input
stringlengths
1
130k
መራኂተ መንግሥቷ ግልጽ በሆነ መልኩ በርካታ ድምፆችን ሊያጡ ይችላሉ።
ከባየርኑ ክርስቲያን ሶሻሊስት ጋር ተጣማሪ የሆነው ፓርቲያቸው እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር ከ አንስቶ ከፍተኛ ሽንፈት ቢገጥመውም ማለት ነው።
ጃማይካ ጥምረት በጀርመን ምርጫ ውጤት መሰረት አዲስ መንግሥት የሚመሰረተው የተለያዩ አሸናፊ ፓርቲዎች ተደራድረው ከተጣመሩ በኋላ ነው።
ጃማያክ ጥምረት ጀርመን እንደ ኢትዮጵያ ከጃማይካዎች ጋር የተለየ ትስስር ኖሯት አይደለም።
የክርስቲያን ዲሞክራቲክ ኅብረትና የባየርኑ ክርስቲያን ሶሻሊስት ኅብረት ጥምረት መለያው ጥቁር ነው።
የነጻ ዲሞክራቶቹ ፓርቲ መለያ ቀለም ቢጫ እንዲሁም የአረንጓዴዎቹ ፓርቲ መለያ አረንጓዴ ቀለም በአንድነት ጥቁር ቢጫና አረንጓዴ ቀለም ቅልቅል ይፈጥራል።
የመቀሌዉ መድረክ የፖለቲካ ፓርቲ ሆነ ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
ምያንማር ማንዴላን ብቻ ሳይሆን በወዲያኛዉ ጠርዝ ፍሬድሪክ ዴ ክላርክንም ትሻለች።
የደጋፊ አድናቂ ወገናቸዉ ጭፈራ ቡረቃ ሲደራ ቅዳሜ የሐያላኑ ሐገራት መሪዎች ለማንዴላ ካሉት በላይ ዉደሳ ሙገሳዉን ያንቆረቆሩላቸዉ ገቡ።
ያቺ ሞቃት ደናማ ዉብ ጥንታዊ ሥልታዊ የሐምሳ ሚሊዮኖች ሐገር።
እንደ በርማ ምያንማር እንደ ራንጉን ያንጉን ስሞች ሁለትነት ሁሉ የሐገር ከተማይቱ የረጅም ጊዜ ጥቅል ታሪክ ሁለት ነዉ።
ያቺን ጥንታዊ ሐገር ያቺን ሰፊ ከተማ ካነፁት ሁለቱ ተቃራኒ ታሪኮች አንዱ ቅዳሜ ተደገመ።
የበርማ ምያንማሮቿ ማንዴላ ከቁም ወይም ከቤት ዉስጥ እስረኝነት ተፈቱ።
ከቦራቂ ፌስተኞቹ ባንዷ ቋንቋ ጨረቃዋ ደማቅዋ ጨረቃ ጨለማዉን በርቃ ደመቀች።
በጎሳዎች የዘመናት ስብጥር የተቀረፀዉ ያ ሕዝብ ከ ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ ጀምሮ ወታደራዊ፥
ሠላም ጠያቂ መነኮሳት ሲዋረዱ ሲሳቀሉ ሲሳቀቁ እያየ ከማዘን መሸማቀቅ በስተቀር ሌላ የማያዉቀዉ ትዉልድ በርግጥ ተደሰተ።
የርዳታ አቀባዮችን ጥድፊያ ሩጫ ስታፈራርቅ የከረመችዉ ራንጉን ያንጉን ባንድ ጀምበር፥
በጥልቅ ደስታ የሚፈነድቅ ያን ያሕል ሕዝብ ሲያስተናግድባም በቅርብ ዘመን ታሪኳ የቅዳሜዉ የመጀመሪያዉ ነዉ።
እንደ ዘንድሮዉ ሁሉ ድሮ ጥንት በጣም ጥንትም ለባለ ሁለት ስሟ ሐገር እንዲያ ነበር።
የብሪታን ቅኝ ገዢዎች ጠላቶቻቸዉን ቀስ በቀስ እያዳከሙ በ የመጨረሻዎቹን የበርማ ጀግኖች ጨፍልቀዉ ሐገሪቱን ከሕንድ ጋር ጠቅልለዉ ይገዟት ገቡ።
ያ ሕዝብ ነፃነቱንም አንደ አንድ የሚያቆሞዉን የሐገሩን የግዛት አንድነትም አጣ።
ሁለተኛዉ የአለም ጦርነት ለበርማ የደስታ ሐዘን ሁለት ተቃራኒ ታሪክ የደመቀበት ነበር።
የብሪታንያ ቅኝ ተገዢዋ የሕንድ አንድ ክፍለ ግዛትነትዋ አብቅቶ የብሪታያ ቅኝ ተገዢ ግን አንድ ሐገርነቷ በ ተመለሰላት።
ያኔ ወጣቱ በርማዊ ነፃነት ነፃነት ይሸተዉ የነፃነት ትግል ወኔዉ ይሞግተዉ ያዘ።
ከግንባር ቀደሞቹ ወጣቶች አንዱ ያሁኒቱ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ተሟጋች አባት ነበር።
አዉግ ሳንና ብጤዎቹ የዩኒቨርስቲ ትምሕርታቸዉን አቋርጠዉ የብሪታንያን ቅኝ ገዢዎች ለመዋጋት ላደራጁት ሐይል ድጋፍ የሚሰጣቸዉ ፍላጋ ከቤጂግ፥
በጦርነቱ መሐል ጃፓኖች ብሪታንያን ድል ሲደርጉ በአዉሮጳ ቅኝ ገዢዎች ሲማቅቅ የነበረዉ ሕዝብ ላፍታም ቢሆን ቦረቀ።
ከባሱ ገዢዎች እጅ መዉደቁን ለማወቅ ግን ብዙ ጊዜ አልፈጀበትም።
ከድጡ ወደ ማጡ መግባቱን እንዳወቀ ወዲያዉ በጃፓኖች አገዛዝ ላይ አመፀ።
አሰልሶ ጃፓኖችን ድል ባደረጉት እንግሊዞች ላይ ያመፀዉን ሕዝብ እንደ ፖለቲከኛ ያደራጁት፥
የትዉልድ ከተማ የድፍን ሐገሯ ስምም እንደ ሕዝብ ሐገሯ ታሪክ ሁሉ የቅኝ ገዚዎችን አጠራር ከሐገሬዉ ስያሜ ጋር የቀየጠ ሁለት ተቃራኒ ነዉ።
በ ይሕን ዓለም የተቀየጠችዉን ሕፃን ግን ወላጆችዋ አዉንግ ሳንን ካባቷ፥
በትግላቸዉ የተከበሩት አዉንግ ሳን የፖለቲካ ፓርቲ መሪነትን ከጄኔራል ማዕረግነት ጋር ደርበዉ የሐገራቸዉን የነፃነት ዕለት እንዳሰሉ፥
የማሕተመ ጋንዲን የሰላማዊ ትግል ፍልስፍናን ከጋንዲም በላይ የቡደሐ እምነት ተፅኖ ከምዕራቡ ዘመናይ ትምሕርት ጋር እንደቀየጠች አደገች።
ደጋፊዎቻቸዉ እንደሚሉት እንደ ማንዴላ ብልሕ ጠንካራ ታጋሽም ይሆኑ ይሆናል።
በ ፖለቲካዉን ተቀይጠዉ ብሔራዊ ሊግ ለዲሞክራሲ የተሰኘዉን ፓርቲ ሲመሰርቱ ግን ከማንም በላይ የስም አካላቸዉ መሠረተ ዉልድ የሆኑትን አባታቸዉን ነበር የሆኑት።
ትናንትም ያሉት አባታቸዉ ከስልሳ አምስት አመታት በፊት ካሉት ብዙም የራቀ አልነበረም።
ሕዝቡ ምን እንደሚፈልግ እዚሕ የተሰበሰባችሁት ሁላችሁም ምን እንደምትሹም አዉቃለሁ።
አንዳዴ አሰልቺ ቢሆንም በየዕለቱ ከአምስት እስከ ስድስት ሰአት ራዲዮ ሳዳምጥ ነበር።
በሰልፈኞቹ እና በሳቸዉ መሐል ማስመሰል የሌለበት ደስታና ፈገግታ መኖሩን ትገነዘባለሕ።
ሕዝቡ እዚሕ ለሳቸዉ ያለዉ ስሜት ግን እነዚያን ፈተናዎች ለመወጣት ለሚያደርጉት ጥረት ከፍተኛ የሕዝብ ድጋፍ እንዳላቸዉ መስካሪ ነዉ።
ከማንዴላ ያስቆጣራቸዉ ይሕ የሕዝብ ድጋፍ መከራን የመቋቋም ችሎታዉ ነዉ።
ከዉጪ በተለይ ከምዕራቡ አለም የጎረፈላቸዉ አድናቆትና ድጋፍም ቀላል የሚባል አይደለም።
የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳት ባራክ ኦባማ ለኔ ጀግናዬ ለበርማ ሕዝብ ደግሞ የመብት ነፃነት አብነት ብለዋቸዋል።
ለጀርመንዋ መራሒተ መንግሥት ለአንጌላ ሜርክል ደግሞ የሰብአዊ መብት ታጋይ አብነት።
ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ፓን ጊ ሙን ሌሎችም የብዙ ሐገር መሪ ዎች አድንቀዉ ድጋፋቸዉን ሰጥተዋል።
ይሕን መሰሉን ድጋፍ ደጋፍ ደግሞ የብሪታንያዉ አምባሳደር ፈተና ያሉትን ትግል ከግብ ለማድረስ ጠንካራ ምርኩዝ ያደርጉት ይሆናል።
ማንዴላ የፈጠሯትን ደቡብ አፍሪቃን መሰል በርማ ወይም ምያንማርን ለመፍጠር ከማንዴላ ድንቅ ተጋድሎ አለማ የወረሱት ትግል ተጋድሎ ፥
አብደላ ሐምዶክ ሱዳንን በጠቅላይ ምኒስትርነት እንዲመሩ የተመረጡት ለወራት ከጦር ሹማምንቱ ጥብቅ ድርድር ላይ የከረሙት ተቃዋሚዎች በእጩነት ካቀረቧቸው በኋላ ነው።
እርሳቸውም በአደባባይ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ እንደከረሙ የሱዳን ዜጎች ዴሞክራሲያዊ እና ለፍትኅ የቆመ መንግሥት ለማቆም ከጎናቸው እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።
የመጣሁት አብረን እንድንሰራ እኛና አገራችንም በኅብረት ወደ አዲስ ምዕራፍ እንድንሻገር ነው።
ልዩነቶቻችንን እንዴት መፍታት እንዳለብን እንስማማ ነፃ ከወጣን ጀምሮ ሁሉም የሱዳን ዜጎች የሚስማሙበት ብሔራዊ መርሐ ግብር መቅረፅ አልቻልንም።
ሱዳን እንዴት መተዳደር አለባት በሚለው ላይ እንስማማ እና ውሳኔውን በሱዳን ዜጎች ለሚመረጥ መንግሥት እንተው ሲሉ ተማፅኖ የተቀላቀለበት ጥያቄ አቅርበዋል።
ሐምዶክ ቃለ መሐላ በፈሙበት ዕለት ቀደም ብሎ የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ተመስርቷል።
በሉቴናንት ጄኔራል አብዱል ፋታኅ አል ቡርሐን የሚመራው እና ከጦሩ እና ከተቃዋሚዎች የተውጣጣው ሉዓላዊ ምክር ቤት ለ ወራት ሥልጣን ላይ ይቆያል።
በአብዮቱ ሥር የሰደደው እና ነፃነት ሰላም እና ፍትኅ የሚለው መፈክር የሽግግር ጊዜው ዋንኛ መርሐ ግብር ይሆናል።
አብደላ ሐምዶክ በሙያቸው የኤኮኖሚ ባለሙያ ሲሆኑ ትምህርታቸውን በኻርቱም ዩኒቨርሲቲ ተከታትለዋል።
የ ዓመቱ ጠቅላይ ምኒስትር ባለፉት ዓመታት የሱዳን ታሪክ ውስጥ ይኸን ሥልጣን የያዙ የመጀመሪያ ሲቪል ናቸው።
አል በሽር ሥልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ከሱዳን የፋይናንስ ሚኒስቴር ሰራተኝነታቸው ተባረዋል።
ኋላም አል በሽር የተቋሙ ምኒስትር እንዲሆኑ ያቀረቡላቸውን ግብዣ አሻፈረኝ ብለው ሳይቀበሉ ቀርተዋል።
በአፍሪካ ልማት ባንክ እና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኤኮኖሚክ ኮሚሽንን ጨምሮ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት በኃላፊነት ሰርተዋል።
በሱዳን የዶይቼ ቬለ ዘጋቢ የሆነው አልሳኖሲ አዳም እንደሚለው በተለይ አል በሽርን ለውድቀት ላበቃቸው ምጣኔ ሐብታዊ ምስቅልቅል መፍትሔ ከጠቅላይ ምኒስትሩ ይጠበቃል።
አልሳኖሲ አዳም ከዚህ በኋላ ትልቁ ችግር ኤኮኖሚውን ከገባበት ምስቅልቅል እንዴት ማውጣት ይቻላል የሚለው ነው።
ሐምዶክ በሙያቸው የኤኮኖሚ ባለሙያ ሆነው የጠቅላይ ምኒስትርነት ሥልጣን መያዛቸው በትክክለኛው ሰዓት በትክክለኛው ቦታ የተገኙ ያደርጋቸዋል።
ብዙ ሰዎች በእጩነት ያቀረቧቸው እና የተስማሙባቸው ለዚህ ይመስለኛል ሲል ተናግሯል።
አል በሽርን ገፍቶ የጣላቸው የሱዳን አብዮት የተጀመረው በዳቦ ዋጋ ማሻቀብ ሳቢያ ነው።
ሐምዶክ የሚረከቡት የሱዳን ኤኮኖሚ ፈተና ግን የዋጋ ግሽበትን በማረጋጋት ብቻ የሚመለስ አይደለም።
ጠቅላይ ምኒስትሩ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እና የሥራ አጥነትን ጨምሮ በአስተዳደር ጉድለት ከዓመት ዓመት ያደጉ ኤኮኖሚያዊ ችግሮች ከፊታቸው ተደቅነዋል።
በትክክለኛው ርዕይ በትክክለኛ ፖሊሲዎች ለምጣኔ ሐብታዊው ቀውስ መፍትሔ እንፈልጋለን ብዬ አስባለሁ።
ቅድሚያ ለሚያስፈልጋቸው ፈተናዎች በማገገሚያ መርሐ ግብሮች አማካኝነት የዜጎቻችንን ችግሮች የሚቀርፍ ዕቅድ ይኖረናል።
በዚህ ሳቢያ ከዓለም አቀፍ ተቋማት የዕዳ ስረዛ አይደረግላትም የውጭ መዋዕለ ንዋይም ቢሆን የተገደበ ነው።
አብደላ ሐምዶክ በአጭር እና ረዥም ጊዜ የሱዳንን የምርታማነት ችግሮች መፍትሔ ልናገኝላቸው ይገባል።
ኤኮኖሚው ያሉበትን የውጤታማነት ችግሮች ካልፈታን በቀር ሌሎች አገሮች እና ወዳጆቻችን ምንም ያክል እርዳታ እና ብድር ቢሰጡን የሚፈይድልን ነገር አይኖርም።
ከዚህ በተጨማሪ የበጀት አስተዳደር እና የፋይናንስ ፖሊሲውን መመርመር ይኖርብናል።
በእርግጥ ሐምዶክ እንዳሉት የሱዳንን ምጣኔ ሐብትም ይሁን ፖለቲካዊ ችግሮች ለመቅረፍ እውቀት ክህሎት እና ያላቸው የአመራር ብቃት ብቻቸውን በቂ አይደሉም።
ከእንግዲህ በመንግሥታዊ ውሳኔዎች በሉዓላዊ ምክር ቤቱ የተካተቱ የጦሩ ከፍተኛ ሹማምንት እና የተቃዋሚ ተወካዮች መስማማት መቻል አለባቸው።
ኢትዮጵያ እና ዪሮ ቦንድ የመሸጥ ዕቅዷ መግቢያ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት መግለጫውን ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፍ ገልጿል።
ጉዳዩን በተመለከተ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትን አስተያየት ለማካተት ያደረግሁት ጥረት የሚመለከታቸው አካላት ስብሰባ ላይ ናቸው በመባሉ ሊሳካ አልቻለም፡፡
በባለሙያ ርዳታ የሚወልዱ እናቶች ብዙ አይባሉም ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
የፖለቲካ ታዛቢዎች በጎርጎሪዮሳዊው ዓም በአፍሪቃ ያልጠበቁት ነገር በመከሰቱ በጣም ተገርመዋል።
የናይጀሪያን ምርጫ ተከትሎም ከስድስት ወር በኋላ ቀጣዩ ታሪካዊ ምርጫ በቡርኪና ፋሶ ተካሂዶ ቡርኪናቤዎቹ አዲስ ፕሬዚደንት መርጠዋል።
ይሁን እንጂ ጎርጎሪዮሳዊው ዓም በአፍሪቃ አስገራሚ የምርጫ ሂደት የታየበት ዓመት ሆኖ ሊመዘገብ አይችልም።
ምክንያቱም በተለያዩ ሃገራት ርዕሳነ ብሔሮች ሕገ መንግሥቱ ከሚፈቅድላቸው በላይ የስልጣን ዘናቸውን ለማራዘም በወሰዱት ርምጃ ውዝግብ ተነስቶዋል።
በቡሩንዲ ፕሬዚደንት ፒየር ንኩሩንዚዛ በስልጣን ለመቆየት ያቀዱበት ድርጊት ደም አፋሳሹን ሁከት ቀስቅሷል።
ፒየር ንኩሩንዚዛ መጀመሪያ ሕገ መንግሥቱን ለማስቀየር ሞከሩ ግን ይህ አልሳካ ሲላቸው ሕገ መንግሥቱን ለሳቸው እንደሚመች አድርገው ቀይረውታል።
ንኩሩንዚዛ ባለፈው ሀምሌ ወር ራሳቸውን እንደገና ለሃገር መሪነቱ ስልጣን አስመርጠዋል።
ልክ እንደ ቡሩንዲ ብዙ አፍሪቃውያን መንግሥታት የፕሬዚደንቶቻቸውን ስልጣን በሁለት ዘመን ገድበዋል።
እርግጥ አፍሪቃውያቱ ሃገራት የተለያዩ አሰራር ቢከተሉም በሁሉም የለውጥ ሂደት መነቃቃት መጀመሩን እንደተገነዘቡት ነው ጃኪ ሲልየ የገለጹት።
ይሁንና ዋናው ነገር በመራጮች ዘንድ የአስተሳሰብ ለውጥ መታየት መጀመሩ ነው።
ቀደም ባሉት ጊዚያት አፍሪቃውያኑ መራጮች ተቃውሞ የማድረግ ፍላጎታቸው ያን ያህል አልነበረም።
መሪዎቻቸው እስከፈለጉት ጊዜ ድረስ በስልጣን የመቆየት መብት እንዳላቸው አድርገው ነበር የሚመለከቱት።
ምርጫ መንግሥታት ወደፊትም በስልጣን ላይ መቆየት የሚችሉበትን ሁኔታ የሚያረጋግጡበት ሂደት ብቻ መሆኑ ቀርቷል።
መራጮች ምርጫን በተመለከተ የአስተሳሰብ ለውጥ በማድረግ ራሳቸው ተሟጋቾች ሆነዋል።
ምርጫውን በቀላሉ ማሸነፍ እንደማይችል የተረዳው መንግሥት ለራሱ መንገዱን ለማመቻቸት በጊዜ ርምጃ ወስዶዋል።
ወቅት በከፊል ራስ ገዟ የዛንዚባር ደሴት ውስጥ የኃይል ተግባር ተካሂዶ የአስመራጩ ኮሚሽን ማዕከል ተይዞ ነበር የድምፅ ቆጠራው እንዲቆም ተደርጓል።
ይህ ሁሉ በአፍሪቃ ምርጫ ምን ያህል ከፍተኛ ሚና እየያዘ መምጣቱን አሳይቶዋል።
የገዢው ፓርቲ እጩ ጆን ፖምቤ ማጉፉሊ አዲሱ የታንዛንያ ፕሬዚደንት ሆነው ቢመረጡም መራጩ ሕዝብ የይስሙላ ምርጫዎችን እንደማቀበል ግልጽ ማድረጉን ሲልየ አስረድተዋል።
የታንዛንያን ምርጫ ስንመለከት ገዢው ፓርቲ ለመጀመሪያ ጊዜ የምርጫው ውጤት እንዳሰበው ላይሆን ይችላል በሚል ስጋት አድሮበት ነበር።
ይህም የሚያሳየው በመራጩ ሕዝብ አስተሳሰብ ላይ ለውጥ መኖሩን ነው።