ህዋ የሚውለው ለሰላማዊ እንቅስቃሴ ነው" ብለው፤ ለጦርነት፣ ለጦር መሳሪያ ማሳለጫነት እንደማይውል ያስረዳሉ። የ'ኢንተርናሽናል የአውተር ስፔስ' ተቋም አባል መሆን፤ ኢትዮጵያን ከመሰል ድርጊቶች እንደሚያግዳትም አክለዋል። ኢትዮጵያ እስካሁን መረጃውን እንዴት ታገኝ ነበር? ኢትዮጵያ እነዚህን መረጃዎች ሳተላይት አምጥቀው ፎቶ ከሚያስነሱ ሀገሮች ትሸምት ነበር። ዶ/ር ሰለሞን የሚያጣቅሱት ከአምስት ዓመት በፊት በተሰራ ጥናት መሰረት ኢትዮጵያ የሳተላይት መረጃን ለመግዛት በዓመት 250 ሚሊየን ብር ታወጣለች። ጥናቱ ለደህንነት የሚወጣውንና ዩኒቨርስቲዎች የሚከፍሉትን አያካትትም። ወጪው ከዓመት ወደ ዓመት እንደሚጨምርም ያስረዳሉ። የከተሞች መስፋፋት፣ ኢንቨስትመንቶች እየጨመሩ ሲሄዱም በዛው መጠን የመረጃው አስፈላጊነት ይንራል። የሚወጣው ገንዘብም እንዲሁ። ሳተላይት ማምጠቅ እነዚህን ወጪዎች እንደሚቀንስ ይጠበቃል። አፍሪካ ውስጥ መሰል ሳተላይት ለሌላቸው ሀገሮች መረጃ መሸጥም ይቻላል። የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተሩ "ትልቅ ቢዝነስ ነው" የሚሉትም ለዚሁ ነው። "ሲያስፈልግ መረጃ እንሸጣለን። ከኛ የላቀ ቴክኖሎጂ ካላቸው ሀገሮች ጋር መረጃ መለዋወጥም ይቻላል፤" ኢትዮጵያ በህዋ ጥናት የት ደረሰች? ዓለም በህዋ ጥናት ቴክኖሎጂ እየመጠቀ ሄዷል። ኢትዮጵያ ከተቀረው ዓለም አንጻር ጀማሪ ናት። አፍሪካ ውስጥ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ አልጄሪያና ግብጽ ጥሩ ስም አላቸው። ኢትዮጵያ "ህዋ ለልማት" የሚል የምሥራቅ አፍሪካ ሀገሮች ትብብር ቢሮ አቋቁማ አበረታች እንቅስቃሴ ማድረጓ ተጠቃሽ ስኬት ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በ2030 ይደረስባቸዋል ብሎ ካስቀመጣው ግቦች አብዛኞቹ የህዋ ቴክኖሎጂን ያማከሉ መሆናቸው፤ ዘርፉን ችላ ማለት እንደማያዋጣ ያመላክታል። ዶ/ር ሰለሞን የመሬት ምልከታ ሳተላይት ማምጠቅ ኢትዮጵያ በህዋ ሳይንስ ዘርፍ እንቅስቃሴ እያደረገች ስለመሆኑ ለዓለም መልእክት ማስተላለፊያ መንገድ እንደሚሆን ያምናሉ። • ኢትዮጵያ ሳተላይት ማምጠቅ ለምን አስፈለጋት? "ቴክኖሎጂው እጅግ አስፈላጊ ነው፤ ሳተላይቱን ማምጠቅ ኢትዮጵያን በህዋ ዘርፍ ጠንካራ ተወዳዳሪና እኩል ተጽእኖ ፈጣሪ ማድረግ የሚያስችል ነው" ሳተላይቱ አንዴ ከመጠቀ በኋላ ከሶስት እስከ አራት ዓመት ያገለግላል። ከዛ በላይ ሊቆይም ይችላል። በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት፤ የመሬት ምልከታ ሳተላይቶች ህዋ ላይ እንዲቆዩ የሚፈቀደው ለስምንት ዓመት ነው። ኢትዮጵያ ከምታመጥቀው ሳተላይት፤ በየአራት ቀኑ የመላው ኢትዮጵያ መረጃ የዓለም ደግሞ በ55 ቀን ይገኛል። በህዋ ምርምር ዘርፍ ቅርብ ጊዜ እውን ይሆናሉ ተብለው ከሚጠበቁ ፕሮጀክቶች ውስጥ ላሊበላ ላይ ይገነባል የተባለው ዓለም አቀፍ ኦፕቲክ ቴሌስኮፕ አንዱ ነው።
news-52817045
https://www.bbc.com/amharic/news-52817045
የኮሮናቫይረስ፡ ሬምዴሲቬር ሐኪሞች እያዳነቁት ያለው የኮሮናቫይረስ መድኃኒት
በጥር 20 አሜሪካ የመጀመርያውን የኮቪድ-19 ተጠቂ አገኘች። በዋሺንግተን፤ ኤቨሬት።
ሰውየው በቻይና ሁቤይ ግዛት ዉሃን ከተማ ዘመዶቹን ጠይቆ መመለሱ ነበር። 35 ዓመቱ ነው። ምንም የከፋ ሕመም አይታይበትም። ያስላል፣ ትኩሳት አለው፤ በቃ ይኸው ነው። ሐኪሞቹ ግን በዚያ ወቅት በቻይና እየሆነ ስላለው ነገር በንቃት እየተከታተሉ ስለነበር ታማሚውን "አይዞህ በቃ ትድናለህ ሂድ" አላሉትም። በዚያ ላይ ሰውየው ደግሞ ከቻይና ነው የተመለሰው። ትንሽ እንየው ብለው በሽተኛውን ያቆዩታል። እንደፈሩትም ሰውየው ትኩሳቱም ሳሉም እየበረታበት መጣ። ትንፋሽም ያጥረው ጀመር። ብሎ ብሎ ኦክሲጂን አስፈለገው። ሳምባውም ምች መቶት ነበር፤ ኒሞኒያ። እነዚህ ሲደማመሩ ምን ማለት እንደሆነ ግልጽ ነበር። ሰውየው በኮቪድ-19 መያዙ እርግጥ ሆነ። ዶ/ር ዳያዝ ወዲያውኑ ለአሜሪካ የመድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ሁኔታውን አሳወቁ። ሰውየው ላይ ክትትሉ በረታ። ለዚህ አዲስ በሽታና ለዚህ በሽተኛ ምን ብናደርግ ይሻላል ሲሉ መከሩ። ምክንያቱም በሽታው መድኃኒት አልነበረውም፤ አሁንም የለውም። ለጊዜው ጥቅል የጸረ-ቫይረስ መድኃኒት የሆነውን ሬምዴሲቬርን ብንሰጠውስ ተባለ። የመድኃኒቱን አምራች ጊሌድ ኩባንያን አማከሩት። ጊሌድ መድኃኒቱን ወደ ሆስፒታሉ ይዞት መጣ። ከዚህ በኋላ የሚቀረው ከመድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ፍቃድ ማግኘት ነበር። ያልታወቀ በሽታ ሲከሰት በሐኪሞች ምክክር አንድ መድኃኒት ተግባራዊ እንዲሆን የሚፈቅደውን ሕግን [ኮምፓሺኔት ዩዝ ኦፍ ድራግስ] በመጠቀም ለ35 ዓመቱ ጎልማሳ ሬምዴሲቬርን በ7ኛው ቀን ሰጡት። ምንም ዓይነት የጎንዮሽ ጉዳት አላስከተለበትም። እንዲያውም እያገገመ መጣ። በተለይ መድኃኒቱን በወሰደ በነገታው የተነቃቃ መሰለ። ዶ/ር ዳያዝ ያንን ምሽት ሲያስታውሱ "ያ በሽተኛ ያንን መድኃኒት ሲወስድ በወረርሽኙ ታሪክ የመጀመርያው ፍጡር ስለሆነ መድኃኒቱ ምን ሊያስከትልበት እንደሚችል በጉጉት ነበር የምንከታተለው" ይላሉ። ከዚያን ጊዜ ወዲህ ነው እንግዲህ ሬምዴሲቬር የተሰኘው ይህ መድኃኒት ላይ በምርምር የተዘመተበት። ሬምዴሲቬር፡ ምን ያህል ፈውስ ይመጣል? ሬምዴሲቬር ጸረ-ቫይረስ መድኃኒቶች መሀል የሚመደብ ነው። ለኮሮናቫይረስ ታማሚዎች እስካሁን የተሻለው መድኃኒት እሱ እንደሆነ በስፋት እየተነገረ ነው። የዩናይትድ ኪንግደም የጤና ሚኒስትር ማት ሃንኮክ "ምናልባት እስካሁን ከሞከርናቸው እጅግ ተስፋ ሰጪው" ብለውታል።መድኃኒቱ ቀደም ሲል ለኢቦላ ታማሚዎች የሚሰጥ ነበር። ሬምዴሲቬር አሁን በዩናይትድ ኪንግደም የብሔራዊ ጤና አገልግሎት ለኮቪድ-19 ታማሚዎች እንዲሰጥ በሚል አቅርቦት እንዳይጓደል እየተሰራ ነው። የዩናይትድ ኪንግደም የመድኃኒት ቁጥጥር ባለሞያዎች ይህን መድኃኒት በተወሰኑ የኮሮናቫይረስ ታማሚዎች ላይ ተግባራዊ ለማድረግ በፈዋሽነቱ ዙርያ በቂ መረጃ ተገኝቷል። ለጊዜው መድኃኒቱ እንደልብ ስለማይገኝ ሕመም ለጠናባቸው ብቻ እየተሰጠ ነው። የኮሮናቫይረስ ህሙማንን ለማከም እንዲውል የተፈቀደው ሬምዴሲቬር በዚህ መድኃኒት ዙርያ ብዙ እየሰራች ያለችው ዩናይትድ ኪንግደም ትሁን እንጂ አሜሪካና ጃፓንም መድኃኒቱን በስፋት ለማምረት ሂደት ላይ ናቸው። አሁንም ቢሆን መድኃኒቱ ላይ የሚደረጉ ምርምሮችና ሙከራዎች በመላው ዓለም ተጠናክረው ቀጥለዋል። የዚህ መድኃኒት ተመራጭ መሆን በሁለት ምክንያት ነው። አንደኛው ከዚህ በፊት ለተለያዩ ጸረ-ቫይረስ ደዌዎች የሚሰጥ መድኃኒት ስለሆነ የሰው ልጅ ላይ የከፋ ጉዳይ እንደማያመጣ ቀድሞም መታወቁ ነው። ሁለተኛው ደግሞ ለኢቦላ ይሰራል ወይስ አይሰራም በሚል ብዙ ክሊኒካል ሙከራዎች የተደረገቡት መሆኑ ነው። እስካሁን በእርግጠኝነት ስለዚህ መድኃኒት የተደረሰበት ነገር ቢኖር ከኮሮናቫይረስ የማገገምያ ጊዜን እንደሚያፋጥን ወይም እንደሚያሳጥር ነው። መድኃኒቱን ከኮሮናቫይረስ እያገገሙ ያሉ ታማሚዎች ሲወስዱት በትንሹ በአራት ቀናት የማገገሚያ ጊዜያቸውን ያሳጥራል። ነገር ግን መድኃኒቱ ስለ ፈዋሽነቱ እስካሁን አልተረጋገጠም። በሽተኞች በሁለት ቡድን ተከፍለው አንደኛው ቡድን መድኃኒቱን እንዲወስድ ሌላኛው እንዳይወስድ በማድረግ ልዩነቱን ማየት ተችሏል። የወሰዱት በተሻለ ፍጥነት አገግመዋል። ተስፋን ያጫረው ሬምዴሲቬር የሊድስ የሕክምና ትምህርት ቤት መምህር የሆኑት ዶ/ር ስቴፈን ግሪፊን "እስካሁን ከተሞከሩ መድኃኒቶች እጅግ ተስፋ ሰጪው" ብለውታል ሬምዴሲቬር። "ለጊዜው እየተሰጠ ያለው በሽታው ለጠናባቸው ብቻ ቢሆንም" ይላሉ ዶ/ር ስቲፈን፣ በቀጣይነት ተደራሽነቱ ሲሰፋ ለብዙ ዜጎች ተስፋን ይሰጣል። ከዚህ መድኃኒት ሌላ ለኮሮናቫይረስ ፈውስ በሚል አሁን በምርምር ላይ የሚገኙት ለኤችአይቪ እና ለወባ ይሰጡ የነበሩ መድኃኒቶች ናቸው። የዶናልድ ትራምፕና የቦልሶኖሮ ተመራጭ መድኃኒት ሃይድሮክሲክሎሮኪን ግን ቢያንስ በዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ዘንድ አልተመረጡም። በርሱ ላይ የሚደረገው ምርምር እንዲቆም ተደርጓል። ድርጅቱ ሃይድሮክሲክሎሮኪን በተመለከተ ጊዜያዊ ውሳኔ ያሳለፈው በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሃይድሮክሲክሎሮኪን መድኃኒትን የወሰዱ ሰዎች ሞታቸው መፋጠኑን ከተመለከተ በኋላ ነው። ስለዚህ ለጊዜው ሜዳው ላይ ያለው ሬምዴሲቬር ነው። የጸረ-ቫይረስ መድኃት የሆነውን ሬምዴሲቬርን ያመረተው ጊሌድ የመድኃኒት አምራች መጀመርያ መድኃኒቱን ሲፈበርከው ለጠቅላላ አንቲቫይራል [ጸረ ቫይረስ] እንዲሆን የነበረ ቢሆንም በኋላ ላይ ለኢቦላ የተሻለው ሆኖ ቆይቷል። የተሻለ ይባል እንጂ መድኃኒቱ በኢቦላ ላይ ያሳየው ውጤት ግን ያን ያህል የሚያስመካ አልነበረም። ሬምዴሲቬር በአሁኑ ጊዜ ቢያንስ በአምስት ዓለም አቀፍ ቤተ ሙከራዎች ውስጥ ምርምር እየተደረገበት ይገኛል። የመድኃኒት ቅመማ ባለሞያዎችም ሆኑ ሐኪሞች ይህ መድኃኒት በምንም መልኩ "ጨርሶዉኑ ፈዋሽ" ተደርጎ መታሰብ እንደሌለበት ያሳስባሉ። ለአንድ በሽታ መድኃኒት ማግኘት እጅግ አዝጋሚ፣ እጅግ አታካችና እጅግ ትዕግስትን የሚፈታተን ሂደት እንደሆነ የጊሌድ ምክትል ፕሬዝዳንት ቶማስ ሲሀላር ያሰምሩበታል። ያም ሆኖ ለጊዜው ዓለም ሬምዴሲቬር ላይ ዐይኑን ጥሏል።